አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-34
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
መንግስቱ  ትእግስትን ከጎኑ እንዳደረገ መኪናዋን በደመነፍስ እየነዳ በሰንዳፍ መስመር ከከተማ ወጣ...ትዕግስትም ስለደነዘዘች ምንም አላለችውም።ልክ ሰንዳፍ ሊደርስ አንድ ኪሎ ሜትር  ያህል  ሲቀራቸው  ወደ ግራ ታጠፈና መኪናዋን ከአስፓልት አወጣት ።ሜዳውን እየሠነጠቀ  አምስት መቶ ሜትር ያህል ከነዳ በኃላ አቆመ።ሞተሩን አጠፋና ወረደ።ትዕግስትም ተከትላው ወረደች።አረንጓዴ ሳር የለበሰው ሜዳ ላይ ቁጭ አለ።እሷም አንድ ሜትር ራቅ አለችና ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች።ከጃኬት ኪሱ ውስጥ ፎቶ አወጣና አትኩሮ ማየት ጀመረ...።ፎቶው የአሮሯ ነው...ይሄ የእሷ ፎቶ እስር ቤትም አብሮት የነበረ ፎቶ ነው።ይሄው ከእስር ቤት ከወጣም ከሁለት አመት በኃላም ከእሱ ጋር አለ..ፎቶውን በአዲስ እና በቅርብ በተነሳችው ዘመናይና ሽቅርቅር  ፎቶም መቀየር አልፈለገም... ስሜቱ ድፍርስርስ አለበት...ሟች ዘመዶቹ ሁሉ በምናብ ተደረደሩበት....እናትና አባቱ ናፈቁት ...እንባው ፈንቅሎት  ተዘረገፈ...ጭንቅላቱን ይዞ በመንሰቅሰቅ አለቀሰ...ትዕግስት ወደእሱ ተጠግታ አቅፋው አብራው ታለቅስ ጀመር...የተወሰነ መረጋጋት ላይ ለመድረስ ከ30 ደቂቃ በላይ ፈጀባቸው።
ድንገት"ምን ታስቢያለሽ?"ሲል ጠየቃት።
"ስለምኑ?"
"ስለአሮሯ ነዎ...የገደላት ይመስልሻል?..."
አንገቷን አቀርቅራ ዝም አለችው።በውስጧ እንደገደላት ነው እያሰበች ያለችው ...ግን እንዴት ብላ አዎ የገደላት ይመስለኛል ልትለው ትችላለ?።ከባድ ነው።
"ግን ምን  አይነት ጭካኔ ቢኖረው ነው የእሷ ገላ ላይ ጉዳት  የሚያደርሰው?ምንስ ብትበድለው እንኳን ግድያ ጥፊ ይገባታል...ሰው እንዴት የገዛ ልጅ ላይ እንዲህ ያደርጋል።"
"ልጅ ሳትሆን የእንጀራ ልጅ"
"ያው ነው..ይህቺ ልጅ እኮ ወላጅአባቷን አታውቅም ...ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋት እሱ ነው።አባቷ ነው።"
ስለአሮራ እና ስለአባቷ ግርማ ፆታዊ ግንኙነት  የምታውቀውን ሁሉ ልትነግረው ፈለገች...ግን የሚፈጠረውን ገመተችና ዝግንን ብሏት ለጊዜውም ቢሆን መልሳ ዋጠችው...በዚህ መሠበር ላይ ሌላ መሠበር መቋቋም አይችልም ብላ አሰበች
"አሁን ምን እናድርግ...ለፓሊስ ሪፓርት እናድርግ...?"የሚል ጥያቄ አቀረበችለት።ከእሱ መልስ ስትጠብቅ ስልኳ ጮኸ...ከኪሷ አወጣችና አየችው"ወይኔ ጉዴ ...እሱ ነው...እራት ሊጋብዘኝ ቀጠሮ ነበረን"
"አንሺዋ"አላት
"አንስቼውስ?ምን እለዋለው?"
"በቃ  ታገኚዋለሻ...ቀርበን እኮ ነው የተሻለ መረጃ ማግኘት የምንችለው"
እነሱ ከመስማማታቸው በፊት ስልኩ ተቋረጠ።
"እንዴት አድርጌ ከገዳይ ጋር እራት በላለሁ..?.."ዘገነናት
"አረ በፈ ጣሪ እንደዛ አላደርግም..ይልቅ አሁን ለፓሊስ እናመልክት እና እነሱ ያደረጉትን  ያድርጉ።"
"አይሆንም ..ፓሊስ እዚህ ውስጥ አይገባም...አሁን  ከንቺ የምፈልገው በትክክል እንደገደላት የሚያረጋግጥልኝ  አንኳር መረጃ እንድታገኚልኝ ነው...ከዛ እባክህ ግደለኝ  እያለ እንስኪማፀነኝ ድረስ ቀስ በቀስ እያንዳንድን የሠውነቱን አካል በየተራ እየገነጠልኩ ለውሻ በማብላት ነው የምጨርሰው.... ደውይለት ...ደውይለትና አሁን 12፡20 ነው 1፡30 ላይ ቅጠሪው ።"
ከፍራቻዋ ሳትወጣ ደወለችቸት ...በሚንቀጠቀጥና በሚርገበገብ ድምፅ ታወራው ጀመር።
"ሄሎ አንቺ እንደዚህ ይደረጋል?"
"ምን አደረኩ?"
"እራት እንብላ ተባብለን ....ትልቅ ቀጠሮ ሰርዤ እቤት ብመጣ የለሽም..ስልክ ብደውል አታነሺም።"
"ጋሽ ግርማ በጣም ይቅርታ  ...አንድ ጓደኛዬ ታማ ሆስፒታል ገባች ብለው ሲደውሉልኝ ደንግጬ ወደ ሆስፒታል ሄድኩ..."
"ውይ የት ሆስፒታል?"
"ሚኒሊክ"
"በቃ መጣልሻለው"
ደነገጠች"አረ አትምጣ ።አሁን እኳ ወጥታ ወደ ቤት እየወሰድናት ነው...እራት የምንበላበትን ቦታ ንገረኝና እስከ 1፡30 ደርሳለው።"
"እርግጠኛ ነሽ"
"አዎ እርግጠኛ ነኝ"
"በቃ እሺ በናፍቆት እጠብቅሻለው"
"እሺ ቸው"ስልኩ ተዘጋ
"በፈጣሪ አሁን ከዚህ ከገዳይ ፊት ቁጭ ብዬ እንዴት ነው ምግብ የሚዋጥልኝ?"ተነጫነጨች።
"ለእኔም ለአሮራም ስትይ  ታደርጊዋለሽ...በይ ተነሽ እንሂድ" አለና መኪና ውስጥ ይዟት ገባ።ሞተሩን ከማስነሳቱ በፊት ከኪሱ ቼክ አዋጣና 200 ሺ ብር  የትዕግስትን ስም ፅፎበት  ፈረመና አቀበላት።
ደንግጣ"ምንድነው?ከሰውዬው ጋር እንድተኛ እየከፈልከኝ እንዳይሆን?።"
"በፍፁም ...የምታደርጊውን እያደረግሽ ያለው ለጓደኝነታችን እንደሆነ አውቃለው...ለዛም ትልቅ ክብር አለኝ ...ግን ማወቅ ያለብሽ  አሁን ከሰውዬው ጋር ጦርነት ውስጥ ልንገባ ነው...ምን እንደሚፈጠር አናውቅም...ማን ቀድሞ እንደሚወድቅም መገመት ከባድ ነው...
የመኪናውን ሞተር አስነሳና ወደአስፓልቱ አስገብቶ የመልስ ጉዞ ጀመሩ
"እና ምን እያልከኝ ነው..?ብሩ እኮ ብዙ ነው።"
"እኔ የሆነ ነገር ከሆንኩ  ሰውዬው የእጅን እንዲያገኝ ለማድረግ ትንሽም ቢሆን የምትንቀሳቀሺበት ብር ያስፈልግሻል..ለዛ ብዬ ነው"
"በፍፅም አንተ ምንም መሆን የለብህም"አለችው በመንዘርዘር
"መሆን ያለበትን ነገር እንዳይሆን ማስቀረት አንችልም... ህይወት ልክ እንደ ፊልም እስክሪፕት ነች።እዛ እስክሪኘት ላይ አፍቃሪና ተፈቃሪዋች አሉ..ገዳይና ተገዳይ ...ሀለቃና ምንዝር..ክፍና ደግ...ምጡቅና ደደብ...ሸርሙጣና  ቁጥብ በእነዚህ ሁሉ የተዋቀረ ብዙ ቅንጭብጫቢ ታሪኳች የታጨቁበት አንድ ወጥ ታሪክ  አለ...ታዲያ ይሄን እንዲያዘጋጅ የተሰጠው ዳሪክተሩ ብዙ ተዋናዬችን ይሰበስብና አንተ አፍቃሪ ሁን ...አንቺ ደግሞ ተፈቃሪ ...አንተ ትገድላለህ አንተ ደግሞ ትገደላለህ...አንተ ደደብን ትተውናለህ አንተ ደግሞ ጂንዬስ ትሆናለህ...እያለ ይደለድላል ።በዛ መሠረት ሁሉም የተሠጠውን ገፀባህሪ በብቃት ለመጫወት ጠንክሮ ይለማመዳል። ብቻውንም ሆነ ከሌላው ጋር ባለው መስተጋብር የተሠጠውን ገፀባህሪ ቦታ ለማግኘትና  ሚናውን በታማኝነት ለመወጣት  በሙሉ አቅሙ ይጥራል።ህይወትም ልክ እንደዚሁ ነው ...
ለያንዳንዳችን የምንጫወተውን የተለየ አይነት ሮል ሰጥታናለች።ልዩነቱ እስክሪኘቱ ተፅፎ አይሰጠንም በተፈጥሮ አእምሯችን ውስጥ የሚቀመጥ ነው።እና የተሠጠንን ሚና ደግሞ የእውነት  እንጫወታለን..አፍቃሪው ከልብ በነፍሱ ጭምር ያፈቅራል ..ከዳተኛውም ቀሺም ምክንያት ፈልጎ ይከዳል...የሚገድለው  ወይ በሽጉጥ ግንባር በርቅሷ ወይ ደግሞ በሳንጃ አንገት ቀንጥሷ ይገድላል።ሁላችንንም የተሠጠንን ህይወት ነው የሚኖረው "...ለተገዳይነት ተፈጥሮ ገዳይ ለመሆን መጋጋጥ  ከተፈጥሯዊ ሚና ማፈንገጥ ነው።እና   አሁን አንቺም ሚናሽን ተወጪ እኔም ሚናዬን እወጣለው። የሚሞተውም ይሞታል...ገዳዩም ይገድላል።"አላት
በዚህ ጊዜ አቶ ግርማ እንዲገናኙ የላከላት አድራሻ ጋር ደርሰው ስለነበረ መኪናዋን ቦታ አስይዞ አቆማት።
👍325🥰2
"በቃ እሺ...ስልክህን እንዳትዘጋ"አለችው።
"አልዘጋም...እና ደግሞ እዚሁ አካባቢ ነው የምጠብቅሽ..ከተቻለሽ በደንብ አስክሪውና ይዘሽው እደሪ ..አንዳንድ ሰው በስካርና በወሲብ ጡዘት ላይ እውነቱን የመለፍለፍ አመል አለው... እና ምንም ነገር ከፈለግሽ ወይ ደውይልኝ..ካልተመቸሽም ሚሴጅ ላኪልኝ"አላት።
"እውነቱ ላይ ለመድረስ የተቻለኝን አደርጋለሁ"አለችና ከመኪናው  ወረደች... እያያት አስፓልቱን ተሻጋራ አቶግርማ ወደሚጠብቃት ሆቴል ገባች።


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍6811👎5🥰4🤔2
‹‹ባል አስይዞ ቁማር››
ምዕራፍ-35
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

በቀጠሯችን መሰረት ወደቃል ቤት እየሄደች ነው።ይህ ቀጠሮ ለእሷ ልክ እንደከዚ ቀደሞቹ ቀጠሮዎች አይነት አይደለም።ቀጠሮውን ሳታሲዘው እንኳን "ለብቻህ ለረጂም ሰዓት ነው የምፈልግህ..በምንም አይነት የማይሰረዝ የሞት ቀጠሮ ነው"ነበር ያለችው።ልክ ስድስት ሰዓት እሱ ቤት ለመገናኘት ነው የተቀጣጠሩት። ሁለት ሰዓት ከቤት ወጣች፤ የውበት ሳሎን ደንበኞቾ ጋር ሄደች ...ከጥፍሯ አንስቶ ቅንድቧን ፀጉሯን እስክታስተካክልላት አራት ተኩል ሆነ...እቤት ሄዳ በሀገሪቱ አለ በተባለች ዲዛይነር በልዩ ሁኔታ ያሰፋችውን የሀገር በሀል ቀሚስ ለብሳ እሱን ደስ ያሰኘዋል ብላ ባሰችው አለባበስ ዘንጣ መኪናዋን እሱ የሚኖርበት ግቢ አስገብታ ሳታቆም ሰዓቱ 6.03 ይል ነበር።የመኪናዋን ሞተር ከጠፋችና  ለእለቱ ልዪ ዝግጅት ማድመቂያ ይሆን ዘንድ ይዛ የመጣችውን ቶርታ ኬክ፤ውስኪ፤ሻማዎች እና ቸኮሌቶችን ከእነ ዘንቢሉ እየተንገዳገደችም ቢሆን ይዛ ወረደችና ወደ ቃል ቤት ልትታጠፍ ስትል አሮጊቷ የቤት አከራይ  ከእቤታቸው ሲወጡ ተገጣጠሙ ።
"ውይ በጌታ መጣሽ?"አሉ ከሞት የተነሳ ዘመዳቸውን ድንገት እንዳዩ አይነት ደንግጠው።አሮጌ ቷ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እንባቸውም እየረገፈ ነው ።
" ማዘር ምን ሆኑ?"
‹‹አረ ምንም አልሆንኩ..ምነው ጠየቅሺኝ?"
"አይ እያለቀሱ ነው ብዬ ነዋ"
"እ አይ ልጄ ጭስ ነገር ነበር ..እቤት ያው ያሮጊት ነገር ታውቂ የለ"
"በሉ እሺ"ብላ መንገዷን ስትቀጥል
"ቆይ ልጄ ቁልፍ ልስጥሸ"አሏትና አስቆሟት፡፡
ውስጧን ክፍት አለው"ምነው ቃል የለም እንዴ?››ለስለስ ባለ ድምፀት ጠየቀቻቸው ።
"ቃል ነው ያልሽው ?"አሉና ወደውስጥ መግባቱን እረስተው ፍዝዝ ብለው ቆሙ፡
"እንዴ እማማ ..ችግር አለ እንዴ?"
"አረ የለም..ማለቴ ቃል ወጣ ብሎ ነው አልቆይም ብሎል"ብለዋት ወደ ውስጥ ገብ ።
"ቃል ደግሞ በዚህ ቀን?ለዛውም እንዲህ አስጠንቅቄህ"ቃል ስሯ ሆኖ ባይሰማትም ተነጫነጨችበት ።
አሮጊቷ አምጥተው ቁልፍን ሰጧት... ነገረ ስራቸው አላማራትም‹..አይናቸውን ከዓይኔ ለምንድነው የሚያሸሹት?›ቁልፉን ተቀብላ እያልጎመጎመች ወደጓሮ ዞረችና የቃልን ቤት ከፍታ ገባች።እንደወትሮ ፅድት እንዳለ  ነው።እሷ ግን ከወትሮ የተለየ የደመቀና የፈካ እንዲሆን ነበር የፈለገችው።ለቧ ላይ እንደሚንቦገቦገው አይነት የደስታ ብርሀን እቤቱም እንደዛው ይሆናል ብላ ጠብቃ ነበር.. በሚገርም ሁኔታ ግን ምን እንኳን እቤቱ በውስጧ በፈለገችው ሆኔታ ባየሸበርቅም  ጠረጰዛው  ግን በምትወዳቸው የምግብ አይነቶች ተሞልቶል። ሞባይሏን አወጣችና ከተለያየ አቅጣጫ አንድ ሶስት ፎቶዎች አነሳችና።‹‹እንደውም ጥሩ አጋጣሚ ነው ።እስኪመለስ አንዳንድ ነገሮችን አስተካክላለሁ› ብላ አሰበችና ወደውስጥ ዘለቀች።የቤቱን መብራት አበራችው...ሌላ አነስ ያለች ጠረጰዛ የክፍሉን አንድ ግድግዳ ተጠግታ ትታያለች።የጠረጰዛውን አቅጣጫ አስተካከለችና ያመጣችውን ኬክ መሀከል ላይ አስቀመጠችው.. የውሰኪ ጠርሙሱን አወጣችና ከጎኑ  አደረገችው...ዝርግ ሰሀኖችን ፈለገችና ቸኮሌቶቾን በመዘርገፍ ቦታ ሰጠዋቸው ።
‹‹አዎ አሁን የጎደለው ሙዚቃና ቃልዬ ብቻ ነው።››አለችና ሙዚቃ ለመክፈት ወደመኝታ ቤት ገባች።ወደጂፓሱ ሄደችና ሶኬቱን ሰካችው.. እላዩ ላይ ፍላሽ ስለነበረ ከፈተችውና ድምፅን መጥና ወደሳሎን ልትመልስ ስትል አይኗ የቃልን አልጋ ላይ  አረፈ..ከተነጠፈው ሰማያዊ የአልጋ ልብስ ላይ ሁለት ነጫጭ ፓስታዎች  ተደራርበው ተቀምጠዎል።ለምን እንደሆነ ባይገባትም አልፋቸው መሄድ አልፈለገችም።ወደኃላ ተመለሰችና የአልጋው ጠርዝ ላይ በመቀመጥ አነሳቻቸው፡፡ ሁለቱንም በሁለት እጆቾ ይዛ ከላይ የተፃፈባቸውን አድራሻ አነበበች፡፡
አንደኛው‹‹ከቃል ለጊፋቲ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ››ይላል።
‹‹የስንብት› ማለት ምን ማለት ነው?።አዎ ገባኝ መድህኔን ልታገባ ስለሆነ እየተሰናታት ነው…።በዚህ መጠን ተበሳጭቶብሻል ማለት ነው..ደግ አደረገ›› አለችና በውስጧ በስኬቶ በመኩራራት ፈነጠዘች፡፡
"እሱን ወደነበረበት አልጋ ላይ ወርወር በማድረግ ሁለተኛውን ገልብጣ፡፡ አድራሻውን ማየት ጀመረች፡፡ በተመሳሳይ ቀለም በአንዳ አይነት የፊደል አጣጣል የተፃፈ ነው፡፡ከቃል ለልዩ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ይላል፡፡በዚህ ወቅት የቤቱ አየር ተበከለ ፤መተንፈስ ብቻ ሳይሆን አይኖቾን ከፍታ አካባቢዋን ሁሉ ማየት ነው ያቃታት.. ፖስታውን  በሚንቀጠቀጡ እጇቾ ቀዳዳ ከፈተችው፡፡
‹ልዩ እንዲህ ያደረኩት አንቺን በአካል አግኝቶ መሰናበት ቀላል ሆኖ ስላላገኘሁት ነው።አንቺና ጊፍቲ ከአባቴ ቀጥሎ በዚህች ምድር ያላችሁኝ የቅርቤም የልቤም ሰዎች ናችሁ።ልዩ እኔ ከአሁን ወዲህ የለውም...እንደምታውቂው ነፍሴ በዚህ አለም ኳኳታና ትርምስ ደስተኛ አይደለችም።ከዚህ በላይ በውስጧ መኳተን ለእኔም ሆነ በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች መልካም መስሎ አልታየኝም።ወደእዚህች ምድር የመጣሁበትን ምክንያት ለመመርመር ፀጥታ ወደአረበበትና በፅሞና ማሰላሰል ወደምችልበት ቦታ ማለቴ ወደገዳም አምርቼያለሁ።ነግሬሽ ባላውቅም ወደእዛ መሄድ የረጅም ጊዜ ውጥኔ ነበር...ግን ያው ይህቺ አለም የራሷ የሆነ ወጥመድ አላትና እስከአሁን ሊሳካልኝ አልቻለም ነበር።
ለማንኛውም እግዚያብሄር ነገሮች እንዲከወኑ የሚፈቅድበት የራሱ የሆነ ጊዜ አለው ...እናም ዛሬ ቀኗ ሆነችና ህልሜ ተሳካ።ካዛሬ ጀምሮ እኔ የመንፈሳዊው አለም ምልምል ወታደር ሆኜ ተመርጬለሁ።ጮርቃ የሆነውን መንፈሳዊ ህይወቴንም ጥልቀት ያለው የበሰለና  ለሌላው የሚተርፍ እስኪሆን ድረስ በልምምድ ተጋለሁ ሁለት አመትም ፈጀብኝ ሀያ አመት ካልሆነም እድሜ ልክ አያስጨንቀኝም...በመንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ ወደ ሰማያዊ ንቃት ለማደግ  ምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።እግዚያብሄርም እንደሚያግዘኝ እተማመናለሁ። አንቺም እንደምትፀልይልኝ ጥርጥር የለኝም።እንግዲህ ልዩ የህይወት አላማዬ አስገድዶኝ በመንፈሳዊ ተልዕኮ ተገድጄ ካልሆነ በስተቀር ከምሄድበት የፅሞናና የፀጥታ ቦታ ወጥቼ ወደእናንተ የምመጣ ስለማይመስለኝ ይህ  ስንብት የመጨረሻችን ነው።ግን ደግሞ በሚቀጥለው አለም በተለየ ሁኔታ እንገናኛለን የሚል የፀና እምነት አለኝ።
በስተመጨረሻ ሁለት ነገሮችን እንድታደርጊልኝ እጠይቅሻለሁ ..የመጀመሪያው ለጊፍቲ ጥሩ ጓደኛ እንድትሆኚያትና ሁለተኛው ደግሞ በተቻለሽ መጠን አባቴን እንድትጠይቂው ነው።ያው አንቺም አባት የለሽም አይደል... አባቴን ሸልሜሻለሁ።የቤቱን ዕቃ ከጊፍቲ ጋር ተማክራችሁ እንደሚሆን አድርጉት ወይ ለተቸገረ ስጡት...ብቻ እንደመሠላችሁ። በስተመጨረሻ በእጆቼ ጣቶች በጥልቅ ምስጋናና በፍፅም ፍቅር የመጨረሻ ምሳ አዘጋጅቼልሻለሁ...ጣፍጦሽ እንደምትበይው እርግጠኛ ነኝ።በይ ቸው..እስከአሁን አብረን በቆየንባቸው ጊዜያቶች ስላሳየሽኝ ደግነት፤ስለ ሰጠሸኝ ፍቅር፡ስለአጎናፀፍሽኝ ደስታ ከልቤ አመሰግናለሁ!! አመስገናለሁ!!! አመሰግናለሁ... የእግዜያብሄር መንፈስ በልብሽ ይንገስ.. .አሜን
...እራሷን ተቆጣጥራ ፌንት በልታ ወደኃላዋ ተዘርራ ሳትወድቅ  ደብዳቤውን አንብባ ጨረስችው.የዛ አይነት ፅናትና ብርታት ከየት እንዳመጣቸ ለራሷም ደነቃት...ምን እየተሠማት እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍301🥰1😢1
ልብ ወለድ በፅዮን fiction ❤️😘:
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-36
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
በየደቂቃዎ በሚሊዬን የሚሆን የሰውነታችን  ሴሎች ሞተው በሚሊዬን የሚሆኑ አዳዲስ ሴሎች ይፈጠራሉ።ያ ማለት በየቀኑ ጥቂት በጥቂት እያረጀን እንፈርሳለን...በየቀኑ ደግሞ ጥቂት በጥቂት እየታደስንና እየተወለድን እንመጣለን።አሮራ ግን አሁን እየተሰማት ያለው ፈፅሞ መታደስ አይደለም ..እንደውም ፈርሶ መበታተን የጀመረ ያለፈ ስርዓት ባረጀ ርዕዬት ሳቢያ ያስገናባው ሀልት እንደሆነች አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው…
እንዴት ግን በ22 አመቴ እንደዚህ አረጀው….?እንዴት በዚህ እድሜዬ በእንደዚህ እይነት መንገድ በሰው ተጠልፌ ለመታልና ለመክሰም ተዘጋጀው…..በብረት ፍርግርግ በተሰራ የመስታወት መስኮት አጠገብ  ባለ ወንበር ተቀምጣ አይኗን ግቢው ውስጥ ባሉ አረንጓዴ ትክሎችና አበቦች አማትራ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎችን  እራሷን በመጠየቅ እየተብሰለሰለች ነው፡፡ጋርዶቹ አሁንም በራፏ ላይ ተገትረው እየጠበቋት ነው፡፡አሮሯ ውጩ ናፍቋታል....መድረክ ላይ እየተወዛወዙ መዝፈን ናፍቋታል...የመንግስቱ ልብን የሚያቀልጡና ውስጥን የሚያሞቁ ውብ የፍቅር ሚሴጆችን ማንበብ በጣም ናፍቋታል...ከዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ እራሷን የምታወጣበትን እና ነፃ ሰው የምትሆንበትን  ቀን  ናፍቋታል።
በራፉ ተከፈተ…‹‹..ምንም አልፈልግም …ውጡልኝ››እይታውን ከመስኳቱ ወደውስጥ ሳትመልስ አምቧረቀች፡፡
ወደውስጥ ዘልቆ እየገባ‹‹እኔንም አትፈልጊኝም ማለት ነው?››አላት..አቶ ግርማ ነበረ….
ድምጹን ስትሰማ አንዘረዘራት‹‹በህይወቴ በዚህ ልክ ሰው ያስጠላኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር…››አለችው ፡፡
‹‹ጥሩ ነው….ዛሬ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ድነሽ ወደአቋምሽ ተመልሰሻል…የግንባርሽ ጠባሳም በቀላል ሰርጀሪ እንደሚስተካከል እርግጠኛ ነኝ››አላት፡፡
‹‹አዎ …ግን መገደሌ ላይቀር ወደአቋሜ መመለስ  ሆነ ጠባሳዬን በሰርጀሪ ማስወገድ ምን ይረባኛል?››
‹‹አትሳሳቺ…   ምንም ቢሆን እኮ ያስደኩሽ ልጄ እና ወለላሽን ያጠጣሺኝ  ፍቅረኛዬ ነሽ…ዝም ብዬማ አልገልሽም…ከተስማማን ለምን ገድልሻለሁ?››አለና ከፊት ለፊቷ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡
‹‹ምንድነው የምትፈልገው …?.በቃ ወደፓሊስ ጣቢያ አልሄድም….ልቀቀኝ…ማለቴ ሙሉ በሙሉ ከህይወትህ አውጣኝ…ንብረቴን አስረክበኝ ከዛ አትደረስብኝ አልደርስብህም››በማለት ለቀናት ስታብሰለስለው የከረመችውን የመደራደሪያ ሀሳብ አቀረበችለት፡፡
‹ጥሩ… ወደፖሊስ ላለመሄድ መወሰንሽ ከስሜት የፀዳ ውሳኔ እየወሰንሽ እንደሆነ የስታውቃል…..ሙሉ በሙሉ ከህይወቴ ውጣ ላልሽውም እኔም ቀድሜ አስቤ ውሳኔ ላይ የደረስኩበት ጉዳይ ስለሆነ ያስማማናል….ያልገባኝ ንብረቴ ያልሽው ነው….?የእናትሽን ውርስ እየጠየቅሽ መሆኑ ነው?››
በድንጋጤና በገረሜታ አፍጥጣ አየችው‹‹የምን ውርስ ትላለህ እንዴ…..?ከ15 አመት ጀመሬ በናይትክለብ እየዘፈንኩ ነው…በአመት ከአምስት ጉዞ በላይ ወጭ ሀገር በመሄድ እንሰራለን…አንድ አልበም አሳትሜ በዛም ብዙ ብር ተገኝቶበታል….ይሄን ቤት በእኔ ብር ነው የገዛሀው…ስሙም በእኔ ነው….አንድ ኤክስካባተር ማሽንም በስሜ እንደተገዛ ነገረኸኛል…ሌላም ብዙ ብዙ…ግን እኔ አሁን ኤክስካባተሩንና ይሄንን ቤት ብቻ ከነሰነዶቹ አስረክበኝ ነው ምልህ…..ከዛ አህቴን ስጠኝ በቃ…የራሳችን ኑሮ እንኖራለን የራስሀን ኑሮ ኑር…ልናስቸግርህ አንፈልግም፡፡››

ከትከት ብሎ ሳቀ

‹‹ምነው የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ…?››አለችው በመፀየፍ አስተያየት፡፡
‹‹አይ ገርሞኝ ነው…. አንቺ በቃ እንደሶስት አመት  ህፃን ልጅ የተነገረሽን ሁሉ ታምኛለሽ ማለት ነው…?የምን  ኤክስካቫተር ነው በአንቺ ስም ያለው…?ማሽኑ  በእህትሽ ስም ነው ያለው….፡፡ይሄ ቤትም እንደዛው…፡፡በስምሽ ያለው አንድ ብቸኛ ነገር ቢኖር የምትነጂያት መኪና ብቻ ነው፡፡››
‹‹ምን አይነት አጋሰስ ሰው ነህ ግን..?››
‹‹አፍሽን መክፈት አቁመሽ የምልሽን ስሚኝ…አሁን ሻንጣሽን ሰብስበሽ ከዚህ ሀገር ትሄጂያለሽ…የፈለግሽን ሀገር ምረጪና ተዘጋጂ… እኔ ጉዞውን አመቻችልሻለው….በሰላምና በፀጥታ ትሄጂያለሽ…ማንንም አታገኚም ያንን ጎረምሳሽንም አታገኚም….ሄደሽም አትደውይለትም….እኔ ሳላውቅና ሳልፈቅድልሽም ወደሀገርቤት መመለስ አትችይም…እዛ አስክትለምጂና ስራ መስራት እስክትጀምሪ የምትጠቀሚበት አንድ 10ሺ ዶላር አዘጋጅልሻለው››
‹‹ቆይ ያን ያህል ጅል እመስልሀለው….?ልጅነቴን ዘርፍክ….ንብረቴን ዘርፈክህ….እናቴን ዘረፍክው…ሞራሊን ዘረፍክ …ባዶ ሙልጬን ወደውጭ ስትልከኝ አሺ ይሁን ብዬ የምሄድ ይመስልሀል…?ከዛ ይልቅ በለመደ እጅህ እንደእናቴ ብትገድለኝ እመርጣለው፡፡››
‹‹አይ እኔም አልገድልሽም..አንቺም እኔ አድርጊ እንዳልኩሽ ታደርጊያለሽ››
‹‹እንደዛ እንደማደርግ በምን እርግጠኛ ሆንክ…?አስገድደህና ጭንቅላቴ ላይ ሽጉጥ በመደቀን ኤርፖርት በራፍ ድረስ ልትወስደኝ ትችል ይሆናል…አውሮፕላን ውስጥ የምታስገባኝ ግን እንዴት አድርገህ ነው?›ስትል  ያልገባትን ጥያቄ የጠየቀችው፡፡
‹‹ለእህትሽ ስትይ የምልሽን ታደርጊያለሽ››
‹‹ማለት .?.አልገባኝም…ይእ ጉዳይ ከእህቴ ጋር ምን ያገናኘዋል?››
‹‹እህትሽ ባንቺ አለመኖር ደስተኛ የሆነች መስለኛል…መኝታ ክፍሏን ሁላ ቀይራለች…አሁን አብራኝ ነው የምትተኛው››
…አሮራ አቅለሸለሻት…ከተቀመጠችበት ወንበር ተንሸራታ ወረደችና  ወለሉ ላይ ተንበረከከች…..
‹‹አንተ..ስጋህ እኮ ነች….የአብራክህ ክፍይ…ለዛውም አንድ ፍረዬ ልጅ…››
‹‹እንግዲህ ነገርኩሸ…..እኔ አንዴ በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ስለተጨመላለቅኩ ግድ አይሰጠኝም….ይሄ ሁሉ እንዳይሆን የምትፈልጊ ከሆነ እንዳልኩሽ አድርጊ… ..አትፈታተኚኝ…በይ ቸው … ነገ ስመጣ መሄድ የምትፈልጊበትን ሀገር መርጠሸ  ጠብቂኝ ››ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳና ወጥቷ ሄደ..አሮራ እዛው በተንበረከከችበት ወለላ ላይ ዝርር ብላ ተኛች፡፡
///
ትዕግስት ከመንግስቱ ጋር ቦሌ አካባቢ የሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ቁጭ ብለው የአሮራን አጎት እዝራን እየጠበቁት ነው፡፡ስለአሮራ ጉዳይ…እስከአሁን የደረሱበትን መረጃ በመነጋር በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው በጋራ ለመወሰን ነው፡፡
‹‹ማታ እንዴት ሆንሽ››ሲል ጠየቃት መንግስቱ  ትዕግስት ማታ ከግርማ ጋርቤርጎ ውስጥ ገብታ አብራ በማደሮ ያጋጠማትን ነገር ነው የሚያወራት፡፡
‹‹ሲኦል ውስጥ ነው ያሳለፍኩት››በአጩሩ መለሰችለት፡፡
‹‹ከማትፈልጊው ሰው ጋር ለእኔ ስትይ አንድትተኚ በማድረግ በፀፀት ስቃጠል ነው ያደርኩት…..ያሰተሳሰብ ብቃቴ ደብዝዞል…..እምቢ ብትይኝ ጥሩ ነበር››አላት
‹‹አይዞህ እንደምንም አምልጬያለው››
የጨገገ ፊቱ በከፊልም ቢሆን ፈገግ አለ…‹‹አትይኝም …?እንዴት ሆኗ?››
የለበሰችውን የቀኝ እግር የጅንስ ሱሪ ወደላይ ሰበሰበችና የተጋጋጠ እግሯን አሳየችው‹‹እንዴ ምን ሆንሽ  ?አምቢ ስላልሽው ደበደበሽ እንዴ?››
‹‹አይደለም….ስናወራ አምሽተን…ለአንተ ያላኩልህን ንግግራችን ካጠናቀቅን በኃላ መተኛ ሰዓታችን ሲደርስ…ከስልኬ ሙዚቃ ከፈትኩና እንድነስ አልኩት ..እሺ ብሎኝ ስንደንስ…በመሀከል ሲያሽከርክረኝ ሆነ ብዬ ተንሸራተትኩና ወለል ላይ ተዘረርኩ… ከዛ በቃ የውሸት ስሬ ዞረ ብዬ ተዘረርኩ….እግሬን አላስነካ አልኩ…የወገቤ ስር ተበጠሰ ..እህህሀህ..ስልበት አደርኩ…በለሊት ተነስቶ የግል ሆሲፒታል ወሰደኝ..እናቴ ጋር ሄጄ ብተኛ ይሻላል አልኩት..
👍518🔥1👏1😁1
ላድርስሽ ሲለኝ…እናቴ ሀይለኛ ሴት እንደሆነችና በሰፈር መታየት እንደሌለበት ነግሬው በራይድ ሸኘኝ..ከዛ ራይዱ እዙሮ አንተ ጋር አምጥቶ ጣለኝ…››ብላ ያጋጠማትን በአጭሩ አስረዳችው፡፡
‹‹በጣም አደገኛ ሴት ነሽ ..››ሲላት አዝራ አጠገባቸው ደርሶ ሰላም ሳይላቸው ወንበር ስቦ እየተቀመጠ ነበር፡፡
ስሜታችን ከምክንያታዊነት ጋር በተቃራኒ ገፅ የሚቆም አይደለም።ግን ነገሮች በምክንያታዊ ትንተና ተደግፈው ማረጋገጫ ከማግኘታቸው በፊት ቀድመው ከፊት እራሳቸውን  ይገለፃሉ ።ቆይቶ  ግን በምክንያት እና  ሳቢያ ትንታኔ የመደገፍና የመረጋገጥ እድል ሊኖራቸው ይችላል።እና ስሜታዊ መሆን ጥሩ የሚሆኑባቸው ብዙ የህይወት አጋጣሚዋች አሉ።ትዕግስት አሁን  ያለችበት የስሜት ንረት ጥሩ ነው አይደለም አታውቅም ..ግድም አይሰጣትም….አሁን የምታውቀውን ሚስጥር  ለመናገር ወስናለች….ውሳኔዋ ምን እንደሚያስከትል መገመት አትችልም….ግን የሆነው  ይሁን ብላ ወስናለች….ሞባይሎን ከፈተችና አተ ግርማና አሮራ ንታ ቤት ቢስጥር አስቀምታ የቀረፀችው የወሲብ ግንኑነታችውን የሚያሳየውን ቪዲዬ ልታሳቸው ዝግጁ ሆነች፡፡
"ይሄንን ቨዲዬ ካየ በኃላ ለእሷ መጨነቅና መፋለሙን ይቀጥላል ወይስ ቁርጥ አርጎለት እስከጭራሹ ይጠላታል..እንደገዛ ልጁ የሚያያት አጎቷስ ምን ይሰማዋል….?"በትዕግስት አእምሮ የሚጉላሉ የስጋት ጥያቄዎች ናቸው።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍5214
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-35
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
መኪና ውስጥ ሆኖ ትዕግስትን ሲጠብቅ ሳዕታት አልፈውታል….እስከአሁን ከእሷ የተሰማ ምንም ነገር የለም….ስልኩ ደጋሞ እየተደወለት  እየበጠበጠው ነው…አነሳው
‹‹.እሺ  ምነው?››በተሰላቸ ድምጻት ጠየቃት፡፡
‹‹እንዴት ምነው …?የት ነህ ?እየጠበቅኩህ እኮ ነው.››
‹‹አልመጣም አትጠብቂኝ››ዘጋባት…የአጎቱ ሚስት ውቢት ነች
…ከደቂቃዎች በኃላ አሁንም ስልኩ ጠራ …እስከወዲያኛው ዘግቶት ቢገላገል ደስ ይለው ነበር….ግን ያንን ማድረግ አይችልም..ድንገት ትእግስት ልትፈልገው ትችላለች…ስልኩን ከዘጋው  ደግሞ አታገኘውም።
አሁን ደግሞ ትብለፅ ነች፡፡
"ሄሎ ምን ፈለግሽ?
‹‹እንዴት ምን  ፈለግሽ ?ስራ ቦታ እኮ ነኝ፡፡ እየጠበቅኩህ ነው ..ወደቤት ውሰደኝ እንጂ?
‹‹አልችልም እዛው እደሪ…››
‹‹አይ አሁኑኑ ናና እቤት ውሰደኝ….ደግሞ  ብቻዬን ማደር እፈልግም››
ደሙ ተንተከተከ‹‹.ሴትዬ እዛ ገስት ሀውስ ውስጥ ተከራይተው ብቻቸውን የተኙ ወንዶች የሉም..?››
‹‹አሉ ምነው?››
‹‹እያንኳኳሽ ከመሀከላቸው የቆመበት ወንድ  ካለ ጠይቂና  እሺ ካለሽ አብረሽው ተኚ››ጠረቀመባት፡፡
15 ደቂቃ በኃላ መልሳ ደውለች….አሁን ከቁጥጥር ውጭ እየወጣ ነወ…‹‹.አንቺ አትሰሚኝም እንዴ …አንደትደውይልኝ አልልኩሽም …››
ከቅዱሙ ቀዝቀዝና ልስልስ ብላ ‹‹..እኔ አይደለሁም ውቢት መጥታ ውለጂው እያለችኝ ነው….››
‹‹ስርሽ ነች አሁን?››
‹‹አዎ ስሬ ነች….ስልኩን ላውድ ላይ አድርጊው››
‹‹እሺ ያው እየሰማች ነው ላውድ ላይ አድርጌዋለው››
‹‹ወቢት .››.አቤት
‹‹ትብለፅ…››አቤት
‹‹ሁታችሁም እየሰመችሁኝ ነው››
‹‹አዎ መንጌ …ሁለታችንም እየሰማንህ ነው፡፡
አሁን ሁለታችሁም ተያይዛችሁ ወደትልቁ ቤት ሄዱና…ከዛ ካናዳ ላለው ባላችሁ በቪዲ ኮል ደውሉለትና አውሩት…ከዛ እርስ በርሳችሁ ተቃቅፋችሁ ተኙ…ካለበለዚያ ወንድ ገዝታችሁ ግብ…እንደፈለጋችሁ..ከሁን በኃላ ግን አንዳችሁ ብትደውሉልኝ..ያላችሁበት መጥቼ ግንባራችሁን ነው የምፈረክሰው…ጠረቀመባቸው…..ከዛ ወዲህ አልደወሉለትም…ተንፈስ አለ፡፡
ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ በስልኩ ሚሴጅ ደረሰው…፡፡
‹‹ሰውዬው አብረን ካላደርን ብሎ ሙጭች አለ….እስከአሁን ምንም የረባ ነገር አላገኘሁም….የምናድርበት ቤርጎ ቁ-202 ነው…አትጠብቀኝ ወደቤት ሄድ..ጥዋት እንገናኛለን፡፡››የሚል መልዕክት ላከችለት፡፡
በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለበት አሰበ… ስልኩን አወጣና ደወለ….
‹‹ሄሎ  የሆነ ስራ ነበረኝ››
‹‹በስልክ ማውራት አልችልም…አሁኑኑ በምልክልህ አድርሻ ና እና አግኘኝ፡፡››
አዎ ሰውዬውን ማሳፈን እንዳለበት ወስኗል…ትዕግስት .እስከ ጥዋት ድረስ ስለአሮራ ምንም ፍንጭ እና ተጨባጭ ነገር ካላመጣችለት ሰውዬውን ያሳፍነውና አንድ ስርቻ ወይም ድብቅ መጋዘን ውስጥ ወስዶ በማስገረፍ በገዛ አንደበቱ በግድ እንዲናዘዝ ያደርገዋል…ቢያንስ እሬሳዋን ያልሆነ ቦታ ጥሎት ከሆነ ያንን ሰብስቦ በክብር እንድትቀበር ያደርጋል….የሰውዬውን ቅሌትና ወንጀልም ሀገር እንዲያውቅ ያደርጋል…ግን ለመንግሰት አሳልፎ አይሰጠውም….አደባባይ ላይ ይሰቅለዋል….እና እሬሳው እንዲቃጠል ያደርጋል አዎ ውሳኔው እንደዛ ነው፡፡
ትእግስት እና አቶ ግርማ የተከራዩበት ክፍል እንደገቡ ነበር ሊከመርባት የፈለገው.."ቆይ ግረምሽዬ የት ይሄድብሀለው..ገና መጠጡን አልጠገብኩም..ትንሽ እየጠጣን እናውራ "አለችና አረጋጋችው።
"የእኔ እመቤት አንቺ ያልሽው ሁሉ ይፈጻማል" አለና ሶፋው ላይ ዘጭ ብሎ ተቀመጠ…ብርጭቆውን አነሳችን ውስኪውን ቀድታ አቀበለችው..ተጎነጨለትና አስቀመጠው..ለራሷም ቀዳችና ከጎኑ ቁጭ አለች፡፡
ከእሱ ዞር እንደማለት አለችና ስልኳን ርከርድ ላይ በማድረግ ወደእሱ ተጠግታ ተቀመጠች።
"ከአሮራ አኮ አንድ ቀን ብቻችንን ከከተማ ወጥተን ለመዝናናትና እንዲህ ዘና ለማለት ቃል ገብታልኝ ነበረ….
‹‹እርሺው….ከዛሬ በኃላ ከእሷ ጋር ለማድረግ ያሰብሽውን ከእኔ ጋር ነው ማድረግ የምትችይው››
‹‹እሱ እንኳን እውነት አይመስለኝም….ስትመጣ ቃሏን ትጠብቃለች…እንደውም ጨበራጩርጩራ ወይም ወንጪ ነው ይዛኝ የምትሄደው ››
‹‹ካልመጣችስ…?››
‹‹ካልመጣች ማለት?እንዴት ላትመጣ ትችላለች?››
‹‹እውነቱን ንገረኝ ካልሺኝ .. እዛው ሰዊድን መኖር ይሻለኛል እያለች ነው….እኔም ልፍቀድላት  ወይስ ተመለሺ ልበላት ?እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገብቼለው››
‹‹እንዴ ስራዋስ? እዚህ እኮ በጣም ታዋቂና እና ዝነኛ እየሆነች ነው…ጥሩ ኑሮ ነው የምትኖረው ...ምን አጥታ ነው ሰው ሀገር ልኑር የምትለው.?.››
‹‹እኔም እንደዛ ነበር ያልኳት ….ግን ያው እናንተ ሴትች አንዳንዴ አመላችሁ አስቸጋሪ ነው….ትምህርት እማራለሁ..ምናምን እያለች ነው››
‹‹ያንተ  የክለብ ስራ ራሱ በተወሰነ መጠን መቀዛቀዙ አይቀርም››
‹‹ለጥቂት ጊዜ አዎ…ግን መፍትሄ አላጣለትም››
‹‹እስቲ አሁን ደውልላትና አገናኘኝ…ሀሳቧን ላስቀይራት እችላለው.፡፡››
‹‹በዚህ ሰዓት…..?›
‹‹ምነው በዚህ ሰዓት እነሱ ጋር ቀን አይደለ….?›
‹‹ቢሆንም መደወል አልችለም…እኔ ስፈልግ ደውልልሀላው..እየደወልክ የምትጨቀጭቀኝ ከሆነ ስልኬን አጠፋለው ብላኛለች…..ስልኳን ካጠፋች ደግሞ ማናችንም ልናገኛት አንችልም…ተይ ባክሽ የእሷ ነገር ከባድ እየሆነብኝ ነው…ለዘላለም ላጣት ነው መሰለኝ…. ብታይ  ጭንቅ ብሎኛል..አሮራ ተመልሳ የምትመጣ አይመስለኝም››ያዘነ መስሎ አንገቱን አቀረቀረ
‹‹ቆይ ጋርዶቾ አብራዋት አይደል የሄዱት››
‹‹ወይ አነሱን እኮ አልፈልጋችሁም ብለቸው አሰናብታቸዋለች… ነገ ወይም ተነገ ወዲያ ሊመጡ እየተዘጋጁ ነው፡፡ትእግስት ተስፋ እየቆረጠች መጣች….አሮራን ገድሎ ሳይቀብራት እንዳልቀረ አሁን ወደማመኑ ላይ ነች።
"አሁን ለሊቱን ሙሉ ስለአሮራ እያወራን እና እየተከዝን እናድራልን ወይስ ስለራሳችን እናውራ…?"አላት በመሠላቸት
ወይ ያው ታውቃለህ..አይደል የእንጀራ ጉዳይ ሆኖብኝ ነው…..እሷ ከሌለች እኮ እኔም ስራ የለኝም.."
"አንቺ እኮ ከዘሬ ጀምሮ ስራ አያስፈልግሽም…"
"እና….ድንጋይ ነው የምበላው
"አይ ፍቅር ነው የምትበይው…ከዛሬ ጀምሮ የእኔ ልዬ ረዳት ሆነሽ ተቀጥረሻል…ደሞዝሽም በእጥፍ ይሆንልሻል…"አላት በኩራት ተወጣጥሮ።
"እና ልደሰት?"
"ተደሰቺ…ትንሽ ቆየት ብለን ደግሞ  እናሰድገዋለን….እንጋባ ይሆናል....ዋናው አንቺ ብቻ ጥሩ ተንከባካቢ ሁኚ፡፡"
አንጀቷ እያረረ በጥርሷ ግን እየፈገገች"በጥም ነው ምንከባከብህ እንጂ "አለችና ተንጠራርታ ጉንጩን ስማ "መጣሁ እየጠጣህ ጠብቀኝ" ብላ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች የሻወሩን ውሀ ለቀቀችና ስልኳን ከፍታ የቀዳችውን የድምፅ ቅጂ ቀጥታ ለመንግስቱ ላከችለት፡፡
🍎🍎🍎
መንግስቱ መልዕክቱ ሲድርሰው የገዛ መኪና ውስጥ ክንዴ ከሚባል በእስር ቤት ቆይታው አብሮት ታስሮ የነበረ  አንድ  የጋንግስተር ብድን መሪ ጋር ነበር።…ገቢናውን ከፍቶ ወረደና  የተወሰነ ራቅ ብሎ ከፈተው…. አዳመጠው…. መልሶ ከፈተው አደመጠው….ወደመኪናው ተመልሶ መግባት አቃተው…መቼም ዳግመኛ አሮራን እንዳማያገኛት ገባው፣….አሁን ለእሷ ሊያደርግላት ሚችለው አንድነገር ቢኖር ሊበቀልላትና በሆነ ስርቻ በግፋ የፈሰሰ ደሞን በሌላ ደም ማጠብ ነው፡፡
👍795👎3👏2😁1
እንደምንም የመኪናውን ገቢና ከፍቶ ገባ…".ፖሊስ ሆነ ሌላ ሰው ማይደርስበት በጣም ድብቅ ቦታ እንድታዘጋጅልኝ እፈልጋለው..ያንን ማድረግ ትችላለህ?"ሲል ጠየቀው
"ቀላል ነው…"
"በጣም ታማኝና ብቃት ያላቸው ከአራት እስከ ስድስት  ሰዎች እፈልጋለው… ከዛ አንድ ሰው እንጠልፋለን፡፡"
"ይልከኸውን ማዘጋጀት ቀላልን ነው፡፡ክፍያው ነው ዋናው…"አለው።
"ክፍያው አሳሳቢ አይደለም…ዋናው በብቃት ስራውን መስራት ነው…እስከነገ አስር ሰዓት ድረስ ሁሉኑ ነገር አዘጋጅና ደውልልኝ….ከዛ ቀጣዩን እንነጋራለን….መንቀሳቀሻ ብር ጥዋት አቀብልሀለው››
"ችግር የለውም"
"አደራ"
"መንጌ ታቀኛለህ እኮ.. ያልኩትን ነገር እፈፅማለው….የማልችለውን አደርጋለው አልልም›፡፡"
"አውቃለው ለዛ ነው አንተን የመረጥኩት..በል ደህና እደር"…ክንዴ ከመኪናው ወርዶ ወደራሱ መኪና ሲሔድ እሱ የራሱን መኪና አንቀሳቀሰ…እቤቱ ሲደርስ ከሊቱ 7፡20 ሆኖ ነበር።

  ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍566👏1😁1
እኔስ ኑሬዋለሁ! ሲከፋኝ ሲደላኝ!
ከንግዲህ ተወልዶ
ሰው ለሚሆን ይብላኝ።

🔘ፀጋዬ ገብረመድህን🔘
👍70🤔9👏3
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-37
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎

ትእግስት እዝራ ዝም ብሎ ስለተቀላቀላቸው ግር ብሏት‹‹ደህና ነህ ጋሽ እዝራ?››ስትል ጠየቀችው።
‹‹እንዴት ደህና  እንደምሆን  ጠበቅሽ?….አሮራ ወደ ውጭ አልሄደችም ማለት ምን ማለት ነው..?ካልሄደች….የት ተሰወረች?››
‹‹እሱን የሚያውቀው ወንድምህ ብቻ ነው፡፡››መንግስቱ መለሰለት፡፡
‹‹ጎረምሳው ምን ለማለት ፈልገህ ነው?…አባቷ ምን ያደርጋታል ብለህ አሰብክ?››
‹‹እኔ እንጃ…አኔ ማስበው ምንም ሊያደርጋት እንደሚችል ነው ፡፡››
‹‹ተሳስተሀል…ወንድሜ አሮራን ከልጁ በላይ ነው ሚወዳት…እርግጥ አንተን ለአመታ አሳስሮሀል ..በዛም ቂም እንደያዝክበትና ሰለ እሱ ጥሩ ልታስብ እንደማትችል አውቃለው….።እረዳሀለውም…።አንተን  ብቻ ሳይሆን በእሷ ዙሪያ የሚያንዣብቡ ብዙ ጎረምሶችን አስደብድቧል ፤ጎድቷቸዋል ወይም ልክ እንደአንተ አሳስሯቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄን ሁሉ የሚያደርው ግን እሷን ከጥቃት ለመጠበቅና የማይሆን ሰው ላይ እንዳትወድቅ አብዝቶ በመጨነቅ ነው…..፡፡ እርግጥ እንደዛ አይነት አካሄዱን እኔ ፈፅሞ አልደግፈውም…ብዙ ጊዜም ተጣልተንበታል…ግን እሷን ለመጉዳት ብሎ እንደማያደርገው አውቃለው….ምን ነካህ አባቷ እኮ ነው››
ትግስት ብልጨ አለባት‹‹አይደለም...ማለቴ እሱ አባቷ ሊሆን አይችልም››
እዝራ አፍጥጦ አያት
‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው….?የስጋ አባቷ አይደለም ግን ደግሞ ከህፃንነቷ ጀምሮ ተንከባክቦ አሳድጎታል ፡፡ትምህርት ቤት እያመላለሰ አስትምሯታል….ኮትኩቶ ባለሞያ ቀጥሮ ድምፃን እንዲሞረድ በማድረግ አሁን ምታውቋትን አይነት ድምጻዊ እንድትሆን አድርጎታል ….ታዲያ ወላጅ አባቷስ ቢሆን ከእዚህ በላይ ምን  ሊያደርግላት እንዴትስ ሊያሳድጋት ይችል ነበር…?ሁለቱም ላይ ተሳስታችኋል በሚል ስሜት አፈጠጠባቸው፡፡
ትዕግስት "እንግዲህ ሁለታችሁም በተረጋጋ ስሜት የማሳያችሁን እዩ ..››አለቸና ስልኳን መሀከላቸው አድርጋ ቪዲዬውን አጫወተችው….
እርቃን የተጣጠፈ ቦርጭ ያለው የግርማ ሰውነት…ሽንቅጥቅጥ ያለ ጠይም ለጋ የአሮራ ሰውነት ሰፊ ነጭ አልጋ ልበስ የተነጠፈበት ግዙፍ አልጋ…ቪዲዬ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የሚታዩ ናቸው፡፡ግርማ እጁን ሰዶ ጡቶቾን ሲጨምቃቸው ይታያል…እጆቹን ሳያነሳ ወደ ከንፈሯ  ሄደና ጎረሳት…መንግስቱ ትንፋሽ እያጠረው ነው…..
አሮራ ግርማን  ከላዮ ላይ ገፍትራ በጥፊ ታልሰዋለች በሚል ምኞት እየተጠባበቀ ነበረ…እየተመለከተ ያለው ግን ተቃራኒውን ነው፡፡እያየ ያለው እንደዛ አይደለም…እጇቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመችና እጇን ወደ ብልቱ  ልክ የጥዋት  ፀሀይ እየሞቀ እንዳለ አራስ ልጅ በዝግታና  በቄንጥ ታሽልት ጀመር…የእሷ እጅ ሲያርፍበት እርዝመቱም ሆነ ውፍረቱ ሲጨምር ያስታውቃል…
መንግስቱ ቪዲዬው እስኪያልቅ  ለማየት ዪያስችል አቅም አጣ….ጭንቅላቱን ያዘና መቀመጫውን ለቆ ወደሽንት ቤት ተንደረረ….. ሊያስመለልሰውም ሊያስቀምጠውም መሰለው….ጉሮሮውንም የሚቧጥጠው ነገር አለ…..ተንርድሮ ፊት ለፊት ያገኘው አንዱ መፀዳጃ ክፍል ገባና በላዩ ላይ ጠረቀመው፡
እዝራ እንደደነዘዘ ነው…ምንም አይነት የሰሜት ለውጥ እየታየበት አይደለም….ዝም ብሎ በእርጋታ የተከፈተለትን ቪዲዬ እያየ ነው..አሁን ሁለቱም እርስ በእርስ ተቆላለፈፈው እየተጮጮሁነው…..ትዕግስት የመንግስቱ  ሁኔታ ስላሳሰባት ስልኩንም ሆነ እዝራን ባሉበት ትታ ወደመንግስቱ ሄደች….
መንግስቱ እንደምንም እራሱን ለማረጋጋት ከወሰነ በኃላ ስልኩን አወጣና ደወለ…
‹‹ክንዴ…ሰውዬውን እየተከታተላችሁት ነው?…›››ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ …በቃ ይታፈን….አዎ ዛሬውኑ ከተቻለ አሁኑኑ››ትዕዛዙን አስተላለፈ…
‹‹እሺ በቃ…ወስዳችሁ ቦታው ላይ ስታደርሱት ደውሉልኝ…ወዲያው እመጣለው..››ስልኩን ዘጋው፡፡
‹‹ያለበት መፃዳጃ ቤት ተንኳኳ…ሲከፍተው ትግስት ነች…ወጣና አልፏት ሄደ …በዝምታ ከኃላው ተከተለችው፡፡ ሲደርስው እዝራ የሚያየውን ቪዲዬ  ጨርሶ ሙሉ የጅን ጠርሙስ በእጁ ይዞ ከነጠረሙሱ እያንቀደቀ እየጠጣ ነው፡፡ሁለቱም ወደየቦታቸው ተመለሱና ቁጭ አሉ፡፡
መንግስቱ በምልክት አሰታናጋጇን ጠራት…ስትመጣ….ሙሉ ብላክ ሌብል ከሁለት ብርጭቆ  ጋር አዘዛት…ትእግስት ሞባይሏን ከነበረበት ቦታ ወደራሷ አንሸራተተችና ከፍተችና ሰዓቱን አየች ..ከረፋዱ 5፡10 ይላል…ፈገግ አለች፡፡
ሰባት ሰዓት እስኪሆን ማንም ማንንም አላናገርነበር….ሁሉም መጠጣቸውን እየተጋቱ ሀሳባቸውን እያመኘዠዘጉ ነበር፡፡
የመጀመሪያውን አረፍተ ነገር የተናገረው እዝራ ነው‹‹መንግስቱ››
‹‹አቤት ጋሽ እዝራ››
‹‹ሽጉጥ አለህ…?››
‹‹አዎ››
‹‹በአንተ ስም የተመዘገበ ካልሆነ ታውሰኛለህ…ወንድሜን ከገደልኩበት በኃላ መልስልሀለው..ካልሆነም ሌላ ግዛልኝ…ብሩን እኔ ከፍላለው››

ትዕግስት አፍጥጣ አየችው..አይኑ ደም ለብሷል…የግንባሩ ስሮች ሁሉ ግትርትር ብለዋል…የተነገረው ሁሉ ከልቡ እንደሆነ እልተጠራጠችም…ፊቷን ወደ መንግስቱ አዞረች….ተመሳሳይ ፊት ገፅታ ነው የሚታያት …ሁለት በበቀልና በመጠጥ የሰከሩ ወንዶች መሀከል ቁጭ  ብላ እየተቁለጨለቀጨች መሆኗን ማመን አልቻለችም‹››
‹‹ጋሽ እዝራ አይዞህ ለእዛ አታስብ…ባይሆን እድር ምናምን ካለው እንዲዘጋጁ ንገራቸው… ሌላው ለእኔ ተውልኝ…ለአሮራ መበቀል የእኔ ሀላፊነት ነው፡፡››
‹‹እናንተ ሰዎች ምን አልባት በህይወት ኖራ የሆነ ቦታ ደብቋት ወይም ቆልፎባት ከሆነ እኮ ችግር ውስጥ እንገባለን፡፡ እናንተ  ከገደላችሁት የሚፈጠረውን አውቃችኃል…በተዘዋዋሪ እሷንም ገደላችኋት ማለት  እኮ ነው››
‹‹አይ ...ያ አይከሰትም…ከመሞቱ በፊትማ ሁሉን ነገር እንዲናዘዝ ይደረጋል…ከገደላትም የት እንደቀበራት ወስዶ ያሳየኛል…ከደበቃትም ካደበቀበት ቦታ አውጥቶ ይሰጠናል..››
‹‹ካልገደላት አትገድሉትም አይደል?›ትእግስት በማፈራረቅ ሁለቱንም በየተራ እያየች በመለማመጥ ጠየቀቻቸው።
ሁለቱ ወንዷች እርስ በርስ ተያዩ…።ለመናገር አሁንም እዝራ ቅድሚያውን ወሰደ‹‹አይ ይሄ አውሬ መሞት አለበት እኔ ምንም ሆነ ምንም እንዲሞት ነው የምፈልገው››
‹‹በቃ ይሞታል››ተስማሙና ብርጭቆቸውን አጋጩ።እና ሁሉም ወደገዛ ሀሳባቸው ተመለሱ።

የሠው ልጅ ልብ እንዲህ ቦታዋን ለቃ ብዙ ሴንቲ ሜትሮች ወደታች ዝቅ ትላለች እንዴ?እንደዛነው መንግስቱን  የተሠማው።
👍574👏3🥰2
አይኖቹን ዙሪያውን ሲያሽከረክር በሆቴሉ የተለያዩ ኮሪደሮች የተሠቀሉት ባለሰፋፊ ፍላት እስክሪን ቲቪዎች በጠቅላላ እያሳዩ ያለው የግርማንና የአሮሯን የወሲብ ጫወታ እየመሠለው ነው? በእሱ እይታ ፊት ለፊት ከመንገድ አሻግሮ ያለው ቢልቦርድም እንደዛው የአሮሯ እርቃን ገላ ነው የሞላው...
...ግን ይሄ ሁሉ ከሆነ በኃላ ለምን በእሷ እንዳልተበሳጨ እየገባው አይደለም... አሁንም በውስጡ ያለው ለእሷ የመንሰፍሰፍና የማዘን ስሜት ባለበት እንዳለ ነው...እንደውም ይበልጥ መጠኑን እየጨመረ እየመሠለው ነው....ግርማ በሆነ ድክመቷ ገብቶ እንዳታለላት በሆነ የልጅነት ክፍተቷ ገብቶ ህይወቷን እንዳጨመላለቀባት ነው እየተሠማው ያለው።በዚህ ምክንያት ይበልጥ ግማሽ ልብና ግማሽ ነፍሱ ታመውበታል።አርራ አሳዘነችው።አርራ ናፈቀችው።በዛ ምክንያት ግርማን በተቃራኒው በፊት ከሚጠላው በላይ ጠላው...በፊት ሊያሰቃየው...ሊቀጠቅጠው... ሊቦጫጭቀው ...ሊበቀለው ከሚፈልገው በላይ ለማድረግ  ቸኮለ...።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
41👍18😱3
ልሂድ አልኩት ነፃነቴን እወደው ነበር እንዳሻኝ መብረር ፍላጎቴ ነበር። ፊቱ ላይ ተተንትኖ የማያልቅ ብዙ ስሜት አነበብኩበት...

አወደዋለሁ ከሱ በላይ ግን ነፃነቴን እወደዋለሁ። ለስሜቱ ግድ ሳይሰጠኝ ከእቅፉ ወጥቼ ወዳሻኝ በረርኩ... በ ረ ር ኩ.. ጥቂት ለማይባሉ ጊዜያቶች ያማረኝ የወደድኩት ላይ እያረፍኩ በረርኩ። አምሮኝ ያረፍኩበት ላይ ሁሉ ግን ጎጆዬን መቀለስ አልቻልኩም...

ቋሚ ማረፊያ ፈለግሁ፣ ጎጄዬ ናፈቀኝ፣ ያን ጊዜ ትዝ አለኝ የት ይሆን? ያለው ያስታውሰኝ ይሆን?

ናፈቀኝ... ስለሱ ሳስብ የተዳፈነ ፍቅሩ ተቆሰቆሰብኝ እቅፉ...፣ በስስት የተሞላ አስተያየቱ...፣ ስሜን ሲጠራ ማቆላመጡ(አፉ ላይ ሲያምር እኮ) ብዙ ነገሩ ትዝ አለኝ።

ለምን ነበር የተለየሁት? ምን አድርጎኝ ነበር? በዚያን ጊዜ  እኔን ለማስደሰት ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በቀስታ እየተንቆረቆሩ ወደ ትውስታዬ መጡ። ከሱ ምን አጥቼ ነው? ምን ነክቶኝ ነው ያን የመሰለ ፍቅር ረግጬ የሄድኩት...ስለሱ ባሰብኩ ቁጥር ናፍቆቱ አንገበገበኝ። 

ልፈልገው ተነሳሁ የት እንዳለ ባላውቅም የጋራ ጓደኛችን ወደነበረው ልጅ ቤት አመራሁ። ሲያየኝ ብዙ መገረም አየሁበት። "ከሳሽ በጣም ተጎሳቁለሻል ታመሽ ነበር" አለኝ። አይ አልኩት መች ነው የተጎሳቆልኩት? ድሮ እንዴት ነበርኩ? አሁንስ ምን የተለየ ነገር ሆንኩ?

ቤቱን በሩቅ አሳይቴኝ በቃ ልመለስ አለ። የድሮ የጓደኝነታችን ወዝ ሙጥጥ ብሎ ጠፍቷል ልክ ለአንድ መንገድ ለጠፋባት ሴት መንገድ አሳይቶ የሚመለስ ሰው ነው የሚመስለው።

ስለሱ ማሰቤን ትቼ ወደ ጠቄመኝ ቤት አመራሁና በሩን አንኳኳሁ ትንሽ ቆይቶ በአንድ ጎልማሳ በሩ ተከፈተ

" አቤት ማንን ፈልገሽ ነው እናትዋ" አለኝ። ቃል አብን ፈልጌ ነበር ይኖራል።

"ጋሼ ሲመሽ ነው የሚመጡ ወይም ስልክሺን ጣፊና ስጪኝ እንዲደውሉብሽ እነግራቸዋለሁ" በቋንቋው ለዛ እየተገረምኩ። እንደማያስፈልግ ነግሬው ወደ ቤት ተመለስኩ

በማግስቱ ወፍ ሳይንጫጫ ውጪ በሩ ስር ቁጭ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ። ቆይቴ በሩ ተከፈተ ወደጎን ሆንኩና የሚወጣውን ሰው መጠባበቅ ጀመርኩ የኔ ቃል የምታምር መኪና ይዟል። ከጎኑ የምታምር ሴት ተቀምጣለች። ከግቢው ከውስጥ " ቻው ዳዲ" የሚል የህፃን ድምፅ ሰማሁ። "ቻው የኔ ልጅ (እጁን ሲያውለበልብ የሚያበራ የጋብቻ ቀለበት አየሁ) ወደ ውስጥ አስገቢያት ብርድ ነው" ላላየኋት ሴት ትዛዝ አስተላለፈ።

ብርድ ነው..... ብርድ ሰውነቴ ተንዘፈዘፈ እንዳያየኝ ፊቴን አዙሬ ትንሽ ተራሙድኩና ጭብጥ ብዬ ተቀመጥኩ። የማስበውን አላውቅም ብዙ ሀሳቦች በፍጥነት ጭንቅላቴ ውስጥ መጥተው ይሄዳሉ?

ምንድነበር የማስበው ያሻኝ ጋ በርሬ ስመጣ ጌጆዬን እንደማገኘው? እንዴት ለሰከንድ እንኳን ስመለስ ጎጆዬን እንደማጣው ሌላ ወፍ ማሳደር እንደሚጀምር ሳላስብ ቀረሁ?

ቀስ ብዬ ተነሳሁናእግሬን እየጎተትኩ መጓዝ ጀመርኩ ሰፈሬ ካለሁበት በጣም ቢርቅም ታክሲ መያዝ አልፈለኩም። እርምጃዌቼ በጨመሩ ቁጥር እኔ አሁን የተሰማኝን ስሜት ድሮ እሱ ሊሰማው ከሚችለው ጋር አነፃፀርኩት። እንዴት አለፈው??

በእውነት የእጄን ነው ያገኘሁት እሱ ግን ተክሷል


አይቀጥልም
ተፃፈበፅዮን


    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍6714😢13
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-38
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎

አቶ ግርማ ናይትክለቡ ውስጥ በሚገኝ የግል ቢሮው ቁጭ ብሎ እያብሰለሰለ ነው፡፡የአሮራን ነገር መስመር እያስያዘ ነው፡፡ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ወደቱርክ ይልካታል….ከዛ ደግሞ እዛ ባሉ ወዳጆቹ አማካይነት ወደ ሌላ ወደፈለገችው ሀገር እንድትሻገር ይረዷታል..ያንን ካደረገ በኃላ ደግሞ እስከወዲያኛው ይገላገላትና ቀጣይ ህይወቱን በአዲስ መልክ ይጀምራ…ይህቺን  ትእግስት የምትባለዋን  ልጅ  ወዷታል..እናም  ቀጣይ ህይወቱን ከእሷ  ጋር መሞከር ፈልጎል፡፡ስለ እሷ ሲያስብ ናፈቀችው፡፡
ስልኩን አወጣና ደወለላት...፡አልተነሳም ተዘጋበት…ከዛ ወዲያው ሚሴጅ መጣለት።
ꔚꔚꔚ
ግርምሽዬ ..ይቅርታ እማዬ ስሬ ስላለች ስልክህን ማንሳት አልቻልም…ምንም አታስብ..አሁን ስብራቴን  ታሽቼ አልጋዬ ውስጥ ተኝቼ እናቴ የሰራችልኝን አጥሚት  እየጠጣሁ ነው፡፡
ꔚꔚꔚየሚል መልዕክት ላከችለት፡፡
ደስ አለው፡፡
ꔚꔚꔚ
‹‹ደህና መሆንሽን ስለሰማሁ ደስ ብሎኛል…..እኔ ብንከባብሽ በጣም ደስ ይለኝ ነበር፡፡ለማንኛውም ቶሎ ዳኚልኝ…የምትፈልጊው ማንኛውም ነገር ካለ ደውይልኝ ወይም በመልዕክት አሳውቂኝ፡፡ እና ደግሞ እየወደድኩሽ ስለሆነ  ደስ ብሎኛል።
ꔚꔚꔚብሎ ፃፈና ላከላት፡፡
እና ሌላ ስልክ ደወለ።መንግስቱን እንዲያግቱለት ወደቀጠራቸው ሰዎች ነው የደወለው።
‹‹እና እንዴት ናችሁ?››
‹‹አቶ ግርማ እየተከታተልነው ነው፡፡››
‹‹በጥንቃቄ ተከታተሉት…ልጁ ወሮ በላ ስለሆነ አቅልላችሁ እንዳታዩት››
‹‹ችግር የለውም..አንድ ሆቴል ውስጥ ከአንደ ሴትንና ከሌላ አንድ ወንድ ጋር ቁጭ ብለው ውስኪ  እየተጋቱ ነው..ፎቶ አንስቼያቸዋለሁ አሁን እልክልሀለው››
‹‹በዚህ በጠራራ ፀሀይ መጠጥ?››አቶ ግርማ በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ የሆነ   የምስራች ሰምተው  እያከበሩ ይመስላል››
‹‹አሪፍ ነው …..ሰከር ማለቱ ስራችሁን በተወሰነ መጠን  ያቀልላችኋል…በሉ አድፍጣችሁ ጠብቁና  ከሰዎቹ ሲነጠል አድርጉትና ያሳየዋችሁ ቦታ ውሰዱት ..ከዛ ደውሉልኝ …..››
‹‹እሺ ሀለቃ››
ስልኩ ተዘጋ፡፡ወዲያው መልእክት መጣ፡፡ፎቶ ነው የተላከለት።ከፈተው ድንዝዝ ነው ያለው ፡፡ታማለች ብሎ ሲጨነቅላት የነበረችው ሴት ከቁጥር አንድ ጠላቱ ጋር በደስታ ሆቴል ቀጭ ብላ መጠጥ እየተጋተች ነው…ከዛም በላይ ደግሞ የገዛ ወንድሙም የጠላቶቹን ቡድን ተቀላቅሏል፡፡ማመን አልቻለም..."መጀመሪያውኑስ እንዴት ባለ አጋጣሚ ከየት የት ብለው ተገናኝተው ተዋወቁ....?"ጭንቅላቱን የበላው ትልቅ ጥያቄ ነበር።
‹‹ምን እየተካሄደ ነው ?››ጠየቀ
አሁን ጠላቶቹ አንድ ላይ ተሰብስበው እየጠጡ ያሉት  የት ቦታ እንዳለ ፎቶው ላይ በግልፅ ያስታውቃል… የመሳቢያውን ኪስ ከፈተና ሽጉጡን አወጣ… ውስጡ ሙሉ ጥይት መኖሩን  አረጋግጦ ጎኑ ሸጎጠና ኮቱን ከማንጠልጠያው ላይ በማንሳት እየተንደረደረ ወደ ውጭ ወጣ….መኪና ውስጥ ሲገባ ጋርዱ እየሮጠ ወደእሱ መጣ …ችላ አለውና መኪናዋን አስነስቶ ተፈተለከ…ከናይት ክለቡ ማዶ መኪና ውስጥ ሆነው ሲከታተሉት የነበሩት መንግስቱ የቀጠራቸው ጋንግስተሮች የመኪናቸውን ሞተር አስነሱና ከኃላ ይከተሉት ጀመር ፡፡
በመንገድ መካከል ወደነዳጅ ማደያ ጎራ አለ...
መኪናዋ ቀይ አብርታለች ።በዛ ላይ ፊኛው ወጥሮታል...መኪናውን ለነዳጅ ቀጂው አስተካክሎ  ሲያቆም ከኃላው በመንግስቱ የተቀጠሩት በክንዴ የሚመራው   አጋች ብድን  ከኃላው መጥተው ተከው ቆሙ። አቶ ግርማ  ነዳጅ ከተሞላ በኃላ ቦታውን ለሌላ ተረኛ በመልቀቅ መኪናውን ጠጋ አድርጎ አቆሙና ከፍቶ ወረደ....የመኪናውን በራፍ መልሰው ዘጋና ወደ ማደያው የካፌ መፀዳጃ ቤት ተንቀሳቀሰ..  ክንዴ  መኪናዋን ወደ ጎሮ በኩል  አንቀሳቀሰና የሽንት ቤቱን በራፍ ዘግቶ አቆመው...
"ቶሎ ብላችሁ ውረድ"የሚል ትዕዛዝ ሰጠ።
መኪና ውስጥ ካሉ አራት አጋቾች ሁለቱ ወረድና ተንደርድረው ወደሽንት ቤት ገብ ...እራሱን አስተው መኪናቸው ውስጥ አምጥተው ሲጥሉት ሁለት ደቂቃ አልፈጀባቸውም...ይህንን ሲያደርጉ  ልብ ብሎ ያያቸው ስው እንኳን አልነበረም።ከዛ አንደኛው ከኪሱ ውስጥ  የመኪናውን ቁልፍ አወጣና  ቀጥታ ወደእሱ መኪና  በመሄድ ከፍቶ ገብቶ  በማንቀሳቀስ..ይዞት ወጣ...ጓደኞቹ ከኃላ ተከተሉት።አምስት መቶ ሜትር ያህል ከተጓዙ ብኃላ ሁለቱ መኪኖች የተለያየ አቅጣጫ ያዙ...። የአቶ ግርማን መኪና እየነዳ የወሰዳት በጥንቃቄ ናይት ክለብ አቅራቢያ ወስዶ አቆማትና አሻራው መኪና ውስጥ እንዳይገኝ በጥንቃቄ ካፀዳዳ ብኃላ ማንም ስያየው ከቦታው ተሠወረ ።
ሌሎቹ ደግሞ አቶ ግርማን ይዘው ቀድመው ወዳዘጋጅት ከከተማው ዳርቻ ወደሚገኘው ስውር ስፍራ ወሰድት።
🍎🍎🍎
መንግስቱ  በመጠጥ ከታጀበ ሀሳብ ውስጥ የስልኩ ድምፅ ማሰማት ነው  ያባነነው። ይጠብቀው የነበረ ስልክ ስለነበረ ቁጥሩን እንኳን ሳያይ አነሳው...
"ሄሎ ተሳካልህ.?
"ምኑ ነው ሚሳካው?"
"ወሽመጡ ብጥስ አለ...በንዴት ከተቀመጠበት ተነሳ..."ውቢት አሁን በዚህ ሰዓት ምን ፈለግሽ ደሞ?"
"ሰውዬ ቀስ በል...አጎትህ መምጣቱን ልነግርህ ነው"
"አጎቴ!!! ምን ሊሰራ?"
የማሾፍ ቃና ባለው የድምፅ  ቅላፄ"በፈጣሪ!! አሁን ሰው ወደቤቱ ሲመጣ ምን ሊሠራ ይባላል..?.ናፍቄው ነዋ የመጣው ...ሚስቱ እኮ ነኝ"አለችው
"አንቺ  ስልክሽን ላውድ ላይ አርገሽው እንዳይሆን?"
"አረ እንደመጣ ነው ደክሞኛል ትንሽ ላሳልፍ ብሎ ወደመኝታ ቤት የገባው"
"እና ታዲያ እኔ  ጋር ምን አስደወለሽ...አብረሽው አትተኚም?"አለና ስልኩን ዘግቶ ወደ መቀመጫው ተመለሰ። በጣም ተበሳጭቶል ።በቅርብ እንደሚመጣ ከሳምንት በፊት ሲደዋወሉ ነግሮት ነበር...እንደዚህ በፍጥነት ይመጣል ብሎ ግን ምንም አይነት ግምት አልነበረውም።
"ገደል ይግባ"ሳያስበው ነው ድምፅን ከፍ አድርጎ የተራገመው።
"ማነው ገደል የሚገባው?"በስካር ምክንያት በተኮላተፈ አንደበት የጠየቀችው ትዕግስት ነች።
"አሁን በዚህ ሰአት ማን ገደል እንዲገባለት እንደሚፈልግ አታውቂም?"አላት እዝራ።
"ገባኝ....አዎ ገደል ይግባ"
🍎🍎
በዚህን ጊዜ በድጋሚ  ስልኩ ድምፅ አሰማ..ሚሴጅ ነው ከፍቶ አነበበው።
🍎🍎
ሀለቃ...እቃውን አግኝተን በጥንቃቄ ቦታው ላይ አድርሰናል።በተመቸህ ሰዓት መጥተህ ማየት ትችላለህ"
🍎🍎ይላል።
ፈገግ አለ።ከመቀመጫው ተነሳ።"ሰዎች የሆነች ጉዳይ አለችብኝ ...ልለያችሁ ነው"
"ካስፈለግንህ እንከተልህ?"ትዕግስት ጠየቀች
"አይ የምታስፈልጉኝ ከሆነ ደውላለሁ...በሉ ይመቻችሁ"አለና ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን መጠጥ ጨለጠና በፍጥነት የሆቴሉን ግቢ ለቆ ወጣ።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11019🥰4😁1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-39
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
መንግስቱ ግርማን አግኝቶ እስኪ ቦጫጭቀው ቸኩሏል፡፡ደግሞ ሲያገኘው ምን ሊነግረው እንደሚችል ሲያስብም ፈርቷል፡፡‹‹ገድያታለው ቢለኝ እና እሬሳዋን የቀበረበት ቦታ ወስዶ ቢያሳየኝስ››ሲል አሰበና ዝግንን አለው፡፡ይሄን በሰማ በደቂቃዎች ውስጥ የግርማን ግንባር በርቅሶ እንደሚገላግለው እርግጠኛ ነው፡፡ጥያቄ ሊሆን የሚችለው ከዛስ የሚለው ነው….? እሷ የሌለችበት አለም እየኖረ እሷ የማትስበውን አየር እየሳበ መቀጠል ይችላል ወይስ እሱም እራሱን አጥፍቶ ይላገላል?፡፡እርግጠኛ መሆን አልቻለም…፡፡መንገድ ጠርዝ አቁሟት ወደነበረችው መኪና መጓዝ ጀመረ፡፡ቀጥታ አሁን ግርማን አግደው ወደአስቀመጡት ቦታ ነው የሚሄደው….ቁልፉን አወጣና ሪሚቱን ተጭኖ  የመኪናውን በራፍ ለመከፍት በሚስብበት ቅፅበት ሁለት ከእሱም የሚገዝፉ ጠብደል ጎረምሶች ልክ እንደ ቅርብ ወዳጅ ከግራና ቀኝ መጥተው ከበቡት፣..በግራ በኩል ያለው እንደውም እጁን ትከሻው ላይ ጣል አደረገበት እና አቀፈው ፡፡መንግስቱ ግራ ገባው…መልካቸውን ተመለከተ ..ካለዛሬም አይቷቸው አያውቅም…ኪስ አውላቂዎች ነበር የመሰሉት… በቀኝ በኩል ያለው ከትልቅ ጃኬቱ እጅን እንደከለለ የሆነ ነገር ወደጎኑ አስጠጋ ..ቆረቆረው፡፡ሹጉጥ መሆኑን አወቀ፡፡
‹‹ነፍሱ ግርግር ሳትፈጥሪ ወደ መኪናው ግቢ ››አለው፡፡
ቀስ ብሎ ገባ ..አንደኛው ቶሎ ብሎ ከኃላ ወንበር ገባ እና ሽጉጡን በስር አሾልኮ ትከሻው  አካባቢ ደቀነበት…ሌለኛው ዘና ብሎ ዞረና ገቢና ገባ፡፡
‹‹በል አሁን ወደ አስኮ ንደው፡፡››
‹‹አስኮ…ለምን?››
‹‹ለሽርሽር…ባክህ አትቀልድ…ወይ ንዳው ካለበለዚያ እዚሁ ደፍተንህ እንሄዳን…ሁለቱም ይመቸናል፡፡››አለው፡፡

መኪናዋን አንቀሳቀሰና ወደአሉት አቅጣጫ አስተካክሎ መንዳት ጀመረ….መንግስቱ ሲጠጣ ከቆየው መጠጥ ጋር ተቀላቅሎ ያጋጠመው ነገር ብዥ እንዲልበት አደረገ…በጣም ነው ግራ የተጋባው..በዚህ ቀን ማን ነው ሊያሳግተው የሚችለው?‹‹አጋቹ ሲታገት›› የሚል ፊልም እየሰራሁ ይሆን እንዴ? ሲል በውስጡ አሰበና ፈገግ አለ፡፡
አጎቱ ትዝ አለው‹‹አጎቴ ነው የላካችሁ?››
‹‹እንዴ አቶ ግርማ አጎትህ ነው እንዴ?›› አንደኛው ጠየቀው፡፡
ክው አለ….‹‹ግርማ ነው ያሳገተኝ?››ጠየቀ…ያሳገተው ሰው በየት በየት ዞሮ ሊያሳግተው እንደቻለ ሊገባው አልቻለም፡፡
‹‹ነፍሱ ዝም ብለሽ ነጂው….ሁሉን ነገር ስትደርሺ ታይው የለ….?ያው እኛ ስራችንን እየሰራን ነው..ነገሩን ፐርሰናል አትድርጊው፡፡››
ሊደራደራቸው ፈለገ‹‹…አይ ችግር የለውም …ስራችሁን እየሰራችሁ እነደሆነም ይገባኛል..ግን ቀጣሪያችሁ ከሚከፍላችሁ እጥፍ ልከፍላችሁ ችላለው…››
‹‹ጥሩ ነበር…. ግን የሞያ ስነምግባራችን አይፈቅድልንም…በዛ ላይ ስራ ያበላሽብናል፡፡››
‹////
ትዕግስት እና እዝራ እዛው በተቀመጡበት ሆነው ሲጠጡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት  ሆነ…..በተለይ ትዕግስት  በመጠጡ እየተዳከመች ነው …እዝራ ያው ቀኑን ሙሉ የመጠጣት የብዙ አመት ልምድ ስላለው ገና ብዙ የሚቀረው ይመስላል፡፡
‹‹ጋሽ እ…ዝራ››ጠራችው ትዕግስት፡፡
‹‹ወዬ ትእግስት፡፡››
‹‹ወደቤ…ት ወሰደኝ››
‹‹ምነው ደከመሽ እንዴ?››
‹‹አዎ ..በጣም …ነው የደከመኝ…. እዚሁ ጠረጴዛ ላይ ልወድቅ ነው››
‹‹እኔ ደግሞ ገና አልጠገብኩም….››
‹‹ስለዚህ ምን ይሻላል….?እዚህ ተ…ዘርሬ ብወድቅ አላሳዝንህም?››
‹‹በጣም ታሳዝኚኛሽ…ግን እንዲህ ማድረግ እንችላለን…እዚህ ክፍል እንያዝና መጠጣችንን ይዘን እንግባ..አንቺ ትተኛለሽ እኔ ደግሞ  አንቺን እየጠበቅኩ መጠጣቴን ቀጥላለሁ፡፡››
‹‹አይ ጭንቅላት…ሁሌ እኮ እንዳስደመምከኝ ነው››እጇን አውለበለበችና አስተናጋጁን ጠራችው..ሂሳብ ነው የጠየቀችው….የታሰረ እሽግ ብር ከቦርሳዋ አወጣችና ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠቸ…ሂሳብ ከፍለው ከጨረሱ በኃላ ጋሽ እዝራ በአንድ እጁ  እሩብ የቀረለትን የውስኪ ጠርሙስ ይዞ በሌላው እጁ እሷን ደግፎ  ወደ ሪሴፕሽን ሩም ሄዱና አንድ ክፍል ተከራይተው ተያይዘው ገቡ፡ጫማዋን አውልቃ በቁሞ ነው አልጋ ላይ የተዘረረችው፡፡እዝራ በራፉን ዘጋና የመጠጥ ጠርሙሱን ይዞ ክፍል ውስጥ ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ተቀመጠ….ከዛ ከኪሱ ውስጥ ሮዝማን ሲጋራውን እና ላይተሩን አወጣና ለኮሰ…መጠጡን እየተጎነጨና ሲጋራውን እያቦነነ በተመስጦ ይመለካታት ጀመር.. ከሴት ጋር አንድ  ክፍል ውስጥ እንዲህ ተፋጦ ሲቀመጥ ስንት አመት አለፈው?፡፡ትዝ አይለውም፡፡
ተኝታለች ብሎ ሲጠብቅ‹‹ጋሽ እ…ዝ…ር››ብላ ጠራችው፡፡
‹‹አቤት››
‹‹ቤቱ እየተገለባበጠብኝ ነው፡፡ሻወር መውስድ ፈልጋለሁ…››
‹‹ብተኚ አይሻልሽም..ስትነሺ ያልፍልሻል››
‹‹አይ መተ…ኛት አይደ…ለም የምፈልገው…እባክህ ደግፈህ ወደ ሻ…ወር ውሰደ…ኝ ፡፡››
ጥያቄዋን ፍላጎቷ ግራ ቢያጋባውም እምቢ ሊላት አልፈለገም..እያጨሰ ያለውን ቁራች ሲጋራ አጠፋና   በእጁ ይዞ የነበረውን ጠርሙስ  አጠገቡ ባለ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠና እራሱን አበረታቷ ተነሳ፡፡ ወደአልጋው ተጠጋ፡፡ክንዷን ያዘና ወደላይ ጎተታት…ተነሳች፡፡ ትከሻው ላይ ተደግፋ እግሯን የመጎተት ያህል እያንቀሳቀሰች ወደሻወር ቤት ተያይዘው ሄዱ…ከፈተና ወደውስጥ ይዟት ገባ፡፡
‹‹ጋሽ እዝራ››
‹‹አቤት››
‹‹ስብ..ር..ብር አልኩ እኮ….››
‹‹እንደአልሽው አሁን ውሀ ሲነካሽ ትጠነክሪያለሽ፡፡››
‹‹እሺ ውሀውን ክፈትልኝ…ቆይ መጀመሪያ ልብሴን ላውልቅ..››
‹‹በቃ እኔ ልውጣልሻ››
‹‹አይ ማውለቁን አግ..ዘኝ እንጂ….አልች…ልም አ…ኮ››
‹‹እርግጠኛ ነሽ››
‹‹ችግር የለውም….አውልቅልኝ…›››
‹‹እሺ ካልሽ….››አለና ያግዛት ጀመረ…ሰውነቷ ላይ ሰማያዊ ፓንት ብቻ ቀረ…
‹‹አሁን በቃ ››ብሎ ሊወጣ ሲል ወደራሷ ጎተተችና ተጠመጠመችበት…እዝራ ግራ ገብቷት ምን ማድረግ እንዳለበት በማሰብ ላይ ሳለ ትእግስት እጆቾን ዘርግታ ውሀው እስከመጨረሻ ከፈተችው….ሁለቱም በውሀው ረሰረሱ…በተለይ እዝራ ከእነልብሱ ነው የረጠበው…ይሄም ጉዳይ ትእግስትን በጣም አዝናናት
‹‹ምንድነው የሰራሽው…?››
‹‹እኔ እንጃ …እንደህ አድርጊ አድርጊ አለኝ…..በቃ አውልቀው..››
ምርጫ ስላልነበረው አወላለቀውና እርቃን ቀረ….እራቅ አለችና አፍጥጣ አየችው‹‹…ጋሽ እዝራ በጣም እንደምወድህ ግን ታውቃለህ››ስትል ያልጠበቀውን ነገር ጠየቀችው፡፡
‹‹አላውቅም….እንዴት ግን እኔን ልትወጂኝ ቻልሽ….?ምርጫሽ ጥሩ አይደለም፡፡››
‹‹ፍቅር የምርጫ ጉዳይ እኮ አይደለም…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው..ፍቅር የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን መለከፍ ነው…ድንገት በመብረቅ መመታት››
ትዕግስት ውሀው ሰውነቷን ሲያረሰርሳት ይሆን  የእዝራን እርቃን ገላ ማየትና ሰውነቱን ሳሙና እየመታች ስታሸው  በውስጧ ተዝለፍልፎ የነበረውን ጥንካሬዋን ሲያገግምና ሲበረታ ታወቃት….
‹‹ትእግስት….››ጠራት እዝራ፡፡
‹‹ወዬ››
‹‹ለአሮራ ስሟን ያወጣሁላት እኔ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ…?››
‹‹አላውቅም….አንተ ነህ ያወጣህላት? ››
‹‹አዎ እኔ ነኝ ያወጣሁላት… አሮራ ማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ብልጭ ስትል የምታያት ልብ ሰንጣቂ  የፀሀይ ብርሀን ማለት ነው…በሌላ ጎኑም ማታ ለመጨረሻ ጊዜ ውስጥሽ በፍራቻ እየተሸበረ እያየች ግን ደግሞ ተሠናብታሽ የምትጠልቀው የመጨረሻዋ የፀሀይ ፍንጣቂ  ማለት ጭምር ነው።ስሙ ኢጣሊያን እያለሁ እስክሞት ድረስ አፍቅሬያት የነበረችው ስፔናዊት ፍቅረኛዬ ስም ነው….እሷ ስትሞትብኝ ነው ሁሉን ነገር ጥዬ ወደሀገር የተመለስኩት ..በዛን ወቅት አሮራ የሁለት አመት ልጅ ነበረች…ሌላ ስም
👍778🤔1
ነበራት እኔ ግን አሮራ አልኳት ከዛ እሱ ጸደቀላት..››
‹‹ያሳዝናል…››
‹‹አዎ ሀያ አንድ አመት ሙሉ አዝኛለሁ…አሁን ልግርሽ የፈለኩት…ይሄ ነገር ይቅርብን ለማለት ነው..››አለና ከውሀውም ከእሷም ራቅ አለ…፡፡
‹‹ለምን ?ደስ አልልህም?››
‹‹አይ….እንደዛ አይደለም..እኔ አንዴ ካፈቀርኩሽ  ላጣሽ አልፈልግም…ፍቅሬ የሞኝ ነው…ብትተይኝ ወይም ጥለሺኝ ብትሂጂ መቋቋም አልችልም.›› አለና ከመስቀያ ላይ ያለውን አንደኛውን ፎጣ ይዞ ሰውነቱን እያደራረቀ ወጣ…..ከዛ ወዲያው ሲጋራውን ከፀረጴዛው ላይ አነሳና ለኩሶ ከሀሳቡ ጋር አንድ ላይ ቀላቅሎ ሟብነን ጀመረ….እሷም ጊዚ አልፈጀችም …፡፡ ለብሳ የነበረው ፓንት አውልቃ ጣለችና  ሌላውን  ፎጣ በማንሳት ሰውነቷን እያደራረቀች   ከሻወር ወጥታ ወደእሱ ሄደች…


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍757
#አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-40
#ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ነው። ትዕግስት ስልኳ ሲጠራ እዝራ ደረት ላይ ተኝታ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ነበር። ተንጠራራና ስልኩን አንስቶ ሰጣት።አየችው ።የምታውቀው ቁጥር አይደለም።ግራ በመጋባት ውስጥ ሆና አነሳችው።
"ሄሎ"ነጎድጓዳማ  እና የሚገፋተር ድምፅ  ነው።
"ትዕግስት ነሽ?"
"አዎ ነኝ...ማን ልበል? አላወቅኩህም።"
"አታውቂኝም ክንዴ እባላለሁ...መንግስቱ  ነበር ከቀናት በፊት  ስልክሽን የሠጠኝ....የእኔ ስልክ ካልሰራልህ በእሷ በኩል ታገኘኛለህ ብሎኝ ነበር"
"እሺ ምን ልታዘዝ?"
"ሰባት ሰዓት አካባቢ ደውዬለት ወደአንተ እየመጣሁ ነው ብሎኝ ነበር ።ከዛ ስልኩ ይጠራል አይነሳም አሁን ደግሞ ጭራሽ አይሰራም.....ምን ነካህ እቃውን ይዘን እየጠበቅንህ ነው በይልኝ።"
"ምን? የምን ዕቃ?"
ስልኩ ተቋርጧል።
መኝታዋን ለቃ ወረደችና እርቃኗን ወለል ላይ ቆመች።
"ምንድነው ችግር አለ?"እዝራ ነው ግራ በመጋባቷ ግራ ተጋብቶ የጠየቃት።
"እኔ እንጃ ...በደንብ አልገባኝም"መንግስቱ ጋር ደወለች። አይጠራም።ገስትሀውስ ደወሐለች..በአይን ካዩት   ሶስት ቀን እንደሆናቸው ነገሯት።
"ወይኔ ጉዴ?!!!ልጅ ምን ሆነ? ክንዴ ነኝ ብሎ የደወለላትን ልጅ ጋር ደወለችለት።
"ወንድሜ ይመስለኛል በጠቀስከው ሰዓት እኛ ጋር ነበረ ..ስትደውልለት ወደአንተ ነበር የመጣው"
"ታዲያ ወደእኔ እየመጣ ከሆነ የሰላሳ ደቂቃ አምስት ሰአት ሙሉ ምን ይሰራል?"
"እኔም አልገባኝም"
"እና ምን ላድርግ? እቃውን ልልቀቀው?"
"ምንድነበረ ስምምነታችሁ?"
"መጥቶ ሊያናግረውና ሰውዬውን ተረክቦ ብራችንን ሊከፍለን ነበራ።"
"አሁን የዕቃው ምንነት ገባት።"
"በቃ ሁኔታውን አጣርቼ መልሼ ደውልልሀለው"
"ቶሎ በይ ካልሆነ ዕቃውን ወደቦታው እንመልሰዋለን።"
"አይ...እሱ ካልመጣ, እኔ መጣለሁ..ስንት ብር ነበር የተስማማችሁት።"
"መቶ ሺ ብር ተስማምተናል።ሰላሳ ከፍሎናል።"
"በቃ እስከጥዋት አቆዩት ፤እስከዛ መንጌ እንኳን ባይገኝ እኔ ጥዋት ቦታው ድረስ ብሩን ይዤ እመጣና እቃውን  ትሰጡኛላችሁ"
"እንደዛ ከሆነ አሪፍ ነው...በቃ ቸው የደረሺበትን ደውለሽ አሳውቂኝ"
"እሺ...ዕቃውን ፎቶ አንስተህ በዚህ ቁጥር ትልክልኛለህ?"
"ይቻላል"ስልኩ ሲዘጋ እዝራ ልብሷን ከመታጠቢያ ቤት አምጥቶ  እንድትለብስ እያቀበላት ነበር።
"ያንተስ አልደረቀ?"
"ለበስኩት እኮ...ከጃኬቱ በስተቀር ሌላው ምንም አይልም"
"በቃ ስንወጣ ጃኬት እንገዛለን ...እኔም ፓንቴ ስላልደረቀ ባዶ ቂጤን መሆኔ ነው።"
"አስወልቆ ሚያይሽ የለ ምን ችግር አለው።ለመሆኑ ምን እየተከሰተ  ነው?"
"እኔ እንጃ ።እየሆነ ያለው እኔንም ግራ እያጋባኝ ነው።መንግስቱ እምጥ ይግባ ስምጥ የሚያውቅ ሰው የለም...ወንድምህ ግርማ ደግሞ..."ንግግሯን ሳትጨርስ  ስልኳ ድምፅ አሰማ... ከፈተችው።እና ቀጥታ ለእዝራ አቀበለችው።የወንድሙ የግርማ ፎቶ ነው።እጅና እግሩ ከወንበር ጋር ታስሮ ሲቁለጨለጭ ይታያል።"
"ማነው ያሳገተው?"ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ጠየቃት።
"ማን ይሆናል ?መንግስቱ ነዋ ።የሚገርመው አሳግቶት የት እንደጠፋ ነው?"ለማንኛውም ተነስ እንውጣና እየሄድን ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገር።"
"እሺ"አለና በሀሳቧ ተስማምቶ ተከተላት።
መንግስቱ ይገኝበታል ብለው የሚጠረጥሩት ቦታ ሁሉ እስከምሽቱ አራት ሰዓት እየተዞዞሩ ፈለጉ...ያቃቸዋል ብለው የሚገምቱት   ሰዎች ጋር ሁሉ እየደወሉ ጠየቁ።አንዳቸውም መንግስቱን እንዳላዩት አረጋገጡላቸው።እሷ ጋም መንግስቱን ፍለጋ የደወሉ ሰዎች ነበሩ።ከካናዳ የተመለሠው አጎቱና ሚስቱ ውቢት በየተራ ደውለውላት መንግስቱ የት እንዳለ የምታውቅ ከሆነ ጠይቀዋት ነበር።እንደማታውቅና ካገኘችው እየፈለጉት እንደሆነ  መልዕክቱን እንደምትነግረው ነግራቸው ነበር...።
"አሁን ከዚህ በላይ ምንም ማድረግ የምንችል አይመስለኝም...ባይሆን ይንጋና ጥዋት ማድረግ የምንችለውን ነገር እናያለን?"
"ትክክል ነሽ"በቃ ወደቤት እንሂዳ አላት እዝራ።ትእግስት ስለእዛ ቤት ስታስብ የሚታያት በደም የተጨማለቀ አንሶላ...ሽጉጥና የአሮራ በጥይት የተበሳሳ ሰውነት ነው።
"አይ እዛ ቤትማ አልሄድም... "

"በቃ  ቤርጎ እንያዛ..."
"እሺ ..ጥሩ ሀሳብ ነው"
"ቆይ እዚህ ሰፈር ያለውን የግርማን ቤት ታውቀዋለህ"
"አዎ አንዴ አይቼው ነበር...ምነው"
"ዘበኛው ካስገባን እዛ እንደር"
"ዘበኛው እኮ እታች ቤት የሚሰራ ነበር...በደንብ ነው የማውቀው"
እና እንሂድ "
"አዎ እንሂድ"ለላደው ቦታውን ነገሩት።ወደእዛው መንዳት ጀመረ።
እዝራ ሲከነክነው የነበረውን  ጥያቄ ጠየቃት"እቤቱን እንዴት አወቅሽው?"
"እንዴ የአሮራን የመጨረሻ ክሊኘ የተቀረፀው እኮ እዚህ ቤት ነው ...ሶስት ቀን አድረናል"
"እ...እንደዛ ነው?"አለ ፈገግ ብሎ።
"አዎ...አይዞህ ከወንድምህ ጋር ምንም የተፈፀመ ነገር የለም....ማለቴ ሙከራው ነበረ ..ግን ሙከራ ብቻ ነው።"
"ይሁን"
ደረሱና ለላዳው ተገቢውን ክፍያው ከፍለው አሰናበቱት እና 
ወደ ጊቢው ተጠጉ።ጭልምልም ብሏል። ከዚህ  በፊት በውጭ መብራት ድምቅምቅ ያለ ነበር።የውጩን መጥሪያ ደጋግመው ተጫኑ።ከደቂቃዎች በኃላ"ማን ነው?"የሚል ድምፅ ከውስጥ ተሰማ።
"ጋረደው እኔ እዝራ ነኝ  ክፈት...ግርማ ልኮኝ ነው?"
የውጩ የብረት በር ወለል ብሎ ተከፈተ...ከፍቹ በበራፉ እራሱን ከልሏል..ትዕግስትና እዝራ ተከታትለው ገብ።በራፍ በፍጥነት ተዘጋ ።ፊት ለፊታቸው ጠብደል ወጠምሻ የሆነ ሰው ሽጉጥ ደቅኖባችዋል።የጠበቁት ጋረደው በቦታው የለም።ደነገጡ።
"ምንድነው...እኔ እዝራ ነኝ የግርማ ወንድ?"
"ሠማሁህ እኮ...አሁን ቀጥሉ ..ወደቤት ግብ"ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ።
እጅ ለእጅ ተያይዘው  እንዳላቸው ወደቤት ተንቀሳቀሱ። ግቢ ውስጥ አራት የሚሆኑ ክላሽ ጭምር የታጠቁ ሰዎች ፈንጠርጠር ብለው በጥንቃቄ ቆመዋል።ሳሎን ሲገብ ወደ ውስጥ (ወደ መኝታ ቤቶች) የሚወስደው  ኮሪደር ላይ ሌሎች ሁለት መሳሪያ  የታጠቁ ሰዎች ይታያሉ።ይዟቸው የመጣው ሰው የደቀነባቸውን  ሽጉጥ  ወደጎኑ መልሶ ሻጠና ወደ ሳፋው በአገጩ እየጠቆመ ተቀመጡና  ለምን እንደመጣችሁ አስረድኝ?"አላቸው።
እንዳላቸው ተቀመጡና በፍራቻ መቁለጭለጭ ጀመሩ።
ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11312🔥8
አራዳ ተንዶ ፡ መሰረቱ ታየ፣
ገና ብዙ ያያል ፡ ሸገር ላይ የቆየ።
😢51🤔8👍2😁1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-41
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከበራፍ ተቀብሎ ወደውስጥ በማስገባት ሶፋ ላይ እንዲቀመጡ ያዘዛቸው የአጋቾቹ መሪ የሚመስለው  ሰው ፊት ለፊታቸው ተቀምጦ በዝምታ እየተመከታቸው ነው፡፡አስተያቱ ደግሞ በሁለቱም ውሰጥ ሽብር ነዛባቸው፡፡ ከተቀመጠበት ድንገት ተነሳና…‹‹እስክመለስ ድረስ ለምን እዚህ እንደመጣችሁ እሰባችሁበት ጠብቁኝ››አለና ተነስቶ ወደውስጥ ገባ፡፡
‹‹ምን ማለት ፈልጎ ነው…?ይሄ ሁሉ ሰራዊት እዚህ ቤት ውስጥ ምን ይሰራል…..?ችግር ውስት ገባን ማለት ነው?››ትእግስት ነች ጥያቄዎቾን ደራርባ እዝራን የጠየቀችው፡፡
‹‹አላውቅም…ቆይ እስኪ በፀጥታ ላስብበት…የሆኑ የሆኑ ነገሮች እየተገጣጠሙልኝ  ነው››አለትና አይኖቹን እንደመጨፈን ብሎ በጥልቀት ማሰብ ጀመረ፡፡
እዝራ አእምሮውን ጥልቅ ደረስ ዘልቆ  በረበረ…ስለወንድሙ አካሄድና አንዳንድ ፈላጎቶች አሰበ ..እና እሱን ለመቋቋምና ለሌሎች ሰዎች  ሳይጎዱ እሱ ባጠፋው ጥፋት ልክ ቅጣቱን ማግኘት እንዲቸል ለማድረግ እንዲያስችለው ነገሮችን  በንቃት ማድረግ እንዳለበት ወሰነ ፡፡በንቃት  ላይ ያለ ሠው  ደግሞ አሁን ላይ መገኘት፤እያንዳንዶን ደቂቃና ሰዓት በጥልቀት መኖር፤ነገሮችን ባሉበት ተፈጥሯዊ ይዘት የመቀበል ችሎታ  እና የሌላውን ህመም በጥልቀት መረዳት ብቃት ሊኖረው የግድ ይላል፡፡እና እዝራ ሀሳብን እልባት ሳያበጅለት  አጋቹ መጣና ጥሎት በሄደበት ቦታ ከእነሱ  ፊት ለፊ ቁጭ አለ፡፡
‹‹እሺ..እዚህ ምን እግር ጣላችሁ?አሁን ልሰማችሁ ዝግጁ ነኝ››አላቸው፡፡
እዝራ ከዚህ ትርምስም  እሱንም ሆነ ሌሎችን የሚወዳቸውን ሰዎች በጥበብ ይዞ መውጣት እንደዳለበት ወስኗል ፡፡አዎ አሁን በንዴት ሳይሆን በስሌታ ማሰብ እንዳለበት እራሱን አሳመነ  …..መጀመሪያ የጠረጠራቸው ነገሮች በትክክል የተፈጸሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳበት ተሰማው… አእምሮውን ለመጠቀም ወሰነ‹‹ከወንድሜ ጋር ወደ እዚህ ቦታ አብረን ለመምጣት ተቃጥረን ነበር፡፡ከዛ ግን ጠፋብኝ…ማለቴ ስልኩ ሁሉ አይሰራም…ሌሎች ቦታዎች  ከፈለኩት በኃላ ምን አልባት በስራ ውጥረት ተዘናግቶ እኔን እረስቶኝ ወደእዚህ መጥቶ ይሆናል ብዬ በመጠራጠሬ ነው የመጣሁት››ሲል ቦታው ላይ የተገኙበትን ምክንያት አብራራለት፡፡
‹‹በዚህ ምሽት  አራት ሰዓት ካለፈ በኃላ?፡፡››ሰውዬው የተናገረውን አንዳላመነው በሚያሳብቅ የድምፃ ቅላፄ ጠየቀው፡፡
‹‹አይገርምም…በጊዜ ከእሷ ጋር ተገናኘተን ትንሽ እየቀማመስን እየተዝናናን ነበር….ከዛ ወደቤት ለመሄድ ላዳ ውስጥ እንደገባን ወንድሜ ጥዋት ወደእዚህ ቦታ እንሄዳለን ብሎኝ እንደነበረ ትዝ አለኝና ላዳው ወደእዚህ እንዲያመጣን ነገርኩት..ይሄው ነው….አሁን ወንድሜ የት ነው?ላናግረው እንደምፈለግ ንገረው፡፡››ማስመሰሉን  ቀጠለበት፡፡
‹‹ወንድምህ እዚህ እንዳለ በምን አወቅክ?››
‹‹ ነገርኩህ እኮ!1ሌላ ቦታ እንደሌላ  አረጋግጬለሁ…እዚህ ካልሆነ ሌላ የት ይሆናል?ብዬ ነዋ››
‹‹እንግዲያው እርምህን አውጣ …ወንድምህ  እዚህ የለም….እኛም ቀኑን ሙሉ ስንጠብቀው ነው የዋልነው››መለሰለት
‹‹ልጁስ ?››እዝራ እንደዋዛ ቀጣዩን ጥያቄ ሰነዘረ፡፡
‹‹የቱ ልጅ?››ኮስተር ብሎ
‹‹መንግስቱ ነዋ…የያዛችሁት ልጅ››
‹‹አለ …ከጀርባ ባለው ክፍል  ነው››
እዝራ በእርካታ ተነፈሰ….ትእግስት በእዝራ ብልጠት ተደመመች‹‹እና ኮሪደሩ ላይ ያሉት ጓደኞችህ ምንድነው የሚጠብቁት?››ስትል ለአጋቹ ሌላ ጥያቄ አቀረበችለት፡፡
‹‹ልጁቷን ነዋ…ስለሷ አልነገራችሁም እንዴ..?እርግጥ እሷን እኛ አይደለንም ያገትናት  ..ቀደም ብላ እዚህ ነበረች›››
‹‹አሮራ ነች?››እዝራ ትንፋሽ በሚያሳጣ ድንጋጤ  ውስጥ ሆኖ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ ..ዘፋኟ….የገዛ ልጁን ለምን እንዳገታ አልገባኝም….?ምን አልባት ወንድ ላይ እየጠንጠለጠለች አስቸግራው ሊሆን ይችላል…..››የራሱን ግምት በማስቀምጥ ማንነቷን አረጋገጠላቸው፡፡
ሁለቱም ልክ እንደነተነጋገረ ሰው ከመቀመጫቸው በርግገው በመነሳት ወደኮሪደሩ ተንደረደሩ…ጠባቂዎቹ መንገዳቸው ላይ እጃቸውን ሰትረው በመደርደር ግድግዳ ሆነው አገዷቸው…ሲያወራቸው የነበረው ሰው ከኃላቸው መጣና‹‹ሰዎች እሷን ለማነጋር የግድ የግርማ ፍቃድ ያስፈልጋል››አላቸው፡፡
‹‹ግርማ እኮ አሁን እዚህ የለም …መፍቀድ የምትችለው አንተ ነህ››
‹‹አይ አቶ ግርማ እዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አቋም በግልፅ ነው የነገረኝ …ልጅቷ ያለእሱ ፍቃድ ማንም ሊያናግራት አይችልም…ከቻላችሁ በስልክ አግኙትና ….ያናግሯት  ብሎ ይንገረኝ፡፡››
ትእግስት ስሜቷን መቆጣጠር አቅታት‹‹እንደውም እስከአሁን የነገርንህን ሁሉ እርሳው…ከግርማ ጋር የተነጋርከውን ብር ለማግኘትና ችግር ሳይፈጣር ከዚህ ጣጣ ውስጥ ለመውጣት ከፈለክ ከእኛ ጋር መስማማት የግድ ይልሀል››አለችው ፍጥጥ ብላ፡፡
ሰውዬው ኩስትርትር አለ‹‹አልገባኝም ..ከእናንተ ጋር ምን ይሁንልኝ ብዬ ነው የምስማማው…የቀጠረን ግርማ ነው…ብራችንንም የሚከፍለን እሱ ነው፡፡እስከአሁን እንደውም ለምን እንዳልመጣና እንደዚህ አይነት እርስኪ ያለው ስራ ካሰራን በኃላ እንዴት እንደዚህ  እንዝላል እንደሆነ ገርሟኛል በዛ ላይ እናንተ እኮ በእኔ ቁጥጥር ስር ነው ያላችሁት...አልገባችሁም እንዴ? አሁን እኮ በቃ ታጋቼ ሆናችኋል፡፡››
‹‹እንደዛ እንኳን አይመስለንም …ይሄንን ምንነግርህ ግርማ መምጣት ስለማይችል ነው››አለው እዝራ፡፡
‹‹መምጣት እንደማይችል!! በምን አወቅክ…?አሁን ከጥዋት ጀምሮ ፈልጌ አጣሁት ስትል አልነበረ እንዴ?››
‹‹ዋሽቼህ ነው፡፡››
ሰውዬው ትዕግስቱ ተሞጠጠበትና ሽጉጡን ከሻጠበት መልሶ አውጥቶ ደቀመነባቸው‹‹መቀባጠሩን አቁማችሁ ትክክለኛ እየሆነ ያለውን ነገር ንገሩኝ…ካለበለዛ ግንባራችሁን አፈራርሰዋለሁ፡፡››
ትእግስት‹‹ቆይ›› አለችና ስልኳን በማውጣት ደወለች‹‹ሄሎ ክንዴ››
‹‹ሄሎ ትእግስት መንጌ ተገኘ እንዴ?››
‹‹አይ እስከአሁን እያፈላለኩት ነው…ግን አሁን የደወልኩት እስከጥዋት ተመልሶ ማይማጣ  ከሆነ ጥዋት ሁለት ሰዓት ድረስ ብሩን ይዤ ለመምጣት እንደተዘጋጀው ልነግርህ ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ያስማማናል››
‹‹ከዛ ግርማን ታስረክበኛለህ ››
‹‹ምን ጥያቄ አለው..ዝግጁ ስትሆኚ ደውይልኝ …የእኛ ልጆች ያገኙሽና በጥንቃቄ ..ማለቴ ፖሊስና ሌላም ሰው እንደማይከተልሽ እርግጠኛ ከሆኑ በኃላ ወዳለንበት ያመጡሻል፡፡››
‹‹እሺ አመሰግናለሁ… ቸው››ስልኩ ተዘጋ፡፡
ሽጉጥ የደቀነባቸው የመንግስቱ አጋች‹‹እና አጋቹን ያሳገታችሁት እናንተ ናችሁ ማለት ነው?››ሲል በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹አይ ያሳገተው መንግስቱ ነበር..እኛ አይደለንም››ትእግስት መለሰች
ከት ብሎ ሳቀ…‹‹የሚገርም የፊልም እስክሪፕት ይወጣዋል..ታጋቹን አላመንኩትም እንጂ ሊነግረኝ ሞክሮ ነበር..ይገርማል….!!ቆይ አንተም በወንድምህ መታገት እጅህ አለበት?››ወደ እዝራ ዞሮ ጠየቀው፡፡
‹‹የለሁበትም…መታገቱ ግን ይገባዋል ባይ ነኝ..አሁን አስገባንና አሮራን እንያት… ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ዋናው ምክንያት የእሷ ከእይታችን መሰወር ነው…እሷ ጤና መሆኗን እንይና ከዛ ቁጭ ብለን ሁላችሁም ብራችሁን አግኝታችሁ ማንም ሰው ሳይጎዳ ከዚህ ትርምስምስ  የምንወጣበትን እና ወደየህይወታችን  የምንመለስበትን  ሁለታ  ላይ ቁጭ ብለን እንነጋገራለን፡፡››
👍644🥰1😁1🤔1
አጋቹ የእዝራን ንግግር ከሰማ በኃላ ወደትእግስት ዞሮ‹‹አንቺ መንግስቱ ምንሽ ነወ?››ሲል ተየቃት
‹‹ጓደኛዬ››
‹‹ ግርማስ? የት ነው ምታውቂው..?››
‹‹የእሱ ሰራተኛ ነኝ..ማለቴ የአሮራ ረዳት ሆኜ ነው የምሰራው፡፡››
አጋቹ በድጋሜ መገረም ሳቅ   ሳቀ…..‹‹እርስ በርሳችሁ ነዋ እየተጠፋፋችሁ ያላችሁት››

እዝራ‹‹እንደዛ መሰለኝ..ስለዚህ ምንልህን  ስማትና አሁን ወደ አሮራ አስገባንና እንያት ….ከዛ ቁጭ ብለን እናንተም ገንዘባችሁን ሳታጡ..ሌላ ወንጀል ውስጥም ሳይገባ ሁኔታዎችን እናስተካክላለን…በዛ ቃል እንገባልሀለን፡፡››አለው፡፡
እንደማሰብ አለና ‹‹ስልካቸውን ተቀባሏቸውና አስገቧችው››ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ስልካቸው ተቀብለውና ፈትሸው ከመንገዳቸው ዞር አሉላቸው…እዝራና  ትእግስት የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፍተው ተከታትለው ወደውስጥ ሲገቡ አሮራ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነበረ ያለችው…ትእግስት ዘላ አልጋ ላይ ወጣችና ወዘወዘቻት፡፡አሮራ ከእንቅልፏ ባና አይኖቾን ስትገልጥ ትእግስትንና አጎቷን በማየቷ ግራ ተጋባች…‹‹የነቃው መስሎኝ ነበር ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ?››ጠየቀች፡፡
‹‹አይደለሽም የእኔ ቆንጆ..የእውነት ነው….አገኘንሽ…በህይወት አለሽ…››ትእግስት መለፍለፏን ሳታቆም እያገላበጠች ትስማት ጀመረ…እዝራም የደስታ እንባ ከአይኖቹ እያረገፈ ግንባሯን ሳመና አልጋውን ተጠግቶ ባለ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡
‹‹እንዴት አገኛችሁኝ …?ጠባቂዎቹ እንዴት ፈቀዱላችሁ…?የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ እንዴ..?ያ የረተረገመ እኮ ዛሬ ወደውጭ ሊልከኝ ነበር..ትኬት ሁሉ ተገዝቶ ነበር…ግን ምን እንደሆነ አላውቅም ቀረ  …እስከመጨረሻው ላጣችሁ ነው ብዬ በጣም ፈርቼ ነበር….›››በማለት ከማያቋርጥ የለቅሶ አጀብ ጋር የሆነውና እና ስላሳለፋቻቸው  የመከራ ቀናት ነገረቻቸው።

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍10016👎3👏3🥰2🔥1
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል
ምዕራፍ-42
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ትእግስት እና  እዝራ ከሁለቱ ወገን አጋቾች ጋር በመነጋገር እና በመደራደር ግርማንና መንግስቱን ፊት ለፊት ለማገናኘት አቅደው ተሳክቶላቸዋል፡፡ከሁለቱም አጋቾች የተውጣጡ ስድስት የታጠቁ  ሰዎች ዙሪያቸውን እየጠበቋቸው አንድ ክፍል ውስጥ እንደበፊቱ እጆቻቸውና እግሮቻቸው ተስረው ሳይሆን ነፃ ሆነው እየተንቀሳቀሱ  ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከአስር  ለበለጡ ደቂቃዎች ቃል ማውጣት የቻለ አልነበረም፡፡
‹‹በጣም ነው የምታስጠላኝ››አለው መንግስቱ ፡፡
‹‹ያደረኩህን ሁሉ ያደረኩት እኮ በራስህው ስህተት ነው…ሁሌ በመንገዴ ላይ ትሰነቀራለህ…በፊት ያሳሰርኩህም አሁን ያሳፈንኩህም ለዛ ነው፡፡››
‹‹አይ የምጠላህ እኔ ላይ ባደረከው ነገር አይደለም…ለዛ ይቅር ልልህ እችላለሁ…፡፡በአንተ አሻጥር መታሰሬ ብዙ ነገር ቢያሳጣኝም መቼም ለገኛቸው የማልችላቸውን ገራሚ የህይወት ልምዶችንም ያገኘሁበት ቦታ ስለሆነ እራሴን እንደተጎጂ እየተመለከትኩ አንተን ስወቅስ መኖር አልችልም፣..እኔ አምርሬ የምጠላህ አሮራ ላይ ባደረከውና እያደረክ ባለኸው ድርጊት ነው፡፡
ምን አደረኳት…?እንዴት ተንከባክቤ እንዳሳደኳት አታውቅም…?የዝና ጣሪያ ላይ እንድትወጣ መደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ አድርጌለሁ…ምን በደልኳት?፡፡››
‹‹የሚገርመው ስትበድላት መኖርህ አይደለም….አሁንም በውስጥህ ምንም አይነት ፀፀት አለመኖሩ ነው….እንዴት ከገዛ ልጅህ ጋር ትተኛለህ?››
ግርማ በጣም ደነገጠ…ይሄንን ነገር ማንም ያውቃል ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር….‹‹ይሄንን እንዴት ነገረችህ?››
‹‹አይ እሷ አልነገረችኝም…እንደማውቅም አታውቅም…ግን ይሄ ሁሉ ውጥንቅጥ ከመፈጠሩ በፊት አንተን በተወሰነ መጠን ሳሰልል ነበር…እና ከእንጀራ ልጅህ ጋር የጎረምሳ አይነት ወሲብ ስትፈፅም የሚያሳይ የተቀረፀ ቪዲዬ አለኝ…ለአሮራ ባላስብ ያንን ቪዲዬ በኢንተርኔት ነበር የምለቀው….ከዛ በዚህ ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ውስጥ እንዴት አንገትህን ቀና አድርገህ መኖር እንደምትችል አይ ነበር?፡፡ግን እሷን አምርሬ ስለማፈቅራት ..እንደዛ ማድረግ አልቻልኩም››
ግርማ እንደበፊቱ ቆጣ ቆጣ የሚለውን ስሜቱን ገርቶ በተዳከመ ድምፅ ጠየቀ‹‹ሌላ ማን ያውቃል…?››
‹‹ስር ስሮ ስትል ላየኋት ትእግስት አሳይቼታለሁ…ወንድምህ አይቷል….ከዚህ ጣጣ በኃላ ደግሞ ፀባይህ እየታየ ሌሎች ቅርብህ ያሉ ሰዎች እንዲያዩት አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ምን ነካህ ደደብ ነህ እንዴ..?እንዴት ለእዝራ ታሳዋለህ…?እንደልጁ እኮ ነው የሚወዳት …በዛ ላይ እብድ ነው ይገለኛል፡፡››
‹‹ቢገድልህ ደስ ይለኝ ነበር..ግን እንደዛ አይነት የተባረከ ንፅህ ሰው በአንተ ቆሻሻ ደም እንዲረክስ አልፈልግም…ያ  ትክክል አይደለም፡፡አሁን ሁላችንንም ትተወናለህ፡፡››
‹‹ሁላችንንም ስትል?››ጠየቀ ግርማ፡፡
ሁላችንንም…እኔንም ፤አሮራንም ፤ትእግስትንም፤ጋሽ እዝራንም…ሁላችንም ከዛሬ ጀምሮ እኛን አታውቀንም ..እኛም አናውቅህም፡፡ያለንበት አትደርስም አንተ ያለህት አንደርስም..ይሄ ያስማማናል፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ….?ከአንተ ጋር እሺ በፊትም አሮራ እንጂ ሌላ የሚያገኛኘን ነገረ የለም…በቀላሉ ላለመደራረስ እንችላለን..ሌሎቹ ግን?››
‹‹ሌሎቹ ምን?››
‹‹ለምሳሌ እዝራ ስራ መስራት ካቆመ አመታት አልፈዋል..በሽተኛ ነው…ከእኔ ብር ካለገኘ እንዴት ይኖራል…?ትግስትም ስራዋን ታሳጣታለህ….አሮራንም እየገነነ ያለው የዘፋኝነት ጉዞዋ ላይ እንቅፋት ነው የምትሆንባት ….ለሁሉም አስፈልጋቸዋለው…ለጊዜው ቢበሳጩብኝም ግን እመነኝ ከእኔው ጋር መቀጠል ነው ሚፈልጉት፡፡››
‹‹እንደዚህ ነው የምታስበው…?››
‹‹አዎ…ግልፅ ነው››
መንግስቱ ከመቀመጫው ተነሳና ቆመ…. አቶ ግርማ ተንደርድሮ ሊያንቀው መስሎት አይኑን አፈጠጠ…መንግስቱ ግን  እግሩን ወደበራፉ አንቀሳቀሰ…..እና አንኳኳ…ተከፈተለት፡፡በራፍ ላይ ያለውን ሰው አነጋገረው..እና ወደቦታው ተመልሶ ተቀመጠ፡፡
በመሀከላቸው መልሶ  ዝምታ ሰፈነ….
‹‹እሺ አሁን ምን እናድርግ?››ግር ነው ጠያቂው፡፡
‹‹ቆይ ጠብቅ አለው….››መንግስቱ
በዛው ደቂቃ በራፉ ተከፈተና ትእግስት አንገቷን አስግጋ ቀድማ ገባች፤ከዛ ጋሽ እዝራ የአሮራን እጅ እንደጨበጣ ገባ…መንግስቱ ተነሳና ተቀበላች…ግራና ቀኝ እሱን ከበው ተቀመጡ….ግርማ በእፍረት አንገቱን ወደምድር አቀረቀረ….
መንግስቱ ንግግሩን ጀመረ……‹‹ወዳጆቼ አሁን ከዚህ ሰው ጋር ስለብዙ ነገሮች እየተነጋገርን ነበር….ከዛ በመጨረሻ ከሁላችንም ትርቃለህ..ከእኔም፤ ከትእግስም ፤ ከአሮራም ሆነ ከወንድምህ ከእዝራ አጠገብ አትደርስም…እኛም አንተ ስር አንደርስም…አልኩት …እሱ ግን ከአንተ እርቃለሁ…ከሌሎቹ ከራቅኩ ግን ሚጎዱት እንሱ ናቸው፡፡ትእግስትም ስራዋን ታጣለች…አሮራም የሙዚቃ ህይወቷ ይበላሻል…..ወንድሜም በእኔ ብር ነው የሚኖረው አለኝ…እኔ እናንተን ወክዬ መወሰን ስላቃተኝ ነው ያስጠራዋችሁ…እና ምንድነው ሀሳባችሁ?፡፡
ትእግስት ጀመረች‹‹እኔ እንኳን እሱ ያለበት ቤት ውስጥ እሱ የሚኖርበት ከተማ ውስጥ ባልኖር ደስ ይለኛል….ስሬ እንዳትደርስ››አለችው፡፡
‹‹ለእኔ ሞተሀል….አበባዬን ቀንጥሰህ ነው ያጠወለግከው…አንዴት ይኖራል ?ብለህ አታስብ …መኖር ቢያቅተኝ በክብር ለመሞት ድፍረት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ስለዚህ ስሬ እንዳትደርስ ››አለው፡፡
አሮራ ጉሮሮዋን አፀዳዳችና መናገር ጀመረች….‹‹እኔ ግን አልስማማም…ዝም ብዬ ልተወው አልችልም››አለች፡፡ ሁሉም በድንጋጤ አይናቸው ፈጠጠ….

የግርማ ፊት በፈገግታ  ፈካ…፡፡እና በፈንጠዝያ መናገር ጀመረ‹‹አውቃለሁ የእኔ ቆንጆ ..የእኔ ነገር እንደማይሆንልሽ በደንብ አውቃለሁ…በመሀከላችን ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት አዝናለሁ…ታያለሽ እክስሻለው፡፡ወደ ውጭም እንድትሔጂ ያሰብኩትን ትቼዋለው….እዚሁ ከእኔ ጋር ነው የምትኖሪው…ለዛ ቃል እገባልሻለሁ፡፡››አላት፡፡

አጎቷ እዝራ ባልጠበቀው መልሷ ግራ ተጋብቶ ‹‹ሮሪ እርግጠኛ ነሽ ከዚህ ሰው ጋር ያለሽን ግንኙነት ማሳቀጠል ትፈልጊያለሽ…?ፈርተሸው ከሆነ እኔ አጎትሽ አለሁ፡፡በህይወቴ ጭምር ከእሱም ሆነ ከሌላ አንቺን ሊያጠቃ ከሚያስብ ሰው ጠብቅሻለው፡፡››አላት ፡፡

‹‹አጎቴ እንደዛ እንደምታደርግ አውቀለሁ፡፡ሁላችሁም እኔን ለመጠበቅ እንደማታቅማሙ አውቀለሁ…ለዛምነው ይሄን ሰው ዝም ብዬ በነፃ ልለቀው የማልፈልገው…እሱነ ከህይወቴ ብቻ በማስወጣት በሰላም እንዲኖር ልፈቅድለት አልችልም…..ልጅነቴንና የዋህነቴን ተጠቅሞ አቆሽሾኛል…እሺ እሱን ይቅር ልለው እችላለሁ….እስክሞት ድረስ ደብድቦኝ ለቀናት አግቶኝ ነበር ፤እሱንም ይቅር ልለው እችላለሁ…ግን የእናቴን ነገር እንዴት ችላ ብዬ እተወዋለሁ?፡፡››ስትል ጠየቀች፡፡
ሁሉም ግራ ተጋብተው እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሮኒ እናትሽ ምን?››እዝራ ነው ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቀው፡፡
‹‹እናቴን በእጆቹ የገደላት ይሄ ሰው ነው….ለዛ ሳይከፍል በነፃ ልለቀው አልችልም››


,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍15014😱3😁2🔥1
(የመጨረሻ ክፍል)
አሮራ
ግማሽ ልቤንና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል 
ምዕራፍ-43
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
🍎🍎🍎
ግርማ ለዘመናት ሸሽጎቸው የነበሩ ሚስጥሮቹ ሁሉ ተዝረክርከውበት  ግራ ተጋብቷል።አሁን የማይፈልጋቸውን ሰዋች ከህይወቱም ሆነ ከአካባቢው እንዴት እንደሚያስወግዳቸው ሳይሆን እራሱን እንዴት ከገባበት ወጥመድና ከእስር ቤት ስጋት ማዳን እንደሚችል ነው እየተጨናነቀ ያለው። በዚህም የተነሳ  አንገቱን ከመድፋት ውጭ  የሚናገረው ነገር አልነበረውም።እዝራ፣አሮራ እና ትዕግስት ፊት ለፊቱ ተቀምጠው  በጥላቻና  በመፀየፍ እየተመለከቱት ነው።
እዝራ  ድንገት አይኖቹን  ወንድሙ ላይ ተክሎ  መናገር ጀመረ"ታላቅ ወንድሜ... በእውነት በዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ ስላንተ በሰማሁት ነገር ሁሉ መደነቄን ልደብቅህ አልፈልግም...እንዴት እንዲህ ደፍሪም ፤ገዳይም ..ዘራፊም ልትሆን ቻልክ?ወላጆቻችን እንዴት እንዳሳደጉን  አውቃለሁ? እንዴት እንዲ ፅንፍ የረገጠ ልዩነት በመሀከላችን ኖረ...?ብቻ እናትና አባታችን እንኳንም በህይወት አልኖሩ..?እንዴ እኔ እንዲህ የተሽማቀቅኩብህ እነሱ ኖረው ቢሆን ኖሮ ልባቸው  እንዴት እንደሚሰበር. ሳስበው ዝግንን ይለኛል።"..
ግርማ የወንድሙን ንግግር ችላ አለና  ወደ አሮራ ዞሮ መናገር ጀመረ...
"በቀደም ባቀረብሽልኝ ነገር ተስማምቼያለሁ"አላት።
"ምንድነው የተስማማችሁት?እኛም እንስማዋ።"ጠየቀ መንግስቱ።
"በቀደም   አንድ መኖሪያ ቤት እና  የኤክስካቨተር ማሽን እንድሰጣትና እንድንለያይ ጠይቃኛለች...ምንም ቢሆን ልጄ ነች... ያንን ባደርግላት ብዙም ቅር አይለኝም...ግን ከእሷም የምፈልገው ነገር አለ ...ይሄ  ስለእናቷ ግድያ...ፓሊስ ምናምን ስለምትለው መረጃ ስለሌለው ነገር መቆፈሩን ታቆማለች..."አለ ...
"አንተ የምትላቸው ንብረቶች እኮ የልፋቴ ውጤቶች ናቸው .. እንተሳሰብ ካልን ንብረቴ  ከዚህ በእጥፍ እንደሚበልጥ እርግጠኛ ነኝ።...የማልከስህ ለምትሰጠኝ ንብረት ስል አይደለም...ለአንተም ሀዘኔታ ተሠምቶኝ ፍፁም አይደለም...አንተን ማልከስህና የማላሳስርህ አንድና ብቸኛው ምክንያት ለትንሿ እህቴ ስል ነው።እሷ አባቴ ምን አጥፍቶ ታሰረ ስትለኝ ምን እመልስላታለሁ?ብዬ ስለማስብ ነው"
"ጥሩ ውሳኔ ነው...ግን እንደእኔ እንደኔ ከእሱ የምትረከቢውን ንብረት ቢቀርብሽ እራሡ ደስተኛ ነኝ..."አላት መንግስቱ።
"ለምን ብዬ ሙልጬን ወጣለሁ..?ስጦታ አይደለም እኮ የጠየቅኩት የለፍሁበትን ንብረቴን ነው...እና ደግሞ እህቴም ከእኔ ጋር እንድትኖር ነው  የምፈልገው።. "
"ሙልጭሽን አትወጪም የእኔ እመቤት ...እኔ ምን ያህል እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ...ፈቅደሽ ብታገቢኝና አብረን ብንኖር ደስ ይለኛል ...ካልሆነም ዛሬውኑ ይሄን ውይይት ጨርሰን  ከእዚህ እገታ ስንላቀቅ አስረክብሻለው።"አላት መንግስቱ
"ምኑን ነው የምታስረክበኝ?።"ግራ በመጋባት ጠየቀችው።
"እኔ ገስት ሀውሱን በስምሽ አዘዋውሬዋለሁ።ያ የ300 ሚሊዬን ብር የሚያወጣው ገስት ሀውስ የእኔም የአጎቴም አይደለም። ያንቺ ከሆነ አንድ ወር አልፎታል።እኔን እሺ ብለሽ አገባሺኝም ብቻሽን ኖርሽም..ወይም ሌላ ሰው አገባሽም  ንብረቱ ያንቺው ነው...ከእሱ ጋር ንብረት መናጠቅ ውስጥ መግባት አያስፈልግሽም"አላት።
እሷ ብቻ ሳትሆን እቤት ውስጥ ያሉት በጠቅላላ በሰሙት ነገር ብዠ ብሎባቸዋል....አሮራ በመገረም ተሞልታ"ለምን ብለህ ነው እንደዛ ያደረከው?"ስትል ጠየቀችው።
"ስለማፈቅርሽ"በአጭሩ መለሠላት።
"እሺ ከወራት በፊት ነው ያደረከው አይደል..ጥሩ በዛን ጊዜ ስለእኔ የነበረህን  ጥሩ ግምት  ነበር  ..ይገባኛል.. ...አሁን ግን ከእዚህ አባት ተብዬ ጋር የነበረኝኝን ግንኙነት አልሰማህም?"
"ሠምቼያለሁ"
"የምታፈቅራት ሴት  የእንጀራ አባቷ መጫወቻ  እንደነበረች ስትሰማ...አልዘገነነህም? "
"አይ አልዘገነነኝም..ግን ደግሞ አልዋሽሽም... አስደንግጦኛልም አበሳጭቶኛልም ።"

"ትክክል እኔም የገመቱኩት እንደዛ ነው ...ከተበሳጨህብኝ ደግሞ በዚህ  ውሳኔህ አትፀናም ማለት ነው"

"አይ ፀናለሁ..ምክንያቱም የተበሳጨሁት በዚህ ሰውዬ እንጂ ፍፁም በአንቺ አይደለም።አንቺ ምን አደረግሽና?"
ሳቀች "እየቀለድክብኝ ነው?"
"ለምን ቀልድብሻለሁ...የምሬን ነው...ለአንቺ ያለኝ ፍቅር  እንዲህ በቀላሉ የሚደበዝዝ አይደለም..."
.ተንደረደረችና ከተቀመጠች ተነስታ ወደእሱ በመሳብ ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት።ሁሉም ያልጠበቁት ስለነበረ ተገረሙ...አቶ ግርማ ግን በሽንፈትና በንዴት አንጀቱ ኩምሸ አለበት። የሚያደርገው ግራ እስኪገባው ድረስ ባለበት ተንቆራጠጠ..
ከመሳሳም ሲላቀቁ ትዕግስት "አንዴ ለብቻህ ላናግርህ?" አለችው።
ምን ሊፈጠር ነው በሚል ሁሉም እርስ በርስ ተያየ...ትዕግስት ከመቀመጫዋ ተነሳችና  የመንግስቱን ክንድ ይዛ አስነሳችውና   ወደጥግ ይዛው ሄደች።
ከዛ በሹክሹክታ "ምነው ችግር አለ እንዴ?"ሲል ጠየቃት ።
"አጎትህ ከካናዳ መጥቶል ..ጠፍተህበት ምድሩን እያሰሰው ነው..ሰምተሀል?"
"አዎ ሰምቼለሁ።"
"የገስትሀውሱን ስም ማዘዋወርህን እንዴት የሚቀበለው ይመስልሀል?"
"እሱን አኔ እወጣዋለሁ..አንዳንድ የማታውቂያቸው ነገሮች አሉ...ሰውዬው የሀብቱ ሁሉ መነሻ ምን ይመስልሻል ..?ከአባቴ የዘረፈ ብር ነው።ቀን ጠብቄ የሚገባኝን ንብረት ወስጄ ነው ለምወዳት ሴት የሠጠሁት...በዚህ ቅር ብሎት የሚያበሳጨኝ አይመስለኝም።"
"ትቀልዳለህ እንዴ...አጎትህ ለዛ ገስትሀውስ ያለው ፍቅርና ኩራት ቀላል አይደለም...እኔ በማቀው እራሱ ያንን ንብረት ለማፍራት በጣም  ለፍቶል...እና  ከቅሬታ በላይ በሆነ ስሜት ውስጥ ነው የሚገባው"
"እንደዛ ከሆነ  የቀሩትንም ንብረቶች ነጥቀዋለው...እሱ የተሳሳተው ለሁሉም ንብረቶቹ ሙሉ ውክልና የሠጠኝ ቀን ነው።"
"አዎ በዛ እኔም አምናለሁ ..አምኖህ ሙሉ ውክልና መስጠት አልነበረበትም...እኔ የምፈራው እርስ በርስ እንዳትገዳደሉ ነው"
"ዋናው የአሮራ የወደፊት ህይወት ይስተካከል እንጂ የእኛ መገዳደል ብዙም አያሳስብም።"
"የአንድን ሰው ህይወት  ለማስተካከል የሌላውን ማውደም ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው..እሺ ንብረቱን እንተወው ሴቶቹን እንዴት ታደርጋቸዋለህ?"
ያልጠበቀው ጥያቄ ስለሆነ ደነገጠ...ግራ ተጋባም"የትኞቹን ሴቶች?"
"ውሽሞችህን ነዋ ...ሁለቱ የጎትህን  ሚስቶች"
"እንዴ!!! እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ ?"
ሁለቱንም ሴቶች አንድ ላይ ስታወጣ አይቼሀለው...እርግጠኛ ነኝ እኚ ሴቶች ነገሩን እንደቀልድ እያዩት አይመስለኝም...እና ጠቅልለህ የአሮራ ልሁን ስትል ዝም ብለው የሚፈቅድልህ ይመስልሀል?"ስጋቷን ጠየቀችው።
"እና ምን ያደርጋሉ?መቼስ ያገባናል ብለው አያስብ"
"ለምን አያስብም...እንደተረዳሁት ከሆነ ሁለቱም አፍቅረውሀል...ያፈቀረች ሴት ደግሞ የትኛውንም አይነት መስዋዕትነት ከፍላም ቢሆን ያፈቀረችውን  ወንድ የራሷ ለማድረግ መጣሯ የተለመደ ነው።"
"አረ ትዕግስት እያጋነንሺው ፤የአጎቴ ሚስቶች ናቸው እኮ"
"አዎ ገባኝ  ...እየተንከባከብካቸው የነበረውም ልክ እንደአጎትህ ሚስቶች ነው...ለማንኛውም ውሳኔህ በጣም  ስሜት የተጫነው መሆኑን እንድታወቅ።የተሠማኝን ተናግሬለው...አሁን ወደ ሰዎቻችን እንመለስና ለውይይታችን እልባት እናብጅለትና ሁለታችሁም በተስማማችሁት መሠረት ለቀጠራችሆቸው አጋቾች  ክፍያቸውን ስጦቸውን ለጊዜውም ቢሆን ከዚህ ግር ግር እንውጣ...ከዛ በሂደት የሚሆነውን እናያለን። "አለችውና ወደነአሮራ ለመመለስ እርምጃ ጀመረች መንግስቱም ስለሰጠችው ጠንካራ ሂስ እያሰላሠለ ከኃላዋ
👍9214👎6🥰5😁2🤔2