#ወላሂ_ገብርኤልን_አላፈቅርሽም
፡
፡
#በናትናኤል_ጌቱ
…
«ሸሌ ነገር ናት! » … ስሟን ሲጠይቅ የተሰጠው ምላሽ ነው። ትልቅ ዳሌ አላት። ጠይም ቆዳዋና ረዘም ያለ ቁመቷ አይን ውስጥ እንድትገባ ያደርጋታል። ስትራመድ የሚውረገረገው ዳሌዋ ደግሞ አይን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቀልብ ይስባል። ስታልፍ ተጠምዝዞ የማያያት የለም።
«ሸሌ ማለት?…እየተከፈላት ምናምን? » ጠየቀ
«አይ!…እንደዛ ሳይሆን ላንኳኳ ሁሉ ትከፍታለች! »
«ቸር ናት ነዋ የሚባለው!…እንዲከፈትልን የምንፈልግ ብዙዎች አለን!»
ወዲያው ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ እሷ ሄደ። የተወሰነ ደቂቃ ካወራት በኋላ ስልኳን ተቀብሎ ተመለሰ።
በሌላ ቀን ሲገናኙ…ወደ አንድ መጠጥ ቤት ነበር ይዟት የሄደው።
ገና ከመቀመጣቸው አንድ ጥንዝል ያለ የተራበ የሚመስል አስተናጋጅ መጣ
«…ምን ልታዘዝ?»
« ለእኔ አንድ በደሌ እና ዳብል ጅን…»
የምታዘውን ለማወቅ ወደሷ ዞረ
«ጃንቦ» አለች ፈጠን ብላ።
«አይገርምም ግን መጀመርያ እንዳየሁሽ እንዲህ እናወራለን ብዬ አላሰብኩም ነበር»
«ማለት?»
«እንዳንቺ ቆንጆ የሆኑ ሴቶች…ትንሽ ማድከም ይወዳሉ »
«በሌላ አማርኛ ቀላል ሆንሽብኝ እያልከኝ ነው»
ልክ ናት! ኑረዲን ከሴቶች ጋር ሲጀናጀን የሚያደርገው አንድ ልምድ አለው። እያወራቸው ዝቅ ዝቅ ያደርጋቸዋል። እልህ ያሲዛቸዋል። ሰፈሩ ውስጥ ወንድ አታስጠጋም የተባለችውን ፎዚያን… እያጣጣለ ነው ልቧን የሰበረው። ፋሽን ተከታይ ነው። ሳይዘንጥ ከቤት አይወጣም። ልብስ በሰዎች ላይ ያለውን ተፅእኖ አሳምሮ ያውቃል። «ሰዎች ገና እንዳዩህ ሚዛንህ ከፍ እንዲል ከፈለክ ደህና ልብስ ያስፈልግሀል» የሚል መመሪያ አለው።
የሚያወራቸው ሴቶች መጀመርያ ላይ «…ጉረኛ ነህ» ምናምን ይሉታል። ከዚያ በኋላ ግን ያለውን ሂደት ያውቀዋል። እያታለለ ወደ አልጋው ይወስዳቸዋል። ከዚያ ጨዋታው አበቃ!!
ትንሽ የማፈር ወይም የዝቅተኝነት ስሜት ተሰምቷት ከሆነ ብሎ አይኖቿን አስተዋለ። ወጥመዱ እንዳልሰራ ገባው። ብርጭቆውን ብድግ አድርጋ ከመጠጡ ግማሹን ባንዴ ከቀነሰችለት በኋላ
«ኑረዲን ነው ያልከኝ ስምህን…አይደል?»
«አዎ!»
«…ይገርማል!…በመስገጃ ሰአትህ መጠጥ ቤት ውስጥ ተጎልተህ…ቂጤን ስታይ እንደ ውሻ አቀንዝሮህ…ቀለልሽብኝ ስትል ትንሽ አታፍርም?» ከት ከት ብላ ሳቀች።
በጥፊ እንደተመታ ሰው ደነገጠ።
«…ሃሃ…ግን ይሄ የድሮ ሰዎች ለጅንጀና የሚጠቀሙበትን ስልት ይዘኸው መምጣትህ ይገርማል»
«ምኑ ነው የድሮ»
«ያው…ሴቷን ዝቅ ዝቅ እያደረክ ራስህን ቆልለህ…በራሴ እተማመናለሁ ምናምን እያልክ ሰክሰህ… ማጥመድ። የተረሳ መስሎኝ ነበር። ስላስታወስከኝ አመሰግናለሁ» ፍርፍር ብላ ሳቀችበት። የተናገረችው እውነት መሆኑ ውስጡን ነካው። በራሱ ተናደደ።
« …በዚህ የድሮ ስልት አጀናጀንህ…ከዚህ በፊት የሆነ ቦታ አይቼሻለሁ አለማለትህም ያስመሰግናል»
ኑረዲን እንደተበለጠ ገባው። ሙሉ በሙሉ ከጨዋታ ውጭ አድርጋዋለች። አብሯት ሊያድር ነበር ፍላጎቱ። «ሸሌ ናት» ነበር ያለው ጓደኛው።
ሞራሉ ስለተነካ ፀጥ አለ። ረዘም ላለ ጊዜ እሷ እያወራች ምሽቱ ገፋ። በጨዋታ ስለተበለጠ ደብሮታል…
በሳቅ መሀል ሁና « …ግን በጣም ስላዝናናኸኝ …አብሬህ ላድር ወስኛለሁ…ከተመቸህ ነው የድሮ ሰው» አለችው። አልጋ እስከሚይዙ ድረስ አላመነም ነበር። «እንደዛ አሸማቃኝ እንደር ትለኛለች…እብድ መሆን አለባት » አለ በልቡ። ብቻ ወደ አልጋ መራችው። ሲንጣትና ስትንጠው አደሩ።
ጠዋት አልጋው ጠርዝ ላይ ሁና እያጨሰች ስልክ ተደወለላት።
«ሄሎ? ማን ልበል?»
«ሰሊዬ…እባክሽ አትዝጊው…ምን አረኩሽ ግን በጣም አፈቅርሻለሁኮ»
«አንተ ጅል!» የደወለውን ሰው ጆሮው ላይ ዘጋችበት።
ኑረዲን « ምን አይነት ደደብ ወንድ ነው?» ሲል አሰበ። «በንደዚች አይነት ሴት ጅል ከተባለ ደደብ ነው ማለት ነው»
ስለ ሰውየው ማሰብ ትቶ እሷን ትክ ብሎ አስተዋላት።
«እንዴት ግን እንደዚህ…ሆንሽ» አላት
ጥያቄው ግልፅ ነው… አጠያየቁም ከልቡ ነው። ካወቀችው ሳምንት ያልሞላት ወንድ ጋር አድራ አፈቅርሻለሁ የሚላት ሰው ላይ ስልክ እየዘጋች ነው።
«…ወንድ ልጅ ሲያፈቅረኝ ያስጠላኛል። አንበሳ የነበረ ወንድ ሲያፈቅር ድመት ይሆናል ፣ ይልመዘመዛል። ቂጥሽን ካልጠረኩልሽ…ሞዴስ ካልቀየርኩልሽ ይላል። አፍቃሪ የሚባል ነገር ደስ አይለኝም። ለወሲብ የፈለኩትን እቀርባለሁ…ሌላው ገደል ይግባ!» እንክት ያለውን ነበር የነገረችው።
«እና ከወንድ ልጅ ወሲብ ብቻ ነው የምትፈልጊው?…ፍቅር ምናምን…»
«ነገርኩህኮ…ፍቅር መጃጃል ነው»
«ግልፁን ለመናገር እኔም ሴቶችን የምቀርበው ለወሲብ ነው። ፍቅር ያስጠላል። እንደ ዛራና ቻንድራ የሚጃጃል ሰው ማየት እንዴት እንደሚቀፈኝ» እሱም የልቡን ነበር የነገራት። ደስ አላት። እሱም ደስ ብሎታል። በጎን ከፈለጋት ሴት ጋር ቢዳራ ምንም የማያፍርበት ግንኙነት እየጀመረ ነው። ከዚህ በፊት አንዲት ሴትጋ ጓደኛ ሁኖ በጎን ሲቀላውጥ ተያዝኩ አልተያዝኩ እያለ ይሸማቀቅ ነበር። «እድሜ ለሰላም!» አሁን ያ ቀረለት። ዘና ብሎ እንዳሻው ይቀላውጣል።
ከዚያስ?
አንድ ሳምንት ሀዋሳ ሄደው ዘሞቱ። ዝሙት…ዝሙት…ዝሙት!!! እስኪያቅለሸልሸው ድረስ። ሳምንቱን ፣ ወሩን ፣ አመቱን… በዚህ መንገድ አሳለፉ። እሱ ወጣት እንደመሆኑ የዘመናት ህልሙ የተሳካ ነበር የመሰለው። ግን እየተላመዳት እንደሆነ አልገባውም ነበር። ቀስ በቀስ ለስራ ጉዳይ እያለች ራቅ ወዳለ ቦታ ስትሄድ ትናፍቀው ጀመር። መጀመርያ የወሲብ ናፍቆት መስሎት ከለመዳቸው ሴቶች ጋር ተወራጨ። ግን ሊወጣለት አልቻለም። እየቆየ ጭራሽ ቻው ስትለው እንባው ይመጣ ጀመር።
ትንሽ ቆይቶ ደወለችለት
«የድሮው ሰው! አንገናኝም እንዴ ዛሬ?»አለችው። ሲከንፍ ነበር የሄደው።
የገዛላትን ስጦታ ሰጣት።
«ፓንት ነው ጡት ማስያዣ?» አለችው። «ይቺ ደግሞ ከዛ ነገር ውጭ ወሬ አታውቅም እንዴ» አለ በሆዱ።
ምሽት አልጋውን እያስጨነቁት እያለ ተደወለላት። ሲጨርሱ ለደወለላት ሰው መልሳ ደወለች
«ሄሎ»
«ሰሊዬ…የኔ ፍቅር»
«ስንት ሲም ነው ያለህ…ኣንተ!…ጅል!» ዘጋችበት።
«ማን ነው?» አለ ኑረዲን
«ምነው ያለ ልማዳችን ጠየከኝ» አለችው። ዙራ ስታየው ክፍት ብሎታል።
«እንዴ…ምን እየሆንክ ነው»
«ምንም» …እንደ ድሮው አልነበረም አዳራቸው። እሷ የሽማግሌ የምትለው አይነት አዳር አሳለፉ።
ለሊት ልብሷን ስትለባብስ ደንግጦ ተነሳ።ለመሄድ እየተዘገጃጀች ነው።
«ምን ሁነሽ ነው?»
«ከዚህ በኋላ እንዳታገኘኝ»
«ምን? ምን አድርጌ»
«ፍቅር ይዞሀል»
የሰጣት ስጦታ ጥቅሉ ተፈቶ መሬት ላይ ወድቋል። ሀብል ነው።
የሚናገረው ጠፋበት… ትታው ልትሄድ ነው
«ወላሂ! አላፈቅርሽም»
«ኸረ ባክህ»
«ሰው አታምኚም እንዴ? …እ…እ ወላሂ…እ ገብርኤልን…አላፈቅርሽም» ጋኔን እንዳለበት ሰው ለፈለፈ… አልሰማችውም። አይኑ እያየ ከእጁ ሾልካ… ትታው ሄደች።
የሆነ ቀን ደወለላት…
«ሰሊዬ…ስልኩን አትዝጊው…በጣም…»
«ጅል!!» ዘጋችበት!!
ካጠገቧ የነበረው ወንድ «ምን አይነት ነፈዝ ሰው ቢሆን ነው በእንዲች አይነት ሴት ጅል የሚባለው» ሲል አሰበ።
✨አለቀ✨

👍1
#ሮዛ_2
፡
፡
#ክፍል_አራት(🔞)
፡
፡
#የራኪን_ማስታወሻ_አነበብኩት
ራኪ እልህ ተጋባችኝ። እኔ ስጽፍ አይታ መጻፍ ጀመረች። ጭራሽ ያልፈጠረባትን። ለምን እንደምትጽፍ ስጠይቃት ያን የምትነግረኝ እኔ ለምን እንደምጽፍ ስነግራት ብቻ እንደሆነ ነገረችኝ፤ ፍርጥም ብላ። ገረመኝ። ለምን የኔ መቸክቸክ ይህን ያህል እንዳሳሰባት አልገባኝም።
አንድ ቀን ማስታወሻ ደብተሯን አልጋዋ ላይ ጥላው ወጥታ ደረስኩ። ከራሴ ጋር ከፍተኛ ዉዝግብ
ዉስጥ ገባሁ። ማንበብ አለብኝ ወይስ የለብኝም በሚል። ግማሽ ሰዓት ከራሴ ጋር ከተጣላሁ በኋላ
ተሸነፍኩ። ለሽንፈቴ የሰጠሁት ሰበብ «ራኪ የምትጽፈውን ማንበቤ ጥሩ ጓደኛዋ እንድሆን ይረዳኛል»
የሚል ነበር። በሩን ከዉስጥ ቆልፌ ቶሎ ቶሎ ማንበብ ጀመርኩ።
ምንም የረባ ነገር አልነበረውም። በየገጹ ትጽፋቸው ከነበሩ ዝብርቅርቅ ያሉ የተበጣጠሱ አረፍተ ነገሮች
የተረዳሁት ወደዚህ ሕይወት እንድትገባ ምክንያት የሆናት ዶ/ር ባይከዳኝ በሕይወቷ ዉስጥ ትልቅ
ቦታ እንደያዘ ብቻ ነው። እሱን ስታስታውስ እናቷን፣ እናቷን ስታስታውስ ሕይወቷን ታየዋለች። ያኔ እናቷ የሞቱ ሰሞን ዶክተር ባይከዳኝን ባታገኘው ራሷን ልታጠፋ ትችል እንደነበረ ጽፋለች። አጻጻፏ
ግን ያስቃል። በየገጹ ትሳደባለች። አንድ ነገር አንስታ ወደሌላው ትዘላለች። የሕጻን ልጅ ደብተር ነው የሚመስለው። ብቻ ከማስታወሻዋ የገባኝ ነገር ባይከዳኝን ትወደዋለች። የመጀመርያዋ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፤ ላለመሞቷ ምከንያት ስለሆነ ሊሆን ይችላል፤ ብቻ ለሱ ልዩ ስሜት እንዳላት በደንብ አድርጌ
ተረዳሁ።
እሱም ደግሞ እንደሚስት ባይሆንም እንደ ሸሌ እንደሚወዳት ጽፋለች። ብዙ ነገር ተባብሯታል
በምናውቀውና የማናውቀው። ለምሳሌ የብርክታዊት ልጅ አቡሻ ልቡን አሞት ዉጭ ሄዶ ካልታከመ
በሁለት ወር ጊዜ ዉስጥ ይሞታል የተባለ ጊዜ ተሯሩጦ፣ በቦርድ እንዲወሰን አድርጎ፣ከአገሪቱ ሐብታም ሰውዬ ስፖንሰር አፈላልጎ፣ ባንኮክ ያሳከመላት እሱ ነው፡፡ ይሄን ታሪከ እኔም አውቀዋለሁ። ሁላችንም እናውቃለን ለምን በማስታወሻ መፃፍ እንደፈለገች ግን ገርሞኛል።
እኔ እስከማውቀው ድረስ አቡሻ ድኖ መመለሱን ነበር።
በመጨረሻ እቡሻ ድኖ ተመለሰ። ልክ ድኖ የተመለሰ ቀን እናቱ ብርከታዊት የልጁን ስም ከአቡሻ ወደ
"ባይከዳኝ" ለመለወጥ ጊዜ አልወሰደባትም። እኛ ግን አሁንም ልጇን አቡሻ ነው የምንለው። ባይከዳኝ
ካልነው ትልቅ ሰው የሆነብን ይመስለናል። ራኪም ስሙ ወደ ባይከዳኝ መለወጡ እንዳልተመቻት ማስተዋሻዋ ላይ ፅፋለች።እናትየው ብርክታዊት ግን ወይ ፍንክች! ያባ ቢላዋ ልጅ።
ብርክታዊት በዚያው ከህክምና በተረፈው ገንዘብ ወዲያው ከሽርሙጥና ሕይወት ተሰናበተች። አሁን ለቡ አካባቢ «ካፕል ሀውስ» ያለው ምርጥ ካፌ ከፍታ አሪፍ ብር ትሰራለች። አትላስ የምትመጣው
ራኪ ወይም እኛ ስንናፍቃት ብቻ ነው።
ራኪ ጠርቀም ያለ ገንዘብ የግድ ሲያስፈልጋትም ዶክተር ባይከዳኝን እንደምትበደረው ጽፋለች
“የተበደርኩት ብር ዝርዝር በሚለው ስር ብዙ ዜሮ ያለባቸው ቁጥሮች ተደርድረዋል። ራኪ ነፃ ስለሆነች ነው መሰለኝ ዶ/ር ባይከዳኝ ይወዳታል። በሞቅታ ቢሆንም ብቻ አንድ ልጅ ከሷ እንዲኖረው እንደሚፈልግና ያንንም እንድትፈጽምለት እንደጠየቃት ከዚህ በፊት በምስጢር ነግራኛለች።
ማስታወሻዋ ላይም ይህንኑ ጽፈዋለች። እንዲህ ብላ
“ .እሺ ባንዳፍ አልኩት። እሺ ስለው ግን ያለኮንዶም ከኔ ጋር ሴክስ ለማድረግ ፈራ። እንደዚያ ሰሞን ሸሌነቴን ጠልቼው አላውቅም። በብስጭት ታመምኩ። …በምን እንደታመምኩ ማንም አያውቅም።
ደግነቱ ያው እንደተለመደው እሱ ከሊኒክ ሄዳ አንዳንድ ቁልፍ ቦታዎች ሲነካካት ወድያው ይሻላታል።
ራኪ ማስታወሻዋ ላይ ባትጽፈውም ከዚህ በፊት እንደነገረችኝ ከሆነ ዶክተር ባይከዳኝ አምስት ትልልቅ
ሴት ልጆች አሉት። የሁሉንም ልጆቹን ፎቶ አሳይቷታል። ትልልቅ ናቸው፤ እንደሱ ረዥም እና ጥቋቁር ናቸው፡፡ የሚገርመው ሁሉም ሐኪም መሆናቸው ነው፡፡ አራቱ አሜሪካ ናቸው። ኢህአዴግ
ስልጣን ካልለቀቀ አገር ቤት መምጣት አይፈልጉም። የመጨረሻዋ ትንሿ ጅማ ሕክምና ትማር ነበር።
ሚስቱም የቆዳ ሐኪም ናት። አሜሪካ ቺካጎ በምትባል ስቴት ነው የምትሰራው። በሦስት ወር አንድ ጊዜ መጥታ ትጎበኛቸዋለች፤ እሱም በተራው አሜሪካ ሄዶ ሚስቱንና ልጆቹን በየተወሰነ ጊዜ ልዩነት ይጎበኛቸዋል። ከሚስቱ ጋር በተኽሊል ስለተጋቡ እስከዛሬም አልተፋቱም። ኾኖም ፈታ ብለው ነው
የሚኖሩት። እሷም በፈረንጅ ትደከላለች፣ እሱም ራኪን ይደከላል።
ዶክተር ባይከዳኝ ከራኪ ዉጭ ግን ሴት ያሻፍዳል እንጂ አይነካም ይባላል፤ ለራኪና ለሚስቱ ታማኝ ነው። ራኪ ሆስፒታል ያሉት ነርሶች እንዴት እሱን ለማጥመድ ቀን ተሌት እንደሚሰሩ ታውቃለች።
እሱ ግን አልተሸነፈላቸውም” ብላኛለች።
ሮዚ ሙች! ምን እንደሚያስፈራኝ ታቂያለሽ? አንድ ቀን ነርሶቹ በር ዘግተው ባይከዳኝን እንዳይደፍሩት ብቻ ነው፤ እመቤቴን የውነቴን ነው፤ እንዴት እኮ እንደሚሻፍዱ ስላላየሻቸው ነው አንቺ!" ብላ ስጋቷን ነግራኝ ታውቃለች።
ራኪ አፍቃሪ ናት። “ሮዚ! አንድ ነገር ልንገርሽ? ባይከዳኝን ቂጤ እስኪንቀጠቀጥ ነው የምወደው!»
ትላለች፤ እንዲህ የምትለው ግን ስትሰክር ወይ ስትጦዝ ብቻ ነው።
ራኪ ነፍሴ!!
ምናለ ፈጣሪ ህልምሸን ቢያሳካው የስንቱን ቀጣፊ ሰባኪ ሕልም ያሳካ የለ? በየቀኑ የስንቱን ሸርሙጣ ወንድ ፀሎት ይሰማ የለ? አንቺ እኮ ገላሽ በአጋጣሚ አጓጉል ስራ ዉስጥ ገብቶ ነው እንጂ ልብሽ ቅዱስ ናት። ራኪ ሙች! ይሄንን እንኳን እኔ እግዚአብሔርም መመስከር የሚችለው ነው። እወድሻለሁ!
#ስሙን_የማይነግረኝ_ዶከተር
ዶከተር የሚለውን ቃል እንደ ዲክሽነሪ ተርጉሚው ብባል "A person full of himself” ብዬ የማስል ይመስለኛል። ሁሉንም ዶክተሮች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ይኸው ነው። ስለ ራሳቸው አውርተው አይጠግቡም።እኛ ዘንድ የሚመጡት በዋናነት ለሴክስ አይመስለኝም። ለጀሮ ነው። ጆሯችን
በልጥጠን ስለምንሰጣቸው ይወዱናል።
አዳዲስ ደንበኞቼ ዶ/ር መሆናቸውን ካወቅኩ የጆሮ ሰርቪስ እያልኩ extra ባስከፍል ስግብግብ ልባል አይገባም። እነሱስ “የካርድ" እያሉ በየሆስፒታሉ መቶ መቶ ብር ይነጩን የለ? ማን ይሞታል!
በዚያ ላይ ጢባራቸው። ዶክተር ሲባሉ ደሞ አንድ አይነት፤ ሁሉም። እጅ በኪስ አድርገን ሴክስ እናርግሽ ማለት ነው የሚቀራቸው። ሲያስጠሉ!
ለነገሩ እኛም ሰፍ እንልላቸዋለን መሰለኝ። እንደምንደነግጥላቸው ስለሚያውቁ ነው የሚንጠባረሩት ማዕረጋቸው የትኛዋንም ሴት እንደሚያስበረግግ አሳምረው ያውቁታልየሚንጠባረሩት። ለዚያ ይመስለኛል ትንሽ ኢጓቸው ሲነካባቸው የሚንጰረጰሩት። ስሙን የማይነግረኝ የነበረ ደምበኛዬን አልረሳውም።
አንድ ከእግሩ ሸፈፍ፣ ከቁመቱ አጠር፣ ከኩራቱ ረዘም ያለ ደምበኛ ነበረኝ። ስሙን እንኳ ለመናገር
የሚጠየፈኝ። Just call me “The Doctor! » ይለኛል ስሙን ተሳስቼ ከጠየቅኩት። ደሞ የኔን ስም
ስንቴ እንደነገርኩትና ስንቴ እንደሚረሳው። ይህ ባህሪው እርር ነበር የሚያደርገኝ። እልህ ስለሚይጠዘኝ
ደሞ እጥፍ አስከፍለዋለሁ፤ አይከራከርም፡፡ ይህም ያናድደኛል። ከወጣሁለት በኋላ ደግሞ በራሴ
እናደዳለሁ። ምናለ እምቢ ባልኩት ብዬ እርር ደብን ትካን እላለሁ።
ዶክተሩ ከፍተኛ የሸሌና የሕዝብ ንቀት አለበት። የሚገርመኝ እንዲህ ሁሉንም ህዝብ ከናቀ ለምን በጊዜ ታንቆ እንደማይሞት ነው። እንዲህ ከሚንቀው ህዝብ ጋር ዘላለም ተናንቆ ከመኖር መታነቅ የሚቀል መሰለኝ፤ ሆ! ስንት አይነት ወንድ አለ!

👍3❤1
ባለፈው አርብ ለት እንደ ሁልጊዘው አምቦውሃና ጂን ቀላልቅሎ በፍጥነት መጠጠት ከጀመረ በኋላ ሆቴል
ይዞኝ ሄደ ሁልጊዜም የተረፈውን መጠጥ ይዞ ነው ወደ ሆቴል የሚገባው። ሩም እንደገባን ከረቫቱን አላላና የሸሚዙን ቁልፎች በግማሽ ፈታቶ አልጋው ጫፍ ላይ እንደተቀመጠ ድንገት በሀሳብ እልም ብሎ ጠፋ። እኔ ከላይ ልብሴን አወላልቄ እየጠበቅኩት ነበር እሱ ብድግ ብሎ ወደ ሶፋው ሄደና ሶፋው ላይ
ተንጋሎ በአንድ እጁ ጂኑን እንደያዘ በሌላ እጁ የዲኤስቲቪውን ሪሞት አንስቶ ዜና ማየት ጀመረ። እኔን መፈጠሬንም ሳይረሳኝ አልቀረም፡፡ ብታገሰው፣ ብታገሰው፣ ሊመጣ ነው?!
ዶክተር በላ! አውልቅና ኮንዶም አጥልቅ….!» አልኩት ሳላስበው። የእውነት አስቤው ሁሉ አልነበረም
እንደዚያ ያልኩት። እሱ እቴ! ለምን ደሙ አይፈላም፣ ይቺን በመናገሬ ብቻ ያን ምሸት የደረሰብኝ መከራና ያየሁትን ፍዳ… እኔ ነኝ የማውቀው። የአንድ ሰዓት ሌክቸረር ለቀቀብኝ። ቋቅ እስኪለኝ።
መጀመርያ ደምስሩ ተገታተረ። ቀጥሎ በዚያች ቁመቱ ሽቅብ በንቀት እያየኝ ተንጰረጰረ። አጫጭር ወንዶች እንኳን ዶክተር ሆነው እንዲሁም ኮምፕሌክሳምና ተንኮለኛ እንደሆኑ አውቃለሁ። የዚህ ሰው
ግን በዛ። አስጠላ።
«ስሚ! ባታውቂኝ ነው እንጂ!» ብሎ ሦስት ተከታታይ ሾርት የምሰራበትን ሰዓት ሙሉ ነዘነዘኝ። አምባረቀብኝ። ዛተብኝ። በአፉ ሸናብኝ ብል ይቀላል። ብቻ ያልሆነው የለም። ሌላ ጊዜ ማንም ወንድ
ምንም አይነት ብር ይከፈለኝ ንቀት ካሳየኝ ጥየው ነው የምሄደው። ይሄ የኔ ባህሪ ነው። ለንቀት ትዕግስት የለኝም። ያን ምሸት ግን ያልጠበቅኩት ስለነበረ ነው መሰለኝ ደንዝዤ ቀረሁ።
ሱሪ አውልቅና ኮንዶምህን አጥልቅ» ማለት ቆይ ምኑ ነው የሚያናድደው? አቤት እንዴት ቆሽቴን
እንዳሳርረው ያን ቀን!
ለሱ ሀኪም መሆን እግዚያአብሔር ከመሆን ለይቶ አያየውም መሰለኝ። «…ባታውቂኝ ነው…» ይለኛል
እንዴ ደሞ? አሁን እሱን ማወቅና ኮንዶም ማጥለቅ ምን አገናኛቸው!? ዶክተር መሆኑን ሲሰሙ ቫይረሶቹ እግሬ አውጭኝ ብለው የሚፈሰጥጡ መሰለው እንዴ?
ከኔ ይበልጥ የጦፈው ግን እሱ ነበር ለካ። በንዴት ሪሰፕሽን ደወለና ሌላ ቦትል ጂን አስመጥቶ መጠጣት ጀመረ። የጀመረውን ትቶ ማለት ነው። ገና እኮ የያዘውን ሳያጋምስ ነው ሌላ የሚያዘው። ሩም ድረስ ያመጣለትን አስተናጋጅ ሁለት የመቶ ብር ኖቶችን አውጥቶ ቲፕ አረገው። አስተናጋጁ ከቁጥጥሩ ውጭ
በሆነ የደስታ ስሜት ጭራውን ቆላለት።እሱም ይሄንን ነበር የፈለገው መሰለኝ፤ ሁሉም ሰው ጭራውን
እንዲቆሳለት። አይገርመውም! እኔ በፍጹም ጭራዬን ለሰው አልቆላም። ባፋንኩሎ፤ “የናትህ እምስ ትለው ነበር ራኪዬ ብትኖር። የማነው በናታችሁ!
“ለመሆኑ ስንት እንደሆንን ታውቂያለሽ? ብሎ ነበር ማንቋረር የጀመረው። በወቅቱ ምን ማለቱ እንደሆነ አልገባኝም ነበር።
Believe it or not ለዚህ አሸዋ ለሆነው 70 ሚሊዮን ህዝብ ሁለት ሺ እንኳ አንሆንም፣ ያለንለት።
ሆኖም እንደምታይው ነው! በቃ.ስለኛ ግድ አጥቷል.…አይንከባከበንም። እንዲያው ያንጓጥጠናል።
yeah…ንቆናል፣ መፈጠራችንንም ረስቶታል፤ yeah…ትዝ የምንለው ታይፎይድ ሲያንደፋድፈው ብቻ
ነው። እንኳን ሕዝቡ ሸሌ ንቆናል። ባንናቅ እንዲህ አትናገሪኝም ነበር።
ይቅርታ ልጠይቀው ስል አስቆመኝ።
"ታምኚያለሽ!?ታክሲ ከህዝብ ጋር ተጋፍተው የሚሄዱ ባልደረቦቼ እንዳሉ?እየዋሸሁ አይደለም። literally ከተራው ህዝብ ጋር ታከሲ የሚጋፉ ሀኪም ጓደኞቹ አሉኝ! Yeah True story ነው የምነግርሽ።
ህዝቡ ነጭ ጋውን ካልለበስን ሀኪም መሆናችንንም ማወቁን እንጃ፤yeah…ይሄ ህዝብ እንዲያከብረን በየመሸታ ቤቱ፣ በየጎዳናው ጋውን ለብሰን መገኘት አለብን?l Tell me አለብን? ይሄ ህዝብ እሺ በስም አይወቀን፤ ነገር ግን በመልክ እንዴት አያውቀንም? 2ሺ የማንሞላ ሀኪሞቹን በመልከ ማወቅ እንዴት
ያቅተዋል?..አሁንማ ስጋ ነጋዴም የኛኑ ጋውን ማጥለቅ ጀምሯል።ህዝቡ ከበሬ አራጅ እኩል ቢያየን የሸፈረድበታል ታዲያ? ዉርደት እኮ ነው ይሄ!
ይንጎራደዳል ደሞ አጠጣጡ ጂን ሳይሆን ጁስ የሚጠጣ ነው የሚመስለው። አስፈራኝ። ስላስፈራኝ ደርቄ አየዋለሁ።
"You see_ህዝብ ብቻ አይደለም የረሳን፣ ጤና ጥበቃ ረስቶናል፤ አንድ ቀን የበሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ በደንብ የምንፈለግበት ቀን ይመጣል ብዬ እጠብቃለው የጤና ባለሙያዎችን ወያኔ ረስታናለች።የወያኔ እንኳ ተይው፤ አይነሳ! ወያኔ ድሮም ደንቆሮ ናት፤ አሁን ደሞ ብሶባታል። እንኳን ሕዝብን እኛንም መስማት አቁማለች። እንኳን እኛን ራሷንም አትሰማም። እርስበርሷ መደማመጥ አቅቷታል…ነጻ አወጣሃለሁ
ብላ የተዋጋቸለትን ሕዝብ እንኳ ትዝ የሚላት ምርጫ ሲደርስባት ነው…ተምቤን ስሰራ ሁሉንም ጉዷን
አይቼዋለሁ? የራሷን ሕዝብ እንኳ ረስታለች። yeah
“ሐኪም የሚንቅ መንግስት እድሜው አጭር ነው። ይሄ ታሪክ የመሰከረው ነው። ሕዝብና ሐኪም የናቀ መንግስት አብቅቶለታል። ወያኔ አልገባትም እንጂ ቢሆን ቢሆን ቄጤማ እያነጠፈች፣ አበባ
እየበተነች፣ዘምባባ እያውለበለበች ነበር ልትንከባከበን የሚገባት። yeah…ተሳሳትኩ? ከተሳሳትኩ እታረማለሁ?
“አሁንማ የንቀቷ ንቀት ፎርጅድ ሐኪም በየጎጡ እንደ አሜባ እያራባች ህዝቡን ልታስጨርሰው ቆርጣ ተነስታለች። የራሷን ሹመኞች ታይላንድ እያሳከመች፣ ህዝቡን በጥቃቅንና አነስተኛ ሀኪም
ታስፈጀዋለች። yeah ተሳሳትኩ?.ለሳል የሬሳ ማድረቂያ መርፌ የሚወጋ ሐኪም በቃለ መሐላ ያስመረቀች በዓለም ላይ ወያኔ ብቻ ናት። yeah ይሄን ታውቂያለሽ? I tell you! ወያኔ ሀኪም ንቃ
ከዚህ በኋላ ብዙ አትራመድም። ከነጻ አውጪነት ተነስታ አሁን እያመነመነች ህዝብና አገር የምትገድል
አደገኛ በሽታ እየሆነች ነው yeah…ተሳሳትኩ? እውነት አይደለም?”
ይህን ተናግሮ ላንቃው እስኪበጠስ ሳቀ! በተናገረው ነገር ኩራት ተሰማው። ወዲያው ደግሞ ፈራ መሰለኝ የሰማው ሰው ካለ በሚል ነው መሰለኝ በሩ መዘጋቱን ሄዶ አረጋገጠ
"ስሚ ደሞ የፈራሁ እንዳይመስልሽ! እኔ ነኝ ወያኔን የምፈራ? ለአቅማዳም ከደረስኩ ጀምሮ እንኳን ሰው ፈጣሪን ፈርቼ አላውቅም! ኦኬ.አይምሰልሽ!…»
ይሄኔ የምር ሳቄ መጣ። ፈርቶ እኮ ነው በሩ መዘጋቱን ሄዶ ያረጋገጠው። የሰካራም ነገር! ቆይ…ሰክሮ
እንዲህ ከፈራ ባይሰክር ኖሮ ምን ሊሆን ነበር? ሽንቱን ሱሪዉ ላይ ሊለቀው ይችል ነበር ማለት እኮ ነው። ሳቄን አፍኜ አቀረቀርኩ። ቆይ እኔ ላይ ጉራውን እንዲህ ከሚቸረችር ጫካ አይገባም? ሁሉም ወንድ ፍርሃቱን በኛ ያስታግሳል። ሲያስጠላ! ቦቅቧቃ ወንድ ያስጠላል!
የያዘው ሩም Luxury Suite ስለነበር በጣም ሰፊ ነው። በዚያ ሰፊ ሩሙ ግራና ቀኝ እየተንጎራደደ ሲያወራ ቲያትር የሚሰራ ነው የሚመስለው..
💫ይቀጥላል💫
Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ
#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email መጠቀም_ትችላላችሁ👇
rozachichinia@gmail.com
ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍2❤1😱1
#ዝረፍ_ዝረፍ_አለኝ
ሽርክተው ሆዱ ላይ
ይጎልጎል አንጀቱ ህብር ቅኔነቱ
ይበጥበጥ ሃሞቱ፡፡
ፊኛውን ሽንትረው
ይንቆርቆር በሆዱ ምስጢር ውል አንቀፁ
የማያልቅ ሽንቱ፡፡
ባዶነቱን ፈትሽ ገቢር ተገብሮውን ከሱሪ ከኮቱ፡፡
ማንደርደሪያው ድረስ ይሩጥ እስከ ቤቱ፡፡
ያንተ ነው የኪሱ ያንተ ነው ጥሪቱ፡፡
ከምስጢሩ ስበር ከጉልጥምቱ መቅኔ፤
ዝረፍ ዝረፍ አለኝ
ንጠቅ ንጠቅ አለኝ የየኔታን ቅኔ፡፡
ሽርክተው ሆዱ ላይ
ይጎልጎል አንጀቱ ህብር ቅኔነቱ
ይበጥበጥ ሃሞቱ፡፡
ፊኛውን ሽንትረው
ይንቆርቆር በሆዱ ምስጢር ውል አንቀፁ
የማያልቅ ሽንቱ፡፡
ባዶነቱን ፈትሽ ገቢር ተገብሮውን ከሱሪ ከኮቱ፡፡
ማንደርደሪያው ድረስ ይሩጥ እስከ ቤቱ፡፡
ያንተ ነው የኪሱ ያንተ ነው ጥሪቱ፡፡
ከምስጢሩ ስበር ከጉልጥምቱ መቅኔ፤
ዝረፍ ዝረፍ አለኝ
ንጠቅ ንጠቅ አለኝ የየኔታን ቅኔ፡፡
#ስቀሽ_አበረድሽኝ
ከጥም ቆራጭ ምንጭሽ ፥ ልጠጣ ጎምጅቼ
ላታልልሽ ዝቼ
ጢሜን ተላጭቼ
ጫማዬን አጥድቼ
በሚያሽበለብል ቃል ፥ ምላሴን ገርቼ
ለበአሌ ላርድሽ ፥ ቢላዋየን ስዬ
ሁዳዴን የጦመ ፥ መልካም ሰው መስዬ
እንደ አታላይ ተኩላ
ሊነጥቅ ሊበላ
ለምድ እንደለበሰ ፥ በበጎች መካከል
ሳር መጋጥ ጀምሮ ፥ መንጋውን ለመምሰል
በዚያው እንደቀረ ፥ የሰርዶ ጣም ወዶ
ጨዋታ ወግሽን ፥ ዠሮየ ተላምዶ
ፍቅር አልብሰሽኝ …
ውሀ ልሰርቅሽ ስል ፥ እርጎ አበድረሽኝ
ነድጄ መጥቼ ፥ ስቀሽ አበረድሽኝ
🧿በናትናኤል🧿
ከጥም ቆራጭ ምንጭሽ ፥ ልጠጣ ጎምጅቼ
ላታልልሽ ዝቼ
ጢሜን ተላጭቼ
ጫማዬን አጥድቼ
በሚያሽበለብል ቃል ፥ ምላሴን ገርቼ
ለበአሌ ላርድሽ ፥ ቢላዋየን ስዬ
ሁዳዴን የጦመ ፥ መልካም ሰው መስዬ
እንደ አታላይ ተኩላ
ሊነጥቅ ሊበላ
ለምድ እንደለበሰ ፥ በበጎች መካከል
ሳር መጋጥ ጀምሮ ፥ መንጋውን ለመምሰል
በዚያው እንደቀረ ፥ የሰርዶ ጣም ወዶ
ጨዋታ ወግሽን ፥ ዠሮየ ተላምዶ
ፍቅር አልብሰሽኝ …
ውሀ ልሰርቅሽ ስል ፥ እርጎ አበድረሽኝ
ነድጄ መጥቼ ፥ ስቀሽ አበረድሽኝ
🧿በናትናኤል🧿
#እንዲሁ_ለምወድሽ
አንቺ ባትኖሪም ፣ ስላንቺ እፅፋለሁ
አንቺ ባትሰሚኝም ፣ ስላንቺ አወራለሁ
አንቺ ባትቀጥሪኝም ፣ አንቺን 'ጠብቃለሁ
ውዴ ሙሽራዬ ፣ ፍቅሬ አፈቅርሻለሁ ።
አንቺ ባትኖሪም ፣ ስላንቺ እፅፋለሁ
አንቺ ባትሰሚኝም ፣ ስላንቺ አወራለሁ
አንቺ ባትቀጥሪኝም ፣ አንቺን 'ጠብቃለሁ
ውዴ ሙሽራዬ ፣ ፍቅሬ አፈቅርሻለሁ ።
#አልነጋም
፡
፡
#በናትናኤል
ዛሬም እንደትናንቱ ፣ እንደ ትናንት ወዲያው ፤ እንደ ጥንቱ ፥ እያለቀሰ መጣ!
እ… ህ… ህ… ህ! አንጀት የሚበላ መንሰቅሰቅ!
እናቱ የሚያለቅስበትን ምክንያት የማታውቅ ይመስል ልቧ በፍርሀት እየተርገፈገፈ ፣ አንዳች ነገር ውርር እያደረጋት
«ወይኔ ልጄን! ምን ሁነህ ነው ? ምን ሆንክብኝ የኔ ጌታ?» እያለች በስስት ደባበሰችው።
«…አትጫወትም አሉኝ! …እህህህህህ!…»
«እነማን ናቸው?» እንዲወጣለት ጠየቀችው እንጂ እነማን እንደሆኑማ በደንብ ታውቃለች። በየቀኑ እንዲህ እያለቀሰ ይመጣል። ብቻ ሌላ ነገር ገጥሞት ቢሆንስ እያለች ነው ልቧ የሚሸበረው።
«እነ ሳምሶን …እህህህ… እነ አብዱ …እህህ…» በመሀል በመሀል ለቅሶውን እያስገባ የሰባቱንም ስም ጠራላት። ያው የምታውቃቸው ስሞች ናቸው።
«አይዞህልኝ የኔ ጌታ!»
እቅፍ ስታደርገው ሙቀቷንና ጠረኗን ስቦ… ለቅሶው እየበረደ ስቅ! ስቅ! የሚለው ብቻ እየቀረ መጣ
«አልነጋምኮ ነበር! ገና ነው …አልነጋም ስላቸው …አይችልበትም ብለው አባረሩኝ»
«አይዞህ በቃ የኔ ጌታ…ምን ያውቃሉ ብለህ ነው እነሱ? »…እቅፏን ጥብቅ አድርጋ አረጋጋችው። ከዚያ ውሀ አውጥታ ፊቱን ካጠበችው በኋላ ዳቦ ቆሎ ሰጥታው ጓዳ ገባች። አንገቷን ወደ ላይ ቀና አድርጋ
«ምን አደረኩህ ጌታዬ? ከቶ ምን በደልኩህ? እግዚኦ!…» ልጇ እንዳይሰማት ድምጿን አፍና ተንሰቅስቃ አነባች።
…
በበነጋታው…
የክረምት እረፍት ላይ ናቸው። ለመጫወት ተሰብስበዋል። ዮሴፍም አብሯቸው አለ።
«አኩኩሉ እንጫወት»
«እሺ»
«ማን ይጨፈን?»
«እኔ እጨፈናለሁ»አለ አንድ ልጅ ። እሱ ሲጨፈን ሌሎቹ ለመደበቅ ሮጡ። ዮሴፍን አንድ መልካሙ የተባለ ወፍራም ልጅ
«ቆይ እኔ ላስደብቅህ» አለና ካንዲት ዛፍ ስር ወስዶ አስቀምጠው። የተጨፈነው ልጅ
«አኩኩሉ» ይላል ጮክ ብሎ። የሚደበቁት ልጆች ቦታ እስከሚያገኙ ድረስ «አልነጋም» እያሉ ይመልሳሉ። ሁሉም ተደብቀው ሲያልቁ ከመሀላቸው አንዱ «ነግቷል» ብሎ ይመልሳል። እናም ቀስ በቀስ ሁሉም ተደበቁ።
አብዱ የተባለው ልጅ «ነግቷል» አለ ጮክ ብሎ። ተጨፋኙ ለማረጋገጥ በሚመስል አኳኋን «ነግቷል?» ሲል ጠየቀ። ወዲያው ዮሴፍ «አልነጋም» ብሎ ሲቃወም ተደመጠ። «አልነጋም!!» …ሁሉም ከተደበቁበት እየወጡ ከበቡት።
ተዋበች የምትባል ጠይም ልጅ «ዮሴፍ…ይሄኮ ጨዋታ ነው…ለምንድን ነው የምትረብሸን?»
«እህ! አልነጋም ኣሃ! እኔ ሲነጋ የማላውቅ መሰለሽ?» አለ እንባ እየተናነቀው። ሲነጋ እንዴት እንደሆነ በአይነ ህሊናው ትውስ አለው። ጎህ ከወደ ምስራቅ ፍንትው ሲል ፣ የቤተ ክርስትያኑ ጉልላቶች የወርቅ እንቁላል መስለው ሲያብረቀርቁ ፣ የመስጂዱ ጫፍ ሰማዩን የሸነቆረው ሲመስል ፣ ደግሞ ደመናው ፀዳል ተንቦግቡጎበት ሲያንዣብብ። ያውቃል እንጂ! ሲነጋ እንዴት እንደሆነማ በደንብ ያውቃል። ይልቅስ ማወቁን እነሱ መዘንጋታቸው በጣም አስገረመው። እንደውምኮ ያኔ ጠዋት ፀሀይን ለረጅም ጊዜ ማን አፍጥጦ ያያታል? እየተባባሉ ሲጫወቱ እሱን ለማሸነፍ ሲፎካከሩት ነበር። ያን ቀን … ቀስ በቀስ እየመሸ ሲሄድ…ትዝ አለው። እና አሁን ነግቷል የሚሉት ምን አይነት አነጋግ ነው?
«በቃ አትችልበትም። አትጫወትም» ብለው አባረሩት።
ዛሬም እንደትናንቱ ፣ እንደ ትናንት ወዲያው ፤ እንደ ጥንቱ ፥ እያለቀሰ ሄደ!
እ… ህ… ህ… ህ! አንጀት የሚበላ መንሰቅሰቅ! እያሰማ። እቅፏ ውስጥ አስገብታ ካፅናናችው በኋላ ፊቱን አጠበችው። ዳቦ ቆሎ አቀረበችለት።
«ደግሞ ወደ ውጭ ከሄድክ ጥቁር መነፀርህን አድርግ አላልኩህም?» ብላው ጓዳ ገባች። እንደተለመደው ተንሰቅስቃ ልታነባ። «ምናለ የኔን ብትሰጠው» ብላ ልትፀልይ።
💫አለቀ💫

❤1
#ሮዛ_2
፡
፡
#ክፍል_አምስት (🔞)
ሲያወራ ቴአትር የሚሰራ ነው የሚመስለው፡፡ ቀጠለና ደሞ ወደኔ በጣም ተጠግቶኝ ማውራት ጀመረ።
አንድ ህዘብ ሞቱን የሚታደግለት ሀኪሙን ከናቀ ምን ተስፋ ያለው ይመስልሻል ?.ንገሪኛ
የያዘውን ጂን ትቶ ቅድም ትቶት የነበረውን ጂን ጠርሙስ መልሶ አነቀ። አንድ ጊዜ ጨልጦለት ሊያበቃ መንጎራደዱን ቀጠለ፤
“ስምሸን ማን ነበር ያልሽኝ
“ሮዛ!”
"…whatever…አንቺ ራሱ ህዝብ ነገር ነሽ! Yeah… እንደማንም ተራ ዜጋ ቆጥረሽኝ ስታበቂ… ሱሪ አውልቅ፣ ኮንዶም አጥልቅ» ትይኛለሽ?! እኛ ፊዚዪሺያን ሸርሙጣ ቤት እንኳ የማንከበር rubish ሆነናል ማለት እኮ ነው! You should be sorry! እሺ! ለተናገርሽው ነገር። yeah.በእውነቱ ከዚሁ በላይ ምን አሳፋሪ ነገር አለ? በውነት ይሄ ለዚች ድሀ አገር የሞት ሞት አይደለምን? ..tell me ከተሳሳትኩ እታረማለሁ…»
አልጋው ጫፍ ላይ በፍርሃት ቁጢጥ ብዬ እንደትንግርት አየዋለሁ…ጡቶቼን በመዳፎቼ ሸፍኜ ሽቅብ እመለከተዋለሁ። ሁኔታዬን ሲያይ የሚለውን በጥሞና እየተከታተልኩ መሰለው መሰለኝ የማውራት ሞራሉ በእጥፍ ጨመረ።
“ለመሆኑ ፊደል ቆጥረሻል? 2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ፈረንሳይ በቻርለስ ደጎል ድል የቀናት ለምን
ይመስልሻል?.…ሴቶቻቸው ለወታደሩ ጭናቸውን ሳይሰስቱ ቤዛ እንዲያደርጉ በማድረጉ ነው፤ yeah…!
Believe it or not። ታሪክ ብታነቢ ይሄን ታውቂ ነበር። ሆኖም ሸርሙጣ ሆነሽ ይሄን ታሪክ ታውቂያለሽ ብለን አንጠብቅም። ተሳሳትኩ? ከተሳሳትኩ እታረማለሁ…።
“ሸርሙጣ መሆንሽ ግን ከማንበብ ሊያግድሽ አይገባም። yeah…!!ሙ…ች! እውነቴን ነው የምልሽ!
ጭንሽን መክፈት ማለት የግድ አእምሮሽን መዝጋት ማለት አይደለም። not necessary! ማንበብ መብትሽ ነው
yeah...why not?"
".እንዲያውም ልንገርሽ…ቪየና በካርል ፍራንዜን የህከምና ትምህርት ቤት ተለማማጅ ሀኪም ሳለሁ
አንድ የማዘወትራት መሸታ ቤት ነበረች። ስሟን በርግጥ ረስቻታለሁ.…።
“ስምሸን ማን አልሸኝ?” ሲድጋሚ ጠየቀኝ።
"የማን? የኔን ነው?”
"ታዲያ የማንን ነው፤ ከኔና ካንቺ ሌላ እዚህ ክፍል ዉስጥ ሰው አለ?” ተበሳጨብኝ።
“የኔ ሮዛ… "
-yeah whatever ብቻ እዚያ ተለማማጅ እያለሁ…የአገሬው ሸርሙጦች ባለጌ ወንበር ላይ ወፋፍራም መጽሐፍ ይዘው ነው የሚቀመጡት። ያየሁትን ነው የምነግርሽ! ምናልባት ላታምኚኝ ትችያለሽ…አዎ!
የምነግርሽን ታምንኛለሽ? No you don't! ባታምኚኝም መናገር ያለብኝን እናገራለሁ።
“ደምበኛ እስኪመጣ መጽሐፍ በዉስኪ እያወራረዱ ነው የሚጠብቁት። Yeah! hookers read books while waiting for their clients! ይህንን በዓይኔ በብረቱ ነው ያየሁት። ባላይ ለማንም ደፍሬ አፌን ሞልቼ ባልተናገርኩ። yeah !! ይሄ ነው ልዩነታችን።
“እዚች አገር እንኳ ሴተኛ አዳሪ የከተማ አስተዳዳሪ መጽሐፍ አያነብም። ቤተ-መጽሐፍት ሳይሰሩ ድንጋይ ጠርበው መንገድ ይሰራሉ። ቅድሚያ ድንጋይ ነው መጠረብ ያለበት የሰው አእምሮ? ንገሪኝ።
የአእምሮ መንገድ ነው የሚቀድመው የእግር መንገድ? ይሄ ሕዝብ የት እንዲሄድ ነው መንገድ የምትሰሪለት? ወዴት እንደሚሄድ ጨርሱኑ የት ያውቀውና! Yeah! ከተሳሳትኩ ልታረም። የማያነብ ሕዝብ የት ደርሶ ያውቃል? Tell me…የት ደርሶ ያውቃል?
“...እንዴት ነው በዚህ ሁኔታ አገር የምታድገው? ለመሆኑ አንቺ በህይወትሽ መጽሐፍ አንብበሽ
ታውቂያለሽ? መጽሐፍ ተይውና መጽሔት አንብበሽ ታውቂያለሽ? እርግጠኛ ነኝ አንድ መጽሐፍ አላነበብሽም። እኔ ዓለምን ዞርያለሁ… በስራ አጋጣሚ ይቺን ዓለም ከሰሜን እስከ ደቡብ ዞርያታለሁ።
believe it or not እንደ ሀበሻ ማንበብ የሚያስፈራው ዘር አይቼ አላውቅም። አውሮፓ ሴተኛ አዳሪ መጽሐፍ ያነባል። እዚህ ግን በየጠንቋይ ቤቱ እየሄዳችሁ መዳፍ ታስነብባላችሁ። የማትረቡ!!
ወደ ሶፋው ሄዶ ቲቪውን ሙሉ በሙሉ አጠፋውና ከጂኑ ተጎነጨለት።
"ስምሽን ማን ነበር ያልሽኝ"?
ዝም አልኩት።
"whatever! —-ስሚ ደሞ ልንገርሽ…ከኦስትሪያ የቡና ቤት ሴት ጋር መተኛት እኮ ላይብረሪን እቅፍ እንደመተኛት ያለ ጥሩ ስሜት ነው የሚሰጠው። አንድ መጽሐፍ ሳታነቢ እኔን አቅፈሽ ለመተኛት በመታደለሽ ፈጣሪሽን ማመስገን ያለብሽም ለዚህ ነው ሙ...ች!
በተናገረው ነገር ከት ብሎ ሳቀና ወዲያው ፊቱን ቅጭም አድርጎ ማወራት ቀጠለ።
" የምሬን ነው የምልሽ! ቢያንስ እነሱን አቅፎ መተኛት አንድ ነገር ነው ሳይንስ፣ ፍልስፍና፣ ሳይኮሎጂ ታወርያቸዋለሽ! ከናንተ ጋር ምን እናውራ? እናንተ የምታውቁት ካካካካ» ብሎ ከጣርያ በላይ ማስካካት ነው That is it !!! አየሽ ብታነቢ አሁን አፍሽን ከፍተሽ እንደ ነብይ እኔ የምናገረውን ዝም ብለሽ አታዳምጪም ነበር ትሞግቺኝ ነበር! ትጠይቂ ነበር። ማን እንደሆንኩ ለማወቅ ትሞከሪ ነበር.
Did you get my point?.."
ልናገር አፌን ስከፍት በምልክት አስቆመኝ
“…እነሱ Association እንዳላቸው ታውቂያለሽ? እዚህ የመንግስት ሰራተኛ እንኳ Association የለውም። They know their rights They know their respossibilities! የጤና ምርመራ
በየሳምንቱ እያካሄዱ ነው ፍቃድ የሚታደስላቸው። ባይገርምሽ ታክስ ከፋይ ናቸው። believe it or not ታክስ ለመንግስት ይከፍላሉ። እዚስ! ለመሆኑ ታክስ ትከፍላላቹ? እንኳን እናንተ ነጋዴው ታክስ ክፈል ሲባል ይበረግጋል። የሚያሳዝን አገር ዉስጥ ነው የምንኖረው የሕዝቡን ጭንቅላት መጥረብ ያስፈልጋል። ወያኔ እየጠረበች ያለችው ግን ድንጋይ ነው…ኦኬ!? ያ ነው ችግሩ።
"So...እዛ የምትለው አገር እየተበዱም ታክስ ይከፍላሉ ማለት ነው፤ ዶክተር?» አልኩት የሞት ሞቴን
ያልጠበቀውን ጥያቄ ስለጠየቅኩት ነው መሰለኝ ደነገጠ። ለነገሩ እኔም ሳላስበው ነበር የተናገርኩት ደነገጥኩ። በሩ መዘጋቱን ለሁለተኛ ጊዜ ገድገድ እያለ ሄዶ ቼክ አደረገ
“.Of course!! That is what I am saying” አለ፤የሚለው ነገር ትንሽም ቢሆን ስለገባኝ ደስ ብሎት፡
እኔ ግን በሆዴ « የአውስትራሊያ ሸሌዎች ሲያሳዝኑ! መንግስት በታክስ ይበዳቸዋል፣ ወንዱ በቁላው
ይበዳቸዋል…ሁለት ጊዜ ከመበዳት ያድነን» ብዬ እየጸለይኩላቸው ነበር።
“.እኛ ለዚህ አሸዋ ለሆነ 70 ሚሊዮን ህዝብ እውቀታችንን ሳንሰስት፣ በምላሹ ወያኔ ለሲጋራ እንኳ የማይበቃንን ደመወዝ ቆንጥራ ትሰጠናለች፡፡ ወያኔ እንደሆን አሽቀንጥራ ጥላናለች።የሙያ
ነጻነታችንን እንኳ ለመስጠት ታንገራግራለች። ማን ያውቃል ይሄኔኮ ነገ ወደ ስራ ስመለስ ሸርሙጣ
ጋር ሄድክ ተብዬ ልገመገም እችል ይሆናል? Who knows! እዚህ አገር አይሆንም ብሎ ማሰብ እኮ
ቀረ። እዚህ አገር ምንም ሊሆን፣ ሊደረግ ይችላል። አገራችን የጉድ አገር ሆናለች እኮ።ይሄኔ ከሸሌ ጋር አደርክ ብለው ይገመግሙኝ ይሆናል…”
ሳቀ። የእውነት የማይመስል ሳቅ ሳቀና ቀጠለ
"...you tell me.እንዴት እኔ ፈቅጄና ወድጄ በማደርገው ነገር እገመገማለሁ? ነጻ ሰው አይደለሁም ማለት ነው? በረሀ ገብተው የተዋጉልን ለምንድን ነበር ታዲያ?አሰብን በጥሩ ዋጋ ሽጦ እኛን ጦጣ ለማድረግ ነበር እንዴ? ከዚህ በላይ ለአንድ አገር ውድቀት ምን ማስረጃ ሊቀርብ ይችላል?…you tell
me! አንድ ሐኪም የት አደርክ ተብሎ መገምገም አለበት?”
«የለበትም» የሚል መልስ አንገቴን በመነቅነቅ

❤1👍1
ሰጠሁ። አጠጣጡ ሲያስፈራ። አዲስ ያስመጣውን ጂን
ከመቼው እንዳጋመሰው….
“…ከሁሉ ከሁሉ እኔን ግርም የሚለኝ የዚህ መላጣ ሰውዬ ነገር ነው፤ ሜዲካል ስኩል dropout ሆኖ በረሀ ገባ። እሱ ባለመማሩ እኛዋጋ መክፈል አለብን እንዴ? ሲጀምር ራሱ ወዶና ፈቅዶ አይደለም እንዴ የዘመተው? ከዳቦና ከነጻነት ነጻነትይሻለኛል ብሎ አይደል እንዴ ሜዲካል ትምህርቱን ጥሎት የጠፋው? ታዲያ እሱ ታግሎ ነጻነቱን ካገኘ በኋላ የኛን ነጻነት መንጠቅ ነበረበት? ደንቆሮ ነው እንዳይባል ብዙ
ያነበበ ሰው ነው፤ ያወቀ ሰው ነው። በዚህ የሚታማ አይደለም። እኛን ለምን ነክሶ እንደያዘን ግን ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው።
“ምናልባት ኢንፌሪየሪቲ ኮምሌክስ ሳይኖርበት አይቀርም… ታዉቂያለሽ? ሊማር የሚፈልገውን ነገር ስላልተማረ እኛን እየቀጣን ሊሆን ይችላል። ያንን ነው የምጠረጥረው። እንጂ He is genius!
ያነበበ ነው። በዚህ አይታማም። Come on! በዚህ ረገድ አቁዋሜ ግልጽ ነው። ሌሎች ከሚመጡ
እሱ መቶ አመት ቢገዛኝ እመርጣለሁ። yeah.!! ተሳሳትኩ? እነዚህ ሰዎች ይሄ ሰውዬ አንድ ነገር
ሲሆንባቸው ምን ሊውጣቸው ነው ብዬ እጨነቃለሁ… በሙሉ እኮ በርቀት ነው የተማሩት። የቤት ስራ የሚሰሩላቸው ሌሎች ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ አያነቡም። yeah !! አገሪቱ ዉስጥ ሰው የለም እኮ!
አንድ ሰው የለም እኮ…፤ እሱ አንድ ነገር ቢሆን ምን ሊሆኑ ነው። እንዴ አገሪቱ ዉስጥ ያሉ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞን…ምንድነው ደሞ ይሄ አሁን የመጣው… (ትንሽ ካሰበ በኋላ)አ...ዎ የክፍለከተማ…የነዚህን በሙሉ ሊቀመንበሮችን ሰብስበሽ «IQ»ዋቸውን ቁልቁል ብትደምሪው…በፍጹም በፍጹም እኮ እሱ
ጫፍ ላይ አይደርሱም! I mean it! ተሳሳትኩ? ከተሳሳትኩ እታረማለሁ።”
“ችግሩ ብቻውን ሆነ። ችግሩ ደረቅ ነው። አይሰማም..ሰው የሚለውን አይሰማም። ድንጋይ ዳቦ ነው ብሎ ሊያሳምንሽ ይሞከራል። ባለፈው እኛ ጋር መጥቶ ሰብስቦን ይሄንኑ ነገሬዋለሁ፤ እስክ
አፍንጫው ነው ያስታጠቅኩት፤ እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም ሐኪም ነው ልክ ልኩን የነገረው። ክፍያ ካልጨመረ አገሩን ጥለንለት እንደምንሄድ በግልጽ ነገረነዋል።
“…አሁን ደመወዝ ሲጨምር ምን እንዳይሆን ነው? You tell me እሱ ለሁለት ሺ ሀኪም ደምወዝ ስለጨመረ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ይናጋል? ምናለበት የአንድ ኢትየጵያዊ ሀኪም ደመወዝ መቶ ሺ ብር ቢሆን? I mean it! ምንድነው ችግሩ? ብዙ ነው? በርግጥ ጠባብ አእምሮ ላለው ሰው ይሄ በጣም ብዙ
ቁጥር ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ካየሽው is it big? No way! አምስት ሺ ዶላር ማለት እኮ ነው።Yeah...! Do the maths"
ቀስ በቀስ ምላሱን ያዝ እያደረገውልሳኑም እየተዘጋ እንደሆነ ተረዳሁ። ሆኖም ስካሩ መናገር ያለበትን
ከመናገር አላገደውም።
“እውነት እንነጋገር ከተባለ መቶ ሺ ብር እኮ አንድ ተራ የጉምሩክ ሰራተኛ በሙስና በአንድ ወር የሚያገኛት ሳንቲም ናት። ለዚህ መላጣ አሁን ይሄ ጠፍቶት ይመስልሻል?። በፍጹም! ኮምፕሌከስ ነው አላሰራ ያለው። He didn't gradutate we did! ገብቶሻል!? እኛ ሀበሾች ስንባል ቅንነት ያንሰናል።
ሳይማር በረሃ መግባቱ ነው እኛን ነክሶ እንዲይዘን ያደረገው። አንድ ተራ ሹም ከዚች ድሀ አገር በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሲመዘብርና ሲያሸሽ አይደለም እንዴ የሚውለው…”
አፉ ፍጹም መተሳሰር ጀመረ። ድምጹን ዝግ እያደረገ መናገር ቀጠለ። ከዚህ በኋላ ብዙ እንደማይገፉ
ስለጠረጠርኩ በትእግስት የሚሆነውን ለማየት ወሰንኩ።
"ዉጭ አገር ሄደን እንስራ፤ እምቢ! እዚህ ኖሯችንን አሻሻሉልን እምቢ! This is ridiculous! እኔ ዛሬ ተነስቼ አገር ብለቅ የቦትስዋና ህዝብ ዘምባባ ይዞ እንደሚቀበለኝ አያውቅም? ያውቃል። ምክንያቱም እሱ አንባቢ ነው። ቢያንስ ያነባል። ያነበበ ሰው ደሞ ይሄ አይጠፋውም። ተሳሳትኩ? ከተሳሳትኩ
_እታረማለሁ።
“እዚህ 50ሺ ድሀ አከሜ የማገኘውን የዓመት ደምወዜን ጋቦሮኒ 5 ሀብታሞችን አክሜ በወር ላገኘው እንደምችል አያውቅም? ያውቃል!! ችግሩ የቅንነት ነው።”
“…Believe it or not! ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ሻንጣዬን ሸክፌ ልሄድ ተነስቼ አውቃለሁ። ቦታስዋና።ሆኖም እናቴን ሳስባት ነው ሀሳቤን የቀየርኩት።”
የዶክተሩ አንደበት ሊዘጋ ቢቃረብም እንባው ባላሰብኩትና ባልጠበቅኩት ሁኔታ ዱብ ዱብ ማለት
ጀመረ። የእውነት ባየሁት ነገር በጣም ደነገጥኩ። አልጠበቅኩም.እንዲያ ሲፎክር ከነበረ ሰው እምባ ይወጣል ብዬ በፍጹም አልጠረጠርኩም።
“… ሕክምና ያጠናሁት እናቴ አንድ የገጠር ሀኪም አጥታ ስለሞተችብኝ ነው። አንድ የገጠር ሐኪም።ሐኪም አይደለም አንድ ጤና ረዳት ቢኖር አትሞትብኝም ነበር። ይሄኔ አብራኝ ነበረች። ይሄኔ ደልቷትትኖር ነበር። ወባ አጣደፋት። ሰው በወባ እንዴት ይሞታል? መዳን እየቻለች? ጉመር ውስጥ ያኔ አንድ
ጤናረዳት እንኳ ቢኖር ዛሬ እናቴ አብራኝ ነበረች። I love you mama! በህይወቴ የመጨረሻው ምኞቼ
ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?.እናቴ ሐኪም ሆኜ ለአንድ ደቂቃ አይታኝ መቶ ጊዜ ደጋግማ ብትሞት አይቆጨኝም፤ አንድ ጊዜ ተነስታ እንድታየኝ ነበር ምኞቼ፡ ምን ዋጋ አለው፤ አመለጠችኝ…!”
You see! አሁን አገሬን ጥሎ መሄድ እናቴን መካድ ሆኖ ይሰማኛል። እናቴን የመሰሉ ስንት ሺ ዜጎች
በኔ መሄድ መከራ ውስጥ እንደሚገቡ ሳስብ ነው ሻንጣዬን መልሼ የማስቀምጠው። እዚህ አገር አንድ
ሀኪም ለስንት ህዝብ እንደሚደርስ ታውቂያለሽ ለመሆኑ? 70 ሚሊዮንን ለሁለት ሺ አካፍዬው።
የምሬን ነው አካፍዬው።…ዳይ ዳይ! ሸርሙጣ መሆንሽ ቁጥር ከመደመር ሊያግድሽ አይገባም እኮ።ይገባል እንዴ?…ዳይ!
እምባውን ጠረገውና አፈጠጠብኝ።
እኔ ደሞ ጭንቅላቴን ብጨምቀው፣ ብሰራው፣ ባወጣ ባወርድ ሂሳቡ አልመጣልሽ አለኝ። ድሮም ከጊቢ
| ጀምሮ የቁጥር ነገር አይሆንልኝም! ዝም ብዬ አንገቴን በአዎንታ ነቀነቅኩለት። እሱ ግን አሻፈረኝ አለ
"ኖ ኖ ኖ ኖ! You have to give me the exact answer! እስክሪብቶና ወረቀት እሰጥሽና
ሰርተሸ እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ። ሶፋ ወንበሩ ላይ ወርውሮት ከነበረው የኮቱ ኪስ የመድኃኒት ማዘዣ የሚመስል አንድ ወረቀት ገንጥሎ ከሚያምር ብዕር ጋር የተጋለጠው ጭኔ ላይ አስቀመጠልኝ።
እስክሪብቶውን ለማንሳት በመዳፌ የሸፈንኳቸውን ጡቶቼን መልቀቅ ነበረብኝ። እንደዚያ ማድረግ
ደሞ አሳፈረኝ። አንሶላውን ጎትቼ ለበስኩትና ሂሳብ መስራት ጀመርኩ።
አእምሮዬ ግን ምንም አልሰራ አለኝ።
ይሄ ሰውዬ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልሱን በትክክል ካልመለስኩለት ዛሬ ቢዝነስ ሁሉ ላይሰጠኝ እንደሚች
ማሰብ ጀመርኩ። መጀመርያ 70 ሚሊዮን ስንት ዜሮዎች እንዳሉት ግራ ገባኝ። የአንድ ቤት፥ የአስር ቤት፣ የመቶ ቤት..እያልኩ ስሰርዝ ስደልዝ ጥቂት ደቂቃዎች ነጎዱ። ከፊቴ ቆሞ እያፈጠጠብኝ እየተንጎራደደብኝ እንደሆነ ሳስብ ደግሞ ይበልጥ ተደናገርኩ።
በርግጥ ቁጥር ላይ ቀሽም እንደሆንኩ
ባውቅም ማካፈል ያቅተኛል ብዬ ግን አስቤም አላውቅም ነበር።
ስዘገይበት እስክሪብቶውንና ወረቀቱን ነጠቀኝ።
“You see! ማካፈል ከማይችል ህዝብ ተወልደን ነው ሀኪም የሆነው፡፡ መቀነስ መደመር የማይችል ህዝብን ህይወት እናድን ብለን ነው በዚች ደሞዝ የምንፎከተው። ታዲያ መከበር ያንሰናል?
"ለመሆኑ እስከ ስንተኛ ክፍል ተምረሻል? አሞሸስ ያውቃል? በጠና ቢያምሸና ማስታገሻ የሚያዝልሽ ሀኪም ማግኘት ባትችይ ምን የምትሆኚ ይመስልሻል?Finished! ትሞታለሽ!

👍4
Just like that! yeah. ብሎ አውራ ጣቱን ከባለጌ ጣቱ ጋር በማጋጨት በጣቶቹ ድምጽ ፈጠረ።
“…Believe t or not እኔ ይቺን አገር ብለቅ 35000 ሰዎች ይሞታሉ። እነዚህን ሰዎች ገድዬ መሄድ ህሊናዬ ስላልፈቀደ ነው አገሬ የቀረሁት። አሁን ገባሽ ምን ማለት እንደሆነ? አንቺ ማካፈል
እንደማትችይው ሁሉ ይሄ ህዝብ መድኃኒት አወሳሰድ እንኳ በቅጡ አያውቅም። እኛ ጥለነው ብንሄድ
I tell you በአስር ዓመት ውስጥ ረግፎ ያልቃል። ይሄን የሚረዳው ግን ማነው ነው ጥያቄው። ወያኔን ተያት ድሮም ሰው የሚላትን አትሰማም። በረሃ ታደርግ እንደነበረው ሕዝቡን ሁሉ በመጀመርያ
እርዳታ እድሜውን የምትቀጥል መስሏት ይሆናል፤ እስኪ እናያለና ቻይና ኔትዎርክ እንደምትቀጥልለት
የሐበሻን ህይወት የምትቀጥልበት ከመሰለው እስኪ እናያለን..."
አንድ ሙሉ ጠርሙስ ጅን ሊያጠናቅቅ ሩብ ያክል እንኳን አልቀረውም ነበር ፊቱ ደም እየመሰለ መጣ በትኩረት ስመለከተው ከዚህ በኋላ እንኳን ሴክስ ሊያደርግ አልጋ ላይ ያለ ድጋፍ መተኛት ከቻለ ጎበዝ ነው።በቁሙ እንቅልፍ ሊጥለው ይችላል።
ስሚኝ..ማነሽ sorry ስምሽ አያዝልኝም ማን ነበር ያልሽኝ...?
"ሮ..ዛ" ለስንተኛ ጊዜ እንደነገርኩት እኔ ራሴ አላስታውስም
"ኦኬ ሮዛ ስምሽ ከባድ ነው አይደል? ትንሽ ለማስታወስ ያስቸግራል..ለለነገሩ ማነስ ቢሆን። ስምሽ እኔ ላይ ምን ይጨምራል ብለሽ ነው? ለጊዜው በጄ ላይ ከሚገኙ 35 ሺ ነፍሶች አንዷ ነሽ ልበል ያ ማለት ደግሞ አንቺ ለኔ ተራ የሆስፒታል ነካርድ ቁጥር ነሽ ማለት ነው እኔ ግን ላንቺ ህይወትሽ ነኝ። see the different ይህንን ነው መረዳት ያቃታችሁ"
ብሽቅ አልኩ!
እኔ ሕይወትሽ ነኝ ይለኛል እንዴ ደፋር! እየሱስ እንዳይሰማህ አልኩ በሆዴ እሱ ግን በስካር ብዛት ዓይኑ ቡዝዝ ብላ ዜሮ አምፖል እስክትመስል ድረስ አንደበቱ ከመናገር ወዳ መላዘዝ እስክትሸጋገር ድረስ እንቅልፍ በቁሞ አዙሮ እስኪደፋው ማውራቱን አላቃመም ነበር።
"..እኮ ማንም ይሁን ስምሽ..። አንቺ ነሽ እኔን እንደ አንድ ተራ ወመኔ "ሱሪ አውልቅ ኮንደም አጥልቅ ብለሽ የምታመናጭቂኝ !? You bitch...!
ይሄንን ተናግሮ ከመቼው ማንኮራፋት እንደጀመረ ሳስብ ዛሬም ድረስ ያስቀኛል።
💫ይቀጥላል💫
#Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ
#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇

👍2
#ትምህርት …
#በትናኤል
እናቱ የሰራችለትን ዘይት የለለው ቁርስ ከበላ በኋላ ወደ ት/ቤት ለመሄድ ደብተሮቹን ማዘጋጀት ጀመረ…ተማሪ ይስማህ። በየቀኑ ስድስት የት/ት አይነቶችን ይማራል። የእለቱን ክፍለ ጊዜ ለማወቅ ሂሳብ ደብተሩ ላይ ማየት አለበት። ሂሳብ ሁልቀን ስለሚማር በጀርባው በኩል ሳምንታዊ ፕሮግራሙን ጥፎበታል።
<<እመይ!...>>
<<አቤት>>
<<ሂሳብ ደብተሬን አላየሽም?>>
<<እኔ መሰልኩህ እንዴ የምማርበት?>> እናትየው የበላበትን እያነሱ አሽሟጠጡት።
<<እመይ!>> ድጋሚ ተጣራ
<<እዛው ፈልግ አንተ!>> ማታ ማታ እያዘጋጀህ እደር ሲሉት ስለማይሰማቸው ጠዋት ጠዋት አፋልጉኝ የሚላቸው ነገር ሳይሰለቻቸው አልቀረም።
<<ኸረ አጥቸዋለሁ እመይ!>>
<<ምን አይነት ደብተር ነው?>> አሉት ምርር እያላቸው።
<<ቢጫ ፣ የሱፍ አበባ ስዕል ያለበት>>
እናትየው እጃቸውን ታጥበው ጓዳ ውስጥ ወድቆ ያዩትን ደብተር መፈለግ ጀመሩ። እናቱ መፈለግ ሲጀምሩ አጠገቡ የነበረች ዱካ ላይ ተዘረፈጠ። ፈልገው እንደሚያገኙለት ያውቃል።
<<ያውልክ!...እንደው ምን አለ እንደተማሪዎቹ ማታ በስነስርዓት አዘጋጅተህ ብታድር አንተዬ?>> ተቀብሏቸው ከሌሎች ደብተሮቹ ጋር ቀላቀለው። ግድግዳው ላይ የተሰቀለውን የአባቱን ፎቶ ለአፍታ ከተመለከተ በኋላ እየተቻኮለ ወጣ።
…
የት/ቤቱ መግቢያ ላይ “በ****ክልል እርጥብ ዋርካ ወረዳ****የ***ወረራ ሰማዕታት መታሰቢያ ዘመናዊ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት” የሚል ጽሁፍ ያለው ታፔላ ይታያል። ተማሪ ይስማህ እዚህ ታፔላ አጠገብ ሲደርስ ይፈዛል። ዛሬም ለመጀመርያ ጊዜ ያየው ይመስል በተመስጦ ተመለከተው። ታፔላው ያረጀ ነው። የእግሩ ብረት እርጅናውን በሚያሳብቅ ዝገት ተወሯል። ነገር ግን ንቅንቅ ብሎ አያውቅም። <<ለምን?>> ይላል ተማሪ ይስማህ። <<ለምንድን ነው የማይወድቀው?>> አለነገር አልጠየቀም። ምክንያት አለው። በዚህች ትንሽ እድሜው ብዙዎች ሲወድቁ ተመልክቷል። አያቱ ባጣዳፊ ህመም ተይዘው…ህክምና ለማግኘት ወደ ራቀ መንደር ሲጓዙ በመሀል ወድቀው ቀርተዋል። አባቱን ከመከላከያ የተተኮሰች ጥይት ከመሬት ስትደባልቀው ተመልክቷል። ታላቅ ወንድሙ በከፍተኛ የደም መፍሰስ ከመሞቱ በፊት ፖሊሶች መሬት ላይ ጥለው ሲረጋግጡት አይቷል። እናቱም ቢሆኑ ኑሮ ገፍቷቸው ለመውደቅ እየተንገዳገዱ ነው። ይሄ ታፔላ ግን ንቅንቅ አይልም። ላዩ ላይ የሰፈረውን እርጅና ከምንም ሳይቆጥር ተኮፍሶ ቁሟል።
#ክፍል_ውስጥ
…መምህሩ ከመምጣታቸው በፊት ተማሪዎች እየተንጫጩ ነበር። መምህሩ ገና ግማሽ ፊታቸው በበሩ በኩል ብቅ ሲል ዝምታ ክፍሉን ሞላው። ተማሪ ይስማህ ከላይ እስከታች አያቸው። ጠይም ቆዳቸው እየጠቆረ ነው። ራሰ በራቸው ተስፋፍቷል። ከኋላ ያላቸው ትንሽ ጸጉር በሽበት ተወሯል። ተማሪ የሚገርፉባትን ጥቁር ጎማ እንደተለመደው ይዘዋል።
<<እንደምን አደራችሁ ተማሪዎች?>> አሉ ድምጻቸውን ጎላ አድርገው
<<እንደምን አደሩ መምህር!>> ከመቀመጫቸው ተነስተው
<<ቁጭ በሉ>>
መምህሩ በወረቀት የጠቀለሉትን ዳስተር ፊትለፊት ለነበረው አመዳም ተማሪ ሰጡት። ተማሪው በጉጉት ተቀብሏቸው ብላክ ቦርዱን ማጽዳት ጀመረ።
<<….ወደ እለቱ ትምህርታችን ከመሄዳችን በፊት …ባለፈው የቤት ስራ ብዬ ሁለት ጥያቄዎች ሰጥቻችሁ ነበር አይደል?>> አሉ
<<አዎ>> ብላ መለሰች ከፊት ለፊት የምትቀመጠዋ ጎበዝ ተማሪ። ተማሪ ይስማህ በመብረቅ እንደተመታ ክው አለ። የቤት ስራ ስለመኖሩም ረስቶታል። መምህሩ የቤት ስራ የማይሰራ ተማሪ እንደማይምሩ የታወቀ ነው።
<<እሺ ጥሩ….ያልሰራ አለ?>> ብለው ጠየቁ
ተማሪዎች እርስ በርስ መተያየት ጀመሩ። ይህንን መተያየት ተማሪ ይስማህ ያውቀዋል። ማን ከማን ጋር አብሮ እንደሚገረፍ ለማወቅ ነው። ከመገረፍ በላይ ብቻን መገረፍ ያማል። ብዙ ጊዜ ሰባት ስምንት ተማሪዎች ጋር አብሮ ሲገረፍ ይቀለዋል። አይብስበትም። ከግርፋቱ በኋላ እርስ በርስ እየተያዩ መሳሳቃቸው አይቀርም። አምስት ተማሪዎች በየተራ ወደ መድረኩ ወጡ። ይስማህ ብርድ እንደያዘው ሁሉ ሰውነቱን አንዳች ነገር እየወረረው ስድስተኛ ሁኖ ወጣ።
<<አቤል!!>> አሉ መምህሩ…መጀመርያ ወደተሰለፈው ተማሪ እያፈጠጡ
<<አቤት መምህር>>
<<ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው?>>
<<እ?>>
<<ባለፈው አስተምሬያችሁ ነበር…>>
ያልሰማቸው ያህል ጥያቄውን ደገሙለት…
<<ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው?>>
ተማሪ አቤል አንገቱን ደፍቶ ጸጥ አለ። ወድያው ዦጥ! ዦጥ! የሚል ድምጽ ክፍሉን ሞላው። አቤል የሚንገበገቡትን እጆቹን እያሻሸ ወደ ወንበሩ ሮጠ።
ቀጣዩ ተረኛ ሮቤል ለእርድ እንደቀረበች ፍየል እየተርበተበተ ቀረበ…
<< እሺ ሮቤል…አንተስ?....ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው?>>
ሮቤል ጣራ ጣራውን ማየት ጀመረ።
<<አታውቅም?>> አሉት። ቀስ ብሎ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀላቸው
<<እሺ እኩልነት ማለትስ ምን ማለት ነው?>>
ሮቤል ጣራ ጣራ መመልከቱን ቀጠለ
<<ምን ቆርቆሮው ላይ ታፈጣለህ?...መልሱ ከሰማይ ዱብ ይልልሀል?>> አንባረቁበትና የያዙትን ጎማ በጀርባው ለቀቁበቁበት። ቁጭ ብለው ከሚመለከቱ ተማሪዎች ውስጥ አንዳንዶቹ መሳቅ ጀመሩ።
ቀጣዩ ተረኛ ተማሪ ይስሀቅ ነው። መምህሩ ይስሀቅን ሲያዩ ቀጡው ፊታቸው ባንዴ መለስተኛ ጸሀይ መስሎ ፈገግ ማለት ጀመሩ…
ይስሀቅ ሰፈር ውስጥ አንቱ ተብለው የሚከበሩት ባለስልጣን ልጅ ነው።
<<እንዴ ይስሀቅ..እንዴት ነህ?>>
ይስሀቅ ፈገግ እያለ <<ደህና>> ሲል መለሰላቸው።
<<አባትህ ደህና ናቸው?>>
<<ደህና ናቸው>>
<<እሺ…>> አሉና ጥቂት አሰብ አርገው
<<ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው?>>
ይስሀቅ ልክ እንደ ሮቤል አንገቱን ወደ ላይ ቀና አድርጎ አንጋጠጠ
<<አታውቀውም?...ባለፈው ሳስተምር አልገባህም ነበር ማለት ነው…እሺ እኩልነት ማለትስ ምን ማለት ነው?>>
ይስሀቅ በዝምታው ጸና።
<<አንተ ሰነፍ!>> አሉና ቂጡን በቀስታ ቸብ አድርገውት ቀጣዩ ተማሪ ላይ አፈጠጡ። ቀጣዩ ተረኛ <ብርሀን ነው> ብርሀን የእህታቸው ልጅ።
<<አጅሬው!>> አሉት
ሳቅ ሳቅ እያለ አያቸው
<<እሺ..ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው? አታውቅም? እሺ እኩልነት ማለትስ ምን ማለት ነው?>>
መልስ አልሰጣቸውም። እሱንም ቂጡን በቀስታ ቸብ አድርገው አለፉት። ተማሪ ይስማህ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ስለ እጣው እያሰበ ጭንቀት ውስጥ ነበር። ጥያቄዎቹን መልሶ መላልሶ እያሰበ በግምት መልስ የመስጠት እቅድ ላይ ነበር። ዲሞክራሲ የሚለውን ምንም ቢያስብ መልሱ ሊመጣለት አልቻለም። እኩልነት የሚለው ግን የሆነ ስሜት ሰጥቶታል። ቢያንስ ከሌሎች እኩልመሆን ማለት እንደሆነ አላጣውም። <<ከሌሎች እኩል መሆን ማለት ነው ብዬ ብመልስ ይተውኝ ይሆን?>> ይህንን በማሰብ ላይ እያለ ተማሪ ብርሀንን በፈገግታ ያሳለፉት መምህር ፊታቸውን ከሰል አስመስለው አጉረጠረጡበት
<<እኩልነት ማለት ምን ማለት ነው?>> ሊመልስ አፉን መክፈት ሲጀምር…ጥቁር ጎማቸውን አወናጭፈው ወገቡ ላይ አቀመሱት። በመቅመድመድ ላይ እያለ እጁ ላይ ደገሙት።
<<ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው?>> አንባረቁበት። ዦጥ! ዦጥ! የሚል ድምጽ ክፍሉን ሞላው።
ተማሪ ይስማህ ህመሙን ዋጥ አድርጎ ወደ ወንበሩ ተፈተለከ። ከዚያ ጽኑ ታፔላ የሆነ ጸባይ ሳይወርስ አልቀረም።

😁3👍1
#ሮዛ_2
፡
፡
#ክፍል_ስድስት(🔞)
፡
፡
#ከዶር_ቃልአብ_ጋር_ያደረግነው_ነገር
ዶ/ር ቃልዓብ የሐረር ሰው ነው።
መሆንም አለበት። ዶክተርነት እንደሱ ከሆነ ብቻ ይምጣብኝ
ምከንቱም በጣም ነጻ ሰው ነው። ዶክተርነቱ የሰጠው አንድ ነገር ቢኖር እንደብዙዎቹ መቆለልን ሳይሆን ነጻነትን ነው። ወላ እሱ ዶክተር ሊሉት እንኳን አይደላውም አቦ። እኔ የማውቃቸው ዶክተሮች(የበዳኝም፣ ግቢ ያስተማሩኝንም ጨምሮ ማለቴ ነው) ዶክተር ካልተባሉ ለጸብ የሚጋበዙ ናቸው።ጓደኛዬ የነበረችው ሰሚራ Introduction to Macroeconocmics"C" "ያመጣችው አስተማሪዋን በስሙ ስለጠራቸው ነው። ወዲያውኑ ነበር « ዋጋሽን ታገኚያታለሽ!» ብሎ የዛተባት። እንደዛተ።አደረገው። ዶክተር ብላ ስላልጠራቸው ብቻ። ዶክተር መሆን ከንደዚህ አይነት ጠባብነት ካላወጣ
ባፍንጫዬ ይውጣ!
ዶክተር ቃለአብ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደላይ በሚገኙ ኪሎ ዩኒቨርስቲዎች በአንዱ የሚያስተምር
የተጨበጨበለት ፕሮፌሰር ዶክተር ነው። የቺቼንያ ሕይወት ላይ Research በሚሰራበት ወቅት የተዋወቅነው። ለሁላችንም በረዳቶቹ በኩል እንድንሞላው በሰጠን Questionaire ላይ የጻፍኩት ነገር ማመን ከብዶት በባትሪ ፈልጎ አፈላልጎ ተዋወቀኝ። መጀመርያ አካባቢ ዶክተር እያልኩ
የምጠራው። እሱ ግን ከመቼው ተግባብቶኝ እንደዚያ እንዳልጠራው እንዳደረገኝ ሳስበው ይገርመኛ።
« አቦ እናሸንና!» ሁለተኛ አንቱ ብለሽ እንዳትጠሪኝ ብሎ በአንድ ጊዜ በመሐላችን የነበረውን ግንብ
አፈረሰው።
«ኸረ ዶክተር ካንተ አይጠበቅም አልኩት እየሳቅኩ።
Shut up bitch! I am here looking for my freedom!” አለኝ።
አልከፋኝም፤ ምክንያቱም ዶክተር ያራዳ ልጅ ነው በዚያ ላይ ከእግዚያአብሔርም ጋ ጀለስ ሳይሆኑ አይቀርም። ለምን ቢባል ከሱ ጋር አስር ደቂቃ ያወራ ማንኛውም ሰው ወዲያውኑ በፍቅሩ ይነደፋልና
ነው። እንደዚህ አይነት ሰዎች ለፈጣሪ የቀረቡ ሳይሆኑ አይቀሩም ሰዎች ራሱ ዶክተር» ብለው ሲጠሩት ብሽቅ ነው የሚለው። አንድ ቀን ብላክ አስወርደን እየጠጣን (ጋባዥ እኔ ነበርኩ) ሞቅ ብሎን ሳለ ለምን ዶክተር ሲሉት እንደሚናደድ ጠየቅኩት።
«ተይ እንጂ ሮዝ! ማንም ሩዝ ነጋዴና አዝማሪ በሚጠራበት ስም ስጠራ እንዴት አይከፋኝም?!»ብሎ ቀለደ።
በሳቅ ልሞት!
ምክንያቱም ያን ሰሞን አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ለሀብታሙም ለነጋዴዉም፣ለዘፋኙም፣ ለጎሳ
መሪውም የክብር ዶክትሬት ያደሉበት ወቅት ነበር። እና አሽሙሯ በደንብ ገብታኛለች። እውነተኛ ምክንያቱ ግን ያ እንዳልሆነ አውቃለሁ።
ብዙ ጊዜ ስናወራ በዚህ ትውልድ ደስተኛ እንዳልሆነ ለመረዳት ችያለሁ።
“በኛ ዘመን ትምህርት ዋጋ ነበራት፤ እንደናንተ ሸርሙጣ አልሆነችም ነበር፤ ገብቶሻል የምልሽ?
ለምሳሌ በጃ ጊዜ እውቀት ሸቀጥ አልሆነችም ነበር። ብር ስላለሽ ወይም ትዝታ ስላንጎራጎርሽ ማንም
አንስቶ ዶክትሬት አይሰጥሽም፤ በፍጹም። ብቸኛው መንገድ ጠንክሮ መማር ነበር። አሁን ሲ ኤም ሲ ነው ጉርድ ሾላ ለካድሬዎች የተከፈተ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አለ፣ ስሙ ጠፋኝ።
እና ይሄን ዶክትሬት ዲግሪ እንደ ጉድ ለተማሪዎቹ እያደለው ነው»አሉ፤ አንቺም ሳያልቅብሽ ይቺን ብላክሽን ቋ አርጊና ሄደሽ ብትጠይቂያቸው ይሰጡሻል! ሙች እውነቴን ነው!”
ከዚያ ቀን በኋላ ዶክ እያልኩ እጠራው ጀመር።
ዶክ ጓደኛዬ እንጂ ደምበኛዬ የምለው ሰው አይደለም፡፡ ብንባልግም በስንት ጊዜ አንዴ ነው የሆኑ ጊዜያት አሉት፣ ከኔ ጋር ማደር የሚፈልግባቸው ጥብቅ ጊዝያት። ከዚያ ዉጭ ግን ጓደኛሞች ነን
ህይወቱ ላይ የሆነ ያልሻረ ቁስል ያለበት ይመስላል። ግን እሱ ሁሌ ጫወታና ሳቅ ዉስጥ ስለሚዋኝ ከኔ ሌላ ይህን ስሜቱን የሚረዳ ላይኖር ይችላል።
"ዶክ ግን ምንድነው ስታየኝ የርቀት ተማሪ»እመስላለሁ እንዴ?” እልኩት ደሳለኝ ሆቴል በሱዙኪው ይዞኝ እየሄደ።
«እንዴት ማለት?» አለኝ ፊቱን ፊትለፊቱ ባለው ጎዳና ላይ ተክሎ
« የርቀት ትምህርት Exam ይመስል በሴሚስተር አንዴ እየመጣህ ስጪኝ ትለኛለሃ! አይደብርህም እንዴ ጠፍተሃል እኮ?
ያን ምሸት የሳቀው ሳቅ! ትራፊክ ቢያየው “ትርፍ በመሳቅ” ብሎ ይቀጣው ነበር።
“You know what?I wish ሚስቴን ይህን ቀልድሽን በሆነ መልኩ በነገርኳት። በጣም sense of humour ያላት ናት። በዚህ ዓለም ከኔ ሌላ እንደ ጆክ የምትወደው ነገር የላትም፤ ነግሬሼላሁ አይደል?
“ኸረ ዶክ! እንዲያውም ስለ ሚስትህ ትንፍሽ ብለህ አታውቅም?”
“እውነትሽን ነው? How come? ይገርምሻል! ተማሪዎቼ ደግሞ ምን እንደሚሉኝ ታውቂያለሽ?
«ስላንተ ሚስት መስማት ሰለቸን፤ add ያደረግናት ኮርስ ሆነችብን እኮ» ነው የሚሉኝ።
ሳቅኩኝ።
እንዲያውም አስተዋውቃችኃለሁ!
“ኸረ ባክ.ህ?! ተባለንዴ…" የሹፈት ሳቅ ሳቅኩኝ።
እሱ ለካ እያሾፈ አልነረም።
No no! She is not like that! እንዲያውም በተቃራኒው She is open and funny, I am sure you two like each other more than we do! ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም። of course ስለ ግንኙነታችን
ልታውቅ የምትችልበት ምንም መንገድ አይኖርም፡፡ ደሞ we are friends nothing else! አይደለም እንዴ ሮዝ? የቀድሞ ተማሪዬ እንደነበርሽ ቀለል አድርጌ እነግራታለሁ። that is it! I hope አሪፍ ታይም እናሳልፋለን
How about lunch? The coming Sunday. Are you free or what?"
“ዶክ አብደኻል እንዴ? ምንድነው የምትቀባጥረው?”
በሳምንቱ ዕሁድ አንጦልጡሎ ሱዙኪው ውስጥ ከተተኝ። ግሎባል ጀርባ አካባቢ ወደሚገኝ ባለ ሦስት ፎቅ ጸጥ ያለ መኖርያ ቤቱ ይዞኝ ሄደ። መርበትበት ማቆም አልቻልኩም። ላቤ ሲንቆረቆር ይሰማኛል።ብርድ ብርድ ሲለኝ መዳፎቼን ጭኖቼ ውስጥ ወሸቅኳቸው። አንድ ወንድ እንዴት አንዲት የሴክስ
ደምበኛውን ከሚስቱ ጋር ለማስተዋወቅ ይደፍራል? ከዚህ በላይ ምን እብደት ይኖራል? በዚህ ጠራራ ጸሐይ ብርድ ብርድ እያለኝ እንደሆነ ሲገባኝ የፍርሃቴ ጥልቀት ተገለጸልኝ።
“ i really hate you Doc! የእብድ ስራ ለምን ታሰራኛለህ! ማበድ ከፈለክ ብቻህን አታብድም እንዴ!?”
“የኔ ቆንጆ! ምንም ነገር የምትፈሪ አይመስለኝም ነበርኮ! ሃሃሃ! ለካንስ ሸሌዎችም ትፈራላችሁ! ይሄ
በሶሲዮሎጂ መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው። ሮዚ! You are such a chicken ! Relax! ምንድነው እንዲህ
መፍራት። you will be fine! ደግሞ ምናባሽ ሆነሽ ነው እንደዚህ እምስ እስክትመስይ ድረስ ቆንጆ ስከርት የለበስሽው፣ ሚስቴን በቅናት ለመግደል እያሴርሽ መሆን አለበት…ሃሃ
እንደሱ ሲለኝ የለበስኳትን ሚኒ ቀሚስ ለመጀመርያ ጊዜ ጎንበስ ብዬ አየኋት፤ ደንግጬ ወደታች መጎተት ጀመርኩ። እውነትም ተራቁቻለሁ፤ ምን ነክቶኝ ነው እንደዚህ ለብሼ የወጣሁት? መኪናው
ውስጥ ስቀመጥ ነው የታወቀኝ። ሚኒ ቀሚሴ ተሰብስቦ ራቁቴን ቀርቻለሁ። ዶክ ሲያጣድፈኝ ምን ላድርግ፣ አጠገቤ ያገኘሁትን ነው የለበስኩት፤ ምናለ ከመነሳታችን በፊት ነግሮኝ በሆነና አለባበሴን በቀየርኩ!
ወደ ግሎባል ሆቴል ጫፍ ስንደርስ ለምን እንደሆነ አላውቅም ዶክ ላይ የሆነ ከወትሮው ቅንዝርነት አስተዋልኩ፤ እንደዚህ በፍላጎት ሲያየኝ ከዚህ በፊት አይቼው አላውቅም ነበር።
ግቢው ሲያምር! አበባ ሞልቶታል፤ ኤምባሲ ነው የሚመስለው። ጋራዥ ውስጥ ጭርጭስ ያለች አንደሸ
የድሮ ቮልስዋገን መኪና ቆማለች

👍8
አሮጌ ብትሆንም ግን ደስ ትላለች፤ ውልውል ተደርጋ የተቀመጠች መኪና ነው የምትመስለው ቤቱ እንደ ሦስት ፎቅ ክብድ የሚል ነገር የለውም
እንዲያውም ጭራሽ ፎቅ ቤት አይመስልም በሌላኛው የግቢው ጥግ አንድ የባስኬት ቦል መጫወች ቅርጫት ይታያል።
ወደ ውስጥ ዘለቅን።
"He...llo Anybody home?ማሬ Are you there?.." ብሎ ተጣራ
ትንንሽዬ ዉሾች ከየት መጡ ሳልል እግሬ ሥር ተንጫጩብኝ። ፈርቼ ወደኃላ ሳፈገፍግ ዶክ መጥቶ ምልከት ሰጣቸው።እሱን ሲያዩ ሦስቱም ድንክ የሳሎን ዉሾች እየሮጡ እላዩ ላይ ተጠመጠሙበት እያሻሸ አቀፉቸው። ልጆቼ ናቸው። ይሄኛው ቴዎድሮስ ነው ስሙ። ቆራጥ ነው። ሽጉጥ አጥቶ ነው
እንጂ ድሮ ነበር ራሱን የሚያጠፋው፡፡ እቺኛዋ ብርቱካን ትባላለች፣ በጣም ነው የምንወዳት። እዚ ቤት የመጣ ሰው ሁሉ ነው የሚወዳት። ይሄ ጎረምሳው በላይ ዘለቀ እያልኩ ነው የምጠራው። ማሬ
ግን “ቢስማርክ” ነው የምትለው። ሳቄ መጣ። ነገር ግን ዶክ ቡችሎችን የሚያሳድገው ልጅ ስለሌለው
እንደሆነ ሲገባኝ በራሴ አፈርኩ።
ቤቱ ጭር ሲልበት እንደገና ተጣራ! “ሄሎ ማሬ! Are you there?"
በጣም ረዥም፣ ወፈር ያለች፣ የወንድ ሰውነት ቢመስልም የደስ ደስ ያላት ፈረንጅ የሳሎኑን ደረጃ ወርዳ
ወደኛ ስትመጣ ተመለከትኩ። ግራ ገባኝ! ምናይነቷ ጅል ነኝ? እስከዚያች ደቂቃ ድረስ ሚስቱ ፈረንጅ ልትሆን አንደምትችል ምንም አልተከሰተልኝም ነበር፤ እሱ ራሱ ለምን እስከዛሬ ሳይነግረኝ ቀረ?
ተዋወቁ! ማሬ this is Roza... I was telling you about!
Oh Finally ! Happy to meet you Roza, ኢኔ ሲሜ ማሪያ!"አለችኝ ከለማጅ አማርኛና ሞቅ ካለ ፈገግታ ጋር my husband told me quit a lot about you
"Really?"
'Yes. I know a lot of stuff about you more than you can imagine!"
የምመልስላት ነገር ጠፍቶኝ ተቁለጨለጭኩ፤ «thank you» ማለት ሲገባኝ እንዲሁ በፈገግታ አለፍኳት
አይፈረድብንም! በዚያች ቅጽበት አእምሮዬ ብዙ ነገር በማሰብ ሊፈነዳ ደርሷል። ምንድነው ስለኔ
የነገራት? አልፎ አልፎ ትበዳኛለች ያልኩሽ ልጅ እሷ ናት» አይላትም መቼም። ካላበደ በስተቀር። ታዲያ ምን ቢያወራላት ነው ስላንቺ ከምትገምቺው በላይ ብዙ አውቃለሁ የምትለኝ?» እሱስ ለምን
ሚስቱ ፈረንጅ እንደሆነች እስካሁን ሳይነግረኝ ቀረ? At least ተዘጋጅቼ እመጣ ነበራ፤ በወሬ መሐል
ነግሮኝ እኔ ዘንግቼው ይሆን እንዴ? እንዴት ዶክ ስለሚስቱ ነግሮኝ ልረሳ እችላለሁ? የጋብቻ ጥያቄ
ቢያቀርቡልኝ ባንዳፍ» ከምላቸው ሶስት ወንዶች አንዱ ነው እኮ ዶክተር ቃልአብ። ከሲስ ነፍሴ ቀጥሎ በጣም የምወደው ሰው ነው ዶክ። ስለዚህ በፍጹም ስለሚስቱ ነግሮኝ ልረሳ አልችልም።
በሚቀጥሉት ደቂቃዎች ስለ ምንድነው የማወራው? የሚለው ጥያቄ ራስ ምታት ለቀቀብኝ። እጄን አስር ጊዜ ከሌላኛው እጄ ጋር እያፋተግሁ ቆየሁ።
ከሰፊው ሳሎን ትይዩ «ሜዘኒን» ላይ «ዳይኒንግ ሩም» አለ። ከዳይኒንጉ ጎን ትንሽዬ የምታምር ባር አለች። ባሯ ጓደኛዬ ሰኑ የምትሰራበትን ጩኒ ፐብን ታከላለች። አራት ባለጌ ወንበሮች አሏት። ልዩ ልዩ
ቮድካና ዉስኪዎች መደርደሪያው ላይ በቄንጥ ተንጠልጥለዋል። መደርደሪያው ከወዳደቀ እንጨትና በወፍራሙ ከተፈተለ ገመድ የተሰራ ቀላል፣ ግን በጣም የሚያምር ነው። ጭንቀት ባናወዘው አእምሮዬ ሆኜም የቤታቸውን ዉበት ማስተዋል ቻልኩ።
ማርያ ናት የስራችው፣ የወዳደቅ ነገር ትወዳለች» አለኝ፤ በመደርደሪያው አሰራር መመሰጤን
አስተውሎ።
"አንተንም ወድቀህ አንስታህ መሆን አለበት…» አልኩትና በራሴው ቀልድ ፈገግ አልኩኝ፤
እሱ ግን እቲ የሳቅ ጥይት ተኮሰ። ቤቱን በሳቅ ረበሸው፤ ተንከተከተ! ወትሮም ትንሽ ነገር በጣም የሚያስቀው ሰው እንደሆነ አውቃለው።
ማሬ ማሬ Listen to this . ብሎ ቀልዱን በእንግዝኛ ክሽን አድርጎ ነገራት። ስሟ ማሪያ ቢሆንም እሱ ግን ማሬ እያለ ነው የሚጠራት
ባልጠበቅኩት ሁኔታ እሷም ትከን ብላ ሳቀች።
| ሳቋን ተከትሎም እንዲህ አላት- What did tell you ማሬ ! She is extremely funny
"Yeahl can see that ብላ ጥላን ወደ ኪችን ሄደች። ዘና የማለት ስሜት ተሰማኝ።
ወደ ኪችን ስትራመድ ከኋላዋ እየገመገምኳት ነበር። ማሪያ ልክ እንደ ብዙዎቹ ፈረንጆት አነስተኛ )
ቂጥ ያላት ብትሆንም ሰውነቷ ወፍራም ሆኖ ነገር ግን ቅልጥፍጥፍ ያለና የሚያምር ነው። ቀጥ ያለችና .
ሁሉ ነገሯ እስትክከል ያለ አይነት ነው። ፀጉሯ ጥቁር ሳይሆን ፊልም ላይ ብሎንድ የሚሉት ወርቃማ ቀለም ያለው ነው። በጣም ረዥም ከመሆኗ የተነሳ እኔን ራሱ ትበልጠኛለች። ሱሪም ሆነ ቁምጣ
| አላጠለቀችም። አንድ ረዥም የወንድ የሚመስል ቀለል ያለ ቲሸርት ነው የለበሰችው።ቲሸርቱ ረዥም ከመሆኑ የተነሳ ቂጧን ሸፍኖላታል። ምናልባት የውስጥ ፓንት አድርጋበት ይሆናል። ጡት መያዣ እንዳላረገች ግን አስተውያለሁ። ከፍሉ ውስጥ በተራመደች ቁጥር ጡቶቿ ዝልል ዝልል ይሉባታል። "
እርጋታ የሚባል ነገር የፈጠረባት አትመስልም። ሁሉንም ነገር በጥድፊያ ነው የምታካሄደው።
የሷን ግዝፈትና ቁንጅና ስመለከት ለምን እንደሆነ አላውቅም ራሴን ጠላሁት። የሆነ የቆሸሽኩ ትንሽ ፍጥረት የሆንኩ አይነት መስሎ ተሰማኝ። ቅልል ያለ አለባበሷን ሳስተውል ደግሞ እኔ ኮተታም የሆኑክ መሰለኝ፤በካፖርት ላይ ጋቢ የዴበርኩ ያህል ተሰማኝ። በርግጥ አጭር ሚኒ ቀሚስና እምብርቴ ላይ
የምትቀር ባለቁልፍ ሸሚዝ ነበር የለበስኩት። ያንን የሚያክል ሂል ጫማ ግን ማድረግ እንዳልነበረብኝ ተሰማኝ፡ ሰው ቤት የተጋበዝኩ ሳይሆን ለኡስማን ቢዝነስ የወጣሁ ነበር የምመስለው።
ማሪያ ወደ ኪችን እንደገባች የሳሎኑን በር ተደግፈን በቆምንበት ዶክተር ቃልዓብ እጁን ከወገቤ አንሸራቶ ቂጤን በስሱ ሲደባብሰኝ ተሰማኝ። በድንጋጤ ክው ብዬ ቀረሁ። ምን እያረገ ነው ይሄ ሰውዬ?
ተስፈንጥሬ ሸሸሁትና በዓይኔ ተቆጣሁት።
"ሮዚ እንደዛሬ አምረሽኝ አታቂም! Swear to heaven ልሞትብሽ እችላለው! So you better be have ምንም ነገር እምቢ እንዳትይኝ" ብሎ በለሆሳስ አንሾካሾከልኝ...

👍5❤1