አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#መመለስ

ሂጂ ጥርግ በይ
እንዳልጎዳብሽ በማግስቱ ግን ነይ
በማግስቱ ስትመጭ ጉዳቴ ተሰምቶሽ
አክመሽ ጉዳቴን ወዲያው እንዳልጠላሽ
ሂጂ ተመልሰሽ
ነይም ሂጂም የሚል መመለስ የሚሉት
ናፍቆትሽን ይዘሽ

🧿በበረከት ታደሰ🧿
#ጮማና_ሽንብራ

ጮማዬን ደብቄ ብቻዬን ልበላው
ጣፋጩን እርጎዬን ሸሽጌ ልጠጣው
ድርቡን ሸማዬን ደብቄ ልለብሰው
ድሃ ጎረቤቴን ምንም እንዳያምረው
"ቸግሮኛል" አልኩት "ለአፌ እቀምሰው"
ጮማዬን ሸሽጌ እጦቴንስነግረው
ድሃ ጎረቤቴን እምባ ተናነቀው
"እኔ አለኝ!" እያለ ሄደ ከቤት ወጣ ሽንብራውን ይዞ ሊያካፍለኝ መጣ።
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_ሁለት


#በሜሪ_ፈለቀ

...ዳግማዊ ስለእኔ ከሰማው ውጪ አብሮኝ በነበረው ቆይታ ሊያውቅ የሚችለው ነገር መኖሩን እንጃ! ነገሩ እኔስ ምን አውቃለሁ? ስለእርሱ አይደለም እኮ አረ ስለራሴ..ስቆላል አይደለም። የሚያውቁኝ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ሲሉ
እሰማለሁ። ዳሩ እንኳን ሌሎች እራሴም ስለራሴ ነኝ' ያልኩትን ላልሆን እችላለሁ።

#አስቀያሚ_አይደለሁም

እግዜር የስሜት ባለቤት ከሆነ የእርሱን ፈገግታ የመሰለ ውበት አለሽ ባሉኝ ማግስት ምን ያደርጋል የሰከነች
አይደለችም ይሉኛል ፤ ፈገግታሽ የሰማይ መልአክትን መጎናፀፊያ ይመስላል ባሉኝ ማግስት እንደሸርሙጣ ታስካካለች ይሉኛል ፤ የሰውነቴን መዋቅር ከምርጥ ቀራፂ ውብ ቅርፅ ጋር ባነፃፀሩት ማግስት ክብሯን አትጠብቅም ለስሜቷ ትተኛለች ይሉኛል።

#ያላዋቂ_አይደለሁም

ቤተሰቦቼን እና በደቦ ያሳደጉኝን የሰፈሬን ሰዎች ጨምሮ የሚያውቁኝ ሁሉ ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ማስተርስ
በማዕረግ መጨረሴን አድንቀው ሳይጨርሱ ምን ያደርጋልኀቆማ መቅረቷ ነው ይላሉ።ማወቅ የሚሹት ነገር ሲኖር
እንዳልጠየቁኝ፣ የዕለት መፍትሄ ሲሹ እንዳላማከሩኝ፤በኪሎ የሚበልጣትን መፅሐፍ ይዛ የምትዞር ጉረኛ ናት
ይሉኛል፡፡

#ስሜት_አልባ_አይደለሁም

ዛር እንዳለበት ባለውቃቢ አብሮኝ እንዳላበደ፣ የሚያደርገኝ ጠፍቶት በስሜት እንዳልሰከረ የሱ እብደት ጎበዝ
ሲያስብለው የኔ ያለመሽኮርመም ብዙ ወንድ የምታውቅ ባለጌ ያስብለኛል።

#አመለ_ቢስ_አይደለሁም፡፡

ግልፅነቴ ደንቆት አንቺን ያገኘ ወንድ አፈስ ባለኝ ቅፅበት
“ለምን ታዲያ አንተ አታፍሰኝም?” ስለው “ሴት ልጅ እንዲህ እትልም” ይለኛል።

#አላማማኝ_አይደለሁም

ሀይማኖቴ ፍቅር ነው። የሰውን ልጅ ሁሉ መውደድ።ራሴን እወዳለሁ። ለዛ ነው ሌሎችን የሚወድ ልብ ያለኝ፡፡

ለራሱ ፍቅር የሌለው ለሌላ ተርፎት የሚለግሰው መውደድ ብትሉኝ ያንቀኛል። በሰውኛ ልኬት ሰውን የመውደድ ጣሪያ ራስን ከመውደድ ልክ መሆኑን ለማሳየት
ይመስለኛል ክርስቶስ ከህግ ሁሉ የበላይ ህግ የትኛው መሆኑን ሲጠየቅ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ' ያለው::
የፈጣሪ ትርጉሙ ለኔ ፍቅር ነው። የማላየውን ፈጣሪ ማምለክ እና መውደድ በአምሳሉ በፈጠራቸው በሰዎች
ሁሉ ውስጥ አለ ብሎ ማመን እነሱን ማክበርና መውደድ ነው።

ፍቅር ከክፋት በብዙ የራቀ ነውና ለክፋት የሆነ ልብ የለኝም። አንዳንዶቹ ግን እንደነሱ በሀይማኖት ካባ ራሴን
ደብቄ አለማስመሰሌን እኔኑ እያሙ እዛው ካባቸው ውስጥ ይደበቃሉ። በልባቸው ጠብታ ቅንነት ሳይኖር ለፍቅርና
እግዜርን ለመፍራት የሚኖሩ ያስመስሉታል። እኔ ግን ከክፉ ልብ ከመነጨ ምርቃት ይልቅ በአንድ ልኩ ከቅን ልብ የሆነ እርግማን ይሻላል ባይ ነኝ፡፡ ኡኡቴ ብርጉድሽ ቀርቶብኝ ፈስሽን በያዝሽልኝ ትል ነበር እናኒ ( አክስቴ)
#ንፉግ_አይደለሁም

መስጠት ከመትረፍረፍ አንጀት የሚፈልቅ ወይም ከመብዛት ማዕድ የሚዘገን አልያም ከመበልፀግ ማህፀን የሚወለድ እንዳልሆነ አውቃለው።

መስጠት ከመንፈስ እንጂ ከሌጣ እውቀት የተጋባ 'መክሊት' አይመስለኝም ።(መክሊት ያልኩት መስጠት ከምግባር ስለሚልቅብኝ ነው።መስጠት በትርፍ ካርዶች የምትቆምርበት ሲሆን ለሰማዩ ፅድቅም ለምድሩ ብድራትም መብቃቱን እጠራጠራለሁ።በየእለት ልመናዋ 'የምሰጠው አታሳጣኝ' እያለች የምትለምን ልበ መልካም አክስት ናት ያሳደገችኝ።

#የአራዳ_ደንባራ_አይደለሁም

ባህሌን አክባሪ መሆኔን ባወደሱ ቅፅበት እናትና አባቴ ባወጡልኝ ስም (ባንቺ ወግ አየሁ) ሲሳለቁ እሰማቸዋለሁ።በእርግጥ አንዳንዴ ቤተሰቦቼ ከአስር ተከታታይ ወንድ ልጅ በኋላ በየደብሩና በየደጀ ሰላሙ ተደፍተው እና በየአዋቂውና ውቃቢው ቤት አፈንድጀው የወለዱኝን ሴት ልጃቸውን እንኳን ለግለሰብ ለአንድ ሃገር ኸረ ምን ለሃገር ለአህጉር ራሱ የሚበዛ ዓረፍተ ነገር ስም ከነተጎታቹ ማንዘላዘል ውዴታ ነው ጥላቻ? ብዬ አስባለሁ።'ባንቺ ወግአገኘሁ'የእኔ ስም የኔ መጠርያ ሳይሆን የወላጆቼ ታሪክ ነው ያለፈ ታሪካቸውን የውልደቴ ፈንጠዝያቸውን፣ ምን አልባትም የሰፈር ሰው 'ሴት ልጅ ፍለጋ ደርዘን ወንድ ታቅፋ ሽሙጥ የተቀባበላቸውን ስላቅ የመልስ ምት! ምን አለፋችሁ ያደለው 'የህይወቴ እርምጃ ከአፍ እስከገደፉ' እያለ መፅሐፍ ይፅፋል የኔ ቤተሰቦች የህይወት ታሪካቸውን ለዓመታት እንዲነበብ በኔ ስም በደማቁ ፅፈውታል።የሚጠራኝ ሁሉ ያነብላቸዋል።

እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል።ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ።ከሰመሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን ዕድል አይሰጡህም ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረብያ ይስላሉ።ልብህን ከከፈትክላቸው የድርሻቸውን ጠርበዉህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።በእርግጥ በአንድ ነገር እስማማለው። እሳት ሳይኖር ጭስ የለም።እሳት ባህሪዬን ከሚያንቀለቅሉት እና ከሚያሰሙኝ ምክንያቶች አንዱ የቢኒያም አይነት ወንዶች ናቸው። የማልቋቋመው 'ወንዳም ውበት' ያላቸው ወንዶች!! ወንዳዊ ውበት የምለው የሰፋ ደረትና ትከሻ ወይም የጎላ አይንና ሰልካካ አፍንጫ አልያም ረጅም ቁመና አይነት የአካል ውቅረቶች አይደሉም።የሆነ እንቅስቃሲያቸው አስተያየታቸው የከንፈር እንቅስቃሲያቸው፣ አስተያየታቸው፣አረማመዳቸው፣የድምፃየው ምት፣አሳሳቃቃቸው፣ ወዘተ ተረፈ....ሽፍደት ያለበት አይነት ጥቂት ወንዶች አሉ። ቢኒ የውሸት ባሌ የዲጉ(ዳግማዊ) ታናሽ ወንድም ከጥቂቶቹ ነው። ገና የወንድሙን ሚስት ሲተዋወቀኝ ነበር።

"ኖ.....ኖ.....ባንቺ አትባልጊ" ያልኩት ለራሴ

በነገራችሁ ላይ ቤተሰቡ በቁልምጫ የመጠራራት ክፉኛ ጥንወት የተጠናወተው ነው። ዳግማዊ-ዲጉ፣ ቅድስት-ኪዱ፣ ቢኒያም-ቢኒ.....እናትየውን ዲጉ 'እናቴ' እያለ ነው የሚጠራቸው፣
ኪዱ 'እታባ' ቢኒ 'እማዬ' ፣ ቹቹ እና የሰፈር ሰው 'አዳዳ'. ...አሁን በናታችሁ ባንቺ ወግ አየሁ ሲቆላጰስ 'ቤች',ይሆናል?....የገረመኝ ሌላ ቁልመጫ የዲጉ ጓደኛ ስም ነው። ስሙ አበጀ ነው።ሲጠሩት 'አጄ' ብለውት እርፍ!!

"የክለብ አመልሽን አልነገርኩትም። ለሶስት ሳምንት ጨዋ መሆን መቼም አያቅትሽም ።" አለችኝ ቹቹ አዳ ከቤተሰቡ ጋር አቀባበል የተደረገልን እለት ማታ ወደ ጆሮዬ ቸጠግታ።

ታውቃለች።የሚያውቁኝ ያውቃሉ። ትንሽዬ ልብ ናት ያለችኝ።ቶሎ የምትግል ቶሎ የምትበርድ። በትንሽዬ ደስታ ምቃ ከደረቴ ልታመልጥ ትፈነጥዛለች። በሚጢጢዬ ሀዘን በረዳ በደረቴ ውስጥ ሟሽሻ ትጠፋለች።ጥሎብኝ በግራ ወይም በቀኝ ጠርዝ የመንጠለጠል ልክፍት ከጥግ እያላተመኝ መካከለኛ አመለካከት ሀጥያት ይመስለኛል። ስለእውነቱ ይሄ የኔ ብቻ ችግር መሆኑን እጠረጥራለሁ።አብዛኞቻችን የተጠረቅንባቸው ጎራዎች ሁለት ፅንፍ ይመስሉኛል። መካከለኛ የሚባል ነገር የማናውቅ እንበዛለን።ወዳጅ ወይም ጠላት፣ህይወት ወይም ሞት፣ መልካም ወይም ክፉ፣ ደጋፊ ወይም ተቃዋሚ....

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሁለቱም ጠርዞች ስላተም፣ ስፈነጥዝም ሳዝንም የሚያበርደኝ ሁካታ ሆኗል።በሁለቱም ዋልታ ስናኝ ከሰው ጋር ማውራት ደስ አይለኝም ። የማደርገው እንደዚህ ነው በፊት በፊት በፀጥታ ረዥም መንገድ በእግሬ መጓዝ በመጠኑ የሚያበርደኝ መድሃኒቴ ነበር።አሁን ግን አብዛኛው እንዲህ ባሉ ቀኖቼ ለዳንኪራ የሚመቸኝን ልብስና ጫማ አደርጋለሁ ፣ ብቻዬን ክለብ እሄዳለው፣ አካሌ ዝሎ እስኪብረከረክ እጨፍራለሁ። ካለማጋነን አይኖችና ቀልቦች የምይዝ ጎበዝ ደናሽ ነኝ። በእንቅስቃሴዬ ስልት በሰውነቴ ላይ የሚደንሱ አይኖች እና ትከሻዬ ላይ ተቆልለው የሚከብዱኝ ቀልቦች ለሁካታው የሰጠሁትን ትኩረት
2👍2😁1
እንዳይሸራርፉብኝ

ተኪላ እጠጣለሁ ያኔ በራሴ እና ከራሴ ጋር ብቻ ነኝ በእርግጥ በእንዲህ ያለ ቀናት መጨረሻዬ ከሆነ ወንድ ጎን ይሆናል።ከሆነ ሰው ጎን መሆኑንና ከሆነ ሰው ጋር መሆን ይለያያል እኮ! በአካል ብቻ አብሮ መሆንና በሁለተና አብሮ የመሆን ነው ልዩነቱ።ከማንም ወንድ ጋር ሆኜ አላውቅም።ከወንዶች ጎን ግን ስሻጥ ኖሪያለሁ።ከየት ያመጣሁት ፈሊጥ እንደሆነ አላውቅም ነጭ ሸሚዝ የሚለብስ ወንድ በራሱ የሚተማመን የሆነ ከጀግንነት ጋር የሚነካካ ነገር ያለው ይመስለኛል።ብታምኑም ባታምኑም ከስንት አንዱ ካልሆነ በቀር የአዲስ አበባ ወንድ ነጭ ሸሚዝ አይለብስም በእርግጥ አንዳንዱ በአቧራ የጠየመ ለነጭ የቀረበ ለብሶ ብቅ ይላል።ሌላኛው ምንጩን የማላውቀው ፈሊጤ ዳንስና ወሲብ ይመሳሰሉብኛል።ጎበዝ የሚደንስ ወንድ የዳንሱ ወለል ላይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አልጋ ላይ እንዳስበዉ እሆናለው።በሰዎች መሃከል በሁካታ ታጅቤ እየተወዛወዝኩ መሆኑ ይረሳኝና የእጁ ንኪኪና የአካሉ እንቅስቃሴ ሁሉ ከሙዚቃው ይልቅ ማቃሰት ያጀበው የራሴ ስሜት ውስጥ ይወረውረኛል በዳንኪራው ወለል ላይ ከሁለት አንዱን ያሟላ ወንድ ሳገኝ አብሬው እደንሳለው።በእንዲህ ያሉ ዉሱን ቀኖቼ ጭፈራ ፣ ተኪላ እና ባለነጭ ሸሚዝ ወይም ጎበዝ ደናሽ ወንድ አንደኛው ከአንዳቸው የማይነጣጠሉ የምሽቱ አካሎች ናቸው።ቹቹ 'የክለብ አመልሽ' የምትለኝ እንደነዚህ ያሉ ቀናቶቼን ስታስታውሰኝ ነው።

ዳግማዊን የውሸት ካገባሁት በኋላ ምንም እንኳን የቤኒን ስበት መቋቋም ቢከብደኝም ከነአመሎቼ የዳግማዊ ሚስት ሆኜ መተወኑን መወጣት ጀመርኩ። ቹቹም ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ። 🙏
👍2
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ(🔞)


#የዊንታ_ማንነት

ቦሌና አካባቢዋን የዊንታን ያህል የምታውቅ ሴት መኖሯን እጠራጠራለሁ። የቦሌ ዙርያን የሌሊት ጉድ እንደ ዊንታ የበረበረ ሰው መኖሩንም እንጃ! ለነገሩ ዊንታን የማታውቅ የዚያ አካባቢ ሸሌ አትገኝም።የአካባቢው ስትሪቶች፣ ኮድ ሶስቶች፣ የክለብና የቡና ቤት ሸሌዎች ጥሎባቸው ዊንታን አይወዷትም፣
ገና ሰፈሩን ስትረግጥ በአይናቸው ቂጥ ነው የሚመለከቷት። ለምን ቢባል ዊንታ እንደነሱ ታጥባ፣ታጥናና፣ ተኳኩላ በሸሌ ደንብ ለብሳ በየሌሊቱ ቢመለከቷትም ከወንድ ጋ ስትሄድ አየናት የምትል ሴት
ግን የለችም። ዝም ብላ በዙሪያቸው ታንዣብባለች። ሌሊቱን ሙሉ ቦሌና ዙሪያውን ታካልለዋለች።የቦሌ መድሃኒአለምና የቦሌ አትላስ ባለመኪኖች መኪናቸውን አቁመው ወይም መኪናቸው ውስጥ አስገብተው ያነጋግሯታል፣ ዋጋ ትደራደራለች፤ ግን ከባለመኪኖቹ ጋ አንድም ቀን ስትሄድ አትታይም።

የቦሌና ዙሪያው ውድ ክለቦች፣ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች ውስጥ ገብታ የፈለገችውን ትጠጣለች፣ በወንዶች ትጋበዛለች፣ ከወንዶችና ከሴቶች ጋ እየተጫወተች አልኮል ትጠጣለች ግን ከግብዣው በኋላ ከማንም ወንድ ጋ ስትሄድ አትታይም። “ከዊንታ ጋ አንሶላ ተጋፍፌያለሁ” የሚል ወንድ በቦሌ ዙሪያ ተሰምቶ አይታወቅም። ይህ ጠባይዋ ለአካባቢው ሸሌዎች ውል አልባ እንቆቅልሽ ሆኗል። በዚህ ሁኔታዋ ግራ የተጋቡት ሸሌዎች ብዙ ነገር ያወሩባታል። ኤሚ በአንድ ወቅት ስለ ዊንታ ሳነሳባት ግንፍል ብሏት እንዲህ ብላኛለች፤

“ባክሽ እሷ ቢዝነስ የምትሰራ ሸሌ አይደለችም፤ እንደ ሸሌ አክት የምታደርግ የመንግስት ጆሮ ጠቢ ነች፤
መልክና ቁመና ሳያንሳት ቢዝነስ የማትሰራበት ሌላ ምን ምክንያት ይኖራታል ብለሽ ነው?እንደነ ኤልሳ
እኛንም እንዳታስቆጥረን ነው የምፈራው."

መሲን ደግሞ በአንድ ወቅት እየጠጣን የድሮ ጓደኞቻችን እያነሳን ስንጥል ስለ ዊንታ የሚገርም ነገር ነገረችኝ"
ሮዝ ሙች እየቃዠሁ አይደለም፤ የሰከርኩ ከመሰለሽም ተሳስተሻል። ከዋናዎቹ ሰዎች ጋ እሌኒን ስብሰባ ስትቀመጥ ሀገዞም አይቷት ነግሮኛል እኮ ነው የምልሽ፤ እኔ በጭራሽ ዊንታ ጆሮ ጠቢ
ስለመሆኗ ተጠራጥሬ ሁሉ አላውቅም። እንዴ ቆይ አንቺ ስታስቢው በሳምንት አንድ እንኳ ቢዝነስ ሳትሰራ እያደረች እንዴት ነው እንደዚያ እየተጫጫሰች፣ እየዘነጠች ልትኖር የምትችለው…። መሲን
ጥርጣሬዋን ሳጣጥልባት ሀገዞምን ስታገኘው ስለዊንታ በደንብ እንደምታውጣጣውና እንደምትነግረኝ ቃል ገባችልኝ።ሀገዞም የዊንታ የረጅም ጊዜ ደንበኛዋ ነው።እሷም "ባሌ" እያለች ነው የምትጠራ።መርማሪ ፖሊስ ሲሆን ሌሎች ግልፅ ያልሆኑ የደህንነት ስራዎቹንም ይሰራል ብላኛለች።

እኔ በበኩሌ መሲም ኤሚም ያሉትን ነገር ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ከብዶኛል። በርግጥ የህውሃት ታጋዮች ድሮ በትግል ወቅት እብድ፣ ለማኝና ዘበኛ ሆነው ደርግን ይሰልሉት እንደነበረ ርእሱን ከማላስታውሰው መፅሀፍ ላይ አንብቤ አውቃለሁ።በዚህ ሰላማዊ ዘመን ግን ሸሌ ጆሮ ጠቢ በየአስፋልቱ እያቆሙ የሚሰልሉ አልመስልሽ አለኝ።

ለምን እንደሆነ አላውቅም ነገሩን አጥርቼ ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት አላስቆም አላስቀምጥ አለኝ። ያን ሰሞን ደግሞ አጋጣሚ ሆኖ በሄርሜላ የልደት በዓል ላይ ዊንታ ተጋብዛ አላገኛትም! ነገሩን እንዴት ላነሳባት እንምችል ግን አልገለጥልሽ አለኝ። ቆይተን ጨዋታው እየደመቀ…ከመጠጡ እየደጋገምንለት
ስንሄድ ሁላችንም ሞቅታ ዉስጥ ገባን። ፈጠን ብዬ ከዊንታ ጎን ተቀመጥኩና ወሬ ጀመርኩ።

“ዊንታ ግን የውነት ጠፍተሻል፣ ደግሞ ባለስልጣን ሆናለች እያሉ እያስወሩብሽ ነው አልኳት።ስቃ ምንም መልስ ሳትሰጠኝ ሌላ ሌላ ወሬ መዘባረቅ ጀመረች። አንቺ በቃ ሁልጊዜ እንዳማረብሽ
ሮዚ ምንድነው ግን ምስጢሩ?…ብላ አሳሳቀችኝ። ወሬ ለመቀየር ያደረገቸው ጥረት ይበልጥ ጥርጣሬ ቢፈጥርብኝም ከዚህ በኋላ ነገሩን ማንሳት ለራሴም አደጋ እንዳለው ሰግቼ ተውኩት።

የሚገርመው ግን ስለ ዊንታ ነገሩ ሁሉ የተዳፈነ መስሎኝ በሌላ ጫወታ ዉስጥ ተዘፍቄ እያለሁ በራሷ ጊዜ ክፍለ-ከተማው በ”ኮምዩኒቲ ፖሊሲንግ” መልምሏት ከማህበረሰብ ደህንነት አጠባበቅ ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በተለያየ ጊዜ መውሰዷን ነገረችኝ። እኔም ይህን ስልጠና መውሰድ
ከፈለኩ ልታገናኘኝ እንደምትችል ገለጸችልኝ። ይህን ጊዜ ጥርጣሬዬ ከፍ አለ። ማን ያውቃል?
Community policing የምትለዋን ነገር ያመጣቻት ሆን ብላ የሚወራባትን አሉባልታዎች እውነትነት ለማለዘብ ብላ ቢሆንስ? በዚያ ላይ ቅድም "ባለስልጣን ሆነሻል አሉ” ብዬ ሸንቆጥ ስላረኳት ለዚያ
ምላሽ እንዲሆን የፈጠረቻት ብልሃት ልትሆን እንደምትችል ጠረጠርኩ።

ከዊንታ ጋር ከሄርሜላ ልደት ምሽት የነበረንን ቆይታ ጨምሮ ነገሮችን በስክነት ለማያያዝ ስሞከር በሷ ዙሪያ የሚወሩት ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ እውነት ባይሆኑም መነሻ እውነት እንዳላቸው ተረዳሁ።

ከስንት ጊዜ በኋላ ደግሞ ለምን መሲ ጮማ ጮማ መረጃ ይዛ አትመጣም። ሀገዞም በስካር መንፈስ ሆኖ ብዙ ነገር ዘባርቆላታል ለካ። መሲ እንደምትለው ከሆነ ሀገዞም ዊንታን በጣም ነው የሚጠላት።ምክንያቱም ከዚህ በፊት ለሴክስ ጠይቋት እስኪ መጀመርያ እከከህን አራግፍ” ብላዋለች።ይሄን በራሱ
አንደበት ነው የነገረኝ አለችኝ። መሲ ከሀገዞም የሰበሰበችው ወሬ ለማመን የሚከብድና ከጠበቅኩት በላይ ዝርዝር ነገር ሆኖ አገኘሁት። አንዳንዶቹ ነገሮች እሱን ራሱ የሚያስጠይቁትና በፍጹም ለመሲ መናገር የሌለበት አይነት ነበሩ። ምናልባት በዊንታ ላይ ቂም መያዙ ምን መደበቅና ምን መናገር እንዳለበት እንኳ እንዳያውቅ ሳይጋርደው አልቀረም።

መሲ ከሀገዞም የሰማችውን ተስገብግባ እንዲህ ተረከችልኝ።

ሀገዞም እንደነገረኝ ዊንታ የመጀመሪያ ተልእኮዋ በ'ክለብ ኤግዞቲካ” ተገኝታ ከጠጪዎቹ መሀል በመገኘት የእጽ ዝውውርን፣ የውጭ ምንዛሪንና ሰዶማውያንን የተመለከቱ መረጃዎችን መሰብሰብ ነበር። ለከለብ ኤግዞቲካ ባለቤቶች ለደህንነት ስጋት የሆኑ ወንጀለኞች በአካባቢው እንዳሉና ለሚልኳት መረጃ ሰብሳቢ ሴት አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርጉላትና ሽፋን እንዲሰጧት አስቀድሞ ተነግሯቸዋል። መረጃ ሰብሳቢ የተባለችው ዊንታ መሆኗ ነው። ለነገሩ ባለቤቱቹ የታጋይ ቤተሰብ ልጆች ስለሆኑ ሁልጊዜም ተባባሪዎች ናቸው ብሎኛል።

“በዚህም መሰረት ዊንታ በክለቡ ውስጥ በአልኮል የናወዘች ሴት መስላ የውጭ ምንዛሪ አቅራቢዎቹ፣ሰዶማውያኑና እጽ አዘዋዋሪዎቹ ቦታ እየጠቀሱ ሲቀጣጠሩ ትሰልላለች። አለቆቿ የሰጧት ሁለተኛው
ተልእኮ ደግሞ በግራንድ ሌከሰስ” ሆቴል ባር ውስጥ እየተዝናና የሚገኘውን ስመ-ጥር ዲያስፖራ ተቃዋሚ ፖለቲከኛን መከታተል ነበር። ፖለቲከኛው ሞቅ ብሎት ሲደንስ አብራው ከደነሰች በኋላ
ረጅም ሰአት አልኮል እየጠጡ ሲዝናኑ ነበር። ዲያስፖራው የአዲሳባ የቤት ልጅ የጠበሰ መስሎት በሱ ቤት በደስታ ሊሞት ደርሶ ነበር» ብሎኛል ሀገዞም።_ያረፈበት ሆቴል አልጋ ድረስ አብራው በመሄድም አለቆቿ ስለፖለቲከኛውና የግንኙነት መረቦቹ የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃዎች እስከ ጥግ አቀብላቸዋለች

መሲ እንደምትለው ከሆን ዊንታ ከወንድ ጋር መኝታ ከፍል ድረስ ዘልቃ አንሶላ የምትጋፈፈው በእንደዚህ አይነት ልዩና ከባድ ተልእኮ ውቅት ብቻ ነው፡፡ ሀገዞም ለመሲ ከነገራት ተጨማሪ መረጃ እንደገባኝ ከሆነ ዊንታ ጀማሪ ጆሮ ጠቢ ሳትሆን አትቀርም።

መሲ ለባሏ ሀገዞም ይህን ስራ ዊንታ እንዴት እንደጀመረቸው ጠይቃው ነበር። ነገሩ ባልተጠበቀ ሁኔታና በአጋጣሚ እንደሆነ ነግሯታል።

" ከዚህ ቀደም ከእንድ መካከለኛው ምስራቅ ዉስጥ ከሚንቀሳቀስ አሸባሪ ቡ
ድን ጋር ግንኙነት እንዳለው ከምንጠረጥረው የመናዊ ባለሀብት ጋር ስትዝናና በኛ ሰዎች ታየች። ሰውየው ለክትትል እጅግ አስፈላጊ ነበር። በወቅቱ እሱን ለመቅረብ አብራው ከምትዝናናዋ ኢትዮጵያዊት ሴት የተሻለ ሰው
አልነበረም። ቶሎ እሷን ለዚሁ ስራ የማሳመንና በፍጥነት አሰልጥኖ ማሰማራት የግድ ሆነ፡፡ መጀመርያ
አመነታች። ሀገራዊ ግዴታዋ እንደሆነና ይህንን ግዴታዋን ቸል ማለት እንደማትችል ጠንከር ያለ ትዕዛዝ
ሲሰጣት ግን ለመተባበር ፈቃደኛ ሆነች። በወቅቱ ከየመናዊው ያገኘቻቸው ቁልፍ መረጃዎች መስሪያ ቤቱን ስላስደሰቱ ጠቀም ያለ ገንዘብ እየተሰጣት ተመሳሳይ የክትትል ተልእኮዎችን በተደራቢነት
እንድታካሄድ ተደረገ። አስፈላጊነቷ ሲያበቃ ትወገዳለች በሚል ነበር አጀማመሯ። ሆኖም በሷ በኩል የሚገኙ መረጃዎች እየበዙ ስለመጡ...."

#እሌኒ_ሌባ

መሲ ከሀገዞም የምታገኛቸውን ጮማ ጮማ ወሬዎች መስማት ሱስ እየሆነብኝ መጣ። ስለዚህ እሷን ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ሳላገኛት መዋል እየከበደኝ መጣ። መሲ ደግሞ ጥሎባት ትወደኛለች
መሰለኝ በቀን በቀን ብንገናኝ እንኳን ደስታውን አትችለውም። ስለዊንታ ማንነት እስክጠግብ ከነገረችኝ በኋላ ሌላ ጮማ ወሬ ከሀገዞም እንዳገኘች በስልክ ነገረችኝ። እሁድ የተለመደችው ሺሻ ቤት ተገናኘን።
በየሳምንቱ እንደምናደርገው አንድ የሺሻ ከፍል በ350 ብር ለግማሽ ቀን ተከራይተን ወጋችንን ከሺሻው ጋር ማንቦልቦል ጀመርን።

አዲሱ ጮማ ወሬ ቀድሞ አብራን “ኩል ክለብ ትሰራ ስለነበረችውና ከአምታት በፊት አብራው ካደረችወሸ ህንዳዊ ደምበኛዋ ብዙ ሺ ዶላር ይዛበት ጠፍታ በኋላም ታስራ ስለተፈታችው እሌኒ ነበር።

እሌኒን ካገኘኋት አመታት ቢቆጠሩም ከዚያ ሚስኪን ህንድ ዶላር ዘርፋ ታሰረች ከተባለ በኋላ እሷን ለማግኘት ምንም ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ ጥቂት ሴተኛ አዳሪ ጓደኞቼ እንዲህ አይነት ስርቆት ዉስጥ
ተሳትፈው አጋጥሞኛል። ፊታቸውን ማየት ነው የሚያስጠላኝ። ለምን እንደሆነ አላውቅም የምትሰርቅ ሴት በጣም ታስጠላኛለች። ወንድ ሲሰርቅ ያን ያህል የምጠላው አይመስለኝም። እኔንጃ ብቻ ሴት ላይ ያስጠላል። ደግነቱ ብዙ ሴቶች ስንትና ስንት ሺ ዶላር ደምበኛቸው ረስቶ ሄዶ በታማኝነት የመለሱ አውቃለሁ። ለምሳሌ ፎዚያ። አቤት ያንቀን ዜጋው እንዴት እንደተደነቀ። ለታማኝነቷ አንድሺ አምስት መቶ ዶላር በጉርሻ መልክ ሰጥቷት አንድ ወር ሙሉ ስትጋብዘን..ስትጋብዘን ብሩ አላልቅ አላት።ፎዜ ደግ።

ፎዚን የመሰሉ ጓደኞቼን ሳስብ ደግሞ እኮራለሁ። ብቻ እንዴትም ቢሆን የምትሰርቅን ሴት እንደማየት የሚያርገፈግፈኝ ነገር የለም። እሌኒ እንደዚያ ጓደኛችን እንዳልነበረች ለገንዘብ ብላ ስርቆት ዉስጥ መግባቷን ስሰማ በቃ ጠላኋት ጠላኋት። እነ ቤሪ ተመላልሰው እስር ቤት ሲጠይቋት እንኳ አንድ
ቀን ሄጄ ሳልጠይቃት ነው ተፈታች የተባለው፡፡ አሁን ደግሞ መሲ ስለሷ ምን ልትነግረኝ ይሆን ብዬ ተንሰፍስፌያለሁ።

እሌኒ ከእስር በኋላ ባለመኪናም የጎዳና ላይ እግረኛ ሸሌም መሆኗን ሰምተሻል” መሲ ያለቸው ነገር ብዙም አልገባኝም። በጥያቄ አዋከብኳት።

ሀግዞም ለመሲ እንደነገራት ከሆነ ዋናው የእሌኒ የወንጀል ስራ ከሁለት ፖሊሶች ጋር በመመሳጠር የተፈጸመ ነው። እንዲያውም እሌኒን ፖሊሶቹ ናቸው የመለመሏት፡፡

እሌኒ ከዚያ ምስኪን ህንዳዊ ብር ሰርቃ ቃሊት ታስራ አልነበር? ያኔ እስር ቤት የምታውቃቸው ፖሊሶች ናቸው ነገሩን ሁሉ ያመቻቹት”

ቆይ ግን እሌኒ ሁለቱ ፖሊሶች ያቀረቡላትን ጥያቄ እንዴት ተቀበለች? ያን ሁሉ አመት ታስራ ወጥታ…”

“ሮዝ! ኢሉን ከኔ በተሻለ የምታውቂያት ይመስለኝ ነበር፤ እሷ እኮ ለገንዘብ ስትል እናቷን ከመሸጥ እንኳ የማትመለስ መሬ ናት አለች መሲ ግንባሯን ከስክሳ ኢሉን በመጠየፍ።

መሲ ብታምኚም ባታምኒኝም እሌኒን ካገኘኋት ብዙ አመት ሆኖናል። ከታሰረች በኋላ ትኑር ትሙት አላውቅም ነበር። ታስራም አልጠየቅኳትም። ሌባ እንደሆነች ሳውቅ በቃ ምን ልበልሽ አቅለሸለሸችኝ።

"I know...ቀላል ታቅለሸልሻለች!"

ሀገዞም የቅርብ ክትትል ዉስጥ ያለቸው የድሮ ወዳጃችን እሌኒ ከሁለት ፖሊሶት ጋር በመጣመር አትላስ አካባቢ የምትፈጽመው ወንጀል መሲ ዘርዘር አድርጋ ተረከችልኝ። አሁን አሁን እንደባሏ በምትቆጥረው ለረጅም ጊዜ ደንበኛዋና አባዲናዋ የነበረው ሀገዞም በእሌሊ ወንጀል ጉዳይ ሳይነግራት የቀረ መረጃ ያለ አይመስለኝም።ሁሉንም ዘክዝኮላታል።

“ሮዚ ነገሩ ምን መሰለሽ እሌኒ ወንጀሉን የምትፈጽመው ከሁለቱ ፖሊሶች ጋ በሽርከና ነው። ማታ ሚኒዋን ለብሳ ሂል ጫማ አድርጋ አትላስ ጋ ትቆማለች። ለቢዝነስ፤ ባለመኪና ፍለጋ። ይሄኔ ሁለቱ
ፖሊሶች ራቅ ሰወር ብለው ይከታተሏታል ልክ መኪና ሲቆምላት ዉስጥ ሳትገባ ዋጋ መደራደር ትጀምራለች። ባለመኪናዎቹ በሚያቀርቡላት ዋጋ ለመውጣት ትስማማለች። ሆኖም ቅድሚያ ገንዘብ
ትቀበላቸዋለች። ሴክስ የምትፈጽመው ሆቴል ሳይሆን መኪና ውስጥ ብቻ እንደሆነ አስቀድማ ታስገነዝባቸዋለች። ከዚያ ከሚወስዳት ባለመኪና ደምበኛዋ ጋ አትላስ ውስጣ ውስጥ ከሚገኙት
መንገዶች በአንዱ እየጠቆመች ስወር ካለው ስፍራ መኪናውን እንዲያቆም ታደርገዋለች። እሷ መኪና ውስጥ ሆና ወሲብ ስትፈጽም ከፖሊሶቹ አንዱ በሴት ድምጽ ይደውላል። እሌኒ ለ"ሴት ደዋይዋ ያለችበትን ተናግራ አሁን ቢዝነስ ላይ እንደሆነች ጨርሳ ቶሎ እንደምትመለስ በመንገር ወደጀመረችው የመኪና ውስጥ ሴክስ ትመለሳለች። ከዚያም ሁለት ፖሊሶች ቦታው ላይ ከች ይላሉ። ጎዳዩ
ላይ የመኪና ውስጥ ወሲብ መፈፀም ወንጀል መሆኑን ገልፀው ባለመኪናውን ወደ እስር ቤት እንደሚወስዱት ይነግሩታል፤ ባለመኪናው በተለይ እጁ ላይ የትዳር ቀለበት ካለ በውስልትና ለረጅም ጊዜ እንደሚታሰር ጭምር
ይነግሩታል። “በጎዳና ላይ የመኪና ውስጥ ወሲብ ሲፈጽም ታስረ” የሚለውን ውርደት የማይፈልገው ባለመኪና ከዚህ ከፍተኛ ቅሌት ለመውጣት መላ ሲዘይድ እሌኒ የዋህ መስላ በገንዘብ እንዲደራደር ሹክ ትለዋለች። ምንም ጥርጥር የለውም ባለመኪናው ከሁለቱ ፖሊሶች ጋር ድርድር ይጀምራል። ሀገዞም እንደነገረኝ ፖሊሶቹ ከባለመኪናዎቹ ከ5 እስከ 20 ሺህ ብር ሲቀበሉ ኖረዋል። የተቀበሎትን ገንዘብ ኋላ ላይ ለይምሰል አንቺ ወደ ጣቢያ ቀጥይ.” ብለው ከሚያዋከቧት እሌኒ ጋር ይካፈላሉ።

የሁለቱ ፖሊሶች ሰለባ የሆኑ ባለመኪኖች በተለያየ ጊዜ ስማቸውንና ማንነታቸውን ደብቀው የደረሰባቸውን በዝርዝር ለፖሊስ ጣቢያዎች በስልክ ሪፖርት በማድረጋቸው ነበር እነ ሀገዞም እሌኒ ላይ ክትትል የጀመሩት።

እሌሊ የሰዶም መንገድ

ከዚህ ወንጀል በኋላ እሌኒ አልተያዘችም። ይበልጥ ክትትሉ ተጧጧፈባት እንጂ። ክትትሉ ሲጧጧፍ ሌላ ያልተጠበቀ ጉድ ተገኘ። ኢሉ ባለመኪና የሆነችበትን መንገድ መሲ በታላቅ ስሜት አወራችልኝ።

“ቆይ ግን ቡሽቲዎች እሌኒን እንዴት መለመሏት?”

መሲ ፊቷን ቅጭም አደረገች፣

“ሮዝ፣ እሱን እኔም አልደረስኩበትም። ሀገዞም እንደሚለው ገና መረጃዎችን ሰብስበው አልጨረሰም።
ሰማያዊዎ ቪቲዝ ቶዮታ መኪና ግን የሷ እንዳልሆነች ደርሰውበታል”

“ታዲያ የማን ናት”

“ክለብ ኤግዞቲካን ከሚያዘወትሩት ሰዶማውያን የምስጢራዊ ማኅበራቸው የተበረከተች ነች።
ለካስ ቡሽቲዎቹ በድብቅ ማኅበር አላቸው። የሚደርሱባቸውን መገለሎች ተደራጅተው ለመታገልና እርስ በርስ ለመጋባት ይጠቀሙበታል። ዉጭ አገር ሲሰደዱ ደግሞ የጥገኝነት ጥያቄ ለማግኘት የዚህ ምስጢራዊ ማኅበር አባል መሆንና የድጋፍ ደብዳቤ ማግኘት ያስፈልጋል። ዉጭ አገር ብዙ አበሾች
ቡሽቲ ሳይሆኑ ቡሽቲ በመሆናችን ከአገር እንደተሰደዱ አድርገው በማውራት በዉ
👍5
ሸት

ጥገኝነት ያገኙ ነበር። አሁን ግን ያ ቀርቷል። ማኅበራቸው ነው የሚመሰክርላቸው። እና እሌኒ መኪናው የተሰጣት ከዚህ ማኅበር ነው። የመኪናዋ ቀለም ራሱ የቀስተደመና አይነት ናት። ለቡሽቲዎቹ ወንዶችን አማልላ በየቀኑ
እንድታመጣላቸው ይቺን መኪና አውሰዋታል። ለአገልግሎቷ ወፈር ያለ ክፍያ እንደሚፈጽሙላት

መረጃ አግኝተናል ነው ያለኝ ሀገዞም..."

እነኑ ደግሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል እስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን

መሲ እውነቷን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የጠቀሰቸወም ክለብ ዉስጥ ሰዶሞች እንደሚበዙ አውቃለሁ።እነሱ ደሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል አስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን ጨምረው በማደንዘዝ ብዙ ወንድ ማጥመድ አይችሉም። ሁል ጊዜ በዚህ መንገድ የሚወስዷቸውን ሰለባዎች አያገኙም።እሌኒ ግን በሴትነቷ ተጠቅማና አማልላ በየቀኑ እነሱ ካሉበት ቤት ድረስ ለዚህ ተግባር በሰጧት መኪና ታቀርብላቸዋለች። መሲ እንደምትለው እሌኒ መኪና ይዛ ሲያዩ ወንዶች
በፍጹም አይጠረጥሯትም። ወንድ የጠማት ሀብታም ሴት ትመስላቸውና ሰተት ብለው ይገቡላታል። ይህንን በመረዳት ነው ቡሽቲዎቹ መኪና በሚስጢር ማሀበራቸው ስም ገዝተው በውሰት የሰጧት።

እሌኒን አምርሬ ጠላኋት። የሆነ ወቅት ላይ ከዚህች የሰይጣን ቁራጭ ጋር አብሬ መስራቴን ሳስብ ዘገነነችኝ። ሰው ሲባል ግን እንዴት አይነት ጨካኝ ፍጡር እንደሆነ….አሁን እሌኒ እዚህ ሁሉ ልቦለድ የሚመስል ወንጀል ውስጥ ትገባለች ብሎ ማን ያምናል?

መሲን ጠየኳት።ቆይ ግን ባልሽ ሀገዞም ይህን ሁሉ እያወቀ ለምንድን ነው እርምጃ የማይወስድባት?

“ሮዝ! እኔም ጠይቄው ነበር፤ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? መጀመርያ ሳቀብኝና…የዋህ ስለሆንሽ እኮ
ነው የምወድሽ ብሎ ከንፈሬን ከነከሰኝ በኋላ «ወንጀል ክትትል ዉስጥ አንድን ተጠርጣሪ አንድ ወንጀል ስለፈፀመ ብቻ ተንደርድሮ መያዝ ብዙ ዱካዎችን እንደማጥፋት ይቆጠራል እንደምታስቢውም ቀላል አደለም እዚህ ድርጅት ውስጥ ከተራ ሰው ጀምሮ ትላልቅ ባለስልጣናት አጅ አለበት በየቲቪው በከረባት ታንቆ የምናየው ባለስልጣን የማታ ማታ መዳርያቸው ነው አንድም ቡሽቲነትን ከሚያስፋፉት ሰዎች እነሱ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ እንጂማ እሌኒን ገና ድሮ ከሁለቱ ከፖሊሶች ጋር የምትፈጽመውን ወንጀል እንደደረስንበት በቁጥጥር ስር አውለናት ቢሆን ኖሮ
ከሰዶማዊያኑ ጋር ስለነበራት ግንኙነት ምንም ማወቅ አንችልም ነበር። አሁንም በሷ ላይ ለጥቂት ወራት ክትትሉ ይቀጥላል። ጊዜው ሲደርስ እሌኒም፣ ሁለቱ ፖሊሶችም፣ የምታገለግላቸው ሰዶማውያኑም ከነማኅበራቸው ተለቃቅመው እስር ቤት ይገባሉ፤ ባለቀስተደመናዋ ቶዮታ ቪትዝም ለመንግስት ገቢ ትደረጋለች።››

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍41
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ_2 ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ(🔞) ፡ ፡ #የዊንታ_ማንነት ቦሌና አካባቢዋን የዊንታን ያህል የምታውቅ ሴት መኖሯን እጠራጠራለሁ። የቦሌ ዙርያን የሌሊት ጉድ እንደ ዊንታ የበረበረ ሰው መኖሩንም እንጃ! ለነገሩ ዊንታን የማታውቅ የዚያ አካባቢ ሸሌ አትገኝም።የአካባቢው ስትሪቶች፣ ኮድ ሶስቶች፣ የክለብና የቡና ቤት ሸሌዎች ጥሎባቸው ዊንታን አይወዷትም፣ ገና ሰፈሩን ስትረግጥ በአይናቸው ቂጥ ነው የሚመለከቷት።…»
#ደርሶኛል

ጠርተሽ ባታቀምሽኝ
ደርሶኝ አጣጣምኩት
የዳቦሽን ጣእም
በጠላሽ አወኩት።
"ውረድ ወይ ፍረድ"

ይሉታል እግዜርን ልባቸው ሲቆስል፤
ቢወርድ ፊቱ ቆመው_የሚያዩት ይመስል፤
ቢፈርድ የሚተርፉ ይፀድቁ ይመስል...
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_ሦስት


#በሜሪ_ፈለቀ


.."የአባቴን ገዳይ ገድዬ ነው ከሃገር የተሰደድኩት።" አለኝ ዳግማዊ ምንም የሚያስደነግጥ ነገር እንዳልነገረኝ ሁሉ በመሀከላችን የትራስ ድንበር አበጅተን በምንተኛበት አልጋ ላይ እንደተገደመ።

"ገድዬ ማለት? "

"በገንዘብ ተጣልተው የገዛ ጓደኛው ነው በስለት ወግቶ የገደለው።"

"ከዛስ?"

"ሰውየው እንዴት እንደሆነ ባላወቅነው ሁኔታ በሶስተኛው ወር ተፈታ።"

"ከዚያ በኋላ ያለውን?" አልኩት አስደንጋጩን የወሬ ክፍል 'ገደልኩት' ያለኝን ለማረጋገ። ደምስሩ ተገታተረብኝ። ፊቱ ተቀያየረ። የአሁን ትንግርት የሚነግረኝ ይመስል ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነው የሚያወራው። ሲያወራኝ ተመሳቀልኩ። ስሜቱን ለመረዳት እየሞከርኩ ስሜቴ ተሳከረ። ልክና ስህተት ውሉ ተጣረሰብኝ።

አባቱ ሲገደሉ በአይኑ አይቷቸዋል። በራፋቸው ላይ ነው የተገደሉት። ዳግማዊ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት በሚወስደው ጭር ያለ ቀጭን መንገድ እየገሰገሰ ሰፈር ሲደርስ ከወዳጃቸው ጋር እየተጓዙ አባቱን በርቀት አይቷቸዋል። እንዲያዩት ስላልፈለገ ወደ ኋላ ቀረት ብሎ ከአይናቸው ሰወር አለ። ቤታቸው መግብያ ጋር ሲደርስ የተቃቀፉ መስለው። ብዙም ሳይቆይ ግን አባትየው ወደቁ። ወዳጃቸው አካባቢያቸውን ቃኘት እያደረጉ ከሩጫ ባልተናነሰ ፍጥነት ከዳግማዊ በተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ጀመሩ። ዳግማዊ እየሮጠ አባተቱጋ ሲደርስ ጣር ላይ ነበሩ። ከደረታቸው የሚፈስ ደማቸውንና በእጃቸው ፍራፍሬና የተጠቀለለ ኬክ መያዛቸውን እኩል ቃኘው። የቅድስት አሰራ አምስት ዓመት ልደት በዓሏ ነበር። በጣር ስቃይ ውስጥ ሆነው እጁን ጨብጠው ቤተሰቡን እንዲንከባከብ ለመኑት። ዳግማዊ ገዳያቸውን ከመከተልና አባቱን ከማንሳት የቱ እንደሚቀድም ግራ ገብቶት ዋለለ። በደመ ነፍስ የእናቱን፣ የእህቱን፣ የኸንድሙን፣ የሚያስታውሰውን ሰው ስም ሁሉ በጩህት ተጣራ።

"እናቴ የኔን ጩህት ሰምታ ስትሮጥ ከቤታችን መግቢያ ደረጃ ላይ ወድቃ እግሯ ተሰብሮ ነው ስታነክስ ያየሻት" አለኝ እያንዘፈዘፈው።

ገዳይ የተፈቱት ገና የፍርድ ሂደቱ እንኳን ሳያልቅ ነበር። ይመለከተዋል ላሉት አካል አቤት አሉ። አቤቱታቸው መልስ ከማግኘቱ አስቀድሞ ገዳይ ሀገር መቀየረቻው ተሰማ። ዳግማዊ ተከተላቸው። የአባቱን አገዳደል ተመሳሳዩን አድርጎ ወደ ሱዳን ተሰደደ። ቤተሰቡም የሚኖርበትን የደብረ ማርቆስ ከተማ ጥሎ ናዝሬት ከተማ።

"አንዳንዴ ህይወት ፍትህ አታውቅም። ይሄኔ ፍትህን በራስ እጅ መስጠት! !" አለ ከቀድሞው ተረጋግቶ።

"ለዚህ ነው ቤተሰቦችህ እንደ መሲህ የሚያዩህ? " አልኩት ያልኩት ተገቢ መሆኑ ግራ እያጋባኝ።

አባቱ ከሞቱ በኋላ በአባትየው የእህል ንግድ ይተዳደር የነበረው ቤተሰብ ውጥንቅጡ ወጣ። ዳግማዊ ለአራት አመታት እዚህ ግባ የማይባል ኑሮ ሱዳን አገር አንገላታው። ይሄኔ ቢኒያም ትምህርቱን አቁሞ እህቱንና እናቱን ማስተዳደር ግድ ሆነበት።

"ባንተ ቦታ ሆኜ ስሜቱን አላውቅም። ግን በምንም ሂሳብ ጠፋት በጥፋት ተጣፍቶ መልሱ ልክ አይመጣም።" አልኩት።

"አንዳንድ ጥቃትና መቀማጥሽ በይቅርታና በተፃፈ ህግ እንደማይዳኝ የሚገባሽ ባሏን ለተቀማች እናቱና አባታቸውን ላጡ ታናናሾቹ ብቸኛ ተስፋቸው የሆነ ወንድ ልጅ ሆነሽ ስታይው ነው። አለኝ።

"ሳትገባኝ ቀርተህ አይደለም።" አልኩት ስሜቱን የጎዳሁት መስሎኝ እጄን አሻግሬ እጆቹን እየዳበስኩ።

"እንደማልገባሽ ይገባኛል።" ሲለኝ የሳሎኑ በር ተንኳኳ እና ለመክፈት ተነሳ። ለምን እንደተከተልኩት ሳላውቅ ተከትየው ሳሎን ሄድኩ። ቢኒያም ነው። ተስተካክሎ መቆም እስኪያቅተው ሰክሯል። እናትየው ከመኝታ ቤታቸው ብቅ አሉ። ከመጣን አራተኛ ቀናችን መሆኑ ነው። ከአታካች የአራት ቀን መሰንበት በኋላ ዛሬ ቢኒያም ስላመሸ ሳንተኛ እየጠበቅነው ነበር።

"ደህና አደራችሁ? ማለቴ አመሻችሁ? አለ ሶስታችንንም ተራ በተራ እያየ። ዳግማዊ ተናዷል። እናት ከዝነዋል። እኔ ካለመዋሸት በሁኔታው ሳቄ መጥቷል።

"ደሞ ተጣላችሁ? " አሉ እናቱ።

"አልተጣላንም። ተጣላችኝ" አለ ቢኒያም በቁሙ ሶፋው ላይ እየወደቀ።

"ማናት?" ጠየቀ ዳግማዊ።

"አለችልህ የሴት ጉድ!!። መለሱ እናት ፍቅረኛው መሆኗን እና ከእርሷ ጋር ሲጣላ እየጠጣ እንደሚያመሽ አከሉበት። ቀጥለውም "ቢቆጠር ከፍቅራቸው ፀባያቸው ይበልጣል። ልጅቷም ብቻዋን አይደለችም የሆነ ጋኔን ቢጤ ያግዛታል። ልጁን ጂል እኮ ነው ያደረገችው።" እየተናገሩ ወደ መኝታ ቤታቸው ተመለሱ።

"አሁን ግባና ተኛ ጠዋት እንነጋገራለን።" አለ ዳግማዊ በቁጣ ወደመኝታ ቤት ለመግባት እየተነሳ።

"ዲጉ ግን ፍሪጅ ውስጥ ነበር እንዴ የከረምሽው?" አለ ቢኒያም ስካርና ሳቅ እየተቀላቀለበት። ዳግማዊ ዘወር ብሎ አየው።

"ማለቴ አልተለወጥሽም።" ሲለው እኔ ሳቄን ለቀኩት። ዳግማዊ እኔንም እሱንም በአንድ ዙር ገላምጦን ገባ። አታምኑትም!! ሰክሮ ሲለፋደድ እንኳን የሚፈታተን መስህብ አለው። ባልተሰማ ለማለፍ የሚከብድ ፍም ስሜት።

"ትልቅ ልጅ እኮ ነው ልትቆጣው ባልሆነ" አልኩት ዳግማዊን እንደቅድማችን እንደተጋደምን። በነገራችሁ ላይ ምንም ተፈጥሮ አያውቅም። የእኔ ምክንያት ዳግማዊ የሚያማልለኝ አይነት ወንድ አይደለም። የእርሱን አላውቅም።

"ቤች 'ፕሊስ' ከቤተሰቤ ጋር እንዴት መግባባት እንዳለብኝ ለኔ ተይልኝ!!" አለኝ እንደተለመደው ጀርባውን አዙሮ እየተኛ።

"አብረን እየዋሸን ነው አላልከኝም? ቤተሰባዊነቱንም አብረን እየኖርነው ነው።"አልኩት። አልመለሰልኝም። ራሱን የቤተሰቡ እረኛ አድርጎ መቁጠሩ ከእድሜው የበዛ ጭምት አድርጎታል።

ከነጋ በኋላ እንቅልፍ እንዲወስደኝ ስገለባበጥ አርፍጄ ተነስቼ ጎዳ ስገባ እታባ ቁርስ እያበሰሉ አገኘኋቸው እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ያለው አጥርና ገደብ ይጨንቃል።የተመጠኑ እና የተለመዱ ጨዋታዎችን ከመጫወት ያለፈ ቅርርብ የላቸውም።እዚህ ቤት መከባበር እና መፈራራት ድንበራቸው ተቀላቅሏል።አብሬአቸው ስቀመጥ ልቤ ምጥ ይይዛታል።
የክፍል አለቃ እነዳስጠነቀቀዉ ተማሪ እጄን ማጣመር ሁሉ ይዳዳኛል ገደባቸውን አፍርሼ ላወራቸው ብሞክርም መልሳቸው አጭርና ለሌላ ጨዋታ የማይጋብዝ ይሆንብኛል ።እታባ ቁርስ ማብሰሉን እንዳግዛቸው ስላልፈቀዱልኝ አገጠባቸው ሆኜ የባጥ የቆጡን አወራለሁ።አንድ ወሬ እጀምራለሁ። ሳልጨርስ ሌላ እጀምራለሁ በዝምታ ከስንት አንዴ ዓይኔን እያዩ ከመስማት ያለፈ አይመልሱልኝም ሁሉም ሰው ሌላን ሰው ወደራሱ የሚጋብዝበት ርቀት ገደብ አለው።ጭራሹኑ ማንንም የማያስደፍረው የራሱ ክልልም ይኖረዋል።እኔ ደግሞ መሰረታዊ ችግሬ የሰዎችን ድንበር መጣስ ደስ ይለኛል። አንድን ሰው ስቀርበውና ቀስ በቀስ አጥሩን እያለፍኩ መዝለቅ የቻልኩ ሲመስለኝ ክብረ ወሰኑን እንዳሻሻለ አትሌት ሀሴት አደርጋለሁ።

"በይ ባልሽን ቁርስ ደርሷል በይው።" አሉኝ እታባ ከወሬዬም ለመገላገል ይመስላል። ለዲጉ መልእክቱን ካስተላለፍኩ በኋላ የማደርገው ሳይገባኝ ወደ ቢኒ ክፍል አመራሁ። ባንኳኳ መልስ የለም። ደግሜ አንኳኳሁ።

"አቤት?" አለ ቢኒ በጎርናና አንደበት። ለመግባት ፍቃድ ሳልጠይቅ ነው የዘለኩት። አልጋው ላይ እንደተጋደመ ሲጋራ እያጨሰ ነበር።እኔ መሆኔን ሲያውቅ ሲጋራውን ለማጥፋት ፈጠነ። እንደ መአት የሚፈራው ሚሴቱ ነኛ!

"አጭስ ችግር የለውም። ጭስ አታባክን ።" አልኩት።

"ልግባ ወይ አይባልም እንዴ? ራቁቴን ብሆንስ?" አለኝ ቀልድ በመሰለ ቅሬታ።

"ጠባሳ አለብህ እንዴ ታድያ? ራቁትክን የሆንክ እንደሆነስ?" መለስኩለት ከንፈሩን
ወደ ጎን ሸፈፍ አድርጎ ፈገግ አለ። ከንፈሩ የሚያቀ
👍4
ነዝር ሽፍደት አለው።"ቁርስ እየጠበቅንህ ነው ።" አልኩት ቀጥዬ።

"ዲጉ ተበሳጭቶብኛል አይደል?" አለኝ ልወጣ ወደ በሩ እያቀናሁ ሳለ።

"ትንሽ"

ኑሮ በሚያህል ከባድ ዝምታ ቁርስ ተበላ።ቄጤማው ተጎዘጎዘ ፣ ቡና ተፈላ፣ እጣን ተጫጫሰ፣ ፈንድሻው ተበተነ፣ ግን ደስ አይልም። ሰዎች የሌሉበት ፍዝ ስነ ስርአት ቀብር አካሄጅ የሚመስል ጨዋታ የሌለበት ስብስብ የማላውቀው ሰው ቤት ተገድጄ ለቅሶ ልደርስ የመጣሁ መሰለኝ። ከሰሞኑ በባሰ ሁኔታ ልቤ በደነች።

"የምትናገረውን ተናገርና ልባችንን አውርደው"አልኩት ዲጉን። ሁሉም ፊቱን አቀጨመ።ኪዱ እንደ ማሳል አደረጋት።

"ምኑን?" ብሎ አፈጠጠብኝ።

"እኔ ምን አውቃለሁ። የማውቀው እንደተናደድክበት ነው።ዲጉ መልስ አልሰጠም። ከፈንዲሻው ጋር እየተጫወተ ዝም።ቢኒ ይጠብቃል። ደቂቃዎች አለፉ። ቃል ለማውጣት አፉን ለማላቀቅ የደፈረ የለም። ቢኒ ለመሄድ ሲነሳ

"ቁጭ በል!" አለው ዲጉ ቁጣና ትእዛዝ ለውሶ። ሁሉም ደነገጠ። እኔ ግን ደስ አለኝ። ቢኒ የተባለውን አደረገ።

"ምን ማድረግህ ነበር?" ብሎ ጀመረ። ነፍስ ያላወቀ ልጁን እንደማቆጣ አባት ወረደበት።ጣልቃ ገብቶ የተቃወመም የደገፈም የለም። ሲጨርስም ከአስፈሪ ፀጥታ ውጪ ጥያቄም መልስም አስተያየትም አልተሰማም።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
👍1😁1
Re-post

#ኢትዮጵያዊ_ነኝ

ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደአክሱም ድንጋይ እንደሮሀ አለት
የጊዜ ሞገድ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ከዋርካ ባጥር ከእምቧይ ተልቄ
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ አደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ተራራ መራጭ
ልክ እንደአሞራ ብርንዶ ቆራጭ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
እንደመሐረብ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ የማልገታ
ኢትዮጵያዊ ነኝ።💚💛❤️

🧿በእውቀቱ ስዩም🧿
#አጀብ_እኛ ° ° °
°
°
°
መጪውን ለመኖር
ዛሬያችን ስንገፋ፣
ብዙ ሸለቆ አለ ° ° °
በነጋችን ተስፋ !!!

🧿ሀብታሙ ወዳጅ🧿
በኑሮ ምጣድ ላይ አንዴ ከተጣድክ ዘንዳ
እሺ ብለህ ብሠል እንዳታወሊዓ።
ምን ህመም ቢኖረው መንደዱ መብሰሉ፣
ሆድ አይታወክም አበስለው ከበሉ።
መጣዱም ካልቀረ ካልበሰሉ መብረድ፣
መቃጠሉ እንዳይብስ ቶሎ በስለህ ውረድ
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_አራት


#በሜሪ_ፈለቀ


"ይቅርታ ዲጉ!" ብቻ ብሎት ወደ ክፍሉ ገባ።

ቀለም አልባ ቀን ከዋልን በኋላ ቢኒ ዛሬም ስላመሸ እታባን እንዲተኙ ነዘነዝን፣ ዲጉ በጥናት ሰበብ (አዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት) ወደ መኝታቸው ሲሄዱ እኔና ዲጉ ጠባቧ ሳሎን ቀረን። ዝንብ እግሯን ወለም ቢላት በሚሰማ አይነት ዝምታ ተወጠርን።

"ኸረ ቢያንስ ቲቪውን ክፈተው።" አልኩት
ሪሞቱን አቀበለኝ።ሽለላ ሲቀረው እየተንጎራደደ እና ሰአቱን በማይክሮ ሰከንድ ልዩነት እየገላመጠ ሲጠብቅ ቢኒ እኩለ ለሊት ላይ ጥንቅቅ ብሎ ተከሰተ። በእጁ የያዘውን ሲጋራ ሲያይ ዲጉ አበደበት።

"ጋጠ ወጥነት ካማረህ ለምን ራስህን ችለህ አትወጣም?" ብሎት በሩን ቆልፎ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ።

"ቆንጆ ናት?" አልኩት። ቢኒን ነው የጠየኩት።

"ማን?"

"እንዲህ ራስህን የምታዝረከርክላት።"

"እ..ሰይጣን እኮ ቆንጆ ነው።" መለሰልኝ።

"ሰይጣንነቷን እንዳይሆን የምትወደው"

"ምኖን እንደምወደው አላውቅም።" በስካር አንደበቱ ስለሷ ገለፃና ትንፋሽ እስኪያጥረው ጠረቀ።ሳላቋርጠው ሰማሁት። ውበቷን፣ ፍቅሪሩን፣ወፈፌነቷን እየፈገገ እና እየጨፈገገ ሳለልኝ።

"እኔ ማለት እይታው የደበዘዘበት ከንቱ ነበርኩ።እሷ የአይኔ መነፅር ናት። ፊቴን አጥርቼ የማይባት፣ ኋላዬን የምቃኝባት፣ ጎኔን የምፈትሽባት።ሳወልቃት አስተካክዬ መርገጥ አልችልም።ያለሷ ወልጋዳ ነኝ"። የገለፀበት መንገድ ቀላልም ከባድም ሆነብኝ።

"ዓለምን በሌላ መነፅር ለማየት ፈሪ ሆነክ እንዳይሆን?" ስለው ዝም አለኝ።

"ደህና አደር!!" ብዬው ወደኋላ የሚጎትተኝን ልቤን ወደ ፊት በሚራመድ እግሬ እየረታሁ ጥየው ገባሁኝ።

"ለእህቱ ምሳሌ ለእናቱ መመኪያ እንዲሆን እፈልጋለሁ።" አለኝ ዲጎ ገና ከመግባቴ ጠብቆ።"የሚያወራው ስለ ህፃን ልጅ እንጂ ሀያ ዘጠኝ ዓመት ስለሞላው ወንድሙ አይመስልም።

"ሁሌ ለሌሎች መኖር ይከብድ ይመስለኛል። የራሱን ስሜት ማዳመጡ ሰውኛ ነው።"

"የራሱ ስሜት ስርአት አልባ መሆን ነው? ለታናሽ እህቱ ዱርዬነት ማስተማር? ህመምተኛ እናቱን እኩለ ሌሊት ድረስ ማስጠበቅ?"

የሚናገረው ከሙሉ ቅንነትና ለቤተሰቡ ተቆርቋሪነት ነው። እንኳን የሌላን ሰው የመኖር ልጓም የራስን የሕይወት አቅጣጫ መወሰን የማይቻልበት አጋጣሚ የትዪለሌ መሆኑን ላስረዳው ምከርኩ። ስሜት፣ ሕይወት፣ ኑረት፣ ህልም፣ ቅዠት....ለእርሱ ከቤተሰቡ የሚበልጥ የለውም።ራሱን እንደ አባትም እንደ ታላቅ ወንድምም እንደ መልካም ልጅም እንዲቆጠር ከአባቱ የመጨረሻ ቃል በላይ የቤተሰቡ በእርሱ ላይ ያለው እምነት አስገድዶታል።አልፈርድበትም። በተቃራኒው የዘመኑን አጋማሽ ለቤተሰቡ መኖሩ አሳዘነኝ።በቤተሰቡ መሃል የሚፈጥረው ኢምንት ክስተት ሳትቀር የእርሱ ሃላፊነት እንደሆነ የሚሰማው መሆኑ ከቤተሰቡ ደስታ በላይ የሚያስደስተው ነገር አለመኖሩን ነገረኝ።

"ሳትዋሽ ንገረኝ አጭሰህ፣ ሰክረህ.. ምናምን አታውቅም?"

"አላውቅም። ቀጭራሽ!! መጠጣት እጠጣለሁ።ሰክሬ ግን አላውቅም" በሰላም?" ልለው ቃቶኝ ነበር።ለእሱ ቀልድ አይሆንም ብዬ ተውኩት።

"እሺ በህይወትህ የሰራኸው ትልቁ እብደት ምንድን ነው?"

"ለምን አብዳለሁ?"

"እሺ ስትበሳጭ ወይ ስትበሽቅ በምንድን ነው ብስጭትህን የምታበርደው?" ስለው ፈጥኖ አልመለሰልኝም።

"ምንም።" አለ እርግጠኝነት በጎደለው ድምፀት።

"አትዋሽ!!" ስለው ፊቱን አዙሮ ተኛ!! ጀርባውን እንደሰጠኝ "አንቺስ? ስትበሳጪ በምንድነው የምታበርጂው?" አለኝ። ለመልሴ ምንም ሳይጓጓ።

"በብዛት ክለብ ወጥቼ እጨፍራለሁ። አንዳንዴ ረጅም ወክ ሳደረግ እረጋጋለሁ" መለስኩለት። ዝም ብሎኝ ተኛ!!

ጠዋት ያለወትሮዬ አርፍጄ ስነቃ ቀድሞኝ ነቅቶ ኮርኒሱ ላይ ፈጧል።

"እስቲ ዛሬ ወጣ እንበል? አዋዋላችንን እንቀይር?" አልኩት።

"ወጥተንስ?"

"እህ...እዚህ ቤት ከገባን ስድስት ቀናችን"

"ቤች በጣም ይቅርታ! ለኔ ብለሽ ብዙ እያደረግሽ እንደሆነ አውቃለሁሁ። እንዴት እንደማመሰግንሽ አላውቅም። እኔ ከእናቴጋ ልቆይ። ከኪዱ ጋ ወጣ በሉ።"

"ኪዱ ነገ ፈተና አላት!!" ስለው መላ እንደሚፈልግ ሰው እንደማሰብ አደረገ። ግን ምንም አልተናገረም።

"ቤን ከስራ ስንት ሰዓት ነው የምትወጣው?" አልኩት ሆን ብዬ ቤተረቡ ለቁርስ በተሰበሰበበት።

"አስር ሰአት ገደማ" አለኝ እየተጣደፈ እየተመገበ።

"ማክያቶ እንድንጠጣ ነበር።" ስለው ምን እንዳስደነገጠው ክው አለ።

"እነማን ?" ሲል ሳቄን አፈንኩት። በቆረጣ ዲጉን አየው።

"እኔና አንተ!!! ኪዱ ነገ ፈተና ናት፣ዲጉ መውጣት አልፈለገም።" ያልኩትን እንዳልሰማ መሰለ።ሲሰርቅ እንደያዙት ህፃን ተቁለጨለጨ።

"እ?" አልኩት መስማቱን ለማረጋገጥ

"እ?" አለኝ መልሶ እንደባነነ ሰው።

"ነፃ በሆንክ ሰዓት ዘወር ዘወር አድርጋት።" አለው ዲጉ ማረጋገጫ ለመስጠት።የወንድሙ አኳኋን የእርሱን ሀሳብ ፍለጋ መሆኑ ገብቶታል።

"እሺ እንደጨረስኩ አመጣለሁ።" አለኝ።

እንዳለው ቀደም ብሎ መጣ።መክሰስ በልተን ወይን እየጠጣን ስንጫወት አመሸን።ወይኑን ለኔ ትቶልኝ ቢራ መጠጣት ቀጠለ። ያላነሳነው እና ያልጣልነው ርዕስ አልተገኘም። ብዙ ዘመን እንደሚተዋወቁ ጓደኛሞች ስለብዙ ነገር አወራን። ፍቅረኛውን ብቻ ያከለችበትን ዓለም ስፋት ላስረዳው ምከርኩ።በፍቅር ስሜት ተሟገተኝ። በተጨባጭ እውነት ተከራከርኩት።በቁም ነገራችን መሃል ከወይኑ ጋር ተደምሮ ውስጤ የሚንቀለቀል ልክፍቴን ለመግታት እታገላለሁ።

"አንቹ?" አለኝ።

"ምናባክ?"

"አሁን እንዴት ነው ያየሽኝ?"

"እንዴት አየሁህ?"

"እንደ ወንንድሜ ሚስት ባልሆነ አስተያየት።"

'ባንቺ እረፊ ለብልግናሽ ልጓም አበጂለት" አልኩት ራሴን፣ እሱን ግን

"ማታ የምትጠጣው ቢራ ጠዋት በጄሪካን ቢሰጡህ አታነሳውም።በል ተነስ እንሂድ!!" ብዬው ለመሄድ ተነሳን።

የሚቀጥለው ቀን የተሻለ ቀን ሆነ።

በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ቤቱን ሳቅ እየሞላው ጨዋታ እየደመቀ መጣ።

በብዙ የሚደመጠው የኔ ሳቅና ወሬ ቢሆንም! ከቤን ጋር ወጥተን መፅሀፍት ገዛን።(ማታ ማታ የማነብላቸውን የግጥም በድብሎች ጭምር።)ከእታባ ጋር ቤተክርስቲያን፣ ከኪዱ ጋር አማርኛ ሲኒማ ሄደናል።(ሁለቱም ለራሴ ስል በፍፁም የማላደርጋቸው ናቸው።)ከቤን ጋር በተለይ ተግባባን።ሁለት ቀን ስልኩን ደብቄበት በሌላ ስልክ እንዳይደውልላት ቃል አስገብቼው ስለነበር ለፍቅረኛው ሳይደውልላት ዋለ።አድርጎት ስለማያውቅ ደጋግማ ስትደውል አላነሳሁላትም።እቤት ድረስ መጥታ ስልኩን ረስቶት መሄዱን ስነግራት እየተውረገረገች እና እያጉተመተመች ወጣች።ውብ ናት!! ቤን ሲሰማ በዲጉ ፊት መደነስ ቃጣው።ጉንጬን ስሞኝ "ቴንኪው"ብሎኝ ወደ ክፍሉ ገባ።

ከፍቅረኛው ውጪ በማንበብና ከቤተሰቡ ገር በመሆን መብሰልሰሉን ቀጥሏል።

"እቤት መምጣት እሷጋ ከመሄድ በላይ እንዲናፍቀኝ አደረግሽኝ" አለኝ የሆነ ቀን።

"እሰይ!! ታረቀችህ?" አሉ እታባ ቤኒ በጊዜ ወደቤቱ የገባ ቀን።

"ከራሴ ለመታረቅ የሞከርኩ ነው እማዬ !!" ብሏቸው ነበር።

በዚ ሁሉ ቀናትና ክስተቶች መሃከል በቀን ቢያንስ ሁለቴ እየደወለች አዲስ ነገር ካለ ለመስማት ለምትጠዘጥዘኝ ቹቹ ወሬ ማቀበል የየእለት ግዴታዬ ነው።

በአንዱ ቀን ማታ እቤት ውስጥ ወይንና ውስኪ ተገዝቶ እየተጎነጨን ስንጫወት አመሸን።በእርግጥ ዲጉ ከመጫወትና ከመጠጣት ይልቅ የኛን ልክ ሲቆጣጠር አመሸ ማለት ይቻላል።በልጅነት ስለሰራናቸው ጥፋቶችና እና ተንኮሎች እየተጫወትን ቤተሰቡ እየተበሻሸቀ ሳይታሰብ እኩለ ሌሊት ሆነ።ዲጉ
👍71
ለመጫወቱም ለመሳቁም ሲሰስት አሰተዋልኩት።በእርግጥ እኔም ቢሆን ስለልጅነቴ የሚያስፈልገውን መርጬ አወራኋቸው እንጂ በብዙ ስርዝ ድልዝ የተማገረ ልጅነቴን አልነገርጓቸውም።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ። 🙏
#ኢትዮጵ!"

ቅድመ ካም ነገዱ፡ የኩሽ ፍሬ ክብሩ
ኢትኤል ታላቁ፡ የናምሩድ በኩሩ
ግራ ጎን አጋሩ፡ ዕንቆጳን ማግባቱ
ከምሥራቅ ሀገሩ፡ ከጊዮን ስሪቱ
"ዮጵ"ን ተሸልሞ፡ ንግሥናን ሰይሞ
ኢትዮጵን አነፃት፡ ጥበብ ተተልሞ።

የኢትኤል ወርቅ፡ "ዮጵ" አክሊል ቢሆንም
የደፋው አክሊል ግን...
የታሪክ ዕዳ ደም፡ ዘውድ ባለቀለም
ሰው ነው ሽልማቱ፡ ጥበብ ነበር ወርቁ
ፍቅር፣ እውነት ሀብቱ፡ "ኢትዮጵ" ናት ዕንቁ።

ቅጥሯን ያስከበረ፡ ዳር ድንበር ከልሎ
ኑቢያና ምስርን፡ ለራሱ ጠቅልሎ
አንገቷን ያቀናው፡ ለዓለም ሥልጣኔ
በጥበበ-ሄኖክ፡ ዓለምን ያነፀ፣ ዛሬን ያዘመነ
ያ’ዳም ቅድሜ ስሪት፡ መነሻ መድረሻው
የትውልዱ ምክነት፡ ታሪኩን ቢያስክደው
ኢትዮጵ ’ምትባል፡ ድብቅ ቅኔ ምስጢር
የት ገባች የጥንቷ፡ ኢትኤል ያ’ነፃት…
ያቺ ታላቅ ሀገር?

ደርቡሽን አባረው፡ ግብፅን ያዋረደ
እኔን ያስቀድመኝ፡ ብሎ የተዳፋ…
ማግዶ የታረደ
መቅደላ ጀግኖ፡ ባ’ድዋ የደገመው
ቃል ኪዳን ሰንደቋን፡ በነጭ ያላስነካው
ባ’ምላክ እጅ ሥራ፡ በጥበብ አሻራው…
ኢትዮጵን የሳለ
ያልመከነው ትውልድ፡ ኢትኤል የታለ?
አሁንማ!...
ሰልጥኖ መሴይጠን፡ እየተመዘዘ
በታሪክ ወለምታ፡ እየደነዘዘ
ጥበብ፣ ፍቅር፣ እውነት…እየደበዘዘ
ኢትኤል ባ’ነፃት…
በ"ኢትዮጵ" ምድር፡ ትውልዱ ቦዘዘ።

🔘 ዳዊት ፈቀደ 🔘
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ_አንድ(🔞)


#ቺቺንያዊው_ፍቅሮቭስኪ


እግር ጥሎኝ ጆሲ ባር ገብቼ ስዝናና ሄለን ፒንክን አገኘኋት። ሄለን አሁንም ኩል ክለብ ውስጥ እንደምትሰራ ነገረችኝ። ማርቲ እዚሁ አዲሳባ መሆኗን እስክትነግረኝ ድረስ እንደሌሎቹ ጓደኞቻችን ዱባይ የገባች መስሎኝ ነበር። ከሄለን ጋር እየጠጣን የሆድ የሆዳችንን ተጫወትን። ሁለታችንም መጀመሪያ ስለተዋወቅንባት ቺቺንያ አንስተን ብዙ የጋራ ትዝታዎቻችንን አነሳን-ጣልን። ሄለን ፒንክ ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችን አሁንም እዚያው ቺቺንያ እንዳሉ ስትነግረኝ ዛሬውኑ ሄደን እንድንጠይቃቸው
በሞቅታ ሀሳብ አቀረብኩ። እውነትም ሞቅ ብሎኝ ነበር። ሄለን ፒንከ አላቅማማችም።

ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ሲል ጆሲ ባርን ለቀን ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችንን ለማግኘት ወደ ቺቺንያ አመራን።
እንዲሁ ሳንተኛ ሌሊቱ ይነጋታል እንጂ ሄለንን ብዙ ክለቦች ልወስዳት እዚያው ጆሲ ባር ውስጥ እያለን አስቀድሜ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር። ምን ጣጣ አለው?! ሲነጋ እኔ አፓርታማ ሙሉ ቀን ተጋድመን
እንውላለን ብዬ አሰብኩ። የዛሬን አያድርገውና ሄለን ፒንክ ባለውለታዬ ነበረች። ሁላችንም በራሳችን
የህይወት ሀዲድ ላይ ፋታ አጥተን ስንጣደፍ በተለያየ ወቅት መልካም የዋሉልንን እንረሳለን።

ሰአቱ ገና ስለነበር እዚያው ቺቺንያ ትልቁ ክለብ ዉስጥ ገብተን በዲጄ ሙዚቃ ወለሉ ላይ በዳንስ እየሾርን ስንጠጣ እስከ ሌሊቱ 9፡30 ቆየን። እንደ ጆሲ ባር ሁሉ እዚህም የከለቡን ለፍዳዳ ወንዶች
ለከፋ እና ጅንጀና እንዲሁም የአብረን እንዝናና ጥያቄ መቋቋም ነበረብን ወንዶች መለፋደድ ከጀመሩ ደግሞ ቶሎ አይፋቱም፡ እምቢ ሲባሉ ይብስባቸዋል። እንደዉሻ ከቂጣችን ስር መርመስመስ ጀመሩ።በዚህን ጊዜ ክለቡን ጥለንላቸው ከትልቁ የቺቺንያ ክለብ ወጥተን ወደ ትንሿ ቪቪያን Tብ አመራን።ከዋናው የቺቺንያ አስፋልት የተወሰኑ ሜትሮችን ገባ ብሎ ነው የሚገኘው፡ ገና እግራችን ከመግባቱ ብሌን በጩህት ተቀበለችን።

"ሮዛ!!! እኔ አላምንም፤ በአገሩ አለሽ? ማርቲ ነግራሻለች? ብዙ ጊዜ ያለሽበትን ሁኔታ እጠይቃት ነበር፤ ከሄሊ ጋር እንኳን አልፎ አልፎ እንገናኛለን፤ ሄሊ ፒንክ እንዳንቺ አልረሳትንም ፤ እየመጣች ትጠይቀናለች ወይ ሮዚና እንዳጠፋፍሽ ግን አላማረብሽም ጥፍጥፍ..."

ብሌን ከባንኮኒው ውስጥ ወጥታ በደስታ ተጠመጠመችብኝ፤ ለደቂቃዎች አለቀቀችኝም። ከብሌን ጋር በጣም ነበር የምንዋደደው። ብሌን አልተለወጠችም፤ ውበትዋ፣ ፍልቅልቅነቷ፣ ሸንቃጣነቷ፣
ተጫዋችነቷና ማራኪ ለዛዋ አሁንም እንዳለ ነው። በህይወቷ ውስጥ የቱንም ያህል ሀዘን፣ ስቃይና መከራ ሲደርስ ብሌን እንደ አይሁዶቹ ቀልድ ፈጥራ ትዝናናበታለች። ይሄ የብሌን ልዩ ተሰጥኦ ነው። ምንም ቢደርስባት ሁሌም ሳቂታ፣ ቀልደኛና ተጫዋች ስለሆነች ሀዘን ለቅጽበት እንኳን ነክቷት የሚያውቅ አይመስልም።

እኔና ሄለንን በአሪፉ ለማስተናገድ ሽር ጉድ ስታበዛ አስቆምናት፡ ብሌን አሁንም ድረስ ያልተወጋና ንጹህ ውስኪ ከሚሸጡ እጅግ ጥቂት ታማኝ የቺቺንያ የባርና የፐብ ባለቤቶች ቀዳሚዋ ነች።

ከብሌን ባሻገር ባንኮኒው አጠገብ አንገቱን ደፍቶ በፍጹም ተመስጦ ጠርሙስ ጎርደን ጂን ወደ ሚጠጣው
ጎልማሳ ማተረች። በቪቪያን ፐብ ውስጥ ከሱ ሌላ ሰው የለም። ጂኑ አልቆ የጠርሙሱ ቂጥ ላይ ሊደርስ
ትንሽ ይቀረዋል፤

“ፍቅሮቭስኪን ልሸኝና ፐቤን ዘግተን ቤቴ እወስዳችኋለሁ፣ አሪፍ ኮንዶሚንየም ገዝቼያለሁ ደሞ።ሄልዬን አሳይቻታለሁ፤ ሮዝ ግን ዛሬ ትመርቂልኛለሽ እሺ!”

ብሌን ጉንጩን በለስላሳ መዳፏ መታ አድርጋኝ ያን ደማቅ ፈገግታዋን ለገሰችኝ፤ ፈገግታዋ አለም ሁሉ በጨለማ ቢዋጥ ለመላው አለም ብርሃን የመለገስ ሃይልና ጉልበት አለው። አይ ብሌን! ሁሌም
ፍልቅልቅ ናት። ግራና ቀኝ ከጉንጮቿ መሀል የተሰደሩት ዲምፕሎቿ በምትስቅበት ወቅት ፈገግታዋን
አድምቀውት የልእልት ገጽታን ያላብሷታል። ከበፊት ጀምሮ ከምትሀታዊ ፈገግታዋ ጀርባ አንድ ከባድ ሀዘን ወይም የማይሽር የህይውት ቁሰል እንዳለ ባስብም ያን ደፍሬ ሳልጠይቃት ነበር ከበርካታ አመታት በፊት ቺቺንያን የለቀቅኩት። በጨዋታ በጨዋታ እድርጌም ቢሆን ከደማቅ ፈገግታዋ አድማስ ማዶ የተደበቀውን የህይወት ስንክሳር ባውቅ ደስተኛ ነኝ። ከአንዳንድ ዝነኛ ኮሜድያን ህይወት ጀርባ ስፍር ቁጥር የሌለው ሀዘንና መከራ እንዳለ ሁሉ፣ የብሌን ውብ ምትሀታዊ ፈገግታ ምናልባትም በህይወት የደረስነባትን አንዳች ከባድ ስብራት መሸፈኛ ጭምብል ሊሆን ይችላል። በፊት የማውቀው ባህሪዋ አሁንም እንዳለ ነው።

ሰብለን ከቀልድና ጨዋታዋ ሌላ ልብ አንጠልጣይ የትርጉም ልቦለድ መጻህፍት መለያዎቿ ነበሩ።መጽሐፍ በማንበብ ከጓደኞቼ ብቸኛዋ ሳትሆን አትቀርም። ነገር ግን ልብ አንጠልጣይ ካልሆነ
አታነብም። የሳንድራ ብራውንን፣ የጃኪ ኮሊንስን፣ የኤሪካ ዮንግን፣ የዳኔላ ስቲልን፣ የአጋታ ክሪስቲን፣የሲድኒ ሼልደንንና የኬን ፎሌትን ስራዎች እንደዉስኪ አንጠፍጥፋ ነው የምትጠጣቸው።

ብሌን ከመደርደሪያው ላይ ሙሉ ሬድ ሌብል አውርዳ ለኔና ለሄለን ከዚያም ለሷ በብርጭቆ ቀዳች።ብርጭቆዎቻችንን አጋጭተን እየጠጣን መጨዋወቱን ቀጠልን። ደሞ ለጨዋታ! ብሌን ጋ ቀልድ፣
ጨዋታና ሳቅ በሽ ነው።

ብሌን እንደገና ወደ ጎልማሳው ጠጪ ማተረች፤

“ሮዝ! አላወቅሽውም እንዴ?”

ጎልማሳውን ገና አሁን ነበር በሙሉ አይኔ የተመለከትኩት። ፊቱን እንደ ሃምሌ ደመና አጨፍግጎታል፣ዝምታው የመርግ ያህል ይከብዳል። በራሱ አለም ውስጥ ነው ያለው። ባዶ ሊሆን ጥቂት የቀረው
የጎርደን ጠርሙሱ ላይ አፍጥጧል። ከገባንበት ቅጽበት ጀምሮ እይታውን ከጠርሙሱ ላይ አላነሳም።
በዙሪያው ያለውን ትእይንት ከነመኖሩም እስኪረሳ ድረስ በራሱ የሀሳብና የትካዜ አለም ተሳፍሮ ሩቅ የነጎደ ይመስላል።

አውቅኩት፤ ብረት አስመጪው ፍቅረዝጊ ነው። ተክለሀይማኖት አካባቢ ትልቅ መጋዘን እንዳለው ይወራ ነበር። አመታቱ የቱንም ያህል ቢረዝሙ ድሮ የሚያውቁት ሰው መሰረታዊ ገጽታ አይጠፋም።
ካልሰከረ እሱም እንደሚያውቀኝ እርግጠኛ ነኝ።

"ፍቅረዝጊ ነው አይደል ብሌን?"

ብሌን እንደ ድሮ አስካካች

ሮዝ ሰፈራችንን ከለቀቅሽ ብዙ ጊዜ ስለሆነሽ የስሙን ለውጥ አላወቅሽም ማለት ነው፡፡ ፍቅረዝጊን
| 'ፍቅሮቭስኪ' ብለን የቺቺንያን የክብር ዜግነት ሰጥተነዋል እኮ። ላለፉት አስር አመታት ዊከ ኤንዶችን ከቺቺንያ ርቆ አያውቅም፤-በተለይ ከዚህ ከቪቪያን ፐብ። በርካታ የቺቺንያ ቆነጃጅት በተገኙበትና ድል ባለ ድግስ ነበር የቺቺንያ ዜግነቱን ያቀዳጀነው”

የማስካካቱና በሳቅ የመንከትከቱ ተራ የኔ ተራ ሆነ። እንዲህ እንዲህ እያለ ጨዋታችን ደራ። ድንገት ብሌን ያልጠበቀችውን ጥያቄ አስከተልኩ፤

“የኔ ውብ! ትዳር መሰረትሽ?”

ብሌን እንደገና በሳቅ ተንከተከተች፤

“አይ ሮዝ፤ አላወቅሽም እንዴ?! ትዳር ማለት እኮ ሾርት ወይም አዳር ገብቶ እንደመውጣት ሆኗል።ባለትዳሮቹ ራሱ ሚስታቸውን እያስተኙ እኛ ጋር አይደል እንዴ የሚያመሹት? ለአንድ ለስድስት ወር ያህል ሞክሬው ነበር-ባል ተብዬው አስካሉ የተባለች ሰራተኛዬን በገዛ አልጋዬ ላይ ሲያንከባልል እጅ ከፍንጅ ይዤው በቀይ ካርድ አሰናበትኩት…” ጣሪያው እስኪሰነጠቅ በራሷ ንግግር ሳቀች።

ሶስታችንም በሞቅታ ውስጥ ነን፤ ብሌንን በሳቅ አጀብናት። ሆኖም የፍቅሮቭስኪ ጎርናና ብሶተኛ ድምጽ ከሳቅና ከጨዋታችን መለሰን። ፍቅሮቭስኪ ከባድ ሀዘን ባረበበበት ጨፍጋጋ ፊቱ ሶስታችንንም በየተራ ገረመመን።ቡናማ ኮቱን በንዴት መሬት ላይ ወረወረው። ባንኮኒውን በግዙፍ ቡጢው በተደጋጋሚ
ነረተው። ጨርቁን ሊጥል ቅጽበት የቀረው
👍2
ወፈፌ ይመስል ነበር።በየተራ አፈጠጠብን፤

“እስቲ ንገሩኝ! እዚህ ሰፈር ውስጥ ምን አይነት ድግምት ነው የተደረገብኝ? ሺ ጊዜ ሰፈሩን በድጋሚ ላለመርገጥ ምዬ ብገዘትም አክለፍልፎ የሚያመጣኝ አዚም አለ። ምንድነው ያረጋቸሁብኝ? ምን
አይነት አፍዝ አደንግዝ ነው የነሰነሳችሁብኝ? ብሌን ምንም ሳትደብቂ ንገሪኝ የምትለማመኚው ቃል።
፣ ጠንቋይ ፣ ሼክ ወይም ቆሪጥ በኔ ላይ ምን እንድታደርጊ ነው ያዘዘሽ? ያው ባንቺ ቤት ስንት ዘመኔ ሌሎች የሰፈሩ ቡና ቤቶችና ፐቦች ጋ ቆይቼ አንቺ ቤት ነው ሁሌም የማሳርገው። ያንቺን ቤት ሳልሳለም ይህን ኩሻንኩሽ ሰፈር የተለየሁበት ጊዜ የለም። ይህን አንቺም አሳምረሽ ታውቂዋለሽ ስለዚህ የዚህ ሰፈር ሴቶች በኔ ላይ ምን እንዳደረጋችሁብን ሳትደብቂ ንገሪኝ ብሌን አንቺን ነው የማናግርሽ"

የሆነ ማይም ቲያትር የሚሰራ መሰለኝ። ፍቅሮቭስኪ አመልካች ጣቱን ብሌን ላይ ቀስሮ ረዘም ላለ ቅፅበት አፈጠጠባት።ብሌን አልፈራችውም ።እንዲህ እያማረረ ይህው ስንት አመቱ።ችላ ግን አላለችውም።ልታረጋጋው ሞከረች፣

“ምነው ፍቅሮቭስኪ….ምን ሆንክብኝ…ኧረ እኔ ካልካቸው ቦታዎች አንዱም ጋ ሄጄ አላውቅም፤ወላዲት አምላክን እኔ እንዲህ አይነት ልማድ የለኝም"

-ፍቅሮሽስኪ አሁንም እይኖቹን ከብሌን ላይ አልነቀለም፤

“ቀጣፊ ሸርሙጣ ነሽ፤ በመጀመሪያ አላመንኩትም እንጂ ሰናይ ሁሌም ቤትሸን ምሸት ላይ ልትከፍቺ ስትይ አዶ ከርቤ እንደምታጨሺና አውሊያሽን እንደምትለማመኚ ብዙ ጊዜ ነግሮኛል። እሱም በስንት ጸበል ነው ከዚህ ስፈር የተነቀለው።እምቢ አልኩት እንጂ ጻድቃኔ ማርያም አብሬው ጸበል እንድጠመቅ በተደጋጋሚ ወትውቶኝ ነበር።”

ፍቅሮቭስኪ እንደገና ባለጌው ወንበር ላይ ተቀምጦ ባንኮኒውን በቡጢው መድቃት ጀመረ፤ አይፎኑን በንዴት ወርውሮ ከአንዱ ግድግዳ ጋር አላተመው፤ ፊቱን በድጋሚ ወደኛ አዞረ። ደም ስሮቹ በቀይ ፊቱ ላይ ተገታትረው

በጉልህ ይታያሉ፤ይህን ጊዜ ሶስታችንም በድንጋጤ ደርቀን ቀረን።

"ወይዘሪት ብሌን! እያወቅሽ አትደብቂኝ፣ ይሄ ድግምታምና መተተኛ ሰፈር ምን አድርጎብኝ ነው ለዘመናት የሰፈሩ ቋሚ እስረኛ ያደረገኝ?! የቢዝነስ አጋሮቼ አርብና ቅዳሜን ሸራተን በጋዝላይት፣
በዱባይና በባንኮክ እየተዝናናን እንድናሳልፍ ለዘመናት በየሳምንቱ ሲወተውቱኝ አንድም ጊዜ እንኳን
ግብዣቸውን ሳልቀበል እዚህ ሰፈር ኩሽና በሚያካክሉ ቤቶች እንድልከሰከስ የሚያደርገኝ ድግምት ምንድን ነው? ብሌን ምንም ቢሆን የዘመናት ደምበኛሽ ነኝ፤ በፈጠረሽ ሚስጥሩን ንገሪኝ!”

ፍቅሮቭስኪ ከተቀመጠበት የባለጌ ወንበር ላይ ተነሳ፤ ሊረጋጋና ሊሰክን አልቻለም፤ ጥቂት የመቶ ብር
ኖቶችን ከቆጠረ በኋላ ባንኮኒው ላይ ወረወረ። ፊቱን ወደ ብሌን መለሰ፤
ብሌን ካንቺ ጋ እኮ ነው የማወራው ለምን እትመልሺልኝም? አልቀየምሽም እውነቱን ብቻ ንገሪኝ ይሄ ሰፈሩን ለመጨረሻ ጊዜ የምረግጥበት ሌሊት ነው። ከነገ ጀምሮ እንደ ሰናይ ለተወሰኑ ቀናት ጸበል
ለመግባት ቁርጥ ውሳኔ ወስኛለሁ። ስለዚህ አትፍሪ በግልጽ የምታውቂውን ንገሪኝ! ለምንድነው የዚህ ሰፈር ባርያና ምርኮኛ የሆንኩት? የትኛው ደብተራ ጋ ነው ያስደገማችሁብኝ? አርብ፣ ቅዳሜና
እሁድ ቤቴን፤ ሚስቴንና ልጆቼን እንድጠላና ከቤት ጥፋ ጥፋ የሚል ምን አይነት መስተባርር ነው ያረጋችሁብኝ? የትኛው ደብተራ ጋ ሄዳችሁስ ነው ለዘመናት ከዚህ ስፈር ጋ በፍቅር እንድወድቅ ያደረገ ማስተፋቅር ያሰራችሁብኝ? የቀራችሁ እኔን በድግምት ማሳበድ ብቻ ነው፡፡ ምኔ ሞኝ ነው!መስተአድርት አሰርታችሁ ሳታሳብዱኝ ነገ ጸበል እገባለሁ። መጥኔ ለናንተ! እኔስ በቃኝ…በቃኝ አልኩ።

ፍቅርቭስኪ ኮቱንና አይፎኑን ጥሎ ውጪ ወዳቆማት ቡናማ ፕራዶ መኪናው አመራ። ብሌን ኮቱንና ስልኩን ይዛ ወደ መኪናው ሄደች። ከአፍታ በኋላ ስጥታው ተመለሰች።

ብሴን በየተራ ተመልክታን ፈገግታውን ብልጭ አደረገች፤

“ፍቅሮቭስኪ በውሳኔው ከጸና ቺቺንያዊ የከብር ዜግነቱን በነገው እለት እንገፈዋለን።" በረዥሙ ሳቀች።

“በቃ ቤቱን ዘጋግተን ወደኔ ቤት እንሂድ። ጉዞ ወደ ብሌን ኮንዶሚኒየም ዳይ ዳይ….” በድጋሚ ሳቀች እኔ ግን ድንጋጤው አለቀቀኝም ነበር።

ሮዚ ደሞ፤ ፍቅሮቭስኪው ታውቂው የለ? ሁልጊዜም እንደዛተ ነው እኮ ሙዳችንን ሰለበው አይደል ይሄ ሰላቢ…ኑ ባካችሁ ቤት ሄደን የሆድ የሆዳችንን እንጫወት…"
ብሌን በራሷ ንግግር ፐቧ እስክትነቃነቅ በሳቅ አስካካች።ፍቅሮቭስኪ በተናገራት ነገር ዉስጥ ዉስጡን ተብከንከናለች ማለት ነው። የንዴት ሳቅ እንደሆነ ያስታውቅባት ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
#ፍላጎት

በራሴ መስታወት ራሴን ታዘብኩት
አሰብኩት አለምኩት ከላይ ታች ቃኘሁት
ጭንቅላት ባዶ ቀፎ ሆኖ ሳልኩት
ከሰው እኩል ብሆን ብዬ አሰብኩኝና
ጨቅላ መሆን መረጥኩ ይስራኝ እንደገና