አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ልሂድ አልሂድ እያልሁ እስተዛሬ ታመነታ ቆየሁ። ታመሪካን መጣ ሲባል አመሪካን እራሷን ይዞ መጣ የተባለ ይመስል ሁሉም ከያለበት እንኳን ደና መጣ ታይሆን እንኳን ደና መጣህልን ሊለው እየሄደ የድርሻውን ቲቦጭቅ።
ያክስቴ ልዥም አይደል እንኳን እኔ በደም ዝምድና ያለይ በስም የሚያውቀው የጎረቤት ልዥ ሁሉ ይሄድ የለ እንዴ!
የኔስ ድርሻ ተሚሻግት ሄጄ ብወስደው ምናለ አልሁና ለሳምንት የጠጅ ወጪዬን እንኳን የሚሸፍን ብር ቢሰጠይ ብዬ ሄድሁልህ ።
ሰላም ብዬው እንደተቀመጥሁ ቤተ ዘመዳ
ዘመዶቹ " አይ ዝናቡ ደና ነህ ግን እንደው በስንት ግዜ ዛሬ ተገናኘን !
ጠፋህ እኮ አንተው! እየመጣህ መጠየቁን ተተውከው ስንት ግዜ ሆነህ" ቲሉይ
እንደው ትለመጥፋቴ ያን ያህል የሚነዘንዙይ መጥፋቴ አሳስቧቸእ የናፍቆታቸውን ታይሆን እኛን ልትጠይቅ ታይሆን ዛሬ ልዣችን ተአሜሪካን መጣ ቲባል ነው የመጣህ እያሉ በነገር የሚሸነጉጡይ መስሎ ትለተሰማይ ውስጤን ጎረበጠይ።
ቢሆንም ሁለት ወዶ አይሆንም እና በአሽሙር የሚዘልፈይን ሰምቼ እንዳልሰማሁ ሆኜ ተቀመጥሁ።
ተቤተ ዘመዱ ጋር ታወጋ በወሬ መሀል ወደይህ የመጣው ታገሩ ተወንዙ የበቀለይውን ኮረዳ አግብቶ ሊወስድ መሆኑን ትሰማ ግር አለይ።
አጠገቤ ወዳለው ታናሽ ወንድሙ አንገቴን አዘመምሁና ስማ እንጂዢአንተው ተዛሬ ስንት አመት በፊት ወንድምህ እዛ አማሪካን ሚሽት አግብቶ መውለዱን ነግረኸይም አልነበር እንዴት ነው ነገሩ? ትለው።
ውይ ዝናቡ አልሰማህም እንዴ አየህ እሄን አለመስማትህ እራሱ ምን ያህል ግዜ እንደተጠፋፋን ነው እሚያሳየው በማለት በነገር ወጋ አርጎ ታለፈይ ቡሀሏ•••
" እሷን እማ ፈታት እኮ! አለይ ።
ምነው ምነው ተወለዱ ቡሀላ ምን አጋጠማቸው ጃል ? ትለው!
ይህቺ ጉዷ እማያልቅ አሜሪካን ፎርጅድ ሚሽት ድራለት ነዋ ቲለኝ ግር አለኝ
ፎርጅድ ፎርጅድ ደግሞ ምን ማለት ነው እሱ ? ትለው ሳቀብይ •••• •••ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍33👎2🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ+ነበረ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ትንፋሽ ወሰድኩና ከመተኛቴ በፊት  ከአያቴ ጋር ለማውራት አፌን ከፈትኩ…አያቴ እንዳልተኙ በመብራቱ አለመጥፋት እና በዕቃ መንኳኳት ማወቅ ችያለሁ፡፡

‹‹አያቴ ጉዴን እየሰሙ ነው አይደል?››
መልስ የለም

‹‹አያቴ ይሰሙኛል?››
መልስ የለም

‹‹እንዴ..ያን የተለመደ ዝምታቸውን ጀመሩ ማለት ነው..?አሁን በዚህ ከእሳቸው ጋር ማውራት በፈለኩ ቀን ዝም ይላሉ..››ብዬ ተሰፋ በመቁረጥ ልተኛ ልብሴን ማውለቅ ስጀምር በጆሮዬ ደምፅ ሰማሁ፣፣

‹ምንድነው… አያቴ ሙዚቃ…?››ወደግድግዳው ተጠጋሁና ጆሮዬን ቀስሬ አዳመጥኩ….ውይ እለተ ምፅአት ደርሶል መሰለኝ…ከአያቴ ቤት የሲሊንዲዮን ዘፈን እየተሰማ ነው…፡፡

‹‹አያቴ እኔ አላምንም…ሰሞኑን በጣም እያስደመሙኝ ነው..ከቤት ለመውጣት መወሰኖት ሳያንስ ጭራሽ የፈረንጅ ሙዚቃ….በአንዴ ግን እንዲህ አይነት ለውጥ አይከብድም.?

አሁንም ፀጥታ ነው….

‹‹አያቴ ምንም የማያናግሩኝ ከሆነ በፊት ለፊት በራፍ ዞሬ መምጣቴ ነው..››

‹‹በፊት ለፊት በራፍ… ተው ይቅርብህ..አታድርገው››

‹‹ምን ?››የባሰ አለ ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም

‹‹ሰምተሀል››
አዎ በደንብ ሰምቼያለሁ… አያቴ ቤት ሴት….አረ አይደረግም…እያናገረችኝ ያለችው ሴት ነች..ወጣት ሴት፡፡

‹‹አያቴ የሉም እንዴ?››
‹‹አያትህ የለም››ለስላሳ ለጋ የሴት ድምፅ መልስ ሰጠኝ፡፡
‹‹ይቅርታ ማን ልበል….?››ግራ በመጋባት ተሞልቼ ጠየቅኩ፡፡

‹በዚህ ውድቅት ለሊት ከአዲስ ሰው ጋር መተዋወቅ አይክብድም..?ይቅርታ ጥዋት እንተዋወቃለን… ባይሆን አሁን የአያትህን መልዕክት ተቀበለኝ..››

ከአያቴ ጋር እቃ ወደምንቀባበልበት ስንጥቅ አመራሁ...ለግላጋ ጠይም የእጅ እጣት ብጣሽ ወረቀት አቀበለኝ.. .ተቀበልኳት እና ወደአልጋው ተመለስኩ… ገለጥኩና ማንበብ ጀመርኩ፡፡

ልጄ ሳልነግርህ ይህን በማድረጌ ይቅርታ..ለአንድ ወር ወደገዳም ሄጄያለሁ…ትንሽ በፅሞና ከእግዚያብሄር ጋር ማውራት አምሮኛል…ልክ የዛሬ ወር ተመልሼ እመጣለሁ...እስከዛ የምወዳት የልጅ ልጄ ማራናታ ካንተ ጋር  እንድትቆይልኝ እፈልጋለሁ፡፡ያው ከሰሎሞን ሚስት ማለት ከእንጀራ እናቷ  ጋር አምርራ ስለማትስማማ እነሱ ጋር መቀመጥ አትችልም…እኔ ወደገዳም መሄዱን ቀድሜ የያዝኩት ቀጠሮ ነው…  ከእግዚያሄር ጋር የያዝኩትን ቀጠሮ ማስተጓጎል አልችልኩም…እሷ ደግሞ ድንገት መጣችብኝ….ግን ያው አንተ ልጄን ከእራሴ በላይ ስለማምንህ ልክ እንደእኔ አረገህ  ከእኔም በላይ እንደምትጠብቃትና እንደምትንከበከባት ቅንጣት ጥርጣሬ አይገባኝም…ቀንም ስራም ሆነ ሌላ ቦታ ስትሄድ ይዘሀት ሂድ…ማታም ጥለሀት ውጭ እንዳታድር..ነግሬሀለው አንተ ወሽካታ..ደግሞ ለእሷም እንዳታስቸግርህ ነግሬያታለሁ...አደራ አንተ ቀልማዳ እናንተ ሁለታችሁ በአለም ላይ እጅግ የምወዳችሁ የልጅ ልጆቼ ናችሁና ተመልሼ እስክመጣ በመደጋገፉ ጊዜችሁን በጥሩ ሁኔታ አሳልፉ.፡፡

ያንተው አያት ሙሉአለም ነኝ፡፡

‹‹እህት ይቅርታ ማራናታ ይሄ ምንድነው..?አያቴ ምንድነው የሰሩት?››

‹‹ያው አያትህ የሰራው እንዳነበብከው ነው›

‹‹እያሾፍሽ ነው እንዴ?››
‹አንተ እንዴት ነው የምታናግረኝ እንግዳህ እኮ ነኝ…ከደበረህ ነገ ጥዋት ተነስቼ ወደ ሀገሬ እበራለሁ..››

‹‹አረ በፈጣሪ ..ነገሩ ዱብ እዳ ሆኖብኝ እንጂ እንደዛ ማለቴ አይደለም...አሁን እራት በልተሻል..?››

‹‹አዎ በልቼያለሁ››
‹‹ሌላ የምትፈልጊው ነገር አለ….?››

‹‹አዎ አንድ ጠርሙስ ቢራ ባገኝ ደስ ይለኝ ነበር..››

‹‹እሺ አሁን አመጣልሻለሁ.››.ከአልጋዬ ተነሳሁና ጫማዬን ማድረግ ጀመርኩ

‹‹ምነው አለህ እንዴ?››ጠየቀችኘ
‹‹አይ የለኝም ግን አታስቢ አሁን ገዝቼ መጠለሁ. ምንድነው ሚመችሽ ማለት ጊርጊስ፤ በደሌ፤ሀረር ..››
‹‹አራት ሰዓት  እኮ አልፏል..የእውነት አሁን በዚህ ሰዓት ሄደህ ልትገዛልኝ ነው?›

‹‹አራት ሰዓት አይደለም ስድስት ሰዓትስ ቢሆን ምን ችግር አለው…የአያቴ አደራ እኮ  ነሽ…››

‹‹በል ስቀልድ ነው..አሁን አልፈልግም ነገ ትጋብዘኛለህ››

‹‹እውነተሽን ነው…?››
‹‹.አዎ አሁን ስለደከመኝ እንቅልፌ መጥቷል …ቻው ደህና እደር..››

‹‹ደህና እደሪ …ለሊት በማንኛውም ሰዓት የምትፈልጊው ምንም ነገር ቢኖር ንገሪኝ..››

‹‹ለሊት ምንም ነገር ብፈልግ?››ሳቅ ባፈነው ድምፅ

‹‹አዎ ምንም ነገር ብትፈልጊ..››

‹‹እሺ ነግርሀለሁ.. .አሁን ደህና እደር››

‹‹ደህና እደሪ›› ብዬ ሳደርግ የነበረውን ጫማ መልሼ አወለቅኩና ወደ አልጋዬ  ወጣሁ...ከልጅቷ ጋር በግድግዳ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ ሆነን የተነጋገርናቸውን ነገሮች መልሼ ሳስብ...ልጅቷ ልክ እንደ አያቴ ተንኮለኛ ቢጤ ነች መሰለኝ ስል አሰብኩና ፈገግ አልኩ…

ስለእዚህች ልጅ አያቴ ለብዙ ቀን አውርተውኛል..በየ15 ቀኑም ደብደቤ እየጻፉ እየሰጡኝ ለረጂም ጊዜ ፖሰታ ቤት ወስጄ የማስገባላቸው አኔ ስለሆንኩ ስለእሷ በመጠኑ አውቃለሁ..…ለምሳሌ የድሬደዋ ልጅ መሆኗን..ከእናቷ ጋር እንደምትኖርና… ጋሽ ሰለሞን የአሁኗን ሚስቱን ከማግባቱ በፊት እናትዬውን አግብቶ እሷን ከወለደ በኃላ እንደተፋቱ ከዛ እናትዬው ልጆን ይዛ ቤተሰቦቾ ጋር ድሬደዋ እንደገባች አውቃለሁ…አያቴም ከቤት አልወጣም ብለው እራሳቸውን ኳራንቲን ከማስገባቸው በፊት ቢያንስ በስድስት ወር አንዴ እየሄዱ እንደሚጠይቋት እሷም አልፎ አልፎ እየመጣች ትጠይቃቸው እንደነበረ መረጃው አለኝ ….ከልጃቸው ከጋሽ ሰለሞን በላይ ከእሷ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸውም አውቃለሁ....ሌላው በ1987 ዓ.ምህረት እንደተወለደች ነግረውኛል…ያ ማለት ይህቺ የሚቀጥለው ክፍል ውስጥ ያለች ወጣት አሁን 25 ዓመቷ ነው፡ በትምህርቷ በአካውንቲንግ ዲግሪ አላት…የእናቷ ቤተሰቦች ሀብታም ነጋዴዎች ስለሆኑ የራሷ ቡቲክ ከፍተውላት እየሰራች እንደሆነም አውቃለሁ...በቃ ስለእሷ የማውቀው ይሄንን ያህል ብቻ ነው ፡፡በተረፈ ቀጭን ትሁን ወፍራም..ቀይ ትሁን ጥቁር..ረጀም ትሁን አጭር ….ትሁት ትሁን መሰሪ ምንም አላውቅም….ምንም ፡፡ ግን ምንም ትሁን ምንም ለአንድ ወር የእኔ ኃላፊት ነች.. ፡፡ ያንን ኃላፊነት ደግሞ ያለምንም ማቅማማት በፍጽም ትዕግስት እና ብቃት እወጣለሁ...ምክንያቱም ያዘዙኝ አያቴ ናቸው..አሁን ልተኛ….ነገ ምን አልባት ረጅም ቀን ሊሆን ይችላል፡፡

ይቀጥላል
👍5944🔥4😁3👎1
ሚስቴ እና አባቷ!? 😡
ክፍል ~~~~ዘጠኝ
ይህቺ ጉዷ እማያልቅ አሜሪካን ፎርጅድ ሚሽት ድራለት ነዋ ቲለኝ ግር አለኝ
ፎርጅድ ፎርጅድ ደግሞ ምን ማለት ነው እሱ ? ትለው ሳቀብይ••••
ምን ያስቅሀል አንተው አለማወቅ ሀጥያት አይደለ! ባእድ ቋንቋ ቀላቅለህ ትታበቃ እኔ ላይ መሳቅ ምን ይሉታል በል ይልቅ እምታወጋይ ተሆነ ነገሩን እንዲገባይ በራሴ አፍ አውጋይ!'።
አልሁት ባሳሳቁ በሽቄ።ተዛ ቡሀላ ነገሩን እንዲህ ብሎ አጫወተይ•••
ዘመድ አዝማዷን ታይተዋወቅ እዛው አሜሪካን ተወልዳ ያደገች ጥቁር አሜሪካዊት ሴት ያገባል !
ዛድያ ተተጋቡ ቡሀላ እነሱ ዘንድ በመጣው ወንድሟ እና በሷ መሀል ያለውን የመልክ ልዩነት ቲያይ ለየቅል ብቻ ታይሆን ጭራስ ታንድ ማህጠን የወጡም አይመስሉ ።
ወንዱሟን ቲያው ዝንጀሮ ቆሞ እምሄድ እይ ሰው ትለመሆኑ የሚያጠራጥር ሆኖ ሳለ እሷ ልቅም ያለይ ቆንጆ ነይ።
ታድያ ሁለቱ አጠገብ ላጠገብ ቁጭ ብለው ባያቸው ቁጥር እንዲሁ ቲያስገርመው !።
መገረም ብቻ አይደለም ቲያስደምመው !።
መደመምም ብቻ አይደለም አንዳንዴ እንደውም ቲያስደነግጠው ይቆይልሀል።
ማንን እንደሚጠይቅ ማንን እንደሚያማክር ግራ እንደተጋባ።
በዚህ መሀል አርግዛ ትወልዳለይ። ዛድያ ህጣኑ አደግ ቲል ወንድሟን መስሎ እርፍ።
ታክስቴ ልዥም ተሚሽቱም ምንም ያልወሰደ ጓጉንቸር ሆኖ ቁጭ።
የልዡ እና የወንድሟ መልክ መመሳሰል ውስጥ ውስጡን እየከነከነውም ቢሆን
ፈጣሪ የሰጠውን ልዥ በጠጋ ተቀብሎ ማሳደጉን ቀጠለ።
ያክስቴ ልጅ ለወንድሙ እንደነገረው ተሆነ•••
በመሀል ወንድማ የሚጠቀምበትን "ላብ ቶብ " ለብቶም"
የሚሉት "ኮምፒተሩን " ባጋጣሚ ክፍት ሆኖ አግኝቶት ኖራል ውስጥ ገብቶ ሲበረብር ተአመታት በፊት ሚሽቱ ተወንድማም፣ ተቤተሰቧም ፣ ብቻዋንም የተነሳያቸውን ትክክለኛውን የቀድሞ መልኳን የየዙ ፎቶዋን ያያል ! ክው አለ።
ያኔ በተፈጥሮ ተፈጣሪ የታደለይውን መልክ ዘመን አመጣሽ በሆነ "ቴክኖሎጂ" "የብላስቲካ ሴርጀሪ" ነው እሚባል ያለይ መሰል ብቻ በሱ ቴክኖሎጂ ገፅታዋን ሙሉ በሙሉ እንደቀየረይ ይደርስበታል።
ዝናቡ የፈረንጅ አፍ እየቀላቀሉበት ለሱ ያልገባውን ነገር ለኔ ሊያወጋይ ሲደክም ግራ እንደገባይ አይን አይኑን እያየሁ ታደምጠው አሁንም ቀጠለና•••
"የቀድሞ ፎቶዎቿን አንድ ባንድ እያሳየ ሲጠይቃት አይን ፍጥጥ !ጥርስ ግጥጥ !ዋሽታ እማታመልጠው ሀቅ ነውና አልካደይውም አመነይ። በጥቅሉ ያገባው በፈጣሪ የተሰራችውን ታይሆን በሰው የታደሰችውን ነው ስልህ!
ሲለይ ይበልጡን ተምያታብይ ። ዝናቡ መዝነብ ተዥመረ መች ያቆማል አሁንም ቀጠለ•••
"ተዛ ቡሀላ የኛ ሰው ሀበሻ ያው እንደእልኸኛነቱ ሁሉ ተረታ /ታሸነፈ/ ቡሀላ ይቅር ባይነቱም የበዛ አይደል !
እውነቱን ታወቀ ቡሀላ ሁሉን ትቶ ይቅር ቢላትም በሷ ብሶ በጀ አላለይም። እውነቱ ተወጣ ቡሀላ ከሱ ጋር መቀጠሉ ጎረበጣት መሰል መፋታቱን መርጣ ተፋቱ። አንዳርጌ ሙት እሄን ስስማ ጉድ ጉድ ጉድ እያልሁ ጭንቅላቴን ይዤ ልጮህ ምን ቀረኝ!" ብሎ ያክስቱን ልጅ ታሪክ ቋጨ።
እንኳን የተዋቡ አባት እንዲህ ናላዬን አዙረውት በደናውስ ግዜ ቢሆን እንዲህ ለራሱ ያልገባውን ወሬ ለኔ አውርቶልዪ ቤት በኩል ይገባኛል።
ምናለ ሰው ለራሱ ያልገባውን ለሌላው ባያወራ
ምን እንዳናደደይ እንጃ ብቻ ብልጭ አለብይ•••
የነገሩ ባለቤት ያልጮኸውን አንተ ምን ቤት ነህ ጭንቅላትህን ይዘህ እምትጮኸው ጎበዝ??" ልለው አሰብሁና መልሼ ታጤነው ስንቱ በማያገባው እየጬኸም አይደል ብዬ•••
" እሄስ ያስጮሀል ዝንቡ ጮኽህ ቢወጣልህ ጥሩ ነበር ሙት!" አልኹት።
"ሙት እውነትህን ነው !ሳልጠጣ ሄጄ እንዢ ሞቅ ቢለኝማ መጮኼ አይቀርም ነበር አሁን ልጩህ እንዴ ? አለዪ
ቆይ እኔ ልውጣና ትጮሀለህ ብዬው ሂሳቤን ከፍዬ ተጠጅ ቤቱ ወጣሁ።
ግቢ እንደደረስሁ መጠጡ በሰጠይ ድፍረት ትልቁቤት በር ላይ ቆምሁና ጮክ ብዬ ተዋቡ የኔ ብዬ ተጣራሁ።
በሩን በስሱ ከፈተይና •••
"በእጇ አባዬ ተኝታል አትጩህ!"
የሚል ምልክት አሳየችይ።
መስማታቸው አይቀርም ብዬ•••
ቅድም የሞተውን ሰው ስም በደንብ ሳላጣራ ስላስደነገጥሁሽ ይቅር በይይ ውብ አለም የስም ስተት ነው " ለጋሼ ዘርጋውም ንገሪልይ አልኋት።
በሩ ላይ እንደቆመይ አንገቷን አዙራ አባቷ ወደተኙበት ገልመጥ አረገይና።
በል አሁን ግባና ተኛ በቃ ደና እደር ። አለችይ።
በጀ እያልሁ በሬን ከፍቼ እስትገባ ቆማ እያየችይ እንደሆነ ያወቅሁት የኔኑ ክፍል በር ልዘጋ ስዞር ነበር ። ቆሜ ታያት እጇን አውለብልባ ተሰናበተችኝና ገብታ በሩን ጠረቀመችው።
በጥዋት ቁርስ ይዛልይ እንደገባይ።
ተዋቡ ላንድ ለሁለት ሳምንት ዘመድ ዘንድ ደርሼ እመለሳለሁ አንድ ሁለት ቅያሪ ልብስ ይዘሽልይ ነይ አልኋት።
ታፏ ቃል ታታወጣ ትክ ብላ እያየችኝ እንባዋ ሁለቱ አይኖቿ ላይ ግጥም ቲል ፊቷን መልሳ ተክፍሌ ወጣይ።
ትንሽ ቀየት ብሎ በሬ ቲንኳኳ ተዋቡ ልብሱን ይዝልይ መጥታ ነው ብዬ ማነው ታልል ብድግ ብዬ ብከፍተው አባቷ ናቸው።
ደንገጥ ብዬ ደና አደርህ ጋሼ ዘርጋው ምነው በጥዋት በሰላም ነው ብለው "ፈልጌህ ነው አንዳርጌ ለባብስና እላይ ቤት ና እጠብቅሀለው " ብሎኝ ተመለሰ።
ለምን ፈለጉይ ብዬ ፈራ ተባ እያልሁ ወደ ትልቁ ቤት ገባሁና ቁጭ አልሁ።
አንዴ አጠገባቸው ወደ ተቀመጠይው ተዋቡ አንዴ ወደኔ እየተመለከቱ •••
"ልጆቼ•••" ብለው መልሰው ዝም አሉ።
ገና መናገር ታይጀምሩ ፊታቸው ተቀያየረ።
ሁለመናቸውን የሀዘን ድባብ ጣለበት።
ልዦቼ እናቴ ገና የአስራ ሁለት አመት ልዥ እያለሁ ነው በወባ በሽታ የሞተችብይ።
ታድያ የናቴን ያህል የምወዳት አንድ ለናቷ የነበረይ አንድ ታላቅ ብቻ ነይ የነበረችይ።
ተዋቡ ትባላለይ ሲሉ እኔና የኔዋ ተዋቡ ግራ በመጋባት ተያየን።
ያንተን ሚሽት እቺ ልዤን ተዋቡ ያልኋት መልኳ ተሷ ጋር ስለሚመሳሰል ነው። እይ ጨቅላ ሆና እናቷ ያወጣይላት ሽም ሌላ ነበር።
አባታችን ብዙም ለልጅዥፊቱ የማይፈታ ሰው ነው። ስለዚህ እንደናትም ፣እንደህትም ፣እንዳባትም የማያት ይችኑ እህቴን ነበር። ተራሴ በላይ እወዳት ነበር።
ማግባት አይቀርምና ባል ታገባይ ቡሀላ አባቴ ብዙም ስለማይቀርበይ ብቸኝነት ያጠቃይ ዥመር።
አብዛኛውን ግዜ እህቴ ዘንድ እየሄድኩ ብቀመጥም ባሏ አመለ ክፉ ነበርና ቲያሰቃያት እያየሁ ስለማያስችለዪ እሷን ሲያስለቅስብይ ሰድቤው ወደ ቤቴ እመለሳለሁ።
ግን አያስችለኝም አሁንም ስናፍቀኝ እሄዳለሁ አሁንም ተጣልቼው እመለሳለሁ።
በይህ ሁኔታ አመታት ቢቆዩም ልዥ አልወለዱም
ችግሩ ተሱ ይሁን ከሷ አላውቅም ብቻ ልዥ አልነበራቸውም።
ጠባቸው እየተደጋገመና እየከረረ ቲመጣ እህቴ ተባሏ በተጣላይ ቁጥር ወደኛ ዘንድ መምጣት ዥመረይ።
ስትመጣ አባቴ ልዥን ቀርቦ ? ምን ከፍቶሽ ነው? ሳይል ፣ ምንድን ነው በመሀከላችሁ ያለው ችግር?"
ብሎ የሚፈታ ችግር ከሆነ መፍትሄ እንዲያበጁለት መፍትሄ ከለለውና የሷ ምርጫ መለያየት ተሆነ እንዲለያዩ ፍላጎቷን ታይጠይቅ ፣ ከፍቷት በመጣች ቁጥር ሴት ልዥ ከቧላ ጋር በተጣላይ ቁጥር ሮጧ ወደቤተሰቦቿ የምትመጣ ከሆነ ደግ አደለም እያለ አሳቆ ሲመልሳት አለቅሳለሁ።
እኔ የባሏን ጠባይ አውቀዋለሁና ተጣልታ መጥታ ሂጂ ብሎ በሚያባርራት አባቴ እጅጉን እናደድ ነበር።
በመጨረሻም እሷው ጋር ሄጄ በሌላኛው ክፍል ውስጥ በተኛሁበት የገዛ ባሏ እህቴን በተኛችበት ገሏት ጠፋ።
ተንቅልፌ እንደተነሳሀ በተኛችበት ታርዳ የሞተይውን የገዛ እህቴን ሬሳ አየሁት።
👍53🔥2👏1
ብለው ክፉኛ ቲያለቅሱ እኔና ተዋቡም በተቀመጥንበት መነፋረቅ ዠመርን።
ለቅሶአቸውን ጋብ አርገው•••
እናም ልጆቼ ተዛን ግዜ ጀምሮ የማውቃቸውም የማላውቃቸውም ባልና ሚስቶይ ተጣሉ ሲባል ውስጤ ይታመማል!። እረበሻለሁ!። እፈራለሁ!።
ክፋ ያለው እንኳን የምድሩን ሰው የላይኛችንም ከፋፍሎ ከመውደድ እንደማይመለስ አውቃለሁ።
እኔ ግን ክፉ ሆኜ አይደለም! አንተን ጠልቼ ልጄን ብወዳት አልጠቅማትም እሄን ጠንቅቄ አውቃለሁ።
ልጆቼ ተውቡ አንዳርጌ•••
ሰሞኑን እዚህ ቤት ውስጥ እናንተን የማያስደስት ውሳኔ የወሰንሁት እሄ ፍርሀቴ በፈጠረብይ መጥፎ ስሜት መሆኑን ተረድታችሁ ይቅር በሉይ።
መሀላችሁ በመግባት ብገፋችሁም ክፉ ካፋችሁ ሳይወጣ እክብራችሁ ትዛዜን ተቀብላኋልና እናንተም በልጆቻችሁ የተከበራችሁ ሁኑ ፣ ተከበሩ ! ፈጣሪ ያክብራችሁ!።
ልጆቼ እዚህ በቆየሁባቸው ቀኖች በብዙ መንገድ በመሀላችሁ ያለውን ጥልቅ ፍቅር መረዳት ችያለሁ።
ያ ክፉ ቀን የፈጠረብኝ ህመም እድሜዬን በሙሉ ሲያባንነኝ ነው የኖረው።
ዛሬም ድረስ ከውስጤ አልጠፋም ሴት ልጆቼ ተባላቸው ተጣሉ ሲባል ሳላውቀው ይቀይረኛል።እፈራለሁ። የህቴ ታሪክ ልጆቼ ላይ እንዳይደገም ስለምሰጋ እይ ክፉ ሆኜ አይደለም ።
ወድጄ አይደለም! ልጆቼ ወድጄ አደለም እያሉ ሲያለቅሱ ምድር ሰማዩ ተደበላለቀብይ።
ተዋቡም ታባቷ ስር ቁጭ ብላ እያለቀሰይ ነው ።
ተፈናጥሬ እግራቸው ስር ተደፋሁ።
"አይገባም የኔ ልጅ !" ብለው ቀና አርገው አቀፉይ ።
ሰውን ክፉ ነው ተማለቴ በፊት ለምን ክፉ ሆነ ብዬ ማሰብ እንዳለብይ የተስተማርሁት ዛሬ ነው ።
እስታሁን ለሆነው ሁሉ ይቅር በሉይ አባቴ የአካሌን ክፋይ፣ ያንድ ልዤን እናት ተዋቡዬን ውብ አለሜን ታሁን ቡሀላ እንኳን የከፋ ነገር ልፈጥምባት በክፉ አይን እንኳን እንደማላያት ቃል አገባሎታለሁ ።
እንደባል ብቻ ታይሆን እንዳባትም ሆኜ አኖራታለሁ ! እኔስ ያለሷ ማን አለኝ !!"
አልኋቸው ።
ግንባሬን ስመው አጥብቀው አቀፉይ!
ተዋቡዬም ተነስታ እኔና አባቷን እቅፍ አረገችን።
/ ተፃፈ/ written /
# በጥላሁን ተስፋዬ
# by Tilahun Tesfaye
•••••••••••••••ተፈፀመ•••••••••••••• ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍4413👏4
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ጥዋት የበረፍ መንኳኳት ነው ከእንቅልፌ ያባነነኘ…በርግጌ ተነሳሁና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ…አሁንም በራፉ ይንኳኳል ግን የውጭ በራፍ ሳይሆን ከአያቴ ጋር የምንወሰነበት ተከፍቶ ያማያውቀው የውስጡ በራፍ ነው የሚንኳኳው…‹‹ውይ ልጅቷን ረስቼያት… በፈጣሪ ምን አይነት ዝፍዝፍ ሰው ነኝ? .እስከ አሁን እንግዳ እያለብኝ እንዲህ ነገር አለሙን ችላ ብዬ እተኛለሁ…?ይሄኔ እኮ እርቧት ይሆናል….?››

‹‹ማራናታ… ደህና አደርሽ?.››

‹‹አዎ ደህና አድሬያለሁ….ልግባ…ልብስህን ለብሰሀል?፡፡››ግራ አጋቢ ጥያቄ ጠየቀቺኝ፡፡

‹‹ውይ እሱ በራፍ የታሸገ ነው …ቆይ በፊት ለፊት ዞሬ መጣሁ..››

‹‹አይ እሽጉን ትናንት አያቴ አስነስቶት ነው የሄደው››…ከሚል ድምፅ ጋር የበር መንሳጠጥ ተሰማና ወለል ብሎ ተከፈተ..ውይ የተሰማኝ ስሜት…. በቅዱሳን መላዕክቱ የገነት በር ሲከፈት ፊት ለፊት በአይኖቼ እያየሁ  ያለሁ   ነው የመሰለኝ...እና ከበሩ መከፈትም በላይ በተከፈተው በራፍ አንገቷን አስቀድማ በማስገግ ብቅ ብላ ወደእኔ ግዛት የገባቸው ልጅ…  በፈጣሪ ሰይጣን አይደል እንዴ የምትመስለው፣ሰይጣን ክብሩን ከመገፈፉ በፊት…ለነገሩ ክብሩን ከተገፈፈም በኃላም ውበቱን አልተነጠቀም…

‹‹አንቺ ይገርማል..አያቴን አይደል እንዴ የምትመስይው?››ሳላስበው አድናቆት ከአንደበቴ አፈትልኮ ወጣ
‹‹ሽማግሌ ፊት ነው ያለሽ እያልከኝ ነው?››

‹‹ይቅርታ …ማለቴ በጣም ቆንጆ ነሽ ለማለት ፈልጌ ነው….››አዎ እውነቴን ነው …ልጅቷ ልክ አያቴን ነው የምትመስለው…ልቅም ያለች የጥቁር   ልጥልጥ  ውብ ነች…፡፡ልክ እንዳየኋት ልቤ ቢጫ ወባ እንደነደፈው ሰው ነው በደቂቃ ውስጥ ፍርፍር ስትል የተሰማኝ፡፡
‹‹ለማንኛወም ቁርስ መብላት ከፈለክ ና ቀርቧል….››ብላኝ በራፉን ክፍት ጥላ ተመልሳ ወደውስጥ ገባች፡፡እንግዳ ሲያፍር ባለቤት ይጋብዛል አሉ….ሲሆን ሲሆን ለሊት ተነስቶ ቁርስ በመስራት እሷን መቀስቀስ የነበረብኝ እኔ ነበርኩ..ዳሩ አጅሪቷ በየት አሲይዛ …በሁሉ ነገር ጥድፍ ጥድፍ ትላለች፡፡በፈጣሪ በዚህ አይነት አጀማመር ይህቺን አንድ ወር እንዴት ነው ተቋቁሜ የምዘልቀው…? አያቴ ምን ነካቸው..?ይሄንንማ አውቀው ሆነ ብለው እኔን ለመፈተን ያደረጉት ነገር ነው፡፡ወይ እዳዬ ለዘመናት ከዳከርኩበት እና ፍዳዬን ካየሁበት የፍቅር ታሪክ ገና ትናንትና መደምደማሚያ አበጅቼለት ተገላገልኩ ስል….

‹‹እዬቤ...››ጥሪው ከተዘፈዘፍኩበት ሀሳብ መዞ  አነቃኝ

‹‹አቤት››

‹‹ቁርሱ ቀዘቀዘ እኮ….በዛ ላይ እርቦኛል››

ተንደርድሬ ተነሳሁና ፊቴን ተለቃልቄ ልብሴንም ሳልቀይር በለበስኩት ቢጃማ ተንንርድሬ ሚቀጥለው ክፍል ገባሁ…..እንግዲህ ይታያችሁ እዚህ ቤት መኖር ከጀምርኩ ሶስተኛ አመቴ ውስጥ ብሆንም አሁን ያለሁበትን ክፍል ስረግጥና የውስጥ ገፅታውን ሳይ ዛሬ የመጀመሪያ ቀኔ ነው፡ክፍሉ በስርአት ቦታቸውን ይዘው በተቀመጡ የቤት እቃዎች የተሞላ ነው፡፡ ቢያንስ ሶስት ቦታ በመፅሀፎች የተሞሉ መደርደሪያዎች ይታያሉ…አልጋው በስርኣት ተነጥፏል፡፡  አልጋውን ተጠግቶ ያለው መካከለኛ መጠን ያለው ጠረጴዛ በምግብ ተሞልቷል…

‹‹ምን ይገትርሀል አልጋ ጠርዝ ላይ ቁጭ በል ››አለችኝ

የእሷን  ግብዣ ችላ አልኩና ግድግዳ ተደግፎ ያተቀመጠ አንድ ደረቅ ወንበር በማንሳት ወደምግብ ጠረጴዛው አስጠግቼ በመቀመጥ አንዴ የቤቱን ዙሪያ መልሼ ደግሞ እሷን ከስር አስከላይ መቃኘት ጀመርኩ… አቀራርባ ስትጨርስ ፊት ለፊቴ አልጋ ጠርዝ ላይ ቁጭ በማለት እሷም ለመብላት ዝግጁ ሆና እጇን ወደምግቡ እየሰደደች‹‹..በል ብላ››.አለችኝ..

‹‹ይሄን ሁሉ ምን ጊዜ ሰራሺው?››የገረመኝን ጥያቄ ጠየቅኳት.፡፡

‹‹እቤትህ ሰዓት የለም እንዴ..?ሶስት ሰዓት ሊሆን እኮ ነው››አመሏ ከመልኳ ተቃራኒ ነው..እስከአሁን እንዳየሆት ለየትኛውም ጥያቄ ቀና መልስ መስጠት አይሆንላትም…

‹‹ይቅርታ .እንቅልፍ ጣለኝ››

‹‹አያቴ ጠንካራ ሰራተኛ ነው እያለ ሲፎክርብህ የነበረው እንዲህ እየተኛህ ነው እንዴ?››

‹‹አጋጣሚ ሆኖ ነው..›› የጠቀለልኩትን ምግብ እየጎረስኩ መለስኩላት፡

‹‹እሺ ቢሾፍቱ ዛሬ ትወስደኛለህ ?››አዲስ ርዕስ ከፈተች

‹‹ለምን…?መሄድ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹አይ የስራህ ቦታ እዛ አይደለ? ስራ ከሄድክ አብሬህ ለመሄድ ብዬ ነው››
‹‹እ ….እንደዛ ነው….ዛሬ ሳይሆን ነገ ነው የምሄደው ….ነገ አብረን እንሄዳለን….ዛሬ የሆነ ጓደኛዬን ከአገር ውጭ ስለምትሄድ እሷን እንሸኛለን››

‹‹እ… .ጄኔራሏን?››

‹‹ምን….?በምን አወቅሽ…?››.ደንግጬ

‹‹ይሄውልህ ስለአንተ የማላውቀው እንዲህ ቆንጆ መሆንህን ብቻ ነበር… አሁን ደግሞ እሱኑም አወቅኩ››ብለኝ እርፍ
‹‹እንዴት…?አሀ ይሄን ሁሉ የነገሩሽ አያቴ ናቸው?››

‹‹አዎ  አያትህ…በነገራችን ላይ አያቴ በየደብዳቤው ስለአንተ ሲዘበዝብልኝ በጣም እበሳጭበት ነበር››

‹‹ለምን? ቀንተሸ?››

‹‹አዎ ብቀና ይፈረድብኛል..?እኔ በአያቴ ቀልድ አላቅም...እና ብቸኛ የልጅ ልጁ ሆኜ መቀጠል ነበር ምፈልገው..››

‹‹እና አሁንስ?››ስል ጠየቅኳት በመገረም፡፡

‹‹አሁንማ አንደኛ አባቴ ከዛች የተረገመች ሚስቱ ሌላ ልጅ ስለወለደ ብቸኛ የልጅ ልጁ መሆኔ ማክተሙን አምኜ ተቀበልኩ ….ሁለተኛ እኔም ሳላስበው ታሪክህን ቀስ በቀስ ሲያስጠናኝ የእውነትም አያቴ አያትህ ይመስለኝ ጀመር…››

ተበሳጨሁ… ልጎርስ አፌ ላይ ያደረስኩትን ምግብ መልሼ ትሪው ላይ በትኜ ተነሳሁና‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው..?››አፈጠጥኩባት

‹‹አቦ ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ማለት ምን ማለት ነው?››እሷስ መች የዋዛ ሆነችና በተቀመጠችበት መልሳ አፈጠጠችብኝ፡፡

‹‹አያቴ ስል ለማሾፍ ወይም ለፉገራ ይመስልሻል…?የእውነት አንቺ ከእኔ በላይ እራስሽን ባለመብት አድርገሽ መጎረርሽ ነው..?››ወረድኩባት
‹‹ባለመብቱንማ በተግባር አየነው እኮ…. እኔ እኮ አይደለሁም የአንድ ሚሊዬን ብር ቼክ የተፃፈልኝ…አሁን እንብር እንብር አትበል ቁጭ በልና ቁርስህን ጨርስ .ደግሞ አያቴን የነጠቅከኝ ሳያንስ ስድብ ትመርቅልኛለህ….አረ አይነፋም…››

በንግግሯ ተሸነፍኩና ተመልሼ ቁጭ አልኩ…ገና በመጀመሪያው ቀን ይሄን ያህል ከተጮጮህን ዋል አደር ስንል..ወይኔ ጉዴ…ጨነቀኝ፡፡

አንድ ክፍል ቀረው
👍17915😁11🥰4👎3🔥2
አትሮኖስ pinned «#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ጥዋት የበረፍ መንኳኳት ነው ከእንቅልፌ ያባነነኘ…በርግጌ ተነሳሁና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ…አሁንም በራፉ ይንኳኳል ግን የውጭ በራፍ ሳይሆን ከአያቴ ጋር የምንወሰነበት ተከፍቶ ያማያውቀው የውስጡ በራፍ ነው የሚንኳኳው…‹‹ውይ ልጅቷን ረስቼያት… በፈጣሪ ምን አይነት ዝፍዝፍ ሰው ነኝ? .እስከ አሁን እንግዳ እያለብኝ…»
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////

ከቁርስ ቡኃላ ልብስ ቀያየርንና ተያይዘን ወጣን….የተወሰኑ ጉዳዬች ስለነበረኝ እዚህም እዛም እሷን አንጠልጥዬ ስራራጥ ሰባት ሰዓት ሆነ…. ቁርስ ሰዓት ላይ ያቆምነውን ወሬ ሆቴል ገብተን ምግብ አዘን ምሳችንን እየበላን ቀጠልነው፡፡ የሚገርመው ደግሞ ወሬውን ድንገት የጀመረችው እሷ ነች….
‹‹አሜሪካዊቷ እስከመጨረሻው ቀይ አሻረችህ አይደል?››
‹‹ማ…?ለእኔ….?አልገባኝም››
‹‹ባክህ ማታ በስልክ ስታወሩ ሰምቼያለሁ››
‹‹አንቺ የሰው ሚስጥር ጆሮን ግድግዳ ላይ ለጥፎ ማዳመጥ ነውር አይደል እንዴ?››
‹‹እናንተ የመሀል ሀገር ሰዎች ደግሞ ኮተታ ኮተቱንም ሚስጥር ታደርጉታላችሁ..ግን የእውነት ሁለታችሁም አንጀቴን ነው የበላችሁት››
‹‹እንዴት?››
‹‹በቃ ፎንቃ ክፍኛ ነው የጠለፋችሁ….ታድላችሁ?››
‹‹እንዴ በዚህ ፍቅር ምክንያት ምን ያህል መከራ እንደተቀበልን ብታውቂ እንደዚህ አፍሽን ሞልተሸ ታድላችሁ አትይም ነበር….››

‹‹እንደእኔ በምቾትና በእንክብካቤ ዝም ብሎ አይነት ኑሮ ከመኖር በፎንቃ ተጠልፎ ስቅይትይት ማለት አይሻልም…?ምናለ በእሷ ቦታ እኔ በሆንኩ››
‹‹ጭረሽ….አንቺ ልጄ ቀልደኛ ነሽ ..››
‹‹እውነቴን እኮ ነው..››
ስልኬ ጠራ…የምጎርሰውን ጋብ አደረኩና አነሳሁት…. ጄኔራሏ ነች
‹‹እሺ ዜና..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ..››
‹‹ዝግጅትስ?››
‹‹ያው ሁሉን ነገር አጠናቅቄ አንተን መምጣት እየጠበቅኩ ነው››
‹‹የት ነሽ?››
‹‹እቤት ነኝ…››
‹‹ያው እንግዳ አለብኝ…እና ማታ ስመጣ ከእንግዳ ጋር ብመጠ ቅር ይልሻል?፡፡
‹‹አረ ፍፅም….ስራ ከሌላችሁ ለምን አሁን አትመጡም..››
‹‹አሁን?››
‹‹ምነው ስራ አለብህ እንዴ?››
‹‹አይ የለብኝም….ግን እንግዳ ያልኩሽ..››
‹‹አውቃለሁ ስለአያትህ የልጅ ልጅ ነው አይደለ የምታወራኝ…በቃ እጠብቃችኋለው… ይዘሀት ና..የእኔም እንግዳ እኮ ነች..ደግሞም ቆንጆ ነች አሉ…እንዴት ነው እውነት ነው እንዴ?›
‹‹አረ ተይኝ..ለማንኛውም እንመጣለን ቸው››ስልኩ ተዘጋ
ጭው አለብኝ..በዙሪያዬ ምን እየተካሄደ ነው…?እኔ መምጣቷን ሳላውቅ ማታ እቤት ስገባ ስላየኋት ጥቁር እንግደ ጄኔራሏ ቀድማ ታውቃለች…፡፡እንዴት..?እኔ ከነጋ ጀምሮ አሁን እንዴት ነው የማደርገው? እንግዳዋን እንዴት እሷ ጋር ይዤት ሄዳለሁ…?ጥያትስ አንዴት ሄዳው…?ምን ብዬስ መጥቼ እቤትሽ አድሬ እሸኝሻለሁ ካልኩ በኃላ እቀራለሁ …››እያልኩ ስብሰለሰል ቆይቼ ይሄው እሷ ሁለታችንንም በእንግድነት እሷ ቤት ሄደን እንደምናድርና አብረን እንደምንሸኛት ትናንትናውኑ ታውቅ ነበር
‹‹ምነው ፊትህን አጨማደድከው?››
‹‹አይ ነገሮች ግራ አጋብተውኝ ነው…ቅድም የነገርኩሽ ጎደኛዬ ጋር አብረን አንሄዳለን…››
‹‹ጄኔራሏ ጋ››
‹‹አዎ ጄኔራሏ ጋ››
‹‹ታፈቅራታለህ አይደል.?››
‹‹ማለት…?››
‹‹አትደንግጥ..ታድለሀል..ፍቅር በፍቅር የሆንክ ሰው ነህ…እኔንስ አንድ ቀን ምታፈቅረኝ ይመስልሀል?››
‹‹ምን አልሽ?››
‹‹አረ አትደንግጥ…ለፈገግታ ነው…ምነው ይሄን ያህል ፍቅር አንገሽግሾሀል እንዴ..?››
ወይ ጉድ ይህቺ ልጅ በቅርቡ እጄ ላይ ምትፈነዳ አደገኛ ፈንጅ ነች‹…አቶ እዬብ ፈተናህ ገና አላለቀም….ወይ አያቴ ከችግሮችህ ሁሉ ቀስ በቀስ ተላቀቅ ብለው መክረውኝ እንድወጣም አግዘውኝ ከብዙ ጥረት በኃላ አብዛኛው ተሳክቶልኝ ነፃ ልወጣ የድል ሪባኑን ልበጥስ መቀሱን እያስተካከለልኩ እያለሁ እራሳቸው ወደተመሳሳይ ችግር የሚጎተት ሌላ ፈተና ያስታቅፉኛል..?ምሳ ጨርሰን ሂሳብ ከፍለን በራይድ ወደ ጄኔራሏ ቤት እየሄድን ሳለ
‹‹እዬቤ በርጫ ገዝተን ብንሄድ ጄኔራሎ ይደብራታል?››ስትል ቀለል አድርጋ ጠየቀቺኝ፡፡
‹‹ትቅሚያለሽ እንዴ?››
‹‹ምነው ?መቃም እንዲህ ያስደነግጣል እንዴ?››
‹‹አይ…ስላልመሰለኝ ነው….ችግር የለውም ስንቃረብ እንገዛለን.››
ወዲያው ስልኬ ጠራ….ወይ ልጄ ደወለች አልኩና አነሳሁት
‹‹የእኔ ማር… የእኔ ጣፋጭ እንዴት ነሽ?››
‹አለሁ አባዬ….እሁድ እንደምንመጣ ታውቀለህ አይደል?››
‹‹አዎ አውቃለሁ…እናትሽ ነግራኛለች.እናም በናፍቆት እየጠበቅኩሽ ነው››
‹‹እሺ እሱን ልንግርህ ነው የደወልኩት…››
‹‹ስለደወልሽ ደስ ብሎኛል››
‹‹የት ነህ አባዬ መኪና ውስጥ ነህ እንዴ..ድምፅ ይሰማኛል››
‹‹አዎ የእኔ ልጅ ….ታክሲ ውስጥ ነኝ….አያቴን ታውቂያቸዋለሽ አይደል?
‹‹አዎ አውቃቸዋለህ… ከእሷቸው ጋር ነህ?››
‹‹አይ ከእሳቸው ጋር ሳይሆን ከልጃቸው ጋር የሆነ ቦታ እየሄድን ነው…ማራናታ ትባላለች ፡፡ስትመጪ ከእሷ ጋር አስተዋውቅሻለሁ››
‹‹እሺ አባዬ ሰላም በልልኝ››
‹‹ቸው እሺ ልጄ›ሥልኩ ተዘጋ
ጊዜ ሳታባክን ጥዝጠዛዋን ቀጠለች‹‹ከልጅህ እያስተዋወቅከኝ ነው እንዴ?››
‹‹አዎ እሁድ ቤተሰቦቼ ሁሉ ይመጣሉ ….ልጄም ትመጣለኝ …አብራን ስታየን ማን ነች ብላ ስትጠይቀኝ በቀላሉ አስረዳታለሁ ማለት ነው፡፡››
‹‹ለእሷ ብቻ ነው..ወይስ ለቤተሰብህ ሁሉ ነው የምታስተዋቀውቀኝ ?››
‹‹አሁን ይህ ምን የሚሉት ጥያቄ ነው፡፡አዎ…የአያቴ የልጅ ልጅ ነሽ….እቤተሰቤ ነሽ ማለት ነው፡ስለዚህ ከሁሉም ጋር አስተዋውሻለሁ››
‹‹እንደዛ ስላልክ ደስ ብሎኛል…..አክስትህ ግን የአያቴ ልጅ ነች ብለህ ብታስተዋውቀኝ ብዙም ደስ አይላትም››
‹‹ለምን…?አክስቴ ምን እንደምትፈልግ በምን ተውቂያለሽ….?አክስቴ እኮ ከአያቴ ጋ ተዋውቀዋል…አያቴ ማለት ለእኔ ምን እንደሆነ እና ምን እዳደረገልኝ በዝርዝር ነግሬታለሁ፤ በዛም የተነሳ በጣም የምታከብረው ሰው ነው……እንደውም አንቺ የእሱ የልጅ ልጅ በመሆንሽ በደስታ ነው የምትተዋወቅሽ››
‹‹አውቃለሁ ግን ፍቅረኛህ ብሆንና ይህቺ ፍቅረኛዬ ነች ብለህ ብታስተዋውቀኝ እንዴት ፍፅማዊ ደስታ እንደምትደሰት ይታየኛል››
‹‹እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ?አክስቴን እኮ በደንብ ምታውቂያት ነው ያስመሰለሺው››
‹‹እኔን ከስጋት ትገላግለኛለች ብላ ተስፋ ታደርግ ነበር .እሷ እኮ አሁንም እነዚህ ልጆች መልሰው ይሳሳቱ ይሆን ብላ እንቅልፍ ተኝታ አታድርም…ታዲያ አንተ እኔን የመሰለች ፍቅረኛ አግኝተህ ወስደህ ብታስተዋውቃት… ታየኝ፡፡እንዲሁ ስለምታሳዝነኝ እንደዛ ብለህ ብታስተዋውቀኝ አይከፋኝም….ምን ችግር አለው? አያታችን ከሄደበት እስኪመለስ የእቃቃ ፍቅረኛ ፍቅረኛ እንጫወትና ከእዛ ተጣልተን ተለያየን ብለን እናውጃለን…እስከዛ ሴትዬህም ወደአሜሪካዋ ተመልሳ ስለምትሄድ ችግር አይኖረውም..
‹‹ውይ ምን አይነት ጉድ ነሽ.?ሳትቅሚ እንደዚህ የለፈለፍሽ ከምርቃና ቡኃላ እንዴት ልትሆኚ ነው?››
‹‹አይዞህ ሀሳብ አይግባህ…ከመረቅንኩ ስሬ ኒዩክልር ብታፈነዳ እንኳን ከአንደበቴ ቃል አይወጣም….››
‹‹እንደዛ ከሆነማ ጫቱን አሁኑን ልግዛልሽ ‹‹.ሹፌር ምቹ ቦታ ስታገኝ ታቋምልኝ….?እቃ ገዛለሁ››

ተፈፀመ
👍149🤔52👎10👏6😱52😢2
#ትቀርያለሽ_ብየ

ግድየለሽምና  ፥ ከልብ ላፈቀረሽ
ሶስቴ ተቀጣጥረን፥ አራት ጊዜ ቀረሽ::

ዛሬም እንደ ወትሮው፥ትቀርያለሽ ብየ
እድል የላከውን፥ እጣ የሚመስል፤ እጦት ተቀብየ፥
አበባ ሳልቀጥፍ
አልጋ ሳላነጥፍ
ሙታንታየን ሳልጥፍ
በትራስጌየ ላይ ፎቶሽን ሳለጥፍ ፥

ትቀርያለሽ ብየ፥

በመስታውቴ ፊት
ከልብ አስቀይሜ
አንድ እፍኝ ነጭ ሽንኩርት
እንደ ተልባ ቅሜ
አየሩን መርዤ፥ ህዋሴን አክሜ፤

ትቀርያለሽ ብየ፥
ጥፍሬን ሳልከረክም
በመቀስ ሳልንደው፥ የጉያየን ሸክም
ትቀርያለሽ ብየ
ጀንበርን ቀድሜ፤ ቤቴ ተከትቼ
ግቤን ያለ ረዳት፥ በጊዜ መትቼ
የከሸፈ ትውልድ አንሶላ ላይ ትቼ
ልተኛ ስዘጋጅ፥ እፎይ ብየ አርፌ
ከወደ በራፌ
“ ውዴ! ደርሻለሁ፥ የሚል ድምጽሽ መጣ”
ከመግባትሽ በፊት፥ እኔ በየት ልውጣ?

🔘ቤኩምሳ🔘
😁146👍87👏18😱16🥰154
​​🖤🖤 #ኑ_ለቅሶ_እንድረስ 🖤🖤
           

ያሳደግችኝ ደብር ተቀመጠች አሉኝ ለቅሶ
ውለታዋ ተዘንግቶ ክብር ማዕረጓ ተድሶ
በትዕቢት ተረማመደ ቅጥር ግቢዋን ጥሶ
ማር ይዘንባል ማር (×3) ነበር ዜማ ቅኝቷ
ስጋጃው በደም ራሰ ጥይት ዘነበ ከቤቷ

ሰንደቅ አላማ ነበር የዘለ ዕለት ውበቷ
ኑ እንድረሳት ለቅሶ ማቅ ለብሷል ጉልላቷ
እንዳትካስ ለብድሯ ወርቀዘቦ ተንቆጥቁጣ
በምን ቃል ይገለፃል በምን ቃል ይገለፃል
በውን ቆሞ እንደማየት ባዳፋ ጫማ ተረግጣ

ቅጥሯን ለተዳፈረ ለናቃት ይስጠው መጥኔ
የአለምን ሀይል ተመክቶ የታበየ ለኩነኔ
አለም በቃኝ ብለው ምለው ያፀኗት በምናኔ
ኑ እንላቀስ ምዕመን ያልሰማ ይስማ መርዶ
ደብራችን አንብታለች መጋረጃዋ ተቀዶ
ደብረ ሀይል ቅዱስ ራጉኤል የልጅነቴ
በመልዐክ ሀይል ምልጃ የፀናችልኝ ህይወቴ
የአባ መሸ ኪላራይሶ  የገብረ ኪዳን ሰንበቴ
የአዝኖና መጠጊያ የነብስ ስጋ ቋቴ
የሀይማኖት መሰረቴ
አፍ መፍቻ ትምህርት ቤቴ
እስኪ ተጠየቁ እስኪ ልጠይቃችሁ
እስኪ ተጠየቁ

መስቀልና እስኬማ ካባ ደርባችሁ
በቀን በአደባባይ ነብስ የቀጠፋችሁ
እንደምን ይቀደሳል የምዕመን ደም ተራምዶ
እንዴትስ ይታረቃል መንፈስ በግፍ ላይ ወርዶ
በምድር የፈታችሁት በሰማይ እንዲፈታ
ግብራችሁን ስታችሁ በማስተስረይ ፈንታ
ባረካችሁን በወኔ ተሳለምን በቃታ

ፊደል ቀራጭ ስንዱዬ እኔን ልጅሽ ፊደል ጠፋኝ
ሀ ብለሽ ያስቆጠርሽው ሆ ብሎ ፊትሽ ደፋኝ
በፀአዳ ግምጃሽ ፈንታ ክልሽን ሳየው ከፋኝ
ህዝቤ በገዛ ሀገሩ ቢገፋ ቢያጎብጠው የኑሮ ቀንበር
የፀለየላት ኢትዮጵያ እንዳትፈርስበት ሀገር
ወዝ የራቀው ገፁን በውሀ እየወለወለ
ረሀብ ጥማቱን ችሎ በደጇ የተጠለለ
መስዋዕቱን ሊሰዋ በገናውን የደረደረ
ከጌታው ጋር ተቃጥሮ ተመስገን ሊለው ነበረ
ደረቱን ተቀረደደ በድኑ ተሽቀነጠረ
ይፅናናበት ማልቀሻችን ምናለን ከደብሩ ሌላ
እንፅናናበት ማልቀሻችን ምን አለ ከደብሩ ሌላ
ድርሳን አላቃጠ መንገድ አልዘጋ ኬላ
ጥበብ እየመገበች ኮትኩታው ነበር ከልላ
ለምጣዱ ሲባል ትለፍ ብለናል አይጧ
ሰስተንላት ነገር ፈርተን ይሄ ቀን እንዳይመጣ

ይልቅ ይልቅ ግፍህን ታጠብ በደልህን ተለቃለቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
የተማመንከው ቢደድር አስተምሮትህ ብረቅም
ከሺህ አመታት ዶሴ ከአባቶቻችን አይልቅም
ብንጠፋ ብናጠፋ ከደጀ ሰላሟ ብንርቅም
የተስፋ ርስታችን ናት ደብራችንን አንለቅም
እኔም አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ
ከአንዲት ቤተስኪያን ወድያ
አቻ ክብር አላውቅም ልጄም በካህን እንጂ በአቶ አይጠመቅም ይኸው ነው !!!

ኑ ለቅሶ እንድረስ.....
😢83👍6315👎2😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በተጨናነቀው የሚኒባስ ታክሲ ሰልፍ  መሀል ገብታ እየተጋፍች ነው ።ታክሲው ወዴት እንደሚሄድ አታውቅም፤ወደየት ቢሄድም  ደንታዋ አይደለም።ብቻ ትኩረቷ ግፊያው ላይ አይኖቾ ደግሞ ዙሪያ ገባውን  በሚተራመሱት ተሣፈሪዎች ኪስና በእጅ ባንጠለጠሉት ዕቃ ላይ ነው።ሰልፉ እየተሳበ…እየተሳበ  ተራቸው ደረሰና እየተጋፉ ወደ ውስጥ ሲገቡ አስቀድማ በአይኖቾ መዝና  ባመቻቸችው ኪስ ውስጥ እጇን ሰደደችና በብርሀን ፍጥነት እስማርት ስልኩን ሞጭልፋ በማውጣት ኪሷ ከተተች፤ከዛም እሱ ከተቀመጠበት ወንበር አንድ ረድፍ ዘላ ተቀመጠች ።

  ሁሉም ተሳፋሪዎች ገብተው መቀመጫ ከያዙ በኃላ  የመውጫው መንገድ ሲከፈትላት ሚኒባሷ ወደ መዳረሻዋ ከመንቀሳቀሷ በፊት ዕቃ እንደረሳ ሰው አስመስላ ለመውረድ ነው እቅዷ።ከዛ በፊት ግን ስልኩን ስዊች ኦፍማድረግ ስላሰበች እጇን ወደሰፊ ኪሷ ሰዳ እዛው ባለበት ለመዝጋት እየሞከረች ሳለ የመብረቅ አይነት የጥሪ ጩኸት አንቧረቀባት...ልክ የሚናደፍ  አደገኛ እባብ ኪሷ ውስጥ አድፍጦ እጇን ቀጨም አድርጎ እንደነከሳት ነገርመላ ሰውነቷን ነዘራት…እጇን ቶሎ ብላ ከኪሷ አወጣች...፡፡ደግሞ ጥሪው ያልተለመደ እና  አንቧራቂ አይነት  ነው።የምታደርገው ግራ ገብቷት ቀና ስትል ልጅ የገዛ ስልኩን ድምፅ ሰምቶ ኪሱን ሲፈትሽ ማግኘት ስላልቻለ ደንግጦ ከተቀመጠበት ተነስቶ የጥሪውን አቅጣጫ በመከተል ወደእሷ እየመጣ አየችው…. ልጁ አንዴ ኪሱን እየፈተሸ አንዴ ‹‹ስልኬን....ስልኬን ማን ጋር ነው..?እዚህ ጋ ስልኬን.."እያለ በመለፍለፍ ወደ እሷ ሲመጣ ከሚያንቧርቀው የጥሪ ድምፅ ጋር የተሳፍሪውን ቀልብ ሁሉ ተቆጣጠረ...::

የሁሉም አይን በሰራቂዋ እና  በተሰራቂው መካከል መሽከርከር ጀመረ... ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ ደመነፍሳዊ ውሳኔ እጇን ወደኪሷ ሰደደችና ስልኩን አውጥታ ልክ ተውሶ እንደሚመልስ ጨዋ ተበዳሪ ዘረጋችለት...እሱም በትህትናና በሚቅለሰለሱ ብርሀናማ ጥቁር አይኖቹ እየተለማመጠ በምስጋና ሊቀበላት እጅን ሲዘረጋ ከግራናከቀኝ ያሉ የማይመለከታቸው ተሳፋሪዎች"

‹‹..ሌባ..ሌባ...በላት..." ከሚል አስጠሊታ የተደራረበ ድምፅ ጋር አንድ በቦክስ አገጯን፣ሌለው  በጥፊ ፊቷን፣አያቷን የሚያህል የተንቋቋ ሽማግሌ ደግሞ በደረቀ እጅ ትከሻዋን….ብቻ ታክሲው ውስጥ የተሰፈሩት ሙሉ ተሳፋሪዎች ተረባረቡባት፡፡

"ኸረ ተዋት...በፈጠሪ ገደላችኋት"ብቸኛ አዛኝ ሆኖ ግማሽ ስንዘራው እላዪ ላይ እያረፈበት ሚከላከልላት እራሱየተዘረፈው ልጅ ብቻ ነበር....፡፡

"ተዋት ይላል እንዴ? እራስህም ሌባ ነህ"እሷን ትተው እሱ ላይ ወረዱበት፡፡

"እንዴ የሠው ልጅ አይደለችም እንዴ? ህግ ባለበት ሀገር ?" ለመከራከር ሞከረ…አገናዛቢ ሰው የለም እንጂ ልጁ ያነሳው ትክክለኛና ወሳኝ ጥያቄ ነው...እዚህ አገር አንድ ሌባ እንደው ቀን ጥሎት በተያዘ ቁጥር እንደማሪያም ጠላት መቀጥቀጥ እጣ ፋንታው ነው…ይሄ ወንጀል እንደሆነ እንኳን የሚያውቅ ሰው ጥቂት ነው፡፡እናም እሷም የገጠማት የተለመደው ነው…መንጋው በአንድነት ልጁ ላይ ወረዱበት…

"ምን የሠው ልጅ ነች ?ይህቺ ሌባ...ይሄኔ አብራችሁ እኛን ለመዝረፍ የተሰማራችሁ አጋሮች ናችሁ...አዎ...ማናውቅ መሠላችሁ …ታክቲካችሁ ነው።"

"ምን የሠው ልጅ ነች ?ይህቺ ሌባ..››ያለው ሰውዬ በጣም ተሳስቷል.. እንደውም መስረቋ እኮ ሰው ለመሆኗ ዋናው ማረጋገጫ ነወ…ስርቆት እኮ የሰው ልጅ ብቻ ያለው ስጦታ ነው፡፡መስረቅ እንዲኖር የግል የሚባል ሀብትና ንብረት መኖር አለበት…ይሄ የእኔ ነው ያም የእኔ ነው በሚል ቁስን በማከማቸት የተካነ ከሰው ልጅ ውጭ ማን አለ…?የግል ሀብትን ማከማቸት ካለ ደግሞ ሌላው ላይ የሚከሰት አጥረት ይኖራል..በእጥረት ተጠቂ ሆኖ ተጎድቼያለሁ የሚል ስሜት ያደረበት ደግሞ  ካከማቸው ላይ ቆንጥሮ መውሰድ የሚጠበቅ ነው…ከዛ ወሳጁ ዘራፊ ወይም ሌባ ይባላል..እንደዚህ እጅ ከፍንጅ ሲያዝ  ይወገዛል፤ይወገራል

"ውረድልን ...ውረድ ››በቅዳሴ ሰአት ቤተክርስቲያን እንደገባ ውሻ እየገፈታተሩ እና እየደቋቆሱ ሁለቱንም ከታክሲው አውጥተው ወረወሯቸውና ከሰልፉ መካከል ሌላ ሁለት ሰው በምትካቸው ጭነው ተክሲዋንአንቀሳቀሷት ።

ልጅ‹‹....ይቅርታ በእኔ ምክንያት ነው የተጎዳሽው...ለማይረባ ስልክ ብዬ አስደበደብኩሽ"እያለ.ከሰልፍ አካባቢ ደግፎ አርቆ ወሰዳት፤እሷ በእፍረት አንደበቷ ተቆልፎል..እሱ ያወራል…

"በፈጣሪ እየደማሸ እኮ ነው?"

እውነትም እንዳለው….ከአፍንጫዋ ደም ብልቅ ብልቅ እያለ ነው።ግን ከመጠነኛ ጥዝጣዜ በስተቀር ጉዳቷን ያህል እየተሰማት አይደለም፡፡

መላ እሱነቱን በቆረጣ በማየት እየገመገመችውና እተደመመችበት፡"አፍንጫዬ ድሮም ይደማል ..ችግር የለውም…አሁን ይተወኛል።" አለችው..፡፡

"ኸረ ግንባርሽ ተነርቶ አብጧል...ነይ በይ"ፍቃዷንም ሳይጠይቅ  እየጎተተ ይዟት ላዳ ውስጥ ገባ።ለምን እንደዚህ እንደሚያደርግ ለራሱም እየገባው አይደለም፡፡ግን ልቡ ላይ የሰረገ የሆነ ኃይል ይህቺን ልጅ የራስሽ ጉዳይ ብሎ ጥሏት ዞር እንዲል አልፈቀደለትም፡፡

"ባክህ በቅርብ ያለ ኪሊኒክ ውሰደን"ለባለ ላዳው ነገረው፡፡

ሹፌሩ"እሺ ..ውይ ምን ሆና ነው?"ላዳዋን እያንቀሳቀሰ ጠየቀ።

"የሚጥል በሽታ አለባት ፤ድንገት አጉል ቦታ ጣላትና ተጎዳች"ብሎ መለሰለት፡፡

እውነትም የሚጥል በሽታ …እፍረት ላይ የሚጥል..ቡጢ እና ጥፊ  ላይ የሚጥል.እስር ላይ የሚጥል አስቀያሚ በሽታ ..መልሱ አስገርሟት ዞር ብላ አየችው፡፡ወጣት ነው ..ሀያ ሰባት ሀያስምንት ቢሆነው ነው። ቆንጆ፤ ቅልስልስና፣ አይንአፍር ቢጤ ይመስላል።

"እግዜር አትርፏታል...ለሁለተኛው ተጠንቀቁላት"ባለላዳው፡፡

"ኸረ እንጠንቀቃለን ..የዛሬን እንኳን ተረፈችልን"
‹‹የሆነ ፊልም እየተቀረፅን ይሆን እንዴ?"ስትል በውስጧ አብሰለሰለች...እንዴ እየሆነ ያለው እኮ እንቆቅልሽ ነው የሆነባት።

መቼስ የላዳ ሹፌር ወሬ ላይ አይታሙም ..ጥያቄውን ቀጠለ"ፍቅረኛህ ነች ?"

ምክንያቱን ባታውቅም ለዚህኛው ጥያቄ የሚመልስለትን መልስ ለመስማት ሰውነቷ ሁሉ ጆሮ ሆነ"አይ ታናሽ እህቴ ነች"ብሎ መለሰለት። በመልሱ ተገረመች። አይናፋር ነው ብላ መገመቷን  ስህተት እንደሆነ ተረዳች…‹‹ይመስላል እንጂ አይደለም። እንደውም ጮሌና ምላሳም ነገር ነው።››አለቸ በውስጧ…

እውነቷን ነው አሁን ባለው ሁኔታ ይልቅስ በተቃራኒው እሷ ነች በእፍረት ምክንያት ፍፁም ጭምት ልጅ የሆነችው።ደግሞስ ከሰራችው ስራ አንፃር ማፈሯም ሆነ አንገት መድፋቷ የሚጠበቅ ሰውኛ ባህሪ ነው፡፡

የላዳ ሼፌሩ"እ ለዛ ነው ምትመሳሰሉት"ብሎ አረፈው፡

"እንመሳሰላለን እንዴ?"መልሶ ጠየቀው፡

"በጣም ነው የምትመሳሰሉት ...ሰው ነግሯችሁ አያውቅም እንዴ?"

"አረ ሁሌ ነው የሚነግሩን ..ሁለታችንም እናታችንን ስለምንመስል ነው።"

ይቀጥላል
👍20322😁19🔥3👎1🤔1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

ክሊኒክ ደረሱ.. ።ከባለላዳው የወሬ ዝባዝንኬ ስለተገላገለች ደስ አለት ..።ወረዱ.. 100 ብር ከፈለው። ወደ ውስጥ ገቡና ካርድ ቆርጠው በድንገተኛ ስም ተራ ሳይጠብቁ ወደህክምና መስጫው ክፍል ገቡ።የሚፈሰው ደም እንዲቆም ተደረገ ፤ያበጠውና የተጫጫረውም የሚደረገው ተደርጎ በፍሻ ተጠቅልሎ በፕላስተር ተለባበደላት.፡፡.አምስት ቀን የሚዋጥ ኪኒኒ አሸከሟት..፡፡ዝም ብላ ፈዛ እያየችው 850 ብር ከፈለ..።ጥዋት ከቤት ስትወጣ እንደቀልድ ኪሷ ውስጥ ሸጎጥ ያደረገችው ከ2ሺ ብር በላይ አላት...ግን ለመክፈልም ሆነ ለመግደርደር ምንም አይነት ሙከራ አላደረገችም….ለምን እንዳልተግደረደረች ደግሞ እሷም መልሱን አታውቅም ፡፡ለብር ቁጠባ ወይም በስስት ምክንያት እንዳልሆነ ግን እርግጠኛ ነች፡፡

እስከአሁን ባደረገው ነገር በውስጡ እርካታ ተሰምቷታል….አዎ አሁን ቢለያት ምንም የሚፀፅተው ነገር እንደሌለ ያውቃል...ግን ይህቺን ልጅ በተመለከተ የሚሰማው ሰሜት አሁንም የተለየ ነው…‹‹ይህቺ ልጅ ሌባ አይደለችም…››ሲል አሰበ..ግን ደግሞ ስትሰርቅ እጅ ከፍንጅ ተይዛለች ለዛውም የገዛ ስልኩን… ቢሆንም ልቡ እውነት ነው ብሎ ሊቀበልለት አልቻለም…ታዲያ እውነታው ከአይኖቹ ምስክርነት ያገኘው ሀቅ ነው ወይስ ልቡ ሹክ የሚለው ትንቢት?….ይሄንን ሳያረጋግጥ እንዴት ይለያታል..?ጨነቀው…፡፡ ‹‹አሁን ስልክሽን ስጪኝ ብላት ሌላ አላማ ያለኝ ነው የሚመስላት››ከውስጡ ጋር የጀመረውን ሙግት ሳያቋርጥ."አሁን እንሂድ..."አላት፡፡

"ከተቀመጠችበት ተነሳችና በዝምታ ተከተለችው” ..ጎን ለጎን እየሄዱ ነው።በሁለቱም ፊት ላይ ጭንቀት ይነበባል.እንዲህ እንደቀልድ በአጋጣሚ እንደተገናኙ በአጋጣሚ መለያየቱን ሁለቱም የፈለጉት አይመስልም፡፡

‹‹...እንዴት ነው የምንለያየው...? ደግመንስ እንገናኛለን? ›በእሷ እምሮ ውስጥ የሚጉላሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

‹‹ያወጣኸውን ብር እንድከፍልህ አድራሻህን ስጠኝ ››ልበለው እንዴ? በነዚህና መሠል ጥያቄዎች በውስጧ ስትብሰለሰል ስልኩ አንቧረቀ...ቅድም እዛ ታክሲ ውስጥ የሠማችው ምን አልባትም መቼም ልትረሳው የማትችለው አስቀያሚ ያለችውን ጥሪ ነው እየሰማች ያለችው..እሱ በዝምታ አንገቱን አቀርቅሯል፡፡

.."ምን አንገቱን ይደፍል ስልኩን አንስቶ ይሄንን ጥሪ በመስማቴ እያተቀሰቀሰብኝ ካለው የእፍረት ስሜት አይታደገኝም እንዴ?""በማለት በሆዷ እያጉረመረመች ሳለ በተመሳሳይ አቅጣጫ እየተጓዘች ያለች አንድ ወጣት.."እህት ስልክሽ እኮ እየጠራ ነው"አለቻት ወደ ጃኬት ኪሴ እየጠቆመች።

"ምን እያለች ነው?"በሚል ስሜት በርግጋ እጇን ወደኪሷ ከተተችና መዠርጣ ሳታወጣ የልጁ ስልክ ነው።እስከአሁን እሷ ጋር ምን ይሰራል?እንዴት አልመለስችለትም?...እሱስ እስከአሁን እንዴት ስልኬን መልሺ አላላትም...? በመሀከላቸው የሆነ የሚያደነዝዝ አይነት አዚም ተረጭቷል ማለት ነው፡፡ከዝምታዋ ሳትላቀቅ እጇ ላይ ያለውን የሚጠራ ስልክ ወደእሱ ዘረጋችለት... በትህትና ተቀበላትና ወደጆሮው ለጥፎ ሄሎ ከማለቱ በፊት ተዘጋበት።

ደዋዩን ማንነት ተመለከተና "ጓደኛዬ ነች በኃላ መልሼ ደውልላታለሁ..."ብሎ መልሶ ስልኩን ወደእሷ ዘረጋው፡፡

"ይሄ ልጅ ያመዋል እንዴ?"በውስጧ ነው ያማችው ፡፡

"ያንተ እኮ ነው..ምን ላድርገው?"

"እ ይቅርታ የእኔ ነው ለካ" ብሎ ኪሱ ከተተ፡፡ ሳቋ አመለጣት.... አብሯት ሳቀ...‹‹.ጥርሶቹ ያምራሉ። ›ስትል በውስጧ አሰበች፡፡
ከሆስፒታሉ ግቢ ወጥተው በአንድ አቅጣጫ እየተጓዙ ነው።ታክሲ ወደሚገኝበት እና ላዳዎች ወደሚቆሙበት ስፍራ።ሁለቱም በምን ሁኔታ ተለያይተው ወደየመዳረሻቸው እንደሚሄድ ግራ እንደገባቸው ነው፡

ምን አድርጋ እንዴት አይነት ዘዴ ፈጥራ ከእሱ ጋር ያላትን ቆይታ እንደምታራዝም እያሰበችበት ቢሆንም ምንም አይነት ዘዴ ወደምናቧ አልመጣላትም…እሱም እደዛ እያሰበ እንደሆነ ግን ተሰምቷታል..ወይንም እንዳዛ እንዲያስብ ፈልጋ ይሆናል ፡፡:

"ቤቴ ድረስ ሸኘኝ ልበለው እንዴ ?..ይሄ ደግሞ ምን አይነት ቅብጠት ነው?››ቢለኝስ፡፡

ድንገት የንዴት በሚመስል ቃና ቆጣና ኮስተር ብላ‹‹በቃ እንለያያ ..በጣም አመሰግናለሁ"አለችው..

ካቀረቀረበት ቀና አለና

"እንለያይ.. እሺ ደህና ሁኚ..." አላት፡፡

ክፈት አላት፡፡እሷ ያልገባት እሱም እንደዛ አይነት መልስ የመለሰላት አስቦበት ወይም እንደዛ ማለት ፈልጎ ሳይሆን ድንገት ከእሱ ፍቃድ ውጭ ከከንፈሩ አዳልጦት ነው፡፡ዘመናትን በሚመስል የተጎተተ ድምፅ"ደህና ሁን ...››አለችው፡

ስህተቱን ለማስተከከል ያደረገው በሚመስል ሁኔታ"ግን እኮ ላዳ ላሳፍርሽ ነበር..."አላት….አሁንም ድንገት አፉ ላይ የመጣለትን ቃል እንደወረወረ ያስታውቅበታል..ቢሆንም የምትፈልገውን ነገር ነው የተናረው..ነገር ግን ያው ሴት ነችና..እሷም እንደቢጤዎቾ መግደርደር አማረት..በመሀል ጣቷ ግንባሯን አሽት አሸት እያደረገች"አይ በታክሲ ሄዳለሁ..አንተ አትቸገር"አለችው፡፡

"ታክሲውንም ቢሆን ላሳፍርሻ ...ሰፈርሽ የት ነው?።››ሲል ጠየቃት፡፡

"ሳሪስ"

"በድንግል ማሪያም … እንዲህ ቆስለሽ ምንም ሳታርፊ ከመገናኛ ሳሪስ...?አይ እንዲማ አይሆንም..የእኔ ቤት እዚ ካሳንቺስ ነው..እንሂድና አንድ ሁለት ሰዓት አርፈሽና ተረጋግተሽ ትሄጂያለሽ።››አላት፡፡

እቤቱ ድረስ ሴት ሲጋብዝ ይሄ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኙ ነው፡፡እቤቱ ከአንድ ሴት በስተቀር ገብታበት አታውቅም…እነድትገባበትም ፍላጎት አድሮበት ፍፅም አያውቅም …ምክንያቱም ያቺ ሴት የዘላለሙ ነች…ልዋጭም ሆነ ቅያሪ የማያስፈልጋት ብቸኛ ምርጫው….ዛሬ ግን የሚሰራቸው ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሩ ውጭ ናቸው..እና ከውስጡ መታገል አልፈለገም..ሊሆን ያለው ነገር እንዲሆን መፍቀድ አለብኝ››አለና ከራሱ ጋር ተማክሮ ወሰነ፡፡ግን ሁኔታውን በትዝብት ለሚከታተል ሰው ሴትን አዳኝ ብሎ እንደሚፈርጀው እርግጠኛ ነው..አረ ልጅቷ እራሷ እንደዛ ማሰቧ አይቀርም››አለ በውስጡ፡፡

እሷም ያልተጠበቀ ግብዣውን ስትሰማ ዘለሽ ሂጂና ተጠምጠሚበት የሚል ስሜት ተፈታተናት ...ግን እንዴት ብላ..?የልቧን መሻት ከግንባሯ እያነበበ የሚያወራ ነው የመሰላት...እንደዛም ሆኖ ግን አንደበቷ እንደልቧ በቀላሉ እጅ የሚሰጥ አይነት አይደለም።

"አረ አይሆንም...ከዚህ በላይ ላስቸግርህ አልፈልግም...አንተም ወደምትሄድበት ብትሄድ ነው የሚሻለው፡"

"የምሄድበትማ ለስራ ነበረ …አሁን ሰዓት አልፎል.. ብሄድም መስራት አልችልም...እኔ ቀጥታ ወደቤት ነው የምሄደው ..ካልደበረሽ አብረሺኝ ብትሄጂና እንዳልኩሽ የታዘዘልሽን ኪኒንም ውጠሽ አረፍ ብለሽ ስትረጋጊ ወደ ቤትሽ ብትሄጂ ደስ ይለኛል።››አላት፡፡

ከአሁን በኃላ ብትግደረደር ሌለ እድል እንደማይሰጣት እርግጠኛ ሰልሆነች "አረ አይደብረኝም..እሺ እንሂድ"አለችው፡፡

እየተከታተለን ያለ ሠው ቢኖር ሁለቱም ፊት ላይ የደስታ ካፊያ እንደተርከፈባቸው የፊታቸው በድንገት ማብረቅረቅ በመመልከት በቀላሉ ይረዳ ነበር፡፡ላዳ አስቆሙና ይዟት ገባ...በስድስት ደቂቃ ውስጥ እቤቱ ደረሱ።

ይቀጥላል
👍14236🥰3😁2🔥1👏1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ክሊኒክ ደረሱ.. ።ከባለላዳው የወሬ ዝባዝንኬ ስለተገላገለች ደስ አለት ..።ወረዱ.. 100 ብር ከፈለው። ወደ ውስጥ ገቡና ካርድ ቆርጠው በድንገተኛ ስም ተራ ሳይጠብቁ ወደህክምና መስጫው ክፍል ገቡ።የሚፈሰው ደም እንዲቆም ተደረገ ፤ያበጠውና የተጫጫረውም የሚደረገው ተደርጎ በፍሻ ተጠቅልሎ በፕላስተር ተለባበደላት.፡፡.አምስት…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እየተከታተለን ያለ ሠው ቢኖር ሁለቱም ፊት ላይ የደስታ ካፊያ እንደተርከፈከፈባቸው የፊታቸው በድንገት ማብረቅረቅ በመመልከት   በቀላሉ ይረዳ ነበር፡፡ላዳ አስቆሙና ይዟት ገባ...በስድስት ደቂቃ ውስጥ እቤቱ ደረሱ።

ግቢ ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲያስገባት የቤቱ አካራይ በረንዳ ላይ ቆመው ነበር..

…ልትጠፋ ደርሳ ጭልጭል እያለች ባለች አይናቸው አንዴ እሷን እንዴ እሱን እያዩ…‹‹ቃል...ሰላም ነው..?ምነው በጊዜ?""አሉት

ለእሷ ከአሮጊቷ ንግግር ስሙ ማን ነው የሚለው ጥያቄዋን በከፊል ተመለሰላት‹‹ቃልአብ፤ቃል ኪዳን፤ቃል…››ከእንዚህ ውስጥ አንዱ ነው ››አለችና በአእምሮዋ ሰሌዳ በደማቁ ፃፈችው፡፡

"ሰላም ነው እማማ..፡፡እንግዳ ስላለብኝ ነው የተመለስኩት"በትህትና መለሰላቸው፡፡

ወደ እሷ  ዞረው… የተለጣጠፈ ፊቷን በጥርጣሬ እያዩ ሰላምታ ሰጧት…እሷም እየገመገሟት  እንደሆነ ስለገመተች  ምቾት አልተሰማትም፡፡አሮጊቷ ንግግራቸውን አራዘሙ "እ...እንግዳ አገኘህ...?ደህና ነሽ ልጄ ..የጊፍቲ ጓደኛ ነሽ እንዴ?"ሲሉ ጠየቋት

የምትመልስላቸው ግራ ገብቶት ዝም ብላ አፍጥጣ ታያቸው ነበር..ጊፍቲ ማን ነች…?ምኑ ነች?››በእምሮዋ የበቀለ ምቾት የማይሰጥ ጥያቄ ነበር፡፡

ቃል ጣልቃ ገባና‹‹አይ የእኔ ጓደኛ ነች››ብሎ መለሰላቸው…አሮጊቷ ሌላ ነገር ሳይዘባርቁ ፈጠን አለና ‹‹ተከተይኝ ››በማለት ወደጓሮ ይዟት ሄደ… ፡

ቤቱን ከፍቶ ቀድሟት ገባ… ተከተለችው...፡፡እዚህ ቤት እንዲህ በአጋጣሚ እና በቀላሉ እንደገባች በቀላሉ እንደማትወጣ ታወቃት….በቃ እናቶች እንዲህ አይነት የመገለጥ እና የትንቢት አይነት ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ተከሻዬ ነገረኝ እንደሚሉ አይነት ነው እሷም ትከሻዋ የነገራት፡፡

ቅልብጭ ያለች  ሶስት ክፍል የወንደላጤ ክፍል ነች። እቃዎቹ  ልክ እንግዳ እንደሚመጣበት አውቆ ቀድሞ ያዘጋጀው ይመስላል ።ብዙ የወንደላጤ ቤት በተለያየ አጋጣሚ  ገብታ አይታ ታውቃለች..የፈለገ ቢጠነቀቁ የሆነ  የተዝረከረከ ነገር እንደማያጣቸው ታዝባለች፡፡ ይሄ ግን እንከን አልባ ነው።

‹‹ነይ እለፊ ያው መኝታ ቤት ግቢና አረፍ በይ ..እኔ ምሳ ልስራና በልተሽ ኪኒኑን ትውጪያለሽ።››አለትና ወርቃማ ቀለም ወደተቀባ የተዘጋ የእንጨት በር በአገጩ እመለከታት፡፡

"አረ አልፈልግም አራበኝም›› አለችው...፡፡

"እኔ እርቦኛል ...ለራሴ እኮ ነው የምሰራው...ለእኔ የሠራሁትን አብረን እንበላለን...ግቢ  ..ከፈለግሽ ቁልፍ ከውስጥ ተንጠልጥሎልሻል ቆልፊና ተኚ...ምሳ ሲደርስ አንኳኳለሁ።››

በንግግሩ አሳፈረት‹‹…እኔ ያላሳብኩትን አታስቢ.ለእንደዛ አይነት ጉዳይ ፈልጌ አይደለም አቤቴ ድረስ ጎትቼ ይዤሽ የመጣሁት››ያለት ነው የመሰላት፡፡

…ከዛ ፈጠን አለችና "አረ ችግር የለውም ››ብላ ተንደርድራ ወደጠቆማት ክፍል ገባች ።በራፍን ዘጋችው..  ግን አልቆለፈችውም።

እንደሳሎኑ ሁሉ መኝታ ቤቱም በስርአት የተያዘና የሚማርክ ነው ።አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች።ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ የድንግል ማሪያም ምስለ ፍቁር ወልዳ ስዕል 40 60 በሚሆን መጠን ተሰቅሎ ይታያል ከዛው ስዕል ስር ከታች የልጁ የምርቃት ፎቶ አነስ ባለ መጠን ተሰቅሏል፡፡

አልጋው ላይ ቁጭ ስትል ድካሟ ሁሉ ካለበት ተሰብሰቦ ሰፈረባት፡፡ለመተኛት ፈለገች፡፡ጎንበስ ብላ ጫማዋን ለማውለቅ ስትሞክር ቅድም ታክሲ ውስጥ ያ ቋቋቴ ሽማግሌ የነረታት ቦታ ኃይለኛ ውጋት ተሠማት።እንዳምንም ጫማዋን አውልቃ አልጋ ላይ ወጣችና አልጋ ልብሱን ገለጥ አደርጋ ከውስጥ ገብታ ተኛች።

ይሄ ተአምር ነው...ለቃል ከአብሮ አደጉና ከፍቅረኛው ከጊፍቲ ውጭ ሌላ ሴት ወደእዚህ ቤት ሲያስገባ አስገብቶም አልጋው ላይ እንድትተኛ ሲፈቅድ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኙ እንደሆነ ሁሉ ለእሷም የማታውቀውም ሆነ የምታውቀው ወንድ መኝታ ክፍሉ ድረስ ገብታ አልጋው ላይ ስትተኛ ይሄ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኟ ነው።እርግጥ ብዙ ጊዜ እጮኛዋ መድህኔ መኝታ  ክፍል ገብታ ታውቃለች… ግን አልጋው ላይ መተኛት ይቅርና ተቀምጣም አታውቅም፡፡  ይሄንን እሷና እግዚያብሄር ብቻ ናቸው የሚያውቁት። ለሌላ ሰው ግን እንደዛ ብላ ብትናገር ከጠቅላላ ሁኔታዋ ከመሽቀርቀሯና ከቅብጠቷ አንፃር በወስጣቸው ባዳበሩት ግምት  ወይ ይስቁባታል..ወይ ያሾፉባታል።ሌላ የውጭ ሰው ሳይሆን ቤተሠቦቾ እራሳቸው እንደማያምኗት ታውቃለች  ። የገዛ እናቷ ሳይቀሩ አንዳንዴ በአግቦ ‹‹አይ የጓደኞቼ ልጇችማ ከነክብራቸው ቆይተው ይሄው በደስታ ሊዳሩ ነው…እኔንስ አምላክ እንዴት ያደርገኝ ይሆን?።››በማለት  በጎን ያላቸውን ስጋት ጠቆም ሲያደረጉ ደጋግማ ሰምታለች፡፡ …ሁሉም እንደዛ በማሰባቸው አትበሳጭም። እንደውም ከእሷ ምንም እንዳይጠብቁ   ስለሚያደርግ  ነፃነቷን ያጎናፅፉታል።

የማይረቡ አርቲቡርቲ ሀሳቦችን እያሰበች ስትብሰለሰል  በራፉ በስሱ ተንኳኳ

"አቤት  ..ክፍት ነው ግባ።››

ቀስ ብሎ ከፈተና ገባ 

"እንዴ የቆለፍሽው መስሎኝ ነበር?"አላት፡፡

"በገዛ ቤትህ  እንዴት ቆልፍብሀለሁ?"

"አይ ምቾት ካልተሰማሽ ብዬ ነው ..ምሳ ደርሷል .እዚህ ላምጣ  ወይስ ወደሳሎን መምጣት ትችያለሽ  ?›› በስንት አማላጅነት እቤቱ የወሰዳትን የክብር እንግዳውን  ጠብ እርግፍ ብሎ   የሚያስተናግድ ትሁት አፍቃሪ መሰላት….እንደዛ ስላሰበችም ፈገግ አለች፡፡

"ኸረ መጣሁ"እለችና አልጋ ልብሱን ከሰውነቷ ላይ ገፍ ከአልጋው ወረደች።ቀድሟት ወደፊት ለፊተኛው ክፍል  ተመለሰ  …. ተከተለችው፡፡ ጠረጴዛው ማዕዛቸው በሚያውድና  ለአይን ማራኪ በሆኑ ምግቦች ተሞልቷል።ገና እንዳየችው ያልነበረባት ረሀብ ተቀሰቀሰባት። ማስታጠቢያ አምጥቶ በቆመችበት  አስታጠባት...ስለምግቡ እያስበች ስለነበረ ሳትግደረደር እጇን  ታጠበችና ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡  ..

"ይሄን ሁሉ ምግብ በግማሽ ሰዓት....ነው ወይስ?››

"ወይስ ምን..?››ቃላቱን ከአንደበቷ ነጠቀና መልሶ ጠየቃት ፡፡

"ያው የወንደላጤ ነገር ከሆቴል  አምጥተህ እንዳይሆን ብዬ ነው፡፡"

ከት ብሎ ሳቀ ..‹‹ጥርሶቹ ውብ ናቸው….፡፡ስትል ለሁለተኛ ጊዜ በውስጧ አደነቀችው፡፡

"አይ በፍፅም አይደለም..የዕድሜ ልክ ምግብ የማብሰል ችሎታ አለኝ፡፡እናቴ አኔን ስትወልድ ነው የሞተችው.አባቴ ነው ያሳደገኝ….፡፡በዚህ የተነሳ ምግብ ማብሰል የጀመርኩት በልጅነቴ ነው፡፡ለእኔም ለአባቴም ለረጅም አመት አበሰል ነበር. ለዛ ነው...እሺ እየበላሽ..."

ታሪኩ አንጀቷን በላት..እሷም አባት የላትም፡፡ከአባቷ የተለየችው ጮርቃ ህፃን ሳለች ነው…እስከአሁን ድረስም አባቷ ይኑር ይሙት አታውቅም…ግን የእሷን ከእሱ ሚለየው ‹የአባት ፍቅር› ከሚባለው የስሜት ክፍተት በስተቀር አባቷ ስለሌለ ጎደለብኝ የምትለው ነገር የለም..፡

ሀሳቧን ገታ ለእሱ መለስችለት "እየበላሁ ነው ....እኔ ግን ማብሰል የምችላቸው ምግቦች ከሶስት አይበልጡም።"አለችው፡፡

‹‹እየቀለድሽ ነው አይደል ?››አላተ…ሲያዮት ቀበጥና ሞልቃቃ አስተዳደግ ያደገች  ልጅ እንደሆነች ተረድቷል ቢሆንም ግን እንደምትለው ፍፅም ማብሰል የማትችል ገልቱ የምትባል እንደሆነች ግን ማሰብ አልፈለገም፡፡እሷ ግን ምንም ልትደብቀው አልፈለገችም፡፡
👍1164
‹‹አይደለም…እንደውም አጋንኜዋለሁ..እንቁላል  መጥበስ ብቻ ነው የምችለው….›› እውነቱን ተናዘዘች….ግን ደግሞ የቤታቸው ሰራተኛ ይሄንን ንግግሯን ብትሰማ ትቃወማት ነበረ.ምንያቱም እንቁላሉንም ቢሆን ሰው አጠገቧ ሆኖ እንዲህ አድርጊ ይሄንን ጨምሪ ካላሏት በስተቀር በቅጡ ማድረግ እንደማትችል ታውቃለችና፡፡

እኚህንና የመሳሰሉትን ወሬዎች እያወሩ በጣም ጣፍጭና እጣት የሚያስቆረጥሙ የሚባሉ  ምግቦችን በልተው  ተነሱ። ከዛ መዳኒቷን እንድትውጥ    ውሀ አቀረበላትና‹‹  በይ ዋጪና ተመልሰሽ መኝታ ቤት ገብተሽ ተኚ ››አላት፡፡

‹‹መድሀኒቱን ውጠሸ ወደቤትሽ ሂጂ ምትለኝ ነበር የመሰለኝ››አለችው››

በንግግሯ ደንገጥ ብሎ‹‹አረ አይወጣኝም፡፡ ለምን መጣሽና ?ልታርፊ  እኮ ነው››

‹‹ስቀልድ ነው››አለችው…የሰጣትን መድሀኒት  ዋጠች…ይሄኔ መድሀኒቱን ዋጪ ያለቻት እናቷ ብትሆን ፊቷ ላይ በትናባት ነበር….ትህትና የተለበሰ ማራኪ ፀባዮ ለራሷም አስደመማት፡፡ከዛ  ልክ እንደለማዳ ድመት  አንገቷን አቀርቅራ ወደመኝታ ቤቱ ገባችና  አልጋ ልብሱን ተከናንባ ተኛች ።

የአንሶላውና የብርድልብሱ ጠረን ሳታስበው በጥልቀት ወደውስጧ ሳበችው …ከመቼ ወዲህ ነው የሌላ ሰው ጠረን በማቅለሽለሽ ፋንታ የደስታ ቅመም በውስጧ መበተን የጀመረው፡፡? አልገባትም.. ደስ የሚል ጭልጥ ያለ እንቅልፍ  ወሰዳት።

ይቀጥላል
👍10314🥰8
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ እየተከታተለን ያለ ሠው ቢኖር ሁለቱም ፊት ላይ የደስታ ካፊያ እንደተርከፈከፈባቸው የፊታቸው በድንገት ማብረቅረቅ በመመልከት   በቀላሉ ይረዳ ነበር፡፡ላዳ አስቆሙና ይዟት ገባ...በስድስት ደቂቃ ውስጥ እቤቱ ደረሱ። ግቢ ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲያስገባት የቤቱ አካራይ በረንዳ ላይ ቆመው ነበር.. …ልትጠፋ ደርሳ ጭልጭል እያለች ባለች አይናቸው…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ስንት ሰዓት   እንደተኛች አታውቅም፡፡ ፍፁም ሰላማዊና ህልም አልባ እንቅልፍ ነበር። ነቃች።ከአልጋ ወረደች።ቀለል ብሏታል። ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ስትገባ ባዶ ነው፡፡ እንደውም ተዘግቷል። ‹‹ባዶ ቤት ጥሎኝ የት ሄደ...?፡፡››ቅር አለት፡፡የቤቱን ዙሪያ ገባ ስትቃኝ መሀል ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አየች፡፡ ወደእዛ ሄደችና አነሳችው… አነበበችው"
                         

ይቅርታ ስምሽን አላወቅኩትም ለማንኛውም
አስቸኮይ ስራ ስላጋጠመኝ ወጥቼያለሁ..
ሳልመጣ የምትሄጂ ከሆነ መኝታ ቤት ኮመዲኖ ላይ የታክሲ ብር አስቀምጪልሻለሁ።
ቤቱን ቆልፊና ፊት ለፊት ለአከራዮ ስጪልኝ።
በይ እግዜር ይማርሽ...አመሰግናለሁ።

አንብባ ስትጨርስ‹‹በቃ..? ››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹አይ እስክትመጣ አልሄድም..››ስትል ቃል አውጥታ ተናገረች… .አጠገቧ ያገኘችው ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡

‹‹ስሜ ልዩ ነው፡፡››ይሰማት ይመስል  በድጋሚ ጮክ ብላ ተናገረች፡፡

"ደግሞ እንዴት ይሄን ሁሉ ነገር አድርጎልኝ ሳላመሰግነው እሄዳለሁ..?እንደውም ጥሩ ምክንያት አገኘሁ ለእማዬ ደውዬ እንግራተና እዚሁ አድራለሁ..ከዛ የሚፈጠረውን አያለሁ››አለች ድንገት ከመቀመጫዋ ተነሳችና….ወደመኝታ ቤት ተመልሳ ገባች.. እንዳለው ኮመዲኖው ላይ ብር አስቀምጦላታል…አነሳችውና ቆጠረችው፡፡ ሶስት መቶ ብር ነው። ኮመዲኖ የታችኛው ቁልፍ እላዩ ላይ እንደተንጠለጠለ ነው፡፡ የምታውቀወ ግን የምትጠላውና የመትጠየፈው ቢሆንም ደግሞ ልትቆጣጠረው የማትችለው ኃይል በውስጧ ሲሰርግ ታወቃት.... የተጣባት የሌብነት መንፈስ አንበረከካት፡፡ ቁልፉን አሽከረከረችው… ተከፈተላት፡፡ ውስጡ ብዙ ሰነዶችና አንድ ላፕቶፕ አለ."ያለምንም ማቅማማት ላፕቶፑን አነሳችውና ፤300ብር በእጇ ጨምድዳ ይዛ መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች….እንዳለት ቤቱን ቆለፈችና ቁልፉን ለአሮጊቷ ሰጥታቸው ሰፈሩን በላዳ ለቃ ወጣች፡፡

መሄድ የነበረባ ወደጦር ኃይሎች ነበር ..ከዛ ወደትምህርት ቤቷ ሄዳ ግቢው ወስጥ ያቆመቻትን መኪና ይዛ ነበር ወደሳሪስ መሄድ የሚገባት ግን አሁን እንደዛ ማድረግ አልቻለችም ቀጥታ…ላፕቶፑን በደረቷ ላይ ለጥፋ ከካሳንቺስ እስከሳሪስ እያለቀስች ነበር የደረስችው...ልክ ላፕቶፕ ካልሰረቅሽ ህይወትሽን ታጪያለሽ ብለው በግዳጅ እንዳሰረቋት ነገር ነው ሁኔታዋ የሚመስለው፡፡

‹‹አሁን ለዚህ ልጅ በዚህ ደግነቱ እንዲህ መዘረፍ ይገበዋል…?.እኔስ ዘራፊና ሌባ መሆን ይገባኝ ነበር…?አረ ጌታ ሆይ እውነት በመንበርህ ካለህ አንድ ነገር አድርግ..ነው ወይስ የሌባ ፀሎት አንተ ጋር ምንም እርባን የለውም…ምንም ሌባ ብሆነ እኮ ያው አንተው ነህ የፈጠርከኝ››ስትል አምርራ ወደፈጣሪዋ አጉረመረመች፡፡
///
እቤት እንደደረሰች በራፍን የከፈተላት ዘበኛ በድንጋጤ ጭንቅላቱን ያዘ፡፡ በረንዳ ስታፀዳ የነበረችው የቤት ሰራተኛም  መወልወያዋን በቁማ ጥላ‹‹  እትዬ..ልዩ ተጎድታለች..እትዬ ልዩ ተፈንክታልሽ መጣች....››እያላች ወደግዙፍ ባለሁለት ፎቅ ህንፃ ገባች..እሷ የሳሎን በረንዳ ላይ ስደርስ እቤት ውስጥ የነበሩት ቤተሰቦቾ በጠቅላላ በእናቷ ፊት መሪነት እየተንጋጉ ዙሪያዋን ከበቧት፡፡
…እናቷ እሪታዋን ለቀቀችው..‹‹ወይኔ ልጄን ይሄው ገደሏት…ወይኔ ምነው እመቤቴ ..?ምነው አንቺም ልጅ አለሽ …የአንድ ብቸኛ ልጅ እናት መሆን ፈተናውና መሳቀቁ ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ካንቺ በላይ የሚያውቀው የለም… ታዲያ ምን አለ ብትሰሚኝ   ››ልክ የሞተችና  ሬሳዋን ተሸክመውላቸው የመጡ ነው ያስመሰሉት፡፡
አዛኙም አሽቃባጩም በአንድነት ከበቧትና  አፋፍሰው ልክ መራመድ እንደማትችል ወደውስጥ ይዘዋት ገቡ፡፡ እሷም ሲደጋግፏት ያልነበረ ህመሟ ከያለበት ተሰብሰቦ ሰፈረባት፡፡ ጭንቅላቷ ላይ የሆነ ቋጥኝ የተጫነባት  ይመስል ውጥርጥር አድርጓታል፡፤ የጭንቅላቷ እብጠት ጥዝጣዜ ነርቯን ነካት
‹‹….እዛ ልጅ ጋር ይሄን ያህል ያለመመኝ እቤቴ ስገባ ለምን ተደበላለቀብኝ፡፡››እራሷን ጠየቀች፡፡
‹‹በሉ እዛ ደክተር ጋ ደውሉለት….በአስቸኮይ መጥቶ ይያተና ካልሆነ ሆስፒታል እንወስዳታለን.››እናቷ ናቸው በለቅሶ የታጀበ ትዕዛዝ የሚየዥጎደጉዱት፡፡
አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የተንጣለለው መኝታ ቤቷ አስገቧት
….‹‹.ዞር በሉላት በቃ አታጨናንቋት….››ብለው አስተኞት፡፡
‹‹ለመሆኑ መንግስት ባለበት ሀገር ከማን ተጣልተሸ ነው..?››በቀጣይ የጠየቋት ጥያቄ ነው
‹ግን በአሁኑ ወቅት ኢትዬጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት ጥያቄ ይጠየቃል..? መንግስት እያለ ምን የማይደረግ ነገር አለ..?ግድያ ፣አስገድዶ መድፈር፣ከገዛ መንደር መፈናቀል…ነገሩ እንዚህ ሁሉ ወንጀሎች መንግስት ባለባቸው በማንኘኛቸውም ሀገሮች ይፈፀማሉ… በአሜሪካም ጭመር….አንዳንዴ እንደውም መንግስት እራሱ በእጅ አዙር ያስፈፅማቸዋል  …አንተ እያለህልን እንዴት እንዲባል?እናቴ ግን ምን ታደርግ  ሳሪስ  ላይ ተቀምጣ ስለእነዚህ ነገሮች በወሬ እንኳን ብትሰማ ከምታየው የቱርክ ፊልም ጋር ስለሚምታታባት እውነት ይሁን ውሸት ትዝም አይሏት….ለነገሩ እኔም እንደእሷው ነኝ…አሁን እራሱ ስለእንደዚህ አይነት ጠንከር ያለ ነገር እንዴት ማሰብ እንደቻልኩ አላውቅም...ምን አልባት ጭንቅላቴን ሲነርቱት  የሆኑ አንቀላፍተው የነበሩ ነርቮችን አነቁብኝ ይሆን እንዴ…?ኸረ አያድርገው…ጌታ ሆይ ስለፖለቲካና ዲሞክራሲ ሚበሉ ህልሞች የሚያስብ የእምሮዬን ክፍሎችን መቼም ንቁ እንዳይሆኑ እማፀንሀለሁ›› ስትል ፀለየች..መቼስ ይሄንንንም እንደሌሎች ፀሎቶቿ ችላ እንደማይልባ አየተማመነች፡፡
እናቷ እሷን መጨቅጨቃቸውን ቀጥለዋል‹‹ዩኒቨርሲቲ አመፅ ተነስቶ ነው…? ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተሸ ነበር እንዴ?ምን  ተከስቷ ነው?›
እናቷ የማትመልሳቸውን አያሌ ጥያቄዎች ያዥጎደጉድባታል…. ዩኒቨርሲቲ ያሏት.. ጥዋት ከቤት ቁርስ በልታ ዩኒቨርሲቲ ክላስ አለኝ ብላ በመውጣቷ ነው ፡፡ደግሞም ሄዳ ነበር….ልዩ የምትማረው ዪኒቲ ዪኒቨርሲቲ ነው..መኪናዋን ይዛ ወደእዛ ነበር የተጎዘችው..አንድ ክላስ እንደተማረች ግን የተለመደ ድብርቷ ተቀሰቀሰባትና መኪናዋን እዛው ግቢ ውስጥ እንዳቆመች፤ስልኳን እንኳን እዛው መኪናዋ ውስጥ ቻርጅ እንደሰካች  በእግሯ ከግቢው ወጣች ፡፡
በተክሲ ስትዲዬም ድረስ ከስቴዲዬም ደግሞ መገናኛ ሄዳ ነው እንግዲህ ያ ታክሲ ላይ ያጋጠማት ታሪክ የተፈጠረው..እንደዛም ስለሆነ ከወትሮ በተለየ ፀፀትና  ንዴት አልተሰማትም ነበር፡፡በጣም ልዩ በሆነ አጋጣሚ ከተለየ እና ተአምራዊ ከሆነ ልጅ ጋር ነበር ያገናኛት.. ምን ያደርጋል? አፈፃፀሙን አበላሸችው… የማትፈልገውን ላፕቶፕ ሰርቃ ያንን የመሰለ አጋጣሚ በማጨመላለቋ እራሷን ተጠይፋለች፡፡አሁን በሰውነቷ ካለው ቁስል በላይ ክፉኛ እየጠዘጠዛት ያለው ይሄ ነው፡፡
..‹‹ግን ወድጄ ነው እንዴ  እንደዛ ያደረኩት?››ስትል እራሷን ለማፅናናት ሞከረች፡፡
ሁሉም መኝታ ቤቷን ለቀው እንዲወጡ ተደረገና በክፍሉ እናቷና እሷ ብቻ ቀሩ፡፡
👍80🥰43🔥1
‹‹እንደው ልጄ እስኪ ማን ነው እዲህ ያደረገሽ..?ንገሪኝና  ለኩማንደር ልደውልለት….››
ኩማንደር ማለት ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ትልቅ ስልጣን ያለው ዘመዳቸው ነው…ልዩ ሁሌ እናቷ ስላላቸው የዘመድ ብዛት ስታስብ ትገረማለች....በእያንዳንዱ ዘርፍ ትልልቅ ቦታ ሚሰሩ ሁለት ሶስት ዘመዶች አሏቸው..እና ምክንያት በተገኘ ቁጥር ይደወልላቸዋል..የሆነ ነገር ያረጉና ከእሳቸውም በምላሹ የሆነ ነገር ይደረግላቸዋል፡፡
‹‹ደውይለት››አለቻቸው፡፡
‹‹እኮ መጀመሪያ የሆነውን  ንገሪኛ?››
‹‹ታክሲ ውስጥ ገብቼ ሞባይል ከሰው ስሰርቅ እጅ ክፍንጅ ያዙኝና ቀጠቀጡኝ..አይገርም? በይ ደውይለትና ለቃቅሞ ይሰራቸው፡፡››
‹‹ልጄ እንደው ምን አይነት ልክፍት ነው…?ህክምናው ካላደነሽ… ፀበሉ ካልፈወሰሽ  ምንድነው የሚሻለው?›› የተለመደ ምሬታቸውን በለቅሶ አጅበው  ቀጠሉ፡፡
‹‹ምን አልባት እስር ያስተካክለኝ ይሆናል…አንድ ሁለት አመት እየገረፍ ወህኒ ቢያቆዩኝ በደንብ ታርሜና ሌብነትን እርም ብዬ ልወጣ እችላለሁ…እማ ግድ የለሽም እንሞክረው.››
ያው እንደዛ የምትላቸው ከአንጀቷ መታሰር ፈልጋ አይደለም..የሚሉትን ለመስማት እንጂ…፡፡እንደውም እንደእስር የምትፈራው ነገር የለም…ይሄ ባህሪዋ ሁሌ ይስገርማታል?‹‹.ሌባ ሆኖ እስር ፈርቶ እንዴት ይዘለቃል?›ስትል በራሷ ታሾፋለች፡፡
እናቷ ሌላ ነገር ለመናገር ከንፈራቸውን ለማነቃነቅ ሲሞክሩ  በራፉ  ተቆረቆረ …እጃቸው ላይ ባለው ናፕኪን  እንባቸውን እያበሱ ሄዳው ሲከፍቱ ዶክተሩና መድህኔ ተከታትለው ወደውስጥ ገቡ…፡፡

ይቀጥላል
🥰56👍4412😁2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ስንት ሰዓት   እንደተኛች አታውቅም፡፡ ፍፁም ሰላማዊና ህልም አልባ እንቅልፍ ነበር። ነቃች።ከአልጋ ወረደች።ቀለል ብሏታል። ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ስትገባ ባዶ ነው፡፡ እንደውም ተዘግቷል። ‹‹ባዶ ቤት ጥሎኝ የት ሄደ...?፡፡››ቅር አለት፡፡የቤቱን ዙሪያ ገባ ስትቃኝ መሀል ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አየች፡፡ ወደእዛ ሄደችና አነሳችው… አነበበችው"…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እናቷ ሌላ ነገር ለመናገር ከንፈራቸውን ለማነቃነቅ ሲሞክሩ  በራፉ  ተቆረቆረ …እጃቸው ላይ ባለው ናፕኪን  እንባቸውን እያበሱ ሄደው ሲከፍቱ ዶክተሩና መድህኔ ተከታትለው ወደውስጥ ገቡ…፡፡

‹‹ደግሞ ለእሱ ማን ደወለ…?››ልዩ ነች በውስጧ ያልጎመጎመችው፡፡  ወዲያው መልሱን አገኘችው..መድህኔ  እነሱ ቤት ውስጥ  ከዘበኛ አንድ ከቤት ሰራተኛ አንድ  የእሷን የቤት ውስጥ እቅስቃሴ የሚሰልሉ ጆሮ ጠቢዎች እንዳሉት በእርግጠኝነት ታውቃለች…..በዚህም አልተሳሳተችም አሁን ደውለው የነገሩት እነሱ ናቸው..መድህኔ የልጅነት ጓደኛዋ ብቻ ሳይሆን እጮኛዋ ነው…፡፡

‹‹ልዩ..ምን ተፈጥሮ ነው..?እንዴት ሳትደውይልኝ….?ማሚስ ብትደውይልኝ..ምን አለበት…?››
‹‹ያው ተደውሎልህ መጣህ አይደል?›› መሽቆጥቆጡ አበሳጭቷት የመለሰችለት ልዩ ነች፡፡
‹‹አረ እኔ ስልክሽ  ከጥዋት ጀምሮ አልሰራ ስላለኝ ግራ ገብቶኝ ለማጣራት ስመጣ ነው በራፍ ላይ ያለው ዘበኛ የነገረኝ››አላት….
ቀኑን ሙሉ ስለእሷ ሲያስብና ሲጨነቅ መዋሉን አልዋሻትም…ግን አሁን እዚህ ሊገኝ የቻለበት ምክንያት እሱ እንዳለው ሳይሆን ልዩ እንደገመተችው ዘበኛው ደውሎ የልዩን መጎዳት ነግሮት ነው በድንጋጤ እያለከለከ ካለበት በሮ የመጣው፡፡

ዶክተሩ ይዟቸው በመጣቸው ዕቃዎች አገላብጦ መረመራትና ቀድሞ የተደረገላት ህክምና እና የተሰጣትን ኪኒን ካየ በኃላ‹‹ወ/ሮ ጥሩነሽ  ተገቢው ህክምና ስለተሠጣት ለጊዜው ሌላ ተጨማሪ ነገር አያስፈልግም… ምግብ ትውሰድ ፤እረፍት ታግኝ….ነገ ተመልሼ መጥቼ አያታለሁ››ብሎ እቃውን ሰብስቦ ወጥቶ ሄደ፡፡  ሶስቱ ብቻ ቀሩ፡፡

‹‹ምን ሆነሽ ነው ፍቅር ?››ቅልስልስ ባለ ንግግር ጠየቃት፡
እሷ ልትመልስለት አፏን ከመክፈቷ በፊት እናቷ  ጣልቃ ገብተው ይመልሱላት  ጀመር…‹‹ጓደኞቾ ሲጣሉ ለማገላገል መሀከል ገብታ እንደዚህ ሆነች..እስኪ ቢጫረሱ ምን አገባሽ…?››
እናቷ ገመና ከታች መሆቸው ነው….እጮኛዋ በድርጊቷ እንዳይከፋው ለመከለላከል ነው እንደዛ ያደረጉት…ልጃቸው ስለተፀናወታት መጥፎ ልክፍት ከእሱ በላይ ደግሞ የእሱ ቤተሰቦች እንዳይሰሙ አብዝተው ይጨነቃሉም፤ ይሳቀቃሉም..
የመድሀኔ ቤተሰቦች ከእሳቸው በላይ ወግ አጥባቂና ለክብራቸው አብዝተው ሚጨነቁ ናቸው..አባትዬው እኔ የቀኝ አዝማች ገ/እግዚያብሄር ሀጎስ ልጅ…›› የዘወትር ፉከራቸው ነው…የልዩ እናት  አባታቸው ፊት አውራሪ ቢሆንም በግልፅ ሲፎክሩበት ሰምታ አታውቅም….ግን ነገረ ስራቸውና ተግባራቸው ያው በአጥንት ቆጠራ ታሪክ ውስጥ እናቷም እንዳሉበት ታውቃለች፡፡ …አንዳንዴ ሰዎች ሲያበሳጯቸው‹‹ እኔ ከማንም ወፍ ዘራሽ ጋር ዝቅ ብዬ አፍ አልካፈትም›ሲሉ ብዙ ጊዜ ሰምታለች…‹‹አረ ተው የአባቴ መንፈስ ይታዘበኛል›› የሚሉትም  ነገር አላቸው.. .እንግደህ ልዩና መድህኔ የሁለት ፊውዳል ቤተሰቦች ውጤት ናቸው…ጥምረታቸውም ፍቅርን ብቻ መሰረት ያደረገ  ሳይሆን የቤተሰብም የእጅ አዙር ፍላጎት ያለበት ነው….፡፡›
መድህኔ ወቀሳውን ቀጠለ‹‹ፍቅር እንዴት እንዲህ ታርጊያለሽ.. ? ቀጥታ አይንሽን አግኝተውት ቢሆንስ? ››
‹‹አሁን የእውነት የሆነ የማላውቀው ወንድ መኝታ ቤቱ ድረስ ሰተት ብዬ ገብቼ አልጋው ላይ ስተኛ ውዬ እንደመጣሁ ቢያውቅ እንዲህ በመንሰፍሰፉ ይቀጥልበት ይሆን…?››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች…‹‹አሁን አውቆ ነው አይደል እንዲህ የሚሆነው? እኔን በፀፀት ለመለብለብ… በአንድ ቀን ውስጥ በልቤ ገብቶ እየተገለባበጠ ያለው ልጅ ላይ የሰራሁት ግፍ መች አነሰኝ…››በማለት በውስጧ አሰበችና ተበሳጨች፡፡
አናም በንዴት ውስጥ ሆና መልስ ትሰጠው ጀመረች‹‹ቢሆንም ይጠፋላ.. ሌላ ምን ይሆናል…?›› መለስችለት፡፡

‹‹የአይን መጥፋት ቀላል አደረግሽው?››

‹‹ምን ችግር አለው..አንተም እማዬም ብር አላችሁ… ይገዛል… ይቀየራል..አሁን ደክሞኛል ልተኛ ነው፡፡›› አለችውና ተሸፋፍነች፡፡

‹‹ና ልጄ ደሙ ጭንቅላቷ ላይ ወጥቷል መሰለኝ ብስጭትጭት ትላለች..አረፍ ብላ ስትረጋጋ እናነጋግራታለን፡፡››

‹‹አረ ካልሆነ  ዊክ ኢንድ ላይ ኢስትአንቡል ወይም ዱባይ ወስዳትና ትንሽ ሪላክስ አድርጋ ትመጣለች…እኔ በህይወት እያለሁም እሷ እንዲህ ድብርት ውስጥ አትገባም፡፡››

‹‹እስቲ ትረጋጋና …እንማከራለን›››ብለው ይዘውት ወጡ…እሷም ወደጥልቅ ሀሳብ ወስጥ ገባች፡፡
//
በማስመሠል ብቃቷ እልል የተባለለትን አርቲስት ታሰንቃለች።በጓደኞቾ መካከል ስትሆን ፈገግታዋ  ከጨረቃ የሚፈነጠቅ ብርሀን በሉት  ፤ቤተሠቦቼ ሲያገኙት ጥርሷ እንደጥርስ ኪኒሊክ አስተዎዎቂ ያለገደብ ይፈለቀቃል። አለባበሷ የታሰበበትና ሽክ ያለ ነው።ከእሷ ላይ አንድ እንከን ማውጣት  ፀጉር መሠንጠቅ  ነው ሚሆነው...ታዲያ የትኛው ስል እይታ ያለው ሰው ነው ወደ ውስጧ ዘልቆ የተሰባበረው እሷነቷን በመገንዘብ ሊያዝንላት የሚችለው...?የትኛውስ ጠንቋይ ነው የነፍሷን መሠንጠቅ በራዕይው አይቶ ፈውስ የሚሆን ቅድስ ዘይት የሚሰጣት?።የትኛውስ የልብ ጓደኛ ነው ውስጧ የተንጣለለውን የሀዘን ባህር አይቶ እንዴ ይህቺ ሴትና ደስታ አይተዋወቁም ብሎ በድፍረት መናገር የሚችለው?።ልቧ ላይ ያረፈውንስ አለምን የሚያህል ጥቁር ጠባሳ የትኛው ምጡቅ ሀኪም ነው  አክሞ ሊያድነው  የሚችለው?

  ከታክሲው ገጠመኝ በኃላ ይሄው ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ቢሆንም ደፍራ ከቤቷ  አልወጣችም...አይደለም ከቤቷ ከክፍሏም አልወጣችም…ዶክተሩ ዛሬ ጥዋት መጥቶ የተለባበዱት ፕላስተሮችን  አላቆላት ፤ባንዴጁን ከላዮ ላይ ጥሎ ንፁህ ሰው መሆኗን አረጋግጦል  ‹‹ለሚያቁነጠንጣሽ ደብርት የሚሆን መድሀኒት››ብሎ የሆኑ ኪኒኖች  ሰጥቷት ሄዷል፡፡
አዎ ዶክተሩ እንዳለው ፊቷ ላይ የነበረው እብጠትና ቁስለት ጠፍቷል.. ያንንን መታጠቢያ ክፍል  ባለ  ትልቅ መስታወት ፊት ለሳዕታት  ቆማ በመመልከት አረጋግጣለች..፡፡ነገር ግን  ልቧ ላይ ያለው ቋጥኝ የሚያህል እብጠት አሁንም ባለበት እንደተነረተ ነው….ልቧ ላይ የተሞነጫጨረው ቁስለትም እንዳለ ነው...እንደውም መግል ይዟል …፡፡ ሲያመረቅዝ የሚለቀው መጥፎ  ጠረን በአፍንጫ እየመጣ እየረበሻት  ነው…፡፡ክፋቱ ደግሞ እናቷን ጨምሮ ሁሉም ሰው ለሶስት ቀን ሙሉ ሲረባረብ የነበሩት ፊት ለፊቷ  ማንም የሚያየውን አካሏ ላይ የሚገኘውን ጭረት ለማዳን ነው…ስለውስጥ ድማቷ  ግን ማንም ቁብ የሰጠው የለም… ዶክተሯንም ጨመሮ…አረ ፍቅረኛዋም ጭምር፡፡
‹‹አሁን ምን ይሰማሻል..?እብጠቱ አካካቢ  ያምሻል…?ፊትሽ ላይስ? ›› እነዚህንና  መስል ጥያቄዎችን ነው  በመጠየቅ የሚያደነዝዟት፡፡
‹‹አሁን ስለ እዛ ልጅ ምን ላድርግ? ››ስትል አሰበች፡፡ከእቤቱ ይዛው የመጣችው  ላፐቶፕ ኮመዲኖዋ  ላይ ቁጭ ብሎ እያፈጠጠባት  ነው… .. እዛ ሀሳብ ውስጥ ከገባች እራስ ምታቷ  መቀስቀሱ የታወቀ ስለሆነ ችላ አለችውና የራሷን  ላፕቶፕ  ወደሚገኝበት አልጋዋ  ላይ ወጥታ  ከፈተችው..ዩቲዩብ ትንሽ አየችና ወደ ፌስ ቡክ  ቀየረችው….ቻት ውስጥ ገባችና ከክላስ ጎደኞቾ  ጋር እያወራች ሰላ ድንገት ትናንት ተልኮላት የነበረ የማታውቀን  ሚሴጅ አገኘች፡፡
👍8911🥰2👎1👏1
ላኪው  ቃል እንደሆነ ይገልፃል… ተስፈንጥራ ለፕቶፖን በእጇ እንደያዘች  ከአልጋው ወረደችና የሚለሰልሰው የቱርክ ሰራሽ ምንጣፍ  ለይ በእግሮቾ  አረፍች፡፡ በቆመችበት ሚሴጁን ማንበብ ጀመረች፡፡
ልዩ እንዴት ነሽ..?እንደተሻለሽ ተስፋ አደርጋለሁ…
ስሜን እንዴት አወቀ ብለሽ ተገርመሽ ይሆናል…
(የእውነትም እንዴት አወቀ…?በማለት እየተገረመች ስለነበር እዕምሮዋን ቀድሞ ስላነበበ አስገረማት)
ትናንትና ኪኒሊክ የሄድን ጊዜ ለካርድ ክፍሏ ስትነግሪያት
እንደድንገት በአዕምሮዬ መዝግቤው ነበር፡፡
እና እሱን ይዤ  ፌስ ቡክ ላይ ስፈልግሽ አገኘሁሽ…
ልዩ እባክሽ አንድ ነገር ላስቸግርሽ ነበር…
አንቺ ጋር ያለው ላፕቶፕ ላይ ዴሰክቶፕ ላይ የተቀመጠ
ቃል የሚል ፎልደር አለ..የስራ ፋይል ነበር…አሱን ካላገኘሁ
ትንሽ ሚበላሽብኝ ነገሮች ስላሉ በሲዲ ገልብጪልኝና  የሆነ የሚመችሽ ሱቅ ወይም ካፌ ብቻ አንድ ቦታ ብታስቀምጪልኝና በደስታና በምስጋና ሄጄ ወስዳለሁ…
ስለመልካም ትብብርሽ እግዜር ይስጥልኝ፡፡

አንብባ ስትጨርስ ንዴቷ ካለችበት ፎቅ ቤት ጣሪያ በላይ ሆኖባት ነበር…‹ላፕቶፖን አሽቀንጥራ ከግድግዳ ጋር አላተመችው
‹‹..ምንድነው እንዲህ ክንፍ የሌለኝ ፃድቅ ልሁን አለ…? እንደሌላው  ሰው ለምን አይሰድበኝም…?.ምን አይነት ውለታ ቢስ ሰው ነሽ ብሎ አይወቅሰኝም…? ቅሌታም መሆኔን እስከዶቃ ማሰሪያዬ ድረስ አይነግረኝም..››ተንጨረጨረች፡
ሞባይሏን አወጣችና ፌስብኳን ከፈተች ..ቻት ውስጥ ገበች፡፡አዎ ኦን ላይን ነው‹አንተ ምን ለማለት ፈልገህ ነው…?ላፕቶፔን ሰርቀሻል  እያልከኝ ነው?››..ብላ በመፃፍ ላከችለት፡፡
አይገርምም ‹የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ›በማለት የራሷን ድርጊት በትዝብት ተቸች፡፡
‹‹አረ ልዩ እንደዛ አላልኩም..ይቅርታ አንቺ ጋር ያለ መስሎኝ ነው…››
‹እሺ አለ ፡፡ታዲያ ምን ይጠበስ? ወስጄዋለሁ .ማለት ሰርቄ ወስጄዋለሁ…ግን የሰረቅኩት ከነፋይሉ ነው...ምንም ነገር አልሰጥህም፡፡››
ላፕቶፑን እሷ እንደወሰደች በትክክል ያውቃል…በጥርጣሬ አይደለም…እቤት ጥሏት በሄደ ቀን እቤቱን ቆልፋ ቁልፉን ለአከራዬ ልታስቀምጥለት ስትሄድ ላፕቶፑን በግልፅ ፊት ለፊት በእጇ ይዛው ነበር…ያንን ደግሞ አሮጊቷ በግልፅ አይታዋታል… ያንንም ሳይጠይቃቸው ነግረውታል፡፡
ቢሆንም ግን …ከዚህ በላይ ሊከራከራትና ወደብስጭት ውስጥ ሊከታት አልፈለገም፡፡‹‹በቃ እርሺው ጥያቄዬን ትቼዋለሁ…. ፋይሉን ከሌላ ቦታ በሌላ መንገድ ለማግኘት ሞክራለሁ..ባይገኝም ችግር የለውም..ሁሉን ነገር  እርሺው..አንቺ ብቻ ሰላም ሁኚ››ብሎ በመፃፍ መለሰላት፡
‹ምን  ያስቀባጥርሀል..?››እየጻፍች ያለችውን ሳትጨርስ ከኦላይን ሲወጣ ተመለከተችው፡፡
መፅፏን አቆመችና ስለእሱ ማጣራት ፈለገች..ወደእሱ ፕሮፋይል ለመግባት መከረች..‹‹ ከመቼው.. ዴአክቲቪት አድርጎታል…ወይኔ ልጅት..ምን እየሆንኩ ነው…..?እንዴት አንድ ሰው በእሱ ልክ ቁጥብ ፤በጣም  የተረጋጋ ሲሆን በተቃራኒው  ደግሞ በእኔ ልክ ቅብዝብዝ ተነታራኪ እና ደግሞ  ምግባረ ብልሹ ሊሆን ይችላል?››በማለት ለፈለፈች….በራፉን ከፈተችና ወጣች…በረንዳ ላይ ቆመችና ጩኸቷን ለቀችው፡፡
‹እማዬ…አንቺ እማዬ……››

ይቀጥላል
👍106🥰1610👎2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ እናቷ ሌላ ነገር ለመናገር ከንፈራቸውን ለማነቃነቅ ሲሞክሩ  በራፉ  ተቆረቆረ …እጃቸው ላይ ባለው ናፕኪን  እንባቸውን እያበሱ ሄደው ሲከፍቱ ዶክተሩና መድህኔ ተከታትለው ወደውስጥ ገቡ…፡፡ ‹‹ደግሞ ለእሱ ማን ደወለ…?››ልዩ ነች በውስጧ ያልጎመጎመችው፡፡  ወዲያው መልሱን አገኘችው..መድህኔ  እነሱ ቤት ውስጥ  ከዘበኛ አንድ ከቤት…»