አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እድሜዬን_ሰጠሁሽ

“ጊዜ ስጠኝ" እያልሽ

የሰጠሁሽ ጊዜ ከድሜዬ ጎደለ

ጊዜ ለጋሽ እኔ

ጊዜ አጥሮኝ ልሞት ነው አሁን ምን
ተሻለ?
-------------------------------------------
ምንም አይከፋኝም

ለስንት እያሰብኩሽ በድንገት መሄዴ

እድሜ እየገበሩ

መልስሽን መጠበቅ ውብ ነበረ ውዴ።
ደስታን ስፈልግ ነው.

ደስታዩ የራቀኝ፤

ፍቅርን ስሻ ነው..

ፍቅር የጠፋብኝ፤

ሰላምን ሳስስ ነው...

ሰላሜን ያጣሁት፤

ፍላጎቴን ስገድል..

ሁሉን አገኘሁት፡፡
••
#ቅድስትና_ትዕግስት


#በሕይወት_እምሻው


ቅድስት ልክ ስምንት ሰዕት ከሩብ ሲል ትዕግስት ቤት ደረሰች፡፡
“ውይ ቅድስትዬ...! ምነው እንዲህ ጠቋቆርሽ...? ፀሐይ እንኳን የለ ዛሬ..! አለች፣ ትዕግስት አራት ጊዜ ጉንጭዋን ስማት ስታበቃ....

“ኧረ ተይኝ ባክሽ....ለእንደኔ ያለ ሰው ከነዚያ ሴቶች ጋር ሦስት ሠዐት ሙሉ ስለ ልብስና ጫማ ማውራት ራሱ፣ ከሰባት ፀሐይ በላይ አያከስልም?” አለች ቅድስት፣ ሶፋው ላይ ዝርፍጥ ብላ እየተቀመጠች...

እናም፣ በተገናኙ ቁጥር የሚያደሩት ተመሳሳይ ወሬያቸው በእንዲህ ሁኔታ ተጀመረ፡፡

“አይ ለእኔ ነው ስለነሱ የምትነግሪኝ ቅድስትዬ? እኔስ ምናቸው
አስመርሮኝ ብረንች መምጣት ተውኩና!”

ደግ አደረግሽ... እኔ የምለው? ማስተርስ ድረስ የተማሩ ሴቶችከልብስና ከወንድ ውጪ ሌላ ነገር ማውራት አለመቻላቸው
አያሳዝንም? በጣም ያሳፍራል እኮ!”
በጣም እንጂ... ዐሥር ሴት ሚኒስትር ቢሾም ታች ያለነው ሴቶች

”ትላንት ስለገዛነው፣ ነገ ስለምንገዛው፣ ልንገዛ ፈልገን ስላጣነው ቶፕ ብቻ ምናወራ ከሆነ፣ ይህች ሀገር እንዴት ብላ ቀና ትላለች...? ሲንፏቀቁ መኖር እኮ ነው!”

“ጎሽ... እኔ እኮ አንቺ ጋር መምጣት የምወደው ለዚህ ነው...
ተንፈስ ስለምታደርጊኝ... ቁምነገር ስለምታዋሪኝ እኮ ነው አንቺ ጋር
መምጣት ደስ የሚለኝ ቲጂዬ!”

“እኔስ ብትይ....! እሺ..... ዛሬስ ምን ተፈጠረ ታዲያ?”

“ምን አዲስ ነገር ይፈጠራል... ያው ሴሞ ሴሞ ነው..ሃሚት ሃሜት... ወሬ... ሰው ቡጨቃ…. እይው የገዛሁትን ልብስ... ይሄ
ሽቶ ደስ አይልም...? እገሊት ጂም ጀመረች.. እንትና ዮጋ ጀመረች
ይሄው ነው ቲጂዬ!”

“አይገርመኝም...ዘለዓለም ያው ናቸው... ዘለዓለም.. ማፈሪያዎች!”
“እህስ!...ዛሬ ደግሞ ያቺ ሶሎሜ መጥታ ጭራሽ ስትጠብስኝ አረፈደች... ደህና ተገላግለናት ነበር፡፡”

“መጣች እንዴ? ዱባይ ቫኬሽን ላይ ነኝ ምናምን ብላ ስታናፋ አልነበረም እንዴ?”
“እንግዲህ ያ የግፍ ዶላር ቶሎ አልቆ ይሆናላ! ወር ሳይሞላት ተመለሰች!”

“አዬ! ለዚህችው ነው ያ ሁሉ ጉራ! ...ግን አንቺን ምን አርጋ አናደደችሽ ቅድስትዬ?”

አረ ተይኝ ገና በሥርዓት እንኳን ሳልቀመጥ እየሮጠች መጥታ ቶፕሽ ያምራል... እኔ የዛሬ ሁለት ዓመት በአራት መቶ ብር ገዝቼው ነበር...በቢጫው አለኝ... አሁን ግን ፋሽን ስላለፈበት ለሠራተኛዬ ስጠኋት' አትለኝም?"

“አታደርገውም!”

"አደረገችው እንጂ ትግስትዬ! አደረገችው!"

እና አንቺስ ዝም አልሻት?”

"ማ? እኔ ቅድስት እንዲህ ባደባባይ ሰድባኝ ዝም የምላት ይመስልሻል?"

“እና... እና ምናልሻት?”

የኔ እናት... ተማስሎብሽ ይሆናል... ይሄ ሌተስት ፋሽን ነው... የጣሊያን እቃ ነው! የገዛሁት ደግሞ አንድ ሺህ ስምንት
መቶ ብር ነው ... አልኳታ!”

'ወይኔ አንቺ... አንጀት አርስ እኮ ነሽ!"

“ታዲያስ...የሆነች ባላገር...ትላንት ብረንች ማለት አቅቷት፣
ብራንች የምትል ሴትዮ፤ አንዴ ዱባይ ሄጄ መጣሁ ብላ ትላጥብኛለች እንዴ?”

ሃሃ... አይ ቅድስት!”

ይልቅ እነሱን ተያቸውና ቲጂዬ የሚበላ ነገር አለሽ? ሁሉም ሰው ዳይት ላይ ነኝ ምናምን ብሎ ደህና ነገር አልበላሁም፡፡”

“ተይ እንጂ...! ዛሬም ዳይት ላይ ናቸው?”

“ታዲያስ! ለተቆራረጠ ሙዝ ሰማንያ ብር ይከፍላሉ... ዳይት ላይ ነኝ... መቀነስ አለብኝ ቅብጥርሶ ይላሉ፡፡ ምናለ ስለአንጎላቸው እንዲህ ቢጨነቁ......!”

“እኮ...! እና ታዲያ ምን ላምጣልሽ?"

“ሥጋ... ቅባት ያለው ነገር ምናምን... አታምጪብኝ! ትንሽ ጨምሬያለሁ ሰሞኑን ደግሞ...”

“ኧረ ተይ! ምንም አልጨመርሽም ቅድስትዬ! እንደውም ሳትከሺ አትቀሪም...”

“አይ ቲጂዬ...ቦዲ ሼፐር አርጌ ነው... ቦርጩን ጥፍንግ አድርጎ ስለያዘልኝ ነው...”

“ፓ! አሪፍ ነገር ነው ባክሽ... የት አገኘሽው? እኔ ፈልጌ ፈልጌ የሚሆነኝ አጣሁ...”

“መድኀኔ ዓለም ሞል ግራውንድ ፍሎር ላይ የሆነ ቤት አለ....
መዓት አላቸው... ዘጠኝ መቶ ብር ነው የገዛሁት... ብዙ አይመችም
ግን ቢያንስ ይሰበስብሻል... አብረን ሄደን ትገዣለሽ ሰሞኑን..."

“እሺ... አስታውሺኝ በቃ... ያስፈልገኛል.... በይ በቃ ሽሮ ላምጣልሽ
እንግዲህ....”

እሺ“ ቲጂዬ...”

ቅድስት የቀረበውን ሽሮ መብላት ጀመረች::

“ውይ ቲጂዬ! ሲጣፍጥ ግን ቅቤ ሞጀርሽበት”

“ሃሃ... ለዚያ እኮ ነው ሚጣፍጠው.."

“ልቀንስ እያልኩሽ ቅቤ ትግችኛለሽ አይደል... አንቺ ምን አለብሽ?”

“ብዪ ባክሽ... ከልኩ አያልፍም..."

“ምን? ቦርጭ?”

“አዎ....”

“ሃሃሃ!”

“ኧረ ቅድስትዬ ሳልነግርሽ... ዮጋ እኮ ጀመርኩ.... ቀጥ አላልኩብሽም ትንሽ?”

“ዮጋ?”

“አዎ... "

“ጎበዝ ነሽ ልጄ... እኔ አንዴ ከሰኒ ጋር ጀምሬ እናቴ... ሁለመናዬ ተላቀቀ፡፡ እሱን ለመጠገን አጥሚት እና መረቅ ስበላልሽ ነው ይሄን ቦርጭ እዚህ ያደረስኩት ቲጂዬ!”

ሃሃሃ... ቀልድሽ እኮ ደስ ሲለኝ ቅድስትዬ!”
አሹፊ አንቺ.... ይልቅ ማን በጣም እንደከሳ ገምቺ...”

እሌሊ..

ማ?

“እሌኒ እሌኒ? መርሻ?”

“እህ!”

“እንዴ? እንዴት አርጋ ከሳች በናትሽ?”

“ሙግግ ብላ መጣች ዛሬ... በሳምንት ሁለት ኪሎ እየቀነስኩ አሁን
ዓሥራ ሁለት ኪሎ ቀንሻለሁ አለችን...”

“ተይ ባክሽ... ያን ሁሉ ሰውነት እንዴት አድርጋ ናደችው በናትሽ?”

“የሆነ ቲቪ ላይ የሚታይ የዳይት ሾው አለ አሉ... እሱን አይቼ ሄጄ ነው አለችኝ...”

“ምን ቲቪ ላይ? እዚህ አገር?”

“አዎ...”

“እና ሄዳ ምን አደረጉላት?”

“ምግብ መጥነው ይሠሩልሻል አሉ... በወር አራት ሺህ ብር እከፍልና ምግቤን ይሠሩልኛል... አሽገው ቤቴ ድረስ አምጥተው ይሰጡኛል አለችኝ...”

“ተይ እንጂ... ምን ቲቪ ነው ልጄ?”

“ፋና መሰለኝ...”

“ለነገሩ እኔ እንዲህ ያለ ነገር ብዙም አይመቸኝ... ግን መቼ መቼ
ነው የሚታየው አለችሽ?”

“እንጃ... እሁድ መሰለኝ... ብቻ ምሳና እራት ዐስራ ሁለት መኮረኒ ተቆጥሮ ነው የሚሰጠኝ ብላ አሳቀችኝ!"

“ሃሃሃ... አትይኝም?”

“ሙች!”

“እና ግን አከሳት?”

በጣም... ምግቡ እህል ቅጠል አይልም፤ ግን ካከሳኝ ምን ቸገረኝ ምናምን አለችኝ...”

“ይገርማል... አምሮባታል በይኛ!”

“ያው መቼስ... ትንሽ ሙግግ ብላለች፣ ረኀብተኛ ነው የምትመስለው፤ ግን ቦርጭዋ ጠፍቶላታል፡፡ ለነገሩ ዛሬ ዕድሜ
ለብራዚል ሂውማን ሄር የማታምር ሴት አለች?”

“ልክ ነሽ እሱስ... ሂውማን ሄር ሴቱን ሁሉ እኩል አደረገው
እኮ.... ምን ዋጋ አለው... ጸጉር ጭንቅላት አይሆን!”

“እኮ!”

የሚገርመኝ ግን ብር ኖሯቸው እንኳን ደህናውን አይገዙም እኮ...
የኔን ዕይው አሁን ከጣልያን ነው ያስመጣሁት... ይኸው ሁለት
ዓመቱ ንቅንቅ አላለም... ከገዛሽ ደህና ነገር ነው... የሚልከሰከስ ሰው አልወድም እኔ...”

“እሺ... ሌላስ ምን አዲስ አለ ታዲያ!”

“ዝናሽም በስንት ጊዜዋ ዛሬ መጥታ ነበር!”

“ተይ እንጂ! እንዴት ናት?”

“አረጀችብኝ.... ጉስቁልቁል ብላለች... ያው እሷን ታውቂያታለሽ.በሜካፕ ኀይል ነው እንጂ እኮ ዕድሜዋ ሄዷል..."

“አዎ እሱስ... ምን ሜካፕ ብትለቀለቅ አንገቷ አሳልፎ ይሰጣት የለ...
ያ.. የአውራ ዶሮ ኩልኩልት የመሰለ አንገት..."

“አንቺ ተይ በስማም... ሃሃሃ!”

“ምን ላርግ ብለሽ ነው....? ደግሞ እኮ ሰው መልክ ባይኖረው ፀባይ
አይኖረውም?
👍1
ያ...ባሏ እንዴት ችሏት እንደሚኖር ነው የሚገርመኝ

እኔ...”

“ውይ! አልሰማሽም እንዴ?”

“ምኑን?”

“አልጋ ለይተዋል አሉ እኮ...”

“ተይ ተይ!”

“ሙች! ቆዩ እኮ... ለንብረት ብለው ነው የማይፋቱት ሲሉ ነበር..."

“ወይ ጉድ... የተጎሳቆለችው ለዚህ ነው በይኛ...."

“ይሆናል እንግዲህ...”

የሚገርመው ፌስ ቡክ ላይ ይሄን ሰልፊ ስትለጥፍ እኮ ነው የምትውለው....
ደህና ፊት እንዳለው ሰው... ለነገሩ ስልኳ
ሌተስት' ስለሆነ አሪፍ አርጎ ያነሳታል... በዐይን እስክታያት ቆንጆ ትመስላለች

ሃሃሃሃ...ስልክ ብትይ...አንቺ ግን እስካሁን አልቀየርሽም እንዴ
ይሄንን ስልክ? ዓመት አለፈው እኮ!”

“አዝዣለሁ ሆድዬ... ሰሞኑን ከካናዳ ይመጣልኛል."

“አይ ደግ አደረግሽ....!”

ቅድስት ሸሮውን ጥረግ አድርጋ በልታ ጨረሰችና እጆቿን ታጥባ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡

“ሽቶሽ ደስ ይላል ቅድስትዬ...” አለች ትዕግስት፣ እቃውን ቦታ ቦታ
አሲዛ ወደ ሳሎን ተመለሰችና አጠገቧ እየተቀመጠች፡፡

“ውይ... ሽቶሽ ብትይ ሳልነግርሽ... ያቺ ሕሊና ያረገችውን ዛሬ...”

“የእነዚህ ሴቶች ጉድ አያልቅ! እሷ ደግሞ ምናረገች በናትሽ....?”

ዋው... ሽቶሽ ደስ ይላል... ምንድነው ስሙ አትለኝም?”

እና ነገርሻት...?”

ደህና ዴኦዶራንት ተቀብታ የማታውቅ ዝተታም የአራት ሺህ ስድስት መቶ ብር ሽቶ ስትመኝ አይገርምሽም? እኔማ ምን አለብኝ

ከነዋጋው ነገርኳት.... ያ አመዳም ፊቷ የበለጠ አመድ መሰለ ...

ሃሃሃ”

“ሃሂ... በጣም ያሳዝናል ብቻ የእነሱ ነገር... ስንት የሚያስጨንቅ ነገር እያለ.. ሃገር እየታመሰች ወሬያቸው ሽቶ..ቅባት.ልብስ ሃሜት... ወንድ... ያሳዝናል በጣም.... መማር ምን ጥቅም አለው

ግን?”

“ምንም!”

ጥቂት ቆይቶ ቅድስት መሄድ እንዳለባት ተናገረችና ተነሳች፡፡

“በቃ ልሂድ ቲጂዬ! የማታው እራት ላይ አለሽ አይደል?” አለቻት እንደቆመች፡፡

“አለሁ ቅድስትዬ...”

“ዋ እንዳትቀሪ... አንቺ ስለምትመጪ ነው የምመጣው ... ከነዚያ ሴቶች ጋር ትርኪምርኪ ማውራት አልችልም... አደራሽን እንዳትቀሪ”

“አልቀርም ቅድስትዬ...”

“ጎሽ... በይ ልሂድና ልበጃጅ...”

“ምን ልትለብሺ አሰብሽ ዛሬ?”

“የሆነ ጥቁር ሌስ ቀሚስ ገዝቻለሁ... አንቺስ?”

“እኔ እንኳን አልወሰንኩም፡፡”

“ጸጉርሽንስ? አትሠሪም?”

“አይ ፍሪዝ ላረገው ነው ባክሽ...”

ለነገሩ ያንቺ ጸጉር በፍሪዝ ያምራል..."

“ታንኪው ሆዴ... በይ ልሂድ...”

“ቻው የኔ ቆንጆ...

እሙጳ.. እሙጿ፡፡ እሙጳ....

እኔ የምልሽ ቲጂዬ...?”

“ወዬ ቅድስትዬ...."

“አንቺ ጋር ስመጣ እኮ ነው አንጎል ያለኝ አንጎል የሚመስለኝ...”

“እኔስ ብትዩ!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካምቀን። 🙏
1👍1
አትሮኖስ pinned «#ቅድስትና_ትዕግስት ፡ ፡ #በሕይወት_እምሻው ፡ ፡ ቅድስት ልክ ስምንት ሰዕት ከሩብ ሲል ትዕግስት ቤት ደረሰች፡፡ “ውይ ቅድስትዬ...! ምነው እንዲህ ጠቋቆርሽ...? ፀሐይ እንኳን የለ ዛሬ..! አለች፣ ትዕግስት አራት ጊዜ ጉንጭዋን ስማት ስታበቃ.... “ኧረ ተይኝ ባክሽ....ለእንደኔ ያለ ሰው ከነዚያ ሴቶች ጋር ሦስት ሠዐት ሙሉ ስለ ልብስና ጫማ ማውራት ራሱ፣ ከሰባት ፀሐይ በላይ አያከስልም?”…»
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_አስራ_ሁለት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#አዲስ_መንገድ


#የነጻነት_ሕመም

የምሽቱ ድባብ የማልቆጣጠረው ስሜት አሳደረብኝ፡፡ የአየሩ ቅዝቃዜ ቆዳዬን ሲነካው፣ ለሳንባዎቼ አየሩ ሲቀላቸው፣ በዓይኔ ላይ የሚጨፍሩት እልፍ አዕላፍ ክዋክብት በውበታቸው ሲያፈዙኝ ነፍሴን ‹‹ተመስገን አምላኬ!›› ብላ እንድትዘምር አደረጓት፡፡
‹‹ምን ላይ ነው ያፈጠጥሺው? እንሂድ እንጂ - በአስቸኳይ መሄድ
አለብን!›› ሲሉ የመጀመሪያዋን የነጻነት መጠጥ እንደተጎነጨሁ ቄስ ሙሪንዚ ትዕግሥት አጥተው ሾር ብዬ እንድሄድ ተናገሩ፡፡ ቄሱ ከሌሎቹ ሴቶችና ወደ ፈረንሳዮች ምሽግ አብሮን ሊሄድ ከተነሣው ከዮሃንስ ጋር በሩ ጋ ይጠብቁናል፡፡ ዮሃንስ በጣም አረፈደ እንጂ መባነኑና እፊት እፊት ማለቱ ባልከፋ፡፡ በዚህ ጊዜ ከዘር ጭፍጨፋው መትረፌንም ሆነ ንጋትን እንደገና ለማየት መቻሌን አላወቅሁም - የግንኙነታችንም መሞት አልታወቀኝ፡፡ ቄሱ በራቸውን ሲከፍቱት ከቤት ወንድ ልጆቻቸው (ከሴምቤባ በስተቀር) ጦሮች፣ ቢላዎችና ቀስቶች ይዘው ወጡ፡፡ ዙሪያችንን በሚገባ ከበው በሩን አስወጡን፡፡ ከጠርጣራ ወንድ የቤት ሠራተኞቻቸውና ክፉ ጎረቤቶቻቸው አደገኛ ዓይኖች ከለሉን፡፡ ከዚያም ወደ ውጪ ወጣንና ወደ መታጠቢያ ቤቱ ከሦስት ወራት በፊት ባመጣኝ በአቧራማው የእግር መንገድ በፍጥነት ተራመድን፡፡ ዓይኖቼ ጨለማውን እየተላመዱት ሲሄዱም ቄስ ሙሪንዚም ሆኑ ዮሃንስ እንደታጠቁ አየሁ፤ ዮሃንስ ረጅም ጦር የያዘ ሲሆን ቄሱ በበኩላቸው ጠመንጃቸውን በትከሻቸው አንግተዋል፡፡ የገዳዮች ቡድን መንገዳችን ላይ ቢያጋጥመን ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ አሰብኩ፡፡ ሰዎች በመንገዱ ሌላኛው አቅጣጫ ከጨለማው ውስጥ ብቅ ሲሉ በድንገት አየናቸው፡፡ ምን አልባትም 60 የሚሆኑ ኢንተርሃምዌዎች በሁለት መስመሮች በሰልፍ ይመጣሉ፡፡ አስፈሪ የደንብ ልብሶቻቸውን ያልለበሱ ቢሆንም ቅሉ ትዕይንቱ ያስበረግጋል፡- እስካፍንጫቸው ታጥቀው በፍጥነት ይጓዛሉ፤ ገጀራዎችን፣ ጠመንጃዎችን፣ ቦንቦችን፣ ጦሮችንና ረጃጅም ማረጃ ቢላዎቻቸውን ይዘው ወደ እኛ በመጠጋት ላይ ናቸው - አንደኛው እንዲያውም ቀስት ይዟል፡፡በአጠገባቸው በጣም ተጠግተን ስለሄድን እንዲያውም የሰውነታቸውን ጠረንና ከትንፋሻቸው የሚመጣውን የሚተናፈግ አልኮል ሳይቀር ማሽተት ችያለሁ፡፡ በሚገርም ሁኔታ በመታጠቢያ ቤቱ ከእነርሱ ተደብቄ ከነበርኩበት ጊዜ ይልቅ በአጠገባቸው ሳልፍ በአንጻራዊነት ፍርሃቴ ቀንሷል፡፡ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን በደኅና እንዲያቆየንና ፍራቻዬን እንዲያረግብልኝ ለመንኩት፡፡
ሌሎቹ ሴቶችና እኔ ኢንተርሃምዌዎቹ ሴቶች መሆናችንን እንዳይለዩ በማለት በቡድን አጀባችን መካከል ራሳችንን ዝቅ አደረግን፡፡ ያለ ምንም ችግርም አለፍን፡፡ እንዲያውም የተወሰኑት ገዳዮች ሰላምታ አቀረቡልን፤ ሲያልፉም ለዮሃንስና ለቄሱ መልካም ዕድል ተመኙላቸው፡፡ አንድም እኛን ሌሊት ድረስ ቆይተን እያደንን ያለን ገዳዮች አድርገው አስበውናል አለያም አምላክ ዓይናቸውን አሳውሯቸዋል … ሁለቱም ምክንያት እንደሆነ አሰብኩ፡፡ በተጨማሪም አሁን ባለው የዘር ፍጅቱ ደረጃ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ቱትሲዎች በአንድ ቦታ በሕይወት ይኖራሉ ብለው አልጠበቁም፤ ወይንም አላመኑም፡፡ በየመንገዱ አስከሬኖች ስለወደቁ እንደዚያ ብለው ለማመን ጥሩ ምክንያት ነበራቸው፡፡
አምላክ ለጸሎቴ ምላሽ ሰጠኝ፡፡ ለገዳዮቹ ያለኝንም ፍራቻ አሽቀንጥሮ ጣለልኝ፡፡ ግን ከሁኔታው ሳየው ጌታ ለቄስ ሙሪንዚና ለዮሃንስ ተመሳሳይ በረከት ያጋራቸው አይመስልም፡፡ ኢንተርሃምዌዎችን በማግኘታችን ሁለቱም ተደናግጠዋል፡፡ ዮሃንስና ቄስ ሙሪንዚ ገዳዮቹ ከእይታችን እንደተሰወሩ የገቡበትን ጣጣ እንደገና አጤኑት፡፡ ቄሱ ‹‹እናንተ ሴቶች ከዚህ በኋላ ብቻችሁን ሂዱ›› አሉን፡፡ ‹‹ፈረንሳውያኑ ከዚህ ቅርብ ናቸው… ሂዱ ቀጥሉ፤ ከእይታችን እስክትሰወሩ እናያችኋለን፡፡›› ቄሱና እኔ በፍጥነት ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ እርሳቸው፣ ወንዶች ልጆቻቸውና ዮሃንስ ከመንገዱ ወደ ጥሻ ውስጥ ለመደበቅ በችኮላ ሄዱ፡፡ ያኔ ሌሎቹ ሴቶችና እኔ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ቦታ ላይ ስለሆንን የምናባክነው ምንም ዓይነት ጊዜ አልነበረንም፡፡ የፈረንሳውያኑ ምሽግ 500 እርምጃዎች ገደማ ይርቃል፤ ስለሆነም እግሮቻችን በቻሉት መጠን በፍጥነት ተጓዝን፡፡
የተተወ የወንጌላውያን ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በተቋቋመው ምሽግ ጋ ስንደርስ ልቤ ድው ድው ይል ጀመር፡፡ የተቀረው ቡድን ከዋናው በር ፊት ለፊት በጣም ፈርቶ ተመስጎ ሳለ እኔ በቻልኩት መጠን በሩን እደበድብና በጣም ጮኬ
‹‹እባካችሁ እርዱን! እባካችሁ እገዛችሁን እንፈልጋለን!›› እል ጀመር፡፡ ከሹክሹክታ በላይ ከተናገርኩ በጣም ረጅም ጊዜ ስለሆነኝ ለመጮህ ካደረግሁት ጥረት የተነሣ ጉሮሮዬን አመመኝ፡፡ ድምጼ የታፈነና በጣም ዝግ ያለ ስለሆነ አይሰማም ለማለት ይቻላል፡፡ ሊያድነን የሚጠብቀን ማንም ሰው ሳናገኝ ስንቀር ሴቶቹ በፍርሃት ራዱ፤ ለቅሶና እዬዬም ጀመሩ፡፡ ከአፍታ በኋላ ስድስት ወይም ሰባት ወታደሮች መትረየሶቻቸውን ወደ እኛ ደግነው በአጥሩ በአንደኛው አቅጣጫ ብቅ አሉ፡፡ ፈረንሳይኛ የምናገረው እኔ ብቻ ስለሆንኩ ባልንጀሮቼን ዝም አስባልኩና ለወታደሮቹ ስለማንነታችንና ስለአመጣጣችን ነገርኳቸው፡፡
ወታደሮቹም በጥርጣሬ ተመለከቱን፣ ጠመንጃዎቻቸውንም እንዳቀባበሉ ናቸው፡፡ ‹‹እውነት ነው! የነገርኳችሁ ሁሉ እውነት ነው… ታድኑን ዘንድ እናንተን ስንጠብቅ ቆይተናል›› አልኳቸው በተስፋ መቁረጥ፡፡
በቡድኑ ውስጥ ካሉት ወታደሮች ትንሹ፣ ኮስታራው፣ መልኩ ፈገግ ያለውና ጸጉሩን የተላጨው ሰውዬ ወደ ዋናው በር መጥቶ በፊታችን ላይ ባትሪ አበራብን፡፡ የአፍንጮቻችንን ቅርጽ እየተመለከተ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ነባሩ አስተሳሰብ ሁቱዎች ደፍጣጣ ቱትሲዎች ደግሞ ሰልካካ አፍንጫ አላቸው የሚል ነው፡፡ ስለሆነም ፈተናውን አልፈን ሳይሆን አይቀርም በሩን ከፍቶ አስገባን፡፡ ይሁን እንጂ መታወቂያ ደብተሮቻችንን ለማየት ሲጠይቀንም መሣሪያውን እንደደገነ ነው፡፡ሴቶቹ በኃይል ሲተነፍሱ ይሰማኛል - ማናቸውም ቢሆኑ መታወቂያዎቻቸውን አልያዙም፡፡ በዚህም ምክንያት ፈረንሳውያኑ እዚያው የሚረሽኗቸው መስሏቸዋል፡፡ ደግነቱ በኔ በኩል መታወቂያዬን ከሦስት ወር በፊት ቤቴን ለቅቄ ስወጣ በኋላ ኪሴ ይዤዋለሁ፡፡ ወታደሩ ቱትሲ የሚል ቃል ከዳር እስከዳር የታተመበትን የኔን መታወቂያ አይቶ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ፡፡ ወዲያውኑ ለሌሎቹ ሴቶች በእርግጠኝነት
‹‹ምንም የምንሆን አይመስለኝም›› ስል አረጋገጥኩላቸው፡፡
ለወራት የታመቀ ፍራቻ፣ ብስጭትና ሥጋት ከነፍሳችን ወንዝ ፈሰሰ፤ በውስጣችን ያለው የስሜት ግድብ ፈረሰ፤ የተወሰኑት ሴቶች ሊቆጣጠሩት በማይችሉት መልኩ አለቀሱ፡፡ የወታደሮቹም አቀራረብ ከዚያ በኋላ ተቀየረ - ድምጻቸው በደግነትና በያገባኛል ስሜት ተሞልቶ ጠመንጃዎቻቸውን ዝቅ አድርገው በሐዘኔታ ያነጋገሩን ጀመር፡፡ በወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየነው የታሸገ ውሃና አይብ ተሰጠን፡፡ ቄሱ እንደገመቱት ፈረንሳውያኑ እንደማይገድሉን አውቀን በጣም ሰፍ ብለን መጉረስ ጀመርን፡፡
‹‹አይዟችሁ ምንም ችግር የለም›› አለ ትንሹ ወታደር፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ቅንጣት ታክል ልትጨነቁ አይገባችሁም … ቅዠታችሁ አክትሟል፡፡ ማንም ሰው እንዲጎዳችሁ አንፈቅድም፡፡ ገባችሁ? ምንም ሥጋት አይግባችሁ፤
👍2
እንንከባከባችኋለን። ለሌሎቹ ተረጎምኩላቸው፤ ወዲያውኑም ሁላችንም እናለቅስ ገባን፡፡ ሁሉ ነገር አብቅቶለታል የሚለው ነገር ግን እውነት አይመስልም፡፡ ለማንኛውም ገዳዮቹ ከእንግዲህ ወደ እኛ እንዳይቀርቡ እንደሚያደርጉ ቃል እየገቡልን ባሉ ትልልቅ መሣሪያ በያዙ የሠለጠኑ ወታደሮች ተከበናል፡፡
ስንረጋጋ አዳኞቻችን ያለነው በጊዜያዊ የመስክ ማቆያ ውስጥ እንደሆነና በመገናኛ ተደዋውለው የጭነት ተሸከርካሪ አስመጥተው በአሥራ ስድስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ዋና ምሽጋቸው እንደምንወሰድ አብራሩልን፡፡ ተሸከርካሪው
እስኪመጣም ትንሽ ማንቀላፋት እንዳለብን ነገሩን፡፡
ከሌሎቹ ተለይቼ ሄድ ብዬ ለረጅም ጊዜ አጥቼው የነበረውን ነገር ሳጣጥም ቆየሁ - አንድ አፍታ ብቻዬን መሆንን፡፡ መሬቱ ላይ ተኝቼ በዙሪያዬ ካለው ከሁሉም ነገር ጋር እነካካ ጀመር - አለቶቹ ጀርባዬን እየወጉት፣ ጣቶቼ እርጥቡን መሬት ነክተው፣ ደረቆቹ ቅጠሎች ጉንጬን እየወጋጉት፣ በጨለማ የሚዘዋወሩት እንስሳት ድምፅ እየተሰማኝ፡፡ አቤት! በሕይወት መትረፌ ይገርማል፡፡
እንደገና በምሽቱ ሰማይ ላይ አፍጥጬ የጌታ ፍጥረት በሆኑት እልቆ መሳፍርት የሌላቸው ክዋክብት ወተት መሰል ድምቀትና አስደማሚ ውበት ተመሰጥኩ፡፡ ጉልሁ የክዋክብቱ ብርሃን የመጣንበትንና ወደ ቤቴ የሚወስደውን መንገድ ማየት አስቻለኝ - ጭራሽ ቤት ካለኝ፡፡ የቤተሰቤ አባላት በደኅና የሆነ ቦታ ተደብቀው ይሆን? ብዬ አሰብኩ፡፡ ወይስ ወደ ቀጣዩ ሕይወት ሄደው ከእኔ በላይ ባለው ዘለዓለማዊ አጽናፈዓለም በሌላኛው አቅጣጫ የሆነ ቦታ ይሆኑ?
አትኩሮቴን እንደገና ወደ መንገዱ መለስኩ፡፡ ወንድሞቼና እኔ ይህን መንገድ ተከትለን እንዴት ወደ ፈለግነው ስፍራ እንሄድ እንደነበር አሰብኩ፡፡ በልጅነታችን ጠዋት ወደ ኪቩ ለመዋኘት፣ ወደ ትምህርት ቤት፣ እሁድ ወደ ቤተክርስቲያን፣ ጓደኞቼንና ዘመዶቼን ለመጠየቅ፣ በክረምት እረፍት አስደናቂ ተግባራትን ወደ ምንፈጽምበት ስፍራ ለማምራት ብቻ ይህ መንገድ ወደምወደው ቦታ ሁሉ ያስኬደኝ ነበር፡፡ በሕይወቴ ሁሉ መንገዱ ተመላልሷል፤ ሆኖም ያ ሕይወት አልፏል፡፡ መንገዱ አሁን የገዳዮችና የአስገድዶ ደፋሪዎች መፈንጫ ሆኗል፡፡ በመጭዎቹ ሰዓታትም ሆነ ቀናት ውስጥ ምንም ይከሰት ምን ነገሮች እንደነበሩት እንደማይቀጥሉ ቀስ በቀስ ሲገለጥልኝ በጥልቅ ብስጭት ውስጥ ገባሁ፡፡ ዓይኖቼን ጨፍኜ
ለእግዚአብሔር አዲስ የምሄድበት መንገድ የመፈለጉ ሥራ የእርሱ እንደሆነ ነገርኩት፡፡

ተንቀጠቀጥኩ፡፡ ቀዝቃዛው አየር ቆዳዬን እንዲያሸበሽብ ሲያደርገው ከዚያን ጊዜ በኋላ በተጨናነቀውና በትንፋግ በተሞላው መታጠቢያ ቤት ውስጥ እንዳልሆንኩ አስታወሰኝ፡፡ በጨለማው የተቀመጡ ሁለት ወንዶችን ድንገት እንኳን ሳገኝ በፍጹም አልፈራሁም፡፡
አንደኛው በድንጋጤ ድንገት ቀጥ ብሎ ቆሞ ከአፍታ በኋላ ‹‹ኢማኪዩሌ ነሽ?›› አለኝ፡፡
‹‹ዢን ፖል?››
‹‹እንዴት በሕይወት ልትተርፊ ቻልሽ?››
‹‹አምላክ አተረፈኝ፡፡ አንተስ እንዴት ተረፍክ?››
‹‹አምላክ አተረፈኝ፡፡››
‹‹እንኳን አየሁህ!›› ‹‹እንኳን አየሁሽ!››
በንግግራችን አስቂኝ አካሄድና እንደገና ከጓደኛ ጋር ጮክ ብሎ ማውራት እንዴት አስቂኝና አስደናቂ ነገር እንደሆነ ሳስበው ልስቅ ቃጣኝ፡፡ ዢን ፖል የወንድሞቼ ጥሩ ጓደኛ ነው፡፡
‹‹ጤና ይስጥልኝ ዢን ባፕቲስት፤ እንኳንም አገኘሁህ›› አልኩት ለተቀመጠው የዢን ፖል ወንድም፡፡ ጅን ባፕቲስት አልመለሰልኝም፡፡ የዚህንም ምክንያት ያየሁት በርከክ ብዬ እጁን በሰላምታ ስጨብጠው ነው፡፡ በልብሱ ውስጥ ድብቅ የሚል አንድ የጣት አንጓ ያህል ርዝመት ያለው የጠገገ ቁስል በአንገቱ ላይ አለበት፡፡ ቁስሉም የተቆጣ፣ ነጣ ያለ ቀለም ያለውና ከጥቁር የቆዳ ቀለሙ ጋር ያለው ተቃርኖ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነው፡፡ በራሱም ላይ ትልቅ ጠባሳ ይታያል፡፡ ገመምተኛ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ እንደዚያ ተመትቶ እንዴት እንደተረፈም ገረመኝ፡፡
‹‹አሁን ብዙም አይናገርም… በጣም አዝኗል›› አለ ዢን ፖል በቀስታ፡፡ ዢን ፖል ራሱ ሰቀቀኑ በጣም የሚታይበት ቢሆንም ተቀምጠን አንዳንድ ወሬ አወራን፡፡ የት እንዳሳለፍኩና በቄሱ ቤት የነበረኝን ጊዜ ገለጽኩለት፡፡ እርሱም በሰሜን ዘር ማጥፋቱ በመጠኑ እንደቆመና ኪጋሊም በአማጽያኑ ቁጥጥር ስር እንደዋለች፣ እኛ የነበርንበት የኪቡዬ ግዛት ግን እስከዚያን ጊዜ ድረስ የአደጋ ቀጣና እንደሆነ አወጋኝ፡፡
‹‹ኪጋሊ ተያዘች?›› ስል ጠየቅሁት ተደናግጬና ተደስቼ፡፡
‹‹አዎ፣ አሁንም ቢሆን ግን ብዙ ግድያ አለ›› ሲል መለሰልኝ፡፡ ‹‹በእርግጥ እዚህ አካባቢ ከበፊቱ እንዲያውም መጥፎ ነው፡፡ ጦርነቱ በጣም እየከፋባቸው ሲመጣ እነርሱም እጅግ እየባሰባቸው መጣ፡፡ ተደናግጠዋል፡፡ በጣም ብዙ ቱትሲዎችን ስላረዱ አሁን ተጨማሪ የሚገደል ማግኘት አልተቻላቸውም፡፡
‹‹ዢን ፖልንና ወንድሙን በምሽጉ ውስጥ በማየቴ ተገርሜያለሁ፤ ምክንያቱም ሁቱ ይመስለኝ ስለነበር፡፡ በጣም ጥቁሮች፣ አጠር ያሉና አፍንጫቸው ድፍጥጥ ያሉ ናቸው - በአውሮፓውያን አስተያየት ትክክለኛው የሁቱ ገጽታ፡፡ ለብዙ ትውልዶች የተካሄዱ የእርስ በርስ ጋብቻዎች ሃሳቡን ያረጀ ያፈጀና ባያሌው በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ስላደረጉት ከአሁን በኋላ ምንም ትክክለኝነት የለውም፡፡ ግን ዢን ፖል ሲያብራራ ሁቱ መምሰላቸው በሕይወት የመኖራቸው አንዱ ምክንያት መሆኑን ይናገራል፡፡ ‹‹ያ … እና የአንድ ገዳይ ደግነት›› አለ በቤተሰቡ ላይ የሆነውን ከመናገሩ በፊት፡፡
‹‹ገዳዮቹ የርዕሰ-ብሔሩ ጠያራ ከተመታ ከሳምንት በኋላ መጡ፡፡ ከኛ ጥቂት ቤቶችን አለፍ ብሎ የሚኖረውን ሁቱውን ጓደኛዬን ሎሬንትን ልጠይቅ ሄጄ በወላጆቼ ቤት መድረሳቸውን ሰማሁ፡፡ ሦስት መቶ የሚሆኑ ገዳዮችን አየሁ - አብዛኞቹ ጎረቤቶቻችንና ወዳጆቻችን ናቸው፡፡ የፊተኛውን በር ሰብረው ገብተው ሁሉንም ሰው ከታተፉት - ወንድሞቼን፣ አራቱን እህቶቼን፣ እናቴንና አባቴን፡፡ ሁሉንም ገደሉ … ቢያንስ የገደሉ መሰላቸው፡፡ የዢን ባፕቲስት ሕይወት ግን አልጠፋችም ነበር - ቢሆንም ታዲያ በእጅጉ እየደማ ቆየ፡፡
‹‹ብዙ ኪሎሜትር ርቀት ጎትቼ በጥሻው ውስጥ ሰው ወደማያውቀን ሐኪም ቤት ወሰድኩት፡፡ ከዚያ በኋላ ሎሬንት ፈረንሳዮቹ እስኪደርሱ ድረስ ቢደብቀንም ሁኔታው ያሰቅቃል፡፡ ደብቆ ቢያድነንም ግን በሕይወት መቆየቱ ሥቃይ ሆነብን፡፡ ሎሬንት በየቀኑ ጠዋት እንዴት አደራችሁ ለማለት ይቀሰቅሰናል፤ ከዚያም የቤተሰቤን አባላት ከገደሉት ሰዎች ጋር ቱትሲዎችን እያደነ ሲገድል ይውላል፡፡ አጥቦ ሊያስወግዳቸው የማይችላቸውን የደም ፍንጣቂዎች ማታ ሲመጣና እራት ሲሠራ በእጆቹና ልብሶቹ ላይ አያለሁ፡፡ ሕይወታችን በእጁ ላይ ስለነበር ምንም ማለት አንችልም፡፡ ሰዎች በአንዴ ጥሩም መጥፎም ነገር መፈጸም እንዴት እንደሚቻላቸው ሊገባኝ አይችልም›› አለኝ፡፡
‹‹የዘር ጭፍጨፋው እየተፈጸመ ያለው በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፣ ዢን ፖል›› አልኩት፡፡ ‹‹ገዳዮቹ ጥሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ግን አሁን ርኩሰት ልባቸውን ተቆጣጥሮታል፡፡››
ለዢን ፖል ለቤተሰቡ አባላት እንደምጸልይላቸው ነገርኩት፡፡ ከዚያም በዘር ጭፍጨፋው ጊዜ በአካባቢያችን ስላሳለፈ በወላጆቼ ላይ የተከሰተውን ነገር ማወቁ እንደማይቀር ተገለጸልኝ፡፡ ጥያቄው እኔ ራሴ በእነርሱ ላይ የተከሰተውን ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ ወይ? የሚለው ነው፡፡
👍1
ለመቀበልስ ጥንካሬው አለኝ ወይ? በእርግጠኝነት መሞታቸውን ካወቅሁ ወደ በፊቱ ማንነቴና ሕይወቴ መመለስ የሚባል ነገር አይኖርም
እውነታውን መጋፈጡ እንደሚሻለኝ ወሰንኩ፡፡ የቤተሰቤን አባላት መሞት ያወቅሁ ማስመሰል እንዳለብኝ ገባኝ፡፡ ያለዚያማ ስሜቴን ላለመጉዳት ዢን ፖል ምንም አይነግረኝም ማወቅ የምፈልገውን ነገር እንዲነግረኝ ማታለል አለብኝ፡፡ የአባቴን ቀይና ነጭ መቁጠሪያ ፍለጋ ወደ ኪሴ ገባሁና አምላክን ጥንካሬ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት፡፡
‹‹እና ዢን ፖል ስለ አባቴ … ያው እንደገደሉት አውቃለሁ፤ የት እንደሆነ ነው እንጂ የማላውቀው፡፡ የምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን እያልኩ ሳስብ ነበር፡፡››
‹‹እንዴ አዎና፣ ለዚያውም እያንዳንዷን ነገር ነዋ፡፡ ሎሬንት እዚያ ስለነበር ሁሉንም ነገር አይቷል፡፡ አባትሽን በኪቡዬ ከተማ ነው የገደሉት፡፡›› ቃላቱ ልቤን እንደጦር ወጉት፡፡ ዓይኖቼን በእጆቼ ሸፍኜና ፊቴን አዙሬ እንባዬን ለመደበቅ ሞከርኩ
‹‹አባትሽ የኔ ወላጆች ከተገደሉ ከአንድ ወይንም ከሁለት ቀናት በኋላ ነው የተገደለው›› ዢን ፖል ቀጠለ፡፡ ‹‹ሚያዝያ 14 መሰለኝ፡፡ ወደ አካባቢያችን አስተዳደር ጽ/ቤት ለቀናት ምንም ላልቀመሱት እግር ኳስ ሜዳ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ምግብ እንዲላክ ለመጠየቅ ይሄዳል፡፡ ያም ትልቅ ስህተት ነው፡፡›› ወይኔ አባቴ! እንዴት እንዲህ ደግ መሆን አስፈለገህ… ለምንስ ይህን ያህል ተሞኘህ? የኪቡዬ አስተዳዳሪ ሁሉም ነገር በእጁ የሆነና ለአባቴም የቅርብ ሰው ነው፡፡ አባቴ ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎች ጽንፈኛ ሁቱዎች ከዚያን ጊዜም በፊት አሳልፈው ሰጥተውት ስለነበር ለምን እነርሱን ማመኑን እንዳላቆመ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ የሚራቡ ሰዎችን ለመመገብ ሲል ግን ሕይወቱን እንዳጣ አውቃለሁ - ለእርሱ ሌላ አማራጭ አይኖርም ዓይኖቼ ተቃጠሉ፤ ጨጓራዬ ተላጠ፡፡ ዢን ፖል ሲቀጥል፡-
‹‹ሎረንት እንደነገረኝ አስተዳዳሪው አባትሽን ሞኝ ብሎ ሰድቦት ወታደሮቹ ወደ ውጪ ጎትተው እንዲያወጡት ይነግራቸዋል፡፡ በአስተዳዳሪው ጽ/ቤት መግቢያ ደረጃዎች ላይ በጥይት መትተው አስከሬኑን ሜዳ ላይ ጣሉት፡፡››
‹‹እንግዲህ… ዢን ፖል ይህን ሁሉ ስለነገርከኝ አመሰግናለሁ፡፡ ምንም ቢሆን ይጠቅመኛል ልጄ›› አልኩ ድምጼን በትክክለኛው ለማድረግ ባለኝ ዐቅም እየተቆጣጣርኩ፡፡ ጨለማው ፊቴን ስለደበቀልኝ አምላኬን አመሰገንኩት፡፡ ‹‹እና እናቴስ በል፡፡ እሷም እንደተገደለች አውቃለሁ፣ ግን እንዴት እንደሆነ እንጃ -››
‹‹አዬ ሮዝ?›› ሲል አቋረጠኝ፡፡ ‹‹በአካባቢያችን መጀመሪያ ከሞቱት ውስጥ አንዷ ነች፡፡ ከአባትሽ ከጥቂት ቀናት በፊት ነው የተገደለችው፡፡ ሎሬንት ከገዳዮቹ አንዱ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ዝርዝር ጉዳይ ያውቃል፡፡ ለማናቸውም እናትሽ የተደበቀችው በአያትሽ ጎረቤት ጓሮ ነበር፡፡ የሆነ ሰው በአቅራቢያው ባለ አካባቢ ይገደል ነበር፡፡ እናልሽ እናትሽ ጩኸቱን ስትሰማ ወንድምሽ ይመስላታል፡፡ ወደ መንገዱ ‹ልጄን አትግደሉት! ዳማሲንዬን አትግደሉብኝ!› እያለች እየሮጠች ወጣች፡፡ ‹ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች!›
‹‹የሚገድሉት ዳማሲንን አልነበረም፤ ግን ገዳዮቹ እናትሽን እንዳዩዋት አሳደዷት፡፡ ገንዘብ ከሰጠቻቸው እንደሚተዋትም ነገሯት፡፡ ተስማማችምና ከወዳጇ ከሙሬንጄ ለመበደር ሄደች፡፡ ሙሬንጄም ሂጅልኝ ትላታለች፡፡ ‹ከቤቴ ሂጂ - በረሮዎችን አንረዳም!›› ብላ ሙሬንጄ ለገዳዮቹ ግቢዋ እንዳይበላሽባት እናትሽን ወደ ጎዳናው ወስደው እንዲገድሏት ነገረቻቸው፡፡ ምስኪን እናትሽን ወደ መንገዱ ዳርቻ ወስደው ቀረጣጥፈው ገደሏት፡፡ የተወሰኑ ጎረቤቶቻችሁ ግን ቀበሯት፡፡ ከተቀበሩት የተወሰኑ ሰዎች ውስጥ አንዷ ነች … ከዘያ በኋላ አስከሬን በጣም ስለበዛ መቃብርም የሚቆፍር ጠፋ፡፡››
የሚነግረኝ እያንዳንዷ ቃል እንደ ግርፋት ሁሉ ታማለች፤ ቢሆንም ግን ለመረጃው እስረኛ ነበርኩ፡፡ ተጨማሪ እንዲነግረኝ ገፋፋሁት፡፡ ‹‹ስለ ትንሹ ወንድሜ ስለ ቪያኒ እንዲያው ሰምተህ ይሆን?›› ስል ጠየቅሁት እንዴት ሕጻን ወንድሜን ከቄሱ ቤት በውድቅት ሌሊት እንዳባረርኩት ሳስታውስ የጸጸት ጦር እየወጋኝ፡፡
‹‹ቪያኒ የተገደለው በኪቡዬ እግር ኳስ ሜዳ ከጓደኛው ከኦገስቲን ጋር ነው፡፡ እዚያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ - ሁሉም ተጨፍጭፈዋል፡፡ በመጀመሪያ ገዳዮቹ በመትረየስ ገደሏቸው፤ ከዚያም በኋላ ቦምቦችን ወረወሩባቸው፡፡ የዳነ ያለም አይመስለኝ፡፡››
እጆቼ ተንቀጠቀጡ፤ ወደ ሳንባዎቼም አየር ማስገባት አቃተኝ፡፡ በቻልኩት መጠን ራሴን አረጋግቼ ስለ ዳማሲን ለመጠየቅ ብሞክርም ስሙን መጥራት እንኳን አቃተኝ፡፡ በሕይወት ኖሮ የሆነ ቦታ ይጠብቀኛል በሚለው ተስፋዬ ላይ የሙጥኝ ብያለሁ፡፡ በመጨረሻ ‹‹ወንድሜ ኤይማብል ያለው ሴኔጋል ነው፤ ይህን ሁሉ ነገርም አያውቅ… ደብዳቤ የምልክበት አድራሻ እንኳን የለኝም…›› አልኩት፡፡
‹‹የዳማሲንን ጓደኛ ቦንን ጠይቂዋ፡፡ ሁሉንም የዳማሲንን ወረቀቶችና እቃዎች ይዟል … ወይንም ቢያንስ በፊት ነበረው፡፡›› ‹‹ለምን?›› ስል ጠየቅሁ ልቤ በጣም እየመታች፡፡
‹‹እንዴ ምክንያቱም ወንድምሽን የደበቀው እርሱ ነበራ፤ እናም ዳማሲን ወደ ዛየር ለመሄድ ሲነሳ ዕቃውን ሁሉ እርሱ ጋ ነበር የተወው፡፡ አሁን ግን ዕቃዎቹን ሁሉ ይጥላቸው ይሆናል - ወንድምሽ ከተደገደለ በኋላ በጣም ተበሳጭቷል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ፡፡››
ቃላቱ እንደ ጥይት መቱኝ፡፡ ‹‹እባክህ አይሆንም … ዳማሲን አይሆንም … እሱንም!››
ከዚያ ወዲያ ለማወቅ አልጓጓሁም፡፡ ቆሜ የተወሰኑ ጫማዎች ያህል ተንገዳገድኩና ራሴን ስቼ ወደቅሁ፡፡ ራሴም መሬት ላይ ተተከለ - በቀዝቃዛው መሬት ላይ መጋደምንና ከሌላው ቤተሰቤ ጋር መተኛትን ፈለግሁ፡፡ ምንም ለመስማት፣ ለማየትም ሆነ ለመዳሰስ አልፈለግሁም፡፡ ብዙ ለቅሶ አለብኝ፡፡ በአቧራው ላይ አነባሁ፡፡ ዢን ፖል አጠገቤ ሆኖ ሊያጽናናኝ ሞከረ፡፡ ከፊቴ ላይ አቧራውን ጠረገልኝ፤ አንገቴንም ቀስ ብሎ አባበሰኝ፤ እኔ ግን እጁን ወደዚያ መነጨቅሁት
‹‹ተወኝ፤ ይህን በራሴ ልወጣው ዢን ፖል አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋሁ ማንም ምድራዊ ኃይል አያጽናናኝም ለአፍታ እንኳን ብቻዬን ተወኝ›› ስለው ወደ ምሽጉ ሌላ ክፍል ዝምተኛ ወንድሙን ይዞ ዘወር አለ፡፡
በጀርባዬ ተንጋልዬ ወደ ሰማይ እያየሁ አለቀስኩ፡፡ አንዳች እንባ በዓይኖቼ እስኪጠፋ ድረስ አነባሁ፡፡ ኢየሱስ በሕልሜ የገባልኝን ቃል አስቤ ከእርሱ ጋር ማውራቴን ቀጠልኩ፡፡ መታጠቢያ ቤቱን ለቅቄ ስወጣ ሁሉም ሞተው እንደማገኛቸው ነግረኸኛል፤ ትክክልም ነበርክ›› አልኩት፡፡
‹‹ሁሉም ሞተዋል፡፡ ሁሉንም በዚህች ዓለም የምወደውን ተነጥቄያለሁ፡፡ ሕይወቴን በእጆችህ አኑሬያለሁ ኢየሱስ … ቃልህን ጠብቀህ ተንከባከበኝ፡፡ እኔ ቃሌን እጠብቃለሁ፡፡ ታማኝ ልጅህም እሆናለሁ፡፡›› ዓይኖቼን ጨፍኜ የቤተሰቤን ምስል አሰብኩት፡፡ እግዚአብሔር አቅርቦ በጥሩ ሁኔታ እንዲይዛቸው ጸለይኩ፡፡

የተሸከርካሪው ድምፅ ድንገት ቀሰቀሰኝ፡፡ ሊነጋ የተወሰኑ ሰዓታት ሲቀሩ መንታ ባውዛዎች ወደ ምሽጉ ሰልተው ገብተው ሌሎቹን ሴቶች በክብ የብርሃን ባሕር ከዢን ፖልና ከዢን ባፕቲስት ጋር እንደቆሙ አጥለቅልቀዋቸዋል፡፡ ተሸከርካሪው አጥሩ ጋ ቆሟል፡፡ ትልቅ ወታደራዊ መጓጓዣ ሲሆን መመሳሰያ ቀለም በተቀባ ሸራ ተሸፍኗል፡፡ ፈረንሳውያኑ ወታደሮች ከኋላ እንድንሳፈርና
👍1
ጸጥ እንድንል አሳሰቡን፡፡
‹‹የሁቱ ኬላዎች በየቦታው አሉ›› ሲል አንደኛው አስጠነቀቀን፡፡ ከምሽጉ አንድ ኪሎሜትር ተኩል ገደማ እንደተጓዝን አንደኛው ኬላ ጋ ደረስን፡፡ የገዳዮቹን ድምጾች ከሸራው በስተጀርባ እሰማ ጀመር፡፡ በዚህ ሰዓት ልዩነቱ የታጠቁ አጃቢዎች ስላሉልን ነው እንጂ እንግዳ ነገር አልሆነብኝም፡፡ እንዲያም ሆኖ በእነርሱ ወገን በመቶዎች የሚቆጠሩ ገዳዮች ሲኖሩ በኛ ወገን ግን በጣት የሚቆጠሩ ወታደሮች ነበሩ፡፡
‹‹ምንድነው የጫናችሁት?›› ሲል አንደኛው ገዳይ ጠየቀ፡፡
‹‹ከኪጋሊ እየመጡ ላሉት የሁቱ ስደተኞች ምግብና ንጹሕ ውሃ እየወሰድን ነው›› ሲል ነጂው ዋሸ፡፡
‹‹ምርጥ ሰው! እነዚህ ቱትሲ እባቦች ኪጋሊ ላይ እየገደሉን ነው… ማለፍ ትችላለህ፣ ቀጥል›› ተባለ፡፡
ነጂው ተሸከርካሪውን እንደገና ኮርኩሮት ወደፊት አቀናን - እንደገናም መንገዳችንን ጀመርን፡፡ እኛን ከኬላው ለማሳለፍ ነጂው የሰጠውን ብልጠት የተሞላበት መልስ አደነቅሁ፡፡ ኪጋሊ በአማጽያኑ ቁጥጥር ስር ስለዋለች በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሁቱዎች ከዚያ ወደ ደቡብ ይገሰግሳሉ፡፡ አጋጣሚው ደግሞ አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ እኛ ክፍለ ሀገር ወደ ኪቡዬ የሚመጡት አንድም ለመስፈር አለያም ኪቩ ሐይቅ ወርደው ወደ ዛየር ለመሻገር ነው፡፡ ብዙ ከጦርነቱ ለማምለጥ እየሞከሩ ያሉ ሁቱ ቤተሰቦች አሉ፤ ግን ብዙ አዳዲስ ኢንተርሃምዌ ገዳዮችም በየስፍራው ተሠራጭተዋል፡፡ በቀጣዩ ኬላ ገዳዮቹ ወዲያውኑ አሳለፉን፡፡ ‹‹ፈረንሳዮች የኛው ናቸው… ሂዱ.. አሳልፋቸው!›› አለ አንደኛው፡፡ በቀጣዮቹም አምስት ኬላዎች የሆነው እንደዚያው ነው፡፡ ሌሊቱን ስንሄድ አድረን ነጋብን - ነጂው መሄዱን ቀጥሎ ወደ አዲስ ሀገር ቢወስደን ተመኘሁ፡፡ ነፍሴ ከሩዋንዳ ወደ ሌላ ዓለም ለመብረር ፈለገች፡፡ መቼ ወይንም የት እንደሚጀምር ባላውቅም አምላክ አዲስ ሕይወት እያመቻቸልኝ እንደሆነ አምኛለሁ፡፡ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ተሸከርካሪው ከዋነኛው ምሽግ ሲደርስ ወዲያውኑ ተበሳጨሁ - አዎን ነጻ ወጥተናል፤ ግን አሁንም በሩዋንዳ መካከል ነበርኩ - ገና በሽብሩ እምብርት፡፡

ከተሸከርካሪው ስወርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ነገር የፈራረሱ የትምህርት ቤት ክፍሎችን ነው፡፡ በበሩ ላይ የተሰቀለው የዕንጨት ማስታወቂያ ርዊምፒሊ የሚል ቃል እንደነገሩ ተጽፎበታል፡፡ በዚህም ምክንያት እናቴ የማስተማር ሥራዋን ወደጀመረችበት ትምህርት ቤት እንደመጣሁ ገባኝ፡፡
በሰቆቃ ተሞላሁ፡፡ በመሆኑም ከክፍሎቹ ሄድ ብዬ ከእግዚአብሔር ጋር ፈጠን ያለ ወግ መጀመር አለብኝ፡፡ ‹‹አምላክ ግን ለምን እዚህ አመጣኸኝ? ለቤተሰቤ ላለቅስ እንደሚገባኝ አውቃለሁ፣ ግን አሁን አልችልም … እባክህ ለመትረፍ የሚያስፈልገኝን ጥንካሬ ስጠኝና ባይሆን ሐዘኑን በኋላ ልዘን፡፡››
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ በትምህርት ቤቱ ግቢ ገብቼ ፈገግ ለማለት ጥንካሬውን አገኘሁ፡፡ እናቴ ለረጅሙ ባለ አንድ ክፍሉና አቧራማ ወለሉ መማሪያ ክፍል የነበራትን ፍቅር አስታወስኩ፡፡ ‹‹ቁምነገሩ በዚህ ትምህርት ቤት የምንማረው ነው እንጂ ትምህርት ቤቱ ምን ይመስላል የሚለው አይደለም›› ትል ነበር፡፡
በመንጋት ላይ ስለሆነና የማለዳዋም ጸሐይ በትምህርት ቤቱ ግቢ ስለወጣች አብረውኝ ያሉትን ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በደንብ ማየት ቻልኩ፡፡ ሌሎች 20 የሚሆኑ ቱትሲዎችም በመዘዋወር ላይ ስለሆኑ ድንገት ሴቶቹና እኔ ምን ያህል እንደተባረክን ገባኝ፡፡ እነዚህ ምስኪን ነፍሶች ላለፉት ሦስት ወራት በጫካ ውስጥ በየጉድጓዱ እየተኙ፣ ሣርና ቅጠል እየበሉ ነው የቆዩት፡፡
ፀሐይዋ በጣም ስለከረረች ዓይኖቼን መከላከል አለብኝ፡፡ ከልዬም ሳለ የማውቃትን ሰው ፊት በጣቶቼ ጥላ አየሁት፡፡ ‹‹ኢስፔራንስ!›› ስል ጮህሁ፡፡ የእናቴ እህት ነች፡፡ ግን የሰማችኝ አልመሰለኝም፡፡
‹‹ኢስፔራንስ! አላወቅሽኝም? ኢማኪዩሌ ነኝ እኮ! አምላክ ሆይ ምስጋና ይግባህ! አንድ ሰው ድኗል!›› አልኩ ጥብቅ አድርጌ እያቀፍኳት፡፡
ከመናገሯ በፊት ረዘም ላለ ጊዜ ጭምቅ አድርጋ አቅፋኝ አጸፋውን መለሰችልኝ፡፡ ምናልባት አእምሮዋን ስታ እንዳይሆን ተጨነቅሁ፡፡ ‹‹እስኪ ይሁን›› አለች ደከም ብላ፡፡ ‹‹እንኳን በሕይወት ኖርሽልኝ፡፡ ሌላዋን አክስትሽንስ አየሻት?›› አለችና ዝግ ብላ በትምህርት ቤቱ ግቢ እህቷ ዣኔትና ሦስቱ ያክስቶቼ ልጆች (ሁሉም ወጣቶችና በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ ያሉ ናቸው) ወደተቀመጡበት ወሰደችኝ፡፡ ከእነርሱ አሥር እርምጃ ያህል ርቄ ቆሜ ከፊት ለፊቴ ያለውን ስሜትን የሚኮረኩር ትዕይንት ስመለከት ቆየሁ፡፡ ፊቶቻቸው በነፍሳት ንድፊያ አባብጠው፣ ከንፈሮቻቸው ተሰነጣጥቀውና ደምተው፣ ሰውነታቸው በእከክና በመግል ተሞልቷል፡፡ አካላቸው እዚህም እዚያም ተቆራርጧል፡፡ ለሳምንታት መመረዙ ወይንም ማመርቀዙ ያስታውቃል፡፡ ከቆምኩበት ሕመማቸው ሸተተኝ፡፡
ጠንቃቃ ቁስል ተንከባካቢዋና መምህርቷ አክስቴ ዣኔት በንጽሕና ላይ እጅግ ትጉህ ስለነበረች እንግዶች እቤቷ ሲመጡ ልጆቿን ሰላም ከማለታቸው በፊት እጃቸውን እንዲታጠቡ ታዝ ነበር፡፡ አሁን ግን ከነልጆቿ እንደ ኋላቀር ህዝቦች ሁሉ ልብሳቸው አላልቆና መቀመጫቸው ወጥቶ እየታየ አቧራ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ በጉልበቴ አረፍ ብዬ ዣንን ለማቀፍ ሞከርኩ፤ እርሷ ግን ከኔ ርቃ እንባዋን ለመደበቅ ሞከረች፡፡ ‹‹አይ ኢማኪዩሌ ማሪኝ… ፈርቼ ነው፡፡ ዓይኖቼን ውሃ ሲያደርጋቸው ታወቀኝ፡፡››
እናቴ በእንባዋ ተሸማቃ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ልትል የምትችለው የነበረው በእርግጥ ይህንኑ መሆኑን አስቤ ፈገግ አልኩ፡፡ ‹‹ዣን ስላገኘሁሽ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡›› ቀስ ብዬ አቀፍኳትና ልጃገረዶቹንም እያንዳንዳቸውን ሳምኳቸው፡፡ ዓይኖቻቸው እንደገና ያንጸባርቁ ጀመር፤ ፈገግታቸውም እየተመለሰ ሄደ፡፡

አምላክን ሕመማቸውን እንዲያድንላቸው ጠይቄ ራሴም ሰውነታቸውን ለማዳን የምችለውን ሁሉ እንደማደርግ ቃል ገብቼ ስለሁላቸውም ጸጥ ብዬ ጸሎት አደረስኩ፡፡ አብሬያቸው ቁጭ ብዬ አሳዛኝ ወሬ ጀመርን፡፡ እርስ በርሳችን በቤተሰባችን ማን እንደተገደለና እያንዳንዳችን ያለፍንበትን ውጣ ውረድ አወሳን፡፡ ዣኔት ሦስት ልጆቿንና ባሏን አጥታለች፤ የኢስፔራንስ ቤተሰብ በሙሉ ተገድሏል፡፡ ደጋጎቹ አያቶቼም ተገድለዋል፤ ቢያንስ ሰባቶቹ አጎቶቼም ዕጣቸው ያው ሆኗል፡፡ ወዲያውኑ ሁላችንም እናለቅስ ገባን … እንባችን ያቆም መሆኑንም ተጠራጠርኩ ለአንድ ሰዓት ገደማ ካወራን በኋላ ኢስፔራንስ ደብዳቤ ሰጠችኝ፡፡ ያን ሁሉ ጊዜ በጫካው ስትቆይ እንዴት እንዳቆየችው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ‹‹ዳማሲን በተደበቅሁበት አግኝቶኝ ይህን ደብዳቤ አደራ ሰጥቶኝ ነው›› አለች፡፡ ‹‹ወደ ዛየር እየሄደ… ነገር ግን አልተሳካለትም፡፡››
ደብዳቤውን ከእጇ ወስጄ እንባ አርጥቦት የደረቀውን ማሸጊያውን አየሁት፡፡ ከአክስቶቼና ከልጆቻቸውም ሸሸሁ፡፡ ከማንም ሰው ጋር አብሮ መሆንን አልቋቋመውም፡፡ የወንድሜን ስም መስማቱ በራሱ ለመሸበር በቂዬ ነው፡፡ እና አሁን ከጻፈልኝ ቃላት ሁሉ የመጨረሻዎቹን ይዣለሁ፡፡ እነርሱን ማንበቡም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እኔን ሲያናግረኝ እንደመስማት ነው፡፡


💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#ባለቀሱት_ቀናሁ

ቀናሁኝ ቀናሁኝ ቀናሁኝ በነሱ
እንባቸው እንደጕርፍ
ወርዶ ባለቀሱ
ቀናሁኝ ቀናሁኝ ቀናሁኝ በነሱ
ከውስጣቸው ወጥቶ
እፎይታን ባገኙ
እኔ ግን . . . እኔ ግን
ሚስጥሬን ታቅፌ
ለሰው ሳልተነፍስ
እህህ ... ታዬን ይዤ
ለሊቱ ረዝሞብኝ
በዝቶብኝ ችግሬ
ማልቀስ መጮህ ሳልችል
አለሁ በትካዜ፡፡
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_አስራ_ሦስት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#ከዳማሲን_የተላከ_ደብዳቤ


ከትምህርት ቤቱ በስተጀርባ ብቻዬን ሆኜ የዳማሲንን ደብዳቤ ከፈትኩት፡፡ ለማንበብ የሚያስቸግረውን የእጅ ጽሑፉን እንዳየሁ በትምህርት ቤት እንዳለን የጻፈልኝን ደብዳ ቤዎች ሁሉ አስታውሼ ልቤ ታመመ፡፡ ፈጽሞ ግልጽ ስሜት የማይንጸባረቅባቸው፣ ግን ሁሌ በፍቅርና በደግነት፣ በማበረታቻና አድናቆት፣ በግሩም ምክርና ረጋ ያለ ተግሳጽ፣ ስለ ወዳጆቻችን በሚያወሱ ወሬዎችና በብዙ ቀልዶች የተሞሉ ደብዳቤዎቹ ትውስ አሉኝ፡፡ ጀርባዬን በትምህርት ቤቱ ክፍል ግድግዳ ላይ አስደግፌ ተቀምጬ አነብ ጀመር፡፡
ግንቦት 6፣ 1994
ውድ (አባባ፣ እማማ፣ ቪያኒ እና) ኢማኪዩሌ ሁላችንም ከተለያየን አንድ ወር ገደማ ሆነን፡፡ ይሄው የቅዠት ኑሮ እየኖርን ነው፡፡ ሁናቴዎች ከሚያሳዩት ነገር ባሻገር አንድ ዘውግ ሌላውን ፈጽሞ የሚያጠፋው የእግዚአብሔር ፍቃድ ሲሆን ብቻ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ምናልባት የእኛ ሕይወት ለሩዋንዳ ድኅነት እንዲከፈል ግድ ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ - እንደገና እንደምንገናኝ በአእምሮዬ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለም፡፡
ከሀገሪቱ ለመውጣት ልሞክር ነው፣ ግን ይሳካልኝ አይሳካልኝ አላውቅም፡፡ በመንገድ ላይ ከገደሉኝ ስለ እኔ አትጨነቁ፤ በሚገባ ጸልያለሁ . . . ለሞትም ተዘጋጅቻለሁ፡፡ ከሩዋንዳ መውጣት ከቻልኩ ሰላም እንደተመለሰ ወዲያውኑ ሁላችሁንም አገኛችኋለሁ፡፡ የደረሰብኝን ሁሉ ቦን
ይነግራችኋል፡፡
የዳማሲን ጓደኛ ቦን በሌላ ጊዜ እንደነገረኝ ወንድሜ ደብዳቤውን እየጻፈ ሳለ እዚህ ሐሳብ ላይ ሲደርስ ዳማሲን ብዕሩን ቁጭ አድርጎ ቀና ብሎ እያየው ‹‹ቦን፣ ወዳጄ እንደሆንክ አውቃለሁ፤ ስሜቴም ሳይጎዳ እንዲቆይ ሞክረሃል፣ አሁን ልትነግረኝ የሚገባህ ሰዓት ላይ ነን - ከቤተሰቤ አባላት የተገደለ አለ እንዴ?›› ቦን ሁቱ ስለሆነ በዘር ጭፍጨፋው ወቅት በነጻነት ይጓጓዝና በአካባቢው ከቱትሲዎች ማንኛቸው እንደተገደሉ ያውቃል፡፡ የወላጆቼንና የቪያኒን ሞት ለራሱ በምስጢር የያዘው ለወንድሜ በጣም ስለሚጠነቀቅለትና ስሜቱን ሳይጎዳ ለመጠበቅ ስለፈለገ ነው፡፡
ዳማሲን በቀጥታ ሲጠይቀው ጊዜ ቦን ከባዱን መርዶ አረዳው፡፡ ጓደኛው የሚወዳቸው የቤተሰቡ አባላት ገና በሕይወት ያሉ እየመሰለው ደብዳቤውን መጻፉን እስኪጨርስ መጠበቅን አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ቦን ለዳማሲን አባታችን፣ እናታችንና ታናሽ ወንድማችን እንደተገደሉና እኔ ምናልባት በሕይወት ተርፌ ሊሆን እንደሚችል ይነግረዋል፡፡ ዳማሲን ቀኑን ሙሉ ማለት ይቻላል አልቅሶ እንደነበር የደብዳቤው ቋሚ ምልክት የሆኑት የእንባ ጠብታዎች ይህንን ይመሰክራሉ፡፡
ዳማሲን ኪቩ ሐይቅን ለማቋረጥ ጀልባ ፍለጋ ከመሄዱ በፊት ደብዳቤውን እንደገና አውጥቶ አባባ፣ እማማና ቪያኒ በሚሉት ቃላት ግራና ቀኝ ቅንፎችን አስቀምጦ የሚከተሉትን አረፍተ ነገሮች አከለ፡፡ ኢማኪዩሌ እንድትጠነክሪ እለምንሻለሁ፡፡ እማማ፣ አባባና ቪያኒ መገደላቸውን አሁን ሰማሁ፡፡ በተቻለኝ ፍጥነት ላገኝሽ እሞክራለሁ፡፡ ራስሽን ሳሚልኝ፤ እቀፊልኝም! በጣም የሚወድሽ ወንድምሽ!
ይህ ካነበብኳቸው ነገሮች ሁሉ የሚሠቀጥጠው ነው፡፡ እንባ ባረጠባቸው ቃላት ላይ የጣቶቼን ጫፎች አላወስኳቸውና ይህንን ደብዳቤ ሳላለቅስ ማንበብ እንደማልችል ተረዳሁ፡፡

በኋላ ላይ እንደደረስኩበት ለዘላለም የኔ ጀግና ሆኖ የሚኖረው ቦን ወንድሜን በቤቱ ከቤተሰቡ ፍላጎት በተጻራሪ ሊሸሽገው ሞክሯል፡፡ በዘር ፍጅቱ የመጀመሪያ ቀናት ዳማሲንን በምስጢር ከአልጋው ስር በደኅና በመደበቅ ሊያቆየው ችሎ ነበር፡፡ የቦን ቤተሰብ ግን ያደረገውን ነገር ሲደርስበት ዳማሲንን ለገዳዮቹ እንዲሰጥ ግፊት ያሳድርበታል፡፡
ይባስ ብሎ ቱትሲ ልጆችን በዘውግ ስም ጥሪ ወቅት ማሸማቀቅ የሚወደው ቡሆሮ ከቦን አጎቶች አንዱ ነው፡፡ ቡሆሮ በሀገሪቱ ወስጥ ካሉ ጽንፈኛ ሁቱዎች ውስጥ አንዱ፣ መጥፎና አደገኛ ገዳይ ሆኖ ነበርና ሲጠራጠርበት ጊዜ ቦን ዳማሲንን በጭራሽ ቤት ውስጥ ማቆየት እንደሌለበት ይረዳል፡፡ አንድ ሌሊትም በጣም አምሽቶ በቤተሰቡ መሬት ራቅ ያለ ጥግ ላይ ጉድጓድ ቆፍሮ በዕንጨትና ቅጠላቅጠል ይሸፍነዋል፡፡ ገዳዮቹ በቡሆሮ ተጠቁመው ከመምጣታቸው በፊት ዳማሲንንም በጥንቃቄ ከመኝታ ክፍሉ ያስወጣና በጉድጓዱ ውስጥ ይደብቀዋል ፡፡
ዳማሲን በጉድጓድ ውስጥ ከሦስት ሳምንታት ለበለጠ ጊዜ ያህል ተደብቆ ሳለ ገዳዮቹ በቡሆሮ ውትወታ በተደጋጋሚ የቦንን ቤት አሠሡ፡፡ እነዚህ አራጆች ግን የማይሰለቹ በመሆናቸው የቦንን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ተከታትለው መጨረሻ ላይ ምግብ ወደ ውጪ ይዞ ሲሄድ ያዩታል፡፡ ሸሻጊው ጓደኛውና ተሸሻጊው ዳማሲን ገዳዮቹ ግቢውን ሊያስሱብን ይችላሉ ብለው ሠግተው ዳማሲን የኪቩ ሐይቅን ተሻግሮ ወደ ዛየር እንዲያቀና ይወስናሉ፡፡ (ቦን የቱትሲዎችን ሕይወት ለማትረፍ ሐይቁን የሚያሻግራቸውን አንድ ደግ ሳምራዊ ዐሳ አጥማጅ ሁቱ ያውቃል፡፡) ዳማሲንን ከጉድጓዱ አውጥቶ በየጥላው እየቆዩና ከጥሻ ጥሻ እየተሸጋገሩ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ወደ ሐይቁ ሄዱ፡፡ መንገዱ ብዙ ጊዜ በመፍጀቱ ግን የዚያ ሌሊት ጀልባ ታመልጣቸዋለች፡፡
ነጋባቸው፡፡ በመሆኑም ዳማሲን ወደ ቦን ቤት ረጅም መንገድ ተጉዞ ተመልሶ አደጋ ላይ መውደቅን ስላልፈለገ ንሴንጄ በሚባል በሐይቁ አካባቢ የሚኖር የእርሱና የቦን ወዳጅ ቤት ቆየ፡፡ ንሴንጄ ቤተሰባችንን የሚወድ ለዘብተኛ ሁቱ ነው፡፡ አባቴ የብዙ ወንድሞቹን የትምህርት ክፍያ በመክፈል አግዟቸዋል፡፡ ስለሆነም ዳማሲንን ለዚያን ቀን መሸሸግ በመቻሉ ደስ ተሰኘ፡፡
የንሴንጄ ወንድም ሳይመን ግን የወንድሙን ያክል ቸር አልነበረም፡፡ ዳማሲንን በቤታቸው ሲደርስ በፈገግታና በወዳጅነት ተቀብሎታል … በማግስቱ ከሰዓት በኋላ ግን ወንድሜ በተኛበትና ንሴንጄም የጀልባ ጉዞውን ለማመቻቸት በወጣበት ሳይመን ከቤት ሾልኮ ወጥቶ የገዳዮቹን ቡድን ፈልጎ ዳማሲንን አሳልፎ ሰጠው፡፡
ከእራት በፊት ሳይመን ወንድሜን ቀስቅሶ ወደ ዛየር ከመሄድህ በፊት ልብሶችህን ልጠብልህ ይለዋል፡፡ ዳማሲንም ልብሶቹን ሁሉ አወላልቆ በውስጥ ልብስ ብቻ ይቀራል፡፡ ሳይመንም ልብሶቹን ይወስድበታል፡፡ (በኋላ ላይ እንደተናገረው ይህን ያደረገው ወንድሜን ከመሞቱ በፊት ለማሳፈርና ለማሸማቀቅ ፈልጎ ነው፡፡) ልብሶቹን ከወሰደበት በኋላም ሳይመን ወንድሜን በደርዘኖች የሚቆጠሩ ገዳዮች ይጠብቁት ወደነበረበት ወደ ዋናው ቤት ይጠራዋል፡፡ ወንድሜም ላይ ያለ ምኅረት ተረባረቡበት፤ እየደበደቡ ወደ መንገድ ጎተቱት፡፡ ከውስጥ ልብሱም ሌላ ምንም አልለበሰም፡፡ እኛ ቤት ትሠራ የነበረች አንድ ሴት ነገሩን ሁሉ አይታ የዳማሲንን የመጨረሻ ሰዓት ዝርዝር ሁኔታ ነግራኛለች፡፡ ‹‹ቆንጆዋ እህትህ የት ነች?›› ብለው ገዳዮቹ ወንድሜን ይጠይቁታል፡፡ ‹‹የት ነች ኢማኪዩሌ?›› በቤተሰብህ ያሉትን በረሮዎች አስከሬኖች አይተናቸዋል፤ እሷ ግን ገና አልተደረሰባትም… የት ነች? ንገረንና በነጻ እንለቅሃለን፤ ካልነገርከን ግን ሌሊቱን ሙሉ ስንከትፍህ እናድራለን፡፡ በል ኢማኪዩሌ የት እንዳለች ንገረንና በነጻ ትሰናበታለህ፡፡››
ፊቱ የተሰባበረውና ያባበጠው ዳማሲን የከበቡትን ገዳዮች አየት አድርጓቸው በሕይወቴ ሙሉ እንዳደረገልኝ ሁሉ በመጨረሻዋም ቅጽበት ለኔ ቆመልኝ
ቆንጆዋ እህቴ የት እንዳለች ባውቅ እንኳን አልነግራችሁም፡፡ ኢማኪዩሌን መቼም አታገኟትም… እናንተ ሁላችሁም ተደማምራችሁ ብትቀርቡ እንኳን በብልሃት አታህሏትም፡፡››
በገጀሮቻቸው እየመቱና እየወጋጉትም ‹‹እንዳንተ ብልህ ነች? አንተ ማስተርስ ዲግሪ እያለህ ያዝንህ፤ አልያዝንህም ወይ? አሁን እህትህ የት እንደተደበቀች ትነግረናለህ አትነግረንም!››
ዳማሲንም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቀጥ ብሎ ቆመና ገዳዮቹ ላይ ሳቀባቸው፡፡ አለመፍራቱ ግራ አጋባቸው፤ ብዙ ቱትሲዎችን ገድለዋል፤ ሲገድሉም የተጠቂዎቻቸውን የአትግደሉኝ ተማጽኖ ማድመጥ ሲያረካቸው ቆይቷል፡፡ የዳማሲን መረጋጋት ደስታቸውን ነጠቃቸው፡፡
ከመደራደር ወይንም በወንድ ልጅ አምላክ እያለ ምህረታቸውን ከመለመን ይልቅ እንዲገድሉት ተገዳደራቸው፡፡ ‹ኑ›› አላቸው፡፡ ‹‹ምን ትጠብቃላችሁ? ዛሬ ወደ አምላኬ የምሄድባት ቀኔ ነች፡፡ በሁላችንም ዙሪያ አምላክ ይታየኛል፡፡ እያየ ነው፣ ወደ ቤቱ ሊወስደኝ እየጠበቀ፡፡ በሏ - ሥራችሁን ጨርሱና ወደ ገነት ላኩኛ፡፡ እንደ ሕፃናት የእቃ እቃ ጨዋታ አድርጋችሁት ሰውን ስትገድሉ ታሳዝኑኛላችሁ፡፡ ግድያ ጨዋታ አይደለም - አምላክን ካስቀየማችሁት አሁን ለተዝናናችሁበት ትከፍሉበታላችሁ፡፡ የምትቆራርጧቸው ንጹሃን ደም በፍርድ ቀን ይከተላችኋል፡፡ እኔ ግን ለእናንተ እየጸለይኩላችሁ ነው… የምትሰሩትን እርኩሰት እንድታዩና እጅግ ሳይዘገይባችሁ የአምላክን ይቅርታ እንድትጠይቁ እጸልይላችኋለሁ፡፡››
እነዚህ የወንድሜ የመጨረሻ ቃላት ናቸው፡፡ የግፍ ግድያውን ሕመም ምንም ባይቀንሰው በገዳዮቹ ፊት በጽናት መቆሙና ይዞት ከኖረው ክብር ጋር መሞቱ ያኮራኛል፡፡
አንደኛው የሳይመን ወንድም፣ ካሬራ የተባለው የወንጌላውያን ቄስ፣ ዳማሲን ሲናገር አላገጠበት፡፡ ‹‹ይህ ልጅ ራሱን እንደ ሰባኪ ቆጠረ እኮ፡፡ እዚህ ጋ ያለሁት ሰባኪ እኔ ብቻ ነኝ እንግዲህ፡፡ ግድያውንም ባርኬያለሁ፡፡ ይህችን ሀገር ከአንድ ተጨማሪ በረሮ በማጽዳታችሁ ባርኬያችኋለሁ›› ብሎ ገዳዮቹን አየት አድርጎ ‹‹ምን ትጠብቃላችሁ? ፈራችሁ እንዴ? አንድ በረሮ እንድትገድሉት ሲለማመጣችሁ ለምንድነው እሱ ጋ የምትገተሩት? ግደሉታ!›› ካሬራ ገዳዮቹን ወንጀል እንዲሰሩ አሸማቆ ገፋፋቸው፡፡

‹‹ቱትሲዎች ስትባሉ ከእኛ ከሁቱዎች በላይ እንደሆናችሁ ልታሳዩ ትሞክራላችሁ›› ብሎ አንዱ ገዳይ ጮኸና በዳማሲን ፊት ላይ ገጀራውን አነሳ፡፡ ‹‹ማስተርስ ዲግሪ ስላለህ በጣም የምትበልጠን ይመስልሃል? እስኪ ማስተርስ ዲግሪ ያለው ሰው አንጎል ምን እንደሚመስል ልየው!››
ገጀራውን በወንድሜ ራስ ላይ ሲሰነዝርበት ወንድሜ በጉልበቶቹ ወደቀ፡፡ ሌላ ገዳይም ወደፊት ተራምዶ መጥቶ ገጀራውን ሁለቴ ሰንዝሮ ሁለቱንም እጆቹን ገነጣጠላቸው፡፡ የመጀመሪያው ገዳይ ገጀራውን ሌላ ዙር ሰነዘረ - በዚህን ጊዜም የዳማሲንን የራስ ቅል ከፍቶ ወደ ውስጥ ለማየት ሞከረ፡፡ ከዚያም በወንድሜ ደም ተጨማልቆ መንደር ለመንደር እየዞረ በሰው ጭንቅላት ውስጥ የማስተርስ ዲግሪን እንዳየ ጉራውን ሲነፋ ዋለ፡፡
የዳማሲን ግድያ ዝርዝር ላይ አተኩሬ መቆዘምን ለራሴ አልፈቅድም፡፡ ሞትን እንዴት እንደተጋፈጣት፣ ከመሞቱ በፊት እንዴት ፈገግ እንዳለ፣ ብሎም ለገደሉት ሰዎች እንዴት እንደጸለየ ብቻ አስባለሁ፡፡ ዳማሲን የኔ ውድ የልብ ወዳጄና ጠንካራ ወንድሜ ነበር፡፡
በኋላ ላይ ከገዳዮቹ አንዱና የዳማሲን የትምህርት ቤት ጓደኛ ስለነበረው ሰማሄ ስለሚባል ሰው ወሬ ሰማሁ፡፡ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ተጎድቶ ለብዙ ቀናት አለቀሰ አሉ፡፡ ያለማቋረጥ ዳማሲንና እርሱ ስላደረጓቸው ነገሮች ሁሉ ያወሳል፡፡ እግር ኳስ መጫወት፣ በቡድን መንፈሳዊ መዝሙር መዘመርና ቤተ-ክርስቲያንን ማገልገል አይነቶቹን ትውስታዎቹን ይጠቃቅሳል፡፡ ለእርሱና ለሌሎች ልጆች ወንድሜ ያሳያቸው የነበረው ደግነት እየታወሰው በደለኝነት ተሰምቶታል፡፡ ሰማሄ ለሚያዳምጠው ሁሉ ጸጸቱን ይገልጻል፡፡
‹‹ከእንግዲህ አልገድልም›› ይላል፡፡ ‹‹የዳማሲንን ፊት ከአእምሮዬ በፍጹም አላወጣውም፡፡ ቃላቱ ልቤን ለዘላለም ሲያቃጥሉት ይኖራሉ፡፡ ይህን ዓይነት ልጅ መግደል ኃጢአት እኮ ነው፡፡››


💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «#ሁቱትሲ ፡ ፡ #ምዕራፍ_አስራ_ሦስት ፡ ፡ #የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች ፡ #ትርጉም_በመዝምር_ግርማ ፡ ፡ #ከዳማሲን_የተላከ_ደብዳቤ ፡ ፡ ከትምህርት ቤቱ በስተጀርባ ብቻዬን ሆኜ የዳማሲንን ደብዳቤ ከፈትኩት፡፡ ለማንበብ የሚያስቸግረውን የእጅ ጽሑፉን እንዳየሁ በትምህርት ቤት እንዳለን የጻፈልኝን ደብዳ ቤዎች ሁሉ አስታውሼ ልቤ ታመመ፡፡ ፈጽሞ ግልጽ ስሜት የማይንጸባረቅባቸው፣ ግን ሁሌ በፍቅርና…»
#የአመሻሽ_ፀፀት


#በኤፍሬም_ስዩም


በመስታወት አየ

በመስታወት ታየ።

በመስታወቱ ውስጥ ምስሉን እያየ ራሱን ጠየቀ፡፡ በአንደበቱና በመታወቂያው ላይ ዋሽቶ የሚናገረውንና ፅፎ ያስቀመጠውን
የእድሜውን ስፍራ ለራሱ መዋሸት አልቻለም፡፡ የደረሰበት የእድሜው መጠን ምን ማለት እንደሆነ የገባው ትላንትና
አምሽቶበት ከነበረው ግሮሰሪ ውስጥ የግሮሰሪው ባለቤት
እንደዘበት ጣል ባደረገው ንግግሩ ነበር፡፡

“እኔ ምልህ” አለው፡፡ ከባልኮኒው ኋላ ተቀምጦ የነበረው፡፡የግሮሰሪው ባለቤት፡፡
አምስት ደብል ጂን እስኪጠጣ ድረስ ከሰላምታ በቀር አንዳችም
ቃላት ሳይተነፍስ ለረዥም ሰአታት እርሡ ላይ ባልተለመደ ሁኔታ ወደ ፅሞና በሚጠጋ ጸጥታ ውስጥ ተቀምጦ የነበረው

የዚህ ቤትና የመጠጥ ደንበኛ...” አቤት ጠራኸኝ እንዴ? “አሉ:: እንደ መባነን ብሎ።

“አረጀህ እንዴ?” በድጋሚ የቤቱ ባለቤት፡፡ ሌላ ደንበኛው ያዘዘው
ብርጭቆ ውስጥ 'redlable' ወስኪ እየቀዱ፡፡

“እንዴት? እንደዛ ልትለኝ ቻልክ? ሽበትኩብህ ወይስ?”አላሥጨረሠውም፡፡ ለአይኑ ሀመም በታዘዘለት ትልቅ ነጭ መነፅር ውስጥ አተኩሮ ካየው በኋላ....” ዝምታ በጣም አበዛህ
ብዬ ነው፡፡” ባለ ግሮስሪው ይህንን ተናግሮ መቀመጫው ላይ
ሰውነቱን እያደላደለ የእጁን ሞባይል ይነካካ ገባ፡፡

እነሆ ከእነዚህ የቃላት ምልልሥ በኋላ በሁለቱ መሃል የነበረ ጭውውት ሲኖር “እሺ” “እሺ” የሚሉትና፡ “ምን አዲስ ነገር
አለ” የሚሉት ቃላት ብቻ ነበሩ፡፡

በመስታወት አየ

በመስታወት ታየ፡፡

አዲስ ነገር የለም ቀልቡም ከርሡ የለም
“አረጀህ እንዴ?” የሚለው ከትላንት ማታ እስከ አሁን ድረስ
ሕሊናውን ሊለቀው አልቻለም፡፡ ጥያቄውን ሽሽት ባልበደለው ሰው ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ “ሁለተኛ እርሱ ቤት ሄጄ ብጠጣ
ሲል፡ ከውሳኔው በኋላ ወደ ቀልቡ ተመለስ

በእጁ መዳፍ ላይ ዘይት አፈሰሰ

መስታወት ፊት ቆሞ ሩቅ ወደ ኋላ በሃሳብ ፈሠሠ፡፡

ከጊዜያት በፊት አርግዛ የነበረች ፍቅረኛው አርግዣለሁ ስትለው
እርሱው በስጣት ብር ማስወረዷን አስታወሰ፡፡ በሰተረሳ ድርጊት

ተናደደ። በተረሳ ድርጊት በመጠን አበደ በተረሳ ድርጊት ተክዝ ብሉ ቆመ። በተረሳ
ድርጊት ሲጋራ ለኮስ፡፡ ለተረሳ ድርጊት መስታወት ፊት ላይ ጭሱን አፈሰሰ፡፡ በመስታወቱ ውስጥ የርሱን የማይመስል ድንግዝ ግዝ ፊት ታየው በሚያየው ድንግዝግዝ ፍርሀት ልቡን ገባው።

ነጭ የተስቀለ ፎጣ አወረደና መስታወቱን ወለወለ፡፡ በያዘው ሲጋራ
ምክንያት ደግሞ መስታወቱ ተመልሶ ጉም ለበሰ፡፡
ሲጋራውን ጥሎ በእግሩ ረግጦ አጠፋው መስታወቱን በድጋሚ ወልውሎ ወደ ተረሳው ነገር ተመለሰ።ተመለሰና እንዲህ አለ...

ይኼኔ ወልዳው ቢሆን ኖሮ የስንት አመት ልጅ ይኖረኝ ነበር።

የዘጠኝ አመት ልጅ ትኖረኝ (ይኖረኝ)ነበር” ራሡ መለሰ፡፡ ዘጠኝ
የሚለውን ቁጥር ተጠራጠረና ጣቶቹን እየነካካ በድጋሚ መቁጠር ጀመረ፡፡ “አንድ

አንድ አንድ

ሁለት

ሦስት

አራት አምስት ስድስት

ሰባት ስምንት..

ዘጠኝ አልተሣሳተም የዘጠኝ አመት ልጅ ይኖረው (ትኖረው) ነበር፡፡ በመስታወት አልፎ ወደ ሚገኘው ምስሉ ላይ አፈጠጠ
አሁን የአለበትን ሁኔታ ለመገመት

ልቡን ለመመዘን

ለመተንበይ ወደፊትን፡፡ አፈጠጠ፡፡ ምንም
አይነት መልስ ለማግኘት አልቻለም፡፡ እርሱ በደጅ የሚያገኛቸው ብዙዎቹ አብሮ እደጎቹ እና አብሮ ተማሮቹ ተለውጠዋል። ለእርሱ የሚታዩት
እጅግ በጣም ተለውጠው ነው፡፡ እነሱ ላይ የሚያየውን ለውጥ ግን እራሱ ላይ ሊያገኘው አልቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት
በነበረበት የቀረ መስሎ ይሰማዋል፡፡ አንዳንዴ ግን የሚደነግጠው
በመንገድ ላይ አንዳንድ ህፃናቶች “ጋሼ? ሰዓት ስንት ነው?" ሲሉት ነው።

“አስር አመት ሞላው” የሚለው የጓደኛው ግጥም ምን ማለት
እንደሆነ ዘግይቶ ተረዳው፡፡ “አስር ዓመት ሞላው” ብሎ ለራሱ በለሆሳስ ከተናገረ በኋላ በቆመበት የሆነ አይነት ድርጊት
ማከናወን አማረው፡፡ ሊያከናውን የሚችላቸውን ነገሮች አብዝኞቹን አጠናቋል፡፡ከጥቂቶች በቀር

ጠዋት ይነሳል

ፊቱን ይታጠባል

ቁርስ የትም ይበላል

ወደ ሆኑ ሰዎች ስልኩን ይደውላል

ካፌ በረንዳ ላይ ጋዜጣ ያነባል።

በቃ፡፡ “ስራህ ምንድን ነው” ለሚሉት ሰዎች የሙሉ ጊዜ
ጸሐፊ ነኝ ብሎ ነው የሚያወራው፡፡ በየመጡት አዳዲስ ዓመቶች
ሁሉ በዚህ ክረምት ድንቅ የሆነ መፅሐፍ አበረክታለሁ በማለት
ምንም ምን ላይሰራ ጊዜዎች ነጉደዋል፡፡ ወይ ልብወለድ ሳይፅፍ፤ ወይ ልጅ ሳያሳቅፍ፡፡

ሃሳቡን መሸሽ ፈለገ

በሃሳቡ ግና በጣም ተፈለገ

መሸሽ አልቻለም በመስታወት ውስጥ ሚመለከተው ምስሉ ሁሉ ሳይቀር “ጊዜ” በሚል ርዕስ የተነደፈ ሃሳብ መስሎ ታየው፡፡
“ሴራው” በነበር የተጎነጎነ እንዲህ የተፃፈ..

የመጠሪያ ስም (ርእስ) = ሠ

የትምህረት ደረጃ = ያልጨረሰ

ዕድሜ = ያጋመሰ።

ከዚህ በላይ ታሪክ ከዚህ በላይ ልክ የሌለኝ ሰው ነኝ!! ብሎ እያሰላሰለ ሳለ ከኋላው አብራው ያደረችው ሴት ልጅ ጮክ ብላ ስትጠራው ተሰማውና “አቤት ጠራሽኝ እንዴ”

ሴቲቱ በማዘን እና በመገረም ስሜቶች መሃል በሆነ ሁኔታ “እንዴ ምን ማለትህ ነው ጠራሽኝ ትለኛለህ እንዴ? ስጠራህማ
ዘመን አለፈኝ እኮ፡፡ አሁንስ አረጀህ መሰለኝ” ብላ የጠራችበት
ምክንያት ስልኩ ደጋግሞ በመጥራቱ እደሆነ ነግራው ስልኩን አቀብላው ወደመጣችበት ተመለሰች፡፡

እርሱ ግን እስከዛሬ ድረስ በቆመበት ቀርቷል፡፡ መስታወት ፊት ለፊት ምስሉን እያየ፡፡

እና

በምስሉ እየታየ፡፡

💫አለቀ💫
👍2
#ሁቱትሲ


#ክፍል_አስራ_አራት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#የስደተኞች_መጠለያው_ምቾት


የፈረንሳዮቹ የስደተኞች መጠለያ የታጠቁ ወታደሮች የሚጠብቁት፣ ለቱትሲዎች ከለላ የሚሰጥና ሁቱዎችን የሚያገል ስፍራ ነው፡፡ ወታደሮቹ ስምንት ታንክ-መሰል ብረትለበስ ተሸከርካሪዎችን በግማሽ ክብ ቅርጽ ከትምህርት ቤቱ ሕንጻዎች ፊት ለፊት ያቆሙ ሲሆን የምሽጉን ውጨኛውን ክፍል ደግሞ ቀን ከሌት ቢያንስ መቶ የሚሆኑ ወታደሮች ይቃኙታል፡፡ እኛም ብረት-ለበስ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ግማሽ ክብ ውስጥ ሙሉ ጊዜ ሰጥተው እንዲከላከሉንና መጸዳዳት ስንፈልግም ወደ ጫካ እንዲወስዱን ከተመደቡ ሰላሳ ወታደሮች ጋር እንኖራለን፡፡
የፈረንሳይ ወታደሮች በተደጋጋሚ ስለምንኖርበት ሁኔታ ይቅርታ ሲጠይቁን ያስቁኛል፡፡ ከመጣንበት ጋር ሲነጻጸር ፍጹም የምቾት ሕይወት በመኖር ላይ ነን፡፡ መጀመሪያ ላይ ከምንጭ ውሃ እናግዝና ገላችንንና ልብሳችንን በሳሙና እናጥብ ነበር!
ውጪ ላይ መተኛታችንን ፈረንሳውያኑ ወታደሮች እንደ ዋና መከራ ቢያዩትም እኛ ግን በደስታ ተቀብለነዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ በቆሻሻና በዛፍ ቅጠላ ቅጠል ተሸፍኜ በአለትና ድንጋይ ላይ በመተኛቴ የተነሳ እያመመኝ ብነሳም ክዋክብት ላይ አንጋጥጬ መተኛቱን ወድጄዋለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ፊት በቀኑ መጀመሪያ ላይ የማየት ያህል ነው፡፡
ምግብ እንድናዘጋጅ አይፈቀድልንም፡፡ ይህ የሆነው ትኩስ ምግብ ስላልነበራቸው ሲሆን አለማዘጋጀታችንም ለእኛ ምንም ችግር አያመጣም፡፡ ወታደሮቹ የታሸገ አይብ፣ ጣፋጭ ኮቸሮ፣ እሽግ የዱቄት ወተትና ፍራፍሬ ይመግቡናል፡፡ የምመገበው የተወሰነ ምግብ ቢሆንም ቀስ በቀስ ሰውነቴ እየጨመረ ሄደ፤ ወገቤም ወደ ውስጥ መግባቱን አቆመ፡፡
ፈረንሳውያን ሥራቸው እኛን መከላከል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይህንን ተግባራቸውንም በሚገባ ተወጥተውታል፡፡ በምሽጉ ውስጥ በቆየሁበት ወቅት አንድም ጊዜ እንኳን በገዳዮቹ ማስፈራሪያ ደርሶብኝ አያውቅም፡፡ ሆኖም ግን ሁቱዎች ብዙውን ጊዜ በውጪው የምሽጉ ክፍል በመሰብሰብ በተደረደሩት ተሸከርካሪዎች መካከል እኛን ለማየት ይሞክራሉ፡፡ በእንስሳት መጠበቂያ ያለን እንስሶች እንደሆንን ሁሉ ያፈጡብናል … ከመጥፋት ጠርዝ ድረስ የታደነ ዘውግ ብቸኛ ቅሪቶች፡፡
‹‹እንስሳት እንደሆናችሁ ሁሉ ያዩዋችኋል፣ ግን እነርሱ ናቸው እንስሶቹ›› አለኝ የወታደሮቹ አበጋዝ አንድ ቀን ጠዋት ከደረስኩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፡፡ ፈረንሳይኛ በጥሩ ሁኔታ እንደምችል ስለተረዳ ብዙ አዋራኝ፡፡ ታሪኬን ነገርኩት፤ በጣም እንዳዘነልኝም ታየኝ፡፡ በሩዋንዳ ቱትሲዎች ያሳለፉትን፣ ታሪካችንንና የዘውግ ግጭቶችን ጣጣ ሁሉ ያውቃል፡፡
‹‹ባንቺና በኔ መካከል የሚቀር ነገር ልንገርሽ፤ የሀገሬ የርዕሰ-ብሔር ከራሱ ጋር አንዴት መታረቅ እንደሚችል አላውቅም - ጸጸቱ እንደማይገድለው›› አለኝ፡፡ ‹‹ብዙ ሁቱዎችን እንዴት ሰው እንደሚገድሉ ስላሠለጠነች ፈረንሳይ በእጆቿ ላይ ደም አለባት፡፡››
በሩዋንዳ ለተከሰተው ነገር የውጪ ዜጋ ወቀሳውን ሲቀበል ስሰማ ይህ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ለነፍሴ ጥሩ ነገር አደረገላት፡፡ ዓለም እየደረሰብን ያለውን ነገር አይቶ ለመርሳት መምረጡን በማወቄ የቄሱን ሬድዮ ስሰማ ብዙ ጊዜ ተስፋ እቆርጥ ነበር፡፡
‹‹ይህን ያህል ስለተረዳኸኝ አመሰግናለሁ›› ስል መለስኩለት፡፡ ‹‹ይህን እያደረጉ ያሉት ሰዎች በጣም መጥፎዎች ናቸው፡፡
‹‹መጥፎ? መጥፎ! ኢማኪዩሌ ከንቱ ግፈኞች ናቸው፡፡ ጭራቆች ናቸው! በደኅና ሁናቴ ላይ እንዳለሽ እንድታውቂ እፈልጋለሁ፡፡ እኔ እዚህ በሥራ ላይ እያለሁ አንዳች ጉዳት አይመጣብሽም›› አለኝ በወገቡ ላይ ያገነደረውን ጠመንጃ መታ መታ እያደረገ፡፡ ‹‹ላንቺ ከመከላከልም በላይ አደርግልሻለሁ፡፡ የተወሰነ ፍትሕም እለግስሻለሁ፡፡ አሁንም ይህ በኔና ባንቺ መካከል ይቅር እንጂ በቀል ከፈለግሽ ያንቺው ድርሻ ነው፡፡ ይፈልጉሽ የነበሩትን ወይንም ወላጆችሽንና ወንድሞችሽን የገደሉትን ሁቱዎች ስሞች ብትሰጭኝ አስገድልልሻለሁ፡፡
ያቀረበው ሐሳብ አስደነገጠኝ፡፡ በመታጠቢያ ቤቱ በነበርኩባቸው የመጀመሪያ ቀናት ሰሞን የተመኘሁት ይህንኑ ነበር፡፡ በኛ ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ የነበሩትን ግድያዎች ቄሱ በነገሩን ጊዜ በቀልን በጽኑ በመፈለጌ ሁቱዎችን የምገድልበት ጠመንጃና መድፍ ቢኖረኝ ተመኝቼ ነበር፡፡ ያ ግን ልቤን ለእግዚአብሔር ምኅረት ከመክፈቴና ከገዳዮቹ ጋር ሰላም ከመፍጠሬ በፊት ነው፡፡
መኰንኑ ያቀረበልኝ ትክክለኛውን በቀል ነው - በኔ ትዕዛዝ የሚገድሉ የሠለጠኑና የታጠቁ ወታደሮችን፡፡ ማድረግ የሚጠበቅብኝ ብቸኛው ነገር አንድ ስም ሹክ ማለትና የቤተሰቤንና በሺዎች የሚቆጠሩትን በየጎዳናው እየበሰበሱ የነበሩትን ሰዎች ደም መበቀል ነው፡፡ በቀሉ ከልቡ የመጣ ቢሆንም በመኰንኑ ድምጽ ውስጥ ዲያብሎስ ይሰማኛል፡፡ በወቅቱ የምፈልገው ብቸኛ ነገር ሰላም ሆኖ ሳለ ይህ መኰንን በግድያ ቃል ኪዳኖች ይፈታተነኛል፡፡ እጄን ወደ ኪሴ አስገብቼ በአባቴ መቁጠሪያ
ጠቀለልኩት፡፡ ‹‹ይህን አደርግልሻለሁ በማለትህ አመሰግናለሁ -››
‹‹የምትፈልጊውን እገድልለሻለሁ!›› ለመግደል በጣም ከመጓጓቱ የተነሣ ንግግሬን እንኳን አላስጨርስ አለኝ፡፡ ‹‹በዚህ ምሽግ የምታውቂው ሁቱ ካለ ንገሪኝና እኔ ራሴ እገድለዋለሁ፡፡ ሁሉንም እጠላቸዋለሁ፡፡››
‹‹አዎን፣ እነዚህ ገዳዮች እንጂ ሁቱዎች ሁሉ ከንቱ አይደሉም መኰንን ሆይ፡፡ በዲያብሎስ ተታለዋል… ከአምላክ ርቀው ሄደዋል እና -››
‹‹ኢማኪዩሌ ሁቱዎች ከንቱ ናቸው›› እንደገና አቋረጠኝ፡፡ ‹‹ያደረጉት ከንቱ ነው፡፡ ይህ የጌታ ፈቃድ አሊያም የዲያብሎስ ሥራ እንደሆነ አትንገሪኝ - የሁቱዎች ሥራ ነው፡፡ እናም ብድራቸውን ያገኟታል፡፡ ሐሳብሽን ከቀየርሽ አሳውቂኝ፡፡ ለሌላ ሰው እኮ ልግደል አልልም፤ ታውቂያለሽ፡፡››
አምላክ የመኰንኑን ልብ በምህረቱ እንዲነካ ጸልዬ ለገዳዮቹም እንደገና ገጀራዎቻቸውን እንዲጥሉና የእግዚአብሔርን ምኅረት እንዲለምኑ ጸለይኩ፡፡ የመኰንኑ ንዴት በሩዋንዳ የጥላቻና ያለመተማመኑ ዑደት በቀላሉ እንደማይሰበር እንዳስብ አደረገኝ፡፡ እንዲያውም ግድያው ካቆመም በኋላ በእርግጠኝነት የባሰ መራር ሁኔታ ሊኖር ይችላል፤ ወደ ባሰ ሽብር የሚፈነዳ መራርነት፡፡ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ምኅረት ብቻ ያንን አሁን ከመከሰት ያቆመው ይሆናል፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ አምላክ ቢያስቀምጠኝ ያንን ማየት እችላለሁ - ሌሎች እንዲኖሩ ማድረግም የሕይወቴ ሥራ ዋነኛ ክፍል ይሆናል፡፡
በቀጣዩ ቀን መኰንኑ ቃሉን መጠበቁን አሳየ - ሁቱዎችን በእውነት ይጠላ ኖሯል፡፡ አንድ እየደማ ያለና ‹‹የዘር ጭፍጨፋ ተራፊ ነኝ፤ የቆሰልኩትም ከቱትሲ አማጽያን ጎን ስዋጋ ነው›› የሚል ሰው ወደ ምሽጉ ገብቶ ይዘዋወራል፡፡ መኰንኑ ግን ስላላመነው ወታደሮቹ አንበርክከውና ጠመንጃዎቻቸውን ራሱ ላይ ደግነው እንዲጠይቁት አደረገ፡፡ መጀመሪያ ላይ ሲጠይቁት የኢንተርሃምዌ አባል መሆኑን ካደ፡፡ ከብዙ ምርመራ በኋላ ግን ተስፋ ቆረጠና ተናዘዘ፡፡ መኰንኑም ለወታደሮቹ ራሱን ሲነቀንቅላቸው ጎትተው ወሰዱት፤ ከዚያ በኋላም በጭራሽ አላየነውም፡፡ ከወታደሮቹ አንደኛው በሌላ ጊዜ ሰውዬው የኢንተርሃምዌ ሰላይ እንደሆነ ማመኑን ነገረኝ፡፡
‹‹ስለሱ አትጨነቂ - ከአሁን በኋላ አያስቸግርሽም›› አለኝ፡፡
ለአክስቶቼና ለልጆቻቸው
በቻልኩት መጠን በቂ ምግብ መቅረቡን በማረጋገጥ፣ መድኃኒት ከወታደሮቹ በማምጣትና ቁስላቸውን በማከም እንክብካቤ አደረኩላቸው፡፡ እንዲያውም ምሽት ላይ እንዳይፈሩ በማሰብ በአቅራቢያቸው እተኛለሁ፡፡ ሆኖም ግን የሚጠበቅብኝን ያህል ጊዜ ከእነርሱ ጋር አላሳለፍኩም፡፡ በሕይወት በመቆየታቸውና ደኅና በመሆናቸው ደስተኛ ነኝ፡፡ ያም ሆኖ ግን ላጣሁት ቤተሰብ ምትክ አይሆኑኝም፡፡ አዲስ ሕይወት መጀመር እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ በመታጠቢያ ቤቱ አብሬያቸው ከነበርኩት ሴቶች ጋር እንኳን መግባባቱ ከበደኝ፡፡ የምንኖረው በምሽጉ የተለየዩ ክፍሎች ተለያይተን ነው፡፡ እናም አንዳችን ላንዳችን ፈገግታ ብናሳይም ብዙም አንነጋገርም፡፡ በዚያች ጠባብ ስፍራ አብረን ለረጅም ጊዜ ብንቆይም እርስ በርሳችን በደንብ አልተዋወቅንም፡፡ የዘወትር ተግባቦታችን በእጅ ምልክቶችና በከንፈር ንባብ ስለነበር ፍራቻን፣ ሽብርንና ተስፋ መቁረጥን ያስተጋባል፡፡ ምናልባት በመታጠቢያ ቤቱ ልናወራ ችለን ቢሆን ኖሮ ጥሩ ወዳጆች ልንሆን እንችል ነበር፡፡ ሆኖም ግን ምሽጉ ውስጥ እርስ በርስ መተያየታችን ብዙ አሰቃቂ ትውስታዎቻችንን ይቀሰቅስብን ጀመር፡፡
ለማናቸውም አዳዲስ ሰው ለመተዋወቅ በርካታ ዕድሎች አሉን፡፡ ከጭፍጨፋው የተረፉ አዳዲስ የቱትሲ ስደተኞች በየቀኑ ይደርሱ ጀመር፡፡ ብዙዎቹ የተወዛገቡ፣ የተምታታባቸውና ኪንያሩዋንዳ ብቻ የሚናገሩ ናቸው፡፡ እኔ ሁለት ቋንቋ ስለምናገር መኰንኑ ሁሉንም አዲስ-ደራሽ ስደተኞች እንድመዘግብለት ጠየቀኝ፡፡ እኔም ለማገዝ ደስተኛ ነኝ፡፡ ዕድሜያቸውንና ስማቸውን እየመዘገብኩ ጉዳታቸውንና የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና እርዳታ ለፈረንሳዮቹ ወታደሮች አሳውቃለሁ፡፡ የግል ታሪካቸውንና ያለፉበትን ችግር ሁሉ እጽፋለሁ፡፡ በዚህ ሂደትም ብዙ አሰቃቂ ታሪኮችን ሰምቻለሁ፡፡ ቢሆንም የተወሰኑ ዘላቂ ጓደኞችን አፍርቻለሁ፡፡ አንድ አዲስ ጓደኛ የሆነችኝ ፍሎረንስ ስትሆን በኔ ዕድሜ ያለች ማራኪና ሽቁጥቁጥ ስትል ፈገግታዋ የሚስብ ሴት ነበረች፡፡ በገጀራ ዓይኖቿ መካከል መትተዋት በፊቷ ላይ ቁልቁል ከሚታየው ጉልህ ጠባሳ በቀር የግምጃ እራፊ ትመስላለች፡፡ እንደ ሌሎቻችን ሁሉ አሰቃቂ የሆነውን ታሪኳን መዝግቤያለሁ፡፡ ፍሎረንስ የመጣችው ከኔ መንደር ብዙም ከማትርቅ ትንሽ ከተማ ነው፡፡ ጭፍጨፋው ሲጀምር ቤተሰቧና ሦስት መቶ ጎረቤቶቿ ገዳዮቹ የቤተክርስቲያንን ቅድስና ያከብራሉ ብለው በማሰብ በአቅራቢያቸው ባለች ቤተክርስቲያን ከለላ ይጠይቃሉ፡፡ ሆኖም ግን ቱትሲዎችን በአንድ ቤት ታጅበው ማግኘታቸው ለገዳዮቹ ነገሩን አቀለላቸው፡፡ በቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ባሉ አግዳሚ ወንበሮች መካከል እየተራመዱ ገጀራዎቻቸውን በመደዳ ግራና ቀኝ እየሰነዘሩ ሰዉን ተራ በተራ መመድመድ አልከበዳቸውም፡፡
‹‹መሣሪያም ሆነ ራሳችንን የምንከላከልበት ምንም መንገድ አልነበረንም›› አለች ፍሎረንስ፡፡ ‹‹የተወሰነ ልመናና ጩኸት ቢሰማም ብዙዎቻችን እዚያ ተቀምጠን የምንታረድበትን ተራ እንጠባበቅ ጀመር፡፡ መገደል እንደሚገባን እንዳሰብን ነው የሆነው - በእርግጥ አግባብ እንደሆነ ሁሉ … ወደኔ ሲመጡ የማስታውሰው ብቸኛ ነገር ገጀራ ወደ ፊቴ ሲሰነዘር ነው፡፡ ከዚያም ወደ አስከሬን መጣያቸው ልጣል ተጭኜ በመወሰድ ላይ ሳለሁ ነቃሁ፡፡››
የፍሎሬንስ ጠባሳ ጥልቅ ቢሆንም ለሞት የሚያደርሳት ግን አልነበረም - ሆኖም ገዳዮቹ በአንድ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ከሌሎች አስከሬኖች ጋር ይወረውሯታል፡፡ ስትነቃ በወላጆቿ አስከሬን ላይ እንደሆነች ይገባታል፤ እህቷም ከነሱ በላይ ታቃስታለች፡፡
‹‹በእህቴ ደረት ላይ የተሰካ ጦር አየሁ … ልትሞት ትንሽ ቢቀራትም ግን በማጓራት ላይ ነበረች፡፡ ወደ እርሷ ለመቅረብ ስሞክር ከኛ ጋር ተሳፍረው ከነበሩት ገዳዮች አንዱ ስንቀሳቀስ አይቶ በቀስቱ ይጓጉጠኝ ጀመር፡፡ እዚህ፣ እዚህ፣ እዚህ ጋ ወጋኝ›› አለች ወደ ደረቷ፣ ሆዷና ጭኖቿ እያመለከተች፡፡ ‹‹ሲወጋኝ ምንም አልተንቀሳቀስኩም፤ እንዲያውም እግዚአብሔር ሕመሜን አርቆ ሕይወቴን እንዲያተርፋት ነበር የጠየቅሁት፡፡ ብዙ ስለደማሁ ገዳዩ የሞትኩ ሳይመስለው አይቀርም፡፡ የጭነት ተሸከርካሪው ከአካንያሩ ወንዝ በላይ ባለ ኢንተርሃምዌዎች ብዙውን ጊዜ አስከሬን የሚጥሉበት ገደል አፋፍ ላይ ቆመ፡፡
‹‹ሁሉንም አስከሬኖች በገደሉ ቁልቁል ሲወረውሯቸው ወንዙ ውስጥ ያርፋሉ›› ስትል ፍሎረንስ ቀጠለች፡፡ ‹‹እግሮቼን ይዘው አየር ላይ ሲወረውሩኝ አስታውሳለሁ፤ የወራጅ ውሃውም ድምፅ በርቀት ይሰማኛል፤ ግን መውደቄን አላስታውስም፡፡ በቀጣዩ ቀን ጠዋት ወንዙ ዳር ጭቃው ላይ ነቃሁ፡፡ ወላጆቼ፣ እህቴ፣ ሁሉ….. ም እዚያ ወድቀዋል፤ ነገር ግን ሁሉም ሞተዋል፡፡ ገደሉን ሽቅብ ሳየው እንዴት እንደዳንኩ ሊገባኝ አልቻለም - የተጣልንበት ጥልቀት ቢያንስ መቶ ሃያ ክንድ ይሆናል፡፡ ማመን የምችለው እግዚአብሔር ለአንድ ዓላማ እንዳተረፈኝ ብቻ ነው፡፡›› ፍሎረንስ በወንዙ ዳር ለአንድ ቀን ከተኛች በኋላ ተነሥታ መሄድ ቻለች፡፡ በአቅራቢያው ወዳለ የደግ ሁቱዎች ቤት የግዷን ሄደች፡፡ አስገብተውና ቁስሏን ጠራርገው ደበቋት፡፡ ‹‹ሕይወቴን ቢያድኑኝም ታዲያ›› ስትል ቀጠለች፤ ‹‹ልጃቸው በጠዋት ይወጣና የሚገደል ቱትሲ እስኪያጡ ድረስ ከኢንተርሃምዌዎች ጋር ሆኖ በከተማዬ ያሉ ቱትሲዎችን መግደሉን ቀጥሏል፡፡ ከዚያ በኋላ ለኔ ምንም ስሜት የሚሰጠኝ ነገር ጠፋ፣ ኢማኪዩሌ፡፡ እህቴና ወላጆቼ ሲሞቱ ለምን የተረፍኩ ይመስልሻል?››
‹‹እግዚአብሔር ለአንድ ዓላማ ነው ያተረፈሽ›› ስል መለስኩላት፡፡ ‹‹ታሪክሽን እየጻፍኩት ነው፤ አንድ ቀንም አንድ ሰው ያነበውና የተከሰተውን ችግር ሁሉ ይረዳበታል፡፡ አንቺ እንደኔ ነሽ፡፡ የተረፍሽው የደረሰብንን ሁሉ እንድትናገሪ ነው፡፡›› በስደተኞቹና በፈረንሳውያኑ አስተናጋጆቻችን መካከል ብዙ የትርጉም ሥራ ስለሠራሁ የተወሰኑትን ወታደሮች ላውቅ ቻልኩ፡፡ ከመካከላቸው ፒየር የተባለው ወታደር በፍቅር ዓይን ያየኝ ጀመር፡፡ የውስጠኛውን የምሽጉን ክፍል ቀን ላይ እንዲጠብቅ ተመድቧል፡፡ ሌሊት ግን ኮከቦቹን እያየሁ ስቀመጥ ከኔ ጋር በማውራት ጊዜውን ያሳልፋል፡፡ ፒየር በዕድሜ ከኔ በተወሰኑ ዓመታት የሚያንስ ወጣት ነው፡፡ ትሁት፣ ለሰው አሳቢና ጥሩ አድማጭም ነው፡፡ በኔ ቤተሰብና በመንደሬ ላይ ተከስቶ የነበረውን ነገር ነገርኩት፤ እርሱም ስለ ቤተሰቡ፣ በፈረንሳይ ስላሳለፈው ሕይወትና ወደ ሩዋንዳ ከመምጣቱ በፊት ስለተለያቸው ሴት የፍቅር ጓደኞቹ ነገረኝ፡፡ የወንድ ጓደኛ እንዳለኝም ሲጠይቀኝ ስለ ዮሃንስና ስለተለያየንበት መላ ቅጡ የጠፋበት መንገድ ነገርኩት፡፡
ከፒየር ጋር ስሆን በአብሮነቱ በጣም ደስተኝነት ይሰማኛል፡፡ ከእርሱ ጋር ማውራት አእምሮዬን ካለሁበት ገሃዳዊ እውነታ ቢያንስ በጊዜያዊነት ያወጣዋል፡፡ ጊዜው ሲሄድ ፒየር ከኔ ጋር የሚሆንባቸውን ሰበብ አስባቦች መፈላልግ አበዛ - የሚበላ ያመጣልኛል፣ ወደ ምንጭ ውሃ ልቀዳ ስሄድ ጥበቃ ያደርግልኛል፤ የማነባቸውን መጻሕፍትም እየያዘልኝ ይመጣል ጓደኞቹ ስለዚህ ጉዳይ ቢቀልዱበትም በእኔ በኩል ምንም ግድ አልሰጠኝም፡፡ በዘር ጭፍጨፋው የማይሰቃይ ጓደኛ ማፍራቴ ለኔ እፎይታ ነው፡፡ ተስፋዎቼንና ህልሞቼን ለእርሱ መንገርም እንደገና ሰው እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ
አንድ ቀን ፖል የተባለው የፒየር ጓደኛ ይህ ወጣት ወታደር በኔ ፍቅር እንደተነካ ሲነግረኝ አሳቀኝ፡፡ ልብሶቼን አልቀየርኩ፤ ለሦስት ወራት ያህል
ገላዬን እንኳን በአግባቡ አልታጠብኩ
‹‹አዬ፣ ፒየር እኮ ሁሌ ስላንቺ ነው የሚያወራው›› ሲል አረጋገጠልኝ፡፡ ‹‹‹በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ብታልፍም ልቧ ክፍት ነው፤ ሳቂታነትና ጨዋታ-አዋቂነትም አላት› ይላል፡፡››
‹‹አይ ምነው በል! እንዲህ ስትቀልዱብኝ ጨዋታ አዋቂ መባል ይነሰኝ?›› አልኩት፡፡ ወዲያውኑ ግን ፖል ቀልዱን እንዳልሆነ ገባኝ - ፒየር በፍቅሬ ተቃጥሎ ኖሯል፡፡
በዚህ የፍቅር ገጠመኝ ኩራት ቢሰማኝም ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ ቤተሰቤን አጥቻለሁ፤ የጦርነቱን መጨረሻ ለማየት እበቃ እንደሆን እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ዮሃንስ እንደዚያ ከጣለኝ በኋላ በፍቅር ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡ ያም ሆኖ ፒየር የተሰበረ ልቤ ሌላ ሰው ድጋሚ መውደድ መቻሉን እንድገነዘብ ረዳኝ፡፡
በዚያ ምሽት እየተጣራ መጥቶ ለእግር ጉዞ ሽርሽር እንዳካሂደው ሲጠይቀኝ ፍቅሩን በኔ ላይ እንዳያባክን ልነግረው ወሰንኩ፡፡ እርሱ ግን ከልቡና በፍቅር ሲናገር ያልተዘጋጀሁበት ነገር በመሆኑ አስደነገጠኝ፡፡
‹‹ኢማኪዩሌ በእውነት ለመናገር ከጓደኛ በላይ ሆነሽብኛል›› ሲል ከልቡ ነገረኝ፡፡ ‹‹በጣም ልዩ ሰው ነሽ፡፡ ጭፍጨፋው፣ ሕመሙ፣ በዙሪያችን ያለው አመፅ ሁሉ ባለበት ሁኔታ ልትሰሚ የምትፈልጊው የመጨረሻው ነገር ይህ ነው፡፡ ግን እንዲያው ካንቺ ፍቅር የያዘኝ ይመስለኛል፡፡ አብሮነትሽን እፈልጋለሁ፡፡›› ያን ሁሉ ሰዓት ሽርሽር ስናደርግ ብዙ እንዲናገር ብጠብቀውም ይቺን ብቻ ተናግሮ ዝም በማለቱና ያን ያህል ግልጽ በመሆኑ አስገረመኝ፡፡
‹‹ፒየር›› ስል በዝግታ መለስኩለት፤ ‹‹ልቤ በሰቆቃ ተሞልቷል፤ አሁን በልቤ ውስጥ የቀረችው ስፍራ ለፈጣሪዬ ብቻ የምትሆን ነች፡፡ በፍቅር መውደቅን ላስበው አልችልም… ወደፊት ለሚገጥሙኝ ፈተናዎች መስጠት ያለብኝን አትኩሮት ማጣት የለብኝም፡፡ ራሴን መንከባከብ እኮ ይኖርብኛል …››
እጄን ያዝ አደረገኝና ‹‹የምናገረው እኮ ከልቤ ነው … እወድሻለሁ፤ አሁንም እንከባከብሻለሁ፡፡ ካንቺ ጋር መሆን እፈልጋለሁ፤ ላጣሽ አልፈልግም፡፡›› ያን ያህል አውጥቶ በመናገሩ ትንሽ ተገርሜያለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ፍቃድ ሳይሆን በአጋጣሚ የተገናኘን ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ ጌታዬ ዮሃንስን ለኔ የፈቀደልኝ ሰው እንዳልሆነ እንዳሳወቀኝ ሁሉ አሁን ፒየርንም እንደማይሆነኝ እያሳወቀኝ ነው፡፡ ይህን ጥያቄ በአዎንታ መቀበል ያለብኝ አይመስለኝም - ዝግጁ ስሆን እግዚአብሔር ፍቅረኛ እንደሚያመጣልኝ ታውቆኛል፡፡ ሲያመጣልኝም ምንም ዓይነት ጥርጣሬም ሆነ ማመንታት አይኖርም፡፡
‹‹አይ ፒየር … አይሆንም፡፡ አሁን ልቤ ከቆሙት ይልቅ ከሞቱት ዘንድ ነው - ማልቀስ እንኳን ገና አልጀመርኩም፡፡ ‹እዬዬም ሲዳላ ነው፡፡› ጓደኝነትህ ለኔ ትልቅ ነገሬ ስለሆነ ላቆየው እፈልጋለሁ፡፡ ስለዚህ እባክህ እንዲሁ ጓደኛሞች እንሁን፡፡››
‹‹አውቃለሁ›› አለ በብስጭት፡፡ ‹‹እንግዲህ ልብሽን ማግኘት ካልቻልኩ እየወደድኩሽም መለያየታችን ግድ ነው፡፡ እንዲሁ እንደዋዛ ደኅና ሁኚ ልበልሻ፣ በይ ደኅና እደሪ ሆዴ፡፡›› ዘንበል ብሎ አፌ ላይ በመሳም አስደነገጠኝ፡፡ የእርሱ ከንፈሮች የኔን ባገኙባት አፍታ ልቤ እንደ ሰም ስትቀልጥ ዓይኖቼን ጨፍኜ የመሳሜ ሙቀት ሕመሜንና ብስጭቴን አስረሳኝ፡፡ ፒየርም ሌሎቹን ወታደሮች ለመቀላቀል ሾር ብሎ ሲሄድ ፈገግታዬ እየከሰመ ሄደ፡፡ የቀረኝ ብቸኛ ነገር እንዳረክ አርገኝ ብዬ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር መተው ነው፡፡

ላይሆንልኝ ነገር ለወንድሜ ለኤይማብል በሕይወት እንዳለሁ ላሳውቀው ፈለግሁ፣ ግን ምንም ዓይነት የመልዕክት መላላኪያም ሆነ የስልክ አገልግሎት የለም፡፡ የስልክ ቁጥሩም ሆነ የምከፍለው ገንዘብ የለኝም፡፡ ኤይማብል 5000 ኪሎሜትር ርቆ ሴኔጋል እየተማረ ስለሆነ እዚያው እንዲቀር ተመኘሁ፡፡ ወደ ሩዋንዳ ከተመለሰ እንደተቀረው ቤተሰቤ ሁሉ ይሞታል፡፡ ስለዚህ መልሼ የማገኘው ጦርነቱ ሲያልቅ ይሆናል፡፡ ግን መቼ ይሆን ጦርነቱ የሚያልቀው? ፈረንሳውያኑ ምንም ወሬ አልነገሩንም፤ የምናዳምጠው ሬድዮም የለን፡፡ ያሉን ብቸኞቹ የወሬ ምንጮች በእጅጉ ወደ ተጨናነቀው ምሽጋችን የሚመጡ አዳዲስ ገቢዎች ናቸው፡፡ በሐምሌ መጨረሻ አካባቢ ቱትሲዎቹ የሩአግ አማጽያን በሰሜን ድል ማድረጋቸውን ሰማሁ፤ በምሥራቅና በደቡብ ግን ጦርነቱ ቀጥሏል፡፡ ፈረንሳውያኑ በበኩላቸው እኛ ያለንበትን ምዕራብ ሩዋንዳን፣ የኪቩ ሐይቅን ዳርቻና የዛየርን ድንበር ጨምሮ ተቆጣጥረዋል፡፡ ለእኛ ጥሩ ዜና ቢሆንም ሁኔታው አሁንም እጅግ አደገኛ ነው፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሁቱ ስደተኞች የኪቩ ሐይቅን ለመጠጋትና ወደ ዛየር ለማምለጥ በመሞከር ላይ ናቸው፡፡
በየቀኑ አዳዲስ የተረፉ ቱትሲዎች በራችን ላይ ይመጣሉ፡፡ ወደ ምሽጉ ከደረስኩ ጀምሮ በሦስት ሳምንታት ቁጥራችን ከተወሰኑ ደርዘኖች ወደ 150 ገደማ አድጓል - እኔም የስደተኞቹን ታሪክና የጤና ሁኔታ እጽፋለሁ፡፡ ብዙዎቹ ስደተኞች አንድም እጅና እግሮቻቸውን አጥተዋል አለያም በሌሎች ዓይነት አሰቃቂ ግርፋቶች ሳቢያ ቋሚ አካላዊ ጉዳቶች ደርሰውባቸው በጽኑ ቆስለዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ ቁስሎቻቸው ክፉኛ የተመረዙ ስለሚሆኑ እንደማይድኑ አውቃለሁ፡፡ እጅና እግሮቻቸውን ያላጡትም ቢሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የሚመጡት የሚወዱትን በማጣት፣ በሐዘንና በአዕምሯቸው በተቀረጸው ሽብር ምክንያት አብደውና ራሳቸውን ስተው ነው ፡፡ በምሽጉ ውስጥ ካስቸገሩኝ ነገሮች አንዱ የወላጅ አልባዎች ነገር ነው፡፡ ለአብነት ዕድሜያቸው ሦስትና አራት ዓመት የነበረውን ከኪጋሊ ወደኛ የመጡትን ወንድማማቾች ፈጽሞ አልረሳቸውም፡፡ ገዳዮቹ ሲደርሱ ወላጆቻቸው በቤታቸው ኮርኒስ ላይ ይደብቋቸዋል፡፡ ወላጆቻቸው ሲገደሉ ልጆቹ ግን ከተወሰኑ ቀናት በኋላ በደግ ሁቱ ጎረቤቶቻቸው ተገኙ፡፡ እነርሱም ወደ ደቡብ ጦርነቱን ለማምለጥ ሲመጡ ያመጧቸዋል፡፡ ሰዎቹ ልጆቹን ለመውሰድ አዳጋች ወደሆነው ወደ ዛየር ሊሄዱ መሆኑን በመግለጽ ለፈረንሳውያን ወታደሮች ይሰጧቸዋል፡፡ ወታደሮቹም በአንዳንድ ምክንያቶች ሰበብ የልጆቹንም ሆነ የጎረቤቶቻቸውን ስም አልጻፉም፡፡ በተጨማሪም ሁለቱም ልጆች በምሽጋችን ሲደርሱ ከባድ ትኩሳት ይዟቸዋል፡፡ በምሽጋችን ውስጥ በጣም በዕድሜ ትንሾቹ ልጆች ምንም ሃይ ባይ ወላጅም ይሁን ዘመድ ስለሌላቸው ለጊዜው እኔው በማደጎ ተቀብዬ እንከባከባቸው ገባሁ፡፡ በፈረንሳዩ መኰንን እገዛ በመማሪያ ክፍሉ ውስጥ አልጋ ዘረጋሁላቸው፤ ትኩሳታቸውን የሚቀንስ መድኃኒትም አገኘሁላቸው፡፡
ሲናገሩ መስማቱ ልቤን ነካው፡፡ የወላጆቻቸውን አስከሬኖች ቢያዩም የሞትን አይምሬነት ለመረዳት ግን ዕድሜያቸው አይፈቅድም፡፡ ትልቀኛው ልጅ ታናሽ ወንድሙን ይንከባከባል፤ አዲስ ለሚያገኟቸው ሰዎችም ትሁት እንዲሆን ያሳስበዋል፡፡ ሦስት አመቱ የሆነው ልጅ ታላቅ ወንድሙን ፍሬንች ፍራይስ የሚባሉትን ጣፋጭ ምግቦችና ለስላሳ መጠጥ እንዲያመጣለት ይጨቀጭቀዋል፤ ታላቅየውም ሁልጊዜ በግሩም ትዕግሥት ይመልስለታል፡፡
‹‹እቤታችን እንዳልሆንን አስታውስ እንጂ … እዚህ ፍሬንች ፍራይስና ለስላሳ ልናገኝ አንችልም፡፡ እማማና አባባ መጥተው እስኪያገኙን መጠበቅ አለብን - ከዚያ ይሰጡናል፡፡ ማስቸገር የለብንም፣ መባለግ አያስፈልግም፤ ያለዚያ የባሰ ችግር ይደርስብናል፡፡›› ታናሽ ወንድሙ ሲያለቅስበት ‹‹አታልቅስ … እማማና አባባ ቶሎ ይመጣሉ፤ ከዚያ ፍሬንች ፍራይስ እንዳሻህ ትበላለህ፡፡ እንጠብቃቸው፤ እማማና አባባ ሁሉንም ነገር
ያስተካክሉልናል፡፡››
እነዚህ ልጆች
በምንም ተዓምር ወላጆቻቸውን በድጋሚ እንደማያዩ አውቃለሁ፤ ከሁኔታው መረዳት እንደሚቻለው ሁሉም ዘመዶቻቸው የሞቱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የወደፊት ሕይወታቸው በሐዘን፣ በመገፋትና የሚያስፈልጋቸውን በመነፈግ እንዳይሞላ ሠጋሁ - ምሬትና ጥላቻ በቀላሉ ስር የሚሰዱበት ዓይነት ሕይወት፡፡ በነዚያ ምስኪን ዓይኖች የጥላቻና ያለመተማመን ቀለበት ሲያደራ ይታየኛል፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር ለምን እንዳዳነኝ የሚያመለክት ሌላ ምክንያት እያሳየኝ እንደሆነ አውቄያለሁ፡፡ አንድ ቀን ስበረታና ዐቅም ሳገኝ በዘር ፍጅቱ ወላጆቻቸውን ያጡትን ልጆች ለማገዝ የምችለውን ሁሉ እንደማደርግ ቃል ገባሁ፡፡ በሕይወታቸው ላይ ተስፋና ደስታን ለማምጣትና ቤተሰቦቻቸውንና የቤተሰብ ፍቅርን የነጠቃቸውን ጥላቻን እንዲርቁ ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡

በነሐሴ መጀመሪያ ላይ መኰንኑ ምሽጉ በጣም ስለሞላ አብዛኞቹን ስደተኞች ሊያጓጉዛቸው እንደሆነ ነገረኝ፡፡ አዲሱ ምሽግ በኪቡዬ ከተማ ባለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ይሆናል፡፡ ንጹሕ ውሃ፣ የተሻለ ምግብና አልጋዎችም ይኖሩታል፡፡ እንዲመቻቸው ብዬ ‹‹ወንዶቹ ልጆቼ›› መጀመሪያ እንዲዛወሩ አደረግሁ፡፡ አክስቶቼና ልጆቻቸውም መሄዳቸውን አረጋገጥኩ - አዎን አሁን ተሽሏቸዋል፤ ግን የተሻለ ሰላም እንዲሰማቸው ከራሳቸው በላይ ጣራና በዙሪያቸው ግድግዳ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሄጄ ሁሉንም ሰው ለመንከባከብ ባቅድም መኰንኑ ቀርቼ በምሽጉ ባለው ሥራ እንዳግዝ ለመነኝ፡፡ አሁንም ቢሆን አስተርጓሚ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተጨማሪም አዳዲስ በሕይወት የተረፉ ሰዎችም መግባታቸውን ቀጥለዋል፡፡
‹‹ያው ከቆየሽ ሕይወት ታድኛለሽ›› ሲል ነገረኝ፡፡ እንዴት አሻፈረኝ እለዋለሁ? እዚያው ቀረሁ፤ ትንንሾቹን ወንድማማቾችም ከዚያን ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አላየኋቸውም፡፡ ሌሎች በረብሻ ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችን ለመንከባከብ የገባሁትን ቃል ግን አልረሳሁትም፡፡ በሩዋንዳ የእነዚህ ዓይነት ልጆች እጥረትም የለም፡፡ በአሮጌው ምሽግ 30 የሚሆኑ ስደተኞች ሲቀሩ ከነርሱ ውስጥ ስምንቱ ፍሎሬንስና ዢን ፖልን ዓይነቶቹ አዲስ ያፈራኋቸው ጓደኞቼ ናቸው፡፡ በጣም ቅርብ የሆኑ አባላትን የያዘችው ትንሿ ቡድናችን እንደ አነስተኛ ቤተሰብ ሆነች፡፡ በእርግጥ ትሥሥራችን በጣም የጠበቀ ስለሆነ ዘጠኛችንም በአንድ ላይ ሆነን ካልሆነ በስተቀር ከምሽጉ አንዛወርም አልን፡፡
ቱትሲ ተፈናቃዮችን መቀበላችንን ብንቀጥልም መጠለያው ግን እያገለገለ ያለው እንደ መሸጋገሪያ ጣቢያ ነው፡፡ በሕይወት የተረፉትን እመዘግብና በአንድ ወይንም በሁለት ቀናት ውስጥ በከተማው ወዳለ ትልቅ መጠለያ እንዲዛወሩ እናደርጋለን፡፡ ከዚያም በነሐሴ መጀመሪያ ለወራት ያልሰማሁትን ነገር ሰማሁ - ጥልቅ፣ የሚያሽካካና ከልብ የሆነ ሣቅ፡፡ ከአዲሶቹ መጭዎች ስደተኞች ጋር ከመጣች አንዲት ሴትዮ ነው ሳቁ የመጣው፡፡ በተሸከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጣ በሰው እየተገፋች የምትሄደውን ይህች ሴትዮ ወታደሮቹ ከመጣችበት የጭነት ተሸከርካሪ እያወረዷት ነው፡፡ ወፍራም ስለሆነችና እግሮቿም በሽተኛ ስለሆኑ መራመድ እንደማትችል አውቄያለሁ፡፡ ይህ ሁሉ መከፋት ባለበት ምን የሚያስቅ ነገር አገኘች ብዬ ተገረምኩ፡፡ በኋላ ሲገባኝ የምትስቀው በሕይወት በመትረፏ ደስታ ተሰምቷት ኖሯል፡፡ወታደሮቹ በጥንቃቄ ተሸከርካሪ ወንበሯን መሬት ላይ ሲያስቀምጡላትና ሁለት ትንንሽ ልጆቿን ሲሰጧት አየሁ፡፡ ልጆቿ የፊቷን የተለያዩ ክፍሎች ሳሟት፤ እንደገናም ትስቅ ገባች - ሳቋም በመጠለያውም ግቢ አስተጋባ፡፡
‹‹አሎይዜ ነች›› አለ ዢን ፖል፡፡ ‹‹በመጠለያችን አንድ ታዋቂ ሰው ገባ ማለት ነው፡፡››
በእርግጥ ስለ አሎይዜ ሰምቼ ነበር፡፡ በልጅነቴ አንድ ሰው ጠንክሮ በመሥራትና በቁርጠኝነት በሕይወቱ የት እንደሚደርስ እርሷን በአርዓያነት እያነሱ ወላጆቼ በጣም ሲያወሩላት ሰምቻለሁ፡፡ አሎይዜ በዘጠኝ ዓመቷ የልጅነት ልምሻ ይዟት መራመድ ቢሳናትም በትምህርቷ ጥሩ ውጤት በማምጣት በሩዋንዳ ካሉ እጅግ ጎበዝ ልጆች አንዷ ለመሆን እንደበቃች ነግረውኛል፡፡ ስለሷ ከሰማሁት የማስታውሰው ያንን ብቻ ነው፤ ግን እንደተባለው በሀገሪቱ ዝና በማግኘቷ በመጠለያው ያሉ ብዙ ሰዎች ስለ እርሷ ሰምተዋል፡፡
ዢን ፖል እንደነገረኝ ባሏ ኪጋሊ ላይ በተመድ ውስጥ ይሠራ ስለነበር አሎይዜ ሁሉንም የሌሎች መንግሥታት መልዕክተኞች ማወቅ ችላለች፡፡ ‹‹ሁሉንም ሰው ስለምታውቅ ለማንም ቢሆን ጥሩ ሥራ ማግኘት ትችላለች›› አለኝ በአድናቆት፡፡ ሰዎች ‹‹አካል ጉዳተኛ ባትሆን ኖሮ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ትችል ነበር ይላሉ፡፡ ቱትሲ እንደሆነች አውቃለሁ፤ ግን የመንግሥት ኮንትራቶችን ለማግኘት ስትል የሁቱ መታወቂያ ደብተር ከዓመታት በፊት ገዝታለች … ይገርምሻል በጣም ቆራጥ ሴት ነች፡፡››
‹‹እንግዲህ ሄጄ ይህችን ዝነኛ እንግዳችንን እመዘግባታለሁ›› ብዬ ደብተሬን ያዝኩና ወደ ተሸከርካሪው ሄድኩ፡፡
አሎይዜ ከተቀመጠችበት ወንበር ሽቅብ እያየችኝ ደስታዋ ወዲያውኑ ተኖ ታለቅስ ጀመር፡፡ ‹‹ወይኔ አምላኬ፣ እናትሽን ቁርጥ እኮ ነሽ … አባትሽንስ ቢሆን! ሁልጊዜ አንቺንም ሆነ ቤተሰብሽን እጠይቃችኋለሁ እያልኩ አስብ ነበር፤ ሆኖም አልቻልኩም፡፡ ምን ይሄን እግር ይዤ እንዴት ይሁንልኝ!
ሴትዮዋ ራሷን የሳተች ወይንም ሌላ ሰው መስያት የተምታታባት መሰለኝ፡፡ እስካሁን አግኝቻት አላውቅ፤ ታዲያ ማንነቴን እንዴት ልታውቅ ትችላለች?
‹‹አእምሮዬን እንደሳትኩ አድርገሽ አትዪኝ ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ፡፡ ማን እንደሆንሽ በደንብ አውቃለሁ፡፡ አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልንና ወላጆችሽ - በጣም ጥሩ ወዳጆቼ ነበሩ፡፡›› አሎይዜ ልጆቿን አስቀምጣ፣ እንባዋን አባብሳ እጆቿን ዘረጋችልኝ፡፡ እንደዋዛ ቀረብ ብዬ እጆቼን ለሰላምታ ስዘረጋላት ክርኔን አፈፍ አድርጋ ጎትታ በደንብ አቀፈችኝ፡፡ ልትለቀኝ አልቻለችም፡፡ ‹‹እናትሽ ሕይወቴን አትርፋኛለች - ያን እንደማታውቂ እወራረዳለሁ! የስምንት ዓመት ልጅ ሳለሁ እናትሽ ትምህርት ብወድም ወላጆቼ ግን ሊያስተምሩኝ አቅሙ እንዳልነበራቸው ትሰማለች፡፡ እናም የአንድ ዓመት የትምህርት ክፍያዬን ሸፈነችልኝ … ታምሜ መራመድ ባቃተኝ ጊዜ እንኳን መክፈሏን ቀጠለች፡፡ በጣም ውለታዋ ስለከበደኝም በሕይወቴ አንድ ደረጃ ላይ መድረስ አለብኝ ብዬ ከማውቀው ከማንም ሰው አጠናን በላይ ማጥናት ጀመርኩ፡፡ ኢማኪዩሌ አሁን ያለኝ ነገር ሁሉ በእናትሽ ውለታ የተገኘ ነው፡፡ መልአክ ነበረች! አሎይዜ በስተመጨረሻም ከረጅም ጊዜ እቅፏ ስትለቀኝ ወደኋላዬ ተንገዳገድኩ፡፡ ከዚህች ጎበዝ ሴት ጋር በገጠመኝ በእንግዳው ክስተትም ተደናግጬ ራሴን ለማረጋጋት ራቅ ብሎ መሄድ አስፈለገኝ፡፡ ‹‹እስኪ ላንቺና ለልጆችሽ ትንሽ ምግብና ውሃ ልፈልግላችሁ›› አልኳት፡፡ ‹‹አሁኑኑ ተመልሼ እመጣና እመዘግባችኋለሁ፡፡››
እየሄድኩ ሳለሁ አሎይዜ ጠርታኝ ‹‹ኢማኪዩሌ እዚህ አንቺ ጋ ያመጣኝ የእናትሽ መንፈስ ነው መሰለኝ! ብድሯ ስላለብኝ አንቺን በማገዝ እከፍለዋለሁ፡፡ እስኪ ላስብበት፣ አንቺን የምረዳበትን መንገድ ልፈልግ›› አለችኝ፡፡
አንዲት በተሸከርካሪ ወንበር የምትሄድና እገዛዋን የሚፈልጉ ሁለት ትንንሽ ልጆች ያሏት ሴትዮ ምን ልታግዘኝ እንደምትችል እያሰብኩ ለሰላምታ እጄን አውለበለብኩና መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እግዚአብሔር በተዓምራዊ መንገዶች እንደሚሄድ ሊያስተምረኝ ነው፡፡
በቀጣዩ ቀን አሎይዜን ስመዘግባት
በሕግ ሁቱ ብትሆንም ባሏ ፋሪ፣ ቱትሲ እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ ያም ማለት ልጀቿ ሳሚና ኬንዛ እንደ ቱትሲ ይቆጠራሉ ማለት ነው፡፡ ለልጆቿ ደህንነት በማሰብ በኪጋሊ ያለውን ቤታቸውን ትታ ወደ ወላጆቿ ቤት ለመደበቅ ሄደች፡፡ ባሏ እሷ ስትሄድ ኮርኒስ ውስጥ የተደበቀ ቢሆንም ይዳን ይሙት የምታውቀው ነገር የለም፡፡
‹‹የእናትሽን ውለታ ለመክፈል ምን ማድረግ እንዳለብኝ ወስኛለሁ›› አለች አሎይዜ፡፡ ‹‹ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ እንዳበቃ ኪጋሊ ወዳለው ቤቴ እወስድሻለሁ፡፡ እንደራሳችን ልጅ ሆነሽ መኖር ትችያለሽ፡፡››
ስለ አሎይዜ ያላመንኩት አንድ ነገር አለ፡፡ ፈገግ ብዬ ስለ ቸርነቷ አመሰገንኳት፡፡ ቢሆንም በመጠለያው የተወሰኑ ጓደኛ ቤተሰቦች እንዳሉኝና አብረን ለመሆን ቃል እንደተገባባንም ነገርኳት፡፡ ትከሻዎቿን ነቅንቃ ከማምናቸው ሰዎች ጋር ለመቆየት መወሰኔ ግሩም ብልሃት መሆኑን ነገረችኝ፡፡ በዚያ ነገሩ ሁሉ የተቋጨ መስሎኛል፤ ሆኖም ግን በቀጣዩ ቀን ይህች ሴትዮ ከጓደኞቼ ጋር በተቀመጥኩበት መጣች፡፡
‹‹ኢማኪዩሌ ጉዳዩን አስቤበታለሁ፤ ታግተኛለች ብለሽ ካሰብሽ ጓደኞችሽን ሁሉ ወደ ኪጋሊ ማምጣት ትችያለሽ፡፡ ዘጠኛችሁንም በቤቴ አስቀምጣችኋለሁ! ቢጣበብም ይመቻል፡፡››
እርስ በርሳችን ተያይተን ተሣሣቅን፡፡ እንደዚህ ያለ እንግዳና ቸርነት የሚታይበትን ስጦታ እንዴት እንደምንቀበለው አናውቅበት አልን፡፡
‹‹አስቡበት›› አለች አሎይዜ ወንበሯን እያሽከረከረች በመሄድ ላይ ሳለች፡፡ ‹‹ከጦርነቱ በኋላ ለማድረግ የምታስቡት ሌላ ምን እንዳለ አላውቅም፡፡ ሁላችሁም ተሸብራችኋል … እናንተ ልጆች እዚያች ከተማ ባለ ምርጥ ቤት ኑሩ ብዬ ልለምናችሁ መገደዴን ላምን አልችልም፡፡ ጦርነቱ እያለቀ ነው - ስለ ወደፊቱ ሕይወታችሁ ማሰብ ጀምሩ እንጂ!››
አሎይዜ ትክክል ነች፡፡ ዋና ከተማዋ በአማጽያኑ ቁጥጥር ስር ውላለች፤ ጦርነቱም ፍጻሜ ሊያገኝ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ሁላችንም ቤተሰቦቻችንን፣ ቤታችንንና ልብሳችንን ሳይቀር ያጣን ሲሆን ከኛ መካከል አንዲት እንኳን ሳንቲም ያለው ሰው የለም፡፡ የአሎይዜን ችሮታ መቀበል ጥሩ ውሳኔ መሆኑን ለመወሰን ረጅም ጊዜ አልወሰደብንም፡፡ በማግስቱም ችሮታዋን ለመቀበልና ለማመስገን በአንድነት ሄድን፡፡
‹‹እኔን አታመስግኑኝ፤ የኢማኪዩሌን እናት እንጂ›› አለች፡፡ ‹‹ይህን የማደርገው ስለ ሮዝ እንጂ ስለ እናንተ አይደለም!››
ለራሷ መሣቅ ጀመረች፤ ከዚያም እንደገና ልባዊ የደስታ ሣቅ በምሽጉ ሙሉ እስኪያስተጋባ ድረስ ቀጠለች፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «#ሁቱትሲ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ #የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች ፡ #ትርጉም_በመዝምር_ግርማ ፡ ፡ #የስደተኞች_መጠለያው_ምቾት ፡ ፡ የፈረንሳዮቹ የስደተኞች መጠለያ የታጠቁ ወታደሮች የሚጠብቁት፣ ለቱትሲዎች ከለላ የሚሰጥና ሁቱዎችን የሚያገል ስፍራ ነው፡፡ ወታደሮቹ ስምንት ታንክ-መሰል ብረትለበስ ተሸከርካሪዎችን በግማሽ ክብ ቅርጽ ከትምህርት ቤቱ ሕንጻዎች ፊት ለፊት ያቆሙ ሲሆን የምሽጉን…»
#እኔ_ግን ....

አውቃለሁ ታውቂያለሽ
ለኔ አትገቢኝም
በውበት ካንቺ ጋር
አልወዳደርም
አውቃለሁ ታውቂያለሽ
ላንቺስ አልገባ
ተንሰፍስፈውልሽ
ባለሀብቶች ሁላ
አውቃለሁ ታውቂያለሽ
አላገኝሽ ከቶ
ከኔ የተሻለ
አገር ምድሩን ሞልቶ
አውቃለሁ ታውቂያለሽ
እንደማትፈልጊኝ
ወይ ዝና ወይ ክብር
ምንም ስለሌለኝ
ይህን ግን አታውቂም
አውቃለሁ ግን እኔ
በእውነት ያፈቀርኩሽ
ብቸኛው ሰው ሆኜ
እንደምናፍቅሽ
ለህይወት ዘመኔ
አውቃለሁ ግን እኔ፡፡