አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
"እና የሳቸው ደም ብዛት እንዳይነሳ የኔ ደም እየተንተከተከ አንድ ወር ልከርም ነው ተዋቡ?
አንድ ወር ሙሉ በይህ ሁኔታ እንድንቀጥል አንቺም ፈረድሽ ተዋቡ?!" ስላት ።
ወደኔ ጠጋ አለይና ፁጉሬን እየደባበሰይ•••
"አንተም እኮ ተሱ ጋር እልህ የተጋባህ ነው እምትመስለው!
እስቲ አሁን እሱ እዚህ ተመጣ ቡሀላ ሁለት ቀን ሄዶ መጠጣት ምን ይሉታል ?! ያው ታፍህ ባታወጣውም ምን ታመጣለህ ጠጣለሁ እያልህ እኮ ነው እሚመስለው!
እንደው ለኔ ስትል እስቲ አንዱዬ ለትንሽ ቀን ጠጥተህ እና አምሽተህ መምጣትህን ተወው።
ምናልባት ያኔ እሱም መለስ ይልና ሀሳቡን ይቀይር ይሆናል!" ብላ አይናይኔን ስታየይ እኔም መልስ ሳልሰጣት ዝም ብዬ አየኋት።
"እእ እንደው በኔ ሞት ለትንሽ ቀን ተወው የኔ አለም እ ለኔ ስትል!!
ምናልባት አለመጠጣትህ እዚህ ብቻህን ትተኛ ተንዴቱ ጋር ተዳምሮ እንቅልፍ የሚነሳህ ተሆነ ደግሞ እኔ አንዳንድ ነገር ገዛለሁ እያልሁ ከተማ እወጣና በዛች ሶስት ሊትር በምትይዘው ቢጫ ጀርካን ሶስትም አራትም ብርሌ ጠጅ ተዛው ተምትጠጣበት ቤት ገዝቼልህ እመጣና አብዋ እንዳያይ ዘንቢሌ ውስጥ ሸሽጌ እዚሁ ክፍልህ ውስጥ አኖርልሀለሁ።
እራት ተበላህ ቡሀላ በርህን ዝግት አርገህ ትጠጣና ትተኛለህ እ አንዱዬ??•••አብዋም ያን ቀን እሄ ይመጣል ብዬ ታላስብ የንዴቴን ታወራ በጠጣህ ቁጥር እምትተናኮለይ ነው የመሰለው ለዛ ነው።
ትንሽ ቀን እንዲህ ብናረግ ሀሳቡን ይቀይር ይሆናል ብዬ እኮ ነው እሺ በለኝ ስሞትልህ !!"
ብላ ጉንጬን ሳም ስታረገይ እንደው አንዳች ስሜት መላ አካላቴን ነዘረይ ።
"እሺ እንዳልሽው እናረጋለን የኔ መለኛ!" አልኋት ፈገግ እያልሁ።
አብዋ ምሳ በልቶ ጋደም እንዳለ እንቅልፍ ጥሎታል ቲነቃ እንዳያጣይ ልሂድ በቃ እንደተባባልነው ተዛሬ ጀምሮ ጠጁን እኔው አመጣልሀለሁ እሺ የኔ ባል!" ብላይ ትትወጣ አንጀቴን በላችይ።
እንዳለችው ያንኑ ቀን ጠጁን ገዝታ ሸሽጋ አስገባችልይ ተራት ቡሀላ ጠጥቼ ተኛሁ።
በበነገው አምጥታ ክፍሌ ያስቀመጠችልኝን ጠጅ ግን ገና እራት ሳታመጣልኝ ቀደም ብዬ ጀምሬው ስለነበር እራት ይዛልይ ስትገባ ሞቅ ብሎይ ነበር።
ተዋቡም እራቴን ይዛልይ እንደገባች ሞቅ እንዳለይ አስተውላ ነው መሰል
እራቱን አስቀምጣ ተጣድፋ ልትወጣ ስትል ክንዷን ያዙሁና ጎትቼ ታጣፊዋ አልጋዬ ላይ አንጋለልኋት •••ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍27😁1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
ከጄኔራሏ ጋር ከአስራ አምስት ቀን በኃላ መገናኘታችን ነው፡፡ በጣም ናቃኛለች፡፡እኔም ሰሞኑን በጣም በተወጣጠረ እና በተጨናነቀ ሁኔታ ላይ ስለነበርኩ ላገኛት አልቻልኩም ነበር…እሷም ለምን እንደሆነ አላውቅም ላግኝህ ብላኝ አታውቅም ፡፡

‹‹እንዴት ነች ልጅህ?››

‹‹ደህና ነች…በጣም ደህና ነች››

‹‹ደህና ነች ስትል ፊትህ ላይ ብርሀን ይረጫል …ታድለሀል፡፡››

‹‹አዎ ..ትክክል ነሽ ታድያለሁ….በተለይ በአካል ካገኘዋት በኃላ ነው በጣም መታደሌን ያወቅኩት፡፡››

‹‹እናትዬውስ…?›

‹‹አናትዬው ምን….?››

‹‹ማለቴ ካየሀት በኃላ አላገረሸብህም?››

‹‹አይ እንዴት ያገረሽብኛል…በሩቅ አየኋት እንጂ በቅርብ አለላወራኋት..በዛ ላይ እህቴ እኮ ነች..››

‹‹መጀመሪያም እኮ እህትህ  ነበረች››

‹‹መጀመሪያማ አለመብሰልና ልጅነት ነው…››

‹‹ብለህ ነው…?››

‹‹አዎ….››

‹‹ይሁንልህ…ለማንኛውም ልሄድ ነው››

‹አልገባኝም….ገና አሁን መምጣትሽ እኮ ነው›

ፈገግ አለችና‹‹ማለቴ ሰሞኑን  መንገድ ልሄድ ነው..››

ይበልጥ ደንግጬ

‹‹ወደየት…?››

‹‹ግብፅ››

‹‹ግብፅ..ለምን …..?››

‹‹አባይን ተከትዬ…››

‹‹አትቀልጂ››

‹‹እሺ ለስራ …››

‹‹የምን ስራ…እዚህ  ስራ ጀምራለው ብለሺኝ አልነበረ እንዴ…?አንተንም አግዝሀለው አላልሺኝም ነበር?››

‹‹አዎ ብዬህ ነበር..ግን…››

‹‹ግን ምን…;?

ያው እንደዛ ከተባባልን በኃላ አንተ ጋር ሆነ እኔ ጋ ብዙ የተቀያየሩ ነገሮች ተፈፅመዋል…..ደግሞ አሁን ያገኘሁትን የስራ እድል በቀላሉ ገሸሽ ላደርው አልፈልግም፡፡››

‹‹ለመሆኑ ምንድነው ስራው…?››

‹‹አንባሳደር ሆኜ ነው የተመደብኩት…››

‹‹ወታደር አምባሳደር……;››
‹‹አዎ፡፡ ምን ችግር አለው…?ብዙ ሰዎች ምታበሽቁኝ ወታደር ተኩሶ ከመግደል ውጭ ሌላ ዕውቀት ያለው አይመስላችሁም….ወታደር እኮ እንደሌላው ሰው ከሙሉ ጭንቅላት ጋር የተፈጠረ ነው፡፡ማንኛውንም ትምህርት ተምሮ የየትኛውም እውቀት ባለቤት የመሆን ብቃትም አቅሙም አለው..እኔም ወታደር ከመሆኔ በተጨማሪ ላይ በውጭ ግንኑነትና ፖለቲካል ሳይንስ ዲግሪ እንዳለኝ አትርሳ…፡፡››

‹‹አረ አታምርሪ እኔ እንደዛ ማለቴ አይደለም…››

‹‹ባክህ ነው…የንግግር ቃናህ እራሱ ይሻክራል፡፡››

‹‹እሺ እንደዛ እንዲሰማሽ ስላደረኩ ይቅርታ ,.እኔ ግን ባትርቂኝ ደስ ይለኝ ነበር..››

‹‹አይ የምን መራራቅ አመጣህ፡ ከአሁን በኃላ እኮ ልንለያይ የማንችል ዘመዳማቾች ሆነናል፡፡አንተ እኮ የጋሽ አያና ልጅ ነህ..ወንደሜ ማለት ነህ;››
የእውነት ተደንቄም ተበሳጭቼም‹‹ግን የእኔ  እጣ ፋንታ  ምን አይነት ነው?››አልኳት ‹‹ምነው ምን ሆነ? ››

‹‹እንዴት ምን ሆነ ትያለሽ..?ዘላለሜን የማፈቅረው እህቶቼን መሆኑ አይገርምም?››

‹‹የማፈቅረው….ከእኔ ፍቅር ይዞሀል እንዴ?››

‹‹እየቀለድሽ ነው….?ካገኘውሽ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ አንቺን ከማፈቀር ውጭ ሌላ ምን ስራ አለኝ ብለሽ ነው››

ዝም አለች……..አንገቷን አቀረቀረችና ለደቂቃዎች በዝምታ ተውጣ አሰበች…እና እንደምንም ፈገግ ለማለት እየጣረች

‹‹ለማንኛውም ይሄንን ርዕስ ለጊዜው እንርሳው››አለችኝ፡፡

‹‹ለጊዜው ማለት?››

‹‹ለጊዜው ማለትማ …ጊዜ የራሱን መልስ አዘጋጅቶ በየልባችን ሹክ እስኪለን በነበረበት ተከድኖ ይቀመጥ ማለቴ ነው፡፡››

‹‹ይሻላል?›››

‹‹አዎ ይሻላል…ሳረሳው የፊታችን እሁድ እቤቴ ሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቼያለሁ.. ልክ 7 ሰዓት እንድትገኝ››

‹‹እኔ?››

‹‹አዎ አንተ..ዋናው የክብር እንግዳዬ ነህ››

‹‹አረ በፈጣሪ እኔ ፓለቲከኞችና ባለስልጣናት ያሉበት ቦታ መገኘት ይጨንቀኛል፡፡››

‹‹አይዞህ አታስብ…ግብዣው ላይ ሚገኙት ጓዶኞቼ እና ጥቂት ዘመዶቼ ናቸው፡፡ ተጋባዦቹ ከአሰር አይበልጡም፡፡››

‹‹እንደዛ ከሆነ እሺ…››
እጇን ወደ ቦርሳዋ ከተተችና ፖስታ ይዛ ወጣች…ከዛ ሰጠችኝ

‹‹ምንድነው?››

‹‹የጥሪ ካርድ››

‹‹በቃል ነገርሺኝ አይደል…አይበቃም፡፡››

‹‹አይ ለአንተ አይደለም››

‹‹እናስ?››

‹‹ ለአያትህ››

በጣም ደነገጥኩ..እስኪ ምን ሚያስደነግጥ ነገር አለ‹‹እየቀለድሽ ነው…?››

‹‹አንተ ምን  አስጨነቀህ..ብቻ የታሸገውን ፖስታ ሳትነካካ ወስደህ ስጣቸው…. መምጣትና አለመምጣቱን እሳቸው ይወስኑ››

‹‹ቀልደኛ ነሽ…እኔማ ምን
ቸገረኝ እሰጠቸዋለሁ…ውሳኔያቸውን ግን እኔው ልንገርሽ  አይመጡም… አታስቢው፡፡››

‹‹እሺ አንተ ብቻ ስጣቸው፡፡››
ተቀብዬ ኪሴ ከተትኩ
////
በተባለው እሁድ ቀን የልቤ ሰው የሆነችውን የጄኔራሏን የሽኝት በአል ላይ ለመታደም…ለዝግጅቱ የሚመጥን ሽክ ያለ አለባበስ ለብሼ አምሬና ተሸቀርቅሬ በእጄ ደግሞ ይመጥናታል ያልኩትን የማስታወሻ ስጦታና አንድ ጠርሙስ ውስኪ አንጠልጥዬ ልክ ከቀኑ ሰባት ሰዓት መኖሪያ ቤቷ በራፍ ላይ ተገኘሁ፡፡ወደውስጥ ለመግባት ግን ትንሽ አመነታሁ፡፡ውስጥ የማገኛቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ጋር እንዴት ብዬ እንደምግባባቸውና እንዴት አይነት ጊዜ አብሬያቸው ላሳልፍ እንደምችል ሳስበው ጨነቀኝ…በተለይ እኛ ጄኔራል የቀድሞ ወዳጇ ተጠርተው ከሆነ ሙዴ ሁሉ ነው የሚከነተው…ለማንኛውም ምርጫ ስለሌለኝ እራሴን አበረታትቼ ወደግቢው ዘልቄ ገባሁ….በሩቅ በረንዳ ላይ አንድ ታዳጊ ልጅ ትታየኛለች…እየቀረብኩ ስመጣ የማየውን ማመን ነው ያቃተኝ ፡፡ልጅተቷ እኔን ሳታይ ተመልሳ ወደውስጥ ሮጣ ገባች ፡፡
በዛች ቅፅበት ምንም ነገር ማሰብ አልቻልኩም።ልክ ልጅቷ እንደወፍ በራ የምታመልጠኝ ይመስል በሩጫ ተከተልኳት……ታአምር ታምሬ እያልኩ ተንደርድሬ ወደቤት ገባሁ።አንድ እግሬን እቤት ውስጥ አንድ እግሬን በረንዳ ላይ አድርጌ ከነሀስ እንደተሠራ ሀውልት ተገትሬ ቆምኩ።ውስጥ ሳሎኑ ሙሉ ነው። የሚገርመው ደግሞ ሁሉንም ሰዎች አውቃቸዋለሁ… በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንዲህ ግራ ገብቶኝ አያውቅም።ወደኃላ ተመልሼ ሮጬ ማምለጥ ወደፊት ሄጄ ሁኔታዎችን መጋፈጥ.."ሁለቱንም ለማድረግ አእምሮዬን መጠቀም ሰውነቴንም ማዘዝ አልቻልኩም።

ጄኔራሏ  ከሌላኛው ክፍል ወጣችና ቀጥታ ወደእኔ መጣች "እንዴ ግባ እንጂ"
ስሬ ደርሳ ክንዴን ቀጨም አድርጋ ያዘቺኝ እና ጎትታ ከተቸነከርኩበት አነቃነቀችኝ።ከውስጥ አፍጥጠው ከሚያዩኝ ሰዎች መካከል አንድ አዛውንት ወደእኔ መንቀሳቀስ ጀመሩ..ማን እንደሆኑ መገመት አትችሉም፤አያቴ ናቸው።ከሶስት አመት በኃላ እንዴት ክፍላቸውን ለቀው እዚህ ሊገኙ ቻሉ?የጥሪውን ካርድ በሰጠዋቸሁ ቀን ፈፅሞ እንዳላስበው በማያሻማ ቋንቋ ነግረውኝ እኔም አምኜያቸው ነበር….እና ታዲያ እንዴት ሀሳባቸውን ቀየሩ?ይሄ ነገር ህልም  ይሆን እንዴ ?
‹‹ና በል አክስትህን ይቅርታ ጠይቅ።›አያቴ ናቸው የተናገሩት፡

ካለሁበት ድንዛዜ ድንገት ባንኜ በአየር ላይ እንደመንሳፈፍ ተንደርድሬ አክስቴ እግር ስር ድፍት አልኩ… እሷም ፈጥና ልታነሳኝ ትከሻዬን ለመያዝ ብትሞክርም እንደምንም አመለጥኳትና እግሯ ስር ተደፍቼ በእንባ እየታጠብኩ ‹‹እቴትዬ በፈጣሪ ይቅር በይኝ..አሳፍሬሻለሁ.››የመጣልኝን ቀባጠርኩ፡፡

ይቀጥላል
👍1067👏1
# ሚስቴ እና አባቷ!?
/በጥላሁን ተስፋዬ/
ክፍል~~~አራት
ተዋቡም እራቴን ይዛልይ እንደገባች ሞቅ እንዳለይ አስተውላ ነው መሰል
እራቱን አስቀምጣ ተጣድፋ ልትወጣ ስትል ክንዷን ያዙሁና ጎትቼ ታጣፊዋ አልጋዬ ላይ አንጋለልኋት•••
አይኗን እያስለመለመይ ሽቅብ እያየችይ •••
"ምን ልትሆን ነው አንዳርጌ እንደው በልጃችን እንደው •••" እያለይ ተአርባ አራቱ ታቦት ያልጠራችው የለለ እስቲመስለይ ድረስ እንድተዋት ስለምነይ ሁለመናዬ አልታዘዝልህ አለይ።
እንኳንስ እንዲህ ለምናይ ደስ ታላላት በስተቀር ታለፍጎቷ ገላዋን መንካት መች ይሆንልኛል።
እንደለቀቅኋት ብድግ ብላ ልብሷን እና ሻሿን ማስተካከል ጀመረይ። ተመውጣታ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቃት ከጀልሁና•••
"ተዋቡ !" ብላት
"ወዬ አለሜ!" አለይችኝ።
እሷን ውብ አለም ብዬ ትጠራት ደስ እንደሚላት ነግራኛለይ። እኔም ብሆን ለሷ ባልነግራትም "አለሜ!" ብላ ስትጠራይ ውስጤ ተጋግሮ የተቀመጠ የሚመስል አንዳች የፍቅር ስሜት ፍንቅል ሲል ይታወቀኛል።
ግን••••አልኃት። "ግን ምን ?" አለችይ ለመሄድ እየተቻኮለይ።
"ተቀናት በፊት መስኮትሽን ሳንኳኳ እየሰማሽ ነው አደል ዝም ያልሽኝ !?" ስላት•••
"ኪኪኪኪኪኪ ••••እና ብሰማህስ ምን እንድሆን ጠብቀህ ነበር እእእእ!?" አለይ ።
"ምናል መስኮቱን ብከፍችው ?"
"ሂድ ወድያ አንተ ብሽቅ ሆሆሆሆ•••ኧረ አንተስ ጉደኛ ነህ!" እያለይ ተክፍሌ ስተወጣ•••
ዛሬ ሳንኳኳ እንድትከፍችልይ አልኋት። መልስ ሳሰጠይ ወደ ትልቁ ቤት ገባይ።
እሷን እያሰብሁ፣ ሁኔታዋን እያስታወስሁ ያመጣይልይን እራት በልቼ፣ የቀረችኝን ጠጅ ጠጥቼ እንደጨረስሁ ተመተኛቴ በፊት መስኮቷን ጎተት አርጌ ሞከርኋት ። አልተከፈተይም። ትንሽ ቆይቼ በስሱ ኳኳኳ አረግሁና አልጋዬ ላይ ተንጋልዬ ድምጤን አጥፍቼ መጠባበቅ ጀመርሁ ።
ድምጥ የለም።መብራቱ ጠፋ ሳትከፍትልይ ተኝታለይ ። እኔም ተኛሁ።
ጥዋት እባቷ ተቤቱ ጓሮ ወዳለው ሽንት ቤት ቲሄዱ ጠብቃ መጣይ ።
ማታ ለምን እንዳልከፈተይልኝ ጠየቅኋት።
"እብድ!" አለችይ እየሳቀይ። እኔው ነኝ እብድ አልሁና••••
"ውብ አለሜ ግን እንደው በሌላ ነገር አትውሰጅብይና አባትሽ ግን እኔ ያልሁት ታልሆነ ተማለታቸውና ተጨቋኝ ባህሪያቸው ባሻገር ጤናቸው ተነ ሙሉ ክብሩ አብሯቸው ያለ ይመስልሻል ??" ስላትይ•••
"እእእእእ ምን ለማለት ፈልገህ ነው አንዳርጌ ? እስቲ ልትል የፈለግኸውን ግልጥልጥ አርገህ ንገረይ !?" አለችኝ እየተቆናጠረይ።
"ምነው ተናደድሽ እንዴ ተዋቡ !" አልኋት ነግሯ አላምርህ ቲለኝ ጥያቄዬን በንጭጩ ልቃጨው እያሰብሁ።
"ኧረ ምን አናደደይ ተደም ብዛት ውጪ ሌላ ምንም በሽታ እንደለለበት ነው የማውቀው አንተ የምታውቀው ታለ ንገረይ?! አለች ቆምጨጭ እንዳለይ።
"ሰው የሚያስበው በጭንቅላቱም አይደል ዛድያ እሄ ደም ብዛት የሚባል ህመም ተማሰብ ጋር የሚያቆራኘው ነገር ይኖር ይሆን እንዴ?
"ቆይቆይቆይቆይ ወዴት ወዴት አባትሽ ማሰቢያቸው ተቃውሷል ልክ አይደለም እብድ ናቸው እያልኸኝ መሆኑ ነው አንዳርጌ ነው ንገረይ !?" አለይ እንደመርገፍገፍ እያደረጋት።
ሁኔታዋ ታየው ነገር ነገር ሸተተይ ። ለምን እንዲህ ብሎ ጠየቀይ ብላ ትትንጨረጨር ገና በወጉ ሳንታረቅ መልሷ ልትጣለይ እያኮበኮበይ መሆኑ ታወቀይና
ኧረ እኔ እንደዛ አልወጣኝም ተዋቡ ምን ሆነሻል ፣ ለምን ነገር ነገር ይልሻል በይ!! እኔ እንዲሁ የምታውቂው ነገር ታለ ብዬ ጠየኩሽ እይ እብድ ናቸው የሚል ነገር ታፌ ወጥቷል ተዋቡ?!" አልኋት ። በረድ አለይና•••
"እኔ እንግዲህ ተደም ግፊት ነው ደም ብዛት ? ውጪ ሌላ ነገር ሲያመው አይቼም አላውቅ እሱም ሌላ በሽታ እንዳለበት አልነገረኝም !" አለች ፈርጠም ብላ።
"እሱማ እሳቸው እንዴት ይነግሩሻል? ማሰቢያውን የታመመ ሰው በምኑ አስቦ ህመሙን ያውቀዋል ? በዙርያው ያለ ሰው ነው እይ የሚረዳው አንቺ ታልነገርሻቸው ማን ይነግራቸዋል ? አልሁ በልቤ ታፌ አውጥቼ ብናገረው አጠገቧ ያለውን ማንቆርቆርያ አንስታ እንደምትወረውርብኝ መች አጣሁት።
እሷስ ትወርውር ተጠቡ ቡህላ ሌላ ሁለተኛ ወር ያባቷ ቅጣት ተሚመጣ አፌን ብዘጋ እና በውስጤ ብልጎመጎም ይሻላል ብዬ እንጂ።
"ምንድን ነው ዝም ብለህ የምታየኝ !?" በውስጤ እያወራሁ ሳፈጥባት ።
እንግዲህ በጤናቸው ሆን ብለው ተሆነ እንዲህ አይነት ፍርድ የፈረዱብን •••
እዚህ ሰው የለውም፣ መሬቱን ፣ የወተት ከብቶቹን ፣ ቤቱ እና ንብረቱንም እኔ ሰጥቿቸው ነው ትዳር የመሰረቱት !!
ስለይህ በትዳራቸው ላይ ተልጄ ባል በላይ እኔ ነኝ የምወስነው ብለው ነው ማለት ነው እንዲህ የሚሆኑት ግድያለም!
ልጄን ይዘህብይ አትሂድ እዚሁ ሁኑ ትላሉ እይ እኔ ትዳሬን ለማቆም የሚበቃ ወረት አጥቼ ነው ተዋቡ ? አንቺን ብዬ እንጂ እንደሳቸውማ ቢሆን ቤቱን ጥየላቸው በሄድኩ!" ስላት•••
አባትሽ እብድ ነው አልከይ ብሏ ቁጣ ቁጣ ሲላት የነበረይው ተዋቡ ወድያው ቁጣዋ ወደ ድንጋጤ ቲቀየር ፊቷ ላይ አየሁ። ክው አለይ። እንዲህ ስደነግጥ አይቼም አላውቅ።
"ውይ በስመአም የሰይጣን ጆሮ አይስማው!
የምን ሰይጣን ነው እንዲህ ያለውን መጥፎ ሀሳብ ሹክ ያለህ በል!?" አለይ።
"ተይኝ ተዋቡ እንዳንታረቅ መሀል ገብተው የፀብ እድሜ ከማራዘም በላይ ሰይጣን መሆን ተዌት ይመጣል?!።
አንዱዬ ሙት እንደዛ አስቦ አይደለም ያባዬን ጠባይ ስለማታውቀው ነው እሺ?!
አዳራ አለሜ ታሁን ቡሀላ እንዲህ እንዳታስብ !" አለችኝ። መጥታ ወገቤን አጥብቃ እያቀፈችኝ።
ምን ላርግ አለሜ አንቺ ጠጅን እይህ ድረስ ስላመጣሽልይ ብቻ ደስተኛ እምሆን ይመስልሿል!
ያንቺ ናፍቆት በምን ይተካል ? ናፍቀሽኝ እኮ ነው እንዲህ ንጭንጭ የሚያረገይ ውባለሜ!" አልኋት።ቃል ታትተነፍስ ደረቴ ላይ እንደተለጠፈይ ቆየይና •••
"ልሂድ በቃ" ብላ ልትወጣ ስትል እጇን ያዝ አድርጌ ዛሬስ መስኮቱን ከፍተሽው አተኝም ?" አልኋት።
ፈገግ እንዳለይ እጇን መንጭቃይ ወጣይ።
አባቷ እንቅልፍ እስቲጥላቸው እራቴ በልቼ ቀስ እያልሁ ጠጄን ታጣጥም ሰአት ገፋሁና
አልጋዬ ላይ ወጥቼ መስኮቷን ጎተት ታረጋት ከፈት እለይ።
አይ ውብአለም ተቸግረሽ እይ በኔ አጨክኝም እኮ እያልሁ ልብሴን አወላለቅሁና በቁምጣ እሷ ዘንድ ልሄድ ተሰናዳሁ። አልጋዬ ላይ ወጥቼ እስተመጨረሻው ልበረግዳት ጎተተተተተት
ታረጋት••••
"ቀርርርርር እያለይ ታሳብቃለይ ።
ያንቺ ማቃጠር ደሞ ምን ይሉታል?አልሁና•••
በብልሀት ድምጧ እንዳይጎላ አድርጌ ለመክፈት በሞክርም ታልጮህ አልከፈትም ትላለይ እንደፍጥርጥርሽ ብዬ እያንቃረርይ ከፈትሁና ዘልዬ ገባሁ። ትደናበር አቅጣጫ ስቼ አባቷ ታሉበት ክፍል እንዳልገባ ብላ ነው መሰል መብራቱን አጥፍታ ፋኖሱን በደበዘዝ ሀይል አብርታ ብርሀኑ ተሷ መኝታ ውጪ እንይሄድ ባንድ በኩል በጨርቅ ጋርዳዋለይ።
ድምጤንም ኮቴዬንም አጥፍቼ ተዋቡ ወደተኛይበት አልጋ እየተጠጋሁ። አባቷ እዛኛው ክፍል ተኝተው ቲያንኮራፉ ተሰማኝ።
አልጋ ውስጥ እንደገባሁ ፋኖሷን ደረገመቻት።
ተዘጋጅታ ስለጠበቀይኝ መሳብም ማውለቅም ታይጠበቅብይ " ግባ በሞቴ "
እያለ ተላይ እስተታች የጨርቅ ዘር ታይለብስ የተንጋለለውን ፣ ተሳምንት በላይ የናፈቀይን ፣ የተዋቡን ገላ እያተረማመስሁ አስጨንቀው ጀመር።
ተዋቡዬ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ•••
"አንተ ቀስ በል እይ አልጋው እስቲያለቅስ አትነቅንቀይ!" አለይ።
👍261
አንቺ ታታለቅሽ አልጋው ምኔ ተነካ ብሎ ነው የሚያለቅሰው ውብ አለም !" አልኋት ጆሮዋን እየነከስሁ።
"አብዬ ሰምቶ ላባብለው እንዳይል ብዬ ነው" ትትለኝ•••
"አባትሽ ቲያንኮራፋ የሚያወጣው ድምጥ ታልጋው ለቅሶ ይከፋል እኮ አይሰማሽም እንዴ ?"እያልሁ ተስር የነበርይውን ተወቡን ብድግ አርጌ ተላይ እንድትሆን ታመቻቻት ተላይ ቁብ ብላ ትጋልበይ ጀመር ።
ትንሽ ቆይታ የአባቷን መኖር ረሳይው መሰለይ ተሚያንኮራፉት አባቷም ተሚያለቅሰው አልጋም በላይ መጮህ ትትዥምር መልሼ ታታች አረግኃትና እስትንጨርስ ድረስ አፍንጫዋን ትቸላት ባንድ እጄ አፏን በመላ አካላቴ መላ አካላን አፍኝ አስጨንቃት ዠመር።
ሁለታችንም ተንዘፍዝፈን ጣፋጭ ቆታችንን እንደቋጨን••• በጀርባችን ተንጋለን በፀጥታ በተግባር የቋጨነውን በሀሳብ ትናጣጥመው ቆየን ።
እዛው እንደተንጋለልሁ እንቅልፍ ሊወስደይ ቲከጅል ፋኖሷን መልሳ አበራቻትና•••
"አንተ እይሁ ልተኛ ነው እንዴ ተነስ እይ ወደ ክፍልህ ሂድ ሆሆሆሆ!" አለይ ። ድምጧ እንዳይሰማ አፏን ገጥማ እየሳቀይ።
ብድግ አልሁና ተመውጣቴ በፊት ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብዬ•••
"ተወገኑ የተለየ አንበጣ ይሆናል ፌንጣ!" ትል ነበር እምዋ፣ እግዜር ይስጣቸው አባትሽ !
ታንቺ ተምሽቴ ለይተው ተባልነት በመስኮት እየዘለለ ወደ ሚገባ ውሽማነት ስለቀየሩይ አመስግኝልኝ እሺ?!"
አልኃት። ሊያመልጣት የሚታገላትን ሳቅ አፏ ውስጥ ብርድ ልብሱን ጎስጉሳ አስቀረችው።
በዚህ መሀል እኔና ሚሽቴ ካለንበትን ክፍል አባቷ ወደ ተኙበት ክፍል የሚያስገባው መሀለኛው በር የተንጠለጠለው መጋረጃ ገለጥ ሲል እኔም የኔ ተዋቡም እኩል አየነው ድምጣችን ብቻ ታይሆን ትንፋሻችን ጠፋ •••ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍37🥰5😱1
ሚስቴ እና አባቷ!? 😡
ክፍል~~~አምስት
በዚህ መሀል እኔና ሚሽቴ ካለንበትን ክፍል አባቷ ወደ ተኙበት ክፍል የሚያስገባው መሀለኛው በር የተንጠለጠለው መጋረጃ ገለጥ ሲል እኔም የኔ ተዋቡም እኩል አየነው ድምጣችን ብቻ ታይሆን ትንፋሻችን ጠፋ••••••
የተገለጠው መጋረጇ ወደ ቦታው ቲመለስ አይተውን ተመልሰው ሄደው ተኙ እንዴ? ብዬ ጆሮዬን ትቀስር ማንኮራፋታቸው ድምጡ ቢቀንስም አሁንም ጨርሶ አልጠፋም።
እያንኮራፉ ነው ።እሳቸው ተሆኑ መጋረጃውን የገለጡት ምንግዜ ተኝተው ምንግዜ ማንኮራፋታቸውን ቀጠሉ እያልሁ በመሀል ወደ ክፋሉ ወለል ትመለከት መጋረጃውን እንደሰው ገልጦ የገባው
ያ ጥላሸት የመሰለ የተዋቡ ድመት ሽቅብ እያየዪ ይንጠራራል።
ደንግጣ ወደ እምትቁለጨለጨው ተዋቡ ጆሮ ጠጋ አልሁን
"ኤድያ ቆሌውን ይግፈፈውና ያ ሻንቅላ ድመትሽ ነው ባክሽ ቄሌያችንን የገፈፈው እሄው እታች ቆሞ እየገላመጠኝ ይንጠራራል ፣ እኔማ አንዳንዴ አስተያየቱን ስመለከት እንደማልወደው ልቡ የነገረው እኮ ነው የሚመስለኝ ።
መጥቶ አጠገብሽ ሊተኛ አስቧል መሰል ሄዶ ላባትሽ ተማቃጠሩ በፊት ቦታ ልልቀቅለት "
ብያት በገዛ ቤቷ እንደልቧ የመሳቅ መብቷን የተነጠቀይው ተዋቡ ታፈናት ሳቅ ጋር ትትታገል እኔ ተነስቼ በገባሁባት መስኮት ወደ ክፍሌ ተመለስሁ።
መስኮቷን ስዘጋት ቅድም ትከፍታት ተጮኸችው በላይ
"ቀርርርርርርር እያለይ ትትጮህ ተሳቀኹይ ኧረ እሚያሳቅቅ ነገር ያሳቆት አቦ
ተዋቡ አቅሏን ስታ ስትጬህ አፏን አፈንኋት ይችን መስኮት ምኗን ላፍናት እናንተው?"
ጥርሴን መንከሴ ተጩኸት ያስጥላት ይመስል ጥርሴን ነክሼ ዘጋኋትና "ነግቶ ተዋቡ ትትነሳ ተውስጥ ትሸጉረዋለይ " እያልሁ ታጣፊዋ አልጋዬን ቁልቁል ታያት አስጠላችኝ።
በላብ ተሚያጠምቅ የፍቅር እሳት ተሚዘንብበት አልጋ ላይ አውርደህ በረዶ ላይ ያስተኛኸይ የተዋቡ አባት የስራህን ይስጥህ ብዬ ሽቅብ ተራገምሁና ተጠቅልዬ ተኛሁ።
ተሁለት ቀን ቡሀላ ዳግም መስኮቷን ከፈተችልይ። ተመግባቴ በፊት
"አባቷ ሰማ አልሰማ እያልሁ ታልሳቀቅ አልጋውንም ተዋቡንም እያስጮሁክ ታሰኛይ እኔም እየጮሁክ የልቤን በማድረስ አባቷ በብስጭት በውድቅት ለሊት በሮ እንዲጠፋ ታላረግሁ እኔ አንዳርጌ አይደለሁም !!"
ብዬ ፈክሬ ገባሁ። ተገባሁ ኋላ ግን ተዋቡ "ተው ቀስበል አለሜ አብዋ እንዳይሰማ !"
እያለይ ስለምነይ ለሷ ትል ተውሁት። አቧቷ በመሀል ድንገት ማንኮሯፋቱን አቁሞ መገላበጥ ቲያበዛ ተዋቡ •••
"ታይሰማን አይቀርም!" ብላ በጭንቀት ነፍሷ ልትወጣ ደረሰይ። እኔም የሷ ጭንቀት ትላስጨነቀይ በመሀል አቋርጬ ድምጣችንን አጥፍተን ትንሽ ቆየንና መገላበጡን አቁሞ ማንኮራፋት ቲጀምር ተነስቼ ወደክፍሌ ተመለስሁ።
ተስድስት ቀን በላይ በግዜ እየገባሁ እክፍሌ እያመሸው ብቆይም አባቷ ሀሳባቸውን ለመቀየር ፍንጭም ታያሳዩ ስለቆዩ ተበሳጨሁ።
እኝህ ሰው በምን ብልሀት ተኔም ተሚሽቴም አናት ላይ ሊወርዱ እንደሚችሉ ቁጭ ብዬ ታሰላስል ዋልሁ። አንድ ሀሳብ ስለመጣልይ ተዋቡ ማታ እራት ይዛ ክፍሌ ትትመጣ ያሰብሁትን ነገርዃት።
ምን አሰብሁ መሰለሽ ውብ አለሜ እኔ ሆን ብዬ ታምሚያለሁ ብዬ እተኛለሁ ። ያኔ አንቺ እንደተጨነቅሽ ሆነሽ •••
"እንዲህ ታሞማ ብቻውን እይህ ክፍል ውስጥ መተኛቱ ደግ አደለም እላይ ቤት ተኝቶ ላስታመው እይ ብለሽ ሀሳብ ታቀርቢያለሽ ።
መቼስ ሰው ናቸውና ታምሜ እያዩ አይሆንም አይሉም አደል?" ስላት።
"ኧረ አይልም አባዬ እኮ እንደሀይለኝነቱ ሁሉ ሩህሩህ ነው !" አለይ።
"ደግ እንግዲህ አንዴ እላይ ቤት ተገባሁ ቡሀላ ተሻለኝም አልተሻለኝም እይህ የሚቀመጡበት ምህንያት ስለማይኖራቸው መሄዳቸው አይቀርም"
"ልክ ብለሀል! አወይ አለሜ እንደው ምን ስትል እሄን መላ አሰብኸው በል !
ታብዋ ጋር ታንቀያየም በሰላም ችግራችንን የምንፈታበት ብልህ መላ ነው።
በል ነገ ተምኝታህም ሳትነሳ የታመምህ መስለህ ተኛ!" ብላይ ወጣይ።
አባቷ ጥዋት ጥዋት እኔ ታለሁባት ክፍል በር ላይ ጠሀይ እንደሚሞቁ አውቃለሁ ። ተንቅልፌ ቀደም ብዬ ብነቃም ሰአታቸው እስክትደርስ እዛው ትገላበጥ ቆየሁ።
ሁለት ሰአት ላይ ተምኝታዬ ተነስቼ በበሩ ፍንጭት ወደ ውጪ አጮለቅሁ።
እተለመደው ቦታ በርጬማቸው ላይ ተቀምጠው ጠሀይ እየሞቁ ዳዊት ቲደግሙ አየኋቸው••••
"ተሀምሳ ዳዊት የልብ ቅንነት" አለይ እምዋ
የኛን ትዳር እያሳመሙ ዳዊት ቢደግሙ ምን ዋጋ አለው።
ለሊቱን አብረን እንዳንሆን መከልከላቸው ታያንስ ቀንም እንደወንድ ወጣ ብለው ስለማይመለሱ እምንገናኝበትን ቀዳዳ ሁሉ ደፍነው በናፍቆት ርሀብ እየቀጡን ዳዊት ትለደገሙ ተቅጣት የሚያመልጡ መሰላቸው እንዴ?
ተመጡ ጀምሮ የለሊቱ ይሁን ቀን እንኳን ተቤት አይወጡም እኮ እናንተው
ተሁለት እስተ አራት ሰአት ጠሀይ ቲሞቁ ይቆያሉ ።
ጠሀይዋ አየል እያለይ ትትመጣ ተነስተው ግቢ ውስጥ ወዳለ አንድ ትልቅ ዛፍ ስር ይሄዱና ቆዳ ለበስ የሆነይ ራድዬናቸውን ከፍተው ምሳ ሰአት እስቲደርስ ጣብያ እየቀያየሩ የባጥ የቆጡን ቲሰሙ ይቆያሉ።
ምሳ በልተው ትንሽ እረፍት ይወስዱና ግቢ ውስጥ እየተንጎራደዱ እሚሰራ ስራ ቢያጡንኳ ምንም ያልሆነውን የግቢውን የንጨት አጥር ቲያጠባብቁ ይውላሉ።
የኛን የትዳር አጥር እያፈረሱ ምንም ያልሆነው የግቢያችንን አጥር ቲያጠባብቁ ታይ "እኝህ ሰው ግን ተቀልባቸው ጋር ታይጣሉም አይቀሩ!" እላለሁ።
በበሩ ፍንጭት መኖራቸውን ታረጋገጥሁ ቡሀላ ወድያው ወደ መኝታዬ ተመለስሁና እኔና ውብዬ ባቀድነው መሰረት እንዳመመው ሰው ማቃሰት ጀመርሁ።
"እህህህም •••እህህህም •••እትትትትት እህህህም•••" ለደቂቃዎይ እንዳቃሰትሁ እሳቸው ሰምተው ምንሆንክም ታይሉኝ እኔ ደከመይ ።
ዦሮዎትም አይስማ እንዴ የተዋቡ አባት አልሁና ትንሽ አረፌ ፣ ትንፋሽ ወስጄ ድምጤን ዘለግ አድርጌ ማቃሰቴን ቀጠልሁ ••• ።
ምንም ታይሉዪ ቆይተው ተዋቡ እምኝታ ቤቷ ሆኖ ሰምታዪ ነው መሰለዪ (መቸስ መስማቷ አይቀርም)
"ባሌ ምጥ ላይ እንዳለይ ሴት እሄን ሁሉ ቲያቃስት አባዬ ምንሆንክ የማይለው አልሰማሁም ለማለት ነው? " ብላ ነው መሰል ተትልቁ ቤት ብቅ ትትል እሳቸውም የሷን መውጣት ጠብቀው•••
"ተዋቡ እሄ ልዥ በደናው ነው?" ብለው ቲጠይቋት ትለሰማሁ ማቃሰቴን ገታ አድርጌ ምላሿን መጠበቅ ዠመርሁ።
እንዳልሰማይ ስትሆን ደግመው ጠየቋት።
" ማነው እሱ ?" አለይ እንዳላወቀይ መስላ።
"ያንቺው አንዳርጌ ነዋ !" አሉ የተዋቡ አባት አያ ዘርጋው።
ጉድ እኮ ነው እናንተ የሷ መሆኔን ታወቁ ዛድያ የሷን ነገር ለኔው ትተውልይ ብሄዱ ምናለ ያንቺው እያሉ ተሷ መነጠል ምን ይሉታል? ።
ባልና ሚሽት ማራራቅ ለትዳር ይጠቅማል የሚል ጥሁፍ ተይትኛው መጥሀፍ ላይ ነው ያነበቡት? እያልሁ በልቤ የኔዋ ተዋቡ•••
"ኧረ እንጃ ! ምን ሆኗል ? መችስ ተነሳ? ምን ሰማህ አቡዋ!?" ትትል ሰማሁ ። አይ ተዋቡ ያልተስተማረይ ምሁር ነይ እኮ እምዋን ይንሳይ።
"እኔ ምን አውቃለሁ ? እየቃዥ ይሁን አሞት ብቻ ሲያቃስት የሰማሁ መሰለዪ" አሏት።
"መች አሁን ነው?" አለይ ተዋቡ።
ኧረ እዚህ ተተቀመጥሁ ዥምሮ እያቃሰተ ነው በጤናውም አይመስለይ!"አሉ።
ጆሮዬን ማመን ተሳነይ ዛድያ ተተቀመጡ ጀምሮ እየሰሙዪ ኖሯል እንደዛ ትንፋሽ እስቲያጥረይዪ ታቃስት ዝም ያሉይ !! እኔስ በጤናዬ ነው እርሶ ግን ጤነኛም አይመስሉዪ አልሁ ባይሰሙኝም ንዴቴን ልትንፍሰው ብዬ።
"እስቲ ቆይ" አለችና ወደ በሬ ተጠግታ አንኳኳይ።
ቲያቀብጠኝ እንዴ ትድገመው ብዬ ዝም ስል•••
👍48🔥1
"ተይው በቃ ተኝቶ እየቃዥ ነው ማለት ነው" አሉ አባቷ። ወድያው •••
" ማማማ •••ማ ነው" አልሁ ቀና ብዬ።
ድምጤን የታመመ ሰው ድምጥ ለማስመሰል እየሞከርሁ።
"እኔ ነዪ በሩን ክፈተው እስቲ" አለዪ ተዋቡ።
"ምን ሆነሀል አመመህ ወይ? አትይውም ከበሩ መከፈት ምን አለሽ !" አሉ ከፍቼላት ወደ ውስጥ እንዳትዘልቅ በሰበቡም አውርታኝ እንዳንታረቅ ሰግተው ነው መሰለይ።
"ምኑን ጠረ ፍቅር የሆኑትን አማች ሰጠኸኝ ፈጣሪዬ!"እያልሁ ተነስቼ በሩን ከፈትሁላትና ተጠቅልዬ ተኛሁ።
በሩን ገፋ አድርጋ ትትገባ ተከትለዋት ገቡ።
"አብዋ እያቃሰተ ነው ብሎኝ እኮ ነው ደናም አይደለህ እንዴ?" አለችይ።
አንዴ እሳቸውን አንዴ እኔን እያየይ።
"ኧረ አሞኛል! እንቅልፍ አልነሳችሁም ብዬ እንጂ እኩለ ለሊት እኮ ነው የጀመረይ።
መዥመሪያ እራስ ምታት ቲያነደኝ ቆየና ለጥቆ ደግሞ ተሆዴ ዥምሮ ብርድ ብርድ እያለ ያንሰፈስፈይ ገባ።
እሱን ቲጨርስ መላ አካላቴን በላብ የሚያጠምቅ ትኩሳት ለቀቀብይ ።
አሁን ተነጋ ደግሞ ቁርጥማት እና ብርድ ብርዱን አልቻልሁትም!"
አልሁ እንኳን ለተዋቡና ላባቷ ለሀኪምም የሚቸግር የህመም አይነት ደርድሬ ታበቃ ህመሙን በተግባር ለማሳየት ታገጬ ዥምሬ መላ አካላቴን ማንቀጥቀጥ ዥመርሁ።
"አውቂያታለሁ ያቺ እርኩስ ታትነድፈው አቀርም በይ አንቺ ሂጅና ትኩስ ትኩስ ነገር አዘጋጅለት!
እኔ ታች መንደር ልሂድና ለመድሃኒት የሚሆን ቅጠላ ቅጠል ፈላልጌ ላምጣለት"
ብለው ተክፍሌ ወጡ።
እኔና ተዋቡ ተያይተን ተሳሳቅን "በይ ሂጂ የደጁን በር ዝጊው " አልኋት።
"ኧረ ቆይ ትንሽ ራቅ ይበል !" አለችይ ፈገግ እንዳለይ።
"እዚህ ተመጡ ቡሀላ ለመዠመሪያ ግዜ ነው አይደል ግቢውን ለቀው ቲወጡ!" ስላት•••
"ሂድ ወድያ ብሽቅ!' ብላይ እየሳቀይ እሷም ተክፍሌ ወጣይና የደጁን በር ዘግታ ቁርስ ይዛልይ መጣይ።
እንደው ስከለከል ነው መሰል ተዋቡን ባየኋት ቁጥር ታሰኘይ ዥመር።
አባቷ ሰሙይ አልሰሙኝ ሳልል በነጣነት
እሷኑ ላጣጥማት ከጀልሁና ታመጣችልኝ ቁርስ በፊት እሷኑ ተሸክሜ
አልጋው ላይ•••የልባችንን አድርሰን ቁርሳችንን በልተን ትንጨርስ ሄዳ የደጁን በር ከፈተችው።
አባቷ ቲመለሱ ምን አዘጋጀሽለት?
እንዳይሏት ለይምሰል አንዳንድ ነገር ሰራርታ ወደ ክፍሌ ታመጣይ ቡሀላ •••
"በል እንግዲህ አብዋ እውነትም የታመምህ ስለመሰለው አመሻሹን እሱም "ወደላይኛው ቤት ይምጣ" ማለቱ አይቀርም እሱ ባይልም እኔው እያመመው እዚህ እንዴት ብቻውን ይተኛል እልና እላይ ቤት እንገባለን ።
እስተዛው መምጫው ስለማይታወቅ ዝም ብለህ ተኛ እኔ አሁን ስራ አለብይ ፣ ወደከብቶቹ ቤትም ተነጋ አልሄድኩም ወተቱን በወጉ አልበው ወደከተማ መውሰዳቸውን አረጋግጬ እመለሳለሁይ" ብላይ ወጣይ።
ትለደከመይ አፍታም ታልቆይ እንቅልፍ ጣለዪ።
አቧቷ እንደመጡ ተንቅልፌ ቀስቅሰው በወጉም ሳልነቃ ምሬቱ እንጥል የሚበጥስ የቅጠላ ቅጠል ዱቄት በጥብጠው ቲግቱኝ እንቢ ማለት አልቻልሁም።
ተጠጣሁ ቡሀላ አንገፈገፈይ።
እሄን ተምጠጣ እንኳን አንድ ወር አንድ አመትስ ተምሽቴ ባልተኛ ምናል አልሁ ።
እንደውም ጤነኛ የነበርሁት ሰውዬ ቅጠላ ቅጠሉን በጥብጠው ተጋቱዪ ኋላ አመመይ።
እንደገባ አጥወለወለይ ፣ ትንሽ ቆይቶ ታልወጣሁ እያለ ይተናነቀይ ገባ።
ተቀኑ ዘጠይ ሰአት ጀምሮ በየሰኮንዱ ወደሽንት ቤት ያሯሩጠይ ገባ ፣
መጣሁ ባለይ ቁጥር ወደ ሽንት ቤት መሮጡ ሰልችቶይ ፍራሼን ይዤ እሽንት ቤቱ በር ላይ መተኛት ተመኘሁ።
ምን አቀበጠይ ።
"ሳልታመም ታምሚያለሁ ብዬ የእውነት አደረከው ኧረ ይቅር በለይ ጌታዬ !"••••
••••ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍42👎1🥰1
አትሮኖስ pinned «#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ //// ከጄኔራሏ ጋር ከአስራ አምስት ቀን በኃላ መገናኘታችን ነው፡፡ በጣም ናቃኛለች፡፡እኔም ሰሞኑን በጣም በተወጣጠረ እና በተጨናነቀ ሁኔታ ላይ ስለነበርኩ ላገኛት አልቻልኩም ነበር…እሷም ለምን እንደሆነ አላውቅም ላግኝህ ብላኝ አታውቅም ፡፡ ‹‹እንዴት ነች ልጅህ?›› ‹‹ደህና ነች…በጣም ደህና ነች›› ‹‹ደህና…»
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

እኔ ይቅርታዬን ሳልጨርስ ምስርም ካለችበት ተንደርድራ መጥታ ልክ እኔ እንዳደረኩት እቴቴ እግር ስር ድፍት አለች።አንዳንድ እግር ተከፍፋልን ።እቤቱ ለቅሶ በለቅሶ ተደበላለቀ።ተረባርበው ሁለታችንንም ከተደፋንበት አነሱን ..እንደተነሳን በግራና ቀኝ ትከሻዋን ተከፋፍለን ተጠመጠምንባት፡፡ ተአምርን ጨምሮ ሌሎቹም እየመጡ ተቀላቀሉን። መላቀሱና መሳሳሙ አልቆ ስርአት ይዘን ለመቀመጥ ምን አልባት ከ20 ደቂቃ በላይ ሳይፈጅ አልቀረም።የዛ ሁሉ አመት ስቃይ….የዛ ሁሉ ጊዜ ቁጭትና ፀፀት ….የዛ ሁሉ ለሊትና ቀን የልብ ድማትና የጨጓራ ቁስለት እንዲህ በአስር ደቂቃ የይቅርታ ቃላቶች እና መላቀሶች መሻሩእና መጠገኑ የሚገርም ነው፡፡ይቅርታ የሚባል ነገር ባይኖር የሰው ልጅ ጠቅላላ ህይወቱ ምን መልከ ይኖረው ነበር ?ብዬ አሰበብኩና ዝግንን አለኝ ፡፡ብቻ ቀስ በቀስ መረጋጋቱ ሲመጣ ወደ ጫወታና መሳሳቅ ገባን።

"አያቴ ግን እንዴት..?"እኔ ነኝ ለመጀመሪያ ጊዜ አያቴን ፊት ለፊት በአካል ከእነአዛውንት ውበቱና ግርማ ሞገሱ በማየቴ እየተደመምኩ የጠየቅኩት፡፡

"እንዴት ምን..?"

"ዛሬ እንዴት ወጡ..አታስበው አልመጣም ብለውኝ ነበርኮ"

‹ሀሳቤን ቀየርኮ…ይሄ ተአምራዊ ቀን እንዲያመልጠኝ ፈፅሞ አልፈለኩም..ስለልጅህ ስለአክስትህ በአጠቃላይ ስለመላው ቤተሠብ ለሁለት አመት በእየለቱ ስታወራልኝ ስለከረምክ ለእኔም ልክ እንደቤተሠቤ ነበር የሚናፍቁኝ.ጄኔራል ሁኔታውንና የተቀደሰ ሀሳቧን አብራርታ ስትነግረኝ በእንቢታዬ መግፋት አልቻለልኩም።"

‹‹እሱሰ እውነቷትን ነው አያቴ. ግን ይሄ በጣም የሚገደርም ውሳኔ ነው ?መቼስ ጋሼ ይሄንን ቢያይ ተገርሞም አያባራም…››

ከዛ ብዙ ብዙ ጫወታ ተጫወትን..ምሳ ቀረበ የሚጣጡ መጠጦች እንደየምራጫችን ታደሉን …በሳቅና ጫወታ ያወራረድን በደስታ ተመገብን፡፡
እስከ10 ሰዓት ስንጫወት ቆየንና ከሳምንት በኃላ ወይ እኔ ሄጄ ልጠይቃቸው ወይ ደግሞ ሁሉም ተሰብስበው እኔ ቤት ሊመጡ ተነጋገርንና እንዳመጣጣቸው ሸኘናቸው….በመጨረሻ እኔና ጄኔራሎ ብቻ ቀረን፡፡ከዛ የተደመምኩባቸውን ጥያቄዎች ተራ በተራ አቀርብላት ጀመር፡፡

"ግን እንዴት?"
"እንዴት ማለት?"
"እነ አክስቴን እንዴት አገኘሽ ?እንዴት አሳመንሻቸው?"

"ቀላል ነበር..የአንተን ማንነት ካወቅኩ በኃላ የወላጆችህን ቤት የተከራዪት ሰዎች ጋር ሄድኩና ያክስትህን ስልክ ተቀበልኩ …ከዛ ወደ ደብረብርሀን ሄድኩ።"
"ደብረ ብርሀን ድረስ?"
"ደብረብርሀን እኮ እዚሁ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ነች።"
"እሺ ይሁን .ከዛስ..?"
"ከዛማ ደረስኩና ደወልኩላት… የሞች እህቷ የድሮ ወዳጅ እንደሆንኩ ነግሬ የቤቷን አድራሻ ጠየቅኩ ።በቀላሉ ነገረችኝ፡፡ቀጥታ እቤት ሄጄ አዋዝቼ ስላንተ ነገርኳት።"

"በፈጣሪ ምን አለች ..?አልተበሳጨችም?"በከፍተኛ ጉጉት ጠየቅኳት

"ወይ መበሳጨት ..እዬብ በህይወት አለ ስላት እህተሽ ከመቃብር ወጣች ያልኳት ነው የመሠላት ..ለአንድ ሰዓት ስታለቅስ፤ ስትስመኘ፤ስትመርቀኝ ምኑን ልንገርህ..እውነት መሆኑን አላመነችም እህትቶችህ..በተለይ በተለይ እማ!!ያው ይገባሀል..አሁንም የፍቅር ስቃይ ፊቷ ላይ አለ…አሁንም በናፍቆት እየቃተተች ነው..አሁንም በማይድነው አጉል በሽታ ተለክፋ ትንፍሽ እንዳጠራት መሆኑን ሁኔታዎን ለደቂቃ አይቶ መረዳት ይቻላል።››

"ልጅህ ደግሞ።"
"ልጄ ምን?"
"አደገኛ አክተር ይወጣታል ..ልክ ስለአንተ ለመጀመሪያ ቀን እንደሰማ ሰው አብራ ስታዳንቅ ሳይ እኔ እራሴ ይሄ ልጅ ዋሽቶኛል እንዴ?በእርግጥስ የእውነት አግኝቶት ያውቃል? ብዬ እራሴን ለመጠየቅ ተገደድኩ"
"አዎ ቆቅ የሆነች ልጅ ነች ያለቺኝ"
"እስማማለሁ"
"እሺ አያቴንስ እንዴት አሳምነሽ አመጣሻቸው?"
ቀላል አልነበረም፣የጥሪ ካርዱን ባንተ በኩል ል እንዳልተስማሙ ከነገርከኝ ቡኃላ ያንተን አለመኖር እየጠበቅኩ ከሶስት ቀን በላይ መመላለስ ነበረብኝ..ቢያለፋኝም ተሳክቶልኛል።በዚህ አጋጣሚ ልንገርህ ..መቼም መቼም አያትህን እንዳታስቀይማቸው።የእውነትም እንደልጃቸው ነው የሚያዪህ።በጣም ነው የሚወድህ"
"አውቃለሁ..እኔም አያቴ ስላቸው ለማስመሰል አይደለም...የእውነት ከልቤ እንደዛ ስለሚሰማኝ ነው።
"ታድለህ"
እንዴት ታድለህ ልትይ ቻልሽ?"
"ብዙ ሰዎች ብዙ ደክመው ብዙ ጥረው የማይሳካላቸውን የሠው መውደድ አንተ በቀላሉ አለህ..አክስትህ..እህቶችህ.ልጅህ..አያትህ ..እኔ..ሁላችንም አምርረን እንወድሀለን "
"የእውነት ..?አንቺም አምርረሽ ትወጂኛለሽ?"
"ከዝርዝሩ ውስጥ የእኔ ነው አጠራጣሪው?"
"አይ እንደዛ ማለቴ አይደለም ..እንዲሁ አለ አይደል ..ለማረጋገጥ ነው የጠየቅኩት"
‹‹አይዞህ አትጠራጠር ..አንተ በጣም ውድድድ የማደርግህ ፤ታናሽ ወንድሜ ነህ?"
"በለው....አየሽ እድሌን?"
"እንዴት?"
"አሁን እኔ እህት የናፈቀኝ ይመስልሻል..?"
"አሁን እኳ ምርጫ የለህም ..የልጅህ እናት አሁንም እንደተራበችህ ነው..እርግጠኛ ነኝ አንተን ሳትይዝ ወደአሜሪካዋ አትመለስም።"
"ይዛኝ ሄዳስ?"
"እሱን እንግዲህ ጊዜ የሚመልሰው አስቸጋሪ ጥያቄ ይሆናል።››

"እሺ እንዳልሽ አሁን ትንሽ ጉዳይ ስላለችብኝ ልሂድ… ነገ እመጣና እዚሁ አድሬ እሸኝሻለሁ..ይቻላል አይደል?"
"በጣም ደስ ይለኛል።ጉንጯን ስሜ ተሠናብቼ ወጣሁ።››

ይቀጥላል
👍808😢2🔥1🤔1
ሚስቴ እና አባቷ!? 😡
ክፍል~~~ስድስት
ምን አቀበጠይ ።
"ሳልታመም ታምሚያለሁ ብዬ የእውነት አደረከው ኧረ ይቅር በለኝ ጌታዬ !"••••
ሚሽቴምኮ አብራይ ተሰቃየይ ነገሩ አብረን ነን እሄን ተንኮል የሸረብነው ቢሆንም ማስታመም ተመታመም አይተናነስምና ለሷ ጭንቀት ስትል ማረይ!!!! " አልሁ ተልቤ።ጭንቁ ቲበዛብይ።
ተምሽቱ አንድ ሰአት አከባቢ የገባሁ ሁሉ ወጥቶ አለቀ መሰለይ ሁሉም ነገር ቀጥ አለ ። ተሶስት ሰአት በላይ በተከታታይ ቲያሯሩጠኝ ስለቆየ ሁለ መናዬ ዝሎ እራሴን ስቼ እዛቹ ታጣፊ አልጋዬ ላይ እንደተዘረጋጋሁ እንቅልፍ ጣለይ።
ምን ያህል እንደተኛሁ እንጃ ብቻ ብንን ትል ተዋቡና አቧቷ እክፍሌ ውስጥ ተቀምጠዋል ።
"ነቅቷል መሰለይ ወደላይ ቤት ይዘነው እንሂድ አደል አቡዋ?" አለች የኔ ተዋቡ ።
ወባ ነች ያመመችው አልሁሽ እኮ ለኔና ላንቺስ ግድ የለም ለህጣና ልጅ አታስቢም ይልቅ ሂጂና እምኝታችሁ ላይ አጎበሩን ዘርጊና ተልጅሽ ጋር ተኚ ! ዛሬን እዚሁ ይደርና እስከጥዋት ለውጥ ከሌለው ከተማ ወዳለው ሀኪም ቤት ይዘነው እንሄዳለን ። አሏት።
ውባ አለሜ እባቷ እንዲያ ሲሏት በሀፍረት ኩምሽሽ ብላ አይን አይኔን ትታየኝ አየኋት።
በንዴት እርርርርርይ ብዬ ልጬህ ምንም አልቀረይ ።
ልጩህ ብልስ መድሀኒት ነው ብለው ያጠጡይ በሽታ አቅም አሳጥቶኛል በምን አቅሜ እጮሀለሁ።
"ወባ ነይ ብለህ ነው አቡዋ እኔ አይመስለኝም " አለይ ኮስተር ብላ።
እቅዳችን ትላልተሳካ እና እንዳለችው ይዛኝ ወደላይቤት እንዳንገባ የማይነቀል እንቅፋት በሆኑባት በገዛ አባቷ ተማፈሯም በላይ ተናደለይ ።
"ወባ ነች አንቺ ነሽ እምውቂው እኔ ይልቅ ሂጂ ልጅሽም ተነስታለይ መሰለይ ድምጣ ይሰማል?" አሏት። እሄን ግዜ ብሽቅ አልሁና •••
"ወባማ አይደለም ያመመኝ!"አልሁ።
"እና እምትንቀጠቀጠው ጎጃምኛ እየጨፈርህ ኖሯል ምን ይላል እሄ!" አሉ አባቷ በቁጣ።
"ኧረ አልተንቀጠቀጥሁም መች ተንቀጠቀጥሁ!"
እንኳን አካልህ ድምጥህም እየተንቀጠቀጠ ነው ተወባ ውጪ እንዲህ የሚያደርግ በሽታ የታለ አንተ ልዥ ሰው የሚልህን ስማ!" አሉይ አይናቸውን አፍጠው"
ዝም አልኋቸው ። ሁለቱም ዝም ብለው ቲያዩኝ እሳቸውን ትቼ ወደምሽቴ ዞርሁና
"እንደኔ እንደኔ ተሆነ ግን
ያመመኝ ወባ ታይሆን ብርድ ነው ተዋቡ።
የዚህን ክፍል ግርግዳ እይው እስቲ ተሰነጣጥቋል እኮ!!!
ያን ግዜ እሄን ቤት ጭቃ ትናስመርገው ሳንቲም ቀነሰልን ብለን በማይረባ ሰው ነው ያስመረግነው።
ምርጉ አይረባ ልስኑ አይረባ ሞላ ግርግዳው እኮ ሽንቁር ብቻ ነው ።
ብርድ የማይገባበት ቀዳዳ የለም ስልሽ እግሬን ትሸፍን ታናቴ በኩል ይገባል፣ አናቴን ትሸፈን ተጎኔ በኩል ይገባል እሱ ነው በየቅጣጫው ትነፍስብይ ሰንብቶ ለበሽታ የዳረገይ!" አልሁ።
"ዛድያ አንተ ምን ቆራጣ ብርድልብስ የለበስህ ይመስል አንዴ እግርህን አንዴ አናትህን እያልህ በፈረቃ አሸፋፈነህ? ሁለመናህን ተሸፋፍነህ ለጥ አትልም አሉኝ አቶ ዘርጋው ።የተዋቡ አባት።
ኡፍፍፍፍ ሚሽቴን ባወራትም መልስ የሚሰጡይ እሳቸው ናቸው ። አሁንስ አበዙት እኝህ ሰው ብዬ በውስጤ ተልጌልጉሜ ታልጨርስ ቀጠል አረጉና•••
"ምርጉም ሆነ ልስኑ ሽግር ታለበት ደግሞ ተሽሎህ ስትነሳ እይሁ ግቢ ውስጥ እዛ እመውጫው በር በስተግራ በኩል ትቆፍርና ድንጋዩንም ጠጠሩም ለይተህ ለምርግ የሚበቃ አፈር ታዘገጀህ ቡሀላ ጭቃ ታቦካለህ።
በየሶስት ቀኑ እያሸህ ፣እያገላበጥህ እስቲበስል ድረስ ለሁለት ሳምንት በደንብ ታቦካኸው ቡሀላ ይህን የተሰናጣጠቀ ግድግዳ አፍርሰህ ወድያ ትጥልና ግጥም አርገህ ትመርገዋለህ ! እስታሁንስ ዝም ያልከው አንተ ለዚህ አንሰህ ነው አንዳርጌ ?
ባይሆን እኔም እስተዛው እዚሁ ስላለሁ ልሱኑ ላይ አግዝሀለሁ !" ሲሉይ •••
ሀሞቴ ፍስስ አለይ።
"በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ " ያለይው ማን ነበርሳ ። እሳቸውን ተቤቴ ላበር በጠነሰስሁር ሴራ እኔኑ ሊያበሩኝ ነው መሰል አሁንስ።
"ለማንኛቸውም እኔ ብርድ እይ ወባ አላመመኝም አላመመኝም አበቃሁ !”
አልሁና ተሸፋፍኜ ተኛሁ አባትና ልጅ ተከታትለው ተክፍሌ ወጡ ። ተውጪ ዘጉብይ።
ጥዋት ላይ ተንቅልፌ ብንን ትል ተምኝታዬ ፊት የሚሽቴ አባት ቁጭ ብለዋል።
"ደና አደርህ አንዳርጌ? አዳርህ እንዴት ነው ለውጥ አለው?"
" ምንም አልል "አልሁ እየተንጠራራሁ።
"አይዞህ ለማንኛቸውም እንዳልኸው ብርድ ተሆነ የመታህ አንድ ተቡና ጋር የምትወሰድ ፍቱን ቅጠል አለይ ታች መንደር ወርጄ ይዤልህ ልምጣ!" ሲሉይ ገና ታያመጡት አንቀጠቀጠይ።
ኧረ በዲማው ጊዬርጊስ !!!
ተሽሎኛል እኮ! እንደኔ ጤነኛ አለ እንዴ!
ብርድ•••••
ኧረ የምን ብርድ ? ለሊቱን ነው በላብ ንቅል ብሎ የወጣልይ !
አብዋ አይድከሙ፣ እውነቴን ነው ምንም የህመም ዘር ውስጤ የለም።
እንኳን ሊበርደይ ሞቆኛል!"
አልኋቸው ቅጠል ላምጣልህ ቲሉኝ በድንጋጤ ያላበኝን እግንባሬ ላይ ችፍ ያለ ላብ እየጠረግሁ።
"ታልህ ይሁን አንዳንድ በሽታ ሄድ መለስ ይላልና መልሶ ታመመህ ንገረይ !"
ብለውይ ተክፍሌ ቲወጡ አንገቴን ሽቅብና ቁልቁል እያወዛወዝሁ በጀ አልኋቸው።
እንኳን የውሸት የእውነት ብታመምስ መች ለርሶ እነግሮታለሁ ሆሆ•••ቅጠል!! አልሄድ ብላቸው እዚሁ ሊገላግሉይ አስበዋል እንዴ እኝህ ሰው።
ሳልወድ በግዳጅ በሳቸው ውሳኔ ተተሰደድኩበት ክፍል ወጥቼ በህመም ሰበብ ወደቤቴ ልመለስ ፣ ስንት አውጥቼ ስንት አውርጄይ ባመጣሁት መላ የውሸት ብታመም መዳኒት ብለው ባጠጡይ ነገር የእውነት ታምሜ ለሶስት ሰአት ያህል ሽንት ቤት ተሯሯጥሁ።
ኪሎዬም ቀነሰ፣ ወዘናዬ ተመጦ ፊቴም ገረጣ፣ አቅሜም ተዳከመ ።
ታሁን ቡሀላ እኝህ ሰው እኔና ምሽቴ ተትዳራችን መሀል ገለል ይበሉ!!! ብለን ሰላማዊ ሰልፍ ታልወጣን በስተቀር ወር ታይሞላቸው ተዛች ቤት ንቅንቅ እንደማይሉ እርግጠኛ ትለሆንኩ ተስፋ ቆረጥሁ።
አዎ እኚ ሰው በመላም በበላም አይወጡም።
ሌላ መላ ለመፈለግ መባዘኑን ይቅርብይ አልሁና የተጎዳውን አካሌን ለመጠገን ለሁለት ቀን ተክፍሌ ታልወጣ ተቀለብሁ።
ተዋቡዬም ጥሩ ጥሩውን እየሰራይ ስለምታመጣልይ በሁለት ቀን ሰውነቴም ጉልበቴም መለስ አለ።
እቤት መጠጣትም በመስኮት እንደሌባ እየገቡ ሚሽቴን ማግኘትም ምርር አለይ።
አመሻሹ ላይ ተዋቡ ታታየኝ ወጥቼ ወደ ጠጅ ቤት ሄድሁ።
ገና ገብቼ አንድ ሁለት እንዳልሁ•••
" ምን ሆነሀል ጃል? ስትገባም ሰላም አላልከኝ፣ ከገባህ ቡሀላም ሀሳብ ገብቶሀል ።
እዚህ አካልህ ተቀመጠ እይ ቀልብህ የለም እኮ በደህና ነው?" አለይ ።
ተጀርባዬ የተቀመጠው ተጠጅቤት ጋደኛቼ መሀል አንዱ የሆነው ዳምጤ።
ቀደም ብሎ ነው መሰል የገባው ሞቅ ብሎታል !
"ደህና ነይ!" አልሁት።
"አሞህ ነበር እንዴ ?ፊትህም ጭር ብሏል ሰሞኑንም መጥተህም አታውቅም ሰላም ነህ ግን ወዳጄ?" አለይ ደግሞ።
ተወኝ እስቲ ዳምጤ አልሁና ያለሁበትን ሁናታ በግርድፉ ነግሬው
"ባልና ሚስት ካንድ ወንዝ ይቀዳሉ" ይባላል የኔ ሚሽት ግን ከኔ ጋር ታይሆን ካባቷ ጋር ሳይሆን አይቀርም ካንድ ወንዝ የተቀዱት አልሁት።
ታለበት ተነስቶ ተጎኔ በመቀመጥ ለወሬ ተመቻቸና •••
"ስማ አባቷማ አባት ነው ከሱ መወለዷ ካንድ ወንዝ ከመቀዳት አይበልጥም ብለህ ነው ? ግን እሄ አባብል በመሰረቱ አይጥመኝም በጣም ነው የሚያናድደኝ !" አለይ።
"የቱ? አልሁት ።ግራ ገብቶይ።
"እሄ •••ባልና ሚሽት ታንድ ወንዝ ይቀዳሉ" የሚሉት ነገር"" አለይ።
👍434🔥1😁1
"እምትናደድበት ነገር ቸግሮሀል መሰል ወዳጄ እሚካፈል ቢሆን ባከፈልኩህ ኧረ እንደውም ሁሉንም በሰጠሁህ
እንዴት
ምን እንዴት አለው አሁን እምትናደድበት አጥተህ ነው በዚህ እምትናደደው
"እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ
"ባልና ሚሽት ካንድ ወንዝ ይቀዳሉ" ብሎ ለመጀመሪያ ግዜ የተናገረው ወይ የጣፈው ግን ማን እንደሆን ታውቃለህ ? ""
ቲለኝ•••
አባቷ የጀመሩይን እሱ ሊጨርሰይ ነው እንዴ አልሁና በሆዴ!!
አብደሀል እንዴ አንተ ሰው እሄ ተስንት ዘመን ዥምሮ ቲወርድ ቲዋረድ የመጣ አባብልም እይደል እንዴ
እንደዛ ሲሉ እሰማለሁ እይ ማን እንዳለው በምን አውቃለሁ ዳምጤ !?" ብለው ።
"እሄን ሰው ባገኘው አንድ ጥያቄ እጠይቀው ነበር አንድ ብቻ !ሳልደግም ሳልሰልስ አንድ ብቻ ጠይቄው ምን እንደሚለኝ በሰማሁ "
ምን ብለህ ነው እምጠይቀው ጃል?አልሁት ለካ እኔ ብቻ አይደለሁም ቀልቤን ያጣሁት እያልሁ።
"ከነኝህ ከንድ ወንዝ ከሚቀዱ ወይ ከሚጨለፉ ባልና ሚሽቶች ስም ዝርዝር መሀል የኔና የሚሽቴን ስም ልታሳየኝ ትችላለህ ወይ ብዬነዋ?
እንደው ባገኘው ይህን ጠይቄ ጉዱን ነበር እማፈላው! መልሱ የናንተ ሽም የለም እንደሚሆን መች አጣሁት!•••
ቀኑን ተወው ሳምንቱን ፣ሳምንቱን ተወው ወርና አመቱን የኔና የባልተቤቴን ሽም ለማግኘት ቢኳትን አያገኘውም ስልህ••
ታይኔ ነው ብሎ መነጥር ቢደረግም፣ ተመነጥሩ ነው ብሎ አጉሊ መነጥር ቢገረግድ ያልሆነውን ተዌት ያመጣናል!"
ተው እይ ጃል ታንድ ወንዝ ባትቀዱ ምን አቆራኛችሁ እህል ውሃ ባንተና በሷ መሀል ባይጣፍ ስሜት ጋልቧችሁ ብትጋቡ እንኳ ተሶስት ወር በላይ አብራችሁ ባልዘለቃችሁ ? ብለው ቱግ ብሎ ተመቀመጫው ተነሳና•••
"እኔና ሚስቴ ነን ታንድ ወንዝ የተቀዳነው?
ስማ ትሰማኛለህ እኔና ሚሽቴ አይደለም
ታንድ ወንዝ ልንቀዳ ተሁለት የተለያዩ ወንዞይ እንኳ አልተቀዳንም
ምን ይላል እሄ •••" አለይ።ቱግ ሲል በረድ ብዬ
እንዴት ? ብለው "እንዴት ማለት ጥሩ ነው" አለና•••
ስለኔ እና ስለሚስቴ እውነቱን ማወቅ እምትፈልግ ተሆነ ልንገርህ አድምጠይ
እኔ እና አሷ ማለት እኔ ወንዝ ትሆን እሷ ተራራ ነይ ተራራ ታውቃለህ አደል
ወንዝ ተራራ ላይ ይወጣል??
በፍፁም አይወጣም! ቁልቁል ተሆነ ይሄዳል ብለው
"ልክ ብለሀል ብሄደም ሽቅብ ታይሆን ቁልቁል ተምዘግዝጎ ባናቱ መፈጥፈጥ ይሆናል እጣ ፋንታው
ዛድያ እሷ ተራራም አይደለይ እኔ ከሷ ጋር የምኖረው ሁሌ እየተፈጠፈጥሁ ስልህ ምን ነካህ ፊቴን ተመልከተው እይ
እውነቱን ተናገር እሄ ድሮ የምታውቀው የዳምጠው ፊት ነው ? በጭራሽ !•••
እሄውልህ የኔ ሚሽት ማለት አዘውትራ የምትለብሰው ልብሱን እኔ ያልወደድሁት እንደሆነ ብቻ ነው። አዘውትራ የምትሰራው ወጥም እኔ ባልበላው ደስ ይለኛል ያልኋትን ነው!"
ተው እንጂ ዳምጤ መስሎህ እንዳይሆን?
"መስሎህ እንዳይሆን ይለኛል እንዴ እሄ ሰው ምን ነካው ዛሬ?
እሄውልህ የኔ ሚስት አጥብቃ የምትይዛት ጋደኛ ምናልባት ይቺ ልዥ ምኗም አይጥመይ፣ ደስ አትለኝም ፣ ያልሁ እንደሆነ ነው!"
ኧረ ተው እታጋነው ዳምጤ! •••
"እስቲ ዝም ብልህ ስማይ ! •••
እኔ ነኝ ያለሁበትን ንዳድ የማውቀው ወይ ጉድ ገና ሲሶውን እንኳ መች ነገርኩህና የውልህ •••
ገብስማ ዶሮ አልወድም የሚል ቃል ታፌ ተወጣ ገብስማ ዶሮ ገዝታ ለመምጣት ተትናገርሁበት ቀን ቀጥሎ ያለውን አመትባል እንደሷ በጉጉት የሚጠብቅ ሰው በመላ ምድሪቱ እግርህ እስቲነቃ ብትፈልግ አታገኝም ስልህ ቲለኝ •••
ካካካካ ኦሮ አሁንስ በግድ ልታስቀይ ነው መሰል አንተ ሰው ብለው
ይልቅ ስማኝማ ለሳቁ ኋላ ትደርስበታለህ ብሎ •••
"ስማኝ ወዳጄ አንዳርጌ•••
ጥቁር በግ አልወድም ታልኋት መግዣ ገንዘብ ብታጣ ብታጣ ስታረግዝ ጠብቃ ጥቁር በግ አማረይ ትለኛለይ።
ያኔ የገባሁበት ገብቼ ተለቅቼም ቢሆን እልወድም ያልኋትን ጥቁር በግ እኔው ገዥቼ እየጎተትሁ ይዧላት እመጣለሁ።
ገና ጥቁሩን በግ ይዤ ስገባ እንዳየይ ደስታዋን እንዴት ብዬ ልግለጥልህ ጃል?
እንደው ተግር ጥፍራ እስተራስ ጠጉሯ ሁለመናዋ ጥርስ እስቲመስለይ ድረስ ስታገጥብይ ትውላለይ።
ዛድያ የገብስማ ዶሮውንም የጥቁር በጉንም ስጋ እንዲች ታልቀምስ ብቻዋን ቅርጥፍ አርጋነው የበላችው። ብትለምነኝም አልቀምሳት ። እየተጠየፍሁ ብብላውስ መች ሆዴ ውስጥ ይረጋልኝ እና•••
ምስር ወጥ ደስ አይለኝም ካልሁ ሳምንቱን ሙሉ ተምስር ወጥ ውጪ አትስራም ስልህ።
እየው አሁን ባለፈ ለት በዶሮው እና በበጉ ግዜ ጠብቃ የማልወደውን እየገዛይ ትታነደኝ ቆይታ የለ ሆን ብዬ ጥቁር በሬ በጣም ነው እምጠላው አልኋት ።
ተዌት ታምጣው ?እንዴት እርጋ ጥቁር በሬ አርዳ ታብግነይ ?
መንደሩን አስተባብራ እቁብ ሰብስባ ቅርጫ ልታሳርድም አሰበይ፣
ዛድያ በሬውን እሷ ሄዳ አትገዛው ነገር ። አልያም ገዥዎቹን
ጥቁር በሬ ታልሆነ ሌላ እንዳትገዙ ብትል ስንት ሰው ባዋጣው ብር ምን ብላ ብቻዋን ታዛለይ ?
ብትል እንኳ ገዥዎቹ ጥቁር በሬ ያለይው ምን አስባ ነው ?
እኛ ልንበላ እይ ለሷ ሰይጣን ልንገብር አላዋጣን ብለው ነገር እንደሚያጠሙባት ጠንቅቃ ታውቀዋለይ ።
ሁሉንም እኔን ሊያናድዱ የሚችሉ ነገሮችን አድርጋ ስታበቃ እሄን ማድረግ ተሳናት ስልህ።
እኔም በዚህ ተረታለይ ብዬ ደረቴን ነፋቼ ትንጎማለል ተቀናት ቡሀላ ዘመድ ጥየቃ ወደኸተማው አብረን ወጣን።
ድንገት እጥርግያው መንገድ መሀል •••
"ዳምጥዬ! "
አለይኝ ትከሻዬን ነካ አድርጋ ።
ሁሌም እንዲህ ብላ ትትጠራይ ለምን እንደሆን እንጃ ልቤ ትርክክ ትላለይ ብቻ ምን ልትለይ ነው ብዬ
"ወዬ!" አልኋት ••••
እስቲ በደንብ እየው ስሞትልህ ዳምጥዬ ያኛው በሬ ደስ አይልም በዲማው ጊዬርጊስ አለችይ።
ዘወር ብዬ ወደአመላከተችይ አቅጣጫ ትመለከት እመንገዱ ዳር ላይ ታለ አንድ ስጋ ቤት ነጭ እተቀባ ግርግዳ ላይ የተሳለ ትልቅ ጥቁር በሬ ነው !
እንደው አንዳርጌ ሙት ነው እምልህ ብልጭጭ አለብይ!" ••••ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍50👏2
አትሮኖስ pinned «#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// እኔ ይቅርታዬን ሳልጨርስ ምስርም ካለችበት ተንደርድራ መጥታ ልክ እኔ እንዳደረኩት እቴቴ እግር ስር ድፍት አለች።አንዳንድ እግር ተከፍፋልን ።እቤቱ ለቅሶ በለቅሶ ተደበላለቀ።ተረባርበው ሁለታችንንም ከተደፋንበት አነሱን ..እንደተነሳን በግራና ቀኝ ትከሻዋን ተከፋፍለን ተጠመጠምንባት፡፡ ተአምርን ጨምሮ ሌሎቹም…»
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_አስራ_አንድ


...ደግመን ልንበድላት አይገባም የዱላን ፍቅር አሳይዋት እሷም ተተወሰነ ጊዜ በኋላ ፍርሃቱ ይወጣላታል!"

"እእ! እሽ ዛሬስ እኛም አስበናታል ና እንጂ አንተስ
ተጫዋት?"

አለሁ የት እሄዳለሁ  አዳሬ ተዚሁ ነው" ብሎ ደልቲ
ከበርኮታው ላይ ተነሳ ጎረምሳው ደግሞ የባራዛ አርጩሜውን ወደ
ደበቁበት ጉቶ ሄዶ ሶስት ለበቆችን አነሳ ደልቲም ከወንዶች ግማሽ ክብ ሰልፍ ገብቶ ወገብ ለወገብ ተያያዘ

አንዱ ጎረምሳ አንደ መፎከሪያ በርኮታውን በቀኝ እጁ ይዞ የመፎከሪያ በሬውን ጥንካሬና ውበት የጓደኝነታቸውን ምሥጢር
ሲደረድር ሁለት ልጃገረዶች አንባራቸውን እያፋጩ: ከፊት ለፊቱ ቆመው ሲያሞጋግሱት ቆይቶ እያቀነቀነ መዝለልና መጨፈር ጀመረ
ከዚያ የእድሜ ጓደኞቹ ተቃቅፈው ሄደው በቃህ ብለው በትህትና
ጠይቀው አጅበው ተሰልፉ አስገቡት ወዲያው ግን
ጧ ጧ፥ጣጣ.ጣ… የሚል ግርፊያ ተሰማና ልጃገረዶች እያውካኩ፥ ብትን ብለው ሲስቁ ቀጭን የሲቃ ልቅሶ ከመካከላቸው ተሰማ"

ያች ባለጌ ናት! አለ ደልቲ ንድድ እያለው"

ኮቶ ምን አደረኩት ..." ካርለት እንባዋ እየረገፈ ሰውነቷ
እየተንቀጠቀጠ፥ ኮቶን ተጠምጥማ ጠየቀቻት ለበለባት የተገረፈችው
ቦታ ሰንበሩ ጀርባዋ ላይ እንደ እባብ ተጋድሞ ቆጠቆጣት እንባዋ
እርግፍ እርግፍ አለ

"ኮቶ ለምን ገረፉኝ ..." አለቻት ህቅ ብላ እያለቀሰች,

"ይእ! ካርለቴ ደንብ ነው ብየሽ! ዘመድሽኮ ነው፤ “ለምን ተኔ ጋር አትደንሽም ብሎ ነው የመታሽ ሄደሽ አብረሽው ደንሽ
ይልቅ  ታለበለዚያ ይደግምሻል"" ስትላት ካርለት ቦታውን ለቃ
ልትሄድ አሰበች ህሊናዋ ተሟገተ

"ኮቶ ለምን እገረፋለሁ!- እኔ'ኮ መመታት አለመድሁም?" ብላ
በቀላው ዐይኗ ትክ ብላ አየቻት

"ይእ!  ስንወለድ እኮ እኛም አለመድነውም ትርጉሙን
ስናውቅ ማድረግ ያለብን ነው ብለን ስናምን ልባችን ደንድኖ ለመድነው አንችስ ሰው መስለሽኝ ስትመጭ የካሮ አፈር  ፈጭተሽ መች ትቀቢ ነበር ቆዳ መልበስ:
በእግር መሄድ እንጨት
መልቀም የተማርሽው እዚህ አይደል ግርፊያም የሚለመደው ስትደፍሪ ነው
የፍቅር ማባያ ይሆንሻል
የተማርሽው እዚህ አይደል
ስትገረፊ መጀመሪያ እንደቃሪያ ያቃጥልሻል ቀጥሎ የፍቅር ማባያ ይሆንሻል በመጨረሻ ደግሞ የሚለበልበው ቃሪያ
ያምርሻል! አይዞሽ የኔ እህት ያን ጊዜ እንደ ሱስ በልቦናሽ
ውል እያለ አምጭ አምጭ' እያለ ተሐመር አንበሶች ክርን ስር ያልወሰውስሻል
ከዚያ ትለምጅዋለሽ" ብላ ደረቷ ላይ አስጠግታ አግባባቻት,

"እሽ ኮቶ ካርለት በጽሞና ስታዳምጣት ቆይታ እንባና ሳቋ ተቀላቀለባት

"እሽ! ዓላማ ታውቂያለሽ ኮቶ" አለቻት  ትክ ብላ በጨረቃ  ብርሃን እያየቻት

"ይእ! ኢላማ ማለትሽ ነው  ማነጣጠሪያ የዓልሞ ተኳሽ
መለያ ነው ኢላማ ተሆነ "

"ልክ ነሽ! የአነጣጠርኩት: ዓልሜ የምመታው ኢላማ አለኝ ኮቶ! ስለዚህ

"ይእ! አይ ካርለቴ መቼም የአንች ነገር እንደ እርጎ ዝንብ ወንዶች መዋያ ጥብሉቅ ማለት ስትወጂ  እስቲ እንደ ሴት ኢላማሽ
ልጅ መውለድ: ለባል ታዛዥ ለመሆን ይሁን የአባት ደንብ ለማክበር ይሁን ኢላማሽ!"

"እንደንስ ኮቶ!  ዳንስ አማረኝ ግርፊያ ፈለግሁኝ... ንኪው ልቤን የፍርሃት እርግጫውን አቆመ
አደፋፈርሽው አስተማርሽው ህዋን የሰው ልጅ በእግሩ ሲረግጥ እኔም በጭንቅላቴ
የመሬትን እንብርት  እነካዋለሁ…ቃሪያውን እየበላሁ ጥቅምና
ጉዳቱን ለሌላው አሳያለሁ  እነ ዲያና ፎሲ ከጉሬላ ጋር ቅጠል በልተውስ ኖረው የለ

"ይእ!- ካርለቴ!" ወዘወዘቻት ትከሻዋን"

"ደህና ነኝ ኮቶ"

"እየቃዠሽ! ቢጫ ሐሞት እንደሚያስተፋ ወባ እንደያዘው ሰው

"የለም ደህና ነኝ ቃል ኪዳን ነው ኮቶ ሰው ለመሆን፥
ጠንካራ ሰው!... በተሰጠኝ የሰውነት ክፍል ሁሉ ተጠቅሜ ከቦርጆ
ወቀሳ ለመዳን ባህሉ ተጠየቀኝ ለዓላማዬ ስል እኔም የእባብንም
አንገት አንቄ ጥርሶቹን ላይ መርዛም ነው የሚባለውን እባብ ጥቅምና
ጉዳቱን ጉሮሮውን ፈልቅቄ ላይ ተገርፌ፥ አልቅሼ: ቧጥጬ ባህሌን ጥሼ ባህል ላሳውቅ ኮቶ!"

"ይእ!  መንደር እንሂድ ካርለቴ?"z

"ተይኝ!  ትንሽ ጊዜ ብቻዬን ተይኝ!  እሽ?"

"ይእ! እሽ " ኮቶ ሄደች ዝምታ ፀጥታ ህሊናን
እንዳይደነብር  እንደሚያረጋጋ ተከብቶች ከአባቷ ከመንደሯ…
ተምራለችና ሄደች
ካርለት ራሷን ከፈተችው... ወደ ራሷ ገባች ... የላላውን
አጠባበቀች የተወጠረውን አላላች የአበጠውን አፈረጠች የቆሸሸውን አፀዳች ካርለት እንደ አዳኝ ውሻ ዐይኗን ጠበብ አድርጋ ደልቲን አየችው አያያትም" ወደ ዳንሱም ልትጋብዘው አትችልም፤ ዳንሱ
እንደገና ተጋጋለ

"ይእ! ካርለቴ ነይ ጋብዥው የገረፈሽን?" ብላ ኮቶ ጠራቻት ወገባቸውን ተቃቀፉ ከዚያ በቄንጥ እንደ ፔንዱለም ፊትና ኋላ
ተወዛወዙና ሶሰት ጊዜ ዘለል: ወዝወዝ… ብለው ሾረው ሄደው ሁለት
ጎረምሶችን ጋበዙ"

የገረፋት ጎረምሳ ካርለት ስትጋብዘው እየሰገረ ሄዶ የካርለትን ጭኖች እንደ መሮ እየሰረሰረ ገብቶ: በእጆቹ ቀጭኑን ወገቧን
ጨምድዶ አሻት ጎረምሳው ሳያቋርጥ እየሰረሰራት ጭኖችዋን በስቶ
ገባ "የት ሊደርስ ነው?" እያለች ሸሸችው እሱ ግን
ወገቧን የጨመደደበትን እጁን እየወጠረ ሲጠጋት ቆየና ከገለዋ ተጣበቀ
የሚታሸው አካሏ የአምቦ ውሃ እንደጠጣ ሰው አስገሳት እሷም
ሰረሰረችው፥ ወዘወዘችው.

ካርለት ያላየች መስላ ደልቲን አየችው ደስ ብሎታል እሷም ደስ አላት ደልቲ አልቀናም ቅናት ባህል እንጂ ተፈጥሯዊ
እንዳልሆነ አሰበች ጭፈራው ቀጠለ ጨዋታው ደመቀ።

"ኮቶ!"

"ዬ ሳቀች ከትከት ብላ ቀጣዩ ዳንስ እስኪጀመር
ቦታቸው ሲመለሱ

"ምን ሆንሽ ካርለቴ?" አለቻት

ሃሣቧን ሳትጨርስው  ደልቲ እጅዋን ያዝ አድርጎ
ከሴቶች መሐል ጠራት የሆነ ነገር እንደ ፍላፃ ተወርውሮ ስሜቷን
አጋጋለው" ፈገግ አለችለት ለስሜቷ-ለደልቲ…

ከዚያ በኋላ ብዙ አልተነጋገሩም ቀስ ቀስ እያሉ ፈንጠር ፈንጠር ብለው ጨረቃን አሹፈውባት ሰማይ ይግቡ መሬት ጠፉ….የኢቫንጋዲ ጭፈራው ግን ቀጥሏል ወደፊትም ለቀናት: ለዓመታት ይቀጥል ይሆናል ከዚያ ግን ይሸነቆራል
ወይንም ለዘመናት
ጥቅም፥ ገንዘብ‥ የተባለው ቆሻሻ ስልክልክ ብሎ ገብቶ ይበክለዋል ደስታም ጥቁር ከል ለብሳ: ተስፋ ቆርጣ: መባዘኗን ትጀምራለች
ካልያም አንድዬ አንች ከርታታ ተዛሬ ጀምሮ መባዘንሽ ያቆማል'
ብሎ ይጠራታል… እግዚኦ ያች ቀን ምናለ ባትደርስ! እግዚኦ!…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቀትር ነው፤ የፀሐይዋ ሙቀት አሸዋው ላይ ነጥሮ እንደ ሐይቅ
ማዕበል እየተንቀሳቀሰ ከርቀት ጀምሮ ይታያል በዚያ አይነቱ ሐሩር የዛፍ ጥላ ህይወት አዳኝ ነው" የሐመር ወንዶች በእንዲህ ዓይነቱ ሙቀት ወቅት ዛፍ ጥላ ሥር ይሄዱና ሲጫወቱ: ሲወያዩ
ቆይተው አሸዋውን ይደለድሉና በበርኮታቸው ጭንቅላታቸውን ደገፍ
አድርገው እረፍት መውሰድ የተለመደ ነው

የሐመር ህይወት የሆነው ከስኬ ወንዝ ከጥም አርኪነቱ ሌላ ከለላ ችግርን መፍቻ በከብት ዝላይ ወቅት የልጃገረዶች መገረፊያ
መጋጌጫ… ማረፊያ ነው ለሰውም ለከብቱም ጫርጫር ሲደረግ ውስጡ ውኃ ይፈልቃል ላዩ መኝታ ይሆናል መወያያ መድረክም  ነው ሐመሮች የከስኬ ናቸው ከስኬም የነሱ ነው ያጌጡበታል
👍25🔥1
ያርፉበታል የተፈታውን ያስሩበታል የላላ
አንድነታቸውን
ያጠብቁበታል
ፍቅራቸውን ያመነዥኩበታል
ከስኬና ሐመር የሚለያዩት በዝናብ ወቅት ከየካቲት እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ብቻ ነው" በዚያ ወቅት አንዱ ሌላውን አይቀርብም ተራርቆ የብቸኝነት
ጣዕሙን ያጣጥማል መለያየት የሚፈጥረውን ናፍቆት ያልማል…
በዝናብ ወቅትከስኬ አትድረሱብኝ
ይላል ፀባዩ ይከፋል:
ይደነፋል፥ የውሃ ኃይሉን እያንዶለዶለ፥ ዛፉን እየገነደሰ: ብቸኝነቱን
የሚዳፈሩትን ሰዎችና ከብቶች እየጠለፈ ይበላል"

በበጋ ወቅት ግን ገራም ነው ዝምተኛ የተመቸ... ይህ ተቀያያሪ ባህሪው ሐመሮችን ይማርካቸዋል ሁሌ ገራም የለም ሁሌም ደንፊ አይኖርም… ሁሉም መቀያየር አለበት
የተፈጥሮም: የሰውም ባህሪ! ይህ ለውጥ የመኖር ቅመም ነው ማህበራዊ ህይወት የሚጣፍጥበት:
ምሥጢሩ የለውጣቸው ፍሰት ነው"

በበጋ ገራሙ ከሰኬ ወንዝ ማረፊያ ነው ከብቶች ጭሮሽ ውሃውን ጠጥተው ይፈነጩበታል፥ይሳረሩበታል ያርፉበታል ይታከኩበታል ዝንጀሮና ጦጣዎች ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ ሲወናጨፉ፥
ቅጠልና ፍሬያቸውን
ሲበላሉ ቆይተው
አሸዋውን ጭረው፥
ውሃ አፍልቀው እየጠጡ
ይዝናኑበታል ለውጥ ነው ለነሱ ለዛፍ ዓለም ፍጡራን ለአሸዋ ላይ መዝናናት በሐመር አሸዋ ጭሮ ውሃ ማፍለቅ የሰው ልጅ ብቻ
ጥበብ አይደለም አውሬዎችና አዕዋፋትም ያን መላ ያውቁታል
ለመኖር ሁሉም የሚያስፈልገውን ማግኘት አይሳነውም ያውም
ሳያዛባ ሳያበላሽ: ሳያዝረከርክ ይጠቀማል ውህደቱ አለ መተሳሰቡ አለ አንዱ ሌላውን በስግብግብነት በግፍ እየቆፈረ ሌላውን
አያደማም ለመኖር ብቻ ይደጋገፋሉ የችግር ምንጩ ሆዳምነት ነው  ያ ደግሞ ገና አየር ላይ ያለ ብክለት ነው በቢጫው በሬ አገር
በሐመር ምድር አስቀያሚው ግዙፍ አካሉን አኮብኩቦ ሙሉ በሙሉ
አላሳረፈም

ስምንት ሐመሮች ከስኬ ወንዝ ካለው የጎሚ ዛፍ ስር ያወጋሉ፤መሳርያቸውን
ጉያቸው እንደሸጎጡ ጠጋ ጠጋ ብለው ሃሳብ ይለዋወጣሉ ከብቶቻቸው
እንደእነሱ ሌላው ዛፍ ጥላ ስር ተጠጋግተው አንዱ የሌላውን ትንፋሽ እያዳመጠ ያመነዥካሉ፤ አዕዋፍ ደግሞ በተንተን ተመልሰው ሰብሰብ እያሉ: ዛፎች ላይ
እያረፉ አንዳንዴም እየበረሩ ያዜማሉ፤ ንፋሱ ያፏጭላቸዋል:
ቅጠሎች ይደንሳሉ፥ እየተንሾካሾኩ ያደንቃሉ… ንቦች ይራወጣሉ
ከአበባ አበባ: ከዛፍ ዛፍ  ባዶ እጃቸውን ወደ ቀፎአቸው ላለመመለስ
እየተራወጡ ይቀስማሉ ሌሎች ውኃ ይቀዳሉ

"ሚሶ!" አለ አንዱ ሐመር ከተቀመጡት መካከል የጥርሱን.መፋቂያ ከአፉ አውጥቶ: ከንፈሩን በቀኝ እጁ ግራና ቀኝ በማፅዳት

"ሚሶ!" አሉት የአደን ጓደኞቹ ዐይኑን እያዟዟረ ከብቶቹን
አሸዋውን: ዛፎችን አዕዋፍንና ሰማዩን. አያቸው

".ጓደኛ መሬት ነው ገመና ይሸፍናል…" ብሎ ንግግሩን
ሳይጨርስው ተወው" ሐመር ላይ ምግብ  አቅርቦ  ማጉረስ
የሚያስፈልገው ለህፃን ብቻ ነው

"ሚሶ!" አለ ቀጣዩ

"ሚሶ! አሉ ሌሎች ጓደኞቹ

ለአደን ስንሄድ የምንተኛበት ዛፍ ሥር የጋራችን ነው
አድነን ግዳይ የጣልነው ሥጋም ተካፍለን ነው የምንበላው፤ ካለ
ጓደኛው እገዛ ጀግና የለም ጓደኛ በጠላት ጥይት ሲወድቅ እስትንፋሱ ሳትወጣ ፈገግ ብሎ አይቶ, አደራውን ሰጥቶ ለዘላለሙ
የሚተኛው ለጓደኛው ነው፥ ጓደኛ ሁሉንም ነው…" ብሎ ንግግሩን አቆመ

"ሚሶ!"

"ሚሶ!"

ጓደኛ አብሮ ይጫወታል፤
አብሮ  ይተኛል አብሮም
ይበላል… አብሮም ይሞታል ጓደኛ ታልመረቀ: ጓደኛ ካልሰጠ ሆድ ቢበላም ባዶ ነው፤ ጋብቻ ማጣፈጫ አይኖረውም ጓደኛ ወተት ነው በትኩስነቱ የሚጠጣ ሲረጋ የሚጠጣ ሲናጥ ቅቤ የሚወጣው" ብሎ
ተናጋሪው አካባቢውን እያዬ ፀጥ አለ

ሁሉም ስለ ጓደኞቻቸው ስለጓደኝነት አሰቡ በልቦናቸው የጓደኝነትን ክብር: ኃይል… አለሙት ጓደኝነት የእርዝማኔው ችካል እጅግ የተራራቀ ነው ከልጅነት  እስከ ሞት
ከማጣት እስከ ማግኘት
ከአለመሆን እስከ መሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ ጫፍ: ከላም ቀንድ እስከ ጅናዋ ጭራ…

"ሚሶ!" አለ ከመካከላቸው  አሸዋውን በእጁ ዘግኖ እየበተነ

"ሚሶ!" አሉት የአደን ጓደኞቹ

"ደልቲ ነጯን ሐመር ሊያገባ ነው" የሶስተኛ ሚስቱን ጥሎሽ ገና ሳይጨርስ ለዚህችኛዋም  ጥሎሽ ጀምር ብለው ሽማግሌዎች
ወስነውበታል ጓደኛችን ሃዘን ገብቶታል" አለ የመጀመሪያ ሚስቱን ካገባ ሰባት ወራት የሞላው

"ሚሶ!" አለ ሌላው መሣሪያውን ጭኑ ላይ አጋድሞ ከወገቡ
ቀና ብሎ እየተቀመጠ

"ሚሶ! አሉት ጓደኞቹ

"ደልቲ እኛ ቁጭ ብለን ብቻውን አያስብም!" ብሎ ዝም አለ ሲቃ በተሞላበት የልብ ጓደኝነት ስሜት ይህኛው ደግሞ የአጫት ገና የአምስት ዓመት ልጅ ስለሆነች አድጋ: ለአካለ መጠን ደርሳ
እስኪያገባት ከወላጆቹ ጋር የሚኖር ነው  በእድሜው የነ ደልቲ ጓደኛ ቢሆንም

ከመካከላቸው አንዱ:
"እኔ አንድ በሬና ጥጃ እሰጣለሁ "
"..እኔ አንዲት ላም" እሰጣለሁ
"እኔ አንድ ወይፈን"
"እኔ ሶስት ቅል ማር" ሁሉም የሚችል የሚችለውን ተናገረ ሶስት በሬ  አምስት  ወይፈን አራት ላምና ሶስት ጥጃ ሆነ ይህ ደግሞ የጥሎሹን ሶስት አራተኛ ይሸፍናል።
ጓደኛሞች ዝም ተባብለው ከራሳቸው ጋር ሲነጋገሩ አንዱ

"ሚሶ" አለ
"ሚሶ!"

በፍጡም ከብቶቹ ከነገ  ጀምሮ ለአጎቱ ይሰጡ
መስጠታችንን እንዳይሰማ ልጃገረዷና ቤተሰቦችዋም እንዳይሰሙ

"… እህ ወንድሜ ምን ነካህ! እኔ ተኩሼ ብጨረፍና ጓደኛዬ ደግሞ ተኩሶ ቢጥል የጨረፈው ገዳይ ሲሆን የጣለው ረዳት እንጂ
ገዳይ ነኝ ብሎ ያውቃል! ከጓደኛው እኩል እንጂ ጓደኛውን የመብለጥ ምኞት ያለው ሐመር ከሽልነት አልፎ ሊፈጠር አይችልም ጓደኛ ሚስት ሲያጭ አዲስ ህይወት ሊጀምር ሲል ጓደኛ ጓደኛውን ይረዳል እንጂ ይህን አደረግሁ ይላል  ለባልንጀር! እንባው
ተናነቀውና ሃሣቡን ተወው"

ለራሴ እንዲህ አደረግሁ ማለት ይሻላል ለጓደኛዬ እንዲህ አደረገሁ ከሚባል ጓደኛ እንደ እናት በውድቅት ጨለማ በተኛበት
የሚዳስስ የመልካም ጊዜ ተጋሪ: የመከራ ጊዜ አጋዥ ነው እህ! ለጓደኛ እንዴት አፍ ተሞልቶ እንዲህ አደረግሁ ይባላል!"

ተውት አሁን የደልቲን በዚህ ጨረስን እየተከታተልን
ደግሞ የሚያስፈልገው ታለ ገመናው ሳይታወቅ እሱም ሳይሳቀቅ ከላይ ከላይ እናነሳለታለን መልካም ሥራ የአደራ እቃ ይመስል
የሚመለስ አይደል ውርስ ነው መልካም ያገኘ መልካም ነገሩን
በተራው ለሚያስፈልገው ያስተላልፋል እንጂ ለሰጠው  ለመመለስ
ፍለጋ አይገባም መልካም የሰራለትንስ የት አውቆት ግና አደራው ከህሊናው አይጠፋም  ስለዚህ ለሌላው ማስተላለፉን አይረሳም ልቦናው አለ!  ውለታውን መልካም ሥራ ለጓደኞቹ በመስራት
ይመልሳል

"በሉ በቃ  አሁን ጨዋታ አምጡ?"

ጨዋታማ ሞልቶ! ያን አውሬ እንዲገሉ ሽማግሌዎች
hመረጡት መካከል ከእኛ ውስጥ አለ?"

"አለ እንጂ  አንተ ራስህ እኔ " ተሳሳቁ

"ኋላ ለኮፍ አድርጋችሁ ሴቱን እንዳታስጨርሱት!"

"ብልቱ እማይታወቅ አውሬ ወርች የለው ግንባር  ምኑን
ነው ቀድመን የምንመታው?"

"ሆድ እቃውን ነው እንጂ  ቀጥሎ ያ ማታ ማታ ብርሃን ፏ የሚያደርገውን ዐይኑን ማጥፋት"

"ምድረ  ወንድ ሃሣብ በሃሣብ ሆኗል አሁንማ ሲሰማ ስንቱን እየወጉ ይገላሉ አሉ ኮ! ጎይቲ ስትናገር አውሬው ተሰው ጋር እንደምስጥ ሲርመሰመስ ነው አሉ ነግቶ የሚመሸው "

"ተዋት እሷን ጓዴ  ይህች ቀላማጅ  ሲያቀብጣት ተሐመር ወጥታ ብልቷን ውሃ በማስነካቷ ይኸው በሌላ ሴት ተለውጣ ፈት
ሆና ቤት ልትውል ነው ከእንግዲህ ካለ እድሜዋ ዐይኗ በእንባ ጠፍቶ ጧሪና መሪ የሌላት ትሆናለች "

"ያችን የመሰለች ቆንጆ ሳትተካ መቅረቷ ያሳዝናል!"

"የአባት ደንብ ሻረቻ ብለው ተክዘው ሌላ ጨዋታ ደግሞ ቀየሩ

💫ይቀጥላል💫
👍431👎1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

በስራ ጉዳይ ወዲህና ወዲያ ስሯሯጥ ቆይቼ ከምሽተ 3 ሰዓት ካለፈ በኃለ ነው ወደ ቤት የገባሁት፡፡ያው የተለመደ የወንደላጤ ቤቴን አየከፈትኩ ሳለ ስልኬ ተንጣረረ...በአንድ እጄ እየከፈትኩ በሌለው እጄ ከኪሴ አወጣሁና አየሁት፡፡ ልጄ ነች፡አነሳሁትና

‹‹ሄሎ የእኔ ጣፋጭ››

‹‹ያንተ ጣፋጭ አይደለሁም..ማለት እናቷ ነኝ››

‹‹ውይ እሪች ይቅርታ …ተአምር መስላኝ ነው››

‹‹አውቃለሁ..አንተ አልተሳሳትክም እኮ የደወልኩት በእሷ ስልክ ነው…አባትና ልጅ ግን የምትገርሙ ሴረኞች ናችሁ››

‹‹እንዴት ማለት››በራፉን ከፍቼ ወደውስጥ ከገባሀ በኃላ አልጋዬ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብዬ ወሬዬን ቀጠልኩ፡፡

‹‹ምን እንዴት አለው…ሁሉን ነገር ሰማሁ….በሚስጥር መገናኘትና መደዋወል ከጀመራችሁ መከራረማችሁን….አረ ጭካኔያችሁ…. ከአንተ  ደግሞ የእሷ አይገረምም፡፡››

‹‹እንዴት?››

‹‹ሰው እንዴት ከገዛ እናቱና አያቱ እንዲህ አይነት ሚስጥር ሰውሮ መቆየት ይችላል….ለዛውም በዚህ እድሜዋ››

‹‹ያው የአባት ጉዳይ ሲሆን ይችላል.ልጄን ደግሞ ታውቂያታለሽ… ልክ እንደአባቷ እስማርት ነች፡፡››

‹‹ይሀቺ ጉራ አሁንም አለቀቀችህም››

‹‹ምነው ተሳሳትኩ አንዴ?››

‹‹አላልኩም….ለማንኛውም በጣም እንዳስደመማችሁኝም እንዳስቀናችሁኝም መናገር እፈልጋለሁ…ለመሆኑ አንተስ እንዴት ነህ…?››

‹‹ይመስገነው… ህይወት እንደጢባ ጢቢ አንቀርቅባ አንቀርቀባ ገና  አሁን በቅርብ ቀን ነው  እያረጋጋቺኝ ያለው››

‹‹በጣም አዝናለሁ››

‹‹ለምኑ?››

‹‹ከእኔ ጋር የሆነው ነገር ባይሆን ኖሮ አንተ አንዱንም ችግር አታይም ነበር…››

‹‹ተይ ተይ ..ችግሩር ያየሁት እኮ ሀገሪቱ ተምሬ በተመረቅኩት ሞያ ስራ ልትሰጠኝ ስላልቻለች ነው››

‹‹ያ እውነት እንዳልሆነ ሁለታችንም እናውቃለን››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹አንተ ስራ አጣሁ የሚለውን እንደሽፋን ተጠቅመህ እራስህን እየቀጣህ ነበር...ቤተሰቦቼ ላይ ከሰራሁት መጥፎ  ስራ አንፃር የተሻለ ህይወት ፈፅሞ አይገባኝም ብለህ በመወሰን ነው በዝቅተኛ ህይወት ውስጥ እራስህን ዘፍቀህ በችግር በመዳከር እራስህን ስትቀጣ የኖረከው…እንጂ ሌላውን ተው አዲስአባ ወላጆችህ ትተውልህ የሞቱት ቤት እንዳለ ታውቃለህ….ባንክ ውስጥም ቢያንስ ከግማሽሚሊዬን ብር በላይ ትተው መሞታቸውን ከቤት ኪራይ እየተሰበሰበ ለዘመናት የተጠራቀመው ብር  እንዳለ ታውቃለህ… ይሄ ሁሉ ሀብት ያለው ሰው በጤናው የፓርኪንግ ሰራተኝነት እና የሆቴል አስተናጋጅ ሆኖ የወጣትነት ህይወቱን አይገፋም…ለዛውም ባለዲግሪ ሆኖ..

‹‹ትክክል ልትሆኚ ትቺያለሽ…..እኔ ግን በዚህ መንገድ አይቼው አላውቅም…እኔ ያምትይውን ብር ሆነ ቤት መጠቀም ያልቸልኩት ሳልፈልግ ቀርቼ ሳይሆን እሱን ለመጠቀም የእቴቴን አይን ማየት ስላልፈለኩ ነው፡፡››

‹‹ተው ተው..ትንሽ ካሰብክበት እኮ የእቴቴን አይን ሳታይ የሚገባህን ንብረትህን እጅህ ማስገባት ትችል ነገር››

‹‹ተይ ተይ .እንደምታስቢው ቀላል አልነበረም››

‹‹አውቃለሁ… ግን ያደረከው ያልኩትን ነው እራስህን መቅጣት.እኔም አኮ ስላደረኩት ነው እንደዛ የምልህ…..?››

‹‹እንዴት?››

‹‹ያው እደምታየኝ አምሮብኛል ሰውነቴ አብረቀርቆል..ግን አሜሪካ ያሳለፍኳቸውን ስድስት አመቶች እንደምታስበው  እንዳይመስልህ.. ከጥዋት እስከ ሊሊት ከሶስት በላይ ስራ እሰራለሁ..ብዙ ብዙ ገንዘብ አገኛለሁ..የማያስፈልገኝን ገንዘብ ለማግኘት ማለት ነው እንደዛ እለፋ የነበረው..  ማንንም አላገኝም ..የትም ሄጄ መዝናናት አልፈልግም….የሳምንት እረፍቴ ከስድስት ሰዓት አይበልጥም ነበር…ማን መሆኔን እራሱ ዘንግቼ በድኔ ልክ እንደሮቦት ሆኜ ነበር የምንቀሳቀሰው…አሁን በቅርብ ጊዜ ግን ይህ ጉዳይ እንዴት ነው..?ለምድነው እንደዚህ የምለፋው..?የምሰበስበው ገንዘብ ለማን ብዬ ነው….?ብዬ ሳስብ  በጣም ግራ ተጋባሁ እና ባለሞያ ጋር ሄድኩ.. ባለሞያውም የህይወት ታሪኬን ካስለፈለፉኝ በኃላ በስተመጨረሻ የደረሰበት መደምደሚያ የምሰራው ስራ ሁሉ እራስን መቅጣት እንደሆነ እና  ከዚህ ወጥመድ የመውጫው መንገድ ግን ይሄ እንዳልሆነ መከረኝ….ለዛ ነው ካለእቅዴ ድንገት ወደሀገሬ ፈጥኜ የመጣሁት..መድሀኒቱ እዚህ ስለሆነ…››

‹‹አልገባኝም›አልኳት

የእውነትም ስላልገባኝ፡፡
‹‹አየህ ያባለሞሞው ውሳኔዬ በጣም ትክክል ነበረ..ይሄው ወደ ሀገሬ ከተመለስኩ በኃላ ካስብኩት በጣም በፈጠነ ጊዜ መድሀኒቱን አግኝቼ እየታከምኩ ነው…አንተን ማግኘትና ያለህበትን ሁኔታ መረዳት ችያለሁ….ይህ ማለት በእየለቱ የት ወድቆ ይሆን በሚል እምሮዬን ሲበላኝ የነበረው ነገር አሁን ድኖልኛል….ሌላው የእቴቴን ይቅርታ ማግኘት ችያለሁ…ያ ደግሞ ምን ያህል የአእምሮ ሰላም እንደሚሰጥ በራስህ ታውቀዋለህ…በነገራችን ላይ አባዬንም ይቅርታ ጠይቄዋለሁ.. አሁን የቀረኝ ትንሽ ነገር ነው…አንተን እና አባዬን ማገናኘት..››

‹‹አንተን እና አባዬን…?››ደንግጬ

‹‹አዎ ምነው ያንን ማድረግ አትፈልግም እንዴ?››

‹‹አረ በጣም ፈልጋለሁ..ግን እንዴት ብዬ አይኑን አያለሁ ?››

‹‹ልክ የማዬን አይን እንዳየህ..ደግሞ እኔ አፍጥጬ ሄጄ እሱን ማናገር ከቻልኩ አንተስ እንዴት ያቅትሀል?፡፡:ከዛ ከእማዬ ጋር መልሰን እናጋባቸዋለን…አንድ ላይ ሆነን ወላጀቻችንን ሆነ እህቶቻችንን አንክሳቸዋለን… በእኛ ምክንያት የቆሰለው ልባቸው ፈፅሞ እንዲድን የተቻለንን እናደርጋለን..ከዛ የእኛም ቁስል ቀስ እያለ ሙሉ በሙሉ ይድናል…ምን ይታወቃል የፈረሰ ተስፋችን መልሶ ይገነባ ይሆናል…እርግጠኛ ነኝ በመጨረሻ እራሳችንንም ይቅር እንላለን፡፡

‹‹አሜሪካ ተመልሰሽ እትሄጂም ማለት ነው?››

‹‹ሄዳለሁ.. ግን ለመኖር አይደለም…ሁኔታዎችን አመቻችቼ አንደኛዬን ጠቅልዬ እመጣለሁ..››

‹‹የእውነትሽን ነው?››
‹‹ምነው ደነገጥክ…እዛ ብኖር ይሻላል እንዴ?››

‹‹አረ እንደዛ ስለወሰንሽ በጣም ደስተኛ ነኝ››

‹‹በጣም ደስተኛ ለምን እንደሆንክ ማወቅ እችላለሁ?››

‹‹እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ…አንድ ቀን ታአምርን ወደአሜሪካ ልውሰድሽ ብትላት ምንድነው የማደርገው? በሚል ስጋት እንዴት እየተሰቃየሁ እንደነበር ግምቱ የለሽም››

‹‹ይገርማል?››

‹‹ምኑ?››

‹‹መልስህ ያልገመትኩት ነው..ለልጅህ ባለህ ፍቅር ቅናት አደረብኝ››

‹‹እሷ እኮ የከሰመ ህይወቴን መልሳ ያለመለመችልኝ  ካሳዬ ነች. .ለእሷ ስል ህይወቴን እሰጣለሁ..››

‹‹በነገራችን ላይ አዲስአበባ ሪል እስቴት ገዝቼያለሁ..ስለዚህ ልክ ጉዳዬን ጨርሼ ከአሜሪካ እንደተመለስኩ ሁለችንም አንድ ላይ እንኖራለን ማለት ነው..››

‹‹አንድ ላይ ስትይ….?ማለት….?እንዴት…?››

የፈራሁት ነገር ዞሮ ሊመጣ ነው ብዬ በማሰብ ተርበበተበትኩ.

‹‹አይዞህ አትደንግጥ…ይሄውልህ እዬቤ እኔ አሁንም በጣም አፈቅርሀለሁ…እሱን ስሜቴን ካንተም ሆነ ከማንም መደበቅ አልችልም፡፡ደግሞም .አንተን ማፍቀር መቼም አላቆምም…ግን ደግሞ ከዚህ በፊት የሰራነውን ስህተት መቼም ደግመን እንድንሰራ አልፈልግምም፤ አልፈቅድምም….፡፡ይሄንን ደግሞ በቀደም እማዬ ሁለት  ጡቶቾን እስይዛ 
ነው ያስማለችኝ..ስለማልኩ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያውም ስህታችን ያስከፈለንን መከራ አይቼ ዳግመኛ ተመሳሳዩን ስህተት ለመፈፀም ጥንካሬው የለኝም፡፡.ቢያንስ ለእናቴ ስል….ለእህቶቼ ስል..ለአንተ ስል…፡፡ስለዚህ ምንም ስጋት አይግባህ
👍798🔥1🥰1😁1
‹‹ሪች አመሰግናለሁ…..ታውቂያለሽ እኔም ወደሻለሁ…ግን ዳግመኛ እቴቴን አንገት ከማስደፋ እኔ አንገቴን ቀንጥሼ ቢያበቃልኝ እመርጣለሁ….እና ቀድመሽ እዚህ ውሳኔ ላይ ስለደረሽም ሆነ ወደሀገርሽ ተመልሰሽ ለመኖር ስለወሰንሽ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ አታውቂም፡፡ብዙ ነገር ነው ያቃለልሺልኝ፡፡››

‹‹ለማንኛውም የፊታችን እሁድ ሁላችንም እንመጣለን….የዛን ጊዜ ቀሪውን እናወራለን››

‹‹እሺ ሪች ደህና እደሪ…ተአምርን ሳሚልኝ›
‹‹እሺ ደህና እደርልኝ›ስልኩ ተዘጋ…..የሆነ ዥው ነው ያለብኝ፡፡ከሪች የሰማዋቸው ነገሮች ሁሉ ያልጠበቅኮቸውና በጣም ያስደሰቱኝ ናቸው…ከማውቃት የተለየች በሳል ሴት ሆና ነው ያገኘኋት፡፡ሰው በስድስት አመት ይሄን ያህል ይቀየራል….?እኔስ በእሷ መጠን በስዬ ይሆን?.እራሴን የጠየቅኩት ጥያቄ ነበር?መልሱ አኔ እንጃ ነው፡፡

ይቀጥላል
👍468🥰5
አትሮኖስ pinned «#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ //// በስራ ጉዳይ ወዲህና ወዲያ ስሯሯጥ ቆይቼ ከምሽተ 3 ሰዓት ካለፈ በኃለ ነው ወደ ቤት የገባሁት፡፡ያው የተለመደ የወንደላጤ ቤቴን አየከፈትኩ ሳለ ስልኬ ተንጣረረ...በአንድ እጄ እየከፈትኩ በሌለው እጄ ከኪሴ አወጣሁና አየሁት፡፡ ልጄ ነች፡አነሳሁትና ‹‹ሄሎ የእኔ ጣፋጭ›› ‹‹ያንተ ጣፋጭ አይደለሁም..ማለት እናቷ…»
ሚስቴ እና አባቷ!? 😡
ክፍል~~~ሰባት
ዘወር ብዬ ወደአመላከተችይ አቅጣጫ ትመለከት እመንገዱ ዳር ላይ ታለ አንድ ስጋ ቤት ነጭ እተቀባ ግርግዳ ላይ የተሳለ ትልቅ ጥቁር በሬ ነው !
እንደው አንዳርጌ ሙት ነው እምልህ ብልጭጭ አለብይ!"•••••
ቲለኝ አልቻልሁም ወሬውን እስኪያከትም አፍኜ የያዝሁትን ሳቅ እንደ ሀምሌ መብረቅ አንባረቅሁት ።
ካካካካካካ ያንተስ ለጉድ ነው ጃል
እና ምን ይሻልሀል ? ብለው•••
ታድያ እሄ ባልና ሚሽት ታንድ ወንዝ ይቀዳሉ ያለ ሰው ጥሁፍን እንዲህ ብሎ ያስተካክልልይ
ባልና ሚሽት ታንድ ወንዝ ይቀዳሉ ተዳምጠው እና ተሳቷ ሚሽቱ በስተቀር ብሎ ያስተካክልልይ።
ይህን ማድረግ የማይችል ተሆነ ግን ተሚስቴ ያፋታ እና ታለወንዟ የሄደይውን የኔዋን ያምጣልይ።
ይህም ታልሆነለት ያለክዳና ታልገጠምክ እያለይ ቲላት እስፓናቶ ቲላት አንጎል ፋቶ እያረገይ
አወላልቃ ታጨርሰይ የኔ ታትሆን የሷ ላረችይ ሚሽቴ የራሷን ግጣም አፈላልጎ ይስጣት።ይህም ተተሳነው ደግሞ•••
በእሳት ምላሷ ተጨጓራዬ ዥምራ በሷ ንዴት ስጠጣ ወደ ጉበቴ ፣ በሷ ብሶት ታጨስ ወደሳምባዬ እየመጣይ ተንቀሳቃሽ ሬሳ ካረገችይ ተይች ሴት እምገላገልበትን መንገድ ጠቁሞይ ፣ ተተቀዳሁበት የተቀዳይውን እማገኝበትን መላ ጀባ ይበለይ ።ያለበለዚያ አልፋታውም
ለሁሉም የማይሰራ ለሁሉም ቲተረት ደስ አይልማ ደስ አይልም!!! ቲለይ ሳቅ በላይ በላዩ እያፈነይ•••
"መፍትሄ ታልሰጠህስ ምን ትሆን ?" አልሁት።
"እሱማ ምን እሆናለሁ ወንድም አለም ነገሩን አጫወትሁህ እንጂ ከነፍጥርጥሯ እኮ ታንጀቴ አፈቅራታለሁ !"
"ካፈቀርካትማ ቻለው እንግዲህ እኔም ትለማፈቅራት እይ እንዳባቷ ጠባይ እማ ቢሆኔ እስታሁን ጥያት በጠፋሁ ነበር!" ብለው••
"ሀሳባችን ፍላጎታችን አልገጥም ቲል የጠላሁትን ትትወድ ፣ የወደድሁትን ትትጠላ ታንድ ወንዝ ተቀድተን ተሆነ በመሀላችን ፍቅር ታይጠፋ ለምን መንገድና ፍላጎታ ተኔ ታቃረነ ብዬ እይ ማፍቀርስ አፈቅራታለሁ።
ብታስከፋይኝም እሷስ በምን ምህንያት ይሆን እንዲህ ተኔ በተቃራኒው ለመሆን የበቃይው ብዬ አስባለሁ እይ አልነካትም።
ባይሆን አንዳንዴ ነገር ቲበዛ እና ትታስከፋይ ወጣ እልና ታፋፉ ላይ ቆሜ ብሶቴን በፉከራም በቀረርቶም ለዱሩም ለጫካውም እነግረዋለሁይ " አለይ።
"ምን እያልህ ነው እምትነግረው ጃል? ብለው እዛው ዠመረዋ •••
ኧ••••ረ ጎራው
ኧ•••••ረ ወንዱ
አረጎራው አረወንዱ
አረጎራው አረወንዱ•••
ተ••••ተሰውት በላይ እግምባር ሲወርዱ
ተ•••••ቆሰሉት በላይ ጠላት ሲያሳድዱ
እ•••••ልፍ ጀግና ወንዶይ በሴቶይ ነደዱ
ኧረ ጎራው
ኧረ ጎራው
ኧረ ወንዱ
ዳሩልይ ብላቸው የግራ ጎኔን
ዳሩልይ ብላቸው ውሃ አጣጪዬን
እ•••••ሳቷን አምጥተው ጠበሱዪ እኔን
እረ ጎራው
ኧረ ወንዱ
ኧረ ጎራው
ስንቱን ዥግና ነዪ ባይ እንዳላሯራጥነው
ስንቱን ወንድ ነዪ ባይ ገርፈን እንዳልጣልነው
ለ••••ፍቅር እጅ ሰጥተን ስንቱን አሳለፍነው
እረ ጎራው
ኧረ ወንዱ
ኧረ ጎራው
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ጀግና ቲመስለን ጡንቻ ያስነካ
ጀግና ቲመስለን •••
ስንት እንደጣለ ሬሳ ያስለካ
የራሷን ሳሰጥ የሰው ታትነካ
በፍቅር ገዳይ ሴት አለይ ለካ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
የዥግናው ልዥ ነይ የበላያ ዘር
ጓንዴ ቢተኮስ የማልበገር
መድፍ ቢንጣጣ የማልደነብር
ጠልፋ ጣለችይ በሀያል ፍቅር
ላገሬ ባልዘምት ባልወጣ ከዱር
ለሚስቴ ዘብ ነይ የቤት ወታደር
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
እጠጅ ቤቱ ውስጥ ያለው በሙሉ በመሀል በመሀል በወኔ እያጨበጨበ ቲያጅበው ቆየ ። ጨርሶ አጠገቤ ተቀመጠ።
እሄውልህ ወዳጄ አንተ ከፋም ለማም በፍቅርህም በጠብህም መሀል የሚገባብህ ሰው የለም እኔኮ የተጀገርሁት የራሳቸውን ሚሽት ፈተው የገዛ ሚስቴን ዘብ ሆኜ ታልጠበኳት በሚሉት አባቷ ነው።
"ያንተው ነገር ለሰሚውም ግራ ነው ኩለው ድረው ተሰጡ ቡሀላ ያንተ እንዢ የሳቸው እንዳልሆነይ አያውቁ ኖራል እንደው እሄን የሚነግራቸውስ ወዳጅ የላቸውም ? ሴት ልዥ እናት እና አባቷን ትተዋለይ ተባሏ ጋም ትተባበራለይ !"ቲባል አልሰሙም" አልይ።
ምን መስሚያ አላቸው እንደው ምን እንደማረግ ግራ ግብት ብሎያል ባክህ!" ብለው•••
" እኔን ቻለው እንዳልኸይ ቻለው ተማለት ውጪ ክፉ አልመክርህ እንግዲ መሄዴ ነው ውዳጄ ቻለው ብሎዪ ተጠጅ ቤቱ ወጣ።
ደሞ መለስ አለና ወደ ዥሮዬ ጠጋ ብሎ ችግር በጉልበት አልያም ጥፋተኛውን በመውቀስ ብቻ አይፈታም ብልሀት ያስፈልጋልይ እኔ ከሰሞኑ ተሞላ ጎደል በኔና በሷ መሀል ያለውን ሽግር እየፈታሁ ነው።
በምን እንደሆነ ታውቃለህ ለምን እንዲህ ትሆኛለሽ ለምን እሄን አደረግሽ ብዬ እምቧ ከረዩ በማለት እንዳይመስልህ ለሚሽቴ የምጠላውን እንደምወድ የምወደውን እንደምጠላ እያረግሁ ገለባብጬ በመንገር ነው ተያ ቡሀላ ተኔ በተቃራኒው የሄደይ መስሏት መስመራችንን ገጥማው ቁጭ አለይ!!
ኪኪኪኪኪኪኪ አሁንም ልድገምልህ በመሀላችሁ ያለውን ችግር ለመፍታት ብልሀተኛ መሆን አልያ መቻል ብቻ ነው ያለህ አማራጭ ቻለው ኪኪኪኪኪኪኪ"
መክሮይ ታይሆን ተሳልቆብይ የወጣ መስሎይ በገንሁ!።
ተጠጅ ቤት ወጥቼ ወደ ቤቴ የሚያደርሰይን መንገድ እንደዥመርሁት ነበር እንደእብድ ብቻዬን ማውራት የዠመርሁት።
ያው ለግዜውም ቢሆን ስካሩ እስቲበርድ እብድ እና ሰካራም አንድ ትለሆኑ ነው መሰል እንደእብድም እንደሰካራምን እያርገይ •••
"በየቤቱ ስንት ጉድ አለ እናንተው በኑሮ ጉያ ውስጥ እንቅፋት ቲመታይ ተሰው ዘር ሁሉ እኔን ብቻ መርጦ የሚመታይ እየመሰለይ ሳማርረው የቆየሁትን አምላኬን ይቅር በላይ አልሁት ።
ሁሉም በሂወቱ ውስጥ በፍቅር መሀል ፣ በስራ መሀል ፣ በጤና መሀል፣ በሰላም መሀል እያደናቀፈ የሚፈታተነው የየራሱ የሆነ እንቅፋት አለው ።
አንዳንዱ በእንቅፋቱ ተመቶ ይወድቅና ተሩጫው ይገታል ፣ አንዳንዱ በእንቅፋቱ ተንገዳግዶ ቆም ይልና መንገዱን ይቀጥላል፣ አንዳንዱ ተራሱ ተእንቅፋቱ ጋር ተላምዶ ሽግሩ ምን እንደሆን እንኳን በወጉ ታይለየው በፈጣሪው አልያም በሌላው ሰው ላይ ቲማረር ይኖራል።
አንዳንዱ እራሱን እንቅፋቱን ፈንቅሎ ይጥለውና ሌሎይንም እንዳይመታ መንገዱን ያቀናል ።
አሁን በኔ ሂወት እንቅፋት የሆኑብዪን የሚሽቴን አባት እንዴት ተኑሮዬ መሀል ፈንቅዬ እንደማወጣቸው ብቻ ነው ማሰብ ያለብይ።
እይ በሳቸው ምህንያት ተዋቡ ፍቅሬን እና ሴት ልዤን ጥዬ ዌትም አልሄድም ፣ ትዳሬን አልበትንም እያልሁ በሀሳብ እንደናወዝሁ ግቢ ደረስሁ።
በበነገው ታልጋዬ ላይ ታልነሳ ጥዋት ቁርስ ይዛልይ እንደመጣይ ወገቧን ይዛ ቁልቁል እያየችይ•••
"ለምን ሄድክ ትናንት ?" ትትለይ •••
"ተይይ እስቲ ተዋቡ በቃ ብስጭትጭት ቲያረገዪ ሄድሁ!
እየሆነ ያለው ነገር ቢያበሳጨይ በኔ ይፈረዳል?"
እንደውም ተሳቸው ጋር ክፉና ደጉን ተምነጋገር ወሩ እስቲሞላላቸው ድረስ ልብሴን ሸክፌ ዘመድ ጥየቃ ልሄድ ወስኛለሁ!" አልኋት።
"እኔን ጥለህ አንዱ ? አታደርገውማ ይልቅ
ቆይ አንድ መላ መጥቶልኛል እነግርሀለሁ መጣሁ አለይችዪና ቁርሱን አስቀምጣልይ ወጣይ።
ትንሽ ቆይታ መጣይና •••ይቀጥላል
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
👍48👏51
ሚስቴ እና አባቷ!? 😡
ክፍል~~~ስምንት
"እኔን ጥለህ አንዱ ? አታደርገውማ ይልቅ
ቆይ አንድ መላ መጥቶልኛል እነግርሀለሁ መጣሁ አለይችይና ቁርሱን አስቀምጣልይ ወጣይ።
ትንሽ ቆይታ መጣይና •••
••••"እሄውልህ አለሜ ትንሽ ቆይተህ ወደ ከተማ ትወጣና ድንገት ከናንተ ቀየ ወደይህ ከተማ የመጣ ሰው የሩቅ ዘመድህ መሞቱን መርዶ እንደነገረህ ሆነህ አዝነህ ትመጣለህ።
ተዛ ተያይዘን ለቅሶ ልንደርስ ሄድን ብለን እንወጣለን ።ያኔ አቡዋ መቸስ እሚያበስል እሚጋግር በለለበት ቤት ብቻውን አይቀመጥ ። ተሰናብቶን ወደ ቤቱ ተመሄድ ውጪ አማራጭ የለውም ።
ከተማ እንቆይና መሄዱን ሰው ልከን ታረጋገጥን ቡሀላ ተያይዘን ወደቤታችን!" አለችይ።
ምናለ እሄን መላሽን ያንን እኔኑ በሽተኛ ታረገዪ ከንቱ መላ በፊት ብትነግሪይ የኔ መለኛ አልኋት ፈገግ እያልሁ።
"ኪኪኪኪኪ ያኔ መች መጣልይ አለሜ?!" አለችይ እየሳቀይ።
በይ ሂጅ እኔም ልሂድ አልኋትና ከተማ ዘወር ዘወር ብዬ ትመለስ እግቢው ውስጥ ተዋቡ ቡና እያፈላይ እሳቸው ተፊቷ ቁጭ ብለው ያወጋለሁ።
ጥድፍ ጥድፍ እያልሁ ገባሁና አጠገባቸው ትደርስ በተማከርነው መሰረት የተረበሽው የደነገጥሁ መስዬ ቆምሁ•••
" ምን ሆነሀል አንዳርጌ ፊትህ ልክ አይደለም !?" አለችይ ተዋቡ ።
"መርዶ ሰምቼ ነው ተዋቡ !" ትላት።
"ውይ የምን መርዶ አለይና ብድግ አለይ !"
አወይ ተዋቡ የኔን አላውቅም እሷ ግን ማስመሰሉን እንዴት አድርጋ እንደምትችልበት እናንተው!
ይገርማል እኮ! ውሸት እንደሆነ እያውቅሁ አደነጋገጧ እኔኑ መልሶ ቲያስደነግጠይ እስቲ ምን ይባላል?"
እንደው ብድግ አለይና ደረቷንም እንደመድቃት እያረጋት••
"ማን ?የትኛው ነው አንተው? ያ ልዥ ነው እንዳትለይ አንዳርጌ! " አለችይ
"እኔ አፈር ልብላለት አዎ ተዋቡ ያ ባለፈው መታመሙን የነገርሁሽ ዘመዳችን ታያርፍ እይቀርም ለጉዳዩ ተነሱ መንደር ወይህ የመጣ ሰው ነውኮ አሁን የወተት ኪራይ ሂሳብ መጨመራችንን ለኮንትራት ደንበኞቻችን እየዞርሁ ትነግር ድንገት አግኝቸው ዥሮዬ ጭው እስቲል ድረስ መርዶዬን ያረዳይ አይ ሰው ከንቱ እንደው ለይህ እድሜ ነው እንግዲህ ተመዋደድ ይልቅ እየተጠላላን፣ ተመደጋገፍ ይልቅ እየተገፋፋን ፣ ተማስታረቅ ይልቅ እያጣላን ፣ አንዳችን ለአንዳችን መፍትሄ ታይሆን ሽግር እየሆንን ፣ የሰው ልዥን ህይወት ማቅለልን ታይሆን ማክበድን ስራየ ብለን የተያያዝነው! እንደው አሁን ያን የመሰለ ወጣይ እንዲህ ባጭሩ ይቀጫልይ ብሎ ያሰበና የገመተ ተዌት ይገኛል!? "
አልሁና እግረ መንገዴን የተዋቡን አባት በነገር ወጋ ወጋ አደረኋቸው።
"ውይይይይይ አቤት መልክ አይ ቁመና እንደው ምን አገኘው?
የኔ ለግላጋ! እይ ጫወታ ! አይ ፈገግታ! ምነው በግዜ ወሰድኸው ፈጣርዬ •••" እያለይ እንባ እንባ እያላት ትትብከነከን እኔ እራሱ እየተወነይ ይሁን የምሯን ለማወቅ ተምታታብይ።
እንደው ተዋቡን ታያት ተልቧ የተንገበገበይ እዪ እያስመስለይ መሆኑን እንኳን አባቷ እኔም ማወቅ ተሳነይ እንዴ ተረጋጊ እዪ ውባለም የተማከርነውን እይ እውነት አይደለም እኮ ልላት ምን ቀረይ እናንተው? ።
አባቷም ግራ ገብቷቸው አንዴ እኔን አንዴ እሷን እያዩ •••
"ታውቂው ኖሯል ተዋቡ "አሉ። እሷ መልስ ታትሰጣቸው •••
"በደንብ ነዋ! አሰምራ ነዋ እምታውቀው ተስንት ወር በፊት እይህ እኛ ዘንድ መጥቶ ጠይቆን ነበር እኮ የተዋቡ አባ !" አልኋቸው
ምኑን ጠጣሁት ቡናውም ይቅርብይ ልሰናዳና እንሄዳለን ብላ ብድግ ትትል።
"ለመሆኑ የት ነው ቦታው !"አሉ አባቷ። በልቤ ምን ሊሉ ይሆን እኝህ ሰው ጉዳቸው አያልቅ መቸስ እያልሁ ቦታውን ትነግራቸው።
" እ እዛ ነው እንዴ? እዛ ነው ልሰናዳና እንሂድ ያለይው? ወቅቱ እኮ ክረምት ነው ወንዝ ይሞላል፣ መሬቱ ረግረግ ነው!! በዛ ላይ መንገዱ ዳገት እና እሾህ የበዛበት አስቸጋሪ መንገድ እንደሆነ እውቃለሁ!
ዛድያ እዛ ነው ልዥ ይዘሽ እምትሄጅው ተዋቡ ለመሆኑ ቦታውን ታውቂዋለሽ አወይ ማበድ! አወይ አቅምን አለማወቅ እናንተው ! እንኳን ለሴት ልዥ ለወንድ በሚፈትን በያ መንገድ ልዥ ይዘሽ ይቅርና ሌጣሽንስ ትችይዋለሽ እንዴ ነገሩ ብታውቂው እግርሽን ለማንሳት ባልዳዳሽ!
በይ አሁን አርፈሽ ተቀመጭ እግርሽን እንዳታነሽ ተዋቡ!" ብለው ወደኔ ዞሩና
"አንዳርጌ ልጄስ መንገዱን ስለማታውቀው ልሂድ ትበል አንተ ግን ያን አስቸጋሪ መንገድ እያወቅህ ሚስትህንና ጨቅላ ልጅህን ይዘህ ለመሄድ አስበህ ነው ልሂድ ስትል ዝም ያልሀት! ያንተን ዘመድ ለመቅበር ሄዳ በዛው የሷ ቀብር እንዲፈጠም ነው አላማህ !? ብለው አፈጠጡብይ።
እምናገረው ጠፍቶይ አፌ ተለጎመ።
"ምንስ ቢሆን ታድያ ብቻውን አይሄድ!" አለይ ተዋቡ።
እሄን ግዜ ብድግ አሉና •••
" አንቺ ልዥ ••• ህጣን ልዥ ይዘሽ በዛ መንገድ መሄድ አትችይም አልሁ እንጂ ብቻውን ይሂድ መች ወጣይ ዘመድ አማች ጎረቤት እንደለለው ለምን ሲባል ብቻውን ይሄዳል !" ።አሉና •••
"መጣሁ ልብስ ልቀይር እኔና አንተ አብረን እንሄዳለን! አንዳርጌ አንቺ ግን አርፈሽ ተቀመጭ እኔው አብሬው እሄዳለሁ"
እያሉ ወደትልቁ ቤት ቲገቡ•••
እኔና ተዋቡ መላቅጡ ጠፍቶን ተፋጠጥን።
"ለብሰው ሊመጡ እኮ ነው ምን ይሻላል? ያልመተውን ሞተ ብዬ ታበቃ ወየት ይዣቸው ልሄድ ነው ተዋቡ ? አልኋት ጨንቆይ።
አይ መቸስ መለኛ አይደለይ ተመቅስፈት መፍትሄው ማምለጥ መሁኑን ወሰነይና ••••
"ሂድ ውጣ አምልጥ ታይወጣ ተግቢ ውጣና እሩጥ አንዳርጌ ! እኔ ገብቼ ተባራሪ ወሬ ስለሰማሁ አባትሽን እዛ ድረስ ወስጄ ሳላደክማቸው የሞተው እውነት እሱ መሆኑን ከሁነኛ ሰው አጣርቼ ልምጣ ብሎይ ወጣ እለዋለሁ !"አለችዪ።
እውነት ነው ሴት ልዥ መለኛ ነይ የሚባለው የኔ ተዋቡ ግን ትለያለይ እናንተው !።
እኔ አብሬህ እሄዳለሁ ሲሉ አንዴ የዋሸነውን ምን ብዬ እንደማስተባብል ማጣፊያው ቸግሮይ ትርበተበት ወድያው ምህንያት መፍጠራ ይገርማል ! እያልሁ
አባቷ ልብስ ቀይረው ታይወጡ ተግቢው በርሬ ጠፋሁ።
በዛው ወደ ጠጅ ቤት።
ጠጅ ቤት ቁጭ ብዬ ተማንም ሳልጫወት እና ሳላወራ እንደው ልብስ ቀይረው ቲወጡና ተግቢው ብን ብዬ መጥፋቴን ቲያውቁ ተዋቡ አለሜን ምን ብለዋት ይሆን ?" አልሁ በልቤ ።
ተማንም ታልቀላቀል ጥጌን ይዤ ጠጄን እየኮመኮምሁ ያባቷንም የሚሽቴንም ሁናቴ እና በይህ አስራ አመስት ቀን ውስጥ ያሳለፍነውን እያሰብሁ በሚያስቀው ትስቅ በሚያናድደው ትናደድ ቆየሁ•••
ብዙ ብቆይም ገና ሁለት ብርሌ ነው የጠጣሀት ሶስተኛውን አዝዤ ቀና ትል •••
ወሬ ተዥመረ እንደሀምሌ ዝናብ እኝኝ እያለ የማያባራው ዝናቡ ሞገስ ሲገባ አየሁት ብቻዬን ማሰብ ስለፈለክሁ ብደበቀው ደስ ባለይ።
ዝናቡ ሁሌም ደስ እማይለይ ስለማላውቀው ሰው ስለሚያወራይ ነው ።
በስምም በአካልም ስለማላውቀው ሰው በይህ ገባ በይህ ወጣ ብሎ ወሬ መስማት ብዙም ምቾት አይሰጠይም።
ገና ሲገባ አይቶያል። ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣና•••
ዛሬ የገጠመይን ጉድ እስክነግርህ ቸኩያለሁ ።አለይ። ለማውራት ምላሱን እየሳለ•••
ምን አጋጠመህ አልሁት። ምን ቸገረዪ ዥሮ አይሞላ እስቲ ተንፍሶ እስቲገላገለው በመስማት ልተባበረውና ተንፍሶ ይገላገለው ብዬ••••
"እሄውልህ ያክስቴ ልዥ ታሜሪካን የመጣው ተሁለት ሳምንት በፊት ነው።
👍51👎1😁1
ልሂድ አልሂድ እያልሁ እስተዛሬ ታመነታ ቆየሁ። ታመሪካን መጣ ሲባል አመሪካን እራሷን ይዞ መጣ የተባለ ይመስል ሁሉም ከያለበት እንኳን ደና መጣ ታይሆን እንኳን ደና መጣህልን ሊለው እየሄደ የድርሻውን ቲቦጭቅ።
ያክስቴ ልዥም አይደል እንኳን እኔ በደም ዝምድና ያለይ በስም የሚያውቀው የጎረቤት ልዥ ሁሉ ይሄድ የለ እንዴ!
የኔስ ድርሻ ተሚሻግት ሄጄ ብወስደው ምናለ አልሁና ለሳምንት የጠጅ ወጪዬን እንኳን የሚሸፍን ብር ቢሰጠይ ብዬ ሄድሁልህ ።
ሰላም ብዬው እንደተቀመጥሁ ቤተ ዘመዳ
ዘመዶቹ " አይ ዝናቡ ደና ነህ ግን እንደው በስንት ግዜ ዛሬ ተገናኘን !
ጠፋህ እኮ አንተው! እየመጣህ መጠየቁን ተተውከው ስንት ግዜ ሆነህ" ቲሉይ
እንደው ትለመጥፋቴ ያን ያህል የሚነዘንዙይ መጥፋቴ አሳስቧቸእ የናፍቆታቸውን ታይሆን እኛን ልትጠይቅ ታይሆን ዛሬ ልዣችን ተአሜሪካን መጣ ቲባል ነው የመጣህ እያሉ በነገር የሚሸነጉጡይ መስሎ ትለተሰማይ ውስጤን ጎረበጠይ።
ቢሆንም ሁለት ወዶ አይሆንም እና በአሽሙር የሚዘልፈይን ሰምቼ እንዳልሰማሁ ሆኜ ተቀመጥሁ።
ተቤተ ዘመዱ ጋር ታወጋ በወሬ መሀል ወደይህ የመጣው ታገሩ ተወንዙ የበቀለይውን ኮረዳ አግብቶ ሊወስድ መሆኑን ትሰማ ግር አለይ።
አጠገቤ ወዳለው ታናሽ ወንድሙ አንገቴን አዘመምሁና ስማ እንጂዢአንተው ተዛሬ ስንት አመት በፊት ወንድምህ እዛ አማሪካን ሚሽት አግብቶ መውለዱን ነግረኸይም አልነበር እንዴት ነው ነገሩ? ትለው።
ውይ ዝናቡ አልሰማህም እንዴ አየህ እሄን አለመስማትህ እራሱ ምን ያህል ግዜ እንደተጠፋፋን ነው እሚያሳየው በማለት በነገር ወጋ አርጎ ታለፈይ ቡሀሏ•••
" እሷን እማ ፈታት እኮ! አለይ ።
ምነው ምነው ተወለዱ ቡሀላ ምን አጋጠማቸው ጃል ? ትለው!
ይህቺ ጉዷ እማያልቅ አሜሪካን ፎርጅድ ሚሽት ድራለት ነዋ ቲለኝ ግር አለኝ
ፎርጅድ ፎርጅድ ደግሞ ምን ማለት ነው እሱ ? ትለው ሳቀብይ •••• •••ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️
👍33👎2🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ+ነበረ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ትንፋሽ ወሰድኩና ከመተኛቴ በፊት  ከአያቴ ጋር ለማውራት አፌን ከፈትኩ…አያቴ እንዳልተኙ በመብራቱ አለመጥፋት እና በዕቃ መንኳኳት ማወቅ ችያለሁ፡፡

‹‹አያቴ ጉዴን እየሰሙ ነው አይደል?››
መልስ የለም

‹‹አያቴ ይሰሙኛል?››
መልስ የለም

‹‹እንዴ..ያን የተለመደ ዝምታቸውን ጀመሩ ማለት ነው..?አሁን በዚህ ከእሳቸው ጋር ማውራት በፈለኩ ቀን ዝም ይላሉ..››ብዬ ተሰፋ በመቁረጥ ልተኛ ልብሴን ማውለቅ ስጀምር በጆሮዬ ደምፅ ሰማሁ፣፣

‹ምንድነው… አያቴ ሙዚቃ…?››ወደግድግዳው ተጠጋሁና ጆሮዬን ቀስሬ አዳመጥኩ….ውይ እለተ ምፅአት ደርሶል መሰለኝ…ከአያቴ ቤት የሲሊንዲዮን ዘፈን እየተሰማ ነው…፡፡

‹‹አያቴ እኔ አላምንም…ሰሞኑን በጣም እያስደመሙኝ ነው..ከቤት ለመውጣት መወሰኖት ሳያንስ ጭራሽ የፈረንጅ ሙዚቃ….በአንዴ ግን እንዲህ አይነት ለውጥ አይከብድም.?

አሁንም ፀጥታ ነው….

‹‹አያቴ ምንም የማያናግሩኝ ከሆነ በፊት ለፊት በራፍ ዞሬ መምጣቴ ነው..››

‹‹በፊት ለፊት በራፍ… ተው ይቅርብህ..አታድርገው››

‹‹ምን ?››የባሰ አለ ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም

‹‹ሰምተሀል››
አዎ በደንብ ሰምቼያለሁ… አያቴ ቤት ሴት….አረ አይደረግም…እያናገረችኝ ያለችው ሴት ነች..ወጣት ሴት፡፡

‹‹አያቴ የሉም እንዴ?››
‹‹አያትህ የለም››ለስላሳ ለጋ የሴት ድምፅ መልስ ሰጠኝ፡፡
‹‹ይቅርታ ማን ልበል….?››ግራ በመጋባት ተሞልቼ ጠየቅኩ፡፡

‹በዚህ ውድቅት ለሊት ከአዲስ ሰው ጋር መተዋወቅ አይክብድም..?ይቅርታ ጥዋት እንተዋወቃለን… ባይሆን አሁን የአያትህን መልዕክት ተቀበለኝ..››

ከአያቴ ጋር እቃ ወደምንቀባበልበት ስንጥቅ አመራሁ...ለግላጋ ጠይም የእጅ እጣት ብጣሽ ወረቀት አቀበለኝ.. .ተቀበልኳት እና ወደአልጋው ተመለስኩ… ገለጥኩና ማንበብ ጀመርኩ፡፡

ልጄ ሳልነግርህ ይህን በማድረጌ ይቅርታ..ለአንድ ወር ወደገዳም ሄጄያለሁ…ትንሽ በፅሞና ከእግዚያብሄር ጋር ማውራት አምሮኛል…ልክ የዛሬ ወር ተመልሼ እመጣለሁ...እስከዛ የምወዳት የልጅ ልጄ ማራናታ ካንተ ጋር  እንድትቆይልኝ እፈልጋለሁ፡፡ያው ከሰሎሞን ሚስት ማለት ከእንጀራ እናቷ  ጋር አምርራ ስለማትስማማ እነሱ ጋር መቀመጥ አትችልም…እኔ ወደገዳም መሄዱን ቀድሜ የያዝኩት ቀጠሮ ነው…  ከእግዚያሄር ጋር የያዝኩትን ቀጠሮ ማስተጓጎል አልችልኩም…እሷ ደግሞ ድንገት መጣችብኝ….ግን ያው አንተ ልጄን ከእራሴ በላይ ስለማምንህ ልክ እንደእኔ አረገህ  ከእኔም በላይ እንደምትጠብቃትና እንደምትንከበከባት ቅንጣት ጥርጣሬ አይገባኝም…ቀንም ስራም ሆነ ሌላ ቦታ ስትሄድ ይዘሀት ሂድ…ማታም ጥለሀት ውጭ እንዳታድር..ነግሬሀለው አንተ ወሽካታ..ደግሞ ለእሷም እንዳታስቸግርህ ነግሬያታለሁ...አደራ አንተ ቀልማዳ እናንተ ሁለታችሁ በአለም ላይ እጅግ የምወዳችሁ የልጅ ልጆቼ ናችሁና ተመልሼ እስክመጣ በመደጋገፉ ጊዜችሁን በጥሩ ሁኔታ አሳልፉ.፡፡

ያንተው አያት ሙሉአለም ነኝ፡፡

‹‹እህት ይቅርታ ማራናታ ይሄ ምንድነው..?አያቴ ምንድነው የሰሩት?››

‹‹ያው አያትህ የሰራው እንዳነበብከው ነው›

‹‹እያሾፍሽ ነው እንዴ?››
‹አንተ እንዴት ነው የምታናግረኝ እንግዳህ እኮ ነኝ…ከደበረህ ነገ ጥዋት ተነስቼ ወደ ሀገሬ እበራለሁ..››

‹‹አረ በፈጣሪ ..ነገሩ ዱብ እዳ ሆኖብኝ እንጂ እንደዛ ማለቴ አይደለም...አሁን እራት በልተሻል..?››

‹‹አዎ በልቼያለሁ››
‹‹ሌላ የምትፈልጊው ነገር አለ….?››

‹‹አዎ አንድ ጠርሙስ ቢራ ባገኝ ደስ ይለኝ ነበር..››

‹‹እሺ አሁን አመጣልሻለሁ.››.ከአልጋዬ ተነሳሁና ጫማዬን ማድረግ ጀመርኩ

‹‹ምነው አለህ እንዴ?››ጠየቀችኘ
‹‹አይ የለኝም ግን አታስቢ አሁን ገዝቼ መጠለሁ. ምንድነው ሚመችሽ ማለት ጊርጊስ፤ በደሌ፤ሀረር ..››
‹‹አራት ሰዓት  እኮ አልፏል..የእውነት አሁን በዚህ ሰዓት ሄደህ ልትገዛልኝ ነው?›

‹‹አራት ሰዓት አይደለም ስድስት ሰዓትስ ቢሆን ምን ችግር አለው…የአያቴ አደራ እኮ  ነሽ…››

‹‹በል ስቀልድ ነው..አሁን አልፈልግም ነገ ትጋብዘኛለህ››

‹‹እውነተሽን ነው…?››
‹‹.አዎ አሁን ስለደከመኝ እንቅልፌ መጥቷል …ቻው ደህና እደር..››

‹‹ደህና እደሪ …ለሊት በማንኛውም ሰዓት የምትፈልጊው ምንም ነገር ቢኖር ንገሪኝ..››

‹‹ለሊት ምንም ነገር ብፈልግ?››ሳቅ ባፈነው ድምፅ

‹‹አዎ ምንም ነገር ብትፈልጊ..››

‹‹እሺ ነግርሀለሁ.. .አሁን ደህና እደር››

‹‹ደህና እደሪ›› ብዬ ሳደርግ የነበረውን ጫማ መልሼ አወለቅኩና ወደ አልጋዬ  ወጣሁ...ከልጅቷ ጋር በግድግዳ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ ሆነን የተነጋገርናቸውን ነገሮች መልሼ ሳስብ...ልጅቷ ልክ እንደ አያቴ ተንኮለኛ ቢጤ ነች መሰለኝ ስል አሰብኩና ፈገግ አልኩ…

ስለእዚህች ልጅ አያቴ ለብዙ ቀን አውርተውኛል..በየ15 ቀኑም ደብደቤ እየጻፉ እየሰጡኝ ለረጂም ጊዜ ፖሰታ ቤት ወስጄ የማስገባላቸው አኔ ስለሆንኩ ስለእሷ በመጠኑ አውቃለሁ..…ለምሳሌ የድሬደዋ ልጅ መሆኗን..ከእናቷ ጋር እንደምትኖርና… ጋሽ ሰለሞን የአሁኗን ሚስቱን ከማግባቱ በፊት እናትዬውን አግብቶ እሷን ከወለደ በኃላ እንደተፋቱ ከዛ እናትዬው ልጆን ይዛ ቤተሰቦቾ ጋር ድሬደዋ እንደገባች አውቃለሁ…አያቴም ከቤት አልወጣም ብለው እራሳቸውን ኳራንቲን ከማስገባቸው በፊት ቢያንስ በስድስት ወር አንዴ እየሄዱ እንደሚጠይቋት እሷም አልፎ አልፎ እየመጣች ትጠይቃቸው እንደነበረ መረጃው አለኝ ….ከልጃቸው ከጋሽ ሰለሞን በላይ ከእሷ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸውም አውቃለሁ....ሌላው በ1987 ዓ.ምህረት እንደተወለደች ነግረውኛል…ያ ማለት ይህቺ የሚቀጥለው ክፍል ውስጥ ያለች ወጣት አሁን 25 ዓመቷ ነው፡ በትምህርቷ በአካውንቲንግ ዲግሪ አላት…የእናቷ ቤተሰቦች ሀብታም ነጋዴዎች ስለሆኑ የራሷ ቡቲክ ከፍተውላት እየሰራች እንደሆነም አውቃለሁ...በቃ ስለእሷ የማውቀው ይሄንን ያህል ብቻ ነው ፡፡በተረፈ ቀጭን ትሁን ወፍራም..ቀይ ትሁን ጥቁር..ረጀም ትሁን አጭር ….ትሁት ትሁን መሰሪ ምንም አላውቅም….ምንም ፡፡ ግን ምንም ትሁን ምንም ለአንድ ወር የእኔ ኃላፊት ነች.. ፡፡ ያንን ኃላፊነት ደግሞ ያለምንም ማቅማማት በፍጽም ትዕግስት እና ብቃት እወጣለሁ...ምክንያቱም ያዘዙኝ አያቴ ናቸው..አሁን ልተኛ….ነገ ምን አልባት ረጅም ቀን ሊሆን ይችላል፡፡

ይቀጥላል
👍5944🔥4😁3👎1
ሚስቴ እና አባቷ!? 😡
ክፍል ~~~~ዘጠኝ
ይህቺ ጉዷ እማያልቅ አሜሪካን ፎርጅድ ሚሽት ድራለት ነዋ ቲለኝ ግር አለኝ
ፎርጅድ ፎርጅድ ደግሞ ምን ማለት ነው እሱ ? ትለው ሳቀብይ••••
ምን ያስቅሀል አንተው አለማወቅ ሀጥያት አይደለ! ባእድ ቋንቋ ቀላቅለህ ትታበቃ እኔ ላይ መሳቅ ምን ይሉታል በል ይልቅ እምታወጋይ ተሆነ ነገሩን እንዲገባይ በራሴ አፍ አውጋይ!'።
አልሁት ባሳሳቁ በሽቄ።ተዛ ቡሀላ ነገሩን እንዲህ ብሎ አጫወተይ•••
ዘመድ አዝማዷን ታይተዋወቅ እዛው አሜሪካን ተወልዳ ያደገች ጥቁር አሜሪካዊት ሴት ያገባል !
ዛድያ ተተጋቡ ቡሀላ እነሱ ዘንድ በመጣው ወንድሟ እና በሷ መሀል ያለውን የመልክ ልዩነት ቲያይ ለየቅል ብቻ ታይሆን ጭራስ ታንድ ማህጠን የወጡም አይመስሉ ።
ወንዱሟን ቲያው ዝንጀሮ ቆሞ እምሄድ እይ ሰው ትለመሆኑ የሚያጠራጥር ሆኖ ሳለ እሷ ልቅም ያለይ ቆንጆ ነይ።
ታድያ ሁለቱ አጠገብ ላጠገብ ቁጭ ብለው ባያቸው ቁጥር እንዲሁ ቲያስገርመው !።
መገረም ብቻ አይደለም ቲያስደምመው !።
መደመምም ብቻ አይደለም አንዳንዴ እንደውም ቲያስደነግጠው ይቆይልሀል።
ማንን እንደሚጠይቅ ማንን እንደሚያማክር ግራ እንደተጋባ።
በዚህ መሀል አርግዛ ትወልዳለይ። ዛድያ ህጣኑ አደግ ቲል ወንድሟን መስሎ እርፍ።
ታክስቴ ልዥም ተሚሽቱም ምንም ያልወሰደ ጓጉንቸር ሆኖ ቁጭ።
የልዡ እና የወንድሟ መልክ መመሳሰል ውስጥ ውስጡን እየከነከነውም ቢሆን
ፈጣሪ የሰጠውን ልዥ በጠጋ ተቀብሎ ማሳደጉን ቀጠለ።
ያክስቴ ልጅ ለወንድሙ እንደነገረው ተሆነ•••
በመሀል ወንድማ የሚጠቀምበትን "ላብ ቶብ " ለብቶም"
የሚሉት "ኮምፒተሩን " ባጋጣሚ ክፍት ሆኖ አግኝቶት ኖራል ውስጥ ገብቶ ሲበረብር ተአመታት በፊት ሚሽቱ ተወንድማም፣ ተቤተሰቧም ፣ ብቻዋንም የተነሳያቸውን ትክክለኛውን የቀድሞ መልኳን የየዙ ፎቶዋን ያያል ! ክው አለ።
ያኔ በተፈጥሮ ተፈጣሪ የታደለይውን መልክ ዘመን አመጣሽ በሆነ "ቴክኖሎጂ" "የብላስቲካ ሴርጀሪ" ነው እሚባል ያለይ መሰል ብቻ በሱ ቴክኖሎጂ ገፅታዋን ሙሉ በሙሉ እንደቀየረይ ይደርስበታል።
ዝናቡ የፈረንጅ አፍ እየቀላቀሉበት ለሱ ያልገባውን ነገር ለኔ ሊያወጋይ ሲደክም ግራ እንደገባይ አይን አይኑን እያየሁ ታደምጠው አሁንም ቀጠለና•••
"የቀድሞ ፎቶዎቿን አንድ ባንድ እያሳየ ሲጠይቃት አይን ፍጥጥ !ጥርስ ግጥጥ !ዋሽታ እማታመልጠው ሀቅ ነውና አልካደይውም አመነይ። በጥቅሉ ያገባው በፈጣሪ የተሰራችውን ታይሆን በሰው የታደሰችውን ነው ስልህ!
ሲለይ ይበልጡን ተምያታብይ ። ዝናቡ መዝነብ ተዥመረ መች ያቆማል አሁንም ቀጠለ•••
"ተዛ ቡሀላ የኛ ሰው ሀበሻ ያው እንደእልኸኛነቱ ሁሉ ተረታ /ታሸነፈ/ ቡሀላ ይቅር ባይነቱም የበዛ አይደል !
እውነቱን ታወቀ ቡሀላ ሁሉን ትቶ ይቅር ቢላትም በሷ ብሶ በጀ አላለይም። እውነቱ ተወጣ ቡሀላ ከሱ ጋር መቀጠሉ ጎረበጣት መሰል መፋታቱን መርጣ ተፋቱ። አንዳርጌ ሙት እሄን ስስማ ጉድ ጉድ ጉድ እያልሁ ጭንቅላቴን ይዤ ልጮህ ምን ቀረኝ!" ብሎ ያክስቱን ልጅ ታሪክ ቋጨ።
እንኳን የተዋቡ አባት እንዲህ ናላዬን አዙረውት በደናውስ ግዜ ቢሆን እንዲህ ለራሱ ያልገባውን ወሬ ለኔ አውርቶልዪ ቤት በኩል ይገባኛል።
ምናለ ሰው ለራሱ ያልገባውን ለሌላው ባያወራ
ምን እንዳናደደይ እንጃ ብቻ ብልጭ አለብይ•••
የነገሩ ባለቤት ያልጮኸውን አንተ ምን ቤት ነህ ጭንቅላትህን ይዘህ እምትጮኸው ጎበዝ??" ልለው አሰብሁና መልሼ ታጤነው ስንቱ በማያገባው እየጬኸም አይደል ብዬ•••
" እሄስ ያስጮሀል ዝንቡ ጮኽህ ቢወጣልህ ጥሩ ነበር ሙት!" አልኹት።
"ሙት እውነትህን ነው !ሳልጠጣ ሄጄ እንዢ ሞቅ ቢለኝማ መጮኼ አይቀርም ነበር አሁን ልጩህ እንዴ ? አለዪ
ቆይ እኔ ልውጣና ትጮሀለህ ብዬው ሂሳቤን ከፍዬ ተጠጅ ቤቱ ወጣሁ።
ግቢ እንደደረስሁ መጠጡ በሰጠይ ድፍረት ትልቁቤት በር ላይ ቆምሁና ጮክ ብዬ ተዋቡ የኔ ብዬ ተጣራሁ።
በሩን በስሱ ከፈተይና •••
"በእጇ አባዬ ተኝታል አትጩህ!"
የሚል ምልክት አሳየችይ።
መስማታቸው አይቀርም ብዬ•••
ቅድም የሞተውን ሰው ስም በደንብ ሳላጣራ ስላስደነገጥሁሽ ይቅር በይይ ውብ አለም የስም ስተት ነው " ለጋሼ ዘርጋውም ንገሪልይ አልኋት።
በሩ ላይ እንደቆመይ አንገቷን አዙራ አባቷ ወደተኙበት ገልመጥ አረገይና።
በል አሁን ግባና ተኛ በቃ ደና እደር ። አለችይ።
በጀ እያልሁ በሬን ከፍቼ እስትገባ ቆማ እያየችይ እንደሆነ ያወቅሁት የኔኑ ክፍል በር ልዘጋ ስዞር ነበር ። ቆሜ ታያት እጇን አውለብልባ ተሰናበተችኝና ገብታ በሩን ጠረቀመችው።
በጥዋት ቁርስ ይዛልይ እንደገባይ።
ተዋቡ ላንድ ለሁለት ሳምንት ዘመድ ዘንድ ደርሼ እመለሳለሁ አንድ ሁለት ቅያሪ ልብስ ይዘሽልይ ነይ አልኋት።
ታፏ ቃል ታታወጣ ትክ ብላ እያየችኝ እንባዋ ሁለቱ አይኖቿ ላይ ግጥም ቲል ፊቷን መልሳ ተክፍሌ ወጣይ።
ትንሽ ቀየት ብሎ በሬ ቲንኳኳ ተዋቡ ልብሱን ይዝልይ መጥታ ነው ብዬ ማነው ታልል ብድግ ብዬ ብከፍተው አባቷ ናቸው።
ደንገጥ ብዬ ደና አደርህ ጋሼ ዘርጋው ምነው በጥዋት በሰላም ነው ብለው "ፈልጌህ ነው አንዳርጌ ለባብስና እላይ ቤት ና እጠብቅሀለው " ብሎኝ ተመለሰ።
ለምን ፈለጉይ ብዬ ፈራ ተባ እያልሁ ወደ ትልቁ ቤት ገባሁና ቁጭ አልሁ።
አንዴ አጠገባቸው ወደ ተቀመጠይው ተዋቡ አንዴ ወደኔ እየተመለከቱ •••
"ልጆቼ•••" ብለው መልሰው ዝም አሉ።
ገና መናገር ታይጀምሩ ፊታቸው ተቀያየረ።
ሁለመናቸውን የሀዘን ድባብ ጣለበት።
ልዦቼ እናቴ ገና የአስራ ሁለት አመት ልዥ እያለሁ ነው በወባ በሽታ የሞተችብይ።
ታድያ የናቴን ያህል የምወዳት አንድ ለናቷ የነበረይ አንድ ታላቅ ብቻ ነይ የነበረችይ።
ተዋቡ ትባላለይ ሲሉ እኔና የኔዋ ተዋቡ ግራ በመጋባት ተያየን።
ያንተን ሚሽት እቺ ልዤን ተዋቡ ያልኋት መልኳ ተሷ ጋር ስለሚመሳሰል ነው። እይ ጨቅላ ሆና እናቷ ያወጣይላት ሽም ሌላ ነበር።
አባታችን ብዙም ለልጅዥፊቱ የማይፈታ ሰው ነው። ስለዚህ እንደናትም ፣እንደህትም ፣እንዳባትም የማያት ይችኑ እህቴን ነበር። ተራሴ በላይ እወዳት ነበር።
ማግባት አይቀርምና ባል ታገባይ ቡሀላ አባቴ ብዙም ስለማይቀርበይ ብቸኝነት ያጠቃይ ዥመር።
አብዛኛውን ግዜ እህቴ ዘንድ እየሄድኩ ብቀመጥም ባሏ አመለ ክፉ ነበርና ቲያሰቃያት እያየሁ ስለማያስችለዪ እሷን ሲያስለቅስብይ ሰድቤው ወደ ቤቴ እመለሳለሁ።
ግን አያስችለኝም አሁንም ስናፍቀኝ እሄዳለሁ አሁንም ተጣልቼው እመለሳለሁ።
በይህ ሁኔታ አመታት ቢቆዩም ልዥ አልወለዱም
ችግሩ ተሱ ይሁን ከሷ አላውቅም ብቻ ልዥ አልነበራቸውም።
ጠባቸው እየተደጋገመና እየከረረ ቲመጣ እህቴ ተባሏ በተጣላይ ቁጥር ወደኛ ዘንድ መምጣት ዥመረይ።
ስትመጣ አባቴ ልዥን ቀርቦ ? ምን ከፍቶሽ ነው? ሳይል ፣ ምንድን ነው በመሀከላችሁ ያለው ችግር?"
ብሎ የሚፈታ ችግር ከሆነ መፍትሄ እንዲያበጁለት መፍትሄ ከለለውና የሷ ምርጫ መለያየት ተሆነ እንዲለያዩ ፍላጎቷን ታይጠይቅ ፣ ከፍቷት በመጣች ቁጥር ሴት ልዥ ከቧላ ጋር በተጣላይ ቁጥር ሮጧ ወደቤተሰቦቿ የምትመጣ ከሆነ ደግ አደለም እያለ አሳቆ ሲመልሳት አለቅሳለሁ።
እኔ የባሏን ጠባይ አውቀዋለሁና ተጣልታ መጥታ ሂጂ ብሎ በሚያባርራት አባቴ እጅጉን እናደድ ነበር።
በመጨረሻም እሷው ጋር ሄጄ በሌላኛው ክፍል ውስጥ በተኛሁበት የገዛ ባሏ እህቴን በተኛችበት ገሏት ጠፋ።
ተንቅልፌ እንደተነሳሀ በተኛችበት ታርዳ የሞተይውን የገዛ እህቴን ሬሳ አየሁት።
👍53🔥2👏1