አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
💰🔮የ እናቴ ልጅ🔮💰
🎈💰ክፍል ሦስት💰🎈.
🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮
ከቤት ወጥቼ ሰፈር ውስጥ ከሚገኝ አንዲት አነስተኛ ሱቅ ጋር ቆምኩኝ ፣ የሱቁ ባለቤት ልጅ ፣በድሪያ ትባላለች ፣ ፈራ ተባ እያለች " ምን ልስጥህ "አለችኝ ዝምብዬ ሳያት ወደዋላዋ አፈግፍጋ ቆመች ልጅ ናት የቀድሞ በጥባጭነቴ እሷም ጋር ተፅህኖ ሳያሳርፍ አይቀርም "እ ብስኩት ስጪኝ ካፒችኖ አለሽ "አልኳት በጨዋ ደንብ "አለኝ "ብላ ሰጠችኝ ብሯን ከፍያት ፣ልሄድስል ከኛ ጊቢ እልፍ ብለው የሚኖሩ ሴት ቀስ እያሉ መጥተው ቆሙ እናም ወደኔ በመዞር "ናቲ እንዴት አደርክ "አሉኝ ከዚ በፊት አናግረውኝም ሆነ ስሜን ጠርተውኝ ስለማያውቁ ደንገጥ አልኩ በዝምታ ሳያቸው "ምነው ናታን የእግዜር ሰላምታ እኮ አይከለከልም "አሉ ለስለስ ብለው
"አይ እኔ ከዚበፊት አናግረውኝ ሰለማያውቁ ገርሞኝ ነው "አልኳቸው በግልፅ
"አሂሂሂ መቼስ ልባችን ቢፈልግስ በየት በኩል እናንተ ከሰው አትቀርቡ ፣ለነገሩ ችግሩ የእናንተም አይደለ እናታቹ ናት እንጂ እንዳትቀርቡ ያደረገች እናንተማ ያው ልጆች ናቹ የተመራችሁትን ነው "ብለው ሽሙጥ መሰል ነገር ተናገሩ ፣ዝምብዬ አየዋቸው እንደ እውነቱ ከሆነ እማማ ሸዋዬ ትልቅ ሰው ባይሆኑ በናቴ የመጣ ቱግ ባልኩ ነበር "እማማ እሺ አሁን ሰላም ይዋሉ "ብዬ መንገድ ልጀምር ስል "ቆይ ቆይ እንደው መጀመሪያ ለደናደርኩ ' ደና ይመስገን ነው መልሱ እእእ የሆነስ ሆነና እኔስ ድንገት ሳገኝህ በውስጤ የሚመላለስ ነገር ነበርና ስለ እናንተ ቤተሰብ ላናግርህ ነበር መቼም አንተ በክፉም ሆነበደግ ታገናኘን ነበር ፣"አሉ
እኚሴቲዮ እየተፈታተኑኝ ነው ግን ትህግስት ላድርግ ብዬ "እሺ ቶሎ ይበሉና ይንገሩኝ"አልኳቸው ወደበድርያ ሳይ የጨነቃት ይመስላል እጇን ታፍተለትላለች ድንቡሽቡሽ ቀይ ፊቷ ያሳዝናል ፣ወደ እማማ ሸዋዬ አተኮርኩ መልሼ
"እኔማ ምን መሰለህ መቼም እዝች ምድር ላይ በሕይወት ስትኖር ክፉ ደግ አለ እንዳማሩ ዘላለም አይኖርም ደስታም እንዳለ አዘን አለ ማገኘትም ማጣትም እንደዛው ፣ እና ከሰው ተለይቶ ምንም ነገር አይሆንም ምንድነው ሁልጊዜም ስለ እናንተ ሳስብ ምንም ብትሆኑ ለኔ ይጨንቀኛል ፣እነዚ ልጆች እናታቸው አንድ ነገር ብትሆን እድር የለ ምን የለ ከሰው አይግባቡ እላለው እንደው በሌላ ነገር አትይብኝ እና ሰው ነንና ነገ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ናቲዬ አይለኛም ብትሆን አንተን ማናገር ለኔ ይቀለኛል ፣ እስኪ አንተ እናትህን እንደምንም ጨቅጭቀ የሰፈሩን እድር እንድትገባ አድርጋት ከሰው ቀስ በቀስ ትቀላቀል "አሉ መጀመሪያ ስላሟረቱብን ውስጤ ደስ ባይለውም የተናገሩት ነገር ከምር አሳሰበኝ ፣ እውነት አንድነገር ቢፈጠር አይበለውና ሆሆሆ እማማ ሸዋዬ ጭንቀት ፈጠሩብኝ
"እእእ እውነት ነው እማማ ልክ ነዎት አናግራታለው ለመልካም አሳቦት አመሰግናለው "ብያቸው ነገር ከመቀጠላቸው በፊት ፈጠን ብዬ ተራመድኩ
"ሰው ነው ብዬ ቀውስ..."ሲሉ ትንሿ በድሪያ ስትስቅ ሰማዋት "አንቺ ደሞ ጥርስሽ ይርገፍ ሻማ ስጪኝ አሁን "ብለው የውሸት እርግማን ሲያወርዱባት ፣ስትስቅ ሳልወድ በግድ ፈገግ እያልኩ ለራሴ የገዛውትን ካፒቺኖ ጨምድጄ እንደያዝኩ ሰፈሩን ለቅቄ ሌላቦታ ለመዋል ፈጠንኩ ፣ወይ እማዬ,,,,,..ኀ
እሷ እንደው ከማንም ጋር ምንም ነገር ለመነጋገር ፍላጎቱም ስሜቱም የላት እና እኔ ምን ማድረግ እችላለው ፣ በተለይ በአሁን ጊዜ ከወንድሜ አቤል በስተቀር ሰውም የላት እሱ ሁሉ ነገሯ ሆኗል አማካሪዋ መልህክተኛዋ አዛኟ ተንከባካቢዋ ...እኔን ማቅረብ በጭራሽ አትፈልግም ኧረ እሱም አልፈቀደልንም ፣አንዳንዴ እልም ብዬ ብጠፋስ እላለው እውነት ያን ያክል ለነሱ ችግር ከሆንኩ ።ሌላ ቦታ ሄጄ እራሴን ልፈትን ብዬ አስባለው የእናቴ በሚስጥር የተሞላ ሕይወት እና የታናሽ ወንድሜ እኔላይ ያለው ጥላቻ መጨመር እያሳሰበኝ መጥቷል ለምን ይሆን?,,,,,,

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍7613👎2👏2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አርባ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ያልተኖረበት የአንድ ወር ቅድመ ክፍያ ቃል ከፍሎ የሄደ ቢሆንም እሷ የስድስት ወር ተጨማሪ ቅድመ ክፍያ ከፈለች...ይሄንን ቅድመ ክፍያ ቃል ሲኖርበት ለነበረ ክፍል ብቻ ሳይሆን ከዛ ቀጥሎ  ለነበረች አንድ ክፍል ቤትም ጭምር ነው የከፈለችው። ክፍሏን እንደአዲስ ቀለም አስቀባችው.....ሙሉ እቃ ፤ አልጋ፤አነስተኛ ፍሪጅ፤ቴሌቪዠን አንድ…»
🎈🔦የ እናቴ ልጅ🔦🎈

💰🔮ክፍል አራት🔮💰
🔦🔦🔦🔦🔦🔦🔦
አንድ ቀን በጣም ደካክሞኝ ስለነበረ ምንም አይነት መጠጥ ሳልጠጣ በጊዜ ወደቤት ገባው ፣ እናቴ ቡና አቀራርባ ቤቱን ሞቅ አድርጋው ነበር አቤል ከሷትይዩ ካለው ሶፋላይ ተቀምጦ የቡና ቁርስ ፈንድሻ እየዘገነ ወደ አፉ ይልካል የኔ መምጣት ግድም አልሰጠው እናቴ ግን ያልተለመደ ስለሆነባት አተኩራብኛለች ፣ ምንም ሳልናገር ሄጄ ከቴሌቪዠኑ አጠገብ ተቀመጥኩ የኳስ ነገር ስለማይሆንልኝ በቲቪ የሚተላለፈው ጨዋታ አይላይት ቢሆንም እራሴንአሳርፌ ማየት ጀመርኩ አቤል ምቾት የሰጠው አይመስልም ሲያጉረመርም ሰማውት እናቴ ደሞ ዝም እንዲል ምልክት ትሰጠዋለች ፣ ውስጤ ቢናደድም ታገስኩ ፣እንደው ይሄልጅ ከዕፃንነታችን ጀምሮ እንደ ታላቅ እነቴ ስወደው ስከላከልለት ኖሬ ያለው ድንገት ሲጎረምስ እኔላይ ያለው ጥላቻ እንዲ አብጦ ሊፈነዳ የደረሰው ፡በኔ አይለኝነት ነው ወይስ ሌላ ችግር አለ ብዬ እራሴን መጠየቄ አልቀረም ብቻ እንደፈለገ ፡ በጣም የሚገርማቹ እኔ የዚ የተንጣለለ ጊቢ ባለቤት ሁሉም ነገር ከየት ይምጣ ከየት የሚነግረኝ ሰው ባይኖርም ሁሉነገር የተሟላበት ቤት ባለቤት ኪኪኪ ውይ ባለቤት አልኩኝ የቆንጆዋ የቤቱ ባለቤት ልጅ እኔ ፡ በእልህ የቤቱን ምግብ አልበላም ብዬ ፡ አንድ የሚገነባ ዕንፃ ላይ የቀን ስራ ተቀጠርኩ ይኽው በዛ ምክንያት ነው ዛል ብዬ የመጣሁት ፡ከእናቴ የኪስ ገንዘብ ለመውሰድ ምን አቅለሰለሰኝ በዛላይ የአቤል ግልምጫ ፡እሱ እንደው ሁሉም የኔ ማለት ከጀመረ ቆየ እሷም የአይኗ ብሌን አድርጋዋለች ፡እናት ግን እንዲ ስታዳላ አይገርምም በርግጥ እኔ ጥፋት የለብኝም ማለት አልችልም ግን እኔን በፀባይ መክራ ከማስተካከል ውጪ ከነ ልጇ እኔ ላይ ማመፅ ተገቢ ነው ? ይሁን እስኪ ዞር ብዬ ወደ እናቴ አየው ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ወደ አቤል መልሳለች ትንሽ ቀናው ምን አለ ከዚ ፍቅር ቀንሳ ትንሽ በሰጠችኝ ፡አሁን እኮ ሁሉንም ነገር ትቼ ሰላማዊ ለመሆን እየጣርኩ ነው የበለጠ የእናቴን ፍቅር ባገኝ እበረታ ነበር ፡ የቀንስራው የመጀመሪያዬ በመሆኑ እጄ ባሬላ የያዝኩበት ውሃ ቋጥሯል ፊቴ አመድ መስሏል ሰውነቴ ዝሏል እናቴ ግን በጭራሽ ግድ አልሰጣትም በርግጥ ብዙም አላየችኝም ።አቤል እኔ ስገባ ያቆመውን ወሬ ነው መሰል ቀጠለላት ፈገግ ፈገግ እያለ የእናቴን ቱኩረት በቀላሉ ነበር የሚስበው "
"እማ ታውቂያለሽ ጋሼ ግዛው ግን ምላሳቸው ምንድነው የሚባለው ጤፍ ይቆላል"ብሎ አቤል ሲስቅ ፡ እናቴ አብራው ሳቀች
"ክፉ ደላላ ነው ምን ሲል ነው የኔን ቤት ያየው መቼም ያለምክንያት አናግሮህ የማያውቀውን ልጅ ስለቤት ሽያጭ አያወራህም "ስትል ሰማዋት ልቤ ደነገጠ ምን የቤት ሽያጭ ፡ሲያወሩ እኔ ካለው እንኳ አልቆጠሩኝም ፡ አቤል ነገሩን ለማለስለስ ቃላት ሲመርጥ ተሰማኝ
"ኧረ እማ ሰውዬውኩ ስለ እኛ ቤት እኮ ያነሳው ጉዳይ የለም ብቻ ቡና እየጠጣው ድንገት ነው መቶ የተቀላቀለው ፡ከዛ ነው እንግዲ የወይዘሮ ሸዋረገድን ቤት በሃያ ሚሊዮን ብር አሻሻጥኳት እያሉ ሲያወሩ የሰማውት ከዛ ወደኔ ዞረው የአበባ ልጅ አይደለህም እንዴ አሉኝ ነኝ አልኳቸው ፡ከዛ ያወንድምህ በወጣበት አንተ ወጣህ " አሉ ሲል እናቴ የኔን ስም እንዳይጠራ እጇን አፏላይ በማድረግ አስጠነቀቀች እኔ ትኩረቴ ቲቪ ላይ የሆነ አስመስዬ ንግግራቸውን ማድመጥ ጀመርኩ "እና እማዬ ሰውዬው ያቁኛል ብዬ እንኳ አልገመትኩም እና ምን አሉኝ መሰለሽ ከእናንተ ቤት እኮ በግማሽ ያንሳል ፡ይኽው በአንድጊዜ አብታም አደረኳት "አሉኝ ብሎ ፈገግታው ይብስ ጨመረ እናቴ"ዝም በለው ባክህ እሱ ለሷብሎ አይደለም ደላላ ለራሱ ጥቅም ነው የሚሰራው "አለችና እናቴ ቡናውን መቅዳት ጀመረች
"እሱስ እማ ባለፈው የማማ ሸዋረገድን ልጅ አይቼው ነበር የሆነች ሱቅ ተከፍቶለት የራሱን ስራ ነው የሚሰራው በዛላይ የቤት መኪናም ገዝቷል አይገርምሽም "አላት እናቴ መልስ ሳትሰጠው የቀዳችውን ቡና ማማሰል ጀመረች ቀስብዬ ወደ አቤል ስመለከት እየተቁነጠነጠ ነው ፡እንዴ ይሄ ነገር ምንድነው የአቤል ፍላጎት አሳሰበኝ ከመቼው ትልቅ ሰው ሆኖ ነው ስለቤት ሽያጭ የሚያወራት በውስጤ ይሄንን ነው መፍራት አልኩኝ እናቴ ወደኔ ዞራ
"ቡና ልቅዳልህ አለችኝ"
"እሺ ግን አልበላውም "አልኳት እየደበረኝ ፡ አቤል የሽሙጥ ሳቅ ሳቀ ፡እናቴ ከተቀመጠችበት ስትነሳ ፡አቤል "ተይ አትነሺ እማ እኔ እሰጠዋለው "ብሎ ወደ ክችን ገባ እናቴ እሺ ብላ ቁጭ አለች
አቤል ወዲያው ነው የተመለሰው ሰአኑላይ ግማሽ እንጀራ በአንድ አይነት ወጥ አድርጎ አምጥቶ አስቀመጠልኝና ከእናቴ አጠገብ በመቀመጥ ፡የቅድሙን ወሬ ድጋሚ እያሰማመረ ያወራት ጀመር እናቴ ወሬው የጣማት አልመሰለኝም በዝምታ ታዳምጣለች ፡ እኔ ይሄኔ ነው አቤል ፍፁም ሌላ ሰው የመሰለኝ ለእናቴአዘንኩላት በሙሉ ልቧ ነው የምትወደው የሷ ምርጡ እና ልዩ ልጇ ነው ****


ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍95😢81👎1🔥1👏1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ጎነኛው መቃብር ስር አንድ ሰው  እንደሀውልት ተገትሮ   ቆሟል...እዛ ያለ ይመስላል እንጂ በድኑ ብቻ እንዳለ ያስታውቃል። ሀዘኑ ሀዘኗን ቀሰበሰባት። ምኑ ይሆን የሞተበት"የማወቅ ጉጉት አደረባት።አንገቷን አሰገገችና ሀውልቱ ላይ የተፃፈውን ፁሁፍ አነበበች ወ/ሮ ቅድስት ሀምሳሉ 1980 ፡፡ 2015ዓ.ም ይላል።እድሜዋን በአእምሮዋ አሰላችው ።የሰውዬው  እድሜ ገመተች ..አርባ አመት ቢሆነው ነው በቃ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ነች ስትል አሰበች።እንዲህ ካሠበች በኋላ ለሰውዬው  ያላት ሀዘኔታ ጨመረ፡፡

ለማታውቀው ሰው በዚህ መጠን ሰታዝን ይሄ የመጀመሪያ ገጠመኞ ነው። ምን አልባት እሷ  ገና ለገና ፍቅረኛ እንዲሆናት  የፈለገችው ሰው  ጥሏት ስለተሠወረ  እንዲህ እንቅሽቅሽ ካለች እሱ ደግሞ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ለዘላለም ጥላው ሞታ ከምድር በታች አፈር ለብሳ ስትቀበር እንዴት ሊያዝን እንደሚችል አሰላችና ሰቀጠጣት...?ያው ለእሱ እያዘነች ቢመስላትም  በተዘዋዋሪ ለራሷ እያዘነች ነው። ወደኋላ  ተመለሰችና ለቃል አባት አምጥታ ሀውልቱ ላይ ካስቀመጥቻቸው አምስት የፅጌረዳ ዝንጣፊዎች መካከል ሁለቱን አነሳች ‹‹ይቅርታ በሚቀጥለው ስመጣ የእነዚህንም ፋንታ ይዤ መጣለሁ... ብድር ነው›› በማለት...ወደሰውዬው ሄደች.. አጠገቡ ቆመች...ከደቂቃዋች በኃላ ዞር ብሎ አያት አየችው.  ።

ጎንበስ አለችና አበባውን በሀውልቱ መሀከል ላይ አስቀመጠችው...፡፡ይደሰታል  ..ያመሰግነኛል ብላ ስትጠብቅ  በቅፅበታዊ ንዴት አይኖቹን አጉረጠረጠባት... ፊቱ በአንዴ ደም ለበሰ...አይኑ ውስጥ የሚንቀለቀል ከገሀነም እሳት የረገፈ ፍም ነው ያየችው..በዚህ መጠን ሰው አስፈርቷትም አስደንግጧትም አያወቅም....፡፡ጎንበስ አለና ያስቀመጠችውን አበባች አነሳና ብጥቅጥቅ አድርጓ ቆራረጣቸው፤ ተበታትነው መሬት ከመርገፍ የዳኑትን ወደ አፍ ከቶ  እያኘከና እየበጣጠቀ መትፍት ጀመረ…፡፡አንድ አምስት እርምጃ ወደ ኃላ ሸሸት አለችው...

‹‹እሷ አበባ ፈፅሞ አይገባትም.››."አሁን ይሄን መቃብር ብንከፍተው ስጋዋን እንዳለነው የምናገኘው..አፈር አይበላትም߹ ከበላትም ለአፈሩ አውዳሚ  አሲድ ነው የምትሆንበት ፤ምስጦችም አይበሏትም ከበሏትም ሰውነታቸው ተመርዞ ያልቃሉ"አላትና ጥሏት ሄደ...በህይወቷ በሞተ ሰው ላይ ሲሰነዘር የሰማችው በጣም መራርና አስከፊው  ወቀሳ ነው ፡፡በመሄዱ እፎይ አለች ..እዛ ከእሷና እሱ ውጭ  ሰው በሌለበት የቀብር ስፍራ  ሲጥ አድርጎ የሚገላግላት መስሏት በፍራቻ መንቀጥቀጥ ጀምራ ነበር ።አይ የሠው ልጅ ከደቂቃዎች በፊት   ለመኖር ያላት ጉጉት ተሟጦ አልቋል ስትል ነበር ..አሁን ደግሞ ህይወቷ ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እየሠጋች ነው።እራሷን አረጋጋችና ኩስ ኩስ እያለች ከኋላ  ተከተለችው፡፡

ከመቃብር ቅጥር ጊቢ  ወጥቶ አስፓልት ጠርዝ ላይ ሲደርስ  እርምጃዋን ከእሱ እርምጃ ጋር ማስተካከል ቻለች....ዝም ብሎ መራመድን ቀጥሏል"ማኪያቶ ልጋብዝህ›› አለችው ..ሀሳብ ድንገት ነው የመጣላት፡፡

"አይ  ማኪያቶ አልወድም...አሁን  ጂን  ነው ምጠጣው"

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው.. እንደውም እኔም እሱን ብጠጣ ጥሩ ይመስለኛል።››

"ጥሩ"
"መኪናዬን ግን  ፊታችን ያለው ሆቴል ነው ያቆምኩት… እዛ ብንጠጣ ቅር ይልሀል..?."ዝም ብሎ አቅጣጫውን ወደነገረችው ሆቴል አስተካከለ።ያ ማለት በሀሳቧ መስማማቱን ማሳያ አድራጋ ወሰደችውና ተከተለችው፡፡እንደዛው ጎን ለጎን እየተራመዱ ምንም ሳያነጋገሩ  ሆቴል ደረሱ..  በፅድ ተክሎች የተከበች ከለል ያለች ቦታ መርጠው ተቀመጡ የሚቀመጡበትንም ቦታ የመረጠችው እሷ ነች..)እሱ ለመጠጡ እንጂ ለቦታው ግድም ያለው አይመስልም፡፡

"ስለደረሰብህ ሀዘን በጣም አዝናለሁ››አለችው ፈራ ተባ እያለች፡፡

የእሷን አስተያየት ችላ አለና"አባትሽ ናቸው?"ሲል ጠየቃት…ደነገጠች

"ምን? ማን?"

"ቀብሩን ነው ያልኩሽ"

"እ...የእጮኛዬ አባት ናቸው...ማለቴ የፍቅረኛዬ...   ማለቴ የማፈቀረው ልጅ አባት"

"በአንድ ፅኚ እንጂ..የምን መወነባበድ ነው?"

"ወድጄ ይመስልሀል"

"የት ነው"

"ማ ?"
"እሱ...የምታፈቅሪው ልጅ"

"ገዳም ገባ"

መልሷን ከሰማ በኃላ ያዝንልኝና  ያፅናናኛል ብላ ስትጠብቅ

‹‹ተገላገለ" ብሎ እርፍ።

"እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ?"

"ያው አንድ ቀን ልቡን ሰብረሺው  ስቃይ ውስጥ ከሚገባ እንዲ በደህናው ጊዜ ገዳም መግባቱ ይሻለዋል"

"እንዴት ልቡን ልሰበር እችላለሁ ከራሴ በላይ እኮ ነው የማፈቅረው"

"እዛ የተኛችው ማለት ቅድም አበባ  የሠጠሻት ሴትም ከአመታት በፊት እንዲሁ አንቺ ያልሺውን ቃል  መቁጠር ከምችለው ጊዜ በላይ ብላኝ ነበር"

"ታዲያ ምን ተፈጠረ?"

"ያው እንዳልኩሽ ነዋ የልብ መሠበር"

"ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው እንደምታስበው አይደሉም"

"ናቸው..ቆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?"

"ጠይቀኝ"

"አሁን ጥሎሽ ገዳም ከገባው ልጅ በፊት ፍቅረኛ ነበረሽ"

"አዎ ነበረኝ"

"ታፈቅሪው ነበር?"

"በወቅቱ አዎ አፈቅረው ነበር"

"ጥሩ ...እንደምታፈቅሪውስ ነግረሽው አታውቂም"

"በወቅቱማ እንዴት አልነግረው ...ፍቅረኛዬ ነበር...እንደማፈቅረው ብዙ ጊዜ ነግሬው አውቃለሁ።"

"በቃ መልሴ ተመልሶልኛል"

ድንግርግሯ ወጣ ።ምን ለማለት እንደፈለገ ምንም አልገባትም።

‹‹የምኑ መልስ?"

"ያው መጨረሻውን አየሽው߹ ከዛ ፍቅረኛሽ ጋር አሁን አብረሽ የለሽም...የሌላ ወንድ ፍቅር ፍለጋ በየመቃብር ሀውልቱ ትዞሪያለሽ ߹ያ ፍቅረኛሽ ግን ምን እየተሠማው እንደሆነ ምን ያህል እንዳዘነ ?በምን ያህል መጠን እየናፈቅሽው እንደሆነ ?ምንም ትዝ ብሎሽ አያውቅም አይደል?።"

ለወንዶች ያለው ውግንናና ለሴቶች ያለው ጥላቻ ጠርዝ የወጣ ነው ብላ ስላሰበች አበሳጫት።

"ምን እያልክ ነው..?ቺት ስላረገብኝ እኮ ነው  የተለያየነው"

"እ እንደዛ ነው?" አለና  ጅኑን አንስቶ ተጋተው
‹‹ምነው?  በቂ ምክንያት አይደለም?"

"ለወንድ አዎ .ለሴት ግን አይደለም"

"አልገባኝም?

"ሴት  መጀመሪያውኑ  ለመለየት  አቀባብለ እየጠበቀች ካልሆነ በስተቀር ፍቅረኛዋ ችት ስላደረገባት ብቻ አታባርረውም"

ዝም አለች። ይሄ  የአስፈሪው እንግዳ ሰው ንግግር ለሌሎች ሴቶች ይስራ አይስራ ባታውቅም  እሷን በተመለከተ ዝንፈት የለበትም...እናም ገፍታ ልትከራከረው አቅም  አላገኘችም።ለተወሰነ ደቂቆች በዝምታ እያሰላሠለች ጅኑን መሳብ ጀመረች።ድንዝዝ እንዲላት ፈልጋለች። ለዛሬም ቢሆን እንኳን  ሁሉን ነገር መርሳት።

"እስቲ ስለራስህ ንገረኝ...ስለእሷ...አበሳጭታህ  ስለሞተችው ሴት"

‹‹እርግጠኛ ነሽ መስማት ትፈልጊያሽ?››

‹‹አዎ በደንብ›› አለችና ለመስማት አቆብቆበች….አቀማመጧን አስተካከለች…ማውራት ጀመረ

‹‹የሶስት አመት ፍቅረኛና የአራት አመት ባለቤቴ ነች፡፡ከባለጉዳይ ጋር ስዳረቅ እና ከሀለቃዬ ጋር ስጨቃጨቅ ቆይቼ በድካም ውልቅልቅ ብዬ ወደ ቤቴ ስመጣ  በገዛ አልጋዬ ላይ ከገዛ ጓደኛዬ ጋር ተኝታ ደረስኩ።ከመተኛቷ በላይ ያበሳጨኝ ከእኔ ጋር ስትተኛ ሰምቼው የማላውቀውን በደስታ የመቃተት ድምፅ መስማቴ ነው። የወሲብ ፊልም አክተሮች እራሱ እሷ እያለከለከች እንዳለው አያለከልኩም። ለማንኛውም በአፍላ ስሜት ነቅናቂ ሙዚቃ በታጀበ ተራክቦ ላይ እያሉ ደረስኩባቸው።

እሱ በመስኮት ዘሎ ፈረጠጠ..እሷን ያዝኳት..።
👍846😁2👏1
አንገቷን ፈጥርቄ ወዘዘዝኳት...ብርቱኳን እየሠነጠቁ ይገባበዙበት የነበረ ቢላዋ መሰለኝ ከአልጋው ጎን ካለ ጠረጰዛ ላይ አየሁ።አነሳሁት...።ልክ እንደፋሲካ ዶሮ አንገቷን በጥሼ ልጥለው ዝግጅ ሆንኩ።ግን ወዲያው ሀሳቤን ቀየርኩ።ምን አልባት እግዚያብሄር የዚህቺን ሴት ነፍስ ዛሬ ወደራሱ ሊወስድ ወስኖ እኔን እንደማስፈፀሚያ መሳሪያ እየተጠቀመብኝ ቢሆንስ...?የሚል ሀሳብ በምናቤ ተሠነቀረብኝ።ይቅርታ እጠይቀዋለሁ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ፈፅሞ እግዚያብሄርን ልተባበረው አልችልም። ወሰንኩ። ቢላዋውን ወለሉ ላይ ወረወርኩና እሷን ገፋታትሬ ከቤቴ አባረርኳት።

በታሪኩ ተመስጬ‹‹እሼ  ከዛስ ምን ተፈጠረ…?አግኝተሀት አታውቅም ?››ስል  ጠየቅኩት

<<ከወር ብኋላ...አገኘኋት ߹በተለመደ የዘወትር የስራ ላይ ገጠመኞች ድክም ብሎኝ እግሬን እየጎተትኩ ተዘግቶ ወደሚጠብቀኝ ቤት እያዘገምኩ ነው።በቤቴና በመስሪያ ቤቴ መካከል ያለውን ድልድይ መሻገር ስጀምር ድንገት አንድ ክስተት አይኔን ያዘኝ።የሆነች እንስት ወደጥልቁ ገደላማ ወንዝ እራሷን ወርውራ ለመሞት አቅዳ ይመስለኛል የድልድዩ የኮንክሪት መከለያ ላይ ወጥታ ትታያለች።አዎ ግምቴ ትክክል ነው እራሷን ለማጥፋት እየተዘጋጀች ነው።ላተርፋት ወሰንኩና እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ቀረብኳት...።ስጠጋት የማውቃት ሴት ነች።ከወር በፊት ከቤቴ ያባረርኮት የቀድሞ ሚስቴ ነበረች።ሀሳቤን ቀየርኩና እርምጃዬን ገታሁ።ፊቴን አዞርኩና ወደቤቴ መራመድ ጀመርኩ።ይህቺን ሴት እግዚያብሄር ሊወስዳት ስለፈለገ የራሱን መውሰጃ መንገድ ለሁለተኛ ጊዜ አዘጋጅቶላት ሳለ እኔ ምን ቤት ነኝ በውሳኔው ጣልቃ የምገበው...?አሁን እንደመሻቴ እሷን ከሞት ብታደጋት ዳግመኛ እግዚያብሄርን መፈታተን አይሆንብኝምን?አዎ ጣልቃ መግባት የለብኝም።"ቾቾቾ" የሚሌ የውሀ መንቦጫረቅ ድምፅ ከኃለዬ ሰማው... ውስጤ በሀዘን ስብርብር አለ..."ነፍስ ይማር ከማለት ውጭ ምን ማድረግ እችላለሁ?ምንም።
//
ከዛ በማግስቱ ከፖሊስ ጣቢያ ሬሳዋን ተረክቤ ቅድም ያየሽው ቦታ አምጥቼ ቀበርኮት..እና ይሄው በየሳምንቱ እየመጣሁ ለምን እንደዛ እንዳደረገቺኝ እጠይቃታለሁ…..ምንድነው ያጎደልኩብሽ….?መቼ ነው እንዲህ አንጀትሽን የሚበጥስ                ስህተት የተሳሳትኩት…..? እያልኩ ጠይቃታለሁ.. እንደታዘብሺው መልስ የላትም

ታሪኩን ነግሯት ሲያበቃ  ትንፍሽ አጥሯት ነበር?‹‹ለምንድነው ግን በድንገት ግራ የሚያጋብ ሰዎች ወደ ህይወቴ የሚገብቡት? ››
ከቦርሳዋ ብሮች አወጣችና ጠረጰዛ ላይ ወረወረች።
"ተነስ እንሂድ"
‹‹እንዴ ገና ጠጥቼ እኮ አልበቃኝም"
"አውቃለሁ...እቤትም ሰፈርም እንቀይር"
"ተይ አንቺ ልጅ እዚሁ ጥለሺኝ ሂጂ።"
"አይ ገና መገናኘታችን እኮ ነው...ደግሞ ሁለታችንም በአንድ አይነት በሽታ ነው እየተሠቃየን ያለነው.. በሽታችን ተመሣሣይ ከሆነ ደግሞ   የምድንበትም የመድሀኒት አይነት ተመሳሳይ ነው የሚሆነው ...እና…››
"እና ምን?"
"እናማ ተነስና መድሀኒታችንን  አብረን እንፈልግ"

ተስማማና ብርጭቆው ውስጥ የቀረችውን ጅን በአንድ ትንፋሽ በመጨለጥ  በሀሳቧ ተስማምቶ ተነሳ።ተያይዘው መኪና ውስጥ ገቡ። የት ነው? ወዴት ነው ብሎ አልጠየቃትም…መኪና ውስጥ ከገቡ በኃላ ምንም አላወሩም..ዝም ብሎ በመስኮት አሻግሮ አይኖቹን ወደውጭ ልኮ በመንገድ ጠርዝና ከማዶ የሚከወኑ ነገሮችን እየታዘበ ነው፤‹‹ምን አልባትም  በድኑ ብቻ ይሆናል አብሯት ያለው።  " እንደፈለገ ይሁን ዋናው እንደእኔ የታመመ የእኔን ህመም የታመመ ሠው ከጎኔ መኖሩን ነው።››ስትል አሰበች፡፡ቀጥታ ወደ ራሷ ቤት ነው ይዛው የሄደችው ߹ወደእናቷ አይደለም?ወደቃል ቤትም አይደለም߹እናቷ ወደአዘጋጀችላት የራሷ አፓርታማ ነው።ለምን እንደዛ ለማድረግ እንደፈለገች አታውቅም...ብቻ ስሜቷ ነው ያዘዛት...።
///
…እቤት ደርሱና ከሆቴል ቴክአዌይ ያሰሩትን ምሳ ከበሉ በኃላ ጀምረዉ የነበርነውን መጠጥ  ቀጠሉበት፡፡
ከአንድ ምናምን ሰዓት ትርኪ ምርኪ ወሬዋች ስያወሩ ከቆዩ በሃላ ድንገት ሰውዬው‹‹…እስኪ ገዳም የገባውን  ሰውዬሽን  ፎቶ አሳይኝ›› አላት
‹‹ለምን ፈለከው?››ጠየቀችው::
‹‹እንዲሁ….ምን ያህል ቆንጆ ቢሆን ነው እንዲህ ስብርብር ሰእስክትይ ያፈቀርሽው የሚለውን ለማወቅ ነው፡፡››አላት፡

ፈገግ አልችና‹‹…የእሱ ዋናው ውበቱ በውስጡ ߹ልቡ ላይ ነው ያለው….ያንን ደግሞ ፎቶ አያሳይም››በማለት ሞባይሏን ከጎኗ በማንሳት ከፍታ ፈልግ ፈልግ አድርጋ አንድ አብረው ሰልፊ የተነሳሱትን ፎቶ ሰጠችው››
ቀረብና ራቅ እያደረገ ደጋግሞ አየውና‹‹….እራሱ ነው››አለ፡፡
ግራ ገባት‹‹እራሱ ምን ?››
‹‹ፎቶውን የጠየቅኩሽ በጣም እየሰከርኩ ስሄድ ነገሮችን የማስታወስ ችሎታዬ ስለሚጨምር የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው፡፡››
‹‹ማለት ቃልዬን ታውቀዋለህ?››
‹‹አይ አላውቀውም..ግን እዛ ሰውዬ ቀብር ላይ ልክ ዛሬ ካአንቺ ጋር እንደተገጣጠምን ከእሱ ጋርም ሁለት ቀን ተገጣጥመናል፡፡››
‹‹ምን?እየቀለድክብኝ እንዳይሆን?››
‹‹አይ በፍፅም እኔ ቀልድ የምወድ ሰው አይደለሁም .››.አላት….ዥው አለባት…ከስካሩ ጋር የሰማችውን ዜና መቋቋም አልቻለችም፡፡
‹‹ቃል ገዳም ካልገባ ከእኔ እየሸሸና እየተደበቀ ነው፡፡እኔ የህይወቴን ትልቁን ቁማር ተበልቼያለሁ፡፡ ምርጥ ፍቅሬን ባል የሚሆነኝን ሰው አስይዤ ቁማር ተጫውቼያለሁ..እናም ተበልቼ እሱን በማስረከብ ባዶዬን ቀርቼያለሁ፡፡ አዎ ቃል ፊት ለፊት እኔ ጋር ቀርቦ ምርጫው እንዳልሆንኩና እንደማያፈቅረኝ መንገር ስለከበደው ተስፋ ቆርጬ ሌላ ህይወት እስክጀምር ተደብቆኝ  እየጠበቀ ነው…አዎ አሁን የገባኝ ያ ነው፡፡ምን አልባትም ተጫውቼ ስለተበላሁት ቁማር ምስጢር አውቆ ተጠይፎኝም ሊሆን ይችላል፡፡ ›› ጭልምም አለባትና ሸርተት ብላ እዛው ሶፋ ላይ ተዘረጋጋች…..
‹‹…ተረጋጊ እንጂ …ማነሽ ቆንጆ ….አረ ተነሽ››የሰውዬው ድምፅ ትንሽ ትንሽ በሰመመን ውስጥ ይሰማታል፡…..
                                  
                 ተፈፀመ
👍115👎57😢19🤔12😱74🔥4🎉1
🔮🎈የ እናቴ ልጅ🎈🔮
💰🏮ክፍል አምስት🏮💰
🔦🔦🔦🏮🏮🔦🔦🔦
የቀንስራ ከጀመርኩ ቆየው ይኸው እንዳይለመድ የለም ለመድኩት ፡እንደበፊቱ ከመድከም ባለፈ አጠነከረኝ አይምሮይንም አሳምኜ ልክ እንደ ስፖርት በመውሰድ ሰጥ ለጥ ብዬ መስራት ጀመርኩ ፡ እናንተዬ ለካ  ፡የነገሩ ክብደት ሳይሆን ኑሯችንን የሚያከብድብን የኛው የመቀበል ጉዳይ ነው  ወሳኙ፡
ይኽው አምኜ በምሰራው ስራ ይበልጥ ጠንካራ ሆኛለው  እንደበፊቱ መጠጣት መቃም ቀርቷል ግን ትንሽ የከበደኝ የሲጋራው ነገር ነው ጨርሶ ለማቆም አልቻልኩም በርግጥ መጠኑን ከበፊቱ ቀንሻለው  ፡ በምግብ በኩል ሆድ ለቆብኛል አብዛኛው ገንዘቤ በምግብ ነው የሚያልቀው ፡እውነቴን ነው በዚ የኑሮ ውድነት መቆጠብ አይታሰብም ፡ምን አልባት ቆጥበህ ጫማ ትገዛ ይሆናል እንጂ  ቆጥበህ ቤት አትገዛም ኪኪኪ እንኳን ታራ ስራ ሰርተኽ ደና ደሞዝ የሚከፈላቸው እንኳ  እኔ ከምገዛው የተሻለ ጫማና ልብስ ቢገዙ እንጂ ሌላ ነገርማ እንጃ  ፡
እኔ በገዛ ፍቃዴ ከእናቴ ጡረተኝነት ለመውጣት እየታገልኩ ነው  ፡ አቤል ግን ከእናቴ ጋር እንደተጣበቀ  ነው  መርካቶም ስትሄድ መከተል ነው  ቤት ውስጥም አብሮ መንጎዳጎድ ነው  ለራሱ የሚሰጠው ጊዜ ያለ አይመስልም ፡ በተቻለው መጠን እየተንከባከባት ነው ፡የሚገርመኝ ደሞ ይህን እንድታውቅለት ይፈልጋል ፡እናቴን የግሉ አድርጎ ነው የቆጠራት ከኔጋ ለማውራት እድሉንም አይሰጣት ፡ እሷም ብትሆን ለሱ ያላት ነገር ከመንሰፍሰፍም በላይ ነው ፡ ,,,,,
ወቅቱ ዝናባማ ነበርና ብርዱም ውጪ የሚያስመሽ ስላልነበረ  ትንሽ ጨለም ከማለቱ ነበር ወደቤቴ ለመግባት የሰፈሬን መንገድ የተያያዝኩት ፡በአካባቢው ላይ የሚጫወቱ ዕፃናትን ሳይ ኑ ግቡ የሚልም የለም እንዴ ፡ምነው የዚን ያክል ሰው ቸልተኛ ይሆናል ፡በርግጥ እንደኛ ሰፋፊ ጊቢ እና ትንሽ የሀብታም ልጅ የሚባሉ ልጆች የሉበትም ፡  ከትናንሽ ቤቶች ውስጥ የወጡ ልጆች ናቸው ቤታቸው አጥር ስለሌለው ሰፈር ውስጥ ከላይ ታች እያሉ ነው የሚጫወቱት ፡ቢሆንም ግን ሲመሽ ግቡ እና አጥኑ የሚል ወላጅ ከሌለ ለነገ ማንነታቸው ከባድ ነው  ፡መብትና ግዴታቸውን የማያውቁ ልጆች ካደጉ በዋላ  ልመልስህ ብትለው ፡ አትችለውም ፡ ስለነሱ እያሰብኩ አንዱ የሰፈራችን ቅያስ ጋር ስደርስ ጉድ አየው ምን አትሉም ወንድሜን ከሴት ጋር ሲነታረክ በዛላይ ዕፃን ልጅ ከተሸከመች ልጅ እግር ሴት ጋር ትንሽ ሸሸግ ብዬ አውቃት እንደሆን ለማረጋገጥ ሞከርኩ ጨርሶ አይቻት አላውቅም ፡ በጣም ተቆጥታ ነው የምታወራው ፡እሱደሞእየለመናት ነው  ምንድነው ጉዳዩ,,,,,,,,,

,ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍7727🤔3
🔮🔦የ እናቴ ልጅ🔦🔮
💰🏮ክፍል ስድስት🏮💰
📣📣📣📣📣📣📣📣
ቤት ከገባው በጣም ቆየው አቤል ግን አልመጣም እናቴ በተደጋጋሚ ወጣ እያለች ትመለሳለች እንደጨነቃት ያስታውቃል ልጇ እንዲ ሲያመሽ የመጀመሪያው ነው ፡ እኔ ብሆን ባድርም ግድ የላት የኔ ነገር ድሮ ነው የበቃት እኔም ብሆን አዘኔታዋን አልፈልገውም ፡ምክንያቱም ለዚሁሉ መገፋት የኔም ድርሻ አለበት ፡ ፍቅሯን ፈልጌ አንዳንዴ ብወቅሳትም ፡ ስህተቱ የኔም መሆኑን ካመንኩ ቆይቻለው እና ዛሬ ላይ ዝቅ ብዬ እየሰራው እራሴን ለማስተካከል መወሰኔ ከዛ አንፃር ነው  ,,,,,,,,,
እናቴ በጣም ሲብስባት ወደ እኔ ዞረች
"ስማ ከለሊቱ ስድስት ሰአት ሆኗል ወንድምህ አልገባም !አንተ ግን እዚ ተቀምጠሃል  ትንሽ እንኳ አይጨንቅህም?!" ብላ አፈጠጠችብኝ
"ምን ማድረግ እችላለው ከመጠበቅ ውጪ ፡እኔና እሱ እንደው ከተራራቅን ቆይተናል ፡ምን እንደሚያደርግ ምን እንደሚያስብ ከነማን ጋር ጓደኛ እንደሆነ አላውቅም ፡ ስለዚ  አዲስ ያመጣው ባህሪም ካለ እንግዲ ከኔ ይበልጥ የሚቀርበው አንቺን ነው "ብያት ፊቴን ወደቲቪው መለስኩ
"ምን ማለት ነው ?!"ብላ ቱግ አለች
"እንዴ ካንቺ ጋር ቀን ላይ የተነጋገራችሁት ነገር ካለ አስታውሺ ፡ ወይም ጓደኛ ካለው ከነሱ ጋር የሚያከብረው ነገር ካለው ፡ አይታወቅም  ትልቅ ልጅ ነው አንዳንዴ የሚያምረው ነገር ሊኖርም ይችላል"ብዬ ዝም ።እናቴ ልትመታኝ የፈለገች መሰለች ተጠግታኝ በቁጣ ስታየኝ ቆይታ
"እሱ እንዳንተ አይደለም ከአጠገቤ ተለይቶ አያውቅም ደጁን አያውቀውም ከመሸ ልጄን አውቀዋለው ይሄኔ አንድ ቦታ ተጨንቆ ነው የሚሆነው ወይኔ ልጄን ተነስ አሁን አፍህን መክፈትህን ትተህ ፍለጋ እንውጣ ፡ "ብላ ጎተተችኝ ፡ወይ እናቴ ምንአለ ከዚሁሉ ፍቅር ትንሽ ቀንሳ በሰጠችኝ ብዬ ተመኘው ፡
  ወደ በሩ ስትጣደፍ ስስ ነገር መልበሷን ልብ አልኩ ለማንኛውም ብዬ ወደክፍሌ ገብቼ ወፈር ያለውን ጃኬቴን ያዝኩላት እና ቀድማኝ የጊቢውን በር ከፍታ እየወጣች "ፍጠን" አለችኝ የቤቱን በር እየዘጋው ፡ መጣው ከማለቴ እናቴ ስትጮኽ ሰማዋት ፡በፈጣሪ ሰውነቴ ለሁለት የተተረከከ ነበር የመሰለኝ ፡ እናንተ ድንጋጤ ለካ ያስሮጣል ከመቼው ፡እናቴ አጠገብ እንደደረስኩ እኔነኝ የማውቀው  ፡እናቴ ደግማ ግን አልጮኽችም ፡አካባቢውን በጥንቃቄ እየቃኘች ከቆየች በዋላ በትልቅዬ ዘንቢል የተቀመጠ ነገር አነሳችና ወደግቢ ገብታ በሩን ዘጋች እኔ እንኳ ከጊቢ ውጪ መሆኔን የዘነጋች ነው የምትመስለው ፡
"እናቴ ኧረ በሩን ክፈቺልኝ"አልኳት ፡
"ናግባ ይሄ ምን ጉድ ነው!"ብላ በሩን ከፍታ አስገባችኝ ወደ ዘንቢሉ እየተጠጋው
"ምንድነው"አልኳት
"ዕፃን ልጅ ነው አይታይኽም "አለችኝ
"አአ አዎ አአ የውት"አልኩኝ በድንጋጤ ቃላቴን እየጎተትኩ ፡ ጉድ ፈላ አቤልን ዕፃን ልጅ ከታቀፈች ሴት ጋር አይቼው ነበር  ይህን ለእናተሰ ብነግራት አታምነኝም ፡በቃ በታማኙ ልጇ የሚመጣባት ሰው አትፈልግም ፡ እናቴ ለአቤል ያላት ፍቅር ጥልቅ ነው ፡እንዲነው እንዲያነው  ብሎ ለእናቴ መንገር ከበደኝ..
"ና ወደቤት ይዘነው እንግባ ማነው አምጥቶ የጣለብኝ ሆሆ ብለው ብለው የትም ሲልከሰከሱ ወልደው መጣያ ያድርጉኝ እኔ ከሰው አልቀርብ አልደርስባቸው ምን ፍለጋ ነው ሀብታም ናት ብለው ነው ፡እስኪ ከዚ ሁሉ ጊቢ የኔ በምን ታያቸው ፡ ልጄን ልፈልግ ወይስ የነሱን ዕፃን ላስተናግድ ምን አይነት ቀን ነው ዛሬ"እያለች እያጉረመረመች ከዘንቢል ውስጥ ድንገት ንቅት ብላ አይኗን የምታቁለጨልጭ ዕፃን አውጥታ ወደላይ በመያዝ "ውይ ጭካኔ ሴት ናት "ብላ ወደኔ ዞረች  ፡እኔ አይምሮዬ ሁሉ አቤል ጋር ነው በቃ አቤል እሱ ቀርቶ ልጁን ልኮልናል ፡ የት ተደብቆ ይሆን ይህን ድራማ የፈጠረው ጉድ ነው አልኩ ፡ እናቴ ዕፃኗን ሶፋው ላይ አጋድማ ዘንቢል ውስጥ ጡጦ ይኖር እንደው ብላ ስትፈላልግ በዛውም አንድ ደብዳቤ አገኘች ደብዳቤውን ይዛ ወደኔ ስትዞር ፡የጊቢ በር ተንኳኳ ሁለታችንም ለአፍታ በድንጋጤ ተያየን ፡ከዛ እኔ እሮጥ ብዬ በር ከፈትኩ አቤል ነበር ምንም ነገር አልሆነም ለመጀመሪያ ጊዜ አከበረኝ ይቅርታ የጓደኛዬ ልደት ነበር አለ ዝም አልኩ ።እናቴ አቤል መምጣቱን ስታይ እፎይ አለች  ፡እና ወደ ዕፃኗ እያሳየች "ጉድ ሆንን እኮ አቡ ተመልከት የጣሉብንን "ስትለው እንደ አዲስ ተገረመ እኔ የፊቱ ገፅታ አስገረመኝ ምንም አልመሰለውም ከጉዳዩ ለመሸሽ እራሱን አሳምኖ እንደመጣ ገባኝ ፡እናቴ የያዘችውን ደብዳቤ ለማንበብ ተዘጋጀች  ,,,,,,,,,,

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍8210😁2🔥1
🎈🔮የእናቴ ልጅ🎈🔮
ክፍል ሰባት💰💰
🔮🎈🔮🎈🔮🎈🔮
በሕይወቴ ውስጥ እንደዛን ቀን የማይነጋ ለሊት አይቼም አላውቅ ፡እናቴ የተፃፈውን ደብዳቤ እጆቿ እየተንቀጠቀጡ ስትገላልጠው ፡ የወረቀቱ ድምፅ በራሱ ሽብርን ለቀቀብኝ ፡ አቤል ተረጋግቶ ወደ እናታችን ተጠግቶ ቆመ ፡ ለራሴ በቃ ለሚመጣበት ነገር ሁሉ ተዘጋጅቷል ማለት ነው ፡በይሆንማ ኖሮ ጉዱን ከቤት ውስጥ አምጥቶ እንዲ ግድ የለሽ አይሆንም ስል አሰብኩ ፡ግን እኔ የሱ ሁኔታ ብዙም አላሳሰበኝም ከዛ ይልቅ እናቴ በጣም የምታምነውን ልጇን ማጣቷን ስታውቅ የሚሰማት መሰበር ነው ያስጨነቀኝ ፡ እናቴ ደብዳቤውን ማንበብ ስትጀምር ይበልጥ ተንቀጠቀጠች ፊቷ ተለዋወጠ ፡ ጉድ ፈላ አልኩኝ ፡በቃ አቤልን ከማነቋ በፊት አንድ ነገር ለመፍጠር ተዘጋጀው ፡እሱን ካጠገቧ አርቄ ነገሮችን ለማረጋጋት...
"እናቴ ደና ነሽ"ብዬ ስጠጋት ደብዳቤውን ጥላ በሕይወቴ አይቼ የማላውቀውን ጥፊ አሳረፈችብኝ፡በድንጋጤ ወደዋላ ተመለስኩ ፡ እንዴ የእናት ጥፊ እንደዚ ያማል እንዴ ? እንጃ ... አፍንጫዬ አካባቢ እርጥበት ተሰማኝ በእጄ ጠርጌ ሳይ ደምቻለው ፡ምንድነው ጉዱ የወንድሜን ንዴት እኔ ላይ እየተወጣችብኝ መሰለኝ ፡ ወንድሜ ደሞ ይባስ ብሎ ከሷ አራቀኝ እና እንዳልጠጋት አስጠነቀቀኝ ፡ በዚ ጊዜ ዕፃኗ ለቅሶዋን አሰማች ፡ሁሉም ነገር ድንግርግር አለብኝ የአፍንጫዬን ስር በጥፊ የበጠሰችኝ ይመስል ደሙ አልቆም አለኝ ፡ እናቴ የዕፃኗን ጩኽት ላለመስማት ሁለቱንም ጆሮዎቿን በመሸፈን
"ዲቃላኽን ይዘኽልኝ ውጣ አንተ አሰዳቢ"ብላ አንቧረቀችብኝ ፡ ማን እኔ ጉድ ነው እንዴት ነው ነገሩ ልጅቷ የኔ እንደሆነች ነው እንዴ የምታስበው ፡ በፍጥነት የጣለችውን ወረቀት አንስቼ አነበብኩት፡"ለናታኒየም ሚጡ ነኝ አዝናለው ልጅህን የማሳድግበት ምንም አቅም የለኝም የፈለከውን አድርገህ እኔን መከራ ውስጥ ከተህ መተኛት ካማረህ ተሳስተሃል ሳልፈልግ የሰጠኸኝን ዘር ልኬልሃለው እንደፈለክ ማድረግ ትችላለህ ቻዎ"እኔ አላምንም ለረጅም ደቂቃ አፌን ከፍቼ አቤልን ማየት ጀመርኩ ፡ ወንድሜ በኔ ላይ አላከከው በትክክል የሱ አሳብ መሆኑን አውቄሃለው ፡ምን ቢጠላኝ የዚን ያክል ግን በኔላይ ያምፃል ብዬ አላሰብኩም እናቴን ለማስረዳት አስቤ ደግሜ ተጠጋዋት ፡ በፍፁም ጥላቻ ተሞልታ ጣቷን ቀስራ
"ዲቃላህን ይዘህ ውጣ አሁኑኑ"አለችኝ ፡አስተያየቷ ስብርብር አደረገኝ ፡በተራዬ እኔ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ ፡ ሕይወቴ ይበልጥ ሲመሰቃቀል ታየኝ ፡አቤል እናቴ ደግፎ እያስቀመጣት ማፅናናት ጀመረ ፡ ግራ ገባኝ እውነት ይሄ የ እናቴ ልጅ ወንድሜ ነው ፡ እስኪ ምን ብበድለው ነው እንዲ የሚያደርገኝ እኔ ላይ ከሚያላክክ ፡ምን አለ ተጥላ ነው ያገኘዋት ቢል ፡ ፍፁም ጤንነቱን ተጠራጠርኩ ፡የምታምነውን እና የምትሳሳለትን እናቱን ፡እንዴት ይዋሻታል ፡ ጠጋ አልኩትና
"አቤል ወጣ ብለን እናውራ"አልኩት ፡
"ከኔጋር የምታወራው ነገር የለም ፡እሷ የምትልህን አድርግ አለኝ አፉን ሞልቶ።ተስፋ ቆረጥኩ ፡ወደበሩ አየው ከምሯን በዚ በለሊት ዕፃን አሲዛ ልታባርረኝ ነው እናቴ ለዛውም ባልወለድኩት ልጅ ይሄን ማመን ከበደኝ ፡ዕፃኗ ለቅሶዋን አላቆም አለች ፡
"ስማ እማዬን አልሰማሃትም ልጅህን ይዘሃት ውጣ"አለኝ አቤል አይኑን በጨው አጥቦ
"እናቴ እሱ ድሮም አይወደኝም እቺ ልጅ ግን....."
"ምን እቺ ልጅምን የኔ አይደለችም ልትል ነው እናትየው በፃፈችው ደብዳቤ አረጋገጠችልን እኮ"አለ አቤል፡እናቴ ድጋሚ በንቀት እያየቺኝ ወደበሩ አሳየቺኝ ከኔጋ ለማውራት ፍላጎት አጥታለች ፡ተስፋ ቆረጥኩ ፡ዕፃኗን አንስቼ አቀፍኳት በጣም ዕፃን ናት የት ነው በዚ ለሊት ይዣት የምሄደው ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎርምስና ጀግንነቴ ተፈተነ አይኖቼ ዕንባ አቀረሩ ፡በዘምቢሉ ውስጥ ተጎዝጉዘው ከነበሩት ወፈር ያለውን ፎጣ ሸፋፍኛት ፡ ወደበሩ ተራመድኩ ፡ እናቴ
"ስማ ዛሬ ለሊት ይለፍልህ ነገር ግን እኔ ከመነሳቴ በፊት ቤቱን ለቀ ጥፋልኝ "አለች እናቴ አሳዘነችኝ ከፊት ከዋላዋ ተኩላው ልጇ በፍቅር ሰበብ ሰቅዞ ይዟታል ምንም የምትመረምረውም ነገር የላት ፡ ,,,,,,,,

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍82😢2113🤔5👏2
👉👉የእናቴ ልጅ👉👉
ክፍል ስምንት
🔮🎈🔮🏮🎈🔮🎈
ለካንስ የሰው ልጅ አንዴ ውሸትን መለማመድ ከጀመረ  እንደ እውነት ነውና የሚቆጥረው ፡ ሌላው ቀርቶ ሰው ሲዋሽ ፊቱ ላይ የሚገለፅ አንዳች እንቅስቃሴ አለ ይባላል  ኖኖ ግን እሱ የሚሰራው ድንገት ተቸግሮ የሚዋሽ ሰው ሲሆን ብቻ ነው ፡ እንጂ ሆነ ብሎ ውሸትን መጠጊያው አድርጎ የሚኖረው ላይ አይደለም  በጣም የሚገርመኝ ደሞ ሰውየው እራሱ ውሸቱን እስከማመን የሚደርስበት ነገር ነው ፡  እውነት ለመናገር የወንድሜን ያላንዳች የገፅታ መለዋወጥ ፡ሁሉንም ነገር በኔላይ ማላከኩ ትልቅ ፍራቻን ፈጥሮብኛል ፡ፍራቻዬ ለራሴ ብቻም አይደለም ፡ ለሱም  ለእናቴም  ጭምር ነው ፡ምክንያቱም ይህን ልምድ ድንገት ያገኘው አይመስለኝመሰ እየተለማመደው ነው የመጣው ፡በዚ አይነት እናቴ በኔላይ ጥላቻ እንዲያድርባት ሰርቷል ማለት ነው ፡ እናቴ በበፊቱ እረባሽነቴ ብቻ ሳይሆን እሱ ፈጥሮ በሚነግራት ነገር ነው ልትጠላኝ የቻለችው ብዬ ደመደምኩ ፡ ይሄ ባህሪ ደሞ ፡ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን አልፎ ወጥቶ የቀረቡትን በሙሉ ሊያሳዝን እንደሚችል ተሰማኝ ፡ከባድ ነገር ነው ፡
👉ዕፃኗን ታቅፌ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ዘጋው ፡ እናቴ እርግማኗን ስታዥጎደጉድብኝ ይሰማኛል ፡በቃ እናቴን መከራከሬ እንደማያዋጣኝ ተገነዘብኩ ፡ምንም ያክል እውነት ብናገር የአቤልን ውሸት መደምሰስ እና የእናቴን ቀልብ መመለስ እንደማልችል ገብቶኛል ፡ ከኔ ይልቅ የታማኙ ለስላሳ ልጇ ቃላት ልቧን ይሞላዋል ፡አይለኛና ጉልበተኛ አልሸነፍ ባይ ብሆንም ፡ይሄ ነገር እናቴ ላይ እና ወንድሜላይ ሲሆን አይሰራልኝም ፡ በተለይ እናቴ የቱንም ያክል ብትጠላኝ ፡ እሷላይ መጨከን የሚችል አንጀት የለኝም ፡ እንኳንስ አንድ ነገር ሆና አይቼ ቀርቶ ፡መንገድ ላይ እንኳ ከሷ ዕድሜ የምትቀርብ ሴቴ አንዳች ችግር ገጥሟት ካየው ውስጤ ስፍስፍ ነው የሚልብኝ ፡  ወንድሜ በዚመጠን ቢጎዳኝም እሱላይ እጄን ማንሳት ይከብደኛል ፡እንደው በጩኽት እንኳ ሳናግረው እናቴ ስለምትከፋ ለሷ ስል ነገሮችን የምተው ነኝ ፡
ዕፄኗ አልጋዬ ላይ ፍልስስ ብላ አንቀላፍታለች ፡ጠጋ ብዬ ሳያት በአንድ ጎን ባለው ጉንጯ ላይ ፈገግ ያለች ትመስላለች ፡ ይሄን ፈገግታ አውቀዋለው አቤል ነው ወደጎን ፈገግ የሚለው  ልጅ እያለን በጣም ነበር የምወድለት ፡ ቅላቷ ልክ እንደ እናታችን ነው እኔም ሆንኩ አቤል ጠይም ነን ፡ ሁለታችንም መልከመልካም ፡ብንሆንም ፡ አቋምን በተመለከተ እንግዴ እኔ ረዘም ያልኩኗ የተስተካከለ አቋም ነው ያለኝ ፡ አቤል ወፈርፈር በማለቱ ቁመቱ ባያሳጣውም ከጊዜ በዋላ የመጣበት ውፍረት ትንሽ የቀነሰበት ነገር አለ ፡ እናታችን ቆጆ ናት ዕድሜዋ ወደ አርባ አምስት ነው ነገር ግን አሁንም ከፈለገች ፡ የምትወደውን ወደ ሕይወቷ ማምጣት የሚችል አቋም ላይ ናት ፡ 
የዕፃኗ መልክ ግን ከፈገግታዋ በቀር እኛ ቤት አይደለም ፡ የማላውቃትን እናቷን ቁንጅና ሳትወርስ አትቀርም ፡በጣም ታሳሳለች ፡ ገና ናት ከሶስት እና ከአራት ወር አታልፍም ፡ ምስኪን ከማይረቡ ሁለት መናጢዎች ተወልዳ ፡በእናቷ እቅፍ ውስጥ መሆን ሲገባት ፡ ምንም በማያውቀው እብዱ ነን ታኒየም ላይ ተጥላለች ፡  ለሊቱን ሙሉ ሳስብ ነበር እንዴት ነው የማደርጋት ፡ እኔም አንዱ ጥግ ወስጄ ጥያት ሕይወቴን ልቀጥል ፡ ወይስ እዚሁ ቤት ጥያት ልጥፋ፡ ወይስ አዝያት እያባበልኩ ፡ልመና ልውጣ ፡ ግራ ገባኝ ፡ እንቅልፍ እሚባል ባይኔ ሳይዞር ነው ያደርኩት ፡  ከለሊቱ አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ፡የክፍሌ በር ተንኳኳ ደንግጬ ተነስቼ ከፈትኩ ፡ አቤል ነበር ኮስተር እንዳለ
"እስካሁን እዚ ነህ ከመነሳቷ በፊት ዲቃላህን ይዘህ አትሄድም "አለ ፡ማመን አቃተኝ
"የኔ ልጅ እንደሆነች ታስባለህ ?"አልኩት በጩኽት እኔ እንደሱ ቀስብሎ ማውራት አልችልም ለዛም ነው ሰው የማይረዳኝ
"ስለሱ አይመለከተኝም እናቴ ያለችህን ሰምተሃል እሷ ከመነሳቷ በፊት ከዚ ብትሄድ ይሻላል"አለኝ ግድ ሳይሰጠው
"ለምን ዲሄንሄ አናስመረምርም "
"ገንዘብ ካለህ አስመርምራ "አለኝ አይኑን እንደማርገብገብ ብሎ ስለዚ ጉዳይ ያሰበበት አይመስልም
"እሱ ወደፊት የማይቀር ነው እኔ ምንም እንዳላረኩ አውቃለው እናቴ እንድታምነኝ ስል ግን ተመልሼ መጥቼ ማስመርመሬ አይቀርም እንዳትረሳ ፡እኔ እንኳን ላስወልድ ቀርቶ የሴት ልጅ ከንፈር በቅጡም ስሜ አላውቅ  "አልኩት ፡በጣም ሳቀ መልሶ አፉን እጁ ላይ በመጫን ወደክፍሉ ገባ ።  ጭንቅላቴን ይዤ አሳብ እንዲመጣልኝ ወተወትኩ ፡ድፍን አለብኝ ፡ ወደ ዕፃኗ ተጠግቼ ቆምኩ ከእንቅልፏ ነቅታ አይኖቿ ይንከራተታሉ ፡ እልህ ያወኝ ፡ማንንም አልለማመጥም የሆንነውን እንሆናለን በቃ ፡ መንጃ ፍቃድ አወጣለው ብዬ ያስቀመጥኩት ጥቂተሰ ብር ነበረኝ እሱንአውጥቼ ያዝኩ ወፈር ያሉ ልቅሶቼን በሻንጣ ከተትኩ  እናቷ የላከችውን የዕፃኗን በቁጥር ያልበዛ ልብስ ያዝኩና  በፎጣ ጥቅልል አድርጌያት ተነስቼ ፡ወደበሩ አመራው እናቴ እንዳትሰማ በጥንቃቄ ነበር የምጓዘው ከግቢው ስወጣ አቤል ተከትሎኝ ኖሮ በፍጥነት ለዘላለሙ ይመስል በሩን ዘጋብኝ ጨለማው ገና አልገፈፈም ፡አምላኬን አንድ ነገር ለመንኩ እባክህ እናቴን ከዚ መሰሪ ልጅ ጠብቃት ፡ ,,,,

ደራሲ unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍8125👏3😁2
💰🔮የ እናቴ ልጅ🔮💰
👉👉ክፍል ዘጠኝ👉👉
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
አንዳንዴ ወዴት እንደምትሄድ ሳታውቅ፡ ግን እግርህ መራመዱ አይገርምህም ? በቃ አንተ መድረሻህን አላሳወከውም ፡እሱ ግን ይንቀሳቀሳል ፡ እግራችን አመፀኛ ሆኖ  'የት እንደምንሄድ ካልነገርከኝ ካልወሰንክ አልንቀሳቀስም 'ቢል ኖሮ ምን ይውጠን ነበር ? በእርግጠኝነት ብዙ ሆቻችን አንድ ቦታ ተዘፍዝፈን እንቀር ነበር😂 ጥሩ እነቱ እግር አልሄድ አይል ፡ የት እንደምሄድ ሳላውቅ ዕፃን ልጅና ሻንጣ ተሸክሜ የሌሊቱን ብርድ ቻል አድርጌ  ጉዞዬን ቀጠልኩ ፡  ሰፈራችን ውስጥ አንድም ነብስ አለመንቃቱ ጠቀመኝ  ማንም አላየኝም  ሌላው ቀርቶ ውሾቹ እንኳ እንቅልፍ ጥሏቸው ጥግጥጉን ተረፍርፈዋል ፡ ተመስገን አይለኛና ተፈሪ በሆንኩበት ሰፈር ልጅ ታቅፌ በለሊት ብታይ ፡እናቶቹ የቡና ማጣጫ ፣ አባቶቹ የመጠጥቤት ውሎ ማድመቂያ ፣ጎረምሶቹ የጫት ቤት ሙድ መያዣ ነበረ የሚያደርጉኝ ፡ 
   ከሰፈራችን ለቅቄ ስወጣ እፎይ አልኩ ፡ የመስቀል አደባባይን አስባልት ይዤ ወደፊት ተራመድኩ  ፡ያው ሰፈራችን ከኢግዝብሽን ማህከል ጀርባ እንደመሆኑ መጠን ፡ በለሊት ወደ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የሚሄድ ሰው አይታጣም እና ጠንቀቅ ማለቱን አልዘነጋሁትም ፡ አልፎ አልፎ ነጠላ የለበሱ እናቶች ባጠገቤ እልፍ ሲሉ እራሴን ሰብሰብ አደርጋለው ፡  ይህ ሁኔታዬ ለራሴ አሳዘነኝ ፡እራስህን በሌላ ሰው መነፅር አይተህ ለራስህ አዝነህ አታውቅም ? አዎ በቃ እንደዛ ....በእስጢፋኖስ በኩል ሳልፍ ቆም ብዬ ተሳለምኩና ፀሎት አደረኩ ' ቅዱስ እስጢፋኖስ ከአምላኬ ጋር አስታርቀኝ ፈጣሪዬ ፈተናዬን ይቀንስልኝ ዘንድ እርዳኝ 'አልኩ  አንድም ቀን ፀልዬ ስለማላውቅ ምን እንደምል ፣እንዴት እንደሚለመንም አላውቅ ፡ግን በራሴ መንገድ ለፈጣሪዬ እንዲደርስልኝ ዕንባ ዘለላዎችን በለሊት አንጠባጠብኩ ፡  የታቀፍኳትን ዕፃን አየዋት የሰላም እንቅልፍ ላይ ነች ፡ በዚ በዚ አድናቂዋ ነኝ አንዴም አላለቀሰች ፡ እኔን ማስጨነቅ አለመፈለጓ ጥሩ ነው ፡ ምን አልባት ፈጣሪዬ በዚ እየረዳኝ ይሆናል ተመስገን ማለትን በዚ አጋጣሚ ተማርኩ ...
👉ለካ ላይችል አይሰጥም የሚሉት እናቶቻችን ወደው አይደለም ፡የአለምን አዙሪት ትችለዋለህ ስቃዩ ከብዶ አልቻልኩም ብትልም ችለህ ቆመ ትራመዳለ ፣ርሃብ አልችልም ብትል ብቸኝነት አልችልም፣ ከሰው መለየት አልችልም  ሰው ማስቸገር አልችልበትም ብትል ፡ ምንም አታመጣም እስትንፋስህ እስካለች ፡አለመቻልን እራሱ ትችለዋለ ......
ከማማ ጋር ጎዳና ከወጣን ሰነባበትን ፡ ቤት ንብረት ያለው ሰው ብቻ አይደለም ለካ የሚያስጠጋህ ፡እነሱንማ አየናቸው ከንፈር ከመምጠጥ በዘለለ ምንም አይፈይዱልህም ፡  ካላቸው ሚሊዮን ብሮች መሃል አስር ብር ሰጥተው ላንተ ባደረጉት ነገር አካብደው ፅድቅ የሚጠብቁ ስንቶቹ መሰሉህ ፡አንድ ስንዝር ሕይወትህን የማይቀይር ሳንቲሞች ሰጥተው ፡ለምን አትሰራም ብለው የምክር አገልግሎት የሚሰጡህ በቱ የሚሉ ቁጠራቸው ፡  ከእነሱ በተሻለ መጠጊያ የሰጠችኝ እትዬ ባዩሽ ምስጋና ይድረሳት ፡ኮልፌ ላስቲክ ወጥራ ነው የምትኖረው ፡ ብዙ ነገር ያየች ናት ፡የኑሮ አጋጣሚ ባዶ እጇን አስቀርቶ ጎዳና ያወጣት ፡ ፊቷ እንደ ከሰል ቢጠቁርም ልቧ የነፃ ፡ አዛኝ ፡ የነበረኝን ገንዘብ በሁለት ወር ውስጥ ለክራይ እና ለሚበላ ለማማ ወተት ስገዛ ጨርሼ መግቢያው ጠፍቶኝ ስንከራተት ውዬ ደክሜ ድልድይ ስር ቁጭ ብዬ  ሳዛጋ ነበር ያገኘችኝ ዕድሜዋ ልክ እንደ እናቴ ነው አርባዎቹ ውስጥ ፡ አጠገቤ መጥታ ስትቆም እብድ መስላኝ ነበር ፡በዋላ ስረዳት ለካንስ አሳዝኛት ኖሯል ፡  ስላለውበት ሁኔታ ጠየቀችኝ ነገርኳት ዕፃኗን ግን የራሴናት ነው ያልኳት ፡ከዚ በዋላማ የማንም ልትሆን አትችልም ፡ ከዛ ነው እንግዲ ወደቤቴ ና ብላኝ የወሰደችኝ ፡መጀመሪያ የእውነት ቤት መስሎኝ ነበር በዋላ ግን የላስቲኳን ቤት ሳይ ቀፈፈኝ እንዴት በዚ መጠን ወርጄ እገኛለው ብዬ ተናነቀኝ ፡ ግን ምን አማራጭ አለኝ ምንም የስቃዬ መጀመሪያ ሊጀምር ነው አልኩ ፡ ባዩሽ ግን ሁሉም ደና ይሆንልሃል አለችኝ ለጊዜው እዚ እረፍ  የጨካኞቹን ቤት አከራዮች ሆድ የምትሞላበት አቅም ላይ አይደለም ያለኽው ከጠበበንም ሰፋ እናደርገዋለን ፡ አለችኝ  አዘን ብሶቴን ዋጥ አድርጌ ይሁን አልኩ ፡  ለጊዜው ነው እንጂ ማማንማ እዚ እንድታድግ አላደርግም ፡ ብዬ ወሰንኩ
   ከባዩሽ ጋር በጣም እየተለማመድን ስንመጣ የዋህ ልቧ ይገርመኝ ጀመረ  ያገኘችውን ሁሉ እኛን ለማስደሰት ብላ ይዛ ትመጣለች ደግ ነች ፡ ይሄ ደግነቷ እንዳምናት አደረገኝና ፡በቃ ማማን እሷ ጋር እያስቀመጥኩ ለምን አልሰራም ብዬ ወሰንኩ  እና ስራ መስራት ከባዩሽጋር ተስማምቼ መንቀሳቀስ ጀመርኩ  ኮልፌ አካባቢ ሰፊዎች አሉ እና ለነሱ ጣቃ ከመኪና ላይ ማውረድ መጫን በቃ ያገኘውትን ነገር ሰራው ፡ ጎዳና ላይ ወጥቶ ላስቲክ ቤት ከመኖር የከፋ ነገር አለ እንዴ ሂሉኝታ ደና ሰንብት አልኩ ፡ጉልበቴን ተጠቀምኩት ፡ ገንዘብ አገኝ ጀመር ፡ እና ገንዘብ ሳገኝ የመጀመሪያ እቅዴ ማማንና ባዩሽን ከላስኪቱ ቤት ማላቀቅ ነበር እናም ተሳክቶልኝ አነስተኛ ቤት ተከራይተን ገባን ፡ ባዩሽ ትንሽ አስቸግራኝ ነበር እኔ ግን አንቺ ማለት የእናቴ ምትክ ነሽ አንቺ በሕይወቴ ውስጥ ቦታ አለሽ ስለዚ መቼም ትቼሽ አልሄድም አልኳት በመጨረሻ ተስማማች ፡ ኑሮ ተጀመረ ፡ አንድቀን ባዩሽ  እንዲ አቸኝ
"እኔ የምልህ ናቲ እንደው የዝህች ልጅ እናት በቃ ዝም ነው የምትባለው ?ምን ልባት እኮ ወደ እናትህ ቤት ተመልሳ መጥታ ልጄን ብላ ጠይቃ ይሆናል ፡መቼም ሴት ልጅ እንዴት እንዳማጠች ስታውቅ ሁሉን ትረሳለች ማለት ከባድ ነው "አለችኝ
"ባያ ዝም በይኝ እሷ በጭራሽ አትመጣም አረብ አገር ሳትሄድ አትቀርም "አልኳት ውሸት ቀላቅዬ ፡እንዴት ብዬ ወንድሜ አላኮብኝ ነው ብዬ አወራለው ለሰሚውም ግራ ነው
"አይ እንደው እኮ ብትመጣ አንዴ እንኳ ጥሩ ነበር ፡የልደት ቀኗን እንኳ አታውቀውም "ስትለኝ በጣም ተገረምኩ ፡እውነት ለመናገር ትዝ ብሎኝም አያውቅ ነበረ ከችግር ለመውጣት ከመፍጨርጨር በቀር
"ባክሽ አንዱን ቀን ማክበር ነው የሦስት ወር ነበረች እሱን አስልቼ ማክበር ነውኪኪኪኪ እንደውም ለምን በሃያ ሰባት አናከብርላትም በቃ የመዳኒዓለምን ቀን ያዢውና ሁለተኛ ዐመቷን እናከብርላታለን"አልኳት ባዩሽ ወይ አንተ ልጅ ብላ ሳቀች "ሌላው ክትባት ወስዳ አታውቅም አይደል በቅርቡ አኪም ሊያያት ይገባል"ብላ አከለች ፡ወይጉድ ማማዬ በዛ መሰሪ ወንድሜ የተነሳ ስንት ነገር ቀርቶባታል ,,,,,,,,,,


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍11117🥰7👏3
👉🔮 የ እናቴ ልጅ🔮👉
🔮🎈ክፍል አስር🎈🔮
👉👉👉👉👉👉👉👉
ይገርማል እንደ ቀልድ ቀን ቀንን እየተካ አመታት ይቆጠራሉ !! ዕፃናት ያድጋሉ ወጣቶች ጎልማሳ ይሆናሉ ጎልማሶች ያረጃሉ  አዳዲስ ሕይወት ይመጣል የቆየውም ያልፋል ፡ ለሁሉም ወር ተራ ነው ፡
👉ዛሬ ለማማዬ ሁለተኛ አመቷን አከበርንላት ፡እኔና ባዩሽ ብቻ በትንሿ የክራይ ቤታችን !!ሁለት ቁጥር ሻማ ሳበራ ፡ ድንገት የባነንኩ ይመስል ያሳለፍኩት ምስቅልቅል ከፊቴ መጥቶ ተደቀነ ፡ የወንድሜ ጭካኔ የእናቴ  ጥላቻ አሁን እንደተደረገ ይታየኝ ጀመር ፡ እንደ አዲስ አንገበገበኝ ያምሽት፡  እናቴ እሩሩ ልብ ቢኖራት ኖሮ  ጨክና  አትተወኝም ነበር  ይቅር ትለኝ ነበር ፡ ለሊቱ ከመንጋቱ በፊት ዲቃላህን ይዘህልኝ ጥፋ በጭራሽ እንዳላይህ የሚለው የእናቴ የቁጣ ቃል ዳግም አይምሮዬላይ ተንጫጫብኝ ፡የአቤል ያፈጠጠ ውሸት እና ማስመሰል ሁሉም ተመላለሰብኝ ፡በጣም ተከዝኩ ፡  .....
ባዩሽ ነበረች ያባነነችኝ "አንተ ምን ሆነሃል ሻማውን ጎትታ ልትጥለው ነበር እኮ "አለችኝ
"ውይ የሆነ አሳብ ውስጥ ገብቼ እኮ "አልኳት
"ምንድነው እሱ ናቲዬ ስራቦታ ችግር አለ እንዴ?"አለችኝ እያሳሰባት ፡
"አይ ስለ ስራ አይደለም እንደው እናቴ ትዝ ብላኝ ...."ብዬ ቀእንጥልጥል ተውኩት
"እንደው ናቲዬ ካመጣህው አይቀር እንደው እኔም ብሆን እያስብኩልህ ነው እስከመቼ ነው ከእናትህ ተደብቀህ ልጅ የምታሳድገው በጣም ያሳስባል?!"አለች
"አይ አይ ተደብቄ አይደለም እሷ ናት በለሊት ከነ ዕፃን ልጅ ያባረረችኝ  ምንም እርህራሄ አነበራትም ይህን ያደረገችው ለክብሯ በማሰብ ነበር  የኔ ነገር ምንም አላስጨነቃትም ፡ በዛላይ የኔ ..."ብዬ ዝም አልኩ
"ያንተ ምን?"
"ተይው በቃ እንደው ስሜታዊ ሆኜ ነው"አልኳትና ዝም ብዬ አየዋት ፡እስከዛሬ ትክክለኛውን ሚስጥሬን አልነገርኳትም ፡
"ንገረኝ ነገርን በውስጥ መያዝ ጥሩ አይደለም ፡"አለችኝ
"አይ እንደው ነገሩ ትንሽ የሚከብድ ነው ፡በእርግጥ እንደሞኝ ካላየሺኝ የደበኩሽን ሚስጥር ዛሬ እነግርሻለው ፡"
"ናቲዬ አንተን እንደሞኝ ላይ በጭራሽ አንተ እኮ ሰው ያደረከኝ ሰው ነህ ፡ "አለችኝ ዕንባ ባዘሉ አይኖቿ እያየችኝ
"እነግርሻለው ግን ያለማቋረጥ ስሚኝ እና ደሞ የምነግርሽ ነገር ለማመን ቢከብድም እውነት ነው "አልኳት ፡አንገቷን ነቅንቃ በጉጉት ጆሮዋን አቅንታ ታዳምጠኝ ጀመር ፡ባዩሽ የኔንና የወንድሜን አስተዳደግ ከመጀመሪያ ጀምሮ ስነግራት ፡ፈገግ እያለች አንዴም ኮስተር እያለች ተከታተለችኝ ፡ በመጨረሻም የአቤልን ለውጥና ፡ በድንንገት የልጅ አባት መሆንና ፡ በኔላይ ያለምንም አፍረት እንዳላከከብኝ ፡እናቴም ይህን አምና መቀበሏንና ፡ሁለቱም ተጋግዘው ከቤት እንዳስወጡኝ ስነግራት ፊቷ በአንዴ ተለዋወጠ ፡ሰውነቷ የተንቀጠቀጠ መሰለ ፡በመገረም እንደ አዲስ ሰው ታየኝ ጀመር ፡ ዝምብዬ የምትለኝን ለመስማት ስጠባበቅ ድንገት ከተቀመጠችበት ተነስታ "እውነትም ሞኝ ነህ የሞኝ ሞኝ ፡እንዴት ባልወለድከው ልጅ የኔናት ብለህ ትሰቃያለህ ፡እንዴት እንዲ እንዲያደርግህ ትፈቅድለታለህ እንዴት ፡ እሺ የሆነስ ሆነና ተመልሰህ ሄደህ እናትህን ማሳመን አልነበረብህም ፡ እንደዛ በዚች ዕፃን ልጅ የተነሳ እንደሴት አዝለህ ወተት እያፈላህ  የተሰቃየኽው ባላረከው ነገር ነው ፡ያሳዝናል ፡ "ብላ ወቀሳም አዘኔታም ያለበት ጩኽት ጮኽችብኝ
ግራገባኝ ነገሩ ከኔ በቀር ለማንም አይገባውም ማለት ነው እኔ እኮ ስለ እናቴ ነው ይህን የምከፍለው  እሷ ከኔ ይልቅ ለአቤል ቦታ አላት ያ ስሜት እንደተጠበቀ ካልኖረ የምታብድ ነው የሚመስለኝ ,,,,,, አይኔን ጨፍኜ ነገሮችን እንደ አዲስ ለማየት ሞከርኩ.......

ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍11824🥰5🔥4
👉👉የ እናቴ ልጅ👉👉
🎈ክፍል አስራ አንድ🎈
🔮🔮🔮🔮🔮🔮🔮
አንዳንድ ሰዎች ልብ ብለን ካየን አብዛኛውን ጊዜ ከራሳቸው ይልቅ በሌላሰው ችግር ነው የሚቸገሩት ፡ የቤተሰባቸው አካል የሆነ ሰው ወይም ጓደኛቸው ፡ በሆነ ሰው የተበላሸውን ነገር ለማስተካከል ሲጥሩ ፡ ጊዜ አቸውን አቅማቸውን ያለ አግባብ ያባክናሉ ፡  እንደ እውነቱ ሁሉም የየራሱን የቤት ስራ ቢሰራ ኖሮ  ስንት አስቸጋሪ ነገሮች በተቀየሩ ነበር !! ነገርግን አንዱ በሕይወት ውስጥ ደክሞ ሲሸሽ ሌላው  ከራሱ ጋር አብሮ የሱንም ድክመት ተሸክሞ ለመለወጥ ይፍጨረጨራል ፡  ከእይወት እንደተረዳውት  ማንም የማንንም ሸክም መሸከም የለበትም ፡የሚለውን ነው ። ከቻልክ ሸክሙ እንዲቀልለት መንገዱን ማሳየት ነው!
👉👉 ባዩሽ ሰሞኑን እንደ አዲስ ሰው ነው ስገባም ስወጣ የምታየኝ ከለት እለት አስተያየቷ ከበደኝ ፡ እይታዋ ውስጥ አዘኔታም ቢኖርም እንደሞኝ አድርጋም የቆጠረችኝ መሰለኝ ፡  ይህ ሁኔታዋ ደሞ እራሴን ደጋግሜ እንድፈትሽ አደረገኝ ፡  ለምንድነው እውነታውን የማላወጣው ፡ ለምን ለእናቴ ደብዳቤ አልፅፍላትም ፡እኔን ማየት ባትፈልግ እንኳ ፅሑፉን ማንበቧ አይቀርም ብዬ አሰብኩ ፡ይሄን አሳብ ደጋግሜ አወጣው አወረድኩት ፡ በመጨረሻ ወሰንኩና ለባዩሽ አማከርኳት ፡
"በዩ አንድ አሳብ አለኝ "አልኳት እራት በልተን ፡ማማንም አስተኝታት ፡ቡና ለማፍላት ስትቀመጥ ጠብቄ።አይን አይኔን እያየች ፡በጭንቅላቷ እንድቀጥል ምልክት ሰጠችኝ
"ምን መሰለሽ ለእናቴ ደብዳቤ ለመፃፍ አስቤ አለው ፡ "ስለምን ጉዳይ ?"አለች ባላወቀ
"ስለ አቤል ፡እንደዋሻት እና ዕፃኗ የኔ አለመሆኗን  ፡ብቻ ብዙ ነገር ወቀሳም ጭምር "አልኳት
"እንዴ ናቲዬ አሁን እሱ በድንገት የሚነገር ነገር አይደለም በመጀመሪያ ዝም ብለህ ወደቤት ተመልሰህ የእናትህን ደንነት ማረጋገጥ አለብህ እሱ ቀስ በቀስ የሚደርስ ነው "አለችኝ
"እና ዝም ብዬ ሄጄ የማትፈልገኝን እናቴን ማየት አለብኝ?አንቺኮ ስላልገባሽነው  የጥላቻዋን ጥግ ብታዪው ኖሮ አጠገቧ መድረስ ያስፈራሻል ፡ እኔ ምን ወዲወዲያ አስባለኝ እስካሁን ንዴቷ ይበርዳል ስለዚህ ዕፃኗ የኔ አለመሆኗን አስረግጬ ነው የምፅፍላት ፡ "
"እንደሱማ አይሆንም እውነት ብትቀበል እንኳ ከዚ በዋላ ማማን አሳልፎ የመስጠት አንጀት አለህ ፡ "አለችኝ ፡ የሰላም እንቅልፋን ወደምትለጥጠው ማማ እያሳየችኝ ፡ፈገግ አልኩ
"በዩ ማማ እኮ መቼም አትለየኝም ምክንያቱም በተዘዋዋሪ ያው ደሜ ናት የትም አላጣትም ቤተሰቤ ናት ፡"አልኳት ፡ ያ ተንከሲስ ልጅ ቢያምን እንኳ ማማን አሳልፌ አልሰጠውም የምፈልገው የእናቴን ይሁንታ ብቻ ነው ፡
"እሺ እናትህ ማወቋን እኔም የምፈልገው ጉዳይ ነው ነገርግን ከደብዳቤው በፊት ሄደህ እያት ምን አልባት ነገሮች ተቀይረው ይሆናል ሁለት አመት ቀላል አይደለም የሰውልጅ አሳቡን ለመቀያየር አንድ ቀን ይበቃዋል ባሁን ጊዜ ፡ ስለዚ ሄደህ በአካል ተገናኛቸው ወንድምህም ቢሆን ተፀፅቶ ይሆናል ፡የዕፃኗ እናትም ብትሆን አርፋ ላትቀመጥ ትችላለች ፡ "አለችኝ አንገቴን በመነቅነቅ ተስማማውላት ፡  ነገ ሁለት አመት ሙሉ ጨክኜ ከጠፋውት ሰፈር የእናቴ ቤት ልሄድ ቆረጥኩ ፡ ስወስን አካባቢው ናፈቀኝ ለገሐር ኤግዚቢሽን ማህከል እስታዲየም ፡ እሲጢፋኖስ ቤተክርስቲያን መስቀል አደባባይ ፡እሄድባቸው የነበሩት የሰፈሬ አቅርያቢያ በሙሉ ናፈቁኝ ፡ይገርማል ሁለት አመት እንዲ አጭር ናት ለካ እራሴን በማማ እና በስራ ወጥሬ አልታወቀኝም ፡ በሁለት አመት ውስጥ ቁም ነገር የሰራውት ማለቴ ለኑሮዬ የተመኘውትን መንጃ ፍቃድ በቅርቡ ማውጣቴ ነበር ፡ የገንዘብ ችግር አሁን የለብኝም እድሜ ለጉልበቴ የአቅሜን አግኝቻለው ፡  የወደፊትም አሳቤ ከዛም በላይ ነው ብዙ እቅዶች አሉኝ ማማ ጠንካራ ሰራተኛ አድርጋኛለች ፡ የነገ መሄዴን እና እናቴን ማግኘቴን ሳስበው ጨነቀኝ ፈርሃት ፍርሃትም አለኝ ፡ ,,,


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍11118😁6👏2
🎈🔦የ እናቴ ልጅ🔦🎈
👉ክፍል አስራ ሁለት👉
💰🏮💰🏮💰🏮💰
አንድ ነገር ስትይዝ ወይም በበነገው የሆነ ጉዳይ ካለህ ፡ አንተም አትተኛ ሌቱም ቶሎ አይነጋ ፡ የሌለ ነውቅርፍፍ የሚልብህ ፡ በዛላይ እያነሳህ የምትጥላቸው አሳቦች መብዛቱ ፡  በባዩሽ ሁሌም እንደቀናው ነው በነገራችን ላይ ፡ከተኛች  ምንድነው የሚባለው ...አዎ  መትረየስ ቢጮህ  አትነቃም ...ብዙ ጊዜ ማማ ለሊት ጡጦ ፈልጋ ወይም ዳይፐሩ ሲረጥብባት ፡ታለቅሳለች ፡ባዩሽ  አትሰማም ፡ ሐዛ ብዬም ነው  ማማን አዳሯን ከኔጋር የማደርገው ፡ ይህ የለሊቱ የህፃናት መቀስቀስ የሚያውቅ ያውቀዋል ፡ቀውጢ በሆነ እንቅልፍ ውስጥ ስትሆን ፡ የህፃን ለቅሶ ስትሰማ  አስበኽዋል ፡ከዛ ተነስተህ ታባብላለህ ፡አልሆን ይልሃል ወተቱ ማለቁን አስተውለህ ጡጦውን አጥበህ ወተት ትሞላለህ ፡ ዝም አልል ሲሉህ ገለጥለጥ አድርገህ መሽናታቸውን ታያለህ ፡ እናም ተራርሰው ታገኛቸዋለህ ፡ ዳይበር ትቀይራለህ ፡እንቅልፍ እንደሰካራም ቢያንገዳግድህም መፍትሄው እሱው ነውናትችለዋለህ  ፡ አስበው እኔ በድንገት ከነዚ ሁሉ ነገሮች ጋር ነው የተፋጠጥኩት ፡ከኑሮ መክበድ ብቻጋርም አይደለም ፡ አንዳንዴ ሳስበው የእናቴን መከራ ሊያሳየኝ ይሆን እንዴ ፡ እላለው ፡ ለብቻዋን በዕድሜ ተቀራራቢ የሆንነውን ልጆቿን አሳድጋለች አንድም ሰው ነብስ እስካወኩበት ጊዜ ድረስ ሲያግዛት አላየውም ፡እና ሳስበው የሁሉም እናቶች ብርታት አስደናቂ ነው ክብር ይገባቸዋል ብያለው። ስለ እናቴ ግን ሌላው ቀርቶ በምን ገቢ እንደምታስተዳድረን እስከዛሬም ድረስ ግልፅ አልሆነልኝም ፡  በእርግጥ በግንብ የተከለለ የተንጣለለ ግቢ ያለው  ቤት አለን  የክራይቤት አደለም ሰርቢስ ቤቶች ቢኖሩም አንድም ቀን አከራይታ አታውቅም ፡ ነገርግን ከሆነ ቦታ ገቢ አላት ግን አትነግረንም ፡ በወር አንዴ ብቻ ትወጣና ቆይታ ትመጣለች የዛን ሰሞን በወሩ መጀመሪያ ማለቴ ነው ፡ጤፉም አስቤዛውም ፡ለኔም የኪስ ገንዘብ ትሰጠኛለች ፡ከየት መጣ ምናምን የመጠየቅ መብት የለኝም ፡  እንዲ ናት እንግዲ እናቴ በሚስጥሮች የተሞላች ፡ ማውራት የማትወድ ..........
👉ባዩሽን ቀስቅሼ ከማማጎን እንድትተኛ ነገሬ ፡ወጣው ፡ የጠዋቱ ብርድ ያንዘፈዝፋል የአምሌ ዝናብ ነው ፡ወይ አይዘንብ ንጭንጭ ያደርገዋል ፡የለበስኩት ባለሹራብ ጃኬት ከብርዱም የሚያስጥል አይመስልም ፡ በዛላይ ከሰውነቴ ተጣብቋል  ሰውነቴ ጨምሯል ፡የምወፍረው እንደው ዝምብሎ ስላልሆነ ተመስገን እላለው በተስተካከለ ቁመናላይ ፈርጠም ያለ አካል ነው ያለኝ ፡ ብዙዎች ይወዱልኛል ፡አዲስ የያዝኩት ጓደኛዬ ወፈር ያለ ነው ፡እና ብዙ ጊዜ ይሄን ሰውነት ይዤ ስንቷን ነበር ጠብ የማደርግበት ይለኛል እስቃለው ፡ እውነት ሴቶች በቁመናህ ማማር ብቻ ጠብ የማለት ጉዳይ አልዋጥልህ ይለኛል ፡  ምናልባት ለሳምንታት ሊሆን ይችላል ፡ከዛ በዋላ ሴት ልጅ ከአንድ ወንድ የምትፈልገው ብዙ ነገር አላት ፡ እሱን ለሴቶቹ ልተወውና ፡  .....
ከአጠና ተራ    ሰባተኛ አቶቢስተራ በሚለው ታክሲ ተሳፍሬ ገባው ፡ የተቀመጥኩት ሦስተኛ ተደርቤ ነበርና ምቾት አልሰጠኝም ፡ እስከምወርድ ተጨነኩ ፡ ይሄ አዲሳባውስጥ የእዝብ ቁጥር መጨመር በየሄድንበት እንግዲ ምርጫ ስለሌለን ያቻችለናል አልችልም ብትል ምን ታመጣለህ !
ሰባተኛ ወርጄ የእስታዲየምን ታክሲ ለመያዝ ተወዘወዝኩ ፡ በዛላይ ካፊያው ፡ ከምሆድበት ቦታጋር ተዳምሮ ይብስ አሸበረኝ ፡ ወደታች አንድ ታክሲ ገንጠል ብሎ ሲሄድ ሰውን ቀድሜ ሮጥ አልኩኝ ፡ ስደርስ 'ይቅርታ አይጭንም 'አለኝ ኤጭ ብዬ ስመለስ  ፡ አንድ ፖጃሮ መኪና ውስጥ የተቀመጠሰው እጅ ተውለበለበልኝ ፡ ጠጋ ስል ሴት ናት ፡ ዕድሜም ተቀራራቢ ነን 'ውይ ለዚች ደሞ ይሄን መኪና ማን ሰጥቷት ነው ፡መቼም በዚ እድሜዋ ሰርታ አትገዛውም ፡ወይ ከውጪ መጥታ ፡ወይ አባቷ አብታም ነው ወይም ሙሰኛ ነው ፡ወይም አብታም ባል አላት ፡ወይ ወይም...'አልኩ ግን ምን አገባኝ ፡! በጣም ስጠጋት ፡አሁን ገባኝ በራሴ መንገድ ትንፋሽን ለሰከንድ የሚያቋርጥ ውበት ፡ ለዚማ እንኳን መኪና ዓለምን ይሰጧታል አልኩ ፡
"ግባ ወንድም "ብላ የመኪናውን በር ስትከፍተው ፈዘዝኩ
"ምነው ወደ እስታዲየም አይደለህም እንዴ?"አለችኝ
"ነኝ እሱማ "
"እና ግባሃ ታዲያ እኔም እኮ ወደዛው ስለሆንኩ ላድርስህ ብዬ ነው ፡ "አለችኝ ተረጋግታ እና በትላልቅ ውብ አይኖቿ ውስጤ ድረስ ሰርስራ እያየችኝ ፡አስተያየቷ አስጨነቀኝ ፡የሌለ አይን አፋር አድርጎኝ ቁጭ አለ
"እሺ ካላስቸገርኩሽ "አልኳትና ገባው ዋው ድሎቱ ፡ ቅድም ካጠና ተራ ስመጣ መቀመጫዬ አሳዝኖኝ ነበር ኪኪኪኪ
"ለምን ታስቸግረኛለህ ፡በነገራችን ላይ አውቅሃለው ፡ግን እረጅም ጊዜ አላየውህም "አለችኝ
"እኔን ታውቂኛለሽ ከምር?የት?"ብዬ ጠየኳት
"የሚገርም ትውውቅ ነው ያለን እዛው ኤግዚብሽን አካባቢ ነው የማውቅህ ከጉርምስናህ ጀምሮ ሁሌም ግን ስትደባደብ ነበር የምታጋጥመኝ ፡ እውነት በጣም ነበር የምትገርመኝ ፡ አንድም ቀን እረፍት የለውም እንዴ ፡ብዬ ሁላ እናቴን ጠይቄያት አውቃለው ፡"
"ከምርሽ !?"አልኳት አፈር ብዬ
"አዎ የእኛ ቤት ከእናተ ቤት በርግጥ ወደውስጥ ገባ ይላል ነገርግን ከእናቴ ጋር ወደ ሱቅ ስንሄድ ብዙ ጊዜ ሰፈር ውስጥ አይክ ነበር ወይ ሰትደባደብ ወይ ስትጎማለል ኪኪኪኪኪ እውነትበጣም ነበር በመገረም የማይህ ፡አሁንእንደዛ አነህ ግን "አለችኝ እየሳቀች ሳቋ እንዴት እንደሚያምር ፡  ይገርማል ሰፈራችን እንደዚህችም አይነት ሴት ነበር ኧረ እኔ ማንንም ልብ ብዬ አይቼም አላውቅ ፡ እንዳለችው ትንሽ ነገር ያስከፋኝና ሰው ካልገደልኩ ነው በዛላይ የሱሴ ብዛት ፡ ይኽው አሁን በማማ ምክንያት ሁሉም ቢቀርም ፡  እኔ የሌለብኝ የሴት ሱስ ነው  ቢኖርብኝማ ይእችን ልጅ አያት ነበር ሆሆሆ እንዴት ነው የምታምረው ፡ ወንድነቴን አስታወሰችኝ እኮ ....
እስታዲየም ስንደርስ ወሬያችን አላለቀም ነበር ፡ፀብ ማቆሜን ስነግራት እየሳቀች ተመስገን አለች ሆሆ የዚን ያክል አሸባሪ ነበርኩ እንዴ አልኩ ለራሴ ፡
ስልኳን ሰጠች ለማመን ከበደኝ ፡እንዲ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም እንኳን በራሷ ፍቃድ ተጠይቃም የምትሰጥ አትመስልም ፡ ተስገብግቤ ነው የተቀበልኳት ፡እሷ እስታዲየም ጥላኝ የምሄድበት ስላለ ነው እንጂ ሰፈር አደርስህ ነበር አለችኝ አመስግኛት ሄድኩ፡የልቤን ምት ጨምራብኝ ሌላ ስራ ጀመርኩ ልቤ ውስጥ
ሰፈር ስደርስ ላለመታወቅ ሽልሽል እያልኩ ነበር ፡ተሳክቶልኝ ፡ማንም ሳያየኝ ቤት ደርሼ የቤቱን መጥሪያ ተጫንኩት ,,,,,,,,,


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍11112🥰11👎4😁2
👉🎈የ እናቴ ልጅ🎈👉
🔮ክፍል አስራ ሦስት🔮
🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮👉
መጥሪያውን ተጭኜ ብዙ ነገር ወደውስጤ ተመላለሰብኝ ፡ፍርሃቴም ጨመረ ፣የእናቴ ቁጡ ፊት መጥቶ ሲደቀንብኝ ፣ወይም የአቤል ተንኮለኛና ትህቢተኛ ፊት ፣ በአንዴ ተመላለሱብኝ ፣ግን ልቤ እየመታ ከዚአካባቢ ተሰወር ቢለኝም እግሬ ግን አልንቀሳቀስ አለ ፣እግሬ በራሱ መመራት ጀመረደሞ ዛሬ ፣ አስገድዶ ያስቆመኝ መሰለኝ ፡ ከቆይታ በዋላ በሩ ተከፈተ ፡ በሩ ሲከፈት ያየውትን ማመን አቅቶኝ ዝም አልኩ ፡ በንሩ የከፈተችልኝ ተለቅ ያለች ሴትዮ ናት ፡በትንሹ እናቴን ትመስላለች ነገር ግን እናቴ አይደለችም ፡ ግራ ተጋብቼ ፈዝዤ ሳያት
"ምን ፈልገህ ነው ጌታው "አለችኝ ድንግርግር አልኩኝ
"ኧራ አንተው ምን ይዘጋሃን ፡አትናገር ከሆን በሩን መልሼው ልግባ"አለችኝ ፡እናቴ የት ሄዳ ነው በሕይወቴ እኛቤት ሌላ ሰው ገብቶ አይቼ አላውቅም ፡እና ማናት ወይስ አዲስ ፀባይ አምጥታ ብቸኝነት ሰልችቷት ፡ማከራየት ጀመረች ፡ወይስ አቤል ቤቱን አሸጣት ፡ዘገነነኝ ፡"አንቺ ማማነሽ "አልኳት ቀጥሎ የምሰማው ነገር እንዳያሳምመኝ ፡እየፈራው
"ኧራ አንተ እራስ ማነኝ ነው የምትል ፡ምን ፈልገህ ነው?"አለችኝ ትህግስቷ እያለቀ
"እኔ የዘውድነሽ ልጅ ነኝ ፡ናታኒየም እባላለው አንቺ ማነሽ ፣እሷ የት ሄዳ ነው?"ብዬ እየተናነቀኝ አከታትዬ ጠየኳት፡ልክ ተናግሬ እንደጨረስኩ መጮኽ ጀመረች ፡ድንብርብሬ ወጣ ፡ ጩኽቷን ሳታቋርጥ ጎትታ ወደውስጥ አስገብታኝ ተጠመጠመችብኝ፡ጭንቀቴ እና ድንጋጤዬ ይበልጥ ጨመረ ፡
"እናቴስ እናቴ ምን ሆና ነው እባክሽ ?ሞታ ነው አንቺ ማነሽ "አልኳት ከእቅፏ ለመውጣት እየታገልኩ ፡ልክ እንደኔ ግዙፍ ናት ፊቷ ብቻ ነው የሴት ቅርፅ ያለው ፡
"እናትህ አለች መቼስ መኖር ከተባለ ፡ብላ ዕንባዋን ማዝራት ጀመረች ፡ከዚ በዋላ ትህግስት አጣው ፡ሴትዮዋን ባለችበት ጥዬ ፡ወደማውቀው ቤት ሮጬ ገባው ፡ስገባ ያየውት ነገር አሳቆ እና አስደንግጦ ባለውበት አቆመኝ ፡ትልቁ ሳሎናችን ልዩ ሆኖ አምሯል  ነገር ግን ፡ ማሃል ላይ በዊልቸር የተቀመጠች ሴት አለች ፡ ምን ልሁን በቁሜ ነበር ከፊቷ ሄጄ የተንበረከኩት ፡እናቴ  እኔ ዘንበል ልበልላት አንገቷን ወደጎን ዘንበል አድርጋ ተቀምጣለች ፡ ሳላስበው ስሜቴ ፈንቅሎኝ ወጣ ፡ በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ ፡ እናቴ እጇ መንቀጥቀጥ ጀመረ  አፍጥጣ ስታየኝ ቆይታ ፡አፏን ለመክፈት ታገለች ፡ልትናገር ፈልጋ ግን አልቻለችም ሲያቅታት የዕንባ ዘለላዎችን ታወርድ ጀመር ፡ ይሄኔ ሴትዮዋ ድንገት ወደቤት ገብታ "እልልልልል ....."ማለት ጀመረች ፡ ቀናብዬ አየዋት ምንድነው እልል ታው የኔ መምጣት ነው  ፡የእናቴን እጅ ያዝኳቸው እንቅጥቃጤ አቸው ለጉድ ነው 
"እሰይ እሰይ ዘውድዬ ተንቀሳቀሰች ፡እንኳን መጣህላት ፡ልጇን ስታይ አነባች "አለች  ተነስቼ ወደ ሴትዮዋ ሄድኩና ያዝኳት"ማነሽ አንቺ ?ምን ሆና ነው?"አልኳት
"ኧረ ዋይ እኔን ልቀቀኝማ ፡ "አለችኝ እያረጋጋችኝ
"እሺ ምን ሆና ነው እናቴ "አልኳት
"እሷማ እንግዲ የዛሬ አመት አካባቢ ነው ፡እኔም እንደው ተቀይማ ከቤተሰቡ ተነጥላ የቆየች እህቴን አፈላልጌ ያገኘውበት ሰሞን ነው ፡ እንደው ይቅርታዋን ተቀብዬ ተደስቼ ፡ ለባለቤቴም ጎጃም ነው የምንኖረው ደውዬ አሳውቄ እህቴን ማገኘቴን ፡ እሱም ፡በደስታዬ ተደስቶ ነበረ ፡መቼም ካገኘዋት በዋላ በቃ እንግዲያውስ ያለችበትን ካወቅኩ ፡ተመልሼ ወዳገሬ ልሄድ እያሰብኩ ፡ እንደው በደንገት አይሆኑ ወነች ዋይ እህቴ ፡  "ብላ ለቅሶዋን ጀመረች
"እሺ ምን ተፈጥሮ ነው "አልኳት ፡አንድም ቀን  እህት አለኝ ስትል ሰምቻት አላውቅም ፡ ለነገሩ መቼ ምን ተናግራ ታውቅና
"እንደው ወደ ማታ ነው አቤልም አልገባ እኔና እሷ እየተጫወትን በር ተንኳኳ ልትከፍት ሄደች ፡እና ብዙ ስትቆይብኝ ምን ሆነች ብዬ ስወጣ ፡ በሩ ላይ ተዘርራ አገኘዋት ፡ እንደው አንዴ ጩኽቴን ብለቀው ፡ እንደው አቤል ከየት መጣ ሳይባል ደረሰልኝ ከዛማ ለሁለት ሆነን ምኑን ከምን እናርገው ፡ ብቻ አቤል ተሸክሟት እኔ ከዋላዋላ ፡ ክኒሊክ አደረስናት ፡ ግን እነሱ የሚችሉትም አልመሰለኝ ፡አንፑላንሱን ጠርተው ከሌላ ወስፒታል ወሰዷት ግን ይኽው እኔ ዝግት ልበል ድንጋጤና አወዳደቋ ከፉመሆን ተጨማምሮ ተዘግታ ቀረች "ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች
"እንዴት ማን እንዳንኳኳ አላያችውም ገፍትረዋት ነው"
"ኧረ ምኑን አውቄ  አኪሞቹ ስትወድቅ አናቷን ተመታለች ፡ቀስበቀስ ደናትሆናለች ነው ያሉት ይኽው አመት ሆናት ያው ነው እኔም ከባሌም ተጣልቼ እዚሁ ነኝ እንዴት አንድያ እህቴን እንዲሆና ልተዋት"
"ለፖሊስ አላሳወቃችሁም "አልኳት ግራ ገብቶኝ
"እሱማ እኔ ደጋግሜ ብዬ ነበረ ፡ አቤል ነው ምንም አያረግም ፡ ያለኝ "አለችኝ
"አሁን እሱ የት ነው "ብዬ ጮውኩ ፡ይሄ ተንከሲስ ምን አድርጓት ነው ፡ ድሮም የእናቴና የሱ ግንኙነት በሬ ካራጁ ነው ፡ እናቴን ጠጋብዬ አየዋት በፍቅር አይን ያየችኝ መሰለኝ እጄን እጇ ውስጥ ሳስገባው ያዝ አደረገችኝ ፡ የአቤልን መምጣት በጉጉት መጠባበቅ ጀመርኩ ፡ ወይኔ እናቴን የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ,,,,,,,,,,,,,

ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
👍12921👏8🥰1
🏮💰የ እናቴ ልጅ💰🏮
🔮ክፍል አስራ አራት🔮
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
ቤት ውስጥ ተቀምጦ እናቴን ማየቱ አባባኝ ፊትለፊቷ ደጋግሞ ማልቀሱ ደካማነቴን እያሳየው እሷን ማስጨነቅ መሰለኝ ፡እና ተነስቼ ወደደጅ ወጣው ፡ ሴትየዋ ተከተለችኝ ፡ "ወዴት ትሄድ ነው እባክህ ጥለኽን አትሂድ  "አለችኝ ዝምብያት ሄጄ ከጊቢውጪ ባገኘዋት ድንጋይላይ ተቀመጥኩ"ኧረ ከመሬቱ አትቀመጥ ወንበር ላምጣልህማ "አለች
"አልፈልግም ወደውስጥ ግቢ ፡ አየር እንዲነካኝ ብቻ ነው የምፈልገው"  አልኳት እሺ ብላኝ እንደገባች ፡ወንድልጅ ተደብቆ የሚያለቅሳትን ተቅሶ  ስለ እናቴ አስነካውት ፡ አቤት ዕንባ ፡ ካደኩ ጀምሮ በምኑም በምኑም የተጠራቀመው ወረደ ለጉድ ፡የእናቴ ቁመናዋ ከስንት ጊዜ አንዴ የማየው የነበር የሳሳ ፈገግታዋ ፡ ውበቷ ፣ ግርማ ሞገስ የተላበሰው ቁጣዋ ፡እየመጣ ከፊቴ ይታየኛል ፡  ማነው የሰው ሸነፋት ፡ ማንን ነው በር ላይ ያናገረችው  ስለምን ጉዳይ ይሆን ፡ጭንቅላቴ በጥያቄ ተሞላ ፡  ለዚ ምላሽ መቼም አቤል ጋር መኖር አለበት ፡  ያለሱ  ማንም ሊያውቅ አይችልም ፡ እያልኩ ከራሴ ጋር እያወራው ቆየው  ፡
"ልጄ እባክህ ግባና እህል ከአፍህ አድርግ ?ብርዱም ከደጅ የሚያስቀምጥ አይደለም !በዛላይ እናትህ አይኗ ከበሩ አልነቀል ብሏል ፡ይኽው የተለየ እንቅስቃሴም እያየውባታ ነው ፡ ድጋሚ ጥለሃትም እንድትሄድ አትፈለግ ፡ ምን አልባች ከዚ ከሆንክ ጤናዋ በቅርቡ ይስተካከል ይሆናል ፡ማን ያውቃል የበሽታዋ መንስህ አንተኑ ማጣቷ ቢሆንስ ?!"አለችኝ እንዳልሄድ እየተማፀነችኝ ። ተመልሼ ቤት ገባው አዘኔን ተቆጣጥሬ ወደ እናቴ ቀረብ አልኩ አይኖቿ ፊቴ ላይ ተንከራተቱ ፡ ከፊለፊቷ ተንበረከኩ  አይኖቿ አሳዘኑኝ እያየዋት መቆየት ቢያቅተኝ ጭንቅላቴን ጉልበቷ ላይ ድፍት አደረኩት ፡  የፈለከውን ያክል ጀግና ብትሆን እናትህ ፊት ልጅ ነህ በቃ ፡ እጇ ጭንቅላቴ ላይ በቀስታ ሲያርፍ ተሰማኝ ፡ እናም ጣቶቿ ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ ። ሴትዮዋ ደግማ እልልል አለች ፡ በውስጤ እቺ ሴትዮ ልታሳብደኝ ነው ፡በየሰአቱ እልልልል ካለች  አስቸጋሪ ነው መቼም
"ናቲዬ እያትማ እጆቿም ተንቀሳቀሱ ፡ ኧረ ታምር ነው በሽታዋ አንተ መሆንህን መች አወቅንና " አለች   እሷን ችላብዬ የእናቴን ጉልበት መሳም ጀመርኩ  እሷም በተሻለ ጭንቅላቴን ታሻሸኝ ጀመር እመኘው የነበረውን ፍቅራን በትንሹ ሳይሆን ባላት አቅም ልትሰጠኝ እየሞከረች መሆኑ ተሰማኝ ፡ 'እናቴ '
👉እንደምንም መሸ ሁለቴ ከጊቢ ውጪ ወጥቼ ዞር ዞር ብዬ መጣው ፡ ሴትዮዋ በወጣው ቁጥር ትማፀነኛለች ፡ እንዳልሄድ ፡ እኔ ዛሬ የትም የመሄድ ፍላጎት የለኝም ፡ የምፈልገው አቤል እቤት ከመግባቱ በፊት እኔን ማግኘት አለበት ብዬ ነው ፡ አንድም የሰፈር ሰው እስካሁን ልብ አላለኝም ፡  ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አካባቢ ፡ ስልክ ተደወለልኝ ፡ ባዩሽ ነበረች ወይኔ ማማዬን በእናቴ ተወጥሬ እረሳዋት ፡  ስልኬን አንስቼ ስርበተበት ፡እናቴ አይኖቿ ወደኔ ተንከራተቱ
"ሄሎ በዩ ቀየውብሽ አይደል "
"ምነው ናቲዬ በሰላምም ነው እስከአሁን ሳትደውልልኝ "አለችኝ
"ሰላም ነኝ በዩ ትንሽ እናቴ እንደጠበቅኩት አላገኘዋትም እእ እናቴ  በቃ  ነገ እነግርሻለው ፡ማማዬ ተኛችልሽ "ስል የእናቴ አይኖች ተርገበገቡ
"አዎ ተኝታለች አባ አባቢ እያለች በር በሩን ስታይ ቆይታ ይኽው አሁን እንቅልፍ ጣላት "አለችኝ
"ይሁን በቃ ለዛሬ እንደምንም ታገሺ እባክሽ ማማዬን ጠብቂልኝ ፡ "አልኳት እንቅልፋም መሆኗን ባውቅም ትኩረት እንድታረግ ካሳሰብኳት ምን አልባት ትሻላለች ብዬ
"በቃ ልታድር ነው ?"
"አዎ ግድ ነው ከዚ በዋላም ወደ ቤቴ መመለሴ አይቀርም በዩ እናቴን የመንከባከብ የመጠበቅ አላፊነት አለብኝ ግድ ነው "አልኳት ባዩሽ ቅር ባለው ድምፅ"እሺ እናወራለን  "ብላ ተሰናብታኝ ስልኩ ተዘጋ
"ናቲዬ እንደው ስለ አንተ ከቤት አወጣጥ ተነግሮኛል ፡ እንደው በጣም ነበር ያዘንኩት ፡ እናንተ ለቁጥር አልበዛቹ አንዲት ዕፃን በቤቱውስጥ ብትኖር ችግር አልነበረውም ፡እውነት ለመናገር እናትህን ያገኘዋት ጊዜ ነበር ስላንተ ተፀፅታ የነገረችኝ ፡ በንዴት ውስጥ ሆኜ ልጄን አቀረርኩት ለያውምከህፃን ልጅጋ እንዴት ሆኖ ይሆን እያልኩ መብከንከን ሆኗል ስራ አለችኝ ፡እኔም ባደረገችው ነገር ወቀስኳት ፡  እሷም ያጠፋውትን ለማስተካከል ፈልጌው ነበር ፖሊስ ጣቢያ ሁሉአመልክቼ ነበር ግን ሁሉን ነገር ዘጋግቶ ነው የጠፋብኝ ፡ ስልኩ እንኳ አይሰራም ፡ አለችኝ ፡ አቤልም እንደፈለገህ ነግሮኛል ፡  "አለችኝ
"ስምሽ ማነበር ያልሽኝ "አልኳት
"ኧራ ስም ምን ያደርግልሃል አክስቴ ብለህ ጥራኝ አቤልም እንደዛ ነው የሚጠራኝ እንደው አሁን አሁን አንዲት ሴት ፀባዩን ቀየረችብን እንጂ አክስት ብሎ ነበር የሚጠራኝ በዪ ሰሞን ግን  በስሜ  ለዛውም ማነሽ ደግነሽ ነው የሚለኝ እንደው ምን አጥፍቼበት እንደው አልገባኝ ብሏል ፡ ግን ስጠረጥር ልጅቱ ናት እንዲ ያደረገችው ፡ እንደው ልብስም በላይዋ ላይ አልቀመጥ ያላት መሳይ እኮ ናት እኔማ ስትር ያለይ ብትሆን በወግ ብንድረው ክብሩ ለኛም አይደል ፡ብቻ ልጅቱ መልክ ሳያንሳት እርቃን የምትሄድ ሆነችብን እና ነው ፡ ሳስበው እሷን ስላልወደድንለት ነው ። እዚ እንኳ ስትመጣ የኔስ ይቅር ዘውድዬ እናት ናት በዛላይ ታማለች አትናገር ነገር ፡ሸፈንፈን ብላ ብትመጣስ ፡ "አለች ደግነሽ እውነትም እንደስሟ ደግ ሳትሆን አትቀርም
"አልገባኝም እዚ ቤት ድረስ ሴት ይዞ ይመጣል ?"ብዬ አበድኩ
"አዬ እስኪ ተወኝ አንተው! ለያውም በማታ አዳሯን ነዋ እናትህ ከበሽታዋ የማታገግመው በሱም ሳይሆን አይቀርም ፡ልጅቱም አታፍር  አቤልም ወዷት ነው መሰል እሷን ነው የሚሰማው ፡"አለች በቁጭት ።ይሄን ስሰማ ይበልጥ አበድኩ ተነስቼ አየር ልቀበል ብዬ ወጣው ።ወጥቼ መሬቱን በእልህ እረገጥኩት በዚ ስሜት ውስጥ ሆኜ ወደፊት ተራመድኩ ሰፈሩ ጭር ብሏል የሐምሌ ዝናብ ሰውን ሁሉ በጊዜ ነው ያስገባው እኔ ብርዱ ተረስቶኝ ንዴት አሟሙቆኛል ፡
ከርቀት ላዳ መኪና ስትመጣ ትታየኛለች  የከድር ሱቅ ጋር ሁለት ጎረምሶች ሲጋራ እያጨሱ ያወራሉ ፡ተተኪ አያጣም ሰፈሩ ። ላዳዋ ድንገት ቆመችና ሁለት ሰዎች ወረዱ ወንድና ሴት ናቸው እየተሳደቡ ነበር ሹፌሩን ፡ በብልግና ስድብ ሞልጯቸው ሲሄድ በግልፅ ታዩኝ አቤል ነው ሴት ይዞ አክስቴ ደግነሽ እንዳለችው ነው ይኽው በአይኔ አየውት ፡ በቃ የድሮ እብደቴ ጀማመረኝ ልጅቷን ፡ አንድ ጥፊ ሳቀምሳት ጮሃ ካጠገቤ ሸሸች አቤልን በግላጭ አገኘውት ፡በጠረባ ከመሬት ደባለኩት ፡ደጋግሜ ረገጥኩት ምኑን እንደመታውትእንኳ አላውቅም ፡ተኝቶ የምሰነዝረውን መቀበል እና'ስለወንድልጅ ኧረረረኡኡኡ' ሲል ባሰብኝ የልጅቷ ጩኽት ሰው ሰቀሰበ ፡ ጎረምሶቹ ሊይዙኝ ሞከሩ አቃትኳቸው ፡እኔ ፀብ ውስጥ ስገባ የሚያገዘኝ አለ መሰለኝ በስውር በቀላሉ ሊያቆሙኝ አልቻሉም ፡ በዚጊዜ ደላላው ጋሼ ግዛው "እንዴ ከየት መጥቶ ነው ወንድሙ እኮ ነው ናታኒየም አይደልእንዴ "አሉ የሰፈር ሰው ሁሉ ሲያዩኝ ተደናገጡ ፡ ልክ ሲበርድልኝ ሁለቱን ጎረምሶች ያዙትና እቤት አስገቡልኝ ብዬ ፡ ከፊት ከፊት ወደቤት ቀድሜ አቸው ገባው የሰፈርተኞቻችን ድምፅ ጆሮዬ ውስጥ ያቃጭላል 'ከየት መጣ ደሞ አርፈነው ነበረ 'እትዬ ወርቄ' ኧረምኑን አውቄ አሁን እናቱ ፖራላይዝ ሆናለይ ማን ሊያስቆመው ነው 'እትዬ የዛብ' ጭራሽ ወንድሙን እንዲ ካደረገ ነገ ለኛ መፍራት ነው' እማማ አብረኽት ። ብቻ ወንዱም ሴቱም ሲወርዱብኝ ይሰማኛል እኔ ግን አቤልን በመደብደቤ የተጠራቀመ
👍7312😁1
እልሄን ያወጣው መሰለኝ ይሄ ግን ስለ እናቴ ነው...


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️❤️
33👍17🥰2👏1
#ይሄው_ነው

አንድ ቤት አድሰው

በፎቶ እጀባ

ሺህ ቤት ያፈርሳሉ

ከካሜራው ጀርባ

🔘ኢዛና🔘
😢101👍24
🔮🏮የ እናቴ ልጀ🏮🔮
🔦ክፍል አስራ አምስት🔦
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
አንዳንዴ ሰፈር ውስጥ እንዲ መፈራቴን ሳስበው ይገርመኛል ፡ ሴቱም ወንዱም ከፊለፊት ሲያየኝ ከመንገዴ ዞር ብለው ነበር የሚሄዱት ፡  እነሱ ድንገት የሚነሳብኝ ነው የሚመስላቸው ኪኪኪ ፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ማንንም ሳይነካኝ አልነካም ፡  አለመነካት ስል አንዳንድ ሰው አለመነካት የሚመስለው  ፡እራሱን ብቻ ነው ፡  እንደዛ ግን አይደለም  ሌሎች ሰወችን የሚያስጨንቁ ፡ አቅማቸውን ተማምነው ችግር የሚፈጥሩ ፡ ስንቶች አሉ በየሰፈሩ እኔ ከነሱ ጋር ስደባደብ ትክክለኛ ነገር ያደረኩ ነው የሚመስለኝ ፡  ለዚ ሁለታዬ እንደውም ሊያመሰግኑኝ ይገባል ፡በወቅቱ የስንቷን ሞባይል ስልክ ነው ያስመለስኩት ፡ ፖሊስ ይወጣው የሚለኝ ካለ ያስቀኛል ፡  ........ፖሊስ እኔ የማውቀውን ጉራንጉር የት ያውቀውና እንዲሁም አንድ ጊዜ ላፕቶፕ ከአንድ ጎረምሳልጅ ተዘርፎ ፡ ፖሊሱ እራሱ እንድረዳው ጠይቆኛል ፡  በጣም ውስብስብ ያለበትን ነገር ፈትቼለታለው ፡  ምክንያቱም ሰፈር ውስጥ ብቻ ሳይሆን አካባቢያችን ላይ ማን ምን እንደሆነ ጠንቅቄ ነበር የማውቀው ፡  ያኔ ማለቴ ነው ።እንግዲ በሁለት አመቴ ስመለስ የተቀየረ ነገር ካለ እናያለን ,,,,,,,,,,,,,,,
👉አቤልን ይዘውልኝ የገቡት ጎረምሶች ግቢውስጥ ሲደርሱ የት እናርገው አሉኝ ፡ ፊታቸው ላይ ፍርሃት ያየው መሰለኝ ፡ ከዚ በፊት አይቻቸው አላውቅም
"አምጡት ወደዚያ ክፍል "አልኳቸው ጊቢው ወስጥ በመደዳ ከተሰራው ሰርቢስ ቤት አንዱን እያሳየዋቸው በዚመሃል አክስቴ ደግነሽ ወጥታ እሪታዋን አቀለጠችው ፡በፍጥነት ሄጄ አፏን ጥርቅም አድርጌ ይዤ"ዝም በይ እናቴ እንዳትረበሽ  "አልኳት ወዲያው ዝም አለች እና "አቤል ምን ሆኖ ነው ?ማጅራት መቺ መታው ? አይይይ እንደው ምን ይሻላል ?ተርፏል ወይስ እንዴት ነው ?ለምን አኪም ጋር አንወስደውም ? ለምንድነው ከዚያ ክፍል የምትከቱት ?"እያለች የማያባራ ጥያቄዋን እያከታተለች  ተከታተለችን
"ብዙ ጥያቄዎች አሉሽ መልሱን በዋላ እሺ አክስቴ "አልኳት ፡የሰርፒስ ቤቷን ከፈትኳት በውስጡ ምንም ነገር አልያዘም አንድ ጥግ ላይ ብቻ የቆየ ምንጣፍ አለ እሱን ዘርግቼ እሰዚ ላይ ተውት አልኳቸው ፡እርስ በእርስ ተያዩና እንዳልኳቸው አደረጉና ፡ ቆሙ
"በቃ አመሰግናለው መሄድ ትችላላቹ "አልኳቸው
"እሺ ናቲ ስትፈልገን አለን ስልክ መለዋወጥ እንችላለን አለኝ ጠቆር ያለው ልጅ እሺ ብዬ ስልኬን ሰጠውት ፡
"ዘኪ እባላለው እሲ ደሞ ቶማስ ፡ "
"እሺ አመሰግናለው ትንሽ ስላስቸገረ ልቀጣው ፈልጌ ነው ፡ እሺ ያን ያክል አልጎዳውም ፡ ይሄ ስለ እናቴ ነው "አልኳቸው
"ያለምክንያት ምንም እንደማታረግ እናውቃለን "አለኝ ቶማስ የተባለው
"የት ሰፈር ናቹ "
"የታች ሰፈር ልጆች ነን "
"እሺ በቃ ሂዱ እንገናኛለን "
"አብሽር ጣጣ የለውም "ብለውኝ ተከታትለው ወጡ ፡አቤል መጠጡ ነው መሰል ዝግት አድርጎታል ጎንበስ ብዬ ሳየው ጭንቅላቱን ብቻ  ይወዘውዛል ፡ተናደድኩበት ፡ሆነብሎ ዝም እንዳለ ገብቶኛል ፡እሱ በዝምታ ነው ሰውን የሚጎዳው ፡
"ስማ ማንነቴን አውቀሃል ሆነ ብለህ የተጎዳህ አታስመስል ቀና ብለህ እየኝ "ብዬ ደነፋውበት
"ተወኝ"ብሎ መሬቱላይ ጥቅልል ብሎ ተኛ
"አልተውህም ለምን እንደማልተውህ ታውቃለህ ፡ ስለ እናቴ ነው! ስለእኔማ በደል አልተናገርኩህም ነበር ቤቱንም ጥዬልህ ወጥቼ ነበር ፡ አንተ ግን አላረፍክም አብዝታ የምትወድህን እናቴንም ጎዳሃት ፡ ማንም የላትም ብለህ አላማህ ምንም ይሁን ምን አይመለከተኝም ነገርግን እናቴ እንዲ ለመሆኗ ምክንያት አንተ እንደምትሆን እርግጠኛ ነኝ ፡ምን አድርገሃት ነው ፡ ተናገር "አልኩትና እጁን እስኪያመው ጨምቄ ያዝኩት ፡ያን ያክል አሞት ሳይሆን ሆነብሎ ጮኽ ፡ስለተናደድኩ በቦክስ ነረትኩት ባሰበት ፡ አክስቴ አነስተኛ ፍራሽና ብርድልብስ ይዛ እየተጠደፈች መጥታ ገባችና"ተው ናቲ ይሞትብሃል ምን አድርጎ ነው ፡ ተው ልጄ እንዲ አትጨክን "አለችኝ አቤልን እየከለለች
"አይ ማውራት አለበት እናቴ በምን ምክንያት ነው እንዲ የሆነችው ይናገር አለበለዚያ ያውቀኛል እንደማላቆም "አልኩት
"እኔ ምን አውቅልሃለው የትም ከርመህ መጥተህ ይህን ጥያቄ ስትጠይቅ አታፍርም ፡ምን እንዳሳለፍን ተውቃለህ "ብሎ ጮኽ አክስቴ ደግነሽ ዞር እንድትል ነገርኳት እምቢ አለች
"አንተ የትም ከርመህ የምትለው እኔን ነው አፍ አለህ በማን ምክንያት ነው የሄድኩት እንዲ ስትል አታፍርም መቼ ነው የምትታረመው"ብዬ ጮውኩ
"ናቲዬ ቆይማ እባክህ ነገ ታወራላቹ ትንሽም ሳይቀምስ አይቀርም በጤናው ይሻላል ፡በዛላይ እናትህ የሰማችው ድምፅ ስላለ በርበሩን በስጋት እያየች ነው "አለች አክስቴ ደግነሽ
"እኮ ስለሷ ነው እኮ ጥያቄዬ ማነው እንዲ ያደረጋት በሩን ስትከፍት በወቅቱ ማነው ያናገራት ፡ ማወቅ አለብኝ ፡እሱ ደሞ እንደሚያውቅ እርግጠኛ ነኝ ፡"አልኩአት ፡አቤል ለመነሳት ተፍጨረጨረ እናም
"በኔ ምክንያት አይደለም ባንተ ምክንያት ነው እንዲ የሆነችው "ብሎ ጮኽ
"ምን እንዴት እባክህ አስረዳኝ እስኪ አብረሃት ያለኽው አንተ "አልኩት ድርቀቱ እየገረመኝ
"በሩን ስትከፍት አንዲት ሴት አገኘቻት ከዛ ,,,,,"ከዛ ብሎ ዝም አለ
"ከዛ ምን?ማናት ያቺ ሴት ?"ባዩሽን ገለል አድርጌ አፋጥጬ ያዝኩት የፈራኝ መሰለ ተጨነቀ
"እእኔ ቶሎ መድረስ ነበረብኝ ግን እኔ ከመድረሴ በፊት ስትዝትብኝ የነበረውን ነገር ነገረቻት !"ብሎ ማልቀስ ጀመረ
"ግልፅ አድርገው እስኪ ምኑን ነው የነገረቻት ማናት እሷ"አልኩት ይበልጥ እየተጠጋውት
"ሚጣ ናት የዕፃኗ እናት  የተስማማንበትን ነገር አፍርሳ ፡ ለእናቴ መጥታ ነገረቻት ፡የዕፃኗ አባት አቤል ነው ፡ ያኛውን ልጅሽን ያለ አጢያቱ ነው የቀጣሽው ፡ አሁን የምፈልገው ልጄን እንድትሰጡኝ ነው አለቻት ፡ ይህን ስትላት ወደቀች እራሷን ስታ በቃ" ከማለቱ አክስቴ ጮኽች"ውይ ውይ የቤቴ ጉድ ዕፃኗ የአቤል ናት ፡ውይ ውይ ዘውድዬ ጉድሽ አላልቅ አለ ፡አዬ መከራሽ "እያለች ወደ እህቷ ፈጠነች ፡እኔና አቤል ተፋጠጥን,,,,,,,,,,,,,

ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍15318👏7😢7🔥6😁5
🔍🏮የ እናቴ ልጅ🏮🔍
🎈ክፍል አስራ ስድስት🎈
🔮🔮🔮🔮🔮🔮🔮🔮
ሰዎች ስለ ሽንፈታቸው ይሁን ስለጥፋታቸው ተፀፅተው የሚያለቅሱት የማይገባህ ጊዜ አለ ፡ እንደው የትኛው ምክንያት እንዳስለቀሳቸው ግራ ያጋባህና ለማባበል ያስቸግርሃል!በእርግጥ እኔ ወንድሜን የማባበል ስሜት ላይ አልነበርኩም፡ ነገሩ ሁሉ ገርምኝ እንጂ .....
.....ስለምኑ ነው አቤል ሚያለቅሰው እናቴን ዋሽቶ አሳምኖ እኔን ከቤት ስላሶጣኝ ?......ነው ወይስ እስከዛሬ ድረስ ፡እውነተኛ ሆኖ ተከብሮ ከኖረበት የእናቴ አይምሮ ውስጥ ተፈንግሎ ስለሚጣል ፡ ተጨንቆ ? ..... ወይስ የኔ የወንድሙ ያለስራዬ መከሰስ እና የእናቴ መጨረሻ አሳዝኖት ተፀፅቶ ?....
...እንጃ አይመስለኝም አቤልን ድሮ የማይበትን መነፅር ቀይሬሀለው ምንም ቢቅለሰለስ ፡እሱን ማመን ይከብደኛል ።
     እሱ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ ጭንቅላቱን በተደጋጋሚ ሲመታ ፡አንገቴን አቀርቅሬ የማስበው ስለ እናቴ ሆነ ምስኪን እናቴ እኔ ላይ ያለጥፋቴ መፍረዷ ክፉኛ አስደንግጧት መቋቋም ሳትችል ቀርታ ስትወድቅ ታየኝ ፡ በእርግጠኝነት ያቺ ልጅ መ'ታ በተናገረችው ብቻ አደለም እናቴ በፀፀት የወደቀችው ፡ከዛ በፊት በአቤል ውሸቶች እኔን ታደርገኝ የነበረው ነገር ሁሉ ፡ በአንዴ መጥተው ነው የታዩዋት ፡ ለዛም ነው ስታየኝ እንደዛ የሆነችው ፡
     ወደ አቤል ጠጋ ብዬ ቆምኩ ፡ቀና ብሎ አየኝ
"አንተ የማትረባ አሁን ይሄን የአዞ ዕንባህን ትተህ ፡ንገረኝ እስኪ ፡ምን አይነት አኪም ጋር ብትወስዳት ነው እስካሁን ምንም ለውጥ ያላሳየችው ?ወይስ ለአኪሞቹ ከፍለህ እንዲ እንድትሆን አስደርገህ ነው ፡"አልኩት አፍጥጬ እያየውት፡ አቤል አይኑን አርገበገበ እና  "እኔ?  ለምን እንደዛ አደርጋለው?  እናቴ እኮ ናት !  የዛን ያክል ጨካኝ እሆንባታለው እንዴ  ሚጣ ናት እናቴን እንድዋሽ ያደረገችኝ እንጂ ታውቃለህ ለእናቴ ምን ያክል የቀረብኩ መሆኔን ያንን ሁሉ ውሸት ግግም ብዬ የዋሸውት እናቴ እንዳትጠላኝ በማሰብ ነበረ ግን ምን ያደርጋል ያቺ የማትረባ መጥታ ረበሸች "ብሎ እንደዕፃን ማልቀሱን ቀጠለ
"እ   አትለኝም በጣም አሳዘንከኝ ! አንተ ደደብ እራስ ወዳድ ፡ሚጣ የምትላት መጥታ ባትረብሽህ ፡ምንም እንዳልተፈጠረ ፡እናቴን ከእኔ ነጥለህ በውሸትህ አጥረሃት ልትኖር ነበረ አይደል?እ  እንደዛ ነበር አሳብህ ?" ውስጤ ተቃጠለ ፡ ለእናቴአዘንኩ እንደው ምን አይነት ልጅ ነው ያፈራችው ፡ ሕይወትን በራሱ ዙሪያ ብቻ አጥብቦ የሚያይ ስለሌላው ደንታ የሌለው፡
"እንደዛ አደለም አንድ ቀን አንተን መፈለጌ እኮ አይቀርም "ብሎኝ እርፍ ።ይበልጥ አበሳጨኝ
"ዕፃኗንስ ስለሷ ምንም አላሰብክም? ነው ወይስ እኔ ያንተ አይነት ልብ ኖሮኝ ከመንገድ የጣልኳት መስሎህ ነው ?"አልኩት
"አይ ያው እኔ.....እባክህ ተወኝ?ልትገድለኝ ካሰብክ አድርገው አታስጨንቀኝ !"ብሎ ጮኽ ፡
"አትጩህ አንተ አስመሳይ ፡እንደውም የዚህን ያክል አንተን ማውራት አይጠበቅብኝም ፡ ከዚ ቀን ጀምሮ ከዚ ክፍል አትወጣም ፡ የኔ እስረኛ ነህ ፡ እዚው ትውላለህ እዝችው ታድራለህ ፡ አንዳች ነገር እፈጥራለው ብትል ፡ሰባብሬ አስቀምጥሃለው ፡ ተውቀኛለህ ሰው ስጠላ ምን ላደርግ እንደምችል"እልኩና እዛው ቁጭ ባለበት በርግጫ ብዬ ወደዋላው አስተኛውት ፡
"እረ በማዬ የዚህን ያክል አትጨክንብኝ ወንድምህ እኮ ነኝ ፡ አቤል ነኝ የእናትህ ልጅ ነኝ አጥፍቻለው ይቅር በለኝ በቃ "ብሎ አልቅሶ ለመነኝ
"ገደል ግባ ተፀፅተህ እንዳልሆነ ይገባኛል ፡ትቀጣለህ ፡ቅጣትህን ደሞ ማግኘት ያለብህ ከኔነው ፡በገዛ ልጅህ የተነሳ እንቅልፍ ላጣውባቸው ለእያንዳንዱ ለሊት አስከፍልሃለው ፡ "ብዬው ወጥቼ በሩን ከዋላ ስቀረቅረው ፡ እየጮኽ ለመነኝ አልሰማ ስለው ዛቻም ጨመረበት ፡ዝምብዬው ወደ ትልቁቤት ገባው ....
👉እናቴ ዌልቸሩላይ እንደተቀመጠች ነው ፡አክስቴ ደግነሽ ፡ለእናቴ ታወራለች እናቴ በዝምታ ውስጥ ነበረች ስገባ በጥያቄ አስተዋለችኝ ፡ ጠጋ ብያት ረጅም ፀጉሯን ደባበስኩት  ፀጉሯ በሁለት አመት ውስጥ ተለውጧል ድብን ያለ ጥቁርነቱን ትቶ ነጣ ያለ ቅልቅል ሆኗል ፡ ፊቷ ገርጥቷል ውበቷ ቀንሷል ፡ጎንበስ ብዬ ግንባሯን ስስማት በረጅሙ ተነፈሰች ፡ ዝቅ ብዬ ወለሉ ላይ ተቀመጥኩ ፡  አይኖቼን ፈልጋ በጥያቄ አስተዋለችኝ ፡ መልስ ባትሰጠኝም እውነቱን ልንገራት ብዬ ፡አቤልን ሰርፒስ ቤት እንደቆለፍኩበት ነገርኳት ፡ አይኗን ከማርገብገብ ውጪ ፡የፊት ለውጥ አላየውባትም ፡ ምን ላደርግ እንዳሰብኩ ነገርኳት ፡ በጣም እንደማልጎዳው ነገር ግን ቅጣቱን እስኪጨርስ ድረስ ማንም እንዳያስቆመኝ ፡አስጠነቀኩ ፡ማስጠንቀቂያው ደግነሽንም እንደሚመለከት ፡ተናገርኩ አክስቴ ደግነሽ ከቃሌ እንደማትወጣ ተናገረች ፡ እናቴ አንገቷን ስትነቀንቅ አይታ አክስቴ ደግነሽ እልልልልልል አለች ፡ የአክስቴ እልልታ ፡ግን ከባድ ነው በዚ አይነት  ቤታችን በውጪ ሰዎች እልልልታ ጊቢ መባሉ አይቀርም ....
   ማታላይ ለአክስቴም ሆነ ለእናቴ ስለ ማማ ነግሬአቸው ትቻት የመጣውት ባዩሽ ከተባለች መልካም ካደረገችልኝ  እና አብራኝ ከምትኖር ሴት ጋር መሆኑን ነገሬአቸው እዚ ከእኛጋር ብትኖር ብዬ አስፈቅጄ በአሳቤ በመስማማታቸው ፡ በጠዋት ተነስቼ ፡ወደ ኮልፌ በረርኩ ማማዬን እና ባዩሽን ላመጣ ፡ አሁን ላይ ብዙ አላፊነት እላዬላይ እንደሚጫን ተሰማኝ በዛላይ እናቴ እንዲ ሆና ከባድ ነው .........


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍66🥰84
🔮🎈የ እናቴ ልጅ🎈🔮
💰ክፍል አስራ ሰባት💰
🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮
በጠዋት ተነስተህ የአዲስ አበባን እሩጫ ስታይ ፡በየት በኩል ነው ንፋስ ገብቶ ቀና እንዳትል ያደረጋት ያስብልሃል ፡ እግረኛው በእግሩ ባለመኪናው............  ትራን ስበፖርት ለመያዝ የሚጣደፉት............. ፡ወከባው ለጉድ ነው ፡ሁሉም በየ አቅጣጫው ኑሮን ለማሸነፍ !!! ፡ዳይ ወደስራ... ተከራይ በሚበዛባት ከተማ፡ በልቶ የማደርን ጥያቄ ለሟሟላት ፡ መልፋት የግድ ነው ።መቼም አሁን ላይ አንድ ስራ የሙጥኝ ብለህ ቀርቶ ፡የተለያየም ገቢ ቢኖርህ ፡ ቤትና መኪና ለመግዛት እቆጥባለው ብትል ፡ የማይቻል ነው ፡  ' የአዲስ አባ ነዋሪ ከምትሰራው ላይ ቆጥበህ  ቤት ግዛ ቤት ጥሩ ነው ማረፊያካለህ ሌላው ይደረሳል ብትለው ' መልሱ የሚሆነው 'ፅድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ 'የምትለዋን የድሮ ተረት ነው የሚያመጣው ።ልክ ነው እውነት አሁንላይ ከቤት ክራይ ተርፎ ፣በየቀኑ ከሚጨምረው የአስቤዛ ዋጋ ተርፎ በየት በኩል ሊቆጠብ ነው ?  እንደው የተሻለ እሰራለው ትንሽዬ ንግድ አለችኝ የሚለው ሰው እንኳ አዲስ አባ ውስጥ ቀርቶ ዳርዳሩን  ወጣብዬ ቤት ልግዛ ብትል ሚሊሆኖች ይጠሩብሃል ' ሲጀመር በርትተህ ከቆጠብክ ነው ፡ እና አንተ የሚያዋጣህ ፡ያለችህን እንኳ እንዳታጣ ፡ በተቻለህ መጠን ገንዘብ ቆጥበህ ከማስቀመጥ ይልቅ ፡ የወሩ ወጪህ ባግባቡ እንዲሄድልህ ፡እራስህን መቆጠብ ነው ያለብህ ፡ፍላጎቶችህን መቀነስ  ለምሳሌ__
መጠጣት ማቆም
ሰው ካልጋበዝኩ ብሎ አጉል መፍጨርጨር ማቆም
አማረኝ ብሎ ትላልቅ ምግቤት ገብቶ ማዘዝ  "
የማታገባትን ሴት እየቀጠሩ መጋበዝ ማቆም......
ብቻ የወር ገቢህን በአግባብ ለመጠቀም ፡ እራስህ መቆጠብ አለብህ ፡ አዲስ አባ ውስጥ  !አዲስ አባ ውስጥ ኪኪኪኪኪ.........
👉የአዲሳባን ማብቂያ የሌለው እሩጫ እየታዘብኩ ፡ በስንት ልፋት ታክሲ አግኝቼ ነው ልጄንና ባዩሽን ይዤ ወደቤት የተመለስኩት ፡ ባዩሽ አሳቡን ስነግራት ፡የሆሸክም ከላይዋላይ የወረደ ያህል ነው የሆነችው ፡ለነገሩ እውነቷን ነው ካለኔ ማን አላት ፡እኔ ከመምጣቴ በፊት የኖረችውን ሕይወት እሷም ሁሌም ፡ስታነሳው ያንገሸግሻታል ፡ዳግም ወደዛ የመመለሱ ነገር የሞት ሞት ነው ፡  ለዚ ነው እናቴ ሰርፒስ ቤት ውስጥ እንድትኖር እንደምትፈቅድላት ስነግራት ፡ ለእናትህ የፈለገችውን ያክል እሆንላታለው ፡ብቻ ዳግም ጎዳና አትተወኝ ያለችኝ ይህን ስትል ፡ወደ እራሴ አስጠግቼ አቀፍኳት ፡ ባዩሽ ማለት እንደ እናቴ ነበረች ፡በሁለት አመትውስጥ ፡ያፈራዋት ደጋፊዬ ፡እንደት መንገድ ጥያት እሄዳለው ።
👉ኮንትራት መኪና አስመጥቼ እቃችንን ሰብስበን ማማን ይዘን ወደ እናቴ ቤት ተመለስን ፡ ቤት ስንገባ አክስቴ ደግነሽ የተለመደ እልልልልልታዋን አቀለጠችው ፡ ደግነሽ እልልልታዋ ባይኖር በሕይወት የምትቆይ አትመስልም ሆሆሆ ፡ ባዩሽን እና ማማን ይዤእናቴ ጋር ቀረብኩ እናቴ ዕፃኗን ስታይ አይኖቿ በዕንባ ተሞሉ ፡እና በድንገት ድምፅ አወጣች ፡
"አአምላኬ.."ስትል ለማመን ከብዶኝ ተንበረከክ ፡ እውነት አንድ አመት ሙሉ ሳትናገር ነው የቆየችው ፡ከሆነ ታምር ነው አልኩ በውስጤ ፡ አጠገባችን አክስቴ ደግነሽ አለመኖሯ ጠቀመን በእልልልታ ማማን ታስደነግጣት ነበር ፡ጥሩ እነቱ ፡ ያመጣነውን እቃ ወደ አንደኛው ሰርፒስ ቤት እያስገባችው ነበር
"እማ ተናገርሽ እኮ "አልኳት በጉጉት እያየዋት፡ አይኖቿን ወደኔ መልሳ ፡እንደምንም አፏን አላቀቀችው
እና "ደደና ሆና ለው  እዚ ካ ካለህ"አለችኝ ፡ማመን አልቻልኩም እናቴ በጣም አስፈልጌያት ነበር ለካ በአንድ ጊዜ ልቤውስጥ ያስቀመጥኩት ቅሬታ ተበትኖ አቀፍኳት ፡ ለውጧ አስደሰተኝ ተነስቼ ማማን ወደሷ አቀረብኳት ፡ማማ ሰው መቅረብ ችግር የለባትም ወደእናቴ ተጠግታ በሚጢጢ እጇ የእናቴን እጆች ያዘች እና "ኢማማ ነና ነሽ "አለቻት እናቴ አለቀሰች ፡የማማን እጅ ያዝ ለማድረግ ሞከረች ቀስ እያለ ተሳካላት ልትስማት እንደፈለገች ስለገባኝ ከፍ አደረኩላት ፡ማማ እራሷ እናቴን አቅፋ ሳመቻት ፡የእናቴ የፀፀት ለቅሶ ተባባሰ ፡እናም እንደበፊቱ ድምፅ አልባ አልነበረም ፡ ባዩሽ አንጀቷ ስላልቻለ ፡ደግነሽን ላግዝ በሚል እያለቀሰች ተነስታ ወጣች ፡ ባዩሽ እንደወጣች አክስቴ ደግነሽ ጥድፍ እያለች ገባች ፡"እህቴ እውነት ድምፅ አወጣች እልልልልልልልል ለፈጣሪ ምን ይሳነዋል  እልልልልልል የእ ናቴ ልጅ አንድያዬ የኔ ልህልት ፡ላንቺ ይህ አይገባም ነበር ፡ ሁሌ እንደተጎዳሽ ይሁና ፡ይሄንስ ማን አየበት ፡ "አለች ደረቷን መታ መታ እያረገች ፡ ማማ የእናቴን ፊት ትስማለች ትዳብሳለች እናቴ አንዳንድ ቃላት ትናገራለችእንደ ማጫወት ደስታዬ ልክ አጣ ፡  ወደ ደግነሽ ዞሬ ለአቤል የሚሆን ቁርስ እንድትሰጠኝ  ነገርኳት ፡እሺ ብላኝ ሄደች
የዛ የመጣችው ምግብ ብዛቱ ግን አስገረመኝ
"ምንድነው ይሄ ሁሉ "
"እንደው ከማታ ጀምሮም አልበላ ብዬ ነው ፡"አለች
"ጭራሽ አጥግበሽ እንዲፈነጭ አድርጊዋ "አልኳት ቢሆንም ግን ፡ይዤለት ወደ ሰርፒስ ቤቱ ሄድኩ ፡ከዋላዬ ፡የአክስቴ ደግነሽ እልልልልታ ተሰማኝ ፡አሁን ደሞ ምንድነው ብዬ ዞሬ አየዋት ፡ወደ ትልቁ ቤት ገብታለች ከነ እልልልልልልታዋ......


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍7421👏16👎1
👉🏮የ እናቴ ልጅ🏮👉
🔮ክፍል አስራ ስምንት🔮
💰🎈💰🎈💰🎈💰🎈
የራሴ ነው የምትለው ሰው ፡ በተለያየ አጋጣሚ ሲያሳዝንህ ፡  ቻል አድርገህ ታልፋለህ ፡ እሱ አንተላይ የሚያደርስብህን ነገር ፡ባለማወቅህ ሳይሆን ፡ምን አልባት ዝምታዬ  የራሱን ድርጊት አሳይቶ ፡ ነገላይ ተፀፅቶ እንዲተወኝ ያደርገዋል ብለህ ይሆናል ፡
   ነገር ግን ከስንት አንዱ መሰለህ ፡ እንደዛ የሚያስበው ፡ ይልቅ ዝምታህን ካለማወቅ ቆጥሮ በበደሉ የሚገፋበት ስንት ሰው አለ! ስትተውለት የማይተውልህ ፡ የተንኮል ድርጊቱን ንቀህ ካጠገቡ ዞር ስትል የሚዞርብህ ፡  ሳይፈልግህ የሚፈልግህ መሳይ፣ ሳይወድህ የሚከተልህ ፣ተወኝ በቃ ስትለው የማይተውህ ፣ አስመሳይ ቤተሰብ አሰመሳይ ጓደኛ አታጣም በሕይወት ውስጥ!!
👉አቤልን ይገባዋል ብዬ ባሰብኩት ልክ ቀጥቼ ፡ ለቅቄዋለው ፡ ነገርግን አይኖቹ ውስጥ አንዳች የተንኮል ቅኔ ይታየኛል ፡ የሆነ አጋጣሚ ጠብቆ ሊፈታ የታሰረ ቅኔ !  እናቴ በሚገርም ፍጥነት ለውጥ አሳይታለች  የኔ መምጣት ጠንክራ እንድትቆም አድርጓታል ፡ መናገር ችላለች በትንሹም ቢሆን መንቀሳቀስ ጀምራለች ፡ ዕድሜ ለማማ ፡አጠገቧ ሆና ፡ስታስለፈልፋት ነው የምትውለው ፡ በዛላይ የአክስቴ ደግነሽና ፡የባዩሽ አብረዋት መኖር ፡ በፊት ከነበረባት ድብርት ያላቀቃት ይመስላል ፡
እስካሁን ድረስ ግን ከአቤል ጋር ስትነጋገር ሰምቻት አላውቅም ፡በሱላይ የወቀሳም ሆነ የምስጋና ቃል አላወጣችም ፡ብቻ እሱ ሲገባ ፡ትኩረቷን እንዳይስብ የማታደርገው ነገር እንደሌለ አስተውያለው ፡  ወይ ከእኛ ጋር ወሬ ትጀምራለች ፡አለዛ ከማማ ጋር መጫወት ትቀጥላለች ፡እንጂ ለአቤል የደና አመሻቹ ሰላምታ ምላሽ ሰጥታ አታውቅም ፡ አቤልን እራሴ ከፈጠርኩለት እስር በፈታውት ጊዜ እናቴ እግርስር ወድቆ የይቅርታ አይነቱን ሁሉ ቢያዥጎደጉድባትም ፡መልስ አልሰጠችውም ፡ዕንባውን አይታ አልራራችለትም ፡  እነደግነሽ በቃ ይቅር በይው ቢሏትም ቃል አልተነፈሰችም ፡  እኔም ያቅሜን በቃ ተይ ብላት ፡ እራሷ መልሳ ፡እኔን እንድተው አስጠነቀቀችኝ ፡እንግዲ ስለልጇ ባህሪ የምታውቀው እሷ ናትና በራሷ መንገድ ታስተካክለው ብዬ እኔም ተውኳት ፡ ደስ ያለኝ ቤታችን ፡በሰው መሙላቱ ከዚ በፊት የነበረው ጭርታ የለም ፡አክስቴ ደግነሽ አስቂኝ ናት የአገርቤቱን ወሬ እያወራች ፈታ ታረጋቸዋለች ፡ ከተማላይ ስለገጠማት ነገርም እያነሳች ፡ሳቅ ትፈጥራለች ፡ ባዩሽም በሕይወቷ ስላሳለፈችው ፡ነገር የማያልቅ ትረካ አላት ፡ማማም አዳዲስ አስቂኝ ቃላት አላት ፡እኔም ስራ ውዬ ነውና የምመጣው ፡ስገባ የምለው አላጣም ፡  አቤል ፡ ሶፋላይ ተቀምጦ እሪሞት ይዞ ፡ ቻናል መቀያየሩን ከኔ ተረክቦታል ፡ እኔ ያሳለፍኩትን እያሳለፈ ነው ፡  እናቴን ሁሉን እንድትተውለት ስጠይቃት ፡'አንተ ዝም በል እኔ ያበላሸውትን እንዴት እንደማስተካክለው አውቃለው ፡እና ደሞ ብቻችንን ስንሆን የምነግርህ ነገር አለኝ 'አለችኝ  እሺ አልኳት እነግርሃለው ላለችኝ ነገር ግን ጓጓው ፡ አንድ ሚስጢር አላት እንደውም ብዙ፣ለምሳሌ ስለ አባታችን አናውቅም ፣ ስለ መተዳደሪያችን አናውቅም እስክናድግ ድረስ ምንም ሳይጎልብን ኖረናል ያለስራ ፡ገንዘቡ ከየት ነው የሚመጣው፣ !!ብቻ ብዙ ጥያቄ አለኝ ያልተመለሰ.....
👉ቅዳሜ ለት ነው በጠዋቱ ቤታችን ሞቅ ደመቅ ብሏል የአዲስ አመት መግቢያም ስለነበር የሆነ ደስስ የሚል ነገር አለው ፡ አክስቴ ደግነሽ ቁርስ እያቀራረበች ታንጎራጉራለች ማማ እናቴ ላይ ተቀምጣ ትጫወታለች ፡ባዩሽ ቡና ለማፍላት ፡ጉድጉድ ትላለች ፡አቤል ከእናቴ ትይዩ ካለው ሶፋ ተቀምጦ ፡እናቴንና የገዛልጁን ፡ያያል ፡አስተያየቱ ውስጥ ቅናት ያለ ይመስላል በእናቴ ይሁን በማማ አልገባኝም ፡ ምን አልባት ይሄ ሁሉ ፍቅር የኔነበር ብሎ ይሆን እንጃ የገዛ ወንድሜ ፡አይገባኝም!
    እኔ ግን በቤታችን የማየው ግርግር ደስታን ፈጥሮልኛል ፡ ሰው ያለሰው ምኑ ያምራል! ከተንኮል ከክፋት የራቀ ስብስብ ቢበዛ ምንኛ ደስ ይላል።
ቁርስ ቀርቦ መመገብ ስንጀምር ስልኬ ጮኽ ፡ ላነሳው ስል አክስቴ ደግነሽ
"እህል ንጉስ ነው "አለችኝ
"ኧረ የስራ ስልክ ይሆናል "አልኳት እንድትተወኝ
"ነገርኩ እንግዲ ፡የት ይሄድብህ ነው ዋላ ትደውላለህ ኧረ"አለች እየተከራከረች ጠርቶ ጠርቶ ዘጋ እናቴ ወደኔ ፈገግ ብላ አይታኝ ጠቀሰችኝ ፡ፈገግ ብዬ በሽሙጥ ወደ አክስቴ ደግነሽ አሳየዋት ፡እና እኩል ሳቅን
"አህ እናትናልጅ በኔ ማሾፍ ጀመራቹ "ብላ እሷም ሳቀች ፡አቤል ደስ ያለው አይመስልም የሚጠጣበትን ብርጭቆ ሆነ ብሎ አስጮኽው
ስልኩ በድጋሚ ጠራ ፡ወደ ደግነሽ አየው ፡
"እሺ መቼስ ያለ ነገር አይደጋገምም ፡ አንሳዋ መቼስ"
"እሺ "ብዬ ላነሳ ስል "አንሳ ና አውራ እንጂ ተነሳ አልኩ እንዴ እዚሁ አውራ ኦራ ምን ሆኗል!"
ወይ አክስቴ ብዬ ፡ስልኩን አየሁት ቁጥሩን አላውቀውም ግን ደስ የሚል ቁጥር አንድ አይነት የሆነ በቃል ለመያዝ የማያስቸግር ።አንስቼ ሄሎ አልኩ ፡ከዛ ወገን ትንሽ ዝምታ ነገሰ  ደግሜ
"ሄሉ "አልኩ ፡ከዛ ወገን ደስ የሚል የሚስረቀረቅ የሴት ድምፅ መጣ የሆነ ቦታ አውቀዋለው
"ናታኒየም "አለች እንዴ ስሜ እንዴት እንደጣፈጠኝ 😂
"አዎ ማን ልበል "አልኩ ግን አውቄያት ነበር መኪና ያሳፈረችኝ ልጅ እንዴ ስልኬን ተቀብላኝ ግን ደውላልኝ አታውቅም ፡ እኔም ለነገሩ ትኩረት የምሰጥበት ጊዜላይ አልነበርኩም
"ብሌን ነኝ የሰፈርህ ልጅ ፡ስልክ ተለዋውጠን ነበር እረሳኽኝ እንዴ "አለች
"እእእ አስታወስኩሽ እንዴ ስልክ ቁጥሬን ምን አድርገሽው ነው እስከዛሬ ሳትደውዪ "አልኩ እየተሽኮረመምኩ
"ልክ ነህ መወቀስ አለብኝ ኪኪኪ ግን ለስራ ጉዳይ እራቅ ብዬ ነበር እና ወከባውስጥ ሆኜ ማለት ነገሮችን ለማስተካከል አሳቤን መሰብሰብ አልቻልኩም  ኪኪኪ እና እንዴት ነህ አንተ"አለችኝ ፡
"እኔ ደና ነኝ ያው በትርፍ ጊዜሽ ስላሰብሽኝ አመሰግናለው "አልኳት
"ኧረ በናትህ ብዙ አትነጫነጭ ኪኪኪ አስተካክላለው ከአሁን በዋላ "አለችኝ ፡ ከሴት ልጅ ጋር እንዲ ሌላ ስሜት ውስጥ ገብቼ አውርቼ አላውቅም ስለዚ የሌለ አይናፋርነት ታየብኝ ፡በተለይ የአክስቴ ደግነሽ አስተያየት
"እሺ እና ሰላም ነሽ "
"ደና ነኝ እእ ስራ ከሌለብህ አሁን ላገኝህ እችላለው ፡ ከሰፈር ወጣ እያልኩ ነው "አለችኝ
"አአሁን?"አልኩ እንደመንተባተብ ብዬ
"አዎ ምነው ችግር አለ"
"አይ የለም "
"በቃ አሁን ውጣ  "አለች ትህዛዝም ይመስላል
"እሺ እወጣለው ፡እየደረስሽ ነው"
"ደቂቃ ይፈጃል ብለህ ነው በርህ ላይ ጠብቀኝ በዛው ነው የማልፈው "አለችኝ
"እሺ "ብዬ ወዲያው መነሳሳት ስጀምር ፡እናቴ በምልክት ወደሷ እንድቀርብ ነገረችኝ እሺ ብዬ ቀረብኳት ፡"እራስህን ጠብቅ ፡ ማንኛውንም ሰው ቢሆን አይኖችህን ገልጠ ህይ ፡ ዳግም አንተን ማጣት አልፈልግም አደራ"
"እማዬ አንዲት ሴት እኮ ናት አትጨነቂ "አልኳት እና ሁሉንም መልካም ቀን ብዬ ልቤ ድው ድው እያለች ወጣው ፡ እንደወጣው ነበር ብሌንን ከነመኪናዋ ያገኘዋት ፡ ሳያት የውበቷ ግርማ እግሬን አኮለታተፈብኝ ፡ሆሆሆ እግር ይኮለታተፋል እንዴዴዴ..........


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍11252🤔6🥰2😁2