አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
574 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ



#ፍሰሀ
===
ልዩ የሆነ ቆይታ ነበር፡፡ሶስቱንም ፈታኞቼን እንዳስደመምኮቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡መድረኩን በስነስርዓት፤ ባጠናውት እና በተዘጋጀውት መጠን ነበር የተወጣሁት፡፡በመጨረሻ ሁሉም ወ/ሮ ክብረወርቅም ጭምር ቆመው ነበር ያጨበጨብልኝ፡፡እኔም በደስታ ሰክሬ ከወገቤ ሽብርክ ብዬ አመሰገንኳቸው፡፡
ለመውጣት ቸኩያለው ቀልቤ ያለው ፌናን ጋር ነው፡፡እስከአሁን ከቤቷ መጥታ ውጭ በረንዳ ላይ ወይም ቢሮዬ ቁጭ ብላ እደምትጠብቀኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡አዎ አይኖቼ መላ እሷነቷን ተርበዋል፡፡ከራሴ በላይ እወደዋለው፡፡ ብዬ የማስበው አባቴ እንኳን ከስድስት ወር ባላይ ተለይቶኝ ሲኖር በዚህ መጠን ናፍቆኝና ተርቤው አላውቅም…
ናፍቆቴ የቱንም ያህል ቢሆን ግን እነሱን ቀድሜ መውጣት በአይን አውጣነት የሚያስፈርጀኝ መስሎ ስለተሰማኝ እንደምንም ስሜቴን ተቆጣጥሬ እየታገስኩ ነው፡፡እነሱ በእርጋታ የሚንቀሳቀሱትን ሽማጊሌውን አስቀድመው እየተጎተቱ ክፍሉን እስኪለቁልኝ መጠበቅ ግድ ሆነብኝ፡፡ይባስ ብሎ አባቴ ወደእኔ መጣ፡፡ተጠመጠመብኝ ፡፡ምን ላድርግ …?መልሼ በተመሳሳይ አቀፍኩት፡፡ለዚህች ቀን አይደል ስንት ወር ሙሉ ሲወተውተኝ የነበረው?እሱ ያልተደሰተ ማን ይደሰታል……?ግን እሱ ያላወቀው እንዲህ መታቀፍ ያለብኝ እኔ ሳልሆን ፌናን መሆኗን ነው፡፡ግድ የለም ..እሱ እኔን ባቀፈኝ መጠን እኔ ደግሞ ከደቂቃ ቡኃላ እሷን አቅፋታለው፡፡.ጭምቅ አድርጌ አቅፋትና ምስጋናዬን አቀርብላታለው፡፡ምስጋናዬን ብቻ ሳይሆን ዛሬ ማታ አፕል አበረክትላታለው፡፡አዎ ጥንት ግሪካዊያን ለሚያፈቅሩት ሰው አፕል ነበር የሚልኩት አንተም የምታፈቅረኝ ከሆነ ከዝግጅቱ ቡኃላ አፕል ላክልኝ የዛን ጊዜ መልሱን ነግርሀለው አይደለ ያለቺኝ?ዋው..ማታ እራት ጋብዛታለው::ከዛ አፕል እሰጣታለው::አፕሉ ውስጥ ደግሞ ቀለበት ይኖርታል::አብረቅራቂ የአልማዝ ቀለበት::ይህንን በማሰቤ ውስጤ ዘላለማዊ በሚመስል ደስታ ተጥለቀለቀ
‹‹በጣም ነው ያኳራኸኝ…እጅግ በጣም ከጠበቅኩት በላይ ጀግና ሆነህልኛል ለካ?አሁን እርግጠኛ ሆነህ ካማፓኒውን በቋሚነት ለመረከብ ተዘጋጅ..››አለኝ አባቴ ሌሎቹ ሊሰሙት በማይችሉት ዝቅተኛ ድምጽ
‹‹እሺ አባዬ አመሰግናለው፡፡››
‹‹ና እንውጣ›› አለኝና ትከሻዬን በኩራት አቅፎ ወደውጭ ይዞኝ ወጣ::በራፍ ላይ እንደደረስን በሃያ ሜትር ርቀት ፌናን ቀድመውን ከወጡት ጋሽ ከበደ እና ከወ/ሮ ክብረወርቅ ጋር ሲያወሩ ለዛውም እየተሳሳቁ ተመለከትኩ
እኔም አባቴም ሳንነጋገር እርምጃችንን እዛው በራፍ ላይ ገታነው::እንዴት አምሮባታል ?ይህ ሁሉ ውበት እንዲህ ጎልቶ እና ፈክቶ የወጣው ከእራሷ ከአፈጣጠር ነው ወይስ ከአለባበሷ…?ልቤ እንደለመደችው ቅልጥልጥ አለች…ግን ከሰዎቹ ጋር የት ተዋውቃ ነው እንዲህ በመፈንጠዝያና በፈገግታ የምታወራቸው……?
‹‹አንተ ተፋላሚህ መታልሀለች::ደግሞ እንዴት ታምራለች……?ልክ እንደእናቷ ››አባቴ ነው በአድናቆትና በስጋት መሀከል በሚዋልል ስሜት የተናገረው…
‹‹አባ እሷ አይደለችም::ይህቺ እኮ የእኔ ረዳት ነች››አረምኩት
‹‹እርግጠኛ ነህ…?ፎቶዋና እኮ እናትዬው ያሳየቺኝ መሰለኝ..ለማንኛውም ና ወደ እነሱ እንሂድ..››አለኝና ተያዘን ስራቸው ደረስን …ፌናን ዞር ብላ እንዳየችኝ ተሸከርክራ ተጠመጠመችብኝ….በጣም እንደናፈቀቺኝ ያወቅኩት ሁሉም እያዩኝ ያለይሉኝታ ልክ እንደ ህጋዊ እጮኛዬ አቅፌ በአየር ላይ ሳንጠለጥላት ነው….
አባቴ ‹‹ክብረወርቅ ልጅሽ ነች እንዴ…?››ብሎ ሲጠይቅ በጆሮዬ ገባ..
‹‹አዎ ልጄ ነች::ፌናን ሰላም በይው…››የሰማውትን መልስ ማመን አቃተኝ….. ምንድነው እየተካሄደ ያለው..?.ከእሷ ሸሸት እልኩና እናትዬው ላይ አፈጠጠኩባት
<<…ምን ተፈጠረ …?በሚል ግራ በተጋባ አሰተያየት ንግግሯን ቀጠለች‹‹እንዲህ ምትግባቡ አይመስለኝም ነበር››ለእኔ ነው የምትለኝ ፡፡
‹‹ፌናን ያንቺ ልጅ ነች…?››አንቱነታውንን እረስቼ የአባቴን ጥያቄ መልሼ ደገምኩ
‹‹አዎ ..ፌናን ልጄ ነች..ምነው …?አልነገረችህም እንዴ……?››
ወደ እሷ ተንደረደርኩና ሁለት ትከሻዋን ጨምድጄ ያዝኳት …ሶስትም ደነገጡ‹‹በጣም ባለጌ ነሽ..በጣም አታለሺኛል..መቼም ይቅር አልልሽም….››
ይሄን ሁሉ ስላት እሷ ምንም እንዳልተፈጠረ በግማሽ ፈገግታ እያደማጠቺኝ ነው…ገፍትሬ አባቴ ትከሻ ላይ ወረወርኳትና ወደቢሮዬ ተንደረደርኩ…
‹‹ምንድነው ነገሩ?ልጄን ምን አደረጋችሁት…?››የአባቴ ድምጽ እየተሰማኝ ነው…ቤሮዬን ገባውና ከውስጥ ቀረቀርኩ.. ቢያንኳኩም ልከፍትላቸው አልፈለኩም..ትንሽ ይብረድለት ብለው መሰለኝ ትተውኝ ዞር አሉ….እኔም ምፈልገው ያንን ነበር፡፡
…….ታንቄበት የዋልኩትን ከረባት ከአንገቴ ፈትቼ ጥዬ ኮቴን አውልቄ በመወርወር ወንበሬ ላይ ቁጭ ብዬ አንገቴን ጠረጳዛ ላይ ደፍቼ አነባው ጀመር::እንዲህ አይነት ለቅሶ ካለቀስኩ ስንት ዓመት እንዳለፈኝ ትዝ አይለኝም::ንፍጤ እስኪዝረከረክ ድረስ ነው ያለቀስኩት፡፡በህይወቴ አንድ ሰው በዚህ መጠን ተጫውቶብኝና አታሎኝ አያውቅም::እንዴ አምኜያት ነበርኮ..?በአድናቆት ፈዝዤያለት አፍቅሬያትና ብዙ ብዙ ህልም አልሜላት ነበር…?እንዴት አንዲህ ትሰብረኛለች?ይህችን ካምፓኒ ለማስተዳደር ብላ……?እኔ እኮ ከካምፓኒው ስራ በላይ ነበር ያፈቀርኳት…
…እያንዳንዷን የሰራዋትን ጥናት ቃል በቃል ታውቀዋለች፤ ምክንያቱም አብረን ነው የሰራነው.፡፡ስለዚህ የእሷ ዝግጅት የእኔን ጥናት አይታና ከእዛ በበለጠና ያንን በሚያጠቃ መልኩ ለማዘጋጀት እድሉን አግኝታለች… .በዛ ላይ ችሎታዋን አውቃዋለው..እና እንዴት ነው ከእሷ በልጬ ይሄን ቦታ የማገኘው…?ተዋረድኩ….፡፡በቃ ሁሉ ነገር አስጠላኝ ::ስራው አስጠላኝ ..ካምፓኒውም አስጠላኝ ..ያፈቀርኮት ልጅ አስጠላቺኝ…ሀገሬም አስጠላቺኝ …፡፡መመለስ አለብኝ…አዎ ወደመጣውበት ሀገር እመለሰላው..ስደት ይሻለኛል..ስራዬን እየሰራው ሶስትኛ ዲግሪዬን ብማር ይሻለኛል..::እንደውም በተጨማለቀ ሀገር የተጨማለቀ ኑሮ ለመኖር ምንድነው እንደዚህ አፈር የሚያስግጠኝ..…?ወሰንኩ…እንባዬን ከጉንጬ ላይ ጠራረግኩ…ኮምፒተሬን ከፈትኩና መጻፍ ጀመርኩ…ለቦርድ አባላቱ ነው::የካምፓኒውን ስራ ስለማልፈልገው ውድድሩ እንዲቀርና ስራውንም በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን የሚገልጽ ደብዳቤ …ፕሪንት አድርጌ ፈረምኩበትና ኮቴን መልሼ በመልበስ ወጣው…ሰራተኞቹ ሁሉ ለምሳ የወጡ ቢሆንም ጸሀፊዬ ግን ስጠብቀኝ ነበር….
‹‹አሁን የቦርድ አባሎቹ ሲመጡ ይሄንን ማመልከቻ አስገቢልኝ›› አልኩና በካኪ ፓስታ የታሸገውን ማመልከቻ ሰጠዋት
‹‹አባትህ ደጋግመው ሲደውሉ ነበር…ምሳ እየጠበቅንህ ነው ፤ደውልኝ ብለውሀል…››
‹‹ዝም በይው::ስልኬን ዘግቼዋለው …ከደወለ ወጥቼ እንደሄድኩና እንደማልመለሰም ንገሪው……››
‹‹አንተ ግን ሰላም ነህ…?›ሁኔታዬ ስላላማራት መሰለኝ የጠየቀቺኝ
‹‹ሰላም ነኝ ….አመሰግናለው…››ጥያት ወጣው…..

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ #ፍሰሀ === ልዩ የሆነ ቆይታ ነበር፡፡ሶስቱንም ፈታኞቼን እንዳስደመምኮቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡መድረኩን በስነስርዓት፤ ባጠናውት እና በተዘጋጀውት መጠን ነበር የተወጣሁት፡፡በመጨረሻ ሁሉም ወ/ሮ ክብረወርቅም ጭምር ቆመው ነበር ያጨበጨብልኝ፡፡እኔም በደስታ ሰክሬ ከወገቤ ሽብርክ ብዬ አመሰገንኳቸው፡፡ ለመውጣት ቸኩያለው ቀልቤ…»
.:
#ፍቅር_ከፈላስፋ





ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ (የመጨረሻ ክፍል)


❤️ፌናን
===
ይሄ እንደሚፈጠር ቀድሞውኑም ጠብቄያለው::ቀድሜ መናገር
ነበረብኝ …ግን ልረብሸው ስላልፈለኩ ነበር እንደዚህ ያደረኩት
::.ሁኔታውን እንዳወቀ አባቱ ትከሻ ላይ ገፍትሮኝ እየተመናጨቀ
ቢሮው ገብቶ ከዘጋ ቡኃላ ሶስቱም ነበር ያፈጠጡብኝ….
‹‹ምንድነው ልጄን ያደረጋችሁት…? ››አሉ አባቱ…..ያው
ያደረግሽው ለማለት ፈልጎ ነው፡፡
‹‹ምንም ያደረኩት ነገር የለም::ግን ተወዳዳሪው እኔ ትሆናለች
ብሎ ስላልጠበቀ ነው የተበሳጨው››መለስኩ
‹‹በዛማ አይበሳጭም::ጥናቱን ሲሰራ ምትረጂው አንቺ ነበርሽ
አይደል…?››
‹‹አዎ …በሙያዬ ፕሮፌሽናል በሆነ ደረጃ
ረድቼዋለው::የማውቀውን ምንም ወደኃላ አላልኩም::ምነው
ጥናቱ አሪፍ አልነበረም እንዴ…?››
‹‹ጥናቱማ ሁላችንንም ያስደመመ እንከን አልባ ነበር…››መለሱ
አባቱ ግራ በተጋባ ስሜት
‹‹ስለዚህ ምንም ያጠፋውት ነገር የለም ማለት ነው››መለስኩ
‹‹ልጄን አባሳጭተሸዋል…የክብረወርቅ ልጅ መሆንሽን አለመናገርሽ
አግባብ ስራ አልነበረም..››በጋለና በሞቀ የንዴት ስሜት
‹‹በቃ ልጄ ላይ አትጩሁባት ..ካልፈለገች አለመናገር መብቷ
ነው::የበደለችው ነገር ከለ ወይም ጥናቱ ላይ ያሳሳተችው ነገር
ካለ ለቦርዱ አቤቱታውን ማቅረብ ይችላል…››እናቴ ተንዘረዘረች
‹‹በቃ አቀዝቅዙት..አሁን እሱ ትንሽ ይረጋጋ እኛ ወደ ምሳው
እንሂድ››አቶ ከበደ ናቸው የተናገሩት
‹‹ሂዱ እኔ ከልጄ ጋር ነው የምበላው ..ጠብቀዋለው››
‹‹ተው አንተ ደግሞ ሰው ሚልህን ስማ ..ትደውልላታለህ ፡፡ቀለል
ብሎት በወጣ ሰዓት ይቀላቀለናል..››ብለው አሳመኑትና የቢሮውን
ህንፃ ለቀን ወጣን..እኔ ግን አብሬያቸው ወደ ሆቴል አልሄድም
አልኩ::ቢቆጡኝም አለሰማዋቸውም::ብቻዬን መሆን ነው
የፈለኩት::የሰራውትን ነገረ ሁሉ አምኜበትና አስቤበት ቢሆንም
ፍሰሀን የመከፋት መጠን ባየው ጊዜ ከፋኝ::ይሄን የመከፋት
ስሜት ደግሞ ብቻዬን ነው ማጣጣም የምፈልገው….
እንግዲህ ለአምስት ሆነን ልንቋደስ የነበረው የምሳ ፕሮግራም
ወደ ሶስት ሰው ዝቅ አለ ማለት ነው፡፡
ሰዓቱ ከቀኑ 8፡10 ሆኖል ፡፡አሁን እራሴን አረጋግቼ ቅድመ
ዝግጅቴን ጨርሼ ሶስቱ የቦርድ አባላት ፊት ለፊት
ቆሜያለው::የጥናት ወረቀቴን ከቦርሳዬ አወጣውና ለሶስቱም
አደልኩ::ሶስቱም ላይ ግራ መጋባት አየው::ሽማግሌው አቶ ከበደ
ግራ ገብቷቸዋል::የፍሰሀ አባት ፈገግ አሉ ::እናቴ ፊቷን
ጨመደደች እና እንደውም ይባስ ብላ በንቀት መልክ ከ10 ገጽ
የማይበልጠውን የጥናት ወረቀቴን በሁለት ጣቷ አንጠልጥላ
እያወዛወዘች‹‹በቃ››አለቺኝ
‹‹ምኑ…?››
‹‹ለወራት ውስጥ ያዘጋጀሽው የመወዳደሪያ የጥናት ወረቀትሽ
ይሄው ብቻ ነው…?››ምን ታርግ መቶ ገፅ ሊሞላ ትንሽ ገጽች
ከሚጎድሉት የፍሰሀ የጥናት ወረቀት ጋር ስታነፃፅረው ከወዲሁ
ሀሞቷ ፈሶ ነው፡፡
‹‹አንዴ የቀረበው ቀርቦል…. እንስማው››አለ የፍሰሀ አባት
ጨፍግጎት የነበረው ስሜት ለቆትና ኩርፊያውንም ረስቶት..
‹‹እሺ ቀጥለላው.. ››ስል..በራፉ ተንኳኳ::ፍሰሀ ሊበጠብጥን
መጣ ይሆን እንዴ……?ወዲያው በሀሳቤ የተሰነቀረ ክፉ ሀሳብ
ነበር
‹‹ይቅርታ… ››አልኩን ሄጄ ስከፍት የፍሰሀ ፀሀፊ ነች
‹‹ይቅርታ ይሄን ለእነሱ ልሰጥ ነበር››አለቺኝ የሆነ ካኪ ፖስታ
አንከርፍፋ
‹‹አንጪ እኔ ልስጥልሽ››
እንደማቅማማት እያለች ሰጠቺኝ..በራፉን ዘጋውና ሂጄ ለጋሽ ከበደ
ሰጠዋቸው..
‹‹ምንድነው…?››
‹‹እኔ እንጃ የፍሰሀ ፀሀፊ ነች ያመጣችው››
<<.አባትዬው ከጋሽ ከበደ እጅ ፓስታውን መንጭቀው ተቀበሉትና
ሸረከቱት …ከዛ ለብቻቸው ያነቡት ጀመር…ምን ይፈጠር ይሆን…?
ብለን ሌሎቻችን በንቃት እየጠበቅን ነው ‹‹ያው ደስ ይበልሽ
ያለውድድር አሸንፈሻል››አሉኝ አንብበው እንደጨረሱ እኔ ላይ
አፍጥጠው
‹‹ምንድነው እሱ…?›› ጋሽ ከበደ ናቸው ጠያቂው
‹‹ያው ስራውን አልፈልግም የሚል ማመልከቻ ነው ያስገባው…
መቼስ ይሄንን አይነት ስውር ብልሀት ከእናትሽ ነው
የወረሺው::ሳትፋለሚ በብልጠት ማሸነፍን ››
‹‹ሰውዬ ምን እያወራህ ነው…?››እናቴ ነች በእሱ ልክ ግላና
እየተንዘረዘረች ዘራፍ ተደፈርኩ በሚል ሰሜት የተናገራቸው
‹‹በቃችሁ…››እኔ ነኝ መሀከል የገባውት..‹‹ይሄ የልጆች ጫወታ
አይደለም::እናንተ በመሀከላችሁ ያለውን የግል ንትርክ በአኔ
አሳባችሁ ማወራረድ አትችሉም::እኔ የተዘጋጀውበትን ሳለቀርብ
ከዚህ አልወጣም::ሳልወዳደርም ማሸነፍ የምፈልግ ሰው
አይደለውም::ምክንያቱም የፍሰሀ አባት አንድ የማያውቁት ነገር
ያለ ይመስለኛል… እኔ የእናቴ ልጅ ብቻ ሳልሆን የአባቴም ልጅ
ነኝ::አባቴ ደግሞ ገነትም ቢሆን በአቋራጭ እንድገባ አድርጎ
አላሳደገኝም…. ››
ጋሽ ከበደ በዛ እርገታቸው መሀከል ገቡ‹‹እወነቷን ነው…የፍሰሀን
ጉዳይ ቡኃላ እንዴት ማድረግ እንዳለብን እንመክራለን::ፕሮግራሙ
ግን በዕቅዱ መሰረት መቀጠል አለብን::ትልልቅ ሰዎች አይደለን
እንዴ…? ስሜታዊ መሆን አሁን ምን ይረባል……?››
‹‹መልስ እንዲመልሱ እድል ሳልሰጣቸው ቀጠልኩ
‹‹አመሰግናለው::ምን አልባት ያቀረብኩት የጥናት ወረቀት መጠን
አነስ ያለች በመሆኗ ከተመደበልኝ ጊዜ ውስጥም ስልሳ ፐርሰንቱን
ብቻ ተጠቅሜ ሙሉውን ዝግጅት ለማጠናቀቅ
እሞክራለው::ስለዚህ ሁላችሁም ምናባችውን ሰብሰብ አድርጋችሁ
በትኩረት እንድትከታተሉኝ እየጠየቅኩ ቀጥታ ወደ ገለፃዬ
እገባለው፡፡››
ካምፓኒው የተቋቋመበት ዓላማ ምንድነው…?ለካምፓኒው
ባለቤቶች ደለብ ያለ ትርፍ በየዓመቱ ማስገኘት?መቶና ሁለት መቶ
ለሆኑ ዜጎች ቋሚ ስራ መፍጠር .. …?ከ5መቶ እስከ 1 ሺ
ለሚሆን ጊዜያዊ ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠር..…?ለመንግስት
ግብር በማስጋባት የዜግነት ግዴታን መወጣት…? በቃ ይሄ ነው
…..…?
እርግጥ ሶስት ሰዎች ያቋቋሙት ካምፓኒ እንዲህ ውጤታማ ሆኖ
በዚህ መጠን ለሌሎችም ሆነ ለሀገር ጥቅም ከሰጠ አስደሳች
ነው…ስኬታማ የሚያሰኝ ነው…ግን በእኔ አስተያየት ተራ ስኬትና
ተራ አላማ ነው፡፡….እኔ ይሄ ካምፓኒ ልዩ እና የማይቻለውን ነገር
አስችሎ ለመላ ሀገሪቱ እንዲያሳይ ነው የምፈልገው…
ኢትዬጵያ 20 ሚሊዬን ዜጎቾ ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩባት
ሀገር መሆን ነበረባት…?ዘወትር በስደት በየባህሩ የምናልቅ
ህዝቦች መሆን አለብን…? ፡፡ይሄ ቁጭት በውስጤ አለ ፡፡ከዚህም
ቁጭት የተመዘዙ የራሴ የሆኑ ሁለት እቅዶች አሉኝ፡፡አንደኛ
በሚቀጥሉት አስር አመት ውስጥ ውጤታማ የቢዝነስ ሰው
በመሆን ሀገሬንና ህዝቤን መርዳት …ሁለተኛ ከአስርአመት ቡኃላ
በቢዝነስ ያገኘውትን እውቅና እና ጥበብ ይዤ ወደፓለቲካ
መግባት እና የዛሬ ሀያ አመት ከተራዘመም ሀያ አምስት አመት
ድረስ ይህቺን ሀገር መምራት …
‹‹ማለት…?››አለች እናቴ በአግራሞት..
‹‹ጠቅላይ ሚኒስቴር መሆን…እና ይህን የሀብት ምንጫችሁ ብቻ
ሳይሆን የስማችሁ መጠሪያ የሆነውን ካማፓኒያችሁን የምፈልገው
መጀመሪያ ለራሴ አላማ ነው…፡፡ካፓኒውን በተለየ መልኩ
ውጤታማ አድርጌ ለዚህች ሀገር የቢዝነስ ሞዴል እንዲሆን
በማድረግ የራሴን ስም መገንባት::ያንን ማድረግ ከቻልኩ
የእናንተን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የራሴንም ህልም ነው
የማጨልመው…
እና እንዴት አድርገሽ ነው የተለየ ካምፓኒ የምታደርጊው……?.በእኔ
እምነት በአሁኑ የካማፓኒ አካሄድ ለሀገሪቱ እድገት እየተጋለ እና
የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው? አዎ ትክክል ነው…
በተቃራኒውን ለሀገሪቱ ውድቀትም በተመሳሳይ አስተዋጽኦ ቀላል
አይደለም…
ንግግሬን ገታ አድርጌ የሶስቱንም ፊት ሳይ ልጅቷ አብዳለች እንዴ
👍8
እያሉ ይመስላል…

በ19 17 ዓ.ም ሀገሪቱ 3.13 ቢ . ዶላር ምርት ለውጭ ገበያ
ስታቀርብ ወደ ውስጥ ያስገባችው ምርት ደግሞ 16.29 ቢሊዬን
ዶላር ነው፡፡ ምን አይነት ኪሳራ ውስጥ ያለች ሀገር መሆኗን እዩልኝ
..ሀገሪቷ ሰርታ ብቻ ሳይሆን ተበድራም ፤ለምናም የሰበሰበችውን
ዶላር ነው እኛ እያወጣን የሚያሰሰፈልገውንም የማያስፈልገውንም
ኮተት ከቻይና እና ከህንድ እየሰባሰብን አምጥተን ለህዝቡ
የምናድለው፡፡እስቲ ገጽ አራት ላይ ክፈቱና የምናስመጣቸውን የዕቃ
ዝርዝሮች ተመልከቷቸው፡፡ከውስጣቸው ምን ያህሉ ነው የግድ
አስፈላጊ የሆኑት ዕቃዎች …?አንዳንዶቹ የሚያሳፍሩ ናቸው….
..…የማንጎ ጁስ ፤የብርቱካን ጁስ ፤ የመንደሪን ጁስ ዶላር
ከፍለን ከሰውዲ እናስመጣለን፡፡ኑግ፤ተልባና ሰሊጥ
እያመረትን..በተጨማሪም የትየለሌ የምናመርትበት መሬት እያለን
ዘይት ዶላር ከፍለን እናስመጣለን……የህፃናትም ሆነ የአዋቂዎች
ልብስና ጫማ ዶላር እየከፈልን እናስመጣለን፡፡ ቆዳውም ጥጡም
በሀገራችን መመረት እየተቻለ….ሌላ የሴቶች መዋቢያዎች
፤አርቴፊሻል ፀጉር፤ አርቴፊሻል ጡት፤ አርቴፊሻል
መቀመጫ፤ሊፒስቲክ ፤ቻፒስቲክ ፤ቅባቶች ፤ዶላር ከፍለን
እናስመጣለን፡፡
ሚሊዬኖች ከድህነት ወለል በታች በሚኖሩባት ሀገር በመከራ
የሚገኘውን ዶላር የምንጠቀምበት አግባብ አይታችሁታል …?ለዚህ
ደግሞ ተጠያቂ ከሆኑት የመንግስት ፓሊስ ቀጥሎ ካምፓኒያችን
ከተጠያቂዎቹ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ቢያንስ የሚያስገባቸውን ዕቃዎች
እንኳን ምን ያህል ትርፍ ያስገኚልኛል ብቻ በሚለው መስፈርት
ሳይሆን መሰረታዊ ነገር ሆኖ በሀገሪቱ መመረት ያልቻለው የትኛው
ነው ብሎ በመምረጥ ዶላሩን እንዴት ነው ለሀገሪቱና ለህዝቡ
ወሳኝ ለሆነ ነገር መጠቀም የምችለው…? የሚለውን ማሰብ
ነበረበት…ቢያንስ እንዲህ ማድረግ ይችል ነበር፡፡.
እና ካምፓኒው የውጭ ሸቀጦችን ከየሀገራቱ እያስመጣ በሀገሪቱ
ማሰራጨት ብቻ ሳይሆን ወሳኝ የሆኑትን ምርቶችንም በማምረት
ወደውጭ መላኩ ላይም እንዲሳተፍ እፈልጋለው…
ስለዚህም ካምፓኒው በሁለት ይከፈላል ወይም አሁን ባለው ላይ
ሌላ እህት ካምፓኒ ይመሰራታል… አሁን ያለውን ካምፓኒ
የምናስመጣቸውን ዕቃዎች ዓይነት ብቻ በማስተካከል ወይም
በመምረጥ በቀረበው ዓዲስ ዕቅድ መሰረት ፋሰሀ እንዲመራው
ሙሉ ድጋፌን እሰጠዋለው….
የሚቋቋመውን እህት ኩባኒያ ደግሞ እኔ መምራት ፈልጋለው…ይሄ
እህት ኩባኒያ ሁለት ስራ ነው የሚሰራው..አንድም በየአመቱ አንድ
ወይም ሁለት ምርቶችን ሀገር ውስጥ ከተቻለ የሀገሪቱን ፍጆታ
በሚሸፍን መጠን ካለሆነም በሚያስመጣው መጠን ፍብሪካ
በማቋቋም እንዲያመርት ማድረግ……ለዚህም እንዲረዳ
ካምፓኒው ከሚያገኘው አመታዊ ትርፍ ቢያንስ 75 ፐርሰንቱ
ወደአዲሱ ክማፓኒ ፈሰስ ማድረግ ይጠበቅበታል…፡፡ከውጭ
ኩባንያዎች ጋር ያለውን ግንኙነት በመጠቀም እና እነሱን
በማነጋገር እና በማሳመንም ያንን እንገዛቸው የነበረውን ዕቃ አገር
ውስጥ ከተቻለ አብረውን በጥምረት እንዲያመርቱ ካልሆነም
በራሳቸውም ሙሉውን ኢንቨስት አድርገው በእኛ ካምፓኒ
እንድናከፋፍልላቸው መስራት አለብን.(.ምክንያቱም በዶላር ገዝተን
በባህር አጓጉዘን በማምጣት ከምናከፋፍል እዚሁ እንዲያመርቱ
አሳምነናቸው በብር እየገዛናቸው በብር ብናከፋፍል ይህቺን ሀገር
በቀጣይነት ከቀውስ ለመታደግ የራሳችንን ሚና መጫወት
እንችላለን…..)
ሌላው እርግጠኛ ነኝ ሶስታችሁም በቂ ብር ለዛውም በዶላር
ዱባይ ወይም ሌላ ውጭ ሀገር አላችሁ ብዬ አስባለው…ያንን ብር
በንጽህ ንግድ ብቻ ያገኛችሁት ነው ብዬ አላስብም ፡፡ከሆነም ጥሩ
ነው..ግን በምንም ተገኘ በምን ውጭ ማስቀመጡ ፌር
አይደለም..
… ለምሳሌ እማዬ .. ያለውሽ ልጅ እኔ ብቻ ነኝ፡፡እኔ ደግሞ እድሜ
ዘመኔን እዚህችው ሀገር ኖሬ መሞት ነው የምፈልገው፡፡ስለዚህ
ለማን ብለሽ ነው ሰው ሀገር ያን ሁሉ ብር ያሰቀመጥሺው..?ነገ
እኔ ልጅሽ ልመራት እቅድ ያለኝ ሀገር ነች…ግን እናንተ እና
የእናንተ ትውልድ በፓለቲካም ሆነ በኢኮኖሚ አሻጥር
ጭምልቅልቋን ያወጧችሆትን ሀገር እኔ ልጅሽ እመራለው ብዬ
ተረክቤ ምን ያህል እንደምሰቃይ ታውቂያለሽ……?ያ ገንዘብ ደግሞ
እውነቴን ነው የእናንተ ብቻ ይመስላችሆል እንጂ የእናንተ ብቻ
አይደለም ፡፡የሀገርም ንብረት ነው…ሀገር አደገች የሚባለው
የእያንዳንዱ ሰው እድገት ተደምሮ ነው..ስለዚህ ሶስታችሁም
ቢያንስ በተለያየ ስጋት ወደውጭ ያሸሻችሁትን ወይም በየቤታችሁ
የቀበራችሁትን ብር ታመጡና ለዚህ ሲስተር ካምፓኒ ማቋቋሚያ
ትሰጡኛላችሁ ማለት ነው፡፡ከዚህ በላይ ገናዘብ ካስፈለገንም
ከመንግስት በአግባቡ እንበደራለን…፡፡
ሶስቱም እርስ በርስ ተያዩ….
እኔ ቀጠልኩ‹‹ ….እና ቀስ በቀስ የምናስመጣቸውን ዕቃዎችን
በተለይ የምግብ ዘይት፤ ሳሙና ፤ወረቀት ፤ጅውሶችን .፤
፤እስኪሪብቶ፤መድሀኒቶች፤ወዘተ ወደ ማምረት እንሸጋገራለን
ሌላ ከዚህ ካምፓኒ ውስጥ አያይዘን የምንሰራው ስራ አለ፡፡
ከአመታዊ ትርፉ እስከ20 ፐርሰንት ተመድቦ በዜጎች ላይ
በተለይም በህፃናትና በታዳጊዎች ላይ የአመለካከት ስራ መስራት፡፡
ለዛም እንዲረዳን የቴሌቪዝን እና የሬዲዬ የአይር ሰዓት ተከራይተን
በመደበኛ ሁኔታ እንሰራለን፡፡በሌላ በኩልም በፊልሞች በስነጽሁፍ
፤በየትምህርት ቤቶችም ጭምር እንሰራለን ..ይሄ ጉዳይ ከሀገር
መውደድን ጋር ቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ሁሉምን ኢትዬጵያዊ ሲጠየቅ
‹‹ ሀገሬን ወዳለው›› ይላል፡፡እንዴት ነው የምትወደው …?መልስ
የለም…ሀገርን መውደድ እያንዳንዱን የሀገር ምርትን መውደድንም
ይጨምራል …አንድ ሙሽራ ቤት ጥሎሽ ሲመጣ እስኪ ታዘብ…
ጫማው ከኢንግላንድ ነው….ጭብጨባው ልዩ ነው….ቀሚሱ
ከእንግሊዝ …ሽቶው ከፈረንሳይ….ሲባል ሁሉ በኩራትና
በፈንጠዝያ ነው፡፡ ከውጭ ሊገኝ የማይችለውን ጥበብ ቀሚሱን
እንኳን ከኢትዬጵያ ነው ማለታቸው ቅር ሚላቸው ሰዎች አሉ ..ይሄ
ደግሞ ከጭብጨባው ማነስ ያስታውቃል፡፡እስከመቼ ነው
የኢትዬጵያ ነገር ሁሉ የማያምር እና የማያስከብር አድርገን
እንገልፀዋለን..…? እንደው ቅድሚያውን ወስደን መስዋዕትነትም
ቢሆን ከፍለን ካላከበርነው ሌላው ሀገር እንዴት እንዲያከብርልን
እንጠብቃለን…?
የውጭ ዕቃ መጠቀም፤ የውጭ ልብስ መልበስ የተሻለ ሰው
ክራይቴሪያ እንደሆነ በማህበረሰባችን በከፍተኛ ሁኔታ ይታመናል፡፡
ይሄንን ስነልቦና ይዘን ደግሞ አስፈላጊ ምርቶችን ሁሉ በሀገር
ውስጥ ማምረት ብንችል እንኳን ምን አልባት ጎረቤት ሀገሮች
ወስደን ካልሸጥን በስተቀር የሀገር ውስጥ ገበያ ማግኘታችን
ያጠራጥረኛል..እና እኛ የምናመርታቸው ማንኛውን ዕቃዎች
ከውጭ እናመጣቸው ከነበሩት ጋር ሲሆን በተሸለ ጥራት ያላቸው
ከላሆነም ግን ተፈካካሪ በሆነ መልኩ አምርተን በተሸለ ዋጋ
ማቅረብ..ህብረተሰቡም ይሄን በሀገር የተመረተ ምርት መግዛቱ
የፈለጉትን ዕቃ ከመግዛት በላይ ትርጉም እንዳለው በማወቅ ፤
ተጨማሪ ጋቢ ለሀገሩ እያስገኘ መሆኑን በማሰብ እንዲገዙ
ማድረግ…ሁለቱንም በጥምረት መስራት አለባት
እስኪ. በሀገራችን ያሉትን ህንዶችንም ሆነ ቻይኖችን
የሚለብሱትን ልብስ እና ሚጠቀሙትን እቃዎች ተካታትላችሁ
ተመልከቱ…አማራጭ ካላጡ በስተቀር ከሀገረቻው ምርት እኩል
የሚያወዳድሩት ምንም አይነት ምርት የለም የሁለት ብር ዕቃ
ብትሆን እንኳን የሀገራቸውን ዕቃ መግዛት የዜግነት ግዴታን
እንደመወጣት እንደሆነ በደንብ ግንዛቤው አላቸው
ሀገር መውደድ ምንድነው.…?እኛ ማንኛውንም ምርት በታማኝነት
ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ማምረት ከዛም ዋጋ ስንተምን
በተገቢውና ስነምግባር ባለው መልኩ መተመን ምን አልባት
ተመሳሳዩን ዕቃ ከውጭ እምጥተን ብናከፋፈል ልናገኘው
👍1
ከምንችለው ትርፍ በግማሽም ያነሰ ሊሆን ይቻላል የምናገኘው…
ግን ምንጎናፀፈው የመንፈስ ልህልና እና ለአገር የምንበረክተው
አስተዋጽኦ መተኪያ አይኖረውም፡፡ገዥውም ያንን በሀገር
የሚመረተውን ምርት ገበያ ላይ ሲያገኝ መቶ ፐርሰንት እንኳን
እርካታ ባይሰጠው ጉዳዩ የግለሰብ ምርትን የመግዛት ጉዳይ ብቻ
ሳይሆን የሀገርንም ምርት የመግዛት እና ያለመግዛት ጉዳይነው
ብሎ የእናት ሽሮ ዘይት ቢያንሰውም ያው ከእናት እጅ የሚፈሰው
ወዘና በራሱ እርካታ አለውና የእየገዛ ማበረታታት…
እና ይሄንን አዲስ ሲስተር ካምፓኒ…እንደእዚህኛው ትርፋማ ብቻ
እንዲሆን አትጠብቁ እንደአንዱ ሞዴል ኤን.ጂ.ኦ ቁጠሩት…ከዛ
ሚለየው የምንጠቀምበትን ብር በእርዳታ መልክ ሰብስበን ሳይሆን
ሰርተን ማግኘታችን ብቻ ነው፡፡ከዛ ውጭ ከውጭ የሚመጡትን
ምርቶች በተለይ ከግብርና ጋር ንክኪ ያለቸውን በእኛው በማምረት
ሆነ በሌሎች መሰል ድርጅቶች ሚመረቱትን ምርቶችን የመጠቀም
ባህልን ስር ነቀል በሆነ መልኩ በህብረተሰቡ ውስጥ ማስፈን፡፡
ይህ የሶስት ወይም የአራት አመት ስራ አይደለም አስር ሃያ አመት
ሊፈጅ ይችላል፡፡እኔ ወደፊት የምመራት ሀገር ቤት ያሉት አይደለም
በአለም ዙሪያ ያሉ ዲያስፖራ የሆኑ የኢትዬጳያ ልጆች
ሜድ.ኢን.ኢትዬጵያ የሚል ማርክ ያለው ምርት ለመግዛት ሱፐር
ማርኬት ከሴፐር ምርኬት ሲያማርጡ ማየት የተለመደ እና የእለት
ተግባር እንዲሆን ነው የምፈልገው ….
ሌላው ፡፡ባለኮከብ ሆቴሎችን ተዎቸው…ትንሽ ገንዘብ ያለው ነጋዴ
እያዳንዱ የቤቱን ፈርኒቺር የሚያስመጣው ከውጭ ነው..የእኛ ቤት
ሰፋ የምግብ ጠረጵዛ ፤ኪችን ካቢኔት ከቻይና ነው ማሚ
ያስመጣችው፡፡.ግን ለምን …?የተለየ ጥራት ስላለው?
አይደለም..፡፡ለጉራ ነው…፡፡ስለዚህ መንግስት እንደዚህ አይነት
አላስፈላጊ ግዢዎችን ወይ ቀረጥ በመጨመር ወይ ደግሞ በሌላ
ዘዴ እንዲቀሩ ወይም እንዲቀንሱና የሀገር ውስጥ አምራቾች
እንዲበረታቱና እዲስፋፉ ማድረግ በዘላቂነት እንደሀገር
የሚጠቅመን ነገር ነው…….
ከውጭ የምናስገባቸውን ነገሮች በየአመቱ እየቀነሱ
የምንሸጣቸው ደግሞ እየጨመሩ መሄድ አለባቸው…ከምንሸጠው
በላይ መግዛት ኪሳራ ነው፡፡በኪሳራ እየኖሩ ደግሞ ከድህነት
መውጣት አይችልም፡፡በድህነት ውስጥ ያለ ማህበረሰብ ደግሞ
በሌላው ማህበረሰብ አይከበርም….፡፡ለሆዱ ሲል ስብዕናውን
ይሸጣል..፡፡ለማግኘት ሲል ክብሩን ያዋርዳል…፡፡የሰው ሀገር ገረድ
ይሆናል…፡፡እና እኔ ለግሌ ስኬት ወይም ለካምፓኒው ስኬት ብቻ
አይደለም መስራት የምፈልገው፡፡ያ ግንጥል ጌጥ ነው..፡፡
እንደህዝብ ታላቅ ወደነበርንበት ማማ መልሰን መውጣት አለብን፡፡
እንደሀገርም ታሪካችን ወደሚተርከው የክብር ሀዲድ ላይ መሳፈርና
በዛም ፀንተን መጓዝ አለብን፡፡ለዛ የቻልኩትን ማድረግ ነው
እቅዴ…
‹‹ጨረስኩ..አመሰግናለው››
ለተወሰኑ ደደቃቃዎች ሶስቱም በድን ሆነው ፀጥ አሉብኝ…ግራ
ገባኝ …፡፡እንዴ እስከአሁን ያወራውት አልገባቸውም እንዴ……?
እግዜር ይስጣቸው ጋሼ ከበደ መናገር ጀመሩ…ወይኔ እያለቀሱ
ነው…፡፡ምን ተበለሻ…..…?
ማህረባቸውን ከኪሳቸው አውጥተው አይናቸውን እያበሱ…‹‹ይቅርታ
ስሜቴ ተነክቶ ነው…ልጅ አለመውለዴ እና እንደ እናንተ
አለመታደሌ እንደዛሬ አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ጠዝጥዞኝ አያውቅም ፡፡
በእውነት ሁለታችሁም እነዚህን የመሰሉ በባለብሩህ አዕምሮ
ልጆች ስለወለዳችሁ ፤ ወልዳችሁም ለእራሳችሁም ሆነ
ለሀገራቸው እንዲተርፍ አድርጋችሁ ስላሳደጋችሆቸው ልትኮሩ
ይገባል፡፡ልጄ ቅድም ከፍሰሀ ጋር በተፈጠረው ጭቅጭቅ የልሆነ
ነገር የሰራሽ መስሎ ስለተሰማኝ በውስጤ ደስ ማይል ነገር
እየተሰማኝ ነበር፡፡አንቺ ግን በጣም የምትገርሚና ጉድ የሆንሽ ልጅ
ነሽ፡፡የእኔን መቶ ፐርሰንት ድጋፍ እንዳለሽ ቃሌን አሁኑኑ
ስጥሻለው፡፡ከዛሬ ጀምሮ ለእኔም ልጄ ነሽ..ነይ ሳሚኝ›› አሉና
እጃቸውን እንደክንፍ ዘረጉልኝ…ተንደርድሬ ጉያቸው ገባው፡፡
መጨመጩኝ..እናቴ ተቀበለቺኝ…የፍሰሀ አበትም ከምጠብቀው
በላይ ተደስቶ ትከሻዬን በመነቅነቅ..‹‹እወነትም የእናትሽ ብቻ
ሳይሆን የአባትሽም ልጅ መሆንሽን አሁን ተቀብያለው፡፡››አሉኝ
ቅድም በጎን ለተናገሩኩት መልስ መሆኑን ነው…
‹‹ስለዚህ ከፍሰሀ ያስታርቁኛል ማለት ነው…?፡፡››
‹‹በሚገባ እንጂ…እናትሽ ብትፈቅድ እንደውም አሁኑኑ አብረሺኝ
ወደእኛ ቤት ብንሄድ…?››ያላሰብኩትን ሀሳብ አቀረቡ
‹‹እንሄዳለን…እማ ይቻላል አይደል?››ወደእናቴ ዞሬ በመለማመጥ
ጠየቅኳት
‹‹አይ ብቻሽንማ አልክሽም››ውይ ብቻሽን ማለት ምን ማለት
ነው…? እሷም አብራኝ መሄድ አማራት እንዴ…? በውስጤ
ያጉረመረምኩት ሀሜት ነው፡፡
‹‹እንደውም ሁላችንም ለምን ወደእኛ ቤት እንሄድም እና
የልጆቻችን ስኬት አናከብርም..…?አቶ ከበደ እርሷም ጭምር››
‹‹አረ እኔ ይቅርብኝ..››
‹‹ግድ የሎትም..››
እያንገራገሩ ተስማሙ..ሁላችንም ተከታትለን.ወደ እነ ፍሰሀ ቤት…
እናገኘው ይሆን……?ይቅር ይለኝ ይሆን….…?የወደፊታችንስ እንዴት
ነው የሚቀጥለው፡፡…?

💫ተፈፀመ💫

ስለተከታተላችሁኝ አመሰግናለው🙏
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2🤔1
አትሮኖስ pinned «.: #ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ (የመጨረሻ ክፍል) ፡ ❤️ፌናን === ይሄ እንደሚፈጠር ቀድሞውኑም ጠብቄያለው::ቀድሜ መናገር ነበረብኝ …ግን ልረብሸው ስላልፈለኩ ነበር እንደዚህ ያደረኩት ::.ሁኔታውን እንዳወቀ አባቱ ትከሻ ላይ ገፍትሮኝ እየተመናጨቀ ቢሮው ገብቶ ከዘጋ ቡኃላ ሶስቱም ነበር ያፈጠጡብኝ…. ‹‹ምንድነው ልጄን ያደረጋችሁት…? ››አሉ አባቱ…..ያው…»
#ሸሌ_ነኝ


#በሕይወት_እምሻው

"ነይ እዚህ ጋር ! ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ...ብርድ ልብሱ ላይ ተኚ" ሲለኝ፣ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር።

ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ግዜ መሽኮርመም። ሰው እንጂ ሴት ያልሆኑኩ መስሎኝ፣ ሥጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ።

አንገቴን እንደሰበርኩ ወደ አልጋው ሄድኩ ሲያገኘኝ እሄድ እንደነበረው አይደለም አካሄዴ።ሰበር ሰካ የለውም፣ ዕዩኝ ዕዩኝ የለውም፣ ተገዝቶ ወደ ሚታረድበት ቦታ እንደሚሄድ በግ ነው አካሄዴ።

ገዥዬ የማያውቀኝ፣ ሰው ፊት ልብሴን ሳወልቅ የመጀመርያዬ እንጀሆነ አያውቅም።

ገዥዬ፣ በገንዘብ ተገዝቼ ከወንድ ለመተኛት ስመጣ የመጀመርያዬ እንደሆነ አያውቅም።

ገዥዬ፣ ለዚህ ስራ ድንግል እንደሆንኩ አያውቅም።

ልብሴን ማውለቅ ሳልጀምር እየፈራው፣ "ይቅርታ....መብራቱን ታጠፋው?" አልኩት።

ዞር ብሎ ዐየኝና፣ "ሃሃ...ሃ! ታሾፌያለሽ እንዴ.? ለምንድን ነው የማጠፋው...? አለኝ። ይስቃል።
ፈራሁ ብለው አያምንም። በሰቀቀን ዝም ብዬ ማውለቅ ጀመርኩ። የአልጋው ጫፍ ላይ ኩምትር እንዳልኩ ድንገት እስካሁን መኖሩን ያላወኩት ብርድ አንዘፈዘፈኝ። ሳል ጀመረኝ።

ይሄን ግዜ ሰውየው ዞር ብሎ ዐየኝና ፤ "ምነው.. ብርድ.. ቲቢ.. ምናምን አለብሽ እንዴ?" አለኝ።

"አይ...በርዶኝ ነው...አያመኝም...አሁን በርዶኝ ነው..." ብዬ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባሁ።

"ኖኖ!...ከላይ ሁኚ...አትግቢ..." አለኝ ቶሎ ብሎ ፣ ቀጭን ትዛዝ ነበር።

እምቢ ብዬ መሄድ እንደማልችል ማወቁ አስከፋኝ። እሺ ብዬው ስለመጣሁ እምቢ ብዬ ስለማልሄድ እርግጠኛ መሆኑን ሳውቅ ከፋኝ። ከነሳሌ ከብርድ ልብስ ወጣሁ። መጥቶ አጠገቤ ተኛ። ሰውነቴ በፍርሃት ተንዘፈዘፈ። ነውስጥ ሱሪ ብቻ ሲቀረው ዕርቃኑን ነው።

እግዜር በሚያውቀው፣ ከማላውቀው ሰው ቤት ለማደር መምጣት አልፈለግኩም ነበር።

የማላውቀው ሰው እጁቹን ጭኖቼ መሀል አስገብቶ እንዲፈነጭ አልፈለግኩም ነበር።

የማላውቀው ሰው ጆሮዬን ተጠግቶ እንዲያቃትትብኝ አልፈለግኩም ነበር። ግን ሰውየው አስገድዶ አላመጣኝም። አልደፈረኝም።

ያስገደደኝ ኑሮ ነው።

የደፈረኝ ድህነት ነው።

ሲነጋና ከኔ ጋር ያለውን ጣጣውን ሲጨርስ፣ የሰጠኝን አምስት መቶ አዳዳስ ብሮች እንደያዝኩ በትእዛዝ ያወለኩትን ልብሴን በከፍተኛ ፍጥነት ለበስኩ። ያወለኩት ክብሬ ግን አልጋው ላይ ቀርቷል።

"ቅዳሜ እመጣለሁ....ማን ብዬ ላስጠራሽ ?" አለኝ በተኛበት።

እንድሄድ ፈልጓል። አገልግሎቴ አብቅቷል። አሁን እንደተፋቀ የሞባይል ካርድ ነኝ። አሁን እንደተጫረ የክብሪት ዕንጨት ነኝ። በድጋሚ በጉጉት የሚያየኝ በሚቀጥለው ቅዳሜ መጥቼ እፎይ ማለት ሲያምረው ነው። ስሜን ነግሬው ዞር አልኩና ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ለመሄድ ስዞር፣

"ማነሽ...እ...በሩን በደንብ ዝጊው!" አለኝ፣ አልጋው ላይ ተገላብጦ ጀርባውን እየሰጠኝ። ፊት እንኳን የማይገባኝ ሰው መሆኔን ሲነግረኝ ነው በጀርባው የሚያናግረኝ፣ የሚታወስ ሰም እንደሌለኝ ሲነግረኝ ነው ማነሽ ያለኝ።

ይሄን ሳስብ ተዛባሁ፣ ተዛነፍኩ።

ካለ አጥንት እንደተፈጠረ ሰው ሰውነቴ ለመቆምም ለመሄድም እምቢ እያለ ወደ ታክሲ ተራው ሄድኩ። ተኝቶ የነጋለት ሰው ይተራመሳል።

ታክሲው ውስጥ ገብቼ መስኮቱን ደገፍ አልኩና ያለ እቅድ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። ከዐይኔ ግድብ የሚፈሰው እንባ ጉንጬቼ ላይ የሚያደርቅ ሳይሆን አዋሽ ወንዝ ለመግባት ያልም ይመስል ይንዠቀዠቃል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው የአንገት ልብሴ ላይ ያርፋል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ጃኬቴ ላይ ያርፋል።

ከክብሬ ጋር አውልቄው የነበረው ሱሬዬ ላይ ያርፋል።

በለቅሶዬ መሃል፣ "አይዞሽ... ሁሉም ያልፋል" የሚል ድምፅ ሰማሁና ዞርኩ። ከእኔ በእድሜ የምታንስ ልጅ ናት።

"ሁሉም ያልፋል" የሚል የታክሲ ጥቅስ አንብባ የምትደለለው ለዚያ ነው። ትንሽ ልጅ ስለሆነች፣ በቂ ስላልኖረች። አንዳንድ ነገሮች እንደኔ ላለው ሰው እንደማያልፍ የሚያስተምራት የህይወት ልምድ ስለሌላት፣ ቀልደኛ!

ዝም ብዬ አየሇትና በእሽታ ጭንቅላቴን ነቅንቄ ተመልሼ ወደ መስኮቱ ዞርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ዛሬ እዚህ ታክሲ ውስጥ እያለቀስኩ ባልተቀመጥኩ፣ ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ ለአምስት መቶ ብር አምስት መቶ ቦታ ባልተሰባበርኩ። ሁሉም ቢያልፍ ኖሮ እኔ ትርሲት የአቶ ከለላውና የወይዘሮ ሥምረት ሴት ልጅ፣ የብሌን ታላቅ እህት፣ የዳዊት ታናሽ እህት፣ የዳግም ፍቅረኛ ሀኜ በቀረሁ። አሁን ግን ትርሲት ሸለዋ ነኝ።

ሸሌ ነኝ፣ ሸሌ ብቻ።

ይህንን ሰውየው ዐይን ውስጥ ዐይቼዋለሁ። ይሄንን ሰውየው ትእዛዝ ውስጥ ሰምቼዋለሁ። ይህንን ሰውየው፣ "በሩን በደንብ ዝጊው" ንግግር ውስጥ አድምጭዋለሁ።

ሸሌ ነኝ።

ለማንበብ ደቂቃ የሚፈጅ ሥም በመስጠት የ'ኔን ሥራ ቅዱስ ማድረግ አይቻልምና፣ የለም፣ አንቺ እኮ 'በወሲብ ንግድ የተሰማራች ሴት' ነሽ!" ብላችሁ አታፅናኑኝ።

ከዛሬ ጀምሮ ሸሌ ነኝ።

በረሀብ እያዛጋሁ ቤቴ ገባሁና ከሰል አቀጣጠልኩ። ሳልበላ ውሃ ላፈላ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ልታጠብ። ሳልበላ በፈላ ውሃ ገላዬን ልታጠብ። ሸሌነቴን በፈላ ውሃ ሙልጭ አድርጌ ልታጠብ።

ውሃው እስኪፈላ፣ ልብሶቼን አውልቄ ከሌሎቹ ልብሶቼ ጋር እንዳይቀላቀሉ በቤቴ አንዷ መአዘን ላይ ሰብስቤ ጣልኳቸው። ብዙ ልብስ የለኝም፤ ግን እነዚህን ልብሶች መልሼ የምለብሳቸው አይመስለኝም።

'ራቁቴን የሰመጠች አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ውሃው እስኪፈላ እየጠበቅኩ ቤቴን ዐየሁት። ለሰው የሚነገር ነገር ስለሌለኝ እንትኑ እዚያ ጋር፣ እትኑ ደግሞ እዛ ጋር አለ ብዬ ላወራችሁ አልፈልግም። በዋጋ ከተሰላ፤ አሁን ያለኝ፣ ዋጋ የከፈልኩበት አምስት መቶ ብር ብቻ ነው። አልጋዬ ላይ የተቀመጠው አምስት መቶ ብር።

ምንአልባት ካልገመታችሁ፣ እንዲህ ያለው ዋጋ ያልከፈልኩበት ብር ለማግኘት ሞክሬ ነበር። ማለቴ ዘልዬ ሸሌ አልሆንኩም። አሳጥሬ ልንገራችሁ። ሁሉንም ሥራ ሰርቻለው። ግን እኔንና እኔን የሚጠብቁ ቤተሰቦቼን ሆድ ፀጥ የሚያደርግ፣ አንገት ቀና የሚያደርግ፣ ደረት አስነፍቶ የሚያስኬድ ሥራ አላገኘሁም።

እውነቴን ነው የምላችሁ፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።

ልድገመው፣ እንጀራ ፍለጋ ሴት የሆንኩት ሰው ሆኜ ስላልተሳካልኝ ነው።

የሥጋ ለሥጋን ኑሮ የመረጥኩት ሌላ ነገር ሆኜ መኖር ስላልቻልኩ ነው። ለምሳሌ የሆነ ሰሞን የሆነ "ኤን ጂ ኦ" ሸሌ የመሆን አዝማሚያ ያሳየነውንም፣ ገብተው የተንቧቹበትንም ሴቶች ሰበሰበና፣ "ከዚህ አስነዋሪና ቆሻሻ ሥራ ነፃ እናውጣችሁ፣....ያልገባችሁትንም እናድናችሁ" አለን።

"አልጋ አንጣፊ ስለሆነች ከአልጋ ለመውደቅ ቅርብ ነች" ብለው ነው መሰለኝ፣ ፕሮጀክቱ ውስጥ አስገቡኝ። ደስ ብሎኝ ገባሁ። ኤን ጂ ኦው፣ "አማራጭ የገቢ ማግኛ ዘዴዎች" በሚል ለግማሻችን ጥልፍ፣ ለግማሻችን ዳንቴል ስራ አስተምሮ፤ "በሉ እንግዲህ ሂዱና ንፁህ ስራችሁን እየሰራችሁ በብልፅግና ኑሮ" ብሎ አንድ ኮንቴነር ቤት ተከራይቶልን ሄደ።

እኔ ከጥልፎቹ መሀል ነበርኩ። እንደተማርኩት እየጠለፍኩ አዲሱንና ንፁሑን ሥራዬን ነጻ መውጫዬ፣ መልካም እጣ ፈንታዬ፣ የእግዜር ካሳዬ አድርጌ ተቀብዬው ሥራ ጀምሬ ነበር።

ብዙዎቻችሁ፣ " እንዴ ሸሌ የሆነች ወይ ለመሆን ያኮበኮበች ሴት ሁሌም ሸሌ ናት" ብላችሁ እንደምታስቡ አውቃለሁ። "በሚኒ ስከርት መንገድ መቆም የለመደች ሴት፣ በ'እስከ ጉልበት' የሥራ ቀሚስ ቢሮ መቀመጥ አትችልም ብላችሁ እንደምታምኑ ከውቃለሁ።

የራሳችሁ ጉዳይ
👍31
እኔ ግን በዛ ሰሞን እፎይታ ተሰምቶኝ ነበር።

ሳልጠፋ ስለተገኘሁ ደስ ብሎኝ ነበር።

ሸሌ መሆን የሚያጓጓኝ ሰሞን፣ የከጃጀለኝ ሰሞን አልጋ አንጣፌ ሆኜ የምሰራበት ቡና ቤት ውስጥ ያሉ የሚቀርቡኝ ሸሌዎችን ገድልና እሮሮ በታላቅ ትኩረት፣ በቀን በቀን እሰማ ነበር። ዐይ ነበር።

በመሸ ቁጥር፣ በ'ኮንደም አድርግ አታድርግ" ጭቅጭቅ፣ በጭንቅላቱ ሳይሆን በእንትኑ የሚያስብ ወንድ ጋር እየተጣሉ በፖሊስ መዳኘት አለ፣ በሚሉት የማስፈራራያ ወሬዎች ተሰላችቼ ነበር።

"በጥፊ ካልመታሁሽ ደስ አይለኝም!" እያለ፣ "ከላይም ከታችም ከሚደበድበኝ ወንድ ጋር አድሬ የከፈለኝን ገንዘብ በድብደባ ያበጠ ፊቴን ለመታከም ማዋሉ መረረኝ" በሚሉ ሴቶች ዋይታ ተማርሬ ነበር።

እሺ...ዝርዝሩ ይቅርባችሁ እና እንዲያው በደፈናው፣ በጨለመ ቁጥር ባለተራ ወንድ እላዬ ላይ ስለማይደፋደፍብኝ የእውነት ደስ ብሎኝ ነበር። ከዚህ እጣ ፈንታ ለጥቂት ስላመለጥኩ፣ ደስ ብሎኝ ነበር።

እናም፣ ቀን ቀን እየጋለ አቅልጦ እንደው ውሃ ሊያፈሰኝ በሚዳዳው ሙቀት፣ ሲመሽ ሲመሽ ጥፍር አውጥቶ ሰውነቴን በሚቦጫጭቅ ብርድ ሳልማረር፣ እዛች ኮንቴነር ውስጥ ቁጭ ብዬ ጥልፊን እጠልፍ ነበር።

በየወሩ፤ "አሁንስ በቃኝ...እንኳን ትርፍ ሊያመጣ ለሚያከስር ስራ ደግሞ!" እያሉ ከጥልፉም ከዳንቴሉም ጎራ ወጥተው ሸሌነትን የመረጡ፣ ወይም ወደ ሸሌነት የተመለሱ ጓደኞቼን እያየሁ እንኳን በንፅህና ጎዳና ለመቀጠል ብዙ ለፋሁ።

ብዙ ታተርኩ፣ ብዙ ወጣሁ፣ ብዙ ወረድኩ።

ንጹህ ስራዬ ግን ከሰው በታች አደረገኝ እንጂ ከፍ አላደረገኝም። ሱቄን የሚደጎበኙ ወንዶች ሁሉ፣ ጥልፍ የጠለፍኩበትን አልጋ ልብስ ከመግዛት ይልቅ እኔን ጠልፈው አልጋ ውስጥ ማስገባት ነበር የሚታትሩት። በአምስተኛው ወር የከሸፈውን ፕሮጀክት ተከትሎ የከሸፈውን ህልሜን ኮንቴነሩ ውስጥ ጥዬ ወደ "ሰጥቶ የመቀበል" አለም መጣሁ።

የዛሬው ሰውዬ የመጀመርያዬ ነበር።
"ሀ" ዬ አንደኛ ክፍሌ።

ሳልዋረድ መብላት ብፈልግም፣ ሳልገላመጥ መኖር ብሻም የሞከርኩት ሁሉ አልሳካ ብሎኝ ሸሌ ሆንኩ።ባላያችሁትና ባልኖራችሁት ሕይወቴ ፈርዳችሁብኝ ብትሰድቡና ብትረግሙኝም፣

ዓለም ስትፈጠር ገና ያኔ ከገበሬነት በፊት፣ ከአናጢነት በፊት፣ ከአስተማሪነት በፊት፣ ከምንም አይነት ሥራ በፊት፣ "ሲወርድና ሲዋረድ" እዚህ የደረሰውን ሥራዬ ግን በእርግማንና በስድብ ወጀብ ከምድረ ገፅ እንደማይጠፋ ታውቁታላችሁ

ምክንያቱም፣ በጨለማ ዝቅ ብዬ ያገኘሁት ገንዘብ እጄን የሚጠብቁ ቤተሰቦቼን ከፍ እንደሚያደርግልኝ አውቃለሁ።

ቀን የተጠየፉኝ ሰዎች ማታ እንደሚያመልኩኝ አውቃለሁ።

ቆሻሻው ስራዬ ንጹሕ እንጀራ እንደሚገዛ አውቃለሁ።

ስለዚህ፣ ወንድ ሊሆን የሚመጣን ወንድ ሴት ሆኜ እያስተናገድኩ እንደ ሰው እኖራለሁ። ሸሌ ነኝ።ከዛሬ ጀምሮ ሸሌ ነኝ።

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
አትሮኖስ pinned «#ሸሌ_ነኝ ፡ ፡ #በሕይወት_እምሻው ፡ "ነይ እዚህ ጋር ! ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ...ብርድ ልብሱ ላይ ተኚ" ሲለኝ፣ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር። ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ግዜ መሽኮርመም። ሰው እንጂ ሴት ያልሆኑኩ መስሎኝ፣ ሥጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ። አንገቴን እንደሰበርኩ ወደ አልጋው ሄድኩ ሲያገኘኝ እሄድ እንደነበረው አይደለም አካሄዴ።ሰበር ሰካ የለውም፣…»
#አኩራፊ_ሰው_ብዙ_ነገር_ያመልጠዋል
===
ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡
ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ለመታደም ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡
ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3ሰዓት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፁፍ ተፅፎበታል፡፡
ማነው ስህተት የሰራው? ማነው ልክ?

አስተያየቶን አድርሱን @atronosebot
#ያቺን_ልጅ_ንገሯት

እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
ልከ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሏት
አዎ እንዳገሬ ነዉ…
እንደ ምንጩ ጣእም እንደ አፈሩ ሽታ
ልጎንጭሽ የምላት…
ልዳብስሽ የምላት ጠዋትና ማታ
ለብሻት የምኖር…
እንደ ቀዩ ጃኖ እንደ ነጩ ኩታ
ጋቢዋ ነኝ እኔ…
ጠላት የተኮሰዉ ንፋስ እንዳይነካት
ሁለት ግዜ ዙሬ…
ወገቡዋ ላይ ያደርኩ የማርያም መቀነት
እንደ አገር አርጅታ…
እንደ አገር አዉግታ ደግሞ ተበሳጭታ
እድሜዉ ይሁን ንዴት ጸጉርዋን አሸብታ
አፋፉ ላይ ቁማ…ብቻዋን ቆዝማ
ድንገት ብታገኟት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
ልክ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሏት
ንገሩልኝ ዘመድ ንገሩልኝ ወገን
እኔ በሷ ፍቅር እንዴት እንደምሆን
እንደተዋለበት ጤናዉን እንዳጣ
በጠላ አስተናግር በጥብጦ እንደጠጣ
ያስለፈልፈኛል ጩህ ጩህ ያሰኘኛል
የቀኑ ሳይበቃዉ ሌሊት ያስዞረኛል
ጎርፉን እጠጣለሁ አፈር እቅማለሁ
ጎርፉን እየጠጣሁ….ሃገሬን እላለሁ
ጨለጥኳት እላለሁ
አፈሩን እየቃምኩ….ሃገሬን እላለሁ
በላሁዋት እላለሁ
ጸጉሬን እነጫለሁ ልብሴን እቀዳለሁ
እንዳይሆን እንዳይሆን እንዳይሆን ሁኛለሁ
እናም ያች የኔ…
የምጠብቃት ሴት የመጣች እንደሆን
መስከረምን አልፋ…
ጥቅምትን ተሸግራ ህዳሩ ሲታጠን
ገላየ ቆሽሾ አካላቴ ዝሎ
ገጼ ተጎሳቅሎ
ድንገት አልፋኝ ብትሄድ…
ፍቅሬ ተዘንግትዋት…
ማንነቴ ጠፍትዋት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት
እንዳገሩ ነበር የሚወድሽ በሏት።

🔘በሰለሞን ሳህለ🔘
አትሮኖስ pinned «#ያቺን_ልጅ_ንገሯት እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያቺን ልጅ ንገሯት ልከ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሏት አዎ እንዳገሬ ነዉ… እንደ ምንጩ ጣእም እንደ አፈሩ ሽታ ልጎንጭሽ የምላት… ልዳብስሽ የምላት ጠዋትና ማታ ለብሻት የምኖር… እንደ ቀዩ ጃኖ እንደ ነጩ ኩታ ጋቢዋ ነኝ እኔ… ጠላት የተኮሰዉ ንፋስ እንዳይነካት ሁለት ግዜ ዙሬ… ወገቡዋ ላይ ያደርኩ የማርያም መቀነት እንደ አገር አርጅታ… እንደ አገር አዉግታ ደግሞ…»
#ሂድ


#በሕይወት_እምሻው


ሞከርኩ፤ እስኪታክተኝ ሞከርኩ። የገነባሁትን ላለማፍረስ፣ የለኮስኩትን ላለማዳፈን፤ ብዙ ሞከርኩ።
እሱ ግን...

በራሱ አባባል፣ "አብላጫ መቀመጫ" ሲያይ የሚንከራተት ዐይኑ አላረፍም። ከፊት ቀድመው የሚመጡ ውድር ጡቶችን ሲያይ መቅበዝበዙን አልተወም።

ሌላ ያያል።

ሌላ ይመኛል።

ሽቶ የተቀባች ባለፈች ቁጥር እንደውሻ ያለከልካል። ቅልብልብ ዐይኑ የየሴቱ ዳሌ ዳሌ ላይ ፈጥኖ ይለጠፋል።

ፍቅሬ ከእኔ ጋር እያለ፣ ገና ድሮ ጥሎኝ ሄዷል።

መቼ እለት ነው የወሰንኩት። ልክ ዓመታት እንዳልታገሰ ሰው ልክ ለዘመናት ዐይቶ ያላየ እንዳልሆነ ሰው፣ አውቆ እንደማይታረም ገባኝና የአምስት ብር ሻይ እየጠጣሁ አምስት አመታት የገነባሁትን ቤቴን ለማፍረስ ተስማማሁ።

"ሄደሀልና ሂድ" ልለው ወሰንኩ።

የተቃጠርንበት ቡና ቤት ቀድሞኝ ተቀምጦ ስፒሪሱን በአላፊ አግዳሚ ሴት ያወራርዳል። የቴኒስ ጨዋታ እንደሚመለከት ሰው ጭንቅላቱ ከቀኝ ወደ ግራ ሲወራጭ ከሩቅ ይታየኛል። ልቤ ሲረግብ ተሰማኝ። ከጀርባው ነው አመጣጤ፣ አጠገቡ ስደርስ ስልክ እንደያዘ ዐየሁ።

ቆም አልኩ።

"ተይ ባክሽ...! ምን የመሰለች ጅራታም ኮኮብ ዐየሁ መሰለሽ አሁን...ግን ካንቺ አይበልጥም....ካንቺ ቂጥ የሚበልጥ ቂጥ የለም" ሲል ሰማሁት።

ውሃ ልኬ የተዛባ መሰለኝ። አውላላ አስፋልት ላይ፣ በጠራራ ፀሐይ፣ በቂጤ ዝርፍጥ ልል ምንም አልቀረኝ። ተንገዳገድኩ። ድንጋጤ አይደለም።

ለአመታት ፍቅሩን የሚጫረቱኝ ሴቶች እንዳሉ አውቃለሁ። ሻሞ ውስጥ እንደምሳተፍ ይገባኛል።

አንዳንዴም ትራፊው እንጀሚደርሰኝ፣ እንጥፍጣፊው፣ ያለቀበቱ እንደሚመጣልኝ ዐውቃለሁ፣ ይሄኛው ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ መሰለኝ።

ላለመወሰን መፍራትን ማቆም መሰለኝ። የተደበቀው በአደባባይ ሲታይ፣ ሰው እየሰማው እንዲህ ሲል፣ ለመያዝ የፈለገ የእኔን "ሂድ በቃ" ሽኝት የጠየቀ መሰለኝ።

ላለመስማት፣ ላለመያዝ መሞከሩን ያቆመ መሰለኝ። ሰምቼ ሂድ እንድለው። ቆርጦልኝ እንዳሰናብተው። እንጥፍጣፊውንም ሊነፍገኝ፣ ያለቀበትንም ሊከለክለኝ የወሰነ መሰለኝ።

ስሜቴን በቅጡ ሳላስተናብር አጠገቡ ደርሼ ተቀመጥኩ።

"እሺ...እደውላለሁ በኋላ..." ወይም ይሄን የሚመስል ነገር ብሎ ስሉኩን ዘጋው።

ይወዳቸው በነበሩት ዐይኖቼ ዐየሁት። ሌላ በማያዩ ዐይኖቹ ዐየኝ። እንደሰማሁ አውቋል። ግን አልደነገጠም። ግምቴ ልክ ነበር።

በደም ስሬ፣ ደም ሳይሆን የበረዶ ውሃ የሚሄድ ይመስል ያንሰፈስፈኝ ጀመር። ዘፋኙ፣ "እትት በረደኝ በርሃ ላይ ቆሜ" ያለው እንዲህ ያለው ነገር ደርሶበት መሆን አለበት።

"ኤፍ..." አልኩት ያለኝን ጉልበት አስተባብሬ።

"እ...?"

ልብ አድርጉልኝ፣ "ወዬ" ዎቹ፣ "ወይ ማርዬ" ዎቹ፣ "ምን አልሽኝ" የኔ ቆንጆዎቹ፣ በ "እ..." ከተተኩ ወራት አልፈዋል።

"እ.." ይለኛል ዝም እንዳይለኝ። አለሁምም፣ የለሁምም ነገር ነው።

"እ..." "አባባሉ፣ እሰማለሁም፣ አልሰማምረ ነገር ነው።

"ከሌላ ሴት ፍቅር ይዞሃል?"

"እ?"

"ሌላ ሴት ወድሃል ወይ?"

ዝም።

መልሱን አውቀዋለሁ ።

"ታውቂያለሽ... የምታዉቂውን ባጠይቂኝ..." ዐይኖቼ ዐይኔን ሳይሸሹ፣ ያልበላውን ጸጉሩን በማፈር ሳያክ መለሰለኝ።

አላልኳችሁም?

"ህም...ነው እያልከኝ ነው ?" አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ ።

የንፍገት ፍቅር ቢቀርብኝ እንደሚሻል ባስብም፣ የሽምያ ፍቅር ወንዝ እንደማያሻግረኝ፣ ዳገት እንደማያስወጣኝ፣ ሌቱን እንደማያነጋልኝ ባስብም፣ እውነቱን መስማት ግን ፈራሁ ግን ደገምኩት ደገምኩት።

"ነው እያልከኝ ነው ኤፊ?"

መበርታት አለብኝ። መጠንከር አለብኝ። ውራጅ ፍቅር አልፈልግም። መሄድን የሚወድ ሰው ቁጭ በል ቢሉት ትርፍ የለሽ ነው። ይሉኝታ እንጂ ፍቅር የማያቆየውን ሰው መያዝ፣ እንቅፋትነት እንጂ ሌላ ምንድን ነው?

"አዎ...ነው..." ጠንከር አድርጎ መለሰልኝ።

ውይ ሲያም። ንግግሩ እንደጥይት አቆሰለኝ። እንደ ቢላ ከተፈኝ። ከመርፌ በላይ ወጋኝ። ግን መበርታት አለብኝ።

ፍቅር ያላሰረውን እግረ ሙቅ ሆኜ ማሰር አልፈልግም። የተነሳ ልቡን፣ "በግፍ ነው" ላስቀምጠው አልሻም። የሸፈተ መንፈሱን "በትንሽ ተገስ" ልደልለው አላቅድም። ግን ሲያም።

ቃላቱ ከጥይት በላይ ያቆስላል።

ከቢላ በላይ ይከትፋል።

ከመርፌ በላይ ይዋጋል።

"እና ልተውህ...? ልትተወኝ ትፈልጋለህ ኤፍ...?

መልሱን የማውቀውን ጥያቄ ጠየኩት።

ይህችኛዋ የፍቅራችን ሬሳ ሳጥን ላይ የምትመታውን የመጨረሻውን ምስማር አቀብለኝ እንደማለት ነበረች።

"እንደሱ አደለም...ማለት...በውለታ መታሰር አልፈልግም ጥሩ ነገር አሳልፈናል ግን..." አለ አሁንም በድፍረት እያየኝ።

"ግን ምን ኤፍ..."

"የምወድሽ አይመስለኝም...ማለቴ አሁን...ዛሬ..."

ንግግሩ ስጋዬን ቦጨቀው።

.....ደም እየፈሰሰኝ ይመስለኛል።

በጆሮዬ፣ በዐይኖቼ፣....በሁለመናዬ ደም እየፈሰሰኝ ይመስለኛል። ሰውነቴ እንደጎማ ሲተነፍስ...ደግሞ ሲግል ይሰማኛል።

አመመኝ።

ፍፁም ታመምኩ።

ዐየሁት። ዐይኖቹ በፍፁም ልበ ሙሉነት ያዩኛል። የሚጠጣውን ስፒሪስ ዐየሁት። ፍቅራችን ጀምሮ እንደተወው ቀዝቃዛ ስፕሪስ ለዛ ቢስ ሆኗል። እሱ ደግሞ ሊተወው...ሊደፋው...እንጂ...ሊያሞቀው አይፈልግም

ዐየሁት።

ፍቅራችን እንደተበሳሳ ጣራ ነው።

በጠብ ጠብ ጀምሮ፣ ቀስ በቀስ እንደሚያበሰብስ...ሙሉ በሙሉ ካልተቀየረ ሁሌም እንደሚያፈስ...እንደሚያለፋ የተበሳሳ ጣራ።

እሱን በማጣቴ ሕይወቴ ውሉ የጠፋ ልቃቂት እንደሚሆን አውቃለሁ።

ፀሐዬን ሰርቆ ጭለማ ውስጥ እንደወረወረኝ እረዳለሁ። ቀስት ደመናዬን ባለ ጥቁር እና ነጭ እንዳደረገው እገነዘባለሁ።

ግን ልሂድ የሚልን ሰው አትሂድ ማለት፣ በመንገዱ ላይ እንደተቸመቸመ ጋሬጣ መሆን ነው።

እንቅፋት መሆን ነው። እንቅፋት መሆን አልፈልግም።

ሳላውቀው ተነሳሁ።

"ኤፊ..."

"ወዬ"

አያችሁልኝ! ሂድ ልለው እንደሆነ ሲያውቅ፣ "ወዬ!" አለኝ...ለደረሰብኝ ሁሉ ከዚህ በላይ ምን ምስክር ምን ያስፈልጋል?

ኤፍ...ሂድ ስለው ወዶኛል።

"ሂ....ድ...." አልኩት በ ሂ እና ድ መሃከል የኪሎ ሜትር ያህል ርቀት እያስቀመጥኩ።

ዝም አለ።

"ኤፊ.."

"ወዬ..."

"መሄድ ስለፈለግክ ሂድ...ቀድሜ ማለት ነበረብኝ...ቢሆንም ዛሬም ቢሆን ሂድ...ጊዜህን መጫረት ሰልችቶኛል...የፍቅር ትራፊ መሮኛል ስለዚህ...ሂ...ድ"

ዝም አለ።

ዝም እንጂ አልሄድም አላለም።

የመዋደዳችን ግብአተ መሬት ለመፈፀሙ ከዚህ በላይ ምን እማኝስ ያሻል?

"ኤፊ?"

"ወዬ መዐዝዬ..."

"ሂድ ግን...እግርህ ጆሮህ እስኪደርስ ብትሄድ የኔን ያህል የሚወድህ ሰው አታገኝም..." አልኩት መሄድ ጀምሬ።

ዝም አለ።

እና...

እንዲህ አድርጌ የምወደውን ሰው ሂድ አልኩት።

ለሚጎዝ እንደሚደረገው፣ ዳቦ ቆሎ ሳይሆን፣ ያልቆረጠ ልቤን ቆርጬ ሰጥቼ ላኩት።

መቀመጫዋ ያበጠ፣ ጡቷ የተወደረ፣ ሰበር ሰካ ባይ ሁላ እንዳሻት ከቀለበችው፣

መዳፍዋ የሰፋ ሁሉ፣ እንዳሻት ከዘገነችው፣ የኔ መሆኑ ካቆመ ዘመንም የለውምና ይሂድ።

....ግን እግሩ ጆሮው ላይ እስኪደርሰ ቢሄድ...እንደኔ የሚወደው ሰው ማግኘቱ ዘበት ነው።

በመንገዴ ላያ፣ ሰማዩን ቀና ብዬ ዐየሁት፣ ፀሃይቱ የት ገባች....?

ቀስተ ደመናውስ ማን በእርሳስ ሳለው..."

....መበረታታት አለብኝ

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍3
አትሮኖስ pinned «#ሂድ ፡ ፡ #በሕይወት_እምሻው ፡ ፡ ሞከርኩ፤ እስኪታክተኝ ሞከርኩ። የገነባሁትን ላለማፍረስ፣ የለኮስኩትን ላለማዳፈን፤ ብዙ ሞከርኩ። እሱ ግን... በራሱ አባባል፣ "አብላጫ መቀመጫ" ሲያይ የሚንከራተት ዐይኑ አላረፍም። ከፊት ቀድመው የሚመጡ ውድር ጡቶችን ሲያይ መቅበዝበዙን አልተወም። ሌላ ያያል። ሌላ ይመኛል። ሽቶ የተቀባች ባለፈች ቁጥር እንደውሻ ያለከልካል። ቅልብልብ ዐይኑ የየሴቱ ዳሌ ዳሌ…»
#ድንግልናዬስ…..?


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሰማዩ ጨፍግጎ በደመና ቢታጠርም ልቤ ግን በደስታ ጮቤ ረግጧል፡፡የአየሩ ቅዝቃዜ ቢያንዘፈዝፍም ውስጤ ግን በሙቀት ተጥለቅልቋል፡፡ምንያቱም ዛሬ ቀኔ ነች ፡፡የደስታ ቀኔ..፡፡ወደ አዲስ የህይወት ምዕራፍ የምሸጋገርበት፤ሙሉ ሰው ፤ሙሉ ሴት የምሆንባት የተቀደሰች የፍቅር ቀን፡፡
ይህቺን የዛሬዋን ቀን ክርስቲያኖች የክርስቶስን ዳግም መምጣት የሚናፍቁትን ያህል ናፍቄ..ጦርነት የዘመተባት ልጇ በህይወት ተርፎ መመለሱን እንደምትናፍቅ እናት ለዓመታት ናፍቄ ያገኘዋት ቀን ነች፡፡ሴት የምሆንባት ቀን ..እንቡጥነቴ ፈንድቶ ወደ አበባነት የምሸጋገርበት ልዩ ቀን ነች፡፡ከአንዱ የህይወት እርከን ወደ ሌላው የምሸጋገርባት ከወርቅ የተሰራች የህይወት ድልድይ፡፡
መኝታ ቤቱ በልዩ ሁኔታ ደምቆል፡፡፡አራቱም ኮሪደሮች ጥግ በተቀመጡ አይንን በሚማርኩ ማስቀመጫዎች ላይ የተሰኩ ነጫጭ ሻማዎች ተለኩሰው ከፍቅር ጋር የተለወሰ፤ከጉጉት ጋር የተቀየጠ…የናፍቆት ብርሀን ይረጫሉ፡፡ከቴፑ አንደበት እየተስፈነጠረ የሚወጣው የዘሪቱ ከበደ ቄንጣዊ ዜማ ውስጥን ይነዝራል፡፡መኝታ ቤቷን ወለል ያለበሰው ነጭ ምንጣፍ እላዩ ላይ ሮዝ እና ቀይ አበባ ተበትኖበት የሆነ የገነት አጸድ መስሏል፡፡
እኔና ፍቅረኛዬ በጣም ተጠጋግተን ጐን ለጐን አልጋው መሀል ቁጭ ብለናል፡፡ልቤ ደም መርጨቷን ልታቆም ትንሽ ነው የቀራት ፡፡ኸረ እንደውም አለማቆሟንም እርግጠኛ አይደለውም፡፡የምተነፍሰው አየር እያጠረኝ ነው፡፡ተስማምቼ..ፈልጌ እና ቆምጬ ነው የመጣውት፡፡ግን ደግሞ ፈርቼያለው….ደንግጬያለው…ጓጉቼያለው….ተስገብግቤያለው… ተንቀጥቅጬያለው….ተሸብሬያለው ፤እንዴት እንዴት እያደረኝ እንዳለም ለማወቅ ግራ ተጋብቼያለው፡፡
ለጊዜው እሱ ምን እየተሰማው እንዳለ መገመት አልችልም ፤ግን በመጠኑ የፈራ ይመስለኛል፡፡ቢሆንም እስከዛሬ ያካበተውን ልምድ ተጠቅሞ ሊያቀልጠኝ… ሊያሟሟኝ መወሰኑን አይን ውሀውን አይቼ ተረዳው እና በደስታ ተንቀጠቀጥኩ፡፡እጁን አንስቶ ተከሻዬ ላይ ጣል አደረገ… ቀጠለ ወደ ታች ዝቅ አደረጋቸውና ጡቶቼን ጨመቅ ጨመቅ ያደርጋቸው ጀመር…ቀጠለ ጉንጩቼን ደጋግሞ ሳማቸው…..አንገቴ ስር ሳመኝ …ደጋግሞ ሳመኝ…. እንደውም ላሰኝ ማለት ይቀላል.፡፡.እናንተዬ አንገት ስር መሳም ..ጆሮ አካባቢ መሳም እንዴ ነው እንዲህ ፍስስ የሚያደርገው..;?እኔማ ከንፈሬ ተነቅሎ አንገቴ አካባቢ እና ጆሮዬ ላይ ተለጠፈ እንዴ ?ብዬ ተጠራጥሬ ነበር፡፡ግን ከንፈሬ ቦታው ላይ መሆኑን ያረጋገጥት በመጨረሻ መነጥቶ ሲጣበቅባቸው ነው፡፡መጠጠኝ… እስክቃትት መጠጠኝ፡፡በስተመጨረሻ የኃላ እግሩ እንደተሰበረ ወንበር ወደ ኃላችን ተያይዘን ተገነደስን፡፡ሰውነቴ በእቶን እሳት የተቀጣጠለ መስሎ ተሰማኝ….ልቤም አቅም እያነሳት እና እየተልፈሰፈሰ እንደመጣ እየታወቀኝ ነው፡፡
ልብሳችንን በምን ፍጥነትና ብርታት አወላልቀን እርቃን እንደቀረን ፍፅም ትዝ አይለኝም፡፡ሰውነቴ ከሰውነቱ ሲጣበቅ…እግሮቼን ፈልቅቆ ጭኔ ውስጥ ሲመሰግ ….እንደፌዴራል ዱላ የገረረ እንትኑ ያለርህራሄ ትንሽ እንኳን ሳያባብለኝ እየሰነጣጠቀኝ እየከፋፈተኝ ወደ ውስጠቴ ሲገባ የሆነ አዲስ አይነት ጣዕም.. አዲስ አይነት ስቃይ… አዲስ አይነት ደስታ ተሰማኝ… ፡፡ሚገርም ነው ስቃይና ደስታ እንዲህ ይደባለቃል….ለቅሶና ሳቅ እነዲህ ይዋሀዳል..?ማቃተት እና ማስካካት እንዲህ ተቀይጦ ከሰው አንደበት ይሰማል….?በቃ ለዘላለም በዛው ብጠፋ ተመኘው…፡፡ወይ ጉዴ.. አዎ የእወነት ልጠፋ ነው መሰለኝ… የፍቅረኛዬ ጉልበት የዐውሬ እየሆነ ነው..የ17 ዓመት ያልፀኑ አጥንቶቼን እያደቀቃቸው ነው…ሰውነቴ እየተተረተረ…እየተበታተነ እየመሰለኝ ነው..፡፡ትንፋሼ ልትቋረጥ የሽርፍራፊ ሰከንድ ጊዜ ሲቀራት ጀግናዬ ተልዕኮውን ከፍጻሜ አድርሶ ተዝለፍልፎ ከጐኔ ተዘረረ፡፡እኔም ከደስታ እና ስቃይ ተቀይጦ የተመረተ እንባ ወደ ውጭ በዝምታ አንጠባጠብኩ………………………….

ከአምስት ደቂቃዎች የዝምታ እና የተመስጦ እረፍት ቡኃላ ፍቅሬን እተጋደመበት ትቼው እየተንሻፈፍኩ እና እየተንቀጠቀጥኩ ሻወር ልወስድ ወደ ባኞ ቤት በመጐተት ገባው፡፡
….›››››››››››››››››››››››››››››››››………..
ከአስር ደቂቃዎች ቡኃላ ስመለስ መኝታ ቤቱ ባዶ ነበር፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ድንገት አንድ የወረቀት ቁራጭ አይኔ ውስጥ ገባ አነሳውተት …የፍቅሬ የእጅ ፅሁፍ ነው፡፡ማንበብ ጀመርኩ…ይገርማል ለእኔው የተፃፈ ነው…
===
ሁለት ዓመት ሙሉ ዋሸሺኝ…በፍቅራችን ቆመርሽበት፡፡ልጃገረድ ነኝ ብለለሽ ስታጃጅይኝና ስታሾፊብኝ ከረምሽ፡፡
አሁን ማድረግ ምችለውም.. የምፈልገውም ነገር አንቺን መርሰሳት ነው..፡፡ለዛም ይረዳኝ ዘንድ ልጠጣ ሄጄያለው፡፡
በፈጠረሽ ስመለስ እቤቴ እንዳላገኝሽ…ካገኘውሽ ልገድልሽ ሁሉ እችላለው፡፡
አየሽ እኔ የቤት ሸርሙጦችን በጣም ነው የምጠየፈው፡፡
===
አንብቤ ስጨርስ አጥወለወለኝ ፡፡በደስተታ ተንተርክኮ የነበረው ልቤ ከመቅፅበት ኩምትርትር አለ፡፡እርክት ብሎ የነበረው ስሜቴ መልሶ ሙሽሽ አለ፡፡ግራ ገባኝ ፡፡ይህ ሁሉ ለዛለለም ይሚበቃ ይመስል የነበረው ደስታ በደቂቃዎች ውስጥ እንዴት እንዲህ ሊበተን ይችላል?፡፡እኔ ከእሱ ውጭ አኮ እንኳን ወሲቡ መጋራት ቀርቶ ከንፈር ተሳስሜ አላውቅም…፡፡እሱ እኮ የልቤን ድንግልና…የከንፈሬን ድንግልና ..እና አሁን ደግሞ ቀሪውንም ድንግልናዬን ነው የወሰደው…፡፡ ታዲያ የቱ ጋ ነው ችግሩ….?.እኔን እንዴት ሸርሙጣ ሊለኝ ቻለ?ቆይ ግን ክብረ -ንፅህና ማለት ምን ማለት ነው?ራሴን ጠየቅኩ…የእውነት ለእሱ ብቻ እንደተኛው… ለእሱ ብቻ እንዳስረከብኩ በምን ላረጋግጥለት እችላለው..?አዎ ትዝ አለኝ …ደም፡፡ በፍጥነት ብርድልብሱን ገለጥኩ… አንሶላዎችን አገላበጥኩ… ፍጽም ንፅህ ነው …ጠብታ ደም አይታበትም… ፡፡ወላሉ ላይ ቆምኩና የለበስኩትን ቀሚስ ወደ ላይ በመግለብ ጐንበስ ብዬ ብልቴን ፈተሸኩ፤ ዙሪያውን ፍም መስሎአል..የመቁሰል መልክቶችም ይዩበታል፡፡
ወይኔ ልጅት ምንም የዋሸውት ነገር የለም እስከዛሬ ድንግል ነበርኩ… ሴት የሆንኩት ዛሬ ነው….አዎ ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት እዚህችው አልጋ ላይ…..፡፡መጮህ አማረኝ …ማልቃስ አማረኝ ..ዕቃዎችን መሰባበር አማረኝ ..እራሴን ማጥፋት ሁሉ አማረኝ ..ግን ዝም ብይ አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብዬ አንገቴን ወደ መሬት አቀርቅሬ ከመነፍረቅ በስተቀር ለጊዜው ሌላ ምንም ነገር ማድረግ አልቻልኩም፡፡

💫ተፈፀመ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍31🤔1
አትሮኖስ pinned «#ድንግልናዬስ…..? ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፡ ፡ ሰማዩ ጨፍግጎ በደመና ቢታጠርም ልቤ ግን በደስታ ጮቤ ረግጧል፡፡የአየሩ ቅዝቃዜ ቢያንዘፈዝፍም ውስጤ ግን በሙቀት ተጥለቅልቋል፡፡ምንያቱም ዛሬ ቀኔ ነች ፡፡የደስታ ቀኔ..፡፡ወደ አዲስ የህይወት ምዕራፍ የምሸጋገርበት፤ሙሉ ሰው ፤ሙሉ ሴት የምሆንባት የተቀደሰች የፍቅር ቀን፡፡ ይህቺን የዛሬዋን ቀን ክርስቲያኖች የክርስቶስን ዳግም መምጣት የሚናፍቁትን ያህል…»
#ሞካሪና_አስሞካሪ


#በሜሪ_ፈለቀ



"ከንፈር መሞከር እፈልጋለሁ።" አልኩት

"እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?"

"እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።" ከንፈሩን አቀበለኝ።

ወራት ነጎዱ……

"ድንግል መሆን አልፈልግም" አልኩት

"ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም? "

"አሁን ነው የምፈልገው።"…… አክሱሙን አቀበለኝ።

ወራት ነጎዱ………

"ጫት ለጥናት ጥሩ ነው ሲሉ ጊቢ ሰማሁ። መሞከር ፈልጋለሁ አልኩት።"

"አይ አይ አይ…… ጥሩ አይደለም ማሬ ስሞትልሽ አትሞክሪ።" አለኝ እያንገፈገፈው

"ልንገርህ ብዬ እንጂ መሞከሬ አይቀርም። እነቤቲ ዛሬ እንቅማለን ብለዋል…… " ሳልጨርስ ቀድሞ

"እሺ በቃ ፍቅሬ እሺ…… መሞከር ከፈለግሽ  እኔም አብሬሽ እሞክራለሁ። ከኔጋ ቃሚ…… " ጫቱንም ፍራሹንም ሰጠኝ።…… መቃም በፈለግኩ ቁጥር ከስራ እየቀረ አብሮኝ ቃመ።

ወራት ነጎዱ………

"ልመረቅ ስለሆነ ስክር ማለት እፈልጋለሁ ክለብ ውሰደኝ" አልኩት……

"እሺ እንደፈለግሽ ሁኚ እጠብቅሻለሁ።" አለኝ…… መጠጡን ቀዳልኝ… እንደፈለግኩ ሆንኩ……

ሰዓታት ነጎዱ……

"ማጨስ እፈልጋለሁ።"

"እማ ስካሩ አይበቃም? ፕሊስ ጭሱ ይቅር? "ለአፉ አለኝ እንጂ የፈለግኩትን ሳልሞክር ማቆሚያ እንደሌለኝ ያውቃል።

"እሺ ገዝቼልሽ ልምጣ? "

"አልፈልግም የተጨሰ ግማሽ የደረሰ ሲጋራ ነው ማጨስ የምፈልገው።… እንደውም ያን ሰውዬ ስጠኝ እለዋለሁ።"

"እሺ እሺ በቃ የተጨሰ አይደል ማጨስ የምትፈልጊው? በቃ እኔ አጭሼ ሰጥሻለሁ።…… ከሌላ ሰው ከንፈር ተውሰሽ አታጨሺም! " አጭሶ ሰጠኝ። አጨስኩ።… እስክመረቅ በጨፈርኩ ቁጥር የተጨሰ ሲጋራ አቀበለኝ።

ዓመታት ነጎዱ…… ብዙ ዓመታት…… እንደተመረኩ ከሃገር ወጣሁ።…… ተራራቅን…… ከጊዜ በኋላ መገናኘት አቆምን።… አገባሁ…… ወለድኩ…… ለበዓል ወደሃገር ቤት ተመልሼ ሳለሁ መንገድ ላይ አየሁት።…… ደነዘዝኩ። ያ ሊነኩት የሚያሳሳ ቆዳው ከስሎ…… የሚያንጠራራ መለሎ ቁመናው ጎብጦ… የሚያኮራ ደልዳላ አካሉ ኮስምኖ… አይሆንም እሱ አይሆንም!

"አቁምልኝ! አቁምልኝ! "ጮህኩኝ ባሌ ላይ… ዘልዬ ወረድኩ እና እጁን ይዤ አስቆምኩት።

"እማ አንቺ ነሽ ስካሬ እያስቃዠኝ ነው? " አለኝ ከቃላቶቹ እኩል የርካሽ መጠጥ ጠረን እየተፋ

"አባ አንተ ነህ? ምን ሆነሃል? በስምአብ ምን አገኘህ? ታመህ ነበር? በስምአብ …… ደህና ነህ? ቆይ ምንድነው የተፈጠረው?"

"አንቺ እማ! አንቺ ነሽ የተከሰትሽው! ሌላ ማን አለ አንቺ "…

የሆነ የአዳም ረታ መፅሃፍ ውስጥ ያለሁ ገፀ ባህሪ የሆንኩ መሰለኝ። እንጂማ እኔ በእውነታው ይህችን ሴት ልሆን አልችልም። በሱስ ምክንያት በተደጋጋሚ አማኑኤል ሆስፒታል እንደነበረ ነገረኝ። በዛ ምክንያትም ስልክ ኖሮት ስለማያውቅ ላገኘሁ እንዳልቻልኩ አብራራልኝ……

"እማ አንቺ ማለት የምትበር ቢራቢሮ ነበርሽ…… ነፃ የሆንሽ… ነፃነትሽን የምትወጂ… ካልሞከርሽ የማታረጋግጪ…… ሁሉን ሞከርሽ እኔን ጨምሮ ሁሉን ተውሽ! ሁሉን አስሞከርኩሽ ከሁሉ ተጋባሁኝና ቀረሁ። " አለኝ።

አይ አይሆንም የአዳም አንዷ ገፀባህሪማ ሆኛለሁ።…… ነፃነት? ሌላውን የገደለ ነፃነት? በሌላው ባርነት ላይ የቆመ ነፃነት? የአባን ገፅ ያከሰለ ነፃነት?

……… አይሆንም ውሸት ነው። እኔማ እውን አይደለሁም…

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
አትሮኖስ pinned «#ሞካሪና_አስሞካሪ ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ ፡ ፡ "ከንፈር መሞከር እፈልጋለሁ።" አልኩት "እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?" "እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።" ከንፈሩን አቀበለኝ። ወራት ነጎዱ…… "ድንግል መሆን አልፈልግም" አልኩት "ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም? " "አሁን ነው የምፈልገው።"…… አክሱሙን አቀበለኝ። ወራት ነጎዱ……… "ጫት ለጥናት ጥሩ ነው ሲሉ ጊቢ…»
#የሚነበብ_ከንፈር 💋

ያው ጀመራት እነዚህን ጉልላት የመሰሉ ዓይኖቿን ከንፈሬ ላይ ታንገዋልላቸዋለች። እንኳን ለምን ቢሮዬ እንዳስጠራኋት እኔው ራሴ አሁን እዚህ ቢሮ መሆኔን ብጠየቅ የማስታውስ አይመስለኝም።

"ዶክተር? ዶክተር? ዶክተር?” አሁን የት እንዳለሁ አወቅኩ። ግንሳ እነዚህን ዓይኖቿን ካላሳረፈቻቸው እንዴት ነው ከዚህ ሌላ ማሰብ የምችለው?

"አቤት ህሊና?” ያልኩበት ድምፀት ለምን እንደፈለገችኝ እሷ ልትነግረኝ እንጂ እኔ ያስጠራኋት አይደለም የሚመስለው።

" ለምንድነው ያስጠሩኝ ዶክተር? ችግር አለ?” ለምንድነበር ያስጠራኋት? እህህህህ ዓይኗን ከከንፈሬ ላይ ካልነቀለች ለምን እንደፈለግኳት በምን አውቃለሁ? ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንደትያትረኛ ተንጎራደድኩ(ተንጎማለልኩ።) እኔ ያየኋቸው ጥቂት የኢትዮጵያ ትያትሮች ላይ ተዋናዩ ታሪኩ ላይ የሚጨምረው ምንም ፋይዳ የሌለውና አስፈላጊነቱ የማይገባኝ መንጎራረድ  መድረኩ ላይ አንድ ሶስቴ ይንጎማለላል። እንደዛዛዛዛ አደረግኩ። እኔ ግን ዓይኗን ሽሽት ነው። ለምን እንደጠራኋት አሁን መጣልኝ። 

ህሊና እኔ በማስተምርበት ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት። እንኳን እንደእኔ አይነቱን ዓይንአፋር እኔ ነኝ ያለ ጀግና ወንድ ብርክ የሚያሲዝ ህልም መሰል ውበት አላት። እኔ እሱ አልነበረም ችግሬ። ቆንጆ ትሁን ፉንጋ ከሴቶች ጋር ተከባብሬ የኖርኩ ሰው ነኝ። አይደርሱብኝም። አልደርስባቸውም። የህሊና ጉዳይ የተለየ ነው። በገባሁባቸው አራት ክላሶች ሁሌ ከፊት ነው የምትቀመጠው። እሱም ባልከፋ! እነኚህ አደንዛዥ ዓይኖቿን ከከንፈሬ ላይ ለደቂቃ አትነቅልም። በስህተት መስሎኝ ተከታተልኳት…… ሃሃሃሃ አቃቂያለችኝ እንጂ ሁላ…… የመጀመሪያ ቀን እቤቴ እንደገባሁ ከንፈሬን በመስታወት አየሁት። ሆ! …… ለዓመታት በልበ ሙሉነት ያስተማርኩት ሰውዬ መንተባተብ እጀምራለሁ። ላብ ያጠምቀኝ ይጀምራል።…… አንዱን ቀን ክላሱን ሳልጨርስ አቋርጬ ወጣሁ። ሆሆ!

ምንድነው የምላት? እባክሽ ዓይኖችሽን ከከንፈሬ ላይ ሰብስቢልኝ? ማስተማር ስላቃተኝ ዓይንሽን አሳርፊልኝ? ምን አስበሽ ነው እንደዚህ የምታደርጊው?  ኡፍፍፍፍ……

"ዶክተር?” አለችኝ ጀርባዬን ሰጥቻት ለብዙ ደቂቃ መቆሜ ግራ ገብቷት መሰለኝ። ደሞኮ ድምፅዋ ራሱ የሆነ የፈጣሪ ምህረት የሚመስል ለዛ አለው።

"አቤት! እ…… እ…… የጠራሁሽ…” መንተባተብ ሲያስጠላ! ኸረ ዶክተር ትልቅ ሰው አይደለህ ምን ያንተባትብሃል? ራሴን ገስፃለሁ።

"ዶክተር ከንፈርዎትን ካላየሁ አልረዳዎትም።” ምን አለች? ምን አለች? ምን…… ምን?ጆሮዬ ሲሰማ ስቶት ነው።

"አቤት?” አልኳት ዓይኖቿን ሳልፈራ ተጠግቻት። ሳቅ እንደማለት አለች። መሰለኝ።

"ትንሽ የመስማት ችግር አለብኝ። ሲያወሩ ከንፈሮትን ካላነበብኩ ሁሉንም ቃላት ላልሰማ እችላለሁ። ባጋጣሚ ለሁሉም መምህሮቼ ስናገር  ለርሶ ሳልነግር ቀርቼ ነው።”

የባሰው መጣ!!!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
አትሮኖስ pinned «#የሚነበብ_ከንፈር 💋 ያው ጀመራት እነዚህን ጉልላት የመሰሉ ዓይኖቿን ከንፈሬ ላይ ታንገዋልላቸዋለች። እንኳን ለምን ቢሮዬ እንዳስጠራኋት እኔው ራሴ አሁን እዚህ ቢሮ መሆኔን ብጠየቅ የማስታውስ አይመስለኝም። "ዶክተር? ዶክተር? ዶክተር?” አሁን የት እንዳለሁ አወቅኩ። ግንሳ እነዚህን ዓይኖቿን ካላሳረፈቻቸው እንዴት ነው ከዚህ ሌላ ማሰብ የምችለው? "አቤት ህሊና?” ያልኩበት ድምፀት ለምን እንደፈለገችኝ…»
#ሁለቱ_ከንፈሮች


#በሜሪ_ፈለቀ


የሳመኝን ሰው እንኳን ስሙን መልኩ እንኳን የሚታወሰኝ ከናይት ክለቡ  እልፍ የሚሽከረከር መብራት ቀለማት ጋር ተበውዞ ነው።……

የዘጠኝ ዓመት ፍቅረኛዬን ከንፈር ያስከዳኝን አሳሳሙን ግን……

ፍቅረኛዬን አልኩ እንዴ? ኸረ ከሁለት ሳምንት በኋላ የማገባው እጮኛዬ ነው። ማለቴ ነበር ማታ ያ ከይሲ እስከሳመኝ ደቂቃ ድረስ…… 

በቃ ተበላሁ።…… እጮኛዬን እፈልግሃለሁ ብዬ ቀጠርኩት።…… ፍትልክ ብሎ ከእጅ እንደወደቀ እቃ ያመለጠኝ

"አላገባህም! " የሚለው ቃል ነው። በቃ ዱብ ነው ነው ከአፌ የወደቀው…… ዝም አለ። አፉ ብቻ አይደለም ገፁም ዝም አለ። ተናደደ? ጠላኝ? ክፋቴ ከቃል በላይ ሆኖበት ነው? በቃ ዝም አለ…… ቀበጣጠርኩ

"ማለቴ መጋባት ያለብን አይመስለኝም።… በአንተ ምክንያትኮ አይደለም…… አንተማ ዕንቁ ነህኮ…… እኔጋ ነው ችግሩ…… "

ከኑሮ ከከበደ ዝምታ በኋላ

"ምክንያትሽን ማወቅ እፈልጋለሁ! " ብሎ የዝምታውን ጭነት ለእኔው አቀበለኝ። ጭጭ…… ፀጥ…… ልጉም…… ዲዳ

ምንድነው የምለው? አንተ ስመኸኝ እንደማታውቀው የሆነ የማላውቀው ሳስበው ሸበላ የሚሆን ሰው ሲስመኝ እኔና አንተ መጋባት እንደሌለብን እንደመገለጥ ፈነጠቀልኝ ነው የምለው?

እጮኛዬ

እጮኛዬ ከመሆኑ በፊት የረዥም ዓመት ቦይፍሬንዴ ነበረ።… ቦይፍሬንዴ ከመሆኑ በፊት የሰፈር ጓደኛዬ ነበር። ጓደኛዬ ከመሆኑ በፊት እቃእቃ በተጫወትን ቁጥር በፀብ የምንጨርስ የእቃቃ ባሌ ነበር።…… ቤተሰብ… ጓደኞቻችን… የሚያውቀን ሁሉ ፍፁም የሆንን ጥንዶች መሆናችንን ነው የሚነግረን።…… እውነት ነው። አንዲት ሴት ባል ይሁነኝ ብላ ልታልም የምትችለው መስፈርት ሁሉ አለው።…… ማታ እንደሳመኝ ልጅ የቆምኩበትን የሚያስረሳ መሳም ብቻ የለውም።

የሳመኝ ሰው

ከአሜሪካ ከመጣች ጓደኛዬጋ ክለብ ሄደን ነው። ሞቅ ባለኝ አሳቻ ሰዓት እንጨፍር አለኝ። እየጨፈርን ነበር…… የሆነ እንደመለስለስም እንደመጠንከርም…… እንደማቀፍም እንደመሳብም… እንደፍቅርም እንደጥላቻም… እንደብዙ ነገር የሆነ አያያዝ ወገቤን ይዞ ሳበኝ…… ሳመኝ ልበለው…… አይደለም…… በከንፈሩ የሆነ ዓለም ፈጠረ… ኖሬበት የማላውቅ ዓለም…… በቃ ይኸው ነው።…… ወደ ናይት ክለቡ ዓለም ስመለስ ተቆናጠርኩ። ተሳደብኩ።…… ተመነጫጭሬ ጥዬው ወደቦታዬ ተመለስኩ…… ወደ ራሴ ሳልመለስ ቀረሁ እንጂ……

"ካንቺ ስለመጣ ደስ ብሎኛል። ለሰርጉ ጓግተሽ ስለነበር ልብሽን እንዳልሰብረው ብዬ እንጂ። እኔና አንቺ ጓደኝነት እንጂ የፍቅር አይነት ቅመም በመሃከላችን እንደሌለ ካወቅኩ ቆይቻለሁ።" አላለም። አምልጦት ከአፉ ወድቆ ነው የሚሆነው ብዬ አሰብኩ። ይሄ ሁሉ ቃልማ አይወድቅበትም።

"ማለት? ማንን ስመህ ነው? " እየቀናሁ ባልሆነ…… 


ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2