አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
​​ቀጠለ የለበሰችውን ፓንት ቁልቁል ወደታች ተረተረው..ሙሉ  በሙሉ  ዕርቃኗን ቀርታ መንዘፍዘፍ ጀመረች…ያቺ አስፈሪ..ያቺ አደገኛ ጀግና ሴት..ያቺ ስንቱ ባለስልጣን ስንቱ የከተማው ሀብታም የእሷን አገልግሎትና እገዛ ፈልጎ ያለችበት ድረስ የሚርመሰመስላት ሴት … ራሷ እንዲህ ድንጉጥ..ተርበትባች እና መጠጊያ የሌላት ደካማ ሴት ሆና ስትታይ እውነት ነው ብሎ ማን ያምናል፡፡
ከዛ ፋሲል‹‹ቅጣትሽ ከእኔ መፀነስ ይሆናል..ትወልጂልኛለሽ››አላት ወደ ጆሮዋ ተጠግቶ፡፡
አቃተተች….ተወራጨች‹‹አይሆንም…ፍፁም አይሆንም…ልጅ መውለድ አልፈልግም …በፈጠረህ?››
አልሰማትም..እንዲሰማትም አይጠበቅበትም…የተሰጠውን ትወና በትክክል መተወን ይጠበቅበታል…ልክ ራሷ እንዳሰለጠነችው፡፡የሱሪውን ቀበቶ ፈታና ሱሪውን ወደታች ዝቅ አድርጎ እርቃኗን በሰንሰለት እጅና እግሯ ተሰትሮ እንደታሰረ ተገናኛት፡፡እየለመነችው..እየተማፀነችው፡፡በመጨረሻ ዝልፍልፍ ብላ አንገቷን ወደታች ቀበረች በዛ ቅፅበት እሱም ከውጥረቱ ረግቦ ነበር፡፡

ሱሪውን ወደላይ መለሰና ግራ እጇን ብቻ ከሰንሰለቱ አላቆላት በሩን ከፍቶ ወጥቶ ሄደ…ባለው ልምድ ከዚህ በኃላ ስሯ መቆየት የለበትም፡፡ ከእብደቷ ስትነቃ ስሯ ካገኘችው መልሳ እሱኑ አስራ ትገርፈዋለች..እስክትረጋጋ  ከፊቷ  ዞር  ማለት አለበት፡፡ ለዚህ ነው ሙሉ ለሙሉ እንኳን ከእስሯ ሳይፈታት መፈርጠጡ፡፡
ነፃ በሆነ እጇ በሰንሰለት እስር ውስጥ ያለውን ሌለኛውን  እጇን  ፈታችና እንደምንም እግሯ ብሬክ እንደሚደንስ ዳንኪረኛ እየተንቀጠቀጠባት ወደሻወር ቤት ገባች…ውሀውን ከላዩ ለቀቀችው.. ከላይ ፀጉሯ ላይ እያረፈ  መላ  ሰውነቷን እያራሰ ቁልቁል ወደወለሉ ሲወርድ እሷ ደግሞ በተሰበረ ልብ እና በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆና እንባዋን እያረገፈችና በሀሳብም እየናወዘች ነበር…..ስታስበው የአለምን ሀጥያት ሁሉ ሰብስባ በተከሻዋ የተሸከመች ይመስላታል..ከሸክሙ ክብደት የተነሳ ትከሻዋ ጎብጧ ግንባሯ መሬት ደርሶ በምላሷ እየላሰች ያለች ይመስላታል..ከዚህ የአእምሮም መጨለም.ከዚህ የልብ መጥቆር…ከዚህ የመንፈስ መታወክ…የትኛው መሲዕ እንደሚያድናት ምንም የምታወቀው ነገር የለም፡፡ለሶስት አመት ብላ የጀመረችው ስራ ዛሬ ነገ ስትል አስር አመት ሙሉ  ሰርታዋለች..እያንዳንዱን ቀን በዚህ ስራ ላይ ባሳለፈችበት መጠን ብዙ ብር እና ብዙ ልብን የሚሰባብር ሀዘን ለራሷ እየሸለመች ነው፡፡በቅርብ ጨከን ብላ ስራዋን እርገፍ እድርጋ ካላቆመች እየሄደች ሳለ ድንገት ተዝለፍልፋ ወድቃ እስከመጨረሻው ሊያበቃላት እንደሚችል እየተሰማት ነው…በቃ ደክሟታል፡፡ይሄ መፅሀፍ  አልቆ  ታትሞ  ገበያ  ላይ  ከዋለ የዛን ጊዜ ሀሳቧ  ይሳካላታል..ነፃ  ትወጣለች፡፡ከዛ ጨለማ ስራዋ  ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ትገላገላለች፡፡ ከዛ በኋላ ምንድነው የምትሰራው….?ለአመታት የሚያኖራት በቂ ብር ባንክ ደብተሯ ውስጥ ስላላት ያ ብዙም አያስጨንቃትም፡፡

ከሻወር ወጣችና ሰውነቷን  በፎጣው  አደራርቃ  ወደአልጋዋ  ሄደችና  ……ጥቅልል ብላ ተኛች፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍686👏3👎2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንችስ


#ክፍል_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ፋሲል ጥሏት ከሄደ ከ5 ሰዓት በኋላ ደወለላት..ከእንቅልፏ ነቅታ እዛው አልጋ ላይ እየተገላበጠች ስታስብ በነበረበት ጊዜ ነበር የደወለላት እና ለእራት የቀጠራት፡፡እየደበታትና ከዛም ተነስቶ እራስ ምታት እየጀማመራት ስለነበር የእራቱን ግብዣ በደስታ ነበር የተቀበለችው…፡፡በዛ ላይ መቼ እንደሆነ ባታውቅም በቅርብ የምታጣው ሰው ስለሆነ እንደመሰናበቻ አሪፍ አሪፍ የተባሉ ጊዜያቶችን ከእሱ ጋር ማሳለፍ ትፈልጋለች፡፡ለዚህ ነው ብዙ ሳታስለምነው በመስማማት ለባብሳና ተቆነጃጅታ ወደቀጠራት ቦታ ሄደችው፡፡

ፋሲል ከሳራ ጋር ያለው ለአንድ አመት ከሁለት ወር የዘለቀ የፍቅር ግንኙነት ህይወቱን ምስቅልቅል አድርጎበታል፡፡እርግጥ የእሱ ህይወት መቼም ከመርመስመስ ርቆ አያውቅም፡፡አሁን ግን ችግሩን የተለየ ያደረገው ማፍቀሩ ነው፡፡22 ዓመት ሆኖት በ11 ዓመት ምትበልጠውን በዕድሜ ታላቁ የሆነችዋን ሴት ከልብ አፍቅሯታል፡፡እርግጥ እሷን ብቻ ሳይሆን ብሯንም ከእሷ እኩል  ነው የሚያፈቅረው፡፡ ግን የሚገርመው ምንነቷን በጥልቀት አያውቅም:: ሀገር ቢያንሾካሹክበትም..ጓደኛቹ ቢያላግጡበትም ለእሱ ለውጥ አያመጣም.. በቃ አፍቅሯታል፡፡ እሷ ግን ታፍቅረው ወይስ  ዝም  ብላ  እንደመደበሪያ  እያየችው ይሆን? በእርግጠኝነት መናገር አይችልም፡፡ግን ማመን የሚፈልገው እንደምታፈቅረው ነው፡፡ቢሆንም ስሜቷን አንብቦ ፍላጎቷን መተንበይ ለእሱ ኪሊማንጀሮን ተራራ በሩጫ የመውጣት ያህል ከባድ ነው የሆነበት፡፡ሁለ ነገሯ ግራ ያጋባዋል…ንግግሯ ግራ ያጋባዋል…አኗኗሯ ግራ ያጋባዋል..የወሲብ ልምዷ ግራ ያጋባዋል..የወደፊት ዕቅዷ ሳይቀር ግራ ያጋባዋል፡፡

እርግጥ እሱ በእሷ ፍቅር ተንኮታኩቶ እንዲወድቅ ካደረገው ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ በየቀኑ ያለስስት የምታስጨብጠው  ረብጣ  ብር  ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይሄ ግራ አጋቢውና  ነፍሱን  ስልብ  የሚያደርገው  የወሲብ አሰራሯ ነው፡፡በቃ እንደኮኬይን ዕፅ ሱስ ሆኖበታል፡፡ሊተውት የማይቻል  ክፉ ሱስ፡፡ግን ቢሆንም ለዘላቂ ጥቅሙ ሲል ማድረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡

ከተቻለ ይህቺን ሴት ፍጹም ማጣት አይፈልግም፡፡ በአስቸኳይ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት ማሰብ ከጀመረ ሰነባብቷል..ዛሬ ዝግጅቱን አጠናቆ ዕቅዱን ወደተግባር የሚቀይርበት ቀን ነው፡፡ ሊያስደንቃት ወስኗል፡፡
የቀጠራት ሆቴል ብዙውን ጊዜ የሚገናኙበት  ነው፡፡ሁለቱም  ከሆቴሉ ባለቤቶች ሆነ ከአስተናጋጆቹ ጋር ጠንከር ያለ ትውውቅ አላቸው….ስትደርስ ሆቴሉ በተስተናጋጆች ተሞልቷል፡፡ከገመተችው በላይ ሰዎች መኖራቸው ብቻ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ ወንድሜ ነው፤ ጓደኛዬ ነው ፤የአጎቴ ልጅ ነው እያለ ያሰታዋወቃት ስድስት ሰባት የሚሆኑ በእሱ በኩል የምታውቃቸው ሰዎች ሁለትና ሶስት ሆነው እዚህና እዛ ተቀምጠው ስታይ ያልተለመደ ነገር ስለሆነባት ግራ ተጋባች…እውነታው በእሱ ሚስጥራዊ ግብዣ  ተጠርተው  የመጡ  የቅርቡ ሰዎች ናቸው፤ሌሎቹ ደግሞ ባጋጣሚ እግር ጥሏቸው የታደሙ የሆቴሉ ቋሚና ድንገተኛ ደንበኞች ናቸው፡፡ሁሉ ነገር ሙሉና ባሰበው መልኩ የተቀናጀ ቢሆንም አንድ ነገር ግን ቅር አሰኝቶታል..

የኤልሳ እዚህ መገኘት  ነው፡፡ኤልሳ  የልጅነት  ፍቅረኛው  ነበረች፡፡ነበረች  ማለት አሁን ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ አቁመዋል ማለት አይደለም፡፡በተለያየ ጊዜ እየተገናኙ ሳባ እንዳታውቅ እየተጠነቀቀ ይገባበዛሉ..አብረው ይቅማሉ.. አብረው ይጨፍራሉ አልፎ አልፎም አብረው  ያድራሉ፡፡ከዛ  በላይ  በጣም  አደገኛው  ነገር ሁሌ ኤልሳ ስለእሱ እና  ስለሳባ  ግንኙነት በምትጠይቀው ጊዜ የሚመልስላት መልስ ፈፅሞ እሷን እንደማያፈቅራት፤ የቀረባት ለገንዘቧ ሲል ብቻ እንደሆነና እንደምንም ጠቀም ያለገንዘብ ከተቀበላት በኃላ አፍንጫሽን ላሺ ብሎ እሷኑ እንደሚያገባ ከመቶ ጊዜ በላይ ነበር እየማለ ያረጋገጠላት፡፡እውነታው  ግን ዛሬ እየሆነ ያለው ነው፡፡ ፋሲል ሳባን የሚያፈቅራትን  ያህል  ኤልሳ  ደግሞ  እሱን  ታፈቅረዋለች፡፡ለዚህ  ነው ስለ ዛሬው ዝግጅት ዕቅድ ሚስጥራዊ ሆኖ ከእሷ ጆሮ እንዲጠበቅ አጥብቆ ተግቶ የነበረው..አልተሳካለትም እንጂ..አሁን ነገር እንዳታበላሽበት ልቡ ፈርቷል፡፡

በቅርቡ ሳባ የገዛችለትን የጣሊያን ሱፍ ለብሶ ዝንጥ ብሏል..ሳባ ልዩ የሆነ ረጅም ብርቱካናማ የራት ልብስ ለብሳለች፡፡ሁለቱም ውብ ሆነዋል፡፡እራት ቀረበ… ወይን ተቀዳ…ምግቡ በመጐራረስ ተበልቶ መአዱ ከፍ ካለ በኃላ ፋሲል ከመቀመጫው ተነሳና ወደመድረኩ ተንቀሳቅሰ፤ ሙዚቃውን አዘግቶ ማይኩን   ተቀበለና ጉሮሮውን አፀዳድቶ መናገር ጀመረ፡፡‹‹የእኔ ፍቅር በአሁኗ ሰዓት እዚህ በታደመው ህዝብ ፊት ላንቺ የምናገረው አንድ ነገር አለኝ››አለ፡፡የሆቴሉ   አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ፀጥ አለ..ለወሬ የቋመጡ ጆሮዎች ከየአቅጣጫው   ተቀሰሩ፡፡እሷ ደስ የማይል ነገር ውስጧ ተፈጠረ‹‹እባክህ አታድርገው…እኔ አንተን መቼም ማግባት አልፈልገም››አለች በልቧ፡፡

‹‹ማይኩን እንደያዘ ወደእሷ ቀረበና ከፊት ለፊቷ  ተንበረከከ፡፡ልክ  በሆሊውድ ፊልም ላይ ሲደረግ እንዳየው እሷ ከምትሰጠው ገንዘብ ቆጥቦ የገዛውን የጋብቻ ቀለበት ከኪሱ ውስጥ አወጣና፡--------

‹‹የእኔ ፍቅር ሚስቴ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ.. ታገቢኛለሽ?››

ሲል በጥርጣሬም በፍራቻም ጠየቃት፡፡በእሷ ላይ ምንም አይነት የስሜት ለውጥ አልታየም፡፡ አልበረገገችም፤ አልተፍለቀለቀችም፡፡ አልተኮሳተረችም፡፡ብቻ በፊት  በነበረችበት ሁኔታ ፀጥ ብላ ተቀመጠች፡፡ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ስለገባት ነው ደንዝዛ የነበረው…ገፍትራው ቤቱን ጥላ ትውጣ…ወይስ ጣቷን ቀስራ እንዲያጠልቅላት ትፍቀድለትና ስለቀጣዩ ጉዳይ ቀስ ብላ ታስብበት.ይሄንን ነገር  የመሞከር ዕቅድ እንዳለው ታውቃለች.ግን እንዲህ በፈጠነ ቀን ለማድረግ ይሞክራል ብላ ፈፅሞ ግምቱ አልነበራትም..ያ ነው በጣም እንድትደነግጥ ያደረጋት፣ይሄንን በማሰላሰል ከእራሷ ጋር ሙግት ገጥማ ባለችበት ጊዜ
ፋሲል አሻግሮ የኤልሳን ፊት መለዋወጥና የአይኗን ማጉረጥረጥ በጎሪጥ ከሩቁ አያትና ,ጀርባውን ሰጣትና አጠገቡ ወዳለችው ሳባ ዞሮ ስሯ በመንበርከክ

‹‹የእኔ ፍቅር ታገቢኛለሽ …?መልስሽን  በጉጉት  እየጠበቅኩ  ነው?››በማለት ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄውን አቀረበላት ፡፡እምቢ ብትለው የጓደኞቹ  እና  የኤልሳ መሳቂያ ሆኖ እንደሚከርም ሲታሰበው ውስጡ ቀዘቀዘበት፡፡
በተቃራኒው ሳባ የጠረጠረችው  ነገር  በመሆኑ  እንደመተከዝ  አለች..አሁን ጥያቄውን መቀበል አለባት.. በምንም አይነት እነዚህ ሁሉ ሰዎች መካከል እምቢ ብላው አጉል ትኩረት መሳብ አልፈለገችም፡፡በምንም አይነት ሁኔታ ግን ግንኙነታቸው ከሳምንት በላይ እድሜ እንደማይኖረው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ሆነች፡፡ሀለቃዋ ስለእዚህ ፍቅረኛዋ ከሰማችበት ቀን አንስቶ ይቅርብሽ እያለች

ስታስጠነቅቃት ነበር፡፡የልጁ ፍላጎት የወሲብ ስሜቷ ላይ ብቻ ተገድቦ እዛ ላይ እንዳማይገታ ደጋግማ ነግራታለች፡፡
👍877👏1😁1
፡፡ እሷ ስትፈራው የነበረው ነገር በመድረሱ አዘነች፡፡ እያዘነችም ጣቷን ዘረጋችለት….መተወን ጀመረች‹‹አዎ የእኔ ውድ አንተን ከማግባት በላይ በህይወቴ ተመኝቼ የማውቀው ሌላ ፍላጎት አላስታውስም ››አለችው፡፡ ቤቱ በጭብጨባ ና በፉጨት ተናጋ፡፡ካሜራ ሆነ ሞባይል በመጠቀም ብዙዎች ምስላቸውን በፎቶ ለማስቀረት ተረባረቡ፡፡በዚህ መካከል ኤልሳ በግራና በቀኝ እጇ ሁለት የቢራ ጠርሙሶች ይዛ ተጠጋቻቸው፡፡አመጣጧ በሳባ እይታ ትክክል ስለነበረ ፊት ለፊት እያየቻት ነው፡፡ቀረበቻቸው ባለ በሌለ ኃይሏ ሁለቱንም ጠርምሶች በአንድ ጊዜ ሁለቱም ተጣማሪዎች ግንባር ላይ  ለማሷረፍ  ሰነዘረች፡፡  ሳባ  ዝግጁ  ሆና ስጠብቃት ስለነበረ ቅጽበታዊ በሆነ ፍጥነት ከራሷ ግንባር ላይ ስትመክት ለፋሲል የተሰነዘረው ግን ግንባሩ ላይ ተፈረካከሰ..ሳባ ሁለቱንም ጠርሙሶች መክታ ማስቀረት ትችል ነበር ግን አላደረገችውም፡፡ እንደውም ያላሰበችው መልካም አጋጣሚ ስለተከሰተላት ውስጧ ተፍነክንኳል፡፡ይህ አጋጣሚ እንደሎተሪ እድል ያልታሰበና አቅልን በደስታ የሚያስት ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡እና እድሏን እስከመጨረሻው ልትጠቀምበት ወሰነችና ትኩረቷን ሰበሰበች፡፡
ከደቂቃዎች በፊት ደስታ ውጦት የነበረው ሆቴል በጩኸት እና በድንጋጤ ተተረማመሰ፡፡ወዲያው የአካባቢው ፖሊሶች ተደውሎላቸው ደረሱ፡፡ኤልሳን ወደ እስር ቤት ፋሲልን ወደ ሆስፒታል ወሰዱት፡፡ሳባም ቃሏን ለፖሊስ ሰጥታ የከፋውና የጨለመ በሚመስል ፊት ግን ከውስጥ በሚፍለቀለቅ  የደስታ  ስሜት ወደ ሆስፒታል ሄደች፡፡

ፋሲል በቢራ ጠርሙሱ አምስት ቦታ የተበታተነው ጭንቅላቱ በጥንቃቄ ተሰፍቶ ከተጠጋገነ በኃላ እዛው እንዲተኛ ተደረገ..ሀኪሙ እንኳን ወደቤት ገብቶ እየተመላለሰ ሊታከም ይችላል ብሎ ነበር ፤ሳባ  ግን  እንዲያ  እንዲሆን አልፈለገችም፡፡
የወደፊት ባሏ ሙሉ ጤናው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲመለስ እንደምትፈልግ በመናገር ቢያንስ ለሶስት ቀንም ቢሆን እዛው ሆስፒታል ተኝቶ ሀኪሞች የቅርብ ክትትል እንዲያደርጉለት አጥብቃ በመከራከር አሳመነቻቸው፡፡

አስፈላጊውን ክፍያ ከፍላ ወደ ቤቷ ስትመለስ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡
ሰባት ሰዓት ላይ ስልኳን አነሳችና ወደአንድ የቅርቧ ወደሆነና ቆሻሻ ስራዎችን ወደሚሰራላት ሰው ደወለች፡፡ችግሩ እንደተፈጠረ  ወደሆስፒታል  በምትመጣበት ጊዜ መንገድ ላይ አግኝታው ስለሁኔታው አብራርታለት ነበር፡፡

‹‹ሄሎ››

‹‹የነገርኩህ ሆስፒታል የመኝታ ቁጥር 13 ተኝቷል››

‹‹አዎ… ፋሲል ፀጋዬ ይባላል››

‹‹ሦስት ቀን አለህ..ነገ ብትፈፅመው ግን  ደስ ይለኛል›››

‹‹አዎ… ከተኛበት እንዲነሳና ዳግመኛ ወደቤቴ መጥቶ ፊቴን እንዲያየኝ አልፈልግም፡፡››
‹‹ሁሉ ነገር በሚስጥር እና በጥንቃቄ ይከወን››

‹‹ቻው››ስልኳን ዘጋች  እና  ተረጋጋታ  እንቅልፏን  ተኛች፡፡በሦስተኛው   ቀን ወንድሙ ፋሲል ማረፉን ደውሎ አረዳት፡፡

ኤልሳ ፍቅረኛዋ የነበረውን ፋሲል ፀጋዬን አስባና አቅዳ በመግደሏ በተጨማሪም የሟች እጮኛው ላይም የመግደል ሙከራ በማድረጓ በሁለት ወንጀል ተከሳ

ከወህኒ ቤት ፍርድ ቤት ስትመላለስ ከቆየች በኃላ በስተመጨረሻ በቀረበባት ክስ ሁሉ ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ የ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባት በቋሚነት ወደ ወህኒ ተወረወረች፡፡አይ!! ምስኪኗ ግልፍተኛዋ አፍቃሪ፡፡

ከዛ በኃላ ሳባ ደስታ የሚሰማት አና ስጋቷ ሁሉ ተወግዶ ሰላም የምታገኝ መስሏት ነበር…፡፡ከገባችበት አጉል ግንኙነት በሰላም የተገላገለችና ቀጣይ ህይወቷን ለማስተካከል እረፍት የምታገኝ መስሏት ነበር ግን ተሳስታ  ነበር.ፈፅሞ የፋሲል ምስል ከምናቧ ሊደበዝዝ አልቻለም፡ቀን ስትቆም ስትነሳ በየምክንያቱ ትዝ ከሚላት በተጨማሪ ልትተኛ ብላ አይኗን ስትጨፍን በህልሟ እየመጣ ያሰቃያት ጀመረ..ስራዋን ተረጋግታመስራት አልቻለችም.፡፡መጀመሪያውኑ ስልችት ብሏት የነበረውን ስራዋን ይበልጥ አንገሸገሻት..ያ ጳውሎስ የተባለው ደራሲ በፍጥነት ስራውን ጨርሶ መፅሀፉን አሳትማ ሁሉን ነገር ድብልቅለልቅ አድርጋ ራሷን ነፃ እስክታወጣ ድረስ ቸኮለች፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍6215
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


..ከአንዱ ለምኖ ለአንዱ በመስጠት ብልጽግናን ማምጣት አይቻለም::

ለታዲዬስ ፣ትንግርት፣ሁሴን፣ዶ/ር ሶፊያ፣ፎዚያ እና ኤልያስ ዛሬ ልዩ ቀን ነች፡፡ለስድስት ወር የለፉበትን ...እንቅልፍ አጥተው ገንዘባቸውንም ዕውቀታቸውንም ያፈሰሱበት የድርጅታቸው የመጀመሪያ ፍሬ እነሱም የሚያዩበት ለማህበረሰቡም የሚያስተዋውቁበት ቀን ነው፡፡

ዝግጅቱ በሸራተን አዲስ የሚካሄድ ሲሆን የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ፣የተለያዩ ሀይማኖት አባቶች፣የኤንባሲ ሰዎች፣ታዋቂ ሙዚቀኞች፣የፊልም አክተሮች፣አትሌቶች፣ነጋዴዎች፣
ለዚህ ድርጅት ከምስረታው እሰከአሁን ከፍተኛ እገዛ ካደረጉት ከየተለያዩ የፌስ ቡክ ግሩፖች የተወከሉ ወጣቶች፣ከተለያዩ ሚዲያዎች የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች እና ካሜራ ማኖች..አዳራሹን
ሞልተውታል፡፡

የዛሬው ዝግጅት ዓለማ በዋናነት ሁለት ሲሆን ሌላም አንድ ንዑስ ዝግጅት አለ፡፡መድረኩን የሚመራው ጋዜጠኛ ሁሴን ነው..ማይኩን ይዞ ወደ መድረክ ወጣና ጉሮሮውን ሞርዶ ንግግሩን
ጀመረ::

‹‹ክቡራን እና ክብሯት ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እዚህ የተገኛችሁ ሁላችሁም እንዲሁም በየቤታችሁ ሆናችሁ ዝግጅቱን በቀጥታ በቴሌቨዥን ስርጭት እየተከታተላችሁ ያላችሁ በአጠቃላይ በድርጅታችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን እስከፍፃሜውም በፅሞና እንድትከታተሉን እየጠየቅን በቀጥታ ወደ ዝግጅቱ እንገባለን፡፡በቅድሚያ የድርጅታችን መሪ የሆኑት ዶ/ር ሶፍያ ፕሮግራሙን በንግግር እንዲከፍቱልን እንጠይቃለን… ዶ/ርን ወደ መድረክ ሸኙልን፡፡››ዶ/ር ሶፊያ በጭብጨባ ታጅባ ወደ መድረክ ወጣችና ማይኩን ከሁሴን ተቀብላ ንግግሯን ማሰማት ቀጠለች፡፡

‹‹ክቡራን እና ክቡራት የመንግስት ባለስልጣናት፣የሀይማኖት አባቶች፣ከተለያዩ የማህበራት ዘርፎችን በመወከል
የተገኛችሁ፣በየቤታችሁም በመሆን እየተከታተላችሁን ያላችሁ በአጠቃላይ..እንኳን ለዚህች ቀን አደረሰን አላለሁ፡፡

የዛሬው ፕሮግራማችን ሁለት ዓላማዎች አሉት፡፡ አንደኛው የወላጆች እና ልጆች የምረቃ በዓል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለድርጅታችን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ነው..እኔ አሁን አትኩሬ የተወሰነ ማብራሪያ ልሰጣችሁ የምፈልገው በመጀመሪያው ላይ ነው..ሁለተኛውን በተመለከተ አቶ ታዲዬስ ቆየት ብሎ ያብራራላችኋል፡፡

እንግዲህ እንደመነሻ ይሆነን ዘንድ የዛሬ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን አካባቢ በበጎ ፍቃደኝነት አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናትን እናሳድጋለን ብለው ከተመዘገቡ በብዙ ሺዋች ከሚቆጠሩ ባለቀና ልቦች መካከል ለጊዜው አቅማችንን መሰረት አድርገን 15ዐ ግለሰቦችንና በቡድን ከመጡት መካከል ደግሞ 5ዐ ዎቹን ወደ ስልጠና አስገብተን ነበር፡፡እንግዲህ በአንድ ወር ስልጠና ውስጥ በድርጅቱ ህግና የስልጠና ማኑዋል የተሰጣቸውን ስልጠና በመከታተል ከ15ዐ ዎቹ ግለሰቦች መካከል 43 በቡድን ሆነው ከመጡት መካከል ደግሞ 31 መስፈርቱን ማሟላት ስላልቻሉ ከይቅርታ ጋር እንደ ፍላጎታቸው ህፃናትን እንዲያሳድጉ ልንፈቅድላቸው አልቻልንም፡፡የተቀሩት እንግዲህ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው እንሆ ዛሬ በእናንተ ፊት መርቀን ልጆቻቸውን በአደራ እናስረክባቸዋለን፡፡››

የደመቀ ጭብጨባ ከአዳራሹ...ቀጠለች ዶ/ር ‹‹ዛሬ አሁን ለነገርኳችሁ ወላጆች የምናስረክባቸውን ልጆችም ለ3 ወር በካምፕ በማስገባት ስልጠና ሰጥተናቸዋል፡፡ልዩነቱ ህፃናቱን አንዴ ወደ ማሰልጠኛ ካስገባናቸው:: የምንፈልገውን ብቃት እስክናገኝባቸው ድረስ የፈጀውን ያህል ይፍጅ እንለፋባቸዋለን፡፡ ልጆቹን ከበሸቀጠ የድህነት መንደር እንዲሁም በስነ- ምግባር እና በሞራል ከዘቀጠ ጎዳና ላይ ነው የምንሰበስባቸው፤አመላቸውን ማረቅ፣ ስነ- ልቦናቸውን መገንባት፣ጤንነታቸውን ማስተካከል፣ ተስጥኦቸውን ለይቶ ማወቅ፤ወዘተ እንደሀሳባችን እስክናሳካ 3 ወር ፈጀብንም ሶስት
አመት ተስፋ አንቆርጥባቸውም፡፡ የራሱ ጉዳይም ብለንም እርግጠኛ ባልሆንበት ሁኔታ ለአሳዳጊ ወላጅ አሳልፈን አንሰጣቸውም፡፡ይህ ነው ልዩ የሚያደርገን.. እንጂማ መአት በህፃናት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች እንዳሉ እናውቃለን...፡፡.››

ወላጅ ለመሆን ስልጠናውን ወስደው መስፈርቱን አላሟላችሁም ብለን ከመለስናቸው ውስጥ የተወሰኑት በጣም ተበሳጭተውብን ነበር፤ላሳድግ ባልኩ መልካም ልስራ ባልኩ እንዴት እከለከላለሁ?የሚል መከራከሪያ ሀሳብ
ነበራቸው፡፡ግን እኛም ያንን ስናደርግ እያዘንን ነው... እየገነባን ያለነው የወደፊቱን ትውልድ
ነው፡፡አንድ ሰው ገንዘብና ፍላጎት ስላለው ብቻ ዝግጁ የሆነ ስነልቦና እንዲሁም የወላጅ ባህሪ
ሳይኖረው ልጅን ያህል ነገር አሳድግ ብለን አንስተን አንሰጠውም..በፍፁም እንደዛ
አናደርግም፡፡በእኛ መአከል ሰልጥነው ልጅ የተረከቡ ሰዎች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት
ከዚህ ከእኛ ጋር ለወሰዷቸው ልጆችም ብቻ ሳይሆን ከአብራካቸው ለወጡትም
ህፃናት፣ለዘመዶቻቸው ልጆች ፣ለጎረቤቶቻቸው ልጆችም ያገኙትን ዕውቀት እንዲጠቀሙበት
እንፈልጋለን፡፡አርአያ እንዲሆኑበት እንፈልጋለን፡፡ ለዛ ነው ማኑዋሉንም አዘጋጅትን ለእያንዳንዱ ያደልነው፡፡

‹‹ልጅ ማሳደግ ማብላትና ማጠጣት ብቻ ሳይሆን..የወደፊት የህይወት ዓላማቸውን፤ ተሰጥኦዋቸውን ከስር ከመሰረቱ እያጎለበቱ መንገድ ማስያዝን ይጠይቃል፡፡ ይሄንን ነው ጠቅላላ የሀገራችን ወላጆች ሊከተሉት የሚገባው መንገድ፡፡ ህብረተሰቡም እንደህብረተሰብ...መንግስትም እንደመንግስት የየራሳቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እጠይቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ አሁን ቀጥታ ወደ ምረቃ በዓሉ እንሄዳለን፤ ክብር የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ ለተመራቂ ወላጅ እና ህፃናት የምስክር ወረቀት ይሰጡልን ዘንድ እንጠይቃለን፡፡››

ሚንስቴሩ በሙሉ ሱፍ ሽክ ብለው በከረባት እንደታነቁ በተጀነነ እርምጃ ወደ መድረክ ወጥተው ከዶ/ር ጎን ቆሙ ፡፡ሁሴን የተመራቂዎቹን ስም ተራ በተራ ሲጠራ ወላጆቹ ከተረከቧቸው ህጻናት ጋር በመምጣት የምስክር
ወረቃታቸውን እየወሰዱ ወደ መቀመጫቸው ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ ተመራቂዎች ውስጥ..ሰሎሞንና የውብዳር አንድ ወንድ ልጅ(እነሱ የጠየቁት ሁለት ቢሆንም በታዲዬስ የሚመራው ቴክኒክ ብድን ግን በዚህ በአንዱ ልጅ ላይ የሚያሳዩት አፈፃፀም ታይቶ ከአመት በኃላ ሌላ ልጅ ሊጨመርላቸው ይችላል እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ከአንድ ልጅ በላይ አይፈቀድላችሁም በማለት ከለከሏቸው) ሌላው..ዶር ሶፊያና ከፕ/ዬሴፍ ጋር አንድ ሴት ልጅ፣ፎዚያ እና ኤልያስ አንድ ሴት ልጅ፣ፅዮን እና ዓላዛር ..ትንግርት እና ሁሴን አንድ ልጅ በመረከብ ከራሳቸው በመጀመር አርዓያነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የምስክር ወረቀት የመስጠት ፕሮግራም ሲጠናቀቅ የክብር እንግዳውንና ዶ/ር ሶፊያ መድረኩን ለቀው ወደ መቀመጫቸው ሄዱ.... ሁሴን ቀጣዩን ፕሮግራም ማስተዋወቅ ጀመረ…፡፡

‹‹ክብሯን እንግዶች ወደ ቀጣዩ ፕሮግራማችን ከመሸጋገራችን በፊት የሙዚቃ እረፍት

እናደርጋለን..ድምፃዊ ሀሊማ እና ሄለን ወደ መድረክ፡፡››

በአካልም በየቤቱም እየተከታተሉ ያሉ አይኖቻቸውን ወደ መድረኩ ላኩ፡፡

የተባሉት ሙዚቀኞች ወደ መድረክ ሲመጡ ታዩ …ሀሊማ ጊታሯን ይዛ ወንበር ስባ ተቀመጠችና ማይኩን ወደ አፏ አስተካክላ አመቻቸች፡፡ሄለን ወደ ፒያኖው አመራች፡፡አብዛኛው ህዝብ አስታወሳቸው፡፡ ባለፈውም በቴሌቨዥን ቃለ መጠየቅ የተደረገላቸው ጊዜ ብቃታቸውን አሳይተዋል፤በአይድል ውድድርም እንደዛው…፡፡ ጀመሩ ሄለን ፒያኖውን ስታናግረው ሀሊማ ጊታሯን እየተጫወተች በድምጿም ታንቆረቁር ጀመር..
👍6413
የብዙነሽ በቀለን <<የእናት ውለታዋን›› ነው የዘፈነችው...ሙዚቃው ሲጠናቀቅ በአዳራሹ የሞላው ህዝብ በጭብጨባና በፉጨት ሸኛቸው፡፡

ሁሴን ሁለተኛው ዝግጅት እንዲቀጥል ወደ ታዲዬስ አስተላለፈ፡፡

ታዲዩስ መድረኩን ተረከበ‹‹እኔ ስለ ሁለተኛው ዝግጅት ጥቂት ነገር ለማለት ነው ..ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት…..ይሄን ለማድረግ ፈልገን ሳይሆን ተገደን ነው..ከአንዱ ለምኖ ለአንዱ በመስጠት ብልጽግናን ማምጣት አይቻለም፡፡ እቅዳችን ድርጅታችን እራሱን በራሱ እያስተዳደረ ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ነው፡፡ለዚህም ይረዳን ዘንድ መንግስትን ከከተማ በራቀ ቦታ 10-20 ሺ ካሬ ሜትር መሬት እንዲሰጠን ፕሮፖዛለችንን አስገብተናል.. እስከ አሁን አሉታዊም ሆነ አውንታዊ መልስ አልተሰጠንም፡፡

ከተሳካልን ግን በዛ መሬት መንደራችንን እንመሰርታለን፤እርሻ እናርስበታለን፤የተለያ የእንጨት ስራ ፣የብረት ስራ ፣የቅርፀ ቅርፅ ስራ፣የጥበብ ስራ፣የፈጠራ ስራ እንሰራበታለን፡፡ የተለያ የስልጠና ማዕከሎችን እንገነባበታለን..በዛን ጊዜ እኛ የምንፈልገው እኛን ለመርዳት የፈለገ አንድ ግንበኛ በአንድ አመት ውስጥ ለ4 ቀንም ቢሆን መንደራችን ድረስ መጥቶ የሚገነባ ነገር በመገንባት በዕውቀቱን እንዲያገለግለን ...የህክምና
ዶክተሩም የሚታከም ነገር ካለ መጥቶ በማከም እንዲያግዘን…ሰዓሊውም በዓመት ለ3 ቀንም ቢሆን ወደ መንደራችን መጥቶ ቢያንስ የስዕል ችሎታ ኖሯቸው ለሚፍጨረጨሩ ህፃናት ትንሽ ዕውቀት አስጨብጠጧቸው ከልምዱ አካፍሏቸው ለእራሱም የመንፈስ እርካታ አግኝቶ እንዲመለሰ ነው የምንፈልገው፤ እዚህ አገር ባለን ችሎታና እውቀት በነጻ በጎ ነገር የምናደርግበት ሁኔታዎች ናቸው መመቻቸት ያለባቸው...እሱ ነው ሰጪውንም ተቀባዩንም የሚጠቅመው.. ሽርፍራፊ ገንዘብ ለተቸገረው መስጠቱን ሁለችንም ካንጀትም ሆነ ከአንገት እናደርገዋለን… ለውጥ ግን አላመጣልንም..፡፡ እኛ መንግስትንም ሆነ ህዝቡን የምናስቸግረዉ ይሄንን ህልማችን የሆነውን የሰላምና የብልፅግና መንደራችንን እስክንገነባ ድረስ እንዲያግዘን ብቻ ነው...ከዛ በኃላ እንዳልኳችሁ ነው…፡፡

መንግስትም የጠየቅነውን መሬት በአፋጣኝ ይሰጠን ዘንድ በዚህ አጋጣሚም ደግሜ ጠይቃለሁ፡፡ትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባ በሚካሄድበት ጊዜና አንድ የትልቅ የሀገር መሪ በሚመጣበት ወቅት በድህነት በጎዳና የሚርመሰመሱትን ህፃናት ከከተማው ዞር
ለማድረግ ከመጨነቅና ከመሳቀቅ ይልቅ አሁን እኛን በማገዝ መሰረታዊ በሆነ መንገድ ዘላቂ መፍትሄ ብናበጅበት ለመንግስትም ለማህበረሰቡም ይጠቅመዋል እላለሁ፡፡

ስለዚህ ሁላቹሁም በግለሰብ ደረጃም ቢሆን

በድርጅት ደረጃ ታግዙናላችሁ ብለን ስላሰብን ነው ፊታችሁ በእምነት የቀረብነው፡፡አላማችንን
ቀለል አድርጋችሁ እንዳታዩት፡፡ ወላጅ የሌላቸውን ህፃናት አሳዳጊ ወላጅ እንዲያገኙ ብቻ አይደለም ውጥናችን…የይስሙላ ወላጆች
ሁሉ ከአብራካቸው ለተፈለፈሉ የገዛ ልጇቻቸው እውነተኛ ወላጅ እንዲሆኑ ማብቃት ነው፡፡
በምንመሰርተው መንደር ውስጥ በምናቋቁመው ማሰልጠኛ ማዕከል በመንግስት ስርዓተ ትምህርት መካተት ሲገባቸው ያልተካተቱትን ግን ደግሞ ለህብረተሰቡ አስፈላጊ የሆኑትን ስልጠናዎችም እንዲሰጡ ማድረግ ነው ዓላማችን፡፡

ልጆች እንደተወለዱ ከህፃንነታቸው ጀምሮ ሚበሉትንና ሚጠጡትን ብሎም ሚለብሱትን ነገር ብቻ ሳይሆን ስለሚያስቡት፣ ስለሚፈልጉት እና ስለሚጠሉት ነገር እየተከታተልን ማገዝ
መቻል አለብን፤ወጣቶቻችን እኛ የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን እነሱ የሚፈልጉትን ትምህርትም
እንዲማሩ እገዛ በማድረግ ኃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል...ለአቅመ አዳም እና ሄዋን የደረሱ ጥንዶች ወደ ጋብቻ ከመግባታቸው
በፊት የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው ስልጠና
የሚያገኙበት ዕድል መፍጠር አለብን፤በፍቅር ህይወት እና በጋብቻ ህይወት መካከል ስላለው
ልዩነት ግንዛቤ እንዲጨብጡ፣ ስለልጆች አስተዳደግ፣ስለቤት አስተዳደር እንዲያውቁ ቀድሞ ስልጠና መሰጠት አለበት ፤ የእኛ ተቋም በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ሽንቁሮች
ሁሉ ለመድፈን የሚጥር ይሆናል….ዋና አላማችን ግን ህፃናቶቹ ናቸው፡፡ስለጋብቻ
የምናሰለጥነው፣ስለቤተሰብ
ምንሰብከው፣ስለልጆች አስተዳድግ የምንደሰኩረው፤ወደ ጎዳና ወጥቶም ሆነ የስም
ወላጆቹ ጋር እየኖረ የህይወት ውሉ የጠፋበት ብኩን ትውልድ ሆኖ የሚያድግ ልጅ እንዳይኖር
ነው፡፡
የቁሳቁስ ዕድገቱንና የቴክኖሎጂ ምጥቀቱን መንግስት እንደ መንግስት ለራሱ ህልውና ሲል ይሰራልናል...እኛ ግን ችላ የተባለውን ግን በህይወት ውስጥ ወሳኝ ስለሆነው መንፈሳዊ ግንባታ ላይ እንደዜጋ መስራት አለብን፡፡ ስለእውነት፣ስለፍቅር፣ስለበጎነት፣ስለሰባአዊነት፣የሚያስተምሩ ተቋሞች መገንባት ያስፈልገናል፡፡ የዛን ጊዜ ነው አንዳችን ለአንዳችን
መኖር የምንጀምረው፡፡

ስግብግብነትን፣ጭካኔ፣ሙስናን እና አድራባይነትን ከውስጣችን አውጥተን በቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም የበለፀገ ደስተኛ ህብረተሰብ መገንባት የምንችለው፡፡ ስለዚህ አብረን እንጣር፡፡ አግዙንና ሀሳባችንን ከግብ እናድርስ እላለሁ፡፡ጊዜችሁንና ቀልባችሁን ሰጥታችሁኝ ስላዳመጣችሁን አመሰግናለሁ፡፡››

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍719🥰1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለሀለቃዋ ትብለጥ ፍቅረኛዋ መሞቱ ድብርት ውስጥ እንደከታት  ተናግራ  የአንድ  ወር ፍቃድ ወሰደች፡፡እረፍቷን ጨርሳ ተመልሳ ከመግባቷ በፊት መጽሀፉም አልቆ እስከወዲያኛው ይገላግላት ይሆናል፡፡አዎ ተስፋዋ ያ ነው፡፡
ሳባ እረፍት ከወሰደች በኋላ ቤት መዋል ጀመረች፡፡ራሷን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስም ኃይለኛ መደበትና ጭንቀት ውስጥ ገባች፡፡እርግጥ ይሄ
የመደበት ችግር አሁን ፍቅረኛዋ ስለሞተ ወይም እሷ ራሷ ስላስገደለችው ድንገት የተከሰተባት በሽታ አይደለም…ከእሷ ጋር ሶስት አራት አመት በደባልነት ኖሯል…ቢያንስ በስድስት ወር አንዴ የሆነ ምክንያት  ፈልጎ ይቀሰቀስባታል፡፡
ይተወኛል ብላ ለ15 ቀን ከቤቷ ሳትወጣ እረፍት ለማድረግ ብትሞክርም ነገሮች ግን እየባሱባት መጡ..በዚህም ምክንያት የስነ-ልቦና ባለሞያ እንድታናግር አንድ  ወዳጇ  ጨቀጨቃትና  በሀሳቡ  ተሰማምታ  የጠቆማት ሆስፒታል ሄደች፡፡
በተቻላት መጠን ጥሩ አለባበስ ለብሳ ፤ከወትሮዋ በተሻለ ነቃ ለማለት፤ የተቻላትን ጥረት አድርጋ በጠዋት ተነስታ መኪናዋን አስነስታ በተሰጣት አድራሻ ሄደች፡፡ቀድማ ደውላ ቀጠሮ አስይዛ ስለነበረ.እንደሄደች ነበር ነርሷ የተወሰኑ ፎርሞችን እንድትሞላ በማድረግ ወደ ዶክተሩ እንድትገባ ያደረገቻት፡፡

ብዙ ጊዜ ለህክምና ወደተለያዩ የከተማዋ ስመጥር ሆስፒታሎች ሄዳ አገልግሎት አግኝታ ታውቃለች…አሁንም የገባችበት የዶክተሩ ምርመራ ክፍል ከዚህ በፊት ከምታውቃቸውና ከጎበኘቻቸው ብዙም የተለየ አይደለም…ግን በራፉን ከፍታ ወደውስጥ እንደገባች ፈዛለች፡፡ለውስጧ ጥልቅ ድረስ እስኪሰማት   ድረስ ደንዝዛለች፡፡

‹‹ጤና ይስጥልኝ አረፍ በይ›› ሲላት ሁሉ አልሰማችውም.አይኗን አይኖቹ ላይ ተክላ በቆመችበት ቅዝዝ ብላ እየተመለከተችው ነው፡፡

እጁ ላይ ያለውን የእሷን ካርድ እየተመለከተ ‹‹ወይዘሪት ሳባ….አረፍ በይ››ሲላት እንደምንም ከመደንዘዝ ለመንቃት እየሞከረች እግሯን የመጎተት ያህል አንቀሳቀሰችና እንድትቀመጥ በተነገራት ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹እሺ ሳባ ዶ/ር ጀማል እባላለሁ.››ሲል ራሱን አስተዋወቃት፡፡

ዝም አለችው

‹‹እስኪ ስለራስሽ ጥቂት ንገሪኝ›› አላት፡፡

‹‹ግራ ገባት..ሀኪም ቤት ለስነ-ልቦና ህክምና የመጣች ሳይሆን የሆነ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላ የሆነ አማላይ ወንድ  ወንበሯን ተጋርቶ ሊጀነጅናት ሙከራ እያደረገ እሷ ደግሞ እየተግደረደረችና እየተሸኮረመመች ያለች ነው የመሰላት፡፡

‹‹ስለእኔ ምን?››

‹‹ስለ ማንኛውም ነገር….ሳባ ማን ነች?ምንድነው የምትወደው? ምንድነው የምትሰራው? ፡፡››

‹‹ስራዬ የሆነ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ ነው ምሰራው…ተቀጥሬ   እንኳን ማለት ይከብዳል…በኮሚሽን ነው የምሰራው፡፡የምኖረው ብቻዬን   ነው…ማለት አንድ ዘበኛ እና ተመላላሽ የቤት ሰራተኛ አለኝ... ጥሩ ኑሮ እኖራለው፡፡ግን ደግሞ ብቸኛ እና ደስታ የራቀኝ ሰው ነኝ..ሁሉ ነገር እየሰለቸኝ ነው…ለምን እንደምኖር እራሱ ግራ እየጋባኝ ነው፡፡››ሁሉን ነገር ተወችና ቀጥታ ወደ መደምደሚያው በመሻገር አሁን ሰላለችበት ሁኔታ ወደማብራራቱ ተስፈነጠረች፡፡

‹‹ጥሩ…. እንዲህ አይነት ስሜት ይሰማሽ የጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው?››

‹‹ሶስት አራት አመት..ግን የከፋ የሆነው ከሀያ ቀን በፊት ጀምሮ ነው፡፡፡››

‹‹በቅርብ በህይወትሽ የተከሰተ ጠንከር ያለ ነገር ነበር?››

‹‹አዎ ለአንድ አመት ፍቅረኛዬ የነበረ  ሰው  ቀለበት  እያሰረልኝ  ሳለ  እኔ የማላውቃት ልጅ ፍቅረኛው ሆና በጠርሙስ ጭንቅላቱን ከፈለችውና ሞተ…ከዛ ወዲህ ይመስለኛል ነገሮች እየባሱ የሄዱት፡፡››የታሪኩን ግማሽ እውነት ነገረችው፡፡

‹‹ገባኝ….ግን የትኛው ነው በጣም ያመመሽ…?››ሲል ጠየቃት

‹‹ከምንና ከምኑ?››

‹‹ከፍቅረኛሽ ሞትና….ከመከዳትሽ?››
ደነገጠች…እንዲህ ፈፅሞ አስባ አታውቅም..‹‹መከዳት…ስለፍቅረኛው ማለትህ ነው?››

‹‹አዎ››

ዝም አለች..ምን እንደምትመልስ ግራ ገባት፡፡ሳባ ልክ እንደጓደኛሽ ቁጠሪኝ ….ነፃ ሁኚ፡፡

‹‹አይ ፋሲልን .ማለቴ ፍቅረኛዬን በተመለከተ የሚሰማኝ ስሜት ግራ የተጋባ ነው…ሞቱ ይሄን ያህል ይረብሸኛል ብዬ ፈፅሞ አስቤ አላውቅም  ነበር….የእኔና የእሱ ግንኙነት በተወሰኑ የጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ ነበር…ፍቅረኛውን በተመለከተ ምንም የሚሰማኝ ነገር የለም..በእርግጥ እስከመጨረሻው ቀን ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም..ባውቅም በእኔ ላይ ማግጦብኛል ብዬ የምበሳጭበት ምክንያት አይታየኝም...እኔም ታምኜለት አላውቅም እሱም ይታመንልኛል የሚል እምነት አልነበረኝም..እውነቱን ለመናገር እንዲታመንልኝም ፍላጎቱ አልነበረኝም.. በአጠቃላይ ስለፍቅረኛው ማወቄ ምንም ትርጉም የሰጠኝ አይመስለኝም፡፡››

‹‹ምን አልባት ትዳሩን ትፈልጊው ነበር…?በእሱ ሞት ምክንያት በመበላሸቱ ተበሳጭተሻል?››

‹‹በተአምር እንደዛ አይነት ፍላጎት አልነበረኝም...ቀለበቱን ሲያደርግልኝ ድንገት ሳያማክረኝ ነበር ያደረገው...ማማከር ሳይሆን ስለወደፊታችን አውርተን እንኳን አናውቅም...እንዳገባው ሲጠይቀኝ በጣም ብዙ በሚያውቁት ሰዎች ፊት ስለሆነ እሱን ላለማሸማቀቅ እና ግርግር ላለመፍጠር ነበር  ጣቴን  የዘረጋሁለት..እና መቼም ላገባው እቅድ አልነበረኝም፡፡ግን የገረመኝ በመሞቱ በውስጤ ቅሬታ ተፈጥሯል …ፈፅሞ ልረሳው አልቻልኩም…ከእሱ የማጣው  አንድ  ብቸኛ  ነገር ወሲብ ነው….ያንን ደግሞ ካሰብኩበት ከሌላ ሰው በቀላሉ ማግኘት እችላለሁ…ያው የእሱን ያህል ሊሆን ባይችልም ማለቴ ነው..እና ለምን ከአዕምሮዬ ላወጣው እንዳልቻልኩ አልገባኝም፡››

‹‹ግን እሱ ብቻ ነው የሚያስጨንቅሽ? ማለቴ እሱ በህይወት እያለስ ሌላ ምቾት የሚነሳሽ ጉዳይ ነበር?››

‹‹እየተጠነቀቀች እራሷን ከመጠን በላይ ላለማጋለጥ እየጣረች ከሁለት ሰዓት በላይ ከዶ/ሩ ጋር አወራች….በጊዜያዊነት የሚያረጋጓትን ሁለት መድሀኒቶችን መውሰድ ከሚገባት የተወሰነ ምክር ጋር ለግሷት ለሳምንት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷት አሰናበታት….

በመምጣቷ ተደስታለች …በዶ/ሩ መስተንግዶ ተደስታለች..ልቧ ለምን እንደደነገጠባት አልገባትም…ያምራል…ከአይኖቹ የሚረጫቸው ብርሀን የሰውን ልብ በቀላሉ ይሰረስራሉ፡፡ንግግሩ እርጋታ የተለባሰና እንዲያወሩ የሚያበረታታ ነው፡፡ በዛ የተነሳ በቆይታዋ ተደስታለችም…የተወሰነ ቀለል የማለት ስሜትም እየተሰማት ነው..ትንሽ ቅር ያላት ቀጠሮ ከሳምንት በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን በኋላ መልሳ ብታገኘው ደስ ይላት ነበር.ደግነቱ ችግር ካለና የተለየ ስሜት ከተሰማት እንድትደውልለት ነግሯት ቁጥሩን ሰጥቷታል፡፡መኪናዋን ራሷ እያሽረከረች ቀጥታ ወደቤቷ ሄደች..አዲሱ ዘበኛዋ በራፉን ከፈተና ወደ ውስጥ አስገባት..፡፡ይሄንን ዘበኛ ከቀጠረች አስር ቀን ቢሆነው ነው፡፡የመጀመሪያውን ዘበኛ ያሰናበተችው የመጀመሪየውን ዘበኛ ከእሷ ጋር አስተዋውቋት ያስቀጠረው ፋሲል ስለነበረ ነው፡፡ከእሱ ጋር የሚያገናኛት ምንም አይነት ትዝታ አትፈልግም፡፡ደግሞ ምን አይነት ሚስጥራዊ ግንኙነት እንዳላቸው ስለማታውቅና በዛም ጥርጣሬ ስለነበራት ያልሰራበትን የሶስት ወር ደሞዙን ሰጥታ አሰናበተችው፡፡

ከዛም እንደተለመደው መኝታ ቤቷ ገባችና ራሷን ሸሸገች..


💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8915🤔3👏1
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ለሀለቃዋ ትብለጥ ፍቅረኛዋ መሞቱ ድብርት ውስጥ እንደከታት  ተናግራ  የአንድ  ወር ፍቃድ ወሰደች፡፡እረፍቷን ጨርሳ ተመልሳ ከመግባቷ በፊት መጽሀፉም አልቆ እስከወዲያኛው ይገላግላት ይሆናል፡፡አዎ ተስፋዋ ያ ነው፡፡ ሳባ እረፍት ከወሰደች በኋላ ቤት መዋል ጀመረች፡፡ራሷን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስም ኃይለኛ መደበትና ጭንቀት ውስጥ…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ

እንደምንም ራሷን ተቆጣጥራ ያዘዛትን መድሀኒት በስርዓቱ ተጠቅማ በቀጠራት ቀን ከሳምንት በኋላ በሰዓቱ ሄደች።እንደደረሰች  በሞቀ  ፈገግታና  ጠበቅ  ባለ ሠላምታ  ተቀበላትና።

"ቁርስ በልተሻል?›› ሲል ጠየቃት፤ግራገባት፡፡ አሰበች   ቁርስ   አልበላችም
..ጭርሱኑም ትዝ አላላት።ሳትመልስለት  የለበሰውን  ነጭ  ጋዎን  አውልቆ መስቀያው ላይ እያንጠለጠለ

"ጥሩ እኔም አልበላሁም...ወጣ ብለን እንብላ"አላትና ወደ መውጫው መራመድ ሲጀምር ቀድማው ከክፍሉ ወጣች፡፡ቆለፈውና ጎን ለጎን እየተራመዱ መኪናውን ወዳቆመበት ቦታ እየመራ ወሰዳት ፡፡ጋቢናውን ከፈተና ካስገባት  በኋላ  እሱ  ዞሮ ገባና አንቀሳቀሰው… ሆስፒታሉን ለቀው ወጡና አስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ የመናፈሻ ድባብ ያለው አሪፍ ሆቴል ይዟት ገባ።ቁርስ እዛው በሉ…ማኪያቶ እየጠጡ ወሬ ጀመሩ።

"ሳምንቱ ጥሩ አለፈ አይደል?"

  "ምንም አይል?"

"እንዴት ምንም አይል... አመመሽ እንዴ ...ደውይልኝ ብዬሽ ነበር?››
"አይ ያን ያህል አላመመኝም..ግን ያው ወጣ ገባ ነበር"
"ያው እንዲህ አይነት ህመም በፍጥነት የሚወገድ አይደለም..  የረጅም  ጊዜ ክትትልና ትዕግስት ይጠይቃል።በተለይ ያንቺ ጥረት ወሳኝነት አለው፡፡

  ምክንያቱም ከበሽታው እንድታገግሚ ለማድረግ የሚያግዙሽ ነገሮች ምን ምን እደሆኑ በዝርዝር ብታውቂያቸውም በሽታው ግን በራሱ ከአንቺ በተቃርኖ ስለሚቆም ተግባራዊ ማድረጉ ፈተና ነው››

‹‹አልገባኝም››

‹‹በቀላሉ ላስረዳሽ… ለምሳሌ ጨጓራ በሽታ ያለበት ሰውን መድሀኒት ትሰጪውና ከዚህና ከዚያ አይነት ምግቦች ተጠበቅ ብለሽ ምክር ብትሰጪው  ትዛዙን ለመተግበር የምግብ አምሮቱን መገደብ ብቻ ነው የሚጠበቅበት፤ ስለዚህ በቀላሉ ይከውነዋል፡፡ እንደአንቺ አይነት ችግር ያለበት  ሰው  ግን  ለምሳሌ  ጠዋት እንደተነሳሸ አልጋሽን አንጥፊ ብትባይ እሺ አነጥፋለሁ ልትይኝ ትችያለሽ፡፡ግን በተጫጫነሽ ቀን እንኳን ተነስቶ አልጋ ማንጠፍ ይቅርና ..አንሶላውንም ከፊትሽ ላይ ማንሳት ላትችይ ትችያለሽ. .ምክንያቱም ነገሮችን እንድትከውኚ የሚያዘው አእምሮሽ ነው…ችግር የተፈጠረው ዋና  ማዘዣ  ጣቢያው  ላይ  በመሆኑ  ነገሮች ሁሉ ቀላል አይሆኑም ፡፡እርግጥ በጣም ጥሩ ነገር አሁን ባለው ሁኔታ አንቺ አስቸጋሪው ደረጃ ላይ አልደረስሽም…እንደምንም ተረባርበን ወደኋላ መመለስና ሁሉን ነገር ማስተካከል አለብን፣አሁን ካለሽበት አንድ ስቴፕ ወደፊት ከሄደ ግን ከባድ ነው የሚሆንብን….ለዚህ ነው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገሽ በከፍተኛ ትእግስት ጤናሽ ላይ ብቻ ማተኮር እንዳለብሽ ከማስጠንቂያ ጋር የምነግርሽ፡፡

"እኔ ደግሞ ትዕግስት ነው የሌለኝ....በቃ ምን ለማግኘት ነው ይሄንን ሁሉ ስቃይ ታግሼ ለመኖር የምጥረው? የሚለው መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነው።›

‹‹ግድ የለም፤ መጀመሪያ ካለሽበት የተጨናነቀ ህይወት ራስሽን አላቂና ዘና ባለ መንፈስ ከዛ በኋላ የምትፈልጊውን ሞት ትሞቺያለሽ››

‹‹አይ ዶክተር እየቀለድክብኝ  ነው አይደል?››

‹‹አይ እየቀለድኩ አይደለም..ለመሆኑ ስራ እረፍት ላይ ነሽ አይደል?"

"አዎ  እረፍት ወስጄያለሁ ..››

‹‹...ምን ያህል?"

‹‹አንድ ወር...ግን ከዛም በኋላ የምመለስ አይመስለኝም  ።››

‹‹ሳባ ...ኑሮ አያሳስብሽም አይደል..?.ማለቴ ፋይናንሺያል?"

"ለመጪው መቶ አመት በዚህ ምድር ላይ ብንኖር  ገንዘብ የሚቸግረኝ አይመስለኝም።››

"ጥሩ አሁን ወደሆስፒታል እንመለስና በቀደም ካቆምንበት እንቀጥል፤››  አላትና ተያይዘው ወደሆስፒታል ሄዱ።ለአንድ ሰዓት ያህል ካወሩ በኋላ ተጨማሪ አንድ ኪኒን አዘዘላትና ሳምንት በተመሳሳይ ቀን እንዲገናኙ ቀጠሮ በመስጠት አሰናበታት።ስትመጣ ከነበረችበት የበለጠ ተደብራ ነበር የተመለሠችው።ይሄ ሳምንት እየጠበቁ እሱ ጋር መመላለስ ብዙም ምቾት እየሠጣት አይደለም። መኪናዋን እየነዳች ወደቤቷ እየተጓዘች ሳለ ስልኳ ጠራ ...አሁን የያዘችውን ቁጥር በጣም ጥቂት የራሴ የምትላቸው ሰዎች ናቸው የሚያውቁት።ከነዛ ውስጥ ማን እንደደወለላት ለማወቅ በመጓጓት በአንድ እጇ መሪውን እንደያዘች በሌላ እጇ  ወደኪሷ  ገባችና  ስልኩን  አወጣች  የደዋዩን  ማንነት  ስታይ   ደነገጠች

...መኪናውን ወደዳር አቆመችና አነሳችው ።

"ሄሎ ራጂ"የ12 አመትና የ5ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ብቸኛና ተወዳጅ ታናሽ ወንድሟ ነው የደወለላት።እሱን እንኳን ደውላ ካናገረችው አንድ ወር ሊሞላት ነው።‹‹ጨርቄን ጥዬ አልሄድኩም እንጂ እኔማ በትክክል አብጄያለሁ››  ስትል በውስጧ አሰበች።ከእዛኛው ጫፍ ወንድሟ እያወራ ነው።

‹‹እህቴ. ምነው ጠፋሽብን...?ብዙ ጊዜ ስንደውል ስልክሽ አይሰራም››ቅሬታውን አሰማ፡፡

‹‹የእኔ ማር ደህና ነኝ..ትንሽ ስራ ስላጨናነቀኝ ነው..ለመሆኑ እናትህ ደህና ነች››

ከራጂ ጋር በአባት እንጂ  በእናት  አይገናኙም።ግን  የራጅ  እናት  ለሳባ  የእንጀራ እናቷ ብቻ ሳትሆን የልጅነት አብሮ አደግ ጓደኛዋ ጭምር ስለሆነች ቀረቤታቸው ዘመናት ያስቆጠረና የተለየ አይነት ነው።

‹‹እማዬማ...ደህና ነች ማለት ይከብዳል?››

ሳባ ደነገጠች"እንዴ ምን ሆነች...?  አመማት እንዴ?››

‹‹እኔ እንጃ እህቴ?.ካንቺ ጋር ተጣልታቹሀል እንዴ?››

‹‹ማንና ማን.. እኔና ስንድ? የት ተገናኝተን...ይሄን ወሬ ከየት አመጣኸው?››

‹‹እህቴ ባትቀየመኝ ኖሮ እንዲህ አትረሳኝም ነበር...አንድ ልጄን አስቀይሜ የአባቷ መንፈስስ እንዴት ይታዘበኛል? እያለች ቀኑን ሙሉ ስታለቅስ ነው የምትውለው.. አይኗ እንዳይጠፋ ፈርቼ ነው የደወልኩልሽ››

ሳባ ጭንቅላቷ ላይ ብው ብሎ የሚነድ እሳት የተነሰነሰባት መሰላት‹‹የእኔ ማር...እናትህ ተሳስታለች...እሷ መቼም  እኔን  ልታስቀይመኝ  አትችልም...  ደግሞም በሆነ ነገር ብቀየምስ በግልፅ እንዲህ አድርገሽኛል እላለሁ እንጂ  እንዴት እቀየማለሁ፤ ከአንተና ከእሷ ውጭ ሌላ ቤተሠብ አለኝ እንዴ?››

‹‹እሱማ የለሽም...ግን?››

‹‹ግን ምን?››

‹‹እኔ እንጃ ባትቀየሚ.ዛሬ እኛ ጋ ትመጪ ነበራ...››

‹‹የት አሰላ?››

‹‹አዎ ››

ብዥ  አለባት  ...መድሀኒት  ስትወስድ  የሚሰማትን  የመደንዘዝ  አይነት ስሜት ይሰማት ጀመረ..፡፡

‹‹ዛሬ ለምን?››

‹‹ነገ  የአባዬ  የሰባት  አመት  መታሰቢያው  አይደለ  እንዴ....?ባትቀየመኝ  በአባቷ መታሰቢያ ቀን ከቤቷ አትቀርም ነበር ብላ እኮ ነው የምታለቅሰው..››

‹‹ራጂ ቆንጆ...አሁን መኪና እየነዳሁ መጥፎ ቦታ ነኝ ያለሁት...ማታ ልደውልልህ››

‹‹እሺ እህቴ እወድሻለሁ፡፡››

‹‹እኔም   እወድሀለሁ    የእኔ    ማር፡፡››ስልኩን    ዘጋችና    ..መኪናዋን    አንቀሳቀሰች ...ወደአስፓልት መሀል ካስገባች በኃላ መጠምዘዣ እስክታገኝ ወደፊት ነዳች፡፡ ከዛ አቅጣጫዋን ለውጣ መንዳት ጀመረች.፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍9111🔥1
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ እንደምንም ራሷን ተቆጣጥራ ያዘዛትን መድሀኒት በስርዓቱ ተጠቅማ በቀጠራት ቀን ከሳምንት በኋላ በሰዓቱ ሄደች።እንደደረሰች  በሞቀ  ፈገግታና  ጠበቅ  ባለ ሠላምታ  ተቀበላትና። "ቁርስ በልተሻል?›› ሲል ጠየቃት፤ግራገባት፡፡ አሰበች   ቁርስ   አልበላችም ..ጭርሱኑም ትዝ አላላት።ሳትመልስለት  የለበሰውን  ነጭ  ጋዎን  አውልቆ…»
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሁሴን ተቀበለውና ቀጠለ <<ታዲዬስ ባለው ነገር ላይ ምንም አልጨምርም.. ቀጥታ ወደ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ገብቼያለሁ፡፡እዚህም ያላችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ አላማችንን የምትደግፉ በስልክም በኢሜልም ሆነ በተመቻችሁ ዘዴ ቃል መግባት ትችላላችሁ ... ከዛ በፊት ግን ይሄንን ዝግጅት የምንጀምረው፤በስጦታ ነው፡፡ስጦታውን የምትሰጠን ሰዓሊ ሰላም ነች.. ሰዓሊ ሰላም ወደ መድረክ…፡፡››

ሰላም ሸንከል ሸንከል እያለች ወደ መድረክ ስትወጣ ትንግርት ከኃላዋ 120 ሳ.ሜ በ 60 ሳ.ሜ ስፋት ባለው በሸራ ላይ የተሳለ ስዕል ይዛ ተከትላት ወጣች፡፡ስዕሉ ለህዝብ እይታ ቀረበ፡፡

<<እኛ ለእኛ›› የሚል ርዕስ አለው፡፡

አንድ ህፃን የተቦተራረፈ ልብስ እና የቆሸሸ ፊት ይዞ አስፓልት ዳር ከሚገኝ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ
ጠርዝ ላይ ቂቢብ ብሎ በመውጣት ሞልቶ በመትረፍ አካባቢውን ሙሉ ከሸፈነው ቆሻሻ ላይ የተጣለ ምግብ ጎንበስ ብሎ የሚፈልግ ይመስላል፤አንደኛው እጁ ግን ወደ አስፓልቱ ተቀስሯል፤በተቀሰረው እጁ አቅጣጫ የቆመች የቤት መኪና ትታያለች፣ከመኪናዋ ውስጥ አንድ በተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኝ የፀዳ ልብስ የለበሰና የተመቸው ህፃን በመስኮት ተንጠራርቶ መፅሀፍ እና ዳቦ ለጎስቆላው ልጅ ሊያቀብለው ሲንጠራራ ያሳያል፡፡

ሁሴን ቃላ መጠየቅ ሊያደርጋት ወደ ሰላም ተጠጋ

‹‹ስምሽን ብታስተዋውቂን?››

‹‹ሰላም እባላለሁ..ሰላም ታዲዬስ፡፡››

‹‹ሰላም እሺ ..…ለምንድነው ወደዚህ መድረክ የወጣሽው?››

‹‹ይሄንን ስዕል ለድርጅቱ በስጦታ ላማበረክት፡፡››

‹‹በጣም ጥሩ ነው ..ማነው የሳለው?››

<<እኔ ነኛ፡››

‹‹ለምን ርዕሱን ..እኛ ለእኛ አልሽው?››

‹‹ለእኛ ከእኛ ውጭ ማንም ስለሌለ ነዋ...ታዲዬስ አባት ባይሆነኝ እኔ ይሄኔ እዚህ

መድረክ ላይ ሳይሆን ሀዋሳ መንገድ ዳር ቁራሽ ዳቦ መግዣ ሳንቲም እየለመንኩ ነበር
ምታገኙኝ…..እባካችሁ የኢትዮጰያ ህዝቦች በጠቅላላ መጥናችሁ ውለዱ፤ልመና የሞራል
ነቀርሳ ነው ማንም ህፃን እንዲለምን አትፍቀዱ፤ጎዳናዎች ከቦታ ወደ ቦታ መተላለፊያዎች እንጂ ፈጽሞ የህጻናት መኖሪያዎች መሆን የለባቸውም፤ታዲ አባቴ ከዛ
የጎዳና ሰቆቃ አውጥተህ ሰው ስላደረግከኝ አመሰግንሀለው እሺ ... ደግሞ በጣም ነው
የምወድህ....ሁላችንም ልጆችህ
እንወድሀለን..ሁሉም የዓለም አባቶች እንደ አንተ እንዲሆኑ እንፈልጋለን..››ይሄን ስትናገር እንባዋን መግታት ስላልቻለች መድረኩ ጥላ ወረደች..አዳራሹን የሞላው ህዝብ ዓይኞች ሁሉ
በዕንባ ፈሳሽ ተሞሉ፡፡ሁሴን ከደቂቃዎች ዝምታ በኃላ መናገር
ጀመረ‹‹እሺ ሰላምን እንደሰማችኋት ይሄንን በነዛ
ትናንሽ እጆቿ የተሳለውን ድንቅ ስዕሏን በስጦታ አቅርባልናለች.. እናም ለጨረታ እናቀርበዋለን..፡፡
ሰላም ማለት የታዲዬስ ልጅ ነች..ቅድም ልዩ ጥኡመ ዜማ ለጆሮችን ያሰሙን ሀሊማ እና
ሄለንም የታዲዬስ ልጆች ናቸው፤ሚጡና ሙሴ
የሚባሉም ልጆች አሉት...በተለይ ሙሴ የልጅ ሳይንቲስት ነው…ስለሱ ሳስብ ምን እንደሚታሰበኝ ታውቃላችሁ ሰው ከሞተ በኋላ
ነፍሱ በሌላ ሰው አካል ሆና ዳግም ወደዚህ ምድር ትመጣለች የሚል እምነት የሚያራምዱ
ማህበረሰቦች አሉ ፤ያ እምነት እውነት ከሆነ የታዲዬስ ልጅ የሆነው ሙሴ የቶማስ ኤዲሰንን
ነፍስ ይዞ ለኢትዬጵያውያን ተስፋ ሊሆን የተፈጠረ ሳይሆን አይቀርም ብዬ እጠረጥራለሁ…. በአጠቃላይ ቅድም ታዲዬስ
የተናገረው ንግግር ለመናገር ብቻ ሳይሆን እሱ በተግባር ስለፈተነው ህጻናትን ከመሰረቱ ኮተኩተን ካሳደግናቸው ገና ከጥዋቱ ፍሬያቸው እንደምናይ ስላረጋገጠ ነው..፡፡

አሁን ወደ ሰላም ሥዕል ጨረታ እንግባ..በነገራችን ላይ ከዚህ ፕሮግራም በኋላ የሰላምን ሌሎች ድንቅ ስዕሎችን ማየት ከፈለጋች በሚቀጥለው ክፍል ጎራ በሉ..(ይሄንን ሲናገር በየቤታቸው ሆነው ዝግጅቱን በቴሌቨዠን ለሚከታተሉት ካሜራው የሰላም ስዕል ወደ ሚገኙበት ክፍል በማዞር ማስቃኘት ጀመረ ..13 የሚሆኑ የተለያየ ርዕስ እና መጠን ያላቸው ስዕሎች በግድግዳው ላይ ተሰባጥረው ለዕይታ ምቹ ሆነው ተሰቅለው አሳየ፡፡

ሰላም ለድርጅቱ በስጦታ ያበረከተችው ስዕል ከሸራተን ሆቴል አልወጣም..በሼኩ ትዕዛዝ ይመስላል በ1ዐዐ ሺ ብር መነሻ የተጀመረውን ጫረታ ፉክክር ዝግጅቱ ላይ ታድመው የነበሩት የሜድሮኩ ስራ አስኪያጅ በሁለት ሚሊዬን ብር እዛው አስቀሩት..ድርጅቶችም ግለሰቦችም ያቅማቸውን ወረወሩ..አጠቃላይ ቃል የተገባውና እጅ በእጅ የተሰጠው በድምሩ 25 ሚሊዬን ብር ሆነ፡፡

ሁሴን ፕሮግራሙን ወደ ሶስተኛው ዝግጅት ሊያሸጋግር ፈለገ‹‹ቅድሚያ ግን ሄለን እና ሀሊማ ወደ መድረክ ዳግም እንዲወጡ አደረገ...የቴዲ አፍሮን ላምባዲና ነው ያቀረቡት፤ ልክ እንዳጠናቀቁ ሁለተኛውን ሙዚቃ ሊቀጥሉ ሲሉ ትንግርት በምልክት አስቆመቻቸው እና ወደ መድረክ ወጣች ፡

‹‹ይቅርታ ለየት ያለ ዜና በስልክ ስለደረሰኝ ነው ወደ መድረክ የወጣሁት..ቴዲ አፍሮ ከሄለን እና ሀሊማ ጋር አዲስ አበባ ላይ አንድ ኮንሰርት በማዘጋጀት ገቢውን ለድርጅቱ እንዲሚያስገባ ነግሮናል.. ለጊዜው 1ዐዐ ሺ ብርም በአካውንታችን ዛሬውኑ እንደሚያስገባ አብስሮናል፤እንግዲህ እዚህ ዝግጅት ላይ የታደሙ ድምጻዊያኖቻችን እና ኮሜዲያኖችም ቅድም እንደሰማችሁት አንድ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁልን ቃል ገብተው ነበር..ይሄ ሁለተኛ ኮንሰርት መሆኑ ነው፡፡እናመስግናለን ››ብላ ወረደች፡

..በዚህ ዜና በጣም የፈነጠዙት ሀሊማ እና ሄለን ናቸው ፤ከሚወዱትና ከሚያደንቁት ለእነሱ እንደ ህልም ከሆነው ቴዲ አፍሮ ጋር በአንድ መድረክ ሊሰሩ ነው..በደስታ በተጥለቀለቀው ስሜታቸው የሚቀጥለውን ሙዚቃ መጫወት ጀመሩ.. የሰርግ ዘፈን ነው‹‹..ሙሽራዬ ሙሽራዬ ... የወይን አበባዬ››ሙዚቃውን ተከትሎ ከጀርባ ካለው በር ወደ መድረክ ሲወጣ የታየው ታዲዬስ ነው፡፡ ቅድም ከለበሰው ልብስ በተለየ አለባበስ ሙሉ ሱፍ ለብሶ ቀኝ እግሩን አስቀድሞ ታየ.. ከኃላው ነጭ የተንዘረፈፈ ቬሎ የለበሰች ወጣት ተከትላዋላች... ርብቃ ነኝ..፡፡እጅ ለእጅ ተቆላልፈው በዝግታ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ወደ መድረኩ ወጡ…ጥጉን ይዘው እንደተጣበቁ ቆሙ፡፡

ሙዚቃው እንደቀጠለ ነው..ሌሎች ጥንዶች በተመሳሳይ ሁኔታ በተመሳሳይ አለባበስ ወጡ ዶ/ር ሶፊያ እና ፕ/ዬሴፍ ናቸው፡፡ ከነ ታዲዬስ ጎን ቆሙ..አሁንም ሌላ ጥንዶች ተከተሉ ፎዚያና ኤልያስ(የእነ ኤልያስ ጋብቻ ልዩነታቸውን በምን ሁኔታ ፈተው ወይም ለመፍታት ተስማምተው ለዚህ ጥምረት እንደበቁ ለጊዜው ከጥንዶቹ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ሰው የለም) ህዝብ ከፍተኛ መደመም ወስጥ ገብቷል..በመጨረሻ ጥንድ ሆነው የወጡት የነ ሀሊማ የሙዚቃ አስተማሪዋ አይነ ስውሯ ፅዬን እና የሰላም የስዕል አስተማሪው ዓልዓዛር ናቸው፡፡ሙዚቃው አልቆ ተቋረጠ..ከዛ አምስቱም የታዲዬስ ልጆች ከያሉበት ወደመድረክ ወጡና ታዲዬስን እና አዲሷን እናታቸውን ርብቃን ከበው ቆሙ..በተመሳሳይ ሌሎች ጥንዶችም ዛሬ ለማሳዳግ የተረከቧቸው ልጆች ወደ መድረክ ወጥተው በእያንዳንዱ ጥንዶቹ መካከል በፈገግታ ቆሙ..ህዝቡ በደስታ እና በዕልልታ አዳራሹን አደበላለቀው፡፡

ሁሴን ወደ መድረኩ ወጣና መናገር ጀመረ….
👍7715🤔2👎1
መቼስ በፕሮግራሙ ትንሽ ግራ ሳትጋቡ አትቀሩም..ይሄ የመጨረሻ ፕሮግራማችን የቀደሙት ፕሮግራሞች ቅጥያ ነው ፡፡እንግዲህ የያዝነው ትውልድን በአዲስ መልኩ መገንባት አይደል..ለዛ ደግሞ ቤተሰብ መመስረት ዋናው መሰረት ነው፡፡ እነዚህ አራት ጥንዶች የማህበሩ መስራቾች እና አባላት ናቸው፡፡ እንደምታዬቸው ሁሉም ጥንዶች ለየራሳቸው ልጅ ለማሳደግ ተረክበዋል፤ ከዛም በተጨማሪም ለሰርግ የበጀቱትን በጀት ለድርጅታችን ገቢ
አድርገዋል..ዶ/ር ሶፊያና ፕ/ዬሴፍ 400 ሺ ብር፣አቶ ታዲዬስ እና ወ/ሮ ርብቃ 1ዐዐ ሺ ብር
፣አቶ ኤልያስ እና ወ/ሮ ፎዚያ 5ዐ ሺ ብር፣በተመሳሳይ አቶ ዓላዛር እና ወ/ሮ ፅዬን 5ዐ ሺ ብር በጠቅላላው 6ዐዐ ሺ ገቢ በማድረጋቸው እኛስ ለምን ጋብቻቸውን በዚህ ፕሮግራም ላይ እውቅና አንሰጠውም በማለት
ነው እንዲህ ፊታችሁ ያቆምናቸው፡፡ ስለዚህ አንዴ በነ ሄለን ሙዚቃ ሙሽራዬ እያልን ወደ
መውጫቸው እንሸኛቸዋለን ….በዛውም ፕሮግራማችንን እናጠናቅቃለን፡፡

እናመሰግናለን፡፡

😔ተፈፀመ😔


ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ። ድርሰቱ ሲያልቅ 500 #Subscriber እንገባለን ብዬ ነበር አልተሳካም አሁንም ቢሆን ድርሰቱ የተመቸው ሌላ ድርሰት #እንዲቀጥል ፍላጎት ያለው ቻናሉን #Subscribe እያደረጋቹ።

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍86👏1813🔥11🥰8
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሃምሳ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ሁሴን ተቀበለውና ቀጠለ <<ታዲዬስ ባለው ነገር ላይ ምንም አልጨምርም.. ቀጥታ ወደ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ገብቼያለሁ፡፡እዚህም ያላችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ አላማችንን የምትደግፉ በስልክም በኢሜልም ሆነ በተመቻችሁ ዘዴ ቃል መግባት ትችላላችሁ ... ከዛ በፊት ግን ይሄንን ዝግጅት የምንጀምረው፤በስጦታ ነው፡፡ስጦታውን የምትሰጠን…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

..በህይወቷ እንዲህ አይነት ድንዛዜ ውስጥ ገብታ አታውቅም...የአባቷን  የሙት አመት መታሰቢያ ቀን መርሳት ማለት ..በቃ እያበቃላት መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ያለፉትን ስድስት አመታት እሷ ነበረች  ቀድማ  ለእንጀራ  እናቷ የምታስታውሳትና ለድግስ የሚያስፈልገውን ነገር ቀድማ የምታሟላው።ሳምንት ሲቀረው ጓዟን ጠቅልላ ወደአሰላ ትሄዳለች።የአባቷን ሀውልት ታሳድሳለች..አካባቢውን ታፀዳለች..በሀውልቱ ላይ ደርቀው የከሰሙ አበቦችን አስወግዳ በምትካቸው አዲስ ትተክላለች..ያሉትንም ውሀ  ታጠጣለች...ቤት ውስጥ በድግሱ የእንጀራ እናቷን ትረዳለች...በዕለቱ ታዲያ አንድም ችግረኛና የኔ ቢጤ በከተማው አይቀርም፤ ቀኑን ሙሉ ወደእነሡ ቤት ሲጓዙና ከድግሱ በልተው ወደቤት ይዘው የሚሄዱትን በፌስታል ተቋጥሮላቸው የሞተውንም ነፍስ ይማር ብለው እነሱንም መርቀው ይሄዳሉ።ይሄ መታሰቢያ ባለፉት ስድስት አመታት በጠቅላላው በአሰላ ከተማ የታወቀ ነው። እሷ ግን ይሄው የዘንድሮውን ረሳችው፡፡ከአይኖቿ የሚንጠባጠበውን እንባ እያበሰች "አባዬ በጣም ይቅርታ፡፡›› አለች፡፡

በዚህ ጊዜ ቱሉ ዲምቱ የክፍያ ጣቢያ ደርሳ የክፍያ ትኬት ለመቀበል መኪናዋን አቁማ ነበር።ታናሽ ወንድሟን ካወራች በኃላ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም።ወደቤቷ ሄዳ እንኳን ቅያሪ ልብስ ለመያዝ አልሞከረችም።ጭራሽ በሀሳቧም አልመጣ፡፡ቀጥታ መኪናዋን አዙራ ወደአሰላ መሄድ ብቻ ነበር የታያት፤እያደረገች ያለውም ያንን ነው።የቤታቸው የውጭ በራፍ ጋር የመኪናዋን አፍንጫ አስጠግታ የመኪናዋን ክላክስ ስታስጓራ አስር ሰዓት  ተኩል  ሆኖ  ነበር። ከሰፈሩ  በግርማ  ሞገሡ  አንደኛ የሆነውን ፊት ለፊቷ የሚታያትን የግንብ አጥር እና ፍረንች ዶር ያሰራችው እሷ ነበረች...አጥሩን ብቻ ሳይሆን ከድሮ ቤታቸው ማለት እትብቷ ከተቀበረበት እና ካደገችበት ቤት ፊት ለፊት ያለውን ቪላ ቤት ያሰራችው እሷ ነች።ግን ይህን ሁሉ ያደረገችው ውድ አባቷ ከሞተ በኋላ ነው።በህይወት እያለ የሚወደውንና መላ ህይወቱን የለፋበትን ግቢ እንዲህ አሳምራውና ቀይራው ቢያይላት ኖሮ እንዴት ይደሰት እንደነበረ ትገምትና የብስጭት እንባዋን  ትዘራለች።ሁሌ ስለእንደዚህ አይነት ጉዳይ አንስተው ከስንዱ ጋር ሲያወሩ"አሁንም  እኮ መንፈሱ ያይሻል...ለእኔና ለወንድምሽ በምታረጊው ነገር ባለበት ሆኖ ይመርቅሻል..ልክ በህይወት እያለ ይኮራብሽ እንደነበረው  አሁንም  ይኮራብሻል..››እያለች ልታፅናናትና ከገባችበት ሀዘን መንጭቃ ልታወጣት  ትሞክራለች።ግን ይህ አይነቱ  የእንጀራ እናቷ የማፅናኛ ንግግር እሷን ይበልጥ ጥልቅ ወደሆነው ሀዘን ውስጥ ነው ጎትቶ የሚሸጉጣት

‹‹አባቴ ባለበት ሆኖ እኔን የሚያየኝ ከሆነማ በጣም ነው የሚያፍርብኝ...በእውነት ይህቺ ልጅ እኔ ያሳደኳት ከአብራኬ የወጣች ልጅ ነች ?››ብሎ መጠየቁ አይቀርም...ምክንያቱም በትክክልም ባለበት ሆኖ ስራዬን የሚያይ ከሆነ ቤቱን ማሳመሬን ብቻ አይደለም የሚያየው..ሚስቱን እና ልጁን መንከባከቤንና መርዳቴን ብቻ አይደለም የሚያየው አመት እየጠበቅኩ በስሙ የአሰላን ድሆች ማብላቴን ብቻ አይደለም የሚያየው...እርግጥ እነዚህን ስራዎቼን ባየ ቁጥር ፈገግ ሊል ይችል ይሆናል፡፡ግን ደግሞ በየዕለቱ በስራ  ህይወቴ  የማሳልፈውን ነገሮች ካየስ..?.በእየዕለት ህይወቴ የሆንኩትንና እየሆንኩ ያለሁትን የሚያይ ከሆነስ..?ልጁ አጨበርባሪ እንደሆነች ሲያይስ.?ልጁ እልል ያለች ፕሮፌሽናል ሸርሙጣ መሆኗን ሲያይስ? ከዛም  አልፎ  ገዳይና  ቂመኛ  መሆኗን ሲያይስ?››እኚህንና መሠል ነገሮችን በውስጧ እያሰበች ሽምቅቅ ትላለች።አባቷ በሄደበት በዛው እንዲመቸውና ፊቱን ወደኃላ ዞሮ እንዳያያት ዘወትር ትፀልያለች።አዎ አባቷም  ሆነ  ሌሎች የሚወዷት ሰዎች ከዛሬ አስር አመት በፊት የነበረችውን ሳባን ብቻ አውቀው በዛ ትዝታ እንዲኖሩ እንጂ ካዛ ወዲህ እንደ አዲስ በውስጧ በቅላ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረቻትን አውሬዋን ሳባን እንዲያውቁ ፈፅሞ አትፈልግም...

የአሁኗን ሳባ ከእነሱ ለመደበቅ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም።
በሀሳብ ጭልጥ ካለችበት የበራፍ መከፈት ነው ያባነናት፡፡ራጂ ነበር ..የከፈተላት።መኪናዋ አዲስ ስለሆነች አይቷት አያውቅም።ማንነቷን ስላለየ  ወጣና ቀረባት፤እህቱ መሆኗን ሲያውቅ እየፈነጠዘ ሰላምም ሳይላት  ወደውስጥ ሮጠ.‹‹..እናቴ ማን እንደመጣ እይ ? እናቴ አላልኩሽም እህቴ  መጣች...እህቴ መጣች" ደስታውንና ፈንጠዝያውን ስታይ ውስጧ ርብሽብሽ አለባት፡፡
‹‹እንደዚህ የሚንሰፈሰፉልኝ ቤተሠቦች እያሉኝ ለምንድነው ብቸኝነት ውስጤን የሚከታትፈው? ›› ስትል እያሠበች ከገቢናው ከፍታ ወረደችና ወንድሟ  ክፍት ጥሎት በሄደው ትንሹ በር ገብታ እራሷ የመኪናውን መግቢያ በራፍ ከፈተችና መኪናዋን ወደ ግቢ ውስጥ አስገብታ ገና በቅጡ ሳታቆም ስንዱ ልጇን አስከትላ እጇን እንደ ክንፍ እያርገፈገፈች ስትመጣ አየቻትና ፈጠን ብላ  መኪናዋን በማቆም ወረደችና… ወደእሷ ተንደረደረች፡

አይን  ለአይን  ሳይተያዩ ገና ሁለት ወርም በቅጡ ያልደፈነ ቢሆንም አሁን በሰላምታ ተቃቅፈው ሲላቀሱ ላያቸው ባለፈው ሁለት አመት ጭራሽ ያልተገናኙ ነው የሚመስለው፡፡

‹‹ለመሆኑ.አለሽ…?ምነው.ከሳሽ?››ፊቷን.እየዳበሰች.በመንሰፍሰፍ.ጠየቀቻት…ስንዱ የሳባ እኩያ ብትሆንም አባቷን በማግባቷና  በዛም  ምክንያት እናቷ መሆን በመቻሏ  ሁሌ  ንግግራቸው የሀያ አመት ልዩነት በመሀከላቸው ያለ ነው የሚመስለው፡፡

ቤት እንደገባች ምግብ ተሰርቶ በልታ ቡና ተፈልቶላት ጠጥታ  ለነገው  ድግስ የሰፈር ሰው ሁሉ ቤታቸው ስራ ላይ  ስለነበረ  እነሱን  ተቀላቅላ  ማገዝ ብትፈልግም ራስ ምታቷ ስለተቀሰቀሰባትና ከሰው ተቀላቅላ ሆይ ሆይታ ውስጥ መሳተፉን ስላልቻለች በስንዱ ገፋፊነት እሷ መኝታ  ቤት  ገብታ እንድትተኛ አድርጋት ወንድሟም እየመጣ እንዳይረብሻት አስጠንቅቃው በራፉን ከውጭ ዘገታባት ወደስራዋ ሄደች፡፡

ሳባም የድሮ የአባቷ መኝታ  ክፍል  አባቷ ይተኛበት የነበረ አልጋ ላይ ወጥታ ኩርምት ብላ ተኛች የተወሰነ  ድካም  ቢኖርባትም እንቅልፍ ሊወስዳት ግን አልቻለም፡፡እስከአሁን ሁለት ጊዜ በዶክተሩ የታዘዘላትን ለሳምንት ያህል በተከታታይ ስትወሰደው የነበረውን መድሀኒት መውሰድ ነበረባት..ጥዋት ለህክምና ብላ ከቤት እንደወጣች ስላልተመለሰች አልያዘችውም ዛሬ የታዘዘላትንም ተጨማሪ መድሀኒት  ወደፋርማሲ  ጎራ  በማለት  ልትገዛ አልቻለችም..ጭራሽ ትዝም አላላት፡፡

‹‹የራሱ ጉዳይ አለችና ››ወደሀሳቧ ተመለሰች፡፡
እዚህ ቤት መምጣት .ከዛም በላይ እዚህ ክፍል መግባት… ከዛም በላይ  እዚህ አልጋ ላይ ተኝቶ ስለአባቷ  ማሰብ  አንኳን  አሁን  እንደዚህ  አእምሮዋ  በጭንቀት እና በድባቴ ምስቅልቅል ባለበት ጊዜ ይቅርና በፊትም ራሷን መግዛትና ስሜቷን ማረቅ በምትችል ጊዜ በጣም ነበር የሚረብሻት…በጣም ነበር ሀዘን ውስጥ የሚጨምራት፡፡ይሄ ቤት የተወለደችበት ነው፡፡እናቷ የሞተችው እሷ ከተወለደች ከአንድ አመት በኃላ ነበር፡፡አዎ  የአንድ  አመት  የልደት  በዓሏ  ሊከበርላት  አንድ ቀን በቀረበት ጊዜ ነው፡እናትዬው ከመሞቷ በፊት ለእሷ የልደት ክብረበዓል የሚሆኑ ሁሉንም ዝግጅት አሰናድታ ጨርሳ ነበር.በድንገተኛ በሽታ ማታ ሁለት ሰዓት አመማት..ወዲያው አፋፍሰው አሰላ ሆስፒታል አስገቧት…አምስት ሰዓት ህይወቷ አለፈ፡፡ ከዛ አባትዬው ለብቻው ሆኖ ነጭ ላቡን ጠብ በማድረግ ምንም እንዳይጎልባት አድርጎ አሳደጋት፡፡ታዲያ ሁል  ጊዜ  የእሷ  ልደት 
👍7913👏1😁1
​​ሲደርስ  አባትዬው ፊት ላይ የሚፈራረቀው ስሜት አሁንም ድረስ ስታስበው ይዘገንናታል.በዚህ የሚወዳት ብቸኛ ልጁ የተወለደችበት የህይወቱ በጣም አስደሳቹ ቀን ነው.በሌላ ጎኑ ደግሞ የልቡ ሰው የነበረችው የልጅነት ፍቅሩና የሚወዳት ሚስቱን የተቀበረችበት ቀን ነው ይሄ ስሜት ውድ አባቷን እስከ እለተ  ሞቱ  ድረስ በተፈራራቂ ስሜት ሲያንገላታውና ሲፈታተነው  የኖረ  የህይወቱ አንዱ ክፍል ነበር፡፡
አባቷ እሷ አድጋ ትምህርት ቤት ገብታ ተምራ፤ ትምህርቷን ጨርሳ ዩኒቨርሲቲ እስክትገባ ድረስ ሚስት አላገባም ነበር..ጭራሽ  በህይወት  ዘመኑ  ሙሉ የማግባትም እቅድ የለውም ነበር..በመጀመሪያ እንደዛ ያደረገው ለልጄ የእንጀራ እናት አላመጣባትም በሚል እሳቤ ቢሆንም ዘመናት እያለፉ ሲመጡ ደግሞ ከነጭራሹ ዳግመኛ ማግባት አያስፈልገኝም ብሎ ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡ ግን ያንን ውሳኔውን ሽሮ በተአምራዊ ሁኔታ ሊያገባ ቻለ፡ለዛውም የገዛ የልብ ጓደኛዋንና የእድሜ እኩያዋን ስንዱን፡
ስንዱ ለሳባ እንዲሁ አባቷን ስላገባች ብቻ የእንጀራ እናቷ ትባል እንጂ ከዛ ይልቅ ጓደኝነቷ የበለጠ ትርጉም አለው፡ከታዳጊነት እድሜያቸው ጀምሮ አብረው ያደጉ በጣም የሚቀራረቡ በሁለት አመት ያህል ብቻ የሚበላለጡ የልብ ጓደኛሞች ነበር

ስንዱም ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ አሰላ ዙሪያ ካለ ገጠር መጥታ እነ ሳባ ሰፈር በመከራየት ትምህርት ስትጀምር እንደ አጋጣሚ ሆኖ ከሳባ ጋር አንድ ክፍል ስለደረሳቸው ትምህርት ቤት አብሮ መሄድና አብሮ መምጣት ከዛም ሚስጥር መቀያየር ጀመሩ፤ ከዛም የልብ ጓደኛሞች ሆኑ፡የስንዱ ለደንቡ ያህል ቤት ትከራይ እንጂ ከትምርት ቤት ውጭ ያለውን አብዛኛውን ጊዜዋን የምታሳልፈው እነሳባ ቤት ሆነ፡፡አቶ በአምላክም በሂደት እየለመዷትና የልጃቸው ጓደኛ ከዛም አልፎ እንደእህት ስለሆነችላት ደስተኛ ሆኑ.እሷንም ልክ እንደልጃቸው ማየት ጀመሩ፡፡ለልጃቸው ልብስ ሲገዙ ለእሷም መግዛት፤ለልጃቸው መፅሀፍ ሲገዙ ለእሷም መግዛት ጀመሩ፡ሁለቱንም መልካም ስራ ሲሰሩ ማሞገስ  ሲያጠፉ  እኩል መቆጣት ከዛም አልፎ  እውቂያቸው ገጠር ወደሚኖሩት የስንዱ ቤተሰብ ድረስ ዘለቀ‹‹ሀይስኩል ስትገባ የቤት ኪራይ መክፈልስ ለምን አስፈለገ?››ተባለና ወደእነ ሳባ ቤት ተጠቃላ ገባች፡ልክ እንደቤቱ አንድ ልጅ የሳባን ክፍል እየተጋራች በመኖር አብረው እየተረዳዱና እያነበቡ በትምህርታቸው ቀጠሉ፡፡
አስራ ሁለተኛ ክፍል ማትሪክ ተቀበሉ፤ሳባ ጥሩ ዉጤት አምጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላትን እድል ስታገኝ ስንዱ አልተሳካላትም፡፡በዛን ወቅት ከቤተሰቦቿ በላይ ያዘነውና ያፅናኗት የሳባአባት አቶ በአምላክ ነበረ፡፡ምክንያቱም ስንዱ ከሳባም በላይ በትምህርቷ ጎበዝ እንደሆነች ነበር የሚረዳው፤እንዴት እንዲህ እንደተበላሸባት አልገባውም...ምን አልባት ከቤተሰብ ተነጥሎ መኖር ያመጣባት የስነ-ልቦና ጫና ይሆናል ሲሉ ደመደመ
ከዛ ቀኑ ሲደርስ እዛው  አሰላ  በግል  ኮሌጅ  እንድትማር  አሳምኗት  ልጁን ዩኒቨርሲቲ.ሊሸኝ.ሄደ፡አዲስ.አበባ. አድርሷት፤ መመዝገቧን አጠናቃና ..የዩኒቨርሲቲውን ዶርም ተረክባ መረጋጋቷን ካረጋገጡ በኋላ ወደአሰላ ሲመለስ መንገድ ላይ በተፈጠረ የመኪና ግጭት አደጋ ደረሰበትና በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተወሰደ.. በጣር ላይ  ሆኖ  ሲሰቃይ  ከጎኑ ማንም አልነበረም፡
በወቅቱ ስልኩንና ሌሎች እቃዎቹን የሰበሰበው ፖሊስ ቅድሚያ የደወለው  ስንዱ ስልክ ላይ ነበር…ምክንያቱም በመጨረሻ በስልኩ የተደወለው ለእሷ ነበር…የደወለላት ወደአሰላ እየመጣ መሆኑን ሊነግራት ነበር ግን ስልኩን ከዘጋ ከ25 ደቂቃ በኃላ ነበር አደጋው የደረሰው.እሷም ይመጣል ብላ ቤቱን አሰማምራና፤ ቆንጆ ምግብ ሰርታ፤ቡና አቀራረባና ቤቱን አጫጭሳ ስትጠብቅ ስለዘገየባት ስትጨነቅ ከ2ሰዓት በኃላ ተደውሎ ሲነግራት ዜናውን ማመን አቅቷት ራሷን ስታ ወደፊቷ ተዘርራ የጠረጴዛው ጠርዝ ጋር ተጋጭታ እስከመፈንከት ደርሳ ነበር
እና ከዛ አደጋ በአራት ወር አታካች ህክምና  ክትትል  በኃላ  የሳባ  አባት  አቶ በአምላክ ሁለት እግሩን አስቆርጦ በዊልቸር እየተገፋ ወደቋሚ  መኖሪያ  ቤቱ ከሁለት ልጆቹ ጋር ተመለሰ፡ሳባም በዛ አመት ትምህርቷን የምትቀጥልበት አእምሮም ሆነ ዝግጅነት ሰላልነበራት ዊዝድሮዋል ሞልታ ነበር ከስንዱ ጋር በመተጋገዝ አባቷን ስታስታምመው የቆየችው፡፡ስንዱም እዳዛው ኮሌጅ የመማሩን ፍላጎት ሙሉ  በሙሉ  ጥላ ሁለቱም እሱን መንከባከቡ ላይ አተኮሩ፡

ከዛ አመቱ አልቆ መስከረም ጠባ፡፡ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ሰዓት ሲደርስ ቤት ውስጥ ጭቅጭቅ ተፈጠረ፤ሳባ አባቴን እንዲህ  ባለ  ሁኔታ ጥዬ አልሄድም  ብላ አሻፈረኝ አለች
አቶ በአምላክ የሱ ህይወት ገና በጎልማሳነት ዕድሜው ላይ ባልታሰበ  አደጋ ስንክልክል ማለቱ ሳይበቃ የልጁ የወደፊት ህይወት ሲሰነካከል ቁጭ ብሎ መታዘብ አልቻለም የሆነ ነገር አድርጎ ልጁን ማሳመንና ወደዩኒቨርሲቲ ሄዳ ያቋረጠችውን ትምህርት እንድትቀጥል ማድረግ አማራጭ የሌለው ግዴታው እንደሆነ ተረዳ.. በወቅቱ.ሳባን ወደከተማ ላካትና ስንዱን አስጠርቶ ፊቱ አስቀምጦ ማዋራት ጀመረ

‹‹ምነው ጋሼ አመመህ እንዴ?››

‹አይ በጣም ደህና ነኝ ግን ልጄ አንድ ውለታ ልጠይቅሽ ነው››

‹‹ጋሼ አንተ አባቴ ነህ የሞተብኝ አባቴ  ምትክ  ነህ ሚቻል  ቢሆን  እግሬን ቆርጬ እሰጥህ ነበር.እና ምንም ነገር አድርጊልኝ በለኝ አደርግልሀለሁ፡›› አለችው.አቶ በአምላክ በስንዱ ንግግር ልቡ ተነካና አይኖቹ እንባ አቀረሩ፡፡ልጅቷ ከራሷ ቤተሰቦች በላይ እሱንና ልጁን እንዲህ አምርራ ለምን እንደምትወድ ግራ ይገባዋል፡እንደምንም ሰሜቱን ተቆጣጠረና ንግግሩን ቀጠለ
‹‹ልጄ እኔም ልክ እንደልጄ ነው የማይሽ የሳባ ህይወት እንደሚያሳስበኝ ያንቺም የነገ ህይወት ያሳስበኛል..ስለዚህ ሁለት ነገር እንድታደርጊልኝ እፈልጋለሁ››

‹‹ዝም ብለህ ንገረኝ.ምንና ምን?››አለችው ስንዱ የሚጠይቃትን ሁሉ ያለማቅማማት ለመፈፀም ለራሷም ጭምር ቃል በመግባት፡በመጀመሪያ ከትራሱ ስር ሁለት ሺ ብር መዘዘና እጇ ላይ አስቀምጠው
‹‹ምንድነው ጋሼ?››
‹‹ነገ ሄደሽ ዶክመንትሽን በመያዝ ኮሌጅ ለመማር ትመዘገቢያለሽ››

‹እንዴ ጋሼ ምን እያልክ ነው…?አሁን ያንተ ጤንነት እንጂ የእኔ ትምህርት ያሳስባል?ገና ልጅ እኮ ነኝ ቀስ ብዬ እማራለሁ..አሁን አንተን መንከባከብ ነው የምፈልገው፡፡ባይሆን ሁለታችንም ተባብረን ሳባ ወደአዲስ አበባ ሄዳ እንድትማር ማሳመን ነው የሚገባን፡››ስትል ነበር የመለሰችለት፡

‹‹እኔም እኮ ለዛ ነው አንቺ ለመማር በመመዝገብና ትምህርትሽን እየተማርሽ እኔንም እንደምትንከባከቢኝ በተግባር ብታሳያት ታምናለች የልጆቼ የወደፊት ህይወት እንዲስነካከል አልፈልግ.እንደዛ ከሆነ በቃ ለሁለተኛ ጊዜ እርባና ቢስ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ››

‹‹ጋሼ እኔ ኮሌጅ ለመማር ስለተመዘገብኩ እሷ ልማር ብላ አትሄድም እንደውም በተቃራኒው አንቺ ትምህርት ቤት በምትሆኚበት  ሰዓት አባቴን ማን ይንከባበዋል ብላ በማሰብ ተቃራኒውን ነው የምታደርገው
‹እና ምን ይሻላል? ያንቺም ትምህርት የሚቀር አይደለም፡እንዴ ሰው መቅጠር እንችላለን…ሰራተኛ ከአሁኑ.ፈልጊ አዎ ያንን ንገሪያት››
‹‹ጋሼ እኔ የተሻለ ዘዴ አለኝ››ነበር ያለችው
‹‹ምን አይነት ዘዴ? ››በጉጉት ጠየቃት፡፡

💫ይቀጥላል💫
ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8413
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ..በህይወቷ እንዲህ አይነት ድንዛዜ ውስጥ ገብታ አታውቅም...የአባቷን  የሙት አመት መታሰቢያ ቀን መርሳት ማለት ..በቃ እያበቃላት መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ያለፉትን ስድስት አመታት እሷ ነበረች  ቀድማ  ለእንጀራ  እናቷ የምታስታውሳትና ለድግስ የሚያስፈልገውን ነገር ቀድማ የምታሟላው።ሳምንት ሲቀረው ጓዟን ጠቅልላ ወደአሰላ ትሄዳለች።የአባቷን…»
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰባት


ደራሲ-ዘሪሁንገመቹዋቤ


‹‹አሁን አልነግርህም...ግን ለወራት ያስብኩበት አንድ ነገር አለ፡፡››

‹‹እኮ ንገሪኛ?››

‹‹አይ መጀመሪያ ከእሷ ጋር ልነጋገር…ግን አንተ ምንም አታስብ እሷን በምንም ዘዴ ቢሆን በምንም አሳምናታለሁ..በእኔ ጣለው…ትሄዳለች፡፡››

‹‹አንቺስ?››

‹‹ጋሼ እኔ እዚሁ ነኝ…የግል ኮሌጆች ምዝገባቸው ለወራት የሚዘልቅ ነው…ጊዜ አለን…ለማንኛውም ብሩ አንተው ጋር ይቀመጥ..ልመዘገብ ስሄድ እወስደዋለሁ›› ብላ ነበር ብሩን መልሳለት የወጣች፡፡

ሳባ በደንብ ትዝ ይላታል..በዛን ቀን ማታ እራት ተበልቶ ቡና ተጠጥቶ እንዳለቀ የሚፈልገውን ነገር ለአባታቸው አቀራረቡና ተያይዘው ወደመኝታ ቤታቸው ሄዱ፡፡ክፍላቸውን ዘጋግተው አልጋቸው ላይ ወጡና ወሬ ጀመሩ፡፡

‹‹ሳቢ አርብ ነው ወይስ ሰኞ የምትሄጂው?››አለቻት ስንዱ

ሳባ ግራ በመጋባት‹‹የት ነው የምሄደው ?›ስትል መልሳ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዲስ አበባ ነዋ….ምዝገባው እኮ ከአርብ እስከ ማክሰኞ ነው፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ?የምን ምዝገባ ነው?ዕድሜ ልኩን ወጥ እየወጠወጠና ልብሶቼን እያጠበ፤ንፍጤን እየጠረገና  ለሀጬን  እያበሰ  ያለእናት  ያሳደገኝን አባቴን እግር አልባ ሆኖ አልጋ ላይ ቀርቶ እያየሁ፤ እኔ  ገና  ለገና  ነገ  ባለድግሪ ለመሆን ብዬ ጥዬው የምሄድ ይመስልሻል…?እንደውም ስለትምህርት ሲጠራ እንዴት እንደሚቀፈኝ ብታውቂ ››
‹‹እንዴት ?ለምንድነው ትምህርት ሊቀፍሽ ሚችለው?›

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..?እንደአንቺ ማትሪክ ሳይመጣልኝ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ አባቴ ልሸኝሽ ብሎ በዛን ጊዜ  አዲስ  አበባ  ይሄድ  ነበር?.ባይሄድ  ደግሞ  ለዛ አደጋ ይጋለጥና እንደዛ ኩሩና ሀገር የማይበቃው  የነበረው  አባቴ  እንዲህ  ተቆራምዶ ቤት ይቀር ነበር…?››

‹‹ምን ነካሽ…..ያ የእግዚያብሄር ፍቃድ ነው፡፡ ደግሞ  አባታችን  በህይወት ስለተረፈልንና ዛሬም በእጆቹ እየዳበሰን ስለሆነ... ዛሬም በአንደበቱ እየመከረንና እየገሰፀን ስለሆነ ማመስገን ነው ያለብን፡፡ዛሬም ስለነጋችን እየተጨነቀና
መንገድ  እያሳየን  በመሆኑ  እድለኞች  ነን፡፡ከእሱ ጋር በመኪና ውስጥ የነበሩት ሰዎች እኮ ግማሹ ወዲያው ነው የሞቱት፡፡››

‹እሱስ  እውነትሽን  ነው…ተመስገን  ነው…አባቴን  ባጣ  ምን  ይዉጠኝ.ነበር?ግን አትልፊ…እኔ የትም አልሄድም፡፡››

‹‹ቆይ ጋሽ በአምላክ.. ለእኔም አባቴ እንደሆነ ታምኛለሽ?››

‹‹ምን ማለትሽ ነው…በጣም እንጂi አንቺ እኮ እህትና ወንድም ስለሌለኝ በውስጤ የነበረውን ቁጭትና ሀዘን ያጠፋሺልኝ ምርጥ እህቴ ነሽ››

‹‹ይሄን  በመስማቴ  ተደስቼያለሁ..ታዲያ  አሁን  ዩኒቨርሲቲ  ብትገቢ  እኔ.አንቺ እዚህ ሆነሽ ከምትንከባከቢው በታች ትንከባከበዋለች ብለሽ ታስቢያለሽ?››

‹‹በፍፁም… እንደውም እሱን በመንከባከብ አንቺ ከእኔ የተሻልሽ ነሽ፡፡››

‹‹እና ታዲያ በእኔ እምነት ይኑርሻ፡፡››

‹‹ባንቺ  እምነት  ሳይኖረኝ  ቀርቶ  እኮ  አይደለም፡፡አመታቱ  ረጅም.መሆናቸው አሳስቦኝ ነው..አራት አመት…››

‹‹አራት አመት ምን አላት? አርባ አመትስ ቢሆን?››

‹‹ምን ነካሽ አንቺም እኮ የራስሽ ህይወት አለሽ…ችላ ብለሽ ልታልፊው የማትችይው የስራ ዕድል ሊያጋጥምሽ ይችላል..?ልታፈቅሪ  ትችያለሽ…ባል ማግባትም ልትወስኚ ትችያለሽ…አንቺ ባትፈልጊ እንኳን ቤተሰቦችሽ ሊያስገድዱሽ ይችላሉ፡፡ያኔ እንዴት ሊሆን ነው…?ትምህርቴን ለሁለተኛ  ጊዜ መልሼ ላቋርጥ ነው…?፡፡የማልወጣውን ነገር መነካካት አልፈልግም፡፡ግድ የለም ይቅርብኝ፡፡እዚሁ የተዘጋውን የአባቴን ሱቅ ከፍቼ እሱን እየሰራው ብንከባከበው ይሻላል፡፡››

‹‹አይ እንደዛ ማደርገው እኔ ነኝ፡፡አንቺ ወደ ትምህርትሽ ነው የምትሄጂው፡፡ ብታፈቅሪስ ላለሽው ቆየሁኮ አፍቅሬያለሁ፡፡››
‹‹ባክሽ ቀልዱን አቁሚ፡፡››

‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም ..እውነቴን ነው፡፡››

‹‹እንዴ አንቺ…?ከመቼ ጀምሮ...?ትራሷን ከፍ አደረገችና ከአንገቷ ቀና ብላ አፋጠጠችባት››
‹‹ቢያንስ ሶስት አመት…፡፡››

‹‹አንቺ ሶሰት  አመት  ሙሉ  አፍቅረሽ  ለእኔ  ሳትነግሪኝ..?እኔ  እኮ  በህልሜ ያናገረኝን ወንድ ማንነት ሳይቀር ነው የምነግርሽ፡፡››
‹‹እንደምታስቢው ለመናገር ቀላል አልነበረም፡፡››

‹‹…እውነትሽን ነው ቀላል አልነበረም….?››ሳባ ተበሳጨች… ከዛ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ትራሷን ወደታች አወረደችና ብርድ ልብሱን ተከናንባ ተኛች፡
‹‹እንዴ ጥለሺኝ እየተኛሽ ነው…?ማን ነው ያፈቀርሺው ብለሽ አትጠይቂኝም?››
‹‹ምን ሊያደርግልኝ… ሶስት አመት ሙሉ የደበቅሺኝን ዛሬ ብሰማው  ምን ይረባኛል… ?.እንደውም ከማያምነኝ ሰው ጋር መተኛት አልፈልግም፡፡›› ብላ ነበር መኝታዋን ለቃ በመውረድ ከላይ ያለውን አልጋ ልብስ ገፋ ስሊፐሯን ተጫምታ ከክፍሉ ለመውጣት ወደበራፍ መራመድ የጀመረች...ለመክፈት እጇን ወደ እጀታው ስትዘረጋ ከስንዱ አንደበት እጅግ አስደንጋጭ መንፈሰን የሚያርድና የሚያደነዝዝ ቃል ነበር የወጣው ፡፡

‹‹ያፈቀርኩት አባትሽን ነው፡፡››

በቆመችበት ደንዝዛ ለደቂቃዎች ቆመች...እንደምንም ፊቷን አዞረችና
‹‹አልሰማሁሽም››ነበር ያለቻት፡፡እውነታው ግን የተናገረችውን ሶስት ቃላት በትክክል ሰምታለች…ግን.አልገባትም.ወይም.ሊታመን የሚችል ዜና ሆኖ አላገኘችውም፡፡

‹‹አዎ ለዛ ነው ሶስት አመት መሉ ሳልነግርሽ በውስጤ አፍኜ የኖርኩት..አባትሽን ስላፈቀርኩ በራሴ አፍሬያለሁ፡፡››

‹‹ቀስ ብላ እግሮቿን እየጎተተች ወደውስጥ ተመለሰችና አልጋ ልብሱን እንደተከናነበች አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡በሰማችው ዜና ደስታ ይሰማት ወይስ ሀዘን ማወቅ አልቻለችም…..አባቷን እኩያዋ የሆነች ልጅ ለዛውም አብራት የምትኖር የገዛ ጓደኛዋ ስታፈቅረው ፡፡

‹‹እርግጠኛ ነሽ ግን?››

‹‹እስከ ዛሬ አመት ማለቴ ጋሼ አደጋ እስኪደርስበት ድረስ እርግጠኛ አልነበርኩም…እንዲሁ ውስጤ የተፈጠረ ቅዠት አድርጌ  በማሰብ ራሴን በመገሰፅ ነገሮችን አዳፍኜ መቀጠልን ነበር የወሰንኩት፡፡ጋሼ የተጎዳ  ጊዜ  ግን በተለይ ዜናውን ፖሊሶች ደውለው ሲነግሩኝ የተሰማኝ ስሜት፤የፈራሁት ፍርሀት፤ላፈቀርሽውና ህይወትሽን ሳይቀር ልትሰጪው ፍቃደኛ ከሆንሺለት ሰው ውጭ ለሌላ ሰው የሚሰማሽ እንዳልሆነ ገባኝ..እውነትም አፍቅሬዋለሁ ብዬ ሙሉ በሙሉ የደመደምኩት የዛኔ ነው››

በወቅቱ ሳባ ምንም ልትላት አልቻለችም….

‹‹ምነው አላመንሺኝም አይደል..?አልፈርድብሽም እኔ ለራሴ  የልቤን  ጩኸት አምኖ ለመቀበል አመታት ከወሰደብኝ አንቺ እንዴት እንዲህ በፍጥነት ትረጂዋለሽ ብዬ አስባለሁ?፡፡››

‹‹አይደለም እኮ …ማለት አባዬ ለአንቺም እንደአባትሽ ነው፤ለእሱ ካለሽ ክብርና መውደድ የተነሳ ምን አልባት ተምታቶብሽ እንዳይሆን ብዬ ነው እኮ…?›

‹‹ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር እኮ..ግን አይደለም..ጋሼ አባቴ ሳይሆን ባሌ እንዲሆን ነው የምፈልገው፡፡›

‹‹አባዬ እኮ 42 አመቱ ነው ፤ከአንቺ  በ22 ዓመት ይበልጣል፡፡››

‹‹አውቃለሁ… ግን ያ  ግድ አይሰጠኝም..››

‹‹እሺ አሁን ያለበት  ሁኔታስ…?››

‹‹እሱም  ጉዳዬ  አይደለም…እኔን የሚያስጨንቀኝ ብቸኛው ምክንያት አንቺ ስለነገሩ ምን ታስቢያለሸ ?የሚለው ነው…፡፡››

‹‹እኔ ደግሞ ምን?››
👍7511👎4👏2
​​‹‹አባትሽን በማፍቀሬ የምትከፊና እንደከዳተኛ የምትቆጥሪኝ ከሆነ ውስጤ በጣም ነው የሚሰበረው…አባትሽን እንዳገባ የማትፈልጊ ከሆነ ዛሬውኑ ማወቅ እፈልጋለሁ…ከዛ ማንም ወደ ማያገኘኝ ቦታ ለዘላለም እጠፋለሁ….ከአባትሽ ሚነጥለኝ ብቸኛው ምክንያት ያንቺ ተቃውሞ ብቻ ነው….››

ሳባ እንባ በአይኖቿ ሞላ….ከተከናነበችው አልጋ  ልብስ  ውስጥ  እጆቿን አወጣችና ወደእሷ ተጠጋች፡፡አቀፈቻት…ጭምቅ አድርጋ አቀፈቻት፡፡

‹‹የእኔ ውድ እኔ እኮ በጣም ነው የምወድሽ….መቼም አንቺን ማጣት አልፈልግም…እኔ ይሄን ነገር ባይሆን ደስ ይለኛል…ምክንያቱም እኔ ለአንቺ የምመኝልሽ በጣም ትልቅ ነገር ነው….ታውቂያለሽ አባቴ ለእኔ ሁለነገሬ ነው.የአለም ጥሩ ነገር ሁሉ ተጠራርጎ ለእሱ  ቢሰጥ  ደስታውን  አልችልም፤ ቢሆንም አሁን ባለበት ሁኔታ እንክብካቤና እርዳታ የሚፈልግ ሰው ነው..እሱን አገባሽ ማለት ሙሉ ህይወትሽን ነው ለእሱ.መስዋዕት የምታደርጊው… መዝናኛ ቦታ ወገብሽን አቅፎ አያንሸራሽርሽም ….ከምትወልጂለት ልጅ ጋር ኳስ አይጫወትም…ሰርግ ቤት ስትጠሪ አብሮሽ ላይሄድ ይችላል…››

ስንዱም እንባዋን ከአይኗ እያበሰች ከእቅፏ ወጣችና  አይን  አይኗን  በስስትና በፍቅር አየተመለከተቻት‹‹እነዚህ የዘረዘርሻቸው ነገሮች ሁሉ ትርፍ ናቸው..ለእኔ.ዋናው ከእሱ ጋር አብሮነትን መጋራት ነው የምፈልገው…አብሮኝ  መኖሩንና አብሬው መኖሩን ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹በእውነት የሚገርም ነገር  ነው..እንዲህ  አይነት  በሚያደነዝዝ  ፍቅር  ውስጥ ያለሽ መሆንሽን ባለማወቄ በራሴ አፍሬያለሁ…ለመሆኑ ይህንን ጉዳይ አባቴ ሲሰማ ምን አለሽ?››
ስንዱ ደነገጠች‹‹እንዴ ምን ነካሽ  ?ጋሼ  ምንም  አያውቅም…..ለእሱ  ዛሬም  እኔ ልጁ ነኝ፡፡››

‹‹እርፍ….ታዲያ  እንዴት ልታደርጊ ነው…?››

‹‹እሱን ለእኔ ተይው…ዋናው ለእኔ  አስጨናቂው የአንቺን  ፍላጎት  ማወቅ ነው፡፡፡››

‹‹እኔማ አንቺን የመሰለች  እናት አግኝቼ ነው፡፡››

‹‹እንግዲያውን ሌላውን ለእኔ ተይና አንቺ ቀጥ ብለሽ ወደትምህርትሽ››

‹‹ከዛ ምን ልታደርጊ?››
‹‹እኔ ትክክለኛው ሰዓት እና አጋጣሚ ሳገኝ እነግረዋለሁ ...ከተሰማማ ደስ ይለኛል..እናት  አገኘሽ  ማለት  ነው...?ካልሆነም  ለእኔ  ችግር  የለውም.  ልጁ  እንደሆንኩ ለአንቺም  እህትሽ  እንደሆንኩ  እቀጥላለሁ ማለት  ነው….ለእኔ  ዋናው  ነገር እሱ በህይወት እስከአለ ድረስ አብሬው መኖሬ ነው..››

‹‹ይገርማል..››

‹‹ምኑ ነወ የሚገርመው?››

‹‹እኔም  እንደአንቺ  አይነት  ፍቅር  አንድ  ቀን  ይይዘኝ  ይሆን  ?ብዬ  አስቤ ነው የተገረምኩት፡›
‹‹ይሄ የእኔ እኮ ልክፍት ነው..ይቅርብሽ…አሁን በይ ከመንጋቱ በፊት እንተኛ››
ተቃቅፈው ተኙ…ከዛ በሶስተኛው ቀን ሳባ በተረጋጋ መንፈስና ሻንጣዋን  ሸክፋ አባቷን በሳቅና በለቅሶ ድብልቅ ሰሜት ተሰናብታና አደራዋን ሁሉ ለስንዱ ሰጥታ ወደ አዲስ አበባ ትምህርቷን ለመቀጠል ሄደች፡፡ስንዱም በአንድ አመት የጊዜ ሂደት አባቷን በከፍተኛ ጥረትና ትጋት አሳምና ማግባት  ቻለች  ፡፡አገር ጉድ እያለ በአመቱ ልጅ ወለደችለት፡፡ይሄው ያ  ልጅ  ዛሬ  12  ዓመት ጎረምሳና የክፉ ቀን አይን ማረፊያዋ ከአንጀቷ ፍቅፍቅ ብላ እንድትስቅ የማድረግ  ችሎታ  ያለው ብቸኛው ወንድሟ ሆነ፡፡

💫ይቀጥላል💫

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍5810🔥2🤔2😁1
አትሮኖስ pinned «#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ ደራሲ-ዘሪሁንገመቹዋቤ ‹‹አሁን አልነግርህም...ግን ለወራት ያስብኩበት አንድ ነገር አለ፡፡›› ‹‹እኮ ንገሪኛ?›› ‹‹አይ መጀመሪያ ከእሷ ጋር ልነጋገር…ግን አንተ ምንም አታስብ እሷን በምንም ዘዴ ቢሆን በምንም አሳምናታለሁ..በእኔ ጣለው…ትሄዳለች፡፡›› ‹‹አንቺስ?›› ‹‹ጋሼ እኔ እዚሁ ነኝ…የግል ኮሌጆች ምዝገባቸው ለወራት የሚዘልቅ ነው…ጊዜ…»
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  ሃያ አራት

ብር፣ አምባር...ሰበረችልዎ!

ትንሸ ስረጋጋ እና አገሩን ስለምድ፣ እኔም ሰው ነኝና ስፈራ ስቼር አልፎ አልፎ ወደ እነዚያ መሸታ ቤቶች ጎራ ማለት ጀመርኩ፡፡ በሕይወት ዘመኔ ከእናቴ ጠላ ውጭ አልኮል መቀማመስ የጀመርኩት እዚያ ነበር፡፡ እንደ እኔ ሊሰደዱ ሞክረው ገንዘብ ያጠራቼው፤ ወይም በማይወጡት ሱስና ዕዳ የተዘፈቁ፤ ያቺን ለማሟላት ሴተኛ አዳሪ የሆኑ የበርካታ አገራት ሴቶች በመሸታ ቤቶቹ ውስጥ ነበሩ፡፡ የሚበዙት ተስፋ ቆርጠው እዚያው በሴተኛ አዳሪነት ሕይወታቼውን የሚገፉ ናቸው፡፡ ከብዛታቼው

የተነሳ አንድ ዓሣ- ዓሣ የሚሸት ጎስቋላ ወንድ ወደ ቡና ቤቶቹ ሲገባ እምስት - ስድስት ሴቶች ይከቡታል፡፡ እነዚያ በሌላው ዓለም ቢሆን እግራቼው ተስሞ ለጋብቻ የሚጠየቁ ቆነጃጅቶች እንዲሀ ሲሆኑ ማዬት፣ እስኪለምዱት አንዳች ግርምት ያጭራል። እኔም ይኼው ነበር የገጠመኝ፡፡ ሴቶች አንዳች አስማተኛ ፍጡራን ናቸው። በዚያ ሲኦል ውስጥ እንኳን ወንድነት፣ ሰው የመሆን፣ የመፈቀር ስሜት፣ እንዲሰማን ያደርጉናል፡፡ ለሕይወት እንድንሳሳ ያደርጉናል፡፡ የቆረጥናትን ተስፋ በሴቶች ፈገግታና የሽቶ ጠረን መልሰን እንቀጥላታለን፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነበር ዛናታ የምትባል ሴት ጋር የተዋወቅሁት፡፡ መጀመሪያ እንዳዬኋት ኢትዮጵያዊ መስላኝ ነበር፡፡ የቀይዳማ መልኳ፣ የሚዘናፈል ጸጉሯ እና በዚያ ሥራ ውስጥ ሆና እንኳን የሚያስታውቅበት ዓይን አፋርነት የኢትዮጵያ ሴቶች ዓይነት ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ እዚያ ቤት ስመላለስ ሴቶቹ አይተውኝ ምንም ጠብ እንደማይለኝ ስላወቁ ለብቻዬ ትተውኝ ነበር፡፡ የዚያን ቀን ግን ማፍጠጤ ጠርቷት መሰለኝ ፈገግ ብላ ወደተቀመጥኩበት መጣች፡፡ ለዚያ ሥራ በተለማመደችው የወንዶችን ስሜት የሚያነሳሳ አረማመድ ሰበር ሰካ ስትል ትልቅ መቀመጫዋና መካከለኛ ጡቶቿ የተለዬ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። በተለይ ግን ጥርሷ! እንደዚያ ዓይነት የጥርስ ንጣት የትም ዓይቼ አላውቅም፡፡ የማላውቀው አገር ልሳን በሚጫነው እንግሊዝኛ... “ምነው ብቻህን?'' አለችኝ፡፡ እንደ ቀልድ ፈገግ ብዬ “እግዚአብሔር_ከነፍጥረቱ ብቻዬን ተወኝ” አልኳት፡፡ አልሳቀችም፤ ዝም ብላ አዬችኝና ኮስተር እንዳለች በማላውቀው ቋንቋ የሆነ ነገር ተናገረች። ግራ መጋባቴን አውቃ በእንግሊዝኛ "እግዚአብሔር_እኔን ልኮልኻል የምትፈልገውን ተናገር" ብላ ባንዴ መኮሳተሯ ወደ ሳቅ ተቀዬረ፡፡ “ምንኛ ነው መጀመሪያ የተናገርሽው?'' “ፈረንሳይኛ፡፡”

“ትችያለሸ?” “ከአረብኛ ቀጥሎ አፌን የፈታሁበት ነው።” “አረብኛም ትናገሪያለሸ?!'' “እንደ ትልቅ ዕውቀት አትዬው፣ በሁሉም ቋንቋ አንድ የረባ ነገር ተናግሬበት አላውቅም!” ተሳሳቅን፡፡ ቢራ እንድትጠጣ ጋበዝኳት፤ አልኮል እንደማትጠጣ ነገረችኝ እና ለእኔ ቢራ፣ ለእርሷ ቀዝቃዛ የሎሚ ጭማቂ ይዛ መጣች፡፡ ከተፋፈገው ክፍል ወጥተን፣ ነፋሻው የቡና ቤቱ አሮጌ የእንጨት በረንዳ ላይ ተቀመጥን። ስትቀመጥ አያታለሁ፣ ቀሚሷን ሰብሰብ አድርጋ በሥርዓት ነበር የተቀመጠችው። ሁለታችንም ዝም ብለን ተቀመጥን፡፡ ጨለማ በዋጠው ውቂያኖስ ላይ አልፎ አልፎ ቀይ መብራቶች ቦግ እልም ይላሉ፤ የባሕር ላይ ድንበር ጠባቂ ጀልባዎች ናቸው: ከመራቃቸው የተነሳ ድምፃቼው የማይሰማ አውሮፕላኖች በጥቁሩ ሰማይ ላይ አብሪ ኮከብ መስለው ያልፋሉ። ዛናታ እንደ ዓመታት ፍቅረኛ ራሷን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ፣ በዝምታ ተቀምጣለች፡፡ ጠረኗ ደስ የሚል የሽቶ፣ የሎሚና የዚያ አገር ሜንት ሲጋራ ድብልቅ ጠረን ነበረው። በቀስታ አቅፌ ጸጉሯን መነካካት ጀመርኩ፣ ልቤ ደረቴን ቀዳ ልትወጣ ደርሳለች... ድንገት ቀና ብላ “ቤቴ ቅርብ ነው ከፈለግህ መሄድ እንችላለን” አለችኝ፡፡ በአክብሮት እንደማልፈልግ ነግሪያት ተሰነባብተን ወደ ዋሻዬ አመራሁ። ዞሬ ሳያት ቆማ እያዬችኝ ነበር። እስከዚያ ዕድሜዬ ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም ነበርና ክፉኛ ፈርቼ ነበር፡፡ በዚያ ልክ ሴት ጋር ስጠጋጋም የመጀመሪያዬ ነበር። ከዚያች ምሽት በኋላ ወደዚያ መሸታ ቤት እግር አበዛሁ፡፡ ዛናታ ባዬችኝ ቁጥር እየተፍለቀለቀች ትመጣለች፤ ቢራዬን ይዠ የሎሚ ጭማቂዋን እየተጎነጨች እናወራለን፡፡ የሆነ ነገር ገብቷታል፤ እንደ እንስሳ በሚያደርጋቼው ወንዶች መኻል ሰው ሰው ሳልሸታት አልቀረሁም፡፡ የሰውነት ሽታ፣ ከሚቀረናው የዓሣ ሽታም በላይ የሰውን

ነፍስ ዘልቆ ይሰማል መሰለኝ!? ብቻ በየምሽቱ እየተገናኜን ወዳጅነታቸንም እየጠነከረ ሄደ፡፡ አንድ ማታ መጠጋጋታችን ወደ ድንገተኛ መሳሳም አለፈ፡፡ እጅግ ጥልቅና ረዥም መሳሳም ነበር። ሎሚ-ሎሚ የሚል መሳሳም። እናም በሚስለመለሙ ውብ ዓይኖቿ እያባበለች ወደ ቤቷ ስትጋብዘኝ እንቢ የማለት ወኔዬ ከዳኝ፡፡ የሴት ልጅ ሰውነት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የዚያን ሌሊት ተዋወቅሁ፡፡ “እኔ አላምንም የመጀመሪያህ ነው?'' አለች እየተፍለቀለቀች! ዝም ብዬ አዬኋት። “እንዳትዋሽ!'' አለች ሊፈነዳ ያሰፈሰፈ ሳቋ ፊቷ ላይ እንደተዘጋጁ፤ በአወንታ ራሲን ነቀነቅሁ፤ ከንፈሬን ስማኝ... አውቄ ነበር፤ _ አውቄ ነበር.... እያለች በሳቅ ተፍለቀለቀች። ድንገት ሳቋን አቁማ... “አገራችሁ ሴት የለም?'” አለችና የሚያምሩ ጥርሶቿ ብርሃናቼውን ረጩ፤ እንደ ተአምር አዬችኝ፡፡ ልክ እንደ ሕፃን ልጅ በዝምታ ጉንጯን ጉንጨ ላይ ለጥፋ ቆዬችና “ሲገርም” አለች ለራሷ፤ ምን እንደገረማት አልገባኝም፡፡ እናም ዛናታ ጋር ያበደ ፍቅር ውስጥ ገባሁ፡፡ አንድ እሷ ነበረች ሙሉ ከተማውን፣ ውሃውን፣ መንገዱን የሞላችው- ለእኔ፡፡ እሷ ጋር ስሆን በስደት አገር ውስጥ ለብቻዬ የተከለለ ሕጋዊ ደሴት ላይ ያረፍኩ መስሎ እስኪሰማኝ ሰላም እሆን ነበር፡፡ እቤቷ _ በሄድኩ ቁጥር ከእሷ እኩል ቤቷ ይገርመኛል፡፡ እግሬ ከኢትዬጵያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥርዓት የተደራጄ ቤት ውስጥ ስገባ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ የቤቷ ንጽህና ገረመኝ፡፡ የቤት ዕቃዎቹ ወደ ሆነ ሕይወት መለሱኝ፡፡ ትንሽ ሕያው ሙዚዬም ነገር። የምኖረው ሌሎች ዘጠኝ ስደተኞች ጋር በምጋራው ጠባብ አሮጌ ክፍል ውስጥ የተገኜውን ነገር እያነጠፍኩ ነበርና የተሰማኝ ስሜት ልዩ ነበር፡፡ የእኔን እንኳን መኖሪያ ከማለት መደበቂያ ዋሻ ማለት ይቀላል፡፡ ማንኪያ፣ ሹካ፣ መጥበሻና ብርጭቆ ዝም ብለው ቁስ አይደሉም። ከነመኖራቼውም ትዝ የማይሉን የቤት እቃዎች ሰውን ተከትለው ባረፈበት የሚረጉ፣ ሰውን በክብር ለማስተናገድ የተሰለፉ፣ ሕያው ቁሶች ናቸው፡፡ ቤት እንዲህ የሚናፈቅ ነገር ነው ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ የተደረደሩትን እቃዎች እያዬሁ ዕንባዬ በዓይኖቼ እንደሞላ ትዝ

ይለኛል።ይኼ እንዴት ሊገለጽ ይችላል!? ከአንድ ወር በኋላ ይመስለኛል፣ ዘናታ ጠቅልዬ ከእሷ ጋር እንድኖር ጠዬቀችኝ፤ አላንገራገርኩም!! ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ... ተማርኩ ሰለጠንኩ ብዬ “የአበሻ ወንዶች አምባ ገነን ባሕሪ የፈጠረው ተረት!” እያልኩ ያጣጣልኩት አባባል ነበር። ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ ሲሉ። የዚያችን ቀን ምሽት ገጠመኝ ባስታወስኩ ቁጥር ግን አባባሉ እንደ በዓል መድፍ አርባ ጊዜ ይጮኸብኛል። ዛናታ ቤት ጠቅልዬ የገባሁ ሰሞን ሁለታችንም ዓለምን ረሳን፤ ራሳችንን ረሳን፤ ስደተኝነታችንን ረሳን፤ ፖሊስ ጋር የአይጥና ድመት ድብብቆሸ እየተጫዎትን የምንኖር ምስኪኖች መሆናችንን ረሳን፤ ፍቅር _ ነፃነት ነው...
👍498😁1
ፍቅር _ የባርነት ሰንሰለትን እንዳጠለቁ መደነስ ነው። ከምሠራበት ቦታ ዓሣ ይዤ ወደ አዲሷ ጎጆዬ ስገባ የሚሰማኝ የአባወራነት ስሜት ልዩ ነበር፡፡ የኔ ቆንጆ ዛናታ በረከሰ ሥራ ውስጥ የከበረ ነፍስ የነበራት ውብ ሚስት ነበረች። ሚስትነትን በቀለበትና በሰርግ ሳይሆን ከልብ በመነጨ ፍቅር መኖር ጀምራ ነበር። አብረን መኖር በጀመርን በወሩ ይመስለኛል፣ ክፍያዬን ከሦስት አሠሪዎቼ ተቀብዬ ወደምትሠራበት ቡና ቤት በኩራት አመራሁ፤ ስታዬኝ ተንደርድራ መጥታ እቅፌ ላይ ወደቀች፡፡ ወደተለመደው በረንዳችን ሄደን እንደተቀመጥን “ዛሬ ክፍያ ተቀብያለሁ” አልኩና የተቀበልኩትን ብር በሙሉ እጇ ላይ አስቀመጥኩላት። እዬሳቀች ታዬኛለች “እስኪ ዛሬ በነፃነት ሌላ ቦታ እንሂድ? የምታውቂው ቆንጆ ቦታ” ብዙ አላሰበችም እየተፍለቀለቀች “ውጭ ጠብቀኝ እንደወጣሁ ነግሪያቼው መጣሁ'' ብላኝ እየተፍለቀለቀች ሄደች። ስትመለስ በትልቅ የጨርቅ ዘንቢል ቢራ፣ ድፍን ሐብሃብ፣ የሎሚ ጭማቂ፣ የተጠበሱ ዓሣዎች ይዛ መጣች። ከብዷት ስለነበር ግራና ቀኝ በማንጠልጠያዎቹ ለሁለት ያዝነው። የዚያን ቀን ምሽት ተያይዘን በባሕሩ ዳርቻ የተሠራውን ዋና

መንገድ ወደ ግራ በመተው ወደ ሰፊው አሸዋማ የባሕር ዳርቻ አቀናን፡፡ መ74. ጨለም ያለና ሰዎችም ብዙ የማይጠቀሙበት ነበር። በሕሩ ዳርቻ ላይ ወዳሉ የጀልባ ላይ ጎጆዎች ነበር ለመሄድ ያሰብነው: እኔ ከምኖርባት ሰፈር ስወጣ የመጀመሪያ ነበር፤ ዘናታ ግን በተደጋጋሚ ትሄድባቸው ስለነበር መንገዱን የምትመራኝ እሷ ነበረች። ጀልባዎቹ በተለይ ለጥንዶች የሚዘጋጁ ሲሆኑ የራሳቼው ትንሽ መኝታ ቤት እና መጸዳጃ ቤት ያላቼው ተንሳፋፊ ጎጆዎች ነበሩ። በዋጋም ርካሽ ናቸው። ወደ እኩለ ሌሊት ስለነበር በመንገዳችን የሰው ዘር አልነበረም። ሁለታችንም ሕገወጥ ነዋሪዎች ነንና ይኼን ወደነዋል። በዚያ ሰዓት ፖሊሶች ሙሉ ትኩረታቼው ጠረፉ አካባቢ በሌሊት ድንበር በሚሻገሩ ስደተኞች ላይ ስለሚሆን አካባቢው ነፃ ይሆናል። ከሩቅ የሚብለጨለጨውን የጀልባዎቹን ብርሃን እያዬን፣ እያወራንና እየተሳሳቅን በየመኻሉም እየተሳሳምን ምድሩም ሰማዩም _ ጠቦን እንደ አገረገዥ በኩራት ስንጓዝ፤ ድንገት ከቀኝ በኩል ከተደረደሩት የዘንባባ ዛፎች ውስጥ የመኪና መብራት ቦግ ብሎ አካባቢውን በሰማያዊ ብርሃን አጥለቀለቀውና መልሶ ጠፋ። ሁለታችንም የጨው ዓምድ ሆነን ቀረን። ያንን መብራት ማንም ስደተኛ የሚያውቀው መብራት ነበር። ሕገወጥ የሰው ዝውውርና አደንዛዥ ዕፅ ተቆጣጣሪ ፖሊሶች መኪና መብራት ነው። ምልክቱ ቁሙ ነበር። ብዙዎች ከዚህ መብራት ማስጠንቀቂያ ለማምለጥ ሲሮጡ በጥይት ሩምታ ተገድለዋል። ማንም ወረቀት የሌለው ስደተኛ ለምን ገደላችሁ የሚላቸው የለም። ባለንበት ቀጥ ብለን ቆምን። ሁለት ፖሊሶች ትንሽ ተራርቀው የእጅ ባትሪ ፊታችን ላይ እያበሩ ቀረቡንና በአረብኛ የሆነ ነገር ተናገሩ፤ ዛናታ የያዝነውን ዘንቢል እንድናስቀምጥና ወደ ፊት እንድንራመድ ነገረችኝ። እንዳለችኝ አደረኩ። ረዘም ያለና ቁጣ የተቀላቀለበት ነገር ሲናገሩ ዛናታም ኮስተር ብላ መለሰችላቼው፤ ጭቅጭቅ ተፈጠረ። በመጨረሻም አንደኛው ወደ እኔ ራመድ ብሎ ክንዴን አፈፍ አደረገና ወደ መኪናው እንድሄድ ጎተተኝ፤ ዛናታ የሆነ ነገር ስትናገር መጎተቱን አቆመና ወደ ኋላዬ ገፋ አድርጎኝ እሷን በምልክት ወደ መኪናው እንድትቀድም አሳያት።

በአንድ ነገር እንደተስማሙ ገብቶኛል። ወደ እኔ ዞራ በተረጋጋ ድምፅ «በቀጥታ ተመልሰህ እቤት ሂድ፤ ጠብቀኝ ቶሎ እመጣለሁ!» አለችኝ፡፡ ግራ እንደተጋባሁ ሳያት ቆጣ ብላ “ሂድ! የምልህን ስማኝ! ካልሰማኻኝ ሁለታችንንም ችግር ውስጥ እንገባለን ሂድ!'' ብላኝ ወደ መኪናው ተራመደች፡፡ ወደ ኋላ ተመልሼ መንገድ ከጀመርኩ በኋላ ትንሽ ራቅ እንዳልኩ አቅጣጫዬን ቀይሬ ከአንዱ ዘንባባ ዛፍ ሥር ቆምኩ፡፡ ይቺን ድርጊት ምነው ባላደረግኋት እላለሁ እስከ ዛሬ። መኪናው ውስጥ ከኋላ አስገብተዋት ሁለቱም ወደጋቢና ገብተው በሩን ሲዘጉ ወደ ሆነ ቦታ ሊሄዱ መስሎኝ ነበር። መኪናው ግን አልተነሳም። ትንሽ ቆይተው አንዱ ፖሊስ ወጣና ሲጋራ ለኩሶ ከመኪናው ወደ ፊት አለፍ ብሎ እያጨሰ ቆመ፤ ሌላኛው ከጋቢና ወጥቶ ዛናታ የገባችበትን የኋላ በር ከፍቶ ገባና ዘጋው፤ ትንሸ ቆይቶ መኪናዋ በቃስታ ከፍ ዝቅ ስትል ትታዬኝ ነበር፡፡ ወደ ፊት ሩጥ ሩጥ የሚለኝን ስሜት የዘንባባ ዛፉን በብስጭት አንቄ ተቆጣጠርኩት፡፡ የራሴን እጅ ነክሼ በምሬት ቆምኩ። የመጀመሪያው ፖሊስ ወጥቶ ቀበቶውን ሲያስር ሁለተኛው በጥድፊያ ወደ መኪናው ተጣደፈ። መኻል ላይ ቆም ብለው ሲጋራ ተቀባበሉ። ሁለተኛው ፖሊስ የመጀመሪያው በወጣበት በዚያው በር ገባና ዘጋው፡፡ ከዚያ በላይ ማዬት አልቻልኩም፤ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤታችን ተጣደፍኩ። ዋጋ ቢስነት፣ ረዳት አልባነት ውስጤን ሞላው። ሰውነቴ በእልኅ ይንቀጠቀጥ ነበር። ደግሞም ራስ ወዳድነቴ ሕይወትን መውደዴ እንጂ እነዚያን ቆሻሾች አጥፍቻቼው ብጠፋስ እላለሁ፡፡ _ ከእህቶቼ አንደኛዋ ላይ ቢሆን የማደርገው ይኼንኑ ነበር?...መሸሽ!? ተንገበገብኩ፤ መንገዴ ላይ ያገኜሁትን ነገር ሁሉ በእግሬ እየጠለዝኩ እንደ እብድ ብቻዬን ለፈለፍኩ፣ ፖሊሶቹን ረገምኩ፣ ከተማዋን ረገምኩ፣ መንግሥትን ረገምኩ፣ አገሪቱን ረገምኩ! ራሴንም ጭምር ረገምኩ፡፡ አእምሮዬ ወደ ኋላ ብዙ ዓመታት ተጉዞ አባቴን አስታወሰ፡፡ አንድ ጧት አባትና እናቴ ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ግቢያችን በር ላይ ልጋጉን የሚያዝረበርብ ውሻ አጋጠማቸው። ውሻው እንዳያቸው ወደ እናቴ ሊነክሳት ሮጠ፤ ከውሻው ፍጥነት የተነሳ አባባ ረዥም መቋሚያውን እንኳን መጠቀም አልቻለም፤ ዘሎ ከእናቴ ፊት

ቆመና ለእናቴ የተሰነዘረው የውሻ ጥርስ የአባቴ ክንድ ላይ ተሰገሰገ። እናቴ ዘላ ወደ ግቢ ተመልሳ በጩኸት እስክትቀሰቅሰን አባባ ውሻው ጋር እየታገለ ነበር። ያ ውሻ የእብድ ውሻ በሽታ በሚሉት የተለከፈ ነበር። አባባ በዚያ ጠንቅ ለወራት በዘለቀ ሕክምና ከሞት አፋፍ ተመልሷል። እኔ ልጁ ግን አንዲት ምስኪን በዝሙት ላበዱ ዉሾች አስረክቤ ወደ ቤት ተመለስኩ። ከሁለት ሰዓት በኋላ ይመስለኛል ዛናታ መጠች። በዝምታ ገብታ ከቤታችን ኋላ ወዳለች ገላ መታጠቢያ ሄደችና ብዙ ቆይታ ተመለሰች፡፡ ትንሿን የኤሌክትሪክ ምድጃ ለኩሳ ሻይ ጣደች፡፡ አልጋችን ጫፍ ላይ ተቀምጨ በዝምታ አያታለሁ። ሻዩ ሲፈላ ቤቱ በቅመሙ ሸታ ተሞላ። በሁለት ብርጭቆዎች ቀዳችና አንዱን ለእኔ አቀብላኝ የራሷን በዝምታ ጠጥታ ጨረሰች።ዕቃዎቹን አጣጥባ “እንተኛ?' አለችኝ። ትንሽ ከእኔ ራቅ ብላ ፊቷን ወደ ግድግዳው አዙራ ተኛች። መብራቱን አጥፍቼ ወደ እሷ ዞሬ ከኋላዋ ሳቅፋት ሰውነቷ በሳግ እየተናጠ እያለቀሰች ነበር። አጥብቄ አቀፍኳት። በዚያች ጎጆ ውስጥ ረዳት አልባ የተረሱ ፍጡሮች ነበርን። ሁለታችንም ስለዚያች ቀን እስከመጨረሻው እንደገና _ አላነሳንም። ይሁንና በውስጤ የኔ የምላቼውን መከላከል የማልችል ደካማ የመሆን ስሜት በየጊዜው እዬተሰማኝ ስሰቃይ ኖሪያለሁ። አውቃለሁ ዛናታ ሴተኛ አዳሪ ነበረች፤ እኔም ጋር ሆነን ብዙ ወንዶች ጋር ትወጣ ነበር፤ ያቺ ምሽት ግን...
👍296🔥2👏1😁1
ለሰባት ወራት አብረን ኖርን፡፡ ለወራት በዘለቀ የነፍስ ግንኙነታችን ስለ ራሴ ያልነገርኳት፣ _ ስለ _ እርሷም _ ያልነገረችኝ _ ነገር _ አልነበረም፡፡ እናትና አባቷን እታውቃቼዉም፣ የተወለደችው ሞሪታኒያ የምትባል አገር ነው፡፡ እስከ ዐሥራ አንድ ዓመቷ ያሳደጋት ፈረንሳዮች የሚያስተዳድሩት የማደጎ ድርጅት ነበር፡፡ ዕድሜዋ ዐሥራ አንድ ሲደርስ ግን የአገራቼው መንግሥት ከቀድሞ ቀኝ ገዣቼው ፈረንሳይ መንግሥት ጋር ባለመግባባቱ፣ ፈረንሳዮች ማሳደጊያውን ዘግተው፣ ልጆቹንም በትነው ሄዱ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኑሮዋ የመከራ ሆነ፡፡ በዋናነት ለቱሪስቶች በእጅ

የተሠሩ ባህላዊ ጌጣጌጦች በመሸጥ፣ በመላላክ፣ልብሳቼውን በማጠብ በኋላም አንዳንድ ታሪካዊ ቦታዎችን በማስጎብኜት ኑሮዋን መግፋት ጀመረች፡፡ ዕድሜዋ 16 ሲደርስ አንድ እንግሊዛዊ ጋር ተኛች፡፡ እርሷ ሰውዬውን ወዳው ነበር። በወቅቱ ብር ሲሰጣት ለእርሷ የፍቅር መግለጫ ነበር የመሰላት፤ ሲቆይ ግን ሌሎችም ጋር ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግ ደረሰችበት፡፡ የፍቅር ታሪኳ ባጭሩ ተቀጨ፡፡ ሌሎች ቱሪስቶችም ብር እየከፈሏት በድብቅ ይወስዷት ጀመሩ። ያለፈችበትን የድህነት ሕይወት በዚህ መንገድ ማለፍ እንደምትችል አሰበች ዓይታው የማታውቀው ብር ማግኜት ጀመረች፤ እናም ሙሉ ለሙሉ የሴተኛ አዳሪነት ሥራ ውስጥ ገባች፡፡ በሞሪታኒያ ሕግ ሴተኛ አዳሪነት በጥብቅ የተከለከለና በእስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ በአንድ ዕድለ ቢስ ምሽት ተደረሰባትና ተያዘች። ለፖሊሶች ያላትን ገንዘብ ገላዋንም ጉቦ ሰጥታ ከእስር ቤት ካስወጧት በኋላ ወደ ሞሮኮ ተሰደደች፡፡ በአንድ በሚያውቃት ፈረንሳዊ ቱሪስት ተረድታ ነበር ወደዚያች ከተማ የደረሰችው። ሰውዬው ወደ ፈረንሳይ እንደሚያሻግራት ቃል ገብቶላት ሞሮኮ እንደደረሱ በአንድ ቅንጡ ሆቴል ለአንድ ሳምንት ያኽል ተዝናንቶባት እንደ ወጣ ቀረ። ከዚያ በኋላ ኑሮዋን በሴተኛ አዳሪነት መግፋት ቀጠለች። ውብ ሰውነቷ ወንዶች የሚሻሙበት ሴት አደረጋት፡፡ እርሷም ገንዘብ ይዘው ጎራ የሚሉ ወንዶችን ከሌሎች ሴቶች ጋር ተሻምታ የምትኖር ሴት ሆነች፡፡ ከዚያ የተረገመ ምሽት በኋላ የምትሠራበት መሸታ ቤት እንዳልሄድ ከለከለችኝ፡፡ ያንን ሥራ ስትሠራ እንዳያት አትፈልግም ነበር፡፡ ሥራዋ ላይ በጣም ቁጡ እና ሞገደኛ ነበረች፡፡ ጋጠወጥ ወንዶች በሚበዙበት በዚያ ጋጠወጥ መሸታ ቤት፣ በቢራ ጠርሙዝ የፈነከተቻቼው፣ እንጀራ ነውና በወንድ ተጣልታ ፊታቼውን በጥፍሯ የተለተለቻቼው ብዙ ነበሩ፤ ራሷ ናት የነገረችኝ፡፡ ለአንተ ብቻ ነው ጨዋ የሆንኩት ትለኛለች፡፡ ድንገት ሰዎች ጋር በእርሷ ምክንያት እንዳልጣላ ትፈራ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ግን እኔ ፊት ሌሎች ወንዶች ጋር ስትወጣ እንዳይ አትፈልግም ነበር። በእርግጥ እኔም ያንን ቦታ ሳስበው ይቀፈኛል፤ ይቀፈኛል ብቻ አይደለም ቅናት

ያንገበግበኛል፡፡ ሥራውን ተይው ልላት አስብና “የማያዋጣ በል ቅንድብ ይስማል እንደሚባለው” ይሆንብኛል፡፡ ሰው ቤት ተቀጥራ ለመሥራት ብዙ ሞክራ ነበር፤ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላት ሴት መቅጠር አልፈለጉም። ይህች ሴት ጋር በባህልም ሆነ በቋንቋ አንገናኝም፡፡ ሞሪታኒያ ከምትባል አገር የተገኜች ሴት አፈቅራለሁ ብዬ ላስብ ይቅርና ከዚያ በፊት ሞሪታኒያ የምትባል አገር የት ናት? ቢሉኝ እምላለሁ! አላውቃትም ነበር፡፡አንድ ቀን የት ነች ሞሪታኒያ? ብዬ ጠዬቅኋት “እዚሀ ነች'ኮ” አለችኝ በአገጯ እየጠቆመች፡፡ እውነትም እዚያው ነበረች፡፡ ሰው አገሩን ይመስላል እንዴ? ሞሪታኒያ በምዕራብ በኩል አትላንቲክ ውቂያኖስ የሚያዋስናት፤ በሰሜን ደግሞ ንዳዳሙን የሰሃራ በርሃ ተንተርሳ የከተመች አገር ናት። በእሳትና ውሃ መኻል ያለች አገር የፈጠረቻት፤ እሳትና ውሃ የሆነች ልጅ ጋር ነበርኩ።

ሞሮኮና ሞሪታንያ ነገረ ሥራቼው እንደ ኢትዮጵያና ኤርትራ ነው። ሲላቼው ታሪክ አጣቅሰው፣ አንዱ የአንዱን ድንበር ይገባኛል ይላሉ፡፡ እንዲያውም ሞሮኮ የሚለያቼውን በርሃ ተሻግራ ሙሉ ሞሪታኒያ የታላቋ ሞሮኮ አካል ነበረች ትል ነበር፤ ማለት ብቻ አይደለም ሞሪታኒያን እንደ አገር እውቅና ሳትሰጣት ቆይታለች፡፡ ቅኝ ገዥዎች በመኻል _ ገብተው ከናካቴው አለያዩዋቼውና _ አረፉት፡፡ ከቅኝ ግዛት ፈረንሳይኛ ቋንቋና ድህነት የተረፋቼው ሕዝቦች የሚኖሩባት አገር ናት፡፡ ይህች ከድፍድፍ ነዳጅ እስከ ወርቅ፣ ከብረት እስከ ዩራኒዬም፣ የተቼራት አገር ሕዝቦቿ ባገኙት ቀዳዳ እንደቀረው አፍሪካዊ ሁሉ የስደትን ጽዋ ይቀምሳሉ፤ ርግማን ነው። ስደት የሚባለው ነገር ምኑን ከምኑ እንደሚቀላቅለው ሳስብ፣ የሆነ ጢማም ተንኮለኛ ሳይንቲስት ይመስለኛል፡፡ ቁጭ ብሎ ዓለምን እንደ ላብራቶሪ ብልቃጥ ፊቱ አቅርቦ፣ እኛን ነዋሪዎቿን ከዚያና ከዚህ እያነሳ የሚጨምረን እና እስክንዋሃድ የሚወዘውዘን፤ የሚበጠብጠን፡፡ ስደት ትርምስ ነው፡፡ ስደት መለያዬት ነው። ደግሞም ስደት መቀላቀል

የሆነ ሆኖ እንደዚያ ስወድቅ ስነሳ አልሳካ ያለኝን ወደ አውሮፓ የመሸገር ሕልም፤ ገላዋን ሸጣ፣ ያጠራቀመቻትን ጥሪት አሟጣ፣ ስደቴን ባላሰብኩት ፍጥነት ያሳካችልኝ ይቺ ሴት ነበረች ብል ማን ያምናል?! የአገሬ የሰርግ ቤት ዘፋኝ “ምን ያለው አማጭ ነው የተክለፈለፈ ማሩን ከወተቱ ቀላቅሎት አረፈ!'' ያለው እንዲህ ያለ ነገር ቢገጥመው ይመስለኛል፡፡ ራስህን ወተት እልክ አልባልና፣ ብልም ግን እውነት አለኝ - ወተትም እንደ እኔ አልተናጠ!! አጥባቂ ሃይማኖተኛ ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደግሁት፡፡ እንኳን ሴተኛ አዳሪነትን የቤት ልጆች ነን የሚሉ ሴቶች ጋር በፍቅር መቀራረብ በሩቅ የምፈራ ነበርኩ፤ ግን ሕይወት እንዲህ ነውና እዚች ልጅ ጋር የጦፈ ፍቅር ውስጥ ወደቅሁ። ከቀለበት ውጭ ልክ እንደ ባለ ትዳር ነበር አኗኗራችን፡፡ ዛናታ ሕልም አልነበራትም፣ የመሰደድም ወደ አገሯ የመመለስም ዕቅድ አልነበራትም፣ በአገሯ ይኼ ሥራ ነውር ነው፤ ግን ደግሞ ሕይወት ነውር አታውቅም፡፡ ያቺ መልካም ሴት እኔ ጋር እስክንገናኝ ምንም ዕቅድ አልነበራትም፤ በቃ ሴተኛ አዳሪ ናት...ትሠራለች ትኖራለች፡፡ እኔን ካገኜች በኋላ ግን ተስፋ ጀመረች፡፡ መጀመሪያ እኔ ከወጣሁ በኋላ ልትከተለኝና አውሮፓ ልንኖር አቀድን፡፡ ስለምንወልዳቼው ልጆች አወራን ... የመጨረሻ ቀን ምሽታችን፣ አሳዛኝ ግን ደግሞ በተስፋ የተሞላ ነበር፡፡ በሌሊት ባሕር ወደምንሻገርባት ጀልባ የሄድነው አብረን ነበር። የመጨረሻ ቃሏ ምን ነበር “ፈጣሪ ይከተልህ!" ብላ ከብር የተሠራ ጫፍና ጫፉ እንደ እባብ ጭንቅላት የተድበለበለ ቀጭን “ብራዝሌት' ግራ እጄ ላይ አጠለቀችልኝ፡፡ “በእኔ አገር ባህል ይኼ ከክፉ መንፈስ ይከላከላል ብለን እናምናለን” አለችኝ፡፡ የእናቴ አምላክ እና የዚች የሰው አገር ሰው አምላክ ተባብረውም ቢሆን አንድ እኔን አንከብክበው ይህችን ውሃ ማሻገር ያቅታቼዋል!? እያልኩ ነበር አርባ ሰባት ስደተኞች በጫነች አሮጌ ጀልባ ባሕር የቀዘፍኩት። እንዲህ ነበር ዛናታ ጋር የተለያዬነው። ብሯን ለመሳፈሪያ፣ አምባሯን ለማስታወሻ፣ ሰውነቷን ለወንድነቴ መጀመሪያ አድርጋ በብዙ ፍቅር ሸኜችኝ።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍449😢3