#ቄስ_ቫላንቲ_ሆይ……
እንዴት ሰንብተዋል ኑሮዎት እንዴት ነዉ
ይሄዉ ተገናኘን መሰንበት ደግ ነዉ
እኔ ብቻየን ነኝ ዛሬም ልክ እንዳምናዉ
የክህደት ባንዴራ ህይወታችን መሀል
ከፍ ብሎ ሲሰቀል
ጥንድ መሆን ህመም ብቻነት ይበጃል
የኔን ነገር ተዉት ይቅር አይነሳ
ግን እንደዉ ግንሳ….
የባለፈዉ ለታ የቫላንቲኖ ቀን
ህዝቤ ያረገዉን መቸም አይረሱትም
ከሰሜን ደቡብ ጫፍ ከምራብ ምስራቅም
ተፋቀርን ያሉ ጥንዶች ባደባባይ
ቀይ አበባ ይዘዉ…
ቀይ ወይን ተጎንጭተዉ…
ጉዋዳ ጎዳናዉን በቀይ አስሸብርቀዉ
ቀይ ጠረጴዛ ቀይ ስጋጃ ላይ
በጥንዶች ተሞልቶ አለም ቀልቶ ሲታይ
እዉነት እንዳይመስሎት ቄስ ቫላንቲኖ ሆይ
እዉነት እዉነት እዉነት
አለም ቀልቶ አይደለም ቀንቶ ነዉ እዉነቱ
እሽ አሁን የት አሉ አምና የቀሉቱ
ቀንተዉ ነዉ በሰዉ ቀይ አበባ ይዘዉ
ሲሉ ሰምታን ሰምተዉ ያለ ሀቁ ናዉዘዉ
ሲነጋ የጠፉት ቀዩን ካርድ መዝዘዉ
በእዉነት ቫላንቲኖ
እርስዎ ደክመዋል እርስዎ ለፍተዋል
ለፍቅረኞች ሲሉ ህይወት ሰዉተዋል
ግና ባደባባይ እዩኝ ያለ ፍቅር
እዩኝ ያለ ህይወት
መሰረት ከሌለዉ
በረከት ከሌለዉ ንፋስ ሽዉ ያለ ለት
ፍጻሜዉ ቀይ ነዉ ቢጫም አይገባበት
ቫላንቲኖ አባቴ….
ግዜዉ ተለዉጡዋል ዘመን ለዛዉ ከፍቱዋል
ታሪክ ተቀይሩዋል
በእርግጥ በእርሶ ዘመን
ንጉስ ወጣቶቹን እንዳይጋቡ አዙዋል
ይህም ክፉ ትዛዝ እርሶን አስከፍቱዋል
አሁን በኛ ግዜ
ወጣቱ ይጋባል ግን ወድያዉ ይፋታል
ለምን?
የተሸበረ ልብ የፈራ ሰዉነት
ትዳርን አይደለም የራሰንም ህይወት
መሸከም ይፈራል
በእዉነት ቫላንቲኖ አለም ተሸብሯል
ቀይ ሲያይ…. ሹፌሩ ይቆማል
ቀይ ሲያይ….ኩዋሰኛዉ ይወጣል
ቀይ ሲያይ….ቀይ ሲያይ
የከፋዉ ሀገሬዉ ልቡ ይሸበራል
ባክዎን አባቴ
ባክዎን አባቴ
የሚቀጥለዉን ዳግመኛ ሲመጡ
ቀይ አበባ ጥለዉ…
እንደ ኖህ እርግብ ከሳር ከቀንበጡ
አረንጉዋዴ ቅጠል ጨፌ ይዘዉ ይምጡ
⚪️በሰለሞን ሰሃለ⚫️
እንዴት ሰንብተዋል ኑሮዎት እንዴት ነዉ
ይሄዉ ተገናኘን መሰንበት ደግ ነዉ
እኔ ብቻየን ነኝ ዛሬም ልክ እንዳምናዉ
የክህደት ባንዴራ ህይወታችን መሀል
ከፍ ብሎ ሲሰቀል
ጥንድ መሆን ህመም ብቻነት ይበጃል
የኔን ነገር ተዉት ይቅር አይነሳ
ግን እንደዉ ግንሳ….
የባለፈዉ ለታ የቫላንቲኖ ቀን
ህዝቤ ያረገዉን መቸም አይረሱትም
ከሰሜን ደቡብ ጫፍ ከምራብ ምስራቅም
ተፋቀርን ያሉ ጥንዶች ባደባባይ
ቀይ አበባ ይዘዉ…
ቀይ ወይን ተጎንጭተዉ…
ጉዋዳ ጎዳናዉን በቀይ አስሸብርቀዉ
ቀይ ጠረጴዛ ቀይ ስጋጃ ላይ
በጥንዶች ተሞልቶ አለም ቀልቶ ሲታይ
እዉነት እንዳይመስሎት ቄስ ቫላንቲኖ ሆይ
እዉነት እዉነት እዉነት
አለም ቀልቶ አይደለም ቀንቶ ነዉ እዉነቱ
እሽ አሁን የት አሉ አምና የቀሉቱ
ቀንተዉ ነዉ በሰዉ ቀይ አበባ ይዘዉ
ሲሉ ሰምታን ሰምተዉ ያለ ሀቁ ናዉዘዉ
ሲነጋ የጠፉት ቀዩን ካርድ መዝዘዉ
በእዉነት ቫላንቲኖ
እርስዎ ደክመዋል እርስዎ ለፍተዋል
ለፍቅረኞች ሲሉ ህይወት ሰዉተዋል
ግና ባደባባይ እዩኝ ያለ ፍቅር
እዩኝ ያለ ህይወት
መሰረት ከሌለዉ
በረከት ከሌለዉ ንፋስ ሽዉ ያለ ለት
ፍጻሜዉ ቀይ ነዉ ቢጫም አይገባበት
ቫላንቲኖ አባቴ….
ግዜዉ ተለዉጡዋል ዘመን ለዛዉ ከፍቱዋል
ታሪክ ተቀይሩዋል
በእርግጥ በእርሶ ዘመን
ንጉስ ወጣቶቹን እንዳይጋቡ አዙዋል
ይህም ክፉ ትዛዝ እርሶን አስከፍቱዋል
አሁን በኛ ግዜ
ወጣቱ ይጋባል ግን ወድያዉ ይፋታል
ለምን?
የተሸበረ ልብ የፈራ ሰዉነት
ትዳርን አይደለም የራሰንም ህይወት
መሸከም ይፈራል
በእዉነት ቫላንቲኖ አለም ተሸብሯል
ቀይ ሲያይ…. ሹፌሩ ይቆማል
ቀይ ሲያይ….ኩዋሰኛዉ ይወጣል
ቀይ ሲያይ….ቀይ ሲያይ
የከፋዉ ሀገሬዉ ልቡ ይሸበራል
ባክዎን አባቴ
ባክዎን አባቴ
የሚቀጥለዉን ዳግመኛ ሲመጡ
ቀይ አበባ ጥለዉ…
እንደ ኖህ እርግብ ከሳር ከቀንበጡ
አረንጉዋዴ ቅጠል ጨፌ ይዘዉ ይምጡ
⚪️በሰለሞን ሰሃለ⚫️
❤1
#የቤት_እመቤት_በመሆን_ውስጥ_እመቤትነት #አለ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
በአንድ ወቅት፣ ያገኘኋቸውን ወንዶች በሙሉ አንድ ጥያቄ ስጠይቅ ነበር፤ "የቤት እመቤት ማለት ምን ማለት ነው?" ከአንድ ወይም ሁለት መልሶች ውጪ የተሰጡኝ ፍቺዎች በሚከተሉት ሐረጎች ሊጠቃለል ይችላል።
"የማትሰራ ሴት"
"ሥራ የሌላት ሴት"
"ገቢ የሌላት ሴት"
"ሥራ አጥ ሴት"
"ሥራ ፈት ሴት"
እነዚህ መልሶች የሰጡኝን ወንዶች መልሼ ይሄንን ጥያቄ ጠየኳቸው።
ነጋ ጠባ አልጋ ማንጠፍ፣ ቆሻሻ ልብስ ማጠብ፣ የታጠበ ልብስ ማጠፍ፣ የታጠፈ ልብስ በየቦታው ማስቀመጥ፤ ከሻይ ማንኪያ እስከ በርሜል ሙልጭ አድርጎ ማጠብ ፣ የታጠበውን እቃ ማድረቅ ከሻይ ማንኪያ እስከ በርሜል ሙልጭ ተደርጎ የታጠበና የደረቀ እቃን በየቦታው ማስቀመጥ፣ ሥራ አይደለም?
በየቀኑ ከኩሽና እስከ ሳሎን ፤ ከሽንት ቤት እስከ ግቢ መጥረግና መወልወል፤
ከሳሎን ጠረጴዛ እስከ ቁም ሳጥን ጀርባ እና አልጋ ሥር ድረስ መጥረግና መወልወል፤
የቤቱን ሁሉ የተጠረገና የተወለወለ ቆሻሻን ሰብስቦ መጣልስ ፤ ሥራ አይደለም ?
ቀን ቆጥሮ አንሶላ ፤ ትራስ ልብስና አልጋ ልብስ መቀየር ፤ ጊዜን አስልቶ የኩሽና እቃ ግልብጥ አድርጎ አውጥቶ ማጽዳት፤ ጊዜን ወስኖ የመስኮትና የበር መስታወትን በጋዜጣ ሲያፀዱ እና ሲያስውቡ መዋል ፤ የአደፈ መጋረጃን መሐወጥ፤ ሥራ አይደለም?
"ምን አለቀ?" ብሎ ቀለብ መሸመት ፤ የተሸመተውን አመጣጥኖ ማዘጋጀት፤ የተዘጋጀውን ማቅረብና ቤተሰብ መመጠብ፤ ሥራ አይደለም? ደግሞ ከሁሉ በላይ፤
ልጅ ማርገዝ፤
ልጅ አምጦ መውለድ፤
ልጅ አጥብቶ ማሳደግ፤
ልጅ ማነጽ፤
ልጅን ለወግ ማብቃት ፤ ሥራ አይደለም?
እናም ወንድሞቼ...
አገልግሎትና ምርታማነት በጥሬ ገንዘብ በሚተመን የኢኮኖሚ ሥርአት ውስጥ በመኖራችን ብቻ ፤
በቀጥታ የገንዘብ ክፍያ የማያስገኝ ሥራ እንደ ሥራ በማይቆጠርበት ዓለም በመኖራችን ብቻ ፤ ይሄንና ሌላም ልዘረዝረው ብል መጽሀፍ የማይበቃውን ሥራ ሁሉ የምትሰራን ሴት "ሥራ የላትም" አትበለኝ።
ይልቅስ፣ በእኛ ሀገር የቤት እመቤት መሆን ፤ ከእመቤትነቱ ሸክሙ ይበልጣልና ፤ ሚዛናችሁን አስተካክላችሁ የቤት እመቤት ማለት ፤ "በዓለም ላይ ከባዱን ፤ ግን ክፍያ የሌለውን ሥራ የምትሰራ ሴት ማለት ናት" በሉኝ።
💫ጨረስን💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

#ብሌን 🇪🇹
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በዮርዳኖስ
"እና መጀመሪያ ምንድነው ምንገዛው?" አለችኝ።ገበያ ደርሰን ነበር ገበያው ያን ያህል አልደራም ቢሆንም በቂ ሱቆች ተከፍተዋል።"አንቺ የፈለግሽውን" አልኳት
"እንደዛ ከሆነ ነይ በዚ እንቁላል እና ወተት አንግዛ"
በአትክልት ተራው አልፈን ወደ እህል ተራ በሚወስደው መንገድ ስንደርስ በአንደኛው መታጠፊያ ይዛኝ ገባች።ወደ ትልቁ የገበያ አዳራሽ ማዕክል እና የቤት እቃዎች በመሸጫዎች መሀል አቋርጠን እዛው ወዳለው ወደ ወተት ተራው ገባን።"ደንበኛዬ አልመጣችም በዛ ላይ ሀይላንድ ያስፈልገኛል መጣው እዚሁ ጠብቂኝ"ብላኝ ሔደች ትኩረቴ እሷ ጋር ስላልነበረ ግድ አልሰጠኝም ነበር።ግራና ቀኙን መቃኘት ጀመርኩ አንዳንድ እቃው ባለሱቆች ገና ከፍተው እቃ በማውጣጣት ላይ ሲሆኑ አብዛኛው ጨርሶ ቁጭ ብሏል።የማውቀውን ሰው ፍለጋ ይመስል ሁሉንም እያስተዋልኩ አያለው።
"ኧረ እማ እንሒድ በቃ ለኔኮ ጫማ አልገዛንም..."
"አይ የልጅ ነገር በቃ ከራስህ ውጪ አታስብም አይደል መጀመሪያ የምንበላውን ልገዛ እስኪ" እናትና ልጅ ትኩረቴን ስለሳቡኝ እሰማቸው ጀመር።
"ገና እኮ ጠዋት ነው ማሙሽ ሱቁም በደንብ ይከፈት እናትህን አታስቸግራት እንጂ" ሌላኛዋ ሴት እንቁላል ለእናትየው እያቀበለቻት የእንቁላል ነጋዴ ነች።
"እሺ እዛጋ ያንን"ህፃኑ ለናቱ እየጠቆማት እድሜው በግምት ወደ ሰባትና ስምንት የሚጠጋ ይመስላል።
"ምን የቱ ጋር?" አለች እናቱ።እኔም ጥቆማውን ተከትዬ አይኔን ጣልኩ
"ምንድ ነው እሱ አትናገርም እንዴ?" እናትየው የታያት አይመስልም እኔ ግን በትክክል አይቼዋለው የልጁ እሳቤ ቀድም የነገረኝ ይመስል ተረድቼዋለው።በቀስታ ወዳየሁት ነገር መራመድ ጀመርኩ።
"ያውና ሰው የሚታረድበት ነገር እኮ ነው!!"
"ምን.... ?በስመአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ!!"
እናትየው እንቁላሉን ስትለቅ ይሰማኛል።እግሬ አየተንቀጠቀጠ ቀረብኩ በቁጥር በዛ ያሉ ስለታቸወና አዲስነታቸው ከሩቅ የሚያብለጨልጭ ባንጋዎች ናቸው ሰውነቴን አየሰቀጠጠኝ አጠገቡ ቆሜ ወደታች አየውት።
"ደሞ ኬት አመጣኸው ይሄንን? ሁለተኛ አንደዚ እንዳትል እሺ አባቴ ሁለተኛ!! ና ከዚ እንሒድ"የናትየው ድንጋጤ ከድምጿ ቃና ይታወቀኛል።የሷ ብቻ አይደለም እኔም ፍርሀቴ ሲጀምረኝ እና ወደነዛ ቀናት በትውስታ የተመለስኩ ሲመስለኝ ይተወቀኛል። ህፃኑ ያለው በአይምሮዬ ተስሎ ታየኝ።
ይሄ ነው እንግዲ የማንነት የትውልድ ኪሳራ፣ ይሄ ነው እንግዲ አዲሱ ለትውልድ የምናስተላልፈው ታሪክ እና ገድላችን ፣ይሄ ነው እንግዲ ሰውነት ከእንስሳነትም ከእቃነትም ተራ አልፎ የረከሰበትና የቀለለበት ዘመንና ትውልድ ፤ይሄ ነው የማንነት ክስረት። ይሄንን የማንነት ውደቀታችን ነው በታናናሾቻችንና በልጆቻችን አይምሮ እየሞላንና እየቀረፅን ያለነው።
"ጉድ እኮ ነው አንቺ ይሄ ህፃን እንኳ እንዲ ይናገር....አጃኢብ!!!
"ሰማሽ አይደል ለነገሩ ምን ያድርግ በሱም አይፈረድም።እነሱስ ቢሆኑ ሰው እንደዚ በተጨካከነበትና በሚጨራረስበት ወቅት እንደዚ በሰፊው ይሄን መነገዳቸው ምን ማለታቸው ነው? እንዲያው ሲያዮት እንኳ አንዴት ይዘገንናል!"።
"ሔዊ ምነው" ደንዝዤ ከቆምኩበት የቡርቴ ጥሪ ከኋላዬ ተሰማኝ።"እንዴ እያለቀሽ ነው እንዴ ሔዋን ምነው የኔ ወድ?"
የተናነቀኝን እንባ እያየች።ግን የድንጋጤ እና የፍረሀት ወይም
የሀዘን እንባ አልነበረም ቁጭትና እልህ እና ንዴት እንጂ።
"የኔ ጥፋት ነው ይዤሽ መውጣትም ሆነ ብቻሽን መተው አልነበረብኝም"እንባዬን አየጠረገች።
"ቡርቴ..?"አልኳት"ሁለቱን ሳምንት ታግቼ ነበር አይደል? ለነገሩ እሱ በጣም ግልፅ ነው ደሞም ይሄንን አባቴም ሆነ አንቺም በደንብ ታውቃላቹ!!
"ምን...? ለምንድነው እንደዚ የምትይው ነይ ከዚ አንሂድ መዳኒትሽን መውሰድ አለብሽ..."እጄን ይዛ ጎተተችኝ።
"አይ አይሆንም ለቀቂኝ!"እጄን አስለቀኳት
"አቁሚ በጭራሽ አልሄድም አሁን ባልሺኝ መሰረት የምጠይቅሽን እሺ በማለት ታደረጊያለሽ!"ጥያቄ ሳይሆን ትዕዛዝ ነበር።
#ሕዳር 20/12 ቀን የታገቱ ተማሪዎች እስካሁን ድምፃቸው አልተሰማም።
ይላል ሙሉ ዜናውን ለማግኘት ፔጁን ተቀላቀልኩ።
January 24
#ከ 35 ሺህ በላይ ተማሪዎች ቤታቸው ናቸው።በአንዳንድ የሀገሪቱ ዮኒቨርስቲዎች ውስጥ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት መደበኛ ት/ታቸውን አቋርጠው የተመለሱ ተማሪዎች ወደ ትም/ት ገበታቸው አልተመለሱም።
#የኢትዮጵያ የሳይንስና የከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር በ22ቱ ዮኒቨርስቲዎች ባካሄደው ምርመራ እና ቅኝት በግማሽ መንፈቅ ዓመት ብቻ የ12 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
=> ታህሳስ 27
ሌሎች የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉና ቁጥራቸውም 4 እንደሚደርስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳዶር በጋዜጣዊ መግለጫ የገለፁበት ቀን
#በሕዳር 20/12 ስለታገቱ ተማሪዎች የጠቅላይ ሚንስተሩ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬተርያት በሰጡት መግለጫ፦አጠቃላይ 27 ተማሪዎች ታግተው እንደነበረና 21ዱ መለቀቃቸው 6ቱ ደግሞ ታግተው እንዳሉ ገልፀዋል።የሚልና ሌሎች ተመሳሳይ የወጡ ዜናዎችን በብዛት ካየሁ ቡሗላ
አሁን ሁሉም በግልፅ የገባኝ መሰለኝ።
የሰጠሗትን ትዕዛዝ ላለመቀበል ጋሼ ቢጠየቁኝስ ምን እላቸዋለው?"ነበር ያለችኝ እኔም
ቃል በገባሁላት መሰረት አባቴ ሳይመለስ ቀድሜ ቤት ለመገኘት ከሷ እንደተለየው ጊዜ ሳላባክን ወደ ኢንተርኔት ቤት ነበር ያመራሁት።እና የምፈልገውን ካየው ቡሗላ ቶሎ እሷ ጋር መሄድ ስለነበረብኝ ባጃጅ አስቁሜ ገባው ውስጤ ብዙ ሀሳብ ይመላለሳል ግን የትኛውን በትክክል መስማት እንዳለብኝ እንጃ። እስካሁን ምንም ባለማወቄ እና በዝምታዬ የተሞኘውም መሰለኝ
ሀገሪቱ ላይ የሚካሄደውና የሰው ሁኔታ ግን ግርምትን የሚያጭር ነው። ምንም እንዳልተፈጠረ መኖራችን አስገርሞኛል። ለምሳሌ ያለሁበት ባጃጅ ሹፌር ዕድሜው ከኔው ጋር ተመሳሳይ ነው። እርግጠኛ ነኝ በነዛ ወጣቶች ላይ የተፈጠረውን/ይቅርታ በኛ ላይ ልበል እንጂ ስለተፈጠረውና ስለተፈፀመው ድርጊት በሚገባ ሰምቷል።እና ናላ በሚያዞር ምንነቱ በማይገባ ዘፈን ባጃጁን መጓጓዣ ሳይሆን ክለብ አስመስሎ እስከቂጡ ከፍቶ ባጃጇን እንደ አየር ያከንፋታል። ተማሪዎች ከየት/ት ቤታቸው ተለቀው በተለያየ ዮኒፎርማቸው ሲተራመሱ ይታያሉ። ይሄን ሁሉ ጊዜ ቤት መጥቼ ቁጭ ስልም ሆነ ስወጣ ማንም ሰው ስለነዛ ልጆች ሲያወራ ና ሲያነሳ አጋጥሞኝ አለማወቁም የማይታመን ነው
ሚድያዎቻችንም ቢሆኑ
ከምንም በላይ ያስገረመኝ ግን የራሴው አባት ነው።ምንም ያሀል ልጁን የሚወድ አባት ሊሆን ይችላል ግን ደሞ ይሄ ትልቅ ራስ ወዳድነት ይመስለኛል።ስለኔ ብቻ ሳይሆን የሌሎቹም ነብስና መጨረሻ ሊያሳስበው ይገባ ነበር።
ለማንኛውም ግን ማወቄንም ሆነ ማስታወሴን በድብቅ ለመያዝ እና ለመቀጠል ወስኛለው ምክንያቱም ማንኛውም ወላጅ ቢሆን ለጁ እንዲያደርግ እማይፈልገውን ነገር ለማድረግ ስለወሰንኩ ነው።በርግጥ አንደማንኛውም ሰባዊ ሰው ሲታይ ልክ የሆነና ተገቢ ድርጊት ሊሆን ይችላል።እንደ ወላጅ ግን አይደለም!
" ደርሳሻል እናት"አለኝ ወጣቱ ባለባጃጅ ድምፁን ከፍ አድርጓ፤ እስኪ ምናለበት ከመጮህ ዘፈኑን ቢቀንሰው ያለኝን ብር ከፍዬ በፍጥነት ወደቤት ገባው።አባቴ ገና አልመምጣቱ ካረጋገጥኩ ቡሗላ ወደ ቡርቴ ሮጥኩ
"ውይ ተመስገን ለትንሽ ነው የደረሽው"አለችኝ
"ቡርቴ..?"
"እ...?"
"ብሌንስ...??"ውስጤ ሲመላለስ የነበረውን ጥያቄ ጠየኳት።
፡
፡
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየታችሁ እንዲሁም ማስተካከል ያለባት ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት

👍1
#ዝግመትሽ_እና_ፍጥነቴ
፡
፡
የፍቅሬን መጠን ነግሬሽ - ካደመጥሺኝ ቡኋላ
ላስብበት ብለሽ ሄድሽ - እንደቆምኩኝ ካውላላ
በብስለት ሁሉን መርምረሽ- ክፉና ደጉን መዝነሽ
ስለ እኔ ጀርባ አጥንተሽ - ጓደኛ ዘመድ አማክረሽ
ከወር በኋላ ብትመጪ- ልትነግሪኝ ፈቀድኩ ብለሽ
የጊዜ አጠቃቀመችን - ልዩነታችን ገረመኝ
ዝግመትሽ እና ፍጥነቴ - ሁለቱም አስደመመኝ
ቆየው እኮ ሌላ አፍቅሬ - ቀለበት አስሬአለሁ
በዚህ ግርግር መሃል - አንቺን እረስቼለሁ
ዛሬ ይሁን ስትይኝ - ምን መልስ እሰጥሻለሁ።
፡
፡
የፍቅሬን መጠን ነግሬሽ - ካደመጥሺኝ ቡኋላ
ላስብበት ብለሽ ሄድሽ - እንደቆምኩኝ ካውላላ
በብስለት ሁሉን መርምረሽ- ክፉና ደጉን መዝነሽ
ስለ እኔ ጀርባ አጥንተሽ - ጓደኛ ዘመድ አማክረሽ
ከወር በኋላ ብትመጪ- ልትነግሪኝ ፈቀድኩ ብለሽ
የጊዜ አጠቃቀመችን - ልዩነታችን ገረመኝ
ዝግመትሽ እና ፍጥነቴ - ሁለቱም አስደመመኝ
ቆየው እኮ ሌላ አፍቅሬ - ቀለበት አስሬአለሁ
በዚህ ግርግር መሃል - አንቺን እረስቼለሁ
ዛሬ ይሁን ስትይኝ - ምን መልስ እሰጥሻለሁ።
#ጫፍ_አልባ_ቁልቁለት
፡
፡
የያዙትን ይዞ ካልተጠላጠሉ
ወደ ላይ ካላሉ
ወ
ደ
ታ
ች
እ
ያ
ዩ
መውደቂያ ካሰሉ
ከውድቀት ዳርዳሩ ከተንደረደሩ
መውደቅ ከጀመሩ
ውድቀት ጫፍ የለውም
ሜዳዉ ቁልቁለት ነው ውድቀት ዳር የለውም
በውድቀት ላይ ውድቀት እየተያያዘ እየተዋዋለ
ከውድቀትም በታች ሌላ ውድቀት አለ።
፡
፡
የያዙትን ይዞ ካልተጠላጠሉ
ወደ ላይ ካላሉ
ወ
ደ
ታ
ች
እ
ያ
ዩ
መውደቂያ ካሰሉ
ከውድቀት ዳርዳሩ ከተንደረደሩ
መውደቅ ከጀመሩ
ውድቀት ጫፍ የለውም
ሜዳዉ ቁልቁለት ነው ውድቀት ዳር የለውም
በውድቀት ላይ ውድቀት እየተያያዘ እየተዋዋለ
ከውድቀትም በታች ሌላ ውድቀት አለ።
👍1
#ብሌን 🇪🇹
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በዮርዳኖስ
ቤቱን የሞላውን ሁካታ ጩኸት ለማስቆም ሁለተኛው ጥይት ተተኮሰ ተኩሱን ተከትሎም ሁሉም ዝም አለ ቤቱን እንደገና ፀጥታ ወረሰው።
ፊትለ ፊታችን ከተጋደመው እሬሳ ትኩስ ደም እየተምዘገዘገ ወደስራችን ቁልቁል ይወርዳል።ግን ሁላችንም በፍራቻና በድንጋጤ ትንፋሻችን እንኳ እንዳይሰማ ሆኖ ዝም አልን ማንም አያለቅስም
መጮህ አይታሰብም ምክንያቱም በተነፈሰው ሁለት ቃል ምክንያት ወደ ሞት የተሸኘውን ሁሉም ስላየ ስቅስቅታ የለም የሚቆራረጡ ትንፋሾች እንጂ ተጨንቆ በተለይም ሰሚም ሆነ ደራሽ እንደሌለ አውቆ ተስፋ እንደመቁረጥ ፈርቶ መሽሽና ማምለጥ እንዳለመቻል ሞትን እያሰቡና ፊት ለፊት እየተጋፈጡት ማልቀስ እየፈለጉ አንዳለማልቀስ መጮህ እየፈለጉ አንዳለመጮህ ምንም ማለትና መደረግ እንዳለመቻል እሚያም ነገር የለም።
የሚከተለውን በማሰብ ማንም ደሙን ለመሸሽ ንቅንቅ አላለም።
ለመዳን መፀለይ ይኑርብኝ ንሰሀ መግባት አላወኩም ግን ሁለመናዬ ይንቀጠቀጣል ልብ ምቴ ለሁሉ እሚሰማ እስኪመስለኝ ድረስ በፍጥነት ይመታል ትንሽ ቆይቶ ግን መቆሙ እማይቀር ይመስላል እየሆነ ያለው እና የማየውን በህለሜ ይሁን በውን እንጃ ግን በህሌሜ ከሆነ ለምን አልባነንኩም ስል አሰብኩ በውኔ ከሆነ ደግሞስ እንዴት ተቋቋምኩት?
አጋቾቻችን አና ገዳያችን እርስ በእርሳቸው መነጋገርና መጯጯህ ጀመሩ።እኛ ብቻ ሳንሆን እነሱም መጠነኛ ድንጋጤ የደነገጡ ይመስላል።እኛን ትተው እርስ በእርስ ጭቅጭቅ ጀመሩ "ለምን?" የሚል ጥያቄና ቁጣም እያቀረቡበት ይመስላል። እሱም ሳይፈራ "እንኳን!"የሚል በሚመስል ልበሙሉነትና ቁጣ በጩኸት ይመልስላቸዋል።ከዚ በላይ ግን የሚሉትን ለመረዳት አልቻልኩም።
ድንገት ያለንባት በረት መሳይ ትንሽዬ ቤት በር ከፍተኛ ድምፅ አሰምቶ ተከፈተ።
እንደገና ጩኸት።
እኛን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ያስደነገጠ ክስተት ሆነ።
"አንዳትንቀሳቀስ...! እንዳትንቀሳቀስ ብያለው እንዳትበላሽ ዋ...!!"አለ ከውጭ የሚመጣ ድምፅ። ጠመንጃውን አስቀድሞ በቀስታ ወደ ውስጥ ዘልቆ ብቅ እንዳለ "ልጆች እዚ ምን እየተካሄደ ነው.."አሉ በዕድሜ ጠና ያሉት ሽማግሌ ሁሉንም በጥንቃቄ እያዮ።የመጀመሪያው አማረኛ ተናጋሪ ናቸው አይናቸው ውስጥም ክፋት ወይምን ጭካኔ አይታይም እንደውም ገፅታቸው ርህራሄ ይነበብበታል።ከሰማይ የመጣ አዳኝ መለዓክ ይሆን እንዴ..?አልያም አምላክ አዝኖ እኛን ለማስመለጥ የላከልን ታዳጊያችን ሰው ይሆኑ?! ብቻ ግን ውስጤ እንደገና በተስፋና ዳንኩ በምትል ትንሽ የደስታ መንፈስ ሲወራጭ ተሰማኝ።እኔን ብቻ ሳይሆን ሁሉም እንደዛ ያሰበ ይመስለኛል።
ግን ድንገት ከመካከላቸው አንድ ተነስቶ "እንዴ....ጋሽ ሽመልስ...! እርሶ ኖት እንዴ...?"አለ ለሰላምታ እቀፉን እያዘጋጀ።አማረኛው ጥርት ያለ ነው ግን እስካሁን አንዲትም የአማረኛ ቃል አልተነፈሰም ነበር።
"እህ...ሙሴ ጎረምሳው አንተም አለህ እንዴ...?ታድያ ምን አያደረጋችሁ ነው?"የፊት ገፅታቸውን ወደ ቁጣ ቀይረው ጠየቁት።
"ኧረ ሰላም ነው ምንም አይደል አጎቴ..."አለ
እንዳሰብነው ሳይሆን ቀረና ሔዶ ተጠመጠመበት ተቃቀፉ ያብቻ አይደለም ሌላ በእድሜ ተለቅ የሚለውና ዋናው አዛዥ የሚመስለውም ተነስቶ በክብር ሰላም አላቸው ና ማውራት ጀመሩ።ሁሉም የሚያውቋቸው ና የተከበሩ የአከባቢው ነዋሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሁኔታቸው መገመት ይቻላል። ግን ተወላጄ እንዳልሆኑ ግለፅ ነው።ባዩት ነገር እንደደነገጡና እንዳዘኑም የፊት ገፅታና አስተያየታቸው ያሳብቃል።በርግጥም ሊያድኑን ፈልገዋል ሆኖም ምንም ያህል ደግ ቢሆኑም አና ሀዘኔታ ቢኖራቸውም ግን እነሱን መቃወም ሆነ እንዲለቁን ማድረግ እንዳልቻሉ ግልፅ ሆኖልን ነበር። አይናቸው ላየ ሀዘኔታ ይነበባል ጥለው ለመሄድ አልፈለጉም። እሳቸውም የማይችሉት ነገር እንደሆነ ተረድተዋል ቢሆንም እርዳታን እሚማፀኑና የሚያለቅሱ አይኖች በተስፋ እሳቸው ከማየትና ከመጠበቅ አልቦዘኑም።
"አይ እንደዛ ከሆነማ እሺ እኔ ደሞ ምን ተፈጠረ ብዬ እኮ ነው።እንዲያ ከሆነማ..."ለአፍ ይበሉ እንጂ ከልባቸው አይደለም የሚናገሩት።
"አይ እርሶን አያሳስቦት ቀላል ነገር ነው ያው እንዳለኮት ነው አንጎዳቸውም ታውቁ የለ..."ይላል ከመጀመሪያው ተነስቶ ያቀፋቸው ሰው።
ፊታቸው ቅራኔን እንደተሞላ ደጋግመው አየተዟዛሩ ካዮን በበሗላ ለአራጆቻችን ጥለውን ወጡ።ግን ውስጤ ተስፋ አልቆረጠም ከሁኔታቸው አንዳየሁት ሰዎችን ይዘው ተመልሰው መተውም ቢሆን ከማዳን ወደ ሗላ እንደማይሉ እርግጠኛ ሆኜባቸው ነበር።
"ምንም ችግር አይፈጠርም..?"አለ አንደኛው ሰው
"የዚው አከባቢ ሰው ናቸው አሳልፈው አይሰጡንም"አለ አጎቴ ሲል የነበረው።
"አይ አይመስለኝም"አለ አዛዡ በአይን ምልክት አንዲከተሉት ትዕዛዝ እየሰጠ።
ወዲያው ሁለት ሰዎች በፍጥነት ተከታትለው ወጡ።
እንደገና ቋንቋቸውን ቀይረው መጨቃጨቅ ጀመሩ መጀመሪያውም ያልተስማሙት አጋቾች እንደገና በነዚ ሰው ምክንያት አለመግባባት የተፈጠረባቸው ይመስላል።ቋንቋውን በፍፁም ሰምቼው አላውቅም ምናልባት ብዙ እማይነገር የአንዱ ብሔር ቋንቋ ሊሆን ይችላል አልያም ደግሞ እዚው ለመግባቢያ የፈጠሩት ሌላ የኮድ ቋንቋ ሊሆን ይችላል።ሁለተኛውን የመሆን እድሉ ግን ሰፊ ይመስለኛል።
እኛ ታዳጊ መልክተኛችኝ አባት ምን ሆነው ይሆን...? አምልጠው ያድኑን ይሆን ወይስ እነሱም ተይዘው እዚው እኛው ጋር ይቀላቀሉ....? በሚል ሀሳብ ውስጥ እንደተዋጥኩ ቀጥሎ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመርኩ።
በግምት 3 ደቂቃ ያህል ይሆናል ምንም የለም እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የሚሆነውን በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቀ ይመስለኛል።ምክንያቱም ከነኚያ ሰው ጋር ተስፋችንን አብረን ልከናል የመሞትና የመዳን ዕድላችን በሳቸው የሚወሰን ሆኗል በሳቸው ምክንያት ተስፋ አልያም ሞት ይቀጥላል በቃ።
ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ። ቢያመልጡ እንጂ ቢያዙ መቼም ይሄ ሁሉ ደቂቃ አይቆዮም ብዬ ደመደምኩ። ምናልባት እስከ ነገ ቢፈጅባቸው ነው ከዛም መተው ያድኑናል ብዬ ሙሉ ለሙሉ ተስፋ አደረኩ ደስም ያለኝ መሰለኝ።አሁን እግዚአብሔርን የምለምነው እስከ ጠዋት በህይወት እንዲያቆየን ብቻ ነው ግን እስኪነጋ ማን ይሙት ማን ይትረፍ የምናውቀው ነገር የለም ምናልባት ሁላችንም በአንድ ሽጉት ቀላሀ ብቻ ልናልቅ እንችል ይሆናል አልያም ሁላችንንም አንተርፋለን።ወይም ምን ይታወቃል እዚሁ በጭድ በተሞላው ቤት ውስጥ እንዳለን ቤንዚን አርከፍክፈው ያነዱን ይሆናል
ብቻ ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም መገመትም ሆነ ማወቅ አይችልም።
በቃ የሚመጣውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለም።
ግን አሁን ትንሽም ቢሆን ተስፋ አለን።
ከአስራዎቹ ደቂቃ ቡሓላ የሄዱት ሰዎች ኮቴና ድምፅ ተሰማን።ባዶዋቸውን እንደተመለሱም እርግጠኛ ሆንኩ።
ግን ሳይሆን ቀረና ያ ተስፋዬን አብሬ የላኩበት ሰው ተስፋዬን ጥሎብኝ አብሯቸው መቶ ነበር
"እህሳ ፈልገኸኝ ነበር? ከመንድ ሲያስመልሱኝ ጊዜኮ ችግር የተፈጠረ መስለኝ"አሉ ድንጋጤያቸውን ለመደበቅ እየጣሩ እንዳሉ በሚያሳብቅ ንግግር።
"አይ ችግር የለም እንደው አግረመንገዶን ከመጡ አይቀር ለምን አንድ ነገር አላሳይዎትምና አላማክሮትም ብዬ እኮ ነው"አለ ዋናቸው ሰው እጁን ትክሻቸው ላይ አስደግፎ ይዟቸው እየወጣ በድጋሜ በዛ ርህራሄ በሞላበት አይናቸው ቃኘት አድርገውን ነበር የወጡት ነገሩ ግራ አጋባኝ ቢሆንም ከኛ ጋር አለመቀላቀላቸውን ወይም መንገድ ላይ አለመገደላቸውን ተስፋ አድርጌ መጠበቅ እንደጀገመርኩ በዛው ቅስፈት ከወደውጪ ተኩስ ተሰማ ልቤ ከልባቸው እኩል አብሮ ምቱን ያቆመ መሰለኝ

ተስፋዬም አብሮ አከተመ።ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጼን አውጥቼ ተንሰቀስኩ ግን እሚሰማ አልመሰለኝም የምችለውን ያህል ጮህኬ አለቀስኩ ግን ድምፄ ሀይል አልነበረውም።ተከትሎኝ ሁሉም መንሰቅሰቅ ጀመረ። በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልቤ አምርሬ አለቀስኩ።በቃ በሕይወት ለመጨረሻ ጊዜ ተስፋ የቆረጥኩ መሰለኝ። ማንም ሆነ ምንም ነገር እንደዚ አስከፍቶኝ አያውቅም ግን ይሄ ከመከፋትም ያልፋል።ጩኸቴም ለቅሶዬም ወደ ውስጥ እንጂ ወደ ውጭ አልሰማልሽ አለኝ።ሰሚ የሌለው ዋይታ ሆነ ባነባው እማያልቅ እማይወጣ ህመም።
ከእንቅልፌ ስነቃ በእንባ ርሼ ነበር።ብድግ ብዬ ተነሳው ገና ሌሊት ነው በተለመደው ሰዓት ነበር የነቃሁት።አልጋዬ ላይ ቁጭ አንዳልኩ እጅና እግሬን አጣምሬ አንገቴን ቀብሬ ማልቀስ ጀመርኩ።ምክንያቱም ዛሬም እዛው ስሜት ውስጥ ነኝ።እስኪ ወጣልኝ አነባው ተነሰቀሰኩ።አሁንም እንደታመምኩ ነኝ ሊያውም ሰው የማያወቀውንና ፍፁም ሊረዳው እማይችለውን ህመም።
ለደቂቃዎች ካነባው ቡሗላ ተነስቼ ደብተርና ወረቀቴን እንደለመድኩት ይዤ ቁጭ አልኩ።
"የነፃነትን ዋጋ የምንረዳው ባጣናት ቅስፈት ብቻ ነው ማንም ሰው ግን ያቺን ቅስበት እስካላየ ድረስ የነፃነት ሙሉ ዋጋ ና የነፃነት ጥጉን መቼም ሊረዳው ሆነ ሊያጣጥመው አይችልም ግን ያቺን ቅስበት ያየ የነፃነት ዋጋዋ እና ውድነቷን ከማንም በላይ ይረዳዋል እና ለመጀመሪያ ጊዜ ይናፍቃታል ሊያገኛትም ሩቅ እኝደሆነ ይሰማዋል ነብሱም ድምጿን ከፍ አድርጋ ነፃነትን ትጣራለች ግን ሰሚ አታገኝም እናም ይህ ሰው እድለኛ ከሆነ ዳግም ነፃነትን አግኝቶ ዋጋዋን ተረድቶ ያጣጥማታል።ያንን ያላየው ግን እንዲያው ትርጉሟ ሳይገባው ይመላለስባታል።ይሔ ሰው ታድያ ነፃነትን ስላጡ ሰዎች ምንም ላይመስለው ይችላል ይሆናል ግን ያቺን ቅስፈትና የነፃነት ዋጋን የተረዳው ግን ግድ ይለዋል ልክ እንደኔ! ለዛም ነው ዝም የማልልው "
ለመጀመሪያ ጊዜ መፃፍ የቻልኩት ይሄንን ብቻ ነው።
፡
፡
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየታችሁ እንዲሁም ማስተካከል ያሐባት ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት።
ፈጣሪ ሁሉንም በያሉበት ይጠብቅልን እናም በሰላም ያገናኘን ።
"ሕመማቹ ህመማችን ነው!!!!"

#አድዋ
የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፤
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣
እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ…
የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እጅጋየሁ_ሽባባው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፤
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣
እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ…
የድል ታሪክሽን አውሪ።
#እጅጋየሁ_ሽባባው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#ሙግት_ወይስ_እውነት?
፡
፡
በፍላጎት መንገድ...
በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ
ገንዘብ እየፈለግሁ...
"ፍቅር ይበልጣል" የሚል ፣ ከንቱ ሙግት ይዤ
እኔም ልክ እንዳንቺ...
ከገንዘብ ወዳጅ ጋር ፣ ተከራክሪያለሁ
ገንዘብ የማይገዛው...
ብዙ ደስታ አለ ፣ ስል አስረድቻለሁ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ግን ደሞ ግን ደሞ...
በማስረዳቴ ውስጥ ፣ አለ የሚያስረዳኝ
ከፍቅር ከገንዘብ...
ከምንም የሚበልጥ ፣ "እውነት " ይሉት አዳኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እናም እውነት ማለት...
በጭራሽ አይደለም!
አንድድ እውነት ለማቆም ፣ አንዱን እውነት መጣል
አትጠራጠሪ!!!
አንዱ ገንዘብ ሲመርጥ ፣ አንዱ ፍቅር ይመርጣልተ
ሒጅ ወደ ፈለግሽው!!!
ከፍቅር ከገንዘብ ፣ ፍላጎት ይበልጣል፡፡
⚫️በላይ በቀለ ወያ⚫️
፡
፡
በፍላጎት መንገድ...
በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ
ገንዘብ እየፈለግሁ...
"ፍቅር ይበልጣል" የሚል ፣ ከንቱ ሙግት ይዤ
እኔም ልክ እንዳንቺ...
ከገንዘብ ወዳጅ ጋር ፣ ተከራክሪያለሁ
ገንዘብ የማይገዛው...
ብዙ ደስታ አለ ፣ ስል አስረድቻለሁ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ግን ደሞ ግን ደሞ...
በማስረዳቴ ውስጥ ፣ አለ የሚያስረዳኝ
ከፍቅር ከገንዘብ...
ከምንም የሚበልጥ ፣ "እውነት " ይሉት አዳኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እናም እውነት ማለት...
በጭራሽ አይደለም!
አንድድ እውነት ለማቆም ፣ አንዱን እውነት መጣል
አትጠራጠሪ!!!
አንዱ ገንዘብ ሲመርጥ ፣ አንዱ ፍቅር ይመርጣልተ
ሒጅ ወደ ፈለግሽው!!!
ከፍቅር ከገንዘብ ፣ ፍላጎት ይበልጣል፡፡
⚫️በላይ በቀለ ወያ⚫️
#ፍቅርና_በቀል
፡
፡
#ክፍል_አንድ
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
‹እሱ….እሷ…እሳቸው›
"ኪስህ በብር ተሞልቶ ካዝናህ በወርቅ ቢታጨቅም ..ከልብህ ፍቅር ከነጠፈ አንተ በጣም ሊታዘንልህ የሚገባ ደስታ የራበህ ደሀ ሰው ነህ ፡፡"
#እሱ…
እሱ ኃይሌ ይባላል…የአርባ አመት ጎልማሳ ነው፡፡እዚሁ አዲስ
አበባ ተክላኃይማኖት መሀል ላይ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ባለቤት ነው፡፡ከህንጻው ኪራይ ብቻ በወር ከሁለት መቶ ሺ ብር በላይ
ገቢ ያገኛል…በዛ ላይ የፎቁ የመጀመሪያው ግራውንድ ፍሎር
ላይ የሚገኘው ሆቴል የእሱ ነው፡፡እራሱ የሚሰራበት
መኖሪያ ቤቱ ሳር ቤት ብስረተ ገብርኤል አካባቢ ሲሆን ቤተመንግስት መሳይ የተንጣለለ ቢላ ነው፡፡ግን እዛ ግቢ
ውስጥ …ሚስት የለችም…እዛ ግቢ ውስጥ ልጆች
አይሯሯጡበትም….እዛ ግቢ ውስጥ ዘመድ አዝማድ ዝር
አይልበትም…..ከአንድ ሽማግሌ ዘበኛ እና ከአንድ የ65 ዓመት
አሮጊት የቤት ሰራተኛ በስተቀር …ከመኖሪያ ቤትነት ይልቅ
የገዳምነት ድባብ ያረበበበት ነው፡፡
ኃይሌ እንዲህ የሞላው ሀብታም ሆኖ …ሁሉ ነገር
የተትረፈረፈለት ሰው ሆኖ ለምን አላገባም ?ይሄ ጥያቄ
በቀላሉ የሚመለስ አይደለም :ለጊዜው ይሄን ጥያቄ
እናቆየው….::ኃይሌ ማግባቱን እሺ አያግባ ለምን እንደዚህ
ብቸኛና ዝምተኛ ሰው ሆነ…?ለምን እንደዚህ ውስጡን ደስታ
የራቀው …ጥርሱን እንደዚህ ሳቅ የናፈቀው ሆነ….? ፡፡ምን
አልባት አንድ ጉድለት ይኖርበት ይሆናል ብላችሁ ገምታችሁ
ይሆናል…የጤና ችግር::ፈጽሞ አታስቡ… የሀኪም ቤትን
ደጃፍ ከረገጠ ከስንት አመት በፊት እንደነበር እሱም
አያስታውስም…::
መልከ ጥፉ ስለሆነ…? ፍጽም አይደለም::…እስኪ ስለኃይሌ
አካላዊ ቁመና በመጠኑ ላውራችሁ..ቁመቱ ሜትር ከሰማንያ
ሁለት ነው፡፡ክብዳቱ ሰባ ዘጠኝ፡፡ አፍንጫው ስገግ ያለ….ክብ
የፊት ቅርጽ ያለው..ጥቁር ሉጫ ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ድፍት
ያለ…ፂሙ ከፀጉሩ አንስቶ አገጩ ላይ ተንዠርግጎ ፈላስፋ
ያስመሰለው… ቀይ ሞዴል መሳይ ሰው ነው፡፡ሲራመድ
በቄንጥ እና በእርጋታ ስለሆነ ዘወትር እየቀያየረ
ከሚለብሳቸው ውድ ሱፍ ልብሶች ጋር ግርማ ሞገሱ
የሚያስፈዝ አይነት ነው፡፡በቃ ማንም ሴት የእኔ በሆነ ብላ
የምትመኘው አይነት ሁሉን አሞልቶ የሰጠው የሚባል አይነት
ወንድ….፡፡ግን እሱ ብቻ ነው የጎደለውን የሚያውቀው….እሱ
ብቻ ነው ከአገኘው ነገር ይልቅ የተነጠቀው እንደሚበልጥ
የተረዳው……አዎ ይህቺ አለም ለእሱ ሳቅ ሳይሆን ለቅሶ ነው
የሸለመችው…፡፡ ፍቅርን ሳይሆን በጥላቻ እሳት መለብለብን…
በበቀል በትር መወገርን ነው የሸለመችው……..
#እሷ……
ሩት የሰላሳ ሁለት አመት ሴት ነች…ጠይም ድንቡሽብሽ ያለ
ፊት በደም ግባት የወረዛ ስዕል መሳይ ባይባልም ማራኪ
መልክ የታደለች ከቁመቷ መዘዝ ፤ከወደ ወገቧ ቀጠን፤ ከወደ
መቀመጫዋ ትንሽ ሰፋ ያለች..እግሮቾ ለብቻቸው ውበትን
የሚዘምሩ ቄንጠኛ ወጣት ነች፡፡
ሩት ቀን እቤቷ ተኝታ ታረፍዳለች፡፡ከሰዓት ለባብሳና ዘንጣ
ትወጣለች….ከዛ ወደ ተክለኃይማኖት ታመራለች…ሆቴል
ትገባለች …ወንበር ይዛ ቁጭ ትላለች፡፡ የፈለገችውን
ታዛለች…እሲኪመሽ እዛው ትቀመጣለች..፡፡በዛ ቆይታዋ…
አምስት እና ስድስት ቢራ ልትጠጣ ትችላለች፡፡ወይም ሁለት
ጠርሙስ ወይን ልትጠጣ ትችላለች…ከፈለገች ደግሞ ሶስት
ጠርሙስ ሚርንዳ እያረፈች ልትጠጣ ትችላለች… ይሄንን
ማድረግ ከጀመረች አንድ ሳምንቷ አይደለም ..አንድ ወሯም
እንዳይመስላችሁ …ያለፉንትን አራት አመታት ተኩል
ያለማቆረጥ እንዲህ አድርጋለች..፡፡
ደግሞ ዘወትር የምትቀመጠው አንድ አይነት ቦታ ነው…የእሷ
መቀመጫ ላይ ማንንም አይቀመጥበትም….፡፡ ሁሌ ሪዘርቭድ
ነው፡፡ለእሷ ብቻ የተፈቀደ ማንም የማይደፍረው መንበር፡፡
ከዛ ሲመሽ ሰክራ እየተወላገደች ወደቤቷ ትገባለች ..አይ
እንደዛማ አታደርግም እሷና ስካር እንዲህ በቀላሉ
አይደፋፈሩም…ሁለት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ከመቀመጫዋ
ተነስታ ትቆማለች፡፡ቦርሳዋን ይዛ በሆቴሉ የጀርባ በር አልፋ
ትወጣለች…፡፡ከዛ አንድ ክፍል ትገባለች፡፡የለበሰችውን ረጅም
ቀሚስ ወይም ጅንስ ሱር በብጣቂ ጉርድ ቀሚስ ትቀይርና
ከንፈሯን ሊፕስቲክ.. አይኖቾን ኩል ትቀባባና ወደ ሆቴሉ
ትመለሳለች፡፡ ስትጠጣ የዋለችበትን ትከፍላለች ወይም
አትከፍልም..እንዳሰኛት ነው፡፡…ከዛ ሆቴሉን ለቃ ትወጥና
እዛው የሆቴሉ መውጫ በራፍ ጋር ካለ የመብራት ፖል ጋር
ተደግፋ ትቆማለች…..፡፡ወንድ ጥበቃ…፡፡የሰከረ እግረኛ
መጥቶ ያነጋራታል…የቀነዘረበት ባለ አሽከርካሪ አቁሞ
ያዋራታል….፡፡
ሩት የፈለገ ቢከፈላት አምስት ሰዓት ሳያልፍ ከዛች ሆቴል
በራፍ ንቅንቅ አትልም…፡፡አሷን የሚፈልጉ ቋሚ ደንበኞቾ
ይሄንን ስለሚያውቁ ሆቴል ገብተው እየጠጡ የእሷ ሰዓት
እስኪደርስ ጠብቀው ነው ሊያነጋግሯት የሚወጡት…፡፡
ለምን እንዲህ እንደምታደርግ ብዙ ሰው ግራ ይገባው ይሆናል
…እሷ ግን በቂ ምክንያት አላት…ወይም አለኝ ብላ ታምናለች፡፡
እንዲህ ስታደርግ ሆቴሉ በረንዳ ላይ ጥጉን ይዞ በመቆዘም
የሚመለከታት አንድ ሰው አለ…..ውስኪውን
እያንቆረቆረ..ሮዝማኑን እያቦነነ….ፀጉሩን በጣቶቹ
እያፍተለተለ፡፡የእሷ ድርጊት የዘወትር እና የማያቋርጥ እንደሆነ
ሁሉ የሰውዬው በረንዳ ላይ በአጭሩ የግንብ ከለላ ተሸሽጎ
እሷኑ እያጮለቀ ማየት የማያቆርጥ ተግባሩ ነው፡፡
ስትደራደር ..ስትሰዳደብ ይታዘባታል.፣አይ መታዘብ እንኳን
አይታዘባትም ግን በውስጡ ቁስል ጥዝጣዜ ይሰቃያል፡፡
አንዳንዴም ባለ መኪኖች መኪናቸውን ጭለማውን አሲዘው
ሲጠሯት እየተውረገረገች ስትሄድ… የመኪናውን በራፍ ከፍታ
ወደ ውስጥ ስትገባ…መኪናዋ ስትርገፈገፍ …ይሄ ሰውዬ
እዛው በረንዳ ላይ ኩርምት ብሎ እንባውን እያንጠባጠበ
..የሲጋራውን ጭስ እያትጎለጎለ ይመለከታታል….
ሰዓቷ ሲደርስ ከመረጠችው ጋር ትሄዳለች…አዎ በሳምንት
ሶስት ወይም አራት ቀን እንደዛ ታደርጋለች….ሌላውን ቀን
ደግሞ….ልደታ ወደሚገኘው ቤቷ ታመራለች፡፡ቤቷ ስላችሁ
ወደ ተከራየችው ቤት አይምሰላችሁ…ወደ ገዛ ቤቷ ነው፡፡
እሰኪ ስለ ቤቷ ትንሽ ላውራችሁ፡፡ምትኖረው ስድስት ክፍል
ያለውና ሁሉ ነገሩ የተሞለለት የድሮ ስሪት ቢላ ቤት ውስጥ
ነው ፡፡ብቻዋን ነው የምትኖረው…..ግቢዋ 1500 ካሬ ሜትር
ስፋት ሲኖረው ውስጡ 15 ክፍል ሚከራይ ቤት አለው…
ፔንሲዬን ነው፡፡ፔንሲዬን በቅርብ የተገነባ ነው ፡፡ቢያንስ በቀን
ከሁለት ሺ ብር በላይ ገቢ ያስገባላታል፡፡ይሄ ሁኔታውን
ይበልጥ አስገራሚና ግራ አጋቢ ያደርገዋል፡፡አንዳንዴም ታዲያ
ከወንዶቹ ጋርም ሆነ ወደ ቤቷ መሄድ ያስጠላታል…::እና
እንዳዛ ዘንጣ…እንደዛ የሚያጓጓ የተገላለጠ ሰውነት ይዛ
እዛው ሆቴል አጥር ስር ቁጭ ትላለች….፡፡እንዲህ
ምታደርገው ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ወይም ሰባት ሰዓት ላይ
ነው፡፡
ከዛም ሸርተት ብላ ኩርምትምት ብላ ትተኛለች፡፡ያ በረንዳ
ቁጭ ብሎ የሚከታተላት ወንድ ኮንፎርት ብርድልብስ አምጥቶ
ያለብሳታል..ትራስ አምጥቶ ጭንቅላቷን ቀና በማድረግ
አመቻችቶ ትራሱ ላይ ያስተኛታል….ከዛም ከጎኗ ኩርምት ብሎ
ቁጭ ይላል….፡፡እሱ ልብስ አያስፈልገውም..እሱ እንቅልፍ
አያምረውም …ሲጠብቃት ያድራል….፡፡
ድርዬ መጥቶ እንዳይደፍራት አይደለም…ሌባም
እንዳይዘርፋት አይደለም... በቃ ትንፋሿን ለማዳመጥ ..በቃ
ከአጠገቧ ብቻ ለመሆን..፡፡እንጂማ አይደለም የእሷን
የእሱንም ደህንነት ከማንኛውም ጥቃት የሚጠብቁ ሁለት
ጋርዶች ከእነሱ በስድስት ሜትር ርቀት ላይ በተጠንቀቅ
ቆመው በንቃት ፈጠው ያድራሉ…ይሄ ሁሌ እሷ እዛ ውጭ
በረንዳ ላይ መተኛት በፈለገች ቀን የሚታይ ትዕይንት ነው፡፡
ከዛ ሲነጋጋ እና ወፎች መንጫጫት
ሲጀምሩ ሩት

👍2❤1
ከእንቅልፏ
ትባንናለች…..ትንጠራራለች
ቀስ ብላ ዓይኖቾን ትገልጥና
አካባቢውና ትቃኛለች…፡፡ያለበሳትን ብርድልብስ ከላዮ ላይ
ትገፍና ትጥላለች..ከዛ ትቆምና ቀሚሷ ላይ ያለውን አቧራ
ለማራገፍ ትሞክራለች..ኩርምት ብሎ ከጎኗ የተቀመጠውን
ሰው ለሰከንድ አፍጥጣ ታየዋለች..ከዛ ፈገግ ትልና ቦርሳዋን
አንጠልጥላ መንገዷን ትቀጥላለች..፡፡ወደቤቷ..፡፡ ..ልብሷን
ልትቀይር…የተሸለ እንቅልፍ ልትተኛ…፡፡
ወንድዪውም የእሷን ከአካባቢው መራቅ አረጋግጦ
ከበረንዳው ተነስቶ ይቆማል..የደነዘዙ እግሮቹን
ያፍታታል..ወደ ሆቴሉ ጓሮ ይሄድና ያቆማት መኪና ውስጥ
ገብቶ ሞተሩን ያስነሳል …..ሞተሩ እስኪሞቅለት በድካም
የዛለ ጭንቅላቱን መሪው ላይ አስደግፎ ትንሽ ያሸልባል…
ከዛም ይባንናል …መኪናዋን ያንቀሳቅሳል ፡፡የሆቴሉን ግቢ ለቆ
ወደ መኖሪያ ቤቱ….ሊተኛ..
እኚ ናቸው ሁለት ፍቅር እና በቀል ያጣበቃቸው ሚስኪን
ነፍሶች…እሷ ና እሱ….ሩት እና ኃይሌ……
#እሷቸው…..
እሷቸው በሁለቱ መሀከል ያሉ ብቸኛው ድልድይ ናቸው፡፡
የማንኛቸው ትክክለኛ አጎት እንደሆኑ ባላውቅም ሁለቱም
በፍቅር አጎቴ እያሉ ነው የሚጠሮቸው፡፡
እኚ አዛውንት ከ8 ዓመት በፊት አውቃቸዋለው፡፡አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ሁለት ኮርስ
አስተምረውኛል፡፡ፕሮፌሰር አብረሀም ይመር ይባላሉ፡፡
….የራሳቸው የማስተማር ጥበብ የሚከተሉ በጥልቅ ዕውቀት
እና በራሳቸው ፍልስፍናዊ መርህ የሚመሩ ሙሉ ምሁር
ነበሩ፡፡እርግጥ አሁን ጡረታ ወጥተዋል፡፡ ሚገርመው ግን
እኚን አዛውንት መምህሬ ስለሆኑ ብቻ አይደለም
የማውቃቸው፡፡ ከንባብ ጋር ቁርኝት ያለው አብዛኛው
ኢትዬጵያዊ ቢያንስ በስም ያውቃቸዋል፡፡
በጻፎቸው በቁጥር ከ8 በላይ በሚሆኑ የፍልስፍና እና የልብ-
ወለድ መጻሀፎች አንቱታን ያተረፉ ጉምቱ ደራሲ ናቸው፡፡
እንደውም ዝም ብዬ ስለ እሳቸው ሳስብ ከዕድሜ መግፋት
በላይ ዕውቀት እና ንባብ ተጋግዘው ያጎበጣቸው
ይመስለኛል፡፡ ለማንኛውም ከእኚ እጅግ ከማደንቃቸው ምሁር
ጋር ህይወት አዙራ ለሁለተኛ ጊዜ አገጣጥማናለች፡፡
ባልታሰበ ሁኔታ የሩት እና የኃይሌ አጎት የሆኑት ፕሮፌሰር
የእዚህ ታሪክ ድር ናቸው..አንድን ከአንዱ የሚያስተሳስሩ .. ፡፡
እኚ ፕሮፌሰር ብዙውን ጊዜ ፂማቸውን አንዠርግገው
ትከሸሻቸውን አጉብጠው ቦርሳቸውን የሚንቀጠቀጠው
ትከሻቸው ላይ አንጠልጥለው በተጎተተ አርምጃ ወደ ትሁት
ሆቴል ይመጣሉ..ሩት ጎን ይቀመጣሉ…እዛ ሆቴል ውስጥ
ከእሷ ጎን ለመቀመጥ ሚፈቀድላችው ብቸኛው ሰው እሳቸው
ብቻ ናቸው፡፡..ከጎኗ ይቀመጡና አሷ የምትጠጣውን
ይጠጣሉ ፡፡ ከቦርሳቸው ውስጥ አንድ መጻሀፍ ያወጡና
ያነባሉ፡፡ እያነበቡም ይጠጣሉ…..ቆይተው ከመጠጡም
ከንባቡም እረፍት ይወስዱና ከእሷ ጋር ማውራት ይጀምራሉ፡፡
ሲያወሯት በፍቀር እና በስስት ነው፡፡እሷም መፍለቅለቅ
ምትጀምረው እሳቸው ሲያወሯት ብቻ ነው፡፡ ምትረጋጋው
አጠጋቧ ሲቀመጡ ብቻ ነው፡፡ሚገርም ቁርኝት ነው ያላቸው፡፡
በፊት በፊት እንደውም አባቷ ይመስሉኝ ነበር፡፡ቆይቼ ነው
አንዳልሆኑ ያወቅኩት፡፡እኚ ፕሮፌሰር ከሩት ጋር ያላቸውን
አይነት ተመሳሳይ ቁርኝት ከኃይሌ ጋርም አላቸው፡፡እሷን
በሚያዩበት ዓይናቸው ነው እሱንም የሚያዩት… እሷን
በሚዳስሱበት ፍቅራዊ መንገድ ነው እሱንም የሚዳስሱት፡፡
ለዚህ ነው ይሄ ትረካ በዋናነት የእነዚህ ሶስት ሰዎች ነው
የምላችሁ፡፡አንዱ በአንድ ህይወት ውስጥ ስር ሰዶ በቅሏል
አንዱ በሌላው ህይወት ውስጥ ተዘረጋግቶ ተኝቷል፡፡
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን