አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ደግ ሰዎችን በምድር የሚያሰቃያቸው በሰማይ ቤት ሊክሳቸው ይሆን እንዴ? እያልኩ እራሴን እጠይቃለው..አጐቴ እንደዛ ተሠቃይቶ መሞት ያለበት ሰው አልነበረም….››
‹‹እንደተረደውት ከሆነ .. አጎትሽን ልክ እንደአባትሽ ነበር የምትቀርቢው?››
‹‹በትክክል ››
‹‹ግን የአባትሽን ማንነት ለማወቅ አልሞከርሽም ?››ቀስ በቀስ እሱ ወደሚፈልገው ርዕስ እየሳበ ወሰዳት…
‹‹አልሞከርሺም እንዴ? ነፍስ ካወቅኩበት ቀን አንስቶ ከዚህ በላይ የምፈልገው ነገር ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ግን እንዴት አባቴ አድርጌ ለማወቅ ልቻል..?ማ ይንገረኝ?››
‹‹እሮዝንስ አልጠየቅሻትም?››
‹‹የእኔ እና የእሷ የጥል መንስዔ ምን ሆነና…አባቴን ንገሪኝ ?ከቆማጣም ውለጂኝ….ከሸፋፋም ውለጂኝ ምንም ቅር አይለኝም.. ብቻ ማንነቱን ልወቅ ብዬ ዕድሜ ልኬን ለመንኳት… ልትነግረኝ ግን ፍቃደኛ አልሆነችም…፡፡አንዴ ሞቷል፤ አንዴ አላውቀውም….መጨበጫ የሌለው ሰበብ ትሰጠኛለች ..ከዛ ከእሷ ጋር መጨቃጨቅ ሰለቸኝና ተውኰት፡፡ እሷም እናቴ መሆኖን ማመን እሰኪከብደኝ ድረስ አስጠላቺኝ እኔም ሆንኩ እማዬ በእሷ ተስፋ ቆርጠናል፡፡ነገ እኛም አንድ ነገር ብንሆን አትደርስልንም..አውሬ ሆናለች…››ተንዘረዘረች
‹‹ምን አልባት ከአጐትሽ ጋር የተካረሩበት ጥልቀት ያለው ቅያሜ በመሀከላቸው ይኖር ይሆን ብለሽ አስበሽ አታውቂም….?››
‹‹ሊሆን ይችላል …እርግጥ እንደተጣሉ አውቃለው..እሱ ጋር ሆና ነበር የምትማረው… ያው ማንም ወላጅ እንደሚያደርገው እሱ ጋር እየተማረች እኔን ዲቃላ ስታረግዝ ቅር ብሎት የተናገራት ክፍ ቃል ሊኖር ይችላል ይሆናል… ምክንያቱም እኔን ባረገዘችበት ወቅት ከእሱም ተጣልታ እቤቱን ጥላለት ወደ እዚህ መጥታ እኔን እንደወለደቺኝ አውቃለው.. ግን እኮ በእሱ ቦታ ማንም ሰው ቢሆን በወቅቱ የሆነ ነገር መናገሩ አቀይቀርም፡፡ ያን ቂም ይዛ አልጋ ላይ ስንት ወር ሲተኛ አልጠይቅም ብላ አሻፈረኝ ማለት ነበረባት…?እሺ እሱስ ይሁን ቢያንስ ሲሞት እንኳን አፈር ማልበስ አልነበረባትም? ቢያንስ እኔን እና እማዬን ማጽናናት አይገባትም ነበር አቤል ለጠየቀችው ጥያቄ መልስ ባይሰጣትም ጊዜው ስለጨለመ የተጠቀሙበትን ሂሳብ ከፈለና ነገ መልሰው ሊገናኙ ተነጋግረው ሰፋሯ ድረስ ሸኝቷት በብዙ ሀሳቦች አዕምሮው እንደተወጣጠረ ወደ ቤርጐ ተመለሰ…

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#ብቻዬን_ላፍቅርሽ

ባልኖረ ሌላ አዳም ከምድር በጠፋ፣
የኔ ብቻ እንድትሆኝ ቢደላም ቢከፋ፣
።።
በሰፊው አለም ላይ ለጥ ባለው ምድር፣
ምናለ አምላክ ፈቅዶ ብቻችንን ብንቀር፣
ሌላ አዳሞች ቀርተው ብቻዬን ባፈቅር፣
መሬት ባዶ ትሁን ማንም አይኑርባት ከኔና አንቺ በቀር፣
።።
ሆንሽና ስስቴ የነፍሴ ጥም አርኪ፣
ቀኔን ምታበሪ ዘወትር ስትስቂ፣
።።
እንዳትሆኝ የሌላ ልቤ ስለፈራ፣
አዳሞችን ጠላው ስላንቺ ስራራ፣
።።
ብቻዬን ላፍቅርሽ ማንም ሳይጋራኝ፣
ከሄዋኔ በቀር አዳም አያሳየኝ፣
።።
አደለም በውን ተኝቼ በህልሜ፣
ከሌላ አዳም ባይሽ ይብሳል ህመሜ፣
አልድነውም እንኳ በቅጡ ታክሜ፣
።።
አዳሞች ራቁ ሽሹ ከኔ ሄዋን፣
ደርሶ የነካትን አልምረውም ነፍሱን፣
።።
ድርድር አላውቅም እኔ በሷ ጉዳይ፣
ጦሬን እመዛለው ባልሆንም ሺ ገዳይ፣
።።
የኔ ብቻ እንድትሆን አምላክ ባክህ እርዳኝ፣
ከኔ ሌላ አዳም በምድር አይገኝ፣
ልሁን ከሷ ጋራ ተጋፊ ሳይኖረኝ፣
ተው አትንካት ብሎ የሚከለክለኝ፣
።።
የውበትሽ ማማር እጅግ ስለ በዛ፣
ሁሉም ይመኙሻል አይተውሽ በዋዛ፣
።።
ሲረባረቡብሽ እጅግ አፈራለው፣
አዳም ከኔ ሌላ ባላይ እመርጣለው፣
።።
ከሰዋራው ልቤ ውዴ ልደብቅሽ፣
ማንም ሳይነካብኝ ብቻዬን ላፍቅርሽ!!
#የሚያስተክዝ_ትዝታ 😔

ያኔ ልጅ እያለሁ ፤ የፍልሰታ ጦምን እስከዘጠኝ ሰአት እፆም ነበር። የፆም አላማ ፤ወደ እግዚያብሄር ለመቅረብ፤ በረከት ለማግኘት እና ሀጢአትን ለማስተረይ እንደሆነ ይታወቃል ። እኔ ግን የምጦመው በፆም ወቅት ቤት ውስጥ ምግብ ስለማይሰራ ነው፤ ጦሙ ሊገባ ሁለት ቀን ሲቀረው እናታችን፤ ያንን ትልቁን ብረትድስት ፤ ለሁለት ወራት ስለማትፈልገው፤ ለእትየ ፋጤ ታከራያቸዋለች፤ እትየ ፋጤ በመላው ዳሞት ብቸኛ የሙስሊም ምግብ ቤት ያላቸው ሴትዮ ነበሩ፤
በፍስክ ወቅት፤ትምርት ቤት ከምንዘምራቸው መዝሙሮች ውስጥ፤
“ሳይንስ ሳይንስ መዳኒቴ
አስታወሰኝ ጤንነቴ (ምን ለማለት ተፈልጎ ነው ግን?)
ፊቴን ታጥቤ ፤ቁርሴን ስበላ
ሳይንስ ትዝ አለኝ፤ ከጤና ጋራ”
የሚለው አይዘነጋኝም፤በፆም ወቅት ግን ፤መዝሙሩን ትንሽ አስተካክለን እንደሚከተለው እንዘምረዋለን፤
ሳይንስ ሳይንስ መዳኒቴ
፦፦፦፦
ፊቴን ታጥቤ ቁርሴን ባልበላም
እናት አገሬ ሁኝልኝ ሰላም
በፆም ወቅት፤ አያሌ ምእመናን ጊዝያቸውን፤ በፆሎትና በስግደት ያሳልፉታል። እኔ ግን በፆም ወቅት ቀኑን የማሳልፈው ፤ አላፊ አግዳሚውን እያስቆምኩ ፤ ሰአት በመጠየቅ ነው። (ዘጠኝ ሰአት ካልሞላ እህል ወደኛቤት አይደርስም፤)
ለምሳሌ ጋሽ በለው በቤታችን በር በኩል ሲያልፉ ጠብቄ፤
“ጋሼ ስንት ሰአት ነው?”
ጋሽ በለው ፤ የእጅ ሰአት ለማሰር ከታደሉት ጥቂት የማንኩሳ ነዋሪዎች አንዱ ነበሩ። ከሴኮ ሰአታቸው የሚመነጨው ኩራታቸው ወሰን አልነበረውም፤ ሰአትን የፈለሰፈው ሰውየ እንኩዋ የሳቸውን ያህል አይንጠባረርም !! የእጅ ሰአቱን ፤የዳሞትን አውራጃ በመወከል ፤በውሃ ዋና ውድድር አሸንፈው፤ ከጃንሆይ የተሸለሙት ነው ይባላል። የዋና ችሎታቸውን ለማጋነን በየጠላ ቤቱ እሚወራው ብዙ ነው፤ አንዳንዴ ጋሽ በለው፤ ሲደብራቸው፤ ጣና ላይ ዳይቭ ገብተው ፤ ቀይ ባህር ላይ ብቅ ይሉና የባህር ሃይላችንን ሰራተኞች “ጉዋዶች በርቱ!” ብለው፤ ይመለሳሉ ይባላል።
በነገራችን ላይ “አሳ በለው በለው” የተባለው ዘፈን ለሳቸው ነው የተዘፈነው ለእሳቸው መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን?፤ እና ሰአት ስጠይቃቸው፤ በኩራት ፈገግግግ ብለው፤ እስክስታ እንደሚመታ ሰው ግራ እጃቸውን ትንሽ ርግፍ ርግፍ አድርገው፤ በክርናቸው ነፋሱን ጎስመው፤ አይበሉባቸውን ወደ ፊታቸው ያመጡና ግንባራቸውን ቁዋጠር ፈታ ሲያረጉ ቆይተው፤
” ሰባት ሰአት ነው” ይሉኛል።
“ትንሽ አጠገባቸው ቆሜ ኦና ሆዴን ሳክ ከቆየሁ በሁዋላ “አሁንስ?”
“ሰባት ካምስት”
“አሁንስ?”
“ወግድ ከዚ”
እኔም ከዚ እወግድና ሌላ ሰአት አስሮ የሚያልፍ ሰው እጠብቃለሁ። ዘጠኝ ሰአት የሚባለው ነገር እየተንቀራፈፈ፤ እሪህ ያለበት ኤሊ እየጋለበ ፤ እስኪመጣ ድረስ እጠብቃለሁ፤
ጦም ሲታሰብ ፍስክ ትዝ ይለኛል፤ ፍስክን ሳስብ ትንሽ ወንድሜ ሞሴ ይመጣብኛል ፤ ሞሴ እንቁላል አጥብቆ ይወዳል ፤ ሞሴ እንቁላል ከመውደዱ የተነሳ የሰጎን እንቁላል ከቤተክስያን ጉልላት ላይ አውርዶ ቢቀቅል አይጠላም፤ ያኔ እንቁላል የሚባል ነገር መኖሩ ትዝ የሚለን በሁለት አጋጣሚዎች ነው፤ በሳይንስ ክፍለጊዜ ስለገንቢ ምግብ ስንማር እና የፋሲካ ሌሊት ፤ የፋሲካ ሌሊት እናታችን በትልቁ ሰታቴ ብስል ያጋም ፍሬ የመሰ ዶሮ ወጥ ሰርታ አስራሁለት ቅቅል እንቁላል ትጥልበታለች ፤
ያገራችን ዶሮዎች፤ ከላይ ጆፌ አሞራ እያንጃበባቸው፤ ከታች ጎረቤት በቅዝምዝም እያባረራቸው ፤ ተሳቀው ጭረው፤ የሚጥሉት እንቁላል ከውሃ ብይ አይበልጥም፤ እንድያውም አንዳንዳንዴ ፤ከዶሮይቱ እንቁላል ፤የዶሮይቱ አይን ይተልቃል፤
ባንዱ ፋሲካ ዶሮ ወጥ ከብበን ስንበላ፤ እናታችን በየፊታችን እንቁላሎችን አስቀመጠችልን፤ ሞሴ ድርሻውን አንስቶ፤ በትንሽ በትንሹ እየቆረሰ፤እየቆጠበ በልቶ ጨረሰ፤በጉንጩ ገበር ላይ ተለክኮ የቀረውን የንቁላል ቅሪት በምላሱ ጠርጎ አጣጣመ፤ከዚያ ፤
“እማዬ”
“አቤት ልጄ ”
“የሚቀጥለው ፋሲካ ስንት ቀን ቀረው?” ይላታል !!
👍21
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ሶስት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...መሀሪ አደገኛ መደንዘዝ…ጥልቅ ጨለማ እና ረጅም ብስጭት ውስጥ ነው ያለው፡፡ያም ቢሆን ግን አሁን ሀሳቡ ተሰብስቧል..ዕቅዱ መስመር ይዞል..ምንም ወደኃላ የሚጐትተው… ሚጨነቅበት ….ሚሳሳለት ነገር የለ፡፡ሚኖረው ለበቀል ብቻ ነው፡፡በቀል ማለት ደግሞ የሚጠሉትን ሰው ተከታትሎ፤ አድብቶና፤ አድፍጧ መግደል ማለት አይደለም፡፡ሞት እማ ግልግል ነው..ሞትማ የዘላለም ፍጹም ፀጥታ..ረብሻ የሌለው ሰላማዊ እረፍት ማለት ነው፡፡አዎ ሞትማ እንዲህ ለሚጠሎቸው ሰዎች የሚለገስ ስጦታ አይደለም፡፡..በቀል ማለት የሚጠሉትን ሰው ተስፋ መስበር ማለት ነው…ያሉትን ነገሮች ሁሉ ተራ በተራ ነጥቆ ባዶ ማስቀረት መቻል ነው…፤ትናትናውን እንዲራገም ነገውን ፍጹም እንዳይናፍቅ ማድረግ መቻል ነው፡፡የእሱ እምነት እንዲህ ነው፡፡ በቀል ላይ ያለው አመለካት እንዲህ ይቃኛል ..ለማድረግ የወሰነውም እንደዚሁ ነው፡፡
መሀሪ አሁን በሙሉ ልቡ በቀሉ ላይ እንዲያተኩር ያደረገው የእናቱ መሞት ነው፡፡አዎ እናትዬው ምንትዋብ ይህቺን ምድር በሽንፈት ከለቀቀቻት እንሆ ዛሬ አስር ቀን አልፎታል ፡፡አሁን በዓለም ላይ ብቻውን እንደቀረ ተሰምቶታል..በሕይወት ለመቀጠል አንድ ምክንያት ብቻ ነው ያለው ..ያም በውስጡ የሚንበለበለው በቀሉ ብቻ ነው፡፡አሁን አብራው ያለችው በቤታቸው ከ10 ዓመት በላይ የኖረችው መስታወት ብቻ ነች፡፡
በዚህ ሰዓት እቤት ነው ያለው፡፡ከሳሎኑ ውስጥ በአንድ ኮርነር ተጠግቶ ካለ ደረቅ ወንበር ላይ ተቀምጧል፡፡መስታወትም ጥቁር በጥቁር እንደለበሰች በቅርብ እርቀት እዛው ሳሎን ውስጥ ኩርምት ብላ ተቀምጣለች፡፡ ከመቀመጫው ተነሳና ወደ ፍሪጁ በማምራት ጠርሙስ አነሳና ብርጭቆ ወይም መለኪያ ሳይፈልግ እንዳለ ከነጠርሙሱ በቁሙ አንደቀድቀው ፡፡በጠርሙሱ ውስጥ ያለው መጠጥ ጅን ወይም ውስኪ አይደለም….አረቄ ነው፡፡
ትኩር ብላ በትካዜ ስትታዘበው የቆየችው መስታወት ከብዙ ደቂቃዎች የዝምታ ጊዜ ቡኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረች
‹‹ይሄ መጠጥ እንዴት ነው?››
‹‹ደህና ነው››አላት በደመ ነፍስ
‹‹እውነቴን እኮ ነው..በጣም እኮ እራስህን እየጐዳህ ነው..ሰዓትህን እስቲ እየው ፤ገና ከጥዋቱ 3 ሰዓት ነው..በዚህ ሰዓት ካቲካላ መጠጣት ..እኔ እንጃ››አለችው በተሰበረ ልብ፡፡ መስታወት ሁኔታዎች በጣም ነው ያስፈሯት፤ ከወራት በፊት ታውቀው የነበረው መሀሪ ዛሬ የለም… ጠፍቷል.. ፡፡ፍጹም ሌላ የማታውቀው ሰው ሆኖባታል፡፡
‹‹ብቻ ጨጓራህን እንዳይልጠው››ማስጠንቀቂያዋን ሰነዘረች
‹‹መሀሪ አዲስ እየጀማመረው እንዳለ እብድ እየጮኸና ፍርፍር እያለ ሳቀ..በጣም ሳቀ‹‹ኪ..ኪኪ..ኪ..ኪ..››
‹‹እንዴ ምን ያስቀሀል?››
‹‹ንግግርሽ ነዋ ያሳቀኝ…አረቄው ጨጓራዬን እንዳይልጠው ፈራሽ..ቀድሞኮ በሰዎች ክህደት ሙሽልቅ ብሎ ተልጧል..እስኪቆስል..ከመቁሰልም አልፎ መግል እስኪቋጥር ድረስ እነዛ ሰዎች ልጠውታል..አሁን መጠጡን የምጠጣው ቁስለቱን እንዲያደነዝዝልኝ ነው..ገባሽ››
‹‹እስከመቼ ታዲያ..?ይሄ አያያዝህ እኮ ዕድሜህን ያሳጥረዋል..በዛ ላይ ሲጋራም ማጬስ ጀምረኸል››
‹‹አይዞሽ አታስቢ ብዙ ዕድሜ አያስፈልገኝም…ሶስት እና አራት አመት ዓላማዬን ወደ ተግባተር ለመቀየር ይበቃኛል፡፡››
‹‹ከዛ ቡኃላስ?››አለችው ስለእሷ እና እሱ የወደፊት ዕጣ ፋንታ አሳስቦት
‹‹ከዛ ቡኃላማ ትርፍ ህይወት ነዋ.. ጠላቶቼን ከተበቀልኩ ቡኃላ የሚኖረኝ ቀሪ ዕድሜዬ ብዙም ማልፈልገው ትርፍ ህይወት››
‹‹ቆይ መሀሪ ቀለመወርቅ እንደሆነ የትም አታገኘውም…ሮዝንም እርሳት ሴት ብትሄድ ሴት ትተካለች፤ቀረባት እንጂ አልቀረብህም..፡፡ሁሉንም ተዋቸውና ክፋታቸውንም በደላቸውንንም ለእግዚያብሄር አሳልፈህ ስጥና ህይወትን ከእንደገና አረጋግተህ ብትቀጥል ይሻላል ብዬ አስባለው…እግዚያብሄርስ በቀል የእኔ ነው ይል የለ፡፡››
‹‹እንደዛ ማድረግ ፍጹም አልችልም፡፡የተበደልኩት እኔ ነኝ በቀሉም የእኔ ነው፡፡ከአሁን ቡኃላ እንደነገርኩሽ ምኖረው በቀሌን ወደተግባር ለመቀየር ነው..ስራዬንም የምሰራው እንደበፊቱ ወገኖቼን ለማገልገል..የከተማው ኑዋሪን ሰላም ለመጠበቅ ምናምን..ምናምን ለሚባለው ዓላማ አይደለም ..ስራዬን የምሰራው ለበቀሌ እንዲረዳኝ ብቻ ነው፡፡ኃይል እና ገንዘብ ማግኛ እንዲሆነኝ፡፡››
መሀሪ ወደ ፍሪጁ አመራና ሌላ ጠርሙስ በማውጣት መጋት ጀመረ፡፡መስታወት አሁን እንደቅድሙ አትጠጣ ብላ ልትቃወመው አልደፈረችም..አሁን ደሙ እየተንተከተከ ነው፡፡የሚያስፈራ አውሬ ሆኖል፡፡
‹‹መስታወት..››አላት ድንገት
‹‹አቤት መሀሪዬ››አለችው እንደመባነን ብላ
‹‹ያልተከፈለሽ የደሞዝ ውዝፍ ምን ያህል ነው?››
‹‹ለምን አስፈለገህ?››
‹‹ልከፍልሽ ነዋ››
‹‹ማን ደሞዜን ክፈለኝ ብሎ ጠየቀህ?››ተበሳጨች፡፡ከእሱ ገንዘብ ሳይሆን ፍቅር ነው የምትፍልገው….
‹‹ምን መሰለሽ መስቲ ..ክፈለኝ ብለሽ ባትጠይቂኝም እኔ አስቤ መጠየቅ አለብኝ..ምክንያቱም በቅርብ ይሄንን ቤት ሸጠዋለው … ይሄንን አገርም ለቃለው››
በድንጋጤ ደንዝዛ ‹‹ቤቱንስ ለምን ትሸጣለህ..?ወዴትስ ነው ሀገር የምትቀይረው?፡፡››
‹‹ቤቱን ምሸጠው መሸጥ ስላለብኝ ነው..ከቤቱ ይልቅ ብሩን ነው የምፈልገው፡፡ሀገሩንም ያው እዚህ መስራት ስለማልፈልግ ወደሌላ ቦታ እንዲያዘዋውሩኝ ጠይቄያለው፡፡ እንደሚሳካም እርግጠኛ ነኝ…ስለዚህ እያዘንኩም ቢሆን የሚገባሽን ከፍዬሽ ልለይሽ እገደዳለው፡፡››
ከዚህ በላይ ልታዳምጠው አልፈለገችም፡፡ ከተቀመጠችበት ተነስታ እየተመናቀረች ወደጓዲያ ሄደች…እንባዋ በጉንጮቾ እየተንኮለለ ነው፡፡
መሀሪም ጠርሙሱን እንደያዘ ወንበር ይዞ ተቀመጠና ተረጋግቶ መጠጣት ጀመረ፡፡መስታወት ታሳዝነዋለች ፡፡አስር አመት ከኖረችበት ቤት ፤ብዙ ተስፋ ከምታደርግበት ቤት በቀላሉ በቃሽ ስትባል ቀልል የሞራል ውድቀት አይሰማትም፡፡ ቢሆንም ምንም ሊያደርግ አይችልም ፡፡የራሱ ሞራል የተንኰታኰተበት ሰው ለሌላ ሰው ሞራል ሊጠነቀቅ አይችልም፡፡ስለዚህ ጉዳይ እያሰላሰለ ሳለ የሳሎኑ በራፍ ተንኰኰ፡፡
‹‹ማነው ?ይግቡ››አለ ከቦታው ሳይነቃነቅ፡፡
በራፉ ገፋ ተደረገና ያንኰኰው ሰው ገባ…ግራ ገባው መሀሪ‹‹ ምን አይነት ቀን ነው ዛሬ? የማይታሰብ ሰው ብቻ ነው እንዴ የሚመጣው?›› ሲል አሰበ
‹‹መግባት ይቻላል?››
‹‹ግቢ ግቢ››አላት ከፊት ለፊቱ የምትቀመጥበትን ወንበር እየጠቆማት
‹‹እሺ›› ብላ ከፊት ለፊቱ ያሳያት ቦታ ተቀመጠች
‹‹ትመጪያለሽ ብዬ አልገመትኩም..››
‹‹እናትህ በመሞቷ በጣም አዝኜለው ያው ልጅ ለቅሶ አይደርስም ስለሚባል ነው በጊዜው ያልመጣውት››
‹‹ምትገርሚ ልጅ ነሽ!!!››
‹‹ዕድሜዬ ነው እንጂ ልጅ ውስጤ ልጅ አይደለም››አለችው የሮዝ ልጅ የሆነችው ሄለን፡፡
‹‹በዛ እንኳን እኔም እስማማለው››መሀሪ መለሰላት
‹‹ግን ካሰብኩት በላይ ተጐሳቁለሀል…አሁን እንዲህ ሆነህ ፤ፊትህን አጥቁረህ ..ጺምህን አጐፍረህ የመጠጥ ጠርሙስ በእጆችህ ጨብጠህ ጠላቶቼ የምትላቸው ሰዎች ቢያዩህ በጣም ደስ ይላቸው ነበር እውነትም አሸንፈነዋል ብለው የድል ጽዋቸውን ያነሱ ነበር››ብላ እስከአሁን ያላሰበውን ሀሳብ አሳሰበችው
‹‹ግን ለቅሶ ልትደርሺኝ ነው የመጣሽው?››
‹‹አንድም ለዛ ነው..››
‹‹ሌላውስ?››
‹‹ምረዳህ ነገር ካለ ማለቴ ባለፈው እንደነገርኩህ እናቴን ለመበቀል የማግዝህ ነገር ካለ ብዬ ነው››
‹‹እናትሽን ግን ለምንድነው ምትጠያት?››
‹‹አንተ ስታያት የምትወደድ ሰው ነች ብለህ ታስባለህ?››
‹‹አይ ማለቴ አንድ እናት ለሌላ ሰው መጥፎና አረመኔ ልትሆን ትችላለች
1👍1
…ለወለደችው ልጆ ግን የምትጨክንበት አንጀት ያላት አይመስለኝም..ያንቺም እናት ምንም እንኳን እኔና መሰሎቼ ላይ ይቅር የማይባል በደል ብትበድለንም..አንቺን ልጆን ግን…››
‹‹ቆይ አንተ አሷ ያደረገችህን በአጭሩ አስረዳ ብትባል ምንድነው መልስህ?››
‹‹ቀላል ነው ማንነቴን አፍርሳዋለች እላለው፡፡››
‹‹የእኔን ደግሞ ማንነቴን ሰውራብኛለች››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ለአንድ ሰባዊ ፍጡር የመጀመሪያው የማንነት ጥያቄው ሸፋፋም ሆኑ ወልጋዳ፤ሽፍታም ሆኑ ሌባ የወላጀቹን ማንነት ማወቅ ነው ..ወደ እዚህች አለም ለመምጣቱ ምክንያቱ የሆኑትን እናትና አባቱን ማወቅ …እኔ የተነፈግኩት ይሄን ነው፡፡ከማን ጋር ተባብራ እንደወለደቺኝ ይሄው አስረአንድ አመት ሆነኝ ለአንድ ሺ ጊዜ ጠይቄያታለው ልትነግረኝ አልቻለችም..ይሄም በውስጤ ቁጣን ቀስቅሷል››
‹‹ለምን ልትነግርሽ አልፈገችም?››
‹‹እኔ እንጃ እሷ አላውቀውም ነው የምትለው እኔ ግን አላመንኮትም፡፡ ምክንያቱም አባቴ ማን እንደሆነ በደንብ እንደምታውቀው ውስጤ ይነግረኛል ..በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡እንደ አሁኑ እንኳን ቢሆን ወንዶቾ ቁጥር ስፍር ስለሌላቸው ከማ እንደወለደችበኝ ለይታ ላታውቅ ትችላለች..ያዛን ጊዜ ግን አይመስኝም››
‹‹ይገርማል!! ›› አለየሚለው ነገር ግራ ገብቶት
‹‹አሁን የት እንዳለች ታውቂያለሽ?››
‹‹ አዲስ አበባ ነው ያለች››
‹‹አዲስ አበባ?››
‹‹አዎ 22 የሚባል አካባቢ እንዳለች ማወቅ ችዬለው››
‹‹ጥሩ ነው ፡፡እዛ ነው መኖሪያ ቤቷ?››
‹‹አይ ውስኪ ቤት ከፍታች አሉ››
‹‹ውስኪ ቤት ..!!ይሻላታል››
እጆን ወደጃኬት ኪሶ በመስደድ ወረቀት እና እስኪርብቶ አውጥታ ጫር ጫር አደረገችና‹‹አሁን ልሂድ፡፡ ይሄ የቤታችን ስልክ ቁጥር ነው ፡፡በማንኛውም ሰዓት እርዳታዬን ከፈለግክ ደውልልኝ››ብላ ወረቀቱን አስጨበጠችውና ከመቀመጫዋ ተነሳች
‹‹እሺ አመሰግናለው…ደውልልሻለው››
‹‹እሺ ደህና ሁን›› ብላ መራመድ ከቀጠች ቡኃለ ድንገት ቆመችና‹‹ልጅ ነሽ ካላልክ አንድ ምክር ቢጤ ነገር ልንገር?››
‹‹ትቺያለሽ››
‹‹ከመጠጥ ውስጥ መደበቅህን አቁም፡፡ የበቀል ሰው ከሆንክ ከመጠጣት ይልቅ በወንጀል እና በበቀል ላይ የሚያጠነጥኑ መጽሀፎችን ..አልፎ አልፎም ፊልሞችንም ብትመለከት አሪፍ ነው..ይጠቅሙኸል››
‹‹አንቺ ታነቢያለሽ እንዴ?››
‹‹አዎ ከዘጠኝ ዓመቴ ጀመሮ ላለፉት ሶስት አመታት ያለማቆረት አንብቤያለው፡፡ ማንበብ ጥሩ ነው፡፡ በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ ነው የሚያደርግህ..ሰዎች ባይስማሙበትም እኔን ጠቅሞኛል››
‹‹ ሰዎች ባይስማሙበትም ስትይ እንዴት?››
‹‹ከመጽሀፍ ያገኘሻቸውን ዕውቀቶች ለተንኮል ብቻ ስለምትጠቀሚበት ማንበቡ ቢቀርብሽ ይሻላል ብለው ይመክሩኛል፡፡..ግን ማይገባቸውም ለተንኮልም ጥበብ እንደሚያስፈልግ ነው...ቀሺም ተንኮለኛ ከመሆን ስል እና አስደማሚ ተንኮለኛ መሆን በጠላት ዘንድም ሳይቀር ክብርን ያሰጣል፡፡ ስለዚህ ቀና በል..ቀሺም ተበቃይ እንዳትሆን፤ለበቀል መልፋትህ ካልቀረ በቀልህ በታሪክ ሲነገር የሚኖር የረቀቀ እና የተወሳሰበ መሆን አለበ ››ብላው እንደተደመመ ጥላው ወጥታ ሄደች፡፡
‹‹አይ እናትና ልጅ በየተራ ወደ ህይወቴ እየመጣችሁ ታስደምሙኛላችሁ አይደል?››ሲል ለራሱን አልጐመጐ፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
1👍1
#ቆንጆ_ነኝ
:::
ስላንቺ ቁንጅና
ስላንቺ ቁመና
ከንፈር እና ዳሌ
ጥርስና ተረከዝ ፣ ፀጉር ገለመሌ
ለጡት ለወገብሽ ፣ ለፀባይሽ ጭምር
በግጥም በዝርው ፣ ባድናቆት ስዘምር
እስከዛሬ ድረስ...
ውበትሽን አግንኜ ፣ ሰርክ መለፈፌ
እኔ ስለራሴ ...
አንዳች ቀን እንኳን ፣ ግጥም አለመፃፌ
ሲትጠዪኝ ቆጨኝ
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
እርግጥ ነው ብዙዎች...
ስለኔ ሳወራ ፣ ድንገት ያኮርፉኛል
ያንተን ሌሎች ያውሩ ፣ ብለው ይነግሩኛል
እኔን ከኔ በላይ...
እርግጠኛ ሆኖ ፣ ሌላ እንዴት ያውቀኛል?!
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
እናም እኔ ማለት...
ቁመቴ ከአክሱም ፣ በእጥፍ ይረዝማል
ጣፋጭ አንደበቴ...
መስማት ለተሳነው ፣ ለስልሶ ይሰማል
ውብ አረማመዴ...
እንኳን መንገደኛን ፣ መንገድን ያቆማል፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የከንፈሬ ወዙ ፣ ጥፍጥናው አያልቅም
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው!
ሺ ሟች ላለማየት ፣ ኗሪ ፊት አልስቅም፡፡
ከአይኔ ብሌን ውስጥ ፣ ብርሐን ይፈልቃል
አይኔን ያየ ሁሉ
ልቡን አሳውሮ ፣ በፍቅር ይወድቃል፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የገላዬ ጠረን ፣ ከሽቱ እጥፍ ነው
መልካም ጠረን ሁሉ...
አለ ባሉት ስፍራ ፣ እኔ አለሁ ማለት ነው፡፡
ፀባየ ትሁት ነኝ ፣ ምጡቅ ነው እውቀቴ
ግርማ ሞገሳም ነው ፣ ተክለ ሰውነቴ
ያየኝ ይወደኛል
የወደየኝ ሁሉ ፣ መቼም አይጠላኝም
ከዚ በላይ እንኳን...
ብዙም ስለራሴ ፣ የማውቀው የለኝም፡፡
እንደውም እንደውም...
አልጎርርም እንጂ ፣
ያፈር ሰውነቴን ፣ በቁንጅና አብየው
ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ፣ ራሴን ነው ማየው፡፡
ብቻ ግን ቆንጆ ነኝ!!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_አራት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...መሀሪ የዲላ ከተማ ኑዋሪነቱን ዛሬ ያበቃለታል፡፡ የመጨረሻው ቀን ነው፡፡ከፍተኛ ውጣ ውረድ ቢያሳልፍም በመጨረሻ ተሳክቶለታል፡፡ ከዲላ ወደ ዱከም ከተማ ተዘዋውሯል፡፡እርግጥ ይሄ የዝውውር ጉዳይ ከላይ እንደተገለፀው እንዲህ በቀላሉ የተሳካ አይደለም፡፡ መቶ ሺ ብር ከኪሱ አውጥቷበታል፡፡ለጉቦ፡፡ዝውውሩን ደግሞ አስቸጋሪ ያደረገው ከአንዱ የኢትዮጵያ ክልል ወደሌላው ክልል መሆኑ ነው፡፡ከደቡብ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል፡፡ ለአንድ መንግስት ስራተኛ በዚህ መልኩ ከክልል ወደ ክልል መዘዋወር ልክ ከኢትዬያ ወደ ጁብቲ የመዘዋወር ያህል የማይታሰብና አስቸጋሪ ሆኖ ነበር ያገኘው፡፡፡፡እስከዛሬ አንድ ሙሉ ድፍን ሀገር መስላ ትታየው የነበረችው ኢትዬጵያ በስነ-ልቦና ብቻ ሳይሆን በተግባርም እንዲህ የተከፋፈለች ብዙ ሀገር መሆኖን የተረዳው በዚህ ዝውውር ጉዳይ ነው፡፡ከአንዱ ክልል ባለስልጣኖች ወደ ሌላው ክልል ባለስልጣኖች ሲማላለስ ይሄም ጉዳይ በጣም አስደንግጦታል፡፡ለማንኛውም ከህግና ከመብት ይልቅ ገንዘብ ኃይል አለውና በገንዘቡ ኃይል የማይታሰብ ነው ያሉትን ጉዳይ እንዲያስቡበት….አይደረግም ያሉትን ነገርም እንዲያደርጉት አስገድዷቸዋል፡፡አሁን ዱከም ገብቷል ፡፡የዱከም ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆኖል፡፡ ዱከምን የመረጣት ለበቅል ተልዕኮው ስትራቴጂካላዊ ቦታ ነች ብሎ ስላመነ ነው፡፡አዲስአባ የከተመችውን ሮዝን ናዝሬት አዲስ ቤት ገዝቶ አዲስ ሚስት አግብቶ እየኖረ ያለውን ቀለምወርቅንና እዛው ዲላ መደበኛ ስራውን እየሰራ ያለውን የቀድሞ ጓደኛውን ኩማንደር ደረሰን ከዱከም እየተስፈነጠረ ለማጥቃት ይመቸኛል ብሎ መርጧታል አሁን ቤቱን ሸጦ አጠናቋል፡፡ለመስታወት የሚገባትን ደሞዝ ሰጥቷት ሸኝቷታል፡፡አሁን ያስፈልጉኛ ብሎ የመረጣቸውን የግል ዕቃዎች ሸክፎ ዝግጁ ሆኖ አጠናቋል፡፡አሁን የቀርው አንድ ነገር ቢኖር ይሄ ቀን መሽቶ ሲነጋ በለሊት ዕቃውን ጭኖ ከተማውን ለቆ ወደ ዱከም መፈትለክ ብቻ ነው፡፡ከዛ ቡኃላ ወደ ዲላ የሚመለሰው ሚስጥራዊ በሆነ መልክ እራሱን ቀይሮ ኩማንደር ደረሰን ለማጥፋት ብቻ ነው፡፡ ወደ ውጭ ሊውጣ ወይስ ትንሽ እቤት ልቆይ እያለ ከራሱ ጋር በመሟገት ላይ ሳለ ሞባይሉ ጮኸ፡፡አነሳው፡፡
‹‹ኄሎ››
‹‹ሄሎ..ማን ልበል?››
‹‹እኔ ነኝ ኩማንደር ..››
‹‹ይቅርታ አላወቅኩሽም ›››
‹‹ሄለን ነኝ››
‹‹እሺ ሄለን ሰላም ነሽ?››
‹‹አለውልህ..የት ነህ?››
‹‹እቤቴ ነኝ››
‹‹ነጻነት ሆቴል ካፌ ውስጥ ነኝ ያለውት፡፡ልትመጣ ትችላለህ?››
‹‹መቼ?››
‹‹አሁን እዛ መናፈሻ ውስጥ ቁጭ ብዬ እየጠበቅኩህ ነው››
‹‹እሺ መጣው›› ብሎ ስልኩን ዘጋውና‹‹ይቺ ጉድ የጉድ ልጅ ደግሞ ምን ልትለኝ ይሆን?››እያለ በማሰላሰል እቤቱን ቆልፎ ወደ ነገረችው ካፌ አመራ፡፡ሊያገኛት፡፡እዛ ሲደርስ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ስለሆነ ጨለም እያለ ነው፡፡
‹‹ሰላም ነሽ ሄለን?››.አላት እጁን ለሰላምታ እየዘራጋ እሷም የተቋጠረ ፊቷን ሳትፈታ የዘረጋውን እጁን እየጨበጠች፡፡‹‹ሰላም ነኝ ቁጭ በል››አለችው ፡፡ተቀመጠ፡፡
‹‹ምን ሆነሻል?››
‹‹ምን ሆንኩ?››
‹‹ጥቁር በጥቁር ለብሰሻል..የተፈጠረ ችግር አለ?››
‹‹ባክህ የአያቴ ወንድም ሞቶ ነው፤ ጥቁር የለበስኩት ግን ቀጥታ ለዛ አይደለም››
‹‹ታዲያ ለምንድነው?››
‹‹የአባቴን ማንነት የማወቅ ዕድሌን ይዞብኝ ስለሞተ ለእዛ ሀዘን ነው››
‹‹አልገባኝም››
‹‹እሱ የአባቴን ማንነት እንደሚያውቅ ነግሮኝ.. ማንነቱንም በማግስቱ ሊነግረኝ ቃል ገብቶልኝ በደስታ እየፈነጠዝኩ ሳለው ነበር ለሊቱን ሞቶ ያደረው››አለችው፡፡ለእሱ ልትነግረው አልፈለገችም እንጂ አጐቷ በበሽታው እንደሞተ ሳይሆን በሮዝ እጅ እንደተገደለ ነው የምታምነው..ለዚህም ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ባያደርጋትም አንድ ሁለት ጠቋሚ ማስረጃዎች አሏት፡፡ይሄንን ግን ለጊዜውም ቢሆን ለዚህ ኩማደር ልትነግረው እልፈገችወም፡፡
‹‹ሲያሳዝን ..ይቅርታ ለቅሶ ስላልመጣው፡፡ አልሰማውም ነበር››አላት
‹‹ግድ የለም ››
‹‹አይዞሽ እሱ ባይነግርሽም የአባትሽን ማንነት እናትሽ በቅርብ እንደምትነግርሽ እተማመናለው››
‹‹አይ… እኔ ደግሞ ካልተገደደች በስተቀር ትነግረኛለች ብዬ አላስብም››
‹‹ታዲያ እንዴት ማስገደድ ይቻላል? እኔ ምን ልተባበርሽ ?››
‹‹አሁን ወደ እዚህ ቀጥሬያት እየመጣች ነው፡፡አብራን እንድታየን እፈልጋለው፡፡››
‹‹እንዴ መጥታለች እንዴ?እዚህ ዲላ ነው ያለችው?››
‹‹አዎ መጥታለች..እራስህን ተቆጣጥረህ እሷ ስትመጣ ሰላም ትላትና ችላ ብለህ ከእኔ ጋር ታወራለህ፡፡ እንጫወታለን››
‹‹አይ ይሄ ምን ይጠቅምሻል?››
‹‹ይጠቅመኛል…አብረን እንደዛ ስታየን ምን እንደሚሰማት ፤ምንስ እንደምታስብ ታውቃለህ ፡፡አንተ እኔን የቀረብከኝ እሷን ለመበቀል እንደሆነ ታስባለች..እርግጠኛ ነኝ በጣም ነው ስሜቷን የሚነካው..ፍራቻ ውስጥ የምትዘፈቀው፡፡››
‹‹እኔ እንጃ …ብቻ ከእሷ ጋር በአንድ ጠረጵዛ ፊት ለፊት እየተያዩ መቀመጥ የምቋቋመው ነገር አይመስለኝም››
‹‹እራስህን የግድ መቆጣጠር አለብህ…በቀል ነው አይደል የምትፈልገው..በቃ ምንም ሳትለፋ እኮ ዕድሉን እያመቻቸውልህ ነው››
‹‹እሺ እንዳልሽ..ግን አንቺ በጣም እየገረምሺኝ ነው››
‹‹እንዴት? ››
‹‹አስተሳሰብሽ ሁሉ ከእድሜሽ በላይ ነው››
‹‹አዎ አንተ ብቻ ሳትሆን ብዙ ሰዎች በተደጋጋሚ እንደዛ ይሉኛል፡፡ ስራሽ እና ንግግርሽ ትልቅ ሰው በተደጋጋሚ አስጠንቷ የላከሽ እንጂ ከውስጥሽ የመነጨ አይመስልም ..ጠቅላላ ነገረ ስራሽ ተዓማኒነት የለውም ይሉኛል..፡፡ይታይህ እኔ ስጋና ነፍስ ያለኝ ህያው ፍጡር ነኝ አይደል? ታዲያ ልክ አንድ ልብ ወለድ መጽሀፍ ውስጥ እንዳለ ገጸ ባሕሪ ተአማኒነት የለሽም ብሎ ትርጉም የሌለው ነገር መናገር ምንድነው፡፡ ››
‹‹እውነታቸውን እኮ ነው የ18 ዓመት ልጅ ብትሆኚ እንኳን አስተሳሰብሽ ይገርማል››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው፡፡ግን እኔ አብዛኛውን ዕውቀቴን ከባለፈ ህይወቴ ይዤ የመጣውት ይመስለኛል፡፡››
‹‹ከባለፈው ህይወቴ ስትይ?››በመገረም ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ ከሁለት መቶ ወይም ሶስት መቶ አመት በፊት ሮም አካባቢ የምኖር ለፖለቲካው አለም እና ለስለላው ጥበብ በጣም ቅርብ የነበርኩ ሴት ነበርኩ፡፡አሁን ደግሞ ይሄው ዕጣ ፋንታዬ ሆኖ ዳግመኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ዝብርቅርቅ ባለ ሁኔታ ተወልጄ እንተ ፊት ለፊት ቁጭ ብዬለው››ብላ ከአዕምሮው በላይ ስለሆነ እና ቅዠት የበዛበት ነገር ነገረችው፡፡‹‹ይህቺ ልጅ እማ ትከሻዋ ላይ ተደላድሎ የተቀመጠ ከራማ አላት፡፡እሱ ነው እንደ እዚህ የሚያስቀባዥራት›› እያለ በማሰላለሰል ላይ ሳለ
‹‹እሺ ሄለን››የሚል የሚያውቀው.. ለዓመታት ሲያፈቅረው የኖረው አሁን ደግሞ እጅግ የሚጠላው ድምጽ ከኃላው ሰማ፡፡ አልዞረም የተቀመጠበት ቦታ ስሩ ባለው የጽድ ዛፍ ጥላ በጨለማ ስለተሸፈነ መልኩ በግልጽ አይታይም እንዳቀረቀረ ጸጥ አለ.፡፡
‹‹ከሰው ጋ ነሽ እንዴ?››እያለች ወንበር ስባ ከመሀከላቸው ተቀመመጠች፡፡
‹‹ጓደኛዬ ነው ተዋወቁ››አለቻት ሄለን
ሮዝም የሄለንን ግብዣ ተቀብላ እጆን ለሰላምታ እየዘረጋች ‹‹ሮዝ እባላለው የሄለን ……››ብላ ንግግሯን ሳታገባድድ አቆመች ፡፡የምታየው ፊት ፈጽሞ ያልጠበቀችው ነው፡፡
ኩማንደር የሮዝ ከገመተው በላይ መበርገግ እና መደንዘዝ አስደሰተውና ተነቃቃ እና መተወን ጀመረ‹‹ኩማንደር መሀሪ እባላለው ሄለን ስላንቺ ብዙ ጊዜ ታወራልኛለች .በእውነት ድንቅ ልጅ ነው ያለሽ››አለና አጥብቆ እጆን እየወዘወዘ ጨበጣት፡፡
‹‹እንዴት ግን ?››አለች ሮዝ
3👍2
ምትናገረው ጠፍቷት አንደበቷ እየተሳሰረባት፡፡
‹‹እንዴት ተዋወቃችሁ ለማለት ፈልገሽ ነው አይደል?፡፡ሄለን ምርጥ ጓደኛዬ ነች››አላት በፈገግታ
‹‹ጓደኛ..!!!አንተ እና እሷ?››
‹‹ምነው ወይዘሮ ሮዝ ችግር አለው እንዴ? ነው ወይስ የዕድሜ ልዩነታችንን አይተሽ ነው …ልጅሽ እኮ ዕድሜዋ ገና ቢሆንም አስተሳሰቦ ልዩ ነው..ስለዚህ እንደታናሽ እህቴም እንደ ሚስጥር ጓደኛዬም ነው የማያት››
ሄለን ከመሀሪ ንግግር ቀጥላ መናገር ጀመረች‹‹ዕድሜዬም ቢሆን እኮ ቀላል አይደለም፤ በሚቀጥለው ሳምንት 13 ዓመት ውስጥ እገባለው….እንደውም ዕድሜዬን በትክክል የምታውቂ መሆኑን እጠራጠራለው..ይታይህ ስታየኝ የ15 ዓመት ልጃገረድ አልመስልም? እየው እስቲ ጡቴን አጎጥጉጦ ከሎሚነት አልፎ ብርቱካን አክሏል… ደግሞ አይገርምህም የወር-አበባ ሁሉ እኮ አይቼያለው..ታዲያ ዕድሜዬን ካልተሳሳተች እንዴት 13 ዓመቴ ብቻ ይሆናል?››አለች ሄለን ፡፡ከተናገረቻቸው ውስጥ ሌሎች ነገሮች እውነት ቢሆንም የወር አበባ አይቼያለው ያለችው ግን ውሸቷን ነው፡፡ቢሆንም ንግግሯ ያሰበችውን ግብ መቶላታል..
ሮዝ ሰውነቷ ተርገበገበ ፡፡ከመቀመጫዋ ተስፈንጥራ ተነሳች፡፡ የሄለንን ክንድ ጨምድዳ ያዘቻት‹‹እንዴ !!ምን ነካሽ? አብደሻል እንዴ?››አለቻት ሄለን
‹‹ነይ እቤት እንነጋራለን.. ››ጎትታ ከመቀመጫዋ አስነሳቻት፡፡
በተረጋጋ ድምጽ‹‹እንዴ ወይዘሮ ሮዛ ችግር አለ እንዴ?››ብሎ ጠየቀ መሀሪ
‹‹ኩማንደር ፀጥ በልልኝ..ካንተ ጋር ንግግር የለኝም››አለችውና ሄለንን ባለ በሌለ ኃይሏ እየጎተተቻት የሰው ሁሉ አይን እንደተተከለባቸው ከካፌው ይዛት ወጥታ ወደቤት ይዛት ሄደች..፡፡ሄለን በሁኔታው የተከፋችና የተበሳጨች ታስመስል እንጂ በውስጧ ከፍተኛ ደስታ ነው የተሰማት፡፡አዎ አሁን ውስጧን ነቅንቃታለች፡፡እርብሽብሽ አድርጋታለች፡፡ለድርድርም ዝግጁ እንድትሆን አመቻችታታለች...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_አምስት
:
ድርሰት በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ኩማንደር መሀሪ የዱከም ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሆኖ ስራ ከጀመረ አንድ ወር ተቆጥሯል፡፡ቀናቷቹ ሲቆጠሩ አንድ ወር አካባቢ ብቻ ይሁኑ እንጂ በተግባር ሲመነዘር ወይም ኩማደሩ የከወናቸውን ነገር ሚዛን ላይ ሲቀመጥ በጣም ብዙ ነው፡፡ከተማዋን ከተገመተው በላይ ፈጥኖ ተቆጣጥሮታል፡፡በከተማዋ ኑዋሪዎችም ስለ እሱ ማውራት በሹክሹክታም ቢሆን ጀምሯል፡፡ጨካኝነቱን፤ጉበኝነቱን እና ከተቋጠረ የማይፈታ ፊቱ መነጋሪያ ሆኖል፡፡ይህን ስለእሱ የሚነገሩትን ነገሮች ቀድሞ የሚያውቁት የዲላ ከተማ ኑዋሪዎች ቢሰሙ ሽንጣቸውን ገትረው ይሄማ የእሱ ባህሪ አይደለም ብለው እንደሚከራከሩለት የማይጠረጠር ነው፡፡ግን እውነታው አሁን ያለበት ሁኔታ ነው....የተለየ ሰው መሆኑ ነው፡፡
ዛሬ የእለት ስራውን አከናውኖ ከቢሮ ወጣና ወደ ምስራቅ ሆቴል በማምራት እራቱን በልቶ ወደ ቤቱ ጉዞ ሲጀምር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሊሆን አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው፡፡ቤቱ በመዘጋጃው ወደ ውስጥ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ሁለተኛው መንገድ ላይ ነው፡፡የሚኖረው ሙሉ ግቢ ለብቻው ተከራይቶ ነው፡ዘበኛ የለውም …የቤት ሰራተኛ የለው፡፡ብቸውን ይባል ብቻውን ይወጣል፡፡ወደ ቤቱ ሲቃረብ አንድ ዘመናይ ሴት የአጥሩን በራፍ ተደግፋ ስትጠብቀው ተመለከተ.. ጨለማው በላይዋ ላይ ስላጠላባት ፊቷን ማየት እና ማንነቷን መለየት አልተቻለውም፡፡በዚህ ሰዓት በራፉን የሙጥኝ ብላ የምትጠብቀው ይሄኔ ባሏ ደብድቦ ያበረራት ሴት ትሆናለች..ታዲያ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በማቅናት ፋንታ ምን ወደ ቤቱ አስመጣት..?ምን አልባት እቤት በመምጣቷ በሀዘኔታ የተለየ የህግ ድጋፍ ያደርግልኛል ብላ አስባ ይሆን..?ይህን እና የመሳሰሉትን ሀሳቦች እያሰበ ተጠጋት …ሲጠጋት ለያት ..ሲለያት ደግሞ ደነገጠ..በጣም ደነገጠ ፡፡ከዛም አልፎ ግራ ተጋባ ፡፡ወደኃላ ይመለስ ወይስ ወደ ፊት ይቀጥል… .?፡፡ሽጉጡን ያውጣ ወይስ ትንሽ ትእግስት ያድርግ...?አንዱንም ነገር ሳይወስን ስሯ ደረሰ..ከኪሱ ቁልፉን በማውጣት ከፈተና ገባ..ከመዝጋቱ በፊት ጀርባውን ታካው ተከትላው ገባች፡፡የውጩን በራፍ ቆለፈውና ..ወደ ውስጥ በመዝለቅ የሳሎኑን በራፍን ከፍቶ..ወደ ውስጥ ገባ፡፡በራፉን ክፍት ትቶ አልፎ ወደመኝታ ቤቱ አለፈ፡፡እሷ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባችና ሳሎንና ባገኘችው ወንበር ተደላድላ ተቀመጠች፡፡ውስጧ ግን አሁንም ትርምስምስ እንዳለ ነው..በሽብር እና በፍራቻ መካከል የተደበላለቀ ውጥንቅጡ የወጣ ስሜት፡፡
መሀሪ ለብሶት የነበረውን የደንብ ልብሱን በቢጃማ ቀይሮ ትንሽ የጐደለለት የውስኪ ጠርሙስ ከሁለት ብርጭቆ ጋር ይዞ ብቅ አለ፡፡በሁለቱም ቀዳና አንዱን አቀብሏት የራሱን ይዞ ከፊት ለፊቷ ባለው ወንበር ተቀመጠ፡፡
‹‹መቼስ ውስኪ ቤት የከፈትሽው የውስኪ አድናቂ ስለሆንሽ ነው ብዬ ነው ውስኪ የጋበዝኩሽ››
‹‹አመሰግናለው…››አለችው እና ከሰጣት ብርጭቆ አንዴ ጠቀም አድርጋ ተጐነጨችለት፡፡
‹‹እራት እንዳልጋብዝሽ ቤቴ ውስጥ የምግብ ዘር የለም››
‹‹በልቼ ነው የመጣውት››
‹‹አይ አሪፍ ነው››
‹‹ትቀበለኛለህ ብዬ ገምቼ የነበረው በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አልነበረም››
‹‹እንዴት ነበር የጠበቅሽው.?››
‹‹እኔ እንጃ ብቻ እቤቴን ማን አሳየሽ ብለህ የምትጮኀብኝ…ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ ብለህ የምታንቧርቅብኝ….ከበራፍህ ገፍትረህ የምታባርረኝ..ብዙ ብዙ መጥፎ ምላሾችን ካንተ እንደምቀበል እያሰብኩ ነው የመጣውት፡፡››
ያሰብሻቸውን ነገሮች ሁሉ ያላደረግኩት ላደርጋቸው ሳልፈልግ ቀርቼ ..ወይም ባንቺ የደረሰብኝን በደል ዘንግቼው ሳይሆን ስላልተዘጋጀውበት ነው ፡፡አመጣጥሽ ፍጹም ድንገተኛ እና ያለሰብኩበት ስለነበረ ደንግጬ ነው፡፡ግን የገረመኝ አንቺ የምትይውን ያህል የተጨነቅሽ እና ወደ እኔ መምጣት የፈራሽ ከሆነ ምን አስመጣሽ..አትቀሪም ነበር፡፡››
‹‹ቀን እጅህ ላይ ቢጥለኝ. ..ቢጨንቀኝ ነው ››
‹‹አልገባኝም… ጉዳይሽ እኔ ጋር እንድትመጪ የግድ አስገድዶሽ ቢሆን እንኳን በቀን ሰው ባለበት ቦታ ጠብቀሽ ልታነጋግሪኝ ትችይ ነበር፡፡እንዴት በዚህ ጨለማ ለዛውም ማንም በሌለበት በቤቴ ለመምጣ ደፈርሽ…?እኔ እኮ ቀን ሲገጥምልኝ ሁኔታዎች ሲመቻቹልኝ በእርግጠኝነት ልገድልሽ ወስኜ ያለው ሰው ነኝ ››
‹‹አውቃለው… እኔም ለዛው ነው በጨለማ ማንም ሳያየኝ እቤትህ ድረስ ሹልክ ብዬ የመጣውልህ››
‹‹አልገባኝም? ምነው ..እራሴን ከማጠፋ እሱ ጋር ሄጄ ያጥፋኝ ብለሽ ነው?››
‹‹አረ እኔማ በጣም መኖር እፈልጋለው….
ግን ግን..!!!››ብላ ተንደርድራ ተነሳችና ጉልበቱ ላይ ተደፋችበት ንግግሯን ቀጠለች ‹‹ ይሄው እንደፈለግክ አድርገኝ መሞት ይገባታልም ካልክ ይሄው አሁኑኑ ግደለኝ..ስጋዬን ቦዳድሰህ ጣለው..ግን እባክህ ልጄን ተውልኝ..እሷን በመጉዳት እኔን ለመበቀል አትሞክር ያ ለአንድ እናት ምን ያል አስቸጋሪና ልትቋቋመው የማትችለው ነገር እንደሆነ እባክህ ይግባህ››
‹‹ተነስተሸ ወደ ቦታሽ ተመለሺና እንነጋገር››
‹‹እንድነሳ …እኔ ላይ ያነጣጠረው የበቀል ጦርህ እሷ ላይ እንደማይሰካ ትንሽ ተስፋ ስጠኝ ››
‹‹መጀመሪያ ተነሺ …ከዛ እንደራደራለን፡፡››
‹‹እሺ በፈለከው መንገድ በህይወቴም ቢሆን እደራደርሀለው፡፡››ብላ በዝግታ ተነሳችና ወደ ቦታዎ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡ብርጭቆዋን አነሳችና በአንዴ አጋባችው፡፡ጨምሮ ቀዳላት፡፡
‹‹እሷ ንግግሯን ቀጠለች‹‹ እባክህ ልጄን ከደበቅክበት አውጣና ስጠኝ ..እናቴ ልታብድ ነው በለቅሶ ብዛት አይኖቾ ሊጠፋ ነው..እባክ መልስልን…አባክህ …በፈጠረህ››

‹‹አይዞሽ ደህንነቷ በጣም በአስተማማኝ ሁኔታ እየተጠበቀ ነው ፡፡ደህና እንደሆነች ደግሞ ደግማ ደጋግማ ለእናትሽ እየደወለች እያናገረቻው መሰለኝ?››
‹‹ወይኔ ጌታዬ እንደፈራውት ባንተ እጅ ላይ ነች ማለት ነው ፡፡ምን አይነት ጨካኝ ነህ ?፡፡ልጄን በምን ዓይንህ አየህብኝ እኔ እያለውልህ..አንገቴን በቆንጨራ ቆራርጠህ እኮ ለውሻ መስጠት ትችል ነበር..ግንባሬን በሽጉጥ መፈርከስም ትችል ነበር..ያም ካላረካህ ሆዴን በሳንጃ ዘንጥለህ አንጀቴን ጐልጉለህ ማውጣት ትችል ነበር..ያስቀየምኩህ ፤የበደልኩህ፤እኔ..ልጄ ምኑም ውስጥ የለችበትም እኮ!!!››
‹‹ከምኑም እንደሌለችበት አውቃለው ፡፡ግን ባጋጣሚ ሲፈርድባት ካንቺ መሀጸን ወጣች…አየሽ አንድ የምትጠይውን ሰው ለመበቀል ቀጥታ ሰውዬው ላይ አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጥቃት ከማድረስ ይልቅ የዛ ሰውዬ ምርጥ የሆኑ ነገሮችን መንጠቅ ይበልጥ በቀልሽን ፍሬያማ እንደሚያደርግ ማወቅ አለብሽ››አላት ዘና ብሎ መጠጡን እየተጐነጨ፡፡
ሮዝ ፊት ለፊቱ በሽንፈት አንገቷን ደፍታ ሞራሏን አንኮታኩታ ሲያያት ውስጡ በእርካታ ተጥለቀለቀ፡፡ ይህ ሁሉ ግ በእሱ ጥረት እና ብቃት የመጣ ድል ሳይሆን በሄለን እስትራቴጂ ውጤት ነው፡፡ሄለን ከቤት እንደጠፋች ያውቃል ፡፡ምክንያቱም በየቀኑ እየደወለች የቀን ውሎዋን ትነግረዋለች ግን ያደረገችውን ሁሉ ያደረገችው በእሱ ተገዳ ወይም ታፍና ሳይሆን በራሶ ሙሉ ፍቃድና ዕቅድ ነው፡፡ቢሆንም የሮዝን ውንጀላ አልጠላውም ..እንደውም በተቃራኒው ተመችቶታል ምክንቱም እንደእዛ ማሰቧ ብቻ በእሷ ላይ የበላይነት እንዲኖረው ያግዘዋል፡፡
ሰዓቱን ተመለከተ ሶስት ሰዓት አልፎል፡፡‹‹አሁን መሸብስ ሂጂና ነገጥዋ ሁለት ሰት አካባቢ ተመልሰሽ ነይ እኔም እስከዛ ተረጋቼ ላስብበት ከልጅሽ እንድርቅ ልጅሽን እንድተውልሽ ከፈለግሽ እንደእዛ ባደርግ አገኝ የነበረውን እርካታ የሚያካክስ ነገር ካንቺ ማግኘት እፈልጋለው እንግዲህ ጥያቄው
👍5
ያ ነገር ምድነው የሚለው ነው..እና ላስብበት..የተገለፀልኝን ጥዋት እነግርሻለው››
እሺ ግን እባክህ አንዴ በስልክም ቢሆን አገናኘኝ››
አሁን አልችልም ጥዋታ ግን ከተስማማን ከእነአካሏ አስረክብሻለው››ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ፡፡እሷም ውጪልኝ ማለቱ እንደሆነ ገባትና ተነስታ በዝግታና በቀሰስተኛ እርምጃ እየተራመደች ወጥታ ሄደች ማንገር ብቻውን ምን ያደርጋል..እንደእዛ እንድታደርግ በአንተ ተገዳ እንደሆነስ ..ድምጾን ስለሰማን ብቻ እንዴት መረጋጋት ይችላል ብለህ ታስባለህ…ምላሶን እና ንግግሮን አትይ አንድ ፍሬ ልጅ እኮ ነች እባክህ እንዳትጎዳት ብላው በከፈተላት በር ወታ ሄደች።
:
ሮዝን ከቤቱ ሸኝቶ በሩን ከዘጋጋ ቡኃላ ወዲያው ሞባይሉን አነሳና ሄለን ጋ ደወለ፡፡ይሄንን ቁጥር እሱ ብቻ ነው የሚያውቀው…፡፡አያቷ እንኳን አታውቀውም፡፡ከአምስት ጥሪ ቡኃላ ተነሳ
‹‹ሄሎ ኩማንደር››
‹‹ሄሎ ሄለን ››
‹‹አለውልህ››
‹‹ለመሆኑ የት እንደሆንሽ ዛሬም አትነግሪኝም?››
‹‹አይ ያለውበት ቦታ ሚስጥር ነው.. ግን ከተማ ውስጥ ያለው እንዳይመስልህ፡፡አንድ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ነኝ ያለውት፡፡ የዚህች መንደር ኑዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ሀገራችን በረሀብ በጣም እየተጠቁ ካሉት ማህበረሰብ እንደማሳያ የሚሆኑ ኑዋሪዋች ያሉበት ነች፡፡›››
‹‹እንዴ ታዲያ ልዝናና ብለሽ ወጥተሸ ረሀብ ካጠቃው መንደር ምን ወሰደሽ?››
‹‹አጋጣሚ ነው የወሰደኝ..››
‹‹ምን አይነት አጋጣሚ?››
አንድ በጣም የምወዳት ጐደኛዬ ነበረች…ወላጆቾ ከብዙ ጊዜ በፊት ይፋቱና ልጆን ከአባቷ ጋር ጥላ ወደ ቤተሰቦቾ ጋር ከዲላ 400ኪ.ሜትር ወደምትርቀው አሁን ወደምገኝባት መንደር በመሄድ ሌላ ኑሮ መስርታ… ሌላ ባል አግብታ ሌሎች ልጆች ወልዳ መኖር ትቀጥላለች..የት ብትለኝ አሁን ማንነቷን ልነግርህ የማልፈልገው መንደር ውስጥ…ታዲያ ይቺ ጓደኛዬ ሰሞኑን ስለዚህ በረሀብ የተጠቃ መንደር ዜና እጆሮዋ ይገባል ..የእናቷ ጉዳይ በጣም አሳሰባት..አማከረችኝ እኔም አጋጣሚውን ተጠቅሜ አብሬት ሄድኩ..ከዲላ 400ኪ.ሜ አካባቢ ርቄ ማለት ነው፡፡ግን ምነው ባልመጣው የሚያሰኝ ነገር ነው የገጠመኝ››
‹‹ምን ገጠመሽ?››
‹‹ምን ገጠመሽ ትላለህ…?.እዚህ እኮ ከ ህዝቡ መካከል የሚበላው ምግብ ሳይሆን የሚያሸተው ምግብ የናፈቀው ቤተሰብ አለ..ሰዉ በጣም እየተጐዳ ነው….››
‹‹አንቺ ልጅ በዕድሜሽ ልክ አስቢ..ከአቅምሽ በላይ ስለሆኑ ነገሮች ስትጨናነቂ ጭንቅላትሽ እንዳይበታተን››አላት ሁኔታዋ እንደከዚህ ቀደሙ ግራ አጋብቶት፡፡
‹‹የሆነ ነገር ለማሰብ እኮ የዕድሜ ርዝመት ብቻውን በቂ አያደርግም..ብዙ የዕድሜ ባለጸጋዎች ከማሰብ ዕዳ ነፃ ናቸው…፡፡እንደውም ልንገርህ እንደ እኔ ትዝብት ሰው እሳት ወደሚንቀለቀልበት የጦር ሜዳ ከመዝመት ይልቅ..ወደ ውስጡ ዘልቆ የሆነ ጠንከር ያለ በሀሳብ ማሰላሰል ያስፈራዋል ፡፡በዚህ የተነሳ 99 ፐርሰንቱ የሰው ልጅ ማሰብ ሲሸሽ ነው የሚኖረው….እኔ ደግሞ ሲፈጥረኝ ማሰብን እንድፈራ ሳይሆን እንድደፍር ሆኜ ነው…ሰዋች በእኔ ግራ የሚጋቡት እነሱ ለማሰብ ዕድሜ ልካቸውን ሲፈሩት የኖሩትን ነገር እኔ በዚህ ዕድሜዬ በድፍረት ማሰብ ስለጀመርኩ ነው››
‹‹አይ አንቺ..ማሰብሽ ጥሩ ነው..ግን ምን ታደርጊዋለሽ እግዚያብሄር ጨከነብን››
‹‹ተው ተው ..ከእግዚያብሄር ላይ ወረድ በል....እንዴ!!! ይህቺ ሀገር እኮ ለ11 ተከታታይ ዓመት ከ11 ፐርሰንት በላይ አድጌያለው ከችግር አረንቋ እያመለጥኩ ነው ብላ ለህዝቦቾ፤ ለአለም መንግስታት እንዲሁም ለሰማዩ መንግስትም ሪፖርት አድርጋለች፡፡ታዲያ ያን ሪፖርት ተመልክተው ‹አይ እነዚህ ሰዎች በሀገራቸው ድርቅ ቢከሰትም ለረሀብ አይዳርጋቸው..ይሄን ያህል ዓመት ሙሉ በዚህን መጠን ሲያድጉና ሲመነደጉ ቆይተው አሁን የገጠማቸውን የምግብ ዕጥረት በራሳቸው ጥሪት ይወጡታል› ብለው አስበው ዝም ቢሉን ምኑ ይገርማል››
‹‹ይሁንልሽ.. ለመሆኑ አሁን አንቺ ምን እየሰራሽ ነው?››
‹‹አጐቴ ከመሞቱ በፊት የተወሰነ ብር ሰጥቶኝ ነበር ..እና እኔም በአቅሚቲእዚህ በጓደኛዬ እናት መንደር ኑዋሪ ለሆኑት ቀን ለጣላቸው ችግረኞች 100 ኩንታል ስንዴ ገዝቼ በነፍስ ወከፍ እንደቤተሰብ ብዛት ከ25- 50 ኪ.ግ ኩንታል ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እያደልኩ ነው..መንግስት ገዛውት የለውን ስንዴ በሙከራ ባቡር ከጅቡቲ አጓጉዞ እስኪደርስላቸው ድረስ ለአንድ ወር እንኳን ቢያቆያቸው ብዬ ነው..››
‹‹እየቀለድሽ ነው?››
‹‹እውነቴን ነው..እንደውም አያቴ አትፈቅደልኝም እምጂ አጐቴ ያወረሰኝን ጠቅላላ ንብረት አዲስ አበባ ያለውን ቤትም ሆነ መኪናዋንም ሸጬ ለዚሁ ተግባር ባውለው ደስ ይለኛል…አንተም ያቅምህን ያህል ብር ብትለግሰኝ ለእነዚህ ሰዎች አውለው ነበር፡፡አየህ ከችግር ሁሉ አስከፊው ችግር አንደኛ ጦርነት ወይም የሰላም እጦት ነው..ከዛ የባሰው ደግሞ የጤና መጐደል እና በሀይለኛ ህመም መሰቃየት ነው..ከሁሉም ምድራዊ መከራዎች የሚበልጠውና አስጠሊታው ግን ረሀብ ነው፡፡ረሀብ የመጨረሻው የሰው ልጅ የመከራ ቀንበር ነው፡፡››
‹‹በቃ ሌላ ወሬ ላውራልሽ››
‹‹እሺ ቀጥል››
‹‹ሴትዬዋ አሁን ቤቴ መጥታ ነበር››
‹‹የቷ››
‹‹ሮዝ ነቻ››
‹‹ምን ልትፈጥር››
‹‹አንቺን ያገትኩባት መስሎት እንዳልጐዳሽ ልትለምነኝ››
‹‹ታዲያ ምን አልካት?››
‹‹በምለው ነገር ከተስማማሽ አልጐዳትም አልኮት››
‹‹አንተ አሁን ትክክለኛ የበቀል ሰው እየሆንክ ነው..እኔስ እኔ አላየዋትም ትላለህ ብዬ ነበር የገመትኩት››
‹‹ተንኮል ከእናትሽ እና ካንቺ ነው የተማርኩት››
‹‹ይሁንልህ…. እና ታዲያ ምን አሰብክ?››
‹‹እኔ እንጃ ለመደራደራደር ለነገ ጥዋት ሁለት ሰዓት አካባቢ ቀጥሬያታለው››
‹‹በቃ አሁን ተኛና አስራ ሁለት ሰዓት እንደዋወል..የሆነ አሪፍ ነገር ሳስብ ልደር››
‹‹እሺ ካልሽ››
ስልኩን ዘጋና..ብርጭቆውን እንደያዘ ወደ መኝታ ቤቱ አመራ...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍3
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ስድስት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ጥዋት ነጋ አልነጋ ብላ ቀድማ የደወለችው ሄለን ነች
‹‹ከእንቅልፍህ ቀሰቀስኩህ እንዴ?››
‹‹አዎ ለሊቱን ሳስብ ስላጋመስኩት አሁን ጭልጥ ያለ እንቅለልፍ ወስዶኝ ነበር›››አላት ሙሉ ለሙሉ ከእንቅልፍ አለም ለመውጣ እየታገለ፡፡
‹‹የሀሳቤን ውጤት ልንገርህ››
‹‹እየሰማውሽ ነው››
‹‹ሴትዬዋን ሁለት ነገር እንድትከውንልህ ተደራደራት››
‹‹የትኛዋ ሴትዬ?››
‹‹ስለማን ነው በዚህን ሰዓት ለማውራት የተቀጣጠርነው የድሮ ፍቅረኛህን ነዋ ››
‹‹እሺ ምን እንድታደርግልኝ ልጠይቃት፡፡››
‹‹አንድ ለእኔ ..እንድ ላንተ ፡፡ለእኔ የአባቴን ማንነት እስከ ሙሉ ታሪኩ በድምጽ ቀድታ እንድታስረክብህ..ሁለተኛው ያው አንተን የከዳችህ ከጐደኛህ ጋር ተመሳጥራ አይደል አሁን ደግሞ ከንተ ጋር ተማሳጥራ እሱን እንድታጠፋው ..እንድታጠፋው ስልህ እንድትገድለው ማለቴ አይደለም..በቃ ያለውን ነገር ሁሉ እድትሳጣው..ባዶውን እንድታሰቀረው.. ስራውንም ጭምር እንዲያጣ ..ከዛም አልፎ እንዲታሰር ብታደርገው ጥሩ ነው፡፡እሾህን በሾህ ይሉሀል ይሄ ነው፡፡››
‹‹ከዛስ?››
‹‹ከዛማ ምን ትፈልጋለህ እኔን ታስረክባታለህ..አንድ ሰው ብቻ ነው የሚቀርህ የእንጀራ አባትህን
እንዴት መበቀል እንዳብህ ብቻ ይሆናል ብቸኛ ጭንቀትህ››
‹‹ ምን ነካሽ …?እሺ እንዳልሽው ኩማደሩን እሷ ተበቀለችልኝ ..እሷንስ ?››
‹‹እሷን በእነዚህ ሁለት ጉዳዬች ተስማምታ ተግባራዊ ካደረገች..ተበቀልካት ማለት ነው..ይበቃታል፡፡››
‹‹ይበቃታል?››
‹‹አዎ ይበቃታል፡፡››
‹‹ምነው ለእናትሽ ማዘን ጀመርሽ እንዴ?››
‹‹በፊትም እኮ አባቴን አልነግር ስላለቺኝና እንደህጻን ልጅ ልይሽ ስለምትለኝ ነው የምጣላት እንጂ ልክ እንደአንተ የመረረ ጠላቴ ሆና አይደለም ፡፡ለማኛውም ቻው የደረስክበትን ደውለህ አስታውቀኝ፡፡ ››
‹‹እሺ ለማንኛውም በስልክም ቢሆን አገናኘኝ እያለችኝ ስለሆነ ስደውልልሽ ..እንደታገተ ሰው እየተወንሽ ታወሪያታለሽ››
‹‹ይመችህ››ብላ በሀሳቡ በመስማማት ስልኩን ዘጋችበት፡፡
እሱማ ከመኝታው ወጥቶ ልብሱን ለበሰና ከሮዝ ጋር ለሚያደርገው ድርድር መዘጋጀት ጀመረ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ኩማንደር መሀሪ ዛሬ ጠንከር ያለ ስራ ይጠብቀዋል፡፡ከመከላል ወደ ማጥቃት የሚሸጋገርበት ቀን ነው፡፡በተለይ ቀለም ወርቅን በተመለከተ፡፡እርግጥ ሌሎቹንም አረሳቸውም…፡፡እርስ በርስ አቋላልፎቸዋል..፡፡
ሮዝ ኩማንደር ደረሰን እንድታጠፋው በድርድር ተስማምተዋል…ተስማምተውም ግን አላመናትም፡፡ በቅርቧ የሚገኝ ሰው እንዲከታተላት አስቀምጦባታል፡፡እርግጥ አሁን እንድትከታላት የመደባበትን ልጅ በቀላሉ አላገኛትም…ሌሎች ብዙ ሰዎችን ከሞከረ ቡኃላ ነው እሷን ያገኘው..አጋጣሚው ደግሞ ያገኛት እሷ ራሷ በሮዝ ላይ ቂም የቋጠረች መሆኖ ነገሩን ቀላል አድርጎለታል፡፡ልጅቷ ሮዘ ውስኪ ቤት በአስተናጋጅነት የምትሰራ ነች፡፡ልጅቷ ሮዝን የተቀየመቻት ምታፈቅረውን ልጅ ..ሚረዳትን ልጅ…ስለተኛችባና እና ስለነጠቀቻት ነው፡፡ልጅቷ በልጁ ላይ የጠለቀ ፍቅር ነበራት ተብሎ ባይደመደምም እሱ ላይ ያላት ተስፋ ወደፊት ያገባኝ ይሆናል ብላ ስታስብ መኖሯ ግን ነገሩን እንደ ትልቅ በደል እንድትወስደው አድርጐታል፡፡ልጅቷ በተገናኙበት ወቅት ለእሱ እንዳጫወተችው ከሆነ የነገሩን መከሰት እንዳወቀች‹ ምን አልባት የእኔ መሆኑን ሳታውቅ ይሆናል አልጋዋን ያጋራችው› ብላ ተስፋ በማድረግ አናግራት ነበር ሮዝን…፡፡.ነገሩ አስደንግጧት ይቅርታ ጠይቃት ልጁን እንደምትተውላት ተስፋ በማድረግ..››ከሮዝ ያገኘችው መልስ ግን ከጠበቀችው በተቃራኒው ነው፡፡
ከትከት ብላ የሹፈት ሳቅ ከሳቀችባት ቡኃላ ‹ወንድ ማለት እኮ ፈረስ ነው፡፡ ፈረስ ደግሞ ግልቢያ የሚችል እና የመጋለብ ፍቅር ያለው ሰው ሁሉ እንዲጋልበው የተፈጠረ እንስሳ ነው..፡፡ካማለሉሽ እና ከተመኘሻቸው እኔ ምጋልባቸውን ወንዶች ሁሉ እያሳደድሽ መጋለብ ትችያለሽ››ብላ ነበር የመለሰችላት፡፡ልጅቷም ታዲያ ከመጀመሪያ ድርጊቷ ይልቅ የመለሰችላት መልስ ውስጧን አቆሰላት፡፡በወቅቱ የሰከረች አስመስላ ግንባሯን በቢራ ጠርሙስ ፈርክሳት ለመሄድ አስባ ነበር ቡሃላ ዋል አደር ስትል ሀሳቧን አስተካከለች…ለኑሮዋ ጓጓች ..የምትደጉማቸውን ቤተሰቦቾን አስቀደመች እና ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ጥላ አንገቷን ደፍታ ስራዋን አርፋ መስራት ጀመረች..ዳሩ ግን አድብቶ የቀረባት ኩማንደር መሀሪ የተቀበረ ብሶቷን ቆስቁሶባት ተባባሪው አደረጋት..አሁን ይህቺ ልጅ ነች ሮዝ በስምምነታቸው መሰረት አየተንቀሳቀሰች መሆኑን እና ያለመሆኑን የየእለት እንቅስቃሴዋን እና ተግባሯን እየተከታተለች ሪፖርት የምታደርግላት፡፡
ቀለመወርቅንም በሰላዬች ካስከበበው ወራቶች አልፈዋል፡፡የቤት ሰራተኛው፤ ዘበኛው እና የሚስቱ ሹፌር የእሱ ጆሮዎች ናቸው፡፡እሱ ላይ ትኩረቱን ጫን ያደረገው ዋና ጠላቱ ስለሆነ ነው፡፡ እናቱን ያሳጣው፤ ንብረቱን የዘረፈው ዋና ጠላቱ..አንዱ የዘለለውን መረጃ አንዱ እንዲነግረው ነው ሰላዬቹን በእሱ ዙሪያ ማብዛቱ ..፡፡የእዛ ፍሬ ታዲያ ዛሬ ማጨድ ሊጀምር ነው፡፡ለዚህም አንድ ሳምንት ሙሉ ሲሯሯጥ ነው የከረመው..አሁን ከጥዋት ጀምሮ ሲጠብቀው የነበረው ስልክ …ተደወለለት
‹‹ሄሎ››
‹‹ሄሎ ክፍሎም››
‹‹ኩማደር አሁን ልንነሳ ነው››
‹‹ጥሩ ነው ዕቃውን እንዳልኩህ በቦታው አስቀመጥክ ? ››
‹‹አዎ አስቀምጬያለው››
‹‹በቃ ልክ ደብረዘይት ስትደርሱ ሚስኮል አድርግልኘኝ››
‹‹እሺ ኩማንደር››
‹‹መኪናዋ ባለፈው ያሳየኸኝ ነች አይደል?››
‹‹አዎ እሷው ነች፡፡ ››
እሺ በቃ ደህና ሁን ››ብሎ ስልኩን ዘጋና ዝግጅቱን ቀጠለ፡፡
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ከረፋዱ አራት ሰአት ተኩል ሲሆን ስልኩ ላይ ሚስኮል ስለመጣለት ሽጉጡን ታጠቀና ቢሮውን ለቆ ከግቢው ወጥቶ በታክሲ ወደ ከደብረዘይ መውጫ ተጓዘ..ራዳር ጭፈራ ቤት ጋ ሲደርስ ወረደና መኪናዋ መጠባበቅ ጀመረ..፡፡ብዙም አላስጠበቀችውም፡፡፡፡አይጥማ ቀለም ያላት ቢታራ ስራቸው ለመድረስ 20 ሜትር ሲቀራት እንድትቆም ምልክት ሰጣት ኩማደሩ ፡፡ሹፌሩም የተደናገጠ በመምሰል አስፓልቱን ለቆ ጥጉን አስያዘ እና አቆመ
‹‹አቤት ጌታዬ ምን አጠፋው?››በመስኮቱ አንገቱን ወደውጭ አስግጐ ጠየቀው
‹‹ጥቆማ ደርሶን ነው …ሁለታችሁም ከመኪናዋ አንዴ ብትወርዱ››
ሁለቱም ወረዱ..
‹‹መኪናዋን እስክፈትሽ ባላችሁበት ቁሙ››ብሎ ለፍተሸ ወደ ሚካናዋ ውስጥ አመራ...ሴትዬ ነች ብሎ የገማታት 30 ዓመት እንኳን የማይሞላት ብስል ቀይ በጣም ቆንጆ የምትባል ወጣት ሆና ስላገኛት ተገርሞል..‹‹ይሄ ሙትቻ ሽማግሌ እንዴት አድርጐ አሳምኖ ነው ሚስቱ ሊያደርጋት የቻለው?›› ሲል በውስጡ እያልጐመጐመ ፍተሻውን ቀጠለ
‹‹ይቅርታ ጌታዬ ያጠፋነው ነገር አለ?››አለችው በሚያምር ድምጽ ቃና …የሆነ ነገር ውስጡን እርብሽብሽ አደረገው፡፡
‹‹እሱን እንግዲህ ከፍተሸ ቡሃላ ነው የምናውቀው..ጥቆማ ደርሶኝ ነው››
የምን ጥቆማ? ››
‹‹ህገ ወጥ ዕቃ በመኪናዋ ውስጥ እንዳለ..››ብሎ መፈተሹን ቀጠለ..ከመቀመጫው ስራ አንድ ጥቁር ፔስታል መዞ አወጣ ፡፡ከፈተና አየው፡፡
‹‹አዝናለው የእኔ እመቤት.. ጥቆማው ትክክል ነው…ሶስት የእጅ ቦንብ እዚህ ፔስታል ውስጥ ይታየኛል፡፡››
‹‹የእጅ ቦንብ? አይደረግም፡፡ እኔ መኪና ውስጥ የእጅ ቦንብ?››ተንደርድራ መጥታ ቀረበችውና በዓይኖ አይታ አረጋገጠች፡፡ኩማንደሩ ቦንቡ በመንገድ የሚተላፉ ሰዎችን ቀልብ እንዲሰብ ስላልፈለገ ቦንቡን ከፔስታሉ ውስጥ ለማውጣት አልፈለገም፡፡
👍41
ይህማ የዚህ ቀሺም ሹፌር ስራ ነው››
‹‹አንተ ይሄን ከየት ነው የመጣኸው?››ብላ ዞር ስትል ሹፌሩ በአከባቢው ድራሹም የለ
‹‹እንዴ ኩማንደር አረ ሹፌሩ የለም››
‹‹ቀና ብሎ ዙሪያውን ቃኘ‹‹ወዴት ተሰለበ?››ጠየቃት
‹‹ምናባቱ አውቅለታለው…አየህ ስራው ስለሆነ ነው ተፈትልኮ የጠፋው ….የትም አይርቅም ፖሊሶቹን አሰማራ.. አሰሳ ቢያደርጉ አሁኑኑ ያገኙታል››
‹‹ተይው የትም አይርቅም… አሰሳ ማድረጉ ቡዙም አስፈላጊ አይደለም››
‹‹ለምን አይደለም?››
‹‹እኛ የምንፈልገው ዋናውን የመከናውን ባለቤት ነው…እሱ እኮ ቅጥረኛ ነው..ማንነቱን አጣርቶ የመቅጠር ሀላፊነቱ የባለቤቱ ነው፡፡ከፈለግነውም በአድራሻው መሰረት ፈልጐ የማቅረቡ ሀላፊነት የባለቤቱ ነው፡፡
‹‹ምነው ኩማንደር ..ባለቤቱ ባለቤቱ አልክ .. ?የመኪናዋ ባለቤት እኮ እኔ ነኝ››
‹‹ጥሩ ነው እንኳንም ሆንሽ..በይ አሁን ግቢና ወደፖሊስ ጣቢያ እንሂድ››
‹‹ፖሊስ ጣቢያ ኸረ በፈጠረህ ..እኔ እንደ ፖሊስ ጣቢያ በህይወቴ የሚያስጠላኝ ቦታ የለም ››
‹‹ያ በመሆኑ አዝናለው … አሁን ግን መሄዱ ብሎም መታሰሩ የግድ ነው፡፡ምክንያቱም በመኪናሽ ውስጥ ይዘሽ እየተንቀሳቀስሽ ያለሽው ነገር በጣም ከባድ ነው፡፡ምናልባት አዲስ አበባ የመንግስት ተቋሞችን..ምን አልባት የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ቢሮ..ምን አልባት ፓርላማውን..ምን አልባት አዲሱን ባቡራችንን ለማውደም ይሆናል እያጓጓዝሽ ያለሽው››
‹‹እንዴ!! አረ በፈጠረህ..አሁን እኔ እንደዛ የማድረግ ብቃት ያለኝ ሰው መስልሀለው?››
‹‹የሰው ማንነት በምርመራ እንጂ በመልክ መች ይታወቃል ብለሽ ነው..ለማኛውም ግቢና እንጓዝ››
‹‹መሾፈር አልችልም››አለችው በብስጭት እና በልመና መካከል ባለ ስሜት
‹‹እሺ እኔ እችላለው››ብሎ በሹፌሩ በኩል ዞሮ በራፉን ከፍቶ ገብቶ መልሶ ዘጋው
‹‹ግቢ›› አላት፡፡ እየተንቀጠቀጠች ገብታ ዘጋችው…ቁልፉን አሽከረከረ እና ሞተሩን አስነሳው ..ማሽከርከር ጀመረ
ስልኮን አወጣችና መደወል ስትጀምር‹‹ለጊዜው ስልክ መደወል አትችይም››አላት
‹‹እንዴ!!! ባለቤቴ ጋር እኮ ነው ያለውበትን ሁኔታ ደውዬ ማሳወቅ አለብኝ››
‹‹ አግብተሻል እንዴ?››
‹‹ማለት?››
‹‹ሽብርተኞች የሚያገቡ አይመስለኝም ነበር..ለማንኛውም እንዳትደውይ››
‹‹ እሺ በፈጠረህ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አትውሰደኝ››
‹‹እየወሰድኩሽ እኮ ነው..ከሁለት ደቂቃ ቡኃላ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ነን..ከአምስት ደቂቃ ቡኃላ ደግሞ ምርመራ ክፍል እራስሽን ታገኚዋለሽ››
‹‹በፈጠረህ እህት የለህም ለአንድ አስር ደቂቃ እንኳን ተረጋግቼ ላስብ ፖሊስ ጣቢያ አትውሰደኝ፡፡ የሆነ ቦታ መኪናዋን አቁምና ልረጋገ››እንደማሰብ አለና ወደ ወርቁ ቢቂላ ሆቴል መኪናዋን አጠፈና አስገባት እና ጥግ አስይዞ አቆመና ሞተሩን አጠፋና ተዘጋተው ተቀመጡ፡፡ሶስት ደቂቃ ያህል በፀጥታ እና በትካዜ ካሳለፈች ቡኃላ መናገር ጀመረች
‹‹ልትረዳኝ አትችልም?››
‹‹ይሄ እኮ በእርዳታ የሚታለፍ ቀላል ነገር አይደለም…ለምሳሌ ቀረጥ ያልተከፈለበት ልባሽ ጨርቅ ይዘሽ ተገኝተሸ ቢሆን በማስጠንቀቂያ ልምርሽ እችል ነበር….ይሄ ግን ከአቅሜ በላይ ነው››
ከአቅምህ በላይ እማ አይደለም ..አየህ በህይወቴ ብዙ ስቃይና መከራ ያሳለፍኩ ልጅ ነኝ፡፡ በአረብ ሀገር በየሰው ቤት ከ8 ዓመት በላይ ገረድ ሆኜ አገልግያለው.. ባለፈው የመን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ባዶ እጄን ወደ ሀገሬ ተመልሼ ግራ ግብት ብሎኝ እና ጭልም ብሎብኝ እያለ ከዚህ ሽማግሌ ጋር ተገናኘው….ላግባሽ አለኝ፡፡ ባላፈቅረውም ጥሩ ብር ስላለው እምቢ ልለው አልቻልኩም፡፡፡አገባውት፡፡ በፍቅር ባይሆንም በድሎት መኖር ከጀመርኩ ገና አመት እንኳን አልሞላኝም…ታዲያ ይታይህ መልሼ ወደ መከራ መልሼ ወደ እስር ቤት…ደግሞ እስር ቤት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ አውቀዋለው፡፡ በአረቦቹ እስር ቤት ከአንድ አመት በላይ ማቅቄያለው…የእናንተም እስር ቤት ከእሱ ቢብስ አንጂ የተሸለ ነው ብዬ አላስብም››
ስለነገረችው ታሪክ የተሰማውን ስሜት በቃላት ይገልጽልኛል ብላ ስትጠብቅ‹‹ቢራ ልጋዝሽ?››በማለት ያልተጠበቀ የግብዣ ጥያቄ አቀረበላት፡፡
‹‹ምን? ›››
‹‹ንግግርሽ ውሀ ያስጠማል..ቢራ ልጋዝሽ ነው ያልኩሽ››
‹‹ከሆነስ ውስኪ ቢሆንልኝ››
‹‹እሱን እንኳን ችላለው ብለሽ ነው? የመንግስት ደሞዝተኛ እኮ ነኝ..፡፡ለማንኛውም እንጠጣውና ተባብረን እንከፍለዋለን ብሎ››አስተናጋጁን ጠራና አንድ ጠርሙስ ጐርደን ጅን እንዲያመጣ አዘዘው፡፡
‹‹ስልክሽን አምጪ››
ፈራ ተባ እያለች ሰጠችው
‹‹ባለሽበት ሁኚ›› አንድ ቦታ ልደውል ብሎ ከመኪናው ወጣ፡፡ ስልኰን የተቀበላት እሱ ሲወጣ እንዳትደውል ወይም ሚሴጅ እንዳትልክ በመጠራጠር ነው፡፡
ወጥቶ ስልክ የደወለው ወደ ናዝሬት ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡የቀለም ወርቅ ቤት እንዲፈተሸ እዛ ለሚገኘው የስራ ባለደረቦቹ ጥቆማ ለመስጠት…በሁለተ ደቂቃ ውስጥ ስለ ቀለምወርቅ ቤት አድራሻ እና መሰል መረጃዎች በዝርዝር ነግሯቸው በአስቸኳይ ቤቱ እንዲፈታሽ እንዲያደርጉ በማሳሰብ ወደ መኪናዋ ተመልሶ በመግባት ከታጋቾ ጐን ቁጭ እንዳለ አስተናጋጁም መጠጡን ይዞ ደረሰ….

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍21
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ሰባት
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
...ኩማንደር መሀሪ እና የቀለምወርቅ ሚስት ዱከም ወርቁ ቢቂላ ሆቴል ግቢ በቆመችው መኪና ውስጥ እንደተቀመጡ ውስኪያቸውን መጋት ከጀመሩ አንድ ሰዓት ተቆጥሯል፡፡፡ሁለቱም ያለምንም ንግግር በየራሳቸው ሀሳብ ሰጥመው ብዙ ብርጭቆ መጠጣት የሚችለው ማን ነው ?የሚል ፍኩክር የገጠሙ ይመስል ሲጋቱት ነበር የቆዩት ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ መሀሪ መናገር ጀመረ፡፡
‹‹ስም አልተቀያየርንም አይደል…?ኩማደር መሀሪ እባላለው››አላት፡፡
‹‹እናት እባላለው….ከፊትም ከኃላም ምንም ቅጥያ የማዕረግ ስም የለኝምም ….ኖሮኝም አያውቅምም››
‹‹እንኳንም አልኖረሽ፡፡››
‹‹ኸረ በኖረኝ በተለይ እንደ አንተ አይነቱ ስልጣን፡፡››
‹‹ምን ያደርግልሻል?››
‹‹ትቀልዳህ እንዴ..?ቦታችን ይቀያየር ነበራ …እኔ አጋች አንተ ታጋች እንሆን ነበር፡፡››
‹‹እንዴ!! አሁን እኮ አጋች እና ታጋች አይደለንም….ወንጀለኛ እና ፖሊስ ነን››
‹‹እሱን እንኳን ተወው፡፡ እኔ ወንጀለኛ እንዳልሆንኩ ውስጥህ በደንብ ያውቀዋል…ብቻ ባስብ ባሰላስል ከእኔ ምን ፈልገህ እንደሆነ ማወቅ ተሳነኝ…እኔ አሁን ማደርግ የምችለው በባንክ ደብተሬ ላይ ያለውን ብር ላንተ መስጠት ነው፤ በዛ ትስማማለህ?››
‹‹ምን ያህል ብር?››
‹‹100ሺ ብር ልሰጥህ እችላለው››
‹‹ኦ 100 ሺ ብርማ አያዋጣኝም››
‹‹የንግድ ድርድርድ እኮ አደረግከው …፡፡አያዋጣኝም ስትል ትንሽ አፍህን አያደናቅፍህም እንዴ!! 5 ሳንቲም አላወጣህበትም …..››አለችው ትኩሳቱ በሚጋረፍ ኃይል በተጫነው ስሜት..አሁን ውስኪው በመላ ሰውነቷ ተሰራጭቶ ሙቀት በመላ ሰውነቷ ስለተበተነባት ድፍረት አግኝታለች….የመጠቃት ስሜትም በውስጧ እየተንቀለቀለ ነው፡፡
‹‹እንግዲህ አያዋጣኝም አልኩ አያዋጣኝም…ይልቅ መጠጡን ቶሎ ጠጣ ጠጣ አድርጊና እንሂድ››
‹‹ወዴት? ››
‹‹ወደ እውነቱ ቦታ ነዋ››
‹‹እውነት ቦታዋ የት ነው?››
‹‹ፖሊስ ጣቢያ ››
ከመኪናው ኩፈን በላይ አልፎ በአየሩ የሚበተን ተንተክታኪ ሳቋን ለቀቀችው‹‹ፖሊስ ጣቢያን ነው እውነቱ ቦታ ያልከው..በዚህ ዘመን እንኳን ከፖሊስ ጣቢያ ከእምነት ቦታዎች ራሱ እውነት እየጠፋች ይመስለኛል››ዘመኑ የስደት ዘመን የሆነው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? በየቦታው የኑሮ ችግር ስለላ ዶላር ፍለጋ ብቻ እንዳይመስልህ ሰው ከቦታ ቦታ… ከሀገር ሀገር የሚንከራተተው፡፡እንደ እኔ እንደ እኔ በዋናነት ሰውን እንዲሰደደድ የሚያደርገው የእውነት እጦት ነው ፡፡..ክፋቱ አፍሪካን ለቀህ ወደ አረቡ አለም ብትሰደድ ..ከአረብ አገር ወደ አውሮፓ ብትሻገር ከዛም ወደ አሜሪካ ብትዘምት..እንዲሁ እንደባከንክ ዕድሜህን ትፈጃለህ እንጂ በዚህ ዘመን እውነትን በተለይ ያልተበከለችውን ንፅሆን እና ድንግሏን እውነት የትም አታገኛትም…ምን አልባት ከክርስቶስ ዕርገት ጋር አለም በቃኝ ብላ አብራ ያረገች ይመስለኛል፡፡››
‹‹እሺ ሰማውሽ…ወደ ዋናው ቁም ነገር እንመለስና አሁን ሁለት መቶ ሺ ብር አለሽ?››
‹‹የለኝም፡፡ ግን ስልክ እንድደውል ከፈቀድክልኝ ሽማግሌው ጋር ልደውልና ብር ይዞልኝ እንዲመጣ ወይም በባንክ እንዲልክልኝ ማድረግ እችላላው፡፡››
‹‹እሺ ፈቅጄያለው ደውይ›› አላት፤ይህን ያላት ከእሷ ጋር በገንዘብ ለመደራደር ዕቅድ ኖሮት ሳይሆን ቀለም ወርቅ ጋር እንድትደውል እና እዛ የተከሰተውን ነገር እንድትሰማ ስለፈለገ ነው፡፡
‹‹አመሰግናለው..ስልኬን ሰጠኛ››
‹‹እኔ ጋር ነው ለካ…››ብሎ ከኪሱ አውጥቶ አቀበላት፡፡
‹‹እንዴ!!! እስከ አሁን እንዴት አይደወልልኝም? እያልኩ ስገረም ነበር ፡፡ለካ ጠርቅመኸው ነው…››አለችና እየተማረረች ስልኮን ከፍታ ቀለምወርቅ ጋር ደወለች፡፡ ይጠራል አይነሳም፡፡ደግማ ደወለች…አሁንም አይነሳም‹‹ይሄ ደግሞ ሙትቻ ሽማግሌ ምናባቱና ነው ስልኩን የማያነሳው…ስልኬ ተዘግተዋ ስለነበረ ማኩረፉ ይሆናል››አለችና የተሰማትን ግምት በመገመት በቤት ስልክ ደወለች፡፡
ከአራት ጥሪ ቡኃላ ሰራተኛዋ አነሳችና ‹‹ሄሎ››አለቻት
‹‹‹‹ሄሎ ቀለመወርቅ እቤት አለ እንዴ?››
‹‹ወይኔ!!! እትዬ ምነው ስልክሽ? ያንቺም የሹፌሩም ብንቀጠቅጥ ብንቀጠቅጥ እምቢ አለን እኮ››
‹‹የጠየቅኩሽን መልሺልኝ እቤት ውስጥ ቀለም ወርቅ አለ?››
‹‹ወይ እትዬ ጉድሽን አልሰማሽ››
‹‹የምን ጉድ .. ?››
‹‹ሰፈራችን ፓሪስ ከተማን መስላልሽ ነበር››
‹‹ምንድነው ምትቀባጥሪው?››
‹‹አንድ መኪና ሙሉ ፖሊስ ግቢያችንን ከበው እቤቱን ምንቅርቅር አድርገው ፈትሸው…››
እናት ትዕግስቶ አለቀ‹‹ምንድነው ሚፈትሹት?››አንቧረቀችባት፡፡
‹‹እኔ አንጃላቸው››
‹‹ምንም ሳያገኙ ወጡ አይደል? ››ጠየቀች… በጐ ነገር ተስፋ በማድረግ
‹‹አይ እትዬ …ሁለት ሻንጣ ሙሉ ቦንብ እና ደግሞ መሳሪያ››
‹‹የምን መሳሪያ? ››
‹‹የሚተኮስ ነዋ…የጦርነት መሳሪያ››
‹‹እና ምን ሆነ››
‹‹ከጋሽዬ ዕቃ ማስቀመጫ መጋዘን ውስጥ ተገኘ››
‹‹ማን ያስቀመጠው? ››
‹‹እኔ ምን አውቄ እትዬ.. ግን ጋሸ ቀለመወርቅን በካቴና እጆቻቸውን ወደኃላ ጠፍረዋቸው እየሰደቧቸው… እያዳፎቸው ..በመኪናቸው ጭነው ይዘዋቸው ሄዱ..ይሄን ልነግርሽ ብደውልልሽ..ብደውልልሽ ስልክሽ እምቢ አለኝ›››
ስልኩን ሰራተኛዋ ጆሮ ላይ ዘጋችባት እና ወደ ኩማደሩ ዞረች፡፡‹‹አንተ ቅድም የደወልከው ቤቴ እንዲበረበር ለማዘዝ ነው አይደል?››
‹‹አዎ ማድረግ ያለብኝ እንደእዛ ነበር…ስራዬን ነው የሰራት….››ቆፍጠን ብሎ መለሰላት፡፡
‹‹ግን ቦንቦቹና መስሪያዎቹ እኛ ቤት ውስጥ እንዳሉ በምን እርግጠኛ ሆንክ?››
‹‹አይ እርግጠኛ እንኳን ሆኜ አልነበረም… ስለተጠራተርኩ እንጂ››
‹‹እኮ እንዴት ልትጠራጠር ቻልክ?››
‹‹ቀላል ነው ..እዚህ የአንቺ መኪና ውስጥ ናሙናው ተገኘ ማለት አንቺ ወይም ባለቤትሽ ከነገሩ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ይኖራችሆል ብሎ መገመት ለዛውም ለአንድ ፖሊስ ቀላል ነው ..አንቺን ሳይሽ ደግሞ በእንደዚህ አይነት ነገሮች ላይ ትሳተፊያለሽ ብዬ ለማመን ደመ ነፍሤ አልተቀበለልኝም፡፡ ስለዚህ ማጣራት አለብኝ ..፡፡አንቺ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ ስትይኝ ያለምንም ማንገራገር ተስማምቼ እስከአሁን እዚህ ያቆየውሽ ለምን ይመስልሻል? እቤታችሁ ተፈትሾ እስኪጣራ ድረስ ነው፡፡››
‹‹ይገርማል !!! ያ ሽማግሌ ከጀርባዬ ምን እየሰራ ነበር?››ለምን እንደሆነ የማይታወቅ ጥያቄ ጠየቀች
‹‹እሱ ከሚወዱት ሰዎች ጀርባ በሚስጥር መንቀሳቀስ ልምዱ ነው››ሳያስበው መለሰላት፡፡
‹‹ማለት..? ታውቀዋለህ እንዴ ?››አለች ግራ እንደማጋባትም እንደመደንገጥም ብላ፡፡
‹‹አይ እኔማ የት አውቀዋለው..ግን አንቺም ብትሆኚ መቼስ የድሮ ታሪኩን በጥልቀት ምታውቂው አይመስለኝም …ከንቺ ጀርባ ይሄንን አይነት ሚስጥራዊ ነገር ሰርቶ ተገኘ ማለት በቀደመ ህይወቱም ደጋግሞ ተመሳሳይን በደል በሌሎች የራሱ በሆኑ ሰዎች ላይ ሲፈፅም እንደኖረ መገመቱ ብዙም አይከብድም››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…ሚያበሳጨው እሱም በአቅሙ ሰው ማጃጃሉ እና ሰውን ዳፋ ውስጥ መክተቱ ነው፡አሁን በል መጠጡም ይብቃኝ ..ልትወስደኝ ትችላለህ››
‹‹ወደ የት ነው የምወስድሽ?››
‹‹ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነዋ››
‹‹ምን ትሰሪያለሽ..?ጉዳይ አለሽ እንዴ?››አላት እየሳቀ
‹‹አልገባኝ››አለችው የእውነትም ግራ ተጋብታ

‹‹እኔ አልፈልግሽም አሁንም ስትንቀሳቀሺ ሌላ ፖሊስ እጅ እንዳትወድቂ ይሄ በፔስታል ያለ ቦንብ እኔው ጋር ይሁንና አስወግደዋለው..አንቺ ምንም የምታውቂው ነገር የለም ..ወደ ናዝሬት ስትመለሺ ፖሊሶቹ ጠርጥረው ጥያቄ ሊያቀርብልሽ ይችላሉ.ተረጋግቸሽ
👍32
ምንም እንደማታውቂ አስረጂያቸው..ስለዚህ ገጠመኝሽም ትንፍሽ እንዳትይ››
‹‹አረ አልልም..በጣም ነው የማመሰግነው ..ከጉድ ነው ያወጣኃኝ…100 ሺ ብሩን ባንክ እንሂድና ልስጥሀ››
‹‹እሱንም አልፈልግም..ከቻልሽ ግን አንዴ የጀመርኩትን መጠጥ እስክጨርስ ትንሽ ጠብቂኝ…ካለሽ ደግሞ የውስኪውን ሂሳብ ክፈይ››
‹‹በደንብ ነው እንጂ የምከፍለው…እንደውም ቦታ ቀይረን ከመኪና ወጥተን ምግብ በልተን ከንደገና እንደ አዲስ መጠጣት ብንጀምር ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹ይሻላል ….. ?አትቸኩይም ?››
‹‹ምን የሚያስቸኩለኝ ጉዳይ አለ?››
አይ ማለቴ ወደ ናዝሬት ተመልሰሽ የባልሽን ሁኔታ ለማጣራት እና ማድረግ ያለብሽ ነገር ካለ እንድታደርጊለት ብዬ ነዋ››አላት የምትለውን ለመስማት ብሎ፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ..በዚህ ዓለም በሽብርተኞች ስጋት እየተናጠች ባለችበት ዘመን..ቦንብና መሰሪያ በቤቱ አከማችቶ የተገኘበት ሰው ምን ላደርግለት የምችል ይመስልሀል…?ዋስ ሆኜ ላስፈለታው..?ወይስ ምን ላደርግለት…?ምንም ብቸኩል ምን ላደርግለት የምችለው ነገር የለም..፡፡ቆይ እንደውም እራስህን ልጠይቅህ ስንት አመት ሚፈረድበት ይመስልሀል?››
‹‹ካነሰ ሀያ አመት አልያም ዕድሜ ልክ››
‹‹ያ ማለት ከእስር ቤት በህይወት የመውጣቱ ጉዳይ የተዓምር ያህል የራቀ ነው››አለችው ሀዘንም ደስታም በተቀላቀለበት ስሜት፡፡
‹‹ስለዚህ ምሳ ወደምንበላበት ቦታ እንንቀሳቀስ እያልሺኝ ነው?››
‹‹አዋ እያልኩህ ነው….እንደውም ዛሬ ወደናዝሬት መመለስም ሆነ ወደ አዲስአባ መሄድ አልፈልግም…እዚሁ ዘና ማለት ብዬ ማደር ነው የምፈልገው›› አለችና ከቦርሳዋ ገንዘብ አውጥታ አስተናገጁን በመጥራት ከፈለችና ሂሳቡን ዘጋች፡፡
እሱም‹‹ ይመችሽ›› ብሎ የመኪናውን ቁልፍ አሽከረከረ እና መኪናውና አስነሳት።
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ኮማንደር መሀሪ ነገሮች እንዳሰበው አልሄዱለትም ቀለምወርቅን የመበቀል እቅዱ በገንዘብ ሀያልነት ከሽፎበታል የፈፀመው ወንጀል ሀያና ከዛ በላይ በእስር ያቆየዋል ብሎ ቢያስብም አስካሁን ድረስ ግልፅ ባሎነለት መንገድ ቀለም ወርቅ አንድ ቀን ሳይቆይ ከእስር ተፈቷል ይህም የቀለምወርቅ እጅ ካሰበው በላይ ረጅም እንደሆነ ኮማንጀር መሀሪ መገንዘብ ችሏል አሁን ውስኪውን እየተጋተ ቀጣይ አቅጣጫውን እያሰላሰለ ይገኛል..

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ስምንት
:
ደራሲ-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


...ሮዝ ከመሀሪ በተሰጣት አስገዳጅ ትዕዛዝ ጋር መሰረት እንቅስቃሴ ጀምራለች፡፡አሁን ወደ ዲላ እየተጓዘች ነው፡፡፡ጉዞዋ ከኩማንደር ደረሰ ጋር ባላት ቀጠሮ መሰረት ፡፡ትናንትና ነበር ለጥንቃቄ ብላ በህዝብ ስልክ የደወለችለት፡፡
‹‹ሄሎ የዲላው ኩማንደር››አለችው ስልኩን እንዳነሳ፡፡
‹‹ማን ልበል››
‹‹ሮዝ እባላለው….››
‹‹ሮዝ እሮዝ››
‹‹እሮዝ ሀሺሾ›› ልበልህ
‹‹ኦ የአዲስ አበባዋ ኢንቨስተር››መለሰላት
‹‹አይ ምኑን ኢንቨስተር ሆንኩት? አረቄ ቸረርቻሪ ላለማለት አፍረህ ነው አይደል?፡፡››
‹‹አይ ዋናው አረቄ መቸርቸሩ ወይም አመድ እየሰፈሩ መሸጡ አይደለም፣የሚያስገኘው ትርፍ ነው፡፡››
‹‹እሺ ይሁንልህ ..ግን በህይወት አለህ እንዴ?››
‹‹አለውልሽ ፡፡ምን እሆናለው ብለሽ ነው?››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…ጨካኝ ልብ ያለው ሰው ምን ይሆናል ››
‹‹ጨካኝ ልብ ስትይ››
‹‹እንዴ ቢያንስ ሶስት አራት ቀን ቢሆንም ጣፋጭ ፍቅር ሰርተናል ብዬ አምን ነበር..››
‹‹ማመን ብቻ ሳይሆን ትክክልም ነሽ ፤ የምን ጊዜውን ጣፋጭ ፍቅር የሰራውት ካንቺ ጋ በነዛ ባልሻቸው ሶስት እና አራት ቀናቶች ውስጥ ነው››
‹‹አይ ባክህ አትሸንግለኝ ፤ይሄን ያህል ትዝታው በአዕምሮህ ተቀርፆ ቢሆን ኖሮማ ቢያንስ እየደወልክ እንዴት ነው ትለኝ ነበር?››
‹‹አይ አንቺ ልጅ ….ያው ወንድ ሙጭጭ ሲልብኝ ይደብረኛል ስላልሺኝ ደበርከኝ እንዳትይኝ በመፍራቴ እኮ ነው እንጂ ሳላስብሽ ወይም ሳልናፍቅሽ ቀርቼ አይደለም.. ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው፡፡ ሙጭጭ የሚሉትማ እዚህም ስሬ ሞልተዋል…ላሀጫቸውን እያዝረከረኩ ዙሪያዬን እየተሸከረከሩኝ ነው…ምን አልባት ልቤ አንተ ላይ ተንጠልጥሎ የቀረው ጀነን ስለላልክብኝ ሊሆን ይችላል››አለችው፡፡የውስጥ ስሜቱን ለመቀስቀስ እና ትኩረቱን ለመሳብ የተናገረችው ንግግር ነው፡፡
‹‹ኸረ በእናትሽ በዚህ ለሊት ሰውነቴን አታሙቂው ..አሁኑኑ በርሬ እንዳልመጣ…፡፡››
‹‹እሱማ ጥሩ ነበር፡፡ ግን አሁን ለተቀጠቃጠለው ስሜቴ አትደርስልኝም..ግድ የለህም ለዛሬው እንዳ አንተ ባይሆኑም ቅርቤ ያሉትን ፈረሶቼ ውስጥ አንዱን ጋልበውና ተንፈስ እላለው ፣ባይሆን ለነገ ብንገናኝ››
‹‹ነገ?››
‹‹ምነው አትፈልግም?››
‹‹ኸረ ፈልጋለው ግን ተነገ ወዲያ ጥዋት የፍርድ ቤት ቀጠሮ አለብኝ ፡፡ነገ መጥቼ ለመመለስ አልደርስም››
‹‹በቃ እኔ እመጣለው ››
‹‹አዎ አንቺ….በቃ ተዘጋጅቼ እጠብቅሻለው…እኔ ናፍቄሽ አይደለማ ምትመጪው ለጉዳይ ስለፈለግሺኝ ነው››
‹‹ምነው ከፋህ እንዴ…? በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ብመታ ችግር አለው››
‹‹አረ የለውም ..ከቻልሽ ሶስትም መምታት ትቺያለሽ…..በደስታ አበባ ይዤ እጠብቅሻለው››
‹‹በቃ ነገ ስምንት ሰዓት ድረስ እደርሳለው ››
‹‹እሺ የእኔ ማር..መቼስ ወደ ቤርጐ እስክወስድሽን ምችል አይመስለኝም ፡፡እንደተገናኘን እዛው ህዝብ ባለበት አደባባይ ብናደርግ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹እኔም የቤርጐ አደለም ያማራኝ ..የመጀመሪያዋን ቀን ታስታውሳለታለህ? ››
‹‹የቷን?››
‹‹የቢሮህን ጫወታ ነዋ..እዛ ደረቅና ሰፊ ጠረጵዛህ ላይ እንድታሾረኝ ነው የምፈልገው››
‹‹በጉጉት አሁኑኑ ፀጥ እንዳልልብሽ››
‹‹ታገስ…. የነገዋን ደስታማ ሳታጣጥም መሞት የለብህም››
‹‹እሺ ጣፋጭ…ለመሆኑ የድሮ ባልሽን ወሬ ትሰሚያለሽ?››
‹‹ከየት ሰማለው ብለህ ነው?››
‹‹..ያው ቅርብሽ ነው ብዬ ነዋ›› መቼስ ከዲላ ተነስቶ ዱከም የገባው የአንቺኝ ትንፋሽ በቅርብ ሆኖ ለመማግ አስቦ ይመስለኛል››
‹‹አይ እኔስ የሚመስለኝ ከአንተ ለመራቅ አስቦ እንደሆነ ነው››
‹‹ከእኔ ጋማ ለምን ይርቃል?››
‹‹እጮኛውን ሳላማገጥክበት…ከእንደገና በስራም ስላጭበረበርከው››
‹‹እሱን እኮ አንቺና እግዚያብሄር ብቻ ናችሁ የምታውቁት እንጂ እሱ አያውቅም››
‹‹ካላወቀ ታዲያ ለምን ግንኙነታችሁን ያቀዘቀዘ እና ችላ ያለህ ይመስልሀል?››በመገረም ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አንቺ ልብን እንክትክት ስላደረግሺበት በዛም የተነሳ ሰው የሚባል ነገር ስላስጠላው ነዋ…››
‹‹አልሰሜን ግባ በለው››አለች እናቴ አለችው ብዙ ጊዜ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ መሆኑ አስገርሞት፡
‹‹ምን አልሺኝ?››አለት ምን ለማለት እንደፈለገች ስላልተገለፀለት፡፡
‹‹አይ ወዲህ ነው..ለማንኝውም ደህና እደር ከዚህ በላይ ኃይልህን አታባክን ..ለነገ እንዳትቸገር››
‹‹እውነትሸን ነው የእኔ አሳቢ… አሁኑኑ ተኝቼ ረጅም ረፍት መውሰድ አለብኝ..ደህና ሁኚልኝ››ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡
እንግዲ በቀጠሮቸው መሰረት አሁን ይሄው ዲላ ደርሳ ወደ ቢሮው እያመራች ነው፡፡ሰዓት ከቀኑ 8.20 ሆኖል፡፡ስትደርስ ቢሮ ውስጥ ባለጉዳይ እያስተናገደ ነበር….5 ደቂቃ ያህል ከጠበቀች ቡኃላ ባለጉዳዩ ሲለቅ እሷ ተተካችና ወደ ውስጥ ገባች..፡፡ከመቀመጫው ተነስቶ በፈገገ ፊት እና በሞቀ ሰላምታ ተቀበላት እና እንድትቀመጥ ጋብዞት በራፉን ሄዶ ቀረቀረውና መጥቶ ከጐኗ ተቀመጠ
‹‹አንቺ እንዴት አምሮብሻል.!!!ይሄንን ውስኪ እየተጋትሽ ፊትሽ ማብረቅረቅ ጀመረ››
‹‹አንተም አምሮብሀል››አለችው….እንዲሁ ለማለት ያህል እንጂ በዚህ ሰዓት ስለእሱ ውበት ሀጃም የላትም፡፡
እጁን በተከሻዋ አሻግሮ አቅፎ ወደራሱ ጐተታትና‹‹ ደክሞሻል ወይስ እንዴት ነው?ብታይ በጣም ነው የተራብኩሽ…››
‹‹አልደከመኝም ግን!!!››አቅማማችበት
‹‹ግን ምን? እንደዚህ ለሊቱንም ቀኑንም ሙሉ በጉጉት ስጠብቅ ቆይቼ ግን እንዳትይኝ››
‹‹አይ እንደዛ እንኳን አልልህም…ግን ለየት በለ መልኩ እንድናደርገው ነው የምፈልገው››
አይኖቹ የወሲብ ብርሀን ረጬ‹‹በፈለግሽው መንገድ ይመቸኛል››
‹‹እንድታስገድደኝ ነው የምፈልገው››
‹‹ማለት?››
‹‹በቃ ያሰኘኝ መደፈር ነው ..ልብሴን ቀዳደህ ….ጭኖቼን በረጋደህ..እየጠፈጠፍክ..ከቻልክ ጀርባዬን እና መቀመጫዬን ሰንበር እስኪያወጣ እየጠፈጠፍክ ››
‹‹እንዴ!!ልብስሽን ከቀደድኩት ምን ለብሰሽ ትወጪያለሽ?››በገረሜታ ጠየቃት
‹‹አታስብ የእኔ ማር ቦርሳዬ ውስጥ ቅያሬ ልብስ ይዤለው››
ያለምንም ንግግር የለበሰችውን ቲሸርት መዥርጦ አወለቀባት ..ይሄንን ሲያደርግ ፀጉሯ ብትንነትን ብሎ ተንጨፈረረ.. ከላይ የለበሰውን የራሱን ልብስ በጥድፊያ አወለቀና ከወገብ በላይ ዕርቃኑን ቀረ..፡፡ከዛ ጐትቶ ከተቀመጠችበት አስነሳት …የለበሰችውን ታይት ባለ በሌላ ሃይሉ በአንደኛው ጐን ያዘና ሸርከተው እና እታች ድረስ አለያየው..የአንደኛዋን እግር እንዳለ ሲሆን አንደኛዋ ተለያይቶ ያደረገችው ቀይ ፓንት ሙሉ በሙሉ ለእይታ ተጋለጠ…ከዛ አሽከረከራት እና ጠረጵዛው ላይ አስደጋፈት ፡፡ለመታገል ሞከረች..እንዳለችው በጥፊ ደረገመት ‹‹አዎ የእኔ ጀግና ጥረት ጥሩ ነው ….. ግን አይሳካልህም ››
‹‹ቀላል ይሳካልኛል..እንደ ባሪያ ቀጥቅጬሽ እንደፈለግኩ ነው የምጫወትብሽ››አላትና ፓንቶንም በአንድ ወገን ባለበት አለያየው፡፡
መቀመጫዋን በእናዛ ሰፌድ እጆች እየደጋገመ ጠፈጠፋት፤ እሷም በላ በሌለ ኃይሎ ታገለችው..እሷ በታገለችው መጠን እሱ ደግሞ እሷን በልዩ ሁኔታ ለማስደሰት ካለው ጉጉት የተነሳ ኃይሉን እየጨመረ በጭካኔ እየቀጠቀጠ እና በግድ እያስገደደ ይገናኛት ጀመር …ባልተለመደ መልኩ ልዩ በሆነ ንዝረት ..ልክ የመጨረሻ ጡዘት ላይ ደርሶ የዘር ፍሬው ወደ ሰውነቷ ሲበትነው ታወቃት፡፡በዛን ቅጽበት ገፈተረችውን ከላዬ ላይ አላቃው ‹ኡ..ኡኡኡኡ››ብላ መብረቃዊ ጩኸቷን አሰማች..ኩማንደሩ በአንዴ እያጣጣመ ከነበረው ከእርካታ ከውስጡ በኖ በምትኩ ድንጋጤ ወረረው‹‹
👍2
….እንዴ ምነካሽ?ያምሻል? እብድ ነሽ እንዴ?››በማለት እየለፈለፈ አፎን ሊያፍናት እጆቹን ወደ አፎ ላከ…ግን አልቻለም፤ አሁን ደግሞ የእሷ ኃይል አይሏል፡፡ ገፍትራው ወደ በራፉ አመራች … ሊያስቆማት ተንደረደረ፤ ሊይዛት ሲከተላት ግማሽ ድረስ ብቻ ወልቆ የነበረው ሱሪው አደናቀፈውና ወደቀ ..ከወደቀበት እሲኪነሳ እሷ የተቀረቀረውን የቢሮ በራፍ ከፍታ በመውጣት የጀመረችውን ጪኸት ቀጠለችበት፡፡ ግቢው ውስጥ የነበሩት ሰዎች በየቢሮው የነበሩት ፖሊሶች ተግተልትለው ወደ እነሱ ተሰበሰቡ..
እሷ ለሚያያት እብድ ትመስላለች..ፀጉሯ ተንጨፍርሮ ወዲህና ወዲያ ተበታትኗል፡፡የለበሰችው ታይት ሱሪ አንደኛው እግር ከላይ እስከታች ሙሉ ለሙሉ ተቀዶ ተለያቷል፡፡ከወገብ በላይ ሙሉ በሙሉ ከወገብ በታች በግምሽ ዕርቃኖን ነች ፡፡አንዱ መቀመጫዋ በግልፅ ለእይታ ተጋልጧል፡፡ በዛ ላይ የጠፈጠፋት አካሏ ደም ቆጥሯል…አንዱ ጡቷ ከጡት ማስያዣዋ አፍንግጦ በመውጣት እሷ በተወራጨች ቁጥር አብሮት ይደንሳል..
‹‹ምን ሆነሽ ነው ? ምን ነክቶሽ ነው?›.አንዱ ፖሊስ ጠየቃት፡፡
‹‹ደፈረኝ…. አስገድዶ ደፈረኝ..አፌን አፍኖ ልብሴን እንደምታዩት ቀዳዶ ተገናኘኝ..ደፈረኝ›› ለፈለፈች ጮኸች፡፡የምትለውን ሲያዳምጡ የነበሩት ግዙፍ የፖሊስ አዛዣ አጀቡን ጥሰው እሷን አልፈዋት ወደ ውስጥ ሲገቡ ኩማንደር ልብሱን ከየጣለበት እያነሳ ለመልበስ ሲፍጨረጨር ደረሱበት..ወዲያው በራፍ ላይ ላሉት ሁለት ፖሊሶች ትዕዛዝ አስተላለፍ‹‹..በአስቸካይ በቁጥጥር ስር አውሉልኝ››እሷ ደግሞ በአስቸካይ ወደ ሆስፒታል ውሰዶት››ብለው በንዴት በሚርገበገብ አንደበት በሚንቀጠቀጥ ድምጻቸው ቆፍጣና ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ ሮዝ በለቅሶ እና በጨኸት ውስጥ እያለች የአዛዠን ትዕዛዝ ስትሰማ በእፎይታ ተነፈሰች ..ልጇን ከመሀሪ ወጥመድ ለማስጠል ከተሰጦት ሁለት ተልኮዎች መካከል አንዱን በድል ተወጣች..ሁለተኛው ደግሞ የዚህን ያህል አይከብዳትም…..-+
እሷ ብቻ ሳትሆን ኩማደር ማሀሪም ተሳካለት ማለት ነው…አንደኛውን ጠላቱን በሌላመኛዋ ተጠቅሞ አስወገደ..አሁን ሁለት ይቀረዋል….የእንጀራ አባቱና አሷ እራሷ…..ሁለቱንም ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚያወድማቸው እርግጠኛ ነው….ከዛስ…?ከዛ እንዴት እንደሚሆን እራሱም አያውቅም…የሚኖርበት ብቸኛ ምክንያት በቀል ነበር..በቀሉ ሲጠናቀቅ ባዶውን ይቀራል…ባዶ ሆኖ መኖር ደግሞ ከባድ ነው…በጣም ከባድ…

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
:
ድርሰት በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
...ኩማንደር መሀሪ ቀለም ወርቅን የመበቀል እቅዱ ከከሸፈበት በኋላ ሌላ እቅድ ወጥኖ ከነበረበት ቦታ ለውጥ አድርጎ ነው ከወራት መሰወር ቡኃላ ነው ሻሸመኔ ላይ ብቅ ያለው፡፡፡ዲላ ከተማ በሚኖርበት ወቅት በዙሪያው ባሉ የቅርብ ሰዎች የጠለቀች ፀሀዩ እዚህ ሻሸመኔ ላይ ድንገት ወጥታለች..በርታለች፡፡
በፊት በሚሰራው ተመሳሳይ ስራ የፖሊስ መኮንን ሆኖ ለዛውም የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ሆኖ ሻሸመኔ ላይ ብቅ ካለ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡ መሀሪ በዚህ ወቅት በከተማዋ ኑዋሪዎች ቅፅበታዊ በሚባል ሁኔታ ስሙ ገኗል፡፡ዕውቅናውን ላየ ሰው ወራቶች ብቻ የኖረ ሳይሆን ስድስት ዓመት ያሳለፈ ነው የሚመስለው፡
በከተማዋ ያተጐናጸፈው ዕውቅና ሶስት ገፅታዎች አሉት ፡፡አንደኛ ዘወትር የተቋጠረ እና የጨለመ ፊቱ…. ሁለተኛው ወሰን አልባ ጉበኝነቱ… እናም ሶስተኛው ለሰው ልጅ ያለው ንቀት እና ጭካኔ ናቸው፡፡ ከሶስቱ መካከል ግን ጉበኝነቱ ቀደምትነቱን ይይዛል፡፡እርግጥ በኢትዬጰያ ለተንሰራፋው ስር የሰደደ ሙስኝነት የሻሸመኔ ከተማ በተለይ ከኮንትሮባንድ ጋር ተያይዞ ዋናዋ መገለጫ እና እንደ ናሙና የምትጠቀስ እንደመሆኗ መጠን እሱ ብቻ ሳይሆን መላ ባለስልጣኖች በሚያስብል ደረጃ ተክነውበታል፡፡ለዚህ መነሻ ምክንያቱም ምን አልባት ከተማዋ በንግድ እንቅስቃሴዋ በጣም የሞቀች እና የደመቀች በመሆኗ እና ከአምስት የሚበልጡ ዋና ዋና በሮች ያሏትና እሱን ተከትሎ ብዙ ሺ ሰዎች በየዕለቱ ለጉዳይ ገብተው የሚወጡባት የንግድ መዲናና ረብጣ ብር ከአንዱ ግለሰብ ወደሌላው ግለሰብ የሚሽከረከርባት ከተማ ስለሆነች ሊሆን ይችላል ብለን የራሳችንን መላ ምት ብንወስድ ብዙም አንሳሳትም፤ኩማደር መሀሪ ከወራቶች መሰወር ቡኃላ ሻሸመኔ ላይ ብቅ ያለው ግን ይሄንን አገናዝቦ ወይም የሚሰበስበው ጉቦ ዓላማው አድርጐ አልነበረም ፡፡ዋና ምክንያቱ ቀለም ወርቅ ነው፡፡ለእናቱ ህይወት እልፈት ምክንያት የሆነው የቀድሞ የእንጀራ አባቱ ቀለም ወርቅ ከገባበት እስር ቤት በገንዘብ ሀይል ወቶ አዲስ ቤት መስርቶ፤ አዲስ ሚስት አግብቶ እዚህ ሻሸመኔ ስለሚኖር ነው፡፡በቀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ለማራመድ እንዲቀለው ስለወሰነ ነው፡፡
የሚገርመው ልክ እሱ ሻሸመኔ ከተማ በከተመበት ተመሳሳይ ወቅት ሌላ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንግዳ ሰው በከተማዋ ተከስቷል፡፡አባ ሽፍንፍን ይባላሉ፡፡መቼስ ይህቺ ዓለም ሁል ጊዜ በተቃራኒ ኩነቶች የተወጠርች ነች..ያም ነው ሚዛኗን ጠብቃ እንድትቀጥል ያስቻላት፡፡ችግር እና ድሎት…ጨለማና ብርሀን…ክፋትና ደግነት…በቀል እና ይቅር ባይነት ወዘተ ወዲህና ወዲያ ወጥረው ያቆሟታል ፡፡እናም እኚ አባ ሽፍንፍን የኩማደር መሀሪ የበቀል መጋኛ አጠናግሮ የሚያተራምሳትን ከተማ እሷቸው ደግሞ በደግነት እና በቸርነት ቀዝቀዝ ያደርጓታል፡፡እሱ ያቀጣጠለውን የክፋት እሳት እሷቸው በበጐነት ፀበል ያዳፍኑታል፡፡
እኚ አባ ሽፍንፍን የተባሉት ቄስ ትክክለኛ ስማቸው ሌላ ነው ፡፡አባ ሽፍንፍን የተባሉት ከአለባበሳቸው በመነሳት ነው፡፡እግር ጠፍራቸው ሚደርስ ጥቁር ቀሚስ ለብሰው ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ ዓይኖቻቸውን ብቻ አስቀርተው በሻርባቸው ይጠቀለሉና በላዩ ላይ ጥቁር የመነኩሴ ቆብ ይደፉበታል፡፡በዛም አያበቁም የተቀረችውን ለእይታ የተጋለጠች ዓይኖቻቸው አካባቢ የቀረችውን የሰውነታውን ክፍል በግዙፍ ጥቁር መነጽር ይጋርዱታል፡፡በቃ ከእሷቸው አካላት በግልጽ የሚታዩት መስቀል የሚጨብጡት የእጆቻቸው ጣቶች ብቻ ናቸው፡፡ከየት እንደመጡ ….?እንዲህ ዓይነት አለባበስ ለምን እንደሚለብሱ…. ?በፊት የት ይኖሩ እንደነበረ… ?ከመላ ምት በስተቀር ማንም በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡ግን የሚገርመው ሻሸመኔ መኖር በጀመሩ በወራቶችጊዜ ውስጥ የኩማደር መሀሪን ያህል ዝናን ታዋቂነትን ተጐናጽፈዋል፡፡ የእውቅናቸው መስመር ግን ለየቅል ነው..
እሷቸው የተቸገረውን ረድተው...የታረዘውን አልብሰው..የተራበውን አጉርሰው ያገኙት ዝና ነው፡፡እኚ ቄስ የገቢ ምንጫቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም፤ ግን በርከት ያለ ብር የባንክ ደብተራቸው ውስጥ አለ፡፡አንዳንድ እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ሲያንሾካሹኩ እንደተሰማው እኚ አባ ሽፍንፍን የተባሉ ቄስ አሜሪካ ሀገር ብዙ አመት ኖረው ጠርቀም ያለ ጥሪት አጠራቅመው ቀሪ ህይወታቸውን ቅድስት ሀገር የሚል መንፈሳዊ ስም ወደተጐናፀፈች ሀገራቸው ተመልሰው የቅድስና ስራ እየሰሩ ለማሳለፍ ወስነው እንደመጡ የሚናገሩ ግለሰቦች አሉ..የተረጋገጠ ባይሆንም
ሌላው ገራሚው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ኩማንደር መሀሪ እና እኚህ አባ ሽፍንፍን የተባሉ ቄስ አንድ ግዙፍ በለአንድ ፎቅ ቪላ በጋራ ተጋርተው ይኖራሉ ፡፡ እሳቸው በምድር ቤቱ ውስጥ ባሉ ክፍሎች ሲኖሩ እሱ ደግማ በላይኛው ወለል ባሉ ክፍሎች ይኖራል፡፡ግን ይህ ቤት በሁለት ግቢ ተከፍሎል እሱ ሚጠቀመው የፊት ለፊቱን ግቢ ሲሆን እሳቸው ደግሞ የጀርባውን ግቢና ነው፡፡ኩማደር መሀሪ ሻሸመኔ የከተመው ለበቀል ነው፡፡እኚ ሚስጥራዊ ቄስ ሻሸመኔ ለምን ጉዳይ እንደተገኙ አይታወቅም..?
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሁለቱም እናትና ልጅ ያለቅሳሉ…ከፊት ለፊታቸው የተቀመጠው ፖሊስ ይጠይቃቸዋል፡፡በደከመ አንደበት በተሰበረ ቃል ይመልሳሉ፡፡ሰዎቹ ሄለን እና አያቷ ናቸው፡፡ቦታው በከተማው ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ነው ፡፡ተከሰው አይደለም የቀረቡት..ለመክሰስ ነው፡፡ ማያውቁትን ጠላታቸውን ለመክሰስ..
‹‹እስቲ ትዕይንቱን ከመጀመሪያው አንስተው አስረዱኝ?›› ፖሊሱ በፖሊሳዊ ግርማ ሞገሱ እንደተኮፈሰ የመጀመሪያ ጥያቄውን ሰነዘረ አሮጊቶ የተሸበሸበ ፊታቸውን ላይ ኮለል እያለ የሚወርደውን እንባቸውን በተጨማደደ እና በቆረፈደ እጃቸው ጠረግ ጠረግ በማድረግ መናገር ጀመሩ ‹‹ከትናንት ወዲያ ነው በቀኑ ኤሌክትሪክ ተቋረጠብን ..ከሰፈሩ የእኛ ቤት ብቻ ነው ተነጥሎ የተቋረጠብን፡፡ መብራት ኃይል አመለከትን …ቆይ ይቀጠልላችኃል አሉን እና ግን ሳይመጡ ዋሉ፡፡ ሲመሽ ያው ትልቁን ቤት ገርበብ አድርገን ኩሽና ሄደን በእንጨት ቡና አፍልተን ከልጄ ጋ ከጠጣን ቡሃላ ወደ ቤታችን በመግባን እራችንን ቀድመን በልተን ስለነበረ በጨለማው ዳበሳ ወደ መኝታችን ነበር ያመራነው፡፡ ሀገር አማን ነው ብለን የተለመደ እንቅልፋችንን ከተኛን ቡኃላ ባልታሰበ ሁኔታ ለሊት ላይ እላያችን ላይ ባትሪ በራብን ፡፡ ባነን ስናስተውላቸው ሁለት ጐረምሶች ናቸው፡፡
አንዱ ልጄ ላይ አንደኛው እኔ ላይ ሽጉጥ ደቅነው ነበር፡፡ ከፍራቻችን አንጻር መተንፈስ እንኳን አልቻልንም ..ወዲያው አንደኛው በጐረነነ ድምጽ ልብሳችንን በአስቸኳይ እንድንለብስ አዘዘን..በዛ በጨለማ በመርበትበት ሁለታችንም ያለውን ፈጸምን፡፡እኔ አቅሜን አውቄ አልተፍጨረጨርኩም ብቻ ለልጄ እፀልይ ነበር..::ጌታዬ በእስተእርጅና እንዳያሳቅቀኝ ..በዛ ጭንቅ ውስጥ እንኳን መማፀኔን አላቆምኩም፡፡ከዛ ቡኃላ ልጄንም እኔንም በገመድ እጆቻችንን ወደ ኃላ ጠፈሩን::ዓይኖቻንን በፍርሀት ከማቁለጭለጭ ውጭ ምንም ማድረግ አልቻልንም፡፡አንደኛው ሽጉጥ እንደደቀነ እኛን ሲጠብቀን ሌለኛው ወደ ውጭ ወጣና ባለ አስር ሊትሩን ጄሪካን ይዞ መጣ… ክዳኑን ከፈተና እቤት ውስጥ ማርከፍከፍ ጀመረ፡፡ መጀመሪያ ውሀ መስሎኝ ነበር ብኃላ ግን ምንነቱን በሽታው ወዲያው ተረዳውት ፣ጋዝ ነው..፡፡ጉዳችን ፈላ አልኩ፡፡…እመብርሀን ድረሺልን አልኩ ..በቁማችን እቤታችንን በላያችን ላይ ዘግተው ሊያነዱን ነው ስል አሰብኩ፡፡እኔ እንኳን በልቼያለውም፤ ኖሬያለውም ለጨቅላዋ ልጄ ሰጋው፡፡ቡኃለ ግን አርከፍክፎ
👍3
ሲጨርስ ሁለታችንንም እየገፈታሩ ከቤት አስወጡን፡፡ ተመስገን ነው … ቢያንስ ከቃጠሎ ተርፈናል..ከዛ ወደ ጎሮ ወሰዱን እና ግቢ ውስጥ ካለ ዛፍ ላይ ሁለታንንም አቆራኝተው አሰሩን፤ አፋችንን አሸጉት እና ጥለውን ወደ ትልቁ ቤት ተመለሱ፡፡ከዛ ግቢውን ለቀው ሲወጡ ተመለከትኩ..ግራ ገባኝ..እቤት ገብተው ምን አደረጉ? እራሴን ጠየቅኩ ..መልስ ላገኝ አልቻልኩም..ወደ ልጄ መልስ ለማግኘት ፊቴን ባዞር አፌ ለካ ታፍኖል ….ከዛ ቡኃላ ከቤታችን ውስጥ እሳት ሲንቀለቀል ነው የያነው..ምን እናድርግ ከእስራታችን ራሳችንን ለመላቀቅ አልተቻለንም...የጐረምሶቹ ጠንካራ እጅ የተበተበው ጠንካራ እስር ነበር...
ከትንሽ ደቂቃ ቡኃላ እሳቱ እየተንቀለቀለ ይወጣ ጀመር… ምን እናድርግ ?እንዳንጮኸ እና እርዳታ እንዲደርስልን እንዳንጠይቅ አፋችን ተለጉሞል ቡኃላ ቆርቆሮ እየተገነጠለ መብረር ጀመረ… ሁሉነገር በእሳቱ ተበልቶ ሊጠናቀቅ ሲል ጭሱን እና የሚንቀለቀለውን እሳት አይተው መሰለኝ ፖሊሶች ደረሱ፡፡ መሳሪያ ተተኮሰ ህዝቡ ተገልብጦ ወጣ… እኛንም ፈቱን ፡፡ ግን ከአመድ በስተቀር ምንም የተረፈልን ነገር የለም፡፡››
‹‹በጣም ይገርምል..በዚህ መጠን ይበቀለናል ብላችሁ የምታስቡት የተጣላችሁት ፤ ቂም ይዞብናል ብላችሁ የምትጠረጥሩት ሰው የለም?››
‹‹ኸረ በፍፁም ››መለሱ አሮጊቷ
‹‹አንቺስ እህት?›› አላት ወደ ሄለን አተኩሮ እየተመለከተ
‹‹ በየትኛውም መጠን ባበሳጨው ከጥፊ ባለፈ ይበቀለኛ ብዬ የማስበው ምንም አይነት ጠላት የለኝም፡፡ ሊኖረኝምም አይችልም…››
‹‹እሺ የሰዎቹን አካላዊ ቁመና ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?››
ሄለን መናገር ጀመረች‹‹ምንም አይለዩም ፡፡ሁለቱም ሰማያዊ ቱታ ለብሰው ጥቁር ጭንብል አጥልቀዋል፡፡ሁለቱም ግዙፍ አቋም ቢኖራቸውም አንደኛው ግን በተለየ መልኩ እንደከባድ ሻምፒዬን ቦክሰኛ ጡንቻው ፈረጣመ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል፡፡››
ፖሊሱ መጠየቅ አለብኝ ብሎ ያሰባቸውን ጥያቄዎች ጨርሶ ቃላቸውን ተቀብሎ ካጠናቀቀ ቡኃላ‹‹በሉ ክትትሉን በተቻለ መጠን በፍጥነት እናካሂዳለን..እርግጠኛ ነኝ የእነዚህ አውዳሚዎችን ዱካ በቅርብ ጊዜ ደርሰንበት ለፍርድ እናቀርባቸዋለን…››በማለት የማጠቃለያ ንግግር አደረገ እና ሊሸኛቸው ተከትሎቸው ወጣ ….በተከሰተው ነገር ከልቡ አዝኗልም ደንግጦልም..ምክንቱም እነዚህ ሰዎች ለሮዝ ቤተሰቦች ናቸው..ከሮዝ ጋ ደግሞ በሆነ አጋጣሚ አንሶላም ታሪክም ተጋርተዋል….ስለዚህ ጉዳዩን እንከአንጀቱ ነው ቃል የገባላቸው፡፡ ነገሩን በትኩረት ሊከታተለው..የምርመራውን ቡድን እራሱ ሊመራው…..
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የፖሊስ ጣቢያውን በራፍ እንደወጡ አንድ ባለ አይጣማ ቀለም ቪታራ መኪና ፊት ለፊት ቆማ ተመለከቱ፡፡ ወዲው አንድ ቄስ ከውስጡ ወጡና ወደ እነሱ ማምራት ጀመሩ..የተለመደውን ሽፍንፍን አለባበስ የለበሱት አባ ሽፍንፍን ነበሩ..አጠገባቸው ሲደርሱ‹‹እቤት የተቃጠለባችሁ እናንተ ናችሁ?››ሲሉ በተረጋጋ እና በተጐተተ ንግግር ጠየቁ አባ ሽፍንፍን…
‹‹አዎ አባቴ..››አሉ አሮጊቷ ፈጠን ብለው
‹‹ስለ እናንተን ጉዳይ አንድ ወዳጄ ከዚህ ደውሎ ነግሮኝ ከሻሸመኔ ነው የመጣውት…አባ ኃይለ ጊርጊስ እባላለው››
ሶስቱም ደነገጡ…. በተለይ ፖሊሱ፡፡ስለ እኚህ ቄስ ዝና ብዙ ብዙ ሰምቷል..ሰምቶም በልቡ አድንቋቸው ነበር ..ሳይታሰብ ዛሬ በአጋጣሚ በአካል ሊያያቸው ስለቻለ ተደሰተ‹‹..ለምን ፊታቸውን ግልጽ አያደርጉትም? ››ሲል በውስጡ የተፈጠረውን ጥያቄ አብሰለሰለ
‹‹ኦ አባቴ እርሶ ኖት እንዴ ?ምን እንርዳዎት?››አለ ፖሊሱ
‹‹በጣም አመሰግናለው ኩማደር ፡፡አሁን ከሻሸመኔ የመጣውት እንዳልኩህ የእዚህን ቤተሰብ መጐዳት ሰምቼ ነው..እነሱን ፍለጋ ወደ ሰፈራቸው ሄጄ ጐረቤቶቻቸውን ስጠይቅ ወደ እዚህ እንዳመሩ ተነገረኝና ወደ እዚህ መጣው ፡፡ ትንሽ ከእነሱ ጋ ለማውራት ፈልጌያለው..ሁኔታዎች ተስተካክለው እቤታቸውን መልሰን ማሰራት እስክንችል ድረስ እኔ ጋ እንዲሆኑ እፈልጋለው….ወደ ሻሸመኔ ልወስዳቸው ነው፡፡ አንተ የምትፈልጋቸው ከሆነ መጥተህ ልታናግራቸው ወይም ደውለህ እንዲመጡ እና እንዲያናግሩህ ማድረግ ትችላለህ..ምን ይመስልሀል?፡፡››
‹‹ኸረ ጥሩ ሀሳብ ነው›› በደስታ ተስማማ
አባ ሽፍንፍን ኩማደሩን ተሰናበቱና ሄለን እና አያቷን ወደ መኪና ውስጥ እንዲገቡ ጋበዞቸው..ሁለቱም ግራ በመጋባ እና በመደነቅ ውስጥ እንዳሉ… ያለምንም መከራከር እግዚያብሄር ከገቡበት መከራ መዞ ሊያወጣቸው ፈልጎ ቄሱን ወደእነሱ እንደላከላቸው በማመን ያለምንም ማቅማማት በእሺታ ያሏቸውን አደረጉ…ጉዞ ወደሻሸመኔ …

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
ልጀንማ ‹‹ስጦታ›› አልላትም!!

#ባለወለድ_ስጦታዎች !

ስጦታ እንደመቀበል የሚያስጠላኝ ነገር የለም ! ስጦታ ….ባፍንጫየ ይውጣ !! ስጦታ የጠላሁት በአጎቴ ምክንያት ነው !! ልጅ እያለን …..ቤተሰብ ዘመድ ወዳጅ ወደቤታችን ሲመጣ የሚሰጠን ስጦታ ያጓጓን ነበር …እንደውም በራቀ ትዝታየ ከሰዎቹ መልክ ይልቅ ስጦታ የያዘ እጃቸውን የማስታወስ አባዜ ነበረብኝ ! የዝምድና ማእረግ ሁሉ የምሰጠው በስጦታው መጠን ነበር!
የመጀመሪያ ደረጃ የዝምድና መዓረግ የሚሰጣቸው ዘመዶች ... ጣፋጭ ይዘው የሚመጡ ኬክ በተለይ (ያኔ ኬክ ብርቅ ነበር )….ሁለተኛ ደረጃ ዘመድ ተብለው የተቀመጡት ደግሞ ፍራፍሬ ይዘው ወደቤታችን ጎራ የሚሉት ናቸው ….ሶስተኛ ደረጃ የዝምድና መዓረግ ላይ ያሉት ተረትና ጨዋታ ታጥቀው የሚመጡ ናቸው ሰባት ቀንድ ሶስት አይን ስላለው ጭራቅ ሲያወሩልን ያመሻሉ ‹ቤድ ታይም ስቶሪ› መሆኑ ነው እንኳን ልንተኛ እንዲቹ ነፍሳችን እንደተጨነቀ ቁልጭ ብለን እናድራለን፡)) አራተኛውና ልዩ የዝምድና መዓረግ የሚሰጠው የእናታችን ወንድም አጎታችን ነው (የሱ ልዩ ነው…የአጎቴ ስጦታ የሆነ የፖለቲካ ሲስተም አለው )
ልጅ ነንና ማን መጣ ሳይሆን ምን ይዞ መጣ ዋናው ጥያቂያችን ነበር … ከአያታችን በስተቀር! …ከሩቅ ገጠር የምትመጣው አያታችን (የእናቴ እናት) እሷ ራሷ የፈጣሪ ስጦታ ነው የምትመስለን … ረዥም ቀጠን ያለች ኮስታራ ሴት ናት ….ግን ስንወዳት አይጣል ! አንዳንዱ ሰው እንዲሁ መገኘቱ ስጦታ ይሆንብን የለ …እንደዛ ነበረች አያታችን ! እንደዛም ሁኖ ታዲያ ስጦታ አታምጣ እንጅ የስጦታዎች ሁሉ ቁልፍ ከንፈሯ ላይ ነው….‹‹ምነው ይሄ ልጅ የተማርቤት ቦርሳው አረጀ›› ካለች አባባ ወዲያውኑ ምን የመሰለ ቦርሳ መግዛቱ አይቀሬ ነው ! ለምን እንደሆነ እንጃ ለማንም የማይበገር የማይመስለኝ ቆፍጣናው አባታችን ለእናቴ እናት ይሽቆጠቆጣል ! እኛን ስትጠራ እሱ ‹‹አቤት›› ሁሉ ይላል፡)) እንግዲህ የስጦታ ማዘዣ ደብዳቤው ላይ ሁሉ የቃል ፊርማ የምታሳርፈው አያታችን ስለሆነችም እንደሆን እንጃ ብቻ እንወዳታለን ! ‹‹አያታችሁ ከፈረመችበት ይሰጣችኋል›› ይባላል ሲቀለድ! እናታችን ታዲያ በዚህ ባህሪያችን እኔም ወንድሜም እህቶቸም ላይ ትበሳጫለች …. ሰው ‹‹ምን ይዠ ልምጣ›› እያለ ከዘመድ ተቆራርጨ ልቅር እንዴ?›› ብላ ቱግ ትልብናለች !
አንድ ቀን ግን እናቴ ‹‹የባህሪ ለውጥ አመጣች›› በጣም ነው የተገረምነው ‹‹ ወንድሟ›› ማለት አጎታችን ስጦታ ሊሰጠኝ ሲል ፈገግ አለች …ከምር ፈገግ አለች …. !! እሱ ስጦታውን ሲያወጣ የሆነች የተንኮል ፈገግታ ፊቷ ላይ አንዣበበችና ‹‹ተቀበል አጎትህ አይደል›› አለችኝ... ጭራሽ? !! በኋላ አይደል እንዴ የማዘር ተንኮል የተገለጠልን ሴት መለኛ ናት የሚባለው በእናቴ ነው የገባኝ፡))
አቤት የማዘር ወንድም ስጦታ ሲገርም . . . እንግዲህ ልክ እንደዓለም ዋንጫ በአራት አመት አንድ ጊዜ ነው ስጦታ የሚሰጠው … ስጦታው ታዲያ ዝም ብሎ አይሰጥም ሂደት አለው ….የመጀመሪያ ቀን ቤታችን የመጣ ጊዜ የሰጠኝ ስጦታ ትዝ ይለኛል! እቤታችን አራት ቀን ከርሞ በአምስተኛው ሊሄድ ሲነሳ ‹‹ኧረግ ረስቸው …አቡቹ ና ስቲ ወዲህ …ስጦታ ገዝቸልህ ረስቸው ›› አለና መጀመሪያ እጁ ጋቢውን እየሰረሰረ ካፖርቱ ላይ ደረሰ ካፖርቱን አልፎ ኮቱ ….ከዛ ከሸሚዙ የደረት ኪስ …..ምዝዝ አድርጎ ምን ቢያወጣ ሩ ነው ?….አንዲት ገና ያልተቀረፀች አዲስ እርሳስ!! እኔማ ያን ሁሉ ቁፋሮ ስመለከት አጎቴ ነዳጅ ሊያወጣ ሁሉ መስሎኝ ነበር፡))
‹‹ይሄው ….ይሄ ተላይ ያለው ማጥፊያው ነው (ይፈነዳ ይመስል በጥንቃቄ እየነካ) …በጣም አትፈግፍገው ቶሎ ያልቃል …ደሞ ስተቀርጥ በምላጭ አባትህ ይቅረጥልህ ….ዘመናዊው መቅረጫ አንዴ ጠርቦ ነው የሚጨርሰው ›› ብሎ ረዥም ምክር ጋር ርሳሷን ሰጠኝ …..ከዛማ ሊፋታኝ ነው እንዴ ….እቤታችን በመጣ ቁጥር ሌላ ስጦታ የለም ‹‹ አቡቹ ያ ርሳስ …እንዴት ነው? ….ጥሩ እየተገለገልክበት ነው? …አዎ በጣም አትቅረጠው… እንደነገርኩህ በምላጭ ….ስእል ደሞ ሳልበት… ስእል ትልቅ ሙያ ነው… ለስእል ዋናው ነገር ርሳስ ነው ርሳስ ካለ ስእል አለ …. አንዳንድ ማስታወሻም ካለ ከጡፍህ ስር በስሱ ለማስታወስ ብትጥፍበት ትችላለህ….በቃልህ ከተያዘልህ በኋላ ታጠፈዋለህ ›› አለኝ ….አጎቴ ሲያካብደው የማውቀው ርሳስ የሆነ ሌላ ተዓምር ነገር መሰለኝ!!
ሌላ ቀን አጎቴ ቤታችን ሲመጣ ደሞ ‹‹ አቡቹ ….ያ ርሳስ ለሂሳብ ጥሩ ነው ….አየህ ሂሳብ እንደሌላው ትምርት አደለም ይሳሳታል ….ስትደምር ትሳሳታለህ ሰው ሁኖ መቸም የማይሳሳት የለም …ስታባዛ ትሳሳታለህ ….በተለይ በተለይ ሰው ሁኖ ሲያካፍል የማይሳሳት የለም …ታዲያ ርሳስ ከሆነ ስትሳሳት ስርዝ ድልዝ የለም በማጥፊያዋ ጠፋ ነው ›› በቃ አጎቴ አዛ አደረገኝ! ….ውይ በምን ቀን ነው ይሄን ርሳስ የተቀበልኩት …የእናቴ የተንኮል ሳቅ ቆይቶ ነው የተገለጠልኝ (ቅጣት መሆኑ ነው) ….
በቃ አጎቴ ስጦታ ከሰጠ እድሜ ልኩን ስለሰጣት ነገር ሲያነሳ ሲጥል ….ስጦታው አላቂ ቢሆንኳ የአጎቴ ምክርና ማስጠንቀቂያ አያልቅም !! እንደዛ አይነት ሰው አጋጥሟችሁ አያውቅም ?….የሆነ ነገረ ሰጥቶ እድሜ ልኩን ስለዛች ነገር አጠቃቀም እንዴት ሊሰጣችሁ እንዳሰበ ….ወሬ ሁሉ ሲያወራ ቀን ከጠፋው ስጦታውን ካሌንደር ያደርገዋል ‹‹ያኔ እንትኑን እንደነገ ልሰጥህ እንደዛሬ ›› እያለ !!
እንደዚህ አይነት ባህሪ ያላቸው ፍቅረኞች አሉኮ ....ለምሳሌ ጓደኛሽን ቀጥረሽው ይዘገይብሽና ደውለሽ " የት ደረስክ " ስትይው " ባለፈው ቅቅል የጋበዝኩብሽ ቤት ደርሻለሁ የኔ ማር ፡))" የቅቅል ግብዣው የፊታችን ግንቦት 20 ሶስት አመት ይሆነዋልኮ:) ሴቶችም አሉ ለ23ኛ አመት ልደትህ ዋሌት ሰጥታህ በሰላሳ ሶስተኛ አመትህ የዋሌቱን አስረኛ አመት በዓል በክትፍ እናክብር የምትል:))
እና የአጎቴ ስጦታ የትዝታ ወለዱ ተከፍሎ አያልቅም!! ዘመዶቻችንኮ ከዛ በኋላ ያመጡት ስጦታ መዓት ተቆጥሮ አያልቅም…. አጎቴ ግን በስጦታ ወለዱ ነበር የሚኖረው !! እንደውም ጭራሸ አንድ ቀን አጎቴ ምናለ.... ለበዓል ዘመዱ ሁሉ እቤት ተሰብስቦ ስጦታውም በዛው ልክ ሲጎርፍልን
‹‹ አቡቹ ….የሰው ስጦታ ቀላል ነገር አይደለም …. ነገ ተምረህ ሰው ስትሆን መክፈልህ አይቀርም! ወረቀት ላይ በዛ በሰጠሁህ ባዲሱ ርሳስ አንድ ባንድ የተሰጠህን መዝግብ፡))›› እንግዲህ ባለፈው አመት የሰጠኝን ርሳስ እኮ ነው ‹‹አዲስ›› የሚለው …የሚገርመው ግን ስንክሳር ስላበዛበት ነው መሰል የአጎቴ ርሳስ ከሌሎች ስጦታዎች ሁሉ የበለጠ መስሎ ይሰማኝ ነበር፡)) ለካስ የቴሌቪዝን ጣቢያዎች ወደው አይደለም አንድን ነገር ደጋግመው ደጋግመው ህዝቡን የሚያዝጉት ሲቆይ ህዝቡ የሚወራው ነገር ተራ ቢሆን እንኳን ውድና ትልቅ ነገር ይመስለዋል፡))
ታዲያ ይሄ አጎቴ አንድ ቀን አያቴ ባለችበት ቤተሰቡ ተሰብስቦ እሱም በእንግድነት መጥቶ ….ከኪሱ የፀጉር ማሰሪያ ሻሽ ነገር አወጣና ‹‹ይሄ ላንች ነው ›› አላት እህቴን …ስጦታ ሳይሆን ሽጉጥ የተመዘዘባት ይመስል ልትሮጥ ነበር ቀጠል አደርጎም …‹‹ጠጉር አቧራ ሲጠጣ ከዋለ ፎረፎር ነው የሚፈጥረው …ፀሃይም ቢሆን ቀላል ነገር አይደለም …ይችን ሸብ ካደረግሽ በቃ …አቧራ የለ የሰው አይን የለ ….አንዳንዴ ሰንፈሽ ባታበጥሪው እንኳ መከሌ ይሆንሻል . . . ባይሆን አያትሽ ተፈረመችበት ነው የሚሰጥሽ ›› አለና ወደአያቴ በኩራት ዞረ …(አያቴ ስጦታውን ይሁን ካለች ማለቱ ነው )…ድንገት እኔም
👍31
እህቴም ወንድሜም ወደአያቴ ሰፍ ብለን በአንድ ላይ ጮህን ‹‹ እንዳትፈርሚ አያቴ››፡))))))))))
ታዲያ ይሄ አጎቴ በቅርቡ መጣና ‹‹አይ አቡቹ …እስታሁን አላገባህም? ….አልወለድክም ?….ልጅኮ የግዜሄር ስጦታ ነው ›› አለኝ
በሆዴ ‹‹ኧረ እንኳን የአጎት ስጦታ ያልሆነ›› እያልኩ … ዝም አልኩ !
‹‹መቸም ልጅ ስትወልድ እኔ ነኝ ስም የምሰጣት ….አዎ ሴት ተሆነች ስጦታ ብያታለሁ …የአጎትህ ስጦታ ነው በሌላ ስም ትጠራትና ውርድ ከራሴ ›› አለኛ … ህ ?….ልጀንማ ስጦታ ብየ ሳዝነዘንዛት አልኖርም በኛ ይብቃ ትውልድ ይዳን ….
‹‹አቡቹ ››
‹‹አቤት አጎቴ ››
‹‹ ስሙን እንዳትረሳው ….በዛ እርሳስ መዝግብና አስቀምጠው›› ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ!!

🔘አሌክስ አብርሃም🔘
👍1
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሀያ
:
ድርሰት በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
፨አንቺስ ተነፈሽ እህቴ … ቁስልሽ ትንሽ ጠገገ
የልብሽ ድማት ረግቶ..ፊትሽ በእፎይታ ፈገገ
እኔ ግን በሞት ዝምታ … ውስጤን በበቀል ያነደድኩ
ራሴን ማከም አቅቶኝ …ሙሉ ደስታዬን ያወደምኩ
ባንቺ ቀናሁኝ በሳቅሽ…በታሪክሽም ተደመምኩ
ለራሴ ለሚስኪኑ ግን….እንባዬን በውስጤ አፈሰስኩ
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
ሰዓቱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓትነው፤ኩማደር መሀሪ ጭላሎ ሆቴል ብቻውን ቁጭ ብሎ ውስኪውን እየተጋተ ነው፡፡እየተጋተ ብዙ ብዙ ነገር ያስባል… አስቦ ይገነባል… የገነባውን መልሶ ያፈርሳል…ማሰቡ ሲሰለቸው.. ከሀሳብ መውጣት እና ዘና ማለት አማረውና አንድ ቆንጆ ሞንዳላ ልጅ ጠራ …እንድታጫውተው፡፡
‹‹አቤት ምን ልታዘዝ?››አለችው አጠገቡ ደርሳ ወደ እሱ ጐንበስ ብላ
‹‹ቁጭ በይ ››አላት..ቁጭ አለች፡፡
ሌላዋ ጓደኛዋ ..ከኃላዋ ተከትላት መጥታ
‹‹ ምን ልታዘዝ ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ፋንታ አምጪልኝ›› አዘዘች ፡፡
ልጅቷ ትዕዛዞን ተቀብላ ሄደች፡፡‹‹ምነው ለስላሳ?አልኮል መጠጥ አትደፍሪም ማለት ነው?››ጠየቃት
‹‹ወድጄ ደፍራለው..እዚህ ቦታ እንዲህ አይነት ስራ እየሰራው እንዴት ነው አልኮል ማልደፍረው?እኔ አልኮልን ደፍራላው የአዳም የልጅ ልጆች ደግሞ እኔን ይደፍሩኛል ፡፡…መድፈር..መደፈር..ደስ አይልም ..?››ከትከት ብላ ሳቀች
‹‹አይ እኔ ያልሽው ብዙም አልገባኝም…የጠየኩሽ ፋንታ ስላዘዝሽ ብዬ ነው?››
‹‹ተይዤ ነው..በቃ ያመጡትን ያምጡ ብዬ››
‹‹እነማን ናቸው ያመጡትን የሚያመጡት››
‹‹ባለቤቶቹ ናቸዋ ..››
‹‹አልገባኝም››… የታዘዘችው ልጅ ፋንታ አምጥታ ከፍተችላትና ወደ ቦታዋ ተመለሰች፡፡
ልጅቷም የፍንታ ጠርሙሱን አነሳችና አንዴ ተጐንጭታለት ኩማደሩ ለጠየቃት ጥያቄ መልስ መመለሷን ቀጠለች
‹‹ባለቤቶቹ የእኛን አልኮል መጠጣት እንደ ግዴታ ነው የሚያስቀምጡት››
‹‹ለምን ተብሎ?››
‹‹አየህ አሁን ፋንታ አዘዝኩ..ድገሚ አትለኝም፡፡ ብትለኝም እኔ እሺ ብዬ አልደግምም፡፡ቢራ ቢሆንስ? ቢያንስ ሶስት አራት ጠርሙስ ትጋብዘኛለህ…ካልሆነም እስከ አስር ጠርሙስ ከዛም በላይ ልትጋብዘኝ ትችላለህ.. እንግዲህ ከእኔ መጠጣት ባለቤቶቹ የሚያገኙት ጥቅም ይታይህ….››
‹‹ቆይ ታዲያ ዛሬስ ምነው ..ፍቃድ ተስጥቶሽ ነው?››
‹‹አይደለም.. ጨጎራዬ ተላጠ..ትናንትና አንዱ ጉረኛ ወንድ ሙሉ ውስኪ አውርዶ ለሁለት..እኔ እና እሱ ብቻ ጨረስነው ፡፡ ..እናም ስሰቃይና ሳጐራ ነው ያደርኩት ፤ሀኪም ቤት ሄጄ ኪኒን አዘውልኝ እሱን ውጬ ነው ትንሽ ተንፈስ ያልኩት፡፡ደግሞ ባለቤቶቹ ብቻ አይደሉም እራሱ ጋባዡም ካልጠጣሽ ሞቼ እገኛለው ብሎ እንቡር ይላል..ለእኛ እንኳን የማዘን ፍላጐቱ ባይኖረው እንዴት ለገንዘቡ አያዝንም እያልኩ ሁሌ እገረማለው… ይሄኔ እኮ ለወር የሚሆን የአስቤዛ ወጪ ለሚስቱ አልሰጥም ብሎ እኮ ይሆናል እዚህ መጥቶ እኔን በውስኪ ሲያጠምቀኝ ያደረው…››
‹‹ለመሆኑ ስምሽ ማናው?››
‹‹ከደንበኞቼ ጥያቄዋች ውስጥ በጣም የሚያስጠላኝ ስምሽ ማነው የሚለው ነው?››
‹‹ለምን?››
‹‹እኔም እውነቱን አልነግርህ አንተም ቁምን ነገር ብለህ በአዕምሮህ አትይዘውም..›››
‹‹እንዴት እንዲህ ልትይ ቻልሽ?››
‹‹ከልምድ ነዋ …ከቡና ቤት ሴቶች መካከል 99 ፐርሰንቱ ትክክለኛ ስማቸውን አይናገሩም …ሌላው ደግሞ ስማችሁ ማን ነው ብለው ከሚጠይቁን ደንበኛቻችን መካከለም አብረውንም ቢያድሩ እንኳን 99 ፐርሰንቱ በማግስቱ ቢጠየቁ አያስታውሱትም››
‹‹ትገርሚያለሽ..ለማኛውም ንገሪኝ››
‹‹ከጠቀመህ ትዕግስት እባላለው››
‹‹እውነተኛውን ነው ወይስ የፌኩን ስምሽ ነው የነገርሺኝ፡፡››
‹‹አይ ትክክለኛውን ነው››
‹‹እኔ ደግሞ ኩማደር መሀሪ እባላለው››
‹‹ኩማደር መሀሪ!!!››የአሸባሪ ስም ፊቷ እንደተጠራባት በረገገች፡፡
‹‹ምነው በረገግሽ?››
‹‹በጣም ነው የማውቅህ››
‹‹ማ እኔን? የት? ››
‹‹እዚሁ ነዋ ፡፡ብዙ ሰዎች ስለአንተ ሲያወሩ ሰማለው››
‹‹ምን ምን እያሉ?››
‹‹ያው ..ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ያወራሉ….ግን አትመስልም…››
‹‹እንዴት አትመስልም ስትይ?››ንግግሯ ግራ አጋብቶት
‹‹እንዴ ስለአንተ ሲያወሩ እኮ ስለሆነ ግዙፍ አውሬ የሚያወሩ ነው የሚመስለው..ግን እንደዛ አትመስልም፡፡ ብዙም አታስፈራም ..ትጫወታለህ››
‹‹ለማኛውም ከዛሬ ጀምሮ ያው ጓደኛ ሆነናል አይደል?››አላት
‹‹ይመቸኛል››
‹‹አሁን ልሄድ ነው፡፡››
‹‹እንኳንም አብረን እንደር አላልከኝ››አለችው…ፈገግ እያለች፡፡
‹‹ለካ እንደዛም ይባላል.?.ብልሽ ግን ምነው ፈርተሺኝ ነው? ››
‹‹አይ በፍፅም አልፈራውህም፡፡እኔ እንደውም እድሌ ሆኖ ጨካኝ የሚባሉ ሰዎች እጣ ክፍሌ ናቸው፡፡ብቻ እንደነገርኩህ በትናንትናው አዳሬ ድክምክም ስላልኩ ነው፡፡››
‹እንደዛ ከሆነ ተስማምተናል፡፡››ብሎ ሂሳቡን ከፈለና ለእሷም በእጆ ድፍን መቶ ብር እስጨብጧት ሆቴሉን ለቆ ወጣ፡፡
ሰዓቱን ሲመለከት ሶስት ሰዓት ተኩል ሆኖል፡፡ወደቤቱ ሳይሆን ወደፖሊስ ጣቢያ ነበር ያመረው፡፡እስኪሰለቸው ቢሮው ሲሰራ ቆይቶ ስምንት ሰዓት ሲሆን አረፍ ሊል ወደ ቤቱ አመራ…መኪና ስላልያዘ በእግሩ ነው እየተጓዘ የነበረው..ውስጥ ለውስጥ ያለውን ሶስተኛ መንገድ ይዞ ቀበሌ 4 ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሊደርስ 400 ሜትር ያህል ርቀት ሲቀረው..የሆነ እንቅስቃሴ ከተቃራኒው መንገድ ተመለከተ…ጐኑ የሻጠውን ሽጉጥ መዥረጥ በማድረግ በእጁ ይዞ መንገዱን በፍጥነት ለቆ ወደአጥር በመጠጋት ጨለማ ውስጥ ተከለለ፡፡አዎ አሁን በግልጽ ይታዩታል… ሁለት ጎረምሶች ናቸው፡፡ፈጠን እያሉ ግራና ቀኛቸውን እየተገለማመጡ ነው የሚጓዙት ..አንደኛው በእጁ ጥቁር ሳምሶናይት ሻንጣ ይዞል፡፡የጉዞቸው አቅጣጫ ወደ እሱ ነው፡፡እየቀረቡት ነው….እነሱ ባያዩትም እሱ በግልጽ እያያቸው ነው፡፡አምስት እርምጃ ርቀት ላይ ሲደርሱ
‹‹ባላችሁበት ቁሙ››ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ አሳተላለፈ፡፡ያላሰቡት ዱብዳ የገጠማቸው ሁለት ጓረምሶች ባሉበት ተገትረው ቆመው ፊታቸውን ድምጹን ወደሰሙበት አቅጣጫ መለሱት፡፡
ኩማደሩ ከተወሸቀበት ጭለማ ቀስ እያለ እየተሳበ ወጣ‹‹እጅ ወደ ላይ››
ሳምሳናይቱን መሬት ላይ አስቀምጠው ሁለቱም እጃቸውን በፍራቻ ወደላይ ሰቀሉት
‹‹እሺ በዚህ ሰዓት ከየት ወደ የት ነው?››
‹‹ጓደኞቻችን ቤት ስንቅም ቆይተን… መሽቶብን አሁን ወደ ቤታችን እየገባ ነው››መለሰ አንደኛው
‹‹እሺ …ሳምሳናይቱ ውስጥ ምንድነው ያለው?››
‹‹ምንም አይደል የስራ ዶክመንት ነው››ዋሹት
ድንገት ለሚጠይቀው ጥያቄ መልስ የሚሰጥውን ልጅ ማንነት ለየው፡፡ቢያንስ እሱ ሻሸመኔ ከገባ ጀምሮ ከሶስት ጊዜ በላይ ከስርቆት ወንጀል ጋር በተያያዘ ፖሊስ ጣቢያ አግኝቶታል፡፡
‹‹አጅሬ አወቅኩህ.. አንተው ነህ..አሁን ወደፖሊስ ጣቢያ እንሂድ ወይስ እንደራደር?››
ንግግሩ ስላልገባቸው ፈጥነው ሊመልሱለት አልቻሉም
‹‹በውድቅት ለሊት ብርድ አታስቀጥቅጡን ..ወደፖሊስ ጣቢያ ልውሰዳችሁ ወይስ እንደራደር? መልሳችሁን እየጠበቅኩ ነው?››
››እንደራደር አለ.. እስከአሁን በፀጥታ ውስጥ የነበረው ፈርጣማ ጥቁር ወጣት››
‹‹እንደዛ ከሆነ ሳምሶናይቱን አንሳና ያዘው››አንስቶ ያዘው
‹‹ፊታችሁን ዞራችሁ ቀጥሉ…››
‹‹ወዴት? ›› ጠየቀ አንደኛው
‹‹ድርድራችን ትንሽ ረዘም ያለ እና ጊዜ የሚፈጅ ነው..እዚህ ብርድ ላይ በዚህ ውድቅት ለሊት መደራር ስለማንችል ወደ እኔ ቤት እንሂድ.. አይዞችሁ ደርሰናል ቅርብ ነው››ሽጉጥ ከኃላ እንደደቀነባቸው ነበር…እሱ ቤት ደረሱ… የግቢውን አጥር በር ከፍቶ
👍41