አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ሄለን እና እናቷ ዲላ ከተማን ለቀው ሻሸመኔ አባ ሽፍንፍን ቤት ከከተሙ አንድ ወር አለፋቸው፡፡በነዚህ ቀናቷች ውስጥ በአባ ሽፍንፍን በሚደረግላቸው እንክብካቤ ደስተኟች ሆነዋል፡፡በተለይ ሄለን ከሲኦላዊው ጨለማ ኑሮ ወደ ገነታዊው ምቾት ኑሮ እንደመሸጋገር ቆጥራው ባጋጠማት እድል ተመስጣበታለች፡፡አሁን የጀመረችው አዲሱ ህይወቷ በጣም ተመችቷቷል….አረ ከመመቸትም በላይ ነው…ትምህርቷንም እዚሁ ሻሸመኔ ጀምራለች…አባ ልክ እንደመጣች ለእሷም ሆነ ለእናቷ ከደርዘን የበለጡ ልብሷችን ነው የገዙላቸው፡፡መቼስ ከለበሱት ልብስ በስተቀር የተቀረው ልብሶቻቸውም ሆነ መላ ንብረታቸው በእሳቱ ወድሞል ..አባ ታዲያ ከተቃጠለው ቤታቸው ጋር የወደመውን ተስፋቸውን ብቻ ሳይሆን ወደአመድእነት የተቀየረውን ቁሳቁሳቸውንም ነው መልሰው እየተኩላቸው ያለው፡፡
በተቃራኒው ለሄለን ሁሉ ነገር የተመቻትና ትክክል የሆነ ይምሰላት እንጂ የእኚህ አባ ሽፍንፍን ሁኔታ በጣም ግራ እየጋባት ነው፡፡ሁለ ነገራቸው ሚስጥር ነው..በአንድ ጎናቸው ስታስባቸው ፍፅም አለምን ችላ ብለው ለነፍሳቸው ብቻ ያደሩ ጻድቅ እና መንፈሰዊ አድባር አድርጋ ትስላቸዋለች…ለድሆች አባት ናቸው ..ለተጠቁት እና ለተበደሉት ደራሽ ናቸው…የጸሎት ክፍላቸው ውስጥ ገብተው ከመሸጉ ያለውሃ እና ምግብ ሶስት እና አራት ቀን በፀሎት ያሳልፋሉ…እኚን የመሰሉት ተግባሮቻቸው እንደ ፍጹማዊ ጻድቅ እንድታስባቸው ያስገድዳታል….
ግን ደግሞ አንዳንዴ መልሳ ፍጹምነታቸው ላይ በአዕምሮዋ ጥያቄ ይጫርባታል፡፡አለማዊ ፌልሞችን አብረዋት ቁጭ ብለው ያያሉ…ሙዚቃ ስታዳምጥ አብረው ባይዘፍኑም አብረዋት ያዳምጣሉ… ያለምንም ተቃውሞ የሙዚቃ ፍቅሯን እንድታዳብር ጊታር ገዝተው ሸልመዋታል….እና እኚን የመሰሉ ሌላኛውን ገጽታቸውን ስትገመመግም ደግሞ ግራ ትጋባለች……..ባለ መንታ ባህሪ ይሆኑባታል፡፡
ሄለን አሁን ሳሎን ብቻዋን ቁጭ ብላ ፊልም እያየች ነው፡፡
‹‹ምነው አንድ ቀን እንኳን እዚህ ክፍል ቢያስገቡኝ…?››ስትል ተመኘች
አባ ቀይ ቀሚስ አድርገው ፊታቸውን በጥቁር ሻርፕ ጠምጥመው እንደተለመደው ጥቁር መነጽራቸውን ሰክተውበታል
ሄለን ከመቀመጫዋ ተነሳችና በፈካ ፊት ተቀበለቻው፡፡አባ ዘወትር ከጐኗ ባይለዩ ደስ ይላታል፡፡ግን ውድ ናቸው፡፡ከደቂቃዎች ባለፈ ለእሷ ጊዜ የላቸውም…ምንም እንኳን እንድም ነገር ሳያጐድሉባ በምቾት ቢያኖሯትም ይሄ ለእሷ ጊዜ ያለመስጠታቸው ጉዳይ አልፎ አልፎም ቢሆን ያበሳጫታል፡፡በዝግታ የሚራመዱት አባ አጠገቧ ሲደርሱ መስቀላቸውን ሊያሳልሞት ወደግንባሯ ሰደዱ እና ካሳላሞት ቡኃላ ከጎኗ ተቀመጡ፡፡እሷግን ተነሳችና ወደ ኩሽና አመራች፤ እጅ ውሃ አመጣችና አስታጠበቻቸው…ምግብ አቀረበች..አብረው እየተጐራረሱ በሉ፡፡ይሄ ለሄለን በሳምንት አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን የሚገኝ እድል ነው፡፡ሁለቱም እስኪጠግቡ ከተመገቡ ቡኃላ መአዱ ተነሳ… አባ በተቀመጡበት ቦታ ሳይንቀሳቀሱ ወሬ ጀመሩ
‹‹እናትሽን ዲላ ሄዱ ነው ያልሺኝ?››
‹‹አዎ አባ?›››
‹‹ይመጣሉ..ወይስ ያድራሉ?›››
‹‹ትመጣለች››
‹‹አይ ጥሩ …በይ እንግዲህ የጀመርሽውን ፊልም እይ..እኔም የሆነች ስብሰባ አለችብኝ ወደ እዛው ላምራ ›› ብለው ከመቀመጫቸው ተነሱ…
‹‹ሊሄዱ ነው?›› አለች ሄለን ቅሬታ በሚነበብበት ድምጸት
‹‹አዎ ምነው ችግር አለ እንዴ?›››እጃቸውን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርገው በፍቅር አይን አትኩረው እየተመለከቷት ጠየቋት
‹‹አይ ምንም ችግር የለም ብቻ…››
‹‹ሄለን ልትነግሪኝ የፈለግሽው ነገር እንዳለ ያስታውቅብሻል ..ግድ የለም ንገሪኝ››
‹‹..ይሄ ጓረቤታችን ያለውን ሰውዬ ያውቁታል..?›››
‹‹የቱን ?››ግርታ ባረበበበት ስሜት ጠየቋት
‹‹ከላይኛው ፎቅ ላይ የሚኖረውን..ፖሊሱን››
‹‹ያን ያህል እንኳን አላውቀውም ምነው ጠየቅሺኝ?›››አጨንቁረው እየተመለከቷት የምትናገረውን ነገር ማዳመጥ ጀመሩ
‹‹እኔ እንጃ አዲስ አልሆነብኝም… ከዚህ በፊት የማውቀው ይመስለኛል..በዛ ላይ ሁል ጊዜ በተለይ ጥዋት ጥዋት ግቢ ውስጥ ጸሀዬን እየሞቅኩ ዘፈን ስለማመድ ድንገት በረንዳው ላይ ቆሞ ቁልቅል ወደ ታች እያየ ሲያዳምጠኝ አይና አፍራለው..
‹‹እንዴ ምን ያሳፍርሻል..ቢያዳምጥሽ ምን ችግር አለው?›››
‹‹እሱማ ምንም ችግር የለውም..ብቻ ዛሬ ጥዋት እንደበፊቱ አዳምጦ ብቻ ዝም አላለኝም….አናገረኝ››
‹‹ስዘፍን ድምጼ በጣም ቆንጆ እንደሆነ ነገረኝ…እሱም ለሙዚቃ ልዩ ፍቅር እንዳለውና ፒያኖ
እንደሚጫወት ካስረዳኝ ቡኃላ ፍቃደኛ ከሆንኩ ሊያለማምደኝ እንደሚችል ነገረኝ››
‹‹ታዲያ ምን አልሽው?››
‹‹እኔማ አስቤበት ነግርሀለው አልኩት››ብላ በዝርዝር አስረዳቻቸው
እሳቸውም ለደቂቃዎች በቆሙበት ካሰለሰሉ ቡኃላ‹‹እና ታዲያ ጥሩ ሀሳብ እኮ ነው..ያስተምርሻ፡፡ እዚሁ ደጃፍሽ እንዲህ አይነት ወርቅ እድል አግኝተሸማ መግፋት የለብሽም››በማለት ስትጨነቅ የዋለችበት ሀሳብ አቃለሉላት፡፡
‹‹ግን ማን እንደሆነ አውቀዋል አይደል..?ፓሊሱ …ኩማንደር መሀሪ የሚሉት ሰውዬ እኮ ነው..››
‹‹ይሁን ግድ የለም….በይ ደህና ሁኚ ››ብለው ግንባሯን ስመዋት በቆመችበት ጥለዋት ወጥተው ሄዱ
ከእሷቸው አገኘዋለው ያለችውን የይለፍ ፍቃድ እንዲህ በቀላሉ ማግኘቶ በጣም ነው ያስደሰታት
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
በመዲናዋ አዲስ አበባ ሳሪስ የተከፈተው ሮዝ ሆቴል በአጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂነትን አግኝቷል፤ገባያው ደርቷል..አብዛኛዎቹ ደንበኞቾ ዲታዎች የሚባሉ አይነቶች ናቸው፡፡ሁሉም የሮዝን ዝና ሰምተው ነው የተሰበሰቡት
‹‹አዲስ አበባ ከገባው የወሲብ ጥሜን የሚቆርጥልኝ..ረሀቤን የሚያራካልኝ ጀግና ወንድ እስከአሁን አልገጠመኝም….እዚህች ከተማ ውስጥ ወ ..ብቻ እንጂ ወንድ የለም ››ብላ አውጃለች ተብሎ ይወራባታል..አንድ ለአንዱ እያወራ እሲኪ ይህቺን ፎካሪ እንያት እየተባባሉ ይመጣሉ… በውበቷም በሳቋም ደንዝዘው እዛው ይቀራሉ..የእሷው ቤት አጫፋሪ …የእሷው ቤት አሞቂ እየሆኑ ይቀራሉ ..ከመካከላቸው ውስን የሆኑት ረጂም ምላስ ያለቸው እና ከእሽጋቸው ያልተፈቱ ብዙ እረብጣ ብሮችን ወርወር ማድረግ የሚችሉ ቱጃሮች ገላዋንም የመዳበስ ጭኖን ፈልቅቀው የመሞቅ ፍቃድ ያገኛሉ..ቀሪዎቹ ምራቃቸውን እንዳዝረከረኩ ይቀራሉ ….
አቤል ግን ደጋግሞ ሚያገኛት ..ደጋግሞ ሚያቅፋት..ደጋግሞ ሚያስተዳድራት ለስሜቷ ቅርብ የሆነ ብቸኛው ሰው መሆን ችሏል….ከንፈሯን እንዲስማት ምትፈቅድለት …እሷም የምትስመው ወዳጅ….‹ሮዝ ከማያውቁት ሰው ጋር ወይም ከማይወዱት ሰው ጋር ወሲብ መፈፀም ደስ ባያሰኝም ቀላል ነው…የልፈቀዱትን ሰው ከንፈር መምጠጥ ግን ያቅለሸልሻል››የሚል እምነት አለት፡፡
የሚገርመው አቤል ከሮዝ ጋር ባለው ግንኙነት በእሷ መንገድ እና ፕሮግራም ነው እየተጓዘ ያለው፡፡፡የምታደርጋቸውን ድርጊቷች በአጠቃላይ ያውቃቸዋል…ከሌሎች ወንዶች ጋር ምትከውነውን መዋደቅም በዝርዝር ይከታተላል ..ግን አንድም ቀን ከእሷ ጋር አንባ-ጓሮ ለመፍጠር ሞክሮ…ወይንም ማድረግ የፈለገችውን ነገር እንዳታደርግ ለማሰናካከል ሙከራ አድርጐ በፍጽም አያውቅም..ብቻ የእየ እለት እንቅስቃሴዋን በግልጽም በሚስጥርም እየተከታተላት በማስታወሻው ላይከመከተብ ተዘናግቶ አያውቅም፡፡
ዛሬ ካለውትሮዋ በጊዜ እቤቷ ገብታ ጥቅልል ብላ ተኝታለች፡፡የሆነ ውስጧ በማታውቀው ነገር እርብሽብሽ እያለባት ነው፡፡እንዲሁ ስትጨነቅ ነው የዋለችው..እርግጥ ይሄ ስሜት ከተጻናወታት ሰነባብቷል ..ሳምንታቶች አልፈዋል….ሀይለኛ የመደበት ስሜት
2👍1
መንፈሶን እያናወጸው ነው፡፡ሚገርመው ለዚህ ስሜት መከሰት ምንም መነሻ ምክንያት የላትም ..ግን እንዲሁ ሁሉ ነገር አስጠልቷታል..መኖር እራሱ ይደክማት ጀምሯል፡፡‹‹ሰው..እንዴት ከለምንም መነሻ እንዲህ እርብሽብሽ ይላል››እራሷን በራሷ ስትጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች ናቸው፡፡በተኛችበት ከሁለት ሰዓት በላይ ብትገለባበጥም እንቅልፍ ሚባል ነገር ሊሞክራት አልቻለም..ያለፈው ምስቅልቅል ህይወቷ ቁርጥራጭ ትዝታዎች ከዚህም ከዚያም እየተበጣጠቁ ይመጡባታል…የልጅነት ህይወቷ…በደረቷ አጐጠጐጤ ስታወጣ የነበራት ደስታ…….ዲላን ለቃ አዲስአበባ አጐቷ ጋር ለመማር ስትመጣ እንዴት ፈንጥዛ እንደነበር..አጐቷ እንዴት ይንከባከባት እንደነበር…እሷም ምን ያህል በመንሰፍሰፍ አጐቷን ከአባትም በላይ ትወደው እንደነበር …...ብኃላ ህልሟን ሲያጨልመው የተሰማትን የጠቆረ ስሜት……በዛን ወቅት የገጠማትን የጸለመ ህይወት….ስለእርግዝናዋ…ወደ ዲላ ተመልሳ ገበና-ከታች በሆነችው እናቷ ጉያ ተሸሽጋ ስለመውለዷ…ከዛ ቡኃላ ስለተቀየረው ስብእናዋ….ስለአሳዘናቻቸው ወንዶች…ስለኩማንደር መሀሪ ምንም አልቀራትም……የሰላሳ አመት የህይወት ትዝታዋን በሁለት ሰዓት ውስጥ መልሳ ከለሰችው…..
እዛው ከትዝታዋ ሳትወጣ ነበር በራፏ የተንኳኳው፡፡እንደምንም ወደቀልቧ ተመለሰች እና ከተኛችበት ተነስታ ልትከፍት ሄደች….አቤል ነበር
ማንነቱን ስታውቅ በደስታ ተጠመጠመችበት እና በሞቀ ሳላምታ ተቀበለችው..በዚህ ድብርት በጠፈነጋት ሰዓት ብቸኛ ማግኘት እና ከጎኗ እንዲሆን የምትፈልገው ሰው ቢኖር አቤል ብቻ ነው…..ወደ ውስጥ ጐትታ አስገባችውና በራፉን መልሳ ቀርቅራ ከሳሎን ወደ መኝታ ቤት ይዛው ገባች..አልጋው ላይ ጎን ለጎን ተቀመጡ
‹‹ሆቴል መስለሺኝ እኮ እዛ ሔጄ ነበር…… እራሷን አሟት ወደ ቤት ሄዳለች አሉኝ ..ስልክሽም ጥሪ አይቀበልም፡፡ከዛ አላስችል ብሎኝ ሳላስፈቅድሽ መጣው….››
‹‹እንኳንም መጣህ… የእኔ የልብ አውቃ…በጣም ድብር ብሎኝ ነበር››
‹‹ምነው… ምን ሆንሺብኝ?››
‹‹ባክህ እርብሽብሽ ብዬለው..?››
ይሄ ስሜትሽ እኮ ሰነባበተብሽ ….ለመሆኑ ዛሬ ደግሞ ምን ገጠመሸ?››
‹‹አላውቅም… ምን አልባት ልጄ ሳትናፍቀኝ የቀረች አይመስለኝም…..››
‹‹ኦ ሄሊ እሷስ እኔንም ናፍቃኛለች..ከሳምንት ቡኃላ መልሼ ለመሄድ እቅድ አለኝ…እንደውም አሁን ለጉዞዬ የሚረዳኝን አንዳንድ ነገሮችን ላይ ብንነጋገር ደስ ይለኛል፡፡››
ሮዝ ልክ መስከረም ወር ላይ በየሜዳ ተራራው ፈክቶ እንደሚታ የአደይ አበባ ፊቷ በርቶ ‹‹የእውነት ፤ልትሄድ ነው…?››ስትል በአድናቆት ጠየቀችው
‹‹አዎ እሄዳለው… የጀመርኩትን ነገር እስካጠናቅቅ መመላለሴ የግድ ነው….እንቺ የእናትሽን ደረት ተንተርሰሽ ለልጅሸ ደግሞ በተራሽ እስክታንተራሺያት ድረስ እረፍት አይኖረኝም››
ሮዝ የተፍለቀለቀው ስሜቷ መልሶ በተስፋ መቁረጥ ጭልም አለ‹‹አይ…ይሳካል ብለህ ነው……?እኔ እንጃ ባክህ..ለማኛውም እስቲ በርታ››
‹‹እበረታለው….. ብቻ የአንቺም ትብብር ወሳኝነት አለው››አለት በሀዘኔታ እና ፍቅር መካከል በሚዋልል ስሜት በትኩረት እየተመለከታት
‹‹እኔ ምን ማድረግ እችላለው?››
‹‹የእሷን ጥያቄ ለመመለስ ሚያስችሉኝን ታሪኮችን ልትነግሪኝ እና ልትተባበሪልኝ ይገባል፡፡››
‹‹ምን አይነት ጥያቄ?››
‹‹አንዱ እና ወሳኙ አባቷ ማን እንደሆነ?››
ተንዘረዘረች‹‹ነገርኩህ እኮ …አባቷ ምን እንደሆነ አላ..ው…ቅ..ም››
‹‹የልጅሽን የተከረቸመ ልብ አለስልሶ ለመክፈት ወሳኙ ቁልፍ ግን ይሄን ጥያቄዋን መመለስ ብቻ ይመስለኛል ፡፡››
‹‹አልችልማ በቃ አላውቀውም አልኮችሁ እኮ!!!….ባውቀውም ልነግራት አልችልም..የእኔን ህመም ሚረዳልኝ እንዴት አንድ ሰው በዚህ አለም ላይ አጣለው…?እንዴት ህመሜን ብቻዬን ስታመም እኖራለው..?እንዴት የቁስሌ ጥዝጣዜ ሌላውን ሰው ሊሰማው አልቻለም..?ቢያንስ የመከራዬ መግል ሽታ እንዴት ነው የእኔ የሆኑትን ሰዎች እንኳን የማይሸታቸው..?››እየተንሰቀሰቀች መነፍረቅ ጀመረች…….ወደደረቱ ጎተተና አቀፎ ግባሯን በመሳም ቃላት ሳይጠቀም ፀጉሯን በማሻሸት ብቻ ያጽናናት ጀመረ
‹‹አቤልዬ›› ለስለስ ባለ ድምጽ ጠራችው
‹‹ወዬ እሮዝ››
‹‹በፈጠረህ አንድ ነገር ላስቸግርህ››
‹‹የፈለግሺውን››
‹‹ልጄ ጋ ደውልና እስኪ አውራት..ካንተጋ ስታወራ ቢያንስ ድምጾን ልስማው››
‹‹ምን ችግር አለው››ብሎ ሞባይሉን አወጣ እና ደወለ…ሞባይሉ ተነሳ
‹‹እንዴ !!አንተ አለህ እንዴ?ከዛኛው ጫፍ የመጣ ማራኪ የሄለን ድምጽ ነበር
‹‹ትክክለኛ ጥያቄ ነው……ባክሽ ከዛሬ ነገ በአካል እመጣለው ብዬ ሳስብ መደወሉን ተዘናጋው..ለመሆኑ ደህና ነሽ?››
‹‹ይመስገነው በጣም ሰላም ነኝ››
‹‹ማዘርሽስ?››
‹‹እኔ እያለውላት ምን ትሆናለች ብለህ ነው ለእሷ እኔ አለውላት…ለእኔ ደግሞ ፈጣሪ አለልኝ.. ስለዚህ ምንም አንሆን አትስጋ..››መለሰችለት
‹‹አሪፍ ገለጻ ነው..ይሄ ጣፋጭ ጫወታሽ በጣም ናፍቆኝ ነበር …እንግዲህ ተዘጋጂ የዛሬ ሳምንት አካባቢ እመጣለው››
‹‹የት?››
‹‹እንዴት….? የት… ?ዲላ ነዋ …ምነው ቀጠሮ እኮ አለን››
‹‹እሱማ አለን ግን…..››.
‹‹ግን ምን ?››
‹‹ዲላን እኮ ለቀናል››
ይሄንን ንግር ስትሰማ ሮዝ ከተቀመጠችበት አልጋ ላይ ተስፈንጥራ በመነሳት ቆመች..አቤልም ደነገጠ
‹‹ለቀናል ስትይ …አልገባኝም?››
‹‹ሻሸመኔ ገብተናል››
‹‹አሁንም አልገባኝም… በምን ምክንያት?››
‹‹አይ አንተ….በእኛ ቤት መጥተህ በሄድክ ማግስት ብዙ ተአምሮች ተከስተዋል..እንደውም ከዛሬ ነገ እያልኩ ተዘናጋው እንጂ ደውዬ ልነግርህ ሀሳቡ ነበረኝ..ባክህ ያልታሰቡ ሰዎች በለሊት እቤታችን ገብተው እኛን አውጥተው ሙሉ ቤታችንን …››በዚህ ጊዜ ላውድ የነበረውን ስልክ አጠፋውና ለብቻው ማደማጥ ጀመር ….ሮዝ እየተንቆራጠጠች ነው ..ከመጮኸ እራሷን ለመግታት እየታገለች ነው…
የሄለን ንግግር ቀጥሏል‹‹…ከእነ ሙሉ ዕቃው አንድደውት ሄዱ››
‹‹እነማን?››
‹‹ማነታቸውን ብናውቅማ ጥሩ ነበር…መቼስ እኔም ሆንኩ እማዬ በዚህ መጠን ሊበቀለን የሚችል ጠላት የለንም….. ምን አልባት የዛች የጓደኛህ ጣጣ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ ..ደግሞም እርግጠኛ ነኝ ከዛ ውጭ አይሆንም››
‹‹እና ታዲያ አሁን ሻሸመኔ ማን ጋር ናችሁ?››
‹‹ሻሸመኔማ ያው ገነት ውስጥ ነን ብልህ ይቀላል …››ያሉበትን ቦታ ሁሉንም በዝርዝር አስረዳችው…ከመጣ ሻሸመኔ ድረስ መጥቶ ሊያገኛት እንደሚችል ነግራው ተሰናበተችው..ከዛ ቡኃላ የሮዝን ዓይን ማየት ነው የከበደው..የተሰበረ ልቧን በምን ቃላት ሊጠግንላት እንደሚችል ….ምን አይነት አይዞሽ ባይት ሊያጽናናት እንደሚችል ሊገለጽለት አልቻለም..ብቻ ዝም ብሎ ወደአልጋው ይዞት ወጣ..አንሶላውን ገለጠ እና ከስር እንድትገባ አደረጋት..ያለምንም መቃወም እንዳደረጋት ሆነችለት..እሱም ልብሱን አወለቀና ተከትሏት ከአንሶላው ውስጥ መሸገ…. ጭምቅ አድርጐ አቀፋት..በጣም ጭምቅ አድርጐ…ከገላው ጋር አጣብቆ…..

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍6
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ህይወት ወራጅ ወንዝ ነው-ክንውኑ ያስደምማል
ምንም ቋሚ ነገር የለም -ሁሉም ይጐርፋል…ይተማል
ተነባብሮ ተደራርቦ- ይፈናጠቃል ይፈሳል
በአጋጣሚ ያጣብቃል-ሳይታሰብ ያላቅቃል
ህይወት ወራጅ ወንዝ ነው -ድንገት ይጠባል… ይሰፋል
መዋኘት መፍሰስ የቻለን- ከአድማስ ባሻገር ያደርሳል
ተንፈራግጦ የታገለን -ከግንድ ያጋጫል ያጠፋል
ህይወት ወራጅ ወንዝ ነው- ነፍስ ይሰጣል…ነፍስ ይነጥቃል፡፡
--------------------------------------------------------------
‹‹ደከመሽ አይደል ?ብዙ ሰዓት እኮ ሰራን››አላት ከጐኗ ተነስቶ ፊት ለፊቷ በመቀመጥ
‹‹አረ አልደከመኝም አምስት ደቂቃም የቆየን አልመሰለኝም››በደስታ በተፍለቀለቀ እና በሚያበራ ፈገግታ መለሰችለት….
ኩማደር መሀሪ ለሄለን በገባላት ቃል መሰረት ፒያኖ ያሰለጥናት ከጀመረ ሳምንት አለፈው..በየቀኑ ከአንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል… አንዳንዴም እስከ ሁለት ሰዓት በራሱ በተዘጋ የወንደላጤ ቤት ውስጥ ያሳልፍሉ..ሰዓቱ ደግሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ያለው ወደ ምሽቱ አካባቢ የተጠጋው ሰዓት ነው የመረጠጡት
ሄለን በመጀመሪያዎቹ ቀናት የኩማደርን ማንነት እና የት እንደምታውቀው ስለምታዉቅ ደንግጣ እና ግራ ተጋብታ ነበር…አዎ ዲላ ይኖር እንደነበረ እና ከሮዝ ጋር ግንኙነት እንደነበረው እሷንም ፍለጋ እቤት ድረስ መጥቶ በነበረበት ሰዓት አግኝታውዋለች በዚህም የተነሳ ያቀረበላትን ጥያቄ ለመቀበል እና ላለመቀበል ከራሷ ጋር ብዙ ተታግላ ነበር..ቡኃላ ግን እስኪ ልሞክረው ብላ ጀመረች..ዋል አደር ስትል ግን ጭራሽ ነገሩን እየዘነጋችው መጣች…አቀራረቡ …ለእሷ የሚያደርገው እንክብካቤ ልክ ተወዳጅ ታላቅ ወንድሞ መስሎ እንዲታያት ማድረግ ችሎል፡፡በአጠቃላይ ስሜቷን ተቆጣጥሯል ፡፡
…ኩማንደር መሀሪ ደግሞ እስከአሁን ብዙ ነገር እያነሳ ከእሷ ጋር ማውራት ቢችልም ስለዲላ ትንፍሽ ብሎላት አያውቅም…ስለእሷ ባሰበ ቁጥር ግራ ይጋባል..በጣም ታሳዝነዋለች…ከክፉ መሀፀን በቅላ….ክፉ እጅ ላይ ወደቀች…ምንም ማድረግ አይችልም..ይሄ በአለም ያለ ነባራዊ ሁኔታ እና በየእለቱ የሚከሰት ተግባር ነው..በዚህን አይነት ጊዜ ለሀጥአን መቀጣጫ ታስቦ የዘነበ መአት ጻድቃኖችን መለብለቡ አይቀርም…..
አብረው ፒያኖ ከመለማመድ ውጭ ስለእናቷ አውርተው አያውቁም ስለእሷ ብታወራ ጥሩ ስሜት እንደማይሰማው ታውቃለች ሄለን ብዙ ነገር ይቀርብኛል ብላም ታስባለች በጋራ እንኳን አቅድውት ስለነበረው ሄለን ስለአባቷ ጉዳይ በራሷ ድምፅ ቀድታ ለሷ እንዲያሰማት አቅደው ነበር ስለሱ እንኳን አንስታ ማውራት አልፈለገችም
ሙዚቃ መለማመዱ ብቻ አይደለም የሚቀርባት…ለአባትነት የቀረበው ወንድምነቱ ይቀርባታል..በጣም ለምዳዋለች…ሰው እንዴት በሳምንት እንዲህ ሰውን ይለምዳል..?ለራሷም እየገረማት ነው…
‹‹ትኩስ ሀይል አይደለሽ…መች በቀላሉ ትደክሚያለሽ››አላት
አልመለሰችለትም..እንደማፈር ብላ አንገቷን አቀረቀረች..
ለደቂቃዎች ዝም ተባባሉ…ዝም ሲል ተፈራዋለች….‹‹ምነው ዝም አልክ?››
‹‹ኦ ይቅርታ በሀሳብ እኮ ጭልጥ አልኩ..ስለአባ ሽፍንፍን እያሰብኩ ነበር››
‹‹ስለእሷቸው ምን የሚያሳስብ ጉዳይ አለ? ምነው የሚያሳስር ወንጀል አገኘህባቸው እንዴ?››
‹‹በፍጹም ….ፃድቅ ናቸው ይባሉ የለ እንዴ .. ?እንዴት ወንጃል ላገኝባቸው እችላለው..?ደግሞስ ወንጀል አገኘውባቸው ብልስ እንደ መላአክ የሚያያቸው የሻሸመኔ ኑዋሪ የሚያምነኝ ይመስልሻል…?ሰላማዊ ሰልፍ ነው የሚወጡብኝ፡፡ ››
‹‹እና ሌላ ስለእሷቸው ምን አሳሰበህ?››
‹‹ብዙ ብዙ ነገር ነዋ..ለመሆኑ አሁን ወደ እኔ ስትመጪ እቤት ነበሩ?››
‹‹አዎ …ትናንት ፀሎት ቤታቸው ገብተው እንደጠረቀሙ ናቸው››
‹‹ለዚህን ያህል ረጂም ጊዜ ይፀልያሉ ማለት ነው?››
‹‹ሁለት ቀን ምን አላት …?ሶስት እና አራት ቀን ነው የሚቆዩት ….እንዴት ሰው ለዚህ ሁሉ ቀን ያለምግብ እና መጠጥ ብቻውን ቤት ዘግተው ማሳለፍ ይችላል?ለእኔም በጣም የሚገርም ተአምር ነው፡፡በቃ የከተማ መናኝ በላቸው››
‹‹አንቺስ አብረሻቸው አትፀልይም?››
‹‹አረ በፍጹም …ወደ ጸሎት ክፍላቸው ሲያስገቡኝ አይደል?››ብላ አይኗን ወደ ኩማንደሩ አንድ የተዘጋ ክፍል ወረወረች…ይህቺ ክፍል ልክ እንደ አባ የፀሎት ክፍል ሁሌ በመጣች ቁጥር ተቆልፎ ነው የምታገኘው..ደግሞ ይህቺ ዝግ ክፍል እታች ምድር ላይ ከሚገኘው የአባ ፀሎት ቤት ጋር በትይዩ አቅጣጫ መገኘቱ ግርምት ይፈጥርባታል…
‹‹ጥሩ ነው…ግን አሁን አሁን እየወደድኮቸው መጥቼያለው መሰለኝ››
ከት ብላ ሳቀችና ‹‹እንዴ …በፊት ትጠላቸው ነበር እንዴ?››
‹‹እንደ እሱ ማለቴ እንኳን አይደለም…በፊት ስለእሷ
ስለእሳቸው ፍቅርም ሆነ ጥላቻ በውስጤ አልነበረም..አሁን ግን..››
‹‹እሺ አሁን እንዴት ልትወዳቸው ቻልክ?››
‹‹ባንቺ ምክንያት ነዋ..እሷ
እሳቸው ወደ እዚህ ባያመጡሽ ከእኔ ጋር አንገናኘም ነበር…››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው››አለችው እንደመተከዝ ብላ
‹‹ይገርምሻል ሄለን አንዳንዴ ሳስበው በውሳኔዬ ላይ ጥርጣሬ ያድርብኛል››
‹‹በየትኛው ውሳኔህ?››
‹‹አንቺን ፒያኖ ላሰልጥንሽ ብዬ መጀመሬን….››ብሩህ የነበረው የሄለን የፊት ገጽታ በአንዴ ጭላሼት ለበሰ
‹‹እሱ እንኳን ትክክል ነህ… እኔም በጣም እራስ ወዳድ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ነው….. ጊዜህን በጣም እየተሸማውብህ ነው..››
‹‹ኖ..ኖ እንደእዛ ማለቴ አይደለም…ካንቺ ጋር ማሳልፋት እያንዳዶ ደቂቃ ለስጋዬም ሆነ ለመንፈሴ ምን ያህል መነቃቃት እና ደስታ እንደሚፈጥርብኝ መገመት አትቺይም…አነቺ እዚህ ቤት ስትገቢ እናቴ እንደመጣችነው መስሎ ነው ሚሰማኝ››
ድፍርስ ብሎ የነበረው ስሜቷ በሰኮንዶች ውስጥ መልሶ አንሰራራ‹‹እና ታዲያ ውሳኔህ ላይ እንዴት ጥርጣሬ ሊያድርብህ ቻለ?››
‹‹አየሽ..ፍቅር ያስፈራኛል…አባቴን እና እናቴን በሞት ከተነጠቅኩ ብኃላ ሌላ ሰው የእኔ ነው ብዬ መቅረብ እና መልመድ ፈራለው…ምክንያም ከመልመድ ውስጥ ፍቅር ተፈልፍሎ መውጣቱ አይቀርም….ያንን ፍቅር ደግሞ በሆነ አጋጣሚ መልሶ የማጣት ዕጣ ቢያጋጥመኝ ዳግም መቋቋም የምችል አይመስለኝም..በዚህ የተነሳ ከእናቴ ሞት ጀምሮ ላለፉት ሶስት አመታት ሰውን ስሸሽ እና በራሴ የብቸኝነት ዋሻ ውስጥ ስወሸቅ ነው የከረምኩት፤ አሁን ግን በዚህች አንድ ሳምንት ውስጥ በጣም እየለመድኩሽ መሆኑን ሳስብ እየፈራው ነው…ማታ ሸኝቼሽ በማግስቱ የመለማመጃ ሰዓታችን ደርሷ እስክትመጪ ጊዜው በጣም ይረዝምብኝ ጀምሯል….››በማለት ከእሱ አንደበት እሰማዋለው ብላ ያላሰበችውን ..የጉርምስና ልቧን በአንዴ የሚደረማምስ የማላውቀው አባቴ አንድ ቀን መጥቶ ይነግረኛል ብላ በተስፋ ትጠብቀው የነበረውን የሚያቀልጥ የፍቅር እና የመፈለግ ዜና የሚያበስሩ ቃላቶችን ለአንድ ሳምንት የተወዋወቀችው ይሄ ኩማደር አበሰራት..ውስጦ በደስታ እረሰረሰ..እንባዋም በአይኖቾ ከፍቃዷ ውጭ ተነኮለለ…
‹‹ኩማደር..ከዚህ በፊት ስለደረሰብህ ሀዘን እና ብቸኝነት በእውነት በጣም አዝናለው..ፍቅርን ማጣት ምን ማለት እንደሆነና በልብ ውስጥ ምን አይነት ሽንቁር እንደሚፈጥር በደንብ አውቃለው..እኔም ሙሉ የቤተሰብ ፍቅር አግኝቼ አይደለም እየኖርኩ ያለውት ..ግን አሁን ያልከው ፍቅርን የመፍራት አባዜህ እኔን ፒያኖ ከማሰልጠን ጋር ምን እንዳቆራኘው አሁንም አልገባኝም?››ጠየቀችው ይበልጥ ሚያመሞቅ ንግግር ከእሱ መስማት ፈልጋ…
‹‹አየሽ ሄለን ይሄ ፒያኖ ልምዳችን ለሶስት ወር ወይም ለአራት
👍1
ወር ቢቆይ ነው..ከዛ ቡኃላ በቃ ግንኙነታችን ይቋረጣል ማለት ነው…አየሽ ያ ማለት ደግሞ ለምጄ አጣውሽ ማለት አይደል… ?ይሄ የሰው ትንፋሽ የለመደው የወንደላጤ ቤቴ መልሶ ቀዘቀዘ ማለት አይደል..?››
‹‹አይደለም…. በፍፅም አይደለም….አኔ በእዚህ ትውውቃችን ምን ያህል ደስተኞች እንደሆንኩ አታውቅም ….እዚህ ቤትህ ስመጣ ለፒያኖ ለመለማመድ ብቻ እንዳይመስልህ…..ልክ ታላቅ ወንድሜ ቤት እንደምመጣ አይነት እየተሰማኝ ነው ምመጣው..መቼም ይሄንን ግንኙነታችንን ማቋረጥ አልፈልግም …ሁሌ ከስርህ የማትጠፋ ታናሽ እህትህ መሆን ነው የምፈልገው ….›› አለችው በፈገግታ
‹‹አመሰግናለው››አላት በእርካታ…አዎ አሁን ቀስ በቀስ የወጣትነት አማኝ ልቧን በመሸርሸር ወደ ሚፈልገው መስመር እያስገባት መሆኑን በመረዳቱ ለስኬታማነቱ እራሱን በውስጡ አደነቀ…..
‹‹እሺ ወንድም ጋሼ አሁን በጣም መሸ ልሂድ›› ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች….
‹‹አንቺ አሪፍ ስምነው ያወጣሺልኝ… ወንድም ጋሼ ነው ያልሺኝ?››እያለ ከመቀመጫው ተነሳ እና እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ውጭ ድረስ ሸኛት ‹‹መልካም ለሊት… መልካም ህልም ››በማለት ወደ ራሱ ጐትቶ ግንባሯን ሳመና በቆመችበት ጥሎት ፊቱን አዙሮ ወደቤት ተመለሰ..
እሷም ልትገምታቸው ላልቻለቻቸው ሴኮንዶች ባለችበት ፈዛ ቆመች..የሆነ የማታውቀው ስሜት ነው የተሰማት ..ከዚህ በፊት እንዲህ ከሰውነቷ ልጥፍ ብሎባትም የሳማት ሰው መኖሩን አታስታውስም……. በጣም ያስገረማት ደገሞ በእሱ መሳሙ ሳይሆን መሳሙን ተከትሎ በውስጧ የተፈጠረባት ምንነቱን መለየት ያልቻለችው ግራ አጋቢ ስሜት ነው...ብዥ ነው ያለባት….እንዴት ከተገተረችበት ተንቀሳቅሳ ዞራ እቤቷ እንደደረሰች ራሱ አታውቅም
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሮዝ እና አቤል ወደ ሻሸመኔ እየሄዱ ነው፡፡በህዝብ ትራንስፖር አይደለም የሚጓዙት….ሮዝ በተከራየችው የቤት መኪና በአቤል ሾፋሪነት ነው፡፡
ሮዝ በዚህ ሰዓት ወደ ሻሸመኔ የምትጓዘው ለመዝናንተ ወይም ለሽርሽር አይደለም…ተገዳ ነው…የምታደርገው ጠፍቷት ነው፡፡እናቷ እና አንድያ ልጆ የሚኖሩበት ቤት ባልታወቁ ሰዎች ተቃጥሎባቸው..ጥሪት አልባ ሆነው ባዶ እጃቸውን በመቅረታቸው ሰው እጅ ላይ ለዛውም በባዕድ ሰው ድጋፍ ስር እንደሆኑ ከሰማች ጊዜ አንስቶ በውጧ ሰላም አልነበራትም…
አደጋውን በሰማች በማግስቱ ሀያ ሺ ብር በባንክ ልካላቸው መላኳንም እንዲያውቁት አድርጋ ነበር..ግን የደረሳት ምላሽ ጭራሽ ብሶቷን የሚጨምር ነበር፡፡
‹‹ያንቺን ሽራፊ ሳንቲም አንፈልግም..እኛ በእግዚዘብሄር ጥበቃ ስር ነው ያለነው…ለእኛ አታስቢ… ብርሽን መልሰሽ አውጪው….እና ለራስሽው ተጠቀሚው›› ብለው ነበር የመለሱላት፡፡
ከዛ ቡኃላ ነው በጣም ከተቀየሟት እናቷ እና ልጆ ጋር ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ወሰና ወደ ሻሸመኔ እየተጓዘች ያለችው..ለዚህም ድጋፍ እና ወኔ ይሆናት ዘንድ ከጐኗ አቤልን አስከትላለች…..
ዝዋይን እስኪያልፉ አቤል መኪናውን እያሽከረከረ እሷ እንቅልፍ የወሰዳት አስመስላ ወንበሯን ወደኃላ ለጥጣ አይኖን በመጨፍን በትካዜ ስትናውዝ ነበር የቆየችው ..አሁን ግን ለመጀመሪሪያ ጊዜ እንደመባነን እና እንደመነቃቃት ብላ መናገር ጀመረች.. ‹‹አብዬ..አሁን ፊት ለፊታቸው ስጋፈጣቸው እንዴት ይቀበሉኝ ይመስልሀል?››
‹‹ቀላል አይሆንም… ግን እወነታውን ከመጋፈጥ ውጭ ሌላ መንገድ የለሽም.››
‹‹እንዴት አድርጌ ነው የምጋፈጠው? ከሚጠሉህ ሰዎች ፊት ለፊት መቆም እኮ በጣም ከባድ ነገር ነው››
‹‹ይህውልሽ ፈፅሞ እንደዚህ እዳታስቢ… አሁን የምትሄጂው ወደሚጠሉሽ ሰዎች ጋር ሳይሆን በጣም የሚወዱሽ እና የሚያፈቅሩሽ ግን ለጊዜው ወደተቀየሙሽ ያንቺ ወደሆኑ ሰዎች ጋር ነው ፡፡››
‹‹አይ አንተ……. እስኪ እንደእዛ ቀለል እያደረግክ ብርታት እና ወኔ ስጠኝ››
‹‹አይ ባዶ ወኔ እየሰጠውሽ አይደፈለም..የሚሰማኝን እውነት እየነገርኩሽ ነው… በጣም ይጠሉኛል ብለሽ በውስጥሽ ጨላማ ሀሳብ ይዘሽማ ከሄድሽ ጥሩ ነገር አይገጥምሽም..ምንም ቢሆን እኮ ለእናትሽም ልጆ..ለልጅሽም እናቷ ነሽ…እርግጠኛ ነኝ በዚህ ምድር ላንቺ ከእነሱ በላይ የምታስቢላቸው ….እነሱም ካንቺ በላይ የሚጨነቁለት እና ክፍውን መስማት የማይፈልጉት ሌላ ሰው ያለ አይመስለኝም….በመሀከላችሁ ቅያሜ እንጂ ስር የሰደደ ጥላቻ ሊኖር አይችልም..፡፡እስኪ ነገሩን በራስሽ ገልብጠሸ አስቢው …አሁን ልጅሽ የፈለገ ነገር ብታጠፋ..ምንም ነገር ብትበድልሽ አምርረሽ ልትጠያት ትችያት ነበር..?እናትሽንስ?››
‹‹እሱን እንኳን እንዴት ብዬ?››
‹‹እኮ በቃ እነሱም እንደዛ ናቸው..››
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሻሸመኔ ሲደርሱ 11 ሰዓት ሆኖ ነበር…ወዲያው ለሄለን ደወለላት
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ ሄለን ሰላም ነሽ››
‹‹አለውልህ አቤል ..አንተስ ?››
‹‹እኔ ሰላም ነኝ መጥቼ ነበር…ሰፈራችሁ የት ነው?››
‹‹ሰፈራችን…››ግራ ገባት እቤታቸውን ትንገረውና ይምጣ ወይስ እሱ ወዳለበት ሄዳ ታግኘው?
‹‹ምነው ድምጽሽ ጠፋ?››
‹‹ሰፈሩን በምልክት ብነግርህ ላታውቀው ትችላልህ ብዬ ሰግቼ ነው..ወይ ለምን አንተ ያለህበትን ቦታ አትነግረኝምና አኔ አልመጣም?››
‹‹አይ ግድ የለሽም አንቺ ብቻ ትክክለኛ የቤታችሁን አድራሻ ስጪኝ …ሌላውን ለእኔ ተይው..አያትሽንም ማግኘት ስላለብኝ እቤት ነው መምጣት የምፈልገው..መቼስ አባ ቅር የሚላቸው አይመስለኝም?››
‹‹ኸረ በፍጹም ››
‹‹እሺ እንግዲያው ንገሪኛ››
‹‹በዝርዝር የነገረችውን በማስታወሻው ላይ መዝግቦ እንደጨረሰ ተሰናብቷት ስልኩን ዘጋው…ሮዝን አስከትሎ እንደመጣ አልነገራም ..ይህንን ያደረገው ቀድሞ ነገር ላለማበለሻሸት ነው፡፡››
‹‹አሁን ቀጥታ እንሂድ አይደል?››ጠየቃት ወደ ሮዝ ዞሮ
‹‹ተው ይቅርብኝ….. መጀመሪያ አንተ ብቻህን ሂድና ነገሩን አጣራ ››
‹‹ኸረ ተይ ዝም ብለሽ ተጋፈጪው ..ካልደፈረሰ አይጠራም ሲባል አልሰማሽም››
‹‹ ተው እኔ አልፈልግም…››
‹‹እሺ እንሂድና አንቺ መኪናው ውስጥ ትጠብቂኛለሽ..እኔ ብቻዬን እንደመጣው አስመስዬ እገባለው ሁኔታውን አይቼ አሪፍ ከሆነ ትቀላቀይናለሽ ካለበለዚያም ዛሬን አድረን ነገ ተነገወዲያ ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን››
‹‹ባይሆን ይሄኛው ዘዴህ ይሻላል››አለችው …ተንፈስ እንደማለት ብላ..አቤልም ያቆመውን መኪና አስነስቶ ነዳው….. የጠቆመችውን ቤት ለማግኘት ብዙም አልተቸገረም..በተስማሙት መሰረት መኪናዋን እራቅ አድርጐ አቆማት እና ሮዝን ጭብጥ እንዳለች መኪናው ውስጥ ትቷት ወደአባ ቤት አምርቶ አንኳኳ …...ራሷ ሄለን ነበረች በሩን የከፈተችለት..በደመቀ ፈገግታ እና በተፍለቀለቀ የፈንጠዝያ ስሜት ነበር ተቀብላ ወደ ውስጥ እንዲገባ የጋበዘችው..ምንም አልተግደረደረም ዘልቆ ወደውስጥ ገባ…ሳሎን ሲደርስ የሄለንን አያት ብቻ ሳይሆን አባ ሽፍንፍንንም ጭምር ነበር ያገኛቸው…ሄለን ከሁለቱም ጋር አስተዋቀቻቸው..ለእናትዬው ስለማንነቱ በጆሮአቸው ሔዳ ሹክ አለቻው..በፊታቸው ላይ ምንም አይነት የስሜት መለዋወጥ አልታየባቸውም…ሄለን ወዲያው ቡና ለማፍላት ጉድ ጉድ ማለት ጀመረች እናትዬውም መክሰስ ነገር ለማዘጋጀት ወደ ኩሽና ሄዱ
‹‹ከአዲስ አበባ ነው የመጣውት አልከኝ?››አሉት አባ
‹‹አዎ አባቴ…እነሄለን በጣም ወዳጆቼ ናቸው የደረሰባቸውን አደጋ ከሰማውበት ቀን አንስቶ ከዛሬ ነገ እመጣለው ስለ እስከዛሬ ቆየው››ብሎ መለሰላቸው …መልሱ በግርምት የታጀበ ነበር..በዚህ ሙቀት ወቅት ለዛውም እቤታቸው ውስጥ ሆነው መላ አካላቸውን ፊታቸውንም ሳይቀር በዚህ መልክ ሸፍነው የፈረንጆችን
👍3
የገና አባትን መስለው ሲያያቸው ለምን አይገረም..እንዲህ አይነት አለባበስ የሚለብስ ቄስም ሆነ መለኩሴ በህይወት ዘመኑ ገጥሞት አያውቅም…በጣም ነው ትኩረቱን የሳቡት..‹‹ቆንጆ ገፃባህሪ ይወጣቸዋል›› ሲል ወሰነ እና መላ ነገራቸውን በአእምሮ መዝግቦ ለመያዝ በጥሞና እያጠናቸው ጭውውቱን ቀጠለ
‹‹አይ ልጄ ኑሮ መች ፋታ ይሰጣል ብለህ ነው..እንኳን ትርምስ የበዛበት የአዲስ አበባ ኑሮ ይቅርና እዚህ እኛ ጋር እራሱ ወከባ ነው…በዚህ ዘመን ህይወት የጽሞና ጊዜ ራሱ ልትሰጠን እየፈቀደች አይደለም…..››
‹‹እውነቷትን ነው አባ …ሰው ከራሱ አልፎ ለሌላው ችግር መድረስ እያቃተው ነው…ብቻ እንኳንም እርሶን ጣለላቸው እንጂ …››
‹‹አይ ልጄ እኔማ ምን አደረግኩላቸው ብለህ ነው..እንደውም በተቃራኒው የእኔ ብቸኝነት ለመቅረፍ ሲያስብ እነሱን ጣለልኝ..የቤቴ ድምቀት ሆነውልኛል…››በዚህን ጊዜ ሄለን የቆላችውን ቡና ልትወቅጥ ከሳሎን ይዛ ስትወጣ አያትዬው ደግሞ የተሰራውን መክሰስ ይዘው መጡና አቀረቡ… አባ ባረኩና አብረው መብላት ጀመሩ.. የአባ እና የአቤል መግባባት የረጂም ጊዜ የሚተዋወቁ ወዳጆች ነው የሚያስመስላቸው..ሄለን እንኳን ተገረማለች..መክሰሱ ተበልቶ እንደተጠናቀቀ እና መአዱ እንደተነሳ… ሄለን የቀዳችውን ቡና ለሶስቱም አቀረበችላቸው…በጫወታ እያዋዙ ጠጥተው ሲኒውን መለሱላት ደገመቻቸው..በዚህን ጊዜ ሰዓቱ 12፡15 ሆኖ ነበር ..ሄለን ቀልቦ ያለው ኩማንደሩ ቤት ነው..ናፍቋታል…ይሄኔ ስራውን ጥሎ እሷን ፒያኖ ለማሰልጠን እቤት ቁጭ ብሎ እየጠበቃት ነው…
‹‹አቤል ይቅርታ ከአባ ጋር የያዝከው ጫወታ የተመቸህ ይመስለኛል…እኔ ጥዬህ ልሄድ ነው››አለችው ቅር እያላትማ እያፈረችም
‹‹የት ልትሄጂ ነው?››ጠየቃት ግራ ተጋብቶ
‹‹የፒያኖ ልምምድ አለብኝ ..እንደውም 15 ደቂቃ አርፍጄያለው››
‹‹ግድ የለለሽም ሂጂ ሳምንቱን ሙሉ እዚህ ነኝ …ማታ ደውልልሻለው››አላት ተሰናብታው ፈጥና ግቢውን ለቃ ወጣች… በጓሮ በኩል ዞራ ከጀራባ ባለው ጊቢ ወደሚገኘው የኩማደሩ ቤት አመራች
ሄለን ወጥታ እንደሄደችም..‹‹ተጫወቱ ኩሽና ትንሽ ስራ ይዤ ነው›› ብለው አያትዬውም ለቀውላቸው ወጡ
..አቤል ይሄን አጋጣሚ ሊጠቀምነበት ፈለገ‹‹አባ እንደው ደፈረኝ አይበሉኝ እና አንድ ነገር ላማክሮት ነበር››
‹‹ልጄ አባትህ ነኝ ቀጥል››ሲሉ አበረታቱት
‹‹ሮዝን ያውቋታል?››
‹‹ሮዝ እሮዝ››
‹‹የሄለን እናት ..አዲስአበባ ያለችው››
‹‹አዎ እናቷ አንድ ሁለቴ ስለእሷ አጫውተውኛል….ለአንተም ወዳጅህ ነች መሰለኝ…?እንደው አትታዘበኝ እና እኔ ስለ እሷ ልጅ ሳስብ እንዲሁ ታሳዝነኛለች››
የአባ ንግግር ለአቤል ደስታ ፈጠረለት… ልክ እንደ አረንጓዴ የመንገድ መብራት ወደፊት እንዲቀጥል አበረታታው.. ‹ቢያውቋት ደግሞ ይገርሞታል…በጣም የምታዛዝን …ማንም ያልተረዳላትን ብዙ መከራ ብቻዋን አፍና የኖረች ምስኪን ነች››
‹‹አዎ እኔም እንደእዛ ነው የሚሰማኝ››
‹‹እና አባ ይህቺ ሮዝ..››
‹‹ሮዝ ምን ሆነች?››
‹‹የእናቷ እና የልጆ ጉዳይ በጣም አሳቧታል››
‹‹አልገባኝ…እንደምታየው እነሱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት….ምንም የሚያሳስብ ጉዳይ ያለ አይመስለኝም››
‹‹አይ አባ እሷን ሰላም የነሳት ከእነሱ ጋር ጥል ላይ ስለሆነች ነው …መታረቅ ትፈልጋለች… ይቅር እንዲሏት ትሻለች››
‹‹አይ ልጄ ታዲያ እነሱን ማስታረቅ እኮ የእኔ ስራ እና ኃላፊነት ነበር …አንተም መልካምም አልሰራህ … ይዘሀት መጥተህ ቢሆን እኮ ..››
ከአፋቸው ነጠቀቸውና ‹‹መጥታለች እኮ ውጭ መኪና ውስጥ ነች ያለችው››
‹‹የት አልከኝ?››
‹‹እዚሁ እናንተው ሰፈር ከግቢው ውጭ ..ዝም ብሎ መግባ ፈርታ እና ተሳቃ ነው››
‹‹ይሄን ሁሉ ሰዓት ውጭ አስቀምጥኸት ነወ? ምነው ልጄ እግዜር የማይወደውን ስራ ነው የሰራሀው..በል ሂድና አምጣት››
‹‹ግን አባ››
‹‹ምንም ግን የለም አምጣት ብዬኸለው አምጣት…››
አቤል ትዛዛቸውን አክብሮ ሮዝን ሊያመጣት ቤቱን ለቆ ወጣ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_አራት
:
ድርሰት፦በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...አቤል ያገኘውን እድል ባለማመን በጥድፊያ ነበር ወደ ሮዝ የሄደው..ኩምሽሽ ብላ መኪና ውስጥ እንደተቀመጠች ነበር ያገገኛት
‹‹ቆየውብሽ አይደል?››
‹‹የምዕተ ዓመት ያህል ነዋ…በዛ ላይ ሄለን ከግቢው ወጥታ በዛች ቀጭን መንገድ ወደ ጀርባ በኩል ስትሄድ ሳያት ምን ተፈጠረ ብዬ ነፍሴ ልትወጣ ነበር….ስልክህን ስደውልልህ ደግሞ አታነሳም››አለችው ስልችት እንዳላት በሚያሳብቅ እና እንባ በተናነቀው ስሜት
‹‹በይ አሁን እንግባ››
‹‹ወዴት ነው የምንገባው?››
‹‹ወደ ውስጥ ነዋ..አንቺ እኚ ቄስ እግዚያብሄር የባረካቸው ናቸው …ገና አብራርቼ እንኳን ስለመጣንበት ጉዳይ ሳልነግራቸው ነው የተረዱኝ…እንደውም አንቺን እዚህ ውጭ አስቀምጪ ይህን ያህል በመቆየቴ በጣም ነው የገሰጹኝ…እሷን ብቻ ይዘኸት ና …እርቁን ለእኔ ተወው ብለውኛል››
‹‹እውነትህን ነው?›› በጉጉት እና በተስፋ ጠየቀችው
‹‹አዎ ተነሽ እንግባ…ለመሆኑ እማዬ ሰላም ነች››
‹‹ሰላም ናቸው… አሁን ልታያቸው አይደል?››
‹‹ወይ አቤልዬ በጣም ነው የፈራውት… ሽንቴ ሁሉ ሊያመልጠኝ ነው››አለች መኪናውን ለቃ ወደ ውጭ እየወጣች
‹‹አይዞሽ ጠንከር በይ›› ብሎ ስትንገዳገድ ደገፋና የመኪናውን በራፍ ዘግቶ እና ቆልፎ ይዞት ወደ አባ ሽፍንፍን ቤት ተጓዘ ..ልክ እቤት ደርሰው የሳሎንን በራፍ አልፋው ወደ ውስጥ እደገቡ እናትዬው በተቀመጡበት ቀና ብለው ሲያዩት እና ልጃቸው ሮዝ መሆኖን ሲያውቁ‹‹ወይኔ ጉዴ!!!›› ብለው ጩኹ….ጩኸታቸው ሮዝን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም አስደነገጠ.
‹‹ግቡ.. ግቡ ››በማለት አባ አቤል እና ሮዝ ተረጋግተው ወደውስጥ እንዲገቡ አበረታቶቸው…
‹‹እማዬ›› አለች ሮዝ ወደውስጥ በዝግታ እየመጣች
‹‹እማዬ አትበይኝ አንቺ ጉድ!! ››አሏት በተቀመጡበት ደንግጠው አፋቸውን በእጃቸው እንደያዙ
‹‹እማ ባክሽ ናፍቀሺኛል …በጣም ናፍቀሺኛል..››አለቻቸው…እናትዬው ፀጥ እንዳሉ ነው… እንባቸው በጉንጫቸው ላይ ተንኳለለ.. ሮዝ ተንደርድራ ወደተቀመጡበት ሄደችና እግራቸው ላይ ተዘረገፈች
‹‹እባክሽ እማ..እኔስ ማን አለኝ? ይቅር በይኝ ..እንደድሮሽ እንደልጅነቴ ተቆጥተሺኝ ና ገርፈሺኝ መልሰሽ አባበብይኝ…እማ ጠረንሽ ናፍቆኛል..እማ ትንፋሽሽ ርቦኛል…››አባ ሽፍንፍን በተቀመጡበት አቤል እንደቆመ ሁኔታውን እየተከታተሉ ነው፡፡
እናትዬው ዝም እንዳሉ ነው….. የሚያደርጉት ግራ ገብቷቸዋል…በዚህ ጊዜ አባ ሽፍንፍን መስቀላቸውን ከኪሳቸውን አወጡና ቆሙ ‹‹እንግዲህ ሰው ሆኖ ለዛውም ልጅ ሆኖ የማያጠፋ የለም…በቃ ይቅር በሏት ››ሲሉ መሸምገላቸውን ጀመሩ
‹‹አባ እርሶ እኮ ስለእሷ ሁሉንም አያውቁም››
‹‹ግድ የለም ሁሉንም ማወቅ አያስፈልገኝም..ግን እርግጠኛ ነኝ ከይቅርታ በላይ የሆነ በደል የለም..በዛ ላይ እናት በልጆ ላይ አትጨክንም..››
‹‹እርሱማ እንዴት ብዬ ጨክናለው?››
‹‹እግዜር ያክብሮት ..እመብርሀን እድሜ ትስጦት›› አባ መረቁ
‹‹በይ ተነሽ ››አሏት እናቷ ጭንቅላቷን እያሻሹ…
‹‹ይቅር አልሺኝ እማ..በቃ ታረቅን?››ባለማን እና በመነፍረቅ ጠየቀች
‹‹ተነሺ አልኩሽ እኮ…››ብለው ተከሻውና አነሱ እና ቀና እንድትል አደረጐትና በስስት እና በናፍቆት ጉንጯን ለመሳም ወደ እሷ በተሳቡበት ደቂቃ ሄለን ለፒያኖ ልምምድ የቀረውን ኩማደሩን ጥበቃ አሰልችቶት በመመለስ የሳሎኑን በራፍ ከፍታ ገባች..ፊት ለፊቷ የሚከወነውን ነገር ስታይ በድንዛዜ ሀውልት ሆና ነው የቋመችው፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሮዝ እና አቤል ሻሸመኔ አባ ሽፍንፍን ቤት ከከተሙ ሶስት ቀን አልፎቸዋል…በእነዚህ ቀናቶች ውስጥ የሮዝ ስሜት ግምሽ ደስታ ግማሽ ሀዘን….ግማሽ ሳቅ ግማሽ ለቅሶ ሁኖ ነው የሰነበተው፡፡ይህ የሆነበት ምክንያት ባላሰበችው ፍጥነት ከእናቷ ይቅርታን አግኝታ የውስጥ ሰላም ብታገኝም…ልጇ ሄለን ግን እስከአሁን አሻፈረኝ እንዳለቻት ነው፡፡በዚህ ክስተት አንድ እውነት ገብቷታል…እናትነት እና ልጅነት መካከል ያለውን ልዩነት…እናትነት የፍቅር ጥግ መግለጫ ነው..እናትነት የይቅር ባይነት የመጨረሻ ማሳያ ነው…ለዚህ ነው ከእናቷ የተመኘችውን ይቅርታ በቀላሉ ያገኘችው..፡፡ከልጇ ግን ቀላል አልሆነላትም..እናት በመሆን እና ልጅ በመሆን መካከል ያለው ልዩነት ይህ ነው
አሁን ሰኣቱ ከጥዋቱ 2 ሰዓት አካባቢ ነው ፡፡ቤተሰቡ በአንድ ጠረጵዛ ዙሪያ ከበው ቁርስ እየበሉ ነው፡፡አባ ሽፍንፍን፤ ሮዝ ፤እናቶ እና አቤል…ሄለንም ጠረጳዛውን ከባ አብራቸው ባትቀመጥም ሳሎን ውስጥ ግን አለች …የቁርስ ሰሀኗን ለብቻዋ ይዛ ሳሎኑ ጥግ ካለ አንድ ኩርሲ ላይ ቁጭ ብላ በፀጥታ እየበላች ነው..ይሄንን ያደረገችው ለሮዝ አልፈልግሽም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው..ቁርሱ እንደተጠናቀቀ ልብሷን ቀይራ ወደውጭ ስትወጣ..አያቶ ወደ ማድቤት አቀኑ…በዚህን ጊዜ ሶስቱ ብቻ ቀሩ..ሮዝ አባ ተነስተው ጥለዋት ከመሄዳቸው በፊት በውስጦ ሚተረማመሰውን ነገር መጠየቅ ጀመረች
‹‹አባ››
‹‹አቤት ልጄ››
‹‹እንደው እርሷም ጨከኑብኝ እኮ?››አለቻቸው
‹‹ምነው ልጄ ?ምን አደረግኩሽ..ሳለውቅ ምን አጠፋው?››
‹‹አይ አጥፍተወ አይደለም..ከእናቴ ስላስታረቁኝ እና የሷን ይቅርታ እዳገኝ ስላደረጉኝ ምን ያህል እንደተደሰትኩና የውስጥ ሰላሜም እንደተመለሰልኝ ልነግሮት አልችልም..ሄለን ላይ ግን ዝም አሉኝ››
‹‹አይ ልጄ መች ዝም አልኩ? አሻፈረኝ አለች እኮ…የአባቴን ማንነት ካልነገረቺኝ እናቴ ነች ብዬ ከእሷ ጋር ምነጋገርበት ጉዳይ የለኝም አለችኝ››
‹‹አይ አባ …እርሶም እኮ አልተጫኗትም?››
‹‹እንዴት እጫናታለው ብለሽ ነው…?እሷ ታዳጊ ወጣት እኮ ነች …ወጣቶችን ደግሞ በፀባይ በማግባባት እንጂ በመጫን እና በማስፈራራት የሆነ ነገር እንዲፈጽሙ ማድረግ ደግ አይደለም…አየሽ ልጄ አሁን በግድ ታረቂያት ብዬ በሳገድዳት እርቃችሁ ከልብ የመነጨ ስለማይሆን የእውነት አይሆንም …የእውነት ካልሆነ ደግሞ ዛላቂ አይሆንም ማለት ነው…እንደምታይው ደግሞ ሄለን ለእኔም በጣም የምወዳት ልጄ ነች…በምንም ነገር ልጫናት አልፈልግም..››ሲሉ ብዙም እንደማይረዶት እንቅጩን ነገሯት፡፡
‹‹እና ምን ይሻለኛል?››ጠየቀች አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ
‹‹የሚሻልሽ ጥያቄዋን መመለስ ብቻ ነው…ለማንኛውም አስቢበት አሁን ልለያችሁ ነው››ብለው የመጨረሻ ምክራቸውን በመስጠት ተለይተዋቸው ወደ ጸሎት ክፍላቸው ገብተው በራፍን ከውስጥ ቀረቀሩት…. ሳሎን ውስጥ አቤል እና ሮዝ ብቻ ቀሩ
‹‹አቤል ምን ይሻለኛል?››አለችው ወደ ክፉ ቀን ጓደኛዋ ዞራ….
‹‹እኔም ግራገብቶኛል ..ግን እኮ አባ ያሉት ነገር እውነታቸውን ነው››
‹‹እኔስ እውነታቸውን አይደለም መች አልኩህ….እውነታቸውን ነው እሺ ምን ላድርግ?››እየጮኸች ከመቀመጫዋ ተነሳች እና ሳሎኑን ለቃ ወደ በረንዳው አመራች
…አቤልም መቀመጫውን ለቆ ተከተላት‹‹እሺ ምን ይሻላል?እኔም እኮ የውስጥ ጭንቀትሽን ሳልረዳ ቀርቼ ሳይሆን ቢጨንቀኝ እና ሌላ ዘዴ አልታየህ ቢለኝ ››
‹‹አውቃለው ለእኔ ስትል እየተጨነቅክ እንደሆነ አውቃለው.. ስለጮህኩብህ ይቅርታ››ብላው በረንዳውን ለቃ ደረጃውን ወረደች እና ግቢ ውስጥ ወዳለች ወደ አንድ የዛፍ ጥላ በመሄድ መሬት ሳር ላይ ተቀመጠች ..አቤልም ያደረገችውን ከማድረግ ውጭ ለጊዜው ሌላ ምርጫ ስላልነበረው ተከተላት እና ሄዶ ስሯ ተቀመጠ…ሁለቱም በዝምታ ተውጠው ውስጣቸው ስለሚብላላው ነገር በየግላቸው ማሰላሰል ጀመሩ….በዚህ ቅጽበት ግን ያልጠበቁት ተፍለቅላቂ ሳቅ ከአካባቢው ተሰማ
👍1
የሄለን ነበር..፡፡ዞር ዞር ብለው ፈለጓት… ግቢው ውስጥ አትታይም…ግራ ገባቸው..፡፡
ወዲያው ግን ሮዝ የልጇ ድምጽ የተሰማበትን አቅጣጫ አወቀች...ከፎቅ ላይ ነው፡፡ፎቅ በረንዳ ላይ ፊቷን ወደእነሱ አቅጣጫ አዙራ ቀልቧን ግን ከፊት ለፊቷ ያለው ሰው ላይ ብቻ አኑራ ትታያለች …ጀርባውን ለእነሱ የሰጠ ሌላ ሰው አብሯት አለ …ፒያኖ የሚያስጠናት ሰው እንደሆነ ወዲያው ነው ያወቀችው…ስሜቷ ተነቃቃ..እዚህ ቤት እግሯ ከረገጠበት ቀን አንስቶ ይሄንን ሰው በአካል ልታየው ብዙ ቀን ሞክራ ነበር ..ዛሬ ተሳካላት፡፡ፊቱን ወደ እኛ ቢያዞር..ብላ በተመኘችበት ቅጽበት ሰውዬው ከመቀመጫው ተነሳና ቋመ …ወደቤት ሊገባ መስሏት ነበር…. ግን ፊቱን ወደ እነሱ አዞረ እና በረንዳውን ተደግፎ ከሄለን ጋር ማውራቱን ቀጠለ..በዚህን ጊዜ ሮዝ አይኖን ማመን አቃታት…አቅለሸለሻት… አጥወለወላት‹‹..እንዴ ..!!እነዴ…!! የፈጣሪ ያለህ!!!››
‹‹ምን ሆንሽ…?ምን ተፈጠረ?›› ግራ በመጋባት ዙሪያዋን እየተሸከረከረ ለፈለፈ… አቤል
‹‹እሱ ነው …እሱ እራሱ ነው››እጇን ወደ መሀሪ ቀሰረች..መሀሪ እጁን አውለበለበላት እና ሄለንን ከመቀመጫዋ አስነቶ እየጎተተ ወደ ውስጥ ይዞት ገባ….ሄለን ቀልቧ ከጫወታዋ እና ከኩማንደሩ ላይ ብቻ ስለነበረ እታች ምድር የሚገኙትን አቤልን እና እናቷን አላየቻቸውም…..
ግራ የተጋባው አቤል‹‹እሱ ማን ነው ?ምን ነካሽ?››
‹‹ተወኝ አቤልዬ….በጣም አደጋ ላይ ነኝ …አክትሞልኛል››
‹‹ ኸረ ምን ሆንሽ? አስጨነቅሺኝ እኮ!!››
‹‹ሄለንን ፒያኖ የሚያሰለጥናት…››
‹‹እ..ምን ሆነ?››
‹‹የዲላው እጮኛዬ ነው››
‹‹እጮኛዬ››በሰማው ቃላት እርግጠኛ መሆን አልቻለወም
‹‹አዎ እርግጠኛ ነኝ በእሷ በኩል ሊበቀለኝ ነው..በቃ ሊያወድመኝ ነው››በለቅሶ ታጅባ ለፈለፈች
‹‹ኸረ ተረጋጊ››
‹‹ምኑን ተረጋጋውት… በአስቸኳይ የሆነ ነገር ማድረግ አለብን..አባን አሁኑኑ ማግኘት አለብኝ››ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደቤት አመራች
‹‹እንዴ እሳቸው እኮ ፀሎት ላይ ናቸው››እያለ ከኃላዋ ተከተላት
‹‹ቢሆንም ላገኛቸው የግድ ነው››እያለች ወደ እናትዬው ጋር ሄደች ኩሽና ..አቤል ሳሎን ቀረ
‹‹እማ ..እማዬ››
‹‹አቤት ምነው ጥድፍ ጥድፍ አልሽ?..ደግሞ ለቅሶው ምንድነው?››
‹‹አባን ፈልጌ ነበር?››
‹‹እንዴ አሁን አብራሻቸው አልነበርሽ እንዴ?››
‹‹ነበሩ ግን ወደ ጸሎት ቤታቸው ገብተዋል››
‹‹እንግዲያውስ እስኪወጡ መጠበቅ ነዋ››
‹‹እማ አልችልም አሁኑኑ ነው የምፈልጋቸው››
‹‹ማይቻለውን..እሳቸው እዚህ ቤት ሲያመጡን የነገሩን ብቸኛ ማስጠንቀቂያ ቢኖር እሷቸው ወደ ፀሎት ቤታቸው ከገቡ ቡኃላ እቤቱ በእሳት ቢቀጣጠል እንኳን በራቸውን እንዳናንኳኳ ነው..ስለዚህ በምንም አይነት ምክንያት ከጸሎታቸው ልንረብሻቸው አንችልም››
‹‹እሺ መች ነው የሚጨርሱት?››
‹‹እኔ ምን አውቄ ልጄ ..ዛሬም…ነገም… ተነገ ወዲያም ሊጨርሱ ይችላሉ››
‹‹ኦ አምላክ..ታዲያ ምን ይሻላል?››
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው ይሄ ሁሉ ጉድ እና ጥድፊያ?››
‹‹እማ ሄለን አደጋ ላይ ነች››
‹‹የምን አደጋ ?ልጄ ምን ሆነች..?››ድንጋጤው በእጥፍ ተባዝቶ በእሷቸው ላይ ተጋባ
‹‹ይሄ ፒያኖ የሚያሰለጥናት ሰውዬ…››
‹‹ኩማደሩ. ምን ሆነ?››
‹‹ምን ይሆናል …ዲላ ነበር የሚኖረው››
‹‹አዎ ሰምቼያለው..ታዲያ ምን ችግር አለው?››
‹‹እኔ አውቀው ነበር››
‹‹እወቂዋ… ታዲያ ማወቅ መልካም ይሆናል እንጂ ምን ክፋት ሊኖረው?››
‹‹እማ አልገባሽም ጥለኞች ነበርን…በጣም ነው የሚጠላኝ..ሊገድለኝ ሁሉ ይፈልጋል›››
‹‹አይ አንቺ ልጅ… በቃ ያንቺ መዘዝ ዘላለም ማለቂያ የለውም ..?ይሄውልሽ ሮዝ በአንቺ የተነሳ ልጄ ከእጣቷ ላይ አንዲት ስንጣሪ ጠፍሯ ያለፍቃዷ ተቆርጣ ብትወድቅባት በቃ… የእኔ እና የአንቺ ነገር ዳግም ላይቀጠል አከተመለት ማለት ነው›› በማለት ጭራሽ በጭንቀት ላይ ጭንቀት ጨመሩባት…ተስፈንጥራ ከማድቤት ወጥታ ሄደች… ሳሎኑን አለፈችና ወደ ውጭ ወጣች‹‹የት ልትሄጂ ነው›› ሳሎን የነበረው አቤል ተከተላት
‹‹አቤል ይሄን ሰውዬ ላነጋግረው እፈልጋለው..እዚሁ ጠብቀኝ››
‹‹ኸረ ሮዝ ተረጋጊና በሰከነ አዕምሮ ነገሮችን አስቢያቸው..ምን አልባት ነገሮች በአጋጣሚ ተገጣጥመው እንጂ እንቺ እንደምትይው የታሰበባቸው ላይሆን ይችላሉ››
ልትሰማው አልፈለገችም..እንደ አመለኛ በቅሎ እየሰገረች ግቢውን ለቃ ወጣች…እንዴት እንደዞረች… እንዴት ግቢውን እንደከፈተችና የፎቁን ደረጃ እንዴት ተንደርድራ እንደወጣች ለራሷም አታውቅም..በራፍንም ሳታንኳኳ በራፍን በርግዳ ከፈተች..ሄለን ፒያኖው ፊት ለፊት ተቀምጣ ጣቶቾን ከወዲህ ወዲያ የሙዚቃ መሳሪያውን በማርመስመስ ሙዚቃ እየተጫወተች ነው፡፡ኩማደሩ ከሄለን ኃላ ቆሞ እጆቹን ተከሻዋ ላይ ጣል አድርጐ በአድናቆት እየተመለከታት ነበር..በራፍ ድንገት ሲከፈት ተገርሞ ዞር አለ፡፡
..የእንግዳዋን ማንነት ሲያውቅ ፈገግ አለ…አዎ እንዳየችው እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበር
‹‹አቤት ምን ነበር?››አለት ሄለን እሷን ያላት በመስሎት ግራ ገብቶት ቀና ስትል አይኗ የተገተረችው ሮዝ ላይ አረፈ….ፒያኖዋን መጫወቷን አቆመች
‹‹ሄለን አንዴ ቤቱን ትለቂልን እና ወደቤት ትሄጂ››
‹‹አልገባኝም…እንደምታይው ስራ ላይ ነው ያለነው..ጉዳይ ካለሽ ለምን አንቺ ሌላ ጊዜ አትመለሺም››አላገጠባት
‹‹ሰይጣኔን አታምጣው..አንቺ ውጪ ብዬሻላ ውጪ ››ተንደርድራ ትከሻዋን ያዘችና ከተቀመጠችበት አንጠልጥላ አነሳቻት
‹‹እንዴ ልቀቂኝ እንጂ ..አብደሻል እንዴ?››
‹‹አዎ አብጄያለው..አሁን ልቀቂና ውጪ ብዬሻለው››
ኩማንደር ውስጡ በደስታ ረሰረሰች ባለፈው አግኝቷት አንዱን ጠላቱን በበቂ መንገድ ተበቅላለታለች የሷ ግን ገና ነው ይህቺን ቀንም በጉጉትቶ ነበር ሲጠብቅ የነበረው… ‹‹የእኔ ቆንጆ ግድየለሽም እስቲ ውጪላት ..ዛሬ ስራ ስለማልሄድ እንደጨረስን እደውልልሽ እና ካቆምንበት እንቀጥላለን››አለት
‹‹ምን አይነት ጣጣ ነው? ለምንድነው የምትከታተይኝ..?ለምንድነው የማትተይኝ…? በቃ አላውቅሽም አታውቂኝም››ብላ እየተማናጨቀች እቤቱን ለሁለቱ ተፋላላጊዎች ለቃ ወደ ቤቷ ተመልሳ ሄደች..
አሁን ሁለቱ ሰዎች እንደተፋጠጡ ናቸው ….. ኩማንደር መቀመጨ ይዞ ቁጭ አለ‹‹እሺ ምንድነበር ጉዳይሽ ወይዘሪት ሮዝ?››
‹‹ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹አልገባኝም..ምንስ ብሰራ ሚስቴ አይደለሽ ሀለቃዬ… ምን አስጨነቀሽ?››
‹‹አታሹፍ… ከዚ በፊትም ነግሬካለው እኔን እንደፈለግክ ማድረግ ትችላለህ..ከፈለግክ ስጋዬን ዘልዝለህ ለውሻ ልትሰጠኝ ትችላለህ.. ልጄን ግን ተዋት ብዙ መከራ ያየውባት..ህይወቴ የተመሰቃቀለባት የመከራይ ውጤት ነች››
‹‹ምን እንደምትይ አልገባኝም?››
‹‹በደንብ ይገባሀል…ከልጄ ጋር ያለህን ግንኙነት አቁም ነው እያልኩህ ያለውት..››
‹‹እውነት እሱን እንኳን አልችልም..እሷን ተዋት ከምትይኝ ህይወትህን አሳልፈህ ስጠኝ ብትይኝ ይቀለኛል››
‹‹እንዴ!!! ምን ማለት ነው?››
‹‹ቀሪ ህይወቴን ከሄልዬ ተለይቼ መኖር አልችልም እያልኩሽ ነው››
‹‹እየቀለድ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ…እኔ እስከማውቅህ ድረስ ብትወልዳት ልታደርሳት ከምትችላት ልጅ ጋር ሌላ ግንኙነት ለመጀመር የሚያስችል የዘቀጠ ስብዕና ያለህ አይመስለኝም››
‹‹እሱማ ድሮ ነበር… አሁን እኮ በጣም ተቀይሬያለው፡፡ አንቺና ውሽማሽ ኩማንደር ደረሰ ብዙ ብዙ ነገር አስተምራችሁኛል…ስለዚህ እስከ አሁን ያልኩሽን በፍፁም የውሸቴን አይደለም..በጣም አፍቅሬያታለው…እሷም ያፈቀረችኝ ይመስለኛል..ይሄን ማረጋገጥ ከፈለግሽ ከእሷም
👍1
ጠይቀሽ መረዳት ትችያለሽ…በመካከላችን ላለው ዕድሜ ልዬነት ብዙ አትጨነቂ..ፍቅር በሁለት ተጣማሪዎች መካከል የሚገኙ ማንኛውንም ልዩነቶች የሚያጠፋበት የራሱ የሆነ ላጲስ አለው››
‹‹አንተ አውሬ …አንተ ጨካኝ..››ተንደርድራ ሄዳ ተከመረችበት ፤ ጠፈጠፈችው ፤በተቀመጠበት እራሱን ከመከላከል በስተቀር ምንም አላደረገም…ምክንያቱም እሷ የብስጭት እና የንዴት ጣሪያ ላይ ስትደርስ እሱ ደግሞ ደስታ እያጥለቀለቀው ነበር
‹‹ኸረ በፈጠረህ …እሺ በምታምነው አምላክ ተለመነኝ….. ልጄን ተውልኝ››
‹‹እንዲህ በቀላሉማ እንዴት ይሆናል…?››
‹‹እሺ እንድትተዋት ምን ላድርግ ..እራሴን ላጥፋልህ..ምን ላድርግ ንገረኝ?››
ከባለፈው ከሰጠሁሽ
ሁለት ትእዛዞች አንዱን አልፈፀምሽም ይሄ ደሞ ያሰብኩትን እንዳረግ አስገድዶኛል
‹‹በፈጠረህ አስብበት..ለልጄ በቃ የመጨረሻዋን እስትንፋሴንም ቢሆን እሰጣለው››
‹‹አይ እንድትሞቼ እንኳን አልፈልግም
አንድ እድል እሰጥሻለሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሄለን አባት ማን እንደሆነ በራስሽ ድምፅ ቀድተሽ በእጄ እንድሰጪኝ ካለበለዝያ እየፈራሽው ያለው ነገር ሁሉ ይሆናል ይሄንን ማድረግ ከቻልሽ ግን ከልጅሽ ጋር ያለው ነገር አያሳስብሽ
‹‹አሺ እግዜር ይስጥልኝ››ብላ ቅዝቅዝ እንዳለች…. በእንባ እንደታጠበች..በስጋት እንደተወጠረች….እቤቱን ለቃ ወጥታ ሄደች

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#ውይ_ወንዶች አሉ ሴቶች እውነታቸውን ነው

ቀልዱ የፈረንጅ ነው ወደኛ ስናመጣው እንዲህ ይነበባል .....
ሰውየው ሚስቴ ጠፋችብኝ ብሎ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታል ...በቃ እንደወጣች የውሃ ሽታ ሆነች ሳምንቷ ...እና ፖሊስ ስለጠፋችው ሚስት አንዳንድ ምልክት ጠየቀ
የባለቤትህ የአይኗ ቀለም ምናይነት ነው ?
የአይኗ ቀለም ? ....እኔጃ
የፀጉሯ ቀለም .?...
እኔጃ አንዳንዴ ቀይ ትቀባዎለች አንዳንዴ ብራውን ....ጎልደን ለመጨረሻ ጊዜ ምን እንደቀባችው አላስታውስም
ቁመቷ ?
ቁመቷ ....እኔጃ ያው አልጋ ላይ እኩል ነበርን
ስሟ ...ስሟ እ ....ርብቃ !
የአባቷ ስም ?
እኔጃ !
የልደቷ ቀን ?
እኔጃ !
ለመጨረሻ ጊዜ የለበሰችው ልብስ ...
አላስታውስም ! ግን የምወዳትን መኪና ይዛ ነው የወጣችው !
እሽ የመኪናዋን ልዩ ምልክት ትነግረኝ ?
በሚገባ ! መኪናየ ቀይ የ2005 ደብል ጋቢና ሃይሉክስ ነች በቀኝ በኩል ባለፈው ፒያሳ አንዱ ሚኒባስ ነካ አድርጓት ጭረት አላት ..ሁለት ጎማ ከስድስት ወር በፊት ቀይሬላታለሁ ታርጋ ቁጥሯ 54397 ነው .....መስተዋት መወልወያው የቀኙ ተበላሽቷል ልክ ሚስቴ ይዛት የሄደች ቀን 12 ሺህ 219 .4 ኪሎ ሜትር ተነድታ ነበር ......30 ሊትር ነዳጅም ነበራት ....
ፖሊሱ የሰውየው ከሚስቱ በላይ ለመኪናው ያለው ፍቅር ገርሞት
ችግር የለም ጌታየ መኪናህን በፍጥነት አግኝተን እንመልስልሃለን
ውይ ወንዶችና መኪና ሴቶች መኪና ያለው ወንድ ሲቀርቧችሁ አደራ .....እኛ እግረኞችን ግን ውድድድ ....እየነፈሰብን ዎክ ማድረግ ይሻላል :)ምንም ቢሆን እኛ እግረኞች ከእናተ በላይ ታክሲ ወላ ባቡር አንወድ ምናባታችን አማራጭ አለን እናተው ጋር ተያይዘን እየኳተንን "ሃኒ ዋናው ፍቅር ነው " ከማለት ውጭ

🔘አሌክስ አብርሃም🔘
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_አምስት
:
ድርሰት፦በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
ለዘመን ለፍቼ…
ውጤት ለመጨበጥ፣ጥቂት ሲቀረኝ
ሚስጥራዊው አምላክ…..
ወደ ኃላ ስቦ፣ባዶ አስቀረኝ፡፡
እኔም መች የዋዛ፣መች ተስፋ ቆርጬ
ከአንዱ ጀመርኩኝ፣በእልክ ተመስጬ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ለጨረቃዋ ከፊል ምግባሯን አስረክባ ፀሀዮ ወደማደሪያዋ ኮብልላለች፡፡ቀኑ ቢጨልምም ጭላሎ ሆቴል ግን በሰውሰራሽ ብርሀን ደምቋል፡፡በውስጡ ከወዲያ ወዲህ የሚተረማመሱ ኮማሪቶች ቤቱን ሞልተውታል፡፡መቀመጫዎች በሙሉ በጠጩዎች ተይዘዋል፡ዲጄው ሞቅ ያሉ ሀገርኛ ሙዚቃዎችን በተከታታይ እየለቀቀ ነው፡፡እድምተኞቹ ግን ግማሾቹ ከሙዚቃው ምት ጋር ከወዲህ ወዲያ እየተውረገረጉ ይጨፍራሉ… ገሚሱ ደግሞ በየራሳቸው ጫወታ እና ሀሳብ ተጠምደዋል፡፡
ከወደ አንድ ጥግ የተቀመጡ ሶስት ሰዎችም መጠጣቸውን እየተጐነጩ በሀሳብ ሰምጠው የተኮራረፉ ጣውንታሞች መስለዋል፡፡በተለይ ሁለቱ ፊታቸው ተጨማዶ ና ዓይኖቻቸው ፈጠው ይታያሉ…ሶስተኛው ግን ምንም አንኳን በሀሳብ ቢዋጥም ፊቱ ላይ የሚነበበው ግን የእርጋታ እና የአሸናፊነት እርካታ ነው፡፡ይህ ሰው ኩማደር መሀሪ ነው፡፡ሁለቱ ደግሞ የዛሬዋ ጐዶሎ ቀን ከእሱ እጅ ላይ የጣላቸው የከተማዋ ሞጃዎች አቶ ዳዊት ይግዛው እና ገመዳ ነገኦ ናቸው፡፡
እንግዲህ በሌሎች መሰል ጓደኞቻቸው እንዲህ አደረጋቸው ተብሎ ሲወራና ሲነገር የሰሙትን ዛሬ የእነሱ ዕጣ ሆኖ በራሳቸው ሊከሰት ነው፡፡በተለይ ገመዳ ነገኦ ይሄ ገጠመኝ የሞት ያህል ነው የሆነባቸው.. ምክንያቱም ለዚህ ውድቀታቸው የገዛ ልጃቸው ተባባሪ ሆኖ ሲያዩ…የገዛ አብራካቸው ክፋይ ለውድቀታቸው ቋምጦ ወደ መቀመቅ ሲጐትታቸው መታዘብ…የሞት ሞት ነው የሆነባቸው፡፡
እኚ ሁለት ሀብታሞች ኮንትሮባንድ ከኬንያ ጭነው በከተማው ሰንጥቀው ወደመሀል ሀገር ሊያስተላልፉ ሲሉ ነው እጅ ከፍንጅ የያዛቸው፡፡አሁን ኮንትሮባንድ የተጫነባቸው መኪኖች እዚሁ ሆቴል ግቢ ውስጥ ተገትረው በራሱ ሰዎች በኤልያስ እና በባሪያው እየተጠበቁ ነው፡፡እሱ ደግሞ እንሆ ከባለቤቶቹ ጋር በአንድ ጠረጵዛ ዙሪያ ተቀምጦ መጠጡን እየኮመኮመ ነው፡፡
‹‹ተጫወቱ እንጂ …መጀመሪያውኑም እኮ እንደእዚህ አይነት ስራ ስትሰሩ አንድ ቀን እንደዚህ አይነት ችግር ላይ እንደሚጥል መቼስ ከልምድ ታውቁታላችሁ….እንግዲህ ምን ይደረጋል፡፡ የመጣውን ችግር እንደአመጣጡ መወጣት ነው››ሲል አላገጠባቸው፡፡
ከሁለቱ ጠና ያሉት አቶ ገመዳ ነገኦ መናገር ጀመሩ ፤ ከዚህ ቅሌት እንዴትም ብለው በየትኛውም መስዋዕትነት መውጣት አለባቸው…ካለበለዚያ በተከበሩበት ሀገር መዋረዳቸው ነው…እሳቸው እኮ የእዚህች ከተማ የተከበሩ ኢንቨስተር፤መንግስት የሚኮራባቸው ልምታዊ ባለሀብት ናቸው…..ታዲያ ይሄንን በስንት ረብጣ ብር እና ጥረት የገነቡትን ክብራቸውን በአንዴ ገደል ሲገባ ምን ይባላል ?፡፡ ወዳጀቻቸው የሆኑ እና ከእሳቸው ጋ በክብር በየአደባባዩ እና በየስብሰባው የሚታዩት እነዛ የመንግስት ትላልቅ ባለስልጣኖች ምን ያህል ያፍሩባቸዋል ….?ባለስልጣኖቹ እንኳን ምን ያፍሩባቸዋል..አብዛኞቹ ያው እንደእሳቸው ማፈሪያዎች ናቸው…‹‹ይሄውልህ ልጄ መቼስ ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም… እኛም ተሳስተናል…››
አቋረጣቸው…‹‹በቃ ምንም አይነት ዝባዝንኪ ዲስኩር አልፈልግም፡፡አሁን ያልኮችሁ መተከዛችሁን አቁሙና ዘና ብላችሁ ጠጡ ብቻ ነው››ቆሌያቸውን ነው የገፈፈው፡፡‹‹ታዲያ ለምን እዚህ አመጣን…. ?ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ አይወስደንም ነበር?›› ሲሉ ሁለቱም በውስጣቸው ማብሰልሰላቸውን ቀጠሉ..
ኩማንደር ችላ ብሎቸው መጠጡን መምጠጥ ጀመረ…ሲጋራ አወጣና ለኩሶ እያጬሰ ስለእነሱ እያሰበ ዘነ ማለቱን ቀጠለ‹‹አዎ የስንቱን ልብ እንዳቃጠላችሁ አሁን በተራችሁ ልባችሁን እንደ እዚህ ሲጋራ አቃጥለዋለው›.›ሲል በውስጡ ዛተባቸው፡፡
ኩማደር ስለ እነዚህ ከጐኑ ስለተቀመጡት ሁለት ግለሰቦች ታሪክ በደንብ ያውቃል፡፡አዎ ሁለቱም በአባ ሽፍንፍን አማካይነት በተቋቋመው የጐዳና ተዳዳሪዎች ማቋቋሚያ ማህበር ውስጥ በህዝበ ክርስቲያኑ ተመርጠው ኮሚቴ ከሆኑ አንስቶ ይከታተላቸው ነበር፡፡ሌላው ግሞ እነሱ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ የገፋፋው ጉዳይ አንደኛው የእሱ አጋር የሆነው የኤልያስ አባትነው፤አንደኛው የእንጀራ አባቱ የወርቅአለማው የልብ ጓደኛ በመሆኑ ነው፡፡
ኩማደር ብርጭቆ ውስጥ ያለውን የመጨረሻውን መጠጥ ጨልጦ ባዶ ካደረገ ቡኃላ አስተናጋጇን ቢል እንድታመጣ አዘዛት..ብዙም አላስጠበቀቻቸው፡፡ እየተውረገረገች ቢሉን ይዛ መጥታ አቀበለችው…ሁለቱም ሂሳቡን ሊከፍሉ እጃቸውን ኪሳቸው ውስጥ በመክተት እኔ ልክፈል እኔ በማለት እርስ በራሳቸው ሲከራከሩ ‹‹ጉቦ መሆኑ ነው?››ሲል አሸማቀቃቸው እና እራሱ ከፍሎ ቀድሞቸው ወጣ ፡፡እየተሸቆጠቆጡ ተከተሉት፡፡ወደ መኖሪያ ቤቱ ነው ይዞቸው የሄደው፡፡እንደደረሰ የወንደላጤ ቤቱን ከፍቶ ገባ ..ተከትለውት ገቡ፡፡ የውስኪ ጠርሙስን ከባታው አነሳ እና ለሁለቱም ቀድቶላቸው ለራሱም ከያዘ ቡኃላ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ፡፡ በማስተዋል ሲመለከታቸው በጣም እንደተረበሹ እና ግራ እንደተጋቡ ነው ተረዳ ..ይህም በመሆኑ ተደሰተ ፡፡
‹‹በነገራችን ላይ ጉዳያችሁ በህግ ይለቅላችሁ ወይስ እዚሁ እንደራደር?››ሲል አስደንጋጭ ግን በልባቸው ሲመኙት የቆዩትን ጉዳይ በጥያቄ መልክ አቀረበላቸው፡፡
‹‹እንዴት ግልፅ አልሆነልንም?››ጠየቁት አቶ ዳዊት
‹‹ንግግሬ አጭር እና ግልጽ ነው ..እኔ በምለው ተስማምታችሁ ..የማዛችሁን አድርጋችሁ ነጻ መውጣት ትፈልጋላችሁ ወይንስ በትክክለኛው መንገድ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳችሁ በሀገሪቷ ህግ መደኘት ነው የምትፈልጉት?››
‹‹አረ ቅበረን..አንተው እንደፈለግክ አድርገን?››ለእሱ መማረካቸውን በመሽቆጥቆጥ አበሰሩት
‹‹አንግዲያው ጥሩ እንጀምራ…››
‹‹አሺ እንዳልክ ››ተርበተበቱ
‹‹ይሄ አሁን የጫናችሁት ኮንትሮባንድ ዋናችሁ ስንት ብር ነው?››
‹‹ሁለት ሚሊዬን ብር አካባቢ ነው››መለሱለት አቶ ዳዊት
‹‹ሲሸጥስ?››
‹‹አራት ሚሊዬን አካባቢ ያወጣል››
‹‹አንድ ሚሊዬን ለእኔ ትከፍላላችሁ››
‹‹አረ እሺ..እሺ››ሁለቱም በአንድ ቃል በደስታ ተስማሙ……..
‹‹እሱ ብቻ አይደለም››በማለት ከስጋት ተንፈስ ያለውን መንፈሳቸውን መልሶ ደግሞ ምን ሊለን ይሆን በሚል ስጋት እንዲወጠሩ አደረጋቸው
‹‹እሺ ሌላ ምን እንታዘዝ?››በለዘበ ድምጽ ጠየቁት ገመዳ ነገኦ
‹‹ወርቅአለማው ጓደኛችሁ ነው አይደል?››
‹‹አዎ ከእኔ ይልቅ ግን ከእሱ ጋር ወዳጆች ናቸው››አሁንም መልሱን የሰጡት አቶ ገመዳ ናቸው፡፡
‹‹ለምጠይቃችሁ ጥያቄ እውነቱን እንድትነግሩኝ ነው ምፈልገው..እሱ ከእናንተ ጋር ይሄንን ስራ አይሰራም እንዴ?››
‹‹ይሰራ ነበር..አሁን ግን እርም ብሎ ካቆመ አንድ ወር አለፈው..ሶስታችንም አንድ ላይ ነበር ይብቃን… አምላክ የያዝነውን ያስበላን ብለን ለማቆም የተስማማነው..ብኃላ እሱ በቃሉ ሲፀና እኔ እና እሱ ግን ይሄው እግዜር ተዋረዱ ሲለን መሰለኝ ቆይ ይህቺን የመጨረሻ ስንል…ቆይ አንዴ ስንል ይሄው ለዚህ ተዳረግን››ሲሉ በፀፀት አንገታቸውን አቀርቅረው አብራተው ያስረዱት አቶ ዳዊት ናቸው ..
የነገሩት ነገር ግን ኩማንደሩን የሚያስደስተው አልነበረም…..ለሁለተኛ ጊዜ በእዚህ ቀለም ወርቅ በሚባል ሰውዬ መበለጡን ሲገነዘብ ውስጡ እርር ድብን አለ…አሁን እፊቱ ቁጭ ብለው ምህረቱን በሚማፀኑት ሰዎች ቦታ እሱን ማየት ነበር የሚፈልገው…ኮንትሮባንድ ሲያመላልስ እጅ ከፍንጅ ይዞት ባዶ ሊያስቀረው ዕቅዱ ነበር..ግን አሁን የሚሰማው ዜና ሀሳቡ እንደተኮላሸበት የሚያረጋግጥ መርዶ
👍1
ነው ‹‹ለመሆኑ ምን ያህል ሀብት ያለው ይመስላችሆል?››
‹‹አንድ አስር ሚሊዬን ብር አካባቢ ይኖረዋል ብለን እናስባለን››
‹‹አሁን ምን አይነት ሰራ እየሰራ ነው?››እሱን የሚያጠምድበት ሌላ ዕቅድ ለማቀድ የሚረዳውን መረጃ ይነግሩት ዘንድ ጥያቄውን ቀጠለ…
‹‹ለጊዜው ምንም እየሰራ አይደለም…በቅርቡ ግን ለእኛ በግልጽ ያልነገረንን አንድ ህጋዊ ስራ መስራት እንደሚጀምር ነግሮናል››
‹‹በሉ አሁን ወደ ቤታችሁ ሂዱ፡፡ ነገ ጥዋት እስከ አራት ሰዓት ድረስ በተነገጋርነው መሰረት ያልኮችሁን ብር ታመጣላችሁ ..ከዛ እቃችሁንም መኪናችሁን ትወስዳላችሁ..ተስማማን››
‹‹ ተስማምተናል..እግዜር ያክብርልን..››በመሽቆጥቆጥ ከመቀመጫቸው ተነሱ ሁለቱም
‹‹ደግሞ እኔን ለማጭበርበር የማይሆን ነገር እንሞክራለን ብላችሁ ቀሪ ህይወታችሁን ሙሉ የምትፀፀቱበትን ነገር ነው ሚደርስባችሁ…››አስጠነቀቃቸው፡፡ማስጠንቀቂያውን በፍራቻ በሚናወጽ መንፈስ አድምጠው ሹልክ ብለው ከቤቱ ወጡ…የፎቁን ደረጃ ቁልቁል ወደ ታች ሲወርዱ እግሮቻቸው ይንቀጠቀጡ ነበር…

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
:
ድርሰት፦በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...አባ ሽፍንንፍን በአይጣማዋ ቪታራ መኪናቸው እራሳቸው እየነዱ ወደ ስብሰባ ስፍራ እያመሩ ነው፡፡በእለቱ የስብሰባ አጀንዳ በእሳቸው አነሳሽነት የተቋቋመውን የጓዳና ተዳዳሪዎች ማቋቋሚያ ድርጅትን ስራ እንቀስቃሴን ለመገምገም እና ቀጠይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ነው፡፡የስብሰባው ቦታ በጽ/ቤቱ ውስጥ ነው፡፡ጽ/ቤቱ የሚገኘው ዜሮ ሶስት ቀበሌ ከጤና ጣቢያው በስተጀርባ በኩል ሲሆን ቤቱ በፊት የተሰራው ለመኖሪያ ቤትነት ነበር… ማህበሩ ሲቋቋም ተከራየውና ቢሮው አደረገው፡፡ ውጭ በሩ ላይ በጥቁር ቀለም ድርብ ጽሁፍ <የሻሻመኔ ከተማ የጐዳና ኑዋሪ ወገኖች ማቋቋሚያ በጐ አድራጐት ድርጅት> ይላል፡፡
አባ ልክ በሰዓቱ ነበር ስብሰባው ቦታ ላይ የደረሱት..ዘበኛው ቶሎ ብሎ በራፉን ከፈተላቸው….ወደ ውስጥ ዘልቀው ገቡና መኪናቸውን ጥግ አስይዘው በማቆም ሞተሩን አጥፍተው ወረዱ ..በተለመደው የእርጋታ እርምጃቸው ወደ ስብሰባው አዳራሽ ዘለቁ…የአባን መስቀል ለመሳለም እና ለእሳቸው ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነሱ ፡፡አባም በፈገግታ እና መንፈሳዊ የአባትነት ጸጋ በተጐናጸፈ ድባብ ሁሉንም አሳልመው ወደመሀል ወንበራቸው በመሄድ ተቀመጡ
…..አባ ተደላድለው ከተቀመጡ ቡኃላ የስራ ባለደረቦቻቸውን በማስተዋል ይመለከቷቸው ነበር ፡፡በዚህ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ አራት ወንዶች እና አንድ ሴት አለች፡፡ከፊት ለፊታቸው ወርቅ አለማው ይታያል..ዳለቻ ቀለም ያለው ሙሉ ሱፍ ለብሶ የፓርላማ ተወካይ መስሏል…ግን መረጋጋት አይነበብበትም…ምን ግዜም እኚ ቄስ ባሉበት አካባቢ ሲገኝ ይጨንቀዋል፡፡የሆነ የውስጥ ሀጥያቱን የሚያነቡበት ይመስለዋል፡፡ከጐኑ የተቀመጠችው ጸባየ ሸጋዋ እና ባለ ጥሩ ስነ-ምግባር ባለቤት የሆነችው ወ/ሮ ይርገዱ ነች፡፡በጣም ምትሽቀረቀር እና ለውበቷ አብዝታ ምትጨነቅ ሴት አይደለችም..ግን ደግሞ ለእራሷ የሚመጥናት አለባበስ ከመልበስ አትቦዝንም.. የዛሬውም አለባበሶ እንደዛው ነው፡፡ከጐኗ አቶ ገመዳ ነገኦ..ከሙሉ ግርማ ሞገሳቸው እና መጀነናቸው ጋር ተኮፍሰዋል…ቀጥሎ አቶ ዳዊት ሽበት የወረረው ጸጉራቸውን እየዳበሱ አቀርቅረው የስብሰባውን መጀመር ይጠባቃሉ….
አባ ሽፍንፍን ስለ ስብሰባው አጀንዳ አጠር ያለች ማብራሪያ እና መግቢያ ንግግር ካደረጉ ቡኃላ እድሉን ለተሰብሳቢዎች ሰጡ ..
በመጀመሪያ ወርቅ አለማው ነበር የስራ ድርሻውን አስመልክቷ እስከአሁን በእሱ በኩል ስለተከወኑ ስራዎች ሪፖርት ማቅረብ የጀመረው
ወርቅአለማው የመሀበሩ ገንዘብ ያዥ ነው፡፡
ጀመረ……
‹‹እንግዲህ እስከአሁን እርዳታ እንዲያደርጉልን ከጠየቅናቸው ድርጅቶች እና ግለሰብ ከሆኑ ምዕመናን መሰብሰብ የቻልነውን የገንዘብ መጠን ሪፖርት አደርጋለው…በመጀመሪያ አንድ የሆላንደ ግብረ ሰናይ ድርጅት 100 ሺ ዶላር ሰጥቶናል..አንድ በህፃናት ላይ ከሚሰራ አገር በቀል ድርጀት ደግሞ የአንድ ሚሊዬን ብር እርዳታ ማግኘት ችለናል..ከግለሰብ ምዕመናኖች ደግሞ በተለያየ ጊዜ የተሰበሰበ ወደ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺ ብር ማግኘት ችለናል…ሌላው የእዚሁ ኮሚቴ አባል ከሆኑት ውስጥ አባታችን በግላቸው መቶ ሺ ብር..አቶ ዳዊት 50 ሺ ብር አቶ ገመዳ 50 ሺ ብር ወይዘሮ ይርገዱ 75 ሺ ብር..የራሴን መግለጽ ካስፈለገ 50 ሺ ብር በአጠቃላይ እስከአሁን በአካውንታችን መግባት የቻለው ብር 3 ሚሊዬን 577 ሺ ብር ማግኘት ችለናል..ቃል የተገባልን ደግሞ ከሁለት ሚሊዬን ብር በላይ ነው…በጣም አስደሳቹ እና የሚገርመው ደግሞ የማህበራችን ዝና በሀገራችን ባሉ በተለያዩ ከተሞች በዚህ አጭር ቀናቶች ውስጥ መናኘቱ ነው፡፡ብዙዎቹ እንዲያውም ለምሳሌ እንደ ሀዋሳ እና ዝዋይ ያሉ ኑዋሪዎች በከተማቸው ቅርንጫፍ ቢሮ እንድንከፍት ሁሉ ጠይቀውናል››አመሰግናለው ብሎ ንግግሩን አጠናቀቀ…
ወይዘሮ ይርገዱ ተረከበችውና ንግግሮን ቀጠለች‹‹ያው እኔ እንድሰራው የተሰጠኝ ከሞላ ጐደል ጥሩ እየሄደልኝ ነው…ማህበራን እስከ አሁን አሁን አቶ ወርቅአለማው ከጠቀሳቸው ድርጅቶች ሌላ ከሶስት የውጭ አገር እና ከሁለት የሀገር ውስጥ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በአካልም ቢሮቸው ድረስ በመሄድና በኢንተርኔት ግንኙነት ፈጥረን ነበር ሁሉም በጐ ምላሽ ነው የሰጡን… ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እርግጠኛውን መልስ እንደሚሰጡን እና ከገንዘብ መጠኑ ጋር እደሚገልጹልን ነግረውናል…ቃላቸውንም እንደሚያከብሩ እተማመናለው..፡፡እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ሌሎችን ማነጋገር እና ማግባባቱን ስራ እንቀጥላለን››አመሰግናለው
ቀጠሉ አዛውንቱ አቶ ዳዊት‹‹በእኔ በኩል የተሰጠኝን ስራ ቢያንስ የመጀመሪያውን ምዕራፍ ማስኬድ ችያለው..ከተሰጡኝ ሀላፊነቶች ውስጥ አንደኛው…ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ለጐዳና ልጆቹ የሚሆን የሞያ ማሰልጠኛ ተቋም ለማቋቋም እና ለመኖሪያ ቦታም ጭምር የሚሆናቸው ህንፃ ለመገንት የሚሆን ቦታ በስንት ጫቅጭቅም ቢሆን የከተማዋ መዘጋጃ ከከተማዋ ወጣ ቢልም ሰፋ ያለ መሬት አስረክቦናል..በሌላ በኩል ደግሞ በቦታው ላይ የሚገነቡ ህንጻዎችን ዲዛይን አንድ የኮንሰልታንት ድርጅት በነጻ እየሰራልን ይገኛል…ለጊዜው ግን አሁን መጩው ጊዜ የክረምት ወቅት በመሆኑ በጣም አጣዳፊ የሆነውን የመጠለያውን ጉዳይ 50 የሚሆኑ ሰርቢስ ቤቶችን ለመስራት በተወሰነው መሰረት ከአንድ ህንጻ ተቋራጭ ጋር ተስማምተናል…በሚቀጥለው ሳምንት የቁፋሮ ስራ እደሚጀምር እርግጠኛ ነኝ››አመሰግናለው
ቀጥሎ የአቶ ገመዳ ተራ ነበር…በተሰጣቸው የስራ ድርሻ ላይ ሪፖርት ሊያቀርብ ማስታወሻቸውን ገለጥ ገለጥ አድገው ለመናገር ጉሮራቸውን እያፀዳዱ ሳለ….የቢሮው በራፍ ተንኳኳ ..እና ተከፈተ…ዘበኛው ነበር..አልፎ ገባና ወደ አባ በመጠጋት በጆሮቸው ሹክ አላቸው‹‹ግባ በለው …ይግባ››አሉት
ዘበኛው እንዳመጣጡ ተመልሶ ወጣና ሌላ ሰው ላከ…የመጣው ሰው በእጁ ጥቁር ሳምሶናይት ይዞል..የዚህ ሰው መምጣት ከቤቱ አንድ ሰው በጣም አስደንግጦል…አቶ ገመዳ….አሁን ፊት ለፊታው የሚያዩት ልጃቸውም ጠላታቸውም የሆነውን ኤልያስን ነው..ምን ሊሰራ እንደመጣ ምንም ሊገምቱ እና ሊገለጽላቸው አልቻለም…‹‹ደግሞ የያዘው ምንድነው?››ግራ ተጋቡ..መቼስ ከእሱ መልካም ነገር አይጠበቅም…እሳቸውን የተመለከተ ምን መአት ይዞባቸው እንደመጣ እስኪሰሙ ነው የቸኮሉት፡፡
‹‹አቤት ወንድሜ ምን እንታዘዝ?››ዝግ ባለ እና በተረጋ ድምጽ ጠየቁት አባ
‹‹አባ ….ኩማደር መሀሪ ልኮኝ ነው.. ለአላማችሁ ማስፈጸሚያ ትንሽ ቢጠቅማችሁ ይህቺን ብር አስረክብልኝ ብሎኝ ነው…እሱ ስብሰባ ላይ ስለሆነ በአካል መጥቶ ማስረከብ አልቻለም››ይህ ንግር ደግሞ የመርዶ ያህል ያስደነገጠው አቶ ዘላለምን ሳይሆነ ቀለምወርቅን ነው
‹‹ኩማደር የቱ?›› እራሱን መቆጣጠር በተሳነው ስሜት ጠየቀ ወርቅ አለማው
‹‹ኩማንደር መሀሪ አልኩ እኮ.. የፖሊስ አዛዡ››በእርጋታ መለሰ ኤልያስ
‹‹እንዴት ሆኖ?››ድጋሚ ጥያቄ አቶ ወርቅአለማው
‹‹ምን ማለት ነው አቶ ወርቅ አለማው..?ነው ወይስ እኛ ማናውቀው ችግር አለ?››ጠየቁት አባ በጥቁር መነጽራቸው ውስጥ አጨንቁረው እያዩት
‹‹ኸረ በፍጹም..ምንም አላውቅም እንዲሁ ገርሞኝ ነው እንጂ..››
‹‹እኮ ምኑ ገረመህ …ከኩማንደሩ ጋ እውቂያ አላችሁ እንዴ?››ጥያቄያቸውን አላቆረጡም አባ
‹‹አረ በዝና እና በስም ብቻ ነው የማውቀው…እንዲሁ አንድ የመንግስት ቅጥረኛ እንዲህ የማህበራችን አላማ ገብቶት ቢሮችን ድረስ መጥቶ ሲለግሰን በማየቴ ተደስቼ ነው…››በማለት ከውስጥ የተሰማውን ስሜት ሸመጠጠ
‹‹ትክክል ነህ
👍1
እሱስ በጣም አስደሳች ነው››
አቶ ገመዳም እስከአሁን የሰሙትን ነገር ሁሉ ማመን ነው ያቃታቸው…ኩማደሩ እንዴት አምኖት ይህን ሁሉ ብር አሸክሞ ላከው..?የሄ እኮ አህያን ለጅብ አደራ መስጠጥ ማለት ነው፡፡…ሌባ እና ፖሊስ ድሮውስ ምን ይለያቸዋል?››ሲሉ በውጣቸው አሰቡ በኮትሮባንድ የተያዘባቸውንም እቃ ለማስለቀቅ የከፈሉትንም ብር እያስታወሱ
‹‹አግዜር ይስጥልን እግዜር ያክብርልን …ቀለም ወርቅ የገቢ መቀበያ ደረሰኝ ይዘኸል እንዴ?.››
‹‹አዎ ይዤያለው››
በል ለጊዜው ስብሰባው በእረፍት ይቋረጥ ‹‹ቁጠር እና ተረከበው… ካርኒም ስጠው በማለት አባ ትዕዛዝ አስተላለፉ
‹‹ቁጭ በል ወንድሜ ..››የያዘውን ሳምሶናይት አቶ ቀለም ወርቅ ፊት ለፊት አስቀመጠውና የተጠቆመበት ቦታ ሄዶ ተቀመጠ..ቀለም ወርቅም ሳምሶናይቱ ውስጥ ያለውን ብር ጠረዛጴዛ ላይ ዘረገፈ እና በሉ ይሄን ሁሉ ብር ብቻዬን ስቆጥር ማደሬ ነው አግዙኝ አላቸው….››ሁሉም መቁጠር ጀመሩ..ሲጠናቀቅ ግማሽ ሚሊዬን ብር ነበር የሆነው….ሌሎች ኮሚቴዎች ላይ ከምስጋና እና ከደስ በስተቀር ሌላ የተለየ ነገር ባይተይም አቶ ገመዳ እና ወርቅ አለማው ግን ፊታቸውንም ውስጣቸውም እንደጨለመ ነበር…ኤልያስን ካሰናበቱት ቡኃላ ስብሰባው ለ30 ደቂቃ ቀጠለና ሲጠናቀቅ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር..ሁሉም ወደየገዛ መኪኖቻው በመግባት ወደ የአቅጣጫቸው ተበታተኑ..ወርቅ አለማውም የተረከበውን ብር በዚያን ሰዓት ባንክ ቤት ወስዶ ገቢ ማድረግ ስለማይችል ቀጥታ ወደቤቱ ነበር ይዞ የሄደው…..ይንን ደግሞ ኤልያስ ተሸሽጎ እቤቱ ድረስ በመከተል አረጋግጦል…አረጋግጦም ለኩማደሩ ነግሮታል፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ኩማንደር መሀሪ የጥዋት ፀሀይ በመኝታ ቤቱ መስኮት ሾልካ አካባውን ስታደምቀው ነው መኝውን ለቆ ወደ በረንዳው የወጣው…ጸሀዬ ለሰስ ብላ ሰለወጣች ደስ ታሰኛለች..በረንዳ ለይ ከሚገኝ አንድ ኩርሲ ላይ ቁጭ ብሎ እሷኑ በመሞቅ መደሰት ጀመረ….አይኑን ከጸሀዬ ላይ ነቅሎ ቁልቁል ወደ ታች ወደ አባ ሽንፍን ቤት ላከ ሳይወቀው ከአንደበቱ ቃላቶች ሾልከው ወጡ‹‹አይ አባ …እንደ አንተ አይነት አባም ታይቶ አይታወቅም…. አሁንማ ሰው ሁሉ ያመልክህ ጀምሯል…እኔ ግን እንደ ሌሎች ሰዋች አላመልክህም..እንደ እነሱ አልወድህም ..እንደውም እረግምሀለው… እናም በጣም ነው የምጠላህ..በጣም..በጣም እጠላኸለው..ቢሆንም ቀጥል በርታ አንተ ምርኩዜ ነህ..አንተ በቄስ እነትህና በበጐ ምግባርህ እኔ በወታደርነቴ እና በጉበኝነቴ ይህቺን ከተማ እናተረማምሳት….አንተም ባለህበት እኔም ባለውበት…መገናኘትም መተዋወቅም አያስፈለገንም፡፡››
ሀሳቡን አስቦ ሳያጠቃልል ሁለቱ ወዳጆቹ የፎቁን ደረጃ ሽቅብ እየወጡ ወደእሱ ሲያመሩ ተመለከታቸውና…ፈገግ አለ….

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1🥰1
#እንዳበድኩኝ_ልኑር

ያ'ለም ነገር ሁላ ደስታን ባያመጣ
እራሴን ጣጥዬ ለሰው ግድ ባጣ
ልብሴ ከላዬ አልቆ አካሌም ደንዝዞ
እራፊ ለብሼ ህሊናዬ ናውዞ
ገራባ እየለቀምኩ ከሜዳ ብተኛ
እብድ ነው ይሉኛል ምድረ በሽተኛ
:
ዛሬማ ድኛለሁ መች ነበር ያበድኩት ?
በተያየንበት ባፈቀርኩሽ ሰአት
ያኔ ጀምሮኛል አንቺን ብቻ መጥራት
ስላንቺ እያሰቡ ስላንቺ መቸገር
በዋልሽበት ውሎ ባደርሽበት ማደር

ባይገባቸው እንጂ አሁንማ ዳንኩኝ
ጨርቄን ቀዳድጄ ሜዳ ላይ አደርኩኝ
እንድታይኝ ብዬ መዘነጤም ቀረ
በአዲስ ማንነት ሁሉም ተቀየረ
እናልሽ አለሜ
ለንደ'ኔ አይነቱ ላፈቀረማ ሰው
ማበድኮ ማለት በሰላም መኖር ነው
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
*የፍትህ ሚዛን መዛነፍ …የእምነት መጓደል ሸክሙ
ደስታን በቁም መዘረፍ…ያለው ሰቆቃ ህመሙ
የተገረዘ ተስፋ…ኑሮው ነገር ዓለሙ፡፡
በቀል ላጨለመው ልብ …ጥቁር ነው የህይወት ቀለሙ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
...አልያስ እና ባሪያው ናቸው…ሁለቱም በዚህን ሰዓት ወደ እሱ ቤት አመጣጣቸው የተልኮቸውን ሪፖርት ሊያቀርቡለት መሆኑን ያውቃል…ሁለቱንም የተለያየ ተልዕኮ ሰጥቶ አሳማርቶቸው ነበር….አሪፍ የምስራችም ይዘውለት እንደመጡ ውስጡ እየነገረው ነው…
‹‹እሺ እንዴት ናችሁ ?››በፍቅር እና በፈገግታ እየተቀበላቸው ጠየቃቸው
‹‹ሁሉም ነገር ሰላም ነው..አንተስ?››ኤልያስ መለሰለት
‹‹ሰላም ነኝ..ይሄውና የጥዋቷን ፀሀይን በፍቅር እየሞቅኮት ነው?››
‹‹አሪፍ ነው ደስ ትላለች..››ባሪያው ነው የተናገረው
‹‹ኑ ወደ ውስጥ እንግባ››በማለት ቀድሞቸው ወደ ቤት ዘለቀ እና ወንበር ይዞ ተቀመጠ..እነሱም ከፊት ለፊቱ ባለው ወንበር ጐን ለጐን ተቀመጡ…
‹‹እሺ ኤልያስ እንዴት ነበር ለሊቱ?››
የሚገርም ሁኔታ ነው የገጠመን…. ልክ ዘጠኝ ሰዓት ሲል ነበር የተሰማራነው..በተነጋገርነው መሰረት ከእኔ ውጭ ሌሎች ሁለት ልጆች ይዤ ነበር የሄድኩት… በኃላ በኩል አጥር ዘለን ነበር የገባነው…ሁለቱን አጋሮቼን ወጭ ጥዬ ወደቤቱ ተጠጋው..የውስጥ መብራት እንደበራ ነው…በያዝኮቸው ማስተር ቁልፎች ተጠቅሜ ቁልፉን ለመክፈት ስሞክር እሯሱ ተከፈተልኝ..ደስ አላለኝም፡፡ፈተና የሌለው ነገር ድሮም አይደላኝ…ወደውስጥ ዘልቄ ገባው..በጓሮ በኩል ባለው በራፍ ስለገባው ቀድሜ ኮሪደር ላይ ነው ያረፍኩት..እንደጠረጠርኩት ውስጥ መልካም ነገር አልገጠመኝም ..ከወደ ሳሎን ድምፅ ይሰማል… ጭቅጭቅ ፡፡ ተጠጋውና ከሳሎኑ ቀጥሎ ባለ አንድ ጨለማ ክፍል ውስጥ በመግባት እራሴን ሸሽጌ ጆሮዬን ግድግዳ ላይ ለጥፌ ማዳመጥ ጀመርኩ……..
‹‹አንቺ አውሬ አመንዝራ ከገዛ ጓደኛዬ ጋ በገዛ አልጋዬ ትወድቂያለሽ?›››ወርቅአለማው ያንቧርቃል
‹‹አረ በፍጹም ምንም አላደረግኩም››ትመልሳለች
‹‹ታዲያ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት እቤቴ ምን አባቱ ይሰራል?››
‹‹በጊዜ እኮ ነው የመጣው ..አንተን እየጠበቀ ነበር››
‹‹አረ ባክሽ እኔን እየጠበቀ..አንቺም ውጭ የማድር መስሎሽ ደውለሽ ጠርተሺው ነው…ደግሞ የእኔን መኪና እያየ እንዴት ተስፈንጥሮ እንደተፈተለከ ይገርማል…እሱን ግድ የለም እሰራለታለው››ይለፈልፋል
‹‹አረ ቀለም …ተረጋጋ››
‹‹ጭራሽ ልረጋጋ..ምን አገኘው ብዬ ልረጋጋ .. ?ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ወንድ ከቤቴ ሲወጣ ደረስኩ …የመኝታ ቤቴ አልጋ ምስቅልቅሉ ወጥቷል…ፓንትሽ ወለሉ ላይ ወድቆ ነው ያገኘውት …አየሽ አልመጣም አድራለው ብዬ ተሰናብቼሽ የወጣውት እውነቴን መሰለሽ..?የሰሞኑ ሁኔታሽ ስላላማረኝ ተጠራጥሬሽ ነው…ትክክል ነበርኩ… ይሄ ሁሉ ሆኖ ምንም አላደረግኩም ትይኛለሽ? ››
‹‹እሺ ከመሰለህም ይቅር በላኝ በቃ››
‹‹ላንቺ የሚሆን ምንም ምህረት የለኝም …አንቺ አይደለሽም ማንም በእኔ ላይ አሻጥር ለመስራት የሞከረ ሰው መጨረሻው መቃብር ነው…በቀል ለእኔ ቀለቤ ነው …የእርካታዬም ምንጭ ነው …አጥፊዎቼን ቀድሜ ማጥፋት የአሸናፊነት እርካታ ያጐናፅፈኛል..ስለዚህ አንቺንም አሁኑኑ አጠፋሻለው››ይሄንን ሁሉ አስጨናቂ እና አሸባሪ ንግረግር እያዳመጥኩ ቢሆንም ፈጽሞ ግን ያለውን ያደርጋል ብዬ አልገመትኩም ነበር…እንጂማ ቢያንስ አንድ ነገር አደርግ ነበር..ከደቂቃዎች ቡኃላ ሚሰቀጥጥ የጣር ድምፅ ጆሮዬን ሰንጥቆ ገባ .. ‹‹.ዋጋሽ ይህ ነው… ለዘላለሙ በሰላም አንቀላፊ››የሚል ንግግር ሰማው..የሆነ ነገር እንዳደረጋት ገመትኩ፡፡ የማደርገው ግራ ገባኝ፡፡
ወዲያው መኝታ ቤቱ ተከፈተ እና ወርቅአለማው ወጣ.. እቤቱን ለቆ ወደውጭ ነው የወጣው ፡፡ ቀስ ብዬ ከተወሸቅኩበት በመውጣት ወደ መኝታ ቤት በፍጥነት ገብቼ የሄድኩበትን ተለወኮዬን ለመወጣት ገንዘብ ያለበትን ሳምሶናይት ይዤ ወደ ሳሎኑ ስወጣ ሴትዬዋ ሳሎን መሀል ወለል ላይ ተዘርራ አየዋት…የሽንኩርት መክተፊያ ቢላዋ ልቧ ላይ ተሰክቷባት ዙሪያ በደም ተጥለቅልቋል .…እራሴን ሁሉ መቋጣጠር አቅቶኝ ነበር.. በያዝኩት ሽጉጥ ግንባሩን ላፈርሰውም አሰብኩ..ግን ምን ላድርግ ያተን ተልዕኮ አጉል ማደረግ እና እራሴንም ማጋለጥ ይሆናል ብዬ በማሰብ እደምንም እራሴን አረጋጋው….በጓሮ በር ተመልሼ ወጣውና ጨለማ ውስጥ ተሸሽጌ እሱን ምን እንደሚሰራ መቃኘት ጀመርኩ…ጓደኞቼም ጠብቁኝ ካልኮቸው ቦታ የሉም… እርግጠኛ ነኝ ቀለምወርቅ ከቤት ሲወጣ ሲያዩት እንዳያያቸው ተሸሽገው እንደሆነ ገመትኩ..ትክል ነበርኩ…፡፡ቀለም ወርቅ ሽማጊሌውን ዘበኛ አንገት በለበሱት ፎጣ አንቆ እያንፈራፈራቸው ነው‹‹አንተ ሙትቻ ሽማጊሌ….ከእጄ እየበላህ ከእጄ እየጠጣህ የዛች ሻርሙጣ ተባባሪ ትሆናለህ?››
‹‹አረ ጌታዬ የሚሉትን ምኑንም አላውቅ››በታፈነ እና በሚርገበገብ የልመና ድምጽ መለሱለት
‹‹አትዋሸኝ..ለምትወረውርልህ ፍርፋሪ ነው አይደል የከደሀኝ..?ለከርስህ ብለህ..?ከርሳም ሙትቻ ሽማጊሌ››ወዝውዞ ወዝውዞ በጣር እስኪቃትቱ ጠብቆ ሲዝለፈለፉለት ለቀቃቸው..መሬት ላይ ዝርግፍ ብለው ተዘረሩ… እየተራገመ እና እየለፈለፈ ወደቤት ተመልሶ ገባ እኔም ልጆቼን ከያሉበት ሰባስቤ ግቢውን ለቀን ወጣን..፡፡
በሰላም ወደቤት ብገባም የሰላም እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን ፈፅሞ አልቻለም እዛ ሳሎን ተዘርራ በደም ተጨማልቃ ያየዋት ሚስቱ በህልሜ እየመጣች ስታቃዠኝ ነበር..አለስችል ሲለኝ ወደ እዚህ ከመምጣቴ በፊት እስኪ ሁኔታውን ልይ ብዬ ከባርች ጋር በዛ በኩል ነበር የመጣነው..ይገርምሀል ድንኳን ተጥሎል ህዝቡ ከያለበት ተገልብጦል ..አቶ ወርቅ አለማው ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ለቅሶውን ‹‹ሚስቴ ሚስቴ ..አካሌ ሚስቴ… ጉድ አደረግሺኝ›› እያለ ያስነካዋል…በጣም ነው የገረመኝ…ሰው ለካ ህይወቱ በድራማ እና በማስመሰል የተሞላ ነው..እየተገረምን ወደ አዚህ መጣን እልሀለው..ብሎ ከለሊት ጀምሮ እሱ ጋር እስኪመጣ ድረስ ያጋጠመው ዘግናኝ ታሪክ በዝርዝር ነገረው…
ይህንን ታሪክ ኩማደር ሲሰማ ይሰቀጥጠዋል ብሎ ጠብቆ ነበር.. በተቃራኒው ተፍለቅላቂ ፊት ነው ያሳየው..ይሄም አልያስን በጣም አስገረመው…‹‹ይሄ ሰው እኔ ከማስበው በላይ አረመኔ ነው ማለት ነው›› ሲል በውስጡ አብሰለሰለ…የኩማንደር ደስታ ግን የመነጨው ከሰዎቹ ስቃይ እና ሞት ሳይሆን ያን ተከትሎ ቀለም ወርቅን እንዴት እንደሚበቀለው ሲታሰበው ነው..በቃ ቀለም ወርቅን ለማጥፋት ጊዜው እንደቀረበች ሲገለጽለት ነው የፈነጠዘው፡፡
‹‹ጥሩ ነው እኔም ለቅሶ ደርሰዋለው..የሚስቱ ቀብር ላይም እገኛለው
አሁን ተነሱ ለእዚህ በድል ለታጀበ ብስራታችሁ ቆንጆ ቁርስ ልጋብዘዛችሁ..ልብሴን ቀይሬ እስክመጣ አንድ አምስት ደቂቃ በትዕግስት ጠብቁኝ ››ብሏቸው ወደመኝታ ቤቱ ገባ…
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሰዓቱ ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ላይ ነው፡፡ ፀሐይ ወደ ማደሪያዋ እየገሰገሰች ባለችበት ሰዓት ኩማደር መሀሪ ወደ ድሮ የእንጀራ አባቱ ቤት እየሄደ ነው፡፡በዚህ አስራአምስት ቀን ውስጥ ወደ እሱ ቤት ሲሄደ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ከአስራአምስት ቀን በፊት ለቀብር ነበር የሄደው....መቼስ ያንን ቀብር ከአንጀቱ አስቦበት ሊያጽናናው እንዳልሆነ እሱም ሆነ ወርቃለማው በደንብ ያውቃሉ.የሄደበት ዋና አላማ በስነልቦና ሊጫነው እና ሊያበሳጨው ስለፈለገ ነው….ዛሬ ደግሞ ለሌላ ብርቱ ጉዳይ ነው አካሄዱ..ደርሶ የውጩን በራፍን አንኳኳ..
ከሶስት ደቂቃ
👍4
ጥበቃ ቡኃላ በራፉን ሰራተኛዋ ከፈተችለት፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_ስምንት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...‹‹ደህና ዋልሽ?››አላት
‹‹ዴና››መለሰችለት በአጭሩ..
‹‹የቤቱ ባለቤት ይኖራል?››
‹‹ማ ጋሺዬ ኖ?››አማርኛ ስለሚቸግራት ብዙ ለማውራት አትደፍርም
‹‹አዎ››
‹‹ግቢ ››በማለት እንዲገባ ጋበዘችው..ገባ፡፡በሩን ዘግታ ከኃላ ተከተለችው፡፡ሳሎኑን ዘልቆ ሲገባ ተደመመ..እጅግ የተዋበ እና የተንጣለለ ቤተ-መንግስት መሳይ ሳሎን ነው እየተመለከተ ያለው፡፡ ባለፈው የመጣ ጊዜ ወደ ሳሎኑ የመዝለቅ ዕድል አልገጠመውም ነበር .....ከድንኳን ነበር የተመለሰው..እንዲሁ የቤቱን ውጫዊ ይዞታ ሲመለከተው አሪፍ የሚባል ቤት እንደሆነ መገመት ከባድ አልነበረም ግን ውስጡን አሁን ሲያየው ከግምቱ በላይ ነው የሆነበት…
‹‹ጥሪልኝ እስቲ…›› አላት ዝምብላ ቆማ አፍጥጣ የምታየውን ሰራተኛ..እንደመባነን አለችና ወደፎቁ መወጣጫ በረረች…ከሁለት ደቂቃ ቡኃላ ቀለምወርቅ መጣ ...የእንግዳውን ማንነት ሲያውቅ ግን ስቅጥጥ አለው‹‹ይሄ ከይሲ ምን ሊፈጥር መጣ?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡መኝታ ቤቱ ያለችው ሽጉጥ ትዝ አለችው..እንደምንም እራሱን ተቆጣጣረ እና ወደ እሱ በእርጋታ ተራምዶ ሰላምታ ሰጥቶት ከቅርቡ ካገኘው ወንበር ላይ ተቀመጥ….ኩማንደሩ ግን እንደቆመ ስለቀረ
‹‹ ተቀመጥ እንጂ.. ›› አለው ፈራ ተባ እያለ.
‹‹ አይ በቤቱ ጥራት እኮ ተደምሜ መቆሜንም ዘነጋውት››አለው
ወርቅ አለማው ያለውን እንዳልሰማ ሆኖ ››ሻይ ወይስ ቡና?››ሲል ጠየቀው
‹‹ቡና ካለይመረጣል››
መለሰለት…..ወርቅአለማው ሰራተኛውን ጠራና ሁለት ቡና እንድታመጣላቸው አዘዛት
‹‹እሺ ሰላም ነህ››ሲል ጠየቀው ወርቅ አለማው…. እወነት የእሱ ሰለም መሆን አሳስቦት ሳይሆን እንዲሁ የሚያወራው ስለጠፋበት ነበር ያንን ጥያቄ የጠየቀው ፡፡
‹‹አዎ ሰላም ነኝ ››በአጭሩ መለሰለት፡፡የታዘዘው ቡና መጣና ለሁለቱም ቀረበላቸው…. ሁለቱም ያለንግግር ትኩሱን ቡና መጠጣት ጀመሩ….. ወርቅ አለማው ጨነቀው እና መናገር ጀመረ
‹‹…እሺ ኩማደር..››
ቀና ቡሎ ዓይኑ ውስጥ ትክ ብሎ ተመለከተው ..አስተያቱ ይበልጥ አስበረገገው..የድሮ ሚስቱን መንፈስ እሱ ላይ ያየው መሰለው፡፡አሁን ኩማንደሩ መናገር ጀመረ ‹‹ወርቅአለማው ባለፈው መጥቼ ነበር …ግርግሩ ትንሽ አስቸጋሪ ስለነበር ሳላናግርህ ነው የሄድኩት…በዛ ላይ ሀዘን ላይ ስለነበርክ ትንሽ ጊዜ ልስጥህ ብዬ ነው፡፡ ለመሆኑ ባለቤትህ ብዙ ታማ ነው የሞተችው?››
አንገቱን ወደ መሬት በማቀርቀር አይኖቹን ወለሉ ላይ ተክሎ እየተቅለሰለሰ ‹‹እሱ እንኳን በጣም ታማ ነበር ለማለት አይቻልም..ብቻ አልፎ አልፎ የጤና መታወክ ያጋጥማት ነበር…..ግን እንዲህ በአንድ ቀን ለሊት አጣታለው ብዬ አስቤ አላውቅም.. ..ምን ይደረጋል እግዚያብሄር ቀማኝ፡፡››
‹‹ኩማንደር ከመቀመጫው ተነስቶ ሳሎን ውስጥ እየተንጐራደደ ተንከትክቶ መሳቅ ጀመረ ቀለምወርቅ ደነገጠ..ምን የተሳሳተ ነገር ከአንደበቱ እንዳመለጠው ሊገለጽለት አልቻለም ፡፡
‹‹ቆይ እግዚያብሄር ቀማኝ እንጂ ነው ያልከው?››
‹‹አዎ መቼስ ሚሰጥም ሚነሳም እሱ ነው›› አለ በሚንቀጠቀጥ ድምጽ.. ኩማናንደር የጀመሩትን ርዕስ ድንገት ቀይሮ ሌላ ርዕስ ውስጥ ገባ
‹‹አንድ ኢንፎርሜሽን ሰምቼ ነበር …ሞች ሚስትህ በሞተችበት ቀን አንድ ዕቃ ተሰርቆብህ ነበር አሉ ..ስለ እሱ ጉዳይ እስቲ ትንሽ ብታስረዳኝ?››
‹‹ኸረ ውሸት ነው ....ኸረ በፍጹም፡፡ ..በእለቱ ከሚስቴ ነፍስ ውጭ ምንም አልተሰረቅኩም››በመርበትበት መለሰለት፡፡
‹‹የእርዳታ ድርጅቱ በእለቱ ግምሽ ሚሊዬን ብር ተረክበህ ወደ ቤትህ ይዘህ ገብተህ ነበር?››ግራ ተጋባ... ግን እጅ መስጠት እንደሌለበት እራሱን በውስጡ አሳመነ.. እና ኮስተር አለ ‹‹በወቅቱ እንዳጋጣመሚ ሆኖ በጥሬ ብር ነበር እርዳታውን የተረከብነው ..ይሄን ደግሞ አንተም በደንብ ታውቃለህ ምክንያቱም ገንዘቡን የለገስከው አንተ ነህ…ጊዜውም መሽቷ ስለነበረ ባንክ ቤት ዝግ ነበር ወደ ቤቴ ይዤ መጣው… በዛው ለሊት ያ መጥፎ አጋጣሚ በሚስቴ ላይ ደረሰ ስለዚህ በማግስቱም ወደ ባንክ ሄጄ ማስገባት አልቻኩም፡፡አሁን ከአራት ቀን በፊት ግን አስገብቼዋለው… ይሄንንም ማወቅ ከፈለግክ ደግሞ ንግድ ባንክ ጐራ ብለህ ማረጋገጥ ትችላለህ..››
‹‹አውቃለው ያስገባኸው ግን በአዋሽ ባንክ ካለህ አካውንት ላይ ወጪ አድርገህ ነው ..ተሳሳትኩ ?›› ወርቅ አለማው ከእስከ አሁን ካለው በበለጠ ሁኔታ ደነገጠ ‹‹መረጃውን ከየት አገኘ.?ለማንም አልተነፈስኩም››ደነገጠ ወርቅ አለማው..ምን ማድረግ እንዳለበት እንኳን አስቦ መወሰን አልተቻለም ይህ የድሮ ሚስቱ ብቸኛ ልጅ በውስጡ ክፉኛ ቂም እንደቋጠረበት በእርግጠኝነት ያውቃል…አድፍጦ አንድ ቀን ባገኘው አጋጣሚ ሊበቀለው ጥረት እንደሚያደርግም ይጠብቅ ነበር …እንዲህ በፍጥነት ይሆናል ብሎ ግን አላሰበም ነበር፡፡
ኩማደር መሀሪ መንጐራደዱን አቋርጦ ወደመቀመጫው ተመለሰና ተረጋግቶ ተቀመጠ..‹‹በጣም ይገርማል ...ይሄ እግዜር አንተን በስንቱ ነው የሚበድልህ? ያን ሁሉ ብር ተሰረቅክ… ሚስትህን ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታለች ብለህ ስለጠረጠርካት .. እግዝብሄር ባንተ ልቦና አድሮ በቅናት ተነሳስቶ የሚያብረቀርቅ ጩቤ በልቧ ውስጥ ሸቀሸቀባት..ይገርማል!!
…››አላገጠበት
ሶፋው ላይ ያለው ወርቅ አለማው ባለበት ሰውነቱ ሁሉ ደነዘዘበት …አይኖቹ ከጉድጎዳቸው በገዛ ፍቃዳቸው ተጐልጉለው በመውጣት ፊት ለፊት ፈጠጡ
ኩማደንደሩ‹ ብረትን ማጣመም እንደጋለ ነው› በሚለው መርህ መሰረት በድል አድራጊነት መንፈስ ዘና ብሎ ንግግሩን ቀጠለ‹‹ሌላው ሽማግሌው ዘበኛህንም በገዛ ፎጣው አንቆ የገደለው እግዜር ይሆን..?አይ ይሄ እግዜር ጭካኔው…›.የኩማደሩ የሽሙጥ ንግግር ለወርቅ አለማው ከሚቆጣጠረው በላይ ሆነበት..
‹‹ምንድነው የምትቀባጥረው?››አንቧረቀበት
‹‹የምታውቀውን እና ያደረግከውን ነገር እየነገርኩህ ነው..››
‹‹አጉል መዘባረቅ አይሆንብህም ታዲያ?››
‹‹ነው ብለህ ነው?››
‹‹እሺ አሁን እቤቱን ለቀህልኝ ልትወጣ ትችላለህ?››
‹‹ይሻልሀል..ክህደቱ ያዋጣኸል?ማታምንልኝ ከሆነ አሁን እንዳልከው እቤትህን ለቅቄ ሄድልሀለው..ግን ነገ በማለዳው ፖሊስ ይዤ እመጣና የሚስትህን ቀብር ተቆፍሮ እንዲወጣ እና አስከሬኖ እንዲመረመር አደርጋለው…›
‹‹አትችልም..ይሄንን የሚወስነው ፍርድ ቤት ነው…›
‹‹እርግጠኛ ነኝ የምትለውን ፍቃዱን በቀላሉ ማግኘት እንደምችል ምትረዳ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ምንድነው ከእኔ የምትፈልገው?››
‹‹እንድንስማማ››
‹‹ምንድነው የምንስማማው?››
‹‹..መጀመሪያ ገድለሀታል ወይስ አልገደልካትም?››
‹‹ገድያታለው››ከአሁን ወዲህ መንፈራገጡ ለመላላጥ ብቻ ካልሆነ ምንም እንደማይረባው ስላወቀ እጅ ሰጠ …
‹‹ሸማግሌውንስ?››
‹‹እሱም ተባባሪዋ ስለሆነ ገድዬዋለው››
‹‹ከገደልከው ቡኃላ እሬስውን እንዴት አደረግከው?››
‹‹ሁለቱም በምግባር አንድ ስለሆኑ አንድ ጉድጐድ ውስጥ ነው የከተትኮቸው..››
‹‹እሺ ጥሩ ነው አሁን ወደ ድርድራችን መግባት እንችላለን››አለው ኩማንደር በእርጋታ እየተመለከተው..
‹‹በምንድነው ምንስማማው?››
‹‹በብር››አጭር መልስ
ሳይወድ በግዱ መስማማት አለበት በብርም ከማረው ተመስገን ነው.‹‹እሺ እንዳልክ.. ስንት ልክፈልህ?››
‹‹አምስት ሚሊዬን››፥
‹‹ምን?››በድንጋጤ ጭንቅላቱን ያዘ
‹‹ምን ያስደነግጥሀል.ያው የራሴን ብር ነው መልሼ ስጠኝ ያልኩህ የዘረፍከኝን የእናቴን ነፍስ ልትመልስልኝ ባትችልም.. የዘረፍከንን ብር ግን ልትመልስልኝ የግድ ይላል...>>
👍4
‹‹ብሩ በጣም በዛ እኮ!!››
‹‹አምስት ሳንቲም ብትጐል አልቀበልም››
‹‹የዛን ያህል ብር እኮ እኔም የለኝም..ከየት አመጣለው?››
‹‹በ 3 ባንኮች ውስጥ ባሉህ ደብተሮች ላይ ሰባት ሚሊዬን ጥሬ ብር እንዳለህ አውቃለው….በእነዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ ያልኩህን ያህል ብር ካላስረከብከኝ በቃ ያልኩህን አደርጋለው..በል ደህና ሰንብት››ብሎ እንደፈዘዘ ቤቱን ጥሎለት ወጣ..
ወርቅ አለማው ከደነዘዘበት መቀመጫ ላይ ተስፈንጥሮ ተነሳና ወደ መኝታ ክፍሉ አመራ፡፡ አልጋው ላይ በጀርባው ተዘርሮ አይኑን ጣሪያው ላይ ተክሎ ምስቅልቅል ሀሳቦችን ያስብ ጀመር ..ደግሞም ተነሳ እና ኮሞዲኖ ላይ የተቀመጠውን ውስኪ ጠርሙስ አነሳ እና ከእነ ጠርሙሱ አፉ ላይ ደቅኖ አንደቀደቀው………. የንዴት እና የሽንፈት አጠጣጥ ነበር፡፡እሩብ ያህሉን አጋመሰ እና ቀሪውን ይዞ ወደ መስኮቱ ተጠጋና በጨለማው እየተሸነፈ ያለውን ውጭ እየቃኘ ምን ማድረግ እንዳለበት ማሰብ ቀጠለ‹‹አምስት ሚሊዬን ብር ቆጥሮ ሲሰጥ ታየው …. ሰውነቱ በላብ ወረዛ‹‹መሆን የለበትም በፍጹም አይደረግም››ወሰነ‹‹አዎ መገደል አለበት …አላርፍ ካለ እሱንም አጠፋዋለው…እናቱ ወደላችበት መቃብር እልከዋለው››በውሳኔው ረካ.. እና ከት ብሎ ሳቀ..የበቀል ሳቅ…..የመብለጥ ሳቅ….የአሸናፊነት ሳቅ……ይሄስ ይሳካለት ይሆን ? ጊዜ ነው ሚመልሰው።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ቀለም ወርቅ ሸዋ በር የሚገኘው የእኛ ሆቴል አንድ ጥግ ውስጥ ደበቅ ያለ ቦታ ተቀምጦ ቢራውን እየኮመኮመ ሰው እየጠበቀ ነው…የሚጠበቀው ሰው መጣለት፡፡ወንድ አፍራሽ ይባለል..፡፡አንዳንዴ የሰው ልጅ አቋምና ባህሪ ከስሙ ጋር ይሄዳል ..ለዚህ ይሆናል
<<ስምን መላዕክ ያወጣዋል>>የሚል ተረት ያለን..ግን መልአክ ብቻ ነው እንዴ ትክለኛ ስም የማውጣ ችሎታ ያለው..?ሰይጣንስ ይህ ችሎታ እንደሌለው በምን አወቅን . ?.ለማኛውም ወንድአፍራሽ እንደስሙም መላ ነገሩ ያስፈራል..ግዙፍ ነው አንድ ሜትር ከዘጠና ሁለት በሆነ ቁመቱ ላይ 103 ኪ.ግራም ስጋ ተሸክሞበታል …አፈፍ አርጎ ቀለምወርቅን በጠንካራ እጁ ጨበጠውና ከፊት ለፊቱ ተቀመጠ
‹‹ምን ይምጣልህ?››አለውና እንድትታዘዘው አስተናጋጆን ጠራለት
‹‹ምን ልታዘዝ?››
‹‹ሶስት ጃንቦ››ግራ ገባት
‹‹ስንት ጃንቦ?››መልሳ ጠየቀችው
‹‹ሶስት ጃንቦ አምጪለት››አላት አመሉን የሚያውቀው ቀለም ወርቅ
‹‹ልጅቷ ፈገግ እያለች ልታመጣ ሄደች ..ወንድአፍራሽ አንድ ጃንቦ የሚያዘው የገንዘብ እጥረት ካለበትና እራሱን በራሱ የሚጋብዝ ከሆነ ብቻ ነው..ካለበለዚያ ቁጥ ቁጥ ማዘዝ እርካታ አይሰጠውም…….እሱ ከመርካቱ በፊት ድንገት ከምንጩ የሚያልቅበት ይመስለዋል፡፡
‹‹እሺ ምን ነበር ስራው?››በማለት ቀጥታ ወደ ቁምነገሩ ገባ ወንድ አፍራሽ
‹‹ያው የተለመደው ነው››
‹‹ይገባኛል..ማለቴ የሚሸኝ ነው ወይስ…››
‹‹አዎ የሚሸኝ ነው››አለው..እስከአሁን የተለያዩ ሰዎችን ላይ ባለው ቂምና በስራ በተፈጠረ መቀናቀን ከአራት ሰዎች በላይ ቀጥቅጦለታል …አስፈራርቶለታል…አንድ ሰው ደግሞ አስወግዶለታል…ለዚህም ሁለቱም ተገቢ ነው የሚሉትን እና የተስማሙበትን ክፍያ ከፍሎታል…በዚህም ምክንያት ደንበኞች ሆነዋል….
‹‹እንግዲያው ጥሩ ነው ግን ሂሳብ ትንሽ ይጨምርብሀል››
‹‹ለምን?›› አለ ቀመለምወርቅ
‹‹ያው ኑሮ ተወደደአ ..ምን ያልጨመረ ነገር አለ ብለህ ነው..፡፡ባለበት በድሮ ዋጋ ያለ የእግዜሩ አየር ብቻ ነው….እነሱም ቢሆኑ ቢያንስ በጥራት ለውጥ ማሳየታቸው አልቀረም››
‹‹እሺ እንዳልክ..ስንት ልክፈልህ?››
‹‹100 ሺ ብር››
‹‹ትገርማለህ …ጭማሪ ቢሉህ እንዲህ ነው እንዴ…?በአንዴ ከ50ሺ ብር ወደ 100 ሺ ብር›››
‹‹አዎ ምን አላት ብለህ ነው….ህይወት ላይ አይደል የምንደራደረው››
‹‹እሺ ይሁን ስራውን ግን ያለምንም መዝረክረክ በጥንቃቄ ነው የምትፈጽምልኝ››
‹‹ለእሱ አታስብ የተከበረ ሞያችንን አናረክስም››አለና እጆቹን አጨብጭቦ አስተናጋጆን ሌላ ሶስት ጃንቦ እንድታመጣለት አዘዛት..አስቀድማ ወዳመጣቻቸው ሶስት ብርጭቆዎች ስታይ ባዶ ናቸው፡፡
‹‹እሺ የሰውዬውን ፎቶ እና አድራሻውን ስጠኝ››ጠየቀ ወንድአፍራሽ
‹‹አያስፈልግህም››
‹‹እንዴት?››
‹‹ሰውዬውን ታውቀዋለህ››
ደንገጥ እንደማለት አለ ..መቼስ ምንም እንኳን ለእሱ ስራ ቢሆን ከሚያውቀው ሰው ይልቅ የማያውቀውን ሰው መግደል ቀለል ይለዋል፡፡
‹‹ማን ነው?››
‹‹ኩማንደር መሀሪ ይባላል የፖሊስ አዛዡ››
ወንድአፍራሽ ከተቀመጠበት በርግጎ ተነሳ… መልሶ ቁጭ አለ..ዙሪያውን ተገለማመጠ
‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››አለው ቀለም ወርቅ የእሱ እንዲህ መበርገግ መልሶ እሱን እያስበረገገው…
‹‹ለምን አልፈራ …ማንን ግደል እያልከኝ እደሆነ ታውቃለህ…?እኔ በአሁኑ ሰዓት በዚህ ከተማ በጣም የሚቀፈኝ እና ትከሻዬ የማይወደው አንድ ሰው ቢኖር እሱ ነው››
‹‹ጥሩ ነዋ››
‹‹ምኑ ነው ጥሩ?››
‹‹እሱን መጥላትህ ነዋ …በዛውም ተገላገልከው ማለት ነው››ሊያበረታው ሞከረ
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ …እጠላዋለው ብቻ እኮ አይደለም ያልኩት…እፈራዋለውም ነው የምልህ››
‹‹ኸረ ተው …. ፍራቻ ባንተ አያምርብህም››
ለደቂቃዎች እንደመተከዝ አለና‹‹ይሄን ልስራው ብል እንኳን ብቻዬን አልወጣውም አንድ ጠንካራ አጋር ማሳተፍ አለብኝ›››
‹‹ጥሩ ነዋ የምታምነው ሰው ካለ ምን ቸገረኝ››
‹‹የማምነው ሰው አለ ሂሳብ ግን በሁለት እጥፍ ይጨምራል››
‹‹ማለት..?››
‹‹ያው እሱም ቢያንስ 100 ሺ ብር ይጠይቃል..ስለዚህ 300ሺ ብር መክፈል ይኖርብሀል››
‹‹ትቀልዳለህ ..ይሄን ያህልማ አልከፍላችሁም››
‹‹እንግድያው ደህና ሁን በሌላ ስራ እንገናኝ›› ብሎ የመጨረሻ የቀረችውን አንድ ብርጭቆ ድራፍት በአንድ ትንፋሽ በመጨለጥ ተነሳ
ቀለምወርቅ ደነገጠ… ብሩን እንዲሁ ለመከራከር ያህል ነው እንጂ መቼስ አምስት ሚሊዬን ብር ለማዳን ሰስት መቶ ሺ ብር መክፈል ጥሩ የሚባል ድርድር ነው… በዛ ላይ የዘላለም የሚባል ጠላቱን አስወግዶለት ነው....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...‹‹አረ ቁጭ በል ..ከጨከንክ ምን አድረጋለው እከፍልሀለው››
‹‹ተመልሶ ቁጭ አለ..እሺ ቅድሚያ ለስራ ማስኬጃ 25 ሺ ብር እፈልጋለው፡፡ሌላው ስራው ሲጠናቀቅ››
‹‹እሺ ››አለና ቀለም ወርቅ ምንም ሌላ ትርፍ ነገር ሳይናገር ከለበሰው ግዙፍ የውስጥ ጃኬት ውስጥ ወንድአፍራሽ የጠየቀውን ቅድሚያ ክፍያ አውጥቶ ሰጠውና በአንድ ሳማንት ጊዜ ውስጥ መጨረሻውን ውጤት እፈልጋለው››ብሎት ተነሳ
‹‹ግድ የለም በሶስት ቀን ለማጠናቀቅ እሞክራለው››
‹‹ይቅናህ››
ብሎት የሆቴሉን ግቢ ለቆ ወጣ
ወንድ አፍራሽ አስተናጋጆን ጠራትና‹‹ሁለት ክትፎ አንድ ጥብስ እና ሶስት ጃንቦ ሲል አዘዛት››አሁን ግራ እደተጋባች ትዛዙን ልታስተላልፍ ወደ ውስጥ ሄደች እሱ ሞባይሉን አወጣና ደወለ
‹‹ሄሎ ኤልያስ››
‹‹ሄሎ ወንድ››
‹‹የት ነህ?››ጠየቀው ወንድ አፍራሽ
‹‹ሸዋ በር››
‹‹እኔም እዛው አካባቢ እኮ ነኝ ለአሪፍ ሽቀላ እፈልግህ ነበር..የእኛ ሆቴል ብቅ ማለት ትችላለህ? ››
‹‹መቼ ?››
‹‹አሁን እዛው ነኝ ››
‹‹እሺ..መጣው››
ስልኩ ከተዘጋ ከ10 ደቂቃ ቡኃላ ኤልያስ መጣለት በሞቀ ሰላምታ ተቀበለው ወዲያው አስተናጋጆ የታዘዘችውን ምግብ ይዛ መጣች…በልተው እንዳጠናቀቁ ኩማንደር የተባለውን የፖሊስ አዛዥ ለመግደል ከተባበረው 30 ሺ ብር እንደሚከፍለው ነገረው..ኤልያስ በሰማው ያልተጠበቅ አስደንጋጭ ዜና ውስጡ እየተንቀጠቀጠ ቢሆንም በላይ ገጽታወ ግን ምንም የስሜት መለዋወጥ ሳይንፀባረቅበት ወንድ አፍራሽም ልክፈልህ ባለው የዋጋ መጠን ሳይከራከር በሀሳቡ ተስማማ..ከነገ ጀምሮ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተስማምተው ለዚህም ማረጋገጫ ኤልያስ 5 ሺ ብር ቀብዲ ተቀብሎ ማታ ሊገናኙና በዝርዝር ጉዳዬች ላይ ሊነጋሩ ተስማምተው ተለያዩ …ኤልያስ ቀጥታ ከወንድ አፍራሽ እንደተለየ..ለኩማደሩ ነበር የደወለው
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ወንድአፍራሽ እና ኤልያስ በቀጠሮቸው መሰረት ተገናኝተዋል፡፡አሁን ሰዓቱ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ የሚገኙት ከበቀለ ሞላ ሆቴል በቀኝ በኩል መቶ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሚገኘው ትንሳኤ ሆቴል ነው፡፡ይሄንን ሆቴል የመረጡበት ምክንያት ዋናው ለኩማንደሩ ቤት ብዙም ስለማይርቅ ነው… ሌላው ደግሞ ወንድ አፍራሽ ቀልቡ ያረፈባት አዲስ ገቢ ልጅ አሁን ያሉበት ሆቴል ውስጥ ስላለች ነው፡፡ሰሞኑን እጁ አጥሮት ነው እንጂ ከጅሏት ነበር፡፡እና አሁን ሁለቱም እዛ ነው ያሉት አንድ ጥግ ይዘው መጠጡን እያወራረዱ ከሰዓታት ቡኃላ ስላለባቸው ተልዕኮ ይወያያሉ፡፡
‹‹ግን አሁን እቤቱ እንዳለ አጣርተህልኛል አይደል?››ወንድአፍራሽ ነው ጠያቂው
‹‹አዎ ባዘዝከኝ መሰረት በቤቱ አካባቢ አድፍጬ ስከታተለው ነበር…ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው ወደቤቱ የገባው.››
‹‹ከገባ ቡኃላ እንደማይወጣ በምን አወቅክ?››
‹‹ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ የለሊት ቢጃማ ለብሶ ስሊፐር ጫማ አድርጎ ከቤቱ በመውጣት ሰፈር ወዳለች አንድ ኪወክስ ሄዶ ሲጋራ በመግዛት ወደቤቱ በመመለስ እቤቱን ዘግቷል..እርግጠኛ ነኝ ተመልሶ የመውጣት ሀሳብ ቢኖረው ኑሮ እንደዛ አይነት አለባበስ አይለብስም ነበር››
‹‹አሪፍ ሰላይ ነሽ..ለዚህ ቅልጥፍናሽ እኮ ነው አንቺን የመረጥኩት››ሲል አደነቀው..‹‹በል አሁን ሰዓቱ እስኪደርስ ዘና እንበል…ሰባት ሰዓት ሲሆን እንንቀሳቀሳለን እስከ ስምንት ሰዓት ሁሉን ነገር ፈጽመን በድል እንመለሳለን››
‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ይሳካልናል?››እልያስ ነው የወንድአፍራሽን የውስጥ ጥንካሬ ለመገምገም የጠየቀው
‹‹አትጠራጠር..እንኳን አንተን ከጐን አሰልፌ ይቅርና እኔ ብቻዬን ብሆን እንኳን ለእሱ አላንስም…ያው እንደማንኛውም ሰው እሱም ሰው እኮ ነው….በጣም ገዝፎ የሚታየን እና አስፈሪ የሚሆንብን ከእነ ማዕረጉ ስለምናስበው እኮ ነው…እኛ ደግሞ እሱን ምናገኝበት ሰአት ወድቅት ለሊት ነው..በዛ ሰዓት ደግሞ ህዝብም እንቅልፍ ላይ መንግስትም ደግሞ በማሸለብ ላይ ሰለሚገኙ ማዕረግ አይሰራም››
ሲል ለመፈላሰፍ ሞከረ
‹‹እንደአፍህ ይሁንልህ..እኔ ግን ትንሽም ቢሆን ፈርቼያለው››አለው ኤልያስ
‹‹መፍራትህ ጥሩ ነው….ከመጠን ያላለፈ ፍርሀት ጥንቃቄን ይወልዳል…ጥንቃቄ ደግሞ የድል በር የምንከፍትበትን ቁልፍ ያስጨብጠናል›..ትል ነበር አያቴ…እና እንኳንም ፈራህ.. እኔም ፍርቼለው..አሁን ግን ዘና በል ጠጣ፤ ጨፍር፤ ተዳራ ከዛ ድፍረት ታገኛለህ ››ብሎ አደፋፈረውና በእጁ ምልክት ሰሞኑን ሲከጅላት የሰነበታትን ልጅ ጠራት..እየተውረገረገችም እየተንዘረዘረችም ወደእሱ ቀረበች
‹‹የእኔ ቆንጆ ተቀመጪ›› አላት ወንድአፍራሽ…
በተቀመጠበት አንዴ ሸምድዳ በመመልከት ገመገመችውና ተቀመጠች…የምትጠጣውን አዘዘች
‹‹በጣም ውብ ነሽ›› አላት ወደጆሮዋ ተጠግቶ
‹‹አንተም ሸበላ ነህ››አለችው ሙዚቃዊ ለዛ በላው ድምጽ ..ደስ አለው ..ወደዳት
‹‹ለዛሬም ቢሆን ላገባሽ እፈልጋለው››
‹‹የምታስርልኝ ቀለበት ከተስማማኝ ችግር የለውም፡፡››
‹‹አረ አስርልሻለው…ሰሞኑን በብር ቀለበት ነው አይደል ይዘውሽ የሚያድሩት ዛሬ እኔ የወርቅ ቀለበት ነው ማጠልቅልሽ››
‹‹እንደዛ ከሆነ እኔም ገነታዊ የሆነ ለሊት እንደምታሳልፍ ዋስትና እሰጥሀለው››አለችው በፈገግታ
በቃ ወደዳት…ሲያያት በመልኳ ከተማረከው በላይ አሁን ቀርቦ ሲያወራት በድምጾ እና በብልጠታዊው ንግግሯ ተማረከ
ወንድአፍራሽ ወደ ኤልያስ ዞረና
‹‹ሰዓት ስንት ሆነ ?››ሲል ጠየቀው
‹‹ሰባት ሰአት እስኪሆን ጠጣ ጨፍር ፤ዘና በል››አለው ኤልያስ..ወንድ አፍራሽም የኤልያስን ምክር ሰምቶ የልጅቷን እጅ እየጐተተ ወደ ዳንሱ ሜዳ ይዞት ሄደ..አብሮት ሊጨፍር
በዚህን ጊዜ ኤልያስ ሽንቱን እንደሚሸና በጐሮ በኩል ወደውጭ ወጣና ለኩማንደሩ ደወለለት››
‹‹እሺ ኩማንደር ሰላም ነው?››
‹‹ሰላም ነው››
‹‹ዝግጅታችሁን አጠናቀቃችሁ?››
‹‹አዎ የእናንተን መምጣት ነው በናፍቆት እየጠበቅን ያለነው››
‹‹እንግዲያው በቃ ከአንድ ሰዓት ቡኃላ እንመጣለን ››
‹‹እሺ እስከዛው ቻው››
‹‹ቻው››ስልኩን ዘጋ ና ወደ ውስጥ ተመለሰ..
ወንድአፍራሽ አሁንም ከልጅቷ ጋር በደስታ እየተፍነከነከ እና እየደነሰ ነው..ከደቂቃዎች ቡኃላ ሰው ሊገል ለፊልሚያ የሚሰማራ ሳይሆን ወደሰርግ ቤት ለመጨፈር ለመሄድ ቀጠሮ ያለው ይመስል ነበር..ወደ ልጅቷ ጆሮ ጠጋ ብሎ ‹‹ዛሬ በእውነት ውድ ቀን ነች›› አላት
እየተፍለቀለቀች‹‹እንዴት?››ስትል ጠየቀችው
‹‹በቃ በሁሉ ነገር ጣፋጭ ነሻ..በጣም ወድጄሻለው..ዛሬ አብረን ነው የምናድረው››
‹‹ይመቸኛል ..የት ነው አልጋ የያዝከው?››
‹‹አልያዝኩም እዚህ አልጋ የለም እንዴ?››
‹‹ብር ስጠኝና ጠይቄ ልምጣ››
‹‹እሺ ቆንጆ አለና ኪሱ ገብቶ አልጋ ለመከራየት ይበቃል ያለውን ብር አውጥቷ ሰጣት..ብሩን ተቀበለችውና ከእቅፉ ሹልክ ብላ በጓሮ በር ወጥታ ሄደች …እሱም ከደናሾቹ መካከል ወጣና ወደ ኤልያስ ሄደ
‹‹ወፍህስ…ወደሌላው በረረችብህ እንዴ?›› ጠየቀው ኤልያስ
‹‹አረ በደንብ አጥምጄያታለው ዛሬ ከእኔው ጋ ነች… አልጋ ልትከራይ ነው የሄዳለች››
‹‹እንዴ ሀሳብህን ቀየርክ እንዴ?››ግራ በመጋት ጠየቀው
‹‹የምኑን ሀሳብ?››
‹‹ሰውዬው ጋር የመሄዱን ነዋ››
‹‹አንተ ደግሞ እንዴት ቀይራለው .. ?ምን ግዜም እኮ ለስራ ቅድሚያ መስጠት የግድ ነው››
‹‹ታዲያ አልጋ ልትከራይ ሄደች ስትለኝ ምን ልበል?››
‹‹እሱማ እውነቴን ነው አየህ ሄደን ስራችንን አጠናቀን ስንመጣ ..ይታይህ ከዚህች የመሰለች ልጅ ጋር ዘና ብል ያንስብኛል
👍3
እንደውም አንተም አንዷን መርጠህ አስቀምጠህ ብትሄድ መልካም ነው››ምክሩን ለገሰው
‹‹ይቅርብኝ‹መብላቷን ሳታውቅ እጆን ታጠበች›
እንዳይሆንብኝ …ወደ ጦር ሜዳ የሚሄድ ወታደር ሚስት ባያገባ ይመረጣል…በመመለሱ አስተማማኝ መሆን ስለማይችል ፡፡››አለው፡፡
‹‹አንተ ደግሞ ያለወትሮህ ዛሬ ሟርት አበዛህ››
‹‹ሟርት አይደለም የተሰማኝን ነገር ነው የነገርኩህ?››
በዚህ ጊዜ የወንድአፍራሽ ሴት ከሄደችበት ተመልሳ መጣች እና ከጐኑ ተወሸቀችበት
‹‹መጣሽ ቆንጆ?››
‹‹ተከራይቻለው የእኔ ዋርካ ››እያለች እላዬ ላይ ተለጠፈችበት እና የመኝታ ቤቱን ቁጥር ነገረችው..
‹‹ስንት ልክፈልሽ? ››አላት
ነገረችው..ከጠየቀችው አስበልጦ ሰጣትና‹‹ አሁን ይሄን ጓደኛዬን እቤቱ አድርሼው እመጣለው…ክፍልሽ ገብተሸ ተኝተሸ ጠብቂኝ….››
‹‹እንዴ ምነው ይፈራል እንዴ… ለምን ብቻውን አይሄድም?››
‹‹ሳይሆን እቤቱ ድረስ አብሬው ሄጄ የምወስደው ዕቃ አለ››
‹‹እሺ ግን ትቆያለህ?››
‹‹አይ አንድ 30 ደቂቃ ብቻ ባስጠብቅሽ ነው…አንቺ ብቻ ዝግጁ ሆነሽ ጠብቂኝ..ደግሞ አስደሳችነትሽ በዚሁ ከቀጠለ ጥዋት አሪፍ ቦነስ ይኖርሻል›› ...ብሎ ጉንጮን ሳማትና ተያይዘው ወጡ ..ወደ ኩማደር መሀሪ ቤት….የቀለም ወርቅን ትዕዛዝ ተቀብለው ሊገድሉት…..
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
መብራት እየበራ ነው ሁሉም ነገር ፍንትው ብሎ ይታያል..ምንም አይነት እንቅስቃሴ ግን አይታይም‹‹ምን እናድርግ››ሲል ኤልያስ ወንድአፍራሽን ጠየቀው ‹‹መጀመሪያ አጥሩን ዘለን ወደግቢ ውስጥ እንግባ››ተስማሙ እና ምቹ በሆነ ቦታ መርጠው በመንጠላጠል ዘለው ገቡ..አጥር በመዝለል ከፍተኛ ልምድ ስላላቸው አልተቸገሩም..በፍጥነት ወደቤቱ ተጠጉ ….በተረከዛቸው እየተራመዱ ድምጽ ላለማሰማት እየተጠነቀቁ የፎቁን ደረጃ ወጡ..…ብዛት ያላቸው ቁልፎች እና ለቁልፍ መሰርሰሪያነት የሚያገለግሉትን መሳሪያዎች በጀርባው አንግቶት ከነበረው ቦርሳ አወጣና በራፍን ያለኮሽታ እና ቅጭታ ሊከፍት ሊሞክር እጁን ወደ በራፍ ሲልክ ንቅናቄ ተመለከተ …ሲሞክረው ተከፈተለት፡፡ደነገጠ..፡፡ወዲያው ሙሉ በሙሉ ከመክፈቱ በፊት እቃዎቹን ወደ ቦርሳው መለሰና ሽጉጡን አወጣ …
ለኤልያስ በተጠንቀቅ እንዲሆን ምልክት ሰጠውና በራፉን ገፋ ሲያደርገው ሙሉ በሙሉ ተከፈተ፡፡…ሁለቱም በግራና በቀኝ በራፉ አቅጣጫ ሆነው በተጠንቀቅ ወደ ውስጥ አተኮሩ…… ያዩትን ነገር ግን ማመን የሚከብድ ነው፡፡ ኩማደሩ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ እግሩን እንደ ስርአት-አልባ የሀብታም ልጅ ጠረጵዛ ላይ ሰቅሎ በቀኝ እጁ ብርጭቆ ጨብጦ ይጠጣል…ሁለቱም ሽጉጣቸውን እንደደቀኑ ወደ ውስጥ ዘልቀው ገቡ…ምንም የመገረም ምንም የመደንገጥ ስሜት ሳያሳይ ዘና እንዳለ ነው….ወንድአፍራሽ ግራ ተጋባ
‹‹‹ይሄን ጥጋበኛ ፈትሸው››ሲል ለኤልያስ ትዕዛዝ አስተላለፈ…ኤልያስ የቀሰረውን ሽጉጥ ጐኑ ሸጐጠና ወደ ኩማንደሩ ተጠጋ
‹‹እግርህን አውርድ››
‹‹ኸረ የተከበራችሁ አንግዶቼ በራሳችሁ ጭንቀት ሽብር አትፍጠሩ ..ይልቅ ኖር ብዬለው…ቁጭ በሉና እየጠጣው ያለውትን መጠጥ ልጋብዛችሁ››
‹‹እያሾፍክ ነው በቁጥጥራችን ስር እኮ ነው ያለኸው…ይልቅ በጨዋ ደንብ ተነስና ተፈተሸ››
‹‹እሺ ካልክ›› አለና ዘና እንዳለ ብርጭቆውን ጠረጵዛ ላይ አስቀምጧት ቆመ ….ኤልያስ ፈተሸው…‹‹ምንም መሳሪያ አልያዘም…››
‹‹ቁጭ በል ››ወንድአፍራሽ ኩማንደሩን አዘዘው
ቁጭ አለና ‹‹አንተም የቀሰርከወን ሽጉጥ ስለማይጠቅምህ አስቀምጠኸው ከእኔው ጋር ቁጭ ብለህ መጠጡን እየጠጣን ዘና ብንል የእኔ ምክር ነው፡፡››
ወንድአፍራሽ የዚህ የኩማደር ትዕቢት ትዕግስቱን እየተፈታተነው ነው… በአስቸኳይ የሚያደርገውን qአድርጎ መገላገል ፈለገ..በዛ ላይ እዛ ሆቴል ትቷት የመጣው ቆንጆ ባይኑ ውልብ እያለችበት ተቸግሯል.... ‹‹አሁን ምላጩን ልስብ ነው ፍቅረኛ ወይም ሌላ ለምትወደው ሰው እንዲደርስልህ የምትፈልገው የመጨረሻ ሰዓት ኑዛዜ ካለህ እድሉን እንሰጥሀለን….መልዕክትህንም እንደምናደርስልህ በተከበረው ሞያችን ስም ቃል እንገባልሀለን››
‹‹ምንም የለኝም››
‹‹እጮኛ የለህም?››ተገርሞ ጠየቀው
‹‹አይ ኑዛዜ ነው የሌለኝ..ነገ ስለማገኛት ማለት የምፈልገውን ነገር ቀጥታ ለራሷ እነግራታለው››
‹‹አልገባህም እንዴ!!! የነገዋን ብርሀን እኮ አታያትም እያልኩህ ነው..ነው ወይስ እጮኛህንም እንላክልህ..?››
‹‹ግድ የለም በህይወት እኔም እሷም ብዙ እንኖራለን››
ወንድአፋራሽ የኩማንደሩን በራስ የመተማመን ጉዳይ ግራ አጋባው…አበሳጨውም፡፡ልብን በጥይት በስቷት ደም ከሰውነቱ ቡልቅ ..ቡልቅ እያለ ሲወጣ..ቤቱን ሲያጥለቀልቅ ለማየት ጓጓ…ውሳኔ ላይ ደረሰ ፡፡ ሽጉጡን አስተካክሎ ምላጩን ከመሳቡ በፊት ግን ከኃላ ጭንቅላቱ ላይ የሆነ ባዕድ ነገር ዳበሰው..ግራ ተጋብቶ በመጠኑ ዞር ሲል የፖሊስ ደንብ ልብስ ለብሶ ፊቱን በጭንብል የከለለ አንድ ግዙፍ ሰው ሽጉጥ ደቅኖበታል ‹‹ሽጉጡህን ወደመሬት ጣል››የሚል ትዕዛዝ ተከተለው
መጀመሪያውኑ በኩማንደሩ የንቀት እና በራስ መተማመን ሁኔታ እየራደ የነበረው ወንድአፍራሽ አሁን ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆረጦ ሽጉጥ የያዘው እጁ ወደታች ተዝለለፈለፈበት….ሽጉጡ ከእጁ ሾለከ እና ወደመሬት ወደቀ….፡፡በዝግታ ሁኔታዎችን ሲከታተል የነበረው ኩማንደር ከቆመበት ተንቀሳቀሰ እና ወንድ አፍራሽ የጣለውን ሽጉጥ አንስቶ ውስጡ ያለትን ጥይቶች አወጣና ቀፎውን ወደ ጠረጵዛው ወረወረው…ፖሊሱ ሽጉጡን እንደደቀነ ወደኃላው አፈገፈገ እና በራፉ ጋር ያለውን ግድግዳ ተደግፎ ሽጉጡን ግን እንደደቀነ በተጠንቀቅ ቆመ..ኩማደር ወደ መኝታ ቤቱ ሄደና አንድ ያልተከፈተ ሙሉ ጐርደን ጅን ውስኪ ከሶስት ብርጭቆ ጋር ይዞ መጥቶ ከፈተው..ከዛ መቅዳት ጀመረ
‹‹.እንዴ እስከአሁን ቆማችሆል እንዴ .. ?አሁን እኮ የተከበራችሁ እንግዶቼ ናችሁ ቁጭ በሉ…››
‹‹እሺ እናመሰግናለን›› ብሎ ኤልያስ ቀድሞ ተቀመጠ…ወንድአፍራሽ ግራ በመጋባት እና ምርጫ በማጣት ተከትሎት ተቀመጠ..የቀዳውን ውስኪ ለሁለቱም አቀበላቸው እና የራሱን ድርሻ ይዞ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ
‹‹እሺ ወንድአፍራሽ አሁን ዘና ብላችሁ ተጫወቱ››አለው ኩማንደር
ወንድ አፍራሽ ስሙን ከኩማንደሩ አፍ ሲሰማ መብክረኩ ጨመረበት‹‹..ስሜን ደግሞ እንዴት አወቀው..?ወይኔ በቃ አልቆልኛል››ሲል በውስጡ አሰላሰለ
ወንዳፍራሽ ኩማደር መሀሪን በትኩረት አየውና ‹‹በጣም የምትደነቅ ሰው ነህ!!! ››ሲል አስተያቱን ሰጠው
‹‹እንዴት?››ጠየቀው መሀሪ …ኤልያስ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ መድረኩን ለእነሱ ትቶ ውስኪውን በእፎይታ ይጐነጫል
‹‹አደገኛ ነሀ›› መለሰለት ወንድአፍራሽ
‹‹ግን ካንተ አልበልጥም..››
‹‹የበላይነቱንማ እንደምጐናፀፍ ገና ስትመጣ ነው የነገርኩህ..ልትሰማኝ አልፈቀድክም እንጂ››
‹‹አዎ መስማት ነበረብኝ›› በቁጭት ተናገረ..ዞር ብሎ ከጐኑ የተቀመጠውን ኤልያስን ሲመለከት ግብዣ እንደተጠራ ሰው በፍጹም መረጋጋት እና በፀጥተ መጠጡን ይመጣል
ወንድአፍራሽ ኤልያስን ‹‹የት ነው ያለኸው?›› ወደጆሮው ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ ጠየቀው
‹‹አንድ ሽጉጥ በደቀነ ፖሊስ ታግቼ በኩማንደሩ ቤት ቁጭ ብዬ ውስኪ እየጠጣው››መለሰለት
‹‹እና ይሄ አያስደነግጥህም?››
‹‹ምኑ?››
‹‹በፖሊስ እጅ መውደቅህ ነዋ?››
ኤልያስ በግድየለሽነት መለሰለት‹‹ብደነግጥስ እራሴን ከመጉዳት ውጭ ምን አተርፋለው…መጀመሪያውኑ ይሄን ስራ እንድንሰራ ስታማክረኝና እኔም ስስማማ..50 ፐርሰንት እንደሚሳካልን 50 ፐርሰንት ደግሞ እንዲህ አይነት ጉዳይ እንደሚያጋጥመን አስቤበት ነው
👍21
የተስማማውት..በዚህች አለም ላይ ሁሌ ስኬታማ እና አሸናፊ መሆን እንደማይቻል ከልምድ ተምሬያለው››
በዚህ ቅጽበት በራፉ ተንኳኳ… በራፍ አካባቢ ያለው ፖሊስ በቀኝ እጁ ሽጉጡን እነወንድአፍራሽ ላይ እንደደቀነ በግራ እጁ በራፉን ከፈተው… ሰማያዊ የለሊት ቢጃማ የለበሰ ጐልማሳ ሰው..አንገቱን አቀርቅሮ ኩምሽሽ እንዳለ ዘልቆ ወደውስጥ ገባ..ሰውዬው ወርቅአለማው ነው..ከሞት መንደር አምልጦ የመጣ ይመስላል..ፊቱ ግርጥት ብሎ አመድ የተነሰነሰበት ይመስላል..ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች አይን ሁሉ እሱ ላይ ተተከሉ..ወንድአፍራሽ አይኑን ማመን አልቻለም..በዚህ ቤት ትርኢት እየተሰራ ያለ መሰለው
ግባ ቁጭ በል››ከእነወንዳፍራሽ ጐን ወንበር ሰጠው..ያለ ምንም ንግግር ኩስስ ብሎ ተቀመጠ
‹‹አትተዋወቁም እንዴ?››ወንድአፍራሽን ጠየቀው
‹‹አረ በደንብ ..ምን እዚህ እንዳገናኘን ነው እንጂ እንቆቅልሽ የሆነብኝ››
‹‹ያው ለሁለተኛ ጊዜ አንድ ስራ ከመስራታችሁ በፊት ከማን ጋ እንደምትሰሩ እና ለማን እደምትሰሩም ጭምር ጥንቃቄ እንድታደርጉ ትምህርት እዲሆናችሁ ነው..አሁን ከእናንተ ያለኝን ነገር ጨርሼያለው…ከፈለጋችሁ መቆየት እንሄዳለን የምትሉም ከሆነ ነጻ ነችሁ››
ወንድአፍራሽ ባለማመን እና በጉጉት ጠየቀው ‹‹ነጻ ናችሁ ስትል?››
‹‹በቃ ወደቤታችሁ መሄድ ትችላላችሁ››አረጋገጠላቸው ኩማደሩ
እናመሰግናለን እግዜር ይስጥልን..ተፈናጥሮ ከመቀመጫው ተነሳ..የጀመረውን መጠጥ እንኳን እስኪጨርስ መታገስ አልቻለም..ይሄን የጭንቅ ቤት ለቆ መብረር አለበት..አዎ ተኝታ እሱን ወደምትጠብቀው ቆንጆ ጋር በሮ መድረስ አለበት….
‹‹ተነስ እንሂድ እንጂ››ኤልያስን እንዲነሳ ጠየቀው
‹‹እኔ መጠጡ ተመችቶኛል..መቆየት እፈልጋለው›› አልተስማማም ኤልያስ
የዚህ ልጅ ፀባይ ምንም ሊገባው አልቻለም.‹‹የራስህ ጉዳይ›› ብሎ ጥሎት እቤቱን ለቆ ወጣ እግሩ የጊቢውን አጥር አልፎ እስኪርቅ ድረስ አላመነም ነበር …ሀሳባቸውን ቀይረው ተመለስ የሚሉት እየመሰለው
ኩማንደር ወደ ቀለምወርቅ ሀሳቡን ሰበሰበ እና‹‹እሺ አቶ ወርቅአለማው…አሁንስ?››
‹‹አሁን ምን?››
‹‹ወደ ድርድራችን እንሂድ ወይስ እንዴት ነው?››
‹‹ምን ምርጫ አለኝ ..ተሸንፌያለው እጅህ ላይ ወድቄያለው..ነገ ጥዋት የጠየቅከኝን ብር በእጅህ አስረክብሀለው››
‹‹ጥሩ የብልህ ሰው ውሳኔ ነው የወሰንከው..ብሩ ግን ወደ 8 ሚሊዬን ብር አድጓል››
‹‹8 ሚሊዬን!!! ››በድንጋጤ ከመቀመጫው ተነሳ››
‹‹ምንም ማድረግ አልችልም ..በራስህ እጅ ያመጣኸው ጣጣ ነው.›
‹‹አረ በፈጠረህ በቃ ተሸነፍኩ እኮ ..የጠየቅከውን 5 ሚሊዬን ብር ልክፈልህ››
በፍፁም አይሆንም… ነገ እስከ ስድስት ሰዓት 8 ሚሊዬን ብር ታስረክበኛለህ ወይም 7 ሰዓት ሲሆን የሚስትህ መቃብር ይቆፈርልሀል››በል ፖሊስ እቤቱ ድረስ መልሰህ ሸኘው››ብሎ ትዕዛዝ አስተላለፈ እና ወደ መጠጡ ተመለሰ…

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2