አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
574 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ዳግም (የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በሕይወት_እምሻው ፡ ፡ ========== "ሳቢ ቅድስትን ነገ ላገኛት ነው..." አለች ሮማን፣ ሳባን ሳይሆን፣ በመብላት ፋንታ በዳቦ አንቃ ሰሃኑ ላይ ወዲህ ወድያ የምታንገላታውን እንቁላል ፍርፍር እያየች። ሳባ ሻይ ትጠጣበት የነበረውን ወፍራም ብርጭቆ ጠረጴዛው ላይ በኀይል ጓ! አድርጋ አስቀመጠችና፣ "አንቺ ግን ጤና የለሽም በቃ? ደሞ ምን…»
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_ሁለት


#በዮርዳኖስ

ከሌሊቱ 10:52 አይኖቼን ስገልጥ ከክፍሌ ጨለማ ጋር ተፋጠጥኩ በዳበሳ መብራቴን አብርቼ በፍጥነት አከባቢዬን ቃኘው።አስማት ወይንም ተዓምር ሊመስል ይችላል ግን አሁን እቤቴ ነኝ።ትንፋሼ ይቆራረጣል።ከፍተኛ ሙቀት ስለተሰማኝ ከብርድልብሴ ወጣው ላብ ጥምቅ አድርጉኛል። ልቤ ክፉኛ ይመታል በፍጥነት ተነስቼ ወደ በሩ አመራው።ነብሴ ስለ ተጨነቀች እንጂ የትም ልሔድ አልነበረም።ተመልሼ አልጋዬ ጫፍ ተቀመጥኩ ቀን ማስበውንና ምፈራው ትውስታ ነው ሌሊት በህልሜ ሳይ እና ስቃዥ የማድረው።

ለሊቱ በሀይለኛ ፀጥታ ተውጧል ምንም ድምፅ የለም።ወደ መስኮቴ በቀስታ ሄጄ ከፈትኩት ሊነጋ ማቅላላት ጀምሯል ካልተሳሳትኩ ከደቂቃዎች ቡሗላ የመስጊድ አዛን መሰማት ይጀምራል።ፍፁም እርጋታ አና ፀጥታ የተሞላው ሌሊት ደስ በሚል እና ሰላምን በሚያስተጋባ ቀዝቃዛ ንፍስ ታጅቧል ። ይሄንን በነፈሰበት አብረውት እኩል በነፃነት ከሚደንሱት ዛፎች ውጪ የሚያስተውለውም ሆነ የሚያጣጥመው ግን ያለ አይመስልም። እንዳለመታደል ሆኖ ግን እኔም እንኳን እንዲ እያስተዋልኩት ልደሰትበትም ሆነ ላጣጣመው አልቻልኩም። ምክንያቱም ደግሞ ከእርጋታውና ፀጥታው ይልቅ ውስጤ ያለው ጩኸት እና ጫጫታ ይበልጡኑ ስለሚሰማኝ እና ስለሚበረታ ነው።ተመልሼ ወደ አልጋዬ አመራው ግን እንቅልፌን ፈራሁት።ቀሪዎቹን ሰዓታት ማሳለፊያ ነገር መፈለግ ሰይኖርብኝ አይቀርም።

ከሌሊቱ11:20 እንቅልፍ የሚባል ባይኔ ዝር አላለም።ሴከንዶች ደቂቃን ደቂቃዎች ሰዓታትን እየተኩ ይሄዳል። ለኔ ግን የቆመ ነው የሚመስለው ።
በማያቋርጥ ቅዠት የተሞላ ቀን እና ለሊቶችን ማሳለፍ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ።ሰው ያላወቀውን ህመም ከታመምኩ ቆየ፣ሊነግሩት በማይቻል ሰው በማይረዳውእና ሊገለፅ በማይቻል ጥለቅ ፍርሀት ውስጥ መዋልና ማደር ከጀመርኩ ሳምንታት አልፈው ወር አስቆጠረዋል።ራሴን ማውራት ወስጤን ማድመጥ እፈራለው ሆኖም ግን ውስጤን ዝም ማሰኘት አልችልም ያለማቋረጥ ይጮሀል።ንዴት፤ቁጭትና ፀፀት፤ቂም፤ተስፋ መቁረጥ ይሁን እልህ በትኛውም ቃል በትክክል ልገልፀው ያልቻልኩት ስሜት ውስጤን አጨልሞታል።

ምናልባት አንዳንዴ ያለሁበትን እረሳለው ስለነበረውም እንደዛው አይምሮዬን ስቼ እቆይና ስመለስ ደግሞ ላመልጠው ካልቻልኩት መጥፎ ትውስታ ውስጥ ራሴን አገኘዋለው።እንደገና ያንንም ልረሳው እና ባዶ ልሆንም እችላለው።ብቻ በዚ ሁኔታ ቀናትን አሳልፍያለው ወደ ራሴ ለመመለስ የሚወስድብኝ ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ ባላውቅም ግን ይሄ ስቃዬ እንዲያበቃና ከዚ ቅዠት መውጣት እፈልጋለው።
ስሜን እንዳላስተዋውቃቹ ልረሳው ስለምችልና በውል ስለማላስታውሰው ይቆያቹ።ግን....ብሩክቲ ነኝ ይሆን እንዴ....? እንጃ።

ከሌሊተለ 11:40 የምፈልገውን አላውቀም ግን የሆነ ነግር ፈልግያለው ያጣሁትን ባላውቅም ግን አንዳች ያጣሁት ነገሮ አለ ግን አይምሮዬ ጥያቄውን ብቻ እንጂ መልሱን አይነግረኝም።
ለደቂቄዎች በወረቀት ላይ ለመፃፍ ሞኩርኩ ግን ምን ልፅፍ አልቻልኩም ከባዶ ነጭ ወረቀቴ ጋር ተፋጠጥኩ ግን የምፅፈው ነገር የለኝም ወይም የምፅፈውን አላውቅም።የነበርኩበት የት ነው አንዴትስ መጣው ማን አመጣኝ ኬትስ ነው የመጣሁት ሌሎቹስ ታድያ...??? መልስ የሚሰጠኝ የለም ግን አይምሮዬ የሚያሰማኝ ያንን ስቃይ የተሞላበትን ቅዠቴን የው።ለምንድነው በደንብ ማስታወስ ማልችለው?እንጃ ቢያምም ግን የግድ ማስታወስ እፈልጋለው ደሞም አለብኝ።
ለሊቱ ነግቶም ከክፍሌ ንቅንቅ አላልኩም አሁንም ከባዶ ወረቀቴ ጋር እይደተፋጠጥኩ ነው ምክንያቱም መመለስ አለብኝ። ስሚ....ስሚ...."ሔዋን ሔዋን "የክፍሌ በር ተንኳኳ።አው ስሜ በትክክል ሔዋን ነው ሔዋን በድሉ እናም የሚጠራኝ አባቴ ነው እቤቴ ነኝ የምማረው እና የነበርኩት ግን university ነው የ3ኛ ዓመት ህክምና ተማሪ።ግን የት? እንጃ።
"ሔዋን" አባቴ ነው "አቤት አባ ግባ"አልኩት።"ሰላም አደርሽ ልጄ" አለኝ።ጥያቄውን እንዲሁ በዘልማድ መመለስ ስላልፈለኩ ትንሽ አሰብ አድርጌ አንገቴን ነቅንቄ "አይ ሲያቃዠኝ ነው ያደረኩት"
"ያስታወሽው ነገር አለ እንዴ?"ፀጉሬን አየዳበሰ ጠየቀኝ አሁንም አሰብ አረኩና "ማስታወስ የማልፈልገው ነዋ...."አልኩት እንባ ሊተናነቀኝ እያለ.....



💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየታቹ እንዲሁም ማስተካከል ያለባትን ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት
👍2
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_ሦስት


#በዮርዳኖስ

"አይዞሽ የኔ ውድ ማድረግ የምትፈልጊው ነገር አለ? ለምሳሌ መውጣት ወይም ሌላ ነገር...?"
እንዲያው ለአመል ይጠይቀኝ እንጂ ባለፉት ቀናት ብዙ ነገር አንዳላደርግ ሲከለክለኝና ሲደብቀኝ እንደነበር አስተውያለው ለምሳሌ ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንዲሁም ሞባይል ኢንተርኔት አንዳላይ አድርጎኛል።ከቤት መውጣቱንም ቢሆን አብሮኝ ካልሆነ አያስወጣኝም።ለኔ ተጠንቅቆ እንደሆነ ቢገባኝ ግን ማወቅ እና ማየትን እፈለጋለው ከቤት መውጣትንም እንደዛው።ግን አባቴ ስጋት ያለበት ይመስላል ደግሞም ይገባዋል ምክንያቱም ለሱ ብቸኛ ልጁ ነኝ ሊያውም ካለናት ያሳደገኝ።ያ ማለት ግን ከናቴ ጋር ተጣልተዋል አልያም ሞታለች ማለት አይደለም ሚስጥሩ ሌላ ነው።ለጊዜው ግን እኔና አባቴ ከአንድ ሰራተኛችን ጋር ነው የምንኖረው።ሰራተኛ ለማለት ግን ይከብዳል እህና አብሮ አደጌ ብላት ይሻላል። ብርቱካን ትባላለች የዋህ እና ንፁ ኢትየጵያዊ ምርጥ እናትና ጠሩ እህት ነች በቃ ከዚ ሌላ መግለጫ የለኝም።
አባቴ ላቀረበልኝ ጥያቄ መልስ"ከስራ ልትቀር...?"አልኩት በዘዴ "አንቺ ከፈለግሽ ካንቺ አይበልጥም"አለኝ
"አይ ብቻዬን ነው መውጣት የምፈለገው ካለሆነ ይቅር"አልኩ።አባቴ በረጅሙ ተንፍሶ"በርግጥ አሁን ይበልጥ ትሻያለሽ ደና ነሽ ግን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወደራስሽ እስክትመለሽና የቅርብ ጊዜ ትውስታሽ እስኪመለስ መጠበቅ አለብሽ ካልሆነ ግን ትንሽ ከደገኛ አይመስለሽም ሔዊ?" መልሶ በጥያቄ መለስልኝ።
"አይ አይመስለኝ እንድረጋጋና ነገሮችን አንዳስታውስ ከፈለክ ነፃ ብታደርገኝ የሚሻል ነው የሚመስለኝ"። እንደማቅማማት አለና "እሺ ወደ ሳሎን ነይና ቁርስ እንብላ"አለኝ እንደ እሽታ ቆጥሬ"አባዬ ስለተረዳኸኝ አመሰግናለው "አቅፌ ሳምኩት።ግን የአባቴን ጥንቃቄ አይታችሁልኛል ምን እንዳስታወስኩ እንኳን ጠይቆ ሊያስታውሰኝ አልፈለገም ምክንያቱም ማስታወስ እንደማልፈልግ ነግሬዋለዋ።
ለወትሮው አባቴ እስካለና እቅፍ ውስጥ ስሆን ፈርቼ አላውቅም በአባቴ መሉ እምነት ና መተማመን ነበረኝ።ልክ በአምላኬ እቅፍ ውስጥ ያለው ያህል ደህንነትና ሰላም ይሰመኝ ነበር።ግን በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የአባቴ እቅፍ ወደማያስጥለኝ ወደማያድነኝ አስፈሪ ገፅታ ወዳለውእና ማለቂያ የሌለው የሚመስል ስቃይ ውስጥ ራሴን ካገኘው ቡሗላ ግን ፍፁም ቀድሞ የነበረኝ ሰላምን ሊሰጠኝም ሆነ እምነት ሊኖረኝና ፍራቻን ሊያስወግድልኝ አልቻለም።

ሳሎን ስንደርስ ቀርስ ቀርቦ ግሩም ቃና ባለው ሻይ ሽታ ታውዶ ነበር።"ደና ደርሽ ሔዊ"አለች ቡርቴ በዝግታ ሔጄ ሳምኳትና"ሽታው በጣም አያስራበኝ ነው ባለሞያ እኮ ነሽ!"አልኳት።"አሱን በደንብ ስትበዪ ነው ማምንሽ በደንብ አትቢና ግን ወይልሽ!"አለች የውሽት ቁጣ እየተቆጣች።
"እሺ እናመስግን"አለ አባዬ ፊቱ ላይ አንዳች ስሜት እየተነበበ እንደተረበሸ ያስታውቃል።
በፊተት ከምወደውና ደንነት እንዲሰማኝ ከሚያደርገኝ ሌላው ነገር የአባቴ ፀሎት ነው ልጅ እያለው እንደሱ ለመፀለይ አለማመድና አንደ አባታችን ፀሎት አደጋግመው ነበር።የሚፀልይበትን እረጋታ እና ድምፅ አወደዋለው በአይምሮዬ ጥሩ ዜማ እንዳለው ተወዳጅ ሙዚቃ ተቀርጿል።"አሜን"ስል የእውነትም አባቴ በሚለው ነገር በአምላኬ ተሰሚነትን አንደማገኝ ወስጤ እረግጠኛ ሆንና አምኜ ነው።እና ይሄንን የአባቴን ፀሎት አድጌም አልጠጎበውም።ደስ ይለኛል ምግብ ላይም ይሁን በምንም አጋጣሚ ሲፀልይ ሰላም ወስጤን ይሞላዋል ከእግዚአብሄር ጋር የምገናኝ የማወራው እና እሚመልስለኝ ነው የሚመስለኝ።
ይሄንን ሁሉ የምላቹ አባቴ ለቁርስ እየፀለየ ነው እኔና ቡርቴ በአሜንታ እየተከተልነው አመስግነን ጨረስን።
ቁርስ በልተን እስክንጨርስና አባዬ ወደ ስራ እስኪካሄድ መጠበቅ በጣም ረዝሞብኝ ነው ቢሆንም ጠበኩ።አባዬ በቅራኔ እንደተሞላ ለመውጣት ሲወጋጅ ድንገት የት እንደምሄድ ጠየቀኝ የት ነው የምሄደው...?
"ገበያ..."አልኩት ዝም ብዬ
ገበያ....??" አለኝ በጥያቄ አይን አያየኝ
" አው አታስብ ቡርቴ የምትገዛው እቃ ስላለ ከሷ ጋር ነው የምሄደው" አልኩት አፌ ላይ አንደመጣልኝ።
"እሺ እንደዛ ከሆነ ገንዘብ ያስፈለግሻል"ከዋሌቱ የተወሰኑ መቶ ብሮችን እያወጣ "ምንያህል ያስፈለግሻል?
"አይ አትቸገር ብዙም አይደል"እንደዛ ከሆነ ካፌ ነገር ብትገቡ ወይም ደስ ያላችሁን ብታደርጉ ጥሩ ነው ብቻ ሚያዝናናቹን" ሰጠኝ።
"ይሄ ደሞ ላንቺ ነው"ለቡርቴ እያቀበላት ገና ከጓዳ እየወጣች ነበር"ለምን....?"አለች ከመጀመሪያው ስላልሰማች"ገበያ ልንሄድ አይደል...!"አልኳት ካፏ ነጥቄ።
"በሉ እሺ ልጆች መልካም ቀን ታዲያ እየተጠነቀቃቹ"ብሎ ስሞን ወጣ ከቡርቴ ጋር መወጣቴ እንዳስደሰተው አና ምን ያህል እንደቀለለው ሳይ ደስ አለኝ።አባቴ አንዲ ነው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ፍቅር መስጠት እና ሰውን መውደድ አይሰስትም አያልቅበትምም።ብዙዎች ሀብታሙ ፓስተር ይሉታል።በርግጥ የራሱ ስራ ያለውና ደሞዝተኛ ነው።ከዛ ውጪ ትጉህ አገልጋይ እና ታታሪ ሰራተኛ ነው።ብዙ ጊዜ በአንድ ቤተ/ያን መገደብ ስለማይወድና ከሁሉም ጋር ህብረት ስለሚያደርግ በዚ ሰዎች ይተቹታል ሆኖም አባቴን ግድ ሰቶት አያውቅም ምክንያቱም ሲበዛ በአንድነት የሚያምንና ልዮነትና ክፍፍል የሚባል ነገር ስለማይወድ ነው።በቤተ/ያን ብቻ አይደለም አባቴ ሲበዛ በኢትዮጵያዊነት አንድነት የሚያምን ነው።ለማንም ሰው ስለብሔሩም ሆነ ስለዘሩ ሲናገር አትሰሙትም።የማይታመን ይሆናል ግን ለኔ እንኳን "እንትን ዘር ነኝ ስለዚ አንቺም እንደዚ ነሽ "ብሎኝ አያውቅም ለዛ እኔም ስለብሔሬም ሆነ ስለዘር ግድ ሰቶኝ አያውቅም።ከአባቴ የተማርኩት ምንም ትርጉምም ሆነ ጥቅም የሌለው ነገር መሆኑን ነው።ግን አባቴ ስለሁሉም ሰው ቢጠየቅ መልሱ "ኢትየጵያዊ ብቻ" የሚል ነው የሚሆነው።እኔም ስለነዚ ነገሮች ለማወቅ ጉቱም ፍላጎቱም አድሮብኝ አያውቅም ደሞም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያስብ የሚገባወና ሊይዘው የሚገባው አመለካከት ነው።ግን እንዴትና ለምን አንደሆነ ባይገባኝ በምማርበት ግቢ በአንድ ብሔር ተሰይሜ እና ተወክዬ ስቀጣ ነበር።ግን እነማን ነበሩ...? በምንስ ወከሉኝ...? መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነው።እነማንን መጠንቀቅ ይኑርብኝ እነማንን ማመን ይኑርብኝ እንኳ አላውቅም

በዚ ምክንያት ነው እስካሁን በፍርሀት እንድኖር የተገደድኩት።

አባቴ እንደወጣ ምን እንደማደርግ ቀድሜ እያቀድኩ ክፍሌ ገባውና ቀለል ያለ አለባበስ ለብሼ በፍጥነት ወደ ቡርቴ ሄድኩ
"ጨርሻለው!" አልኳት
ዞራ በአግራሞት ከላይ እስከ ታች አየችኝ።እኔም ግራ ገብቶኝ እንደገና አለባበሴን አየሁት ጅንስ ሱሪ፣ፓካወት እና ሸሚዝ ብዙ ጊዜ የማዘወትረውን እና ሚመቸኝን አለባበስ ነው የለበስኩት።
"ያጠፋሁት ነገር አለ? አለባበሴ ምን ሆነብሽ?"አልኳት
"አይ...ቶሎ..ጨረሽ ብዬ ነው"

"ልጅት ምን ሆነሻል ልብስ ስለብስ ጊዜ ፈጅቶብኝ አያወቅም ሁሌም እንዲ ነበርኩ"አልኳት ፊቷ ላይ የማየውን ስሜት ለመረዳት በጥንቃቄ እያየሗት።

"አይ ሔዊ ግን እኮ እንደዚ መልበስ ካቆምሽ ቆይተሻል"አለች።አሁን ገባኝ በራፍ ላይ እንደቆምኩ ለሴኮንዶች እያሰብኩ አፈጠጥኩባት እና ተጠግቻት
"ቢያንስ ለምን ያሀል ጊዜ..?"ጠየኳት።
"እንጃ 1...3 ዓመት እና ከዛ በላይ ይሆናል"
"እሺ ቡርቴ አንዳስታውስ እንድትረጂኝ እፈለጋለው አትረጂኝም...?"እጆቿን የዤ ጠየኳት።"
ሔዊዬ አንቺ አስታውሽና ደና ሁኝልኝ እንጂ ለምን ብዬ ነው ማልረዳሽ"
"ምንም ነገር ቢሆን የጠየኩሽን ታደርጊያለሽ?"
"ደስ ያለሽን" "ግን አባዬ ሳያውቅ ነው"
"ማለት..? ግን ለምን
👍51
.?"አለች ፊቷን አኮሳትራ

"አይዞሽ መጥፎ ነገር አይደለም"ተያይዘን ወጣን።


ጠዋቱ ደመናማና ቀዝቃዛ ነው።በግምት 3 ሰዓት ይሆናል የነጌሌ ገበያ በብዛት ከዚን ሰዓት ቡሗላ ነው የሚደራው።

ነገሌ ቦረና ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 600 ኬ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ከሚተዳደሩ ከተሞች አንዷ ስትሆን በአሁኑ ወቅት የጉጂ ዞን ዋና ከተማም ነች።ከዛ በተረፈ ግን የትንሿ ኢትዮጵያ ምሳሌ ነች ኬትኛውም ብሔረሰብ የመጡ ሰዎች በእኩል አና በአንድነት የሚኖሩባት ሁሉንም በአንድ አቅፋ የያዘች ከተማ ናት።
በአባ ገዳ ስረዓት ከሚተተዳደሩትም ውስጥ አንዷ ነች በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ሀውልቶችም ትለቁና የሚታወቀውም የአባ ገዳ አባት ሀውልት ነው።
የከተማዋ አየር ሞቃት የሚባል አይነት ሲሆን ብዙ ነገራ ከአዳማ ናዝሬት ጋር አንደሚያመሳስላትም ይነገርላታል።በአመት ሁለት ጊዜ ዝናብ ምታገኝ ቢሆንም ግን በነዚ የፀደይ ወቅት ላይ አልፎ አልፎ ደመናና ወቀቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊያገኛት ይችላል።
በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎችም በእርሻ ስራና በንግድ ስራ የተሰማሩ ሲሆን በከብት ቀንድ ሀብትም የታደለች ናት።ሱማሌ ጠረፍ እና ድንበር መሆና ደሞ በመጠኑ ለንግድ ስራ አመቺ አድርጓታል።
ለማንኛውም ተወለጄ ያደኩት እዚው ትንሿ ኢትዮጵያ ነገሌ ቦረና
ውስጥ ነው።

የጠዋቱን አየር አያጣጣምን ከቡርቴ ጋር መንገድ እንደጀመርን
"ቡርቴ...?" አልኳት ጠይቂኝ ባለችው መሰረት ጥያቄን መርጬ
"ለምንድነው እዚ ያለሁት ከት/ት አንዴትና ለምን መቼ መጣው?"
"ይሄንን እኮ ሁለት ቀን በፊት ጠይቀሽኝ ነግሬሻለው በርግጥ ዶክተሩ አንዲ ሊሆን እንደሚችል ነግሮን ነበር። ይኸውልሽ አሁን ሀገሩ ላይ ያለው
ሁኔታ በተለይም በዮንቨርሲቲዎች አከባቢ ግጭትና አለመረጋጋት ስላለ አብዛኛውን ተማሪ ወደ ቤቱ ተመልሶ ቁጭ ብሏል።እና አንቺም እንደምትመጪ ነገርሽን አና ግን መጣለው ባልሽበት ቀን አልመጣሽም ከዛ ቡሗላ ብንጠብቅም አልመጣሽም ነበር በስለክሽም ልናገኝሽ አልቻልንም ጓደኞችሽ እዛ እንደሌለሽ ነበር የነገሩን።ግን መጣለው ካልሽበት ከአንድ ሁለት ሳምንት ና ከዛበላይ ከቆየሽ ቡሗላ ነው የመጣሽው አና ምንም አታስታውሺም ነበር እንደዚ ሆነሽና ታመሽም ነበር"

"ማን አመጣኝ ታዲያ...?"
"እንጃ ጋሼ ነው ይዘውሽ ወደቤት የመጡት ስለክም ልብስም አልያሽም ነበር እና አንድ የማናውቀው ሰው ይመስለኛል እስከዚ ያመጣሽ እና ጋሼም በሰው በሰው መሰለኝ ያገኘሽ በደንብ አልነገረኝ።"
"ኬት ነበር የመጣሁት??" "እንጃ ብንጠይቅም መልስ ስላጣን ዶክተር ጋር ነበር የወሰድንሽ እናም ለማገገም ጊዜ እንደሚያስፈለግሽ ተረዳን።" "ዶ/ሩ ምን አለ..?"
"ጭንቀትና የአይምሮ መታወክ ነው ብሎ ነው የገመተው ግን እሱን ማረጋገጥ ሚቻለው አንቺን ጠይቆ ስትመልሺ ብቻ ነው ሆኖም ለጊዜው መጨናነቅና መረበሽ ስለሌብሽ ጋሼም ሆነ ዶ/ሩ ማንኛቸውም እንዳይጠይቁሽ ሆኗል"
"የት እንደነበር ወይም ምን ሆኜ አንደነበር ትንሽም አንኳን ምንም አታውቁም...?" በአሉታ አንገቷን ነቀነቀችልኝ።
"አይ አይመስለኝም ይሄማኮ ግልፅና ለመገመት እንኳን በጣም ቀላል ነው ቡርቴ !!!"እንደመጮኽ አልኩባትና ትቻት ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ።አባቴ በትክክልም የሆንኩትን ያውቃል እኔን መጣለት ሰውንም በትክክል። ለዛ ነው ምን አስታወሽ ብሎ እንኳን ያልጠየቀኝ መስማት ስለሚፈራ ወይም ስላልፈለገ ነው።ዜናስ እንዳልሰማ የተደረኩበት ምክንያትስ..?የአባቴ ስጋትና ጥንቃቄስ...?ምናልባት እንዳላስታወስ ተፈልጎና ሆን ተብሎ ቢሆን....?
ሁለቱይ ሳምንት የት ነበርኩ...?ማስታወስ አለመቻሌ ንዴት እየጫሰብኝ የመጣ መሰለኝ..



💫 ይቀጥላል💫

ለአስተያየታችሁ እንዲሁም ማስተካከል ያለባት ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት
👍2
#ቄስ_ቫላንቲ_ሆይ……

እንዴት ሰንብተዋል ኑሮዎት እንዴት ነዉ
ይሄዉ ተገናኘን መሰንበት ደግ ነዉ
እኔ ብቻየን ነኝ ዛሬም ልክ እንዳምናዉ
የክህደት ባንዴራ ህይወታችን መሀል
ከፍ ብሎ ሲሰቀል
ጥንድ መሆን ህመም ብቻነት ይበጃል
የኔን ነገር ተዉት ይቅር አይነሳ
ግን እንደዉ ግንሳ….
የባለፈዉ ለታ የቫላንቲኖ ቀን
ህዝቤ ያረገዉን መቸም አይረሱትም
ከሰሜን ደቡብ ጫፍ ከምራብ ምስራቅም
ተፋቀርን ያሉ ጥንዶች ባደባባይ
ቀይ አበባ ይዘዉ…
ቀይ ወይን ተጎንጭተዉ…
ጉዋዳ ጎዳናዉን በቀይ አስሸብርቀዉ
ቀይ ጠረጴዛ ቀይ ስጋጃ ላይ
በጥንዶች ተሞልቶ አለም ቀልቶ ሲታይ
እዉነት እንዳይመስሎት ቄስ ቫላንቲኖ ሆይ
እዉነት እዉነት እዉነት
አለም ቀልቶ አይደለም ቀንቶ ነዉ እዉነቱ
እሽ አሁን የት አሉ አምና የቀሉቱ
ቀንተዉ ነዉ በሰዉ ቀይ አበባ ይዘዉ
ሲሉ ሰምታን ሰምተዉ ያለ ሀቁ ናዉዘዉ
ሲነጋ የጠፉት ቀዩን ካርድ መዝዘዉ
በእዉነት ቫላንቲኖ
እርስዎ ደክመዋል እርስዎ ለፍተዋል
ለፍቅረኞች ሲሉ ህይወት ሰዉተዋል
ግና ባደባባይ እዩኝ ያለ ፍቅር
እዩኝ ያለ ህይወት
መሰረት ከሌለዉ
በረከት ከሌለዉ ንፋስ ሽዉ ያለ ለት
ፍጻሜዉ ቀይ ነዉ ቢጫም አይገባበት
ቫላንቲኖ አባቴ….
ግዜዉ ተለዉጡዋል ዘመን ለዛዉ ከፍቱዋል
ታሪክ ተቀይሩዋል
በእርግጥ በእርሶ ዘመን
ንጉስ ወጣቶቹን እንዳይጋቡ አዙዋል
ይህም ክፉ ትዛዝ እርሶን አስከፍቱዋል
አሁን በኛ ግዜ
ወጣቱ ይጋባል ግን ወድያዉ ይፋታል
ለምን?
የተሸበረ ልብ የፈራ ሰዉነት
ትዳርን አይደለም የራሰንም ህይወት
መሸከም ይፈራል
በእዉነት ቫላንቲኖ አለም ተሸብሯል
ቀይ ሲያይ…. ሹፌሩ ይቆማል
ቀይ ሲያይ….ኩዋሰኛዉ ይወጣል
ቀይ ሲያይ….ቀይ ሲያይ
የከፋዉ ሀገሬዉ ልቡ ይሸበራል
ባክዎን አባቴ
ባክዎን አባቴ
የሚቀጥለዉን ዳግመኛ ሲመጡ
ቀይ አበባ ጥለዉ…
እንደ ኖህ እርግብ ከሳር ከቀንበጡ
አረንጉዋዴ ቅጠል ጨፌ ይዘዉ ይምጡ

⚪️በሰለሞን ሰሃለ⚫️
1
አትሮኖስ pinned «#ቄስ_ቫላንቲ_ሆይ…… እንዴት ሰንብተዋል ኑሮዎት እንዴት ነዉ ይሄዉ ተገናኘን መሰንበት ደግ ነዉ እኔ ብቻየን ነኝ ዛሬም ልክ እንዳምናዉ የክህደት ባንዴራ ህይወታችን መሀል ከፍ ብሎ ሲሰቀል ጥንድ መሆን ህመም ብቻነት ይበጃል የኔን ነገር ተዉት ይቅር አይነሳ ግን እንደዉ ግንሳ…. የባለፈዉ ለታ የቫላንቲኖ ቀን ህዝቤ ያረገዉን መቸም አይረሱትም ከሰሜን ደቡብ ጫፍ ከምራብ ምስራቅም ተፋቀርን ያሉ ጥንዶች ባደባባይ…»
#የቤት_እመቤት_በመሆን_ውስጥ_እመቤትነት #አለ


#በሕይወት_እምሻው


በአንድ ወቅት፣ ያገኘኋቸውን ወንዶች በሙሉ አንድ ጥያቄ ስጠይቅ ነበር፤ "የቤት እመቤት ማለት ምን ማለት ነው?" ከአንድ ወይም ሁለት መልሶች ውጪ የተሰጡኝ ፍቺዎች በሚከተሉት ሐረጎች ሊጠቃለል ይችላል።

"የማትሰራ ሴት"

"ሥራ የሌላት ሴት"

"ገቢ የሌላት ሴት"

"ሥራ አጥ ሴት"

"ሥራ ፈት ሴት"

እነዚህ መልሶች የሰጡኝን ወንዶች መልሼ ይሄንን ጥያቄ ጠየኳቸው።

ነጋ ጠባ አልጋ ማንጠፍ፣ ቆሻሻ ልብስ ማጠብ፣ የታጠበ ልብስ ማጠፍ፣ የታጠፈ ልብስ በየቦታው ማስቀመጥ፤ ከሻይ ማንኪያ እስከ በርሜል ሙልጭ አድርጎ ማጠብ ፣ የታጠበውን እቃ ማድረቅ ከሻይ ማንኪያ እስከ በርሜል ሙልጭ ተደርጎ የታጠበና የደረቀ እቃን በየቦታው ማስቀመጥ፣ ሥራ አይደለም?

በየቀኑ ከኩሽና እስከ ሳሎን ፤ ከሽንት ቤት እስከ ግቢ መጥረግና መወልወል፤

ከሳሎን ጠረጴዛ እስከ ቁም ሳጥን ጀርባ እና አልጋ ሥር ድረስ መጥረግና መወልወል፤

የቤቱን ሁሉ የተጠረገና የተወለወለ ቆሻሻን ሰብስቦ መጣልስ ፤ ሥራ አይደለም ?

ቀን ቆጥሮ አንሶላ ፤ ትራስ ልብስና አልጋ ልብስ መቀየር ፤ ጊዜን አስልቶ የኩሽና እቃ ግልብጥ አድርጎ አውጥቶ ማጽዳት፤ ጊዜን ወስኖ የመስኮትና የበር መስታወትን በጋዜጣ ሲያፀዱ እና ሲያስውቡ መዋል ፤ የአደፈ መጋረጃን መሐወጥ፤ ሥራ አይደለም?

"ምን አለቀ?" ብሎ ቀለብ መሸመት ፤ የተሸመተውን አመጣጥኖ ማዘጋጀት፤ የተዘጋጀውን ማቅረብና ቤተሰብ መመጠብ፤ ሥራ አይደለም? ደግሞ ከሁሉ በላይ፤

ልጅ ማርገዝ፤

ልጅ አምጦ መውለድ፤

ልጅ አጥብቶ ማሳደግ፤

ልጅ ማነጽ፤

ልጅን ለወግ ማብቃት ፤ ሥራ አይደለም?

እናም ወንድሞቼ...

አገልግሎትና ምርታማነት በጥሬ ገንዘብ በሚተመን የኢኮኖሚ ሥርአት ውስጥ በመኖራችን ብቻ ፤

በቀጥታ የገንዘብ ክፍያ የማያስገኝ ሥራ እንደ ሥራ በማይቆጠርበት ዓለም በመኖራችን ብቻ ፤ ይሄንና ሌላም ልዘረዝረው ብል መጽሀፍ የማይበቃውን ሥራ ሁሉ የምትሰራን ሴት "ሥራ የላትም" አትበለኝ።

ይልቅስ፣ በእኛ ሀገር የቤት እመቤት መሆን ፤ ከእመቤትነቱ ሸክሙ ይበልጣልና ፤ ሚዛናችሁን አስተካክላችሁ የቤት እመቤት ማለት ፤ "በዓለም ላይ ከባዱን ፤ ግን ክፍያ የሌለውን ሥራ የምትሰራ ሴት ማለት ናት" በሉኝ።

💫ጨረስን💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1
አትሮኖስ pinned «#የቤት_እመቤት_በመሆን_ውስጥ_እመቤትነት #አለ ፡ ፡ #በሕይወት_እምሻው ፡ ፡ በአንድ ወቅት፣ ያገኘኋቸውን ወንዶች በሙሉ አንድ ጥያቄ ስጠይቅ ነበር፤ "የቤት እመቤት ማለት ምን ማለት ነው?" ከአንድ ወይም ሁለት መልሶች ውጪ የተሰጡኝ ፍቺዎች በሚከተሉት ሐረጎች ሊጠቃለል ይችላል። "የማትሰራ ሴት" "ሥራ የሌላት ሴት" "ገቢ የሌላት ሴት" "ሥራ አጥ ሴት" "ሥራ ፈት ሴት" እነዚህ መልሶች…»
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_አራት


#በዮርዳኖስ

"እና መጀመሪያ ምንድነው ምንገዛው?" አለችኝ።ገበያ ደርሰን ነበር ገበያው ያን ያህል አልደራም ቢሆንም በቂ ሱቆች ተከፍተዋል።"አንቺ የፈለግሽውን" አልኳት
"እንደዛ ከሆነ ነይ በዚ እንቁላል እና ወተት አንግዛ"
በአትክልት ተራው አልፈን ወደ እህል ተራ በሚወስደው መንገድ ስንደርስ በአንደኛው መታጠፊያ ይዛኝ ገባች።ወደ ትልቁ የገበያ አዳራሽ ማዕክል እና የቤት እቃዎች በመሸጫዎች መሀል አቋርጠን እዛው ወዳለው ወደ ወተት ተራው ገባን።"ደንበኛዬ አልመጣችም በዛ ላይ ሀይላንድ ያስፈልገኛል መጣው እዚሁ ጠብቂኝ"ብላኝ ሔደች ትኩረቴ እሷ ጋር ስላልነበረ ግድ አልሰጠኝም ነበር።ግራና ቀኙን መቃኘት ጀመርኩ አንዳንድ እቃው ባለሱቆች ገና ከፍተው እቃ በማውጣጣት ላይ ሲሆኑ አብዛኛው ጨርሶ ቁጭ ብሏል።የማውቀውን ሰው ፍለጋ ይመስል ሁሉንም እያስተዋልኩ አያለው።
"ኧረ እማ እንሒድ በቃ ለኔኮ ጫማ አልገዛንም..."
"አይ የልጅ ነገር በቃ ከራስህ ውጪ አታስብም አይደል መጀመሪያ የምንበላውን ልገዛ እስኪ" እናትና ልጅ ትኩረቴን ስለሳቡኝ እሰማቸው ጀመር።
"ገና እኮ ጠዋት ነው ማሙሽ ሱቁም በደንብ ይከፈት እናትህን አታስቸግራት እንጂ" ሌላኛዋ ሴት እንቁላል ለእናትየው እያቀበለቻት የእንቁላል ነጋዴ ነች።
"እሺ እዛጋ ያንን"ህፃኑ ለናቱ እየጠቆማት እድሜው በግምት ወደ ሰባትና ስምንት የሚጠጋ ይመስላል።
"ምን የቱ ጋር?" አለች እናቱ።እኔም ጥቆማውን ተከትዬ አይኔን ጣልኩ
"ምንድ ነው እሱ አትናገርም እንዴ?" እናትየው የታያት አይመስልም እኔ ግን በትክክል አይቼዋለው የልጁ እሳቤ ቀድም የነገረኝ ይመስል ተረድቼዋለው።በቀስታ ወዳየሁት ነገር መራመድ ጀመርኩ።

"ያውና ሰው የሚታረድበት ነገር እኮ ነው!!"
"ምን.... ?በስመአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ!!"
እናትየው እንቁላሉን ስትለቅ ይሰማኛል።እግሬ አየተንቀጠቀጠ ቀረብኩ በቁጥር በዛ ያሉ ስለታቸወና አዲስነታቸው ከሩቅ የሚያብለጨልጭ ባንጋዎች ናቸው ሰውነቴን አየሰቀጠጠኝ አጠገቡ ቆሜ ወደታች አየውት።

"ደሞ ኬት አመጣኸው ይሄንን? ሁለተኛ አንደዚ እንዳትል እሺ አባቴ ሁለተኛ!! ና ከዚ እንሒድ"የናትየው ድንጋጤ ከድምጿ ቃና ይታወቀኛል።የሷ ብቻ አይደለም እኔም ፍርሀቴ ሲጀምረኝ እና ወደነዛ ቀናት በትውስታ የተመለስኩ ሲመስለኝ ይተወቀኛል። ህፃኑ ያለው በአይምሮዬ ተስሎ ታየኝ።

ይሄ ነው እንግዲ የማንነት የትውልድ ኪሳራ፣ ይሄ ነው እንግዲ አዲሱ ለትውልድ የምናስተላልፈው ታሪክ እና ገድላችን ፣ይሄ ነው እንግዲ ሰውነት ከእንስሳነትም ከእቃነትም ተራ አልፎ የረከሰበትና የቀለለበት ዘመንና ትውልድ ፤ይሄ ነው የማንነት ክስረት። ይሄንን የማንነት ውደቀታችን ነው በታናናሾቻችንና በልጆቻችን አይምሮ እየሞላንና እየቀረፅን ያለነው።
"ጉድ እኮ ነው አንቺ ይሄ ህፃን እንኳ እንዲ ይናገር....አጃኢብ!!!

"ሰማሽ አይደል ለነገሩ ምን ያድርግ በሱም አይፈረድም።እነሱስ ቢሆኑ ሰው እንደዚ በተጨካከነበትና በሚጨራረስበት ወቅት እንደዚ በሰፊው ይሄን መነገዳቸው ምን ማለታቸው ነው? እንዲያው ሲያዮት እንኳ አንዴት ይዘገንናል!"።

"ሔዊ ምነው" ደንዝዤ ከቆምኩበት የቡርቴ ጥሪ ከኋላዬ ተሰማኝ።"እንዴ እያለቀሽ ነው እንዴ ሔዋን ምነው የኔ ወድ?"
የተናነቀኝን እንባ እያየች።ግን የድንጋጤ እና የፍረሀት ወይም
የሀዘን እንባ አልነበረም ቁጭትና እልህ እና ንዴት እንጂ።
"የኔ ጥፋት ነው ይዤሽ መውጣትም ሆነ ብቻሽን መተው አልነበረብኝም"እንባዬን አየጠረገች።
"ቡርቴ..?"አልኳት"ሁለቱን ሳምንት ታግቼ ነበር አይደል? ለነገሩ እሱ በጣም ግልፅ ነው ደሞም ይሄንን አባቴም ሆነ አንቺም በደንብ ታውቃላቹ!!

"ምን...? ለምንድነው እንደዚ የምትይው ነይ ከዚ አንሂድ መዳኒትሽን መውሰድ አለብሽ..."እጄን ይዛ ጎተተችኝ።

"አይ አይሆንም ለቀቂኝ!"እጄን አስለቀኳት
"አቁሚ በጭራሽ አልሄድም አሁን ባልሺኝ መሰረት የምጠይቅሽን እሺ በማለት ታደረጊያለሽ!"ጥያቄ ሳይሆን ትዕዛዝ ነበር።

#ሕዳር 20/12 ቀን የታገቱ ተማሪዎች እስካሁን ድምፃቸው አልተሰማም።
ይላል ሙሉ ዜናውን ለማግኘት ፔጁን ተቀላቀልኩ።
January 24
#ከ 35 ሺህ በላይ ተማሪዎች ቤታቸው ናቸው።በአንዳንድ የሀገሪቱ ዮኒቨርስቲዎች ውስጥ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት መደበኛ ት/ታቸውን አቋርጠው የተመለሱ ተማሪዎች ወደ ትም/ት ገበታቸው አልተመለሱም።

#የኢትዮጵያ የሳይንስና የከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር በ22ቱ ዮኒቨርስቲዎች ባካሄደው ምርመራ እና ቅኝት በግማሽ መንፈቅ ዓመት ብቻ የ12 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።
=> ታህሳስ 27
ሌሎች የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉና ቁጥራቸውም 4 እንደሚደርስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳዶር በጋዜጣዊ መግለጫ የገለፁበት ቀን

#በሕዳር 20/12 ስለታገቱ ተማሪዎች የጠቅላይ ሚንስተሩ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬተርያት በሰጡት መግለጫ፦አጠቃላይ 27 ተማሪዎች ታግተው እንደነበረና 21ዱ መለቀቃቸው 6ቱ ደግሞ ታግተው እንዳሉ ገልፀዋል።የሚልና ሌሎች ተመሳሳይ የወጡ ዜናዎችን በብዛት ካየሁ ቡሗላ
አሁን ሁሉም በግልፅ የገባኝ መሰለኝ።

የሰጠሗትን ትዕዛዝ ላለመቀበል ጋሼ ቢጠየቁኝስ ምን እላቸዋለው?"ነበር ያለችኝ እኔም
ቃል በገባሁላት መሰረት አባቴ ሳይመለስ ቀድሜ ቤት ለመገኘት ከሷ እንደተለየው ጊዜ ሳላባክን ወደ ኢንተርኔት ቤት ነበር ያመራሁት።እና የምፈልገውን ካየው ቡሗላ ቶሎ እሷ ጋር መሄድ ስለነበረብኝ ባጃጅ አስቁሜ ገባው ውስጤ ብዙ ሀሳብ ይመላለሳል ግን የትኛውን በትክክል መስማት እንዳለብኝ እንጃ። እስካሁን ምንም ባለማወቄ እና በዝምታዬ የተሞኘውም መሰለኝ
ሀገሪቱ ላይ የሚካሄደውና የሰው ሁኔታ ግን ግርምትን የሚያጭር ነው። ምንም እንዳልተፈጠረ መኖራችን አስገርሞኛል። ለምሳሌ ያለሁበት ባጃጅ ሹፌር ዕድሜው ከኔው ጋር ተመሳሳይ ነው። እርግጠኛ ነኝ በነዛ ወጣቶች ላይ የተፈጠረውን/ይቅርታ በኛ ላይ ልበል እንጂ ስለተፈጠረውና ስለተፈፀመው ድርጊት በሚገባ ሰምቷል።እና ናላ በሚያዞር ምንነቱ በማይገባ ዘፈን ባጃጁን መጓጓዣ ሳይሆን ክለብ አስመስሎ እስከቂጡ ከፍቶ ባጃጇን እንደ አየር ያከንፋታል። ተማሪዎች ከየት/ት ቤታቸው ተለቀው በተለያየ ዮኒፎርማቸው ሲተራመሱ ይታያሉ። ይሄን ሁሉ ጊዜ ቤት መጥቼ ቁጭ ስልም ሆነ ስወጣ ማንም ሰው ስለነዛ ልጆች ሲያወራ ና ሲያነሳ አጋጥሞኝ አለማወቁም የማይታመን ነው
ሚድያዎቻችንም ቢሆኑ
ከምንም በላይ ያስገረመኝ ግን የራሴው አባት ነው።ምንም ያሀል ልጁን የሚወድ አባት ሊሆን ይችላል ግን ደሞ ይሄ ትልቅ ራስ ወዳድነት ይመስለኛል።ስለኔ ብቻ ሳይሆን የሌሎቹም ነብስና መጨረሻ ሊያሳስበው ይገባ ነበር።
ለማንኛውም ግን ማወቄንም ሆነ ማስታወሴን በድብቅ ለመያዝ እና ለመቀጠል ወስኛለው ምክንያቱም ማንኛውም ወላጅ ቢሆን ለጁ እንዲያደርግ እማይፈልገውን ነገር ለማድረግ ስለወሰንኩ ነው።በርግጥ አንደማንኛውም ሰባዊ ሰው ሲታይ ልክ የሆነና ተገቢ ድርጊት ሊሆን ይችላል።እንደ ወላጅ ግን አይደለም!
" ደርሳሻል እናት"አለኝ ወጣቱ ባለባጃጅ ድምፁን ከፍ አድርጓ፤ እስኪ ምናለበት ከመጮህ ዘፈኑን ቢቀንሰው ያለኝን ብር ከፍዬ በፍጥነት ወደቤት ገባው።አባቴ ገና አልመምጣቱ ካረጋገጥኩ ቡሗላ ወደ ቡርቴ ሮጥኩ
"ውይ ተመስገን ለትንሽ ነው የደረሽው"አለችኝ
"ቡርቴ..?"
"እ...?"
"ብሌንስ...??"ውስጤ ሲመላለስ የነበረውን ጥያቄ ጠየኳት።


💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየታችሁ እንዲሁም ማስተካከል ያለባት ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት
👍1
#የደም_ቀን #የካቲት_12


አገር ተቃጠለ ፣
እሳተ ጎመራ ወረደ ከሰለ፣
ጭስ አመድ አዋራ ሰማዪን ሸፈነው ፣
ጥቁር ሰማይ ጥቁር !
ሸፈነው ጨለማ በሞት በእናት ቅድስት ሃገር፣
በጀግናው ህዝብ ላይ የጠላት ግፍ ቀንበር፣
ፋሺስት አስተጋባ ፋስ ተሰነዘረ ፣
ባካፋ መዶሻ ህዝቡ ተወገረ፣
የሰው ጭንቅላት ኳስ
አባቶች ታረዱ፣
እናቶች ታረዱ፣
ቤት ንብረት ፈረሰ ከብቶቹ ተነዱ፣
ዓለም መና ቀረ .. ...

🔘በገብረክስቶስ ደስታ🔘
👍1
#ዝግመትሽ_እና_ፍጥነቴ


የፍቅሬን መጠን ነግሬሽ - ካደመጥሺኝ ቡኋላ

ላስብበት ብለሽ ሄድሽ - እንደቆምኩኝ ካውላላ

በብስለት ሁሉን መርምረሽ- ክፉና ደጉን መዝነሽ

ስለ እኔ ጀርባ አጥንተሽ - ጓደኛ ዘመድ አማክረሽ

ከወር በኋላ ብትመጪ- ልትነግሪኝ ፈቀድኩ ብለሽ

የጊዜ አጠቃቀመችን - ልዩነታችን ገረመኝ

ዝግመትሽ እና ፍጥነቴ - ሁለቱም አስደመመኝ

ቆየው እኮ ሌላ አፍቅሬ - ቀለበት አስሬአለሁ

በዚህ ግርግር መሃል - አንቺን እረስቼለሁ

ዛሬ ይሁን ስትይኝ - ምን መልስ እሰጥሻለሁ።
አትሮኖስ pinned «#ዝግመትሽ_እና_ፍጥነቴ ፡ ፡ የፍቅሬን መጠን ነግሬሽ - ካደመጥሺኝ ቡኋላ ላስብበት ብለሽ ሄድሽ - እንደቆምኩኝ ካውላላ በብስለት ሁሉን መርምረሽ- ክፉና ደጉን መዝነሽ ስለ እኔ ጀርባ አጥንተሽ - ጓደኛ ዘመድ አማክረሽ ከወር በኋላ ብትመጪ- ልትነግሪኝ ፈቀድኩ ብለሽ የጊዜ አጠቃቀመችን - ልዩነታችን ገረመኝ ዝግመትሽ እና ፍጥነቴ - ሁለቱም አስደመመኝ ቆየው እኮ ሌላ አፍቅሬ - ቀለበት አስሬአለሁ…»
#ጫፍ_አልባ_ቁልቁለት


የያዙትን ይዞ ካልተጠላጠሉ

ወደ ላይ ካላሉ










መውደቂያ ካሰሉ
ከውድቀት ዳርዳሩ ከተንደረደሩ
መውደቅ ከጀመሩ
ውድቀት ጫፍ የለውም
ሜዳዉ ቁልቁለት ነው ውድቀት ዳር የለውም
በውድቀት ላይ ውድቀት እየተያያዘ እየተዋዋለ
ከውድቀትም በታች ሌላ ውድቀት አለ።
👍1
#ብሌን 🇪🇹


#ክፍል_አምስት


#በዮርዳኖስ

ቤቱን የሞላውን ሁካታ ጩኸት ለማስቆም ሁለተኛው ጥይት ተተኮሰ ተኩሱን ተከትሎም ሁሉም ዝም አለ ቤቱን እንደገና ፀጥታ ወረሰው።
ፊትለ ፊታችን ከተጋደመው እሬሳ ትኩስ ደም እየተምዘገዘገ ወደስራችን ቁልቁል ይወርዳል።ግን ሁላችንም በፍራቻና በድንጋጤ ትንፋሻችን እንኳ እንዳይሰማ ሆኖ ዝም አልን ማንም አያለቅስም
መጮህ አይታሰብም ምክንያቱም በተነፈሰው ሁለት ቃል ምክንያት ወደ ሞት የተሸኘውን ሁሉም ስላየ ስቅስቅታ የለም የሚቆራረጡ ትንፋሾች እንጂ ተጨንቆ በተለይም ሰሚም ሆነ ደራሽ እንደሌለ አውቆ ተስፋ እንደመቁረጥ ፈርቶ መሽሽና ማምለጥ እንዳለመቻል ሞትን እያሰቡና ፊት ለፊት እየተጋፈጡት ማልቀስ እየፈለጉ አንዳለማልቀስ መጮህ እየፈለጉ አንዳለመጮህ ምንም ማለትና መደረግ እንዳለመቻል እሚያም ነገር የለም።

የሚከተለውን በማሰብ ማንም ደሙን ለመሸሽ ንቅንቅ አላለም።
ለመዳን መፀለይ ይኑርብኝ ንሰሀ መግባት አላወኩም ግን ሁለመናዬ ይንቀጠቀጣል ልብ ምቴ ለሁሉ እሚሰማ እስኪመስለኝ ድረስ በፍጥነት ይመታል ትንሽ ቆይቶ ግን መቆሙ እማይቀር ይመስላል እየሆነ ያለው እና የማየውን በህለሜ ይሁን በውን እንጃ ግን በህሌሜ ከሆነ ለምን አልባነንኩም ስል አሰብኩ በውኔ ከሆነ ደግሞስ እንዴት ተቋቋምኩት?

አጋቾቻችን አና ገዳያችን እርስ በእርሳቸው መነጋገርና መጯጯህ ጀመሩ።እኛ ብቻ ሳንሆን እነሱም መጠነኛ ድንጋጤ የደነገጡ ይመስላል።እኛን ትተው እርስ በእርስ ጭቅጭቅ ጀመሩ "ለምን?" የሚል ጥያቄና ቁጣም እያቀረቡበት ይመስላል። እሱም ሳይፈራ "እንኳን!"የሚል በሚመስል ልበሙሉነትና ቁጣ በጩኸት ይመልስላቸዋል።ከዚ በላይ ግን የሚሉትን ለመረዳት አልቻልኩም።

ድንገት ያለንባት በረት መሳይ ትንሽዬ ቤት በር ከፍተኛ ድምፅ አሰምቶ ተከፈተ።
እንደገና ጩኸት።
እኛን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ያስደነገጠ ክስተት ሆነ።
"አንዳትንቀሳቀስ...! እንዳትንቀሳቀስ ብያለው እንዳትበላሽ ዋ...!!"አለ ከውጭ የሚመጣ ድምፅ። ጠመንጃውን አስቀድሞ በቀስታ ወደ ውስጥ ዘልቆ ብቅ እንዳለ "ልጆች እዚ ምን እየተካሄደ ነው.."አሉ በዕድሜ ጠና ያሉት ሽማግሌ ሁሉንም በጥንቃቄ እያዮ።የመጀመሪያው አማረኛ ተናጋሪ ናቸው አይናቸው ውስጥም ክፋት ወይምን ጭካኔ አይታይም እንደውም ገፅታቸው ርህራሄ ይነበብበታል።ከሰማይ የመጣ አዳኝ መለዓክ ይሆን እንዴ..?አልያም አምላክ አዝኖ እኛን ለማስመለጥ የላከልን ታዳጊያችን ሰው ይሆኑ?! ብቻ ግን ውስጤ እንደገና በተስፋና ዳንኩ በምትል ትንሽ የደስታ መንፈስ ሲወራጭ ተሰማኝ።እኔን ብቻ ሳይሆን ሁሉም እንደዛ ያሰበ ይመስለኛል።

ግን ድንገት ከመካከላቸው አንድ ተነስቶ "እንዴ....ጋሽ ሽመልስ...! እርሶ ኖት እንዴ...?"አለ ለሰላምታ እቀፉን እያዘጋጀ።አማረኛው ጥርት ያለ ነው ግን እስካሁን አንዲትም የአማረኛ ቃል አልተነፈሰም ነበር።
"እህ...ሙሴ ጎረምሳው አንተም አለህ እንዴ...?ታድያ ምን አያደረጋችሁ ነው?"የፊት ገፅታቸውን ወደ ቁጣ ቀይረው ጠየቁት።
"ኧረ ሰላም ነው ምንም አይደል አጎቴ..."አለ

እንዳሰብነው ሳይሆን ቀረና ሔዶ ተጠመጠመበት ተቃቀፉ ያብቻ አይደለም ሌላ በእድሜ ተለቅ የሚለውና ዋናው አዛዥ የሚመስለውም ተነስቶ በክብር ሰላም አላቸው ና ማውራት ጀመሩ።ሁሉም የሚያውቋቸው ና የተከበሩ የአከባቢው ነዋሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሁኔታቸው መገመት ይቻላል። ግን ተወላጄ እንዳልሆኑ ግለፅ ነው።ባዩት ነገር እንደደነገጡና እንዳዘኑም የፊት ገፅታና አስተያየታቸው ያሳብቃል።በርግጥም ሊያድኑን ፈልገዋል ሆኖም ምንም ያህል ደግ ቢሆኑም አና ሀዘኔታ ቢኖራቸውም ግን እነሱን መቃወም ሆነ እንዲለቁን ማድረግ እንዳልቻሉ ግልፅ ሆኖልን ነበር። አይናቸው ላየ ሀዘኔታ ይነበባል ጥለው ለመሄድ አልፈለጉም። እሳቸውም የማይችሉት ነገር እንደሆነ ተረድተዋል ቢሆንም እርዳታን እሚማፀኑና የሚያለቅሱ አይኖች በተስፋ እሳቸው ከማየትና ከመጠበቅ አልቦዘኑም።

"አይ እንደዛ ከሆነማ እሺ እኔ ደሞ ምን ተፈጠረ ብዬ እኮ ነው።እንዲያ ከሆነማ..."ለአፍ ይበሉ እንጂ ከልባቸው አይደለም የሚናገሩት።
"አይ እርሶን አያሳስቦት ቀላል ነገር ነው ያው እንዳለኮት ነው አንጎዳቸውም ታውቁ የለ..."ይላል ከመጀመሪያው ተነስቶ ያቀፋቸው ሰው።
ፊታቸው ቅራኔን እንደተሞላ ደጋግመው አየተዟዛሩ ካዮን በበሗላ ለአራጆቻችን ጥለውን ወጡ።ግን ውስጤ ተስፋ አልቆረጠም ከሁኔታቸው አንዳየሁት ሰዎችን ይዘው ተመልሰው መተውም ቢሆን ከማዳን ወደ ሗላ እንደማይሉ እርግጠኛ ሆኜባቸው ነበር።

"ምንም ችግር አይፈጠርም..?"አለ አንደኛው ሰው
"የዚው አከባቢ ሰው ናቸው አሳልፈው አይሰጡንም"አለ አጎቴ ሲል የነበረው።
"አይ አይመስለኝም"አለ አዛዡ በአይን ምልክት አንዲከተሉት ትዕዛዝ እየሰጠ።
ወዲያው ሁለት ሰዎች በፍጥነት ተከታትለው ወጡ።
እንደገና ቋንቋቸውን ቀይረው መጨቃጨቅ ጀመሩ መጀመሪያውም ያልተስማሙት አጋቾች እንደገና በነዚ ሰው ምክንያት አለመግባባት የተፈጠረባቸው ይመስላል።ቋንቋውን በፍፁም ሰምቼው አላውቅም ምናልባት ብዙ እማይነገር የአንዱ ብሔር ቋንቋ ሊሆን ይችላል አልያም ደግሞ እዚው ለመግባቢያ የፈጠሩት ሌላ የኮድ ቋንቋ ሊሆን ይችላል።ሁለተኛውን የመሆን እድሉ ግን ሰፊ ይመስለኛል።

እኛ ታዳጊ መልክተኛችኝ አባት ምን ሆነው ይሆን...? አምልጠው ያድኑን ይሆን ወይስ እነሱም ተይዘው እዚው እኛው ጋር ይቀላቀሉ....? በሚል ሀሳብ ውስጥ እንደተዋጥኩ ቀጥሎ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመርኩ።

በግምት 3 ደቂቃ ያህል ይሆናል ምንም የለም እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የሚሆነውን በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቀ ይመስለኛል።ምክንያቱም ከነኚያ ሰው ጋር ተስፋችንን አብረን ልከናል የመሞትና የመዳን ዕድላችን በሳቸው የሚወሰን ሆኗል በሳቸው ምክንያት ተስፋ አልያም ሞት ይቀጥላል በቃ።
ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ። ቢያመልጡ እንጂ ቢያዙ መቼም ይሄ ሁሉ ደቂቃ አይቆዮም ብዬ ደመደምኩ። ምናልባት እስከ ነገ ቢፈጅባቸው ነው ከዛም መተው ያድኑናል ብዬ ሙሉ ለሙሉ ተስፋ አደረኩ ደስም ያለኝ መሰለኝ።አሁን እግዚአብሔርን የምለምነው እስከ ጠዋት በህይወት እንዲያቆየን ብቻ ነው ግን እስኪነጋ ማን ይሙት ማን ይትረፍ የምናውቀው ነገር የለም ምናልባት ሁላችንም በአንድ ሽጉት ቀላሀ ብቻ ልናልቅ እንችል ይሆናል አልያም ሁላችንንም አንተርፋለን።ወይም ምን ይታወቃል እዚሁ በጭድ በተሞላው ቤት ውስጥ እንዳለን ቤንዚን አርከፍክፈው ያነዱን ይሆናል
ብቻ ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም መገመትም ሆነ ማወቅ አይችልም።
በቃ የሚመጣውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለም።
ግን አሁን ትንሽም ቢሆን ተስፋ አለን።

ከአስራዎቹ ደቂቃ ቡሓላ የሄዱት ሰዎች ኮቴና ድምፅ ተሰማን።ባዶዋቸውን እንደተመለሱም እርግጠኛ ሆንኩ።
ግን ሳይሆን ቀረና ያ ተስፋዬን አብሬ የላኩበት ሰው ተስፋዬን ጥሎብኝ አብሯቸው መቶ ነበር

"እህሳ ፈልገኸኝ ነበር? ከመንድ ሲያስመልሱኝ ጊዜኮ ችግር የተፈጠረ መስለኝ"አሉ ድንጋጤያቸውን ለመደበቅ እየጣሩ እንዳሉ በሚያሳብቅ ንግግር።
"አይ ችግር የለም እንደው አግረመንገዶን ከመጡ አይቀር ለምን አንድ ነገር አላሳይዎትምና አላማክሮትም ብዬ እኮ ነው"አለ ዋናቸው ሰው እጁን ትክሻቸው ላይ አስደግፎ ይዟቸው እየወጣ በድጋሜ በዛ ርህራሄ በሞላበት አይናቸው ቃኘት አድርገውን ነበር የወጡት ነገሩ ግራ አጋባኝ ቢሆንም ከኛ ጋር አለመቀላቀላቸውን ወይም መንገድ ላይ አለመገደላቸውን ተስፋ አድርጌ መጠበቅ እንደጀገመርኩ በዛው ቅስፈት ከወደውጪ ተኩስ ተሰማ ልቤ ከልባቸው እኩል አብሮ ምቱን ያቆመ መሰለኝ
👍1
ተስፋዬም አብሮ አከተመ።ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጼን አውጥቼ ተንሰቀስኩ ግን እሚሰማ አልመሰለኝም የምችለውን ያህል ጮህኬ አለቀስኩ ግን ድምፄ ሀይል አልነበረውም።ተከትሎኝ ሁሉም መንሰቅሰቅ ጀመረ። በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልቤ አምርሬ አለቀስኩ።በቃ በሕይወት ለመጨረሻ ጊዜ ተስፋ የቆረጥኩ መሰለኝ። ማንም ሆነ ምንም ነገር እንደዚ አስከፍቶኝ አያውቅም ግን ይሄ ከመከፋትም ያልፋል።ጩኸቴም ለቅሶዬም ወደ ውስጥ እንጂ ወደ ውጭ አልሰማልሽ አለኝ።ሰሚ የሌለው ዋይታ ሆነ ባነባው እማያልቅ እማይወጣ ህመም።

ከእንቅልፌ ስነቃ በእንባ ርሼ ነበር።ብድግ ብዬ ተነሳው ገና ሌሊት ነው በተለመደው ሰዓት ነበር የነቃሁት።አልጋዬ ላይ ቁጭ አንዳልኩ እጅና እግሬን አጣምሬ አንገቴን ቀብሬ ማልቀስ ጀመርኩ።ምክንያቱም ዛሬም እዛው ስሜት ውስጥ ነኝ።እስኪ ወጣልኝ አነባው ተነሰቀሰኩ።አሁንም እንደታመምኩ ነኝ ሊያውም ሰው የማያወቀውንና ፍፁም ሊረዳው እማይችለውን ህመም።
ለደቂቃዎች ካነባው ቡሗላ ተነስቼ ደብተርና ወረቀቴን እንደለመድኩት ይዤ ቁጭ አልኩ።

"የነፃነትን ዋጋ የምንረዳው ባጣናት ቅስፈት ብቻ ነው ማንም ሰው ግን ያቺን ቅስበት እስካላየ ድረስ የነፃነት ሙሉ ዋጋ ና የነፃነት ጥጉን መቼም ሊረዳው ሆነ ሊያጣጥመው አይችልም ግን ያቺን ቅስበት ያየ የነፃነት ዋጋዋ እና ውድነቷን ከማንም በላይ ይረዳዋል እና ለመጀመሪያ ጊዜ ይናፍቃታል ሊያገኛትም ሩቅ እኝደሆነ ይሰማዋል ነብሱም ድምጿን ከፍ አድርጋ ነፃነትን ትጣራለች ግን ሰሚ አታገኝም እናም ይህ ሰው እድለኛ ከሆነ ዳግም ነፃነትን አግኝቶ ዋጋዋን ተረድቶ ያጣጥማታል።ያንን ያላየው ግን እንዲያው ትርጉሟ ሳይገባው ይመላለስባታል።ይሔ ሰው ታድያ ነፃነትን ስላጡ ሰዎች ምንም ላይመስለው ይችላል ይሆናል ግን ያቺን ቅስፈትና የነፃነት ዋጋን የተረዳው ግን ግድ ይለዋል ልክ እንደኔ! ለዛም ነው ዝም የማልልው "
ለመጀመሪያ ጊዜ መፃፍ የቻልኩት ይሄንን ብቻ ነው።


💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየታችሁ እንዲሁም ማስተካከል ያሐባት ነገር በ @yemirtwutet ላኩላት።

ፈጣሪ ሁሉንም በያሉበት ይጠብቅልን እናም በሰላም ያገናኘን ።

"ሕመማቹ ህመማችን ነው!!!!"
👍1
#አድዋ

አድዋ ነጭ ነዉ አድዋ ጥቁር
አድዋ ነፍስ ነዉ አድዋ ፍጡር
በአጥንት ተዋጅቶ በደም የሚኖር
ህሊና ማይሽረው የተኖረ ተዓምር
ማን አለ እንደኛ ጥቁር የጥቁር ዘር
አድዋ ስሜ ነው ለእኔነቴ ክብር
የአለም ጥቁር ዋጋ የህልውናው ሚስጢር
ትላንት ነኝ ዛሬ በሞቱት የምኖር፡፡

እንኳን ለ 124 ተኛው #የአድዋ ድል አደረሳችሁ።

💚 💛 ❤️
#አድዋ

የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፤
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣
እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ…
የድል ታሪክሽን አውሪ።

#እጅጋየሁ_ሽባባው

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#ሙግት_ወይስ_እውነት?


በፍላጎት መንገድ...
በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ
ገንዘብ እየፈለግሁ...
"ፍቅር ይበልጣል" የሚል ፣ ከንቱ ሙግት ይዤ
እኔም ልክ እንዳንቺ...
ከገንዘብ ወዳጅ ጋር ፣ ተከራክሪያለሁ
ገንዘብ የማይገዛው...
ብዙ ደስታ አለ ፣ ስል አስረድቻለሁ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ግን ደሞ ግን ደሞ...
በማስረዳቴ ውስጥ ፣ አለ የሚያስረዳኝ
ከፍቅር ከገንዘብ...
ከምንም የሚበልጥ ፣ "እውነት " ይሉት አዳኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እናም እውነት ማለት...
በጭራሽ አይደለም!
አንድድ እውነት ለማቆም ፣ አንዱን እውነት መጣል
አትጠራጠሪ!!!
አንዱ ገንዘብ ሲመርጥ ፣ አንዱ ፍቅር ይመርጣልተ
ሒጅ ወደ ፈለግሽው!!!
ከፍቅር ከገንዘብ ፣ ፍላጎት ይበልጣል፡፡

⚫️በላይ በቀለ ወያ⚫️
#ፍቅርና_በቀል የተሰኘውን የዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ግሩም ድርሰት ይለቀቅልን የምትሉ እስቲ አብሮነታችሁን አሳዩን ከ 100 👍 በኋላ እንጀምረዋለን።
👍1