አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በሕይወት_አንድ_ጥግ

ትላንትና እሁድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውየ መጣና በሩን አንኳኳ…… እኔ ፣መአዛና የመአዛ እናት ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር ! ሮዛ ጎረቤቴ አብሮ አደጌ ናት ! አስቴር ደግሞ እናቷ . . .ለእኔም እናቴ ማለት ነች ኧረ …የእኔና የሮዛ ፍቅር ለብቻው ነው ከህፃንነታችን ጀምሮ ንፁህ የሆነ ምንም ፆታዊ ክጃሎት ውል ያላለበት ፍቅር እንዳለን አገር መንደሩ ምስክር ነው … እህቴ !!
ሮዚ ዩኒቨርስቲ ቆይታ ለእረፍት መምጣቷ ነበር ፡፡ የሚገረመው እናቴና የሮዛ እናት አስቴር የመረረ ጥል ያላቸው ኩርፈኞች ናቸው ! ግን እኔም እነሮዛ ቤት ሮዛም እኛ ቤት ልጆች ነን ! ስለእናቴ አስቴር ፊት ከተነሳ …‹‹ውይ ውይ የሷን ነገር አታንሳብኝ ጋኔል ….ምን ያረጋል እንዳንተ እይነት መለአክ ወለደች ››ትለኛለች እናቴን ለእኔ ታማልኛለች ! ‹‹ ቱ ሰው አይደለችምኮ !›› ትላታለች ! በእናቴ የመጣብኝን ሰው ይቅር ብየ አላውቅም አስቱ ግን ስትረግማት እንኳን ምርቃት የሚመስለኝ ለምን እንደሆነ እንጃ !
እሮዛ እኛ ቤት ስትመጣ ደግሞ እናቴ በተራዋ ለሮዛ ስለእናቷ ክፋት ጋኔልነት ትነግራታለች ‹‹ እናትሽ ….ምን እናት ናት እች እቴ …የሰይጣን ቁራጭ ከጥላዋ የተጣላች …እኔ ለሷ እንዲህ አልነበርኩም ….›› እያለች
እኔ እና ሮዚ እናቶቻችንን ረስተን እብድ ያለ ጓደኝነታችንን ቀጥለን አለን ! የሮዚ አባት በሂወት የሉም ! ‹‹ችግር የለም አባባን እንካፈላለን ›› ትላለች አንዳንድ ቀን ስንቃለድ አባባ የምትለው የእኔን አባት ነው ! ‹‹እናቶቻችን አባባን እንዳይካፈሉ ብቻ ›› እላታለሁ ‹‹ባለጌ ስድ ›› ብላ ትግል ትጀምረኛለች ቀይ ፊቷ በሃፍረት ይቀላል ! ሮዛ ቆንጆ ናት ግን ምኗ ነው ቆንጆ ቢባል አላውቅም እንዲሁ ጠቅለል አድርገው ሲመለከቷት በጣም ቆንጆ የምታሳሳ ኑሮ ምችት ያላት ልጅ ነች ! አንዳንዴ ሰውን ስንወድ ፍቅራችን የወደድነው ሰው ላይ ጎዶሎውን ሞልቶ ያሳየናል መሰል ሮዛ ጉድለት የላትም ለእኔ ! አዎ #ፍቅር አፍንጫ ፀጉር አይን ቁመት ጥርስ ከንፈር ሳይሆን አይቀርም ! ለነገሩ የሚጠይቃት ጎረምሳ ብዛትም ለሳቢነቷ ምስክር ነው !
ሮዛን የጠየቁትን ጎረምሶች እኔ እና ሮዚ የእለት ውሎ መመዝገቢያችን ላይ እንመዘግብ ነበር ! የሚገርመው ‹‹ዳይሪያችን›› አንድ ነበረች ሁለታችንም ውሏችንን ምንመዘግብባት ! ለሮዛ የሚላክ የፍቅር ደብዳቤ አብረን ነው የምናነበው እኔም ለሴት የምልከው አብረን ፅፈን እናውቃለን ! ታዲያ ሮዛ ብትሞት ለፍቅር አትሸነፍም ትምህርቷ ላይ አትደራደርም . . . ልቧ የገባም ወንድ የለም ‹‹ወንዶች ጅል ይመስሉኛል›› ትላለች አባቷ እናቷ ላይ ያደረሰው በደል ሁሉ (ነብሱን ይማረውና ) መጥፎ ጠባሳ ጥሎባታል ! አባቷ አይጠጣ አያጨስ ግን እናቷን መቀጠቀጥ ሱስ የሆነበት ሰው ነበር ጥርሷን ሁሉ አውልቆት ወርቅ ጥርስ አስተክሎላታል ! ሮዛ ልብ ውስጥ የነበረውን ወንድን የመሻት ተፈጥሯዊ ስሜትም ነቅሎ ባዶውን ትቶታል !
(አሁንም ነብሱን ይማረውና ግን የሚምረው አይመስለኝም )
እና ……ትላንትና እሁድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውየ መጣና በሩን አንኳኳ…… እኔ ፣መአዛና የመአዛ እናት ቡና ተፈልቶ ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር ! እንዳጋጣሚ ለበሩ የምቀርበው እኔ ስለነበርኩ ተነስቼ በሩን ከፈትኩ ! ከተወለደ ጀምሮ ዛሬ ገና የዘነጠ የሚመስል ሙሉ ግራጫ ልብስ የለበሰ ቀጫጫና ረዥም ሰውየ በሩ ላይ እየተሸቆጠቆጠ ቁሟል ! ሰውየው ሙሉ ልብስ ቢለብስም ለምን እንደሆነ እንጃ ሙሉ ልብስ የለበሰ አይመስልም . . . መቼም ሕይወት በሰወች አይን ፊት ስታጎለህ እንኳን ሙሉ ልብስ ሙሉ ብርጌድ አሰልፈህ ብትመጣ ግርማ ሞገስ የሚባል ነገር አይጠጋህም ! ቅልል ትላለህ ! እማማ ሩቅያ እንደሚሉት ‹‹ቀድረ ቀላል ›› ትሆናለህ !
ሰላም አልኩት … እየተሸቆጠቆጠና ዳማከሴ እንደሚያሽ ሰው እጆቹን አርሰ በእርስ እያፋተገ ሰላምታየን ከወገቡ ጎብጦ መለሰልኝ ! ከርዝመቱ እና ከእንቅስቃሴው ፍጥነት የተነሳ ለሰላምታ ከወገቡ ሲታጠፍ ከላይ ተምዘግዝጎ የመጣ የሆነ ወገቡ ላይ ተሰብሮ የሚወድቅ ባህር ዛፍ ነበር የሚመስለው !
‹‹ይ….ሄ የነሮዛ ቤት ነው አይደል …›› አለና እራሱ መልሱን መለሰው ‹‹አዎ ነው አውቀዋለሁ ›› አነጋገሩ የሚርበተበትና ከአፉ የሚወጡት ቃላት በጠባብ በር እንደሚወጣ ብዙ ህዝብ የሚገፋፉ የሚተሸሹ ይመስላሉ ዝም ብየ ስመለከተው ‹‹ እ. … የሮዛ እናት ይኖራሉ ወይም አባቷ ›› አለና መልሶ ለራሱ ‹‹ አውቃለሁ አባቷ እንኳን በህይወት የሉም …ግን እናቷ . . . ›› ተርበተበተ
‹‹እናቷ አለች ›› አልኩት
‹‹ልግባ ? ›› ሲል ገነት በር ላይ የቆምኩ መልአክ የሆንኩ እስኪመስለኝ ወደቤቱ ውስጥ በጉጉት አይኖቹን ልኮ ለማየት እየሞከረ ለመነኝ (ምን የተቀመጠ መስሎት ይሆን እነዲህ የጓጓው )
‹‹ግባ ›› ብየ በሩን ለቀኩለት ገባ !! አረማመዱ የሆነ የሚጮህ አይነት ነው የሚራመድ ሳይሆን በአንድ እግሩ ብቻ የሚዘል አይነት ላይ ታች ያረገርጋል …. እድሜው ሰላሰ አምስት ቢሆን ነው ! የሮዛን እናት ( አስቱ ነው የምንላት) በሁለት እጁ ሰላም ብሎ ወደሮዛ ዞረ እርሷንም በሁለት እጁ ሰላም አላት ! ሲመለስ የእኔን እግር ረገጠና ተንገዳግዶ ጠረንጴዛ ጫፍ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ባዶ ስኒ ከነበለው ! ስኒው ስር ቀርቶ የነበረው የረጋ የቡና ዝቃጭ ምንጣፉ ላይ ጥቁር ደብ መስሎ ተረጨ ! (ይሄ ሰው መርዶ ይዞ ነው እንዴ የመጣው ምን ያደናብረዋል )
ከ አስቱ ፊት ለፊት ተቀመጠ ! ሁላችንም ምን እንደሚል ለመስማት አይን አይኑን እናየው ጀመረ ‹‹ እ …ሰላም ነዎት ታዲያ እትየ ….አስቴር ›› አለ
‹‹እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ ›› ፊቷ ላይ ‹‹የት ይሆን የሚያውቀኝ ›› የሚል ግርታ ይታያል በፈገግታ ልትሸፍነው ብትሞክርም አልተሳካላት !
‹‹ልጆች ሰላም ናቸው ….ማለቴ ልጅዎት …አዎ አንድ ልጅ ብቻ ነች ያለችዎ ›› አለ ወደሮዛ አየት አድርጎ ያጠናውን ነበር የሚናገረው ያስታውቃል …..ፊቱን አልቦት ነው መሰል በመዳፉ አንዴ ሞዠቀው እና መዳፉን አየት አድርጎ በኮቱ እጅጌ እንደገና ግንባሩን ጠረገው !
‹‹ደህና ናት ›› አለች አስቱ እናም ኮስተር ብላ አየችኝ ! ትካሻየን በቀስታ ወደላይ ሰበኩት … እርሷ ያየችኝ ‹‹ማነው›› ማለቷ ሲሆን እኔም በትካሻየ ምላስ ‹‹እኔጃ ›› አልኳት ለትንሽ ደይቃ እንግዳውም አቀርቅሮ አኛም እንግዳው ላይ አፍጥጠን እንደቆየን እንግዳው ተናገረ
‹‹አንተ አብርሃም ነህ …እዚህ ጎረቤት ያለከው ልጅ አይደለም እንዴ ›› አለኝ
‹‹አ . . .አዎ ››
‹‹ያው ለሮዛ ወንድሟ ማለት ነህ …ማዘርም ጋር ትቀራረባለህ ያው ልጃቸው ማለት እኮ ነህ ››
‹‹አዎ ያው ልጀ ማለት ነው ›› አለችው አስቱ
‹‹ጥሩ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ስለምናወራ ላረጋግጥ ብየ ነው ›› አለ ወደአስቱ በፈገግታ እየተመለከተ . . .ፈገግታው ይጨንቃል ከንፈሮቹ ወይ በደንብ አይከፈቱ ወይ አይገጠሙ ሄድ መለስ እያሉ ይንቀጠቀጣሉ ! በማጭድ የተጋጠጠ የሚመስል ፂሙ ቅሪቱን ጉንጩ ላይ ዘርቶት በሽተኛ አስመስሎታል … ጥላሸት የተዘራበት አጥንታም ጉንጭ ! ደግሞ እኮ ሲያረጉ አይቶ ‹ኦ › ቅርፅ ! አፉ በፂሙ ተከቦ ሲታይ በኮሸሽላ ዙሪያውን የታጠረ የደረቀ የውሃ ጉድጓድ ይመስላል ! ወቸ ጉድ ምን ሊል ይሆን . . .ጭንቀት ገደለኝ
‹‹ የመጣሁት ሌላ የሚመጣልኝ ሰው ስለሌለ ነው .ላቀው እባላለሁ .›› አለና ድንገት ቁሞ አስቱን ሰላም አላት እኔንም ሮዛን ግን ረሳን ….‹‹ እ….ያው የመጣሁት መጥቼ መናገር ስላለብኝ እና
👍3🔥1
. . . ›› ስልኩ ጮኸች ልክ እንደአይጥ ነበር ፂው ፂው እያለች የጮኸችው …. ገና ሳያወጣት ስልኳን ‹‹ቀድረ ቀላል ›› መሆኗን አውቂያታለሁ … እጁን እስከክንዱ ሱሪው ኪስ ውስጥ ከተተና ዙሪያዋን በፕላስተር መቀነት የተተበተበች ቀይ ስልክ አወጣ (ይሄው እንዳልከዋት ናት ካልኳትም ትብሳለች) …. ስልኳን ከኪሱ ሲያወጣት ጩኸቷ ተቋረጠ … የሆነ ነገሯ ኪሱ ውስጥ ስለቀረ እንደገና ኪሱን ፈትሾ ክዳኗንና ባትሪዋን አወጣ ተበታትና ነበር የወጣችው . . .በጥንቃቄ ገጣጠመና ኮቱ ኪስ ውስጥ አስቀምጦ ወሬውን ቀጠለ
‹‹ ….እና የመጣሁት መጥቼ እርሰዎን ለማግኘት ነበር…..ያው አገኝቼዎታለሁ ›› ብሎ ፈገግ አለ ! አስቱን እንዳገኛት ለራሱ አላመነም መሰል !
‹‹አዎ አግኝተኸኛል …ከየት ነው ግን የመጣሃው እንደው ዘነጋሁህ መሰል አላወኩህም ›› አለች በጨዋነት
‹‹አ ……ይ አልዘነጉኝም ….ድሮም አያውቁኝም ›› አለ
‹‹ኧረ ….እንደዛ ነው ? …እምምም ታዲያ እኔን እንዴት አወከኝ ››
‹‹አላወኩዎትም . . . ያው ልተዋወቅዎት ነው የመጣሁት ›› እልሄን ነበር ያስጨረሰኝ ….ኤጭጭ ወደዚያ ማን እንደሆንክ ተናገር ›› ማለት አመሮኝ ነበር ! እግዜር ይይለት መንዛዛቱን ቀጠለው
‹‹ ሰው እኮ ደፍሮ ካልተዋወቀ መቸስ …››
‹‹ልክ ነው ›› አለች አስቱ እንዲናገር ለማደፋፈር እንጅ ያላለቀ አረፍተ ነገር መቸም ቢሆን ልክ ሁኖ አያውቅም !
‹‹የመጣሁት . . . ለዚህ ነው እኔም ››
‹‹ለምን ? ›› አለች አስቱ ገርሟት
‹‹ያው ለመተዋወቅና ከተዋወቅን በኋላ አንዳንድ ቤተሰባዊ ጉዳዮችን ለመነጋገር ››
‹‹ይሄው ተዋወቅን እስቲ የመጣህበትን ንገረኝ ›› አስቱ ትንሽ ኮስተር ያለች መሰለኝ
‹‹የመጣሁት ያው ሮዛን …ማለቴ ልጅዎትን ሮዛን ላገባት ስለፈለኩ እርስዎ እንዲፈቅዱልኝ ነው …. እባክወትን እማማ አስቴር ›› ብሎ ተንደርድሮ አስቱ እግር ስር ተደፋ …ቀስ ብየ ወደ ሮዛ ዞርኩ ሶፋ ላይ ሳይሆን ኤሌክትሪክ ወንበር ላይ እንዳስቀመጡት የሞት ፍርደኛ ደርቃ ቀርታለች ፡፡ ሙልት ያሉ ቀይ ጉንጮቿ ገረጥተው አይኗ ባዶ ጠርሙዝ መስሏል !
‹‹ኧረ ተነስ ተነስ የኔ ልጅ›› አለች አስቱ ምኑም ምኑም እንዳልጣማት ታስታውቃለች ! ልጁ ተነስቶ ቆመና ‹‹እሽ አሉኝ ማዘር›› ሲል በጉጉት ጠየቀ
‹‹አክብረኸኝ ስለመጣህ ተባረክ ….ግን አሁን ዘመኑ ሰልጥኗል ማነህ …….››
‹‹ላቀው›› አለ እራሳችሁ ተነጋገሩ እዛው ›› ብላ ሮዚን አጋፈጠቻት
ሮዚ በርግጋ ተነሳች ከዛም ‹‹ ምናይነቱ ነው ›› ብላ ወደገዋዳ ገባች
አስቱ ግራ ተጋብታ እንዲህ አለችው ‹‹ እንደው ወጉም በሃሉም እንዲህ አልነበረም … ቢጠፋ ቢጠፋ ያንተ ቢጤ እንኳን አንድ ሁለት ሰው ይላካል . . .ሰተት ተብሎ ነውር እኮ ነው ››
‹‹አስቤ ነበር . . .›› አለ አንገቱን ደፍቶ ግን ሰው አጣሁ ! ዘመድም የለኝም … እና ደግሞ የምነግራቸው ሰወች ሁሉ ‹‹ለራስህ ሳትሆን ሚስት …ጠግበህ ሳትበላ ሌላ እዳ መጨመር እያሉ አሸማቀቁኝ ….አስቤ ነበር ሰው የለኝም …..አስቤ ነበር ሮዛን ስለወደድኳት ነው …እንደው እሽ ቢሉኝም ቀጥሎ ምን አባቴ አደርግ እንደነበር እንጃ እራሴ እሷን በማሰብ ከሚፈነዳ እንዲህ ነገሩን አፈንድቸው ይለይለት ብየ ነው ….ሮዛን እወዳታለሁ ሮዛ ቀይ ቆንጆ ልጅ ናት ….. ሰው ለራሱ ሽማግሌ ቢሆን አልኩ ….ትክክለኛው ሽማግሌ እኔ ነኝ የሮዛን ፍቅር ምን ያህል እንዳለምኩት የሚያውቅ ሽማግሌ ማን አለ ….በማድርባት የፈራረሰች ቤት ብርሃን የዘራችው ማናት ሮዛ ናት ….ሮዛ የእርሰዎ ልጅ …….ማንም እንደሰው በማያይብኝ አገር እንደጥራጊ በተጣልኩበት መንደር ሰው መሆኔን ለልቤ የነገረው የሮዛ ፍቅር ነው …..ሮዛ የእርሰዎ ልጅ ›› ወደበሩ መንገድ ጀመረ አነጋገሩ ተረጋግቶ ነበር ፍርሃቱ ሁሉ ጠፍቶ !
‹‹… መቼስ የፈጣሪ ትልቅነት ይሄን ፍቅር ሰው እንኳን ቀና ብየ የማላይ ትንሽ ሰው ላይ ጥሎት ሰው ፊት አቆመኝ …እንደው ሰው ልሁን ብየ እንጂ እሱስ እሽ ቢሉኝም ሮዛን የት እንደምወስዳት እንጃ … ሮዛ እኮ … አራት አመት ከልጅነቷ ጀምሮ አስራ ሁለተኛ ክፍል እስክትሆን . . . ዩኒቨርስቲ እስክትገባ ስወዳት ስወዳት ስወዳት ከረምኩ . . .
አልተማርኩም ..... እንደው የእግዜር ነገር እኔ ላይ ይሄን ፍቅር ቢጥለው እኔው ሽማግሌ ሆንኩ …ሆድህን ሳትሞላ ይላሉ ፍቅር በሆድ ይመስል ለራስህ ሳትሆን ይላሉ ምንድነው እኔ እኔ ማለት ?….ለራስ ከሆኑ በኋላ በተረፈው ይፈቀራል እንዴ . . . እራስን ጥሎ እንጅ ለሌላው መኖር … ሮዛን ….የእርስዎን ልጅ ወድጄ ስንት አመት ሙሉ ……ዘመድ የለኝም ሮዛን እያሰብኩ ሽ እልፍ ሁኜ ኖርኩ . . . ማንም አይደለሁም ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ይባል እንጅ ቅሉ ስለራሴ አብዝቼም አሳንሼም የምቆርሰው የሌለኝ ኑሮ ቆራርሶ እዚህ ያደረሰኝ ከንቱ ነኝ …ሮዛ የአንቱ ልጅ ግን በሂወቴ ውስጥ ትልቋ ቁራሽ ትልቅ ድርሻየ ነበረች ! ሮዛ የአንቱ ልጅ . . .
‹‹ . . . ሳያት እኮ ልቤ ውስጥ ገነት ይፈጠራል … ፍቅሯ እንደግዜር የገነቱ አስተዳዳሪ …መንገዱ ምንድነው የሚነጠፍበት …ሮዛ ስታልፍ ቢጫ ይሆናል … ሮዛ ስትስቅ በደስታ አለቅሳለሁ እጆቿ እንደሩቅ አገር ህልም ናቸው እግሮቿ … ደህና ዋልሽ አልከዋት አንድ ቀን አየት አድርጋኝ በዝምታ አለፈች …..አየችኝ አይኖቿ አዩኝ ቢያንስ የምታይ ሰው ነኝ በክፉም ይሁን በደግ መታየት መኖርን ነው የሚገልፀው ሮዛ አየችኝ አይኖቿ ካለመኖር ፈውሰውኝ ይሄው አለሁ ….›› አለና በሃሴት ፈገግ አለ ከንፈሮቹ አልተንቀጠቀጡም በነፃነት ፈገገ !
ከተቀመጠበት ተነሳና ከቤት ወጣ ሲወጣ አንዴ የበሩ ጉበን አናቱን ገጨው …. ደህና ዋሉም አላለ ! ተከትየው ወጣሁና በሩ ላይ ቁሜ በግርምት አየሁት . . .የማይሰማ ነገር እያነበነበ በጣም የሰፋው ሱሪው እጅግ በጣም የሰፋበት ኮቱ እየተርገበገቡ እየተውለበለቡ …..ሆድ የባሰው አገር ባንዲራ መስለው …..ወደታች ወረደ እየተጣደፈ . . . ከሩቅ ሳየው ከኋላው አሳዘነኝ ! ከዛ በኋላ እስከማታ እኔም ሮዛም አስቱም ስለዚህ ጉዳይ አንዲትም ነገር ትንፍሽ አላልንም በየፊናችን እያሰብነው እንደነበር ግን አያጠየይቅም !
ማታ ወደቤቴ ስሄድ አስቱ ሮዚ ሸኘችኝ እንደሁል ጊዜው እኛ ግቢ በር ላይ ቁመን ከላይ ጨረቃ ከታች የነፍሳት ሲርሲርታ እና የንፋስ ፉጨት ማየለበት ጨለማ ውስጥ ሮዛ ለስለስ ባለ ድምፅ እንዲህ አለችኝ ‹‹አብርሽ የቅድሙ ሰውየ አሳዘነኝ ሙሉ ቀን ሌላ ነገር ማሰብ አልቻልኩም . . . ››
‹‹እኔስ ብትይ ››
‹‹ግን እዚህ ሰፈር አይተኸው ታውቃለህ እንዴ ››
‹‹እኔጃ አላስታወስኩትም ›› ዝምምምምምምምምምመምምምም
ምምምምምምምምምምምምም ዛፎች ይንኮሻኮሻሉ ነፍሳት ሲር ሲር ፂው ፂው ይላሉ …ጨረቃ እንደትልቅ የቅቤ እንክብክብ ወዛም ብርሃኗ በእኛ ላይ እየቀለጠ ፍስስስ ይላል …..የጨለማ ድርቀቱን እያረሰረሰ …
‹‹ ቁመቱ ደግሞ ሲያምር ›› አለች ሮዛ ልስልስ ባለ እንደጨረቃ በሚቀልጥ ድምፅ ….. ለመጀመሪያ ጊዜ ወንድ ስታደንቅ ሰማሁ !

💫ተፈፀመ💫

🔘አሌክስ አብርሃም🔘
👍1
አትሮኖስ pinned «#በሕይወት_አንድ_ጥግ ትላንትና እሁድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውየ መጣና በሩን አንኳኳ…… እኔ ፣መአዛና የመአዛ እናት ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር ! ሮዛ ጎረቤቴ አብሮ አደጌ ናት ! አስቴር ደግሞ እናቷ . . .ለእኔም እናቴ ማለት ነች ኧረ …የእኔና የሮዛ ፍቅር ለብቻው ነው ከህፃንነታችን ጀምሮ ንፁህ የሆነ ምንም ፆታዊ ክጃሎት ውል ያላለበት ፍቅር እንዳለን አገር መንደሩ ምስክር ነው … እህቴ !! ሮዚ…»
#የሆድና_የልብ_ድርቀት
:
#ድርሰት_በአለመየሁ_ገላጋይ
:
:
ያን ሰሞን ክፉኛ ሆዴ ተቆልፎ፣ጉሮሮዬ ከእህል ተኳርፎ፣ነፍሴን ጠኔ ሊነጥቀኝ ከወደ ሆዴ በድን አደረገኝ።ከደረቴ ዝቅ ብሎ ከብሽሽቴ ከፍ ብሎ ሞቼ ነበር ማለት እችላለሁ።እንቅስቃሴ የለ፣ድምፅ የለ፣እህል ቤቴን ምን ነካብኝ?

ሐኪም ዘነድ ሄድኩ ።
በአፉ አልቻልኩም ማለት ሲቀረው ጥዬ ሄድኩ።
የሐበሻ መዳኒት ጀምር የሚል ምክር ተከትዬ የሚከብድ ደጃፍ ቆረቆርኩ ። አጭር መዳኒተኛ ሆዴን በጣቱ ሲነካው ኮንክሪት የተሞላ የፍየል ስልቻ ምስጋና ይንሳው ።

<<ግንበኛ ነውዴ የፈጠረክ?>>ያለኝ መሰለኝ ሲያየኝ ።
<<ግንበኛ ተጠናውቶኝ እንደሆነ እንጂ እንደማንኛውም ሰው የፈጠረኝስ አናጢ ነው>>
ልለው ከጀለኝ ።

መዳኒት አዋቂው ሰላቢ ሳይሆን አይቀርም፣ ስበላ የኖርኩትን ሁሉ ጠየቀኝ ።

<<ምንም!>>አልኩት

<<የምትጠጣውስ?>>

<<ምንም! አንዳንዴ ጠጅ>>

<<ለመሆኑ የምትበላው ነገር አለህ ? >>

<<ባይኖረኝማ ገላገለኝ ነበር>> አልኩት

<<ብቻ ከምግቡ ጋር እየተያየን እናድራለን>>

<<አይነጥላ ነው>>

<<እ?>>

<<አይነጥላ ነው>>

<<መድሀኒቱ ማርከሻው ምንድን ነው?>>

<<ሆዳም>>

<<እ?>> የሰደበኝ መሰለኝ ።

<<ሆዳም ሰው ካለህ ቤትህ ማስቀመጥ። እንዳይበላ ለሚያደርግ አይነጥላ መድሀኒቱ ብዙ የሚበላ ሆዳም ነው።>>

በአይነ ህሊናዬ ሆዳም አሰብኩ የለም። በፊት የሆዳም አገር የምትመስልህ ኢትዮጵያ ለመድሀኒትነት......

መዳኒተኛው በሙንጭርጭር ፁሁፍ የመድሀኒት ማዘዣ ፃፈለኝና
<<ከዚህ ዝቅ ስትል አረቄ ኮማሪት አለች >>

<<አረ ደንበኛዬ ናቸው>>

<<ጥሩ ይሄንን ወረቀት ለሷ ስጣት >> አለኝ

የተጠየቁትን ሂሳብ ከፍዬ ወደ ኮማሪቶ ሄድኩ። ሶስት ቡትሌ አረቄ ፣በቀን ሶስት መለክያ ፣ ጧት አንድ ፣ ከምሳ በኋላ አንድ፣ ማታ አንድ ብሎ ሳይፅፍልኝ አልቀረም ። የተጠቆምኩበት ቤት ሄጄ ደጃፍ ላይ ቆምኩ።

<<ግባ፣ ግባ፣ ግባ፣...>> ተባልኩ ልጠጣ የመጣው መስሎቸው። ኮማሪቶን ጠቅሼ የተሰጠኝን ወረቀት ወደእሶ አስተላለፍኩ። ኮማሪቷ
ወረቀቱን አንብባ አንዲት ደዘደዘ ሴት አስረከበቺኝ።

<<ምን ላድርጋት ?>>

<<እሷ ስትበላ እያት>>

ሃምሳ ብር ከፍዬ ይዣት ወደ ቤት ሄድኩ ።
ይቺ ሴት እንደነቀዝ እህል ቦርቡራ ውቅር አበያተ ምግብ የሰራች ተአምረኛ ነች ።
ስትበላ ዶሮ የምታጥብ ትመስላለች። ትሰቀስቅና፣ቸፍ ቸፍ አድርጋ ወደ አፎ ትወረውረዋለች።ምግቡን መሬት ላይ አለማንጠሯ
እንጂ ትእይንቱስ የቅርጫት ኳስ ነው።

የእኔ ስራ ፈዞ ማየት ሆነ ።

እንሆ ከሆድ ድርቀት ወደ ሆዳም ድርቀት ተሸጋገርኩ ።በቀን ሶስት የነበረውን የአይነ ጥላ መግፈፍ ፕሮግራም በቀነሰ ስድስት ጊዜ አሳደገችው።

<<ቻይና የተገኘው ነገር ሁሉ ይበላል >> ሲባል ከሰማች

<<እዚያ ውሰደኝ >> ትለኛለች
ቀኝ እጇን ቁርጥማት ካመማት <<በምን ልበላ ነው ?>> እኔ ሰው አጉርሶ አያጠግበኝም >>እያለች ታለቅሳለች ።
<<አፄ ዮሐንስ ሲነግሱ 5 ሺህ ሰንጋ ተጥሎ ነበር>> ከተባለች፦
<<ያኔ ብወለድ ኖሮ >> ትልና ሎተሪ ለአንድ ቁጥር እንዳመለጠው ሰው ትቆጫለች ።

በአስራ አምስተኛው ቀን ይዣት ኮማሪቷ ጋር ሄድኩ

<<አይነጥላህ ለቀቀህ?>> አለችኝ ኳማሪቷ
<<እጅግ በጣም>> አልኩ ሴትየዋን ወደ አረቄው ቤት እየገፋሁ።
<<አሄሄ አልተሻለህም። ቢሻልህ ኖሮ ትሻማት ነበር ከተሻማሀት እሷ ስለማትወድ አኩርፋ እራሷ ትመጣ ነበር። ስለዚህ እስኪሻልህ አንተ ጋር ትሁን >> ብላ መለሰችኝ። 😳

አስተያየት ካሎ @atronosebot አድርሱን።
👍3
#ከፍትፍቱ_ፊቱ
:
መትረየስ ደግነው
ስወጣ ስገባ
ከሚገላምጡኝ ፣
ያላችሁበት ድረስ
ልምጣና ቀጥቅጡኝ ።
#የሚስት_ያለህ

የክረምቱ ብርድ ደመናው ቢያስፈራኝ
ሚስት ፈለኩና አቅፋ ምታሞቀኝ
ሰማዩን እያየሁ ፎቶ ተነሳሁኝ
ፖስታ ቁጥሬንም በጋዜጣ አውጥቼ
የሚስት ያለህ እያልኩ ጠበኩኝ ጓጉቼ
ሀሳቤም ተሟልቶ በላይ ከገመትኩት
አስር ሺህ ደብዳቤ ደረሰኝ በሳምንት
ሁሉንም በተራ ቸኩዬ ባነበው
ወንዶች የላኩት ነው #ሚስቴን ውሰድ ብለው
አትሮኖስ pinned «#የሆድና_የልብ_ድርቀት : #ድርሰት_በአለመየሁ_ገላጋይ : : ያን ሰሞን ክፉኛ ሆዴ ተቆልፎ፣ጉሮሮዬ ከእህል ተኳርፎ፣ነፍሴን ጠኔ ሊነጥቀኝ ከወደ ሆዴ በድን አደረገኝ።ከደረቴ ዝቅ ብሎ ከብሽሽቴ ከፍ ብሎ ሞቼ ነበር ማለት እችላለሁ።እንቅስቃሴ የለ፣ድምፅ የለ፣እህል ቤቴን ምን ነካብኝ? ሐኪም ዘነድ ሄድኩ ። በአፉ አልቻልኩም ማለት ሲቀረው ጥዬ ሄድኩ። የሐበሻ መዳኒት ጀምር የሚል ምክር ተከትዬ…»
#የትንሽ_ትልቅ_ፀብ

<<ተከራይተህ ነው?>> አለኝ።ስድስት አመት ቢሆነው ነው።
<<አዎ>> ሁኔታው እንዳዋቂ ያሽቆጠቁጣል ።

<<ዘልዛላ ሰው ነው ቤት መስራት ሲገባው የሚከራየው ትላለች እናቴ>>

<<እናትህ ልክ ናቸው >>አልኩ በአፌ።በሆዴ ግን ባለጌዋ እናትህ ሳይሆኑ አይቀሩም።

<<ዘልዛላ ነህ?>>

<<ውጣ፣ እቃዎቹን ላዘገጃጅ።>>የተነጠቀ የታላቅነት ስፍራዬን ላስመልስ ሙከራ አደርኩ።

<<ዘልዛላ ግን ምንድን ነው?>> እሱም የተነጠቀ የትንሽነት ስፍራውን ለማስመለስ እየጣረ ይሆን?

<<አላውቅም፣ወደ ውጭ ፣ ያለኝ ጊዜ ትንሽ ነው። ቶሎ እቃዎቹን ቦታ ቦታ ላሲዛቸው።>>

ወጣ፣ ከቤቴ። ከህይወቴ ማስወጣት እንዳልሆነልኝ ግን አንዳች ነገር ነግሮኛል። በነጋታው ጠዋት አንኳክቶ ስከፍት

<<እኛ ቤት በግ ተገዝቷል፣ አንተ አትገዛም?>>

የትንሽነት ቦታው እንደፈቀደለት ሲሆን መስሎኝ በፍቅር አየሁት።

<<እኔ አልገዛም>>

<<እማዬ ዘልዛላ ነው ለአዲስ አመት በግ የማይገዛው ብላለች። ዘልዛላ ነህ እንዴ ?>>

እንደትልቅ ሰው ቆጥሬው የትልቅ ሰው ማብራርያ ዘዴዎችን ተጠቀምኩ። ፊት መንሳት፣ ሳይሰናበቱ በር መዝጋት።በዚህ ሀፍረት እራሴን ቀጣኝ። ቀስ ብዬ አድብቼ ወጣሁ። አምሽቼ ገባሁ ።

በጠዋት ሲንኳኳ የቀጠርኳት ጓደኛዬ መስላኝ ነበር
እሱ ነው። አጭር አዝማሪ መስሎ በሬ ላይ ተገትሯል። ነጭ በነጭ ለብሶ ባለጌነቱን ሸፋፍኗል። ከያዛቸው የአዲስ አመት ማብሰርያ ወረቀቶች አንዱን መዝዞ ሰጠኝ።

<<አልገዛም>> አልኩት።

<<አትግዛ ግን ውሰደው>>አለኝ። እሱ በለጠኝ።<<ቆይ>> ብዬው መኝታ ቤት ከሰቀልኩት ኪሴ ውስጥ አስር ብር አምጥቼ ሰጠሁት።ስእሉ መላቅጥ የለውም።ልጅነቱ ስእሉ ላይ አሸንፎታል።እንደርችት ያሉ የተለያዩ ቀለማት ተረጭተው አንድ ቢጫ ቀለም በስህተት ቁልቁል ተምዘግዝጋለች።ጠረጴዛው ላይ ጣል አድርጌው ወደ ኪችን ገባሁ።

ጓደኛዬ ስትመጣ <<ኦሆሆሆሆሆ>> እያለች ነበር

<<ምነው?>>

<<አረ ተወው፣ ዝም ብዬ ነው።>>

ሆዴን ቆረጠኝ።ያለአንዳች ጉዳይ ዝም ብላ አልተብሰከሰከችም።

<<ምንድንነው ንገሪኝ>>

<<ተወው ምን የደርግልሀል?>>

<<እንዴት ነው ኦሆሆሆይ ብሎ ከተገረሙ በኋላ ተወው ማለት?>> አኮረፍኩ።

<<ይሄ እናንተ መደዳ ያለው ትንሽ ልጅ>>

<<እ>>

<<እሱ ዘልዛላ ነው ሌላ ፈልጌ አላለኝ መሰለህ>>

<<እናቱ...>> ስል አረጋጋችኝ።ቀኔ ተበላሸ።ይሄ የገሀነም ፍሬ የሆነ ልጅ ቀኔን አበላሸው።የሚገርመው ደግሞ በጠዋት አንኳኳ።
ጓደኛዬን እኔ ፊት ቢመክራት ምን እላለሁ?የቴሌቪዥኑን ድምፅ ከፍ አድርጌ በሩን ከፈትኩ።ከበሩ ራቅ ብሎ ቆሟል።ስለማላስገባው ተንደርድሮ በእግሬ ስር ሊሾልክ? እግሬን ግጥም አደረኩ።

<<አስገባኝ>> አለኝ።የአመት በአል ልብሱ በቀይ ወጥ ተነካክቶ....

<<ለምን?>>

<<ስእሌን አያለው>>

<<አታይም>>

<<መብቴ ነው፣ ብሸጥልህም ስእሉ ሲናፍቅኝ የማየት መብት አለኝ።>>

<<ይህም ስእል ሆኖ >>አልኩት

<<የሚገባኝ እኔ ነኝ፣አስገባኝ>>

ፀብ ተካሮ ጓደኛዬ እንዳትሰማ አስገብቼ አሳየሁት።ቀሰብ፣እራቅ እያደረገ ተደመመበት።አይኑም እንባ ያቀረረ መሰለኝ፤ጉደኛ ነዋ!

<<ስእሉ ምንድን ነዎ የሚለው ?>>

<<ይሄ ከላይ የሚመጣው መልአክ ነው፤ መላእክቱ ሲመጡ ሴጣን ሸሽቶ በዚህ በኩል በሩን ቀዶ ሲገባ>>

ቀስ ብዬ አስወጣሁት።

በቀጣዩ ቀን መልሶ አንኳኳ።

<<ስእሌን ልይ>>

<<ምን እዳ ገባሁ>>

<<መብቴ ነው፣ብሸጥልህም አልውሰደው እንጂ ማየት እችላለው>>

<<እንደውም ውሰደው>>

<<አልወስድም፤ አንዴ ገዝተህኛል>>እንባው አቀረረ?መቼም ጉደኛ ነው።

አስገብቼ አሳየሁት። ቀረብ፤ ራቅ እያደረገ ዛሬ ደግሞ ፈገግ አለ።

<<ስእሉ ምንድን ነዉ የሚለው?>>

<<ይቺ እናቴ ናት፤ ይሄ አባቴ ነው። ሲመጣባት እኔን አቅፋኝ ጀርባዋን ስትሰጠው።>>

አሳዘነኝ? ዉጣ ሳልለው ወጣና በር ላይ ሲደርስ እየሳቀ

<<ውሸቴን ነው>> አለኝ።

ደነገጥኩ።የነገረኝን በመንገሩ ልቤ እንደሚነካ ቀድሞ አውቋል።ፈራሁት፤ተናደድኩበት።ከቤት ስወጣ እኔም እየሳኩ።

<<ቀደድኩት>> አልኩት።

<<ምኑን?>> የትልቅ ሰው ድንጋጤ።

<<ስእሉን>>

የጎረምሳ ለቅሶ በትከሻው እያሳየ

<<እበቀልሀለው>>አለኝ።እውነትም ተበቀለኝ። የበሬ ቁልፍ ውስጥ አሸዋ ሞጅሮ መክፈቻው አልገባ አለኝ።ስታገል ግማሽ ሌሊት አለፈ።በኮንትራት ታክሲ እናቴ ቤት ሄድኩ።ጠዋት ሰራተኛ አምጥቼ ምንም ማዶረግ ስላልተቻለ ቁልፉ ተገነጠለ።ስገባ ንዴት ማብረጃ ፊልም ማየት አልቻልኩም።እሽሽሽሽሽ..ይላል።ዲሹን አዙሮ፤አዟዙሮብኛል ማለት ነው።ካልታረኩት ሌላ ተንኮል ሳይጨምር በሁለቱ ብቻ በአጭር ጊዜ እንደሚያሳብደኝ ገባኝ።ኡሁሁሁሁሁሁ....

🔘 አለቀ 🔘
👍5
#እጅ_በጆሮ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
:
ማምሻውን ነው

ዝናብ ያረሰረሰውን የሰፈራችንን ኮብልስቶን መንገድ በጥንቃቄ እየረገጥኩ ወደ ቤት አዘግማለሁ። በረገጥኩት ቁጥር በድንጋዬቹ መሀከል የተኛው ውሃ ፊጭ ፊጭ ይላል።ዘንቦ ማባራቱ ስለሆነ ይበርዳል

ፊጭ ፊጭ እያደረኩ መራመዴን ስቀጥል፤ ከዚህ በፊት አይቼ በማላወቀው ብዛት በመንገዴ ላይ ከሰል አቃጣጥለው፤በቆሎ ጠብሰው፤በተርታ ተሰድረው ገብያ የሚጠብቁ ሶስት ሴቶችን አየሁ።

የመጀመርያዋ ወጣት ቢጤ ናት።አጠገቧ ከባድ ዝናብ ያዘመመው ወልጋዳ ጃንጥላና ኩምትር ብሎ የተቀመጠ ሕፃን ይታየኛል።ከእሷ ቀጥሎ ያሉት ሴቶች ሌጣቸውን ናቸዉ።ከእርሷ መግዛትን መረጥኩና ስደርስ፤

<<እናት....በቆሎ ጥብስ ስጪኝ ?>>አልኩ።
አንዴ፤እሳቱ ከተንተረከከው ከሰል ምድጃ ዙርያ አልቆላቸው የተቀመጡ ሶስት በቆሎዎችን፤ ከዝያ ደግሞ ሕፃኑን ልጅ አፈራርቄ እያየሁ።ከብርድ የማያስጥል ቡትቶ ቢጤ ለብሷል።ክሳቱ የሚያሳቅቅ፣የፊቱ መገርጣትአንጀት የሚያንሰፈስፍ ልጅ ነው።ሲርበው የከረመ ይመስላል?

<<የቱን ላድርግልሽ?>> አለችኝ።

<<የቱ ይሻላል?>>

<<ይቺኛዋ ቆንጆ ናት....በደንብ በስላለች ግን አላረረችም....አየሽ?>> አለችኝ። አንዶን በቆሎ መሬት ላይ ከነሽፋናቸው ከተቀመጡ ጥሬ በቆሎዎች ገንጥላ፣ባመጣችው ሽፋን ጥቅልል አድርጋ ልታሳየኝ እየሞከረች።

ተቀበልኳት።

<<ስንት ነው?>> አልኩ ልጁን፤ በተለይ አይኖቹን ሰርቄ እያየሁ። ከርታታ አይኖቹ ልገዛው የተቀበልኩት በቆሎ ላይ ናቸው።

ሁኔታው ያሳብቃል ፤ ማሙሽ በጣም እርቦታል።

<<ስድስት ብር>> አለችኝ።

<<እሺ ሁለት ስጪኝ>> አልኩና አስራ ሁለት ብር አውጥቼ ሰጠኋት።ሌላ ቆንጆ ነው ያለችውን መረጠችና ልትሰጠኝ ስጠቀልል ዘደ ልጁ ዞርኩ። አንደኛውን በቆሎ ልሰጠው ጎንበስ ስልከደረስኩ ጀምሮ ዐይኑን ከእኔ ላይ ያልነቀለው ልጅ ባልጠበቁት ፍጥነት ፍንጥር ብሎ ተነሳ።

<<እንካ ማሙሽ>> አልኩት። ስፍስፍ እያልኩ....ለመንጠቅ በሚቀርብ ሁኔታ ሲበበለኝ አንጀቴ እየተላወሰብኝ።

<<እግዜር ይስጥልኝ የኔ እመቤት....ሙሉ ይስጥሽ የኔ እመቤት...ሙሉ ሙሉውን ይስጥሽ.....>>(የምርቃት ዝናብ አዘነበችብኝ)

ምንም ሳልናገር ፤ የማይገባኝ ምርቃት ሽሽት ፊጭ ፊጩን አፍጥኜ ወደ ፊት መራመድ ጀመርኩ።

ዐስር ከማይሞላ እርምጃ በኋላ ግን ልገልፀዉ በማልችለው ምክንያት ዞር አለኩ። ልጁን ተመለከትኩት። ሳገኘው እንደነበረው ኩምትር ብሎ ተቀምጦል ። እጆቹ ላይ በቆሎ የለም። ወደ መድጃው ተመለከትኩ። ሁለት የበሰሉ በቆሎዎች ዳር ይዘው ተቀምጠዋል።

ሚዛኔን እንደመሳት አደረገኝ። አንገቴን ወደ ቤቴ አቅጣጫ አዙሬ ለመሄድ ብሞክር፤ እግሮቼ ከረጠበው መንገድ የመረጉ ይመስል ለገሙብኝ።

ከራበዉ ልጇ ፤ ሰው የገዛለትን በቆሎ ለምን ነጠቀችው ? ብዬ ፈርጄባት አደለም ማዘኔ።

ይህንን ብያኔ ለመስጠት እኔ ማነኝ......?

ኑሮዋን የማልኖር - እኔ፤ ተራራዋን የማልወጣ -እኔ፤ ቁልቁለቷን የማልወርድ -እኔ ፤ በምን ስልጣኔ ልፍረድባት እችላለወ....? የስድስት ብር በቆሎ ከሚበላ ሶስት ትልልቅ ባሀ ሁለት ብር ዳቦዎች ልትገዛለት አስባ ይሆናል...... ቤት የሚጠብቃት ሌላ ትንሽ አፍ ከዚህ ስድስት ብር መክፈል እንዳለበት ስለምታውቅ ይሆናል ....አስራ አምስት ወይ ሃያ ብር እየከፈለች የምትኖርበት የቀበሌ ቤትን ፤ ግማሽ የቤት ኪራይ ልትከፍልበት ወስና ይሆናል....

ማዘኔ- ይህንን እንድታደርግ ያደረጋትን ፤የእናትነት እንስፍስፍ አንጀቷን ያደነደነውን፤ የኑሮዋን ትግል አስቤ ነው። ማዘኔ - የልጆን መቁለጭለጭ እያየች ፤ የልጆን ረሀብ እየተመሀከተች ፤ እንዲህ ያለውን ውሳኔ እንድወትስን ያደረጋትን እጅ በጆሮ ሕይወቷን አስቤ ነው.....

ኀይል አሰባስቤ እርምጃዬን ስቀጥል ፤ በቀኝ እጄ የያዝኩት ለብ ያለ በቆሎ እጄ ላይ እየቀዘቀዘ ፤ በዐይኖቼ ውስጥ ያቀረረው ትኩስ እንባ እየወረደ ነበር።😣

🔘 አለቀ 🔘

ማንኛውንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን።
👍2
አትሮኖስ pinned «#እጅ_በጆሮ : #በሕይወት_እምሻው : : ማምሻውን ነው ዝናብ ያረሰረሰውን የሰፈራችንን ኮብልስቶን መንገድ በጥንቃቄ እየረገጥኩ ወደ ቤት አዘግማለሁ። በረገጥኩት ቁጥር በድንጋዬቹ መሀከል የተኛው ውሃ ፊጭ ፊጭ ይላል።ዘንቦ ማባራቱ ስለሆነ ይበርዳል ፊጭ ፊጭ እያደረኩ መራመዴን ስቀጥል፤ ከዚህ በፊት አይቼ በማላወቀው ብዛት በመንገዴ ላይ ከሰል አቃጣጥለው፤በቆሎ ጠብሰው፤በተርታ ተሰድረው ገብያ የሚጠብቁ ሶስት…»
#አበባ_ባለበት
:
#በሕይወት_እምሻው
:
ታማኝ ፍቅረኛ ነው።

ልክ እንደዝያ 'ፍቅራዲስ ነቃጥበብ' እንደዘፈነችለት ልጅ፤ወዳጀ ብዙ ነው እንጂ ለእኔ ታማኝ ነው።ጨዋታ አዋቂና ፈገግታውን በአገኘው ቦታ የሚበትን፤ያየውን ሁሉ አቅርቦ የሚያቅፍ ነው እንጂ፤ ታማኝ ነው።

ልክ እንደ ፍቅራዲስ ልጅ፤ የኔውንም በዚህ ባህሪውፐ ጥላ እንዳለበት ዛፍ ከበውት ይውላሉ።

እንደ መስከረም አደይ ነቅለውት፤ ሊያጌጡበት ይሽቀዳደማሉ። ጥርሱን ሲያሳያቸው፤ ልቡን ያገኙ እየመሰላቸው በደስታ ትርክክ ይላሉ።

ግን የኔ ነው። ታማኝ ነው።

ያም ሆኖ ሰውነኝና ፤ ሴት ነኝና ፤ ቅናት ባጠገቤ ሽው ማለቱ ፤ጎኔን ጎንተል ማድረጉ ፤ ሲልም ሚዛንና አቅሌን እስክስት መገፍተሩ አይቀርም።

<<ወዳጀ ብዙ አጀበ ብዙ
ውበትን ከምንጩ የቀዳው ከወንዙ
አሳሳቁ ቁጥብ- ምጥን ነው ፈገግታው
እሱን ብቻ ስሙኝ ያሰኛል ጨዋታው
እንደ ጥቢ ተክል የመስከረም አደይ
እንደ ሮዝ አበባ የፈካ በፀደይ
አበባ ባለበት ንብ አይጠፋበትም
ተፈጥሮው ልዩ ነው ይስባል ከየትም>>

በየካፌው ስንገባ ትላልቅ ጡቶቻቸውን አስቀድመው መተው ለሰላምታ የሚለጠፉበት ቆነጃጅት ፤ትእግስቴን ይፈታተኑታል።አብረውኝ የተማሩ ናቸው ብሎ የሚያስተዋዉቀኝ ፤ በልብሳቸው ወግ አጥባቂ መስለው ፤ እሱን ሲያዩ እንደሆነ ነገር የሚሰራቸው ቁሌታም ሴቶች ያንገረግቡኛል።

ትላንት ባንክ ስሄድ ተዋውቋቸው ፤ በነጋታው ሲያገኙት ጠፍቶ ያገኙትን የልጅነት ፍቅረኛቸውን እንዳገኙ የሚያንሰፈስፋቸው ሴቶች እብድ ያደርጉኛል ።

ቢሆንም ታማኝነቱን ስለማውቅና የፍቅር አዲስን ''አበባ ባለበት ንብ አይጠፋበትም''ምክር ስለምሰማ ፤አበባዬን እንዳይደርቅ ዉሃ ከማጠጣት ፤ እንዲደሰት ከመንከባከብ በሌላ እንዳይወሰድ ከመንጠንቀቅ በቀር ፤ምንም አድርጌ አላውቅም።ማለቴ...አላውቅም ነበር ...

ለምን <<ነበር>> አልኩት።

ሜላት፤ እዚያ በየሳምንቱ የእነ ግሩም መዝሙርን ጃዝ ሊያይ የሚሄድበት ቤት፤ ብቻዋን ቁጭ ብላ ቮድካዋን እየለበለበች በጃዝ ስትወዛወዝ አግኝቶ የተዋወቃት ልጅ ናት።

ይሄን እንዴት አወኩ? ነግሮኝ ታማኝ አይደል? ይነግረኛል እኮ...ፈስ ስለሌለበት ዝላይ አይፈራምና ይነግረኛል። ዛሬ ከነ እገሌ ጋር ተዋወኩ...ዛሬ ከነእገሌ ጋር ዋልኩ...ብሎ ይነግረኛል።መጀመርያ ላይ የጃዝ ፍቅሩን ስለማውቅ ነገሩ ብዙ አልከነከነኝም ነበር። ነገሩ ያሲክከኝ የጀመረዉ፤ በተከታታይ ሦስት ሐሙስ እዛው ቤት -በዚያው አኳኋን ብቻዋን አግኝታው አብረው ሲጠጡና በጃዝ ሲመሰጡ እንደነበር፤ በለመደው ሁሉንም ተናግሮ የመሸበት ማደር ፖሊሲው ሲነግረኝ ነው ።እውነቱን ተናግሮ ፤ እሷ ጋር አምሽቶ ፤ እኔ ጋር ሲያድር ከነከነኝ።

የሚላት ጉዳይ ተለይቶ የረበሸኝ በሦስት ምክናያቶች ነው።

አንደኛ- ጃዝ መወደዷ...ስንትሽ ሁሌም ብዙ ጃዝ የሚወዱ ሴቶች አላውቅም፤ ጃዝ የሚወዱ ሴቶች ማቹር ናቸው....አለ አይደል....ምጥቅ......ያሉ...ምናምን እያለ ያወራኛል።

( እኔ ጃዝ አሌወድም.....አብሬው ልደንስ ፤ ልዘፍንበት....ስልቱን ልከተለው የማልችለውን ሙዚቃ እንዴት ብዬ ልውደድ? ወጣ ሲሉት የሚወርድ....በረደ ሲሉት የሚሞቅ....ጭራና ቀንድ የሌለዉ ሙዚቃ ምኑ ይወደዳል? የጨረባ ተዝካር ነገር....አንዳንዱማ ያስቀኛል....በተለይ ስንትሽና ጓደኞቹን መንግስተ ሰማያት ያለ ትኬት የገቡ ያክል ፤ በመንፈስ የሚንሳፈፉበት...ምስጥ የሚሉበት ሙዚቃ፤ ለእኔ የአሮጌ ቮልስቫገን ሞተር ሲነሳ ይመስለኛል....የቆሼ መኪና ፤ ቆሻሻ ከብዶት ሲሄድ የሚያሰማው የማቃሰት ድምፅ ይመስለኛል... እንደዝያ አይነት ጫጫታና ትርምስ ከፍዬ ከምሰማ ማዕድ ቤት ያሉትን ድስቶቼን በነፃ አላጋጭም? ጭልፋና መጥበሻ አላማታም? ልዩነቱ ምንድን ነው?....ጲሪሪሪሪ....ጪሪሪሪሪ..ፂፂ
ብሎ ሙዚቃ አለ...? አንዳንዱማ ቆርቆሮ ሲፋቅ ሁሉ ይመስላል....

የሜላት ጃዝ መውደድ ግን ፤ ለስንትሽ እሷን ከሴት ሁሉ ለይቶ የሚያሳየው ብርሀን ነገር መሰለኝና ሰጋሁ...

ሁለተኛ - ሁሌም ብቻዋን መሆኗ ....

''ሴት ልጅ ብቻዋን ሬስቶራንት ስትበላ ፣ መጠጥ ስትጠጣ ሳያት ፤ አንድ ነገር ይታየኛል ....ኮንፊደንስ ! ስለዚህ ደስ ትለኛለች ይላል ስንትሽ...(እኔ ደግሞ ሴት ልጅ ብቻዋን ሬስቶራንት ከበላች። ወይ መጠጥ ቤት ገብታ ፣ ሌላ ሰው እየጠበቀች ሳይሆን ብቻዋን ከጠጣች .... ሁለት ነገር ይታየኛል ...ወይ ሴት ጓደኞች የሌሏት ምቀኛ፤ ወይ የሰው ባል የምትቀማ ሴሰኛ ነገር ፤ ወይ ደግሞ ወንድ ለማጥመድ ታጥባና ተቀሽራ የወጣች ሴት አዳሪ ....ይሄው ነው ...) የሜላት ሳታሰልስ ብቻዋን ጃዝ ቤት ሄዳ መጠጣት ግን ፣ ለስንትሽ እሷን ከሴት ሁሉ መርጦ በሚያምር አንፀባራቂ ትሪ የሚያቀርብለት መሰለኝና ፈራሁ።

ሦስተኛ - ስንትሽ ወዳጅ ብዙና በሄደበት የሚሞቅለት ይሁን እንጂ ፤ ብዙ ሰው ይወቅ እንጂ
ብዙ የቅርብ ጓደኛ ግን የለውም። ፍቅሩ ጊዜያዊ ፣ በሰዐታት የሚቆጠር ፣ በደቂቃዎች ወደሌሎች የሚተላለፍ ነው። ከዚህ ዓይነቱ ትውውቅና መዋደድ ተርፈው ስልካቸው ተይዞ በየእለቱ የሚደውልላቸው ፣ ዓመት በዓል ሳይሆን ቴክስት የሚላክላቸው ሰዎች ፣ ከእጆቼ ጣቶች ቁጥር አይበልጡም። ሜላት ግን በሳምንት አንድ ግዜ ደጃዝና ቮድካ ድብልቅ ትውውቅ፣ እዚህ ዝርዝር ውስጥ ቸ...ስ ብላ ገባች። ይሄ ካልረበሸኝ ምን ይረብሸኝ ? የሚያስቅ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ፣ ቴሌቪዥን ላይ ትወደዋለች የሚለውን ጃዝ ሙዚቃ ባየ ቁጥር ፣ ሬድዮ ላይ የሙላቱ አስታጥቄ ወይ የሌላ ጃዝ ሙዚቃ በመጣ ቁጥር (መኪና እየነዳ ሳይቀር) ሰከንድ ሳያባክን ይደውልላታል። ቴክስት ይልክላታል።

<<ሄይ....ሰማሽው? ሄይ...ኤልቲቪ እያየሽ ነው ....?አሁኑኑ ቀይሪው ....የማይልስ ዴቪስን ታሪክ እያሳዩ ነው !.....አጅሪት...ስለ ሚቀጥለው ሳምንቱ የጆርጋ መስፍን ኮንሰርት ሰማሽ ....? አይ ኖው !እኔ ራሴ ማመን አልቻልኩም ....በጭራሽ ....ዊ አር ሶ ጎይንግ ልብስ ሁሉ ሳልገዛ አልቀርም ከጆርጋ ጋር ለመተዋወቅ። ቻው በቃ ...ሲያልቅ እደውልልሻለው....>>

ጦፍኩ።

ይህቺ ልጅ በጃዝና በቮድካ አባብላ ፣ በሙላቱ አስታጥቄ .....በጆርጋ አለሳልሳ ፣ ስንትሽን ልትቀማኝ የተላከች የሌሊት ወፍ መሰለችኝ ። የምታዳልጥ የሴት ድጥ....የምታደረድር የሴት ገድል....ተንሸራቶ ቢገባስ ? ተንቀራቶ አልጋዋ ውስጥ ቢወድቅስ ?

ሜላት ከሌሎቹ አጃቢ ሴቶች ትለይበት እንደሆን ለማወቅ ብዙ ብዘይድም ምንም ፍንጭ አጣሁ። ከእሷ ጋር የከረረ የስልክ ግኑኝነት ይኑረው እንጂ በእኔ ላይ ያለው ባሕርይው አልተለወጠም። ያገኛት ቀን እንዳገኛት ይነግረኛል። እያወራት ሳገኘው ሳያቋርጥ፣ሳይርበተበት ይቀጥላል። ይባስ ብሎ ቴክስት ልካለት ካሳቀችው አንብቦልኝ እንድስቅለት ይጠብቀኛል።

አንድ ቀን እንደዋዛ ጠጋ አልኩትና፣ ''እስቲ ባሌን እንደህ ያማለለችው ልጅ ስልክ ስጠኝ....እኔም ልወቃት ፤ እኔንም ካማለለችኝ'' አልኩት።

አላንገራገረም።

''አሪፍ...ቁጥሯን ቴክስት አደርግልሻለው'' ብሎ፣ አንገቴ ላይ ሳመኝና ሄደ። ደቂቃ ሳያልፍ የሌሊት ወፎ ቁጥር መጣልኝ።መዘገብኩት። ትንሽ ቆይቼ ሙሉ ስሟን አስገብቼ ፌስቡክን አሰስኩ።

ከመቶ በለይ ፎቶ አላት። ምነው ልታይ ልታይ አለች?

ድብን ያለች ቀይ ናት። በየፎቶው አሞጥሙጣ የምትነሳው ከቀይ ሊፒስቲክ ጋር የተፈጠረ የሚመስል፣ ''አንጀሊና ጁሊ'' ከንፈር አላት ... ሙሉ ፎቶዎቿ ላይ ደግሞ ያበጠ ቂጧንና ሙትት ያለ ወገቧን፣ አንዴ ዛፍ እየተደገፈች ፣ሲላት
👍1
ወንበር እያቀፈች፣ በኩራት ትታያለች። ጡት መያዣ የማያውቁ ታላላቅ ጡቶቿን በብርድም በሙቀትም ክርር ካሉ ጫፎቻቸው ጋር ለኤግዚብሽን አቅርባለች።

አልቆልኛል።

ይህ በሆነ በሳምንቱ ያ በየቀኑ ሲንሰፈሰፍለት (ሲንሰፈሰፉለት) የነበረው የጃዝ ኮንሰርት ደረሰ።ስንትሽ ሥራ ውሎ ልብስ ለመቀየር ሲመጣ የክትና የድግስ - ቀይ ጠበቃ ቀሚስ ግጥም አድርጌ ለብሼ ጠበኩት።

''እንዴ ...ምንድን ነው ይሄ ዝነጣ ...?'' አለኝ። እጆቼን ይዞ ባለማመን እያየኝ።

''ኮንሰርት አብሬህ ልሄድ ነዋ !''አልኩኝ ፍልቅልቅ እያልኩ። ''እ....የምን ኮንሰርት?'' ፊቱ ጭልም ፣ቅጭም እያለ ጠየቀኝ።

''እንዴ ...ታሾፋለህ እንዴ....የጃዙን ኮንሰርት ነዋ!''

''ማሬ....አታሹፊ.....'' ብሎ ፣እጆቼን ለቀቀና ወደ መኝታ ቤት ሄደ።

ተከተልኩት።

''ብመጣ ችግር አለው?'' ቱግ እያልኩ ጠየቅኩ።

''እንዴ...ምን ችግር አለው....ኤክሴፕት ጃዝ አትወጅም ....ሪመንበር? አለኝ፣ በሹፈት ጉንጮቼን በእጆቹ እየቆነጠጠ፣እንደ ህፃን ልጅ እያየኝ....

''አዎ ግን አንተ የምትወደውን መውደድ እፈልጋለው....

እመጣለሁ.....'' አልኩት። ሣቅም ኮስተርም ብዬ።

''እኔ የምወደውን ሁሉ መውደድ የለብሽም ፣እኔን ከወደድሽኝ እኮ ይበቃል። የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መዉደድ የለበትም እኮ..'' አለኝ

የዝነጣ ሱፉን እየለበሰ፣ዐይን ዐይኔን እያየኝ።

''መምጣት እፈልጋለው በቃ! ስንትሽ....ሌላ ምክንያት ካለህ ንገረኝ....'' አልኩ ፣ሆድ እየባሰኝ። የሜላት ጡትና ቂጥን አስቀምጦ፣ በቮድካ የራሱ ቀይ ከንፈሮቿን እያየ ሲቋምጥ ታይቶኝ....

''ሌላ ምን ምክንያት ይኖረኛል?''

''እንጃ....ከሌለህ ደስ ነው ሊልህ የሚገባው...እመጣለው.....አልኩ። ሜላትን ከአንጎሌ ገፍትሬ ለማውጣት በመፈለግ ራሴን እየነቀነኩ....

ማምረሬ ሲገባው ልብሱን ለብሶ ጨረሰነና ፣

''ግን ቲኬት የለኝም .....አለ።

'' እዛው እንገዛለን ....''ቶሎ ብዬ መለስኩ።

''አሎቆ ቢሆንስ....ሁሉም ሰው እኮ እንዳንቺ ጃዝ አይጠላም .....አለ እየሳቀ።

''እንሞክርና እመለሳለው....''

''ባናገኝስ.....''

''ምነው በጣም አከላከልከኝሳ ....ልቅርልህ በቃ..''
አልኩ።ጦፍ ቦዬ አልጋው ላይ ዘጭ እያልኩ።

''ማሬ....ኧረ ነይ በናትሽ ....እኔኮ እንዳንተገለቺ ነው...በዛ ላይ የሦስት ሰአት ኮንሰርት ነው...በአንቺ ጃዝ መጥላት....''አጠገቤ ተቀመጠ።

''የሦስት ሰዐት?'' አልኩ ቀና ብዬ እያየሁት።

''አዎ ....ምነው?''

''ምንም ...ረጅም ነው....''

''ሃሃ...አዎ...''

''ዘፋኙ ማነው ...? እነማን ይዘፍናሉ?'' አልኩት። የሚያምር በሉጫና ከርዳዳ መሃል ያለውን ፀጉሩን እየነካካሁ።

''ማሬ...ዘፋኝ የለም እኮ....ባንድ ብቻ ነው...''

''ማለት...መሳርያ ብቻ ? ጲሪሪሪ..ፂፂፂ..ብቻ ...?ኦህ ማይ ጋድ !''
አልኩ ራሴን እየያስኩ።

ከት ብሎ ሣቀ።

''ሪል ጃዝ እኮ እንደዛ ነው ....ለዚህ ነው ቅሪ ያልኩሽ ግን ከመጣሽ ነይ...ትኬቱ ነው ያሳሰበኝ''

ወሬአችን ሳያልቅ ሳሎን የተወው ስልኩ ጮኸ።

ብዙ ሳይቆይ ተመለሰ።

''ማነው አልኩት።

''ሜላት ናት...እናቴን አሟት ሆስፒታል መንገድ ላይ ነን አለችኝ...'' አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ።

''ውይ .....ምስኪን....'' አልከለኝ። ፊቴን ከሆዴ የደስታ ስሜት ጋር ማመሳሰል አቅቶኝ እየታገልኩ።

''ያሳዝናል....በጣም ጓጉታ ነበር....ከባድ ነገር እንዳልሆነ ተስፋ እናድርግ እንግዲህ...በያ ተነሽ...
በጣም ረፈደ...በስአት ይጀምራል ተብሏል....ደህና ቦታ እንዳናጣ....'' አለኝ። ቶሎ ቶሎ እያወራ።

አሁን የመሄድ ፍላጎቴ በሜላት መቅረት ተዘጋ።

ጃዝ...? ኤጭ ! ሦስት ሰዐት ሙሉ የሚያንቋርር የማይጨበጥ ሙዚቃ ያለዘፋኝ....በዚያ ላይ በዝናብ ከቤቴ ወጥቼ...በዛ ላይ ጃዝ የሚጫወቱት ሰዎች የሚወጥሩት ነገር ትዝ አለኝ።

አይደንሱ...አይስቁ...መድሀኒት እንደሚቀምም ሰው...ለካንሰር ፈውስ እንዳገኘ ሰው የሚጎርሩት ነገር ያበሳጫል ...መንኮራኩር እንዳመጠቀ ሰው የሚንጠባረሩት ነገር ያናድደኛል....

አልሄድም።

''ስንትሽ በቃ አንተ ሂድ...ቲኬትም ሊቸግር ይችላል...አንተ እንደዚህ ጓግተህ ቲኬት ፍለጋ በዝናብ ላንከራትትህ አልፈልግም...ሂድ በቃ...'' አልኩ፣ አልጋዬ ላይ በፍፁም ፍስሀ ተደላድዬ እየተኛሁ።

ምንም አላለም። ሥቆ ሳመኝና እየተጣደፈ ወጣ።

በአሸናፊነት ስሜት ሣቅ ብዬ ፣ ምቾቴን ለመጨመር ያጣበቀኝን ቀሚስ አውልቄ ፒጃማዬ ውስጥ ስገባ ግን ፤ ከየት መጣ ያላልኩት ፣ ከዚህ በፊት የማላውቀዉ ጥርጣሬ፣ እንደተዉሳክ ሆዴ ውስጥ እየሮጠ የገባ ይመስል ዕረፍት ነሳኝ።

ሌላ ጊዜ ጮኸ ብሎ የሚያወራው ስንትሽ፣ሳሎን ሆኖ ከሜላት ጋር ያወራውን አልሰማሁም። ሀወትሮው ለሰው ሟች የሆነው ስንትሽ፣ በሜላት እናት መታመም የተጨነቀ አይመስልም። ነይ ሲለኝ ቆይቶ ልቅር ስለው ውትወታዉን በፍጥነት ማቆሙን አላስተዋልኩም።ህምም...ትንሽ ቆይቼ ስልኬን ሳየው የሜላት ቁጥር እንዳለኝ ትዝ አለኝ። አላመነታሁም።

ደወልኩ።

''ሄሎ...አለች ጮክ ብላ። (ከባድ ጫጫታ ውስጥ ናት....የትኛው ሆስፒታል ነው?)

''ሄሎ....ሜላት?''

''አዎ....በደነብ አይሰማም....ማል ልበል?''(ጫጫታ መሀል ጲጲጲሪሪሪሪ ሙዚቃ የሚያጫውት ሆስፒታል የቱ ነው ? )

''እ...ሜላት ነሽ...?''

''አዎ....ይቅርታ ኮንሰርት ላይ ነኝ...ማል ልበል ?'' (ለድንገተኛ ህሙማን ኮንሰርት የሚደግሰው ሆስፒታል ስሙ ማነው ?)

አበባ ባለበት ንብ አይጠፋበትም።

ሜላት አበባዬን ቀስማብኛለች።

🔘 አለቀ 🔘

ማንኛውንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን።
👍31
አትሮኖስ pinned «#አበባ_ባለበት : #በሕይወት_እምሻው : ታማኝ ፍቅረኛ ነው። ልክ እንደዝያ 'ፍቅራዲስ ነቃጥበብ' እንደዘፈነችለት ልጅ፤ወዳጀ ብዙ ነው እንጂ ለእኔ ታማኝ ነው።ጨዋታ አዋቂና ፈገግታውን በአገኘው ቦታ የሚበትን፤ያየውን ሁሉ አቅርቦ የሚያቅፍ ነው እንጂ፤ ታማኝ ነው። ልክ እንደ ፍቅራዲስ ልጅ፤ የኔውንም በዚህ ባህሪውፐ ጥላ እንዳለበት ዛፍ ከበውት ይውላሉ። እንደ መስከረም አደይ ነቅለውት፤ ሊያጌጡበት…»
#ንስሐ
:
#በዓለማየሁ_ገላጋይ
:
አዲስ የፈለቀ ፀበል ነው ፣ከባለቤቴ ጋር ሄደናል። ወደ ፀበል ከመግባቷ በፊት ንስሀ የሚቀበሏት አባት አጠገቧ ተቀምጠው፣ አፋቸውን በማጎናፀፍያቸው ሸፍነው ጭንቅላታቸውን በአወንታ ይወዘዉዙታል ።

<<ምን ይሆን የምትናዘዝ ?>> ጓጓሁ።

አካባቢው ጭጋጋማ ነው። የምንቀመጥበት ጠፍጣፋ ድንጋይ እንኳ በእርጥበቱ የወረዛ ነው። አንዳንድ ፀበልተኞች ገና አፀዱን ሲያልፉ ይለፈልፋሉ። እኛ ከዚህ ተርፈናል።

ቄሱ አሁንም ሚስቴን ያናዝዟታል። ምን ይሆን የምትናዘዘው ? ምን ተሳሳስታ?....

ቄሱ ብዙ ሰዓት አናዘዋት ወደ እኔ መጡ ። የክርስትና ስሜን ከጠየቁኝ በኋላ

<<ንስሃ ይዞ ፀበል ደግ አይደለምና በሆድህ ያለውን፣ሥጋ ያሳሳትህን፣ ጋኔን የገፋፋህን ሳትደብቅ ተናገር። ንስሃ ግባ ማለቴ ነው።>>

አሁንም ልቤ ባለቤቴጋ ነው፤ ምን ብላ ንስሃ ገብታ ይሆን ? ባውቀው።

<<ያው ሴትጋ እሄድ ነበር>>

እራሳቸውን ነቅንቀው አፋቸውን ጋርደው ጠየቁ

<<ሌላ ሴት ገር?>>

<<አዎ>>

<<ስንት ናቸው?>>

<<ብዙ ናቸው አባቴ>>

<<ሌላስ? ከሃይማኖትህ ውጪ ያሉ ሴቶች ጋ ደርሰሃል?>>

<<አዎ፣ ይፍቱኝ አባቴ >>

<<እግዚሐብሄር ይፍታህ፣ ሌላስ?>>

<<ሌላ'ኳ ሀጥያት የምለው የለኝም>>

ቀና ብለው አዩኝ። ከዚህ ሌላ ምን ታደርግ መሰለኝ።

<<ሰው መድሀኒት አላቀመስክም?>>

<<በፍፁም>>

<<በሐሰት አልመሰከርክም?>>

<<እንደውም>> ከእኔ ወደ ሌላ ተጠማቂ ሊሸጋገሩ ሲሉ ጥቂት ብር አዎጥቼ ሰጠሁ። ደንብ ነው። ጨምሬ ጨማምሬ ብሰጣቸውና የባለቤቴን ንስሀ ቢነግሩኝ ብዬ ጓጓሁ። እንደገና እጄን ቱታ ኪሴ ከትቼ ዳግም ሰጠኋቸው ። ብሩን ከቁብ አለመቁጠራቸው ለመጠየቅ አለበረታታኝም። የባለቤቴ ንስሃ ግን ሆዴ ገብቶ ወደ ቁርጠት መቀየር ጀመረ።

ሌላ ወንድ ደርሶባት ይሆን ?

እንደወረፋ የሚቆጠረው ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ እንደቶጎለትኩ ሳሰላስል ከወደጠበል ቤት አቅጣጫ አንድ አፈድፋጅ ተመለከትኩ። ብጣቂ ነጠላውን መስቀለኛ አጣፍቶ ከወድያ ወዲህ ይላል።

ጠራሁት፣ መጣ። የተቀመጥኩበት አጎንብሶ ጆሮውን ሲሰጠኝ እኔ እጄን አስቀደምኩ ። አስጨበጥኩና ችግሬን ነገርኩት።

<<የባለቤቴን ንስሃ እንዲነግሩኝ ፈልጌ ነው >>

<<እሳቸው ናቸው?>> አለ በብሩ መብዛት ተርበትብቶ

<<አዎ>>

<<ግድየለም፣ ማናዘዛቸውን ይጨርሱና እጠይቃቸዋለው>> ብሎኝ ሽብርክ ሽብርክ እያለ ሄደ።

ቄሱ ማናዘዛቸውን ሳይጨርሱ እኔና ባለቤቴ የጠበሉ ወረፋ ደረሰን። ተጠቅመን ስንወጣ ያንን አፈድፋጅ ጠራሁት ። ከባለቤቴ ዘወር አድርጌ ጠየከለት።

<<ታድያስ ? አባ ምን አሉ?>>

<<አባማ ባልና ሚስት ካንድ ወንዝ ይቀዳል አሉ>> 😳

ማንኛውንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን።
👍3😁2
#ዘላፊ_ሰፈር
:
#በዓለማየሁ_ገላጋይ
:
:
ጋሽ ጉሩሙ በስተርጅና አጎታቸው መኪና አወረሷቸው። ለቅሶ ላይ :-

<<አይ አብዬ>> ሲሉ ተሰሙ

<<አይ አብዬ፤ ጉልበቴ ከላመ፣ አይኔ ከደከመ ጉልበቷ የላመ፣ፍሬኗ የደከመ መኪና ታወርሰኝ? ማውረስህ ካልቀረ ቀደም ብለህ ሞተህልኝ ቢሆን ምናለ?>>

የአጎታቸውን ሰልስት አውጥተው ሰልስቷ የወጣ ሲትሮይን መኪናቸውን ይዘው ወደ ሠፈራቸው። የዘላፊ ሠፈር ሰው ለቅሶውን እረስቶ እልልልል....
እያለ መኪናዋን ተቀበለ። <<ዘላፊ ሰፈር አለፈላት>> ተባለ ።

<<ጋሽ ጉሩሙ>>

<<አቤት>>

<<ነገ በሌሊት ጠበል ያደርሱኛል፤ አደራዎን አደራዎ፤ እንቅልፍ እንደይጥልዎ>>

ለወትሮው በወረት፤ ኋላም የዘላፊ ሠፈረን አፍ በመፍራት <<እሺ>> አሉ ሲብስ ምክንያት ለመደርደር ከጀሉ፣

<<ነዳጅ...>> ሲሉ

<<እንገፋታለን>> የዘላፊ ሠፈር መልስ

<<ፍሬን...>> ሲሉ

<<እንጎትታታለን>>

ጋሽ ጉሩሙ እንዲህ ሲሉ ተሰሙ

<<ጉድ ነሽ ዘላፊ ሰፈር ፣ የሰው ውርስ ወደራስሽ ማዞር>>

አንድ ቀን የታየች እናት ሦስት ኪሎ አሻሮ ጀርባቸው ላይ አድርገው ጋሽ ጉሩሙን ተጣሩ፤

<<ቶሎ፣ ቶሎ ....ነገም የዓመት ፣ተነገወድያም ሠንበት ፣ቶሎ ወደ ወፍጮ ቤት>> ምርኩዛቸውን አስቀድመው ወደ መኪናዋ አመሩ

ጋሽ ጉሩሙ ግልፍ አላቸው ።

<<እኮ ወዴት ? አህያ መሰለቸዎት? ወፍጮ ቤት?አይ የታየች እናት!! መኪና መሆኗን እረሷት?>>

ከዛች ቀን አንስቶ ዘላፊ ሠፈር ተረብ፣ ስድብ ልግጫ፣ ግልምጫ በሚኪናዋና በጋሽ ጉሩሙ ላይ ማውረድ ጀመረ።

የመጀመሪያ ቀን ምክር መሰል የነገር ክርን አሳረፋባቸው።

<<ጋሽ ጉሩሙ >> አሉ የታየች እናት

<<የትዬ ድንቂቱ ልጅ ምጥ የያዛት፣ ጊዜ መኪናዎ ላይ ያሳፈሮት ጊዜ ነጠላዋን አይጥ በላባት፤ ኋላ ይሄ አይጥ ፍሬኑን በልቶበት ገደል እንዳይከቶት።>>

በቀጣዩ ቀን፣ ክስ መሰል የነገር መጥርያ ደረሳቸው የጋሽ ጋረደው ልጅ ዝልቦ ክሱን አቀረበ

<<ጋሽ ጉሩሙ ልብሴን ቀደዱብኝ፣ ያሳልፉኝ።>> አለ።

<< እንዴት ቀደዱብህ?>> ሲባል....

<<መንገድ ዳር ቆሜ ጋሽ ጉሩሙ ፍሬን እንቢ ሲላቸው እጃቸውን በመስኮት አውጥተው ልብሴን ይዘው ቆሙ>>

<< አይ ጋሽ ጉሩሙ!!>>

ዘላፊ ሠፈር ነገር ጠራቂ፣ ሣቂና አሟሟቂ ሆነው ጋሽ ጉሩሙን ማድበን ቀጠሉ ። አንድ ጠዋት ሲነሱ መኪናዋ ላይ <<መሽናት ክልክል ነው>> የሚል ፁሁፍ ተለጥፎ አገኙ። በቀጣዩ ቀን መሽናት መከልከላቸው እልህ የከተታቸው ሳይሆኑ አልቀረም ገርበብ ብሎ የማይገጠም የመኪናዋን በር ገመዱን ፈትተው የኋላ መቀመጫ ላይ....

....መኪናዋን ለማፅዳት አስር ባሊ ውሀ ፈጀ።

ቢቸግራቸው መኪናዋ ላይ ባህላዊ መቀስቀሻ (ሴንትራል ሎክ) ገጠሙላት ። ምን ገጠሙላት ደረደሩላት እንጂ። ብረት ምጣድ፣ ሳፋ፣ ትሪ፣ መዘፍዘፍያ፣ ገረወይና....አንዱን ባንዱ ላይ አነባብረው ትንሽ ሲነካ እንዲናድና እንዲቀሰቅሳቸው መኪናዋ ላይ ጠመዱ። ያን ለሊት አልተኙም። ሲናድ፣ ሲነሱና፣ ምንም ሲያጡ፣ መልሰው ሲደረድሩ፣ ሲናድ...መጨረሻ እየተንኳኳ እየሰሙ በመሰልቸት ትተውት ተኙ። ጠዋት ባህላዊ መቀስቀሻው በሙሉ ተወስዶ መኪናዋ የበር ማሰሪያዋ ተከፍቶ....

....አስር ባሊ ውሀ።

ቢቸግራቸው መለማመጥ ከጀላቸው የሚኪናዋን ሞተር እያሞቁ ዉሀውን ሲቀይሩ ፣ በአጠገባቸው እንቅርት የምታክል ብቅል ይሁን አሻሮ ጣል አድርገው በብትር መሬቷን ጠቆም ጠቆም እያደረጉ የታየች እናት ሲያልፉ

<<የታየች እናት ፣ ይምጡ ወፍጮ ቤት ላድርሶት >> አሉ።

<<እቸኩላለሁ>> አሉ አሽሟጣች ፊት አሳይተው። ይሄኔ ጋሽ ጉሩሙ ግልፍ አላቸው።

<<እንደ ባጃጅ በሦስት እግር እየሄዱ የእኔን መኪና ይንቃሉ>>

<<ኤሊም አራት እግር አላት>>

<<😡>>
👍3
አትሮኖስ pinned «#ዘላፊ_ሰፈር : #በዓለማየሁ_ገላጋይ : : ጋሽ ጉሩሙ በስተርጅና አጎታቸው መኪና አወረሷቸው። ለቅሶ ላይ :- <<አይ አብዬ>> ሲሉ ተሰሙ <<አይ አብዬ፤ ጉልበቴ ከላመ፣ አይኔ ከደከመ ጉልበቷ የላመ፣ፍሬኗ የደከመ መኪና ታወርሰኝ? ማውረስህ ካልቀረ ቀደም ብለህ ሞተህልኝ ቢሆን ምናለ?>> የአጎታቸውን ሰልስት አውጥተው ሰልስቷ የወጣ ሲትሮይን መኪናቸውን ይዘው ወደ ሠፈራቸው። የዘላፊ ሠፈር ሰው ለቅሶውን…»
🌼 #አሜን_በእንቁጣጣሽ 🌼

#አሜን_በእንቁጣጣሽ
በአለም ከነበረን~የክብር ከፍታ
የተጠናወተን~ኃይለኛው በሽታ
አሽቀንጥሮን ከላይ~ያወረደን ቁልቁል
ዘርማንዘር ቆጠራ~ሰንኮፉ ይነቀል
።።።።።።።።።።።።።።
#አሜን_በእንቁጣጣሽ
ያገራችን ተስፋ~እንደ ፀሀይ በርቶ
ዝናዋ እንደቀድሞ~ዳር እስከዳር ናኝቶ
በአመተ ምህረት~ሁለት ሺህ ደርዘን
በሰውነት እንጂ~በዘር አንመዘን
።።።።።።።።።።።።።
#አሜን_በእንቁጣጣሽ
አዲሱ እንቁጣጣሽ~የአደይ ስጦታ
ኩርፊያን በፈገግታ~ሀዘንን በደስታ
ጥላቻን በፍቅር~ፀብን በይቅርታ
ያሳየን ቀይሮ~የመስከረም ፀሀይ
ባገራችን መሬት~ባገራችን ሰማይ
።።።።።።።።።።።።።
#አሜን_በእንቁጣጣሽ
በሰሜን በደቡብ~በምእራብ በምስራቅ
ወዲህ ወዲያ ማዶ~ቅርብም ሆነ እሩቅ
ውዱ ኢትዮጵያዊ~በአለም ላይ ያለህ
እንኳን ለእቁጣጣሽ~ሠላም አደረሰን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍1
🌼 #መስከረም 🌼

#ከወዲያ........
ቢጫ ዘለላዎች - ነፋሻማ መስኮች
የመስቀል ወፍ ልጆች...
ሠማያዊ ሰማይ የደመና ወራሽ
የፀሐይ ጨረሮች፤

#ከወዲህ...
የብርሐን ፍላፃ ፊታቸው ላይ በርቶ
ወርቅ ያንፀባረቁ - ቆነጃጅት ሴቶች
እንቁ እንቁ ውበት፥
የንጋት ፍካቶች
ጧ ... ፍንድት ያሉ...
ወር ያልወሰናቸው - ቀያይ አበባዎች
ድንግል... ልጅ እግሮች፤

#ከወዲያ...
ደርባባ ደርባባ... ዘንካታ እናቶች፥
ወርቀ ዘቦ ጥለት - የእርጋታ ንግሥቶች
ፍክት ድምቅ ያሉ የሐበሻ ቀሚሶች...
ከፅንሳቸው ፈልቀው
ዘለው ሚቦርቁ የኤቶጽ ህፃናቶች
ሀገር ተረካቢ... ባለብዙ ተስፋ
...ፍንድቅ ፈንድሻዎች
ሰርክ ሲመረቁ፥
ጃኖ በለበሱ ሸበቷም አባቶች፤

#ከወዲህ...
የቄጠማ ጉዝጓዝ....
ጭሱ ሚስለመለም የጀበና ቡና፥
በከርቤ የተዋዛ የሚያውድ ሽታ
ኢትዮጽያዊ ባህል የፍቅር ናሙና
ከላይ የሚያበራ ውብ ቀስተ ደመና፤

እዮሐ አበባዬ መስከረም ጠባዬ፥
ልምላሜ ፍቅር ሠላሜና ክብሬ
እንኳን ደረሰልሽ...
መልካም አዲስ አመት እምዬ ሀገሬ!

🔘 ጷጉሜ 6-2011

🌼 እንኳን ለአዲስ አመት በሠላም አደረሳችሁ🌼
👍1
#የማጀት_ስር_ወንጌል

ሙያተኛ ሀገሬ ከማጥገብ ጎደለ በረከት እራቀው የገበታሽ ለዛ፣
ተሻምቶ ለመጉረስ ከበላነው ይልቅ የደፋነው በዛ፡፡
ሙያሽ ባያስደፍር አጀብ ቢሰኙበት፣
ማዕዱ ቢሙላላ ዓይነቱ ቢያምርበት፣
አበዛዙ አይደለም አበላሉ ላይ ነው የገበታሽ ውበት፡፡
እየተማመንን! የፉክክር ቅሚያ በርሃብ እየናጥን፣
ከደፋነው ጠግቦ ውሻችን በለጠን፡፡
ከምርት አላነስን፣
ጎተራችን ሙሉ ጀግና አራሽ መች አጥተን፣
ማሰብ የጎደለው አያያዛችን ነው ገደል የከተተን፡፡
ይልቅ ግዴለሽም! ከምግባር ምጣድ ላይ ሳንበስል አንጋግተሸ ከማዕድ አትምሪን፣
ገበታሽ እንዲያምር ከእግዜር የሚያስታርቅ ፍቅር አስተምሪን፡፡
ገበታ ዕድሜ ነው ባለ ማሰብ መክነን፣
ሳንፀነስ ጃጀን፣
ሳንጣድ አረርን፣
ከዘመን ገበታ ከፊደል አቅድመን ዘር እየቆጠርን፡፡
ገበታ ሀቅ ነው በክፋት ሊጥ ጋግረው ያሻገቱት እውነት፣
በሆዳም እስክስታ ረግጠው ያፈኑት የምስኪናን ጩኸት፡፡
እስከ ልጠይቅሽ በጥም ደዌ ደቆ የረሃብ ጠኔ ደፍቶት እልፍ ትውልድ ያልፋል፣
ቢራ ለመጥመቂያ ሚበተን ገብስ ግን ከሀገር መች ይጠፋል፡፡
ከሆድ በማይሻገር የማጀት ቤት ዕውቀት አጥብበሽ አትለኪን፣
እስቲ መኖር ይግባን ከማስተዋል መቅደስ ሰው መሆን ስበኪን፡፡
ዘመን ካልገበረው ከችጋር ተራራ ከሲኦል ዳር ኑሮ፣
እንዴት ነው መሻገር ከመርፌ ቀዳዳ በጠበበ አይምሮ፡፡
ከምስኪን ዘመን ላይ የማይኖሩበትን ዕድሜ መበዳደር፣
ለአንዲት ማምሻ ደስታ በአያት እስትንፋስ ላይ ቁማር መደራደር፣
ያሳፍራል አይደል?
እያደጉ ማነስ እያነሱ መዝቀጥ፣
አጎንብሶ ያፀናን የድሃ እናት ጉልበት በጭካኔ መርገጥ፣
ያሳምማል አይደል?
መንገስ ከሚያባላስ መጥገብ ከሚያቃቅር ማግኘት ከሚያጎለን፣
ማጣት ውሎ ይግባ ባርነት ይሰንብት ድህነት ይግደለን፡፡
ከረፈደ ፀፀት ደረት እየደቁ ከእግዜር ቢዋቀሱ፣
ትርጉሙ ምንድነው ሲኖር ተቃቅሮ ሲሞት መላቀሱ፡፡
በእናታችን አድባር በፍቅሯ ይሁንብን፣
መድመቅ ካጋደለን ቆሽሸን ይመርብን፡፡
በመጠማት ሲቃ እስትንፋስ እስኪያንቃት ነፍሳችን ትርበትበት፣
ብቻህን ከመጥገብ አብሮ መራብህ ነው ሰው የመሆን ውበት፡፡
በድፍን ግልብ እሚያጋድል ህዝብ የመሆን መንጋ አይንዳን፣
በማሰብ ስር እንፈወስ በሰውነት ፀበል እንዳን፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን ከመንጋነት ሚያግድ እረኛ አያሻህም ከህሊናህ በላይ፣
ስታስብ መሪ ነህ በብስለት ከፍታ በማስተዋል ሰማይ፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን የጎጥ አረም ነቅለህ በአንድነት መስክ ላይ ፍቅር ትዘራለህ፣
በወረወሩብህ የጥላቻ ድንጋይ ትውልድ የሚያፋቅር ድልድይ ታበጃለህ፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን ዝምታህ ኃያል ነው ጀግና የሚያንበረክክ፣
ከፈሪ ቀረርቶ ከባዶ ሰው ጩኀት፣
ሀገር ላምስ ከሚል በመንደር አጀንዳ በአሽኮለሌ ተረት፡፡
አየህ! ሰው ስትሆን ነጻ ነህ እያሉህ መታሰር ያምርሃል፣
መቀመቅ መበስበስ፡፡
የኖርክለት እውነት ሀገር እስኪፈታ፣
በሀቁ እስኪመዘን ስለ በርባን ክብር የቆሸሸው ፍቅር የታሰረው ጌታ፣
ከድል ታሪክ ሰማይ ከሥልጣኔ ዳር ከጥበብ ከፍታ፣
እንሻገራለን ህዝብነትን ትተን ሰው የሆንን ለታ፡፡
በትረ ጥበበ ቢካን ዓለም ሊያንቀጠቅጥ ድል ሥልጣን ቢሰጠው፣
ጀግና መሪ አይደለም ብርቱ ተመሪ ነው ሀገር ሚለውጠው፡፡
አስተውል ወዳጄ ጠልተን ላንጣላ ችለን ላንጋደል ነደን ላንፋጀው፣
የኛው ትርምስ ነው በልቶ ለሚያባላ ጠላት ሚበጀው፡፡
ስጋና ደም እንጂ የአንድነታችን ውል የፍቅራችን ቀለም፣
ያሰመርነው ክልል የታጠርንበት ዘር ቋንቋችን አይደለም፡፡
ከመዋሃድ መቅደስ ትውልድ እናስተምር፣
ዘመን ይመርቀን ፍቅራችን ምን ጎድሎት ደማችን ያስታርቀን፡፡
በልጆቿ አጥንት በደም ኪዳን ምለን የገባንላት ቃል፣
ከጩኀት ያለፈ ዘመን የሚሻገር ተግባር ይጠይቃል፡፡
በአንድ ሃሳብ ተጋምደን በድል ድር እናብር ውድቀታችን ያንቃን፣
ሠርተን እናሳምን ሆነን ድል እንንሳ የአፍ ጀግንነት ይብቃን፡፡
ምስኪኒቷ እናቴ! በሞላ ጎዳና ባልጠበበ ድንበር በዘር ገመድ ታግዳ፣
ነጻ ነኝ ትላለች መንጋነት ያሰረው ባሪያ ትውልድ ወልዳ፡፡
የጀግንነት እብሪት ልባችንን ደፍኖት ማሰብ እየከዳን፣
እንዴት ነው ነጻነት እንዳበደ ፈረስ ስሜት እየነዳን፡፡
ገድሎ የመንገስ ጥማት ጩኀት ላገነነ አመጽ ላጀገነው፣
ለዚህ ምስኪን ትውልድ በጅምላ እየነዱት፣
በመንጋ እያሰበ ነጻነት እንዴት ነው?
ነጻነት ምርጫ ነው አምሮ ቢደላደል ጥፋት ያመነነው የመንጋዎች መንገድ፣
እንቅፋቱን ወዶ ለኖሩለት እውነት ለብቻ መራመድ፡፡
ነጻነት ማመን ነው ቀን ወዶ ቢያጀግን ቀን ጠልቶ ቢከዳም፣
ቢቆሽሹም ቢደምቁም እራስን መቀበል ራስን መምሰል ነው የነጻነት ገዳም፡፡
ነጻነት ማሰብ ነው በአንድነት መለምለም የኔነትን አረም ከህሊና ማጥፋት፣
ዘር ሆኖ ከማነስ ሀገር ሆኖ ማበብ ዓለም ሆኖ መስፋት፡፡
ንገሯት ለሀገሬ በጀግኖቿ ትግል ድንበር ባታስደፍር ከእጀ ገዥ ብትወጣ፣
ነጻ ነኝ እንዳትል በገዛ ልጆቿ በእጅ አዙር ተሸጣ ፡፡
ስሩን ካልሸመነው በመዋሃድ ጥለት በማስተዋል ሸማ፣
ታሪክ አናደምቅም በጭብጨባ ድግስ በሆይ ሆይታ ዜማ፡፡
ምን ብናቀነቅን በየሰልፉ ሜዳ ወኔ ብንደግስም፣
በፈረሰ አይምሮ በደቀቀ አንድነት ሀገር አናድስም፡፡
በጭፍን ከመሮጥ አስቦ ማዝገም ነው የመራመድ ውሉ፣
ሁሉም እንቅፋቶች እስኪጥሉን ድረስ ምርኩዝ ይመስላሉ፡፡
በድፍን ግልብ እሚያጋድል ህዝብ የመሆን መንጋ አይንዳን፣
በማሰብ ስር እንፈወስ በሰውነት ፀበል እንዳን፡፡
ከእግዜር ልንወዳጅ ለምህረቱ ጥላ እምባ ብንደግስም፣
ልብን ሳይመልሱ ለንስሃ መሮጥ ከጽድቅ አያደርስም፡፡
ውብ ነገን እናውርስ ትላንትን አክመን በይቅርታ ፀበል፣
ትውልድ ይጨርሳል ያረገዝነው እምባ የቋጠርነው በቀል፣
ከመስጠት አንጉደል ከቀማኞች ገደል ተረግጠን ብንጣል፣
ካሸከሙን በቀል ምናወርሰው ፍቅር ሀገር ይለውጣል፡፡
ከዕድሏ ጣሪያ ላይ ዘር የቀዳደው ሽንቁሯ ቢበዛም፣
ያ ከንቱ ፎካሪ ባፈጀ ቀረርቶ ሺህ ጉራ ቢነዛም፣
ሚሊዮን ዘር ቢሸጥ አንድ ሀገር አይገዛም፡፡
ኢዮጵያዊነት ነው የትርታችን ልክ የነፍሳችን ግጥም፣
መልስ ቤት በራቀው በከረመ ፀሎት ሰርክ ብታንጋጥም
አጎንብሳ ድሃ ባፀናችው ጉልበት ብትረጋገጥም
ነፍሷን አደህይታ ባሻረችው ቁስል ብትገሸለጥም፣
ሀገር ሆና ገዝፋ በየ ጎጣጎጡ አትርመጠመጥም፡፡
የዘመን እውነት ነን ከደግነት ሰማይ በጥበብ የኖርን፣
ትዕግስትም ልክ አለው ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን፡፡
ማተብ አስሮን እንጂ ተጣልተን እንዳንቀር በክፍፍል ገደል፣
ከሀገር ክብር በልጦ ሞት ብርቃችን አይደል፡፡
ንገሩት ለዛ ሰው ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ ኃይል እንደ ተራራ ገዝፎ ቢከመርም፣
ክንዱን አፈርጥሞ እልፍ የሰገደለት ጀግና ቢሰድርም፣
ዓለም የሞተበት የጠላት ማርከሻ ጦር ቢደረድርም፣
በአንድ ዓይናችን ሰላም በኢትዮጵያችን ክብር አንደራደርም!!!

🔘ሕሊና ደሳለኝ🔘
👍3
አትሮኖስ pinned «#የማጀት_ስር_ወንጌል ሙያተኛ ሀገሬ ከማጥገብ ጎደለ በረከት እራቀው የገበታሽ ለዛ፣ ተሻምቶ ለመጉረስ ከበላነው ይልቅ የደፋነው በዛ፡፡ ሙያሽ ባያስደፍር አጀብ ቢሰኙበት፣ ማዕዱ ቢሙላላ ዓይነቱ ቢያምርበት፣ አበዛዙ አይደለም አበላሉ ላይ ነው የገበታሽ ውበት፡፡ እየተማመንን! የፉክክር ቅሚያ በርሃብ እየናጥን፣ ከደፋነው ጠግቦ ውሻችን በለጠን፡፡ ከምርት አላነስን፣ ጎተራችን ሙሉ ጀግና አራሽ መች አጥተን፣ ማሰብ…»