አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_አንድ


#በሜሪ_ፈለቀ


እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል።ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ።ከሰመሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን ዕድል አይሰጡህም ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረብያ ይስላሉ።ልብህን ከከፈትክላቸው የድርሻቸውን ጠርበዉህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
“አካበድሽ ባንቺዬ ለሦሥት ሳምንት ነው እኮ ሚስቱ የምትሆኚው።" ቹቹ ለመልሴ እየተንገበገበች ፊቷን በሞላው
ዓይኗ አፈጠጠችብኝ። የዓይኗ ትልቀት ዓይኗ ፊቷ ላይ ያለ አካል ሳይሆን ፊቷ ዓይኗ ላይ ያለ ይመስለኛል። ከአፏ
የምትተፋቸው ቃላት ተሰካክተው ጆሮዬ ሲቀልባቸው የህንድ ፊልም ታሪክ ጭብጥ ነገር ነው የመሰለኝ።

"እንዴ?! ቢሆንስ ለምን ሁለት ሰዓት አይሆንም:: ስሜት የማይሰጠኝን ሁለት ደቂቃስ ቢሆን ለምን አሳልፋለሁ? እያልሽኝ ያለሽው ግን ገብቶሻል?" ይሄን ያልኩት ራሴን ስቆልል አልነበረም:: ራሱን የሚወድ ሰው ታውቁ ከሆነ በምንም ልኬት የእኔን ያህል አይሆንም።ደስታን የማይደምርልኝ የትም ቦታ መገኘቴን ራሴን እንደማባከን እቆጥረዋለሁ፡፡ ሚስት ከመሆን በላይ ብክነት ደግሞ ያለ አይመስለኝም። ያውም የውሸት
ሚስት። የሚብሰው ደግሞ በውል ለማላውቀው ወንድ!! መሳጭ
የሶስት ሰዓት ህንድ ፊልም የሚወጣው ጭብጥ ስለመሆኑ አመናችሁልኝ?

“ባንቺዬ እንደውለታ ቆጥረሽ ዋዪልኝ:: ቆይ አንቺ አድቬንቸር ትወጂ የለ? እንደሱ ቁጠሪው: ትንሽ ጭምትነት ከማብዛቱ
ውጪ ዳጊም ቢሆን የሚደብር ወንድ አይደለም:: በማሪያም?
በምትወጂው ነገር ይሁንብሽ እንቢ እንዳትዪኝ? ስሞትልሽ? ቅበሪኝ በቃ!" እሷ ይሄን እያለች እዚህ ታሪክ ውስጥ ያልገባኝ
ነገር እንዳለ አሰላለሁ።

ቹቹ እኔ በምሰራበት መንግስታዊ ያልሆነ የውጪ ሀገር በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ የስራ ባልደረባዬ ናት። ወሬ
አፍቃሪነቷ ቅጥ የለሽ ቢሆንም የልቧ ገራገርነት ይይዘኛል። ቁርስና ወሬ ቀርቦላት ምርጫ ቢሰጣት ወሬ በሻይ ትመርጣለች።አንዳንዴ ከእውነቴ አወራታለሁ:: ብዙ ጊዜ ግን ትሰለቸኛለች።
ቢሆንም ስለራሷ የወደቀ ስሜት ስለሚሰማት ታሳዝነኛለች።ወሬዋ እበጂ እበጂ ቢለኝም 'አልሰማሽም'ብያት አላውቅም።እሷም ሰሚ አገኘው ብላ ነው መሰለኝ አታዝንልኝም። የረብ የለሽ ቀዳዳዋ ማራገፍያ ታደርገኛለች። የዛሬ ስልቀጣዋን ለየት የሚያደርገው ጆሮ የሚይዝ ረብ ስላለው ነው፡፡ ቢያንስ ቅደም ተከተል አለው:: ቢበዛ ደግሞ የስልቀጣው ቅጥያ አካል መሪ ተዋናይ እኔ እንድሆን መፈለጓ የሆነ ቶሎ ቢያልቅ የሚያሰኝ ትረካ ዓይነት ቅብ አለው።
በእርግጥ እብደት ቅልቅል ቅብም አለው።

ናዝሬት የሚኖሩት የዳግማዊ ቤተሰቦች እኔ ቬሎ ካለመልበሴ ውጪ ሰርግ ቀረሽ ድግስ ደግሰው አስር ዓመት ያላዩትን
ልጃቸውን እና አግብቻለሁ ብሎ የዋሻቸውን ሚስቱን (እኔን) ሲቀበሉን ነበር ሀቀኛውን እብደት ማበድ የጀመርኩት።እናቱ ለሰአታት ያልቆመ እምባቸውን እያፈሰሱ አገላብጠው ሲስሙኝ እና ቤተዘመድ በስለት እንደወለዱት ጨቅላ በስስት
ዓይናችንን እያዩ ሲመርቁን መሀከላቸው
ቆሜ ሚስቱ አይደለሁም' ማለት ዳድቶኝ ነበር፡፡ዳግማዊ ከአዲስ አበባ ጀምሮ
ለመድረክ እንደሚለማመዱት ተውኔት ሲደጋግም የነበረውን ውሸት ለሚታክት ያህል ጊዜ ሲዋሽ ስሰማው ጆሮ እየመረጠ የሚስማ ቢሆን ተመኘሁ።

ከተጋባን ሁለት ዓመታችን ነው። እሷ ትምህርት ላይ ስለሆነች
ነው ለጊዜው ልጅ የመውለዱን ሀሳብ ያራዘምነው:: ትምህርቷን አቋርጣ ስለመጣች እሷ ከሦስት ሳምንት
በኋላ ትመለሳለች::......" ከታደሙት ሰዎች መሃከል ስለጋብቻችን
ለጠየቀው ሁሉ ያለመሰልቸት እነዚህን መልሶችና ምክንያቶች ይደረድራል።

ጥንቅቅ ያለ ስርዓታም መሆኑ ልብ የሚስቅዝ ነገር አለው፡፡ሰዎች በየቦታው ፍፁም ትክክል መስለው ሲታዩ ሰውኛ
አይመስለኝም።ከራሱ እየተቧቀሰ ከካባቢው በቀረፀለት የትክክለኝነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ
አሳዛኝ ይመስለኛል። ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ፡፡ ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም:: ራስን ለመሆን ጥንቃቄ አያሻም፡፡ መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋ ጥቂት እብደት፣ ጥቂትም ስህተት፣ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ::
ከአራት ሰዓት ባልበለጠ ከመላው ቤተሰቡ እና ወዳጆቻቸው ጋር በነበረኝ ሰርግ መሰል ቆይታ የገባኝ ነገር ሁሉም ለዳግማዊ ልክ አልባ ፍቅርና ክብር እንዳላቸው ነው፡፡ ቆንጅዬው ወንድሙ
ቢኒያምና የመጨረሻዋ እህቱ ቅድስት ዓይኑን እንኳን በድፍረት እያዩ አያወሩትም በእርግጥ እርሱም ለእናቱ ያለው ፍቅር
እና ለቤተሰቡ የሚያደርገው ጥንቃቂ የልክፍት አይነት ነው።የዚህ ትስስር ቋጠሮ የተለየ ነገር እንዳለው ቢገባኝም
አልጠየቅኩትም፡፡

የዚህ ቀሽም የቹቹ ድርሰት ዋና ገፀባህሪ ለመሆን ስክሪፕቱን እንዴት እንዳነበብኩት እና እንዳሳመነኝ ልንገራችሁ።

ቹቹን ካወቅኳት ጀምሮ ስለ አዳዳ ቸርነት አውርታ አይበቃትም::
ደጋግሜ ከመስማቴ የተነሳ አንድ የሆነ መንደር ውስጥ የማውቃቸው ሴትዮ ሁሉ ይመስሉኛል:: አዳዲ የዳግማዊ እናት
ለቹቹም አሳዳጊዋ ናቸው:: በልጅነቷ አባቷ ሲሞት እናቷ ለቅርብ ወዳጃቸው ለአዳዲ እንዲያሳድጓት በአደራ ሰጥተዋት ነው ዛሬ ከእናቷ በላይ የምትወዳቸውን አዳዳን ያገኘቻቸው:: ምንም ዓይነት የደም ትስስር እንደሌላቸው ማውራት አትፈልግም።የሴትየዋን ጥሩነት በዝምድና ትስስር ስትለዋውሰው ግራ
ይጋባኛል። በምን ሂሳብ በደም መቀላቀሉ የሴትየዋን እንደሚያከብደው አይገለጥልኝም:: እንደ እኔ እንደውም ያለ
ምንም ደም ግምድ ደግ መሆናቸው ዋጋቸውን የሚጨምረው ይመስለኛል።

እኔ እንኳን በማስታውሰው መጠን አዳዳ ብዙ ጊዜ ታመው የዕድሜያቸው ፍፃሜ ጫፍ ላይ እየተንጠለጠሉ ከሞት ጋር
ተጨባብጠው የተመለሱበትን ወቅት በቹቹ ስራ መቅረትና መምጣት አስታውሳለው። ተለይቷቸው አሜሪካ ከገባ ዓመታት ለሆነው እና በየቀኑ ድምፃቸውን ካልሰማ ለማያምነው ዳግማዊ የእናቱ በሰበብ አስባብ ራሳቸውን እየሳቱ ሆስፒታል መገኘት
ከእርሳቸው እኩል ከሞት ጋር እንደመፋጠጥ ጭንቅ እንደነበረው
ቹቹ ከነገረችኝ በላይ ቤተሰሱን ስቀላቀል ገብቶኛል። ዳግማዊ የእናትየው በየእለቱ
ሚስት አግብተህ ዓለሜን ኣሳየኝና ከሞትኩም አይቆጨኝ ጭቅጭቅ ሲበረታበት ነው አንድ እለት ታመው ከሞት አፋፍ እንደተመለሱ “ሞቼም ቢሆን እኮ ይኸው ነበር::' ሲሉት አዳልጦት አግብቻለሁ ያላቸው:: የአንድ ቃል
ቅጥፈት ይዛበት የምትመጣውን የተግተለተለ መዓት በዛች ቅፅበት አላሰባትም ነበር። ሚስቱን ከቤተሰቡ ጋር ማስተዋወቅ እንደ ልጅ ግዴታ መሆኑም አልተገለጠለትም። ምናልባትም
ከእናቱ የቅፅበት እልልታ ጋር ሲያነፃፅረው የተናገረው ውሽት ክብደት አልገዘፈበትም

“መዋሸት አይታክትህም?" ብዬው ነበር በሰርግ መሰል ዝግጅቱ ላይ የታደምን ቀን ማታ እንደ ባልና ሚስት ወደ ተዘጋጀልን መኝታ ቤት እንደገባን፡፡

“አብረን እየዋሸን ነው::” አለኝ ኮስተር እንዳለ። ምንም እንዳልመሰለው
ለማስመሰል ይሞክራል እንጂ መዋሸቱ
እንደጎረበጠው ያስታውቅበታል፡፡

የቀጠፈውን ቅጥፈት እናቱ ቢያውቁ ሊፈጠር የሚችለው ቀውስ
ለብቻው ከሚሸከመው በላይ ስለተቆለለበት ነበር ከቤተሰቡ በተለየ
በእድሜ ለምትቀርበው እና እራሱን ሆኖ ለሚያወራት ቹቹ እውነቱን የነገራት እና የውሸት ጋብቻ የመፍጠሩን ድርሰት
የፃፈችው እርሷ ናት። ይሄ ድርጊት ለእኔ ብቻ ይሆን ቅሽምና የመሰለኝ አልገባኝም ምክኒያቱም ዳግማዊም የተሻለ መፍትሄ
በማጣቱ ይሁን ወይም ስለኔ
👍5
ያወራችለት ነገር እንዲተማመንብኝ አድርጎት ባልገባኝ ምክንያት አይቶኝ እንኳን የማያውቀኝን ሴት እንደሚስት በቤተሰቡ መሃከል
እንድንጎማለል ለመስማማት ከጥቂት ቀናት ያለፈ ጊዜ አልፈጀበትም።

የቹቹ ልመና አልዋጥ ብሉ ጉሮሮ ላይ
እንደተሰነቀረ ጠብሰቅ ያለ እህል ትንፋሼን አሳጠረኝ፡፡ ነገሩ የሚሰጠኝን ትርጉም እንኳን ሳላመዛዝን ተስማማሁላት፡፡

ምናልባት በህይወቴ የመጀመሪያው የራሴን ምቾት ሳላሰላ ለሰው ብዬ ያደረግኩት ድርጊት ይመስለኛል። ለዳግማዊ የውሸት ሚስት ለመሆንና ለቤተሰቡ ለመዋሸት አይደለም አሳማኝ
ጭራሹኑ ምንም ምክንያት ለራሴ መስጠት አልችልም።በምክንያታዊነት ስሌት የነፈዝ ድርጊት መሆኑን በጭንቅላቴ
ባምንም ደመ ነፍሴ ግን እያደረግኩት ያለሁት ነገር ተገቢ እንደሆነ አሳምኖኛል። ደግሞስ የሰው ልጅ እያንዳንዱ እርምጃና
ድርጊቱን ከምክንያት ጋር ማጋባት ይችላል? በአብዛኛው የድሮ የአማርኛ ልብ ወለድ መፅሐፎች ላይ ያሉ ገፀ-ባህሪያት ናቸው ፍፁምና ለየሰከንድ እርምጃቸው እንከን አልባ ምክንያት
የሚጠቀስላቸው። ስጋ ለበሱ የሰው ልጅ
በምክንያት የማይቀምራቸው ቁጥር አልባ ሀሳቦች፣ እምነቶችና ድርጊቶች አሉት። ለዳግማዊ ሚስት ለመሆን የወሰንኩት ውሳኔ ከእነዚህ እንደ አንዱ ነው። ይሄም ቢሆን ጥያቄ አልባ አይደለም፡፡ አንዳንዴ
“ምን ሆኜ ነው ግን?” እላለሁ፡፡ ግን አላፈገፈግኩም።

ዳግማዊ ወደ ቤተሰቦቹ ሳይወስደኝ በፊት ለአራት ቀናት አዲስ አበባ ቹቹ
ቤት ለሶስት አብረን በማሳለፋችን እንደቤተሰብ ትንሽ ለመተያየት ጊዜ ነበረን።የማይስበኝ ዓይነት ፊት ነው ያለው። ጅል የሚያስመስሉት ያሞጠሞጡት ጉንጮቹ ሲስቅ ከመለጠጣቸው የተነሳ ትንንሽ ጆሮቹን ሊከልሏቸው ይቅረባሉ። ጉንጫም ወንድ ከጀርባ እንኳን ባላየው የቅርፃም ሴት ዓይነት ቂጥ ያለው ይመስለኛል።

የዳግማዊን ግን ልክ ነኝ የሶስት ሳምንት ፈቃድ የሞላሁ እለት ቹቹ በደስታ ሰክራ ጠረኗ እራስ ምታት ቢያሲዘኝም የሚከረፋ ብብቷን ገልባ
ልታቅፊኝ ስትንደረደር ታቀፍኩላት፡፡ አንዳንዴ ይህቺ ሴትዮ የሸራ ጫማዋን ገበር በብብቷ ይዛው ነው እንዴ የምትዞረው? እላለሁ። ደግሞ በሁሉም አለባበስ ያለሽራ ጫማ እትጫማም።
ስለሚመቸኝ ነው' ትለኛለች ። የሽራዋ ክርፋት ቢታጠኑት እንደ ዲኝ፣ ቀበርቾ፣ ጎማ ምናምን ቡዳ የሚያስለቅቅ ይመስለኛል፡፡

ሰው እንዴት ሁሌ ይጠነባል? ሳስበው ሰላሳዎቹ አጋማሻ ላይ ብትሆንም ከምታገኘው ወንድ ጋር ሁሉ ከአንድ ለሊት የዘለለ የፍቅር ታሪክ የሌላት ለዚህ ይመስለኛል። በእጅ አዙር እንድትፀዳ ልነግራት ብዙ ጊዜ ሞክሪያለሁ ይብሱኑ ራሷን በንፁህ ሂሳብ አስልታ ሰዎችን ስትፀየፍ ሳያት ለራሷ የሰጠችውን
የንፁህነት ግምት የምፈጠፍጥባት ስለሚመስለኝ ዝም እላታለሁ። ትክክል የሆነው እውነቱን እንድታውቅ ማድረጉ
ቢሆንም በእኔ ምክንያት ለደቂቃም ቢሆን የወደቀ ስሜት እንዲሰማት ማድረግ ያቅተኛል። አንዳንዴ ትክክል መሆን
ብቻውን ዋጋው ትልቅ አይመስለኝም:: የሚቀበለው ሰው ጋር የሚረግጠው ቁም ነገር ይመስለኛል ትክክል የሚያስብለው
ምንስ ልክ ቢሆን ከማቅናት ይልቅ ካደቀቀ ልክነቱ የቱ ጋር ነው?

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ። 🙏
👍2
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ (🔞)


#ኤርሚ_ጂግሎ

ዕሁድ ጠዋት…። ማንንም ማግኘት የማልፈልግበት የግል ክፍለ ጊዜዬ ናት። አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስሞኑን የጀመርኳትን መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር። አብሮ አደጌ ፌሩዝ ናት ከለንደን የላከችልኝን። “fifty Shades of Grey” ይላል ርዕሱ፡፡ አንድ ክርስትያን ግሬይ የተባለ የ27 አመት ወጣት ቢልዬነር
የሚመራውን ድብቅ የፈንጠዝያ አለም የሚተርክ መጽሐፍ ነው። ዋናው ባለታሪክ በወሲብ ወቅት ሴቶችን በማሰቃየት እርካታን የሚያገኝ ካዲስት ነው። ፌሩዝ «ብዙ ሚሊዮን ፈረንጅ በሸሚያ ያነበበው
ነው ሲባል ሰምቻለሁ፤ እኔ እንደምታውቂው ማንበብ አልወድም፣ አንቺ መጽሐፍ ማንበብ ስለምትወጂ
ነው የላኩልሽ» ብላኛለች። ምን አይነት መጽሐፍ ቢሆን ነው ብዬ ነበር የጀመርኩት።
ከጀመርኩት በኋላ ግን ታሪኩ ለማቆም ቸገረኝ፡፡

ሞባይሌ ስታቃጭል ያቆምኩበትን ገጽ ከአናቱ ላይ አጥፌ ከአልጋዬ በመውረድ ስልኬን ቻርጅ ወደ ሰካሁበት ቡፌ አመራሁ። ስልኬን ማጥፋት ረስቼ እንጂ እሁድ ጠዋት ማንንም ባላናግር ደስ ይለኝ ነበር።

የሞባይሌን ስከሪኔ "Ermi Gigolo” እንደደወለ ነገረኝ። ፈገግ አልኩኝ። እንደዚያ ብዬ ስሙን ሴቭ ማድረጌ ልክ አልነበረም።
ጂግሎ(Gigolo) የሚለው ቃል ኤርሚያስን የሚገልፅ ቢሆንም ስልኬ ላይ በዚያ ስም ሴቭ ማድረጌ ትክክል እንዳልሆነ ታውቆኛል። ጂግሎ ማለት በእንግሊዝኛ ከሴቶች ገንዘብ ተቀብሎ የወሲብ አገልግሎት የሚሰጥ ወንድን የሚወክል ቃል ነው።ስለዚህ ኤርሚን ይገልፀዋል።ሆኖም ይሄ ደዋዮቼን በቀላሉ ለማስታወስ በሞባይሌ ላይ ከዋና ስማቸው አጠገብ የማሰፍረው ቅጽል ከዚህ በፊት ብዙ መዘዝ አምጥቶብኛል

ለምሳሌ አንድ ምሽት ዳንኤል ከሚባል የብስኩት ፋብሪካ ያለው ወዳጄ ጋ እየተዝናናሁ ሳለ ሽንቴ መጣ ተነስቼ ባዝ ሩም ሄደኩ። ለካንስ ሞባይሌን እዚያው ጠረጴዛው ላይ ረስቼው ነበር። ከመጸዳጃ ቤት ስመለስ ዳኒ እሳት ለብሶና እሳት ጎርሶ ጠበቀኝ። የሚያስጠላ የስድብ ናዳም አወረደብኝ። መፃዳጃ ቤት
በሄድኩበት ቅጽበት ለካ የኔን ስልከ አንስቶ የራሱን ቁጥር ሲደውል እኔ የሱን ስልክ ሴቭ አድርጌዋለሁ።ሴቭ ማድረጌ አልነበረም ችግሩ። ሴቭ ያደረኩት «ዳኒ ቦርጮ ብዬ ነበር።

እኔ ምን ላድርግ ታዲያ! ሺ ዳንኤል ነው የማውቀው። “ዳኒ ኮንትራክተር” ፣ዳኒ አርቲስቱ” ኢምፖርተር”፣“ዳኒ ካናዳ"፣"ዳኒ ቦርጮ፣"ዳኒ ዲዛይነር”፣”ዳኒ ሸፋዳ”፣” ዳኒ ሾርት”፣ “ዳኒ ቆለጥ፣ "ዳኒ ፓስተር"

ዳኒ የበገነበት ምክንያት ከቁጣውና ከስድቡ በኋላ ግልጽ ሆነልኝ፤

“ብሽቅ ሸርሙጣ ነሽ! ያ ሁሉ እንክብካቤ እያረኩልሽ ከኔ “ቦርጩ” ብቻ ነው ትዝ የሚልሸ? ይሄ ለኔ ያለሽን መራር ጥላቻ ያሳየኛል። ድሮም ከሸሌ ምን ይጠበቃል! እናንተ ከልብ የሚወዳችሁና
የሚንከባከባችሁት አትወዱም…አንቺ ደህና ሰው ትመስይኝ ነበር፤ የሸሌና የሰይጣን ደህና የለውም "እውነተሸ ነው።"

በንዴት ስልኬን ከመሬት አጋጭቶ ሊሰብረው ሁሉ ቃጥቶ ነበር። ስኮሳተርበት ነው የተወው።

ኤርሚ ጂግሎም ስሙን ምን ብዬ ስልኬ ላይ ሴቭ እንዳደረግኩት ቢያውቅ ምን ሊሆን እንደሚችል ስገምት ዘገነነኝ። ነገ ማታ በመኪናው ከክለብ አሪዞና ፒክ እንደሚያደርገኝ ከተነጋገርን በኋላ ስልኩን ዘግቼ ወዲያው ስሙን ቀየርኩት። Ermi Stud ብዬ ሴቭ አደረኩት። ከgigolo ይልቅ Stud ቢባል ያኮራዋል እንጂ አያሸማቅቀውም።

ኤርሚ ጂግሎ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ከክለብ አሪዞና ይዞኝ ወደ ዮድ የባሕል ምግብ ቤት ወሰደኝ።
ዬድ አሪፍ ክትፎ ከበላን በኋላ ከክለብ ክለብ እየገባን፣ እየጠጣን፣ እየጨፈርን አሪፍ የማይረሳ ምሽት አሳለፍን

ኤርሚ ደም ግፊት ካለባት ሹገር ማሚ ወዳጁ ኑኑሻ ጋ ዱባይ አንድ ዓመት ቆይቶ መመለሱ ነበር።ከኑኑሻ ጋር የተዋወቁት ኤርሚ ጀንግል ጂም ፊትነስ ሴንተር ውስጥ ኤሮቢክስ በሚሰራበት ወቅት ነበር ኑኑሻ የዱባይን መሬት ለመጀመሪያ ጊዜ ከረገጡ የሀበሻ ሴቶች ኣንዷ እንደነበረች ነግራዋለች።
ሃብታም ነጋዴ ናት። እኔና ኤርሚ ጂግሎን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀን ደግሞ ኡስማን ዘ ፒምፕ ነበር።

ኤርሚ ጂግሎ ፈረንጆቹ 'six pack የሚሉት የሚያምር የሆድ ቅርጽ አለው። ፈርጣማና ጡንቸኛ ሰውነቱ ከቁመናው ጋር ተደማምሮ የትኛዋንም ሴት ያፈዛል። አብረን በትዝናናንባት በዚያ ምሽት እንኳ
ብዙ ሴቶች ከቦይፍሬንዶቻቸው እቅፍ ዉስጥ ሆነው ኤርሚ ጂግሎን በስርቆሽ ሲያዩት ነበር።

ኤርሚን በአካል ሳላውቀው በፊት መጀመርያ ያወቅኩት በፎቶ ነው። አትላስ ኡስማን ዘ ፒምፕ የትራቭል ኤጀንሲ ቢሮ ዉስጥ ቁጭ ብዬ ኡስማንን እየጠበቅኩ እያለ ሼልፍ ላይ የሚያምር ካታሎግና
አልበም ተቀምጠው አየሁ። መዝዤ ስገልጠው ኤርሚ ጂግሎ የአልበሙን ግማሽ ሞልቶታል።በተለያዩ ፓንቶት፣ በቁምጣ፣ ጥብቅ በሚያደርግ ቦዲ፣ ወንድነቱጋ አበጥ ያለ ነገር እንዳለ በሚያሳብቅ የወንድ ታይት፣ ገጠር ውስጥ በሬ ጠምዶ ሲያርስ፣ ፈረስ ሲጋልብ.የሌለው አይነት ፎቶ…ያልተነሳው
አይነት አነሳስ የለም። መአት ፎቶ ነው ያለው። በሌላኛው አልበም ደግሞ የብዙ ሴቶችን ፎቶ የያዘ ካታሎግ ተመለከትኩ። እሱን ትቼ የኤርሚ ጂግሎን ካታሎግ በድጋሚ እያየሁ ሳለ ኡስማን ዘ ኪንግ
በሩን በርግዶ ገባ። ሰርቆ እንደተያዘ ሌባ ክው አልኩኝ። ምን እንዳስደነገጠኝ ገርሞኛል። ኡስማንም ድንጋጤዬ ገርሞት ምን እያረኩ እንደነበር ጠየቀኝ። ኤርሚ ጂግሎ ሞፈርና ቀንበር ተሸክሞ የሚያምር ገበሬ መስሎ ደረቱን አጋልጦ የተነሳውን እጅግ የሚያምር ፎቶ አሳየሁት። ኡስማን ነገሩ ገብቶት መሳቅ
ጀመረ። ምንድነው ሮዚ! በቆንጆ ወንድ ፎቶ ሴጋ መምታት ጀመርሽ ማለት ነው…” ብሎ የማያባራ ሳቅ ሳቀብኝ፣ በጣም ሳቀብኝ። ሲስቅብኝ ደግሞ ይበልጥ ተሸማቀቅኩ።

ፎቶው ላይ ስለተመለከትኩት ልጅ ጠየቅኩት። አጠር አድርጎ አብራራልኝ።

“ ኤርሚያስ ይባላል…ቱሪስት ሴት ክላይንቶቻችን ጠይም የሐበሻ ወንድ ካልወለድክ ብለው
እስጨነቁኝ፡፡ ጥያቄው ሲበረታብኝ ኤርሚያስን በስንት አደን አገኘሁት፡፡ እንደምታይው ጠይምነነቱና
ቁመናው ይማርካቸዋል ወንዶቻችሁ ጡንቻቸው ደቃቃ ነው» እያሉ ብዙ የመለመልኳቸውን
ወንደች አጣጥለውብኝ ነበር። ኤርሚያስ ነው በመጨረሻ የገላገለኝ…” አለኝ፡፡

ከዚያ በፊት እንደዚያ አይነት ነገር እዚህ እግር ዉስጥ ሰምቼ አላውቅ ስለነበር በጣም ተገረምኩ ኡስማንን አፍጥጬ ስመለከተው ሌላ ነገር የፈለኩ መስሎት
"ችግር የለውም ሮዚ፤ አንድ ምሽት እንዲቸገርልሽ ማድረግ እንችላለን” አለኝ። “ሂድ እዛ ሞዛዛ፣ አስቀያሚ” ብዬው ልወጣ ስል እጄን ይዞ
እስቀመጠኝ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኡስማን በኤርሚ ጉዳይ እንደሳቀብኝ ነው። “እኔ ቢሮ ዉስጥ በኤርሚ ፎቶ ሮዛ ምን ስታደርግ እንደያዝኳት ነገርኳችሁ?” እያለ ለነራኪ አሳልፎ ሰጠኝ። መሳቂያ አደረገኝ ።ራኪ እንኳን ይሄን ጮማ ወሬ አገኝታ....።

ከስንት ጊዜ በኋላ ኡስማን ደውሎ ጊዮን ቀጠረኝ። አብሮት መልአክ የመሰለ ጠይም ወንዳ ወንድ ልጅ
ተቀምጧል። ጥቁር መነጽር በማድረጉ ግን በደንብ አለየሁትም ነበር። ጠጋ ብዬ ሳየው ልቤ ቀጥ ልትል ምንም አልቀራት። ይህን ልጅ የት ነው የማውቀው ብዬ ስጨነቅ "ሮዝ ኤርሚያስ ይባላል...ተዋወቁ" አለኝ እየጠቀሰኝ። አሁን ማን መሆኑ መጣልኝ። ካታሎጎ ላይ ያየሁት ሰው ነው። ኤርሚ ጂግሎ።

ኤርሚን ሰኡስማን ያስተዋወቀችው ደግሞ ሳቢ ናት። ሳቢ ከኡስማን ወፎች ሲኒየሯ ናት። አንድም ቀን ያለማቋረጥ ኤሮቢክስ ስፖርት የምትሰራ ንቁና ታታሪ ሴት ጥሪ ብባል ከሷ ሌላ የማውቀው የለም የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጀምረ
👍51😁1
ው ይተውታል። ሳቢ ግን ሕይወቷ ሙሉ ከጂም ቤት ርቃ አታውቅም
“ሴት ልጅ ገላዋ ሀብቷ ነው፤ ሀብት ደግሞ የትም አይጣልም” የምትለው አባባል አላት። ውብና ሸንቃጣ
ሰውነቷን እንደ ሳቢ በጂምና በአመጋገብ የምትጠብቅ ሴት ከየት ትገኛለች?

ሳቢ ትንሽ ውፍረት ቢያገኛት ወይም በሆነ ምክንያት አማላይ የሰውነት ቅርጽዋ ቢበላሽ ከመቅጽበት ራስዋን የምታጠፋ ነው የሚመስለኝ። ህልውናዋ የተመሰረተው ኡስማን በሚያመጣቸው ነጭ ወንድ ደምበኞቿ ላይ ነው። ነጮች ረጅም፣ ቀጭን፣ ሸንቃጣና አማላይ የሰውነት ቅርጽ ያላትን ሴት እንደሚወዱ አሳምራ ታውቀዋለች። አንድ ቀን ስለ ፈረንጆች ስናወራ “አፍሪካውያን ወፍራም ሴትንና ቀጭን መጽሀፍን፣ ነጮች ደግሞ ወፍራም መጽሀፍንና ቀጭን ሴትን ይወዳሉ።” ብያት ይኸው እስከዛሬ
አባባሉ ከኣፏ አልወጣም። ወንዶች የሚያመልኩሽ ገላሽን አስከጠበቅሸላቸው ድረስ ብቻ ነው” ብላ ታምናለች።

ዞሮ ዞሮ ሳቢ ኤርሚ ጂግሎን አጠመደችው! በጂንግል ጂም ፊትነስ ሴንተር ዉስጥ። ፈጥና ደግሞ ከኡስማን ጋር አገናኘችው።

ኤርሚ መጀመርያ ላይ የኡስማንን ወፍራም ክፍያ ማመን አቅቶት ነበር፡፡ ከሴት ጋር በተዝናናሁ ይሄ ሁሉ ዶላር ከተሰጠኝ እኔ ምን ገዶኝ" ብሎ በሙሉ ፍላጎት ለኡስማን ፈረመ። ኡስማን መጀመርያ ያደረገው ነገር ቢኖር ፈረንጅ ፕሮፌሽናል ፎቶግራፈር ቀጥሮ ኤርሚን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ወስዶ ለሰባት ቀናት ፎቶ ማስነሳት ነበር። ጤፍ ሲዘራ፣ በሬ ጠምዶ ሲያርስ፣ ፈረስ ሲጋልብ፣ ጎጆ ቤት በር ላይ ባላገር መስሎ ቆሞ፣ አረንጓዴ ማሳ ላይ ከብቶችን በገጠር ቁምጣ ሆኖ ሲጠብቅ…ወዘተ። አንድ ሳምንት ሙሉ ከፈረንጅ ፎቶ ግራፈር ጋር ከረመ፡፡ ከዚያ ፕሮፋይሉ ዱባይ ተልኮ በከለር ታትሞ ካታሎግ ዉስጥ ሰፈረ።

ኤርሚ ጂግሎ የወሲብ አገልግሎቱን የሚሰጠው በኡስማን በኩል የሴቶች የበላይነትን ለሚያቀነቅኑትና በገንዘባቸው ወንድን መግዛት እንደሚችሉ የሚያምኑትን የአውሮፓ ፣ የአሜሪካና የአውስትራሊያ ነጭ ሴቶች ብቻ አልነበረም፤ በነዚህ አገራት ብዙ አመት ከመኖር ተመሳሳይ የህይወት ዝንባሌን
ካገኙ እንዲሁም በተለያየ የጤና ችግሮች ሀኪም ወሲብ እንዲፈጽሙ ለሚመከራቸው አበሻ ሴት ዲያስፖራዎችም ጭምር እንጂ። ኤርሚ ከነገረኝ ነገር ሁሉ የገረመኝ ደግሞ ብዙ ሴት ደምበኞቹ ከሴክስ ይልቅ አብሯቸው ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ እንዲታይ መፈለጋቸው ነው።

#የኤርሚ_ጂግሎ_ህይወት_አቀበትና #ቁልቁለት

ኤርሚ ጂግሎ 14 አባላት ካሉት ሰፊ ድሀ ቤተሰብ የተገኘ የምስራቅ ሀረርጌ ልጅ ነው። ከ14ቱ ሁለቱ ብቻ ናቸው ሴቶች። የተቀሩት ወንዶች ናቸው። ሁሉም ወንድሞቹ እንደሱ ረጃጅምና ግዙፍ እንደሆኑ ነግሮኝ ያውቃል። አንድ ተክለሀይማኖት ሲኒማ ራስ አካባቢ ጄኔሬተር የሚነግድ ዘመዱ ኤርሚን ታዳጊ ሳለ አዲሳባ ይዞት መጣ። ኤርሚ በተላላኪነትና በእቃ አውራጅነት መስራት ጀመረ። ገና በታዳጊነቱ ገንዘብ ለመደ። ጡንቻው ፈረጠመ። ገንዘብ ለማግኘትም ጠንከሮ መስራቱ የግድ ነበር። እቁብ
እየጣለና የሚያገኘውን ገንዘብ እያጠራቀመ ኑሮን መታገሉን ተያያዘው። ከልጅነቱ ጀምሮ ስሙኒ እየከፈለ ሲኒማራስ ጀርባ ባሉ ቪዲዮ ቤቶች ፊልም ሲመለከት ያመልካቸው የነበሩት ፈርጣማ ጡንቸኛ የፊልም አክተሮች ሰውነት እንዲኖረው ከፍተኛ ፍላጎት አሳደረ።
ተመሳሳይ ፍላጎት ከነበራቸው የስራ አጋሮቹ ጋ ጎላ ሚካኤል በሚገኝ ስፖርት ቤት ተመዝግቦ ክብደት ማንሳት ጀመረ። አመታት ነጎዱ፡፡ ኤርሚ ተሳካለት። ጡንቻማና ፈርጣማ ሆነ፤ የግዙፍ ወንዳ ወንድ ተከለ ቁመና ባለቤት ሆነ። የትኛዋም ሴት ገና ስታየው ጋሻዋ የመከታዋ! ተገንዋ፣ ከለላዋ እንደሆነ
እንድታስብ የሚያደርግ አንዳች ኃይልን ተጎናጽፏል። ሲበዛ ወንዳ ወንድ ነው፡፡ በዚያ ላይ ዘናጭና እንዴት ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የሚያውቅ ልጅ ነው።

ሁሌም ለአመጋገቡ፣ ለአለባበሱና ለንጽህናው ከፍተኛ ትኩረት ያደርጋል። ገንዘብ እያገኘ ሲመጣ ፍላጎቱም እየጨመረ መጣ። ንጹህና ቅባት ሴቶች የሚበዙበት ጂም መፈለግ ጀመረ። ከሌላ የሲኒማ ራስ ወዳጁ ጋ “ጀንግል ጂም ፊትነስ ሴንተር” በተባለው የከተማዋ ቁጥር አንድ ስፖርት ቤት ተመዝግቡ፡፡
ኤርሚ እንዳወራኝ ከሆነ የጂሙ አብዛኛው ተጠቃሚዎች ሴቶች ነበሩ። ሊያውም ውፍረት፣ ኮሌስትሮል፣ የተበላሸ የሰውነት ቅርጽ፣ የስብና የቅባት ክምችት ያስቸገራቸው ሀብታም ሴቶች። በእግር
እየመጡ ጂም የሚሰሩት እሱና ጓደኛው ብቻ ነበሩ። ከነሱ ውጭ ሁሉም በመኪና ነበር የሚመጣው።ኤርሚ የበታችነት ተሰማው። ሰርቶ መኪና የሚገዛበትን ጊዜ ሲያስበው ካረጀ በኋላ እንደሚሆን
አወቀ። ካረጀ በኋላ ደግሞ መኪና መንዳት ሳይሆን በእግር መሄድ ነው የሚፈልገው። ስለዚህ ቶሎ መኪና የሚገዛበትን መንገድ ሲያማትር ኑኑሻን አገኛት። ኑኑሻ አገር ያወቃት ባለመኪናና ባለሀብት ናት።

"ሮዝ ሙች! በዚያ ጂም ዉስጥ ወንዶች ብርቅ ነበርን። አብሮኝ ተመዝግቦ መስራት የጀመረው ጓደኛዬ አንድ እለት አሳዛኝ ክስተት ገጠመው። በዙሪያው የነበሩ ሴቶችን ትኩረት ለማግኘት በማሰብ ከአቅሙ በላይ የሆነ ግዙፍ ዳምፔል ከማሸን ላይ አንስቶ በጀርባው ተኝቶ በሁለት እጆቹ ሊያነሳ ዳምፔሉ ደረቱ
ላይ ወደቀበት። ተረባርበን ዳምፔሉን አነሳንለት። እሱ ግን አልተነሳም። በነኑሻ መኪና ሐኪም ቤት አደረስነው። ለሶስት ወር አልጋ ይዞ ለመታከም ተገዶ ነበር። ያን ቀን የሱ ዉድቀት ቢሆንም ለኔ
ግን አዲስ ምዕራፍን ከፈተልኝ።

“እሱን ሐኪም ቤት ለማድረስ መኪና የተባበረችን ኑኑሻ እሱን አልጋ አሲዘን ለቤተሰቦቹ ደውለንላቻው እንዲመጡ ካደረግን በኋላ «የት ነው ቤትህ ልሸኝህ» አለችኝ። ሁለታችንም የስፖርት ትጥቅ እንደለበስን ነበር። ደግሞ ልብሳችንን ስፖርት ቤት ትተነው ነበር የወጣነው። ቤቴ ኮልፌ እንደሆነ ስነግራት የሷ
ቤት እዚሁ ሳርቤት ስለሆነ እሷ ጋር ደርሰን እንደምትሸኘኝ ቃል ገባችልኝ። ተስማማሁ። ወደሷ ቤት እየነዳችው “ደግሞ እግርህ በቁምጣ በጣም ያምራል፤” አለችኝ እየፈራች። አመሰግናለሁ» አልኩ በጨዋ ደምብ። ቤቷ በዘበኛ ነው የሚጠበቀው። ዉስጥ ግን ማንም የለም። “ይሄን በሚያከል ቤት
ብቻሸን ስትኖሪ አትፈሪም?” አልኳት። «እፈራለሁ» አለችኝ። ከዚያ በመሐል ረዥም ዝምታ ተፈጠረ።

የምለው ግራ ገባኝ።አየሽ ሮዝ ጅል ነበርኩ ያኔ። እሷ "እፈራለው" ስትል አብሪያት እንድሆን መፈለጓን እየነገረችኝ ነበር ለካ። እኔ ግን ዝም አልኳት።ቆየችና ደግሞ..."ከዚ በኋላ መሽቷል አልሸኝክም ከፈለክ እዚሁ ማደር ትችላለክ"አለችኝ አፍ አውጥታ የሞት ሞቷን።ያን ምሽት ሌሊቱን ሙሉ ሴክስ ስናደርግ አደርን።

በጊዜ ሂደት ኤርሚ የጂም ቤቱ ሴቶች የሚሻኮቱበት ወንድ ሆነ። በውጪ የይምሰል አፍቃሪ ሆኖ እየቀረበ ከሁሉም
ተጠቀመ፡ ጂንግል ጂም ፊትነስ ሴንተር ጤናውን በስፖርት የሚጠብቅበት ብቻ ሳይሆን እንጀራውን የጋገረበት ምጣድ ሆነ። ጂም ቤቱ ኑኑሻና ሳቢን አገናኘው። ከኡስማን ውብ ወፎች አንዷ የሆነችው ሳቢ ደግሞ ከኡስማን ዘ ፒምፕ ጋ አገናኘቸው።

ከኤርሚ ጂግሎ ጋር አብረን በተዝናንበት ምሽት እንዴት ከኡስማን ጋር የሚሰራውን ስራ እርግፍ አድርጎ ትቶ እድሜ በእጥፍ ከምትበልጠው ከኑኑሻጋ ዱባይ መኖርን እንደመረጠ ጠየቅኩት። ጣቶቹን በረጅም ጸጉሩ መለል እያፍተለተለ ከብላክ ሌብሉ ተጎነጨለት፤

"ሮዝ ፤ ከብዙ የህሊና ትግል በኋላ ነበር የወሰንኩት። ከ'መጥፎ' እና ከ‹በጣም 'መጥፎ' ነበር ምርጫዬ።
የሀረርጌ አብሮ አደጎቼና የተክለሀይማኖት ጓደኞቼ የደረሱበትና የሚመሩትን ህይወት እኔ ከምመራው ህይወት ጋ ሳነጻጽረው ህሊናዬ ውስጥ ውስጡን ሊያሳብደኝ ደረሰ። እኔ ለወሲብ ገንዘብ
👍5
የምቀበል
ሸርሙጣ ስሆን እነሱ ትዳር መስርተው ወልደውና ከብደው የክብር ህይወትን ይመራሉ። በዚያ ቢያቆም ጥሩ ነበር። ዘመዶቼና ጓደኞቼ በሆቴሎች፣ በክለቦችና በሌሎች ስፍራዎች ከነጭ ሴቶች ጋ
ሲያግኙን የማያሳምን ሰበብ ፈጥሮ መዋሸቱ ታከተኝ። አዲሳባ እንደምናስበው ሰፊ አይደለችም፤ ጥቂት የመዝናኛ ስፍራዎች ስላሉ በሄድሽበት ሁሉ የምታውቂያቸውን ሰዎች ማግኘትሽ አይቀርም። አንድ እለት ከአባቴ ባልተናነሰ በድሃ አቅሙ ያሳደገኝ አጎቴ ከጨርጫሳ ጀርመናዊት አሮጊት ጋ ሂልተን የዉሃ
ና ፍል ዉስጥ አገኘኝ። አጎቴ ሀብታም ነጋዴ ሆኗል። እኔም ጀርመናዊቷም በዋና ልብስ ብቻ ዉሀ ዉስጥ እየተንቦራጨቅን ነበር። ያን እለት መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ ወይም እዚያው ዉሀ ዉስጥ
ሰምጬ ብቀር ደስተኛ ነበርኩ። አየሽ ሮዚ! በሕይወታችን ደስታ የሚሰጡ የሚመስሉን ነገሮች ፍጹም ደስታ የሚያርቁን ናቸው፤ እኔ ሲኒማራስ በያይነቱና ሽሮ በልቼ ስውል የነበረኝ ደስታ ከኡስማን ያን ሁሉ ዶላር እያፈስኩ ከማገኘው ደስታ የበለጠ ነበረ። ፈጣሪ በማይወደው ስራ ዉስጥ እስካለሽ ድረስ
ህሊናሽ እንደመርፌ እየወጋ ሰላምሸን ይነሳሻል…”

ድንገት የኤርሚን ፊት ትካዜ ወረሰው፤ ለአፍታ በመካከላችን ዝምታ ሰፈነ። ዝምታውን መስበር ፈለግኩና አፌ ያመጣልኝን ጥያቄ ጠየቅኩት፤

"አጎትህ ሲያገኙህ ግን ምን አሉህ?"

ኤርሚ ባልጠበኩት ሁኔታ በቁጣ አፈጠጠብኝ፤

“ቆይ እኔ የምለው ሮዝ፤ ለምንድነው ጥያቄ የምታበዢብኝ?የሕይወቴን ሲሶ ከሴት ጋር ነው ያሳለፍኩት ያንቺን ያህል የምትጠይቅ ሴት አላየሁም።በፈጠረሽ ጥያቄ አታብዥብኝ ጥያቄ አልወድም በተጠየቁ ቁጥር ለፍረድ የቀረብኩ ይመስለኛል ህሊናዬ የሚጠይቀኝ አንሶ ደግሞ አንቺ..."

ክው ብዬ ቀረሁ። በሰላም እያወራኝ ድንገት ሲቆጣኝ ቀልቤን ገፈፈው፡፡ በሌላ እንዳይጠረጥረኝ ብዬ ዝምታን መረጥኩ፡ከአፍታ በኋላ የጨዋታ ርእሱን ቀየርከት። በራሱ ጊዜ ካላወራ ምንም ጥያቄ ላለማንሳት ወሰንኩ።ከብዙ ዚጠጥና ጨዋታዎች በኋላ ጥቂት የመቆስቆሻ ሀሳብ ሳቀርብለት ሳያስበው ምክንያቱን መናገር ጀመረ።

“በየሆቴሉ፣በየክለቡናበየመዝናኛስፍራው ከነጮቹ ጋ ሆኜ የማገኘው የቅርብ ሰው ሲበዛብኝ ከአዲሳባ ርቄ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ። ከቱሪስቶቹ ጋ ሆኜ የማገኛቸው ጓደኞቼና ዘመዶቼ ሁሉ ስራዬን የሚያውቁብኝ እየመሰለኝ በሀፍረት ልቀውስ ደረስኩ። ከፈረንጆቹ ጋ በመንገድ ላይ ስሄድ ለደቂቃዎች
የሚያፈጥብኝ ሁሉ ሸርሙጣነቴን ጠንቅቆ የሚያውቅ ያህል ተሰማኝ። በጣም ተጠራጣሪ ሆንኩ።
አዲሳባ መኖር የጀመሩት 2ቱ ታናናሽ እህቶቼ ስራዬን ሲያውቁ የሚሰማቸውን አስቤ ተረበሽኩ፣እንቅልፍ አጣሁ። ማንም የማያውቀኝ ሩቅ አገር መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ። በዚህ መብሰልሰል መሀል ነበር ኑኑሻ ወደ አእምሮዬ የመጣቸው። ዱባይ አብረን እንድንኖር ብዙ ጊዜ ትወተውተኝ ነበር። ኑኑሻ በጣም እንደምትወደኝ አውቃለሁ፥ ሮዝ ሙች! በጣም ነው የምታፈቅረኝ። ከሷ ጋ የነበረኝን ግንኙነት
አለመቁረጤ ጠቀመኝ። ከዚያ ሁሉ ጊዜ በኋላ ደውዬ ሳገኛት ፊትዋን አላዞረችብኝም። የሌት ተቀን ሀሳቤ በተገኘው አጋጣሚ አዲሳባና ኢትዮጲያን መልቀቅ ነበር። ተሳካልኝ፤ ከዚያም በየሰከንዱ ህሊናዬን ክፉኛ ከሚቀጠቅጠኝና ቀና ብዬ እንዳልሄድ ካደረገኝ ቆሻሻ ህይወት ወጣሁ፤ አሁን የኑኑሻን ንግድ በበላይነት የማስተዳድር የቢዝነስ ሰው ሆኛለሁ…” ካለኝ በኋላ በረዥሙ ተነፈሰ። ዝም ተባባልን።

“..ይቅርታ ግን እሺ፤ሮዝ

“ለምኑ?”

ቅድም ሳላስበው ጮህኩብሽ መሰለኝ?”

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍21
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ_2 ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ (🔞) ፡ ፡ #ኤርሚ_ጂግሎ ዕሁድ ጠዋት…። ማንንም ማግኘት የማልፈልግበት የግል ክፍለ ጊዜዬ ናት። አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስሞኑን የጀመርኳትን መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር። አብሮ አደጌ ፌሩዝ ናት ከለንደን የላከችልኝን። “fifty Shades of Grey” ይላል ርዕሱ፡፡ አንድ ክርስትያን ግሬይ የተባለ የ27 አመት ወጣት ቢልዬነር የሚመራውን ድብቅ የፈንጠዝያ አለም የሚተርክ…»
#መመለስ

ሂጂ ጥርግ በይ
እንዳልጎዳብሽ በማግስቱ ግን ነይ
በማግስቱ ስትመጭ ጉዳቴ ተሰምቶሽ
አክመሽ ጉዳቴን ወዲያው እንዳልጠላሽ
ሂጂ ተመልሰሽ
ነይም ሂጂም የሚል መመለስ የሚሉት
ናፍቆትሽን ይዘሽ

🧿በበረከት ታደሰ🧿
#ጮማና_ሽንብራ

ጮማዬን ደብቄ ብቻዬን ልበላው
ጣፋጩን እርጎዬን ሸሽጌ ልጠጣው
ድርቡን ሸማዬን ደብቄ ልለብሰው
ድሃ ጎረቤቴን ምንም እንዳያምረው
"ቸግሮኛል" አልኩት "ለአፌ እቀምሰው"
ጮማዬን ሸሽጌ እጦቴንስነግረው
ድሃ ጎረቤቴን እምባ ተናነቀው
"እኔ አለኝ!" እያለ ሄደ ከቤት ወጣ ሽንብራውን ይዞ ሊያካፍለኝ መጣ።
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_ሁለት


#በሜሪ_ፈለቀ

...ዳግማዊ ስለእኔ ከሰማው ውጪ አብሮኝ በነበረው ቆይታ ሊያውቅ የሚችለው ነገር መኖሩን እንጃ! ነገሩ እኔስ ምን አውቃለሁ? ስለእርሱ አይደለም እኮ አረ ስለራሴ..ስቆላል አይደለም። የሚያውቁኝ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ሲሉ
እሰማለሁ። ዳሩ እንኳን ሌሎች እራሴም ስለራሴ ነኝ' ያልኩትን ላልሆን እችላለሁ።

#አስቀያሚ_አይደለሁም

እግዜር የስሜት ባለቤት ከሆነ የእርሱን ፈገግታ የመሰለ ውበት አለሽ ባሉኝ ማግስት ምን ያደርጋል የሰከነች
አይደለችም ይሉኛል ፤ ፈገግታሽ የሰማይ መልአክትን መጎናፀፊያ ይመስላል ባሉኝ ማግስት እንደሸርሙጣ ታስካካለች ይሉኛል ፤ የሰውነቴን መዋቅር ከምርጥ ቀራፂ ውብ ቅርፅ ጋር ባነፃፀሩት ማግስት ክብሯን አትጠብቅም ለስሜቷ ትተኛለች ይሉኛል።

#ያላዋቂ_አይደለሁም

ቤተሰቦቼን እና በደቦ ያሳደጉኝን የሰፈሬን ሰዎች ጨምሮ የሚያውቁኝ ሁሉ ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ማስተርስ
በማዕረግ መጨረሴን አድንቀው ሳይጨርሱ ምን ያደርጋልኀቆማ መቅረቷ ነው ይላሉ።ማወቅ የሚሹት ነገር ሲኖር
እንዳልጠየቁኝ፣ የዕለት መፍትሄ ሲሹ እንዳላማከሩኝ፤በኪሎ የሚበልጣትን መፅሐፍ ይዛ የምትዞር ጉረኛ ናት
ይሉኛል፡፡

#ስሜት_አልባ_አይደለሁም

ዛር እንዳለበት ባለውቃቢ አብሮኝ እንዳላበደ፣ የሚያደርገኝ ጠፍቶት በስሜት እንዳልሰከረ የሱ እብደት ጎበዝ
ሲያስብለው የኔ ያለመሽኮርመም ብዙ ወንድ የምታውቅ ባለጌ ያስብለኛል።

#አመለ_ቢስ_አይደለሁም፡፡

ግልፅነቴ ደንቆት አንቺን ያገኘ ወንድ አፈስ ባለኝ ቅፅበት
“ለምን ታዲያ አንተ አታፍሰኝም?” ስለው “ሴት ልጅ እንዲህ እትልም” ይለኛል።

#አላማማኝ_አይደለሁም

ሀይማኖቴ ፍቅር ነው። የሰውን ልጅ ሁሉ መውደድ።ራሴን እወዳለሁ። ለዛ ነው ሌሎችን የሚወድ ልብ ያለኝ፡፡

ለራሱ ፍቅር የሌለው ለሌላ ተርፎት የሚለግሰው መውደድ ብትሉኝ ያንቀኛል። በሰውኛ ልኬት ሰውን የመውደድ ጣሪያ ራስን ከመውደድ ልክ መሆኑን ለማሳየት
ይመስለኛል ክርስቶስ ከህግ ሁሉ የበላይ ህግ የትኛው መሆኑን ሲጠየቅ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ' ያለው::
የፈጣሪ ትርጉሙ ለኔ ፍቅር ነው። የማላየውን ፈጣሪ ማምለክ እና መውደድ በአምሳሉ በፈጠራቸው በሰዎች
ሁሉ ውስጥ አለ ብሎ ማመን እነሱን ማክበርና መውደድ ነው።

ፍቅር ከክፋት በብዙ የራቀ ነውና ለክፋት የሆነ ልብ የለኝም። አንዳንዶቹ ግን እንደነሱ በሀይማኖት ካባ ራሴን
ደብቄ አለማስመሰሌን እኔኑ እያሙ እዛው ካባቸው ውስጥ ይደበቃሉ። በልባቸው ጠብታ ቅንነት ሳይኖር ለፍቅርና
እግዜርን ለመፍራት የሚኖሩ ያስመስሉታል። እኔ ግን ከክፉ ልብ ከመነጨ ምርቃት ይልቅ በአንድ ልኩ ከቅን ልብ የሆነ እርግማን ይሻላል ባይ ነኝ፡፡ ኡኡቴ ብርጉድሽ ቀርቶብኝ ፈስሽን በያዝሽልኝ ትል ነበር እናኒ ( አክስቴ)
#ንፉግ_አይደለሁም

መስጠት ከመትረፍረፍ አንጀት የሚፈልቅ ወይም ከመብዛት ማዕድ የሚዘገን አልያም ከመበልፀግ ማህፀን የሚወለድ እንዳልሆነ አውቃለው።

መስጠት ከመንፈስ እንጂ ከሌጣ እውቀት የተጋባ 'መክሊት' አይመስለኝም ።(መክሊት ያልኩት መስጠት ከምግባር ስለሚልቅብኝ ነው።መስጠት በትርፍ ካርዶች የምትቆምርበት ሲሆን ለሰማዩ ፅድቅም ለምድሩ ብድራትም መብቃቱን እጠራጠራለሁ።በየእለት ልመናዋ 'የምሰጠው አታሳጣኝ' እያለች የምትለምን ልበ መልካም አክስት ናት ያሳደገችኝ።

#የአራዳ_ደንባራ_አይደለሁም

ባህሌን አክባሪ መሆኔን ባወደሱ ቅፅበት እናትና አባቴ ባወጡልኝ ስም (ባንቺ ወግ አየሁ) ሲሳለቁ እሰማቸዋለሁ።በእርግጥ አንዳንዴ ቤተሰቦቼ ከአስር ተከታታይ ወንድ ልጅ በኋላ በየደብሩና በየደጀ ሰላሙ ተደፍተው እና በየአዋቂውና ውቃቢው ቤት አፈንድጀው የወለዱኝን ሴት ልጃቸውን እንኳን ለግለሰብ ለአንድ ሃገር ኸረ ምን ለሃገር ለአህጉር ራሱ የሚበዛ ዓረፍተ ነገር ስም ከነተጎታቹ ማንዘላዘል ውዴታ ነው ጥላቻ? ብዬ አስባለሁ።'ባንቺ ወግአገኘሁ'የእኔ ስም የኔ መጠርያ ሳይሆን የወላጆቼ ታሪክ ነው ያለፈ ታሪካቸውን የውልደቴ ፈንጠዝያቸውን፣ ምን አልባትም የሰፈር ሰው 'ሴት ልጅ ፍለጋ ደርዘን ወንድ ታቅፋ ሽሙጥ የተቀባበላቸውን ስላቅ የመልስ ምት! ምን አለፋችሁ ያደለው 'የህይወቴ እርምጃ ከአፍ እስከገደፉ' እያለ መፅሐፍ ይፅፋል የኔ ቤተሰቦች የህይወት ታሪካቸውን ለዓመታት እንዲነበብ በኔ ስም በደማቁ ፅፈውታል።የሚጠራኝ ሁሉ ያነብላቸዋል።

እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል።ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ።ከሰመሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን ዕድል አይሰጡህም ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረብያ ይስላሉ።ልብህን ከከፈትክላቸው የድርሻቸውን ጠርበዉህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።በእርግጥ በአንድ ነገር እስማማለው። እሳት ሳይኖር ጭስ የለም።እሳት ባህሪዬን ከሚያንቀለቅሉት እና ከሚያሰሙኝ ምክንያቶች አንዱ የቢኒያም አይነት ወንዶች ናቸው። የማልቋቋመው 'ወንዳም ውበት' ያላቸው ወንዶች!! ወንዳዊ ውበት የምለው የሰፋ ደረትና ትከሻ ወይም የጎላ አይንና ሰልካካ አፍንጫ አልያም ረጅም ቁመና አይነት የአካል ውቅረቶች አይደሉም።የሆነ እንቅስቃሲያቸው አስተያየታቸው የከንፈር እንቅስቃሲያቸው፣ አስተያየታቸው፣አረማመዳቸው፣የድምፃየው ምት፣አሳሳቃቃቸው፣ ወዘተ ተረፈ....ሽፍደት ያለበት አይነት ጥቂት ወንዶች አሉ። ቢኒ የውሸት ባሌ የዲጉ(ዳግማዊ) ታናሽ ወንድም ከጥቂቶቹ ነው። ገና የወንድሙን ሚስት ሲተዋወቀኝ ነበር።

"ኖ.....ኖ.....ባንቺ አትባልጊ" ያልኩት ለራሴ

በነገራችሁ ላይ ቤተሰቡ በቁልምጫ የመጠራራት ክፉኛ ጥንወት የተጠናወተው ነው። ዳግማዊ-ዲጉ፣ ቅድስት-ኪዱ፣ ቢኒያም-ቢኒ.....እናትየውን ዲጉ 'እናቴ' እያለ ነው የሚጠራቸው፣
ኪዱ 'እታባ' ቢኒ 'እማዬ' ፣ ቹቹ እና የሰፈር ሰው 'አዳዳ'. ...አሁን በናታችሁ ባንቺ ወግ አየሁ ሲቆላጰስ 'ቤች',ይሆናል?....የገረመኝ ሌላ ቁልመጫ የዲጉ ጓደኛ ስም ነው። ስሙ አበጀ ነው።ሲጠሩት 'አጄ' ብለውት እርፍ!!

"የክለብ አመልሽን አልነገርኩትም። ለሶስት ሳምንት ጨዋ መሆን መቼም አያቅትሽም ።" አለችኝ ቹቹ አዳ ከቤተሰቡ ጋር አቀባበል የተደረገልን እለት ማታ ወደ ጆሮዬ ቸጠግታ።

ታውቃለች።የሚያውቁኝ ያውቃሉ። ትንሽዬ ልብ ናት ያለችኝ።ቶሎ የምትግል ቶሎ የምትበርድ። በትንሽዬ ደስታ ምቃ ከደረቴ ልታመልጥ ትፈነጥዛለች። በሚጢጢዬ ሀዘን በረዳ በደረቴ ውስጥ ሟሽሻ ትጠፋለች።ጥሎብኝ በግራ ወይም በቀኝ ጠርዝ የመንጠለጠል ልክፍት ከጥግ እያላተመኝ መካከለኛ አመለካከት ሀጥያት ይመስለኛል። ስለእውነቱ ይሄ የኔ ብቻ ችግር መሆኑን እጠረጥራለሁ።አብዛኞቻችን የተጠረቅንባቸው ጎራዎች ሁለት ፅንፍ ይመስሉኛል። መካከለኛ የሚባል ነገር የማናውቅ እንበዛለን።ወዳጅ ወይም ጠላት፣ህይወት ወይም ሞት፣ መልካም ወይም ክፉ፣ ደጋፊ ወይም ተቃዋሚ....

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሁለቱም ጠርዞች ስላተም፣ ስፈነጥዝም ሳዝንም የሚያበርደኝ ሁካታ ሆኗል።በሁለቱም ዋልታ ስናኝ ከሰው ጋር ማውራት ደስ አይለኝም ። የማደርገው እንደዚህ ነው በፊት በፊት በፀጥታ ረዥም መንገድ በእግሬ መጓዝ በመጠኑ የሚያበርደኝ መድሃኒቴ ነበር።አሁን ግን አብዛኛው እንዲህ ባሉ ቀኖቼ ለዳንኪራ የሚመቸኝን ልብስና ጫማ አደርጋለሁ ፣ ብቻዬን ክለብ እሄዳለው፣ አካሌ ዝሎ እስኪብረከረክ እጨፍራለሁ። ካለማጋነን አይኖችና ቀልቦች የምይዝ ጎበዝ ደናሽ ነኝ። በእንቅስቃሴዬ ስልት በሰውነቴ ላይ የሚደንሱ አይኖች እና ትከሻዬ ላይ ተቆልለው የሚከብዱኝ ቀልቦች ለሁካታው የሰጠሁትን ትኩረት
2👍2😁1
እንዳይሸራርፉብኝ

ተኪላ እጠጣለሁ ያኔ በራሴ እና ከራሴ ጋር ብቻ ነኝ በእርግጥ በእንዲህ ያለ ቀናት መጨረሻዬ ከሆነ ወንድ ጎን ይሆናል።ከሆነ ሰው ጎን መሆኑንና ከሆነ ሰው ጋር መሆን ይለያያል እኮ! በአካል ብቻ አብሮ መሆንና በሁለተና አብሮ የመሆን ነው ልዩነቱ።ከማንም ወንድ ጋር ሆኜ አላውቅም።ከወንዶች ጎን ግን ስሻጥ ኖሪያለሁ።ከየት ያመጣሁት ፈሊጥ እንደሆነ አላውቅም ነጭ ሸሚዝ የሚለብስ ወንድ በራሱ የሚተማመን የሆነ ከጀግንነት ጋር የሚነካካ ነገር ያለው ይመስለኛል።ብታምኑም ባታምኑም ከስንት አንዱ ካልሆነ በቀር የአዲስ አበባ ወንድ ነጭ ሸሚዝ አይለብስም በእርግጥ አንዳንዱ በአቧራ የጠየመ ለነጭ የቀረበ ለብሶ ብቅ ይላል።ሌላኛው ምንጩን የማላውቀው ፈሊጤ ዳንስና ወሲብ ይመሳሰሉብኛል።ጎበዝ የሚደንስ ወንድ የዳንሱ ወለል ላይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አልጋ ላይ እንዳስበዉ እሆናለው።በሰዎች መሃከል በሁካታ ታጅቤ እየተወዛወዝኩ መሆኑ ይረሳኝና የእጁ ንኪኪና የአካሉ እንቅስቃሴ ሁሉ ከሙዚቃው ይልቅ ማቃሰት ያጀበው የራሴ ስሜት ውስጥ ይወረውረኛል በዳንኪራው ወለል ላይ ከሁለት አንዱን ያሟላ ወንድ ሳገኝ አብሬው እደንሳለው።በእንዲህ ያሉ ዉሱን ቀኖቼ ጭፈራ ፣ ተኪላ እና ባለነጭ ሸሚዝ ወይም ጎበዝ ደናሽ ወንድ አንደኛው ከአንዳቸው የማይነጣጠሉ የምሽቱ አካሎች ናቸው።ቹቹ 'የክለብ አመልሽ' የምትለኝ እንደነዚህ ያሉ ቀናቶቼን ስታስታውሰኝ ነው።

ዳግማዊን የውሸት ካገባሁት በኋላ ምንም እንኳን የቤኒን ስበት መቋቋም ቢከብደኝም ከነአመሎቼ የዳግማዊ ሚስት ሆኜ መተወኑን መወጣት ጀመርኩ። ቹቹም ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ። 🙏
👍2
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ(🔞)


#የዊንታ_ማንነት

ቦሌና አካባቢዋን የዊንታን ያህል የምታውቅ ሴት መኖሯን እጠራጠራለሁ። የቦሌ ዙርያን የሌሊት ጉድ እንደ ዊንታ የበረበረ ሰው መኖሩንም እንጃ! ለነገሩ ዊንታን የማታውቅ የዚያ አካባቢ ሸሌ አትገኝም።የአካባቢው ስትሪቶች፣ ኮድ ሶስቶች፣ የክለብና የቡና ቤት ሸሌዎች ጥሎባቸው ዊንታን አይወዷትም፣
ገና ሰፈሩን ስትረግጥ በአይናቸው ቂጥ ነው የሚመለከቷት። ለምን ቢባል ዊንታ እንደነሱ ታጥባ፣ታጥናና፣ ተኳኩላ በሸሌ ደንብ ለብሳ በየሌሊቱ ቢመለከቷትም ከወንድ ጋ ስትሄድ አየናት የምትል ሴት
ግን የለችም። ዝም ብላ በዙሪያቸው ታንዣብባለች። ሌሊቱን ሙሉ ቦሌና ዙሪያውን ታካልለዋለች።የቦሌ መድሃኒአለምና የቦሌ አትላስ ባለመኪኖች መኪናቸውን አቁመው ወይም መኪናቸው ውስጥ አስገብተው ያነጋግሯታል፣ ዋጋ ትደራደራለች፤ ግን ከባለመኪኖቹ ጋ አንድም ቀን ስትሄድ አትታይም።

የቦሌና ዙሪያው ውድ ክለቦች፣ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች ውስጥ ገብታ የፈለገችውን ትጠጣለች፣ በወንዶች ትጋበዛለች፣ ከወንዶችና ከሴቶች ጋ እየተጫወተች አልኮል ትጠጣለች ግን ከግብዣው በኋላ ከማንም ወንድ ጋ ስትሄድ አትታይም። “ከዊንታ ጋ አንሶላ ተጋፍፌያለሁ” የሚል ወንድ በቦሌ ዙሪያ ተሰምቶ አይታወቅም። ይህ ጠባይዋ ለአካባቢው ሸሌዎች ውል አልባ እንቆቅልሽ ሆኗል። በዚህ ሁኔታዋ ግራ የተጋቡት ሸሌዎች ብዙ ነገር ያወሩባታል። ኤሚ በአንድ ወቅት ስለ ዊንታ ሳነሳባት ግንፍል ብሏት እንዲህ ብላኛለች፤

“ባክሽ እሷ ቢዝነስ የምትሰራ ሸሌ አይደለችም፤ እንደ ሸሌ አክት የምታደርግ የመንግስት ጆሮ ጠቢ ነች፤
መልክና ቁመና ሳያንሳት ቢዝነስ የማትሰራበት ሌላ ምን ምክንያት ይኖራታል ብለሽ ነው?እንደነ ኤልሳ
እኛንም እንዳታስቆጥረን ነው የምፈራው."

መሲን ደግሞ በአንድ ወቅት እየጠጣን የድሮ ጓደኞቻችን እያነሳን ስንጥል ስለ ዊንታ የሚገርም ነገር ነገረችኝ"
ሮዝ ሙች እየቃዠሁ አይደለም፤ የሰከርኩ ከመሰለሽም ተሳስተሻል። ከዋናዎቹ ሰዎች ጋ እሌኒን ስብሰባ ስትቀመጥ ሀገዞም አይቷት ነግሮኛል እኮ ነው የምልሽ፤ እኔ በጭራሽ ዊንታ ጆሮ ጠቢ
ስለመሆኗ ተጠራጥሬ ሁሉ አላውቅም። እንዴ ቆይ አንቺ ስታስቢው በሳምንት አንድ እንኳ ቢዝነስ ሳትሰራ እያደረች እንዴት ነው እንደዚያ እየተጫጫሰች፣ እየዘነጠች ልትኖር የምትችለው…። መሲን
ጥርጣሬዋን ሳጣጥልባት ሀገዞምን ስታገኘው ስለዊንታ በደንብ እንደምታውጣጣውና እንደምትነግረኝ ቃል ገባችልኝ።ሀገዞም የዊንታ የረጅም ጊዜ ደንበኛዋ ነው።እሷም "ባሌ" እያለች ነው የምትጠራ።መርማሪ ፖሊስ ሲሆን ሌሎች ግልፅ ያልሆኑ የደህንነት ስራዎቹንም ይሰራል ብላኛለች።

እኔ በበኩሌ መሲም ኤሚም ያሉትን ነገር ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ከብዶኛል። በርግጥ የህውሃት ታጋዮች ድሮ በትግል ወቅት እብድ፣ ለማኝና ዘበኛ ሆነው ደርግን ይሰልሉት እንደነበረ ርእሱን ከማላስታውሰው መፅሀፍ ላይ አንብቤ አውቃለሁ።በዚህ ሰላማዊ ዘመን ግን ሸሌ ጆሮ ጠቢ በየአስፋልቱ እያቆሙ የሚሰልሉ አልመስልሽ አለኝ።

ለምን እንደሆነ አላውቅም ነገሩን አጥርቼ ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት አላስቆም አላስቀምጥ አለኝ። ያን ሰሞን ደግሞ አጋጣሚ ሆኖ በሄርሜላ የልደት በዓል ላይ ዊንታ ተጋብዛ አላገኛትም! ነገሩን እንዴት ላነሳባት እንምችል ግን አልገለጥልሽ አለኝ። ቆይተን ጨዋታው እየደመቀ…ከመጠጡ እየደጋገምንለት
ስንሄድ ሁላችንም ሞቅታ ዉስጥ ገባን። ፈጠን ብዬ ከዊንታ ጎን ተቀመጥኩና ወሬ ጀመርኩ።

“ዊንታ ግን የውነት ጠፍተሻል፣ ደግሞ ባለስልጣን ሆናለች እያሉ እያስወሩብሽ ነው አልኳት።ስቃ ምንም መልስ ሳትሰጠኝ ሌላ ሌላ ወሬ መዘባረቅ ጀመረች። አንቺ በቃ ሁልጊዜ እንዳማረብሽ
ሮዚ ምንድነው ግን ምስጢሩ?…ብላ አሳሳቀችኝ። ወሬ ለመቀየር ያደረገቸው ጥረት ይበልጥ ጥርጣሬ ቢፈጥርብኝም ከዚህ በኋላ ነገሩን ማንሳት ለራሴም አደጋ እንዳለው ሰግቼ ተውኩት።

የሚገርመው ግን ስለ ዊንታ ነገሩ ሁሉ የተዳፈነ መስሎኝ በሌላ ጫወታ ዉስጥ ተዘፍቄ እያለሁ በራሷ ጊዜ ክፍለ-ከተማው በ”ኮምዩኒቲ ፖሊሲንግ” መልምሏት ከማህበረሰብ ደህንነት አጠባበቅ ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በተለያየ ጊዜ መውሰዷን ነገረችኝ። እኔም ይህን ስልጠና መውሰድ
ከፈለኩ ልታገናኘኝ እንደምትችል ገለጸችልኝ። ይህን ጊዜ ጥርጣሬዬ ከፍ አለ። ማን ያውቃል?
Community policing የምትለዋን ነገር ያመጣቻት ሆን ብላ የሚወራባትን አሉባልታዎች እውነትነት ለማለዘብ ብላ ቢሆንስ? በዚያ ላይ ቅድም "ባለስልጣን ሆነሻል አሉ” ብዬ ሸንቆጥ ስላረኳት ለዚያ
ምላሽ እንዲሆን የፈጠረቻት ብልሃት ልትሆን እንደምትችል ጠረጠርኩ።

ከዊንታ ጋር ከሄርሜላ ልደት ምሽት የነበረንን ቆይታ ጨምሮ ነገሮችን በስክነት ለማያያዝ ስሞከር በሷ ዙሪያ የሚወሩት ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ እውነት ባይሆኑም መነሻ እውነት እንዳላቸው ተረዳሁ።

ከስንት ጊዜ በኋላ ደግሞ ለምን መሲ ጮማ ጮማ መረጃ ይዛ አትመጣም። ሀገዞም በስካር መንፈስ ሆኖ ብዙ ነገር ዘባርቆላታል ለካ። መሲ እንደምትለው ከሆነ ሀገዞም ዊንታን በጣም ነው የሚጠላት።ምክንያቱም ከዚህ በፊት ለሴክስ ጠይቋት እስኪ መጀመርያ እከከህን አራግፍ” ብላዋለች።ይሄን በራሱ
አንደበት ነው የነገረኝ አለችኝ። መሲ ከሀገዞም የሰበሰበችው ወሬ ለማመን የሚከብድና ከጠበቅኩት በላይ ዝርዝር ነገር ሆኖ አገኘሁት። አንዳንዶቹ ነገሮች እሱን ራሱ የሚያስጠይቁትና በፍጹም ለመሲ መናገር የሌለበት አይነት ነበሩ። ምናልባት በዊንታ ላይ ቂም መያዙ ምን መደበቅና ምን መናገር እንዳለበት እንኳ እንዳያውቅ ሳይጋርደው አልቀረም።

መሲ ከሀገዞም የሰማችውን ተስገብግባ እንዲህ ተረከችልኝ።

ሀገዞም እንደነገረኝ ዊንታ የመጀመሪያ ተልእኮዋ በ'ክለብ ኤግዞቲካ” ተገኝታ ከጠጪዎቹ መሀል በመገኘት የእጽ ዝውውርን፣ የውጭ ምንዛሪንና ሰዶማውያንን የተመለከቱ መረጃዎችን መሰብሰብ ነበር። ለከለብ ኤግዞቲካ ባለቤቶች ለደህንነት ስጋት የሆኑ ወንጀለኞች በአካባቢው እንዳሉና ለሚልኳት መረጃ ሰብሳቢ ሴት አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርጉላትና ሽፋን እንዲሰጧት አስቀድሞ ተነግሯቸዋል። መረጃ ሰብሳቢ የተባለችው ዊንታ መሆኗ ነው። ለነገሩ ባለቤቱቹ የታጋይ ቤተሰብ ልጆች ስለሆኑ ሁልጊዜም ተባባሪዎች ናቸው ብሎኛል።

“በዚህም መሰረት ዊንታ በክለቡ ውስጥ በአልኮል የናወዘች ሴት መስላ የውጭ ምንዛሪ አቅራቢዎቹ፣ሰዶማውያኑና እጽ አዘዋዋሪዎቹ ቦታ እየጠቀሱ ሲቀጣጠሩ ትሰልላለች። አለቆቿ የሰጧት ሁለተኛው
ተልእኮ ደግሞ በግራንድ ሌከሰስ” ሆቴል ባር ውስጥ እየተዝናና የሚገኘውን ስመ-ጥር ዲያስፖራ ተቃዋሚ ፖለቲከኛን መከታተል ነበር። ፖለቲከኛው ሞቅ ብሎት ሲደንስ አብራው ከደነሰች በኋላ
ረጅም ሰአት አልኮል እየጠጡ ሲዝናኑ ነበር። ዲያስፖራው የአዲሳባ የቤት ልጅ የጠበሰ መስሎት በሱ ቤት በደስታ ሊሞት ደርሶ ነበር» ብሎኛል ሀገዞም።_ያረፈበት ሆቴል አልጋ ድረስ አብራው በመሄድም አለቆቿ ስለፖለቲከኛውና የግንኙነት መረቦቹ የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃዎች እስከ ጥግ አቀብላቸዋለች

መሲ እንደምትለው ከሆን ዊንታ ከወንድ ጋር መኝታ ከፍል ድረስ ዘልቃ አንሶላ የምትጋፈፈው በእንደዚህ አይነት ልዩና ከባድ ተልእኮ ውቅት ብቻ ነው፡፡ ሀገዞም ለመሲ ከነገራት ተጨማሪ መረጃ እንደገባኝ ከሆነ ዊንታ ጀማሪ ጆሮ ጠቢ ሳትሆን አትቀርም።

መሲ ለባሏ ሀገዞም ይህን ስራ ዊንታ እንዴት እንደጀመረቸው ጠይቃው ነበር። ነገሩ ባልተጠበቀ ሁኔታና በአጋጣሚ እንደሆነ ነግሯታል።

" ከዚህ ቀደም ከእንድ መካከለኛው ምስራቅ ዉስጥ ከሚንቀሳቀስ አሸባሪ ቡ
ድን ጋር ግንኙነት እንዳለው ከምንጠረጥረው የመናዊ ባለሀብት ጋር ስትዝናና በኛ ሰዎች ታየች። ሰውየው ለክትትል እጅግ አስፈላጊ ነበር። በወቅቱ እሱን ለመቅረብ አብራው ከምትዝናናዋ ኢትዮጵያዊት ሴት የተሻለ ሰው
አልነበረም። ቶሎ እሷን ለዚሁ ስራ የማሳመንና በፍጥነት አሰልጥኖ ማሰማራት የግድ ሆነ፡፡ መጀመርያ
አመነታች። ሀገራዊ ግዴታዋ እንደሆነና ይህንን ግዴታዋን ቸል ማለት እንደማትችል ጠንከር ያለ ትዕዛዝ
ሲሰጣት ግን ለመተባበር ፈቃደኛ ሆነች። በወቅቱ ከየመናዊው ያገኘቻቸው ቁልፍ መረጃዎች መስሪያ ቤቱን ስላስደሰቱ ጠቀም ያለ ገንዘብ እየተሰጣት ተመሳሳይ የክትትል ተልእኮዎችን በተደራቢነት
እንድታካሄድ ተደረገ። አስፈላጊነቷ ሲያበቃ ትወገዳለች በሚል ነበር አጀማመሯ። ሆኖም በሷ በኩል የሚገኙ መረጃዎች እየበዙ ስለመጡ...."

#እሌኒ_ሌባ

መሲ ከሀገዞም የምታገኛቸውን ጮማ ጮማ ወሬዎች መስማት ሱስ እየሆነብኝ መጣ። ስለዚህ እሷን ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ሳላገኛት መዋል እየከበደኝ መጣ። መሲ ደግሞ ጥሎባት ትወደኛለች
መሰለኝ በቀን በቀን ብንገናኝ እንኳን ደስታውን አትችለውም። ስለዊንታ ማንነት እስክጠግብ ከነገረችኝ በኋላ ሌላ ጮማ ወሬ ከሀገዞም እንዳገኘች በስልክ ነገረችኝ። እሁድ የተለመደችው ሺሻ ቤት ተገናኘን።
በየሳምንቱ እንደምናደርገው አንድ የሺሻ ከፍል በ350 ብር ለግማሽ ቀን ተከራይተን ወጋችንን ከሺሻው ጋር ማንቦልቦል ጀመርን።

አዲሱ ጮማ ወሬ ቀድሞ አብራን “ኩል ክለብ ትሰራ ስለነበረችውና ከአምታት በፊት አብራው ካደረችወሸ ህንዳዊ ደምበኛዋ ብዙ ሺ ዶላር ይዛበት ጠፍታ በኋላም ታስራ ስለተፈታችው እሌኒ ነበር።

እሌኒን ካገኘኋት አመታት ቢቆጠሩም ከዚያ ሚስኪን ህንድ ዶላር ዘርፋ ታሰረች ከተባለ በኋላ እሷን ለማግኘት ምንም ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ ጥቂት ሴተኛ አዳሪ ጓደኞቼ እንዲህ አይነት ስርቆት ዉስጥ
ተሳትፈው አጋጥሞኛል። ፊታቸውን ማየት ነው የሚያስጠላኝ። ለምን እንደሆነ አላውቅም የምትሰርቅ ሴት በጣም ታስጠላኛለች። ወንድ ሲሰርቅ ያን ያህል የምጠላው አይመስለኝም። እኔንጃ ብቻ ሴት ላይ ያስጠላል። ደግነቱ ብዙ ሴቶች ስንትና ስንት ሺ ዶላር ደምበኛቸው ረስቶ ሄዶ በታማኝነት የመለሱ አውቃለሁ። ለምሳሌ ፎዚያ። አቤት ያንቀን ዜጋው እንዴት እንደተደነቀ። ለታማኝነቷ አንድሺ አምስት መቶ ዶላር በጉርሻ መልክ ሰጥቷት አንድ ወር ሙሉ ስትጋብዘን..ስትጋብዘን ብሩ አላልቅ አላት።ፎዜ ደግ።

ፎዚን የመሰሉ ጓደኞቼን ሳስብ ደግሞ እኮራለሁ። ብቻ እንዴትም ቢሆን የምትሰርቅን ሴት እንደማየት የሚያርገፈግፈኝ ነገር የለም። እሌኒ እንደዚያ ጓደኛችን እንዳልነበረች ለገንዘብ ብላ ስርቆት ዉስጥ መግባቷን ስሰማ በቃ ጠላኋት ጠላኋት። እነ ቤሪ ተመላልሰው እስር ቤት ሲጠይቋት እንኳ አንድ
ቀን ሄጄ ሳልጠይቃት ነው ተፈታች የተባለው፡፡ አሁን ደግሞ መሲ ስለሷ ምን ልትነግረኝ ይሆን ብዬ ተንሰፍስፌያለሁ።

እሌኒ ከእስር በኋላ ባለመኪናም የጎዳና ላይ እግረኛ ሸሌም መሆኗን ሰምተሻል” መሲ ያለቸው ነገር ብዙም አልገባኝም። በጥያቄ አዋከብኳት።

ሀግዞም ለመሲ እንደነገራት ከሆነ ዋናው የእሌኒ የወንጀል ስራ ከሁለት ፖሊሶች ጋር በመመሳጠር የተፈጸመ ነው። እንዲያውም እሌኒን ፖሊሶቹ ናቸው የመለመሏት፡፡

እሌኒ ከዚያ ምስኪን ህንዳዊ ብር ሰርቃ ቃሊት ታስራ አልነበር? ያኔ እስር ቤት የምታውቃቸው ፖሊሶች ናቸው ነገሩን ሁሉ ያመቻቹት”

ቆይ ግን እሌኒ ሁለቱ ፖሊሶች ያቀረቡላትን ጥያቄ እንዴት ተቀበለች? ያን ሁሉ አመት ታስራ ወጥታ…”

“ሮዝ! ኢሉን ከኔ በተሻለ የምታውቂያት ይመስለኝ ነበር፤ እሷ እኮ ለገንዘብ ስትል እናቷን ከመሸጥ እንኳ የማትመለስ መሬ ናት አለች መሲ ግንባሯን ከስክሳ ኢሉን በመጠየፍ።

መሲ ብታምኚም ባታምኒኝም እሌኒን ካገኘኋት ብዙ አመት ሆኖናል። ከታሰረች በኋላ ትኑር ትሙት አላውቅም ነበር። ታስራም አልጠየቅኳትም። ሌባ እንደሆነች ሳውቅ በቃ ምን ልበልሽ አቅለሸለሸችኝ።

"I know...ቀላል ታቅለሸልሻለች!"

ሀገዞም የቅርብ ክትትል ዉስጥ ያለቸው የድሮ ወዳጃችን እሌኒ ከሁለት ፖሊሶት ጋር በመጣመር አትላስ አካባቢ የምትፈጽመው ወንጀል መሲ ዘርዘር አድርጋ ተረከችልኝ። አሁን አሁን እንደባሏ በምትቆጥረው ለረጅም ጊዜ ደንበኛዋና አባዲናዋ የነበረው ሀገዞም በእሌሊ ወንጀል ጉዳይ ሳይነግራት የቀረ መረጃ ያለ አይመስለኝም።ሁሉንም ዘክዝኮላታል።

“ሮዚ ነገሩ ምን መሰለሽ እሌኒ ወንጀሉን የምትፈጽመው ከሁለቱ ፖሊሶች ጋ በሽርከና ነው። ማታ ሚኒዋን ለብሳ ሂል ጫማ አድርጋ አትላስ ጋ ትቆማለች። ለቢዝነስ፤ ባለመኪና ፍለጋ። ይሄኔ ሁለቱ
ፖሊሶች ራቅ ሰወር ብለው ይከታተሏታል ልክ መኪና ሲቆምላት ዉስጥ ሳትገባ ዋጋ መደራደር ትጀምራለች። ባለመኪናዎቹ በሚያቀርቡላት ዋጋ ለመውጣት ትስማማለች። ሆኖም ቅድሚያ ገንዘብ
ትቀበላቸዋለች። ሴክስ የምትፈጽመው ሆቴል ሳይሆን መኪና ውስጥ ብቻ እንደሆነ አስቀድማ ታስገነዝባቸዋለች። ከዚያ ከሚወስዳት ባለመኪና ደምበኛዋ ጋ አትላስ ውስጣ ውስጥ ከሚገኙት
መንገዶች በአንዱ እየጠቆመች ስወር ካለው ስፍራ መኪናውን እንዲያቆም ታደርገዋለች። እሷ መኪና ውስጥ ሆና ወሲብ ስትፈጽም ከፖሊሶቹ አንዱ በሴት ድምጽ ይደውላል። እሌኒ ለ"ሴት ደዋይዋ ያለችበትን ተናግራ አሁን ቢዝነስ ላይ እንደሆነች ጨርሳ ቶሎ እንደምትመለስ በመንገር ወደጀመረችው የመኪና ውስጥ ሴክስ ትመለሳለች። ከዚያም ሁለት ፖሊሶች ቦታው ላይ ከች ይላሉ። ጎዳዩ
ላይ የመኪና ውስጥ ወሲብ መፈፀም ወንጀል መሆኑን ገልፀው ባለመኪናውን ወደ እስር ቤት እንደሚወስዱት ይነግሩታል፤ ባለመኪናው በተለይ እጁ ላይ የትዳር ቀለበት ካለ በውስልትና ለረጅም ጊዜ እንደሚታሰር ጭምር
ይነግሩታል። “በጎዳና ላይ የመኪና ውስጥ ወሲብ ሲፈጽም ታስረ” የሚለውን ውርደት የማይፈልገው ባለመኪና ከዚህ ከፍተኛ ቅሌት ለመውጣት መላ ሲዘይድ እሌኒ የዋህ መስላ በገንዘብ እንዲደራደር ሹክ ትለዋለች። ምንም ጥርጥር የለውም ባለመኪናው ከሁለቱ ፖሊሶች ጋር ድርድር ይጀምራል። ሀገዞም እንደነገረኝ ፖሊሶቹ ከባለመኪናዎቹ ከ5 እስከ 20 ሺህ ብር ሲቀበሉ ኖረዋል። የተቀበሎትን ገንዘብ ኋላ ላይ ለይምሰል አንቺ ወደ ጣቢያ ቀጥይ.” ብለው ከሚያዋከቧት እሌኒ ጋር ይካፈላሉ።

የሁለቱ ፖሊሶች ሰለባ የሆኑ ባለመኪኖች በተለያየ ጊዜ ስማቸውንና ማንነታቸውን ደብቀው የደረሰባቸውን በዝርዝር ለፖሊስ ጣቢያዎች በስልክ ሪፖርት በማድረጋቸው ነበር እነ ሀገዞም እሌኒ ላይ ክትትል የጀመሩት።

እሌሊ የሰዶም መንገድ

ከዚህ ወንጀል በኋላ እሌኒ አልተያዘችም። ይበልጥ ክትትሉ ተጧጧፈባት እንጂ። ክትትሉ ሲጧጧፍ ሌላ ያልተጠበቀ ጉድ ተገኘ። ኢሉ ባለመኪና የሆነችበትን መንገድ መሲ በታላቅ ስሜት አወራችልኝ።

“ቆይ ግን ቡሽቲዎች እሌኒን እንዴት መለመሏት?”

መሲ ፊቷን ቅጭም አደረገች፣

“ሮዝ፣ እሱን እኔም አልደረስኩበትም። ሀገዞም እንደሚለው ገና መረጃዎችን ሰብስበው አልጨረሰም።
ሰማያዊዎ ቪቲዝ ቶዮታ መኪና ግን የሷ እንዳልሆነች ደርሰውበታል”

“ታዲያ የማን ናት”

“ክለብ ኤግዞቲካን ከሚያዘወትሩት ሰዶማውያን የምስጢራዊ ማኅበራቸው የተበረከተች ነች።
ለካስ ቡሽቲዎቹ በድብቅ ማኅበር አላቸው። የሚደርሱባቸውን መገለሎች ተደራጅተው ለመታገልና እርስ በርስ ለመጋባት ይጠቀሙበታል። ዉጭ አገር ሲሰደዱ ደግሞ የጥገኝነት ጥያቄ ለማግኘት የዚህ ምስጢራዊ ማኅበር አባል መሆንና የድጋፍ ደብዳቤ ማግኘት ያስፈልጋል። ዉጭ አገር ብዙ አበሾች
ቡሽቲ ሳይሆኑ ቡሽቲ በመሆናችን ከአገር እንደተሰደዱ አድርገው በማውራት በዉ
👍5
ሸት

ጥገኝነት ያገኙ ነበር። አሁን ግን ያ ቀርቷል። ማኅበራቸው ነው የሚመሰክርላቸው። እና እሌኒ መኪናው የተሰጣት ከዚህ ማኅበር ነው። የመኪናዋ ቀለም ራሱ የቀስተደመና አይነት ናት። ለቡሽቲዎቹ ወንዶችን አማልላ በየቀኑ
እንድታመጣላቸው ይቺን መኪና አውሰዋታል። ለአገልግሎቷ ወፈር ያለ ክፍያ እንደሚፈጽሙላት

መረጃ አግኝተናል ነው ያለኝ ሀገዞም..."

እነኑ ደግሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል እስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን

መሲ እውነቷን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የጠቀሰቸወም ክለብ ዉስጥ ሰዶሞች እንደሚበዙ አውቃለሁ።እነሱ ደሞ በየቀኑ የሚያገኟቸውን ወንዶች በአልኮል አስክረውና በመጠጥ ውስጥ የእንቅልፍ ኪኒን ጨምረው በማደንዘዝ ብዙ ወንድ ማጥመድ አይችሉም። ሁል ጊዜ በዚህ መንገድ የሚወስዷቸውን ሰለባዎች አያገኙም።እሌኒ ግን በሴትነቷ ተጠቅማና አማልላ በየቀኑ እነሱ ካሉበት ቤት ድረስ ለዚህ ተግባር በሰጧት መኪና ታቀርብላቸዋለች። መሲ እንደምትለው እሌኒ መኪና ይዛ ሲያዩ ወንዶች
በፍጹም አይጠረጥሯትም። ወንድ የጠማት ሀብታም ሴት ትመስላቸውና ሰተት ብለው ይገቡላታል። ይህንን በመረዳት ነው ቡሽቲዎቹ መኪና በሚስጢር ማሀበራቸው ስም ገዝተው በውሰት የሰጧት።

እሌኒን አምርሬ ጠላኋት። የሆነ ወቅት ላይ ከዚህች የሰይጣን ቁራጭ ጋር አብሬ መስራቴን ሳስብ ዘገነነችኝ። ሰው ሲባል ግን እንዴት አይነት ጨካኝ ፍጡር እንደሆነ….አሁን እሌኒ እዚህ ሁሉ ልቦለድ የሚመስል ወንጀል ውስጥ ትገባለች ብሎ ማን ያምናል?

መሲን ጠየኳት።ቆይ ግን ባልሽ ሀገዞም ይህን ሁሉ እያወቀ ለምንድን ነው እርምጃ የማይወስድባት?

“ሮዝ! እኔም ጠይቄው ነበር፤ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? መጀመርያ ሳቀብኝና…የዋህ ስለሆንሽ እኮ
ነው የምወድሽ ብሎ ከንፈሬን ከነከሰኝ በኋላ «ወንጀል ክትትል ዉስጥ አንድን ተጠርጣሪ አንድ ወንጀል ስለፈፀመ ብቻ ተንደርድሮ መያዝ ብዙ ዱካዎችን እንደማጥፋት ይቆጠራል እንደምታስቢውም ቀላል አደለም እዚህ ድርጅት ውስጥ ከተራ ሰው ጀምሮ ትላልቅ ባለስልጣናት አጅ አለበት በየቲቪው በከረባት ታንቆ የምናየው ባለስልጣን የማታ ማታ መዳርያቸው ነው አንድም ቡሽቲነትን ከሚያስፋፉት ሰዎች እነሱ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ እንጂማ እሌኒን ገና ድሮ ከሁለቱ ከፖሊሶች ጋር የምትፈጽመውን ወንጀል እንደደረስንበት በቁጥጥር ስር አውለናት ቢሆን ኖሮ
ከሰዶማዊያኑ ጋር ስለነበራት ግንኙነት ምንም ማወቅ አንችልም ነበር። አሁንም በሷ ላይ ለጥቂት ወራት ክትትሉ ይቀጥላል። ጊዜው ሲደርስ እሌኒም፣ ሁለቱ ፖሊሶችም፣ የምታገለግላቸው ሰዶማውያኑም ከነማኅበራቸው ተለቃቅመው እስር ቤት ይገባሉ፤ ባለቀስተደመናዋ ቶዮታ ቪትዝም ለመንግስት ገቢ ትደረጋለች።››

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

rozachichinia@gmail.com

ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍41
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ_2 ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ(🔞) ፡ ፡ #የዊንታ_ማንነት ቦሌና አካባቢዋን የዊንታን ያህል የምታውቅ ሴት መኖሯን እጠራጠራለሁ። የቦሌ ዙርያን የሌሊት ጉድ እንደ ዊንታ የበረበረ ሰው መኖሩንም እንጃ! ለነገሩ ዊንታን የማታውቅ የዚያ አካባቢ ሸሌ አትገኝም።የአካባቢው ስትሪቶች፣ ኮድ ሶስቶች፣ የክለብና የቡና ቤት ሸሌዎች ጥሎባቸው ዊንታን አይወዷትም፣ ገና ሰፈሩን ስትረግጥ በአይናቸው ቂጥ ነው የሚመለከቷት።…»
#ደርሶኛል

ጠርተሽ ባታቀምሽኝ
ደርሶኝ አጣጣምኩት
የዳቦሽን ጣእም
በጠላሽ አወኩት።
"ውረድ ወይ ፍረድ"

ይሉታል እግዜርን ልባቸው ሲቆስል፤
ቢወርድ ፊቱ ቆመው_የሚያዩት ይመስል፤
ቢፈርድ የሚተርፉ ይፀድቁ ይመስል...
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_ሦስት


#በሜሪ_ፈለቀ


.."የአባቴን ገዳይ ገድዬ ነው ከሃገር የተሰደድኩት።" አለኝ ዳግማዊ ምንም የሚያስደነግጥ ነገር እንዳልነገረኝ ሁሉ በመሀከላችን የትራስ ድንበር አበጅተን በምንተኛበት አልጋ ላይ እንደተገደመ።

"ገድዬ ማለት? "

"በገንዘብ ተጣልተው የገዛ ጓደኛው ነው በስለት ወግቶ የገደለው።"

"ከዛስ?"

"ሰውየው እንዴት እንደሆነ ባላወቅነው ሁኔታ በሶስተኛው ወር ተፈታ።"

"ከዚያ በኋላ ያለውን?" አልኩት አስደንጋጩን የወሬ ክፍል 'ገደልኩት' ያለኝን ለማረጋገ። ደምስሩ ተገታተረብኝ። ፊቱ ተቀያየረ። የአሁን ትንግርት የሚነግረኝ ይመስል ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነው የሚያወራው። ሲያወራኝ ተመሳቀልኩ። ስሜቱን ለመረዳት እየሞከርኩ ስሜቴ ተሳከረ። ልክና ስህተት ውሉ ተጣረሰብኝ።

አባቱ ሲገደሉ በአይኑ አይቷቸዋል። በራፋቸው ላይ ነው የተገደሉት። ዳግማዊ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት በሚወስደው ጭር ያለ ቀጭን መንገድ እየገሰገሰ ሰፈር ሲደርስ ከወዳጃቸው ጋር እየተጓዙ አባቱን በርቀት አይቷቸዋል። እንዲያዩት ስላልፈለገ ወደ ኋላ ቀረት ብሎ ከአይናቸው ሰወር አለ። ቤታቸው መግብያ ጋር ሲደርስ የተቃቀፉ መስለው። ብዙም ሳይቆይ ግን አባትየው ወደቁ። ወዳጃቸው አካባቢያቸውን ቃኘት እያደረጉ ከሩጫ ባልተናነሰ ፍጥነት ከዳግማዊ በተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ጀመሩ። ዳግማዊ እየሮጠ አባተቱጋ ሲደርስ ጣር ላይ ነበሩ። ከደረታቸው የሚፈስ ደማቸውንና በእጃቸው ፍራፍሬና የተጠቀለለ ኬክ መያዛቸውን እኩል ቃኘው። የቅድስት አሰራ አምስት ዓመት ልደት በዓሏ ነበር። በጣር ስቃይ ውስጥ ሆነው እጁን ጨብጠው ቤተሰቡን እንዲንከባከብ ለመኑት። ዳግማዊ ገዳያቸውን ከመከተልና አባቱን ከማንሳት የቱ እንደሚቀድም ግራ ገብቶት ዋለለ። በደመ ነፍስ የእናቱን፣ የእህቱን፣ የኸንድሙን፣ የሚያስታውሰውን ሰው ስም ሁሉ በጩህት ተጣራ።

"እናቴ የኔን ጩህት ሰምታ ስትሮጥ ከቤታችን መግቢያ ደረጃ ላይ ወድቃ እግሯ ተሰብሮ ነው ስታነክስ ያየሻት" አለኝ እያንዘፈዘፈው።

ገዳይ የተፈቱት ገና የፍርድ ሂደቱ እንኳን ሳያልቅ ነበር። ይመለከተዋል ላሉት አካል አቤት አሉ። አቤቱታቸው መልስ ከማግኘቱ አስቀድሞ ገዳይ ሀገር መቀየረቻው ተሰማ። ዳግማዊ ተከተላቸው። የአባቱን አገዳደል ተመሳሳዩን አድርጎ ወደ ሱዳን ተሰደደ። ቤተሰቡም የሚኖርበትን የደብረ ማርቆስ ከተማ ጥሎ ናዝሬት ከተማ።

"አንዳንዴ ህይወት ፍትህ አታውቅም። ይሄኔ ፍትህን በራስ እጅ መስጠት! !" አለ ከቀድሞው ተረጋግቶ።

"ለዚህ ነው ቤተሰቦችህ እንደ መሲህ የሚያዩህ? " አልኩት ያልኩት ተገቢ መሆኑ ግራ እያጋባኝ።

አባቱ ከሞቱ በኋላ በአባትየው የእህል ንግድ ይተዳደር የነበረው ቤተሰብ ውጥንቅጡ ወጣ። ዳግማዊ ለአራት አመታት እዚህ ግባ የማይባል ኑሮ ሱዳን አገር አንገላታው። ይሄኔ ቢኒያም ትምህርቱን አቁሞ እህቱንና እናቱን ማስተዳደር ግድ ሆነበት።

"ባንተ ቦታ ሆኜ ስሜቱን አላውቅም። ግን በምንም ሂሳብ ጠፋት በጥፋት ተጣፍቶ መልሱ ልክ አይመጣም።" አልኩት።

"አንዳንድ ጥቃትና መቀማጥሽ በይቅርታና በተፃፈ ህግ እንደማይዳኝ የሚገባሽ ባሏን ለተቀማች እናቱና አባታቸውን ላጡ ታናናሾቹ ብቸኛ ተስፋቸው የሆነ ወንድ ልጅ ሆነሽ ስታይው ነው። አለኝ።

"ሳትገባኝ ቀርተህ አይደለም።" አልኩት ስሜቱን የጎዳሁት መስሎኝ እጄን አሻግሬ እጆቹን እየዳበስኩ።

"እንደማልገባሽ ይገባኛል።" ሲለኝ የሳሎኑ በር ተንኳኳ እና ለመክፈት ተነሳ። ለምን እንደተከተልኩት ሳላውቅ ተከትየው ሳሎን ሄድኩ። ቢኒያም ነው። ተስተካክሎ መቆም እስኪያቅተው ሰክሯል። እናትየው ከመኝታ ቤታቸው ብቅ አሉ። ከመጣን አራተኛ ቀናችን መሆኑ ነው። ከአታካች የአራት ቀን መሰንበት በኋላ ዛሬ ቢኒያም ስላመሸ ሳንተኛ እየጠበቅነው ነበር።

"ደህና አደራችሁ? ማለቴ አመሻችሁ? አለ ሶስታችንንም ተራ በተራ እያየ። ዳግማዊ ተናዷል። እናት ከዝነዋል። እኔ ካለመዋሸት በሁኔታው ሳቄ መጥቷል።

"ደሞ ተጣላችሁ? " አሉ እናቱ።

"አልተጣላንም። ተጣላችኝ" አለ ቢኒያም በቁሙ ሶፋው ላይ እየወደቀ።

"ማናት?" ጠየቀ ዳግማዊ።

"አለችልህ የሴት ጉድ!!። መለሱ እናት ፍቅረኛው መሆኗን እና ከእርሷ ጋር ሲጣላ እየጠጣ እንደሚያመሽ አከሉበት። ቀጥለውም "ቢቆጠር ከፍቅራቸው ፀባያቸው ይበልጣል። ልጅቷም ብቻዋን አይደለችም የሆነ ጋኔን ቢጤ ያግዛታል። ልጁን ጂል እኮ ነው ያደረገችው።" እየተናገሩ ወደ መኝታ ቤታቸው ተመለሱ።

"አሁን ግባና ተኛ ጠዋት እንነጋገራለን።" አለ ዳግማዊ በቁጣ ወደመኝታ ቤት ለመግባት እየተነሳ።

"ዲጉ ግን ፍሪጅ ውስጥ ነበር እንዴ የከረምሽው?" አለ ቢኒያም ስካርና ሳቅ እየተቀላቀለበት። ዳግማዊ ዘወር ብሎ አየው።

"ማለቴ አልተለወጥሽም።" ሲለው እኔ ሳቄን ለቀኩት። ዳግማዊ እኔንም እሱንም በአንድ ዙር ገላምጦን ገባ። አታምኑትም!! ሰክሮ ሲለፋደድ እንኳን የሚፈታተን መስህብ አለው። ባልተሰማ ለማለፍ የሚከብድ ፍም ስሜት።

"ትልቅ ልጅ እኮ ነው ልትቆጣው ባልሆነ" አልኩት ዳግማዊን እንደቅድማችን እንደተጋደምን። በነገራችሁ ላይ ምንም ተፈጥሮ አያውቅም። የእኔ ምክንያት ዳግማዊ የሚያማልለኝ አይነት ወንድ አይደለም። የእርሱን አላውቅም።

"ቤች 'ፕሊስ' ከቤተሰቤ ጋር እንዴት መግባባት እንዳለብኝ ለኔ ተይልኝ!!" አለኝ እንደተለመደው ጀርባውን አዙሮ እየተኛ።

"አብረን እየዋሸን ነው አላልከኝም? ቤተሰባዊነቱንም አብረን እየኖርነው ነው።"አልኩት። አልመለሰልኝም። ራሱን የቤተሰቡ እረኛ አድርጎ መቁጠሩ ከእድሜው የበዛ ጭምት አድርጎታል።

ከነጋ በኋላ እንቅልፍ እንዲወስደኝ ስገለባበጥ አርፍጄ ተነስቼ ጎዳ ስገባ እታባ ቁርስ እያበሰሉ አገኘኋቸው እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ያለው አጥርና ገደብ ይጨንቃል።የተመጠኑ እና የተለመዱ ጨዋታዎችን ከመጫወት ያለፈ ቅርርብ የላቸውም።እዚህ ቤት መከባበር እና መፈራራት ድንበራቸው ተቀላቅሏል።አብሬአቸው ስቀመጥ ልቤ ምጥ ይይዛታል።
የክፍል አለቃ እነዳስጠነቀቀዉ ተማሪ እጄን ማጣመር ሁሉ ይዳዳኛል ገደባቸውን አፍርሼ ላወራቸው ብሞክርም መልሳቸው አጭርና ለሌላ ጨዋታ የማይጋብዝ ይሆንብኛል ።እታባ ቁርስ ማብሰሉን እንዳግዛቸው ስላልፈቀዱልኝ አገጠባቸው ሆኜ የባጥ የቆጡን አወራለሁ።አንድ ወሬ እጀምራለሁ። ሳልጨርስ ሌላ እጀምራለሁ በዝምታ ከስንት አንዴ ዓይኔን እያዩ ከመስማት ያለፈ አይመልሱልኝም ሁሉም ሰው ሌላን ሰው ወደራሱ የሚጋብዝበት ርቀት ገደብ አለው።ጭራሹኑ ማንንም የማያስደፍረው የራሱ ክልልም ይኖረዋል።እኔ ደግሞ መሰረታዊ ችግሬ የሰዎችን ድንበር መጣስ ደስ ይለኛል። አንድን ሰው ስቀርበውና ቀስ በቀስ አጥሩን እያለፍኩ መዝለቅ የቻልኩ ሲመስለኝ ክብረ ወሰኑን እንዳሻሻለ አትሌት ሀሴት አደርጋለሁ።

"በይ ባልሽን ቁርስ ደርሷል በይው።" አሉኝ እታባ ከወሬዬም ለመገላገል ይመስላል። ለዲጉ መልእክቱን ካስተላለፍኩ በኋላ የማደርገው ሳይገባኝ ወደ ቢኒ ክፍል አመራሁ። ባንኳኳ መልስ የለም። ደግሜ አንኳኳሁ።

"አቤት?" አለ ቢኒ በጎርናና አንደበት። ለመግባት ፍቃድ ሳልጠይቅ ነው የዘለኩት። አልጋው ላይ እንደተጋደመ ሲጋራ እያጨሰ ነበር።እኔ መሆኔን ሲያውቅ ሲጋራውን ለማጥፋት ፈጠነ። እንደ መአት የሚፈራው ሚሴቱ ነኛ!

"አጭስ ችግር የለውም። ጭስ አታባክን ።" አልኩት።

"ልግባ ወይ አይባልም እንዴ? ራቁቴን ብሆንስ?" አለኝ ቀልድ በመሰለ ቅሬታ።

"ጠባሳ አለብህ እንዴ ታድያ? ራቁትክን የሆንክ እንደሆነስ?" መለስኩለት ከንፈሩን
ወደ ጎን ሸፈፍ አድርጎ ፈገግ አለ። ከንፈሩ የሚያቀ
👍4
ነዝር ሽፍደት አለው።"ቁርስ እየጠበቅንህ ነው ።" አልኩት ቀጥዬ።

"ዲጉ ተበሳጭቶብኛል አይደል?" አለኝ ልወጣ ወደ በሩ እያቀናሁ ሳለ።

"ትንሽ"

ኑሮ በሚያህል ከባድ ዝምታ ቁርስ ተበላ።ቄጤማው ተጎዘጎዘ ፣ ቡና ተፈላ፣ እጣን ተጫጫሰ፣ ፈንድሻው ተበተነ፣ ግን ደስ አይልም። ሰዎች የሌሉበት ፍዝ ስነ ስርአት ቀብር አካሄጅ የሚመስል ጨዋታ የሌለበት ስብስብ የማላውቀው ሰው ቤት ተገድጄ ለቅሶ ልደርስ የመጣሁ መሰለኝ። ከሰሞኑ በባሰ ሁኔታ ልቤ በደነች።

"የምትናገረውን ተናገርና ልባችንን አውርደው"አልኩት ዲጉን። ሁሉም ፊቱን አቀጨመ።ኪዱ እንደ ማሳል አደረጋት።

"ምኑን?" ብሎ አፈጠጠብኝ።

"እኔ ምን አውቃለሁ። የማውቀው እንደተናደድክበት ነው።ዲጉ መልስ አልሰጠም። ከፈንዲሻው ጋር እየተጫወተ ዝም።ቢኒ ይጠብቃል። ደቂቃዎች አለፉ። ቃል ለማውጣት አፉን ለማላቀቅ የደፈረ የለም። ቢኒ ለመሄድ ሲነሳ

"ቁጭ በል!" አለው ዲጉ ቁጣና ትእዛዝ ለውሶ። ሁሉም ደነገጠ። እኔ ግን ደስ አለኝ። ቢኒ የተባለውን አደረገ።

"ምን ማድረግህ ነበር?" ብሎ ጀመረ። ነፍስ ያላወቀ ልጁን እንደማቆጣ አባት ወረደበት።ጣልቃ ገብቶ የተቃወመም የደገፈም የለም። ሲጨርስም ከአስፈሪ ፀጥታ ውጪ ጥያቄም መልስም አስተያየትም አልተሰማም።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
👍1😁1
Re-post

#ኢትዮጵያዊ_ነኝ

ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደአክሱም ድንጋይ እንደሮሀ አለት
የጊዜ ሞገድ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ከዋርካ ባጥር ከእምቧይ ተልቄ
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ አደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ተራራ መራጭ
ልክ እንደአሞራ ብርንዶ ቆራጭ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
እንደመሐረብ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ የማልገታ
ኢትዮጵያዊ ነኝ።💚💛❤️

🧿በእውቀቱ ስዩም🧿
#አጀብ_እኛ ° ° °
°
°
°
መጪውን ለመኖር
ዛሬያችን ስንገፋ፣
ብዙ ሸለቆ አለ ° ° °
በነጋችን ተስፋ !!!

🧿ሀብታሙ ወዳጅ🧿
በኑሮ ምጣድ ላይ አንዴ ከተጣድክ ዘንዳ
እሺ ብለህ ብሠል እንዳታወሊዓ።
ምን ህመም ቢኖረው መንደዱ መብሰሉ፣
ሆድ አይታወክም አበስለው ከበሉ።
መጣዱም ካልቀረ ካልበሰሉ መብረድ፣
መቃጠሉ እንዳይብስ ቶሎ በስለህ ውረድ