አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ግን ክፋቱ በፈለግናት  ጊዜ ስለምናገኛት…በጣራናት ጊዜ ሮጣ ስራችን ስለምትገኝ ዋጋዋን ብዙም አናውቀው…. እንደድንገት ስትነጠለን  እና ከእጃችን ተንሸራታ ስናጣት ግን  አንድ ሰው ብቻ እንዳልነበረች ይገለጽልናል…መላ ዓለም እሷን እንደማይተካልን  ትምህርት እናገኛለን…ግን ትምህርት ቀድሞ ያጣኸው ነገር ወደፊት ዞሮ መጥቶ እንድታስተካክለው እድሉን ካላገኘህ ጥቅም የለውም..በደንብ ስትፀፀት እድትኖር ብቻ ነው የሚያግዝህ፡፡

ውሃም በቀላሉ ነው የምናገኘው..እኛ እራሱ በዋናነት የተሰራነው ከውሀ ነው ..ምድርም ሶስት እጆ ውሀ ነው….በቀላሉ ብቻ ሳይሆነ በርካሽም እናገኘዋለን.. ሰውነታችን ከየትኛውም መጠጥ በተሻለ በውሀ ይረካል…በውሃ ጤነኝነት ይሰማዋል…የውስጥ መጠማታችንን ብቻ ሳይሆን በአካልም መዛላችንን በውሀ ነው የምናክመው….ሰውነታንን የምንታጠበው የቆሸሸ ሰውነታችንን ለማጽዳት ብቻ አይደለም ውኃው በሰውነታችን ላይ ሲያርፍ መነፍስን የማረጋጋት እና የአዕምሮ ውጥረትን የማከም ኃይል ስላለው ነው…ግን ‹‹ወይ ስታጠብ ቀለል ይለኛል›› በማለት ያገኘነውን ጥቅም እናቃልለዋለን እንጂ ውሀ መድሀኒት ነው ብለን ዕውቅና መስጠት አንፈልግም ..ወሃ የደም ግፊት መድሀኒት ነው..ውሀ የኩላሊት መድሀኒት ነው…ውሃ የራስ ምታት መድሀኒት ነው…..ወሃ የበሽታዎች ሁሉ ፈውስ ነው…
‹‹የእኔ ውሃ ግን  አንቺ ነበርሽ…››አሏት እዝን እንዳሉ፡፡
‹‹ማለት……….?››አለቻቸው አሳዝነዋት፡፡
‹‹አዎ እኔ ጡረታ እስክወጣ ድረስ በዚህች ሀገር ላይ በጣም ስኬታማ ከሆኑ ጥቂት ሰዎች መካከል አንድ  ነኝ ብዬ አስብና እመፃደቅ ነበር….አምስት ስድስት ዲግሪዎች ስላሉኝ አንቱ የምባል ፕሮፌሰር ስለሆንኩ በቃ እታበይ ነበር….ልክ ጡረታ ስወጣ ግን ግማሽ ህይወት ብቻ ስኖር እንደነበር ተገለጽለኝ..እንደው ወደኃላ ተመልሶ የኖሩትን ህይወት ማስተካከል ቢቻል ካሉኝ ዲግሪዎች መካከል አንድን ብቻ አስቀርቼ ሌሎቹን በልጆች እና የልጅ ልጆች መቀየር ብችል ደስ ይለኝ ነበር..ከዛሬ 40 አመት በፊት አግብቼ ዛሬ የ35 ዓመት ልጅ እና የአምስት አመት የልጅ ልጅ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ በጣም ስኬታማ እና ሙሉ እሆን ነበር..ይሄን ቁጭቴን ባንቺ ነበር እየተፅናናው ለመኖር እውተረተር የነበረው…አሁን ግን….››
‹‹እንዲህ እማ አይዘኑ››
‹‹ተይኝ ልዘን…እነዛ ሁሉ ያገኘዋቸው ግኝቶች …እነዛ ሁሉ የተሸለምኮቸው ሽልማቶች እኔ ካለፍኩ በኃላ ማን ይረከባቸዋል..ማን ነው ሊኮራባቸው የሚችል የእኔ ሰው  ……….?
‹‹አሁን ወደኃላ ተመልሰው አድሉን ቢያገኙ እኮ መልሰው ተመሳሳዩን ነው የሚያደርጉት››
‹‹በፍጽም አላደርገውም..ህይወት ሚዛን መጠበቅ አላባት…እድሜሽን ሙሉ ገንዘብ ለማካበት ሰትባክኚ ቆይተሽ ካረጀሽ እና ጥርስሽ ከረገፈ በኃላ ልዝናና ብትይ አያምርብሽም… ደስታ ሚያመነጨው የሰውነትሽ ዕጢም እንዘይሙን ማምረት ስለሚያቆም አትቺይም….ወንደላጤ ሆነሽ ስትንዘላዘይ ኖረሽ በእኔ ዕድሜ ላግባ ብትይ እንዴት ተደርጎ..እንደው ሚስትዬዋ ተገኝታ ማግባት ቢቻል እንኳን እንዴት መውለድ ይቻላል..…….?ቢወለድ እራሱ የማያሳድጉትን ልጅ  እንዴት ….?ሁሉ ነገር በጊዜው ነው የሚያምረው››
‹‹እና እንዴት መሆን አለበት ይላሉ…….?››ጠየቀቻቸው
‹‹የተወሰነ መማር..የተወሰነ ገንዘብ መስራት… የተወሰን ቁጥር ያለው ቤተሰብ መመስረት…በቃ ከሁሉም የሚያስፈልገውን እና የምትጠቀሚበትን ያህል መውሰድ ነው…አየሽ አኔ አሁን ተማርኩ ከምላቸው ትምህርቶች መካከል ሁለቱን ዲግሪዎች ለአንድ ሰምንት እንኳን አልሰራሁባቸውም…እንዲሁ ለጉራ ካልሆነ በስተቀር  ያን ያህል ፋይዳ አልነበራቸውም …
በልተው እንደጨረሱ እጇን ታጥባ  እሳቸው ቢራቸውን እየጠጡ እሷ ደግሞ ወኃዋን ይዛ ወሬውን ቀጠሉ
‹‹እቤቱን እንግዲህ  ሰጥቼዎታለሁ…..››
‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም ….እኔ እኮ ለራሴ የሚበቃ የጡረታ ብር አለኝ..ተከራይቼ ሌላ ቦታ እኖራለሁ..ቤቱ የሚገባወ ለዘመዶችሽ ነው..››
‹‹አይ ይሄ ቤት የሚገባው ለእናቴ ነበር..ግን እናቴ ከተወለደችበት አካባቢ ንቅንቅ ማለት አለትፈልግም….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ይሸጥና ብሩን ይጠቀሙበታ››
‹‹አይዞት ለእሷ አያስቡ …በቂ የሆነ ብር ሰጣታለሁ..ይሄ ቤት ግን የሚሸጥ አይደለም…እሺ ጣሪያና ግድግዳው መሸጥ ቀላል ነው…እነዚህ ግቢውን የሞሉትን ዛፎች በስንት ብር ተምኜ ልሽጣቸው…?እነዚህ ዛፎቹን የወረሯቸውን በሺ የሚቆጠሩ ወፎች ስንት ስንት ብር ያወጣሉ...?ዝንጀሮዬን ስንት ልሽጠው..…?ጉሬዛዬንስ….?አዩ አንዳንድ ነገሮች ከሚሰጡት ጥቅም አንፃር ብቻ ሳይሆን ካለቸው ትርጉም  በመነሳት ዋጋ ሊወጣላቸው አይቻልም….አሁን ለአንድ ሀብታም ብሸጠው እኚ አሁን የጠቀስኩሎትን ሁሉ አንድ ሰምንት የሚያቆያቸው ይመስሎታል….?.ዛፎቹን ጨፍጭፎ መሬቱን ነፃ በማድረግ ፎቅ ነው ሚገነባበት…ወፎችስ እድሜ ለክንፋቸው በስደት  በመሸሽ  ነፍሳቸውን ለማቆት ይሞክራሉ..፤ሎሎቹስ….?

‹‹እሱስ ከባድ ነው››
‹‹ስለዚህ ቤቱ አይሸጥምም… ለሌላ ዘመድም ቢሆን ተላልፎ አይሰጥም…ይሄ ቦታ የሚገባው ለእርሷ ብቻ ነው..የእያንዳንዶን ዕጽዋት ሚስጥር የሚያውቁትና የሚረዱት እርሶ  ኖት… ስለዚህ የእርሶ ነው››
ፈገግ አሉ..
‹‹ምነው .. …….?ተሳሳትኩ እንዴ..…….?››አለቻቸው ፈገግታቸው የምፀት ስለነበረ ገርሞት
‹‹ስንት ዓመት ልኖር ብለሽ..…….?በተለይ አንቺ በሌለሽበት..ሁለት አመት ሶስት አመት..ከዛስ ያው የፈራሽው  መድረሱ አይቀርም..እነዚህ ሁሉ የለፋንባቸው ነገሮች አጥፊ እጅ መግባታቸው እና መውደማቸው አይቀሬ ነው…››
‹‹ስለዚህ አንድ ነገር እናድርጋ››
‹‹ምን…….?››
ከመቀመጫዋ ተነሳች..ንስሯ ለማድረግ የፈለገችውን ቀድሞ ገብቶታል ፤ ካለበት ዛፍ ላቆ ልክ ትሪኢት እደሚያሳይ የአየር ኃይል የጦር ጄት መገለባበጥ ጀመረ… እንዲህ የሚያደረግው ሲደሰት ነው…በስንት ቀኑ ፈታ አለ….. 
ወደእሳቸው ቀረበች… ግራ ገብቷቸው በዝምታ ያዩታል…. ከጀረባዋ ቆማ  ፀሎት እንደሚያደሰርስ   የፕሮቴስታንን ፓስተር ሁለት እጇን በጭንቅላታቸው ላይ ጫነችና አይኖቾን ጨፈነች…በፍጽም መመሰጥ ውስጥ ገባች….ቀስ እያለ ሰውነቷ ሲግል ይታወቃታል..አዎ ከልቧ ጀምሮ ኃይል እየተሰበሰብ በደምስሯ በመራወጥ ወደ እጆቾ እየፈሰሰ ነው…ከዛ ወደ ፕሮፌሰሩ ጭንቅላት መተላለፍ  ጀመረ…አይኖን የጨፈነች ቢሆንም እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ይታያታል… ኃይል የሞላው ሀመራዊ ቀለም  ከፕሮፌሰሩ ጭንቅላት አንስቶ ወደ አንገታቸው..ከዛም  ትከሻቸው እያለ ወደመላ ሰውነታቸው ተሰራጨ… መንዘፍዘፍ ጀመሩ….ኦ.. ሽበት የወረረው ነጭ ፀጉራቸው...ከግንባራቸው እየተነሳ ወደ መሬት ይረግፍ ጀመር…በዛው ቅፀበት ሌላ ደማቅ ጥቁር ሉጫ ፀጉር ከእያንዳንዱ የራስ ቅል ቀዳዳቸው በመብቀል ወደ ውጭ በመውጣት ጭንቅላታቸውን ሞላው…

ይቀጥላል

#YouTube ላይ subscribe እያደረጋችሁ ቤተሰቦች #የYou tube subscriber ቁጥር 100 በሞላበት በማንኛውም ሰአት ቀጣዩን እለቃለው ለናንተ ለቤተሰቦቼ ቀላል ነው 1 ደቂቃ ይበቃዋል ወይም ከዛ በታች በሉ አሁን ጀምሩ።
👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8510😁7👏4👎1
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ለዓመታት ጎብጦ እና አጎንብሶ የነበረ ትከሻቸው ቋቋቋቋቋ የሚል ድምጽ እያሰማ በመላቀቅ መቃናት ጀመረ…የተጨማደደ እና ተኮመታትሮ የነበረ ቆዳቸው ልክ የሽማግሌ ገፃ-ባህሪ ለመጫወት ጭንብል አጥልቆ እንደነበረ አክተር  ከፊታቸው ተሞሽልቆ በመነሳት መሬት ወደቀ…
ወዲያው መለስተኛ አውሎ ንፋስ ተነሳና እየተሸከረከረ መጥቶ እዚህም እዛም በዙሪያችን የወደቀውን የፕሮፌሰሩን የተወገደ አካል ከአካባቢው ጠራርጎ በአየር ላይ ተሸክሞ ሄደ ..
ከዛ…. ሁሉ ነገር እንዳሰበችው እንደሆነ ካረጋገጠች በኃላ እጆቾን ከጭንቅላታቸው አነሳችና…ወደመቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች…

አየቻቸው‹‹…..እንዴት አባቱ የሚያምር ጎረምሳ ሆኖል›ስትል እራሷ በሰራችው ተአምር እራሷ ተደነቀች   …‹‹ውይ እነዛ የአባቴ ዘመዶች መተው ሚወስዱኝ ባይሆን  ኖሮ ይሄን  ፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ቆንጅዬ  ጎረምሳ አግብቼ  መኖር ነበር….›ስትል የምፀት ፈግታ ፈገግ አለች፡
ፕሮፌሰሩ ቀስ እያለ ከሰመመኑ ነቃ…
‹‹ወይ ልጄ ምድነው ያደረግሺኝ…….?ራስ ምታቴ እና ጭንቀቴ እኮ ለቆኝ ሄደ››
‹‹አሞህ ነበር እንዴ…….?››
‹‹ምን አልሽኝ…….?››ግራ ተጋብተው
‹‹ ይቅርታ አሞት ነበር እንዴ…….? ለማለት ፈልጌ ነው››
‹‹አንቺን አልረብሽሽም ብዬ ነው እንጂ እንደምትሄጄ ከሰማሁበት ቀን አንስቶ ጤናም የለኝ ነበር..››
‹‹አይ እንኳን ተሸሎት››
‹‹አረ መሻል ብቻ አይደልም …››ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አይናቸው እጃቸው ላይ አረፈ..ተጨማዶ ና ተሸብሽቦ የነበረ እጃቸው አሁን በለግላጋ  ጣት እና ለስላሳ ቆዳ ተሸፍኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም… ግራ በመገባት እና  ባለማመን በጃኬታቸው ሸፈኑት..መልሰው ገለጡ…
‹‹ቆይ መጣሁ›› ብለው….ትተዋት ወደቤት በፍጥነት መራመድ ጀመሩ…ከኃላ ተከተለቻቸው…ቀጥታ ወደመኝታ ቤታቸው ሄደው የቁምሳጥናቸው መስታወት ፊት ለፊት  ነው የቆሙት….
‹‹የምን ታአምር ነው.…….?.እኔ የት ሄድኩ……….?ማን ነው ይሄ..…….?እኔ ማነኝ…….…….? ››ፊታቸውን እየዳበሱ ለፈለፉ…
መልስ መስጠት ጀመረች‹‹አሁን የ30 ዓመት ወጣት ሆነዋል..ማለት ሆነሀል፡፡…የሚፀፀቱበት ምንም ነገር የለም..ቀጣይ 45 ዓመት ተሰጥቶታል …. ስዚህ ቅድም እንዳሉት ሚዛናዊ ኑሮ ይኑሩበት..ማለቴ ኑርበት…››
‹‹ምን ጉድ ነው….…….?እኔ ወጣት…አንደገና መወለድ እኮ ነው…….?››
‹‹አዎ ነው..ልክ እንደንስር እንደገና የመታደስ ዕድል..››አለቻቸውና ቤታቸው ለቅቄ ወደራሴ ቤት አመራሁ ..ወደ እናቴ ለመሄድ ልዘጋጅ
////
ንጋት ላይ ነው ጉዞ የጀመሩት፡፡የንጋቱን ቀዝቃዛ አየርን  እየማጉ ሰማዩን ሰንጥቀው ቁልቁል የኢትዬጵያን ደቡባዊዉን መልካ ምድር እየቃኙ እየተጓዙ ነው፡፡እስኪ ትንሽ ከላይ ሆነው ቁልቁል ወደታች ሳያዩ ከፊል ኢትዬጵያ ምን እንደምትመስል አብረናቸው እንመልከት፡

ኢትዬጵያ 12 ታሪካዊ ቅርሶችን በዩኒስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡እነዚህም፤ የአክሱም ሀውልቶች፣ የላሊበላ አብያተክርቲያናት፣ የጎንደር ፋሲል ቤተመንግስት፤የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልካዓ ምድር፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣የታችኛው አዋሽና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የመስቀል ደመራ፣ የሲዳማ ፊቼ ጨንበላላ፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርአት ናቸው። ሌሎችም ለማስመዝገብ   ላይ ያለ አሉ  በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በእቅድ ደረጃ የተያዙ ቅርሶችም እንደ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኦመር ዋሻ፣ የጌዲዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መልከዓምድር፣ የመልካ ካንቱሬ የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች ናቸው። በማይጨበጥ ባህላዊ ቅርስነት ደግሞ የአማራና የትግራይ የሻዳይና የአሸንዳ በዓላት የጥምቀት በዓል ይጠቀሳሉ። 
ኢትዬጳያ ግን ለቱሪስት ኢነደስትሪው ግብአት የሚሆኑ ሀብቶቾ እነዚህ ብቻ አይደሉም…ሀገሪቱ እራሱ ሙሉ በሙሉ በዩንሰኮ ቅርስነት ብትመዘገብ አያንስባትም…ግን በዛ መጠን የሚያስብ በዛም መጠን የሚሰሩ ልጆች ወልዳ አለማሳደጎ በጣት የሚቆጠሩትን ብቻ ማስመዝገብ ችላለች፡፡

ይገርማችኋል ይህቺ ሀገር ሙሉ ነች፡፡ሙሉ ስላችሁ ለምሳሌ አየር ፀባዮ  ደጋ ጥቂት ፈቅ ስትሉ ወይና ደጋ ..ብዙም ሳትርቁ ቆላ ታገኛላችሁ፡፡ይሄ ድንቅና መድሎ ያለበት የተፈጥሮ ስጦታ ነው…መልካ ምድሯን ስንመለከት  ለጥ ያለ ሜዳ…ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ..እሱ ሲገርማችሁ ጭው ያለ ገደል…በሌላ ጎኑ እንደጣባ አህያ የተራቆተ መሬት…እንደ ደብረብርሀን የሱፍ በግ ጥቀጥቅ ያለ ጫካ…ኩሬ ሀይቅ ወንዝ….አቤት እነዛ አሜሪካኖቹ ይሄን መልካ ምድር ከዚህ የተመጣጠነ ምግብ ከሆነ አየሯ ጋ ቢያገኙት.. አቤት ይሮፖዎች ያ በቆፈን የሚያኮራምት በረዶ ገላግሎቸው እንዲህ ሚዛኑን የጠበቀ አየር ቢያድላቸው ምን ያህል ተአምራዊ ህይወት ይኖሩ ነበር.. ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ ቀመር አለት መሰለኝ ለእነሱ ሀብት ከቆፈን ጋር ስታድል ለእኛ ምርጥ አየር ከችጋር ጋር.. ያስቃል….እነሱ በቱሪስት ሆነው መልካምድሯን አይተው ለመደሰት እና አይሯን ምገው ሀሴት ለማድረግ ምቾት ባለው አይሮፕላን መጥተው ገንዘባቸውን ከስክሰው ከረምረም ብለው ይመለሳሉ..እኛ በስደት መልክ ከችግር ለመላቀቅ በእግር ተጉዘን በባህር ተጉዘን ሀገራቸው እንገባና ጉልበታችንን አንጠፍጥፈን አንገታችንን ደፍተን ስንባዝን ስንባዝን እንኖርና በዛው የውሀ ሽታ ሆነን እንቀራለን የእነሱ አንድ ነፍስ በእኛ ስንት ነፍስ እንደሚመነዘር ስሌቱ አይታወቅም ..ምን አልባት የብራችን ምንዛሬ ወይም ዋጋ ልዩነትን ያህል የነፍሳችንም ዋጋ ልዩነት ይኖረው ይሆናል…

….ይሄን ሁሉ ይምታስበው.ይሄን ሁሉ የምትመኘው በአየር ላይ ሆና ንስሯ ጀርባ ላይ ተጣብቆ ነው እየተጓዙ ያሉት… 

ያው ሰው በተፈጥሮ በመጨረሻው የህይወቱ ማብቂያ ሰዓት ቁጭት ውስጥ መግባቱ እና ፀፀቱን መናዘዙ ተለመደ አይደል..እሷም ያው በግማሽም ሰው በመሆኗ መጠን ከሰውም ኢትዬጵያዊ ስለሆነች ያው ያ ደግሞ ክርስቶስም ለስጋው አደላ የእንደሚባለው ለእሷም ለዘመዶቿ ተቆጭታ ነው እንጂማ የእሷ የአባቷ ዘመዶች በምድራዊ ዕውቀት የማይመዘን ብቃት እንዳላቸው ታውቃለች፡፡

ለማንኛውም አሁን ደሎ ደርሰዋል…ግን ቀጥታ ወደእናቷ ቤት መሄድ አልፈለገችም ..በመጀመሪያ ያደገችበትን ጫካ ልትሰናበት ፈለገች..መቼስ የደሎመና ጫካ ጫካ ብቻ አይደልም …ውስጡ  የቡና ተክል የተሰገሰገበት ነው..ልጅ ሆነው እንጨት ለቀማ ከእኩዬቾ ጋር ስትሰማራ ከቡናው ተክል ድፍኑን ሸምጥጠውን ይመጡት ነበር..የቡና ተክል ጥሬ ሆኖ ድፍን አረንጓዴ ነው …እየበሰለ ሲሄድ ቢጫ እየሆነ ይመጣል በስተመጨረሻ ሙሉ ብስል  ሆኗል የሚባለው ሙሉ ቀይ ሲሆን ነው..ታዲያ በዛን ጊዜ ፍሬውን ቀፈው ይመጣሉ…ቀዩ የቡና ገለፈት በወስጡ የያዘው ፈሳሽ ልዩ ጣዕም አለው….ሌላው የሚገርማት ይሄ አሁን ከላይ ወደታች የማታየው የደሎ ጫካ ወይም ሀራና ደን የመንግስት ነው…በውስጡ ከደኑ ጋ ተሰባጥሮ ሚገኘው የቡና ተክል ደግሞ የግለሰብ ነው….የኢትዬጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲህ ተዋህደው በስምም ሲጠቀሙ በዚህ ደን ብቻ ነው ያየችው፡፡
👍7011😢2😁1🤔1
ንስሯ ያዶት ወንዝ ውስጥ እንዲጥላት ነገረችው….አምዘግዝጎ ወሰደትና ለመዋኘት በሚመች ቦታ ከስምንት ሜትር ርቀት ላይ ስትደርስ ከተጣበቀበት እራሱን አላቀቀና ወደሰማይ ተመልሶ ተንሳፈፈ..  ተምዘግዝጋ በመውረድ ዳይቭ ገባች……ከእነልብሷ ቦጭረቅ..ደግነቱ ገና ጥዋት ስለነበረ ሰው የለም…እንግዲህ ይሄ የመጨረሻ የምትዋኝበት ቀኗ ነው… ከእናቷ እንደሰማችው አሁን የምትዋኝበት ቦታ እናቷና አባቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙበት ቦታ ነው…….ደጋግመውም ሲገናኙበት የነበረ ቦታ ነበር …እናም አባቷ እናቷን ወደዘመዶቹ ይዞት የሄደው በዚህ አሁን በምትዋኝበት ቦታ ይዞት በመጥለቅ ነው….አዎ ወደአባቷ መኖሪያ ስፍራ የሚወስደው ስውር መንገድ እዚህ አካባቢ ከዚህ ከያዶት ወንዝ ጥልቅ ወለል ላይ ነበር… አሁንም የአባቷ ዘመዶች ዛሬ ማታ ሲመጡ በዚሁ ቦታ  ሾልከው ይሆናል የሚመጡት እናንም ይዘዋት ሚሄዱት.. በዚሁ መንገድ ሊሆን ይችላል….ሰማየሰማያትን ሰንጥቀውም ይዘዋት ሊመጥቁ ይችላሉ….

ዋናዋን ስትጨርስ…በእግሯ ነው ወደቤቷ መጎዝ የጀመረች..ንስሯ መምጣቷን ለማብሰር ቀድሞ እናቷ ጉያ ተሸጉጡ ነው ያገኘችው..እናቷ እቤቱን በቡና አጫጭሳ..ቆንጆ የምትወደውን ገንፎ ቁርስ ሰርታላት ..እርጎ በኩባያ አቅርባላት ነበር የተቀበለቻት፡፡

‹ሀርሜ ደህና ነሽ?››

‹‹ደህና ነኝ ልጄ …›.ብላ አገላብጣ ከሳመችኝ በኃላ የረጠበ ልብሷን እንድትቀይር ሌላ የራሷን ቀሚስ አቀበለቻት…ልብሷን ቀይራ የደረበችላትን ነጭ ጋቢ ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ ገንፎዋን በቀንድ ማንኪያ እየዛቀችና በቅቤ አየለወሰች መዋጥ እና እርጎዋን በላዩ መማግ ጀመረች፡፡
ቡና ተጠጣ…

‹ሀርሜ…›

‹‹ማልታቴ ገረ ኮ››

‹‹ትኝት ብለን እነዋል›

‹‹ቶሌ››አለችና የዘራጋቸውን ሲኒም ከቦታው ሳታነሳ ከበርጩማዋ ላይ በመነሳት በራፉን ቀርቅራ ወደአልጋ ይዛት ሄደች ፣..ብርድልብሱን ገልጣ ገባች..ተከተላት ገባች..ንስሩም ተክትሎቸው ግን ደግሞ እንደእነሱ ብርድልብሱ ውስጥ ሳይገባ ከላይ ሁለቱ መካከል ጉብ ብሎ አደፈጠ…..

እናትዬው ጉያዋ ውስጥ ሸጎጠቻት….እሷም አንገቷ ስር ሰርሰራ ገባችና ከሰውነቷ ተጣበቀችባት….እናቷ እንደበቀደም ለታው አይነት ስሜት ላይ አይደለችም..በቀደም ወደአባቷ እንደምሄትድ ስትነግራት ጠንካራ ነበረች ..እያጀገነቻትም ነበረ….እስኪገርማት ድረስ ቀለል አድርጋ ነበር ያየችው…ምን አልባት በወቅቱ ስለልጇ መሄድ ሳይሆን ስለዕድሜ ልክ ፍቅረኛዋ ነበር እያሰበች  የነበረው…በወቅቱ ልጇን ስታወራት የነበረውን ነገር ሁሉ ለእሱ ካላት ናፍቆት በተሸፈነ ስሜት ነበር ..አሁን ግን ስብር ብላለች..አስተቃቀፎ ሁሉ የማፈን ያህል ነው…ጨምቆ መልሶ ወደሆድ በመክተት የመደበቅ ያህል..አዎ ድብት ብሎታል..ልጇ ከመጣች ጀምሮ በሁለቱም ዓይኖቾ ያቀረረ የእንባ ዘለላ ይታይ ነበር…ከሆነ አስፈሪ ስሜት ጋር እየታገለች ነው….ስለዚህ ጉዳይ ኬድሮን እያሰበች ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት ..ምንም ጭንቀት የሌለበት ምንም  ህልም ያላለመችበት ዝም ያለ  ነበር..የሆነ የሞቀ ፈሳሽ ግንባሯ ላይ ሲንጠባጠብ ነው ከእንቅፏ የባነነችው.. ባለችበት ምንም እንቅስቃሴ ሳታደርግ አይኗን ገለጠችና እናቷ ከአንገቷ ቀና ብላ አይን አይኖቾን ስታይ በእጆቾ ጉንጮቾን ስትዳብስ….. ተመለከተች.. ለካ ግንባሯ ለይ እየተንጠባጠበ ሲያርሳት  የነበረው የእናቷ እንባ ነበር…

‹‹ሀርሜ ምን ሆንሺብኝ?

‹‹ከሄድሽ በኃላ እንድትመለሺ እፈልጋለሁ››

‹‹እንዴ እማ …አንዴ ከወሰዱኝ እኮ ላይመልሱኝ ይችላሉ››

‹‹ግድ የለሽም ..እንድትመለሺልኝ እንደምፈልግ ብቻ ለአባትሽ ንገሪው ፤እሱ አንድ መላ አያጣም…እኔ ያንቺን መመለስ እንደምፈልግ ካወቀ ያደርገዋል..››

‹‹አይ እማ እንደዛ ማድረግ የሚችል አይመስለኝም…››

‹‹አይ ልጄ አባትሽን የት ታውቂዋለሽ…እሱ እኮ ያለዘመዶቹ ፍቃድ ወደዚህ ምድር ሲመላለስ ነበር..እነሱ ሳይፈቅድ እኔን ማፍቀር ችሏል..ወደ ሀገሩ ይዞኝ መሄድ ችሎል..እና በአባትሽ ተማመኚ››
እንዴት አድርጋ ልታስረዳት እንደምትችል ግራ ገባት፡  እሷ በአባቷ ብቃት ሳትተማመን ቀርታ ሳይሆን አሁንም እስር ላይ እንዳለ ስለምታውቅ ነው…ይሄንን ደግሞ ለእናቷ ልትነግራት እና ጭራሽ ቅስሞን ሰብራ ተስፋ ቢስ ልታደርጋት አልፈለገችም..‹‹ግን ምንድነው እነሱጋም አማባገነንነት አለ እንዴ…?እንዴት በእኔ እድሜ ሙሉ ያራሳቸውን አካል አስረው ያኖራሉ….››ምንድነው ከሁለት አንባገነንና በፍቃድ መኖርን ከማያበረታቱ አፋኝ ፍጡሮች ነው እንዴ የተገኘሁት…››በውስጧ አብሰለሰለች፡፡.ወደ እዛ የመሄድ ፍላጎቷ ቀነሰ…

‹ልጄ አንቺ ግን አባትሽን ካየሽና የተወሰነ ጊዜ ከቆየሽ በኃላ ተመልሰሽ መምጣት ትፈልጊያለሽ አይደል፡፡››

‹‹እንዴ ሀርሜ ትጠራጠሪያለሽ እንዴ..እኔ እኮ ጭሩሱኑ መሄድ አልፈልግም››

‹‹እንደዛማ አይሆንም..መሄድሽን ካንቺ በላይ እኔ ነኝ የምፈልገው….ለአባትሽ ሳፈቅረው እንደኖርኩ አንቺ ካልሄድሽ ማን ያስረዳልኛል…አንቺ ሄደሽ አየሽው ማለት እኮ እኔም አየሁት ማለት ነው..ስያቅፍሽ እኔን እዚህ ሆኜ ይሞቀኛል…ሲስምሽም እዚህ ሆኜ እኔን እንደሳመኝ ስለምቆጥረው እንባዬን በደስታ አፈሳለሁ››

‹‹በቃ ሀርሜ ዝም ብለሽ እቀፊኝ ና እንተኛ …››

‹‹እሺ በማለት ትረሱን ዝቅ አደረገችና ከእሷ ተስተካከለችና አቀፈቻት…››

ለሁለተኛ ጊዜ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞት ሄደ 

አይመሽ የለ መሸ ..ሁለት ሰዓት አካባቢ እናቷ ከመኝታዋ አስነሳቻትና ወደ ሻወር ቤት ይዛት ገባች ..ሻወር ቤቱን ከመዝጋቷ በፊት ንስሩ በራፍን የመገንጠል ያህል በረግዶት ገባና የሻወሩ እጄታ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ..እናት በዝምታ በራፍን ዘጋች..ወደሶፊያ ቀረበችና የለበሰችውን የራሷን ቀሚስ አወለቀችላት ፤ፓንቷንም አወለቀችላት፤ መላመላዋን ቀረቸ፡፡ ትንሽ ከእሷ ፈንጠር ብላ አየችትና ጎትታ ወደሻወሩ አስጠጋቻት..ንስሩ ውሀውን ከላይ ለቀቀው ከፀጉሯ ጀምሮ ሠውነቷ ራሠ ..እናቷ ሳሙናውን ከማስቀመጫው
አነሳችና መላ ሠውነቷን በአረፋው አዳረሰችና ትፈትግላት ጀመር...ልክ እንደልጅነቷ...እያገላበጠች ..ከዛ እንደማሰብ አለችና ሳሙናውን ካነሳችበት ቦታ የሆነ ነገር አነሳችና ስሯ ከፊት ለፊቷ ቁጢጥ አለች ..ከዛ ስትጓበኝ እንደመጣችው  የሀገሯ ደን ተንጨፍርሮ ያደገውን የብልቷን ፀጉር ትላጭላት ጀመር..ኬድሮን ከላይ ቁልቁል እናቷን እያየቻት እንባዋ  ይረግፍ ጀመርን ፡፡የጭንቋ ሰዓት ደረሰች… 
ለሊት ለስድስት አስር ጉዳይ …እቤቱን ለቀው ጊቢ ውስጥ ሶስቱም እርስ በርስ ተጣብቀው ተቀምጠዋል..እሷ እናቷና ንስሯ...አብሮነታቸውን ሊጠናቀቅ አስር ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው..እርስ በርሳቸው መነጋገር አልቻሉም…አሷማ ሰውነቷ ሁሉ እየተንቀጠቀጠ ነው….ይሄው ሶስት ቀኑ ወደንስሯ አዕምሮ ዘልቆ ለመግባት እንኳን  ድፍረቱን ማግኘት አልቻለችም..አሁን በዚህች በመጨረሻ ሰዓት ሳይቀር  ልታደርገው  ድፍረቱ የላትም..ምን አይነት ሰቆቃ ላይ እንዳለ..ምን አይነት ሀዘን በውስጡ እንደሚብላላ ለማወቅ የሚያስችል ጭካኔውን ከየት ታምጣው  ....ውይ ደቂቃዎቹ ደግሞ እንዴት ነው የሚበሩት..7 ደቂቃ ቀረው…እናቷ ጉልበቷ ላይ አስደግፋ ጭንቅላቷን ታሻላት ጀመር…5 ደቂቃ ሲቀራው ንስሩ ከስራቸው በተተት ብሎ ተነሳና በቅርብ እርቀት  ካለ ጉቶ መሳይ  እንጨት ላይ አረፈ…ከእናቷ ጉልበት ላይ ቀና አለች….ክንፉን ዘረጋና በመንቁሩ ከክንፉ ስር የሆነ አረንጎዴ ብጣሽ ቅጠል አወጣና በቅፅበት ዋጠው..ገረማት‹‹…ከመቼ ወዲህ ነው ቅጠል በሊታ
👍794👏2
የሆነው…›› ስትል እራሷን ጠየቀች፡ለመሄጃ 3 ደቂቃ ቀረው….ንስሩ ከነበረበት ጉቶ ጥቅልል ብሎ በመንሸራተት  መሬት ላይ ተዘረረ..እናቷም እሷም በደቂቃ ውስጥ ስሩ ደረሱ..አገላበጡት…ከአይኖቹ ደም እየፈሰሰ ነው…‹‹ወይኔ እማ ቅጠሉ….. ቅጠሉ ነው..መርዝ ነው የተጠቀመው..እማ ምን እናድርግ…?››የማሰቢያ ጊዜ ሳያገኙ ግቢያችን በሰማያዊ ብርሀን ተሞላ…ቀና ስትል በሰማይ ላይ ዲስክ መሳይ መንኮራኩር ብርሀን እየረጨች ሰማየ ሰማያትን በመሰንጠቅ እነሱ  ወዳሉበት አቅጣጫ እየወረደች ነው….መጡ ማለት ነው…መጡ መሰለኝ….ወይኔ ንስሬ….

 ተፈፀመ…

ያው አልቋል ብዙ ጥያቄ እንደሚኖራቹ አልጠራጠርም ግን አልቋል ቀጣዩ ድርሰት ደሞ ምንድን ነው ቢያንስ ርእሱን ልንገራቹና YouTube ቻናሉን ከ 100 Subscriber አለፍ ስታደርጉት እንደተለመደው እንጀምረዋለን የቀጣዩ ድርሰት ረዕስ #ትንግርት የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ረጅም ልብ ወለድ መፅሀፍ ነው ስለዚህ ቶሎ እንዲጀመር #YouTube እየገባቹ #Subscribe አድርጉ Link ከታች አለላችሁ አሁኑኑ ከ 100 Subscriber አሳልፉትና እንጀምረው👍

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😱70👎38👍2216👏8🤔4🎉3😢1
🍃በ'ነሱ ቤት🍃
🍄ክፍል ሠላሳ አራት🍄
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
መሳይ ጌታነህን ስታገኘው  በመጀመሪያ የመጣላት ነገር ከበጎ አድራጊ ዎቹ ጋር አገናኝቷት ጉዳይዋን በማሳዘን እንድትነግራቸው መክሯት ዞር የሚል መስሏት ነበር ።ነገር ግን መኪናው ውስጥ አስገብቷት  እርዳታ ሊያደርጉላት የሚፈልጉት ሰዎች ቤተሰቡ መሆናቸውን እና ይህንን ድጋፍ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው በመተማመን ሲያወራ ግራ መጋባት ውስጥ ከተታት ። እናም ልቧ ፈራ ይሄልጅ የእውነት ቁም ነገረኛ ነው ወይስ አይምሮው ንክ ነው ሲያወራ እራሱ  ያልተረጋጋ መሆኑ ያሳብቅበታል ብላ ማሰቧን አላቆመችም ። ከረጅም ጉዞ በዋላ ከዚበፊት በምታውቀው መንደር ውስጥ ታጥፎ ገባ እናም አካባቢው ላይ ያላት ትውስታ አንድ በአንድ መጣባት ።ከአስራ ስምንት አመት በፊት በዚ መንደር ውስጥ ተመላልሳበታለች ። በመጨረሻም ልጇን አርግዛ ስትባረር በዚሁ ድንብርብር እያለች ወጥታበታለች ። በጣም በተጠጋች ቁጥር ያ የአብታሞች መንደር የቀለም ለውጥ ከማድረጋቸው በስተቀር እንዳሉ ናቸው ፣ ልቧ መምታት ጀመረ ፊቷን ወደ ጌታነህ አዙራ ተመለከተችው ። በዝምታ ወደፊት ለፊቱ እያየ ነዳ ትንሽ ሄድ ብሎም አንድ ግዙፍ የተንጣለለ ጊቢ ጋር ሲደርስ አቆመ ።የመሳይ ልብ አብሮ የቆመ መሰለ ።ይህንን ጊቢ ታውቀዋለች ።ጌታነህ ከመኪናው ወርዶ እየከፈተላት እንድትወርድ ጠየቃት መንቀሳቀስ አልቻለችም ።እጇን ያዝ አድርጎ እንድትወርድ ለመናት ፣ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ ።
"እባክህ....."አለች ቃላት እያማጠች
"እባክሽ ውረጂና ከቤተሰቦቼ ጋር ላስተዋውቅሽ እኔ የዛ ባለጌ ወንድም ነኝ የመስፍን ከዚቤት የሚገባሽን እንድታገኚ እስከመጨረሻው ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ አትፍሪ "አላት  መሳይ እንደምንም ከመኪናው በመውረድ ጌታነህ ላይ አፈጠጠች "ባቢ አንተ ነህ እንዲ ትልቅ የሆንከው "አለችው
"አንቺ ታውቂኛለሽ እኔ ግን ምንም ነገር አላስታወስኩሽም ነበር "አላት በመገረም እያያት
"እኔ አልረሳም ትንሽ ልጅ ነበርክ ልታስታውሰኝ አትችልም ግን እንዴት አወቅክ "አለችው ተገርማ
ጌታነህ አብላካትን እንዴት መጀመሪያ ከጓደኞቹጋር እንዳገኛት ፣ከዛ ምን ሲፈጠር እንደነበረ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ፈጠን ፈጠን እያለ ነግሯት በረጅሙ ተነፈሰ ።የአብላካት መጨረሻ ሞት እንዳይሆን ፈርቷል።  መሳይ የሚንቀጠቀጠውን እጇን ማስቆም አቅቷታል ። ጌታነህ ሁኔታዋን ሲያይ ትንሽ ማረጋጋት ያስፈልጋል ብሎ በማሰብ ተመልሰው መኪናውስጥ ገብተው መነጋገር እንደሚችሉ ነግሯት መኪናውስጥ ገቡ እናም ስለቤተሰቦቹ ሁኔታ አወራት አብላካተሸ መታመሟን እና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ስታወራ በቴሌቭዥን ቤተሰቡ ሁሉ እንዳይዋት እና ማንነቷንም እንዳወቁ ከዛ በጣም መደናገጣቸውን ።ከዛ ልጅቷ የራሳቸው ዘር መሆኗን አምነው ለማሳከም እንደፈለጉ አወራት ። መሳይ ያለፈውን አስታውሳ እልህ ያዛት አይሆንም ብላ ጌታነህ ላይ ጮኽች ።
"እንዴት አይሆንም ትያለሽ እኛም እኮ በልጅቷ ላይ መብት አለን ቤተሰባችን ናት ዝም ብለን ስትሞት ልናይ ነው"አላት ተቆጥቶ
"እኛ አትበል አውጥተው ጥለውኛል ከመስፍን አላረገሺም እርሺው ብለው ነው የወረወሩኝ አሁን ምን ተገኘ"ብላ አለቀሰች
"እየነገርኩሽ ነው እንኳን ወላጆቼ መስፍንም ተፀፅቷል ልጁ እንደሆነች አምኗል በወቅቱ የነበረው ነገር አሁን ላይ የለም "አላት ሊያግባባት እየጣረ
"አይ ከነሱ አምሳንቲም አልፈልግም "አለች በደከመ ድምፅ ውስጧ ግን ሲሸነፍ ይታወቃታል
"ላንቺ አይደለም ለአብላካት ነው  መዳን አለባት እኔም ከዚ በዋላ እህት ይኖረኛል  እባክሽ እራስ ወዳድ አትሁኚ "አላት ቀናብላ ስታየው ቆይታ ።አንገቷን በመነቅነቅ ።ውስጧ እያዘነ ተስማማች ። ሌላስ ምን መላ አላት የታመመች ልጅ ይዛ ብትኮራ ምን ሊያዋጣት ። ጌታነህን ተከትላ ወደ ጊቢው ዘለቀች ።ጊቢው ውስጥ እንደገቡ መናፈሻ በመሰለው ስፍራ ላይ ክብ ጠረቤዛ ከበው ተቀምጠው የነበሩት የጌታነህ ወላጆች ቆም ብለው ጠበቋቸው ። ሲቀርቧቸው የጌታነህ እናት የነበረባትን ትምክህት ጣል አድርጋ  ይቅር በይኝ በማለት የመሳይ እግር ላይ ተደፋች መሳይ ያልጠበቀችው ነገር ስለነበር ድንብርብሯ ጠፋ ደጅ ላይ የፎከረችው ነገር ጥሏት ጠፋ የጌታነህን እናት ከመሬት ላይ በማንሳት ፣አቅፋት አለቀሰች ። ጌታነህ ሁኔታው አስለቀሰው ። መሳይን ወላጆቹ ደጋግመው ይቅርታ እየጠየቁ ሲያይ ወላጆቹን እንዲ ተቀይረው በማየቱ ጉድ አለ ። ለማንም ግድ የሌላቸው የሱ ኩሩ ወላጆች ተንበረከኩ ።ይሄ መቼስ ስለ አብላካት ነው ሌላ አይደለም 'ይሄ ቆሞ የቀረ ልጃቸው የልጅ አባት ሊሆን ነው'ብሎ በውስጡ ሳቀ ። ብቻ በፍጥነት ሄዳ ትታከም ......
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨?፨?፨??
አብላካት እናቷ የሄደችበት ጉዳይ ተሳክቶ ሁሉም ነገር ሰላም እንዲሆን በልቧ ደጋግማ ፀለየች ። እናቷን እዚ ምድር ላይ ብቻዋን ጥሎ መሄድ በጣም ያማል ያ እንዲሆን ፈጣሪዋ እንደማይፈቅድ ለራሷ እየተናገረች ትፅናናለች ። ሰሚር ስልኩን እየነካካ አልፎ አልፎ ትክዝ ብላ የተቀመጠችውን አብላካትን ያያል ። ከቆይታ በዋላ ስልኩ ተደወለ አንስቶ ሲያየው ሰመረ ነው ተነስቶ ሊወጣ ፈልጎ ነበር መልሶ ተወው እና አነሳው
"ሃሉ "
"ሰሚር የት ነው ያለኽው እባክህ ልምጣ ሚጣ ጋር ውሰደኝ "አለው ቅስሙ ስብር ብሎ
"እኔ አሁን እሷው ጋር ነኝ እናቷ ስለወጣች አብሬያት ልቆይ ብዬ ነው"
"እሺ አቅጣጫውን ንገረኝ እመጣለው "አለው ሰሚር የሰመረ ሁኔታ አሳዘነው እሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለአብላካት ጥሩ ነበር ታዲያ ለምን አብሯት እንዳይሆን ይከላከላል ?በጭራሽ!   ።አቅጣጫውን ነገረው ሰመረ እሺ ብሎ ስልኩን ዘጋው ።
"እሺ ለማን ነው ደሞ ቤቴን የምትነግረው ኪኪኪ ስንት ሺብር ይዘን መጣን አሉክ ?"አለችው አብላካት እግሯን እያሻሸች
"ሲመጡ ታያለሽ ምን አስቸኮለሽ "
"ስንት ናቸው"
"አንድ ነው ስታይው የምትወጂው ይመስለኛል"ብሎ ሳቀ
"ማነው "አለች ኮስተር ብላ
"ሲመጣ ማንነቱን እራሱ ያስተዋውቀናል"
"ደረቅ "ብላ ለመነሳት ስትል ወጋት በከባዱ አቃሰተች አስተናጋጁ ሰሚር በድንጋጤ ሄዶ አቀፋት እጆቹ ላይ ልፍስፍስ ስትልበት "አቢ አቢ ደና አይደለሽም አቢ..........."እያለ ተጣራ ,,,,,,,,,,,,

,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍504👏1
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
👁ክፍል ሠላሳ አምስት👁
🌻🌻🌻🌻
አስተናጋጁ ሰሚር አብላካትን ታቅፎ ይዟት ከቤት ወጣ
በፍርሃት ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ አካባቢውን ወዲወዲያ አየ ። የነአብላካት ጎረቤቶች ያለወትሮ ቤታቸው ተከተዋል  አይኖቹን አሻግሮ ሲያይ የሰፈር ጎረምሶች ተቀምጠው ሲጫወቱ አየ እናም ጮክ ብሎ
"እባካቹ እርዱኝ እባካቹ "አለ  ጎረምሶቹ ተሯሯጡ
"ምንድነው፣ ምን ሆነች ?አብላካት ነች ?ምን ተፈጥሮ ነው ?ኧረ በደንብ ያዛት !"  የተለያየ ጥያቄ እያከታተሉ በአስተናጋጁ ሰሚር ዙሪያ ተሰባሰቡ ።
"እባካቹ ልትሞትብኝ ነው ! ድንገት እራሷን ሳተች አኪም ቤት መድረስ አለባት መኪና ጥሩ ልኝ ፍጠኑ እባካቹ "እያለ ወደፊት ተሸክሟት እንደመሮጥ አለ
"እሺ እሺ  ዳንኤል እቤት ካለ መኪና እንዲያመጣ እንንገረው  "አለ አንደኛው ወደ ጎረቤት ቤት እየሮጠ
"እባካቹ ቶሎ በሉ !?አቢዬ ጠንከር በይ አይዞሽ ተንፍሺ ...." እያለ ሰሚር ፈጠን ለማለት ሞከረ 
እንዲ ሲዋከብ የሰፈር ጎረምሶችም ፣በድንጋጤ እርዳታ ፍለጋ ወዲወዲያ እያሉ  ሲከተሉት ከርቀት አንድ መኪና በነሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት ሦስት ጎረምሶች አስገድደው ሊያሰቆሞቱ ወደሱ ተሯሯጡ እናም አስቆሙት ትንሽ እንደማንገራገር ሲል አስተናጋጁ ሰሚር እጁላይ አብላካትን ታቅፎ ሲመጣ የሰፈር ሰው አጅቦት ሲለቃቀስ አየ ።ከመኪናው በፍጥነት ወጣ ። አስተናጋጁ ሰሚር ሲያየው እንባ ተናነቀው "ሰሚር ምን ተፈጠረ ደና ነች ና ና ልቀበልህ" ብሎ ተጠጋው
"ሰመረ ፍጠን እንኳን መጣህልን ቶሎ አኪም ጋር መድረስ አለባት ትንፋሿ እየተቆራረጠነው "አለ ሰመረ ከእጁ ተቀበለውና የመኪናው የዋላ ወንበር ላይ በጥንቃቄ አስተኛት አስተናጋጁ ሰሚር ገብቶ እግሩላይ ጭንቅላቷን አስደገፋት ። ሰመረ በፍጥነት ገብቶ መኪናውን አስፈነጠራት በጣም ደንግጧል አልቦታል ደጋግሞ ለፈጣሪው ይፀልያል .....
"ምን ተፈጥሮ ነው ስደውል ደናነች ብለኽኝ ነበር"
"አዎ ድንገት ነው ለመነሳት ስትሞክር አቃስታ የወደቀችብኝ "አለ አስተናጋጁ ሰሚር
"ምግብ አልበላችም ?"
"ያን ያክል አልወሰደችም " አለ አስተናጋጁ ሰሚር ።
ሰመረ የልብ ምቱ አስፈራው አብላካት በዚ ዕድሜዋ ያሳለፈችው ፈተና አስጨነቀው የዛሬን ደና ከሆነች ሊጠብቃት ቃል ገባ ብቻ ምንም አትሁን እንጂ የሚከፈለውን መስዋት ከፍዬ አሳክማታለው  ወላጆቼንም ቢሆን አስቸግሬ በነሱ ዙሪያ ያሉትንም ሰዎች አሰባስቤም ቢሆን ፈጣሪ እባክህ እንድትሞት አታድርግ ,,,,,,,,,,,,,


,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍9921🎉2👏1😁1
👁በ'ነሱ ቤት👁
🍄ክፍል🍄🍄
ሠላሳ ሥድስት
🌻🍃🌻🍃🌻🍃
በነ ጌታነህ ቤት ሰላም የወረደ ይመስላል ፣ ቤተሰቡ ከእንግዳዋ መሳይ ጋር የተረጋጋ ወሬ ይዘዋል ፣ በመሃል በመሃል መሳይ ላይ ቅሬታ ቢታይም ። ግንኙነታቸውን ጤናማ ለማድረግ የበኩላቸውን እየጣሩ ነው የሚገኙት ። ጌታነህ በመሃል ሆኖ ሁለቱንም ወገን ለማስማማት መልካም አሳብ ሲያጋራ ነው የቆየው  በዚ ደሞ ውጤታማ ሆኗል ። በተለይ መስፍን እና መሳይ ሲተያዩ ሊፈጠር የነበረውን የሰላም መደፍረስ እንዲቀር አድርጓል ።  በዚም እናቱ ኮርታበታለች ። ያለውን ቁርሾ ሁሉ ትተው የታዳጊዋን ሕይወት ማትረፉላይ ማተኮር እንዳለባቸው ተመካከሩ እናም ።መሳይ ሁሉን ትታ ስለልጇ ተሸንፋ ተስማማች ፣ ለመጀመሪያ ጊዜም ለልጇ መመኪያ የሚሆናት ግዙፍ ቤተሰብ እንዳላት አስባ ስለልጇ ተፅናናች ። በመጨረሻም ወደቤቷ ለመሄድ ተነሳች ፣ መስፍን ፈጠን ብሎ ሊሸኛት ተነሳ እሷ አያስፈልግም አለች ፣አስራ ስምንት አመታቶችን በሱ ምክንያት አፈር በልታለች ምን እንደሰራት በአጭር ጊዜ ለዛውም በሰአታት ምንም እንዳልተፈጠረ መርሳት አልችል አለች ። ጌታነህ ነገሩ ስለገባው ፣ጠጋብሎ 'መስፍን ተረጋጋ እንዲ በፍጥነት አይሆንም ። ጌዜ ያስፈልጋታል ባንተ የተነሳ ምን እንዳሳለፈች አታውቅም 'አለውና እኔ እሸኛታለው ፣ አብላካትንም በዛው አያታለው ከዶክተሯ ጋርም ስላለው ነገር እነጋገራለው ። እናም በአፋጣኝ ወደውጪ ሄዳ እንድትታከም እናደርጋለን እናንተም ተዘጋጁ አላቸው። የጌታነህ ወላጆች በአንድ ቃል ሁሉንም ነገር ተዘጋጅተናል ጊዜ የለም ልጃችን በሕይወት እንድትቆይ ማድረግ ያለብንን ሁሉ እናደርጋለን ። መስፍን በመሃል ጣልቃ ገብቶ 'እኔ ኩላሊት ልሰጣት ዝግጁ ነኝ እንኳን አንዱን ሁለቱንም ሰጥቻት ብሞት አይቆጨኝም ፣ ልጄን እንደገደልኩ የማነሳትም እኔነኝ እላለው እባካቹ ይህን ማድረግ አትከልክሉኝ 'ብሎ ለመነ ሁሉም በዝምታ አለፉት ። መሳይ ያ ኩሩና ትህቢተኛው የሀብታም ልጅ መስፍን አልመስል አላት ።ወይ ጊዜ ስንት ነገር ይቀይራል ብላ ተገረመች ። በዚ መሃል ስልኳ ጮኾ አነሳችው በፍርሃት ፣ስልኩ ላይ ሰሚር አብላካት ሆስፒታል መግባቷን ሲነግራት ስልኩን በቁሟ ለቀቀችው ሁሉም ደነገጡ ። ጌታነህ በፍርሃት የወደቀውን ስልክ ሲያነሳው የሰሚር ድምፅ መጣ "ሃሉ ምንድነው "አለው ጌታነህ
"ሃሉ ኧረ ደና ነች እኮ አሁን"አለው
"ሰሚር ነህ ምን ተፈጠረ"
"አይ ድንገት እራሷን ስታብኝ አኪም ቤት ወስደናት ነበር እክምና ተደርጎላት አሁን ደና ነች"
"ጥሩ መጣን በቃ"አለው
"እሺ አብሮኝ ሰመረ አለ ጓደኛህ "አለ ሰሚር ድንገት ሲገናኙ ቅሬታ እንዳይፈጥር በማሰብ
"ምን ከየት አወቀ የት አገኘህ ለሱ ደውለህ ነው እንዴ "አለው ግራ በመጋባት
"አይ ልክ እንደ እናንተ ሳገኘው ስለሷ ነግሬው ነበር ባጋጣሚ ሊረዳት ሲመጣ ታማ አገኛት እና አብረን ነው አኪም ቤት ይዘናት የሄድነው ።እሱ መኪና ይዞ ባይመጣ ነገሩ ሌላ ነበር "አለው እንዳይቆጣው እየፈራ
"አንተ ግን እሱ ጋር ማስቸገር አልነበረብህም እኔ እንደምጨርሰው ነግሬህ ነበር ።እሺ ይሁን መጣን"አለውና ስልኩን ዘጋው ።አፋቸውን ከፍተው ሲሰሙት የነበሩት ቤተሰቦቹ ሰላም መሆኑን ሲነግራቸው እፎይ አሉ ከዛም አንድላይ ለመሄድ ተነሱ ።,,,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍12521👏1
👁በ'ነሱ ቤት👁
🍃🍄ክፍል ሠባት🍄🍃
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ሆስፒታል ሲደርሱ አስተናጋጁ ሰሚር ነበር የተቀበላቸው ፣እናም በፍጥነት ያለችበትን ክፍል ጠየቁት እሱም አብላካት የተኛችበትን ክፍል ካሳያቸው በዋላ እውስጥ ሰው ስላለ ትንሽ መጠበቅ እንዳለባቸው ሊያስረዳቸው ሞከረ ።
ጌታነህ ማነው ሰው ብሎ ቆጣ አለበት ፣ሰሚር ሲፈራ ሲቸር  ነገረው "አይ ሰመረ ነው ማለት..."
"ሰመረ "አለው እና ዝም አለ ። የአብላካት እናት መሳይ "ማነው ሰመረ ?"ብላ ጠየቀች
"ከዚ በፊት እኮ ስለሱ ነግራሽ ታውቃለች ያ መንገድ ላይ አግኝቷት የረዳት ኧረ እንደውም እኮ የጌታነህም ጓደኛ ነው "አለ አስተናጋጁ ሰሚር ጭንቅ እያለው ።የጌታነህ ቤተሰቦች እርስ በእርስ ተያይተው ።"ሰመረ የኛ እንዴ እሱም ያውቃል "አሉ ። አስተናጋጁ ሰሚር አንገቱን ነቅንቆ አዎ የሚል ምልክት አሳያቸው።
"እና መግባት አንችልም ነው እሱ ካልወጣ "በማለት ጌታነህ እየተመናቀረ ሄዶ አብላካት የተኛችበትን ክፍል አንኳኳ!
ከውስጥ ሰመረ የአብላካትን እጅ በእጁ አቆላልፎ አይኖቹ ዕንባ እንዳዘሉ በቀስታ የምታወራውን ያዳምጣል ፣አብላካት ለራሷ የመጨረሻዬ ነው ብላ ስላሰበች ለሰመረ የሚሰማትን ስሜት ሳትደብቅ ነበር እየነገረችው ያለችው ፣ሰመረ አንዳች ነገር ሳይናገር እጇን እያሻሸ ግንባሯን እየነካካ ያዳምጣታል እናም ደሞ ዕንባው አምልጦት ከፊቷ አልቅሶ ደክሞ እንዳያደክማት እየተጠነቀቀ ነው ።ግን አልችል ብሏል የአብላካት ለሱ ያላት ስሜት ትልቅ መሆኑን ሲያውቅ ልቡ መረበሹን አበዛበት እናም ጎንበስ ብሎ ግንባሯን ሳም ካደረጋት በዋላ"ሚጣ ተይ እሺ እንዳበቃለት ሰው አታውሪ ምንም አትሆኚም "አላት
"ግንኮ ዛሬ አብቅቶልኝ ነበር ነገም ምን ሊፈጠር እንደሚችል አላውቅም ፣ለዚነው እንዲ በፍጥነት ላንተ ያለኝን ስሜት የምነግርህ ፣ጤነኛ ብሆን ኖሮ መቼም የምነግርህ ነገር አልነበረም ፣እንዲሁ ፍቅሬን ይዤው ነበር የምኖረው ፣ አሁንግን ሁሉንም ይዤው ከምሞት ብነግርህ ይሻላል ፣በርግጥ ዛሬ አንተ ባትመጣ አልናገረውም ነበር ግን መጣህ እድሜ ለሰሚር ፣እሱን በጣም ነው የማመሰግነው እኔ አይሆንም ያልኩትን ነገር ሁሉ ቢያደርግም ፣ግን ውጤቱ ክፋት የለውም ፣አንተን በመጥራቱ ሁሉም ነገር ቀሎኛል "አለችው እና ተነፈሰች
"የኔ ሚጢጢ"አላት
"አብላካት ነው ስሜ "ብላ ፈገግ አለች
ጠጋ ብሎ ጉንጯን ሳም አድርጓት ሲመለስ በሩ ተንኳኩቶ ምላሽ ሳይጠብቅ ተከፈተ ። እናም ጌታነህ ገብቶ ሲያፈጥ ሁለቱም እርስ በእርስ ተያዩ ፣አብላካት ተገረመች እና ደሞ የሰሚር ስራ ነው ሁሉንም ሰበሰበ እሺ ይሁን እኔን ለማዳን ካለው ጉጉት የተነሳ ነው ደሞም እናቴ ልታገኘው ሄዳ አልነበር እንግዲ መፍትሄ አገኘው ብሎ ሊያደርቀኝ ይሆናል ።ብላ አሰበች ጌታነህ እራሱን ተቆጣጥሮ ሰመረን ሰላም ካለው በዋላ እሷን ጎንበስ ብሎ አይን አይኗን ሲያይ ቆይቶ
"አይዞሽ ሁሉም ነገር በቅርቡ ያበቃል ደና ትሆኛለሽ እሺ እርዳታ ሊያደርጉልሽ ፍቃደኛ የሆኑት ቤተሰቦቼም አብረውኝ እዚ መጥተዋል አንቺ ብቻ በርቺ እሺ"አላት እና ፀጉሯን ደባበሳት ፣አንገቷን ነቀነቀች በመስማማት ሰመረ በመገረም ሲያየው  ግድ ሳይሰጠው ።
"እባክህ ቤተሰቦቼ እና የአብላካት እናት ቆመዋል አስገባቸው "አለው
"ከልብህ ነው እነሱ ሊረዷት ይፈልጋሉ ሙሉ ወጪ ችለው "አለው
"እሱን በደንብ እናወራበታለን ከነምክንያቱ አሁን ተጨንቀዋል አስገባቸው "አለው ።ግራ የተጋባው ሰመረ ወጣ ብሎ እነሱን አሰገባቸው ለሰላምታ እንኳ ጊዜ ሳይሰጡት ተቻኩለው ወደውስጥ ገቡ ፣እናት ስፍስፍ ብላ ከአልጋው አጠገብ በርከክ ብላ አብላካት ላይ ተደፋች ፣መስፍን ለመጀመሪያጊዜ የካዳት ልጁን ሲያያት ልቡ በፀፀት ዘለለበት የጌታነህ ወላጆች በቁንጅናዋ ለየት ያለችው የልጅልጃቸው አንሰፈሰፈቻቸው ።
አብላካት ግራ እንደገባት ነው ሁሉንም በተራ ተራ እያየቻቸው ነበር ፣በተለይ በሩን ተደግፎ ዕንባውን ኮለል እያደረገ የሚያወርደውን ጎልማሳ አይታ አይኗን መንቀል አቃታት,,,,,,,



ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍13519😱8
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
👁ክፍል ሠላሳ ሥምንት👁
🍃🌻🍃🌻🍃🌻
አብላካት የሁሉንም መንሰፍሰፍ ስታይ ሆድ ቢብሳትም ስሜቷን ዋጥ አድርጋ እናቷን ወደሷ እንድትጠጋ አድርጋ በጆሮዋ "እማ ለምንድነው እንዲ ማለቴ የዚህን ያክል ለኔ የሚሆኑት ፣ስለ እርዳታው ሳይሆን እያለቀሱ እኮ ነው ?"አለቻት
"የኔ አበባ አትጨነቂ እነሱ ያው አሳዝነሻቸው ነው የሚሆነው በዛላይ ያው የጌታነህ ቤተሰቦች ናቸው ።እሱን ደሞ ታውቂዋለሽ አይደለ "ብላት ሌላ ነገር ላለመናገር እራቅ አለች ። መስፍን አላስችልህ ብሎታል ።ሄደህ እቀፋት አፅናናት የሚል ስሜት እየገፋፋው ነው ።  የጌታነህ እናት ጠጋ ብላ እጇን በአብላካት እራስ ላይ ጣል አድርጋ እያሻሸቻት፣
"አይዞሽ የኔ ውድ የፈጀው ይፍጅ እንጂ ከነገ ጀምሮ ዝግጅትሽ ይካሄዳል ፣ እሺ "አለቻት አብላካት ሁሉም ነገር ግር ቢላትም እሺ ብላ ዝም አለች ፣ ቀጥሎ መስፍን ጠጋብሎ እጇን በስስት ይዞ ሲነካካት ፣አይኗን ከሱ ላይ መንቀል አቃታት ፣በዚጊዜ የአብላካት እናት ሳግ ስለተናነቃት ቶሎ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች ፣ ጌታነህም አብሯት ወጣ ፣ከደጅ ሰመረ እና አስተናጋጁ ሰሚር ተቀምጠው ሲጠብቁ አገኟቸው ። ሰመረ እነሱ ሲወጡ ቀረብ ብሎ ችግር እንዳለ ጠየቀ ።"ምንም ችግር የለም ሁሉም ይፈታል እናመሰግናለን "አለው ጌታነህ
"ቀይ ቀይ ቀይ እንዴት እንዴት ነው የምታናግረኝ ደርሰህ ቤተሰብ ልሁን አልክ እኮ "አለው ሰመረ
"ስማ ካንተጋር የምጨቃጨቅበት ጊዜየለኝም ከአኪሟ ጋር መነጋገር እና በአሰቸኳይ ፕሮሰሷን ማስጀመር አለብኝ "ብሎ ጥሎት ሄደ
"በጣም ጎረርክ ጉዳዩን ቀድሜ ብሰማ ይሄን ማድረግ የማልችል ይመስልሃል ?!"አለው ጌታነህ ዝም ብሎት ሄደ ።ወደ አስተናጋጁ ሰሚር ዞሮ
ሰሚር አንተ ነህ ቀድመህ ብትነግረኝ ኖሮ የዚ ጉረኛ እጅ ላይ አትወድቅም ነበር "አለዎ
"ኧረ እኔ የሷን መዳን ነው የምፈልገው "ብሎ አቀረቀረ
"ቢሆንም እሱ ከሷ ምን እንደሚፈልግ እያወቅክ "ሲል የአብላካት እናት ስትሰማ ቆይታ "እባክህ ጌታነህ ከሷ ምንም አይፈልግም ሊሆንም አይችልም"አለችው
"አይ አንቺ ስለማታውቂ ነው "አለ ሳያስበው ቆጣ ብሎ
"ምንም ማወቅ አያስፈልገኝም አይሆንም አልኩ ህ እኮ"አለችው እሷም ኮስተር ብላ
"እንዴት እንዲ ትያለሽ ያብላካት እናት "አለ
"ምክንያቱም እሱ አጎቷ ነው ፣መስፍን ደሞ አባቷ ነው እነዛ እውስጥ ያሉት አያቶቿ ናቸው "አለችው በጩኽት። ሰመረ እና አስተናጋጁ ሰሚር ጆሮ አቸውን ተጠራጥረው እኩል አፍጥጠው እያይዋት
"ምን!!!?"ብለው ጠየቋት ።ደገመችላቸው ሰመረ የዞረበት መሰለው ሄዶ ወንበር ላይ ተቀመጠ
ከራሱ ጋር ማውራት ጀመረ"ጌታነህ የአብላካት አጎት መስፍን የአብላካት አባት በየት በኩል ነው እንዴ ከየት ወደየት ነው  "ጨንቅላቱን በሁለት እጆቹ ማሻሽት ጀመረ ደጋግሞ ሆሆሆሆ ይላል ,,,,,,አስተናጋጁ ሰሚር ከአብላካት እናት ጋር ስለሆነው ነገር ይነጋገራል በጣም ተገርሟል የሕይወት አዙሪት ከየት ወደየት ቤተሰቡን አዙራ አምጥታ እንዳገናኘች ተገርሟል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨

ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍1115
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
ክፍል ሠላሳ ዘጠኝ
👁👁👁👁👁
አብላካት ወደ ውጭ ወጥታ በፍጥነት እንድትታከም በስተመጨረሻ ያገኘቻቸው የጣሏት ቤተሰቦቿ ገንዘብ ስራውን ሰራ ። ገንዘብ ካለህ በሰማይ መንገድ አለ እንደሚባለው ፣ አብላካትን ግራ ያጋባትና ሚስጢር ያደረጉባት ነገር ቢኖር የመስፍን ጉዳይ ነው ፣ መስፍን ተመርምሮ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ንፁ መሆኑን ካረጋገጠ በዋላ ለልጁ ኩላሊቱን ሊለግሳት በተስማማ ጊዜ ፣ የሱ ቤተሰቦች ለነገሩ አዲስ ሆነው ባይከራከሩትም ፣አብላካት ግን እንዴት 'ማንነቴን ጠንቅቆ የማያውቀኝ ሰው በዚመጠን ሊረዳኝ ፈለገ 'ብላ እናቷን በጥያቄ አፈጠጠች ፣ የአብላካት እናት ግን ምክንያቱን ወደፊት ልትነግራት እንደምትችል እና ለጊዜው ግን በጎ አድራጎቱን አመስግና እንድትቀበል አግባባቻት ፣
የመስፍን ኩላሊት እናም የጤና ጉዳይ መልካም ካልሆነ ፣ሰመረ በድፍረት እሱ ለአበበ ላካት ኩላሊቱን ሊያጋራ ቃል ገብቶ ነበር ። መሳይ የሰመረን ሁኔታ ስታይ ለልጇ ያለውን አመለካከት ወዳዋለች ፣ ልጇ አሁንም ድረስ ለሷ ዕፃን ብትሆንም ፣ የሰመረን አላፊነት የሚሰማው  ሰውነት ግን ስላየች ተማምናበታለች ። ጌታነህ ደሞ አሁን ላይ ከሰመረ ጋር የነበረው ፉክክር ቀርቶ ፣ አላፊነት እንደሚሰማው አጎት ፣ ሰመረ ሌላ ነገር በአብላካት ላይ እንዳይከጅል እየተከላከለ ይመስላል ።
በመጨረሻ አብላካት ከጌታነህ እና ከመስፍን ጋር እንድትሄድ በመወሰኑ ፣ ሁኔታው ባይመቻትም ድና ለእናቷ ልጅ ለመሆን ስለጓጓች ፍቃደኛ ሆነች ፣በሽኝቷ ጊዜ እናቷ አልቅሳ መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማት እንደምትፀልይላት ነግራ አቅፋ ተሰናበተቻት ፣አስተናጋጁ ሰሚርም ፣የጌታነህ ቤተሰቦችም ፣በፈረንሳይ ቅር አቅፈው ተሰናበቷት ። ሁሉንም ከተሰናበተች በዋላ ፣በአይኖቿ ሰመረን ፈለገችው ፣ጥግ ላይ ቆሟል ዝምብላ ስታየው ፣ሰውነቱ ቅጥቅጥ እያለበት እንደምንም ቀረባት ፣
"ምንድነው ጌታው መጥቼ ልሰናበተዎት እንዴ"አለችው በቀልድ ። ጌታነህ ሲገላምጠው ቢያይም ፣እጁን የአብላካት አገጭ ላይ አሳርፎ የግዱን ፈገግ እያለ" የኔ ሚጢጢ አንቺ ጠንካራ ራ ልጅ ነሽ በሙሉ ጤንነት እንደምትመለሺ አምናለው ፣"አላት
"በመጀመሪያ ደረጃ ሚጢጢህን ሄደ ፈልግ እሺ ! ስሜን ላስታውስህ እንዴ ?"
"ሚጣ አይደለውም !አብላካት ነው ስሜ ! ልትይኝ ነው አይደል አቢዬ  ይታወሳል ቂያለሽ ይሄን ድምፅሽን ሁሌም እናፍቀዋለው !ደና ሁኚልኝ እሺ !"አላት አይኖቹ እንባ እያቆረዘዙ ። አብ ላካት የማትቆጣጠረውስሜት ገፍቶ ሰመረን እንድታቅፈው አደረጋት እሱም አላስቻለውም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፋት ሁሉም ተያይተው ዝም አሉ ፣ ጌታነህ ግን ብዙም አልተደሰተም ፣ ምክንያቱም ጌታነህ የጓደኝነታቸው ጊዜ ላይ በሴቶች ላይ ያላቸውን አመለካከት ስለሚያውቅ በዛ ስሜት የወንድሙ ልጅ እንድትታሰብበት በጭራሽ አይፈልግም ፣እራሱም ታማኝ ስላልነበረ ማንንም አያምንም ። ሁለቱንም ቆጣ እንዳለ ካላቀቃቸው በዋላ ሰመረን የማስጠንቀቅ አይነት እይታ አይቶት አብላካትን ይዟት ሄደ,,,,,,,,,,,,,
👁👁👁👁👁👁👁👁👁👁👁👁
የአብላካት እናት በየቀኑ ስልክ እየተደዋወለች ፣ስላለው ነገር ከጌታነህ ኢንፎርሜሽን ታገኛለች የልጇ ሁኔታ በፍፁም ጤንነት ላይ እንዳለ በማወቋ ደስተኛ ነች ። አልፎ አልፎም እነ ጌታነህ ቤት ሄዳ ተጫውታ ትመለሳለች ፣  ቅዳሜ ቀን ነው የመጨረሻ እክምናዋ የሚደረግበት ፣ተብላ ለሊቱን ሙሉ ስትቃዥ ነበር ያደረች ፣ ሲነጋጋ እንደተጨነቀች ስልክ እየጠበቀች ቆየች ፣ ሰአት በሄደ ቁጥር ልቧ መምታቱን መጨነቁን ከፍ አደረገች ፣ጌታነህ አልደወለም ፣ ተነስታ ቤተ ክርስቲያን ሄደች ፣ፀሎቷን በእንባ ታጅባ አደረገች ፣ከቤተክርስትያን ተመልሳ ወደቤቷ አቅጣጫ ለመሄድ መንገድ ጀምራ ተወችውና ወደነ ጌታነህ ቤት ገሰገሰች ፣እነሱጋር ስትደርስ እነሱም ተጨንቀው አገኘቻቸው ፣ ለረጅም ሰአት ተፋጠው ቆዩ ፣ ጌታነህ አልደወለም ፣የአብላካት እናት ለቅሶ ጀመረች ፣ የጌታነህ እናትም አገዘቻት ሁለቱም ሲለቃቀሱ ፣የጌትነህ አባት መገሰፅ ጀመረ ፣አታሟርቱባት ብሎም ተቆጣ ፣ "እስካሁን መደወል ነበረበት"ብላ ባሰባት ።የጌታነህ እናት"ኧረ እኔ ፈራው  "አለች በመሃል ስልክ ጮኽ ሦስቱም በፍርሃት ተያዩ ፣የሚጮኽው የመሳይ ስልክ ነበር እየተንቀጠቀጠች ስልኳን አነሳችው ,,,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍12214👏3😁3👎1
በ'ነሱ ቤት
👁ክፍል አርባ👁
🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄
ሰመረ እንቅልፍ ከራቀው ቆየ ፣አብላካት ለእክምና ከአገር ከወጣች ጀምሮ አይምሮው እረፍት አጥቷል ፣ቀልቡ ከሷው ጋር ነበር አብሮ የሄደው ፣ ቤተሰቦቹ እስኪታዘቡት ድረስ ፈዟል ፣ስራ ቦታው ላይም ብዙም መቀመጥ አልቻለም ፣  አብላካት አንድ ነገር ብትሆንስ ፣ እክምናው እንደታሰበው ባይሳካስ ፣ ብሎ ፈርቷል ፣ እራሱንም መውቀሱን አልተወም ፣ 'ምነው አብሬያቸው በሄድኩኝ ኖሮ ፣ 'በሚል ቁጭት ።
የአብላካት እናት ጋር መሄድ እና ከጎኗ መሆን ፈልጎ ነበር። ነገር ግን ፈራ እናት ናትና ፣አብላካት ለሷ ዕፃን ልጇ ነች ፣ ልጇን ላታልልባት አጉል ላደርግባት የመጣው አይነት ወንድ አድርጋ ብታስበኝስ ' በሚል ።
  ዛሬን ግን ማደር የሚችል መስሎ አልታየውም በጣም ከመጨነቁ የተነሳ ወደ አስተናጋጁ ሰሚር ደወለ ........
"ሄሎ "አለው በፍጥነት
"ሰሚር እንዴት ነህ "አለው ሰመረ ልቡ እየመታበት
"ደና ነኝ ሰመረ ፣ ምነው ድምፅህ ልክ አይደለም ጌታነህ ደወለልህ እንዴ ?አቢ እንዴት ናት?"አለው አከታትሎ
"ኧረ እኔጋር አልደወለም ፣አንተን ልጠይቅህ እኮ ነበር ፣ምን አልባት ወይዘሮ መሳይ ጋር ከተደወለ ብዬ እኮ ነው!"አለው ቅር እያለው
"ኧረ እሷ ጋር አልተደወለም ።ቅድም ደውዬላት ነበር ፣ግን አልደወለም በጣም ጨንቆኝ እነጌታነህ ቤት ኤጃለው አለችኝ ፣እዛም አልተደወለም ፣አሁንም ድረስ እዛው ናት ፣"አለና በረጅሙ ተነፈሰ። ሰመረ ጭንቅላቱን መታ መታ አደረገ እና "እኔ ነኝ ጥፋተኛው አብሬያት መሄድ ነበረብኝ "አለ
"አይዞህ ሰመረ ምንም አትሆንም ጠንካራናት "አለው አስተናጋጁ ሰሚር በማፅናናት ።ነገር ግን እሱም ፈርቶ ነበር ፣ ........
"እሺ እባክህ በማንኛውም ሰአት የሰማኽው ነገር ካለ ደውልልኝ "አለው
"እደውላለው እሺ"ብሎት ተሰናብቶት ስልኩን ዘጋው
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአብላካት እናት በፍርሃት እንደተዋጠች ስልኳን አነሳችው መስመር ላይ የሚቆራረጥ ድምፅ ይሰማታል የጌታነህ ነበር ተጨነቀች "ም ምን እያልከከኝ ነው አ  አ ይሰማኝም "ተንተባተበች
"አቢ እ....ሷ...."ድምፁ ይቆራረጣል ። የአብላካት እናት የተጣራ ድምፅ ስላልደረሳት ተንቀጠቀጠች ፣የጌታነህ አባት ክፉነገር የሰማች ስለመሰለው ልቡ እየመታ ከመሳይ ሞባይሏን ተቀብሎ "አቤት ጌታነህ እስኪ እየተንቀሳቀስክ አውራ ወይም ዝጋውና  እኔ ልደውል "አለው
"እሺ አ....እ.....ደና ነች.."አለው። የጌታነህ አባት የመጨረሻውን ቃል ሲሰማ ተረጋጋ
"እሺ እሺ እኔ እደውላለው "ብሎ ስልኩን ዘግቶ ወደሚስቱ በመሄድ "ደና ነች "ብሎ አቀፋት ።የአብላካት እናት በእፎይታ ሶፋው ላይ ዘጭ ብላ ተቀመጠች ፣እናም ዕንባዋን ያለማቋረጥ ተብሎ ስነካው ጀመር ፣የጌታነህ እናት እንድትረጋጋ እየነገረች አባበለቻት .....
ቆይቶ የጌታነህ አባት ወደ ልጃቸው ደወሉ  ተነሳላቸው
"ሄሉ ጌትዬ እንዴት ናቹ "አሉት
"ደና ነን አባዬ አሁን ይሰማል"አለ
"አዎ አሁን ይሻላል ፣ሁሉም ነገር በሰላም ተጠናቀቀ"
"አዎ አባዬ ትንሽ ግን ችግር አለ ማለቴ ፣እሷ ላይ አይደለም ማማለቴ ወንድሜ እስካሁን ሊነቃ አልቻለም ዶክተሮቹ ወደሱ ክፍል እንድገባ አልፈቀዱልኝም እኔ ትንሽ ፈርቻለው"አለ በጭንቀት
"ምን መስፍን ማለት ምንድነው ፍፁም ጤነኛ መሆኑን አረጋግጠው የለ እንዴ "አሉት
"ልጄ ምን ሆነ!"አለች የጌታነህ እናት በጩኽት
"ተረጋጊ እስካሁን አልነቃም ከማደንዘዣው ነው እእ ጌትዬ አንተ ተረጋጋ እና ጠብቅ ምንም አይሆንም "አሉት
"እሺ አባ ፣በቃ በዋላ እደውላለው ዶክተሩ እየጠራኝ ነው ...."ብሎ ስልኩን ዘጋው አባት ክው እንዳሉ ሶፋው ላይ ተቀመጡ የጌታነህ እናት ሆዷን በሁለት እጆቿ ጨብጣ ወዲወዲያ ትል ጀመር ፣የአብላካት እናት የልጇን ሰላም መሆን ብታረጋግጥም ፣የመስፍን ነገር ደሞ ያልጠበቀችው ነገር ሆነባት ፣ በመጨረሻው ሰአት ይቅርታዋን በሚያገኝበት ሰአት አንድ ነገር እንዳይሆን ፈራች ፣ለአብላካት እውነታውን ሳታሳውቃት አንድ ነገር እንዳይሆን ፀለየች.......



ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍12012🥰8
አንቺ_ማለት_እኮ…..

ሲድህ የቆየ ህጻን የቆመባት ቅጽበት
በእሁድ እና ሰኞ መካከል ላይ ያለች
የአዲስ ሳምንት ሰዓት
ወይም ደግሞ ሀይሌ ሲድኒ ላይ ቲርጋትን
እስከ መጨረሻው ድል ድረስ ሲፈትን
የከፋ ኑሮውን በድንገት የረሳ
ልቡ የተሰቀለ
ሰባ ሚሊዮን ሕዝብ በእግሩ ተሸክሞ
በደስታ ሲያስጨፍር ከድል በላይ ቆሞ
በዛ ትልቅ ታ'ምር
ያገራችን መዝሙር በሲቃ ሲዘመር
ባንዴራ ሲሰቀል ከፍ ብሎ ከሰማይ
አንቺ ማለት ያ ነሽ የዛች ሰዓት ክፋይ

አንቺ ማለት እኮ…

እንደውም ባለፈው የሱዳን ጨዋታ
ከጭንቁ በኋላ…
ከአዳነ ቀጥሎ
ሁለተኛውን ጎል ሳላዲን ሲያገባ
የነበረው ሆታ የነበረው ፌሽታ
የነበረው ጩኽት የነበረው ደስታ
ያ ቅጽበት አንች ነሽ
ስለ ኳስ ሲነሳ ሁሉ 'ሚያስታውስሽ
አንቺ ማለት እኮ…
የዘጠና ሰባት ያገራችን ምርጫ
ሚያዝያ ሰላሳ መስቀል አደባባይ
የታየው ተአምር
የነበረው ተስፋ የነበረዉ ሲሳይ
የፍቅር ምልክት የአዲስ ዘመን ምኞት
በወኔ ቀስቅሶ በይነጋል ሞልቶት
የነበረች ሰዓት የነበረች ቅጽበት
አንቺ ማለት ያ ነሽ…
ታሪክ የማይረሳሽ የታሪክ ምልክት

አንቺ ማለት እኮ…

ዘጠኝ ወር የሆነው የእርግዝና ዘመን
አምስት ቀን ጨምሮ ኡደት ሙሉ ሲሆን
ምጥ የሚሉት ስቃይ ከተፈጥሮ ጋራ ተዳብሎ ሲመጣ
የጀርባ ክትከታ የእጅ እግር ቁርጥማት የሆድ ላይ ቆረጣ
‘’የእናቴ ድረሺ’’ የኡኡታው መአት ሕመም በፈረቃ
እንዳይሆኑ ሆኖ ሰዓቱን ጨርሶ ለእፎይታ ሲበቃ
የህጻኑ ለቅሶ የእናትዬው ደስታ የተመስገን ሲቃ
የዘመድ አዝማዱ የእልልታ ቡረቃ
ለቅሶና ፈገግታን በአንድ ያዋሃደ ረቂቅ ሙዚቃ
እውነቱን ልንገርሽ….
አንቺ ማለት ያ ነሽ
በልብ እና በነፍስ ዓለም የሚያደምጥሽ

አንቺ ማለት እኮ…

በረሃ የበላው ሲራራ ነጋዴ ግመል የሚነዳ
ሃሩር ለወበቀው ሙቀት ላቃጠለው ፀሀይ ፀሀይ ወልዳ
ሚራዥ ላሰቃየው ዋዕይ ላነደደው ገላው ለተጎዳ
አቧራ ላፈነው ረሞጭ ለላጠው እንጥል ጥሙ ወርዳ
ፀሀይ ካጠቆረው ከግዙፍ ዐለት ስር
በሆነ አይነት ምትሀት በሆነ አይነት ታ'ምር
የፈለቀች ውሀ የበረሃ ጸበል
እፎይታ የምትሰጥ ጥም ቆርጣ የምትጥል
ሕይወት አለምልመሽ ትንፋሽ ምታረዝሚ
አንቺ ማለት ይህ ነሽ…
ከበረሃው መሀል ውሃ ላይ ምትቆሚ
ሌላ እውነት ልንገርሽ…
ፒካሶ ነዳፊው ፒካሶ ሰዐሊው
የሰላም ምልክት ለዓለም ያቀበለው
አንቺን በነጭ እርግብ ወክሎ ስሎ ነው
ድግሞም የኛ ሎሬት
ሜትር አርቲስታችን አፈወርቅ ተክሌ
‘’የታል የኔ ስዕል የትኛው ነው ምስሌ?’’
ብለሽ ብትጠይቂው…
ከአደይ አበባ ጋር የሳለሽ አንቺን ነው
መዝገቡ ተሰማም…
የሎሬቱን ብሩሽ አመስግኖ ወራሽ
ተራራ ጫፍ ላይ ነው
ከነ ጥበብ ልብስሽ ከነ ሙሉ ግርማሽ
ኢትዮጵያ ናት ብሎ ቁጭ አርጎ የሣለሽ

‘’አንቺ ማለት እኮ’’ ….....

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘

YouTube ቻናሉን subscriber እያደረጋቹ 110 ሲገባ #ትንግርት የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ረጅም ልብ ወለድ መፅሀፍ ይጀምራል ስለዚህ #Subscribe እያደረጋቹ Link ከታች አለላችሁ አሁኑኑ ከ 110 Subscriber አሳልፉትና እንጀምረው👍

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍49👏8🥰6😁32🔥1😢1
#ስንት_ጊዜ_ሆናችሁ?

መሃል አዲስአባ…ሸገር ላይ እያላችሁ..
የእንቁራሪቶች ድምፅ በደንብ ከሰማችሁ
በክር የታሰረ ጢንዚዛ ካያችሁ
የማርያም ፈረስን መንገድ ካገኛችሁ
በእፉዬ ገላ ‹‹ያዘኝ አትያዘኝ›› ከተጃጃላችሁ…

ስንት ጊዜ ሆናችሁ ?

ሱዚ የሚዘሉ
ፔፕሲ የሚራገጡ
ሸክላ እየፈጩ በርበሬ ነው የሚሉ
ሙሽራ ሙሽራ እቃ እቃ እቃ እቃ የሚጨዋወቱ
ጢቢ ጢቢ ሰርተው እየተጫወቱ የሚፈነድቁ ሴት ልጆች ካያችሁ

ስንት ጊዜ ሆናችሁ ?

በኮባ ጠመንጃ የሚተኳኮሱ
ኳሷን ከስልክ እንጨት ድብን አርገው አስረው ቴዘር የሚመቱ
በሽቦ መኪና የሚወዳደሩ
መሬትን ቆፋፍረው ብይ የሚጫወቱ
ልጆችን ካያችሁ
ዛፉን ተፈናጥጠው ሆምጣጤ የሚያወርዱ
ከአመት እስከ አመት እርግብ የሚያረቡ
በሌሊት ተነስተው ለእግር ኳስ ቡድን ስፖርት የሚሰሩ ፈርጣማ ጎረምሶች
ሰፈር ውስጥ ካያችሁ

ስንት ጊዜ ሆናችሁ ?

አዲሳባ መሃል የአሞራ ክንፍ ቪላ
የቀይ ሸክላ ውብ ቤት በአይናችሁ ካያችሁ
ሰንሰልና ሃረግ አጥር ሆነው ቆመው በጎን ካለፋችሁ
ላላ ያለ ጉንጉን ሁለት ቦታ ከፍላ የተሰራች ጉብል ከገጠመቻችሁ…
‹‹አትሸኟትም ወይ መሄዷ አይደለም ወይ›› እያሉ ሲዘፍኑ ካንጀቷ ምታለቅስ ሙሽራ ካያችሁ
ፅዋ ተሸክመው እያሸበሸቡ ወይ እየዘመሩ የሚጓዙ ሴቶች
መንገድ ካገኛችሁ

ስንት ጊዜ ሆናችሁ ?

በድፎ ዳቦና በሚሪንዳ ብቻ ልደቱን የሚያከብር ትንሽ ልጅ ካያችሁ
‹‹በሙሽራ ቀሚስ›› እየፈነደቀች ወዲህ ወዲያ የምትል ትንሽ ልጅ ካያችሁ
በሚያበራ ጫማ ወይም በ‹‹ኦክስጅን ባግ›› ጓደኛ የሚያቀና ህፃን ልጅ ካያችሁ

ስንት ጊዜ ሆናችሁ ?

በውይይት ታክሲ በረድፍ ተቀምጣችሁ ከተጓጓዛችሁ
ለአንዲት ነገር ብቻ መርካቶ ሸመታ ጎራ እንኳን ካላችሁ
አምስት ሳንቲምና ስሙኒ ካያችሁ
እሱ እንኳን ቢጠፋ የአንድ ብር ሳንቲም ከኖረ በእጃችሁ

ስንት ጊዜ ሆናችሁ ?

በናና የተፈላ ሻይ ፉት ካላችሁ
ሽልጦን ከወዳጅ ከተካፈላችሁ
አሹቅ አነባብሮን መክሰስ ካረጋችሁ
ቤት የተዘጋጀ የሰነፍ ገብስ ቆሎ ዝግን ካረጋችሁ
ከጎረቤት ጋር ሰብሰብ ብላችሁ ቡና ከጠጣችሁ…

ስንት ጊዜ ሆናችሁ ?


🔘በህይወት እምሽዉ🔘


YouTube ቻናሉን subscriber እያደረጋቹ 110 ማስገባት አልቻላችሁም አሁንም እደግመዋለሁ 110 ሲገባ #ትንግርት  የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ረጅም ልብ ወለድ መፅሀፍ ይጀምራል ስለዚህ #Subscribe እያደረጋቹ Link  ከታች አለላችሁ አሁኑኑ ከ 110 Subscriber አሳልፉትና እንጀምረው👍 5 ሰው ብቻ..ዳይ

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍67🥰146👏3
👁በ'ነሱ ቤት👁
🍄ክፍል አርባ አንድ🍄
👁👁👁👁👁👁👁
በነ ጌታነህ ቤት ሳምንቱ በውጥረት ነበር ያለፈው ።ቤተሰቡ የጌታነህን የጭንቀት ድምፅ በስልክ እየሰሙ ልባቸው በፍርሃት እየራደ ነበር ። የአብላካት እናትም ወደቤቷ ሳትሄድ ጭንቀታቸውን ስትጋራ ስትፀልይ ነው የሰነበተችው ። 
  ሰኞ ጠዋት ላይ ለቁርስ ሰብሰብ እንዳሉ ፣የጌታነህ እናት ፣ለመሳይ በትህትና አብላካት የመስፍንን አባትነት ማወቅ አለባት ስትል አወራቻት ፣የአብላካት እናት እንደመሳቀቅ ብላ "አይ በንደዚ መልኩ አይሆንም እኔ ነኝ ቀስብዬ የምነግራት "አለቻት
"ምን መሰለሽ እኔ በጣም ፈርቻለው ልጄ አንድ ነገር ቢሆን ...."ብላ አሳቧ ስለዘገነናት በንጥልጥል ትታው አለቀሰች
"ተይ ተይ የመስፍን እናት እሱ ምንም አይሆንም ፈጣሪ አለ ። እኔ መነገሩን ጠልቼ አይደለም ነገር ግን ልጄ ገና ከእመሟ አላገገመችም እዚ ስትመጣ አለሳልሰን ቀስብለን ብንነግራት ይሻላል ፣ለመረዳትም እንዳይከብዳት ፣ የዛሬ ልጆች ታውቂያለሽ በቀላሉ አሚን ብለው ሁሉን አይቀበሉም ፣አባቷ ላደረጋት ነገር  ሁሉ ለምን የሚል ብዙ ጥያቄዎች ይኖሯታል ፣ ለዚ ደሞ መልስ ለመስጠት መዘጋጀት አለበት ሁላችንም አላፊነት አለብን ከአባቷ በተጨማሪ "አለች መሳይ ፣ አንዳንዴ ለመስፍን ይቅርታ ማድረጓ ልክ መሆኑን ትጠራጠራለች ፣ያሳለፈችውን የልጅነት ጊዜዋን ፣ ሳትወድ በግድ የትንሽ ትልቅ የሆነችበትን መንገድ ፣እንዲሁም ልጇን ለማሳደግ ከላይ ታች የተንከራተተችበትን የተራበችበትን የሰው ፊት ያየችበትን ያንን ወቅት ስታስታውስ ፣የመስፍን በደል ለይቅርታ የሚያበቀው አይመስላትም ፣ መልሳ ደሞ ተፀፅቶ ልጇን ለማዳን ኩላሊቱን ሊያጋራት መሆሰኑን ደሞ ስታስብ ሁለተኛ እድል ይገባዋል ትላለች።
"ግን አንቺ እንዳሰብሽውም ላይሆን ይችላል ፣ጌታነህ ሊያሳምናት እና ሊያረጋጋት ይችላል"አለቻት
"አይ ትንሽ እንጠብቅ ፣መስፍን ከእግዚአብሔር ጋር ምንም አይሆንም አትፍሪ"አለቻት መሳይ መልሳ
"እሺ እንዳልሽ "ብላ ሳህኗ ላይ ያለውን ምግብ ለመብላት ሞከረች ። በዚ ጊዜ ስልኳ ጠራ ፣ጌታነህ ነው ብላ ስልኳን በፍጥነት አነሳችው
"አቤት ጌትዬ"አለች ፍርሃቷን እያፈነች
"እማ ደና ነሽ "
"ደና ነኝ ጌትዬ ልጄስ"
"ልጅሽ ደና ነው ጠንክሮ ቆሞሃል "አላት ደስ በሚል ስሜት
"እሰይ እልልልልል በጠዋቱ መልካሙን አሰማኽኝ ፈጣሪዬ እሰይ !ጌትዬ ድምፁን ልስማው እባክህ ፣"አለችው
"እሺ እሰጥሻለው"ብሎ ትንሽ ካስጠበቃት በዋላ ለመስፍን ሰጠው
"ኤሎ እማ "አለመስፍን
"የኔ ውድ ደና ሆንክልኝ ፣"
"ደና ነኝ እማ ጌታነህን ታውቂው የለ ሲያካብድ እኮ ነው አስደነገጠሽ አይደል "አላት
"ተው ተው ጌትዬማ አስቸጋሪ ነገር ካልደረሰ በስተቀር እኔን አያስጨንቀኝም ነበር ።አሁን ደና ከሆንክልኝ ተመስገን አቢስ እንዴት ናት አብራቹ ናቹ "
"አዎ እማዬ ታናግሪያታለሽ "
"ደስ ይለኛል"
"እሺ"ብሎ አስተላለፈላት
"ሃሉ "አለች አብላካት በትህትና
"እንዴት ነሽ ማማዬ ተሻለሽ ጠነከርሽ "
"አዎ እድሜ ለእናንተ ከፈጣሪጋር ሰላም ሆኛለው አመሰግናለው"አለች አብላካት
"የገባሻል ሁሉም ነገር የኔ ውድ እስኪ እናትሽን አናግሪያት "ብላ ስልኳን ለመሳይ ሰጠቻት ፣መሳይ ስልኩን ይዛ ማልቀስ ጀመረች ፣አብላካት በማፅናናት ታባብላት ጀመር ፣"እናቴ አሁን ዝም ብለሽ ያለገደብ መሳቅ ብቻ ነው ያለብሽ ፣እሺ "ብላ ተቆጣቻት ፣መሳይ እራሷን ቀስ በቀስ አረጋጋች እና በደስታ እያወራቻት መሳቅ ጀመረች ፣ደስታዋ ከልብ የመነጨ የእናትነት ፍቅርን ያዘለ ንፁህ ነበር ።
ጌታነህ ስልኩን ተቀብሎ ሳምንት እንደሚመለሱ እና ለየት ያለ ዝግጅት ቢያደርጉላቸው እንደሚወደድ ነግሯቸው ተለያዩ ........

ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍129🔥1710👏9😁2
#ሲጨልም

ወደ ሰባዎቹ የሚጠጉ የሚመስሉ አንድ አረጋዊ “ልጄ” አሉት አስተናጋጁን፡፡ “የወሰድኩትን መድኃኒት ይዤብህ መጣሁ፣ እባክህን የሰጠኸኝን ወስደህ . . .”

አላስጨርሳቸውም፡፡ ግርግዳው ላይ ወደተለጠፈው ጽሑፍ አመለከታቸው፡፡‘የተሸጠ መድኃኒት አይመለስም አረጋዊው’ በለሰለሱ ቃላት መማፀን ያዙ፡፡

“ሰውዬ ዞር በል! ስራ ልስራበት! ለእንቶ ፈንቶ ጉዳይ የማባክነው ጊዜ የለኝም. . .” አለ ቁጣው እየተወለደ፡፡

“ዛሬ በዚህ ሰውዬ እንድጨቀጨቅ ተፈርዶብኛል ልበል?”

“እባክህን ልጄ አሳፋሪ ነገር ደርሶብኝ ነው ዘመድና ዕድር የለለኝ በመሆኑ እንጂ . . . ” አሉ ትሁት በሆነች ፈገግታ ሊያባብሉት እየሞከሩ፡፡

“ቅናሽ ዋጋ ብትከፍለኝም . . .”

“ይሄ ሰውዬ ነካ ያረገዋል ልበል?” አለና ሌሎች መድኃኒት ገዥዎችን ያስተናግድ ገባ፡፡ “ከያዙ አይለቁ” 

“ድህነት ቢፈትነኝ ነው ልጄ” አለ¸ያደፈና የነተበ ነጠላቸውን እያሳዩት፡፡ ነጠላው ከሰውነታቸው በከፋ ሁኔታ ያረጀውን ኮታቸውን ደብቆላቸዋል፡፡

“አቅሜ የደከመ ባይሆን ኖሮ . . . ” ጫማ ካገኘ የከረመ እግራቸውን እያዩ፡፡ አንዲት ተስተናጋጅ “አልመልስም ካለ አልመልስም ነው፡፡ ለምንድነው የሚነዘንዙት?” አለች በሚነጫነጭ ድምጽ “ይሄኮ ፋርማሲ እንጂ አዛውንቶች የሚጦሩበት የድኩማን መርጃ ድርጅት አይደለም”

አነጋገሯን ያልወደደው የሚመስል ሌላኛው ጎልማሳ ደግሞ “መድኃኒቱን ሙሉ በሙሉ የገዙት ከዚሁ መደብር ነው?” የሚል ጥያቄ አመጣ፡፡

“አዎ ዶክተሩ ፅፎ በሰጠኝ መሠረት”

“ምን ያሕል ፈጀብዎት?”

“ሰባ ሁለት ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም፡፡ መድኃኒቱን ወስደው ግማሹን እንኳን ቢሰጡኝ ምን አለበት?” አሉ በሃዘኔታ፤ “የሁለታችንንም የጋብቻ ቀለበት አስይዤ ነው ከማምነው ሰው የተበደርኩት”

“መድኃኒቱን ለምን መመለስ ፈለጉ?” ዘንቢል ያንጠለጠሉ ያንዲት ምስኪን እናት ጥያቄ፡፡

በዚህ ጊዜ አስተናጋጁ ጣልቃ ገባ፡፡ “ባህላዊ ሕክምና ብትከታተል ኪስ እንደማታራቁት ገብቷቸው ይሆናላ! ወይ ፀበል ሊያጠምቋት! ወይ . . .”

“ኧይ ልጄ! ጉዳዩን ብታውቀው ኖሮ ያፌዝክበት ምላስህን ታፍርበት ነበር . . .” አሉ እንባ እየተናነቃቸው፡፡

“መድኃኒቱን ምን ላድርገው? ልዋጠው ወይስ ሽንት ቤት ልጨምረው?”

“ለባለቤቴ ነው የምገዛላት ብለው አልነበር? በጠና ታማብኛለች የእድሜዬ ጀምበር እየጠለቀ ባበት ሰዓት ለእህል ያላነሱና ለትምህርት ያልደረሱ ሦስት ልጆች በትናብኝ እንዳትሄድ ፀልይልኝ ብለውኝ አልነበር?”

“ማለቱንስ ብዬህ ነበር ልጄ! . . . ብዬ ነበር”

“እና ሩብ ሰዓት ያህል እንኳን ሳይቆዩ ሃሳብዎን አስሰርዞ የገዙትን መድኃኒት የሚያስመልስ ምን ተአምር ተፈጠረ?! ቅድም የማይመለከተኝን ነገር ሲዘላብዱልኝ ነበር እኮ” አረጋዊው አንገታቸውን ደፉ፡፡ “እኮ ምን ቢፈጠር ነው . . . ?”

“ቤቴ ሳልደርስ ነው አንተ ዘንድ የመጣሁት”

“ለምን?” የሌሎቹ ጥያቄ፡፡

“ሰፈርተኞቼ ደጄ ላይ ሲጯጯሁ አየሁ፡፡ ባቤቴን በህይወቷ ልደርስላት አልቻልኩም!” አሉ አረጋዊው ድምጻቸው እየሻከረ፡፡ እንባቸው እየወረደ፡፡ በመድኃኒት ሻጩ ፊት ላይ ፀፀት ድንጋጤ እየታየ ድፍን መቶ ብር አውጥቶ በሻካራ እጆቻቸው ላይ አኖረው፡፡ ሌሎቹም ኪሶቻቸውን ይፈታትሹ ጀምር፡፡

“ይባርካችሁ ልጆቼ! ከፈን መግዣ ስላልነበረኝ እንጂ . . . ” እንባ ተናነቃቸው፡፡

መንሰቅሰቃቸውን እየቀጠሉ ወጡ፡፡

ፀጥታ!😔..😔..😥


YouTube ቻናሉን subscriber እያደረጋቹ ምርጥ ምርጥ ስራዎች

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢91👍437🤔2
#ውርሰ_ውበት

ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን..

በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው

ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ

ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ

ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት

ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ

ፀባይሽ ግን ውዴ...

እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው

ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ

እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸዉ

🔘ልዑል ሀይሌ🔘


YouTube ቻናሉን subscriber እያደረጋቹ ምርጥ ምርጥ ስራዎች ታገኙበታላቹ Subscribe አድርጉና ረጅም ልብወለድም እንጀምርበት😘

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍30😁18👏3🤔1
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
👁ክፍል አርባ ሁለት👁
👁👁👁
የቤቱ ድባብ ለየት ብሏል ሁሉም በጉጉትና በደስታ ከመሞላታቸው በተጨማሪ ፣ዘፈኑም ሽርጉዱም ደርቷል ፣የጌታነህ እናት ዘመዶቿን ጠርታ የደስታዋ ተካፋይ አድርጋቸዋለች ፣ መሳይ ከልብ ምቷ ጋር ከጉጉታጋር ጥግ ይዛ ተቀምጣ ትቁለጨለጫለች ፣ አሳቧ ሁሉ እዛ የለም ፣በተደጋጋሚ ሰአቷን ታያለች ፣ እነገታነህ እስከ አስር ሰአት ቤት እንደሚደርሱ አሳውቀዋል ፣ እሷም ቶሎ ሰአቱ ቆጥሮ ልጇን ለማየት ጓጉታለች ፣  የጌት ነህ እናት ደሞ በዚ ቀን ለሁሉም ቤተሰቦቿ የልጇን ልጅ ለማስተዋወቅ ቆርጣ የነሱን መድረስ እየተጠባበቀች ነው ፣የአብላካት እናት ይቆይ ብትላትም ፣እሷ ግን ፣መገላገል ፈልጋለች ።
እንግዶቹ የጥሪው ምክንያት በግልፅ ባይገባቸውም ፣የጌታነህ እናት በዛ በተንጣለለ ቬላ ቤቷ ጋብዛ የማይቀር ሆኖባቸው በደስታ ታድመው ፣የቀረበላቸውን እየተቋደሱ ያወካሉ ፣   ሌላ ጥግ ላይ ሰመረ እና አስተናጋጁ ሰሚር ተቀምጠው ፣የነ አብላካትን መድረስ ጓጉተው እየጠበቁ ፣ነው
በተለይ ሰመረ አብላካት ይዛው የሄደችውን ልቡን ይዛለት እስክትመጣ ከራሱጋርም አይመስል ፣
አብላካትን የመጀመሪያ ጊዜ ያገኛትን እለት እያስታወሰ በመገረም በውስጡ ከራሱ ጋር ይነጋገራል ፣ያቺልጅ ትንሽ ልጅ ነበረች ከመቼው ትልቅ ሰው ሆና ተቆጣጠረቺኝ ፣ ይሄማ የፈጣሪ ስራ ነው ፣የኛን የተበላሸ አካሄድ ማስተካከያ የተላከች ናት ፣ኧረ እንደውም በኔ እና በጌት ነህ አማካኝነት ከወላጅ አባቷ እንድትገናኝ አዟዙሮ ያመጣት አስቦ ነው ፣ ሆሆ ነገሩ እኮ የማይታመን ነው ። አብላካት የመስፍን ልጅ ፣ የኔ የልብ ህመም ፣የጌታነህ የወንድም ልጅ ፣ ። በተለይ ደሞ ህመሟ ነው ቤተሰቧን እንድታቅ ያደረጋት ፣ የመስፍን ወላጆች ግን ክፋታቸው ለክፉ አልሰጣቸውም ፣እንዲማሩበት ሁለተኛ እድል ተሰጣቸው ፣እነሱም ተማሩበት ፣ ወይ ጉድ ፣
"ሰመረ "
"አቤት ሰሚር
"አልሰማኽኝም እንዴ
"እም ምን አልከኝ
"እየደረሱነው እያሉ እኮ ነው አልሰማህም እንዴ ፣የጌታነህ አባት ደውሎ ይዣቸው እየመጣው ነው አለ "
"ኧረ ማማነው ያለው "
"መሳይ ናታ አሁን ነግራኝ ስትሄድ አላየሃትም ኧረ ወንድሜን ከራስህ ጋር አልነበርክም ማለት ነው "
"ወይኔ ልብ አላልኳትም "አለ ሰመረ
"ኧረ አትጨነቅ አሁን ሁሉም ነገር አልቋል እኮ ልትደሰት ነው የሚገባው ።ይልቅ ወጣ ብለን እንጠብቃቸው እንዴ"አለው
"አይ እዚው ብንሆን ይሻላል ፣ግርግሩም በዝቷል ፣ይሄ ሁሉ ሰው መጥራት ነበረባቸው ግን ?"አለ ሰመረ አብላካት እንድትጨናነቅ አልፈለገም
"ያው ታውቃለህ በ'ነሱ ቤት ላጠፉት ጥፋት ማካካሻ ነው ፣ "ብሎ ሰሚር ፈገግ አለ
ሰመረ ተከትሎ ፈገግ አለ ፣
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አብላካት በቀጥታ ከመኪናው እንደወረደች ፣እናቷን ነበር የፈለገችው ፣መሳይ አይኗ ሲንከራተት አይታ ሮጣ መጥታ ተጠመጠመችባት ፣ተቃቅፈው አለቀሱ ፣ የጌት ነህ እናት መጥታ እስክታላቅቃቸው ድረስ ፣ሊላቀቁ አልቻሉም ነበር ፣ የጌታነህ እናት አብላካትን ተቀብላ እያገላበጠች ስትስም ፣እንግዶቹ ሁሉ የመሰላቸው ወይ የጌታነህ ወይ የመስፍን እጮኛናት ብለው ነበር ያሰቡት ፣አብላካት የጌታነህን እናት አይኖቿ ውስጥ እያየች ደጋግማ ስትስማት ፣የጌታነህ እናት አንጀቷ ተላወሰ ፣ መስፍን ወደ መሳይ በመሄድ እጁን ዘረጋላት ፣መሳይ ትንሽ ካቅማማች በዋላ አቀፈችው እና "አመሰግናለው ልጄን አተረፍክልኝ አመሰግናለው "ብላ አለቀሰች
"አይ ልጃችን ናት መሳይ እባክሽ ቅሬታሽን አንሺ ልኝ እድሜ ልኬን መክፈል ያለብኝን ዋጋ ላንቺና ለልጄ እከፍላለው ቃሌ ነው "ብሎ ከፊቷ ተንበረከከ
"ኧረ ተነስ እባክህ ተነስ ይቅር ብዬሃለው ፣ፈጣሪ እንዲ እንዲሆን ስለፈለገ ይሆናል ፣ተነስ በቃ"ብላ ጎተተችው ፣
አብላካት የሁለቱን ሁኔታ አየት አድርጋ ወደ ጌታነህ ዞረች ጠቀስ አደረጋት ፈገግ አለች ፣ እናም አይኖቿን ወደሌላ አቅጣጫ አሽከረከረች ፣ የፈለገችውን አገኘች ሰመረ አይኖቹ እሷላይ ሲንከራተቱ ያዘቻቸው....

..
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
157👍88👏3😁2
#ያሳፈርኩህ_እንዳታፍር_በመፈለጌ_ነው

‹‹ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ያምሻል?›› ስል እናቴ ላይ በብስጭት ጮህኩባት ... አንድ ጥግ ላይ ኩርምት ብላ እና አንገቷን ደፍታ በቁጣ የምደነፋባትን ንግግር ሁሉ ስታዳምጠኝ ትልቅ ወንጀል ሰርቶ ዳኛ ፊት የቀረበ ወንጀለኛ እንጅ የሰባት አመት ልጇ የሚጮህባት እናት አትመስልም ነበር !
ብስጭቴ ልክ አልነበረውም እንዲያውም ከንዴቴና ከቁጣየ የተነሳ እናቴ አስጠላችኝ ‹‹አሁኑ ብትሞች ግልግል ነበር›› ስል ጮህኩባት እውነቴን ነበር እንዲህ ከምታሳፍረኝ ብትሞት እና ብገላገል በሰላም እኖር ነበር ! እንዴት እንዳስጠላችኝ እንደቀፈፈችኝ ! ደምስሬ ተገታትሯል እንባየ በአይኖቸ ሞልቶ በእልህና በጥላቻ አስቀያሚዋ እናቴ ፊት እየተንቀጠቀጥኩ ነበር ! አርሷ ግን አንገቷን ደፍታ አሮጌ ጫማወቿን አቀርቅራ እየተመለከተች በዝምታ የምላትን ሁሉ ታደምጥ ነበር !
እናቴ ካለአባት ብቻዋን ነበረ ያሳደገችኝ ….እኔን ለማሳደግ ብቸኛ የገቢ ምንጯ የነበረው በምማርበት ት/ቤት ውስጥ ለመምህራንና ተማሪወች ምግብ በማዘጋጀት የሚከፈላት አነስተኛ ክፍያ ነበር ! እንዲህም ሁኖ የምማርበት ትምህርት ቤት የሃብታም ልጆች መማሪያ ስለነበርና እኔም በልብስም ሆነ በመማሪያ ቁሳቁሶቸ ከማንም ስለማላንስ ስለእናቴ ማንነት ማንም አያዉቅም ነበር እኔም ስለእናቴ ተናግሬ አላውቅም !
በእናቴ የማፍረው ደሃ ስለሆነች ብቻ አልነበረም አንድ አይን ብቻ የነበራት ሴት ስለነበረች እንጅ ! በእውነትም እናቴ አስቀያሚ መልክ ነበራት ! የግራ አይኗ የነበረበት ቦታ ባዶ ጉድጓዱ ብቻ ቀርቶ አንዲት ትንሽ አይኗ ብቻ እየተቁለጨች ድንገት ለተመለከታት ከማስቀየም አልፎ ትቀፍ ነበር ! የብዙ ጓደኞቸ እናቶች አይኖቻቸው በኩል ተከበውና አምረው ስመለከት የእናቴ አንድ አይን ያሳፍረኛል ! ምንም ማድረግ አልችልም ‹‹ምንም ቢሆን እናቴ ናት ›› እያልኩ ነገሩን ለመቀበል ብሞክርም አልቻልኩም ! በእናቴ መልክ በጣም እሳቀቅና አፍር ነበር! በእርግጥም የእናቴ አንድ አይናነት ለእኔ የማልቋቋመው የሃፍረት ምንጭ ነበር !
ቢሆንም እናቴን ማንም ስለማያውቃትና ስለዚህም ጉዳይ ተናግሮኝ የሚያውቅ ተማሪ ስላልነበር እናቴን ሳያት ካልሆነ በስተቀር ትዝ አትለኝም ነበር ! በአንድ የተረገመ ቀን ታዲያ እማርበት ወደነበረው የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪወች ብቻ ወደሚገኙበት አጥር ውስጥ እናቴ ስትመጣ አየኋት ! ራሴን ልስት ምንም አልቀረኝም ... ተማሪወቹ የእናቴን አይን ሲመለከቱ በሳቅ አውካኩ አሾፉባት የእማማ ፊት ላይ ግን ምንም መከፋት ሳይታይ ወደእኔ ትራመድ ነበር …..ድንገት ወደኋላየ ሮጥኩ ‹አላውቃትም እችን ሴት ወዲያ በሉልኝ ›› እያልኩ ሮጥኩ ! ይሁንና ተማሪ ጓደኞቸ መዘባበቻ አደረጉኝ
‹‹አንተ እናትህ አይኗ የት ሂዶ ነው? ››
‹‹እናትህ 'ሆረር' ፊልም የምትሰራ ነው የምትመስለው ››
‹‹እናትህ በአንድ አይኗ ሽንኩርት ስትከትፍ እጇን አብራ አትከትፍም ?ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ›› ተማሪው አሽካካ ተውካካ ለዘላለሙ ልቤን የሚሰብር የእናቴ ድርጊት ሁኖ ተሰማኝ ! ከዛን ቀን በኋላ የትምህርት ቤት ጓደኞቸ የነበሩ ህፃናት የሚስቁት የማሾፍ ሳቅና የሚወረውሩብኝ ቃል የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ነበር ! እድሜ ላሳፈረችኝ እናቴ ! እጠላታለሁ ! እቤቴ ማታ ስመለከታት እንኳ የጓደኞቸ ሳቅ ነው የሚታወሰኝ !
በዚህ ሁኔታ አብሪያት ልኖር ስላልቻልኩ ትንሽ ከፍ ስልና ነብስ ሳውቅ እናቴን ትቻት ወደሌላ ሩቅ አገር ትምህርት ቤቱ ባመቻቸው እድል ተጠቅሜ ተሰደድኩ ! እዛም ማንነቴን በማያውቁ ሰወች መሃል በደስታና በኩራት እኖር ጀመረ ! አድጌ ዩኒቨርስቲ ስገባ ስራ ስይዝ እና ሚስት አግብቸ ልጆች ስወልድ ሁሉ እናቴን አይቻትም ስለእርሷም ወሬ ሰምቸ አላውቅም ነበር ! ትልቅና የሚያምር የግሌ መኖሪያ ቤት ቆንጆ ሚስትና የሚያማምሩና ጎበዝ ልጆች አሉኝ !
ሚስቴም ሆነች ልጆቸ ትክክለኛውን ነገር አያውቁም ነበር ! ስለእናቴ ሲጠይቁኝ እንዲህ እላቸው ነበር ‹‹ እናቴ ውብ ነበረች... በተለይ አይኖቿ ጨረቃን የሚያስንቁ ከውስጣቸው ብርሃን የሚረጩ ውቦች ነበሩ የእናቴን አይን ተመልክቶ በፍቅሯ የማይማረክ የለም ግን ከብዙ አመታት በፊት ሙታለች ›› በቃ!! በዚህም የውሸት ታሪክ ታላቅ ኩራት ሰማኛል !
አንድ ቀን ግን ይህ ውብ ኑሮየን የሚያደፈረስ አሰቃቂ ነገር ተፈጠረ ! የቤቴ በር ተንኳኳ ….ትልቁ ልጀ በጉጉት በሩን ከከፈተው በኋላ በድንጋጤ እየጮኸ ወደቤት ተመለሰ ….ሁላችንም ያስደነገጠውን ነገር ለመመልከት በእኔ መሪነት ክፍቱን ወደተተወው በር ተንጋጋን ይህች አሰቃቂ እናቴ በር ላይ ቁማ ነበር ! ከበፊቱ የበለጠ ተጎሳቁላና የፊቷ አጥንት ቀርቶ የአይኗ ጉድጓድ የባሰ ሰፍቶ ይታያል አንድ አይኗ ሲቁለጨለጭ አንዳች አስፈሪ አውሬ ትመስል ነበር !
ድንጋጠየን ተቋቁሜ ‹‹ምን ልርዳሽ ሴትዮ›› አልኳት አጠያየቄ ግልምጫ የታከለበትና ፍፁም የማላውቃት ሴት መሆኗን የሚያሳይ ነበር
‹‹ የኔ ልጅ ላይህ ጓጉቸ ነበር ….›› ብላ መናገር ከጀመረች በኋላ ወደሚስቴና በድንጋጤ የእናታቸውን ቀሚስ ጨምድደው ወደቆሙት ልጆቸ በዛቹ አንድ አይኗ ተመልክታ እንዲህ አለች ‹‹ ይቅርታ አድራሻ ተሳስቶብኝ ነው ›› ከዛም ተመልሳ መንገድ ጀመረች ጀርባዋ ጎበጥ ብሏል ፀጉሯም ግማሽ በግማሽ ነጭ ሁኗል ! እውነቱን ለመናገር ምንም አላዘንኩም እንደውም በየሄድኩበት እየተከተለች ኑሮየን መበጥበጧ አበሳጨችኝ !!
ከአንድ አመት በኋላ ድሮ እማርበት የነበረው ትምህርት ቤት ያስተማራቸውን ተማሪወች ጠርቶ የምስረታ በአሉን ሲያከብር የክብር እንግዳ አድርጎ ስለጠራኝ ወደጥንት መንደሬ በአሉ ላይ ለመገኘት ሄድኩ ! እናቴ የነበረችበት የጥንት መንደር ምንም ሳይሻሻል ከነ ደሳሳ ቤቶቹ እዛው ነበር !
በአሉን ተሳትፌ ልመለስ ስዘጋጅ አንድ እንደእናቴ የተጎሳቆለ ሰው ወደእኔ እየተጣደፈ መጣና እንዲህ አለኝ
‹‹ እናትህ ሙታለች … !! ›› እውነት እላችኋለሁ ትልቅ እረፍት ተሰማኝ ካሁን በኋላ መሳቀቄ ሃፍረቴ ሁሉ አብሮ ሞተ ! የማፍርበት የኋላ ታሪኬ መቃብር ወረደ ! እፎይይይይይይይይይ! ይሄ መርዶ ሳይሆን ‹‹የምስራች›› ነበር!!
ይሁንና ‹የምስራቹን › ያበሰረኝ ሰው አንድ አሮጌ ፖስታ ከአሮጌ ኮቱ ኪስ አውጥቶ ሰጠኝና ‹‹እናትህ አደራ ስጥልኝ ብላኝ ነው ›› ብሎ ፖስታው ጋር ትቶኝ እየተጣደፈ ሄደ !ፊቱን ሲያዞርና ከእኔ ለመራቅ ሲጣደፍ አንዳች ቆሻሻ ነገር የሚሸሽ ነበር የሚመስለው ! ፖስታውን ከፍቸ ድሮ የማስታውሰው የእናቴ የእጅ ፅሁፍ ጋር ተፋጠጥኩ አጭር እና ግልፅ መልእክት ነበር !
‹‹ የምወድህ ልጀ እድሜ ልክህን ሳሳፍርህ እና ሳሳቅቅህ በመኖሬ ይቅር በለኝ …. ለትልቅ ደረጃ መድረስህን እቤትህ ድረስ መጥቸ በአንድ አይኔ በማየቴ ደስ ብሎኝ ቀሪ እድሜየን ኑሪያለሁ ! ውድ ልጀ ያሳፈርኩህ እንዳታፍር በመፈለጌ ነው ….በልጅነትህ አደጋ ደርሶብህ አንድ አይንህ ጠፍቶ ነበር እድሜ ልክህን በአንድ አይን እንድትኖር የእናት አንጀቴ ስላልቻለ የራሴን አንድ አይን ልለግስህና በቀሪው አንድ አይኔ ደስታህን ልመለከት ስለፈለኩ ይሄንኑ አድርጊያለሁ !! በዚህም እኮራለሁ ልጄ ! ………እናትህ ››
ከውስጥ የማይወጣ ፀፀት ተሰማኝ ያን ፊት እንደገና ማየት ተመኘሁ ግን😢😢
👍87😢456😱3👏2
#የትብብር_ጥያቄ
የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ለማድረግ የሚጠይቀው ውስጣዊ ቅንነትን፣ለሰዎች መልካም ማሰብን፣ደግነትን ብቻ ነው።አሁን በቅንነት የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ እንድትተባበሩ ነው።ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
7👍2👏1😁1
#ባራኪ
.
.
አንቺ ዳቦ ሆነሽ
ለበረከት ቀርበሽ፣
እኔ ቄስ ብሆን
የነፍስ አባት ቆራሽ፣
.
.
"ክቡርነትዎ አባ ቄሱ፣
በረከቱ ላይ ይቀድሱ፣
ቀድሰውም ይቁረሱ፣
ቆርሰውም
ለምእመናኑ ያዳርሱ፣"
.
.
ብባል ወስነው ቢፈርዱብኝ፣
መቁረሱ ግዴታ ቢሆንብኝ፣
.
.
በመስቀሉ
ባርኬ ቀድሼሽ፣
ሶስት ቦታ
ከፍዬ ቆርሼሽ፣
እንዲህ ነበር የማከፋፍልሽ ፣
.
.
አንደኛው ለራስ ለቆራሹ፣
ሁለተኛው ለቄስ ለቀዳሹ፣
ሶስተኛው
ለነፍስ አባት
በፀሎቱ ምእመናንን ላስታዋሹ፣
.
.
እልና ሁለመናሽን
እከተዋለሁ ከኪሴ፣
ማንም እጅ አትገቢም
አንቺ ነሽ የራሴ፣
.
.
ባንቺ የመጣ
አልፈራም ኩነኔ፣
ገሀነም ልውረድ
እንጂ
ምንጊዜም ነሽ የኔ!!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘

በቅንነት #Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😁22👍141👎1🥰1
🍄👁በ'ነሱ ቤት👁🍄
👁ክፍል አርባ ሶስት👁
🍄👁🍄👁🍄👁🍄
ሰመረ ፈልጋ ስላየችው ደስ የሚል ልዩ ስሜት ተሰማው ።ከቤተሰቧ ቀጥሎ ለሷ አስፈላጊ ሰው መሆኑን ልቡ ነገረው ።እናም ሂሉንታ ለሚሉት ነገር ቦታ ሳይሰጥ ወደሷ ፈጠነ ፡ አብላካት ልቧ ምቱን ሲቀይር ተሰማት  ፡አስተናጋጁ ሰሚር የሁለቱን ሁኔታ በጉጉት ይመለከት ጀመር ፣ጌታነህ ሰመረ ወደ አብላካት ሲመጣ አይቶ ምን ማድረግ እንዳለበት ለማሰብ ጊዜ ከማግኘቱ በፊት ፣ሰመረ አብላካት አጠገብ ደርሶ ቆመ ፣አብላካት እንደመጣ ያቅፈኛል ብላ ስትጠብቅ አጠገቧ ሲደርስ ፍዝዝ ብሎ ቆሞ ሲያያት ግራ ገባት ለመናገር ፈልጋ ከንፈሮቿ ሲንቀጠቀጡ ዝምታን መረጠች ፣ሰመረ ፍዝዝ ብሎ ሲያያት ቆይቶ " ሚጣ የኔ ውድ ዳግም ተያየን ደስ ሲል"ብሎ እንባ ባዘሉ አይኖቹ አያት
"ሰሙ ዳግም የማገኝህ አልመሰለኝም ነበር "ብላ ተጠጋችው ፣ሰመረ ተጠመጠመባት ። ተቃቅፈው ደስታቸውን ሲገላለፁ የሁሉንም ትኩረት ሳቡ ። መስፍን የልጁን ሁኔታ አይቶ እንዳትጎዳበት አሳብ ገባው ፣ሰመረን ያውቀዋላ ከወንድሙ ጋር በየናይት ክለቡ ሲዞር ለሊቱን ከተለያዩ ሴቶች ጋር ሲያነጉት ሁሉንም ያውቃል ። ሰመረ ለልጁ መገኘት አስተዋፅዖ እንዳለው ቢሰማም ፣ ወንዶች ባሕሪያችን አስቸጋሪ ነው ልጄን ቢጎዳብኝስ ምን ሊፈጠር ነው ብሎ ተጨነቀ ። ጌታነህ በበኩሉ ከሰመረ ጋር ምንም ነገር ለመነጋገር ባልፈለገ ሁኔታ ወደ አስተናጋጁ ሰሚር ሄዶ እንኳን ደስ አለን ብሎ ጨበጠው ። ሰሚር በደስታ ተዋጠ ለአብላካት መትረፍ የሁሉም አስተዋፅዖ ነበረው ።
ሰመረ አብላካትን ለቆ በደስታ አስተዋላት ይበልጥ ቆንጆ ሆናለች ልብ ብሎ ሲያያት የመስፍን የሆኑ ምልክቶች ፊቷላይ መሳሉን አስተዋለ ለራሱ ገረመው አብላካት ከመሳይ እና ከመስፍን አጣምራ የያዘችው ቁንጅና ልዩ ነበር ። ይሄን ውበት ደሞ ይዛ ወደሱ እንደምትመጣ ሲያስብ ልቡ በአሴት ጨቤ እረገጠ ።
  ድንገት ጮክ ብሎ አንድ ድምፅ ሲመጣ ሁሉም በአንድነት ወደ አንድ አቅጣጫ ዞሩ ፣የጌታነህ እናት ነበረች እንግዶቿ እንዲያዳምጧት በትህትና ተናገረች ሁሉም ፀጥ አለ ።የአብላካት እናት በምልክት ለመነቻት ፣ለንግዶቹም ለአብላካትም አዲስ የሆነውን ነገር ልትናገር መሆኑን ገብቷታል ፣አብላካት የመስፍንን አባትነት ስትሰማ እንዳትጎዳባት ፈርታለች ፣የጌታነህ እናት ግን ቆርጣ ተነስታለች ሁሉም በአንድነት እንዲሰሟት ፈልጋለች .....

***

👁በ'ነሱ ቤት👁
🍄ክፍል አርባ አራት🍄
👁🍄👁🍄👁🍄👁
የጌታነህ እናት የሁሉንም ትኩረት መሳቧን ካረጋገጠች በዋላ ፣ጉሮሮዋን አጥርታ ንግግሯን ጀመረች
  "ጥሪዬን አክብራቹ እዚ የደስታዬ ተካፋይ ለመሆን የመጣቹ የምወዳቹ ዘመድ ጓደኞቼ ላመሰግናቹ እወዳለው ፣ ዛሬ ለኔ የተለየ ቀን ነው ፣ ምክንያቱም በጣም ስፈራውና ሲያስጨንቀኝ ከነበረው  የሕይወት መስመር በፈጣሪ ፍቃድ ወጥቼ በትክክለኛው መንገድ ላይ የቆምኩበ ፣ ነው ። ከዚበፊት በልጆቼላይ የነበረኝ አላፊነት ላይ ቸልተኛ በመሆኔ ብዙ ያጠፋውት ነገር ነበር ፣ በዛም ተቀጥቼበታለው ፣ነገር ግን ፈጣሪ ቅጣቱን አላረዘመብኝም ፣ እንደበደሌ ሳይሆን ምህረትን ልኮልኛል ፣ "ብላ እንባዋን ከአይኖቿ ጠረግ አደረገች በዛውም ትንፋሽ ወሰደች ።ጌታነህ ባልተመቸው አይ ነት አስተያየት ያያታል 'ምንድነው ይሄ ሁሉ ይቅርታ እዝቤ ምን እንደምታወራ ሲገባው አይደል ይልቅ ወደገደለው ብትገባስ ማሚ ደሞ 'የላል በውስጡ ፣
የጌታነህ እናት ንግግሯን ቀጥላ "እእ ዛሬ የምነግራቹ ታሪክ ስለ አንዲት ታዳጊ ልጅ ነው ,,,,,,,,,,,,"ብላ ስለ አብላካት የህመም ሁኔታና እንዴት እንዳገኟት በሰፊው ካብራራች በዋላ መልሳ ዝም አለች ፣እንግዶቹ ስለ በጎ አድራጎታቸው መደሰታቸውን በጭብጨባ ገለፁ ፣ የአብላካት እናት ወደልጇ በመሄድ አጠገቧ ቆመች ፣ቀጥሎ በሚነገረው ነገር ችግር ውስጥ እንዳትገባባት ፈርታለች ። መስፍን ወደ አብላካት እያየ ፈገግ ሲል ምላሽ ሰጠች ፣ ሰመረ አብላካትን እጇን ያዝ ሲያደርጋት ወደሱ ዞረች "ሚጣ ገኒ ለምትናገረው ነገር ምንም ይሁን ምንም ተዘጋጂ እሺ ፣የኔ ጠንካራ"ብሎ አንሾካሾከ አብላካት ምን በሚል አስተያየት አየችው  ፣ልቡ አዘነላት እጇን አጥብቆ ያዛት
የጌታነህ እናት ቀጠለች" እና ይህች ልጅ በኛ ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ምክንያት ያራቅናት  የልጃችን ልጅ ናት !  አአዎ የመስፍን ልልጅ ናት ፣"ብላ አለቀሰች ፣እዛ የታደመው ዘመድ አዝማድ በአንዴ ሃሃ አለ የሚሰሙትን ማመን ነበር ያቃታቸው ፣ሁሉም እርስ በእርስ እየተነጋገሩ ወደ አብላካት ፊታቸውን አዞሩ ፣ መስፍን በደስታ ፊቱ እያበራ ከጌታነህ ጋር ተሳስቆ ተቃቀፈ ፣የአብላካት እናት ልጇ እንዳትወድቅባት የፈራች ይመስል ዞራ አቀፈቻት ፣ሰመረ እጇን አጥብቆ እንደያዛት ነበር ። አስተናጋጁ ሰሚር ጭንቅላቱን በቀኝ እጁ እያሻሸ ወደነ አብላካት እያየ ቀጥሎ ለሚፈጠረው ነገር ተጨንቆሃል ፣  አብላካት በሰማችው ነገር አንዳች ነገር ሳይገርማት እናቷን አቅፋ በመቆሟ ፣ የጌታነህ እናት ግራ በመጋባት ስታይ ቆይታ ፣ከነበረችበት ቦታ በፍጥነት እየተራመደች በመምጣት ጌታነህን እና መስፍንን እጃቸውን ይዛ በማላቀቅ "ምንድነው ?"ብላ ጠየቀች
"ውይ ማሚ ሁሉንም ነገር እዛ እያለን ነገረናታል ለምን ይመስልሻል ልጅሽ የታመመው ፣ አቢ ስለጉዳዩ ስታውቅ እራሷን መቆጣጠር አቅቷት ነበር በዚ የተነሳ ደንግጦ ነበር የታመመው ፣ በዋላ የሱ ሁኔታ ከሷ ሲብስ እሷ ተረጋጋች ፣ ሁሉንም ነገር ለማስተካከል ለለፋው ለትንሹ ልጅሽ አስቢ እድሜ ለሱ በይ !"ብሎ ጌታነህ ደረቱን መታ እያደረገ ጎረረ ። በዚ ጊዜ ትልቅ ነገር በመገላገሏ ጌታነህን አቀፈችው ። ቀጥላ ወደ አብላካት በመሄድ "ሃያትሽን ይቅር ትያታለሽ የኔ ውድ"አለቻት "ይቅር እንድንባባል አስቦ ይህን ሁሉ ነገር ፈጣሪ ካደረገ እኔ ማነኝና ይቅር የማልለው "አለች አብላካት ተረጋግታ "የኔ ውድ የልጅ አዋቂ ነሽ ባንቺ ኮርቻለው ነይ ልቀፍሽ "ብላ አቀፈቻት ።የጌታነህ አባት መጥቶ ተቀላቀላቸው ።አብላካት እስኪደክማት ከዘመድ አዝማዱ ጋር ትውውቅ አደረገች ፣ ሰመረ ብቻዋን ሊያገኛት ቢጥር አልተሳካለትም ያም ያም ይወስዳታል ፣እንኳን እሱ እናቷም ልታወራት አልቻለችም በአብታም ዘመዶች ተከበበች ፣
ጌታነህ ሰመረ አይኖቹ ሲንከራተቱ ሲያይ ትንሽ እራራለት ፣ ወደሱ በመሄድ "እሺ መቼም እኔና አንተ ወደፊት ትንሽ ፋይት ማድረጋችን አይቀርም"አለው
"አሁን ደሞ ለምኑ ነው "አለው ሰመረ
"ያው እህቴን በተመለከተ "አለው
"እእእ ,,"ብሎ ሊቀጥል ሲል
"ኪኪኪኪኪ ኧረ ስቀልድህ ነው ጓደኛዬ ተረጋጋ"ብሎ እጁን ዘረጋለት
"አመሰግናለው እንኳን ደስ አለህ መቼም እንዲ ይሆናል ብለን ባላሰብነው ሁኔታ ነው ሚጣን ያገኘናት"አለው
"አዎ ማን ያቺ ምስኪን ልጅ የኛው መሆኗን ይገምታል ፣"አለ ጌታነህ
"በጣም እኔማ እስካሁን ማመን ተስኖኛል ሚጣ የጌታነህ ቤተሰብ "ብሎ በፈገግታ አፉን ያዘ
"ሚጣ ስትላት ብትሰማ አቢ ትገልሃለች "ብሎ ሳቀ
"ሚጣ አይደለም ስሜ አብላካት ነኝ ነው የምትለው ፣እንደሱ ስትለኝ በጣም ነው ደስ የሚለኝ ኪኪኪ"ብሎ  ሞኛሞኝ የሚያስመስል ሳቅ ሳቀ ።ጌታነህ ሲያየው ቆይቶ"ውይ ጓደኛዬ የሌለ አንግ ይዛሃለች "ብሎ ሳቀበት እና"ብቻ ተጠንቀቅ እጇን የገፋኽው እለት ከኔ ነው ፀብህ ይህን አላፊነት የሰጠውህ ምንም ማድረግ ስለማልችል ነው ፣ምክንያቱም ስላንተ እዛ በነበርንበት ጊዜ ነግራኛለች በጣም ወዳሃለች በፍቅር ጣልቃ መግባት ነገር ማበላሸት ነው ። እና አደራ !"አለው ።ሰመረ አንገቱን ነቅንቆ
👍9217