አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#እግዜር_አደራውን_ሲበላ ግርግር ከማይወዱ ጓደኞቼ ዛብሎን አንደኛው "ነው። እይታዎቹ በወፍ በረር የተኮረጁ አይደሉም፤ ስለማያውቀው ነገር ከተወራ ይሰማል ረጋ ብሎ ስለሚያወራ፣ ስለሚያውቀው ነገር ብቻ ስለሚያወራ እያዳመጠ ስለሚያወራ፣ መናገር .. ሲጀምር የማይሰማው የለም። ጨዋታው ብዙ ሰው ላይ ያለው እመነኝ፣ ቅዱስ ነኝ ዓይነት ስብከት የለበትም። ክላስ አለው!! አጠገቡ ያለ ሰው ስለማያውቀው ነገር…»
#ኀሰሳችን_ከሽፎ_እንጂ

ጥዑም ጊዜ ላይ ነበርን። ወይን እየተጎነጨን፣ እየተሳሳምን፣ ድንገት ሳላቅድ፣ ሳልቀምር፣ ሳላስብበት ከአንደበቴ የውስጤ እውነት አመለጠኝ፡፡

ትክ ብዬ ሳያት ፈገግ ብላ “እችን የመሰለች ልጅ ጠበስክኣ?" አለችኝ ወደ ራሷ እያመለከተች፤ በትንሹ ፈገግ አልኩ። ፈገግታዬን እንደ መስማማት ቆጥራ በሚያምር ፈገግታዋ እያየችኝ "እናትህማ መርቀውሃል" ስትለኝ ይሄኔ ነበር የልቤ እውነት ያመለጠኝ።

ታውቂያለሽ ግን አንቺ ሕልሜ እንዳልሆንሽ፤ የመጣሽበት መንገድ፣ ዕቅድሽ፣ መርሕሽ ከእኔ ጋ መች ይሄዳል? አልኳት።

ሽማግሌ ከላክሁኝ በኋላ፣ በጋራ ስለምንወልዳቸው ልጆቻች ስናወራ ከርመን እንዴት እንዲህ ይባላል? ሁሉ እውነት እንዴት ይወራል? የልብ እውነት ሁሉ ይዘረዘራል?! ትበሳጫለች ብዬ ነበር ግን ደግሞ የጠበኩትን የፊት መለዋወጥ አላየሁም። ረጋ እንዳለች፣ ፊቷ ሳይለዋወጥ ትክ ብላ አየችኝ፤ ቅፍፍፍ የሚል  ስሜት ዋጠኝ፤ ምን አለ አስማተኛ በሆንኩ እና እንዳልሰማች ማድረግ አልያም እንዳልተናገርኩ መሆን ብችል።

ቃላቱን እርግጥ አድርጋ

“ትክክል!! ጊዜው አሳዝኖን ነው አብረን የሆነው፤ አብረን ሆነን በስሱ ሌላ የፍለጋ ሙከራ ስላልተሳካልን ነው የምንጋባው። አንዲት ቀን 'Messenger ህን ከፍቼ አይቻለሁ፡፡ የምታወራቸውን እንስቶች ቀልብ ለመግዛት የምትሄድባቸውን መንገዶች፣ መሻፈዶች፣ ላጤ ነኝ ጨዋታዎች፣ ብልግናዎች ተመልክቻለሁ፤ ሁሉም ከእኔ ጋ አንድ ዓይነት ነበሩ። የማደርገውን ነበር የምታደርገው፤ ከፍቶኝ ነበር እንዳላኮርፍ፣ እንዳልጨቀጭቅህ፣ እንዳልጣላህ ካንተ አለመሻሌ አሸማቀቀኝ። የብዙ ሰዎች ትዳር እንዲህ እንደሆነ አይቻለሁ፤ ከገቡ በኋላ በልጆቻቸው ይጽናናሉ፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሚስትና እና ባላቸውን እየከሰሱ ኑሮን ይገፉታል።

ለዛ ነው እንከን የለሽ ትዳር የሚያስሱት ቆመው የሚቀሩት! በቆዩ ቁጥር መለኪያቸውን እየቀየሩ ካጣጣሉት፣ ከተጠየፉት የኑሮ ቀንበር ላይ ራሳቸውን ያገኙታል። ለዛ ነው እንደሚታረድ በግ ሁሉን እያወቅኩ ሽማግሌ ስትልክ፣ ቀለበት ስታጠልቅልኝ፣ የልቤን እውነት አፍኜ የምከተልህ።"

ሲዘበራረቅብኝ ይታወቅኛል። ግራ ገባኝ፤ የሕይወት አጋርን በዚህ ደረጃ አለማወቅ ምን ይባላል? እችን ልጅ ነገሮች በዚህ ደረጃ ይገባታል ብዬ አላሰብኩም። ሴት ልጅ ትታልልህልሀለች እንጂ አታታልላትም እኔ እንዲህ እንደሚሰማኝ እንጂ እሷ እንደዚህ እንደሚሰማት አላውቅም ነበር።

ለምን ታድያ አብረን እንሆናለን ሁለታችንም እንዲህ
ከተሰማን?

"እንሂድ"

ምን አልባት ጊዜያችን፤

ምን አልባት ዕድሜያችን አሳዝኖን?

ምን አልባትም በዙሪያችን ያለ ውትወታ?

ምን አልባት ዘራችንን ለመተካት ካለን ፍላጎት?

ምን አልባት መላመዳችን እንዳንለያይ አግቶን ይሆን?

ምን አልባት አንዳችን ለአንዳችን ካለን ውስጣዊ ስሜት ይሆን?

ምን አልባት በዙሪያችን ካሉት ሰዎች የበለጠ ስለምንዋደድ??

ምን አልባት በስሱ ሌላ ለማግኘት ያሰስነው ኀሰሳ ስላልተሳካ??

ሰው የልቡን ሁሉ አለማውጣቱ ይሆን ቁርኝታችንን
ያላሳደፈው? ባለጋራችንን አለማወቅ ጠቀሜታ ይኖረው ይሆን? አንዳንድ ዕውቀት ምቾት አይሰጥም። ዕውቀት ትካዜን ታበዛለች እንዲል መጽሐፉ፤ አንዳንድ ውይይቶች ሽንቁር ያበጃሉ። የጀመርኩትን ወይኔን በአንድ ትንፋሽ ወደ ጉሮሮዬ አንቆረቆርኩት።

እንደዚህ ዓይነት ሎጂክ ተዘባዝቦ ግንኙነት፣ ትዳር መመሥረት ይቻል ይሆን? እንዳለችው ፍርሀት ነው? እጦት ነው? መላመድ ነው? ምንድን ይሆን በትክክል ያጋመደን?

ምን አስቸኮለን? ምን አሸበረን? ይሄን እውነታ ከተዘራዘሩ በኋላ እንዴት ጎጆ ይቀለሳል? ልጅ ሳይመጣ፣ ንብረት ሳናፈራ፣ ኑሮ ሳይንጠን የግንኙነታችንን መዓዘን መገምገም እንዳለብን ነው የገባኝ። አሁን የምጎዳት ነገ ከምሰብራት አይበልጥም፤ ዛሬ የሚሰማኝ ሕመም ነገ ከሚጋረጥብኝ መከራ አይበልጥም።

ማሬዋ ሰው ውድ ፍጡር ነው። ችኮላችን ብልጣብልጥነታችን፣ በራሳችን ማስተዋል መንጠልጠላችን የእኛ የራሳችን የሆኑት ሰዎች ጋ አንድንሸዋወድ ያደርገናል። ጊዜ እንውሰድ፣ ተነጣጥለን ዙሪያችንን፣ መንገዳችንን እንመርምር፤ ብልግናችንን ይቅር እንበለው። የቆምንባቸውን ስፍራዎች እንቃኛቸው፣ ከፈጸምናቸው ጥፋቶች ጋ እንፋጠጥ፣ እናርማቸው፣ እናበጃጃቸው። ብቸኝነት አባብቶን፣ አቻ ግፊት ወትውቶን፣ መላመድ አሳስሮን፣ የቤተሰብ ግፊት ገፈታትሮን ኑሮ አይመሰረትም። የሁሉም ጓዳ እንዲህ ነው ተብሎ አዲስ ጎጆ አይበጅም፤ ሁሉም ሄዷል ተብሎ እንኳን በስሕተት መንገድ በትክክለኛ መንገድ መሄድ ተገቢ አይደለም።

ከመጣንበት መንገድ የምንሄድበት ሩቅ ነው። ራሳችንን ከእርስ በእርሳችን ነጣጥለን እናጢነው። የአሰተውሎት መንገድ ደግሞ አሜን ካልነው ባሻገር ያለውን እውነታ መጋፈጥን ይጨምራል።

ያኔ የውስጣችን እውነት ፍንትው ብሎ ይታየናል፤ ለውሳኔም ይረዳናል። ስሕተታችንን ለማረም ከፍርሀት ጋ መጋፈጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

ከዚህ ሁሉ መንገድ በኋላ መመለስ እንዳስፈራት ታስታውቃለች። እኔም የወጠንኩትን፣ የለመድኩትን፣ የወሰንኩትን ዳግም ለመመርመር እና ለመከለስ ሳስብ ደስስ የማይል የሚቀረዝዝ ስሜት ሲወረኝ እየተሰማኝ ነው።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
27👍3
#ከሳሽን_መስክርልኝ_ይሉታል

አለሌ ነበርኩ፤ ከሕንድ እስከ እብድ የቀረኝ የለም የምል አለሌ! የተኛኋቸው ሴቶች ጠቢቡ ሰለሞን ከተኛቸው የሚያንስ አይደለም፤ አልቆጠርኳቸውም እንጂ፡፡

ጀንጅኜ መዳረሻዬ ማራኪ ሆቴል ነው። ሆቴሏ ከመኖሪያዬ ራቅ ያለች ሸጎጥ ያለ ሰዋራ ስፍራ ላይ የምትገኝ ነች። አስተናጋጆቹም ምቹ ናቸው። በእርግጥ ጉርሻ ምቹ የማያደርገው የለም።  ፈረንጁ እና መስኪ የሚባሉ አስተናጋጆችን የበለጠ አውቃቸዋለሁ፤ ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኛል።

መስኪ የምትባለው አስተናጋጅ ትንሽ ተለቅ ትላለች። ፊት ከሰጠሁት ይጎነትለኛል ብላ ይሆን፣ ተፈጥሮዋ ሆኖ ይሆን፣ ብዙ : ሴት ስለማመላልስ ይሆን፣ ስለማጨስ ወይም ስለምጠጣ ይሆን እኔ'ንጃ ብቻ አትስቅልኝም አትኮሳተርብኝምም። ፊቷ ወጣትነትን ቢሸኝም ውበቷ ግን እንዳለ ነው፤ ምንም ያህል ቲፕ ብሰጣት አመሰጋገኗ ሆነ አስተያየቷ አይለይም፤ ተመሳሳይ ነው፡፡

ክላሴ ውስጥ አጭሼ፣ ጠጥቼ፣ ባልጌ ሹልክ ብዬ በጓሮ እሄዳለሁ። በሌላ ቀን ሌላ ሴት ይዤ እመጣለሁ። ካልጠረረብኝ ሴት አልደግምም። ሁሉንም እንደ ሙዳቸው  እና እንደ ፍላጎታቸው እሰክሳቸዋለሁ። ላጤነቴ በነጻነት ታየሁ አልታየሁ ብዬ ሳልሳቀቅ ለመባለግ አግዞኛል።

ጓደኞቼ ሁሉ ሲያገቡ፣ የቤተሰቦቼ የአታገባም  ውትወታ በበረታ ወቅት ሶልያና የምትባል ልጅ ተዋወቅሁ። ባገኘኋት በሁለተኛው ቀን ይዣት ለመተኛት በት በት አልኩ፣ ግን አልተሳካልኝም። በውስጤ ስንቷ እንደ አንቺ አካብዳ ጭኗን ሳትከፍት የቀረች የለችም ብዬ ፈገግ ስል

"ምነው?" አለቺኝ።

እርጋታሽ ደስ ይላል

“ውስጤ እንደ ላዬ የተረጋጋ እንዳይመስልህ"

ይሆናል ግን፣ ውስጥም ላይም አንድ ላይ ከመንቀዥቀዥ ይሻላል ስላት

ከንፈሯን ገለጥ አድርጋ ሳቅኩኝ ዓይነት ፈገግ አለችልኝና

"በነገራችን ላይ አንተም ረጋ ያልክ ነህ"

ትዝብት ፈገግ ስልባት

“ውስጥህ ወዲህ ወዲያ ስለሚል ነው እርጋታህ ያልታወቀህ" ይሆናል

ሶልያና የበዛ እርጋታ አላት። እርጋታዋ ይረብሸኛል። ከደስታ ይልቅ ለድብርት አጋልጦ ነው የሚሰጠኝ።

አብሪያት የምሆነው እስክወስባት ድረስ ብቻ  ነበር። መስማት ትፈልጋለች ብዬ የማስበውን እነግራታለሁ፣ ሲኒማ እጋብዛታለሁ ትያትር ትጋብዘኛለች ከንፈሯ ጋር ሳልደርስ ቀናቶች ነጎዱ።

የወሲብ ወሬ ለማውራት በጭራሽ አትመችም፤ ወሲብ ነክ  ከተወራ ለመቀጠል ፊቷ አይጋብዝም፤ ወሲብ ነክ ቀልድ ባወራ ራሱ ለይሉኝታ እንኳን ፈገግ አትልም። መንፈሳዊ ጉባኤዎች ትጋብዘኛለች፤ ለእሷ ደስ እንዲላት አንዳንድ አሰልቺ፣ አንዳንድ ማራኪ ስብከቶችን እሰማለሁ። ቀልቧን ለመግዛትም መንፈሳዊ መጽሐፍ እያነበብኩ፤ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ዕውቀት አለኝ ዓይነት ወሬ ሳወራት ቀልቧ ሲሳብ፣ ወሬው ሲጥማት አያለሁ።

ሳይታወቀኝ የኔን መንገድ እየተውኩ በእሷ መንገድ መመላለስ ቀጠልኩ። ከሌሎች ስለተለየች ይሆን፣ እንደምፈልገው አለመሆኗ ይሆን፣ የምፈልገውን ስላልሰጠችኝ ይሆን ብቻ ቀልቤን ገዝታዋለች። አዋዋሏን ሥራዬ ብዬ እከታተላለሁ፤ ካልተደዋወልን ይታወቀኛል፤ እንቅስቃሴዋ እየገቡኝ መጡ፤ ሳላገኛት የት እና ምን እያረገች እንደሆነ መገመት ቻልኩ፤ ከደወለችልኝ ስግብግብ ብዬ አነሳለሁ፤ በሂደት መንገዷ ምቾት ሰጠኝ፤ ከተመላለስኩበት መንገድ በተሻለ ይሄኛው መንገድ ጣፈጠኝ። ሶልያና ወሲብ የአካል ልፊያ ሳይሆን የነፍስ ውሕድት እንደሆነ አሳይታኛለች፤ ወሲብ ከፍቅር ውጪ ያልተቆራኘ አድራጎት እንዳልነበር ገባኝ፤ ሳላቀው መርኋን ኮረጅኩ፤ ኑሮ ከበፊት በተለየ ጣፈጠኝ።

የድሮ አመሌ ውል ሲለኝ፣ ይዣቸው የምተኛቸው ሴቶች ውልብ ብዬባቸው ሲደውሉ ሳላቅማማ የድሮ ስልክ ቁጥሬን ቀየርኩ። የትላንት የውድቀት መንገዳችንን  ካልቀየርነው ለለውጣችን ሳንካ ይሆናል።

አሁን ፈልጌ መጽሐፍ ቅዱስ አነባለሁ፣ እጾማለሁ፣ ጉባኤ. እከታተላለሁ፣ ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ፣ ከሶልያና ጋ እንፋቀራለን። የትናንት መንገዴን አልተረኩላትም። ለዛሬው ማንነቴ ግን መሀንዲሷ እሷ ናት። ለአምላኬ ስንቴ በእሷ ምክንያት ምስጋና እንዳቀረብኩለት፤ የትናንት ሕይወቴን እንዴት አሁን  እንደማልወደው፤ ስለ ሴት አውልነት ሲነሳ ምንም ሐሳብ አልሰጥም።

ያ ዘመን ያሳፍረኛል።

ሶልያና አንድ ዕለት ስትፍነከነክ መጣች። የደስታዋን ምንጭ ስጠይቃት

“እቴቴ ሥራ አገኘች"

የት?

"ባንክ"

በቀላሉ ፍንክንክ የምትል አይደለችም፤ የእናቷ ጉዳይ ግን ስስ ጎኗ ነው፤ ብቻዋን ስላሳደገቻት ይሆን፣ እናት እና ጓደኛዋ ስለሆነች ይሆን፣ ብቻ ስፍስፍ ትልላታለች።

እናቷ ምን እንደምትሠራ አላውቅም ነበር። በትምህርት ያልገፋች ስለሆነች ማጽዳት፣ መላላክ ይሆናል ብዬ ገምቼ ምንድን ነው የምትሠራው፣ የት ነው የምትሠራው ብዬ ጠይቂየት አላውቅም። እሷም ሥራ ነች አልመጣችም፣ ሥራ ቀየረች ነው እንጂ የት እና ምን እንደምትሠራ ነግራኝ
አታውቅም። በረባው ባልረባው ወሬዎቿ መሀል እቴት ሳትል አትውልም። የድሮ ሥራዋስ ስላት፤ “ውይ የድሮ ሥራዋን እኮ አትወደውም ግድ ሆኖባት እንጂ" አለችኝ።

ስለ እኔ እንደ ነገረቻት እና እንደ ወደደችኝ የነገረችኝ ዕለት እንዴት ደስ እንዳለኝ። የምንወደው ሰው በሚወደው ሰው ከመወደድ በላይ ምን ደስታ አለ? ባሻዬ ብላ ቴክስት አደረገችልኝ። (ደስ ስላት እና ስትቀልድ ባሻዬ ነው የምትለኝ)

“ከእቴት ጋ እንደምንመሳሰል ነግሬህ አውቃለሁ ኣ?"

ሁሌ ብዬ የሳቅ ስቲከር ላኩላት።

“እንደ እሷ ቆንጆ ነኝ ግን?" ብላ ፎቶዋን ላከችልኝ። ያየሁትን ማመን አልቻልኩም። ክው! ድርቅ አልኩ፤ የላከችልኝን ፎቶ አገላብጬ አየሁት፤ አልቀየር አለ።

የማራኪ ሆቴል አስተናጋጇ መስኪ የሶልያና እናት ናት። ሁለቱ አብረው ሆነው እና አንድ የመስኪን ማራኪ እንግዳ መቀበያ ጋ የተነሳችውን ፎቶ ላከችልኝ። ውስጤ ታወከ፤ ያ ሴት አውል አብርሃም፤ ያ በየጊዜው ቁጥር ስፍር ከሌላቸው ሴቶች ጋ የሚጋድመው፣ ሱሰኛው አብርሃም፤ ያ በጥሩ አይን አይታው የማታውቀው አብርሃም የአንድ ልጇ ሶልያና እጮኛ ነኝ ብሎ ፊቷ እንዴት ይቆማል??

ትናንቴ ተከተለኝ፤ እግዜር " በተጸጸትንበት ትናንታችን ይቀጣናል እንዴ? ስንቴ ያመሰገንኩበት ጉዳይ መጨረሻው እንዴት እንደዚህ ሆነ??

አንዳንደ ትናንት ትናንት ላይ ብቻ አይቆምም። ዛሬያችንን የፈለገ ከትናንት አርቀን ሰቅለነዋል ብንል እንኳን፣ ጥለነው ብዙ መጥተናል ያልነው ትናንት ነጋችን ላይ በሁለት እግሩ ቆሞ እናገኘዋለን።

በነዚያ ሁሉ የአለሌነት ዘመኖቼ ከእኔ እኩል ዘልዛላነቴን ቆማ የታዘበች እናት ፊት ከልጇ ጎን ቆሞ መታየት አቃተኝ። የማደርገው ጠፋኝ! ጠፋሁ። የሆነውን ሁሉ የማስረዳበት ቋንቋ ስላላገኘሁ ምንም ሳልላት ጠፋሁ።

ብዙ መብከንከን እና ድብርት የተሸከመ ቀን እያለፈ እንዳለ አንድ ተሾመ የሚባል በደንብ የሚያውቀን የጋራ ወዳጃችን ከብዙ ጊዜ በኋላ አግኝቼው፣ ከብዙ ጨዋታ በኋላ ከሶልያና ጋ ስላንተ አንስተን ተጨዋውተን ነበር ሲለኝ ሰፍ ብዬ ምን አወራችሁ አልኩት። ከዲያሪዋ ላይ ፎቶ አንስታ የላከችለትን ምስል ከሞባይሉ እንዳነበው ሰጠኝ።

“አብርሃም እኮ ተለየኝ። በእርግጥ ሰዎችም ስለተለየኝ ራሴን የጣልኩ ይመስላቸዋል፤ ስልኩን ስለማያነሳልኝ ዱካክ እየበላ የሚያሰቃየኝ ነው የሚመስላቸው፤ ከእኔ መሸሹ ብቻ የመቆም ድፍረቴን የናጠው ነው የሚመስላቸው።

ግን አይደለም!

ሁሉን ነገር ተራ ማድረጉ አስደንግጦኝ ነው! አብረን ሳለን ያልወጣንበት የሐሳብ መሥመር፤ ያልተንሸራሸርንበት ስፍራ፤ ያልነገርኩት ገመና አልነበረም፤ ያልሆንነው አለመሆንን ብቻ ነበር!!
19👍8
በየደቂቃው ከጭንቅላቴ የሚፈልቀውን ዝባዝንኬ ሳላስቀር፣ በአጠገቤ ውል ያለውን ሳይቀር ነበር የምተነፍስለት። እንዳልቆም አድርጎ ያፍረከረከኝ፤ ያሳለፍነውን፣ ያገዘፍኩትን ነገር አንድ ሳይቀር ነው አሳንሷት የሄደው፡፡ ትረካ የሌለው መለያየት፣ ውጣ ውረድ የሌለው ፍቺ፣ የማይተነፈስ ሕመም ለማይታይ ጠባሳ ይዳርጋል፡፡ እንዴት በዚህ መጠን ተራ ይሆናል? እንዴት እየተፍለቀለቅሁ የምተርከውን ትዝታዬን እንደዚህ ያባክነዋል?

እንዴት ጥሩ ምክንያት አይፈበርክም?

እንዴት አካሄዱን ወዝ አያላብሰውም?

በዚህ መጠን ተራ አድርጎኝ እንዴት ይሄዳል? ያውቅ የለ ማን እንዳሳደገኝ፤ ለክብሬ ለግንኙነታችን ያለኝን ቦታ እያወቀ።

እችን ብቻ ነበር የምናክለው?

አብረን ስንሆን የእኔ ነው ብዬ አይደል እርቃኔን የተንጎማለልኩት?

የነበረን ነገር ቢያይል አይደለ ድክመት እና ስጋቴን መግለጼ?

ያሳለፍነውን ውብ ጊዜያት ካለጥንቃቄ በአካሄዱ ተረማምዶበት ነው ያናወዘኝ፣ እንጂ'ማ መለያየት ተፈጥሯዊም አይደል? ነፍስስ ኵስጋ ይለይ የለ? መሄዱ አይደለም፣ አካሄዱ ነው መላቅጡ የጠፋ ዱካክ ውስጥ የዘፈቀኝ።

አወዳደቃችን ውስጥ የጠያችን ግዝፈት እና ተራነት አሻራ በጉልህ አለ፡፡ ምን አለ አለሳልሶ ቢጥለኝ? ምን አለ ሲተወኝ ይሉኝታ ቢስ ባይሆን፡፡ አብረን በነበረን ጊዜ እንደምወደው እያንዳንዱ ዳናዬ ምስክር ነበር። ሰው ለሚወደው አይደለም ላሸነፈው ጠላቱ እንኳ ይራራ የለ?

ምን አለ ራርቶልኝ ቢሆን...

ምን አልባት እኮ የእኔ ብቻዬን የመሆን ፍርሀት ሲያርደኝ መለማመጤን አይቶ ነው ለእኔ ያለው ስሜቱ የተከለለበት፤ ምን አልባት ከእኔ የተሻለ ሰው አግኝቶ በእጁ እስኪያረጋት ወረት አውሮት ነው።

ምን አልባት እንዲህ መሙለጭለጭ ማንነቱ ይሆን ይሆናል። እሱ እንዳልሄድበት ከመጣው መንገድ በላይ እኔስ አልሄድኩም? ለእናቴስ የጀመርኩትን የደበቅኋት፣ የማትወደውን የሆንኩት ነገ ስነግራት አታፍርብኝም ብዬ አይደል? ከራስ ሰው ጋ መንዘላዘል ትዝታውም ሁኔታውም ይጣፍጣል ብዬ አይደል ከእናቴ የዘወትር ስጋት ራሴን ጥዬ ያገኘሁት?

ይሂድ! መሄዱ አይደለም ያጎሳቆለኝ!

ይሄ ማለቂያ የሌለው የምን አልባት ጉዞ ነው ከሰውነት ተራ ያወጣኝ። ምን አልባት ቃል ገድፌ የማይወደውን ብዬ፣ ወይ ምን አልባት ያልዋልኩበትን ነግረውት ይሆን? ወይ የሆንኩትን አገዛዝፈው አሻክረውት ይሆን? ይሄ እና ሌሎች የምን አልባት መላምቴ ነው ጭንቅላቴን ያጣበበው፤ እንዲህ እንደባተልኩ አልቀርም፤ እረሳዋለሁ። ያኔ እዚህ የዘራውን እዛ ሲያጭድ መሰስ እያለ ይመጣል፤ ያኔ የእኔን የምን አልባት የመላምት ችንካርን ይቀምሰዋል።"

ተሾመ ረጋ ብሎ ነበር የሚመለከተኝ። ሶልያና ያለችውን ሳነብ አንዱም ቃል አልለሰለሰኝም። ልቤን የጥፋተኝነት ስሜት ሸቀሸቀኝ። እያነበብኩ እንባዬ ሲንከባለል ተሾመ ተረጋግቶ ከመቀመጥ በቀር ምንም አላደረገም። ስቃይህ ከስቃይዋ አይበልጥም ብሎ ይሆናል።

ሶልያና ሕመሟን ከመቼ ጀምሮ ነው እንዲህ ለሰው ማጋራት የጀመረችው? አንዳንድ በደል የሌለንን ማንነት እና ባሕሪ ይወልዳል ማለት ነው።

አለሌ ብሆንም ስንቴ እየወደድኩ ተትቻለሁ፤ እየለመንኩ ተረግጫለሁ፤ ከእኔ የተሻለ ጋ ሄዳለች ብዬ ናፍቆቴን ፊት ነስቻለሁ። ጭር ያለ ስፍራ ተሸጉጬ አልቅሻለሁ። በሌላ አሳብቤ ተነጫንጫለሁ። ስንት ጓደኛ ሽምግልና ልኬያለሁ፤ የኔ ያድርጋት ብዬ ጸልያለሁ፤ አለመፈለጌን ለመርታት አነቃቂ ንግግር ሰምቻለሁ፤ ሴት እንዲህ ነች ብዬ ተቦትርፌያለሁ። ጥላኝ ማን ጋ እንደሄደች እያሰብኩ አርሬያለሁ።

ቃሏን እያጣቀስኩ ከስሻለሁ፤ ናፍቄ ረግሜያታለሁ። ይሄ እንዲህ ሆኖ ሳለ የሚወዱትን በገዛ ፍቃድ እንደመተው ያለ ሕመም ግን የትም የለም!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢199
አትሮኖስ pinned «#ከሳሽን_መስክርልኝ_ይሉታል አለሌ ነበርኩ፤ ከሕንድ እስከ እብድ የቀረኝ የለም የምል አለሌ! የተኛኋቸው ሴቶች ጠቢቡ ሰለሞን ከተኛቸው የሚያንስ አይደለም፤ አልቆጠርኳቸውም እንጂ፡፡ ጀንጅኜ መዳረሻዬ ማራኪ ሆቴል ነው። ሆቴሏ ከመኖሪያዬ ራቅ ያለች ሸጎጥ ያለ ሰዋራ ስፍራ ላይ የምትገኝ ነች። አስተናጋጆቹም ምቹ ናቸው። በእርግጥ ጉርሻ ምቹ የማያደርገው የለም።  ፈረንጁ እና መስኪ የሚባሉ አስተናጋጆችን የበለጠ…»
#አንዲት_ዕድሜ_ለስንት_ትሆናለች

በጨዋታችን መሀል "ባል ፈልግልኝ" አለችኝ ምን ዓይነት? አልኳት።

“ጥሩ ፀባይ ካለው ይበቃኛል።" የምሯን እንደሆነ ሁለ ነገሯ ይናገራል። ጉጉቷ አንጀቴን በላው።

ፍቅረኛ ኖሮሽ ያውቃል? አልኳት።

ጥያቄውን ለማለስለስ ስታገል በደረቁ ወጣብኝ።

“ዛሬ ነገ እያለ ሕልሙ ላይ ተመስጦ ድክመቴን እያጎላ፣ እያሳጣ ከዛሬ ነገ እንጋባለን እያለ ቀኔን ዕድሜዬን በልቶ ተልካሻ ምክንያቶችን ጠቃቅሶ ተለየኝ። አሁን ሌላ ከእኔ በአስር ዓመት የምታንስ ጉብል አግብቶ ወልዶ ይኖራል"

ምናለ ...

ካልወደድካት፣ ካላገባሃት ብትተዋት፤ ቀኗን ባታኝከው! ውበቷ ሳይደበዝዝ፣ የከጀለችውን አማርጣ በጊዜዋ ታግባ፡፡ ጊዜ ለሴት ልጅ ከወንድ ልጅ የበለጠ ትርጉም አለው።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍178🥰2
አትሮኖስ pinned «#አንዲት_ዕድሜ_ለስንት_ትሆናለች በጨዋታችን መሀል "ባል ፈልግልኝ" አለችኝ ምን ዓይነት? አልኳት። “ጥሩ ፀባይ ካለው ይበቃኛል።" የምሯን እንደሆነ ሁለ ነገሯ ይናገራል። ጉጉቷ አንጀቴን በላው። ፍቅረኛ ኖሮሽ ያውቃል? አልኳት። ጥያቄውን ለማለስለስ ስታገል በደረቁ ወጣብኝ። “ዛሬ ነገ እያለ ሕልሙ ላይ ተመስጦ ድክመቴን እያጎላ፣ እያሳጣ ከዛሬ ነገ እንጋባለን እያለ ቀኔን ዕድሜዬን በልቶ ተልካሻ ምክንያቶችን…»
በሽርፍራፊ ትዝታ
በልብ ስር የሚዋቀር
አለ ናፍቆት የማይገልፁት
ራስ ጋር ብቻ የሚቀር
እስከኖሩ አብሮ የሚኖር
የሞቱ'ለት የሚቀበር!

🔘ያብስራ🔘
👍137
ስትመጪ እንዳይመስልሽ የሌለው የሄድኩኝ
በሬን ነቀልኩልሽ አንቺ ስለሌለሽ ቤቴን ስለናድኩኝ።
ማንኳኳት ቀረልሽ...
በር የለውም ቤቴ ግቢ እንደመጣሽ
የምትገቢበት ነው ባለፈው ያስወጣሽ።
የህይወት በር ነኝ ያለው ያንቺ ጌታ
በር ልክ አይደለም የበር ቦታ ነው የሀቀኛ ቦታ።

አየሽ...

በር አይደለም ህይወት በርማ ይዘጋል ለጠላው ለናቀው
በርማ ክፍት ነው ላቀፈ ላሞቀው
በር ህይወት አይደለም የኔ ዕድል ሀምሳሉ
የበሩ ቦታ ነው...
ማንንም የሚሸኝ ማንም የሚገባው ለፈቀደው ሁሉ።

የበሩ ቦታ ነው የአፍቃሪሽ ልኩ
ቅርብ ነች ለማለት ስትሔጂ እየለኩ
ክፍት ቦታ መሆን... ባዶ ቦታ መሆን
የሄደን ጥበቃ ከመጠበቅ መጉደል
በርን ከፍተሽ ለሄድሽ በርን እንደመንቀል።

በሬን ነቀልኩልሽ እንዳትቸገሪ
መቸገር ስራው ነው የተጓዥ አፍቃሪ።

የበሩ ቦታ ነው የአፍቃሪሽ ልኩ
ቅርብ ነች ለማለት ስትሔጂ እየለኩ
ክፍት ቦታ መሆን... ባዶ ቦታ መሆን
የሄደን ጥበቃ ከመጠበቅ መጉደል
በርን ከፍተሽ ለሄድሽ በርን እንደመንቀል።

በሬን ነቀልኩልሽ እንዳትቸገሪ
መቸገር ስራው ነው የተጓዥ አፍቃሪ።

ግቢ እንደመጣሽ በር የለውም ቤቴ ሳትቅለሰለሺ ነቃቅዬዋለው ደግሞ ዝግ ነው ብለሽ እንዳትመለሺ።

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
22👍2
    ዓይንሽ እሳት ሳቅሽ እሳት እጀሽ እሳት
ታዲያ ምን ይገርማል ባንቺ ቃል ብሳሳት?
    አይንሽ ውኃ ሳቅሽ ውኃ እጀሽ ውኃ
  ታዲያ ምን ይገርማል ብሆንሽ አምሀ?
    በጋና ክረምቱ ዝናብና ውርጩ
ሳቅሽ ነው እላለሁ የአቡሻኽር ምንጩ?
                     እሰይ...

             ከቤቴ እወጣለሁ
             ከደጄ እወጣለሁ
            ዶፍ ይውረድ በላዬ
     ሳቅሽ እንደዝናብ ካሳደገኝ ብዬ ፡፡

            ደስታ ሲያስገመግም
             ሰኔ ሲያስገመግም
   ዮም ፍሰሐ ኮነ በኤልያስ ግርግም፡፡

ወረደልህ  ቢሉኝ ደመና በክስተት
    ዘነበልህ ቢሉኝ ወለላና ወተት
ሲደመም ቢኖርም እግዜርን ላመነው
            ታዲያ ለኔ ምነው
ሳቅሽ ተነጥሎ ተዓምር የሆነው?

             ስንት ለመዘነ
             ስንት ለፈተነ

ሲደመም ቢኖርም እግዜርን ላመነው
           ታዲያ ለኔ ምነው
ሳቅሽ ተነጥሎ ተዓምር የሆነው?

            ስንት ለመዘነ
            ስንት ለፈተነ
  ስንት ለወጠነ ለኔ አይነት አለቃ
ከዚህ ሁሉ ሜዳ እንዴት እጅሽ በቃ?

ሞትም ባንቺ ፉጨት አልሰማም ካልጠራኝ ህይወት ባንቺ ፉጨት አልሰማም ካልጠራኝ
    እስኪ ጠይቂልኝ ካንቺ እንደሰራኝ !!!

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
9👍1
#አይሸጥም

እቤቴ ሊጠይቀኝ የመጣ ሁሉ፤ አጠገቤ ያለ ባለ ፎቅ ሁሉ፤ ባጋጣሚ የሚደልል እና በድለላ የሚኖርበት ሁሉ፤ ዘመድ አዝማድ ሁሉ፤ የመኖርያ ቤቴን ስፋት ከሰፈራችን መዘመን እና ከቦታ ዋጋው መናር ጋር እያስተያዩ “አትሸጪውም?” ይሉኛል፡፡

ብሸጠው የማገኘውን ሰምቼው የማላቀውን ገንዘብ መጠን ይነግሩኛል መልሴ ሳላወጣ ሳላወርድ አንድ ነው እሱም አ ል ሸ ጠ ው ም ብቻ እነሱ ግን ከመወትወት ሰንፈው አያቁም። አንዳንዱ “እሺ እማማ እርሶ ይሄን ያህል ይበሉን እና እንግዛዎት” ይሉኛል፤ ግን የእውነት... አክሱም ወይ ላሊበላ አልያ ደግሞ ፋሲለደስ በስንት ቢሸጥ ያዋጣል? ታሪክ ይሸጣል?

ይሄ ግቢ እኮ ባሌ ሽኮረመመ ጃጰማኘ ያጣጣምንበት፤ ፍቅር የዘራንበተ፤ፍቅር ያጨድንበት የተጨቃጨቅንበት የተኮራረፍንበት የተመካከርንበት ያቀድንበት ያዘንበት የሳቅንበት የወለድንበት ስፍራ ነው።

ይሄ ስፍራ እኮ የጸነስኩት ልጆቼ ያሳደኩበት፤ ልጆቼ ፀሐይ ያሞኩቅበት፤ ልጆቼን የገረፍኩበት፤ ልጆቼን ያስታረቅኩበት ልጆቼን የዳኘሁበት እዚህ ግቢ እዚ ቤት ነው!!

ቤትሽን ሽጭልኝ የሚሉኝ መስሏቸው ነው? አይደለም! ታሪክሽን ነው ልግዛሽ ያሉኝ! ይሄ ስፍራ ለኔ ጥዑም የትዝታዬ መዓዛ የሚያውደኝ ቦታ ነው፡፡ ከዋናው Vila ጎን ከዛ ከምትታየው ጥንጥዬ ክፍል ተነስተን ተካሰን ተበድረን ታግለን ነው ያስፋፋነው!!

አቅም የሆነኝ፣ የሕይወት ጣዕም ያልተሟጠጠብኝ ትላንቴ ላይ ተተክዬ ነው፡፡ ትላንትሽን ሽጭልኝ ነው የሚሉኝ፤ እኔ ከትላንቴ ውጪ ምን አለኝ?? እዚ እረጭ ያለ ግቢ ውስጥ የልጆቼ የጨቅላነት፣ ጩኸት እና የጨዋታቸው ጫጫታ ይሰማኛል፡፡

ይሄ ቤት ልክ እንደ ዋርካ ሥራሥር ትዝታዎቼ ውስጥ ጠልቋል። ጠዋት ጠዋት በሬ ላይ ቁጭ ብዬ የምሞቀው ፀሐይ ከየትም ስፍራ ካለችው ፀሐይ የበለጠ ምቾት አላት።

ከቤቴ ውስጥ ልጆቼን፣ ባሌን የማያስታውሰኝ የትኛው የቤት ክፍል ነው? የትኛው የግቢዬ ጠርዝ ይሆን?

የቱም!

ትላንቷ ላይ ለከተመች አሮጊት ታድያ ይሄ ምን ያህል ገንዘብ ይተካላታል?

ለዚህ ነው ትላንቴን የማልሸጠው!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
24👏4
#አንተ_የሌለህ_ጊዜ

ተማሪ እያለን ለብዙ ጊዜ የፍቅር ሕይወትን ተጋርተናል፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ ትልቅ ሰው ከሆንን፤ የተለያየ የሕይወት መሥመር ውስጥ ከሰመጥን፣ አጀንዳዎቻችን ከተቀየሩ፣ ፍላጎት እና ሕልማችን ሌላ ከሆነ በኋላ በድንገተኛ ግጥምጥሞሽ ሥራ አገናኘን፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ከብዙ ዓመታት በኋላ ስንገናኝ አድገን፣ በስለን ስለነበረ የወዳጅነት ሰላምታ ሰላም ተባባልን፡፡ ሁለታችንም አይናችን የጣት ቀለበት ሲያስስ ተገጣጠምን፤ ሁለታችንም አግብተናል። ያገናኘን ሥራ ላይ ተጠመድን፣ ደጋግሞ ሥራ አገናኘን፤ ደጋግመን 'email' ተለዋወጥን።

አንድ ቀን ማኪያቶ እየጠጣን ከላይ ከላይ እየተጨዋወትን በሕይወቷ ስላለፈችበት ፈታኝ ጊዜ ማወቅ ፈለግሁ። ለምን የመጣችበትን አስቸጋሪ ሕይወቷን ለማወቅ እንደፈለግኩ አላውቅም።

የህይወትሽ አስቸጋሪ ጊዜ መቼ ነበር አልኳት?

አየችኝ፤ በትንሹ ፈገግ አለች፤ ፈገግ ስትል ዲምፕል አላት፤ ጥርሶቿ እንደ ድሮው ያምራሉ። ከፊት ለፊት በግንባሯ የመጡትን ዘለላ ጸጉሮቿን በቄንጥ ወደኋላ መለሰቻቸው።

ዝም ብዬ ስመለከታት...

“አንተ የሌለህ ጊዜ። ማለቴ የተውከኝ ለታ" አለችኝ። ስትቀልድ መስሎኝ ሳቅሁ። “እማ ትሙት" አለችኝ። በእናቷ ምላ ዋሽታ አታውቅም፡፡ ግርምቴን መደበቅ አልቻልኩም፤ ሁለ ነገሬ ጆሮ ሆነ

አየኋት

“ያ ጊዜ ላልበሰለችው ሄርሞን ፈታኝ ጊዜዋ ነበር። እወድህ ነበር፤ እያንዳንዱ ነገሬ ከአንተ ጋ ተሳስሮ ነበር። ውጤት መጣልኝ፣ ክፍለሀገር ተመደብኩኝ፤ ምክንያቱን ባላወቅኩት ምክንያት ራቅከኝ፤ ሁሉ ነገር ላይ ስልጣን የሰጠኸኝ ልጅ ገሸሽ ስታደርገኝ የማደርገው ጠፋኝ። በጨቅላ ጭንቅላቴ ቀልብህን እንደ ድሮ ወደ እኔ ለመመለስ ባተልኩ፤ ግን አልሆነም።

ወደ ተመደብኩበት ዩኒቨርስቲ ወደፊት መራመድ እንደመብረር እየከበደኝ ሄድኩ። ቀልቤን፣ ሳቄን ትቼ ነበር የሄድኩት። አዲስ ቦታ መልመድ ለእኔ ቀላል እንዳልሆነ ታውቃለህ፤ ሁሉ ነገሬን ላንተ እንደማነበንብ ታውቃለህ። ስላ'ንተ ለሁሉ እንደማወራ ታውቃለህ፤ ጓደኞቻችን ሁሉ የጋራ ነበሩ። ዶርም ሜቶቼ ለሚያወሩት ቋንቋ ባዳ ነበርኩ፤ አብሮነታቸው ሲደራ ባይተዋርነት አራቆተኝ፤ የማይወዱኝ ይመስለኛል።

“የካምፓስ ምግቡ አልተስማማኝም፤ አዲስ ዩንቨርስቲ በመሆኑ ሁሉም ነገር ገና ነበር፡፡ ናፍቆት ገላዬን በላው። ምግቡ ስለማይስማማኝም ብዙ አልበላም። ሰለልኩ፤ የጨጓራ ሕመም ጨፈረብኝ"

መቼ ደውለሽልኝ ታውቂያለሽ? በእኔ የምታውቂው ሰው ሆኖ ማን አለ ያልዘጋሽው? አልኳት ኮስተር ብዬ!

“እንደማትፈልገኝ ሁሉ ነገርህ ይናገር ነበር፤ ስልክህ ረጅም ሰዓት ይያዛል፤ በፍጥነት ተቀያየርክ፤ ለስሜቴ መጠንቀቅ አቆምክ። እንደቀለልኩብህ ድርጊትህ ይናገር ነበር። አንተ ላይ ስልጣን አልባ እንደሆንኩ አሳየኸኝ። ነገሮችን ለማስተካከል በአፍላ ጭንቅላቴ ተፍጨረጨርኩ። ጓደኞቼ ሊሰሙኝ እንጂ መንገድ ለማሳየት ጥበብ እና ልምዱ አልነበራቸውም። ታላላቆቼ ጋ በዛ ዕድሜዬ በዚህ ጉዳይ የማውራት ስልጣኔ አልዳበረም፤ ነውር ነበር።

ሸሸሁ!

የባሰ የቀዘቀዘ ድምጽ እንዳልሰማ ሸሸሁ፤ አዲስ የተወዳጀሃት ልጅ እንዳለች ስድስተኛ ስሜቴ አንሾካሾከልኝ። ስደውል በእሷ ፊት ተራ ጓደኛዬ ነች ዓይነት ወሬ እንዳታወራኝ ሰጋሁ። አትደውይልኝ እንዳትለኝ ስለሰጋሁ ሸሸሁ።

ላ'ንተ ያለኝ ፍቅር የባሰ አጣጥለኸኝ እንዳይቋጭ ስለሳሳው ሸሸሁ!

የጋራ ጓደኞቼ በልቤ ያለውን ፍርሀት እንዳይነገሩኝ ሁሉንም ዘጋኋቸው « አነባቸው የነበሩ ፍቅር ነክ ልብ-ወለድ ጽሑፎች ውስታዬን ተስቅሰው ናፍቆቴን እንዳያባብሱት ማንበብ አቆምኩ፤ የፍቅር ፊልሞች ትዝታዬን ገላልጠው እንዳያሳምሙኝ ማየት ተውኩ፤ ያች ሄርሞን ከመሸሽ ውጪ የመጋፈጥ አቅም አልነበራትምና ሸሸች።

የጀመርኩት የ"psychology" ትምህርት ካለ ምርጫዬ ስለነበር ችግር ሲገጥመኝ የምሸሸግብህ፣ የምታጽናናኝ አንተ ስትለወጥብኝ፣ ስትገፋኝ የልቤን የማጫውተው ጓደኛ አለመኖሩ፣ የምግቡ አለመስማማት፣ የጨጓራ ሕመሜ ኑሮዬን አጠየፈው። ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን . ረጅም ሰዓት እቀመጣለሁ፣ ስብከት አዳምጣለሁ፣ ጉባኤ እከታተላለሁ::

ፆታዊ ፍቅር ስለሌለው፣ የሁሉ ነገር መሠረት ክርስቶስ እንደሆነ ስለሚነገር፣ በፈተናው የጸና የተባረከ ነው ስለሚባል፣ ብዙ ነገሮች በዲያቢሎስ ስለሚላከክ፣ የጭንቀታችን ችግር መፍቻ ጸሎት፣ ንሰሃ መሆኑን በአማረ፣ እና በሚጣፍጥ ቋንቋ ስለሚያስተምሩ ጣፈጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስን የሙጥኝ አልኩ። ችግሮቼ እየቀለሉኝ መጡ። አዳዲስ ሃይማኖተኛ ጓደኞች ተወዳጀሁ።

የመጀመሪያ ዓመት ጨርሼ ስመጣ ግሬይ ሱሪ፣ ቀይ ቲሸርት አድርገህ ቆመህ አየሁህ። ሳይህ ከእስራቴ፣ ከሱሴ መላቀቄ ነው የተገለጠልኝ። የሆነ ቀጫጫ ልጅ፣ ኖርማል ወንድ፣ ለአይን የማይሞላ ልጅ አየሁኝ። ለካ ችግራችንን የምናይበት መንገድ የገዘፈ ስለሆነ ነው ከችግራችን በታች የምንሆነው።

ዕውቀትና ልምድ ያለው ሰው መውጫ መሰላሉን ስለማርዮን ነው ለካ እንቅፋታችን የሚፈነጭብን። ርግጥ ከስቃይ የምናገኘው ጥበብ ያበስለናል። ከስኬት ከምናገኘው እውቀት ከውድቀት የምናገኘው ጥበብ እጅግ ትልቅ ነው።

ያኔ ሳይህና ሰላም ስልህ የተሰማኝ ስሜት አስገረመኝ፤ እረስቼህ ነበር። አንድ የማውቀውን ሰው ሰላም እንደማለት ነበር ያ ወቅት የሕይወቴ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር፤ ነገር ግን በዛ ፈታኝ ወቅት ያዳበርኩት ብስለት ለቀሪው ሕይወቴ ጫንቃ እያበቀልኩበት ነበር።

ጸጥ አልኩ፣ ትንሽ ጸጸት፣ ትንሽ ግርምት፣ ትንሽ | ግርታ ተደማምሮ ሁካታ ቢሞላብኝም ፀጥ አልኩ።ዝምታ ከመላምት ውጪ የሚያስተላልፈው አንድም ተጨባጭ መልእክት የለምና ፀጥ አልኩ።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1410
ማንም ከሰበረህ ...

ማንም ከቆረጠህ ...

ማንም ካቆሰለህ ...

ዱር ከበቀለ ዛፍ...

በምን ትhያለህ?

🔘ፈይሰል አሚን🔘
4🤔3
#የቃል_ቅሌት

ከሚሊዮናት ውስጥ
የቅርብ ዘመድ ጠፍቶ
አንድ ረዳት አጥቶ
ጠባብ ኩሽና ውስጥ
ቢገኝ አንድ አዛውንት
ደርቆ ተኮራምቶ
ከዚህ ዓለም ጣጣ
በሞት ተለያይቶ
በሰላም “አረፈ”
“ተገላገለ” እንጂ
እንዴት “ሞተ” ይባላል?!?
“ቃል”ም እንደሰው ልጅ
ለካ እንዲህ ይቀላል!!
👍2😢1
ማጣት ክፉ አይደለም

:

አንዳንዴም ደግ ነው
ገብቶት ለወደደው

:

ስንቱ ጤነኛ ሰው – ማግኘት አሳበደው

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍61
አትሮኖስ pinned «ማጣት ክፉ አይደለም : አንዳንዴም ደግ ነው ገብቶት ለወደደው : ስንቱ ጤነኛ ሰው – ማግኘት አሳበደው 🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘»
Forwarded from Button Bot
ተማሪ ነህ 🤗