አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሁለት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ #ፍስሀ መፅሃፍ መደብሩ ቆሜያለሁ ነገረ ስራዋን በአትኩሮት እየተከታተልኩ ነው፡፡ ገዢው የሆነ መፃፍ ርዕስ ነገሯት ‹‹እንደዚህ የሚባል መጽሀፍ አለሽ.?››ጠየቃት ‹‹አለኝ ግን ለምን ፈለግከው?›› ‹‹አልገባኝም?ልገዛሽ ነዋ.?›› ‹‹እሱማ ልትገዛኝ ነው ?ለምን መጽሀፉን ልትገዛው ፈለክ ነው ጥያቄዬ?›› ‹‹ለምንስ ብፈልገው…»
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ሦስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ሆቴል ፍለጋ ብዙም አራቅንም ..እዛው ዞር ብለን ዋቤ ሸበሌ ነበር የገባነው…እንደተቀመጥን ነው የምንበላውን በማዘዝ ወደጭቅጭቃችን የገባነው…እኔን ፍለጋ ይሄን ያህል መንገድ ይጓዛል ብዬ አልገመትኩም ነበር…እርግጥ ነገሮችን በፍጥነት እንዲህ እንዲሆኑ አድርጌ ስልኬንም፤ አድራሻዬንም አጠፋፍቼ ከመስሪያ ቤቴ የጠፋውት አውቄ ነው …ለእሱ የማሰቢያ እና የመረጋጊያ ጊዜ እንዲያገኝ በማሰብ ….እንጂማ ስራዬን እሱ ስላለ መልቀቄ አይደለም..እንደዛማ አይታሰብም…ሰው በገዛ ግዛቱ ውስጥ በታነፀ ቤተመንግስት ሊነግስበት ያሰበውን ወንበር ሌላ ተቀናቃኝ ልቀቅ ስላለው በቀላሉ ይለቃል…አይ በፍፁም ይሄ የነገስታት ባህሪ አይደለም..እሱ በንግስናው ኃይል ተማምኖ ወግጂልኝ ቢለኝ እኔ በቀላሉ ምኞቱን ላሳካለት አልችልም..ምክንያቱም እኔም ከእሱ እኩል ኃይል ያለኝ ንግስት ስለሆንኩ…
‹‹እኔን ፍለጋ እንዲህ መባከንህ አስደስቶኛል››አልኩት
‹‹ጉረኛ አትሁኚ… ስለአንቺ አንዳንድ ነገር ሳጣራ ከበፊትም ጀመሮ በካምፓኒው አንቺን በተመለከተ ያለው ነገር ትክክል ስላልመሰለኝ ያንን ለማስተካከል ነው..የአንድ አዲስ መሪ ስራ የወደፊት የካምፓኒውን አካሄድ ማስተካከል ብቻ ሳይሆን ወደኃላም ተመልሶ በባለፍት መሪዎች አላግባብ የተሰሩ ስራዎች ካሉ ለእነዛ እርማት እንዲደረግ ማሰድረግም ጭምር ነው…
‹‹ስለመሪነት ጥሩ ግንዛቤ እያገኘህ ነው››
‹‹አዎ…አስተዳደግሽ፤ የቤተሰቦችሽ ሁኔታ እና የህይወት ገጠመኞችሽ የፈጠሩብሽ ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ ካምፓኒያችንም ላንቺ የሰጠው ቦታ ለህይወትሽ መበላሸት አንድ አስዋፅኦ እንዳበረከተ ተሰምቶኛል..እኔም ነገሩን በደነብ ሳላጣራ በእሳቱ ላይ ቤንዚል ጨመርኩበት››አለኝ እጆቹን እያፍተለተለ…አይገርማችሁም አንዳንድ ሰው ወደ ህይታችሁ ድንገት ከመንገድ ጎራ ብሎ ይገባና ገና በሁለት እግሩ እንኳን ተስተካክሎ ሳይቆም አፍርሼ ልስራችሁ ይላል፡፡
‹‹ያው ቸኩሎ መፍረድ የአንተ ብቻ ሳይሆን…የእኛ ኢትዬጵያውያን ዋና ችግር ነው.. ለወሬ ያለን ፍቅር ለራሳችን ካለን ፍቅር በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡እንደህዝብ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ተምረዋል በሚባሉት የህብረተሰብ ደረጃ ጨምር የ<critical thinking >ልምምድ የለንም… የሆነ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት የሰማነውን ወሬ ‹‹ለምን?›› ‹‹እንዴት?›› ‹‹የት?›› ‹‹ መቼ?›› ብለን በመጠየቅ የነገሩን ብልት በታትነን የማየት የምናደርገው ጥረት ለዜሮ የቀረበ ነው፡፡የሰማነውን ወሬ ወይም መረጃ በዚህ መጠን መመርመር ደግሞ የመረጃዎችን ጥራት ለመጨመር..እርግጠኝነቱን አስተማማኝ ለማድረግ እና እወነተኝነቱን በአስተማማኝ መንገድ ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገዶች ናቸው፡፡ እኛ ግን እንደዛ አናደርግም…በዛም ምክንያት ውሳኔያችን ቡዙ ግዜ የጥድፊያና በስህተት የተሞላ ነው››አልኩት… ከገባው ብዬ
‹‹አዎ ትክክል ነሽ››አለኝ ኮራና ጀነን ብሎ
‹‹አየህ አሁንም ተሳሳትክ..ትክክል መሆኔን እንዴት በዚህ ቅፅበት ልታረጋግጥ ቻልክ….?››
ግራ ገባውና ‹‹ማለቴ….››ብሎ ሊያብራራልኝ ሲሞክር መልሼ ጣልቃ ገባውና
‹‹ግዴለም ብታስረዳኝም አታሳምነኝም..ይልቅ ህይወቴ እንደተበላሸ ስትናገር ነበር…እስቲ እንዴት እንዲያ ልታስብ እንደቻልክ አስረዳኝ..….?››
‹‹ይሄ ምን ማስረዳት ያስፈልገዋል…በዛ ነጥብ ዲግሪ ተመርቀሽ በትንሽ ደሞዝ በፀሀፊነት እየሰራሽ ነው..በቀደም አያትሽ ከሚሆን ሰው ጋር አግኝቼሻለው…ዛሬ ደግሞ ተራ የሽያጭ ሰራተኛ ሆነሽ መጽሀፍ ስትቸረችሪ ነው ያገኘውሽ…ህይወትሽ እርጋታ የሌለው ምስቅልቅሉ የወጣ ነው….ከዚህ በላይ የህይወት መበለሻሸት ከየት ይመጣል››በቃ በእሱ ቤት የእኔን ህይወት ብጥርጥር አድርጎ አጥንቶ ጨርሶል..
‹‹እውነት ግን ምንድነው ….?››ጠየቅኩት
ግራ ተጋባ‹‹….ምን አልሺኝ….?››
‹‹እውነት ምንድነው..….?››ፍጥጥ ብዬ ጥያቄዬን ደገምኩለት
‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው….….?እውነት ሀቅ ነው…በትክክል የተተገበረ ወይም የተነገረ ክንውን ነው..በቃ ይሄው ነው፡፡››
‹‹እሱ ብቻማ አይደለም…እውነት እረቂቅ ነው..እውነት ጥልቅ ነው…የሰማህው ነገር ሁሉ እውነት ሊሆን አይችልም..ለምን ይመስልሀል እኔ እና አንተ አንድ አይነት ነገር ከአንድ ሰው በእኩል ሰዓት ብንሰማ የምንረዳበት መንገድ አንድ አይነት ሊሆን አይችልም…ምክንያም ሁለታችንም በየራሳችን አዕምሮ ተጠቅመን ነው ተርጉመን ነገሩን ለመገንዘብ የምንጥረው…..ስንተረጉም ደግሞ የበፊት የህይወት ልምዳችን..የምንከተለው የሀይማኖት አይዲኦሎጂ፤ ከተወለድንበት አካባቢ ማህበረሰብ የቀሰምነው ባህል፤ የራሳችን ፍላጎት…..እነዚህና ሌሎችም በአተረጋጎማችን ላይ የየራሳቸውን ስውር ተፅዕኖ ያሳድራብናል…… የሰማነው እውነት በግማሽ ይበረዛል ማለት ነው…ያየነውም እንደዛ..፡፡ሌላ ምሳሌ ልስጥህ የአንድ ወጣት ልጃገረድ ፎቶን ሶስት ወጣት ወንዶች ቢያዩት እና ከሳዕታት ቡኃላ ምን እንዳዩ ቢጠየቁ..አንድ የተቀሰረ አስጎሚዥ ጡቶች ያላት ወጣት ይልሀል…ሌላው የሚያምረ መቀመጫ ያላት ሞዴል መሆን የምትችል ወጣት ይልሀል…ሌላው ደግሞ የሚያምር ቁንጅና ያላት ግን ልቧ በሀዘን የተሰበረ፤የእኔ ያለችውን ነገር በመጠበቅ በናፍቆ እየተሰቃየች መሆኖን አይኖቾ ውስጥ ያጋቱት እናባዋ የሚመሰክሩ ፤ ግን ደግሞ ያልሸነፍ ባይነት እና የራስን ስሜት የመቆጣጠር ጥረት በፊቷ ላይ የሚነበብባት፤ከዕድሜዋ በላይ የምታውቅ ወጣት ነች ይላል፡፡አየህ ሶስቱንም አስተያየት ሰጪዎች አንድ አይነት ስዕል ከአንድ አይነት እርቀት ላይ አይተው የተረዱት ነገር የተለያየ ነው፡፡እውነቱ የማናኛቸው ነው…….?አየህ እውነት እንደሽንኩርት ነው ሚባለው ለዛ ነው…በላጥከው ቁጥር ሌላ አዲስ ነገር..አሁንም ስትልጠው ሌላ ሚስጥር…..አንዳንዴማ ማብቂያ ሁሉ ላይኖረው ይችላል….ጲላጦስ እኮ እኔ ማውቀው አለማወቄን ነው ያለውም አንድም ለዛ ነው….ያወቀ የመሰለው ሁሉ እሱ ገና ጀማሪ ተማሪ ነው….
‹‹ወይ አንቺ ልጅ…እያወራን የነበረውን ቁም ነገር እኮ አወሳስበሽ ድራሹን አጠፋሽው….››
‹‹አይ አሁን ያወራውት ነው ትክክለኛው ቁም ነገር….አየህ የእኔ ህይወት ብልሽትሽት ማለቱን ለመወሰን በአንድ ሰምንት ውስጥ ያየሀቸው ወይም የሰማሀቸው ቅንጭብጫቢ ታሪኮች ላንተ በቂዎች መሆናቸው አስገራሚ ነው››
‹‹እኛ ካምፓኒ በፀሀፊነት እንደምትሰሪ ማንም ተናገረው ማንም እውነት ነው…..በቢዝነስ ማነጅመንት ዲግሪ እንዳለሽም አንቺ እራስሽ አትክጂም…ሹገር ዳዲሽንም በአይኔ ነው ያየውት››
በዚህ ጊዜ ምግቡ ቀርቦልን እየበላን ነበር እያወራን ያለነው..ሁሉን ነገር ጨርሶ ሳያውቅ እንደአወቀ የሚያወራው ነገር ብሽቅ አደረገኝ ‹‹ሌላውን ተወው ….ሹገር ዳዲዬ መሆኑን በምን አረጋገጥክ…….?››
‹‹አይቼሻለው አልኩሽ እኮ..አንቺም አረጋግጠሽልኛል…››
‹‹ዋሽቼህ ቢሆንስ…….?››
‹‹በምን ምክንያት ትወሺኛለሽ ….?››
‹‹ላስቀናህ ፈልጌ››
ሳቁን ለቀቀው…
‹‹ምን ያስቅሀል….?››
‹‹ለምን ብዬ ቀናለው…አፈቅሬሽ ነበር እንዴ….?››
‹‹እኔ እንጃ… ሰው አንድ ሰውን ላይ ካለምክንያት ትኩረት ካደረገና ምክንያት እየፈለገ ጥዋትና ቀን የሚነጫነጭበት ከሆነ ያው በእኔ ግምት ፍቅር ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡››
‹‹እንደ ህይወትሽ ለራስሽ ያለሽ ግምት የተዘበራረቀ ነው…አንዳዴ መሬት የሚወረድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰማይ ላይ ልንጠልጠል የሚል…›› አለኝ …በመበሳጨትና ስሜቱን ለመቆጣጠር በሚጥር የስሜት መደበላለቅ
‹‹እሺ ተሳስቼ ይሆናል..ለምን
👍1
እንደመጣህ እውነቱን እራሰህ ንገረኛ…….?››
‹‹አይ የመጣውት ለሁለት ነገር ነው…አንደኛ ያው ባለፈው ያሥፈረምሺኝ የሰራተኞች አመታዊ በዓል ነገ ስለሆነ እንዳትቀሪ ልነግርሽ ነው፡፡››
‹‹ሁለተኛውስ….?››

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሦስት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ ...ሆቴል ፍለጋ ብዙም አራቅንም ..እዛው ዞር ብለን ዋቤ ሸበሌ ነበር የገባነው…እንደተቀመጥን ነው የምንበላውን በማዘዝ ወደጭቅጭቃችን የገባነው…እኔን ፍለጋ ይሄን ያህል መንገድ ይጓዛል ብዬ አልገመትኩም ነበር…እርግጥ ነገሮችን በፍጥነት እንዲህ እንዲሆኑ አድርጌ ስልኬንም፤ አድራሻዬንም አጠፋፍቼ ከመስሪያ ቤቴ የጠፋውት አውቄ…»
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_አራት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


‹‹ሁለተኛው ቢሮ በሰራተኛ አስተዳደር አንድ ኤክስፐርት ለመቅጠር ይፈልጋሉ…እዛ ቦታ እንድታመለክቺ ልመክርሽ ነው…››
‹‹እንዴ!!! በስነምግባር ጉድላት ከስራው የተባረረ ሰው እኮ መልሶ መዋዳደር እንደማይችል ይታወቃል..ለዛውም ከበፊቱ ከፋ ባለ የስራ መደብ….?››
‹‹ግድ የለሽም በማነጅመንት እናየዋለን…ያ ውሰኔ የእኔ የግሌ ነበር..እንደውም ባንቺ መባረር ማናጅመንቱ ብዙም ምቾት አልተሰማቸውም..ስለዚህ አንቺን ለመመለስ ብዙም አያንገራንግሩም..››
‹‹አንተስ.?››አልኩት በብልጣ ብልጥነቱ ተደምሜ..
‹‹እኔ ድምፀ-ተአቅቦ አደርጋለው….በእነሱ ድምጽ መልሰሽ በሚገባሽ ቦታ ትቀጠሪያለሽ..ህይወትሽ ይስተካከላል….ግን ቅድመ ሁኔታ አለው››
‹‹ምን ?የፍቅር ጥያቄ እንዳይሆን››
‹‹ቢሆንስ?››አለኝ ፊቱን ጨምድዶ
‹‹አይ እንቢ ስለማልልህ ይቅርብህ ልልህ ነው››
በግርምት አፍጥጦ ለደቂቃዎች አየኝና ‹‹እያስፈራራሺኝ ነው…….?››
ማስፈራራት አይደለም.. ለእኔ ፍቅር ማለት መላላስ እና መወሳሰብ አይደለም…ሁሌ አድቬንቸር ነው…ሁሌ ሚተረመመስ ነገር ፈልጋለው…››
‹‹ግን .ጤነኛ አዕምሮ ነው ያለሽ...?እንዴት ሰው የሚተረማመስ ነገር ያስደስተዋል.?››
‹‹አየህ የተረማመሰውን ነገር በጥበብ ሳስተካክል የሚሰማኝ የአሸናፊነት እና የውጤታማነት ደስታ ነው የፍቅር እርካታዬ…ሁል ጊዜ በፍቅር ውስጥ ጌም እንዲኖር እፈልጋለው…ላሸንፍም ልሸነፍም እችላለው..ዋናው ሁል ጊዜ ምጫወተውን ማጣት የለብኝም …ጥሩ ቁማርተኛ ካልሆንክ ከአኔ ጋር በፍቅር መዝለቅ አትችልም እና ይቅርብህ ብዬ ልመክርህ ነው፡፡››
‹‹ምን ጉድ ነሽ በፈጣሪ…እኔ ቅድመ ሁኔታ ያልኩት አንድ ከዛ ከሹገር ዳዲሽ ጋር ያለሽን ፍቅርም ሆነ የስራ ግንኙነት ታቆሚያለሽ ልልሽ ነው..ሌላው እዚህ መፃሀፍት መደብርም ያለሽን ስራ እንደዛው….
‹‹ያስቃል..››አልኩት..እውነትም ገርሞኝ
‹‹ምኑ ገረመሽ?››
‹‹በዚህ ምድር ላይ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ .. givers , takers , matcher ይባላሉ፡፡ < givers > ምንም ነገር ሲሰጡህ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ነው…ሲያፈቅሩህ የእነሱን ማፍቀር ብቻ እንጂ የእነሱን መፈቀር አለመፈቅር አያስጨንቃቸውም..ሲለግሱህም ከአንተ በመልሱ ምንም የሚጠብቁት ነገር የለም…እንደዚህ አይነት ሰዎች የአለም በጣም ደሀ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ ግን ሰማያዊ ስብዕና ያላቸው ናቸው… በተቃራኒውም የአለም በጣም ሀብታሞቹና ባለትልቅ ገቢ ባለቢቶችም እንዚሁ < givers > የሚባሉ ሰዎች ናቸው..ምክንያቱም ለአበባ ያደረጉት በእጥፍ ከሰለሞን ይደረግላቸዋል…ይሄ የተፈጥሮ ህግ ነዋ፡፡‹‹ለማታውቀው ወገንህ አንድ ስትሰጥ ከማታቀው ዘጠኝ ተጭምሮ አስር ሆኖ ይመለሰልሀል…›› የሚለው ዋና መመሪያቸው ነው..እነእየሱስ ፤ ነብዩ ሙሀመድ፤እነማዘር ትሬዛ..እነአበበች ጎበና እነሲስተር ዘቢደር፤ማህተመጋንዲ፤ማንዴላ ወዘተ …እነዚህ ዝም ብለው በነፃ ሲሰጡ በመኖራቸው ሀብታምነትን ብቻ ሳይሆን በታሪክ ማህደር ዘላለማዊነትንም የተጎናፀፈ ናቸው….
ሌላው‹‹ takers› የሚባሉት ናቸው …ከሌላው መቀበልን ብቻ ነው ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱት..ሁሌ ማትረፍን ብቻ ነው የሚያስቡት…ለእነሱ ዋናው ውጤት ነው …ምን ያህል አተርፋለው እንጂ በእኔ ማትረፍ ውስጥ እነማን ይጎዳሉ… ?የማን ቤት ይፈርሳል..?የማን ነፍስ ይነጠቃል ?አያስጨንቃቸውም..፡፡የአለም ሙሰኞች፤ ኮንትሮባንዲስቶች፤ቅጥረኛ ነፍስ ገዳዬች… ሀሺሽ ነጋዴዎች እዚህ ግሩፕ ውስጥ ይጠቃለላሉ..
ሶስተኛዎቹ ‹matcher› የሚባሉት ናቸው፡፡በሰጡት ልክ መቀበልን ይፈልጋሉ….ሁል ጊዜ በህይወት ሚዛን እየጠበቁ መጓዝ ዓላማቸው ነው…ዲፕሎማቶች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው…‹በሰጥቶ መቀበል መርህ› የሚጓዙ ናቸው… በዚህ ህግ ስትሰጥ በተሻለ መጠን እንደምትቀበል እርግጠኛ መሆን አለብህ››.እከክልኝ ልከክልህ…መመሪያቸው ነው፡፡
‹‹እና እኔ ከሶስቱ የትኛው ነኝ.?››አለኝ
‹‹እራስህን ፈልገዋ….አሁን ይብቃን እንሂድ….››
‹‹ስላልኩሽ ነገር እኮ ምንም አላልሺኝም...?››
‹‹እየሄድን መኪና ውስጥ ነገርሀለው….››
‹‹እሺ ››ብሎ ሂሳብ ሊከፍል አስተናጋጁን ደረሰኝ ሲጠይቀው..እንደተከፈለ ነገረው…
‹‹ማን ነው የከፈለው...?››አይን አይኔን እያየ ባለማመን ጠየቀኝ..የእኔም ጥያቄ ስለነበረ ልመልስለት አልቻልኩም
‹‹እዛ ጥግ ተቀምጦ የነበረው ሰውዬ ጥቁር ሱፍ ለብሶ የነበረው ..›› አስተናጋጁ አብራራልን
‹‹ማነው አውቀሺዋል….?››
‹‹አዎ፡፡ ተነስ እንሄድ በቃ…የእኔ ሰው ነው››አልኩት…
የአይኖቹ ቀለማት ሲቀየሩ ታወቀኝ
‹‹ምንድነው እንዲህ አይነት ነገር… ሰው በሰው ነገር እንዲህ ጥልቅ ሲል ሲያበሳጨኝ ..ከፈለገ ሌላ ቀን አይጋብዝሽም.?…››ይሄንን እጃችንን ታጥበን ከሆቴሉ እየወጣን በነበረበት ጊዜ ነው የሚነጫነጭብኝ..
‹‹ ምንድነው የደበረህ ….?ይክፈል…እንደውም ጥሩ ነው››
‹‹ለምን ይከፍላል .?አሁን አራት መቶ የማትሞላ ብር ከፈለ አልከፈለ ለእኔ ምኑ ነው ጥሩ…ጉረኛ በይው…››
ሁሉን ነገር ከማሸነፍና ከመሸነፍ ጋር የሚያገናኝ ምን አይነት ሰው ነው… .?አሁን አበሳጨኝ ‹‹እውነትህን ነው….እንደውም ብሩን ስጠኝ ልመልስለት…››አልኩት
ፈገግ አለ..‹‹የት ታገኚዋለሽ ወጥቷል እኮ››
‹‹አይ ያ ፊት ለፊት ያለው ብቲክ የእሱ ነው.. ስጠኝና አፍንጫው ላይ ወርውሬለት ልምጣ..ነገ ይሄንን እንደውለታ ቆጥሮ ሊለፋደድብኝ ይችላል››
ጥርስ በጥርስ ሆነ‹‹ ..በደስታ ብሩን አውጥቶ ሰጠኝ..‹‹ጠብቀኝ ››አልኩና አስፓልት ጠርዝ ላይ አቁሜው በዝብራ ተሸገርኩና ሁለት ልጆች ታቅፋ ለምትለምን ለማኝ እጆ ላይ አስጨበጥኮት ሴትዬዋ መብረቅ እንደመታት አይነት በድንጋጤ ፈዛ ለመጮህም ዳድቶት ስትርበተበት ፊቴን አዞርኩና መልሼ አስፓልቱን ተሸግሬ ወደእሱ ስሄድ እያጨበጨበ ጠበቀኝ …ሁኔታው የብሽቀት ነው…‹‹ጀግና ነሽ… ሸወድሽኝ ማለት ነው››አለኝ ለንቦጩን ጥሎ
‹‹አይ አልሸወድኩህም..አሁን ጋብዘኸኛል ማለት ነው….ስለዚህ ዘና ማለት ትችላለህ›› አልኩት
‹‹ግን ታውቂያለሽ አይደል …በጣም እብድ ልጅ ነሽ…የምትገርሚ እብድ…ነይ በይ ላድርስሽ..››
‹‹አይ.. አንተ በዚሁ ሄድ እኔ በዚች ጋ አቋራጬ መንገድ አለች …በዛ ሄዳለው.››
‹‹አረ ችግር የለም አደርስሻለው..››
‹‹ለራሴው ነው..በዚህ አቋራጭ አምስት ደቂቃ ነው የሚፈጅብኝ..አንተ ግን ገና መብራት ጠብቀህ አደባባይ ዞረህ 30 ደቂቃም አይበቃ..››
‹‹ይሁን ግን መልሱን አልነገርሺኝም እኮ...?››
‹‹እ እረሳውት ነገ 12 ሰዓት አይደል መነሻው ..እመጣለው..አንተም ባትለኝ ያ ፕሮግራም እንዲያመልጠኝ አልፈልግም››
‹‹ጥሩ ነው ስራውን ደግሞ ካዛ ስንመለስ ሰኞ ታመለክቺያለሽ..››
‹‹አይ አላመለክትም ቅዳሜ ወይም እሁድ እዛ ዝግጅቱ ላይ ሁሉም ሰራተኞች ባሉበት እኔን በተመለከተ በተሳሳተ መረጃ በማባረርህ ስህተት መስራትህን ተናግረህ ይቅርታ ትጠይቀኛለህ..ከዛ ሞራሌን በመንካትህ ለመካስ ይሄ ያልከኸውን አዲስ ቦታ በእድገት እንደሰጠኸኝ ለሁሉም ታበስራለህ….አንተ ራስህ እንደዛ ታደርጋለህ…እንደዛ ሲሆን ነው ሁሉ ነገር ተፈታ የሚባለው ከዛ እንዳልከው ስለሹገር ዳዲዬ እና ሰለ መፃሀፍ መደብሩ እናወራለን በል ቻው ››እልኩና ምንም እንዲናገር ዕድሉን ሳልሰጠው ፈዞ በደነዘዘበት ጥዬው ሄድኩ

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
አትሮኖስ pinned «#ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ ‹‹ሁለተኛው ቢሮ በሰራተኛ አስተዳደር አንድ ኤክስፐርት ለመቅጠር ይፈልጋሉ…እዛ ቦታ እንድታመለክቺ ልመክርሽ ነው…›› ‹‹እንዴ!!! በስነምግባር ጉድላት ከስራው የተባረረ ሰው እኮ መልሶ መዋዳደር እንደማይችል ይታወቃል..ለዛውም ከበፊቱ ከፋ ባለ የስራ መደብ….?›› ‹‹ግድ የለሽም በማነጅመንት እናየዋለን…ያ ውሰኔ የእኔ…»
.:
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_አምስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


እንዲህማ የእሷ መቀለጃ አልሆንም….እንዴ!!! ከሚገባት በላይ እኮ ፊት ሰጠዋት..አረ ፊት መስጠትም ብቻ አይደለም..ልቤንም ገልብጬ ነው የውስጥ ገበሩን ያሳየዋት….ካልጠፋ ሰው እሷን ምሳ ለመጋበዝ ጊዜዬን ማባከኔ ነው የሚቆጨኝ… መኪናዬን አስነስቼ ወደ ቢሮ እየተጎዝኩ ነው ፡፡ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩ ያለውት..አሁን በቃ ይህቺን ልጅ እበቀላታለው…፡፡እንዲህ ፊጥ እንዳለችብኝ ልኳን እንድታውቅ እና ጥሩ ትምህርት እንድታገኝ አደርጋለው…፡፡አዎ የእሷን አንገት ለማስደፋት ያስችለኝ ዘንድ ዘዴዬን መቀየር አለብኝ…፡፡አዎ ምርጥ ሀሳብ መጣልኝ… ስልኬን አወጣውና ደወልኩ፡፡ ለሳምንት ስልኳን ማንሳት አሻፈረኝ ብዬ ሳበሳጫት ወደከረምኳት ፍቅረኛዬ ጋር……..
‹‹አንተ በህይወት አለህ……..?ይደብርሀል ብዬ ነው እንጂ ግራ ከመጋባቴ የተነሳ ቢሮ ሁሉ ልመጣ አስቤ ነበር…ምነው ይሄን ያለህ……..?.››ተንጣጣችብኝ
‹‹ ሳሮን…ትንሽ ስልክ የማነሳበት ሁኔታ ላይ አልነበርኩ››
‹‹እንዴ ቢያንስ ሚሴጄን አትመልስም…..?››
‹‹ይቅርታ አጥፍቼያለው..››
‹‹እንዲህ ይቅርታ በማለት ብቻማ አንላቀቅም…..››
‹‹እኮ ልክስሽ ነው…ነገ እና ተነገ ወዲያ ካምፓኒያችን የዓመታዊ በዓሉን በቢሾፍቱ ያከብራል…››
‹‹እና …..?››
‹‹እና እኔ ያው ሀለቃ እንደመሆኔ መጠን ከፍቅረኛዬ ጋር እንድገኝ እድሉ ተሰጥቶኛል..››
‹‹ከፍቅረኛህ ነው ወይስ ከባለቤትህ…..?››
‹‹ያው ሁለቱንም ቢሉ አንቺው ነሽ ሌላ ማን አለ…..?››
‹‹አስደሰትከኝ….እና ምን አድርጊ እያልከኝ ነው…..?››
‹‹እናማ ተዘጋጂ ..ነገ 1 ሰኣት መኪናዬ በራፍሽ ላይ ቆማ ትጠብቅሻለች …››
‹‹እውነትህን ነው…..?››
‹‹እውነቴን ነው..ደግሞ አሁን ትንሽ ብር በባንክ አስገባልሻለው ፤የመጨረሻ የምትይውን መዘነጥ ዘንጠሸ እንድትመጪ ነው የምፈልገው… ካልሆነ ብዙ ቆንጆዎች ሳላሉ ትነጠቂያለሽ…››
‹‹አረ እኔ ልጅት……በመዘነጥ ማን ጫፌ ደርሶ…›
ለነገሩ ጨቅጫቃ ባትሆኚ በመልክና በመዘነጥ እንኳን ማንም ስርሽ አይደርስም…በተለይ በመዘነጥ›› በውስጤ ነው ያጉረመረምኩት …ስልኩን ከመዝጋቴ በፊት ግን..ትራፊክ ያዘኝ…ስልኩን ዘግቼ አንሸራትቼ ብለቀውም ትራፊኩ አልተሸወደልኝም..ምን ነካኝ አንዲህ አይነት ቀሺም ባህሪ እኮ አልነበረኝም….
ጥዋት ሳሮን ጋር ስደርስ አንድ ሰዓት ከሩብ ነበር፡፡እውነትም በዝነጣ ማን ጫፍሽ ይደርሳል….…..?ነው ያልኩት ገና እንዳየዋት …ዓይኖች ሁሉ ዛሬ የእኔዋ ንግስት ላይ ሲንከባለሉ መዋላቸው ነው…..በተለይ ያቺ ትዕቢተኛ …እሷ እንደሆነ ለጥሩ ምላስ እንጂ ለጥሩ አለባበስ ደንታ የላትም…. በደስታ እየተፍለቀለቅኩ እሷን ይዥ ቢሮ ስደርስ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡
እሷን እዛው መኪና ውስጥ እንድትጠብቀኝ አድርጌ ወረድኩና ወደቢሮ ግቢ ሄድኩ ….. አንድ ባስና፤ አንድ ሚኒባስ ቆሟል …ሰው ይተራማመሳል…አቶ ሰይፉ እንዳዩኝ በደስታ እየተፍለቀለቁ ወደእኔ መጡ..‹‹እንዴት ናችሁ… ሰው ሁሉ መጣ …..?›ለሰላምታ የዘረጉልኝን እጃቸውን እየጨበጥኩ ጠየቅኳቸው…
‹‹የመጡ ይመስለኛል …….አሁን ወደ መኪና እየገቡ ነው ..ለማጣራት እንዲመቸን መኪና ውስጥ ከገቡ ቡኃላ ይሻላል..ሁሉም መጥተው ከሆነ ….ከአስር ደቂቃ ቡኃላ እንነሳለን……..››
…በአምስት ደቂቃ ውስጥ ሁሉም ወደየመኪኖቹ ገብተው ቦታ ቦታ እንዲይዙ ተደረገ ..የእኔ አይን አንድ ሰው እየፈለገ ነው…. እስከአሁን አላየዋትም…ቆይ ወደባስ ውስጥ ገብታ ይሆናል …ብዬ ባስ ውስጥ ገባውና ሰራተኞችን ሰላምታ ለመስጠት በሚመስል ሁኔታ ፊት ለፊት ቆሜ እጄን ለሰላምታ እያውለበለብኩ አይኖቼን ከጥግ እስከጥግ አንከባለልኩ…. ባሱ ባዶ ነው..ማለቴ እሱማ ሙሉ ነው እሷ የለችም እንጂ …‹‹መልካም ጉዞ ››ብዬ ከባሱ ወረድኩና ወደ ሚኒባሶ ሄድኩ…ገብቼ ተመለከትኩ .. እዛም የለችም…
አቶ ሰይፉን አስጠራዋቸው…እያለከለኩ መጡ
‹‹እሺ ጨረሳችሁ…..?››
‹‹አዎ ሁሉም ተሞልተው መጥተዋል..ልንቀሳቀስ ነው››
‹‹እርግጠኛ ናችሁ…››
‹‹አዎ መዝገቡን ዘርገግተው በየስሙ ፊት ለፊት ረይት የተደረገበትን እያሰዩኝ… እይ አመስት ሰዎች ናቸው የቀሩት እነሱ ደግሞ በተለያየ ምክንያ መሄድ እንደማይችሉ ቀድመው አሳውቀዋል…››
ዙሪያ ጥምዝ መሄድን አቁሜ ‹‹ፊናንስ››
‹‹ፊናን እ..ረስቼት ነበር››
‹‹እንዴት ይረሷታል…..?››አልኳቸው …እስቲ ምን ማለቴ ነው…..?፡፡እሷ የእኔ ችግር እንጂ የእሳቸው ችግር አይደለችም፡፡
‹‹አይ ያው ስራ ለቃለች ብዬ ነዋ…. ትናንት ግን ደውዬላት ልመጣ እችላለው ብላኝ ነበር… ቆይ እስኪ ልደውልላት ›› አሉና ስልካቸውን አውጥተው ደወልሉላት…..ስልኳ አይሰራም
‹‹ታዲያ ምን ይሻላል…..?››ጠየቅኳቸው…ልክ ዝግጅቱ ሰርግ ሆኖ እሷ ደግሞ የሰርጉ ሙሽራ ሆና እንደዘገየች ነገር አንገቴን በሀዘን ሰብሬ
‹‹ረፍዶባትም ከሆነ በትራንስፖር መምጣት ትችላለች ..ስልኳን ስትከፍት እንድታየው መልዕክት ልክላታለው››ብለውኝ ወደስራቸው ሄዱ…
‹‹እኔም እያግረመረምኩ በራፉ አካባቢ በጥበቃ ስራ ላይ ወደነበረው ዘበኛ ሄድኩና የምፈልገውን ነገር ነገርኩት ..ከዛ ወደመኪናዬ አመራው፡፡እንደደረስኩ ‹‹ፍቅር ውጪ››አልኳት
‹‹ምነው..አንሄድም እንዴ…..?››
‹‹አይ ምን አንቀዠቀዠን…እነሱ ይቅደሙን… ቁርስ በልተን ቀስ ብለን እንከተላቸዋለን..››ብዬ ፊት ለፊት መንገድ ተሸግሮ ወደሚገኝ ካፌ ይዤት ገባውና ለእይታ የሚመች ቦታ መርጠን ተቀመጥን….ባሱም ሆነ ሚኒባሱ ተከታትለው ሲወጡና ሲሄዱ እያየው ነው…ቁርሱን አዘን ቢመጣም ለአመል ያህል ከመነካካት ውጭ የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም …አይኔ ቢሮችን በራፍ አካባቢ እደተሰካ ነው…..አሁን ፌናንን እየጠበቅኩ ነው ብላችሁ መቼም አትታዘቡኝም….ምን አልባት አርፍዳ ብትመጣ ወደዝግጅቱ ቦታ የምትመጣበት መኪና አጥታ እንዳትቀር ስለሰጋው….ካልመጣች እኮ እቅዴ ሁሉ በዜሮ ተባዛ ማለት ነው፡፡ ዘበኛው በነገርኩት መሰረት ከወዲህ ወዲያ እየተንጎራደደ እየጠበቃት ነው..እንደመጣች እንዲደውልልኝ ተነጋግረናል.. ቢሆንም በእሱ ላይ ብቻ እምነቴን ጥዬ ቁጭ ማለት እቻልኩም…አይኖቼ እዛው እንደተሰኩ ናቸው…
‹‹ከደቂቃዎች በፊት ፍልቅልቅ ነበርክ አሁን ደግሞ… ››አለቺኝ ሳሮን
‹‹አሁን ምን ሆንኩ…..?››
‹‹እኔ እንጃ…. ገባያ የሄደች እናቱን የሚጠብቅ ህጻን ልጅ ነው የምትመስለው..››
‹‹ትንሽ የፕሮግራሙ ቅንጅት ጥሩ ስላልመሰለኝ ነው እንጂ የምትይውን ያህል ምንም አልሆንኩም...››
‹‹ታዲዬ ምን አስጨነቀህ…..? ››
‹‹እንዴ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው……..?አሁን ምኔ ነው የተበሳጨ የሚመስለው…››ሰዓቴን ተመለከትኩ ሁለት ከሩብ ሆኖል …አንድ ሰዓት ድረሺ የተባለች ሴት ሁለት ከሩብ ድረስ ዘግይታ ትመጣለች ብሎ ማሰብ የዋህነት መሆኑ ስለገባኝ
‹‹በይ ከጨረሽ ተነሺ እንሂድ ››አልኳት
‹‹እሺ ››አለችና ተነሳች….ተያይዘን ካፌውን ለቀቅንና ቢሮ በራፍ ላይ ወደ ቆመችው መኪናችን አመራን….. ልክ እንደደረስን ዘበኛው እየተንቀዠቀዥ ወደ እኔ ሮጦ መጣና ‹‹ጌታዬ አልመጣችም››አለኝ ….‹‹እሺ›› አልኩትና ተጨማሪ ነገር እንዳይናገር ፊትን ከስክሼበት ፈጠን ብዬ መኪና ውስጥ ገባው እና እሷም እስክትገባ ጠብቄ መኪናውን አስነሳውት …ወደቢሾፍቱ ጉዞ ጀመርን….
‹‹ማነች…..?››አመዴን ቡን አደረገችው ..
‹‹ምኗ…..?››
‹‹ስትጠብቃት የነበረችው ሴት…አሁን ዘበኛው እንዳልመጣች የነገረህ ልጅ››አቤት የሴት ደመ ነፍስ
👍2
..ለ

መሆኑ ስንት የስሜት ህዋሳት ነው ያላቻው.?በተለይ ትኩረት ካደረጉ በዙሪያቸው የሚደረግ ነገርን እንደካሜራ ነው የሚሰበስቡት ..ዝም ቢሉ እንኳን እየሰራህ ያለህው ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን አውቀው ከመናገር በሆድ ውስጥ ይዞ ማስቀረት የተሻለ ነው ብለው ስለወሰኑ ነው..ይህ ችሎታቸው በግልጽ የገባኝ በቅርብ ነው.. ይሁን እንጂ በቀላሉማ እጄን አልሰጥም ‹‹አረ በናትሽ የምጠብቃት ሴት ብትኖር አንቺን ምን ይሁንልኝ ብዬ ነው ለምኜ ያስመጣውሽ…..?››
‹‹አለመንከኝም እኮ….ተለምነን ማናውቅ አደረግከን እንዴ… ገና ከአፍህ ወጥቶ ሳይልቅ ነው እሺ ያልኩህ….ሳስበው ለምን አንተን አፍቅሬ እደምሰቃይ ግርም ይለኛል…..?››
‹‹ምነው…..? የምፈቀር አይነት ሰው አይደለውም እንዴ…..?››ንግግሯ ግራ አጋብቶኝ ነው የጠየቅኳት…
‹‹እሱማ ማንኛዋም ሴት ብትሆን ይሄንን ውበትህን ስታይ መደንዘዞ የሚጠበቅ ነው..በዛ ላይ የተማርክና ሀብታም ነህ..ይሄ ለመጀመሪያ ፍቅር ለማስያዝ በቂ እንደውም ከበቂም በላይ ነው ፡፡ችግሩ ግን ከአንተ ጋር በፍቅር ለመቆየት የጠቀስኮቸው ኮሊቲዎችህ በቂ አይደሉም..ሴት ልጅ ትኩረት ትፈልጋለች….ሁልጊዜ የፍቅረኛዋ አይኖች በእሷ ዙሪያ ሲንከባለሉ ማየት ትፈልጋለች…ሲያገኛት የሚያቅፋት አስተቃቀፍ ወይም የሚስማት አሳሳምን ሳይቀር ትልቅ ትርጉም ትሰጠዋለች…ሲደውልላት የድምጽን ቅላጼ …እኚ ሁሉ ለአንድ ሴት ትርጉም አላቸው….››
‹‹እና በእነዚህ ሁሉ ዜሮ ነህ በይኛ…..?››
‹‹ዜሮ አልልህም… ግን ደግሞ ከደረጃ በታች መሆንህን ብደብቅህ መዋሸት ይሆንብኛል….እንደምወድህ እንጂ እንደምትወደኝ አይሰማኝም…››
‹‹እንዳዛ እንዲሰማሽ ምን ላድርግ…..?››
‹‹እኔ እንጃ…የሆነ ነገር ታደርጋለህ ብዬ አጠብቃለው….››
‹‹እስቲ ምን አይነት ነገር…..?››
‹‹አንድ ሴት ይሄ ፍቅረኛዬ ነው ብላ በተረጋጋ ስሜት እንድትቀመጥ ፍቅረኛዋ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅበት አታውቅም››
‹‹እኔ እንጃ.. ምንአልባት ሲያገባት እንዳትይኝ…››
‹‹እሱም ትክክል ነህ ግን በፍቅረኝነት እና በጋብቻ መካከል እጮኝነት የሚባል ነገር አለ ….ቀለበት ማሰር››አይ ሴት ..እነሱም አይወንዶች እንደሚሉ እኔም አይ ሴት!! ልበላ…..ቀስ ብላ በውስጧ ስታብላላው የከረመችውን ሀሳብ እንደቀልድ ዘረገፈችው…ፌናን እዚህ ዝግጅት ላይ መጥታ ቢሆን ኖሮ ይሄ የቀለበት እቅድ ጥሩ ነበር..እዚሁ ዝግጅት ላይ ፌናን እየተመለከተች ላደርገው እችል ነበር……አሁን ግን …!!
‹‹አስብበታለው…››አልኳት በደፈናው
‹‹እንደምታስብበት እኔም ተስፋ አደርጋለው››አለቺኝ በማመንና በላማመን መካከል በሚዋልል ስሜት
ጭቅጭቃችንን ጋብ አድርገን በዝምታ የሆነ ደቂቃዎች ያህል እንደተጓዝን የገባንበትን የፍጥነት መንገድ ጨርሰን ቢሾፍቱ መውጫ ጋ ለመድረስ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረን መኪናዬ መንተፍተፍ ጀመረች.. ምንድነው……..?ጠይቄ ሳልጨርስ ሞተሯ ጠፋብኝ… እንደምንም ዳር እስየዤ አቆምኩና ከፈኑን ከፍቼ ብልሽቱን አገኝ ብዬ ለመነካካት ብሞክር ለውጥ ማምጣት አልቻልኩም…ድሮውም የመንዳት እንጂ ስለመኪና ቴክኒካል ዕውቀቱ ስለሌለኝ አልተሳካልኝም… ስላልተሳካልኝ ደግሞ አልተገረምኩም…
‹‹ምን ይሻለናል ታዲያ……..?››አለቺኝ
‹‹ እኔ እንጃ… እስኪ ሰዎቹ ደርሰው እንደሆነ ልደውል›› አልኩና አቶ ሰይፉ ጋር ደወልኩ…
‹‹አቶ ሰይፉ መኪናዬ ተበላሽታ ቆመችብኝ››
‹‹የት ነው የቆምከው..…..?››ጠየቁኝ….ነገርኳቸው
‹‹በቃ ሚኒባሷን ልላክልህ››
‹‹አዎ ላክልኝ…››
‹‹በአስር ደቂቃ ውስጥ ይደርሳል››አሉኝ…
እንግዲህ እስከዛ ጋቢና ቁጭ ብለን የጀመርነውን እንጨርሳ
‹‹አይ ይብቃን… ለመዝናናት ነው የመጣውት ይሄንን ውብ ቀኔን ላበላሻቸው አልፈልግም..ደግሞ በጥሩ መዝጊያ ነው የደመደምነው…››አለቺኝ ….ተስማማውና ጋቢና ገብተን ሙዚቃ ከፍተን በዝምታ እያዳመጥን ጥበቃችንን ቀጠልን…
ከስንት ደቂቃ ቡኃላ እንደሆነ በትክክል ባላውቅም የሆነች ነጭ አዲስ ዲኤክስ መኪና ከኃላችን መጣችና ስራችን ስትደርስ አቀዝቅዛ ከፊታችን ተስተካክላ በመቆም ክላክስ አደረገች…‹‹ምንድነው…..?›› ብዬ ጋደም ካልኩበት ቀና በማለት እንገቴን በመስኮት ወጣ አድርጌ ስመለከት……ያቺ የተረገመች እየደነሰች ከመኪናው ወርዳ ወደእኛ እየመጣች አየዋት..አዎ በትክክል እሷ ራሷ ነች…እስከ ዛሬ ለብሳ ካየዋት የተለየ አይነት አለባበስ ነው የለበሰችው…እላዩ ላይ የተሰፋ የሚመስል ሰማያዊ ግን ደግሞ አጭር ቀሚስ ለብሳለች ..ቀሚሱ ከላይ አንድ ክንዷን ሲሸፍን አንዱ ክንዷ ግማሽ ደረቷ ጭምር ባዶ ነው…እዛ የተራቆተው ደረት ላይ ከቀሚሱ ጋር የሚመሳሰል ሰማያዊ የአንገት ጌጥ ተነጥፎበታል…ያደረገችው የጆሮዋ ጌጥም ተመሳሳይ ቀለም ያለው ነው፡፡አይኖቾ ..የአይኖቾን ቅንድቦች ተኩላቸዋለች…እና ስትኮላቸው የአማልክት አይኖች መስለዋል…ከንፈሮቾ ተውኝ….ፀጉሯን በትናው በንፋሱ በአየር ላይ ይንሳፈፋል….እኔ ባለውበት በኩል መጣችና ወደመስታወቱ ቀረበች…ደግሞ የተቀባችው ሽቶ ….ወይ ልቤ ስውር አለላችሁ…
‹‹አቤት››
‹‹መኪናችን ተበላሽቶብን ነበር..ሌላ መኪና እየጠበቅን ነን… እናመሰግናለን›አለቻት ምኑም ያልገባት የእኔዋ ሞኝ
‹‹እኮ እርዳታውን ይዤ መጣው…ጋሽ ሰይፈ ናቸው ሂጅላቸው ያሉኝ..ከባለቤትህ ጋር መሆንህን ስለነገሩኝ ነው እንዳትንገላቱ ፈጥኜ የመጣውት ››አለችኝ ችፍ ባለ ፈገግታ ተሞልታ
‹‹ማለት…..?››አሁንም ሳሮን ሁኔታው ስላልገባት መልሳ ጠየቀች
እሷን ችላ አለቻትና…‹‹እስኪ ክፈተው ምን ሆኖ ነው…..?››አለቺኝ በቄንጣዊ አቋቋም ቋማ ወገቧን በአንድ እጆ ይዛ ቁልቁል እያየችኝ
አንደበቴ ተቆልፎል..እንደምንም ኮፈኑን ከፈትኩላት …እየተውረገረገች ሄደችና አንገቷን አቀረቀረችና መነካካት ጀመረች…
‹‹እንዴ ማን ነች……..?ታውቃታለህ…..?››
‹‹አዎ..አውቃታለው››
‹‹ጭራሽ እስከወዲያኛው እንዳታበላሽብህ …ተነሳ እያት….››ትዕዛዝ ይሁን ምክር ባለየለት ስሜት፡፡
እንደምንም እየተጎተትኩ ወረድኩና ወደእሷ ተጠጋው…ስሯ ደርሼ ላወራት አፌን ስከፍት‹‹ሄድና እስኪ ሞክረው››አለቺኝ
‹‹ምን..…..?››
‹‹ሞክረው››
‹‹ታሾፋለች እንዴ …..?..ይሄ ጉራዋ እኮ ነው የሚያበሳጨኝ ..የተቀባችው ጥፍር ቀለም እንዳይበላሽ እየተጠነቀቀች ነካ ነካ ስላደረገችው የሚስተካከል ነገር ይኖራል...?ነው ወይስ የእሷ ትንፋሽ ለሞተር መድሀኒት ነው..?››እያልኩ በውስጤ እያጉረመረምኩ ተመለስኩና ሳይመስለኝ ወደ ገቢናዬ ገብቼ ቁልፉን አሽከረከርኩ…በአንድ ምት ሞተሩ ተንደቀደቀ……..ደነገጥኩ…ኮፈንኑ ጠረቀመችና ..ዘይት ምናምን የነካካ እጇን እንዳንከረፈፈች..
‹‹በሉ እዛው እንገናኝ…ቅደሙኝ ችግር ካለ ከኃላ እከተላችሆለሁ…አይዞችሁ››በማለት እንዳአመጣጧ ባደረገችው ባለተረከዝ ሰማያዊ ጫማ ቀጭ ቋ እያለች የመደነስ ያህል እየተውረገረገች ወደመኪናዋ ሄደች…
‹‹እንዴ !!ንዳው አለችህ እኮ ንዳው እንጂ በመስኮት እኮ ወጣህ››
‹‹እ …››አልኩና ከገባውበት መደንዘዝ በመከራ እራሴን ስቤ በማውጣት መኪናውን አስነሳውና አስፈተለኩት… በእስፖኪዬ እያየዋት ነው …በ50 ሜትር ርቀት ከኃላ እየተከተለቺኝ ነው….
‹‹ትናንት ያልከኝ አሁን ገባኝ››አለቺኝ ሳሮን
ይህቺ ደግሞ መነጫነጭ ቋሚ ስራዋ ነው‹‹ምኑ ነው የገባሽ..?››
‹‹በደንብ ዘንጪ ስትለኝ ብዙም ትኩረት አልሰጠውትም ነበር..እርግጥ በተቻለኝ መንገድ ዘንጬ ነበር የመጣውት… አሁን ግን አንተ በምትፈልገው መጠን እንዳላረኩት ገባኝ…››
‹‹እንዴት ሊገባሽ ቻለ..? ››
‹‹አየዋ.መዘነጥ ምን ማለት
👍21
እንደሆነ በአይኔ አየው….እዛ ስንደርስ ደግሞ ሌሎቹ እንዴት የዘነጡ ሴቶች እንደሚያጋጥሙን አላውቅም ….››
‹‹አይዞሽ…ከዋናዋ ነው የጀመርሽው…››
‹‹እ!! ነው እንዴ……..? ገባኝ ››አለችና ዝም አለች
እሷ ዝም ብትልም የእኔ አዕምሮ ግን ዝም ሊል አልቻለም..፡፡ድንጋጤም ደስታም ውስጤን እያተረማመሰው ነው፡፡ስላየዋት ደስ ብሎኛል፡፡የመጣችበት አኳሀን በተለይ አዘናነጧ ከገመትኩት በጣም የራቀ በመሆኑ ምቾት አልሰጠኝም..ከባድ ፈተና እንደሚገጥመኝ ገመትኩ…በውስጤ የማነስ ስሜት እየተራወጠ ነው…እራሴን በጣም ማጠንከር አለብኝ፡፡እንደውም ቅድም ሳሮን ያነሳችልኝን የቀለበት ጉዳይ አሁን ላስብበት እችላለው…አዎ ምንም ይፍጅ ምንም እሷን አንገት ሳላስደፋ አልመለስም…..፡፡ወሰንኩ፡፡ጉዞ ወደ ጦር ሜዳ፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «.: #ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ እንዲህማ የእሷ መቀለጃ አልሆንም….እንዴ!!! ከሚገባት በላይ እኮ ፊት ሰጠዋት..አረ ፊት መስጠትም ብቻ አይደለም..ልቤንም ገልብጬ ነው የውስጥ ገበሩን ያሳየዋት….ካልጠፋ ሰው እሷን ምሳ ለመጋበዝ ጊዜዬን ማባከኔ ነው የሚቆጨኝ… መኪናዬን አስነስቼ ወደ ቢሮ እየተጎዝኩ ነው ፡፡ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩ ያለውት..አሁን…»
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ስድስት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ወደ ደብረዘይት በራሴ መኪና ለመሄድ የወሰንኩት ከነጋ ቡኃላ ነው፡፡አባቴ ሀሳቤን ተቃውሞኝ ነበር…
‹‹ህብረት የመፍጠሪያ እና ወዳጅነትን ለማጎልበት ታስቦ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ለብቻ ተገንጥሎ መሄድ ጥሩ ስሜት አይፈጥርም ››አለኝ.
‹‹እንዴ ምን ችግር አለው..?››
‹‹ችግርማ አለው… አንዳንዴ ማድረግ ስላቻልሽ ብቻ ሁሉን ነገር የግድ ማድረግ አይኖርብሽም…አንቺ በግል መኪናሽ ስትሄጅ ሌሎች የስራ ባለደረቦችሽ ላይ ምን አይነት ስሜት ነው ሊፈጥር የሚችለው….በተለይ እኔ እና አንቺ ለእንዲህ አይነት ጉራ ስንል ያለንን ነገር መጠቀም አያምርብንም››አለኝ
‹‹እንዴት አባ..? ለምን …...?ማን ይከለክለናል..?››ጥያቄዬን ደረደርኩለት
‹‹የእኛ አይደለማ ..ሰርተን የገዛነው መኪና አይደለም..የእናትሽ ላብ ነው››
‹‹እንዴ…. !!!እናቴ ታዲያ የእኔ አይደለች..?››
‹‹…እናትሽ ያንቺ ነች ማለት ንብረቷ ሁሉ ያንቺ ነው ማለት አይደለም…››
‹‹አባ አንተ ደግሞ..ደግነቱ እናቴ እንደአንተ አታስብም…›› ሀሳቡ ውስጤ ገብቶ ቢቧጥጠኝም ምክሩን ሰምቼ ግን መኪናውን ጥዬ ለመሄድ አልፈለኩም…..መኪና መያዜ ከሰውዬው ጋር ላለኝ ወሳኝ ፊልሚያ ያግዘኛል የሚል ግምት አሳድሮብኛል፡፡እና ቀድሜ ደብረዘይት በመድረስ የተቀበልኳቸው እኔ ነኝ፡፡ቡድኑ ያረፈው ቢን ኢንተርናሺናል ሆቴል ነው፡፡ለአለቅዬ ብቻ ሆቴሉ አይመጥነውም ተብሎ አሻም አፍሪካ ሆቴል ነው የተያዘለት…ሰው ሁሉ እንደ አመዳደቡ ሁለት ሁለት እየሆነ በየክፍሉ እየገባ ባለበት ሰዓት እኔ ሆቴሉ በረንዳ ላይ አረፍ ብዬ ማኪያቶ ነገር በመጠጣት ላይ ሳለው አቶ ሰይፉ ወደእኔ መጡ…..
‹‹ፌናን ላስቸግርሽ ነው..?››
‹‹ምነው ምን ቸገሮት..?››
‹‹ባክሽ ሰውዬችን መኪናዬ ተበላሽታብኝ አጉል ቦታ ቆሚያለው ብሎ ደወለልኝ ..…ሚኒባሶ መካኒክ ፍልጋ እስክትሄድ እዛ እንዳይቸገር ባንቺ መኪና ሄደሽ ብታመጪው…..መኪናውን ልጆቹ አሰርተው ያመጡለታል››
‹‹ችግር የለውም እርሶ አዘውኝ እንዴት እምቢ እላለው ››ብዬ ከመቀመጫዬ ተነሳውና መኪናዬን ወደአቆምኩበት ሄድኩ….አጋጣሚው ደስ ብሎኛል…ገቢና ከጎኔ አስቀምጬ እየነቆርኩት ይዤው መጣለው…ሀሳቤ እንደዛ ነበር..
ስደርስ ያላሰብኩት ነገር ነው የገጠመኝ… ከሰው ጋር ነው…ደስ አላለኝም..ለምን ደስ አላለኝም…..?አይ እንዲሁ ይመስለኛል..በቃ አለ አይደለ ብቻውን ነው ብዬ ሰለገመትኩ መደናገር ተፈጥሮብኝም ይሆናል…፡፡
መኪናዬ አቁሜ ወደ እነሱ እየሄድኩ ነው ያሰብኩት…ከእነሚስቱማ አልጭነውም….ይዣቸው ከመሄዴ ለመገላገል የመኪናዋን ብልሽት ቀላል ከሆነ እስኪ ልየው…እድሜ ለአባቴ የመኪና የአካል ክፍል ብትንትን አድርጌ እንዳውቅ አድረርጎኛል…ጫን ያለ ብልሽት ካልሆነ በስተቀር የእኔንም ሆነ የአባዬን መኪና ቱታዬን ለብሼ መሬት ላይ እየተንከባለልኩና በዘይት እየተጨመላለቅኩ የምጠግነው እና ሰርቢስ የማደርገው እራሴው ነኝ….
እሱ ባለበት አቅጣጫ ወደመስኮቱ ተጠጋው..እኔን በማየቱ እጅግ ደንግጦል…እንደህጻን ልጅ ነው የተረብተበተው..እንደዛ ሲርበተበት ደግሞ እኔ ውስጤ እንዲቁነጠነጥና ..መቁነጥነጤን ተከትሎ እንድሾርበት አስገደደኝ..፡፡ያው እንደከዚህ ቀደሙ.. ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ ደረጃ ተሸቀርቅሯል…፡፡መቼስ የካምፓኒ ማናጀር ለመሆን ከመዳከር ይልቅ ፕሮፌሽናል ሞዴል ለመሆን ትንሽ ቢጥር አመት ሳይሞላ የሀገሪቱ አይኖች ሁሉ ማረፊያ ይሆን ነበር….፡፡እሷም ቆንጅዬ ነች …አዘናነጧ ግን ጭንቀት የወለደው አይነት ይመስላል…እሱን ላለማሳጣት እየጣረች በሚመስል ሁኔታ....፡፡ግን ምን ማለቴ ነው....?እየተናገርኩ ያለውት እኮ ትርጉም የሚሰጥ አይነት አይደለም..፡፡ጭንቀት ያለበት አዘናነጥ ማለት ምን ማለት ነው…..?እንደውም እኔ ስለእሷ የሰጠውት አስተያየት ይመስለኛል ከጭንቀት የተወለደው…፡፡ለማንኛውም የመኪናውን ኮፈን አስከፍቼ ስመረምረው ብልሽቱ አስቂኝ ነበር…ለማስተካከል ግማሽ ደቂቃ አልፈጀብኝም…እንደዛ በመሆኑ ደግሞ የተሰማኝ ስሜት ልነግራችሁ አልችልም…
…. አሁን ከኃላ እየተከተልኳቸው ነው…..በእስፖኪዬ ወደኃላ እያየኝ መሆኑን በደንብ አውቃለው…ከተማ ውስጥ ገብተን ጌትሼት ጋር ስደርስ ነበር ሚኒባሶ መካኒክ ይዛ ስትመጣ አግኝተን የመለስነው…..
የመጀመሪያው ፕሮግራም ከምሳ ግብዣ ነበር የሚጀምረው...እዛው ብዙሀኑ ያረፈበት ሆቴል እየተጫወትን ከበላን ቡኃላ በወጣው ፕሮግራም መሰረት በከተማዋ መታየት ያለባቸውን ቦታዎች ወደማየት ነው ያመራነው …ስምንት ሰዓት ሲሆን ተንቀሳቀስን፡፡
መቼስ ቢሾፍቱን ስትጎበኝ በዋናነት በሁሉም አዕምሮ ሚመጣው ሀይቆቾ ናቸው..ቢሾፍቱ ፤ሆራ ፤ባቦጋያ ፤ኩሪፍቱ፤ጨለቅለቃ.. መቼስ መታደል ነው…አንድ መለስተኛ ከተማ ይሄ ሁሉ ሀይቆች ባለቤት መሆን በራሱ ትልቅ ድልብ ሀብት ነው፡፡ለከተማዋ ብቻ አይደለም ለሀገሪቱም ጭምር..፡፡በዛ ለይ ከመዲናዋ 50 ኪሎ ሜትር ብቻ እርቃ መገኘቷ….ለአንድ ቀን እንኳን ለስራ ወደሀገሪቱ የመጣ ሰው ጎራ ብሎ አንድ ሁለት ሰዓት ዘና ብሎ ሊመለስባት በሚችልበት ቦታ ላይ መገኘቷ ሌላ እድል ነው…ግን ከተማዋም ሆነች ሀገሪቱ 5 ፐርሰንቱን እንኳን አልተጠቀመችበትም…አለም አቀፍ ቱሪስቶችን በልዩ ሁኔታ እንዲስብ ተደርጎ ፕሮሞሽን አልተሰራለትም… ፡፡ሌሎች ሀገሮች መሰል የተፈጥሮ ፀጋ ባለመታደላቸው አርቴፊሻል ወንዝ እና ሀይቅ በመስራት የቱሪስት ገቢያቸውን በሚያጧጡፈበት በዚህ ቴክኖሎጂ በመጠቀበት ዘመን እኛ ግን ተፈጥሮ በቸርነቷ የለገሰችንን የነፃ ችሮታ እንዲሁ ባልባሌ ሁኔታ ለዘመናት በማባከነ ስንዴ እንለምናለን…ያሳዝናል፤የእኔ ነገር ሳላስበው ወደንጭንጬ ገባው…ለዛውም በዚህ ዘና በማያ ቀኔ… ..ቅድሚያ ሆራ ሀይቅ ነው የሄድነው…ሆራ በከተማዋ ካሉት ሀይቆች በስፋት ትልቁ ነው..ዙሪያውን በተራራ የተከበበ ሲሆን ተራራው ላይ ደግሞ ዘመናዊ የሚባሉ ሎጆችና ሆቴሎች አልፎ አልፎም ቢሆንም ታንፀው ወደአካባቢው ለመዛናናት የሚመጡትን ቱሪስቶች ሆነ ሀገርኛ ቱሪስቶችን ለማስተናገድ እየሞከሩ ነው ፡፡አሪፍ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው ..አብዛኛው በጀልባ ባህሩን ሰንጥቆ በመጓዝ ተዝናንቷል....12 ሰዓት ወደየአረፍንበት ሆቴል ነው የተመለስነው..ለማታ እራት ፕሮግራም ለመዘጋጀት….የእራቱ ፕሮግራም ፕራሚድ ሆቴል ነው የሚከናወነው፡፡አንድ ሰዓት ሁሉም እዛ ተሰባስቦ መገኘት አለበት፡፡
አንድ ሰዓት ከሩብ ሲል ፕራሚድ በሚገኝ የስብሰባ አዳራሽ ሁሉም ስታፎቻችን ቦታቸውን ይዘው ለፕሮግራሙ ዝግጁ ሆነው ነበር…ልክ እንደባለፈው አመት ዘንድሮም የፕሮግራሙ መሪ እኔ ስለሆንኩ ወደ መድረኩ ወጥቼ ሁሉንም አንዴ ቃኘው…የካምፓኒው ከፍተኛ ሀላፊዎች አለቃዬንና ሚስቱን በግራና ቀኝ አጅበው የፊተኛውን ረድፋ ላይ ተደርደረረዋል፡፡
ጉሮሮዬን አፀዳዳውና ማይኩን ፈታትሼ ንግግሬን ጀመርኩ…
‹‹››የተከበሩ የድርጅታችን ስራ አስኪያጅ ፤ እኛን አክብረው በመሀከላችን የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የተከበሩት የስራ-አስኪያጃችን እጮኛ….የተከበራችሁ የስራ መሪዎችና ድንቅና ምርጥ የካማፓኒያችን ሰራተኞች እንኳን ለዚህ አመት የካማፓኒያችን ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ …አደረሰን፡፡…››
አደራሹ በጭብጨባ ተናጋ…
ፋታ ወስጄ ንግግሬን ቀጠልኩ፡፡
…የዚህ ዓመት በዓላችን ከዚህ በፊቱ የተለየ ይሆናል ፡፡አንደኛ በዓላችን ነው..ሁለተኛ ወጣቱንና እና ካምፓኒያችንንም ሆነ የእያንዳንዱን ሰራተኛ የግል ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብለን ሁለችንም ተስፋ
👍1
ያደረግንባቸውን አዲሱን አለቃችንን እንኳን ወደካማፓኒችን በሰላም መጡ ብለን አቀባበል ለማድረግ ሲሆን …ሶስተኛውን ምክንያት ደግሞ ቡኃላ አካባቢ ነግራችሆለው…..አሁን አቶ ሰይፉን ወደመድረክ ጋብዛለው …..የዓመቱን አጠቃላይ የካምፓኒችንን የስራ እቅስቃሴ ውጤት የሚገልጽ አጭር ሪፖርት ያቀርብልናል..
አቶ ሰይፈ ወደ መድረክ ሸኙልን፤
አቶ ሰይፈ የካምፓኒውን በአመቱ ከወጭ ያስመጣቸውን ፤የሸጣቸውን…ምን ያህል እንዳተረፈ.. የሚቀጥለው አመት እቅዱን በዘርዝር ለማቅረብ 7 ደቂቃ ብቻ ነው የፈጀባቸው…
ሲጨርሱ አመስግኜ መድረኩን ተረከብኩ….
…‹‹ምርጥ ሀለቃችን ከዛም በላይ አባታችንን የሆነኑትን አቶ ሰይፉን እናመሰግናለን፡፡እንግዲህ ከሪፖርቱ እንደተረዳነው.ካምፓኒው በዓመቱ ለመንግስት ሶስት መቶ ሰማንያ አምስት ሚሊዬን ብር ቫት ሰብስቦ ሲያስረክብ ከሀምሳ ሚሊዬን ብር በላይ ደግሞ ዓመታዊ ግብር ለመንግስት መክፈሉን ነው፡፡ለእኛ ሚከፈለንን ደሞዝ ችሎ ሌሎች ወጪዎችንና ስራ ማስኪጃዎችን ሸፍኖ እንደሰማነው ሁለት መቶ ሀማሳ ሚሊዬን ብር በላይ ንጽህ ትርፍ አግኝቷል፡፡
ይሄንን ደግሜ የማነሳው እያንዳንዳችን ምን ያህል ጠቃሚ ዜጎች መሆናችንን መናገር ስለፈለኩ ነው…..ብዙዎቻችን ለሀገራችን ከደሞዛችን ተቀናንሳ ለመንግስት በግብር መልክ የምትገባ ሶስት መቶና አራት መቶ ብር ብቻ ይመስለናል አስተዋጽአችን…ይሄ ሲጠሩት ሚከብደውን ሚሊዬን ብሮችም መንግስታችን እንዲያገኝ የእያንዳንዳችን እጅ አለበት..በዚህም ደስ ሊለንና ልንኳራ ይገባል…ካምፓኒያችን 18 ፐርሰንት አመታዊ ትርፍ እንዲያገኝ የእያንዳንዳን ጀግንነት እና ታታሪነት ያስገኘው ውጤት በመሆኑ በዚህም ልንኮራ ይገባናል…እያንዳንዳችን ከራሳችን አልፈን ለካምፓኒያችን ፤ከዛም አልፈን ለሀገራችን ወሳኝ ሰዎች እንደሆን አውቀን ልንኮራ ይገባል…
አደራሹ በጭብጨባ ታፈነ…አይኖቼን ወደ ፍሰሀ ስልክ አቀርቀሮ እጆቹን የይስሙላ ያህል እርስ በርስ በማጋጨት ለማጨብጨብ እየሞከረ ነው..እርግጠኛ ነኝ መቼም ንግግሯን አቁማ መድረኩን ለቃ በወደረደችልኝ እያለ አምላኩን እየተማፀነ ነው..እኔ ደግሞ እንዲህ በቀላሉ አላቆምም…...ንግግሬን ቀጠልኩ
‹‹…..እና በቀጣይነትም በየቀኑ በስራችን የምናደርገው ጥረትና …ጥረቱን ተከትሎ የሚመጣው ውጤት የእለት ኃላፊነታችን መወጣት .ወይንም ለሚከፈለን ደሞዝ መጠን መስራት ብቻ ሳይሆን ምን ያህል ከፍ ያለና ሀገር መንገድ የምትገናበትን.. ደሀ ዜጎች የሚታከሙበት ሆስፒታል ምታንጽበትን፤ሀገር ድንበር ለሚጠብቁ ወታደሮች የምታኖርበት ገንዘብ እንድታገኝ እያገዝን እንደሆን እና ከራሳችን ያለፈ ለሀገር ወገን የተረፈ ነገር እደምንሰራ እያሰብን በተሻለ ጥንቃቄ በላቀ ጥራትና ፍጥነት ወጤታማ ስራ መስራታችንን አንደምንቀጥል ቃል የምንገባበት ክብረበዓላችን ስለሆነ ደስ ሊለን ይገባል ..አይደል እንዴ…..?
‹‹አዎ ልክ ነሽ……ልክ ነሽ…››
‹‹አዎ ልክ ነኝ..ግን አንድ መተወቅ ያለበት ነገር ደግሞ አለ…እኛ በላባችን ካምፓኒያችንን ስናሳድግ… በጥረታችን ሀገራችንን ስንደጉም የግል ጎጆችን ደግሞ መረሳት የለበትም…..በእየለቱ የሚከሰተው የዋጋ ግሽበት ያንን ተከትሎ ትከሻችንን እያጎበጠው ያለው የኑሮ ጫና በዓመት በሚሰጥ የደሞዝ ጭማሪ ብቻ መቋቋም እንደማይቻል ቢታወቅም ከምንም ይሻላል ያው ካምፓኒያችን የሆነ ነገር እንደሚያስብልን እገምታለው…በተለይ ዓዲሱ አለቃችን ካላቸው ስብዕና አንፃር የእያንዳንዳችን ኑሮ እንደሚያስጨንቃቸው እገምታለው፡፡
ንግግሬን ሳልጨርስ እስከአሁን ከተጨበጨበው በላይ ጭብጨባ እስከአሁን ከተጮኸው በላይ ጩኸት ..ተጮኸ…..መቼስ ለቅጥረኛ ሰራተኞች ደሞዝ ዋናው ስስ ብልታቸው ነች..….ይቺን አይነት ቅስቀሳ ደግሞ አለቆችን እንደማታስደስት ከልምድ አውቃለው….እና አለቃዬ ፊት ላይም በትክክል ብስጭቱን እያየውት ነው፡፡
እንግዲህ ይህን ያህል ካልኩ ይበቃኛል …..በቀጣይ የካምፓኒያችን ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ፋሰሀ ወደ መድረክ ወጥተው ለሰራተኞቻቸው የሆነ ነገር እንዲሉ እጋብዛለው…››ብዬ ጋበዝኩት

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስድስት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ ...ወደ ደብረዘይት በራሴ መኪና ለመሄድ የወሰንኩት ከነጋ ቡኃላ ነው፡፡አባቴ ሀሳቤን ተቃውሞኝ ነበር… ‹‹ህብረት የመፍጠሪያ እና ወዳጅነትን ለማጎልበት ታስቦ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ለብቻ ተገንጥሎ መሄድ ጥሩ ስሜት አይፈጥርም ››አለኝ. ‹‹እንዴ ምን ችግር አለው..?›› ‹‹ችግርማ አለው… አንዳንዴ ማድረግ ስላቻልሽ…»
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ሰባት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ

...ከአዳራሹ ሳይሆን ትንሽ ወደኃላ ተመልሼ ልጀምርላችሁ፡፡ እስከ አሁን አዋዋላችን በጣም ግሩም የተባለ ነበር..ከተለያዩ ሰራተኞችም ጋር በየምክንያቱ የመነጋገር ስሜታቸን ማዳመጥ፤ የመቀላለድ እና እስከዛሬ ከነበረው በተሸለ የመግባባት አጋጣሚውን ስንጠቀምበት ነበር የዋልኩት…ከፌናን ጋር ግን ከሩቁ ከመተያየት በስተቀር ፊት ለፊት የመገናኘቱ አጋጣሚ አልነበረም….ምን አልባት ሰላም ያዋልኩትም እንደዛ ስለሆነ ይሆናል..የማታውን ፕሮግራም ለመጀመር አዳራሽ ከገባን ቡኃላ ከቀኑ ከነበረው አለባበሷ በተቃራኒ በጣም ረጅም ግን ደግሞ በተመሳሳይ ውብ ያደረጋትን ደማቅ ቀይ ቀሚስ ለብሳ ወደመድረኩ ስትወጣ ነበር ያየሆት…
ምትፈልገው የሆነ ዕቃ ኖሮ እሱን ለመውሰድ ወደ መድረክ የወጣች ነበር የመሰለኝ ግን ተሳስቼ ነበር… ፊት ለፊት ቆማ …ልክ ለአመታት የመድረክ ልምድ አንዳለው ፓለቲካኛ በሙሉ በራስ መተማመን ንግግሯን ጀመረች….እኔ እራሱ ምን አይነት እንከፍ ነኝ..እስኪ ቀደም ብዬ ፕሮግራማቸውን ባየው..እርግጠኛ ነኝ ከአስር ደቂቃ ባፊት እንኳን አውቄ ቢሆን እዚህች መድረክ ላይ እንድትወጣ ፈጽሞ አልፈቅድላትም ነበር…. ከመጀመሪያው ንግግሯ ነው የነገር ጦሮን በስውር የወረወረይብኝ..እስኪ እዚህ ሁሉ ሰው መካከል አቶ ፍሰሀና እጮኛቸው ማለት ምን ማለት ነው……..?እጮኛዬ ትሁን አትሁን አልነገርኮት ከየት አባቷ አወቀች…..?አቤት ወስጤ እንደተቃጠለላችሁ ..ሰውነቴ ሁሉ ሲንቀጠቀት ይታወቀኛል…ደግሞ ይህቼ ከጎኔ የተቀመጠችው መፍለቅለቅ ምን የሚሉት ነው…?የማንም ስርዓት አልባ መድረክ ላይ ወጥታ በዘጠና ምናምን ሰዎች ፊት‹‹.. የፍሰሀ እጮኛ… ››ብላ ስለተናገረችላት የእውነት እጮኛዬ የሆነች መሰላት እንዴ..?አናደደቺኝ……..
ከዛ አስተዳዳሪው ወጣ..የካማፓኒውን ሪፖርት እያቀረበ ቢሆንም ምን እንደለ አንዱንም አልሰማው…እያብሰለሰልኩ ያለውት ስለእዛች የተረገመች ልጅ ነው…እንዴት አድርጌ ነው አንገቷን ላስደፋ የምችለው….…እግዜር ይስጠው ሽማግሌው ሪፖርቱን አላንዛዛውም…ጨርሶ አመስግኖ መድረኩን ለዛች እብድ ለቀቀላት….እሷ ማለት ያቺ የተረገመች ወጥታ ስትናገር ብዙም ቁብ አልሰጣዋትም ነበር ..ግን ሽማግሌው ያቀረበውን ሪፖርት እያብራራች እየበታተነች ሳልወድ በግድ እየመረረኝ እንድሰማውና አደረገች…
ከፍተኛ ጥቃት ነው የተፈፀመብኝ ..በእኔ ብቻ አይደለም በካማፓኒውም…..ሰራተኞቹን ጠቃሚ ከሆኑት በላይ ጠቃሚ እንደሆኑ እዲሰማቸው…በትዕቢት ልባቸው እንዲወጣጠርና ነገሮች ለእኔ ከባድ እንዲሆኑብኝ ያሴረችው ሴራ ነው በእያንዳንዱ የዋህ ሰራተኛ አዕምሮ በጥበብ የበተነችው ..አዎ ንግግሯን ሰምተው ያጨበጨብላት ሰራተኞቹ የተናገረችው ሁሉ ለእነሱ አስባ ይመስላቸዋል…የእሷን ሴራ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው…እንደውም እሷን ማባረሬ በጣም ትክክለኛ ውሳኔ ነው..እና ይቅር ብያት እንድትመለስ የማስበውን ነገር ትቼዋለው..ለዚህችማ አይገባትም…ይህቼ ወጥ ረጋጭ ካቅሟ በላይ የምትንጠራራ… መኪና ተከራይታ ወይም ደግሞ ከሹገር ዳዲዋ ተውሳ እዚህ ይዛ በመምጣት ለመጎረር የምትጥር ከአቅም በላይ ለመኖር ስቃዬን ለምታይ ሴት ማዘን…
ወደመድረክ ስትጋብዘኝ የውስጥ ስሜቴ እየተተረማምሰ ነበር…የተዘጋጀውበትን ንግግር ሁሉ ቃላቶች ብትንትን ብለው ከአዕምሮዬ ተሰደዋል…ብቻ በደመነፍስ ወጣውና ወደጆሮዋ ጠጋ ብዬ‹‹በጣም በጣም ባለጌና መሰሪ ልጅ ነሽ ››አልኳት…ቆሽቴን እንዳሳረረቺኝ ቆሽቷን ላሳርርረው ብዬ..እሷ እቴ ምን በወጣት የመረቅኳት ይመስል ፈገግ ብላና ድምጽን ለሁሉም እንዲሰማ አድርጋ ‹‹አመሰግናለው አቶ ፍሰሀ …በእውነት ለካምፓኒዬ እና ለምወዳቸው የስራ ባለደረቦቼ ከዚህ በላይ መናገር ችዬ ብናገርና ባገለግል ደስ ይለኛል››ብላ ጭራሽ ያረረው ቆሽቴ እንዲከስል አድርገ መድረኩን ለእኔ በመልቀቅ ከኃላዬ ቆመች….

❤️ፌናን

የማታውን ፕሮግራም አትጠይቁኝ…ብዙሀኑ የተደሰቱበት እኔና ሰውዬው በየምክንያቱ በተገናኘን ቁጥር ስንጠዛጠዝና ስንነቋቆር ያሳለፍንበት ገራሚ ምሽት ነበር…በተለይ ፍቀረኛው የእኛኑ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ስትከታተልና ስትጠብቀን ነው ያመሸችው…አራት ሰዓት ሲሆን ይዛው ትሂድ ወይም ይዟት ይሂድ አላውቅም ብቻ ተያይዘው ወጡ….ወደ ማደሪያቸው…
እኔም ከ30 ደቂቃ ቡኃላ ቡድኑን ተለይቼ ወደማደሪያዬ ሄድኩ…..ገብቼ አልጋዬ ላይ እንደተዘርርኩ ነበር እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ ያለው....ትንሽ መጠጥ የቀማመስኩ ጊዜ እንዲሁ ነው የሚያደርገኝ…ክፋቱ እንቅልፌ ቶሎ ያልቅብኛል…ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ ሙለ በሙሉ እንቅልፌን ጨርሼ ፈጠጥኩ…እዛው እየተገላበጥኩ በውስጤ የሚተረማመሰውን ሀሳብ ማመንዠግ ቀጠልኩ… በዚህ ውድቅት ለሊትም ሀሳቤ ስለእሱው ነው….ምን እየሰራው ነው…….?ከልጁ ጋር ምን እንደዚህ አይነት ጫወታው ውስጥ አሰጋባኝ..….? እሱ አልሸነፍ ባይ ስለሆነ ነው..ወይስ እኔ የማሸነፍ ሱስ ስላለብኝ….….?ነው ወይስ ቀጥታ ከአላማዬ ጋር የሚገናኝ ትግል ነው…….?እንዴት እንደዛማ አይሆንም የእኔ ዓላማ በእሱ መሸነፍ ላይ እንደማይመሰረት እርግጠኛ ነኝ..እና ምንድነው ችገሬ…….?ይሄንን ሳስብ የለበስኩትን አንሶላና ብርድልብስ ከላዬ ገፍፌ ከአልጋዬ ወረደኩ….አፍቅሬው ብቻ እንዳይሆን…….?ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ…….?ቆይ እስኪ ፍቅር እንዴት ነበር..….? አውቃለው እንዴ…….?
በሀያ አመቴ አካባቢ አንድ ሁለት የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር ፍቅር ፍቅር መጫወት ጀምሬ ነበር..ግን እኩዬቼ ቢሆንም እኔ በማስበው ልክ ሊያስቡልኝ ስላልቻሉ..እኔ ፍቅርን በምተረጉምበት ልክ ሊተረጉሙልኝ ሳላልቻሉ ከአንዱ ጋር አንድ ወር ከሌለኛው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር አብረን መዝለቅ የቻልነው…፡፡ያው ወንዶች ከሴት በእኩል ዕድሜ ሊበስሉ እንደማይችሉ ዘግይቼ ነው የተረዳውት…ማለት ያው የ18 ዓመት ሴት አንድ ቤትን እማወራት ሆና በደንብ ማስተዳደር ትችላለች አንድ የ18 ዓመት ወንድ ግን እራሱንም የማስተዳደር ብቃት ላይ አይደርስም…የድሮ አባቶቻችን እንዲሁ በዘፈቀደ አይደለም ወጣቶችን ሲያጋቡ ቢያንስ ወንዱ ከሴቷ በ5 ዓመት ቢበልጣት ጥሩ እንደሆነ የሚመክሩት እና እንደዛም እንዲሆን በተቻላቸው መጠን የሚጠነቀቁት…
የእሳትነቱን ዘመን ካለፍኩ ቡኃላ ደግሞ ፍቅርን በተመለከተ አንድ ቅድመ ሁኔታ ለራሴ አስቀመጥኩ… የማፈቅረው ሰው እኔ እንደምወደው እሱ ግን እንክትክት እስኪል ድረስ እንደሚያፈቅረኝ እርግጠኛ ስሆን ብቻ ነው እጄን ዘርግቼ ልቀበለው የምችለው፡፡ይሄን ለምን እንዳልኩ ማስረዳት አለብኝ መሰለኝ..ወንድ ልጅ በደንብ እንዳፈቀራት እርግጠኛ ሳትሆን እጇን የሰጠችና ወደጋብቻ የገባች ሴት ብዙ ጊዜ ከሳሪ ነች፡፡ምክንያቱም አብዛኛቹ ወንዶች የፍቅር ጫፍ ላይ የሚደርሱት በመጀመሪያዎቹ የፍቅር ጊዜያቶች ነው…ከዛ ወደግንኙነት ሲገቡ ፤ ከዛም አልፎ ወደ ትዳር ሲሸጋገሩ የማፍቀር መጠናቸው እየወረደ ነው የሚመጣው..ቢያንስ በግንኙነት ፍቅር ላይ የነበረ ስሜቱ ወደ ትዳር ሲገባ መውደድ ላይ አርፎ እንዲረጋጋ ከፍቅር መጀመር አለበት....ለሴት ልጅ ግን ተቃራኒው ነው ፡፡በግንኙነት እና በመላመድ ስሜቷ እያደገና እየጎለበተ ነው የሚመጣው.. ፡፡ በግንኙነት ወቅት መውደድ ከቻለች፤በትዳር ውስጥና በመላመድ ወደላይ ነው የምታሳድገው ወደፍቅር …አብዛኛዋ ሴት እንደዚህ ነች…እና እኔም የምወደውን እና እሱ ደግሞ የሚያፈቅረኝን እንዳገኘው እርግጠኛ እስክሆን ድረስ ለማንም ልቤን ከፍቼ አልሰጥም፡፡ለዚህ ፍሰሀ ለሚባለውም ቢሆን
👍31
ተመልሼ ለመተኛት ብሞክርም አልተሳካልኝም…አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ሲሆን ቢጃማዬን ሳልቀይር የሚነበብ መጽሀፍ ይዤ ከመኝታ ክፍሌ ወጣውና ወደመናፈሻው አመራው…እስኪ እንደአባቴ የዛሬዋ ፀሀይ ስትወጣ ልቀበላት…ፊቴን ወደ ቢሾፍቱ ሀይቅ አዙሬ ተቀመጥኩና ንባቤን ጀመርኩ…በመሀል ዓይኖቼን ወደጥልቁ የቢሾፍቱ ሀይቅ በመጣል ተፈጥሮ ምን ያህል ልብን ስልብ እንደምታርግ እያተዘብኩ ..ደግሞ መልሼ ወደ ንባቤ እመለሳለው..በነገራችን ላይ ይሄ ሀይቅ በሀገራችን በጥልቀት ሁለተኛው ነው፤ የሚበለጠው የሻላ ሀይቅ ብቻ ነው…የሆነ የእግር ኮቴ ከጀርባዬ ወደእኔ ሲመጣ ተሰማኝ…..አዎ እየቀረበኝ ቢሆንም አቀርቅሬ ንባቤን እንደቀጠልኩ ነው….
‹‹በዚህ ሰዓትም የሚያነብ ሰው አለ….?››
እንዴ ይሄንን ድምጽ አውቀዋለው….እሱ ነው.. ከንባቤ ቀና አልኩና አንገቴን ወደኃላዬ አሽከረከተርኩ
በድንጋጤ ወደኃላው አፈገፍጋለው ሲል ወድቆ ነበር…ሳቄን ለቀቀቅኩት…..
‹‹አንቺ በትርፍ ጊዜሽ ሰይጣንም ሆነሽ ትሰሪያለሽ እንዴ….?››
‹‹አዎ… ለዚህ ነው አንተን የመሰሉ መላዕክቶችን ለመፈታተን ችሎታው ያለኝ››
‹‹ምን ትሰሪያለሽ እዚ….?››
‹‹አቶ ፍሰሀ …አንተስ ምን ትሰራለህ….?››የጠየቀኝን ጥያቄ መልሼ ጠየቅኩት

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ #ፍሰሀ ...ከአዳራሹ ሳይሆን ትንሽ ወደኃላ ተመልሼ ልጀምርላችሁ፡፡ እስከ አሁን አዋዋላችን በጣም ግሩም የተባለ ነበር..ከተለያዩ ሰራተኞችም ጋር በየምክንያቱ የመነጋገር ስሜታቸን ማዳመጥ፤ የመቀላለድ እና እስከዛሬ ከነበረው በተሸለ የመግባባት አጋጣሚውን ስንጠቀምበት ነበር የዋልኩት…ከፌናን ጋር ግን ከሩቁ ከመተያየት በስተቀር…»
ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ስምንት



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


❤️ፌናን

እንዴ ይሄንን ድምጽ አውቀዋለሁ….እሱ ነው.. ከንባቤ ቀና አልኩና አንገቴን ወደኃላዬ አሽከረከርኩ
በድንጋጤ ወደኃላው አፈገፍጋለው ሲል ወድቆ ነበር…ሳቄን ለቀቀቅኩት…..
‹‹አንቺ በትርፍ ጊዜሽ ሰይጣንም ሆነሽ ትሰሪያለሽ እንዴ….?››
‹‹አዎ… ለዚህ ነው አንተን የመሰሉ መላዕክቶችን ለመፈታተን ችሎታው ያለኝ››
‹‹ምን ትሰሪያለሽ እዚ….?››
‹‹አቶ ፍሰሀ …አንተስ ምን ትሰራለህ….?››የጠየቀኝን ጥያቄ መልሼ ጠየቅኩት
‹‹እኔማ እዚሁ ነው መኝታ ቤቴ..በጥዋት ሀይቁ ምን እንደሚመስል ልየው ብዬ ነበር የወጣሁት…
‹‹እኔም እዚሁ ነው ያደርኩት….ና ቁጭ በል እስኪ›› አልኩት ካለወትሮዬ ተለሳልሼ
…እሱም ምንም ሳይል ጎኔ ካለው ወንበር ላይ ቁጭ አለ እና ጥያቄውን ቀጠለ‹‹ሁሉም ሰራተኞች አንድ ቦታ ነው መኝታ የተያዘላቸው አላሉኝም ነበር እንዴ….?››
‹‹ትክክል ናቸው… እኔ ግን የእናንተ ሰራተኛ ስለአይደለው በራሴ ነው የያዝኩት››
‹‹ምነው አይወደድብሽም…….? ለአንድ ቀን አዳር 3 ሺብር አካባቢ መሰለኝ የሚያስከፍሉት››
‹‹አዎ ይወደዳል ግን እስፖንሰር አለኝ…››
‹‹ታራኪኛዋ ……አንቺማ ይኖርሻል ለምን አይኖርሽም…….?››
ጫወታውን ወደሌላ ቀየርኩት ‹‹ሚስትህስ..….?››
‹‹ትናንት እጮኛህ ስትይኝ ነበር አሁን ደግሞ ሚስትህ አለሺኝ .. ለማንኛው ተኝታለች፡፡
‹‹ጥሩ ነው…..››
‹‹በረንዳ ላይ እኮ ሆኜ ወደ እዚህ ሳይ የማነች ኪሊዬፕትራ ነገር እንዲህ ባለ የንጋት ውበት ላይ እንዲህ አይነት ውበት ይዛ በሀይቅ ዳርቻ ብቻዋን የምትቆዝም ..ለዛውም በለሊት ልብስ ብዬ በመደመም ነበር እኮ ወደእዚህ የመጣሁት…››
‹‹ኪሊዬፕትራ አልከኝ…››
‹‹አዎ ምነው..በጣም እኮ ነው የምትመሳሰሉት››
አይ መመሳሰሉን እንኳን ተወው ..ግን በጣም የምወዳት ሴት ነች…››
‹‹አዎ በጣም ቆንጆ ነበረች አሉ››
‹‹ምን ታውቃለህ ስለእሷ ..እስኪ ንገረኝ..››አልኩት…እሱ እንደቀልድ ስሟን ቢጠራም ይህቺ ሴት ለእኔ ጀግናዬ ነች…
‹‹አረ ምንም አላውቅ የሆነች ቆንጆ ግብፃዊ ነች አይደል….?፡፡››
‹‹እኔ ልንገርህ ….?››አልኩት ስለእሷ ዕድሉን ባገኘው ቁጥር ማውራት ስለሚያስደስተኝ
‹‹ንገሪኝ እስኪ››
‹‹…አሁን የምትላት ኪሊዬፕትራ በተወለደችበት ዘመን ግብጽን ይመሯት የነበሩት የሮማ የዘር ግንድ ያላቸው ነገስታት ነበሩ….እሷም ከነዛ ነገስታት የዘር ግንድ በተዋረድ የተገኘች በግብጽምድር ተወልዳ በአባይ ወንዝ ፀበል ሰውነቷን ታጥባ ያደገች የንጉስ እና የንግስት ልጅ ነበረች፡፡ታዲያ ግብጽን ለ300 ዓመት ከገዟት እንዚህ የሮም ዝርያ ያላቸው ነገስታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በግብጽን ቋንቋ ማንበብና መፃፍ የቻለችው ይህቺ ብልህ ኪሊዬፕታራ ነች፡፡የግብጽን ቋንቋ በማወቋ የሀገሩን ታሪክ፤ ባህል እና ፓለቲካውንም በጥልቀት ለመመርመር የቻለች ሴት ነበረች ፡፡(ይህ ምንን ያሳያል …አንድን ሀገር እመራለው ብለህ ከመነሳትህ በፊት የዛን ህዝብ ቋንቋውን፤ ባህሉን ፤ስነልቦናውን ዝቅ ብለህ መማርና ማወቅ እንዳለብህ ነው)እሷ በዛ ዘመን ይሄ የገባት እንስት ነበረች….)
የሚያበሳጨው ልክ እንደአንተ አብዛኛው ሰው ስለእሷ ሲያወራ ቀድሞ የሚታየው አፍዛዣ ውበቷ ብቻ ነው..ሴት መሆን የሚያበሳጭህ እዚህ ላይ ነው…ምን ያህል ታስባለች….? ሳይሆን ምን ያህል ቋንጆ ነች ….?በሚለው መስፈርት ነው ቀድመው የሚመዝኑህ …ለማንኛውም ይህቺ ጀግና ውበቷ ብቻ አይደለም አፍዛዥ፤ድምጻም ምትሀታዊ ነበር… ባዶ ድምጽ ብቻም አልነበረም ለአንድ መሪ የሚያስፈልገው ከፍተኛ የኮሚኔኬሽን ጥበብንም የተካነች ነበረች… በተለይ ፍልስፍና ፤የንግግር ጥበብ ፤ሂሳብ እና ስነ ከዋክብት በጥልቀጥ አጥንታለች…(እዚህ ላይም መሪነት ሌላው የሚፈልገው ብቃት በሶስት እና አራት ዲስፒሊኖች እውቀት ሊኖርህ እንደሚገባ ነው..ይህንን በተግባር በማድረግ ያስተማረች ጀግና ሴት ነች)
ኪሊዬፕትራ አድጋ የተወለደች አይነት ሴት ነበረች…በ14 ዓመቷ የግብጽ ንጉስ የነበረው አባቷ ምክትል ገዤ አደረጎ ሾሟት ነበር… እናቷ በሚስጥራዊ ሁኔታ ከሞተች ቡኃላም የእሷን ሀላፊነት ትወጣ ነበር … አባቷ በሰጣት በምክትልነት ስልጣን ለአራት አመት በመስራት ጥሩ የአስተዳደር ልምድ አገኘች…፡፡ 18 ዓመት ሲሆናት አባቷ በመሞቱ ስልጣኑን ወሰደች…በትክክል ንግስናው የሚገባው ለታናሽ ወንድሞ ነበር…ለዚህም እንዲረዳት ተቀናነቃኝ የነበረውንና የንግስናውን መንበርም ለመውሰድ መብት የነበረውን የ10 ዓመቱን ወንድሟን አገባችው…በዘመኑ በነገስታቱ ልምድ መሰረት እርስ በርስ መገባባት የተለመደ ነበር…የዘር ግንዳቸውን ከሌላው ተራ ማህበረሰብ ጋር ላለመቀየጥ እና ቁንጅናቸንም እንዳይበረዝ እንደዛ ያደርጉ ነበር….ለዚህም ማረጋገጫ የኪሊዬፕትራ አባትና እናትም ወንድም እና እህት ነበሩ…እና የእሷን ለየት የሚያደርገው ወንድሟን ያገባችበት ምክንያት የተለየ መሆኑን ነው …ለገዛ አላማዋ ለስልጣን በአስተማማኝ ለመቋጣጠር ስለፈለገች ነበረ በ18 ዓመቷ የ10 ዓመቱን ወንድሟን ያገባችው ….
‹‹እሺ ከዛስ .. ….?እንዲህም ጨካኝ ነበረች እንዴ….?››ሲል በመደነቅ ጠየቀኝ
-መቼስ በዛ ዘመን ተወልዳ..በዛ ላይ ፍትሀዊ ባልሆነውና በወንድ ህግ በሚመራው አለም እየኖረች በእብሪተኛ ወንዶች ዙሪያዋን ተከባ ቆንጆ እና የተማረች ስለሆነች ብቻ በየዋህነት ዓላማዋን ማሳከት አትችልም ነበር…ስለዚህ ዘመኑ ሚጠይቀውን ዘዴ ሁሉ በመጠቀም የወንዶች ዓለም የሚጨፈለቅ እና የሚፈረካከስ መሆኑን በተግባር ማድረግ የሚገባትን ሁኑ በማድረግ ማሸነፍ እደሚቻል ያስመሰከረች ጀግናዬ ነች››
‹‹ታሪኳ አለቀ..….?››አለኝ በቅሬታ
-አላለቀም፤ ገና መጀመሩ ነው….ታናሽ ወንድሟን ባገባች በአራት ወራት ውስጥ የእሱን ስም ከህጋዊ ዶክመንቶች ላይ ሁሉ በሚስጥር እንዲወገድ አደረገች..መገባያያ ገንዘብን በእሷ ምስል ብቻ እንዲታተም አደረገች፤ በወንዶች የበላይነት የሚመራውንና ከእነሱ ገርባ መሸሸግን የሚሰብከውን የወንዶችን ህግ እንቢኝ አለችና በተግባር ተቃወመች…የዘውዱን ስልጣን ሙሉ በሙሉ በአስተማማኝ ሁኔታ ተቆጣጠረች..ይሁንና የመጀመሪያ ሶስት አመት የአገዛዝ ዘመኗ እንዳሰበችው ጥሩ እና ውጤታማ አልነበረም… የናይል ወንዝ መጠን የቀነሰበት፤ የተዘራው ምርት የጠፋበት፤ የረሀብ ዘመን ስለነበረ ሌላ ፈተና ገጠማት.. ህዝብ ተራበ ይህንንም ተከትሎ ፖለቲከኞች ፊታቸውን ያዞሩባት ጀመር….ያው የታወቀ ነው…የአንድ ሀገር ኢኮኖሚው ሲደቅ ፓለቲካውም ይበላሻል፤በእሷ ላይም የሆነው እንደዛ ነው፡፡ በዚህ ወቅት እሷም ውጥረት ሲበዛባት መሰለኝ የፖለቲካ ስህተት ሰራች…
‹‹ምን አይነት ስህተት…….?››
በውስጥ ያተፈጠረውን የፖለቲከ ሽኩቻውን ሳትፈታ ከሮማዊያን የተወሰኑ አንጃዎችና ከሶሪያ መንግስት ጋር መጋጨት ጀመረች.. .. ረሀብ ራሱ ከባድ ጦርነት ነው በዛ ላይ ሌላ እውነተኛ ጦርነት….ሮማዊያን ተናሽ ወንድሞን ከእሷ ገንጥለው አስነሱባት እሱን እየረዱ ይወጎት ጀመረ…በስተመጨረሻ አሸነፎትና እሱን ለንግስና አበቁት ..
‹‹ሰታሳዝን..››
‹‹አይ እሷ እንዲታዘንላት እንደምታውቃቸው አይነት ሴት አንገቷን ደፍታ የምታለቃቅስ ደካማ ሴት አይደለችም…ለእሷ ሁሌ ሌለ መንገድ አለ …መሸነፋን አልቀበል ብላ አዲስ ጦር አደራጅች… በምስራቅ ግብጽ በኩል ወንድሟ ላይ ጦርነት ከፈተች……ከዛ ወንድሞን እያሸነፈች ስትመጣ…. ወንድሞ ወደስልጣን ያመጡትን የሮማው ጁሊዬስ ቄሳርን እርዳታ ጠየቀ…በጋራ ጥምረት ፈጥረው እሷን
1👍1
ይወጓት ጀመሩ…አጅሪት አሰበች ሁለቱን በቀጥታ ጦርነት ልታሸንፋቸው አትችልም..እና ዘዴ ዘየደች.. ፡፡
ለቄሳሩ የግል መኝታ ቤት የሚያምር የምንጣፍ በስጦታ ላከችለት..ተገርሞ ጥቅልሉን ምንጣፍ መኝታ ቤቱ አስገባና አስፈታው …፡፡ከዛ ልብ ቀጥ አለች..አይኖቹ ፈጠጡ ..ማመን አልቻለም..በንግስና ዘመኑ አጋጥሞት የማያውቅ ሰርፐራይዝ ነበረ …፡፡ከስጦታ ሁሉ ወደር የሌለው ስጦታ… የአለም ውቧ ኪሊዎፓትራ ይመስለኛል እርቃኗን ነች ከምንጣፉ ውስጥ ብቅ…. ከዛ ቄሳር ምን ማድረግ ይችላል…….?ምን አቅምስ ኖሮት….….?፡፡ለአንድ ጀግና ጦር አዝምቶ አንድ ሀገርን እንደመማረክ ያአንድን ሴት ውብ ገላ ተራምዶ ወይም አይቶ እናዳላየ ችላ ብሎ መሄድ ቀላል አይሆንለትም፡፡ጦርነት ሲገጥም ከውጫዊው አለም ጋር ነው፡፡ፍቅርን ሲገጥም ግን ከራሱ ጋር ነው…ከገዛ ልቡ ጋር፡፡ለአንድ ሰው ደግሞ እራስን እንደማሸነፍ ከባድ የሚሆንበት ነገር የለም….ቄሳርም የገጠመው ይሄ ነው፡፡የኪሊዬፓትራ ውበት እንዳየ ልቡ ነች ቀድማ እጅ የሰጠችው..ልብ ከተማረከ ደግሞ ሰው ሌላ ምን ይቀራዋል….መንበርከክ እንጂ…
ከወንዱሟ ጋር የነበረውን ጥምረት ሽሮ ከእሷ ጋር አዲስ ጥምረት ፈጠረና እሷን ይወጉ የነበሩ የእሱን ጦር ፊታቸውን ወደ ወንድሟ እዲያዞሩ አደረገ …ከዛ ምን ሆነ በአራት ወር ውስጥ የንግስና ወንበሩን መልሳ ከወንድሟ ነጠቀች ..ይሄ ሁሉ ሲሆን የእሷ እድሜ 22 ብቻ ነበር ..በዚሁ አጋጣሚ ከ55 ዓመት ዕድሜ ካለው ጁሊዬስ ቄሳር ትንሹ ቄሳርን ወለደች… እሱ ግን በቅርብ ያገባት ሚስት ስለነበረችው ልጁን አምኖ ሊቀበል አልቻለም….ቡኃላ ግን እንዲሁ እንደቀልድ በቃ አልፈልግሽም ብለው ሚረሷት ሴት ስላልነበረች ቄሳር በሚስጥር ወደሮም ወስዶ አግብቶት ነበር… ከማግባትም በላይ የእሷን ምስል በቪኑስ ቤተመቅደስ እንዲተከል አድርጎ ነበር.. ቪኒስን ታውቃታለህ አይደል…….?
‹‹እኔ እንጃ እሲኪ ንገሪኝ…….?››
ቪኒሱ የግሪክ አንደኛዋ አማልክት ነች ..አፍሮዲትን አታውቃትም…ሰውና አማልክትን እኩል የማንበርከክ አቅም ያላት የፍቅር አምላክ ማለት ነች…እና እንደእሷ ነሽ ሊላት ነው መሰለኝ ከዛ ቤተመቅደስ ውስጥ ምስሏን እንዲቋም ያደረገው….እንድትመለክለት ፡፡ይገርምሀል በወቅቱ በሮም ሁሉም ሴት እሷን ለመሆን ነው የሚጥረው..እንደ እሷ መልበስ ፤የእሷ አይነት የፀጉር አሰራር ለመስራት..እሷ ምትቀባቸውን ቅባትና ሽቶዎች ለመጠቀም የሁሉም ዘመናዊ ለመሆን የሚሹ የወቅቱ ሮማዊያን ሴቶች የየእለት ጥረት በተቻለ መጠን እሷን ለመምሰል ነበር ፡፡ቡኃላ ግን ቄሳርን በሰው እጅ መገደሉን ተከትሎ ወደግብፅ ለመመለስ ተገደደች….
ይሄም ሩጫዋን እንዲገታ አላደረጋትም፡፡ ግብጽን ኀያል ለማድረግና ጠንካራ መንግስት ለመመስራ ቀጣይ ኢላማዋን ማርክ አንቶኒ ላይ ነበር ያነጣጠረችው..ማርክ አንቶኒ በቄሳር ዘመን የምስራቅ ሮም ገዣ የነበረ የታወቀ ጦረኛ እና ጀግና መሪ ነበር…እና ይህ ጀግና እራሱን እንደ ቡቻስ(የወይንና የድግስ አምላክ)እንደሆነ የሚያስብ ሰው ነበር..ይሄንን ሰው ለማጥመድ ድክመቱን ስታጠና ይሄንን ታሪክ ነው ያገኘችው…በግሪክ አፈታሪክ ውስጥ ደግሞ ይሄ የወይን እና የድግስ አምላክ ከፍቅር አምልክቷ አፍሮዲት ጋር ፍቀር የሰራበት አጋጣሚ ነበር…፡፡ታዲያ እሷ ምኗ ሞኝ ነው…ልክ እንደአፍሮዲት ተውባ እንደአፍሮዲት ለብሳ ዝግጅቷን ከጨረሰች ቡኃላ…አፍሮዲት እዚህ ቦታ ትገኛለች ››የሚለው ወሬ በዚህ አስፈላጊ ጀግና ጆሮ በወሬ አመላላሾች አማካይነት እንዲደርስ አደረገች..አጅሬ ዘወትር በምናብ ሲጎመዥበት የኖረ ህልማዊ ምኟቱን ስለነበረ ከእና ግርማ ሞገሱ፤በአጃቢዎቹ ተከቦ እሷ አለች ወደተባለችበት ስፍራ ገጭ…..ከዛ ሲያይ አይኑን ማመን አልቻለም..እውነትም አፍሮዲት… ስንት ሀገር ለማስገበር ድፍረቱ የነበረው ያ ጀግና ልብ በቀላሉ ቅልጥልጥ አለች..እጅ ሰጠ… በቀላሉ ተማረከላት..ሀገሩ የሰጠችውን ግደጅ እስከወዲያኛው ትቷ አንቺ ነሽ ሀገሬ አላት ===
‹‹መጨረሻው ታዲያ እንዴት ሆነ….?›› አለኝ በጉጉት
አይዞህ ወደመጨረሻው እየሄድን ነው ..…ማርክ አንቶኒ እና ኪሊዮፓትራ የጦፈ ፍቅር ውስጥ ገብተው ለመዳከር ያጠፉት ደቂቃ አልነበረም...አብረው መስከር ፤በጋራ መቆመር ፤በጥምረት አደን መውጣት ..ከዛ በግብጽ ላይ አይኑን የሚጥል ጠላት ሲመጣ ጠላትን ማደባየት ጀመሩ …ይገርምሀል አንቶኒ ያገባ ሰው ቢሆንም ሁሉን እረስቶ ከእንደገና በግብጽ ባህል መሰረት አገባት ፤ 3 ልጅ ወለደችለት …..ሚስቱንም ሀገሩንም አስካደችው…ቢሆን እሷ አላማዋን አሳካች ..ለሀገሯ ግብፅ ዘመን የማይሽረው ውለታ ዋለችላት…በዚህ ዘመን ኪሊዮፓትራ ሀገሯን ሀያል የምትፈራና የሰለጠነች ሀገር ልታደርጋት ችላለች…በየትኛው ዘመን እደሆነ ለማወቅ ባልችልም ስልጣኗን አስተማማኝ ለማድረግ ሁለት ወንድሞቾን እና አንድ እህቷን ጭምር አስገድላለች፡፡ስልጣን ቀናተኛ አይደለች፡፡
….ያው መቼስ የሰው ልጅ ፈተና አያልቅምና ሮማ ዳግመኛ በኪሊዮፓትራ ላይ ጦርነት ከፈተችባት.. በባህር ኃይል የተሳተፈበት በታሪክ የሚታወቅ አደገኛ ጦርነት ተካሄደ፡፡ኪሊዮፓትራ የራሷ የሆነ የምታዛቸው የጦር መርከቦች ነበሯት ፤ ማርክ አንቶንዬም እንደዛው… ቆይቶ ግን የሮማ ጦር ሁለቱን ለማዳከም ሁለቱ መሀከል ሰንጥቀው በመግባት ቆረጦቸውና ለያዮቸው….በሮም ወታደር መሸነፎን ስትረዳ ከተማረከች ቡኃላ ሚደርስባትን ውረደትና በማሰብ ይመስላል ወይም በሌላ ባልታወቀ ምክንያት በአደገኛ የእባብ መርዝ አራሷን አስነድፋ ሞተች… አየህ አንዳንዴ ጀግና የሚያሰኝህ በአስፈላጊው ሰዓት አስፈላጊውን ውሳኔ የመወሰን ብቃት ሲኖርህ ጭምር ነው…ወሳኔው እራስህንም ማጥፋት ቢሆንም….እና በጦርነተ ሽነፈት ላይ ተጨማሪ የሚስቱን ሞት የሰማው ጀግናው ማርክ አንቶኒዬም እሷ የሌለችበት ህይወት ለምኔ..እሷ ማትስበውን አየር እንዴት እስባለው…እሷ ማትኖረውን ህይወት እኔ እንዴት ሆኜ ኖራለው አለና በገዛ ጩቤው እራሱን ሰቅስቆ ገደለ…እናም አንተ የምትላት ኪሊዮፓትራ መጨረሻዋ እንዲህ ሆነ እልሀለው…
‹‹የሚገርም ታሪክ ነው››
‹‹አዎ የሚገርም ታሪክ ነው…አየህ በወንዶች አለም በየአንዳንዱ ውጤታማ ወንድ ጀርባ አንድ ጠንካራ ሴት አለች በሚል ሽፋን አይደል ወንዶች ሁል ጊዜ የፊተኛውን እና ወሳኙን ቦታ በማጭበርበርም ቢሆን የሚይዙት…...በኪሊዮፓትራ ታሪክ ደግሞ ከእሷ ውጤታማነት ጀርባ ሌሎች አለም የሚያውቃቸው ጠንካራ ወንዶች ነበሩ…..ጁሊዬስ ቄሳር እና ማርክ አንቶኒዬ፡፡
‹‹አንድ ቦታ ሄደን እንምጣ…››አለኝ ድንገት ….በነገርኩት ታሪክ ስሜታዊ መሆኑን በደንብ ያስታውቅበታል፡
‹‹መቼ….?››
‹‹አሁኑኑ….?ከ30 ደቂቃ ቡኃላ እንመለሳለን…..እምቢ እንዳትይኝ››ምን እንደምለው ግራ ገባኝ ….ያልጠበቅኩት ጥያቄ ነው
‹‹አልልህም …ልብሴን ቀይሬ እንሄዳለን..››
‹‹አይ ችግር የለውም..እንደዚሁ እንሂድ››
‹‹ሁለታችንም በቢጃማ..….?››
‹‹አዎ ››አለኝና ከተቀመጠበት በመነሳት እጄን በመጎተት መኪናውን ፓርክ ወዳደረገበት ቦታ ይዞኝ ሄደ
‹‹ቡኃላ ከሚስቴ አጣላሺኝ እዳትል››እያልኩ …ግን ደግሞ ያለተቃውሞ ተጎተትኩለት..የት ይዞኝ ሊሄድ ይሆን..….?

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «ፍቅር_ከፈላስፋ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ ፡ ፡ ❤️ፌናን እንዴ ይሄንን ድምጽ አውቀዋለሁ….እሱ ነው.. ከንባቤ ቀና አልኩና አንገቴን ወደኃላዬ አሽከረከርኩ በድንጋጤ ወደኃላው አፈገፍጋለው ሲል ወድቆ ነበር…ሳቄን ለቀቀቅኩት….. ‹‹አንቺ በትርፍ ጊዜሽ ሰይጣንም ሆነሽ ትሰሪያለሽ እንዴ….?›› ‹‹አዎ… ለዚህ ነው አንተን የመሰሉ መላዕክቶችን ለመፈታተን ችሎታው ያለኝ››…»
#ፍቅር_ከፈላስፋ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ



ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


#ፍሰሀ
===
እየጎተትኳት መኪናው ጋር ስንደርስ ቀጥ አልኩ…ለካ የመኪናዬን ቁልፍ አልያዝኩም ‹‹ሶሪ ፊናን ሁለት ደቂቃ››
‹‹ምነው››ግራ ገብቷት
‹‹የመኪና ቁልፍ ይዤ መጣሁ…››በማለት እዛው ጥያት በሶምሶማ ወደ መኝታ ቤቴ ሄድኩ…እመቤቲቱን እዳልቀሰቅሳ በቀስታ ከፍቼ ገባውና ወደ ኮመዲኖ ሄጄ የመኪናዬን ቁልፍና ሞባይሌን በቀስታ አንስቼ በዝግታ እየተራመድኩ ልወጣ በራፍ አካባቢ ስደርስ ‹‹ማሬ ››የሚል ድምጽ ወደ ኃላዬ እንድዞር አስገደደኝ..
‹‹ተነሳሽ እንዴ? ››
የተጨናበሰ አይኗን በእጆቾ እያሻሻች ‹‹አዎ ..ወዴት ነው…?››አለቺኝ
እየተንደረደርኩ ወደውስጥ ተመለስኩና ግንባሯን ስሜ ‹‹መጣው ተኝተሸ ጠብቂኝ..ወይንም እታች ወርደሽ ቁርስ መብላትም ትቺያለሽ››
‹‹እንዴ ምን ማለትህ ነው..? ምትሄድበት ቦታ አብሬህ እሄዳለው..አምስት ደቂቃ ጠብቀኝ……››
‹‹አይ ምን አስቻኮለሽ ..ዘና ብለሽ ተነሽ…ብዙም አልቆይም መጣው….››እልኳትና መልሷን ሳልሰማ ተንደርድሬ ወጣሁና በራፍን መልሼ በላይዋ ላይ ዘግቼባት እየተንደረደርኩ የሆቴሉን ደረጃ በመውረድ ወደምትጠብቀኝ አስደማሚዎ ፊናን ተመልሼ ሄድኩ….
ስደርስ‹‹እኔስ ሚስትህ አፍና አስቀረችህ ብዬ ወደ ክፍሌ ልመለስ ነበር››በሚል ሽርደዳ ተቀበለቺኝ
‹‹አይ ተርፌያለው›› አልኩና መኪናዋን ከፍቼ እሷን አስቀድሜ በማስገባት ዞሬ መሪውን በመጨበጥ ግቢውን ለቀን ወጣን… አስፓልቱን እንደያዝን ….‹‹ወዴት እንደምትወስደኝ ለማወቅ ጓጉቼለው››አለቺኝ
‹‹ይገርምሻል በጫወታሽ በመማረክ ከአንቺ ጋር ተጫማሪ የብቻችን ጊዜ ለማሳለፍ ስለፈሉኩ እንጂ ወደየት እንደምወስድሽ ምኑንም አላውቅም…››አልኳት…እውነትም በዚህ ጥዋት ለዛውም በለሊት ልብሷ ያለች ሴት ወዴት ይዣት ልሄድ እንደምችል ምኑንም አላውቅም…ሳቋን ለቀቀችው..ስትስቅ በጣም ታምራለች…ኪሊዬፓትራም ስትስቅ እንዲህ ታምር ነበር እንዴ ..?እሷም ስትስቅ የጁሊዬስ ቄሳር እና የማርክ አንቶኒዬን ልብ አሁን የእኔ ልብ ቀጥ እንዳለው ቀጥ ይልባቸው ነበር እንዴ…‹‹አንተ ይሄ ጥሩ ስነ-ምግባር ነው…?››አለቺኝ በትዝብት
‹‹እንዴት ምን አጠፋው?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት
‹‹ አንተን ብላ ኪሎ ሜትር አቋርጣ አምናህ የመጣችውን ፍቅረኛህን መኝታ ቤት ውስጥ ዘግተህባት ከሌላ ሴት ጋር ለብቻችን ሆነን ማውራት አማረኝ በሚል ተቀባይነት በሌለው ምክንያት እንዲህ ማድረግህ?››
‹‹በነገርሺኝ ታሪክ ነው የተማርኩት…ኪሊዬፓትራ ያፈቀሩት ሁለቱም ጀግኖች ባለትዳር ነበሩ..በእሷ ፍቅር ሲሸነፍ ትዳር ስላለን ይቅርብን አላሉም፡፡››
‹‹ጥሩ ተማሪ ነህ..ክፍ ክፉውን ብቻ መርጠህ አዕምሮ ውስጥ አስቀረህ….ደግሞ ፍቅር ያዘህ እንዴ?››
መኪናውን ዝም ብዬ በሰርክል አድርጌ ወደ ሆራ መስመር እየነዳውት ነው…
‹‹ማ እኔ ካንቺ ፍቅር…?››
‹‹አይ ድንገት እንደው ተሳስተህ አፍቅረኸኝ እንደሆነ ብዬ ነው?››
‹‹አይ እንደዚህ አይነት ስህተትማ አልሳሰትም……››አልኳት.
.እውነት አልተሳሳትኩም እንዴ..ካልተሳሳትኩ ታዲያ ምን እንደዚህ ያደርገኛል …?አንዴት ስለእሷ በየሰዓቱ የተዘበራረቀ አይነት ስሜት ሊሰማኝ ቻለ…?. ስታበሳጨኝ ምበሳጭላት ሳታስቀኝ ምስቅላት ምኔ ስለሆነች ነው ..?እራሴን የጠየቅኩትና በርግጠኝነት መልስ ላገኝላት ያልቻልኩት ጥያቄ ነው፡፡ምክንያቱም ከራስ ልብ ውስጥ እውነተኛ መልስ ማግኘት ከአንደበት ቃላት አውጥቶ ለሌላ ሰው ድንገተኛ መልስ እንደመመለስ ቀላል አይደለም፡፡
መከላከያ ኮሌጅ አካባቢ ስንደርስ ስልኬ ተንጫረረ…ሳየው የአባቴ ነው….‹‹ወይ ዳድ ነው የደወለው ማንሳት አለብኝ››አልኩን መኪናዬን ዳር ላይ አቆምኩ...ከምንቆም ቀይሪኝና አንቺ ንጂ ››አልኳትና ስልኩን አንስቼ እያዋራው ከገቢናው ወጥቼ ዞርኩ እሷም ዞረችና መሪውን በመጨበጥ በዝግታ ትነዳ ጀመር …እኔም አዕምሮዬን ሰብስቤ የናፈቀኝን አባቴን ማዋራት ቀጠልኩ….
‹‹እንዴ ዳድ አበዛሀው እኮ…በጣም ነው የናፈቅከኝ››ተነጫነጭኩበት….
‹‹ልጄ እኔም …..በጣም ነው የናፈቅከኝ››
‹‹አይ አይመስለኝም… ብናፍቅህማ ይሄን ያህል እትቆይም….››
‹‹አሁን መምጫዬ ደርሷል..ለመሆኑ ስራው እንዴት እየሄደልህ ነው፡፡››
‹‹አሪፍ ነው አባዬ…. በጣም አስደሳች እየሆነ ነው….አሁን ሰራተኛችንም ሆነ ስራውን በደንብ ለምጄዋለው… አንዳንድ ውጤታማ ለውጦችንም ለማድረግ እያሰብኩ ነው››
‹‹አይ አሪፍ ነው…ለመሆኑ ሰራተኞቹ በአንተ ላይ እምነት ያሳደሩ ይመስልሀል….መቼም ታውቃለህ ልጄ የምትመራቸውን ሰራተኞች ቀልብ ማሸነፍ ሳትችል ውጤት ማምጣት አትችልም››
‹‹አዎ ትክክል ነህ ዳድ..ሀላፊዎቹም ሆኑ ተራ ሰራተኞች በጣም ታዛዥና ተግባቢ ናቸው..እርግጥ አልደብቅህም አልፎ አልፎ አልታዘዝ ባዬችና ስርአት የሌላቸው ሰራተኞች አሉ ..እነሱንም የሚገባቸውን ትምህርት የሚሰጥ ቅጣት እየቀጣው ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ችያለው››ይሄንን ስናገር በቆረጣ ፊናንን እያየዋት ነው….ምን ያህል ትበሳጫለች የሚለውን ለማየት..በተቃራኒው የሹፈት ሳቅ እየሳቀች እንደሆነ ነው መታዘብ የቻልኩት ፡
‹‹ልጄ ሰራተኞችን በጥበብ ያዝ …ዝም ብለህ ቀጥታ አትላተም…››አባታ ምክሩን ቀጠለ
‹‹አይ አባ …ሁሉን የምታገስ ከሆነም እንዴት ብዬ ነው በሶስት ወር የምትፈልገውን ውጤት ማግኘት የምችለው..በዛ ላይ አንደኛው ወር እያለቀ ነው..››
‹‹ልጄ አሁን የደወልኩልህ ስለዛ ላወራህ ነው…ለዛ የሚሆን ጊዜ የለንም …ስብሰባው ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲደረግ ተወስኗል..››
‹‹ብዥ ነው ያለብኝ….እንኳንም እኔ እየነዳው አልሆነ ….መኪናዋን መንገድን ስቼ ከሆነ ግንብ ጋር እላተም ነበር..
‹‹እንዴ አባ ..በአንድ ወር ምን አይነት ተአምር ልሰራ ነው…እሰከአሁን እኳን ሙሉ በሙሉ የካማፓኒውን አሰራር እና የእያንዳዱን ሰራተኛ ብቃትና ጉድለት አጥንቼ አልጨረስኩም…እነዚህን ነገሮች በጥልቀት ሳላውቅ ደግሞ የካምፓኒው ጥሩ ጎኑንና ለውጥ የሚያስፈልገውን ቦታ ለይቷ ማወቅ ያስቸግረኛል…..በሶስት ወር ምን አይነት የተለየ ነገር ማድረግ እችላለው ብዬ ስጨነቅ ጭራሽ አንድ ወር?፡፡..አልችልም አባ … የእውነት የመጣው ይምጣ እንጄ በአንድ ወር ውስጥ የምትፈልገው ነገር ላሳካው አልችልም ››
‹‹አውቃለው ልጄ..እኔም ያማትችለውን ነገር አድርግ ብዬ ላስጨንቅህ አልፈልግም››
‹‹እና ታዲያ እንሸነፍ…ዕድሜ ልክህን የለፋህበትን ካምፓኒ እጅ ሰጥተን ለሴትዬዋ እናስረክባት…እሷ ለሴት ልጄ ሰጥታ ድርጅታችንን ድምጥማጡን እንድታጠፋው እንፍቀድላት…እንዴ አባዬ አንዴት እንዲህ በቀላሉ ተሸናፊ ሆንክ…?. ህልሜንማ እነዲህ ፍቺ አልባ አታድርገው…››
‹‹ልጄ አሁን መስፈርቱ ተቀይሯል ..አንተም ሆንክ የሴትዬዋ ልጅ የምትወዳደሩት በምታቀርብት ፕሮፕዛል ጥራት እንዲሆን ተወስኗል….ክምፓኒውን በጥልቀት ምን ያህል አውቃችሁታል …ወደፊትስ የት እንዲደርስ ለማድረግ ትችላላችሁ… …በዛ ነው የእያንዳንዳችንን ድምጽ በተለይ ልዩነት የሚያመጣውን የሰውዬውን ድምጽ ማግኘት የምትችሉት››
‹‹እንደዛ ከሆነማ ቀላል ነው…››
‹‹እንዴት ቀላል ነው ልትል ቻልክ.?.››
‹‹እንዴ አባ አንደኛ አሁን በካምፓኒው እንድሰራ እድል በማግኘቴ ምክንያት ብዙ ዕውቀቶችን አግኝቼያለው….ይሄ ደግሞ ለፕሮፖዛሉ በቂ ግብአት እንዳገኝ ያግዘኛል..ሁለተኛ የካምፓኒውን ሀላፊዎች ሆነ ኤክስፐርቶችን ሁሉ ቀኑ እስኪደርስ ድረስ መጠቀም እችላለው፤ ከእነሱ የማገኘው እገዛም ሆነ ግብአት ቀላል አይደለም…ሌላው አስፈላጊወም ከሆን ረዳት
👍7
ቀጥሬ እንዲያግዘኝ ማደረገ እችላልው..ይሄን ሁሉ አድርጌ አንዲት ሴት ማሸነፍ ካቃተኝም ያንተ ልጅ አይደለውም ማለት ነው››የምሬን በብስጭት ፎከርኩ
‹‹እንደምታደርገው አምናለው ልጄ.. ላስጠነቅቅህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ወሳኙን የመለያ ድምጽ የያዙት ሰውዬ ቀላል ሰው እንዳልሆኑ ነው….ሁል ጊዜ የተለየ ነገር ይፈልጋሉ…ከዚህ ቀድመው የማያውቁትን ወይንም በጣም ሊያስደምማቸው የሚችል ነገር ካላገኙ ድምጻቸውን ማግኘትን አታስበው..….በተረፈ ዝርዝሩን ስመጣ እናወራለን..እኔም አግዝሀለው››
‹‹መች ነው የምትመጣው ?››
‹‹ከአስር ቀን ቡኃላ መጣለው››
‹‹እሺ ቻው አባ እወድሀለው››
ስልኩን ዘግቼ አካባቢዬን ስቃኝ ለካ መኪናውን ዳር ይዛ በማቆም በተመስጦ ዝም ብላ እያዳመጠቺኝ ነበር
‹‹እንዴ ምነው መኪናውን አቆምሽ..?››ጠየቅኳት
‹‹አይ እዚህ ትንሽ እድንቆይ ፈልጌ ነው››
‹‹አባቴ እኮ ደውሎ .በጣም ደባሪ ነገር ነው የነገረኝ..››
‹‹ሰማውኮ…ነገሩ በደንብ ባይገባኝም መረበሽህን ከንግግርህ ተረድቼያለው…››
‹‹አዎ ባክሽ ላንቺ መንገር ይኑርብኝ ወይስ አይኑርብኝ አላወቅም እንጂ ትንሽ የሚረበብሽና ያልጠበቅኩት ነገር ነው ..››
‹‹ከደበረህ ተወው…ግን የካማፓኒው ስራ-አስኪያከጅ ለመሆን አንድ ተቀናቃኝ አለችብህ መሰለኝ…ከንግግራችሁ የተረዳውት ያንን ነው…››
‹‹አልተሳሳትሺም…ግን እወጣዋለው››
‹‹ለምን ከሴት ጋር ስለሆነ ፉክክሩ…?.ሴት ደካማ ስለሆነች?››ኮስተርና በስጨት ብላ
‹‹አይ ማለቴ….››የምላት ጠፋኝ
‹‹ለመሆኑ ልጅቷን ታውቃታለህ..?ማለቴ የትምህርት ዝግጅቷን ?የስራ ልምዷን? የተፈጥሮ ብቃቷን..?››
‹‹አይ አላውቅም…ግን ያው በእኔ ዕድሜ አካባቢ እንደሆነች አውቃለው…ስለዚህ ሌላውን መገመት ብዙም አይከብደኝም…››
‹‹ሴት መሆኗን እና በአንተ ዕድሜ ላይ ምትገኝ መሆኗን ብቻ በማወቅህ የእሷን ብቃት ካንተ በታች ዝቅ አድርገህ ለመያት በቂ መረጃ ሆነህ …ብቻ እግዜር ይሁንህ ..፡፡ግን እንደ ምክር ልስጥህ …ማንኛውም ጦረነት ውስጥ ስትገባ ምንም አይነት መንገድ የባለጋራህን ችሎታ ዝቅ አድርገህ አለማየት ይጠቅምሀል በሌላ ጎኑም በራስህ ላይ ያለህን በራስ መተማመንም ማጣት የለብህም…ይሄ ትክክለኛውን ዝግጅት እንድታደርግና በዝግጅትህም መጠን በብቃት እድትፋለም ያግዝሀል፡፡
‹‹ምን አበሳጨሽ አንቺ?›› አልኳት..መበሳጨት ከንግግሯም አልፎ በፊቷ ላይ በግልጽ ስለተነበበ..
‹‹አይ እንዲሁ ነው…ለማንኛውም ይሄ የምታየው ጨለቅለቃ ሀይቅ ነው…የሚደነቁ አይነት ወፎች በአካባቢው አሉ… ለተወሰነ ደቂቃ ወርደን በግር እንራመድ››አለቺኝ
በደስታ ተስማምቼ ወረድኩ መኪናውን በመቆለፍ ወደእሷ በመሄድ የአስፓልቱን ዳር ይዘን ቀኝ እጄን ተከሻዋ ላይ ጣል አድርጌ አካባቢውን የወረሩት ደግሞ ስንጠጋቸው እየተበተኑ ሰማዩን በውበት እየሞሉ በመንሳፈፍ ዛፎቹ ላይ የሚያርፉትን እንደ ዳክዬ ፤ፓሮት፤ ፍላሚንጎ ፤ ብዙ ስማቸው የማላውቃቸውን የተለያየ እና ገራሚ ዝርያ ያለቸውን ወፎችን እየተመለከትን ስንራመድ..
‹‹ፀጥ አልሽ ምነው?››
‹‹እኔ እንጃ ከአባትህ ጋር ስታወራ አባቴ ናፈቀኝ?››
‹‹አባትሽ…ታዲያ አውሪያቸዋ..›› ስልኬን አቀበልኳት..ስልኩን ተቀብላኝ ቁጥሩን እየመታች ሸርተት ብላ እጆን ከትከሻዬ ላይ አወረደችና ወደኃላ ቀረች..ገባኝ ፡፡የማወራውን ነገር እንድሰማባት አልፈለገችም ማለት ነው…ስለዚህ ፈጠን ፈጠን ብዬ ወደፊት በመሄድ በመሀከላችን የነበረውን ርቀት አሰፋውት
===
❤️ፌናን

ይህ የተረገመ ልጅ በደቂቃዎች ነው ስሜቴን ያደፈራረሰው….ከአባቱ ጋር ያወራው ወሬ በራሱ ግርታ ፈጥሮብኛል በዛ ላይ የእሱ ለሴት ያለውን ዝቅ ያለ ግምት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አናዳጅ ሆኖ ነው ያገኘውት ..…እንደው ወንዶች ምንም ቢማሩ፤ ምንም ያህል ዘመናዊ ነን ቢሉ እብሪት አይለቃቸውም..ስሜቴን መደፍረስ ተከትሎ ዝም በማለቴ ለጠየቀኝ ጥያቄ በሰጠውት መልስ ለአባቴ እንድደውል ስልኩን ሲያቀብለኝ አላቅማማውም…ከእሱ ወደኃላ ቀርቼ አባቴን እያወራውት ነው…
‹‹እንዴ…አንቺው ነሽ ማሬ ..ስደውልልሽ እኮ ስልክሽ ይጠራል አይነሳም…ሳይለንት ላይ አድርገሽው ያላየሽው ነበር የመሰለኝ፡፡››
‹‹አይ አባ መኝታ ቤቴ ረስቼው ከልጆች ጋር ዞር ዞር እያልን ስለሆነ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ነው….በቃ ተዝናኑ ..››
‹‹እሺ አባ .ከመዝጋትህ በፊት ግን እማዬ ደውላ ነበር እንዴ?››
‹‹አዎ ምነው ማታ ደውላ ነበር››
‹‹ያለችህ አዲስ ነገር አለ?››
‹‹አዎ ከስድስት ወር ቡኃላ ለማድረግ ቀጠሮ ይዛበት የነበረው ወደ ሶስት ወር ዝቅ ብሎል..ከዛሬ ሶስት ወር ቡኃላ የልብ ቀዶ ጥገናውን ታደርጋለች..ስለዚህ ከዛ በፊት ከሀያ ቀን ቡኃላ ወደሀገር ቤት እንደምትመጣ ነግራኛለች..ግን ምነው..?የሰማሺው ነገር አለ እንዴ?››
‹‹አረ የለም ..እንዲሁ በህልሜ ስላየዋት ነው..በል አባ ቻው ..ደውልልሀለው..እና በጣም እድሀለው፡፡›› ስልኩን ዘጋውና ወደ እሱ ፈጠን ብዬ ሄድኩ…..

#ፍሰሀ

ስልኩን አናግራት ጨርሳ ስትመጣ ልክ ፍቅረኛዋን አናግራ እንደመጣች ነገር ነው ከጨገጋት ስሜት ወጥታ እየተፍለቀለቀች የመጣችው….ግን ፍቅረኛውን እንደሆነ ያናገገረችው በምን አውቃለው…››በውስጤ የተጫረ ጥያቄ ነበር..ደግሞ ወዲያውኑ ፍቅረኛዋንስ አናግራ ብትመጣ አንተ ምንህ ተነካ…..››እራሴን የጠየቅኩት ጥያቄ ነበር… አይ መነካት ሳይሆን ለምን ትዋሸኛለች ?››ለአዕምሮዬ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሞከርኩ..መጥታ ልጥፍ ስትልብኝ ሁሉንም እረሳውትና ጠረኗን እየማግኩ ውቡን ተፈጥሮ፤ የሚያማምሩ ወፎችን ዝማሬ ወደማዳመጥ ተሸጋገርኩ..
ታብራራልኝ ጀመር‹‹ይሄን ሀይቅ በበጋ ብትመጣ አሁን እንዲህ እንደምታዬው አታገኘውም…››
‹‹እንዴት?››
‹‹ይደርቃላ..ባዶ ይሆናል፡፡ከዛ የአካባቢው ሰዎች ለግብርና ስራ ይጠቀሙበታል ….ሽንኩርት፤ ቲማቲም ፤በቆሎ ጭምር ያመርቱበታል..ክረምት ሆኖ ዝናብ መዝነብ ሲጀምር ግን ከከተማው ሁሉ ተሰብስቦ የሚመጣው ጎርፍ ተጠራቅሞ የሚተኛው እዚህ ስለሆነ ተንጣሎ ይተኛል….የሚገርም ሀይቅ ይሆናል..ያንንም ተከትሎ ከዚህ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አህጉር አቋራጭ ወፍች ጭምር እንደምታየው መጥተው እዚህ በጊዜዊነት በመስፈር አካባቢውን የበለጠ ውብ ያደርጉታል….በዛ ላይ አዚህ አካባቢ ቆመህ ፊትህን ወደ ሀይቁ አዙረህ ማዶ አሻግረህ ስታይ የሚገርም የተፈጥሮ እይታ ነው አይንህን የሚሞላው…ያ ተራራ ይታይሀል..ኤረር ተራራ ይባላል፡፡አስር የአዲስአበባ ወጣት አቁመህ ኤረር ተራራ የት ይገኛል ብትል አንድ ሰው ብቻ ቢመልስልህ ነው…
‹‹እኔ እራሴ አላውቅም …››
‹‹ይሄ ተራራ እንደምታዬው አስደማሚ ሰንሰለታማ ተራራ ሲሆን ብቻው እንደሙዚዬም ሊጎበኝ ሚችል ታሪክ ያለው ነው፤በውስጡ ከ300 በላይ ዋሻዎች አሉት ፡፡ከዛም በላይ የአብረሀ አጽብሀ ቤተመንግስተ እና የልብነድንግል ቤተመንገስቶች ነበሩበት..አሁንም ፍርስራሹ ይገኛል…በዛ ላይ በጣም ብዙ ደብሮች በተራራው ላይ እንደነበሩ ታሪክ ይናገራል..ከዛም አልፎ የኢትዬጵያ ማዕከላዊው ስፍራ ወይም እንብርት ይሄ ተራራ እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ..ይሄም አንዱ ድንቅ ሚስጥር ነው፡፡አሁንም ከታሪካዊነቱ በተጨማሪ አካባቢው በአሁኑ ጊዜ በደን የተሸፈነ እና ለፍፁም መደመምና ከራስ ጋር ለመማከር ተመራጩ ቦታ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ከዚህ 9ኪሎ ሜትር ብቻ ብትሄድ ዝቋላ ገዳምን ታገኘዋለህ…ዝቋላ ስትሄድ ታራራ ታገኛለህ ፤
ሀይቁም ታገኛለህ..ሀይቁ የሚገርም ገበቴ ውስጥ ያለ የሚመስል ዙሪያውን በቄጤማ የተከበበ ነው፡፡አካባቢው ዙሪያውን በየአመቱ በሚነሳ ሰደድ
👍103