አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቆንጆ_ነኝ
:::
ስላንቺ ቁንጅና
ስላንቺ ቁመና
ከንፈር እና ዳሌ
ጥርስና ተረከዝ ፣ ፀጉር ገለመሌ
ለጡት ለወገብሽ ፣ ለፀባይሽ ጭምር
በግጥም በዝርው ፣ ባድናቆት ስዘምር
እስከዛሬ ድረስ...
ውበትሽን አግንኜ ፣ ሰርክ መለፈፌ
እኔ ስለራሴ ...
አንዳች ቀን እንኳን ፣ ግጥም አለመፃፌ
ሲትጠዪኝ ቆጨኝ
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
እርግጥ ነው ብዙዎች...
ስለኔ ሳወራ ፣ ድንገት ያኮርፉኛል
ያንተን ሌሎች ያውሩ ፣ ብለው ይነግሩኛል
እኔን ከኔ በላይ...
እርግጠኛ ሆኖ ፣ ሌላ እንዴት ያውቀኛል?!
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
እናም እኔ ማለት...
ቁመቴ ከአክሱም ፣ በእጥፍ ይረዝማል
ጣፋጭ አንደበቴ...
መስማት ለተሳነው ፣ ለስልሶ ይሰማል
ውብ አረማመዴ...
እንኳን መንገደኛን ፣ መንገድን ያቆማል፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የከንፈሬ ወዙ ፣ ጥፍጥናው አያልቅም
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው!
ሺ ሟች ላለማየት ፣ ኗሪ ፊት አልስቅም፡፡
ከአይኔ ብሌን ውስጥ ፣ ብርሐን ይፈልቃል
አይኔን ያየ ሁሉ
ልቡን አሳውሮ ፣ በፍቅር ይወድቃል፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የገላዬ ጠረን ፣ ከሽቱ እጥፍ ነው
መልካም ጠረን ሁሉ...
አለ ባሉት ስፍራ ፣ እኔ አለሁ ማለት ነው፡፡
ፀባየ ትሁት ነኝ ፣ ምጡቅ ነው እውቀቴ
ግርማ ሞገሳም ነው ፣ ተክለ ሰውነቴ
ያየኝ ይወደኛል
የወደየኝ ሁሉ ፣ መቼም አይጠላኝም
ከዚ በላይ እንኳን...
ብዙም ስለራሴ ፣ የማውቀው የለኝም፡፡
እንደውም እንደውም...
አልጎርርም እንጂ ፣
ያፈር ሰውነቴን ፣ በቁንጅና አብየው
ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ፣ ራሴን ነው ማየው፡፡
ብቻ ግን ቆንጆ ነኝ!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_አራት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...መሀሪ የዲላ ከተማ ኑዋሪነቱን ዛሬ ያበቃለታል፡፡ የመጨረሻው ቀን ነው፡፡ከፍተኛ ውጣ ውረድ ቢያሳልፍም በመጨረሻ ተሳክቶለታል፡፡ ከዲላ ወደ ዱከም ከተማ ተዘዋውሯል፡፡እርግጥ ይሄ የዝውውር ጉዳይ ከላይ እንደተገለፀው እንዲህ በቀላሉ የተሳካ አይደለም፡፡ መቶ ሺ ብር ከኪሱ አውጥቷበታል፡፡ለጉቦ፡፡ዝውውሩን ደግሞ አስቸጋሪ ያደረገው ከአንዱ የኢትዮጵያ ክልል ወደሌላው ክልል መሆኑ ነው፡፡ከደቡብ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል፡፡ ለአንድ መንግስት ስራተኛ በዚህ መልኩ ከክልል ወደ ክልል መዘዋወር ልክ ከኢትዬያ ወደ ጁብቲ የመዘዋወር ያህል የማይታሰብና አስቸጋሪ ሆኖ ነበር ያገኘው፡፡፡፡እስከዛሬ አንድ ሙሉ ድፍን ሀገር መስላ ትታየው የነበረችው ኢትዬጵያ በስነ-ልቦና ብቻ ሳይሆን በተግባርም እንዲህ የተከፋፈለች ብዙ ሀገር መሆኖን የተረዳው በዚህ ዝውውር ጉዳይ ነው፡፡ከአንዱ ክልል ባለስልጣኖች ወደ ሌላው ክልል ባለስልጣኖች ሲማላለስ ይሄም ጉዳይ በጣም አስደንግጦታል፡፡ለማንኛውም ከህግና ከመብት ይልቅ ገንዘብ ኃይል አለውና በገንዘቡ ኃይል የማይታሰብ ነው ያሉትን ጉዳይ እንዲያስቡበት….አይደረግም ያሉትን ነገርም እንዲያደርጉት አስገድዷቸዋል፡፡አሁን ዱከም ገብቷል ፡፡የዱከም ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆኖል፡፡ ዱከምን የመረጣት ለበቅል ተልዕኮው ስትራቴጂካላዊ ቦታ ነች ብሎ ስላመነ ነው፡፡አዲስአባ የከተመችውን ሮዝን ናዝሬት አዲስ ቤት ገዝቶ አዲስ ሚስት አግብቶ እየኖረ ያለውን ቀለምወርቅንና እዛው ዲላ መደበኛ ስራውን እየሰራ ያለውን የቀድሞ ጓደኛውን ኩማንደር ደረሰን ከዱከም እየተስፈነጠረ ለማጥቃት ይመቸኛል ብሎ መርጧታል አሁን ቤቱን ሸጦ አጠናቋል፡፡ለመስታወት የሚገባትን ደሞዝ ሰጥቷት ሸኝቷታል፡፡አሁን ያስፈልጉኛ ብሎ የመረጣቸውን የግል ዕቃዎች ሸክፎ ዝግጁ ሆኖ አጠናቋል፡፡አሁን የቀርው አንድ ነገር ቢኖር ይሄ ቀን መሽቶ ሲነጋ በለሊት ዕቃውን ጭኖ ከተማውን ለቆ ወደ ዱከም መፈትለክ ብቻ ነው፡፡ከዛ ቡኃላ ወደ ዲላ የሚመለሰው ሚስጥራዊ በሆነ መልክ እራሱን ቀይሮ ኩማንደር ደረሰን ለማጥፋት ብቻ ነው፡፡ ወደ ውጭ ሊውጣ ወይስ ትንሽ እቤት ልቆይ እያለ ከራሱ ጋር በመሟገት ላይ ሳለ ሞባይሉ ጮኸ፡፡አነሳው፡፡
‹‹ኄሎ››
‹‹ሄሎ..ማን ልበል?››
‹‹እኔ ነኝ ኩማንደር ..››
‹‹ይቅርታ አላወቅኩሽም ›››
‹‹ሄለን ነኝ››
‹‹እሺ ሄለን ሰላም ነሽ?››
‹‹አለውልህ..የት ነህ?››
‹‹እቤቴ ነኝ››
‹‹ነጻነት ሆቴል ካፌ ውስጥ ነኝ ያለውት፡፡ልትመጣ ትችላለህ?››
‹‹መቼ?››
‹‹አሁን እዛ መናፈሻ ውስጥ ቁጭ ብዬ እየጠበቅኩህ ነው››
‹‹እሺ መጣው›› ብሎ ስልኩን ዘጋውና‹‹ይቺ ጉድ የጉድ ልጅ ደግሞ ምን ልትለኝ ይሆን?››እያለ በማሰላሰል እቤቱን ቆልፎ ወደ ነገረችው ካፌ አመራ፡፡ሊያገኛት፡፡እዛ ሲደርስ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ስለሆነ ጨለም እያለ ነው፡፡
‹‹ሰላም ነሽ ሄለን?››.አላት እጁን ለሰላምታ እየዘራጋ እሷም የተቋጠረ ፊቷን ሳትፈታ የዘረጋውን እጁን እየጨበጠች፡፡‹‹ሰላም ነኝ ቁጭ በል››አለችው ፡፡ተቀመጠ፡፡
‹‹ምን ሆነሻል?››
‹‹ምን ሆንኩ?››
‹‹ጥቁር በጥቁር ለብሰሻል..የተፈጠረ ችግር አለ?››
‹‹ባክህ የአያቴ ወንድም ሞቶ ነው፤ ጥቁር የለበስኩት ግን ቀጥታ ለዛ አይደለም››
‹‹ታዲያ ለምንድነው?››
‹‹የአባቴን ማንነት የማወቅ ዕድሌን ይዞብኝ ስለሞተ ለእዛ ሀዘን ነው››
‹‹አልገባኝም››
‹‹እሱ የአባቴን ማንነት እንደሚያውቅ ነግሮኝ.. ማንነቱንም በማግስቱ ሊነግረኝ ቃል ገብቶልኝ በደስታ እየፈነጠዝኩ ሳለው ነበር ለሊቱን ሞቶ ያደረው››አለችው፡፡ለእሱ ልትነግረው አልፈለገችም እንጂ አጐቷ በበሽታው እንደሞተ ሳይሆን በሮዝ እጅ እንደተገደለ ነው የምታምነው..ለዚህም ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ባያደርጋትም አንድ ሁለት ጠቋሚ ማስረጃዎች አሏት፡፡ይሄንን ግን ለጊዜውም ቢሆን ለዚህ ኩማደር ልትነግረው እልፈገችወም፡፡
‹‹ሲያሳዝን ..ይቅርታ ለቅሶ ስላልመጣው፡፡ አልሰማውም ነበር››አላት
‹‹ግድ የለም ››
‹‹አይዞሽ እሱ ባይነግርሽም የአባትሽን ማንነት እናትሽ በቅርብ እንደምትነግርሽ እተማመናለው››
‹‹አይ… እኔ ደግሞ ካልተገደደች በስተቀር ትነግረኛለች ብዬ አላስብም››
‹‹ታዲያ እንዴት ማስገደድ ይቻላል? እኔ ምን ልተባበርሽ ?››
‹‹አሁን ወደ እዚህ ቀጥሬያት እየመጣች ነው፡፡አብራን እንድታየን እፈልጋለው፡፡››
‹‹እንዴ መጥታለች እንዴ?እዚህ ዲላ ነው ያለችው?››
‹‹አዎ መጥታለች..እራስህን ተቆጣጥረህ እሷ ስትመጣ ሰላም ትላትና ችላ ብለህ ከእኔ ጋር ታወራለህ፡፡ እንጫወታለን››
‹‹አይ ይሄ ምን ይጠቅምሻል?››
‹‹ይጠቅመኛል…አብረን እንደዛ ስታየን ምን እንደሚሰማት ፤ምንስ እንደምታስብ ታውቃለህ ፡፡አንተ እኔን የቀረብከኝ እሷን ለመበቀል እንደሆነ ታስባለች..እርግጠኛ ነኝ በጣም ነው ስሜቷን የሚነካው..ፍራቻ ውስጥ የምትዘፈቀው፡፡››
‹‹እኔ እንጃ …ብቻ ከእሷ ጋር በአንድ ጠረጵዛ ፊት ለፊት እየተያዩ መቀመጥ የምቋቋመው ነገር አይመስለኝም››
‹‹እራስህን የግድ መቆጣጠር አለብህ…በቀል ነው አይደል የምትፈልገው..በቃ ምንም ሳትለፋ እኮ ዕድሉን እያመቻቸውልህ ነው››
‹‹እሺ እንዳልሽ..ግን አንቺ በጣም እየገረምሺኝ ነው››
‹‹እንዴት? ››
‹‹አስተሳሰብሽ ሁሉ ከእድሜሽ በላይ ነው››
‹‹አዎ አንተ ብቻ ሳትሆን ብዙ ሰዎች በተደጋጋሚ እንደዛ ይሉኛል፡፡ ስራሽ እና ንግግርሽ ትልቅ ሰው በተደጋጋሚ አስጠንቷ የላከሽ እንጂ ከውስጥሽ የመነጨ አይመስልም ..ጠቅላላ ነገረ ስራሽ ተዓማኒነት የለውም ይሉኛል..፡፡ይታይህ እኔ ስጋና ነፍስ ያለኝ ህያው ፍጡር ነኝ አይደል? ታዲያ ልክ አንድ ልብ ወለድ መጽሀፍ ውስጥ እንዳለ ገጸ ባሕሪ ተአማኒነት የለሽም ብሎ ትርጉም የሌለው ነገር መናገር ምንድነው፡፡ ››
‹‹እውነታቸውን እኮ ነው የ18 ዓመት ልጅ ብትሆኚ እንኳን አስተሳሰብሽ ይገርማል››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው፡፡ግን እኔ አብዛኛውን ዕውቀቴን ከባለፈ ህይወቴ ይዤ የመጣውት ይመስለኛል፡፡››
‹‹ከባለፈው ህይወቴ ስትይ?››በመገረም ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ ከሁለት መቶ ወይም ሶስት መቶ አመት በፊት ሮም አካባቢ የምኖር ለፖለቲካው አለም እና ለስለላው ጥበብ በጣም ቅርብ የነበርኩ ሴት ነበርኩ፡፡አሁን ደግሞ ይሄው ዕጣ ፋንታዬ ሆኖ ዳግመኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ዝብርቅርቅ ባለ ሁኔታ ተወልጄ እንተ ፊት ለፊት ቁጭ ብዬለው››ብላ ከአዕምሮው በላይ ስለሆነ እና ቅዠት የበዛበት ነገር ነገረችው፡፡‹‹ይህቺ ልጅ እማ ትከሻዋ ላይ ተደላድሎ የተቀመጠ ከራማ አላት፡፡እሱ ነው እንደ እዚህ የሚያስቀባዥራት›› እያለ በማሰላለሰል ላይ ሳለ
‹‹እሺ ሄለን››የሚል የሚያውቀው.. ለዓመታት ሲያፈቅረው የኖረው አሁን ደግሞ እጅግ የሚጠላው ድምጽ ከኃላው ሰማ፡፡ አልዞረም የተቀመጠበት ቦታ ስሩ ባለው የጽድ ዛፍ ጥላ በጨለማ ስለተሸፈነ መልኩ በግልጽ አይታይም እንዳቀረቀረ ጸጥ አለ.፡፡
‹‹ከሰው ጋ ነሽ እንዴ?››እያለች ወንበር ስባ ከመሀከላቸው ተቀመመጠች፡፡
‹‹ጓደኛዬ ነው ተዋወቁ››አለቻት ሄለን
ሮዝም የሄለንን ግብዣ ተቀብላ እጆን ለሰላምታ እየዘረጋች ‹‹ሮዝ እባላለው የሄለን ……››ብላ ንግግሯን ሳታገባድድ አቆመች ፡፡የምታየው ፊት ፈጽሞ ያልጠበቀችው ነው፡፡
ኩማንደር የሮዝ ከገመተው በላይ መበርገግ እና መደንዘዝ አስደሰተውና ተነቃቃ እና መተወን ጀመረ‹‹ኩማንደር መሀሪ እባላለው ሄለን ስላንቺ ብዙ ጊዜ ታወራልኛለች .በእውነት ድንቅ ልጅ ነው ያለሽ››አለና አጥብቆ እጆን እየወዘወዘ ጨበጣት፡፡
‹‹እንዴት ግን ?››አለች ሮዝ
3👍2
ምትናገረው ጠፍቷት አንደበቷ እየተሳሰረባት፡፡
‹‹እንዴት ተዋወቃችሁ ለማለት ፈልገሽ ነው አይደል?፡፡ሄለን ምርጥ ጓደኛዬ ነች››አላት በፈገግታ
‹‹ጓደኛ..!!!አንተ እና እሷ?››
‹‹ምነው ወይዘሮ ሮዝ ችግር አለው እንዴ? ነው ወይስ የዕድሜ ልዩነታችንን አይተሽ ነው …ልጅሽ እኮ ዕድሜዋ ገና ቢሆንም አስተሳሰቦ ልዩ ነው..ስለዚህ እንደታናሽ እህቴም እንደ ሚስጥር ጓደኛዬም ነው የማያት››
ሄለን ከመሀሪ ንግግር ቀጥላ መናገር ጀመረች‹‹ዕድሜዬም ቢሆን እኮ ቀላል አይደለም፤ በሚቀጥለው ሳምንት 13 ዓመት ውስጥ እገባለው….እንደውም ዕድሜዬን በትክክል የምታውቂ መሆኑን እጠራጠራለው..ይታይህ ስታየኝ የ15 ዓመት ልጃገረድ አልመስልም? እየው እስቲ ጡቴን አጎጥጉጦ ከሎሚነት አልፎ ብርቱካን አክሏል… ደግሞ አይገርምህም የወር-አበባ ሁሉ እኮ አይቼያለው..ታዲያ ዕድሜዬን ካልተሳሳተች እንዴት 13 ዓመቴ ብቻ ይሆናል?››አለች ሄለን ፡፡ከተናገረቻቸው ውስጥ ሌሎች ነገሮች እውነት ቢሆንም የወር አበባ አይቼያለው ያለችው ግን ውሸቷን ነው፡፡ቢሆንም ንግግሯ ያሰበችውን ግብ መቶላታል..
ሮዝ ሰውነቷ ተርገበገበ ፡፡ከመቀመጫዋ ተስፈንጥራ ተነሳች፡፡ የሄለንን ክንድ ጨምድዳ ያዘቻት‹‹እንዴ !!ምን ነካሽ? አብደሻል እንዴ?››አለቻት ሄለን
‹‹ነይ እቤት እንነጋራለን.. ››ጎትታ ከመቀመጫዋ አስነሳቻት፡፡
በተረጋጋ ድምጽ‹‹እንዴ ወይዘሮ ሮዛ ችግር አለ እንዴ?››ብሎ ጠየቀ መሀሪ
‹‹ኩማንደር ፀጥ በልልኝ..ካንተ ጋር ንግግር የለኝም››አለችውና ሄለንን ባለ በሌለ ኃይሏ እየጎተተቻት የሰው ሁሉ አይን እንደተተከለባቸው ከካፌው ይዛት ወጥታ ወደቤት ይዛት ሄደች..፡፡ሄለን በሁኔታው የተከፋችና የተበሳጨች ታስመስል እንጂ በውስጧ ከፍተኛ ደስታ ነው የተሰማት፡፡አዎ አሁን ውስጧን ነቅንቃታለች፡፡እርብሽብሽ አድርጋታለች፡፡ለድርድርም ዝግጁ እንድትሆን አመቻችታታለች...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_አምስት
:
ድርሰት በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ኩማንደር መሀሪ የዱከም ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆኖ ስራ ከጀመረ አንድ ወር ተቆጥሯል፡፡ቀናቷቹ ሲቆጠሩ አንድ ወር አካባቢ ብቻ ይሁኑ እንጂ በተግባር ሲመነዘር ወይም ኩማደሩ የከወናቸውን ነገር ሚዛን ላይ ሲቀመጥ በጣም ብዙ ነው፡፡ከተማዋን ከተገመተው በላይ ፈጥኖ ተቆጣጥሮታል፡፡በከተማዋ ኑዋሪዎችም ስለ እሱ ማውራት በሹክሹክታም ቢሆን ጀምሯል፡፡ጨካኝነቱን፤ጉበኝነቱን እና ከተቋጠረ የማይፈታ ፊቱ መነጋሪያ ሆኖል፡፡ይህን ስለእሱ የሚነገሩትን ነገሮች ቀድሞ የሚያውቁት የዲላ ከተማ ኑዋሪዎች ቢሰሙ ሽንጣቸውን ገትረው ይሄማ የእሱ ባህሪ አይደለም ብለው እንደሚከራከሩለት የማይጠረጠር ነው፡፡ግን እውነታው አሁን ያለበት ሁኔታ ነው....የተለየ ሰው መሆኑ ነው፡፡
ዛሬ የእለት ስራውን አከናውኖ ከቢሮ ወጣና ወደ ምስራቅ ሆቴል በማምራት እራቱን በልቶ ወደ ቤቱ ጉዞ ሲጀምር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሊሆን አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው፡፡ቤቱ በመዘጋጃው ወደ ውስጥ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ሁለተኛው መንገድ ላይ ነው፡፡የሚኖረው ሙሉ ግቢ ለብቻው ተከራይቶ ነው፡ዘበኛ የለውም …የቤት ሰራተኛ የለው፡፡ብቸውን ይባል ብቻውን ይወጣል፡፡ወደ ቤቱ ሲቃረብ አንድ ዘመናይ ሴት የአጥሩን በራፍ ተደግፋ ስትጠብቀው ተመለከተ.. ጨለማው በላይዋ ላይ ስላጠላባት ፊቷን ማየት እና ማንነቷን መለየት አልተቻለውም፡፡በዚህ ሰዓት በራፉን የሙጥኝ ብላ የምትጠብቀው ይሄኔ ባሏ ደብድቦ ያበረራት ሴት ትሆናለች..ታዲያ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በማቅናት ፋንታ ምን ወደ ቤቱ አስመጣት..?ምን አልባት እቤት በመምጣቷ በሀዘኔታ የተለየ የህግ ድጋፍ ያደርግልኛል ብላ አስባ ይሆን..?ይህን እና የመሳሰሉትን ሀሳቦች እያሰበ ተጠጋት …ሲጠጋት ለያት ..ሲለያት ደግሞ ደነገጠ..በጣም ደነገጠ ፡፡ከዛም አልፎ ግራ ተጋባ ፡፡ወደኃላ ይመለስ ወይስ ወደ ፊት ይቀጥል… .?፡፡ሽጉጡን ያውጣ ወይስ ትንሽ ትእግስት ያድርግ...?አንዱንም ነገር ሳይወስን ስሯ ደረሰ..ከኪሱ ቁልፉን በማውጣት ከፈተና ገባ..ከመዝጋቱ በፊት ጀርባውን ታካው ተከትላው ገባች፡፡የውጩን በራፍ ቆለፈውና ..ወደ ውስጥ በመዝለቅ የሳሎኑን በራፍን ከፍቶ..ወደ ውስጥ ገባ፡፡በራፉን ክፍት ትቶ አልፎ ወደመኝታ ቤቱ አለፈ፡፡እሷ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባችና ሳሎንና ባገኘችው ወንበር ተደላድላ ተቀመጠች፡፡ውስጧ ግን አሁንም ትርምስምስ እንዳለ ነው..በሽብር እና በፍራቻ መካከል የተደበላለቀ ውጥንቅጡ የወጣ ስሜት፡፡
መሀሪ ለብሶት የነበረውን የደንብ ልብሱን በቢጃማ ቀይሮ ትንሽ የጐደለለት የውስኪ ጠርሙስ ከሁለት ብርጭቆ ጋር ይዞ ብቅ አለ፡፡በሁለቱም ቀዳና አንዱን አቀብሏት የራሱን ይዞ ከፊት ለፊቷ ባለው ወንበር ተቀመጠ፡፡
‹‹መቼስ ውስኪ ቤት የከፈትሽው የውስኪ አድናቂ ስለሆንሽ ነው ብዬ ነው ውስኪ የጋበዝኩሽ››
‹‹አመሰግናለው…››አለችው እና ከሰጣት ብርጭቆ አንዴ ጠቀም አድርጋ ተጐነጨችለት፡፡
‹‹እራት እንዳልጋብዝሽ ቤቴ ውስጥ የምግብ ዘር የለም››
‹‹በልቼ ነው የመጣውት››
‹‹አይ አሪፍ ነው››
‹‹ትቀበለኛለህ ብዬ ገምቼ የነበረው በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አልነበረም››
‹‹እንዴት ነበር የጠበቅሽው.?››
‹‹እኔ እንጃ ብቻ እቤቴን ማን አሳየሽ ብለህ የምትጮኀብኝ…ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ ብለህ የምታንቧርቅብኝ….ከበራፍህ ገፍትረህ የምታባርረኝ..ብዙ ብዙ መጥፎ ምላሾችን ካንተ እንደምቀበል እያሰብኩ ነው የመጣውት፡፡››
ያሰብሻቸውን ነገሮች ሁሉ ያላደረግኩት ላደርጋቸው ሳልፈልግ ቀርቼ ..ወይም ባንቺ የደረሰብኝን በደል ዘንግቼው ሳይሆን ስላልተዘጋጀውበት ነው ፡፡አመጣጥሽ ፍጹም ድንገተኛ እና ያለሰብኩበት ስለነበረ ደንግጬ ነው፡፡ግን የገረመኝ አንቺ የምትይውን ያህል የተጨነቅሽ እና ወደ እኔ መምጣት የፈራሽ ከሆነ ምን አስመጣሽ..አትቀሪም ነበር፡፡››
‹‹ቀን እጅህ ላይ ቢጥለኝ. ..ቢጨንቀኝ ነው ››
‹‹አልገባኝም… ጉዳይሽ እኔ ጋር እንድትመጪ የግድ አስገድዶሽ ቢሆን እንኳን በቀን ሰው ባለበት ቦታ ጠብቀሽ ልታነጋግሪኝ ትችይ ነበር፡፡እንዴት በዚህ ጨለማ ለዛውም ማንም በሌለበት በቤቴ ለመምጣ ደፈርሽ…?እኔ እኮ ቀን ሲገጥምልኝ ሁኔታዎች ሲመቻቹልኝ በእርግጠኝነት ልገድልሽ ወስኜ ያለው ሰው ነኝ ››
‹‹አውቃለው… እኔም ለዛው ነው በጨለማ ማንም ሳያየኝ እቤትህ ድረስ ሹልክ ብዬ የመጣውልህ››
‹‹አልገባኝም? ምነው ..እራሴን ከማጠፋ እሱ ጋር ሄጄ ያጥፋኝ ብለሽ ነው?››
‹‹አረ እኔማ በጣም መኖር እፈልጋለው….
ግን ግን..!!!››ብላ ተንደርድራ ተነሳችና ጉልበቱ ላይ ተደፋችበት ንግግሯን ቀጠለች ‹‹ ይሄው እንደፈለግክ አድርገኝ መሞት ይገባታልም ካልክ ይሄው አሁኑኑ ግደለኝ..ስጋዬን ቦዳድሰህ ጣለው..ግን እባክህ ልጄን ተውልኝ..እሷን በመጉዳት እኔን ለመበቀል አትሞክር ያ ለአንድ እናት ምን ያል አስቸጋሪና ልትቋቋመው የማትችለው ነገር እንደሆነ እባክህ ይግባህ››
‹‹ተነስተሸ ወደ ቦታሽ ተመለሺና እንነጋገር››
‹‹እንድነሳ …እኔ ላይ ያነጣጠረው የበቀል ጦርህ እሷ ላይ እንደማይሰካ ትንሽ ተስፋ ስጠኝ ››
‹‹መጀመሪያ ተነሺ …ከዛ እንደራደራለን፡፡››
‹‹እሺ በፈለከው መንገድ በህይወቴም ቢሆን እደራደርሀለው፡፡››ብላ በዝግታ ተነሳችና ወደ ቦታዎ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡ብርጭቆዋን አነሳችና በአንዴ አጋባችው፡፡ጨምሮ ቀዳላት፡፡
‹‹እሷ ንግግሯን ቀጠለች‹‹ እባክህ ልጄን ከደበቅክበት አውጣና ስጠኝ ..እናቴ ልታብድ ነው በለቅሶ ብዛት አይኖቾ ሊጠፋ ነው..እባክ መልስልን…አባክህ …በፈጠረህ››

‹‹አይዞሽ ደህንነቷ በጣም በአስተማማኝ ሁኔታ እየተጠበቀ ነው ፡፡ደህና እንደሆነች ደግሞ ደግማ ደጋግማ ለእናትሽ እየደወለች እያናገረቻው መሰለኝ?››
‹‹ወይኔ ጌታዬ እንደፈራውት ባንተ እጅ ላይ ነች ማለት ነው ፡፡ምን አይነት ጨካኝ ነህ ?፡፡ልጄን በምን ዓይንህ አየህብኝ እኔ እያለውልህ..አንገቴን በቆንጨራ ቆራርጠህ እኮ ለውሻ መስጠት ትችል ነበር..ግንባሬን በሽጉጥ መፈርከስም ትችል ነበር..ያም ካላረካህ ሆዴን በሳንጃ ዘንጥለህ አንጀቴን ጐልጉለህ ማውጣት ትችል ነበር..ያስቀየምኩህ ፤የበደልኩህ፤እኔ..ልጄ ምኑም ውስጥ የለችበትም እኮ!!!››
‹‹ከምኑም እንደሌለችበት አውቃለው ፡፡ግን ባጋጣሚ ሲፈርድባት ካንቺ መሀጸን ወጣች…አየሽ አንድ የምትጠይውን ሰው ለመበቀል ቀጥታ ሰውዬው ላይ አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጥቃት ከማድረስ ይልቅ የዛ ሰውዬ ምርጥ የሆኑ ነገሮችን መንጠቅ ይበልጥ በቀልሽን ፍሬያማ እንደሚያደርግ ማወቅ አለብሽ››አላት ዘና ብሎ መጠጡን እየተጐነጨ፡፡
ሮዝ ፊት ለፊቱ በሽንፈት አንገቷን ደፍታ ሞራሏን አንኮታኩታ ሲያያት ውስጡ በእርካታ ተጥለቀለቀ፡፡ ይህ ሁሉ ግ በእሱ ጥረት እና ብቃት የመጣ ድል ሳይሆን በሄለን እስትራቴጂ ውጤት ነው፡፡ሄለን ከቤት እንደጠፋች ያውቃል ፡፡ምክንያቱም በየቀኑ እየደወለች የቀን ውሎዋን ትነግረዋለች ግን ያደረገችውን ሁሉ ያደረገችው በእሱ ተገዳ ወይም ታፍና ሳይሆን በራሶ ሙሉ ፍቃድና ዕቅድ ነው፡፡ቢሆንም የሮዝን ውንጀላ አልጠላውም ..እንደውም በተቃራኒው ተመችቶታል ምክንቱም እንደእዛ ማሰቧ ብቻ በእሷ ላይ የበላይነት እንዲኖረው ያግዘዋል፡፡
ሰዓቱን ተመለከተ ሶስት ሰዓት አልፎል፡፡‹‹አሁን መሸብስ ሂጂና ነገጥዋ ሁለት ሰት አካባቢ ተመልሰሽ ነይ እኔም እስከዛ ተረጋቼ ላስብበት ከልጅሽ እንድርቅ ልጅሽን እንድተውልሽ ከፈለግሽ እንደእዛ ባደርግ አገኝ የነበረውን እርካታ የሚያካክስ ነገር ካንቺ ማግኘት እፈልጋለው እንግዲህ ጥያቄው
👍5
ያ ነገር ምድነው የሚለው ነው..እና ላስብበት..የተገለፀልኝን ጥዋት እነግርሻለው››
እሺ ግን እባክህ አንዴ በስልክም ቢሆን አገናኘኝ››
አሁን አልችልም ጥዋታ ግን ከተስማማን ከእነአካሏ አስረክብሻለው››ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ፡፡እሷም ውጪልኝ ማለቱ እንደሆነ ገባትና ተነስታ በዝግታና በቀሰስተኛ እርምጃ እየተራመደች ወጥታ ሄደች ማንገር ብቻውን ምን ያደርጋል..እንደእዛ እንድታደርግ በአንተ ተገዳ እንደሆነስ ..ድምጾን ስለሰማን ብቻ እንዴት መረጋጋት ይችላል ብለህ ታስባለህ…ምላሶን እና ንግግሮን አትይ አንድ ፍሬ ልጅ እኮ ነች እባክህ እንዳትጎዳት ብላው በከፈተላት በር ወታ ሄደች።
:
ሮዝን ከቤቱ ሸኝቶ በሩን ከዘጋጋ ቡኃላ ወዲያው ሞባይሉን አነሳና ሄለን ጋ ደወለ፡፡ይሄንን ቁጥር እሱ ብቻ ነው የሚያውቀው…፡፡አያቷ እንኳን አታውቀውም፡፡ከአምስት ጥሪ ቡኃላ ተነሳ
‹‹ሄሎ ኩማንደር››
‹‹ሄሎ ሄለን ››
‹‹አለውልህ››
‹‹ለመሆኑ የት እንደሆንሽ ዛሬም አትነግሪኝም?››
‹‹አይ ያለውበት ቦታ ሚስጥር ነው.. ግን ከተማ ውስጥ ያለው እንዳይመስልህ፡፡አንድ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ነኝ ያለውት፡፡ የዚህች መንደር ኑዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ሀገራችን በረሀብ በጣም እየተጠቁ ካሉት ማህበረሰብ እንደማሳያ የሚሆኑ ኑዋሪዋች ያሉበት ነች፡፡›››
‹‹እንዴ ታዲያ ልዝናና ብለሽ ወጥተሸ ረሀብ ካጠቃው መንደር ምን ወሰደሽ?››
‹‹አጋጣሚ ነው የወሰደኝ..››
‹‹ምን አይነት አጋጣሚ?››
አንድ በጣም የምወዳት ጐደኛዬ ነበረች…ወላጆቾ ከብዙ ጊዜ በፊት ይፋቱና ልጆን ከአባቷ ጋር ጥላ ወደ ቤተሰቦቾ ጋር ከዲላ 400ኪ.ሜትር ወደምትርቀው አሁን ወደምገኝባት መንደር በመሄድ ሌላ ኑሮ መስርታ… ሌላ ባል አግብታ ሌሎች ልጆች ወልዳ መኖር ትቀጥላለች..የት ብትለኝ አሁን ማንነቷን ልነግርህ የማልፈልገው መንደር ውስጥ…ታዲያ ይቺ ጓደኛዬ ሰሞኑን ስለዚህ በረሀብ የተጠቃ መንደር ዜና እጆሮዋ ይገባል ..የእናቷ ጉዳይ በጣም አሳሰባት..አማከረችኝ እኔም አጋጣሚውን ተጠቅሜ አብሬት ሄድኩ..ከዲላ 400ኪ.ሜ አካባቢ ርቄ ማለት ነው፡፡ግን ምነው ባልመጣው የሚያሰኝ ነገር ነው የገጠመኝ››
‹‹ምን ገጠመሽ?››
‹‹ምን ገጠመሽ ትላለህ…?.እዚህ እኮ ከ ህዝቡ መካከል የሚበላው ምግብ ሳይሆን የሚያሸተው ምግብ የናፈቀው ቤተሰብ አለ..ሰዉ በጣም እየተጐዳ ነው….››
‹‹አንቺ ልጅ በዕድሜሽ ልክ አስቢ..ከአቅምሽ በላይ ስለሆኑ ነገሮች ስትጨናነቂ ጭንቅላትሽ እንዳይበታተን››አላት ሁኔታዋ እንደከዚህ ቀደሙ ግራ አጋብቶት፡፡
‹‹የሆነ ነገር ለማሰብ እኮ የዕድሜ ርዝመት ብቻውን በቂ አያደርግም..ብዙ የዕድሜ ባለጸጋዎች ከማሰብ ዕዳ ነፃ ናቸው…፡፡እንደውም ልንገርህ እንደ እኔ ትዝብት ሰው እሳት ወደሚንቀለቀልበት የጦር ሜዳ ከመዝመት ይልቅ..ወደ ውስጡ ዘልቆ የሆነ ጠንከር ያለ በሀሳብ ማሰላሰል ያስፈራዋል ፡፡በዚህ የተነሳ 99 ፐርሰንቱ የሰው ልጅ ማሰብ ሲሸሽ ነው የሚኖረው….እኔ ደግሞ ሲፈጥረኝ ማሰብን እንድፈራ ሳይሆን እንድደፍር ሆኜ ነው…ሰዋች በእኔ ግራ የሚጋቡት እነሱ ለማሰብ ዕድሜ ልካቸውን ሲፈሩት የኖሩትን ነገር እኔ በዚህ ዕድሜዬ በድፍረት ማሰብ ስለጀመርኩ ነው››
‹‹አይ አንቺ..ማሰብሽ ጥሩ ነው..ግን ምን ታደርጊዋለሽ እግዚያብሄር ጨከነብን››
‹‹ተው ተው ..ከእግዚያብሄር ላይ ወረድ በል....እንዴ!!! ይህቺ ሀገር እኮ ለ11 ተከታታይ ዓመት ከ11 ፐርሰንት በላይ አድጌያለው ከችግር አረንቋ እያመለጥኩ ነው ብላ ለህዝቦቾ፤ ለአለም መንግስታት እንዲሁም ለሰማዩ መንግስትም ሪፖርት አድርጋለች፡፡ታዲያ ያን ሪፖርት ተመልክተው ‹አይ እነዚህ ሰዎች በሀገራቸው ድርቅ ቢከሰትም ለረሀብ አይዳርጋቸው..ይሄን ያህል ዓመት ሙሉ በዚህን መጠን ሲያድጉና ሲመነደጉ ቆይተው አሁን የገጠማቸውን የምግብ ዕጥረት በራሳቸው ጥሪት ይወጡታል› ብለው አስበው ዝም ቢሉን ምኑ ይገርማል››
‹‹ይሁንልሽ.. ለመሆኑ አሁን አንቺ ምን እየሰራሽ ነው?››
‹‹አጐቴ ከመሞቱ በፊት የተወሰነ ብር ሰጥቶኝ ነበር ..እና እኔም በአቅሚቲእዚህ በጓደኛዬ እናት መንደር ኑዋሪ ለሆኑት ቀን ለጣላቸው ችግረኞች 100 ኩንታል ስንዴ ገዝቼ በነፍስ ወከፍ እንደቤተሰብ ብዛት ከ25- 50 ኪ.ግ ኩንታል ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እያደልኩ ነው..መንግስት ገዛውት የለውን ስንዴ በሙከራ ባቡር ከጅቡቲ አጓጉዞ እስኪደርስላቸው ድረስ ለአንድ ወር እንኳን ቢያቆያቸው ብዬ ነው..››
‹‹እየቀለድሽ ነው?››
‹‹እውነቴን ነው..እንደውም አያቴ አትፈቅደልኝም እምጂ አጐቴ ያወረሰኝን ጠቅላላ ንብረት አዲስ አበባ ያለውን ቤትም ሆነ መኪናዋንም ሸጬ ለዚሁ ተግባር ባውለው ደስ ይለኛል…አንተም ያቅምህን ያህል ብር ብትለግሰኝ ለእነዚህ ሰዎች አውለው ነበር፡፡አየህ ከችግር ሁሉ አስከፊው ችግር አንደኛ ጦርነት ወይም የሰላም እጦት ነው..ከዛ የባሰው ደግሞ የጤና መጐደል እና በሀይለኛ ህመም መሰቃየት ነው..ከሁሉም ምድራዊ መከራዎች የሚበልጠውና አስጠሊታው ግን ረሀብ ነው፡፡ረሀብ የመጨረሻው የሰው ልጅ የመከራ ቀንበር ነው፡፡››
‹‹በቃ ሌላ ወሬ ላውራልሽ››
‹‹እሺ ቀጥል››
‹‹ሴትዬዋ አሁን ቤቴ መጥታ ነበር››
‹‹የቷ››
‹‹ሮዝ ነቻ››
‹‹ምን ልትፈጥር››
‹‹አንቺን ያገትኩባት መስሎት እንዳልጐዳሽ ልትለምነኝ››
‹‹ታዲያ ምን አልካት?››
‹‹በምለው ነገር ከተስማማሽ አልጐዳትም አልኮት››
‹‹አንተ አሁን ትክክለኛ የበቀል ሰው እየሆንክ ነው..እኔስ እኔ አላየዋትም ትላለህ ብዬ ነበር የገመትኩት››
‹‹ተንኮል ከእናትሽ እና ካንቺ ነው የተማርኩት››
‹‹ይሁንልህ…. እና ታዲያ ምን አሰብክ?››
‹‹እኔ እንጃ ለመደራደራደር ለነገ ጥዋት ሁለት ሰዓት አካባቢ ቀጥሬያታለው››
‹‹በቃ አሁን ተኛና አስራ ሁለት ሰዓት እንደዋወል..የሆነ አሪፍ ነገር ሳስብ ልደር››
‹‹እሺ ካልሽ››
ስልኩን ዘጋና..ብርጭቆውን እንደያዘ ወደ መኝታ ቤቱ አመራ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ስድስት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ጥዋት ነጋ አልነጋ ብላ ቀድማ የደወለችው ሄለን ነች
‹‹ከእንቅልፍህ ቀሰቀስኩህ እንዴ?››
‹‹አዎ ለሊቱን ሳስብ ስላጋመስኩት አሁን ጭልጥ ያለ እንቅለልፍ ወስዶኝ ነበር›››አላት ሙሉ ለሙሉ ከእንቅልፍ አለም ለመውጣ እየታገለ፡፡
‹‹የሀሳቤን ውጤት ልንገርህ››
‹‹እየሰማውሽ ነው››
‹‹ሴትዬዋን ሁለት ነገር እንድትከውንልህ ተደራደራት››
‹‹የትኛዋ ሴትዬ?››
‹‹ስለማን ነው በዚህን ሰዓት ለማውራት የተቀጣጠርነው የድሮ ፍቅረኛህን ነዋ ››
‹‹እሺ ምን እንድታደርግልኝ ልጠይቃት፡፡››
‹‹አንድ ለእኔ ..እንድ ላንተ ፡፡ለእኔ የአባቴን ማንነት እስከ ሙሉ ታሪኩ በድምጽ ቀድታ እንድታስረክብህ..ሁለተኛው ያው አንተን የከዳችህ ከጐደኛህ ጋር ተመሳጥራ አይደል አሁን ደግሞ ከንተ ጋር ተማሳጥራ እሱን እንድታጠፋው ..እንድታጠፋው ስልህ እንድትገድለው ማለቴ አይደለም..በቃ ያለውን ነገር ሁሉ እድትሳጣው..ባዶውን እንድታሰቀረው.. ስራውንም ጭምር እንዲያጣ ..ከዛም አልፎ እንዲታሰር ብታደርገው ጥሩ ነው፡፡እሾህን በሾህ ይሉሀል ይሄ ነው፡፡››
‹‹ከዛስ?››
‹‹ከዛማ ምን ትፈልጋለህ እኔን ታስረክባታለህ..አንድ ሰው ብቻ ነው የሚቀርህ የእንጀራ አባትህን
እንዴት መበቀል እንዳብህ ብቻ ይሆናል ብቸኛ ጭንቀትህ››
‹‹ ምን ነካሽ …?እሺ እንዳልሽው ኩማደሩን እሷ ተበቀለችልኝ ..እሷንስ ?››
‹‹እሷን በእነዚህ ሁለት ጉዳዬች ተስማምታ ተግባራዊ ካደረገች..ተበቀልካት ማለት ነው..ይበቃታል፡፡››
‹‹ይበቃታል?››
‹‹አዎ ይበቃታል፡፡››
‹‹ምነው ለእናትሽ ማዘን ጀመርሽ እንዴ?››
‹‹በፊትም እኮ አባቴን አልነግር ስላለቺኝና እንደህጻን ልጅ ልይሽ ስለምትለኝ ነው የምጣላት እንጂ ልክ እንደአንተ የመረረ ጠላቴ ሆና አይደለም ፡፡ለማኛውም ቻው የደረስክበትን ደውለህ አስታውቀኝ፡፡ ››
‹‹እሺ ለማንኛውም በስልክም ቢሆን አገናኘኝ እያለችኝ ስለሆነ ስደውልልሽ ..እንደታገተ ሰው እየተወንሽ ታወሪያታለሽ››
‹‹ይመችህ››ብላ በሀሳቡ በመስማማት ስልኩን ዘጋችበት፡፡
እሱማ ከመኝታው ወጥቶ ልብሱን ለበሰና ከሮዝ ጋር ለሚያደርገው ድርድር መዘጋጀት ጀመረ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ኩማንደር መሀሪ ዛሬ ጠንከር ያለ ስራ ይጠብቀዋል፡፡ከመከላል ወደ ማጥቃት የሚሸጋገርበት ቀን ነው፡፡በተለይ ቀለም ወርቅን በተመለከተ፡፡እርግጥ ሌሎቹንም አረሳቸውም…፡፡እርስ በርስ አቋላልፎቸዋል..፡፡
ሮዝ ኩማንደር ደረሰን እንድታጠፋው በድርድር ተስማምተዋል…ተስማምተውም ግን አላመናትም፡፡ በቅርቧ የሚገኝ ሰው እንዲከታተላት አስቀምጦባታል፡፡እርግጥ አሁን እንድትከታላት የመደባበትን ልጅ በቀላሉ አላገኛትም…ሌሎች ብዙ ሰዎችን ከሞከረ ቡኃላ ነው እሷን ያገኘው..አጋጣሚው ደግሞ ያገኛት እሷ ራሷ በሮዝ ላይ ቂም የቋጠረች መሆኖ ነገሩን ቀላል አድርጎለታል፡፡ልጅቷ ሮዘ ውስኪ ቤት በአስተናጋጅነት የምትሰራ ነች፡፡ልጅቷ ሮዝን የተቀየመቻት ምታፈቅረውን ልጅ ..ሚረዳትን ልጅ…ስለተኛችባና እና ስለነጠቀቻት ነው፡፡ልጅቷ በልጁ ላይ የጠለቀ ፍቅር ነበራት ተብሎ ባይደመደምም እሱ ላይ ያላት ተስፋ ወደፊት ያገባኝ ይሆናል ብላ ስታስብ መኖሯ ግን ነገሩን እንደ ትልቅ በደል እንድትወስደው አድርጐታል፡፡ልጅቷ በተገናኙበት ወቅት ለእሱ እንዳጫወተችው ከሆነ የነገሩን መከሰት እንዳወቀች‹ ምን አልባት የእኔ መሆኑን ሳታውቅ ይሆናል አልጋዋን ያጋራችው› ብላ ተስፋ በማድረግ አናግራት ነበር ሮዝን…፡፡.ነገሩ አስደንግጧት ይቅርታ ጠይቃት ልጁን እንደምትተውላት ተስፋ በማድረግ..››ከሮዝ ያገኘችው መልስ ግን ከጠበቀችው በተቃራኒው ነው፡፡
ከትከት ብላ የሹፈት ሳቅ ከሳቀችባት ቡኃላ ‹ወንድ ማለት እኮ ፈረስ ነው፡፡ ፈረስ ደግሞ ግልቢያ የሚችል እና የመጋለብ ፍቅር ያለው ሰው ሁሉ እንዲጋልበው የተፈጠረ እንስሳ ነው..፡፡ካማለሉሽ እና ከተመኘሻቸው እኔ ምጋልባቸውን ወንዶች ሁሉ እያሳደድሽ መጋለብ ትችያለሽ››ብላ ነበር የመለሰችላት፡፡ልጅቷም ታዲያ ከመጀመሪያ ድርጊቷ ይልቅ የመለሰችላት መልስ ውስጧን አቆሰላት፡፡በወቅቱ የሰከረች አስመስላ ግንባሯን በቢራ ጠርሙስ ፈርክሳት ለመሄድ አስባ ነበር ቡሃላ ዋል አደር ስትል ሀሳቧን አስተካከለች…ለኑሮዋ ጓጓች ..የምትደጉማቸውን ቤተሰቦቾን አስቀደመች እና ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ጥላ አንገቷን ደፍታ ስራዋን አርፋ መስራት ጀመረች..ዳሩ ግን አድብቶ የቀረባት ኩማንደር መሀሪ የተቀበረ ብሶቷን ቆስቁሶባት ተባባሪው አደረጋት..አሁን ይህቺ ልጅ ነች ሮዝ በስምምነታቸው መሰረት አየተንቀሳቀሰች መሆኑን እና ያለመሆኑን የየእለት እንቅስቃሴዋን እና ተግባሯን እየተከታተለች ሪፖርት የምታደርግላት፡፡
ቀለመወርቅንም በሰላዬች ካስከበበው ወራቶች አልፈዋል፡፡የቤት ሰራተኛው፤ ዘበኛው እና የሚስቱ ሹፌር የእሱ ጆሮዎች ናቸው፡፡እሱ ላይ ትኩረቱን ጫን ያደረገው ዋና ጠላቱ ስለሆነ ነው፡፡ እናቱን ያሳጣው፤ ንብረቱን የዘረፈው ዋና ጠላቱ..አንዱ የዘለለውን መረጃ አንዱ እንዲነግረው ነው ሰላዬቹን በእሱ ዙሪያ ማብዛቱ ..፡፡የእዛ ፍሬ ታዲያ ዛሬ ማጨድ ሊጀምር ነው፡፡ለዚህም አንድ ሳምንት ሙሉ ሲሯሯጥ ነው የከረመው..አሁን ከጥዋት ጀምሮ ሲጠብቀው የነበረው ስልክ …ተደወለለት
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ ክፍሎም››
‹‹ኩማደር አሁን ልንነሳ ነው››
‹‹ጥሩ ነው ዕቃውን እንዳልኩህ በቦታው አስቀመጥክ ? ››
‹‹አዎ አስቀምጬያለው››
‹‹በቃ ልክ ደብረዘይት ስትደርሱ ሚስኮል አድርግልኘኝ››
‹‹እሺ ኩማንደር››
‹‹መኪናዋ ባለፈው ያሳየኸኝ ነች አይደል?››
‹‹አዎ እሷው ነች፡፡ ››
እሺ በቃ ደህና ሁን ››ብሎ ስልኩን ዘጋና ዝግጅቱን ቀጠለ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ከረፋዱ አራት ሰአት ተኩል ሲሆን ስልኩ ላይ ሚስኮል ስለመጣለት ሽጉጡን ታጠቀና ቢሮውን ለቆ ከግቢው ወጥቶ በታክሲ ወደ ከደብረዘይ መውጫ ተጓዘ..ራዳር ጭፈራ ቤት ጋ ሲደርስ ወረደና መኪናዋ መጠባበቅ ጀመረ..፡፡ብዙም አላስጠበቀችውም፡፡፡፡አይጥማ ቀለም ያላት ቢታራ ስራቸው ለመድረስ 20 ሜትር ሲቀራት እንድትቆም ምልክት ሰጣት ኩማደሩ ፡፡ሹፌሩም የተደናገጠ በመምሰል አስፓልቱን ለቆ ጥጉን አስያዘ እና አቆመ
‹‹አቤት ጌታዬ ምን አጠፋው?››በመስኮቱ አንገቱን ወደውጭ አስግጐ ጠየቀው
‹‹ጥቆማ ደርሶን ነው …ሁለታችሁም ከመኪናዋ አንዴ ብትወርዱ››
ሁለቱም ወረዱ..
‹‹መኪናዋን እስክፈትሽ ባላችሁበት ቁሙ››ብሎ ለፍተሸ ወደ ሚካናዋ ውስጥ አመራ...ሴትዬ ነች ብሎ የገማታት 30 ዓመት እንኳን የማይሞላት ብስል ቀይ በጣም ቆንጆ የምትባል ወጣት ሆና ስላገኛት ተገርሞል..‹‹ይሄ ሙትቻ ሽማግሌ እንዴት አድርጐ አሳምኖ ነው ሚስቱ ሊያደርጋት የቻለው?›› ሲል በውስጡ እያልጐመጐመ ፍተሻውን ቀጠለ
‹‹ይቅርታ ጌታዬ ያጠፋነው ነገር አለ?››አለችው በሚያምር ድምጽ ቃና …የሆነ ነገር ውስጡን እርብሽብሽ አደረገው፡፡
‹‹እሱን እንግዲህ ከፍተሸ ቡሃላ ነው የምናውቀው..ጥቆማ ደርሶኝ ነው››
የምን ጥቆማ? ››
‹‹ህገ ወጥ ዕቃ በመኪናዋ ውስጥ እንዳለ..››ብሎ መፈተሹን ቀጠለ..ከመቀመጫው ስራ አንድ ጥቁር ፔስታል መዞ አወጣ ፡፡ከፈተና አየው፡፡
‹‹አዝናለው የእኔ እመቤት.. ጥቆማው ትክክል ነው…ሶስት የእጅ ቦንብ እዚህ ፔስታል ውስጥ ይታየኛል፡፡››
‹‹የእጅ ቦንብ? አይደረግም፡፡ እኔ መኪና ውስጥ የእጅ ቦንብ?››ተንደርድራ መጥታ ቀረበችውና በዓይኖ አይታ አረጋገጠች፡፡ኩማንደሩ ቦንቡ በመንገድ የሚተላፉ ሰዎችን ቀልብ እንዲሰብ ስላልፈለገ ቦንቡን ከፔስታሉ ውስጥ ለማውጣት አልፈለገም፡፡
👍41
ይህማ የዚህ ቀሺም ሹፌር ስራ ነው››
‹‹አንተ ይሄን ከየት ነው የመጣኸው?››ብላ ዞር ስትል ሹፌሩ በአከባቢው ድራሹም የለ
‹‹እንዴ ኩማንደር አረ ሹፌሩ የለም››
‹‹ቀና ብሎ ዙሪያውን ቃኘ‹‹ወዴት ተሰለበ?››ጠየቃት
‹‹ምናባቱ አውቅለታለው…አየህ ስራው ስለሆነ ነው ተፈትልኮ የጠፋው ….የትም አይርቅም ፖሊሶቹን አሰማራ.. አሰሳ ቢያደርጉ አሁኑኑ ያገኙታል››
‹‹ተይው የትም አይርቅም… አሰሳ ማድረጉ ቡዙም አስፈላጊ አይደለም››
‹‹ለምን አይደለም?››
‹‹እኛ የምንፈልገው ዋናውን የመከናውን ባለቤት ነው…እሱ እኮ ቅጥረኛ ነው..ማንነቱን አጣርቶ የመቅጠር ሀላፊነቱ የባለቤቱ ነው፡፡ከፈለግነውም በአድራሻው መሰረት ፈልጐ የማቅረቡ ሀላፊነት የባለቤቱ ነው፡፡
‹‹ምነው ኩማንደር ..ባለቤቱ ባለቤቱ አልክ .. ?የመኪናዋ ባለቤት እኮ እኔ ነኝ››
‹‹ጥሩ ነው እንኳንም ሆንሽ..በይ አሁን ግቢና ወደፖሊስ ጣቢያ እንሂድ››
‹‹ፖሊስ ጣቢያ ኸረ በፈጠረህ ..እኔ እንደ ፖሊስ ጣቢያ በህይወቴ የሚያስጠላኝ ቦታ የለም ››
‹‹ያ በመሆኑ አዝናለው … አሁን ግን መሄዱ ብሎም መታሰሩ የግድ ነው፡፡ምክንያቱም በመኪናሽ ውስጥ ይዘሽ እየተንቀሳቀስሽ ያለሽው ነገር በጣም ከባድ ነው፡፡ምናልባት አዲስ አበባ የመንግስት ተቋሞችን..ምን አልባት የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ቢሮ..ምን አልባት ፓርላማውን..ምን አልባት አዲሱን ባቡራችንን ለማውደም ይሆናል እያጓጓዝሽ ያለሽው››
‹‹እንዴ!! አረ በፈጠረህ..አሁን እኔ እንደዛ የማድረግ ብቃት ያለኝ ሰው መስልሀለው?››
‹‹የሰው ማንነት በምርመራ እንጂ በመልክ መች ይታወቃል ብለሽ ነው..ለማኛውም ግቢና እንጓዝ››
‹‹መሾፈር አልችልም››አለችው በብስጭት እና በልመና መካከል ባለ ስሜት
‹‹እሺ እኔ እችላለው››ብሎ በሹፌሩ በኩል ዞሮ በራፉን ከፍቶ ገብቶ መልሶ ዘጋው
‹‹ግቢ›› አላት፡፡ እየተንቀጠቀጠች ገብታ ዘጋችው…ቁልፉን አሽከረከረ እና ሞተሩን አስነሳው ..ማሽከርከር ጀመረ
ስልኮን አወጣችና መደወል ስትጀምር‹‹ለጊዜው ስልክ መደወል አትችይም››አላት
‹‹እንዴ!!! ባለቤቴ ጋር እኮ ነው ያለውበትን ሁኔታ ደውዬ ማሳወቅ አለብኝ››
‹‹ አግብተሻል እንዴ?››
‹‹ማለት?››
‹‹ሽብርተኞች የሚያገቡ አይመስለኝም ነበር..ለማንኛውም እንዳትደውይ››
‹‹ እሺ በፈጠረህ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አትውሰደኝ››
‹‹እየወሰድኩሽ እኮ ነው..ከሁለት ደቂቃ ቡኃላ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ነን..ከአምስት ደቂቃ ቡኃላ ደግሞ ምርመራ ክፍል እራስሽን ታገኚዋለሽ››
‹‹በፈጠረህ እህት የለህም ለአንድ አስር ደቂቃ እንኳን ተረጋግቼ ላስብ ፖሊስ ጣቢያ አትውሰደኝ፡፡ የሆነ ቦታ መኪናዋን አቁምና ልረጋገ››እንደማሰብ አለና ወደ ወርቁ ቢቂላ ሆቴል መኪናዋን አጠፈና አስገባት እና ጥግ አስይዞ አቆመና ሞተሩን አጠፋና ተዘጋተው ተቀመጡ፡፡ሶስት ደቂቃ ያህል በፀጥታ እና በትካዜ ካሳለፈች ቡኃላ መናገር ጀመረች
‹‹ልትረዳኝ አትችልም?››
‹‹ይሄ እኮ በእርዳታ የሚታለፍ ቀላል ነገር አይደለም…ለምሳሌ ቀረጥ ያልተከፈለበት ልባሽ ጨርቅ ይዘሽ ተገኝተሸ ቢሆን በማስጠንቀቂያ ልምርሽ እችል ነበር….ይሄ ግን ከአቅሜ በላይ ነው››
ከአቅምህ በላይ እማ አይደለም ..አየህ በህይወቴ ብዙ ስቃይና መከራ ያሳለፍኩ ልጅ ነኝ፡፡ በአረብ ሀገር በየሰው ቤት ከ8 ዓመት በላይ ገረድ ሆኜ አገልግያለው.. ባለፈው የመን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ባዶ እጄን ወደ ሀገሬ ተመልሼ ግራ ግብት ብሎኝ እና ጭልም ብሎብኝ እያለ ከዚህ ሽማግሌ ጋር ተገናኘው….ላግባሽ አለኝ፡፡ ባላፈቅረውም ጥሩ ብር ስላለው እምቢ ልለው አልቻልኩም፡፡፡አገባውት፡፡ በፍቅር ባይሆንም በድሎት መኖር ከጀመርኩ ገና አመት እንኳን አልሞላኝም…ታዲያ ይታይህ መልሼ ወደ መከራ መልሼ ወደ እስር ቤት…ደግሞ እስር ቤት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ አውቀዋለው፡፡ በአረቦቹ እስር ቤት ከአንድ አመት በላይ ማቅቄያለው…የእናንተም እስር ቤት ከእሱ ቢብስ አንጂ የተሸለ ነው ብዬ አላስብም››
ስለነገረችው ታሪክ የተሰማውን ስሜት በቃላት ይገልጽልኛል ብላ ስትጠብቅ‹‹ቢራ ልጋዝሽ?››በማለት ያልተጠበቀ የግብዣ ጥያቄ አቀረበላት፡፡
‹‹ምን? ›››
‹‹ንግግርሽ ውሀ ያስጠማል..ቢራ ልጋዝሽ ነው ያልኩሽ››
‹‹ከሆነስ ውስኪ ቢሆንልኝ››
‹‹እሱን እንኳን ችላለው ብለሽ ነው? የመንግስት ደሞዝተኛ እኮ ነኝ..፡፡ለማንኛውም እንጠጣውና ተባብረን እንከፍለዋለን ብሎ››አስተናጋጁን ጠራና አንድ ጠርሙስ ጐርደን ጅን እንዲያመጣ አዘዘው፡፡
‹‹ስልክሽን አምጪ››
ፈራ ተባ እያለች ሰጠችው
‹‹ባለሽበት ሁኚ›› አንድ ቦታ ልደውል ብሎ ከመኪናው ወጣ፡፡ ስልኰን የተቀበላት እሱ ሲወጣ እንዳትደውል ወይም ሚሴጅ እንዳትልክ በመጠራጠር ነው፡፡
ወጥቶ ስልክ የደወለው ወደ ናዝሬት ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡የቀለም ወርቅ ቤት እንዲፈተሸ እዛ ለሚገኘው የስራ ባለደረቦቹ ጥቆማ ለመስጠት…በሁለተ ደቂቃ ውስጥ ስለ ቀለምወርቅ ቤት አድራሻ እና መሰል መረጃዎች በዝርዝር ነግሯቸው በአስቸኳይ ቤቱ እንዲፈታሽ እንዲያደርጉ በማሳሰብ ወደ መኪናዋ ተመልሶ በመግባት ከታጋቾ ጐን ቁጭ እንዳለ አስተናጋጁም መጠጡን ይዞ ደረሰ….

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍21
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ሰባት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ኩማንደር መሀሪ እና የቀለምወርቅ ሚስት ዱከም ወርቁ ቢቂላ ሆቴል ግቢ በቆመችው መኪና ውስጥ እንደተቀመጡ ውስኪያቸውን መጋት ከጀመሩ አንድ ሰዓት ተቆጥሯል፡፡፡ሁለቱም ያለምንም ንግግር በየራሳቸው ሀሳብ ሰጥመው ብዙ ብርጭቆ መጠጣት የሚችለው ማን ነው ?የሚል ፍኩክር የገጠሙ ይመስል ሲጋቱት ነበር የቆዩት ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ መሀሪ መናገር ጀመረ፡፡
‹‹ስም አልተቀያየርንም አይደል…?ኩማደር መሀሪ እባላለው››አላት፡፡
‹‹እናት እባላለው….ከፊትም ከኃላም ምንም ቅጥያ የማዕረግ ስም የለኝምም ….ኖሮኝም አያውቅምም››
‹‹እንኳንም አልኖረሽ፡፡››
‹‹ኸረ በኖረኝ በተለይ እንደ አንተ አይነቱ ስልጣን፡፡››
‹‹ምን ያደርግልሻል?››
‹‹ትቀልዳህ እንዴ..?ቦታችን ይቀያየር ነበራ …እኔ አጋች አንተ ታጋች እንሆን ነበር፡፡››
‹‹እንዴ!! አሁን እኮ አጋች እና ታጋች አይደለንም….ወንጀለኛ እና ፖሊስ ነን››
‹‹እሱን እንኳን ተወው፡፡ እኔ ወንጀለኛ እንዳልሆንኩ ውስጥህ በደንብ ያውቀዋል…ብቻ ባስብ ባሰላስል ከእኔ ምን ፈልገህ እንደሆነ ማወቅ ተሳነኝ…እኔ አሁን ማደርግ የምችለው በባንክ ደብተሬ ላይ ያለውን ብር ላንተ መስጠት ነው፤ በዛ ትስማማለህ?››
‹‹ምን ያህል ብር?››
‹‹100ሺ ብር ልሰጥህ እችላለው››
‹‹ኦ 100 ሺ ብርማ አያዋጣኝም››
‹‹የንግድ ድርድርድ እኮ አደረግከው …፡፡አያዋጣኝም ስትል ትንሽ አፍህን አያደናቅፍህም እንዴ!! 5 ሳንቲም አላወጣህበትም …..››አለችው ትኩሳቱ በሚጋረፍ ኃይል በተጫነው ስሜት..አሁን ውስኪው በመላ ሰውነቷ ተሰራጭቶ ሙቀት በመላ ሰውነቷ ስለተበተነባት ድፍረት አግኝታለች….የመጠቃት ስሜትም በውስጧ እየተንቀለቀለ ነው፡፡
‹‹እንግዲህ አያዋጣኝም አልኩ አያዋጣኝም…ይልቅ መጠጡን ቶሎ ጠጣ ጠጣ አድርጊና እንሂድ››
‹‹ወዴት? ››
‹‹ወደ እውነቱ ቦታ ነዋ››
‹‹እውነት ቦታዋ የት ነው?››
‹‹ፖሊስ ጣቢያ ››
ከመኪናው ኩፈን በላይ አልፎ በአየሩ የሚበተን ተንተክታኪ ሳቋን ለቀቀችው‹‹ፖሊስ ጣቢያን ነው እውነቱ ቦታ ያልከው..በዚህ ዘመን እንኳን ከፖሊስ ጣቢያ ከእምነት ቦታዎች ራሱ እውነት እየጠፋች ይመስለኛል››ዘመኑ የስደት ዘመን የሆነው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? በየቦታው የኑሮ ችግር ስለላ ዶላር ፍለጋ ብቻ እንዳይመስልህ ሰው ከቦታ ቦታ… ከሀገር ሀገር የሚንከራተተው፡፡እንደ እኔ እንደ እኔ በዋናነት ሰውን እንዲሰደደድ የሚያደርገው የእውነት እጦት ነው ፡፡..ክፋቱ አፍሪካን ለቀህ ወደ አረቡ አለም ብትሰደድ ..ከአረብ አገር ወደ አውሮፓ ብትሻገር ከዛም ወደ አሜሪካ ብትዘምት..እንዲሁ እንደባከንክ ዕድሜህን ትፈጃለህ እንጂ በዚህ ዘመን እውነትን በተለይ ያልተበከለችውን ንፅሆን እና ድንግሏን እውነት የትም አታገኛትም…ምን አልባት ከክርስቶስ ዕርገት ጋር አለም በቃኝ ብላ አብራ ያረገች ይመስለኛል፡፡››
‹‹እሺ ሰማውሽ…ወደ ዋናው ቁም ነገር እንመለስና አሁን ሁለት መቶ ሺ ብር አለሽ?››
‹‹የለኝም፡፡ ግን ስልክ እንድደውል ከፈቀድክልኝ ሽማግሌው ጋር ልደውልና ብር ይዞልኝ እንዲመጣ ወይም በባንክ እንዲልክልኝ ማድረግ እችላላው፡፡››
‹‹እሺ ፈቅጄያለው ደውይ›› አላት፤ይህን ያላት ከእሷ ጋር በገንዘብ ለመደራደር ዕቅድ ኖሮት ሳይሆን ቀለም ወርቅ ጋር እንድትደውል እና እዛ የተከሰተውን ነገር እንድትሰማ ስለፈለገ ነው፡፡
‹‹አመሰግናለው..ስልኬን ሰጠኛ››
‹‹እኔ ጋር ነው ለካ…››ብሎ ከኪሱ አውጥቶ አቀበላት፡፡
‹‹እንዴ!!! እስከ አሁን እንዴት አይደወልልኝም? እያልኩ ስገረም ነበር ፡፡ለካ ጠርቅመኸው ነው…››አለችና እየተማረረች ስልኮን ከፍታ ቀለምወርቅ ጋር ደወለች፡፡ ይጠራል አይነሳም፡፡ደግማ ደወለች…አሁንም አይነሳም‹‹ይሄ ደግሞ ሙትቻ ሽማግሌ ምናባቱና ነው ስልኩን የማያነሳው…ስልኬ ተዘግተዋ ስለነበረ ማኩረፉ ይሆናል››አለችና የተሰማትን ግምት በመገመት በቤት ስልክ ደወለች፡፡
ከአራት ጥሪ ቡኃላ ሰራተኛዋ አነሳችና ‹‹ሄሎ››አለቻት
‹‹‹‹ሄሎ ቀለመወርቅ እቤት አለ እንዴ?››
‹‹ወይኔ!!! እትዬ ምነው ስልክሽ? ያንቺም የሹፌሩም ብንቀጠቅጥ ብንቀጠቅጥ እምቢ አለን እኮ››
‹‹የጠየቅኩሽን መልሺልኝ እቤት ውስጥ ቀለም ወርቅ አለ?››
‹‹ወይ እትዬ ጉድሽን አልሰማሽ››
‹‹የምን ጉድ .. ?››
‹‹ሰፈራችን ፓሪስ ከተማን መስላልሽ ነበር››
‹‹ምንድነው ምትቀባጥሪው?››
‹‹አንድ መኪና ሙሉ ፖሊስ ግቢያችንን ከበው እቤቱን ምንቅርቅር አድርገው ፈትሸው…››
እናት ትዕግስቶ አለቀ‹‹ምንድነው ሚፈትሹት?››አንቧረቀችባት፡፡
‹‹እኔ አንጃላቸው››
‹‹ምንም ሳያገኙ ወጡ አይደል? ››ጠየቀች… በጐ ነገር ተስፋ በማድረግ
‹‹አይ እትዬ …ሁለት ሻንጣ ሙሉ ቦንብ እና ደግሞ መሳሪያ››
‹‹የምን መሳሪያ? ››
‹‹የሚተኮስ ነዋ…የጦርነት መሳሪያ››
‹‹እና ምን ሆነ››
‹‹ከጋሽዬ ዕቃ ማስቀመጫ መጋዘን ውስጥ ተገኘ››
‹‹ማን ያስቀመጠው? ››
‹‹እኔ ምን አውቄ እትዬ.. ግን ጋሸ ቀለመወርቅን በካቴና እጆቻቸውን ወደኃላ ጠፍረዋቸው እየሰደቧቸው… እያዳፎቸው ..በመኪናቸው ጭነው ይዘዋቸው ሄዱ..ይሄን ልነግርሽ ብደውልልሽ..ብደውልልሽ ስልክሽ እምቢ አለኝ›››
ስልኩን ሰራተኛዋ ጆሮ ላይ ዘጋችባት እና ወደ ኩማደሩ ዞረች፡፡‹‹አንተ ቅድም የደወልከው ቤቴ እንዲበረበር ለማዘዝ ነው አይደል?››
‹‹አዎ ማድረግ ያለብኝ እንደእዛ ነበር…ስራዬን ነው የሰራት….››ቆፍጠን ብሎ መለሰላት፡፡
‹‹ግን ቦንቦቹና መስሪያዎቹ እኛ ቤት ውስጥ እንዳሉ በምን እርግጠኛ ሆንክ?››
‹‹አይ እርግጠኛ እንኳን ሆኜ አልነበረም… ስለተጠራተርኩ እንጂ››
‹‹እኮ እንዴት ልትጠራጠር ቻልክ?››
‹‹ቀላል ነው ..እዚህ የአንቺ መኪና ውስጥ ናሙናው ተገኘ ማለት አንቺ ወይም ባለቤትሽ ከነገሩ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ይኖራችሆል ብሎ መገመት ለዛውም ለአንድ ፖሊስ ቀላል ነው ..አንቺን ሳይሽ ደግሞ በእንደዚህ አይነት ነገሮች ላይ ትሳተፊያለሽ ብዬ ለማመን ደመ ነፍሤ አልተቀበለልኝም፡፡ ስለዚህ ማጣራት አለብኝ ..፡፡አንቺ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ ስትይኝ ያለምንም ማንገራገር ተስማምቼ እስከአሁን እዚህ ያቆየውሽ ለምን ይመስልሻል? እቤታችሁ ተፈትሾ እስኪጣራ ድረስ ነው፡፡››
‹‹ይገርማል !!! ያ ሽማግሌ ከጀርባዬ ምን እየሰራ ነበር?››ለምን እንደሆነ የማይታወቅ ጥያቄ ጠየቀች
‹‹እሱ ከሚወዱት ሰዎች ጀርባ በሚስጥር መንቀሳቀስ ልምዱ ነው››ሳያስበው መለሰላት፡፡
‹‹ማለት..? ታውቀዋለህ እንዴ ?››አለች ግራ እንደማጋባትም እንደመደንገጥም ብላ፡፡
‹‹አይ እኔማ የት አውቀዋለው..ግን አንቺም ብትሆኚ መቼስ የድሮ ታሪኩን በጥልቀት ምታውቂው አይመስለኝም …ከንቺ ጀርባ ይሄንን አይነት ሚስጥራዊ ነገር ሰርቶ ተገኘ ማለት በቀደመ ህይወቱም ደጋግሞ ተመሳሳይን በደል በሌሎች የራሱ በሆኑ ሰዎች ላይ ሲፈፅም እንደኖረ መገመቱ ብዙም አይከብድም››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…ሚያበሳጨው እሱም በአቅሙ ሰው ማጃጃሉ እና ሰውን ዳፋ ውስጥ መክተቱ ነው፡አሁን በል መጠጡም ይብቃኝ ..ልትወስደኝ ትችላለህ››
‹‹ወደ የት ነው የምወስድሽ?››
‹‹ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነዋ››
‹‹ምን ትሰሪያለሽ..?ጉዳይ አለሽ እንዴ?››አላት እየሳቀ
‹‹አልገባኝ››አለችው የእውነትም ግራ ተጋብታ

‹‹እኔ አልፈልግሽም አሁንም ስትንቀሳቀሺ ሌላ ፖሊስ እጅ እንዳትወድቂ ይሄ በፔስታል ያለ ቦንብ እኔው ጋር ይሁንና አስወግደዋለው..አንቺ ምንም የምታውቂው ነገር የለም ..ወደ ናዝሬት ስትመለሺ ፖሊሶቹ ጠርጥረው ጥያቄ ሊያቀርብልሽ ይችላሉ.ተረጋግቸሽ
👍32
ምንም እንደማታውቂ አስረጂያቸው..ስለዚህ ገጠመኝሽም ትንፍሽ እንዳትይ››
‹‹አረ አልልም..በጣም ነው የማመሰግነው ..ከጉድ ነው ያወጣኃኝ…100 ሺ ብሩን ባንክ እንሂድና ልስጥሀ››
‹‹እሱንም አልፈልግም..ከቻልሽ ግን አንዴ የጀመርኩትን መጠጥ እስክጨርስ ትንሽ ጠብቂኝ…ካለሽ ደግሞ የውስኪውን ሂሳብ ክፈይ››
‹‹በደንብ ነው እንጂ የምከፍለው…እንደውም ቦታ ቀይረን ከመኪና ወጥተን ምግብ በልተን ከንደገና እንደ አዲስ መጠጣት ብንጀምር ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹ይሻላል ….. ?አትቸኩይም ?››
‹‹ምን የሚያስቸኩለኝ ጉዳይ አለ?››
አይ ማለቴ ወደ ናዝሬት ተመልሰሽ የባልሽን ሁኔታ ለማጣራት እና ማድረግ ያለብሽ ነገር ካለ እንድታደርጊለት ብዬ ነዋ››አላት የምትለውን ለመስማት ብሎ፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ..በዚህ ዓለም በሽብርተኞች ስጋት እየተናጠች ባለችበት ዘመን..ቦንብና መሰሪያ በቤቱ አከማችቶ የተገኘበት ሰው ምን ላደርግለት የምችል ይመስልሀል…?ዋስ ሆኜ ላስፈለታው..?ወይስ ምን ላደርግለት…?ምንም ብቸኩል ምን ላደርግለት የምችለው ነገር የለም..፡፡ቆይ እንደውም እራስህን ልጠይቅህ ስንት አመት ሚፈረድበት ይመስልሀል?››
‹‹ካነሰ ሀያ አመት አልያም ዕድሜ ልክ››
‹‹ያ ማለት ከእስር ቤት በህይወት የመውጣቱ ጉዳይ የተዓምር ያህል የራቀ ነው››አለችው ሀዘንም ደስታም በተቀላቀለበት ስሜት፡፡
‹‹ስለዚህ ምሳ ወደምንበላበት ቦታ እንንቀሳቀስ እያልሺኝ ነው?››
‹‹አዋ እያልኩህ ነው….እንደውም ዛሬ ወደናዝሬት መመለስም ሆነ ወደ አዲስአባ መሄድ አልፈልግም…እዚሁ ዘና ማለት ብዬ ማደር ነው የምፈልገው›› አለችና ከቦርሳዋ ገንዘብ አውጥታ አስተናገጁን በመጥራት ከፈለችና ሂሳቡን ዘጋች፡፡
እሱም‹‹ ይመችሽ›› ብሎ የመኪናውን ቁልፍ አሽከረከረ እና መኪናውና አስነሳት።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ኮማንደር መሀሪ ነገሮች እንዳሰበው አልሄዱለትም ቀለምወርቅን የመበቀል እቅዱ በገንዘብ ሀያልነት ከሽፎበታል የፈፀመው ወንጀል ሀያና ከዛ በላይ በእስር ያቆየዋል ብሎ ቢያስብም አስካሁን ድረስ ግልፅ ባሎነለት መንገድ ቀለም ወርቅ አንድ ቀን ሳይቆይ ከእስር ተፈቷል ይህም የቀለምወርቅ እጅ ካሰበው በላይ ረጅም እንደሆነ ኮማንጀር መሀሪ መገንዘብ ችሏል አሁን ውስኪውን እየተጋተ ቀጣይ አቅጣጫውን እያሰላሰለ ይገኛል..

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ስምንት
:
ደራሲ-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ሮዝ ከመሀሪ በተሰጣት አስገዳጅ ትዕዛዝ ጋር መሰረት እንቅስቃሴ ጀምራለች፡፡አሁን ወደ ዲላ እየተጓዘች ነው፡፡፡ጉዞዋ ከኩማንደር ደረሰ ጋር ባላት ቀጠሮ መሰረት ፡፡ትናንትና ነበር ለጥንቃቄ ብላ በህዝብ ስልክ የደወለችለት፡፡
‹‹ሄሎ የዲላው ኩማንደር››አለችው ስልኩን እንዳነሳ፡፡
‹‹ማን ልበል››
‹‹ሮዝ እባላለው….››
‹‹ሮዝ እሮዝ››
‹‹እሮዝ ሀሺሾ›› ልበልህ
‹‹ኦ የአዲስ አበባዋ ኢንቨስተር››መለሰላት
‹‹አይ ምኑን ኢንቨስተር ሆንኩት? አረቄ ቸረርቻሪ ላለማለት አፍረህ ነው አይደል?፡፡››
‹‹አይ ዋናው አረቄ መቸርቸሩ ወይም አመድ እየሰፈሩ መሸጡ አይደለም፣የሚያስገኘው ትርፍ ነው፡፡››
‹‹እሺ ይሁንልህ ..ግን በህይወት አለህ እንዴ?››
‹‹አለውልሽ ፡፡ምን እሆናለው ብለሽ ነው?››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…ጨካኝ ልብ ያለው ሰው ምን ይሆናል ››
‹‹ጨካኝ ልብ ስትይ››
‹‹እንዴ ቢያንስ ሶስት አራት ቀን ቢሆንም ጣፋጭ ፍቅር ሰርተናል ብዬ አምን ነበር..››
‹‹ማመን ብቻ ሳይሆን ትክክልም ነሽ ፤ የምን ጊዜውን ጣፋጭ ፍቅር የሰራውት ካንቺ ጋ በነዛ ባልሻቸው ሶስት እና አራት ቀናቶች ውስጥ ነው››
‹‹አይ ባክህ አትሸንግለኝ ፤ይሄን ያህል ትዝታው በአዕምሮህ ተቀርፆ ቢሆን ኖሮማ ቢያንስ እየደወልክ እንዴት ነው ትለኝ ነበር?››
‹‹አይ አንቺ ልጅ ….ያው ወንድ ሙጭጭ ሲልብኝ ይደብረኛል ስላልሺኝ ደበርከኝ እንዳትይኝ በመፍራቴ እኮ ነው እንጂ ሳላስብሽ ወይም ሳልናፍቅሽ ቀርቼ አይደለም.. ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው፡፡ ሙጭጭ የሚሉትማ እዚህም ስሬ ሞልተዋል…ላሀጫቸውን እያዝረከረኩ ዙሪያዬን እየተሸከረከሩኝ ነው…ምን አልባት ልቤ አንተ ላይ ተንጠልጥሎ የቀረው ጀነን ስለላልክብኝ ሊሆን ይችላል››አለችው፡፡የውስጥ ስሜቱን ለመቀስቀስ እና ትኩረቱን ለመሳብ የተናገረችው ንግግር ነው፡፡
‹‹ኸረ በእናትሽ በዚህ ለሊት ሰውነቴን አታሙቂው ..አሁኑኑ በርሬ እንዳልመጣ…፡፡››
‹‹እሱማ ጥሩ ነበር፡፡ ግን አሁን ለተቀጠቃጠለው ስሜቴ አትደርስልኝም..ግድ የለህም ለዛሬው እንዳ አንተ ባይሆኑም ቅርቤ ያሉትን ፈረሶቼ ውስጥ አንዱን ጋልበውና ተንፈስ እላለው ፣ባይሆን ለነገ ብንገናኝ››
‹‹ነገ?››
‹‹ምነው አትፈልግም?››
‹‹ኸረ ፈልጋለው ግን ተነገ ወዲያ ጥዋት የፍርድ ቤት ቀጠሮ አለብኝ ፡፡ነገ መጥቼ ለመመለስ አልደርስም››
‹‹በቃ እኔ እመጣለው ››
‹‹አዎ አንቺ….በቃ ተዘጋጅቼ እጠብቅሻለው…እኔ ናፍቄሽ አይደለማ ምትመጪው ለጉዳይ ስለፈለግሺኝ ነው››
‹‹ምነው ከፋህ እንዴ…? በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ብመታ ችግር አለው››
‹‹አረ የለውም ..ከቻልሽ ሶስትም መምታት ትቺያለሽ…..በደስታ አበባ ይዤ እጠብቅሻለው››
‹‹በቃ ነገ ስምንት ሰዓት ድረስ እደርሳለው ››
‹‹እሺ የእኔ ማር..መቼስ ወደ ቤርጐ እስክወስድሽን ምችል አይመስለኝም ፡፡እንደተገናኘን እዛው ህዝብ ባለበት አደባባይ ብናደርግ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹እኔም የቤርጐ አደለም ያማራኝ ..የመጀመሪያዋን ቀን ታስታውሳለታለህ? ››
‹‹የቷን?››
‹‹የቢሮህን ጫወታ ነዋ..እዛ ደረቅና ሰፊ ጠረጵዛህ ላይ እንድታሾረኝ ነው የምፈልገው››
‹‹በጉጉት አሁኑኑ ፀጥ እንዳልልብሽ››
‹‹ታገስ…. የነገዋን ደስታማ ሳታጣጥም መሞት የለብህም››
‹‹እሺ ጣፋጭ…ለመሆኑ የድሮ ባልሽን ወሬ ትሰሚያለሽ?››
‹‹ከየት ሰማለው ብለህ ነው?››
‹‹..ያው ቅርብሽ ነው ብዬ ነዋ›› መቼስ ከዲላ ተነስቶ ዱከም የገባው የአንቺኝ ትንፋሽ በቅርብ ሆኖ ለመማግ አስቦ ይመስለኛል››
‹‹አይ እኔስ የሚመስለኝ ከአንተ ለመራቅ አስቦ እንደሆነ ነው››
‹‹ከእኔ ጋማ ለምን ይርቃል?››
‹‹እጮኛውን ሳላማገጥክበት…ከእንደገና በስራም ስላጭበረበርከው››
‹‹እሱን እኮ አንቺና እግዚያብሄር ብቻ ናችሁ የምታውቁት እንጂ እሱ አያውቅም››
‹‹ካላወቀ ታዲያ ለምን ግንኙነታችሁን ያቀዘቀዘ እና ችላ ያለህ ይመስልሀል?››በመገረም ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አንቺ ልብን እንክትክት ስላደረግሺበት በዛም የተነሳ ሰው የሚባል ነገር ስላስጠላው ነዋ…››
‹‹አልሰሜን ግባ በለው››አለች እናቴ አለችው ብዙ ጊዜ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ መሆኑ አስገርሞት፡
‹‹ምን አልሺኝ?››አለት ምን ለማለት እንደፈለገች ስላልተገለፀለት፡፡
‹‹አይ ወዲህ ነው..ለማንኝውም ደህና እደር ከዚህ በላይ ኃይልህን አታባክን ..ለነገ እንዳትቸገር››
‹‹እውነትሸን ነው የእኔ አሳቢ… አሁኑኑ ተኝቼ ረጅም ረፍት መውሰድ አለብኝ..ደህና ሁኚልኝ››ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡
እንግዲ በቀጠሮቸው መሰረት አሁን ይሄው ዲላ ደርሳ ወደ ቢሮው እያመራች ነው፡፡ሰዓት ከቀኑ 8.20 ሆኖል፡፡ስትደርስ ቢሮ ውስጥ ባለጉዳይ እያስተናገደ ነበር….5 ደቂቃ ያህል ከጠበቀች ቡኃላ ባለጉዳዩ ሲለቅ እሷ ተተካችና ወደ ውስጥ ገባች..፡፡ከመቀመጫው ተነስቶ በፈገገ ፊት እና በሞቀ ሰላምታ ተቀበላት እና እንድትቀመጥ ጋብዞት በራፉን ሄዶ ቀረቀረውና መጥቶ ከጐኗ ተቀመጠ
‹‹አንቺ እንዴት አምሮብሻል.!!!ይሄንን ውስኪ እየተጋትሽ ፊትሽ ማብረቅረቅ ጀመረ››
‹‹አንተም አምሮብሀል››አለችው….እንዲሁ ለማለት ያህል እንጂ በዚህ ሰዓት ስለእሱ ውበት ሀጃም የላትም፡፡
እጁን በተከሻዋ አሻግሮ አቅፎ ወደራሱ ጐተታትና‹‹ ደክሞሻል ወይስ እንዴት ነው?ብታይ በጣም ነው የተራብኩሽ…››
‹‹አልደከመኝም ግን!!!››አቅማማችበት
‹‹ግን ምን? እንደዚህ ለሊቱንም ቀኑንም ሙሉ በጉጉት ስጠብቅ ቆይቼ ግን እንዳትይኝ››
‹‹አይ እንደዛ እንኳን አልልህም…ግን ለየት በለ መልኩ እንድናደርገው ነው የምፈልገው››
አይኖቹ የወሲብ ብርሀን ረጬ‹‹በፈለግሽው መንገድ ይመቸኛል››
‹‹እንድታስገድደኝ ነው የምፈልገው››
‹‹ማለት?››
‹‹በቃ ያሰኘኝ መደፈር ነው ..ልብሴን ቀዳደህ ….ጭኖቼን በረጋደህ..እየጠፈጠፍክ..ከቻልክ ጀርባዬን እና መቀመጫዬን ሰንበር እስኪያወጣ እየጠፈጠፍክ ››
‹‹እንዴ!!ልብስሽን ከቀደድኩት ምን ለብሰሽ ትወጪያለሽ?››በገረሜታ ጠየቃት
‹‹አታስብ የእኔ ማር ቦርሳዬ ውስጥ ቅያሬ ልብስ ይዤለው››
ያለምንም ንግግር የለበሰችውን ቲሸርት መዥርጦ አወለቀባት ..ይሄንን ሲያደርግ ፀጉሯ ብትንነትን ብሎ ተንጨፈረረ.. ከላይ የለበሰውን የራሱን ልብስ በጥድፊያ አወለቀና ከወገብ በላይ ዕርቃኑን ቀረ..፡፡ከዛ ጐትቶ ከተቀመጠችበት አስነሳት …የለበሰችውን ታይት ባለ በሌላ ሃይሉ በአንደኛው ጐን ያዘና ሸርከተው እና እታች ድረስ አለያየው..የአንደኛዋን እግር እንዳለ ሲሆን አንደኛዋ ተለያይቶ ያደረገችው ቀይ ፓንት ሙሉ በሙሉ ለእይታ ተጋለጠ…ከዛ አሽከረከራት እና ጠረጵዛው ላይ አስደጋፈት ፡፡ለመታገል ሞከረች..እንዳለችው በጥፊ ደረገመት ‹‹አዎ የእኔ ጀግና ጥረት ጥሩ ነው ….. ግን አይሳካልህም ››
‹‹ቀላል ይሳካልኛል..እንደ ባሪያ ቀጥቅጬሽ እንደፈለግኩ ነው የምጫወትብሽ››አላትና ፓንቶንም በአንድ ወገን ባለበት አለያየው፡፡
መቀመጫዋን በእናዛ ሰፌድ እጆች እየደጋገመ ጠፈጠፋት፤ እሷም በላ በሌለ ኃይሎ ታገለችው..እሷ በታገለችው መጠን እሱ ደግሞ እሷን በልዩ ሁኔታ ለማስደሰት ካለው ጉጉት የተነሳ ኃይሉን እየጨመረ በጭካኔ እየቀጠቀጠ እና በግድ እያስገደደ ይገናኛት ጀመር …ባልተለመደ መልኩ ልዩ በሆነ ንዝረት ..ልክ የመጨረሻ ጡዘት ላይ ደርሶ የዘር ፍሬው ወደ ሰውነቷ ሲበትነው ታወቃት፡፡በዛን ቅጽበት ገፈተረችውን ከላዬ ላይ አላቃው ‹ኡ..ኡኡኡኡ››ብላ መብረቃዊ ጩኸቷን አሰማች..ኩማንደሩ በአንዴ እያጣጣመ ከነበረው ከእርካታ ከውስጡ በኖ በምትኩ ድንጋጤ ወረረው‹‹
👍2
….እንዴ ምነካሽ?ያምሻል? እብድ ነሽ እንዴ?››በማለት እየለፈለፈ አፎን ሊያፍናት እጆቹን ወደ አፎ ላከ…ግን አልቻለም፤ አሁን ደግሞ የእሷ ኃይል አይሏል፡፡ ገፍትራው ወደ በራፉ አመራች … ሊያስቆማት ተንደረደረ፤ ሊይዛት ሲከተላት ግማሽ ድረስ ብቻ ወልቆ የነበረው ሱሪው አደናቀፈውና ወደቀ ..ከወደቀበት እሲኪነሳ እሷ የተቀረቀረውን የቢሮ በራፍ ከፍታ በመውጣት የጀመረችውን ጪኸት ቀጠለችበት፡፡ ግቢው ውስጥ የነበሩት ሰዎች በየቢሮው የነበሩት ፖሊሶች ተግተልትለው ወደ እነሱ ተሰበሰቡ..
እሷ ለሚያያት እብድ ትመስላለች..ፀጉሯ ተንጨፍርሮ ወዲህና ወዲያ ተበታትኗል፡፡የለበሰችው ታይት ሱሪ አንደኛው እግር ከላይ እስከታች ሙሉ ለሙሉ ተቀዶ ተለያቷል፡፡ከወገብ በላይ ሙሉ በሙሉ ከወገብ በታች በግምሽ ዕርቃኖን ነች ፡፡አንዱ መቀመጫዋ በግልፅ ለእይታ ተጋልጧል፡፡ በዛ ላይ የጠፈጠፋት አካሏ ደም ቆጥሯል…አንዱ ጡቷ ከጡት ማስያዣዋ አፍንግጦ በመውጣት እሷ በተወራጨች ቁጥር አብሮት ይደንሳል..
‹‹ምን ሆነሽ ነው ? ምን ነክቶሽ ነው?›.አንዱ ፖሊስ ጠየቃት፡፡
‹‹ደፈረኝ…. አስገድዶ ደፈረኝ..አፌን አፍኖ ልብሴን እንደምታዩት ቀዳዶ ተገናኘኝ..ደፈረኝ›› ለፈለፈች ጮኸች፡፡የምትለውን ሲያዳምጡ የነበሩት ግዙፍ የፖሊስ አዛዣ አጀቡን ጥሰው እሷን አልፈዋት ወደ ውስጥ ሲገቡ ኩማንደር ልብሱን ከየጣለበት እያነሳ ለመልበስ ሲፍጨረጨር ደረሱበት..ወዲያው በራፍ ላይ ላሉት ሁለት ፖሊሶች ትዕዛዝ አስተላለፍ‹‹..በአስቸካይ በቁጥጥር ስር አውሉልኝ››እሷ ደግሞ በአስቸካይ ወደ ሆስፒታል ውሰዶት››ብለው በንዴት በሚርገበገብ አንደበት በሚንቀጠቀጥ ድምጻቸው ቆፍጣና ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ ሮዝ በለቅሶ እና በጨኸት ውስጥ እያለች የአዛዠን ትዕዛዝ ስትሰማ በእፎይታ ተነፈሰች ..ልጇን ከመሀሪ ወጥመድ ለማስጠል ከተሰጦት ሁለት ተልኮዎች መካከል አንዱን በድል ተወጣች..ሁለተኛው ደግሞ የዚህን ያህል አይከብዳትም…..-+
እሷ ብቻ ሳትሆን ኩማደር ማሀሪም ተሳካለት ማለት ነው…አንደኛውን ጠላቱን በሌላመኛዋ ተጠቅሞ አስወገደ..አሁን ሁለት ይቀረዋል….የእንጀራ አባቱና አሷ እራሷ…..ሁለቱንም ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚያወድማቸው እርግጠኛ ነው….ከዛስ…?ከዛ እንዴት እንደሚሆን እራሱም አያውቅም…የሚኖርበት ብቸኛ ምክንያት በቀል ነበር..በቀሉ ሲጠናቀቅ ባዶውን ይቀራል…ባዶ ሆኖ መኖር ደግሞ ከባድ ነው…በጣም ከባድ…

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
:
ድርሰት በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ኩማንደር መሀሪ ቀለም ወርቅን የመበቀል እቅዱ ከከሸፈበት በኋላ ሌላ እቅድ ወጥኖ ከነበረበት ቦታ ለውጥ አድርጎ ነው ከወራት መሰወር ቡኃላ ነው ሻሸመኔ ላይ ብቅ ያለው፡፡፡ዲላ ከተማ በሚኖርበት ወቅት በዙሪያው ባሉ የቅርብ ሰዎች የጠለቀች ፀሀዩ እዚህ ሻሸመኔ ላይ ድንገት ወጥታለች..በርታለች፡፡
በፊት በሚሰራው ተመሳሳይ ስራ የፖሊስ መኮንን ሆኖ ለዛውም የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ሆኖ ሻሸመኔ ላይ ብቅ ካለ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡ መሀሪ በዚህ ወቅት በከተማዋ ኑዋሪዎች ቅፅበታዊ በሚባል ሁኔታ ስሙ ገኗል፡፡ዕውቅናውን ላየ ሰው ወራቶች ብቻ የኖረ ሳይሆን ስድስት ዓመት ያሳለፈ ነው የሚመስለው፡
በከተማዋ ያተጐናጸፈው ዕውቅና ሶስት ገፅታዎች አሉት ፡፡አንደኛ ዘወትር የተቋጠረ እና የጨለመ ፊቱ…. ሁለተኛው ወሰን አልባ ጉበኝነቱ… እናም ሶስተኛው ለሰው ልጅ ያለው ንቀት እና ጭካኔ ናቸው፡፡ ከሶስቱ መካከል ግን ጉበኝነቱ ቀደምትነቱን ይይዛል፡፡እርግጥ በኢትዬጰያ ለተንሰራፋው ስር የሰደደ ሙስኝነት የሻሸመኔ ከተማ በተለይ ከኮንትሮባንድ ጋር ተያይዞ ዋናዋ መገለጫ እና እንደ ናሙና የምትጠቀስ እንደመሆኗ መጠን እሱ ብቻ ሳይሆን መላ ባለስልጣኖች በሚያስብል ደረጃ ተክነውበታል፡፡ለዚህ መነሻ ምክንያቱም ምን አልባት ከተማዋ በንግድ እንቅስቃሴዋ በጣም የሞቀች እና የደመቀች በመሆኗ እና ከአምስት የሚበልጡ ዋና ዋና በሮች ያሏትና እሱን ተከትሎ ብዙ ሺ ሰዎች በየዕለቱ ለጉዳይ ገብተው የሚወጡባት የንግድ መዲናና ረብጣ ብር ከአንዱ ግለሰብ ወደሌላው ግለሰብ የሚሽከረከርባት ከተማ ስለሆነች ሊሆን ይችላል ብለን የራሳችንን መላ ምት ብንወስድ ብዙም አንሳሳትም፤ኩማደር መሀሪ ከወራቶች መሰወር ቡኃላ ሻሸመኔ ላይ ብቅ ያለው ግን ይሄንን አገናዝቦ ወይም የሚሰበስበው ጉቦ ዓላማው አድርጐ አልነበረም ፡፡ዋና ምክንያቱ ቀለም ወርቅ ነው፡፡ለእናቱ ህይወት እልፈት ምክንያት የሆነው የቀድሞ የእንጀራ አባቱ ቀለም ወርቅ ከገባበት እስር ቤት በገንዘብ ሀይል ወቶ አዲስ ቤት መስርቶ፤ አዲስ ሚስት አግብቶ እዚህ ሻሸመኔ ስለሚኖር ነው፡፡በቀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ለማራመድ እንዲቀለው ስለወሰነ ነው፡፡
የሚገርመው ልክ እሱ ሻሸመኔ ከተማ በከተመበት ተመሳሳይ ወቅት ሌላ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንግዳ ሰው በከተማዋ ተከስቷል፡፡አባ ሽፍንፍን ይባላሉ፡፡መቼስ ይህቺ ዓለም ሁል ጊዜ በተቃራኒ ኩነቶች የተወጠርች ነች..ያም ነው ሚዛኗን ጠብቃ እንድትቀጥል ያስቻላት፡፡ችግር እና ድሎት…ጨለማና ብርሀን…ክፋትና ደግነት…በቀል እና ይቅር ባይነት ወዘተ ወዲህና ወዲያ ወጥረው ያቆሟታል ፡፡እናም እኚ አባ ሽፍንፍን የኩማደር መሀሪ የበቀል መጋኛ አጠናግሮ የሚያተራምሳትን ከተማ እሷቸው ደግሞ በደግነት እና በቸርነት ቀዝቀዝ ያደርጓታል፡፡እሱ ያቀጣጠለውን የክፋት እሳት እሷቸው በበጐነት ፀበል ያዳፍኑታል፡፡
እኚ አባ ሽፍንፍን የተባሉት ቄስ ትክክለኛ ስማቸው ሌላ ነው ፡፡አባ ሽፍንፍን የተባሉት ከአለባበሳቸው በመነሳት ነው፡፡እግር ጠፍራቸው ሚደርስ ጥቁር ቀሚስ ለብሰው ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ ዓይኖቻቸውን ብቻ አስቀርተው በሻርባቸው ይጠቀለሉና በላዩ ላይ ጥቁር የመነኩሴ ቆብ ይደፉበታል፡፡በዛም አያበቁም የተቀረችውን ለእይታ የተጋለጠች ዓይኖቻቸው አካባቢ የቀረችውን የሰውነታውን ክፍል በግዙፍ ጥቁር መነጽር ይጋርዱታል፡፡በቃ ከእሷቸው አካላት በግልጽ የሚታዩት መስቀል የሚጨብጡት የእጆቻቸው ጣቶች ብቻ ናቸው፡፡ከየት እንደመጡ ….?እንዲህ ዓይነት አለባበስ ለምን እንደሚለብሱ…. ?በፊት የት ይኖሩ እንደነበረ… ?ከመላ ምት በስተቀር ማንም በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡ግን የሚገርመው ሻሸመኔ መኖር በጀመሩ በወራቶችጊዜ ውስጥ የኩማደር መሀሪን ያህል ዝናን ታዋቂነትን ተጐናጽፈዋል፡፡ የእውቅናቸው መስመር ግን ለየቅል ነው..
እሷቸው የተቸገረውን ረድተው...የታረዘውን አልብሰው..የተራበውን አጉርሰው ያገኙት ዝና ነው፡፡እኚ ቄስ የገቢ ምንጫቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም፤ ግን በርከት ያለ ብር የባንክ ደብተራቸው ውስጥ አለ፡፡አንዳንድ እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ሲያንሾካሹኩ እንደተሰማው እኚ አባ ሽፍንፍን የተባሉ ቄስ አሜሪካ ሀገር ብዙ አመት ኖረው ጠርቀም ያለ ጥሪት አጠራቅመው ቀሪ ህይወታቸውን ቅድስት ሀገር የሚል መንፈሳዊ ስም ወደተጐናፀፈች ሀገራቸው ተመልሰው የቅድስና ስራ እየሰሩ ለማሳለፍ ወስነው እንደመጡ የሚናገሩ ግለሰቦች አሉ..የተረጋገጠ ባይሆንም
ሌላው ገራሚው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ኩማንደር መሀሪ እና እኚህ አባ ሽፍንፍን የተባሉ ቄስ አንድ ግዙፍ በለአንድ ፎቅ ቪላ በጋራ ተጋርተው ይኖራሉ ፡፡ እሳቸው በምድር ቤቱ ውስጥ ባሉ ክፍሎች ሲኖሩ እሱ ደግማ በላይኛው ወለል ባሉ ክፍሎች ይኖራል፡፡ግን ይህ ቤት በሁለት ግቢ ተከፍሎል እሱ ሚጠቀመው የፊት ለፊቱን ግቢ ሲሆን እሳቸው ደግሞ የጀርባውን ግቢና ነው፡፡ኩማደር መሀሪ ሻሸመኔ የከተመው ለበቀል ነው፡፡እኚ ሚስጥራዊ ቄስ ሻሸመኔ ለምን ጉዳይ እንደተገኙ አይታወቅም..?
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሁለቱም እናትና ልጅ ያለቅሳሉ…ከፊት ለፊታቸው የተቀመጠው ፖሊስ ይጠይቃቸዋል፡፡በደከመ አንደበት በተሰበረ ቃል ይመልሳሉ፡፡ሰዎቹ ሄለን እና አያቷ ናቸው፡፡ቦታው በከተማው ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ነው ፡፡ተከሰው አይደለም የቀረቡት..ለመክሰስ ነው፡፡ ማያውቁትን ጠላታቸውን ለመክሰስ..
‹‹እስቲ ትዕይንቱን ከመጀመሪያው አንስተው አስረዱኝ?›› ፖሊሱ በፖሊሳዊ ግርማ ሞገሱ እንደተኮፈሰ የመጀመሪያ ጥያቄውን ሰነዘረ አሮጊቶ የተሸበሸበ ፊታቸውን ላይ ኮለል እያለ የሚወርደውን እንባቸውን በተጨማደደ እና በቆረፈደ እጃቸው ጠረግ ጠረግ በማድረግ መናገር ጀመሩ ‹‹ከትናንት ወዲያ ነው በቀኑ ኤሌክትሪክ ተቋረጠብን ..ከሰፈሩ የእኛ ቤት ብቻ ነው ተነጥሎ የተቋረጠብን፡፡ መብራት ኃይል አመለከትን …ቆይ ይቀጠልላችኃል አሉን እና ግን ሳይመጡ ዋሉ፡፡ ሲመሽ ያው ትልቁን ቤት ገርበብ አድርገን ኩሽና ሄደን በእንጨት ቡና አፍልተን ከልጄ ጋ ከጠጣን ቡሃላ ወደ ቤታችን በመግባን እራችንን ቀድመን በልተን ስለነበረ በጨለማው ዳበሳ ወደ መኝታችን ነበር ያመራነው፡፡ ሀገር አማን ነው ብለን የተለመደ እንቅልፋችንን ከተኛን ቡኃላ ባልታሰበ ሁኔታ ለሊት ላይ እላያችን ላይ ባትሪ በራብን ፡፡ ባነን ስናስተውላቸው ሁለት ጐረምሶች ናቸው፡፡
አንዱ ልጄ ላይ አንደኛው እኔ ላይ ሽጉጥ ደቅነው ነበር፡፡ ከፍራቻችን አንጻር መተንፈስ እንኳን አልቻልንም ..ወዲያው አንደኛው በጐረነነ ድምጽ ልብሳችንን በአስቸኳይ እንድንለብስ አዘዘን..በዛ በጨለማ በመርበትበት ሁለታችንም ያለውን ፈጸምን፡፡እኔ አቅሜን አውቄ አልተፍጨረጨርኩም ብቻ ለልጄ እፀልይ ነበር..::ጌታዬ በእስተእርጅና እንዳያሳቅቀኝ ..በዛ ጭንቅ ውስጥ እንኳን መማፀኔን አላቆምኩም፡፡ከዛ ቡኃላ ልጄንም እኔንም በገመድ እጆቻችንን ወደ ኃላ ጠፈሩን::ዓይኖቻንን በፍርሀት ከማቁለጭለጭ ውጭ ምንም ማድረግ አልቻልንም፡፡አንደኛው ሽጉጥ እንደደቀነ እኛን ሲጠብቀን ሌለኛው ወደ ውጭ ወጣና ባለ አስር ሊትሩን ጄሪካን ይዞ መጣ… ክዳኑን ከፈተና እቤት ውስጥ ማርከፍከፍ ጀመረ፡፡ መጀመሪያ ውሀ መስሎኝ ነበር ብኃላ ግን ምንነቱን በሽታው ወዲያው ተረዳውት ፣ጋዝ ነው..፡፡ጉዳችን ፈላ አልኩ፡፡…እመብርሀን ድረሺልን አልኩ ..በቁማችን እቤታችንን በላያችን ላይ ዘግተው ሊያነዱን ነው ስል አሰብኩ፡፡እኔ እንኳን በልቼያለውም፤ ኖሬያለውም ለጨቅላዋ ልጄ ሰጋው፡፡ቡኃለ ግን አርከፍክፎ
👍3
ሲጨርስ ሁለታችንንም እየገፈታሩ ከቤት አስወጡን፡፡ ተመስገን ነው … ቢያንስ ከቃጠሎ ተርፈናል..ከዛ ወደ ጎሮ ወሰዱን እና ግቢ ውስጥ ካለ ዛፍ ላይ ሁለታንንም አቆራኝተው አሰሩን፤ አፋችንን አሸጉት እና ጥለውን ወደ ትልቁ ቤት ተመለሱ፡፡ከዛ ግቢውን ለቀው ሲወጡ ተመለከትኩ..ግራ ገባኝ..እቤት ገብተው ምን አደረጉ? እራሴን ጠየቅኩ ..መልስ ላገኝ አልቻልኩም..ወደ ልጄ መልስ ለማግኘት ፊቴን ባዞር አፌ ለካ ታፍኖል ….ከዛ ቡኃላ ከቤታችን ውስጥ እሳት ሲንቀለቀል ነው የያነው..ምን እናድርግ ከእስራታችን ራሳችንን ለመላቀቅ አልተቻለንም...የጐረምሶቹ ጠንካራ እጅ የተበተበው ጠንካራ እስር ነበር...
ከትንሽ ደቂቃ ቡኃላ እሳቱ እየተንቀለቀለ ይወጣ ጀመር… ምን እናድርግ ?እንዳንጮኸ እና እርዳታ እንዲደርስልን እንዳንጠይቅ አፋችን ተለጉሞል ቡኃላ ቆርቆሮ እየተገነጠለ መብረር ጀመረ… ሁሉነገር በእሳቱ ተበልቶ ሊጠናቀቅ ሲል ጭሱን እና የሚንቀለቀለውን እሳት አይተው መሰለኝ ፖሊሶች ደረሱ፡፡ መሳሪያ ተተኮሰ ህዝቡ ተገልብጦ ወጣ… እኛንም ፈቱን ፡፡ ግን ከአመድ በስተቀር ምንም የተረፈልን ነገር የለም፡፡››
‹‹በጣም ይገርምል..በዚህ መጠን ይበቀለናል ብላችሁ የምታስቡት የተጣላችሁት ፤ ቂም ይዞብናል ብላችሁ የምትጠረጥሩት ሰው የለም?››
‹‹ኸረ በፍፁም ››መለሱ አሮጊቷ
‹‹አንቺስ እህት?›› አላት ወደ ሄለን አተኩሮ እየተመለከተ
‹‹ በየትኛውም መጠን ባበሳጨው ከጥፊ ባለፈ ይበቀለኛ ብዬ የማስበው ምንም አይነት ጠላት የለኝም፡፡ ሊኖረኝምም አይችልም…››
‹‹እሺ የሰዎቹን አካላዊ ቁመና ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?››
ሄለን መናገር ጀመረች‹‹ምንም አይለዩም ፡፡ሁለቱም ሰማያዊ ቱታ ለብሰው ጥቁር ጭንብል አጥልቀዋል፡፡ሁለቱም ግዙፍ አቋም ቢኖራቸውም አንደኛው ግን በተለየ መልኩ እንደከባድ ሻምፒዬን ቦክሰኛ ጡንቻው ፈረጣመ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል፡፡››
ፖሊሱ መጠየቅ አለብኝ ብሎ ያሰባቸውን ጥያቄዎች ጨርሶ ቃላቸውን ተቀብሎ ካጠናቀቀ ቡኃላ‹‹በሉ ክትትሉን በተቻለ መጠን በፍጥነት እናካሂዳለን..እርግጠኛ ነኝ የእነዚህ አውዳሚዎችን ዱካ በቅርብ ጊዜ ደርሰንበት ለፍርድ እናቀርባቸዋለን…››በማለት የማጠቃለያ ንግግር አደረገ እና ሊሸኛቸው ተከትሎቸው ወጣ ….በተከሰተው ነገር ከልቡ አዝኗልም ደንግጦልም..ምክንቱም እነዚህ ሰዎች ለሮዝ ቤተሰቦች ናቸው..ከሮዝ ጋ ደግሞ በሆነ አጋጣሚ አንሶላም ታሪክም ተጋርተዋል….ስለዚህ ጉዳዩን እንከአንጀቱ ነው ቃል የገባላቸው፡፡ ነገሩን በትኩረት ሊከታተለው..የምርመራውን ቡድን እራሱ ሊመራው…..
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የፖሊስ ጣቢያውን በራፍ እንደወጡ አንድ ባለ አይጣማ ቀለም ቪታራ መኪና ፊት ለፊት ቆማ ተመለከቱ፡፡ ወዲው አንድ ቄስ ከውስጡ ወጡና ወደ እነሱ ማምራት ጀመሩ..የተለመደውን ሽፍንፍን አለባበስ የለበሱት አባ ሽፍንፍን ነበሩ..አጠገባቸው ሲደርሱ‹‹እቤት የተቃጠለባችሁ እናንተ ናችሁ?››ሲሉ በተረጋጋ እና በተጐተተ ንግግር ጠየቁ አባ ሽፍንፍን…
‹‹አዎ አባቴ..››አሉ አሮጊቷ ፈጠን ብለው
‹‹ስለ እናንተን ጉዳይ አንድ ወዳጄ ከዚህ ደውሎ ነግሮኝ ከሻሸመኔ ነው የመጣውት…አባ ኃይለ ጊርጊስ እባላለው››
ሶስቱም ደነገጡ…. በተለይ ፖሊሱ፡፡ስለ እኚህ ቄስ ዝና ብዙ ብዙ ሰምቷል..ሰምቶም በልቡ አድንቋቸው ነበር ..ሳይታሰብ ዛሬ በአጋጣሚ በአካል ሊያያቸው ስለቻለ ተደሰተ‹‹..ለምን ፊታቸውን ግልጽ አያደርጉትም? ››ሲል በውስጡ የተፈጠረውን ጥያቄ አብሰለሰለ
‹‹ኦ አባቴ እርሶ ኖት እንዴ ?ምን እንርዳዎት?››አለ ፖሊሱ
‹‹በጣም አመሰግናለው ኩማደር ፡፡አሁን ከሻሸመኔ የመጣውት እንዳልኩህ የእዚህን ቤተሰብ መጐዳት ሰምቼ ነው..እነሱን ፍለጋ ወደ ሰፈራቸው ሄጄ ጐረቤቶቻቸውን ስጠይቅ ወደ እዚህ እንዳመሩ ተነገረኝና ወደ እዚህ መጣው ፡፡ ትንሽ ከእነሱ ጋ ለማውራት ፈልጌያለው..ሁኔታዎች ተስተካክለው እቤታቸውን መልሰን ማሰራት እስክንችል ድረስ እኔ ጋ እንዲሆኑ እፈልጋለው….ወደ ሻሸመኔ ልወስዳቸው ነው፡፡ አንተ የምትፈልጋቸው ከሆነ መጥተህ ልታናግራቸው ወይም ደውለህ እንዲመጡ እና እንዲያናግሩህ ማድረግ ትችላለህ..ምን ይመስልሀል?፡፡››
‹‹ኸረ ጥሩ ሀሳብ ነው›› በደስታ ተስማማ
አባ ሽፍንፍን ኩማደሩን ተሰናበቱና ሄለን እና አያቷን ወደ መኪና ውስጥ እንዲገቡ ጋበዞቸው..ሁለቱም ግራ በመጋባ እና በመደነቅ ውስጥ እንዳሉ… ያለምንም መከራከር እግዚያብሄር ከገቡበት መከራ መዞ ሊያወጣቸው ፈልጎ ቄሱን ወደእነሱ እንደላከላቸው በማመን ያለምንም ማቅማማት በእሺታ ያሏቸውን አደረጉ…ጉዞ ወደሻሸመኔ …

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
ልጀንማ ‹‹ስጦታ›› አልላትም!!

#ባለወለድ_ስጦታዎች !

ስጦታ እንደመቀበል የሚያስጠላኝ ነገር የለም ! ስጦታ ….ባፍንጫየ ይውጣ !! ስጦታ የጠላሁት በአጎቴ ምክንያት ነው !! ልጅ እያለን …..ቤተሰብ ዘመድ ወዳጅ ወደቤታችን ሲመጣ የሚሰጠን ስጦታ ያጓጓን ነበር …እንደውም በራቀ ትዝታየ ከሰዎቹ መልክ ይልቅ ስጦታ የያዘ እጃቸውን የማስታወስ አባዜ ነበረብኝ ! የዝምድና ማእረግ ሁሉ የምሰጠው በስጦታው መጠን ነበር!
የመጀመሪያ ደረጃ የዝምድና መዓረግ የሚሰጣቸው ዘመዶች ... ጣፋጭ ይዘው የሚመጡ ኬክ በተለይ (ያኔ ኬክ ብርቅ ነበር )….ሁለተኛ ደረጃ ዘመድ ተብለው የተቀመጡት ደግሞ ፍራፍሬ ይዘው ወደቤታችን ጎራ የሚሉት ናቸው ….ሶስተኛ ደረጃ የዝምድና መዓረግ ላይ ያሉት ተረትና ጨዋታ ታጥቀው የሚመጡ ናቸው ሰባት ቀንድ ሶስት አይን ስላለው ጭራቅ ሲያወሩልን ያመሻሉ ‹ቤድ ታይም ስቶሪ› መሆኑ ነው እንኳን ልንተኛ እንዲቹ ነፍሳችን እንደተጨነቀ ቁልጭ ብለን እናድራለን፡)) አራተኛውና ልዩ የዝምድና መዓረግ የሚሰጠው የእናታችን ወንድም አጎታችን ነው (የሱ ልዩ ነው…የአጎቴ ስጦታ የሆነ የፖለቲካ ሲስተም አለው )
ልጅ ነንና ማን መጣ ሳይሆን ምን ይዞ መጣ ዋናው ጥያቂያችን ነበር … ከአያታችን በስተቀር! …ከሩቅ ገጠር የምትመጣው አያታችን (የእናቴ እናት) እሷ ራሷ የፈጣሪ ስጦታ ነው የምትመስለን … ረዥም ቀጠን ያለች ኮስታራ ሴት ናት ….ግን ስንወዳት አይጣል ! አንዳንዱ ሰው እንዲሁ መገኘቱ ስጦታ ይሆንብን የለ …እንደዛ ነበረች አያታችን ! እንደዛም ሁኖ ታዲያ ስጦታ አታምጣ እንጅ የስጦታዎች ሁሉ ቁልፍ ከንፈሯ ላይ ነው….‹‹ምነው ይሄ ልጅ የተማርቤት ቦርሳው አረጀ›› ካለች አባባ ወዲያውኑ ምን የመሰለ ቦርሳ መግዛቱ አይቀሬ ነው ! ለምን እንደሆነ እንጃ ለማንም የማይበገር የማይመስለኝ ቆፍጣናው አባታችን ለእናቴ እናት ይሽቆጠቆጣል ! እኛን ስትጠራ እሱ ‹‹አቤት›› ሁሉ ይላል፡)) እንግዲህ የስጦታ ማዘዣ ደብዳቤው ላይ ሁሉ የቃል ፊርማ የምታሳርፈው አያታችን ስለሆነችም እንደሆን እንጃ ብቻ እንወዳታለን ! ‹‹አያታችሁ ከፈረመችበት ይሰጣችኋል›› ይባላል ሲቀለድ! እናታችን ታዲያ በዚህ ባህሪያችን እኔም ወንድሜም እህቶቸም ላይ ትበሳጫለች …. ሰው ‹‹ምን ይዠ ልምጣ›› እያለ ከዘመድ ተቆራርጨ ልቅር እንዴ?›› ብላ ቱግ ትልብናለች !
አንድ ቀን ግን እናቴ ‹‹የባህሪ ለውጥ አመጣች›› በጣም ነው የተገረምነው ‹‹ ወንድሟ›› ማለት አጎታችን ስጦታ ሊሰጠኝ ሲል ፈገግ አለች …ከምር ፈገግ አለች …. !! እሱ ስጦታውን ሲያወጣ የሆነች የተንኮል ፈገግታ ፊቷ ላይ አንዣበበችና ‹‹ተቀበል አጎትህ አይደል›› አለችኝ... ጭራሽ? !! በኋላ አይደል እንዴ የማዘር ተንኮል የተገለጠልን ሴት መለኛ ናት የሚባለው በእናቴ ነው የገባኝ፡))
አቤት የማዘር ወንድም ስጦታ ሲገርም . . . እንግዲህ ልክ እንደዓለም ዋንጫ በአራት አመት አንድ ጊዜ ነው ስጦታ የሚሰጠው … ስጦታው ታዲያ ዝም ብሎ አይሰጥም ሂደት አለው ….የመጀመሪያ ቀን ቤታችን የመጣ ጊዜ የሰጠኝ ስጦታ ትዝ ይለኛል! እቤታችን አራት ቀን ከርሞ በአምስተኛው ሊሄድ ሲነሳ ‹‹ኧረግ ረስቸው …አቡቹ ና ስቲ ወዲህ …ስጦታ ገዝቸልህ ረስቸው ›› አለና መጀመሪያ እጁ ጋቢውን እየሰረሰረ ካፖርቱ ላይ ደረሰ ካፖርቱን አልፎ ኮቱ ….ከዛ ከሸሚዙ የደረት ኪስ …..ምዝዝ አድርጎ ምን ቢያወጣ ሩ ነው ?….አንዲት ገና ያልተቀረፀች አዲስ እርሳስ!! እኔማ ያን ሁሉ ቁፋሮ ስመለከት አጎቴ ነዳጅ ሊያወጣ ሁሉ መስሎኝ ነበር፡))
‹‹ይሄው ….ይሄ ተላይ ያለው ማጥፊያው ነው (ይፈነዳ ይመስል በጥንቃቄ እየነካ) …በጣም አትፈግፍገው ቶሎ ያልቃል …ደሞ ስተቀርጥ በምላጭ አባትህ ይቅረጥልህ ….ዘመናዊው መቅረጫ አንዴ ጠርቦ ነው የሚጨርሰው ›› ብሎ ረዥም ምክር ጋር ርሳሷን ሰጠኝ …..ከዛማ ሊፋታኝ ነው እንዴ ….እቤታችን በመጣ ቁጥር ሌላ ስጦታ የለም ‹‹ አቡቹ ያ ርሳስ …እንዴት ነው? ….ጥሩ እየተገለገልክበት ነው? …አዎ በጣም አትቅረጠው… እንደነገርኩህ በምላጭ ….ስእል ደሞ ሳልበት… ስእል ትልቅ ሙያ ነው… ለስእል ዋናው ነገር ርሳስ ነው ርሳስ ካለ ስእል አለ …. አንዳንድ ማስታወሻም ካለ ከጡፍህ ስር በስሱ ለማስታወስ ብትጥፍበት ትችላለህ….በቃልህ ከተያዘልህ በኋላ ታጠፈዋለህ ›› አለኝ ….አጎቴ ሲያካብደው የማውቀው ርሳስ የሆነ ሌላ ተዓምር ነገር መሰለኝ!!
ሌላ ቀን አጎቴ ቤታችን ሲመጣ ደሞ ‹‹ አቡቹ ….ያ ርሳስ ለሂሳብ ጥሩ ነው ….አየህ ሂሳብ እንደሌላው ትምርት አደለም ይሳሳታል ….ስትደምር ትሳሳታለህ ሰው ሁኖ መቸም የማይሳሳት የለም …ስታባዛ ትሳሳታለህ ….በተለይ በተለይ ሰው ሁኖ ሲያካፍል የማይሳሳት የለም …ታዲያ ርሳስ ከሆነ ስትሳሳት ስርዝ ድልዝ የለም በማጥፊያዋ ጠፋ ነው ›› በቃ አጎቴ አዛ አደረገኝ! ….ውይ በምን ቀን ነው ይሄን ርሳስ የተቀበልኩት …የእናቴ የተንኮል ሳቅ ቆይቶ ነው የተገለጠልኝ (ቅጣት መሆኑ ነው) ….
በቃ አጎቴ ስጦታ ከሰጠ እድሜ ልኩን ስለሰጣት ነገር ሲያነሳ ሲጥል ….ስጦታው አላቂ ቢሆንኳ የአጎቴ ምክርና ማስጠንቀቂያ አያልቅም !! እንደዛ አይነት ሰው አጋጥሟችሁ አያውቅም ?….የሆነ ነገረ ሰጥቶ እድሜ ልኩን ስለዛች ነገር አጠቃቀም እንዴት ሊሰጣችሁ እንዳሰበ ….ወሬ ሁሉ ሲያወራ ቀን ከጠፋው ስጦታውን ካሌንደር ያደርገዋል ‹‹ያኔ እንትኑን እንደነገ ልሰጥህ እንደዛሬ ›› እያለ !!
እንደዚህ አይነት ባህሪ ያላቸው ፍቅረኞች አሉኮ ....ለምሳሌ ጓደኛሽን ቀጥረሽው ይዘገይብሽና ደውለሽ " የት ደረስክ " ስትይው " ባለፈው ቅቅል የጋበዝኩብሽ ቤት ደርሻለሁ የኔ ማር ፡))" የቅቅል ግብዣው የፊታችን ግንቦት 20 ሶስት አመት ይሆነዋልኮ:) ሴቶችም አሉ ለ23ኛ አመት ልደትህ ዋሌት ሰጥታህ በሰላሳ ሶስተኛ አመትህ የዋሌቱን አስረኛ አመት በዓል በክትፍ እናክብር የምትል:))
እና የአጎቴ ስጦታ የትዝታ ወለዱ ተከፍሎ አያልቅም!! ዘመዶቻችንኮ ከዛ በኋላ ያመጡት ስጦታ መዓት ተቆጥሮ አያልቅም…. አጎቴ ግን በስጦታ ወለዱ ነበር የሚኖረው !! እንደውም ጭራሸ አንድ ቀን አጎቴ ምናለ.... ለበዓል ዘመዱ ሁሉ እቤት ተሰብስቦ ስጦታውም በዛው ልክ ሲጎርፍልን
‹‹ አቡቹ ….የሰው ስጦታ ቀላል ነገር አይደለም …. ነገ ተምረህ ሰው ስትሆን መክፈልህ አይቀርም! ወረቀት ላይ በዛ በሰጠሁህ ባዲሱ ርሳስ አንድ ባንድ የተሰጠህን መዝግብ፡))›› እንግዲህ ባለፈው አመት የሰጠኝን ርሳስ እኮ ነው ‹‹አዲስ›› የሚለው …የሚገርመው ግን ስንክሳር ስላበዛበት ነው መሰል የአጎቴ ርሳስ ከሌሎች ስጦታዎች ሁሉ የበለጠ መስሎ ይሰማኝ ነበር፡)) ለካስ የቴሌቪዝን ጣቢያዎች ወደው አይደለም አንድን ነገር ደጋግመው ደጋግመው ህዝቡን የሚያዝጉት ሲቆይ ህዝቡ የሚወራው ነገር ተራ ቢሆን እንኳን ውድና ትልቅ ነገር ይመስለዋል፡))
ታዲያ ይሄ አጎቴ አንድ ቀን አያቴ ባለችበት ቤተሰቡ ተሰብስቦ እሱም በእንግድነት መጥቶ ….ከኪሱ የፀጉር ማሰሪያ ሻሽ ነገር አወጣና ‹‹ይሄ ላንች ነው ›› አላት እህቴን …ስጦታ ሳይሆን ሽጉጥ የተመዘዘባት ይመስል ልትሮጥ ነበር ቀጠል አደርጎም …‹‹ጠጉር አቧራ ሲጠጣ ከዋለ ፎረፎር ነው የሚፈጥረው …ፀሃይም ቢሆን ቀላል ነገር አይደለም …ይችን ሸብ ካደረግሽ በቃ …አቧራ የለ የሰው አይን የለ ….አንዳንዴ ሰንፈሽ ባታበጥሪው እንኳ መከሌ ይሆንሻል . . . ባይሆን አያትሽ ተፈረመችበት ነው የሚሰጥሽ ›› አለና ወደአያቴ በኩራት ዞረ …(አያቴ ስጦታውን ይሁን ካለች ማለቱ ነው )…ድንገት እኔም
👍31
እህቴም ወንድሜም ወደአያቴ ሰፍ ብለን በአንድ ላይ ጮህን ‹‹ እንዳትፈርሚ አያቴ››፡))))))))))
ታዲያ ይሄ አጎቴ በቅርቡ መጣና ‹‹አይ አቡቹ …እስታሁን አላገባህም? ….አልወለድክም ?….ልጅኮ የግዜሄር ስጦታ ነው ›› አለኝ
በሆዴ ‹‹ኧረ እንኳን የአጎት ስጦታ ያልሆነ›› እያልኩ … ዝም አልኩ !
‹‹መቸም ልጅ ስትወልድ እኔ ነኝ ስም የምሰጣት ….አዎ ሴት ተሆነች ስጦታ ብያታለሁ …የአጎትህ ስጦታ ነው በሌላ ስም ትጠራትና ውርድ ከራሴ ›› አለኛ … ህ ?….ልጀንማ ስጦታ ብየ ሳዝነዘንዛት አልኖርም በኛ ይብቃ ትውልድ ይዳን ….
‹‹አቡቹ ››
‹‹አቤት አጎቴ ››
‹‹ ስሙን እንዳትረሳው ….በዛ እርሳስ መዝግብና አስቀምጠው›› ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ!!

🔘አሌክስ አብርሃም🔘
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ
:
ድርሰት በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
፨አንቺስ ተነፈሽ እህቴ … ቁስልሽ ትንሽ ጠገገ
የልብሽ ድማት ረግቶ..ፊትሽ በእፎይታ ፈገገ
እኔ ግን በሞት ዝምታ … ውስጤን በበቀል ያነደድኩ
ራሴን ማከም አቅቶኝ …ሙሉ ደስታዬን ያወደምኩ
ባንቺ ቀናሁኝ በሳቅሽ…በታሪክሽም ተደመምኩ
ለራሴ ለሚስኪኑ ግን….እንባዬን በውስጤ አፈሰስኩ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሰዓቱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓትነው፤ኩማደር መሀሪ ጭላሎ ሆቴል ብቻውን ቁጭ ብሎ ውስኪውን እየተጋተ ነው፡፡እየተጋተ ብዙ ብዙ ነገር ያስባል… አስቦ ይገነባል… የገነባውን መልሶ ያፈርሳል…ማሰቡ ሲሰለቸው.. ከሀሳብ መውጣት እና ዘና ማለት አማረውና አንድ ቆንጆ ሞንዳላ ልጅ ጠራ …እንድታጫውተው፡፡
‹‹አቤት ምን ልታዘዝ?››አለችው አጠገቡ ደርሳ ወደ እሱ ጐንበስ ብላ
‹‹ቁጭ በይ ››አላት..ቁጭ አለች፡፡
ሌላዋ ጓደኛዋ ..ከኃላዋ ተከትላት መጥታ
‹‹ ምን ልታዘዝ ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ፋንታ አምጪልኝ›› አዘዘች ፡፡
ልጅቷ ትዕዛዞን ተቀብላ ሄደች፡፡‹‹ምነው ለስላሳ?አልኮል መጠጥ አትደፍሪም ማለት ነው?››ጠየቃት
‹‹ወድጄ ደፍራለው..እዚህ ቦታ እንዲህ አይነት ስራ እየሰራው እንዴት ነው አልኮል ማልደፍረው?እኔ አልኮልን ደፍራላው የአዳም የልጅ ልጆች ደግሞ እኔን ይደፍሩኛል ፡፡…መድፈር..መደፈር..ደስ አይልም ..?››ከትከት ብላ ሳቀች
‹‹አይ እኔ ያልሽው ብዙም አልገባኝም…የጠየኩሽ ፋንታ ስላዘዝሽ ብዬ ነው?››
‹‹ተይዤ ነው..በቃ ያመጡትን ያምጡ ብዬ››
‹‹እነማን ናቸው ያመጡትን የሚያመጡት››
‹‹ባለቤቶቹ ናቸዋ ..››
‹‹አልገባኝም››… የታዘዘችው ልጅ ፋንታ አምጥታ ከፍተችላትና ወደ ቦታዋ ተመለሰች፡፡
ልጅቷም የፍንታ ጠርሙሱን አነሳችና አንዴ ተጐንጭታለት ኩማደሩ ለጠየቃት ጥያቄ መልስ መመለሷን ቀጠለች
‹‹ባለቤቶቹ የእኛን አልኮል መጠጣት እንደ ግዴታ ነው የሚያስቀምጡት››
‹‹ለምን ተብሎ?››
‹‹አየህ አሁን ፋንታ አዘዝኩ..ድገሚ አትለኝም፡፡ ብትለኝም እኔ እሺ ብዬ አልደግምም፡፡ቢራ ቢሆንስ? ቢያንስ ሶስት አራት ጠርሙስ ትጋብዘኛለህ…ካልሆነም እስከ አስር ጠርሙስ ከዛም በላይ ልትጋብዘኝ ትችላለህ.. እንግዲህ ከእኔ መጠጣት ባለቤቶቹ የሚያገኙት ጥቅም ይታይህ….››
‹‹ቆይ ታዲያ ዛሬስ ምነው ..ፍቃድ ተስጥቶሽ ነው?››
‹‹አይደለም.. ጨጎራዬ ተላጠ..ትናንትና አንዱ ጉረኛ ወንድ ሙሉ ውስኪ አውርዶ ለሁለት..እኔ እና እሱ ብቻ ጨረስነው ፡፡ ..እናም ስሰቃይና ሳጐራ ነው ያደርኩት ፤ሀኪም ቤት ሄጄ ኪኒን አዘውልኝ እሱን ውጬ ነው ትንሽ ተንፈስ ያልኩት፡፡ደግሞ ባለቤቶቹ ብቻ አይደሉም እራሱ ጋባዡም ካልጠጣሽ ሞቼ እገኛለው ብሎ እንቡር ይላል..ለእኛ እንኳን የማዘን ፍላጐቱ ባይኖረው እንዴት ለገንዘቡ አያዝንም እያልኩ ሁሌ እገረማለው… ይሄኔ እኮ ለወር የሚሆን የአስቤዛ ወጪ ለሚስቱ አልሰጥም ብሎ እኮ ይሆናል እዚህ መጥቶ እኔን በውስኪ ሲያጠምቀኝ ያደረው…››
‹‹ለመሆኑ ስምሽ ማናው?››
‹‹ከደንበኞቼ ጥያቄዋች ውስጥ በጣም የሚያስጠላኝ ስምሽ ማነው የሚለው ነው?››
‹‹ለምን?››
‹‹እኔም እውነቱን አልነግርህ አንተም ቁምን ነገር ብለህ በአዕምሮህ አትይዘውም..›››
‹‹እንዴት እንዲህ ልትይ ቻልሽ?››
‹‹ከልምድ ነዋ …ከቡና ቤት ሴቶች መካከል 99 ፐርሰንቱ ትክክለኛ ስማቸውን አይናገሩም …ሌላው ደግሞ ስማችሁ ማን ነው ብለው ከሚጠይቁን ደንበኛቻችን መካከለም አብረውንም ቢያድሩ እንኳን 99 ፐርሰንቱ በማግስቱ ቢጠየቁ አያስታውሱትም››
‹‹ትገርሚያለሽ..ለማኛውም ንገሪኝ››
‹‹ከጠቀመህ ትዕግስት እባላለው››
‹‹እውነተኛውን ነው ወይስ የፌኩን ስምሽ ነው የነገርሺኝ፡፡››
‹‹አይ ትክክለኛውን ነው››
‹‹እኔ ደግሞ ኩማደር መሀሪ እባላለው››
‹‹ኩማደር መሀሪ!!!››የአሸባሪ ስም ፊቷ እንደተጠራባት በረገገች፡፡
‹‹ምነው በረገግሽ?››
‹‹በጣም ነው የማውቅህ››
‹‹ማ እኔን? የት? ››
‹‹እዚሁ ነዋ ፡፡ብዙ ሰዎች ስለአንተ ሲያወሩ ሰማለው››
‹‹ምን ምን እያሉ?››
‹‹ያው ..ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ያወራሉ….ግን አትመስልም…››
‹‹እንዴት አትመስልም ስትይ?››ንግግሯ ግራ አጋብቶት
‹‹እንዴ ስለአንተ ሲያወሩ እኮ ስለሆነ ግዙፍ አውሬ የሚያወሩ ነው የሚመስለው..ግን እንደዛ አትመስልም፡፡ ብዙም አታስፈራም ..ትጫወታለህ››
‹‹ለማኛውም ከዛሬ ጀምሮ ያው ጓደኛ ሆነናል አይደል?››አላት
‹‹ይመቸኛል››
‹‹አሁን ልሄድ ነው፡፡››
‹‹እንኳንም አብረን እንደር አላልከኝ››አለችው…ፈገግ እያለች፡፡
‹‹ለካ እንደዛም ይባላል.?.ብልሽ ግን ምነው ፈርተሺኝ ነው? ››
‹‹አይ በፍፅም አልፈራውህም፡፡እኔ እንደውም እድሌ ሆኖ ጨካኝ የሚባሉ ሰዎች እጣ ክፍሌ ናቸው፡፡ብቻ እንደነገርኩህ በትናንትናው አዳሬ ድክምክም ስላልኩ ነው፡፡››
‹እንደዛ ከሆነ ተስማምተናል፡፡››ብሎ ሂሳቡን ከፈለና ለእሷም በእጆ ድፍን መቶ ብር እስጨብጧት ሆቴሉን ለቆ ወጣ፡፡
ሰዓቱን ሲመለከት ሶስት ሰዓት ተኩል ሆኖል፡፡ወደቤቱ ሳይሆን ወደፖሊስ ጣቢያ ነበር ያመረው፡፡እስኪሰለቸው ቢሮው ሲሰራ ቆይቶ ስምንት ሰዓት ሲሆን አረፍ ሊል ወደ ቤቱ አመራ…መኪና ስላልያዘ በእግሩ ነው እየተጓዘ የነበረው..ውስጥ ለውስጥ ያለውን ሶስተኛ መንገድ ይዞ ቀበሌ 4 ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሊደርስ 400 ሜትር ያህል ርቀት ሲቀረው..የሆነ እንቅስቃሴ ከተቃራኒው መንገድ ተመለከተ…ጐኑ የሻጠውን ሽጉጥ መዥረጥ በማድረግ በእጁ ይዞ መንገዱን በፍጥነት ለቆ ወደአጥር በመጠጋት ጨለማ ውስጥ ተከለለ፡፡አዎ አሁን በግልጽ ይታዩታል… ሁለት ጎረምሶች ናቸው፡፡ፈጠን እያሉ ግራና ቀኛቸውን እየተገለማመጡ ነው የሚጓዙት ..አንደኛው በእጁ ጥቁር ሳምሶናይት ሻንጣ ይዞል፡፡የጉዞቸው አቅጣጫ ወደ እሱ ነው፡፡እየቀረቡት ነው….እነሱ ባያዩትም እሱ በግልጽ እያያቸው ነው፡፡አምስት እርምጃ ርቀት ላይ ሲደርሱ
‹‹ባላችሁበት ቁሙ››ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ አሳተላለፈ፡፡ያላሰቡት ዱብዳ የገጠማቸው ሁለት ጓረምሶች ባሉበት ተገትረው ቆመው ፊታቸውን ድምጹን ወደሰሙበት አቅጣጫ መለሱት፡፡
ኩማደሩ ከተወሸቀበት ጭለማ ቀስ እያለ እየተሳበ ወጣ‹‹እጅ ወደ ላይ››
ሳምሳናይቱን መሬት ላይ አስቀምጠው ሁለቱም እጃቸውን በፍራቻ ወደላይ ሰቀሉት
‹‹እሺ በዚህ ሰዓት ከየት ወደ የት ነው?››
‹‹ጓደኞቻችን ቤት ስንቅም ቆይተን… መሽቶብን አሁን ወደ ቤታችን እየገባ ነው››መለሰ አንደኛው
‹‹እሺ …ሳምሳናይቱ ውስጥ ምንድነው ያለው?››
‹‹ምንም አይደል የስራ ዶክመንት ነው››ዋሹት
ድንገት ለሚጠይቀው ጥያቄ መልስ የሚሰጥውን ልጅ ማንነት ለየው፡፡ቢያንስ እሱ ሻሸመኔ ከገባ ጀምሮ ከሶስት ጊዜ በላይ ከስርቆት ወንጀል ጋር በተያያዘ ፖሊስ ጣቢያ አግኝቶታል፡፡
‹‹አጅሬ አወቅኩህ.. አንተው ነህ..አሁን ወደፖሊስ ጣቢያ እንሂድ ወይስ እንደራደር?››
ንግግሩ ስላልገባቸው ፈጥነው ሊመልሱለት አልቻሉም
‹‹በውድቅት ለሊት ብርድ አታስቀጥቅጡን ..ወደፖሊስ ጣቢያ ልውሰዳችሁ ወይስ እንደራደር? መልሳችሁን እየጠበቅኩ ነው?››
››እንደራደር አለ.. እስከአሁን በፀጥታ ውስጥ የነበረው ፈርጣማ ጥቁር ወጣት››
‹‹እንደዛ ከሆነ ሳምሶናይቱን አንሳና ያዘው››አንስቶ ያዘው
‹‹ፊታችሁን ዞራችሁ ቀጥሉ…››
‹‹ወዴት? ›› ጠየቀ አንደኛው
‹‹ድርድራችን ትንሽ ረዘም ያለ እና ጊዜ የሚፈጅ ነው..እዚህ ብርድ ላይ በዚህ ውድቅት ለሊት መደራር ስለማንችል ወደ እኔ ቤት እንሂድ.. አይዞችሁ ደርሰናል ቅርብ ነው››ሽጉጥ ከኃላ እንደደቀነባቸው ነበር…እሱ ቤት ደረሱ… የግቢውን አጥር በር ከፍቶ
👍41
አስገባቸው..መልሶ ቆለፋው …ሽጉጥ የያዘውን እጁን እነሱ ላይ እንደደቀነ በአንድ እጁ የቤቱን በራፍ ከፈተና..‹‹የተከበራችሁ እንግዶቼ ግቡ ››በማለት ጋበዛቸው.. እነሱም ግራ እንደተጋቡ በዝግታ ወደውስጥ ገቡ ፡፡መልሶ ቀረቀረውና ቁልፉን ኪሱን ውስጥ ከተተው፡፡
‹‹ተቀመጡ …ዘና በሉ ››ሶፋውን ጥለው ደረቅ ወንበሩ ላይ ጐን ለጐን ተቀመጡ
ልብስ ቀይሬ ልምጣ በማለት እስከአሁን ደቅኖባቸው የነበረውን ሽጉጥ እዛው እነሱ ፊት ለፈት የሚገኝ ጠረጵዛ ላይ ወርወር አድርጎት ወደመኝታ ቤት ገባ፡፡
ግራ ተጋቡ..አላመኑም..እርስ በርስ ተያዩ፡፡‹‹ባሪች አንሳው…››አለው ኤልያስ የተባለው ወጣት
‹‹ምኑን ››መልሶ ጠየቀው አንሳው ያለው ምኑን እንደሆነ እያወቀ ግን ስለፈራ
‹‹ሽጉጡን ነዋ…አስፈራርተን እንዲለቀን እናደርጋለን፡፡›› አለው በሹክሹክታ
‹‹ምን ነካህ አምልጠንስ? አሳዶ ይይዘናል..ማን መሰለህ ?ኩማደሩ እኮ ነው፡፡››መለሰ ባርያው የሚባለው፡፡
‹‹እሺ እንግደለዋ..እኛ እንደሆን ማን ይጠረጥራል..በራሱ ሽጉጥ ደፍተነው እንሂድ››የተሸለ ያለውን ሀሳብ አቀረበ
‹‹እኔ አንጃ ቢቀርብን እና የሚለንን ብንሰማ ይሻል ይመስለኛል››አሁንም ሁኔታውን ስላላማረውና ውስጡም በጣም ስለፈራ ተቃወመ….
ኤልያስ ግን ተሳበና ከጠረጵዛው ላይ ሽጉጡን አነሳ ..ልክ አንስቶ ወደፊት ሲቀስር ኩማደሩ ቢጃማውን ለብሶ የወስኪ ጠርሙስ ከሶስት ብርጭቆ ጋር ይዞ ከመኝታ ክፍሉ ሲወጣ ተገጣጠሙ ፡፡
‹‹አስጠበቅኮችሁ አይደል …››
‹‹ባክህ ባለህት ቁም›› አንባረቀበት ኤልያስ
‹‹ኸረ ተረጋጋ… ሰው ሰው ቤት በእንግድነት መጥቶ ባለቤቱን እንዴት እንዲህ ያመናጭቃል.. ?አረ ነውር ነው››አለው ኩማንዳሩ ተረጋቶ
ኤልያስ ተበሳጨ‹‹እየቀለድኩ አይደለውም… አሁን ቁልፉን አውጣና በራፉን ክፈትልን በሰላም እንሂድበት ..ካለበለዛ ግንባርህን ነው ምፈረክሰው››አለ ሽጉጡን እንደደቀነበት ከመቀመጫው ተነስቶ ..ባሪያውም ተከትሎት ተነስቶ ከጐኑ በመቆም ግራ በመጋባት አይኑን ማቁለጭለጭ ጀመረ፡፡
‹‹አይ ውይይታችንን አከናውነን ከተስማማን ወደቤታችሁ ካልተስማማን ደግሞ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነው የምትሄዱት እንጂ እንደዚህማ አይሆንም ››አላቸው
‹‹ሰውዬ አይታይህም እንዴ ?የገዛ ሽጉጥህን ደቅኜብሀለው እኮ!!!››
‹‹እንግዲያው የሚከፈትላችሁ በር የለም …በምልህ ካልተስማማህ ተኩስ››አለው በልበሙሉነት
‹‹ካልክ እንግዲህ….›› ብሎ ኢላማውን አስተካከለ…፡፡ባሪያው ተጨንቆ ‹‹ተው ኤልያስ ይቅርብን ››ሲል ለማስጠንቀቅ ሞከረ …ግልፍተኛው እና ችኩሉ ኤልያስ ግን ሊሰማው አልፈቀደም…የሽጉጡን አፈ ሙዝ በኩማደር መሀሪ ግንባር አስተካክሎ ቃታውን ሳበ…..

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
1
#እንዴት_ነህ_አቦወለድ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ከቶ እንደምን አለህ
ኑሮ እንዴት ይዞሃል
አሁንም ልጅ ነህ ወይ
ወይስ ጎርምስሃል
መጎርመሱንማ ጎርምሰን ነበረ
የቀመስነው ሁሉ ኮምጣጤ ሆኖብን ከሬት የመረረ
እንዳንተ ሚጣፍጥ የልጅነት ጊዜ ናፍቆን እንደቀረ
ቀልድ ሁሉ ጠፍቶብን የፊታችን ጅማት በመናደድ ብዛት እንደተገተረ
መጎርመሱንማ ጎርምሰን ነበረ
....እንዴት ነህ አቦ'ለድ .......!
የልደታችን ቀን
ከሻማችን ጀርባ
ከእስታር ብጥብጥ ጣገብ ከፈንዲሻው በላይ የምትቀመጠው
ሁለት ብር ለሌለን
እሽግህን ፈጠህ በችርቻሮ ዋጋ በስሙኒ ሂሳብ ሱቅ የምትሸጠው
ጠጠር ከረሜላን
ጋሌጣ ብስኩትን
የፉትቦል ማስቲካን በዋጋ ምትበልጠው
እንዴት ነህ አቡወለድ እንዴት ነህ ሳቂታው
የኛን አትጠይቀኝ የኛ እዳ ገብስ ነው
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አቡወለድ
በኢቶጲስ ዘመን ልጆች የማይታወቅ የማይወደድ
👍2
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ_አንድ
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
..ኤልያስ ምላጩን ሳበው …ቀጭ የሚል ድምጽ እንጂ ዷ የሚል ፍንዳታ ወይም ጨኸት አልተሰማም ፡፡ ግራ በመጋት እራሱ ደነገጠ..ተስፋ ባለመቁረጥ ዳግመኛ ሞከረ … መልሶ ምላጩን ሳበው..አሁንም ቀጭ የሚል ተመሳሳይ ድምፅ ነው የተሰማው፡፡
በዚህ ጊዜ ግን ለኤልያስ እንቅስቃሴ ብዙም ትኩረት ሳይሰጥ ኮማንደሩ የያዘውን የውስኪ ጠርሙስ እና ብርጭቆ ጠረጵዛው ላይ አስቀመጠና ከለበሰው የቢጃማ ኪስ ውስጥ አንድ በመጠኗ በጣም አነስተኛ የሆነች ሽጉጥ አወጣና ወደ እነሱ አቅጣጫ አነጣጠረ እና ተኮሰ፡፡ ቷ..የሚል እስደንጋጭ ድምጽ አሰማች ..ሽጉጧ፡፡ ሁለቱም ግራና ቀኝ ፍንችር ብለው ወደቁ ..ሌላ ተመልካች ሰው ቢኖር ኖሮ እንዴት አድርጐ ቢተኩስ እንዴት አድርጎ ቢያነጣጥር ነው በአንድ ተኩስ እና በአንድ ጥይት ሁለቱን ያነጠፋቸው ብሎ ይገረም ነበር፡፡ኩማደሩ ግን ሽጉጡን በግራ እጁ እንደያዘ በቀኝ እጁ የውስኪውን ጠርሙስ አንስቶ በሶስቱም ብርጭቆ ላይ ቀድቶ እስኪያጠናቅቅ ሁለቱም በድንጋጤ በተጋደሙበት እንዳሉ ነበሩ፡፡
‹‹ኸረ ተነሱ ግድግዳው ለተመታው እናንተ ምን አዘረራችሁ?››
በሰመመን ሰሙትና እንደምንም ተነስተው እየተዞዞሩ እራሳቸውን በእርግጥ አለመመታቸውን ለማረጋገጥ ፈተሹ …በአንድነት ወደኃላቸው ዞረው ከጀርባቸው ያለውን ግድግዳ ተመለከቱ …ጥይቷ ግድግዳውን በስታዋለች፡፡
‹‹ቁጭ በሉ..ግን ላስጠንቅሰቃችሁ ከአሁን ቡኃላ ብታበሳጩኝ ግድግዳውን ሳይሆን ግንባራችሁን ነው የምፈረክሰው፡፡›› ፈራ ተባ እያሉ ወደመቀመጫቸው ተመለሱ፡፡ ውስኪ የተቀዳበትን ብርጭቆ አቀበላቸው እና የራሱን ይዞ ተቀመጠ፡፡
‹‹እኔ ካላወቃችሁኝ ኩማንደር መሀሪ እባላለው..የእናንተስ?››
‹‹እኔ ባርያው እባላለው ››አለው ጠቆር ያለው ፈርጣማ ወጣት፡፡
‹‹እውነተኛ ስምህ ነው የጠየቅኩህ ?››
‹‹ከማል ነው የምባለው፡፡ ግን በዚህ ስም ከነቤተሰቦቼ በስተቀር ሌላ የሚያውቀኝ ሰው የለም… ሁሉም ባሪያው ነው የሚሉኝ ››
‹‹እሺ አንተስ .. ?››አለው ወደሌለኛው ዞሮ
‹‹ኤልያስ እባላለው››
‹‹እሺ ሳምሶናይቱ ውስጥ ያለው ምንድነው?መቼስ አሁንም ፋይል ነው አትሉኝም?››
‹‹50 ሺ ብር ነው››መለሰ ባሪያው፡፡
‹‹ከየት ነው የመነተፋችሁት? ››
‹‹ከአንድ ሀብታም ነው››
‹‹50 ሺ ብር መሆኑን በምን አወቃችሁ? ቆጥራችሁታል እንዴ?››
‹‹አይ እኛ ወደ ሰራ ከመሰማራታችን በፊት ጥናት አካሂደን ነው ፡፡ይሄ ሰውዬ ትናንት ነው ይሄንን ብር ይዞት ወደ ቤቱ የገባው፡፡ደግሞ ብሩን ሰራ ሰርቶ ወይም ነግዶ ያገኘው አይደለውም ፡፡አንድ የመንግስት ፕሮጀክት ለአንድ ኮንትራክተር በተጭበረበረ ጫረታ እንዲያገኝ ስላደረገው …ከኮንትራክተሩ የተሰጠው ብር ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ነው፡፡ ለመሆኑ ብሩን ምን ታረጉታላችሁ?››
‹‹ያው ሁሌ እንደምናደርገው… እኩል እኩል እንካፍለዋለን››ኤልያስ መለሰለት፡፡
‹‹እሺ ያ ማለት ለምሳሌ ለአንተ የደረሰህን ሃያ አምስት ሺ ብር ምን ታርገዋለህ? መቼስ ትንሽ ሚባል ገንዘብ አይደለም?››
‹‹ብዙ ብር ነው እንዴ…?አይመስለኝም፡፡ያው እኔ ሁል ጊዜ እንደማደርገው ዙሪያዬ ካሉ ጀለሶቼ ጋር እንጨፍርበታለን …ለአስራአምስት ቀንም ሆነ ለአንድ ወር ዘና እንልበታለን ››
‹‹በቃ…››
‹‹በቃ››
‹‹ሌላ ምንም ፍላጐት ወይም አላማ የለህም?››
‹‹የለኝም››
‹‹ግን እኮ እንዲህ ባለው አጋጣሚ እንዲህ ጠቀም ያለ ብር ስታገኝ ህይወትህን ለመቀየር ለምን አትጠቀምበትም..?ሁልግዜ ሌባ መሆን ይቅርና ሁል ጊዜ ፖሊስ መሆንም ይሰለቻል››
‹‹አኔ አላማዬ ሌባ ሆኜ አባቴን ማበሳጨት ብቻ ነው፡፡››
‹‹ማለት?››
‹‹ተከብሬበታለው….በሚልበት ከተማ እሱ ልጅ እኮ ሌባ ነው የሚባለውን እየሰማ እንዲሳቀቅ እና እንዲሸማቀቅ ነው ምፈልገው››ብሎ መለሰለት፡፡ገረመው ..ይሄ እንእደሱ በቀል ላይ ያለ ጓረምሳ እንደሆነ ተረዳ፡፡
‹‹አባትህ አበሳጭቶኸል ማለት ነው፡፡?››ይበልጥ እንዲያብራራለት የሰነዘረለት ጥያቄ ነው፡፡
‹‹አበሳጭቶኸል የሚለው አይገልፀውም..አባቴ በገንዘቡ የሚመካ… ሰው ጤፍ የሆነ ዲክታተር ሰው ነው..እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ብሎ ጦርነት የሚያስነሳ ..ገንዘብ ስላለው ብቻ የእሱ አመለካከት ገዢ እና ፍጹም እንደሆነ የሚያስብ ነው፡፡እኔ ደግሞ እንደሌሎቹ የቤተሰቦቻችን አባላት ያለውን ሁሉ ዝም ብዬ አልቀበለውም፡፡ያልመሰለኝን ነገር አልመሰለኝም ብዬ እመልስለታለው…ይሄ ደግሞ ያበሳጨዋል፡፡‹….ከዛ የተነሳ ልጄ አይደለህም….. እቤቴን ለቀህ ውጣ› ብሎ አባረረኝ፡፡እኔም አልተለማመጥኩትም …ወጣው፡፡ ከነባርች ጋር ተቀላቀልኩ..ይሄው ይሄንን ስራ ብቻ እየሰራው እኖራለው..እሱን እንኳን ከ5 ጊዜ በላይ ዘርፌዋለው..ከዛ ቡኃላ ሽምግሌ ቢልክብኝ ..ተመልሰህ ወደ ቤት ግባና የፈለግከወን ላድርግልህ ቢለኝ አልሰማውትም..ሊያስፈራራኝም ሊያስደበድበኝም ሞክሮ ነበር፡፡ ግን ይሄውና እኔም እንዳበሳጨውት እሱም እንደተበሳጨብኝ እና እንዳፈረብኝ እዚህቺው ከተማ ውስጥ እየተገፋፋን እንኖራለን፡፡››
‹‹ይገርማል…አንተስ ባሪያው? ››
‹‹የእኔ እንኳን የተለየ ነው››
‹‹እኮ እንዴት እንደሚለይ ንገረኝ››
‹‹ከእኔ ታሪክ አንፃር የኤልያስ ጥጋብ የሚባል ነው፡፡እናቴ እኔ እና ሶስት ወንድሞቼን ቀበሌ 8 አስፓልት ዳር በምትገኝ ባዘመመች የቀበሌ ቤት አረቄ እና ጠላ እየቸረቸረች ታሳድገን ነበር፡፡ብኃላ ግን አንዱ ሀብታም ፎቅ ሊያንጣልልበት ፈለገና ከመዘጋጃው ጋር ስለተስማማ የአካባቢው ጭርንቁስ ቤቶች ሁሉ እንዳለ ተጠራርገው እንዲፈርሱለት ስለተደረገ… የእኛም መጠለያ አብራ የመወገድ እጣ ደረሳት፡፡እኛንም ከከተማወ አውጥተው አሰፈሩን፡፡እናቴ እንዴት አድርጋ እንደምታሳድገን ግራ ገባት፡፡ያለአባት አራት ልጅ ማሳደግ በጣም ከባድ ነበር፡፡እንጀራ እየጋገረች ገባያ ድረስ እየወሰደች ኑሮችንን ለመግፋት ሞከረች …አልቻለችም..፡፡ቡኃላ ተስፋ ቆረጠች መሰለኝ በብስጭት ብዙም ሳትቆይ ድንገት በበሽታ ተመታ ወደቀች …አልተነሳችም ፡፡ሞተች፡፡
ካዛ ያው ታለቅ እኔ ስነበርኩ የወንድሞቼን ሀላፊነት ሳልወድ በግድ ባልፀና ጫንቃዬ ተረከብኩ ፡፡የቀን ስራ እየሰራው የእለት ጉርሳችንን ለማግኘት ጣርኩ..ሲጋራ እና መስቲካ እያዞኩ በመሸጥ ወንድሞቼን ለመቀለብም ሞከርኩ …ግን አርኪ አልነበርም..ቀስ በቀስ ግን በአጋጣሚ በቀረብኮቸው ጓደኞቼ ገፋፊነት ወደ እዚህ ስራ ገባው..አሪፍም ሆነልኝ ፡፡የተሸለ ቤት ተከራይቼ የተሸለ ምግብ በመመገብ ወንድሞቼን ማኖር ጀመርኩ.. ከእናቴ ሞት ብኃላ ያቆረጡትን ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ቻልኩ …ምን አልባት ብታሰር ወይም በዚህ ስራ ላይ አደጋ ቢደርስብኝ ወንድሞቼ መልሰው ወደ እዛ የዘቀጠ ድህነት እንዳይመለሱ ጠርቀም ያለ ብር በባንክ ቤት ላሰቅቀምጥላቸወም ቻልኩ..››
‹‹ይገርማል….ሶስቱንም ወንድሞችህን ታስተምራለህ?››
አዎ እኔ የመማር ዕድሉን ባላገኝም እነሱን ግን በደንብ አስተምራለው፡፡ትንሹ ዘንድሮ ስምንተኛ ክፈል ማትሪክ ይወስዳል..መካከለኛው ፕሪፓራቶሪ ተማሪ ነው፡፡ሌላው ጐንደር ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ አመት የህክምና ተማሪ ሆኖልኛል››
‹‹እየቀለድክ ነው?››
‹‹በፍጹም..የነገርኩህ ሁሉ እውነት ነው››
‹‹ቆይ ወንድሞችህ ይሄንን ስራ እንደምትሰራ ያውቃሉ?››
‹‹አያውቁም..የአየር ባየር ንግድ እየነገድኩ እንደማኖራቸው ነው የሚያውቁት፡፡››
‹‹በጣም ይገርማል …››ብሎ ለደቂቃዎች በጸጥታ ተውጦ ካሰላሰለ ብኃላ‹‹….ከዛሬ ጀምሮ አብረን ነው የምንሰራው››አላቸው፡፡ሁለቱም እስር ቤት ነው ምከታችሁ
👍2
ያላቸው ያህል ነው የተደናገጡት..መደናገጥም ብቻ ሳይሆን ጆሮአቸውንም ጭምር ነው የተጠራጠሩት
‹‹ይቅርታ ኩማንደር… አልሰማንህም››አለው ኤልያስ
‹‹አብረን ነው የምንሰራው ..አየህ አንተ ይህን ስራ የምትሰራው አባትህን ለማበሳጨት ነው …ባሪያው ደግሞ ወንድሞቹን አስተምሮ ጥሩ ደረጃ ለማድረስ ነው..እኔም የራሴ የሆነ ዓላማ አለኝ..ማንኛውንም ስራ ከመስራታችሁ በፊት ጥናታችሁን ወደተግባር ከመቀየራችሁ በፊት እንማከርበትና ወይ እናፀድቀውና
እንድትገብሩት እናሳልፈዋለን ወይም እንሽረዋለን..እኔም በእኔ በኩል እንዲሰሩልኝ የምፍልጋቸው ስራዎች ይኖሩኛል..ምን ይመስላችሆል?››
‹፣እንዴ ኩማደር!!! የእውነትህን ከሆነ ለእኛ ይሄ ታላቅ እድል ነው››አለ ባሪያው
‹‹እሺ ኤልያስስ?›››
‹‹እንዴት ያለ ቀሽት ስራ እንደምንሰራ እያታሰበኝ ከአሁኑ ውስጤ በደስታ እየተፍነከነከ ነው››
‹‹እንግዲያው ጥሩ ከዛሬ ጀምሮ እኛ ሶስታችን ሚስጥራዊ አጋሮች ሆነናል..ታዲያ ይሄ ሚስጥር ከሶስታችን ውጭ አንድ ሰው ጆሮ ቢገባ ስቃዩ በእናንተ ይብሳል›› አስጠነቀቃቸው፡፡
‹‹ኸረ እርስ በርሳችን እራሱ ስለዚህ ጉዳይ አንተ በሌለህበት አናወራም››በማለት ሚስጥሩ እንደተጠበቀ እንደሚቆይ ባሪያው አረጋገጠለት…. ኤልስም በግንባር ንቅንቅታ መስማማቱን ገለጸ..
‹‹እንግዲያው ከመንጋቱ በፊት ትንሽ አረፍ ማለት ስላለብን ከፈላጋችሁ እዚሁ ሶፋ ላይ አረፍ በሉ ወደቤት እንሄዳለን የምትሉ ከሆነም መልካም መንገድ››
‹‹ብንሄድ ይሻላል››አለ ባሪያው ፈጥኖ ባለማመን
‹‹እሺ እንደፈለጋችሁ››ብሎ ተነስቶ የተቆለፈውን በራፍ ከፈተላቸው..ባለማመን እርስ በርስ ተያዘው እየታከኩ ወጡ
‹‹እንዴ ቆይ እንጂ››አለ ኩማደር፡፡ደግሞ ምን ሊለን ነው ብለው ባሉበት ተገትረው ቆሙ ፡፡ ጠረጵዛው ስር ያለውን ሳምሶናይት አነሳና ‹‹እቃችውን እረስታችሁ ሄዳችሁ እኮ !!!›› ብሎ አቀበላቸውና ወደ ውስጥ ተመልሶ በራፉን ቆልፎ ወደ መኝታ ቤት ገባ…
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
እሁድ.. እለተ-ሰንበት አካልም መንፈስም እፎይታ የሚያገኝበት እለት ነች… ዘመድ ከዘመዱ የሚጠያየቅበት… ወዳጅ ከወዳጁ የሚደዋወሉበት… ፍቅረኛ ከፍቅረኛ የሚገናኝበት… የተራራቀ የሚቀራረብበት ቅዱስ የተባለች የእርጋታ ቀን ፡፡
የሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቅጥር ግቢ ነጭ በነጭ በለበሱ ህዝበ ክርስቲያን ተጣቧል፡፡ሁሉም ባሉበት ቦታ በመቆም ስርዓተ ቅዳሴውን በጽሞና ይከታተላሉ..መንፈሱን ወደ ቤቱ.. ወደ ገዛ ችግሩ እየሮጠ የሚያስቸግረው አንዳንድ ያልተረጋጋ ምዕመንም እንደምንም እራሱን ለመቆጣጠር በመሞከር በቆመበት ይቁነጠነጣል፡፡
ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ለፈጣሪያቸው ውዳሴ ማቅረብ የጀመሩት ካህናት ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ሲሆን ተልዕኮቸውን አጠናቆቁ..ከዛም ብራኬና የጠበል እደላው ፕሮግራም መካሄድ ጀመረ፡፡ ህዘብ በጣም ብዛት ያለው ስለሆነ የካህኑን እጅ ለመሳለም አንዱ በአንዱ ላይ እየወጣ ይተረማመስ ነበር …እንደምንም ተሳክቶለት ከተሳለመ ብኃላ ወደ ጠበሉ ይሄዳ ፡፡ጠበሉን ብዛት ያላቸው ዲያቆኖች በባልዲ በመያዝ ሰው በተቀመጠበት እየተዘዋወሩ ነው የሚያድሉት፡፡
ከደቂቃዎች ቡኃላ የጠበል ዕደላው ፕሮግራም ተጠናቀቀ፡፡አንድ ጥቁር ቀሚስ የለበሰ ወጣት ሰባኪ ጥቁር ልባስ ያለውን መጽሀፍ ቁዱሱን በቀኝ እጁ ይዞ ወደ መድረኩ በመውጣት ጉሮሮውን አጸዳዳ፡፡በሚስረቀረቅ ተስገምጋሚ ድምጽ ስብከቱን ማሰማት ጀመረ.. ምዕመናኑ በጠቅላላ ባሉበት ተረጋግተው ስብከቱን በጽሞና እየተከታተሉ ነው፡፡ከወጣቱ አንደበት የሚፈልቁ ዓረፍተነገሮች በአማረኛ ቋንቋ የታንቆለጳጰሱ ከማጽናናት እና ተስፋ ከማስጨበጥ ይልቅ የሚያስፈራሩ እና የሚያርዱ ናቸው፡፡ስለእየሱስ ክርስቶስ መምጫ ቀን (ስለእለተ ምጽአት) ነው ስብከቱ፡
፡‹መንግስ-ተሰማያት ቀርባለች እና በወንጌል አምናችሁ ንሰሀ ግቡ..ብኃላ ለቅሶ እና ጥርስ ማፎጨት እንዳይሆንባችሁ ከአሁኑ ተዘጋጁ..በንሰሀ ታጠቡ..ተንኮል ምቀኝነት አስወግዱ ..አልያ እሳቱ ከማይጠፋበት ትሎቹ ወደማያንቀላፉበት ዘላለማዊ ገሀነም መጣል ይሆናል እጣ ክፍላችሁ…ከሞት ቡኃላ ስለለው ነፍሳችሁ እጣፋንታ ተጨነቁ..አለም አላፊና ጠፊ ነች…ሰጋም ረጋፊ ነች..ነፍስ ግን ወደዘላለማዊነት ትሸጋገራለች……….. ››እያለ መጽሀፍ ቅዱስ የሚያግዘው መረጃ ምዕራፍ እና ቁጥር እየጠቀሰ ለ40 ደቂቃ ስብከቱን ሰበከ እና አጠናቀቀ…ግን አሳርጐ መድረኩን ከመልቀቁ በፊት የተወሰኑ ማሳሰቢያዎች አሉኝ በማለት አንድ ሁለት መልዕክቶችን ከስተላለፈ ቡኃላ‹ ሶስተኛውን ማሳሰቢያ አባታችን ይናገሩልናል› በማለት መድረኩን በቅርብ እርቀት ለሚገኙት አባ ሽፍንፍን ለቀቀላቸው፡፡
አባ ሽፍንፍን ከተቀመጡበት ተነስተው ወደመድረኩ በማምራት ማይኩን በቀኝ እጃቸው ጨበጡና መናገር ጀመሩ፡፡አለባበሳቸው ያው እንደዘወትሩ የተሸፋፈነ እና መላ አካለቸውን የከለለ ነው፡፡ቤተክርሰቲያኑ ቅፅር ግቢ የሚገኙ ምዕመናኖች በአጠቃላይ ከእሳቸው አንደበት የሚነገረውን መልዕክት ለማዳመጥ ከበፊት ይበልጥ ነቃ ነቃ አሉ፡፡ እሷቸውም የወርቅ ቅብ መስቀላቸውን አውጥተው ካማተቡ ቡኃላ ለህዝቡ ሰላምታ አቅርበው ንግግራቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ….
‹‹እንግዲህ የተወደዳችሁ ምዕመናን ምን ጊዜም አንድ ሰው አንድ ነው… ብቻውን ምንም ተዐምር ሊፈጥር አይቻለውም፡፡ ህብረት ካለ ግን የማይቻል ነገር.. የማይተገበር ተአምር የለም፡፡በተለይ እኛ ክርስትያኖች ነን የምንል ክርስቲያኖች መሆናችንን በስም ብቻ ሳይሆን በተግባርም ማሳየት አለብን ብዬ አምናለው፡፡ አሁን ወንድማችን በስብከቱ እንዳስገነዘበን ጌታ በፍርድ ዘመን ሲመጣ ተርቤ አብልታችሁኛል? ታርዤ አልብሳችሁኛል? ታስሬ ጠይቃችሁኛል? ብሎ ጥያቄ ሲያቀርብልን ጌታ ሆይ መች መጥተህ እንዲህ አድርጉልኝ አልከንና ?ብለን መልሰን እንጠይው ይሆናል….ግን ይሄ የሚያዋጣ አይመስለኝም፡፡
ምክንያቱም እዚሁ የቤተክርስቲያናችንን አጥር ከበው የሚኖሩ ምንዱባን የእግዚያብሄር ወኪሎች ናቸው …እነሱን ሲበርዳቸው እግዚያብሄርንም እንደሚበርደው ማሰብ አለብን..ሲራቡም እግዚያብሄር እንደሚራብ መዘንጋት የለብንም..፡፡አንድ ቀን እነሱን ምሳ አበላን ማለት አንድ ቀን እግዚያብሁርን እንደጋበዘንው መቁጠር አለብን፡፡ይህ ሁሉ ክርሰቲያን ይሄ ሁሉ ምዕመን እያለ እንዴት ነው ይሄ ሁሉ የእኔ ቢጤ ቤተክርስቲያናችንን ከቦ በብርድና በፀሀይ እየተንቃቃ ከሰዋዊነት በታች ዝቅ ብሎ የሚኖረው? ለመሆኑ ሁላችንም ብንተባበር አንድ ችግረኛ ለመቶ ምዕመናን ይደርሳልን? አይመስለኝም፡፡
በአጭሩ እኔ ለማት የፈለግኩት ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት በከተማችን ውስጥ በችግር የሚማቅቁትን ወገኖቻንን ለመርዳት ትንሽ ሙከራ ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡እነዚህ ድሆች በምፅዋት ገንዘብ የእለት ጉርሳቸውን አግኝተው እንዲኖሩ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውን ቀስ በቀስ የሚችሉበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው እቅዴ…ሁሉም እንደየ አቅሙ እና እንደየ ችሎታው የሆነች ነገር መስራትና ከዛች በሚያገኘው ገንዘብ መኖር እንዲችል ማገዝ ነው ህልሜ.. ለዚህም ተግባር የሚንቀሳቀስ በቤተክርስቲያናችን ስም አንድ ጎዳናዎች የሰው ጅ መመላለሻዎች እንጂ መኖሪያ መሆን የለባቸውም ›በሚል መሪ ቃል የሚንቀሳቀስ ማህበር በማቋቋም በተቀናጀ መልኩ እርዳታ የሚያሰባስብ እና እቅዱን ወደተግባር የሚተረጉም ከህዝበ ክርስቲያኑ የተመረጠ አንድ ኮሚቴ እንዲቋቋም ከሰበካ ጉባዬው ፍቃድ ስላገኘን በዚህ ጉዳይ ላይ ህዝብ አስተያያት እንዲሰጥበት እና ኮሚቴዎችን እንዲመርጥልኝ እና እስከመጨረሻውም ከጐናችን እንዲሆን ለመጠየቅ ነው ፊታችሁ የቆምኩት፡፡
1👍1