ቀጥሬ እንዲያግዘኝ ማደረገ እችላልው..ይሄን ሁሉ አድርጌ አንዲት ሴት ማሸነፍ ካቃተኝም ያንተ ልጅ አይደለውም ማለት ነው››የምሬን በብስጭት ፎከርኩ
‹‹እንደምታደርገው አምናለው ልጄ.. ላስጠነቅቅህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ወሳኙን የመለያ ድምጽ የያዙት ሰውዬ ቀላል ሰው እንዳልሆኑ ነው….ሁል ጊዜ የተለየ ነገር ይፈልጋሉ…ከዚህ ቀድመው የማያውቁትን ወይንም በጣም ሊያስደምማቸው የሚችል ነገር ካላገኙ ድምጻቸውን ማግኘትን አታስበው..….በተረፈ ዝርዝሩን ስመጣ እናወራለን..እኔም አግዝሀለው››
‹‹መች ነው የምትመጣው ?››
‹‹ከአስር ቀን ቡኃላ መጣለው››
‹‹እሺ ቻው አባ እወድሀለው››
ስልኩን ዘግቼ አካባቢዬን ስቃኝ ለካ መኪናውን ዳር ይዛ በማቆም በተመስጦ ዝም ብላ እያዳመጠቺኝ ነበር
‹‹እንዴ ምነው መኪናውን አቆምሽ..?››ጠየቅኳት
‹‹አይ እዚህ ትንሽ እድንቆይ ፈልጌ ነው››
‹‹አባቴ እኮ ደውሎ .በጣም ደባሪ ነገር ነው የነገረኝ..››
‹‹ሰማውኮ…ነገሩ በደንብ ባይገባኝም መረበሽህን ከንግግርህ ተረድቼያለው…››
‹‹አዎ ባክሽ ላንቺ መንገር ይኑርብኝ ወይስ አይኑርብኝ አላወቅም እንጂ ትንሽ የሚረበብሽና ያልጠበቅኩት ነገር ነው ..››
‹‹ከደበረህ ተወው…ግን የካማፓኒው ስራ-አስኪያከጅ ለመሆን አንድ ተቀናቃኝ አለችብህ መሰለኝ…ከንግግራችሁ የተረዳውት ያንን ነው…››
‹‹አልተሳሳትሺም…ግን እወጣዋለው››
‹‹ለምን ከሴት ጋር ስለሆነ ፉክክሩ…?.ሴት ደካማ ስለሆነች?››ኮስተርና በስጨት ብላ
‹‹አይ ማለቴ….››የምላት ጠፋኝ
‹‹ለመሆኑ ልጅቷን ታውቃታለህ..?ማለቴ የትምህርት ዝግጅቷን ?የስራ ልምዷን? የተፈጥሮ ብቃቷን..?››
‹‹አይ አላውቅም…ግን ያው በእኔ ዕድሜ አካባቢ እንደሆነች አውቃለው…ስለዚህ ሌላውን መገመት ብዙም አይከብደኝም…››
‹‹ሴት መሆኗን እና በአንተ ዕድሜ ላይ ምትገኝ መሆኗን ብቻ በማወቅህ የእሷን ብቃት ካንተ በታች ዝቅ አድርገህ ለመያት በቂ መረጃ ሆነህ …ብቻ እግዜር ይሁንህ ..፡፡ግን እንደ ምክር ልስጥህ …ማንኛውም ጦረነት ውስጥ ስትገባ ምንም አይነት መንገድ የባለጋራህን ችሎታ ዝቅ አድርገህ አለማየት ይጠቅምሀል በሌላ ጎኑም በራስህ ላይ ያለህን በራስ መተማመንም ማጣት የለብህም…ይሄ ትክክለኛውን ዝግጅት እንድታደርግና በዝግጅትህም መጠን በብቃት እድትፋለም ያግዝሀል፡፡
‹‹ምን አበሳጨሽ አንቺ?›› አልኳት..መበሳጨት ከንግግሯም አልፎ በፊቷ ላይ በግልጽ ስለተነበበ..
‹‹አይ እንዲሁ ነው…ለማንኛውም ይሄ የምታየው ጨለቅለቃ ሀይቅ ነው…የሚደነቁ አይነት ወፎች በአካባቢው አሉ… ለተወሰነ ደቂቃ ወርደን በግር እንራመድ››አለቺኝ
በደስታ ተስማምቼ ወረድኩ መኪናውን በመቆለፍ ወደእሷ በመሄድ የአስፓልቱን ዳር ይዘን ቀኝ እጄን ተከሻዋ ላይ ጣል አድርጌ አካባቢውን የወረሩት ደግሞ ስንጠጋቸው እየተበተኑ ሰማዩን በውበት እየሞሉ በመንሳፈፍ ዛፎቹ ላይ የሚያርፉትን እንደ ዳክዬ ፤ፓሮት፤ ፍላሚንጎ ፤ ብዙ ስማቸው የማላውቃቸውን የተለያየ እና ገራሚ ዝርያ ያለቸውን ወፎችን እየተመለከትን ስንራመድ..
‹‹ፀጥ አልሽ ምነው?››
‹‹እኔ እንጃ ከአባትህ ጋር ስታወራ አባቴ ናፈቀኝ?››
‹‹አባትሽ…ታዲያ አውሪያቸዋ..›› ስልኬን አቀበልኳት..ስልኩን ተቀብላኝ ቁጥሩን እየመታች ሸርተት ብላ እጆን ከትከሻዬ ላይ አወረደችና ወደኃላ ቀረች..ገባኝ ፡፡የማወራውን ነገር እንድሰማባት አልፈለገችም ማለት ነው…ስለዚህ ፈጠን ፈጠን ብዬ ወደፊት በመሄድ በመሀከላችን የነበረውን ርቀት አሰፋውት
===
❤️ፌናን
ይህ የተረገመ ልጅ በደቂቃዎች ነው ስሜቴን ያደፈራረሰው….ከአባቱ ጋር ያወራው ወሬ በራሱ ግርታ ፈጥሮብኛል በዛ ላይ የእሱ ለሴት ያለውን ዝቅ ያለ ግምት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አናዳጅ ሆኖ ነው ያገኘውት ..…እንደው ወንዶች ምንም ቢማሩ፤ ምንም ያህል ዘመናዊ ነን ቢሉ እብሪት አይለቃቸውም..ስሜቴን መደፍረስ ተከትሎ ዝም በማለቴ ለጠየቀኝ ጥያቄ በሰጠውት መልስ ለአባቴ እንድደውል ስልኩን ሲያቀብለኝ አላቅማማውም…ከእሱ ወደኃላ ቀርቼ አባቴን እያወራውት ነው…
‹‹እንዴ…አንቺው ነሽ ማሬ ..ስደውልልሽ እኮ ስልክሽ ይጠራል አይነሳም…ሳይለንት ላይ አድርገሽው ያላየሽው ነበር የመሰለኝ፡፡››
‹‹አይ አባ መኝታ ቤቴ ረስቼው ከልጆች ጋር ዞር ዞር እያልን ስለሆነ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ነው….በቃ ተዝናኑ ..››
‹‹እሺ አባ .ከመዝጋትህ በፊት ግን እማዬ ደውላ ነበር እንዴ?››
‹‹አዎ ምነው ማታ ደውላ ነበር››
‹‹ያለችህ አዲስ ነገር አለ?››
‹‹አዎ ከስድስት ወር ቡኃላ ለማድረግ ቀጠሮ ይዛበት የነበረው ወደ ሶስት ወር ዝቅ ብሎል..ከዛሬ ሶስት ወር ቡኃላ የልብ ቀዶ ጥገናውን ታደርጋለች..ስለዚህ ከዛ በፊት ከሀያ ቀን ቡኃላ ወደሀገር ቤት እንደምትመጣ ነግራኛለች..ግን ምነው..?የሰማሺው ነገር አለ እንዴ?››
‹‹አረ የለም ..እንዲሁ በህልሜ ስላየዋት ነው..በል አባ ቻው ..ደውልልሀለው..እና በጣም እድሀለው፡፡›› ስልኩን ዘጋውና ወደ እሱ ፈጠን ብዬ ሄድኩ…..
#ፍሰሀ
ስልኩን አናግራት ጨርሳ ስትመጣ ልክ ፍቅረኛዋን አናግራ እንደመጣች ነገር ነው ከጨገጋት ስሜት ወጥታ እየተፍለቀለቀች የመጣችው….ግን ፍቅረኛውን እንደሆነ ያናገገረችው በምን አውቃለው…››በውስጤ የተጫረ ጥያቄ ነበር..ደግሞ ወዲያውኑ ፍቅረኛዋንስ አናግራ ብትመጣ አንተ ምንህ ተነካ…..››እራሴን የጠየቅኩት ጥያቄ ነበር… አይ መነካት ሳይሆን ለምን ትዋሸኛለች ?››ለአዕምሮዬ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሞከርኩ..መጥታ ልጥፍ ስትልብኝ ሁሉንም እረሳውትና ጠረኗን እየማግኩ ውቡን ተፈጥሮ፤ የሚያማምሩ ወፎችን ዝማሬ ወደማዳመጥ ተሸጋገርኩ..
ታብራራልኝ ጀመር‹‹ይሄን ሀይቅ በበጋ ብትመጣ አሁን እንዲህ እንደምታዬው አታገኘውም…››
‹‹እንዴት?››
‹‹ይደርቃላ..ባዶ ይሆናል፡፡ከዛ የአካባቢው ሰዎች ለግብርና ስራ ይጠቀሙበታል ….ሽንኩርት፤ ቲማቲም ፤በቆሎ ጭምር ያመርቱበታል..ክረምት ሆኖ ዝናብ መዝነብ ሲጀምር ግን ከከተማው ሁሉ ተሰብስቦ የሚመጣው ጎርፍ ተጠራቅሞ የሚተኛው እዚህ ስለሆነ ተንጣሎ ይተኛል….የሚገርም ሀይቅ ይሆናል..ያንንም ተከትሎ ከዚህ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አህጉር አቋራጭ ወፍች ጭምር እንደምታየው መጥተው እዚህ በጊዜዊነት በመስፈር አካባቢውን የበለጠ ውብ ያደርጉታል….በዛ ላይ አዚህ አካባቢ ቆመህ ፊትህን ወደ ሀይቁ አዙረህ ማዶ አሻግረህ ስታይ የሚገርም የተፈጥሮ እይታ ነው አይንህን የሚሞላው…ያ ተራራ ይታይሀል..ኤረር ተራራ ይባላል፡፡አስር የአዲስአበባ ወጣት አቁመህ ኤረር ተራራ የት ይገኛል ብትል አንድ ሰው ብቻ ቢመልስልህ ነው…
‹‹እኔ እራሴ አላውቅም …››
‹‹ይሄ ተራራ እንደምታዬው አስደማሚ ሰንሰለታማ ተራራ ሲሆን ብቻው እንደሙዚዬም ሊጎበኝ ሚችል ታሪክ ያለው ነው፤በውስጡ ከ300 በላይ ዋሻዎች አሉት ፡፡ከዛም በላይ የአብረሀ አጽብሀ ቤተመንግስተ እና የልብነድንግል ቤተመንገስቶች ነበሩበት..አሁንም ፍርስራሹ ይገኛል…በዛ ላይ በጣም ብዙ ደብሮች በተራራው ላይ እንደነበሩ ታሪክ ይናገራል..ከዛም አልፎ የኢትዬጵያ ማዕከላዊው ስፍራ ወይም እንብርት ይሄ ተራራ እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ..ይሄም አንዱ ድንቅ ሚስጥር ነው፡፡አሁንም ከታሪካዊነቱ በተጨማሪ አካባቢው በአሁኑ ጊዜ በደን የተሸፈነ እና ለፍፁም መደመምና ከራስ ጋር ለመማከር ተመራጩ ቦታ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ከዚህ 9ኪሎ ሜትር ብቻ ብትሄድ ዝቋላ ገዳምን ታገኘዋለህ…ዝቋላ ስትሄድ ታራራ ታገኛለህ ፤
ሀይቁም ታገኛለህ..ሀይቁ የሚገርም ገበቴ ውስጥ ያለ የሚመስል ዙሪያውን በቄጤማ የተከበበ ነው፡፡አካባቢው ዙሪያውን በየአመቱ በሚነሳ ሰደድ

👍10❤3
እሳት ተቃጥሎ ተቃጥሎ የማያልቅ ደን አለበት..ያንን ገዳም የመሰረቱት ፃድቁ ገብረመንፈስ ቅዱስ ናቸው…ግን እንደማንኛውም ሌሎች ገዳሞች በአህመድ ግራኝ ጦርነት ጊዜ ወድሞ ነበር…..ከቆይታ ቡኃላ ግን ሳህለ ስለሴ ተመልሶ እንዲገነባ አድርገዋል፡፡ሚኒሊክም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲደራጅ አድርገዋል….እና ይህች ከተማ በውብ ሀይቆቾ እና በልዩ ተፈጥሮዋ ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ ስፋራዎችም ዙሪያዋን የተከበበች ነች…እና እነዚህን አንድ ላይ ማስተሳሰር ቢቻል ታዲያ አንደኛው ቱሪስት የሚፈስበት ስፍራ አይሆንም ትላለህ?፡፡››
‹‹ሚገርም ነው››
‹‹አዎ ባጣም የሚገርም ተፈጥሮ ››.
‹‹አይ ስለ ሀይቁ ወይም ስለነገርሽን ታሪካዊ ስፍራዎች አይደለም ማወራው….››
‹‹እና ስለምንድነው?››
‹‹ስለአንቺ ..በየቀኑ እያበሰልሺብኝ ነው የምትመጪው››
‹‹ስለእኔ እኮ ከመሬት ጀምረህ ነው…አንድ ኪቦርድ መጠቅጠቅ ብቻ የምትችል ቀንዝንዝ ወጣት ፀሀፊ..ለዛ ነው የአሁኑ መደነቅህ››
‹‹መሳሳሰቴን ተረድቼያለው…››
‹‹ጥሩ ነው..አሁን ይብቃን እንሂድ…ሚስትህም ከዚህ በላይ መጠበቅ የለባትም..እና ደገሞ ከእስታፍ ጋርም የምንቀላቀልበት ሰዓት እየደረሰ ነው››አለቺኝ
‹‹እሺ ብዬ ወደመኪናው አመራን..አዎ አራት ሰዓት የቁርስ ፕሮግራም አለን… ከስድስት ሰዓት እስከ አስራአንድ ሰዓት ግን ኩሪፍቱ እንሄዳለን ….በኩሪፍቱ ዝግጅት ብዙ ፕሮግራሞች አሉ ሰራተኞች የሚሸለሙት በዛ ፕሮግራም ላይ ነው..የተቀያየሙ ካለ የሚታረቁት በዛ ፕሮግራም ላይ ነው….የዚህ ዓመታዊ በዓል ዋናው ፍሬ ቁምነገሩና ከሰዓት በመዝጊያው ፕሮግራ ሚከወነው ነው፡፡እና እወነቷን ነው..ገና ረጅም ቀን ነው የሚጠብቀን….
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

❤1👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
❤️ፌናን
ህይወትን እንደፈለገው ያሽከረከራት ጀግና ማን ነው….….?ለሆነ የተገደበ ጊዜ አይደለም…ለሆነ ዓመታትም ብቻ ማለቴ አይደለም..የእድሜ ልክ የህይወት ዘመኑን በሙሉ ህይወትን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ እያሾራት ያለው ወይንም ከታሪክ ማህደር ውስጥም ቢሆን እደዛ አድርጎ በፈለገው አይነትና ሁኔታ እስከወዲያኛው በመኖር የተሳካለት ማነው…….?አይ ሕይወትማ እንዲህ ልፍስፍስ አትመስለኝም… ፡፡በቃ እንዲህ እንደዋዛ በቀየስንላት መንገድ የምትጓዝ ወይም በቀደድንላት ቦይ የምትፈስ አይደለችም ..::እኛ በእሷ ላይ ባለን ፍላጎት ልክ እሷም ራሷ በእኛ ህይወት ላይ የሆነ መርምረን ልንደርስበት የማንችለው ስውር ሚስጥራዊ ፍላጎት አላትና …እኛ በህይወት ላይ ያለን ፍላጎትና ህይወት በእኛ ላይ ያላት ፍላጎት አንድ አይነት በሚሆንበት ጊዜ መንገዳችንም አንድ አይነት መነሻ እና ተመሳሳይ መዳረሻ ይኖረዋል ….እናም የኑሮ መስመራችን አልጋ በአልጋ የሚባል አይነት ስያሜ ይሰጠዋል..፡፡ይህ ግን ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የሚከሰት አይደለም ፤የእኛ ፍላጎት እና ህይወት እየፈሰሰችበት ያለበት መስመር ብዙ ጊዜ ተቃራኒ መስመርም ስለሚይዝ ብዙዎቻችን ሁለት ምርጫ እንመራጣለን፡፡ አንድም የራሳችን የውስጥ ፍላጎትና ብቻ በማዳመጥ ሕይወት በተቃራኒው እየተጓዘች እደሆነ ብናውቅም ትግላችንን መቀጠል..ብንቆስልና ብንላላጥም ከዛም እልፎ እስከሞት የሚያደርስ መከራ ቢገጥመንም እስከመጨረሻዋ እስትንፋስ መፋለም …ሌሎቻችን ደግሞ ፍላጎታችንና ከህይወት ተቃራኒ መሆኑን በተረዳን ጊዜ ቆም ብለን በማሳብ እንዴት ነው የእኛ ፍላጎት ውጤታማ የሚሆንበት መንገዱ በዚህ ቢሆንም ህይወት ግን እየወሰደችን ያለው በዚህ ነው…እና ህይወት መንገዷን በእኛ ፍላጎት እስክታስተካክል ድረስ ፍሰታችንን ከእሷ ፍሰት ጋር አስተካክለን እንዴት መጓዝ እንችላለን..….?የእኛ ቀን እስኪመጣ ከእነ አቋማችን መቆየት ስለሚገባን ሳንቆስል ፤ ሳንላላጥና ስንሰባበር ለመቆየት ህይወት እስከ አስገደደችን ድረስ በማፈንፈልገውም መንገድ ቢሆን መጓዝ ብልህነት ነው በማለት ሁለተኛው መንገድ ይመርጣሉ….እና የትኛው ነው የተሸለ ዘዴ ….?የሚለው አጠያያቂ መልስ ነው ያለው….
ህይወትን እንደ ወንዝ ቁጠሩት ..እዛ ወንዝ ከመግባታችሁ በፊት ወንዙ በስክነት የሚፈስ የረጋ መሆኑን ስላያችሁ በቁጥጥራችሁ ውስጥ እደሚሆን ገምታችሁ ለመዋኘት ወደ ውስጥ ትገባላችሁ…ከዛም እንደ እናንተ ፍላጎት ስትፋልጉ ከወንዙ ፍሰት በተመሳሳይ አቅጣጫ በቀላል ጉልበት ወይንም ትንሽ ተጨማሪ ጉልበት በማውጣት ከወንዙ ፍሰት በተቃራኒ ወደላይ እየዋኛችሁ እያላችሁ ድንገት ሳታስቡት ደራሽ ወንዝ እየተስገመገመ ስራችሁ ቢደርስ ምንድነው ምታደርጉት..?ጥያቄው ያ ነው፡፡ በጀመራሁት መንገድ ከፍሰቱ በተቃራኒ መዋኘታችሁን ትቀጥላላችሁ ወይስ አቅጣጫ ትቀይራላችሁ…..?ውሳኔያችሁ በጽናት ወደፊት ለመሄድ ከሆነ ያንን የሚያስገመግም እየተገለባበጠ የሚመጣ ማዕበል እየሰነጣጠቃችሀ ወደፊት የምትቀጥሉበት በቂ ኃይል አላችሁ..? ማዕበሉ ይዞ እያገላበጠ የሚመጣቸውን ግንድና መሰል ባዕድ ነገር ጋር የሚፈጠረውን መጋጨትና መላተም ተቋቁማችሁ ለመዝለቅ ጉዞችሁን ትቀጥላላችሁ ..? ወይስ የትም ይወሰደኝ የትም ቢያንስ ድንገተኛው ደራሽ እስኪቀንስ ድረስ በህይወት መቆየት የምችለው ከፍሰቱ ጋር አብሬ በአንድ አይነት አቅጣጫ ስፈስ ነው፤ለዛም እንዲያግዘኝ አንድ ግንድ ጉማጅ ላይ ተጠምጥሜ የወሰደኝ ድረስ መሄድ አለብኝ ማዕበሉ እስኪቀንስ ወይም ወደ ዳር እስኪተፋኝ መታገስ ነው የሚጠቅመኝ ብላችሁ ያንን ታደርጋላችሁ …...?እንግዲህ በደራሽ ውሃ በሚናጠው ወንዝ መሀከል ሆኖ ከፍሰቱ በተቃራኒ አቅጣጫ መጓዝ መሞከር መጋጋጥን፤ በግንድ መገጨትን ፤ብሎም ሞትንም ጭምር የሚያስከትል ቢሆንም የወንዙ ፍሰትን ተከትሎ መጓዝም የት ድረስ ..?ለምን ያህል ጊዜ..? ይዞን እንደሚጓዝ ስለማናውቅ የማናውቀውና ዓለም፤ የማናውቀው ሀገር ድረስ መጓዝና፤ በማናውቀው ኑሮ ውስጥ ተጠምዶ መጣልን ሊያስከትልብን ይችላል……
ይሄ ሁሉ ምቀበጣጥረው ቸግሮኝ ነው…የቸገረኝ ከዚህ ፍሰሀ ከሚባለው ልጅ ጋር ሳላስበው ቀስ በቀስ እየሰመጥኩበት ያለው ውስብስ ጉዳይ ነው…እርግጥ እኔ እና እሱን ያገናኘችን ህይወት ነች..ምን ማለቴ ነው..? ሁሉንስ ሰው የምታገኛኘውም የምታለያየው ያቺው የህይወት አጋጣሚ አይደለች....?..ለማን
ኛው ከቢሾፍቱ የካማፓኒውን ዓመታዊ በዓል ከተመለስን አስር ቀን አልፎናል…በአስር ቀን ውስጥ ብዙ ነገሮች ሆነዋል…..ያው መቼስ ወደ ስራዬ እንደምመለስ ትገምታላችሁ..አዎ ተመልሼያለው ፡፡ለዛው በተለየ የስራ ዘርፍ…፡፡.አሁን በዋናነት እየሰራው ያለውት ግን እሱ ለረጂም ዓመታት የዚህ ካማፓኒ ስራ አስኪያጅ ለመሆን የሚያስችለውን ድምጽ ለማግኘት እያዘጋጀው ያለውን ፕሮፕዛል በረዳትነት ማገዝ ነው..በረዳትነት ያልኳችሁ እዲሁ ለእሱ ሞራል ነው እንጂ አብዛኛውን ስራ እየሠራው ያለውት እኔው ነኝ..እርግጥ ሙሉ ቀኑን አንዳንዴም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት እና አራት ሰዓት ድረስ ፊት ለፊት ተፋጠን ስንጨቃጨቅ ፤በሀሳብ ስንከራከተር ፤አንዱን ሀሳብ ስናፈርስ ደግሞም ሌላውን ስንገነባ ነው ውለን የምናመሸው……
በዚህ አስር ቀናት ውስጥ ከምነግራችሁ በላይ ተቀራርበናል…ከመቀራረብም አልፈን ተለማምደናል… ተለማምደናል ማለት ግን ምን ማለት ነው…?መለማመድ በጥልቀት ስሜትን መጋራትን የሚያመለክት ቃል ይመስለኛል…የግንባሩን ቋጠር ፈታ አይቼ ምን እየተሰማው እንዳሆነ ማወቅ ችላለው…..ሲፈግግ እንዴት ነው የፈገገው… ..?የሚለውን በማየት የደስታ መፍገግ ነው…....?የሽሙጥ ነው…...?የቅሬታ ነው…...? መተንተን ጀምሬያለው…እሱም እንደዛው ይመስለኛል፡፡ግን ችግሩ የዚህ ነገር ማብቂያው የት ነው የሚለውን መገመት አለመቻሌ ነው…?ለመሆኑ መጨረሻ አለው ወይ..? የሚለውም እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም ….ሁኔታዎች ወደ ወሰዱን ዝም ብለን እንሄዳለን ወይስ ከሁኔታዎች ጋር በመቃረን የየግላችን መዳረሻ በማሰብ እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንገባለን….
ይገርማችሆል !!አሁን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አልፎል… ግን ቢሮ ነኝ ያለውት …እርግጥ አጠገቤ የለም ምንአልባት ወደ መጽዳጃ ቤት መሰለኝ የሄደው…. ወጣ ባለበት ሰዓት ነው እያወራዋችሁ ያለውት… ቆይ ምን እንኳን ለስራ ቢሆንም እስከዚህን ሰዓት ድረስ ስትቆዩ አንቺስ እሺ ይሁን አባትሽን አስረድተሸ ካሳመንሺው ሌላ ችግር የለብሽም… እሱ ግን ፍቅረኛው እንዴት ነው ይሄን ያህል ክፍተት ልትሰጣችሁ የቻለችው..? ካላችሁኝ ስለእሷ ልነግራችሁ የሚገባኝ ነገር አለ….የዛን ቀን ትዝ ይላችሆል አይደል....?ከእሱ ጋር ስንቀዠቀዥ በለሊት ልብሴ ተያይዘን የወጣን ቀን…ተመልሰን ሆቴላችን ስደርስ ሶስት ሰዓት ሆኖ ነበር…መኪናውን በስርዓት አቁመን ወርደን ጎን ለጎን ወደመኝታ ቤታችን እየሄድን ሳለ ፍቅረኛ የሆቴል በረንዳ ላይ ሆና ስጠብቀን ነበር ላካ..ተንደርድራ ፊታችን ገጭ…. ገና ወደ እኛ እየተንደረደረች ስትመጣ ሳያት ሁኔታዋ ጥሩ እንዳልሆነ ስለተረዳውና ስለከበደኝ ቶሎ ብዬ በፍቅራኛዋና በእኔ መካከል ያለውን ክፍተት ፈንጠር ብዬ በማስፈት እርምጃዬን ሽሽት በሚመስል መልኩ ሳራዝም …..አጅሪት እሱን ጥላ ወደእኔ በመንደርደር ፊቴ ገጭ ብላ አስቆመችኝ…
‹‹ምነው የወንድ ችግር አለብሽ እንዴ..?››ቀጥታ እንዲሁ ነው ያለቺኝ
‹‹ምን እያልሽ ነው..?››
‹‹በውድቅት ለሊት ፍቅረኛዬን ከጉያዬ ሰርቀሽ በመውሰድ ለምነሽ

👍1
አብረሺው ትሸረሙጪያለሽ…?›› ሰቅጣጭ ቃለት ነው ከአንደበቷ የሚወጣው … በዛ ላይ ሰውነቷ ሁሉ ይንቀጠቀጣል….ግን እዚህ ጋር ሁል ጊዜ ስለ እንደዚህ አይነት ጉዳይ ሳስብ ግራ ሚገባኝ አንድ ሴት ፍቅረኛዬ ማገጠብኝ ብላ ስትገምት ከራሷ ፍቅረኛ ጋር መጣላትና መነጋገር ሲገባት በምን ስሌት ነው አማጋጭ ከምትባለዋ ሴት ጋር መጣላቱን የምትመርጠው…...?ውልም ሆነ ቃል ያላት ከራሷ ጓደኛ ጋር እንጂ ከማታውቃት ሴት ጋር አይደለ…..?መቼስ አንድን ወንድ በውስጡ መጀመሪያውኑ ለመሳሳት የተዘጋጀ አድፋጦ የሚጠብቅ ስሜት ከሌለው በስተቀር እንዲሁ አንድ ሴት ስለሳቀችለት ብቻ ተንደርድሮ ወደ መማገጥ አይገባም….እንደ እኔ የሴት ፈገግታም ሆነ የመጠጥ ስካር ምክንያት ብቻ ናቸው….፡፡
እሱ የሚያደርገው ግራ ገብቶት ከኃላዋ እየጎተተ አደብ እንድትገዛ እኔን ትታ ከእሱ ጋር እንድትነጋገር ይማፀናታል፡፡ያም ሆነ ይህ እኔ ስሜቷን ስለተረዳውና ያደረኩትም ነገር ትክክል አለመሆኑን ስለተሰማኝና በውስጤም ፀፀት ነገር እየጠዘጠዘኝ ስለነበር እስከመጨረሻው ልታገሳት ወስኜያለው…
‹‹‹ይቅርታ ነገሩ እድምታስቢው አይደለም…በመካከላችን ምንም እንደዛ አይነት ነገር የለም..ሊኖርም አይችልም… ቢሆንም አጥፍተናል .. አንቺን አስፈቅደን ነበር መሄድ የነበረብን››አልኳት በተለሳለሰ ድምፀት
‹‹ምን ?ከፍቅረኛሽ ጋር ልተኛ ብለሽ ነው ፍቃድ የምትጠይቂኝ…..?ትንሽ እንኳን እንጥፍጣፊ የሴትነት ክብር በውስጥሽ የለም…ቆይ እንደውም ››አለችና በአንገቷ ካንጠለጠለችው ግብዳ ቦርሳ ውስጥ ሌላ አነስታኛ ቦርሳ በማውጣት ከፈተችና ድፍን መቶ ብር በማውጣት ‹‹ እንቺ ….ይሄ ከፍቅረኛዬ ጋር ለተኛሺበት ክፍያ ነው…ስላስደሰትሺልኝ ክፍያው ይገባሻል… ይሄን ተቀበይና ሁለተኛ ግን እኔ ስላለውለት ስሩ እንዳትደርሺ›› አለቺኝ….
የዚህን ጊዜ የሆነ ነገር አዕምሮዬን ወጋኝ…ጠቅ …. ትግስቴ አለቀ…እኔ ደግሞ ትግስቴ ሲሟጠጥ እንደሰው መጮህ ወይም መንፈራገጥ አይሆንልኝም… በተቃራኒው ፀጥ ነው የሚያደርገኝ….በፀጥታ የታጠረ ፍጽም እርጋታ እላበሳለው…እኔን ለማብሸቅ ብላ የዘረጋችውን ብር ከእጇ ላይ መንጭቄ ተቀበልኳት….እና ከመሀከላችን ገፍተር አድርጌ እሷን ካወጣዋት ቡኃላ ወደእሱ በመቅረብና እላዩ ላይ በመለጠፍ ቲሸርቱን ጨምድጄ ወደ እኔ አስጎነበስኩትና ከንፈሩን በከንፈሬ ጎረስኩት…ለአራት ወይም ለአምስት ሰከንድ ያህል ይመስለኛል መጠጥኩት… ሰው እስኪሰበሰብ እሪ ብላ ጮኃች ….የቀራት እርግማንና ስድብ የለም…..
እሱ በሁለት ያበዱ ሴቶች መካከል ሚካሄደው ተውኔታ መሳይ ጦርነት አፈዝዞት ደንዝዞል…‹‹አሁን ለከፈልሺኝ መቶ ብር ተገቢውን አገልግሎት ለፍቅረኛሽ ሰጥቼልሻለው....ሌላ ጊዜም የምትከፍይኝ ከሆነ በተሸለ መንገድ አስደስትልሻለው…ቻው›› ብያት እዛው እሱም እንደደነዘዘ እሷም በሰው ተከባ እየጮኸች ባለችበት ጥያቸው ወደመኝታ ክፍሌ….
ከዛ ቡኃላ እሷ ወዲያውኑ ወደአዲስ አበባ የተመለሰች ይመስለኛል..በቁርስ ፕሮግራም ላይ ሁለቱም አልተገኙም ነበር፤ በኩሪፍቱ ፕሮግራም ላይ ደግሞ ብቻውን ነበር የመጣው…
ያ ክስተት ከተከሰተ አስር ቀኑ ነው እስከዛሬ ስለእዛ ቀን ሆነ ስለፍቅረኛው አንስተን አናውቅም….ግን እስከአሁን ጣዕሙ ይሰማኛል…የምኑ..? የከንፈሩ ነዋ…፡፡አዎ ከንፈሬ ላይ ታትሞ ቀርቷል… እና ትዝ ባለኝ ቁጥር ከንፈሬን በገዛ ከንፈሬ በመምጠጥ በምናቤ ወደ እዛች ቀን በመሄድ አጣጥመዋለው…አዎ ሙቀቱ እስከዛሬ ይሰማኛል..ከንፈር እንዲህ እንደጋለ ምጣድ ይሞቃል እንዴ…..?የሚጣፍጥ ቃጠሎ ነበረው…...?
ውይ በቃ መጣ …
‹‹እንዴ ምንድነው..? ››ዘበኛውን መአት ዕቃ አሸክሞ መምጣቱ ገርሞኝ ነበር የጠየቅኩት….. የእኔን ጥያቄ ችላ ብሎ ‹‹እዚህ ጠረጳዛ ላይ አስቀምጠው..››አለውና እንዲያስቀምጥ ካደረገው ቡኃላ አመስግኖት በእጁም የሆኑ ብሮችን አስጨብጦ ሸኘው…..
ምግብ ….ወይን ጠረጴዛ ላይ አስተካክሎ ያዘጋጀው ነበር…
‹‹ምንድ ነው..?››መልሼ ጠየቅኩት
‹‹ሆቴል ሄደን እራት እንብላ ብልሽ እንደተለመደው ግግም ማለትሽ አይቀርም ..ካንቺ ጋር እራት ለመብላት የመጣልኝ ይሄ ዘዴ ብቻ ነው….በዛ ላይ ርቦኛል››
‹‹ምግቡስ ይሁን ወይኑ ምን የሚያደርግ ነው ..?…አንድ ካምፓኒውን በጥልቅ ተሀድሶ አፈራርሶ በአዲስ መልክ ለማነጽ ደፋ ቀና ለሚል ተራማጀ አለቃ ረዳቱን ለዛውም ቢሮ ውስጥ ወይን በማጠጣት ለማስከር መሞከር አግባብ ነው…..?››
‹‹ አሁን ቀልዱን አቁሚና ላፕቶፕሽን ዘግተሸ እጅሽን ታጠቢና ቅረቢ… በዛው ብርጭቆ አምጪልን›› አለኝ….ተነሳውና እንዳለኝ አደረጌ ወደ ምግቡ ስቃረብ ከመቀመጤ በፊት ደማቅ ቀይ ፅጌረዳ አበባ ከጠረጰዛው ላይ አንስቶ አስታቀፈኝ
‹‹እንዴ !!ምንን አስመልክቶ ነው..?››ውስጤን የተሰማኝን ደስታ ለመቆጣጠር እየሞከርኩ ጠየቅኩት…
‹‹ያው ጓደኝነታንን በማስመልከት…ከልብሽ በቅንነት ሰውን ለመርዳት ወደኃላ የማትይ የስራ አጋሬ መሆንሽን በማስመልከት››አለኝ ኮስተር ብሎ
‹‹እንደዛ ከሆነ ነጭ ቢሆን ይሻል ነበር››
‹‹ምኑ..?››
‹‹የአበባው ቀለም…ቀይ-የሚያስጨንቅ ወይም ትንፋሽ ሚያሳጥር ፍቅርን መግለጫ ነው፡፡ነጭ ቢሆን ግን ታማኝነትን እና ቅንነትን መግለጫ ስለሆነ ስለእኔ ያልከኸውን በትክክል ይገልጽልህ ነበር፡፡ ወይም ቢጫ ብታደርገው ጓደኝነትን ስለሚገልጽ የተሻለ ነበር..ሮዝ ደግሞ ጥልቅ ስሜትንና ኃይልን መግለጫ ነው… ለወደፊቱ አበባ ስጦታ ስትሰጥ ከሚሰጠው ትርጉም ጋር አቆራኝተህ እንድታደርገው ነው ማብራራልህ…እርግጥ ብትሳሳትም አልፈርድብህም ምክንያቱም ላፈቀሩት አበባ መስጠት የእኛ ባህል አይደለም …ግን ስንኮርጅ ያው በትክክል ከነትርጉሙ ቢሆን አሪፍ ነው ለማለት ያህል ነው፡፡ለተጨማሪ ዕውቀት የጥንት ግሪካዊያን አፍቅሬሻለው ሊሉ ሲፈልጉ ትኩስ የተቆረጠ አፕል ነበር በስጦታ ልባቸውን ለሰረቀቻቸው ውብ ሚያበረክቱት..ያው እንደሚታወቀወ አፕል ተቆርጦ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ እነሱ የፍቅር መግለጫ አድረገው ይገለገሉበት ነበር…አንተም ምን አልባት አንድ ቀን እኔን ተሳስተህ የምታፈቅረኝ ከሆነ ያንን ስሜትህን ለማስረዳት ብዙም አትቸገር አንድ ሶስት ኪሎ አፕል እቤቴ ድረስ ከላክልኝ ይገባኛል….
‹‹ልትበይው ነው ወይስ ለሰፈራችሁ ሰዎች ሁሉ ልታድይው….ለማንኛውም መቼም ምሳሳት አይመስለኝም…አሁን እራቱን እንጀምር ››አለኝ
…. ተስማምቼ እየተጎራረስን በላን…..ወይኑን ግን ከእራትም ቡኃላ ስራ እየሰራን ቀጠልንበት..እርግጥ እልዋሻችሁም የወይኑ ጠርምሱ ግማሽ ድርስ እስኪደርስ ብቻ ነበር ስራችንን መቀጠልን የቻልነው…. ከዛ ላፕቶፓችንን አጠፋፍተን እና ዘጋግተንና የእንግዳ ማረፊያ ሶፋ ላይ ጎን ለጎን በመቀመጥ ዘና ባለ ስሜትም እያወራን ነበር የጠጣነው…እና በዚያን ጊዜ ምን አወራችሁ …...?ምነስ የሆነ ዓዲስ ነገር አለ …..?ካላችሁኝ ያስታወስኩትን ያህል እንግራችሆለው

👍4
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍሰሀ
===
መቼስ ያለውበትን ሁኔታ በጥቂቱም ቢሆን ግንዛቤው ይኖራችሆል ብዬ አስባለው፡፡ለዚህ ለዓላማዬ መሳካት ቁልፍ ለሆነው የፕሮፖዛል ዝግጅት ሙሉ ጊዜዬን ሰጥቼ ጠብ እርግፍ እያልኩ ነው….በሌላ ጎን ደግሞ ይህቺ ፌናን የምትባል ልጅ እራሷን የቻለች የቤት ስራ ሆናብኛለች፡፡በቃ የሆነ ነገር ሳታውቁት ከቁጥጥራችሁ ውጭ በሆነ ስሜት ስተት ብሎ ከደምስራችሁ ጋር በመስረግ በመላ ሰውነታችሁ ጋር ተዋህዶባችሁ ያውቃል…በቃ ልቤ ላይም ፤ አዕምሮዬ ውስጥም፤ እታች የእግሯቼ ጥፍሮች ላይም በእኩል መጠን ያለች ነው የሚመስለኝ..፡፡እንደእዚህ እንዴት ሆነ ……?አላውቅም….፡፡በቃ አፍቅሬያታለው፡፡ማፍቀሬን ደግሞ በውስጤ ስላፈንኩት እየተጎዳው ነው...ህመሙ ልቤ ስር እስኪሰማኝ ድረስ የተጎዳውበት ነው….
ስራውን በተመለከተ ረዳቴ ሆና በጣም እያገዘቺኝ ነው..እርዳታዋ በጣም ጠቃሚና ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳ እራሴን እስክታዘብ ድረስ ነበር ስደመምባት የነበረው፡፡ ….አሁን ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ ያለው ፕሮፖዛል እሷ ባታግዠኝ ኖሮ በራሴ እሰራው ከነበረው ጋር በሀሳቤ ሳመዛዝነው ደነግጣለው..፡፡ልጅን እንደ ቁጥር አንድ ጀግና በሚያስበው አባቴ ፊት ተዋርጄ ነበር…፡፡አሁን ግን እድሜ ለፌናን አይደለም ከአንዲት ልምድ አልባ ወጣት ሴት ጋረ ይቅርና ከማንም በስራው እድሜ ጠገብ ልምድ ያለው ሰው ጋር ተወዳድሬ ቦታውን በእጄ ማስገባት እችላለው፡፡፡የዛን ያህል በራሴ እንድተማመን አድርጋኛለች ፡፡አሁን በዛ እርግጠኛ ሆኜያለው ፤ ይገርማችሆል ፌናን ጭቅጭቆ እራሱ ሱስ ይሆንባችኃል…….አሁንም ቢሮ ጭቅጭቅ ላይ ነን፡፡ ስለዚሁ የፕሮፖዛል አንዱ ክፍል የሆነ የሰራተኛ ደሞዝን በተመለከተ እየተነጋገርን ነው…
‹‹አሁን ለሰራተኟች እየተከፈለ ያለው ደሞዝ መስተካከል አለበት ..››የሚል ሀሳብ አቀረበች
ወዲያው ነው የተቃወምኳት‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ……?በተመሳሳይ የስራ መደብ በመንግስት ቤት ከሚከፈላቸው ሰራተኞች ጋር ሲነፃፀር ቢያንስ አርባና ሀምሳ ፐርሰንት የእኛ ጭማሪ አለው..እና በዚህ ላይ አሁን በምናደርገው ማሻሻያ ላይ የ5 ፐርሰንት ጭማሪ ማድረጋችን በጣም ምክንያታዊና በቂ ነው ብዬ አስባለው፡፡››
‹‹አልስማማም..››አለቺኝና ንግግሯን ማብራራት ቀጠለች‹‹ይሄውልህ በመጀመሪያ ደሞዝን በተመለከተ የመንግስትን እስኬል ማነፃፀሪያ ማድረግ ትክክል አይመስለኝም፡፡››
‹‹ለምን ………..?መንግስት እንደዛ ለምን እንደሚከፍል ታውቂያለሽ ፡፡ሀገሪቱ ደሀ ስለሆነች ነው፡፡እኛም ደግሞ መክፈል ሰለቻልን ብቻ ዝም ብለን መክፈል የለብንም ….ገበያውን ማበላሸት ነው የሚሆነው››
‹‹ላስቁምህ..ይህቺ ገበያውን ማበላሸት ነው የምትለው ቀሺም ምክንያት ነች ..እዚህ ሀገር ላይ የሰው ጉልበት ዋጋን በተመለከተ በጣም የተዛባ አመለካከት አለ…መንግስት ሀገሪቱ ደሀ ስለሆነች ከዚህ በላይ የተሻለ ደሞዝ መክፈል አልችልም ይላል..ግን እውነቱ ያ ብቻ ይመስልሀል…?፡፡እንደእኔ ግንዛቤ ዋናው ችግሩ ያመለካከት ነው……በየመስሪያ ቤት በቋሚ እና አላቂ ንብረቶች ላይ የሚከሰትን ብክነትና ብልሽትን የተወሰነ ግንዛቤ በመፍጠር እና የተወሰነ የጥንቃቄ እርምጃ በማድረግ ለዓመታዊ ዕቃ ግዢ የሚወጣውን ወጪ በ50 ፐርሰን መቀነስ ብንችል ከዛ በተገኘ ገንዘብ ቢያንስ የእያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ላይ የ25 ፐርሰንት የደሞዝ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለህ ታስባለህ…?.ባለስልጣኗች በሙስና የሚቀራመቱትን ገንዘብ የተወሰኑ ክፍተት ያላቸውን አሰራሮች በማሻሻል እና የተወሰነ ቁጥጥር በማድረግ ቢያንስ 50 ፐርሰንቱን ማስጣል ቢቻል የሰራተኛውን ደሞዝ 200 ፐርሰንት ማሳደግ አይቻልም ትላለህ…?የተቀላጠፈ የስራ ቢሮክራሲ ተፈጥሮ የእያንዳንዱን ሰራተኛ የስራ ውጤታማነትን በተወሰነ ስልተና እና ማነቃቃት በአንድ እጥፍ ማሰደግ ቢቻልና አጠቃላይ የሀገሪቱን ዓመታዊ ምርታማነትን የእውነት 11 ፐርሰንት ማሳደግ ማይቻል ይመስልሀል? እንደዛ ከሆነ ድግሞ በየአመቱ ስንት ፐርሰንት ለሰራተኛ ደሞዝ መጨመር ይቻላል…?አየህ የሀገሪቱን የድህነት ችግር ለመቅረፍ እየሞከርን ያለነው በተሳሳተ የድህነት አመለካከት ነው….
‹‹እኔ እንጃ የምትያቸውን ነገሮች በቀላሉ ማድረግ ይቻላል የሚለውን መቀበል ይከብደኛል››አለኳት…
ተቃውሞዬን ችላ ብላ ቀጠለች‹‹አንዳንዴ ይገርመኛል አንድ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ስንት እና ስንት ለሀገር ደህነንነት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዩችን ሲዳኝ ውሎ፤ የሚሊዬን እና ቢሊዬን ሙስና ወንጀሎችን ሲመረምር ቆይቶ ወደቤቱ የሚወስደው አንድ ቪትስ መኪና እንኳን አጥቶ በታክሲ ሰልፍ ይዞ እየተጋፋ ወይም በባስ ታጭቆ እየተንገላታ ወደቤቱ ሲሄድ የሚፈጥርበት ስሜት ይታይህ…ይሄ ሰው የሚከፈለውስ ደሞዝ ስንት ነው…?ልጁ ቢታመምበት የግለሰብ ሆስፒታል ወስዶ ማሳካም አቅም ይኖረዋል ወይ ….?እና ሄዶ ሄዶ ሙስና ውስጥ ሳይገባ ምን የህል ጊዜ በጽናት መቆየት ይችላል …?በእሱ ላይ የሚመጣውን የድህንት ችግር መታገስ አለበት ብለን እንፍረድበት በልጁ ላይስ ሲሆን …?ክፋቱ ደግሞ ማንም ሰው ለወቅቱ የሚያስፈልገውን ለችግሩ ሚበቃውን ያህል ብቻ ዘርፎ አያቆምም..፡፡አንዴ መዝረፍ ከተጀመራ ሱስ ነው የሚሆነው…ለዛውም አደገኛ የሀሽሽ ሱስ አይነት …፡፡ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ማሟላት ያቃተው ዳኛ ዘራፋ ሲጀምር…ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ማሟላት ያቃተው መሀንዲስ መዝርፈ ሲጀምር…. ለመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ማሟላት ያቃተው የባንክ ማናጀር መዝረፍ ሲጀምር ..ሀገር ሁሉ በዘራፊዎች መነኸሪያ ሆና ታርፈዋለች….. በጣም የሚያስጠላው ደግሞ መዝረፍ ውስጥ የገባ ሰው በዘረፋው ብቻ አይደለም ሀገሪቱን የሚጎዳው የስራ ሞራሉም ቀን በቀን አየወረደ ስለሚመጣ ነው…ተጫሪ ገንዘብ በቀጥታ ለኪሱ የሚያስገባለት ገንዘብ የማያገኝበትን ስራ ዞር ብሎ ለማየት ፍላጎቱ ወደ ዜሮ እየተንደረደረ ይሄዳል …
አሁን እኮ ለሙሰኞችና ቀማኞች ይቅራታ እንዲባሉ ምክንያት እየሰጠሽላቸው ነው››
በፍጽም እንደዛ አይደለም ..ምንም ሳይቸግረው በስነምግባር ጉድለትና በስግብግብነት በሽታ ብቻ በመጠቃታቸው በሙስና የሚጨማለቁ ቡዙ ዜጎች እንዳሉ አውቃለው…ግን ሳይፈልጉ ችግርና እጦት አንደርድሮ እዛ አዝቅጠት ውስጥ የጨመራቸው የመንግስት ሰራተኞች ቀላል ቁጥር የላቸውም እያልኩህ ነው…እንደዚህ አይነት ሰዎች ደግሞ አንድ ንጽህ ህሊናቸው በሆነ ምክያት ከጨቆየ ይሰባራሉ… በራሳቸውም ስለሚያፍሩ ብኩን ዜጎች እንደሆኑ ይቀራሉ..እያወራውልህ ያለውት ስለእነዛ ሰዎች ነው..በነዛ ጠቃሚ ሰዎች ውድቀት መንግስት የደሞዝ ክፍያ ስርዓትና አሰስተሳሰብ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ፡፡እያልኩህ ነው…
‹‹ቆይ…. እንደምታውቂው የሰው ልጅ ፍላጎት ማብቂያ የለውም፡፡የሆነ ነገር በሰጠሸው ቁጥር ሌላ ተጨማሪ ነገር ይጠይቅሻል..ታዲያ ምን ያህል ቢከፈል ነው በቂ ሚባለው?፡፡››
‹‹ለችሎታውና ለአገልግሎቱ የሚመጥነውን ቢያንስ ዝቅተኛውን ክፍያ ማግኘት አለበት….አንድ ምሳሌ ልስጥህ በመዘጋጃ ቤት የሚሰራ መሀንዲስ 5 ሺብር ደሞዝ እየተከፈለው የሀምሳ ሚሊዬን ብር ባጀት ያለው ሰማይ ጠቀስ ህንፃ እንዲቆጣጠር ይመደባል…. እና መንግስን ወክሎ ባለሀብቱ በተሰጠው ቦታና በፀደቀለት ዲዛይን መሰረት ህንጻውን እየገነባ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚሰማራበት ጊዜ ያገኘውን ስህተት ለባለቤቱ ተናግሮ የማሳገጃ ትዕዛዝ ሊፅፍ ሲል ባለሀብቱ 20 ሺብር ማለት የአራት ወር ደሞዙን በአንድ ቀን ቢሰጠው አልፈልግም ለማለት የሚያስችል ስብዕና ጽናት ከመቶ ሰው

መካከል በአንድ የሚገኝ ይመስልሀል…?ምክንያቱም ይሄ መሀንዲስ መጀመሪያውኑም እዛ ቦታ የገባው እስኪነቃበት እንዲህ አይነት ገቢዎችን በሙስና ለመሰብሰብ ነው…..በማንኛውም ሰአት ቢባረር የሚያጣው ደሞዝ የሚያስቆጭ አይደለም…ደሞዙ አስራአምስትና ሀያ ሺ ብር ቢሆንስ ያለኝ ይበቃኛል የሚሉት ከመቶ ሀማሳ ፐርሰንት ወይም ከዛ በላይ ይሆናል…፡፡ያን ያህል ስራውን በትክክል የሚሰራ በተቋሙ ውስጥ ከተገኘ ደግሞ የሌሎቹንም አጥፊዎች ጥፋት ለማረምና በጊዜ ለማጋለጥ የተሻለ ዕድል ይኖር ነበር…በዚህም ምክንያት መዘጋጃው በየወሩ ሚሊዬን ብር የሚያወጡ የሚባክኑ መሬቶችና መሰል ዘረፋዎችን ማዳን ይችል የነበረውን ቢያንስ ዝቅተኛውን ተገቢ ደሞዝ ለመክፈል ባለመቻሉ በብዙ እጥፍ ንብረትና መሬት ያዘርፋል፡፡…በዛ ላይ ጥሩ የሚከፍል አካል በጣም ጥሩና ተፎካካሪ ግለሰቦችን ወደራሱ መሳብና ያሉትንም ማቆየት እድሉ ሰፊ ነው፡
‹‹እና ምን እያልሺኝ ነው››
‹‹የምትከፍለው ደሞዝ ሳይሆን ሊያሳስብህ የሚገባው እንዴት እያንዳንዱን ሰራተኛ አሁን ካላቸው ውጤታማነት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ እችላለው የሚለውን ነው…በተለይ ጎበዝ እና ውጤታማ የሆኑት ላይ በማተኮር››
‹‹አልገባኝም››
‹‹አየህ ብልጥ የስራ መሪ አብዛኛውን ጊዜውን የሚያጠፋው በጣም ውጤታማ እና ታታሪ በሆኑት ሰራተኛች ላይ ነው..እናሱን ይበልጥ በማትጋት..እነሱን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግ..እነሱ የቸገራቸው ነገር ከስር ከስር እየተከታተሉ በመቅረፍ…››
‹‹ይሄም ንግግርሽ አልገባኝ…. ጎበዞቹማ ሰራተኞች ቀድሞውንም ጎበዞች ናቸው..እንደውም ደካማውን ጎበዝ እንዲሆን መጣሩ ነው የሚያዋጣው››
‹‹እሱ የቀሹም የስራ መሪ ዘዴ ነው..ጊዜህን ከሰነፍ ጋር ስታጠፋና ስትጨቃጨቅ ብዙ ነገርህን ነው የምታጣጣው…ዝቅተኛ የስራ ትጋትና ውጤት ያለው ሰውን ጎበዙን ይበልጥ ጎበዝ እንዲሆን ስታደርግ ውጤታማዎቹን ሰራተኟችን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን እያደረግክ ስትሄድ ያንን እያዩ እራሷቸውን ቢያንስ ወደ መሀከለኛ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ይጥራሉ..….ከዛ መሀከል ድረስ ከመጡልህ በቀላሉ ወደላይ መሳብ አይከብድህም ……ግን ያንተ ቅድሚያ ትኩረት የካምፓኒውን ኮከቦች ላይ ነው መሆን ያለበት…፡፡ለምን እንዳዛ እንደምመክርህ ታውቃልህ ትኩረትህ ውጤታማዎቹ ላይ ሲሆን ሁሌ በፈገግታ ተሞልተህ ነው የምትውለው… ሁል ጊዜ በውጤት ላይ ተጨማሪ ውጤት ስለማምጣት ነው አዕምሮህን የምትጠቀምበት..
..ደካማ የሰራ አፈፃፀም ካላቸው ሰዎች ላይ ቀልብህ የሚውል ከሆነ ግን ሁል ጊዜ ስለተበላሸ ነገር ነው የምታስበው..ሁል ጊዜ እድታቆጣ ያደርጉሀል …ሁልጊዜ በብስጭት ነው የምታናግራቸው….ያንተንም የስራ ሞራል ያወርዱብሀል..እነሱን ለማስተካከልና ለማሳደግ ስትጥር ያንተም ብቃት አብሮ እየወረደ ሊሄድ ይችላል…እና 80 ፐርሰንቱን ጊዜህን ውጤታማዎቹን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የቀረህን 20 ፐርሰንት ደግሞ ደካሞችን ለማስተካከል እና ወደመስመር ለማስገባት ተጠቀምበት…..
እሺ ገባኝ ተቀብዬሻለው…..ግን ወደዋናው ነጥብ እንመለስና አሁን የካምፓኒውን ደሞዝ እንዴት እንዳርገው እያልሺኝ ነው››
‹‹ደሞዝ አከፋፈሉ በውጤት ላይ ያተኩር ባይ ነኝ ፡፡የተሻለ የሰራ የተሸለ ገንዘብ እደሚያገኝ እርግጠኛ የሚሆንበት አሰራር ነው መዘርጋት ያለበህ….ዲግሪና ማስተርስ ስለተሸከመ ወይም አስርና ሃያ አመት በካምፓኒው ውስጥ ስለኖረ ሳይሆን በእያንዳንዱ ወር የስራ ትጋቱ ለካምፓኒው ምን ያህል የተሸለ ስራ ስርቷል ?ምን ያህልስ ትርፍ አስገኝቷል…? በቀጥታ የስራ ውጤቱ ተመዝኖ መሆን አለበት…..የትምህርት ዝግጅትና የስ ልምድ የሚጠቅመው መጀመሪያ ሰው ለመቅጠር ብቻ ነው መጠቀም ያለብን ..ከተቀጠረ ቡኃላ የተሻለ ለማደግና የተሻለ ደሞዝ ለማግኘት የተሻለ ውጤታማ መሆን እንዳለበት ሁሉም ሰራተኛ በግልጽ አውቆ በዛ መልኩ መስራት አለበት..ከምፓኒውም ሁሉ ጊዜ በእድገት ላይ ላለ ሰው ተጨማሪ የሚገባው ክፍያ ሊከፍለው ይገባል …ትክክለኛ የሚለካ እና ሚመዘን ውጤት በትክክል ኪስ የሚገባ ገቢ እና ጥቅማ ጥቅማ ማስገኘት አለበት…
‹‹ስለዚህ ይሄን በጅምላ በዓመት 5 ፐርሰንት ጭማሪ የምንለውና አሰራር ይቅር ነው የምትይው፡፡››
‹‹ አዎ..ምን አልባት አሁን ያለውን መነሻ ደሞዝ አንዴ በትክክል አጥንቶ ማሻሻል ያስፈልግ ይሆናል ….ከዛ ቡኃላ ግን ይሄ ካምፓኒ ለሌላውም ካምፓኒ ሞዴል የሆኑ ሰራተኟችን የሚሰሩበት… ደካሞች በራሳቸው ለቀው የሚሄዱበት መሆን አለበት..እሱ እዛ ካምፓኒ እኮ አምስት አመት ሰርቷል ተብሎ የሚኮራበት መሆን አለበት….ቀላል ምሳሌ ልስጥህ ሁለት ተሳቢ መኪና ሚነዱ ሁለት ሸፌሮች አሉ እንበል..ሁለቱን አዲስ መኪና ሰጠሀቸው…ከስድስት ወር ቡኃላ ደሞዝ መጨመር ቢያስፈልግ…ጅቡቲ ስንት ጊዜ ተመላለሱ….በእያንዳንዱ መመላለስ ስንት ቀናት ነበር የፈጀባቸው…?፡እያዳንዳቸው የገጠማቸው ችግር ምንድነበር…?የካምፓኒውን እገዛ ሳይጠይቁ ወይንም ተጨማሪ ወጪ ሳያስወጡ እንዴት ተወጡት?መኪናቸው ላይ የደረሰበት አደጋ አለ….?.አደጋ ከደረሰስ በእነሱ እንዝላልነት ነው ወይስ ከቁጥጥራቸው በላይ በሆነ ችግር…?መኪናውስ ስንቴ ተበላሸቶ ገራዥ ገብቷል..? ስንትስ ብር ድርጅቱን አስወጥቷል…?እነዚህናን መሰል ነገሮች ተዘርዝረው ውጤት ተሰልቶ የውጤታማነታቸው ልዩነት ቁልጭ ብሎ ይታያል..በዛ ስሌት መሰረት ካስገኘው ተጨማሪ ጥቅም ሀያ እና ሰላሳ ፐርሰንት ቢጨመርለት ይሄ ሰው ለሚመጣውስ ምን ያህል ይተጋል.?.ያኛውስ ደካማ ውጤት ያገኘው ለማሻሻል ምን ያህል ይነሳሳል…?.መልሱ ቀላል ነው፡፡
‹‹አሁን ተስማምቼለው››
‹‹አመስግናለው››

👍3❤1
ውድ አንባብያን ያለፈው ክፍል ላይ በስተት ክፍል 21 22 የተባለው በስተት ነው ምንም የታሪክ መቆራረጥ የለም መልካም ንባብ
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሦስት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍሰሀ
‹‹አሁን ተስማምቼለው››
‹‹አመስግናለው››
‹‹አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር?››
‹‹አለቃ እኮ ለመጠየቅ ፍቃድ አይጠይቅም››
‹‹አሁን እኮ የስራ ሰዓት አይደለም …ስለዚህ አለቃ ምናምን ብሎ ነገር የለም..››አልኳት
‹‹እሺ ጠይቀኝ››አለቺኝ አቀማጧን እያስተካከለች
‹‹የዛን ቀን እሷን ለማናደድ ብለሽ ያደረግሺውን እንደሆነ ባውቅም ግን በምንም አይነት ከአዕምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም….ከአዕመሮዬም ብቻ አይደለም ከህልሜም ማስወገድ አልቻልኩም….ሙሉ አዕምሮዬ በአንቺ ከንፈር ተሞልቷል…ምነው አሁንም አንድ ሰው አበሳጭቷት በሳመቺኝ እያልኩ በየቀኑ ነው የምፀልየው…
‹‹እየቀለድክ ነው አይደል?››አለቺኝ በፈገግታ እና በመኮሳተር መካከል በሚዋልል ስሜት
‹‹አይደለም…››አልኩና እንደምንም እራሴን አደፋፍሬ እጇን በመዶፎቼ መካከል አስገባውና እያሻሸው ንግግሬን ቀጠልኩ..አልተቃወመችኝም፡፡
‹‹አይደለም..እውነቴን ነው…ከህይወቴ አንድ አመት ተቀንሶ ያንን አይነት መሳም አንድ ጊዜ ደግማ ትሳምህ ብባል እስማማለው …እና እባክሽ..››
‹‹እንዲህ አይጠየቅም እኮ …አንድን ሴት እንዴት ልሳምሽ ብለህ ትጠይቃታለህ…ነውር እኮ ነው፡፡ነው ወይስ ውጭ ስለኖርክ ነውር የሚባል ነገር እረስተሀል?››
‹‹እንደዛ ማለቴ አይደለም..ፍቅረኛዬ እንድትሆኚ እየጠየቅኩሽ ነው››
በጥያቄዬ ምንም የመገረም ስሜት አልታየባትም ‹‹ከዛም በፊት ፍቅረኛ አለሽ ወይ ተብሎ ይጠየቃል…በዛ ላይ አንተም ፍቅረኛ አንዳለችህ አውቃለው..ታዲያ ፍቅረኛ ያለችውን ሰው መጥበስ የምፈልግ ይመስልሀል…?››
‹‹የእኔን እርሺው አብቅቶለታል..አንቺን ፍቅረኛ አለሽ ወይ ብዬ ያልጠየቅኩሽ ግን መልሱን ስለፈራው ነው..አለኝ ካልሺኝ ምን እንደምሆን አላውቅም…››
‹‹የእውነት ልንገርህ አለኝ ብልህም ምንም አትሆንም ..ሁሉም ወንዶች አንዱን ሴት ለማሰመን እንዲህ ነው የሚሉት..››
‹‹እወነቴን ነው …ትክክለኛ የሚሰማኝን ነው እየነገርኩሽ ያለውት..እኔ እስከዛሬ የነበሩት የፍቅር ገጠመኞቼ በአጋጣሚ የተከሰቱ ስለነበሩ እንዲህ አይነት ውስብስብ ነገሮችን አላውቃቸውም…››
‹‹ይሁን ግን የእሳትእራትን የፍቅር ታሪክ ታውቃለህ
አላውቅም እስኪ ንገሪኝ…
የአሳት እራት ፍቅረኛው እየመሰለችው ነው አንፖል በበራ ቁጥር ሲሽከረከር እምታየው ….ሴቷ ለፍቅር ዝግጁ ስትሆን የራሷን ብርሀን ከሰውነቷ አመንጭታ በመርጨት ነው ምልክት የምትሰጠው.. በዛ ብርሀን ተስቦ ወደ እሷ ይሄድና ፍቅሩን ያጣጥማል…እና ይሄ የዋህ አፍቃሪ የሚያምር እና የሚንበለበል ብርሀን ባየበት ሁሉ አፍቃሪ ያገኘ እየመሰላው ተንደርድሮ ምስግ ነው…የሚንበለበል እወነተኛ እሷት ውስጥም ቢሆን ከመግባት ስሜቱን መግታት አይችልም…ከገባና ደግሞ ታውቃለህ እርር ክስም ማለቱ አይቀርም …
‹‹እና ምን ለማለት ነው..››አልኳት ምሳሌዋ ግራ አጋብቶኝ
‹‹ከእኔ ጋር የሚጠብቅህ ፍቅር መንደድ እና መክሰምንም ሊያስከትልብህ ይችላል ብዬ እያመከርኩህ ነው››
‹‹ሰምቼሻለው..እሺ በይኝ እንጄ መንደዱም መክሰሉም አያስጨንቀኝም››
‹‹ወደ እኔ ተሳበች እና ወደ ከንፈሬ ተጠጋች…ከበቀደም ለታው መሳም በላይ የጠለቀ..ከዛ በላይ የሚያደነዝነዝና ረጅም ትንፋሸ አስቋራጭ ነበር… ከተቀመጥኩበት ሶፋ ተንሸራትቼ ወለል ላይ በጉልበቴ እስከምንበረከክ ድረስ አቅል የሚያሳጣ አይነት መሳም ነበር የሳመቺኝ….ቆይ የአሳሳም ጥበብን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሚያሰለጥን ተቋም አለ እንዴ…?.እንደዛ ካልሆነማ እንዲህ አይነትን አደንዛዣ አሳሳም ጥበብ ልትጎናፀፍ ትችላለች፡፡
እንደምንም ገፍታ ነበር ከንፈሯን ከከንፈሬ ያለቀቀችው….
ትንፋሽ ወስጄ እራሴን ካረጋጋው ቡኃላ‹‹እና እሺ አልሺኝ ማለት ነው..ፍቅረኛሞች ሆነናል ማለት ነው››ስል በመንሰፍሰፍ አይነት ስሜት ጠየቅኮት
‹‹በፍጽም አልሆንም….ስብሰባው ተካሄዶ የዚህን የፕሮፖዛል ውጤት ካወቅክ ቡኃላ መልሰህ ምትጠይቀኝ ከሆነ የዛን ጊዜ መልሱን ነግርሀለው››
ምን ማለቷ እንደሆነ ግልጽ ሊሆንልኝ አልቻለም‹‹ፕሮፖዛሉ ውጤትና የእኔ እና አንቺ ጉዳይን ምን አገናኘው…?.››
ተገናኘም አልተገናኘውም ያልኩህን ከማድረግ ውጭ ምንም ምርጫ የለህም…ከፈለክ ወይም ከዛ ቡኃላም ፍቅርህ የሚኖር ከሆነ እዚሁ አጠገብህ ጋር ስለምገኝ ጠይቀኝ….አንድ ሰምንት አይደል የሚቀረው..?ሳምንት መታገስ ያቅትሀል?
ይብላኝ ላንቺ እንጂ እኔስ ጠብቃለው….ስሜቴ በሳምንት የሚጠፋ መስሎሽ ነው…?ከአመታት ቡኃላም ብትይኝም ተመሳሳይ ጥያቄ ነው የምጠይቂኝ….የፍቅር ጓደኛዬ ሁኚ ብዬ…..
‹‹እናያለን…››አለቺኝ
‹‹እናያለን ››አባባሏ አስፈራኝ..የሆነ እሳት በውስጤ እንዲጫር አደረገብኝ….
❤️ፌናን
===
እለቱ እሁድ ነው…ያው ይሄ ዓረፍተ ነገር ብቻ የሚገልፀው ሀሳብ አለ አይደል…….?እለቱ ዕሁድ ከሆነ ብዙ ነገሮች የሚረጋጉበት ቀን ነው ማለት ነው..፡፡ወከባና መተረማማስ በጣም የሚቀንስበት ቀን…የስራ ስልክ ሲያወሩ ከመዋል ተገላግለው ቤተሰብን ወይም ወዳጅ ዘመድን በመደወል እንዴት ናችሁ….? የሚባልበት ቀን …የታመመ የሚጠየቅበት ፤ያዘነን የሚያፅናኑበት ለመንፈስ የቀረበ ስራ የሚሰራበት ቀን፡፡
በቤታችን ውስጥ ነው ምንገኘው..እኔ አባቴና እናቴ ብቻ ..ወይ ሳልነጋራችሁ እናቴ ከውጭ ተመልሳ ከመጣች ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ነው…ደግሞ በዚህ ዘመን ከውጭ ተመልሶ መምጣት ብርቅ ነው እንዴ….? እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለው…
ለማኛውም የዛሬዋ ቀን ልዩ ቀን እንድትሆን ስለፈለኩ ለሁሉም የቤቱ ሰራተኞች ፍቃድ ሰጥቼያቸዋለው…ግን ከመሄዳቸው በፊት ቀኑን ሙሉ ሲያግዙኝ እና ለእለቱ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ሲሰሩልኝ ነው የዋሉት ..ልክ እንደምፈልገው፡፡አሁን ሰዓቱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ነው፡፡እናቴ የገዛ መኝታ ቤቷ እንደተኛች ነው..አባቴ ደግሞ ያው እንደልማዱ ላይብረሪው ውስጥ እራሱን ዘግቶ ወይ እያነበበ ነው ወይ ደግሞ እየጻፈ ነው..ብቻ እዛ ነው ያለው፡፡
እኔ ደግሞ የምግብ ጠረጵዛው በምግብ እየሞላው ነው….ልክ እንደጨረስኩና ነገሮች በፈለኮቸው መሰረት እንደተማቻቹና ቀልብ ሳቢ እንደሆኑ ካረጋገጥኩ ቡኃላ ወደእናቴ መኝታ ቤት አመራው
===
..በዝግታ ሳንኳኳ ‹‹ግቡ››የሚል የደከመ ድምጽ ፍቃድ ሰጠኝ… በራፉን ገፋ አድርጌ ገባው…እናቴ አልጋዋን በወረቀት ሞልታ አፍንጫዋ ላይ የሰካችው መነጻር ከፍ ዝቅ አያደረገች አንገቷን አቀርቅራ ወረቀቷቹ ላይ አፍጥጣለች፡፡
‹‹እንዴ እማ የተኛሽ መስሎኝ ነበር እኮ….?››
‹‹በዚህ ሰዓት…….?አረ አልተኛውም››
‹‹ይሄ ሁሉ ወረቀት ምንድ ነው….?››
‹‹የካምፓኒውን የስድስት ወር ሪፖርት ልከውልኝ ነው..እስኑ እያየውት ነው››
‹‹ምነው ተዲያ ተኮሳተርሽ ….….?የጠፋ ነገር አለ እንዴ…….?››
‹‹አይ የለም…..አንድ ብቻ ደስ ያላለኝ ነገር አለ…››
‹‹ልትነግሪኝ ትቺያለሽ….?››
‹‹የሰውዬው ልጅ ስር-አስኪያጅ ከሆነ ምን ያህል ጊዜ ሆነው….?››
‹‹ወር ከሀያ ቀን …››
‹‹እና ምን አድርጎ ነው በዚህ አጭር ጊዜ በጣም የተለየ ትርፍ ሊገኝ የቻለው…….?››
‹‹ጎበዝ ነው ብዬ ነግሬሻለው እኮ….›››አልኳት በፈገግታ ተሞልቼ
‹‹አይ ይሄንን ስራ ጥርሴን የነቀልኩበት ነው..የፈለገ ጎበዝ ቢሆን ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሊታይ የሚችል ልዩነት ማምጣት የሚችል ሰው አይኖርም… ምን አልባት ስራውን በደንብ የሚያውቅና ካምፓኒውን ቀድሞ

👍3
በጥልቀት ያጠና ሰው ካረዳው በስተቀር…››
‹‹እንደዛ አይነት ሰው ማን አለ…….?ማንን ጠረጠርሽ….?››
….የበታተነችውን ወረቀት እየሰበሰበችና ወደመህደራቸው እየመለሰች‹‹….አንቺ ካረዳሽው እንዲህ አይነት ውጤት ሊያመጣ አይችልም….አንቺን ነው የምጠረጥረው፡፡እንዴት ሰው እርሱ የሚታረድበትን ቢላዋ በፍቃደኝነት ይሞርዳል?››
‹‹ያው በደነዘ ቢላዋ ከመገዝገዝና ጣርን ከማብዛት መታረጃን በደንብ ሞርዶ ያለምንም ስቃይ በስል ቢላዋ ቶሎ መገላገል ይሻሸላል ብዬ ነዋ፡፡ያው መታረዱ ቁርጥ ከሆነ እንደዛ ይሻላል.››
‹‹እየቀለድኩ አይደለም››አለቺኝ በፊት ከነበራት የዘወትር መኮሳተር ላይ ሌላ መኮስተር አክላበት
ተጣጋዋትና ወደ አልጋው ጎንበስ ብዬ በማቀፍ ጉንጮን ሞጭሙጩ በመሳም…‹‹ዛሬ ስለዚህ ጉዳይ ማውሪያ ቀናችን አይደለም››አልኳት
...አልተስማማችም‹‹…ነው እንጂ …አምስት ቀን ብቻ ነው የቀረን፡፡ያንን ካምፓኒ እንድታስተዳድሪ እፈልጋለው፡፡.ነግሬሻለው
… አውቀሽም ሆነ በዚህ በቸልተኝነትሽ ቦታውን ካጣሽ ያበቃልኛል..››
‹‹ያበቃልኛል ስትይ….?››
‹‹ልትጠፋ ጭል ጭል እያለች ያለችው ልቤ ቀጥ ነው የምትለው፡፡ሄጄ የልብ ትርንስፕላንት ሳይደረግልኝ እዚሁ ያበቃልኛል እያልኩሽ ነው››
‹‹እማ እንዲህማ አታሳቂኝ፡፡››
‹‹እንድትሳቀቂ ሳይሆን እውነቱን አውቀሽ ማድረግ ያለብሽን እንድታደርጊ ነው እየነገርኩሽ ያለውት››
‹‹እሺ እሱን ነገ ተነገ ወዲያ እንነጋገርበታልን…ዛሬ ለእኛ ልዩ ቀን ነች… አሁን ተነሽ በ20 ደቂቃ ውስጥ ሽክ ብለሽ ለብሰሽ ሳሎን የእራት ጠረጵዛ ላይ ተገኚልኝ››
‹‹እንዴ!!! እውነትሽን ነው?››
‹‹እወነቴን ነው፡፡በይ ተነሽ 20 ደቂቃ ብቻ ነው ምሰጥሽ››ብዬ ድጋሚ ግንባሯን ስሜ ወጣው…..
===
ቀጥታ አባቴ ወደሚገኝበት ላይብረሪ ነው የሄድኩት…..
ጠረጵዛ ላይ አቀርቅሮ ይጽፋል….ስገባም አይሰማኝም…‹‹አባ..››
ትከሻውን ወዘወዝኩት….
‹‹ምን ተፈጠረ?››አለኝ ካቀረቀረበት ቀና ሳይል….
‹‹ተነስ… በቃ ፈልግሀለው››
‹‹ቆይ የጀመርኮትን ልጨርስ››
‹‹ነገ ትጨርሰዋለህ… ተነስ፡፡››
‹‹አይ ለደራሲ ነገ የሚባል ቀን የለውም ፡፡የመጣለትን ሀሳብ ወዲያውኑ በዛኑ ደቂቃ በወረቀት ካላሰፈረ በቃ ያ ሀሳብ በኖ ይጠፋል…መቼም ተመልሶ አይመጣለትም..ነገ ልፃፍ ቢል እንኳን ሌላ የተለየ ሀሳብ ነው ሊጽፍ የሚችለው፡፡.››
‹‹ውይ በቃ አባ ተነስ››እጁ ላይ ያለውን ብዕር ተቀብዬ ክዳኑን ከድኜ በማስቀመጥ ጎትቼ እስነሳውት…ይዥው ቀጥታ ወደመኝታ ቤታችን ነው የወሰድኩት
‹‹ …ምን እየሰራሽ ነው….?››ጠየቀኝ….የእሱን ቁም ሳጥን ከፍቼ ልብስ ስመርጥ እያየ…
ይሄንን ሸሚዝ ይሄንን ሱፍ፤ ይሄን ጫማ ..ሁሉንም መረጥኩና ከየቦታቸው እያወጣው ጠረጵዛ ላይ አድርጌ ‹‹ይሄንን ፂምህን ተላጭተህ፤ ይሄንን የመረጥኩልህን ልብስ ለብሰህ በ15 ደቂቃ ውስጥ ሳሎን ከች በልልኝ…››ብዬ ምን እንደሚለኝ ግራ ገብቶት በአግራሞት እየተመለከተኝ ሳለ ጉንጩን ስሜ ተንደርድሬ መኝታ ቤቱን ለቅቄ ወጣውና በላዩ ላይ ዘግቼ የቀሩ ነገሮችን ለማስተካከል ወደሳሎን ተመለስኩ
ቀድሞ የደረሰው አባቴ ነው፡፡እንደምፈልገው አምሮበታል‹‹….የምግብ ሽታ ያልተራበንም ሰው ያስርባል››አለኝ እና ቁጭ አለ
‹‹የእኔ ውድ አባት ትንሽ ታገስ››እያልኩት ሳለ ከላይ ከፎቅ ወደታች የሚወርድ ቋ…ቋ..ቋ የሚል የእግር ኮቴ ድምጽ ስንሰማ ሁለታችንም እይታችንን ወደ ላይ ላክን…. እናቴ ከአስደማሚ ግርማ ሞገሷ ጋር ንግስት የሚያስመስላትን ልብስ ለብሳ በእርጋታ ወደታች እየወረደች ነው…አባቴ ሳያስበው መሰለኝ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…መሀከል መንገድ ድረስ ሄዶ እጆን ያዘና አምጥቶ ወንበር ስቦ ካስቀመጣት ቡኃላ ከፊት ለፊቷ ሄዶ ተቀመጠ …..
‹‹አባትሽ እንዲህ ሲያምርበት አንቺስ ምነው በሽርጥ?››አለቺኝ እናቴ..ይሄንን አስተያየት የሰጠችው ቀጥታ አባቴን አምሮብሀል ማለት ከብዶት ነው..
‹‹እኔማ ዛሬ አገልጋያችሁ ነኝ..እራት ያዙ፤ ብሉ ፤ጠጡ …የጎደለ ነገር ካለ ጠይቁኝ››
በሁለቱም ፊት ላይ መደነቅ የወለደው ፈለገግታ ተረጨ
‹‹እንዴ ልጆቹ ሁሉ የት ሄዱ?››
‹‹በዚህ ግዙፍ ጊቢ ውስጥ ከአባት እናት እና ልጅ በስተቀር አንድም ፍጡር የለም… ድመትና ውሾች እራሱ የሉም …ሁሉም እረፍት እንዲወጡ አድርጌያለው››
ሁለቱ ተያዩ››ምን እየተካሄደ ነው?›› እየተባባሉ እርስ በርስ የሚጠያየቁ ይመስላል
‹‹የዚህ ሁሉ ዝግጅት ምክንያት ሊነገረን ቢችል.?››አባቴ ነው የተጠየቀው… ከቀረበው ምግብ የሚመቸውን ወደ ሰሀኑ እየወሰደ….
‹‹የቤተሰብ ቀን ነው››እኔ ነኝ የመለስኩት
‹‹ታዲያ ሁሉም እኮ ቤተሰቦቻችን ናቸው…ቤተሰብ ማለት እናትና አባት ወይም ልጅ እና እናት አይደለም..በአንዱ ቤት ውስጥ እየተሳሰብና እየተረዳዱ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ቤተሰብ የሚለውን ስያሜ ያጠቃልላቸዋል…››አባቴ ነው
‹‹አባ አቁም..ዛሬ እንደዛ አይነት ዝርዝር ፍልስፍናዊ ትንተና ለመስማት ዝግጁ አይደለሁም::በአጭሩ ዛሬ እናትና አባቴን ፈልጋቸዋለው::ብቻቸውን..ለምን ፈልጋቸዋለሁ?ዝግጅቱ ገና መጀመሩ ነው..በቅድሚያ እራቱ ይበላ ..ተረጋጉ ..ጊዜው ሲደርስ የሚሆነው ይሆናል››ሁለቱም አቀረቀሩ
‹‹ሰምተናል እሺ … አንቺም ቁጭ በይና እራትሽን ብይ.››እናቴ ነች….ከጎኗ ቁጭ አልኩና ያዝኩ….
አባቴ እጅን ወደ እናቴ ሰሀን ይልክና ከራሷ እንጃራ ቆርሶ የእሷን ወጥ ከዚህም ከዛም አጠቃቅሶ ያጎርሳታል….እኛ ቤት ውስጥ የእናቴን ምግብ የሚበላ ሰው የለም…እሷ የምትበላው ምግብ እህል ቀጠል አይልም…ጨው የለው..ዘይት ለመደሀኒት ነው የሚገባበት..ጮማ በደረሰበት አትደርስም…ከምትበላቸው የህል ዘሮች የማትበላቸው በመቶ እጥፍ ይበዛሉ….ሰው ለደሀ ያዝናል….እያለው ሁሉ ነገር ፊቱ ተደርድሮለት ግን ደግሞ መብላት የማይችልስ ሰው አያሳዝንም.? ከፍቅረኛህ ጋር አንድ አልጋ ላይ ትተኛለህ ግን ደግሞ ጭኗን መግለጥ አትችልም ብትባል?ፍቅረኛ አጥቷ ባዶ አልጋ ታቅፎ ከሚተኛው ሰው የበለጠ የምትሰቃየው አንተ አይደለህን.? ቀድሞውንም የሌለው አንደምንም እራሱን አሳምኖ ሁሉን ነገር ለጊዜውም ቢሆን ረስቶ በእንቅልፍ ይዋጥና እፎይ ይላል..አጠገቡ ከተኛች ግን በተገላበጠች ቁጥር ልብ ትገላባጠላች.. ትንፋሿ ከሩቅ በገረፈው ቁጥር አንጀቱ በወሲብ እረሀብ ይገላበጥበታል..እና ስቃዩ ኖሮህ ግን ደግሞ መጠቅም ሳትችል ይብሳል….የእናቴ ነገር እንዲያ ነው፡፡
…እኔ ድግሞ አባቴን አጎርሳለው….እናቴ በህይወቷ ማንንም ሰው ስታጎርስ አይቼ አላውቅም…እኔ ደግሞ ማጉረስ ብወድም እሷን ግን አጉርሼት ማውቅበት ጊዜ መኖሩን አላስታውስም…ለምን ይመስላችሆል?ህፃን እያለው ጀመሮ እባቴ ሲያጎርሰኝ ለሳዕታት ስሬ ቁጭ ብሎ ልጄ ይህቺን የመጨረሻ ጉረሺልኝ...ለእኔ ስትይ …….እያለ እባብሎም፤ እያታለለም ሲያበላኝ እሷ አንድ ቀን ተሳስታ እንኳን እጆን ወደ አፌ ዘርጋታ አታውቅም..እኔም ሳለውቀው ይህቺን ቂም ይዤባት አድጌያለው መሰለኝ እጄ አሁን ሁሉን ነገር ረስቼያለው ባልኩበት ጊዜ እንኳን ለእሷ አይዘረጋልኝም::ምግቡ አልቆ ከምግብ ጠረጵዛው ተነስተን ወደ ሶፋው ተሸጋግረን ተቀምጠናል:: እኔም ሽርጤን አውልቄ ፊት ለፊቴ የወይን ብርጭቆዬን አድርጌ ለንግግር እየተዘጋጀው ነው::አባቴ ውስኪ ይዞል …እናቴ ግን ያው እንደተለመደው ንጽህ ውሀዋን ፊት ለፊቷ አስቀምጣለች…ምሲኪን…..
ሁለቱም ምን አስባ ነው….? በማለት የምለውን ነገር ለመስማትና በህይወቴ አድርጌው የማላውቀውን እና አሁን እያደረግኩ ያለውትን ይሄ ሁሉ ጠብ እርግፍ በምን ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ አፌ

👍1👎1
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
‹‹የዛሬዋን ቀን ለዓመታት ሳስባትና ስዘጋጅባት የነበረች ቀን ነች::በምን አይነት ሁኔታ ላድርገው?እንዴት ቢሆን ይሻላል?ለብዙ ለብዙ ቀናት ሳብሰለስለው ነው የኖርኩት….እና ይቺ ቀን ዛሬ ነች ደቂቃዋም አሁን…..››
‹‹ይሄን ያህል ያሰጨነቀሽ ነገር ምን ቢሆን ነው?››እናቴ ነች
‹‹እዚህ ቤት ያለው ሚስጥር..በእናንተ ሁለታችሁ መካከል ያለው ሚስጥር……የማትጨቃጨቁበት፤ የማትለያበት ሚስጥር….?››
<<እንዴ ልጄ ምን እያልሽ ነው…….?እንዲህ ይባላል እንዴ..….? ሰው እኮ አባትና እናቴ እየተጨቃጨቁና እየተጣሉ እረበሹኝ እያለ ነው ሚሰቃየው..ለምን አልተጣላችሁም ብሎ መጨነቅ ምን የሚሉት ነው….?››አለች እናቴ
አባቴ እንዳቀረቀረ ነው..ምን ለማለት እንደፈለኩ ለእሱ በደንብ እደሚገባው አውቃለው…በጥልቀትም ባይሆን ብዙ ጌዜ እያነሳሳውበት ስጨቀጭቀው ስለነበር ከእናቴ በተሸለ ምን ለማለት እንደፈለኩ ማወቁ ብዙም አይግርምም….
‹‹በመሀከላችሁ የታፈነው ነገር ነዋ የሚያስጨንቀኝ…መቼ ይሆን የሚፈነዳው ….?እያልኩ ሁሌ እንቅልፍ እስካጣ ድረስ አስባለው…ሲፈነዳስ?የፍንዳታው ፍንጥርጣሪ እያዳንዳችንን ምን ያህል ይጎዳናል? ከፍንዳታው ቡኃላም እንዲህ አንድ ላይ በአንድ ቤት ጣሪያ ውስጥ መኖር እንቀጥላለን?ወይስ ብትንትናችን ይወጣል?ሁሌ ያስጨንቀኛል››
‹‹የምን መአት ነው የምታወሪው?እኔና አባትሽን እንዴት ይለያያሉ ብለሽ አሰብሽ….ወደ አባቴ ዞረችና በጥርጣሬና ግራ በመጋባት እየመረመረችው‹‹ምን አልካት…….?››ብላ ጠየቀችውና ወዲያው እራሷ መልሱን መመለስ ጀመረች ‹‹ይቅርታ አንተ ምንም ልትላት እንደማትችል አውቃለው››ብላ መልሳ እኔው ላይ አፈጠጠችብኝ
‹‹ቆይ እናንተ ምንድን ናቹሁ.?››
‹‹ምን ማለት ነው.?ሰዎች ነና››
‹‹አይደለም… የሁለታችሁ ግንኙነት ምን ስያሜ ነው የምትሰጡት?የውጭ ሰዎች እንደሚሉት ባልና ሚስት ናችሁ?.እኔ እንደማውቀው አንድ የጋራ ቤት ተጋርተው የሚኖሩ ደባል ናችሁ…..….የትኛውን ናችሁ….?››
‹‹ተረጋጊ….አባትሽ ለእኔ ምኔ እንደሆነ ታውቂያለሽ .. ….?ባሌ ብቻ እንድልሽ ትፈልጊያለሽ.?ባልማ ማንም ወንድ ባል ሊሆን ይችላል ..እሱ ህይወቴ ነው…፡፡ህይወቴን ለማቆየት በየሰው ሀገር እየተንከራተትኩ ሰውነቴን በየጊዜው እያስተለተልኩ መከራዬን እደማይ ታውቂያለሽ…ለምን ይመስልሻል?ለሀብቴ አይደለም..አሁን ለእኔ ገንዘብ ምን ያደርግልኝ ይመስልሻል?ያማረኝን የማልበላና ያሰኘኝን የማልጠጣ ሰው ነኝ…፡፡እና ለተጨማሪ ጊዜያቶች አብሬው ለመኖር ፍላጎት ባይኖረኝ ኖሮ ምን እንደማደርግ ታውቂያለሽ?አንድ ወርም ሆነ ሁለት ወር ያሰኘኝን በልቼ ያማረኝን ጠጥቼ ይህቺን ህይወት እሰናበት ነበር..ግን ከእሱ ላለመለየት ስለምፈልግ ነው እያዳንዳን የሀኪም ቃል ከፈጣሪዬ ቃል በላይ በየቀኑ እየደገምኩ በዛ መሰረት ለመጓዝ ምጥረው….እና ደግሞ ከእሱ በተጨማሪ አንቺም አለሽ››ንግግሯ ፀጥ አሰኘኝ…ሀሳቤን በታተነቺብኝ….እሷ እንደዛ በስሜት እየተንቀጠቀጠች ስትናገር አባቴ ደግሞ እንባውን በጉንጮቹ እያረገፈ ነበር…እኔ ደግሞ አባቴ ጉንጮች ላይ እንባ ሲወርድ ከማይ አለም አብቅቶላት ምጽአት ቢታወጅ ይቀለኛል….ግን ይገርማችሆል በዚህ የስሜት መጨፍገግ ላይም ሆኜ ምን እንደተዛብኩ ታውቃላችሁ?እማዬ ስለአባቴ የሚሳማትን ተንትና በስተመጨረሻ ደግሞም አንቺም አለሽ ስትል…ለእሷ እኔ የሆን እንጎቻ ነገር እንደሆንኩ ነው የተሰማኝ….ልጣፊ ነገር፡፡
ጥያቄዬን ቀጠልኩ ‹‹እና እንድምትይው አባቴን የምታፈቅሪው ከሆነ እንዴት እንዲህ ትጨክኚበታልሽ? ሀያ አምስት አመት ሙሉ ልጅን አቅፎ ሲተኛ ትንሽ ህሊናሽን አይቆረቁርሽም?ነው ወይስ የአንድ ሚስትን ግዴታና ኃላፊነት አታውቂም.?››
አባቴ ንግግሬ አስጨንቆት ይንቋራጠጣል….
‹‹ስለማታውቂው ነገር አትዘባርቂ…››
‹‹እኮ አሳውቂኝ… የሆነው ነገር ሁሉ እንዴት እንደዛ ሲሆን እንደኖረ የማወቅ መብት አለኝ…ንገሪኝና ልረዳው….ከለበለዛ…!!!››
‹‹ካለበለዛ ምን ….?››አይኗን አጉረጥርጣ ጠየቀቺኝ..ዛሬ ምንም ብትቆጣ …ምንም ያህል ብትኮሳተር ልፈራትና ልሸነፍላት አልችልም ….አባቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በመካከላችን ገባ
‹‹ወዴ በቃሽ….ይሄንን ነገር እንዳለ ተይው ››
‹‹አልተወውም አባ::ለአንተ ስል አልተወውም››
‹‹ለእኔ አስበሽ ከሆነ ብትተይው ነው በጣም የምትጠቅሚኝ…እናትሽ እንዳለቺው እስከዛሬም የኖርነው የፈለግነውን አይነት ኑሮ ነው …ሁለታችንም እየሆነ ባለው ነገር ደስተኞች ነን::ስለዚህ አንዳንድ ነገሮችን ባሉበት መተው መልካም ነው..››
‹‹አልተውም አልኩ እኮ..አባ ዛሬ እውነቷን ሳላውቅ አላድርም››
‹‹ተውሽም አልተውሽም እኛ ምንም የምንነግርሽም የምንልሽም ነገር የለም…እና ምን ልታደርጊ ነው?››እናቴ ነች…ምንም ልታመጪ አትቺይም በሚል ስሜት የተናገረቺው
‹‹አፋታችሁለው….አባቴ ካንቺ እንዲፋታና ይሄንን ቤት ለቆልሽ እንዲወጣ አደርጋለው::ከዛ በቅርብ ሌላ ሚስት እድረዋለው::እና ደግሞ ያንን ካምፓኒሽን አልፈልገውም::አንቺንም ጭምር አልፈልግሽም.››
ዝም አለች… ዝም ብሎ ማፈጠጥ ብቻ….የሆነ 5 ደቂቃ ያህል መሰለኝ ዝም ያለችው …ግን የ5 ዓመት ያህል ርዝመት ነበረው..አስፈሪ ምንጩ ከወደሲኦል ሚመስል ዝምታ….እና ከዝምታዋ ወደ መዳካምና አንገቷን ዘንበል አድርጋ ወደጎን ልትወቀድቅ ስትል አባቴ ፈጠን ብሎ ያዘት ..ከዛ ቡኃላ የነበረውን መሯሯጥና መተረማመስ አትጠይቁኝ..በስንት ማናፈስ …መዳሀኒቷ ከመኝታ ቤት አምጥተን አውጠናት በመከራ ነው አይኖቾን የገለጠችው….እና እንደገለጠች…
.‹‹ወደመኝታ ቤቴ ውሰደኝ …ደከመኝ ልተኛ >>አለችው አባቴን ስልምልም ባለ ድምጽ
‹‹እሺ›› አለና ከተቀመጠበት ተነስቶ ሰቅስቆ አቀፋትና የፎቁን ደረጃ ማውጣት ጀመረ….እኔም ቀደምኩና ከፊት ለፊቱ መኝታ ቤቷን ከፈትኩለት …ወደውስጥ ገባውና ብርድልብሱን ገለጥኩለት…. ቀስ ብሎ አስተኛት…
ወደእሷ ተጠጋውና ‹‹እማ ይቅርታ››እጆን አናሳችና ፊቴ ላይ እሰቀምጣ በመዳበስ‹‹‹..በጣም ነው የምወድሽ…የእኔ ልጅ በመሆንሽ ሁል ጊዜ እንደኮራውብሽ ነው…ግን እንድታውቂ የምፈልገው አባትሽን ደግሞ ካቺም በላይ ነው የምወደው››አለቺኝ …ከሳለፉነው ሁኔታ ጋር የማይገናኝና በተቃራኒ የሆነ ልስልስ ያለና ወደልብ የሚሰርግ የፍቅር ንግግር ነው ያሰማቺኝ…በመጠኑ ተንፈስ አልኩ
‹‹በቃ አሁን ሂዱ…ልተኛ ››
‹‹እኔ አብሬሽ ልቆይ››አባቴ ነው ተናጋሪው
‹‹አይሆንም… ካመመኝ መጥሪያውን እጫናለው…››
ባለችው ተስማምተን ለቀንላት ተያይይዘን ወጣን..ወደሳሎን ነበር የተመለስነው….‹‹አባ ውስኪውን መጠጣት ነው የምፈልገው›› አልኩት
ባዶ ብርጭቆ አናሳና ቀዳልኝ …የራሱንም ጎዶሎ ሞላ …..በዝምታ መጠጣት ጀመርን…እኩለ ለሊት ሊቃረብ ሲል ነበር አባቴ ማውራት የጀመረው….

Forwarded from Markdown List 📋
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
❤️ፌናን
===
‹‹….ምን አልባት ትክክል ነሽ››አለኝ
‹‹ምኑን አባ…?››
‹‹እውነቱን የማወቅ መብት አለሽ …እናም ነገርሻለው››
አቀማመጤን አስተካከልኩ..በስካርና በድካም እየታጠፉ የነበሩ ጆሮዎቼን ሲነቃቁና ሲዘረጋጉ ይታወቀኛል…
‹‹በዚህ የታፈነ በምትይው የእኔ እና የእናትሽ ኑሮ ውስጥ ባጣም ተጎጂው እኔ ሳልሆን እናትሽ ነች››
‹‹ማለት…?››
‹‹የመፋታቱን ሀሳብ አንቺ ከመወለደሽም በፊት ሆነ ከተወለድሽ በኃላ ደጋግሜ አቅርቤላት ነበር::ግን ከተለየዋት እራሷን እንድምታጠፋ ደጋግማ ስላስጠነቀቀቺኝ ነው ጥያቄዬን አቁሜ ሀሳቤንም ቀይሬ ዝም ብዬ እንደምታይው መኖር የጀምርኩት..››
‹‹መኖራችሁ ካልቀረ ታዲያ እንደ ሰዎቹ በስርዓት አትኖሩም..…?እንደባልና ሚስት››
‹‹እንደዛ መኖር አንችልም..ታሪኩን ከመጀመሪያ ላስረዳሽ…እናትሽ የአዲስአባ ልጅ ብትሆንም የእናቷ ቤተሰቦች የአንቦ ኦሮሞዎች እንደሆኑ ታውቂያለሽ››የሚናገርውን ነገር ማስረዳት ስለከበደው ዙሪያ ጥምዝ እንደሚሽከረከር ገባኝ ..አሁን እያለኝ ያለው እኮ ያንቺ ሰም መቼስ ፌናን እንደሆነ ታውቂያለሽ አይደል …?ቢጤ ነው፡፡
‹‹…..እና ልክ እኔ እና እናትሽ እንደተጋባን ሰሞን የእናቷ ታናሽ ወንድም ስሙ ቶሌራ ይባላል ..በውድቅት ለሊት በራፋችንን አንኳክቶ ይመጣል….ሲመጣ ሰው አይመስልም…ልብሱ በጭቃና በከሰል ብናኝ በክቷ፤በደረቀ ደም ተለውሶ ነበር…ማንነቱን በመልኩ ሳይሆን በድምጹ ነበር እናትሽ የለየችው…ከዛ አፋፍሰን ወደቤት አስገብተን ሰውነቱን እንዲታጠብ አድርገን ልብሱን ቀይረን የቆሰለውን የተቻለንን ያህል የመጀመሪያ እርዳታ እንዲያገኝ አድርገን አስተኛነው…
‹‹ምን ሆኖ ነበር…?››
ይሄ ልጅ ብሩህ ጭንቅት ያለው ድንቅ ልጅ ነበር…ግን ያው እንደማንኛውም የዘመኑ ወጣት ፓለቲካ ውስጥ እስከአንገቱ ነበር የገባበት::እኔም ሆንኩ እናትሽ እንደው ባጋጣሚ ወይ እኛ ሄደን ወይ ደግሞ እሱ ሊጠይቃና በመጣ ቁጥር ነገሮችን በእርጋታ እንዲይዛቸው ልንመክረው ሞክረን ነበር::አዎ ያቅማችንን ጥረን ነበር:: ግን ያው ታውቂያለሽ አንዳንዴ ፓለቲካ ልክ እንደልክፍት ነው::ሰው ተይ ባለሽ ቁጥር ይበለጥ ይብስብሻል..እና ይሄ የማታውቂው አጎትሽ ሚስጥራዊ የኦነግ አባል ሆኖ በአንቦ ከታማ ይንቀሳቀስ ነበር::.እና ህዝቡን ያነሳሱና መንግስትን በመቃወም ከተማዋን ያምሶታል ::በዛም ምክንያት ብዙ የመንግስትና የግል ንብረት ይወድማል::ከወታደሩም ከኑዋሪውም ከ12 ሰዋች በላይ ይሞታሉ…እና የዚህ ጉዳይ መሪ ይሄ አጎትሽ እንደሆነ በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ ደህነነቶች መረጃ ይደርሳቸውና ለሊቱን አድፍጠው ሊይዙት ወደቤት ሄደው ሲከቡት አንዱን ገድሎ ሁለቱን አቁስሎ አጥር ዘሎ ያመልጣል፡፡እድል ከእሱ ጋር ነበረችና ከሰል በጫነ መኪና መሀል በድብቅ ተወሽቆ በለሊት አዲስአበባ ይገባና እንደነገርኩሽ በውድቅት ለሊት ወደእኛ ቤት ይመጣል፡፡
‹‹ታዲያ እንዲት አደረጋችሁ…?››ጥያቄዬን ቀጠልኩ..እኔ መስማት ከምፈልገው የወላጆቼ የጋብቻ ታሪክ ውጭ የሆነ ሀገራዊ እና ፓለቲካዊ ታሪክ ለምን እንደሚነግረኝ ፍንጩን እንኳን ማወቅ አቅቶኝ ፡፡
‹‹ለጊዜው ምን አልባት የእኛ ቤት አስታማማኝ ላይሆን ስለሚችል እና በጥቆማ መጥተው ቢፈትሹ ሊያገኙት ስለሚችሉ ብለን ሊነጋጋ ሲል አቃቂ የሚኖር አንድ ጎደኛዬ ቤት ወስደን አስተኛነውና እዛው ህክምና እንዲያገኝ አድርገን በዘላቂነት ምን ማድረግ እንዳለብን ማሰብ ጀመርን::እናትሽ ለእሱ ያላት ፍቅር ይሄን ያህል ነው ተብሎ ከሚለካው በላይ ነበር…‹አይኔ እያየ አይገሉብኝም ወይም አስርቤት አይጥሉብኝም ብላ በድብቅ ከሀገር ይዛው ልትስወጣው ተነሳች…ቢያንስ እስከድንበር ልትሸኘው::ስሰማ ተቃወምኩ….የተቃወምኩት ለማድረግ ያሰበቸው ነገር አግባብ አይደለም ብዬ አይደለም..ለእሱ ያላትን ፍቅር ስለማውቅ ከዛ በላይም ላድርግለት ብትል የምቃወምበት ምክንያት አይኖረኝም ነበር::ችግሩ ግን በዛን ጊዜ አንቺን እርጉዝ ነበረች::የአራት ወር አርጉዝ ነበረች….‹‹ልጄን ይዘሽ ይሄንን የመሰለ አደጋ ልጋፈጥ ስትይኝ ቁጭ ብዬ አላይሽም ››አልኳት
‹‹ታዲያ ምን ይሁን? ግደሉት ብዬ ብቻውን ልልቀቀው ወይ…?››ብላ ህሊና የሚሞግት ጥያቄ አቀረበችልኝ
‹‹እኔ እስከፈለግሺው ቦታ ይዤው እሄዳለው::ይሄን አደጋ ለመጋፈጥ ካንቺ ይልቅ እኔ እሻላለው››የሚል ሀሳብ አቀረብኩላት
በወቅቱ አሻፈረኝ አይሆንም አለች….‹‹ለምን…?››ያቀረብኩላት ጥያቄ ነበር
‹‹የሆነ ነገር ከሆንክ ምን ብዬ አወራለው ነው ያለቺኝ…‹‹በእኔ ቤተሰብ ይሄንን ያህል መከራ እንድትጋፈጥ አልፈቅድም›› አለቺኝ ….በዚህ ጉዳይ ከሁለት ቀን በላይ ተጨቃጨቅን… ቡኃላ ሽማግሌም መሀላችን ገብቶ በእኔ መሄድ ተስማማን…
ከዛ እኔና አጎትሽ ጨላማን ተገን አድርገን ከአዲስ አበባ በእግር ወጣን .. ግማሽ መንገድ በግር ሲመቻችልን ደግሞ መኪና በመጠቀም ሞያሌ ድረስ ሸኘውት..እዛ ለመድረስ 8 ቀን ነበር የፈጀብን…ከዛ ደላሎች ወደኬንያ እንዲያሸጋግሩት አመቻችቼ…ድንበር ማቋረጡንም ካረጋገጥኩ ቡኃላ በስኬት ተመለስኩ….
‹‹ከዛስ…?››
‹‹ከዛማ…ከከተማ ይዤው ወጥቼ እንዳስመለጥኩት ደህነቶች መረጃ ደርሶቸው ነበረና እቤቴ ሳልገባ ከመንገድ ነው የጠለፉኝ…››
‹‹ወይ አባ አንተን..…?ታዲያ ምን አደረጉህ…?››
‹‹ከዛም አሁን ሙዚዬም ይሁን ተብሎ የተዘጋው ማዕከላዊ አስገቡኝ::በፊልም ላይ አይቼው ማለውቀውን..በመፃፍም ላይ እንኳን ማንበቤን ትዝ የማይለኝን አይነት ስቃይ አሰቃዩኝ::መፈጠሬን እስክጠላ…ሰው ምን አይነት ፍጡር ነው? ብዬ እስክጠይቅ ድረስ……?እግዜር እንዴት እንደዚህ አይነት ፍጡር ይፈጥራል…? ብዬ ሙግት ውስጥ እስክገባ ድረስ….‹‹እግዜር ሰውን በመፍጠሩ ተፀፀተ› የሚትለው መፃፍ ቅዱስ ላይ ከአመታት በፊት ያነበብኩት ጥቅስ ትርጉም በደንብ እስኪገባኝ ድረስ አሰቃዩኝ››
‹‹አንተን..?ስለአስመለጥከው ብቻ…?››
‹‹አዎ …የት ነው ያደረስከው..…?በድርጅቱ ውስጥ አንተስ የነበረህ ኃላፊነት ምንድነው?ውጭ ካሉት ጋር መመሪያ እየተቀበልክ ክፍለሀገር ላሉት አባሎቻችሁ ሽብር እዲፈፅሙ ምታሰማራቸው አንተ ነህ ወይ?ቀጣዩ የድርጅቱ እቅድ ምንድነው?ሌሎችስ እዚህ ከተማ ውስጥ ሆነ በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ያሉ አባሎቻችሁን ዝርዝር ?›› የማይጠይቁኝ ጥያቄ የለም..እያንዳንዶ ነጠላ ጥያቄ ከብዙ ማሰቃየትና ገሀነማዊ ቶርቸር ቡኃላ ነበር የምትከተለው፡፡እንዴት አንድ ሰው በገዛ ወንድሙ ላይ በዚህ መጠን ሊጨክን ይችላል?ምን ለማግኘት …?ስንት ዓመት በዚህ ምድር ላይ ለመኖር?በፓለቲካ ልዩነት ብቻ የገዛ ወገንን በየምክንያቱ ከዚህም ከዛም እየሰበሰብ በጭለማ ቤት አጉሮ ጥፍር እየነቀሉ እና ብልት ላይ ሀይላንድ እያንጠለጠሉ በማሰቃየት የሚያስገኘው ውጤት ስልጣን ብቻ አይደለም ዘላለማዊነትስ ቢሆን ያዋጣል እንዴ?በእኔ ሚዛን አያዋጣም፡፡ያንን መከራ በራሴ ላይ ደርሶ ከማያቴ በፊት በሰው ልጅ ላይ የሚሰራ የመጨረሻው አሰቃቂ ወንጀል ወይም ግፍ ግድያ ይመስለኝ ነበር…አንድን ሰው ግንባሩን በጥይት አፍርሶ መግደል፡፡ለካ አሱ ቸር እና አዛኝ የሆኑ ወንጀለኞች የሚፈጽሙት ቀላል ከሚባሉ ቅጣቶች ውስጥ የሚካተት ነው?ብዙም ሊጨክኑበት የማይፈልጉትን ሰው በእንክብካቤ የሚያስወግዱበት ዘዴ…ይህንነ አሁን እየተነጋርኩ ያለውትን ንግግር ሴሜቱ በትክክል የሚሰማው ተመሳሳዩ ነገር የደረሰበት ሰው ብቻ ነው፡ግን ከሰው ውጭ ሌላ ፍጡር በራሱ ፍጡር ላይ ይሄንን ያህል ይጨክናል?ለምሳሌ አንበሳ በአንበሳ

👍5
ላይ?ጅብ በጅብ ላይ…? ነብር በነብር ላይ..…?በፍጽም አይመስለኝም፡፡እና እኛ ከአውሬዎቹ በላይ አውሬነት በውስጣችን ተሸክመን የምንዞር አደገኛ ፍጥሮች ነን ማለት ነው…?፡፡
‹‹እንዴ አንተ ኦነግ ነበርክ እንዴ…?››
‹‹ወይ ኦነግ…የት ብዬ?አንደኛ እኔ በወቅቱ በነበረው የኦነግ የፖለቲካ ፕሮግራም የማምን ሰው አልነበርኩም፡፡ሁለተኛ የማምንበትም ቢሆን እንኳን እኔ በፓለቲካ ጫወታ የሚያስደስተኝ አይነት ሰው አይደለውም፡፡እና እንኳን ልሆን ቀርቶ ኦነግ የሆነ ሰው የማውቀው እጎትሽን ብቻ ነበር፡፡ግን ለእነሱ እሱን እንዲያመልጥ መርዳቴ እና ስሜም ገመዳ መሆኑ ብቻ ለኦነግነቴ በቂ እንደውም ከበቂ በላይ መረጃ ነበር…››
‹‹እሺ ታዲያ እንዴት አደረጉህ…?››የዚህ አሰቃቂ ታሪክ መጨረሻ ማወቅ ጓጓው…አናቴን እዚህ ስሬ ቁጭ ብሎ እያየውት ገድለውት ይሆን እንዴ…? ብዬ እስካስብ ድረስ፡፡ምን ማለቴ ነው…? ያለፈውን ታሪኩን እየነገረኝ ስሬ ቁጭ ብሎ እየነገረኝ ያለው በህይወት ስለተረፈ አይደል እንዴ…? ለአንድ ወር ያህል የአምላክ እርግማን እንደወረደበት እባብ ከቀጠቀጡኝና ከተለተሉኝ ቡኃላ ምንም የሚፈልጉትን መረጃ ሲያጡ ደከማቸው መሰለኝ ጨለማ ቢት ወረወሩኝ፡፡ከሚሸት ቁስሌ፤ከሚከረፋ ላቤ ጋር ድቅድቅ ጨለማና የታፈነ ቤት ወስጥ ወረወሩኝ፡፡ለአንድ ሰው የመጨረሻው ቅጣት ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ…? ብቻውን እንዲሆን ማድረግ፡፡ በብቸኝነት ላይ ጭለማ፤ ረሀብና ጥማት ስትጨምርበት በቃ ሁሉን ነገር ነው የምትጠይው… እያንዳንዷን ደቂቃ እንዴት እንደምትረዝምብሽ ልነግርሽ አልችልም?ሰው በተፈጥሮ ብቻውን እንዲኖር አይደለም የተፈጠረው….መከራም ሆነ ስቃይ ረሀብም ሆነ መታረዝ ከሰው ጋር ከሆነ ይችለዋል…፡፡ማንኛውም እስረኛ ጨለማ ቤት ውስጥ ለብቻው ስድስት ወር ከሚዘጋበት ከሰው ጋራ እድሜ ልክ ቢታሰር ይምርጣል….፡፡
እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም…
‹‹ቡኃላ እናትሽ በምታውቃቸው ሰዎችን የእያንዳንዱን ባለስልጣን ደጅ ፀንታ ለአራት ለአምስቱ ባለስልጣናት ያላትን ብር አስረክባ አስፈታቺኝ…፡፡ቀጥታ ከማዕከላዊ በለሊት አምጥተው በራፎ ላይ ጣሉላት፡፡ወዲያው አፋፈሳ ሆስፒታል ወሰደቺኝ …አንድ ወር ከ15 ቀን አልጋ ይዤ ተኛው…በስንት ጥረት እና የህክምና እርዳታ በመጨረሻ ዳንኩ፡፡ግን አንድ የዘላለም ጠባሳ ሸልመውኝ ነበር…ፈጽሞ ልድነው የማልችለው››
‹‹ምን..?››
‹‹የዘር ፍሬዬን አፍርሰውት ነበር፡፡ሽንት ለመሽናት ከምጠቀምበት በስተቀር ለሴት የሚሆን የስሜት መነሳሳት ሆነ የማድረግ ችሎታ እንዳይኖረኝ አድርገውኝ ነበር…እና ይህ እንደተፈጠረ እናትሽን በዛ ወጣትነት ጊዜዋ ቀሪ ዘመኗን ሙሉ ከእኔ ጋር እንድታባክነው አልፈለኩም ነበርና እንድንፋታ የተቻለኝን ጥሬ ነበር፡፡ግን ይሄው 25 ዓመት እስከዘሬ አልተሳካልኝም፡፡በዚህ ታሪክ ውስጥ በእሷ ልክ የተጎዳ የለም፡፡የእኔ እንኳን አንዴ የሆነው ሆኖብኛል.. እሷ ግን ሁሉን ነገር ማድረግ እየቻለች ነው…፡፡እናም ደግሞ አብራኝ እንዳትተኛ እና እልጋችንም እንዲለያየ ያስገደድኳት እኔ ነኝ ፡፡ሰውነታችን ሲነካካ የእሷ አካል ሲግል እኔ ግን በንዴትና በቁጭት ሲሸማቀቅ፤ እሷ ልትሰመኝ ሲያምራት እኔ ደግሞ ያንን እያየው ስሳቀቅ ..፡፡በቃኝ አልኳት..፡፡በቃን አካላችንን በማነካካት ስቃያችንን ለምን ገሀነማዊ እናደርገዋለን እልኳት…?ጥዬሽ እንዳልጠፋ ከፈለግሽ በማሀከላችን ያለውን ክፍተት ጠብቂ አልኳት.፡፡.መለያየት የለብንም ምትይ ከሆነ የፈለግሽውን ነገር በፈለግሽ ጊዜ ከሌላ ሰው ጋር በውጭ ብታደርጊ ምንም ተቃውሞ የለኝም አልኳት …፡፡ሀሳብሽን ቀይረሽ መፋታት አለብኝ በምትይበት ቀን በደስታ እሸኝሻለው ብያታለው፡፡ያው እስከዛሬ ያንን ጥያቄ ይዛ አልመጣችም..እና አልጋችንንም ብቻ ሳይሆን መኝታ ቤታችንንም እንደለየን ይሄው ለዓመታት አለን፡፡
ተቃቅፈን እስኪደክመን ድረስ ነው የተላቀስነው……አንዳችን አንዳችንን ማፅናናት አላሰኘንም፤ አልሞከርንምም፡፡አዎ የምንወደውን የጋራ ዘመዳችንን እንደተረዳን ነገር ነው ሁኔታችን፡፡እያንዳንዱ ሰው ለካ በውስጥ የሆነ ሀገር የሚያህል ሚስጥር ቀብሮ ነው የሚኖረው፡፡እንዴት ይሄን ጉድ እኔ ልጃቸው እንኳን ሳላውቅ እንባውን እየጠራረገ እና የኔንም እያበሰልኝ መናገሩን ቀጠለ‹‹እና እናትሽ ለእኔ ስትል ነው እንዲህ የሆንከው የሚል ፀፀት ውስጧን እንዳሰቃያት ነው..ለዛ እራሷን በመቅጣት እድሜዋን ጨርሳዋለች፡፡እንደዛ የተበሳጨችብሽ ለዛ ነው፡፡ቁስሏን ነካክተሸ ስለደማሽባት…››
‹‹አሀ እኔንም ከተወለድኩ ጀምሮ ትኩረት ምትነፍገኝ በዚህ ታሪክ ምክንያት ነዋ..እኔን እርጉዝ ሆና ባይሆን እሷ ነበረች የምትሄደው..አንተ ላይ ሚደደረስብህ ነገር አልነበረም..እና እኔን ስታይ በአንተ ላይ የደረሰው መከራ ነው የሚታያት ማለት ነው..አይደል..?፡፡››
‹‹እሱን እርሺው ልጄ ..አንዳንድ ነገሮች እኛ ፈለግንም አልፈለግንም መሆን ባለበቸው መልኩ ከመሆን አያመልጡም፡፡ያው መቼስ እኛ ሰዎች ነንና እንዲህ ቢሆን ኖሮ …?እንዲ ባደርግ ኖሮ እያልን በፀፀት እራሳችንን እንቀጣለን እንጂ መሆን ያለበት ይሆናል››
‹‹አንድ የመጨረሻ ጥያቄ››
‹‹አሁንማ ዋናውን ነገር አውቀሻል.. የፈለግሺውን ጠይቂኝ… ከነገርኩሽ በላይ ሚከብድ ጥያቄ ልትጠይቂኝ አትቺይም..››
‹‹እማዬ…?›› ጥያቄውን ጀምሬው መጨረሱ ከበደኝ
‹‹እማዬ ምን..?››
‹‹እማዬ ታዲያ ይሄን ሁሉ አመት ..ማለቴ ጓደኛ እንኳን የላትም ብለህ ታስባለህ?ማለት ላንተ ላትነግርህ ትችላለች…››
‹‹ግዴለም ሳትጨናነቂ ጠይቂኝ ….ለማለት የፈለግሺው ገብቶኛል…በስንት ውትታና ጭቅጭቅ ከአስር አመት በፊት አንድ በጣም የሚወዳት ሰው ነበርና ከእሱ ጋር ጀምራ ነበር….እኔ አውቄ ማለት ነው ..ነግራኝና አስፈቅዳኝ፡፡አስፈቅዳኝ ብቻ ሳይሆን ገፋፍቼያት፡፡እንደዛ ብታደርጊ እኔም ስለአንቺ መጨነቁ ይቀንስልኛል ብያት..››
‹‹ታዲያ እንዴት ሆኑ..?››
‹‹ስድስት ወር እንኳን አልዘለቀችበትም..››
‹‹ምነው ..?ተጣሉ.. ..?››
‹‹አይ መጣላት እንኳን አይመስለኝም….ሰውዬው በፊት ከሚያፈቅራት በላይ እያፈቀራት ሲመጣ ይረብሻት ጀመር…››
‹‹እንዴት እድርጎ ነው የሚረበሻት..?››
‹‹ትተሸው ነይ ላግባሽ እያለ ነዋ››
‹‹እንዴ!!!! ሰውዬው በአንተ ላይ ስለተፈጠረው ነገር ያውቃል እንዴ..?››
‹‹በፍጽም አያውቅም…፡፡ያው እንደማንኛውም ለትዳሯ ታማኝ እንዳልሆነች ሴት ወይም ባጋጣሚ እንደተሳሳተች እና ከእሱ ፍቅር ይዟት በዛው ግንኙነቱ ውስጥ የቆች አድርጎ ነበር የሚያስበው፡፡ግን ያ አይበቃኝም አለ…እሱም ሚስቱ የሞተችበት እና ለአመታት ብቻውን የሚኖር ነበርና ሙሉ በሙሉ ፈለጋት…››
‹‹ምን አይነት ደፋር ነው!!!››
‹‹ድፍረት አይደለም… እናትሽ አሻፈረኝ አለች እንጂ አኔም በሰውዬው ሀሳብ ተስማምቼ ነበር፡፡ለእናትሽ በጣም ጥሩ ሰው ነበር…ያፈቅራት ነበር…..በዛ ላይ ስራቸው አንድ ላይ ነው…››
‹‹ምን…..?ማነው አውቀዋለው…..?››
‹‹የአለቃሽ የፍሰሀ አባት ነው፡፡ሁለቱም የተለያዩ ካምፓኒዎችን ነበር የሚመሩት ከዛ አዋህደውት ነው አሁን የምታውቂውን ግዙፍ ካምፓኒ የመሰረቱት፡፡ግን በትዳሯ መወሀድ ካምፓኒዎቻቸውን እንደማዋሀድ ቀላል አልሆነላቸውም....››
‹‹አሁን ገባኝ…››
‹‹ምኑ ነው የገባሽ..?››
‹‹አይ ከምሰማቸው ነገሮች ተነስቼ ብዙ ጊዜ በዚህ ሰውዬ እና በእናቴ መካከል የሆነ አለመጋባባት እንደለ እገምት ነበር….አሁን ምክንያቱ ግልጽ ሆነልኝ…ሁለቱም የየራሳቸው ልጆች ካምፓኒውን ተረክበው እንዲመሩላቸው አጥብቀው የሚጥሩበትንም ዋና ምክንያት ተገለፀልኝ…..ሳያስቡት

ጦርነት ውስጥ ገብተዋል….››
‹‹ይሆናል ››አለኝ አባቴ….
‹‹አዎ እንዳዛ ነው ..››አልኩት
‹‹አንድ የመጨረሻ ነገር ልንገርሽ››
‹‹ምንድነው አባ››
‹‹አጎትሽ..ያ አስመለጥኩት ያልኩሽ፡፡ከዘመናት የስደት ኑሮ ቡኃላ ሰሞኑን ሊመጣ ነው፡፡ በመንግስት ጥሪ ወደሀገሩ ሊመለስ መሆኑን ደውሎ ነግሮኛል…››
‹‹የራሱ ጉዳይ›› አልኩት
‹‹ዝም አለኝ…
ሁለታችንም ድክምክም ብለን በስካር እና በሀዘን አንገታችንን ደፍተን… ተደጋግፈን ወደመኝታ ቤታቸን ስንሄድ ከላሊቱ 10 ሰዓት አልፎ ነበር ፡፡እንደገባን አልጋችን ላይ ወጥተን እቅፍቅፍ ብለን ስንተኛ ወደጆሮ ተጠጋውና ‹‹አባ አይዞህ እሺ እኔ ልጅህ ሁሌ ከእቅፍህ ውስጥ አልወጣም …ሁሌ …እና ደግሞ በጣም ነው ውደድድድድ ማደርግህ››አልኩት
ግንባሬን ሰመና ‹‹አውቃለው …እኔም ሁለ ነገሬ ነሽ….አሁን ሁሉን ነገር እርሺና ተኚ ››አለኝ
‹‹እ……ሺሺሺሺ››ረጂም ትንፋሽ...
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
‹‹ይሆናል ››አለኝ አባቴ….
‹‹አዎ እንዳዛ ነው ..››አልኩት
‹‹አንድ የመጨረሻ ነገር ልንገርሽ››
‹‹ምንድነው አባ››
‹‹አጎትሽ..ያ አስመለጥኩት ያልኩሽ፡፡ከዘመናት የስደት ኑሮ ቡኃላ ሰሞኑን ሊመጣ ነው፡፡ በመንግስት ጥሪ ወደሀገሩ ሊመለስ መሆኑን ደውሎ ነግሮኛል…››
‹‹የራሱ ጉዳይ›› አልኩት
‹‹ዝም አለኝ…
ሁለታችንም ድክምክም ብለን በስካር እና በሀዘን አንገታችንን ደፍተን… ተደጋግፈን ወደመኝታ ቤታቸን ስንሄድ ከላሊቱ 10 ሰዓት አልፎ ነበር ፡፡እንደገባን አልጋችን ላይ ወጥተን እቅፍቅፍ ብለን ስንተኛ ወደጆሮ ተጠጋውና ‹‹አባ አይዞህ እሺ እኔ ልጅህ ሁሌ ከእቅፍህ ውስጥ አልወጣም …ሁሌ …እና ደግሞ በጣም ነው ውደድድድድ ማደርግህ››አልኩት
ግንባሬን ሰመና ‹‹አውቃለው …እኔም ሁለ ነገሬ ነሽ….አሁን ሁሉን ነገር እርሺና ተኚ ››አለኝ
‹‹እ……ሺሺሺሺ››ረጂም ትንፋሽ...
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍሰሀ
===
በህይወቴ በጣም የተፈተንኩበት አንድ ሳምንት ነው እያሳለፍኩ ያለውት…በጣም አስጨናቂና ትንፋሽ የሚያሳጣ አይነት ሳምንት…. ደግነቱ ስራዎቼን ቀድሜ ማጠናቀቄ በጀኝ እንጂ በዚህ አይነት የጨፈገገ ስሜት እንዴት እሰራው እንደነበር ማሰቡ እራሱ ይከብደኛል ፡፡
ምክንያቱ አለመኖሯ ነው……ይሄው አይኖቼ አይኖቾን ካዩ አንድ ድፍን ሳምንት ተቆጠረ…የቤተሰብ ጉዳይ ስላጋጠመኝ ድሬደዋ ሄጃለው ነበር ያለቺኝ…እኔማ ደርሶ መልስም ቢሆን ልምጠና አንዴ አይቼሽ ልመለስ ብያት ነበር..ብትመጣም አታጋኘኝምና አትልፋ.. ይልቅ ዝግጅትህ ላይ አተኩር ፤ፍልሚያውን በድል ከተወጣህ ቡኃላ ደውልልኝ..እስከዛ እኔም እዚህ ያለውን ነገር ጨርስና እመለሳለው ካልሆነም ያለውበትን አድራሻ እነግርህና ትመጣለህ›› ስላለቺኝ… ምርጫ አጥቼ በናፍቆቷ እየተሰቃየሁ ባለቺው ተስማምቼ እጄን አጣጥፌ ቁጭ አላልኩም፡፡ምናልባት ድሬደዋ የሄደችበትን አድራሻዋን ባገኝ ብዬ ከሶስት ቀን በፊት በፊት ትሰራበት ወደነበረ ከዚህ በፊትም እንዲህ በጠፋችበት ጊዜ ወደአገኘዋት ሜክሲኮ መጽሀፍት ቤት ሄጄ ነበር ……መኪናዬን ቦታ አስይዤ በማቆም ወደ መጻሀፍ መደብሩ አመራው::ሁለት በአስራዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው ያሉት…አንደኛው ደንበኛ እያስተናገደ ስለነበረ ነፃ ወደሆነው ተጠጋሁ…
‹‹ምን መፃሀፍ ልስጥህ…..? ››አለኝ… እዚህ ቤት መፃሀፍ እንጂ ሴት ፍለጋ የሚመጣ ሰው ይኖራል ብሎ ስላልገመተ መሰለኝ ቀጥታ ስለመፃፍ የጠየቀኝ ፡፡
‹‹ፌናንን ፈልጌ ነበር..ሰሞኑን መጥታ ነበር?››
‹‹አይ ቆየች.. አስራ አምስት ቀን ሆኗታል››
‹‹ጓደኛዋ ነኝ …ማለቴ የመስሪያ ቤት ጎደኛዋ..ስልኳ አልሰራ ብሎኝ ነው ..ቢሮ ደግሞ እሷ ብቻ የምትሰራው አፋጣኝ ስራ ነበር..እና እቤቷን ልትጠቁመኝ ትችላለህ፡፡››
‹‹እቤታቸው ቤቴል አካባቢ እንደሆነ ነው እንጂ ትክክለኛውን ቦታ አላውቅም…ግን ትንሽ ብትጠብቅ እኮ ጋሼ ስለሚመጡ ትጠይቃቸዋለህ››
‹‹ጋሼ ማነው…..?››
‹‹አባቷ ናቸዋ››
‹‹እርግጠኛ ነህ ይመጣሉ?››
‹‹አዎ እንደሚመጡ ደውለው ነግረውኛል፡፡››
‹‹አይ እንደዛ ከሆነማ አሪፍ ነው.. እጠብቃቸዋለው ››አልኩ…ግን ደግሞ ወዲያው ሌላ ጥያቄ በውስጤ ተፈጠረ…‹‹ከአባቷ በጣም ትግባባላችሁ ማለት ነው?››ጠየቅኩት
‹‹እንዴ አሰሪዬ አይደሉ ለምን አንግባባም?››ሲለኝ እየገባኝ የመሰለኝ ጉዳይ መልሶ ድንግርግር አለብኝ
‹‹አሰሪዬ ስትል..…..?››
‹‹ይሄ የመፅሀፍ መደብር እኮ የእሷቸው ነው …ሌላም ቦታዎችም አላቸው››ሊያብራራልኝ ሞከረ…
‹‹ይሄ መጻሀፍ ቤት የፌናን አባት ነው?››
‹‹አዎ ››አለኝ ይሄን ሁሉ ሳታውቅ ነው እንዴ ጓደኛዋ ነኝ የምትለው በሚል ስሜት ..
ገረመኝ..ከዚህ በፊት እዚህ ባገኘዋት ጊዜ በትርፍ ጊዜዋ ተቀጥራ እንደምትሰራ ነበር የነገረቺኝ ፡፡ይሄ ሁሉ መዋሸት ለምን አስፈለገ?
በውስጤ የተፈጠረ የመደነቅ ጥያቄ ነበር…
‹‹አባቷ ጎበዝ ናቸው ማለት ነው?››አልኩት ልጁን….ስለእዚህች ሚስጥር ስለሆነች ልጅ ሌላ ተጨማሪ ሚስጥር እንዲነግረኝ በመፈለግ ለመጎትጎት ፈልጌ
‹‹እንዴ…!!!››አለና ዝም አለ
‹‹ምነው…..?››
‹‹ጋሼን አታውቃቸውም እንዴ?››
ነገሮች እንዳይበላሹ ዋሸውት‹‹አውቃቸዋለው››
‹‹አይ ጎበዝ ናቸው ስትል ገርሞኝ ነው››
‹‹ለምን ይገርምሀል…..?››
‹‹ጎበዝ ናቸው ማለት ነው ስትል በጉብዝናቸው ጥርጣሬ ያለብህ ይመስላል..እሷቸው እኮ ይሄንን የከፈቱት እኛንም ለመርዳት ነው እንጂ ጎበዝ ለመሆን አይደለም…አስተማሪነታቸው እና ደራሲነታቸው ብቻ ለጉብዝናቸው በቂ ነው››
‹‹እሱስ እወነትህን ነው››አልኩት ልክ አስተማሪም ሆነ ደራሲ መሆናቸውን እንደማውቅ ሆኜ…‹‹ አሀ የአስተማሪና የደራሲ ልጅ ነሻ?.ለዛ ነው ነገሮችን መበታተን እና መልሶ መሰብሰብ ሚያስደስታት….አሁን ገባኝ››ብዬ በወስጤ አብሰለሰልኩ…አሁን በዘዴ ብዙ ነገር እያወቅኩ ነው…ይበልጥ ለማወቅ ሌላ ዘዴ መጣልኝ፡፡
‹‹እስቲ የእሳቸው መፃሀፍ ይኖራል..…..?››
‹‹የቱን ልስጥህ……..?››
‹‹ሁሉንም የለኝም… አሪፍ ያልከውን …››
በፈገግታ ከዚህም ከዛም አየመዘዘ አምስት መፃሀፍ እጄ ላይ ዘረገፈ…
‹‹እንዴ…? ይሄን ሁሉ እንደፃፍ አላውቅም ነበር››መደነቄን መደበቅ አልቻልኩም
‹‹11 መፃሀፍ እኮ ነው ያላቸው..ይበዛብሀል ብዬ ነው የቅርቦቹን ብቻ መርጬ የሰጠውህ…. ልጁን እያዳመጥኩ ግን ደግሞ መፃሀፎቹን እያገላበጥኩ በማየት ላይ ሳለው አይኖቼ የመፃፍ ጀርባ ላይ የታተመ የደራሲው ፎቶ ላይ አረፈ ..ደነገጥኩ…. እባብ ሱሬው ውስጥ እንደገባበት ሰው አይነት ነው አደነጋገጤ ..ሰውዬውን አውቃቸዋለው፡፡ሌላውን መፃሀፍ ጀርባ ገለበጥኩ ፎቶ የለውም……ሌላውን ገለጥኩ አዎ እራሳቸው ናቸው…ከመቀመጫዬ ተነሳው….
‹‹ሂሳቡ ስንት ነው…..?››
‹‹የየትኛው…..? ››
‹‹የሁሉም››
መፃሀፎቹን ከእጆቼ ወሰደና ጀርባቸው ላይ ያለውን ዋጋ ደምሮ ነገረኝ..ከፍዬ መልስም ሳልጠይቅ ወጣሁ…
‹‹እንዴ አትጠብቃቸውም……..?››ልጁ ግራ ተጋብቶ ጠየቀኝ
‹‹ተመልሼ መጣለው ››ቻው..ተንደርድሬ መኪናዬ ውስጥ ገባውና አሁንም ድጋሜ የመጽሀፉን ጀርባ ላይ ያለውን ፎቶ አየሁት…ንዴትም ደስታም የተቀላቀለበት ስሜት ነው ተሰማኝ፡፡እኚን እኮ ነው ሹገር ዳዲዋ እንደሆኑ የነገረቺኝ ፡፡ለካ አባቷ ናቸው…?ሲያስደስት..ግን እንዴት ነው የምታስበኝ ?ይሄን ሁሉ ውሸት እንዴት ስትዋሸኝ ትከርማለች……? ስለእሷ የማላውቀው ሌላስ ምን አለ……?ይህቺ ልጅ እስከመቼ ነው እየራቀቀችብኝና እየጠለቀችብኝ የምትሄደው…?ለማንኛውም በእሷ በመታለሌ ከተበሳጨውት ይበልጥ ሹገር ዳዲዋ ናቸው ብዬ ለቀናት በንዴት ስንጨረጨር እና እንቅልፍ ሳጣበት የነበረው ጉዳይ ውሸት ሆኖ አባቷ በመሆናቸው የተደሰትኩት በእጥፍ ይበልጣል…
ከዛን ቡኃላም ስልኳ አይሰራም…ካላጋነንኩት ለመቶ የቀረብ መልዕክቶችን ልኬላታለሁ…ምንአልባት ከከፈተችው ወዲያው እድትደውልልኝ በማለት..ግን አንደዛ አልሆነም…ይገርማችሆል አንዳንዴ በውድቅት ለሊት ስምንትና ዘጠኝ ሰዓት ከእንቅልፌ ድንገት በርግጌ እነሳና ስልኬን አንስቼ እሞክርላታለው….ግን የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ዛሬ ግን በተቻለኝ መጠን ስለእሷ ከማሰብ እራሴን መግታትና እና ትኩረቴን ሰብሰብ አድርጌ ስለፍፃሜው ጦርነት ብቻ ማሰብ ነው የምፈልገው፡፡ቀኗ ዛሬ ነች…ማንነቴን ለአባቴም ለሌላውም ሰው የማሳይበት ቀን፡፡ይህቺን ቀን አብራኝ ለወራት የለፋችው ፊናን ከጎኔ ብትሆን ኖሮ የበለጠ ጠንካራ የበለጠ ልበሙሉ እሆን ነበር…አይ የኔ ነገር አሁንም መልሼ ወደእሷ ወሰድኮችሁ አይደል፡፡

👍5❤1