አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አቶ_ከበደ
:
:
ለራሱ ጉዳይ ሳይቀር አካልቦ አግኝቶኝ፣ ከከተማችን ውድ ከሆነ ምግብ ቤት ፣
''ምሳ እንቦላ'' ፤ ኪስን ከሚያደርቅ ኬክ ቤት ፣ ''ቁርስ እናድርግ'' ገቢን ከሚፈታተን ሻሂ ቤት ፣ ''ሻይ ቡና እንበል'' ብሎኝ ፣ ከመግደርደር በቀር ፣ ከማስፈራራት በቀር ከፍሎ የማያውቀዉ አንድ ወዳጄ፤ ዛሬም ''እኔ ኪሴን አካለሁ፤ አንቺ ትከፍያለሽ '' በተሰኘችው የተበላች ብልጠቱ ሲያነፍረኝ፤ አንድ ሰሞን ''መንገደኛ'' ከተሰኘ መፅሀፍ ውስጥ የተዋወኳቸዎን አቶ ከበደን መሆን አማረኝ።
ለመሆነ አቶ ከበደ ማንናቸው ? አቶ ከበደ የአቶ ደበበ ወዳጅ ናቸው።

አቶ ከበደ በቀበሌ መዝናኛ መጠጥ ቤት በተደጋጋሚ ሒሳብ ሲከፍሉ ፤ አቶ ደበበ ደግሞ ፤ ''በእኔ ልክፈል'' ማግደርደር በ።ረታቸው በኩል ካለው የኮታቸው የውስጥ ኪስ እየገቡ መበርበራቸውን አላቆሙም።

አቶ ከበደ ዘወትር ይከፍላሉ ። አቶ ደበበ ዘወትር ያችኑ ቦታ ይበረብራሉ ። ከፍለው ግን አያቁም።

ሁኔታው ያስመረራቸው አቶ ከበደ አንድ ቀን ፣ ''ደበበ ፣ እሱ ነገር ብር ከሆየ ክፈለው። ተባይ ተሆነም ግደለው '' አሏቸው።

ይህቺ ታሪክ በይሉኝታ እግረ ሙቅ ተይዘን ለደበበዎች ከበደ መሆን ላቃተን ደህና አደፋፋሪ ናት። እስቲ አሁን ላይ ኪሳችሁን በማከክ ላይ ያላችሁ ደፈር በሉና ክፈሉት😁

መልካም ምሳ።
አትሮኖስ pinned «#አቶ_ከበደ : : ለራሱ ጉዳይ ሳይቀር አካልቦ አግኝቶኝ፣ ከከተማችን ውድ ከሆነ ምግብ ቤት ፣ ''ምሳ እንቦላ'' ፤ ኪስን ከሚያደርቅ ኬክ ቤት ፣ ''ቁርስ እናድርግ'' ገቢን ከሚፈታተን ሻሂ ቤት ፣ ''ሻይ ቡና እንበል'' ብሎኝ ፣ ከመግደርደር በቀር ፣ ከማስፈራራት በቀር ከፍሎ የማያውቀዉ አንድ ወዳጄ፤ ዛሬም ''እኔ ኪሴን አካለሁ፤ አንቺ ትከፍያለሽ '' በተሰኘችው የተበላች ብልጠቱ ሲያነፍረኝ፤ አንድ…»
#ይሸታታል
:
:
#በሕይወት_እምሻው
:
:
ለምኖርበት ሕንፃ የፅዳት ተጠሪ ስለሆንኩ ፣ በየወሩ እየዞርኩ ለሰራተኞች የሚከፈለዉን ደሞዝ መዋጮ እሰበስባለው።
ቅዳሜ እንደተለመደው እየዞርኩ የአንዷን ጎረቤቴን በር አንኳኳሁ።

ከፈተች።

ከእሷ ቀድሞ ከቤቷ ውስጥ የወጣው የትኩስ እንጀራ ሽታ አወደኝ። የትኩስ እንጀራ ነገር አይሆንልኝም። ቁንጣን ይዞኝ ፣ ''ማር እንኳን አልስም '' ብዬ እንኳን ፣ የማልጨክንበት ነገር ቢኖር ትኩስ እንጀራ ነው ።

ሳይርበኝ ሆዴ ተላወሰ።

ምግብ ሳያሰኘኝ ሞረሞረኝ።

''ሄይ....የፅዳት ነው አይደል....?'' ስትለኝ ወደራሴ መለስ አልኩና ፣

''አዎ....የፅዳት ብር እየሰበሰብኩ ነው.....። ውይይ....ትኩስ እንጀራ ነው የሚሸተኝ አይደል?''
አልኳት፣ ከተናገርኩት ውስጥ ''ትኩስ እንጀራ ነው የሚሸተኝ አይደል?'' የሚሉት ቃላት ያለ ፍቃዴ ከአፌ ስለወጡ እያፈርኩ።

መልስ ሳትሰጠኝ፣ ብሩን ለማምጣት መሰለኝ ወደ መኝታ ቤት ገባች።
አኔ እዛው በሩ ደፍ ላይ ወደ ውስጥ ሳልገባም፣ ወደ ውጭ ሳልወጣም፣ ቆሜ ትኩስ እንጀራውን መማግ፣በአፍንጫዬ መመገብ ጀመርኩ።

አንዳንድ ጠረኖች የሉም? የሰከንድ ስብርባሪ ሳይፈጅባቸው ዐሥርት አመታት ወደኋላ የሚወስዷቹህ? በልጅነታችሁ ያሸተታችሁት አበባ፣ በልጅነታችሁ የበላችሁት ማስቲካ፣ በልጅነታችሁ የተቀባችሁት ቅባት ፣ ዳግም ስታገኙት በቅጽበት ጊዜን ሽሮ መልሶ ልጅ አድርጎችሁ አያውቅም?

የእንጀራ ሽታ እዛው በቆምኩበት ልጅ አደረገኝ።

በዚህ ሒሳብ ሳስበው የራበኝ እንጀራ አልነበረም ። ውል ያለኝ ልጅነቴ ነው ፣ የራበኝ ትዝታዬ ነው።

እናቴ፣ እንጀራ ጋግራ ስትጨርስ እንጎቻ ሰርታልኝ በበርበሬ የምትሰጠኝ።

ትንሽ ሳለሁ ዘወትር ቤታቸው ተልኬ በሄድኩ ቁጥር እንጀራ ሲጋግሩ ከገጠመኝ ፣ ''የኔ ኮረሪማ...ነይ ይሸትሻል'' ብለው ቆረስ አድርገው የሚያጎርሱኝ ፣ እማማ የምወድሽ።

የዘመን ናፍቆት ነው ሆዴን የሞረሞረኝ።

ባለ እንጀራዋ ጎረቤቴ በርካታ ሰውነቷን እየጎተተች ብሩን ይዛ ተመለሰች።

''ይሄው'' አለችኝ።

''በይ ሂጂ እንጂ ምን ቀረሽ?'' ዓይነት አስተያየት ዐይታኝ በሩን ልትዘጋው እየዳዳት።

''ትኩስ እንጀራ በጣም ነው የምወደው !'' አልኳት። (ማነው እንዲህ ፈጣጣ ያደረገኝ? ሥነ ምግባሬ ወዴት ገባ?)

''ተይ እንጂ....? እኔ ደሞ ስጠላ...የሚጠባበቀው ነገር ያስጠላኛል'' አለችኝ በሩን አጥብቃ እንደያዘች።

''በሚጥሚጣም ቢሆን አትወጂም...? እኔ ግን ነፍሴ ነው....አሁን ሲሸተኝ ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቂያለሽ..''(ምነው እነደዚ ቀላዋጭ ሆንኩ ግን)

ዐረፍቴ ነገሬን ሳልጨርስ ፈጠን አለችና፣ ''አይ እኔ እንጀራ ካደረ ነው የምወደው....'' በሩን መዝጋት እየጀመረች ነው።

ይሄን ግዜ በመሀላችን ምቾት የሚነሳ ዝምታ ሰፈነ።

ሳላውቀው ዐይኔ እምባም ያቀረረ መሰለኝ።

የእማዬ ትኩስ እንጎቻ በሚጥሚጣ፣ የእማማ የምወድሽ የማይዘጋ በር ትዝ ብሎኝ እምባዬ ሊያመልጠኝ መሰለኝ።

ምን ሆና ነው ?

ስስት ነው ? (ቁራሽ እንጀራ ልትሰሰት የሚገባት ሰው አትመስልም። ብትሰስትስ ብበላ አንድ መሶብ ሙሉ እንጀራ አልበላ፣ ለምንስ በፍጥነት በሩን እላዬ ላይ መዝጋት ፈለገች? ብቻዋን ለመሆን ብትቸኩልስ? ብቆይ አንድ ሳምንት አልቆይ ....)
ይህቺ በእድሜ ዐርባ ቤት ያለች ሴት ምን ያህል ተንጋዳ ብታድግ ነው እንዲህ ያለውን ነውር የምታደርገው?

በዝግታ የምትዘጋው በሯ፣ እኔ ላይ ብቻ ሳይሆን መሀበራዊ ህይወታችን ላይ፣ እኔ ላይ ብቻ ሳይሆን ፣ ልማድና ጉርብትናችን ላይ ለዘላለም የሚጠረቀም ታላቅ በር መሰለኝ።

ከስጥ ላይ ሊበላ እጁን ሲዘረጋ እንደተመታ ልጅ ሽምቅቅ አልኩ። እግሬ ጎማ ኖሮት እየተነዳሁ በፍጥነት ብጠፋ እየተመኘሁ...ሀገሬ ላይ ሆኜ ሀገሬ እየናፈቀችኝ ፣ ወደ ቤት ተራመድኩ።

ኢትዮጵያውያን ልማድና ወጋችን ፣ መተሳሰባችን ፣ መሐበራዊ ሕይወታችን እና ጉርብትናችን በብዙ ተፈትኖ አልፎል።

ቢሆንም...

''እንኳን በአንድ ምጣድ ቢጋገር በመተ ፣

ይሸታታል ትቅመስ ፣

ይሸተዋል ይቅመስ ፣

ማለት ድሮ ቀርቶ ፣'' ተብሎ የተተረተው ለረሀብና ለቸነፈር ጊዜ እንጂ፣ ቋሚና ከፍ ለማለት የሚገዳደር መካከለኛ ገቢ ኖሯቸው በአፓርትመንት ውስጥ ለሚኖሩ ጎረቤታሞች ነው ብዬ አስቤ ግን አላውቅም።

🔘አለቀ🔘

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት🙏

ያበረታናል እና እቺን 👍 እየገጫጭሁን።
👍31
አትሮኖስ pinned «#ይሸታታል : : #በሕይወት_እምሻው : : ለምኖርበት ሕንፃ የፅዳት ተጠሪ ስለሆንኩ ፣ በየወሩ እየዞርኩ ለሰራተኞች የሚከፈለዉን ደሞዝ መዋጮ እሰበስባለው። ቅዳሜ እንደተለመደው እየዞርኩ የአንዷን ጎረቤቴን በር አንኳኳሁ። ከፈተች። ከእሷ ቀድሞ ከቤቷ ውስጥ የወጣው የትኩስ እንጀራ ሽታ አወደኝ። የትኩስ እንጀራ ነገር አይሆንልኝም። ቁንጣን ይዞኝ ፣ ''ማር እንኳን አልስም '' ብዬ እንኳን ፣ የማልጨክንበት…»
#የማንነቴ_ማተብ
:
:
ሦስተኛ ክፍል መሰለኝ ስለ ሰንደቅ ዓላማችን ለመጀመርያ ግዜ የተማርኩት።

የተማርኩት፣ ሰንደቅ አላማዬ የነፃነቴ ምልክት ፣ የማንነቴ ማተብ ፣ እንደሆነች ነው።

የተማርኩት፣ ሰንደቅ አላማዬ የተሰራችው ከሦስት ቀለማት እንደሆነ ነው።

ቀለሞቹም አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ናቸው። ምሳሌያቸውም እንደሚከተለው ነው።

💚አረንጓዴው ተሰፋን፣ ልምላሜንና ሀብትን ይወክላል።

💛ቢጫው በሐይማኖት፣ በአበባና በፍሬ ይመሰላል።

ቀዩ ደግሞ ለፍቅር፣ ለመሰዋትነትና ለጀግንነት ምሳሌ ይሆናል።

የተማርኩት ይሄንን የው።

ስለዚህ፣ ለእኔ ሠንደቅ አላማዬ ከጊዚአዊ አስተዳደር ፣ ከአላፊ ህግና ደንብ፣ ከተለዋዋጭ አጀንዳ በላይ ናት።

ሰንደቅ ዓላማዬ ዘውድ ከደፋ አንበሳ፤ ቀይ መደብ ላይ ከሰፈረ ቢጫ ኮኮብ፣ ሐውልትና እና የፋብሪካ ማሽን ጥርስ፣ ሰማያዊ መደብ ከተቀመጠ ቢጫ ኮኮብ በላይ ናት።ሰንደቅ አላማዬ ከወቅት ጋር የማትለዋወጥ፣ በዘመን የማትናወጥ፣ ይልቁንም ዘላአለም ፀንታ የምትኖር የነፃነቴ ምልክት ፣ የማንነቴ ማተብ ናት። 💚💛❤️
#የበግ_ወግ
:
#በአለማየሁ_ገላጋይ
:
:
ያን ሰሞን አሞኝ ከረመ።

የታመምኩበትን ምክንያት አምጰረጵር ሲጠየቁ ተገርዞ ነው አሉ። ከአንገታቸው ይገረዛቸውና የታመምኩበትን የምናውቅ እኔና አንድዬ ብቻ ነን። ሁከት ላስተምርክ በሚል በዱላ አናቴን የበጠበጡኝ እራሳቸው ፣ አምጰርጵር ናቸው።

''ከነ ሸለፈቱ ልጄ ጥግ አይደርስም ብዬ እራሴ ገረዝኩት ። ይላሉ አሉ።

ያም ሆነ ይህ አሞኝ ከረመ።

አምጰርጵር አያያዜን ሲያዩት ከህግ ባይሆን ከህሊና ወቀሳ አላመለጡም ኖሮ እንዳገግምበት እንደ እሳቸው አጭር ቀጭን በግ ገዝተው አመጡ፣ ለገመምተኛ ሰው ገመምተኛ በግ ይገዛል?

በጉ ማስጠንቀቅያም ነበረው ፣ ማስጠንቀቅያው የ አንጰርጵር ነው።

''ሳሚዎል'' ይሉኛል ።

''እንሆኝ አምጰርጵር ''እላቸዋለሁ ።

''ስሜ አምጰርጵር አደለም ፣አምበርብር ነው ከንቱ!''
ከተቆጡ በኋላ ''ለማንኛውም በጉን ከሳምንት በፊት አትረደው ?''

''ለምን?''

''ከንቱ! ይሄ ምቀኛ ህዝብ አይኑ ደም ይልበሳ!''

በጉ በእል ሊያገግም ነው? ወይስ እኔ በሱ? አልገባኝም!!

በገመምተኛ ጉልበቴ እያመላለስኩ በጉን ሳር ማስጋጥ ጀመርኩ።

መቼም በጉ የለም ማለት ይቀላል ። አንጰርጵር የገዙት በግ ሳይሆን አቧራ የጠጣ የበግ መተማመኛ ዲክላራሲዎን ነው ማለት ይቀላል።

ስለበጉ እገልፃለሁ....

...በጉ ለቀድሞ ባለቤቶቹ ከበሮ ነበር ፣ የፀጉሩ መመለጥ የሚያረጋግጠው ይሄንኑ ነው። ያ ግዙፍ የበጉ ባለቤት ዝናብ ሲሆንበት ጭንቅላቱ ላይ ጣል አድርጎት የሚወጣዉ ይሄንን መከረኛ በግ ነበር ።ምናልባትም ሚስቱ ሲበርዳት በጉን አቀብሉኝ ብላ አንገቷ ላይ ትጠመጥመው ይሆናል

በጉ(መቼም እሱ ፈጣሬ በግ ብሎ ስለፈጠረው ይሄንኑ ስያሜ መንፈግ ከእግዚሐብሄር ጋር መጣላት ስለሆነብኝ ነው) ከአንገቱ እስከ ጭራው (ላቱ ያላልኩት አውቄ ነዉ) ፍሎጥ የገባበት ነው የሚመስለው ። ሳር ለመጋጥ ጎንበስ ሲል የኋላ እግሮቹ ብድግ ይላል።

የፊትና የኋላ እግሮቹን በማፈራረቅ እያነሳ ...በሚዛንኛ...አንድ ሦስቴ ሳር ከነጨ በኋላ ፍዝዝ ቡዝዝ ብሎ በሃሳብ ይኖግዳል ። ይሄንን ስመለከት ይሄ በግ ያሳለፈውን መከራ እያብሰለሰለ እንደሆነ እጠረጥራለው። ሀሳቡን ለማናጠብ ሳሩን ነጨት አድርጌ ስሰጠው ከጭንቅላቱ ጎንበስ ሲል ያመሰገነኝ ይመስለኛል። ሳሩን ከእጄ ላይ ነጨት ፣ ነጨት ያደርጋል።

ካመሰገነ ምኑን በግ ሆነ?

በዚህ ሁኔታ ፣ ሁለቱ ገመምተኞች ስንወጣና ሳይታወቀን ሳምንት አለፈን። አስረኛው ቀን ላይ ይመስለኛል ፀትተኛው በግ፣ የበግ ወግ ለማድረስ ድምፅ ማውጣት ጀመረ ። ብቻ እንደበጎቹ ''ባ...ኸ... ማለት ስላቃተው ''ሳ....አ... ነበር የሚለው ።

''ሳ...ኣ...

ስንወጣ ..ስንገባ..ለምዶኝ ''ሳሚ'' ሊለኝ ይሆን እንዴ?

አዎ!

ደጃፌ ሳይከፈት ካረፈደ

''ሳ...ሚሚሚ'' ይል ጀመር። 😃

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍31
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
:
እንደ እህቴ ቆንጆ አደለሁም ። ሕይወቴን ሙሉ በተደጋጋሚ የሰማሁት አንድ ነገር ቢሆን እንደ እህቴ ቆንጆ አለመሆኔን ነው።የሁለት አመት ታላቄ ናት።ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ የአባትና የአያታችንን ስም ሰምቶ እስኪያረጋግጥ ፤ አንድ ቤት ውለን ማደራችንን እስኪያውቅ ድረስ፣ በመልክ መራራቃችንን የሚያውቅ ሰው ሁሉ፣ እህትማማቾች መሆናችንን አያምንም ነበር።

''የሆነ ነገራችሁ ግን ይመሳሰላል....አለ አይደል....ደማችሁ'' እያሉ፣ ሊያፅናኑኝ የሚተጉ ሰዎች አንዳንዴ ይከሰታሉ።እኔና እህቴ በደም እንኳን ብንመሳሰል ከፎቶ ሾፕ በፊትን በኋላ ነው የመንሆነው።በፊቱ እኔ...በኋላዋ እሷ። በዚህ ላይ እህቴ ራሷን መጠበቅ ፣ ውበቷን መጨመር ታውቅበታለች። እኔ አጎፍሬው ስዞር፣ ቅንድቧን መቀንደብ የጀመረችው፣ አስራ አምስት ሳይሞላት ነው።እኔ በቋሚነት በሄር ባንድ አፖሎ አስይዤው ስሄድ፣ ለታክሲ የሚሰጠንን ገንዘብ አጠራቅማ ጸጉሯን መቶከስ የጀመረችው ዘጠነኛ ክፍል እንደገባን ነው።

እንደ እህቴ ቆንጆ አይደለሁም። ግን ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ። መደበቅያዬ ትምህርትና መፅሀፍት፣ ብቸኛ የውዳሴ ምንጩ ጉብዝናዬ ስለነበር ፣ ትምህርቴ ላይ ቀልድ አላውቅም ነበር። ገናና ተማሪ ነበርኩ። ከሴክሽን አንደኛ የምወጣ፣ እህቴ ተንጠልጥላ ስታልፍ ፣ ደብል የምመታ።

የእህቴ ምኞት አንዱን ሀብታም በገመዜ አግብታ የድሎት ኑሮ መኖር ነበርና ሃያ ሁለት አመት ሳይሞላት አገባች። የመጀመርያ ድግሪዬን በህግ (ያው በከፍተኛ ማእረግ ተመርቄ)ከእሷ ጋር የመነፃፀር ዘመኔ አበቃ ብዬ እፎይ ባልኩበት ግዜ ግን፣ የእማዬ፣ ''ምናለ እንደሷ ብትሆኚ'' ንዝንዝ ጭራሽ ባሰ።

ለእማ የእኔ በማእረግ ተመርቆ የብዙ መሦርያ ቤቶች፣ ''እኛ ነን የምንቀጥራት'' ሽምያ ብዙ አላኮራትም። በተመረኩ በቀናት ውስጥ ቤት ተቀምጠን እንዲህ አለችኝ፣

''በይ እንደ እህትሽ አንቺም ቶሎ አግቢ።''
''እንዴ! ማስተርሴን ሳልሰራ?'' አልኳት።
''ማግባት በወጣትነት ይሻላል፣ በተለይ እንዳንቺ አይነቱ....''
በተለይ እንዳንቺ አይነቱ ማለት ምን ማለት ነው ? በዚህ ማስጠላትሽ ላይ እድሜ ስትጨምሪበት፣ እንኳን የሚያገባሽ በዕንጨት የሚነካሽ አታገኚም ማለት ነው?

ተውኳት ማስተርሴን ሠራሁ። ኢንተርናሽናል ሎው ነው የተማርኩት። ኤ ደርድሬ ከመመረቄ በፊት ነው ስራ ያገኘሁት። ያውም የኮራ የደራ ኢንተርናሽናል ኤንጂኦ። በዜሮ አመት ልምድ 27050 ብር ስቀጠር በድንጋጤ እንጥሌ ዱብ ሊል ምንም አልቀረው።ለነእማ ስነግራቸው፣ ሌንጬቻቸው እስኪንጠለጠል ድረስ ደነገጡ። አባዬ ጎበዝ አለኝ። እማ ግን ከድንጋጤዋ መልስ ስትል ፣ ''ይሁን...ገንዘብ ብቻውን ምን ይራሰራል ይልቅ ቶሎ አግቢ'' ነበር ያለችኝ።

ኤንጂኦ!

ኤንጂኦ በእህቴ አይነት ሰዎች የተሞላ ነው። በራሳቸው አምረው በገንዘብ ይበልጥ የቆነጁ፣ ፉንጋ ሆነው መተው፣ በገንዘብ ሀይል ደም ግባት ያበጁ ይበዙበታል። ከሚሰሩት በላይ የሚከፈላቸው ሴቶች፣ ቋ ቀጭ ጫማቸውን ሲያንቋቁ ይውላሉ። ውድ ሽቶቸውን በየኮሪደሩ እየረጩ ሲወዛወዙ ያመሻሉ። ሲፎራ ሊፒስቲክ ተለቅልቀው ፣ የ 700 ብር ፓውደር ፊታቸው ላይ ነስንሰው፣ በሳምንት ሁለቴ የሚተኮስ ውድ የብራዚል ጸጉራቸውን ሰክተው፣ በዋክስ ሙልጭ ተደርጎ የተላጨ እግሮቻቸውን በአጭር ቀሚስ አጋልጠው ወዲህ ወዲህ ሲሉ ያረፍዳሉ ይውላሉ

ይሄን ስራ ይዤ ለመቆየት አካባቢዬን መምሰል ነበረብኝ። እንዴት አድርጌ እንደምመስል ግን መንገዱ ጠፋኝ እኔ አሁንም ዩኒቨርስቲ ያለሁ ድክርት ተማሪ ነው የምመስለው። ወፋፍራም እና ቀጭን ሰውነቴ ላይ፣ የሚወዛወዙ ሹራቦቼ ከትልቅ መነፅሬ ቡናጫ (ቡኒና ግራጫ) ሱሪዎቼ ጋር ተደምረው ፣ እድሜ ላይ 20 ዐመተ ይጨምራሉ። ከተማሪዎች ጋር መጨቃጨቅ የሰለቻት የሃይል ስኩል ላይበረርያን እንጂ የኤንጅኦ ሰራተኛ አልመስልም። ሥራ በጀመርኩ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከሁሉ ጋር የሚግባባው ቄንጠኛው የሥራ ባልደረባዬ ቶማስ ቢሮዬ መጣና፤ ኦፊስ ፓርቲ ጋበዘኝ።

''መቅረት አይቻልም!'' አለኝ ማንነቴን አጢኖ።

''እህ....እስቲ ላስብበት'' (መቀላቀሉን እፈልገዋለሁ ግን ምን ለብሼ ልሄድ ነው ብዬ ተጨንቄ ነው)

''ማሰብ የለም ...መምጣት ብቻ ነው...መምጣት'' ብሎኝ ጥሎኝ ሄደ።ቶማስ በሄደ በደቂቃ ውስጥ አጠገቤ የምትቀመጠውን የዘናጭ ጥግ ጠራኋት።

''ሜሪ...''

''ወዬ..''

''ልብስ የት ነው የምትገዢው?''

''ማርቲስ ኮሌክሽን ሂጂ'' አለችኝ። ከስራ እንደወጣን ሄድኩ። ልብሶቹን ሁሉ እየነካካው በፍርሀት ከቃኘው በኋላ የምትሸጠውን ዘናጭ ልጅ...
''ማታ እራት አለብኝ...ሾፒንግ ሞቴ ነው ....አስቲ አማርጪኝ በናትሽ'' አልኳት። ሰባ ምናምን ነገር ሳልሞክር አልቀረሁም። አላበኝ። በመጨረሻ ከጉልበቴ ትንሽ ከፍ የሚል ፣ በጣም የሚያምር ብሩህ አረንጓዴ ቀሚስ መረጠችልኝ። ''ሲያምርብሽ!'' አለችኝ (የሚከፈላት እንዲህ እንድትል ስለሆነ ከቁብ አልቆጠርኳትም)

''እውነት?'' አልኳት ዝም ላለማለት።

''ውይ በጣም...ሰፊ ነገር ለብሰሽ ስትመጪ ወፍራም ትመስይ ነበር....በጣም ያምራል ሰውነትሽ።'' (ቢከፈላትም ደስ አለኝ....)

''ስንት ነው?'' አልኩኝ።

''950.....ሴል ላይ ነው'' አለችኝ ፈጠን ብላ።

ወይ ሴል እቴ!

ትንሽ አቅማምቼ....

''እሺ በቃ እወስደዋለው....'' አልኩና፣ አንዴ ዞር ብዬ ቂጤን ዐየሁት። ፍጥጥ ብሏል።

''አይዞሽ በጣም አምሮብሻል...ግን....እግርሽን ዋክስ ብታደርጊ ጥሩ ነው....'' አለችኝ።

አስጠቅልዬ ወጣሁ።

''ፐፐፐ ሌላ ሰው መስልሽ የለ እንዴ! ዛሬ ላይብረሪ የምትሄጂ አትመስይም አለኝ ቶማስ፣ ገና ሲያየኝ።

ዐስራ ምናምን ከሚሆኑ የሥራ ልጆች ጋር እንደ ተቀመጥኩ አስተናጋጅ መጣና ፣ ''ምን ልታዘዝ ?'' አለኝ።

''ሁላችንም ቮድካ ይዘናል...ቮድካ አጠጭም..? የሚል ድምፅ ሰማሁና ወደ ቀኝ ዞርኩ። አይቼው የማላውቅ የሚያምር ልጅ ነው።

እኛ ቤሮ ነው የሚሰራው..?
''አይ...መጠጥ ብዙ አደለሁም...ቶሎ እሰክራለዉ...'' አልኩ፣ ትኩር ብዬ ማየቴን ሳላቋርጥ።

''አይዞሽ...ባንዴ እኮ አንድ ብርጭቆ ነው የሚያመጣልሽ...'' አለና ፈገግ አለ። የፈጣሪ ያለ! በእነዚህ ጥርሶቹ እህል አላምጦ ያውቃል?

ነ.....ጭ.....ናቸው።

ትንሽ ተከራክረን ቀይ ወይን፣ ጣፋጭ የአገር ውስጥ ወይን አዘዝኩ። ''የት ዲፖርትመንት ነው የምትሰሪው?'' አለኝ ፣ ወይኑ እንደመጣ። ነገርኩት።

''እኔ ኮሚኒኬሽን ነኝ ግን ልለቅ ነው....'' አለኝ።

''ውይ.... ለምን ?

''የተሻለ ነገር አግኝቼ ነው...ዩ ኤን ዲፒ ልሄድ ነው'' አለኝ።

ከፊቴ ላይ ለምን ? የሚሀውን ቃል አንብቦ ነው?

''አሪፍ.....'' አልኩና ወይኔን ጎንጨት አልኩ።

''ቀሚስሽ በጣም የምራል'' አለኝ በጣም ተጠግቶኝ...

''አመሰግናለው...'' አልኩ፣ ፀጉራም እግሮቼን እንዳያይ ቀሚሱን ያለ አቅሙ ወደ ታች እየጎተትኩ።

''ዋጋውም ያምራ.....'' አለኝ።አሁንም ተጠግቶ ድምፁን ዝቅ አድርጎ። በአንድ ግዜ ፊቴ የምጠጣውን ወይን መሰለ።

ምንም ሳይለኝ እጆቹን ወደ አንገቴ ጀርባ ልኮ ፣ እረስቼው የነበረውን የዋጋ ወረቀት በጠሰው። ሽምቅቅ አልኩ። በሚያምሩ ጥርሶቹ ሣቀና፣ ''አዲስ ነው ማለት ነው....?'' አለ። ዝም ብዬ ያዘዝኩትን ጥብስ በጣቶቼ ማማሰል ቀጠልኩ።

''ምን አይነት ምግብ ነው የምትወጅዉ?'' (ለምንድን ነው ጥርሱ እንዲህ የሚያምረው?)

''አኔ....''

''አዎ...አንቺ
👍61
''ሽሮ...'' አልኩ፣ የግዴን ቀና ብዬ እያየሁት።(ለምንድን ነው መልኩ እንዲህ የሚያምረው?)

''አዲስአባ አለ የተባለ ሽሮ ቤት እወስድሻለው... መቼ ይመችሻል?''(እወስድሻለው? ማለት....ለብቻችን...?ፈልጎኝ ነው...? ማለቴ ደስ ብየው ነው?)

''ማለት...በቡድን'' አልኩትንሽ ተርበትብቼ። (ለምንድን ነው እንዲህ አድርጎ የሚያየኝ?)

''ኖ...እኔና አንቺ...''

''እሺ ....'' ሆዴ ተገለባበጠ።

'"መቼ ይመችሻል ታድያ?''

''እ...ዛሬ ምንድን ነው...?''

''አርብ...''

''ሰኞ...ከስራ በኋላ ?''

''አሪፍ...በቃ ሰኞ እንሄዳለን...''

''እሺ...''

''ግን አደራሽን...''

ቀና ብዬ አየሁት። ምኑን ነው አደራሽን የሚለው ?

''ምኑን? አልኩት፣ ወይኔን ብድግ አድርጌ እየተጎነጨሁ።

''ለዛም ቀን አዲስ ቀሚስ እንዳትገዢ...'' ትን ሊለኝ ነበር።

''ቀልዴን ነው...'' አለና ትከሻዬን እንደቀልድ ነካኝ። (ወይኑ ነው እጁ ይሞቃል?)

''ገባኝ...'' አልኩ እንደምንም።

''ኦኬ...ስልክሽን ስጪኛ...''

ስልኬን ለጥናት ቡድን ወይም ለግሩፕ አሳይመንት ካልሆነ ለወንድ፣ ለአንድ ወንድ፣ ያውም እራት ሊጋብዘኝ ለፈለገ ቆንጆ ሰጠሁት።
ይሄ ሊጎነጎን የደረሰ የእግሬን ፀጉር ቅዳሜ ወይም እሁድ ዋክስ መደረግ አለብኝ። እንደ ሴቶቹ ሙልጭ አድርጌ መላጨት አለብኝ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
አትሮኖስ pinned «#ቆንጅዬ : #በሕይወት_እምሻው : : እንደ እህቴ ቆንጆ አደለሁም ። ሕይወቴን ሙሉ በተደጋጋሚ የሰማሁት አንድ ነገር ቢሆን እንደ እህቴ ቆንጆ አለመሆኔን ነው።የሁለት አመት ታላቄ ናት።ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ የአባትና የአያታችንን ስም ሰምቶ እስኪያረጋግጥ ፤ አንድ ቤት ውለን ማደራችንን እስኪያውቅ ድረስ፣ በመልክ መራራቃችንን የሚያውቅ ሰው ሁሉ፣ እህትማማቾች መሆናችንን አያምንም ነበር። ''የሆነ…»
#የቱ_ይበልጣል ?
:
:
በአንዱ ቀን የቀጠርኩት ሰው እስኪመጣ ፣ ከከተማችን ቅንጡ የገብያ ማእከሎች በአንዱ ውስጥ ያለ ግብ እዞራለው።

ለዲሪቶነት ለሚቀርብ ሱሪ የሃምሳ ኪሎ ጤፍ ሒሳብ የሚያስከፍሉ ሞልቃቃ ቡቲኮች ።

ርካሽ ኬክ በ 50 ብር የሚሸጥባቸው ኬክ ካፌዎች።

አምስት ካሬ የማይሞላ የቄንጠኛ የግድግዳ ወረቀት ጥቅልን፣ በሺ ብር የሚያቀርቡ ሱቆች።

በመሀል ከድካም ብዛት እግሮቼ አልሄድ ሲሉኝ ፣ ግድግዳና ጣርያ ወደሌለው ሞባይልና ተከታዬቹን ወደ ሚሸጥ ሰፋ ያለ ሱቅ ጋር ደገፍ ብዬ ቆምኩ። የአዲስ አበባ ፀሀይ የተጫወተበት ፊት ያለው ጎልማሳ ፣ ከሱቁ ባለቤት ጋር ጮክ ብሎ ይነጋገራል ። ድርድር መሰለኝ።እንዲህ ያወራሉ።

...አንቺ ደግሞ....የማይረባ ከቨር እየሸጥክልኝ በየዐስራምስት ቀኑ ታመላልሽኝ ጀመር አይደል ..?

ኸረ አባት እኛ የማይረባ እቃ አንይዝም..እቃችን ሁሉ ብራንድ ነው።

ባክሽ ብራንድ ምናምን አትበይኝ...እዚህ ሱቅ ለከቨር ብቻ የከፈልኩት ገንዘብ ሌላ ሱቅ ያስከፍታችኋል ልጅቱ በመሽኮርመም ሣቀችና ወሬያቸውን ቀጠሉ።

ምን ሆነብህ የምር....?

ባለፈው ሌላ ልጅ ነበረች መሰለኝ...400 ብር ከፍዬ የገዛሁት ከቨር ስልኬ አንዴ ሲወድቅ ስንጥቅጥቁ ወጣ...ስልኬም ለጥቂት ነው የተረፈው...

''የእኛ እቃ?....''

''አዎ...አልኩሽ እኮ...የቻይና እቃ እየሸጣችሁልን.. ለከቨሩም ከቨር መግዛት ሳያስፈልገን አይቀርም በዚ አይነት።

ልጅቱ እንደገና በመሽኮርመም የታጀበ ሣቅ
ሣቀችና

''በቃ እኔ ዛሬ መርጬ እሰጥካለው...ከአራተኛ ፎቅ ብትጥለው እንኳን ከተሰበረ በኔ ነው...ሃሃሃ

ሃሃሃ...እሺ አሳይኝ..

ከአምስት ወይ ስድስት በላይ የተለያዩ ሽፋኖችን በፍፁም ጥንቃቄ፣ በከፍተኛ ትግስት ሲመርጥ ይታየኛል። እኔ ለእሱ ደከመኝ። እኔ ለእሱ ታከተኝ። በትጋቱ እየተገረምኩ የስንት ሺ ብር ሞባይል ቢይዝ ነው ይሄ ሁሉ ጭንቀት ? ብዬ እያሰብኩ ሳለ ወሬአቸው እንደ ቅድሙ ጮክ ብለው ሲቀጥሉ ማዳመጤን ቀጠልኩ።

እርግጠኛ ነሽ በቃ ይሄ ይሁን አይደል ? (ጎማ የሚመስል እጅግ ወፍራም እና ቄንጠኛ ሽፋን ይዞ)

''አዎ አልኩህ እኮ...''

''እሺ ስንት ነው...?''

እንግዲህ ኳሊቲ ነገር ብለሀል ..ይሄ የቻይና አደለም..የአውሮፓ ነው..

''እሺ ስንት ነው...?''

''አምስት ከሀምሳ..''

''አምስት መቶ ሃምሳ ብር ለሞባይል ሽፋን...?'' ብዬ እያሰብኩ ሣለ ሰውየው ያለምንም ክርክር ኪሱ ገብቶ ገንዘብ ቆጥሮ ሲሰጣት ዐየሁ።

''አምስት ከሰላሳ ነው ያለኝ ይበቃሻል...''

''እሺ ካልክ ምን ይደረጋል ...?

ገንዘቡን ተቀብላ ፣ እሱም አዲሱን የአውሮፓ ሽፋን ለስልኩ ሲያጠልቅ ፣ የምጠብቀው ሰው ደውሎ ከሕንፃው ውጪ እየጠበቀኝ እንደሆነ ሲነግረኝ ትቺያቸው ወጣሁ። ወጥቼ የጓደኛዬ መኪና ውስጥ ገባሁና ልንቀሳቀስ ስንዘጋጅ የሚከተለውን አየሁ።

ከብዙ መጨነቅና መጠበብ በኋላ አምስት መቶ ሀምሳ ብሩን ሆጭ አድርጎ ቄንጠኛ የሞባይል ሽፋን የገዛው ጎልማሳ የሞተር ብስክሌቱን አስነስቶ ቱ...ር... ሲል አየሁት

''ሄልሜት'' አላደረገም

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_ሁለት
:
:
... ''ወይኔ... ወይኔ! ኸረ በማርያም ቀስ በይ...ሥጋዬን እንዳትቦጭቂው!'' አልኩ በጩኸት።

ከዚያ ቁንጅናውን ይዞ ከአዲሱ መሥርያ ቤቴ ሊለቅ ለተዘጋጀው፣ ''ቀሚስሽ ያምራል ሽሮ ልጋብዝሽ...'' ምናምን ብሎ ላሽኮረመመኝ፣ የመጀመርያው ወንድ ልጅ እራት እየተዘጋጀው ነው። የእግሮቼን ፀጉሮች በሞቀ ሰም እያስላጨሁ ነው።

ከብስጭት የተሰራ የሚመስል ፊት ያላት ሴትዬ ናት፣ ያለርህራሄ የምትላጨኝ።ሕመሙን መግለፅ አይቻልም። መጀመርያ ለፕላስተርነት ከሚቀርብ ነገር የተሰራውን ፤ በአራት-አራት መአዘን የተቆራረጠ ነገር ታመጣለች። ከዚያ ምድጃ ለይ የተጣደው ሰም ውስጥ ትከተዋለች። ደቂቃ ቆይታ ታወጣዋለች። ጸጉራሙን ቦታ እየመረጠች አንዴ ባቴ፣ አንዴ ቁርጭምጭምቴ አካባቢ፣ ሲላት ጉልበቴ ጋር ትለጥፈዋለች። ይይዛል። ይሄን ግዜ ይሞቃል እንጂ አያምም። ከዛ ግን የጭቃ ጅራፎን ታመጣዋለች። በአንድ ምት ጫፉን ይዛ ላጥ አድርጋ ስታነሳው ፣ ፀጉሬን ይዞ ሲነሳ፣ ከነቆዳዬ፣ ከነስጋዬ የተነሣ ይመስል፣ ነፍሴን ከሥጋዬ የሚያላቅቅ ሕመም ይሰማኛል። ከዛ ይሄንኑ ዐሥሬ አሥራ አንዴ፣ አሥራ ሁለቴ ትደጋግመዋለች። ህመሙን መገለፅ አይቻልም። በትንሹ ሊገልፀው የሚችለው ነገር፣ እሳት በተነከረ አለንጋ እነደመገረፍ ያለ ነው ብላችሁ ነው።

አንዱን የለጠፈችውን ላ...ጥ አድርጋ ባነሳች ቁጥር፣ ወይኔ፣ ወይኔ፣ ኸረ ቀስ ብዬ እጮሀለው።

''የመጀመርያሽ ነው?'' አለችኝ ፊቷን እንዳቀጨመች።

''አዎ...''

ዝም አለች።

''ሥጋዬም አብሮ የተነሳ ያህል ነው የሚያመኝ...'' አልኩ ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ። ቀጥላ የምታነሳው የትኛውን ይሆን በሚል ስጋት ተወጥሬ።

''ሲያጌጡ ይመላለጡ ነው እንግዲህ...'' አለችና ላ...ጥ ! ቀላል እየተላላጥኩ ነው?

ሴቶች ግን ምን ሆነው ራሳቸው ላይ እንዲህ አይነት ሥቃይ የሚያበዙት? ቅንድብ ሲቀነደቡ እዬዬ! ካስክ ሲገቡ መቃጣል፣ ዋክስ ሲደረጉ ስቃይ ....ምን ሆነን ነው?

ቁርጭምጭሚቴ ጋር ላ....ጥ! አደረገችኝ።

''ወይኔ .... አረ ይሄ ነገር ማደንዘዣ ያስፈልገዋል...! አልኩ።
''ሃሃ...'' አለች ፊቷ ሳይፈታ፣ ጥርሷ ሳይታይ። ምን አይነት ሳቅ ነው? መአከላዊ ገራፌ የነበረችና በሰው ስቃይ የምትደሰት ዓይነት ሰው ትመስላለች
ላ....ጥ!

''አይዞሽ ጨርሻለው አሁን...''

ጥርሶቼን እንደበረደው ሰው እያንገጫገጭኩ ፣ ዐይኖቼን ጨፍኜ እንድትጨርስ ተመኘሁ።

''አሁን ይሻላል.... ሌላ ግዜ እንደዚህ አትቆዬ...ባደገ ቁጥር ይባስ ያማል....'' አለችኝ! ፎጣዬን ያለ ፍቃዴ እስከ እንትኔ ድረስ ከፍ አድርጋ። ''ሱሪ አድርገሽ አይመችም'' ብለው አስወልቀውኝ፣ የእነሱን ፎጣ አገልድሜ በውስጥ ሱሪ ነው ያለሁት። ክው ብዬ ፎጣውን በእጆቼ ልመልስ ስል፣

''እንዴ...ምንድነው የሚታየኝ እዛ ጋር....? ደን እያለማሽ ነው እንዴ?'' አለችኝ(ገራፊዋ ቀልድም ትችላለች)። ሣቅኩ።

''እውነት ምንድን ነው እንደዚህ መዝረክረክ...አንድ በይው እንጂ....''አለችኝ እንደተኮሳተረች።

''እህ...'' አልኩ (እሱም አለ ለካ)

''ብራዚሊያን አትፈልጊም? '' አለችኝ በተኛሁበት ቁልቁል እያየችኝ። ''ብራዚሊያን ደሞ ምንድን ነው?'' አልኳት በፍርሃት እያየኋት።

'' ሆ....ያዲስ አበባ ልጅ አደለሽም እንዴ?''

''ነኝ ግን ሰምቼው አላውቅም።''

ነገረችኝ።

''እንዴ! ሴቱ እሱንም ከፍሎ ያስላጫል እንዴ?'' አልኩኝ፣ ከልክ በላይ ደንግጬም፣ ተገርሜም።

''ድብን አርጎ ነዋ...እንኳን ሴቱ ወንዱም ጀምሮል አሁንማ...'' ማመን አልቻልኩም።

(ወንድ ልጅ እዛ ጋር ያለውን ጸጉር ያስለጫል ? ለምን? ታየኝ አንዴ ወደ ግራ...አንዴ ወደ ቀኝ እያደረጉ ሲላጮዋቸው...የፈጣሪ ያለህ)

''እኛ ወንድ አንሰራም...ሴት ግን እንሰራለን...'' አለችኝ።
''እ...'' አልኩ እያቅማማሁ። እግሬን እንዲህ ያመመኝ ፣ ሥሥ ''ብልቴ'' ቢነካ ምን ልሆን እንደምችል አስቤ።
''ከእግር ብዙ አያምም...'' አለችኝ ሐሳቤን የሰማች ይመስል።

''ግን...ለምን ይላጫል ሴቱ...ማለቴ፣ቤታቸው... እራሳቸው በምላጭ ነካ ነካ...ላጨት ላጨት አያደርጉትም?''

በዚያ ፊቷ ፈገግ ማለት የምትችለውን ያህል ፈገግ ብላ፣ ''አይ...በምላጭ ለዛውም ራስሽ ፣ አይመችም እኮ...ሴቱ ደሞ እየወፈረ ቦርጩ ከልሎት እንትናቸውን ካዩ ዘመን ያለፈባቸውም ስንት አሉ እኮ...'' አለች። (ይህቺ ሴትዮ ቀላል ትቀልዳለች እንዴ...) በጣም ሳቅኩ።
''የዛሬ ወንዶች እዛ ጋር ጸጉር ሲበዛ አይወዱም አሉ....እኔ ምን ዐውቃለሁ ...ሴቶቹ እንደዛ ይሉኛል...በወር...በወር እየመጡ ዋክስ የሚያደርጉ ከስተመሮች አሉኝ።

(የዛሬ ወንዶች እዛ ጋር ጸጉር አይወዱም?...እና... ለሽሮ እራት እንትኔን በሞቀ ሰም ላስላጭ?)

''ለምንድን ነው የማይወዱት?'' አልኳት።

''እንጃ...ስንፍና ይሆናላ!...ፈልጎ ላለማግኘት..ሃሃሃ (ሆሆይ ምን ጣጣ ውስጥ ገባሁ...?)

''ስንት ብር ነው?'' አልኩ! በተኛሁበት እያየኋት።
''ከላይ ከላይ ከሆነ 300 ብር...ብራዚሊያን 500 ብር ነው። እንደኔ ግን ብራዚሊያኑ ይሻልሻል። ጥርት ያለ ነው ፣ በዛ ላይ ይቆይልሻል (ከላይ ከላይ የቱ ጋር ነው...?ብራዚሊያንስ ምን ምንን ነው የሚያካትተው ብዬ ለመጠየቅ ፈለኩ )

ቡራዚሊያን ሲሆን አንዲት ፀጉር አትቀርም...በየትም በኩል...''(ሐሳቤን ትሰማለች ልበል?)

''እሺ... ብራዚሊያን ይሁንልኝ...'' አልኩኝ፣ እየፈራሁም ፣ አዲስ ነገር ለማድረግ በመዘጋጀቴም በራሴ እየኮራሁ።

እሷ፣ አዳዳዲስ ፕላስተሮች ሰፋ ያለ ድስት ውስጥ የሚንተከተክ ሰም ውስጥ ስትነክር ፣ እኔ ለመጀመርያ ጊዜ ከፀጉር ነፃ የሆኑ እግሮቼን እርስ በእርስ አነካካሁ። አወይ መለስለሳቸው።ያማርኩ መሰለኝ።

''እሺ....እንጀምር...'' (ከመቼው ሞቀላት?)

''እሺ.... አልኩ ደንበር ብዬ...''?

''እ...ፓንትሽን አውልቅያ ...! አወለቅኩ።

''እግርሽን ወደ ላይ!'' አዘዘችኝ። የፈጣሬ ያለህ!

ከእኔ በቀር ማንም ነክቶት የማያውቅ ጓዳ ጎድጓዳዬን በረብራ አንዲት ፀጉር እንኳን ለወሬ ነገሪነት ሳታስቀር ላጭታ ጨረሰች ።

በረደኝ።

''ዕይ....ው!'' አለችና የፊት መስታወት ሰጠችኝ።

''እ...?'' አልኩ ደንግጬ።

''ዕይው ...ቅር ያለሽ ቦታ ካለ...'' (ወይ ጉድ! ምኑ ቅር ይለኛል?) ዐየሁት ሞልጫኝ የለ እንዴ! ገና ከማህፀን የወጣች አራስ ሴት ልጅ መስያለው።

''አሪፍ ነው?'' አለችኝ፣ መስታወቱን ልትቀበለኝ እየተዘጋጀች።

''አ...አዎ...'' መስታወቱን እየመለስኩላት።

''በሚቀጥለው ስትመጪ ዲዛይን እሰራልሻሀው..''

''እ?..''

''ዲዛይን....የልብ ቅርፅ ምናምን...''

ወይ ጉድ...!

''እሺ...''አልኩ እየተነሳሁ። ገላዬ የኔ አልመስል አለኝ። የተከፋፈትኩ መሰለኝ። መስኮቱም በሩም እንደተከፈተ ቤት ፣ ንፋስ ተመላለሰብኝ...ሱሪዬን ፍለጋ ዞር ስል ፣

''በይ ይልመድብሽ...እርገጠኛ ነኝ ይወደዋል..''

ትታኝ ሄደች።

የሚያየው ወንድ እንደሌለና፣ በምናልባት ከታየ፣ በዚህ ሁሉ ስቃይ እንዳለፍኩ እንደማያውቅ ብታቅ ታዝንልኝ ይሆን።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍21
አትሮኖስ pinned «#ቆንጅዬ : #በሕይወት_እምሻው : #ክፍል_ሁለት : : ... ''ወይኔ... ወይኔ! ኸረ በማርያም ቀስ በይ...ሥጋዬን እንዳትቦጭቂው!'' አልኩ በጩኸት። ከዚያ ቁንጅናውን ይዞ ከአዲሱ መሥርያ ቤቴ ሊለቅ ለተዘጋጀው፣ ''ቀሚስሽ ያምራል ሽሮ ልጋብዝሽ...'' ምናምን ብሎ ላሽኮረመመኝ፣ የመጀመርያው ወንድ ልጅ እራት እየተዘጋጀው ነው። የእግሮቼን ፀጉሮች በሞቀ ሰም እያስላጨሁ ነው። ከብስጭት የተሰራ…»
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_ሦስት
:
:

.... ''ውይ ዛሬ ደግሞ ሌላ ሆነሻል....እንዴት እንዳማረብሽ....'' አለኝ፣ ገና እንደተገናኘን።

ቀድሞ ደረሶ እየጠበቀኝ ነበር። ግርግር የበዛበት ምግብ ቤቱ ደንገዝገዝ ያለ ነው ። እንደውም ለጨለማ የቀረበ ነው። ተበሳጨሁ። ይሄን ሁሉ ተሰቃይቼ ውጤቱን ማሳየት የማልችልበት ቤት ይቀጥረኛል ? ስቃዬ የባከነ መሰለኝ።

''እውነት ልዩ ሆነሻል ዛሬ...'' (ህእ! ያለፍኩትን ስቃይ ባየህ!) እንደነገሩ ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳምንና እግሮቼን አነባብሬ ቁጭ አልኩ። አወይ አለሳለስ! አጭር ቀሚሴ ይበልጥ አጥሮ ስንት ያየሁባቸው እግሮቼና ግማሽ ጭኖቼ ተጋለጡ።

''ቤቱን ወደድሽው?'' አለ ፣ ጭኖቼን ያላየ ለመምሰል እየሞከረ። ''አዎ...ደስ ይላል።'' (ግን በጣም ጨለማ ነው...ምን ዋጋ አለው...)

''እሺ.... ስራ እንዴት ነው?''

''ደህና...ነው።''

''እየለመድሽ ነው ?''

''ምንም አልል...''

የተነባበሩት እግሮቼን ስነጣጥላቸው ከየት መጣ ያላልኩት ብርድ ቀጥ ቦሎ ማሕፀኔ ውስጥ የገባ መሰለኝ። መልሼ አነባበርኳቸው።

የተወራለት ሽሮ መጥቶ መብላት ጀመርን።

''ሽሮው እንዴት ነው ?''

''በጣም አሪፍ ነው።''

''አላጋነንኩም አይደል?'' እንጀራ ጠቅልሎ እየጎረሰ

''በጭራሽ በጣም ይጣፍጣል'' አልኩ፣ አንድ ጎርሼ እየተቅለሰለስኩ።

''ከኔ ግን አይበልጥም...''

(ዛሬም ትን ሊለኝ ነበር።ኧረ ፍጥነት ፣ በዚ አይነት እዚያ ጋር መላጨቴ ደግ ኘድርጌለሁ።)

ዝም ብዬ ጉርሻየን ማላመጥ ቀጠልኩ።

''ምነው ?'' አለኝ።

''ምነው?'' መለስኩ።

''አጠፋው እንዴ?'' (ኧረ አላጠፋክም። የኔ ሰፈፍ የሌለው ማር...የኔ ጌታ)

''አይ...''

በልተን ጨርሰን ወጣን።
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ዛሬም እንደወትሮ ተቀጣጥረን ተገናኝተናል። ከተገናኘን ጀምሮ በሳምንት ቢያንስ ሦስት ግዜ እንገናኛለን። ጸጉሬ አልበቀለም። ቀሚሴም አጭር ነው።ጸጉሬም ይተኮሳል።ከንፈሬም ቀለም ይቀባል። ግን ከ ''ዛሬ አምሮብሻል አንዳንድ ገፋ ያሉ ማባበሎች፣ መለጠፎች፣ መነካቶች ውጪ ምንም አልተፈጠረም። ምንም አልሆነም።

እስከዛሬ ለምን አልተሳሳምንም?

አልወደደኝም?

''ምንድን ነው የምታስቢው?'' አለኝ።

''ምንም...''

''ካንቺ በጣም የምወደው ነገር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? (ምን የኔ ጌታ.....ምን?)

''በጣም ስማርት ነሽ....(ስማርት ፊት.....ካልጠፋ ካልጠፋ ነገር ማንም የሚለኝን ነገር ይለኛል....? ይሄን ሁሉ ሆኜለት ጎበዝ ብቻ ብሎኝ ያልፋል?) መላ ሰውነቴ ኩምሽሽ አለ።

''ታንክስ....'' አልኩ የግዴን።

''ዛሬ ምሽቱ ደስ ይላል...ለምን ትንሽ ወክ አናደርግም?'' አለኝ፣ ብርጭቆው ውስጥ የቀረችውን እንጥፍጣፊ ማክያቶ ጨልጦ። ተነስተን ወጣን።የሚገርም ምሽት ነበር እውነትም ለመሳሳም የተሰራ ምሽት። ትልቅ ጨረቃ፣ ንፋስ የሌለው ግን ቀዝቀዝም፣ ለብም ያለ ውብ አየር። ሰው ያልበዛበት ዛፋም መንገድ። (አረ ሳመኝ በናትህ!)

''ሴት ልጅ ስማርት ስትሆን ደስ ይለኛል....''(እግሬን አላየም ? ቅርፄን አያይም?...ይሄንን ኬክ ወጥቄ ወጥቄ ሆዴ ተንቀርፍፏል እንዴ?)

''ቀስ በል...በሂል መሄድ አልለመድኩም አልኩት።ወሬውን ከስማርትነቴ ለመቀየር...

''ደከመሽ..?''

''እ...ትንሽ....''

''ኡፍ ግን በጣም አምሮብሻል....አለባበስ ደግሞ ስታውቂበት...''(እንዲህ ነው ወሬ....!)

''እውነት?...'' አልኩት ዞር ብዬ እያየሁት።
(ጎበዝ ነሽ ከመባል ውጪ ከወንድ ያገኘሁት የመጀመርያ አድናቆት ነው.....)

''እና ደግሞ ይሄ ቀሚስ....ይቅርታ ግን ሰውነትሽ..''
(ኧረ ይቅርታ አያስፈልግም። አወድሰኝ የኔ ጌታ...እስኪ ነጋ...ክርስቶስ እስኪመጣ አቁመህ አወድሰኝ...አድናቆት የተጠማች የሴት ነፍሴን፣ ደግመህ ደጋግመህ እያወደስክ አረስርሳት...)

''ሰውነትሽ በጣም ያምራል....''(የቱ ጋር የኔ ጌታ? ዘርዘር አድርገዋ...እግሬ ነው....ቂጤ ነው....ዐይኔ ነው... ወይስ ፀጉሬ በትንልኛ የኔ ጌታ...ቅኔ ተቀኝልኝ....!)

''እውነት?'' አልኩኝ።

''በጣም....በተለይ እግሮችሽ....''

''እግሬ ብቻ ነው ደስ የሚልህ ?'' እጁን ጨብጬ ጠየኩት።

አልቦታል።

''ኧረ....ኖ.... ፊትሽ.... ፀጉርሽ... በጣም ቆንጆ ነሽ ...'' ልቤ ምንጃርኛ ጨፈረ።( በጣም ቆንጆ ነሽ ነው ያለው ወይስ ጆሮዬ ነው?)

እጁን የበለጠ አጥብቄ ያዝኩት። (የቅንድቤና የእግሮቼ ውበት እመቤት...ያቺ ባለ ዋክስ ሴትዮ ትመስገን። ደሞዝ ይጨመርላት። ከስተመር ይብዛላት። አሜን።)

''ብዙ ሰው ግን እህቴን ነው ቆንጆ ናት የሚለው..''

''አላምንም...እህትሽ ሰላም ተስፋዬ ምናምን ካልሆነች አላምንም...ብትሆንም አንቺ ጥግ አትደርስም።'' (ሰዎች...ሰከርኩ። በቃላት ብስብስ ብዬ ሰከርኩ....)

''ፎቶዋን ብታይ እንዲህ አትልም....'' እጆቹን ጭምቅ እንዳደረኩ።

''አሳይኛ...''

ቆምኩና ስልኬን ከፈትኩ።

የእህቴን ፎቶዎች አሳየሁት።

''ኧረ በናትሽ ጫፍሽ አትደርስም!'' አለ።

''ባክህ አትፎግረኝ....በጣም ታምራለች....'' ስልኬን ቦርሳዬ እየከተትኩ መለስኩለት።

''በርግጥ ቆንጆ ናት...ማለት ሁሉ ነገሯ ለየብቻው ሲታይ ጥሩ ነው ግን...እንዳነቺ ደም ግባት የላትም....አንቺ እኮ...አንቺ እኮ...በጣም ሴኪሲ ነሽ....''

ፀጉር አልባ እግሮቼ ተንቀጠቀጡ። ሙልጭ ተደርጋ ከተላጨችው የሴትነት ሽንቁሬ ወንዝ ቢጤ መፍሰስ ጀመረ። ቆም አልኩና ተጠጋሁት።

ሳምኩት።

ከንፈሩን ግጥም አድርጌ ሳምኩት።

አንዳንድ ሴቶች በቁርጥ ስጋና ቱርቦ ተደልለው ወደ አልጋ ይሄዳሉ። አንዳንዶቹ ውድ ሽቶ ሲሰጣቸው፤ ገና ሳይቀቡት ልብሳቸውን ለሰጭያቸው ያወልቃሉ። አንዳንዶቹ ለቪትዝ የውስጥ ሱሪያቸውን ያስዘልቃሉ። አንዳንዶቹ ጂ ፕላስ ምናምን ቤት ሲያዩ ጭኖቻቸው ይከፈታሉ። አንዳንዶቹ ላሳቃቸው ወንድ ገላቸውን ይቸራሉ።

የእኔ ምስ ግን አንድ ነው፤ ''ቆንጅዬ'' መባል ''የኔ ቆንጆ'' መባል።....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍31
አትሮኖስ pinned «#ቆንጅዬ : #በሕይወት_እምሻው : #ክፍል_ሦስት : : .... ''ውይ ዛሬ ደግሞ ሌላ ሆነሻል....እንዴት እንዳማረብሽ....'' አለኝ፣ ገና እንደተገናኘን። ቀድሞ ደረሶ እየጠበቀኝ ነበር። ግርግር የበዛበት ምግብ ቤቱ ደንገዝገዝ ያለ ነው ። እንደውም ለጨለማ የቀረበ ነው። ተበሳጨሁ። ይሄን ሁሉ ተሰቃይቼ ውጤቱን ማሳየት የማልችልበት ቤት ይቀጥረኛል ? ስቃዬ የባከነ መሰለኝ። ''እውነት ልዩ ሆነሻል…»
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_አራት (የመጨረሻ ክፍል)
:
:

....የእኔ ምስ ግን አንድ ነው ''ቆንጅዬ'' መባል ''የኔ ቆንጆ'' መባል።ከእህትሽ ታምሪያለሽ ብሎኝ አብሬው ያለሁት የመጀመርያ ቦይፍሬንዴ ፣ ለአልጋ ዝግጁ የሚያደርገኝን ቃል ጠንቅቆ ያውቀዋል። ወደ አልጋ ሊያስገባኝ ሲፈልግ ውድ ምሳ፣ ወይ የሻማ እራት አይጋብዘኝም። ወይን አያጠጣኝም። ስጠቶ አሽጎ አያመጣልኝም።

''ቆንጅዬ'' ሲለኝ ፍንክንክ እላለዉ። ''የኔ ውብ'' ሲለኝ ወከክ እላለሁ። ''የኔ ቆንጆ'' ሲለኝ ሙክክ ብዬ እበስላለው። ''ካንቺ በላይ ቆንጆ የለም'' ሲለኝ ሲራገብ እንደዋለ ክሰል ትርክክ እላለሁ። እንኳን ጭኖቼ ሁለንተናዬ ይከፈታል። ብርግድግዴ ይወጣል።

ቆንጆ መባሉ እኔም እንደሴቱ ወግ ደርሶኝ ቦይ ፍሬንድ ኖሮኝ ፤ የአልጋ ላይ ንግስት መሆንን ብቻ አደቸም የሰጠኝ። እሱ ቆንጆ ባለኝ ቁጥር ተጨማሪ የራስ መተማመን በመርፌ እንደተወጋ ሰው ያደርገኛል። እነቃለሁ። እነሳለሁ። ወደ ፊት እራመዳለሁ።

ቆንጅዬ ሲለኝ የደስታ ክትባት እንደተከተብኩ ሁሉ ሁለንተናዬ እየሣቀ፣ እየፈነጠዘ፣ እየተፍነከነከ በኔን ጀምሬ እጨርሰዋለሁ።

ያኔ ነው አለምም በራሳቸው ለሚተማመኑ የምትመች ቦታ መሆኗን ያወኩት።

እንዲህ ያለው ቀን በቦይፍሬንዴ ተስሜ፣ በፍቅር ተሽሞንሙኜ ውዬ ከቤቱ ስወጣ ሰበር ሰካ እል የለ ? ከአንገቴ ቀና ፣ ከትከሻዬ ነቀል ፣ ከእግሮቼ ፈንጠር እያልኩ እሄድ የለ? ይሄን ግዜ የሚያየኝ ወንድ የለም። ይሄን ግዜ የማታየኝ ሴት የለችም። ጸጉሬን በእጆቼ ወደ ግራ ወደ ቀኝ መታ አድርጌ፣ ደረቴን ነፋ አድርጌ በጎዳና ላይ ሽር ብትን ስል፣ የሚያዩኝ ሥራ ፈትተው፣ ''ዛሬ ደግሞ ምን እናድርግ ? ማንን እንልከፍ....?'' ምናምን ብለው ብቻቸውን የቆሙ ቦዘኔ ወንዶች ብቻ አይደሉም። ከሴት ጋር የቆሙ ፣ ከሴት ጋር የተቀመጡ፣ ከሴት ጋር የሚበሉ ፣ ከሴት ጋር የሚጠጡ፣ ከሴት ጋር የሚራመዱ ወንዶች ሁሉ ፣ አፍጥጠው ያዩኛል።

ከሴት ጋር ስል ዝም ብለው ቱታ ወይ ድርይ ለብሰው፣ ሻሽ ሽብ አድርገው የወጡ ሴቶችን አደለም። ቦርጫም ወይ ብጉራም ፣ ቂጣቸው ከጭናቸው ጋር የተቀላቀለ ዓይነት አይስቤ ሴቶችንም አይደለም።

ቂቅ.....ቋ ብለው የወጡ ፣ በከፍተኛ ሂል ጫማ ላይ የቆሙ ፣ በሂውማን ሄር ያበዱ፣ አንጀታቸው ሙትት፣ ቂጣቸው ውጥት ያሉ ቆንጆ ሴቶችን ማለቴ ነው። እንዲህ ዓይነቷ ሴት ጋር ያሉ ወንዶች ናቸው እኔን ለማየት የሚዞሩት። የሚሰርቁት ዐይኖቻቸውን የሚያንከራትቱት። እህቴን የሚመስሉ ሴቶችን ወገብ አቅፈው የሚሄዱ ወንዶች ናቸው፣ አንገታቸውን አዙረው እኔን ዐይተው ከንፈራቸውን እንደ ምግብ የሚልሱት። ነገሮች ፍፁም ተለዋውጠዋል ። የቁንጅና ጣኦት ፣ በየጎዳናው የምመለክ ጣዖት ሆኛለው። ከእነዛ ውብ ሆነው ከተወለዱ የኤንጅኦ ሴቶች ጋር ምሳ ስወጣ ፣ (በ ''ማን ይበለጥ ያምራል'' አደራደር ቃተኛ ተኮልኩለን ተቀምጠን) ምድረ ሀብታም ወንድ ፣ ምግቡና አጠገቡ ያለች ሴቱን ትቶ አይኑን እኔ ላይ ይሰካል ። እጆቼን ልታጠብ ቋ ቀጭ እያልኩ ስነሳ፣ የሠራውን ጉርሻ አፍርሶ እየተደናበረ ይከተለኛል ።

ሰከርኩ። በመፈለግ፣ በፍላጎት በመታየት፣ ብዛት ብስብስ ብዬ ሰከርኩ።በራስ መተማመኔ በዝቶ በዝቶ፣ ወደ ትዕቢትነት ለመቀየር እስኪደርስ ድረስ በወንዶች የአድናቆት ብዛት ሰከርኩ።

አንዱን ቀን ከቢሮ ሴቶች ጋር እራት ልንበላ አንዱ ቤት ተቀምጠናል። ከገባን ጀምሮ በመጥቀስና በማፍጠጥ መሀል ባለ ሁኔታ የሚያየኝ ፣ ብዙም የማያምር ግን ወንዳ ወንድ ልጅ ፣ ከእኛ ቀጥሎ ያለውን ወንበር ዘሎ ያለው ወንበር ተቀምጧል። አላየውም እልና ዐየዋለሁ። ዐይኖቻችን ሲገናኙ ወሬ እንደያዘ ሰው ፣ ወደ ጓደኞቼ እመለሳለሁ። ደግሞ አሁንም እያየኝ ይሆን ብዬ አስብና ቀና ብዬ ዐየዋለሁ።

አሁንም እያየኝ ነው።

ምን ፈልጎ ነው?

ትቼው ጨዋታውን ቀጠልኩ።

''ስሚ'' አለችኝ ከሰባቱ አንዷ ፣ ደጎረሰችውን ጥብስ ፍርፍር ጨርሳ ሳትውጥ።

''እ....'' አልኩ ፣ ሃሳቤ ከወንዳ ወንዱ ልጅ ሳይላቀቅ። አላየውም...አላየውም.... አላየውም.. ዐየሁት።

እንዳፈጠጠ ነው።

ተሽኮረመምኩና ዐይኖቼን ሰበርኩ።

ሆ!

''....እና ስልኳን ካልሰጠሽኝ ብሎ ወጥሮኛል ...ልስጠው?'' አለችኝ ሕይወት።

ልጁን ሳይ፣ ያለችውን ሁሉ አልሰማሁም።

''ምን?'' አልኳት እያየኋት።

''እንዴ ....አልሰማሽኝም እንዴ?''

''አዎ....ሶሪ....ማነው ስልኳን ያለሽ....?''

እንደገና አየሁት። አየኝና ተነሳ። ቁመቱ መዐት ደልዳላ ነገር ነው።

የት ሊሄድ ነው ?

ሕይወት ታወራለች። በዐይኔ ተከተልኩት።

''እና ልስጠው ?'' አለች ሕይወት።

''ስጪው...'' አልኩና ብድግ አልኩ።

የት ሊሄድ ነው ? ዐየሁት ። ወደ መታጠብያ ቤት ነው የሚሄደው ። ተከተልኩት። ኮራደር ጋር ስደርስቆሞ አገኘሁት።

''እምም...በጣም ታምሪያለሽ....'' አለ።ድምፁ ቁመናውን የሚመጥን ነጎድጓድ ነው።በቆምኩበት ፈገግ አልኩ።

''አመሰግናለው አይባልም እንዴ ?'' አለኝ።

''...ይባላል። አመሰግናለሁ። ሽንት ቤት ልገባ ነው. አንዴ....በቆመበት በቄንጥ እየተራመድኩ ጥዬው ሄድኩ። ዐይኖቹ ቂጤ ላይ ተለጥፈው ይሰሙኛል። ድንገት ዞር ብዬ አየሁት። ልክ ነበርኩ።

'' እጠብቅሻለው....'' አለ ጮክ ብሎ። (አዎ ትጠብቀኛለህ።) ያልመጣ ሽንቴን አልሸና ነገር። ሊፒስቲኬን አስተካክዬ እጆቼን ታጥቤ ወጣሁ። እዛው ቆሟል።

''የምር ጠበቅከኝ አይደል...?'' አልኩ፣ አጠገቡ ስደርስ።

''የእኔ ቆንጆ አንቺ ካልተጠበቅሽ ማን ይጠበቃል ታድያ ?'' (እውነት ነው። እኔ ካልተጠበቅኩ ማን ይጠበቃል?)

ስልኬን ሰጥቼው ወደ ወንበሬ ተመለስኩ።

''ስልክሽ ሲጮህ ነበር'' አሉኝ።ዐየሁት። ቦይፍሬንዴ አራት ግዜ ደውሏል። አንድ ቴክስትም አለኝ። ቴክስቱን ከፈትኩት።

''ቆንጅዬ ናፈቅሽኝ...ማታ አትመጪም?''

ለጀመርያ ጊዜ መልስ ሳልሰጠው ስልኬን አስቀመጥኩና ሕይወትን እያየሁ።

''ማነው ስሙ ስልኬን የምትሰጪው ልጅ?'' አልኳት።

''እንዴ...ያን ሁሉ ስለፈልፍ አትሰሚም ነበር እንዴ...እንዴ ቆይ ደግሞ...ማንነቱን ሳታውቂ ነው ስልኬን ስጪው ያልሽኝ እንዴ?'' አለችኝ በመገረም (ከፈለገኝ ማንነቱ ምን ያደርግልኛል? ''ቆኖጆ ናት ፣ ስልኳን አምጡልኝ፣ ከኔ ጋር እንድትሆን ልልፋ፣ ልድከምላት'' ካለ፣ እኔ ምን ቸገረኝ)

''እ....ጫጫታው አልሰማ ብሎኝ ነው...'' አልኩና ዋሸሁ።

''ቢኒያም ነው ...ያ ዶክመንተሪ የሚሰራልን ልጅ...'' አለች ሕይወት።

ቢኒያም ያሚ! ከማማሩ ብዛት ቢሮ ውስጥ በአባቱ ስም የሚጠራው የለም። ሴቶች ሁሉ ቢኒያም ያሚ ነው የምንለው። ቢኒያም ጣፋጭ...

ቢኒያም ያሚ እኔን ፈለገኝ?...ከዛ ሁሉ ዉበት መሀል እኔን መሠጠኝ?

ቦይፍሬንዴ ደወለ። ዘጋሁበት።

ጭካኔ ሊመስል ይችላል ግን ፣ ''ማንም አይወደኝም ፣ አስቀያሚ ነኝ።'' ብላ ታስራ ትሠቃይ የነበረች የሴትነት ነፍሴን ፣ በአንዲት ቃል ከፈታት ወንድ ጋር በውለታ ብቻ ታስሬ መቆየት አልፈልግም። ይህንን አዲስ ቁንጅና ለዓለም ማካፈል ፣ ለብዙ ወንዶች መበተን አለብኝ። አይመስላችሁም? አስቲ አውሩኝ ከበታች ባለው አድራሻ ሀሳባችሁን ላኩ

🔘አለቀ🔘

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍5🔥1
አትሮኖስ pinned «#ቆንጅዬ : #በሕይወት_እምሻው : #ክፍል_አራት (የመጨረሻ ክፍል) : : ....የእኔ ምስ ግን አንድ ነው ''ቆንጅዬ'' መባል ''የኔ ቆንጆ'' መባል።ከእህትሽ ታምሪያለሽ ብሎኝ አብሬው ያለሁት የመጀመርያ ቦይፍሬንዴ ፣ ለአልጋ ዝግጁ የሚያደርገኝን ቃል ጠንቅቆ ያውቀዋል። ወደ አልጋ ሊያስገባኝ ሲፈልግ ውድ ምሳ፣ ወይ የሻማ እራት አይጋብዘኝም። ወይን አያጠጣኝም። ስጠቶ አሽጎ አያመጣልኝም። ''ቆንጅዬ''…»
#ፍቅፋቂ
:
:
#በሕይወት_እምሻው
:
:
''ዝም ጭጭ! ጩኸት አደለም ብትተነፍሺ በዚህ ጩቤ ነው የምዘለዝልሽ!'' ብሎ አስፈራርቶኝ ነው እዚህ ሜዳ ላይ ያጋደመኝ።

በዚህ ውርጭ፣ በዚህ ጨለማ፣ ሰው ዝር በማይልበት ጥግ፣ ልብሴን ገፎ ቆዳዬን ከአፈር እያነካካ፣ አጥንቴን ከድንጋይ እያማታ የሚያደርገኝን የሚያደርገኝ በጩቤ አስፈራርቶ ነው።

''ሥጋሽን እዘለዝለዋለሁ!'' አለ።

አሁንስ እየዘለዘለኝ አይደለም?

ባልተዘጋጀሁበት፣ ባልጋበዝኩት የወንድ ጩቤው፣ በዚህ በማላውቀው ሰውነቱ....ስጋዬን እየዘለዘለ አይደለም?

አፌን በአንድ እጁ አፍኖ ፣ በሌላው እጁ የተራቆቴ አካላቴን በፍፁም ስግብግብነት ይቧጥጣል።

ስስ ቆዳዬን ባልተከረከሙ ግርድፍና ጨካኝ ጥፍሮቹ ይቀረድዳል፣ እንደ ሎሜ ይጨምቀኛል፣ እንደ ቆሻሻ ልብስ የሸኛል።

ምን አይነት ሰው ነው....?

ከእኔ የስቃይ ጉድጓድ ደስታን የሚቀዳ፣ ስሜን እንኳን ሳያውቀው፣

መልኬን እንኳን ሳያየው ፣ ጓዳ ጎድጓዳዬን ጠርምሶ የገባ፣ ይሄ ምን አይነት ሰው ነው።

አመመኝ።

ለምን አመሸሁ...ባላመሽ ጥሩ ነበር።

ለእማ እንዴት አድርጌ እነግራታለሁ?

አባዬማ ከሰማ ደሙ ከፍ ብሎ እዛው ክልትው ይላል....እማ ''አታምሺ'' ስትለኝ ባላመሽ፤ ላይብረሪ ባልቆይ፣ ይሄ ሁሉ አይመጣም ነበር...

ለመሆኑ...ለመሆኑ...ይህን የሰው እንስሳ....፣ ይሄን ሳልሞት ገሃነም የወሰደኝ ሰው እከሰዋለሁ.?

የት? የሰፈር ፖሊስ ጣብያ...?ፖሊሶቹ ምን ይሉኛል...? ''ለምን በዚህ ሰዐት...?''....ለምን እንዲህ አይነት ልብስ...?...ለምን አልጮኸሽም...? ''ፈልጋ ነው !'' ይሉኝ ይሆን?

የለም አልከስም።

ከሳሽን ተከሳሽ፣ ተበዳይን ጥፋተኛ በሚያደርግ ሕግ ፊት አልቆምም። የተደፋ አንገቴን ይበልጥ ለሚያስደፋኝ አንካሳ ፍትህ፣ እያነከስኩ አልሄድም።

አውልቆ ያልጨረሰው ታይቴ ተረከዜ ጋር ሳይደርስ ተሰንቅሮ ጠፍንጎ ይዞኛል። አፌን ሲከድን አብሮ የያዘው አፍንጭያ መተንፈስ ተከልክሎ ፊቴ ላይ ሲያብጥ ይሰማኛል።

በአይኖቼ ብቻ በእንባ መስታወት ተጋርደው ይሄን ሁሉ የሚሰራኝን ሰው ለማየት ይሞክራሉ። ግን፣ ጨለማው እንዳይ የፈቀደው ጥላውን ብቻ ነው። ሰውነቴን ሰንጥቆ ከገባው ሰውነቱ ጋር ብድግ ምልስ የሚለው የጭንቅላቱ ጥላ ብቻ ይታየኛል።

''ዋ ! እጮሀለው ብትይ!'' አለኝ ደግሞ...የአፍንጫዬን አየር ለማግኘት፣ ከእጆቹ ጥፍነግ ነፃ ለማውጣት ስጥር ተሰምቶት ነው፣ እጁ ሲንሸራተት ትጮሀለች ብሎ ፈርቶ ነው።

ግን እንዲህ ያለ ሰው ፣ ፍርሀትን ያውቃል ? ሌሎቹን የሚያስፈራራ ሰው ይፈራል ? ከገደለ ወድያ የሚፎክር ሰው ሊፈራ ይችላል?

ወይኔ....ወይኔ....ሕመሙ ቀዶኝ የገባው የሰላ ምናምንቴው ውስጤን ይሞርደኛል።

ያመኛል።

ወይኔ እናቴ! ወይኔ...! እንዳላብድ ሌላ ነገር ላስብ

ያቺን ታሪኳ ቡቲክ ያየኋትን ቡትስ ክረምት ሳይገባ በገዘኋት ኖሮ። ውድ ናት፣ ግን በገዛኋት ኖሮ። ቀብድ እንኳን...50 ብር እንኳን ሰጥቻት ብመጣ ጥሩ ነበር። አባዬ ይሞላልኝ ነበር...ከምንም ልብስ ጋር ትሄድ ነበር። በዛ ላይ ትመቻለች። ሱሪ ባደርግ ቀሚስ ባደርግ...ታይት ባደርግ...

ወይኔ ይሄ ታይት ሰንጎ ይዞኛል። የደም ዝውውሬን አቁሞታል። ይሄ ሰውዬ አይበቃውም............? የት ፈልቶ ነው እኔ ላይ ሊሰክን የመጣው.......?

ምን አድርጌ ነው የሕይወቴን ብርሀን አለማስጠንቀቅያ ድርግም ሊያደርግ የመጣው ?
ቴዲስ ምን ይለኛል.....? ቴዲዬ.. ያምነኛል? እንዲህ ሆኜ ነው ብለው ያምነኝ ይሆን...? ይተወኝ ይሆን...?

አፌን እንዳፈነ ተነሳ።

እኔን ያለሁበት ጥሎኝ አፌን እንዳፈነ በርከክ ብሎ ተነሳና ሲሰቀስቁኝ በነበሩ እጆቹ ሱሪውን እየለበሰ፣ ጩቤውን አብለጨለጨና ''እጮሀለው ብትይ ተመልሼ ብትንትንሽን ነው የማጣው!'' ብሎኝ ስ..ል..ብ..አለ፣ ሄደ።

''ተመልሼ እበታትንሻለው !'' ነው ያለው? ምን ቀረኝና ምኔን ተመልሶ ሊመጣና ሊበታትን ነው? በመሰቅሰቅያ መነሳት እስካቸግር መሬት ላይ ተበታትኜ እያየኝ እንዲህ ይለኛል....?

የሰዐት ግምቴ ጠፋ። ግን መሽቶ የነጋ መሰለኝ። እዚያው ውዬ አድሬ የሰው ዘር ያላገኘኝ ፣ ወይ አግኝቶኝ ፤ ''ይህቺማ የሰው ጭላጭ ሆናለች..... የሰው ቅርፊት....ተዋት እዚሁ በስብሳ ትለቅ ...'' ብለው የተውኝ መሰለኝ።

ቤተሰቤም የሆኑኩትን ሰምቶ አናውቃትም ያለ፣ አልሰማንም ያለ መሰለኝ። የተረፈኝን ሰውነቴን፣ ፍቅፋቂዬን ፤ ሰብስቤ ይዤ ቤቴ ስገባ ግን 4:10 ገበር። ይሄ ሁሉ የገሃነም ጉዞ በመደበኛ ሰዐት አቆጣጠር አጭር ነበር።

አዎ.... ሕይወቴና ማንነቴ ለዘላለም የተለወጠው፣ የአንድ እጅ ጣት በማይሞሉ ደቂቃዎች ነው። ቀጫጭን የደም መስመሮች የሸፈናቸው እግሮቼ አላነቃንቅም እያሉኝ ፣ ተነቃንቄ ፣ አላስኬድም እያሉኝ ሄጄ ፣ ቤቴ እንደገባሁ እናቴን ዐየኋት።

ቤቴ፣

ጠዋት ቤቴ ሳለሁ ንፁህ ነበርኩ። ጠዋት ቤቴ ሳለሁ ሙሉ ነበርኩ።

እናቴ፤

ጠዋት ስትሰናበተኝ ንጹህ ነበርኩ። ጠዋት ቁርስ አብልታ ስትሸኘኝ ሙሉ ነበርኩ።

ቆዳዬን እንደ ጃኬት፣ እንደ ቀሚስ አውልቄ ብገባ ተመኘሁ። መርከሴን ፣ ክርፋቴን ደጅ ጥዬው ብገባ ደስ ባለኝ....

እናቴ፣ ''ልጄን.........ልጄን! ምን ሆነሽብኝ ነው ?'' ብላ ልትይዘኝ ስትጠጋ፣ የሳሎኑ መሬት ላይ ስዘረርና ፤

''ጎድዬ መጣሁ እማዬ.....! ጎድዬ መጣሁልሽ....'' ስላት እኩል ሆነ። 😥

🔘አለቀ🔘

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት ምርጦቼ ። 🙏
👍31
አትሮኖስ pinned «#ፍቅፋቂ : : #በሕይወት_እምሻው : : ''ዝም ጭጭ! ጩኸት አደለም ብትተነፍሺ በዚህ ጩቤ ነው የምዘለዝልሽ!'' ብሎ አስፈራርቶኝ ነው እዚህ ሜዳ ላይ ያጋደመኝ። በዚህ ውርጭ፣ በዚህ ጨለማ፣ ሰው ዝር በማይልበት ጥግ፣ ልብሴን ገፎ ቆዳዬን ከአፈር እያነካካ፣ አጥንቴን ከድንጋይ እያማታ የሚያደርገኝን የሚያደርገኝ በጩቤ አስፈራርቶ ነው። ''ሥጋሽን እዘለዝለዋለሁ!'' አለ። አሁንስ እየዘለዘለኝ አይደለም?…»
#ዐልቦ
:
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_አንድ
:
''ፍ...ቅ...ር...ተ!''

ስሜ በሴት ሲጠራ ሰማሁና እጆቼን አጎንብሼ ክሰል ከምጎለጉልበት ማዳበርያ ሳላወጣ ቀና አልኩ።

ሴት ናት።

ለሰፈራችን ከልክ በላይ የለበሰች፣ ለተቦዳደሰ ኬር መንገዳችን ከሚመጥነው በላይ ሸላይ ጫማ ያደረገች ፣ ቂ...ቅ ያለች ሴት ናት። ከመስታወት የተሰራ የሚመስለው ባለ ረጅም ስፒል ጫማዋ በሚፈቅድላት ፍጥነት ሚዛኖን ላለመሳት ፣ አንዴ መሬቱን፣ አንዴ እኔን፣ አንዴ ሰፈሩን፣ እያየች አጠገቤ ደረሰች።

አላምንም፣ በጭራሽ አላምንም፣ እስከዳር ናት።

የልጅነት ጓደኛዬ እስከዳር፣ ለዐስራ ስምንት ዐመት ያላየኋት አብሮ አደጌ፣ አሜሪካ ከሄደች ወሬዋን ሰምቼ የማላውቀው፣ የአሁኗ ዲያስፖራ የጥንቷ ባልንጀራዬ እስከዳር ናት።

የአሜሪካ ኑሮ እንደ እጅ ስራ ፎቶ ሞላት፣ አቀላት፣ እንጂ ፣ መሰረቱን በሳተ መልኩ አልተለወጠችም።

እስከዳር ናት!

በዚህ አኳኋኗ ልታቅፈኝ አጠገቤ ሰትደርስ እጆቼ ከሰል ሲቦረቡሩ እንደነበር ታወሰኝ ። ልጄ ያበረሸበት '' ቲቢን በጋራ እንከላከል'' የሚለው ቀበሌ የሰጠኝ ካኔተራዬ ትዝ አለኝ ፣ ጭኔ ላይ የተቦተረፈው ቱታዬ ተከሰተልኝ።

በምን አይነት ቀን ተያዝኩ....? በምን ዓይነት አሳቻ ሰአት ላይ ተገኘሁ ? እግዜሩ ምይ በደልኩት ?ዐስራ ስምንት አመት ጠብቆ ጡቶቻችን ቶሎ እንዲወጡልን የውሃ እናት ካጠባችን የልጅነት ጓደኛዬ፣የዛሬ ዲያስፖራ
- ዘናጭ- ቆንጆ - ብራም - ደስተኛ - ያለፈላት ሴት ፊት በዚህ ሁኔታ ያገናኘኛል? ለእንዲህ ያለ ክፉ አጋጣሚ አሳልፎ ይሰጠኛል?

ሐሳቤ ሳያልቅ ደረሰችብኝ።

''ወይኔ...ጥላሸት በጥላሸት..ምንድን ነው የምታቦኪው ፍቅርዬ? ነይ ቀስ ብለሽ እቀፊኝ...'' አለችኝ።

እያፈርኩ መዳፎቼ ቢጫ እና ነጭ ሸሚዞን እንዳይነካ አንጨፍርሬ ለወጉ አቀፍኳት።

''ኦህ ማይ ጉድነስ...! ፍቅርዬ...ደህና ነሽ...? ምንድን ነው እንዲህ የተጎሳቆልሽው...? ኑሮው ነው ? እኔማ አገኝሻለውም አላልኩ፣ ምንድን ነው ይሄ ሁሉ...? ሰፈራችን የት ደረሰ...? ምን ሆኖ ነው ሁሉ ነገር ብትንትኑ የወጣው...? ሰውስ የት ሄደ...?

የጥያቄ ጎርፍ።

''የቱን ልመልስል....? ብዙ ጥያቄ ነው...ደህና ነሽ ግን...? መቼ መጣሽ?'' አልኩ የተቦተረፈውን ቱታ ሱሪዬን በረጅም አሮጌ እና ቆሻሻ ካኔተራዬ ለመሸፈን እየሞከርኩ፣ ጎላ ድስትን በሚጢጢ ድስት ክዳን እንደመክደን እየሆነብኝ።

''ሦስት ሳምንቴ...ዋ....ው! እኔማ...''አለችኝ! በዐይኖቿ እያጠናችኝ። ሰው እንዴት በዐስራ ስምንት ዓመት ውስጥ ዐይኑ በአንድ መስመር እንኳን አይከበብም....? የኔን ዐይኖች ዐሥራ ስምንት መስመሮች ያጅቧቸዋል ።

ካኔተራዬን ይበልጥ ወደ ታች ጎተትኩት።

''ፍቅርዬ ምንድነው እንዲህ ውድቅድቅ ያልሽው? እንዳገባሽ፤ እንደወለድሽ ሰምቼ ነበር....ምንድን ነው ግን...በጣም እኮ ነው የተጎሳቆልሽው፤ ኑሮሽ ጥሩ አይደለም?'' አለች ዙርያ ገባውን እያየች።

ያላረጀ ዐይኗ ማየት ቢችል፤ ኑሩዬ ጥሩ እንዳልሆነ መልስ አትፈልግም ነበር።

ቡና እና ሻይ ፊት ለፊት ፣ ቀልጦ አገር ያቀልጥ በነበረው መንደር ውስጥ፣ በፍርስራሽ በተከበበ እና በግማሹ የፈረሰ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው። ቤቱ በልማት ተገምጧል። ነገ ደሞ ስልቅጥ ተደርጎ ይበላል።

ፈገግ ብዬ ዝም አልኳት።

''እንግባ አይባልም ታድያ?.....''ስትለኝ፣ በከሰል ንክር እጄ እየመራሁ ቤት ወደምለው የግድግዳና የጣርያ ድምር ወሰድኳት።ገባን። እፈረው ቤት ገባን።

ሳሎን ብለን የምናጋንናት ሦስት በሦስት ክፍላችን ውስጥ ፣ ከሞቱት አባትና እናቴ ከወረስኳቸው ፎቶዎች - ሁለቱ አሉ። ሌላው ለወሬ አይበቃምና ይቅርባችሁ።

እኔና ባሌ በርሄ... ቤርዬ ከስድስት ወር ልጃችን ጋር፣ በንፅፅር ሳሎኑን ፈረስ በምታሰኝ፤ በቅርጽ ለቱቦ በምትቀርብ ክፍል ውስጥ እንተኛለን። ትልልቆቹ ልጆቻችን ሰምሃልና ዳንአረል ሳሎን ይተቻሉ።

ይኼወ ነው።

''አይ ካንት ብሊቭ! እስከ ዛሬ እዚህ ቤት እንደምትኖሪ...! ልጆች ሆነን እዚ ሳሎን ጋሽ አባይ እጅ በጆሮ ያስሲያዙን ትዝ ይልሻል?''

አለችኝ።

''እህ...አዎ....ዛሬ ደሞ እኛን ኑሮ እጅ በጆሮ አሲዞናል....ያው የቀበሌ ቤት አይደል...አዲስአባ ዛሬ ለእኛ ዓይነቱ ቦታ የላትም...ስለዚህ የቤተሰብ ቀበሌ ቤት ወርሰን እንኖራለን....እንኖር ነበር ...አሁን እንደምታይው ነው...ሰፈሩ ሁሉ ፈርሶ...ሰው ሁላ...''

''አይ ኖው ! ዋር ዞን እኮ ሚመስለው ! ያልደወልኩለት ሰው የለም እኮ..ግን ሁሉም ሰው ከዚህ ሰፈር እንደወጣ ሰማሁ ለምሳሌ ሀውልት ቦሌ ምን የመሰለ ቤት ሠርታለች አሉኝ። ሠመረና ቢኒ፣ ሁሉም አግብተው ገርጂ አካባቢ መሆናቸውን ሰምቼአለሁ። ፈትለ አሜሪካ ናት...ራሄሌ ስዊድን ነው የምትኖረው፤ ሌላ... ሌላ ኦ...ታሪኳ እንኳን ከዛ መቃብር ከሚመስል ቤት ወጥታ፣ ሰሚት ምን የመሰለ ፓላስ ውስጥ መሰለሽ የምትኖረው...''

ወደ ላይ ሊለኝ ፈለገ።

እሷ አንድ ቦታ ላይ ሩጫ ጀምረን ጥለውኝ የሄዱትን ደርበውኝ የሮጡትን፣ የሰፈራችንን ልጆች የዛሬ ኑሮ ስትነግረኝ፣ ወደ ላይ ሊለኝ ፈለገ። ስሜቴ የገባት አልመሰለኝም።ይሄ አሜሪካ የስሜት ማንበብያ በቀዶ ጥገና ያስወጣል እንዴ?

ቀጠለች፣

''...ግን ፍቅር...ምን ሆነሽ ነው ያ ሁሉ ሰው ሲወጣ አንቺ ብቻ እኮ የቀረሽው...ማለቴ ኦልሞስት ትዊንቲ ይርስ..ዛት ኢዝ ኤ ሎንግ ታይም ኖት ቼንጅ...መቼም ህልምሽ ይሄ አይመስለኝም..ምን ሆንሽ...''

''ለስላሳ ነገር ላምጣልሽ?'' አልኳት ፍንጥር ብዬ ተነስቼ።

''ለስላሳ ላምጣልሽ..ምን ይሁንልሽ...?''

''ኦ ኖ...ለስላሳ አልጠጣም....ዳይት ላይ ነኝ... አታይኝም ተዝረጥርጬ...'' አለችኝ። ልብሷ ብቻ ሳይሆን ቆዳዋ እንደጠበባት ያስተዋልኩት ገና አሁን ነው።

''አሜሪካ ያወፍራል መሰለኝ....''

''አዎ ምግቡ...ዝም ብለን በመኪና ስለምንዞር፣ በዚያ ላይ....በነገርሽ ላይ...መኪና ያቆምኩት በፊት ጠጅ ቤት የነበረበት ቦታ ነው። ሴፍ ነው አይደል..? የሆኑ ልጆች እንደ ጉድ ሲያዩኝ ነበር..''

ሣቅ አልኩና ፣ ''ሰላም ነው...ምንም አይሆንም እና ምንም አትበይም...?''ባዶ ቤት አጉል ሰአት መጣሽ...'' አልኳት።

''ኖ ፣ ዛት ኢዝ ሶ ኦኬ ይልቅ...ማታ እንውጣ... አንቺም ፈታ በይ...ቀና ቀና ብሏል ዘፋኙ...'' አለች ብድግ ብላ።

''ማን ነው እሱ ደግሞ?''

''አብርሃም ወልዴ ነው ማነው?...አይ ላቭ ዛት ሶንግ ! ''

''እሺ ፣ ግን...ባሌን ልንገረው መጀመርያ...'' አልኩ እያቅማማው። የማስበው ልለብሰው ስለምችለው ልብስ ነው። የማስበው ስለተንጨበረረው ጸጉሬ ነው። ታኮዋ ስለላላችው፣ ብቸኛዋ ''የውጪ ጫማዬ ነው።

''ኦ ማይ ጋድ! ዋት ኢዝ ዚስ...ናይንቲን ሰርቲስ..? የሱን ፍቃድ መጠየቅ አለብሽ እንዴ..?

''እንዴ አስኩ..ትዳር እኮ ነው..በዛ ላይ ህፃን ልጅ አለኝ..መያዝ አለበት''

''ቢሆንም..ኤኒ ዌይ...አስካሁን አለመጠየቄ ይገርማል..ማነው ስሙ ባልሽ...?

''በርሄ...በርሄ ይባላል።''

ልክ እንዲህ ስላት ፣ እጆቿን እያማታች፣ በሹል ጫማዋ የተቦረቦረ ሊሾ መሬቴን እየደቃች፣ ''ኖ ዌይ...! '' አለች።

''ምነው...አታውቂም ነበር...? ቤሪን እንዳገባሁ...'' አልኳት ፊቷን እየሰለልኩ። የዋሸችኝ መሰለኝ...

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት።
👍31
አትሮኖስ pinned «#ዐልቦ : : #በሕይወት_እምሻው : #ክፍል_አንድ : ''ፍ...ቅ...ር...ተ!'' ስሜ በሴት ሲጠራ ሰማሁና እጆቼን አጎንብሼ ክሰል ከምጎለጉልበት ማዳበርያ ሳላወጣ ቀና አልኩ። ሴት ናት። ለሰፈራችን ከልክ በላይ የለበሰች፣ ለተቦዳደሰ ኬር መንገዳችን ከሚመጥነው በላይ ሸላይ ጫማ ያደረገች ፣ ቂ...ቅ ያለች ሴት ናት። ከመስታወት የተሰራ የሚመስለው ባለ ረጅም ስፒል ጫማዋ በሚፈቅድላት ፍጥነት ሚዛኖን…»