አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_አምስት(🔞)


#የጣሊያን_ጫማ_የምትሸጠዋ_ልጅ

ሰኞ የሾፒግ ቀናችን ነው።ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ካሉ ዊስኪ ቤቶች በዊክኤንዱ ያገኘነውን ዶላር ፈንክተን ሾፒንግ እንወጣለን፡፡ ያማረንን ሸምተን ለሚቀጥለው ወር አርብ ቅዳሜና እሁድ የሚሆኑ ቀሚሶች ገዝተን፤ ዉድ ሽቶዎችን ሸካክፈን ወደ ቤታችን እንሄዳለን፡፡ ዛሬ ከራኪ ጋር ነው የወጣነው፣አዲስ የገዛቻትን እኛ ወዳጆቿ"በእምሴ»ብለን የምንጠራትን “አቶዝ”መኪናዋን ይዛ ጠበቀችኝ፡፡ መጀመርያ ለክረምት የሚሆነንን ቡትስ ለመግዛት ፒያሳ ጣይቱ አካባቢ ሄድን፡፡ አንድ የጣሊያን ጫማ ብቻ ከሚሸጥበት
ክልሶች ቤት ገባን፡፡የምትሸጠዋ ልጅ ፊቷ አዲስ እልሆነብኝም፡፡ የሆነ ቦታ የማውቃት መሰለኝ ባወጣ ባወርድ የት እንደማውቃት ግን ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ አብራኝ ተምራ ሊሆን ይችላል ብዬ ለጊዜው ልረሳት ሞከርኩ፡፡ ጭንቅላቴን ግን ከነከነኝ።

እንዳንድ ወንዶችን መንገድ ላይ ወይም ቲቪ ላይ ሳያቸው የሆነ ቦታ እንደማውቃቸው እርግጠኛ እሆንና
ነግር ግን የት እንደሆነ ማስታወስ ያቅተኛል፡፡ በዚህን ጊዜ ምናልባት አብሪያቸው ያደርኳቸው ሰዎች ሊሆኑ
እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ፡፡ ብዙዉን ጊዜ ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጡልኝን ምልክቶች አገኛለሁ፡፡
ጥሎብኝ ስም እንጂ መልከ አልረሳም፡፡ ለምሳሌ ያለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሮማን ልጇ ቤኪን ልታዝናናው ቦራ ይዘነው የሄድን ቀን አንድ መልከመልካም አባት ሶስት የሚያማምሩ ልጆቹን ይዞ እኛ ወደቆምንበት ሸርተቴ መጫወቻው ጋ ሲመጣ አየሁት፡፡ የት ነበር የማውቀው እያልኩ እየሰረቅኩ ሳየው ምንም
ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ የሰውየውን ፊት ግን አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ መልኩን በደንብ የማውቀው ሰው በትክክል የት እንደማውቀው ሲጠፋብኝ እርር ድብን ነው የምለው፡፡ አእምሮዬን ያሳክከኛል፡፡ ይህን ሰው የት እንደማውቀው ለማስታወስ ጭንቅላቴን መጭመቅ ጀመርኩ፡፡ ልጆቹ ሲያማምሩ! ሴት ልጁ በተለይ እንዴታባቷ እንደምታምር! ስታድግ ጉዷ ፈላ!

ትንሽ ቆይታ ሚስቱ ናት መሰለኝ ሶስት ትኬት ይዛ እነርሱ ወዳሉበት መጣች፡፡ ደርባባ ናት፡፡ ልጆቹ እናታቸውን ነው የሚመስሉት፡፡ ሮለር ኮስተር ልታጫውታቸው ነው መሰለኝ ትኬት ለሶስቱም አደለቻቸው እነሱ ግን"ፈሪ ዊል” ካልተጫትን ብለው እሪ አሉ፡፡ ትንሽ በቅብጠት የሚያድጉ ልጆች ሳይሆኑ አይቀርም አባት ሴት ልጁን ጉንጯን ስሞ ቀና ሲል ዓይን ለዓይን ተጋጨን፡፡ ምን እንዳየች ጥንቸል ድንገት ክው ሲል አየሁት፡፡ ምንድነው እንዲህ የሚያስበረግገው? እንደዚያ ከልጆቹ ጋር በፍቅር ሲጫወት የነበረው ሰውዬ
በአንድ ጊዜ አመዱ ቡን አለ፡፡ ከዚያ አይኔን ሰብሬ ቀና ስል እንደገና አይኖቻችን ተገጩ ሁለታችንም አንገታችንን ሰበርን፡፡ ኮስተር ብዬ ወደርሱ አቅጣጫ ማየት ጀመርኩ፡፡ ቤኪ ደግሞ ይባስ ብሎ ወደሱ ልጆች ሮጦ አመለጠን አሱን ለመያዝ ወደነሱ ስጠጋ ሰውየው ተርበተበተ።የሚገባበት ጠፋው ከዚያ ለሚስቱ በጆሮዋ የሆነ ነገር ብሏት ሊሄድ አለና እንደገና ሀሳቡን ቀየረ መሰለኝ ተመለሰ።ሚስቱ ደንግጣ እየተከተለችው ምን እንደነካው ትጠይቀዋለች።ከዚያ ቦታ መሄድ እንዳለባየው ተቆጥቶ እያመናጨቀ ካስረዳት በኋላ ሦስቱንም ልጆቹን አፈፍ አፈፍ እያደረገ መኪናው ውስጥ ከተታቸውና እያካለበ ይዟቸው ሄደ።ልጆቹ የ 'ፌር ዌል' መጫወቻ ትኬታቸውን እንደያዙ ሳንጫወት አንሄድም በማለት እሪታቸውን አቀለጡት።
በተለይ ትንሹ ልጅ መጫወቻ አካባቢውን በለቅሶ በአንድ እግሩ አቆመው አባትየው አንጠልጥሎ መርሴዲስ መኪናው ውስጥ ወረወረው።

ሮማንን ስለሁኔታው ስጠይቃት"ምን እንደማያውቅ ሰው እኔን ትጠይቂኛለሽ ያው የሆነ ቀን የበዳሽው ደንበኛሽ ይሆናላ"አለችኝ።ቀጥላም ቸመሳሳይ ገጠመኞቿን አስታወሰች፡፡ብዙ ቀን እንደዚህ የሚርበተበቱ ባለትዳር ወንዶች ገጥመውኛል። አይገርምሽም ለምጀዋለሁ:: ትዝ ይልሻል እኔ አንቺና ፍቅርተ ዞላ ሪስቶራት ላዛኛ እየበላን በጥግ በኩል የሚያምር መነጽር አድርጎ የነበረው ሰውዬ ዝም ብሎ ለተወሰኑ
ደቂቃ ካየኝ በኃላ ደንግጦ ያዘዘውን ምግብ ሳይበላ ሂሳብ ከፍሎ የወጣውን እኔና ፈፍቅርተ በሳቅ ምን እንሁንደ እንዴ
እንዲህ ከሚርበተበት ሚስቱን አርፎ አይበዳም ነበር እንዴ ማን እኛ ጋር
ተልከስከስ አለው፡፡ አይገርምሽም ግን ባለትዳር ወንዶች ሲባሉ!አለችኝ፡፡

እኔ ከልጆቿ ይልቅ ሚስትዬው እሳዘነችኝ፡፡ ይሄኔ እኮ በዓለም ላይ ከኔ ባል ሌላ የሚታመን ወንድ አልተፈጠረም ብላ ትምል ይሆናል፡፡ ስታሳዝን!

አሁን እዚህ ፒያሳ የጣሊያን ጫማ ቤት ውስጥ የምታስተናግደን ልጅ የት እንደማቃት ማስታወስ ተስኖኛል ልጅቷ
ዞር ስትል ራኪን ቀስ ብዬ ጠየቅኳት፡፡ ካለዛሬ እይታት እንደማታውቅ ነገረችኝ፡፡ እድሜዋ በግምት 29 ቢሆን ነው። ጸጉሯ ቡናማ ሲሆን ወደ ኃላ አሲዘዋለች፡፡ ራኪ የተለያዩ ቡትስ ጫማዎችን ከመራረጠች
በኋላ የወደደችውን ቡኒ ቡትስ ለልጅቷ እሳየቻት፡፡ የቡትስ ጫማው ቁመት የቁመታምዋን ራኪ ጉልበት ያልፋል።

ቆንጀ! ዋጋው ስንት ነው?

"አላያችሁትም? ዋጋው እኮ ተለጥፎበታል "

ተቀጥፏል የተባልነው'ን ለማየት ገልበጥ አደረግነው፡፡ 3500 ብር” ሁለታችንም በአንድ ድምጽ ጮህን
እዚህ ቤት ደግሞ ታበዙታላችሁ አልኩኝ፤


በተፃፈበት ዋጋ ነው የሚሸጠው?አይቀንስም” ራኪ ጠየቀች

ሽራፊ ሳንቲም አይቀንስም፡፡ ያው ታውቁት የለ…fixed price ነው"

ካልሽ እሺ ብዙ አንከራከርሽም፡፡ እንዴት ነው ብዙ ይበረከታል?” እልኩ፡፡

እንጀው ለአመል ነው እንጂ ይሄን ጥያቄ የጠየቅኩት የዚህ ቤት ጫማ እቻዬ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
መልከቀናዋ አስተናጋጅ ጫማውን ከእጄ ተቀብላ በለስላሳ የእጆቿ መዳፎች ጫማው የተሰራበትን ቆዳ ጥንካሬ ለማሳየት ቆዳውን ማጣጠፍ ማሻሸት ጀመረች።

ያው ታውቁት የለ? እኛ ጋር ብራንድ ጫማ ብቻ ነው የሚሸጠው።

ራኪ ልጅቷ ያለችውን መልሳ እረጋገጠች…. ለነገሩ ማርክ ያለው የጣልያን ቡትስ ነው የምትሸጡት ዋጋችሁ ግን አይቀመስም ሙች

« ያው እህቱ እንደምታውቂው አሪፍ እቃ ዋጋውም ዋጋውም ቆንጠጥ ያደርጋል እይደል!?» በዚያ ላይ የውስጡን
ቆዳ አይተሸዋል? ሲንተቲክ እንዳይመስልሽ…እይውማ.….» ብላ እንደ ቡና ፈለቀቀችው።

አዎ አይቼዋለሁ…እምስ ማለት ነው፤ ንቅንቅ የለም…።” አለቻት ራኪ።

ልጆቷ የሰማችውን ማመን ያቃታት ይመስል በሳቅ ፍርፍር እለች፡፡ ራኪ እንደሁ የድሬዳዋ ልጅ ነኝ እያለች
ብልግና መናገርን ፋሽን አድርጋዋለች፡፡ እኔ ራሱ ያለችውን ስሰማ ድንግጥ እልኩኝ፡፡ ቀን ቀን ለምን እንደሆነ አላውቅም ደርሶ አይናፋር እሆናለሁ፡፡

ልጅቷ ሳቋን ማቆም ተቸገረች፡፡

ድንገት መጣችልኝ አስታወስኳት…ሲገርም ልጅቷን የት እንደማውቃት አስታወስኩኝ፡፡ በራኪ አነጋገር ፍልቅልቅ እያለች ስትስቅ ነው ፊቷ በደንብ የመጣልኝ፡፡ ኡስማን ዘ ፒምፕ ቢሮ፡፡ አትላስ ጋር የነበረው ኡስማን ዘ ፒምፕ ቢሮ ለመጀመርያ ቀን ስሄድ ሚኒስከርት አድርጋ ያስተናገደችኝ የኡስማን ልዩ ረዳት ናት፡፡ ገረመኝ፡፡ ለኡስማን ሴቶችን የምትመለምለው ከዚህ ሆና ነው ማለት ነው፡፡ ቀን ቀን እምስ የመሰለ
የጣሊያን ጫማ እየሸጠች ማታ ማታ እምሷን ለጣሊያን ታስደሰድባለች፡፡ ሲገርም፡፡
እንዳወቅኳት ቀልቧ ሳይነግራት የቀረ አይመስለኝም፡፡ሂሳብ ከፍለን እስከንወጣ ድረስ ተቁነጠነጠች፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት(🔞) ፡ ፡ #የጣሊያን_ጫማ_የምትሸጠዋ_ልጅ ሰኞ የሾፒግ ቀናችን ነው።ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ካሉ ዊስኪ ቤቶች በዊክኤንዱ ያገኘነውን ዶላር ፈንክተን ሾፒንግ እንወጣለን፡፡ ያማረንን ሸምተን ለሚቀጥለው ወር አርብ ቅዳሜና እሁድ የሚሆኑ ቀሚሶች ገዝተን፤ ዉድ ሽቶዎችን ሸካክፈን ወደ ቤታችን እንሄዳለን፡፡ ዛሬ ከራኪ ጋር ነው የወጣነው፣አዲስ የገዛቻትን እኛ ወዳጆቿ"በእምሴ»ብለን…»
#እንዳልፈቀር

እኔስ ልውደድ ላፍቅር
ልቤም ይሰባበር
ይሁን አይጎዳኝም
እራሴው ልቸገር
ግን አምላክ አደራ
አትስጠኝ አፍቃሪ
ልቤ ማፍቀር ሳያውቅ
አልሁን ተፈቃሪ።
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_ስድስት (🔞)


#የማሊው_ዲፕሎማት


ይህ ክለብ ብዙ የሰማሁለትና መንገድ ዳር በመሆኑ ሁልጊዜ የማየው ቢሆንም፣ እንዳጋጣሚ ሆኖ ከዚህ በፊት ሰርቼበትም ሆነ ተዝናንቼበት አላውቅም፡፡ ታም ታም ክለብ ይባላል፡፡ በቅሎ ቤት አካባቢ ግሎባል ሆቴል ስር ይገኛል ከሌሊቱ 6፡30 አካባቢ ሴኔጋላዊቷ የራኪ ጓደኛ ደውላ ራኪን እዚህ ክለብ ቀጠረቻት፡፡ ራኪ ዜጋ
ከሆነች ሴት ጋር ቀጠሮ ካላት የሌዝቦ ቢዝነስ ልትሰራ እንደሆነ ከልምድ አውቃለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ አብረን ካልሄድን ብላ ሙዝዝ አለች፡፡ በእርግጥ ስራ ሳይኖረን ሲቀር አንዳንድ ጊዜ ጭሰት እንወጣለን፡፡በምንም መልኩ ግን ከወንድ ጋር አናድርም፡፡ ገላችንን ተጣጥበን ወንድ የሚባል ቆሻሻ እንዳይነካን ተጠንቅቀን ቀሽት ቀን እናሳልፋለን፡፡ እንደዚህ አይነት ቀን ሲያጋጥመን የሴቶች ቀን ብለን እንጠራዋለን፡፡ከሸሌነት ወጥተን እንደሌላው ሰው ሁሉ በራሳችን መንገድ የምንዝናናበት ምሽት ነው፡፡ በእንደዚህ አይነት ምሸቶች የምንሰማቸው ሙዚቃዎች ከሌላው ጊዜ ይበልጥ ስሜት ይሰጡናል፡፡ የስራችን ጸባይ ሆኖ አንዳንድ ጊዜ መዝናናት ራሱ ስራ ይሆንብንና ሙዚቃ ማጣጣም እስኪያቅተን ድረስ ስሜት የምናጣበት
አጋጣሚ አለ፡፡ ጓደኛሞች ተሰብስበን ከምንሰራበት ቦታ ራቅ ብለን እንደዚህ አብረን ጭሰት ስንወጣ ግን የምር ዘና እንላለን፡፡ ከወንዶች ዓለም የጸዳች ምሽት እንዴት ዉብ እንደሆነች ማን ባወቀልን፡፡

ዛሬ ታም ታም የመጣሁትም ለዚሁ ነው፡፡ እኔ ራኪና ሴኔጋላዊቷ ጥሎብኝ ስሟ አይያዝልኝም ሆነን ነው ዛሬ የምንጫጫሰው፡፡ ይህች ሴኔጋላዊት ከራኪ ጋር ቢዝነስ ጓደኝነታቸው በርትቷል፡፡ ቅናት ነገር ቆንጠጥ አደረገኝ፡፡ በፊት የስራ ግንኙነት ብቻ ነበር የነበራቸው፡፡ አሁን ግን ከዚያ ከፍ ያለ ነገር እየጠረጠርኩ ነው፤

ታም ታም ክለብን በብዛት የአፍሪካ ዲፕሎማቶች ያዘወትሩታል፡፡ ዲጀ ዲክ ወደ ኮዚ ክለብ ከመዛወሩ በፊት እዚህ ቤት ለአንድ ወር ሰርቷል፡፡ አንድ ቀን ለምን ከዚህ ቤት ቶሎ ለቀቅክ ስንለው የአፍሪካ ዲፐሎማቶችን ስልጣን ቶሎ ቶሎ እንዲለቁ ለማስተማር ነው» ብሎ አስቆናል፡፡ ታም ታም እግረኛ ጠጪ የሚገባበት ቤት አይመስልም፤ የመኪናው ሰልፍ ህንጻውን አልፎ ማዶ ደርሷል፡፡ የመኪናው ጥራትና ብዛት ሲታይ በእኩለ ሌሊት ግሎባል ሆቴል የሚካሄድ የሰርግ ስነ ስርዓት ያለ ነው የሚመስለው፡፡

ትንሽ መጎንጨት እንደጀመርን አንዳንድ “ኮድ ሶስቶችን" በቤቱ ውስጥ ማስተዋል ጀመርኩ፡፡ ኮድ ሶስቶችን ገና ሳያቸው ነው የምለያቸው፡፡ ጥሎብኝ አልወዳቸውም፡፡ ጨዋ መስለው በእንጀራዬ ስለገቡ ሳይሆን የሆኑ ራሳቸውን የሚዋሹ ፍጥረቶች አድርጌ ነው የማስባቸው፡፡ የሰሞኑ አዲሱ ፋሽን ደግሞ «ኮድ ሶስት
ሆኖ በየሆቴሉ ቢዝነስ መስራት ሆኗል፡፡ “ኮድ ሶስቶች” የቤት ልጆች የሚባሉ አይነት ሆነው በአሪፍ አሪፍ ናይን ክለቦች ውስጥ enetrance ከፍለው እንደተቀረው ሰው ለመጠጣትና ለመዝናናት የመጡ መስለው የሚሸራሞጡ ናቸው ዋና አላማቸው ሀብታም መስለው የታዮቸውን ወንዶች መጥበስና ከነርሱ ጋር ቢዝነስ መስራት ነው።ብዙውን ጊዜ "ኮድ ሦስቶች" ቀን ቀን ቀን ቀን ወይ ተማሪ ወይ የቢሮ ሰራተኛ ናቸው ማታ ግን ደህና ሰው መስለው ወንዶችን ያጠምዳሉ፡፡ወንዶች ከሸሌ ጋር ማደር ይቀፋል ይላሉ። ከነዚህ "ኮድ ሶስቶች" ጋር ሲያድሩ ግን ከሸሌ ጋር እንዳደሩ ስለማያውቁ ይደሰታሉ ኮንደም ለማጥለቅ እንኳ እያስቡም፡፡ በነሱ ቤት ድንግል የቤት ልጅ ጠብሰው ሞተዋል፡፡

ሰዓቴን ተመለከትኩ ከሌሊቱ 9፡00 ይላል። በክለቡ ውስጥ ከገባን ሁለት ሰዓት ቢሆነንም እስካሁን ከአፍሪካ ሙዚቃ ውጪ አንድም ሙዚቃ አልሰማንም የማሊው ድምፃዊ አሊ ፋርካ ቱሬ ሌላው ደሞ ሴቷ ኡማ ሳንጋሪ ሙዚቃቸውን የምወድላቸው ሴኔጋሎቹ ሳሊፍ ኬይታ፣ ዩሱ ንዶር እና እስማኤል ሎ የኮንጎው አዊሎ ሎንጎማ የደቡብ አፍሪካዋ ጎበዟ ድምፃዊ ሻካ ሻካ፣ ማርታ አሻጋሪ 'እምቢ እምቢ' ብላ ከአረብኛ ወደ አማርኛ የተረጎመችው የአልጄሪያው ካሊድ አዲ አዲ የሚለው የአረብኛ ዘፈን፤የደቡብ አፍሪካ የሬጌ ዘፋኝ ላኪ ዱቤ፣ አይቮሪኮስታዊ አልፋ ብሎንዲ ሁሉንም ነፍሳችን እስኪወጣ ጨፈርንባቸው:: እድሜ ለጓደኛዬ ዲጄ ዲክ ሙዚቃን ማጣጣም አስተምሮኛ
ዘፈኖችን እንደምወድ ስለሚያውቅ አሪፍ አሪፍ ኮሌከሽኖችን ይሰጠኛል፡፡ ስማቸውንና ታሪካቸውን ይነግረኛል፡፡በእንግሊዝኛ የተጻፉ የአፍሪካ ሙዚቃ ላይ ያተኮሩ መፅሄቶችን ያመጣልኛል፡፡ እኔ ከሌለሁ እንኳን : እስኪ ይሄን ለዛች ለተማረች ሸሌ ስጧት ብሎ ያስቀምጥልኛል ፡፡ እሱ እነዚህን መፅሄቶች የሚያገኘው በእንግሊዝኛው ኤፍ ኤም የራሱ ሬዲዩ ፕሮግራም ስላለው ነው፡፡ ደግሞ ብዙዎቹ ዘፋኞች ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምናምን እዚህ አገር ሲመጡ እሱ ነው ጠብ እርግፍ ብሎ የሚያስተናግዳችው።

ዲጄ ዲክ እንደነገረኝ ከሆነ እነዚህ የአፍሪካ ዘፋኞች ሌላ የአፍሪካ አገር ሲሄዱ ሰኪውሪቲ ተመድቦላቸው
ሰው በፊርማ እንዳያጨናንቃቸው ስለሚፈሩ ብዙም ከሆቴላቸው ሳይወጡ ነው ቀኑን የሚያሳልፉት።
አዲሳባ ሲመጡ ግን ለማኝ ይሁኑ ዘፋኝ ማንም የሚያውቅላቸው ስለሌለ በጣም ይገረማሉ፡፡ ዲጀ ዲክ የነገረኝን ከዚህ ጋር የተያያዘ ገጠመኙን መቼም አልረሳውም፡፡

...አልፋ ብሎዲን ደጃቩ ክለብ ይዤው ሄጄ ማንም ዞር ብሎ የሚያየው ጠፋ፡፡ ከዚህ በፊት የሱን ዘፈን የሚጫወት ልጅ እዚህ ቤት ይሰራ እንደነበረ አውቅ ስለነበረ ነው ሆን ብዬ ይዤው የሄድኩት፡፡ የሱን ዘፈን የሚከትፈው ልጅ ያሬድ ይባላል፡፡ ገና ገብተን ቁጭ ከማለታችን ያሬድ የሚባለው ልጅ በባንድ ታጅቦ
መጫወት ጀመረ፡፡ መጀመርያ የቦብን "three little birds" ከዚያ ደግሞ የአልፋ ብሎንዲን “Jerusalem" (Cocody Rock» እና «I wish you were here» የተሰኙትን ስራዎች አከታትሎ ዘፈነና ከመድረክ ወረደ፡፡ ብሎንዲ የራሱ ዘፈን ሲከተፍ በስሜት ቁጭ ብሎ ይኮመኩማል፡፡ ከታፊው ሙዚቃውን ጨርሶ እኛ በተቀመጥንበት ስኩል ሲያልፍ እጁን አፈፍ አድርጌ።

"በጣም አሪፍ ነው ወንድሜ! አድናቂዎችህ ነን ደስ ብሎናል" አልኩት፡፡

ቴንኪው! ቴንኪው!» ብሎኝ ሊሄድ ሲል እንደገና እጁን አፈፍ አድርጌ

"በተለይ ይሄ ጓደኛዬ ቅልጥ ያለ አድናቂህ ነው፡፡ ከዚህ በፊት አስተዋውቂያችሁ ይሆናል ምን አልባት ካስታወስከው? አልኩት ከአልፋ ብሎንዲ ጋር እያጨባበጥኩት፡፡

ይቅርታ አላውቀዉም ፊቱ ግን አዲስ አልሆነብኝም፣ያው ብዙ ሰው እዚህ ቤት ስለሚመጣ ሁሉንም ማወቅ ለኛ ለአርቲስቶች ከባድ ነው፤ ይቅርታ ወንድሜ የት ነበር የማውቅህ አለው አልፋ ብሎንዲን እንደገና እየጨበጠው

ለነገሩ እሱ አማርኛ አይችልም ግን ያው እድናቂህ ነው እልኩት ለከታፊው ያሬድ፡፡

"ነው እንዴ ምንድነው ጃማይካዊ ነው?» አለኝ ከታፊው።

አይ ጃማይካዊ እንኳን አይደለም፤ እይቬሪኮስታዊ ነው፣ እንዳንተው ሙዚቃ ይሞካከራል አልኩት፡፡

« ኦኬ…በርታ በለው እንግዲህ ፊቱ ጃማይካዊ ነው የሚመስለው ለዛ ነው የሆነ ቦታ የማውቀው የመሰለኝ ብሉን ከመድረክ ጀርባ ሄደ፡፡
አልፋ ብሉንዲ የምናወራው ግራ ገብቶት እንድተረጉምለት አይን አይኔን ያየኛል፡፡

የሆነውን ሁሉ ያወራነውን ሁሉ ነገርኩት፡፡ በሎንዲ በጣም ሳቀ፡፡ ከተወለደ እንደዛ ስቆ ሁሉ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ደስ አለው፡፡ባለመታወቁ አልከፋውም እንዲያውም ደስ ብሎታል፡፡

ቆየና ደግሞ <<You know what?>> I used to think I was kind of celebrity, only until today ብሎ
እንደ አዲስ እንባው
👍51
እስኪመጣ ሳቀ፡፡

ሁልጊዜ ከሚያንጠለጥቀት ቦርሳው
<<i wish you were here » የሚለውን ሲዲውን አውጥቶ
አውቶግራፍ ፈርሞ አስተናጋጇን ጠራትና አኑን ለዘፈነው ልጅ እንድትሰጥለት አደራ ብሏት እንድ ሁለት ኦሮምኛ
ዘፈኖችን ሰምተን ከዴጃቩ ክለብ ወጣን፡፡

ብሎንዲ ሲዲው ላይ ምን ብሎ እንደጻፈለት ሊያሳየኝ አልፈለገም፡፡
This is between me and
Ethiopian Alfa Blondi" ብሎኝ ያ ደስ የሚል ሳቁን ለቀቀው፡፡ ከስንት ጊዜ በኃላ በቅርቡ ለአንድ ለፈረንሳይ ሬዲዬ ኢተርቪው ሲለጥ በህይወቱ በጣም ከገረሙት ገጠመኞች አንዱ
The ethiopian alpha blondi has no idea who alpha blondi is ብሎ የዚህን ከታፊ ልጅ አጋጣሚ ሲተርክ ሰማሁት ብሎ ዲጄ ዲክ ተረከልኝ፡፡

በምን ነበር ይህን ታሪክ ያነሳሁት ታም ታም ክለብ ብዙ አፍሪካውያን የሚመጡበትን ምክንያት እያወራሁ ነበር አንዱ ምክንያታቸው የአፍሪካ ሙዚቃ ብቻ ስለሚዘወተር ነው፡፡ የአፍሪካ ሙዚቃዎች ከወገብ በታች ነው የሚንጡት፡፡ ምታቸው በተለይ ለነዚህ በረሮ “ኮድ ሶስቶች የተመቿቸው ይመስላል፡፡ የዜጎቹን ነቅንዝር
ስሜት ለመፈታተን ቂጣቸውን እያሾሩ በዳንስ ሰበብ ይዋሰባሉ። አብዛኞቹ ተሳክቶላቸዋል።

በአፍሪካውያኑ ዲፕሎማቶች ግዙፍ ክንዶች ታቅፈው ዊስኪያቸውን ውድ ወይናቸውን ቮድካቸውን ማርቲኔያቸውን፡ አማሩላቸውን፣ ሳምቡካቸውንና ተኪላቸውን እየተጎነጩ ነው ያልታደሉትም
ወለሉ ጥግ ቆመው ያቅማቸውን ይናጣሉ፡፡

አልኮላቸውን እያጣጣሙ በአፍሪካ ሙዚቃዎች ወዝወዝ ለማለት የመጡ ጥቂት የሀበሻ ጥንዶች አልፎ አልፎ ይታዩኛል፡፡ በቅርብ ርቀት ከፊት ለፊቴ ረጅም ቀይ የእራት ልብስ የለበሰች ቆንጅዬ ልጅ ባሏ እንደሆነ በርግጠኝነት መናገር ከሚቻል ልጅ ጋር በተደጋጋሚ እየደነሱ ወደ ቦታቸው ሲመለሱ ተምልከቼያለሁ፡፡ሁለቱም የጋብቻ ቀለበት አድርገዋል። ባል ጥቁር ቢራቢሮ
ልብስ በነጭ ሸሚዝ አድርጓል፡፡ ጥንዶቹ ስገምት በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ይመስላሉ ቁመታቸው በመቀስ የተከረከመ ያህል እኩል ነው፤ ረጃጅሞች ናቸው፡፡ሚስት ከወገቧ ቀጠን ብሎ ሰፋ ያለ ዳሌ ስላላት በምትደንስብት ወቅት በሁሉም ወንዶች ቅንዝራዊ ዓይን ዉስጥ ትገባለች፡፡ ወገቧ መቅጠኑ የወንዶች ልብ ቀርቶ ቀርቶ ሴቶችም እንድናያት ያስገድደናል፡፡ የተስተካከለ የሰውነት ቅርጽ ነው ያላት መልኳም ለክፉ
አይሰጥም:: ከንፈሯ ያምራል፡፡ ሙሉቀን መለሰ … ከንፈርሽ እንጆሪ ቀይ ጽጌረዳ ወፍ ጭ ሳይል ማልዶ የፈነዳ...

ሲል የተቀኘው የዚህችን አይነት ሴት ከነፈር አይቶ መሆን አለበት። በስተግራ በጥቂት ሜትሮች እርቀት ሬድ ሌብሉን ተገንጥሎ የሚጎነጨው ግዙፍ አፍሪካዊ ከቅድም ጀምሮ ዓይኑን ከሷ ላይ አልነቀለም ያረገው ዥንጉርጉር ጀለቢያና ዥንጉርጉር ኮፍያ ከግዝፈቱ ጋር ተደምረው የአንድ የምእራብ አገር ዲፕሎማት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ቢያንስ ኪሎውንና ወዙን በማየት ቀላል ሰው እንዳልሆነ መናገር አይከብድም፡፡ አንገቱና እና ሁለት እጆቹ በወርቅ ሀብሎች እና ጌጦች ደምቀዋል፡፡ ከፊት ለፊቴ ባለው መስታወት ቁልጭ ብሎ ስለሚታየኝ የጠረጠርኩት ነገር ስላለ በአይነ ቁራኛ እየተከታተልኩት ነው
ባልየው ለደቂቃዎች ለሽንት ዞር ሲል ጠብቆ ሀበሻዋን ሴት በአይኑ ቋንቋ በተደጋጋሚ ሲያጫውታት ተመልከቼያለሁ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ኮስተር ብላ ስትገላምጠው ነበረ ፡፡ ኋላ ላይ ግን ሊገባኝ ባልቻለ ምክንያት እየተሽኮረመመች ቁጥብ ፈገግታዋን መለገስ ጀምራለች፡፡ እድሜው በግምት ሀምሳ አጋማሽ ላይ የሚጠጋው ይሄ አፍሪካዊ ዲፕሎማት እንደሆነ የጠረጠርኩት ሰውዬ ሙሉ ትኩረቱ በዚህች ሴት ላይ ነው፡፡ ሌላ ስራ ያለውም አይመስልም፡፡

ዲፕሎማቱ የባለትዳሯን ትኩረት ለማግኘት በሚመስል መልኩ የቤቱ ዳንሰኞች በማሊ ሙዚቃ ሲደንሱ
ለማረኩት ሁለት ዳንሰኞች ሁለት ሁለት ጊዜ መቶ መቶ ዶላሩን ጡት መያዣቸው አካባቢ ሸጉጦላቸዋል ይህን ሁሉ ወጥመድና ድራማ እንደኛ በልምድና በእውቀት ያልቀሰመው የልጅ ባል ነሸጥ ባረገው ቁጥር ሚስቱን እያባበለ ለዳንስ ይጋብዛል፡፡ባል ከፍተኛ የሞቅታ ስሜት ውስጥ እንዳለ ሁለመናው ይናገራል
ዲፕሎማቱ እያንዳንዷን ቅጽበት ከቀድሞው በላቀ ትኩረት ይከታተላል፡፡ ራኪና በሌዚቢያን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት መረብ ከዓመት በፊት የተዋወቀቻት ሴኒጋላዊት ጓደኛዋ የራሳቸው፣የጨዋታ ደሴት ገንብተዋል፡፡ ሁሉቱም ለክለቡ ሌላ አይነት የእንቅስቃሴ ድባብ በድን ሆነዋል፡፡በራሳቸው ጨዋታ ከክለቡ ውስብስብ ዓለም ራሳቸውን አግልለዋል፡፡ እኔን መፈጠሬንም ረስተውኛል፡፡ ራኪ አንዳንድ ግዜ ብቻ እንግሊዝኛ ቃል ሲጠፋባት «እንትን ምን ነበረ የሚባለው በእንግሊዝኛ?» እያለች ትጠይቀኛለች
እንጂ ጫወታቸውን እንድቀላቀል ብዙም ፍላጎት አላሳዩኝም፡፡

እንደገና ዲፕሎማቱ በማሊ ሙዚቃ ከሚደንሱት የከለቡ ዳንሰኞች ለአንዷ መቶ ዶላር ሸጎጠላትና ወደ ቦታው ተመለሰ አሁን ደግሞ የሀበሻው ሚስት ዓይን በዲፕሎማቱ ላይ እንዳረፈ ተመለከትኩ፡፡

በአጠገቤ ባንኮኒ ተደግፈው እንደኔው ትእይንቱን የሚከታተሉት ሁለት “ኮድ ሶስቶች በመጠጥ የታጀበ ጨዋታ ከጆሮዬ ደረሰ፤

ይሄ ጮማው የማሊ ዲፕሎማት ማን ላይ ወጥመዱን እንደዘረጋ እያየሽ ነው?” “ያ ግድንግዱ? ደሞ ማሊ መሆኑን እንዴት አወቅሽ?
ማክዳን አውጥቷታል፡፡ እሷ ናት የነገረችኝ፡፡ ማሊ ኤምባሲ ውስጥ ነው የሚሰራው።

"እና ማን ላይ ነው የሻፈደው?”

እዚያ ጋር ቀይ ረጅም ቀሚስ ከለበሰችው ሴት ጋር” “እንዴ እሷ እኮ ከባልዋ ጋር ነው የመጣቸው አብደሻል?!

"እኔ ሳልሆን ያበድኩት ሰውየው ነው፡፡ ከባልዋ ጋር እንደሆነች እያወቀ እኮ ነው የሚጠቅሳት፡፡ አጠገብዋ ያለው ወንድ ባሏ መሆኑ ግልጽ ነው መቼም፤ አያውቅም አይባልም?»

«አንቺ ግን ምን አይተሽ ነው ቆይ?የምታወሪው እውነት አይመስለኝም፡፡”

“እይ ቲጂ! ዝናውን ባትሰሚ ነው፡፡ ረጅም ስምንት ቁጥር ወገብ እና ሰፋ ያለ ዳሌ ያላት ሴት ካየ ለምን ገዳም የገባች መነኩሴ አትሆንም አይለቃትም፡፡ ለማየት ያብቃሽ ዛሬ የሆነ ጉድ ያሳየናል፡፡ ማከዳንም ከዚህ በፊት እዚሁ ግሎባል ለሁለት ሳምንት ተከራይቶ ያስቀመጣት ለዛ ነው"

“ለንዳንቺ አይነቷ ሲንቢሮ ሴት ቦታ የለውም፣ አትቀላውጪ እያልሸኝ ነው?”

“ኦፍ ኮርስ! ያው አንቺ ለቢዝነሱ አዲስ ስለሆንሽ እንጂ ዌስት አፍሪካዎች የሚወዱት ገዘፍ ብላ ወፈር ያለች
ሴት ነው፡፡ በተለይ ለነሱ ትለቁ ቁም ነገር ቂጥ ነው፡፡ ቂጥ ከሌለሽ ጭንቅላት የሌለሽ ነው የሚመስላቸው
ብታዪ”

ሁለቱም ጮክ ብለው ሳቁ፡፡

የኮድ ሶስቶቹን ወግ በንቃት እያዳመጥኩ ትእይንቱን በትኩረት መከታተል ቀጥያለሁ ሌላም ተመልካች ያለው ፊልም በመሆኑ ዘና ብያለሁ፡ባልዋ የስልኩን ጥሪ ተከትሎ ወደ ውጪ ተጣደፈ፡፡ በዚህ ጭው ባለ
ሌሊት የሚደውለው ማነው? ለነገሩ ያለበትን ሁኔታ ባያውቅ ነው እንጂ ለሽንቱ እንኳ ባልተነሳ ነበር፡፡ሚስቱ በተደጋጋሚ ስልክ ሊያናግር መውጣቱ እንዳስከፋት ከፊቷ ገጽታ ላይ አንብቤያለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ተነስቶ ስልክ አናግሮ ሲመለስ ተጨቃጭቀዋል ስልኩን ልየው ማን ነው የሚደውልልህ? ስትለው እሱ በጥያቄዋ ተበሳጭቶ ሲጨቃጨቁ ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
3👍1
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስድስት (🔞) ፡ ፡ #የማሊው_ዲፕሎማት ፡ ፡ ይህ ክለብ ብዙ የሰማሁለትና መንገድ ዳር በመሆኑ ሁልጊዜ የማየው ቢሆንም፣ እንዳጋጣሚ ሆኖ ከዚህ በፊት ሰርቼበትም ሆነ ተዝናንቼበት አላውቅም፡፡ ታም ታም ክለብ ይባላል፡፡ በቅሎ ቤት አካባቢ ግሎባል ሆቴል ስር ይገኛል ከሌሊቱ 6፡30 አካባቢ ሴኔጋላዊቷ የራኪ ጓደኛ ደውላ ራኪን እዚህ ክለብ ቀጠረቻት፡፡ ራኪ ዜጋ ከሆነች ሴት ጋር…»
#ፅጌረዳ

ከነገሮች ሁሉ ለምወዳት
ከሷ የበለጠ ስጦታ ባጣላት
ለፅጌረዳዬ
እራሷን ሰጠኋት፡፡
#የእግዜር_ጥበብ

እኔ አልዋሽም
አይንሽ ኮከብ ነው ብዬ
የሞተን የሚያነቃ ድንቅ ጨረርን አይቼ
እኔ አልዋሽም
ከንፈርሽ እንጆሪ ነው ብዬ
ለመንካት የሚያሳዝን ቸኮሌትን አይ
እኔ አልዋሽም
መልክሽ ጠይም ነው ብዬ
ስም ያልወጣለትን ልዩ ቀለምን አይቼ
እኔ አልዋሽም
ቁመናሽ መለሎ ነው ብዬ
የሚያፈዝ ተክለ ሰውነትን አይቼ
እኔ አልዋሽም
ፈገግታሽ ልዩ ነው ብዬ
የጠዋት ጀንበርን በአይኔ አይቼ
አዎ የኔ ልዕልት ፈፅሞ እኔ አልዋሽም
ውበትሽን በቃላት በጣም አሳንሼ።
👍1
#ውበቴ_ማማሩ

ቢመቸኝ፦
ይህ ኮከብ አይኔ
በረዶ ጥርሴን አይቼ
ቢመቸኝ፦
የውስጥ ውበቴን
የሃሳብ ምጥቀቴን ገምቼ
ቢመቸኝ፦
እንዲህ በቁመናዬ ተማርኬ
በኔነቴ ተደምሜ
አዎን ቢመቸኝ፦
እራሴን አገባ ነበር
ሰማንያ ፈርሜ፡፡
Forwarded from አትሮኖስ (.) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_ሰባት (🔞)


..ሁለት ጊዜ ተነስቶ ስልክ አናግሮ ሲመለስ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ስልክህን ልየው ማነው የሚደውልልህ ስትለው እሱ ሰጥያቄዋ ተበሳጭቶ ሲጨቃጨቁ ነበር፡፡ አሁን ስልክ ለማናገር ሲወጣ በልምምጥ
ዓይን አነፈይቷት ነው የወጣው:: ሚስት በቅናት እየነደደች እንደሆነ እጠጣጧ ያስታውቃል። አሁንም ስልኩን ሊመልስ ሲወጣ ፊቷን እንደ ሀምሌ ዳመና ከስክሰዋለች፡፡ ባልዋ ላይ ጥርጣሪ ያደረባት እንደሆነ ማንም መገምት ይችላል፡ ስልክ እናግሮ ሁለት ጊዜ ከተጎነጨ በኃላ ለሽንት ተነስቶ ሲወጣ ሞባይሉ ስልኩ ከተጠበቀት የሱሪ ኪሱ ወደ ሶፋው ተንሸራትቶ ወደቀ፡፡ ሚስት ስልኩን አፈፍ አድርጋ መበርበር ጀመረች፡፡ ባል እስኪመጣ ከስልክ ማውጫው የደዋይ ስም አይታ ስልኩን ቦታው ላይ አስቀመጠጭለት ሞቅታ ላይ ያለው ባል ሆኑ ጉዱን አላወቀ ሽንቱን ሸንቶ ሶፋው ላይ ተመልሶ ቁጭ አለ። አፍታም ሳይቆይ
ስልኩ ሲጠራ በድጋሚ ስልክ ለማናገር ሚስቱን ይቅርታ ጠይቋት ተነሳ፡፡

ሚስት ለባሏ የዉሸት ፈገግታ አሳይታው ምንም እንዳልተፈጠረ ቀሚሷን እየነካካች ትጫወታለች።በቀል እያሰበች እንደሆነ ግን አጠጣጧን አይቶ መገመት ይቻላል፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ነበር ዲፕሎማቱ በደማቅ ፈገግታ እጁን ለሰላምታ የዘረጋላት፡ ከጨበጠችው በኋላ ሙሉ ፈገግታዋን ለገሰችው። በምን ቋንቋ እንደሚግባቡ ባላውቅም ጥቂት ቃላትን እንደተለዋወጡ የሞባይል ስልኳን በሞባይል ስከሪኑ ላይ መዝገቦ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከኋላዩ የተቀመጡት ኮድ ሶስቶች ማንሾካሾክ ቀጠሉ፤ ልክ እንደ እግር ኳስ ኮሜንታተር ክስተቱን ለኢትዬጵያ ህዝብ በቀጥታ እያስተላልፉ ነው የሚመስለው አወራራቸው፡፡

“ አላልኩሽምካ ቲጂ፤ አልነገርኩሽም፤ ይህ ፍልጥ! በገገማ እኮ ነው የሚገቡት"

ሲገርም ሀይሚዬ! አንቺ ራሱ ቀድመሽ ማወቅሽ ትገርሚያለሽ፡፡ እኔ ይህንን በአይኔ ባላይ እመቤትን አላምንሽም ነበር፡፡ ሃይሚ ግን ምን ቢላት ነው በናትሽ ስልኳን በዚህ ፍጥት የሰጠችው ባሏን እዚህ አስቀምጣ ደሞ ገና እግሩ ሳይወጣ እንዲህ አይነት ፈጣጣ ስራ አይሸክክም?

« እኔ በፍጹም ሀበሻ ሴት እንደዚህ የምታረግ አይመስለኝም ነበር…እመቤቴን!»

ቲጂዬ ዘንድሮኮ በባለትዳሮቹ ብሷል፣ አልሰማሽም፡፡ ያው ገንዘባቸው ነው አስማቱ፡፡ ለነገሩ ማክዳ ብዙ ነገር ነው ስለ ሰውዬው ያወራችልኝ፣ ለአንድ ሌሊትም ቢሆን የሰው ፍቅረኛ ወይም ሚስት ነጥቆ መተኛት ሆቢው ነው ስትለን ነበር፡፡ እንደትልቅ ጀብዱ ነው የሚያወራው"

ለምን ስልኳን እንዲህ በፍጥነት እንደሰጠችው ግን እስካሁን ግልጽ አልሆነልኝም፡፡ ከዚህ በፊት
ይተዋወቃሉ ማለት ነው? ስትይ?
"ማለቴ ከዚህ በፊት በድብቅ ይጠልዛት ከነበረና ዛሬ ባጋጣሚተገናኝተው ከሆነ ብዬ ነው»

« እይምሰልሽ…ባሏ በሆነ ነገር ያበሳጫት ይመስለኛል፡፡ የሆነ ልትበቀለው የፈለገችው ነገር ሳይኖር አይቀርም።>>

በጉጉት ልሞት ነው። ዛሬ ክትክት የማይቀር ነው።ባልየው ይሄን ጠብደል ካየው በእርግጠኝነት በጥይት ይገድለዋል

« ሀይሚ ይሄን አፍሪካዊ ስጋ በስቶ የሚገድል ጥይት መኖሩንም እንጃ እስኪ አታፍጭባቸው እንዳይባንኑ…»

«ጥንት እያዩንም ባካሽ...በነሱ ቤት እኮ ማንም አያያቸው።አፍሪካዊው ግን ሚስት በማሻፈድ የተመረቀ ነው የሚመስለው እይው እስኪ ምንም እኮ ፍርሃት እንኳ የለበትም።>>

ሊሆን ይችላል። ማክዳ እንደነገረችኝ አሪፍ ቪላ ተከራይቶ ነው የሚኖረው፡፡ በር ላይ ካየሻት ሲልቨር ፔዦዋ የሱ ናቱ።
እኔኮ ሲገባ አይቼ እየተጠራጠርኩ ነበር፡፡ ደሞ በገንዘብ ስስት አያውቅም፡፡ ግን ያው መቀርቀርያ የሚያክለውን እቃውን የምትቋቋሚ ከሆነ ነው፡፡ለዛም ሳይሆን አይቀርም ከመልክ ይልቅ ቀጠን ያለ
መግብ እና ገዘፍ ያለ ቂጥ ላይ የሚሻፍደው፡፡ ለነገሩ ሁሉም ያው ናቸው፡፡”

የኮድ ሶስቶቹ አይነት ጥርጣሬ እና ግምት እኔ ልቦና ውስጥም ተፈጥሯል፡፡ ባል ከስልክ ንግግሩ ተመልሶ ከሚስቱ ጋር እያወጋ ነው፡፡ እሱ ጎርደን ጂን ሚስት ቮድካ በኦሬንጅ እየተጎነጩ ነው፡፡ ሁለቱም በሞቅታ ስሜት ውስጥ ናቸው፡፡ ዓይኔን ወደ የማሊው ዲፕሎማቲክ ወንበር ሳዞር ዲፕሎማቱ በቦታው የለም፡፡
ሲጠጣው የነበረው የሬድ ሌብል የውስኪ ጠርሙስ ከነብርጭቆው ተነስቷል፡፡ ሂሳብ ከፍሎ እንደወጣ
ገመትኩ፡፡ ገረመኝ፡፡ አይኔን ከቦታው ዞር ያደረኩ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ስራውን ሰርቶ ሄደ! አልኩኝ በልቤ፡፡

ጥግ ላይ ያሉት ነጭ ጀለቢያና ጥምጣም ያደረጉት አራት ሱዳናዊያን ከዲጄው ክፍል በተለቀቀው የሱዳናዊው መሀመድ ዋርዲ “ሰበርታ" የተሰኘ ዘፈን አንድ እጃቸውን ከፍ አድርገው የአውራ ጣትና
የመሀል ጣታቸውን እያፋተጉ ከምቱ ጋር ይወዛወዛሉ፡፡ ሀበሾቹና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ዜጎችም በሙዚቃው በጋለ ስሜት ደምቀዋል፡፡ ቤቱ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በሙዚቃው የተለየ ትዝታ ያለው ይመስላል፡፡ ሁሉም አይኑን ጨፍኖ በሙዚቃው ተመስጦ ይወዛወዛል፡፡

ባልና ሚስቱም በዚህ ተመሳሳይ የውዝዋዜ ምት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ሁሉም በሞቅታ ስሜት ውስጥ
ስለሆኑ ይሉኝታ የሚባል ነገር የለም፡፡ ከሰዓታት በፊት ላይነሱ ከወንበራቸው የተሰፉ ይመስል በቦታቸው ሆነው አንገታቸው እስኪሰበር ሲወዛወዙ የነበሩት ሁሉ አሁን እድሜ ለአልኮል ቆመው በሚችሉት በማይችሉትም፣በሚያውቁትም በማያውቁትም ሙዚቃ ይውረገረጋሉ፡፡ አዝናኝ ትዕይንት ነው ራሱን ገለል አድርጎ መመልከት ለቻለ፡፡

ድንገት ሚስት ሞባይል አቃጨለ፡፡ሚስት ግራ በመጋባት ስሜት ኮስተር ብላ የደዋዩን ስልክ ከተመለከተች በኋላ ለማነጋገር እርሷም በተራዋ ባሏን ባለበት ትታው እየተመናቀረች ወደ ውጭ ወጣች
ባል ውዝዋዜውን አላቆመም፡፡ ብቻውን አይኑን ጨፍኖ በወርዲ ዘፈን ይወዛወዛል፡፡ ሙዚቃው አበቃ፡፡ በሙዚቃው ላይ ሙዚቃ ተከተለ። ሚስት ቦታዋ ላይ አልተመለሰችም፡፡
በርካታ ደቂቃዎች ነጎዱ ሚስት የለችም የባል የፊት ገጽታ ተቀያየረ ማን ቢደውላልት ነው ይሄን ሁሉ ደቂቃ
የምታወራው” በሚል በተራው መብሰልሰል የጀመረ ይመስላል፡፡ በቅናት እና በብስጭት ስሜት ሆኖ በጥድፊያ ወደ ውጪ ወጣ፡፡ የሚያስበውን በስካር የጋለውን መላ ሰውነቱ የሚያሳብቅ ይመስላል።

ውጪ ለደቂቃዎች ቆይቶ ቦታው ተመለሰ፡፡ ሚስት የለችም የፊቱ ቅላት ጨምሯል ዓይኖቹ ደም ሐብሰዋል። በንዴትና በቁጣ ወይም በጭንቀት ይሆናል።ስልኳ ላይ ደውሎ ሞባይሉን ጆሮው ላይ ደገነ መልስ ያገኘ አይመስልም፡፡ በተደጋጋሚ ደወለ፡ ሚስት ስልኩን ልትመልስለት እልቻለችም እጆቹ መንቀጥቀጥ ጀመሩ። ተስፋ ባለመቁረጥ ደጋግሞ ስልኳ ላይ ይደውላል፤ መልስ የለም።ባል አስተናጋጁነሸ የሴቶች
ሸንት ቤት እንዲወስደው ጠየቀ፡፡ አስተናጋጁ ታዘዘ፡፡ ፊት ፊት እየመራ ወደ መፀዳጃ ቤት ወሰደው፡፡ ቮድካው ስላልተስማማት እያስመለሰች ይሆን? ብሎ ገምቶ መሆን አለበት።
ኮድ ሶስቶቹ ጨዋታቸውን የሚያደምቁበት ጉዳይ አግኝተዋል፤

ማስኪን ሚስቱ ያየችውን አይታ እንደተቀነጠሰችበት እስከአሁን አላወቀም፤ ሀይሚዬ አያሳዝንንም? እኔ
ወንድ ልጅ የዋህ ሲሆን እንዴት አንጀቴን እንደሚበላኝ፡፡”

“ምኑ ያሳዝናል ይሄ ጅል ነገር ነው እንጂ፤ ካልጠፋ ክለብ ማን ሚስቱን እዚህ ይዘህ ና አለው እነዚህ እንደሆነ ልምዳቸው ነው የሰው ሚስት መስረቅ፡፡ ጭራሽ ጀግንነት ነው የሚያረጉት፡፡ያው እንዲህ ዓይን በአይን አታይውም እንጂ እዚህ ክለብ፣ ሌላም ያፍሪካ ዲፕሎማቶች ያሉበት ቦታ በተደጋጋሚ ተከስቷል።

ከደቂቃዎች በኋላ የከለቡ መግቢያ በር አካባቢ ከባድ ጩኸትና ትርምስ ተፈጠረ፡፡ እነ ራኪን ጥያቸው
ወደ ትርምሱ ተጣደፍኩ፡፡ ባል ጨርቁን ጥሎ
👍31
ማበድ ነው የቀረው፡፡ የጥበቃ ሰራተኞቹ እና አስተናጋጆቹ ከበውታል፡፡ ጥቁር ሱፍ ኮቱን በንዴት መሬት ላይ ጥሎታል፤

“ሚስቴን ሚስቴን ማን ነው የወሰዳት? አረ ሚስቴን ምን ስለለብኝ?”

“ወንድም ተረጋጋ እንጂ! በንዴትና በጩኸት የሚሆን ነገር የለም፡፡ መጀመሪያ አእምሮህን አረጋጋ! ሽንት
ቤት ቼክ አድርገሀል?ተሳስታ የወንዶች ሽንት ቤት ገብታ እንዳይሆን፡፡”

የአስተናጋጆቹ ሃላፊም ሊያረጋጋው እየሞከረ ነው፡፡

ሰውዬ እንኳ ሽንት ቤት የቢራ ካሳ የሚቀመጥበት ዕቃ ቤት ፈልገናታል…የለችም፡፡» ሌላው የቤቱ ጋርድ
መለሰ፡፡

«ስልኳ ስዊችድ ኦፍ ነው የሚለው? እስኪ እንደገና ደውለው…ወይም ቁጥሯን ስጠኝ ለኔ»

«አትሰማም እንዴ ስልኳ ይጠራል ግን አይነሳም» ባል መለሰ፤

ምን አይነት ሰይጣን ነዉ የሰለባት ገና እኮ አዲስ ሙሽሮች ነን። ሰርጋችንን ከፈፀምን ሁለት ወር አልሞላንም
ሚስቴን ውለዱልኝ!! ምን ዋጣት ይባላል አሁን?

በሰውየው አጠቃላይ ሁኔታ ግራ የተጋባው ሄድ ዌተር ጥያቄ አቀረበ የኔ ወንድም እባክህ ለማንኛውም ተረጋጋ
ሞባይሏ ላይ ደውለህላታል”

ሊያውም ከ200 ጊዜ በላይ!!! <<ጥሪ አይቀበልም>> ነው የሚለው እያልኩህ።እባካችሁ እዚህ ህንፃ ላይ ሁሉንም ክፍሎች ፈትሹልኝ፡-

ምንድነው ተቀያይማቹ ነበር እንዴ? ምን አልባት አኩርፋ ወደ ቤቷ ሄደ ከሆነ ወሬ ለማየት ከመጡ ጠጪዎች ጎልማሳው ሰውዬ ጠየቀ፡፡

<<አረ አንዴም በከፉ ተያይተን እናውቅም አዲስ ሙሽሮች ነን ስልህ>> ባል ዋሸ

ባል እርዳታ ሲያጣ የስካር ቃና በተጫጫነው ድምጽ እዬዬውን አቀለጠው፡፡ የጥበቃ ሰራተኛው ጣልቃ
ገባ፡

"የኔ ወንድም የአምስት ዓመት ህጻን እኮ አይደለችም በየክፍሉ በባትሪ ብርሃን የምንፈልጋት! ቆይ ምን አይነት ልብስ ነበር የለበሰችው? መልኳን ግለፅልኝ ምን ትመስላለች?"

"ቀይ ረጅም ናት፡፡ በጣም ቆንጆ ናት፡፡ አሁን እኮ አብረን ነበርን፡፡ ያያት ሰው የለም? ረጅም ቀይ የእራት
ልብስ ለብሳ ነበር…በጣም ቆንጆ ናት…ቀይ ቆንጆ"

«በጣም ቆንጆ ናት» ሲል እንዳንዶቻችን አፋችንን እፍነን ሳቅን፡፡ሚስኪን!!

"አይተናታል አረ፡፡በጣም ሼፒ ናት፡፡ አሪፍ ዲነር ድሬስ ነው የለበሰችው፡፡» አለች “ኮድ ሶስት” የምትመስል
ልጅ፡፡ የጥበቃ ሰራተኛው ለረጅም ጊዜ ያህል የረሳውን ጉዳይ ያስታወሰ ያህል ገጽታው ተለዋወጠ ፤

እንደሰ! ቆይ ቆይ…ነጭ ረዥም የእራት ልብስ የለበሰችዋ ናት እንዴ?»

ባልየው ጉጉት ባፈነው ድምጽ «አዎ!»

ጥቁር የሚያብለጨልጭ ቦርሳ ይዛ ነበር…?

"አዎ"

«ስልከ ልታወራ ወጥታ ነበር?»

"አዎ…አዎ እሷ ናት…የት ናት ልክ ነህ እሷ ናት….አይተሀታል?» ባል በጉጉት ጠየቀ፡፡

«ኦ ታድያ እኳ እሷ ሄዳ የለ እንዴ!» አለ ጥርጣሬ ባዘለ ድምጽ፡፡ « “ሲዲ” ታርጋ ከተጻፈበት ቬዥ መኪና መኪና ውስጥ ስትገባ አይቼያታለሁ፡፡ ከዲፕሎማቱ ሰውዬ ጋር እየተሳሳቁ ነው የሄዱት፡፡ አብሯችሁ አልነበረም እንዴ ስውየው?

«ምን» ባል ጮኸ፡፡

ደግሞ መኪና ውስጥ እየተሳሳሙ ቆይተው እኮ ነው የተንቀሳቀሱት፡፡ሁለት ደቂቃ እኮ አይሞላም ወደ አብዬት መስመር ነው የነዳው…እንዴ…አሁን አሁን እኮ ነው…ብትሮጥ ሁሉ ትደርስበታለህ ጌታው፡፡

ባል በማመንና ባለማመን ዓለም ውስጥ በድንጋጤ ሆኖ ስካሩ ሲተን ይታያል፡፡ከገጽታው፣ከድንጋጤው እና ከህፍረት ስሜቱ መሬት ተሰንጥቃ እንድትውጠው የተመኘ ይመስላል፡፡ያ ሁሉ የስካር ስሜት
ከመቅጽበት ተነነ፡፡ ውለዱልኝ ያላት ሚስቱን እነቁልኝ ያለ ይመስላል፡፡ላዳ ታክሲ ይዞ እንዲከተለው ሰዎች ቢያበረታቱትም እሱ ማንንም የሚሰማ አይመስልም፡፡ ድንገት በዚያ ቁመቱ ዧ! ብሎ አስፋልቱ ላይ ተነጠፈ፡፡አስተናጋጆቹ ዉሀ ለማምጣት ወደ ዉስጥ ተራወጡ፡፡እንደዚያ ቀን ወንድ አሳዝኖኝ አያውቅም።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ እባካችሁ Like እና Share እያደረጋችሁ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት (🔞) ፡ ፡ ..ሁለት ጊዜ ተነስቶ ስልክ አናግሮ ሲመለስ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ስልክህን ልየው ማነው የሚደውልልህ ስትለው እሱ ሰጥያቄዋ ተበሳጭቶ ሲጨቃጨቁ ነበር፡፡ አሁን ስልክ ለማናገር ሲወጣ በልምምጥ ዓይን አነፈይቷት ነው የወጣው:: ሚስት በቅናት እየነደደች እንደሆነ እጠጣጧ ያስታውቃል። አሁንም ስልኩን ሊመልስ ሲወጣ ፊቷን እንደ ሀምሌ ዳመና ከስክሰዋለች፡፡ ባልዋ ላይ…»
#ነቃሁብሽ

እኔ ምንም የለኝ ከአንደበትሽ ጋራ
አምርሮ ቢዘልፈኝ ቅንጣትም አልፈራ
መደበቅ ቢያቅትሽ በአይኖችሽ ቋንቋ
መውደድሽ ደርሶኛል አታውሪልኝ
በቃ።
ጠብቄሽ ነበረ
ሲራክ
#ጠብቄሽ_ነበረ
.
ገጣሚ ደበበ ሰይፉ
አንባቢ ሲራክ @siraaq
Forwarded from አትሮኖስ (.) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ውበትሽ_ይበስላል

ውበትሽ ልዩ ነው ብዬ የነገርኩሽ
ውሸቴን አይደለም እንደው ልደልልሽ
እውነት ነው ልንገርሽ........
ልክ እንደ ግጥም ተጽፎ እንዳደረ
ልክ እንደ ዜማ ሲታሽ የተዋበ
ልክ እንደ ጥበብ ሲለቀም የኖረ
እያደር ይበስላል ውበትሽ ያበራል
ዛሬን ላስተዋለሽ የነገን ይጓጓል።
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ትምክህተኛው_ምሁር

(ቀንና ዓ.ም አልተገለጹም)

ከሌሊቱ 9:25 ሆኗል፡፡ሜሪ ባር እንደወትሮዋ በሰው ተጨናንቃለች፡፡ የቤቱ ሙቀትና አለቅጥ መታፈን
የተወሰኑ ወንዶችን ጃኬት አሰወልቋል።፡ከዲጀው ከፍል ለሳልሳ ዳንስ የሚጋብዝ ሞቅ ያለ ላቲንኛ ሙዚቃ ተለቋል።
ከፈሉ ወንድ መሀል ላይ የጋበዛትን ሴት ወገብ ይዞና እጇን እያዞረ በሙዚቃው ምት ሴቷን እንደእንዝርት ያሾራል፡፡ በዚህች ጠባብ ባር ሴትን እንደ እንዝርት ማዞር ጥበብ ይጠይቃል፡፡ እንኳን ሴትን
ማሾረሸ ይቅርና ከባለጌ ወንበር መውረድ ጥበብ ይጠይቃል፡፡ ከባለጌ ወንበር ወርዶ ሽንት ቤት ደርሶ መምጣት
ራሱ በሜሪ ባር ትልቅ ጥበብ ይጠይቃል፡፡ በዚህ አቅል በሚያስት ሞቅትና ትርምስ የአልኮል ሞቅታን
አልፈው ወደ ስካር እርከን የገቡት ጥቂት ወንዶች የሚጋብዟትን ሴት ጡትና ቂጥ
እያሻሹ የሁለትዮሽ ጨዋታ ይጫወታሉ፡፡

ኮትና ሱሪው የተለያየ ደማቅ ቀለም ያለው ሱፍ የለበሱ አዛውንት ከወደ ጥግ የማርታን ቂጥ ቸብ እያደረጉ
መቀባጠር ጀምረዋል፡፡ባለጌ ወንበሩ ላይ ለመቀመጥ በተደጋጋሚ ቢሞከሩም አልተሳካላቸውም ፡፡ እኚህ ሰው ቅሌታም ስለሆኑ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ አንተ እያልን እንጠራቸዋለን፡፡ ሽማግሌው ከእኩለሌሊት ጀምሮ አልኮል እያፈራረቀ ሲጠጣ ቆይቷል።ቮድካ፡ ጎርደን ጂን፡ኋይት ሆርስ_ደብል ደብሉን ሲልፈው
ነበር፡፡አሁን አልኮሉ ንፋስ እንደሚያውለበልበው አንሶላ ራሰ በራውን አዛውንት እያወዛወዘው ነው፡፡
የአይኑ አቀላል ያስፈራል።ጎርናና ድምጹ በስፒከሮች አልፎ የሚመጣውን ደምጽ አሸንፎ ለሜሪ ባር ታዳሚ በጉልህ ይሰማል፡፡ አንዳንድ ድምጽ አለ ለማሰማት ምንም የማይበግረው።

"ማነሽ ስምሸን ማን ነበር ያልሽኝ_አዎ ማርቲ ታውቂያለሽእኔ እኮ እዚህ አገር የመጀመሪያ ዲግሪ ብርቅ
በነበረበት ሰዓት ፒኤችዲዬን ከእንግሊዙ ኬምብሪጅ ዩኒቨርሲት ያገኘሁ ሰው ነኝ፡፡ያውም በዲሰቲንከሻን ነበር የጨረስኩት፡ትሰሚያለሽ እኔ አለማየሁ ባልኖር ድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩት የ75 ሰዎች ህልውና
አሁኑኑ ቀጥ ትላለች፡፡ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ይገባሻል? እያንዳንዱ ሰራተኛዬ በአማካይ 7 ሰዎችን በስሩ ያስተዳድራል ብንል እንኳ በትንሹ የ1225 ሰዎች ሮሮ በቀጥታም ይሆን በተዘዋዋሪ በኔ እጅ ናት ማለት ነው፡፡ የሚያሳዝነው ይቺ አገር የኔ አይነት ዕውቀት ያላቸውን ሰዎች አትንከባከበንም፡፡ ይህቺ አገር በንደኛ
አይነቱ በሳል ሰው መመራት ሲኖርባት ደንቆሮ ያሽከረከራታል። እድሏ ነው፡፡ ህዝቧም ደንቆሮ ይበዛዋል፡፡
ምን እየተካሄደ የምናውቅ እኔም ጨምሮ ጥቂት ነን፡፡ በጣት ብንቆጠር ነው፡፡ ይገባሻል ግን የማወራው »

ማርታ ከመስማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም::ፒኤችዲ እና ዲስቲንክሽን የሚሉት ቃላት የቦታ ስም ይሁኑ
የኮንዶም ስም በርግጠኝነት ማወቋንም እንጃ፡፡ በዚህ ቤት ውስጥ ከኔና ከዉባለም ዉጭ ኮሌጅ ገብቶ የወጣ
የለም፡፡ በሜሪ ቤት ትልቁ የትምህርት ደረጃ 12ኛ ከፍልን ያጠናቀቀ ነው፡፡ ማርታ ለምሳሌ የጅማዋን የፈርንጅ አራዳ ሰፈር ለቃ ወደ አዲስ አበባ የተሰደደችው የ5ተኛ ከፍል ትምህርቷን አቋርጣ ነው። ምን ታድርገው የሸርሙጥና ሙያዋ የማያገናኛት አይነት ሰው የለም፡፡አዛውንቱ ምሁር የሚናገረውን ባትረዳም በትኩረት ማድመጧ ለሰውየው ጡሩንባ በቂ ነው፡፡ካደረገችው ሀምራዊ ሚኒ ስከርት አናት አፈትልኮ የወጣው ቀይ ቢኪኒዋ አማላይ ቂጥዋን ለሁለት ከፍሎ የሜሪ ባር ወንድ የአይን ማረፊያ ሆናል።ከመቅጽበት የሀበሻ ወንድን የቅንዝር ስሜት የሚፈታተን ሞንዳላና አማላይ የሰውነት ቅርፅ አላት፡፡ ትምህርት ምን ይሰራላታል አሪፍ ቂጥ ካላት? ከማንም ተማረ ተመራመረ ከሚባል ዚጋ የተሻለ ገቢ
በቂጧ ምክንያት ታገኛለች፡፡ ቂጥና ጭንቅላት ተመሳሳይ ገቢ የሚያስገኙበት ዘመን ላይ ደርሰናል።
አብሯት ያለው ምሁር አዛውንትም ገና ሜሪ ባር እንደገባ የጠራት እንደማግኔት ወንዶችን በሚስበው አማላይ ቂጧ ተማርኮ እንጂ በጭንቅላቷ ተማርኮ አይደለም፡፡
ቤተልሔም ትስሚኛለሽ!

ስሜን ስንቴ ነው የምትረሳው?እኔ ማርታ ነኝ ተበሳጨችችበት፡፡ፐ

"oh! My apologies madam! ምን ላድርግ ብለሽ ነው…የኔ እውቀት ውቅያኖስ ነው፡፡ ተራ የሸርሙጣ ስም በመሸምደድ አእምሮዬ መጣበብ የለበትም፡፡ መቼስ በዚህ እነጋገሬ ቅር እንደማይልሽ ነው፡፡ ይህ ቦታ እኔን እንደማይመጥን አንቺም ታውቂዋለሽ፡፡ ስም ማስታወስን እውቀት ልለው አልችልም፡፡ ነገሩ እዚህ ቤት ያላችሁት አርባ ሃምሳ ሰዎች እውቀት ተደምሮ የኔን ጠብታ አይሆንም፡፡ ይሄንን ማንም መመስከር ይችላል፡፡ አገሪቱ እንደኔ እይነት ምሁር ያላት በቁጥር ነው፡፡ ይሄ ልብስ ለብሶ የሚወጣ ህዝብ በሙሉ
ደንቆሮ ነው፡፡ ገብቶሻል I am one in a millionyou should know that

ምሁሩ በአቅራቢያው የነበሩ ጠጪዎችን ብርቱ ግልምጫ ቢያስተናግደም ግድ አልነበረውም፡፡የተንቋረረ የስካር ድምጹ የሙዚቃውን ድምጽ ጥሶ ለሁሉም የመሰማት ልዩ ኃይል አለው፡፡

“ማነሽ .…ቤተልሔም…ኦህ ተሳሳትኩ መሰለኝ.….My apologies again hahaha….. …ማርታ ነው ያልሸኝ
ስምሸን? ለነገሩ ስምሽ ማንስ ይሁን ያው ሸሌ መሆንሽን ይፍቀዋል እንዴ ሃሃሃሃሃ! ለማንኛውም ዛሬ ከኔ ጋር ልታድሪ ነው፣ትልቅ ኩራት ሊሰማሽ ይገባል፡፡ይህን ሌሊት ልዩና ታሪካዊ ቀን እንደሆነ ጽፈሽ
ማስቀመጥ ይኖርብሻል፡፡ ለመሆኑ ዲያሪ የመያዝ ልምድ አለሽ? ለመሆኑ መጻፍና ማንበብ ትችያለሽ? ዛሬ ከኔ ጋር የምታሳልፊው ሌሊት፣ በቀሪ ህይወትሽ በኩራት ስታወሪውና ስታስታውሺው የምትኖሪው ሌሊት ነው፡፡ለማንኛውም አሁን ወደ ሆቴሌ እንሂድ! ተነሽ መኪናዬ ውስጥ ገብተሸ ጠብቂኝ…ከፍ ብሎ
ነጭ መርሴዲስ አለልሽ ጋቢናውን ከፍተሽ ቁጭ በይ…

ማርታ ባለችበት ደርቃ ታየዋለች፤

አዛውንቱ አንድ እጁን ኪሱ ከቶ ሌላኛው እጁን ምሁራዊ ትንታኔ እንደሚያቀርብ ሰው ያንቀሳቅሳል።
ግራ ቀን መወዛወዙን እላቆመም፡፡ ንፋስ እንደሚያወዛውዘው በረሀ ላይ እንዳለ ብቸኛ ዛፍ ወዲያ ወዲህ ይላል፡፡

"እ! ምን ሆኛለሁ ሂሳብ መክፈሉን ዘንግቼዋለሁ፡፡እስቲ አስተናጋጁ ቢል እንዲያመጣ ንገሪው"

አስተናጋጁ ደረሰኙን ቦርሳ መሃል አድርጎ ከባዶ ብርጭቆዎቹ አጠገብ አስቀመጠ።
ምሁሩ ደረሰኙን አንስቶ ተመለከተ

አንተ አሽከር...ና.. ወደዚህ እስኪ...627 ብር ቼክ ልፃፍልህ ወይስ በካሽ ልክፈልህ?
Nono better pay you in cash ሰባት መቶ ብር ስጠው
መልሱ በቶሎ ይምጣ፤ተራ ሰው ያስተናገድክ እንዳይመስልህ!»

አንዳንደሸ ሰው ሲጠጣ ጉራው ልክ የለውም፡

"ማነሽ...መኪና.. ውስጥ ግቢ ብዬሽ ነበር! ድንቁርና አለባችሁ….አትሰሚኝም ማለት ነው?

ቢዝነስ አልሰጠኸኝም እኮ»

እሱንም ረስቼዋለሁ፡፡ስንት ነው የምከፍልሽ?

"ስምንት መቶ ብር!

"ትክክለኛ ማንነቴን ብታውቂ እኮ ከፍለሽኝ ለመተኛት የምታስቸግሪኝ አይነት ሰው ነበርኩ፡፡ለማንኛውም
ሂሳብሽ ይኸው ማርቲ ብሩን ቆጥራ ተቀበለች፡፡
ምሁሩ በዚህ ድርጊቷ ባልተጠበቀ ሁኔታ ቱግ አለ፤

አየሽ ተራ ነሽ…ተራ…የሰው ተራ! ድሮስ ከሸርሙጣ ምን ይጠበቃል'ዶክተር አለማየሁ ሂሳብ ያሳስታል
ብለሽ ነው?አንቺ እንዲህ የህይወት ያህል የተስገበገብሽለትን ገንዘብ በእውቀቴ አምስት ደቂቃ ሥራ
እንደማገኘው ብታውቂ በሀፍረት እግሬ ላይ ወድቀሽ ይቅርታ በጠየቅሽኝ ነበር፡፡አልፈርድብሽም፡፡After all you are just a whorel»

ዶ/ር አለማየሁ ከአጠገቡ ንግግሩን የሰሙት ወንዶች ከፉ ግልምጫ አረፈበት፡፡ማርቲ የቁጣ ምላሽ አልሰጠችውም፤እንደ ጀማሪ
👍51
ሸሌዎችም የቢራ ጠርሙስ ጭንቅላቱ ላይ ለመስበር አልቃጣችም፡፡ቢያንስ ሁለት ወር
በሽርሙጥና ህይወት ለቆየች ሴት እንዲህ ያሉ ስድቦች እንደምርቃት የሚታዩ ናቸው፡፡ማርቲ በዚህ ሙያ
6 ዓመታትን አስቆጥራለች::ማርቲ በዚህ ዲፓርትመንት(Prostitution) የዶክትሬት ዲግሪ እንዳላት ምሁሩ
አልተረዳም፡፡ዱላ ሲበዛ ቀለብ ይሆናል የሚባለው በእንደዚህ አይነቱ አጋጣሚ ሳይሆን አይቀርም።

«የመውጫ 400 መቶ ብር ትጨምርልኛለህ? በጊዜ ለመውጣት ትንሽ ዋጋው ይወደዳል…”
« 400 መቶ ብር ነው ውድ?..በይ እንቺ ለኔ ለዶከተር አለማየሁ 400 መቶ ብር ማክያቶ አይገዛም።ገባሽ"ብሩን ቆጥሮ ሰጣት፡፡
እሺ ጠብቀኝ ዶከተር !የመውጪያ ቆርጬ፣ ቦርሳዬን ይዤ መጣሁ!

ለጥፋትሽ ይቅርታ መጠየቁ አይቀድምም?»

አንዳንድ ሰው ለራሱ ያለው ግምትና ከብር ያስገርማል፡፡እንዲህ ያለ ራስ ወዳድነትና ጉራ ያንገሸግሸኛል።
የምሁሩ ስኬትና እውቀት የቱን ያህልስ ቢሆን ለማርታ ምኗ ነው?ምሁር ተብዬው እንዴት ይሄን መረዳት ይሳነዋል?

"ካጠፋሁ ይቅርታ ዶክተር!"

ባለጌ ወንበሩ ላይ ታግሎ በመቀመጥ ማርታን መጠበቅ ጀመረ፡፡አዛውንቱ የአልኮል ዘር ሲጋት ማርቲ
ከአንዲት ስፕራይት ውጭ ምንም አልነካችም፤በምንም መልኩ አልኮል ከማይጋበዙ ጥቂት የሜሪ ባር
ሴቶች አንዷ ነች፡፡ዶ/ሩ በመጠጥ ብዛት የቀሉት እይኖቹን በመወርወር ክፍሉን መማተር ጀመረ፡፡ማርታ ልብሷን ቀይራና የጨዋ አለባበስ ለብሳ መጣች፡፡ምሁሩ አጠገብ ረዘም ላለ ቅጽበት ከቆመች በኋላ ሊለያት እንዳልቻለ ስተረጋግጥ ወደ ሩት ጆሮ ተጠጋች፡፡ለሩት አንዳች ነገር አንሾካሾከችላት፡፡

“ባክሸን ሩት ዛሬ ከዚህ ጉረኛ ሰውዬ ጋር ብተኛ ጸጸቱ አያኖረኝም፡፡ ልቀንጠስ!እንደዚያ ነው የሚሻለው፡፡
አቦሬውን ሲከፍትብኝ እንዲያድር አልፈልግም፡፡ቀን እኔ ቤት ነው የምንቅመው፡፡ምሳ፣በርጫና ሺሻ በኔ
ነው፡፡አሪፍ ብር ተቀቢዬዋለሁ፤ ቻው!!!

ማርቲ ወጣች፡፡

የሚካኤል በላይነህ ቆንጆ ዜማ ከዲጄው ክፍል ተለቋል፡፡የተወሰኑ ጠጪዎች ይደንሳሉ፡፡ሌሎች ሞቅ ያሉ
ሙዚቃዎች ተከተሉ፡፡ምሁሩ መጠበቅ ሰለቸው፡፡

“ማነህ!…አስተናግጅ!ያቺ ቤተልሔም የሚሏትን ልጅ ፍጠኚ በላት ቦርሳ ይዞ ለመምጣት እንዴት ይኸን ያህል
ጊዜ ይፈጅባታል? ደንቆሮ!»

«ጌታዬ! ቤተልሔም የምትባል ልጅ እዚህ ቤት የለችም…»
.
«ምን ይላል ይሄ! አሁን ከኔ ጋር ቁጭ ብላ ያየሃትን ሴት ትረሳለህ? እንተ ማሀይም»

«ጌታዬ፤ ማርታን ማለትዎ ነው? አብራዎ የነበረችው ማርታ ነበረች»

whatever! የት ተሰወረች»

የምሁሩን እያንዳንዷን ድርጊት ሲከታተሉ
የነበሩት ወንዶችና የማርቲ ጓደኞች በሳቅ ተንከተከቱ፡፡በተለይ ሩት ኤልሳና ቴሪ (ትርሲት) ሳቃቸውን መቆጣጠር ተስኗቸዋል፡፡አስተናጋጁ ሲያውቅም እንዳላወቀ ሆኖ "ቆይ እስቲ ውስጥ ልንገርልዎ" ብሎ ተንቀሳቀሰ፤

ሁለት፣ሦስት፣አራት ዘፈን ከዲጄው ክፍል ተለቀቀ አሁን የምሁሩ ትግስት ተሟጠጠ። ባንኮኒው አጠገብ ወዳሉት ሁለት አስተናጋጆች አመራ።

“ይቺ ማርታ የምትሏት ሴታችሁ ቦርሳ ይዤ ልምጣኔ ብላ እንደገባች ወደኔ አልተመለሰችም፡፡ወይ ጥሯት
ካልሆነም ገንዘቤን ትመልስልኝ"

ግዙፉ የቤቱ ቦዲጋርድ በንዴት ቱግ ብሏል፤

"አንተ ሰውዬ ምን ነክቶሀል?አጠገብህ ረዘም ላለ ጊዜ ቆይታ አይደለም እንዴ የወጣችው?» ምሁሩ ግራ
በመጋባት ስሜት የቤቱ ቦዲጋርድ ላይ አፈጠጠበት፤

ምናልከኝ አንተ እኔን ነው እንደዚህ ደፍረህ የምትናገረው? አታውቀኝም ማለት ነው? ዶከተር ዓለማየሁን
ሳታውቅ ነው እዚህ አገር መታወቂያ አውጥተህ የምትኖረው? ይቺ በደንቆሮ የምትመራ አገር

"ዶክተር እባክህ ችግር ውስጥ ራስህን አትከተት፣ የምትላት ሴት አብራህ ነበረች፣ ስትወጣ ተሰናብታህ ነው የወጣቸው"

"ስለየትኛዋ ማርታ ነው የምታወራኝ?የኔዋ ማርታ ሀምራዊ ሚኒስከርት ነው ያደረገችው ፡፡ጥራልኝ የምልህ
ያቺን ማርታ ነው አስተናጋጁ ሰከን ብሎ መናገር ጀመረ እዚህ ቤት አንድ ማርታ ነው ያለችው::ማርታ ያልከው አይነት ልብስ አድርጋ ነበር፡፡ግን ቦርሳ ይዛ
ልብሷን ቀይራ ረዘም ላለ ጊዜ ከፊት ለፊትህ ቆማ ነው የወጣችው፡፡ፊቷን እንዴት መለየት ያቅተሀል?ነው
ወይስ ስታይ የነበረው ቀይ ቢኪኒዋን እና ሀምራዊ ሚኒስከርቷን ብቻ ነበር? ዶክተር ሆነህ እንዴት እሷን ማየት ይሳንሀል»

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ዶክተሩ አንቱ ብሎ ሲጠራው የነበረው አስተናጋጅ አሁን በንቀት እንተ እያለ ነወሸ የሚጠራው፡፡ምሁሩ አሳት ለበሰ ደም ስሮቹ በጠይም ፊቱላይ ተገታተሩ፤
ትሰማኛለህ እንዳንተ አይነት መሀይም እንደዚህ ሊያሾፍብኝ አይችልም፡፡1200 ብሬን የማትመልሱልኝ ከሆነ ነገ የዚህ ባር
ባለቤትም ሆነ ማርታ ለሚደርስባቸው እንግልት ተጠያቂ አይደለሁም» ጋርዱ ሳቁ አመለጠው፡፡የምሁሩ ጠይም ፊት በብስጭት ቀላ፡፡መላው የሜሪ ባር ታዳሚ ንትርኩን በሙሉ በትኩረት እየተከታተለ ነው
“የዲጄው ከፍል ሙዙቃ ውዝግቡን ተከትሎ ተዘግቷል፡፡
ከሌላ አቅጣጫ የሰማይ ስባሪ የሚያከለው ሌላ የቤቱ ጋርድ ወደ ምሁሩ በብስጭት ተጠጋ ከመነሻው
አንስቶ በምሁሩ ድርጊት እንደተበሳጨ ሁለመናው ያሳብቃል፡፡

"ሰውዬ! ልታሰፈራራን አትሞክር። በአንድ ጥፊ ከመሬት ጋር እንዳላመሳስልህ፡፡ በደረሰብህ ነገር እጅግ ልታፍር ይገባል፡፡በቃ ለዛሬው ተገንትረሀል፡፡ከዚህ የበለጠ ውርደት ከፈለግክ ጆሮህን አንጠልጥዬ
እንደ ጅራፍ እጮህካለሁ፡፡ ካልሆነ ግን የቤቱን ሰላም እትበጥብጥ!ማርታን ነገ በጊዜ መጥተህ ማነጋገር ትችላለህ ተግባባንን

ጋርዱ ምኑሩን ከነ ኮቱ እና ከረባቱ አንገቱን በአንድ እጁ አንጠልጥሎት ነበር የሚያወራው:: የውርደት የሀፈርትና የፍርሀት ስሜቱ የምሁሩን ስካር ድራሻባቱ አጠፋበት
« ነገሩ በናንተ አልፈርድም፣ ይቺ በደንቆሮ የምትመራ አገር! ለማንኛውም ነገ ማንነቴን አሳያታለሁ. :
እቺ ሾላካ ሸርሙጣ በገዛ ገንዘቤ ታዋርደኝ!ካጠፋሁ ይቅርታ!» አለው አንጠልጥሎት ለነበረው ጋርድ፡፡

ምሁሩ የውርደት ማቁን እንደተከናነበ ሜሪ ባርን ለቆ ወደ ነጭ መርሴዲስ ፈንደድ ፈንደድ እያለ ተራመደ
መኪናው ጋር እስኪደርስ ድረስ የሜሪ ባር ሸሌዎች እየተቀባበሉ ሲያስካኩበት ይሰማው ነበር፡፡

በነገታው ምሽት ማርቲ ፔሬድ ስለነበረች አልገባችም ፡፡ እንኳንም አልገባች፡፡ እኛ የሰማነውን ዜና ብትሰማ ማዘኗ አይቀርም ነበር፡፡ ባለ ነጭ መርሴዲሱ ምሁር ትናንት ከሜሪ ባር ወደሆቴሉ እየነዳ ሳለ ከባህርዳር ጫት ይዞ ይገባ ከነበረ አይሱዙ ጋር ተላትሞ ሕይወቱ ማለፉን በአካባቢው ስኳር ድንች የሚሸጡ ልጆች
ነገሩን፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍6
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ #ትምክህተኛው_ምሁር (ቀንና ዓ.ም አልተገለጹም) ከሌሊቱ 9:25 ሆኗል፡፡ሜሪ ባር እንደወትሮዋ በሰው ተጨናንቃለች፡፡ የቤቱ ሙቀትና አለቅጥ መታፈን የተወሰኑ ወንዶችን ጃኬት አሰወልቋል።፡ከዲጀው ከፍል ለሳልሳ ዳንስ የሚጋብዝ ሞቅ ያለ ላቲንኛ ሙዚቃ ተለቋል። ከፈሉ ወንድ መሀል ላይ የጋበዛትን ሴት ወገብ ይዞና እጇን እያዞረ በሙዚቃው ምት ሴቷን እንደእንዝርት…»
#የሚሽጥ_ልብ

አልሰማ አለ ልቤ
አልሰማ አለ ቀልቤ
በግልጽ ብነግረው
የውስጥ ስሜቴን
ብቻነት መምረጤን
ለኔ እኔ መብቃቴን
ባስረዳው ጭንቀቴን
አሻፈረኝ አለ
አንድ ሰው እያለ
ሰዎች ምን ተሻለ....?
ብቻነት ከጠላ
ፍቅር ጀምር ካለ
ልብን የሚገዛ
አንድ ሰው የታለ?