አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

የንስሯ ጭንቅላቷ ላይ ማረፍ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት….በመከራ አይኗን ገልጣ ዙሪያዋን ስትቃኝ እራሷን  እዛው ቅድም የተዘረረችበት ወለል ላይ እርቃኗን አገኘችው….ባለ ላደውም የሞተ እስኪመስል ድረስ ትንፋሹ ጠፍቶ እግሮቾ  መካከል ጭንቅላቱን ቀብሮ በተመሳሳይ እርቃኑን ተዘርሯል ….ቀስ ብላ ከላዮ ላይ ገልበጥ  አደረገችውና እና እራሷን በማላቀቅ  ሾልካ ወደ ሻወር በመሄድ ለ5 ደቅቃ ውሃ በላይዋ ላይ አፈሰሰችና..
ከዛ ወደመኝታ  ቤቷ ተመልሳ ቢጃማ ለበሰችና ባለ ላዳውን እንደምንም እየጎተተችም እየደገፈችውም ወስዳ አልጋው ላይ በማስተኛት ብርድልብስ ካለበስችው በኋላ ወደሳሎን አመራች…..ንስሯም ተከተላት..፡፡
አዎ ሊነጋ  መሆኑን ከውጭ የሚሰማውን የወፎች  ዝማሬ በማዳመጥ ተረዳች …ሳሎኖ እንደደረሰች ተስተካክላ ከተቀመጠች በኋላ ንስሯ ያየውን  እንዲያሳየት… ያወቀውን እንዲያሳውቃት አዕምሮዋን ከእሱ ጋ አቆራኘችው…
ሰላምና አባቷ…ፍቅራቸው ከአባትና ከልጅም የዘለል አይነት ነው..ኤርምያስ እንዳለው እናትም አባትም ወንድምም እህትም ሆነው ነው ያሳደጎት…ግን አሁን ስላለችበት ሁኔታ ብቻ ያለውን ታሪክ ከንስሯ በተረዳችው የሚከተለውን ነው
ቀጥታ ቤታቸው ገባች… መኝታ ቤት ወደመሰላት ክፍል ተጓዘች… አዎ ትክክል ነች ያልተነጠፈ እና የተዝረከረከ አልጋ … አልጋው ላይ የተዘረረች ውብ ለጋ  ሀዘን የሰበራት ወጣት ተኝታለች…..ወለሉ ጠቅላላ በመጠጥ ጠርሙሶች እና በተበታተኑት ልብሶች ተሞልቷል..አንድ ግዙፍ  አራት መአዘን  ፍሪጅ አልጋውን ተደግፎ   ይታያል…ትኩረቷን ወደፍሪጁ አመዘነበት… ውስጡን አየችው… .ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ ያስብላል… …ነጭ ሱፍ ለብሶ ነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ያደረገ  እንቅልፍ የተኛ የሚመስል ሰው ፍሪጅ ውስጥ ይታያል.. ..አባቷ ነው ….የሰላም አባት..አሁን የሆነ ነገር የገባት ነው..ልጅቷ እንደጠረጠረችውም  አደጋ ላይ ነች…ሰላም አባቷን አጥታለች..ሰላም አባቷን መሬት ውስጥ ቀብራ ለዘላላም ለመለየት ድፍረቱንም ጭካኔውንም ለማግኘት አልቻለችም….
/////
ነገሩን በዝርዝር ለመረዳት  አምስት ቀን ወደኃላ እንመለስ 
እንደማንኛውም ቀን እየተጎራረሱ እራት በሉ…እያተሳሳቁ ዜናና ፊልም አዩ…አራት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታቸው አመሩ….ሰላም አባቷን መኝታ ቤት አስገብታ እንዲተኙ ካደረገች  በኃላ ግንባራቸውን ስማ ተሰናብታ ወደመኝታዋ ልትሄድ ስትል

‹‹ሰላሜ››ሲሉ ጠሯት

‹‹አቤት አባ›››

‹‹አብረሺኝ ተኚ››
ዘላ አልጋው ላይ ወጣችን ብድርብሱን ገልጣ ከውስጥ በመግባት እቅፋቸው ውስጥ ገባች…..ይህ አዲስ ነገር አይደለም..ተለያይተው ከሚተኙበት ይልቅ አንድ ላይ የሚተኙባቸው ቀናቶች የበዙ ነበሩ..ሁለቱም ትንሽ ሲከፋቸው ወይንም አመም ሲያደርጋቸው..ወይንም እንዲሁ ለብቻ መተኛት ሲደብራቸው ዛሬ እኔ ጋር ትተኚ..?ዛሬ አብረሀኝ ትተኛ..? እየተባባሉ አንድ ቀን እሷ ክፍል አንድ ቀን እሳቸው ክፍል ይተኛሉ..እና የተለመደ ነው፡፡
ችግሩ ንጊ ላይ ከእንቅልፏ ባና ከእቅፋቸው ስትወጣ ነበር የተፈጠረው….እጃቸውን ከሰውነቷ ላይ ሳታነሳ በተለየ ሁኔታ ቀዘቀዛት…..ቀስ ብለ ወጣችና አየቻቸው..ጸጥ ያለ ፊት ነበር..ዝም ያለ ፊት…እጇን ወደ አንገታቸው ላከች ….ትንፋሽ አልባ ሆነዋል..

‹‹አባዬ ..አባዬ›› ወዘወዘቻቸው…ጮኸች……..ወደመኝታ ቤቷ  በሩጫ ሄደችና የልብ ማዳመጫ መሳሪዋን አመጣች…ምንም  የለም..?…ጮኸች…ሁሉ ነገር ረፍዶ ነበር..ፀሀይ በጠለቀችበት ቀርታ ነበር…ጨረቃ በደመናው ሙሉ በሙሉ ተሸንፋ ከስማ ነበር…ምጽአት ደርሶ  ነጋሪት እየተጎሰመ እና መለከት እየተነፋ ነበር…..
አባቷ እርግጥ ህመም ላይ ከነበሩ ወራት አልፏቸዋል….ግን እየተንከባከበቻቸው እና በትክክል የህክምና ክትትል እያደረገችላቸው ነበረ…ምንም የተለየ እና ለሞት የሚያሰጋ ምልክት አልተመለከተችም….የት ጋር ነው የተሸወደችው…..?ማወቅ አልቻለችም…፡፡ ለሳዕታት እሬሳውን ላይ ተኝታ ስትነፈርቅ ቆየች…ስልክ ደውላ ለወዳጆቾ ልትናገር ፈለገችና መደወል ከጀመረች በኃላ መልሳ ተወችው

‹‹አባቴን ልቀብር…..?አባቴንም ፈጽሞ አልቀብርም…….ለሳዕታት ካሰበች በኃላ ወሰነች‹‹..አብሬው እሞታለሁ..ግን ለመሞት እስክቆርጥ ድረስ እሱም አይቀበርም›› አለችና…ባላት የህክምና እውቀት በመጠቀም ሬሳው እንዳይበሰብስ አድርጋ በባለመስታወት ፍሪጅ ውስጥ በማድረግ መኝታ ቤት ውስጥ ሬሳውን ደብቃ አስቀመጠች….እና ይሄ ነው የሚያስጨንቃት…እና በዚህ ጊዜ ነበር ኤርምያስ ላዳ ውስጥ የገባችው….ይሄን ችግር ነበር እሱ ሊያውቅና ሊረዳላት ያልቻለው…..በዚህ ከቀጠለች  በጥቂት ቀናት ውስጥ ወይ አዕምሮዋ ተነክቶ ጨርቋን ጥላ ይለይላታል ወይንም እዛው መኝታ ቤት ውስጥ እራሷን አጥፍታ ከአባቷ ጋር ወደመቃብር ትጓዛለች..ከሁለቱ የተለየ የነገ ዕጣ ፋንታ የላትም….
ንስሯ ይዞላት የመጣው ታሪክ ይሄ ነው..በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው…‹‹እና እንዴት ልረዳት እችላለሁ…...?›ስትል እራሷን ጠየቀች፡መቼስ ምንም  ተአምረኛ ብትሆን ከሞተ  አራት ቀን የሆነው እና በፍሪጅ ውስጥ በቅዝቃዜ የደረቀ ሬሳን  ህይወቱን ካሄደችበት መልሳ በማዋሀድ ነፍስ  ልትዘራበት አትችልም…ይሄ የማይቻል ነው… ቢሆንም ቢያንስ ልጅቷ የአባቷን ሞት አምና እንድትቀበል እና እንድትቀብረው…ከዛም እንድትጽናና የሚያስችል አንድ ዘዴ መዘየድ እንዳለባት ተሰማት…አዎ ያንን ማድረግ ትፈልጋለች…
ሀሳቧን ሰብስባ ውሳኔ ላይ ሳትደርስ በፊት የሳሎኗ  በራፍ ተንኳኳ..ግራ ገባት …በዚህ ጥዋት ማን ነው የሚያንኳኳው .. ..?ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሆነም፡፡

‹‹…ማነው..?››ከተቀመጠችበት ሳትነሳ

‹‹እኔ ነኝ ..››

የፕሮፌሰር ድምጽ ነው..ተነሳችና ከፈተችላቸው‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..በጥዋት እንዴት ተነሱ..?››

‹‹አረ ጨርሶውኑም አልተኛሁም…ከሰው ጋር ስለሆንሽ ነው እንጂ  ለሊቱን አብሬሽ ስጫወት ማደር ነበር የፈለግኩት››

‹‹ምነው በሰላም..?››

‹‹እኔ እንጃ ብቻ  ትናፍቂኛለሽ…ከፍቶኛል››

‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..እስቲ ግቡ››

‹‹አሁን አልገባም.. በኋላ ግን እፈልግሻልሁ››

‹‹ለምን አይገቡም..?››

‹‹አይ አሁን እንግዳ ይፈልግሻል››

‹‹ማንን እኔን....?››ግራ ገብቷት 

‹‹አዎ አንቺን››ብለው ከበራፍ ላይ ገለል ሲሉ ከጀርባቸው በአዕምሮዋ ውስጥም የሌለ ሰው ብቅ አለ…አንድ ጥቁር ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሎ አንገቱን ደፍቶ ቋማል..ፕሮፌሰሩ  ወደክፍላቸው ተመለሱ….

‹‹እንዴ መላኩ ..ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ....?ሰሚራን አመማት እንዴ..?››

‹‹አረ እሷስ ደህና ነች››

‹‹ታዲያ ምነው በለሊት....?››እስቲ ግባ ብላ ወደውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ አደረገችው…

‹‹ምን ሆንክ..?››ፊት ለፊቱ ቆማ በገረሜታ እያየቸችው ዳግመኛ የመጣበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ያልሆንኩት ነገር አለ..አሸንፈሻል …ሰሚርን አስመርምሬያታለሁ..ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆናለች..››

‹‹አሪፍ ነዋ .ታዲያ ደስ አላለህም..?››

‹‹አዎ ብሎኛል…››
‹‹እና ታዲያ አሁን ለምን መጣህ..?››

‹‹ስምምነታችንን ላከብር ነዋ..በሶስት ቀን ውስጥ ትተሀት ካልመጣህ ብለሽ ፎክረሻ አድራሻሽን ሰጥተሸኝ ነበር  እኮ..የሆነ ነገር ለማድረግ ኃይል እንዳለሽ አሳይተሸኛል…እንቢ ብዬ በዛው ብቀር ደግሞ ፍቅሬን  መልሰሽ በሽተኛ ብታደርጊብኝስ..?››
👍12010🥰1👏1🎉1
ሳቋ አመለጣት ..ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች……

‹‹ይሄውልህ…››ብላ የውስጧን ልትግረው ስትጀምር ባለ ላዳው ማለት ኤርሚያስ ሆዬ ከመኝታ ቤት ውልቅልቁ የወጣውን ሰውነቱን እየጎተተ ሳሎን ደረሰና ግራ በመጋባትና በድንጋጤ አንዴ እሱን አንዴ እሷን እያየ  ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ በመጋባት ሲዋልል እሷንም ንግግሯን እንድታቆርጥ አደረገት ….

ይቀጥላል



#YouTube ቻናል ላይ ገብታቹ subscribe ብቻ አድርጉ ቤተሰቦች ዛሬ 1000 Subscriber እጠብቃለው 110,000 ቤተሰብ ይሄ ትንሽ ነው አንብባቹ እንደጨረሳቹ ወደ YouTube ሄዳችሁ Subscribe የምትለዋን መጫን ብቻ😘
👇
https://www.youtube.com/@atronose

Follow my channel on WhatsApp 👇👇

https://whatsapp.com/channel/0029VaDdoKaJENxsTyh8E43Z
👍70😱109🥰2🤔2
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
👁ክፍል ሃያ ዘጠኝ👁
🍀🌻🍀🌻🍀🌻🍀
አስተናጋጁ ሰሚር አብላካት አጠገብ ተቀምጦ ፈዞ ቀረ አይምሮው ብዙ ቦታ እረገጠበት ፣አብላካትን ማን ሊረዳት ይችላል ? በየ ቤተህምነቱ እርዳታ ይጠይቁ ወይንስ በመገናኛ ቡዙሃን እንደምንም ብለው ያስነግሩ ፣ ምን ይሻላል እራሱ ጋር ምን ያክል ገንዘብ እንዳለ አሰበ ..በጣም ጥቂት ገንዘብ ነው በባንክ የቆጠበው ምን አልባት ለሦስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት ሊያደርግላት የሚችል ብቻ ነው ከዛስ ...ጭንቅ ብሎት ዞር ብሎ ሲያያት  አየችው እሷም ቢሆን በፍርሃት ተሸብባለች አንድ ነገር እንደሆነች ጠርጥራለች ባይሆንማ ዶክተሩን ባናገሩት ቁጥር እናቷም ሰሚርም እንዲ አመዳቸው ቡን አይልም  ።
"ሰሚ የሆንኩት ነገር ምንድነው ?"አለችው
"አቢ ለዚ ነገር በጣም መዘጋጀት አለብሽ  እእ ማለት አንቺ ጠንካራ ልጅ ነሽ ትወጪዋለሽ እተማመንብሻለው ..."ብሎ ዝም አለ
"ሰሚ እእ በጣም ከባድ ነገር ነው ?እእ ነው አይደል በቃ ገብቶኛል ከእናቴም ከአንተም ሁኔታ ተረድቼዋለው እእእእ" ብላ እንደማልቀስ አለች
"አቢ እባክሽ ጠንከር በይ አንቺ በቀላሉ አትሸነፊም"አላት እንዴት ብሎ እንደሚያበረታት እየከበደው
"ምንድነው ሰሚ ልሞት ነው ?ንገረኝ በቃ ልሞት ነው?"አለችው እንዲነግራት እየገፋፋችው ።በዚ ጊዜ ዶክተሩ ወደ አብላካት መጣ አብላካት የመረመራትን ዶክተር ስታየው ተነሳች በጥያቄ አይን ስታየው  እራሱን ተቆጣጥሮ ሊያበረታት በመወሰን እጇን ያዝ አድርጎ ስላለችበት ሁኔታ ሊያወራት እንደሚፈልግ በመንገር ወደ ምርመራ ክፍሉ ይዟት ገባ......
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሰመረ ከማፊ ገር ተገናኝቶ ምሳቸውን አንድ ሆቴል ውስጥ እየበሉ ቢሆንም ቀልቡ ግን ከሷ አልነበረም ።ማፊ በተደጋጋሚ ደንነቱን እየጠየቀች ታጎርሰዋለች ለደቂቃ መለስ ይልና እንደገና ትክዝ ይልባታል። በዋላ ሲበዛባት "ሄ ምንድነው እሱ ሰላም አይደለህም ? በጣም እየጠፋህብኝ ነው እንዴ አታስጨንቀኛ"አለችው
"ውይ ይቅርታ ስለ ድርጅቱ እያሰብኩ እኮ "ብሎ ዝም አለ
"ምነው ድርጅቱ ምን ሆነ አከሰርከው እንዴ ኪኪኪ"ብላ ሳቀች
"አይ አንዳንድ ደስ የማይሉኝ ሰራተኞች አሉ ስራቸውን በአግባቡ የማይሰሩ "አለ ለማምለጥ ያለው ነገር እንጂ ።አሳቡስ አብላካት ጋር ነበር ።ያቺ ትንሽ ልጅ ስልኬን የማታነሳው በሷ ቤት መጫወቷ ነው ? ወይስ ጌታነህ እንዳለው አግኝቶ ተቆጣጠራት እያለ ሲያስብ ነው የቆየው ።ደጋግሞ ደውሎ ስልክ ስላላነሳች ያለ ነገር አደለም ብሎም ፈርቷል ።
"ቆይ ያን ያክል ያሳስብሃል እንዴ ስለድርጅት ምናምን አንተ እኮ ወጣት ነህ አባትህ ይጨነቅ ፈታ በል ይሄ የኛ ጊዜ ነው መዝናናት ነው ያለብን ድርጅቱ ምንም አይሆንም ሰራተኞቹንም መከታተል አቁም የቻሉትን ይስሩ እንዴ ?"አለች በግድ የለሽ አስተያየት
"ነው ብለሽ ነው እሺ "አላት ከልብ ባልሆነ ምላሽ
"ዛሬ ከኔ ጋር ማደር ትፈልጋለህ ? ከፈለክ ይሄን ውጥረትህን ድራሹን ነው የማጠፋልህ ምን ይመስልሃል ቆንጆ አለችው"ሰመረ ዝምብሎ ሲያያት ቆይቶ ጭንቅላቱን በእሺታ ነቀነቀላት
"ምንድነው አትናገርም ? ኩራት ነው ስማ ይሄን የመሰለ ሰውነት አግኝተህ ነው ። ስንቱ የሚዝረከረክበት እኮ ነው  ላንተ ስለተፈቀደ ልትደሰት ይገባል "ብላ ሰውነቷን ነቅነቅ አደረገች
"እሺ እኮ ነው ያልኩሽ ወደ ስራ ተመልሼ የማስተካክለው ነገር አለ እንደጨረስኩ እደውልልሻለው "አላት
"እንደሱ ነው የሚባለው ቆንጆ ሆኜ እመጣልሃለው "ብላ ወደፊት ተንጠራርታ ከንፈሩን ሳመችው  ሰመረ ደንገጥ አለ ሌሎች ተመጋቢዎች እንደሚያይዋቸው እርግጠኛ ነበር ። ማፊ አፈር ሲል የሚረብሽ ሳቋን ለቀቀችው  ሰመረ ነገረስራዋ እንደገረመው ነው አንዳንዴ የሷ መኖር ደስ ይለዋል ከሆነ ውጥረት መንጭቃ በግድ ታስወጣዋለችና.....
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አስተናጋጁ ሰሚር ከተቀመጠበት ሳይነሳ አብላካት የገባችበትን የምርመራ ክፍል አትኩሮ እያየ ነው ምን አልባት መቋቋም አቅቷት ብትጮህስ  ብሎ ፈርቷል ። የደረሰባት ነገርልብ የሚሰብር ነው እንኳንስ በሷ እድሜ እሱም ይህን ነገር መቋቋም አይችልም ..
ከረጅም ቆይታ በዋላ አብላካትና ዶክተሩ ተከታትለው ወጡ እናም እጇን እየጨበጠ ተሰናበታት አብላካት ዶክተሩን ተሰናብታ በቀስታ እየተራመደች ወደ አስተናጋጁ ሰሚር ስትመጣ  አያትና  ግር አለው አጠገቡ ስትደርስ በረጅሙ ተነፈሰች ።
"አቢ ደና ነሽ"አላት ።አብላካት በፍፁም ተቀይራ ስሜት አልባ ሆናለች አስተናጋጁ ሰሚርን ዝም ብላ ስታየው ቆይታ
"ደና መሆን እንዴት ነው? ኪኪኪኪ በነገራችን ላይ ነብስ ካወኩ ጀምሮ ደና መሆን እንዴት እንደሆነ ግልፅ ሆኖልኝ አያውቅም  እእእእ እናቴን አየሃት "አለችው
"አይ "አለ ዕንባው ኮለል እያለ
"ሰሚ እያለቀስክ ነው ተው በናትህ እረፍ አንተ እንዲ ከሆንክማ ጥሩ አይደለም ። ያው ትንሽ ጊዜም ቢሆን የምኖረው ዝምብለህ አስቀኝ ደስ ይለኛል "አለችው በማፅናናት
"አይ አይ አንቺ ምንም አትሆኚም ነገ እጥበቱን ትጀምሪያለሽ ከዛ የሚረዱን ሰዎች እንፈልጋለን  እና ትድኛለሽ እሺ "አላት እቅፍ አድርጓት
"እሺ ግን ያንን ሁሉ ገንዘብ ከየት እናመጣለን በዛ ላይ ኩላሊት የሚሰጥ ሰው ያስፈልጋል ተው ስለኔ እርሳው ብዙ ተስፋ አታድርግ ሰሚ እናቴን ግን ላንተ ነው አደራ የምሰጥህ ፣በፍፁም እንዳትለያት እሺ "አለችው ቅዝዝ እንዳለች
"ተይ በቃ ዝም በይ ምንም አትሆኚም አልኩሽ ።እኔና መሳይ የሚረዱን ሰዎች እናፈላልጋለን አንቺ ዶክተሩ እንዳለው እረፍት ታደርጊያለሽ እሺ የኔ ቅመም አንቺ ጠንካራ እና በቀላሉ የማትሸነፊ ብርቱ ልጅ ነሽ ይሄን አውቃለው "አላት አስተናጋጁ ሰሚር እያለቀሰ ።አብላካት እንደዛ ሲሆን ስታይ እሱኑ ማባበል ጀመረች እናም ለእናቷ እና ለሱም ስትል መበርታት ፈለገች ። ከውስጥ የመሳይ ቤተሰቦች ካላቹ ወደዚ ኑ የምትለዋን ነርስ ሲሰሙ አብላካትም አስተናጋጁ ሰሚርም በአንድነት ተነስተው ወደተጣራችው ነርስ ቀረቡ ።ነርሷ የአብላካት እናት ወዳለችብት ክፍል በመጠቆም አሁን ደና ነች ገብታቹ ልታናግሯት ትችላላቹ ። ብላቸው ሄደች አብላካት እራሷን ማጎበዝ ጀመረች ስለ እናቷ ........

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍9818🔥9
በ'ነሱ ቤት
🍀🍀ክፍል ሠላሳ🍀🍀
🍀🍀🍀
የጌታነህ ወላጆች ግራ በመጋባት እርስ በእርሳቸው እየተወነጃጀሉ ነው የሰነበቱት ። እናት 'አንተ ነህ ሳት ብሎክ የተናገርከው እንጂ ጌታነህ ከዚቤት አርግዛ ስለተባረረች ሰራተኛ እንዴት ሊያቅ ይችላል በወቅቱ እሱ የስድስት አመት ልጅ ነበር ስለዚ ጉዳይ ሊገባው ወይም ሊያስተውልበት የሚችል አጋጣሚ ሊኖር አይችልም 'አለች አባት በበኩሉ 'በጭራሽ ከኔ ምንም ነገር አልሰማም ይልቅ አንቺ ጓደኞችሽን ሰብስበሽ ማውራት ልማድሽ ነው ።ይሄንንም የልጅሽን ነውር እንደጀብድ አውርተሽ ይሆናል 'ብሎ መልሶ እሷው ላይ ጮኽ ። ብዙ ቃላት ተወራወሩ ብዙ ብዙ ተባባሉ ።
የጌታነህ ወንድም መስፍን በበኩሉ በወንድሙ የስድብ ናዳ ቅስሙ ተሰብሯል ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣትነት ብዙ የራቀ መስሎ ተሰማው ፣በተለይ ደሞ ጌታነህ በጭካኔ 'ዘላለም እንደትልቅ የማትከበር በዚ ዕድሜህ በየ ናይት ክለቡ ከጎረምሳና ከትናንሽ ሴቶች ጋር ስትንዘላዘል አይደብርህም በጉርምስና ጊዜ የቤት ሰራተኞች እየደፈርክ  ኖርክ እሱ አልበቃ ብሎ አስረግዘህ ላንተ ሲባል ሰራተኛዋን ከነእርግዝናዋ አስባረርክ እና አንተ ነህ እኔን ለመቆጣት የተነሳኽው 'ብሎ ሲወቅሰው ከዚ በፊት ተሰምቶት የማያውቅ ስሜት ነበር የተሰማው።እናም በዚ ምክንያት እንደሌላው ጊዜ ከቤት ሳይወጣ ነው የሰነበተው ። የቤት ሰራተኞቹ የዛን ለት ማታ የተፈጠረውን ፀብ በፍፁም አልረሱትም እርስ በእርስ መንሾካሸካቸውን ቀጥለዋል በተለይ የጌታነህን እያንዳንዷን ቃል ሰምተዋታል 'ሆሆሆ ሀብታም ግን ጉዱ ብዙ ነው አንቺ 'ትላለች አንዷ ሌላኛዋ'እእ በደሃ ነብስላይ ገንዘብ አለኝ ብለው ይጫወታሉ ወይ እድላችን ' ሌላኛዋ መልሳ 'በ'ነሱ ቤት ሚስጢር እንደተሸፋፈነች የምትቀር መስሏቸዋል ።ጌታነህ እኮ የሚያቅ አልመሰላቸውም እሰይ እኔ እሱ ተመችቶኛል አጥረገረጋቸው እኮ 'ትላለች ። ብቻ እነጌታነህ ቤት ተቀጥሮ የሚሰራው ከዘበኞች እስከ ቤት ሰራተኞች ወሬአቸው የመስፍን ሴሰኝነት ላይ እና የወላጆቹ ለሱ የመደበቅ ጉዳይ ላይ ነው።የመስፍን ከቤት መውጣት ማቆም ደሞ ሌላው ትኩረታቸውን የሳበ ነገር ነው ።እናም እርስ በእርሳቸው በይ በይ አንቺንም እንዳይጠራሽ እና ጉድ እንዳያደርግሽ ሰሞኑን አድፍጧል ይባባሉና ይስቃሉ መልሰው ። መልሰው ደሞ አይ ተፀፀቷል ምሳ እንኳ ክፍሉ ስወስድለት ቀና ብሎም አያየኝ ።ትላለች ከሰራተኞቹ አንዷ መልሰው ከንፈር ይመጡለታል  አይ ጋሼ መስፍን ምፅፅፅ....
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አብላካት የኩላሊት እጥበቱን ከጀመረች ሁለት ሳምንት ሆኗታል  ገንዘቡን የሚከፍለው አስተናጋጁ ሰሚር ነበር እጥበቱ በተደረገ ቁጥር ሦስት ሺብር መከፈል አለበት ሰሚር በባንክ ያስቀመጠውን ነበር እያመጣ የሚከፍለው  ።እናም ከዚ በዋላም የቀረው ገንዘብ ጥቂት ስለሆነ ጨንቆታል ።የአብላካት እናት ከእመሟ እንዳገገመች ልጇ ያለችበት ሁኔታ ይበልጥ አስጨንቋት እንደ እብድ በየመንገዱ መለፍለፍ ጀምራለች ። ሰሚር በሁለቱም መሃል ሆኖ ለማፅናናት ለማገዝ የተቻለውን ነገር ከማድረግ አልተቆጠበም ። አንዳንድ የሚያውቃቸውን ሰዎች ግድ ማናገር እንዳለበትም ተሰምቶታል ። እናም ስራ ቦታ ለሚያውቃቸው ሁሉ ስለሁኔታው በማስረዳት የተቻለውን ገንዘብ አሰባሰበ  ያገኘው ገንዘብ ለጊዜው እፎይታ ሰጠው  ቢያንስ ለአንድ ወር ያክል ያሳርፋል ግን ከዚያስ እስከመቼ ነው በዚ ሁኔታ የሚቀጥለው።
አብላካት እረፍት ማድረግ ስላለባት ከቤት መውጣቱን አቁማለች ። ጋደኛዋ ሳምራዊት እየመጣች ትጠይቃታለች ፣ልታፅናናት ትሞክራለች ፣ነገርግን ሳምራዊት በባህሪዋ ፎልፏላ ስለሆነች አብላካትን ስታይ ማልቀስ ትጀምራለች የበለጠ አዘን ውስጥ ትከታታለች ። ስትረጋጋ ደሞ ለሰመረ እንድትደውል ትገፋፋታለች ምን አልባት ሊረዳት እንደሚችል ትነግራታለች ።አብላካት ደሞ እኔና እሱ እንዲ የሚያባብል ግንኙነት አልፈጠርንም ለምን ብሎ ይረዳኛል እኔ እንደው ከአሁን በዋላ ለማንም አልጠቅምም ትላለች ። ደጋግሞ ደውሎ አለማንሳቷ ትዝ ሲላት ልደውልለት ይሆን ትልና መልሳ ያለችበትን ሁኔታ ስታይ ይደብራታል ።አቅመቢስነቷን ለማንም ማሳየት አልፈለገችም በቃ የኖርኩትን ያክል ኖሬ ልሙት ።ትላለች የሷ ጭንቀት እናቷ ነች አንጀቷን ትበላታለች ፡ በአሳብ ሰውነቷ አልቋል ።
  ሳምራዊትም አስተናጋጁ ሰሚርም እናቷም ከተለያየ ሰው ገንዘብ መጠየቁን ተያያዙት ፣በተለይ እናትየው በየቤተ እምነቱ መለመን ጀመረች ጎረቤቶቿም ስለጉዳዩ ካወቁ ወዲ በጣም አዝነው ትብብራቸውን አሳዩ ። በዚህም ሁኔታ ገንዘቡ እየተሰበሰበ መጣ ነገርግን በአኪሞቹ የተነገራቸውን ገንዘብ መሙላት አልተቻለም ። ስለዚህም ሳምራዊት በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን ይነገር  አንድ በጎ አድራጊ አናጣም ታዳጊ ናትና ማንም አይጨክንባትም ባለችው መሰረት ። እንደምንም ብለው ሊያስነግሩላት ቆረጡ ። እናም ለመጀመሪያ ጊዜ የአብላካት እናት በቴሌቪዥን መስኮት እያለቀሰች ታየች  ይህም የሆነው አንድ ጋዜጠኛ በሳምራዊት ወንድም በኩል ስለተገኘ እና እሱም ታሪኩን ሲሰማ ሊተባበራቸው ፍቃደኛ በመሆኑ ነበር ። እና የአብላካት እናት ስለ ልጇ ሕይወት ስትል አደባባይ ወጥታ አለቀሰች በተሌቭዥን መስኮት ላይ እየታየች  ልጄን አድኑልኝ ብላ አነባች.........
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የጌታነህ እናት ወደ ሳሎን እየገባች ሳለ  የባለቤቷ ጩኽት ተሰማት ድንግጥ ብላ ባለችበት ቆመች ። መልሳ ምን ሆኖ ነው ብላ ወደባሏ አፈጠጠች ሁኔታውን ስታይ ትኩረቱ በቴሌቭዥኑ ላይ መሆኑን አወቀች ምንም ስላልገባት መልሳ አየችው  ።ጠጋ ስታለው እጁን ብቻ እየጠቆመ አሳያት በቴሌቪዥኑ ውስጥ የምታለቅሰው ሴት በጣም የምታምር ልጅ እያሳየች "እባካቹ አንድ ልጄን አድኑልኝ "ስትል አየች ወደባሏ ዞራ እና በሚል አስተያየት አየችው
"መሳይ እኮ ናት ሰራተኛችን መሳይ.."ብሎ ጮኽ
"ምን !"ብላ አፍጥጣ ቀረች............


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11217🎉2😁1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ልሄድ ነበር››አላት ሚለው ጠፍቶት..አንዴ ኬድሮንን  አንዴ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን መላኩን እያየ

‹‹አይ መኝታ ቤት ተመልሰህ ትጠብቀኝ..አብረን ነው ምንወጣው››

ግር አለው‹‹ይቅርታ አልሰማሁሽም..?››

‹‹እሱን ልሸኝና እመጣለሁ …መኝታ ቤት ተመልሰህ ጠብቀኝ…››

ባለማመን ወደኋላው ዞረና.. ወደመኝታ ቤት ተመለሰ

ከመላኩ ፊት ላይ ግራ የመጋባት  ጥያቄ  ስላነበበች‹‹ባለቤቴ ነው..?›› አለችና  ሳይጠይቃት መለሰችለት….

‹‹እንዴ….ባለቤቴ…ታዲያ እኔን…....?››

‹‹እኔ ለቀልድ ነበር እደዛ ያልኩህ ..የእውነት ታዳርገዋለህ አላልኩም ነበር…..››ከተቀመጠበት ተነስቶ ተንደርድሮ ጉንጯን እያገላባጠ ሞጨሞጫት

‹‹በእውነት በጣም ነው ደስ ያለኝ…በቃ ሁለቴ ህይወት ሰጥተሸኝል….ሰሚርን  አዳንሺልኝ አሁን ደግሞ ነፃነቴን ስትሰጪኝ››

‹‹አይ ግድ የለም››አለችና ከእቅፉ እየወጣች…ጭምቅ አርጎ ሲያቅፈትና ሲስማት መተንፈስ አቅቶት ነበር…በቃ በሽታዋ ሁሉ ሊነሳባት እና ሀሳቧን ልትቀይር ትንሽ  ነበር የቀራት….. 

እንደመደንገጥ አለና ወደመኝታ ቤቱ ገልመጥ በማለት ሲስማት ማንም እንዳላየው ለማጣራት ሲሞክር በቆረጣ አይታ ለራሷ ፈገግ አለች   ..‹‹በቃ ልሂድ.. ሌላ ቀን ከሰሚር ጋር መጥተን እንጠይቅሻለን ….በቃ ዘመድ እንሆናለን..››እያለ ይዞ የመጣውን ሻንጣ ይዞ ለመሄድ አንጠልጠሎ ተዘጋጀ፡፡

‹‹ሰላም በልልኝ..ግን እኔን ለመጠየቅ አትልፉ.. ዛሬ ለሊት ወደውጭ ልበር ነው….››ስትል ዋሸችው

‹‹ዉይ !!!ምነው?በሰላም..?››እንደመደንገጥ ብሎ፡፡

‹‹አይ በሰላም ነው …ቤተሰብ እዛ ስለሆነ እዛ ለመኖር ነው››

‹‹እሺ በቃ እግዜር ካንቺ ጋር ይሁን …ዕድሜ ልክ ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታሽ አለብኝ ››እያለ ሳሎኑን ባለማመን  ለቆ ወጣ……

‹‹ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈልኩልህ ብታውቃው..ባንተ ምክንያት ይህቺን አለምና ንስሬንም ጭምር እንደአጣሁ ብትሰማ›› ስትል አሰበች

….ይህን ሁሉ ልትነግረው ያልፈለገችው ቢያንስ በስተመጨረሻ ጥሩ ልሁንለት ብላ ነው ….በፀፀት ያልደፈረሰ የፍቅር ህይወት ይገባዋል ብላ ስላሰበች ነው….አሁን  የእነሱን ሰሚራ ለማዳን የሆነችውን እና  ያጣችውን ዘርዝራ ባታወራው ከማዘን በስተቀር ለእሷ ምንም አይፈይድላትም..በእሱ ህይወት ላይ ግን ቁጭትን ይፈጥርበታል…..ደስታው ላይ ደመና ያጠላል…. ያንን አስባ ነው እውነቱን የደበቀችው፡፡
/////

ሀሳቧን ሰብስባ ቀጥታ ወደመኝታ ቤቴ ሄደች…. ስትደርስ ባዶ ነው..ግራ ገባት….‹‹ እንዴ በጓሮ በር ሾልኮ ፈረጠጠ እንዴ..? ››ብላ ሳታሰላስል ከሻወር ቤት የውሃ መንሾሾት ድምጽ ሰማችና ወደ እዛው ሄደች..ደረሰችና ብርግድ አድርጋ  ከፈተችው…. ድንገት መሳሪያ እንደተደቀነበት ምርኮኛ ኩም ብሎ ደነገጠ..እጆቹን የተንዘላዘለ እንትኑ ላይ ሸፈናቸው….
‹‹አረ ልቀቀው ..ለሊቱን  እስክጠግብ እኮ ሳየው ነው ያደርኩት››

‹‹እብድ ነሽ..አስደነገጥሸኝ እኮ …››አለና ቀስበቀስ ለቀቀው
‹‹ህፃን ሆነህ እናትህ በቂቤ በደንብ ያሹልህ እና ይጎትቱልህ ነበር እንዴ..? ›› 

‹‹‹ምን እንዲሆን ነው የምትጎትትልኝ..?››

‹‹እንዲህ እንዲንጀላጀል ነዋ….ሜትር ከምናምን እንዲሆንልህ››

‹‹ትቀልጂያለሽ..ቆይ ማን ነበር ሰውዬው… ውሽማሽ መስሎኝ እኮ ተበላሁ ብዬ ነበር››

‹‹አይደለም ዘመዴ ነው…እንዴት ነው እኔም አወላልቄ ልግባ እንዴ..?››

‹‹ወዴት....?››

‹‹ወደሻወር ነዋ..እጠበኝ ልጠብህ››

‹‹ኸረ በፈጠረሽ..ስወደሽ እንዳታደርጊው››

ሳቋ አመለጠት‹‹እንዴ !!ይሄን ያህል…...?››

‹‹እንዴ…እሳት እኮ ነሽ…እኔ እንጃ የዛሬ ወር ድረስ ተከፍቶ ባገኝ እንኳን ለመክደን አልሞክርም…እንዴት እንዴት አይነት የወሲብ ጥብብ ነው..የሆነ ህልም ውስጥ እኮ ነው ያስገባሺኝ..በአየር ላይ ሁሉ እየተንሳፈፍኩ ይመስለኛል…አሁን ሳስበው ደግሞ እንዴት በአየር ላይ መንሳፈፍ ይቻላል እላለው....?ከግድግዳ ጋር ግን እዳጣበቅሺኝ በእርግጠኝነት አውቃለሁ..ግን አጥንቶቼ ስብርባራቸው ለምን እንዳልወጣ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ…ብቻ ግራ ተጋብቻለሁ.፡፡እኔ በህይወት ፍቅር እንጂ ያጣሁት የወሲብ ችግር ገጥሞኝ አያውቅም….ቁጥራቸውን ከማላስታውሳቸው ሴቶች ጋር ወሲብ ፈጽሜያለሁ..በአንድ ለሊት ስድስት ሰባቴ …ግን ከንቺ ጋር ያደረኩት አንድ ዙር ወሲብ እድሜ ልኬን ከደረኩት ጋር የማይነፃፀር እና የተለየ ነው››

‹‹ወሲብ ደጋግመን የምፈፅመው ለምን እንደሆነ ታውቃልህ..?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ ግን ስገምት ..ለኮፍ ለኮፍ ከሆነ ወዲያው ወዲያው ያምርሀል…በሁለት ደቂቃ በራፍ ላይ ደፍቶ ተልኮውን የሚያጠናቅቅ  ሰውና በ20  ደቂቃ  ውስጠ ውስጥ በርብሮ ግዳጁን ያጠናቀቀ እኩል መልሶ አያሰኛቸውም….ለዛ ነው ››
‹‹ይሁንልሽ ››አለና የሻወሩን ውሃ ዘግቶ… ፎጣውን አገለደመና ከሻወሩ ቤት ወጣ …ተከተለችውና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለች፡፡

‹‹እሺ ቁርስ ትጋብዘኛለህ አይደል..?››አለቸው

‹‹አንቺን ለመሰለች ቆንጆ እንኳን ቁርስ አራሴንስ ብጋብዝሽ ቅር አይለኝም..››

‹‹እራስህንማ  እንዴት ልትጋብዘኝ ትችላለህ…..?››

‹‹ለምን አልችልም..?››ሲል ጠየቃት  ኮስተር ብሎ

‹‹እኔ ልቡን ለሌላ ሰው ጠቅልሎ ያስረከበና ቀፎውን ብቻ ያለ ሰው ምን ያደርግልኛል…....?››

‹‹አይ የምታወሪው ስለ ሰላም ከሆነ ተስፋ  ቆርጬያለሁ….አሁን የምፈለገው ምን እንደሆነች ብቻ አውቄ ልረዳት ነው…ያንን ማድረግ  ከቻልኩ ይበቃኛል…ካዛ….››

‹‹ከዛ ምን…..?››

‹‹እኔ እንጃ… የላዳ ሹፌር ነው ብለሽ ካልናቅሺኝ በጣም ነው ያፈቀርኩሽ..?››

‹‹ያፈቀርኩሽ ስትል..?››
‹‹ያፈቀርኩሽ ነዋ..በጣም ነው የተመቸሺኝ ….የሆነ የማላውቀውን አለም ነው ያሳየሺኝ…ላጣሽ አልፈልግም….››

‹‹ስለእኔ ምንም እኮ አታውቅም....?››

‹‹ማወቅ አልፈልግም..አንቺ ብቻ እሺ በይኝ እንጂ…..››ንግግሩን ሳይጨርስ ንስሯ እየበረረ የመኝታ ቤቱን በር በርግዶ  በመግባት  እንደቀናተኛ አባ ወራ አልጋ ላይ ተኮፍሶ  ጉብ አለ….

ይሄንን በድንገት ያየው ባለ ላዳው ከተቀመጠበት በርግጎ ወድቆ ነበር..

‹‹አይዞህ አይዞህ…›››ሳቋ እያመለጣት
‹‹አይዞህ….!!›

‹‹የማታው ንስር አይደል..?››

‹‹አዎ ነው››

‹‹ምን ይሰራል  እዚህ..?››
‹‹እዚህ ምን ትሰራለህ ..?ብሎ መጠየቅ ያለበት እሱ ነው..ምክንያም እሱ የገዛ ቤት ውስጥ ነው ያለው››

‹‹ማታ የእኔ ነው ያልሺው እወነትሽን ነው እንዴ..?››

‹‹አይ የእኔ አይደለም..እኔ ነኝ የእሱ….››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ይገባል..››እያለ ልብሱን መልበስ ጀመረ……..
‹‹ሰላምን እንድትረዳት ልናግዝህ እንችላለን››አልኩት  

‹‹ልናግዝህ ስትይ....?አንቺና ማን..?››

‹‹እኔና ንስሬ››

ፈገግ አለ….‹‹ትቀልጂብኛለሽ አይደል..?››

‹‹የምሬን ነው…›

‹‹አንቺ እሺ ይሁን …ይሄ እንስሳ እንዴት አድርጎ ነው የሚረዳኝ..ደግሞስ አንቺስ ብትሆኚ በምን መልኩ ልትረጀኝ ትችያለሽ .. ..?እኔ እንኳን ገና ችግሯን  ማወቅ አልቻልኩም››
👍11015😁4👏2😱2👎1
‹‹እኔ ግን  አውቄያለሁ››
ሱሪውን ለብሶ ከላይ እራቃኑን እንደሆነ አጠገቡ ያለ ወንበር ላይ ቁጭ አለ‹‹እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…..?እንኳን የእሷን  ታሪክ ይቅርና እኔን  ካወቅሽ እራሱ 24 ሰኣት አልሞላውም››
‹‹የፈለኩትን ነገር ማወቅ እችላለሁ…ንስሬ ከረዳኝ የፈለኩትን ነገር….››

‹‹አላምንሽም››

‹‹እሺ ጥቂት ደቅቃ ታገሰኝ ››አልኩና ወዲየው ትኩረቴን ወደንሰሬ በመመለስ ከአዕመሮው ጋር ተቆራኘው…..ለሶስት ደቆቃ ከቆየሁ በኃላ

‹‹እሺ ስማኝ …እንድታምነኝ አንተ ብቻ የምታውቀውን የራስህን ሚስጥር ነግራሀለው….ደቡብ አፍሪካ ለ2 ወር ታስረህ ነበር….ከሶስት ሴቶችና ከእንድ ተካልኝ ከሚባል ልጅ ጋር በደባልነት አንድ  ቤት ውስጥ ትኖሩ ነበር…ከሶስቱ ሴቶች  መካከል  ሁለቱን ሴቶች ታወጣቸው ነበር…..››

‹‹በቃ በቃ…..››

‹‹ያው እንድታምን ብዬ ነው…..››
‹‹አመንኩ እኮ …አደገኛ ጠንቆይ ነሽ….ምክንቱም ይሄንን ታሪኬን ለማንም ተናግሬ አላውቅም ..በተለይ የሁለቱ ሴቶችን ጋር ያለኝን ግንኝነት››

‹‹ምክንያቱም መንታ እህትአማቾች ስለሆኑ ትክክለኛ ስራ እንዳልሰራህ ስለሚሰማህ እና ፀፀት ስላለብህ..››ብላ ጨመረችለት፡፡

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…ግን አሁን ሰላም ምንድነው ችግሯ..ከፍቅረኛዋ ጋር ተጣልታ ነው…..?››

‹‹ፍቅረኛ የላትም….ማለቴ በፊት  ነበራት… ከተለያዩ ግን  አመት አልፏቸዋል…እረስታዋለች››

ፈገግ አለ‹‹ይሄንን በመስማቴ ደስ አለኝ….እሺ ሌላ ታዲያ ምን ሆና ነው…..? ስራ ተበላሽቶባት ነው..?››
‹‹ያለችበትን ችግር ምትገምተው አይደለም..››

‹‹እሺ ንገሪኛ..? ››

‹‹አባቷ ሞቶባት  ነው..››

መጀመሪያ ተደናግጦ ከተቀመጠበት ተነሳ..ከዛ መልሶ ቁጭ አለ..ለደቂቃ ተከዘ

‹‹እስከአሁን ያልሺው ሁሉ ትክክል ነው..ይሄ ግን የማይመስል ነው..አልነገርኩሽም እንዴ አንድ ሰፈር እኮ ነው የምንኖረው ..ዕድራችንም አንድ ነው….ቢያንስ እኔ ባልሰማ እናቴ ሰምታ ትነግረኝ ነበር..በዛ ላይ   እሷን የሀዘን ልብስ ለብሳ አያት ነበር ….››
‹‹አባቷ እንዲቀበሩባት ስለማትፈልግ ..መኝታ ቤቷ ውስጥ እንዳይበሰብሱ በማድረግ  ድብቃቸዋለች››

‹‹እንዴ!!!! ታዲያ ዝም ትያለሽ እንዴ....?እራሷን ብታጠፋስ....?ይሄንን ሁሉ ቀን የአባቷን እሬሳ ታቅፋ ለብቻዋ ስታድር ጄኒ ቢያጠናግራስ .. ..?እንዴ በቃ ብታብድስ…..?››ይሄን ሁሉ ሚናገረው በጥድፊያ ልብሱን እየለበሰና በተመሳሳይ ጊዜ ወደውጭ እየተንደረደረ ነው….እሷም ከኃላው  ኩስ ኩስ እያለች   ሚለውን ታዳምጣለች…

‹‹እውነት ከሆነ በጣም ነው የማዝንብሽ…..እንዳወቅሽ ልትነግሪኝ ይገባ ነበር…አንድም ሰከንድ ማባከን አልነበረብሽም ..አባቷን እንዴት እንደነፍሷ እንደምትወዳቸው ብታውቂ እንደዚህ ቸልተኛ አትሆኚም ነበር….››ወቀሳውን ሳያቆርጥ ከግቢው ወጥቶ በእግሩ ሊነካ ሲል…

‹‹ና በመኪና ላድርስህ….››ስትለው በደመነፍስ ተከተላትና ማጉረምረሙን ሳያቆርጥ  መኪና ውስጥ ገባ….ሞተሩን እስነስታ መንዳት ጀመረች..ፀጉሩን ይነጫል ….ጨንቅላቱን ይቀጠቅጣል..ከንፈሩን ይነክሳል
‹‹እንዲህ ከሆንክማ እንዴት ልንረዳት እንችላልን....?››አለችውት የእሱም ከቁጥጥር ውጭ መሆን አሳስቧት

‹‹እንዴት ልሁን ታዲያ …..?ሳለምዬ የአባቷን ሬሳ ታቅፋ አምስት ቀን ብቻዋን ባዶ ዝግ ቤት ውስጥ አድራለች እያልሺኝ እኮ ነው…››

‹‹እኮ አሁን ካለችበት ሁኔታ ይልቅ ወደፊት የሚከሰተው ነገር ይበልጥ ይጎዳታል… ስለዚህ እንዴት ልንረዳ እንደምንችል ለማሰብ ያንተ መረጋጋት ያስፈልጋል እያልኩህ ነው››

‹‹እሺ ንጂው…በእግዚያብሄር ፍጠኚ …ደግሞ ንስርሽ ከኃላ እየተከተለን ነው››

‹‹አዎ እሱ በጣም ያግዘናል…››

‹‹በፈጠረሽ …ምንም ነገር እንድትሆንብኝ እልፈልግም›››

‹‹አይዞህ…. ምንም አትሆንብህም…››

ከ25 ደቂቃ በኃላ ሳሪስ ደረሱ ..መኪናውን አቁመው ወደበራፍ  በመከተታል ተንደርደረው ደረሱ... ንስሯ ቀድሞ ግቢው ውስጥ ገባ..መጥሪያውን ተጫኑ..ደጋግመው  ተጫኑ…. እጃችን እስኪዝል በየተራ አንኳኩ ..ከውስጥ ከፋች ሊመጣ አልቻለም..

‹‹ትግስቴ አልቆል…  የግንቡን አጥር ዘለዬ  ልገባ ነው….››አላት በጭንቀት 

‹‹ግንቡ ላይ የተሰካውን የጠርሙስ ስብርባሪ እንዴት አድርገህ ታልፈዋለህ..?››

‹‹የራሱ ጉዳይ…የቆራረጠኝን ያህል ይቁረጠኝ… ››

‹‹ቆይ የተሻለ ዘዴ አለኝ ››አለችው
‹‹ምንድነው....?››

ንስሯን ጠራችው … ከገባበት ግቢ እየተመዝገዘገ መጣና  የፈለገችውን ሳትነግረው በመረዳት የለበሰችውን ልብስ አንገቷ አካባቢ በመንቁሯ ይዞ እያሽከረከረ ወደአየር ላይ ይዞት በመውጣት አጥሩን አሻግሮ ጊቤው ውስጥ ወለል ላይ አሳረፈት…  ከውስጥ የተቀረቀረውን በራፍ  ከፈተችለት…ኤርምያስ ተንደርድሮ ገባ..

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው....?ምንድነሽ አንቺ..?›› እያለ ገፍትሯት ወደሳሎን ሮጠ… ሊያንኳኳ ሲሞክር ብርግድ ብሎ ተከፈተለት..ተከትላው ገባች..ወደየት እንደሚሄድ ግራ ገብቶት ሲደነጋገር ቀደመችውና ወደመኝታ ቤቱ አመራች..ምክንያቱም ቅድም ንስሯ በምናብ  እቤቱን በደንብ ስላስቃኛት ስለነበር  ታውቀዋለች..፡፡

መኝታ ቤት ሲገቡ …ሰላም ወለል ላይ ተዘርራ ግንባሯን ግዙፉ ፍሪጅ ላይ እስደግፋ በአንድ  እጇ የመጠጥ ጠርሙስ ጨብጣ በሌላ እጇ  የተለኮሰ ሲጋራ  ወደ ከንፈሯ በመላክ ወደውስጥ እየመጠጠች  ጭሱን  ወደውጭ እያትጎለጎለች  ትታያለች  …ከጎኖ 10 ሜትር የሚሆን የተጠቀለለ ሰማያዊ ሲባጎ ገመድ ይታያል….. ኤርምያስ ከእሷ ቀድሞ እሷንም ተራምዶ ወደፍሪጁ ሄደና ውስጡ ያለውን አየ…….

ወደኬድሮን በመዞር  ‹‹…እውነትሽን ነው…..››በማለት ከወገቡ ሽብርክ ብሎ ሰላም ጎን ወላሉ ላይ ተዘረፈጠ..እሷ በቃ ትንኝም በአካባቢዋ ያለ አልመሰላትም.. ፍጽም ደንዝዛለች…ጭርሱኑ ጠፍታለች…..

ይቀጥላል


አሁንም #YouTube ላይ እየገባቹ subscribe አድርጉ ባለፈው 1000 ሰው subscribe ያረጋል ብዬ 5 ሰው አድርጓል ብዙ ነው አይደል😃 እሺ ዛሬ 995 ሰው እጠብቃለዉ YouTube ሄዳችሁ Subscribe የምትለዋን ብቻ እየተጫናቹ መድረግ ባትችሉ እንኳን እዚሁ Telegram ላይ ለሌሎች እንዲደርስ #Share አድርጉ
👇
https://www.youtube.com/@atronose

Follow my channel on WhatsApp 👇👇

https://whatsapp.com/channel/0029VaDdoKaJENxsTyh8E43Z
👍12814😢8😁4
🌻በ'ነሱ ቤት🌻
🍀ክፍል ሠላሳ አንድ🍀
🍀🌻🍀🌻
የጌታነህ እናት ወይዘሮ ገነት የምትሰራው ነገር ግራ እስኪገባት ድረስ ሆነች። አንዴ በቴሌቭዥን የምታያት የቀድሞ የቤት ሰራተኛዋ መሳይ በዕንባ ታጅባ የምታደርገውን የእርዳታ ጥሪ ልቧ ተሰብሮ ታያለች ቀጥላ ባለቤቷ ከወዲያወዲ እያለ ።'አይ ውርደት አይ መዋረድ ሰሞኑን ያለምክንያት አደለም እዚ ቤት እሳት እየነደደ ያለው ፈጣሪ የሰራነውን ስራ እንድናይ ሊያደርገን ነው ተመልከች አጥያታችን ፈጦ ወጣ "አላት ። ወይዘሮ ገነት ባለቤቷ ከሚናገረው ነገር ይልቅ ። መሳይን ስታባርራት የነበረውን ሁኔታ በአይምሮዋ እያመጣች ማመላለስ ጀመረች ፣በወቅቱ ምን ያክል ጭካኔ እንዳሳየች ሲሰማት በራሷ አፈረች፣የልጇን ብልግና ለመሰወር ብላ አንዲት ቆንጆና ምስኪን ታዳጊ ልጅ ውሻ አድርጋ ከልጇ ዞር እንዳደረገች የታሰባት ዛሬ ነው ። አጠገቧ ባገኘችው ሶፋ ላይ ዘጭ ብላ በመቀመጥ ጭንቅላቷን በሁለት እጆቿ ይዛ በፀፀት ተንገበገበች ፣  ባለቤቷ ቁጣ ቁጣ እያለው"ይሄ የማይረባ ልጅሽ ምን ያክል ወንጀል ሲያሰራን እንደነበር አስተዋልሽ ዛሬ ፣እ ሁሌም ዕፀፁን ለመደበቅ ትታገይለት ነበር ተመልከች እንዳልጠቀምሽው ። በአርባ አመቱ እንኳን ሰው መሆን አቅቶት ዛሬም ጥፋት እያጠፋ ቀሚስሽ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል ።እውነቱን ነው ጌታነህ ዘላለሙን የማያድግ ልጅ ነበር ስታሳድጊ የነበርሽው "ብሎ ጣቱን ወደሷ ቀሰረ። ወይዘሮ ገነት በንዴት ተነስታ ቆመች"ምን እያልክ ነው አንተ እራስህን ነፃ ማውጣትህ ነው።አንተ አይደለህ እንዴ ወንዶች ልጆችህን መክረ ዘክረህ እንደ አባትነትህ ማስተካከል የነበረብህ ፣ ነገር ግን ያንን እያደረክ ነበር ወይ ?በፍፁም ፣ ከዛ ይልቅ ባጠፉ ቁጥር ከመገሰፅ ይልቅ ምን ነበር የምትለኝ 'ልጅሽን ስርሃት አሲዢ 'ልክ ያንተም አላፊነት እንዳልሆኑ ሁሉ !እንግዲ እኔ የጠቀምኳቸው መስሎኝ ራርቼላቸው ይሆናል ፣ አንተ ግን በነሱም ሆነ በኔም ሕይወት ላይ ትልቁን ድርሻ መውሰድ ነቀረብህ !ታውቃለህ እኔም ብሆን አንተን ሳገባ ያን ያክል በዕድሜ የበሰልኩ አልነበርኩም"ብላ ተንጣጣችበት ። ባለቤቷ የራሱን አሳብ በንዴት ሊናገር ሲል ። ልጃቸው መስፍን ድምፅ ሰማው ብሎ ወደሳሎን መጣ "እማዬ ምንድነው ጩኽቱ ሰላም አይደላችሁም?!"ብሎ ጠየቀ
"ምን ሰላም አለ አንተ እያለህ"አለው አባቱ ቱግ ብሎ
"ስርሃትህን ያዝ አንተ ሰው አትጩኽበት አንዴ የፈሰሰ ውሃ ይታፈስ ይመስል ይልቅ መፍቴሄ ብታመጣ ይሻላል"አለች ወይዘሮ ገነት ለልጇ እየተከላከለች ።መስፍን ድንብርብር ብሎ አባቱን አየው ።ሰሞኑን ደሞ ሁሉም ነገር እኔላይ ነው እንዴ የተነሳው አለ ለራሱ።
"ምን አጠፋው ደሞ ሳምንቱን ሙሉ ከቤት አልወጣውም ...."ብሎ ሊቀጥል ሲል
"በመጀመሪያ ደረጃ አንተ ለጥፋት መውጣት አይጠበቅብህም እዚሁ የምታጠፋቸው ስላሉልህ ። ሲቀጥል ደሞ ቀድሞ ያጠፋሃቸው ጥፋቶች ቤትህ ድረስ ሊመጡልህ ስለሚችሉ ውጪ መውጣት አይጠበቅብህም! ችግሩ ያንተን ስእተት ችግር ማስተካከል ያለብን ዛሬም እኛ መሆናችን ነው እንጂ!"ብሎ ተቀመጠ። ወይዘሮ ገነት በባሏ እየተናደደች ።መስፍንን እጁን ይዛ ወደክፍሉ ሄደች እራሴው አረጋግቼ የተፈጠረውን እነግረዋለው ፣ አለዛ ልጄ በሰሞኑ ሁኔታው እራሱን ሊያጠፋም ይችላል አለች..........
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መሳይ አስተናጋጁ ሰሚርም የአብላካት ጓደኞችም አሰባስበው አምጥተው የሰጧትን ገንዘብ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆና ደጋግማ ትቆጥራለች ፣ የገንዘቡ አለመሙላት ልጇን በየቀኑ እንደሚገልባት ተሰምቷታል። አብላካትን ዞራ ተመለከተች በፀጥታ ተኝታለች ትንፋሿ እንኳን ጎልቶ አይሰማም ። መሳይ አዘነች ምነው ፈጣሪ ይሄን ሁሉ ነገር በኔ ላይ አመጣህብኝ ? ከልጅነቴ ጀምሮ አንድም ቀን ከአሳብ እና ከችግር ከአዘን እንዳልላቀቅ ማነው የረገመኝ ምንስ ባጠፋ.....
አብላካት ተኝታ እያለመች ነው ፍፁም ፀጥ ያለ ና ማንም የማይታይበት አውላላ ሜዳ ላይ ቀስ እያለች እያዘገመች 'ሰው ሁሉ የት ሄዶ ነው ፡እሺ ሰውስ ባይኖር አንዳንድ እንስሳቶች እንኳ አይታዩም እንዴ ኡፍፍፍፍ እንዴት ደክሞኛል ደሞ  'እያለች ትጓዛለች ሄዳ ሄዳ አንድ ወንዝ ጋር ደረስች ለመጠጣት አስባ ዝቅ ስትል በውሃው ውስጥ የሚርመሰመሱ ትላትሎች አይታ በድንጋጤ አፈገፈገች ። እናም በሌላ አቅጣጫ መጓዝ ስትጀምር ደረቅ እና ቢጫ ሰአር የወረረው ስፍራ ደረሰች የሰአሩ መጠውለግ አሳዘናት በቃ እዚ አካባቢ ዝናብ አይጥልም ማለት ነው ብላ አሰበች ። መንገዷን ቀጥላ ወደፊት ስትሄድ ቢጫው ሰአር እየረዘመ እየረዘመ መጣ ለመራመድ ሲያስቸግራት ከፊቷ የተጋረደውን ሳር ገለል ስታደርገው ፊትለፊቷ ሰመረ ቆሞ አገኘችው ። በዚ ጊዜ በደስታ ተፍለቀለቀች ።ሰመረ ግን ምንም አይነት ፈገግታ ሳያሳያት  ወደዋላዋ እየጠቆመ
"የት እየሄድሽ ነው ተመለሺ "አላት
"እንዴ ወደቤቴ ነዋ"
"አይ አይ ቤትሽ ወደዚ አይደለም በይ ተመለሺ"
"ግንኮ "
"ነገርኩሽ ነይ እኔው እወስድሻለው "ብሎ እጇን እየጎተተ ወደዋላ መለሶ ይዟት መሄድ ጀመረ
"እሺ አትጎትተኝ ቀስ እያልን መሄድ አንችልም ?በዛላይ የምነግርህ ነገር ነበረኝ "
"ንገሪኝ እሰማሻለው"
"እሺ ግን አንዴ መቆም እንችላለን "
"እሺ ነይ ብሎ ወደራሱ አስጠጋት"
"እ እኔ በጣም በጣም አፈቅርሃለው ይሄንን ሳልነግርህ ሩቅ ቦታ ልሄድ ነበር እኮ"
"እንዴ እኔን ጥለሽማ በፍፁም አትሄጂም ።ደሞ እኔም አፈቅርሻለው እኮ ሚጣ"
"ሚጣ አይደለውም !አብላካት ነው ስሜ !ድጋሚ ሚጣ እንዳትለኝ "
"እሺ በቃ "ብሎ እቅፍ አድርጎ ሊስማት ጠጋ ጠጋ ሲላት አንዲት አሞራ መጥታ በመሃላቸው ብር ብላ ስትገባ 'ዋይ 'ብላ ብንን አለች
  መሳይ በፍጥነት ወደልጇ ተጠግታ ግንባራን እያሻሸችላት "የኔ ውድ አይዞሽ ህልም ነው ፣መጥፎ ህልም አይተሽ ነው እኔን  እኔ ልሳቀቅ ዓለሜ አይዞሽ እስከመጨረሻው አልለይሽም "አለቻት
"እማ የኔ ውድ እናት ያን ያክል የሚያሳስብ አይደለም ህልም ህልም እላለው "አለቻት እና ወደ እናቷ አቅጣጫ በመዞር ጥቅልል ብላ ተኛች ።ወዲያው በአሳቧ ወደ ሰመረ ገሰገሰች በህልሟ የተሰማት የተለየ ስሜት ገርሟታል እውነት ከሰመረ ጋር በውንም እንዲ ይሰማኝ ይሆን ?  ልቧ እንደ አዲስ ለሰመረ ሲመታ አዘነች ።ሰመረን እንደፈለገችው ሳታገኘው ስሜቷን ሳታጋራው ወደ ማይቀረው መሄዷን ስታስበው በአልጋዋ ላይ እንዳለች ተቁነጠነጠች ።ሁኔታዋንስትከታተላት የነበረችው መሳይ ይህንን ከማይ ብላ እናም ዕንባዋም ሊመጣ ሲታገላት መጣው ብላት ወጣች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጌታነህ በስንት ጊዜው እንየውን አግኝቶ የጦፈ ወሬ ይዘዋል ።ጌታነህ ስላሳለፈው ነገር እየነገረው እንየውን በሚያስቀውም በማያስቀው ያስቀዋል ። ስለሰመረም ትንሽ አሜት መሰል አውርተው ቦጨቁት ።ሰመረ የተቀየረባቸው ያቺን ትንሽ ልጅ አብላካትን ካገኘ ጀምሮ እንደሆነ አወሩ መልሰው ደሞ መራራቃቸው ከዛ ቢጀምርም ።ልጅቷናት ለማለት አይቻልም በሚለው ደሞ ተስማሙ ። በዛውአጋጣሚ  እንየው እሷን ልጅ እጅህ ማስገባቱ አልሆን አለህ አይደል ብሎ ጀመረው ይሄን ጊዜ የጌታነህ በህልህ የተሞላ ልብ ድጋሚ ተነሳሳ እናም የሆነ ያልሆነ ውሸት ከነገረው በዋላ ።ወደ አብላካት ደወለ ይጠራል ብዙ ጊዜ ሞክሮ ስልኳ ዝግ ነበረ ዛሬ ስለሰራለት ደስ አለው 'አንሺው አንቺ ትንሽዬ በቀቀን "አለ ስልኩ ቢጠራም አልተነሳም አቅበጠበጠው  በጣም ስሜታዊ ሆኖ  ሚሴጅ ፃፈላት "አንቺ ፈልፈላ ለምንድነው ስልኬን የማታነሽው ካንቺ ምን ፈልጌ መስሎሽ ነው 
👍8610🔥1👏1
አመዳም የደሃ ልጅ አመድሽን ላራግፍልሽ ነው እኮ ያልኩሽ " ብሎ ሴንድ አለው እና ተመልሶ እንየው ጋር ሄዶ ተቀመጠ ፣በጣም ስለተናደደ እንየው የሚለውን መስማት አቆመ ። በዚ አጋጣሚ አስተናጋጁ ሰሚር መጥቶ አጠገባቸው ሲቆም ጌታነህ አይቶት "ደብል ውስኪ "አለው
"እንዴ ሳንበላ ደሞ በቀን"አለው እንየው
"ፈለኳ ተሎበል አንተ ደሞ "አለው አስተናጋጁ ሰሚር እነ ጌታነህ በመምጣታቸው ተደስቶ ነበር የመጣው ይምጣ ስለ አብላካት ሁኔታ ነገሮ እርዳታቸውን ለመጠየቅ ቆርጦ ነበር ።ከሁኔታው ግን ሲረዳ ጌታነህ ተናዷል በዚ ሁኔታ ለማናገር በመፍራቱ ተወው  እናም ወደ ትህዛዙ ሄደ ።
ጌታነህ በንዴት ውስጥ ሆኖ ስልኩን ጠረቤዛው ላይ ሲያሽከረክር ሳለ ሜሴጅ ገባ አቢ ይላል በደስታ ሚሴጁን ሊያነብ ሲል ስልኩ ጠራ እናቱ ነበረች የእናቱን ጥሪ ዘግቶ የአብላካትን መልስ ማንበብ ጀመረ " አትጨነቅ እኔ መንገደኛ ነኝ ያንተ ገንዘብ አያስፈልገኝም መልካም ነገር ሁሉ እመኝልሃለው ለስድቡ አመሰግናለው ትልቁ"ይላል ጌታነህ ግራ ገባው  ። የእናቱ ስልክ መልሶ ጠራ አነሳው
"አቤት ማሚ"
"ማታ እንዳታመሽ የምናወራው ነገር አለ "
"ሰላም ዋልክ ልጄ ?አይቀድምም ማሚ"
"ድምፅህን ስሰማ መዋልክን አረጋገጥኩ እኮ አሁን ቁም ነገር ነው በፍፁም እንዳታመሽ እጠብቅሃለው"
"እሺ እንደፈለግሽ እኔም የትም የመሄድ ስሜት አልነበረኝም "
"ጡሩ "አለችና ስልኩን ዘጋችው ።ጌታነህ መልሶ ለአብላካት ሚሴጅ ፃፈ
"የት ልትሄጂ ነው አረብ አገር እንዳይሆን ብቻ"ብሎ ሴንድ አደረገ መልሱ እረዘመበት ቢያይ ቢያይ ዝም ሆነ አስተናጋጁ ሰሚር መጥቶ ትህዛዙን አስቀመጠ። እናም ለመናገር ሲል ።ጌታነህ ሚሴጅ ገባለት
"አረብ አገር አይደለም መንገዴ ወደ አባቴ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ነው የፃፍኩልህ እባክህ መልሰህ አትፃፍ " ይላል ።ጌታነህ እቺ ትንሽ በቀቀን ምንድነው የምታወዛግበኝ ብሎ ውስኪውን ጎንጨትአድርጎ አስቀምጦ ቆም አለ መልሶ ተቀመጠ ።አጠገባቸው እንደጅብራ የቆመውን አስተናጋጅ አየው በእጁ አነስተኛ የእርዳታ ጥሪ ወረቀት ይዟል
"ምንድነው አንተ ደሞ !"አለው
"እቺን እንድትቀበሉኝ ነው "
"ምንድነው እርዳታ ነው "
"አዎ"
"በቃ እዛው ወረቀትህን የምትፈልገውን እንሰጥሃለን አለው "እንየው
"እስኪ ላንተ ነው "አለና ጌታነህ ተቀበለው ወረቀቱ ላይ ለማመን የከበደው ስም ተፅፏል  የኩላሊት ታማሚዋን የአስራ ስምንት አመቷን ታዳጊ እናትርፋት ..........
"ምንድነው አንተ ይሄ"ብሎ አፈጠጠበት ።አስተናግዶ ጁ ሰሚር  ስለሁሉም ነገር አንድም ሳያስቀር ነገራቸው ጌታነህ ደነገጠ ።ከአብላካት ጋር ሲፃፃፍ የነበረውን ሚሴጅ መልሶ አነበበው ። ለምን እንደው ባያውቅም ከወትሮ በተለየ ልቡ አዘነበት ....

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍9417😢8😱4😁1
#በኔ_ቤት

በኔ ቤት……
ፍየል ቅጠል አይታ
ሳትበላ ታድራለች
ዶሮ ጥሬ ረግጣ
ልፆም ነው ትላለች
ውሻ ስጋ እያየ
በረሀብ ይሞታል
ሰው እህል ቀርቦለት
ባዶ ድስት ይከፍታል

በኔ ቤት……
አንበሣ ሚዳቋን
አቅፎ ይስማታል
ጅብ ስጋ ላይበላ
ምሎ ይገዘታል
ዕባብ ሰውን አይቶ
አይተናኮልም
ነብር ጎሽ አይጥልም

በኔ ቤት……
አንድ ብር ላይ ያለው
ትንሹ እረኛ መሳቁን ያቆማል
የሰፌዱም ስፌት
ሳንቲም ላይ ይሆናል
ወተት የጠጣ ህፃን
ሰክሮ ተንገዳግዶ
የአስር ዓመት ልጅ
አስር ልጆች ወልዶ
የሰፈር አዛውንት
ሰፈር ይቦርቃል
ሩቅ ያለው ቀርቦ
ቅርብ ያለው ይርቃል


አሁንም…
ከጣልሺኝ ቦታ ላይ
ብቻዬን ቁጭ ብዬ
ታምራዊ ስዕል
በአይምሮዬ ስዬ
ሀሳቤን ጥጃለሁ
ማይበስል ማይመስል
ዳግም በህይወቴ
አገኝሽ ይመስል

ልዑል ሀይሌ

#YouTube Subscribe እያረጋቹ ቤተሰቦች👇

https://www.youtube.com/@atronose
👏30👍2712🥰2😁1
እመኚኝ !!

ነይ ግቢ በሞቴ
እቤት ማንም የለም
የለችም እናቴ
እመኚኝ ግዴለም
ምንም አናደርግም
ወደ ውስጥ ገብተሽ
በሩን ብዘጋውም
አንድ ላይ ተቀምጠን
አብረን ብናወጋም
ከንፈርሽን ልስም
ወዳንቺ ብጠጋም
ብስምሽም እንኳን
ስጋት እንዳገባሽ ምንም አናደርግም... በፀጉሮችሽ መሃል
ጣቴን ባንሸራሽር
ጠረንሽን ቢሸተኝ
ገብቼ አንገትሽ ስር
እጄ ሚይዘው አጥቶ
ጡትሽን ቢነካካ እየጨባበጠ
መጠኑን ቢለካ
እንዳትጠረጥሪኝ ለሌላ
እንዳይመስልሽ ውዴ
ሙች እመኚኝ...
.
.
.
በዚህ ሁሉ መሃል በስሜት
ገንፍዬ ልብስሽን ባወልቅም
ልብሴን ወዲያ ጥዬ
እርቃንሽን ሆነሽ እርቃኔንም ሆኜ
አልጋው ላይ ብጥልሽ
በክንዴ ዘግኜ በሚገርም ሁኔታ
ፍቅር ብንሰራም እመኚኝ አለሜ
እኔ ልሙትልሽ
ምንም አናደርግም😂


#YouTube Subscribe እያረጋቹ ቤተሰቦች👇

https://www.youtube.com/@atronose
😁68👍366👎4
👁በ'ነሱ ቤት👁
🌻ክፍል ሠላሳ ሁለት🌻
🌻🌻🌻
ጌታነህ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ እንዳለ ዘርግፎ ለአስተናጋጁ ሰሚር እያስረከበ ወደ እንየው በመዞር እሱም ልክ እንደሱ እንዲያደርግ ነገረው ። እንየው የጌታነህ ሁኔታ የጤና አልመሰለውም ዝምብሎ እያየው ነበር ።ጌታነህ በእንየው መረጋጋትና የጥርጣሬ አስተያየት ተቆጣ ። አስተናጋጁ ሰሚር አረጋጋውና እርዳታው የግድ ዛሬ መሆን እንደሌለበት ነገም ተነገ ወዲያም ይደርሳል ብቻ የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉላት እባካቹ አላቸው ። ሁለቱም ተስማሙ  ።ጌታነህ ከሬስቶራንቱ እንደወጣ በቀጥታ ወደቤቱ ነበር የሄደው አይለኛ ድብርት ተጫጭኖታል ።ስለ አብላካት የሰማው ነገር  ምቾት ነስቶታል ቤት ሲገባ ወላጆቹ እናም ወንድሙ ሳሎን ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል ።ሁኔታቸው ግን ያስፈራ ነበር በከባድ ዝምታ ውስጥ ነበሩ ሁኔታቸው ደስ ስላላለው ወደክፍሉ ሊገባ መንገድ ጀመረ  በዚጊዜ እናትየው ሶፋው ላይ እንዲቀመጥ በትህዛዝ ተናገረችው ። ጌታነህ እየደበረው ተቀመጠ በውስጡ ምነው ወደቤት ባልመጣው የሚል አሳብ መጣበት ።እናቱን ቀናብሎ ሲያያት አንድ ነገር ለመናገር ስታምጥ አስተዋለ ።ወደአባቱ ሲያይ  ወደ መስፍን ፊቱን አጨፍግጎ ዞሯል መስፍን በዕንባ የራሱ አይኖቹን እየጠራረገ እና በተደጋጋሚ በአፍንጫው የሚወጣድምፅ እንዳለ አስተዋለ ። ጌታነህ አሁን ይበልጥ ተረበሸ ። ከረጅም ዝምታ በዋላ እናት እያማጠች መናገር ያለባትን ነገር ሁሉ ከስር መሰረቱ አፈረጠረጠችው ። መስፍን ተነፋረቀ ጌታነህ የሚሰማውን ሁሉ ለማመን ከበደው ።  ጭራሽ እያወሩ ያሉት ስለአብላካት መሆኑን ሲያውቅ አፉን ያዘ የሚሆነው ጠፋው  በተደጋጋሚ ምን አይነት አገሮች ጣሚ ነው ምን አይነት አጋጣሚ ነው .....እያለ ጮኽ
እናት ከመስፍን የጌታነህ ባሰባት ...
"ተረጋጋ ጌታነህ ምን ሆነሃል መስፍን እንኳ እንዳንተ አላበደም ። ልጅቷ በዚ ሰአት ችግር ውስጥ ናት እናቷን አፈላልገን ልንረዳት ይገባል "አለችው
"ማሚ አልገባሽም እኮ ልጅቷን .."ብሎ ጭንቅላቱን ያዘ
"ልጅቷን ምን?"አለችው እናት ደንገጥ ብላ
"ልልጅቷን አውቃታለው ማለቴ..."ብሎ ሊቀጥል ሲል
"አምላኬ የት ነው የምታቃት "ብላ እናት ተነሳች እሷን ተከትሎ አባትየውም ብድግ አለ
"ተው ጌታነህ በሌላ መልኩ ነው እንዳትለን ተው !!"አለ አባትየው በድንጋጤ
መስፍን የሚገባበት ጠፋው
"አይ እንደዛ ነገር አልተፈጠረም ግን ሊሆን ነበር ።ምን እንደሰራቹ ተመልከቱ ልጅቷን በተደጋጋሚ የፍቅር ጥያቄ አቅርቤላት ነበር በእርግጥ አንድ ቀን ነው ያገኘዋት ከዛ በዋላ በስልክ ልቀርባት ሞክሬ አለው ላገኛት ብዙ ቀጠሮ አስዣታለው ነገርግን ፍቃደኛ አልነበረችም እልህ ውስጥ ከታኝ ነበር በአካል ባገኛት ነገር ይበላሽ ነበር ።ወይ ፈጣሪዬ ለካ ለዚነበር የጠበቅከኝ አመሰግናለው አምላኬ "ብሎ ተንበረከከ
"ልጅቷእኮ ገና ታዳጊ ናት እንዴት ሌላ ነገር አሰብክ "ብሎ መስፍን ድንገት ጮኽ
"ምን ታወራለህ ደሞ አፍ አለኝ ብለህ ዝም በል "አለ አባት በብስጭት ። የጌታነህ እናት ። ጌታነህ ሌላ ግንኙነት አለን የሚላት መስሏት ደንግጣ ነበር ።ያ ባለመፈጨሩ ቅልል አላት ።እናም እርስ በእርስ መነታረካቸውን ትተው ልጅቷን ማዳን እንዳለባቸው አፅኖት ሰጥታ ተናገረች ።ሁሉም በእሷ አሳብ ተስማሙ እናም አብላካትን በፍጥንት ወደ ውጪ ወስደው ማሳከም እንዳለባቸው  እናም የአብላካትን እናት መሳይን  ማግኘት እና ላደረጉት ነገር ይቅርታ ጠይቀው መካስ ያለባትን ሁሉ ለመካስ ቃል ተገባ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አስተናጋጁ ሰሚር ከጌታነህ ያገኘውን በርካታ ገንዘብ ይዞ ወደነ አብላካት የሄደው ከስራ እንደወጣ ነበር ። አስባልቱን ጨርሶ ቅያስ ውስጥ ሲገባ አንድ አሳብ መጣለት እነገታነህ ይሄን ሁሉ ገንዘብ ከሰጡት ሰመረ ደሞ የተሻለ ነገር እንደሚያደርግ ተማመነ አብላካት እንዳትነገርው ያለችውን ነገር ወደጎን በመተው የሞባይል ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ወደ ሰመረ ደወለ ..........

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11319😁10🥰3👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////

ወደቀልቧ እስክትመለስ እና መኝታ ቤቷ ውስጥ ያልጋበዘቻችው ሰዎች እንደገቡ ለመገንዘብ ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባት ….

‹‹እንዴት ብትደፍረኝ ነው ግን ሰተት ብለህ መኝታ ቤቴ ድረስ  ሚስትህን ይዘህ የገባኸው……?.›

ኤርሚያስ ግራ ተጋባ … ተርበተበተ……‹‹ይቅርታ..ማለት ሚስቴ አይደለችም…. አላውቃትም..ይቅርታ ማለቴ አውቃታለሁ ግን ይሄውልሽ እሷ….››
አቋረጠችው ‹‹…ውጣልኝ …ውጡልኝ..››ጭንቅላቷን በእጆቾ ይዛ ጩኸቷን ለቀቀችው….

‹‹እሺ እንወጣለን..አንቺ ብቻ ተረጋጊ… እንወጣለን…ይሄው እየወጣን ነው…››የሚያደርገው ጠፍቶት ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበራፉ ፊቱን አዞረ…

ኬድሮን‹‹አባትሽን ላገናኝሽ ነው የመጣሁት››አለቻት

ከተቀመጠችበት ወንበር ንቅንቅ ሳትልል
ከትከት ብላ ሳቀች..የምፀት ሳቅ…..የእብደት ሳቀ..የንዴት ሳቅ

‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ከሞተው አባቴ ጋር ምታገናኚኝ….…?ነው ወይስ ከበድኑ ነው ልታገኛኚኝ ያሰብሺው…..አመሰግናለሁ በድኑ በእጄ ስለሆነ አትልፊ  ….››

‹‹አይ እዲያናግርሽ ማድረግ እችላለሁ››

‹‹እንዲያናግረሽ አልሽ…..ኤርሚያስ ምን በድዬሀልው..…?››አለችው ወደእሱ ዞራ

እየተርበተበተ‹‹..ሰላም አንቺ ምን በወጣሽ.. አረ ምንም አልበደልሺኝም  …ለምን እንደዛ ልትይ ቻልሽ…?››

‹‹እንዴ ያንተ ሳያንስ ሌላ ሰው ይዘህ መጥተህ እድታሾፍብኝ ታደርጋለህ……?በሀዘኔ እንዴት ታላግጣላችሁ….…?በቁስሌ እንዴት ጨው ትነሰንሳላችሁ…?ይሄ ምን አይነት ጭካኔ ነው …?…››

‹‹አረ በፍፅም እንደዛ አይደለም….አንቺን ለመርዳት እንጂ ሌላ ምንም አላማ የለንም››

‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው ከአባቴ የምታገናኘኝ……?.››

‹‹እሱን አንዴት እንደሆነ አላውቅም ..ግን ታደርገዋለች ››አለ አንዴ ኬድሮንን አንዴ ሰላምን በማፈራረቅ እያየ
ልታስረዳት ሞከረች‹‹እመኚኝ  የሙት መንፈስ ማናገር እና ከሚወዶቸው ሰዎች  ጋር የማገናኘት ችሎታ አለኝ…መቼስ ስለዚህ ጉዳይ ሰምተሸ አታውቂም  ለማለት አቸገራለው….››

‹‹ሰምቼማ አውቃለው..በመጽሀፍ ቅዱስ ላይም አንብቤያው..ግን ..››>

‹‹ምንም ግን የለም…››ብላ ንስሯን እንዲመጣ በአዕምሮዬ መልዕክት አስተላለፍችለት ….. ክንፉን እየማታ መጣና  አልፎን ፈሪጁ ላይ ጉብ  ሲል  ሰላም  በድንጋጤ ተንደርድራ ልትሰፍርበት ስትል ቦታ ቀየረና አመለጣት….

‹‹አባቴን ..አግዙኝ…. አባቴን አንዳይነካብኝ››

‹‹አይዞሽ የእኔ ንስር ነው ..ምንም አያደርግም…››

‹‹እርግጠኛ ነሽ ……?አባቴን አይነካውም…?››አለች… በእሷ ግምት የኬድሮን ንስር  የአባቷን በድን አካል ለመዘንጠል ይዳዳል ብላ ነው

‹‹እንዴ ንስር የሞተ ነገር እንደማይነካ አታውቂም…››

‹‹አላውቅም››አለች

‹‹እኔም አላውቅም ››በማለት ድጋፍ ሰጣት  ኤልያስ

ማብራሪያዬን በኩራት ቀጠልኩ ‹‹ንስር ኩሩ ነው…እራሱ አባሮ… እራሱ ታግሎ …እራሱ ገድሎ ካልሆነ ነክች አያደርግም…ለማንኛውም አሁን ተዘጋጂ ቁጭ በይ ››….ቁጭ አለች…
‹‹ይሄሁልሽ አሁን ንስሬ ያግዘኝና ከአባትሽ መንፈስ ጋር አገናኝሻለሁ...ማለት የእኔን አንደበት ተጠቅመው አባትሽ ቀጥታ ያናግሩሻል..በእኔ አንደበት በራሳቸው ድምፅ››

‹‹እሺ››

‹‹ኤርምያስ አንተ ደግሞ ካለህበት እንዳትነቃነቅ..ምንም የሚረብሽ ነገር ካለ ትኩረቴን ስለሚበታን መሀል ላይ ግንኙነቱ ሊቋረጥ ይችላል››

‹‹አረ በፍጽም ይሄው ንቅንቅ አልልም..ትንፋሼ እራሱ አይሰማም››አለና በተቀመጠበት ጭብጥብጥ አለ

ሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኑን ሳታረጋግጥ አዕምሮዋን ከንሰሯ ጋር አገናኘቸው..ለደቂቃዎች ተመሰጠች …ይሄን ነገር ከዚህ በፊት አድርጋው አታውቅም ‹‹..ግን ማድረግ አያቅተኝም›ስትል በራሷ ተማመነች….አዎ ንስሯ የአባቷን ነፍስ ካለችበት እንድትመጠ እየጋበዘ  ነው..ወይ ብዙም አላስቸገራትም ….ቀጥታ አባትዬው በኬድሮን አንደበት ልጃቸውን ማናገር ጀመሩ……

‹‹ልጄ ሰላሜ…››

ባለማመን መለሰች‹‹ወይ አባዬ..››ተንደርድራ ሬሳውን እያየች
‹‹እዛ ለምን ትፍልጊኛለሽ….…?አይ ልጄ ስጋዬ ውስጥ አይደለሁም.. …ግን ደግሞ ወደዘላለም ማረፊያዬም መሄድ አልቻልኩም..ከሁለቱም ሳልሆን በአየር ላይ ተንጠልጥዬ አለሁልሽ፡፡

‹‹ምነው አባዬ……? እኔ ልሰቃይልህ…..እኔ በአየር ላይ ለዘላለም ተንጠልጥዬ ልቅር››

‹‹አይ ለምን ልጄ…? ለምን..…?ለአንቺማ ይሄ አይገባም…ትቼሽ ስለሄድኩ ይቅርታ ልጄ..ምን ላድርግ የአማላክ ጥሪ ነው….እባክሽ ልጄ ከዚህ በላይ እንድሰቃይ አታድርጊኝ…››

‹‹እንዴ አባዬ እኔ አንተን ማሰቃየት…?››

‹‹አዎ እናቴ… እዚህ እቤቴ ውስጥ በድን አካሌን ታቅፈሽ እንደዚህ ሆነሽ እንዴት እፎይ ብዬ ወደዘላለም የሚወስደኝን  መንገዴን እቀጥላለሁ..…?አልችልም ልጄ ..አካሌ መሬት ሳይገባ ነፍሴ ወደአምላኮ ልትሄድ ይከብዳታል..ልጄ እባክሽ በአምላክ  ስራ ጣልቃ አትግቢ..››

‹‹እንዴት አባ……? እንዴት ጣልቃ ገባሁ……?.››

‹‹እንዴ ሞትን የፈጠረውን አምላክ  እኮ እየተቃወምሽው ነው..ተሳስተሀል እያልሺው ነው››

‹‹አዎ ተሳስቷልማ..እንዴት አንድ አባቴን ይነጥቀኛል..…?እንዴት ባዶዬን ያስቀረኛል….…?.››

‹‹አየሽ ልጄ …ሞት እርግጥ በጥፋታችን ምክንያት የተሸለምነው ቅጣታችን ነው…ይሁን እና በዚህ ምድር ለመኖር እስከመጣን  ድረስ   ሞታችንም በጣም አስፈላጊ ነው..››

‹‹እንዴት አባ .. …?ሞት ደግሞ እንዴት ነው ጠቃሚ የሚሆነው.?››

እግዜር ፈጥሮ ምድር ላይ ቢረሳንስ ምን ይውጠናል….…?አርጅተን መንቀሳቀስ አቅቶን እቤት እስክንቀር…. ቆዳችን እስኪጨማደድ እና  ወበታችን እስኪረግፍ ድረስ አልወስዳችሁም ቢለን ማነው የሚጎዳው……?.ጥርሳችን ረግፎ ገንፎ እንኳን  ማኘክ እስኪያቅተን ቢተወን …አይናችን ለግሞ  የልጅ ልጆቻችንን ከጎረቤቶቻችን ልጆች መለየት እስኪያቅተን ..መኝታ ቤታችን ከሽንት ቤታችን መለየት እስኪሳነን ድረስ ኑሩ ብንባል ሽልማት ነው ቅጣት…ዕርግማን ነው ምርቃት…?››

‹‹እንዴ አባዬ.. …!!!አንተ እኮ ገና ነህ …ሰባ አመት እንኳን አልሆነህም..…?››

‹‹እኮ እግዚያብሄር ይወደኛል ማለት ነዋ..…?ምላሴ ጣዕም መለየት ሳይሳነው፤አይኖቼ ማንበብ ሳያቆሙ ፤እግሮቼ ላምሸው ከዘራ ሳልይዘ አስታወሶኛል…››

‹‹ግን እኮ አባ እኔን ጥለህ ነው የሄድከው…?››

‹‹የሞት መጥፎው ክፍል ያ ነው….አዎ ሁልግዜ የሆነ ነገር ጥለሽ መሄድሽ አይቀርም…ማንም ቢሆን ከዚህ ምድር ሲሰናበት የሆነ ነገር በጅምር ጥሎ መሄዱ የሆነ የሚወደውን ሰው ሳይሰናበት ማምለጡ ያለ እና ግዳጅም ነው….እና ልጄ አንቺ አፈር ካላቀመሺኝ እና በሀዘን መቆራመድሽን እስካላቆምሽ ድረስ ጉዞዬን መጀመር አልችልም… ብጀምርም ቶሎ አልደርስም..ሀዘንሸ ወደኃላ ይስበኛል….ለቅሶሽ  መንገዴን እያጨቀየው ያዳልጠኝ እና አላላውስ ይለኛል…..››

‹‹አባ አረ እኔ እንዲህ የበደልኩህ አልመሰለኝም…?››

‹‹በደልሺኝ እኮ አላልኩም.. ግን  በቃ..አንዳንዴ መሆን ያለበት ነገር እንዲሆን መተው ነው..ታግለሽ ልታሸኝፊው ከማትችይው ነገር ጋር መታገል  ከድካም ውጭ እርባን ያለው ውጤት አያስገኝም ››

‹‹እና ምን ላድርግ አባ…?››
👍8910🥰3👎1🔥1😁1
‹‹በቃ አልቅሰሽ ቅበሪኝ….ከዛ በኃላ ሞተ የእያንዳንዱ ሰው ዕጣ ፋንታ መሆኑን አምነሽ ተቀበይና ወደ ህይወትሽ ተመለሺ…የራስሺኝ ሰው ፈልገሽ ኑሮሽን  ኑሪ….የእኔ በድን ታቅፈሽ እዚህ ቤት ባሳለፍሽው ስድስት ቀናት ውስጥ ስራ ላይ ብትሆኚ ኖሮ ሰንት ነፍስ  እንደምታታርፊ አስበሽዋል….… ?ስንት ያንቺን ክትትል የሚፈልጉ ህመምተኞችን እርግፍ አድረግሽ በመተውሽ  በያሉበት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሆኑ ታውቂያለሽ….…?ያባትሽን መንፈስ ለዘላለም ለማስደሰት እውነታውን ተቀብለሽ  ፈገግ በይ ..በእኔ ስም የአዛውንቶችን ጤንነት ተንከባከቢ…እኔን እያሰብሽ ሞያሽን በጥንቃቄ እና በታማኝነት ስሪ..እያንዳንዱ ሰው ባንቺ እጅ ታከሞ በመዳኑ ተደስቶ ፈገግ ሲል  እኔም ባለሁበት  ፈገግ እንዳልኩ በማሰብ ውስጥሽ ሀሴት ታድርግ….›.

‹‹አዎ አባ እውነትህን ነው..እንዳልከው አደርጋለሁ››

‹‹ስለዚህ ተስማምተናል››

‹‹አዎ አባ ..ተስማምተናል››

‹‹በቃ ደህና ሁኚ ልሄድ ነው

‹‹አባ ከመሄድህ በፊት ››

‹‹እሺ ምንድነው…?››

‹‹ግን ገነት ነው ምትገባው አይደል…?››

‹‹አይ ልጄ..መች ሄድኩና አውቀዋለሁ ..ግን ምንም አይት ፍራቻ እየተሰማኝ አይደለም….እረፍትና እፎይታ ነው ዙሪያዬን የከበበኝ….የሚታየኝ  አንፀባራቂ ብርሀን እንጂ ፅልመት አይደለም….እና ፈጥኜ የመሄድ ፍላጎት ነው ያለኝ…ባከሽ ልጄ እንድዘገይ አታድርጊኝ..››

‹‹እሺ አባ ..አንድ የመጨረሻ ጥያቄ››

‹‹ምን ልጄ…?››

‹‹እማዬን ታገኛታለህ…?››

‹‹አዎ ልጄ ተስፍ አደርጋለሁ..በጣም መቸኮሌ አንድም ለዛ ይመስለኛል››

‹‹እንደምወዳትና በጣምም እንደናፈቀቺኝ ንገርልኝ››

‹‹እሺ ነገርልሻለሁ››
ደግሞ ቀኔ ደርሶ ወደእናንተ  ስመጣ ከእናንተ ጋር አብሬያችሁ መኖር ነው የምፈልገው››

‹‹እሺ ልጄ  እንዳልሽ…ደህና ሁኚልኝ…››

‹‹እሺ አባ ደህና ሁን››

ይቀጥላል

#YouTube ላይ subscribe
እያደረጋችሁ ቤተሰቦች ከ110,000 እዚ ካላችሁት ሩቡ እንኳን subscribe ቢያደርግ አስባችሁታል ይሄን ድርሰት ያነበበው ሁሉም ቢያደርግም ቀላል አደለም ግን አብዛኞቻችን አንብበን ነው የምንወጣው ስለዚህ አንብባችሁ ስትጨርሱ ወደ #YouTube ሄዳችሁ Subscribe
እያደረጋቹ #አመሰግናለው
👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12222😢15👎6😁4
👁በ'ነሱ ቤት👁
ክፍል ሠላሳ ሦስት
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
አስተናጋጁ ሰሚር ደጋግሞ የሰመረን ስልክ ሞከረ ይጠራል አይነሳም  በጣም ጓጉቶ ስለነበር ሰመረ ባለማንሳቱ ቅር አለው ። ለአብላካት አንድ የተሻለ ነገር እንደሚፈጥርላት ተማምኗል ፣ የተለየ ነገር ባያደርግ እንኳ ብዙ ገንዘብ ሊረዳት ይችላል ።
እነ አብላካት ቤት ሲደርስ ቆም ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ ፣አብላካት ፊት ሲቀርብ ጭንቀት ማሳየት አይፈልግም ልክ እንደወትሮው  እየቀለደ ዘና ሊያደርጋት ነው የሚፈልገው ።
   እናም በር ከፍቶ ሲገባ መሳይ ቡና እያፈላች ከአብላካት ጋር እየተጫወቱ አገኛቸው ይህንን ስሜት ሲያይ የአብላካትን እናት አመሰገናት ፣ በዚ ጉዳይ ላይ ደጋግሞ መክሯታል ልጇን ማዳን ከፈለገች በፊትለፊቷ ማልቀስና ደካማነቷን ማሳወቅ ሳይሆን ፣ በተቻላት መጠን ስለህመሟ እንዳታስብ ማዝናናት ጠንካራመሆኗን መንገር ከፈጣሪ ጋር ሁሉ ነገር እንደሚቀየር መንገር ነው ብሏታል።እና ዛሬ እንደዛ ስታደርግ ስላየ ተደሰተ ። ሁለቱንም ጉንጫቸውን ስሞ ተቀመጠ እና አብላካትን ፣ በቀልድ
"አንቺ ሚጣ ምንድነው እንደዚ የሚያስቅሽ"አላት
"ስነስርሃት ሚጣ እንዳትለኝ ፣ደሞ ያሰመረን ተገላገልኩ ስል አንተም ሚጣ ትለኛለህ ዋ.."አለች
"አውቄ ነው ኪኪኪኪ የኔ ትልቅ ገና ትልቅ ትሆኛለሽ አምናለው ሀላ ያውቃል አንቺ ብቻ ፈገግ በይ"አላት በሰአን ላይ የቀረበውን የቡና ቁርስ ፈንዲሻ እየዘገነ
"አይ ሰሚ ምላስህ እኮ "አለች አብላካት የሆዷን በሆዷ ይዛ ለነሱ ስትል እየሳቀች
"ሰሚሬ አንተ እኮ እንደታናሽ ወንድሜ ነህ አንተ ባትኖር ምን ይውጠኝ ነበር ፈጣሪ ይጠብቅ "አለች መሳይ። ሰሚር ፈገግ ብሎ መልስ ሊሰጥ ሲል ስልኩ ጮኽ በፍጥነት አንስቶ
"ሃሉ "አለ
"ሃሉ ማን ልበል ወንድም ደውለህልኝ ነበር"አለው
"አዎ አዎ"ብሎ ተነስቶ ወደደጅ ወጣ ።
"እኮ ማን ልበል "
"ሰሚር እባላለው የአብላካት ጓደኛ ነኝ አስታወስከኝ"አለው
"እህ አዎ አዎ ሰሚር አስተናጋጁ "
"አዎ እንደቴ ነህ ሰላም ነው"አለው ሰሚር
"ደና ነኝ እንዴት ናቹ እናንተ ፣"
"ደና ነን"
"ሚጣ እንዴት ናት ማለቴ አብላካት"
"ደና ነች እእ ያው..."ብሎ ሰሚር ዝም አለ
"ያው ምን አብላካት ደና አደለችም እንዴ ?"አለው ሰመረ
"ያው ትንሽ ታማለች እእ ብቻ አስቸጋሪ ሁኔታላይ ነው ያለችው "አለው ሰሚር እየተጠነቀቀ
"ምንድነው እሱ የት ነው ያለችው ስልኳን ደጋግሜ ብሞክር የማታነሳው ለዛ ነው የት ነው ያለችው ሆስፒታል ናት"ሰመረ ተርበተበተ። አስተናጋጁ ሰሚር የሰመረን ድምፅ መለዋወጥ ሲሰማ ገባው በቃ ሰመረ ይወዳታል ስለዚህ ልነግረው ይገባል ምናልባትም ፈጣሪ የአብላካትን መጪ ሁኔታ ተመልክቶ ቢሆንስ ሰመረን ያዘጋጀላት ብሎ አሰበ
"ሆስፒታል አደለችም ለጊዜው ነገር ግን በሳምንት ሦስት ቀን ሆስፒታል የሚያስኬዳት ህመም ነው ያለባት በጣም አሳዛኝ ሁኔታላይ ነው ያለችው"አለው
"ምን ምን እያልክ ነው ?!የምትለውን ታውቃለ ይሄን ያክል ምንድነው እየቀለድክብኝ ነው እንዴ"አለው ሰመረ በቁጣ
"ከምሬን ነው ዛሬም ልደውልልህ የተገደድኩት እርዳታ ስለሚያስፈልጋት ነው በፍጥነት የኩላሊት ንቅለተከላ ካላደረገች ቅስሟ ተሰባብሮ ቶሎ ትሞታለች "አለ ሰሚር እንባ እያነቀው
"ምን ምምን ኩላሊቷ...."ብሎ ዝም አለ ስልኩም ተቋረጠ ። ስልኩን አየው ተዘግቷል ።ጠበቀ ጠበቀ እና መልሶ ደወለ ካገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው ይላል ። ቅር እያለው ወደቤት ገባ ። መሳይ አየቸው እና ቀስብላ መጥታ እርዳታ አገኘን እንዴ አለችው ። አስተናጋጁ ሰሚር ከነ ጌታነህ ያገኘውን ገንዘብ አውጥቶ ዘረገፈው ፣ ብዙ ነው ነገር ግን ለጊዜው ነው ። አብላካት የናቷ ፊት ሲፈካ ስታይ ።ልቧ ተነካ  ፈጣሪ ለሷ ሲል ቢምራት ተመኘች ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጌታነህ ምሽቱን ሙሉ ከቤተሰቦቹ ጋር አንዴ በቁጣ አንዴ በተረጋጋ መንፈስ ሲማከር ነው የቆየው ፣ በመጨረሻ የተስማሙበት ጉዳይ መሳይን እንደምንም ብሎ ማናገርን ነው ከዛ በዋላ በፍጥነት ልጅቷን ወደውጪ ሄዳ የምትታከምበትን መንገድ ማመቻቸት ።ከዛ በዋላ ሁሉንም ነገር እንድታውቅ ማድረግ በዚ አሳብ ተስማምተው ሁሉም እያብሰለሰሉ ወደመኝታቸው ሄዱ ። ጌታነህ ነገሩ ሁሉ ሌላ ሰው አድርጎታል ልቡ በጭራሽ አላርፍ አለው ፣አስተናጋጁ ሰሚር የሰጠውን የእርዳታ ወረቀት አውጥቶ ተመለከተው ስልክ ቁጥሮች አሉት ። ነገ ደውሎ አድራሻቸውን እንዲያሳውቁት ሊጠይቃቸው ወሰነ ።እንቅልፍ መተኛት እስኪያቅተው ድረስ ስለ አብላካት አሰበ ፣ፈጣሪ ያቺን ልጅ እንዳላገኛት ስላላደረገኝ አመሰግነዋለው እሺ ብትለኝ ኖሮ ትልቅ ስህተት ውስጥ ገብቼ ነበር ። ይሄ የተረገመ ወንድሜ አጥፍቶ አጥፍቶኝ ነበር ። እንደስራዬ ያልከፈልከኝ ፈጣሪ አመሰገናለው ።አለ ደጋግሞ ።ስለ ጓደኞቹም አስቦ ይህንን ጉድ ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን ። ብሎ አሰበ ። ብቻ እንድቺው ሲገለባበጥ ሲጨነቅ አደረ...


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍14715😁4😢4
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ቫይብሬት ላይ የተደረገ ሞባይል ስልክ ላይ ሲደወል እንዳለ ንዝረት ተንቀጠቀጥችና አዕምሮዋን ከንስሯ ጋር አላቀቀች…
ሰላም ወደኬድሮን ተንደርድራ መጥታ እግሯ ሰር ድፍት አለችና‹‹በጣም አመሰግናለሁ….እግዜር ይስጥሽ››

‹‹ተነሺ ..እኔን አታመስግኚ…እሱ በጣም ስለለመነኝ ነው እንዲህ ያደረኩልሽ…››አለቻት

‹‹ኤርሚ እግዜር ይስጥልኝ….አንተንም በጣም  ነው የማመስግንህ..ምን አይነት ሰላም በውስጤ እንደተሰራጨ አትገምትም››አለች ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ

‹‹በነጋራችን ላይ በጣም ነው የሚያፈቅርሽ …እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ሲያፈቅርሽ ነው የኖረው….አንድም ቀን አንቺን ማፍቀር አቁሞ አያውቅም..ግን በኑሮ ደራጃ ስለምትለያዩ እሺ አትለኝም የሚል ፍራቻ በውስጡ ስላለ  ካንቺ ሲሸሽ ነው የኖረው››አፈረጠችለት

ባለማመን አንዴ ኬድሮንን አንዴ እሱን በማፈራረቅ ማየት ጀመረች..ኤርምያስም የተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ወደወለሉ እንደደፋ ሚገባበት ጠፍቶታል እጆቹን እያፍተለተለ ነው…

‹‹አላውቅም ነበር…ኤርምያስ እኔን ማፍቀር….…?››

‹‹አዎ….ኤርምያስ አንቺን…››

‹‹እሺ ጥሩ ነው…አሁን ምን እናደርግ …ኤርሚ እርዳኝ ለእድር ሰዎች ንገራቸው…አባቴ ዛሬውኑ እንዲቀበር እፈልጋለሁ….››

‹‹አረ እሺ… ችግር የለውም… አሁኑኑ ነግሬያቸው ልምጣ …ስልካቸውን ስለማላውቅ እናቴ ጋር ሂጄ …››ብሎ ተነሳ 

ኬድሮን የተለየ ሀሳብ አመጣች‹‹ቆይ መጀመሪያ የሬሳ ሳጥን እንግዛና አባትሽኝ  በሳጥኑ ውስጥ በማድረግ  ማዘጋጀት አለመብን..አሁን ዕድርተኛው መጥተው ጓደኞቸው ተሰብስበው እንገንዝ ማለታቸው አይቀርም …እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሀሚት ላይ ይጥልሻል…በህግም ሊያስጠረጥርሽ ይችላል››

‹‹ታዲያ ምን እናድርግ››አለች ግራ ገብቷትና ያለሳበችውን ነገር ስላነሳው ደንግጣ

‹‹ግድ የለም እኔና ኤርሚ ሳጥኑን ይዘን እንምጣ..ሁሉንም ከጨረስን  ብኃላ ለሌላው ሰው እንናገራለን….››

‹‹አስቸገርኮችሁ አይደል…?›› 

‹አረ አትጨነቂ …እኔን እንደእህትሽ ቁጠሪኝ… ኤሪሚም  ያው ያንቺው ነው..››አለችና ምትናገረው ጠፍቷት በመቁለጭለጨ ላይ ሳለች የደነዘዘውን ኤርሚያስን ይዛው ወጣች…

መኪናው ውስጥ ገብተን የሬሳ ሳጥን ወደሚሸጥበት ቦታ  እያመሩ ሳለ…

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው ያደረግሽው……?.››ሲል ጠየቀት

‹‹ያው ላንተ ስል ነው››

‹‹በጣም ነው የማመሰግንሽ….ግን  እንደማፈቅራት ለእሷ ባትነግሪያት ጥሩ ነበር››

‹‹ለምን…?››

‹‹ያው አንደኛ መንገሩ ምንም ውጤት አይኖረውም ሁለተኛ እኔ እና አንቺ……››

‹‹አይ እኔና አንቺ የሚባል ነገር የለም…አኔን እርሳኝ…እኔ ሁለት ቀን ብቻ ነው የቀረኝ..››

‹‹ምን ለመሆን…?››

‹‹ለመብረር…››

‹‹እንዴ የት አሜሪካ ወይስ አውሮፓ……?››

‹‹በለው ከሁለት አንዱ….ስለዚህ እሷኑ ጠበቅ አድርግ.ደግሞ በትክክል ይሳካልሀል….

እንደምታፈቅራት ስነግራት የልቧን ምት በደንብ ታዝቤያለሁ. ዋናው ከዚህ ሀዘን እስክትወጣ ከስሯ አትለይ …….

‹‹እንዴ ወዴት ነው የምለየው….ከእሷ የሚበልጥ ምን ሌላ ጉዳይ ይኖረኛል››

‹‹ምንም ››

‹‹አንቺ ልትበሪ መሆንሽን መስማቴ  ግን ቅር አሰኝቶኛል››

‹‹እኔን እርሳኝ አልኩህ እኮ››

‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ልርሳሽ…?››
/////

የሰላምን አባት የቀብር ሁኔታ ካመቻቸችና ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱንም አንድ ላይ ከለቀስተኞች ጋር ጥላቸው እናም በውስጧ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታቸው መልካሙን ሁሉ እየተመኘችላቸው ወደቤቷ ነው የተመለሰችው…ድክምክም ብሏት ነበር…ግቢውን አስከፍታ ስትገባ ግን ድካሟን ሁሉ ከላዮ የሚያበንላት አስደሳች ሁኔታ ነው የጠበቃት…

ግቢው መሀል ላይ ባለች ክፍት ቦታ ጠራጴዛ እና ወንበር ወጥቷል፤…ጠረጵዛው በልዩ ሌዩ ምግቦችና መጠጦች ተሞልቷል …ከዛ አልፎ ዙሪያው በየጥጋጥጉና በየቦታው የዛፍ ቅርንጫፎች ላይም ሳይቀር የተለያዩ የምግብና የፍራፍሬ አይነቶች ተቀምጠዋል…የተለያዩ ጥራጥሬዋች በየቦታው ተበትኗል….በጊቤዋ ውስጥ ያሉ እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እንግዳ የሆኑ ወፎች ሳይቀሩ ግቢውን ወረውት የተበተነላቸውን ጥራጥሬ በደስታ ይለቅማሉ… ጦጣና ዝንጆሮዎቾም ሙዙን እየላጡ ይውጣሉ …የማይፈነጭ እና የማያስካካ ፍጥረት በግቢው አይታይም..  የሆነ እንስሳት አግብቶ ሌሎቹ ሠርግ ተጠርተው አሼሼ ገዳሜ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው….ሌላው ይቅር እያንዳንዱ  ተክል   ስሩ ተኮትኩቶና አፈር ታቅፎ ውሃ ጠግቦ እስኪተፋ ድረስ ጠጥቶ ይታያል….በቃ በግቢው አንድም ያልተደሰተ ፍጥረት አልነበረም..ይሄ ሁሉ በፕሮፌሰሩ የተደረገው እነሱ በተደሰቱበት መጠን እኔ እንደምደሰት በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡

‹‹አትመጪም…  ይሆን ብዬ በስጋት ላይ ነበርኩ …እንኳን በሰላም መጣሽ››አሏት ከእድሜ ጫና የተነሳ ያጎበደድት ፕሮፌሰር…

‹‹አይ እፈልግሻለሁ ብለውኝ የለ..…….?በዛ ላይ  አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረኝ …ማታ ወደ እናቴ  እሄዳለሁ.አዎ ነገ ሙሉውን ቀን ከእሷዋ ጋር ነው ማሳለፍ የምትፈልገው………››

‹‹ጥሩ ጥሩ..ነይ እዚህ ጋር ቁጭ በይ›› ብለው ምግብ በሞላበት ጠረጴዛ ዙርያ ከበው ከተቀመጡ ወንበሮች ውስጥ አንድን ሳቡላት… አመስግና ተቀመጠች፡፡

የእጅ ውሀ አመጡላት …‹‹አረ እራሴ እታጠባለሁ›› ብላ በራሷ ተጣበች… ሳሀን ስባ ምንም እንኳን የምግብ ፍላጎት ባይኖራትም እሷቸውን ለማስደሰት ስትል ብቻ መብላት ጀመረች… እሳቸውም ከፊት ለፊቷ ተቀምጠው በስስት እያዮት መመገብ ጀመሩ…

‹‹የሚጠጣ ምን ልቅዳልሽ…….?››

‹‹ውሀ ››

‹‹ወይን ወይም ሌላ ነገር አይሻልሽም…….?››ካለወትሮዋ ዉሀ ማለቷ አስገርሞታል

‹‹አይ ውሀ ነው የምፈልገው….››

‹‹እሺ ካልሽ ››ብለው ውሀ ቀዱላት፡፡

‹‹ጋሼ በዚህ ምድር በኖርኩበት ዓመት የተረዳሁት ነገር ቢኖር  ምድር መተኪያ የሌላቸው ሁለት ነገሮች መታዳሏን ነው ….አዎ  እናትና ውሃ የዚህ ዓለም ሁለት ልዩዎች  ናቸው…››

‹‹እንዴት ልጄ..…….?እንዴት እንደዛ ተረዳሽ…?››

‹‹እናታችን መጀመሪያ ገነታችን ነች..ከተፈጠርንበት ቀን አንስቶ እስክንወለድበት ቀን ድረስ በእናታችን መሀፀን ውስጥ ገነታዊ ኑሮ ነበር የምነኖረው… ያ ስፍራ ሁሉ ነገር በፍፅምና  እንከን አልባ  ስፍራ  ነበር..ሁላችንም ከዛ ያለፍላጎታችን ተገፍትረን ስንወጣ(ስንወለድ) እሪ ብለን ለቅሶችንን የምንለቀው  ምን እንዳጣን በደመነፍስ ስለሚገባን ነው…አዳም እና ሄዋን በሰሩት ሀጥያት ከገነት ወደምድር ተባረሩ የሚባለው ሌላ አይደለም ከእናት መህፀን ወደምድር ተገፍትሮ መውጣት ነው…ከዛ በኋላም ቢሆን  እናት ምን ጊዜም እናት እንደሆነች ነው ምትቀጥለው… እንዳላረጀን እና እንዳላበቃልን የሚሰማን እናታችን በሰላሳ አመታችንም እንደ ህፃን ስትቆጣን ስናይ ነው..ጭንቅላታችንን ስትዳብስልን…ተይ አንቺ ልጅ ብርድ ይመታሻል ስትለን  ነው፡፡
👍918👏4😢4🔥2🥰2🤔1
ግን ክፋቱ በፈለግናት  ጊዜ ስለምናገኛት…በጣራናት ጊዜ ሮጣ ስራችን ስለምትገኝ ዋጋዋን ብዙም አናውቀው…. እንደድንገት ስትነጠለን  እና ከእጃችን ተንሸራታ ስናጣት ግን  አንድ ሰው ብቻ እንዳልነበረች ይገለጽልናል…መላ ዓለም እሷን እንደማይተካልን  ትምህርት እናገኛለን…ግን ትምህርት ቀድሞ ያጣኸው ነገር ወደፊት ዞሮ መጥቶ እንድታስተካክለው እድሉን ካላገኘህ ጥቅም የለውም..በደንብ ስትፀፀት እድትኖር ብቻ ነው የሚያግዝህ፡፡

ውሃም በቀላሉ ነው የምናገኘው..እኛ እራሱ በዋናነት የተሰራነው ከውሀ ነው ..ምድርም ሶስት እጆ ውሀ ነው….በቀላሉ ብቻ ሳይሆነ በርካሽም እናገኘዋለን.. ሰውነታችን ከየትኛውም መጠጥ በተሻለ በውሀ ይረካል…በውሃ ጤነኝነት ይሰማዋል…የውስጥ መጠማታችንን ብቻ ሳይሆን በአካልም መዛላችንን በውሀ ነው የምናክመው….ሰውነታንን የምንታጠበው የቆሸሸ ሰውነታችንን ለማጽዳት ብቻ አይደለም ውኃው በሰውነታችን ላይ ሲያርፍ መነፍስን የማረጋጋት እና የአዕምሮ ውጥረትን የማከም ኃይል ስላለው ነው…ግን ‹‹ወይ ስታጠብ ቀለል ይለኛል›› በማለት ያገኘነውን ጥቅም እናቃልለዋለን እንጂ ውሀ መድሀኒት ነው ብለን ዕውቅና መስጠት አንፈልግም ..ወሃ የደም ግፊት መድሀኒት ነው..ውሀ የኩላሊት መድሀኒት ነው…ውሃ የራስ ምታት መድሀኒት ነው…..ወሃ የበሽታዎች ሁሉ ፈውስ ነው…
‹‹የእኔ ውሃ ግን  አንቺ ነበርሽ…››አሏት እዝን እንዳሉ፡፡
‹‹ማለት……….?››አለቻቸው አሳዝነዋት፡፡
‹‹አዎ እኔ ጡረታ እስክወጣ ድረስ በዚህች ሀገር ላይ በጣም ስኬታማ ከሆኑ ጥቂት ሰዎች መካከል አንድ  ነኝ ብዬ አስብና እመፃደቅ ነበር….አምስት ስድስት ዲግሪዎች ስላሉኝ አንቱ የምባል ፕሮፌሰር ስለሆንኩ በቃ እታበይ ነበር….ልክ ጡረታ ስወጣ ግን ግማሽ ህይወት ብቻ ስኖር እንደነበር ተገለጽለኝ..እንደው ወደኃላ ተመልሶ የኖሩትን ህይወት ማስተካከል ቢቻል ካሉኝ ዲግሪዎች መካከል አንድን ብቻ አስቀርቼ ሌሎቹን በልጆች እና የልጅ ልጆች መቀየር ብችል ደስ ይለኝ ነበር..ከዛሬ 40 አመት በፊት አግብቼ ዛሬ የ35 ዓመት ልጅ እና የአምስት አመት የልጅ ልጅ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ በጣም ስኬታማ እና ሙሉ እሆን ነበር..ይሄን ቁጭቴን ባንቺ ነበር እየተፅናናው ለመኖር እውተረተር የነበረው…አሁን ግን….››
‹‹እንዲህ እማ አይዘኑ››
‹‹ተይኝ ልዘን…እነዛ ሁሉ ያገኘዋቸው ግኝቶች …እነዛ ሁሉ የተሸለምኮቸው ሽልማቶች እኔ ካለፍኩ በኃላ ማን ይረከባቸዋል..ማን ነው ሊኮራባቸው የሚችል የእኔ ሰው  ……….?
‹‹አሁን ወደኃላ ተመልሰው አድሉን ቢያገኙ እኮ መልሰው ተመሳሳዩን ነው የሚያደርጉት››
‹‹በፍጽም አላደርገውም..ህይወት ሚዛን መጠበቅ አላባት…እድሜሽን ሙሉ ገንዘብ ለማካበት ሰትባክኚ ቆይተሽ ካረጀሽ እና ጥርስሽ ከረገፈ በኃላ ልዝናና ብትይ አያምርብሽም… ደስታ ሚያመነጨው የሰውነትሽ ዕጢም እንዘይሙን ማምረት ስለሚያቆም አትቺይም….ወንደላጤ ሆነሽ ስትንዘላዘይ ኖረሽ በእኔ ዕድሜ ላግባ ብትይ እንዴት ተደርጎ..እንደው ሚስትዬዋ ተገኝታ ማግባት ቢቻል እንኳን እንዴት መውለድ ይቻላል..…….?ቢወለድ እራሱ የማያሳድጉትን ልጅ  እንዴት ….?ሁሉ ነገር በጊዜው ነው የሚያምረው››
‹‹እና እንዴት መሆን አለበት ይላሉ…….?››ጠየቀቻቸው
‹‹የተወሰነ መማር..የተወሰነ ገንዘብ መስራት… የተወሰን ቁጥር ያለው ቤተሰብ መመስረት…በቃ ከሁሉም የሚያስፈልገውን እና የምትጠቀሚበትን ያህል መውሰድ ነው…አየሽ አኔ አሁን ተማርኩ ከምላቸው ትምህርቶች መካከል ሁለቱን ዲግሪዎች ለአንድ ሰምንት እንኳን አልሰራሁባቸውም…እንዲሁ ለጉራ ካልሆነ በስተቀር  ያን ያህል ፋይዳ አልነበራቸውም …
በልተው እንደጨረሱ እጇን ታጥባ  እሳቸው ቢራቸውን እየጠጡ እሷ ደግሞ ወኃዋን ይዛ ወሬውን ቀጠሉ
‹‹እቤቱን እንግዲህ  ሰጥቼዎታለሁ…..››
‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም ….እኔ እኮ ለራሴ የሚበቃ የጡረታ ብር አለኝ..ተከራይቼ ሌላ ቦታ እኖራለሁ..ቤቱ የሚገባወ ለዘመዶችሽ ነው..››
‹‹አይ ይሄ ቤት የሚገባው ለእናቴ ነበር..ግን እናቴ ከተወለደችበት አካባቢ ንቅንቅ ማለት አለትፈልግም….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ይሸጥና ብሩን ይጠቀሙበታ››
‹‹አይዞት ለእሷ አያስቡ …በቂ የሆነ ብር ሰጣታለሁ..ይሄ ቤት ግን የሚሸጥ አይደለም…እሺ ጣሪያና ግድግዳው መሸጥ ቀላል ነው…እነዚህ ግቢውን የሞሉትን ዛፎች በስንት ብር ተምኜ ልሽጣቸው…?እነዚህ ዛፎቹን የወረሯቸውን በሺ የሚቆጠሩ ወፎች ስንት ስንት ብር ያወጣሉ...?ዝንጀሮዬን ስንት ልሽጠው..…?ጉሬዛዬንስ….?አዩ አንዳንድ ነገሮች ከሚሰጡት ጥቅም አንፃር ብቻ ሳይሆን ካለቸው ትርጉም  በመነሳት ዋጋ ሊወጣላቸው አይቻልም….አሁን ለአንድ ሀብታም ብሸጠው እኚ አሁን የጠቀስኩሎትን ሁሉ አንድ ሰምንት የሚያቆያቸው ይመስሎታል….?.ዛፎቹን ጨፍጭፎ መሬቱን ነፃ በማድረግ ፎቅ ነው ሚገነባበት…ወፎችስ እድሜ ለክንፋቸው በስደት  በመሸሽ  ነፍሳቸውን ለማቆት ይሞክራሉ..፤ሎሎቹስ….?

‹‹እሱስ ከባድ ነው››
‹‹ስለዚህ ቤቱ አይሸጥምም… ለሌላ ዘመድም ቢሆን ተላልፎ አይሰጥም…ይሄ ቦታ የሚገባው ለእርሷ ብቻ ነው..የእያንዳንዶን ዕጽዋት ሚስጥር የሚያውቁትና የሚረዱት እርሶ  ኖት… ስለዚህ የእርሶ ነው››
ፈገግ አሉ..
‹‹ምነው .. …….?ተሳሳትኩ እንዴ..…….?››አለቻቸው ፈገግታቸው የምፀት ስለነበረ ገርሞት
‹‹ስንት ዓመት ልኖር ብለሽ..…….?በተለይ አንቺ በሌለሽበት..ሁለት አመት ሶስት አመት..ከዛስ ያው የፈራሽው  መድረሱ አይቀርም..እነዚህ ሁሉ የለፋንባቸው ነገሮች አጥፊ እጅ መግባታቸው እና መውደማቸው አይቀሬ ነው…››
‹‹ስለዚህ አንድ ነገር እናድርጋ››
‹‹ምን…….?››
ከመቀመጫዋ ተነሳች..ንስሯ ለማድረግ የፈለገችውን ቀድሞ ገብቶታል ፤ ካለበት ዛፍ ላቆ ልክ ትሪኢት እደሚያሳይ የአየር ኃይል የጦር ጄት መገለባበጥ ጀመረ… እንዲህ የሚያደረግው ሲደሰት ነው…በስንት ቀኑ ፈታ አለ….. 
ወደእሳቸው ቀረበች… ግራ ገብቷቸው በዝምታ ያዩታል…. ከጀረባዋ ቆማ  ፀሎት እንደሚያደሰርስ   የፕሮቴስታንን ፓስተር ሁለት እጇን በጭንቅላታቸው ላይ ጫነችና አይኖቾን ጨፈነች…በፍጽም መመሰጥ ውስጥ ገባች….ቀስ እያለ ሰውነቷ ሲግል ይታወቃታል..አዎ ከልቧ ጀምሮ ኃይል እየተሰበሰብ በደምስሯ በመራወጥ ወደ እጆቾ እየፈሰሰ ነው…ከዛ ወደ ፕሮፌሰሩ ጭንቅላት መተላለፍ  ጀመረ…አይኖን የጨፈነች ቢሆንም እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ይታያታል… ኃይል የሞላው ሀመራዊ ቀለም  ከፕሮፌሰሩ ጭንቅላት አንስቶ ወደ አንገታቸው..ከዛም  ትከሻቸው እያለ ወደመላ ሰውነታቸው ተሰራጨ… መንዘፍዘፍ ጀመሩ….ኦ.. ሽበት የወረረው ነጭ ፀጉራቸው...ከግንባራቸው እየተነሳ ወደ መሬት ይረግፍ ጀመር…በዛው ቅፀበት ሌላ ደማቅ ጥቁር ሉጫ ፀጉር ከእያንዳንዱ የራስ ቅል ቀዳዳቸው በመብቀል ወደ ውጭ በመውጣት ጭንቅላታቸውን ሞላው…

ይቀጥላል

#YouTube ላይ subscribe እያደረጋችሁ ቤተሰቦች #የYou tube subscriber ቁጥር 100 በሞላበት በማንኛውም ሰአት ቀጣዩን እለቃለው ለናንተ ለቤተሰቦቼ ቀላል ነው 1 ደቂቃ ይበቃዋል ወይም ከዛ በታች በሉ አሁን ጀምሩ።
👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8510😁7👏4👎1
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ለዓመታት ጎብጦ እና አጎንብሶ የነበረ ትከሻቸው ቋቋቋቋቋ የሚል ድምጽ እያሰማ በመላቀቅ መቃናት ጀመረ…የተጨማደደ እና ተኮመታትሮ የነበረ ቆዳቸው ልክ የሽማግሌ ገፃ-ባህሪ ለመጫወት ጭንብል አጥልቆ እንደነበረ አክተር  ከፊታቸው ተሞሽልቆ በመነሳት መሬት ወደቀ…
ወዲያው መለስተኛ አውሎ ንፋስ ተነሳና እየተሸከረከረ መጥቶ እዚህም እዛም በዙሪያችን የወደቀውን የፕሮፌሰሩን የተወገደ አካል ከአካባቢው ጠራርጎ በአየር ላይ ተሸክሞ ሄደ ..
ከዛ…. ሁሉ ነገር እንዳሰበችው እንደሆነ ካረጋገጠች በኃላ እጆቾን ከጭንቅላታቸው አነሳችና…ወደመቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች…

አየቻቸው‹‹…..እንዴት አባቱ የሚያምር ጎረምሳ ሆኖል›ስትል እራሷ በሰራችው ተአምር እራሷ ተደነቀች   …‹‹ውይ እነዛ የአባቴ ዘመዶች መተው ሚወስዱኝ ባይሆን  ኖሮ ይሄን  ፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ቆንጅዬ  ጎረምሳ አግብቼ  መኖር ነበር….›ስትል የምፀት ፈግታ ፈገግ አለች፡
ፕሮፌሰሩ ቀስ እያለ ከሰመመኑ ነቃ…
‹‹ወይ ልጄ ምድነው ያደረግሺኝ…….?ራስ ምታቴ እና ጭንቀቴ እኮ ለቆኝ ሄደ››
‹‹አሞህ ነበር እንዴ…….?››
‹‹ምን አልሽኝ…….?››ግራ ተጋብተው
‹‹ ይቅርታ አሞት ነበር እንዴ…….? ለማለት ፈልጌ ነው››
‹‹አንቺን አልረብሽሽም ብዬ ነው እንጂ እንደምትሄጄ ከሰማሁበት ቀን አንስቶ ጤናም የለኝ ነበር..››
‹‹አይ እንኳን ተሸሎት››
‹‹አረ መሻል ብቻ አይደልም …››ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አይናቸው እጃቸው ላይ አረፈ..ተጨማዶ ና ተሸብሽቦ የነበረ እጃቸው አሁን በለግላጋ  ጣት እና ለስላሳ ቆዳ ተሸፍኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም… ግራ በመገባት እና  ባለማመን በጃኬታቸው ሸፈኑት..መልሰው ገለጡ…
‹‹ቆይ መጣሁ›› ብለው….ትተዋት ወደቤት በፍጥነት መራመድ ጀመሩ…ከኃላ ተከተለቻቸው…ቀጥታ ወደመኝታ ቤታቸው ሄደው የቁምሳጥናቸው መስታወት ፊት ለፊት  ነው የቆሙት….
‹‹የምን ታአምር ነው.…….?.እኔ የት ሄድኩ……….?ማን ነው ይሄ..…….?እኔ ማነኝ…….…….? ››ፊታቸውን እየዳበሱ ለፈለፉ…
መልስ መስጠት ጀመረች‹‹አሁን የ30 ዓመት ወጣት ሆነዋል..ማለት ሆነሀል፡፡…የሚፀፀቱበት ምንም ነገር የለም..ቀጣይ 45 ዓመት ተሰጥቶታል …. ስዚህ ቅድም እንዳሉት ሚዛናዊ ኑሮ ይኑሩበት..ማለቴ ኑርበት…››
‹‹ምን ጉድ ነው….…….?እኔ ወጣት…አንደገና መወለድ እኮ ነው…….?››
‹‹አዎ ነው..ልክ እንደንስር እንደገና የመታደስ ዕድል..››አለቻቸውና ቤታቸው ለቅቄ ወደራሴ ቤት አመራሁ ..ወደ እናቴ ለመሄድ ልዘጋጅ
////
ንጋት ላይ ነው ጉዞ የጀመሩት፡፡የንጋቱን ቀዝቃዛ አየርን  እየማጉ ሰማዩን ሰንጥቀው ቁልቁል የኢትዬጵያን ደቡባዊዉን መልካ ምድር እየቃኙ እየተጓዙ ነው፡፡እስኪ ትንሽ ከላይ ሆነው ቁልቁል ወደታች ሳያዩ ከፊል ኢትዬጵያ ምን እንደምትመስል አብረናቸው እንመልከት፡

ኢትዬጵያ 12 ታሪካዊ ቅርሶችን በዩኒስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡እነዚህም፤ የአክሱም ሀውልቶች፣ የላሊበላ አብያተክርቲያናት፣ የጎንደር ፋሲል ቤተመንግስት፤የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልካዓ ምድር፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣የታችኛው አዋሽና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የመስቀል ደመራ፣ የሲዳማ ፊቼ ጨንበላላ፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርአት ናቸው። ሌሎችም ለማስመዝገብ   ላይ ያለ አሉ  በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በእቅድ ደረጃ የተያዙ ቅርሶችም እንደ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኦመር ዋሻ፣ የጌዲዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መልከዓምድር፣ የመልካ ካንቱሬ የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች ናቸው። በማይጨበጥ ባህላዊ ቅርስነት ደግሞ የአማራና የትግራይ የሻዳይና የአሸንዳ በዓላት የጥምቀት በዓል ይጠቀሳሉ። 
ኢትዬጳያ ግን ለቱሪስት ኢነደስትሪው ግብአት የሚሆኑ ሀብቶቾ እነዚህ ብቻ አይደሉም…ሀገሪቱ እራሱ ሙሉ በሙሉ በዩንሰኮ ቅርስነት ብትመዘገብ አያንስባትም…ግን በዛ መጠን የሚያስብ በዛም መጠን የሚሰሩ ልጆች ወልዳ አለማሳደጎ በጣት የሚቆጠሩትን ብቻ ማስመዝገብ ችላለች፡፡

ይገርማችኋል ይህቺ ሀገር ሙሉ ነች፡፡ሙሉ ስላችሁ ለምሳሌ አየር ፀባዮ  ደጋ ጥቂት ፈቅ ስትሉ ወይና ደጋ ..ብዙም ሳትርቁ ቆላ ታገኛላችሁ፡፡ይሄ ድንቅና መድሎ ያለበት የተፈጥሮ ስጦታ ነው…መልካ ምድሯን ስንመለከት  ለጥ ያለ ሜዳ…ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ..እሱ ሲገርማችሁ ጭው ያለ ገደል…በሌላ ጎኑ እንደጣባ አህያ የተራቆተ መሬት…እንደ ደብረብርሀን የሱፍ በግ ጥቀጥቅ ያለ ጫካ…ኩሬ ሀይቅ ወንዝ….አቤት እነዛ አሜሪካኖቹ ይሄን መልካ ምድር ከዚህ የተመጣጠነ ምግብ ከሆነ አየሯ ጋ ቢያገኙት.. አቤት ይሮፖዎች ያ በቆፈን የሚያኮራምት በረዶ ገላግሎቸው እንዲህ ሚዛኑን የጠበቀ አየር ቢያድላቸው ምን ያህል ተአምራዊ ህይወት ይኖሩ ነበር.. ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ ቀመር አለት መሰለኝ ለእነሱ ሀብት ከቆፈን ጋር ስታድል ለእኛ ምርጥ አየር ከችጋር ጋር.. ያስቃል….እነሱ በቱሪስት ሆነው መልካምድሯን አይተው ለመደሰት እና አይሯን ምገው ሀሴት ለማድረግ ምቾት ባለው አይሮፕላን መጥተው ገንዘባቸውን ከስክሰው ከረምረም ብለው ይመለሳሉ..እኛ በስደት መልክ ከችግር ለመላቀቅ በእግር ተጉዘን በባህር ተጉዘን ሀገራቸው እንገባና ጉልበታችንን አንጠፍጥፈን አንገታችንን ደፍተን ስንባዝን ስንባዝን እንኖርና በዛው የውሀ ሽታ ሆነን እንቀራለን የእነሱ አንድ ነፍስ በእኛ ስንት ነፍስ እንደሚመነዘር ስሌቱ አይታወቅም ..ምን አልባት የብራችን ምንዛሬ ወይም ዋጋ ልዩነትን ያህል የነፍሳችንም ዋጋ ልዩነት ይኖረው ይሆናል…

….ይሄን ሁሉ ይምታስበው.ይሄን ሁሉ የምትመኘው በአየር ላይ ሆና ንስሯ ጀርባ ላይ ተጣብቆ ነው እየተጓዙ ያሉት… 

ያው ሰው በተፈጥሮ በመጨረሻው የህይወቱ ማብቂያ ሰዓት ቁጭት ውስጥ መግባቱ እና ፀፀቱን መናዘዙ ተለመደ አይደል..እሷም ያው በግማሽም ሰው በመሆኗ መጠን ከሰውም ኢትዬጵያዊ ስለሆነች ያው ያ ደግሞ ክርስቶስም ለስጋው አደላ የእንደሚባለው ለእሷም ለዘመዶቿ ተቆጭታ ነው እንጂማ የእሷ የአባቷ ዘመዶች በምድራዊ ዕውቀት የማይመዘን ብቃት እንዳላቸው ታውቃለች፡፡

ለማንኛውም አሁን ደሎ ደርሰዋል…ግን ቀጥታ ወደእናቷ ቤት መሄድ አልፈለገችም ..በመጀመሪያ ያደገችበትን ጫካ ልትሰናበት ፈለገች..መቼስ የደሎመና ጫካ ጫካ ብቻ አይደልም …ውስጡ  የቡና ተክል የተሰገሰገበት ነው..ልጅ ሆነው እንጨት ለቀማ ከእኩዬቾ ጋር ስትሰማራ ከቡናው ተክል ድፍኑን ሸምጥጠውን ይመጡት ነበር..የቡና ተክል ጥሬ ሆኖ ድፍን አረንጓዴ ነው …እየበሰለ ሲሄድ ቢጫ እየሆነ ይመጣል በስተመጨረሻ ሙሉ ብስል  ሆኗል የሚባለው ሙሉ ቀይ ሲሆን ነው..ታዲያ በዛን ጊዜ ፍሬውን ቀፈው ይመጣሉ…ቀዩ የቡና ገለፈት በወስጡ የያዘው ፈሳሽ ልዩ ጣዕም አለው….ሌላው የሚገርማት ይሄ አሁን ከላይ ወደታች የማታየው የደሎ ጫካ ወይም ሀራና ደን የመንግስት ነው…በውስጡ ከደኑ ጋ ተሰባጥሮ ሚገኘው የቡና ተክል ደግሞ የግለሰብ ነው….የኢትዬጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲህ ተዋህደው በስምም ሲጠቀሙ በዚህ ደን ብቻ ነው ያየችው፡፡
👍7011😢2😁1🤔1
ንስሯ ያዶት ወንዝ ውስጥ እንዲጥላት ነገረችው….አምዘግዝጎ ወሰደትና ለመዋኘት በሚመች ቦታ ከስምንት ሜትር ርቀት ላይ ስትደርስ ከተጣበቀበት እራሱን አላቀቀና ወደሰማይ ተመልሶ ተንሳፈፈ..  ተምዘግዝጋ በመውረድ ዳይቭ ገባች……ከእነልብሷ ቦጭረቅ..ደግነቱ ገና ጥዋት ስለነበረ ሰው የለም…እንግዲህ ይሄ የመጨረሻ የምትዋኝበት ቀኗ ነው… ከእናቷ እንደሰማችው አሁን የምትዋኝበት ቦታ እናቷና አባቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙበት ቦታ ነው…….ደጋግመውም ሲገናኙበት የነበረ ቦታ ነበር …እናም አባቷ እናቷን ወደዘመዶቹ ይዞት የሄደው በዚህ አሁን በምትዋኝበት ቦታ ይዞት በመጥለቅ ነው….አዎ ወደአባቷ መኖሪያ ስፍራ የሚወስደው ስውር መንገድ እዚህ አካባቢ ከዚህ ከያዶት ወንዝ ጥልቅ ወለል ላይ ነበር… አሁንም የአባቷ ዘመዶች ዛሬ ማታ ሲመጡ በዚሁ ቦታ  ሾልከው ይሆናል የሚመጡት እናንም ይዘዋት ሚሄዱት.. በዚሁ መንገድ ሊሆን ይችላል….ሰማየሰማያትን ሰንጥቀውም ይዘዋት ሊመጥቁ ይችላሉ….

ዋናዋን ስትጨርስ…በእግሯ ነው ወደቤቷ መጎዝ የጀመረች..ንስሯ መምጣቷን ለማብሰር ቀድሞ እናቷ ጉያ ተሸጉጡ ነው ያገኘችው..እናቷ እቤቱን በቡና አጫጭሳ..ቆንጆ የምትወደውን ገንፎ ቁርስ ሰርታላት ..እርጎ በኩባያ አቅርባላት ነበር የተቀበለቻት፡፡

‹ሀርሜ ደህና ነሽ?››

‹‹ደህና ነኝ ልጄ …›.ብላ አገላብጣ ከሳመችኝ በኃላ የረጠበ ልብሷን እንድትቀይር ሌላ የራሷን ቀሚስ አቀበለቻት…ልብሷን ቀይራ የደረበችላትን ነጭ ጋቢ ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ ገንፎዋን በቀንድ ማንኪያ እየዛቀችና በቅቤ አየለወሰች መዋጥ እና እርጎዋን በላዩ መማግ ጀመረች፡፡
ቡና ተጠጣ…

‹ሀርሜ…›

‹‹ማልታቴ ገረ ኮ››

‹‹ትኝት ብለን እነዋል›

‹‹ቶሌ››አለችና የዘራጋቸውን ሲኒም ከቦታው ሳታነሳ ከበርጩማዋ ላይ በመነሳት በራፉን ቀርቅራ ወደአልጋ ይዛት ሄደች ፣..ብርድልብሱን ገልጣ ገባች..ተከተላት ገባች..ንስሩም ተክትሎቸው ግን ደግሞ እንደእነሱ ብርድልብሱ ውስጥ ሳይገባ ከላይ ሁለቱ መካከል ጉብ ብሎ አደፈጠ…..

እናትዬው ጉያዋ ውስጥ ሸጎጠቻት….እሷም አንገቷ ስር ሰርሰራ ገባችና ከሰውነቷ ተጣበቀችባት….እናቷ እንደበቀደም ለታው አይነት ስሜት ላይ አይደለችም..በቀደም ወደአባቷ እንደምሄትድ ስትነግራት ጠንካራ ነበረች ..እያጀገነቻትም ነበረ….እስኪገርማት ድረስ ቀለል አድርጋ ነበር ያየችው…ምን አልባት በወቅቱ ስለልጇ መሄድ ሳይሆን ስለዕድሜ ልክ ፍቅረኛዋ ነበር እያሰበች  የነበረው…በወቅቱ ልጇን ስታወራት የነበረውን ነገር ሁሉ ለእሱ ካላት ናፍቆት በተሸፈነ ስሜት ነበር ..አሁን ግን ስብር ብላለች..አስተቃቀፎ ሁሉ የማፈን ያህል ነው…ጨምቆ መልሶ ወደሆድ በመክተት የመደበቅ ያህል..አዎ ድብት ብሎታል..ልጇ ከመጣች ጀምሮ በሁለቱም ዓይኖቾ ያቀረረ የእንባ ዘለላ ይታይ ነበር…ከሆነ አስፈሪ ስሜት ጋር እየታገለች ነው….ስለዚህ ጉዳይ ኬድሮን እያሰበች ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት ..ምንም ጭንቀት የሌለበት ምንም  ህልም ያላለመችበት ዝም ያለ  ነበር..የሆነ የሞቀ ፈሳሽ ግንባሯ ላይ ሲንጠባጠብ ነው ከእንቅፏ የባነነችው.. ባለችበት ምንም እንቅስቃሴ ሳታደርግ አይኗን ገለጠችና እናቷ ከአንገቷ ቀና ብላ አይን አይኖቾን ስታይ በእጆቾ ጉንጮቾን ስትዳብስ….. ተመለከተች.. ለካ ግንባሯ ለይ እየተንጠባጠበ ሲያርሳት  የነበረው የእናቷ እንባ ነበር…

‹‹ሀርሜ ምን ሆንሺብኝ?

‹‹ከሄድሽ በኃላ እንድትመለሺ እፈልጋለሁ››

‹‹እንዴ እማ …አንዴ ከወሰዱኝ እኮ ላይመልሱኝ ይችላሉ››

‹‹ግድ የለሽም ..እንድትመለሺልኝ እንደምፈልግ ብቻ ለአባትሽ ንገሪው ፤እሱ አንድ መላ አያጣም…እኔ ያንቺን መመለስ እንደምፈልግ ካወቀ ያደርገዋል..››

‹‹አይ እማ እንደዛ ማድረግ የሚችል አይመስለኝም…››

‹‹አይ ልጄ አባትሽን የት ታውቂዋለሽ…እሱ እኮ ያለዘመዶቹ ፍቃድ ወደዚህ ምድር ሲመላለስ ነበር..እነሱ ሳይፈቅድ እኔን ማፍቀር ችሏል..ወደ ሀገሩ ይዞኝ መሄድ ችሎል..እና በአባትሽ ተማመኚ››
እንዴት አድርጋ ልታስረዳት እንደምትችል ግራ ገባት፡  እሷ በአባቷ ብቃት ሳትተማመን ቀርታ ሳይሆን አሁንም እስር ላይ እንዳለ ስለምታውቅ ነው…ይሄንን ደግሞ ለእናቷ ልትነግራት እና ጭራሽ ቅስሞን ሰብራ ተስፋ ቢስ ልታደርጋት አልፈለገችም..‹‹ግን ምንድነው እነሱጋም አማባገነንነት አለ እንዴ…?እንዴት በእኔ እድሜ ሙሉ ያራሳቸውን አካል አስረው ያኖራሉ….››ምንድነው ከሁለት አንባገነንና በፍቃድ መኖርን ከማያበረታቱ አፋኝ ፍጡሮች ነው እንዴ የተገኘሁት…››በውስጧ አብሰለሰለች፡፡.ወደ እዛ የመሄድ ፍላጎቷ ቀነሰ…

‹ልጄ አንቺ ግን አባትሽን ካየሽና የተወሰነ ጊዜ ከቆየሽ በኃላ ተመልሰሽ መምጣት ትፈልጊያለሽ አይደል፡፡››

‹‹እንዴ ሀርሜ ትጠራጠሪያለሽ እንዴ..እኔ እኮ ጭሩሱኑ መሄድ አልፈልግም››

‹‹እንደዛማ አይሆንም..መሄድሽን ካንቺ በላይ እኔ ነኝ የምፈልገው….ለአባትሽ ሳፈቅረው እንደኖርኩ አንቺ ካልሄድሽ ማን ያስረዳልኛል…አንቺ ሄደሽ አየሽው ማለት እኮ እኔም አየሁት ማለት ነው..ስያቅፍሽ እኔን እዚህ ሆኜ ይሞቀኛል…ሲስምሽም እዚህ ሆኜ እኔን እንደሳመኝ ስለምቆጥረው እንባዬን በደስታ አፈሳለሁ››

‹‹በቃ ሀርሜ ዝም ብለሽ እቀፊኝ ና እንተኛ …››

‹‹እሺ በማለት ትረሱን ዝቅ አደረገችና ከእሷ ተስተካከለችና አቀፈቻት…››

ለሁለተኛ ጊዜ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞት ሄደ 

አይመሽ የለ መሸ ..ሁለት ሰዓት አካባቢ እናቷ ከመኝታዋ አስነሳቻትና ወደ ሻወር ቤት ይዛት ገባች ..ሻወር ቤቱን ከመዝጋቷ በፊት ንስሩ በራፍን የመገንጠል ያህል በረግዶት ገባና የሻወሩ እጄታ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ..እናት በዝምታ በራፍን ዘጋች..ወደሶፊያ ቀረበችና የለበሰችውን የራሷን ቀሚስ አወለቀችላት ፤ፓንቷንም አወለቀችላት፤ መላመላዋን ቀረቸ፡፡ ትንሽ ከእሷ ፈንጠር ብላ አየችትና ጎትታ ወደሻወሩ አስጠጋቻት..ንስሩ ውሀውን ከላይ ለቀቀው ከፀጉሯ ጀምሮ ሠውነቷ ራሠ ..እናቷ ሳሙናውን ከማስቀመጫው
አነሳችና መላ ሠውነቷን በአረፋው አዳረሰችና ትፈትግላት ጀመር...ልክ እንደልጅነቷ...እያገላበጠች ..ከዛ እንደማሰብ አለችና ሳሙናውን ካነሳችበት ቦታ የሆነ ነገር አነሳችና ስሯ ከፊት ለፊቷ ቁጢጥ አለች ..ከዛ ስትጓበኝ እንደመጣችው  የሀገሯ ደን ተንጨፍርሮ ያደገውን የብልቷን ፀጉር ትላጭላት ጀመር..ኬድሮን ከላይ ቁልቁል እናቷን እያየቻት እንባዋ  ይረግፍ ጀመርን ፡፡የጭንቋ ሰዓት ደረሰች… 
ለሊት ለስድስት አስር ጉዳይ …እቤቱን ለቀው ጊቢ ውስጥ ሶስቱም እርስ በርስ ተጣብቀው ተቀምጠዋል..እሷ እናቷና ንስሯ...አብሮነታቸውን ሊጠናቀቅ አስር ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው..እርስ በርሳቸው መነጋገር አልቻሉም…አሷማ ሰውነቷ ሁሉ እየተንቀጠቀጠ ነው….ይሄው ሶስት ቀኑ ወደንስሯ አዕምሮ ዘልቆ ለመግባት እንኳን  ድፍረቱን ማግኘት አልቻለችም..አሁን በዚህች በመጨረሻ ሰዓት ሳይቀር  ልታደርገው  ድፍረቱ የላትም..ምን አይነት ሰቆቃ ላይ እንዳለ..ምን አይነት ሀዘን በውስጡ እንደሚብላላ ለማወቅ የሚያስችል ጭካኔውን ከየት ታምጣው  ....ውይ ደቂቃዎቹ ደግሞ እንዴት ነው የሚበሩት..7 ደቂቃ ቀረው…እናቷ ጉልበቷ ላይ አስደግፋ ጭንቅላቷን ታሻላት ጀመር…5 ደቂቃ ሲቀራው ንስሩ ከስራቸው በተተት ብሎ ተነሳና በቅርብ እርቀት  ካለ ጉቶ መሳይ  እንጨት ላይ አረፈ…ከእናቷ ጉልበት ላይ ቀና አለች….ክንፉን ዘረጋና በመንቁሩ ከክንፉ ስር የሆነ አረንጎዴ ብጣሽ ቅጠል አወጣና በቅፅበት ዋጠው..ገረማት‹‹…ከመቼ ወዲህ ነው ቅጠል በሊታ
👍794👏2
የሆነው…›› ስትል እራሷን ጠየቀች፡ለመሄጃ 3 ደቂቃ ቀረው….ንስሩ ከነበረበት ጉቶ ጥቅልል ብሎ በመንሸራተት  መሬት ላይ ተዘረረ..እናቷም እሷም በደቂቃ ውስጥ ስሩ ደረሱ..አገላበጡት…ከአይኖቹ ደም እየፈሰሰ ነው…‹‹ወይኔ እማ ቅጠሉ….. ቅጠሉ ነው..መርዝ ነው የተጠቀመው..እማ ምን እናድርግ…?››የማሰቢያ ጊዜ ሳያገኙ ግቢያችን በሰማያዊ ብርሀን ተሞላ…ቀና ስትል በሰማይ ላይ ዲስክ መሳይ መንኮራኩር ብርሀን እየረጨች ሰማየ ሰማያትን በመሰንጠቅ እነሱ  ወዳሉበት አቅጣጫ እየወረደች ነው….መጡ ማለት ነው…መጡ መሰለኝ….ወይኔ ንስሬ….

 ተፈፀመ…

ያው አልቋል ብዙ ጥያቄ እንደሚኖራቹ አልጠራጠርም ግን አልቋል ቀጣዩ ድርሰት ደሞ ምንድን ነው ቢያንስ ርእሱን ልንገራቹና YouTube ቻናሉን ከ 100 Subscriber አለፍ ስታደርጉት እንደተለመደው እንጀምረዋለን የቀጣዩ ድርሰት ረዕስ #ትንግርት የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ረጅም ልብ ወለድ መፅሀፍ ነው ስለዚህ ቶሎ እንዲጀመር #YouTube እየገባቹ #Subscribe አድርጉ Link ከታች አለላችሁ አሁኑኑ ከ 100 Subscriber አሳልፉትና እንጀምረው👍

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😱70👎38👍2216👏8🤔4🎉3😢1
🍃በ'ነሱ ቤት🍃
🍄ክፍል ሠላሳ አራት🍄
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
መሳይ ጌታነህን ስታገኘው  በመጀመሪያ የመጣላት ነገር ከበጎ አድራጊ ዎቹ ጋር አገናኝቷት ጉዳይዋን በማሳዘን እንድትነግራቸው መክሯት ዞር የሚል መስሏት ነበር ።ነገር ግን መኪናው ውስጥ አስገብቷት  እርዳታ ሊያደርጉላት የሚፈልጉት ሰዎች ቤተሰቡ መሆናቸውን እና ይህንን ድጋፍ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው በመተማመን ሲያወራ ግራ መጋባት ውስጥ ከተታት ። እናም ልቧ ፈራ ይሄልጅ የእውነት ቁም ነገረኛ ነው ወይስ አይምሮው ንክ ነው ሲያወራ እራሱ  ያልተረጋጋ መሆኑ ያሳብቅበታል ብላ ማሰቧን አላቆመችም ። ከረጅም ጉዞ በዋላ ከዚበፊት በምታውቀው መንደር ውስጥ ታጥፎ ገባ እናም አካባቢው ላይ ያላት ትውስታ አንድ በአንድ መጣባት ።ከአስራ ስምንት አመት በፊት በዚ መንደር ውስጥ ተመላልሳበታለች ። በመጨረሻም ልጇን አርግዛ ስትባረር በዚሁ ድንብርብር እያለች ወጥታበታለች ። በጣም በተጠጋች ቁጥር ያ የአብታሞች መንደር የቀለም ለውጥ ከማድረጋቸው በስተቀር እንዳሉ ናቸው ፣ ልቧ መምታት ጀመረ ፊቷን ወደ ጌታነህ አዙራ ተመለከተችው ። በዝምታ ወደፊት ለፊቱ እያየ ነዳ ትንሽ ሄድ ብሎም አንድ ግዙፍ የተንጣለለ ጊቢ ጋር ሲደርስ አቆመ ።የመሳይ ልብ አብሮ የቆመ መሰለ ።ይህንን ጊቢ ታውቀዋለች ።ጌታነህ ከመኪናው ወርዶ እየከፈተላት እንድትወርድ ጠየቃት መንቀሳቀስ አልቻለችም ።እጇን ያዝ አድርጎ እንድትወርድ ለመናት ፣ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ ።
"እባክህ....."አለች ቃላት እያማጠች
"እባክሽ ውረጂና ከቤተሰቦቼ ጋር ላስተዋውቅሽ እኔ የዛ ባለጌ ወንድም ነኝ የመስፍን ከዚቤት የሚገባሽን እንድታገኚ እስከመጨረሻው ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ አትፍሪ "አላት  መሳይ እንደምንም ከመኪናው በመውረድ ጌታነህ ላይ አፈጠጠች "ባቢ አንተ ነህ እንዲ ትልቅ የሆንከው "አለችው
"አንቺ ታውቂኛለሽ እኔ ግን ምንም ነገር አላስታወስኩሽም ነበር "አላት በመገረም እያያት
"እኔ አልረሳም ትንሽ ልጅ ነበርክ ልታስታውሰኝ አትችልም ግን እንዴት አወቅክ "አለችው ተገርማ
ጌታነህ አብላካትን እንዴት መጀመሪያ ከጓደኞቹጋር እንዳገኛት ፣ከዛ ምን ሲፈጠር እንደነበረ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ፈጠን ፈጠን እያለ ነግሯት በረጅሙ ተነፈሰ ።የአብላካት መጨረሻ ሞት እንዳይሆን ፈርቷል።  መሳይ የሚንቀጠቀጠውን እጇን ማስቆም አቅቷታል ። ጌታነህ ሁኔታዋን ሲያይ ትንሽ ማረጋጋት ያስፈልጋል ብሎ በማሰብ ተመልሰው መኪናውስጥ ገብተው መነጋገር እንደሚችሉ ነግሯት መኪናውስጥ ገቡ እናም ስለቤተሰቦቹ ሁኔታ አወራት አብላካተሸ መታመሟን እና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ስታወራ በቴሌቭዥን ቤተሰቡ ሁሉ እንዳይዋት እና ማንነቷንም እንዳወቁ ከዛ በጣም መደናገጣቸውን ።ከዛ ልጅቷ የራሳቸው ዘር መሆኗን አምነው ለማሳከም እንደፈለጉ አወራት ። መሳይ ያለፈውን አስታውሳ እልህ ያዛት አይሆንም ብላ ጌታነህ ላይ ጮኽች ።
"እንዴት አይሆንም ትያለሽ እኛም እኮ በልጅቷ ላይ መብት አለን ቤተሰባችን ናት ዝም ብለን ስትሞት ልናይ ነው"አላት ተቆጥቶ
"እኛ አትበል አውጥተው ጥለውኛል ከመስፍን አላረገሺም እርሺው ብለው ነው የወረወሩኝ አሁን ምን ተገኘ"ብላ አለቀሰች
"እየነገርኩሽ ነው እንኳን ወላጆቼ መስፍንም ተፀፅቷል ልጁ እንደሆነች አምኗል በወቅቱ የነበረው ነገር አሁን ላይ የለም "አላት ሊያግባባት እየጣረ
"አይ ከነሱ አምሳንቲም አልፈልግም "አለች በደከመ ድምፅ ውስጧ ግን ሲሸነፍ ይታወቃታል
"ላንቺ አይደለም ለአብላካት ነው  መዳን አለባት እኔም ከዚ በዋላ እህት ይኖረኛል  እባክሽ እራስ ወዳድ አትሁኚ "አላት ቀናብላ ስታየው ቆይታ ።አንገቷን በመነቅነቅ ።ውስጧ እያዘነ ተስማማች ። ሌላስ ምን መላ አላት የታመመች ልጅ ይዛ ብትኮራ ምን ሊያዋጣት ። ጌታነህን ተከትላ ወደ ጊቢው ዘለቀች ።ጊቢው ውስጥ እንደገቡ መናፈሻ በመሰለው ስፍራ ላይ ክብ ጠረቤዛ ከበው ተቀምጠው የነበሩት የጌታነህ ወላጆች ቆም ብለው ጠበቋቸው ። ሲቀርቧቸው የጌታነህ እናት የነበረባትን ትምክህት ጣል አድርጋ  ይቅር በይኝ በማለት የመሳይ እግር ላይ ተደፋች መሳይ ያልጠበቀችው ነገር ስለነበር ድንብርብሯ ጠፋ ደጅ ላይ የፎከረችው ነገር ጥሏት ጠፋ የጌታነህን እናት ከመሬት ላይ በማንሳት ፣አቅፋት አለቀሰች ። ጌታነህ ሁኔታው አስለቀሰው ። መሳይን ወላጆቹ ደጋግመው ይቅርታ እየጠየቁ ሲያይ ወላጆቹን እንዲ ተቀይረው በማየቱ ጉድ አለ ። ለማንም ግድ የሌላቸው የሱ ኩሩ ወላጆች ተንበረከኩ ።ይሄ መቼስ ስለ አብላካት ነው ሌላ አይደለም 'ይሄ ቆሞ የቀረ ልጃቸው የልጅ አባት ሊሆን ነው'ብሎ በውስጡ ሳቀ ። ብቻ በፍጥነት ሄዳ ትታከም ......
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨?፨?፨??
አብላካት እናቷ የሄደችበት ጉዳይ ተሳክቶ ሁሉም ነገር ሰላም እንዲሆን በልቧ ደጋግማ ፀለየች ። እናቷን እዚ ምድር ላይ ብቻዋን ጥሎ መሄድ በጣም ያማል ያ እንዲሆን ፈጣሪዋ እንደማይፈቅድ ለራሷ እየተናገረች ትፅናናለች ። ሰሚር ስልኩን እየነካካ አልፎ አልፎ ትክዝ ብላ የተቀመጠችውን አብላካትን ያያል ። ከቆይታ በዋላ ስልኩ ተደወለ አንስቶ ሲያየው ሰመረ ነው ተነስቶ ሊወጣ ፈልጎ ነበር መልሶ ተወው እና አነሳው
"ሃሉ "
"ሰሚር የት ነው ያለኽው እባክህ ልምጣ ሚጣ ጋር ውሰደኝ "አለው ቅስሙ ስብር ብሎ
"እኔ አሁን እሷው ጋር ነኝ እናቷ ስለወጣች አብሬያት ልቆይ ብዬ ነው"
"እሺ አቅጣጫውን ንገረኝ እመጣለው "አለው ሰሚር የሰመረ ሁኔታ አሳዘነው እሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለአብላካት ጥሩ ነበር ታዲያ ለምን አብሯት እንዳይሆን ይከላከላል ?በጭራሽ!   ።አቅጣጫውን ነገረው ሰመረ እሺ ብሎ ስልኩን ዘጋው ።
"እሺ ለማን ነው ደሞ ቤቴን የምትነግረው ኪኪኪ ስንት ሺብር ይዘን መጣን አሉክ ?"አለችው አብላካት እግሯን እያሻሸች
"ሲመጡ ታያለሽ ምን አስቸኮለሽ "
"ስንት ናቸው"
"አንድ ነው ስታይው የምትወጂው ይመስለኛል"ብሎ ሳቀ
"ማነው "አለች ኮስተር ብላ
"ሲመጣ ማንነቱን እራሱ ያስተዋውቀናል"
"ደረቅ "ብላ ለመነሳት ስትል ወጋት በከባዱ አቃሰተች አስተናጋጁ ሰሚር በድንጋጤ ሄዶ አቀፋት እጆቹ ላይ ልፍስፍስ ስትልበት "አቢ አቢ ደና አይደለሽም አቢ..........."እያለ ተጣራ ,,,,,,,,,,,,

,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍504👏1