አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ከወገቤ በላይ ወደፊትና
ወደኋላ ሄድ መለስ እያልኩ፣ አፌን በእጆቼ እየያዝኩ፣ የተመሳቀለ ጸጉሬን እየፈተልኩ፣ አፍጥጨ እያየኋት ጠየቅኳት፡፡

“ቲጂዬ ሳሙኤል የሚነግረው ይመስልሻል?”ድምፄ እየተንቀጠቀጠ፡፡

ነገሩን አልኩሽ እንጂ የት ተገናኝተው ይነግረዋል...?”

እፎይታ ተሰማኝ፡፡

የምሆነው ጠፋኝ፡፡ ተንስቼ አንዴ ወዲህ፣ አንዴ ወዲያ በጭንቀት ስንጎራደድ ዝም ብላ ታየኛለች፡፡

“ኩኩዬ በቃ ረጋ በይ... ዋናው እኮ፣ ይሄ ወሬ ከሳሙኤል ወደ ደሬ የሚደርስበትን መንገድ ካላ ማሰብ ነው፡፡ ማለቴ የወሬውን መንገድ ማጥፋት፤ አለ አይደል፣ ዱካ ማጥፋት” አለችኝ፡፡ ትንሽ ቆየት ብላ፡፡

በግርምት ዐየኋት። ልክ ናት። በጣም ልክ ናት።

ቶሎ ብላ፡፡

ቲጂ ከመርዛማ ውስኪ ውጪ የፖሊስ ጭንቅላት ነው ያላት፡፡

የውስልትና ዱካዬን ለማጥፋት፣ አብሬው በወሰለትኩት ሳሙኤልና በእጮኛዬ መካከል ያለውን የግንኙነት መሥመር
ማሰብ የመማገጤን ወሬ ወደ እጮኛዬ ደሬ ሊያደርስ የሚችለውን መንገድ
ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡

ኦኬ... ሳሙኤል... ሳመኤል ጋር መደወል አለብኝ፡፡

ባለሁበት እየተንቆራጠጥኩ ደወልኩለት፡፡

“ሄሎ ሳሙኤል ...የት ነህ?”

“ሄሉ...ቢሮ ነኝ... ምነው? እንደዛ ቻው እንኳን ሳትይኝ በናትሽ...?”

“በናትህ ሳሙኤል ጊዜ የለኝም... ስማ ይልቅ...”

“እ...?”

“ስለ ተፈጠረው ነገር ለማንም አላወራህም አይደል? በናትህ ለማንም
እንዳትናገር፡፡”

“ህም... ካሁን በኋላ አልናገርም እሺ” ሣቀ፡፡

“ሳሙኤል በማርያም! አታሹፍ፤ እጮኛ እንዳለኝ ታውቃለህ፡፡

በናትህ ለሰው ነገርክ እንዴ?”

“ዌል... ለዳጊ ኦሬዲ ነግሬዋለሁ

ሃሞቴ ፈስሰ፡፡ ውሃ ልኬ ተዛባ፡፡
ትንፋሽ ሰብስቤ፣

“ማነው ዳጊ... ዳጊ ማነው?”

እንዴ...! ዳግምን ረሳሸው እንዴ... የዛሬ ወር ኣካባቢ ሮሃ ምግብ ስንበላ አግኝተሽኝ ያስተዋወቅኩሽ የቢሮ ጓደኛዬ ትዝ አይልሽም...?”

“እህህ... እንዴ... አብሮህ የሚሰራው ቀዩ ልጅ ባልሆነ... አብሮህ የሚሰራው ያ ቀዩ ጸጉረ ሉጫው ልጅ ነው?” እንደ ጉድ
ተርበተበትኩ፡፡ እንደ ጉድ ተንተባተብኩ፡፡
መሆኑን አረጋገጠልኝ፡፡

ዳግም ሰማ አልስማ፣ ጉዳይ ኖሮኝ አይደለም መርበትበቴ፡፡ ብርክ
የያዘኝ ዳግምን አንድ ሁለቴ ከእጮኛዬ ደሬ እህት ጽዮን (በማላቀው
ምክንያት አምርራ ትጠላኛለች) ጋር ካፌ ቡና ሲያንቃርር ስላየሁት ነው፡፡

ተበጠበጥኩ፡፡

“ሳሙኤል... በናትህ የዳጊን ቁጥር ስጠኝ... ልደውልለት...” አልኩ፣
በድንጋጤ በሰለለ ድምፄ፡፡

“እ... ኦኬ... ቴ ክስት አደርግልሻለሁ” አለኝ፣ በፍጹም ግዴለሽነት፡፡

ስልኩን ዘግቼ ወዲህ ወዲያ እየተራመድኩ፣ ባሏ እንደሞተባት
ባልቴት ወገቤን ይዤ እያረገድኩ ቁጥሩን ስጠብቅ፤ ማን ደወለ? ጽዮን፡፡

“ኦህ... ማይ ... ጋድ!

የማደርገው ጠፍቶኝ
ስልኩን፣ አንዴ ቲጂን እያየሁ
ስርበተበት አንደኛው ጥሪ አበቃ፡፡ የሚካሄደው ነገር ያልገባት ቲጂ ፣

“ንገሪኝ እንጂ... ምንድነው እሱ...?" እያለችኝ ጽዮን እንደገና ደወለች፡፡ እነሳሁት፡፡

“ሄሎ..." አልኩ አሁንም በሰላላ ድምፄ
“አንች ሽርሙጣ! ድሮም አውቄው ነበር ..እይ ኔቨር ላይክድ ዩ
ለኔ ወንድም እንደማትመጥኚ አውቀው ነበር... ሽ...ር...ሙ..ጣ

ነገር ነሽ"

አለቀልኝ፡፡

      ጨርሰናል

አንባብያን በንደዚች ያለች አጋጣሚ ፎንቃችሁን ያጣችሁ እስኪ እጅ እያወጣቹ  ባይመለስም ትምህርት ነውና ንገሩን እስቲ ።


ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች ለናንተ ቀላል ነው ለኛም ማበረታቻ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍715👎3👏3
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አራት:- ትንሹ ተዐምር (2)

የታዴን ጥያቄ ተከትሎ ሃኪሙ መናገሩን ቀጠለ “…ዳሪክ ያለበት ሁኔታ እንዲህ ነው። ከደረሰበት ጉዳት፣ ህይወቱን ለመመለስ፣ ከተደረጉትም ከፈተኛ ኦፕራሲኖች የተነሳ ኢንድዩስድ ኮማ ውስጥ ልናስገባው ግድ ነበር። አሁን በደንብ ለማየት ባንችልም ይህ ልጅ እስከ መጨረሻው ያለመንቃት እድል አለው። የምንችለውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን። ነገር ግን አሁንም ህይወቱ የማለፍ፣ ኮማ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ወይም እስከ ህይወቱ ፍጻሜ የመቆየት፣ ወይም ቢነቃም ለከፍተኛ አካል ጉዳት የመጋለጥ እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው። እጅግ በጣም አዝናለሁ …ግን በህክምና እይታ የምናየው ይህ ነው። ….”

  ያስደነግጣል። ሃኪሙ የሚነግረን ልብን ያርዳል። ግን አንድ ነገር አለ። ሃኪሙ እንዳለው ይህ የህክምና እይታ ነው። የሰዎች እውቀት ጥግ ነው ይህን እያለ ያለው።

“…ዶክተር አንድ ጥያቄ ልጠይቅ?...” አልኩት

“…በሚገባ!...”  ዶክተሩ ወደኔ ዞሮ እያየኝ

“…መትረፉ ራሱ ተዐምር ነው ብለሃል አይደል?...”

“…አዎ ብያለሁ…”

“..ስለዚህ ዋናው ህይወቱ መትረፉ ነው ….” አልኩኝ  “ …የወደፊቱን የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ህይወቱን ያተረፈው ተዐምር ላያኖረው አልጀመረም።….ተዐምሩ ሊቀጥል ይችላል።….  አሁን ካላስቸገርን ማየት እንችላለን ዳሪከና ሳሌምን?....” ጠየቅኩኝ… በእውነትም ለማየት ጓጒቼ ነበር።

“…ልክ ነሽ…” አለ ሃኪሙ “…ህይወቱ መትረፉ ለኔ ከ አእምሮዬ ልክና መጠን በላይ ነው። ተዐምር ነው። ነገር ግን በህክምና እይታ ወደፊት ሊሆን የሚችለውን የመናገር ሃላፊነት አለብን። ማየት እንችላለን ወይ ብለሽ ለጠይቅሽ አዎ። የሁለቱንም ሁኔታ በቅርብ ወደ ምንከታተልበት  ወደ ICU ተውሰድዋል። በፈለጋችሁ ጊዜ ማየት ትችላላችሁ …” አሉንና ተለያየን።
*
*
  መጀመሪያ ታዴና ሌሎች የነበሩ የቅርብ ሰዎች ሳሌምንና ዳሪክ እየገቡ ጎበኙ። በመጨረሻም  እኔ እድሉን አገኘሁ። 

  ….እንግዲህ መጀመሪያ ሳሌምን ቀጥሎም ዳሪክን ስመለከት፣ ሳይ ያየሁት ይህንን ነው። ሳሌም ሳሌምን አትመስልም። ዳሪክም ሌላ ዳሪክ ሆኗል።

በተለይ ዳሪክ ያለበት ሁኔታ ያሳዝናል፣ ያንሰፈስፋል። አሁንም አየዋለሁ፦ ዳሪክን። ሳቅ የሚፈስበት ጠይም ፊቱ ጸጥ ብሏል። ፊቱ ላይ የሚታየው ስቃይ ከሱ አልፎ ለሌላ ሁሉ የሚሰማ ነው።

እጠይቃለሁ፦ እኔ።

ይመልሳል፦ ሃኪሙ።

“…ፊቱ ሲታይ ያመመው ይመስላል። ህመም ላይ ይሆን?....” ጠይቅኩኝ

“…ያለማቋረጥ የህመም ማስታገሻ መደሃኒት እየተሰጠው ነው።…” የተሰቀለውን መድሃኒት አሳየኝ “…ግን የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ ህመም አለው። ስለዚህ ህመም ቢኖርበት አይገርመኝም። ቅድም እንዳልኩት መትርፉ በራሱ ተዐምር ነው።… ኦ አር (OR) የነበረው ሁኔታና የሃኪሞችን ሪፖርት ሳነብ በቃ ይሄ ልጅ ከዚህ ዓለም እንዳይሄድ የሆነ ሃይል እየጠበቀው ያለ ነው የሚመስለው። በእንደ እዚህ አይነት ነገር ብዙም አላምንም። ነገር ግን ሶስት ጊዜ የልብ ትርታው ቆሞ የተመለሰም ሰው አይቼ አላውቅም። በቃ ነፍሱ በሁለት ሃይላት ጦርነት ውስጥ ያለች ነው የመሰለኝ። አንዱ ሊያድነው ሌላው ደሞ ሊወስደው የሚታገሉ ያህል ነው የሆነው።….”

ሃኪሙ ፈገግ አለ “…ዳሪክ በእድሜ ትንሽ ነው፣ በተክለ ሰውነቱም ትልቅ አይደለም። ግን እንደ ትንሽነቱ አይደለም። ‘…አልሞትም፣ ቀኔ ዛሬ አይደለም…’ ብሎ ታግሎ ያሸነፈ ነው የሚመስለው። ስለዚህ … ‘ትንሹ ተዐምር’…” ብለነዋል።

  …ሌሊቱን ሳልተኛ በማሳለፌ ወደ ቤት ሄጄ አረፍ ከማለቴ በፊት ….የዛን ለት ጠዋት ይህን ያህል ነው ያየኋቸው፦ ሳሌምና ዳሪክን። ወደ ቤቴ እየሄድኩኝ ማሰብ ጀመርኩኝ። በአንድ በኩል የሁለቱ ሁኔታ የሚያሳዝን፣ ልብን የሚስብር ነው። በሌላ በኩል ደሞ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ አልፈው በህይወት መትረፋቸው እጅግ በጣም ትልቅ ድልና እድል ነው።

   ተስፋ አለ። እምነት፣ ተስፋና ፍቅር ቤተሰቦች ናቸው። ተስፋ ካለ፣ እምነት አለ። ሁለቱን ደሞ የሚያያዝው ታላቅ ወንድም ፍቅር ነው። አሁንም ለርግቦቹ ተሰፋ አለ። እምነት ይህን ተስፋ ያያል። ህይወት ይሆናል። በመጨረሻ ፍቅር ደሞ ሁሉንም አያይዞ ያስራል።  ….ተስፋ አለ። በእምነት አይን ይህ ተስፋ ሲታይ ህይወትን ይሰጣል። ከህይወት ቡሃላ ደሞ ዳግመኛ ያ ታላቅ ፍቅር ለዳሪክና ሳሌም ይሆናል። አሁንም ቢሆን እነዚህ ሁለት ፍቅሮች እንደገና አይን ለአይን እየተያዩ አለምን የሚረሱበት፣ እጅ ለእጅ ተያይዘው እየተሳሳቁ በዙሪያቸው ያሉትን ሁሉ በደስታ የሚያሰክሩበት፣እስከ ፍጻሜያቸው ላይለያዩ በመውደድ ሰንስለት የሚቆራኙበት ቀን ቅርብ ነው። እንኳንም በህይወት ኖሩልን። እንኳንም ተረፉልን። ጌታ ይመስገን።

  ዳሪክን ሃኪሞቹ ‘ትንሹ ተዐምር’ ብለውታል። ትክክል ስም ነው። መልካም ስም ነው። ይገልጸዋል። ትንሹ ተዐምር ጀምሯል። ተዐምሩም ላያልቅ አልጀመረም። ትንሹ ተዐምር ትልቅ ሊሆን፣ ሊሰፋ፣ ሊያድግ፣ ሊወርስ ዛሬ ጀመረ።

ልቤ እርፍ አለ። ቤት ሄጄ ለሚቀጥሉት ብዙ ሰዐታት ተኛሁ።

   … የተረፈውን ቀንም … ሌሊቱንም በሚገባ አርፌ በሚቀጥለው ቀን በማለዳ እንደገና ዳሪክና ሳሌምን ላይ ሄድኩኝ። ትላንትና ቀኑን ለጥቂት ሰዐታት አርፎ ሌሊቱን ያደረው ታዴ ድካም ይታይበታል። እሰከ ከሰዐት እኔ ልቆይ እንደምችል ነገሬው ቤት ሄዶ እንዲያርፍና እንዲመለስ ሃሳብ ሳቀርብ አላመነም። “…ተባረኪ ልጄ…” ብሎ ወዲያውኑ ሄደ።

ሁለቱን ፍቅሮች ላያቸው ስገባ ዳሪክ ያለበት ሁኔታ ለውጥ የሌለው ነው፣ ሳሌም በሌላ በኩል ወደ ራሷ ወደ መልኳ መለስ ብላለች። ብቅ እያለች ነው።

አንዴ ዳሪክ ክፍል ሌላ ጊዜ ደሞ ሳሌም ጋር እየተመላለስኩ ሳያቸው፣ ያሉበትን ሁኔታ ስከታተል አረፈድኩኝ።

ወደ እኩለ ቀን አካባቢ ሳሌም ክፍል ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ ሙቪ እያየሁ ነበር።

ያላመንኩት፣ያልጠበቅኩት ነገር ሆነ።

ድክም ያለ ድምጿን ሰማሁት። በተሰባበሩ ቃላት፣ ድምጿ እየተጎተተ  “…የ.. ት ..ነው  ያ.. ለ.. ሁ ት?...”

ወደ ሳሌም ዞር ስል፣ ትላልቅ አይኖቿ ሽፋናቸው ገርበብ ብለው ተከፍተዋል።


© hassed agape fiker

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍6711🤔1
#ትንግርት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


...‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም፡፡>> በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ አባረረችኝ፡፡

በእንደዚህ ሁኔታ ነበርሰ ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ ተቀበላት፡፡."

ትምህርቷንም እንድትቀጥል አደረጋት፡፡ በወቅቱ እሱ ጋር ስትመጣ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ አሁን በዲፕሎማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሦስተኛ አመት ተማሪ ነች፡፡

....ሁሴን የሀሳብ ውቅያኖስ ተንፈራግጦ ሲወጣ እቤቱ ሞቆና ተጫጭሷ ነበር፡፡ ፎዚያ ቅድም የለበሠችውን ልብስ አውልቃ ድርያ ለብሳለች፡፡ ብዙውን ጊዜ የምትሸፍነውን ፀጉሯን በነፃነት ለቃዋለች፡፡ አጭር ቢሆንም ሉጫ ስለሆነ ለውበቷ ልዩ ድምቀት ለግሷታል፡፡

‹‹እሺ ፎዚያ ትምህርት እንዴት ነው?›› አላት፡፡

‹‹አሪፍ ነው፡፡አሁንማ ልጨርስ አራት ወር ብቻ ቀረኝ እኮ!››

‹‹በጊዜ ስራ ፈልጉ ማለትሽ ነው?››

‹‹ለስራው እንኳን ብዙም ጉጉት የለኝም፡፡ ዋናው ተምሬ እዚህ ደረጃ መድረሴ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ዕቅዴ አንተን በተሻለ መንገድ መንከባከብ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ባክሽ? እኔን ለመንከባከብ እኮ ሦስት ዓመት ሙሉ ኮሌጅ ገብቶ መማር አያስፈልግሽም ነበር

‹‹...እንዲህ ብለህ አታሳምነኝም...አንተ ለእኔ ምርጥ ወንድሜ ብቻ ሳትሆን አባቴም ጭምር ነህ ፡፡ብዙ ነገር አድርገህልኛል፡፡አላህ አንተን ባይጥልልኝ ኖሮ ዛሬ ዕጣ ክፍሌ የሰው ቤት ግርድና ካልሆነም ሽርሙጥና ነበር፡፡ስለዚህ የእኔ አንተን ለመንከባከብ መወሰን ያንስብሀል እንጂ አይበዛብህም፡፡››

‹‹...ፎዚ ለእኔም እኮ ምርጥ እህት ሆነሽኛል፡፡ ይሁን እንጂ እህትም አንድ ቀን የታለቅ ወንድሟን ቤት ጥላ የራሷን ቤት ትገነባለች፡፡ የወንድም ኃላፊነት ደግሞ እህቱ እዚህ ደረጃ እንድትደርስለት ማበረታታትና መደገፍ ነው፡፡ እርግጥ ነገሮች ቀላል አይደሉም፡፡ እኔም እኮ አንድ ቀን ስራ ይዘሽ ፣የፍቅር ጓደኛ አበጅተሸና ትዳር መስርተሸ ጥለሺኝ እንደምትሄጂ ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል፤ ቢሆንም ግን የግድ መቀበል እንዳለብኝ አምናለሁ፡፡

የፈላውን ቡና በመቅዳት ስኳር ጨምራ በማማሰል አቀበለችውና ለራሷም ቀድታ ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹እንግዲህ ውሳኔዬ የማይቀየር ነው፡፡ ምን አልባት አግብተህ ባለቤትህ ቤቱን ከተረከበችኝና ከልብ እንደምትንከባከብህ እርግጠኛ ከሆንኩ.. ያኔ ያልከውን አደርግ ይሆናል፡፡›

‹‹ዝም ብለን በባዶ ሜዳ እኮ ነው የምንጨቃጨቀው፡፡>>

‹‹እንዴት ማለት?›› ሁሴን ሊላት የፈለገው ምን እንደሆነ ስላልገባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ አሁን በቅርብ የማገባ ይመስልሻል? >>

‹‹ለምንድነው የማታገባው?››

‹‹ማን ነች ፍቃደኛ ሆና እኔን ልታገባኝ የምትችለው?››

‹‹በጣም ዕድለኛዋ ሴት ነቻ፡፡›› ፎዚያ ከምሯ ነው እውነተኛ ስሜቷን የምታወራው፡፡

‹‹አይምሰልሽ .. በዙሪያዬ ያሉ ሴቶች ሁሉ በፍቅር እንጂ ትዳርን ለሚያህል ቁም ነገር ብቁ እንዳልሆንኩ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡››

‹‹ይሄ አንተን በተመለከተ ትክክለኛ ምልከታ ነው ብዬ አላስብም፡፡›› አለች ቅሬታን በዛለ ድምፅ፡፡

‹‹እንዴት ... ? ሌላው ይቅር በአንቺ አመለካከት እኔ ለትዳር የምሆን ግለሠብ እመስልሻለሁ?›› ሲል ጠየቃት ፡፡

‹‹እውነቱን ልንገርህ?›› በታፈነ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዋ!.. ንገሪኝ ... ትክክለኛ ስሜትሽን ንገሪኝ፡፡››
‹‹እንግዲያው እኔ ሙሉ በሙሉ ያንተ አይነት ወንድ እስከማገኝ ትዳር ሚሉት ነገር አልሞክርም፡፡››
ደነገጠ፡፡ እንደምትወደው ያውቃል፡፡ ይሄን ያህል ተፅዕኖ ውስጥ እንደከተታት ግን ልብ ብሎ አስተውሎት አያውቅም፤ ውይይታቸው ከወትሮው በመጠኑም ቢሆን ጠንከር እያለ ስለመጣበት ርዕስ ለመቀየር ተገደደ፡፡

‹‹ኦ! ይሄ ቡናሽ ልዩ ነው፤ ከደባሪው እራስ ምታቴ ገላገለኝ›› አላት፡፡

‹‹ስለተሻለህ ደስ ብሎኛል፤በነገራችን ላይ ቀን ትንግርት መጥታ ነበር፡፡››

‹‹እንዴት ሳትደውልልኝ መጣች ..…?››

‹‹እኔ እንጃ፡፡ ሁኔታዋ ግን ከወትሮው የተለየ ሆነብኝ፡፡ ሁሉ ነገሯ ወደ ኖርማል ተመልሷል... አገባች እንዴ?›› የገረማትን ነገር ጠየቀችው፡፡

‹‹አይመስለኝም.. ስራ ግን ቀይራለች›› መለሠላት፡፡

<<ለማንኛውም የሆነ ዕቃ አምጥታልሃለች፡፡ >>

‹‹ምን አይነት ዕቃ? >> ለማወቅ በተጣደፈ ስሜት ጠየቃት፡፡

‹‹እኔ እንጃ ሥዕል መሠለኝ፤ታሽጓል፡፡ መኝታ ቤት አስቀምጬልሀለሁ፡፡››

ተስፈንጥሮ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ፡፡ በግምት ሠማንያ በስልሳ የሚሆን በፍሬም የተወጠረ፤ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ሸራ አገኘ፡፡ በጥድፊያ ልባሱን አነሳው፡፡የሚያፈዝ ስዕል ነው፡፡ የጥንት ንግስቶች የሚለብሱትን አይነት አብረቅራቂ ወርቀዘቦ ልብስ የለበሠች እንስት ትታያለች፡፡ እግሮቿ መሬት አይረገጡም፡፡ በአየር ላይ የምትራመድ ትመስላለች፡፡ ፀጉሯን ንፋሱ እያንሳፈፈው በአየር ላይ ተበታትኖ ሲታይ ሰማይ ጠቀስ ማማ ላይ የተሰቀለ የታላቅ ሀገር የተከበረ ባንዲራ ይመስላል የእጆቿ ጣቶች ውበታቸው የገነት ደናግሎችን አይነት ነው፡፡ በቀኝ እጇ ዓይነ ሥውሮች የሚጠቀሙበትን አቅጣጫ መጠቆሚያ ነጭ ዘንግ ይዛለች፡፡ ፊቷ የተለየ ነው፡፡ እንደ ሠው ዓይን፣ አፍንጫ፤ ከንፈር ሳይሆን በቦታው የሙሉ ጨረቃ ቅርፅ ይታያል፡፡ በጨረቃዋ ዙሪያም በህብረ ቀለም የደመቀ የብርሃን አምድ ያንፀባርቃል፡፡የሥዕሉ ጥልቀትና ምጥቀት... ውስጡ የተዳፈነውን የፍቅር እቶን ቀሠቀሠበት፡፡ የናፍቆት እሳት መላ ሰውነቱን ሲለበልበው ተሠማው፡፡

ትንግርት መጽናኛ የሚሆነውን ውድ ስጦታ ስላበረከተችለት ከልብ አመሠገናት፡፡ ፊት አልባ ሥዕል የተሳለላት ድብቋ ደራሲ ግን በምን ተአምር በአካል ሊያገኛት እንደሚችል ከመቼውም ጊዜ በላይ ግራ ገባው፡፡ ስዕሉን እንደታቀፈ ወደ አልጋው ሄደና በጥንቃቄ ተኛ፡፡ የቀለሙ ሽታ ከደራሲዋ ሰውነት የሚመነጭ መግደላዊት ማሪያም የክርስቶስን እግር ያጠበችበትን የአልባስጥሮስ ሽቶ አይነት እንደሆነ ሁሉ በረጅሙ ስቦ ወደ ውስጡ ማገው.. የስሜቱ ጥጋ.. ጥግ ድረስ ገብቶ ለውስጡ ሀሴት እንዲሰጠው በመመኘት ፡፡ በስዕሏ ፋንታ ዋናዋንም አንድ ቀን በአካል አግኝቷት እዚሁ አልጋው ላይ እንዲህ አቅፎት በእጆቹ እየዳበሳት..በከንፈሮቹ እየመጠጣት. በትንፋሹ እያጋላት... በሙቀቱ እያቀለጣት... በፍቅሩ እያሰከራት አብሯት እንደሚተኛ ተስፋ በማድረግ…፡፡...

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች  በባለፈው #ፖስት 10 ሰው ብዬ 2 ሰው ብቻ ነው #ሰብስክራይብ ያደረገው 10 ሰው #ሰብስክራይብ አድርጉና ቀን በቀን እንልቀቅ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍116👏1513👎2😁1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ...‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም፡፡>> በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ አባረረችኝ፡፡ በእንደዚህ ሁኔታ ነበርሰ ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ ተቀበላት፡፡."…»
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አምስት፦ ስስ ፈገግታ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር 

“..ሙሉ ስምሽን ንገሪኝ?...”

“…ሳሌም ታደሰ ሃይሉ…”

“…ያለንበትን አመተ ምህረት ንገሪኝ?...”

“…ሁለት ሺ አስር…”

“…ያለንበትን ወር ታስታውሻለሽ?...”

“…ጁላይ …”

“…የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ማነው?....”

“…ባራክ ኦባማ….”

እዚህ ጋር ሳሌም ትንሽ የተናደደች መሰለች “… ይህን ሁሉ ጥያቄ የምጠየቀው ለምንድን ነው? …” የሚጠይቃት ሃኪም ላይ በትላልቅ አይኖቿ አፈጠጠች። “…የት ነው ያለሁት ንገሩኝ….”

( ….ቅድም … መጀመሪያ እይኖቿ ገርበብ ብለው ተከፈቱ ፦ የሳሌም። በሰከንዶች ውስጥም   ሙሉ በሙሉ ተከፍተው ታይ ጀመር። አዎ ሆኗል። አዎ ተደርጏል። አዎ ተፈጽሟል። ሳሌም ነቅታለች። እንዲህ በፍጥነት መሆኑ ሃኪሞችን ቢያስደንቅም ሳሌም ተመልሳለች። አሁን ይኸው እያወራች ነው ፦ ከሃኪሟ ጋር። እኔም በግርምት፣ በድንቅ ሳሌምን አያለሁ። ወሬውን እሰማለሁ።…)

“…ሳሌም ስሚኝ… በደንብ ስሚኝ…” ሃኪሙ  ቀረብ ብሎ አይን አይኗን እያየ “…ያለሽው ሆስፒታል ነው። ርዳታ እየተደረገልሽ ነው። ለምጠይቅሽ ጥያቄዎች መልስ መስጠት አለብሽ። የማስታወስ ችሎታሽን እንዳልጠፋ ወይም እንዳልቀነሰ ለማወቅ ያስችለኛል።….”

ሃኪሙ 'ሆስፒታል' ሲል ሳሌም ግራ በመጋባት አይነት አየችውና የተኛችበትን ክፍል ዙሪያውን መመልከት ጀመረች።

“…ሳሌም እይኝ። ወደ እኔ ተመልከች። ፎከስ …. ለመጨረሻ ጊዜ  የምታስታውሽውን ንገሪኝ። የት ነበርሽ? ምን እያደረግሽ ነበር? ከማን ጋር ነበርሽ?...” ጥያቄውን ቀጠለ።

ሳሌም አሁንም ግራ በመጋባት ማየት ቀጠለች። ለጥቂት ጊዜ አይኗን ክፍት ክድን አደረገችና “…ት/ቤት ነበርኩኝ መስለኝ ….  አይደል?.....” ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች

“…እርግጠኛ ነሽ?....”

“…አይደለም!...” ሳሌም የሆነ ነገር ያገኘች ይመስል በደስታ “…ከክላስ መልስ….ካፌው … ካፈው ውስጥ ነበርኩኝ። ከ ‘ዲ’… ጋር  ‘ከኔ መልዐክ’ …ጋር ነበርኩኝ….” ከዛ ቡሃላ ፊቷ ተቀየረ። በድንጋጤ፣ በጭንቀት ለሰከንዶች ጸጥ አለችና ጮኸች “…ዳሪክ…ዳሪክ…ዳሪክ… የኔ መልዐክ የት ነው ያለው?...ላየው እፈልጋለሁ። የት ነው ያለው?...ዳሪክ!…ዳሪክ!...ዳሪክ!...” ስሙን እየጠራች ከአልጋው ላይ ለመነሳት መጣጣር ጀመረች። ነገር ግን አቅሙም፣ ሃይሉም አልነበራትም። የሰውነቷም ህመም ሊያንቀሳቅሳት አልቻለም።

ከሁኔታዋና ከጩኸቷ የሆነውን ነገር ሁሉ እንዳስታወሰች ታስታውቃለች።

“…ሳሌም እንድትረጋጊ እፈልጋለሁ። ተረጋጊና ስሚኝ።…” ሃኪሙ ሊያረጋጋት እየጣረ። 

ሳሌም ግን የምትረጋጋበት ሁኔታ ላይ አልነበረችም “…ዳሪክ!.. ዳሪክ!... የኔ መልዐክ!... የኔ ፍቅር!... ዳሪክ !... ዳሪክ!.... ላይህ እፈልጋለሁ፣… አይኑን ማየት እፈልጋለሁ….  አሳዩኝ?  ልየው እባካችሁ?...እባካችሁ?...እባካችሁ? …. አይኑን ብቻ ልየው?...  ልየው?...በህይወት እንዳለ ብቻ፣ ሲተነፍስ ብቻ ልየው?... የኔ መልዐክ፣ የኔ ቆንጆ፣ የማፈቅርህ፣…  ልይህ አንድ ጊዜ….” እንባዋ እየወረደ፣ እያለቀሰች መለመን ጀመረች።

እንደገና ከተኛችበት ለመነሳት መታገል ጀመረች። ስትታገል ሰውነቷ ላይ የተሰካው አይቪ ና  ሌሎች የህክምና መሳሪያዎች ሊነቀሉ ሆነ።

ሃኪሙ ጥብቅ አድርጎ ያዛት።

“…ዳሪክ!... የኔ መልዐክ!... በህይወት አለ ብቻ በለኝ? አይኑን ብቻ አሳዩኝ? ዳሪክ!...ዳሪክ!...” በሳግ ድምጿ እየተቆራረጠ

“…ሳሌም ስሚኝ… ተረጋጊና ስሚኝ። ዳሪክ አለ። በህይወት አለ። አልሞተም።…”

“…አልሞተም? በህይወት አለ?...” ማልቀሷን አቁማ በጉጉት ጠየቀች

“…እህ…” በአውንታ ነቀነቀ

“…የት ነው ያለው?...”

“…እዚሁ ሆስፒታል ውስጥ ነው ያለው። …ተጎድቷል ግን በህይወት አለ። …”

“…ላየው እችላለሁ? ልየው? … እባክህን?.. እባክህን?.. እባክህን?…” የሃኪሙን አይን አይን እያየች መለመን ጀመረች።

“…..የተኛበት ክፍል ድረስ ሄደሽ ብታይው ደስ ይለኛል። ችግሩ ግን አሁን ባለሽበት ሁኔታ አንድ ርምጃ እንኳን የመራመድ አቅም የለሽም። ከጥቂት ቀናት ቡሃላ ….”

“…ጥቂት ቀናት ?....” ሳሌም ደንግጣ ጠይቀች። ድንጋጤዋ ለሚቀጥለው ሰከንድ የምትተነፍሰውን አየር የተቀማች፣ ጸሃይ በአይኗ ፊት ለዘላለም እንዳትወጣ የተከለከለች ያህል ነው።

“….ቀናት ቀርቶ ደቂቃዎች መቆየት አልችልም። …. ‘ዲ’ ዬን፣ ‘የኔን መልዐክ’፣ ‘የኔን ውድ’፣… በየደቂቃው ‘የምወድሽ’… ብሎኝ የማይጠግበውን ሳላይ ከዚ በላይ አንድ ደቂቃ መቆየት አልችልም።…” ሳሌም እንደገና እንባዋ መውረድ ጀመረ። “…አልገባህም እኮ ዶክተር እወደዋለሁ እኮ! …. አፈቅረዋለሁ እኮ!... እኔ እኮ በጣም አብዝቼ፣ ከልቤ፣ ከነፍሴ እወደዋለሁ እኮ!.... እወደዋለሁ እኮ!... ፊቱን ማየት እፈልጋለሁ፣ አንድ ጊዜ ብቻ….”

ሳሌም አንድ ጊዜ ሃኪሙን፣ ሌላ ጊዜ ነርሷን፣ ደሞ እኔን በተማጽኖ እያየች፣ እንባዋ ከትላልቅ አይኖቿ እንደ ጉድ እየፈሰሰ ድምጿ እየተቆራረጠ

“..እ..ወ..ደዋለሁ እኮ!”

“..አፈ ..ቅ..ረ..ዋ..ለሁ እኮ!"

“…እ.ወደ..ዋለሁ እኮ!...”

“…እ..ወ..ደ..ዋ..ለ..ሁ እኮ!...”

“… ‘የምወድሽ’ ይለኛል  እኮ ….  ሲጠራኝ  እኮ ‘የምወድሽ’…. እያለ ነው እኮ …. ማየት እፈልጋለሁ …. ‘የኔን መልዐክ’ ማየት አለብኝ…. ‘የምወድሽ’… ሲለኝ መስማት እፈልጋለሁ። እወደዋለሁ እኮ!... ፊቱን ማየት እፈልጋለሁ፣ አንድ ጊዜ ብቻ ….”

   ሳሌም ተማጽኖዋ፣ አለማመኗ፣ የቃላት አወጣጧ በጣም ያሳዝን ነበር። ሃኪሙም ነርሷም የሚያደርጉት አጥተው፣ ግራ ተጋብተው ሲተያዩ ሃሳብ መጣልኝ። የዛን ሰሞን የተጀመረው ፌስ ታይም (Face Time)።

“…እኔ አንድ ሃሳብ አለኝ…” አልኩኝ

ሳሌምም ሌሎቹም ዞር ብለው ተመለከቱኝ።

“….እንዲተያዩ ማድረግ እንችላለን። ‘ፌስ ታይም’ በመጠቀም። የምፈልገው ሌላ ‘አይፓድ’ ወይም ‘አይፎን’ ነው አልኩኝ…” ስልኬን እያወጣሁ።

ሃኪሙና ነርሷ ዝም ብለው ሲያዩኝ እንዳልገባቸው ስለተረዳሁ የፈስ ታይም አጠቃቀምን አጠር አድርጌ አስረዳሁ።

“…በጣም ጥሩ ሃሳብ…” አለች ነርሷ “…የኔን ስልክ መጠቀም እንችላለን…”ብላ ስልኳን አቀበለችኝ።

የሳሌም ፊት በደስታ አበራ።

ርግቦቹን በ‘ፌስ ታይም’ እንዲተያዩ ለማድረግ የፈጀው ደቂቃዎች ነበር።

ሳሌም ለመጀመሪያ ጊዜ ዳሪክን  ስታየው  ዳሪክ ያለበት ሁኔታ የሚያስደነግጣት፣ ልቧን በሃዘን የሚሰብረው ነበር የመስለኝ። ግምቴ ግን በትልቁ  ስህተት ነበር። የሆነው ተቃራኒ ነው።

ሳሌም  አላለቀሰችም።  

ሳሌም አላዘነችም። 

ይልቅስ በእንባዋ ታጥቦ በቀላው ፊቷ ላይ የበቀለው የፈገግታ ዘር ነው ፦ ‘ስስ ፈገግታ’።

ቀና ብላ በእፎይታ አየችኝና “… በህይወት አለ፣ የኔ መለዐክ አልሞተም።….”  የስልኩን መስታወት ቀስ ብላ በእጇ እየዳሰሰች

… ከዛ ቡሃላ አልተናገረችም፣ ቃል አልወጣትም። ዝም ብላ ታየው ጀመር። ያኔ ካፌው ውስጥ ቁጭ ብላ ስታየው እንደነበረው፣ ዝም.. ጸጥ ብላ በፈሻ ተጥቅለሎ ዳሪክ የማይመስለውን ዳሪክን ፊቱን በፍቅር፣ በመውደድ፣ በስስት ታየው ጀመር። ... ታየው ጀመር። ትክ ብላ  …ውስጡን ሰርስራ፣ በዐጥንቶቹና በጅማቶቹ ላይ ተንሸራታ፣ በደም ባንቧዎቹ ውስጥ ዋኝታ፣ በልቡ ትርታዎች ላይ ተሰፈንጠራ ፦ አዎ ነፍሱ ላይ  ነፍሷ ላይ የምትደርስ ‘ስኪመስል ታየው ጀመር።
👍475
ስታየው፣....ስታየው፣...ስታየው፣ ….ስስ ፈገግታዋ ከናፍርቷን አልፎ እየሰፋ ጉንጮቿን፣ አይኗን እየሞላ ፊቷ ላይ ፈሰሰ። እርጋታዋ መጣ። ጸጥታዋ ሆነ። ሳሌም ተመልሳ ሳሌም ሆነች። ሳሌም ተመልሳ ‘ሳሌም፣ሳሌም’ አለች።

በሳሌም ፊት ላይ የሚታየው ያ ‘ስስ ፈገግታ’ ዋጋው የማይገመት፣ የከበረ የፍቅር ብርሃን ነው።

ስስ ፈገግታዋ … ውበት ነው። በጸደይ ወቅት በሰፊ ሜዳ ላይ በብዛት አንድ ላይ ከፈነዱ እንቡጥ አበባዎች የበለጠ ቁንጅና ነበረው። ውብ ነው። ያምራል። ይስባል።

ስስ ፈገግታዋ … ብሩህ ነው። ፈገ ግታዋ ከሳሌም አንባ ቡሃላ ብቅ ሲልና እየሰፋ ሲሄድ  ከድቅድቅ የክረምት ጨለማ ላይ የማለዳ ጸህይ ብሩህ ሆና ብቅ ስትልና ብርሃኗ እየጨመረ ሲሄድ ያህል ነው።

ስስ ፈገግታዋ … የእውነት ነው ህይወት አለው። በቀለማት መስመር ክንፎቹ ያማረ ቢራቢሮ ከታሰረበት ቅርፊቱ ተላቆ፣ ነጻ ሲወጣ  ህይወት ሲዘራ፣ ሲበር፣ ክብ እየዞረ ሲጨፍር፣ ሲደንስ …. ይህንንም ከማየት ይበልጣል።

ስስ ፈገግታዋ …. የሳሌም!
*
*
ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍462
#ፍንጣሪው!

#አሌክስ_አብርሃም

የሆቴሉ በረንዳ ላይ አራት ሰዎች እየጮሁ ፖለቲካ ያወራሉ፣ እዚህ ጋ ብቻየን ቡና እየጠጣሁ ለተቀመጥኩ እኔ ሳልፈልግ ወሪያቸው ይደርሰኛል። በወሪያቸው መሀል አንዱ ጮክ ብሎ ...

"ያኔ ቦንብ ተወርውሮበት የሳቱት ጊዜ ..." አለ
ሌላኛው አቋርጦት "አልሳቱትምኮ" አለ። ዞር ብየ አየሁት፤ ምን እኔ ብቻ የሆቴሉ ሰው በሙሉ ወደተናጋሪው ዞረ። ደልደል ያለ ወዛም ጎልማሳ ነው። እኔም እንደሳቱት ነበር የማውቀው! የዚህ አገር ዜና ምኑ ይታመናል ብየ ጆሮየን አቆምኩ! አንዱ ከጥግ በማያገባው ገብቶ " ካልሳቱት እንዴት የምስራቹን (ማለቴ መርዶውን) እስካሁን ደበቁን? " አለ።

"ስተውታል እንጅ! ወዲያው መግለጫ ሰጥቶ የለም እንዴ?!" ሌላኛው በክርክር ድምፅ መለሰ።

" ምናለ እኔን ብትሰሙኝ ዓመት አላወራ ፤ ደብቀውን ነው እንጅ አልሳቱትም፣ 'የቦንቡ ፍንጣሪ እሱን ጭንቅላቱ ላይ ምክትሉንና አማካሪዎቹን ደግሞ ልባቸውን አግኝቷቸዋል ብሎ አንድ የታሪክ ምሁር ነግሮኛል" አለ፤ ጋባዢ ነው መሰል ማንም አልተከራከረውም!

"ለዛ ነዋ በሶስት ቀን ሰላሳ ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪ ያስጨፈጨፈው" አለ ከመካከላቸው በዝምታ የቆየው ሰውየ!

"ማን?" አለ ያ በማያገባው የሚገባው ሰውየ ግራ ገብቶት።
"ግራዚያኒ ነዋ !" አለው ደልዳላው እና ወዛሙ ሰውየ! ሁሉም ጉጉቱ ረገብ ብሎ ወደየራሱ ጨዋታ ዞረ። እኔ ደግሞ ፖለቲካ መስሎኝ ለካስ ታሪክ ነው የሚያወሩት! በነሞገስ አስገዶም ቦንብ ስለተወረወረበት ግራዚያኒ ምናምን። ድሮም ጮክ ብለው ሲያወሩ መጠርጠር ነበረብኝ።

ቡናየን ፉት አልኩና ቀና ብየ ወደሰማይ አየሁ ፤ ሰው አልባ የመንገደኞች አውሮፕላን በዝግታ የሚንሳፈፉበት ደመናማ ቀን ነበር። እስቲ ቡና ድገሚኝ!


ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍36😁27🔥43
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ስድስት፦ የሳሌም ሰሌዳ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

የኔ መልዐክ… የኔ ቆንጆ፣ የልቤ ግማሽ ዳሪክ ፦

   ዛሬ  ጃንዋሪ 15, 2011 ሲሆን ቀኑ ደሞ ቅዳሜ ቀን ነው። ያለኸው ኤቨረት (Everett) ከተማ ውስጥ የሚገኝ የህሙማን እንክብካቤ ማዕከል ነው። ስትነቃ አጠገብህ ከሌለው አትደንግጥ እኔ  በፍጥነት እመጣልሃለሁ።
                                       ያንተ ብቻ ሳሌም!

  ይህ ጹህፍ የሰፈረው ዳሪክ የተኛበት ክፍል ውስጥ ግድግዳ ላይ በተሰቀለ ትንሽ ነጭ ሰሌዳ ላይ ነው። በቀላሉ በዳስተር ወይም በእጅ ዳሰሳ መጥፋት በሚችል የተለያየ ቀለማት ባላቸው ማርክሮች መልዕክቱ ተጽፏል። ሳሌም ይህንን መልዕክት በየቀኑ፣ በጥንቃቄ አስውባ ትጽፋለች። መሽቶ ሲነጋ የወሩን ቀን ትቀይራለች። የሳምንቱን ቀን ታድሳለች፦ ሰሌዳው ላይ። ማዕከሉ ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ነርሶች ይህንን Salem’s Board (የሳሌም ሰሌዳ) ብለው ሰይመውታል።

ይህ የሳሌም መልዕክት ብቻ የሚጻፍበት የሳሌም የፍቅር ሰሌዳ ነው። ዳሪክ ከገባበት ሰመመን ሲወጣ፣ አይኖቹን ሲከፍት፣ ሲነቃ ምናልባት ሳሌም አጠገቡ ከሌለች እንኳን እንዳይደነግጥ፣ እንዳይሸበር …ሰሌዳው ላይ የተጻፈውን መልዕክት አይቶ እንዲረጋጋ በሳሌም ታስቦ የተዘጋጀ የሳሌም የፍቅር ቦርድ ነው።

ሰባት ወራት አልፈዋል…

  ሳሌም በሆስፒታሉ ውስጥ ከነቃች ቡሃላና ዳሪክ በህይወት መኖሩን ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ ከ አደጋው ለማገገም የወሰደባት ጥቂት ሳምንታት ብቻ ነበር። በአስደናቂ ፍጥነት ሙሉ በሙሉ ድና ተነሳች።  ሃኪሞች፣ ነርሶች፣ የሆስፒታሉ የአካል ብቃት ባለሙያዎች (Physical Thearapists) የሚሉትን፣ ከአደጋው ለማገገም የሚሰጡትን መመሪያና ልምምድ ተግታ ስትሰራ ለሆነ ተልዕኮ እየተዘጋጀች ያለች ነበር የምትመስለው። የትጋቷም ፍሬ ሲታይ ጊዜ አልፈጀም። ሳሌም ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተነስታ፣ ወደ ድሮ አካላዊ ማንነቷ ተመለሰች።

   ዳሪክ ግን ያው …ከአደጋው ቡሃላ ያለው ዳሪክ ነው። አሁንም አይኖቹ እንደተከደኑ ነው። በማሽን ርዳታ ይተነፍሳል። በሆዱ ላይ ባለ አነስተኛ ቀዳዳ በአነስተኛ ቱቦ በማሽን ምግብ ይሰጠዋል። ዳሪክ አሁንም ጥልቅ ሰመመን ውስጥ ያንቀላፋል። ሆስፒታሉ ውስጥ ለስድስት ሳምንታት ያህል ሲረዳ ከቆየ ቡሃላ አሁን ወደ ሚገኝበት፣ ተመሳሳይ ታካሚዎች ርዳታና እንክብካቤ ወደሚያገኙበት ማዕከል ተዘዋወረ። ሰባት ወራት… ዳሪክ አሁንም ዝም ብሎ በሰላም ተኝቷል። ሰባቱ ወራቶች ለዳሪክ አልጋ በአልጋ አልነበሩም።ሰባቱ ወራት መኝታ፣ ሰመመንና እንቅልፍ ብቻ አልነበሩም። ሶስት ጊዜ በተለያዩ ኢንፌክሽኖች ሆስፒታል ገብቶ ታክሞ ወጥቷል።

ባለፉት ሰባት ወራት በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ሳሌም ሁሌም ከዳሪክ ጎን ናት። ሳይጋነን ሃያ አራት ሰዐት አጠገቡ ነበረች። ምናልባት ወደ ቤተ ከሄደች ልብስ ለመቀየርና፣ ሻወር ለመውሰድ ነው። ዳሪክ በተኛበት አነስተኛ ክፍል ውስጥ ቀኑን ሙሉ አብራው ነች። ሌሊት ደሞ  ከአልጋው አጠገብ አነስተኛ የምትታጠፍ አልጋ ዘርጋታ ትተኛለች። ሁሉን ነገር ትታ ጊዜዋን በሙሉ ሙሉ በሙሉ ዳሪክን ለመንከባከብ ሰጥታ ነበር።

በጸሀያማ ቀን  … ሳሌም ከዳሪክ ጋር ናት።

በዝናባማ ውሽንፍር ቀን … ሳሌም ዳሪክ አጠገብ ነች።

በረዶ ለቀናት ሳያቋርጥ ቢወርድ …ሳሌም ከዳሪክ ጎን አልሄደችም።

ከሰኞ እስከ አርብ … ሳሌም ከዳሪክ ጋር አብራው ነበረች።

ቅዳሜና እሁድ ሳሌም ….ዳሪክን ብቻውን አልተወችውም።

ሳሌም በትላልቅ ውብ አይኖቿ የተከደኑትን የዳሪክ አይኖች እያየች፣ እንደ አጥር ዙሪያውን ከብባው አብራው ነበረች። ሳሌም ዳሪክን ለ አፍታ መለየት አልቻለችም።

  ባለፉት ወራት እኔና ሳሌም ከመቀራረባችን የተነሳ እንደ እህቶች ሆነናል። ባለኝ ጊዜ በሙሉ፣ ከሳምንቱ አብዛኛውን ቀን ከሳሌምና ዳሪክ ጋር አሳልፋለሁ። ሁለቱን ከማየት የበለጠ ደስ የሚል ነገር ምን አለ? የሁለቱን ፍቅር ማየት በራሱ ህይወት ነው። ፍቅር የለም ትለኛለህን? መውደድ ሞተ ትይኛለሽን?  እነዚህን ወጣቶች ማየት ግን፣ እነዚህን ልጆች መመልከት ግን ፍቅር ዛሬም መኖሩን ህያው ማረጋገጫ ነው።

ዳሪክን ለመንከባከብ ከሳሌም ጋር ብዙ ሌሊቶች አሳልፌያለሁ። ሳሌም ሌሊት ስትተኛ አንድ አይኗን ብቻ ጨፍና የምትተኛ ነው የምትመስለኝ። አንዳች ኮሽታ ከሰማች፣ ዳሪክ የሚተነፍስበት ማሽን ትንሽ ድምጽ ካወጣ፣ የነርሶች ኮቴ ከተሰማ…ሳሌም ተነስታ ቁጭ ብላለች። የዳሪክ ነገር ፈጽሞ፣ ፈጽሞ አይሆንላትም።

   ሳሌም ትነቃለች ፦ እጅግ ማልዳ። ተነስታ የዳሪክን እጆች ይዛ ትጸልያለች። ቀኑን በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፋ ትሰጣለች። በመቀጠል የመጀመሪያ ስራዋ የሳሌም ሰሌዳ ላይ የተጻፈውን  ነገር አጥፍታ እንደገና አሳምራ መጻፍ ነው። ቀኑን ሰሌዳው ላይ ትቀይራለች። መልዕክቱን በተለያዩ ቀለማት አሳምራ ስትጽፍ፣ ጥንቃቄዋ የሆነ ውስብስብ ጥበብ …አርት የምትሰራ ነው የምትመስለው። 

አንድ ማለዳ በሰሌዳው ላይ በጥንቃቄ ስትጽፍ ገርሞኝ አያታለሁ። “…ሴሌምዬ ትገርሚኛለሽ እኮ አጻጻፍሽ፣ጥንቃቄሽ …”

ሳሌም ፈገግ አለች “…አየሽ ሳዬ…. የኔ መልዐክ፣ የኔ ቆንጆ የሚነቃበት ጊዜን አላውቀውም። ምናልባት ምግብ ለማምጣት ወይም ባዝ ሩም በሄድኩበት ቅጽበት ቢነቃ … የት ነው ያለሁት? ቀኑ መቼ ነው? ብሎ ሊደነግጥ አይገባውም።…”

ሳሌም መጻፏን ቀጠለች።

    ሳሌም እንግዲህ እንዲህ ናት። ለዳሪክ ያላት ሃሳብ ይህን ያህል ነው። አጠገቡ በሌለችበት ጥቂት ደቂቃዎች ቢነቃ እንኳን ብላ እስክታስብለት ድረስ። ብዙዎች እኮ እኔን ጨምሮ ይህ ልጅ እስከ መጨረሻው ላይነቃ ይችላል ብለን አምነን ሊሆን ይችላል። ለሳሌም ግን የዳሪክ ከዚህ ከገባበት ሰመመን መውጣት፣ መንቃት ጥያቄ አይደለም። እንደሚነቃ አምናለች። እንደሚነቃ አይታለች። እንደሚነቃ እርግጠኛ ነች። የጸሀይን መውጣትና መግባት ያህል የዳሪክ መንቃት ለሳሌም የረገጠ ሃቅ ነው። የሷ ጥያቄ … መቼ ነው የሚነቃው የሚለው ነው? የማታውቀው ያ ዳሪክ አይኖቹን የሚከፍትበትን እለት ነው። የሳለም ዝግጅትም ለዛች እለት ነው።

    ቦርዱ ላይ መጻፍ ያለባትን ከጻፈች ቡሃላ ሳሌም ዳሪክን ንጽህና ትጀመራለች። ጸጉሩን ታበጥራለች። ፊቱንና ጥርሱን ታጸዳለች። ጥፍሩ መቆረጥ ካለበት በጥንቃቄ ትቆርጣለች። የመኝታውና አንሶላና አልጋ ልብስ ትቀይራለች ወይም ነርሶቹ እንዲቀይሩ ትጠይቃለች። ክፍሉ ውስጥ ያሉትን ጠረጴዛዎች ወንበሮች አጽድታ ታዘጋጃለች።…የዳሪክ ክፍል ሁሌም ስንዱ፣ ጽድት ያለና የተዋበ ነው። 

ይህን ሁሌ ለምን እንደምታደርግ ስት ጠይቅም …መልሷ “…የኔ ፍቅር ሲነቃ ምስቅልቅል ያለ ቤት ውስጥ ራሱን ማግኘት የለበትም…”  በአጭሩ መልሷ ይህ ነው።

ሳሌም ለዳሪክ የሳምንቱን ቀናት መርሃ ግብር አውጥታለች።

ሰኞ፦

…የሙቪ ቀን ነው። ሳሌም ከዳሪክ ጋር ቁጭ ብላ፣ እጁን ይዛ ሙቪ ታያለች። ብዙ ጊዜ ሁለቱም የሚያዩት የፍቅር ሙቪ ነው። ዲር ጆን፣ ዘ ኖት ቡክ ከቆዩትም ታይታኒክና ስሊፕለስ ኢን ሲያትል የሚሉትን ፊልሞች ሳሌም ስታይ ደርሼ አውቃለሁ።

ማክሰኞና አርብ ፦

… ጠዋት የመጻህፍት ቀን ነው። ሳሌም ዳሪክ የሚወዳቸውን የተለያዩ የአማርኛና የእንግሊዝኛ መጻህፍት ለዳሪክ ድምጿን ልስልስ አድርጋ ታነብለታለች። ከሰዐት ቡሃላ ደሞ ቀስ እያለች የእግሮቹንና የእጆቹን ጡንቻዋች ነርሶቹ ያሳዯትን ስፖርት ታሰራዋለች። ይህም በመኝታ ብዛት አካሉ እንዳይመነምን ይረዳዋል።
👍40🥰64👏2
እሮብና ቅዳሜ ፦

…መንፈሳዊ ቀናት ናቸው።  ሳሌም ለዳሪክ መጽሐፍ ቅዱስን ታነብለታለች። መንፈሳዊ ውብ መዝሙሮችን ታስደምጠዋለች ወይም አብረው ስብከት ይሰማሉ።

ሃሙስ ፦

…ብዙውን የስፖርት ቻናል ትከፍታለች። ዳሪክ የሚወዳቸውን የባስኬት ቦል፣ የፎት ቦል ወይም የሶከር ጨዋታዎች ቁጭ ብላ ታያለች። ዳሪክ ከሳከር(የማንቺስተር ዩናይትድ)፣ ከፉት ቦል ደሞ (የሲሆክስ) ቡድኖች ደጋፊ ነው። ሳሌም ብዙም የስፖርት አድናቂ ባትሆንም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ግን ተከታትላ ትከፍትና የዳሪክን እጆች ይዛ ዝም ብላ ታያለች። 

እሁድ፦

… በአብዛኛው የቤተሰብ ቀን ነው። ዳሪክን ለማየት የሚመጡ ወዳጆችና ቤተሰቦች፣ የሁለቱ ጓደኞችን ሳሌም ተቀብላ ሲጫወቱ የሚውሉበት ቀን ነው።

አንዳንድ ጊዜ ሳሌም የዚህ አለም ሰው አትመስለኝም። ለፍቅሯ ያላት መሰጠት። ለፍቅረኛዋ ዳሪክ ያላት ታማኝነት የዚህ የፍጥረታዊ፣ የምድራዊ አይመስልም።

በአንድ እለት ውስጥ…24 ሰአታት…1440 ደቂቃዎች…86400 ሰከንዶች አሉ። በነዚህ ውስጥ ሁሉ ልቧ ከዳሪክ ጋር ነው። ለኛ የሚያደክመው ቀን ለሳሌም ምንም አይደለም።

ለዳሪክ ፈጽሞ ሳሌም አትደክምም። ይልቅስ ፊቷ በደስታ ያበራል።

ለዳሪክ ምንም ቢሆን ሳሌም አትሰለችም። ይልቅስ ትላልቅ አይኖቿ “…ሰላም… ሰላም…” ይላሉ።

ለዳሪክ፣ ለፍቅሯ ሳሌም አትታክትም። ሃዘንና ደካም አይታይባትም። ይልቅስ በከናፍርቷ ላይ ከበዛ ሳቅ፣ ካነሰም ደሞ ስስ ፈገግታዋ እንዳለ ነው።

ሳሌም ትልቁ ደስታና እርካታ ዳሪክን መንካበከብ ነው። የሳሌም ትልቁ ምስጋና ደሞ ዳሪክ ዛሬም አጠገቧ መኖሩ ነው። ዳሪክ ትንፋሽ መተንፈሱ፣ የልብ ምቱ መሰማቱ … ዳሪክ በህይወት መኖሩ ብቻ የምስጋናዋ ምንጭ ነው። አንዳንዴ በማለዳ ተነስታ የዳሪክን እጆች ይዛ በጸጥታ ስትጸለይ እንዲህ የምትል ይመስለኛል  “…አባት ሆይ ተመስገን። ዛሬም ዳሪክ ..የኔ መልዐክ አጠገቤ በህይወት አለ!....”

ቀናት አርጅተው ሌሎች አዲስ ቀናት ይወልዳሉ። ሳምንታት እንደ በልግ ቅጠል ወድቀው ያልፋሉ። ክረምት በበጋ፣ ጸደይም በበልግ ተወርሰው ይሄዳሉ .... ሳሌም ግን ያው ሳሌም ነበረች:- በየቀኑ።

በማለዳ እጆቹን ይዛ ትጸልያለች … ከዛም … ‘የሳሌም ሰሌዳ’… ላይ በመጻፍ ቀኗን ትጀምራለች።

የኔ መልዐክ፣  የነፍሴ ክፋይ ዳሪክ
   ዛሬ ጃንዋሪ 16, 2011 ሲሆን ቀኑ ደሞ እሁድ ነው…ውብ ጸሀያማ ቀን ነው። ያለኸው   ኤቨረት ከተማ...

ሳሌም አፍቃሪና አማኝ ነበረች።

የሳሌምን ተስፋ ሊያደበዝዝ፣ አምነቷን ሊነቀንቅ ያለው  ሁኔታ የተፈጠረው ግን በሰባተኛው ወር አጋማሽ ላይ ነበር…
*
*
ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍279🥰2
#ትንግርት


#ክፍል_አስር


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


...ከጊዜ ማህፀን ውስጥ አስደናቂና አሰቃቂ የህይወት ታአምራቶች ተፀንሰው ሲወለዱ ታዝበናል፡፡

የግቢውን በር ዘበኛው እንደከፈተለት መኪናውን ቦታ አስይዞ ለመቆም እንኳን ትዕግስት አልነበረውም፡፡ ሞተሩን አጠፋና እየተንደረደረ ወደ ቤት ገባ፡፡ የውብዳር ብቻዋን መለስተኛ አዳራሽ በሚያክለው ሳሎን ቁጭ ብላ በባለ 36 ኢንች ፍላትስክሪን ሶኒ ቴሌቭዥን ፊልም እየተመለከተች ነው፡፡ ሊያናግራትም አልፈለገም፡፡ዞር ብሎም አላያትም፡፡ ሳሎኑን ሰንጥቆ መኝታ ቤቱ የገባው ላፕቶፑን ፍለጋ ነበር፡፡ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ ከፈተው፡፡ ዲስኩን አውጥቶ ከተተውና እስኪጫወትለት መጠበቅ ጀመረ፡፡ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፡፡

አምስት ሺ ብር ያወጣበት መረጃ ነው፡፡ ላለፉት ሦስት ቀናቶች ሠው ቀጥሮ ሚስቱን ሲያሰልላት ነበር፡፡ ቅጥረኞቹ ባዘዛቸው መሰረት ተከታትለዋታል፡፡ አዋዋሏን ቀርፀው ሙሉ መረጃውን በማስረከብ ብራቸውን ተቀብለው ተሰናብተውታል፡፡ በአንደበታቸው የነገሩት ነገር ባለመኖሩ ምስሉን አይቶ ጥርጣሬውን ከአዕምሮው እስኪፍቅ ቸኩሏል፡፡ሠሎሞን የውብዳርን ለማሠለል የወሰነበት ምክንያት ፀባይዋ፣ አለባበሷ፣አነጋገሯ ጠቅላላ ሁኔታዋ ከበፊቱ በተጋነነ ሁኔታ እየተለወጠ ስለመጣበት ነው፡፡ በእርግጥ መጣላትና መናቆር ከጀመሩ ዓመታት ቢቆጠርም እንደ አለፉት ሦስት ወራቶች ነገሮች መጠን አልፈው አያውቁም፡፡ በዚህም የተነሳ ስድስተኛ የስሜት ህዋሱ እንዲከታተላት ሹክ አለው፡፡

ኮምፒውተሩ መጫወት ጀመረ፡፡ መናፈሻ ቦታ ነው፡፡ ያምራል፡፡ ግቢው በዛፎች እና በአበቦች የደመቀ ነው፡፡ ትክክለኛ ቦታውን መለየት አልቻለም፡፡ የውብዳር የሚያምር ነጭ የፕላስቲክ ወንበር ላይ ተቀምጣለች፡፡ ከጎኗ የወንድ እግር ይታያል፡፡ ፊት ለፊታቸው ለስላሳ መጠጦችና በርገር ተቀምጧል፡፡ፊልሙ ተንቀሳቀሰ፡፡ የወንድየው እጅ ወደ የውብዳር ሰውነት ተንቀሳቀሰ ፡፡ እጁን እጇ ላይ አርጎ ያሻሻታል፡፡ ቀስ በቀስ የሠውዬው አካል እየታየ መጣ፡፡ እስከ ወገብ .. እስከ ደረቱ .. ፊቱ ከመጋለጡ በፊት ግን ነጭ የደንብ ልብስ የለበሰች አስተናጋጅ እፊት ለፊት ተደንቅራ ስክሪኑን ሞላችው፡፡‹‹ብሽቅ›› አለ ሠሎሞን፣የማወቅ ጥሙን በፍጥነት ማርካት ስላልቻለ ተበሳጭቶ፡፡

ከውስን ደቂቃዎች መቋረጥ በኋላ ፊልሙ ዳግም መጫወት ጀመረ፡፡ ሆቴል ውስጥ ነው፡፡ የሁለተኛ ቀን ቀረፃ መሆኑ የሚያስታውቀው የለበሠችው ልብስ የተለየ በመሆኑ ነው፡፡ አለባበሷ ወደ ግማሽ እርቃንነት ያዘነበለ ነው፡፡ አብሯት ያለው ወንድ ማንነት ወዲውኑ ነበር በእስክሪኑ ፊት ብቅ እንዳለ የለየው፡፡ በደንብ ያውቀዋል፡፡ ሹፌሯ ነው፡፡ ተንፈስ አለ፡፡ ማየቱን ግን አላቆመም፡፡ ቀጠለ፡፡ ሁለቱም ፊት ለፊት በማራኪ ብርጭቆ ውስኪ ቀርቧል፡፡ ግራ ገባው፡፡ ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡ በሳቅ የታጀበ ወሬ ያወራሉ፡፡

ምስሉ ድምፅ አልባ ቢሆንም የከንፈር እንቃስቃሴያቸው ሲታይ፣ በአብዛኛው እሱ ያወራላታል እሷ ትንከታከታለች፡፡ነገሮች
በተመሳሳይ ሁኔታ ለደቂቃዎች ከቀጠሉ በኋላ
አይን የሚስብ ነገር ድንገት ተመለከተ፡፡

የሹፌሩ እጅ በጠረጴዛው ስር አሻግሮ ወደ የውብዳር ጭን እያመራ ነው….፡፡ የለበሰችውን አጭር ጉርድ ቀሚስ ወደ ላይ ገፋ አድርጎ ማሻሸት ጀመረ፡፡ እሷም ግራና ቀኟን ተገላምጣ ከተመለከተች በኋላ ብሩህ የሆነ ፈገግታ ለግሳው፣ ከመቀመጫዋ ወደ ፊት ሸርተት ብላ ተጠጋችለት፡፡ ጣቶቹን ጭኖቿ መሀል ሰነቀራቻውና ማርመስመስ ጀመረ፡፡ ተጋጥመው የነበሩትን እግሮቿን ቀስ በቀስ እያላቀቀች... እየከፈተች መጣች፡፡ መረጋጋት እንዳልቻለች ከፊቷ መቀያየር መረዳት ይቻላል፡፡

ከንፈሮቿ ለንግግር በዝግታ ተነቃነቁ፡፡ የሆነ ነገር መለሰላትና እጆቹን ሰብስቦ አስተናጋጁን ጠራ፡፡ የማይሰማ ነገር እየነገረው እጁን ወደ ኪሱ ሠደደ፡፡እሷ ቀድማ ቦርሳዋ ገባችና
የተወሰኑ የብረ ኖቶችን አውጥታ ቀድማ ለአስተናጋጁ ሠጠችው፡፡
አስተናጋጁ እየተንደረደረ እንግዳ መቀበያ ቢሮ ሲገባ ታየ፡፡ ዳግመኛ እጁን ወደ ጭኖቿ አላከም፡፡ይልቁንም ወደ መጠጡ ሠደደና
ደጋግሞ ይጎነጭ ጀመር፡፡
እሷም ተመሳሳዩን እርምጃ ወሰደች  የተወሰነ ደቂቃ ካጠፋ በኋላ አስተናጋጁ ተመልሶ መጣና የማይሰማ ነገር ነገራቸው፡፡ ዝርዝር ብሮች አውጥቶ አስጨበጠውና እጆቿን ይዞ ከተቀመጠችበት አስነሳት፡፡ ወገቧን አቀፈና በጓሮ በር
ይዟት ወጣ። ፊልሙ ተቋረጠ፡፡ ሠሎሞን ላፕቶፑን
ወርውሮ
ከግድግዳ ጋር ሊያላትመው ፈለገ፡፡
ስሜቱን መቆጣጠር እየተሳነው መጥቷል፡፡ በዛ ሠፊ ሆዱ ሙሉ እሳት እየነደደበት ነው፡፡ፊልሙ መጫወቱን ቀጥሎል፡፡ አሁንም ወገቧን እንዳቀፋት ነው፡፡ የሆነ ፎቅ ደረጃ እየወጡ ነው፡፡ በመደዳ የተደረደሩ በሮች ይታያሉ፡፡
የተወሰኑትን ክፍሎች አልፈው ከሄዱ በኋላ ቆሙ፡፡ 2ዐ3 ቁጥር የተለጠፈበት ክፍል አጠገብ ሲደርሱ ከፍቶ ወደ ውስጥ ጎተታት፡፡ እየተፍለቀለቀች ተጎተተችለት፡፡ ቦርሳዋን ወለል ላይ ጥላ ጫማዋን ለማውለቅ ስትጣደፍ ይታያል፡፡ ትእይንቱ ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻለም፡፡ በራፉ ከውስጥ ተዘጋ፡፡ጠቅላላ ሠውነቱ ላይ ውሃ እንደከለበሱበት ሠው በላብ ተጠመቀ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበት ማሠብ እንኳን ተሳነው፡፡ መጮኽ... ማበድ... ዕቃ መስበር አሠኘው፡፡ ከሁሉ ነገር በላይ ፊት ለፊት መታለሉ አበገነው፡፡
፨፨፨

የውብዳር ሹፌር ያስፈልገኛል ብላ የጠየቀችው ከአምስት ወር በፊት ነበር፡፡እሷ እራሷ መንዳት እየቻለች ሹፌር ለምን እንዳስፈለጋት ሲጠይቃት፤ ከልብ ድካም በሽታዋ ጋር በተያያዘ ሀኪም ላልተወሠነ ጊዜ መንዳት እንደከለከላት ነበር ያስረዳችው፡፡ ለጉዳዩ ብዙም ትኩረት ሳይሰጠው ፡

‹‹ታዲያ ፈልጊና ቅጠሪያ ምን ችግር አለው፤ ገንዘብ እንደሆነ አለሽ›› ነበር ያላት፡፡
‹‹ገንዘብ ማን ጠየቀህ? የምታውቀው ደህና ሹፌር ካለ እንድታናግርልኝ እንጂ..፡፡››

‹‹እኔ በአንዲት ቀበጥ ወይዘሮ ትእዛዝ በየሱፐር ማርኬትና በየፀጉር መፈሸኛ ቤት ሲንከራተት ለመዋል ትዕግስት ያለው ሹፌር አላውቅም፡፡››

‹‹ባንተ ቤት አሽሙር ተናግረህ ልብህ ውልቅ ብሎል፡፡ በአጭሩ አልችልም ወይም ፍላጎት የለኝም አትልም፡፡ ይብላኝ ላንተ እንጂ ችግር የለውም፡፡ ካገኘሁ አገኘሁ ካላገኘው ደግሞ ለጊዜውም ቢሆን በታክሲ እጠቀማለሁ፡፡ ልጆቹን ወደ ት/ቤት የማመላለሱን ጉዳይ ግን አስብበት›› በማለት ነበር እየተቆናጠረች በቆመበት ጥላው የሄደችው፡፡

ሹፌሩ ተገኝቶ መኪናውን ለመያዝ ግን ሁለት ቀን ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡ ከየት አገኘሽው? በስንት ብር ቀጠርሽው? የመሳሰሉትን ጥያቄዎች አልጠየቃትም፡፡ ሹፌሩ የሃያ አራት ዓመት ገደማ አፍላ ጎረምሳ ነው፡፡ ‹‹ሳምሶን እባላለሁ›› ነበር ያለው በመጀመሪያ ቀን ሲተዋወቀው፡፡ ሚስቱና ልጆቹ ግን ሳሚ እያሉ ነው በቁልምጫ የሚጠሩት፡፡ ስራ እንደጀመረ ሰሞን ነገረ ስራው ሁሉ ባይጥመውም፣ ዋል አደር ሲል ግን ለልጆቹ የሚያደርገውን እንክብካቤና ልጆቹም ምን ያህል በፍቅር እንደተቀበሉት ሲገነዘብ ቅሬታውን ችላ ብሎ ተወው፡፡ይሄዋ ዛሬ ችላ የማለቱን ፍሬ እየተመለከተ ነው፡፡

ላፕቶፑን እንደያዘ እየተንደረደረ ወደ ሳሎን ሄደ፡፡ የውብዳር አሁንም ተረጋግታ ፊልሟን እያየች ነው፡፡ እሪሞቱን ከጠረጴዛ ላይ አነሳና ፊልሙን አጠፋው፡፡

ቀና ብላ አየችውና በንዴት የደፈረሱ አይኖቹን እየተመለከተች‹‹ምን ነው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ ከምታይው የተሻለ ሌላ ልብ አንጠልጣይ ፊልም አብረን እንድናይ ስለፈለኩ ነው፡፡ >> በማለት ከጐኗ ተቀምጦ ላፕቶፑን ለመክፈት ተዘጋጀ፡፡
👍7311😱9👏2👎1
የውብዳር ግራ ገባት…የባለቤቷ ነገረ ስራው አላማራትም፡፡ ከእሷ ጋር አብሮ ለማየት የሚጓጓለት ፊልም ምን አይነት ነው? ስትል በውስጧ አሰላሰለች፡፡ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ይሄንን የመሰለ ግብዣ ከእሱ ቀርቦላት አያውቅም፡፡

‹‹እየቀለድክ ነው?›› አለችው፡፡

በፍፁም በህይወቴ እንደዛሬ አምርሬም አላውቅም፡፡ አንቺ መሪ ተዋናይ ሆነሽ የተወንሽበትን ፊልም አብረን ብናይ ምን አለበት? ምንም ቢሆን እኮ ታማኟና ተወዳጇ ባለቤቴ ነሽ፡፡ >> በማለት ላፕቶፑን ከፈተውና ወደ እሷ አስጠጋላት፡፡በፍራቻና ግራ በመጋባት መመልከት ጀመረች፡፡ከጉሮሮዋ መድረቅ የተነሳ አፏን የምታረጥብበት ምራቅ አጣች፡፡ ሠውነቷ ሲንቀጠቀጥና እየዛለ ሲሄድ ለራሷም ይታወቃታል፡፡ መንቀሳቀስም ሆነ መናገር አልቻለችም፡፡ ከምትመለከተው ፊልም ላይም ፊቷን ዞር ማድረግ አልሆነላትም፡፡ እስኪጠናቀቅ አየች፡፡

ሠሎሞን ማለቁን ሲያይ ዘጋውና ከጐኗ ተነስቶ ፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡

‹‹እሺ አሁን መነጋገር የምንችል ይመስለኛል፡፡ >>

ለመናገር ከንፈሯን ማላቀቅ አልቻለችም፡፡ በፍራቻ የቀዘቀዙ ዓይኖቿን አንከባለለችበት፡፡

‹‹መልስ ስጪኝ እንጂ?››

<ምን ልበልህ?»

‹‹መነጋገር አለብን እኮ ነው የምልሽ፡፡ >>

<<መቼ?>>

<<ዛሬ አሁን እዚሁ::>>

‹‹አልችልም ነገ፡፡›› እየተጐተተች
ከተቀመጠችበት ለመነሳት ስትሞክር ተንጠራርቶ ክንዷን ጨመቀና መልሶ አስቀመጣት፡፡

መነጋገርማ አለብን‹‹እንዴት ነው ይሄ ጎረምሳሽ….በደንብ አድርጎ ነው አይደል የሚያርስሽ..አዎ! ሁለት ስራ ፈት አውደልዳየች በእኔ በሞኙ ብር በየቤርጎው እየተሸከረከራችው ስትምነሸነሹና አለማችሀ ስትቀጩ ...ወይ ነዶ!›› ተንዘረዘረ.. በጥፊ ሊያላጋትም ፈለገ፡፡መልሶ ተወው፡፡

‹‹እሺ ምን ይሻላል?››

<<ምኑ?>>

‹‹ምኑ ትለኛለች እንዴ?…..ትሰሚያለሽ! እንደውም ካንቺ ጋር መነጋገር አልፈልግም፡ ውሳኔዬን ግን በጥሞና እንድታደምጪኝ እፈልጋለሁ፡፡ ከአሁን ሠዓት ጀምሮ የግል ዕቃዎቼን ብቻ ይዤ ቤቱን ለቅቄልሽ እወጣለሁ፡፡ የምትጠቀሚበትን መኪና አንድ ገዝቼልሻለሁ አሁንም ያንቺው ነው፡፡ ቤቱንም ከጎረምሳሽ ጋር ቅበጪበት... ጨፍሪበት... እንዳሻሽ ሸርሙጪበት፤ ስሙ ባንቺ ስላልሆ ግን የመሸጥ የመለወጥ መብት የለሽም፡፡ ከዛ በተረፈ ከዛሬ ጀምሮ ለልጆቼ ከሚያስፈልገዉ ውጪ በስተቀር ሠባራ ሳንቲም ከእኔ አታገኝም፡፡ ወደ ክስ እሄዳለሁ ብትይ ግን ይሄንን ጉድሽን በአስር ሺ ኮፒ አባዝቼ ፣ለእነዛ ተመፃዳቂና ጉረኛ ዘመዶችሽ በነፍስ ወከፍ አድልልሻለሁ፡፡ በዛም ብቻ አላበቃም በጠበቃዬ በኩል ለፍርድ ቤቱም በማስረጃነት አቀርበዋለሁ፡፡ ከዛ በኋላ ምን አልባት ከእኔ ንብረት መካፈል ብትችይ እንኳን ከዘመዶችሽና ከጎረቤቶችሽ የሚደርስብሽን ውርደት ተቋቁመሽ እዚህ ከተማ ውስጥ መኖር የምትችይ አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም የሚሻልሽን ከውሽማሽ ጋር ተማክረሽ መወሰን ትችያለሽ፡፡›› በማለት ተነስቶ እርምጃ ከጀመረ በኃላ ቆሞ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

‹‹...ሌላ አንድ ነገር ይቀረኛል፡፡ በማንኛውም ሠዓት ልጆቼን ማየት ስፈልግ መኪና እልካለሁ ፣ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ትልኪልኛለሽ፡፡ ሳስብሽ ትክክለኛ ሚስት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ እናትም የመሆን ብቃቱ ያለሽ አይመስለኝም ፡።>>

እንባዋን እያረገፈች ፣አንደበት ተሳስሮ ፣ሠውነቷ በድንጋጤና በፀፀት ተኮማትሮ እያያት ያለ ምንም ሀዘኔታ ጥሏት ወደ መኝታ ቤቱ ገባ፡፡ እቃዎቹን ሠብስቦ ቤቱን ጥሎላት ሲወጣ እሱ ከእሷ ውጭ የወሰለተባቸው ከበርካታ አጋጣሚዎች ውስጥ አንዱ እንኳን ትዝ አላለውም፡፡ልክ ዕድሜ ዘመኑን ሙሉ ሌላ ሴት በዓይኑ ቀና ብሎ ሳያይ በታማኝነት የኖረና ድንገት መከዳቱን አውቆ ልቡ የተሰበረ ሰው አይነት ነበር የውሳኔው ቅፅበታዊነት..፡፡

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች 
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8714
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ...ከጊዜ ማህፀን ውስጥ አስደናቂና አሰቃቂ የህይወት ታአምራቶች ተፀንሰው ሲወለዱ ታዝበናል፡፡ የግቢውን በር ዘበኛው እንደከፈተለት መኪናውን ቦታ አስይዞ ለመቆም እንኳን ትዕግስት አልነበረውም፡፡ ሞተሩን አጠፋና እየተንደረደረ ወደ ቤት ገባ፡፡ የውብዳር ብቻዋን መለስተኛ አዳራሽ በሚያክለው ሳሎን ቁጭ ብላ በባለ 36 ኢንች ፍላትስክሪን ሶኒ…»
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ሰባት፦ በሰላም ሂድ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

“…ቲርርርርርር!…” 

“…ቲርርርርርር!…”

“…ቲርርርርርር!…”

የዛን ቀን … ስልኬ በማለዳ ሲጮህ በእንቅልፍና በመንቃት መካከል ሆኜ አየሁት።

ደብዘዝ ያለ ጨለማው ክፍል ውስጥ የሳሌም ስም የስልኬ መስታወት ላይ ሲያበራ ደንግጬ አነሳሁት “…ሄሎ…”

“…ሳዬ…” አለችኝ ሳሌም “…የኔ መልዐክ አሞት ሆስፒታል ነው ያለው ዛሬ ልትመጪ ትቺያለሽ…”

ልቤ በውስጤ ሲደነግጥ ይሰማኛል። ላለፉት አራት ቀናት በራሴ  ነገሮች  ስዋከብ ጊዜ አጥቼ ዳሪክን ለመጠይቅ አልሄድኩኝም ነበር።

“…ወይ ምን ሆነ? ምን ተፈጠረ? ምን አገኘው?....” ጥያቄን በጥያቄ ላይ አከታተልኩ

“…ትላንት ትንሽ አሞት ሆስፒታል ነው ያደርነው። ብዙም ክፉ አይደለም። ብቻዬን ስልሆንኩኝ ነው። ከቻልሽ ነይልኝ…” የሳሌም ድምጽ ከድካም ወይም ከሃዘን ድክም እንዳለው ያስታውቃል።

“…እሺ! …  እሺ!...አሁን እመጣለሁ…” ብዬ ስልኬን ዘጋሁና መዘጋጀት ጀመርኩኝ።

ያ ቀን የጀመረው እንግዲህ እንደዚህ ነው። አንዳንድ ቀን ከእሁድ እስከ ከእሁድ ብቻ አይደለም። አንዳንድ ቀን መንጋትና መምሸት ብቻ አይደለም። አንዳንድ ቀን የጸሐይ በምስራቅ መውጣትና በምዕራብ መጥልቅ ብቻ ሆኖ አይሄድም። አንዳንድ ቀን በሃያ አራት ሰዐት ብቻ አያልቅም ። አንዳንድ ቀን ለየት ያለ ነው። ቀኑ ይዞ የሚመጣው ደስታ፣ ሃዘን፣ ተሰፋ፣ ድል፣ ድካም፣ ብርታት ቀኑን በተለየ በልብ ማህደራችን፣በአእምሮችን የትውስታ ኮሮጆ ውስጥ ለዘመናት እንዲቀመጥ ያደርገዋል።

ይህ ከነዚህ ቀናት አንዱ ነው። ረጅም ቀን ነው።

ሆስፒታሉ ውስጥ ስደርስ ሳሌምና ቀድሞኝ የደረሰው ታዴ ቁጭ ብለዋል።

“…ዳሪክ እንዴት ነው?...” ሁለቱንም ሰላምታ እየሰጠሁኝ ጠይቅኩኝ።

“…ደህና ነው። አሁን የሆነ ምርመራ ይደረግለት ብለው ውስደውታል።…” ሳሌም መለሰች

“…ትገርሚኛለሽ እኮ ሴሊና…” ታዴ ወደ ሳሌም ዞረ “…እውነቱን ብትናገሪ፣ ሃቁን ብትጋፈጪ አይሻልም?...”

“…ማለት? አልገባኝም? የምኑን እውነት?...” ሳሌም ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች

“…ዳሪክ ትንሽ አይደለም ያመመው። ታሟል። በጠና ህመም ላይ ነው። እውነቱ ይሄ ነው። ያለበት ሁኔታ ሳያንስው ይሄው ስንት ጣጣ እየበዛበት ስንት ጊዜ ነው ሆስፒታል የሚመላለሰው። እስከ መቼ ነው እውነታውን የምትክጂው የኔ ልጅ?...” ታዴ ኮስተር ብሎ ሳሌም ላይ አፈጠጠባት።

ሳሌም አባቷን አተኩራ እያየች ለመልስ ስትዘጋጅ ከዳሪክ ሃኪሞች አንዱ መጣና ታዴን ማነጋገር እንደሚፈልግ ተናግሮ ይዞት ሄደ።

“…እስክ እዚህ ድረስ የከፋ ነው እንዴ ህመሙ ሴለም?...”

“…እሱ ዝም ብሌ ነው ባክሽ ሳዬ። እነዚህ ሃኪሞች የማይሉት ነገር የለም። እነሱን እየሰማ ነው። ትላንትናና ዛሬማ ከነሱ እግር ስር ነው።…”ሳሌም ግድግዳው ላይ አይኗን ተክላ በሃሳብ ሄደች።

የሁለቱን ሁኔታ ሳይ በአባትና በልጅ መካከል ክፍተት፣ ሰፊ ልዩነት እየመጣ መሰለኝ።

ለደቂቃዎች ሁለታችንም ዝም ብለን ቁጭ አልን።

  ከዛም ሳሌም መናገር ጀመረች።

“…አውቃለሁ….”አለች ሳሌም “…አውቃለሁ ብዙዎች በዳሪክ ሁኔታ ተሰፋ ቆርጠዋል። ከሁሉም ሰው አይን ውስጥ የማየው ተስፋ የመቁረጥ ነው። እኔ ግን ተስፋ አልቆርጥም። አለም በሙሉ፣ የሰው ልጆች ሁሉ በአንድ ላይ በዛ በኩል ተሰብስበው ቢቆሙና ተስፋ ቢቆርጡ እኔ ግን ለብቻዬ ከፍቅሬ ጋር ቆሜ ማመኔን እቀጥላለሁ። አምናለሁ። አንድ ቀን አይኖቹ ተከፍተው እንደማይ አምናለሁ።

አይኔንም፣ ልቤንም፣ ጆሮዎቼንም ከፍቼ እየሰማኋት ቀጠለች።

“… ሳዬ ታስታውሺያለሽ  የኦፒትሚስት (አውንታዊ ሰው)፣ የፒሲሚስት (አሉታዊ ሰው)ና  በብርጭቆ ውስጥ ያለው ግማሽ ውሃ ታሪክ …”

ራሴን ነቀነቀኩ “…አስታውሳለሁ…”

ሳሌም እንደገና ታሪኩም ትነግረኝ ጀመር። “….በጠረጴዛው ላይ ብርጭቅቆ አለ። ብርጭቆው ውስጥ ግማሽ ድረስ ውሃ ሞልቷል።አውንታዊው ሰው መልካሙን አየና ‘…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ሙሉ ነው..’ አለ። …አሉታዊው ሰው ደሞ ጉድለቱና አየና ‘…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ጎዶሎ ነው…’ አለ። …ሁላችንም ይህን ታሪክ እዚህ ድረስ እናውቃለን። እኔ ግን ከነዚህ ሁለት ሰዎች በተጨማሪ የእምነት ሰው ቢመጣ ምን ሊል ይችላል? ብርጭቆው ውስጥ ያለው ውሃ እንዴት ይመለከታል? ብዬ አሰብኩኝ። የእምነት ሰው ቢመጣ፣ …ያመነ ሰው ቢመጣ ያን ብርጭቆና ውሃውን አያያም። ይልቅስ የውሃውን ምንጭ ይመለከታል። ያመነ ሰው እንዲህ ይላል ‘…የውሃው ምንጭ ስላማይቋረጥ ይህ ብርጭቆ ሞልቶ ይትረፈረፋል።

ሳሌም ፈገግ ብላ ቀጠለች ….ስለዚህ እኔ አባባሉን እንዲህ አስተካከልኩት

      An optimist says “the glass is half full.”
      አውንታዊው ሰው ‘…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ሙሉ ነው..’ ይላል

      A pessimist says “the glass is half empty.”
      አሉታዊው ሰው ደሞ “…ይህ ብርጭቆ ግማሹ ደረስ ጎዶሎ ነው…” ይላል

      A man of faith says “don’t worry guys there is always a refill.”
      የእምነት ሰው ደሞ “…አትጨናነቁ ብርጭቆው  ሁሌም ሞልቶ ይትረፈረፋል።…” ይላል

..ወደ ኔ ሁኔታ ስመልሰው። ዳሪክን በተመለከተ አሉታዊ ሰዎች ጉድለቱን አይተው ‘…ኦ ዳሪክ እኮ ሙት ነው...’ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። አውንታዊ ሰዎች ደሞ ‘..ኦ ዳሪክ ትንፋሹ አለ፣ ልብ ምቱ ይሰማል ስለዚህ ተሰፋ አለው…’…ሊሉ ይችላሉ። እኔ ግን የእምነት ሰው ነኝ። አማኝ ነኝ። ከዚህ ሁሉ አሻግሬ የህይወትን ምንጭ፣ ጌታን አያለሁ። አምናለሁ። ስለዚህ የኔ መልዐክ ጌታ አዲስ ህይወት ሲሰጠው፣ ሲነቃ፣ ሲነሳ፣ ሲራመድ፣ ሲያወራኝ፣ እጄን ይዞ አብሮኝ ሲጓዝ፣ ‘..የምውድሽ..’ ሲለኝ፣ አይን አይኔን እያየ ሳያቋርጥ ሲስቅ … የኔን መልዐክ ሳገባው፣ አብረን በአንድ ቤት ስንኖር፣ ስንደሰት፣ስንጣላ፣ስንላፋ፣እንደ ልጆች ስንሯሯጥ፣ ደሞ ስንኮራረፍ፣ መልሰን ስንታረቅ፣ አብረን በመንገድ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንጓዝ፣ የልደት ስጦታ ስንለዋወጥ፣ የመጀመሪያ ልጅ ስንወልድ፣ የህጻኑ ለቅሶ ሌሊት ቁጭ አድርጎ ሲያሳድረን፣ ልጅ ማሳደግ ስንማር፣ ደሞ ሌሎች ልጆች ሲኖሩን፣ ልጆቻችንን ስናሳድግ፣ ልጆቻችን እንዴት እንደተገናኘን ሲጠይቁን፣ የፍቅር ታሪካችንን ስንነግራቸው፣ ደሞ ልጆቻችን ጎርምሰው ሲያስቸግሩ ‘..ምን እናድርግ?..’ ብለን ስንጨነቅ፣ ስንመካከር፣  የህይወትን አቀበት ስንወጣ ቁልቁለቱን ስንወረድ፣ የመኖር ተራራ ላይ ወጥተን የድልን ዜና ስናበስር ፣ደሞ ሸለቆ ውስጥ ስንድረስና አብረን ስንጸልይ፣  አብሮ እድሜያችን ሲጨምር የመጀመረያው ሽበት ጥቅጥቅ ያለው ጸጉሩ ላይ ሲወጣ ‘…ውይ የኔ ፍቅር አረጀህ እኮ ስለው…’….  እሱም መልሶ ‘..አይ አላረጀሁም…’ ብሎ ሲከራከረኝ፣ ስናረጅ፣ ወገባችን ሲጎብጥ፣ ተደጋግፈን የቤታችንን ደረጃ ስንወጣና ስንወርድ  ይህ ሁሉ ይታየኛል። አምናለሁ። አየዋለሁ…አምናለሁ…አየዋለሁ። አምኜ አምኜ መልሼ ደሞ አምናለሁ። ያመንኩትን ደሞ አየዋለሁ። ይሄ ለሰዎች ጤናማ ላይመስል ይችላል። ያመመኝ ሊመስላቸው ይችላል። ግን እኔ ምንም አይገደኝም። ሰዎች ምንም ቢያስቡ አይደንቀኝም። እኔ አማኝ ነኝ እንጂ ታማሚ አይደለሁም። በጌታ አምናለሁ። በፍቅር አምናለሁ። ይህ ማመን እንጂ መታመም አይደለም። የምለው ትንሽ ገብቶሻል ሳዬ?....”
👍556👎1
" አዎን በደንብ ይገባኛል የኔ ቆንጆ!" እንባዬ አይኔ ውስጥ ግጥም ብሎ አያታለሁ። የሚገርም ነው! …ሳሌም ፍቅሯ፣ እምነቷ የሚገርምና የሚደንቅ ነው።

“የታመምኩኝ ይመስልሻል ሳዬ?”

“አይመስለኝም በጭራሽ ሴለም! በፍጹም እንደዛ አላስብም!...”

ዝም ብላ ብታወራኝ፣ ብትቀጥልልኝ ደስ ባለኝ ነበር። ግን ታዴና ሃኪሙ መጥተው ሳሌምን ማነጋገር እንደሚፍልጉ ነገሩን።

“…እሺ … ነይ ሳዬ እንሂድ…” ስትለኝ ተከትዬ ሄደኩኝ። አንዲት ትንሽ ቢሮ ውስጥ ገብተን ሶስቱም ሲቀመጡ ወንበር ስላልነበር እኔ ጥግ ላይ ቆምኩኝ።

ክፍሉ ለትንሽ ሰከንዶች በጸጥታ ተዋጠ።

ቀጥሎም ሃኪሙ መናገር ጀመረ “…እንግዲህ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ከ ሚስተር ሃይሉ (ታዴ መሆኑ ነው) ጋር በዳሪክ የጤና ሁኔታ ስንነጋገር ነበር። የዳሪክ የጤና ሁኔታ እየባሰ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። …ኮማ ውስጥ እንዳለ፣ በማሽኖች ርዳታ እየኖረ እንዳለ የታወቀ ነው። አሁን ደሞ ከደረሰበት አደጋና በተለያየ ጊዜ ካጋጠሙት ኢንፌክሽኖች የተነሳ ሁለቱ ኩላሊቶቹ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል። አሁን ዳያለሲስ ያስፈልገዋል። በ'ርግጥ እሰክ መጨረሻው ዳያላሲስ ሊያስፈልገውም ላያስፈልገውም ይችላል። ”

“ታዲያ ምን ችግር አለው የሚያስፈልገው ነገር ይደረግለታ …. ሳሌም ነበረች

“ዳያለሲስ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ? ” ንግግሯን ሃኪሙ አቋረጣት

“…አላውቅም!...” ሳሌም መለሰች

ሃኪሙ አጠር አድርጎ ኩላሊቶቹ ለተጎዳ ወይም ለማይሰራ ሰው በማሽኖች ደሙ እንደሚጣራ አስረዳንና ቀጠለ “…ጥያቄው ግን። ለዚህ ልጅ እንደገና ሌላ መስመር ሰውነቱ ውስጥ መክተት አለብን ወይ? በሌላ ማሽን የሰውነቱን ስራ መስራት አለብን ወይ? ስቃዩ እጅግ አልበዛበትም ወይ? ከ አደጋው ቡሃላ እንኳን ስንት ጊዜ ለህክምና እኛ ጋር እንደተመላለሰ አስታውሱ። ህይወቱን ለማቆየት ብለን ብዙ ስቃይ አልጨመርንበትምን?.....እነዚህና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ከህግ ተወካዩቹና  ሚስተር ሃይሉ ጋር ተነጋግረን  ምናልባት ይህን ልጅ በሰላም ከስቃዩ፣ ከህመሙ እንዲለይ፣ እንዲሄድ  ብናደርግ የሚለውን ሃሳብ አንስተን ጊዜ ውሰደን ተወያይተን ተስማምተናል። አሁን እዚህ ያለነው ለአንቺ ውሳኔውን ለመናገርና በአካልም በስነ ልቦናም ዝግጁ እንድሆኚ ለማድረግ ነው። …ትክክል ነኝ አይደል?...” ወደ ታዴ ዞረና ጠየቀ።

ታዴ ራሱን በ አውንታ ነቅንቆ አቅርቅሮ ዝም አለ። የሳሌምን አይኖች ለማየት የደፈረ አይመስልም።

ዱብ እዳ ነው። እኔ በድንጋጤ ሰውነቴ ይንዘፈዘፍ ነበር።

ሳሌም አየኋት። በፊቷ ላይ ምንም አይነበብም።

“..በሰላም እንዲሄድ ማለት ምን ማለት ነው?....” ተረጋግታ ጠየቀች።

ሃኪሙ መናገሩን ቀጠለ “…እውነታውን ካየነው ዳሪክ እየተነፈሰ ያለው ሙሉ በሙሉ በማሽን ርዳታ ነው። ማሽኖችን ካቆምናቸው ዳሪክ በሰላም ከዚህ አለም መሄድ ይቻላል። የሚጠበቀው ከሚወዱት ሰዎች ‘…በሰላም ሂድ…’ የሚል ፈቃድ ብቻ ነው… ‘..በሰላም ሂድ!..” ማለት ለኛ፣ በህይወት ላለነው ከባድ ውሳኔ ነው። ግን ደሞ እንደ ዳሪክ ላሉ ታማሚዎች ርፈትና ከስቃይ መገላገል ሊሆን ይችላል።…”

መጀመሪያ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም። “…በሰላም ሂድ!..” ሁለት ቃላቶች። እንዴት ቀላል ሁለት ቃላቶች ናቸው። ይህ ሃኪምስ እንዴት ቅልል አድርጎ ነው የሚያወራው። በሰላም ሂድ ማለት እኮ ይሙት ማለት ነው። በአእምሮዬ ቃላቶቹ ይመላለሱ ጀመር....

በሰላም ሂድ!
በሰላም ሂድ!
በሰላም ሂድ!
በሰላም ሂድ!

አሁንም እንደገና ሳሌም አየኋት።

ሳሌም ቃል አልወጣትም ይልቅስ ሃኪሙን …ደሞ አባቷን …አባቷን እንደገና ደሞ ሃኪሙን በርጋታ እየመላለሰች በነዛ ትላልቅ አይኖቿ አየቻቸው።

የሳሌም አስተያየቷ የሶስትዮሽ ቃላት ውጤት ነው ፦ ሃይል፣ ከፍታና ርጋታ።

አስተያየቷ ሃያል ነው። የሆነ እምቅ ሀይል አለው።

አስተያየቷ ከፍ ያለ ነው። ከሆነ ከፍታ ላይ ሆና በንቀት የምታያቸው ነው የምትመስለው።

አስተያየቷ ጸጥ ያለ ነው። እንደ ሰላማዊ ውቂያኖስ ውሃ ርግት ያለ። እዛ ውሃ ውስጥ ግን ሊፈነዳ ያለ ግዙፍ የሱናሚ ተራራ ያለ ይመስላል።

ምንም ሳትናገር ተነስታ  ክፍሉን ለቃ ወጣች።
*
*

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍56😢157😱3👏1
የፍቅር ‘ርግቦች
ክፍል ስምንት፦ አምስት ጠባሳዎች
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

“…እንድንነጋገር ትፈልጊያለሽ ሴሊና? እዚህ ውሳኔ ላይ እንዴት እንደደረስን?...” ታዴ ሳሌምን እያየ ይጠይቃል።

ሳሌምን ተከትለን መጥተን ሶስታችንም ዳሪክ የተኛበት የሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ ቆመናል። ዳሪክ አሁንም ከሄደበት የምርመራ ክፍል አልተመለሰም።

ሳሌም ምንም ምላሽ አልሰጠችም። ይልቅስ በዛው እርጋታዋ ወደ አልጋው ሄደችና ሌሊት ዳሪክ ተኝቶ ካደረበት አልጋ ፍራሽ ላይ አልጋ ልብሱንና አንሶላውን ማውጣት ጀመረች።

“…እየሰማሽኝ ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ እንወያይ?...”

ሳሌም ጸጥ።

ከትራሶቹ ላይ የትራስ ልብሶቹን ታውልቃለች። ቀጥላም ቆሻሻውን አንሶላ፣ አልጋልብስና የትራስ ጨርቆች ክፍሉ ጥግ ላይ ያለው የላውንደሪ ቅርጫት ውስጥ ከተተች።

“..እሺ መልስ ባትሰጪኝም ሃሳቡን ግን እነግርሻለሁ።…” ታዴ ማውራት ጀመረ “… ይህ ልጅ በስቃይ ነው ያለው። ከዛን ርጉም ቀን ጀምሮ ይኸው መከራ ላይ ነው። ስንት ጊዜ ሆስፒታል መጣ? ስንት ጊዜ ታመመ? ሃኪሞቹ በሙሉ ተስፋ እንደሌለው ነግረውኛል። የቀረው እድሜውን በሙሉ በስቃይ ላይ ስቃይ እንደሆነ አስረግጠውልናል። ደሞ ይህን ውሳኔ እኔ በራሴ አይደለም የወሰንኩት። ሃኪሞቹ፣ ዳሪክን እዚህ ሃገር እንዲመጣ ያደረጉት ቤተሰቦችም ተስማምተዋል። እየሰማሽኝ ነው ሴሊና?...”

ሳሌም ዝም።

አሁን ፍራሹ ላይ ንጹህ አንሶላና አልጋ ልብስ እያለበሰች ነው።

ታዴ ቀጠለ “…በዛ ላይ ያንቺስ ህይወት እስከ መቼ ነው እንዲህ የሚቀጥለው? ላለፉት ሰባት ወራት ዳሪክን ሃያ አራት ስትንከባከቢ አለሽ። ትምህርትሽን አቁመሻል። ፈጽሞ ስለ ራስሽ ማሰብ ትተሻል። ሃያ አመት እንኳን ያልሞላሽ ለጋ ልጅ ህልምሽ፣ ህይወትሽ፣ ወደፊትሽ ሁሉ እንደ ጉም ሲበን፣ ሲበተን እንደ አባት ዝም ብዬ ማየት አለብኝ? አለብኝ እስኪ ንገሪኝ?...”

የታዴ አነጋገር ግራ የገባው ሰው ንግግ ር ነው። ለወሰነው ውሳኔ ርግጠኛነት የተሰማው አይመስልም። የድጋፍ ድምጽ ከሁለታችንም የሚፈልግ ነው የሚመስለው።

ሳሌም ክፍሉ ውስጥ ሰው የሌለ ይመስል በፍጹም ዝምታ ያነጠፈችውን አልጋ በጥንቃቄ ታሳምረው ጀመር።

ለጥቂት ሰከንዶች ዝም ብሎ ሳሌምን ሲያያት ቆየ፦ ታዴ።

“..እንደዚህ ነው? አትመልሺልኝም? አታወሪኝም?..” በንዴት ጮኸ

ሳሌም መሬት ሆናለች።

ጸጥ።

ምንም እንዳልተፈጠረ፣ አንዳች ነገር እንዳልሰማች በታላቅ ርጋታ …ትራሶቹን በአዳዲስ የትራስ ሽፋኖች ውስጥ ማስገባት ጀመረች።

ዝምታዋ ሲቀጥል የአባቷ ንዴትም አብሮ ጨመረ። በቁጣና በእልህም ንግግሩን ቀጠለ “..እንግዲህ ምንም አልሽ ምን ውሳኔውን ወስነናል። በጥቂት ቀናት ውስጥ ይተገበራል። ያፈቀረ አንቺ ብቻ አይደለሽም። በስሜት ማስብሽን አቆሚ። በምክንያታዊነት መሰረት ላይ ሆነሽ ለአን ቺም፣ ለዳሪክም የሚጠቅመውን አድርጊ። ከዳሪክ ብትለይ የምትሆኚው ምንድን ነው? ምን ትሆኚያለሽ? እስኪ ተናገሪ ምንድን ነው የሚሆንብሽ? ምንስ ነው የሚመጣብሽ?...”

ሳሌም በርጋታ አንዴ ቀና ብላ አየችውና “…አባቴ!...” አለችው

ቃሉ ከአፏ ሲወጣ ታዴ ንግግሩን አቆመ።

“…አባቴ አይታይህም? የማደረግውን አትመለከትም?...”

ታዴ አንዴ ሳሌምን አንዴ ደግሞ ዙሪያውን ገርሞት ተመለከተ። እኔም ደንቆኝ እያየሁ ነበር፦ በ አካባቢው ላይ ሳሌም እያረገችው ያለ ነገር ካለ ብዬ። የማየው ግን ምንም ነገር አልበረም። እኛው ሶስታችን በአንዲት የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ነው ያለነው።

“…ምንድን የምታወሪው? ምን እያደረግሽ ነው?...” ታዴ ጠየቀ

ሳሌም በረጅሙ ተነፈሰች “…የምወደው…የኔ መልዐክ… ከመምጣቱ በፊት አልጋውን እያነጠፍኩ፣ ክፍሉን እያዘጋጀሁለት ነው። አይታይህምን?...ትልቅ ስራ እኮ አለኝ። ስራዬ እሱን ማፍቀር ነው። ስራዬ እርሱን መንከባክብ ነው። ተልዕክዬ ከልቤ ፍቅሬን መውደድ ነው። ከጌታ ቀጥሎ የመጀመሪያ፣ ቅድሚያ የምስጠው ፍቅሬን ነው። ለሌላ ነገር አሁን ጊዜ የለኝም። አቅም አልባ ነኝ። ለክርክር፣ ለጸብ፣ ለጥላቻ ጉልበት የለኝም። እባክህን?....”

ታዴ ንዴት በሚንቦገቦግበት አይኖቹ ለአፍታ ዝም ብሎ ሳሌምን ተመለከታትና ወጥቶ ሄደ።

….ያ ቀን ረጅም ነው። ዘንካታ ረጅም ሳይሆን የሆነ ጠውላጋ የማ ይሄድ፣ የማይገፋ ቀን ነው። ታዴ ወጥቶ ከሄደ ቡሃላ የመጀመሪያዎቹን ሰዐታት ከሳሌም ጋር ምንም አልተነጋገርንም። አላወራንም። በመሃል ዳሪክ ከሄደበት ምርመራ ሲመለስ ሳሌም ሁሌ እንደምታደርገው በጥንቃቄ አጸዳድታ፣ አስውባ አሳመረቸው። ስትጨርስም አልጋው አጠገብ ተቀምጣ አይፓዷን ከሄድ ፖን ጋር አያያዘች። ሄድ ፎኗን ጆሮዋ ላይ ሰካች። በክፍሉ ውስጥ ዳሪክ ላይ ከተሰኩት ማሽኖች ውጪ የሚሰማ ነገር አልነበረም። ጸጥታ።

ጥቂት ረጅም፣ እንደ ዔሊ የሚጎተቱ ሰዐታት አለፉ። አንድ ደቂቃ የሳምንትን ያህል፣ አንድ ሰዐት የሃምሌን ያህል ረዘመ።

ሳሌም የገባችበት ፈተና ክብደት ቢገባኝም፣ አብሪያት መሆን ብፈልግም ምናልባት ከዳሪክ ጋር ብቻዋን መሆን ትፈልግ ይሆን የሚል ሃሳብ ብቅ አለብኝና “..ሴለም ምናልባት ከዳሪክ ጋር ለብቻ ጊዜ ማሳለፍ ትፈልጊ ይሆን?...” ጠይቅኳት

“ ምናልሽ ሳዬ?...” ሄድ ፎኑን ከጆሮዋ ላይ እያወረደች።

ጥያቄውን ደገምኩኝ።

“…ኖ… ኖ…በጭራሽ…” መለሰችልኝ “…እንዲያውም ብትችይ አብረሽኝ ብትሆኚ በጣም ደስ ይለኛል።…”

“….እንደዛ ከሆነ እሺ….” ከተነሳሁበት መልሼ ተቀመጥኩኝ።

“….ሳዬ በጣም አመሰግናለሁ እሺ አለችኝ….” መልሳ ደግሞ

“…ለምኑ?...”

“….በዚህ ሁሉ አብረሽኝ ስለምትሄጂ። ስጠራሽ ዝም ብለሽ ስለምትመጪልኝ። በቃ ብቸኛ እህቴ ስለሆንሽልኝ።…”

በውስጤ፣ ልቤ ስፍስፍ አለላት “….ምንም ችግር የለም የኔ ቆንጆ። እንዳውም እኔ ነኝ ማመስገን የሚገባኝ። አመሰግናለሁ።…”

“…አንቺ ደሞ ለምኑ ነው የምታመሰግኚው ሳዬ?...” ተገርማ

“….በቃ እውነተኛ ፍቅር፣ አምነትና ለሌላ ሰው መኖር ህያው ሆኖ በአንቺ ሲንቀሳቀስ እያየሁኝ ስለሆነ።…”

ሳሌም በ'ምወደው ስስ ፈገግታዋ ፊቷን ሞላችው። ፍቅር፣ አምነት፣ ትህትናና ሰላም በአንድ ላይ በሳሌም ፊት ላይ እዩኝ፣ እዩኝ ይላሉ፦ ስታምር እኮ።

በዛ ረጅም ቀን ያወራነው ይህን ያህል ብቻ ነው። ጸጥ ብለን፣ ዝም ተባብለን ቀኑን ውለን መሸ።

….መሽቶ ከገፋ ቡሃላ እንደገና ታዴ መጣ። መምጣቱ ግን የለወጠው ነገር የለም። ሶስተኛ ሰው የዝምታውን ባህር ውስጥ ከመቀላቀሉ ውጪ። ሶስታችንም ተዝግተን ተቀምጠን የዳሪክ የመተንፈሻ ማሽን ብቻ አየር ሲያስወጣና ሲያስገባ ይሰማል።

ታዴ ከመጣ በግምት ከአንድ ሰዐት ቡሃላ ሳሌም ቀኑን ሙሉ ይዛ የዋለችውን አይ ፓዷን አስቀመጠችና ወደ ታዴ ዞረች....

“…አምስት ናቸው!... ታውቃለህ?...” የተጫነንን የዝምታ ቀንበር ሰበረችው።

“….ምን አልሽኝ? ምኑ?...” ደንግጦ ጠየቃት
👍533😁2🥰1
….ምን አልሽኝ? ምኑ?...” ደንግጦ ጠየቃት

በእርጋታዋ ሳሌም መናገር ጀመረች “….አምስት ናቸው!.... በዳሪክ…የኔ መልዐክ ጀርባ ላይ ያሉት ጠበሳዎች። የተበታተኑ አምስት ጠባሳዎች። ሁልጊዜ በየቀኑ አያቸዋለሁ። ማንም ሰው ሳያየኝ እጄን አስገብቼ እዳስሳቸዋለሁ። አምስት ቦታ ነው በጥይት የተበሳሳው። ፍቅሬ ዛሬ መተንፈስ ምጥ የሆነበት፣ ሳንባው አልሰራ ብሎ በዚህ ማሽን የሚተነፍሰው በነዛ አምስት ጥይቶች የተነሳ ነው።…ግን እነዚህ አምስት ጠበሳዎች ከየት መጡ? የመጡት እኔን ካፈጠጠብኝ ሞት ሊታደጉ ነው። እኛ ሁላችን አፍንጫችንን አልፎ ሲገባ የማናስታውሰው የህይወት ስትንፋስ፣ …አየር… ዳሪክ ያጣው ለኔ ነው ….እኔ እንድተነፍስ ነው። እነዚህ አምስት ጠበሳዎች የፍቅሬ ህያው ማህተሞች ናቸው። እነዚህ አምስት ጠባሳዎች ከብዙ መጻህፍት የበለጠ ፍቅርን ይተርኩልኛል። የመውደድን ጥንካሬና ጉልበት ያሳዩኛል። የኔ መልዐክ ሳይሳሳ፣ ሳያቋርጥ፣ከነፍሱ፣ ከልቡ ምን ያህል እንደወደደኝ ያሳዩኛል። ዛሬ ባያወራኝም እንኳን...'የምውደሽ'...ብሎ ባይጠራኝም ነገር ግን ጀርባው ላይ ባሉት ምልክቶች ‘…እወድሻለሁ እኮ!...’ …. ‘…አፈቅርሻለሁ እኮ!... እሳሳልሻለሁ እኮ!...’ …. ‘….የኔ ውድ ነሽ እኮ!...” ይለኛል።….”

ሳሌም እያወራች እኔ እንባዬ በአይኖቼ ውስጥ እየሞላ ነበር።

ጥቂት ዝም አለችና ቀጠለች “…አባቴ እለምንሃለሁ። በታላቅ ትህትና፣ በጌታ ስም እጠይቅሃለሁ።…ፍቅሬን አትውሰድብኝ።… መውደዴን አትንጠቀኝ።… ለአንዲት ልጅህ በሰው አእምሮ የማይታሰብ ዋጋ የከፈለላትን አንድ ልጅ ህይወት ‘ሂድ’ አትበለው? ወረቀት ላይ ለሱ የህግ ተወካይ ስለሆንክ ብቻ በአንዲት ፊርማ ህይወቴን፣ ፍቅሬን፣ መውደዴን፣ መልዐኬን አትቀማኝ?....እባክህን አባቴ፣…እባክህን… እባክህን …አባቴ …ዳሪክን አትቀማኝ….” በሚያሳዝን ሁኔታ ትለምነው ጀመር።

ሳሌም አይን አይኑን በልመና ስታየው ታዴ የጭንቁን ማውራት ጀመር “…ሴሊና እኔ እኮ ብቻ አይደለሁኝም የወሰንኩት ሃኪሞቹም፣ ስፖንሰር ያደረጉት ቤተሰቦችም ሁላችንም ተወያይተን ነው እኮ…።….. ልጄ አንቺ እኮ እየሆነ ያለው ነገር አይታይሽም። ፍቅር በሚባል ስሜት ተሽፍነሻል ። ዳሪክም አንቺም ስቃይ ላይ ናችሁ እኮ። ለሁለታችሁም…”

ሳሌም ግን አቋረጠችውና አሁንም በሚያሳዝን ሁኔታ ልመናዋን ቀጠለች “…ልጅህ ቢሆን ይህን ታደርግ ነበር? እባክህን አባቴ …እለምንሃለሁ? እማጽንሃለሁ?....”

ታዴ የሳሌም ልመና መቋቋም የማይችለው ሁኔታ ላይ ሲደርስበት አሁንም ተነስቶ ክፍሉን ለቆ ወጣ። የታዴ ነገር እኔ ማመን አቅቶኛል። የዛሬ ሰባት ወር ሆስፒታሉ ውስጥ ስለ ሁለቱ ፍቅር ያወራሁት ታዴ አልመስል አለኝ። ለምን እንዲህ ጨከነ? እንዴትስ ለልጁ ርህራሄው ፈጽሞ ጠፋ? ግራ የሚያጋባ፣ መልስ የሌለው ጥያቄ።

ታዴ ወጥቶ ሲሄድ ወደ ሳሌም ዞርኩኝ “…ምንድን ነው ሚሻለን ሴለም?...”

“…አታስቢ ሳዬ…” በእርጋታ መለሰችልኝ “…ጌታ ያለው ይሆናል። አባቴ ሃሳቡን ይቀይራል ብዬ አምናለሁ። አሻግራ ወደ ውጪ በመስኮት እያየች። “…አሁን ስለመሸ ለመኝታ እንዘጋጅ ካለስቸግርኩሽ እዚህ ታድሪያለሽ ሳዬ?...”

እርጋታዋ እንዳለ ቢሆንም ሳሌም ብቻዋን መሆኑ ያስፈራት ትመስል ነበር። እሺ ብዬ የሆስፒታሉን ታጣፊ አልጋ ከዳሪክ አልጋ አጠገብ ዘረጋነውና ለእንቅልፍ ተዘጋጀን።

ረጅሙ፣ ዝምታ የነገሰበት ቀን አልፎ መሽቷል። የዘረጋነው አልጋ ላይ ተጋደምኩ እንጂ እንቅልፍ ግን ለኔ ቅርብ አልነበረም።

ቆይተን “…ሴለም ተኝተሻል?...” አልኳት

“…አልተኛሁም ይሄ ሌሊት እንደ ቀኑ ሳይረዝም አይቀርም….”

“…የሆነ ነገር እንስራ፣ እንጫወት ወይም እናውራ…”

“…ጥሩ ሃሳብ ምን እናድርግ ሳዬ?...”

ለአፍታ አስብኩና “….ለምን ስለ አንቺና ዳሪክ አትነግሪኝም?...”

“….ማለት… ምን ልነግርሽ ሳዬ?...”ወደ እኔ ዞራ በፈገግታ

“…በቃ ሁሉንም ነገር ከጅማሬው ጀምሮ…”

“…መስማት ትፈልጊያለሽ ሳዬ?...”

“….አዎ… ከልቤ… ሁሌም…”

“…እሺ …” ስትለኝ በደስታ ከተኛሁበት ተነስቼ ቁጭ አልኩኝ።

ሳሌም ለሰከንዶች ከየት እንደምትጀምር እያሰበች ይመስል በመስኮቱ አሻግራ ውጪውን ስታይ ቆየች። ጥርት ባለው የክረምት ሰማይ ላይ ግማሽ ጨረቃና፣ ከዋክብት ደምቀዋል። ከሰማዩ በታች የሲያትል ከተማ ረጃጅም ፎቆች ከርቀት ይታያሉ። እነዚህ ጉዕዝ ፎቆች፣ የተሸረፈችው ጨረቃና ከዋክብት ሁሉም ታሪኩን ለመስማት እንደእኔው ያቆበቆቡ፣ የቋመጡ መሰለኝ።

ሳሌም ከዳሪክ አጠገብ ተኝታ በዝግታ የዳሪክን እጆች እየዳሰሰች… አይን አይኑን እያየች.... ጀመረች። የጀመረችውንም.... ቀጠለች። የዛን 'ለት ሌሊት አንዳንዴ እየሳቅኩኝ፣አንዳንዴ እየተከዝኩኝ፣ አንዳንዴ በደስታ እንባዬ እየመጣ ከሳሌም አፍ የሚፈሰውን የሁለቱን 'ርግቦች የፍቅር ታሪክ ሳዳምጥ አደርኩኝ።….ያ ሌሊት ምናልባትም ሶስታችን አንድ ላይ ያሳልፍነው የመጨረሻ የደስታ ሌሊት ሳይሆን አይቀርም።

…..ከ72 ሰዐታት ቡሃላ ....ዳሪክን ለማይቀረው ጉዞው እያሰናዳነው ነበር፦ ሳሌምና እኔ።
*
*
ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍5110😁2👏1
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ለሁለት ወራት ድምፅዋን አልሠማም፡፡ አልደወለችለትም፡፡ ምንም አይነት አዲስ ጽሁፍም አላከችለትም፡፡ እሷ ልታገኘው ካልፈለገች እሱ ሊያገኛት የሚችልበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ ይሄ ሁኔታ ሁሴንን እጅግ ሲያስጨንቀውና ሲያበሳጨው ነው የከረመው፡፡ ዛሬ ግን በሀሳብ የሚያባክነው ጊዜ አላገኘም፤ውጥረት ላይ ነው ያለው፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ በዋቤ ሸበሌ ሆቴል የሚስጥር የግጥምና የአጫጭር ልብ ወለድ መጽሐፍ ይመረቃል፡፡

ሁሴን፣ሠሎሞን እና ትዕንግርት ነገሮችን ሁሉ በታቀደላቸው ዕቅድ መሠረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከወዲህ ወዲያ ይሯሯጣሉ፡፡

‹‹አሁን ምን ቀረ?›› ሠሎሞን ነው የጠየቀው፡፡

‹‹ምንም ... የእንግዶቹ መምጣት ብቻ..፡፡›› ሁሴን መለሰ፡፡

‹‹የሚዲያ ሠዎችስ .. ያረፍዱ ይሆን?›

‹‹ኧረ ደርሰዋል...ሆቴል ሻይ ቡና እያሉ ናቸው፡፡››

‹‹በትክክልም መድረስ አለባቸው፡፡ ይሄን የመሠለ ግራ የገባው ታሪክ ለመዘገብ የማይጓጓ የወሬ ሠው የት ይገኛል ብለህ ነው?››ሰሎሞን ነው ተናጋሪው፡፡

‹‹እስቲ ዛሬ እንኳን ስድብህን ዋጠው፡፡›› አለው ሁሴን እንደመበሳጨት ብሎ

<እንዴ  ቁጭ ብላችሁ ታወራላችሁ እንዴ......? እንግዶች እኮ መምጣት ጀምረዋል፡፡ ውጭ ናቸው›› ትንግርት ነች በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ እየገባች የምታወራው፡፡

‹‹በቃ የቀረን ነገር የለም ... ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡ ዘና የሚያደርጉን ሙዚቃኞች ከነ ሙዚቃ መሳሪያቸው መጥተዋል፡፡ ዝግጅቱን በንግግር የሚከፍቱልን የክብር እንግዳችን የደራሲን ማህበር ፕሬዘዳንትም በሠዓቱ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ሠጥተውናል፡፡
ለእድምተኞች ከመጽሐፍ በመቀንጨብ የሚያነቡ ሠዎችም ተመድበዋል፡፡ ያው እንደተነጋገርነው በመጀመሪያ አንቺ ታነቢያለሽ ሌላውን እኔ ጨምራለሁ፡፡ ይሄ ቀፈታም
ኢንጂነር እንደሆነ አይኖቹ ብር ላይ የሚገኝ ቁጥር እንጂ ፊደል ማንበብ ካቆሙ ዘመናት አልፈዋል፡፡ ስለዚህ የእሱ ኃላፊነት እንግዶች በስርዓት መስተናገዳቸውን መቆጣጠር ነው፡፡›› ንግግሩን ገታ አደረገና አይኖቹን ሠሎሞን ላይ ተክሎ ንግግሩን ቀጠለ ‹‹ደግሞ ዛሬ እንዴት ነው አለባበስህ? ሚስትህን ጥለህ ከቤት ስትኮበልል ወጣት የሆንክ መሰለህ
እንዴ?>>

‹‹ሰውዬ እንደውም ዛሬ ከዕድምተኞቹ ውስጥ አንዷን ምርጥ ካገኘሁ መጥበሴ አይቀርም፡፡›› አለው ሠሎሞን፡፡

‹‹ምን አልባት ከአስተናጋጆቹ መካከል ከሆነ እስማማለሁ፡፡ ዝግጅቱን ለመታደም ከሚመጡት ውስጥ ግን ላንተ ነፍስ የምትስማማ የምትኖር አይመስለኝም፡፡ ደራሲ ወይም ገጣሚ አፍቅረህ ልታብድ ነው...እስቲ በእኔ ይብቃ››ተሳሳቁ!!

‹‹ግን ዛሬም አትመጣም ማለት ነው?! >> ትንግርት ነበረች ጠያቂዋ፡፡ መልሱን ከሁሴን አንደበት ለመስማት በጉጉት ስሜት አይኖቿን እያቁለጨለጨች፡፡

‹‹በቃ ስለ እሷ እያወራችሁ ስሜቴን አታደፍርሱት፡፡ እንዲያውም ሠዓቱ ደርሷል በራፉን ክፈቱና እንግዶችን ወደ ውስጥ አስገቧቸው፡፡››

ሠሎሞን ተንደርድሮ በሩን ከፈተና ውጭ የተጠራቀሙትን እንግዶች ወደ ውስጥ እንዲገቡ ይጋብዛቸው ጀመር፡፡ ጋዜጠኞችም ከካሜራ ባለሞያቸው ጋር እየተንጋጉ ገቡ፡፡ በ3ዐ ደቂቃ ውስጥ ከተጠሩት ሠዎች
አብዛኞቹ ስለተገኙ ፕሮግራሙን ለማስጀመር ሁሴን ወደ መድረኩ ማይኩን በቀኝ እጁ የተወሰኑ ወረቀቶችንና በእለቱ ለምረቃ የተዘጋጀውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ በግራ እጁ ይዞ ወጣ፡፡መድረኩ ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ከሩቅ እንዲነበብ ታስቦ በባነር ላይ የተጻፈ ፅሁፍ ተለጥፏል፡፡ እንዲህ ይነበባል፡፡

የመፅሀፍ ምረቃ በዓል

የመፅሀፍ አይነት፦ የግጥምና አጫጭር ልቦለድ መድብል

ርዕስ፦ የጨረቃ ፍካት

ደራሲ፦ ምስጢር በለጠ

አሳታሚ፦ ፍካት ማተሚያ ቤት

የታተመበት ቀን፦ ሠኔ 2ዐ ቀን 2007 ዓ.ም.

ሁሴን ከአትሮኖሱ ጀርባ ቆሞ ጉሮሮውን ጠራረገና ንግግሩን ጀመረ፡፡ ከተለያዩ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ጣቢያ የመጡ ጋዜጠኞች ካሜራቸውንና መቅረፀ ድምጻቸውን በዙሪያው ቀሠሩ፡፡

‹‹ክቡራንና ክብርት የጥበብ አፍቃሪዎች

በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ከጥበብ ማዕዱ ለመቋደስና የደስታችን ተካፋይ
ለመሆን እዚህ ስለተገኛችሁ በደራሲዋ እና በራሴ ስም የከበረ ምስጋናዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡በማስከተልም ስለደራሲዋ
አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮች መናገር እፈልጋለሁ›› መጽሀፉን አነሳና ወደ ታዳሚው
በማሳየት ንግግሩን ቀጠለ፡፡

‹‹ይሄ መጽሐፍ
ሠባት አጫጭር ልብ ወለድ እና ሠላሳ የተመረጡ ግጥሞች የተካተቱበት ባለ ሁለት መቶ ሃያ ገጽ መጽሐፍ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል አራቱ አጭር ልብ ወለዶች እና ሃያ የሚሆኑት ግጥሞች በተለያየ ጊዜ በፍኖተ ጥበብ ጋዜጣ ላይ ለህትመት የበቁና በአንባቢ
ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው፡፡ለዚህም
የጋዜጣው አንባቢ የሆናችሁ መመስከር ትችላላችሁ፡፡ ሌሎቹ ግን በደራሲዋ የቀረቡ ከዚህ በፊት ያልተነቡ አዳዲሶች ናቸው፡፡

የመሸጫ ዋጋው ሰላሳ ሁለት ብር ነው፡፡ ዋጋው ካለው የወረቀት ውድነትና ይሄን ተከትሎ አሳታሚ ድርጅቶች ከሚጠይቁት ዋጋ አንፃር ተሠልቶ የተተመነ ስለሆነ ተመጣጣኝ ነው ብለን እናስባለን፤ ስለ መጽሐፉ ይሄን ያህል ካልኩ ስለ ደራሲዋ ደግሞ ጥቂት ነገር ማለት ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ደራሲዋ አሁን በመሀከላችን... >> ንግግሩን አቋረጠና ወደ ውስጡ ትንፋሹን ደጋግሞ ሳበ፡፡ እንደ ማሳል አለና በተንቀረፈፈ ሁኔታ ንግግሩን ቀጠለ ፡፡

‹‹...አሁን በመሀከላችን የለችም፡፡ ማለቴ እዚህ ዝግጅት ላይ እንድትታደምና የድካሞን ውጤት፤ የዘራችውን ዘር ፍሬ እንድታጣጥም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም በአካል አላውቃትም፤ መኖሪያ ቤቷን፣ ስልኳን፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥሯን አላውቅም፡፡ ላውቅ ያልቻልኩትም እኔ ማወቅ ስላልፈለግኩ ሳይሆን እሷ እንዳውቅ ስላልፈለገች ነው፡፡››

ከእድምተኞች አካባቢ ጉምጉምታ በዛ፣ የጋዜጠኞች ጆሮ ይበልጥ ተቀሠረ፣ካሜራዎቻቸውን ከወዲያ ወዲህ በፍጥነት ማሽከርከር ቀጠሉ፡፡ ብዛት ያላቸው ሠዎች በተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልካቸው ሳይቀር ንግግሩንም ሆነ የዝግጅቱን ድባብ በተቻላቸው መጠን በመቅረፅ ላይ ናቸው፡፡‹‹... ያው እንዳልኳችሁ ምስጢር ከሁለት ዓመት ለበለጠ ጊዜ የፍኖት ጥበብ ጋዜጣ ቋሚ አምደኛ ነች፡፡ ጽሁፎችን የምትልከው በፖስታ ቤት በኩል ሲሆን አድራሻዋን ግን አትፅፍም፡፡ ጽሁፎቿ በጣም ማራኪ ብስለት ያልተለያቸውና ዘና የማድረግ ደረጃቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ዛሬም ድረስ የእሷ አድናቂ እንድሆን ተገድጄያለሁ፡፡ በነገራችን ላይ በግል ስልኬም ትደውልልኛለች፤ እውነቴን ነው የምላችሁ መፃፍ ብቻም ሳይሆን ማውራትም ትችልበታለች፡፡ የምትጠቀመው ስልክ የሕዝብ ነው አንድ ቀን ከልደታ፣ በሌላ ሳምንት
ከመገናኛ፣ ሲያሰኛት ከሳሪስ አካባቢ ባለ የሕዝብ ስልክ ነው የምትደውልልኝ፡፡ ከምታስቡት በላይ ግራ አጋቢ የሆነች ፍጡር ነች፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ ላገኛት እንደምፈልግ ነግሬያት ብማፀናትም ጥያቄዬን ልትቀበል አልቻለችም፡፡

በመጨረሻ እሷን ከተደበቀችበት ጉድጓድ እንዴት አድርጌ ለማውጣት እችላለሁ? ብዬ ሳስብ የፃፈቻቸውን ፅሁፎች የማሳተም ሃሳብ በአዕምሮዬ ተሠነቀረና አማከርኳት፤ ነገሩ ግን እንደገመትኩት አልሆነም፡፡ ጽሁፎቿን የማሳተም ፍላጎት እንደሌላትና እኔ ማሳተም ከፈለኩ ግን እንደማትቃወመኝ እናም ውክልናውንም እንደምትሠጠኝ ነግራኝ ከዛ አልፎ ግን ከእኔ ጋር ለመገናኘት ለጊዜው ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት አረዳችኝ፡፡ እንዳለችውም ውክልናውን በፖስታ ቤት ላከችልኝ..
👍8710🥰1👏1
በዚህም መሠረት መጽሐፍ በእኔ አማካይነት እና በጓደኞቼም እገዛ ታትሞ እንሆ ዛሬ ለምረቃ በቃ ፡፡ እኔም ጋዜጠኛ እንደመሆኔ
መጠን እዚህ ያላችሁ ጋዜጠኞች መዓት ጥያቄ
በአዕምሮአችሁ እየተጉላላ መሆኑ ቢገባኝም አሁን ወደ ዝግጅቱ በቀጥታ እንድንገባ እየጠየቅኩ በስተመጨረሻ ላይ ግን በተቻለ መጠን ለጥያቄያችሁ መልስ ልሠጣችሁ እንደምሞክር ቃል እገባለው፡፡ በመቀጠል የእለቱን የክብር እንግዳ የሆኑት የደራሲያን ማህበር ፕሬዘዳንት በንግግር እንዲከፍቱልን በክብር እጠይቃለሁ›› በማለት መድረኩን ለፕሬዘዳንቱ አስረከበ፡፡

ፕሬዘዳንቱም ንግራቸውን በመገረም ጀምረው በመደነቅ ጨረሱና መድረኩን መልሠው ለሁሴን አስረከቡ፡፡

ሁሴን ንግግሩን ቀጠለ ‹‹በመቀጠል የደራሲዋ አድናቂዎች ከመጽሐፉ የተወሠነ ጽሁፍ በመቀነጫጨብ ለዕድምተኞቻችን ያቀርቡልናል፡፡ የመጀመሪያዋ አቅራቢ ትንግርት ትሆናለች፡፡ ትንግርት ወደ መድረኩ ብትመጪልን፡፡ በነገራችን ላይ ትንግርት በሞያዋ ሠዓሊ ነች፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት በአልያንስፍራንስ የመጀመሪያ የሥዕል
ኤግዚብሽኗን ታቀርባለች፡፡

ጋዜጠኞች ይህቺን ልጅ ብትከታተሏት ድንቅ ታሪክ ከጀርባዋ እንደምታገኙ በምስጢር ሹክ ልላችሁ እወዳለሁ፡፡›› በማለት ነጭ የአበሻ ቀሚሷን ለብሳ በቄንጠኛ እርምጃ ወደ መድረኩ ለተቃረበችው ትዕንግርት መድረኩን ለቀቀላት፡፡

እሷም ያለምንም የመግቢያ ንግግር ቀጥታ መጽሐፉን ገልጣ ወደ ማንበብ ነበር የገባችው፡፡ ‹እናቴ› በሚል ርዕስ የተፃፈውን አጭር ልቦለድ ነበር የምታነበው፡፡ አዳራሹ በፀጥታ ተሸበበ፤ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ መቁነጥነጣቸውን አቁመው በተመስጦ በማዳመጥ ላይ ናቸው፡፡ የታሪኩ ፍሠትና የቃላቶቹ ውበት ብቻ አልነበረም እንዲመሠጡ ያስገደዳቸው፡፡ የተራኪዋም ድንቅ ችሎታ አፍ ያስከፍታል፡፡ የምታነበው ድርሠት በሦስት ገፀ ባሕርያት የተዋቀረ ነው፡፡ አንድ ወጣት ሴት፣ አንድ አዛውንት እናት እና ጎረምሳ ወንድ፡፡ የሦስቱንም ንግግር
በተለያየ የድምፅ ቅላፄ ሳታምታታ እየቀያየረች ስታቀርብ ቀድሞውንም ሕይወት ላለው ድርሠት ድርብ ሕይወት ዘራችበት፡፡ በዚህም ችሎታዋ እድምተኛውም ሆነ ጋዜጠኞች በሙሉ በእጅጉን ተደነቁባት፡፡ ሠሎሞንና ሁሴንም በመገረም ፈዘው ነበር፡፡

የሙዚቃ እረፍት ከተደረገ በኋላ ሌሎች ሦስት
አንባቢዎች ፎዚያንም ጨምሮ የመረጡትን
በንባብ አሠሙ፡፡በአጠቃላይ የመጽሀፍ ምረቃ በዓሉ ከተለመደው የተለየ ብዙ አስገራሚ
ነገሮች የታመቁበት ነበር፡፡ እያንዳንዱ ጋዜጠኛ
ያገኟቸውን መረጃዎች በቅደም ተከተል አጠናቅሮ በየሚሠሩበት ሚዲያ ላይ
ለማቅረብ ከፍተኛ ጉጉትና መቻኮል ይታይባቸው ነበር፡፡ሁሴንም እንዲህ ያሠፈሠፈውን እያንዳንዱን ጋዜጠኛ ነገሮችን በምንም መልኩ እንደተረዱት እና በምን መልኩም ለሕዝብ ለማስተጋባት እንደወሠኑ
ለማወቅ ጓጓ፡፡ መጽሀፉም በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል? ወይስ አንባቢ አጥቶ በየመጽሃፍ መሸጫ መደብሩ የብል ሲሳይ ሆኖ
ይቀራል? የሚለውን ጥያቄ ሌላ ያስጨነቀው ጉዳይ ነበር የሆነበት፡፡ መልሶቹን ለማግኘት ግን የተወሠኑ የጊዜ ሽክርክሮችን በትዕግስት መጠበቅ እንዳለበት አልጠፋውም፡:
ግን የተወሰኑ የጊዜ ሽክርክሮችን በትግስት መጠበቅ እንዳለበት አልጠፋውም።

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች 
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍7726
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ለሁለት ወራት ድምፅዋን አልሠማም፡፡ አልደወለችለትም፡፡ ምንም አይነት አዲስ ጽሁፍም አላከችለትም፡፡ እሷ ልታገኘው ካልፈለገች እሱ ሊያገኛት የሚችልበት ምንም መንገድ የለውም፡፡ ይሄ ሁኔታ ሁሴንን እጅግ ሲያስጨንቀውና ሲያበሳጨው ነው የከረመው፡፡ ዛሬ ግን በሀሳብ የሚያባክነው ጊዜ አላገኘም፤ውጥረት ላይ ነው ያለው፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ በዋቤ…»
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ዘጠኝ፦ 4 አይኖች 2 ልቦች
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

ከሰባ ሁለት ሰዐታት ቡሃላ …

   ይዘንባል፦ዝናቡ። ዝግ ብሎ፣ ችፍ ችፍ እያለ፣ በዛፎቹ፣ በሜዳው ሳሩ ላይ ልስልስ ብሎ ይወርዳል። በማለዳ ከእንቅልፌ ተነስቼ፣ በሆስፒታሉ ክፍል መስኮት  መስኮት አሻግሬ የዝናቡን አወራርድ እያየሁ ነው። የዝናቡ ግልገል ጠብታዎች በመሬት ላይ ተከታትለው ሲያርፉ የሚሰሩት ክበቦች ሃሳብን ይሰርቃል። ቀኑ ዝናባማ ነው። ይህን ቀን ላለማየት ጸሀይ ራሱ የተደበቀች ነው የምትመስለው።

ዞር ብዬ ሳሌምን አየኋት። በ'ርጋታዋ የዳሪክን እጅ ይዛ እየጸለየች ነው። በልብዋ የምትለውን፣ ለጌታ የምትናገረውን ለአፍታ መስማት ብችል ብዬ ተመኘሁ። (((ባለፉት ሰባ ምናምን ሰዐታት ብዙ አዲስ ነገር ሆኗል። በህይወቴ ባይኔ አየዋለሁ ብዬ የማላውቀውን፣ የክፋት ሁሉ ምንጭ የሆነ ሰው ትላንት አይቻለሁ። ይህን ሰውም ሳሌም ፍቅርና ይቅርታ ከልቧ ስታፈስለት በአይኖቼ አይቼ መጥቻለሁ። ይህን ታሪክ ሌላ ጊዜ እጽፋለሁ ...))))

ጸሎቱን ስትጨርስ በዝምታ ዳሪክን ማዘጋጀት ጀመርን፦ ሳሌምና እኔ። የለበሰውን አረንጓዴ ጋውን አውለቅን። ሌላ  ሙሉ ለሙሉ ነጭ የሆስፒታሉን ልብስ ማልበስ ጀመርን። ወደ ጎን ስናዞረው ባለፈው  ሳሌም ስታወራለት የነበረውን አምስት ጠባሳዎች አየኋቸው። አምስት የዳኑ፣ የደረቁ ጠባሳዎች ግን ደሞ ብዙ ነገር የሚናገሩ፣ የሚተርኩ የተበታተኑ ጠባሳዎች። አልቻልኩም። የዳሪክ ለሞት መታጨት …ሌሊቱን ሙሉ ሲጨንቀኝ፣ ሆዴን ባር ባር ሲለኝ፣ ሲያሳዝነኝ…ከእንባዬ ጋር ስታገል ነው ያደርኩት። በቃ አሁን ግን አልቻልኩም። እንባዬ ከአይኔ ፈንቅሎ ይወርድ ጀመር። ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ። ማዘጋጀቱን ትቼ፣ አልጋው አጠገብ ካለው ወንበር ላይ ቁጭ አልኩኝና አጎንብሼ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ።

ሳሌም መጥታ አቀፈችኝ “…ሳዬ…ሳዬ… አሁን የምናልቅስበት ጊዜ አይደለም። አሁን ፍቅሬን የምናዘጋጅበት ጊዜ ነው። ወደፊት አትቅደሚ። የወደፊቱን የሚያውቀው ጌታ ብቻ ነው። እኛ የሚጠበቅብን አሁንን መኖር ነው። አሁን የኔ መልዐክ በህይወት አለ። ለወደፊቱ ደግሞ ጌታ ያለው ይሆናል።…”

ለቅሶዬ በውስጤ እያንቀጠቀጠኝ፣ ሰውነቴን እያረገበገበው እንደምንም ጸጥ አልኩኝ። ሳሌም ቀና ብዬ ሳያት…ያው ናት። ጸጥ፣ርግት ያለች ሳሌም። የማትነቃነቅ ጽኑ ተራራ። የመከራ ንፋስ የማያናውጣት ውብ ሰማያዊ ባህር። ምን አይነት ልጅ ናት? ምን ጉድ ናት? እንደገና ደግሞ መልሼ በራሴ አፈርኩኝ። እሷ ልታዝን፣ ልታለቅስ እኔ ደግሞ ላጽናናት ሲገባ በተቃራኒው መሆኑ አሳፈረኝ።

…..እንደገና አየኋት። በ'ርጋታ በትላልቅ ውብ አይኖቿ፣ ስስ ፈገግታዋን አጅባ ታየኛለች። እነዚህ ትላልቅ ውብ ሁለት አይኖች፣ ከአመታት በፊት ዳሪክ ያዩ አይኖች፣ ከአመታት በፊት የዳሪክ ልብ የወሰዱት 'ርግት ያሉ አይኖች...
*
*
*
ከሰባ ሁለት ወራት በፊት…

  አዲስ አበባ፦ወሎ ሰፈር፣ አንዲት ትንሽ ቸርች ግቢ ውስጥ… ቅዳሜ ነው። ግቢ ….ሜዳ፣ ጥግ ላይ በቆርቆሮ የተሰራ አዳራሽ፣ ከአዳራሹ አጠገብ ትናንሽ ክፍሎች። ሜዳው ላይ አዋራው ይጨሳል፦ ዳሪክና ጎዳኞቹ ከሚጫወቱት የእግር ኳስ የተነሳ። በቸርቹ ድጋፍ የሚደርግላቸው ልጆች ቅዳሜ ኳስ ይጫወታሉ ግቢው ውስጥ። ዳሪክ አንዱ ነው። ጨዋታው ሲሞቅ  ከተዋጫዋቾቹ አንዱ ያጎናት ኳስ አቅጣጫዋን ስታ በግቢው ውስጥ ጥግ ወዳሉ አነስተኛ ክፍሎች አመራች። ዳሪክ ኳሷን ለማምጣት ተከትሎ ሄደ። ያች ድቡልቡል ኳስ፣ ቀስ እያለች ትሄድ ጀመር…. ክብልል፣…. ክብልል፣… ክብልል ….የምትሄድበትን ታውቅ ይመስል… ክብልል ክብልል… “..ና…. እያለችው …ክብልል … ያቺ ኳስ ታዳጊው ዳሪክ ምናልባትም የህይወቱን አቅጣጫ በሚገርም ሁኔታ ወደ ሚቀይረው ሌላ ታዳጊ ልጅ ጋር፣ ፍቅሩ ጋር እየሄደች መሆኑን ፈጽሞ አላወቀም። ክብልል፣ አሁንም ክብልል ….በመጨረሻም … ያቺ ኳስ ...በስፍራና ጊዜ ኡደት ውስጥ የሚፈለገው ስፍራና ጊዜ ላይ ሄዳ ቀጥ አለች። ቆመች። …ዳሪክ ኳሷ ጋር ሲደርስ ያየው ነገር ሙሉ በሙሉ አይኑን ቀማው፣ የሰማው ነገር ልቡን ወሰደው። አንዲት ክፍል …. በትንሹ ገርበብ ብሎ የተከፈተ በር….አንዲት ታዳጊ…. ለስላሳ ሙዚቃ ከፊቷ ካለው ኦርጋን ላይ በ‘ርጋታ ትጫወታለች። ዳሪክ ከምንም በፊት ያየው ጣቶች ነው። አለንጋ የሳሌም አስር ጣቶች በነጭና በጥቁር የፒያኖ ቁልፎች ላይ ከወድያ ወዲህ እንደ ውብ ዳንሰኞች ይስግራሉ፣ በዝግታ ይጓዛሉ። ሙዚቃው በ'ርጋታ ይፈሳል። ….ያማሩ ውብ የጥፍር ዘውዶች ከደፉት አለንጋ ጣቶች ቀጥሎ ደሞ ያየው ፊቷን ነው።  … ብቅ ልትል እንደተዘጋጀች የማለዳ ጸሀይ በረጅም ጽጉሯ በክፊል ተሸፍኗል። … ‘ርግት ያለው ፊቷ የጣቶቿ ደቀ መዝሙር ነው። ፊቷ ጣቶቿን ይከተላል። ጣቶቿ በፒያኖው ላይ ወደ እዚህ ጥግ ሲመጡ፣ ፊቷ አብሮ ዘንበል ይላል። ወደ ዛኛው ጥግ ሲሄዱም እንዲሁ። መዝሙሩን ተከትላ አንዳንዴ አይኗን ጨፈን ደግሞ አንዴ ከፈት … ሰበር ሰካ የሚሉ ቆንጆ ጣቶች፣'ርግት ያለ ቆንጆ ሽራፊ ፊት ፣ዝግ ካለው የሙዚቃው ስልት ጋር የሚንቀሳቀሰው ጸጉሯ የተዘናፈለበት የሳሌም ትከሻ…ውብ ትዕይንት ነው። የዳሪክ ጊዜ ቆመ። ህዋሳቶቹ ባሉበት ዝም አሉ። የልብ ትርታው ረገበ። ‘ስትንፋሱ በሳንባው ውስጥ ተረጋጋ።  ሁሉም ስሜቶቹ ወደ ሳሌም ሄዱ። ዳሪክ ኳሷን ትቶ …ቀጥ፣ ቆም፣ ድርቅ ….  በቃ ሳሌምን እያያት …ፍዝዝ አለ።
    በዚያው ቅጽበት ሳሌም የሆነ ሃይል የነገራት ይመስል ዞር ብላ ወደ ዳሪክ ተመለከተች። ሁለት የሳሌም ትላልቅ አይኖች፣ ሁለት የዳሪክ አይኖች ተገናኙ። ለመጀመርያ ጊዜ ተያዩ። አይኖቿን ሲያይ የሆነ ነገር ወረረው። ከውስጧ፣ ከነፍሷ የሆነ ነገር፣ የሳሌም ቁራጭ የተላለፈበት፣ የመጣበት መሰለው። ምንድን ነው? እንዴት ያለ ስሜት ነው? እኔ አላውቅም። ይህን ማንም ሊያስረዳው ወይም ሊጽፈው አይችልም።
     አሁን የዳሪክ የረገበ የልብ ትርታ ጨመረ። አሁንም ግን ፍዝዝ እንዳለ ነው። አልተነቃነቀም። አልሄደም። ዝም ብሎ ሳሌምን ያያል። ሳሌም የዳሪክ ሁኔታ ገርሟት ፈገግ አለች ፦ ያ የሁልጊዜ ስስ ፈገግታ በከናፍርቶቿ መሃል ብልጭ፣ ብቅ አለ። ያ ፈገግታ ዳሪክን አጠናቀቀው። ሳሌም ፦ በአይኗ ጀመረችው። ሳሌም፦ በፈገግታዋ ጨረሰቸው። ይህ ሁሉ የሆነው ምናልባትም በሲሶ ደቂቃ ነው። በነዚያ አርባ ምናምን ሰከንዶች ዳሪክ ፍቅር በሚባለው ጎዳና ዘጠና ዲግሪ ዞሮ መንገድ … ሳሌም ሊወድ “…ሀ…” ብሎ ጀመረ። ይህ የፍቅሩ አልፋ ነው። የመውደዱ መነሻ ነው።

ከፍቅሩ አልፋ ቀን ጀምሮ ዳሪክ ሳሌምን ማየት ርሃቡ ሆነ።
  
ሳታየው ያያታል።

ተደብቆ ያያታል።

ስትሄድ ያያታል።

ከሩቅ ያያታል።

ማየት፣ማየት፣ ማየት ደሞ ማየትና ማየት። ዝም ብሎ ሲያያት ቀናትና ሳምንታት አለፉ።

በዚህ አለም ቋንቋ የሁለት አለማት ልጆች ናቸው፦ ዳሪክና ሳሌም። ሃብታምና ድሃ ተብሎ በተራራቀ ሰው ሰራሽ መደብ ላይ የተቀመጡ ታዳጊዎች።

ዳሪክ ፦ ብቻውን ነው። ከጥቂት አመታት በፊት ወላጆቹ ተከታትለው ሞተዋል። ወላጆቹ ሞቱ፣ ተቀበሩ። ከዛን ቀን ጀምሮ ዳሪክን ሊያይ የመጣ የቅርብም፣ የሩቅም ዘመድ የለም። ዳሪክ ወሎ ሰፈር ውስጥ ካሉት ችግረኛ ጎረቤቶቹና የሰፈር ሰዎች በቀር ማንንም አያውቅም። ብቸኛ ነው።ዳሪክ መንግስት ት/ቤት ይማራል። ጎበዝ ተማሪ ነው። ታግሎ ይሰራል። በሳምንቱ መጨረሻ የታክሲ ረዳት ነው። በሳምንቱ የስራ ቀናት ደሞ ይማራል። ከ'ርዳታ ድርጅቱ ከሚያገኘው ጋር ተዳምሮ በቂው ነው።
👍443👏1
ሳሌም፦ ሰፊና ብዙ ናት።

የምትኖረው ሃብታም አያቶቿ ቤት ነው። በአመት ሲበዛም በሁለት አመት እየመጣ የሚያያት አባቷ ለብዙ አመታት አሜሪካ የኖረ ዲያስፖራ ነው። ሳሌምን እጅግ ይወዳል።  ከምትጽፍበት እርሳስ ጀምሮ እስከ ላፕቶፕ ድረስ ተጭኖ ይመጣላታል፦ ከሃገረ አሜሪካ። እናቷን አታውቃትም። በልጅነቷ እንደሞተች ነው ። እንግዲህ ሳሌም ትኖራለች፦ ቦሌ። ትመጣለች፦ በሹፌርና መኪና። ትሄዳለች ፦ በሌላ መኪና። ይኸው ነው።

ዳሪክ ሳሌምን ከማየት ውጪ እድልም ተሰፋም አልነበረውም።

ሁለቱን ያስተያያችው ጌታ ግን የበለጠ አላማ ነበረው። ዩኒቨርስን፣ ሁኔታዎችን አመቻችቶ እንዲገናኙ ...

አንድ ቀን …

ሳሌም ሙዚቃ መጫወት ስትጀምር ትመሰጣለች። ትሄዳለች። አትሰማም። አታይም። በሙዚቃው ትሰፍፋለች። ሰዐት ይረሳል። የዛን ለት ተመስጣ እየተጫወተች፣ የሚወስዳትን መኪና ስትጠብቅ ጊዜው መምሸቱን አላስተዋለችም። በመሃል ስልኳ ላይ ዛሬ መኪና እንዳትጠብቅ በታክሲ ወደ ቤት እንድትመጣ መልዕክት ገብቷል። አላየቸውም። ቆይቶ ደሞ ባትሪ የጨረሰው ስልክ ላይበራ ተኝቷል።
ሳሌም መምሸቱን ስታውቅ ተጣድፋ ተነሳችና ወደ በሩ አመራች። የቸርቹ ግቢ ጭር ብሏል። ሰው የለም።

“…ውይ ልጄ  እስካሁን እዚህ ነሽ እንዴ?....” በሩን የሚጠብቁት ዘበኛ ነበሩ። ሰው መኖሩንም ያወቁ አይመስሉም።

“…ይቅርታ አባባ ስልኬ ባትሪ ጨርሷል። የሚወስደኝ ሹፌር ደሞ ቀረ። ስልክ ካሎት ልዋስና ልደውል?...” በትህትና ጠየቀች

“….የቸርቹን ስልክ መጠቀም እንችላለን ብለው በሩ ላይ ካለችው ትንሽ ክፍል ውስጥ የመስመር ስልክ አወጡ።….”

“…አመሰግናለሁ!...” ብላ የስልኩን እጀታ አነሳች። ማሰብ ጀመረች። ሌላ ጣጣ። ቁጥሮቹን ከየት ታምጣቸው? የሹፌሩን፣ የቤተሰቧን ስልክ አታውቅም። ሁሉም ያለው የሞባይል ስልኳ ላይ ነው። አሰበች። አሰበች። ምንም ነገር ሊመጣላት አልቻለም። ስልኩን በቦታው መለሰችና ለመሄድ ተነሳች።

ሳሌም ወደ በሩ ስታመራ “…ምነው ልጄ?...”አሏት ዘበኛው “….ማግኘት አልቻልሽም የመሂናውን ነጂ…”

“….አይ በቃ በእግሬ እሄዳለሁ አባባ….” ሳሌም የማንንም ቁጥር እንደማትውቅ መናገሩ አሳፍሯት ነበር።

“….ልጄ ተጠንቀቂ መጥፎ ሰፈር ነው….”  አሉ ዘበኛው ሳሌም ከኋላዋ እያዩ “….ጌታ ከ አንቺ ጋር ይሁን።….”

ሳሌም ፈሪ አይደለችም። ግን የዛንለት የምትሄድበት መንገድና ጨለማው እያስፈራት እየተደነቃቀፈች መጓዝ ጀመረች። በኮረንኮንቹ ለደቂቃዎች ሄዳ ወደ ግራ ስትታጠፍ ከየት መጡ ሳይባሉ ሶስት ጎረምሶች ከየጥጋ ጥጉ ወጥተው ከፊት ለፊቷ ተደረደሩ።

ሳሌም ልቧ ደረቷን አልፎ ይወጣ ይመስል እንደ ታንቡር ይጮህ ጀመር። ጨለማ ነው ባ‘ካባቢው ሰው የሚባል አይታይም።

“…ም…ን … ም.. ንን   ፈልጋችሁ?” ሳሌም ራሷን ለመቆጣጠር እየፈለገች

ጠቆር ያለው አንዱ ቀደሞ መናገር ጀመረ “…የቸርች በግ? የቅባት ልጅ ምነው ዛሬ ብቻሽን?...”

“…እ.. እ…”  ሳሌም በፍርሃት መርበትበት ጀመረች።

“…ተረጋጊ እኛ ጀለሶችሽ ነን። መጀመሪያ እንተዋወቅ እኔ ቦዲ እባላለሁ…” እጁን ዘረጋና የሳሌምን ቀኝ ጨበጠ።

“…ካቹ…” አለ ሌላኛው

“…ዲናሬ…” አለ ሶስተኛው

“….ምንም አናረግሽም። የምፍለገው ነገር ያለሽን ነው። ያለሽን ጩባ፣ ኮይን ምናምን እጄ ላይ ዱቅ ታደርጊያለሽ። ከዛ ቀጥ ብለሽ ትከተይናለሽ። ወስደን ድፍን መሆንሽን በየተራ….”  ቦዲ እጇን በትልቅ ሻካራ እጆቹ ጥብቅ አድርጎ ሲያወራ ሳሌም የሚለው ባይገባትም አደጋ ከፊቷ እንዳለ ገብቷታል።

“…እያረፍሽው ነው ያልኩትን ነገር?...” ጸጉሯን ሊነካ ሲጀመር

ብፈራም ለመታገል መሞከር አለብኝ ብላ አሰበች። “…ጫፌን እንዳትነካኝ…” እጁን ከጸጉሯ ላይ ስተገፈትረው ሁለተኛውንም እጇን ያዘው። ሁለቱን እጇን በአንድ እጁ ግጥም አድርጎ ሲይዝ መፈናፈኛ አጣች።

“…እጮሃለሁ…” ሳሌም የሞት ሞቷን እየታገለች

“…እንደዛማ አታደርጊም…” ትልቅ ሲንጢ አወጣ። “….ብትጮሂም ማንም አይደርስልሽም።….”

ሳሌም ተሰፋ ቆረጠች። ድቅድቅ ጨለማ፣ የማትውቀው ሰፈር በሶስት ጉልበተኞች ፊት ናት። ጌታ ሆይ እባክህን። ጌታ ራሱ እንዲወርድ ወይም ከመላዕክቶቹ አንዱን እንዲልክ በልቧ አጥብቃ ተመኘች።

“….ፒስ ነው ጀለሶች?...” ድንገት ከኋላዋ ድምጽ ሰማች

ሳሌም ዞር ስትል አንድ ጠይም፣ ረዘም ያለ፣ ከርዳዳ ጸጉር ያለው ልጅ ከኋላዋ እየመጣ ነው። መጣ። ቀረበና ቆመ። “…ሰላም ነው ጀለሶች?...”

“…ሰላም ነው አቡቲ? እንዴት ነሽ?...” ሁሉም  እየተቀለሰልሱ ሰላም አሉት።

“…ምን እያረጋችሁ ነው ፍሬንዴን?...” በሳሌምና በሶስቱ መካከል ቆመ

“…ታውቃታለህ እንዴ ቺኳን?...” ቦዲ ጠየቀ

“…አዎ…” ጠይሙ ልጅ መለሰ “…ከባድ ጀለሴ ናት!...”

“…አላወቅንም አቡቲ ይመችሽ …በቃ እንሸበለላለን….” ብለው ሶስቱም ወደፊት መንገዳቸውን ቀጠሉ።

ሳሌም የተነጋገሩት ምንም ባይገባትም ከደቂቃዎች በፊት አውሬ የነበሩት ሶስቱ ባለጋራዎቿ በጠይሙ ልጅ ፊት እንደ ለማዳ የሳሎን ውሻ ሹክክ ብለው መንገዳቸው ሲቀጥሉ ግን የሆነ ተዐምር  መስሏት ፈዘዛ ታያለች። 

ሳሌም የሆነውን ማመን አቃታት። አየችው፦ ጠይሙን ልጅ። እንደ መልዐክ ሳታስበው ብቅ ያለው፣ በሷና በአጥፊዎቿ መካከል የተገኘው ፦ ጠይም ከርዳዳ ጸጉር ያለው ልጅ።

“…አመሰግናለሁ…”  አይን አይኑን እያየች “….አመሰግናለሁ …”

“…ችግር የለውም…እዚህ ሰፈር ብቻሽን፣ በምሽት መሄድ የለብሽም። አደገኛ ነው።…”

“…እሺ.. ሁለተኛ አላደርገውም…” ባለችበት ደርቃ ቆማ

“…ልሸኝሽ?...” ልጁ ጠየቃት

ሳሌም አላቅማማችም “…እሺ…”

መሄድ ሲጀምሩ ሳሌም ሳታስበው በእጇ  ክንዱን ይዛው ነበር። ከፍርሃቷ፣ ከድንጋጤዋ፣ ከመሸበሯ። ዋናው አስፋልት ድረስ እስኪወጡ ድረስ አልለቀቀችውም።

በአስፋልቱ እግረኛ መንገድ ላይ እየሄዱ መነጋገር ጀመሩ። 

“…ቸርች አውቅሻለሁ ኦርጋን ስትጫወቺ… ስምሽን ግን አላውቀውም…”

“…ሳሌም ያንተስ?...”

“…ዳሪክ….”

ጥቂት ዝም ተባባሉ። “…እኔ ግን ቸርች አይቼህ አላውቅም?...”

“…በቸርቹ ከሚረዱት ልጆች አንዱ ነኝ። እኔም እኮ ሙዚቃ እወዳለሁ።…በትርፍ ጊዜ በ'ርዳታ ድርጅቱ ጊታር እየተማርኩ ነው።…”

“…እውነት። እኔም ጊታር እሞክራለሁ…” ሳሌም መለሰች

“…ትቺያለሽ?...  እኔ በጣም ጀማሪ ነኝ።…”

“…አዎ ከፈለግክ አንዳንድ ኪዎች ላሳይህ እችላለሁ።…”

ዳሪክ ፊቱ በደስታ ተፍልቀለቀ “…በጣም ደስ ይለኛል ካልስቸገርኩሽ?...”

“….አልቸገርም።…”

ለሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ተቀጣጠሩ፦ ቸርች።

በተቀጣጠሩበት ቀን ሲገናኙ ከጥናታችው ይልቅ ያሳለፉት ሲያወሩ ነው።ዳሪክ ሲጠቀለል ሁለት ነገር ነው። ዳሪክ ደስታና ሳቅ ነው። ሳቁ ደግሞ ተላላፊ ነው።

ሳቁን ማስተላለፍ ካልቻለ ደግሞ ቀልድ ያመጣል። አንዴ ሰፈሩ የሰማውን፣ አንዴ እንደ ክበበው ገዳ (ሸምሱ) እየሆነ … “..መቶ ብር አማረኝ…” እያለ ሳሌምን ሲያስቃት፣ ሲያፍነከንካት ቆዩ። በሚቀጥለውም ቀንም፣ ከዛም፣ ቀጥሎም እንዲሁ። ዳሪክ ሳሌም ልብ ውስጥ የገባው በሳቆች ሰረገላ፣ በደስታ ፈረሶች ላይ ሆኖ ነው። ብዙ ጊዜ እንደምታውቀው ጓደኛዋ “..ዲ..” ብላ አቆላምጣ ልትጠራው ስትጀምር ጊዜ አልፈጀባትም።

አንዳንዴ አርፍዶ ይመጣል። ብዙ ጊዜ የሚያረፍደው ለዕለት ጉርሱ…ለስራው ሲሮጥ ነው። ሳሌም ግን ይህን አታውቅም።

አርፍዶ ሲደርስ “…አንተ ዲ ምን ሆነህ ነው?...” ሳሌም ትጠይቃለች።
👍347🔥1😁1