#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
:
✍ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...‹‹አረ ቁጭ በል ..ከጨከንክ ምን አድረጋለው እከፍልሀለው››
‹‹ተመልሶ ቁጭ አለ..እሺ ቅድሚያ ለስራ ማስኬጃ 25 ሺ ብር እፈልጋለው፡፡ሌላው ስራው ሲጠናቀቅ››
‹‹እሺ ››አለና ቀለም ወርቅ ምንም ሌላ ትርፍ ነገር ሳይናገር ከለበሰው ግዙፍ የውስጥ ጃኬት ውስጥ ወንድአፍራሽ የጠየቀውን ቅድሚያ ክፍያ አውጥቶ ሰጠውና በአንድ ሳማንት ጊዜ ውስጥ መጨረሻውን ውጤት እፈልጋለው››ብሎት ተነሳ
‹‹ግድ የለም በሶስት ቀን ለማጠናቀቅ እሞክራለው››
‹‹ይቅናህ››
ብሎት የሆቴሉን ግቢ ለቆ ወጣ
ወንድ አፍራሽ አስተናጋጆን ጠራትና‹‹ሁለት ክትፎ አንድ ጥብስ እና ሶስት ጃንቦ ሲል አዘዛት››አሁን ግራ እደተጋባች ትዛዙን ልታስተላልፍ ወደ ውስጥ ሄደች እሱ ሞባይሉን አወጣና ደወለ
‹‹ሄሎ ኤልያስ››
‹‹ሄሎ ወንድ››
‹‹የት ነህ?››ጠየቀው ወንድ አፍራሽ
‹‹ሸዋ በር››
‹‹እኔም እዛው አካባቢ እኮ ነኝ ለአሪፍ ሽቀላ እፈልግህ ነበር..የእኛ ሆቴል ብቅ ማለት ትችላለህ? ››
‹‹መቼ ?››
‹‹አሁን እዛው ነኝ ››
‹‹እሺ..መጣው››
ስልኩ ከተዘጋ ከ10 ደቂቃ ቡኃላ ኤልያስ መጣለት በሞቀ ሰላምታ ተቀበለው ወዲያው አስተናጋጆ የታዘዘችውን ምግብ ይዛ መጣች…በልተው እንዳጠናቀቁ ኩማንደር የተባለውን የፖሊስ አዛዥ ለመግደል ከተባበረው 30 ሺ ብር እንደሚከፍለው ነገረው..ኤልያስ በሰማው ያልተጠበቅ አስደንጋጭ ዜና ውስጡ እየተንቀጠቀጠ ቢሆንም በላይ ገጽታወ ግን ምንም የስሜት መለዋወጥ ሳይንፀባረቅበት ወንድ አፍራሽም ልክፈልህ ባለው የዋጋ መጠን ሳይከራከር በሀሳቡ ተስማማ..ከነገ ጀምሮ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተስማምተው ለዚህም ማረጋገጫ ኤልያስ 5 ሺ ብር ቀብዲ ተቀብሎ ማታ ሊገናኙና በዝርዝር ጉዳዬች ላይ ሊነጋሩ ተስማምተው ተለያዩ …ኤልያስ ቀጥታ ከወንድ አፍራሽ እንደተለየ..ለኩማደሩ ነበር የደወለው
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ወንድአፍራሽ እና ኤልያስ በቀጠሮቸው መሰረት ተገናኝተዋል፡፡አሁን ሰዓቱ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ የሚገኙት ከበቀለ ሞላ ሆቴል በቀኝ በኩል መቶ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሚገኘው ትንሳኤ ሆቴል ነው፡፡ይሄንን ሆቴል የመረጡበት ምክንያት ዋናው ለኩማንደሩ ቤት ብዙም ስለማይርቅ ነው… ሌላው ደግሞ ወንድ አፍራሽ ቀልቡ ያረፈባት አዲስ ገቢ ልጅ አሁን ያሉበት ሆቴል ውስጥ ስላለች ነው፡፡ሰሞኑን እጁ አጥሮት ነው እንጂ ከጅሏት ነበር፡፡እና አሁን ሁለቱም እዛ ነው ያሉት አንድ ጥግ ይዘው መጠጡን እያወራረዱ ከሰዓታት ቡኃላ ስላለባቸው ተልዕኮ ይወያያሉ፡፡
‹‹ግን አሁን እቤቱ እንዳለ አጣርተህልኛል አይደል?››ወንድአፍራሽ ነው ጠያቂው
‹‹አዎ ባዘዝከኝ መሰረት በቤቱ አካባቢ አድፍጬ ስከታተለው ነበር…ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው ወደቤቱ የገባው.››
‹‹ከገባ ቡኃላ እንደማይወጣ በምን አወቅክ?››
‹‹ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ የለሊት ቢጃማ ለብሶ ስሊፐር ጫማ አድርጎ ከቤቱ በመውጣት ሰፈር ወዳለች አንድ ኪወክስ ሄዶ ሲጋራ በመግዛት ወደቤቱ በመመለስ እቤቱን ዘግቷል..እርግጠኛ ነኝ ተመልሶ የመውጣት ሀሳብ ቢኖረው ኑሮ እንደዛ አይነት አለባበስ አይለብስም ነበር››
‹‹አሪፍ ሰላይ ነሽ..ለዚህ ቅልጥፍናሽ እኮ ነው አንቺን የመረጥኩት››ሲል አደነቀው..‹‹በል አሁን ሰዓቱ እስኪደርስ ዘና እንበል…ሰባት ሰዓት ሲሆን እንንቀሳቀሳለን እስከ ስምንት ሰዓት ሁሉን ነገር ፈጽመን በድል እንመለሳለን››
‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ይሳካልናል?››እልያስ ነው የወንድአፍራሽን የውስጥ ጥንካሬ ለመገምገም የጠየቀው
‹‹አትጠራጠር..እንኳን አንተን ከጐን አሰልፌ ይቅርና እኔ ብቻዬን ብሆን እንኳን ለእሱ አላንስም…ያው እንደማንኛውም ሰው እሱም ሰው እኮ ነው….በጣም ገዝፎ የሚታየን እና አስፈሪ የሚሆንብን ከእነ ማዕረጉ ስለምናስበው እኮ ነው…እኛ ደግሞ እሱን ምናገኝበት ሰአት ወድቅት ለሊት ነው..በዛ ሰዓት ደግሞ ህዝብም እንቅልፍ ላይ መንግስትም ደግሞ በማሸለብ ላይ ሰለሚገኙ ማዕረግ አይሰራም››
ሲል ለመፈላሰፍ ሞከረ
‹‹እንደአፍህ ይሁንልህ..እኔ ግን ትንሽም ቢሆን ፈርቼያለው››አለው ኤልያስ
‹‹መፍራትህ ጥሩ ነው….ከመጠን ያላለፈ ፍርሀት ጥንቃቄን ይወልዳል…ጥንቃቄ ደግሞ የድል በር የምንከፍትበትን ቁልፍ ያስጨብጠናል›..ትል ነበር አያቴ…እና እንኳንም ፈራህ.. እኔም ፍርቼለው..አሁን ግን ዘና በል ጠጣ፤ ጨፍር፤ ተዳራ ከዛ ድፍረት ታገኛለህ ››ብሎ አደፋፈረውና በእጁ ምልክት ሰሞኑን ሲከጅላት የሰነበታትን ልጅ ጠራት..እየተውረገረገችም እየተንዘረዘረችም ወደእሱ ቀረበች
‹‹የእኔ ቆንጆ ተቀመጪ›› አላት ወንድአፍራሽ…
በተቀመጠበት አንዴ ሸምድዳ በመመልከት ገመገመችውና ተቀመጠች…የምትጠጣውን አዘዘች
‹‹በጣም ውብ ነሽ›› አላት ወደጆሮዋ ተጠግቶ
‹‹አንተም ሸበላ ነህ››አለችው ሙዚቃዊ ለዛ በላው ድምጽ ..ደስ አለው ..ወደዳት
‹‹ለዛሬም ቢሆን ላገባሽ እፈልጋለው››
‹‹የምታስርልኝ ቀለበት ከተስማማኝ ችግር የለውም፡፡››
‹‹አረ አስርልሻለው…ሰሞኑን በብር ቀለበት ነው አይደል ይዘውሽ የሚያድሩት ዛሬ እኔ የወርቅ ቀለበት ነው ማጠልቅልሽ››
‹‹እንደዛ ከሆነ እኔም ገነታዊ የሆነ ለሊት እንደምታሳልፍ ዋስትና እሰጥሀለው››አለችው በፈገግታ
በቃ ወደዳት…ሲያያት በመልኳ ከተማረከው በላይ አሁን ቀርቦ ሲያወራት በድምጾ እና በብልጠታዊው ንግግሯ ተማረከ
ወንድአፍራሽ ወደ ኤልያስ ዞረና
‹‹ሰዓት ስንት ሆነ ?››ሲል ጠየቀው
‹‹ሰባት ሰአት እስኪሆን ጠጣ ጨፍር ፤ዘና በል››አለው ኤልያስ..ወንድ አፍራሽም የኤልያስን ምክር ሰምቶ የልጅቷን እጅ እየጐተተ ወደ ዳንሱ ሜዳ ይዞት ሄደ..አብሮት ሊጨፍር
በዚህን ጊዜ ኤልያስ ሽንቱን እንደሚሸና በጐሮ በኩል ወደውጭ ወጣና ለኩማንደሩ ደወለለት››
‹‹እሺ ኩማንደር ሰላም ነው?››
‹‹ሰላም ነው››
‹‹ዝግጅታችሁን አጠናቀቃችሁ?››
‹‹አዎ የእናንተን መምጣት ነው በናፍቆት እየጠበቅን ያለነው››
‹‹እንግዲያው በቃ ከአንድ ሰዓት ቡኃላ እንመጣለን ››
‹‹እሺ እስከዛው ቻው››
‹‹ቻው››ስልኩን ዘጋ ና ወደ ውስጥ ተመለሰ..
ወንድአፍራሽ አሁንም ከልጅቷ ጋር በደስታ እየተፍነከነከ እና እየደነሰ ነው..ከደቂቃዎች ቡኃላ ሰው ሊገል ለፊልሚያ የሚሰማራ ሳይሆን ወደሰርግ ቤት ለመጨፈር ለመሄድ ቀጠሮ ያለው ይመስል ነበር..ወደ ልጅቷ ጆሮ ጠጋ ብሎ ‹‹ዛሬ በእውነት ውድ ቀን ነች›› አላት
እየተፍለቀለቀች‹‹እንዴት?››ስትል ጠየቀችው
‹‹በቃ በሁሉ ነገር ጣፋጭ ነሻ..በጣም ወድጄሻለው..ዛሬ አብረን ነው የምናድረው››
‹‹ይመቸኛል ..የት ነው አልጋ የያዝከው?››
‹‹አልያዝኩም እዚህ አልጋ የለም እንዴ?››
‹‹ብር ስጠኝና ጠይቄ ልምጣ››
‹‹እሺ ቆንጆ አለና ኪሱ ገብቶ አልጋ ለመከራየት ይበቃል ያለውን ብር አውጥቷ ሰጣት..ብሩን ተቀበለችውና ከእቅፉ ሹልክ ብላ በጓሮ በር ወጥታ ሄደች …እሱም ከደናሾቹ መካከል ወጣና ወደ ኤልያስ ሄደ
‹‹ወፍህስ…ወደሌላው በረረችብህ እንዴ?›› ጠየቀው ኤልያስ
‹‹አረ በደንብ አጥምጄያታለው ዛሬ ከእኔው ጋ ነች… አልጋ ልትከራይ ነው የሄዳለች››
‹‹እንዴ ሀሳብህን ቀየርክ እንዴ?››ግራ በመጋት ጠየቀው
‹‹የምኑን ሀሳብ?››
‹‹ሰውዬው ጋር የመሄዱን ነዋ››
‹‹አንተ ደግሞ እንዴት ቀይራለው .. ?ምን ግዜም እኮ ለስራ ቅድሚያ መስጠት የግድ ነው››
‹‹ታዲያ አልጋ ልትከራይ ሄደች ስትለኝ ምን ልበል?››
‹‹እሱማ እውነቴን ነው አየህ ሄደን ስራችንን አጠናቀን ስንመጣ ..ይታይህ ከዚህች የመሰለች ልጅ ጋር ዘና ብል ያንስብኛል

👍3
እንደውም አንተም አንዷን መርጠህ አስቀምጠህ ብትሄድ መልካም ነው››ምክሩን ለገሰው
‹‹ይቅርብኝ‹መብላቷን ሳታውቅ እጆን ታጠበች›
እንዳይሆንብኝ …ወደ ጦር ሜዳ የሚሄድ ወታደር ሚስት ባያገባ ይመረጣል…በመመለሱ አስተማማኝ መሆን ስለማይችል ፡፡››አለው፡፡
‹‹አንተ ደግሞ ያለወትሮህ ዛሬ ሟርት አበዛህ››
‹‹ሟርት አይደለም የተሰማኝን ነገር ነው የነገርኩህ?››
በዚህ ጊዜ የወንድአፍራሽ ሴት ከሄደችበት ተመልሳ መጣች እና ከጐኑ ተወሸቀችበት
‹‹መጣሽ ቆንጆ?››
‹‹ተከራይቻለው የእኔ ዋርካ ››እያለች እላዬ ላይ ተለጠፈችበት እና የመኝታ ቤቱን ቁጥር ነገረችው..
‹‹ስንት ልክፈልሽ? ››አላት
ነገረችው..ከጠየቀችው አስበልጦ ሰጣትና‹‹ አሁን ይሄን ጓደኛዬን እቤቱ አድርሼው እመጣለው…ክፍልሽ ገብተሸ ተኝተሸ ጠብቂኝ….››
‹‹እንዴ ምነው ይፈራል እንዴ… ለምን ብቻውን አይሄድም?››
‹‹ሳይሆን እቤቱ ድረስ አብሬው ሄጄ የምወስደው ዕቃ አለ››
‹‹እሺ ግን ትቆያለህ?››
‹‹አይ አንድ 30 ደቂቃ ብቻ ባስጠብቅሽ ነው…አንቺ ብቻ ዝግጁ ሆነሽ ጠብቂኝ..ደግሞ አስደሳችነትሽ በዚሁ ከቀጠለ ጥዋት አሪፍ ቦነስ ይኖርሻል›› ...ብሎ ጉንጮን ሳማትና ተያይዘው ወጡ ..ወደ ኩማደር መሀሪ ቤት….የቀለም ወርቅን ትዕዛዝ ተቀብለው ሊገድሉት…..
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
መብራት እየበራ ነው ሁሉም ነገር ፍንትው ብሎ ይታያል..ምንም አይነት እንቅስቃሴ ግን አይታይም‹‹ምን እናድርግ››ሲል ኤልያስ ወንድአፍራሽን ጠየቀው ‹‹መጀመሪያ አጥሩን ዘለን ወደግቢ ውስጥ እንግባ››ተስማሙ እና ምቹ በሆነ ቦታ መርጠው በመንጠላጠል ዘለው ገቡ..አጥር በመዝለል ከፍተኛ ልምድ ስላላቸው አልተቸገሩም..በፍጥነት ወደቤቱ ተጠጉ ….በተረከዛቸው እየተራመዱ ድምጽ ላለማሰማት እየተጠነቀቁ የፎቁን ደረጃ ወጡ..…ብዛት ያላቸው ቁልፎች እና ለቁልፍ መሰርሰሪያነት የሚያገለግሉትን መሳሪያዎች በጀርባው አንግቶት ከነበረው ቦርሳ አወጣና በራፍን ያለኮሽታ እና ቅጭታ ሊከፍት ሊሞክር እጁን ወደ በራፍ ሲልክ ንቅናቄ ተመለከተ …ሲሞክረው ተከፈተለት፡፡ደነገጠ..፡፡ወዲያው ሙሉ በሙሉ ከመክፈቱ በፊት እቃዎቹን ወደ ቦርሳው መለሰና ሽጉጡን አወጣ …
ለኤልያስ በተጠንቀቅ እንዲሆን ምልክት ሰጠውና በራፉን ገፋ ሲያደርገው ሙሉ በሙሉ ተከፈተ፡፡…ሁለቱም በግራና በቀኝ በራፉ አቅጣጫ ሆነው በተጠንቀቅ ወደ ውስጥ አተኮሩ…… ያዩትን ነገር ግን ማመን የሚከብድ ነው፡፡ ኩማደሩ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ እግሩን እንደ ስርአት-አልባ የሀብታም ልጅ ጠረጵዛ ላይ ሰቅሎ በቀኝ እጁ ብርጭቆ ጨብጦ ይጠጣል…ሁለቱም ሽጉጣቸውን እንደደቀኑ ወደ ውስጥ ዘልቀው ገቡ…ምንም የመገረም ምንም የመደንገጥ ስሜት ሳያሳይ ዘና እንዳለ ነው….ወንድአፍራሽ ግራ ተጋባ
‹‹‹ይሄን ጥጋበኛ ፈትሸው››ሲል ለኤልያስ ትዕዛዝ አስተላለፈ…ኤልያስ የቀሰረውን ሽጉጥ ጐኑ ሸጐጠና ወደ ኩማንደሩ ተጠጋ
‹‹እግርህን አውርድ››
‹‹ኸረ የተከበራችሁ አንግዶቼ በራሳችሁ ጭንቀት ሽብር አትፍጠሩ ..ይልቅ ኖር ብዬለው…ቁጭ በሉና እየጠጣው ያለውትን መጠጥ ልጋብዛችሁ››
‹‹እያሾፍክ ነው በቁጥጥራችን ስር እኮ ነው ያለኸው…ይልቅ በጨዋ ደንብ ተነስና ተፈተሸ››
‹‹እሺ ካልክ›› አለና ዘና እንዳለ ብርጭቆውን ጠረጵዛ ላይ አስቀምጧት ቆመ ….ኤልያስ ፈተሸው…‹‹ምንም መሳሪያ አልያዘም…››
‹‹ቁጭ በል ››ወንድአፍራሽ ኩማንደሩን አዘዘው
ቁጭ አለና ‹‹አንተም የቀሰርከወን ሽጉጥ ስለማይጠቅምህ አስቀምጠኸው ከእኔው ጋር ቁጭ ብለህ መጠጡን እየጠጣን ዘና ብንል የእኔ ምክር ነው፡፡››
ወንድአፍራሽ የዚህ የኩማደር ትዕቢት ትዕግስቱን እየተፈታተነው ነው… በአስቸኳይ የሚያደርገውን qአድርጎ መገላገል ፈለገ..በዛ ላይ እዛ ሆቴል ትቷት የመጣው ቆንጆ ባይኑ ውልብ እያለችበት ተቸግሯል.... ‹‹አሁን ምላጩን ልስብ ነው ፍቅረኛ ወይም ሌላ ለምትወደው ሰው እንዲደርስልህ የምትፈልገው የመጨረሻ ሰዓት ኑዛዜ ካለህ እድሉን እንሰጥሀለን….መልዕክትህንም እንደምናደርስልህ በተከበረው ሞያችን ስም ቃል እንገባልሀለን››
‹‹ምንም የለኝም››
‹‹እጮኛ የለህም?››ተገርሞ ጠየቀው
‹‹አይ ኑዛዜ ነው የሌለኝ..ነገ ስለማገኛት ማለት የምፈልገውን ነገር ቀጥታ ለራሷ እነግራታለው››
‹‹አልገባህም እንዴ!!! የነገዋን ብርሀን እኮ አታያትም እያልኩህ ነው..ነው ወይስ እጮኛህንም እንላክልህ..?››
‹‹ግድ የለም በህይወት እኔም እሷም ብዙ እንኖራለን››
ወንድአፋራሽ የኩማንደሩን በራስ የመተማመን ጉዳይ ግራ አጋባው…አበሳጨውም፡፡ልብን በጥይት በስቷት ደም ከሰውነቱ ቡልቅ ..ቡልቅ እያለ ሲወጣ..ቤቱን ሲያጥለቀልቅ ለማየት ጓጓ…ውሳኔ ላይ ደረሰ ፡፡ ሽጉጡን አስተካክሎ ምላጩን ከመሳቡ በፊት ግን ከኃላ ጭንቅላቱ ላይ የሆነ ባዕድ ነገር ዳበሰው..ግራ ተጋብቶ በመጠኑ ዞር ሲል የፖሊስ ደንብ ልብስ ለብሶ ፊቱን በጭንብል የከለለ አንድ ግዙፍ ሰው ሽጉጥ ደቅኖበታል ‹‹ሽጉጡህን ወደመሬት ጣል››የሚል ትዕዛዝ ተከተለው
መጀመሪያውኑ በኩማንደሩ የንቀት እና በራስ መተማመን ሁኔታ እየራደ የነበረው ወንድአፍራሽ አሁን ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆረጦ ሽጉጥ የያዘው እጁ ወደታች ተዝለለፈለፈበት….ሽጉጡ ከእጁ ሾለከ እና ወደመሬት ወደቀ….፡፡በዝግታ ሁኔታዎችን ሲከታተል የነበረው ኩማንደር ከቆመበት ተንቀሳቀሰ እና ወንድ አፍራሽ የጣለውን ሽጉጥ አንስቶ ውስጡ ያለትን ጥይቶች አወጣና ቀፎውን ወደ ጠረጵዛው ወረወረው…ፖሊሱ ሽጉጡን እንደደቀነ ወደኃላው አፈገፈገ እና በራፉ ጋር ያለውን ግድግዳ ተደግፎ ሽጉጡን ግን እንደደቀነ በተጠንቀቅ ቆመ..ኩማደር ወደ መኝታ ቤቱ ሄደና አንድ ያልተከፈተ ሙሉ ጐርደን ጅን ውስኪ ከሶስት ብርጭቆ ጋር ይዞ መጥቶ ከፈተው..ከዛ መቅዳት ጀመረ
‹‹.እንዴ እስከአሁን ቆማችሆል እንዴ .. ?አሁን እኮ የተከበራችሁ እንግዶቼ ናችሁ ቁጭ በሉ…››
‹‹እሺ እናመሰግናለን›› ብሎ ኤልያስ ቀድሞ ተቀመጠ…ወንድአፍራሽ ግራ በመጋባት እና ምርጫ በማጣት ተከትሎት ተቀመጠ..የቀዳውን ውስኪ ለሁለቱም አቀበላቸው እና የራሱን ድርሻ ይዞ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ
‹‹እሺ ወንድአፍራሽ አሁን ዘና ብላችሁ ተጫወቱ››አለው ኩማንደር
ወንድ አፍራሽ ስሙን ከኩማንደሩ አፍ ሲሰማ መብክረኩ ጨመረበት‹‹..ስሜን ደግሞ እንዴት አወቀው..?ወይኔ በቃ አልቆልኛል››ሲል በውስጡ አሰላሰለ
ወንዳፍራሽ ኩማደር መሀሪን በትኩረት አየውና ‹‹በጣም የምትደነቅ ሰው ነህ!!! ››ሲል አስተያቱን ሰጠው
‹‹እንዴት?››ጠየቀው መሀሪ …ኤልያስ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ መድረኩን ለእነሱ ትቶ ውስኪውን በእፎይታ ይጐነጫል
‹‹አደገኛ ነሀ›› መለሰለት ወንድአፍራሽ
‹‹ግን ካንተ አልበልጥም..››
‹‹የበላይነቱንማ እንደምጐናፀፍ ገና ስትመጣ ነው የነገርኩህ..ልትሰማኝ አልፈቀድክም እንጂ››
‹‹አዎ መስማት ነበረብኝ›› በቁጭት ተናገረ..ዞር ብሎ ከጐኑ የተቀመጠውን ኤልያስን ሲመለከት ግብዣ እንደተጠራ ሰው በፍጹም መረጋጋት እና በፀጥተ መጠጡን ይመጣል
ወንድአፍራሽ ኤልያስን ‹‹የት ነው ያለኸው?›› ወደጆሮው ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ ጠየቀው
‹‹አንድ ሽጉጥ በደቀነ ፖሊስ ታግቼ በኩማንደሩ ቤት ቁጭ ብዬ ውስኪ እየጠጣው››መለሰለት
‹‹እና ይሄ አያስደነግጥህም?››
‹‹ምኑ?››
‹‹በፖሊስ እጅ መውደቅህ ነዋ?››
ኤልያስ በግድየለሽነት መለሰለት‹‹ብደነግጥስ እራሴን ከመጉዳት ውጭ ምን አተርፋለው…መጀመሪያውኑ ይሄን ስራ እንድንሰራ ስታማክረኝና እኔም ስስማማ..50 ፐርሰንት እንደሚሳካልን 50 ፐርሰንት ደግሞ እንዲህ አይነት ጉዳይ እንደሚያጋጥመን አስቤበት ነው

👍2❤1
የተስማማውት..በዚህች አለም ላይ ሁሌ ስኬታማ እና አሸናፊ መሆን እንደማይቻል ከልምድ ተምሬያለው››
በዚህ ቅጽበት በራፉ ተንኳኳ… በራፍ አካባቢ ያለው ፖሊስ በቀኝ እጁ ሽጉጡን እነወንድአፍራሽ ላይ እንደደቀነ በግራ እጁ በራፉን ከፈተው… ሰማያዊ የለሊት ቢጃማ የለበሰ ጐልማሳ ሰው..አንገቱን አቀርቅሮ ኩምሽሽ እንዳለ ዘልቆ ወደውስጥ ገባ..ሰውዬው ወርቅአለማው ነው..ከሞት መንደር አምልጦ የመጣ ይመስላል..ፊቱ ግርጥት ብሎ አመድ የተነሰነሰበት ይመስላል..ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች አይን ሁሉ እሱ ላይ ተተከሉ..ወንድአፍራሽ አይኑን ማመን አልቻለም..በዚህ ቤት ትርኢት እየተሰራ ያለ መሰለው
ግባ ቁጭ በል››ከእነወንዳፍራሽ ጐን ወንበር ሰጠው..ያለ ምንም ንግግር ኩስስ ብሎ ተቀመጠ
‹‹አትተዋወቁም እንዴ?››ወንድአፍራሽን ጠየቀው
‹‹አረ በደንብ ..ምን እዚህ እንዳገናኘን ነው እንጂ እንቆቅልሽ የሆነብኝ››
‹‹ያው ለሁለተኛ ጊዜ አንድ ስራ ከመስራታችሁ በፊት ከማን ጋ እንደምትሰሩ እና ለማን እደምትሰሩም ጭምር ጥንቃቄ እንድታደርጉ ትምህርት እዲሆናችሁ ነው..አሁን ከእናንተ ያለኝን ነገር ጨርሼያለው…ከፈለጋችሁ መቆየት እንሄዳለን የምትሉም ከሆነ ነጻ ነችሁ››
ወንድአፍራሽ ባለማመን እና በጉጉት ጠየቀው ‹‹ነጻ ናችሁ ስትል?››
‹‹በቃ ወደቤታችሁ መሄድ ትችላላችሁ››አረጋገጠላቸው ኩማደሩ
እናመሰግናለን እግዜር ይስጥልን..ተፈናጥሮ ከመቀመጫው ተነሳ..የጀመረውን መጠጥ እንኳን እስኪጨርስ መታገስ አልቻለም..ይሄን የጭንቅ ቤት ለቆ መብረር አለበት..አዎ ተኝታ እሱን ወደምትጠብቀው ቆንጆ ጋር በሮ መድረስ አለበት….
‹‹ተነስ እንሂድ እንጂ››ኤልያስን እንዲነሳ ጠየቀው
‹‹እኔ መጠጡ ተመችቶኛል..መቆየት እፈልጋለው›› አልተስማማም ኤልያስ
የዚህ ልጅ ፀባይ ምንም ሊገባው አልቻለም.‹‹የራስህ ጉዳይ›› ብሎ ጥሎት እቤቱን ለቆ ወጣ እግሩ የጊቢውን አጥር አልፎ እስኪርቅ ድረስ አላመነም ነበር …ሀሳባቸውን ቀይረው ተመለስ የሚሉት እየመሰለው
ኩማንደር ወደ ቀለምወርቅ ሀሳቡን ሰበሰበ እና‹‹እሺ አቶ ወርቅአለማው…አሁንስ?››
‹‹አሁን ምን?››
‹‹ወደ ድርድራችን እንሂድ ወይስ እንዴት ነው?››
‹‹ምን ምርጫ አለኝ ..ተሸንፌያለው እጅህ ላይ ወድቄያለው..ነገ ጥዋት የጠየቅከኝን ብር በእጅህ አስረክብሀለው››
‹‹ጥሩ የብልህ ሰው ውሳኔ ነው የወሰንከው..ብሩ ግን ወደ 8 ሚሊዬን ብር አድጓል››
‹‹8 ሚሊዬን!!! ››በድንጋጤ ከመቀመጫው ተነሳ››
‹‹ምንም ማድረግ አልችልም ..በራስህ እጅ ያመጣኸው ጣጣ ነው.›
‹‹አረ በፈጠረህ በቃ ተሸነፍኩ እኮ ..የጠየቅከውን 5 ሚሊዬን ብር ልክፈልህ››
በፍፁም አይሆንም… ነገ እስከ ስድስት ሰዓት 8 ሚሊዬን ብር ታስረክበኛለህ ወይም 7 ሰዓት ሲሆን የሚስትህ መቃብር ይቆፈርልሀል››በል ፖሊስ እቤቱ ድረስ መልሰህ ሸኘው››ብሎ ትዕዛዝ አስተላለፈ እና ወደ መጠጡ ተመለሰ…
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍2
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሰላሳ
:
✍ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ወርቅአለማው ሳይወድ በግድ 8 ሚሊዬን ብሩን ለኩማደሩ በዛሬው ቀን ለማስረከብ ተዘጋጅቷል…አዎ ምርጫ የለውም.…ግን ብሩን ማስረከብ ማለት እንዲሁ ከናጠጠ ኑሮው ወደ ድህነት መንደር ያሽቀነጥረዋል የሚለው አገላለጽ ብቻ አይገልፀውም..ይሄንን ሀብት ያፈራው በብዙ ፈተና እና መከራ ነው…ብዙ ሰው ከድቶ …ብዙ ሰው ገድሎ ከህሊናውም ከአምላኩም ተቀያሞ ያካበተውን ገንዘብ ነው፡፡ …አሁን በዚህ ወቅት ቀለምወርቅ ለመኖር ያለው ፍላጐት ተንጠፍጥፎ አልቆ ጥቂት ጠብታ ብቻነች የቀረችው….ሰሞኑን እቤቱን ዘግቶ ብቻውን ደረቅ አልኮል ሲጋት ነው የሚውለው … የሚያድረው፡፡ዛሬ ቀጠሮው ስምንት ሰዓት ላይ ነው…ስምንት ሰዓት ላይ በተቃጠሩት ቦታ በሚስጥር ይሄድና ያስረክበዋል…ከዛ ቡኃላ ምን እደሚያደርግ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም…መኖር ከቻለ ይኖራል….መኖር ከደከመው ደግሞ እራሱን ያጠፋል…ወይም ሁሉም ነገር በቃኝ ብሎ ንሰሀ ገብቶ ወደ አንዱ ገዳም በመግባት መልኩሶ ቀሪ ህይወቱን በፃም እና በፀሎት ያሳልፋል…መቼስ አንዳንዴ ስንሸነፍ ወይም ስንሰበር አይደል ፊታችንን ወደፈጣሪ ማዞር የምንጀምረው ‹‹እሁድ የትንሳኤ እና የሰላም ቀን ነች..ምነው ለእኔ ሲሆን የውድቀቴ እና የመክሰሚያ እለት ሆነች›› ሲል ከራሱ ጋር አጉረመረመ
ኮማንደር መሀሪ በዛሬው እለት ሌላም አንድ ሰው ለብርቱ ጉዳይ ቀጥሮል እሳቸውም አባ ሽፍንፍን በመሰረቱት የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በታማኝነትና ከልብ የሚሰሩትን ወይዘሮ አረገዱን ነው ይሄም ደሞ ግልፅ ነው ወረቅአለማው ያለውን ገንዘብ ጠቅላላ በመረከብ ራቁቱን ያስቀረዋል..አዎ ዋናው የኩማንደሩ ሀሳብ ከድሮ የእንጀራ አባቱ በሚቀበለው ገንዘብ ለመፈንጠዝ እና ሀብታም ለመሆን አይደለም..እንደውም ብሩን ተቀብሎት ቢያቃጥለው እንኳን ግድ የለውም…ዋናው ዓላማው እሱን ወደነበረበት የድህነት አዘቅት በመመለስ መበቀል ብቻ ነው እና ከሱ የሚቀበለውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለአባ ሽፍንፍን ድርጅት መለገስ አስቧል እናም ለዚ ነው የወይዘሮ አረገዱ የዛሬ ቀጠሮ
ቀለም ወርቅ ከዘይዘሮ አረገዱ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ተቃጥረዋል እሱም ከቀጠሮ ሰአት ቀደም ብሎ በመኪናው በሁለት ሻንጣ የተሞላ ብር አጭቆ በቀጠሮው ቦታ ቀደም ብሎ ነው የተገኘው ኮማንደር ሰአት ባይጠብቅና ወዲያው ተረክቦት እፎይ ብሎ ድህነቱን አሜን ብሎ ተቀብሎ ስለቀሪ ህይወቱ ቢጨነቅ ነው ሚሻለው
የማይደርስ የለም ሰአቱ ደረሰ ኮማንደር መሀሪ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ነው ነገሮችን የሚያስኬደው ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ነው አብዛኛውን ስራ የጨረሰው ለአባ ሽፍንፍን የበጎ አድራጎት ድርጅት በቋሚነት የገንዘብ ድጋፍ በሚያደርጉት በአንዱ ድርጅት ስም 8 ሚሊዎን ብር ድጋፍ እንደሚገኝና ይሄንንም እንዲያስጨርሱ በአባ ሽፍንፍን መራጭነት ወይዘሮ አረገዱ ተወክለው ነው የተላኩት
ቀለም ወርቅ ያለውን ሙሉ አስረክቦ ወደ ኦና ቤቱ በመጓዝ ላይ ይገኛል ይሄ ቤት ለጊዜው ብሎ የተከራየው ኦና ቤት ነው በዚ ቤት ምን ያሆል ጊዜ እንደሚቆይ እሱም አያውቀውም
ኮማንደር ለረጅም ጊዜ በተለያዩ ሙከራዎች ከጁ እያመለጠ እችን ቀን በጉጉት ሲጠብቃት የነበረች ቀን ነች የእንጀራ አባቱን ባዶ አስቀርቶታል በሀሳቡ የእናቱን ሀሳብ ያሳካ ያህል ነው የተሰማው ደስ የሚል በቀል።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አባ ሽፍንፍን ቤተክርስቲያን ቆይተው ቅዳሴ አስቀድሰው ወደቤታቸው እየተመለሱ ነው፡፡ በቤት መኪናቸው ናቸው..እራሳቸው ናቸው እየሾፈሩ ያሉት..በውስጣቸው ግን ብዙ ሀሳብ እየተተረማመሰ ነው..የዛሬዋ ቀን ብዙ በጣም ብዙ ነገሮችን ያከናወኑባት ቀን ነች…ለዓመታት የዘሩትን ዘር ያጨዱበት ውብ ቀን…ይሄንን እያሰቡ ጐጐቲ ድልድይ ጋር እንደደረሱ ያላሰቡት ነገር ገጠማቸው.. ልክ ድልድዩን ተሻግረው ሃያ ሜትር ያህል ሳይጓዙ የመኪናቸው መሪ አልታዘዝ አላቸው ..አስባልቱን እንደምንም ለቀቁና ፍሬን ይዘው ለማቆም ሞከሩ… ግን ተሳክቶላቸው ከማቆማቸው በፊት አንድ እግረኛ ላይ ወጡ… በቃ ሄዱበት እና ፊትለፊት ካገኙት አንድ የግንብ አጥር ጋር ተላትመው ቆሙ…. ወዲያው አካባቢው ድብልቅልቁ ወጣ.. ድሮም ሰው የማያጣው አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ የሚካሄድበት ቦታ መሰለ..፡፡ አምፑላንስ ቢደርስም የተገጨው ሰው እስትንፋሱ ወዲው ነበረ የተቋረጠችው…የሞቹ ማንነት እንደታወቀ ዘመዶቹ በቅርብ አካባቢ ስለነበሩ በአንዴ ሰፈሩን አጥለቀለቁት…በጣም ተሰሚና በአካባቢው በሀይለኝነታቸው የሚታወቁ ቤተሰቦች ናቸው…ደግነቱ በወቅቱ ፖሊስ በአካባቢው ደርሶ ስለነበረ ደንዝዘውና ፈዘው የነበሩትን አባሽፍንፍንን ቶሎ ብለው ከግርግሩ መካከል በማውጣት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘዋቸው ሄዱና ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ አደረጓቸው… ይህም ክስተት እንደ ሰደድ እሳት በአንዴ ተሰራጭቶ በከተማዋ የዕለቱ መነጋገሪያ ሆነ …
ሄለንም ሆነች አያቷ ወሬውን እንደ ሰሙ ነበር እየበረሩ ፖሊስ ጣቢያ የደረሱት ግን በወቅቱ ምንም ማድረግ አልቻሉም መረጃዎች አጠናቅረው በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ እና ምን አልባት ፖሊስ ፍርድ ቤቱ የዋስ መብታቸውን ሊያከብርላቸው እንደሚችል ተነግሮቸው ወደ ቤት ተመለሱ….ቤት እንደተመለሱ ሮዝ ከአዲስ አበባ ተመልሳ ቤት ቁጭ ብላ ነበር የጠበቀቻቸው ሮዝ ከአቤል ጋር ወደ አዲስ አባባ ሄዳ ነበር ይህም በኮማንደር ትዛዝ ነበር አዲስአበባ እግሯ እንደረገጠ ነበር ሆቴሏን የዘጋችው መዝጋት ብቻም አይደለም ዕቃዎቾንም ነው የሸጠችው …ይሄን ያደረገችው በእሷ ፍቃድ አይደለም…በመሀሪ ትዕዛዝ እንጂ፡፡ ሄለንን እንዲተውላት.. እንዳይጐዳባት ነው፡፡ ለዛ ስትል ኩማደሩ እንዳዘዛት እያደረገች ነው… በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሆቴሏን ዘግታ ያላትን ሁሉ ሸጣ ብሩን አምጥታ ለእናቷ እንድታስረክብ አስጠንቅቆታል....የሆነውን ስትሰማ በጣም ነው የደነገጠችው…ግን ቀጥታ አባን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ከመሄዶ በፊት አንድ የምትሄድበት ቦታ አላት… አዎ ኩማደር መሀሪን አግኝታ በቀጣይ ከእሷ ምን እንደሚፈልግ ማወቅ አለባት ልጆን ከጥቃት ለመከላለከል እራስሽን አጥፊ ቢላት ራሱ ከማድረግ ወደኃላ አትልም አዲስአበባ ሳለች ደውሎላት ዛሬ ሰባት ሰዓት ላይ ቀጥሯታል.. አሁን ደግሞ 6 ሰዓት ሆኖል …እና መሄድ አለባት ደግሞ የቀጠሮ ሰዓቶን አርፍዳ ደርሳ ልታበሳጨው አትፈልግም..
ከሰባት ሰዓት እስከ አስራሁለት ሰዓት አንድ ቦታ ተጐልታ ኩማንደሩን ስትጠብቀው ነው የዋለችው….ሊመጣና ሊያገኛት ግን አልቻለም፡፡ በዛ ላይ ስልኩም ጥሪ አይቀበልም…አውቆ እሷን በሀሳብ ለማሰቃየት ሆነ ብሎ እንደእዛ እንዳደረገ እርግጠኛ ነች…ይሄኔ ተሸሽጐ ቀኑን ሙሉ ሲመለከታት እና ሲደሰትባት እንደዋለ ጠርጥራለች ይሄም በጣም አንጀቷን አድብኗታል…
ሄለን አባ ሽፍንፍንን ለመጠየቅ ከፖሊስ ጣቢያ እንደተመለሰች የመጣለት አንድ አሳብ በአስቸኳይ ኩማደር መሀሪን መፈለግ ነው… አዎ እሱ ብዙ ሊረዳት የሚችላቸው ጉዳዬች አሉ ቶሎ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ማድረግ ይችላል የዋስ መብታቸው እንዲጠበቅ እና ውጭ ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ሊረዳት ይችላል… በዛ ላይ ከወንጀል ነጻ ሆነው እንዲወጡ የሚያደርግ ጐበዝ ጠበቃ ሊያገኝላቸው ይችላል. ስለዚህ ቅድሚያ እሱን ማግኘት እንዳለበት ወሰነች..ክፋቱ ግን ስልኩ ጥሪ አይቀበልም እቤቱ ሄደች እንደተቆለፈ ነው በእሁድ ቀን ስራ እንደሌለበት ብታውቅም ምን አልባት ለአስቸኳይ ስራ ተፈልጐ ገብቶ እንደሆነ ብላ ቢሮው ድረስ ሄዳ ጠይቃ ነበር ..ከነጋ እንዳልገባና

ማንም እንዳላየው ነገሯትና ወደ ቤት ተመለሰች.. ቀኑን ሙሉ ከእነሱ ቤት ወደ እሱ ቤት እየተመላለሰች… ከአሁን አሁን መጥቶ ይሆን ብላ ስትሰቃይ በየአስር ደቂቃ ልዩነት ስልኩን ከፍቶ ይሆን ብላ ስትሞክር ዋለች…
12 ሰዓት ላይ አያቷ የሰሩትን እራት እና መኝታ የሚሆን ፍራሽ ይዛ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ለአባ አስረከበች… ልታናግራቸው ሞክራ ነበር.. ግን በጣም መደበት ውስጥ ናቸው.. ድንጋጤውም ብስጭቱም አለቀቃቸውም…. ምንም ሊሏት አልፈለጉም ብቻ ይዛላቸው የሄደችውን ዕቃ ተረክበዋት ሸኟት።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሄለን ለአያቷ የሆነ ቦታ ደርሼ መጣው በማለት ተናግራ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ ወደ ኩማንደር ቤት አመራች ..አሁንም አልመጣም… እንደተለመደው ቁልፍ ከተሸሸገበት ቦታ አነሳችና ከፍታ ገባች.. መልሳ ከውስጥ ቅረቀረችውና ሶፋው ላይ ሄዳ ተኛች..ቀኑን ሙሉ ከወዲህ ወዲያ ስትባዝን ስለቆየች ደክሞታል… አዎ እዚሁ ተኝታ እስኪመጣ መጠበቅ እና አባሽፍንፍንን ከገቡበት መከራ እንዲወጡ እንዲያግዛት ማሳመን አለባት.. እሷቸው እሷን ከነአያቷ በዛ በመከራ ጊዜያቸው ጐዳና ከመውደቅ እና በረሀብ ከመጠበስ ታድገዋቸዋል..ታዲያ ዛሬ ነው ያንን ውለታቸውን በጥቂቱም ቢሆን ለመመለስ መሞከር ያለባት..አዎ ለዚህ ደግሞ ኩማንደር ይረዳታል..በዛ እርግጠኛ ነች..ይሄንን እና የመሳሰለውን እያሰበች ሳታውቀው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞት ጥርግ አለ..በእንቅልፍ ተውጣ ምን ያህል ሰዓት እንደቆየች ባታውቅም የሞባይሎ መንጫረር ነበር ከእንቅልፎ ያባነናት..ፈጠን ብላ አነሳችው..አያቷ ነበሩ
‹‹ወይ እማዬ››
‹‹ምነው ልጄ..? የት ጠፋሽ....?››
‹‹ወይ እማዬ ሳልነግርሽ ..አባን የሚረዳ ጠበቃ ለማናገር ሀዋሳ ሄጄ መሸብኝና እዛው አደርኩ››
ታዲያ አትናገሪም… ሰው ያስባል አትይም እንዴ..?››
‹‹ይቅርታ እማ …ስለዞረብኝ በትክክል ማሰብ አልችልም.››
‹‹እሱስ ሁላችንም ነን እንደዛ የሆነው..ታዲያ የሄድሽበት ቀናሽ..?››
‹‹አዎ ቀንቶኛል ..በጥዋት እመጣለው
በይ ደህና አደሪ››ስልኩ ተዘጋ..የዋሸችው ውሸት ለራሶም አስገርሞታል…እና እዚሁ ስጠብቀው ማደሬ ነው ማለት ነው…ፈገግ አለችና ከሳሎኑን ለቃ ወደመኝታ ቤት አመራች….አልጋ እንደተነጠፈ ነው..አልጋ ልብሱን ብቻ ገለጥ አደረገችና ብርድ ልብሱ ላይ ጋደም አለች .. አዕመሮዋ በብዙ መተረማመስ ውስጥ ነው…‹እኚ ቅድስ ሰው ምን መአት ነው የመጣባቸው....?አሁን ከወንጀል ቅጣት ነፃ ቢሆኑ እንኳን በአዕምሮ ፀፀት ሲሰቃዩ ነው የሚኖሩት…ዝንብ ገድለው የማያውቁ ሰውዬ የሰውን ነፍስ የሚያህል በእጃቸው ጠፍቶ….!!!ግን በምን መመዘኛ ነው የዝንብ ነፍስ ከሰው ነፍስ ይበልጥ ሚዛን የሚደፋው....?››እራሷን ጠየቀችና ፈገግ አለች..
ለረጅም ደቂቃዎች ብትገላበጥም እንቅልፍ ሊወስዳት ስላልቻለ በተኛችበት ሆና ኮመዲኖ ላይ ያሉ መጽሀፎችን እያነሳች ማገለባበጥ ጀመረች..
💫ይቀጥላል💫
🔘ነገ የመጨረሻውን ክፍል ይዘን እንቀርባለን🔘

#ክፍል_ሰላሳ_አንድ ( #የመጨረሻ_ክፍል )
:
✍ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
ከአንደኛው መጽሀፍ መሀል ያየቻቸው ሁለት ፎቶዎች ግን ተስፈንጥራ አልጋዋን ለቃ ወለሉ ላይ እንድትቆም አደረጋት…፡፡.ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው..የምታየውን ማመን አልቻለችም..የኮማንዳሩና የወላጅ እናቷ ፎቶ ነው…አንዱ ፎቶ ሁለቱም በዋና ልብስ ሆነው ሙሉ በሙሉ አቅፎት መዋኛ ገንዳ ውስጥ ሆነው የተነሱት ነው…ሌላው ደግሞ ከንፈር ለከንፈር እየተሳሳሙ…… ይሄን ያህል ሄደዋል ብላ አታስብም ነበር ..ስልኮን አነሳችና ደወለች..እሮዝ ጋር ነው..ተነሳ..?
‹‹አሁኑኑ እፈልግሻለው››
‹‹ምነው ልጄ ምን ሆንሺብኝ..?››
‹‹መቀባጠሩን ተይና በአስቸኮይ ኩማደሩ ቤት ነይ››ስልኩን ጠረቀመችው
ሮዝ የለበሰችውን የለሊት ቢጃማ እንኳን ለመቀየር ጊዜ ማባከን አልፈለገችም…ብን ብላ ነው ግቢውን ለቃ ወደኩማንደሩ ቤት የበረረችው ..ልጄን… ልጄን ምን አደረክብኝ....?የሳሎኑን በር በርግዳ ከፈተችና ወደውስጥ ገባች…
‹‹ምን አደረገብኝ ..?ምነ ሆንሺብኝ ..?ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ስትል ገፍትራ ከላዬ አራቀቻት….››
‹‹ይሄ የመቼ ፎቶ ነው....?››ሄለን ነች ጠያቂዋ
‹‹የቱ..? እኔጃ..››ግራ ተጋብታ መለሰች
በእጇ የያዘችውን ፎቶ ወረወረችላት .ደረቷ ላይ አርፎ ወደመሬት ወደቀ… ጎንበስ ብላ አነሳችውና ተመለከተችው..
‹‹እሺ መንም አልጀመርንም ብለሽኝ አልነበር..?››ሄለን ነች በሽሙጥ የጠየቀቻት
‹‹ያው ድሮ እኮ ነው…ግን ከተለያየን ብዙ አመት አልፎናል..?››
‹‹በቀደምለታ የመጣሽው እንታረቅ ልትይው ነበር....?››
‹‹አረበፍጽም ..ስንለያይ ተጣልተን ስለነበረ ቂም ይዞብኛል..አንቺን በማጥቃት እንዳይቀለኝ ስለፈራው ከአንቺ እንዲርቅ ልለምነው ነው…››
‹‹ኦኬ አሁን በጣም ገባኝ….ለመሆኑ ኩማደሩን እንደማፈቅረው ታቂያለሽ..?››
‹‹አታደርጊውም ልጄ..እኔ በህይወት እያለው አታደርጊውም››
‹‹አትጠራጠሪ አደርገዋለው..እንደውም ማግባት ሁሉ የምፈልገው እሱን ነው››
‹‹አረ ተይ ልጄ…እራስሽን ወጥመድ ውስጥ ለምን ትከቺያለሽ....?እሱ እኮ ውስጡ በቀል እንጂ ፍቅር የለበትም…..››
እሱ እኔን አይመለከተኝም…እንደውም እኔም አንቺን ለመበቀል ስለምፈልግ ጥሩ አጋጣሚ ነው…ለመሆኑ ምን ያል ብትበድይው ነው .. ..?ለነገሩ አንቺ አይደለሽ ምንም ብታደርጊው አይደንቀኝም….ለማንኛመው ከዛሬ ጀምሮ በመሀከላችን እንዳትገቢ ልነግርሽ ነው..አሁን የድሮ ፎቶሽን ይዘሽ ወጭልኝ…;››
‹‹በፈጠረሽ ልጄ›› እግሯ ላይ ተደፋች..
‹‹ምንም ብታርጊ ሀሳቤን አታስቀይሪኝም…ምን አልባት በአንድ ነገር..››
‹‹ምንድነው ልጄ …የፈለግሽውን ጠይቂኝ..ከዚህ ሰይጣን ራቂለኝ እንጂ ያልሺኝን ሁሉ አደርጋለው››
‹‹ያው የእኔን ጥያቄ ታውቂያለሽ… ተመሳሳይና የማይቀየር ነው…የአባቴን ማንነት ከነገርሺኝ እተወዋለው…››
‹‹አባቴን....?››ከተደፋችበት ተነሳችና መቀመጫ ይዛ ተቀመጠች
‹‹አዎ ንገሪኝ..ከእሱ እንድርቅ ከፈለግሽ ንገሪኝ››
‹‹እሺ ቁጭ በይ….ነግርሻለው››
ሁለቱም ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ
‹‹እንግዲያው ንገሪኝ ካልሽ ምርጫ የለኝም ነግርሻለው….ግን ለምትሰሚው ነገር እራስሽን አዘጋጂ››
‹‹ግድ የለሽም መግቢያውን ተይና ወደዋናው ታሪክ በቀጥታ ግቢልኝ››
‹‹ይሄውልሽ ልጄ ግማሽ ዕድሜዬን ይሄንን ታሪክ ለሌላ ሰው ይቅርና ለእኔው ለእራሴው ለመናገር ስሸሸው የኖርኩትን ነገር ነው፡፡ይሄው ዛሬ ሳልወድ በግድ ለመናገር ተገድጄያለው፡፡እስከዛሬ ነገሩን ሚስጥር አድርጌው የኖርኩት ለእናቴ ስል ነበር..አሁን ደግሞ ለመናገር የተገደድኩት ለአንቺ ለልጄ ስል ነው..ከእናቴ ስሜትና ደህንነት ይልቅ የልጄን ስሜት እና ደህንነት አስቀድሜ ነው..መቼስ አናቴ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለምታውቅ ይቅር ትለኛለች ብዬ አስባለው፡፡
ማንኛውም የሰው ልጅ በትዝታ ፈረስ ፊቱን ወደ ኃላው አዙሮ ትናንትናውን ሲያይ መዝለል የሚፈልገው ወይም አለማሰብ የሚመኘው ወይም ምነው ባልኖርኩት ኖሮ ብሎ የሚጠየፈው በጊዜዎች ክፍተት መሀከል የተከወነ ጨለማ ታሪክ ይኖረዋል፡፡የእኔን የተለየ የሚያደርገው ግን ያለፈ ህይወቴ ውስጥ የተከሰተው ጠባሳ አይደለም መሰረዝ እንዲደበዝዝ ማድረግ እንኳን የማይቻል ስለሆነ ዕድለኛ አይደለውም፡፡
ልጄ አንቺ ለእኔ ማለት የበደሌ ምልክት፤ የክስረቴ ትርፍ ነሽ፡፡ሰው ህይወቱን የሚያሳጣው …ማንነትን የሚያወድመው ነገር ከስሮ በዛው ልክ ህይወቱን የሚያለመልምለት እና ለመኖሩ ምክንያት የሆነ ነገር ያተርፋል…እኔ ማለት እንዲያ ነኝ..የነገ ተስፋዬን፤ለመኖር የሚረዳኝን ሞራሌን፤ማንነቴን አጥቼ በምትኩ ግን አንቺን አገኘው፡፡
‹‹አረ የምትይው ነገር ምንም እየገባኝ አይደለም…››መለሰችላት ሄለን
‹‹የእኔ ህይወት ለእኔም ለእራሴ ብዙ ጊዜ አይገባኝም፡፡ግን ቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ፡፡አንቺን የወለድኩሽ ተደፍሬ ነው፡፡መቼ? ገና 15 ዓመት ሳይሞላኝ፡፡ማን የደፈረኝ ይመስልሻል..?የምትወጂው አጓቴ ነው፡፡ላስተምርሽ ብሎ ከእናቴ በአደራ ተቀብሎ አዲሳባ ወስዶ ደፈረኝ ..አስረገዘኝ …››
‹አጎቴ!!!!.. አጎቴ ማለት የማዬ ወንድም … አንቺን››
‹‹አዎ አጎቴ እኔን …ያ ማለት ደግሞ አንቺ የእሱ ልጅ ነሽ… አባትሽ ነው፡፡
‹‹እኔ አላምንም…››ሄለን ምትሆነው ምትናገረው ነገር ጠፋት
‹‹ልጄ ነፍስ ካወቅሽበት ጊዜ አንስቶ አባቴ ማን ነው ?ብለሽ ስትጠይቂኝ..የተለያየ ሰበብ እየፈጠርኩ ልነግርሽ ያልቻልኩት ነገሩ ለሰሚውም ግራ ሰለሆነብኝ ነው፡፡ ልጄ እስቲ አስቢው በገዛ አጐቴ ተደፍሬ አንቺን እንደወለድኩሽ ስትሰሚ በአንቺ ሰነ-ልቦና ላይ የሚያደርሰውን መረበሽና ተፅዕኖ በምን ማረጋገጥ እችላለው? እንደእኔ ስብርብር ብትይብኝስ.?.ከሁሉም በላይ ደግሞ ይሄ ጉዳይ እናቴ ጆሮ ይሄ ዜና ቢደርስስ ?የገዛ መንትያ ወንድሟ ከመሀጸኖ ፈልቅቃ አምጣ የወለደቻትን እና አደራ አሳድግልኝ ብላ ያስረከበቻትን ጨቅላ ልጆን በድልዱም ቢላዎ ገዝግዞ እንዳረዳት እና ህይወቷን እንዳበከተባት ብትረዳ በድንጋጤ ህይወቷ ባያልፍ እንኳን ጨርቋን ጥላ ማበዶ ይቀራል ብለሽ ታስቢያለሽ…?.ለዚህ ነው ከአንቺ ጋር ስጋጭ እና ስጣላ የኖርኩት፡፡ ለዚህ ነው እራሴን እንደ ጥፋጠኛ አስቆጥሬ ስባልግ እና ስንዘላዘል በገዛ ስህተቴ እደወለድኩሽ እዲታሰብ አድርጌ ግማሽ ዕድሜዬን እንደጋጠወጥ እና እንደ አለሌ ሸርሙጣ እየታሰብኩ በመኖር እራሴን ያሰቃየውት...እርግጥ አልዋሽም ሸርሙጣ የሚለው ስም አይገባኝም አልልሽም..በደንብ ይገባኛል..፡፡ግን በሽታ ሆኖብኝ ነው፡፡ከመደፈሬ ጋር የተፀናወተኝ እኔ እራሴ የምጠየፈው እና የምፀፀትበት ክፉ በሽታዬ ነው፡፡
ልጄ እንግዲህ እውነቱ ይሄ ነው፡፡አባትሽ የምትወጂው አጐትሽ ነው..ከአሁን ቡኃላስ እሱን መውደድሽን ትቀጥያለሽ…?እንግዲህ እሱ የአንቺ ጉዳይ ነው፡፡እኔን ግን ካጠፋውት በላይ ስቀጣ የኖርኩ ሚስኪን እናት ነኝና እባክሽ ይቅር በይኝ እና ቀሪ ህይወቴን ትንሽም ቢሆን ተስፋ እንዲኖራት እርጂኝ፡፡ከእዚህ ሰውዬ ራቂ..እሱን በጣም በድዬዋለው….ሊያገባኝ ሲዘጋጅ ነው ጥዬው ወደአዲስ አበባ የገባውት ..ስለዚህ ለአመታት ሊበቀልኝ ሲጥር እደነበረ አውቃለው..እና ልጄ ….
…ሄለን ከተቀመጠችበት ተነስታ ተንደርድራ ነው እግሯ ላይ የተደፋችባት….‹‹እማዬ የምትችይ ከሆነ ይቅር በይኝ..ባክሽ ይቅር በይኝ››እየነፈረቀች ተማፀነቻት
ሮዝ ከገባችበት መደንዘዝ ውስጥ እንደምንም ነቃችና እሷም ተከትላት ቁጢጥ በማለት ልጆን ከተደፋችበት አንስታት አቀፈቻት… አገላብጣ ሳመቻት ‹‹ልጄ ….ልጄ

..ልጄ››ተንሰፈሰፈች
‹‹እማ ..ይቅር አልሺኝ?ሳላውቅ ነው ሳመናጭቅሽ የኖርኩት..ሳላውቅ ነው ሀጥያትሽን ሳበዛው የኖርኩት››
‹‹ያንቺ ጥፋት እኮ አይደለም.. አታልቅሺ ልጄ››
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አባ ሽፍንፍንን እንደማንኛውም እስረኛ በእለቱ በተለያየ ወንጀሎች ተጠርጥረውም ሆነ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ከታሰሩ 13 እስረኞች ጋር ነው ያሰሯቸው.. በእለቱ ብዛት ያላቸው የከተማዋ ኑዋሪዎች ወሬውን ሰምተው እሳቸውን ለመጠየቅ በፖሊስ ጣቢያ ቅጥር ግቢ ሲያጨናንቁት ነው ውለው ያመሹት..፡፡በእለቱ ወደ አመሻሹ ላይ ሁለት ሰዋች እርስ በርስ በመደባደብ አንድ ሰው ደግሞ ሌላ ሰው ደግሞ በስርቆት ወንጃል ከእስረኞቹ ጋ ተቀላቅለው 13 የነበሩት እስረኞች ቁጥር ወደ 16 አድጎ ጠባቧ የማቆያ ክፍል ተጨናንቃለች…ለአባ ሽፍንፍን ግን እስረኞቹም በማክበር የተለየ እንክብካቤ ነበር ያደረጉላቸው…ፍራሻቸውን በስርአት የሚዘረጉበት በቂ ቦታ ሰጥቷዋቸዋል…ሌላው ተደራርቦ ና ተጨናንቆ ሲተኛ እሳቸው ግን ለቀቅ ብለው ባልተጨናነቀ ሁኔታ ነበር ጀርባቸውን ያሳረፉት…በእለቱ ያጋጠማቸውን ነገር እና የሚያስከትልባቸውን ውጣ ውረድ ሲያሰላስሉ እንቀልፍ አልወሰዳቸውም ነበር…ከለሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ከእሳቸው በቅርብ ርቀት የተኙ ሌሎች እስረኞች ሲንሾካሾኩ ሰሙ… ምንድነው ብለው የለበሱትን አልጋልብስ ከጭንቅላታቸው ገለጥ አድርገው ለማየት ቀና ሊሉ ሲሉ አንድ እጅ ጉሮሮቸውን ፈጠረቃቸው ..ሊወራጩ እግሮቻቸውን ሲያንቀሳቅሱ ሌላው ጠንካራ እጅ በፍጥነት እግሮቻቸውን ከመሬቱ ጋር ሰፍቶ አስቀራቸው፡፡ የሚፋለሟቸውን ሰዎች ማንነቱ ጨለማ በመሆኑን መለያት አልተቻላቸውም…ጉሮሮቸውን ፈጥርቆ የያዘው አፋቸውንም አፈናቸውና ወደ ጆሮቸው ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ ‹‹አንተ የተረገምክ ቄስ …ላፈሰስከው ወንድማችን ደም ቅጣቱን እየከፈልንህ ነው…. እርስ በርሳችን ተደባድበን አንተን ተከትለን የታሰርነው አውቀን መታሰር ፈልገን ነው ….አንተን ለማጥፋት ..ወንድማችን እንዳያያት የፈረድክበትን የነገዋን ፀሀይ አንተም አታያትም›› አባ ድምጽ አልባ መቃተት ቃተቱ…ግን እራሳቸውን ማትረፍ አልቻሉም ቀስ በቀስ እየዛሉ…እየዛሉ …መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ ተሸነፉ …እጅሰጡ…..እስትንፋሳቸው ተቋረጠች
ጥዋት የአባ ሽፍንፍን ከተኙበት እንደተሸፋፈኑ ከእንቅልፍ ሊነሱ አልቻሉም ነበር…ሲቀሰቀሱ ባለመስማታቸው ከላያቸው ላይ ሸፈናቸውን አልጋ ልብስ ሲገልጡት…ከእነ ግርማ ሞገሱ ያለውን የአባን የፊት ገጽ አልነበረም የተገኘው…ለመጀመሪያ ጊዜ ፊታቸው ሙሉ በሙሉ በግልጽ ለእይታ ታጋልጦ ነበር…ጉድ ተባለ በማረፊያ ክፍል ውስጥ ጩኸት እና ትርምስ ነገሰ ..ፖሊሶች አመጽ የተነሳ መስሎቸው መሳሪያቸውን አቀባብለው እና ደቅነው ቆመጣቸውን ቀስረው አካባቢውን ከበቡት…የአባ ሽፍንነፍን እሬሳ በአስቸኮይ ተሸፋፍኖ ወጣ ..ለምርመራም ወደ ሆስፒታል ተላከ ..ይሄንን የሰማው የከተማው ህዝብ ፖሊስ ጣቢያውን ወረረው ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ስምንት ፖሊሶችን የጫነች ፒካፕ መኪና የፍርድ ቤት የፍተሻ ትዕዛዝ ይዛ ኩማንደር መሀሪ ቤት ደረሰች፡፡ አራቱ ፖሊሶች በፊትለፊት በኩል ያለውን የአባ ሽፍንፍን ግቢ ሲያንኮኩ የከፈተችላቸው ሮዝ ነበረች…የትዕዛዝ ወረቀቱን አሳዬት እና አልፈዋት ወደ ውስጥ ገቡ ጠቅላላ የአባ ሽፍንፍን ቤትን በርብረው ሊፈትሹ ወደ ውስጥ ገቡና ከሳሎንጀመሩ
የተቀሩት አራቱ ፖሊሶች ደግሞ በጀርባ በኩል ያለውን የኩማደር መሀሪን አጥር ጊቢ አልፈው ደረጃውን በመጠቀም ወደ ላይ ወጡ …ሲያንኮኩ ሄለን ነበረች የከፈተችላቸው…እነሱም የያዙትን የፍተሸ ትዕዛዝ ወረቀት አሳዬት እና ገፍተዋት ወደ ውስጥ ገቡ ምድር ባለው የአባ ሽፍንፍን ቤት የሚደረገው ፍተሸ እና እላይ ፎቅ ላይ የሚደረገው የኩማደር ቤት ፍተሸ ከ30 ደቂቃ ቡኃላ ከአባ ሽፍንፍን የፀሎት ቤት ወደ ላይኛው ኩማደር ወደሚኖርበት ፎቅ የሚያስወጣ መሾለኪ አግኝተው አንዱ ፖሊስ ወደ ላይ ለመውጣት መሰላል ተጠቅሞ በመውጣት ለመሹለክ ጭንቅላቱን ሲያስተካክል እላይ ኩማደር መሀሪ ቤት ከነበሩት ፖሊሶች አንድ ደግሞ በዛው ተመሳሳይ መተላለፊያ ወደታች ሊወርድ እግሩን ሲያስቀድም ተገጣጠሙ
አባ ሽፍንፍ....ኮማንደር
ኮማንደር..አባሽፍንፍን አንድ ሰው ሆነው ተገኙ
💫ተፈፀመ💫
ስለነበረን ቆይታ አጅግ በጣም አመሰግናለው🙏

#በሕይወት_አንድ_ጥግ
ትላንትና እሁድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውየ መጣና በሩን አንኳኳ…… እኔ ፣መአዛና የመአዛ እናት ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር ! ሮዛ ጎረቤቴ አብሮ አደጌ ናት ! አስቴር ደግሞ እናቷ . . .ለእኔም እናቴ ማለት ነች ኧረ …የእኔና የሮዛ ፍቅር ለብቻው ነው ከህፃንነታችን ጀምሮ ንፁህ የሆነ ምንም ፆታዊ ክጃሎት ውል ያላለበት ፍቅር እንዳለን አገር መንደሩ ምስክር ነው … እህቴ !!
ሮዚ ዩኒቨርስቲ ቆይታ ለእረፍት መምጣቷ ነበር ፡፡ የሚገረመው እናቴና የሮዛ እናት አስቴር የመረረ ጥል ያላቸው ኩርፈኞች ናቸው ! ግን እኔም እነሮዛ ቤት ሮዛም እኛ ቤት ልጆች ነን ! ስለእናቴ አስቴር ፊት ከተነሳ …‹‹ውይ ውይ የሷን ነገር አታንሳብኝ ጋኔል ….ምን ያረጋል እንዳንተ እይነት መለአክ ወለደች ››ትለኛለች እናቴን ለእኔ ታማልኛለች ! ‹‹ ቱ ሰው አይደለችምኮ !›› ትላታለች ! በእናቴ የመጣብኝን ሰው ይቅር ብየ አላውቅም አስቱ ግን ስትረግማት እንኳን ምርቃት የሚመስለኝ ለምን እንደሆነ እንጃ !
እሮዛ እኛ ቤት ስትመጣ ደግሞ እናቴ በተራዋ ለሮዛ ስለእናቷ ክፋት ጋኔልነት ትነግራታለች ‹‹ እናትሽ ….ምን እናት ናት እች እቴ …የሰይጣን ቁራጭ ከጥላዋ የተጣላች …እኔ ለሷ እንዲህ አልነበርኩም ….›› እያለች
እኔ እና ሮዚ እናቶቻችንን ረስተን እብድ ያለ ጓደኝነታችንን ቀጥለን አለን ! የሮዚ አባት በሂወት የሉም ! ‹‹ችግር የለም አባባን እንካፈላለን ›› ትላለች አንዳንድ ቀን ስንቃለድ አባባ የምትለው የእኔን አባት ነው ! ‹‹እናቶቻችን አባባን እንዳይካፈሉ ብቻ ›› እላታለሁ ‹‹ባለጌ ስድ ›› ብላ ትግል ትጀምረኛለች ቀይ ፊቷ በሃፍረት ይቀላል ! ሮዛ ቆንጆ ናት ግን ምኗ ነው ቆንጆ ቢባል አላውቅም እንዲሁ ጠቅለል አድርገው ሲመለከቷት በጣም ቆንጆ የምታሳሳ ኑሮ ምችት ያላት ልጅ ነች ! አንዳንዴ ሰውን ስንወድ ፍቅራችን የወደድነው ሰው ላይ ጎዶሎውን ሞልቶ ያሳየናል መሰል ሮዛ ጉድለት የላትም ለእኔ ! አዎ #ፍቅር አፍንጫ ፀጉር አይን ቁመት ጥርስ ከንፈር ሳይሆን አይቀርም ! ለነገሩ የሚጠይቃት ጎረምሳ ብዛትም ለሳቢነቷ ምስክር ነው !
ሮዛን የጠየቁትን ጎረምሶች እኔ እና ሮዚ የእለት ውሎ መመዝገቢያችን ላይ እንመዘግብ ነበር ! የሚገርመው ‹‹ዳይሪያችን›› አንድ ነበረች ሁለታችንም ውሏችንን ምንመዘግብባት ! ለሮዛ የሚላክ የፍቅር ደብዳቤ አብረን ነው የምናነበው እኔም ለሴት የምልከው አብረን ፅፈን እናውቃለን ! ታዲያ ሮዛ ብትሞት ለፍቅር አትሸነፍም ትምህርቷ ላይ አትደራደርም . . . ልቧ የገባም ወንድ የለም ‹‹ወንዶች ጅል ይመስሉኛል›› ትላለች አባቷ እናቷ ላይ ያደረሰው በደል ሁሉ (ነብሱን ይማረውና ) መጥፎ ጠባሳ ጥሎባታል ! አባቷ አይጠጣ አያጨስ ግን እናቷን መቀጠቀጥ ሱስ የሆነበት ሰው ነበር ጥርሷን ሁሉ አውልቆት ወርቅ ጥርስ አስተክሎላታል ! ሮዛ ልብ ውስጥ የነበረውን ወንድን የመሻት ተፈጥሯዊ ስሜትም ነቅሎ ባዶውን ትቶታል !
(አሁንም ነብሱን ይማረውና ግን የሚምረው አይመስለኝም )
እና ……ትላንትና እሁድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውየ መጣና በሩን አንኳኳ…… እኔ ፣መአዛና የመአዛ እናት ቡና ተፈልቶ ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር ! እንዳጋጣሚ ለበሩ የምቀርበው እኔ ስለነበርኩ ተነስቼ በሩን ከፈትኩ ! ከተወለደ ጀምሮ ዛሬ ገና የዘነጠ የሚመስል ሙሉ ግራጫ ልብስ የለበሰ ቀጫጫና ረዥም ሰውየ በሩ ላይ እየተሸቆጠቆጠ ቁሟል ! ሰውየው ሙሉ ልብስ ቢለብስም ለምን እንደሆነ እንጃ ሙሉ ልብስ የለበሰ አይመስልም . . . መቼም ሕይወት በሰወች አይን ፊት ስታጎለህ እንኳን ሙሉ ልብስ ሙሉ ብርጌድ አሰልፈህ ብትመጣ ግርማ ሞገስ የሚባል ነገር አይጠጋህም ! ቅልል ትላለህ ! እማማ ሩቅያ እንደሚሉት ‹‹ቀድረ ቀላል ›› ትሆናለህ !
ሰላም አልኩት … እየተሸቆጠቆጠና ዳማከሴ እንደሚያሽ ሰው እጆቹን አርሰ በእርስ እያፋተገ ሰላምታየን ከወገቡ ጎብጦ መለሰልኝ ! ከርዝመቱ እና ከእንቅስቃሴው ፍጥነት የተነሳ ለሰላምታ ከወገቡ ሲታጠፍ ከላይ ተምዘግዝጎ የመጣ የሆነ ወገቡ ላይ ተሰብሮ የሚወድቅ ባህር ዛፍ ነበር የሚመስለው !
‹‹ይ….ሄ የነሮዛ ቤት ነው አይደል …›› አለና እራሱ መልሱን መለሰው ‹‹አዎ ነው አውቀዋለሁ ›› አነጋገሩ የሚርበተበትና ከአፉ የሚወጡት ቃላት በጠባብ በር እንደሚወጣ ብዙ ህዝብ የሚገፋፉ የሚተሸሹ ይመስላሉ ዝም ብየ ስመለከተው ‹‹ እ. … የሮዛ እናት ይኖራሉ ወይም አባቷ ›› አለና መልሶ ለራሱ ‹‹ አውቃለሁ አባቷ እንኳን በህይወት የሉም …ግን እናቷ . . . ›› ተርበተበተ
‹‹እናቷ አለች ›› አልኩት
‹‹ልግባ ? ›› ሲል ገነት በር ላይ የቆምኩ መልአክ የሆንኩ እስኪመስለኝ ወደቤቱ ውስጥ በጉጉት አይኖቹን ልኮ ለማየት እየሞከረ ለመነኝ (ምን የተቀመጠ መስሎት ይሆን እነዲህ የጓጓው )
‹‹ግባ ›› ብየ በሩን ለቀኩለት ገባ !! አረማመዱ የሆነ የሚጮህ አይነት ነው የሚራመድ ሳይሆን በአንድ እግሩ ብቻ የሚዘል አይነት ላይ ታች ያረገርጋል …. እድሜው ሰላሰ አምስት ቢሆን ነው ! የሮዛን እናት ( አስቱ ነው የምንላት) በሁለት እጁ ሰላም ብሎ ወደሮዛ ዞረ እርሷንም በሁለት እጁ ሰላም አላት ! ሲመለስ የእኔን እግር ረገጠና ተንገዳግዶ ጠረንጴዛ ጫፍ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ባዶ ስኒ ከነበለው ! ስኒው ስር ቀርቶ የነበረው የረጋ የቡና ዝቃጭ ምንጣፉ ላይ ጥቁር ደብ መስሎ ተረጨ ! (ይሄ ሰው መርዶ ይዞ ነው እንዴ የመጣው ምን ያደናብረዋል )
ከ አስቱ ፊት ለፊት ተቀመጠ ! ሁላችንም ምን እንደሚል ለመስማት አይን አይኑን እናየው ጀመረ ‹‹ እ …ሰላም ነዎት ታዲያ እትየ ….አስቴር ›› አለ
‹‹እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ ›› ፊቷ ላይ ‹‹የት ይሆን የሚያውቀኝ ›› የሚል ግርታ ይታያል በፈገግታ ልትሸፍነው ብትሞክርም አልተሳካላት !
‹‹ልጆች ሰላም ናቸው ….ማለቴ ልጅዎት …አዎ አንድ ልጅ ብቻ ነች ያለችዎ ›› አለ ወደሮዛ አየት አድርጎ ያጠናውን ነበር የሚናገረው ያስታውቃል …..ፊቱን አልቦት ነው መሰል በመዳፉ አንዴ ሞዠቀው እና መዳፉን አየት አድርጎ በኮቱ እጅጌ እንደገና ግንባሩን ጠረገው !
‹‹ደህና ናት ›› አለች አስቱ እናም ኮስተር ብላ አየችኝ ! ትካሻየን በቀስታ ወደላይ ሰበኩት … እርሷ ያየችኝ ‹‹ማነው›› ማለቷ ሲሆን እኔም በትካሻየ ምላስ ‹‹እኔጃ ›› አልኳት ለትንሽ ደይቃ እንግዳውም አቀርቅሮ አኛም እንግዳው ላይ አፍጥጠን እንደቆየን እንግዳው ተናገረ
‹‹አንተ አብርሃም ነህ …እዚህ ጎረቤት ያለከው ልጅ አይደለም እንዴ ›› አለኝ
‹‹አ . . .አዎ ››
‹‹ያው ለሮዛ ወንድሟ ማለት ነህ …ማዘርም ጋር ትቀራረባለህ ያው ልጃቸው ማለት እኮ ነህ ››
‹‹አዎ ያው ልጀ ማለት ነው ›› አለችው አስቱ
‹‹ጥሩ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ስለምናወራ ላረጋግጥ ብየ ነው ›› አለ ወደአስቱ በፈገግታ እየተመለከተ . . .ፈገግታው ይጨንቃል ከንፈሮቹ ወይ በደንብ አይከፈቱ ወይ አይገጠሙ ሄድ መለስ እያሉ ይንቀጠቀጣሉ ! በማጭድ የተጋጠጠ የሚመስል ፂሙ ቅሪቱን ጉንጩ ላይ ዘርቶት በሽተኛ አስመስሎታል … ጥላሸት የተዘራበት አጥንታም ጉንጭ ! ደግሞ እኮ ሲያረጉ አይቶ ‹ኦ › ቅርፅ ! አፉ በፂሙ ተከቦ ሲታይ በኮሸሽላ ዙሪያውን የታጠረ የደረቀ የውሃ ጉድጓድ ይመስላል ! ወቸ ጉድ ምን ሊል ይሆን . . .ጭንቀት ገደለኝ
‹‹ የመጣሁት ሌላ የሚመጣልኝ ሰው ስለሌለ ነው .ላቀው እባላለሁ .›› አለና ድንገት ቁሞ አስቱን ሰላም አላት እኔንም ሮዛን ግን ረሳን ….‹‹ እ….ያው የመጣሁት መጥቼ መናገር ስላለብኝ እና

👍3🔥1
. . . ›› ስልኩ ጮኸች ልክ እንደአይጥ ነበር ፂው ፂው እያለች የጮኸችው …. ገና ሳያወጣት ስልኳን ‹‹ቀድረ ቀላል ›› መሆኗን አውቂያታለሁ … እጁን እስከክንዱ ሱሪው ኪስ ውስጥ ከተተና ዙሪያዋን በፕላስተር መቀነት የተተበተበች ቀይ ስልክ አወጣ (ይሄው እንዳልከዋት ናት ካልኳትም ትብሳለች) …. ስልኳን ከኪሱ ሲያወጣት ጩኸቷ ተቋረጠ … የሆነ ነገሯ ኪሱ ውስጥ ስለቀረ እንደገና ኪሱን ፈትሾ ክዳኗንና ባትሪዋን አወጣ ተበታትና ነበር የወጣችው . . .በጥንቃቄ ገጣጠመና ኮቱ ኪስ ውስጥ አስቀምጦ ወሬውን ቀጠለ
‹‹ ….እና የመጣሁት መጥቼ እርሰዎን ለማግኘት ነበር…..ያው አገኝቼዎታለሁ ›› ብሎ ፈገግ አለ ! አስቱን እንዳገኛት ለራሱ አላመነም መሰል !
‹‹አዎ አግኝተኸኛል …ከየት ነው ግን የመጣሃው እንደው ዘነጋሁህ መሰል አላወኩህም ›› አለች በጨዋነት
‹‹አ ……ይ አልዘነጉኝም ….ድሮም አያውቁኝም ›› አለ
‹‹ኧረ ….እንደዛ ነው ? …እምምም ታዲያ እኔን እንዴት አወከኝ ››
‹‹አላወኩዎትም . . . ያው ልተዋወቅዎት ነው የመጣሁት ›› እልሄን ነበር ያስጨረሰኝ ….ኤጭጭ ወደዚያ ማን እንደሆንክ ተናገር ›› ማለት አመሮኝ ነበር ! እግዜር ይይለት መንዛዛቱን ቀጠለው
‹‹ ሰው እኮ ደፍሮ ካልተዋወቀ መቸስ …››
‹‹ልክ ነው ›› አለች አስቱ እንዲናገር ለማደፋፈር እንጅ ያላለቀ አረፍተ ነገር መቸም ቢሆን ልክ ሁኖ አያውቅም !
‹‹የመጣሁት . . . ለዚህ ነው እኔም ››
‹‹ለምን ? ›› አለች አስቱ ገርሟት
‹‹ያው ለመተዋወቅና ከተዋወቅን በኋላ አንዳንድ ቤተሰባዊ ጉዳዮችን ለመነጋገር ››
‹‹ይሄው ተዋወቅን እስቲ የመጣህበትን ንገረኝ ›› አስቱ ትንሽ ኮስተር ያለች መሰለኝ
‹‹የመጣሁት ያው ሮዛን …ማለቴ ልጅዎትን ሮዛን ላገባት ስለፈለኩ እርስዎ እንዲፈቅዱልኝ ነው …. እባክወትን እማማ አስቴር ›› ብሎ ተንደርድሮ አስቱ እግር ስር ተደፋ …ቀስ ብየ ወደ ሮዛ ዞርኩ ሶፋ ላይ ሳይሆን ኤሌክትሪክ ወንበር ላይ እንዳስቀመጡት የሞት ፍርደኛ ደርቃ ቀርታለች ፡፡ ሙልት ያሉ ቀይ ጉንጮቿ ገረጥተው አይኗ ባዶ ጠርሙዝ መስሏል !
‹‹ኧረ ተነስ ተነስ የኔ ልጅ›› አለች አስቱ ምኑም ምኑም እንዳልጣማት ታስታውቃለች ! ልጁ ተነስቶ ቆመና ‹‹እሽ አሉኝ ማዘር›› ሲል በጉጉት ጠየቀ
‹‹አክብረኸኝ ስለመጣህ ተባረክ ….ግን አሁን ዘመኑ ሰልጥኗል ማነህ …….››
‹‹ላቀው›› አለ እራሳችሁ ተነጋገሩ እዛው ›› ብላ ሮዚን አጋፈጠቻት
ሮዚ በርግጋ ተነሳች ከዛም ‹‹ ምናይነቱ ነው ›› ብላ ወደገዋዳ ገባች
አስቱ ግራ ተጋብታ እንዲህ አለችው ‹‹ እንደው ወጉም በሃሉም እንዲህ አልነበረም … ቢጠፋ ቢጠፋ ያንተ ቢጤ እንኳን አንድ ሁለት ሰው ይላካል . . .ሰተት ተብሎ ነውር እኮ ነው ››
‹‹አስቤ ነበር . . .›› አለ አንገቱን ደፍቶ ግን ሰው አጣሁ ! ዘመድም የለኝም … እና ደግሞ የምነግራቸው ሰወች ሁሉ ‹‹ለራስህ ሳትሆን ሚስት …ጠግበህ ሳትበላ ሌላ እዳ መጨመር እያሉ አሸማቀቁኝ ….አስቤ ነበር ሰው የለኝም …..አስቤ ነበር ሮዛን ስለወደድኳት ነው …እንደው እሽ ቢሉኝም ቀጥሎ ምን አባቴ አደርግ እንደነበር እንጃ እራሴ እሷን በማሰብ ከሚፈነዳ እንዲህ ነገሩን አፈንድቸው ይለይለት ብየ ነው ….ሮዛን እወዳታለሁ ሮዛ ቀይ ቆንጆ ልጅ ናት ….. ሰው ለራሱ ሽማግሌ ቢሆን አልኩ ….ትክክለኛው ሽማግሌ እኔ ነኝ የሮዛን ፍቅር ምን ያህል እንዳለምኩት የሚያውቅ ሽማግሌ ማን አለ ….በማድርባት የፈራረሰች ቤት ብርሃን የዘራችው ማናት ሮዛ ናት ….ሮዛ የእርሰዎ ልጅ …….ማንም እንደሰው በማያይብኝ አገር እንደጥራጊ በተጣልኩበት መንደር ሰው መሆኔን ለልቤ የነገረው የሮዛ ፍቅር ነው …..ሮዛ የእርሰዎ ልጅ ›› ወደበሩ መንገድ ጀመረ አነጋገሩ ተረጋግቶ ነበር ፍርሃቱ ሁሉ ጠፍቶ !
‹‹… መቼስ የፈጣሪ ትልቅነት ይሄን ፍቅር ሰው እንኳን ቀና ብየ የማላይ ትንሽ ሰው ላይ ጥሎት ሰው ፊት አቆመኝ …እንደው ሰው ልሁን ብየ እንጂ እሱስ እሽ ቢሉኝም ሮዛን የት እንደምወስዳት እንጃ … ሮዛ እኮ … አራት አመት ከልጅነቷ ጀምሮ አስራ ሁለተኛ ክፍል እስክትሆን . . . ዩኒቨርስቲ እስክትገባ ስወዳት ስወዳት ስወዳት ከረምኩ . . .
አልተማርኩም ..... እንደው የእግዜር ነገር እኔ ላይ ይሄን ፍቅር ቢጥለው እኔው ሽማግሌ ሆንኩ …ሆድህን ሳትሞላ ይላሉ ፍቅር በሆድ ይመስል ለራስህ ሳትሆን ይላሉ ምንድነው እኔ እኔ ማለት ?….ለራስ ከሆኑ በኋላ በተረፈው ይፈቀራል እንዴ . . . እራስን ጥሎ እንጅ ለሌላው መኖር … ሮዛን ….የእርስዎን ልጅ ወድጄ ስንት አመት ሙሉ ……ዘመድ የለኝም ሮዛን እያሰብኩ ሽ እልፍ ሁኜ ኖርኩ . . . ማንም አይደለሁም ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ይባል እንጅ ቅሉ ስለራሴ አብዝቼም አሳንሼም የምቆርሰው የሌለኝ ኑሮ ቆራርሶ እዚህ ያደረሰኝ ከንቱ ነኝ …ሮዛ የአንቱ ልጅ ግን በሂወቴ ውስጥ ትልቋ ቁራሽ ትልቅ ድርሻየ ነበረች ! ሮዛ የአንቱ ልጅ . . .
‹‹ . . . ሳያት እኮ ልቤ ውስጥ ገነት ይፈጠራል … ፍቅሯ እንደግዜር የገነቱ አስተዳዳሪ …መንገዱ ምንድነው የሚነጠፍበት …ሮዛ ስታልፍ ቢጫ ይሆናል … ሮዛ ስትስቅ በደስታ አለቅሳለሁ እጆቿ እንደሩቅ አገር ህልም ናቸው እግሮቿ … ደህና ዋልሽ አልከዋት አንድ ቀን አየት አድርጋኝ በዝምታ አለፈች …..አየችኝ አይኖቿ አዩኝ ቢያንስ የምታይ ሰው ነኝ በክፉም ይሁን በደግ መታየት መኖርን ነው የሚገልፀው ሮዛ አየችኝ አይኖቿ ካለመኖር ፈውሰውኝ ይሄው አለሁ ….›› አለና በሃሴት ፈገግ አለ ከንፈሮቹ አልተንቀጠቀጡም በነፃነት ፈገገ !
ከተቀመጠበት ተነሳና ከቤት ወጣ ሲወጣ አንዴ የበሩ ጉበን አናቱን ገጨው …. ደህና ዋሉም አላለ ! ተከትየው ወጣሁና በሩ ላይ ቁሜ በግርምት አየሁት . . .የማይሰማ ነገር እያነበነበ በጣም የሰፋው ሱሪው እጅግ በጣም የሰፋበት ኮቱ እየተርገበገቡ እየተውለበለቡ …..ሆድ የባሰው አገር ባንዲራ መስለው …..ወደታች ወረደ እየተጣደፈ . . . ከሩቅ ሳየው ከኋላው አሳዘነኝ ! ከዛ በኋላ እስከማታ እኔም ሮዛም አስቱም ስለዚህ ጉዳይ አንዲትም ነገር ትንፍሽ አላልንም በየፊናችን እያሰብነው እንደነበር ግን አያጠየይቅም !
ማታ ወደቤቴ ስሄድ አስቱ ሮዚ ሸኘችኝ እንደሁል ጊዜው እኛ ግቢ በር ላይ ቁመን ከላይ ጨረቃ ከታች የነፍሳት ሲርሲርታ እና የንፋስ ፉጨት ማየለበት ጨለማ ውስጥ ሮዛ ለስለስ ባለ ድምፅ እንዲህ አለችኝ ‹‹አብርሽ የቅድሙ ሰውየ አሳዘነኝ ሙሉ ቀን ሌላ ነገር ማሰብ አልቻልኩም . . . ››
‹‹እኔስ ብትይ ››
‹‹ግን እዚህ ሰፈር አይተኸው ታውቃለህ እንዴ ››
‹‹እኔጃ አላስታወስኩትም ›› ዝምምምምምምምምምመምምምም
ምምምምምምምምምምምምም ዛፎች ይንኮሻኮሻሉ ነፍሳት ሲር ሲር ፂው ፂው ይላሉ …ጨረቃ እንደትልቅ የቅቤ እንክብክብ ወዛም ብርሃኗ በእኛ ላይ እየቀለጠ ፍስስስ ይላል …..የጨለማ ድርቀቱን እያረሰረሰ …
‹‹ ቁመቱ ደግሞ ሲያምር ›› አለች ሮዛ ልስልስ ባለ እንደጨረቃ በሚቀልጥ ድምፅ ….. ለመጀመሪያ ጊዜ ወንድ ስታደንቅ ሰማሁ !
💫ተፈፀመ💫
🔘አሌክስ አብርሃም🔘

👍1
#የሆድና_የልብ_ድርቀት
:
#ድርሰት_በአለመየሁ_ገላጋይ
:
:
ያን ሰሞን ክፉኛ ሆዴ ተቆልፎ፣ጉሮሮዬ ከእህል ተኳርፎ፣ነፍሴን ጠኔ ሊነጥቀኝ ከወደ ሆዴ በድን አደረገኝ።ከደረቴ ዝቅ ብሎ ከብሽሽቴ ከፍ ብሎ ሞቼ ነበር ማለት እችላለሁ።እንቅስቃሴ የለ፣ድምፅ የለ፣እህል ቤቴን ምን ነካብኝ?
ሐኪም ዘነድ ሄድኩ ።
በአፉ አልቻልኩም ማለት ሲቀረው ጥዬ ሄድኩ።
የሐበሻ መዳኒት ጀምር የሚል ምክር ተከትዬ የሚከብድ ደጃፍ ቆረቆርኩ ። አጭር መዳኒተኛ ሆዴን በጣቱ ሲነካው ኮንክሪት የተሞላ የፍየል ስልቻ ምስጋና ይንሳው ።
<<ግንበኛ ነውዴ የፈጠረክ?>>ያለኝ መሰለኝ ሲያየኝ ።
<<ግንበኛ ተጠናውቶኝ እንደሆነ እንጂ እንደማንኛውም ሰው የፈጠረኝስ አናጢ ነው>>
ልለው ከጀለኝ ።
መዳኒት አዋቂው ሰላቢ ሳይሆን አይቀርም፣ ስበላ የኖርኩትን ሁሉ ጠየቀኝ ።
<<ምንም!>>አልኩት
<<የምትጠጣውስ?>>
<<ምንም! አንዳንዴ ጠጅ>>
<<ለመሆኑ የምትበላው ነገር አለህ ? >>
<<ባይኖረኝማ ገላገለኝ ነበር>> አልኩት
<<ብቻ ከምግቡ ጋር እየተያየን እናድራለን>>
<<አይነጥላ ነው>>
<<እ?>>
<<አይነጥላ ነው>>
<<መድሀኒቱ ማርከሻው ምንድን ነው?>>
<<ሆዳም>>
<<እ?>> የሰደበኝ መሰለኝ ።
<<ሆዳም ሰው ካለህ ቤትህ ማስቀመጥ። እንዳይበላ ለሚያደርግ አይነጥላ መድሀኒቱ ብዙ የሚበላ ሆዳም ነው።>>
በአይነ ህሊናዬ ሆዳም አሰብኩ የለም። በፊት የሆዳም አገር የምትመስልህ ኢትዮጵያ ለመድሀኒትነት......
መዳኒተኛው በሙንጭርጭር ፁሁፍ የመድሀኒት ማዘዣ ፃፈለኝና
<<ከዚህ ዝቅ ስትል አረቄ ኮማሪት አለች >>
<<አረ ደንበኛዬ ናቸው>>
<<ጥሩ ይሄንን ወረቀት ለሷ ስጣት >> አለኝ
የተጠየቁትን ሂሳብ ከፍዬ ወደ ኮማሪቶ ሄድኩ። ሶስት ቡትሌ አረቄ ፣በቀን ሶስት መለክያ ፣ ጧት አንድ ፣ ከምሳ በኋላ አንድ፣ ማታ አንድ ብሎ ሳይፅፍልኝ አልቀረም ። የተጠቆምኩበት ቤት ሄጄ ደጃፍ ላይ ቆምኩ።
<<ግባ፣ ግባ፣ ግባ፣...>> ተባልኩ ልጠጣ የመጣው መስሎቸው። ኮማሪቶን ጠቅሼ የተሰጠኝን ወረቀት ወደእሶ አስተላለፍኩ። ኮማሪቷ
ወረቀቱን አንብባ አንዲት ደዘደዘ ሴት አስረከበቺኝ።
<<ምን ላድርጋት ?>>
<<እሷ ስትበላ እያት>>
ሃምሳ ብር ከፍዬ ይዣት ወደ ቤት ሄድኩ ።
ይቺ ሴት እንደነቀዝ እህል ቦርቡራ ውቅር አበያተ ምግብ የሰራች ተአምረኛ ነች ።
ስትበላ ዶሮ የምታጥብ ትመስላለች። ትሰቀስቅና፣ቸፍ ቸፍ አድርጋ ወደ አፎ ትወረውረዋለች።ምግቡን መሬት ላይ አለማንጠሯ
እንጂ ትእይንቱስ የቅርጫት ኳስ ነው።
የእኔ ስራ ፈዞ ማየት ሆነ ።
እንሆ ከሆድ ድርቀት ወደ ሆዳም ድርቀት ተሸጋገርኩ ።በቀን ሶስት የነበረውን የአይነ ጥላ መግፈፍ ፕሮግራም በቀነሰ ስድስት ጊዜ አሳደገችው።
<<ቻይና የተገኘው ነገር ሁሉ ይበላል >> ሲባል ከሰማች
<<እዚያ ውሰደኝ >> ትለኛለች
ቀኝ እጇን ቁርጥማት ካመማት <<በምን ልበላ ነው ?>> እኔ ሰው አጉርሶ አያጠግበኝም >>እያለች ታለቅሳለች ።
<<አፄ ዮሐንስ ሲነግሱ 5 ሺህ ሰንጋ ተጥሎ ነበር>> ከተባለች፦
<<ያኔ ብወለድ ኖሮ >> ትልና ሎተሪ ለአንድ ቁጥር እንዳመለጠው ሰው ትቆጫለች ።
በአስራ አምስተኛው ቀን ይዣት ኮማሪቷ ጋር ሄድኩ
<<አይነጥላህ ለቀቀህ?>> አለችኝ ኳማሪቷ
<<እጅግ በጣም>> አልኩ ሴትየዋን ወደ አረቄው ቤት እየገፋሁ።
<<አሄሄ አልተሻለህም። ቢሻልህ ኖሮ ትሻማት ነበር ከተሻማሀት እሷ ስለማትወድ አኩርፋ እራሷ ትመጣ ነበር። ስለዚህ እስኪሻልህ አንተ ጋር ትሁን >> ብላ መለሰችኝ። 😳
አስተያየት ካሎ @atronosebot አድርሱን።

#የትንሽ_ትልቅ_ፀብ
<<ተከራይተህ ነው?>> አለኝ።ስድስት አመት ቢሆነው ነው።
<<አዎ>> ሁኔታው እንዳዋቂ ያሽቆጠቁጣል ።
<<ዘልዛላ ሰው ነው ቤት መስራት ሲገባው የሚከራየው ትላለች እናቴ>>
<<እናትህ ልክ ናቸው >>አልኩ በአፌ።በሆዴ ግን ባለጌዋ እናትህ ሳይሆኑ አይቀሩም።
<<ዘልዛላ ነህ?>>
<<ውጣ፣ እቃዎቹን ላዘገጃጅ።>>የተነጠቀ የታላቅነት ስፍራዬን ላስመልስ ሙከራ አደርኩ።
<<ዘልዛላ ግን ምንድን ነው?>> እሱም የተነጠቀ የትንሽነት ስፍራውን ለማስመለስ እየጣረ ይሆን?
<<አላውቅም፣ወደ ውጭ ፣ ያለኝ ጊዜ ትንሽ ነው። ቶሎ እቃዎቹን ቦታ ቦታ ላሲዛቸው።>>
ወጣ፣ ከቤቴ። ከህይወቴ ማስወጣት እንዳልሆነልኝ ግን አንዳች ነገር ነግሮኛል። በነጋታው ጠዋት አንኳክቶ ስከፍት
<<እኛ ቤት በግ ተገዝቷል፣ አንተ አትገዛም?>>
የትንሽነት ቦታው እንደፈቀደለት ሲሆን መስሎኝ በፍቅር አየሁት።
<<እኔ አልገዛም>>
<<እማዬ ዘልዛላ ነው ለአዲስ አመት በግ የማይገዛው ብላለች። ዘልዛላ ነህ እንዴ ?>>
እንደትልቅ ሰው ቆጥሬው የትልቅ ሰው ማብራርያ ዘዴዎችን ተጠቀምኩ። ፊት መንሳት፣ ሳይሰናበቱ በር መዝጋት።በዚህ ሀፍረት እራሴን ቀጣኝ። ቀስ ብዬ አድብቼ ወጣሁ። አምሽቼ ገባሁ ።
በጠዋት ሲንኳኳ የቀጠርኳት ጓደኛዬ መስላኝ ነበር
እሱ ነው። አጭር አዝማሪ መስሎ በሬ ላይ ተገትሯል። ነጭ በነጭ ለብሶ ባለጌነቱን ሸፋፍኗል። ከያዛቸው የአዲስ አመት ማብሰርያ ወረቀቶች አንዱን መዝዞ ሰጠኝ።
<<አልገዛም>> አልኩት።
<<አትግዛ ግን ውሰደው>>አለኝ። እሱ በለጠኝ።<<ቆይ>> ብዬው መኝታ ቤት ከሰቀልኩት ኪሴ ውስጥ አስር ብር አምጥቼ ሰጠሁት።ስእሉ መላቅጥ የለውም።ልጅነቱ ስእሉ ላይ አሸንፎታል።እንደርችት ያሉ የተለያዩ ቀለማት ተረጭተው አንድ ቢጫ ቀለም በስህተት ቁልቁል ተምዘግዝጋለች።ጠረጴዛው ላይ ጣል አድርጌው ወደ ኪችን ገባሁ።
ጓደኛዬ ስትመጣ <<ኦሆሆሆሆሆ>> እያለች ነበር
<<ምነው?>>
<<አረ ተወው፣ ዝም ብዬ ነው።>>
ሆዴን ቆረጠኝ።ያለአንዳች ጉዳይ ዝም ብላ አልተብሰከሰከችም።
<<ምንድንነው ንገሪኝ>>
<<ተወው ምን የደርግልሀል?>>
<<እንዴት ነው ኦሆሆሆይ ብሎ ከተገረሙ በኋላ ተወው ማለት?>> አኮረፍኩ።
<<ይሄ እናንተ መደዳ ያለው ትንሽ ልጅ>>
<<እ>>
<<እሱ ዘልዛላ ነው ሌላ ፈልጌ አላለኝ መሰለህ>>
<<እናቱ...>> ስል አረጋጋችኝ።ቀኔ ተበላሸ።ይሄ የገሀነም ፍሬ የሆነ ልጅ ቀኔን አበላሸው።የሚገርመው ደግሞ በጠዋት አንኳኳ።
ጓደኛዬን እኔ ፊት ቢመክራት ምን እላለሁ?የቴሌቪዥኑን ድምፅ ከፍ አድርጌ በሩን ከፈትኩ።ከበሩ ራቅ ብሎ ቆሟል።ስለማላስገባው ተንደርድሮ በእግሬ ስር ሊሾልክ? እግሬን ግጥም አደረኩ።
<<አስገባኝ>> አለኝ።የአመት በአል ልብሱ በቀይ ወጥ ተነካክቶ....
<<ለምን?>>
<<ስእሌን አያለው>>
<<አታይም>>
<<መብቴ ነው፣ ብሸጥልህም ስእሉ ሲናፍቅኝ የማየት መብት አለኝ።>>
<<ይህም ስእል ሆኖ >>አልኩት
<<የሚገባኝ እኔ ነኝ፣አስገባኝ>>
ፀብ ተካሮ ጓደኛዬ እንዳትሰማ አስገብቼ አሳየሁት።ቀሰብ፣እራቅ እያደረገ ተደመመበት።አይኑም እንባ ያቀረረ መሰለኝ፤ጉደኛ ነዋ!
<<ስእሉ ምንድን ነዎ የሚለው ?>>
<<ይሄ ከላይ የሚመጣው መልአክ ነው፤ መላእክቱ ሲመጡ ሴጣን ሸሽቶ በዚህ በኩል በሩን ቀዶ ሲገባ>>
ቀስ ብዬ አስወጣሁት።
በቀጣዩ ቀን መልሶ አንኳኳ።
<<ስእሌን ልይ>>
<<ምን እዳ ገባሁ>>
<<መብቴ ነው፣ብሸጥልህም አልውሰደው እንጂ ማየት እችላለው>>
<<እንደውም ውሰደው>>
<<አልወስድም፤ አንዴ ገዝተህኛል>>እንባው አቀረረ?መቼም ጉደኛ ነው።
አስገብቼ አሳየሁት። ቀረብ፤ ራቅ እያደረገ ዛሬ ደግሞ ፈገግ አለ።
<<ስእሉ ምንድን ነዉ የሚለው?>>
<<ይቺ እናቴ ናት፤ ይሄ አባቴ ነው። ሲመጣባት እኔን አቅፋኝ ጀርባዋን ስትሰጠው።>>
አሳዘነኝ? ዉጣ ሳልለው ወጣና በር ላይ ሲደርስ እየሳቀ
<<ውሸቴን ነው>> አለኝ።
ደነገጥኩ።የነገረኝን በመንገሩ ልቤ እንደሚነካ ቀድሞ አውቋል።ፈራሁት፤ተናደድኩበት።ከቤት ስወጣ እኔም እየሳኩ።
<<ቀደድኩት>> አልኩት።
<<ምኑን?>> የትልቅ ሰው ድንጋጤ።
<<ስእሉን>>
የጎረምሳ ለቅሶ በትከሻው እያሳየ
<<እበቀልሀለው>>አለኝ።እውነትም ተበቀለኝ። የበሬ ቁልፍ ውስጥ አሸዋ ሞጅሮ መክፈቻው አልገባ አለኝ።ስታገል ግማሽ ሌሊት አለፈ።በኮንትራት ታክሲ እናቴ ቤት ሄድኩ።ጠዋት ሰራተኛ አምጥቼ ምንም ማዶረግ ስላልተቻለ ቁልፉ ተገነጠለ።ስገባ ንዴት ማብረጃ ፊልም ማየት አልቻልኩም።እሽሽሽሽሽ..ይላል።ዲሹን አዙሮ፤አዟዙሮብኛል ማለት ነው።ካልታረኩት ሌላ ተንኮል ሳይጨምር በሁለቱ ብቻ በአጭር ጊዜ እንደሚያሳብደኝ ገባኝ።ኡሁሁሁሁሁሁ....
🔘 አለቀ 🔘

👍5
#እጅ_በጆሮ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
:
ማምሻውን ነው
ዝናብ ያረሰረሰውን የሰፈራችንን ኮብልስቶን መንገድ በጥንቃቄ እየረገጥኩ ወደ ቤት አዘግማለሁ። በረገጥኩት ቁጥር በድንጋዬቹ መሀከል የተኛው ውሃ ፊጭ ፊጭ ይላል።ዘንቦ ማባራቱ ስለሆነ ይበርዳል
ፊጭ ፊጭ እያደረኩ መራመዴን ስቀጥል፤ ከዚህ በፊት አይቼ በማላወቀው ብዛት በመንገዴ ላይ ከሰል አቃጣጥለው፤በቆሎ ጠብሰው፤በተርታ ተሰድረው ገብያ የሚጠብቁ ሶስት ሴቶችን አየሁ።
የመጀመርያዋ ወጣት ቢጤ ናት።አጠገቧ ከባድ ዝናብ ያዘመመው ወልጋዳ ጃንጥላና ኩምትር ብሎ የተቀመጠ ሕፃን ይታየኛል።ከእሷ ቀጥሎ ያሉት ሴቶች ሌጣቸውን ናቸዉ።ከእርሷ መግዛትን መረጥኩና ስደርስ፤
<<እናት....በቆሎ ጥብስ ስጪኝ ?>>አልኩ።
አንዴ፤እሳቱ ከተንተረከከው ከሰል ምድጃ ዙርያ አልቆላቸው የተቀመጡ ሶስት በቆሎዎችን፤ ከዝያ ደግሞ ሕፃኑን ልጅ አፈራርቄ እያየሁ።ከብርድ የማያስጥል ቡትቶ ቢጤ ለብሷል።ክሳቱ የሚያሳቅቅ፣የፊቱ መገርጣትአንጀት የሚያንሰፈስፍ ልጅ ነው።ሲርበው የከረመ ይመስላል?
<<የቱን ላድርግልሽ?>> አለችኝ።
<<የቱ ይሻላል?>>
<<ይቺኛዋ ቆንጆ ናት....በደንብ በስላለች ግን አላረረችም....አየሽ?>> አለችኝ። አንዶን በቆሎ መሬት ላይ ከነሽፋናቸው ከተቀመጡ ጥሬ በቆሎዎች ገንጥላ፣ባመጣችው ሽፋን ጥቅልል አድርጋ ልታሳየኝ እየሞከረች።
ተቀበልኳት።
<<ስንት ነው?>> አልኩ ልጁን፤ በተለይ አይኖቹን ሰርቄ እያየሁ። ከርታታ አይኖቹ ልገዛው የተቀበልኩት በቆሎ ላይ ናቸው።
ሁኔታው ያሳብቃል ፤ ማሙሽ በጣም እርቦታል።
<<ስድስት ብር>> አለችኝ።
<<እሺ ሁለት ስጪኝ>> አልኩና አስራ ሁለት ብር አውጥቼ ሰጠኋት።ሌላ ቆንጆ ነው ያለችውን መረጠችና ልትሰጠኝ ስጠቀልል ዘደ ልጁ ዞርኩ። አንደኛውን በቆሎ ልሰጠው ጎንበስ ስልከደረስኩ ጀምሮ ዐይኑን ከእኔ ላይ ያልነቀለው ልጅ ባልጠበቁት ፍጥነት ፍንጥር ብሎ ተነሳ።
<<እንካ ማሙሽ>> አልኩት። ስፍስፍ እያልኩ....ለመንጠቅ በሚቀርብ ሁኔታ ሲበበለኝ አንጀቴ እየተላወሰብኝ።
<<እግዜር ይስጥልኝ የኔ እመቤት....ሙሉ ይስጥሽ የኔ እመቤት...ሙሉ ሙሉውን ይስጥሽ.....>>(የምርቃት ዝናብ አዘነበችብኝ)
ምንም ሳልናገር ፤ የማይገባኝ ምርቃት ሽሽት ፊጭ ፊጩን አፍጥኜ ወደ ፊት መራመድ ጀመርኩ።
ዐስር ከማይሞላ እርምጃ በኋላ ግን ልገልፀዉ በማልችለው ምክንያት ዞር አለኩ። ልጁን ተመለከትኩት። ሳገኘው እንደነበረው ኩምትር ብሎ ተቀምጦል ። እጆቹ ላይ በቆሎ የለም። ወደ መድጃው ተመለከትኩ። ሁለት የበሰሉ በቆሎዎች ዳር ይዘው ተቀምጠዋል።
ሚዛኔን እንደመሳት አደረገኝ። አንገቴን ወደ ቤቴ አቅጣጫ አዙሬ ለመሄድ ብሞክር፤ እግሮቼ ከረጠበው መንገድ የመረጉ ይመስል ለገሙብኝ።
ከራበዉ ልጇ ፤ ሰው የገዛለትን በቆሎ ለምን ነጠቀችው ? ብዬ ፈርጄባት አደለም ማዘኔ።
ይህንን ብያኔ ለመስጠት እኔ ማነኝ......?
ኑሮዋን የማልኖር - እኔ፤ ተራራዋን የማልወጣ -እኔ፤ ቁልቁለቷን የማልወርድ -እኔ ፤ በምን ስልጣኔ ልፍረድባት እችላለወ....? የስድስት ብር በቆሎ ከሚበላ ሶስት ትልልቅ ባሀ ሁለት ብር ዳቦዎች ልትገዛለት አስባ ይሆናል...... ቤት የሚጠብቃት ሌላ ትንሽ አፍ ከዚህ ስድስት ብር መክፈል እንዳለበት ስለምታውቅ ይሆናል ....አስራ አምስት ወይ ሃያ ብር እየከፈለች የምትኖርበት የቀበሌ ቤትን ፤ ግማሽ የቤት ኪራይ ልትከፍልበት ወስና ይሆናል....
ማዘኔ- ይህንን እንድታደርግ ያደረጋትን ፤የእናትነት እንስፍስፍ አንጀቷን ያደነደነውን፤ የኑሮዋን ትግል አስቤ ነው። ማዘኔ - የልጆን መቁለጭለጭ እያየች ፤ የልጆን ረሀብ እየተመሀከተች ፤ እንዲህ ያለውን ውሳኔ እንድወትስን ያደረጋትን እጅ በጆሮ ሕይወቷን አስቤ ነው.....
ኀይል አሰባስቤ እርምጃዬን ስቀጥል ፤ በቀኝ እጄ የያዝኩት ለብ ያለ በቆሎ እጄ ላይ እየቀዘቀዘ ፤ በዐይኖቼ ውስጥ ያቀረረው ትኩስ እንባ እየወረደ ነበር።😣
🔘 አለቀ 🔘
ማንኛውንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን።

#አበባ_ባለበት
:
#በሕይወት_እምሻው
:
ታማኝ ፍቅረኛ ነው።
ልክ እንደዝያ 'ፍቅራዲስ ነቃጥበብ' እንደዘፈነችለት ልጅ፤ወዳጀ ብዙ ነው እንጂ ለእኔ ታማኝ ነው።ጨዋታ አዋቂና ፈገግታውን በአገኘው ቦታ የሚበትን፤ያየውን ሁሉ አቅርቦ የሚያቅፍ ነው እንጂ፤ ታማኝ ነው።
ልክ እንደ ፍቅራዲስ ልጅ፤ የኔውንም በዚህ ባህሪውፐ ጥላ እንዳለበት ዛፍ ከበውት ይውላሉ።
እንደ መስከረም አደይ ነቅለውት፤ ሊያጌጡበት ይሽቀዳደማሉ። ጥርሱን ሲያሳያቸው፤ ልቡን ያገኙ እየመሰላቸው በደስታ ትርክክ ይላሉ።
ግን የኔ ነው። ታማኝ ነው።
ያም ሆኖ ሰውነኝና ፤ ሴት ነኝና ፤ ቅናት ባጠገቤ ሽው ማለቱ ፤ጎኔን ጎንተል ማድረጉ ፤ ሲልም ሚዛንና አቅሌን እስክስት መገፍተሩ አይቀርም።
<<ወዳጀ ብዙ አጀበ ብዙ
ውበትን ከምንጩ የቀዳው ከወንዙ
አሳሳቁ ቁጥብ- ምጥን ነው ፈገግታው
እሱን ብቻ ስሙኝ ያሰኛል ጨዋታው
እንደ ጥቢ ተክል የመስከረም አደይ
እንደ ሮዝ አበባ የፈካ በፀደይ
አበባ ባለበት ንብ አይጠፋበትም
ተፈጥሮው ልዩ ነው ይስባል ከየትም>>
በየካፌው ስንገባ ትላልቅ ጡቶቻቸውን አስቀድመው መተው ለሰላምታ የሚለጠፉበት ቆነጃጅት ፤ትእግስቴን ይፈታተኑታል።አብረውኝ የተማሩ ናቸው ብሎ የሚያስተዋዉቀኝ ፤ በልብሳቸው ወግ አጥባቂ መስለው ፤ እሱን ሲያዩ እንደሆነ ነገር የሚሰራቸው ቁሌታም ሴቶች ያንገረግቡኛል።
ትላንት ባንክ ስሄድ ተዋውቋቸው ፤ በነጋታው ሲያገኙት ጠፍቶ ያገኙትን የልጅነት ፍቅረኛቸውን እንዳገኙ የሚያንሰፈስፋቸው ሴቶች እብድ ያደርጉኛል ።
ቢሆንም ታማኝነቱን ስለማውቅና የፍቅር አዲስን ''አበባ ባለበት ንብ አይጠፋበትም''ምክር ስለምሰማ ፤አበባዬን እንዳይደርቅ ዉሃ ከማጠጣት ፤ እንዲደሰት ከመንከባከብ በሌላ እንዳይወሰድ ከመንጠንቀቅ በቀር ፤ምንም አድርጌ አላውቅም።ማለቴ...አላውቅም ነበር ...
ለምን <<ነበር>> አልኩት።
ሜላት፤ እዚያ በየሳምንቱ የእነ ግሩም መዝሙርን ጃዝ ሊያይ የሚሄድበት ቤት፤ ብቻዋን ቁጭ ብላ ቮድካዋን እየለበለበች በጃዝ ስትወዛወዝ አግኝቶ የተዋወቃት ልጅ ናት።
ይሄን እንዴት አወኩ? ነግሮኝ ታማኝ አይደል? ይነግረኛል እኮ...ፈስ ስለሌለበት ዝላይ አይፈራምና ይነግረኛል። ዛሬ ከነ እገሌ ጋር ተዋወኩ...ዛሬ ከነእገሌ ጋር ዋልኩ...ብሎ ይነግረኛል።መጀመርያ ላይ የጃዝ ፍቅሩን ስለማውቅ ነገሩ ብዙ አልከነከነኝም ነበር። ነገሩ ያሲክከኝ የጀመረዉ፤ በተከታታይ ሦስት ሐሙስ እዛው ቤት -በዚያው አኳኋን ብቻዋን አግኝታው አብረው ሲጠጡና በጃዝ ሲመሰጡ እንደነበር፤ በለመደው ሁሉንም ተናግሮ የመሸበት ማደር ፖሊሲው ሲነግረኝ ነው ።እውነቱን ተናግሮ ፤ እሷ ጋር አምሽቶ ፤ እኔ ጋር ሲያድር ከነከነኝ።
የሚላት ጉዳይ ተለይቶ የረበሸኝ በሦስት ምክናያቶች ነው።
አንደኛ- ጃዝ መወደዷ...ስንትሽ ሁሌም ብዙ ጃዝ የሚወዱ ሴቶች አላውቅም፤ ጃዝ የሚወዱ ሴቶች ማቹር ናቸው....አለ አይደል....ምጥቅ......ያሉ...ምናምን እያለ ያወራኛል።
( እኔ ጃዝ አሌወድም.....አብሬው ልደንስ ፤ ልዘፍንበት....ስልቱን ልከተለው የማልችለውን ሙዚቃ እንዴት ብዬ ልውደድ? ወጣ ሲሉት የሚወርድ....በረደ ሲሉት የሚሞቅ....ጭራና ቀንድ የሌለዉ ሙዚቃ ምኑ ይወደዳል? የጨረባ ተዝካር ነገር....አንዳንዱማ ያስቀኛል....በተለይ ስንትሽና ጓደኞቹን መንግስተ ሰማያት ያለ ትኬት የገቡ ያክል ፤ በመንፈስ የሚንሳፈፉበት...ምስጥ የሚሉበት ሙዚቃ፤ ለእኔ የአሮጌ ቮልስቫገን ሞተር ሲነሳ ይመስለኛል....የቆሼ መኪና ፤ ቆሻሻ ከብዶት ሲሄድ የሚያሰማው የማቃሰት ድምፅ ይመስለኛል... እንደዝያ አይነት ጫጫታና ትርምስ ከፍዬ ከምሰማ ማዕድ ቤት ያሉትን ድስቶቼን በነፃ አላጋጭም? ጭልፋና መጥበሻ አላማታም? ልዩነቱ ምንድን ነው?....ጲሪሪሪሪ....ጪሪሪሪሪ..ፂፂ
ብሎ ሙዚቃ አለ...? አንዳንዱማ ቆርቆሮ ሲፋቅ ሁሉ ይመስላል....
የሜላት ጃዝ መውደድ ግን ፤ ለስንትሽ እሷን ከሴት ሁሉ ለይቶ የሚያሳየው ብርሀን ነገር መሰለኝና ሰጋሁ...
ሁለተኛ - ሁሌም ብቻዋን መሆኗ ....
''ሴት ልጅ ብቻዋን ሬስቶራንት ስትበላ ፣ መጠጥ ስትጠጣ ሳያት ፤ አንድ ነገር ይታየኛል ....ኮንፊደንስ ! ስለዚህ ደስ ትለኛለች ይላል ስንትሽ...(እኔ ደግሞ ሴት ልጅ ብቻዋን ሬስቶራንት ከበላች። ወይ መጠጥ ቤት ገብታ ፣ ሌላ ሰው እየጠበቀች ሳይሆን ብቻዋን ከጠጣች .... ሁለት ነገር ይታየኛል ...ወይ ሴት ጓደኞች የሌሏት ምቀኛ፤ ወይ የሰው ባል የምትቀማ ሴሰኛ ነገር ፤ ወይ ደግሞ ወንድ ለማጥመድ ታጥባና ተቀሽራ የወጣች ሴት አዳሪ ....ይሄው ነው ...) የሜላት ሳታሰልስ ብቻዋን ጃዝ ቤት ሄዳ መጠጣት ግን ፣ ለስንትሽ እሷን ከሴት ሁሉ መርጦ በሚያምር አንፀባራቂ ትሪ የሚያቀርብለት መሰለኝና ፈራሁ።
ሦስተኛ - ስንትሽ ወዳጅ ብዙና በሄደበት የሚሞቅለት ይሁን እንጂ ፤ ብዙ ሰው ይወቅ እንጂ
ብዙ የቅርብ ጓደኛ ግን የለውም። ፍቅሩ ጊዜያዊ ፣ በሰዐታት የሚቆጠር ፣ በደቂቃዎች ወደሌሎች የሚተላለፍ ነው። ከዚህ ዓይነቱ ትውውቅና መዋደድ ተርፈው ስልካቸው ተይዞ በየእለቱ የሚደውልላቸው ፣ ዓመት በዓል ሳይሆን ቴክስት የሚላክላቸው ሰዎች ፣ ከእጆቼ ጣቶች ቁጥር አይበልጡም። ሜላት ግን በሳምንት አንድ ግዜ ደጃዝና ቮድካ ድብልቅ ትውውቅ፣ እዚህ ዝርዝር ውስጥ ቸ...ስ ብላ ገባች። ይሄ ካልረበሸኝ ምን ይረብሸኝ ? የሚያስቅ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ፣ ቴሌቪዥን ላይ ትወደዋለች የሚለውን ጃዝ ሙዚቃ ባየ ቁጥር ፣ ሬድዮ ላይ የሙላቱ አስታጥቄ ወይ የሌላ ጃዝ ሙዚቃ በመጣ ቁጥር (መኪና እየነዳ ሳይቀር) ሰከንድ ሳያባክን ይደውልላታል። ቴክስት ይልክላታል።
<<ሄይ....ሰማሽው? ሄይ...ኤልቲቪ እያየሽ ነው ....?አሁኑኑ ቀይሪው ....የማይልስ ዴቪስን ታሪክ እያሳዩ ነው !.....አጅሪት...ስለ ሚቀጥለው ሳምንቱ የጆርጋ መስፍን ኮንሰርት ሰማሽ ....? አይ ኖው !እኔ ራሴ ማመን አልቻልኩም ....በጭራሽ ....ዊ አር ሶ ጎይንግ ልብስ ሁሉ ሳልገዛ አልቀርም ከጆርጋ ጋር ለመተዋወቅ። ቻው በቃ ...ሲያልቅ እደውልልሻለው....>>
ጦፍኩ።
ይህቺ ልጅ በጃዝና በቮድካ አባብላ ፣ በሙላቱ አስታጥቄ .....በጆርጋ አለሳልሳ ፣ ስንትሽን ልትቀማኝ የተላከች የሌሊት ወፍ መሰለችኝ ። የምታዳልጥ የሴት ድጥ....የምታደረድር የሴት ገድል....ተንሸራቶ ቢገባስ ? ተንቀራቶ አልጋዋ ውስጥ ቢወድቅስ ?
ሜላት ከሌሎቹ አጃቢ ሴቶች ትለይበት እንደሆን ለማወቅ ብዙ ብዘይድም ምንም ፍንጭ አጣሁ። ከእሷ ጋር የከረረ የስልክ ግኑኝነት ይኑረው እንጂ በእኔ ላይ ያለው ባሕርይው አልተለወጠም። ያገኛት ቀን እንዳገኛት ይነግረኛል። እያወራት ሳገኘው ሳያቋርጥ፣ሳይርበተበት ይቀጥላል። ይባስ ብሎ ቴክስት ልካለት ካሳቀችው አንብቦልኝ እንድስቅለት ይጠብቀኛል።
አንድ ቀን እንደዋዛ ጠጋ አልኩትና፣ ''እስቲ ባሌን እንደህ ያማለለችው ልጅ ስልክ ስጠኝ....እኔም ልወቃት ፤ እኔንም ካማለለችኝ'' አልኩት።
አላንገራገረም።
''አሪፍ...ቁጥሯን ቴክስት አደርግልሻለው'' ብሎ፣ አንገቴ ላይ ሳመኝና ሄደ። ደቂቃ ሳያልፍ የሌሊት ወፎ ቁጥር መጣልኝ።መዘገብኩት። ትንሽ ቆይቼ ሙሉ ስሟን አስገብቼ ፌስቡክን አሰስኩ።
ከመቶ በለይ ፎቶ አላት። ምነው ልታይ ልታይ አለች?
ድብን ያለች ቀይ ናት። በየፎቶው አሞጥሙጣ የምትነሳው ከቀይ ሊፒስቲክ ጋር የተፈጠረ የሚመስል፣ ''አንጀሊና ጁሊ'' ከንፈር አላት ... ሙሉ ፎቶዎቿ ላይ ደግሞ ያበጠ ቂጧንና ሙትት ያለ ወገቧን፣ አንዴ ዛፍ እየተደገፈች ፣ሲላት

ወንበር እያቀፈች፣ በኩራት ትታያለች። ጡት መያዣ የማያውቁ ታላላቅ ጡቶቿን በብርድም በሙቀትም ክርር ካሉ ጫፎቻቸው ጋር ለኤግዚብሽን አቅርባለች።
አልቆልኛል።
ይህ በሆነ በሳምንቱ ያ በየቀኑ ሲንሰፈሰፍለት (ሲንሰፈሰፉለት) የነበረው የጃዝ ኮንሰርት ደረሰ።ስንትሽ ሥራ ውሎ ልብስ ለመቀየር ሲመጣ የክትና የድግስ - ቀይ ጠበቃ ቀሚስ ግጥም አድርጌ ለብሼ ጠበኩት።
''እንዴ ...ምንድን ነው ይሄ ዝነጣ ...?'' አለኝ። እጆቼን ይዞ ባለማመን እያየኝ።
''ኮንሰርት አብሬህ ልሄድ ነዋ !''አልኩኝ ፍልቅልቅ እያልኩ። ''እ....የምን ኮንሰርት?'' ፊቱ ጭልም ፣ቅጭም እያለ ጠየቀኝ።
''እንዴ ...ታሾፋለህ እንዴ....የጃዙን ኮንሰርት ነዋ!''
''ማሬ....አታሹፊ.....'' ብሎ ፣እጆቼን ለቀቀና ወደ መኝታ ቤት ሄደ።
ተከተልኩት።
''ብመጣ ችግር አለው?'' ቱግ እያልኩ ጠየቅኩ።
''እንዴ...ምን ችግር አለው....ኤክሴፕት ጃዝ አትወጅም ....ሪመንበር? አለኝ፣ በሹፈት ጉንጮቼን በእጆቹ እየቆነጠጠ፣እንደ ህፃን ልጅ እያየኝ....
''አዎ ግን አንተ የምትወደውን መውደድ እፈልጋለው....
እመጣለሁ.....'' አልኩት። ሣቅም ኮስተርም ብዬ።
''እኔ የምወደውን ሁሉ መውደድ የለብሽም ፣እኔን ከወደድሽኝ እኮ ይበቃል። የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መዉደድ የለበትም እኮ..'' አለኝ
የዝነጣ ሱፉን እየለበሰ፣ዐይን ዐይኔን እያየኝ።
''መምጣት እፈልጋለው በቃ! ስንትሽ....ሌላ ምክንያት ካለህ ንገረኝ....'' አልኩ ፣ሆድ እየባሰኝ። የሜላት ጡትና ቂጥን አስቀምጦ፣ በቮድካ የራሱ ቀይ ከንፈሮቿን እያየ ሲቋምጥ ታይቶኝ....
''ሌላ ምን ምክንያት ይኖረኛል?''
''እንጃ....ከሌለህ ደስ ነው ሊልህ የሚገባው...እመጣለው.....አልኩ። ሜላትን ከአንጎሌ ገፍትሬ ለማውጣት በመፈለግ ራሴን እየነቀነኩ....
ማምረሬ ሲገባው ልብሱን ለብሶ ጨረሰነና ፣
''ግን ቲኬት የለኝም .....አለ።
'' እዛው እንገዛለን ....''ቶሎ ብዬ መለስኩ።
''አሎቆ ቢሆንስ....ሁሉም ሰው እኮ እንዳንቺ ጃዝ አይጠላም .....አለ እየሳቀ።
''እንሞክርና እመለሳለው....''
''ባናገኝስ.....''
''ምነው በጣም አከላከልከኝሳ ....ልቅርልህ በቃ..''
አልኩ።ጦፍ ቦዬ አልጋው ላይ ዘጭ እያልኩ።
''ማሬ....ኧረ ነይ በናትሽ ....እኔኮ እንዳንተገለቺ ነው...በዛ ላይ የሦስት ሰአት ኮንሰርት ነው...በአንቺ ጃዝ መጥላት....''አጠገቤ ተቀመጠ።
''የሦስት ሰዐት?'' አልኩ ቀና ብዬ እያየሁት።
''አዎ ....ምነው?''
''ምንም ...ረጅም ነው....''
''ሃሃ...አዎ...''
''ዘፋኙ ማነው ...? እነማን ይዘፍናሉ?'' አልኩት። የሚያምር በሉጫና ከርዳዳ መሃል ያለውን ፀጉሩን እየነካካሁ።
''ማሬ...ዘፋኝ የለም እኮ....ባንድ ብቻ ነው...''
''ማለት...መሳርያ ብቻ ? ጲሪሪሪ..ፂፂፂ..ብቻ ...?ኦህ ማይ ጋድ !''
አልኩ ራሴን እየያስኩ።
ከት ብሎ ሣቀ።
''ሪል ጃዝ እኮ እንደዛ ነው ....ለዚህ ነው ቅሪ ያልኩሽ ግን ከመጣሽ ነይ...ትኬቱ ነው ያሳሰበኝ''
ወሬአችን ሳያልቅ ሳሎን የተወው ስልኩ ጮኸ።
ብዙ ሳይቆይ ተመለሰ።
''ማነው አልኩት።
''ሜላት ናት...እናቴን አሟት ሆስፒታል መንገድ ላይ ነን አለችኝ...'' አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ።
''ውይ .....ምስኪን....'' አልከለኝ። ፊቴን ከሆዴ የደስታ ስሜት ጋር ማመሳሰል አቅቶኝ እየታገልኩ።
''ያሳዝናል....በጣም ጓጉታ ነበር....ከባድ ነገር እንዳልሆነ ተስፋ እናድርግ እንግዲህ...በያ ተነሽ...
በጣም ረፈደ...በስአት ይጀምራል ተብሏል....ደህና ቦታ እንዳናጣ....'' አለኝ። ቶሎ ቶሎ እያወራ።
አሁን የመሄድ ፍላጎቴ በሜላት መቅረት ተዘጋ።
ጃዝ...? ኤጭ ! ሦስት ሰዐት ሙሉ የሚያንቋርር የማይጨበጥ ሙዚቃ ያለዘፋኝ....በዚያ ላይ በዝናብ ከቤቴ ወጥቼ...በዛ ላይ ጃዝ የሚጫወቱት ሰዎች የሚወጥሩት ነገር ትዝ አለኝ።
አይደንሱ...አይስቁ...መድሀኒት እንደሚቀምም ሰው...ለካንሰር ፈውስ እንዳገኘ ሰው የሚጎርሩት ነገር ያበሳጫል ...መንኮራኩር እንዳመጠቀ ሰው የሚንጠባረሩት ነገር ያናድደኛል....
አልሄድም።
''ስንትሽ በቃ አንተ ሂድ...ቲኬትም ሊቸግር ይችላል...አንተ እንደዚህ ጓግተህ ቲኬት ፍለጋ በዝናብ ላንከራትትህ አልፈልግም...ሂድ በቃ...'' አልኩ፣ አልጋዬ ላይ በፍፁም ፍስሀ ተደላድዬ እየተኛሁ።
ምንም አላለም። ሥቆ ሳመኝና እየተጣደፈ ወጣ።
በአሸናፊነት ስሜት ሣቅ ብዬ ፣ ምቾቴን ለመጨመር ያጣበቀኝን ቀሚስ አውልቄ ፒጃማዬ ውስጥ ስገባ ግን ፤ ከየት መጣ ያላልኩት ፣ ከዚህ በፊት የማላውቀዉ ጥርጣሬ፣ እንደተዉሳክ ሆዴ ውስጥ እየሮጠ የገባ ይመስል ዕረፍት ነሳኝ።
ሌላ ጊዜ ጮኸ ብሎ የሚያወራው ስንትሽ፣ሳሎን ሆኖ ከሜላት ጋር ያወራውን አልሰማሁም። ሀወትሮው ለሰው ሟች የሆነው ስንትሽ፣ በሜላት እናት መታመም የተጨነቀ አይመስልም። ነይ ሲለኝ ቆይቶ ልቅር ስለው ውትወታዉን በፍጥነት ማቆሙን አላስተዋልኩም።ህምም...ትንሽ ቆይቼ ስልኬን ሳየው የሜላት ቁጥር እንዳለኝ ትዝ አለኝ። አላመነታሁም።
ደወልኩ።
''ሄሎ...አለች ጮክ ብላ። (ከባድ ጫጫታ ውስጥ ናት....የትኛው ሆስፒታል ነው?)
''ሄሎ....ሜላት?''
''አዎ....በደነብ አይሰማም....ማል ልበል?''(ጫጫታ መሀል ጲጲጲሪሪሪሪ ሙዚቃ የሚያጫውት ሆስፒታል የቱ ነው ? )
''እ...ሜላት ነሽ...?''
''አዎ....ይቅርታ ኮንሰርት ላይ ነኝ...ማል ልበል ?'' (ለድንገተኛ ህሙማን ኮንሰርት የሚደግሰው ሆስፒታል ስሙ ማነው ?)
አበባ ባለበት ንብ አይጠፋበትም።
ሜላት አበባዬን ቀስማብኛለች።

👍3❤1
#ንስሐ
:
#በዓለማየሁ_ገላጋይ
:
አዲስ የፈለቀ ፀበል ነው ፣ከባለቤቴ ጋር ሄደናል። ወደ ፀበል ከመግባቷ በፊት ንስሀ የሚቀበሏት አባት አጠገቧ ተቀምጠው፣ አፋቸውን በማጎናፀፍያቸው ሸፍነው ጭንቅላታቸውን በአወንታ ይወዘዉዙታል ።
<<ምን ይሆን የምትናዘዝ ?>> ጓጓሁ።
አካባቢው ጭጋጋማ ነው። የምንቀመጥበት ጠፍጣፋ ድንጋይ እንኳ በእርጥበቱ የወረዛ ነው። አንዳንድ ፀበልተኞች ገና አፀዱን ሲያልፉ ይለፈልፋሉ። እኛ ከዚህ ተርፈናል።
ቄሱ አሁንም ሚስቴን ያናዝዟታል። ምን ይሆን የምትናዘዘው ? ምን ተሳሳስታ?....
ቄሱ ብዙ ሰዓት አናዘዋት ወደ እኔ መጡ ። የክርስትና ስሜን ከጠየቁኝ በኋላ
<<ንስሃ ይዞ ፀበል ደግ አይደለምና በሆድህ ያለውን፣ሥጋ ያሳሳትህን፣ ጋኔን የገፋፋህን ሳትደብቅ ተናገር። ንስሃ ግባ ማለቴ ነው።>>
አሁንም ልቤ ባለቤቴጋ ነው፤ ምን ብላ ንስሃ ገብታ ይሆን ? ባውቀው።
<<ያው ሴትጋ እሄድ ነበር>>
እራሳቸውን ነቅንቀው አፋቸውን ጋርደው ጠየቁ
<<ሌላ ሴት ገር?>>
<<አዎ>>
<<ስንት ናቸው?>>
<<ብዙ ናቸው አባቴ>>
<<ሌላስ? ከሃይማኖትህ ውጪ ያሉ ሴቶች ጋ ደርሰሃል?>>
<<አዎ፣ ይፍቱኝ አባቴ >>
<<እግዚሐብሄር ይፍታህ፣ ሌላስ?>>
<<ሌላ'ኳ ሀጥያት የምለው የለኝም>>
ቀና ብለው አዩኝ። ከዚህ ሌላ ምን ታደርግ መሰለኝ።
<<ሰው መድሀኒት አላቀመስክም?>>
<<በፍፁም>>
<<በሐሰት አልመሰከርክም?>>
<<እንደውም>> ከእኔ ወደ ሌላ ተጠማቂ ሊሸጋገሩ ሲሉ ጥቂት ብር አዎጥቼ ሰጠሁ። ደንብ ነው። ጨምሬ ጨማምሬ ብሰጣቸውና የባለቤቴን ንስሀ ቢነግሩኝ ብዬ ጓጓሁ። እንደገና እጄን ቱታ ኪሴ ከትቼ ዳግም ሰጠኋቸው ። ብሩን ከቁብ አለመቁጠራቸው ለመጠየቅ አለበረታታኝም። የባለቤቴ ንስሃ ግን ሆዴ ገብቶ ወደ ቁርጠት መቀየር ጀመረ።
ሌላ ወንድ ደርሶባት ይሆን ?
እንደወረፋ የሚቆጠረው ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ እንደቶጎለትኩ ሳሰላስል ከወደጠበል ቤት አቅጣጫ አንድ አፈድፋጅ ተመለከትኩ። ብጣቂ ነጠላውን መስቀለኛ አጣፍቶ ከወድያ ወዲህ ይላል።
ጠራሁት፣ መጣ። የተቀመጥኩበት አጎንብሶ ጆሮውን ሲሰጠኝ እኔ እጄን አስቀደምኩ ። አስጨበጥኩና ችግሬን ነገርኩት።
<<የባለቤቴን ንስሃ እንዲነግሩኝ ፈልጌ ነው >>
<<እሳቸው ናቸው?>> አለ በብሩ መብዛት ተርበትብቶ
<<አዎ>>
<<ግድየለም፣ ማናዘዛቸውን ይጨርሱና እጠይቃቸዋለው>> ብሎኝ ሽብርክ ሽብርክ እያለ ሄደ።
ቄሱ ማናዘዛቸውን ሳይጨርሱ እኔና ባለቤቴ የጠበሉ ወረፋ ደረሰን። ተጠቅመን ስንወጣ ያንን አፈድፋጅ ጠራሁት ። ከባለቤቴ ዘወር አድርጌ ጠየከለት።
<<ታድያስ ? አባ ምን አሉ?>>
<<አባማ ባልና ሚስት ካንድ ወንዝ ይቀዳል አሉ>> 😳

👍3😁2