አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-41
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከበራፍ ተቀብሎ ወደውስጥ በማስገባት ሶፋ ላይ እንዲቀመጡ ያዘዛቸው የአጋቾቹ መሪ የሚመስለው  ሰው ፊት ለፊታቸው ተቀምጦ በዝምታ እየተመከታቸው ነው፡፡አስተያቱ ደግሞ በሁለቱም ውሰጥ ሽብር ነዛባቸው፡፡ ከተቀመጠበት ድንገት ተነሳና…‹‹እስክመለስ ድረስ ለምን እዚህ እንደመጣችሁ እሰባችሁበት ጠብቁኝ››አለና ተነስቶ ወደውስጥ ገባ፡፡
‹‹ምን ማለት ፈልጎ ነው…?ይሄ ሁሉ ሰራዊት እዚህ ቤት ውስጥ ምን ይሰራል…..?ችግር ውስት ገባን ማለት ነው?››ትእግስት ነች ጥያቄዎቾን ደራርባ እዝራን የጠየቀችው፡፡
‹‹አላውቅም…ቆይ እስኪ በፀጥታ ላስብበት…የሆኑ የሆኑ ነገሮች እየተገጣጠሙልኝ  ነው››አለትና አይኖቹን እንደመጨፈን ብሎ በጥልቀት ማሰብ ጀመረ፡፡
እዝራ አእምሮውን ጥልቅ ደረስ ዘልቆ  በረበረ…ስለወንድሙ አካሄድና አንዳንድ ፈላጎቶች አሰበ ..እና እሱን ለመቋቋምና ለሌሎች ሰዎች  ሳይጎዱ እሱ ባጠፋው ጥፋት ልክ ቅጣቱን ማግኘት እንዲቸል ለማድረግ እንዲያስችለው ነገሮችን  በንቃት ማድረግ እንዳለበት ወሰነ ፡፡በንቃት  ላይ ያለ ሠው  ደግሞ አሁን ላይ መገኘት፤እያንዳንዶን ደቂቃና ሰዓት በጥልቀት መኖር፤ነገሮችን ባሉበት ተፈጥሯዊ ይዘት የመቀበል ችሎታ  እና የሌላውን ህመም በጥልቀት መረዳት ብቃት ሊኖረው የግድ ይላል፡፡እና እዝራ ሀሳብን እልባት ሳያበጅለት  አጋቹ መጣና ጥሎት በሄደበት ቦታ ከእነሱ  ፊት ለፊ ቁጭ አለ፡፡
‹‹እሺ..እዚህ ምን እግር ጣላችሁ?አሁን ልሰማችሁ ዝግጁ ነኝ››አላቸው፡፡
እዝራ ከዚህ ትርምስም  እሱንም ሆነ ሌሎችን የሚወዳቸውን ሰዎች በጥበብ ይዞ መውጣት እንደዳለበት ወስኗል ፡፡አዎ አሁን በንዴት ሳይሆን በስሌታ ማሰብ እንዳለበት እራሱን አሳመነ  …..መጀመሪያ የጠረጠራቸው ነገሮች በትክክል የተፈጸሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳበት ተሰማው… አእምሮውን ለመጠቀም ወሰነ‹‹ከወንድሜ ጋር ወደ እዚህ ቦታ አብረን ለመምጣት ተቃጥረን ነበር፡፡ከዛ ግን ጠፋብኝ…ማለቴ ስልኩ ሁሉ አይሰራም…ሌሎች ቦታዎች  ከፈለኩት በኃላ ምን አልባት በስራ ውጥረት ተዘናግቶ እኔን እረስቶኝ ወደእዚህ መጥቶ ይሆናል ብዬ በመጠራጠሬ ነው የመጣሁት››ሲል ቦታው ላይ የተገኙበትን ምክንያት አብራራለት፡፡
‹‹በዚህ ምሽት  አራት ሰዓት ካለፈ በኃላ?፡፡››ሰውዬው የተናገረውን አንዳላመነው በሚያሳብቅ የድምፃ ቅላፄ ጠየቀው፡፡
‹‹አይገርምም…በጊዜ ከእሷ ጋር ተገናኘተን ትንሽ እየቀማመስን እየተዝናናን ነበር….ከዛ ወደቤት ለመሄድ ላዳ ውስጥ እንደገባን ወንድሜ ጥዋት ወደእዚህ ቦታ እንሄዳለን ብሎኝ እንደነበረ ትዝ አለኝና ላዳው ወደእዚህ እንዲያመጣን ነገርኩት..ይሄው ነው….አሁን ወንድሜ የት ነው?ላናግረው እንደምፈለግ ንገረው፡፡››ማስመሰሉን  ቀጠለበት፡፡
‹‹ወንድምህ እዚህ እንዳለ በምን አወቅክ?››
‹‹ ነገርኩህ እኮ!1ሌላ ቦታ እንደሌላ  አረጋግጬለሁ…እዚህ ካልሆነ ሌላ የት ይሆናል?ብዬ ነዋ››
‹‹እንግዲያው እርምህን አውጣ …ወንድምህ  እዚህ የለም….እኛም ቀኑን ሙሉ ስንጠብቀው ነው የዋልነው››መለሰለት
‹‹ልጁስ ?››እዝራ እንደዋዛ ቀጣዩን ጥያቄ ሰነዘረ፡፡
‹‹የቱ ልጅ?››ኮስተር ብሎ
‹‹መንግስቱ ነዋ…የያዛችሁት ልጅ››
‹‹አለ …ከጀርባ ባለው ክፍል  ነው››
እዝራ በእርካታ ተነፈሰ….ትእግስት በእዝራ ብልጠት ተደመመች‹‹እና ኮሪደሩ ላይ ያሉት ጓደኞችህ ምንድነው የሚጠብቁት?››ስትል ለአጋቹ ሌላ ጥያቄ አቀረበችለት፡፡
‹‹ልጁቷን ነዋ…ስለሷ አልነገራችሁም እንዴ..?እርግጥ እሷን እኛ አይደለንም ያገትናት  ..ቀደም ብላ እዚህ ነበረች›››
‹‹አሮራ ነች?››እዝራ ትንፋሽ በሚያሳጣ ድንጋጤ  ውስጥ ሆኖ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ ..ዘፋኟ….የገዛ ልጁን ለምን እንዳገታ አልገባኝም….?ምን አልባት ወንድ ላይ እየጠንጠለጠለች አስቸግራው ሊሆን ይችላል…..››የራሱን ግምት በማስቀምጥ ማንነቷን አረጋገጠላቸው፡፡
ሁለቱም ልክ እንደነተነጋገረ ሰው ከመቀመጫቸው በርግገው በመነሳት ወደኮሪደሩ ተንደረደሩ…ጠባቂዎቹ መንገዳቸው ላይ እጃቸውን ሰትረው በመደርደር ግድግዳ ሆነው አገዷቸው…ሲያወራቸው የነበረው ሰው ከኃላቸው መጣና‹‹ሰዎች እሷን ለማነጋር የግድ የግርማ ፍቃድ ያስፈልጋል››አላቸው፡፡
‹‹ግርማ እኮ አሁን እዚህ የለም …መፍቀድ የምትችለው አንተ ነህ››
‹‹አይ አቶ ግርማ እዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አቋም በግልፅ ነው የነገረኝ …ልጅቷ ያለእሱ ፍቃድ ማንም ሊያናግራት አይችልም…ከቻላችሁ በስልክ አግኙትና ….ያናግሯት  ብሎ ይንገረኝ፡፡››
ትእግስት ስሜቷን መቆጣጠር አቅታት‹‹እንደውም እስከአሁን የነገርንህን ሁሉ እርሳው…ከግርማ ጋር የተነጋርከውን ብር ለማግኘትና ችግር ሳይፈጣር ከዚህ ጣጣ ውስጥ ለመውጣት ከፈለክ ከእኛ ጋር መስማማት የግድ ይልሀል››አለችው ፍጥጥ ብላ፡፡
ሰውዬው ኩስትርትር አለ‹‹አልገባኝም ..ከእናንተ ጋር ምን ይሁንልኝ ብዬ ነው የምስማማው…የቀጠረን ግርማ ነው…ብራችንንም የሚከፍለን እሱ ነው፡፡እስከአሁን እንደውም ለምን እንዳልመጣና እንደዚህ አይነት እርስኪ ያለው ስራ ካሰራን በኃላ እንዴት እንደዚህ  እንዝላል እንደሆነ ገርሟኛል በዛ ላይ እናንተ እኮ በእኔ ቁጥጥር ስር ነው ያላችሁት...አልገባችሁም እንዴ? አሁን እኮ በቃ ታጋቼ ሆናችኋል፡፡››
‹‹እንደዛ እንኳን አይመስለንም …ይሄንን ምንነግርህ ግርማ መምጣት ስለማይችል ነው››አለው እዝራ፡፡
‹‹መምጣት እንደማይችል!! በምን አወቅክ…?አሁን ከጥዋት ጀምሮ ፈልጌ አጣሁት ስትል አልነበረ እንዴ?››
‹‹ዋሽቼህ ነው፡፡››
ሰውዬው ትዕግስቱ ተሞጠጠበትና ሽጉጡን ከሻጠበት መልሶ አውጥቶ ደቀመነባቸው‹‹መቀባጠሩን አቁማችሁ ትክክለኛ እየሆነ ያለውን ነገር ንገሩኝ…ካለበለዛ ግንባራችሁን አፈራርሰዋለሁ፡፡››
ትእግስት‹‹ቆይ›› አለችና ስልኳን በማውጣት ደወለች‹‹ሄሎ ክንዴ››
‹‹ሄሎ ትእግስት መንጌ ተገኘ እንዴ?››
‹‹አይ እስከአሁን እያፈላለኩት ነው…ግን አሁን የደወልኩት እስከጥዋት ተመልሶ ማይማጣ  ከሆነ ጥዋት ሁለት ሰዓት ድረስ ብሩን ይዤ ለመምጣት እንደተዘጋጀው ልነግርህ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ያስማማናል››
‹‹ከዛ ግርማን ታስረክበኛለህ ››
‹‹ምን ጥያቄ አለው..ዝግጁ ስትሆኚ ደውይልኝ …የእኛ ልጆች ያገኙሽና በጥንቃቄ ..ማለቴ ፖሊስና ሌላም ሰው እንደማይከተልሽ እርግጠኛ ከሆኑ በኃላ ወዳለንበት ያመጡሻል፡፡››
‹‹እሺ አመሰግናለሁ… ቸው››ስልኩ ተዘጋ፡፡
ሽጉጥ የደቀነባቸው የመንግስቱ አጋች‹‹እና አጋቹን ያሳገታችሁት እናንተ ናችሁ ማለት ነው?››ሲል በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹አይ ያሳገተው መንግስቱ ነበር..እኛ አይደለንም››ትእግስት መለሰች
ከት ብሎ ሳቀ…‹‹የሚገርም የፊልም እስክሪፕት ይወጣዋል..ታጋቹን አላመንኩትም እንጂ ሊነግረኝ ሞክሮ ነበር..ይገርማል….!!ቆይ አንተም በወንድምህ መታገት እጅህ አለበት?››ወደ እዝራ ዞሮ ጠየቀው፡፡
‹‹የለሁበትም…መታገቱ ግን ይገባዋል ባይ ነኝ..አሁን አስገባንና አሮራን እንያት… ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ዋናው ምክንያት የእሷ ከእይታችን መሰወር ነው…እሷ ጤና መሆኗን እንይና ከዛ ቁጭ ብለን ሁላችሁም ብራችሁን አግኝታችሁ ማንም ሰው ሳይጎዳ ከዚህ ትርምስምስ  የምንወጣበትን እና ወደየህይወታችን  የምንመለስበትን  ሁለታ  ላይ ቁጭ ብለን እንነጋገራለን፡፡››
👍644🥰1😁1🤔1
አጋቹ የእዝራን ንግግር ከሰማ በኃላ ወደትእግስት ዞሮ‹‹አንቺ መንግስቱ ምንሽ ነወ?››ሲል ተየቃት
‹‹ጓደኛዬ››
‹‹ ግርማስ? የት ነው ምታውቂው..?››
‹‹የእሱ ሰራተኛ ነኝ..ማለቴ የአሮራ ረዳት ሆኜ ነው የምሰራው፡፡››
አጋቹ በድጋሜ መገረም ሳቅ   ሳቀ…..‹‹እርስ በርሳችሁ ነዋ እየተጠፋፋችሁ ያላችሁት››

እዝራ‹‹እንደዛ መሰለኝ..ስለዚህ ምንልህን  ስማትና አሁን ወደ አሮራ አስገባንና እንያት ….ከዛ ቁጭ ብለን እናንተም ገንዘባችሁን ሳታጡ..ሌላ ወንጀል ውስጥም ሳይገባ ሁኔታዎችን እናስተካክላለን…በዛ ቃል እንገባልሀለን፡፡››አለው፡፡
እንደማሰብ አለና ‹‹ስልካቸውን ተቀባሏቸውና አስገቧችው››ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ስልካቸው ተቀብለውና ፈትሸው ከመንገዳቸው ዞር አሉላቸው…እዝራና  ትእግስት የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፍተው ተከታትለው ወደውስጥ ሲገቡ አሮራ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነበረ ያለችው…ትእግስት ዘላ አልጋ ላይ ወጣችና ወዘወዘቻት፡፡አሮራ ከእንቅልፏ ባና አይኖቾን ስትገልጥ ትእግስትንና አጎቷን በማየቷ ግራ ተጋባች…‹‹የነቃው መስሎኝ ነበር ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ?››ጠየቀች፡፡
‹‹አይደለሽም የእኔ ቆንጆ..የእውነት ነው….አገኘንሽ…በህይወት አለሽ…››ትእግስት መለፍለፏን ሳታቆም እያገላበጠች ትስማት ጀመረ…እዝራም የደስታ እንባ ከአይኖቹ እያረገፈ ግንባሯን ሳመና አልጋውን ተጠግቶ ባለ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡
‹‹እንዴት አገኛችሁኝ …?ጠባቂዎቹ እንዴት ፈቀዱላችሁ…?የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ እንዴ..?ያ የረተረገመ እኮ ዛሬ ወደውጭ ሊልከኝ ነበር..ትኬት ሁሉ ተገዝቶ ነበር…ግን ምን እንደሆነ አላውቅም ቀረ  …እስከመጨረሻው ላጣችሁ ነው ብዬ በጣም ፈርቼ ነበር….›››በማለት ከማያቋርጥ የለቅሶ አጀብ ጋር የሆነውና እና ስላሳለፋቻቸው  የመከራ ቀናት ነገረቻቸው።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍10016👎3👏3🥰2🔥1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-42
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ትእግስት እና  እዝራ ከሁለቱ ወገን አጋቾች ጋር በመነጋገር እና በመደራደር ግርማንና መንግስቱን ፊት ለፊት ለማገናኘት አቅደው ተሳክቶላቸዋል፡፡ከሁለቱም አጋቾች የተውጣጡ ስድስት የታጠቁ  ሰዎች ዙሪያቸውን እየጠበቋቸው አንድ ክፍል ውስጥ እንደበፊቱ እጆቻቸውና እግሮቻቸው ተስረው ሳይሆን ነፃ ሆነው እየተንቀሳቀሱ  ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከአስር  ለበለጡ ደቂቃዎች ቃል ማውጣት የቻለ አልነበረም፡፡
‹‹በጣም ነው የምታስጠላኝ››አለው መንግስቱ ፡፡
‹‹ያደረኩህን ሁሉ ያደረኩት እኮ በራስህው ስህተት ነው…ሁሌ በመንገዴ ላይ ትሰነቀራለህ…በፊት ያሳሰርኩህም አሁን ያሳፈንኩህም ለዛ ነው፡፡››
‹‹አይ የምጠላህ እኔ ላይ ባደረከው ነገር አይደለም…ለዛ ይቅር ልልህ እችላለሁ…፡፡በአንተ አሻጥር መታሰሬ ብዙ ነገር ቢያሳጣኝም መቼም ለገኛቸው የማልችላቸውን ገራሚ የህይወት ልምዶችንም ያገኘሁበት ቦታ ስለሆነ እራሴን እንደተጎጂ እየተመለከትኩ አንተን ስወቅስ መኖር አልችልም፣..እኔ አምርሬ የምጠላህ አሮራ ላይ ባደረከውና እያደረክ ባለኸው ድርጊት ነው፡፡
ምን አደረኳት…?እንዴት ተንከባክቤ እንዳሳደኳት አታውቅም…?የዝና ጣሪያ ላይ እንድትወጣ መደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ አድርጌለሁ…ምን በደልኳት?፡፡››
‹‹የሚገርመው ስትበድላት መኖርህ አይደለም….አሁንም በውስጥህ ምንም አይነት ፀፀት አለመኖሩ ነው….እንዴት ከገዛ ልጅህ ጋር ትተኛለህ?››
ግርማ በጣም ደነገጠ…ይሄንን ነገር ማንም ያውቃል ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር….‹‹ይሄንን እንዴት ነገረችህ?››
‹‹አይ እሷ አልነገረችኝም…እንደማውቅም አታውቅም…ግን ይሄ ሁሉ ውጥንቅጥ ከመፈጠሩ በፊት አንተን በተወሰነ መጠን ሳሰልል ነበር…እና ከእንጀራ ልጅህ ጋር የጎረምሳ አይነት ወሲብ ስትፈፅም የሚያሳይ የተቀረፀ ቪዲዬ አለኝ…ለአሮራ ባላስብ ያንን ቪዲዬ በኢንተርኔት ነበር የምለቀው….ከዛ በዚህ ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ውስጥ እንዴት አንገትህን ቀና አድርገህ መኖር እንደምትችል አይ ነበር?፡፡ግን እሷን አምርሬ ስለማፈቅራት ..እንደዛ ማድረግ አልቻልኩም››
ግርማ እንደበፊቱ ቆጣ ቆጣ የሚለውን ስሜቱን ገርቶ በተዳከመ ድምፅ ጠየቀ‹‹ሌላ ማን ያውቃል…?››
‹‹ስር ስሮ ስትል ላየኋት ትእግስት አሳይቼታለሁ…ወንድምህ አይቷል….ከዚህ ጣጣ በኃላ ደግሞ ፀባይህ እየታየ ሌሎች ቅርብህ ያሉ ሰዎች እንዲያዩት አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምን ነካህ ደደብ ነህ እንዴ..?እንዴት ለእዝራ ታሳዋለህ…?እንደልጁ እኮ ነው የሚወዳት …በዛ ላይ እብድ ነው ይገለኛል፡፡››
‹‹ቢገድልህ ደስ ይለኝ ነበር..ግን እንደዛ አይነት የተባረከ ንፅህ ሰው በአንተ ቆሻሻ ደም እንዲረክስ አልፈልግም…ያ  ትክክል አይደለም፡፡አሁን ሁላችንንም ትተወናለህ፡፡››
‹‹ሁላችንንም ስትል?››ጠየቀ ግርማ፡፡
ሁላችንንም…እኔንም ፤አሮራንም ፤ትእግስትንም፤ጋሽ እዝራንም…ሁላችንም ከዛሬ ጀምሮ እኛን አታውቀንም ..እኛም አናውቅህም፡፡ያለንበት አትደርስም አንተ ያለህት አንደርስም..ይሄ ያስማማናል፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ….?ከአንተ ጋር እሺ በፊትም አሮራ እንጂ ሌላ የሚያገኛኘን ነገረ የለም…በቀላሉ ላለመደራረስ እንችላለን..ሌሎቹ ግን?››
‹‹ሌሎቹ ምን?››
‹‹ለምሳሌ እዝራ ስራ መስራት ካቆመ አመታት አልፈዋል..በሽተኛ ነው…ከእኔ ብር ካለገኘ እንዴት ይኖራል…?ትግስትም ስራዋን ታሳጣታለህ….አሮራንም እየገነነ ያለው የዘፋኝነት ጉዞዋ ላይ እንቅፋት ነው የምትሆንባት ….ለሁሉም አስፈልጋቸዋለው…ለጊዜው ቢበሳጩብኝም ግን እመነኝ ከእኔው ጋር መቀጠል ነው ሚፈልጉት፡፡››
‹‹እንደዚህ ነው የምታስበው…?››
‹‹አዎ…ግልፅ ነው››
መንግስቱ ከመቀመጫው ተነሳና ቆመ…. አቶ ግርማ ተንደርድሮ ሊያንቀው መስሎት አይኑን አፈጠጠ…መንግስቱ ግን  እግሩን ወደበራፉ አንቀሳቀሰ…..እና አንኳኳ…ተከፈተለት፡፡በራፍ ላይ ያለውን ሰው አነጋገረው..እና ወደቦታው ተመልሶ ተቀመጠ፡፡
በመሀከላቸው መልሶ  ዝምታ ሰፈነ….
‹‹እሺ አሁን ምን እናድርግ?››ግር ነው ጠያቂው፡፡
‹‹ቆይ ጠብቅ አለው….››መንግስቱ
በዛው ደቂቃ በራፉ ተከፈተና ትእግስት አንገቷን አስግጋ ቀድማ ገባች፤ከዛ ጋሽ እዝራ የአሮራን እጅ እንደጨበጣ ገባ…መንግስቱ ተነሳና ተቀበላች…ግራና ቀኝ እሱን ከበው ተቀመጡ….ግርማ በእፍረት አንገቱን ወደምድር አቀረቀረ….
መንግስቱ ንግግሩን ጀመረ……‹‹ወዳጆቼ አሁን ከዚህ ሰው ጋር ስለብዙ ነገሮች እየተነጋገርን ነበር….ከዛ በመጨረሻ ከሁላችንም ትርቃለህ..ከእኔም፤ ከትእግስም ፤ ከአሮራም ሆነ ከወንድምህ ከእዝራ አጠገብ አትደርስም…እኛም አንተ ስር አንደርስም…አልኩት …እሱ ግን ከአንተ እርቃለሁ…ከሌሎቹ ከራቅኩ ግን ሚጎዱት እንሱ ናቸው፡፡ትእግስትም ስራዋን ታጣለች…አሮራም የሙዚቃ ህይወቷ ይበላሻል…..ወንድሜም በእኔ ብር ነው የሚኖረው አለኝ…እኔ እናንተን ወክዬ መወሰን ስላቃተኝ ነው ያስጠራዋችሁ…እና ምንድነው ሀሳባችሁ?፡፡
ትእግስት ጀመረች‹‹እኔ እንኳን እሱ ያለበት ቤት ውስጥ እሱ የሚኖርበት ከተማ ውስጥ ባልኖር ደስ ይለኛል….ስሬ እንዳትደርስ››አለችው፡፡
‹‹ለእኔ ሞተሀል….አበባዬን ቀንጥሰህ ነው ያጠወለግከው…አንዴት ይኖራል ?ብለህ አታስብ …መኖር ቢያቅተኝ በክብር ለመሞት ድፍረት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ስለዚህ ስሬ እንዳትደርስ ››አለው፡፡
አሮራ ጉሮሮዋን አፀዳዳችና መናገር ጀመረች….‹‹እኔ ግን አልስማማም…ዝም ብዬ ልተወው አልችልም››አለች፡፡ ሁሉም በድንጋጤ አይናቸው ፈጠጠ….

የግርማ ፊት በፈገግታ  ፈካ…፡፡እና በፈንጠዝያ መናገር ጀመረ‹‹አውቃለሁ የእኔ ቆንጆ ..የእኔ ነገር እንደማይሆንልሽ በደንብ አውቃለሁ…በመሀከላችን ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት አዝናለሁ…ታያለሽ እክስሻለው፡፡ወደ ውጭም እንድትሔጂ ያሰብኩትን ትቼዋለው….እዚሁ ከእኔ ጋር ነው የምትኖሪው…ለዛ ቃል እገባልሻለሁ፡፡››አላት፡፡

አጎቷ እዝራ ባልጠበቀው መልሷ ግራ ተጋብቶ ‹‹ሮሪ እርግጠኛ ነሽ ከዚህ ሰው ጋር ያለሽን ግንኙነት ማሳቀጠል ትፈልጊያለሽ…?ፈርተሸው ከሆነ እኔ አጎትሽ አለሁ፡፡በህይወቴ ጭምር ከእሱም ሆነ ከሌላ አንቺን ሊያጠቃ ከሚያስብ ሰው ጠብቅሻለው፡፡››አላት ፡፡

‹‹አጎቴ እንደዛ እንደምታደርግ አውቀለሁ፡፡ሁላችሁም እኔን ለመጠበቅ እንደማታቅማሙ አውቀለሁ…ለዛምነው ይሄን ሰው ዝም ብዬ በነፃ ልለቀው የማልፈልገው…እሱነ ከህይወቴ ብቻ በማስወጣት በሰላም እንዲኖር ልፈቅድለት አልችልም…..ልጅነቴንና የዋህነቴን ተጠቅሞ አቆሽሾኛል…እሺ እሱን ይቅር ልለው እችላለሁ….እስክሞት ድረስ ደብድቦኝ ለቀናት አግቶኝ ነበር ፤እሱንም ይቅር ልለው እችላለሁ…ግን የእናቴን ነገር እንዴት ችላ ብዬ እተወዋለሁ?፡፡››ስትል ጠየቀች፡፡
ሁሉም ግራ ተጋብተው እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሮኒ እናትሽ ምን?››እዝራ ነው ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቀው፡፡
‹‹እናቴን በእጆቹ የገደላት ይሄ ሰው ነው….ለዛ ሳይከፍል በነፃ ልለቀው አልችልም››


,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍15014😱3😁2🔥1
(የመጨረሻ ክፍል)
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-43
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
ግርማ ለዘመናት ሸሽጎቸው የነበሩ ሚስጥሮቹ ሁሉ ተዝረክርከውበት  ግራ ተጋብቷል።አሁን የማይፈልጋቸውን ሰዋች ከህይወቱም ሆነ ከአካባቢው እንዴት እንደሚያስወግዳቸው ሳይሆን እራሱን እንዴት ከገባበት ወጥመድና ከእስር ቤት ስጋት ማዳን እንደሚችል ነው እየተጨናነቀ ያለው። በዚህም የተነሳ  አንገቱን ከመድፋት ውጭ  የሚናገረው ነገር አልነበረውም።እዝራ፣አሮራ እና ትዕግስት ፊት ለፊቱ ተቀምጠው  በጥላቻና  በመፀየፍ እየተመለከቱት ነው።
እዝራ  ድንገት አይኖቹን  ወንድሙ ላይ ተክሎ  መናገር ጀመረ"ታላቅ ወንድሜ... በእውነት በዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ ስላንተ በሰማሁት ነገር ሁሉ መደነቄን ልደብቅህ አልፈልግም...እንዴት እንዲህ ደፍሪም ፤ገዳይም ..ዘራፊም ልትሆን ቻልክ?ወላጆቻችን እንዴት እንዳሳደጉን  አውቃለሁ? እንዴት እንዲ ፅንፍ የረገጠ ልዩነት በመሀከላችን ኖረ...?ብቻ እናትና አባታችን እንኳንም በህይወት አልኖሩ..?እንዴ እኔ እንዲህ የተሽማቀቅኩብህ እነሱ ኖረው ቢሆን ኖሮ ልባቸው  እንዴት እንደሚሰበር. ሳስበው ዝግንን ይለኛል።"..
ግርማ የወንድሙን ንግግር ችላ አለና  ወደ አሮራ ዞሮ መናገር ጀመረ...
"በቀደም ባቀረብሽልኝ ነገር ተስማምቼያለሁ"አላት።
"ምንድነው የተስማማችሁት?እኛም እንስማዋ።"ጠየቀ መንግስቱ።
"በቀደም   አንድ መኖሪያ ቤት እና  የኤክስካቨተር ማሽን እንድሰጣትና እንድንለያይ ጠይቃኛለች...ምንም ቢሆን ልጄ ነች... ያንን ባደርግላት ብዙም ቅር አይለኝም...ግን ከእሷም የምፈልገው ነገር አለ ...ይሄ  ስለእናቷ ግድያ...ፓሊስ ምናምን ስለምትለው መረጃ ስለሌለው ነገር መቆፈሩን ታቆማለች..."አለ ...
"አንተ የምትላቸው ንብረቶች እኮ የልፋቴ ውጤቶች ናቸው .. እንተሳሰብ ካልን ንብረቴ  ከዚህ በእጥፍ እንደሚበልጥ እርግጠኛ ነኝ።...የማልከስህ ለምትሰጠኝ ንብረት ስል አይደለም...ለአንተም ሀዘኔታ ተሠምቶኝ ፍፁም አይደለም...አንተን ማልከስህና የማላሳስርህ አንድና ብቸኛው ምክንያት ለትንሿ እህቴ ስል ነው።እሷ አባቴ ምን አጥፍቶ ታሰረ ስትለኝ ምን እመልስላታለሁ?ብዬ ስለማስብ ነው"
"ጥሩ ውሳኔ ነው...ግን እንደእኔ እንደኔ ከእሱ የምትረከቢውን ንብረት ቢቀርብሽ እራሡ ደስተኛ ነኝ..."አላት መንግስቱ።
"ለምን ብዬ ሙልጬን ወጣለሁ..?ስጦታ አይደለም እኮ የጠየቅኩት የለፍሁበትን ንብረቴን ነው...እና ደግሞ እህቴም ከእኔ ጋር እንድትኖር ነው  የምፈልገው።. "
"ሙልጭሽን አትወጪም የእኔ እመቤት ...እኔ ምን ያህል እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ...ፈቅደሽ ብታገቢኝና አብረን ብንኖር ደስ ይለኛል ...ካልሆነም ዛሬውኑ ይሄን ውይይት ጨርሰን  ከእዚህ እገታ ስንላቀቅ አስረክብሻለው።"አላት መንግስቱ
"ምኑን ነው የምታስረክበኝ?።"ግራ በመጋባት ጠየቀችው።
"እኔ ገስት ሀውሱን በስምሽ አዘዋውሬዋለሁ።ያ የ300 ሚሊዬን ብር የሚያወጣው ገስት ሀውስ የእኔም የአጎቴም አይደለም። ያንቺ ከሆነ አንድ ወር አልፎታል።እኔን እሺ ብለሽ አገባሺኝም ብቻሽን ኖርሽም..ወይም ሌላ ሰው አገባሽም  ንብረቱ ያንቺው ነው...ከእሱ ጋር ንብረት መናጠቅ ውስጥ መግባት አያስፈልግሽም"አላት።
እሷ ብቻ ሳትሆን እቤት ውስጥ ያሉት በጠቅላላ በሰሙት ነገር ብዠ ብሎባቸዋል....አሮራ በመገረም ተሞልታ"ለምን ብለህ ነው እንደዛ ያደረከው?"ስትል ጠየቀችው።
"ስለማፈቅርሽ"በአጭሩ መለሠላት።
"እሺ ከወራት በፊት ነው ያደረከው አይደል..ጥሩ በዛን ጊዜ ስለእኔ የነበረህን  ጥሩ ግምት  ነበር  ..ይገባኛል.. ...አሁን ግን ከእዚህ አባት ተብዬ ጋር የነበረኝኝን ግንኙነት አልሰማህም?"
"ሠምቼያለሁ"
"የምታፈቅራት ሴት  የእንጀራ አባቷ መጫወቻ  እንደነበረች ስትሰማ...አልዘገነነህም? "
"አይ አልዘገነነኝም..ግን ደግሞ አልዋሽሽም... አስደንግጦኛልም አበሳጭቶኛልም ።"

"ትክክል እኔም የገመቱኩት እንደዛ ነው ...ከተበሳጨህብኝ ደግሞ በዚህ  ውሳኔህ አትፀናም ማለት ነው"

"አይ ፀናለሁ..ምክንያቱም የተበሳጨሁት በዚህ ሰውዬ እንጂ ፍፁም በአንቺ አይደለም።አንቺ ምን አደረግሽና?"
ሳቀች "እየቀለድክብኝ ነው?"
"ለምን ቀልድብሻለሁ...የምሬን ነው...ለአንቺ ያለኝ ፍቅር  እንዲህ በቀላሉ የሚደበዝዝ አይደለም..."
.ተንደረደረችና ከተቀመጠች ተነስታ ወደእሱ በመሳብ ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት።ሁሉም ያልጠበቁት ስለነበረ ተገረሙ...አቶ ግርማ ግን በሽንፈትና በንዴት አንጀቱ ኩምሸ አለበት። የሚያደርገው ግራ እስኪገባው ድረስ ባለበት ተንቆራጠጠ..
ከመሳሳም ሲላቀቁ ትዕግስት "አንዴ ለብቻህ ላናግርህ?" አለችው።
ምን ሊፈጠር ነው በሚል ሁሉም እርስ በርስ ተያየ...ትዕግስት ከመቀመጫዋ ተነሳችና  የመንግስቱን ክንድ ይዛ አስነሳችውና   ወደጥግ ይዛው ሄደች።
ከዛ በሹክሹክታ "ምነው ችግር አለ እንዴ?"ሲል ጠየቃት ።
"አጎትህ ከካናዳ መጥቶል ..ጠፍተህበት ምድሩን እያሰሰው ነው..ሰምተሀል?"
"አዎ ሰምቼለሁ።"
"የገስትሀውሱን ስም ማዘዋወርህን እንዴት የሚቀበለው ይመስልሀል?"
"እሱን አኔ እወጣዋለሁ..አንዳንድ የማታውቂያቸው ነገሮች አሉ...ሰውዬው የሀብቱ ሁሉ መነሻ ምን ይመስልሻል ..?ከአባቴ የዘረፈ ብር ነው።ቀን ጠብቄ የሚገባኝን ንብረት ወስጄ ነው ለምወዳት ሴት የሠጠሁት...በዚህ ቅር ብሎት የሚያበሳጨኝ አይመስለኝም።"
"ትቀልዳለህ እንዴ...አጎትህ ለዛ ገስትሀውስ ያለው ፍቅርና ኩራት ቀላል አይደለም...እኔ በማቀው እራሱ ያንን ንብረት ለማፍራት በጣም  ለፍቶል...እና  ከቅሬታ በላይ በሆነ ስሜት ውስጥ ነው የሚገባው"
"እንደዛ ከሆነ  የቀሩትንም ንብረቶች ነጥቀዋለው...እሱ የተሳሳተው ለሁሉም ንብረቶቹ ሙሉ ውክልና የሠጠኝ ቀን ነው።"
"አዎ በዛ እኔም አምናለሁ ..አምኖህ ሙሉ ውክልና መስጠት አልነበረበትም...እኔ የምፈራው እርስ በርስ እንዳትገዳደሉ ነው"
"ዋናው የአሮራ የወደፊት ህይወት ይስተካከል እንጂ የእኛ መገዳደል ብዙም አያሳስብም።"
"የአንድን ሰው ህይወት  ለማስተካከል የሌላውን ማውደም ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው..እሺ ንብረቱን እንተወው ሴቶቹን እንዴት ታደርጋቸዋለህ?"
ያልጠበቀው ጥያቄ ስለሆነ ደነገጠ...ግራ ተጋባም"የትኞቹን ሴቶች?"
"ውሽሞችህን ነዋ ...ሁለቱ የጎትህን  ሚስቶች"
"እንዴ!!! እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ ?"
ሁለቱንም ሴቶች አንድ ላይ ስታወጣ አይቼሀለው...እርግጠኛ ነኝ እኚ ሴቶች ነገሩን እንደቀልድ እያዩት አይመስለኝም...እና ጠቅልለህ የአሮራ ልሁን ስትል ዝም ብለው የሚፈቅድልህ ይመስልሀል?"ስጋቷን ጠየቀችው።
"እና ምን ያደርጋሉ?መቼስ ያገባናል ብለው አያስብ"
"ለምን አያስብም...እንደተረዳሁት ከሆነ ሁለቱም አፍቅረውሀል...ያፈቀረች ሴት ደግሞ የትኛውንም አይነት መስዋዕትነት ከፍላም ቢሆን ያፈቀረችውን  ወንድ የራሷ ለማድረግ መጣሯ የተለመደ ነው።"
"አረ ትዕግስት እያጋነንሺው ፤የአጎቴ ሚስቶች ናቸው እኮ"
"አዎ ገባኝ  ...እየተንከባከብካቸው የነበረውም ልክ እንደአጎትህ ሚስቶች ነው...ለማንኛውም ውሳኔህ በጣም  ስሜት የተጫነው መሆኑን እንድታወቅ።የተሠማኝን ተናግሬለው...አሁን ወደ ሰዎቻችን እንመለስና ለውይይታችን እልባት እናብጅለትና ሁለታችሁም በተስማማችሁት መሠረት ለቀጠራችሆቸው አጋቾች  ክፍያቸውን ስጦቸውን ለጊዜውም ቢሆን ከዚህ ግር ግር እንውጣ...ከዛ በሂደት የሚሆነውን እናያለን። "አለችውና ወደነአሮራ ለመመለስ እርምጃ ጀመረች መንግስቱም ስለሰጠችው ጠንካራ ሂስ እያሰላሠለ ከኃላዋ
👍9214👎6🥰5😁2🤔2
ተከተላት።
ታሪኩ ይቀጥላል እኔ ግን አበቃው።
ተፈፀመ

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍44😢12👎9🤔7
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ደሎ  ከተማ በአረና ጥቅጥቅ ደን የተሸፈነች በደቡብ ኦሮሚያ ባሌ ዞን ውስጥ የምትገኝ የወረዳ ከተማ ስትሆን ለሁለት የተከፈለችው ያዶት በሚባል ግዙፍ ወንዝ ነው፡፡ያዶት ወንዝ ለከታማዋ ኑዋሪ ህይወት ነው፣ውበት ነው፣የአይን ማረፊያቸው እና ትምክህታቸው ነው፣ከውጥረታቸው መተንፈሻ ነው፣የሚኮሩበት መዝናኛቸው የሚደምቁበት ጌጣቸው ነው፡፡ ከተማዋ ቆላ እንደመሆኗ መጠን አየሩ በጣም ይሞቃል ፤ በላብ ሚያጥብ ሙቀት፡፡ቀይ  በንፋስ በሚበተን አፈር  እና አቧራ ሲያሰቃየው የዋለው ኑዋሪ ሀብታም ደሀ ሳይል ወደ ያዶት ይነጉዳል፡፡ልብሱን ያወላልቅ እና ወራጅ ወንዝ ውስጥ ይመሰጋል፣እንደ ዓሳ ብቅ ጥልቅ ይላል፣እየተንሳፈፈ ይዋኛል፡፡ ይሄ ትልቁም ትንሹም ወንድም ሴቱም በኩልነት ያለ ልዩነት የሚያደርገው ነው፡፡ሁሉም እርቃኑን በፓንት ብቻ ጎን ለጎን እየተንቧራጨቀ መዋኘት ለእንግዳ ሚያስገርም እና ሚያስደምም ትዕይንት ቢሆንም ለኑዋሪው ተራና የተለመደ የየእለት ደርጊት ነው፡፡

አንድ የዛ ከተማ ኑዎሪ ሌላውን ኑዋሪ ቢያንስ በዓመት አንድ ቀንም ቢሆን እርቃኑን ወይም እርቃኗን የማየት አጋጣሚና ዕድል ይኖረዋል፡፡የደሎ ኑዋሪዎች ዋናተኛ ናቸው፡፡ህጻናት ከ5 አመት ጀምረው ነው ከታላላቆቻቸው ጋር ወደ ያዶት ወንዝ ወረድ በማለት ዋና መማር የሚጀማሩት፡፡ያዶት መዋኛና ከሙቀት አካልን ማቀዝቀዣ ብቻ አይደለም፡፡የከተማው ሰው ሁሉ ልብሱን የሚያጥበው እዛው ወንዝ ነው፡፡ልብሱን በጀርባው አዝሎ ወይ በሻንጣ ሞልቶ ማጠቢያ ሳፋውን ተሸክሞ በመምጣት ወይም ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ በመፈተግ ፅዳቱን ይጠብቃል፡፡ይህ የተለመደና ለከተማዋ እንደባህል የሚታይ እሴት ነው፡፡
በዘመኑ ኑዋሪው ለመጠጥም ሆነ ለምግብ ማብሰያ የሚጠቀሙበትን ውሀ የሚቀዳው ከዚሁ ያዶት ወንዝ ነበር፡፡ውሃው በአብዛኛው ሚመላለሰው በአህያ ጀርባ ነው፡ይሄንን በመስራት የሚታዳደሩ ከሀምሳ በላይ የሚሆኑ ግለሳቦች አሉ፡፡አህያው ላይ የእንጨት ኮርቻ ይጫንና፡፡ኮርቻው ላይ በአንደኛው ሁለት ባለ 25 ሊትር ጄርካን በሌለኛው ወገን እንደዛው ሁለት ጀሪካን በአንዴ አራት ጄሪካን ወይም 100ሊትር ጭኖ ከወንዙ አንድና ሁለት ኪሎ ሜትር በማጓጓዝ ይሸጣል፡፡ለመጠጥ የሚሆን ውሀ የሚቀዳው ግን ገና ሰማይና ምድር እንደተላቀቀ ከ12 ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ባለው ጊዜ  ነው፡፡የዚህ ምክንያት ያዶት ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ተራራዎችን ሰንጥቆ ፤ጫካውን አቋርጦ ስለሚመጣ የሰውና የአውሬዎች ንክኪ ሳይበዛበትና ሳይደፈርስ  የጠራ ውሀ ለማግኘት ነው፡፡
እና በጊዜው  በዚህ ልምድ መሰረት  ለቤቱ የመጠጥ ውሃ መቅዳት እና በለሊት ተነስቶ ወደ ያዶት በሮ በመሄድ የጠራ ውሀ ቀድቶ ቁርሰ ቀማምሶ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የበሻዱ የዘወትር ተግባሯ ነበር፡፡ይሄኛው የበሬዱ ልምድ ከእድሜ ልክ ፍቅረኛዋ ከሆነው ተአምረኛው ፍጡር ጋር የሚያቆራኘው ቀጥተኛ ነገር አለ፡፡
በሬዱ እንደወትሮዋ ከእንቅልፏ ባና ጃሪካኗን አንጠልጥላ ለመያዝ የምትጠቀምበትን ጨርቅ በትከሻዋ ጣል አድርጋለች የቤቱን በራፍ ከፋታ የግቢያቸውን የቆርቆሮ አጥር አልፋ ቁልቁል ወደ ያዶት ወንዝ እየነጎደች ነው፡፡..ግን ከቤቷ ብዙ ከራቀችና ከተማውን ለቃ ወጥታ በወንዙና በከተማው መካከል ያለውን ባዶና  ወጣ  ገባ ስፋራ ከደረሰች በኃላ ነበር የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር እንዳለ  ያስተዋለችው፡፡ከወትሮዋ ፈጠን ብላለች፡፡አዎ ገና ለሊት ነበር፡፡
የተወሰነ ፍራቻ ቢሰማትም ወደ ኋላዋ አልተመለሰችም፡፡ የባህርዛፍ ደን ያለበትን መንገድ ሰንጥቃ ስታልፍም ከነፍራቻዋ ነች፡፡ወደ ኋላዋም ሆነ ወደ ፊት ለፊቷ እየተሸከረከረች ብትገላመጥ ምንም የሚታይ የሰው ዘር  አላየችም፡፡በደን ወደተሸፈነው የወንዙ ዳርቻ ስትደርስ ጉሬዛዎች ከዛፍ ወደዛፍ እየተንጠላጠሉ ሲዘሉ እያየች ቢሆኑም እርምጃዋን አልገታችም፡፡የያዶት ወንዝ ሿሿሿሿ…  ብሎ ሲፈስ ከሩቅ ይሰማታል፡፡ደረስችና ቀሚሷን በመጠኑ ሰብስባ ወደወንዙ አንድ ሜትር ያህል ገባ በማለት ጄሪካኑን መሙላት ጀመረች፡፡

ግማሽ እንደደረሰች ከወንዙ መሀል የሆነ የሚንቦጫረቅ ድምጽ ሰማችና አውሬ መስሏት ጄሪካኗን ጥላ በርግጋ ከወንዙ በመውጣት እራቅ ብላ መመልከት ጀመረች፡፡እሷ ጥላ የወጣችውን ጄሪካን በውሀው ግፊት ወደ መሀል ተምዘግዝጎ አውሬ ወደመሰላት አካል ሲጓዝ ተመለከተች፡፡ ደግነቱ ሰማሁት ያለችው ድምጽ የአውሬ ሳይሆን የሰው ነበር፡፡መጀመሪያ ዕርቃኗን የምትዋኝ ሴት መስሏት ነበር..፡፡
አስተውላና ተረጋግታ ሳታየው ግን ቀይ ጥቅልል ጥቁር ፀጉር ያለውና በውሀው ለስልሶ ግንባሩ ላይ ድፍት ያለበት የሆነ የአማልክት አይነት መልክ ያለው ወጣት የእሷን ጄርካን ይዞ በፍራቻዋ እየሳቀባት  ተመለከተችው፡፡

‹‹ይህን ያህል ፈሪ ከሆንሽ በዚህ ሰዓት እንዴት እዚህ ቦታ ተገኘሽ?››ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅ አውጥቶ አናገራት፡፡ድምጹ በጆሮዋ እየተንቆረቆረ ወደ ውስጧ ሰርጎ ሲገባ የሆነ በመንፈስ የመሞላት አይነት ግራ አጋቢ ስሜት ተሰማት፡፡
‹‹የነጋ መስሎኝ ነዋ፤አንተስ በዚህ ለሊት እዚህ ቦታ ለዛውም ወንዙ ውስጥ ምን ትሰራለህ?››ስትል መልሳ የራሷን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔማ አንቺ እንደምትመጪ አውቄ እየጠበቅኩሽ ነው››

‹‹የት አውቀህ ነው የምትጠብቀኝ?››

ከወንዙ መሀል እሷ ባለችበት አቅጣጫ ወደ ዳር ቀረብ እያለ‹‹እርግጥ አላውቅሽም፤ ግን ውሀ ልትቀጂ በለሊት ስትመጪ ሁሌ አይሻለሁ››አላት፡፡

‹‹አንተ ሁል ጊዜ  ለሊት እዚህ ምን ትሰራለህ?››

‹‹እቤቴ እዚሁ ቅርብ ነው፡፡በዚህ ሰዓት መዋኘት ያስደስተኛል፤ከያዶት ጋር በሹክሹክታ ምስጢር የምናወራው በዚህ ሰዓት ነው፡፡እያንዳንዱን አዲስ ቀን በደስታ የምቀበለው እዚሁ ሆኜ ነው፡፡››

‹‹በል እሺ ጄሪካኔን ስጠኝና ዉሀዬን ልቅዳ፡፡›› አለችው፡፡ ከማታውቀው ሰው ጋር በአጉል ሰዓት አጉል ቦታ ሆና አጉል አይነት ወሬ ከዚህ በላይ ማውራት አስፈሪ ቢሆንባትም ጄሪካኑን ግን የእውነት እንዳለችው እንዲመልስላት አልፈለገችም ነበር፡፡ 

..‹‹ልቅዳልሻ…እስከዛ አንቺ አውሪኝ፡፡››ብሎ ጄርካኑን በሁለት እጇቹ ወደታችኛው የውሀው ጥልቃት ደፍቆ… ዷዷዷ በሚል ድምጽ በመታጀብ መሙላት ጀመረ፡፡

ለስለስ ባለ ሰርሰሪ ድምፅ ‹‹አውሪኛ …እስክሞላልሽ›› በማለት በድጋሚ ጠየቃት፡፡
ግራ በመጋባት

‹‹ምን ላውራህ?››ስትል መለሰችለት፡

‹‹አሁን ብጠልፍሽስ?››

‹‹ጠልፈህ ምን ታደርገኛለህ?››

‹‹በሀገራችሁ ተጠልፎ ምንድነው የሚደረገው.? አገባሻለኋ፡፡››

‹‹ሆሆይ…ጠልፎ ማግባት እንዲህ ቀልድ ሆነ እንዴ?አረ ቶሎ ሙላና ስጠኝ ልሂድበት፡፡››

‹‹ቀስ በያ ቆንጆ ስለሆንሽ እኮ ነው ልጥለፍሽ ያልኩሽ፡፡››

ምን አይነት መልስ መመለስ እንዳለባት ግራ ተጋባች ‹‹..ለመሆኑ እቤቴ ቅርብ ነው ምትለኝ እዚህ ቅርብ ከጫካ እና ከጅብ ጉድጎድ በስተቀር ምን ቤት አለ.?››ሲከነክናት የቆየውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹እውነቴን ነው፡፡የእኔ ቤት እዚሁ ቅርብ ነው፤ግን  በአይን አይታይም፡፡ፀባይ ከላሽ አንድ ቀን ወስድሻለሁ››

‹‹ኸረ ይቅርብኝ››ብላ ከወንዙ አውጥቶ ያቀበላትን ጃሬካን በያዘችው ጨርቅ በጀርባዋ አዝላ ለመሄድ ዝግጁ ሆነች፡፡እንግዳው ሰው ግማሽ አካሉን ወንዝ ውስጥ ግማሽ እርቃን አካሉን ደግም ለእይታ አጋልጦ ለእሷ እያስጎበኘት በአይኖቹ ሸኛት እሷም እየተገላመጠች ወደ ፊት በመንደርደር አመለጥኩ በሚል እፎይታ ግን ደግሞ ትንሽ ብቆይስ? በሚል ግራ አጋቢ ቁጭት ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡

ይቀጥላል
👍17427🥰5🤩5👏2
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ደሎ  ከተማ በአረና ጥቅጥቅ ደን የተሸፈነች በደቡብ ኦሮሚያ ባሌ ዞን ውስጥ የምትገኝ የወረዳ ከተማ ስትሆን ለሁለት የተከፈለችው ያዶት በሚባል ግዙፍ ወንዝ ነው፡፡ያዶት ወንዝ ለከታማዋ ኑዋሪ ህይወት ነው፣ውበት ነው፣የአይን ማረፊያቸው እና ትምክህታቸው ነው፣ከውጥረታቸው መተንፈሻ ነው፣የሚኮሩበት መዝናኛቸው የሚደምቁበት ጌጣቸው ነው፡፡…»
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///



እቤት ስትደርስ ሰዓቱ ገና ለአስራ ሁለት ሰዓት እሩብ ጉዳይ ነበር‹‹ሁለተኛ ሰዓት ሳላይ እና መንጋቱን ሳላረጋግጥ ንቅንቅ አልልም ..ቅዱስ ሚካኤል ነው ከመአት ያወጣኝ ፡፡››ብላ ስህተቷን ዳግመኛ ለለመድገም  ለራሷ ቃል ገባች፡፡ግን ደግሞ ያለማቋረጥ ስለእሱ ከማሰብ እራሷን ማቀብ አልቻለችም‹‹ይሄ ሰው የሆነ ነገር አድረጎኝ ቢሆንስ ?››ስትል አሰበችና በፍርሀት ራደች፡፡ደግሞ የደሎ መና ኑዋሪ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ምክንያቱም ከተማዋ በሁለት ቀበሌ ብቻ የተዋቀረች በመሆኗ  ኑዋሪዎቹ ቢያንስ በመልክ እርስ በርሱ ይተዋወቃሉ፡፡ ያንን ወንዝ ውስጥ በግማሽ እርቃን ሆኖ ያየችውን ሰው ግን ከዚህ በፊት የትም ቦታ አይታው እንደማታውቅ እርግጠኛ ነች፡፡ የደሎ ህዝብ እርስ በርስ ከመተዋወቁ የተነሳ ለምሳሌ የጉልት ነጋዴዎች በመደዳ አስር ሆነው ቢቀመጡ ምሳ ሰዓት ሲሆን አንዱ ይቀርና ዘጠኙ ምሳ ለመብላት ወደየቤታቸው ይሄዳሉ፡፡አንዱ የሁሉንም ደንበኛ   በታማኝነት ያስተናግዳል፤በታታሪነት ይሸጣል፤ የተቀበለውን ገንዘብ በተገቢው ቦታ ያስቀምጣል፡፡
ቀኑ ተገባዶ መሽቶ ወደ መኝታዋ ስትሄድ እንኳን  ሀሳቧ ያዶት ወንዝ ላይ  እንደተጣበቀ ነበር …ጀርባዋን የጥጥ ፍራሽ ላይ አሳርፋ በተለመደው ሰዓት ብትተኛም እንቅልፏ ሁሉ የተቆራረጠ ..ለሊቱ የረዘመና የተንቀራፈፈ ሆነባት፡፡ክፋቱ ደግሞ አያቷ በኢጣሊያንን ወረራ ለመፋለም አድዋ ዘምተው በድል ሲመለሱ ከጠላት ማርከው ለግላቸው ካስቀሩት አንዱ ብርቅዬ  የእጅ ሰዓት ነበር…ይህ ሰዓት ማሰሪያው ቢበላሽም ዋና ሰዓት ቆጣሪው ግን በትክክል ያለዝንፈት ይሰራል፡፡ይህን የዘመኑ ተአምራዊ ዕቃ አያትዬው ከሞቱ በኋላም ቤተሰቡ ግድግዳ ላይ አንጠልጥለው ይጠቀሙበታል…በሬዱም ማታ ሰዓቱን ከወላጆቾ ክፍል ወደራሷ ክፍል በማዘዋወር ከራስጌዋ ሰቅላው ስለነበር በየሆነ የጊዜ ክፍት አየተነሳች ሰዓቱን ትመለከት ነበር፡፡በወቅቱ ሰዓት ሚባል ተአምራዊ ማሽን በከተማዋ ብርቅ ነበር፡፡ምን አልባትም ይህ ሰዓት በግለሰብ ደረጃ በከተማውም ያለው ብቸኛው ቅርስ  ሳይሆን አይቀርም፡፡ያው በወቅቱ ማህበረሰቡ የጊዜ ልኬትን በተወሳሰበ ማሽን ሳይሆን ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ የሰዓት አቆጣጠር ጥበብ ነበር በራስ መንገድ በመስፈር የሚገለገለው፡፡
በሬዱ ግን ዕድሜ ለጀግናው አያቴ እያለች በመሀል ከእንቅልፏ ተነስታ ሰዓቷን ታያለች…ገና 8፡20….መልሳ ለመተኛት ትሞክራለች..ብዙ ከመሰላት ቆይታ በኃላ ሰመመን ከመሰለ እንቅልፏ ትባንንና ብድግ ብላ ፋኖሷን ለኩሳ ሰዓቷን ታያለች 9፡35…‹‹ሰዓቱ ተሳስቶ ይሆን እንዴ?›› የሚል ስጋት በውስጧ ይሰነቀርና በቤታቸው ሽንቁር አጮልቃ ውጩን ትመለከታለች፡፡ ግማሿ ጨረቃ ሰማዮ አናት ላይ በስሱ ስትጓዝ ፤ ከዋክብቶች ደግሞ ሰፊው ሰማይ ላይ ተበትነው ሲደንሱ ታያለች… ወደምድር ስታይ ሁሉ ነገር ጨለማና በፀጥታ የታጠረ ይሆንባታል…ሰዓቱ እንዳልተበላሸ ውስጧን ታሳምንና መልሳ ትተኛለች..
ቆይታ ቆይታ ስትነቃ ምንም የተቀየረ ነገር አይኖረም….ከቤታቸው በአቅራቢ ካለው መስኪድ የመጀመሪያ አዛን  ትሰማለች…በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የዶሮ ማራኪ ድምፅ እና የወፎች ጥዑም ዝማሬ ይናፍቃታል….ግን ምንም የሚሰማ ነገር የለም…መልሳ ለመተኛት ትሞክራለች‹‹ሰውዬው ምን አይነት አዚም ነው ያስነካኝ?›በራሷ ጥያቄ ውስጧ ራዳ..…ተኝታ ተኝታ ስትባንን የወፎች ብስራት ዜማ ሰማች… በርግጋ ከመኝታዋ ወረደችና ሰዓቷን ተመለከተች 11፡40 ይላል.. ከዛ በላይ ታግሳ መጠበቅ አልፈለገችም..ቀስ ብላ ተነሳችና ቤተሰቦቾን እንዳትቀሰቅስ እየሰጋች ሹክክ ብላ   ጄሪካኗንና ማዘያ ጨርቋን  ይዛ በቀስታ በራፉን ከፍታ ወጣች…

.ያስፈራል፤ከጭለማው ጋር አይኗን እስክታለማምድ ደቂቃዎች ወስደውባት ነበር….በጭራሮ ታጥሮ በጭራሮ በር የተዘጋውን የጊቢያችውን  አጥር መሸንጎሪያ አውጥታ ከፈተችና ወጣች… ግን መቀጠል አልቻለችም… ልቧ ለሁለት ተከፈለ..‹‹ሂጂ ችግር የለውም፡፡››እሯሷን ለማበረታታት ሞከረች፡፡
‹‹..አረ ተይ ሰው አግኝቶ ባይተናኮልሽ እንኳን አውሬስ ቢዘነጥልሽስ…?›ሌላ የፍራቻ ስብከት ከውስጧ በመመንጨት ይረብሻት ጀመር፡፡ ከግቢያችው መሀል ተጋድሞ የነበረው መቻል በጩኸት ያንቧርቀው ጀመር…አንድ ሀሳብ መጣላት፤ተመልሳ ወደ ጊቢ ገባችና ወደ እሱ ሄደች፡፡ቀስ ብላ በሹክሹክታ ልክ እንደልብ አውቃ ጎዳኛ መጮሁን ተወና እግሯ ስር ሽብልል ብሎ ተኛ፡፡
.‹‹አብረን እንሂድ ተነሳ…››አለችውና መንገዷን ይዛ ወደ መውጫው እርምጃዋን  ቀጠለች ..ተከተላት..::
አዎ አሁን ቀለል አላት‹‹…ቢያንስ ካንተ ጋር መሄድ ይሻላል……››ብላ ውሻዋን አስከትላ ጉዞዋን ቀጠለች...ወንዙ ጋር ስትደርስ ገና ጭለማው እንደመግፈፍ እያለ   ነበር፡፡መቻል ከኃላ ከኃላዋ ኩስ ኩስ እያለ ነው፡፡በዛፎቹ ላይ ያሉት ወፎች የለሊት ዝማሬያቸውን ያሰማሉ..እንደደረስች ጄሪካኗን አንከርፍፋ ለአስር የሚሆን ደቂቃ ፈዛ ወዲህና ወዲያ አይኖቾን በማንከራተት የሆነ ነገር ትፈልግ ነበር..፡፡

‹‹እንዴ ምንድነው የምፈልገው….?ጄሪካኑን ይዤያለሁ… የወንዙም ውሀ በእግሬ ላይ እያለፈ ወደ ፊት እየተመመ ነው..እና ለምን ጎንበስ ብዬ  አልቀዳም ..?ለምን በብርድ እንዘፈዘፋለሁ….?›› እያለች ከራሷ ጋር ሙግት በገጠመችበት ቅፅበት ውሻዋ ማንቧረቅ ጀመረ….. ግረ ገብቷት አይኖቾን ስታቁለጨልጭ ከወንዙ መሀል ብልቅ ብሎ ወጣ…፡፡
‹‹የፈጣሪ ያለህ.!!›› ጩኸቷን ለቀቀችው...ደግነቱ  የእሷ ጩኸት ከመቻል ጩኸት ስለማይበልጥ ተውጦ ቀረ…፡፡

"ዛሬም ደነገጥሽ?››
‹‹ምን አይነት ሰው ነህ…..?ቤትህ  ወንዙ ውስጥ ነው እንዴ?››በመገረም ጠየቀችው፡፡
ፈገግታ የተርከፈከፈበትን አንፀባራቂ ፊቱን ወደእሷ አቅጣጫ አዙሮ‹‹አዎ …ከፈለግሽ ነይ ልብስሽን አውልቂና ግቢ ….በዛውም ቤቴን አሳይሻለሁ››አላት፡፡

‹‹ቤትህን ባየው ደስ ይለኝ ነበር… ግን ዋና  አልችልም››አለችውና ለቀልድ ምላሽ ሰጠች፡፡
‹‹የደሎ ልጅ ሆነሽማ ዋና አልችልም ብትይ አላምንም…ደሎዎች እንኳን ሰዎቹ እንስሳቱም ዋናተኛ ናቸው፡፡››

‹‹ቢሆንም ይቅርብኝ ..ባይሆን ሌላ ጊዜ›› እለችና ጎንበስ ብላ ጄሪካኗን ወደ ውኃ ውስጥ ከተተቸው…መቻልም ድምፅን አጥፍቶ በሜትሮች ርቀት መሬት ላይ ለጥ ብሎ ሁለቱንም እየታዘበ ነው፡፡
‹‹እንግዲያው ቀረብሽ ››ብሎ መልሶ ወደ ውሀ ውስጥ እራሱን ደፈቀና ሙሉ በሙሉ በመስመጥ እራሱን ከእይታ ሰወረ…የሆነ ነገሯን ይዞ የሄደ ነው የመሰላት…፡፡
እንዳላት ልብሷን አወላልቃ ወንዙ ውስጥ መግባት እና አብራው መዋኘት በጣም አሰኝቷት ነበር..ግን ፈርታ ነው እምቢ ያለችው፤በዚህ ሰዓት እርቃኗን ወንዝ ውስጥ ከማታውቀው ሰው ጋር…‹‹ግን ምን ችግር አለው…?ባደረግኩት ኖሮ››ስትል ቁጭት ውስጥ ገባች…አንድን ነገር እኩል መፈለግ እና እኩል አለመፈለግ እንዴት ነው የሚቻለው፡፡በዚህ ደቂቃ በእሷ ላይ እየታየ ያለው ስሜት እንደዛ አይነት ነው...በሁለት ጫፍ ወደግራና ቀኝ በእኩል ኃይል መወጣጠር፡
👍1175😁4
ከአሁን አሁን ከሰመጠበት ይወጣል ብላ  ስትጠብቀው ምንም አይነት ምልክት ሳይታይ…ውሀ ውስጥ የደፈቀችው ጄሪካን ሞላ..፡፡ጎትታ ከወንዙ ውስጥ አወጣችውና ዳር ላይ አስቀመጠችው….ጄሪካኗን ተሸክማ ጉዞዋን መቀጠል ነበረባት …ግን እግሯ ሊንቀሳቀስላት አልቻለም...ምትሆነው ግራ ገባት .መጮኸ አማራት…ከነልብሷ ዘላ ወንዝ ውስጥ ለመግትም ፈለገች…ግራ በመጋባት ልቧ እየዋለለ ሳለ ልጅ ብልቅ ብሎ ወጣ….ሳይታወቃት‹‹ተመስገን›› አለች፡፡

ይቀጥላል
👍123😁142👏1
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// እቤት ስትደርስ ሰዓቱ ገና ለአስራ ሁለት ሰዓት እሩብ ጉዳይ ነበር‹‹ሁለተኛ ሰዓት ሳላይ እና መንጋቱን ሳላረጋግጥ ንቅንቅ አልልም ..ቅዱስ ሚካኤል ነው ከመአት ያወጣኝ ፡፡››ብላ ስህተቷን ዳግመኛ ለለመድገም  ለራሷ ቃል ገባች፡፡ግን ደግሞ ያለማቋረጥ ስለእሱ ከማሰብ እራሷን ማቀብ አልቻለችም‹‹ይሄ ሰው የሆነ ነገር አድረጎኝ…»
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሶስት
፡፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

አይኑን አይታ በመጠኑ ከተረጋጋች በኃላ‹‹ቻው በቃ.. ልሂድ››አለችው፡፡

‹‹አረ ትንሽ ቆይ..እስቲ ስምሽን ንገሪኝ?››

‹‹ምን ያደርግልሀል?››

‹‹ያው የቆንጆ ልጅን ስም ማወቅ ያጓጓል ..ለዛ ነው፡፡››

በንግሩ አፈረችና አቀረቀረች፡፡በጀርባው ተንጋሎ በመዋኘት ወደ እሷ እየተጠጋ…እንደመለመንም እንደማሳዘንም በሚመስል የድምፅ ቅላፄ..፡፡‹‹ንገሪኛ ፡፡››አለት..

‹‹በሬዱ››መለሰችለት፡፡

‹‹አንቺ ቆንጆ ስምሽም ቆንጆ አሪፍ ነው፡፡››አላት፡፡

ፈራ ተባ እየለች ‹‹ያንተስ..?››ጠየቀችው፡፡

‹‹የእኔን ሌላ ቀን ከእነ ትርጉሙ አነግርሻለሁ፡፡››

‹‹እንዴ ሌላ ቀን እንጋናኛለን እንዴ?››በድንጋጤ ጠየቀችው፡፡ጥያቄዋ  ማረጋጋጫ እንዲሰጣት  የመፈለግ አይነት ነው፡፡

የልብ አውቃ ነው‹‹እንዴ !!!ትቀልጂያለሽ እንዴ ..?እኔ እና አንቺ ገና ብዙ ጊዜ ይኖረናል …ብዙ ታሪክ እንጽፋለን፡፡››ሲል ፍርጥም ብሎ መለሰላት፡፡

‹‹የምን ጊዜ…?የምን ታሪክ..?››

‹‹የፍቅር ታሪክ ፡፡››

‹‹የፍቅር ….?ምን አይነት

አይን-አውጣነት ነው…አረ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር አላውቅም፡፡››አለችው፡፡

‹‹እንደማታውቂ አውቃለሁ…. እኔም እንዳንቺው አላውቅም ….ግን አብረን እንማረዋለን፡፡››ብሎ ይበልጥ አሳፈራት፡፡

‹‹በል ይበቃሀል አሁን ልሂድ..ብላ የግዷን ጄሪካኗን አንጠልጥላ ተሸከመችና ፊቷን አዞረች፡፡

‹‹በይ ደህና ዋይልኝ..ነገ በዚህን ሰዓት እጠብቅሻለሁ፡፡››

መራመዷን ሳታቋርጥ‹‹አታስበው…..ግን የእውነት እቤትህ እዚሁ ሳይሆን አይቀርም ?›› አለችው ፡፡

‹‹አሳይሻለው ብዬሽ የለ..? አሳይሻለው፡፡››መቶ ሜትር ያህል ከራቀች በኃላ ዞር ብላ አየችው.. ደብዛው የለም‹‹…መልሶ ሰምጦ ይሆን..?ይሄ አፍዛዝ ውበት ያለው ልጅ ሰይጣን ሳይሆን አይቀርም..?የወንዝ ሰይጣን…ግን እንዲህ አይነት ጠንበለል ሰይጣን ካለማ ይገርማል?››ስትል አብሰለሰለች፡፡
ቤተ-ክርስቲያን ግድግዳ ላይ የተለጠፈው ስዕል በቅዱስ ሚካኤል እግር ተጨፍልቆ የሚታየውን አስፈሪው ሰይጣን በምናቧ መጣባትና..ከዚህኛው ጋር አስተያይታ በራሷ አፈረች..‹‹..በስመአብ ይቅር ይበለኝ…››አለች፡፡
///

በተረጋገጠ ሁኔታ ከዛ የወንዝ ዓሳ ፍቅር ያዛት፡፡በቃ ህሊናዋን ማዘዝ፤እርሷን መቆጣጠር እስኪሳናት ድረስ አደጋ ላይ ወደቀች፡፡ የሚገርመው ደግሞ ይሄ የሆነው ከስድስት ወር ግንኙነት በኃላ አይደለም…ሶስት ወርም አይሞላውም….በአንድ ሳምንት ውስጥ ነው ስሜቷ ተርገብግቦ እዚያ ደረጃ ላይ የደረሰው፡፡
ሁኔታዋን እራሷ በራሷ ስትታዘበው የዓይኖቾ ቅንድቦች መገለጥ እሱን ለማየት ባለት ፍላጎት የሚታዘዙ፣የከንፈሯ መሸልቀቅ እና የጥርሶቾ መላቀቅ ለእሱ ንግግር መመሰጧን ለማብሰር የሚውሉ ምልክቶች እንደሆኑ፣የእግሮቾ መንቀሳቀስ እሱ ወዳለበት ለመሄዱ ባላት ፍላጎት  የሚሰሩ እየመሰላት  ከመጣ ቀናቶች አልፈዋል…፡፡አዕምሮዋንማ  በቃ  ሙሉ በሙሉ በምርኮ ተቆጣጥሮታል፤ከእሱ መልክ በስተቀር ሌላ ምንም ምስል የልተለጠፈባቸው  ኦና ሆኖባታል….፡፡

ከተገናኙ በሰባተኛ ቀናቸው  ነው፡፡ሰሞኑን ታደርግ እንደነበው የውሀ መቅጃ ጄሪካኗን ተሸክማ ከለሊቱ  11፡30 አካባቢ ሲሆን ያዶት ወንዝ ደርሳ ወንዙ ጠርዝ በመቆም ከላይ ከጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ እያፏጨና እየተስገመገመ የሚመጣው የውሀው ማዕበል እግሯን እያቀዘቀዘላት  ደንዝዛ ቆማለች፤አይኖቾ ወንዙ ውስጥ ተተክሏል …ፈዛለች….ቡልቅ ብሎ ከወንዙ የሚወጣውን  የፍቅር ዓሳዋን ጥበቃ ፡፡ ሊታክታት ትንሽ ነው የቀራት…..‹‹ግን ጥበቃ እንዴት ይሰለቻል…? በተለይ  ከገነት ወንዝ የተቀዳ የፍቅር ጠበል ይዞ የሚመጣን የልብ ጀግናን መጠበቅ ሲሆን ይከብዳል፡፡››አለች…
ግን ደግሞ አሁንም ጥበቃዋን  ቀጥላለች…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ…. .በቆመችበት  እግሯን ደነዘዛት፤ባፈጠጠችበት አይኖቾን ቆጠቆጣት፤የያዘችውን  ጄሪካን እንኳን አላስቀመጠችም፤ አንከርፍፋ  እንደያዘችው ነበር….፡፡ ሌላ 10 ደቂቃ በጥበቃ ባከነ....ሰማዩ ፈገግ እያለ ለመንጋት እየተግደረደረ ነው…፡፡
‹‹ልጅ የለም...ምን ዋጠው……?.የታበቱ ሄደ?››አእምሮዋን ያጨናነቁባት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡በዚህ አይነት ሁኔታ 15 ደቂቃ ከጨመረች  ነግቶ ሰው መምጣት ይጀምራል…ሰው መምጣት ጀመረ ማለት ደግሞ እሱም የመምጣቱ ጉዳይ አከተመ ማለት ነው?እሱ ሰው እንዲያየው  እንደማይፈልግ በውስጧ ታምናለች፡፡ እንደውም አንዳንዴ መንግስት እጅ ላለመግባት በድብቅ ተሸሽጎ የሚኖር ሽፍታ ሁሉ ይመስላታል፡፡  ማስረጃው ደግሞ….ሰለእሱ አንድ የምታወቀው ነገር ቢኖር እሱን ማግኘት ከጀመረችበት  የአንድ ሳምንት ጊዜ  ውስጥ አንድም ቀን በደንብ እስኪነጋ እና ሰው ወደወንዙ መምጣት  እስኪጀምር  አብሯት ቆይቶ አለማወቁና ከወንዝ ውጭ በየትኛውም የከተማው ክልል አይታው አለማወቋ ነው፡፡
በደመነፍስ አንድ ውሳኔ ወስነች፡፡ጄሪካኗን በቁሟ ለቀቀችው፡፡ከድንጋይ ጋር ተጋጭቶ ጓ…ጓ..ጓ የሚል ድምጽ አሰማና  ቦታ ይዞ ተቀመጠ ፡፡ጄሪካኗን ለማዘያም ለብርድ መከላከያም ብላ  ተከናንባ  የነበረውን ፎጣ ከላዮ ላይ ገፈፈችና ስሯ ያለ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አንጠለጠለችው፡፡ከዛ ከፍ የሚል ድንጋይ ላይ ወጣች…ቀጥሎ ተወርውራ ወንዙ መሀከል ዳይቨ ሰመጠች……፡፡
ልክ እግሮቾ ድንጋዩን ለቀው በመስፈንጠር አየር ላይ እያለ ነበር ልብሷን ማውለቅ እንዳነበረበረባት ያስታወሰችው‹‹….ምን መሆኔ ነው …?ከነልብሴ መሆኔ አንደኛ እንደልብ ለመዋኘት አያመቸኝም …ሁለተኛ  እርጥብ ልብስ ለብሼ እየተንዘፈዘፍኩ ወደ ቤት ስመለስ ሰው በመንገድ ላይ ሲያገኘኝ ምን ይለኛል…? ቤተሰቦቼስ.…?የራሳቸው ጉዳይ …አሁን አንዴ ገብቼያለሁ…፡፡› በማለት እራሷን ለማፅናናት ሞከረች፡፡
ለአንድ ሁለት ደቂቃ ያህል  እየዋኘች ወደ ላይ ወደታች ተገለባበጠች..ከዛ ወደስር  ወደወንዙ ጥልቅ ሰመጠችና አፏን ዘግታ  ዓይኖቾን ከፍታ ማሰስ ጀመረች፤ግን አልተመቻትም ፡፡ወዲያው ወደ ላይኛው የውሀ ወለል ወጣችና ወደ ዳር ተጠጋች…..
ከወንዙ ሳትወጣ የለበሰችው  ቀሚስ ወደላይ ሞሽልቃ አወለቀችና  ዳር ላይ ከሚገኝ ድንጋይ ላይ በማስቀመጥ በፓንት ብቻ ወደ ውስጥ ተመልሳ በመስመጥ ውስጥ ለውስጥ እንደዓሳ ነበሪ  እየተሹለከለከች መዋኘቷን ቀጠለች፡፡በወንዙ የመሀከለኛ ወለል እየዋኘች ሳለ የሆነ ጠንካራና ፈርጣማ ክንድ ያለው ፍጥረት ከስሯ  በማታስበው  ፍጥነት እና ድንገተኝነት ሰቅስቆ ገብቶ በጀርባው አዝሏት ወደላይ የወንዙ ወለል ይዞት ሲወጣ እሪታዋን አቀለጠችው …

ይቀጥላል
👍19736😁8👏4👎1
#መቃብሬ_ላይ_ሚፃፍ

ጥብቅ ማሳሰብያ ሸክላን ለምትሰሩ
እዚህ መቃብር ላይ ዐፈር አትዘገኑ!!
ሲነድ ሲቃጠል ሲጨስ በመኖሩ፣
ሲቃጠል ለሚኖር፣
ለጀበና መስሪያ አይሆንም አፈሩ።

ኑረዲን ኢሳ
55😢21👍14👏4🔥1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አራት


///

የሚሰቀጥጥ የድንጋጤ ጩኸት…‹እስቲ ምን  መሆኔ ነው..…?ይሄ እንደሚከሰት እንዴት ቀድሜ ሳላስብ ……?ወንዙ ውስጥ ዘልዬ ስገባ እሱን ፍለጋ አይደለ እንዴ ….? እና ላገኘው እንደምችል  እና ሊያዝለኝ ወይም ሊያቅፈኝ እንደሚችል  እንዴት ሳልገምት…..…? ገምቼስ ከሆነ አሁን እንዲህ ለገዛ እራሴ እስኪሰቀጥጠኝ  ድረስ መጮኼ  ምን የሚሉት ቅብጠት ነው……? ››
ብላ እሯሷን በሯሷ ታዘበች፡፡ 

እንግዳው ሰው ግን ጩኸቷን  ከቁብ አልቆጠረም ..እንደዛው በጀርባው እንዳዘላት  ወንዙን መሀል  በቁመቱ በመሰንጠቅ ከነበሩበት ሁለት መቶ ሜትር ያህል  ርቀት  ይዞት ተሰፈነጠረ ….ከፍራቻ ይሁን ከፍቅር አታውቅም ጥምጥም አለችበት….ዞሮ ተመለሰና ልብሷ  ያለበት ቦታ ሲደርስ ወደዳር በመጠጋት  ድንጋዩን  በእጁ ይዞ እረፍት ወሰደ… ከዛው ከውሀ ውስጥ ሳይወጡ  እሷም አንገቱ ላይ ተንጠልጥላ  እንደተጣበቀችበት ማውራት ጀመሩ

‹‹ምን አይነት ሰይጣን ነህ….…?››

‹‹ቆንጆ ሰይጣን…?››መለሰላት፡፡

‹‹ሂድ ከዚህ …እንዴት እንዲህ ታስደነግጠኛለህ ?››የኩርፊያ በሚመስል የድምጽ ቅላፄ ገሰፀችው፡፡

‹‹ደነገጥሽ እንዴ የእኔ ፍቅር..…?ደግሞ እንዲህ ድንቅ የዋና ችሎታ እያለሽ ነው ሳምንት ሙሉ ስትግደረደሪ የነበረው…?››

‹‹መዋኛት አልችልም መች አልኩህ..…? አልፈልግም እንጂ ፡፡››

‹‹ ዛሬ ታዲያ  ምን ተገኘ…?››

‹‹ውሀ ልቀዳ ነዋ…››

መልሷን እንደሰማ ሳቁን ለቀቀው፡፡ ..ደነገጠች‹‹ ..ምን ተሳሳትኩ..…?››መለስ ብላ ከአንደበቷ የወጣውን ንግግር አሰበች…‹‹ውይ ምን አይነት ቀሺም ነኝ…?፡፡››አለች 

ጄሪካኗን እዛ ዳር ጥላ ልብሷን አውልቃ  ወንዙ መሀከል ገብታ  ውስጥ ለውስጥ እየተሹለከለከች  እየዋኘች  አግኝቷት  ዉሀ ልቀዳ ነው ብላ መመለሷ እንኳን ለእሱ ለእሷም አስቂኝ ነው፡፡

‹‹የቀረው መስሎሽ ደነግጠሽ  ነው አይደል….…?ከአንደበትሽ መስማት ደስ ስለሚለኝ ነው እንጂ እኮ ከፈለግኩ ከልብሽ ማንበብ እችላለሁ…ያው ስለማፈቅርሽ ልብሽን ሰርስሬ በመግባት ልሰልልሽ አልፈልግም….››

‹‹ምን ታስፈራራኛለህ…ከቻልክ አድርገው››ፎከረችበት፡

‹‹እንግዴያው ገባሁ… ወንዙ ውስጥ የገባሽው መዋኘት ፈልገሽ ሳይሆን ስለቀረሁብሽ ደንግጠሸ ነው… እኔን ፍለጋ ነው ሳታስቢበት በደመነፍስ   የገባሽው››

‹‹እንዴ ጥንቅር ብለህ ቅራ ….ምንድነው ሚያስደነግጠኝ…?›››

‹‹ብታምኚ ምን አለበት… እኔ እንደወደድኩሽ አንቺም ወደሺኛል…›› 

‹‹አሁን ወሬ አታብዛ..እንዴት አድርጌ ነው አንተን ልወድህ  የምችለው……?››

‹‹ምን ማለት ነው…?››

‹‹ሰው ሁን ሰይጣን እንኳን መለየት አልቻልኩም፡፡ወይ ምን ይታወቃል ብዙ ሰው ጨፍጭፈህ በወንጀል የምትፈለገ የመንግሰት ታዳኝ ልትሆንም ትችላለህ፡ አይ እንደዛ አይደለም ብለህ እራስህን መከላከል የምትፈልግ ከሆነ እስኪ   ከተማ ውስጥ አግኘኝና ልደነቅ…ወይንም  ደግሞ ቤትህ ውሰደኝ…››

‹‹እስኪ ምን ማለቴ ነው ለሳምንት የማውቀውን ሰው ከታማ አግኘኝ ምለው....?እሺ አግኝቶኝ ምን ያድርገኝ….…?እቤትህ ውሰደኝ ማለትስ… …?ይሄኛውማ  ባስ  ያለ ዕብደት  ነው›ሥትል በውስጧ
በእፍረትን በቁጭት ተብሰለሰለች፡

እሱ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹እንደዛ ካደረግኩ ብቻ ነው እዳማፈቀርሺኝ የምታምኚው…?››

‹‹ማምነው ሳይሆን..ምን አልባት ላፈቅርህ የምሞክረው››አለችው ..፡
እውነቱ ግን ከተማ ባያገኛትም ወይም  እቤቱ ፍቃደኛ ሆኗ ባይወስዳትም ..አንዴ በመጨራሻው አቅሟ አፍቅራዋለች…. ምንም ሚቀንስ ምንም ሚጨምር ነገር የለም….፡፡
እሱ ግን  አላሳፈራትም ..ውስጧን አንብቦ ይመስላል ‹‹እሺ ሰሞኑን እቤቴ ወስድሻለሁ...አሁን ግን አንቺን ማዘሉ ከበደኝ ….ውረጂልኝ››አላት…

በጣም ነው  የደነገጠችው፡፡.ለካ ይሄን ሁሉ የምትቀደው አጆቾን በአንገቱ ዙሬያ ጠምጥማ በጀርባው በኩል ከእርቃን ሰውነቱ ላይ እንደተጣበቀች ነበር…በርግጋ  እጆቾን ከአንገቱ  አላቀቀችና በጀርባዋ  ወደኃላ ወንዙ ላይ ተዘረረች….፡፡

‹‹ለዚህ እኮ ነው ምወድሽ…ፐ በተለይ እርቃንሽን ውብ ነሽ››ብሏት  ጭርሽ አሳፈራት፡፡

እዛው ወንዝ ውስጥ ጥላው  ወጣችና ጀሪካኑን ወደወንዙ መሀል ወረወረችለት…‹‹ወሬውን ተውና ልብሴን እስክለብስ ድረስ ሙላልኝ…››አለችው፡፡

‹‹ታዛዥ ነኝ የእኔ እመቤት ..››…..ብሎ ተስፈንጥሮ ጄሪካኑን ቀለበና ይቀዳላት ጀመረ ..እሷም ብስብስ ያለውን ቀሚሷን ካስቀመጠችበት ቦታ አነሳችና ለበሰችው፡፡

ተንዘፈዘፈች..፡፡በለሊት መዋኘት ውሀ ውስጥ ይሞቃል….ችግሩ ከወንዙ ውስጥ ሲወጡ ነው፡፡አየሩ ቀዝቃዛ ስለሆነ እንኳን እርጥብ ልብስ ደርበውበት ይቅርና ደረቅም ልብስ ቢለብሱበት መብረዱ አይቀርም ነበር….፡፡

ጄሪካኑን ሞልቶ ወደ ዳር አወጣላትና አቀበላት…ተቀበለችውና አንጠልጥላ ከፍ ያለ የግንድ ጉማጅ ላይ በማስቀመጥ  ዞራ  በጀርባዋ    በፎጣው  አዘለችና ስትጨርስ‹‹በል ቻው››አለችው
በቀዝቃዛው አየርና በረጠበቅ ልብሷ ምክንያት ሰውነቷ ሲንዘፈዘፍ ታዝቦፈኲ ‹‹ከቀሚስሽ ላይ ውሀው እኮ እየተንጠፈጠፈ ነው››አላት፡፡

‹‹ቅድም አንሸራቶኝ እኮ ወንዙ ውስጥ ከነ ልብሴ ገባሁ…...ለዛ እኮ ነው መግባቴ ካልቀረ ልዋኝ ብዬ የቀጠልኩበት..››አለችው  እፍረት እየተሰማት፡፡
‹‹ግን እኮ ተንሸራተሽ ሳይሆን ዘለሽ ስትገቢ ነው ያየሁት››ብሎት እርፍ
‹‹እና እንኳን ዘለልኳ…. በራሴ ቀሚስ ምን አገባህ?››

የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ ቢጤ ሆነችበት…እንደውሸታምና ቀልማዳ ሴት ሆና በእሱ መገመት አትፈልግም..እሱ ደግሞ ካለ ባህሪው ምንም አይነት ሽራፊ ውሸት ሰምቶ እንዳልሰማ አውቆ እንዳላወቀ ማለፍ አይሆንለትም፡፡

‹‹አትበሳጪ …ባይሆን ቀሚስሽን ላድረቅልሽ››

‹‹እንዴት አድርገህ ነው የምታደርቅልኝ…?  ››

‹‹እስኪ ጠጋ በይ››

‹‹ለምንድነው የምጠጋው..››

‹‹ግድ የለሽም እኔ ከወንዙ ከምወጣ አንቼ ጠጋ በይ››

‹‹…ምን ታማጣለህ?›› በሚል እልክ ተጠጋችለት ….እጁን ሰነዘረና ውሀ የሚንጠፈጠፍበትን የቀሚሷን ጠርዝ  ጨበጠው…. ማመን አልቻለችም ….ችስስስስስ በማለት እየተነነ  ፍም የሞላበት ጊርጊራ ውስጥ እጣን ሲጨመር የሚወጣ  አይነት ጭስ ለአንድ ደቂቃ ያህል  ከልብሷ  ተነነ  …. እናም  ኩርምት እስኪል ድረስ  ቀሚሷ ደረቀ ..አፏን በአድናቆት ከፍታ ምን እንደምትናገር ግራ ገብቷኝ እያለ ተስፈንጥሮ ውሀ ውስጥ ሰምጦ እንደወትሮው  ተሰወረባት…..


ይቀጥላል
👍171🥰2118
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

እለቱ እሁድ …ሰማይና ምድሩ ከመላቀቁ በፊት በሚባልበት  የለሊቱ የጊዜ ክፍል ላይ ነው፡፡ ኦርቶዶክሶቹ ቤተሰቦቾ ተነስተው  አምላካቸውን ለመማፀን ቅ/ሚካኤል  ቤተክርስቲያን ተያይዘው ግቢውን ለቀው እንደወጡ እሷም ተስፈንጥራ መኝታዋን ለቀቀችና እቤቱን በታናናሽ ወንድሞቾ ላይ ከውጭ መለስ አድርጋባቸው ግቢውን ለቃ  ቁልቁለቱን በመንደርደር እንቅፍት እያላተማት  ወደ ያዶት ሩጫዋን ቀጠለች..ይገርማል ጄሬካን እንዳልያዘች  እንኳን ትዝ ያላት  የወንዙን የለሊት ሿሿታ ድምጽ ለጆሮዋ ከደረሰ በኃላ ነበር፡፡

‹‹ወይ ጉዴ….ምን መሆኔ ነው …? እሱስ እንዴት ይታዘበኝ…?›ስትል በውስጧ እራሷን ታዘበች፡፡
እንደዛም ቢሆንም ግን እርምጃዋን አልጋታችም ….ቀጥታ ወደ ወንዙ አመራች…፡፡ በእለቱ  የተለየ መንቀዥቀዥ፤ የተለየ መቀበጥበጥ.፤የተለየ መቁላላት 🤭 እየታየባት  ነበር… ምክንያቱ ስታስብ ሀሳቡን ካልቀየረ በስተቀር  እቤቴ እወስድሻለሁ ስላላት ያ በውስጧ የፈጠረባ ጉጉተና ደስታ ይመስላታል… .‹‹.እስኪ እሱ ቤት መሄድ እንዴት ነው እንደዚህ ሊያጓጓኝ የቻለው..?›እራሷን ጠየቀች፡፡

ከዚህ በፊት ዘመድ ካልሆነ በስተቀር ወንድ ልጅ ቤት ሄዳ ጣዕሙን ቀምሳ  እንኳን አታውቅም…
.‹‹ወስዶ ሌላ ነገር ቢያደርገኝስ…?››.ሀሳቡን በማሰቧ እራሱ ሰውነቷ  ተንቀጠቀጠባት……ማድረግ ቢፈልግ ስንት ቀን ሙሉ በውድቅት ለሊት ማንም በሌለበት እየተመላለሰችለት አይደል…? እርቃን ገላዋን ከገላው አጣብቃ ስትዋኝ አልነበር እንዴ?እንደዛ ማድረግ ቢፈልግ ማን ይከለክለው ነበር….?እንደዚህ ማሰቧ አጽናናት ፤ እና ፈገግ አለች፡፡

‹‹ ..ፈገግታሽ ያምራል››አላት ወንዝ ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለ ..ለካ  ሳታስበው ደርሳ  ወንዙ ጠርዝ አካባቢ ቆማ ነበር በሀሳብ ስትባዝን የነበረው፡፡

‹‹ደህና አደርክ››አለችው  እንደመባነን ብላ

‹‹አዎ አድሬለሁ…ነይ ግቢ››አላት

‹‹ወዴት ነው የምገባው?››

‹‹ወደ ወንዙ ነዋ››

‹‹አልገባም …ቀጠሮ እኮ ነበረን ፤እረሳኸው እንዴ…?››

በሚያበሽቅ ና ተስፋ በሚያስቆርጥ የንግግር ቃና‹‹የምን ቀጠሮ?›› አላት ፡ 

ትንሿን ለንቦጯን ጥላ‹‹ተወው በቃ››አለችው፡፡ 

ፈገግ አለና‹‹..ኩሪፊያሽን እኮ በጣም ስለምወድልሽ ነው..እቤቴን ላሳይሽ አይደል ቀጠሯችን….?ነይ ግቢና አምስት ደቂቃ አብረን ዋኝተን እንሄዳለን..››

‹‹አምስት ደቂቃ ብቻ!!!››

‹‹አዎ.. አምስት ደቂቃ ብቻ››
‹‹..ተስማምታ  ቀሚሷን አወለቀችና ደረቅ ቦታ አጣጥፋ በማስቀመጥ በፓንት  ብቻ  ዘላ እጠገቡ ቦጭረቅ አለች››..….አንጠልጥሎ አቀፋትና ይዞት ወደ ውሀ ውስጥ ሰመጠ …ከእቅፉ ለመውጣት ተንፈራገጠች… አልቻለችም፡፡ ይዟት ውስጥ ለውስጥ እየዋኘ ነው፡፡ ሳታስበው ከንፈሩን ከንፈሯ ላይ አጣበቀው..የሆነ በቃላት ልትገልፀው  የማትችለው የኤሌክትሪክ ንዝረት አይነት ሞገድ ከጎረሰው ከንፈሯ ተነስቶ እላይ ጭንቅላቷ. ድረስ እንደገና ከዛው ከተጎረሰው ከንፈሯ  ተነስቶ ወደታች እግር ጥፍሯ  ድረስ በመሰራጨት አንዘፈዘፋት ….የምትዋኝ ሳይሆን የምትንሳፈፍ ነበር የመስላት… ለ5 ደቂቃ በእንደዛ አይነት ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ከዋኙ በኃላ የተደረመሰ ጉድጓድ  ያለው  የመሬት ስንጥቅ የወንዝ ወለል ላይ  በአይኗ  ገባ ….
‹‹አለየውም ይሆን ?››ብላ በማሰብ  ልታስጠነቅቀው ፈልጋ ለመናገር ከንፈሯን ለማለቃቀቅ ብትጥርም አልቻለችም …ይዟት እያመራ ያለው ወደዛው አቅጣጫ ነው….የሚያስፈራ አይነት ጉድጓድ ነው …እንደውም አስፈሪ የአውሬ አፍ ይመስላል…ዳሩ ምንም ማድረግ ሳትችል ይባስ ብሎ ከንፈሩን ከከንፈሯ ሰውነቱን ከሰውነቷ እንዳጣበቀ በስንጥቁ መሬት  አፉ ውስጥ    ገባና ወደጥልቁ. ይዞት  ጭልጥ አለ….

‹‹ወይኔ ልጅት …..ምን አይነት ተአምር ነው….?ምን አይነት ቀበጥ ልጅ ነኝ…?እንዴት ደፍሬ ነው ከዚህ ሰይጣን ጋር የተወዳጀሁት…?.መወዳጀቱንስ እሺ ልወዳጅ እንዴት የማያስብ አዕምሮ ቢኖረኝ ነው ቤትህን ካላሰየህኝ ብዬ ወጥሬ የያዝኩት…?›ስትል ግትልትል ጥያቄዎችን እራሷን ጠየቀች…መልስ መላሽ ግን አልነበረም .. ወደ ሲኦል ይዞት እየጠለቀ ያለ ነው የመሰላት…, ‹‹ግን ሲኦል የት ነው የሚገኘው››.…..? ከምድር በላይ ሰማይ ላይ ነው ወይስ ከምድር በታች ካለ ስምጥ ጨለማ ውስጥ….?አይ አሁን ይዞኝ እየሰመጠ ያለው ከምድር እንብርት ከሚገኝ ጨለማ ነው   ..››በፍራቻ ተቀፍድዳ ነፍሷ ጭምር እየቃተች ቢሆንም እዕምሮዋ ግን በሀሳብ ግትልትል ከመብሰልሰል እራሷን መግታት አልቻለችም፡፡ አዎ ምንም እየታያት አይደለም‹‹….ደግሞ አንደርስም እንዴ…?›አለች ፡፡

..በቃ ሲኦል ውስጥ መቼስ ያለው የሚንቀለቀል እቶን እሳት ነው…ነፍስ አባቷ ብዙ ጊዜ ሲናገሩ ሰምታለች…አይ እሳት ብቻም አይደለም ሰውነትን የሚበጣጥስ ቀዝቃዛ በረዶም አለ ብለዋታል…‹‹ግን እቶን እሳት እና ቀዝቃዛ ግግር በረዶ በአንድ የሲኦል ካምፕ ውስጥ እንዴት መገኘት ይችላሉ…?ሁለቱ እርስ በርሳቸው አይጠፋፉም እንዴ…?››ሀሳቧ ለራሷ አስገረማት.‹‹ የእኔ ነገር አሁን ስለዚህ የማስብበት ሁኔታ ላይ ነኝ…?›› ቤተሰቦቾን እሬሳዋን እንኳን ሳያገኙት ቀጥታ በጎሮ በር ወደሲኦል መሄዷ በጣም ልብ ሰባሪ ገጠመኝ ነው የሆነባት…?ከሀሳብ ቅርቃር ውስጥ ሳትወጣ  ከንፈሩን ከከንፈሯ  ድንገት ሲያነሳ የተለየ አዲስ አይነት ከልብ የመነጠቅ አይነት ስሜት ተሰማት ፡፡

…አዎ እግሮቾ ለስለስ የሚል ነገር ላይ ቆመዋል…እጆቹ ከሰውነቷ ተላቀቁ  .. ሰውነቱንም ከሰውነቷ አለያየው… ግን በጨለማ ደብዝዞ እና ጨፍና  የነበሩትን አይኖቾን መግለጥ ፈራች…‹‹.ሲኦል ደርሰናል ማለት ነው..?››ስትል ጠየቀች.. ግን የእሳቱም ወላፈን እያቃጠለት አይደለም.. የበረዶው ቅዝቃዜውም ለሰውነቷ እየተሰማት  አይደለም…በተቀራኒው   ከገነት የሚመነጭ አይነት   አየር በአፍንጫዋ እየሳበች  ነው::እንደዛ መሆኑ ደግሞ ጥሩ ነገር እንዲሰማት  እያደረገ ነው፡፡

‹‹ደርሰናል ግለጪ››የሚል ድምጽ ሰማች…

ይቀጥላል
👍165😱3720👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

‹‹ጎሽ ጥለኸኝ አልተሰወርክም…አጠገቤ አለህ ማለት ነው? ››ስትል የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰችና…በከፍተኛ ፍራቻ እና ጥርጣሬ ዓይኖቾን ገለጠች…..ወንዝ የሚባል ነገር ስራቸው  የለም…የሲኦል ምልክትም አይታያትም…. በሳር ፤ በትናንሽ አረንጓዴ ቁጥቆጦች እና የሚያማምሩ በቀለማት  በተሸቆጠቆጡ አበቦች የተሞላ ወብ ቦታ ነው…ግን ግራ አጋቢ ቦታ…፡፡
ከስር መሬት ከላይም መሬት ነው የሚታያት ..ግዙፍ ዋሻ መሰል  ነው እንዳትል ምኑም ዋሻ አይመስልም…የተለመደው አይነት ምድርና ሰማይ ነው የሚታየኝ ብላም እንዳትገምት በቆመችበት መሬት እና ወደላይ አንጋጣ  በምታየው መሬት(ሰማይ)  መካከል ያለው ልዩነት  የሚታወቀውን   ሰማይ  ከመሬት የሚርቀውን ያህል እርቆ አይደለም የሚገኘው…በግምት ከመቶ ሜትር አይበልጥም፣
‹‹ተገልብጠን ከምድር ስር ይሆን እንዴ ያለነው….?ማለቴ ምድርን ከታች ወደ ላይ የምናያት..ማለቴ አሁን ላለሁበት ሚስጥራዊ ቦታ ምድር ሰማይ  ትሆን እንዴ…?›ስትል በውስጧ ብትጠይቅም ለመግለጽ የፈለገችውን  ሀሳቡ ለእሷው ለራሷ ተምታታባት…

ትክክለኛ መልስ ለመግኘት ወደ እሱ ዞረችና ‹‹የት ነው ያለነው…..?›› ስትል ጠየቀችው

‹‹እቤቴ››አላት

አበባ.. ትንንሽ ቁጥቋጦች.. እዚህም እዛም የሚፈልቁ  ምንጮች… ለጥ ያለ ማለቂያው የማይታወቅ ሜዳ ነው የሚታያት‹‹ ….ይሄ ነው ቤትህ…..?››

‹‹አይ አይደለም….››አላት ፍርጥም ብሎ

‹‹….ቆይ ቆይ…›› እሰከአሁን በሁኔታው ተመስጣ ልብ ያላለችውን  ነገር አየች…., ልብስ ለብሶም ሆነ እንደዚህ ሙሉ እርቃኑን ፊት ለፊቷ ቆሞ አይታው አታውቅም ነበር….እስከዛሬ ግምሽ አካሉ በውሀ እንደተሸፈን ከእምብርቱ በላይ ነበር የምታየው….በጣም ተገረመች…የምታየው ፍጥረት  ሰው አይደለም….….?ሰው ካልሆነ ታዲያ ምንድነው ከተባለ መልሱ ለመግለፅ በጣም ይከብዳል…?፡፡ ምን ተብሎ እንደምትገለጽው እሷም ምንም አልገባትም  ..እንደዚህ አይነት ፍጡር እሷ አይታ አታውቅም…፡፡እግሮቹ  ጣት አልባ ናቸው… ልሙጥ እና እንደሰፌድ የተዘረጉ…ወይም የዓሳ ክንፍ የመሰሉ …..ብልቱ ደግሞ ምታህለው…ያልተገረዘች የሴት ቂንጥር በሏት… ወደ ፊት እንደባቄላ  ነው አጎንቁላ  የምትታየው…
ወይኔ ጉዴ››አለችና ሳቋ አመለጣት…ያሳቀት …?ስንት ቀን አሁን ቢደፍረኝስ .. ?እያለች የተጨነቀችው አጉል  መጨነቅ በምናቧ መጥቶባት ነው …‹‹አሁን በዚች እንኳን መድፈር ሽንቱንስ መሽናት ይችላል…?›› የሚል ሀሳብ አሰበችና ሳቋን አረዘመችው …
ሌላው በትክክል ሰው አይደለም ብላ ያሰበችው ዋናው ምክንያት  ባለጭራ መሆኑ ነው..ጭራ አለው፡፡ ጭራው ደግሞ ከኃላ ከመቀመጫው የላይኛው ክፍል በቅሎ ወደታች በመሄድ በእግሮቹ መካከል አልፎ ወደፊት ተቆልምሟል.‹‹.እንደውም ከእውነተኛው ብልቱ ይልቅ ጭራውን እንደብልትነት ቢጠቀምበት ያዋጣዋል›› ስትል በውስጧ  አሰበችና ድጋሚ  ፈገግ አለች፡፡

‹‹ስለእኔ ተፈጥሮ አስበሽ እና ተመራምረሽ ጨረሽ?››ብሎ አስበረገጋት
‹‹አይ ምን እመራመራለሁ….?እንዲሁ አዲስ  ነገር ሆኖብኝ ነው እንጂ..››በአፍረት መለሰችለት፡፡
‹‹ግን አልፈራሺኝም…››
‹ለምን እንዳልፈራውህ እኔንም ገርሞኛል…?››የእውነትም ለምን እንዳልተንቀጠቀጠች…?ለምን ፊቷን አዙራ ወደተንጣለለው ሜዳ ፈርጥጣ እንዳልሮጠች …?ለምን ያንን ጆሮ ሰንጣቂ የዘወትር ጩኸቷን እንዳላስነካችው ?ለእሷም አልገባትም…በቃ ከመደነቅና ከመገረም ውጭ በስሜቷ ላይ ያስከተለው የጥላቻውም ሆነ የፍራቻ ስሜት አልነበረም….
‹‹ስለዚህ ወደቤት መሄድ እንችላለን?›› አለና ጎንበስ ብሎ የቆመበትን አካባቢ መሬት በእጁ ሲነካ በአስገራሚ ፍጥነት አብረቅራቂ የወርቅ ሳጥን ከተሰነጠቀው መሬት ተፈልቅቆ  ወጣ…..
‹‹ፓንትሽን  አውልቂ››አላት
‹‹ለምን …? ምን አስበህ ነው…?››ስትል ግራ በተጋባ ስሜት ጠየቀችው፡
‹‹በዚህች ዕቃዬ ምን አስባለሁ?›› አላት እና አሳፈራት….እሷም ልትለው የፈለገችው  በዚህ ዕቃህ ምን ለማድረግ አስበህ  ነው…›ነበር..ያው ልቧን በትክክል ነው ያነበበው፡ 

‹‹እንደዚህ ሆነሽ ወደ እኔ ቤቴ መግባት አትችይም  …..ጨረር ይጎዳሻል››

መከራከሯን ትታ ፓንቷን አወለቅችና እጆቾን እፍረቷ ላይ አደራርባ ቆምች….በእጁ ካንጠለጠለው ሳጥን  የሆነ ሰማያዊ መልከ ያለው የጠፈርተኞችን የሚመስል ልብስ አወጣና  አለበሳት….ሙሉ በሙሉ በልብሱ ተጠቀለለች …ከዛ እጁን ወደ ፊት ሲዘረጋ  እስከአሁን እይታዋ ውስጥ ያልገባ ግን ከቆመችበት በአንድ ሜትር ርቀት የነበረ ወርቅማ የብረት በር ወለል ብሎ ተበረገደ……ከዛ እቤት ሳይሆን አይታ የማታውቀው በምናቧ እንኳን ገምታው የማታውቀው በተረት አለም ብቻ የሚገኝ አይነት ምትሀታዊ የዘመነ ፤ የፀዳ  እና ፀጥ ረጭ ያለ ከተማ ከፊታቸው ተነጠፈ…‹‹..እርግጠኛ ነኝ ይሄ ሁሉ እስከአሁን የሆነውና ያያሁት እውነት አይደለም….ህልም ላይ ነኝ ..ገና ከእንቅልፌም አልተነሳሁም›› በማለት እራሷን ለማፅናናትም ለማረጋጋትም ሞከረች….፡፡ግን አልተሳካላትም፡፡

…ምንም አይነት እሱን መሳይም ሆነ ሌላ ፍጡር ሳታይ ነው በወርቃማ ብርሀን ያሸበረቀውን ከተማ ሰንጥቀው እሱ ቤት የደረሱት፡፡ ይዞት የገባው አንድ  ከግድግዳው ሰማያዊው ብርሀን የሚተፋ  ቤት ውስጥ ነው ፡፡አራት ክፍል ቢኖሩትም ሁሉም  ባዶ ነበሩ..ምንም ዕቃ የላቸውም…

‹‹እንዴ…ይሄ ነው ቤትህ..?››

‹‹አዎ ምነው… ?

አልወደድሺውም…?››

‹‹አይ ቤቱማ አሪፍ ነው..ግን ባዶ እኮ ነው….ቤትን ቤት የሚያሰኘው ደግሞ ጣሪያና ግድግዳ ብቻ ሳይሆን ውስጡም የሚገኝ መጠቀሚያ ቁሳቁስ ነው….››

‹‹ባዶ…››አለና ወደውስጥ ገብቶ ግድግዳውን ተጠጋና ማብሪያ ማጥፊያ የሚመስል ነገር ተጫነ..
ተአምር ተፈጠረ…ድፍን ግድጋዳው እየተከፋፈተ ፍሪጅ …ቴሊቭዝን የመሳሰሉት ዕቃዎች… ወለሉም እየተከፈተ ጠረጵዛ ወንበር በመውጣት እቤቱን ሞሉት…. አደመቁት….. 

ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉን ነገር ችላ ብሎ‹‹አረፍ በይ …››አላት 

‹‹ምን ጉድ ነው….!!እስኪ መኝታ ቤትህን አሳየኝ..?››ሌላ ተአምር ለማየት ከመጓጓት የመነጨ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

መጣና እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ይዟት ሄደ …ወደ ቀጣዩ ክፍል….በተመሳሳይ ባዶ ነበር…
-‹‹የትኛውን ልጫን …››አለችው ግድግዳ ላይ ወደተለጠፉት ማብሪያ ማጥፊያ እጇን እየሰነዘረች
‹‹አልጋ ከፈለግሽ ነጩን ተጫኚ..››

ተጫነችው፡፡

ከእምነበረድ ይሁን ከእንጨት ይሰራ ለጊዜው መለየት ያቃታትን   ነጭ አንሶላ ….ነጭ አልጋልብስ የለበሰ አልጋ ከወለሉ ውስጥ ተአምራዊ በሆነ ክስተት በመውጣት  ተዘረጋ…..

‹‹ወይ እዚህ ላይስ መተኛት እፈልጋለሁ..››

‹‹ታዲያ ተኚያ …ማን ከለከለሽ››

‹‹ግን ይሄንን የለበስኩትን ደባሪ ልብስ ማውለቅ እችላለሁ?››

‹‹ቆይ… ››ብሎ ወደሳሎን ሄደ…. ምን እንዳደረገ ባታውቅም ወዲያው ሰማያዊው የነበረው የቤቱ መብራት  ወደ ብርማ አይነት ተለወጠ…እሱ ተመልሶ እሷ ወዳለችበት መጣ

‹‹አሁን ትችያለሽ አውልቂው››አላት፡፡ 
‹‹ወይ እንዴት ደባሪ መሰለህ ››አለችና ለማውለቅ ብትሞክርም  የተቆላለፉትን ነገሮች እንዴት ልትፈታታቸው እንደምችል አልገባትም... ምታደርገው ግራ ገባት

‹‹አቦ ምን ቆመህ ታየኛለህ ? ናና ከእዚህ  ወጥመድ ውስጥ አውጣኝ እንጂ››ቁጣ የተቀላቀለበት ልመና አሰማች፡፡
👍11913🤔5👎2👏2😢1
‹‹ፀባይ ይኑርሻ..››እያለ ወደእሷ ተጠጋና የሆኑ አንድ ሶስት ቁልፎችን ጫን ጫን ሲያደርጋቸው የለበሰችው ልበስ በመፈታታት ወለሉ ላይ ዝርግፍ ብሎ  ወደቀ…እርቃኗን ቀረች፡፡

ይቀጥላል
👍83😱29🥰5🔥21
አትሮኖስ pinned «#ተአምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ // ‹‹ጎሽ ጥለኸኝ አልተሰወርክም…አጠገቤ አለህ ማለት ነው? ››ስትል የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰችና…በከፍተኛ ፍራቻ እና ጥርጣሬ ዓይኖቾን ገለጠች…..ወንዝ የሚባል ነገር ስራቸው  የለም…የሲኦል ምልክትም አይታያትም…. በሳር ፤ በትናንሽ አረንጓዴ ቁጥቆጦች እና የሚያማምሩ በቀለማት  በተሸቆጠቆጡ አበቦች የተሞላ ወብ ቦታ ነው…ግን ግራ…»
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹ፀባይ ይኑርሻ..››እያለ ወደእሷ ተጠጋና የሆኑ አንድ ሶስት ቁልፎችን ጫን ጫን ሲያደርጋቸው የለበሰችው ልበስ በመፈታታት ወለሉ ላይ ዝርግፍ ብሎ  ወደቀ…እርቃኗን ቀረች፡፡
‹‹እንዴ..!!!››በድንጋጤ በርግጋ የእጇን መዳፎች በማነባር ቶሎ ብላ ብልቷ ላይ ከደነችው--ለካ መለመላዋን ነው ይዟት የመጣው…..ዘግይቶ ነው ይሄን የተረዳችው፡፡

‹‹ልቀቂው ….በጣም  እኮ ነው የምታምሪው››

‹‹ሂድ እዛ…ሌላ ቀለል ያለ ሚለበስ ነገር የለህም..?››

‹‹የለኝም…››

ቶሎ ብላ አልጋ ላይ ወጣቸና አንሶላ የመሰለውን ጨርቅ ይሁን ልስልስ በረት ያለየችውን ልብስ  ገልጣ ገባች

‹‹እኔም አብሬሽ ልተኛ…?››

በመለማመጥ ጠየቃት…

‹‹ከውስጥ ሳትገባ..ከላይ ከሆነ ተኛ››

እሱ ‹‹እሺ ››ብሎ የሜትር ያህል ርቀት በማሀላቸው ትቶ እንዳለችው ከላይ ተኛ

‹‹ምን እያደረግኩ ነው..?እስቲ አንድ ሴት ለዛውም ልጃገረድ ነኝ ብላ በአካባቢዋ ባሉ ወጣቶች ላይ ጉራዋን የምትነዛ  እንዴት ለመጀመሪያ ቀን የመጣችበት ለዛውም በጥልቀት እኳን የማታውቀው የወንድ   ቤት ውስጥ ዘላ  ከመግባቷ አልጋ ላይ ትወጣለች…ይሄ ቅብጠት ነው ጅልነት….?ወይኔ ይሄ ግራ አጋቢ ፍጡር ምን አስነክቶኛል….?››ስትል አጉረመረመች፡፡

ደግሞ እሺ አልጋ ላይ መውጣቷ ሳያንስ  እሱም  ከጎኗ እንዲተኛ መፍቀዷ የዋህነትቷ ውጤት እንደሆነ እና ቆይቶ የሚያፀፅት ስህተት እንደሚያሰራ እንዲሁ ታወቃት….?

‹‹በጣም ቆንጆ እኮ ነህ….?ቆንጆ ና የምትገርም ፍጡር ››ይህን የተናገረችው እሷ እሯሷ መሆኗን ማመን አልቻለችም… ‹‹በቃ ለይቶልኛል…››አለች በውስጧ፡፡

‹‹አፍቅረሺኛል ማለት ነው.?›› እሱ ደግሞ ጭራሽ የዲፕሎማሲ ቃና በሌለው ጥሬ ንግግሩ  ፀፀቷን አናረው፡፡

‹‹ኸረ በፍጽም… ባፈቅርህስ ምን ታደርግልኛለህ..?ሰው አይደለህ አላገባህ…››የገዛ ልቧ  ግን ሰው ሆነ ሌላ ፍጡር ዋናው ማፈቀርሽ ነው እያላት ነው…

‹‹ሰው ባልሆንስ ከተመቸውሽ ብታገቢኝ ምን አለበት.?››

‹‹ምንም የለበትም …ግን ያው ባገባህስ ምን ዋጋ አለው ብዬ ነው.?››

‹‹እንዴት.? ››

‹‹እንትንህ እኮ ባቄላ ነው የምታህለው..ለእኔ ተፈጥሮ የሚስማማ ሆኖ አይደለም የተፈጠረው……እና ምንም ማድረግ አልችልም››

‹‹እንዴ ግን እንደዚህ እየተናገርኩ ያለሁት እኔው ነኝ…››ስትል የራሷን ባህሪ ባለማመን ጠየቀች..ለነገሩ እውነቷን ነው በጊዜው ተደብቆ የሚያዳምጣት ሰው ቢኖር እኮ  በቃ የአራት አምስት አመት አሪፍ ልምድ ያለት ባልቴት  ነው የምትመስለው…በአዲሱ የባህሪ ለውጧ እራሷን ከፉኛ ታዘበች፡፡

‹‹እና ታዲያ ወደውስጥ እንዳልገባ ለምን ከለከልሺኝ.?››

‹‹ዝም ብዬ ነዋ››

‹‹ዝም ብለሽ ከሆነማ ልግባ ..››ከእሷ አንደበት የሚወጣውን መልስ ሳይጠብቅ ተስፈንጥሮ ከውስጥ ገባ…ግን ሰውነቱ ከሰውነቷ ለማስጠጋት አልደፈረም ….ድርጊቱን ችላ አለችና…

‹‹ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ.?››ስትል የሁለቱንም ትኩረት ወደሌላ አቅጣጫ ዘወረችው፡፡

‹‹ጠይቂኝ››

‹‹እዚህ ማለት ከራስህ ወገን ሚስት አላገባህም.?››

‹‹እኛ ጋር ማግባት የሚባል ነገር የለም..ቃሉም አይታወቅም….››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው የምትኖሩት . .?እንዴትስ ነው የምትዋለድት.?››

‹‹የምንኖረው ያው ሁለታችንም እራሳችንን ችለን ነው..ሴቷም ሆነች ወንድ ራሳቸውን ችለው ነው የሚኖሩት…ግንኙነትም ለመፈፀም በሁለቱ ፃታዎች መሀከል በእለቱ ያለ ስሜት ብቻ ነው ወሳኙ…

ለመውለድ ግን እዚህ እንደእናንተ በአጋጣሚ ወይም ሁሉም እንደፈለገው አይደለም የሚወልደው….

‹‹እና እንዴት ነው.?››ጠየቀችው ገርሟት 

‹‹በአመት ስንት አዲስ ልጅ መወለድ አለበት.? የሚለውን የሚወስኑት የማህበረሰቡ የበላይ ጠባቂዎቹ ናቸው፡፡በተወሰነው ቁጥር መሰረት መውለድ የሚፈልጉ ሴቶች ይወዳደራሉ…..ከዛ እድሉ ቀንቶቸው የተመረጡት ሴቶች ከተመረጡ ወንዶች  ጋር ግንኙነት በመፈፀም አርግዘው ይወልዳሉ..
የተወለደውን ማሳደጉ የሁሉም ኃላፊነት ነው ..በእናት እና ልጅ መካከል ያለው ቁርኝት እንደእናንተ አይደልም …እናት ትወልዳለች ከዛ ታስረክባለች..መውለድ ማለት ለማህበረሰቡ የተለየ አስዋፅኦ ማበርከት ማለት  ነው እንጂ እናትም ሆነች አባት በሚወለደው አዲስ ልጅ ላይ የተለየ ኃላፊነትም ሆነ የተለየ መብት የላቸውም…››

‹‹ይገርማል…..ግን ደስ አይልም ..ልክ እንደ ማሽን ነው የምታስቡት ››

‹‹ብለሽ ነው ?ታዲያ እንደእናንተ የሰው ልጆች በስሜት መሞላትና በሆነ ባልሆነው መሳቀቅና ማልቀስ ይሻላል?

‹‹ቆይ ግን ይሄ ቦታ የት  ነው ሚገኘው ?ምድር ላይ ነው?››አዲስ ርዕስ ከፈተች፡፡

አይ ከምድር በጣም ቅርብ የሆነ በመጠን ግን ከመሬት በጣም የሚያንስ ራሱን የቻለ ፕላኔት ነው፡፡

‹‹ስሙ ምን ይባላል?››

‹‹እኛ ኬድሮን እንለዋለን…የዕውቀት ምድር ማለት ነው ››

‹‹በእኛ በሰው ልጆችስ ስያሜው ምንድን ነው?››

‹‹አይ በሰው ልጆች አይታወቅም…››
‹‹እንዴት አይታወቅም ?ከምድር በጣም ቅርብ ነው አላልክም?››

‹‹ነው፡፡ ግን እራሳችንን ከጥቃትና ከውድመት ለመታደግ ባለን ለዘመናት በዳበረ እውቀትና ጥበብ አማካይነት ለእይታ እንዲሰወር አድርገነዋል..ለክ ቅድም ስትመጪ ከተማው ሙሉ በሙሉ ከእይታሽ ተሰውሮ እንደነበረ ሁሉ የእኛ ፕላኔት ምድር ላይም ሆነ ማርስ ላይ ሆነሽ እስከአሁን በተፈጠሩት  በማንኛውም መሰሪያ ሊታይ የማይችል የተሰወረ እንዲሆን አድርገናል፡፡የሰው ልጅ ምደር ብቸኛዋ  ህይወት የምታኖር ፕላኔት እንደሆነች ነው የሚያውቀው...ግን ደግሞ እኛ የምድር አፍንጫ ስር በማርስና በመሬት መካከል ተሰንቅረን ለአመታት በስኬት   እየኖርን ነው፡፡ደግሞም አስፈላጊ ሲሆን ምድር ገብተን ብዙ ቡዙ ተልኮዎችን ፈፅመን ኮሽ ሳይል እንመለሳለን፡፡››

‹‹ወደፊትስ…?.››

‹‹ወደፊት እንግዲህ አናውቅም…በቴክኖለሎጂ ፍጥነት የሰው ልጅ መቼም  ከእኛ የተሻለ መራቀቅ ላይ ይደርሳሉ ብዬ አላስብም››

‹‹ግን የእኛ ምድር ትለያለች አይደል?››ስትል ጠየቀችው፡፡

ይቀጥላል
👍153😱1512😁9🤔4🥰1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፈል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ግን የእኛ ምድር ትለያለች አይደል?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹የእውነቱን ስነግርሽ ምድር በጣም እድለኛዋ ፈለክ ነች…ምድር በስነ-ህይወት የታጨቀች..እግዚያብሄር ጥበቡን የገለፀባት የመዳፍ ስራ መገለጫ ወርክ ሾፑ ነች ማለት ይቻላል…፡፡ይሄ የሆነው ዋናው ምክንያት በፀሀይ ውስጥ የያዘችው ስፍራ ነው… ለፀሀይ በጣም ቅርብ የሆኑ ስነ-ፈለኮች በጣም ሞቃትና በጨረር የታጨቁ ናቸው..በዚህ ምክንያት  ህይወት ሊበቅልባቸው ምቹ አይደሉም፡፡ከፀሀይ በጣም የራቁ ፈለኮች ደግሞ በቂ ብርሀን ከፀሀይ ስለማይደርሳቸው በጣም ቀዝቃዛ ይሆናሉ..በዚህም የተነሳ ህይወት ያለውን ነገር ለማኖር ምቹዎች አይደሉም.. በዚህ ግን መሬት  የታደለች ነች፡፡ በጣምም ያራቀች እጅግም ያልቀረበች አራተኛውን ወይም መሀከለኛውን ስፍራ የያዘች ነች… ስለዚህ የተመጠነ ብርሀን እና ሙቀት ነው የሚደርሳት ..በዛ  ምክንያት በስነ-ህይወት የተንበሸበሸች ነች…፡፡ለምሳሌ ማርስ ህይወት አላት የላትም የሚባለው ክርክር ሁል ግዜ የሚነሳውና የሚያጨቃጭቀው አንድም ከመሬት ቀጥሎ የምትገኝ ፈለክ ስለሆነች ነው፡፡ሌላው እንደመሬት ከአለት የተሰራች ፕላኔት ስለሆነች ይመስለኛል፡፡ እውነታው ማርስ ከመሬት በላይ በቀዝቃዛ አየር የታጠረች ነች..ግን በተደጋጋሚ ጊዜ  በመሄድ እንደታዘብኩት ከመሬት ጋር ብዙ የሚያመሳስሏት ነገሮች አሉባት፡፡

‹‹እውነት ማርስ ላይም ሄደሀል?፡፡››

‹‹አዎ ያው እንደነገርኩሽ አሁን ያለንበት ማለት ኬድሮን እኮ የምትገኘው  በመሬትና በማርስ መካከል ነው፡፡ ስለዚህ ወደመሬትም ወደማርስም መሄድ ለእኛ ተመሳሳይ ነው፡፡ልክ እናንተ አሜሪካ ወይም አውሰትራሊያ እንደምትሄዱት ማለት ነው፡፡››

‹እና እንዴት ነች.ማለቴ ምን ትመስላለች?››

‹‹ልክ እንደእናንተ መሬት ወቅቶች ይፈራረቁባታል..ልክ  እንደመሬት ተራራ እና ሸለቆ አቀበትና ቁልቁለት ያላበት ነች…እንደውም ከኤቨረስት በእጥፍ የሚያስከነዳ  ግዝፈት ያለው ተራራም  ባለቤት ነች..ያንን በአይኔ  ነው ያየሁት፡፡››

‹‹ግን ውሀ አላት?››በጉጉት ጠየቀችው፡፡

…አይ በገጽ ላይ ውሃ አይገኝባትም ወይም እኔም ሆንኩ ወገኖቼ ማርስን በተደጋጋሚ ብንጎበኝም የውሀ ጠብታ እንኳን አጋጥሞት አያውቅም…፡፡ግን ደግሞ ለቴክኖሎጂ በጣም ወሳኝ የሆኑ ድንቅ ድንቅ መአድናትን የምናገኘው ከማርስ ነው፡፡ግን ደግሞ ህይወት ያለቸውን ነገሮች እንስሳትም ሆነ እፅዋቶችን ከምድር እየወሰድን ነው የምናላምደውና የምናራባው››

‹‹እናንተ ጋር ግን ውሀ አለ አይደል?››

‹‹አዎ እንደምድር የተትረፈረፈ አይሁን እንጂ ውሀ አለ….ውሀ ከሌላ እኮ ህይወትም የለም...ደግሞ እኛ ቁጥራችን እንደሰው ልጆች እንደምድር አሸዋ የትረፈረፈ አይደለም…የአንድ ጥቂት ሀገር ቁጥር ያህል እንኳን አንሆንም በዚህ የተነሳ የሚያስፈለግነም ሪሶርስ ጥቂት ነው፡››

‹‹ደስ ይላል..ግን ከእኛ ምድርና ከእናንተ ኬድሮን የትኛው ይሻላል?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡

የሰው ልጅ ባይኖርባት ምድር ትሻል ነበር..››የሚል ግራ አጋቢ መልስ መለሰላት፡፡

‹‹እንዴ እኔም እኮ የሰው ልጅ ነኝ?››አለችው እንደማኩረፍ ብላ፡፡

ግን ደግሞ በነገራት ነገር በጣም ነው የተደመመችው..ሁሉ ነገር ከእሷ የማሰብ አቅም በላይ ነው የሆነባት፡፡

ሳያስቡት  ዝም ተባባሉ...ዝም ብሎ ተፋጦ መተያየት…አስተየየቱ  ግን አላማራትም ..እውነቱን ለመናገር ሳታየው ሳይሆን አተኩሮ ውስጧ ድረስ ሲያያት ነው  መላ ትኩረቷን እና ስሜቷን ወደራሱ የሰበሰበው….ሳሚው ሳሚው አሰኘት ..እንደዛ ባሰበችበት ቅፅበት እሱ ከንፈሩን ወደከንፈሯ ሲያንቀሳቅስ ተመለከተች....ወይም ያንቀሳቀሰ መስሏትም ሊሆን ይችላል…..ግን እንዴትም ሆኖ ይሁን እንዴት ከንፈሯ ከከንፈሩ  ተጣብቋል….

ቅር አላለትም ..ይልቅ በመጠጣት መጠን ትመጠው ጀመር….ካለችበት ቦታ የተለየ ሌላ ዓለም ላይ የምትንሳፈፍ መስሎ እየተሰማት ነው…ግን  የሆነ ነገርም በጭኗ መካከል እየሰረሰረ ሲገባ እየታወቃት ነው…‹‹እንዴ ምንድነው ጉዱ …›አለች፡፡ሰውነቱ ከታች ወደእሷ ሰውነት አልተጠጋም ..እዛው እነበረበት ቦታ ነበር….ጭራው ይሆን እንዴ...?በደመነፍስ  እየቃተተች እጇን ወደኃላው ስትሰድና ስትዳብስ የጭራውን ጫፍ ወደላይ ተጠቅልሎ ጀርባው ላይ ተጣብቆ ባለበት ጨበጠችው….እየሰረሰራት ያለው ጭራው አይደለም..አዎ ያንን አረጋገጠች….፡፡‹‹ ታዲያ ምንድነው….?›ስትል ጠየቀች፡
አረ የእሱ መሰርሰር ብቻ ሳይሆን እሷም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ግፊት እግሯን እየከፈተችለት ነው… ደስ የሚል ለስላሳ ነገር ነው….ገባ …እየገፋ ወደውስጠቷ ከመሰመጥ ይልቅ እየተሸከረከረ የመቦርቦር  አይነት  ባህሪ ያለው አካል  ነበር የሚሰማት…ፍጽማዊ ሀሴት ውስጥ እየገባች ነው…ምንም ይሁን ምን እያሰደሰታትና እያስፈነጠዘት ነው..ደግሞ ገብቶ ገብቶ ሚያልቅም አልመሰላትም..ማህፀኗን አልፎ እንብርቷ አካባቢ ደርሶ እየወጋጋት መሰላት…‹ወይ ይሄ ነገር በአፌ ሊወጣ ነው እንዴ ?››ስትል በጣር ውስጥ ሆና እራሷን የስጋትና ጭንቀት ጥያቄ ጠየቀች፡፡
መሳሳሙን አላቆረጡም….እሷ በማቃሰት እና በጣር በመወራጨት ላይ ነች‹‹……ወይኔ ሰነጣጠቀኝ…››ሥትል ጮኸች፡፡ ልትቋቋመው የማትችለው የደስታ እና የስቃይ  ድብልቅ ስሜት … ከንፈሩን ለቃ በድጋሚ ጮኸች…መጮህ ብቻ ሳይሆን ብርድ ልብሱን በድንገት ከላያቸው ላይ ገፋ በመጣል… እንዲያ እስትንፋሷን ሊያቆርጥ የነበረው ነገር  ምን እንደሆነ ለማወቅ  ወደ ጭኗ ስትመለከት ተግባሩን የጨረሰ ብልት …ከብልቷ ውስጥ  በመውጣት እየተሸበለለ  ወደ ሰውነቱ እየተሳበ ሲገባ ተመለከተች፡፡

‹‹ ..ምን ጉድ ነው ….?ግማሽ ሜትር ይሆናል እኮ….!!!!››ስትል ተደነቀች፡
ቅድም ባቄላ  የምታህል ብልት ነበረ  አካሉ ላይ እንደመብቀል ብላ ያየችው … በተአምራዊ ተፈጥሮ ምን እንደምትልና ምንስ እንደምታስብ ነው ግራ የገባት….?በዛ ላይ እንዲህ ለሰሚው ግራ በሆነ መንገድ ድንግልናዋን  ማስረከቧም ሌላ  ለማንም ልታስረዳው የማትችለው ልዩ ስሜት ነው የፈጠረባት..የሰይጣን ይሁን የመላዕክ ዝርያ ያለው ፍጡር መሆኑን ለይታ   እርግጠኛ ላልሆነችበት  ፍጡር ይሄ ሁሉ የህይወቷን ወሳኝ ነገር ያለምንም ማንገራገርና ተቃውሞ እንካ ብላ ማስረከቧ ተአምር ነው የሆነባት.፡፡ብልቷ በደም ተሸፍኗል …እናም ደግሞ ዝልግልግ ሀመራዊ ፈሳሽም ጭኗ መሀከል  ይታያታል…ከእሱ ብልት የወጣ የዘር ፍሬ መሆንኑ አልተጠራጠረችም…
በአጠቃላይ ግን ስሜቷን ስታዳምጥ ደስታ  ነው የሚሰማት….ክፋቱ .ደስታዋን   በደንብ አጣጥማ ሳትጨርስ ጆሮ ሰንጣቂ ጩኸት  በቤቱ ውስጥ ተሰማ..ከጩኸቱ በላይ የእሱ ድንጋጤ አስበረገጋት …ሁለቱምም አልጋውን ለቀው በመውረድ መኝታ ቤቱ ወለል ላይ ፊት ለፊት ቆመው ተፋጠዋል፡፡

‹‹ምንድነው …ምን ሆንክ.?››

‹‹ምንድነው የሰራሁት… .?ይሄ ድምፅ ማለት ይቅር የማይባል ስህተት በአንድ የማህበሩ አባል ሲሰራ የሚሰማ  ድምጽ ነው….ቅጣቱ ቀላል እንዳይመስልሽ››

‹‹እንዴ!! ታዲያ አንተ  ምን ጥፋት ሰራህ .?ላንተ መሆኑንስ እንዴት አወቅክ.?››

‹‹ድምጹ ነዋ ..ከውጭ ሚሰማሽ የሚመስለው ድምጽ ሌላ ቤት አይሰማም ..ጥፋት ያጠፋው ሌላ ቢሆን ኖሮ ድምጽ ለእኛ አይሰማንም ነበር..››

‹‹ቆይ ምን እንዳጠፋህ ታውቃለህ.?››

‹‹አዎ››
👍1098👎2🥰1
‹‹ምንድነው.?››
‹‹ካንቺ ጋር ግንኙነት ማድረጌ….በማህበረሰባችን የበላይ ጠባቂዎች ልዩ ፍቃድ ካልተሰጠው በስተቀር ከሌላ ፍጥረት ጋር የሚደረግ ግንኙነት ፈጽሞ ይቅር የማይባል የህግ ጥሰት ነው…እኔ ወደምድር የተላኩት ለሌላ ትልቅ ሚስጥራዊ ተልዕኮ ነበረ .እርግጥ የተላኩበትን ነገር በብቃት ከውኛለሁ…ግን ደግሞ ያልታዝኩትን እና ያልተፈቀደልኝን ስራ መስራቴ ትልቅ ስህተት ነው…፡ከሰው ልጆች ጋር ምንም አይነት ወሲባዊ ግንኙነት ላለመፈፀም ደንብ የወጣው ከሺ አመታት በፊት ነው፡፡በጊዜው በምድር በምንኖር ጊዜ መላ የማህበረሰባችን አካል በሰው ልጅ ሊዋጥ እና ሊጠፋ ትንሽ ነበር የቀረው…ከምድር ሸሽተን ወደኬድሮን የመጣንበት አንዱ ምክንያት ይሄ ነው..ሆሞ ሳቢያን የሚባለው የሰው ልጅ ዝርያ ስንት ሚመስሉትን ፍጥረቶች በውስጡ ውጦ አጥፍቶል መሰለሽ .እኛም በከፊልም ቢሆን ከነህልውናችን ሰርቫይብ ማድረግ የቻልነው ወደዚህ በመምጣታችን  እና ከሰው ልጅ ጋ ምንም አይነት ንክኪ እንዳይኖረን በማድረጋችን ነው…ግን አሁን እኔ ምን አደረግኩ..ይሄው ለብዙ ሺ አመታት ፀንቶ የኖረውን ህጋችንን ጣስኩ….ለምን ?ባንቺ ፍቅር ስለደነዘዝኩ››

‹‹አንተ ብቻ እኮ አይደለህም እኔም ጭምር ነኝ የደነዝኩልህ?››

‹‹ቢሆንም …ላንቺ መገለጥና መታየት አልነበረብኝም...ባታይኝና ባላገኝሽ ይህ የተፈጠረው ሁሉ መቼም አይፈጠርም ነበር፡፡››

‹‹እና ታዲያ አሁን ምንድነው የሚሆነው.?››

‹‹አንቺን ከዚህ ማውጣት እና ወደመሬት ማለቴ ወደቤትሽ መመለስ አለብኝ፡፡››

‹‹አንተስ...?››

‹‹እኔን እርሺኝ፡፡››አለና ሰውነቱን ወጣጠረ …ጭራው ወደላይ ወደወገቡ ሄደና ሰውነቱን እየሰረሰረና ቅርፅን እየቀየረ መጣና በደቂቃ ውስጥ አብረቅራቂ ክንፍ ሆነ..የሰውነቱ ጠቅላላ ገፀ-መልኩ ተቀየረ …

ይቀጥላል
👍8614😁10😱7🥰2🔥1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
‹‹እና ታዲያ አሁን ምንድነው የሚሆነው.?›› 

‹‹አንቺን ከዚህ ማውጣት እና ወደመሬት ማለቴ ወደቤትሽ መመለስ አለብኝ፡፡››

‹‹አንተስ...?››

‹‹እኔን እርሺኝ፡፡››አለና ሰውነቱን ወጣጠረ …ጭራው ወደላይ ወደወገቡ ሄደና ሰውነቱን እየሰረሰረና ቅርፅን እየቀየረ መጣና በደቂቃ ውስጥ አብረቅራቂ ክንፍ ሆነ..የሰውነቱ ጠቅላላ ገፀ-መልኩ ተቀየረ …የሚያበራና የሚንፏለለ አንጸባራቂ ብርሀን ከውስጡ ይፈስ ጀመር.. እጁን ወደ አንገቷ ስር ሰዶ  ጥፍር በመሰለ ነገር ወጋት..የሆነ የመርፌ ውግ አይነት ስሜት ነው የተሰማት …ወዲያው ድንዝዝ ነው ያላት …ከዛ በኃላ የሆነውን ነገር አላወቀችም….

ስትነቃ…. ያዶት ወንዝ ዳር እራሷን ስታ እርቃኗን ጥቅልል ብላ ተኝታ ነው  ሰዎች ያገኟት….አፋፍሰው ወስደው ለቤተሰቦቾ አስረከቧት…ከዛ በቤታቸውና በጠቅላላ መንደሩ አስፈሪ ትርምስ ተፈጠረ…ሁኔታዋ ሲታይ ተደፍራለች… ነፍስ እንደዛራች ያለችበትን እና የሆነውን ነገር ማመን ነው ያቃታት…ምን እንደሆነች በቤተሰቦቾም ብትጠየቅም የሚጨበጥ ነገር መናገር አልቻለችም‹‹ሴይጣን ደፍሯት ነው›› ተባለ..ተከራክራ ልታሳምናቸው አልቻለችም …እሷ ‹‹ተደፍሬ ሳይሆን በፍቃዴ  ነው›› ብትልም ሰሚ አልነበረም… ያንን የሰይጣን እና መላአክ ድብልቅ የሆነ ፍጡር ለማግኘት ከቤተሰቧ እየተደበቀች  ለወራት ያዶት ወንዝ ላይ በለሊት በመሄድ ወንዙን ብታስስም በለቅሶ እየታጠበች በልመና ብትጣራ.. ብትፈልግ ብትጠብቅ ከየት ታምጣው .?
‹‹ወገኖቹ ምን አድርገውት ይሆን...?ምን አለ ለአንድ ሰከንድ እንኳን ተመልሶ ቢመጣና  ቢገለፃልኝ .?እና ሰላም መሆኑን ባውቅና ብረጋጋ..!!!› የዘወትር ምኞቷ ነበር..ግን ምንም መፍትሄ አልነበረውም፤ዳግመኛ ልታገኘው አልቻለችም..ግን ልትረሳውም አልቻለችም..ምክንያቱም አርግዛለታለች.. ስላረገዘችለትም ደስ ነበር ያላት ..ማንም ምንም ቢላት ግድ አልነበራትም ነበር…ቢያንስ በልጁ ውስጥ  እሱን በማየት ነው ለዓመታት የተፅናናችውና..የተረጋጋችው፡፡ ..እርግዝናዋ ከባድ ነበር ፤በአመት ከስድስት ወሯ ነበር መውለድ የቻለችው..የሰውነቷ አወቃቀር እና መላ ተፈጥሮዋ ልክ እንደ እሷ የሆነ እና ከአንገቷ በላይ ያላት መልክ እና  ነገረ ስራዋ የእሱን የምትመስል ልጅ ወለደች…፡፡ከተአምረኛው ፍጡር ተአምረኛ ልጅ ወለደች..ሰው ሁሉ ግን  የገዛ ዘመዶቾንም ጨምሮ  ከዳቢሎስ  ወለደች ነበር ያሏት .‹‹. ይሁን እንኳንም ወለድኩለት   ፡፡›አለች፡፡ስሟንም ኬድሮን  አለቻት፡፡ ይሄም አባቷ የሚኖርበትን ስውር ፕላኔት ለማስታወስ አስባ ነው፡፡የበሬዱ ታናሽ ወንድሞ ደግሞ ሰውን ግራ አታጋቢ አለና ‹‹ሶፊያ›› አላት፡፡በዚህ የተነሳ ‹ኬድሮን› እና ‹ሶፊያ› የተባለ ሁለት ስም ኖራት፡፡
የበሬዱ ዲንቃ ፍቅር….ምናባዊ አይነት ነው ቢባልም…..ግን ደግሞ ምናባዊ ብቻ ነው ተብሎም ድምዳሜ የሚሰጠው አይደለም… ታሪኩ በአጠቃላይ ተአማኒነት የሚጎድለው ልብ አንጠልጣይ ልብ ወለድ ከሚመስል ታሪክ ውስጥ እውነተኛ የምትጨበጥና የምትታቀፈ ልጅ ተገኝታለች፡፡

….ህልም እና ቅዣት ከሚመስለው የፍቅር ግንኙነት ተጨባጭ ኬድሮን አሁን አለች … መቼስ ልጅቷም እራሷ ከተአምራዊ ነገር የታጠረ የወደፊት ታሪክ እንደሚኖራት እንዲሁ የልጅነት ገፅታዋን ብቻ አይቶ መተንበይ ከባድ  አይደለም፡፡
የፍጥረት ምንጩ ከማይታወቅ አባትና ሰው ከሆነች እናት የተወለደችው ኬድሮን ከውልደቷ ጀምሮ  ልዩ ክስተት ሆና ነው በዚህ ምድር የተከሰተችው፡ሁሉ ነገሯ ከሰው የማይገጥም እና ተለየ የሆነው ገና ከውልደቷ  ጀምሮ ነው፡፡የተወለደችው  እንደማንም የሰው ልጅ በዘጠኝ ወሯ አይደለም..አንድ አመት ከስድስት ወር በእናቷ ማሀፀን ውስጥ ዘና ብላ ኖራለች…ምን አልባት በሰው ልጅ የህይወት ታሪክ በእናቱ ማህጻን  ከበቂ በላይ ለሆነ ጊዜ በመንደላቀቅ እና በምቾት በመኖር ሪከርዱ በእጇ  ሳይሆን አይቀርም…
እርግጥ ብዙዎቹ ይሄንን ታሪክ ሲሰሙ ባለማመንና በመጠራጠር ክርክር ውስጥ ይገባሉ‹..እናቷ እሷን የፀነሰችበትን ቀን ተሳስታ ነው፡፡ ›የአብዛኞቹ መላምት ነው..ግን ይሄ እንዳልሆነ ከመጀመሪያ ሳምንት የጽንሰቷ ጊዜ አንስቶ እስክትገላገል ድረስ የሀኪም ክትትል ውስጥ ስለነበረች ትርክቷ በሳይንስ መረጃ የተደገፋ ነው…ይሄም በተወለደችበት ሳምንት በኢትዬጴያ ሬዲዬ የቀትር ዜና ላይ‹‹በባሌ ክፍለሀገር በደሎ መና ከተማ ኑዋሪ የሆነች በሬዱ ዲንቃ የምትባል ወጣት ሴት በአንድ አመት ከስድስት ወር ጤነኛ የሆነች ሴት ልጅ መገለገሏን ከከተማው ጤና ጣቢያ በደረሰን ዜና ማወቅ ተችሏል፡፡…››የሚል ዜና ተነግሮ ስለነበረ ከመወለዷ የከተማዋ ዝነኛ እና ታወቂ እንድትሆን ተገዳለች፡፡

የኬድሮን ተአምራዊነት በዚህ ብቻ አልተገታም ፤እራሷን ችላ መቀመጥ የጀመረችው በሶስት ወሯ ነው…በስድስተኛ ወሯ መራመድ ጀመረች፤ በአንድ አመቷ በእቤታቸው ውስጥ በኩል ደረጃ ይነገሩ የነበሩትን አማርኛ እና ኦሮሚኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፋ ማውራት ቻለች፡፡
ይሄ ሁኔታዋ  ሰው ሁሉ እንዲፈራትና እንደሌላ ፍጡር እንዲቆጥራት አደረገ፡፡አንዳንዴ እሷ ራሷ ስለራሷ ስታስብ  ያው በአንድ አመት ከስድስት ወር እናቷ ማህፀን ስትቆይ ብዙ ነገር ተምራ ብዙውን ነገር እዛው ጨርሳ የወጣች ይመስላታል…እሷ ምትለው እውነት ከሆነ ደግሞ በዘጠኝ ወራቸው የሚወለዱ የሰው ልጆች እድገታቸውን ሳይጨርሱና ማወቅ ሚገባቸውን ጠንቅቀው ሳያውቁ ፤እራሳቸውን የመርዳት አቅሙ ሳያዳብሩ ቸኩለው እንደሚወለዱ ፍንጭ የሚሰጥ ክስተት ነው ማለት ይቻላል፡፡ለምሳሌ ከሰው ልጅ ውጭ ያለ ሌላ እንስሳት ተመልከቱ…ገና ከመወለዳቸው በራሳቸው ለመቆም ይፍጨረጨራሉ..በቀናት ውስጥ የራሳቸውን ምግብ በራሳቸው ቃርመው መመገብ ይጀምራሉ፡፡ከእናታቸው የሚፈልጉት የተወሰነ የደህንነት ጥበቃ እንድታደርግላቸውና መንገድ እንድታሳያቸው ብቻ ነው  ..የሰው ልጅ ግን ልፍስፍስ ነው…በእናቱ ማህፀን ዘጠኝ ወር አሳልፎ ከተወለደ በኃላ ሌላ ዘጠኝ አመት እናቱ ጉያ ውስጥ ተወትፎ በመነፍረቅ ሲልወሰወስ ይገኛል..በሀያ አመቱ  እንኳን እራሱን ችሎ ከቆመ ጠንካራ ና ጀግና ተብሎ  ይሞገሳል..ሰው እራሱን ለመቻል ለሃያ ረጅም አመታት ማደግ… መማር… መሰልጠን ..መጠንከር ይጠበቅበታል፡፡እሷ ግን እንዲ እንዳልሆነች ገና በጥዋቱ ነው የምታውቀው …፡፡
የእሷ ልዩ መሆነ ከውልደቷ ነው የሚጀመረው ቢባልም እውነታው ግን ከዛም ሳብ ይላል ..ከጽንሰቷ ነው የሚጀምራው…ከአባቷ  ማንነት….

ይቀጥላል
👍124😁34😱1615👏10🥰3🤔3👎1