አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሀዋሳ

ሁሴን ወደ ሲዩዘርላንድ ከበረረ ሀያ ቀን አልፎታል፡፡ያለፉትን ሀያ ቀናት የእሱንም ቦታ ተክታ ለስራው ከላይ እታች በመሯሯጥ ብታሳልፍም ከናፍቆት ግን ማምለጥ አልቻለችም፡፡አዎ ሁሴን ባልተለመደ መልኩ በጣም ናፍቋታል፡፡እራሷን በሌላ ሰው ህልውና ላይ ይሄን ያህል መለጠፍ አትፈልግም ነበር፤ምንም ቋሚና ዘላቂ ነገር እንደሌለ ህይወት ደጋግማ አስተምራታለች፡፡የእኔ የምትለው ነገር ሁሉ አንድ ቀን በሰላምም ሆነ በአደጋ ብቻ በሆነ ምክንያት እንደሚለያትና ለዛም ዝግጁ ሆና መጠበቅ እንዳለባት የዘወትር መፈክሯና መመሪያዋ ነበር፡፡አሁን ግን መልሳ ደከመች፤እናም ባሏ ናፈቃት፡፡እለቱ ሰንበት ስለሆነ የቤቷ ሳሎን ሶፋ ላይ ጋደም ብላ ቴሌቪዢን እየተመለከተች ነው፡፡
አይድል ፕሮግራም..በሀዋሳ የሚካሄድ የማጣሪያ ውድድር እየተመለከተች ነው፡፡

በአብረሀም ወልዴ የሚመራው የዳኞች ቡድን
የዳኝነት ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ተወዳዳሪዎች በቅደም ተከተል ወደ መድረክ እየወጡ የተዘጋጁበትን ዘፈን በመዝፈን ተፈጥሮ
የቸረቻቸውን ድምጽና በጥረታቸው ያደበሩትን
ችሎታ በማዋሀድ ዳኞቹንም ሆነ ተመልካቾችን
በማሳመን ለአዲስአበባው ውድድር ለማለፍ ይጥራሉ፡፡ጥቂቶች ይሳካላቸዋል ፤ሌሎቹ ደግሞ አንገት ደፍተውና ፈዘው ከመድረኩ
ይሰናበታሉ፡፡ትንግርት ሁሌ ይህን ፕሮግራም ስታይ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የሚሰማት፡፡

ዘና የሚያደርገት እንዳለ ሁሉ የሚያሳዝኗትም
ተወዳዳሪዎች አሉ፡፡ከችሎታቸው በላይ
ጉጉታቸው የናረ፣ብዙ ተስፋ አድርገው መጥተው በዳኞቹ ቁርጥ ያለ ሞያዊ
አስተያየት ሽምቅቅ የሚሉ ወጣት ጨቅላዎች፤ ያሳዝኗታል፡፡ችሎታው እያላቸውም ፍራቻቸውን ብቻ ማሸነፍ ተስኗቸው ያላቸውን ነገር መግለጽ ባለመቻላቸው አጉል የሚሆኑም አሉ፤እነሱም ያሳዝኗታል፡፡

...አሁን ግን እያየች ያለቻው ድንቅና የሚያስደምም ችሎታ ነው፡፡አስር ሁለት አመት የማይበልጣቸው ሁለት ሴት ልጆች ናቸው የሚታዩት፡፡አንደኛዋ ጊታሯን ይዛ የተዘጋጀላት መቀመጫ ላይ ተቀመጠችና በጣቶቿ የጊታሩን ክሮች በመነካካት ፈታተሸች፤ሌለኛዋ ከፊት ለፊቷ በሜትሮች ርቀት ማይኩን ይዛ ::

አብረሀም ወልዴ መናገር ጀመረ....

‹‹እሺ እንኳን በሰላም መጣችሁ እያልኩ እራሳችሁን እንድታስተዋውቁ ዕድሉን ልስጣችሁ ፡፡››

‹‹ስሜ ሀሊማ ታዲዬስ ይባላል፡፡ የምጫወትላችሁ የተፈራ ካሳን ‹አባብዬ› የሚለውን ዘፈን ነው፡፡››

‹‹አሪፍ ነው፡፡ባለጊታሯስ ስምሽ ማነው ?››

‹‹ስሜ ሄለን ታዲዬስ ይባላል፤ጊታርና ፒያኖ ተጨዋች ነኝ።

<<እህት አማቾች ናችሁ ?››አረጋኸኝ መሀከል ገብቶ ጠየቀ፡፡

‹‹አዎ እህቴ ናት፡፡››

ይሄ ሁሉ ሲሆን ትንግርት ስትከታተል የነበረው በግማሽ ልቧ ነበር፡፡እህትማማቾች ነን ሲሉ ግን ትንሽ ግር አላት፡፡በእኩል ዕድሜ ላይ ናቸው፡፡የትኛዋ ታላቅ የትኛዋ ደግሞ ታናሽ ትሆን? ስትል እራሷን ጥያቄ ጠየቀች፡፡ ደግሞ ምናቸውም አይመሳሰልም <<የእናት ሆድ ዥንጉርጉር›› ይባል የለ ብላ ለራሷ መልስ ሰጠች፡፡

‹‹በሉ ቀጥሉ..መልካም ዕድል፡፡››ከዳኞቹ ፍቃድ አገኙ፡፡

ሄለን እነዛ ቀጫጭንና ለጋ ጣቶቾን የጊታሩ ክሮች ላይ ማርመስመስ ጀመረች ፡፡ የሙዚቃ መሳሪያውን ምት ተከትሎ የሀሊማ ተስረቅራቂና ማራኪ ድምጽ ይንቆረቆር ጀመር፡፡ በአዳራሹ የሞላው ተመልካች ብቻ ሳይሆን በየቤቱ በቲቪ ፕሮግራሙን የሚከታተለው ህዝብም ፀጥ የሚያሰኝ አደንዛዥ ድምጽ ነበር፡፡በዚህ ዕድሜ በእንዲህ አይነት ችሎታ? እንዴት ነው በዚህ ዕድሜ የሙዚቃ መሳሪያን ስልተ-ምት ጠብቆ ስይደናገሩና ሳይንሸራተቱ በዚህ ልክ መዝፈን የቻሉት?፡፡

ዳኞቹ ሳይቀር አፋቸውን ከፈቱ፡፡ደግሞ በሙዚቃው ሁለቱም ጉንጮች ላይ እንባ እየተንጠባጠበ ነው፡፡ሲጨርሱ የአዳራሹ ሰው ሁሉ አረንጎዴ ካርዱን እያወዛወዘ ከመቀመጨው ተነሳ፡፡ደኞቹም እያጨበጨቡ ቆሙ .. መድረክ ድረስ በመሄድ በየተራ አቅፈው ሳሟቸው፡፡

አስተያየት መስጠት ተጀመረ..የመጀመሪያው ዳኛ

‹‹በእውነት ሀዋሳ እናንተን የመሰሉ ባለድንቅ ችሎታ ሙዚቀኞችን ስላፈራች እድለኛ ነች፡፡

እኛም እዚህ መጥተን እናንተን ስላገኘን እድለኞች ነን፤በቃ ልዩ ናችሁ፡፡››

ሁለተኛው ዳኛ…..

‹‹ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ሙዚቃው ከህይወታችሁ ጋር የሚያይዘው ጉዳይ አለ? ሁለታችሁም ስታለቅሱ ነበር፡፡እኔንም አስለቅሳችሁኛል፡፡ምከንያት ነበራችሁ?››

ሀሊማ መናገር ጀመረች‹‹አዎ ሁለታቸንም አባታችንን በጣም እንወደዋለን፡፡እርግጥ ሁሉም ሰው አባቱን በጣም ይወዳል፡፡እመኑን የእኛ አባት ግን ልዩ ሰው ነው፡፡›› አዳራሹ በሳቅና በጭብጨባ ተናጋ፡፡

ሄለን ቀጠለች‹‹ታዲያ አንተ አባታችን ባትሆን ኖሮ እኛ ዛሬ እንዲህ አምሮብን ሙዚቃ እየተጫወትን እንዲህ አዳራሽ ሙሉ ህዝብ እያጨበጨበልን አንታይም ነበር.፡፡ምክንያም እድሉም ጊዜውም አይኖረንም ነበር፡፡አዎ አባት ባትሆነን ኖሮ ይሄኔ ሁለታችንም አሞራ ገደል
አካባቢ ከሚገኝ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተበላሽቶ የተጣለ ምግብ ከቆሻሻው በመለየት በመመገብ ላይ ነበርን፡፡…እና ከእንደገና ስለፈጠርከን አመሰግናለሁ ...ታዲ እንወድሀለን፡፡››

ዳኞቹም ታዳሚዎቹም ከልጆቹ ችሎታ በላይ በንግግራቸው ድንግርግር እንዳሉ ፊታቸውን በመመልከት ማወቅ ይቻላል፡፡

‹‹እባክህ አቶ ታዲዬስ እዚህ አዳራሽ ውስጥ ካላህ ወደ መድረክ ወጥተህ አንድ ነገር በለን››ከዳኞቹ መካከል አንድ ተናገረ፡፡ በአዳራሹ ያላው ታዳሚ እርስ በርሱ ዞር ዞር በማለት መተያየት ጀመረ፡፡ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ መድረክ የሚወጣ ሰው ለመመልከት፡፡

‹‹ታዲ ና እንጂ››ሄለን ከመድረክ ተማፀነች፡፡

የሁለት ልጆች አባት ሳይሆን ተደባበዳቢ ቦዴ ጋርድ የሚመስል ጠይም ደንዳና ወጣት ወደ መድረኩ ወጣና ሁለቱንም ልጆቹን አቅፎ
ጉንጮቻቸውን ከሳመ በኃላ ማይኩን ተቀብሎ መናገር ጀመረ፡፡‹‹ታዴዬስ ማለት እኔ ነኝ፡፡ልጆቼ

ስለእኔ ያሉት ትንሽ ተጋኗል፡፡እውነታው በተቃራኒው ነው፡፡እነሱ ልጆቼ በመሆናቸው
በአሁኑ ወቅት በአለም በጣም እድለኛው ሰው
እኔ ነኝ፡፡ምን አልባት ችሎታቸውን አይታችሁ
ስታጨበጭቡላቸው ነበር፡፡ግን እመኑኝ መድረክ የመጀመሪያ ቀናቸው ስለሆነ የችሎታቸውን ግማሽም አላሳዮችሁም...እናም
ሁላችሁም እዚህ አዳራሹን የሞላችሁ ሁሉ ብትቀኑብኝ አይገርመኝም፡፡ምክንያቱም እኔ የእነዚህ ዕንቁ ልጆች አባት ነኝ፡፡አመሰግናለሁ፡፡>> ብሎ ወረደ፡፡ፕሮግራሙ ቢያልቅም ትንግርት
ስለልጆቹም ሆነ ስለአባትዬው ልትረሳ
አልቻለችም፡፡የሆነ ያልተለመደ ነገር ነው
የሆነባት፡፡<<አባታችን ባትሆን የቆሻሻ ገንዳ ላይ
ምግብ እንለቃቅም ነበር›› ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?ግን የእውነት አባታቸው ነው ?

አልመሰላትም፡፡እንዴት አድርጎ ቢያሳድጋቸው
ነው በዚህ መጠን ሊወዱት የቻሉት?እውነትም
እሱ እንዳለው የሚቀናበት አባት ነው ? አለችና ቲቪውን አጥፍታ አየር ለመቀበል ቤቷን ለቃ ወደ ውጭ ወጣች፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች እያደረጋቹ አደለም በየቀኑ ለመልቀቅ እየሞከርኩ ነው እናንተም ማበረታታችሁን ቀጥሉ አመሰጎናለሁ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12214👏3🔥1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል ስድስት


እስከ አሁን እዚህ ነሽ!?


ከተለያዬን ከዓመት በኋላ (በትክክል ዓመት የሞላው እንኳን አይመስለኝም)፣ አዘውትረን እንሄድበት ወደነበረው የሜክሲኮው ሬስቶራንት ሄድኩ። ለነገሩ ከዚያም በፊት ብዙ ጊዜ ሄጃለሁ፡፡ ብቻዬንም፣ ጓደኞቼም ጋር። ትዝታዬ ደብዝዞ ሌላ ትዝታ ቢጻፍበትም፣ እዚያ ቤት በሄድኩ ቁጥር ግን አስታውሳት ነበር። በተለይ እነዚያን ሳያቋርጡ ዘፈን የሚያንቆረቁሩ “ስፒከሮች” ሳይ፣ ማሂሰላምን አስታውሳት ነበር፡፡ ሳልወድ በግድ የዘፈኖቹን ግጥሞች ለማድመጥ እሞክራለሁ "ሰው ሲደሰት ዜማውን፣ ሲያዝን ግጥሙን ይሰማል" ያለው ማን ነበር!?.... የዘፈኖቹን ግጥሞች ለመያዝ አእምሮዬ ይሰንፋል፤ ያውም እኔ...ግጥም እስትንፋሴ ነው የምል እኔ። የዚያን ቀን ቤቱን ስለምወደው፣ እዚያው ሰው ቀጥሬ ነበር... ሴት ቀጥሬ። በዕድሜና በቁመት የምትበልጠኝን ሴት ቀጥሬ፡ አፏ ሥር ተለግቼ፣ ሳቋንና ወሬዋን ሰምቼ የማልጠግብላት ሴት ቀጥሬ፡፡ ስገባ ማንን አገኜሁ?...ማሂሰላምን _ ከእነባሏ...ደነገጥኩ! የእውነት ደነገጥኩ። መጀመሪያ አራት ዓመት አብራኝ የቆዬች ፍቅረኛዬን (አብሮኝ የቆዬ ጠይም ሰውነት ብል ይቀላል) የሆነ ሌላ ሰው ጋር ማዬት በራሱ ለመልመድ ጊዜ የሚወስድ የመደናገር ማዕበል ያስነሳል፡፡ ቀጥሎ ሰላም ማለት አለብኝ ወይስ የለብኝም? የሚል ጥያቄ ይከተላል....ግራ ተጋባሁ፡፡ ትንሽ ምቾት ነሳኝ- ነገሩ ...አልተነጋገርንም ሰላም አልተባባልንም፡፡ ለምን ሰላም እንዳላለችኝ ገርሞኛል፡፡ እንዲያውም እንደማታውቀኝ ዓይኗን እኔ ላይ ላለማሳረፍ ስትጥር ነበር፡፡ ይኼን ነገሯን ሳይ፣ እኔም ሰላም የማለት ዕቅዴን ተውኩትና ሩቅና ሩቅ ሆነን ተፋጠጥን፡፡ ቢያንስ ለእርሷ ጀርባዬን ሰጥቼ የምቀመጥባቼው ክፍት ወንበሮች ነበሩ፤ ግን ፊት ለፊቷ የምንተያይበት ወንበር ላይ ተጣድኩ፤ ደንብሬ መሆን አለበት፡፡

ድባቡ የሚጨንቅ ነበር፡፡ በመካከላችን እንደ ወተት የነጣ ልብስ የለበሱ ሦስት ከብ ጠረጴዛዎች አሉ። ሁሉም ጠረፔዛዎች ላይ፣ የሚያንጸባርቁ ሹካና ማንኪያዎች ተደርድረው፣ መኸላቼው ላይ፣ ብርጭቆ ውስጥ የቆሙ ደማቅ ጽጌሬዳዎች ተቀምጠዋል። በቀኝ በኩል ባሉት ሰፋፊ ወርደ ሰፊ መስኮቶች ላይ፣ ጣል የተደረጉት ነፋሱ ከውጭ ሲገፋቼው፣ መጋረጃዎቹ የእርጉዝ ሴት ቀሚስ መስለው፣ በአየር ይወጠሩና መልሰው ይረግባሉ፡፡ ነፋስ እያረገዙ ነፋስ የሚያስወርዱ መጋረጃዎች: ለመጀመሪያ ጊዜ ሳገኛት፣ እዚያ አንዱ ነጭ መጋረጃ አጠገብ ያለው ወንበር ላይ ተቀምጣ ነበር ያገኘኋት። በየጥጋጥጉ ከተሰቀሉት ስፒከሮች፣ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ይፈሳል፡፡ ከማሂሰላም ኋላ ያለው ግድግዳ፣ በትልቅ “ካንቫስ” ላይ በታተመ ፎቶ ተሸፍኗል፡፡ ስስ ነጫጭ መጋረጃዎች፣ ከውጭ በሚ7ፋቼው ነፋስ ረጋ ብለው ይንቀሳቀሳሉ። የወይን ጠርሙዝ ነው...ዘንበል ብሎ፣ ከውስጡ ወይኑ እንደ ፏፏቴ ቁልቁል ይወርዳል....ቀይ ደም የመሰለ ፏፏቴ...ጨነቀኝ። ቀጥሎ በመጋረጃው በኩል የሚገባው ስስ ነፋስ፣ ወደ አውሎ ነፋስ ተቀይሮ ቤቱን የሚገለባብጠው፣ የጠርሙዙ ወይን ወደ ጎርፍ ተቀይሮ እንደ ባሕር ቤቱን የሚሞላው ...የሆነ እንደዚያ ዓይነት ትርምስ ነገር እንደሚፈጠር ያወቅሁ ያኽል ጨነቀኝ፡፡ ማሂ ሰላም፣ የባሏን እጆች በእጆቿ እያሻሼች በዝምታ ታዬዋለች፤ እሱን ለነካችው፣ የእጇ ልስላሴ እኔን ይሰማኛል፡፡ ባሏ ሳያቋርጥ ያወራል፤ምን እንደሚያወራት እንጃ። ገና በአንድ ዕይታ እንደማታፈቅረው አውቂያለሁ፡፡ዓይኖቼ ሴት ላይ ፈጣን ናቸው። እንኳን አራት ዓመት አብራኝ የቆየች ሴት፣ በታክሲ እየከነፍኩ በቅጽበት የማያት ሴት ፊት ላይ ያለች ተንኮል አልስትም ብል፣ ቢጋነን እንጂ የለዬለት ቅጥፈት አይሆንም፡፡ ማሂሰላምና ባሏ አልተቀላቀሉም ዘይት እና ውሃ ነበሩ፡፡ ስታፈቅር እንደምትሆነው ዓይኖቿ ዙሪያዋን አልረሱም፤ ይቃብዛሉ፤ ዙሪያዋን ትቃኛለች። ስታፈቅር እንደዚያ አይደለችም፡፡ ያፈቀረችው ላይ ብቻ የሚተከሉ ዓይኖች ነበሩ ያሏት። ምስክር ነኝ በእሷ ተፈቅሬ ነበርና፡፡ አንድ ጠባብ ክፍል፣ _ የምታፈቅረው ሰውና ትርኢት የሚያሳይ ዝሆን ተቀምጠው፣ ያንን ዝሆን አየሽው? ብትባል፣

የቱን? የምትል፤ ላፈቀረችው መሰጠት ተፈጥሮዋ የሆነው ማሂሰላም፣ እሱ ላይ ብቻ እልነበሩም ዓይኖቿ።.. አይታኛለች፣ ያውም ገና ስገባ- ከሩቅ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለው ድራማ ነበር፡፡ ጥሩ አፍቃሪ እንጂ፤ ጥሩ ተዋናይ አልነበረችም፡፡ ባሏ ጋር በጨረፍታ እያዬኋቼው “ከሩቅ ሲያዩን ይኼን ነበር የምንመስለው?” እላለሁ፣ ለራሴ ...አሁንም ቆንጆ ናት ...አሁንም ቀለል ባለ አለባበስ ነበረች፡፡ከላይ ቀያይ አበባ ጣል ጣል ያለበት፣ ነጭ፣ ሰፊ፣ ስስ ሸሚዝ ለብሳለች ...ጡቶቿ ተለቅ አሉብኝ ...ይኼ ሰውዬ ምን አድርጓቼው ነው!? ...ምናልባት ከአሜሪካ ልኳ ያልሆነ የጡት ማስያዣ አምጥቶላት ይሆናል ማን ያውቃል? መቼስ መተዋወቅ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ለማሂ ጡቶች ዓይኔን ጨፍኜ የጡት ማስያዣ ብመርጥ፣ ቁጥሯን አልስተውም፡፡ በዚያ ቅጽበት ያስታወስኩት ነገር፣ በአራት ዓመት ቆይታችን አንድም ስጦታ ሰጥቻት አለማወቄን ነው። በአጋጣሚ ከመደርደሪያው ላይ መጽሐፍ አንስታ ልውሰደው? ካለችኝ ውሰጅው እላታለሁ፤ በቃ። ሸሚዟን ሳይ ድንገት ከስንት ጊዜ በኋላ እቤቴ የረሳችው “የውስጥ ልብስ” ትዝ አለኝ። ከጠረጴዛው ስር እግሯ ይታዬኛል፤ የአንድ እግሯን ጫማ አውልቃ በጫማዋ ትጫዎታለች፤ የቆዬ ልማዷ ነበር። ጸጉሯ ግን ተቀይሯል፣ እንደ በፊቱ በቼልታ አለቀቀችውም፣ በሥርዓት ተሠርቷል። ሲመቼው እንደሚሆነው፣ ጥቁርና የሚያብረቀርቅ ጸጉር፡፡ እንዲህ ጠቁሮ ዓይቼው አላውቅም፤ ዐሥር ጊዜ ጸጉሯን ትነካካለች፡፡ ከሴቶች አጥብቄ የምጠላው ባሕሪ! ሳውቃት እንደዚያ አልነበረችም፡፡ ዓይኖቼ እጅ ሆነው ልስላሴዋ እንዲሰማኝ አድርገውኛል-ሙቀቷም...ሰውነቴ ሲነቃቃ ይሰማኛል፡፡ ፊት ለፊቷ ነው የተቀመጥኩት- ከባሏ ኋላ...መልኩ አይታዬኝም፤ ሁለት ጆሮዎቹ ከርፈፍ ያሉ፣ ከኋላ እንዲሁ ጎልማሳ የሚመስል፣ጸጉሩ ላይ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት፡፡ በትከሻው ላይ አሻግራ ታዬኛለች፣ እንደምታዬኝ ሳላያት አውቃለሁ፡፡ አስተናጋጁ ሊታዘዘኝ መጣ፤ ፊቱ ላይ የእፍረት ፈገግታ አለ፡፡ ያውቀኛል‐ያውቃታል፣ ያውቀናል፡፡ ትንሽ እንደምቆይ ነገርኩት…“ለምን ትቆያለህ? መጥታለች'ኮ!" አለማለቱም ጨዋ ሆኖ ነው፡፡ እስቲ የሚመጣውን ጉድ ልይ! ብሎ ነው መሰል

ትሪውን አቅፎ የታፈነች ዓይንአፋር ፈገግታው ስትከስም አንድ ጥግ ቆመ (እንዲህ ትርኢት ለማዬት ከጓጓ፣ለምን ረዘም ረዘም ያሉ ቢላዋዎች ከወጥቤት አምጥቶ! አንድ ለእኔ፣ አንድ ለባሏ ሰጥቶ ፍልሚያ ጀምሩ አይለንም?) አስተናጋጁ እኔጋ ደርሶ ሲመለስ፣ ድንገት ማሂሰላም ጋር ዓይንለዓይን ተገጣጠምን፡፡ ፊቷ ብስጭትና ጉጉት ሲያንዣብብበት ታዘብኩ። የተበሳጨችበትን ለመረዳት ትንሽ ደቂቃዎች ነበር የወሰደብኝ። እሷ ጋር እዚህ ቤት ስንመጣ ቀድሚያት ከደረስኩ፣ ምንም ነገር ሳላ'ዝ እንደምጠብቃት ታውቃለች፡፡ ምንም አለማዘዝ የሆነች ሴት የመጠበቅ ምልክቴ ነው። ምክንያት ኖሮኝ ሳይሆን፣ ደመነፍሳዊ ልምድ። ጨራርሰው ስለነበር፣ ባሏ የወንበር መደገፊያው ላይ ያንጠለጠለውን ጃኬት ሊያነሳ ዞር ሲል፣ የሆነ ነገር አለቸውና መልሶ ተቀመጠ፡፡ አስተናጋጁን በምልክት ጠርታ ቡና አዘዘች፤ ከሩቅ በከንፈሯ እንቅስቃሴ ነው ቡና ማዘዟን ያወቅኩት
👍56🤔2🥰1
"ቡና" ስትል ውብ ከንፈሯ እንደሚያፏጭ ሰው ሰብሰብ ብሎ በትንሹ ከፈት አለ፤ ማሂ ሰላም ቡና አትወድም፣ ለመቆዬትና የቀጠርኳትን ሴት ለማዬት እንደፈለገች ገብቶኛል፡፡ ስልኬን አወጣሁና የቀጠርኳትን ልጅ ይቅርታ ጠይቄ የቀጠሮውን ቦታ ቀዬርኩ፡፡ ተነስቼ ስወጣ ማሂ ያዘዘችውን ቡና ይዞ የሚመጣው ሌላ አስተናጋጅ ጋር ተላለፍን፡፡ እዚህ ቡና ውስጥ ገብቼ ብሟሟ... የሚል ሐሳብ ውልብ አለብኝ፡፡ ላለፈው ሕይወት ቀንቻለሁ፤ ለሚመጣው ደግሞ ጓጉቻለሁ! ሁሉም አይለፈኝ የሚል በሽታ፡፡ በቀጣዩ ቀን ጧት ገና ከእንቅልፌ ሳልነቃ ስልኬ ጠራ...ማሂ ሰላም ነበረች፡፡ ክፉኛ ደንግጫለሁ፡፡ በስንት ጊዜዋ! ልክ ስልኩን ሳነሳው አብረን እንዳደርን ሁሉ ሰላምታ ሳታስቀድም

“ማናት? አብርሽ!'' አለችኝ፡፡ ድምጿ ውስጥ ፍርኃት ነበር፣ ... ቅናት ነበር፣... እልኅ ነበር !

“ሰላምታ አይቀድምም...?" አልኩ የሆነ የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቶኛል፣ እስቲ ማሸነፍን ምን አመጣው? “ሰላም!..... አውቃለሁ በአንተ ሕይወት አይመለከተኝም...ግን ማ'ናት?'' የደከማት መሰለች አሁን ደግሞ። “ባክሽ! እሱን ተይው ትላንት አዬሁሽ...በጣም አምሮብሻል። በጣም ነው ያማርሽው፡፡ ለምንድን ነው ሰላም ያላልሽኝ ግን?'' አልኳት፡፡ ልክ ያልኩትን እንዳልሰማች ድርቅ ባለ ድምፅ “ማናት?'' አለችኝ! "ጓደኛዬ ነው!'' በረዢሙ ተነፈሰችና፣ ለራሷ በሚመስል ድምፅ ... “አውቃለሁ! የቀጠርከው ወንድ አልነበረም፣ ውሸት አያምርብህም!'' አለችኝ ፡፡ ዝም ተባብለን ቆዬን፡፡ ከኋላዋ ሙዚቃ ይሰማኛል፡፡ “ለምንድን ነው ግን የማታገባው? ...ቢያንስ በዬሬስቶራንቱ ከመዞር ታርፋለህ" አለችኝ። እንዲሁ ዝም ከማለት የተናገረችው ነገር ነበር የሚመስለው። “አንቺ መቼ አረፍሽ?'' ሳቀች...የሆነ ለስላሳ ድምፅ የሌለው ሳቅ፣ ትንፋሿ ነበር እንደሳቀች የሚያሳብቀው፡፡ ከመጀመሪያው በረዘመ ዝምታ ከቆዬን በኋላ “ስትናፍቀኝ እሄዳለሁ! የእውነት ትናፍቀኛለህ...ምናባቴ ይሻለኛል? ግን'ኮ ጥሩ ሰው አይደለህም፣ ምንሀም ለሴት ጥሩ አይደለም፣ ግን...ትናፍቀኛለህ` ዝም አልኩ...ዝም ተባብለን ቆዬን!...ከኋላዋ ዘፈን ይሰማኛል፡፡ ከረዢም ዝምታ በኋላ ....ለመስማት በሚያስቼግር ድምፅ፣ “አርግዣለሁ" አለችኝ፡፡

ይኽ ከሆነ ከሦስት ዓመት በኋላ ይመስለኛል፣ እዚህ ቦሌ ኤድናሞል የሚባል ሕንፃ ላይ ማሂሰላምን ዳግመኛ አዬኋት፤ አንዲት የምታምር ሕፃን ይዛ። ዓይኔን ማመን አልቻልኩም። ያቺ በአዋቂ ቀራፂ የተሠራች የምትመስል ውብ ሴት የለችም፤ የጤና ነው ወይ? እስከምል በማይታመን ውፍረት ተውጣ ነበር! “ወላድ በድባብ ትሂድ ቆንጆ ሞልቷል” ቢባልም የማይደገሙ መልኮች አሉ፤ የሴት ልጅ ውበት እንደ እጅ አሻራ ነው፤ የአንዷ ሴት ውበት ሌላዋ ላይ ፈጽሞ አይደገምም፤በተለይ የማሂሰላም የሚደገም አይመስለኝም። የኔ ዘመን ማስታወሻዎች፣ የፊታውራሪ ማንትስ ቤትና የከተማዬ ተራራ ብቻ አይደሉም፤ እነዚያ ውብ ሴቶች ናቸው፡፡ ቤት ሲያፈርሱ ቢያንስ ሰበብ አለው “የተሻለ መገንባት ምናምን' የሴት ልጅ ውበት ግን መቼም በምንም የማይተካ ቅርስ ነው። እንደ አበባ የሚከስሙ፣ ቅርጽና ውበታቼው እንዲህ የሚቀዬር ቅርሶች፤ ከትዳር አድማስ ማዶ የሚጠልቁ ውብ የጧት ፀሐዮች፤ ትዳር ስጠላ! እሷን ባላፈቅራትም __ ከአምልኮ የማይተናነስ ጥሞና ውስጥ የሚያስገባኝ ውብ ሰውነቷ፣ በጊዜ እንዳይለወጥ በምን ዓይነት ጥበብ ጠብቄ ባኖርኩት? እል ነበር! ... አሁን በዚያ የለም፤ ፎቶዋ የለኝም፡፡ ፎቶ ሙቀት የለውም ይቀዘቅዛል፣ የቆንጆ ሴት ፎቶ ለእኔ ውበቷን ዘላለማዊ ለማድረግ አድርቀው የሆነ የመስተዋት ቤት ውስጥ እንዳስቀመጧት ውብ ቢራቢሮ ነው፡፡ ነበር ውስጥ ሙቀት የለም!! እንዳገባት በአንደበቷ ሳይሆን በድርጊት፣ በዓይኖቿ በመላ ሰውነቷ ተማጽናኛለች። እያንዳንዱ ቆዳዋ ላይ ያለው ጥቃቅን ሽንቁር፣ ሚሊዮን አፍ ሆኖ በሚሊዮን ቋንቋ ለምኖኛል ... ማንም ቢሆን ለእብደቱ ለደስታው ቋሚ ርስት ይፈልጋል፤ ርስቷን ነው

የነጠቅኋት ... እናም ወደማታውቀው ርስት ተሰደደች የእሷ ወዳልሆነ፤ ባሏ የስደት ምድር እንጂ ሰው አልነበረም። ስደተኛ ገላዋ ስደተኛ ባል አገባ፤ ጠመንጃ አንስታ ሰውነትሀ ርስቴ ነው መልስ አትል ነገር፤ ለጦርነትም እኮ _ጸንቶ የሚቆም ተፋላሚ ያስፈልጋል፡፡ የሐሴት ምርት ያፈስኩበት ችግኝ ሆኜ መጥቼ ዛፍ የሆንኩበት፣ እንቡጥ ሆኜ መጥቼ አበባ የሆንኩበት፣ ንብ ነህ ወዳጄ ስታርፍብኝ “ኔክታሬን' ስትቀስም አልከለከልኩህም፤ አሳልፈህ ዝንብ እንዲሰፍርብኝ ለምን ተውከኝ!?... የሚል ሙሾ ይወርዳል በሐሳቤ፡፡ ከጀርባዋ ዝም ብዬ አዬኋት ከምንም በላይ የገረመኝ ማሂ ሰላም ተረከዘ ረዥም ጫማ ተጫምታ ነበር። ጠይምነቷ ወደ ቀይ ዳማነት መንገድ ጀምሯል (ወይስ ሜካፕ ተጠቅማ ይሆን?) ዝም ብዬ አዬኋት፤ የመኪና ቁልፍ አንጠልጥላለች- ከንቱ! ውድ ቦርሳ ይዛለች- ከንቱ! ውድ ስልክ ይዛለች- ከንቱ! አለባበሷ የሐብታም ሴት ወይዘሮ ይመስላል- ከንቱ! ያቺ ለአካባቢዋ ግድ የለሽ የነበረች ልጅ አንዴ ልብሷን አንዴ ጸጉሯን ታስተካክላለች፣ አካባቢዋን ቀና እያለች ትቃኛለች፣ እንደ ጅራታም ኮከብ ትጣደፋለች፤ እኔ ውስጥ ግን ልክ እንደ ማታ ጀምበር በቀስታ ነበር የጠለቀችው፡፡ ከጎኗ ድክ ድክ የምትል ልጇ ጋር ...ሄደች ...ሄደች ... ሄደች ...ሄደች... ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍445😁5😢3
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዶ/ር ሶፊያ ከአራት ወራት ቆይታ በኃላ ነበር ለሌላ ስራ ወደ ሀዋሳ የተመለሰችው፡፡ዛሬ አምስተኛ ቀኗ ነው፡፡መቼስ የሀዋሳ ውበት
ይበልጥ ፈክቶ ይበልጥ ጎልቶ የሚታየው በገዛ
እግር በዝግታ እየተጓዙ ሲያጣጥሙት ነው፡፡

ዶ/ር ሶፊያም ይሄንን እውነት በመገንዘብ
የእለቱን ስራዋን ካጠናቀቀች በኃላ የምሽቱን
አየር ነፋሻማነትና ተስማሚነትንም ከግምት
በማስገባት በእግር ዞር ዞር ለማለት ወሰነችና መኪናዋን ሆቴል ግቢ ውስጥ ትታ በእግሯ ወጣች፡፡ለ3ዐ ደቂቃ በከተማው ተሸከረከረች፡፡
ጉዞዋ አስደሳችና መንፈሷን ያረጋጋላት ቢሆንም ደከማት፤ ወደ ካፌ ጎራ ብላ እረፍት ለመውሰድ ከወሰነች በኃላ መልሳ ሀሳቧን
ቀየረችና ጫማዋን እያስጠረገች ወጪ
ወራጁን መቃኘት እንደሚሻላት አመነች፡፡

ባለችበት አስፓልት አቅጣጫ ጠርዝ ላይ
ወዳለው ሊስትሮ አመራች፡፡ ሊስትሮው ከጐኑ በግምት መቶ የሚሆኑ መፅሀፎች ለሽያጭ ዘርግቷል፡፡እሱም ሊስትሮ ወንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ በተመስጦ እያነበበ ነው፡፡ተጠጋችው ፤ግንብ አጥር ተደግፎ የሚገኘው አግዳሚ ወንበር ላይ ቁጭ አለች፡፡

‹‹አንተ ነህ የምትጠርገው?››
ቀና ሳይል <<አዎ እኔ ነኝ፡፡ግን አሁን ስራ ስለያዝኩ እዛ ማዶ ያለው ልጅ ጋር ብታስጠርጊ››አላት በትህትና፡፡

ደነገጠች<< ...አዋ እራሱ ነው፡፡››አወቀችው ፡፡ የዛሬ ወር ሚኒባስ ውስጥ 2ዐዐ ብር ያበደራት ልጅ፡፡ ደነቃት፡፡ በምንም አይነት ሊስትሮና መፅሀፍ ሻጭ ይሆናል ብላ አልገመተችም
ነበር::

<<ችግር የለም ጨርስና ትጠርግልኛለህ ... አልቸኩልም፡፡››አለችው፡፡
ንባቡን እንደቀጠለ ‹‹እንደተመቸሽ፡፡››አላት ፡፡
ከአስር ደቂቃ ጥበቃ በኃላ የሚያነበውን መፅሀፍ አጥፎ አስቀመጠና ቀናም ብሎ ሳያያት ወደ መሬት ወርዶ እግሯን የሊስትሮ ዕቃው ላይ እስክታስቀምጥ ጠብቆ ጫማዋን ያፀዳላት ጀመር፡፡

‹‹‹ይቅርታ የምንተዋወቅ መሰለኝ?››አለችው፡፡
ቀናም ብሎ ሳያያት ‹‹ይሆናል፡፡››

‹‹አስታወስከኝ ግን?››

‹‹ስለአንቺ እያሰብኩ ስላልነበረ አላስታወስኩሽም፡፡››

‹‹አንድ ቀን ከአዲስአባ ስንመጣ ሚኒባስ ውስጥ ብር አበድረኸኝ ነበር››
ማንነቷን ለማረጋገጥ ቀናም ብሎ ሳያያት ስራው ላይ እንዳቀረቀረ ‹‹አስታወስኩ፡፡››አላት፡፡

‹‹እንዴት እንደዛ ትሸውደኛለህ ግን?››

‹‹መስሎሽ ነው፡፡››

<< መስሎኝማ አይደለም፡፡በወቅቱ አንተን ለማግኘት እኮ ሀዋሳን ቀላል አላሰስኮትም፡፡››

‹‹እኔን ለመፈለግ እኮ የዛን ያህል መልፋት አልነበረብሽም፡፡እኔ ማለት ያ ዕብድ ነኝ፣እኔ ማለት ያቺ ሁለት ልጆች ስሯ አስተኝታ የምትለምነው እናት ትታይሻለች ..እሷ ማለት ነኝ፣እኔ ማለት የተራበ ጨቅላ፣የታረዘ አዛውንት ማለት ነኝ፡፡››

‹‹እሱ ገብቶኛል፡፡ባልከው መንገድም ለማድረግ ሞክሬያለው ግን ደግሞ አንተንም አግኝቼ ማመስገን ውስጤ በጣም ፈለገ፡፡››

‹‹እሺ ይሁን፤ምስጋናውን ተቀብዬለሁ፡፡››

‹‹እንደዚህማ በደረቁ አይሆንም፤ ቢያንስ እራት ጋብዤህ ነው ማመስገን የምፈልገው፡፡››

‹‹ደስ ይለኝ ነበር ፤እኔ ግን እራት የምበላው ከጓደኞቼ ጋር ነው፡፡ >>

‹‹‹ምን ችግር አለው ታዲያ ፤ደውልላቸውና ይምጡ፤አብረን እንበላለን፡፡›› በቀላሉ ልትለቀው አልፈለገችም፡፡

‹‹ስልክ የለኝም፤እነሱም የላቸውም፤ቤት ነው ሚጠብቁኝ፡፡››

<<በቃ ችግር የለውም ፤አብረን እንሄድና ይዘናቸው እንወጣለን፡፡››

‹‹ለምን ትቸገሪያለሽ?››

‹‹አልተቸገርኩም፡፡››

<<እኛ የምንበላው እዛው ሰፈር ነው፤ያ ደግሞ ላንቺ የሚመችሽ ቦታ አይደለም፡፡››

‹‹ግድ የለም ይመቸኛል፡፡››

‹‹እንግዲያው እኔ አንድ ሰዓት ነው ከዚህ የምነሳው፤አሁን 12 ሰዓት ነው ፤ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ተመልሰሽ ነይ፡፡ >>

‹‹አይ እዚሁ እጠብቅሀለው፡፡››አለችው፡፡

አፍጥጦ አያት፡፡ሰው እንደዚህ ችክ ሲልበት አይወድም፡፡‹‹ ግን ምን ቸገረኝ፤የራሷ ጉዳይ... መቀመጡ ሲደክማት ተነስታ ትሄድ የለ›› ብሎ ወደ ንባቡ ተመለሰ፡፡እሷም ወጪ ወራጁን እያየች ስለ እሱ ማሰብ ጀመረች ፡፡በአጋጣሚ በእጇ ገብቶማ ዳግመኛ አያመልጣትም፡፡ 12፡ 3ዐ ላይ ስልኳ ጮኸ ፡፡ አነሳችው፡፡ የቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ነው፡፡

‹‹ሄሎ ልዑል፡፡››

‹‹አመሰግናለሁ..ሌላ ቀጠሮ አለብኝ፡፡››

‹‹አዎ ፡፡አንድ የድሮ የልብ ጓደኛዬን በአጋጣሚ አግኝቼ እራት ካልጋበዝኩሽ ስላለ ከእሱ ጋር ነው የማመሸው፡፡››

‹‹እሺ..ቻው አመሰግናለሁ፡፡››

ለአንድ እሩብ ጉዳይ መፅሀፎቹን ሰበሰበና በቦርሳውን ጠቀጠቃቸው፡፡ አንዱን በአንድ ተከሻው ሌላውን በሌላ ትከሻው አነገተና የሊስትሮ ሳጥኑን በቀኝ እጁ በመያዝ
መንገዱን ቀጠለ፡፡ተከተለችው፡፡እሷ እሱ የገረማትን ያህል እሱም ገርማዋለች፡፡ እንዲህ ችኮ ሴት ገጥሞት አያውቅም፡፡.

ወደ እሱ ቤት ጉዞ ጀምረው ግማሽ መንገድ ላይ እንደደረሱ‹‹ስሜን አልጠየቅከኝም?›› አለችው ፡፡

‹‹ስላላስፈለገኝ ነው ያልጠየቅኩሽ›› አላት፡፡
‹‹መተዋወቅ እኮ ክፋት የለውም፡፡››

‹‹ክፋት አለው መች ወጣኝ?፡፡››

‹‹ሶፊያ እባላለሁ...ያንተስ?››

‹‹ከዚህ በፊት በፈለገሽው ስም ልትጠሪኝ ትችያለሽ ብዬሽ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ስም መለያ ነው፣እኔነቴን አይወክልም፡፡ አንቺ እኔን ከሌላ የሰው ልጅ ለይተሸ ለመጥራት ያስፈልገኛል ካልሽ የሚመችሽን ተጠቀሚ፡፡››

‹‹ሶቅራጦስ ይመችሀል?››

‹‹ዋናው ላንቺ ይመችሽ፡፡ይሄን ስም በፊት አንድ ታላቅና ቅዱስ ሰው ተጠቅሞበታል፡፡››

‹‹አውቃለሁ፤እኔም ለዛ ነው የመረጥኩት።

‹‹ደግ›› ይሄንን ሁሉ ሲያወሩ ብዙ የዉስጥ ለውስጥ መንገዶችን አልፈው ነበር፡፡ ግንብ አጥር ያለው ቤት ጋር ሲደርሱ የሊስትሮውን ዕቃ መሬት አስቀመጠና ከኪሱ በማውጣት መክፈት ጀመረ፡፡

‹‹5 ደቂቃ ጠብቂኝ መጣሁ፡፡ ››ብሏት እንደተገተረች ጥሏት ወደ ውስጥ ገባ ብትፈራም ጭለማ ውስጥ ቆማ መጠበቅ ጀመረች፡፡ ሰዓቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ሆኗል በአራት ህፃናት ተከቦ መጣ፡፡ ሁሉም እየቧረቁ ስሩ ኩስ ኩስ ይላሉ፡፡የሁሉዎ ተቀራራቢ ነው በ7 እና በ12 ዓመት መሀል ሲሆን ከአራቱ ሦስቱ ሴቶች ናቸው

‹‹ጓደኞችህስ?››

‹‹እኚው›› አላት ወደ ልጆቹ እየጠቆመ፡፡

ከፈለግሽ ተከተይን በማለት ከእነሱ ጋር በፈገግታ እያወራና እየተሳሳቀ ቀድሟት መንገዱን ቀጠለ፡፡ ብዙም ከማይርቅ አንድ መንገድ ዳር ካለ ደከም ያለ ምግብ ቤት ገቡ ፡፡ ተከትለቻቸው፡፡አንድ ጠረጴዛ ከበው ተቀመጡ፡፡አንድ ለእሷም ሳበላት ፤ ተቀመጠች፡፡

እርጅና የተጫጫናቸው አሮጊት ከጓዲያ ወጡና‹‹ ... ልጆቼ መጣችሁ? በስንት ጊዜያችሁ ፤ናፍቃችሁኝ ነበር፡፡››

‹‹ሰላም ኖት ማዘር?››ታዲዬስ ነው፡፡

‹‹ሰላም ነኝ ፤ይመስገነው፡፡ደግሞ እንግዳ ይዛችሁ ነው የመጣችሁት?››

‹‹አዎ... ምግብ ቤት አጥታ ስትንከራተት መንገድ ላይ አግኝተናት ነው ይዘናት የመጣነው፡፡››

‹‹በሞትኩት.. ለሀገሩ እንግዳ ነቻ?››መጣሁ ብለው ተመልሰው ወደ ውስጥ ገቡ፡፡

‹‹ስምሽ ማን ነው? አለቻት ጎኗ የተቀመጠችውን ትንሽ ልጅ ፡፡

‹‹ሶፊያ..ያንቺስ?››

<<ሚጣ ነው?»

‹‹ሚጣ ታዲዬስ››

‹‹እሱ ምንሽ ነው? አለቻት በጣቷ እየጠቆመች፡፡እሱን ቀጥታ ጠይቃ ማይሆን መልስ ሰጥቷት ከምትበሳጭ በጎን ትክክለኛ ስሙን ለማወቅ መሞከሯ ነበር፡፡

በተኮላተፈ አንደበት‹‹አባቴ›› ብላ መለሰችላት

‹‹አንቺስ እናት ስምሽ ማነው?››

<<ሄለን>>

<<ሄለን ማ?>>

‹‹ሄለን ታዲወስ››

‹‹አባትሽ ታዲወስ የታለ?››
👍6510👎1🔥1🤔1
‹‹እንዴ ይሄው፤ አታውቂውም እንዴ?›› በማለት ባላዋቂነቷ ሳቀችባት፡፡ ስለ እዚህ ልጅ ይበልጥ ለማወቅ በጣረች ቁጥር እየራቀባት መጣ‹‹ስንት እህቶች አሉሽ?››

<<አራት>>

‹‹ወንድሞችስ››

«አንድ»

<<እናታችሁስ>>

<< እናት የለንም፤ የሁላችንም ሞተዋል፡፡››
በዚህ ጊዜ አሮጊቷ በትሪ ሙሉ እንጀራ ቆልለው
ልሙጥ ሽሮ በላዩ ላይ ፈሰስ አድርገው ይዘው
በመምጣት መሀከል ላይ አስቀመጡ፡፡ልጆቹ
መብላት ጀመሩ ፡፡ እሷም ልክ እንደነሱ ለራሷም እየጎረሰች እነሱንም እያጎረሰች ተመሳሰለቻቸው፡፡ ያሮጊቷ ሽሮ እንደሚታየው
አይደለም፤ልዩ ጣዕም አለው፡፡ ከአስር አመት
በፊት የሞቱትን አያቷን አስታወሳት፡፡ እሳቸው
ነበሩ እንዲ አይነት ሽሮ ያበሏት የነበሩት፤ ከዛ
በኃላ ግን በአጋጣሚ እንኳን እንደዚህ አይነት ምግብ አግኝታ አታውቅም፡፡ ሆቴል
ከምትበላው ምግብ ጋር ሲነፃፀር ልዩነቱ የትየለሌ ቢሆንም ለእሷ ግን መሰጣት፡፡
ከጨረሱ በኃላ የምግብ ሂሳቡን ልትከፍል ስትል ቀድሟት ከፈለ ፡፡ስለፈራችው ብዙ
አልተከራከረችውም ፡፡ ከምግብ ቤቱ ወጡ…፡፡

‹‹ጨለማው ያስፈራል ልጆቹን ላስገባና እሸኝሻለሁ፡፡››

‹‹እሺ ››ብላ ተከለተለችው፡፡እንደቅድሙ ግን ከአጥሩ ውጭ ቆማ ልትጠብቀው
አልፈለገችም ፡፡ከልጆቹ ጋር ተጋፍታ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ግቢው ሰፊ ነው፡፡ አምስት ሰርቪስ ቤቶችና አንድ በጣም ዘመናዊ የሆነ የተንጣለለ ቪላ ቤት አለ፡፡ ከሰርቪሶቹ ውስጥ አንዱን ተከራይቶ እንደሚኖር ገመተች፡፡ልጆቹ ግን ወደ ትልቁ ቤት እየተሯሯጡ ገቡ፡፡በረንዳ ላይ ሲደርሱ ቆመና << እንግዳዋን ሸኝቼያት መጣሁ እግራችሁን እየታጠባችሁ ጠብቁኝ›› ብሎ ፊቱን ሲያዞር እሷ ከህፃናቱ ጋር የቤቱን በራፍ አልፋ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ቤቱ ከስምንት በላይ ክፍሎች ከሰፊ ሳሎን ጋር ከነ ሙሉ ቤት ዕቃው አለው፡፡ ረጅሙ ሶፋ ላይ አንድ የአስር አመት ልጅ ፎጣ ለብሳ ተኝታለች፡፡

‹‹ቅር ካላለህ ትንሽ ብቆይ? ››አለችው፡፡

‹‹በንዴት ፊቱን እንዳጠቆረ ምንም ሳይመልስላት አልፎት ወደ አንደኛው ክፍል ሄደና ከፍቶ ገብቶ ዘጋው፡፡መኝታ ቤቱ እንደሆነ ገመተች፡፡

እሷም በቀስታ እርምጃ ወደ ተኛችው ልጅ በመሄድ ከጎኗ ሶፋው ላይ ተቀመጠች፡፡

‹‹ስምሽ ማነው?››

«ሠላም»

‹‹ሠላም ማን?››ተመሳሳይ መልስ መለሰችላት፡፡

‹‹ምንሽን ነው የሚያምሽ?››

‹‹እግሬን፡፡››

‹‹እኔ ዶክተር ነኝ፤ልይልሽ?››

‹‹እሺ›› ብላ ፈቀደችላት፡፡ቀስ ብላ የለበሰችውን ብርድ ልብስ ገልጣ ስታይ ዝግንን አላት፡፡ የልጅቷ ቀኝ እግር ጥምዝዝ ብሎ እንዳልሆነ ሆኗል ፡፡ ጣቶቿ አቅጣጫቸውን ለውጠው በተቃራኒው ናቸው ፡፡ግን አዲስ ጉዳት አይደለም፡፡እንደተጠማዘዘ የዳነና የቆየ ነው፡፡

‹‹ምን ሆነሽ ነው ሰላም?››

‹‹ልጅ ሆኜ አባቴ ነው እንዲህ ያደረገኝ፡፡››

ደነገጠች

‹‹ታዲዬስ ነው እንዲህ ያደረገሽ?››

‹‹ኧረ አይደለም ..አይደለም>>
ልጅቷ ተንገፈገፈች፡፡

‹‹አይ አባቴ ስላልሺኝ እኮ ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ያ ክፉውን የድሮውን አባቴን ማለቴ ነዋ፡፡ሊለምንብኝ ነው እንዲህ ያበለሻሸኝ፡፡አሁን ግን የለም ታስሯል..ታዲ ነው ያሳሰረው፡፡››

‹‹አሁን ታዲያ እንዴት አመመሽ..አልዳነልሽም ነበር?>>

‹‹አይ ድኖልኛል ...ግን ሰሞኑን ወለም ስላለኝ ነው ህመሙ የተነሳብኝ፡፡››

‹‹እኔ ዶክተር ስለሆንኩ ነገ መድሀኒት ይዤልሽ መጣና ትድኚያለሽ እሺ፡፡››
‹‹ታዲ እኮ ሀኪም ቤት ወስዶኝ ነበር.፡፡ መድሀኒትም ተሰጥቶኛል፡፡››

‹‹አይ ጥሩ ነው››ብላ ትኩረቷን ወደ ሌሎቹ ልጆች ስትመለስ ተለቅ ተለቅ ያሉት የትናንሾቹን እግር እያጠቡ ተመለከተች፡፡

‹‹አንቺ የታዲዬስ ምኑ ነሽ?›› ጠየቀቻት ሰላም፡፡

‹‹ጓደኛው፡፡››

<<ጓደኛ እኮ የለውም፤አንቺን ከየት አገኘሽ?››

‹‹ብቻውን ነው እንዴ የሚኖረው?››ሚስት የለውም ወይ ለሚለው የውስጥ ጥያቄዋ መልስ ለማግኘት የተሰነዘረ ጥያቄ ነው፡፡

‹‹አይ አይደለም፤ከእኛ ጋር ነው ሚኖረው፡፡ ብታይ በጣም ነው የሚወደን ፡፡እኛም ውድድ ነው ምናደርገው፡፡››

ወሬዋን ሳትጨርስላት ታዲዬስ ከተከተተበት ክፍል ወጣ፡፡ ወደ ቴሌቨዥኑ ሄደና የህፃናት የካርቶን ፊልም ከፈተ ‹‹ፊልም እያያችሁ ጠብቁኝ ሸኚቼያት ልምጣ፡፡›› ሲላቸው ሁሉም በአንድነት ‹‹እሺ ታዲዬ›› አሉት ፡፡ ከተቀመጠችበት ፍራሽ ተነሳችና ሠላምን ግንባሯን ስማት ሌሎቹን ጉንጫቸውን በመሳም ተሰናብታቸው ወጣች፡፡የውጭ በራፉን ከፍተው እንደወጡ‹‹ታድለህ›› አለችው ምን ብላ ከእሱ ጋር ወሬ እንደምትጀምር ግራ ገብቷት፡፡

‹‹ለምኑ?>>

‹‹ልጆችህ በጣም ይወዱሀል፡፡››

‹‹እኔም በጣም እወዳቸዋለሁ፡፡››

‹‹ግን እነዚህን ሁሉ ህፃናት ያለእናት ማሳደግ በጣም አይከብድም?››

‹‹አይከብድም፡፡ልጆቹ የተንደላቀቀ የቅምጥል ኑሮ የለመዱ አይደሉም፡፡ ይህቺን ህይወት ሀ ብለው ሲጀምሩ በጣም ከከፋ እና ከዘቀጠ የድህነት መንደር ውስጥ ነው ፡፡እኔ ከእዛ ትንሽ የተሻለ ነገር ነው የማደርግላቸው፡፡ከበረንዳ ማደር ወደ ቤት ውስጥ፤ ጆንያ ከመልበስ ብርድልብስ ወደ መልበስ፤ ትርፍራፊ እና የተጣለ ምግብ ከመመገብ ልሙጥ ሽሮም ቢሆን መብላት... ይሄው ነው ብዙ አይጠይቁኝም፤ይሄንን ማድረግ ደግሞ አይከብደኝም፡፡››

‹‹ግን እኮ ብቻህን ከምትቸገር ብዙ በህፃናት ላይ የሚሰሩ እርዳታ ድርጅቶች አሉ ፤ኮምንኬት ብታደርጋቸው ይረዱሀል፡፡››

‹‹እኔ እርዳታ አልፈልግም ፡፡እነሱ ከፈለጉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ህፃናት በየመንደሩ እና በየጎዳናው አሉ፡፡እነዚህ የእኔ ድርሻ ናቸው፡፡ ምን አልባት በምቾት እያኖርኳቸው መስሎ ያልተሰማሽ ከሆነ የተሳሳትሽ ይመስለኛል፡፡ እነዚህን ልጆች ግን ከምንም ነገር በላይ የሚርባቸው ፍቅር ነው፡፡ደግሞ እነዚህን ልጆች የማሳድጋቸው ደሀ ወይም ወላጅ አልባ
ስለሆኑ ከመሰለሽ ተሳስተሸል፡፡ሚጣ የኔ ልጅ ነች..ሌሎቹ አራቶቹ ደግሞ ወላጅ አልባ ብቻ ሳይሆኑ ጂኒዬሶችም ጭምር ናቸው..ለዛ ነው፡፡››

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹ተይው በቀላሉ አይገባሽም፡፡››

እውነትም የዚህ ልጅ ነገር በቀላሉ አይገባም፡፡ ሊስትሮ እየሰሩ አምስት ልጆች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ ማሳደግ፤ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፡፡ወሬያቸውን እልባት ሳያበጁለት ዋናው አስፓልት ጋር ደርሱ፡፡

‹‹አሁን ታክሲ ወይም ባጃጅ ያዢና ወደ ሆቴልሽ ሂጂ፤እኔም ወደ ልጆቼ ልመለስ፡፡››

‹‹እሺ ስለ እራት ግብዣው አመሰግናለሁ፡፡ ልጆችህን ደግሞ በጣም ወድጄያቸዋለሁ፡፡ አንተም ጥሩ አባታቸው ብቻ ሳትሆን እናታቸውም ጭምር ነህ፡፡ደግሞ ቅድም የተናገርከው ልክ ነው ፤ ለሰው ልጅ ምግብ ብቻ ሳይሆን ፍቅርም መሰረታዊ ነገር ነው ፡፡›.ብላው ተሰናበተችው፡፡ እሱም ፊቱን አዙሮ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ታዲዬስን እንዳገኘችው ለአንድ ወር ሙሉ በአዕምሮዋ ሲጉላላ የከረመውን ዕንቆቅልሽ በቀላሉ የምትፈታ መስሏት ነበር የተደሰተችው፡፡አሁን ግን ሌላ ተጨማሪ እንቆቅልሽ ጨምራ በመብሰልሰል ወደ ክፍሏ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ #Share እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅንነት እባካቹ👍
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8812😁4👎1🥰1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ዶ/ር ሶፊያ ከአራት ወራት ቆይታ በኃላ ነበር ለሌላ ስራ ወደ ሀዋሳ የተመለሰችው፡፡ዛሬ አምስተኛ ቀኗ ነው፡፡መቼስ የሀዋሳ ውበት ይበልጥ ፈክቶ ይበልጥ ጎልቶ የሚታየው በገዛ እግር በዝግታ እየተጓዙ ሲያጣጥሙት ነው፡፡ ዶ/ር ሶፊያም ይሄንን እውነት በመገንዘብ የእለቱን ስራዋን ካጠናቀቀች በኃላ የምሽቱን አየር ነፋሻማነትና ተስማሚነትንም…»
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟ሰውን የሚያስከብረው ጌጣጌጥ ነው ብለህ ጌጥ አታብዛ።የሰው ልጅ ክብሩ እውነተኛ ቃሉ እና ቅንነቱ መሆኑን ተረዳ ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟ተማረ ተመራመረ ብለህ ሰውን አታድንቀው ።ምንም ቢያውቅ ቢራቀቅ የሞቱን ቀን
አያውቅም ብለህ እዘንለት

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟የጋለ ምጣድ አትንካ ትቃጠላለህ።በስሜት ያበደን ሰው እይዛለሁ አትበል ታዝናለህ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟መንፈሳቸው እንደ ብረት ከቀዘቀዘባቸው ስዎች ጋር መኖር በጣም ከባድ ነው።አንተ እነርሱን
እስክታሞቅ እነርሱ አንተን ያበርዱሀልና ተጠንቀቅ ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟ፈረስ የፈለግበት ድረስ ያድርስህ እንጂ ፈረሱ የፈለገበት አትድረስ ። እንዲሁም ፍቅር
በሚመስል ነገር ስክረህ በከንቱዎች ምክር አትራመድ ።

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟መስማትና መስማማት ይለያያልና የስማህ ሁሉ የተስማማ መስሎህ አትዘናጋ ።
መስማማት ማድረግ ነውና የተስማማ ስውን በተግባር ታየዋለህ። ስዎች በጆሮ ሲስሙህ
ራሳቸውን ይነቀንቃሉ በልባቸው ሲያዳምጡህ ግን ከቀድሞ   ስህተታቸዉ ይርቃሉ ::ይለወጣሉ::
ተረድተውሀላ!!

#ወዳጄ_ሆይ!

🌟ንግግርህ ፣አስተሳስብህን ፣ኑሮህን የምትመራበትን መመሪያህን ማሳያህ ነውና  ንግግርህን በማስተዋል አድርገው
አፍና በራፍ እኩል ይከፈታል።❤️

ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ ለ500 እኮ ትንሽ ነው የቀረው እባካቹ ቤተሰቦች
ሰብስክረይብ እያረጋቹ ያደረጋችሁ ደግሞ ሌሎች እዲያደርጉ #Share እያደረጋቹ አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍28👏186🥰1
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዶ/ር ሶፊያ በማግስቱ ከምሽቱ 12፡3ዐ ላይ መኪናዋን እያሽከረከረች ታዲዮስ ቤት ደረሰች፡፡ሦስት ኩርቱ ፔስታል ሙሉ ስጦታ ይዛለች ፤ለአምስቱም ልጆች ፡፡በመከራ እየተንገዳገደች ነበር ዕቃዎቹን ተሸክማ በረንዳው ላይ ማድረስ የቻለችው፡፡መሬት አስቀመጠችውና በራፉን አንኳኳች፡፡ ሃያ አምስት ዓመት የሚሆነው ባለ ሹሩባ ፀጉር መልከ መልካም ወጣት ከፈተላት፡፡

‹‹አቤት ምን ነበር?››ዓይኑ ያልተለመደ ነገር በማየቱ የመገረም ፊት እያሳያት፡፡

‹‹ታዲዬስን ፈልጌው ነበር፡፡››

‹‹ይቅርታ ታዲ ከአንድ ሰዓት በኃላ ነው የሚመጣው፡፡››

<< አመጣጤማ ሰላምን ልጠይቃት ነበር፤የታዲ ዘመድ ነኝ፤ማታ እዚህ በነበርኩበት ሰዓት የሰላምን መታመም አይቼ ስለነበር አሳስቦኝ ነው፡፡››

ፈራ ተባ እያለ በራፉን በሰፊው ከፈተላት እና አንዱን ፔስታል ለእሷ ትቶ ሁለቱን ወደ ሳሎን ውስጥ በማስገባት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠላት‹‹እህት .. እንግዲህ አረፍ በይ ትንሽ ስራ ላይ ነን፡፡ ››ብሏት ጥሏት ሄደና በመደዳ ካሉት ክፍሎች መሀከል ወደ መጀመሪያው ክፍል ገባ፡፡ ሶፋው ላይ ቁጭ አለች፡፡ልጁ ከገባበት ክፍል አካባቢ የፒያኖ ድምፅ ይሰማታል፤የሚመስጥ ክላሲካል ሙዚቃ፡፡ዝም ብላ በደመነፍስ ባዶውን ሳሎን ለቃ የሙዚቃውን ድምፅ ተከትላ ወደ ክፍሎቹ መራመድ ጀመረች፡፡የመጀመሪያው ክፍል በራፍ አጠገብ ስትደርስ እርምጃዋን ገታችና ቆመች፡፡በራፉ ገርበብ ብሎ ስለነበር አንገቷን አሰገገች፡፡
እንደመጣች በራፉን የከፈተላትን ልጅ ሹሩባ ቀድሞ ታያት፡፡ይበልጥ ስትጠጋ ሠላምን አየቻት፡፡ በሹክሹክታ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባች፡፡ሠላም ወንበር ላይ ቁጭ ብላለች፡፡ ከፊቷ የስዕል ሸራ ተወጥሮላት ፊቷ በቀረበላት የተዘበራረቀ ቀለም በቀጫጫ እጆቿ የያዘችውን ብሩሽ እያጠቀሰች የሆነ ስዕል ትስላለች፡፡ወጣቱ ቀና ብሎ ሶፊያን ተመለከታትና መልሶ ቀልቡን ሰላም ወደምትስለው ስዕል መለሰ፡፡ ልትረብሻቸው ስላልፈለገች ክፍሉን በቀስታ ለቃ ወጣች፡፡

ወደ ሳሎን ልትመለስ ካሰበች በኃላ የፒያኖው ድምፅ የሚንቆረቆረው ከሚቀጥለው ክፍል እንደሆነ ስታውቅ ሀሳቧን ቀየረችና ወደዛው አመራች፡፡ገርበብ ያለውን ክፍል በተመሳሳይ ገፋ አድርጋ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ መሀከል ወለል ላይ አንድ መለስተኛ ፒያኖ ተመለከተች፡፡ አንድ ወጣት ግን አይነስውር የሆነች ምታምር ሴት ሁለቱን ሴት ህፃናት ተራ በተራ ጣታቸውን እየያዘች ታለማምዳቸዋለች፡፡ ግድግዳውን ተደግፋ በተመስጦ ትከታተላቸው
ጀመር፡፡ከአስር ደቂቃ ቆይታ በኃላ ዓይነ ስውሯ
አስተማሪ አዳምጡ አለቻቸውና ሁለቱን ሴት
ልጆች መቀመጫቸውን ይዘው እንዲቀመጡ

በማድረግ ጣቶቾን ፒያኖው ላይ ማርመስመስ ጀመረች፡፡ልጆቹ ብቻ ሳይሆኑ ዶ/ር ሶፊያም
ድንዝዝ ብላ ነው የተከታተለቻችው፡፡እሷ
እራሷም ከሙዚቃው ስልት ጋር ከወዲህ ወዲህ አንገቷን ስታወናጭፍ እረጅም ጥቁር ፀጉሯ በአየሩ ላይ ይበተናል፡፡የተመልካች ልብን
ስልብ ያደርጋል ፡፡ስትጨርስና ጣቶቾን
ስትሰበስብ ሳታስበው አጨበጨበችላት፡፡

ሁለቱም ህፃናት ልጆቹ እያቀፋ በመሳም
ፍቅራቸውን ገለፁላት፡፡
ሄለን ‹‹ፅዬንዬ እኔም ሳድግ እንደአንቺ መጫወት እፈልጋለሁ፡፡አንቺን መሆን ነው የምፈልገው፡፡››አለቻት፡፡
ፅዬን በግምት እጇን ወደ እሷ ላከቻና የለበሰችውን ጃኬት ይዛ ወደ ራሷ ጎትታት ጉያዋ ውስጥ ሸጉጣ አቀፈቻት ‹‹በቅርብ ቀን
እንደ እኔ ብቻ ሳይሆን ከእኔም በላይ ትጫወቺያለሽ፡፡ አንቺ ምርጥ ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ሀሊማ ደግሞ ምርጥ ድምፃዊ እንደምትሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡››ብላ በማበረታታት ጉንጯን ሳመቻት፡፡

ዶ/ር ሶፊያ ቀስ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣችና ሶስተኛው ክፍል ገባች፡፡ አንድ የአስራ ስምንት አመት ወጣት ሴት የአማርኛ ፊደል ተራ በተራ ብላክ ቦርድ ላይ እየፃፉች ሚጣን እያስተማረቻት ነው፡፡

እስከአሁን ያላየችው ወንዱን ልጅ ብቻ ነው፡፡ እሱ አራተኛው ክፍል ውስጥ ይሆናል›› ስትል ገመተች‹‹ለመሆኑ እሱስ ምን እየተማረ ይሆን?›› ለማወቅ በጣም ጓጓች.. ወደ አራተኛ ክፍል አመራች ፡፡እስከአሁን ካየቻቸው ሶስቱም ክፍሎች በተሻለ ይሄኛው በእጥፍ ሰፋት አለው፡፡ ግን ቤት ሳይሆን ኳተት ማጠራቀሚያ ክፍል ነው ማለት ይቻላል፡፡በኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች፣በብረታ ብረት ቁርጥራጮች፣በተበላሹ ቴሌቨዢኖች፣ሬዲዬኖች
ገመዳ ገመዶች ተሞልቷል፡፡ዕድሜው ከ1ዐ የማይበልጠው የሰውነቱ ግዙፍነት ግን የ15 ዓመት ታዳጊ የሚያስመስለው ድንቡሽቡሽ ልጁ ኮተቶቹ መሀከል ወለል ላይ ተዘርፍጦ ላፕቶፕ ኮምፒተር ላይ አፍጥጧል፡፡ድምፅ ብታሰማውም ሊሰማት አልቻለም፡፡ሹክክ ብላ ወጥታ ወደ ሳሎን ተመለሰች እና ስላየችው ነገር በግርምት ማሰላሰል ጀመረች፡፡

አንድ ሰዓት ሲሆን ሁሉም የእለት ስራቸውን አጠናቀው ከየአስተማሪዎቻቸው ጋር ከየክፍላቸው ወጡ፤ ከወንድዬው ልጅ በስተቀር፡፡ ሠላምንም አስተማሪዋ ደግፎት አመጣትና ከእሷ ጐን እንድትቀመጥ ከረዳት በኃላ‹‹ይቅርታ ቅድም በስራ መሀል ስለነበርኩ በቅጡ አላናገርኩሽም…የቤቱ ህግ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ስራ ይቀድማል፡፡አላዛር እባላለሁ፡፡››በማለት እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት፡፡ እሷም እየጨበጠችው‹‹ሶፊያ እባላለሁ›› አለችው፡፡

‹‹አሁን ሠላምን መጠየቅ ትችያለሽ..ያው ከጎንሽ አስቀምጪልሻለሁ፡፡ እኔ ሽንት ቤት ደርሼ መጣው›› ብሎ ወደ ጓሮ ሄደ ::

‹‹አመሰግናለሁ››ብላው የሰላምን ግንባሯን ሳመቻት፡፡

‹‹ትመጪያለሽ ብዬ ስጠብቅሽ ነበር ::>> አለቻት ሠላም በመምጣቷ መደሰቷን በፈገግታዋ እያረጋገጠችላት፡፡

‹‹ይሄው መጣሁልሽ፤ ለመሆኑ የሚያምሽ ተሻለሽ?»

‹‹አዎ ...ዛሬ ሚጠዘጥዘኝ ትቶኛል፡፡››

‹‹አይ ጥሩ ነው፡፡››ንግግሯን ሳትጨርስ ሌሎቹ ልጆች ከያሉበት መጥተው ወረሯት ፡፡ግማሹ ግንባሯን ግማሹ ጉንጮን ሳሟት፡፡እሷም በየተራ ሳመቻቸው፡፡ለሚያያቸው ዕውቂያቸው የአንድ ቀን ብቻ አይመስልም፡፡

አላዛር ከጓሮ ተመለሰና ከሚጠብቁት ጓደኞቹ ጋር ከተቀላቀለ በኃላ ድምፅን ከፍ አድርጐ << ሶፊ ልንሄድ ነው››ሲላት ልጆቹን ‹‹ቆይ አንዴ መጣሁ >>ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደ እነ አላዛር ሄደች፡፡

‹‹ይቅርታ እኔ የታዲ ዘመድ ነኝ፤ ከሁላችሁም ጋር ብተዋወቅ ደስ ይለኛል፡፡››

አይነስውሯ ቀድማ ለሰላምታ እጇን እየዘረጋችላት‹‹ፅዬን እባላለሁ›› አለቻት፡፡

‹‹ዶ/ር ሶፍያና፡፡››
‹‹ቤቲ..ቤተልሄም፡፡›› እባላለሁ..ሌላዋ ቀጠለች፡፡
አላዛር መሀል ገብቶ ማብራሪያ በመስጠት ቀጠለ ‹‹...ፂ እንዳየሻት አሪፍ የሙዚቃ ሰው ነች፡፡ጊታር እና ፒያኖ ነፍስ አድርጋ ትጫወታለች፡፡የያሬድ ግርፋ ነች፤ በሞያዋ የሙዚቃ አስተማሪ ነች፡፡እዚህም እንዳየሻት የሄለን እና የሚኪያ የሙዚቃ አስተማሪ ነች፡፡…

ቤቲ ደግሞ ሀይ‐ስኩል አማርኛ ቲቸር ነች፡፡
የስድስት ኪሎ ምሩቅ ነች፡፡እዚህ ያሉትን ህፃናት አማርኛም ሆነ እንግሊዘኛ ቋንቋ በፕሮግራም
ታስተምራቸዋለች፡፡አንዳንዴ
ሂሳብም ቀልቀል ለማድረግ ትሞክራለች ግን ቀሺም ነች፡፡ሂሳብ እና ጠቅላላ ዕውቀትን በተመለከተ ጂኒዬሱ ነው የሚያስተምራቸው፡፡

ጂኒዬሱ ስል ታዲዬስን ማለቴ ነው፡፡እኔ ያው
እዚህ ቤት የቀለም ሽታ የምትወድ አንድ ሰላም
የምትባል ልዩ ነፍስ ያላት ልጅ አለች ፤እሷን ስዕል አስተምራታለሁ፡፡አስተምራታለሁ ማለት
እንኳን ይከብዳል ስትስል
አያታለው፤የምትፈልገውን ቁሳቁስ አቀብላታለው ማለቱ ነው የሚሻለው ፡፡

ምክንያቱም አሁን ባለንበት ሁኔታ ችሎታችን እኩል ነው፤ከስድስት ወር በኃላ ደግሞ እኔ ቁጭ ብዬ ከእሷ መማሬ አይቀርም፡፡››
👍7811👎1👏1🤔1
‹‹በጣም ደስ ይላል፡፡እዚህ በትርፍ ጊዜያችሁ እነሱን እየረዳችሁ ነው አይደል?››
‹‹አይ በክፍያ ነው..ከእሁድ በስተቀር ከትምህርት ቤት ሲመለሱ በቀን ለሁለት ሰዓት እናስተምራቸዋለን፡፡የአንድ ሰዓት ይከፈለናል፤የአንዱ ሰዓት ደግሞ የእኛ ምርቃት ነው፡፡››

‹‹ጂኒዬሱ ነዋ..በየወሩ ሁለት ሁለት ሺ ብር ለእያንዳንዳችን ይከፍለናል.፡፡በይ ሌላውን ሌላ ጊዜ …አሁን እንሂድ››
ግራ ገባት ::ይሄ ታዲዬስ የሚባል ልጅ ምን አይነት እንቆቅልሽ የሆነ ሰው ነው?አንድ በሊስትሮና በመፅሀፍ ሽያጭ ሚተዳደር ልጅ እንዴት ይሄንን ሁሉ ወጪ ሸፍኖ እንዲህ አይነት የተለየ ነገር ሊሰራ ይችላል? በውስጧ ጠየቀች፡፡

‹‹ቆይ ወንዱ ልጅ እዛ ቅራቅንቦ ውስጥ ላፕቶፕ እየጎረጐረ ነበር..››

‹‹ሳይንቲስቱን ነው?››አላት ቀልቃላው አላዛር፡፡

‹‹ወፍራሙን ህፃን ልጅ እኮ ነው ምልህ››

‹‹ገብቶኛል..እሺ እሱ ምን?››

‹‹ማለቴ ማንም አስተማሪ አጠገቡ የለም ምን እየሰራ ነው?››

‹‹ጥያቄሽ ሰፊ ነው..በአጭሩ ግን እሱ ምንም ዓይነት አስተማሪ ሊያስተምረው አይችልም፡፡ ከትምህርት ቤት መጨረሻ ደረጃ ነው የሚወጣው ፡፡ ሰነፍ ስለሆነ አይምሰልሽ ዕውቀቱ ከአስተማሪዎቹ ችሎታ በላይ ስለሆነ አይረዱትም፤እሱም እነሱን መረዳት ይቸግረዋል፡፡ እንደምታውቂው የእኛ ሀገር ትምህርት ከወረቀት ወደአዕምሮ ኮፒ ማድረግ ከዛ በፈተና ቀን ከአዕምሮ ደግሞ ወደ ወረቀት መልሶ ኮፒ ማደረግ ወሃ ቅዳ ውሃ መልስ አይነት ነው፡፡ሳይንቲስቱ ግን እንደዛ አይነት ነገር አይገባውም፡፡ እሱ የሚግባባው ከታዲዬስ ጋር ብቻ ነው፡፡የፈጠራ ችሎታውን ግን አትጠይቂኝ..፡፡ወደፊት ኢትዬጵያ ሚያልፍላት ከሆነ በዚህ ልጅ ይመስለኛል
፤ቶማስ ኤዲሰን በይው..፡፡ በይ ብዙ ጥያቄ ያለሽ ትመስያለሽ..ለሌላ ጊዜ አቆይው፡፡››

ሁሉም ተሰናብተዋት ሲወጡ ከኃላ እየተጐተተ ለነበረው አላዛር የቢዝነስ ካርዷን አቀበለችው ‹‹ደውልልኝ››ደስ እያለው ወጣ፡፡

እነሱን ሸኝታ የሳሎኑን በራፍ ዘጋችና ወደ ልጆቹ
ተመለሰች... እየተገረመች፡፡እዚህ ቤት አንድ ድምጻዊ ለመሆን ተስፋው ያላት ልጅ ፤አንድ የሙዚቃ ተጫዋች ለመሆን በሚንተከተክ
ፍላጎት የተሞላች ልጅ፤አንድ የወደፊት ሰዓሊ ለመሆን መንገዱን የጨበጠች ልጅ ..አንድ በልጅነቱ በፈጠራ ጥማት ተለከፈ
ልጅ‹‹..ይገርማል !!››አለች፡፡ እኚ ሁሉ ባለ ትልቅ
ርዕይ ባለቤት ህጻናት የተገኙት ከየጎዳናው
ነው፡፡ይሄ ማለት ደግሞ ስንቱ ሰብሳቢና መንገድ መሪ አጥቶ በየቆሻሻ ጉድጓዱ የአንጀቱን የረሀብ ጩኸት ለማስታገስ ሲል
የተጣለ ምግብ በመፈለግ ብቻ ተሰነካክሎና ባክኖ ቀርቶ ይሆን? እግዜር ብቻ ነው የሚያውቀው ፡፡

‹‹እሺ ልጆች አሁን ስጦታ አምጥቼላችኃለው..ግን በመጀመሪያ ወንድማችሁን ጥሩት››አለች፡፡

‹‹አይ እሱ እኮ አይጠራም፡፡እራሱ ሲፈልግ ነው የሚወጣው፡፡››ሀሊማ ነች የመለሰችው፡፡

<<ለምን?>>

‹‹አይሰማማ፡፡ቢሰማም እሺ አይልም፡፡››አለቻት ሰላም፡፡

... ፔሳታሎቹ ወስጥ የታጨቁትን ቁሳቁች ሰፊው ጠረጴዛው ላይ ተራ በተራ ዘረገፈችው፡፡ ልብሶች፣ኳሶች፣ደብተር፣እስኪሪብቶዎች፣መፅሀፎች ያላመጣችላቸው ነገር የለም፡፡

ለእያንዳንዱ ሚደርሳቸውን ያህል ለየብቻ አምስት ቦታ መደበችና የየራሳቸውን በየተራ አስረከበቻቸው ፤በቦታው ያልተገኘውን የሙሴን ብቻ አስቀርታ፡፡

ስጦታውን ተከትሎ ከልጆቹ ፈገግታና ፍንጠዝያ ጠብቃ ነበር፡፡ልጆቹ ግን መፅሀፉን
ብቻ አስቀርተው ሌሎች ስጦታዎቹን ተራ በተራ መለሱላት፡፡

‹‹ምነው...አልወዳዳችሁትም እንዴ?›› ‹‹በጣም ወደነዋል እናመሰግናለን፡፡ግን ከመጽሀፉ ውጭ ልንቀበልሽ አንችልም፡፡›› ሄለን ነች የመለሰችላት፡፡

<< ለአሁኑ ሚበቃንን ያህል ስላለን ነው፡፡ወደ ፊት የሚያስፈልገን ከሆነ ደግሞ ታዲን ማስገዛት እንችላለን፡፡ሰውን ማስቸገር አግባብ አይደለም፡፡››

‹‹እኔ መቼ አስቸገራችሁኝ አልኩ?››

‹‹አንቺ ባትይም አይገባም፡፡በሰው ስጦታ ላይ ጥገኛ መሆን ለእኛ ይከብዳል፡፡ ከቤተሰቦቻችን የተለየ ህይወት መኖር ነው ምንፈልገው፡፡››አለች ሰላም፡፡

ዶክተር ሶፊያ ግራ ገባት ፤ ‹‹የቱን ከየቱ አገናኝተው ነው ያቆላለፉት?›› ስትል አሰበች፡፡ ምን ማለት እንዳለባት ግራ ገብቷት እያሰላሰለች ሳለ ታዲዬስ ገብቶ ተቀላቀላቸው፡፡ ለሁሉም ሰላምታውን ካደረሰ በኃላ‹‹ምን ሆናችሁ?››ሲል ጠየቃቸው፡፡

‹‹እኔ እንጃ እነዚህን ስጦታዎች ልጆችህን ያስደስታሉ ብዬ ገዝቼ አመጣሁ፤ግን ከመጽሀፉ በስተቀር አንቀበልም አሉኝ››

‹‹እስቲ ዶክተር ቁጭ በይና እንነጋገርበት፤ እናንተም ተቀመጡ፡፡›› ብሎ ቀድሞ ወንበር ያዘ፡፡ ሁሉም ትዕዛዙን አክብረው ተቀመጡ ፡፡ መናገር ጀመረ፡፡

‹‹እንግዲህ ይህቺ እንግዳችንን በእኛ ቅር እንደተሰኘች ነው የምትናገረው፡፡ስጦታ አምጥታላችሁ ነበር እናንተ ግን ልትቀበሏት አልቻላችሁም ለምን ?

‹‹አንቀበልም አላልንም...አመሰግነን ያመጣችውን መጽሀፍ ወስደናል›› ሄለን ነች የመለሰችው፡፡

‹‹ልብሶቹን፤መጫወቻዎቹን ሌሎች ሁሉንም ያመጣሁላችሁን ግን እምቢ ብላችኋል››

‹‹አዎ መልሰናል››ሰላም መለሰች..፡፡

ታዲዬስ ቀጠለ ‹‹ምክንያታችሁን ለእኔም ለእሷም አስረዱን እስቲ ሚጣ ቀጥይ፡፡ ለምንድነው ስጦታውን አልቀበልም ያልሽው?››

‹‹ለምሳሌ ያመጣችልኝ ቀሚስንና ቢጃማን አልቀበልም ያልኩት የሚበቃኝን ያህል ስላለኝ ነው?>>

‹‹የሚበቃኝን ያህል ማለት ምን ማለት ነው?››ዶ/ር ሶፊያ በገረሜታ ጠየቀቻት፡፡

‹‹ሦስት ቀሚስ እና ሁለት የለሊት ቢጃማ

‹‹ታዲያ ተጨማሪ ሌላ ቢኖርሽ ምን ችግር አለው?»

‹‹ችግር አለው እንጂ፡፡ብዙ ልጆች አንድ ልብስ እንኳን አጥተው እራቁታቸውን እየሄዱ እንደሆነ እያወቅኩ እኔ ደግሞ የማለብሰውን ብዙ ልብስ መሰብሰብ እንዴት ይሆንልኛል?››

ሶፊያ ግራ ገባት ፡፡አንድ የዘጠኝ አመት ልጅ እንዴት እንዲህ ልታስብ ትችላለች፡፡መልስ ባታገኝም እራሷን ጠየቀች፡፡

‹‹እሺ ሄለንስ ምክንያትሽን ልትገልጪልን ትችያለሽ?ምክንያትሽ ከሰላም ጋር ተመሳሳይ ነው?>>

‹‹አዎ ሰላም ያለችው እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ ምናገረው ለምሳሌ አንተ ያሉህ ልብሶች ሶስት ሱሪዎች እና ሶስት ሸሚዞች እና ሶስት ጫማዎች ናቸው፡፡በቁም ሳጥን ሙሉ የሚሞላ ልብስ ገዝተህ ዝንጥ ማለት ትችል ነበር፡፡ግን አንተ በቂዬ ነው ብለህ ለዛ የምታወጣውን ብር ለእኛም ሆነ ለሌሎች ልብስ እየገዛህ ታለብስበታህ፡፡የእኔ ምሳሌ አንተ ነህ::አሁን የሚያስፈልገኝን ያህል ልብስ አለኝ... ከዛ በላይ መሰብሰብ ስግብግብነት ነው::››

መልሱ ምን እንደሚሆን እያወቀ ጠየቃቸው <<የሁላችሁም መልስ ተመሳሳይ ነው? >> ተመሳሳይ መሆኑን ሁሉም ግንባራቸውን በመነቅነቅ አረጋገጡለት፡፡

ዶ/ር ልጆቼ ያሉትን ሰምተሸል…የምትይው ይኖርሻል?››

ለተወሰነ ሰከንድ ዝም አለችና ‹‹ምን እንደምል አላውቅም::ትናንት ባጋጣሚ ሳያችሁ በጣም ስለወደድኳችሁ ነው የፍቅሬን መጠን ይገልፅልኛል በሚል ተስፋ ካለኝ ገንዘብ ላይ በጣም ጥቂቷን ቆንጥሬ እነዚህን ስጦታዎች ገዝቼላችሁ የመጣሁት፡፡ያንን በማድረጌ እኔ የተደሰትኩትን ያህል እናንተም በደስታ ትቀበሉኛላችሁ ብዬ በማሰብ ነበር፡፡አሁን ለምሳሌ እኔ በቤቴ ያለኝ ልብስ ቁም ሳጥን ሙሉ ሞልቶ ሌሎች ትላልቅ ሻንጣዎች ተጠቅጥቆ ተርፏል፡፡ምን አልባት በቁጥር 5ዐዐ በላይ እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን ያንተ ልጆች እንደተናገሩት ትርፍ ልብሶች
እንዳሉኝ ተሰምቶኝ አያውቅም
👍894
ትናንት እራሱ ለእነሱ ይሄንን ስጦታ ስገዛ እግረ መንገዴን ለራሴም ሶስት ጥንድ ጫማዎች ገዝቼያለሁ.. እቤቴ ግን ቢያንስ ከመቶ በላይ ጫማዎች አሉኝ ፡፡በእነሱ ግን መርካት ባለመቻሌ እና ተጨማሪ ያስፈልገኛል ብዬ በማመኔ ነው የገዛሁት፤እንጂ ትርፍ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም፡፡አነዚህ አንድ ፍሬ ህፃናት ግን ከምንጠቀምበት በላይ አንሰበስብም ሲሉ እነሱን ተከራክሬ ለማሳመን ምን አይነት ሞራል ይኖረኛል?›› ብላ ንግግሯን ደመደመች፡፡

‹‹በቃ እኔ ላስታርቃችሁ ፤ አሁን እሷ ቅር እንዳይላት ያመጣችውን ስጦታ አመስግናችሁ ተቀበሏት፡፡ከዛ እሁድ ጓደኞቻችንን ልንጠይቃቸው ስንሔድ ለሚያስፈልጋቸው በእሷ ስም እንሰጣቸዋለን..ይሄ ያስማማናል?፡፡››

ሁሉም በፈገግታ ሀሳቡን ተቀበሉት፡፡የእሷን ጉንጭ በማመስገን እየሳሙ መልሰውላት የነበረውን ስጦታ ከያስቀመጡበት በመውሰድ ወደመቀመጫችው ተመለሱ፡፡

በዚህ ጊዜ ሳይንቲስቱ ሙሴ ከመሸገበት ክፍል ፈንደድ ፈንደድ እያለ መጥቶ ተቀላቀላቸው፡፡ታዲዬስ ወደራሱ ስቦ ግንባሩን ሳመው፡፡ዶክተር ሶፊያ የሙሴ ድርሻ የሆነውን ስጦታ ልትሰጠው ስትንቀሳቀስ‹‹ዶ/ር ተይው ….እሱን አስረድቶ ለማሳመን ለሊቱም አይበቃንም፡፡ይልቅ አሁን ሁላችንም ለእራት እንውጣ >> የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡›› ሁሉም በደስታ ተስማሙ፡፡

‹‹እስክትዘገጃጁ ታክሲ ጋር ልደውል?››

‹‹እኔ መኪና ይዤያለሁ›› አለችው ዶክተሯ፡፡

‹‹ውጭ የቆመችው መኪና ያንቺ ነች እንዴ?››

<<አዎ>>

ተያይዘው ወጡ፡፡መኪናው ውስጥ ገቡ፡፡ ውጪው በጣም ጨልሟል፡፡ ከተማዋ መብራት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል፡፡

‹‹መብራት ጠፍቷል እንዴ..?እናንተ ጋር ጄኔሬተር አለ ማለት ነው ? >> ስትል ጠየቀችው ዶክተር ሶፊያ እነሱ ቤት ለብቻው ተነጥሎ መብራት እየበራበት ሞሆኑ ገርሟት፡፡

‹‹እኛ እኮ ሀገሪቱን በመብራት አናስቸግርም ..እድሜ ለሙሴ እራሳችንን ችለናል፡፡››

<<እንዴት?>>

‹‹ሙሴ በራሱ ፈጠራ ከፀሀይ ሃይል የሚያመነጭ የራሳችንን በቂ ሀይል እንድናገኝ አድርጎናል..ነጻ ከወጣን አንድ አመት ሆነን፡፡ መብራት ኃይል የራሱን ቆጣሪ በብስጭት መሰለኝ ከቆረጠው ቆየ፡፡››

ወደ ግዙፉ ታዳጊ በአትኩሮት እየተመለከተች‹‹ይሄ ሙሴ ነው የሰራው ?>> ስትል ባለማመን ደግማ ጠየቀችው ፡፡

‹‹አዎ ይሄ የእኛ ሙሴ፡፡›› ፍርጥም ብሎ አረጋገጠላት

‹‹ለመሆኑ ስንት አመቱ ነው?››

‹‹አስር ወይም አስራ አንድ ይሆነዋል..ነገሮችን ለመስራት ግን ዋናው ዕድሜ አይመስለኝም ስጦታ እና ጥረት ካለ የእናት ጡት መጥባት ሳያቆሙ በፊትም ተዓምር መስራት ይቻላል፡፡››አለት፡፡

‹‹እሱስ እውነትህን ነው... በእንደ እናንተ አይነት የጉድ ቤት የማይቻል ነገር የለም !! እሺ አሁን ወዴት ልንዳ?›› አለችው፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የትልቅ ሆቴል ስም ነገራት፤ ወደዛው አሽከረከረች፡፡‹‹እዛ አካባቢ የሚገኝ ምግብ ቤት ለመጠቀም ፈልጎ ይሆናል፡፡›› ስትል ገመተች፡፡ደረሱ ፡፡መኪናውን ቦታ አሲይዛ አቆመች፡፡

ወርደው ግን ያመሩት እንደጠበቀችው ወደአነስተኛ ምግብ ቤት ሳይሆን ወደ ዋናው ባለኮከብ ሆቴል ነው፡፡ትናንት እራት ከበሉበት የአሮጊቷ ምግብ ቤት ጋር ሲነፃፀር የሲኦል እና የገነት አይነት ልዩነት አለው፡፡ተከትላቸው ወደሆቴሉ ገባች፡፡ሲገቡ አስተናጋጆቹ ሁሉ ተንጋግተው በመምጣት በሞቀ ሰላምታና በደመቀ ፈገግታ ተቀብለው ቦታ ሰጧቸው፡፡ እያንዳንዶቹን ህፃናት በየስማቸው እየጠሯቸው ያናግሯቸው ነበር፡፡ሶፊያ በጣም ነበር የተደመመችው፡፡የቤቱ ቋሚ ደንበኞች እንደሆኑ በእርግጠኝነት አመነች፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል እየተጫወቱና እየተዝናኑ ከቆዩ በኃላ መልሳ ቤት ድረስ ሸኘቻቸው፡፡ሲለያዩ‹‹ለእራት ግብዣው አመሰግናለሁ፡፡››አለችው፡፡

<<ችግር የለውም›› መለሰላት ታዲዬስ፡፡

‹‹አንድ ነገር ላስቸግርህ?››



<<ምን ልታዘዝ>>

‹‹ነገ ቁርስ ብጋብዝህ ደስ ይለኛል?››

<< ነገ?>>

‹‹አዎ ነገ ሁለት ሰዓት አካባቢ፡፡››

‹‹ይቻላል ስራ ቦታ ታገኚኛለሽ፡፡››አላትና ልጆቹን ይዞ ወደ ቤቱ ሲገባ እሷም መኪና• አስነስታ በተደመመ ስሜት ወደ ቤርጎዋ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ ለ500 እኮ ትንሽ ነው የቀረው እባካቹ ቤተሰቦች
ሰብስክረይብ እያረጋቹ ያደረጋችሁ ደግሞ ሌሎች እዲያደርጉ #Share እያደረጋቹ አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍68🥰43😁2👏1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ዶ/ር ሶፊያ በማግስቱ ከምሽቱ 12፡3ዐ ላይ መኪናዋን እያሽከረከረች ታዲዮስ ቤት ደረሰች፡፡ሦስት ኩርቱ ፔስታል ሙሉ ስጦታ ይዛለች ፤ለአምስቱም ልጆች ፡፡በመከራ እየተንገዳገደች ነበር ዕቃዎቹን ተሸክማ በረንዳው ላይ ማድረስ የቻለችው፡፡መሬት አስቀመጠችውና በራፉን አንኳኳች፡፡ ሃያ አምስት ዓመት የሚሆነው ባለ ሹሩባ ፀጉር መልከ መልካም…»
#ፍቅር_የመሸባት_ሀገር


እዛ ሰው ይሞታል፣ እዛ ደም ይፈሳል
እዚህ ይጨፈራል ፣ እዚህ ይደነሳል
እዛ ሰው ያለቅሳል፣እዚህ ሳቅ ይነግሳል።
፨፨፨
እዛም እኛዎች ነን፣አዚም እኛ ባዮች
የደላን እኛው ነን ፣ እኛው ተበዳዮች
አንድነትን ሰብከን፣የምንሆን ብዙዎች፡፡
እኛው ነን የሞትነው፣እኛው ነን ቀባሪ
እኛው ነን ሙሾ አውራጅ፣እኛው ነን ጨፋሪ
አንድ ነን እያልን ፣ ልዩነት ፈጣሪ፡፡
፨፨
እዛ እኛ ስንሞት፣ እዚ እኛ ስንጨፍር
እዛ እኛን ስንቀንስ፣እዚ እኛን ስንደምር
ሙሾን ከደስታ ጋር የምንደባልቀው
እኛው እያነባን ፣ እኛው የምንስቀው
እኛው ለነፃነት ፣ ታግለን የምናልቀው
እኛው ባርነትን፣ፈቅደን የምንሞቀው
እዚ እየረሳን ፣ እዛ ም'ናፍቀው
ፍቅር መሽቶብን ነው፡፡
፨፨
እንዲህ ነው ሚኖረው....
ፍቅር የመሸበት፣ሀቅ ያልገባው ሀገር
እዛ እኛ ሙሾ አውራጅ ፣ እኛ አዚ ምንጨፍር፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢20👍11👏43🔥2
#እኔና_ጊዜ

ጊዜ አጥቼ እንጂ፣ ፍቅሬን ለማስረዳት
የሰማንያ ሚስቴን፣ በጣም ነው ምወዳት፡፡

ተወጥሬ እንጂ፣ ሀገሬን በማልማት
መቼ ዝም እል ነበር?፣ ልጄ ‘በራብ’ ሲሞት፡፡

ቸኩዬ ነው እንጂ፣ ስሮጥ ለቁም-ነገር

ሁለት ሰው ገጭቼ፣ አላመልጥም ነበር!!!

በተለይ በተለይ…
ጊዜ አጣሁኝ እንጂ፣ ጥቂት ፋታ ባገኝ ስለ ጊዜ ጥቅም፣ የምለው ነበረኝ !!!

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😁25👍8🥰5
ካንተ ቤት......
ቋንጣ ተሰቀለ
ሻኛ ተቆረጠ፣ ወይን እየተጠጣ፣
፨፨
ያ’ዳም ዘር ወንድምህ
ያለ ሁዳዴ ፆም በ’ራብ የ’ተቀጣ፡፡
፨፨
ይገርማል
አንተ ማለትኮ...
አንተ ማለት ጥጋብ ያለልክ ሠልቃጭ፣
እሱ ማለት ደግሞ...
እሱ ማለት ሚስኪን ካንተ ቤት ቀላዋጭ፣
፨፨
እንዲህ ነው ተፈጥሮ እግዜሩ  ሲያዳላ፣
አንዱ ፆሙን ሲያድር ሌላኛው ሲበላ፡፡
፨፧
በተራበች ነፍሱ
........ቀልቡ እየዋለለ፣
ድህነት ሰቅዞት
.......ሳይበላ እየዋለ፣
ሂወት ጨክናበት
ቆዳ ምላሽ ሊያገኝ
..........በጌቶቹ ቅዬ ፍሪዳ እየጣለ፣
ለሁዳዴው ፆም ፍቺ
በግ ሲጠባ ያድራል ቢለዋ እየሳለ፣
፨፨
እንዲህ ነው ተፈጥሮ እግዜሩ ሲያዳላ፣
አንዱ ፆሙን ሲያድር ሌላኛው  ሲበላ፡፡
፨፨
ትቀምሰው ያጣች ነፍስ ቁራሽ ንጣይ ቅምሻ፣
በጣር ሲቃ ታንቃ ስታጣ መድረሻ፣
ፍርድ አጥተን ከሰማይ የ'ግዜር እጅ መንሻ፣
ሠው የሠው አገልጋይ ሠው የመንደር ውሻ፣
ሲ..ጎ..መ..ጅ ይኖራል በ.በ.ሊ.ቶ.ች ጉርሻ፡፡



👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍243😁2
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል ሠባት


“አበባም ይሁን ድንጋይ፣ በግድ እስካሸከሙን ድረስ ያው ሸክም ነው!”

ማኀደረ-ሰላም!

አገባሁ!! ድል ባለ ሰርግ ዮናስ የሚባል ከአሜሪካ የመጣ ሰው አገባሁ፡፡ አስተያዬት ሰጪዎች ግን ለባለቤቴ የሚሉት “አፈስክ” ነው። አስተፋፈሱ የየቅል ይሁን እንጂ፧ እኔም ባለቤቴ ያገባኝ ሳይሆን ያፈሰኝ ነው የሚመስለኝ፡፡ በሆነ ግዴለሽ መዳፍ! እንደ አልባሌ ነገር የትም ተበታትኜ ከተደፋሁበት አፋፍሶ ያገባኝ ነው የሚመስለኝ። ለራሴ ቢቀፈኝም ከወዳደቅሁ እኔ ገጣጥሞ፣ በወጉ ያልተቃኜች በድን ሚስት የምትባል ፍጥረት የሠራ ነው የሚመስለኝ፡፡ በድፍን አዲስ አበባ ከላፍቶ እስከ ሜክስኮ፣ ከቦሌ እስከሃያሁለትና መገናኛ፣ ከተበታተንኩበት ለቃቅሞ የገጣጠመኝ ልክ እንደተሰበረ ብርጭቆ፣ ከነስንጥቄ ተጠጋግኜ የሆነ ደግ ሰው ቤት የተቀመጥኩ፣ ውስጤ ፍቅር የማይቋጥር እንዲሁ ቅርስ ነገር ...የዕድለ ቢስነት መታሰቢያ ቅርስ። ታዲያ መልስ ሲባል ባሌ አልፈልግም ብሎ ወደ አባቴ ቤት የሚመልሰኝ መስሎ ነበር የተሰማኝ፡፡ባደረገዉ...!

ብዙ ሰዎች ሲሉ እንደሰማሁት ትዳር የአዲስ ሕይወት ጅማሬ፣ ያለፈ ታሪካችንን አጀንዳ ዘግተን ለአዲስ ነገ “ሀ” ብለን ርምጃ የምንጀምርበት ምዕራፍ መስሎኝ ነበር፡፡ ግን ለእኔ እንደዚያ አልነበረም፡፡ ያለፈ ታሪኬን፣ ትዝታዬን፣ ሕመሜንና ደስታዬን ሁሉ ልክ እንደ ልብስና ሌላ ሌላ ኮተቴ ሁሉ በአእምሮዬ ሻንጣ አጭቄ ነበር ወደ አዲሱ ቤት ያዘገምኩት፡፡ ያው አዲስ አበባ ይባል እንጂ ሩቅ ነበር ለእኔ፡፡ ሰሚት ወደ ሚባል ሰፈር፡፡ አሜሪካ ይሁን አንታርቲካ፣ ሰሚት ይሁን ቃልቲ፣ ከምወዳት ሰፈሬ ሜክሲኮ ከራቀ ሩቅ ነው፤ ሩቅ ነበር ለእኔ። ስደት በርቀት ካልተለካ በስተቀር ስደት ነበር ለእኔ፡፡ ልደታን ወረድ ብዬ ካላዬሁ ያዛጋኛል፡፡ የዋቢ ሸበሌ ሆቴልን አጥር ታክኬ ካላለፍኩ ዓለም ምልክት የሌላት ምድረበዳ ትመስለኛለች፡፡ በ'ኮሜርስ' ዙሪያ ካላንዣበብኩ አዲስ አበባ የዋልኩ አይመስለኝም፡፡ ብሔራዊ ቲአትር በር የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችንና የቲያትር “ፖስተሮችን” ካላዬሁ፣ የዕለት መዝሙረ ዳዊቱን ሳይደግም እንደወጣ ሃይማኖተኛ ቅር ቅር ሲለኝ ይውላል፤ ስንት የማናውቀው ሱስ አለብን!? እትብት የሚባለው ነገር በሥጋ እንጂ በነፍስ አይቆረጥም መሰል!? የተወለድንበት ሰፈር ላይ ያለ የማይታይ የመንፈስ ችካል ላይ ተቋጥሮ፣ በረዥም ክር ከእኛ ጋር የተሳሰረ ነገር ነው፤ የትም ብንሄድ ይስበናል፡፡ ሻንጣዬን ከፍቼ ልብሶቼን ቦታ ቦታ ሳሲይዝ፣ አእምሮዬም በሰፊው ተከፍቶ አሮጌ ትዝታዬን በአዲሱ ቤቴ ውስጥ እንደ ፎቶ መደርደር ጀመረ፡፡ እያንዳንዱን ልብስ ለብሼ፣ ምን እንዳደረኩ አውቃለሁ፡፡ እያንዳንዷን ቀሚስ እንዴት እንደገለብኩ፣ ሱሪዎቼን በእብደት ቁልቁል እንዳንሸራተትኳቼው አውቃለሁ፡፡ ከምንወዳቼው ጋር ስንት ጊዜ ልብሳችንን አውልቀን ስንት ጊዜ ለብሰናል?...ማነው የቆጠረው? በደመነፍስ ስንት ዓይነት ፈጣን አወላለቅ ተምረናል፡፡ ገና ቀጠሮ ስንይዝ፣ ውዶቻችን ልብሳችንን ለማውለቅ እንዳይቼገሩ ቀለል ያለውን አልመረጥንም? ልብስ ብዙ ብዙ ነገር ነው፡፡ ቢታጠብም የማይለቅ አሻራ፣ ከመተቃቀፎቻችን የቀረ ጠረን ሁሉ ዘላለማዊ ነው፤ ልብሶቼን እወዳቸዋለሁ፡፡ ውድ

ቅርስ እንደሚሰበስቡ ሰዎች፣ የእኔ ሰብስቦች ልብሶቼ ነበሩ። ውድ ሆነው አይደለም የተለዬ “ብራንድ” ያላቼው ወይም በአድናቆት የት አገኘሻቼውን የሚባልላቸው አልነበሩም። ለፋሽን ግድ የለኝም፣ለውበትም ያን ያኽል አልጨነቅም፡፡ምቾታቸው ድሎቴ ነው: ውስጣቼው ኑሪያለሁ ከቤቴ፣ ከሕይወቴ፣ ከአገሬም በላይ ልብሶቼ ውስጥ ኖሪያለሁ፣ መደበቂያዎቹ ነበሩ። የእኔ የራሴ ባንዲራዎች ነበሩ፡፡ ልብሶች ተራ ነገር አይደሉም፣ የግል ባንዲራዎቻችን ናቸው፡፡ አገር ባንዲራውን፣ ሰው ልብሱን ከጣለ ምን ቀረው? ሁለቱም እብደት ነው፡፡አረጄ ብለን የምንወረውረው ልብስ፣ ልብስ ብቻ አይደለም፤ የዕድሜ አሻራችን ጭምር እንጂ፡፡ ካለነገሩ አይደለም የለበስነውን ልብስ ተመሳሳይ ሌሎች ለብሰውት ስናይ ውስጣችን በቅሬታ የሚሞላው? ሌሎች ባንዲራችንን የነጠቁን ስለሚመስለን ነው፡፡ ግድግዳው፣ ጣሪያው፣ መኝታ ቤቱ፣ ሳሎኑ፣ መታጠቢያ ቤትና ማብሰያ ቤቱ ሁሉ ቁጥር ስፍር በሌለው ትዝታዬ ተሞልቶ፣ ገና ሳምንት ሳይሞላኝ አዲሱ ቤት ዕድሜ ልኬን የኖርኩበት አሮጌ ዋሻ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከምንም በላይ ያመመኝ እና ያደከመኝ፣ ደስተኛ መስዬ ለመታዬት አደርገው የነበረው ጥረት ነበር። እንዴት ሰው ዕድሜውን በሙሉ ሌሎችን ለማስደሰት እና ተቀባይነት ለማግኘት ሲባዝን ይኖራል? ...እኩል ምድር፣ እኩል ሰብአዊ ክብር፣ ተሰጥቶን እንዴት ነው አንዱ ለማኝ አንዱ ተለማኝ የሚሆነው!? ባለቤቴ በአዲስ ትዳር ናውዞ ሲሟዘዝ፣ አብሬው መሟዘዝ፣ ሲስቅ- መሳቅ፣ በስሜት ሲግል፣ እሳት ላይ ቢጥዱት የማይሞቅ ቀዝቃዛ ሥጋዬን የሞቀ ለማስመሰል መጣር፣ ባል~ ባል ለመሆን ሲደክም፣ ሚስት - ሚስት ለመምሰል መፍገምገም- ብዙ ማስመሰል፤ግን ብዙ መቀጠል አልቻልኩም።

እስከ መቼ ነው እንዲህ የምኖረው!? ያልኩት ገና በሳምንቱ ነበር፤ በተጋባን በሳምንቱ። የቤተዘመዱ ዕልልታ እንኳን፣ ካንዱ ቤት ሌላው ቤት ግድግዳ የሚነጥር የገደል ማሚቱው አልጠፋም ነበር። እልልልል ሲባል አእምሮዬ ይኼ እልልታ ለማነው? ይላል። ባለቤቴ ጋር የተዋወቅነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የመጀመሪያ ድግሪዬን ሥሠራ ነበር። የዛሬን አያድርገውና ጥርስ የማያስከድን ተጫዋች ልጅ ነበር። በግሩፕ ከነበረ ጓደኝነት እንደ አንዳቼው ከማዬት ባለፈ በግል እንኳን ያን ያኽል ቅርበት አልነበረንም፡፡ እንዲያውም ጓደኛዬ ሃይሚ “ይኼ ወሬኛ መጣ''እያለች እንድንርቀው ስለምትገፋፋኝ ብዙም አልቀርበውም ነበር። ልንመረቅ እንድ ዓመት ሲቀረን፣ ምን ሰይጣን ሹክ እንዳለው እንጃ፣ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ሱዳን ተሰደደ ተባለ፡፡ ወሬው ከዬት እንደመጣ አላስታውስም። ሁልጊዜ ከክላስ በኋላ የማይጠፋባት ፎቶ ኮፒ ቤት የሆነ ነገር ኮፒ ላደርግ ስሄድ እግረ መንገዴን እዚያ ያገኜሁትን ጓደኛውን “ዮኒ የት ሄዶ ነው?'' ብዬ ጠየቅሁት፤ እሱም እንዳላወቀ ነገረኝ፤ ያኔ ከአንድ ሰሞን ያለፈ ወሬ አልነበረም፤ በቃ ተረሳ። እሱ እንደገና ከተገናኜን በኋላ፣ እንደነገረኝ ከሆነ ለዓመታት ብዙ ብዙ ችግር እሳልፎ አሜሪካ ገባ፡፡ አሁን ኑሮው እዚያዉ አሜሪካ ነው፡፡ ገና ሳንጋባ በግልጽ እንደነገረኝ፣ ታክሲ ይነዳል፣ የጽዳት ሥራ ይሠራል። በዚሁ ታታሪነቱ ለቤተሰቦቹም ለራሱም ተርፏል፡፡ ዮናስ ከሰርጋችን አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ነበር ስድስት ኪሎ ውልና ማስረጃ ድንገት የተገናኜነው፡፡ የዚያን ቀን ግጥጥሞሸ ይገርመኛል፣ አለቃዬ የሆነ ፋይል እንድታመጣለት ሰናይት የምትባል ቢሮ የምትጋራኝ ሠራተኛ ሊልክ ወደ ቢሯችን ይመጣል። በአጋጣሚ ወጥታ ስለነበር ሲጨናነቅ ሳዬው “በዚያው የምሄድበት ጉዳይ ስላለኝ እኔ አመጣልሀለሁ" ብዬው ፋይሉን ላመጣ ሄድኩ፡፡

ታዲያ ፋይሉን ተቀብዬ ስወጣ ከእንግዳ ማስተናገጃው አካባቢ ስሜ ከኋላ ሲጠራ ሰምቼ ዞር ብል፣ የጠራኝ ሰው ከስንትና ስንት ዓመት በፊት የማውቀው ዮናስ ሆኖ አገኜሁት። እውነቱን ለመናገር መጀመሪያ አላስታወስኩትም _ ነበር፣ ከዕድሜው በላይ ትልቅ ሰው መስሏል፤ ሲናገር ነው ያስታወስኩት፡፡ ከኮሌጅ ጀምሮ ሲናገር ዓይኑን በከፊል ከደን የሚያደርገው ነገር ነበር፡፡ ባልሳሳት ወደ ዐሥራ አምስት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ሳንተያይ ቆይተን ነበር፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ነገራችን ሁሉ ፍጥንጥን
👍466😢2
ያለ ነበር፡፡ ያ ጊዜ የአብርሐም ነገር ያንገሸገሸብኝ፣ ሕይወትም ስልችት ብሎኝ ሥጋዬ በደመነፍስ የሚንገላወድበት ጊዜ ነበር፡፡ የሆነውን ሁሉ ከእኔ እኩል ትሰማ የነበረችው ጓደኛዬ ሃይሚ እንኳን ልንጋባ መሆኑን ያወቀችው ነገሩ ሁሉ አልቆ ለሚዜነት ስጠይቃት ነበር፡፡ አደነጋገጧ ሁሉ ትዝ ይለኛል፤ ረዘም ላለ ጊዜ ሳንገናኝ ቆይተን ምሳ ልጋብዝሸ ብዬ ቀጠርኳትና "አንድ ጥሩ አንድ መጥፎ ዜና አለኝ" አልኳት

“በናትሽ ዛሬ ጥሩ ሙድ ውስጥ አይደለሁም፣ ስለዚያ አብርሃም ስለሚባል ሰውዬሽ ምንም እንዳታወሪኝ አለችኝ'' በምሬት እየተንገሸገሸች፤

“አንዱ ስለ እሱ ነው"

“መጥፎው ዜና ስለ'ሱ ከሆነ ንገሪኝ!” ተሳሳቅንና

“ተለያዬን” አልኳት።

“ማለት?”

“በቃ ከዚህ በኋላ የእኔና የሱ ነገር አበቃ”

“ለስንተኛ ጊዜ መሆኑ ነው?" አለች፣ እያሾፈች፡፡

“ይኼ ከምር ነው!”

“እሱ ነው ያለሽ?''

“አይ! እኔ ነኝ!" “ያንችን እንኳን ተይው፤ እስከሚደውልልሸ ነው!!" “እሺ! ሁለተኛው ዜና.. ላገባ ነው ! " አልኳት። ቀና ብላ አይታኝ በሳቅ ፈረሰችና... “ማሂ! አሁን ፈቃድ ጠይቂ እና ሁለት ሰባት በራሴ ወጭ ጸበል እንሄዳለን!” “እውነቴን ነው አባባ ይሙት!" በአባባ ከማልኩ እንደማልቀልድ ታውቃለች፡፡ የያዘችውን ሹካ ከእጇ ላይ ጥላ... “ቆይ! ቆይ! አባባ ይሙት ነው ያልሽው?. የምታገቢው? ባል ከሰማይ ዘነበ በዚህ ፍጥነት?” ሌላው ሁሉ ይቆዬንና ማንን ነው "ያው በይው! ታውቂዋለሽ ፤ ከአሜሪካ የመጣ ልጅ ነው!" "እኮ! ማነው ደግሞ እሱ?" “ዮናስ! ኮሌጅ እያለን ትምህርቱን አቋርጦ ሱዳን የሄደ ልጅ... የሆነ ተጨዋች ልጅ፣ ረሳሽው?'' አፍጥጣ ስታዬኝ ቆይታ በረዥሙ ተነፈሰች። “ሱዳን የሄደው ልጅ ከአሜሪካ መጣ? እና ሊያገባሽ ነው? አንችም እሺ አልሽው እ!?'' አለችና በሽሙጥ ከንፈሯን ጠመም አድርጋ መለሰችው፡፡ ፊቷ ግን በብስጭት ተቀያይሮ ነበር። በረዥሙ ተንፍሳ የነበርንበትን ሬስቶራንት ዙሪያ በዓይኗ ቃኜችና የሆነ ነገር ልትናገር ገና ከንፈሯን ስታላቅቅ … … “ምንም አስተያዬት ምክር አልፈልግም፤ በቃ ሚዜዬ ነሸ፣ ካልፈለግሸ ደግሞ የራስሸ ጉዳይ!''አልኳት፡፡ ዝም አለች፤ዝምታዋ ግን መልሶ እኔን አስደነገጠኝ። ይኼን የተናገርሽው አንች ነሸ? በሚመስል ግርምት ትክ ብላ አዬችኝ፤ ወዲያው ዓይኖቿ ድንገት በዕንባ ተሞሉ። ተነስቼ ጠረጴዛውን ዞርኩና ከኋላዋ አቅፊያት ማለማመጥ ጀመርኩ። ገፋ አድርጋኝ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደች። ግራ ገብቶኝ

ወገቤን ይዠ ቆምኩ። እንደተመለሰች ኮስተር ብላ አስተናጋጁን ጠራቸዉና ሒሳባችንን ከፍላ “እንሂድ!” ብላ ቦርሳዋን አነሳች። በብልግናዬ ራሴን እየረገምኩ ተከተልኳት።በጭራሽ እንደገና አገኛታለሁ አላልኩም ነበር፤ ግን ማታ ደወለች። 15 ስልኩን ከማንሳቱ የይቅርታ መዓት አዥጎደጎድኩበት “እስቲ ዝም በይ! የደወልኩት የሚያስፈልግሽ ነገር ካለ እንድትነግሪኝ ነው፤ ሌላውን ከሰርግሽ በኋላ እናወራለን አለችኝ፤ ስልኩን እንደዘጋሁ አለቀስኩ። ሃይሚ ሚዜዬ ሆና ባገባም፤ ባልገባኝ ምክንያት እስከ ዛሬ ስለ ዮናስም ሆነ ስለ ሁኔታው አንድም ቃል ተንፍሳ አታውቅም፡ይኼ የእርሷ ባሀሪ አልነበረም። በጣም ወሬ ከመውደዷ የተነሳ አብርሃም ጋር እንደነበርኩ የማይጠየቅ ነገር ሁሉ ነበር የምትጠይቀኝ። “ሃይሚ አትባልጊ" ብዬ ካልተኮሳተርኩ በስተቀር በጭራሽ ጥያቄዋን አታቆምም። አሁን ግን “ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም” ሆነ። እንዲያውም ከዚያ በኋላ የሌላትን ባሕሪ ቁጥብ ሆና ቀረች፡፡ በቀን ዐሥር ጊዜ የምትደውለው ልጅ ካገባሁ በኋላ ጠፋች፡፡ አልፎ አልፎ ለዚያውም ጉዳይ ሲኖራት ነበር የምንደዋወለው። እቤት የምትመጣውም የሆነ ዝግጅት ኖሮ ስጠራት ብቻ ነበር፤ ለዚያውም አትቆይም። ዮናስ ለሰርጋችን፣ የሦስት ወር ፈቃድ ወስዶ ነበር ከአሜሪካ የመጣው። እያንዳንዷን ቀንና ሰዓት በስስት ሲቆጥርና ከዚህ ጊዜው ላይ እያንዳንዷን ሰከንድ እኔን ለማስደሰት ባለ በሌለ አቅሙ ሲጥር፣ ለእኔ ግን ሦስት ወር እንደዘላለም ነበር የራቀብኝ፡፡ ቶሎ አልቆ ወደመጣበት እስኪመለስ ጓጉቼ ነበር፤ ለሌላ ነገር አይደለም ወደዚያ ጠቅልሎ እስኪወስደኝ ድረስ ብቻዬን መሆን ነበር ፍላጎቴ፡፡ አሜሪካ ሄጃ ኑሮዬን ለመቀዬር አይደለም!... እዚሀስ ኑሮ ምናለኝ? እንዲያውም እዚያ በበርሚል ይታለባል ከሚሉት የሰማይ ላም፣በስኒም ቢሆን እዚህ እጄ ላይ ያለው ወተት ሳይሻል ይቀራል!? መሄድ ነው የምፈልገው...መሄድ። ከዚህች አገር መራቅ። ከትዝታዬ መሸሽ።

ተወልደን ካደግንበት ምድር የሚያፈናቅሉን ጠላት ብለው የፈረጁን ብቻ አይደሉም፤ አፈቀርናቼው ብለን አፈር እንዳይነካቼው ራሳችንን ከጫማቼው ሥር ያነጠፍንላቼው ጭምር እንጂ፡፡ እንዲያውም ይኼኛው ስደት ያማል፤ እየገፉን በልባችን ይዘናቼው እንሰደዳለን፡፡ ፈጣሪ በቸርነቱ ካልገላገለን ዕድሜ ልካችንን ነፍሳችንን የሚያነቅዙ ነቀዝ ተፈቃሪዎች፡፡ ተምሪያለሁ፡፡ በአካውንቲንግ ሁለተኛ ድግሪዬን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይዤ፣ በአዲተርነት እየሠራሁ ነበር፡፡ የገንዘብ ችግር አልነበረብኝም። የረባ ነገር ባላደርግ እንኳን ለራሴ በምፈልገው ልክ እኖራለሁ፡፡ የደረሰብኝ ነገር _ ስም የሌለው መዘበራረቅ ነው፡፡ ይኼ ነገር ወደ አእምሮ ሕመም ከፍ እንዳይል ስፈራ ነው የቆዬሁት፡፡ ብዙ ሴቶች በቀላሉ እንደ ቀልድ የሚያልፉት ነገር እንደሆነ አውቃለሁ፤ እኔ ግን አልቻልኩም፡፡ ከፍጥረቴ ልፍስፍስ ሆኜ ይሆናል፡፡ ወይም እኔ የተጋጨሁት ድንጋይና እነሱ የተጋጩት ድንጋይ ጥንካሬው ተለያይቶ አላውቅም...ብቻ ተጎድቻለሁ። ማልቀስ አልፈልግም፤ግን ሙሉ ቀን፣ ሙሉ ሌሊት ዕንባዬን አፍኜ መኖር ስቃይ ነው የሆነብኝ፡፡ ብቻዬን የምሆንበት አጋጣሚ ባገኝ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት አልቅሼ እንዲወጣልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ አንዲት ጠብታ ዕንባ ውስጤ እንዳትቀር አድርጌ ማልቀስ፡፡ አንዳንዴ እመኛለሁ፣ ፋርማሲ ውስጥ የሚያስለቅስ መድኃኒት ይኖራቼው ይሆን? ልክ የእንቅልፍ ክኒን እንደሚባለው በቃ የሚያስለቅስ፡፡ ዕንባ የሚያፈስ አይደለም፣ ከልብ ስቅስቅ አድርጎ የሚያስለቅስ፣ ውስጤ ያለውን እልኽ፣ የበታችነት፣ መገፋት፣ መጠላት፣ እንደ ጨው አሟሙቶ የሚያወጣ ዕንባ የሚያጎርፍ መድኃኒት፡፡ ሴት ደግሞ ዕንባ ቸገራት? የሚል አይጠፋም፡፡ እዚህ አገር ሴት ልጅ ከመበደሏ በላይ የሚያመመው ማልቀሻ አገር ማጣቷ ነው። ድፍረቱ የለኝም እንጂ የሆነ ሆቴል ክፍል ይዠ እስኪበቃኝ ባለቅስ ደስታዬ ነበር፡፡ ሰው ክፍል ይዞ መፋቀር ብቻ ነው እንዴ!? ክፍል ይዞ ቢያለቅስ፣ ኡኡ... ቢልስ!? ...ያም ስሜት ይኼም ስሜት፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍464👎2🔥2😢1
#አድዋ

የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል – ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፥ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፤
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካአጥንት፣
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፤
በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኧው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ
አፍሪካ፣
እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ…
የድል ታሪክሽን አውሪ።

#እጅጋየሁ_ሽባባው

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍24🥰7🤩1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ታዲዬስ ባለፈ ህይወቱ አንዴ አግብቶ ነበር፤ካገባት ሴት ውጭም ፍቅረኛ አለችው፤እስኪ በህይወቱ ውስጥ ስለነበሩና አሁንም በልብ ስፍራ ይዘው ስለሚገኙ ሁለት ሴቶች ታሪክ እንመልከት፡፡

ከሰባት አመት በፊት ታዲዬስ በምህንድስና ሞያ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ላይ በኤም.ኤች አማካሪ ድርጅት በሪዘዳንት ኢንጂነርነት ተቀጥሮ እየሰራ የነበረ ወጣት መሀንዲስ ነበር፡፡ በወቅቱ በማታው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሳይኮሎጂ መማር ከጀመረ ሁለት አመት አልፎት ነበር፡፡ ተከራይቶ ሚኖረው ከደራራ ሆቴል በጀርባ በኩል ያለውን መንገድ ተሸግሮ ከሚገኙ ቤቶች መካከል በአንድ ነው፡፡የተከራያት ቤት ባለሁለት ክፍል ስትሆን የቤቱ ባለቤት አቶ ቂጤሳ የተባሉ አዛውንት ናቸው፡፡አዛውነቱ የሚኖሩት ከብቸኛ
ሴት ልጃቸው ጋር ነው፡፡በጊቢው የሚኖር ሌላ ሰው አልነበረም፡፡

ታዲዬስ ከስራ ሲመጣ በስራ ጉዳይ ከሰዎች ጋር ሲጨቃጨቅ ስለዋለ ዝልፍልፍ ብሎ ነበር፡፡ ቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ እስኪዘረር ነው የቸኮለው፡፡የውጭውን የቆርቆሮ በር ከፍቶ ገባ ፡፡ የአቶ ቂጤሳ ብቸኛ ልጅ መርጊቱ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ስትክዝ አጋጠመው፡፡

‹‹..ሰላም ዋልሽ?››አላት፡፡

‹‹አልመለሰችለትም፡፡›› ብዙም አልደነቀውም፡፡ እንኳንም እንዲህ በደበታት ቀን ይቅርና በሰላሙም ቀን ያን ያህል ሚነገርለት ቅርርብ አልነበራቸውም፡፡ እንደውም ከእሷዋ ይልቅ በተሻለ ሁኔታ ከአባቷ ከአቶ ቂጤሳ ጋር ይግባባል፡፡አልፏት ትልቁን ቤት ዞረና ወደ ተከራየው ሰርቢስ ቤት አመራ፡፡ገብቶ አልጋው ላይ አሪፍ ከማለቱ በራፉ በቀሰስተኛ ሁኔታ ተንኳኳ፡፡መርጊቱ ነበረች፡፡

‹‹ሰላም ነሽ.. ፌናን፡፡››

‹‹ሰላም ነኝ...መፅሀፎችህን ልመልስልህ ነበር፡፡››ተመለከታት፡፡ በእጆቿ ሶስት መፅሀፎች ይዛለች፤ከእሱ የተዋሰችው ሁለት መፅሀፍ ብቻ ነው ‹‹ሶስት አድርጋ ለምን ትመልስልኛለች?››ግራ ገባው ፡፡በዛ ላይ ሁኔታዋ ጉስቅል ብላለች፤ ስታለቅስ እንደቆየች በአይኖቿ መቅላትና በጉንጮቿ ቲማቲም መምሰል ተረዳ፡፡

‹‹ምነው ..ሰላም አይደለም እንዴ?››

‹‹አይ ሰላም ነው..መጽሀፍህን ልመልስልህ ነው፡፡እነዚህ ካንተ የተዋስኳቸው ናቸው..ይሄ ደግሞ ራሴ የምወደው መፅሀፍ ነው እንደማስታወሻ ይሁንልኝ፡፡››

ተቀበላት..ፊቷን አዙራ ለመሄድ ከተንቀሳቀሰች በኃላ መልሳ ቆመች <<ታዲ..>>ብላ ጠራችው..ደነገጠ ፡፡እንደዚህ በቁልምጫ ጠርታው አታውቅም፡፡

‹‹እዚህ ሀገር እስካለህ አባዬን አደራ፡፡..››

‹‹እንዴ!! ምን ማለትሽ ነው?››

<< አንተ በጣም ጥሩ ሰው ነህ...ይሄንን ውለታ ዋልልኝ››እንባዋ ዝርግፍ ብሎ ፊቷን አጠበው፡፡ ታዲዬስ ከተቀመጠበት ተነሳና ክንዷን ይዞ ወደ ቤት በማስገባት ከአልጋው ጎን ያለ ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጣትና እሱ ከአልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ‹‹ምን ሆነሻል..እስኪ ንገሪኝ?››አላት፡፡

‹‹አይ የሚነገር አይደለም፤ብቻ ሀገር ለቅቄ ልሄድ ስለሆነ ነው፡፡››

‹‹ወዴት..?አባትሽ ያውቃሉ?››

‹‹ኧረ በፍጽም..አንተ ብቻ ነህ የምታውቀው፡፡››

‹‹እሺ የት ነው የምትሄጂው?››

‹‹የእውነቱን ንገሪኝ ካልክ ወዴት እንደምሄድ እኔም አላውቀውም፤ግን መሄዴ ግድ ነው፡፡››

‹‹መርጊቱ....እባክሽ እስኪ እንደወንድምሽ ወይም እንደ ሚስጥረኛ የሴት ጓደኛሽ አይተሸኝ ንገሪኝ?››

‹‹አይ ታዲ.. ያለሁበትን ሁኔታ እንኳንስ በአንደበቴ ለሌላ ሰው ላወራ፤ ለእራሴም መልሼ መናገር ይዘገንነኛል፡፡››

‹‹ለሆነ ሰው ካልተናገርሽማ ለችግርሽ መፍትሄ አታገኚም፡፡ይሄውልሽ እኔ የምትነግሪኝን ታሪክ ሰምቼ ልፍርድብሽ፣ልታዘብሽ ወይንም ላፌዝብሽ ፈልጌ አይደለም…ግን አንቺ መፍትሄ አልባ መስሎሽ ድፍን ያለብሽን ነገር ምን አልባት መውጫ መንገዱ ለእኔ ይገለፅልኝ ይሆናል፡፡››

‹‹አርግዤ ነው፡፡››

<<አርግዤ?>>


«አዎ!>>

‹‹በቃ ስላረገዝሽ ብቻ ነው አቅመ ደካማ አባትሽን ጥለሽ ለመኮብለል የወሰንሽው?››

«አልገባክም እኮ...::>>

‹‹ኧረ በደንብ ገብቶኛል..ካልሆነ እኮ ማስወረድ ትቺያለሽ፡፡››

‹‹ሞክሬያለሁ...ውርጃውን ከሞከርኩት እንደምሞት ተነገረኝ፡፡›› እየነፈረቀች ብሶቷን ተነፈሰች ፡፡

ተረጋግታ ዝም እስከምትል በትዕግስት ጠበቃት፡፡እሷም ትንፋሽ ወስዳ ንግሯን ቀጠለች‹‹.... እና ታዲዬስ ነገ በለሊት አባዬ በተኛበት ሹልክ ብዬ እሄዳለሁ...አደራ አጽናናው፤ደግሞ አሁን የነገርኩህን እንዳትነግረው..፡፡‹ትምህርት ጨርሳ ስራ መያዝ ባለመቻሏ ሰሞኑን ስትበሳጭ ነበር፤ስራ ፍለጋ ይሆናል ወደ ሌላ ሀገር የሄደችው በለው

‹‹ቆይ ተነጋግረን እኮ አልጨረስንም..ልጁ ቢወለድ ምን ችግር አለው?፤አባቱ እንኳን እምቢ ቢል ሰርተሸ ታሳድጊዋለሽ፡፡››

‹‹አልገባህም ያልኩህ እኮ ለዚህ ነው፡፡››

<<እንዴት?>>

‹‹ያረገዝኩት ባለፈው ከአሜሪካ መቶ ከነበረው ከአባዬ ታናሽ ወንድም ነው፡፡››በዚህ ጊዜ ነበር መርጊቱ ምን አይነት አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች ታዲዬስ የተረዳው::

<< የዛን ጊዜ አዲስ አበባ ይዞኝ ሄዶ እንደነበር ታስታውሳለህ አይደል..?ታዲያ አንድ ቀን በየጭፈራ ቤት እያዞረ ማላውቀውን መጠጥ ሲያጠጣኝ ካመሸ በኃላ ሁለታችንም ስክር ብለን ወደ ቤርጎ መግባታችንን አስታውሳለሁ..ከዛ ጥዋት ስነቃ እኔም ሆንኩ አጎቴ ዕርቃናችንን ተቆላልፈን ተኝተን ነበር፡፡ በርግጌ ተነስቼ የሆነውን ስመለከት ጭኔም አንሶላውም በደም ነጠብጣብ እርሷል፡፡አጎቴ
ሳየው በእርካታና በደስታ ይፍነከነካል፡፡ በጊዜው ባብድ ምንም መለወጥ ምችለው ነገር አልበነበረም፡፡አየህ እሱ ሆነ ብሎ አስቦ አቅዶ ያደረገው ነገር ነበር፡፡

በጣም የሚገርመው ግን በማግስቱም፣በሚቀጥለዉ ቀንም እሰከሚሄድ ድረስ በተመሳሳይ ደጋግመን በሀጥያቱ እራሳችንን አጨቀየን፡፡ ይሄው ውሎ አድሮ መዘዙ ተመዞ ለእኔ ለብቻ ተረፈ፡፡››

‹‹ለእሱ ማርገዝሽን ለምን አትነግሪውም..ምን. አልባት እኮ?››

አላስጨረሰችውም‹‹…እርሳው ፡፡ ላንተም እንዴት እንደነገርኩህ ግራ ገብቶኛል፡፡በፍፁም አላረገውም ፤ አጎቴን ልጅ ፀንሼልሀለው ብዬ ልነግረው አልችልም፡፡ደግሞ በህይወት ዘመኔ ከእሱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዲኖረኝ  አልፈልግም፤በል ለማንኛውም ቻው››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ጎንበስ ብላ ግንባሩን ስማ ወደ መውጫዋ አመራች፡፡

ታዲዬስ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ደመ ነፍሱ ሹክ አለው፡፡ የቤቱን ደጃፍ ተሻግራ ከመውጣቷ በፊት እጇን ይዞ አስቆማትና ‹‹መርጊቱ አንቺም አንድ ውለታ ዋይልኝ?››ሲል ጠየቃት፡፡

ገርሟት አፍጥጣ አየችውና <<እኔ በዚህ ጊዜ ላንተ ውለታ?››

‹‹አዎ ለእኔ፡፡››

‹‹እሺ ምን ላድርግልህ?››

‹‹ነገ እሁድ አይደል?››

«አዎ۰::>>

‹‹በቃ ነገ ዋይና ሰኞ ትሄጂያለሽ፤በሰንበቱ አባትሽንም ማሳቀቅ ጥሩ አይደለም፡፡››

‹‹ምንም ለውጥ እኮ የለውም፡፡››

‹‹አውቃለሁ፤ለእኔ ስትይ አንድ ቀን ...>>

ለደቂቃ በቆመችበት ካሰላሰለች በኃላ ‹‹እሺ እንዳልክ›› አለችው፡፡

‹‹አመሰግናለሁ...የሰጠሸኝን አደራ እንድወጣ ከፈለግሽ የሰጠሁሽን አደራ ፈፅሚ፡፡››

‹‹እሺ አልኩህ እኮ፡፡አንድ ቀን አይደል አንተን ደስ ካሰኘህ ግድ የለም እውላለሁ፡፡››ብላው ወጥታ ሄደች፡፡
👍8910
በጊዜው ታዲዬስ እሷን ከሸኘ በኃላ እረፍት አላገኘም…፡፡በምን ዓይነት መንገድ ይህቺን ልጅ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ሊረዳት እንደሚችል በቀላሉ ሊገለጽለት አልቻለም፡፡ እንዲሁ በሀሳብ ሲባዝን አምሽቶ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን የቻለው፡፡ሞባይል ስልኩን አነሳና ያሰበውን ወደተግባር ለመቀየር ያግዙኛል ወዳላቸው ሶስት ሰዎች ጋር  በተከታታይ የደወለው፡፡እቅዱን ለሁሉም በዝርዝር አስረዳና በእፎይታ እራሱን ለእንቅልፍ አሳልፎ ሰጠ፡፡

በማግስቱ ማለዳ 12 ሰዓት ነበር የአቶ ቂጤሳ ቤት በሶስት ሰዎች የተንኳኳው፡፡ድምፁን ሰምታ በድንጋጤ በመበርገግ በሩን ለመክፈት መኝታዋን ለቃ በራፍ ላይ ቀድማ የተገኘችው መርጊቱ ነች፡፡ ይሄ ያልተለመደ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ሰዓት ማን ነው?ማን ሞተ..…?‹‹ተልባ ቆይዋ እያለች..ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት››የሚለው ሀገራዊ ብሄል በአዕምሮዋ ተሰነቀረ፡፡እሷን ማን ቀደማት?የትኛው ዘመድ ነው ከእሷ ጋር ፉክክር የገጠመው…?ማነው ቀድሟት የሞተው?ምን አለ አንድ ቀን ዘግየት ብሎ ቢጠብቋት ወይም ምን አለ አንድ ቀን ፈጠን ብትል? በሰከንዶች ሽርፍራፊ ይሄን ሁሉ እያሰላሰለች በራፉን ስትከፍት ሶስት ጎልማሳ ወንዶች በራፉን ሞልተው ቆመዋል፡፡

‹‹ምንድ ነው? ምን ተፈጠረ?››

‹‹ተረጋጊ ሰላም ነው፡፡››

‹‹በዚህን ሰዓት የምን ሰላም?››

‹‹ኧረ ሰላም ነው ፤ አባትሽን ማናገር ፈልገን ነው፤ቤተክርስቲያን ሳይሄዱ ልንደርስባቸው ስለፈለግን ነው በማለዳ የመጣነው፡፡

በድንጋጤ የሚንቀጠቀጠው ሰውነቷ ሳይረጋጋ ከበራፉ ገለል አለችና እንዲገቡ ፈቀደችላቸው፡፡

‹‹ግቡ ..ይቅርታ ቤቱ ግን እንደተዝረከረከ ነው፡፡››

‹‹አረ ግድ የለም፤ይልቅ አባትሽን ቀስቅሺልን፡፡››

‹‹እሺ ››ብላ ዞር ስትል አቶ ቂጤሳ ተነስተው ከመኝታ ቤታቸው በመውጣት ሳሎን ደርሰው ነበር::

መርጊቱ ትታቸው ወደ መኝታ ቤት ገባችና ጆሮዋን ግድግዳ ላይ ለጥፋ ማዳመጡን ቀጠለች፡፡

‹‹ሰዎች ምነው በሰላም ነው? አረ ቁጭ በሉ፡፡››

በተርታ ተገትራው የነበሩት ሶስት ሰዎች በአክብሮት እጅ እንደመንሳት አሉና ‹‹የመጣንበትን ጉዳይ ሳንናገር መቀመጥ አንችልም፡፡››

‹‹እኮ ቁጭ በሉና ትናገራላችሁ፡፡››

‹‹ኧረ ግድ የለም ቆመን ይሻላል፡፡››

‹‹እሺ ምን እግር ጣላችሁ?››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን እንድትሰጡን ልንጠይቅ ነው፡፡››

‹‹ልጃችሁን ለልጃችን?››አቶ ቂጤሳ ቃሉን መልሰው ደገሙት፡፡መኝታ ክፍል ሆና ስታዳምጥ የነበረችው መርጊቱ የምትሰማው ነገር የተዓምር ያህል አስደነገጣት፡፡ማን ነው
ላኪው? መቼስ እዚህ ቤት ከእኔ ሌላ ሌላ ሴት የለም፡፡የትኛው አፍቃሪዬ ነው እኔን ሳያማክር ለጋብቻ ሚስኪኑ አባቴ ጋር የላከው? በፍቅር የሚጎመዣትና ስትወጣ ስትገባ የሚለክፏትን አንድ ሶስት ወንዶች በምናቧ መጡላት፡፡ከእነሱ መካከል አንድ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነች፡፡ አሳቃትም፣ አሳዘናትም፡፡ሁለቱም ስሜት እኩል ነው የተሰማት፤አንድ ላይ ተዋህዶ አንድ ላይ ተጨፍልቆ፡፡መቼስ እርጉዝ መሆኗን እያወቀች ብትፈልግ እንኳን ይሄንን የጋብቻ ጥያቄ መቀበል አትችልም፤በሀጥያት ላይ ሌላ ሀጥያት አትጭምርም፡፡ጆሮዋን የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ እንደለጠፈች ሳሎን የሚካሄደውን ትዕይንት መከታተል ቀጠለች፡፡

‹‹ለመሆኑ ልጁ ማን ነው?››አባቷ ጠየቁ፡፡

‹‹እኮ ማ ነው? የእሱንና የቤተሰቦቹንም ማንነት ንገሩኝ?››

ያው እርሷ ባያውቁም ልጃችንና ልጆት ለረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ነበሩ፤በጣም ይዋደዳሉ፤ያው አሁን መምጣታችን ነገሩን ሁሉ በእርሷ ፍቃድ እንዲሆን ስለፈለግን ነው፡፡››

‹‹ሰዎች ለምን የጠየቅኳችሁን አትመልሱም..? ልጁ ማን ነው?››ጋሽ ቂጤሳ ትግስት አጠራቸው፡፡

መርጊቱ ደግሞ ከሽማግሌ ተብዬዎቹ የምትሰማው ነገር ግራ አጋባት‹…እንዴ እንዲህ አይነት ውሸት አለ እንዴ?ማነው እንዴህ በድፍረት አይን ያወጣ ውሸት አሲዞ ሽማግሌዎችን የሚልክ?እሱ ተዋርዶ እነሱንም የሚያዋርድ?›› ተንደርድራ ወጥታ ለሽማግሌዎቹም ለአባቷም ምንም አይነት ፍቅረኛ እንደሌላትና ማንንም ማግባት እንደማትፈልግ ነግራቸው ነገሩን ለማሳጠርና ሁሉንም ከድካም ለመገላገል ወሰነችና ወደ ሳሎን ሳሎን ለመግባት መኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ አንድ እግሯን ስታነሳ ‹‹ጌታዬ ልጁ ታዲዬስ  ነው፡፡››የሚል ድምጽ ከሽማግሌዎቹ ሰማች... ባለችበት ደንዝዛ ቆመች፡፡

‹‹ታዲዬስ….ታዲዬስ የቱ?››

‹‹ታዲዬስ መሀንዲሱ ..እዚሁ እርሶ ቤት የሚኖረው፡፡››

አቶ ቂጤሳ ከመደንገጣቸው የተነሳ በተቀመጡበት እጆቻቸውን ጭንቅላታቸው ላይ ጫኑና አንገታቸውን ወደ መሬት ደፍተው ማሰላሰል ጀመሩ፡፡‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል?››አንድ ቀን እንኳን የረባ ጫወታ ሲጫወቱ፣ሲቀላለዱ ወይም ሲላፉ አጋጥሞቸው አያውቅም፡፡ሁለቱም እርስ በርስ ከመሳሳብ ይልቅ የመገፋፋት ባህሪ ነበር ዘወትር የሚያታይባቸው፡፡እንዴት ከእሷቸው በዚህን መጠን ግንኙነታቸውን መሰወር ቻሉ?

‹‹እሺ ያላችሁትን ሰምቼያለሁ፤ጉዳዩን ከልጅቷም ከዘመድ አዝማድም ጋር ልማከርበትና መልሱን ለሳምንት ልስጣችሁ፡፡››
በደመነፍስ እግሯን እየጎተተች በጓሮ በር ወጥታ ወደ ታዲዬስ ክፍል አመራች፤አንኳኳች፤ ከፈተላትና ወደ መኝታው ተመለሰ፡፡ ምንም ሳትናገር ወደውስጥ ገባችና በራፉን ዘጋችውና ወደ አልጋው በመውጣት ከውስጥ በመግባት ዝም ብላ ከጎኑ ተኛች፡፡ በአድናቆትና በዝምታ ተመለከታት፡፡ በጣም ደንግጣለች፤ በእንቅልፍ ልቧ እየተጓዘች የመጣች ትመስላለች፡፡ዝም ብሎ አይኖቾ እንባ ያመነጫሉ፡፡ከሃያ ደቂቃ የዝምታ ጊዜ በኃላ << ታፈቅረኝ ነበር እንዴ?››በማለት ያልጠበቀውን አደናጋሪ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

ግራ ተጋባ‹‹ምን አልሺኝ?››

‹‹ታፈቅረኝ ነበር ወይ ?ሳትዋሽ ንገረኝ፡፡››

‹‹በፍቅር እኮ ውሸትም ይሉኝታም አይገባም፤ፈጽሞ አፍቅሬሽ አላውቅም፡፡››

ሰውነቷ በደቂቃዎች እንደበረዶ ቀዘቀዘባት‹‹ታዲያ ለምን?አስበኸዋል ግን? ሰው ያፈቀረውን እንኳን ለማግባት ሞራል ባጣበት ጊዜ አንተ የማታፈቅራትን ለዛውም እርጉዝ የሆነችን ሴት ለማግባት መስዋዕትነትን ለመክፈል የፈለከው ?ነው ወይስ የውሸት ድራማ እየተጫወትክ ነው፡፡?››

‹‹የውሸት አይደለም፤ የእውነት ነው የማገባሽ..ማለቴ እንጋባለን፤አብረን እንኖራለን፡፡…ያለምንም ግንኙነት፤ልጅሽን ወልደሽ ሁኔታዎች ከተስተካከሉ በኃላ አልተስማማንም ብለን እንፋታና አንቺም የፈለግሽውን ማለት የሚያፈቅርሽንና የምታፈቅሪውን ታገቢያለሽ፤ እኔም እንደዛው፡፡››

‹‹እኮ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ገብተህ ይሄን ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ለምን ለመግባት ፈለክ?እኔ ምን አድርጌልህ አውቃለሁ? አንድ ቀን እንኳን ልብስህን ልጠብልህ ወይም ቤትህን ላፅዳልህ ብዬህ አላውቅ፡፡››
ስለተደረገልሽ ብቻ አይደለም የሆነ ነገር ማድረግ ያለብሽ፡፡ደግሞም ላንቺ ብዬ አይደለም፤ ለአባትሽ ስል ነው፡፡አንቺ እንዳልሽው በዚህ ዕድሜያቸው ጥለሻቸው ብትጠፊ እርግጠኛ ነኝ ለአንድ ወር በህይወት አይቆዩም፤በመጨረሻ ዕድሜያቸው ለእሳቸው ይሄ አይገባቸውም፡፡››


ይቀጥላል

ዛሬ በጠዋት ተከስተናል ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ እስከማታ የተወሰነ ሰው #Sebscribe ካደረገ በክፍል #31 እንገናኛለን #Shareም አይረሳ  አመሰግናለሁ፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12112😱5😢2
#ስለ_አድዋ_አጭር_ማስታወሻ

ነገ አድዋ ነው የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የልደት ቀን፡፡ አድዋን ሳስብ ብዙ ነገሮችን አስባለሁ የተራራ ጫፎች እንደ ጦር ተስለው ይታዩኛል፡፡ ድራጎንን ገድሎ ብሩታይትን ከፍርሃት ነፃ ያወጣው ሰይፍ ነጸብራቅ #ምኒልክ መዳፍ ውስጥ ይታየኛል፡፡

አድዋ የነፃነት ቀን እንደሆነ አልጠራጠርም ነጭ ቡጢ በጥቁር መዳፍ የከሸፈበት፣ ብርቱ የንቀት ቋጥኝ የተደረመሰበት፣ አንገት በሃፍረት ከመዘለስ የዳነበት ቦታ እንደሆነ አልዘነጋም፡፡ አድዋ እኮ ግዑዝ ተራራ አይደለም ገበየሁን ያህል የጦር ሳተና ውጦ ጭጭ ያለ ጨለማ፣የእምየን ትዕግስት ተፈታተነ፣ የባራቴሪን ትዕቢት ትቢያ ያደረገ የነጭን ሴራ የበታተነ ሞገድ ነው፡፡ አድዋ የተራራ ሰንሰለት ብቻ አይደለም #የጣይቱን የሴትነት ብልሃት ያንጸባረቀ መስተዋት፣ የባልቻን ያህን ድፍረት ያሰናዳ ፣ የአባ መላን ብልሃት የሸረበ፣ለወገን ሃይል ወኔን ያቀበለ፣የባሻ አውአሎም ምስጢረኛ፣ ጀግኖችን በደም አጥምቆ የሀገር ፍቅር ማተብን ያሳሰረ መንፈስ ነው አድዋ፡፡ አድዋ ለኢትዮጵያውያን በዓል ብቻ አይደለም.. .ሳንባን በኩራት ወጥሮ ደረት የሚያስነፋ አየር፣ አንገትን ከመዘለስ ታድጎ ቀና የሚያደርግ ምርኩዝም ጭምር ነው፡፡

አድዋ የሰላም ወዳድ ትውልድና ህዝብ ቋሚ ምስክር አርማ ነው ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ የጣይቱ ንግግር መጥቀስ በቂ ነው

“እኔ ሴት ነኝ፡ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡" ተጨማሪ ካስፈለገ አያልቅም

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፤ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ ሀበሻ" የሚለው ስነ ቃላዊ ግጥም ውስጥ የምንይልክን ብሎም የኢትዮጵያውያንን ሰላም ወዳድነት ማሳያ ነው በግጥሙ ውስጥ በግልጽ እንደተመለከተው #ምኒልክ ባያነሳ ጦር አይደለም የተባለው . . .ጋሻ ነው፡፡ ጋሻ ደግሞ ራስን ለመከላከል እንጂ ጠላትን ለማጥቃት የሚውል መገልገያ አይደለም፡ እናም ሀበሻ በአዘቦት "የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል. ." እንደሚለው ምኒልክ ክተት አውጆ ጋሻውን አነሳ፣ ሀገሬው አልገዛም ባይ፣ አሻፈረኝ ባይ፤ በየጎራው ላይ" እያለ ባለትዳሩ ምሽቱንና ልጁን፣ ያላገባው ኮረዳና አጎጠጎቴውን (የከንፈር ወዳጁን) ተሰናብቶ ተከትሎት አድዋ ላይ ተገናኙ እናም አድዋ ከገፊዎች ሳይሆን ከተገፉት ጎራ ቆመ ግዑዝ መልክዓ ምድር ብቻ አይደለም፤ የሀበሻ የልብ ወዳጅም ጭምር ነው፡፡ .ስለዚህም አድዋ"
፨፨
የአድዋን በዓል ስናነሳ በቅድሚያ ከሚጠቀሱት ቋሚ ቅርሶች አንዱ የአፄ ምኒልክ ሐውልት ነው፡፡ ሐውልቱን ያሠሩት ንግሥት ዘውዲቱ ሲሆኑ የቆመው የአባታቸው የአፄ ምኒልክ ማስታወሻ እንዲሆን ታስቦ ነው፡፡

የሐውልቱን ንድፍ ያወጣው ጀርመናዊ አርክቴክት ሀርቴል ስፔንግለር ነበር፡፡ ሐውልቱም የተቀረፀው ጀርመን ሀገር ሲሆን የተሰራውም ከነሐስ ነው፡፡ ሐውልቱ ከጀርመን ሃገር ተሠርቶ ከመጣ ወዲህ የሚቆምበት ቦታ በዝግጅት ላይ እያለ ንግሥት ዘውደቱ በድንገት መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡ ነገር ግን የተጀመረውን ሥራ የንግሥቲቱን አልጋ የወረሱት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እንዲጠናቀቅ በማድረግ በንግሥናቸው በዓል ዋዜማ ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም. በታላቅ ክብር በንጉሠ ነገሥቱ ተገለጠ፡፡

ከሐውልቱም ግርጌ ዘመን የማይሽረው ጥቅስ የተቀረፀ ሲሆን እንዲህም ይነበባል፡-

‹‹ከትልቅ ወይም ከትንሽ ቢሆን መወለድ ሙያ አይደለም ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው፡፡››

ሃውልቱ በዳግም ፋሽስታዊ ወረራ ወቅት በማርሻል ግራዚያኒ ወርዶ ተቀብሮ የነበረ ቢሆንም ከነፃነት በኋላም ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ

እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ቀድሞ በነበረበት ቦታ ሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም. እንዲቆም ተደርጓል፡፡

እምየ ምኒልክ ከአድዋው ድል በኋላ ብዙ መሰረተ ልማት በመዘርጋትና ስልጣኔን በማስገባት የሰላም ጊዜ ጀብደኝነታቸውን አስመስክረዋል፡ከነዚህ አንዱ ለሆነው የባቡር ፕሮጀክት ህዝቡ አንድ አንድ ጠገራ ብር ለማዋጣት ማቅማማቱን ሲሰሙ ታህሣሥ 29 ቀን 1900 ለመምህር አካለ ወልድ በፃፉት ደብዳቤ ላይ ይህን ብለው ነበር "ስለምድር ባቡር ሥራ ገንዘብ አውጡ ባልነው ሰው አለቀሰ ብለው የላኩብኝ ደብዳቤ ደረሰኝ… ይህስ ከእንቅልፌ ለምን ቀሰቀሳችሁኝ እንደማለት ያለ ነው እንጂ በጭራሽ አንዳንድ ብር አውጡ ቢባል የሚጎዳ ሆኖ አይደለም።" እኔም እላለሁ ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅስ መሪ ይብዛልን . . . ለመንቃት ግን አናመንታ፡፡

የአድዋ ዝክሬን የማጠቃልለው አፄ ምኒልክ ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን በጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ ሲሆን እንዲህ ይነበባል

"የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት። በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ። አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፣ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ'' አኔም ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ፡፡

🔸ዋግሹም ካሳ🔸


#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍346😁2
ዋ ! አድዋ !
(ሎሬት ፀጋዬ ገ /መድኅን

አድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥጉዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
አድዋ …
በአንቺ ብቻ ህልዉና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና …
ዋ !
አድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነቱዋ
በሞት ከባርነት ስርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰውብሽ እለት
አድዋ …
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
አድዋ ..
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
አፅምሽ በትንሳዔ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ህዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘዉ መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው በለው በለው በለው
ዋ …አድዋ !…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው በለው
ዋ …አድዋ …
አድዋ የትናንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና ::
ዋ ! . . . . .ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ . . . ..

#Share and #subscribe my #YouTube

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍25🥰32