አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ከሌላ እንዳትቆጥር

ይሀዉልህ ዉዴ
ትላንትና ማታ

እንባዬን አፍስሼ
አፈር ትቢያ ልሼ
ከእግርህ ወድቄ ማረኝ ተዉ ማለቴ
ታቦት እየጠራዉ መማል መገዘቴ

                 ከሌላ እንዳትቆጥር

ደግሞም ታቦታቱን ጠርቼ ጠርቼ
አንተም ዝም ብትል
የሞተች እናትህን መቃብር አዉጥቼ
በሷ ሞት እያልኩኝ ያኔ መለመኔን
አንተንም እያስማልኩ.......
ቅዱሱን መፅሐፍ በእጆችህ አስይዤ
አልተውሽም ስትል በደስታ ፈንጥዤ
ያኔ መጨፈሬን

                     ከሌላ እንዳትቆጥር

ከወትሮዉ በሌላ
ካልለመድከዉ ገላ
እራሴን ሰጥቼ ደባብሰኝ ማለቴን
ሳመኝ እቅፍ አርገኝ ብዬ መማፀኔን
ላለፈ ስህተቴ
ከእቅፍህ ገብቼ ንስሀ መግባቴን

                   ከሌላ እንዳትቆጥር

አንተን ከረሳሁኝ
ባንተ ከማገጥኩኝ
ሳት ብላኝ ነብሴ
ሌላዉን ከሻተች ሞት ይሁነኝ ዋሴ።

ስቅበዘበዝ ልሙት ልክ እንደ ይሁዳ
የሄድኩበት እግሬ ይቅር ምድረ በዳ።

ነፍሴንም አይማረዉ
እግዜሩም ይጣላኝ
እኔ አንተን ከረሳዉ
ያቀፍኩበት እጄን ለምጥ እከክ ይዉረሰዉ
ብዬ መገዘቴን
በራሴ ጨክኜ ርግማን ማዝነቤን

         አደራ እንዳትቆጥረዉ
         እባክህ በሌላ

         ሰክሬ ነዉ እንጂ
         ባሌ ትዝ ብሎኝ
         ለደቂቃም እንኳን እንዲያዉ ለቅፅበቱ
         አንተ የኔ እንድትሆን አልሻም በእዉነቱ።

🔘ትዝታ ወልዴ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍129
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

አቶ ፍሰሀ በቀይ ቆዳ በተለበጠ መቀመጫው ላይ ተቀመጦ ስልክ እያወራ ነው። ከድሮም ጀምሮ ይህን ወንበር ይወደዋል፡፡

"ተረጋጋ ክቡር ዳኛ"

ጁኒየር በበሩ ደጃፍ ላይ ቆሞ  ተመለከተውና እና እጁን አውለበለበለት።
እያወራ የነበረውን የገመድ አልባውን ስልክ በእጁ ሸፍኖ ለልጁ በሹክሹክታ፣ ‹‹ዳኛውን እያወራሁት ነው›› አለው..ከዛ ወደስልኩ ትኩረቱን ሰብስቦ"አሁን ወደ ድምዳሜ እየዘለልክ ነው እናም እንዲሁ በከንቱ ነው እየተበሳጨህ ያለኸው " አለው

"..ፍሰሀ ነገሩን አቃለህ ልታየው አይገባም….እሷ እናቷ ተገድላበታለች።አሁን የህግ ድግሪ እና የከፍተኛ አቃቤ ህግ ስልጣን በእጇ አስገብታለች..በዚህም ምክንያት የመስቀል ጦርነት ላይ ነች። እነዚህ ወጣት ሴቶች አካሄዳቸው እንዴት እንደሆነ መገመት ከባድ ነው…. ታውቃለህ?። ››

ለአፍታ አዳመጠ። “ክብር ዳኛ ተረጋጋ፣ ምንም ሚከሰት አዲስ ነገር የለም፣አንተ ብቻ ዝም ብለህ አፍህን ዝጋ፣ ይሄ ሁሉ ነገር በቅርብ ያልፋል። የሰሎሜን ልጅ ለእኔ ተውልኝ፡፡››አለው ልጁ ጁኒየር ላይ ዓይኑን ተክሎ ንግግሩን ቀጠለ።"ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ጅራቷን በውብ እግሮቿ መካከል ሸጉጣ ወደ መጣችበት ከተማ ትመለሳለች ።ምንም አታስብ የእኔም ልጅ ምርጫውን በከፍተኛ ድምፅ አሸንፎ ፓርላማ ይገባል…፣ አንተም ጊዜህን ጠብቀህ በክብር ጡረታ ትወጣለህ፣ እና ያ እስኪሆን አንድ አመት አለን።››አለናን ተሰናብቶት ተንቀሳቃሽ ስልኩን በጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው።

"በኢየሱስ ስም …ይሄ ዳኛ ተንበቅብቆ ሊያንበቀብቀኝ እየሞከረ ነው….እባክህ ቢራ ስጠኝ
›› አለና…መቀመጫውን ለቆ ወደ በረንዳ ወጣ…..ልጁ ጁኒዬርም ለእሱና ለአባቱ አንድ አንድ ቢራ ከፍሪጅ ውስጥ አወጣና አባቱን ተከትሎ ወደበረንዳው ወጣ…..አንዱን ቢራ ለአባቱ አቀብሎት አንደኛውን ለራሱ ያዘና ከፊት ለፊቱ የበረንዳውን ግድግዳ ተደግፎ ቆመ፡፡

ወዲያው የእንስሳት እርባታ ድርጅት ውስጥ ለ30 አመት የሰራው ሱልጣን ከፊት ለፊት የውጪን በራፍ አልፎ ተከሰተ … በጭንቀት ተወጣጥሯል፣ የሰሌን ኮፍያ በጭንቅላቱ ላይ አድርጎ አንገቱን ደፍቶ ከፊት ለፊታቸው በአራት ሜትር ርቀት ላይ ቆመ፡፡

ሱልጣን ከከተማው ጥግ ከምትገኝ አንድ የገጠር ከተማ ተወልዶ ያደገ ሲሆን እስከ ስድስተኛ ክፍል ተምሮ ያቆረጠና በአባሮ ኢንተርፕራይ ስር የሚተዳደረውን የእንስሳት እርባት ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ከሠላሳ አመታት በላይ ያገለገለ አገልጋይ ነው ፣ ሚስት ያገባው እዛ ድርጅት ውስጥ ስራ ከጀመረ በኋላ ነው….አምስት ልጅ ወልዶ ያሳደገውም አዛው ድርጅት ተቀጥሮ ከብቶችናና ፈረሶችን በመንከባከብ በሚያገኘው ደሞዝ ነው….ከአሁን ወዲህ ባለው ቀሪ ዘመኑም ከዛ ውጭ መስራት የሚችለው ሌላ ስራ ይኖራል ብሎ አያምንም…ለዛም ነው ለሰራው ስህተት በመንቀጥቀት ይቅርታ ለመጠየቅ ጌታው ፊቱ የቆመው፡፡

አቶ ፍሰሀ እሱ ምንም ከመናገሩ በፊት "ምን እንደምትል አውቃለሁ። ምንም የማዳምጥህ ነገር የለም… በአጭሩ ከስራ ትባረሀል››አለው
ጁኒየር በቆመበት ሆኖ አባቱን በድንጋጤ ተመለከተ..እንደዛ አይነት ውሳኔ ሰማለው ብሎ አልጠበቀም…..‹‹አይ አባዬ ትንሽ ሊያስደነግጠው ፈልጎ ነው እንጂ የእውነትማ አያባርረውም››ሲል በውስጡ አሰበ፡፡

"ጋሽ ፍሰሀ እንዴት እንዲህ ታደርጋለህ ?። እዚህ ለሠላሳ ዓመት በላይ ለአንተና ለቤተሰቦችህ አገልግያለው።"አዛውንቱ ሱልጣን መለማመጡን ቀጠለ፡፡

"ጥሩ ለዛ ሚመጥን በቂ የስራ መፈለጊያና የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፈልህ አደርጋለው "

"ግን ... አንድ የመጨረሻ እድል ብትሰጠኝ ምን አለበት? "

" መቶ ሺ ብር ልሸጠው የማስበውን ልዩ ፈረሴን እኮ ነው በእንዝላልነት እንዲሰበር ያደረከው፣በቃ ከአሁን ወዲያ ቢድን እንኳን ምን አልባት የጋሪ ጎታች ፈረስ ይሆን እንደሆን እንጂ ለውድድር የሚያገለግል የግልቢያ ፈረስ አይሆንም፡፡ከዚህ በፊትም ስንት ከብቶች ውጭ አሳድረህ በጅብ እንዳስበላህ አትረሳውም አይደል…አንተ ላይ ያለኝ ትግስት አልቋል፡፡››

አቶ ፍሰሀ አየር ወደውስጡ ሳበ ። "ጌታ ሆይ፣ እኛን ውጥንቅጥ ውስጥ የሚያስገባን ነገር ከፊታችን ተደቅኖ እያለ ስለእሱ እንኳን ተረጋግተን ማሰብ አልችልም። በቃ ከፊቴ ጥፋልኝ…ሰኞ ቼክህ እንዲዘጋጅልህ አደርጋለው፣እዎ እርባታ ድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል ጋር አስቀምጥልሀለው…ከዛሬ ጀመሮ እዚህም ሆነ የስራ ቦታ አይንህን ማየት አልፍግም፡፡››ቁርጥ ያለውን የመጨረሻ ውሳኔውን አሳወቀው፡፡፡

"አንድ ተጨማሪ እድል ስጠኝ ጋሽ ፍሰሀ በልጆቼ እምላለው…ሁለተኛ አላሳዝንህም፡፡››

"ይህን ንግግር ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ሰምቼዋለሁ።አሁን በጥበቃ እያስገፈተርኩ ሳላስወጣህ በክብር ጊቢዬን ለቀህልኝ ውጣ፡፡››
"ጋሽ ፍሰሀ…"

"ደህና ሁን… እና መልካም ዕድል "

አባቱን ተወና የልጁን የጁኒዬርን አይን አይን ማየት ጀመረ …ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያውቀውና ሲንከባከበው የኖረ ልጅ ስለሆነ የአባቱን ሀሳብ ለማስለወጥ የሆነ ነገር ይላል ብሎ ነበር የጠበቀው.. ጁኒየር ግን ዓይኖቹን ወደመሬት ደፋ ፡፡ ጋሽ ሙስጠፋ በመጨረሻ
ያደረገው ቦት ጫማ ላይ የተጣበቀውን ጭቃ እያራገፈ እንገቱን እንደደፋ ጊቢውን ለቆ ወጣ።የግቢው በር መዘጋቱን እንደተሰማ ጁኒየር ወደአባቱ ተመለከተና"እንደምታባርረው አላውቅም ነበር" ሲል በቁጭት ተናገረ።

" በቃ..ከአሁን ወዲህ ከእሱ ምንም ጥቅም ማግኘት አይቻልም…እድሜው ገፋቷል ጉልበቱም ደክሞል…ዛሬ ፈረሱን እንዲሰበር ካደረገ ነገ ራሱን ይሰብርና የእድሜ ልክ ሸክም ነው የሚሆንብን።"

"ቢሆንስ!ማባረሩ አስፈላጊ ነበር? ለጥፋቶቹ ልትጮህበት..ወይንም በገንዘብ ልትቀጣው ትችል ነበር ፣ወይንም ደግሞ አንዳንድ ኃላፊነቶቹ አንስተሀው ቀላል ስራ ላይ እንዲመደብ ማድረግ ትችል ነበር ፡፡››

‹‹ነገርኩህ እኮ ከአሁን በኋላ አያስፈልገንም….ከዛፎች ትምህርት መውሰድ አለብህ..ቅርንጫፋቸው ላይ ያሉ ቅጠሎች ሲደርቁ ወዲያው ከላያቸው ላይ አራግፈው ያስወግዷቸዋል….ህይወት እንደዛ ነው….››

‹‹ቢሆንም ውሳኔ ጭካኔ የታከለበት ነው፡፡››

"ይህን ንግድ የምትሠራ ከሆነ ልጄ፣ ልብህ እንደብረት ጠንካራና ደንዳና መሆን አለበት።

ሥራው ሁልጊዜ አስደሳች አይደለም፣ ታውቃለህ። ደንበኞችን የሚያምር እራት ከመጋበዝና ከሚስቶቻቸውና ከሴት ልጆቻቸው ጋር ከመሽኮርመም የበለጠ ብዙ ነገር አለ።››በማለት ልጁን በአሽሙር ወጋው፡፡

ጁኒዬር ሱልጣን ላይ የተወሰደውን ከባድ ቅጣት ለመቀበል ከብዶት ራሱን ወዘወዘ፣ ከዛ በእጁ ከያዘው ቢራ አንዴ ተጎነጨለትና‹‹ቅድም ከዳኛው ጋር በስልክ ስታወራ ነበር….ስለሰሎሜ ልጅ መሰለኝ?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አዎ ….ዛሬ ዳኛውን ለማናገር ቢሮው ሄዳ ነበር››

‹‹ እንዴ?››

"አድርጋዋለች፣ ይህን ለማድረግ ጊዜ እንዳላጠፋች አስተውል። ዳኛው በሁኔታው በጣም ነው የተደናገጠው፡፡ ዳኛ ጡረታ በመውጫ ጊዜው እንዲህ አይነት ፈታኝ ጉዳይ ስለተጋረጠበት ለስሙ ፈርቷል።"

"አለም ከእሱ ምን ፈለጋ ነው?"
44👍7
"ሊቁ የተባለው እብድ በሳይካታሪስት ዶ/ሮች ሲመረመር ለምን ሁለት ዶ/ር ብቻ እንዳየውና ለውሳኔ ለምን እንደቸኮለ አንዳንድ ጥያቄዎችን ጠየቃችው።ምክንያቱም ሁለቱ ዶክተሮች ወንጀለኛውን በተመለከተ ሁለት የተለያየ ሙያዊ አስተያየት ነበር የሰጡት…እንደእሷ አመካከት የሁለቱን ዶ/ሮች አስተያየት ፍትሀዊ ለማድረግ ሶስተኛ ዶ/ር መጋበዝ ነበረበት ባይ ነች….ዳኛው በምን መስፈርት የአንደኛውን ዶ/ር ሞያዊ አስተያየት ውድቅ አድርጎ የአንደኛውን ዶ/ር አስተያየት ሊቀበሉት እንደቻሉ ነው ጥያቄዋ ።"

"ይገርማል….እንደእዛ አይነት ጉዳይ ነበር እንዴ?››

‹‹አዎ ነበር…እሷም ያንን ፈልፍላ በማውጣቷ የአደገኝነቷ አንድ ማሳያ ነው››

"ታዲያ… ስለ ልጅቷ ምን አሰብክ?"ጁኒዬር በጭንቀት ጠየቀ፡፡

‹‹ከዳኛው  ጋር እስማማለሁ። እሷ ለሁላችንም ስጋት ነች። ከመካከላችን አንዱ ሰሎሜን እንደገደላት ታስባለች፣ እና ማን እንደሆነ ለማወቅ ቆርጣለች።"

‹‹የምትገርም ሴት ነች"

"አዎ…የምትገርም ሴት ነች….ሆንም በእርግጥ በማናችንም ላይ ምንም አይነት መረጃ የላትም።"

"እርግጥ ነው።"ጁኒየር አባቱን በትኩረት ተመለከተ።

‹‹ግን እሷ ስል የሆነ ጭንቅላት ያላት ሴት ነች።››

"ስል ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን አማላይ አቋምና ውብ መልክም አላት›› አባት እና ልጅ ተሳሳቁ።

"አዎ ጥሩ ነች. አብዛኛው ነገሮቾ ልክ እንደ እናቷ ነው››የጁኒየር ፈገግታው ደበዘዘ

"አዎ እስማማለሁ….አሁንም ትናፍቅሀለች አይደል?»አቶ ፍሰሀ የልጁን አጠቃላይ ሁኔታ በማጥናት ጠየቀ።

"አንዳንድ ጊዜ."

አቶ ፍሰሀ ቃተተ። "የእሷ ሞት በአንተ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ማሳደሩን ሳስበው ይገርመኛል..አውቃለው የቅርብ ጓደኛህን ስታጣ ማዘንህ የሚጠበቅ ነው… ያንተ ግን እነዚህን ሁሉ አመታት ለሞተች ሴት ማለቃቀስ ሞኝነት ነው..የእሷን ሀዘን እንደምንም ከውስጥህ ማስወገድ አለብህ… ያለ በለዚያ መቼም ሰው መሆን አትችልም። ።››
ጁኒየር ተቃወመ፡

“የምትለውን ያህል አልሰበረኝም››

‹‹ ሰሎሜ ከሞተች በኋላ ለረጅም ጊዜ ተበሳጭተህ ነበር. ከዛን ጊዜ በኃላ በስርአቱ እንኳን መተንፈስ አልቻልክም። ኩማንደሩን ተመልከት። የሰሎሜን ሞት በፀጋ ተቀብሎ ህይወቱን ወደፊት ቀጥሏል ።"

"እኔ…እስከዛሬም ድረስ እሷን እንዳማስብ እንዴት አወቅክ?" "

" ያ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ግልጽ ነው?"

"አባዬ ተሳስተሀል ..እሷ ከሞተች በኃላ ሶስት ሚስቶች ማግባት ችያለው…ይልቅ ይሄንን ምክር ለኩማንደሩ ብትነግረው ይሻላል…እሱ ነው በአርባአምስት አመቱም ወንደላጤ ሆኖ የሚኖረው.. የዛ ምክንያቱ ደግሞ እሷ ነች."

"ያንተ ሶስት ሚስት ማግባት ሊኮራበት የሚገባ ነገር ነው…?ካሰሎሜ ሀዘን አገግመህ ቢሆን ኖሮ ከአንድ ሚስት ጋር ነበር ፀንተህ የምትኖረው….እስከአሁን ሲያገባ የነበረው በድንህ ስለሆነ ሴቶቹ ጥለውህ ይሄዳሉ፣….መንፈስህ ከእሷ ጋር ተቀብሯል?" አባትዬው ጮኸበት፣ ንዴቱ ጨመረ። " ሴቶች እያገቡ መፍታት የጤነኝነት ምልክት አይደለም…በዚህ ምርጫ ውድድርህ አንደ አንድ ሂስ የሚቀርብብህ ይሄ ሴት አያያዝህ ነው››

‹‹አባዬ እኔ እኮ አይደለም የምወዳደረው…እኔ ለአንተ ስል ነው የምወዳደረው…በምርጫው ብሸነፍ  እኔ  አልተሸነፍኩም  ..ምክንያቱም  መጀመሪያውኑም  አልፈልገውም  ነበር
…ባሸንፍም…ህዝቡን ወይም ከተማዋን ወክዬ ሳይሆን አንተን ወክዬ ነው የምገባው››

‹‹ባንተ ቤት ንግግር ማሳመርህ ነው..በዚህ ጉዳይ ቀልድ እንደማልወድ ጠንቅቀህ ታውቃለህ…..በአንተ እንዝላልነት አንድ እንቅፋት ቢገጥመን እና ይሄ ለአመታት የለፋሁበትና ገንዘቤን የከሰከስኩበት ጉዳይ ቢሰናከል…እኔና አንተ አንተዋወቅም….ከአሁኑ ቤቴንም ኩባንያዬንም ለቀህ ለመሄድ ተዘጋጅ፡፡››

‹‹አታደርገውም አይባልም….ግን አባዬ እኔን አይደለም መፍራት ያለብህ….የሰሎሜን ልጅ ፍራ….ለአመታት የገነባሀውን ነገር ሁሉ ወደፍርስራሽ እንዳትቀይርልህ፡፡››

"አታስብ ..እኛ ንፁሀን መሆናችንን እናሳምናታለን ። እኛ የተከበረን ዜጎች ነን።" "ስለዚህ አካሄዳችን እንዴት ነው?"

"አታሏት"

"አታሏት!አልገባኝም" ጁኒየር መልሱን ለመስማት ጓጓ፡፡፡

‹‹አንደምታያት ቅንዝንዝ እና ቅንዝራም ነገር ነች..በፍቅር አይኗቾን ለመጋረድ መሞከር በጣም አዋጪው ዘዴ ይመስለኛል፡፡››

"እንዲህ ዓይነቱን ደስ የማይል ወጥመድ በቀላሉ የምትወድቅ ይመስልሀል?"ጁኒየር ፈገግ አለ።

"መሞከር ነው..ካልሞከርን እንዴት እናውቃለን…አንተም ሆንክ ኩማንደር ገመዶ ሞክሯት…ከሁለት አንዳችሁ በለስ ይቀናችሁ ይሆናል….በእናቷ ጊዜ ልምድ ስላላችሁ ለአንድ ሴት መፋለም ያን ያህል የሚከብዳች አይመስለኝም….ግን እወቅ በምንም አይነት ሁኔታ ከእሷ ጋር ወደአልጋ እንዳትሄድ…በምንም አይነት?››

‹‹እንዴ ለምን››

‹‹ነገርኩህ…ያ የሆነ ቀን ከእኔ ምንም አይነት ከለላ የለህም…ቀጥታ እጅህን ሄደህ እሰሩኝ ብለህ ለመንግስት እንደሰጠህ ቁጠረው፡፡››

‹‹እውነትህን አይደለም አይደል?››

‹‹ሚካኤልን ብያለው››

ጁኒዬር ደነገጠ..አባትዬው ሚካኤልን ብለው ከማሉ ምንም የሚቀየር ነገር እንደሌለ እና የመጨረሻ ሀሳባቸው እንደሆነ ያውቃል፡፡ግን ምናቸውም አልገባውም‹‹…በፍቅር እንድትወድቅልህ አታላት ..ግን አብረሀት እንዳትተኛ..ምን አይነት ግራ የተጋባና የተወሳሰበ ትዕዛዝ ነው››ሲል በውስጡ ይወዛገብ ጀመር፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2826🥰2
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// አቶ ፍሰሀ በቀይ ቆዳ በተለበጠ መቀመጫው ላይ ተቀመጦ ስልክ እያወራ ነው። ከድሮም ጀምሮ ይህን ወንበር ይወደዋል፡፡ "ተረጋጋ ክቡር ዳኛ" ጁኒየር በበሩ ደጃፍ ላይ ቆሞ  ተመለከተውና እና እጁን አውለበለበለት። እያወራ የነበረውን የገመድ አልባውን ስልክ በእጁ ሸፍኖ ለልጁ በሹክሹክታ፣ ‹‹ዳኛውን እያወራሁት ነው›› አለው..ከዛ…»
#ታምናለህ?

“ውስኪን ከብርጭቆ
መጎንጨት አንስቶ
ጭኗን ከገለጠች…
ማውራት እንቶፈንቶ ፤
አያድርስ በደሉ !
የሀብታም ሰው ግፉ
ተናግሯል መጽሐፉ”
ብሎ የሚታዘብ…
አረቄ ቤት ያለ …
የዛ ድሀ ምኞት ፤

በሴቶች ታጅቦ...
ውስኪ መጠጣት ነው
እ’ሱም ገንዘብ ኖሮት።

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍75
#ተመስገን

ለውሀ ቢቀረጥ ለማየት ቢከፈል
ለጠሀይ ቢቆጠብ አየር ቢከለከል
ለመስማት ቢያስጨንቅ ለማሽተት ቢቀጣ
አቤት የእኛ እጣ!
ዋጋ ቢወጣለት እያወሩ መስማት
በደረሰኝ ቢሆን መራመድ መተኛት
እግዚኦ የኮመቴው የህግ አውጭው መዓት!
ይህን ሳይ ብቻ ነው ወደ ላይ ማንጋጥጥ
የዓለም ማጣቴን ... በስድብ የማለውጥ
ውድ መነፅር ሳጣ ከጎኔ ማተርኩኝ
መኪና አልባ ስሆን አቀርቅሬ አየሁኝ
ማየት የተሳነው እግር አልባም አለ
እንዴት ብዬ ላማር ሁሉ ኖሮኝ ሳለ?
ስድብ ከቶ አልክም ለዝምታው ዳኛ
ጤና ቢሰጠኝ ነው ሰርቼ ምተኛ
አላማርረውም ቤት ሳልገዛ ብዬ
የጎዳናውን ጉድ እያየሁኝ ባይኔ
ባለ መፅናናት ነው በፀጋው ማመስገን
ያለን ነው የሚበዛ ለእኛ ካልተሰጠን
ተመስገን ተመስገን
ይሄ ነው ክፍያው ደግሞ ለቀጣይ ቀን

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
14👎1
#ለካስ



ማበጠር ቸግሮኝ ገለባን ከፍሬ፣
እንዲው እንደባከንኩ መልስ አጥቼ ኖሬ፣
ለዚው ጥያቄዬ ለሚወብቅና ለሚያንቀጠቅጠኝ፣
ተመስገን ነው ዛሬ ግዜ ምላሽ ሰጠኝ።


ይኸው የግዜው መልስ ...


ስንዴን ከእንክርዳዱ የምንለይባቸው
ገንዘብና ዝናም ለካስ ወንፊት ናቸው።

🔘ሄኖክ ብርሃኑ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
9👍2👏2
#ሀገሬን_አትንኩ

ዝንጀሮ
ያኔ ጥንት ድሮ..
መጀመርያ የመቀመጪያዬን
ማረፊያ መንበሬን.. .
ብላ ተናግራለች ብለው ሲተርቱ
አልገቡኝም ነበር አበው አዛውንቱ
ዛሬ ፍቺ አገኘሁ ተፈታልኝ ቅኔ
ለካስ የሚያሞቀኝ ትንፋሹ ነበረ
የምስኪን ወገኔ !
ብሄድ ብጓዝ ብድህ ብሸሽም በርሬ
ማረፊያ ወንበሬ
መሸሸጊያ አድባሬ
እሷ ናት ኢትዮጵያ
እሷ ናት ሀገሬ !
አሁን መሯል ደሜ ..
ግራ ጉንጬን ምቱት ሰንዝሩብኝ ጡጫ
ሲሻችሁ ነርቱኝ በዱላ በርግጫ.. .
ብቻ ግን
ብቻ ግን.. .
ሀገሬን አትንኳት የኔን መቀመጫ ።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
7👍4🥰1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
ፀሐይ ከምዕራቡ አድማስ በላይ ልክ እንደ አንድ ግዙፍ ብርቱካንማ ዲስክ ተንጠልጥላ ነበር፣ ብሩህ ነሐስ ትመስላለች። ሰማዩ ቀዝቃዛ እና የሚረብሽ አይነት ነው፡፡ ከከተማ ወጣ ብሎ የሰሜኑ ንፋስ የጠነከረ ይመስላል። ተክለሀይማኖት ቤተክርሲቲያኑ በራፍ ጋር ስትደርስ መኪናዋን ጥግ አስይዛ አቆመችና መጀመሪያ ተሳለመች…ከዛ ቀጥታ ወደ መቃብር ስፍራዎች ነው ሄደችው። ወደ እናቷ መቃብር ሄዳ አታውቅም ስለዚህ የመቃብር ድንጋዬች ላይ የተጻፉትን ፅሁፎች እያነበበች መፈለግ ጀመረች፡፡ከአስር ደቂቃ አሰልቺ ሚመስል ፍለጋ በኋላ ተሳካላትና አገኘችው፡፡የእናቷ የመቃብር ድንጋዮች ላይ የበቀሉት ሣሮች ረዥም እና አረንጓዴ ናቸው፡፡
ወደመቃብሩ ለመጠጋት ፈራች …ከእናቷ መንፈስ ጋር ለማውራት ዝግጁ የሆነች አልመሰላትም፡፡አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው የእምነበረድ ምልክት ከመቃብሩ አናት ተተክሏል፡፡ የእናቷ ሙሉ ስም ፤ የእናቷን የትውልድ ቀን እና የሞት ቀን ተፅፎበታል፡፡እሰከዛሬ አይታ የማታውቀው ውብ የሚባል ፎቷዋ ከፅሁፎቹ በላይ አለ - ሌላ ምንም ነገር የለውም. ፡፡

‹‹ሩጫዬን ጨርሼለሁ….››የመሰለ አንድ ጥቅስ እንኳን ከስር ቢያሰፍሩበ ስትል አሰበችና ልቧ አዘነባት።መልሳ ስታስበው እርባን የሌለው ነገር እንደሆን ሲገባት ቅሬታዋን ሰረዘችው፡፡

እናቷ ሰሎሜ በጣም ወጣት እና ቆንጆ እና ሙሉ ተስፋ የነበራት ሴት ነበረች፣ነገር ግን ማንነቷ በተገቢው መንገድ እንዳይገለፅ በአጭሩ እንድትቀጭ ተደርጓል፡፡ ከመቃብር አጠገብ ተንበረከከች። በእናቷ ቀብር አጠገብ ምንም አይነት ሌላ የቅርብ ዘመድ መቃብር ባለመኖሩ ቅር አሰኛት፡፡እሷ የሚሰማትን አይነት ብቸኝነት እናቷም የሚሰማት አድርጋ ነው የወሰደችው፡፡ በውትድርና አገልግሎት ላይ እያለ የሞተ አባቷ አስከሬን እዛው በተሰዋበት ጦር ሜዳ ነው የተቀበረው፡፡ሰሎሜ ገና  ልጅ እያለች የሞተው አያቷ በትውልድ ከተማው
ኮፈሌ ነው የተቀበረው።በዚህ የተነሳ የሰሎሜ መቃብር ብቸኛ ነበር። ድንጋዩን ስተነካው ከጠበቀችው በላይ ቀዝቃዛት . የእናቷን የመጀመሪያ ስም የተቀረጹትን ፊደሎች በጣቷ እየዳበሰች መረመረች፣ ከዚያም የልቧ ምት እንደሚሰማት እጇን ከፊት ለፊቱ ባለው ሳር ላይ ጫነች።ከተፈጥሮ በላይ በሆነ መንገድ ከእሷ ጋር መነጋገር እንደምትችል ማሰቧ ሞኝነት መስሎ ተሰማት ፣ ነገር ግን የደረቀ ሳር መዳፏን ሲወጋ "እናቴ" ብላ ወደቀልቧ ተመለሰች።

"ማማ. እማዬ." ስሞቹ ለምላሷ እና ለከንፈሯ እንግዳ ነገር ሆኖ ተሰሟት። ከዚህ በፊት በየትኛውም አጋጣሚ ተጠቅማበት አታውቅም።በዚህ ጊዜ ከጎን በኩል ስሟ ሲጠራ ሰማች…ግራ ገባት..የሆነ እርኩስ መንፈስ ሊተናኮላት እየሞከረ ነው የመሰላት…፡፡
"አሌክስ….›› በድንጋጤ ዙሪያውን ተመለከተች..በዚህ ስም የአዲስአበባ አብሮ አደግ ጓደኞቾ ናቸው የሚጠሯት፡፡እንዴት እዚህ ተገኙ። ሚመታው ልቧ ላይ እጇን እየጫነች፣ በፍርሃት ተንፈሰች።ዞር ስትል ያልጠበቀችውን ሰው ነው ያገኘችው፡፡

" አስደነገጥከኝ … እዚህ ምን እየሰራህ ነው?"
ጁኒየር ፍሰሀ አጠገቧ ተንበርክኮ በመቃብሩ ቆሚ ድንጋይ ላይ እቅፍ አበባ አስቀመጠ። ለአፍታ በራሱ ጥሞና አቀረቀረና ከዛ ፊቱን ወደ አለም አዙሮ ፈገግ አለላት፡፡

"በደመ  ነፍስ  ወደ  አረፍሽበት  አፓርታማ  ደውዬ  ነበር…ነገር  ግን  ስልኩ  የሚያነሳ አልነበረም።"
"የነበርኩበትን ሆቴል ለቅቄያለው … የት እንደገባው እንዴት አወቅክ?"

"በዚች ከተማ ውስጥ ስለሚከወነው ሁሉም ነገር መረጃውን በቀላሉ ማግኘት እችላለው ." "ወደ መቃብር ስፍራ እንደምመጣ ግን ማንም አያውቅም።››

" በአንቺ ጫማ ውስጥ ብሆን የት እንደምሆን  ለመገመት  ሞከርኩኝ. በመምጣቴ እንዳላስደበርኩሽ አገምታለው."

"አይ. ምንም አይደለም…አሌክስ ስትለኝ እኮ በጣም ነው ግራ የተጋባሁት."

‹‹እንዴ ለምን?››

‹‹በዚህ ስም የተወሰኑ የቅርብ ጓደኞቼ ብቻ ናቸው የሚጠሩኝ…እዚህ እንግዳ በሆንኩበት ከተማ ይሄን ስም ተጠቅሞ የሚጠራኝ ሰው ይኖራል ብዬ እንዴት ልገምት?››

‹‹ያው እኔም ጓደኛሽ ለመሆን ካለኝ ጉጉት የተነሳ ነው ይሄን ስም የተጠቀምኩት…ባለፈው እዛ ፍርድ ቤት እራስሽን ስታስተዋውቂን ስሜ አለም ይባላል..ጓደኞቼ አሌክስ ብለው ይጠሩኛል ስትይ …እኔም አሌክስ የሚለውን ስም ስለተመቸኝ ቀለብ አድርጌ በምናቤ አስቀመጥኩት››

‹‹አይ ጥሩ ነው..ደስ ብሎኛል….ብዙ ጊዜ ወደ እናቴ መቃብር አበባ ታመጣለህ ?"ስትል ጠየቀችው፡፡

ፈጥኖ አልመለሰላትም።

" በተወለድሽበት ቀን ሆስፒታል ነበርኩ፣ ከመታጣብሽ በፊት ከነደምሽ አይቼሻለሁ።" አላት፡፡ፈገግታው ክፍት እና ሞቅ ያለ ነው፣

‹‹ጥሩ ..እሺ መጀመሪያውን ጥያቄ መልስልኝ፣ብዙ ጊዜ አበቦችን እዚህ ታመጣለህ?."

" በበዓላቶች ቀን ብቻ ነው ። እኔ ፤ አባቴ እና ኩማንደር ገመዶ በልደቷ፣ ገና፣ ፋሲካ፣ሲሆን አንድ ላይ እናመጣለን። መቃብሯን ለመንከባከብ የሚያስፈልገውን ወጪ በጋራ እንሸፍናለን።"

"ለምን ?የተለየ ምክንያት አላችሁ?"
ያልተለመደ  አይነት  አሰተያየት  አያት….ከዛ  "ሁላችንም  እናትሽን እንወዳታለን…ምክንያታችን ያ ነው፡፡›› ሲል መለሰላት፡፡

ለስለስ  ባለ  የድምፅ  ቃና  "የሚገርመው  ግን  ከእናንተ  አንደኛችሁ  እንደገደላችኋት አምናለሁ" አለችው ።

" ተሳስተሻል አሌክስ ፤እኔ አልገደልኳትም።"

"አባትህስ?

እሱ ያደረገው ይመስልሃል?"

ራሱን  በምሬት  ነቀነቀ "አባቴ  እንደ ሴት ልጅ ነበር ሚንከባከባት፡፡. እሷም እንዲሁ እንደአባቷ ነበር የምታየው."

"እና ኩማንደር ገመዶስ?"

ማብራርያ የማያስፈልግ መስሎት ትከሻውን ነቀነቀ። "ገመዶ ፈጽሞ ሊገድላት አይችልም ››
አለም በእጇ አንጠልጥላ የነበረውን ባለ ፀጉር ጃኬቷን ለበሰች ። ፀሀይዋ እየጠለቀች ነበር፣
"ዛሬ ከሰአት በኋላ በሕዝብ ቤተመጻሕፍት ውስጥ የተወሰነ ጊዜ አሳልፌ ነበር፣ የቆዩ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ እትሞችን መለስ ብዬ ለማንበብ ሞክሬያለው።"

"ስለ እኔ የሆነ ነገር አገኘሽ?"

"ኦህ አዎ፣ ስለከነማ እግር ኳስ ቡድን ተሳትፎህ ሁሉም ነገር ተፅፏል።;;›› ተንከትክቶ ሳቀ.. ንፋሱ ቆንጆ ጸጉሩን አውለበለበለት፡

"አንተ እና ገመዶ የቡድኑ ዋና እና ምክትል አንበል ነበራችሁ።"

"በሚገርም ሁኔታ አዎ…..የማይበገሩ፣ እውነተኛ እግር ኳስ ተጫዋቾች እንደሆን ነበር የምናስበው።"

" በጊዜው ወጣት የነበረችው እናቴ ወደ ቤታችሁ የምትመጣ ንግስት ነበረች። በእረፍት ሰአት ከገመዶ ጋር ስትስማት የሚያሳይ ፎቶ አይቼያለሁ።››

ያን ፎቶግራፍ ባየች ጊዜ እንግዳ ነገር ነበር የተሰማት። በፊት አይታው አታውቅም ነበር። በሆነ   ምክንያት   አያቷ   ከብዙዎቹ   ጋር   ላለማቆየት   መርጣለች፣ ለብዙ ደቂቃዎች ፎቶግራፉን ካየች በኋላ እናቷ ሳትሆን እራሷ እንደሳመችው ይሰማት ጀመር። ወደ አሁኑ ጊዜ ስትመለስ፣ "እስከእዛን ጊዜ ድረስ ከእናቴ እና ከገመዶ ጋር ጓደኛ አልነበርክም አይደል?"ስትል ጠየቀችው፡፡

ጁኒየር የሳር ቅጠል አነሳና በጣቶቹ በመቆራረጥ ማውራት ጀመረ። "ዘጠነኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ በኩየራ በሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የምኖረው"

"በምርጫህ?"
43👍6🔥1
"አይ፣የእናቴ ፍላጎት ነበር፡፡ ያልተፈለገ ባህሪ አንዳለምድ በማለት በውድቀት ለሊት ሻንጣዬንና የትምህርት ቁሳቁሶቼን አሸክማ ወደ አዳሪ ትምህርት ቤት ላከችኝ ።ከስምንተኛ
ክፍል ወደዘጠነኛ ከተዘዋወርኩ በኃላ ግን ጎረመስኩ መሰለኝ..በፍፅም ወደእዛ አዳሪ ትምህር ቤት አልመለሰም ብዬ አመፅኩ ..የአባቴን ድጋፍ አገኘሁና እዚሁ ሻሸመኔ ሀይእስኩል ተመዘገብኩ፡፡››

'"እናትህ ምን አለች?"

" ደስ አላላትም ነበር…በግልፅም ተቃውማ ነበር፡፡በወቅቱ ነገር ግን በወቅቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ማድረግ የምትችለው ብዙ ነገር አልነበረም.፡፡አባዬ እኔን በእዚሁ ሀይእስኩል ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን  ወደ ከነማው ታዳጊዎች እግር ኳስ ቡድን እንድቀላቀል አጥብቆ ይፈልግ ነበር።በወቅቱ የነበረው አሰልጣኝ ግን እኔ ላይ ብዙም ፍላጎት አላሳየም ነበር፣ ነገር ግን አባዬ ለቡድኑ አዲስ ዩኒፎርም እንደሚገዛ ቃል በመግባት ጉቦ ሰጠው። አሰልጣኙም ተቀበለኝ ፡፡..ጁኒየር እየሳቀ ታሪኩን ቀጠለ ‹‹ስለዚህ ለእግር ኳስ ብድኑ አባል ሆንኩ፡፡ የመጀመርያው የልምምድ ቀን ሊያባረረኝ ተቃርቦ ነበር። ሌሎቹ የቡድኑ አባላትም በእንቅስቃሴዬ ደካማነት ብቻ ሳይሆን በከተማው ውስጥ በጣም ሀብታም የሆነ ሰው ሰውዬ ብቸኛ ወንድ ልጅ በመሆኔ ተበሳጩተውብኝ እንደነበረ አስታውሳለው?"

‹‹እንዴት ተቀበልከው ታዲያ?››

"የሀብታም ልጅ መሆን በጣም ከባድ ስራ ነው፣ ግን አንድ ሰው የግድ ያንን ስራ መስራት አለበት" አለ በሚስብ ፈገግታ። " ለማንኛውም፣ ወደቤት ተመለስኩና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱንም እና እግር ኳስን ቡድኑን በጣም እንደምጠላ ለአባቴ ነገርኩት። እንደ ገመዶ አይነቱን ጉልበተኞች እና ትቢተኛ ወጣቶች ጋር ከመዋል ይልቅ አዳሪትምህረት ቤት ካሉ የገረጡ ትንንሽ ፊት ያላቸውን ደካሞች ጋር መኖር እንደምመርጥ ነገርኩት።"

"በቀጣይ ታዲያ ምን ሆነ፧?"

"እናቴ ራሷን ታማ አለቀሰች። አባቴ በንዴት ራሱን ሳተ። ከዚያም ወደ ውጭ አወጣኝ እና እጆቼ ለመያዝ እስኪዝል ድረስ የኮስ ልምምድ እንዳደርግ አስገደደኝ››

"አስፈሪ ነበር?"

"በእርግጥ አይደለም። ፍላጎቶቼን በልቤ ቀብሬ እንጂ ጥሩ ተጫወች መሆን እፈልግ ነበር ። ባይሳካልኝ እንኳን እዚህ ውጭ መጫወት፣ መብላት፣ መጠጣት እና መተኛት እንዳለብኝ አውቅ ነበር።….መሄድ ትፈልጊያለሽ?"

"አይ፣ ጫወታህን እንድትቀጥል እፈልጋለሁ።" "ይህ መደበኛ ምርመራ ነው እንዴ?"

በቁጣ በታከለበት ፈገግታ።"ውይይት ብንለው ይሻላል" ስትል መለሰችለት፣

"ከዛ በእግር ኳስ ክለቡ ያለህን ተሳትፎ ቀጠልክ ?››ብላ ጀምረው ወደነበረበት የጫወታ ርዕስ መለሰችው፡፡

ጁኒየር ‹‹አዎ፣ እኔ ግን በአንድ ጨዋታ ውስጥ እንኳን አልተጫወትኩም፣ ነበር። ለአውራጃ ሻምፒዮን ሺፕ አልፈን ነበር።"አንገቱን ዝቅ አደረገ እና ፈገግ አለ። ‹‹ከዛ ዋንጫ ጫወታ ቀን ደረሰ…ቡታጅራ ነበር ጫወታው፡፡ቀድመው አገቡብን.. ልንሸነፍ ሆነ … በሰዓቱ ላይ ጥቂት ሰከንዶች ብቻ ቀሩ። ››አሰልጣኙ ወደ ቤንች ሲመለከት እኔን አየ፣ከዛ ስሜን ጮኸ ተጣራ። ከፍራቻዬ የተነሳ በሱሪዬ ላይ መሽናት ነበር የቀረኝ››

"ከዛ እንዴት ሆነ?፧"በጉጉት ጠየቀችው፡፡
እንደምንም እራሴን አጠነካክሬ ቡድኑን ለመቀላቀል ሮጬ ወጣሁ። በሜዳው ላይ ያለው ንጹህ ማሊያ የኔ ብቻ ነው።ገመዶ ሜዳ ውስጥ ነበር" አለም ከጋዜጣ ዘገባዎች ይህን ታውቅ ነበር.

"አዎ የኔ መሲህ። መምጣቴን ሲያይ አቃሰተ፣ እና አሰልጣኙ የነገረኝን የጨዋታ ታክቲክ ለውጥ ስነግረውም ጮክ ብሎ ዓይኖቼን መሀል እያየኝ ኀእንዲህ አለኝ። ፣ ከጎሉ በግራ በክል ሁን ፣ እንደምንም ብዬ ኳሷን ወደአንተ ልካታለው…ወደጎል ለጋት..እርግጠኛ ነህ ታደርገዋለህ››አለኝ…ለአፍታ ጁኒየር ዝም አለ፣ ትዝታ ውስጥ ሰጥሟል።
"የዛን ቀኑን ሁኔታ በህይወት እስካለው ድረስ መቼም አልረሳውም። ከዛ ያገኘነውን ቅጣት ምት ሲመታ ገመዶ እግር ስር ነው ያረፈው …ሁለት ተጫዋቾችን ሸውዶ አለፈና ከእኔ ተሻለ ሁለት አማራጭ እያለው ለእኔ አቀበለኝ……በደመነፍስ ወደጎሉ ላኳት …የተዘናጋውን በረኛ አለፈችና መረብ ላይ አረፈች፡፡ከዛ በኃላ የሆነውን ነገር ምን ብዬ ላስረዳሽ ››

"አባትህ ደስተኛ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ."

ጁኒየር አንገቱን ወደ ኋላ ነቀነቀና እና እንባ አስኪወጣው ሳቀ ።

"አጥሩን ዘሎ ወንበሩን ጥሎ ወደ ሜዳው ቀረበ ..ሜዳው ውስጥ መግባት ነው የቀረው፡፤

"እናትህስ?"

"እናቴ! የእግር ኳስ ጨዋታ ብትሞት እንኳን ማየት አትፈልግም ።የአረመኔዎች ጫወታ ነው ብላ ታስባለች።ግን ከአባቴ በስተቀር ማንም ስለ እኔ ምን ቢያስብ ግድ አልነበረኝም። በዚያ ምሽት በጣም ነበር የኮራብኝ ።ጥቋቁር አይኖቹ በማስታወስ ያበሩ ነበር።ከዛ በፊት ገመዶን አግኝቶ አያውቅም ነበር፣ ነገር ግን በእለቱ የእግር ኳስ አባላትን እና ሁሉንም አቀፋቸው። ያ ምሽት የጓደኝነታችን መጀመሪያ ነበር። ብዙም ሳይቆይ የገመዶ አባት ሞተ፣ እና ወደ እኛ ቤት መጥቶ እንዲኖር ምክንያት ሆነው ።››

ለተወሰነ ደቂቃ በመሀከላቸው ፀጥታ ሰፈነ….ዝም ብሎ በፅሞና ሲመለከታት ቆየና "ጌታ ሆይ፣ በዚያን ጊዜ የነበረችውን ሰሎሜን ትመስያለሽ" አለ በለሆሳስ። "በባህሪ ብዙ አትመሳሰሉም , ነገር ግን የአንቺ አገላለጽ. ከእርሷ ጋር ተመሳሳይ ነው..በዛ ላይ ሁለታችሁም ተመሳሳይ አይነት የማዳመጥ ጥራት አላችሁ." እጁን ዘርግቶ ፀጉሯን ነካ። "እሷም እንደአንቺ ማዳመጥ ትወድ ነበር።ቢያንስ የሚያወራውን ሰው እደተረዳችው እንዲያስብ ታደርጋዋለች። ዝም ብላ ለሰዓታት ማዳመጥ ትችላለች"

"መጀመሪያ ወደ እሷ የሳበህ ያ ነው?"

" አይ" አለ በሚገርም ፈገግታ። "ወደ እሷ የሳበኝ የመጀመሪያው ነገር ዘጠነኛ ክፍል እያለው የወንድ ልጅ የጉርምስና ምኞት ነበር። ሰሎሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ ሳያት ቀልቤን ነበር የሰለበችው፣ በጣም ቆንጆ ነበረች።"

" አሳደድካት?"

"ሄይ፣ ደንግጬ ነበር እንጂ አላበድኩም።የገመዶ ፍቅረኛ ነበረች" አለ በማያሻማ ሁኔታ።

‹‹ስለዚህ ምንም ጥያቄ አልነበረም››

" ተነሺ። ብንሄድ ይሻለናል:: ብርዱ ኃይለኛ እየሆነ ነው:: በዛ ላይ ጨለማው እየጠነከረ ነው.››
አለም ከተቀመጠችበት ቀድማ ተነሳች…ተክትሏት ተነሳ፡፡"ጁኒየር አበቦቹን ስላመጣህ አመሰግናለሁ."አለችው

"ምንም አይደል።"

"ለእሷ ያላህን ለዘመናት የማይደበዝዝ አሳቢነት አደንቃለሁ."

"በእውነቱ ከሆነ ዛሬ ወደዚህ የመጣሁበት ድብቅ ምክንያት ነበረኝ።" "ወይ?"

"ኡህ-ሁህ"  አለ  ሁለቱንም  እጆቿን  በመያዝ"  ወደ  ቤታችን  ለእራት  ልጋብዝሽ ነበር››አላት..ሀሳቡ ቀደም ብሎ ያሰበበት ሳይሆን ድንገት የመጣለት ነው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
32👍25
አትሮኖስ pinned «#ቋጠሮ_ሲፈታ ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ፡ ፡ /// ፀሐይ ከምዕራቡ አድማስ በላይ ልክ እንደ አንድ ግዙፍ ብርቱካንማ ዲስክ ተንጠልጥላ ነበር፣ ብሩህ ነሐስ ትመስላለች። ሰማዩ ቀዝቃዛ እና የሚረብሽ አይነት ነው፡፡ ከከተማ ወጣ ብሎ የሰሜኑ ንፋስ የጠነከረ ይመስላል። ተክለሀይማኖት ቤተክርሲቲያኑ በራፍ ጋር ስትደርስ መኪናዋን ጥግ አስይዛ አቆመችና መጀመሪያ ተሳለመች…ከዛ ቀጥታ…»
#ይናፍቀኝ_ነበር

ዞሮ ዞሮ ከቤት
ይላል የኛ ተረት ::

አቧራው ፀሃዩ ይናፍቀኝ ነበር፤
አፈሩ ጠጠሩ ይናፍቀኝ ነበር::

የመንደር ጭስ ማታ…….
ይናፍቀኝ ነበር የሳር ቤት ጥቀርሻው
መደቡ ምሰሶው፤
ማገሩ ግድግዳው፤ አጥሩና ጥሻው::

የፈራረሰ ካብ………
ቀጭን ጠባብ መንገድ በመንደር የሚሮጥ፤

ቅጠል የሸፈነው፡
ሳር ያለባበሰው፤
እነዚህ እነዚህ ይናፍቁኝ ነበር፤

የተቆላ ቡና ፤
የሚወቀጥ ቡና፤
የጎረቤት ቡና አቦል ሁለተኛ፤
የተረጨ ቆሎ የሚያርቅ መጋኛ፤
የሚጨሰው ዕጣን………

እንጀራ በመሶብ ወጥ የፈሰሰበት
ያገልግል እንጀራ፤ የሚቧጠጥ ፍትፍት፤
የክክ ወጥ የሽሮ፤
የስጋ የዶሮ፡፡

ይናፍቀኝ ነበር ቅራሪ ጉሽ ጠላ፤
ይናፍቀኝ ነበር ፊልተር ዞማ ኮላ፡፡

ያገራችን ድግስ……..
ከበሮው ጭፈራው፤
ዝላዩ እስክስታው፤ ስካሩ ሁካታው፡፡

ትርክምክሙ ነገር ግፍያው ትንቅንቁ፤
ኳኳታው እርግጫው ዘፈን ድብልቅልቁ፡፡

“አሸወይና ወይና“
“እስቲ እንደ ጎጃሞች“
“አሲዮ ቤሌማ… ኦሆሆ አሀሀ…"
የቄስ ትምህርት ቤት
የህፃናቱ ድምፅ፤

“ሀ...ሁ…ሂ…ሃ…“ ዜማ ነበር የናፈቀኝ
የጽጌ ጭፈራ ነበር የናፈቀኝ፡፡

ከበሮ ፅናፅል፤
ሆሳዕና ጥምቀት፤
ፋሲካ ገና ሁዳዴና ስግደት፤
ቡሄ ሆያ ሆዬ፤
የእስላሞች አረፋ የኦሮሞች ሸጎዬ፤
የቁልቢ ገብርዔል፤
ልደታ፤
ፍልሰታ፡፡

ዕንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ፤
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡

ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት፤
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡

ሌላም ብዙ ነበር…
ሌላም ….ደግሞ ሌላ…..፡፡

ያገሬ ሰው ነበር እኔን የናፈቀኝ፤
ጠይም ቆዳ ነበር እኔን የናፈቀኝ፤
ቀይ ዳማ ነበር ጥቁር ቆዳ ነበር፤
ቁርንጫጭ ከርዳዳ፤ ዞማ ጠጉር ነበር፤

ያገራችን ቋንቋ…
ያገሬ ሙዚቃ ያገራችን ዜማ፤
ጥበብ እጀ ጠባብ ያገራችን ሸማ፤
ነበረ ናፍቆቴ ለሁሉም…
ለሁሉ፡፡

ለሸዋ፤ ለወሎ፤ ለትግሬ፤ በጌ ምድር፤
ለጎጃም ወለጋ፤ አሩሲ ኢሉባቡር፤
ኤርትራ ገሙጎፋ፤
ሲዳሞና ከፋ፡፡
ለሁሉም ለሁሉ ነበረ ናፍቆቴ፤

አለብኝ ትዝታ
ዘመዶቼ ሳሙኝ፤
ጓደኞቼም ጋብዙኝ፤
ሊስትሮ ጨብጠኝ::

ባለጋሪ ንዳ መንደሩን አሳየኝ፤
ያገሬ ልጅ ቆንጆ “ቤት ለእንግዳ በዪኝ“፡፡

አለብኝ ትዝታ…..
አዲስ አበባ ላይ ነበረ ናፍቆቴ
መናገሻ ነበር፤ እንጦጦ ነበረ፤
ኤረር ጋራ ነበር፤ ዝቋላ ነበረ፤
ጃን ሜዳ ነበረ፤ ኮተቤ ነበረ፤
ገፈርሳ ነበረ፤ ጉለሌ ነበረ፤

አዲሱ ከተማ…
“መርካቶ ዲጂኖ ችምችም ያለው መንደር“
ከተማው እንብርት ደጃች ውቤ ሰፈር
የቸርችል ጎዳና፤
የባቡሩ ጣቢያ፤
ቢሾፍቱ ነበረ፤ ናዝሬት፤ ሞጆ አዋሽ::
ድሬዳዋ ነበር፤
ዓለምማያ ነበር::

ሐረርጌ ነበረ የተወለድኩበት
እናትና አባቴን ጥዬ የሄድኩበት::
የሚካዔል ጓሮ…
ሐረርጌ ነበረ፡፡
ዞሮ ዞሮ ከቤት…
አገሬ ነበረ እኔን የናፈቀኝ::
ኢትዮጵያ ነበረች


🔘ገብረክርስቶስ ደስታ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
10🔥1🥰1
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ቦሔ_አምላክ_አለ

ከተወለድኩበት፥በመንገዴ የዋለ፤
ቦሔ አምላክ አለ።
ቢጎድል እንኳ፥በሱ እምነቴ፤
በምህረቱ፦
ደብረታቦር ሆኗል ቤቴ።
(ብርሀኑ አለ በህይወቴ!)
.
.
.
ከእምነቴ ብጎድልበት፤
ከቤቴ ደጅ፦
ንጉስ ሳኦል፥ባይመጣበት፤
ባርቅ፦ድል ባይነሳበት፤
ብርሀን አርጓል በቤቴ ላይ፦
ክብሩን ገልጧል፥በኔ ህይወት!
ቦሔ አምላክ አለ
.
.
.
ሰማርያ አውራጃ፥ባልሆንም እረኛ፤
ፅድቄ ባይመዝንም፦
ብርሀኑን ለማየት፥ባልሆንም ተረኛ፤
ብርሀኑን ሲገልጥ፦
ቀን ነው ብዬ፥የምጠብቅ፤
ወላጆቼ ባይፈልጉኝ፥ባያመጡ ሙልሙል ለስንቅ፤
የኔ ነገር፥ቢሆን ወረት፤
ክብሩን ገልጧል፥በኔ ህይወት!
(ብርሀን አርጓል፥በኔ ህይወት!)


🔘ሃይማኖት ሹመት 🔘


 
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
6👍4
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
ጁኒዬር አለምን ይዞ ወደ ወላጆቹ ቤት ሲደርስ ሳሎን ያለው አባቱ ብቻ ነው፡፡አቶ ፍሰሀ ከመቀመጫቸው ተነስተው እጇን እየጨበጡ"ጁኒየር ስላገኘሽ እና እንድትመጪም ስላሳመነሽ ደስ ብሎኛል" አላት፡፡

"እኔም  እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ።"

"ደህና….ተቀመጪ››
ተቀመጠች፡፡

"ምን ትጠጫለሽ?"ሲል ጁኒዬር ጠየቃት፡፡ "ነጭ ወይን ካለ ደስ ይለኛል….  እባክህ" አለች.

አቶ ፍሰሀ  በጥቋቁር አይኖቹ ትኩር ብሎ እያያት "ነጭ ወይን,? እንዳጋጣሚ ባለቤቴም የነጭ ወይን አፍቃሪ ስለሆነች ከእኛ ቤት ጠፍቶ አያውቅም… አሁን ትመጣና ትቀላለናለች
፡፡››አላት

ጁኒየር መጥሪያውን ሲጫን የቤቱ አገልጋይ ከውስጠኛው ክፍል እየሮጠች መጣች…ነጭ ወይን አምጥታ ለአለም እንድትቀዳላት አዘዛት፡፡ወይኑ መጣና ተቀዳላት..አቶ ፍሰሀና ልጃቸው ጁኒዬር ቢራ ያዙ፡፡

‹‹ጁኒዬር ወደቤት ይዞሽ እንዲመጣ ጠይቄው ነበር..እንዲህ በፍጥነት ይሳካለታል አላልኩም ነበር፡፡››

አለም ግራ ተገባች..እናም ወደ ጁኒዬር ዞር ብላ‹‹ወደእዚህ እንድመጣ ያንተ ፍላጎት መስሎኝ ነበር እኮ››

‹‹እሱማ የእኔም ፍላጎት ነው››አላት በእፍረት አንገቱን አቀርቅሮ፡፡ አለምም ወደ ፍሰሀ ዞራ "እሺ ለምን ነበር የፈለከኝ?"አለችው፡፡

በእሷ ቀጥተኛነት ለጊዜው ያልተደሰተ ይመስላል፣ ቢሆን እሱም በተመሳሳይ መንገድ መለሰላት

"ጠላቶች እንድንሆን… አንቺን በደንብ ማወቅ እፈልጋለሁ።"አላት፡፡

"እኔም የመጣሁት ለዚህ ነው አቶ ፍሰሀ።"አለችው ፍርጥም ብላ፡፡

እሷን ትንሽ ጊዜ ወስዷ ሊያጠናት ሞከረ። "እንዴት ጠበቃ ለመሆን ፈለግሽ?"የተለመደ ግን ደግሞ ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

"የእናቴን ግድያ ለመመርመር ወንጀለኛውን ለፍርድ ለማቅረብ እንድችል.››

መልሱ በድንገት ወደ ከንፈሮቿ የመጣ ነው፣ ይህም መልሷ እንሱን ብቻ ሳይሆን አለምን እራሷን አስገርሟታል። እሷ ከዚህ በፊት የእናቷን ገዳይ መፈለግ ዋና ግቧ እንደሆነ ተናግራ አታውቅም።በዚህ የእናቷ ግድያ ወንጀል ላይ እሷ ራሷም በአያቷ ዘንድ ይፋዊ ተጠርጣሪ ሆና መቅረቧ ነገሩን በቁርጠኝነት እንድትይዘው ገፊ ምክንያት ሆኗታል፡፡ በመጨረሻ ሞት አፋፍ ላይ የምትገኝ አያቷ ለእናቷ ሞት ዋና ተጠያቂ እሷ እንደሆንች በግልፅ ቃል ደጋግማ ነግራታለች።አያቷ የተናገረችው ስህተት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሌላ ማስረጃ እስካላገኘች ድረስ ጥፋቱን እስከ ህይወቷ ድረስ ይዛ ለመኖር ትገደዳለች ። እና አሁን ከሻሸመኔ ከተማ ሃያሎቹ ጋር ተፋጣ የምትገኝት ዋና ምክንያት ራሷን ነፃ ለማውጣት ነው፡፡

አቶ ፍሰሀ "ባል የለሽም? ልጆችስ?"ሲል ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

"አይ የለኝም።

" "ለምን?"

"አባ" አለ ጁኒየር በአባቱ እፍረት ማጣት አፍሮ ‹‹አለም ልተዝናና እንጂ በጥያቅህ እንድታጨናንቃት ይዣት አልመጣሁም››

" ጁኒየር ምንም ችግር የለውም። ይህ የተለመደ ጥያቄ ነው።"አለች አለም፡፡

" እሺ እንደዛ ካልሽ መልስሽ ምንድነው?"አቶ ፍሰሀ ጠየቃት፡፡

"ጊዜ ወይም ዝንባሌ የለኝም."

"በዚህ በእኛ አካባቢም ተመሳሳይ ብዙ ጊዜ እና በቂ ዝንባሌ የለንም."

ጁኒየር በጠወለገ እይታ አባቱን ተመለከተው።የተነገረው አሽሙር እሱን የሚመለከት እንደሆነ ያውቃል"አባዬ የከሸፉብኝን ትዳሮቼን እየጠቀሰ ነው።››በማለት አብራራላት፡፡

"ጋብቻዎች? ስንት ነበሩ?"አለም በጉጉት ጠየቀች
"ሶስት" በማለት ተናዘዘ።

"እና አንዳቸውም እኔን አያት የማድረግ ፍላጎቱም ሆነ ብቃት አልነበራቸውም››አቶ ፍሰሀ ዋና ቅሬታውን ተናገረ፡፡

በዚህ መካከል ከፎቁ ወደታች የሚወርድ የጫማ ኳኳታ ሰሙና በተመሳሳይ ሦስቱም ዞሩ። አንዲት ሴት በተከፈተው በር ላይ ቆማ ነበር። አለም የአቶ ፍሰሀ ሚስት እና የጁኒዬር እናት መሆኗን አወቀች።  ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ፀጉሯ ድረስ ምን እንደምትመስል አእምሮአዊ ምስል ቀርጾ ነበር። ወይዘሮዋ ግን የአለምን አእምሮአዊ ምስል ተቃራኒ ነበረች።

ጁኒዬር እናቴ ጀማይካዊት ነች ስላላት..የሆነች ፈርጣም ..ጠቆር ያለች.. ከንፈረ ትልልቅ…የፀጉሯ ድሬድ መቀመጫዋን የሚነካ አይነት አድርጋ ነበር የሳለቻት…እሷ ግን ቅንጥስጥስ ያለች ቀጭን…ቀይ ቆንጆ ግን ደግሞ ስልችት ያለው ፊት ያየዘች…ሀበሻ መሳይ
ሴት ነች፡፡ጁኒዬር ያንን አፍዛዣ መሳይ ውበቱን እና ለስላሳ ባህሪውን ከማን እንደወረሰው አሁን በግልፅ ገባት ፡፡

"ሃኒ ይህቺ አለም ጎበና ነች" አለ አቶ ፍሰሀ ።

የጁኒዬር እናት ባለቤቷን ችላ ብላ ፈካ ያለ ፊቷ አብርቶ ቀጥ ያለ ቀጭን ከንፈሯ ወደቀኝ በመጠምዘዝ ‹‹አለም ወደቤታችን እንኳን በሰላም መጣሽ…ሳራ እባላለው..የጁኒዬር እናት ነኝ
››አለችና ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

አለም ከሴትዬዋ ንግግር የፍሰሀ ባለቤት ከመሆኗ በላይ የጁኒዬር እናት በመሆኗ ኩራት እንደሚሰማት ነው የተረዳችው፡፡

"አመሰግናለሁ።"ስትል መለሰች፡፡

ጁኒየር ከተቀመጠበት ተነሳና አንድ ብርጭቆ ነጭ ወይን ቀዳና ለእናቱ አቀበላት.. ። በሚያብረቀርቅ ፈገግታ‹‹አመሰግናለው የእኔ ልጅ››በማለት ተቀበለችው፡፡

እሱም ጎንበስ ብሎ እናቱን የለሰለሰ ስርጉድ ጉንጯን ሳመ። "ራስ ምታትሽ እንዴት ነው?"

"ሙሉ በሙሉ አልተወኝም፣ ነገር ግን እንቅልፍ ረድቶኛል። ስለጠየቅከኝ አመሰግናለሁ።"

አለም የሴትዬዋን እጇች ስታይ ተገረመች …እጇ ነጭ ሲሆኑ … በአውሎ ንፋስ እንደተመታ አበባ በቀላሉ ተሰባሪ ይመስላል።

ባሏን " መቼስ ስለከብቶችና ፈረሶች እያወራህ እያሰለቸሀት ነው አይደል?"አለችው፡፡
"በራሴ ቤት ውስጥ፣ ስለምንስ ባወራ አንቺን ምን ጨነቀሽ?" አቶ ፍሰሀ ቱግ አለ፡፡ ጁኒየር ንግግራቸውን ከዛ በላይ እንዳይጠነክርና አለም ፊት እንዳያሳፍሩን ፈጠን ብሎ ጣልቃ ገባ፡፡

"እማዬ ስለ እርባታ አይደለም እያወራን ያለነው ። አባዬ ከሚስቶቼ  ወራሽ የሚሆን ልጅ ለመውለድ ባለመቻሌ እየወቀሰኝ ነበር።"ሲል አብራራላት፡፡

"ጊዜው ሲደርስ ከትክክለኛ ሴት ጋር ልጆች ትወልዳለህ››.አለችና  ወደ አለም ዘወር ብላ ጠየቀች፡- “ወ.ሪት አለም በፍፁም አላገባሁም ስትይ ሰምቻለሁ ልበል ?” ብላ ጠየቀችው።
"ልክ ነው"

"እንግዳ ነገር ነው…ቢያንስ የወንድ ጓደኛ ሊኖርሽ ይገባ ነበር፡፡››

"አለም የወንድ ጓደኛ የለኝም አላለችም እኮ

››ጁኒየር አስተካከላት. "በቃ መራጭ ነች"ሲል አከለበት፡፡

"አዎ ከጋብቻ እና ቤተሰብ ከመመሥረት ይልቅ ሙያዬን መርጫለሁ።ለጊዜው፣ ለማንኛውም ነገር ጊዜ የለኝም። ግን እናቴ የሆነ ሙያ ባለቤት ለመሆን ፍላጎት እንዳላት ገልጻ ታውቃለች?"

"እሷን እስከማውቃት ድረስ እንደዛ አይነት ምኞት አልነበራትም" ሲል ጁኒየር መለሰ፣ አለም በፀፀት ስሜት "በጣም ቀድማ በልጅነቷ ነበር የወለደችኝ" አለች።

"ምናልባት ያለዕድሜ ጋብቻ ውስጥ መግባቷ  እና ልጅ መውለዷ ወደ ሥራ እንዳትገባ አግዷት ይሆናል….ሰሎሜ የራሷን ምርጫ ነው ተግባራዊ ያደረገችው."ሲል መለሰላት፡፡
"የምታውቀውን ስለነገርከኝ አመሰግናለሁ.››

‹‹ አንድ ጊዜ እኔ እሷና ጀማል ለመዝናናት ወደወንዶ ገነት ሄደን ነበር፡፡በፍል ውሀ ስንታጠብና ስንዋኝ ከዋልን በኃላ በጣም ደክሞን ዛፍ ጥላ ስር ሳሩ ላይ ተዘርረን ሰማዩን አንጋጠን ስለ ምኞታችን ስናወራ እንደነበር ትዝ ይለኛል…ሁላችንም የዋና ልብስ ብቻ ነበር የለበስነው…እና እሷም በመሀላችን ተኝታ ነበር፡፡
44👍2
እኔ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋች መሆን ፈልግ ነበር…በወቅቱ ለእነሱም የነገርኳቸው ያንን ነው፡፡ ገመዶ ግን እንዴትም ብሎ እንዴት የሆነ ብር አግኝተ ሀብታም መሆን ነበር ምኞቱ ፤ ሀብታም መሆን እስከቻለ ድረስ ምንም አይነት ስራ ቢሰራ ግድ አይሰጠውም ነበር።እኔ ደግሞ የሀብታም ልጅ ስለነበርኩ እንደእሱ ላስብ አልችልም…. ሰሎሜ መሆን የምትፈልገው ግን ሚስት ብቻ ነበር።" ለአፍታ ቆም አለ እና እጆቹን ቁልቁል ተመለከተ።

‹‹እና አሁን ሳስበው ከእኔ በስተቀር ሁሉም ምኞታቸው የተሳካ ይመስለኛል…ሰሎሜ በአጭሩ ብትቀጭም ሚስት ሆና ልጅ መውለድ ችላለች…ገመዶም በዚህም ብሎ በዛ የሚፈልገውን ያህል ብር አግኝቷል ብዬ አስባለው ፡፡እኔ ብቻ ነኝ ያልተሳካልኝ፡፡››

አቶ ፍሰሀ ጆሮውን ወደውጭ እያቀና"ስለ ገመዶ ስትናገሩ ድምፁን የሰማሁ ይመስለኛል" አለ ፡ ፡

አለም ዘወር ስትል የተባለው ኩማንደር በበሩ በኩል ሲመጣ አየችው። የኩማንደሩ አስገራሚ መገለጥ ድንጋጤ ላይ ጥሏታል።

“ሄይ ገመዶ›› አለው  ጁኒዬር፡፡

"ግባ።›› አቶ ፍሰሀ ወደ ክፍሉ ውስጥ እንዲዘልቅ በምልክት ጠራው። ሳራን ያላያት መስሎ ችላ አላት።አለምን እዛ ቤት በዛን ሰዓት በማየቱ እየተገረመ…..‹‹ሁላችሁንም ሳላም ብያለው…››በማለት ጃኬቱን አወለቀና ወንበር ስቦ ተቀመጠ፡፡

ጁኒዬር ተነስቶ ከፍሪጅ ውስጥ ዘወትር የሚጠጣውን አይነት ቢራ አምጥቶ ከፈተለትና ወደ ወንበሩ ተመልሶ ተቀመጠ፡፡

‹‹ዛሬ አለም እንግዳችን ነች››አለው አቶ ፍሰሀ፡፡

‹‹‹አየሁ እኮ …በየሄድኩበት እሷን ማግኘት መቻሌ እያስገረመኝ ነው››
ሁሉም ስለሚያወራው ነገር ግራ ተጋባ፡፡እሷም የዋዛ አልነበረችምና ወደእሱ በትኩረት እያየች"እዚህም የሆነ ነገር እንዳይነግሩኝ ልታስጠነቅቃቸው ነው ተከትለኸኝ የመጣኸው››አለችው፡፡

‹‹አረ..እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ..?ይሄ እኮ ቤቱ ነው››አቶ ፍሰሀ ነው ጣልቃ ገብቶ የተናገረው፡፡

፥‹‹ጥዋትም ..ዳኛውን እያወራው ሳለ ..ድንገት ቢሮውን ገፍትሮ ከፍቶ በመግባት ጣልቃ በመግባት ዝም አስብሏቸዋል….አሁንም እንደዛ ለማድረግ ፈልጎ እንደሆነ ብዬ ነው፡፡››

ኩማንደሩ ኮስተር እንዳለ"አንድ ሰው ቀጥተኛ ጥያቄ ሲጠይቀኝ የራሴን አስተያየት እሰጣለሁ…ጥዋት ያደረኩት እንደዛ ነው፡፡” ሲል መለሰላት፡፡
በዚህ ጊዜ ጭቅጭቃቸው ያላማረው አቶ ፍሰሀ
‹‹እናንተ ተጫወቱ..እኔ አቃቢ ፥ህጓን በግል ላናግራት እፈልጋለሁ። ከፈለግሽ ወይንሽን ይዘሽ ነይ" አላት ና ቀድሟት ከመቀመጫው ተነሳ፣እሷም ከተቀመጠችበት ያለምንም ማቅማማት ተነሳችና ተከተለችው ።እንዴት እንደ
ሆነ ሳታውቅ ከወንበሯ ተነስታ ወደ ኮሪደሩ ገባች። ሳሎኑን ለቆ ወደምድር ቤት ሲወርዱ ዙሪያውን ተመለከተች። ግድግዳዎቹ በቀይ የበግ ቆዳ ልጣፍ የተሸፍነ ነው… እና በፍሬም የተለበጡ በርካታ የፈረስ ፎቶግራፎች በተርታ ተደርድረዋል።
"ይሄንን ቤት ጁኒየር ገና ዳይፐር ያደርግበት በነበረበት ጊዜ እኔ ራሴ ነኝ ነድፌ የሠራሁት።››አላት፡፡

"አለም ሳይነግራት ቤቱን መገንባቱን ብቻ ሳይሆን ቤቱን በራሱ ፍላጎት እንዳስጌጠው ታውቅ ነበር። የሳራ ባህሪ የሚያንፀባርቅ ምንም ነገር በቤቱ የለም። ቤቱ በጣም አስቀያሚ ነበር፣ ነገር ግን በሚያስደነግጥ እና ይቅርታ በሌለው መጥፎ ጣዕም ውስጥ ስለነበር ልክ እንደ ፍሰሀ የራሱ የሆነ ማራኪ ውበት ነበረው። ይህ ቤት ከመሰራቱ በፊት እኔ እና ሳራ ጆ የምንኖረው በኪራይ ቤት ውስጥ ነበር። አለም ‹‹ወይዘሮ ሳራ የተዘናጋች እና ራሷን የረሳች አይነት ሴት  ትመስላለች። ቤቱ ምኑም የእሷን አይመስልም፡፡››ስትል በውስጧ አሰበች፡፡

አቶ ፍሰሀ ግራጫ ቀለም ከተቀባው ግድግዳ ተጠግቶ ያለ በቀይ ቆዳ የተለበጠ ሶፋ ላይ ተቀመጠና….እሷም እድትቀመጥ ጋበዛት፡፡እንዳላት አደረገች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
24👍24
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

ከዛ ጉሮሮውን አሟሸና መናገር ጀመረ"ከእድሜሽ በላይ ለማሸነፍ ስጥር ነው የኖርኩት…እናም ቡዙ ነገር አግኝቼ .. ብዙ ነገር አጥቻለሁ፣ ወጣቷ ሴት…ኪሳራ አያስደነግጠኝም። ሀብታም መሆን የበለጠ አስደሳች ነገር ነው፣ ግን ኪሳራም የበለጠ አስደሳች ነው። እራስን የሚያንፁና የሚገነቡ ጥቅሞች  አሉት። ››

‹‹ከከተማዋም አልፎ በሀገሪቱም የተሳካልህ የቢዝነስ ሰው መሆንህን አውቃለው፡፡ገንዘብ ስላለህም የፈለከውን ነገር በፈለከው ሰዓት ማድረግ እንደምትችል እንደምታምንም አውቃለው፡፡››አለችው በልበሙሉነት፡፡

"ታዲያ ካወቅሽ ይህን አስቂኝ ምርመራ ለምን አትተይውም?"ሲል ቀጥታ ወደሚፈልገው ርዕስ ገባ፡፡

"ይህ መቼም የሚሆን አይመስለኝም ..አላደርገውም››

"እናትሽን የገደልኩት እኔ እንደሆንኩ እንዴት ታስቢያለሽ? እሷ ከጁኒየር ምርጥ ጓደኞች መካከል አንዷ ነበረች:: በየእለቱ ከዚህ ቤት ትወጣና ትገባ ነበር::እርግጥ ካገባች በኋላ ብዙም አትመጣም ነበር… እናትሽን ለመጉዳት ጣቴን አንስቼ አላውቅም።››

አለም እሱን ማመን ፈለገች። በወንጀል ጉዳይ ተጠርጣሪ ቢሆንም እሷ ግን በጣም ታደንቀው ነበር። በውይይታቸው ከተገነዘበችው እና ለምርመራዋ ስትል ከሰበሰበችው መራጃ እንደተረዳችው ከምንም ነገር ተነስቶ ኢምፓየር መገንባት ችሏል።በማህበረሰቡ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነበር. አሳማኝ ባህሪ ነበረው። ነገር ግን በቀለማት ያሸበረቀ ስብዕናው ከጀርባ ሚሰራቸውን ቆሻሻ ድርጊቷች በቀላሉ እንዳይገለፁ ምክንያት እንደሆኑ በደንብ ታውቃለች።ቢሆንም ግን ለፍሰሀ ያላት አድናቆት እንደፍላጎቷ ሙሉና ጠንካራ አልነበረም..፡፡

ደገመችና ‹‹ምንም ቢሆን ምንም ምርመራውን ማቋረጥ አልችልም" አለች ።

‹‹ለምን ?››

" ብፈልግ እንኳን ዋና አቃቢ ህጉን በስንት መከራ ካሳመንኩት በኃላ ወደኃላ እንድመለስ መጠየቅ ያሳፍራል ፡፡"

"ስሚ" አለና አይኖቾን በትኩረት እያየ " ስህተት እንደሰራሽ ንገሪው፣ እናም ነገ በዚህ ሰአት እዚህ የመጣሽበትን ጉዳይ እንኳን እንደማያስታውስ ዋስትና እሰጥሻለሁ..ስራውንም ለቀሽ ወደአዲስአበባ መመለስና ቆንጆ የጥብቅና ቢሮ ማቋቋም ትችያለሽ….እናትሽ የልጄ የልብ ጓደኛ ነች…አንቺን ለማቋቋም የሆነ ነገር ማድረግ ለእኔ ያን ያህል የሚከብድ ጉዳይ አይደለም ።"

" አላደርገውም "

"እሺ፣ እንግዲያውስ ዋና አቃቢ ህጉን ለእኔ ተይልኝ..እኔ አናግረዋለው።"

"አቶ ፍሰሀ… ››ጮክ ብላ ተናገረች "የኔ ሀሳብ አልተረዳህልኝም"ትኩረቱን እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆን "ልጅህ በምርጫ ያለውን ተሳትፎ የሚጎዳ ምንም ነገር ለማድረግ እቅድ የለኝም…ያ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንደማደርግና እያንዳንዱን እንቅስቃሴዬንና ምርመራዬን በከፍተኛ ሚስጥር እንደማከናውን ቃል እገባለው…ማድረግ የምችለው ያንን ብቻ ነው፡፡››

"የአንድ ሙሉ ከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ ቢሆንም ሀሳብሽን አትቀይሪም ማለት ነው?"

"ከተራቡ ህፃናት ዳቦ እየወሰድኩ ነው የሚመስልህ…?ነው ወይስ ያንተ ልጅ ይህቺን ከተማ ወክሎ የተወካዬች ምክር ቤት ከገባ በኩልፎ ወንዝ ወተት እንደሚንዠቀዘቅ እና ህዝቡ በቁንጣን እንደሚሰቃይ ነው የምታስበው?"

" ተይ እንጂ ..እኔ እንደዛ አላልኩም "

" እንግዲያው አቋሜን በግልፅ አሳውቂያለው..እኔ ሁላችሁንም በግል ለማጥቃትና ለማውደም ምንም እቅድ የለኝም…ግን ደግሞ የእናቴን ገዳይ ለፍርድ ለማቅረብ ህይወቴንም የሚያስከፍለኝ ቢሆን ግድ የለኝም..እስትንፋሴ እስካለች ድረስ ወደፊት እቀጥላለው››

‹‹በቃ የመጨረሻ ውሳኔሽ ይሄ ነው?"

‹‹አዎ..እኔን ማስቆሚያ ብቸኛው መንገድ እኔንም እንደእናቴ ማስወገድ ነው….በዛ ጉዳይ ላይ ልታስብበት ትችላላችሁ፡፡››

‹‹ንግግርሽ በጣም….››አቶ ፍሰሀ ንግግሩን አቋረጠ..እንደዛ ያደረገው ልጁ ጂኒዬር በራፉን ከፍቶ ስለገባ ነው፡፡

ጁኒየር በሩን በድንገት ከፍቶ አንገቱን ወደ ውስጥ አሰገገና"ሄይ, በሰላም ነው ..በጣም መሸ እኮ…እራት ሊቀርብ ነው" ፡፡

"በጣም ጥሩ ….ውይይታችን ጨርሰናል…..ግን እራቱ ይቅርብኝ ….ቀጥታ ወደቤቴ ነው መሄድ የምፈልገው››አለች አለም።

አቶ ፍሰሀ ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው "እዚህ በቁም ነገር እየተነጋገርን ነበር። ዳግመኛ በግል ቢሮዬ ውስጥ ከሰው ጋር እያለው አንዳታቋርጠኝ፣ ።››
ጁኒየር "ንግግራችሁ በጣም ግላዊ ወይም በጣም ከባድ እንደሆነ አላውቅም ነበር።"ሲል ለአባቱ ቅሬታ ምላሽ ሰጠ፡፡

"አቶ ፍሰሀ.. እባክህ, ምንም አይደለም…በበቂ መጠን ተጋግረናል እኮ..የቀረም ነገር ካለ ሁለተችንም እዚሁ ከተማ ውስጥ ነን..ደጋግመን መገናኘታችን አይቀርም በእውነቱን ለመናገር፣ ጁኒየር ስላቋረጠን ደስተኛ ነኝ። ምን ያህል እንደመሸ አሁን ነው ያስተዋልኩት… አሁን መሄድ አለብኝ።"

ሁሉም ተያይዘው ወደሳሎን ተመለሱ፡፡ሳሎኑ ባዶ ነበር፡፡ገመዶም ሆነ ሳራ አልነበሩም፡፡

‹‹ለራት ብትቆይ ግን ደስ ይለኛል››አቶ ፍሰሀ ናቸው ተናጋሪው

‹‹አይ ይቅርብኝ..ደህና እደሩ››

ጁኒየር  ኮቷን ከያዘላት በኋላ መኪናዋ ድረስ ሸኛት ..ወደ እሱ ዘወር አለችና ።"ጁኒየር አመሰግናለው …ደህና እደር።"አለችው
" እጇን ያዘና ጎንበስ ብሎ ሳመው… ከዛ መዳፏን ወደ ላይ አዙሮ ሳመው። "የምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ እንደዚህ ታሽኮረምማለህ?"

የማይገባ ፈገግታ ፈገግ አለላት ፡፡

"ለፍቅር በቀላሉ ተጋላጭ ነህ እንዴ?"ሌላ ጥያቄ አስከተለች፡፡ "እንደዛ ነኝ እንዴ..?አይ አይደለሁም."ፈገግታው እየሰፋ ሄዶ ፡፡
‹‹ለማንኛም መልካም ምሽት››አለችና መኪና ውስጥ ገብታ አካባቢውን ለቃ ተፈተለከች ጁኒዬር ወደቤት ተመለሰና ቀጥታ ወደእናቱ መኝታ ክፈል አመራ እና በስሱ አንኳኳ
‹‹እማዬ ፣ ልግባ?››

" ውዴ እባክህ ግባ" ሳራ ፈቀደችለት… በልጇ ጉብኝት በጣም እንደተደሰተች ግልጽ ነው። ርካሽ የንባብ መነፅሯን አውልቃ እያነበበች የነበረውን መፅሃፉ ከጎኗ አስቀመጠች፡፡

‹‹አትቀመጥም››

‹‹አይ  ይሁን››  አለና  አልጋው  ጎን  በመቆም፡፡ 

"መጽሐፉ  እንዴት  ነው?"  ሲል ጠየቃት፡፡መፅሀፉን ገዝቶ ያመጣላት እሱ ነበር፡፡

"በጣም አስደሳች ነው።››ስትል በአጭሩ መለሰችለት፡፡ "ጥሩ፣ ስለተደሰትሽበት ደስ ብሎኛል"

ሳራ እናቱ እንደመኆኗ መጠን በውስጡ የሚገላበጠውን ጭንቀት ተረዳችና። "ምንድነው ችግሩ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

"ምንም።"

"አንድ የተሳሳተ ነገር ሲኖር ማወቅ እችላለሁ."
"ከተለመደው የተለየ ነገር የለም ከአሌክስ..ማለቴ ከአለም ጋር የነበራቸውን ውይይት በማቋረጤ አባቴን አበሳጭቼዋለው››

"አባትህ የጋራችን በሆነው መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ሲኖር ራሱን እንዴት መምራት እንዳለበት እስካሁን አልተማረም። በቤታችን የጋራ እንግዳችን ሆና የመጣችን ሴት ለግል ውይይት ብሎ ክፍል ውስጥ በማስገባት ማዋራት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ስለሆነ አንተም ፣ ውይይቱን በማቋረጥ ባለጌ የመሆን መብት አለህ።››አለችው

‹‹እማዬ…››

"ለማንኛውም በግል ምን እየተወያዩ ነበር?"

"ስለ እናቷ ሞት ይመስለኛል….ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም."

"እርግጠኛ ነህ? ዛሬ ማታ ሁሉም ሰው በጣም የተጨናነቀ ስሜት ላይ እንዳለ መረዳት ችያለው።"

" ችግርም ካለ አባዬ ሁል ጊዜ እንደሚያደርገው ይቆጣጠረዋል። በእርግጠኝነት ምንም የሚያስጨንቅ ነገር አይኖርም።››
38👍4
ስለ አለም ምርመራ ለእናቱ የመንገር ፍላጎት አልነበረውም። ሳራ በህይወቷ ውስጥ የሚረብሻት ነገር እንዲኖር አትፈልግም..ወዲያው ነው የምትሰባበረው።ባለቤቷ ፍሰሀ ከእሷ ጋር ስለ ንግድ ሥራ ተወያይቶ አያውቅም ፣ በተለይም መጥፎ በሚሆንበት ጊዜ እሷ ጆሮ እንዳይደርስ በጣም ይጠነቀቃል። እሷም በዛው ልክ ስለኢንተርፕራይዙ ስኬትም ሆነ ውድቀት ለመስማት ምንም አይነት ጉጉት አሳይታ አታውቅም፡፡

እሷ በቤቱ ውስጥ ልክ እንደ ውብ አሻንጉሊት ነበረች፣ በጸዳ ክፍል ውስጥ እንደታሸገች ምትኖር ነበርች፡፡፣ ለብርሃንም ሆነ ለሌላ ጎጂ ነገር እራሷን በጭራሽ አታጋለጥም።ጁኒየር እናቱን ይወዳታል፣ ግን በደንብ እንዳልተንከባከባት ያውቃል፡፡

"ስለ እሷ ምን አሰብሽ?"ሲል ጠየቃት፡፡

"የሰሎሜን ሴት ልጅ ማለትህ ነው? ምንም እንኳን የእንደዚህ አይነት ደማቅ ሴት አድናቂ ባልሆንም በአካል በጣም ማራኪ ነች፣በእርግጥም እሷ በጣም ኃይለኛ ነች አይደል? ከእናቷ የበለጠ ቁም ነገር ያላት ትመስለኛለች… ሰሎሜ ትንሽ ደደብ ነገር ነበረች፣ እንደማስታውሰው ሁል ጊዜ ትስቅ ነበር።" ቆም ብላ ጭንቅላቷን ወደ አንድ ጎን ነቀነቀች፣ የሩቅ ሳቋን የምትሰማ ያህል ምታዳምጥ ትመስላለች። "ያህቺኛዋን ልጅ ግን ስትስቅ እንዳየኋት አላስታውስም።"

‹‹አዎ…በተወሰነ መልኩ ትክክል ነሽ››አላት

" ምስኪን የእኔ ልጅ እሷ ስትሞት በጣም ተጎድተህ እንደነበረ አውቃለሁ፣ የምትወደውን ሰው ማጣት ምን እንደሚመስል አውቃለሁ። ያ ባንተ ህይወት ውስጥ የተከሰተ ከባድ መከራ ነበር።››

‹‹አዎ እማዬ….በመሞቷ በጣም አዝኛለሁ››
በጣም ለስላሳ የነበረው ድምጿ በድንገት ተለወጠ። "ጁኒየር፣ በተለይ በሌሎች ሰዎች ፊት አባትህ እንዲያሳፍርህ መፍቀድ የለብህም።››ስትል ወደቀደመ ውይይታቸው መለሰችው፡፡

" ምንም ማለት አይደለም አባዬን ታውቂዋለሽ… ለክፋት ብሎ ሳይሆን ልማድ ሆኖበት ነው እንደዛ የተናገርኝ››

"እንዲህ እንድታስብ ነው የሚፈልገው። ሁል ጊዜ ለእሱ የብልግና ድርጊት ምክንያት እንድትፈልግለት ይፈልጋል። ፍሰሀ የሚያውቀው አንድ ድምፅ ብቻ ነው። ቁጣና ስድብ፡፡ልጄ እሱ እንደ እኛ ለስላሳ እና ገር መሆን አያውቅም። ልክ እንደ ገመዶ በሚገባው መንገድ ከእሱ ጋር መነጋገር አለብህ። ፍሰሀ አንተ ላይ በሚጮኸው መንገድ ገመዶን ሲያናግረው አይተህ ታውቃህ..?በፍፁም እሱን ደፍሮ አይዘረጥጠውም። ››

"አባዬ ገመዶ ምንም አይነት ስህተት እንደማይሰራ ያስባል። መላ ካምፓኒውን ከእኔ ይልቅ ኩማንደሩ ቢያስተዳድርለት ይመርጣል።አንድም ቀን በእኔ ስራ እርካታ ተሰምቶት አያውቅም››ብሎ በምሬት የተጠራቀመ  ቅሬታውን  ተናገረ፡፡

"ያ ፈፅሞ እውነት አይደለም!" ሳራ በሳምንታት ውስጥ ከነበራት የበለጠ ጠንካራ መንፈስ በማሳየት ተቃወመች። "ፍሰሀ በአንተ በጣም ይኮራብሃል። እንዴት ማሳየት እንዳለበት ግን አያውቅም። እሱ በጣም ከባድ ሰው ነው። በዙሪያው ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለመቋጣጠር እንዲችል ሁሌ ጠንክራ እና ኮስታራ ሆኖ መታየት እዳለበት ነው የሚያምነው ። አንተም በእሱ መጠን ጠንካራ እንድትሆንለት ይፈልጋል።"
ጁኒየር ፈገግ አለ፣ "እሺ እናቴ፣ አሁን ወጣ ብዬ ራሴን ዘና ላድርግ…ነገ ጠዋት እየተንገዳገድኩ እመጣለሁ።››
ሳቀች ። በእሱ ፍቅር ውስጥ የተደበቀ ጥንካሬ እና ቀልድ ሁልጊዜ ያስደስታት ነበር። "ተስፋ አደርጋለሁ፣ ነገር ግን ጥንካሬ ፍሰሀ በአንተ ውስጥ ማየት የሚፈልገው መንፈስ ነው።››
ጁኒየር ‹‹ደህና እደሪ እማዬ››አለና ጎንበስ ብሎ ጉንጯን ሳመ፡፡

‹‹ቀስ ብለህ ንዳ..ደግሞ ብዙ እንዳትጠጣ ››የተለመደ የእናትነት ምክሯን ለገሰችው፡፡
እናቱን መኝታ ቤት ለቆ ወደሳሎን ሲመለስ አባቱን ምቹ ወንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ ቢራውን እየተጎነጨ በሀሳብ ተውጦ አገኘው፡፡

"ያቺን ልጅ ወደዚህ ቤት ለማምጣት በአንተ ላይ መደገፍ እንደምችል አውቅ ነበር. እንደ አስብኩት ተሳክቷልሀል. የነበራትን ቁርጠኝነትና ጉጉት የሚሸረሽር ነገሮችን ማድረግ ችለናል.. ብልህ ከሆነች ብዙ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ይህንን የጀመረችውን ነገር ታቆማለች..ደግሞ ብልህ ነችም ብዬ አስባለው፡፡››አለው
" ባታደርገውስ?"ጁኒዬር ጥርጣሬውን አነሳ፡፡
"እሷ ካላደረገች እኛም ያንን ድልድይ እናቋርጣለን" አለ አቶ ፍሰሀ።ከተቀመጠበት በመነሳት ፈገግ አለ እና በፍቅር ስሜት የጁኒየርን ጉንጩ ነካ በማድረግ "ደህና እደር ልጄ"ብሎ ወደመኝታ ቤቱ ተጓዘ፡፡
ጁኒየር አባቱ ወደመኝታው ሲሄድ ቆሞ ተመለከተው። በጣም ጥሩ ስሜት ስለተሰማው፣ በቆመበት ፈገግ አለ። አባቱ በእርሱ ቅር እንዳልተሰኘበት ገባው። ሴቶችን በማስተናገድ ረገድ የነበረው ልምድ በጣም የተዋጣለት ነበር። አለም የተረገመች ማራኪ ሴት ነበረች። አባቱ ባይነግረውም ኖሮ ለማንኛውም ያማልላት ነበር። ኮሪደሩን አቆርጦ ወደ ከፊት ለፊት በር ሲወጣ በመስታወት ውስጥ ለተመለከተው የገዛ ቆንጆ ቁመናው ሰላምታ ሰጠ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2218
ሀገር ማለት ሰው ነው ሰው ማለት ሀገ'ር
ከቶ ማይወስነው ዳርቻ ድንበር
ጥቅሳችን ነበር!
.
ጥያቄ1?
.
ሀገር ሰው ከሆነ በአፈር ማይለካ
የምንሰማው ሁሉ ካልሆነ ትረካ
ሀገር ሰው ከሆነ ድንበር ማይወስነው
ቃላችን የት ገባ? ከወዴት አደረስነው?
.
ጥያቄ2?
.
ለሰላም ለፍቅር ለህዝቦች ነፃነት
በዕኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት
መሰረተ ፅኑ ስብዕናን ያልሻርን
ህዝቦች ነን በስራ ለስራ የቆምን
.
ተንገዳግደን ሳለ ቆመናል እያልን
ተበታትነን ሳለ አበርን እያልን
በጠዋት ተነስተን ምንዘምረው ዲስኩር
እውነት ይገልፀናል? እስኪ በየት በኩል?
.
.
መልስ!!
.
........???.......

🔘ኪሩቤል አሰፋ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍31
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
እንደ ቤቱ ሁሉ በረቱም የተሠራው ከድንጋይ ነው። በረቶቹ በሁለት ረድፎች መተላለፊያ ተከፍለዋል በመደዳ ተደርድረዋል።በዚህ እርባታ ድርጅት የሚደልቡ ሰንጋዎች ቀጥታ ወደውጭ ገበያ ነው የሚቅርቡት፡፡ከላሞቹ የሚገኘው ወተት ግን እዛው ግቢ ውስጥ ባለ ፋብሪካ ተቀናብሮ እና ታሽጎ በዋናነት በሻሸመኔና ለአዋሳ ገበያ ይቀርባል፡፡ በግዙፉ ግቢ ውስጥ አንድ ኪሎ ሜትር ርቆ ግዙፍ የሆነ የእጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካ የሚያሰማው ድምፅ ይሰማል፡፡ይሄ ጣውላ የሚመረትበት የእንጨት ፋብሪካ ነው፡፡ፋብሪካው የሚጠቀምበትን ጥሬ እቃ ከከተማዋ በቅርብ ኪሎ ሜትሮች ላይ ከሚገኝ ሶሌ ከሚባል ቀበሌ ላይ ከሚገኝ ግዙፍ ደን ነው የሚመጣው…ደኑም በአብዛኛው የአቶ ፍሰሀ የግል ሀብት ነው፡፡እናም ይህ ፋብሪካ በቀን ከ10 መኪና በላይ ጣውላ አምርቶ ወደ አዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች ይልካል፡፡በተጨማሪም ከአካባቢው ከዚህ ፋብሪካ ወደ አፍንጫዋ የገባው የበሰበሰ ሳርና የእበት ሽታ በተወሰነ መጠን ረበሻት፡፡ በጸጥታ ወደዚያው አመራች፣ የተከፈተ ክፍል አልፋ ገበች። በአንድ ጊዜ ብዙ ፈረሶችን የሚለማመድበት ክብ ሜዳ አየች።ወዲያው ኩማንደር ገመዶ በጋጣው ውስጥ ካሉ ፈረሶች ጋር በቁጭት ሲያወራ ሰማች። ፈረሱ በርግጎ ለመውጣት ሞከረ።

"ተረጋጋ፣ተረጋጋ ››ይለዋል

"ምን  ነካው?"ስትል  ጠየቀችው….  ዞር  ብሎ  አላያትም  ወይም  ድምጿን  በመስማቱ መገረሙን አላሳየም።

‹‹የምታምር ፈረስ ነች..ምን ሆና ነው?›› ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

"ምንም አልሆነችም..ግን ሁሉ ጊዜ የሆነ ነገር እንደሆነች ማስመሰል ትወዳለች…እሷ ከእኔም ሆነ ከማንም በላይ ብልህ እንደሆነች ታስባለች።
እውነታው ግን አዎ እንደምታስበው በጣም ጎበዝ ነች ፤ ለሳዕታት ያለድካም በፍጥነት መጋለብ ትችላለች ፣ በውጤቱ መጨረሻ ግን መጎዳቷ አይቀርም።ስነግራት ስለማትሰማኝ..ስትጎዳም አታሳዝነኝም"አላት፡፡

እፍኝ እህል ዝቆ በውስጥ እጁ ላይ በማድረግ ፈረሱን እያበላው ነው።

"ይህ ለእኔ የተላለፈ ማጣቀሻ ነው አይደል? እንደ ማስፈራሪያ ልውሰደው?" ።” ስትል ጠየቀችው
ኮስተር ብሎ‹በፈለግሽው መንገድ መውሰድ ትችያለሽ››አለ

‹‹እሺ..ግን ታውቃለህ አይደል..?በጣም ትሁት የሆንክ ሰው ነህ››አለችው፡፡ የእሷን ስላቅ ችላ ብሎ"ስለ ፈረስ ብዙ አታውቂም አይደል?" ሲል ጠየቃት፡፡

"ግልፁን ለመናገር…አላውቅም" ብላ መለሰችለት።

"እዚህ ለመምጣት እንዴት አሰብሽ?"

"ጁኒየር ጋብዞኝ."

‹‹ጥሩ መራጭ ነሽ››

የአለም ደም በንዴት ተንተከተከ"የጁኒየር ወይም የሌላ የማንም ሰው አይደለሁም። እኔ እደምታስበው በቀላሉ የምዘገን ሴት አይደለሁም።››

ጀርባውን  አዙሮ  ወደ ተቃራኒው  የሕንፃው  ጫፍ  ተራመደ"ቆይ! ጥቂት ጥያቄዎችን ልጠይቅህ እፈልጋለሁ።"አለችው

"ጠይቂኝ"

"ገመዶ…እባክህ ከስራ ውጪ በሆኑ ጉዳዬች ላይ ማውራት እፈልጋለሁ ። የራሴን የማወቅ ጉጉት ለማርካት ነው" አለችው::

"ቴክኒኩን አውቀዋለሁ አቃቢ ህግ፡፡ እኔ እራሴ ብዙ ጊዜ ተጠቅሜበታለሁ። አንቺ ከተጠርጣሪው ጋር በቸልተኝነት ትጫወቻለሽ፣ በመዘናጋት ሊደብቀው የፈለገውን ነገር ዘርግፎ ይነግርሻል…ከዛ መራጃሽን ታጠናክሪያለሽ ።"

"እንደዚያ አይደለም ማውራት ብቻ ነው የምፈልገው."

"ስለ ምን?"

"ስለ ሶሌዎች "

"ስለ እነሱ?"

እግሩን አንፈርክኮ  ቆመና፣ እጆቹን ወደ ጂንሱ የኋላ ኪስ ውስጥ አስገባ ፣ አቋሙ የሚያስፈራራ ወንድ ሆኖ ነው የተሰማት። እያናደዳት ቢሆንም ስሜቷን ቀስቅሷታል።

"ፍሰሀ እና ሳራ ደስተኛ ትዳር ያላቸው ይመስልሀል?"

ጥያቄዋ ከጠበቀው ውጭ ስለሆነበት ዓይን ዓይኗን እያየ "ምን?"ሲል አፈጠጠባት፡፡ "እንዲዚህ አትየኝ ፡ የምጠይቀው የአንተን አስተያየት እንጂ ሞያዊ ትንታኔ አይደለም።" "በእግዚያብሄር ስም … ልዩነት ምንድነው?"

"ሳራ ጆ…. ፍሰሀ እንዲያገባት  የምጠብቃት አይነት ሴት አይደለችም  …ለዛ ነው የጠየቅኩህ።"
"ስለ ጉዳዩ አስቤበት አላውቅም." " አብረው ይተኛሉ ?››
‹‹ በአልጋ ላይ የሚያደርጉት ወይም የማያደርጉት ነገር የኔ ጉዳይ አይደለም። በተጨማሪም
፣ ግድ የለኝም። ››

"እሺ…አቶ ፍሰሀ ሌሎች ሴቶችን ጋር ይሄዳል?"

ከጥቋቁር  ዓይኖቹ ጀርባ ብስጭት ተመለከተች። ከእሷ ጋር ያለው ትዕግስት እየተሟጠጠ ነበር።

"ሳራ ጆን እንደ ስሜታዊ ሴት ነው የምታስቢያት?"

"አይ" አለም መለሰች።"ጋሽ ፍሰሀ ጤናማ የወሲብ ፍላጎት አለው ብለህ ታስባለህ?" "እንደ ምግብ ፍላጎቶቹ ከሆነ አዎ እንደዛ አስባለው።"

"ግንኙነታቸው ጁኒየር ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል?"

"እንዴት ያንን ማወቅ እችላለው? እሱን ጠይቀው።" "እሱንም መጠየቄ አይቀርም፡፡››

"አንቺን በማይመለከትሽ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባሽ እንደሆነ የሚነግርሽ ሰው መኖር አለበት››

የሱ ስላቅ እንዲያስፈራራት አልፈቀደችም።"የወላጆቹ ግንኙነት ጁኒየር ለሶስት ያልተሳካ ትዳር ዳርጎታል… ለምን እንደሆነ ታብራራልኛለህ? ››

‹‹ይህ አንቺን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም…አልኩሽ እኮ!!››

"የእኔ ጉዳይ ነው."ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡

"እንዴት? "

‹‹ምክንያቱም ጁኒየር እናቴን ይወዳት ስለነበረ።››ቃላቱ በእርጋታ ከአንደበቷ ወጡ ፡፡

የኩማደሩ ኮስታራ ፊት የበለጠ ተኮሰታተረ ፡፡ ‹‹ማን ነገረሽ?››

‹‹ሁለታችሁም እንደምትወዷት ነግሮኛል።››
ለረጅም ጊዜ አፈጠጠባት፣ ከዚያም ትከሻውን ነቀነቀና ‹‹በአንድ ወይም በሌላ መንገድ እንወዳት ነበር…ታዲያ ምን ይጠበስ.?››

"ለዚህ ነው የጁኒየር ትዳሮች ያልሰሩት? አሁንም እናቴን በልቡ ታቅፎ ይዞ ስላለ ነው?"

" እዚህ ጉዳይ ላይ ምን አይነት አስተያየት መስጠት አልችልም."

‹‹እባክህ››

"ሰሎሜ ከጁኒየር ትዳሮች ጋር ምንም ግንኙነት ያላት አይመስለኝም። የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማው በየመዝናኛ ስፍራው ከሚያገኛቸው ሴቶች ጋር ለመቅበጥ እንዲችል በየተወሰነ ዓመት ሚስቶቹን ይፈታል ።የእኔ ግምት ይሄ ነው፡፡››

የሰጠው መግለጫ እሷን ለማስከፋት ታስቦ ነበር, እናም ተሳክቶለታል፡፡ ቢሆንም  ምን ያህል እንዳበሳጫት ላለማሳየት ሞከረች።

"በዚህ ጉዳይ የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማው ለምን ይመስልሃል?" "ጄኔቲክስ. ምን አልባት ከእናቱ የወረሰው ለስላሳ ባህሪ ይመስለኛል››

"አንተስ?"

"የማደርገው ማንኛውንም ነገር  አስቤና ተጨንቄ ስለማደርገው የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማኝም."

"ግድያ ቢሆንም እንኳን?"

ፈገግታው ጠፋ እና ዓይኖቹን ጨፈነ። "አግብተህ ታውቃለህ?"

"አይ።"

"ለምን ሳታገባም?"

‹‹ማግባት እኮ ሀይማኖታዊ  ግዳጅ አይደለም …ይሄ የፍላጎት ጉዳይ ነው…ልክ እንደአንቺ ማለት ነው››

‹‹ገባኝ። እስኪ ስለ አባትህ ንገረኝ?" ቀስ በቀስ ኩማደሩ ፈረሶቹ ወደሚዝናኑበት ሜዳ ተጠጋ
….እሷም ከኃላ ከኃላ እተከተለችው ነው። ጠንከር ባለ ቀዝቃዛ እይታ ተመለከታት።

አለም "አባትህ ገና ትምህርት ቤት እያለህ እንደሞተ አውቃለሁ። ጁኒየር ዛሬ ነግሮኛል። ከሞተ በኃላ እዚህ ከነጁኒዬር ጋር ለመኖር መጣህ።"

‹‹አለም… ስለማወራው ነገር የማወቅ ጉጉት አለሽ?።"

"የማወቅ ጉጉት የለኝም። ከምርመራዬ ጋር የተያያዙ እውነታዎችን እየፈለግኩ ነው።››

"ኦህ፣ እርግጠኛ ነሽ?እንደ ጋሽ ፍሰሀ የወሲብ ሕይወት ያሉ ተዛማጅ ነገሮች ለምርመራሽ ስለምትፈልጊያቸው ነው የምትቆፍሪው?።››
47👍8
"ያ እኔ የምከተለው የምርመራ መንገድ ነው፣ ኩማንደር ። እንደህግ ኦፊሰርነትህ ያንን መለየት ትችላለህ፣ አይደል? ››

ዓይኖቹ ይበልጥ ቀዝቃዛ ሆነዋል… ምንም ለመናገር ፍላጎት ያለው አይመስልም "እናቴ በሞተችበት ምሽት ምን እንደተከሰተ ማወቅ እፈልጋለው?"ስትል ጥያቄዋን ቀጠለች፡፡

" ይህ በሬ ወለደ ነው…ያንቺ ፍላጎት ከሽማግሌዬ ጋር ምን አገናኘው?"

"ምናልባት ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም ይሆናል ፣ ግን አንተ ንገረኝ ። ምንም ችግር ከሌለው ስለሱ መናገር ለምን ትፈራለህ ?"››
"ጁኒየር የኔ አባት እንዴት እንደሞተ ነግሮሃሻል?"

ጭንቅላቷን በአሉታ ነቀነቀች። ኩማደር መራራ ሳቅ ሳቀ ‹‹ለምን ስለአባቴ ማውራት እንደማልፈልግ መገመት አትችይም. ?››ፊት ለፊቷ ቆመና ዓይን ዓይኗን እያየ

"እሺ መስማት ከፈለግሽ ልንገርሽ…አባቴ የራሱ ትውከት አንቆት ነው የሞተው፣ ራሱን ለማዳን እስኪያቅተው ድረስ ሰክሮ ነበር። በጣም የሚያስደነግጥ ነበር፣ በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ከክፍል አስጠርቶኝ አባቴ መሞቱን ሲነግረኝ የተሰማኝን መገመት አትችይም፡፡"

"ገመዶ…በጣም አዝናለው" አለም እጇን አነሳች እና እጇቹን ያዘች። ወደ ጎን ገሸሽ አደረገው እና ንግግሩን ቀጠለ"አባቴ የከተማው ሰካራምና፣ መሳቂያ፣ ዋጋ የሌለው ሰው ነበር። መሞቱን ስሰማ አላለቀስኩም ነበር።እንደውም ደስ ብሎኝ ነበር። እሱ ብኩን ሰው ነበር። አንድም የጽድቅ ስራ ሰርቷ የማያውቅ ጨካኝ የቁጭት ልጅ ነበር…ለእኔ አባቴ ነው ብዬ መጥራት ያሳፍረኛል ። ለእሱ እኔም ተጠያቂ ነበርኩ. እንደ ሞኝ፣ ቤተሰብ መሆናችንን እሰብኩ እና እያስመሰልኩ ነበር። እኔ ኳስ ስጫወት ለማየት እንዲመጣ ሁል ጊዜ እጨቀጭቀው ነበር ፡፡አንድ ቀን እንደምንም ብሎ በጨዋታው ቦታ ተገኘ ። ግን አስጠይ ትዕይንት ነበር የተፈጠረው፣ ሰክሮ ስለመጣ አንዴ ሲወድቅ አንዴ ደግሞ ባነር እያፈረሰ በመረበሽ ቦታውን አተረማመሰው…በወቅቱ በሃፍረት ልሞት ደርሼ ነበር። ዳግመኛ እንዳይመጣ ነገርኩት፤ ጠላሁት፤ተጠላን›› ሲል ነገራት፡፡

አለም ይህን የሚያቃጥል ቁስሉን እንዲያስታውስ ስላስገደደችው ተጸጸተች፤ ነገር ግን በነጻነት መናገር በመቻሉ ተደሰተች። የልጅነት ህይወቱ ስለ ሰውዬው ብዙ ነገር እንድትገነዘብ እረድቷታል፡፡እሱ በልጅነቱ ተገልሎ በበደል ስለኖረ ሰው እየገለፀ ነበር፣ ፡፡

"አንተ ልጅ እያለህ በትምህርት ቤት ጥሩ መሪ እንደሆንክ ተነግሮኛል፣››

" ያ ..ከፊል እውነት ነው…ትምህርት ቤት ከሰሎሜ በስተቀር ሌሎች ልጆች ሁሉም ያሾፉብኝ ነበር…. ከዚያም ከፍ እያልኩ ስሄድ መፋለምን መቧቀስ ተማርኩኝ…. ልጆች በእኔ ላይ ማሾፍና መሳቅ አቆሙ…. ሁሉም ልጆች ጠላቴ ከሚሆኑ ይልቅ ጓደኛዬ ቢሆኑ እንደሚሻል ተገነዘቡ ."ከንፈሩ በንቀት ጠመዘዘና ትንፋሽ ወስዶ ንግግሩን አራዘመ"ወይዘሪት አቃቤ ህግ፣ እኔ ሌባ ነበርኩ። ልበላው የምችለውን ማንኛውንም ነገር ሰርቄ ነበር የማገኘው….መዋያዬ አቦስቶና አራዳ ነበር፡፡ ››
የምትለው ነገር አልነበራትም። እሱም እንደማይኖራት ያውቅ ነበር። ለዛ ነው የነገራት። ፣ምንም እንኳን እሷ የምትቀምሰው ምግብ አጥታ ባታውቅም የልጅነት ጊዜያቸው ብዙም ልዩነት እንደሌለው አላወቀም። አያቷ ለአካላዊ ፍላጎቶቿ ለሟሟላት ችላ ነበር ፣ነገር ግን የስሜት ስንጥቆቾ ሁል ግዜም ክፍት ነበሩ ። አለም የበታችነት ስሜት እየተሰማት እና እንደማትወደድ እያሰበች ነበር ያደገችው።

በስሜታዊነት "ይቅርታ ገመዶ›› አለችው፡፡

‹‹ትእይንቱ ከተፈፀመ ቆይቷል…. አሁን ምንም አይነት ርህራሄ አልፈልግም …ያ ያሳለፍኩት ህይወት ጠንካራና እና ጨካኝ አድርጎኛል፣ እና እንደዛ በመሆኔ ደግሞ ወድጄዋለሁ። ለራሴ መቆምን ቀደም ብዬ ተምሬያለሁ፡፡ ምክንያቱም በእርግጠኝነት ማንም ሊጋፈጠኝ እንደማይደፍር እርግጠኛ ነበርኩ። ከራሴ በቀር በማንም ላይ አልመካም፣ በተለይ ወደ ሽማግሌው አባቴ ደረጃ ዝቅ ማለት እንደሌለብኝ ልጅ ሆኜ ነበር ራሴን ያሳመንኩት።››

"እና ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ጠንክረህ ሰራህ …አይደል? …በጣም ስሜታዊ ነህ።"
"ሰዎች… ያ ሽማጊሌ አባቴን እንደነበረ እንዲረሱት እፈልጋለሁ።ማንም ከእኔ ጋር እንዲያገናኘው አልፈልግም። መቼም።››ጥርሱን አንቀጫቀጨ እና ያቋረጠውን ንግግር ቀጠለ "ለአርባ ሦስት ዓመታት ያህል የእሱ ልጅ በመሆኔ በሀዘን አሳልፌያለሁ። አሁን ሰዎች ሊረሱት ሲሉ፣ አንቺ መጥተሽ የማያስደስት ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀምረሻል፣ የሞቱ ጉዳዮችን እያነሳሽ ነው፣ ለሁሉንም ሰው እኔ የዛ ሰውዬ ልጅ እንደሆንኩ እያስታወሻቸው ነው። እኔ ወዳለሁበት ለመድረስ ከጉድጓድ ውስጥ ወጣሁ…በጠንካራ ግፊት ወደ ኋላ ጎትተሸ ልትመልሺኝ እየሞከርሽ ነው። ››

" እርግጠኛ ነኝ የአባትህን ጥፋት ማንም በአንተ ላይ ለማላከክ አይደፍርም ።"

‹‹እንደዛ ይመስልሻል? በራስሽ ሲደርስ በቅርብ ትረጂዋለሽ… ምክንያቱም አንቺን ከሰሎሜ ጋር ማወዳደር ይጀምራሉ."

"ያ አያስጨንቀኝም። ንጽጽሮችን እቀበላለሁ።"

"እርግጠኛ ነሽ?"

" ማለት?"

"እናትሽ ..ቅድስት አልነበረችም."

" እኔም ትሆናለች ብዬ ጠብቄ አላውቅም."

"ምናባዊ እናት በራስሽ አእምሮ  ውስጥ የፈጠርሽ ይመስለኛል እና ሰሎሜ ያንን ክፍተት እንድትሞላልሽ እየጠበቅሽ ነው."

"ይህ አስቂኝ ነው….ግን እንዳስጠነቀቅኩሽ አስታውሺ" አለ በለሆሳስ።ትንፋሽ ወሰደና ንግግሩን ቀጠለ "ወደ አዲስ አበባሽ ተመለሺ፣ በዲዛይነር የተሰሩ ቅንጡ ልብሶችህን እና መግለጫዎችሽን የሆኑትን አጭር ቀሚስ እየለበሽ ዘና በይ። ያለፈውን ትተሽ ሂጂ፡፡ እዚህ ያለ ማንም ሰው በሰሎሜ ላይ የተፈጠረውን ያለፈውን ጊዜ ታሪክ ማስታወስ አይፈልግም… በዚህ ጊቢ በረት ውስጥ የሞተችው ሰሎሜ እንደሞተች በሰላም ብንተዋት ይሻላል"አላት፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
32👍28
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

አለም በረጅሙ ተነፈሰችና "እናቴ እዚህ አካበቢ ነው የተገደለችው አይደል?"

"ትክክል እዚህ ነው የሞተችው" ብሎ በቁጣ መለሰላ፡፡

"የት? የትኛው ጋጣ አካባቢ?"

ዝም አላት…
‹‹ኩማንደር ሬሳዋን የት እንዳገኘህ አሳየኝ” ስትል ተማፀነችው፡፡

በረድፍ ካሉት የፈረስ ጋጣዎች ሁለተኛ ጋጣ ላይ ወሰዳትና። "እዚህ ነው የሞተችው"ብሎ ነገራት፡፡
አለም ሙሉ በሙሉ ደንዝዛ ቆመች፣ ከዚያም ወደ ገመዶ እስክትቀርብ ድረስ በዝግታ ወደፊት ሄደች። ወደ ጋጣው ዞረች። በውስጡ ምንም ፈረስ ሆነ ድርቆሽ አልነበረም, ወለል የተሸፈነው በጎማ ብቻ ነው. በሩ ተወግዷል ..ክፍት ነበር"ያ አደጋ ከተፈጠረ ጀምሮ በዚህ ጋጣ ውስጥ ፈረስ ገብቶበት አያውቅም?።"ስትል ጠየቀችው፡፡

በንቀት፣ "ጋሽ ፍሰሀ ስሜታዊ ስለሆነ ይሄን ውሳኔ ወስኗል›› አላት።

አለም በደም የተጨማለቀ አስከሬን በጋጣው ውስጥ እንደተጋደመ በምናቧ አሰበችና ..ተንቀጠቀጠች፡፡ ጠያቂ አይኖቿን ወደ ገመዶ አነሳች።ቆዳው በጉንጩ አጥንቶቹ ላይ በደንብ የተለጠጠ ይመስላል፣ ፡፡
ወንጀሉን የተፈጸመበትን ቦታ መጎብኘት ያሰበችውን ያህል ቀላል አልነበረም።"ስለ ጉዳዩ በዝርዝር ንገረኝ እባክህ?››አለችው፡፡
እያመነታ፣

“በጎኗ ተኝታ ነበር፣ ጭንቅላቷ በዚያ ጥግ ላይ ነበር፣ እግሮቿ እዚህ ነበሩ” እያለ በዝርዝር አስረዳት፡፡ባደረገው ቦቲ ጫፍ አንድ ቦታ እየነካ፡፡" በደም ተሸፍና ነበር፤ፀጉሯ በደም ተነክሮ ነበር… በሁሉም ቦታ ላይ ደም ነበር."

"ስንት ሰአት ነበር?" ብላ ጠየቀች።

" ሳገኛት?"

‹‹አዎ››

"ንጋት ላይ ነበረ. 12 ሰዓት ከሰላሳ አካባቢ."

"በዚያ ቀን አንተ እዚህ ምን ታደርግ ነበር?"

"ብዙውን ጊዜ ወደቢሮ ከመሄዴ በፊት ወደእዚህ መጥቼ ፈረሶቼን አይቼና ምግብ እንደተሰጣቸው አረጋግጬ ነበር የምሄደው››

"ሌሊቱን ሙሉ ቤትህ ነበርክ ?"

"ተጨማሪ መልስ ከፈለግሽ ፣ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት በኩል አቅርቢው።" "እንደዛ አቅጃለሁ."

ወደ ኃላዋ ዞረችና ወደፊት ተንቀሳቀሰች…ከኃላ ተጠጋት፣ ክንዷን ይዞ ወደ እሱ አስጠጋት። ከባድ እና ጠንካራ ወንድ ነው። "ወ.ሪት አለም" በብስጭት እና ትዕግስት በማጣት አጉረመረመ

"ብልህ ነሽ… ይህን ጉዳይ ተይው። ካላደረግሽው ግን አንድ አካል ሊጎዳ ይችላል።"

"ማለት?"

ሰውነቱን ወደ እሷ ይበልጥ አቀረበ።‹‹ ሴትን የመግደል አቅም ነበረው?›› ስትል እራሷን ጠየቀች…በአጠቃላይ ለሴቶች ዝቅተኛ አመለካከት ያለው ይመስላል፤ነገር ግን እንደ ጁኒየር ሁሉ እሱም ሰሎሜን ይወዳት ነበር. እሷም በአንድ ወቅት እሱን ማግባት ትፈልግ ነበር። ምናልባት ገመዶን ጨምሮ ሁሉም ሰው ሰሎሜ ጎበና የተባለ ሌላ ሰው አግብታ እሷን እስክትፀንስ ድረስ እንደሚጋቡ ያስብ ይሆናል።አለም ገመዶ በማንኛውም ሁኔታ ሰሎሜን ሊገድላት እንደሚችል ማመን አልፈለገችም፤ነገር ግን እሱ ጨካኝ፣ ትዕቢተኛ፣እንደሆነም መካድም አልቻለችም ። ገዳይ ግን?አይመስልም። ወይም እሷ ሁልጊዜም ለፈርጣማ ሰውነትና ጥቋቁር ሰርሳሪ አይኖቹ ላላቸው ወንዶች ደካማ ስሜት ስላላት ይሆናል።

‹‹እናቴን ማን እንደገደላት እና ለምን እንደገደላት እስካውቅ ድረስ ይህን ምርመራ የማቋረጥ ሀሳብ የለኝም። የእናቴን ገዳይ ለማወቅ ህይወቴን በሙሉ ጠብቄአለሁ። አሁን እዚህ ደርሼ ተስፋ አልቆርጥም"

አለም ከጋጣው በወጣችበት ደቂቃ ኩማንደሩ የእርግማን መአቱን አዥጎደጎደ ።ከቀናት በፊት በአቶ ፍሰሀ ከስራው የተባረረው ሙስጠፋ በአቅራቢያው በሚገኝ ጋጣ ውስጥ ተደብቆ የሚያወሩትን ሁሉ ሰምቷቸው ነበር። በቦታው የተገኘው በአጋጣሚ እንጂ ንግግራቸውን ለማዳመጥ አስቦ አልነበረም። ብቸኝነት ስለተሰማውና ግራ ስለተጋባ ነበር በጨለማ ውስጥ ጭብጥብጥ ብሎ ሲተክዝ የነበረው… ከስራ ስላባረረው የቀድሞ አሠሪው እያሰላሰለ እንዴት ቂሙን እንደሚወጣ ማሰብ ብቻ ነበር የሚፈልገው። አሁን ግን በአጋጣሚ ያላሰበውን የኩማንደሩን እና የአለምን ውይይት ቃል በቃል ሰምቷል፡፡ እና የሰማው ነገር ደግሞ ለእሱ ልክ ከሰማይ እንደወረደ መና ነው የቆጠረው ፣ እሷ በደንብ የሚያውቃት የሰሎሜ ሴት ልጅ መሆኗን አውቋል፣ እዚህ የተገኘችው የእናቷን ግድያ ለመመርመር እንደሆነ በመስማቱ ተደንቋል። አቶ ፍሰሀ ላይ በቀሉን ለመወጣት ወርቃማ እድል እንዳገኘ ተሰምቷታል እና ያ የማይረባ ልጁንም ደህና አድርጎ ያጠፋዋል። ወደ ሠላሳ ዓመታት ጉልበቱን አንጠፍጥፎ አገልግሎት ነበር።ደህና፣ በመጨረሻ እድል ለሙስጠፋ ፈገግ እንዳለችለት ገባው ፡፡እሱ በትክክል ካርዶቹን መጫወት ከቻለ በመጨረሻ የተወሰነ ገንዘብ ሊያገኝ እንደሚችል  አሰበ፡፡ የአሁኑ አዲሷ ሚስቱ ገንዘብ ስለሌለው እያመነጫጨቀችው ነው…እንደውም ከቤቷ ገፍትራ ወደበረንዳ ልትጥለው ቋፍ ላይ እንደሆነች ተረድቷል….ታዲያ በዚህ ሚስጥር የሆነ ገንዘብ ማግኘት ከቻለ ሀሳቧን እንደሚያስቀይራት እርግጠኛ ነው፡፡

ኩማንደሩ ስራውን ጨርሶ ጋጣውን ለቆ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በትዕግሥት ማጣት ባለበት ተወሽቆ ነበር ያሳለፈው።ሙስጠፋ ትኩስ ገለባ ውስጥ የተጠቀጠቀበት ጋጥ ከመውጣቱ በፊት በአካባቢው ሌላ ሰው እንደሌለ ለማረጋገጥ ብዙ ጊዜ ጠብቋል።ከዛ ቀጥታ በጥላ ከተሸፈነው ኮሪደር ወርዶ አካባቢውን ለቆ ወደከተማ ሔደና ሁለት መለኪያ አረቄ ጠጥቶ ራሱን ካበረታታ በኃላ ስልኳን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለበት ማሰብ ጀመረ….ግን በከተማ ውስጥ እሷን የሚያውቁ ሰዎች በቁጥር ስለነበሩ ቀላል ስራ አልነበረም….እንምንም በሁለተኛው ቀን ማግኘት ቻለና በኤርገንዶ ስልኩ ደወለላት…፡፡ ከአምስት ጥሪ በኃላ ስልኩ ተነሳ፡፡

"ወ.ሪት አለም ነሽ?"

"አዎ ማን ልበል?"

"ማወቅ አያስፈልገሽም ..እኔ አውቅሻለሁ እና ያ በቂ ነው።"

ግራ መበጋባት‹‹አልገባኝም ?" አለችው፡፡
"ስለ እናትሽ ግድያ ሁሉንም አውቃለሁ።"

ሙስጠፋ በድንገት ዝምታ ውስጥ በመግባቷ እየተደሰተ ..እስክታገግም ጠበቃት፡፡ ለእሷ ሚያደነዝ አይነት ድብዳ ዜና ነው የሆነባት፡፡

‹‹እየሰማሁ ነው።››አለችው፡፡

‹‹አሁን ማውራት አልችልም.፡፡"

‹‹ለምን አይሆንም?"

‹‹ስለማልችል ነው ..ጉዳዩ አደገኛ መሆኑን የምታውቂ መሰለኝ።››

በስልክ ከእሷ ጋር ለመግባት አደገኛ እንደሆነ አስቦል… አንድ ሰው ሰምቷት ለአቶ ፍሰሀ ወይም ለኩማንደሩ ሹክ ሊላቸው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለው፡፡

‹‹መልሼ እደውልልሻለሁ።"አላት፡፡

‹‹ግን "

‹‹መልሼ እደውልልሻለሁ አልኩሽ እኮ…ስልኬን ጠብቂ…ደህና ሁኚ።››

ሙስጠፋ እሷ በምትገደልበት ጊዜ በቦታው ነበር.. እርሱ ጣልቃ ሳይገባ በተደበቀበት ሆኖ ሲመለከት ነበር ።ያንን ምሽት እንደ ትላንትናው የሆነውን ሁሉ ያስታወሰ። ይህን ሁሉ ጊዜ በሚስጥር ነበር ያያዘው። አሁን ግን የሚያወራበት ጊዜ መድረሱን አውቋል ። እናም ስለ ጉዳዩ ሁሉ ለዐቃቤት ሕጓ ለመናገር እስከ ሞት ድረስ ክፍያ ሊያስከፍለው እንደሚችል ያምናል…ግን ደግሞ ጥሩ ገንዘብም ሊያገኝበት የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው፡።
/////
44👍5