#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_አስራ_አራት
/////
እለተ እሁድ ነው፡፡ረፋድ ላይ ቁርሴን ከበላሁ በኃላ ወደአልገዬ ተመልሼ ልጄ የላከችልኝን የእናቷን ማስታወሻ በተመስጦ እያነበብኩ ነው፡፡ይሄ ታሪክ የአፈላነት ጊዜ ታሪካችን ነው፡፡ትኩስ ወጣት ሆነን የኖርነው፡፡ወጣትነት ውስጥ የሚንፎለፎል ኃይል አለ።"ልክ የኒዩክሌር ኃይል አይነት።ወደማብራት ኃይል ተቀይሮ ልማትን ሚያሳልጥ...ወደአውዳሚ ቦንብ ተቀይሮ ለጦርነት ውሎ ከተማን የሚያፈርስ ወጣትነት ከተራራ የሚገዝፍ ነገሮችን የማድረግ ጉጉት እና ሳይታክቱ የመሞከር ትጋት ..ቢወድቁ በፍጥነት ተነስቶ የመቆም ፅናት፡፡ አዎ ከሰው ልጅ የዕድሜ እርከኖች ጎልደን ኤጅ የሚባለው ነው ወጣትነት፡፡ ህፃንነትና ታዳጊነት ከኃላው ትቶ ጎልማሳነትና አዛውንትነትን ከፊቱ አስቀምጦ ከህይወት ዘንግ የመሀል አንጓ ላይ ያለ በዕንቁ ያሸበረበቀ ጌጥ ነው።
ወጣትነት ውበት በመጨረሻው እንጥፍጣፊ አቅሙ የሚጎመራበት ስሜት ክላይማክሱን ገጭቶ የሚንፎለልበት የአበባነት እድሜ ነው።የፍቅር ኮንሰርት ቢዘጋጅ የዳንሱን መድረክ የሚሞላው ወጣት ነው...የጦርነት ነጋሪት ቢመታ ለመስዋዕትነት ግር ብሎ የጦር ካንፑን የሚያጨናንቀው ወጣት ነው።አብዬት አንስቶ ከተማውን በድንጋይ አጥሮ አስፓልቱን በጎማ ጭስ የሚያጥነው ወጣት ነው....ለድጋፍ ሰልፍ ቲሸርትና ኬፕ ገድግዶ ጎዳናውን በመፈክርና በባንዲራ የሚያጣብበውም ያው ወጣት ነው። በቀደድለት ቦይ የሚፈስ ፤ባሳዩት መንገድ የሚነጉድ ወጣት ነው።ቤተ እምነቱ የሚሻማው ቤተመንግስቱም የሚፈራው ያው ወጣት ነው...፡፡ ወጣት ሆነህ ጥበብ ቀድሞ ከበራልህ ቤተእምነትም ሆነ ቤተመንግስት አያታልሉህም....፡፡ፓለቲከኛው በስሜትህ ጢባጢብ አይጫወትብህም ...፡፡አዎ የነቃህ ወጣት ከሆንክ ለእሱ ወደስልጣን ማማ መስፈንጠሪያ እስፕሪንጉ ለመሆን በምንም አይነት ሁኔታ ፍቃደኛ ልትሆን አትችልም" ግን ወጣትነት በብዙ ችኮላ ፤ፋታ በማይሰጥ ጉጉት፤ ስር ባልሰደደ ዕውቀትና ልምድ የሚጓዝ በመሆኑ ከስህተት ሊፀዳ አይችልም፡፡እርግጥ ሙሉ የሰው ልጅ ከስህተት ጋር የእድሜ ልክ ትስስር አለው…ወጣትነት ላይ ግን ይለያል..እኔም እንደአብዛኛው ሰው ህይወቴን ያጨመላለቅኩት በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ በሰራሁት ስህተት ነው፡፡ውይ እስቲ መዘበራረቁን
ገታ አድርጌ እጄ ላይ አንከርፍፌ የያዝኩትን ከሪች ማስታወሻ ፎቶ ተንስቶ በልጄ አማካይነት በቴሌግራም የተላከልኝን ቀጣይ ታሪክ ላንብብላችሁ፡፡
ሰኔ 5 2008 ዓ.ም
11 ኛ ክፍል ሆነን ነው፡፡ማታ 11 ሰዓት ሆኖ ከትምህርት ቤት ከገባን በኃላ በምን ሰዓት በየት እንደሄደ ሳላውቅ እዬብ ከቤት ወጥቶ ጠፋ..ሰፈር ዞር ዞር ብዬ ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም.ግራ ገባኝ…ማታ እራት ሰአት ላይም ተመልሶ አልመጣም.. እነእማዬ ሲጠይቁኝ ጓዳኛዬ ጋ አብረን እናጠናለን ሲል ሰምቼለሁ ብዬ ዋሸሁ…የቤቱ ሰው ሁሉ ከተኛ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ የክፍላችን መስኮት ከፈትኩለት.ዘሎ ገባ፡፡
‹‹እስከአሁን አልተኛሽም እንዴ?››
‹አፈር ብላ…ዝም ብለህ ከቤት ወጥተህ እስከእዚህን ሰዓት ድረስ ትቆያለህ?››
‹‹የእኔ ውድ እህት …አሳስብኩሽ እንዴ ..?
ድንገተኛ በረከት አጋጥሞኝ ነው፡፡››
‹‹የምን በረከት ነው?››
‹‹ባክሽ ሶፊያ ጋር ነበርኩ››
አቤት የደነገጥኩት
ድንጋጤ‹‹ሶፊያ የት? .ለምን?.ከእሷ ጋር ምን አባህ ትሰራለህ?››
ተንሰረዘረኩበት ፤አዎ ሶፊያን በደንብ አውቃታለሁ...አረ እንደውም. የክፍላችን ልጅና ለእኔም ጓደኛዬ ነች..የተበሳጨሁበት ጉዳይ ግን ወደጎን ነው፡፡ሶፊያ እዬብዬን በጣም እንደምትወደው አውቃለሁ፡፡.ማለት እንደምታፈቅረው አውቃለሁ….ብዙ ጊዜ ደጋግማ ‹ወንድምሽን አፈቅረዋለሁ› …ብላ ነግራኝ ፊት ነስቻታለሁ፡፡እንደዛ ስትለኝ የማቀርብላት ምክንያት ‹ወንድሜ ጎበዝ ተማሪ ነው..ያለጊዜው ፍቅር ምናምን እያልሽ እንድታዘናጊው አልፈልግም› የሚል ነበር››ዋናው ምክንያቴ ግን ያ አልነበረም…እዬብን ፍቅረኛም ሆነ ጓደኛ በሚል የብእር ስም አንድ ሴት መሀከላችን ገብታ እንድትሻማኝ አልፈልግም፡፡
‹‹እረጋ በይ እቤቷ ነበርን››አለኝ.በሚያበሳጭ የድምፅ ቃና..
‹ለመሆኑ እስከዚህን ሰአት እቤቷ ጎረምሳ ስታቆይ እቤተሰቦቾ ምንም አይሏትም?››
‹‹አታስቢ የእኔ እህት… ብቻዋን ነበረች››
‹‹ብቻዋን?››
‹‹አዎ ምነው ደነገጥሽ…ገጠር ሄደዋል… ብቻዋን ስለምታድር ነው የጠራቺኝ››
‹‹እና ምነው ብቻዋን ጥለኸት መጣህ ..የሆነ ነገር ቢያስደነግጣትስ…?አብረሀት አታድርም ነበር?››
‹‹እንኳን አድሬ ላመሸሁትም ሞቼልሻለሁ…አንቺ ጓደኛሽ እንዳንቺ መሰለችሽ.. አስጮኸችኝ እኮ››
‹እስጮኸችኝ ማለት…?መታህ ነው
አስደንግጣህ?››
‹‹አይ አንቺ ልጅ በቀላሉ አይገባሽም…ወሲብ ፈፀምን ….ወሲብ እንደዚህ እንደሚጥም ዛሬ በእሷ አወቅኩ፡፡››
‹ወሲብ .ወይኔ እቴትዬ…ወይ እግዚያብሄር ድረስ..ከተቀመጥኩበት አልጋ ተነሳሁ .እንባዬ አራት መስመር ሰርቶ በጉንጮቼ ላይ መፍሰስ ጀመረ…ወለሉ ላይ ተዘርፍጬ መሬቱን አሰስኩት..እዬቤ ያላሰበው ዱብ እዳ ነው የገጠመው...በጣም ግራ ገባውም በጣምም ደነገጠ.
‹‹አንዴ ምን ሆነሻል.?አረ ደምፅሽን ቀንሺ.እነቴቴ አንዲሰሙ ተፈልጊያለሽ እንዴ?›
‹‹አንተ እንዴት እንዲህ ትሰራለህ…?ምን ነክቶህ ነው?››
‹‹ምን ችግር አለው ?ይሄ እኮ ማንም ወጣት የሚሰራው ኖርማል ነገር ነው›
‹አይደለም እኔስ ወጣት አይደለሁ ለምን ሳልሰራሁም…?ለምን ቆይ?
‹‹እሱን እግዲህ እራስሽን መጠየቅ ነው››
‹‹አይደለም..በሽታውስ እንዴት እንዲህ እንዝላል ትሆናለህ.?.በዛ ላይ ብታረግዝብህስ…?ምን አባህ ልታደርግ ነው…ደግሞ ቤተክረስቲያን ይሄን ሁሉ ዘመን የተመላለስከው ለዚህ ነው፡፡ይሄ እኮ ዝሙት ነው..››
‹‹አረ በፈጠረሽ..እኔ ፀፀት እንዲሰማኝ ለማድረግ የሚያስቸልሽን አንድም ምክንያት እኮ አልቀረሽም..እኔ እኮ አስቤበት አልነበረም አሷ ጋር የሄድኩት..ድንገት ነው ሳናስበው ወደወሲብ የገባነው….ጥሩነቱ ግን እሷ ሁሉንም አዘጋጅታ ነበር የጠበቀችኝ.››
‹‹ሁሉንም ማለት?››
‹ኮንደም ነበራት..ልታረግዝ አትችልም አትፍሪ... በሽታውም እንደዛው…››
‹‹እሷማ አዎ እንደዛ ታደርጋለች …ልምድ ያላት ሸርሙጣ ነች፡፡እሺ የእግዚያብሄር ቃልን መጣሱስ? ዝሙቱስ?›
‹እሱን አንግዲህ አንዴ ተሳሳትኩ ወደኃላ መልሼ አልውጠው…ማድረግ የምችለው ንሰሀ መግባት ነው…እሱን አስብበታለሁ…አሁን እንተኛ ደክሞኛል አለኝና ልብሱን ፊቴ አወላልቆ ከውስጥ ገባና ከጭቅጭቄ ለማምለጥም ጭምር መሰለኝ ጥቅልል ብሎ ተኛ፡፡
‹‹እኔማ ከሻርሙጣ ጋር አብሬ አልተኛም›› አልኩና አልጋ ልብሱን ከላዩ ገፍፌው ትራሴን ወሰድኩና ምንጣፍን ወለሉ ላይ ዘርግቼ ተኛሁ…ተነስቶ እንዲለምነኝ ፤ጉንጬን፤ ግንባሬን እየሳመ ይቅርታ እንዲጠየቀኝ…እቅፍ አድርጎ ፀጉሬን እያሻሸ ሁለተኛ አልመለስበትም ብሎ በስሜ እየማለ ቃል እንዲገባልኝ ፈልጌ ነበር….እሱ እቴ ዝም አለኝ….ደረቅ ወለል ላይ ብገላበጥ..እህህ ብል ምንም ጭራሽ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ ማንኮራፋት ጀመረ..

👍37
ምን ላድርግ ግራ ሲገባኝ ቀስ ብዬ ከወለሉ ተነሳሁና ወደአልጋዬ ተመለስኩ፡፡ ብርድልብሰን ገልጬ ሰርስሬ ከውስጥ ገባሁና ጉያው ውስጥ ተሸጎጥኩ…የእሱ ያልሆነ አስጠሊታ ጠረን በአፍንጫዬ እየማግኩ ፤በለቅሶ እያታጠብኩና በንዴት እተንጨረጨርኩ እንቅልፍ ወሰደኝ..እንግዲህ በዛን ቀን ነው ሴይጣን እንኳን የማያስበውን ምኞት በውስጤ የተፀነሰው‹‹…እዬብ ባሌ እንጂ ወንድሜ መሆን አልነበረበትም….በዚህ ጉዳይ እግዚያብሄር ስህተት ሰርቶል›› ብዬ ሙግት መግጠም ጀመርኩ….ከዛን ቀን በኃላ ትምህርት ቤት ከእኩዬቼ ጋር ፃታዊ ስለሆነ ጉዳይ በሹክሽክታ ስናወራ እነሱ ልባቸውን ስላስደነገጠው ወንድ ማንነት አንስተው ሲያወሩልኝ በእኔ ምናብ ድንቅር ብሎ እቅሌን እስክስት የሚያስጨንቀኝ የእዬብ ምስልና ማንነት ሆነ….ከማንም ጋር ሰሙን አንስቼ መናገር የማልችለው የውስጥ እምቅ ብሶቴ…የሚጠዘጠጥዝ የብቻ ህመሜ ፡፡
////
ይቺን ቀን አዎ በደንብ አስታውሳታለሁ፡፡ከጓደኛዋ ጋር ያሳለፍኩትን የፍቅር ታሪክ ሳልደብቅ በጉጉትና በመደነቅ የነገርኳት ያለምንም መሸማቀቅ በኩራት ነበር፡፡በጣም የምወዳት እህቴ ብቻ ሳትሆን ብቸኛዋ የልብ ጓደኛዬ ጭምር ስለሆነች እንዲህ አይነት አዲስ ልምድና አስደማሚ የወጣትነት ገጠመኜን ከእሷ ውጭ ለማን ልንገር እችላለሁ?፡፡ያገኘሁት ግብረ መልስ ግን ከጠበቅኩት ፍፁም ተቃራኒ እና አብሻቂ ነበር፡ለእቴቴ ብነግራት እራሱ የዛን ያህል አንባጎሮ አታስነሳም ነበር፡፡በጣም ነበር የበሸቅኩባት…ይህቺ ልጅ የእኔ መደሰት አያስደስታትም እንዴ? ስል አሰብኩ እንጂ ስለምታፈቅረኝ ቀንታ ነው የሚል ሀሳብ ፈፅሞ በምናቤ አልመጣም ነበር፤እንዴት ሆኖ?፡፡እንደውም በዚህ ድርጊቷ ቂም ይዤባት የዛን ሰሞን የፈፀምኳቸውን ሁለት ተመሳሳይ ታሪኮች ሚስጥር አድርጌ ሳልነገራት ደብቄያታለሁ፡እስቲ ቀጣዩን ላንብብ
ሰኔ 14-2008 ዓ.ም
ለሊት ተነስቼ ጊዬርጊስ ቤ.ክርስቲያን ሄደኩ ። ‹‹እባክህ ያሳደከኝ ፈረሰኛው ጊዬርጊስ በእእምሮዬ የተሰነቀረብኝን መጥፎ ሀሳብ ከውስጤ እጠብልኝ። …አባክሽ እመብርሀን እኔ ሀጥያተኛ ልጅሽን ተመልከችኝ .. ምንድነው በውስጤ የበቀለው ጨለማ ሀሳብ? ምንድነው አእምሮዬን እየበላው ያለው ሀጥያት?›› በጥልቅ ሀዘን አንገቴን ደፍቼ ከዚህ ከገባሁበት እንድወጣ አምላክ እንዲረዳኝ ሠማዕቱ ቅድስ ጊዬርጊስ እንዲያማልደኝ...እናቱ ድክመቴን አይታ ምርኩዝ እንድትሆነኝ ፀለይኩ...
ሳስበው ግን ፀሎቴ ከልቤ የመነጫ አልመሰለኝም… ምክንያቱም እለት በእለት ይሄን መጥፎ ሀሳብ ከምናቤ አውጣልኝ ብዬ በተማፀንኩ ቁጥር ይባስኑ ሀሳብ ልክ እንደክፉ የነቀርሳ በሽታ በመላ አከላቴ እየተሰራጨ ጭራሽ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረኝ።በቃ ከእሱ ውጭ በዚህ ምድር ምን አለኝ ብዬ እስካስብ ድረስ...በአጋጣሚ በእዛን ጊዜ ከመስፍን ጋር ተቀራረብን ።
መስፍን አስተማሪ ነው።የተዋወቅነው ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ስናገለግል ነው።ሁለታችንም የፍቅር ተጣማሪ ሆነን የምንሰራበት መንፈሳዊ ድራማ ላይ ተመደብን። ድራማው ለሰንበት ት/ቤቱ ገቢ ለማስገኘት በትልቅ ደረጃ ለህዝብ በክፍያ እንዲታይ የታሰበ ስለነበረ ልምምድ ጠንከር ያለና በየቀኑ ለሁለት ወር በተከታታይ የሚደረግ ነበር...እንግዲህ ይህ የድራማ ልምምድም አልቆ ድራማውም ለህዝብ ከቀረበ በኃላ እንደበፊቱ የመገናኘት አጋጣሚው ተቋረጠ...በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን ብቻ መገናኘት ሆነ...ለእኔ ሁኔታው ምንም የተለየ ነገር አልነበረውም... ::ለመስፍን ግን የተለየ የሆነበት ይመስለኛል፡፡ከተለያየን በኃለ፤ ናፍቆት ያስቸግረው እንደጀመር ደጋግሞ ነግሮኛል...እንዳፈቀረኝ እንደዛው" እስኪደነግጥ ጮህኩበት..አለቀስኩ ...በተገተረበት ጥዬው ወደቤቴ ገባሁ...፡፡እስቲ ምን እንደዛ ያደርገኛል?በጨዋ ደንብ ነው አፍቅሬሻለሁ ያለኝ።እኔም መመለስ የሚገባኝ በተመሳሳይ መንገድ ነበር?በራሴ አፈርኩም ተበሳጨሁም።
"አፍቅሬሻለሁ ሲለኝ ወዲያው በአእምሮዬ የመጣው ለእዬቤ ያለኝ ፍቅር ነው።ከእሱ ጉያ መንጭቄ ልውሰድሽና የራሴ ላድርግሽ ያለኝ አድርጌ ነው የወሰድኩት። አሁን ግን ተረጋግቼ ሳስበው እሱ በእኔ ልብ ስለበቀለው ሴጣናዊ ሀሳብ በምን መንገድ ሊያውቅ ይችላል?። ቢያውቅማ እንኳን ለፍቅር ሊጠይቀኝ በጓደኝነትም ከጎኔ ሆኖ ለማውራት ያፍርብኝ ነበር።እንዲሁ በነገሩ ስብሰለሰል አንድ ወር አሳለፍኩ ..ድንገት ግን አንድ ነገር በአእምሮዬ ብልጭ አለልኝ...ለፀሎቴና ለለቅሷዬ እግዚያብሄር የላከልኝ መልስ ቢሆንስ?።ከእዚ በልቤ ከበቀለው ክፍ ሀሳብ ሾልኬ የማመልጥበት የድህነት መንገዴ ቢሆንስ...?አዎ የመስፍኔን ጥያቄ መቀበል አለብኝ"ስል ወዲያውኑ ወሰንኩ።ወዲያው አእምሮዬ"ሪች ግን እኮ አታፈቅሪውም ?"ብሎ አስጠንቅቆኝ ነበር።የሰጠሁት መልስ ግን"አይ ግድ የለም የማፈቅረው ወንድሜ ጋር ያልሆነ ነገር ውስጥ ገብቼ ዘላለሜን ስፀፀት ከመኖር ለጊዜውም ቢሆን የማላፈቅረውን ሰው አግብቼ እድሌን ልሞክር"አልኩት።ከዛም ብዙም ጊዜ ሳላጠፋ ውሳኔዬን ለመስፍኔ ነገርኩት።ውሳኔዬን በደስታ ተቀብሎ ሽማግሌ ለቤተሠቦቼ ለመላክ ዝግጅት ጀመረ፡፡ይሄንን ጉዳይ ለእዬቤ የነገርኩበት ቀን ትዝ ይለኛል።ማታ ነው።ክፍላችን ገብተን ልብሳችንን አወላልቀን አልጋችን ላይ ወጥተን ጋደም ካልን በኃላ ነበር።
"እዬቤ"
"ወዬ ሪች"
"አንድ ነገር ልነግርህ ፈልጌ ነበር"
"ንገሪኛ..ቶሎ በይ እንቅልፍ ሳያሸንፈኝ"
"ማለቴ እንትን..?"
"እንትን ምን?"
"ማለቴ……››ጨነቀኝ…እኔ እራሴ ውስጤ ያላመነበትን ነገር እንዴት አድርጌ በቀላሉ ልነግረው እችላለሁ?
"ሴትዬ ጤነኛ ነሽ...የሆነ በፍቅር ጠብ ያደረገሽን ወጣት የፍቅር ጥያቄ ልትጠይቂ እኮ ነው የምትመስይው።
"ላገባ ነው"አፈረጥኩት፡፡
"ምን ?ምን?
አልሰማሁሽም"
"ላገባ ነው"
"ማግባት ማግባት….ባል ማለትሽ ነው....?"ከተኛበት ተነሳና ቁጭ አለ...ወደታች አይኔን እያየ አፈጠጠብኝ።
‹‹ የፈራሁት ደረሰ›› አልኩ በውስጤ...፡፡
"ምነው ከሁለት ወር በኃላ እኮ 18 ዓመት ይሞላኛል።"
"እና 18 ዓመት ሞላሽ ማለት ለማግባት ብቁ ሆንሽ ማለት ነው?"
"አዎ"
"ያምሻል እንዴ?ለመሆኑ ይሄ ባል ከየትኛው ፕላኔት ነው እንዲህ ድንገት ድብ ያለው።"
"ከዚሁ"
"ማነው ሰውዬው?"
"መስፍን"
"መስፍን? መስፍን ?አውቀዋለሁ፡፡"
"አዎ...አስተማሪው..ሰንበት ትምርት ቤት…››
"እንዴ!! መስፍን ዘገየ እንዳይሆን?"
"አዎ ነው"
"እኔ ይሄንን እንዲህ በቀላሉ ላምን አልችልም...?ብሎ መልሶ ጥቅልል ብሎ ተኛ ።
"እዬቤ›› "
"በቃ ደህና እደሪ…. አሁን ምንም ማለት አልችልም፡፡"
‹‹የዛን ቀን ነገሮች በዚህ ሁኔታ አለፉ...አምኖ ለመቀበል አንድ ወር አካባቢ ፈጀበት..፡፡ከዛ በድርድር ተስማማን...፡፡ትምህርቴን ሳልጨርስ እንዳላገባና ማትሪክ ከመጣልኝ ዪኒቨርሲት ገብቼ ለመማር መስፍን ፍቃደኛ መሆኑን አረጋግጪ አለኝ።ለመስፋን ነገርኩት ፤እስማማለሁ አለ።በቃ ሰላም ወረደ።ሽማግሌም ተላከ...፡፡ቀለበት አሰረልኝ።ይፍዊ እጮኛው ሆንኩ።ቀስ በቀስ በእኔ ምክንያት እዬቤና መስፍኔ እየተቀራረብ መጡ። ስንኮራረፍ የሚያስታርቀን ስንጨቃጨቅ የሚያግባባንን ሀሳብ የሚያፈልቅ የነገር አባታችን ሆኖ እርፍ አለ…እናም እንደዛ በመሆኑ አንድአንዴ ይከፋኛል አንዳንዴም ያበሳጨኛል።

👍47🔥1🥰1😁1
///
አንብቤ ስጨርስ ስቅስቅ ብዬ እያለቀስኩ ነበር በእውነት ይሄን ያህል እንደተሰቃየች በፍፅም አላውቅም ነበር…መስፍንንም ያገባችው ወዳው እንጂ ከእኔ ፍቅር መሸሻ እንዲሆናት እንደሆነ ለአንዲትም ደቂቃ ተጠራጥሬ አላውቅም፡እንደዛ አይነት ትንሽ ትርጣሬ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ መስፍንን እንድታገባው ፍፅም አልፈቅድላትም ነበር፡የእሷ ውሳኔ እኮ ማስተዋል የጎደለውና ከድጡ ወደማጡ የሚባል አይነት ነው፡፡አንድ ሰው ወደ ጋብቻ ሲገባ በፍፅም ልቡ ፈቅዶ በፍፅም ነፍሱም አፍቅሮ መሆን አለበት …በተለይ ጋብቻው ሀይማኖታዊ ሲሆንና እሷ እንዳደረገችው በተክሊል ሲሆን ደግሞ ፍፅም በእውነት ላይ የተመሰረት…በፍፅም ፍቃደኝነት ላይ መስረት ያደረገ መሆን አለበት …የእሷ ወሳኔ ግን በመንፈሳዊ አይን አይደለም በስጋዊ አይን እራሱ ሊያደርጉት የማይገባ የማይረባ ውሳኔ ነበር፡እና ለዚህም እኔም ከእሷ እኩል በደለኛ ነኝ….ለዚህም ይሄው እሰከዛሬ እየከፈልኩበት ነው..፡
✨ይቀጥላል✨

👍28❤1👏1
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
"ይእ!ጥሩ ነው እንጂ ካርለቴ ባልሽ በመታሽ ቁጥር የፍቅር ጥገትሽ ይጨምራል ለባልሽ የሚያስገሳውን ፍቅር ትሰጭዋለሽ እሱም እንደ ክረምት ዝናብ በፍቅሩ ያርስሻል ያን ጊዜ ይበልጥ
ትቀራረባላችሁ
በሐመር ሴት ሁለት ሶስት እስት ትወልድ ድረስ ባሏ
እንዲመታት ሰበብ ትፈጥራለች ልጃገረድ እያለሽ በኢቫንጋዲ
ላይ ዘመድሽ አብረሽኝ አልደነስሽም ብሎ ወይ ሌላ ምክንያት ፈጥሮ ይገርፍሻል" ዝምድናውን ለማጥበቅና አንድትግባቡ መፈለጉን ስለምታውቂ አትቀየሚውም ዘመድሽ ካልገረፈሽ ጠልቶሻል ወይንም ተቀይሞሻል ማለት ነው" ችግር ቢመጣ አይደርስልሽም
"ዘመድሽ ከብት ሲዘል እየፎከርሽ የምትገረፊውም የእሱን ዝምድና ለመግለፅ ሲሆን ያን አይቶ መከታሽ ይሆናል" ባልሽ ዘንድ
ስትሄጂም እንዲቀርብሽ:
ዘመድ እንዲሆንሽ
እንዲመታሽ ታደርጊያለሽ ያኔ ይመታሽ ይመታሽና
የኔ ሸጋ ... የኔ ወለላ
አርጊ ያልኸኝን ከአሁን ጀምሮ አንተን
አደርጋለሁ ስጭኝ ያልኸኝን እሰጥሃለሁ ማስደሰትና ልጅ መውለድ ይሆናል ስራዬ ስትይው እንደ ማሽላ
ዱቄት አፍሶ ደረቱ ላይ ነስንሶሽ ጫካ ውስጥ ይገባል አንች ደግሞ
እንደ አለቅት ደረቱን እየበሳሽ ሙቅ ልቡ ወስጥ ትገቢና ጎዝጉዘሽ
ትተኛለሽ ልቡ ውስጥ ሆነሽ ጡትሽን ሲዳስሰው ሁለመናሽን ሲያሸው
ለሴት ልጅ ከዚህ የበለጠ ምን ደስታና ጣእም ያለው ህይወት ይኖራታል!" አለች ጎይቲ ያቆመችውን ፀጉር መስራት ለመጀመር ካርለትን ወደ ጉያዋ ሳብ እያደረገቻት።
"ጎይቲ ታዲያ ዱላ ለሐመር ሴት የፍቅር መግለጫ ነው?"
"ይእ! ልጃገረድ ሆነሽ ዳንስ ቦታ የለመድሽው ፍቅር ባልሽ ዘንድ ስትሄጂም የሚጠብቅሽ ፍቅር ዱላ ነው"
"እናንተ አገር የፍቅር መግለጫችሁ ምንድን ነው?"
"መተሳሰብ: መሳሳም …"
"ይእ! ታለ ግርፊያ መተሳሰብ የተኮመታተረው ስሜትሽ ተመታቶ ሳይፍታታ መሳሳም በአፍንጫዬ ይውጣ! ምን ኑሮ ነው
እቴ!"
"ስላለመድሽው እንጂ …"
"ይእ! በይ ዝምበይ
እኔ የሌሎችን ነገርሁሽ እንጂ እኔማ ልምዴን ተገፍፌ እንደ ምትታለብ ላም ዳሌየንና ጡት ስሬን
የሚያሽ ባል አግብቻለሁ" እንዲያው ግን ካርለቴ ከሎ የልምዴን ሰጥቶኝ እንዲህ ማህፀኔ ቢደርቅ እኮ አይከፋኝም ነበር, ከዛሬ ነገ
ወንድ ወንድ ይሸተኛል ስል ከዛሬ ነገ የወንዶችን ለበቅ ያነሳል ስል ዕጣ ፋንታዬ እንዲህ ይክፋ ካርለቴ!" ብላ ምርር ብላ አዘነች
"አዝናለሁ ጎይቲ
ግርፊያ ለሐመር ልጃገረድ እንዲህ እንደ ውቅያኖስ ወለል የጠለቀ ትርጉም ያለው አይመስለኝም ነበር!
ስትላት ጎይቲ ውቅያኖስ ያለችው ባይገባትም
"ይእ! የአባት ደንብ አይደል ካርለቴ እናትሽ ባልሽ ዘንድ
ከመሄድሽ በፊት ባልሽ ሲመታሽ አታልቅሽ የባልሽ ጓደኞች ወደ ቤትሽ ሲመጡ ከጎሽ ቆዳ የተሰራ ጫማቸውን ጠመንጃቸውን ተቀብለሽ ተቀብለሽ ቤት አስገቢ ቀጥለሽ ከውጭ ቁርበት አንጥፈሽ ሸፈሮ ቡና አፍይላቸው" የባልሽን የአደን ጓደኛ ሚሶ'
የዝላይ ወቅት ጓደኛውን ባርግያ በይ በባራዛ አርጩሜ ገርፈው
ምን ተሰማሽ? ሲሉሽ ፈገግ ብለሽ ምንም በያቸው ያን ጊዜ በማርና ወተት ያደገች ተጨዋች ናት ብለው ይግባቡሻል" ለባልሽም
አንችን አሞጋግሰው ስለሚነግሩት ይቀርብሻል"
"ሲመቱሽ ካለቀስሽና አንገትሽን ከደፋሽ ግን ከብትና ፍየል አልጠበቀችም ቀፎ አልሰቀለችም ድሀ አደግ ጨዋታ የማታውቅ
እንደ አነር ቁጡና ክፉ ናት ብለው ይጠሉሻል" ያን ሲሰማ ደግሞ ባልሽም ይጠላሻል ይርቅሻል ውሎው ከሌላ ሴት ጋር ይሆናል እያሉ ዘመዶችሽ መክረውሽ አለት ድንጋይ ልብሽ ውስጥ ጨምረሽ
ጠንካራ እሆናለሁ ብለሽ ባልሽ ዘንድ ሄደሽ የጠበቅሽውን ሁሉ
ስታጭው ምነው አትራቢ ምነው አታዝኝ!" ብላ ጎይቲ እንባዋን ፀጥ ብሎ እንዲፈስ ከፈተችው
ካርለትም ዐይኖችዋ በእንባ እንዳቀረዘዙ ጎይቲን እያባበለች አንድ ቃል በህሊናዋ ብልጭ ብሎ ድርግም አለ ፈለገችው
ያን ቃል ፈረንሳዮች ፍላጀላሲዬን ይሉታል እንግሊዞች ደሞ
ፍላጄሌሽን ደስ አላት ህሊናዋ ከትውስታው ክፍል ጀባ ያላትን ቃል ወደ ኖረበት ተመልሶ ሳይገባ አፈፍ አድርጋ ስለያዘችው
ፍላጀላሲዬን ስርዓት ባለው ወይንም ሃይል በተሞላበት
መንገድ በሃይማኖት ተከታዮች የሚፈፀም ግርፊያ ነው" በብዙ
የሃይማኖት ተቋማት ፍላጀላሲዬን በመባል የሚታወቀው ግርፊያ
የርኩስ መንፈስ የማስወጫ ስልትና መፈወሻ ዘዴ ተደርጎ ይቆጠራል"በጥንት "ዘመን የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በግርፊያ መሰቃየትን እንደ
አምልኮዋዊ ፀጋ ይቆጥሩት ነበር በነዚህ ህዝቦች እምነት መገረፍ ወይን በአካላዊ ጉዳት መሰቃየት ከሃጢያታቸው መንፃታቸውን፥ከመቅሰፍት
መዳናቸውን የሚያረጋግጡበት
ሆኖ ሲታመንበት ቆይቷል
በሰሜን አሜሪካ ህንዶች: በስፖርታዎችና በሮማውያን
ግርፊያ የአማልክትን ወይንም የቅድመ አያቶችን
ምስል ጭንብል
ባጠለቀ ገራፊ የሚፈፀም ነበር" ይህ ድርጊት በአስራ ሶስተኛው ክፍለ
ዘመን አጋማሽና በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመንም ቀጥሎ እንደ ጀርመን: ሆላንድ በመሣሰሉት አገሮችም ተስፋፍቶ ቆይቷል በብዙ አገሮች በበዓላት ቀን ወንዶች ጀርባቸውንና ደረታቸውን በአለንጋ
ይገረፋሉ።
ይህ አምልኮዋዊ እምነት እ.ኤ.አ. በ1349 ዓ.ም እንደነበሩት ፓትሪያርክ ክሌመንት በመሳሰሉ የሃይማኖት አባቶች ከረር ያለ ተቃውሞ ግርፊያ እየቀነሰ ቢመጣም በአሁኑ ዘመንም በደቡብ
የአውሮፓ ሀገሮች በላቲን አሜሪካውያንና በመካከለኛውና ሩቅ
ምስራቅ አገሮች የተለመደ ነው ለምሳሌ በታይዋን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በየአመቱ በስቅለት ቀን እንደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መገረፍ: መሰቃየት: እጅና እግርን በሚስማር መቸንከር
የእየሱስ ክርስቶስን ፍቅር እንደ ማግኘት ምድራዊ ሃጢያትን እንደ መቀነስና ለሰማያዊው ህይወት በክብር መዝገብ እንደመመዝገብ
ይቆጠራል
ከዚህ ውጭ ግን ዘመንሁ በሚለው ህብረተሰብ በሁለቱም ፆታ ግርፊያ በብዙ ግለሰቦች የወሲብ ስሜት መቀስቀሻ ወይንም የወሲብ ስሜት ማርኪያ ስልት እንደሆነና የገራፊ ልብሶችና የመግረፊያ
አለንጋዎች የሚሸጡባቸው የወሲብ ሱቆች
በርካታ እየሆኑ
መጥተዋል እኒህ ግርፊያን እንደ ወሲባዊ የችግር መፍትሔ የሚቆጥሩ
ሰዎችን የስነ አዕምሮ ጠቢባን የስነ-አዕምሮ
ችግር ያለባቸው እንደሆኑ በመቁጠር ብዙ መላ ምቶችን እየደረደሩ ቢሆንም
የመገረፍ ፍላጎት ወይንም ሱስ ግን አንድም የተፈጥሮ ባህሪ ውጤት ወይንም እምነት የፈጠረው ፍላጎት ስለመሆኑ አያጠራጥርም ብላ አሰበችና የሐመሩ ግርፊያም ባህላዊ እምነት የፈጠረው የህሊናና
የአካል ዝግጁነት ውጤት ነው ብላ ደመደመች።
እየጨለመ ሲመጣ የእሳቱ ወጋገን ይበልጥ እየጎላ እየጎላ መጣ ወጣቶች ለስነ-ስርዓቱ ከሰበሰቡት እንጨት በተጨማሪ ከጫካ
ግንዲላውን: ጭራሮውን እየተሸከሙ እያመጡ ይከምራሉ ጥቂት ጎረምሶች ደግሞ ለወጠሌ ጥብስ የሚሆነውን ችካል በጩቤያቸው ይጠርባሉ ሌሎች የእድሜ ጓደኛ ጎረምሶች ደግሞ ከሳቱ ርቀው ተሰብስበው ያወጋሉ፤ አንዳንዴም
በተቀቡት ዥንጉርጉር የአኖ ቀለም ከሹልሹላቸው
ለዳንሱ ዝግጅት
የሰጎን ላባ ሰክተው
ጨሌያቸውን አንገታቸው
ላይ ደርድረው ግንባራቸው ላይ የጨሌ ገመድ
ቋጥረው ዳንሱንና ድሪያውን ናፍቀው ውስጥ ለውስጥ ይቋምጣሉ አልደርስ ብሏቸው"
"ሚሶ!" አለ አንዱ
አለ አንዱ ከመሀላቸው የአደን ጓደኞቹን የሰአት ማሳለፍያ ጨዋታ ሊያወጋቸው።

👍25
ሚሶ አሉት እነሱም እንደደንቡ የአደን ጓደኞቹ ሲጠራሩም ሆነ ሲጨዋወቱ ስም አይጠራሩም ቀረቤታቸውን መግባባታቸውን ጓደኝነታቸውን የምትገልፀው ቃል ሚሶ የምትለው ቃል ናት።
የወኛርኪ መንደር ጎረምሶች አደን ወርደው ሁለት አንበሳ
ገለው መመለሳቸውን ሰምታችኋል?"
"ኧረ የለም! ከማን ሰማህ አንተ?"
"እኔማ ትናንት ሌሊት ሽማግሎች ልከውኝ ሄጀ ነበር
"እነማን ገዳይ ተባሉ እህ?" ሁሉም የሚለውን
አቆበቆቡ
"አይኬና ቦዳ ናቸው" አለ ረጋ ብሎ
"ቀንቷቸዋላ! እኛ ነን እንጂ አሸዋ ላይ ስንተኛ ቀኑ ነጎደ
ምናለ ወንድነቱ እንዲደርሰን
እኛስ ብንሄድ?" አለ አንዱ
ከመካከላቸው
"እኔ በበኩሌ ልቤ ተነስቷል እንኳን ይኸን ሰምቼ" አለ ሌላውም።
"በፊት ቆይ አስኪ ያየሁትን ላውጋችሁ የሰው ጨዋታ
አታቆርፍዱ!" አለ መጀመሪያ የተናገረው ጎረምሳ
"እስቲ አውጋን?"
"ዛሬ ረፋዱ ላይ ከብት ልፈቅድ ስሄድ አይ የአየሁት ነገር!"
"ምን አየህ?" ጓጉ ጓደኞቹ ለመስማት
"እኔ ሳያቸው መጀመሪያ ደነገጥሁ ተዚያ ልቤን ድንገት ነሸጥ አደረገኝ እንዲያው ምን ልበላችሁ አቁነጠነጠኝ
"እ! አትናገርም ምን እንዳየህ?" ጓደኞቹ የመስማት ጉጉታቸው ይበልጥ ጨመረ።
"እእ! ጎዳናውን ለቅቄ ሽንቴን ልከፍል በዛፎች ከለል ስል
ኮሽታ ሰማሁ ያች መናጢ ቀበሮ መስላኝ ወደል ድንጋይ አማትሬ
አንስቼ አድፍጬ ዛሬ በጠዋት እጄ ላይ ጣለሽ አንች መናጢ! እያልሁ ቅጠሉን ከለላ አድርጌ ስሳብ የሰው ድምፅ ሰማሁ እነማን ይሆኑ ደግሞ ብዬ በቅጠሎች ተከልዬ አጮልቄ ሳይ ሴትና ወንድ
ናቸው።
ማንና ማን ይሆኑ? እያልሁ አፍጥጬ ሳይ ኮቶ ናት
የእኛዋ አጠገቧ ቦዳ አለ የገደለውን አንበሳ ጎፈር
ደፍቶ ኮቶ የወሰደችለትን በለሻ በወተት እያማገ
ይውጣል" እሷ አንዴ በጀርባው አንድ ጊዜ ደግሞ ከፊት ለፊቱ እንደ ድመት
በዳሌዋ እየታከከች ጨሌውን ታስተካክላለች
ጎፈሩን ትነካካለች
እሱ ግን በለሻውን እንደ ኮንሶ ልቃቂት እያዥሞለሞለ እየጎረሰ ወተቱን በላዩ ላይ እየሰመጠጠ ያላምጣል እእ! ያን ሳይ እህል
ቀምሼ የማላውቅ ይመስል ወስፋቴ እሪ! አለ
ትናንት ወኛርኪ ሄጄ አይቸው ተምኔው እዚህ መጣ? ኮቶንስ እንዴት አገኛት? አይ የሐመር ልጃገረድ ገዳይ ስታነፈንፍ ማን ይስተካከላታል! እያልሁ ሳስብ እኔን ቅጠል አልብሰው ገትረውኝ አፍ ላፍ ገጠሙላችኋ! ገጠሙ ገጠሙ.. ለካ ሴትና ወንድ አፍ ላፍ ሲገጠሙ ለተመልካቹ የሚነካከሱ ነውና የሚመስሉት! አንገቷን ቆልምሞ ሲነክሳት ሲጨባብጣት ኮቶ
ታሁን አሁን ጮኸች ብትጮህ ምናባቴ ነው የማደርግ ልገላግል
ብሄድ በጥርሷ ነው የምትዘለዝለኝ ስል ኧረ እሷ እቴ! ከቅንቡርስ
እንደምትታገል ጉንዳን
ግብግብ ስትገጥመው ብታዩ ይደንቃችኋል አይ ጥንካሬ! ጅማት ናት ጅማት! እንኳን ልትጮህ ድምጿ ይሰማልጀ መሰላችሁ
ስትሞጨሙጨው!
ቁልቁል ሆና ሽቅብ
ያን ሳይ እኔ ምንም የማላውቅ የእቅፍ ጨቅላ
ሆኜ ቁጭ!" ብሎ ዝም አለ
"እእ! በለው ..." እያሉ አውካኩ ጓደኞቹ
ኧረ ይገርማችኋል ታሁን አሁን ተላቀቁ ስል እነሱ
እየተተካኩ: ላይና ታች እየሆኑ ሲናከሱ ፈዝዥ እንዳለሁz
"እእ! ሲሰሙት ዘላለም የሚጥም ጉድ እሽ ተዚያ በኋላስ? ኧረ ባክህ ቶሎ ጨርሰው ." አለ አንዱ ጎረምሳ አቋርጦት
"እየነገርኳችሁ
ተዚያማ ለእነሱ እኔ ፈርቼ ድንገት የሐመር መንገደኛ ቢመጣ ምን ይውጣቸዋል ብዬ ዞር ብዬ ቃኝቼ
አንገቴን እስትመልስ ጠላታችሁ ጥፍት ይበል' ኮቶ ጠፋችብኝ ምኑ
ይክተታት ምኑ ጥፍት አለችብኝ ሄደች እንዳልል ድምጿ ይሰማኛል አለች እንዳልል አትታየኝም
ለካስ አጅሪት " ብሎ
ዝም ሲል ጓደኞቹ በግድ ጎትጉተው የሆነውን ሰሙ"
"ሚሶ!" አለ ሌላው ደግሞ
"ሚሶ!" አሉት"
"ኧረባካችሁ አደን እንውረድ ተው ቀናችን አይለፍ?"
"እኔ በበኩሌ ፈቃደኛ ነኝ
የማይመቸው አለ?"
"ተመቼን አልተመቼን ጠፍተንም ቢሆን መሄድ ነው እንጂ
"መቼ እንውረድ እህ?" ተባብለው አስራ ሰባት ላይ ልጥ ቋጠሩ ለቀጠሮው ቋጠሮ በየቀኑ ቋጠሮውን በመፍታት በተስማሙበት
ትክክለኛ ቀን ለመሄድ
"ሚሶ!"
"ሚሶ!"
"ካርለቴን ደልቲ ሊያገባት ነው አሉ እንግዲህ ዝም ልንላት ነው?
"እእ! ይኸውላችሁ ጨዋታችንን ሊያቆረፍደው ነው ድፍን አገር የሚያውቀውን ነገር ምን አዲስ ጨዋታ አለው ብለህ ነው፤ አዲሷ ተእንግዲህ በዘመዶችዋ መጎንተሏ የት ይቀራል" ብለው አፍ
አፉን አሉትና ተሳሳቁ
"እእ! ምንድነው ጊዜው ረዘመ'ሳ!"
"አይዞህ! ሌሊቱ ብዙ ነው
አንላቀቅም "
"ባራዛ አርጩሜ ቆርጣችኋል?" ብሎ ጠየቀ ከመሃላቸው አንዱ።
"እእ! እሱ መቁረጣቸው ለመግለፅ ሌሎች ከዚህ ሌላ ጨዋታ ጀመሩ የምሽቱ ጭፈራ እስኪጀመር"
💫ይቀጥላል💫

👍29🔥2👎1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
///
ከጄኔራሏ ጋር የነበረን የጋለ የፍቅር መሳሳብ ቀስ በቀስ እየተዳፈነ የጓደኝነት ቁርኝታችን እየጠነከረ መጥቶል፡፡ይሄን አይነት የስሜት ለወጥ በመከሰቱ ልደሰት ወይስ ይክፋኝ እስከአሁን መለየት አልቻልኩም፡፡ ነግቶ ከእንቅልፌ ስባንን እሷ ከጎኔ ተኝታለች..እስክትነቃ ጠበቅኩና
"ደህና አደርሽ?" በሚል በአክብሮት በታሸ ለስላሳ ንግግር ተቀበልኳት፡፡
"አዎ ..ደህና አድሬያለሁ..ነጋ እንዴ?"
አዎ ነግቷል.. አታይውም እንዴ? በክፍላችን ብርሀን ተጥለቅልቆ ደሰ ሲል፡›
‹‹ብርሀን ብቻ ነው እንዴ ደስ ሚለው?››.
‹‹ጨለማማ ያው ጨለማ ነው ምኑ ደስ ይላል?››
ጨለማ ያን ያህል አስፈሪ አይደለም።በድፍረት ላጣጣመው ጨለማ የራሱ ውበት አለው።ጨለማ ደግሞ ከብርሀን በላይ ፈጣን ነው።ሁል ጊዜ ብርሀን በጨለማ ቀድሞ የተያዘውን ግዛት አስለቅቆ ነው አለሁ እዚህ ነኝ የሚለው።እኛም ወረተኛና ፍርደ ገምድል ስለሆን ኃላ ስላየነው አንፀባራቂና ደማቁ ብርሀን አጋነን እናወራለን እንጂ ቀድሞ ቦታው ላይ የነበረውን ጨለማ ትዝ አይለንም፡፡
ከእሱ ማምለጥ ባንችልም መሞከራችን አይቀርም።ደግሞ እኮ የብርሀኑ ውበትና ድምቀት ሙሉ ሆኖ የሚታየው በድቅድቁ ጨለማ ሰንጥቀን ማለፍ ሲችል ነው።ደግሞ ወታደር ብትሆን ለጨለማ ያለህ እይታ ይቀየር ነበር፡፡
‹‹እንዴት?››
‹‹ጨለማ ወሳኝ ወዳጅህ የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚዎች ይኖራሉ...ከጠላት አይታ ከልሎ ህይወትህን ያተርፍልሀል….ከብርሀን በተሻለ መረጋጋተትና ትንፋሽ መውሰጃ ሰላማዊ እረፍት ዕድሎችን ያመቻችልሀል…ኦ እኔ ጨለማ ወዳለሁ…በተለይ ድቅድቅ ጨለማ፡፡
‹‹በስመአብ በይ››
‹‹አልኩ.. አሁን ስንት ሰዓት ሆነ?››
"ሁለት ሰዓት ሆኗል"
"ስራ ትገባለህ እንዴ?"
"ማታ አስራሁለት ሰዓት ነዎ..አንችስ?"
"እኔኮ ስራ የለኝም.?."
"አንድ ጄኔራል ለዛውም በዚህ ጊዜ..."
እጄን ያዘችና ወደ ሆዷ ወሰደችኝ፡፡ ያሳረፈችኝን ቦታ ዳበስኩት፡፡ የታረሰ ቦይ መስሎ ያስታውቃል፡፡ ...ብርድልብስን ከነአንሶላው ገለጥኩና አየሁት እንብርቷን ከፍ ብሎ ወደታች በመውረድ ፓንቷ ውስጥ ድረስ የሚዘልቅ አስፈሪና ሰፊ ጠባሳ አለ፡፡
.‹‹..እስከዛሬ እንዴት ሳላየው?"
"አይኖችህ መቀመጫዬ ላይ ነበር የሚንከባለሉት..ለዛነው ያላየኸው"
"እውነቴን ነው ..ማታ እንኳን እርቃንሽን ሆነሽ ከስሬ ቆመሽ ነበር"
"ባክህ እንዳታየው በዘዴ ስለጋረድኩት ነው"
"ምን ሆነሽ ነው?"
"ቆስዬ ፡፡በጦርነቱ ላይ ቅስዬ ላለፍት ሶስት ወራት በከፍተኛ የህክምና ክትትል ጦርሀይሎች ተኝቼ ነበር...፡፡ገና ከወጣሁ አንድ ወር አይሆነኝም..፡፡.አሁንም ከሆስፒታል ወጣው እንጂ ህክምናውን ሙሉ በሙሉ አላጠናቀቅኩም ...በሳምንት አንድ ቀን ቼክአኘ አለኝ፡፡..እና በአጠቃላይ ከስራ ውጭ ነኝ፡፡
‹‹ስትድኚ ትመለሺያለሽ አይደል?››
‹‹ከዚህ በፊት እኮ ነግሬህ ነበር..መመለስ እንደማልችል ሀኪሞቹ ተስማምተው ፅፈውልኛል...መጀመሪያ ከፍቶኝ ነበር...ቆይቼ ሳስበው ግን ውሳኔውን በፀጋ ተቀብዬዋለሁ።››
"ይገርማል.. ታዲያ እንደዚህ ከፍተኛ ህክምና ላይ እያለሽ ነው እንደዛ አልኮል ስትጠቀሚ የነበረው ።››
‹‹አንድ ቀን ነው የጠጣሁት.. እሡኑም ቦርድ መውጣቴን የሠማው ቀን ..››..
"አረ ተይ...ከሰውዬሽ ጋር የመጣሽ ቀንስ..?"
"እ በቃ..የወታደር ነገር አንዳንዴ እንዲህ ነው...አየህ ከተወረወረ ቦንብ መሀል አምልጠህ የሚንጣጣ መትረየስ ሸውደህ፤ ታንክና ድሽቃ ሳይገልህ በህይወት ተርፈህ አሁን አልኮል በብርጭቆ ስለጠጣሁ ይገለኛል ብለህ ለማመን ይከብድሀል...እና መጠጣት እንደሌለብህ ብታምን እንኳን ትንሽ ከተበሳጨህ ወይም ድብርት ውስጥ ከገባህ እኔ እንዳደረኩት ታደርጋለህ...፡፡
"አሁን ቁርስ ልጋብዝሽ"
"የት እቤትህ ወስደህ"
"አረ እዚሁ ሆቴል"
"እቤትህ ስልህ ምነው ደነገጥክ...ሴትየዋ አለች እንዴ?"
‹‹አይ የለችም"ብዬ ስለጋሽ ሙሉአለም ታሪክ ስነግራት ማመን ነው ያቃታት።
"እሺ እኔ ቤት ሄደን እንዋላ"
"እኔ ቤት ...እዚህ አዲስ አባ ቤት አለሽ"
"አዎ ብዙም ባልጠቀምበትም ቤት አለኝ››
‹‹ታዲያ ቁርስ በልተን እንሂድ?..›
‹‹ምነው ቁርስ መስራት እትችልም አሉህ እንዴ?››
‹‹እስከዛ ይርብሻል ብዬ ነዋ;››
‹‹ለራስህ አስብ ..አንተ ወታደር እኮ ነኝ..አስርና ሀያ ቀን ያለምግብ ያሳለፍኩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ...በል ተነስ ››አለችና …አልጋዋን ለቃ በመውረድ ልብሷን መለባበስ ጀመረች፡፡.
‹‹አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ››
‹‹ጠይቀኝ››
‹‹ስንት አመትሽ ነው?››
‹‹ምን?››ደንግጣ
‹‹አይ ለሌላ እኮ አይደለም….በዚህ ዕድሜሽ እንዴት ይሄ ሁሉ ብዬ ነው፡፡››
‹‹እስኪ ገምት ስንት እሆናለሁ?››
‹‹35››
‹‹ብዙም አልተሳሳትክም…10 ብቻ ጨምርበት፡፡››
‹‹የእውነትሽን ብቻ እንዳይሆን?››
‹‹ምነው አረጀሁብህ?››
‹‹አረ አቋምሽና ጠቀሽወ እድሜ ፈፅሞ አይመሳሰልም››አልኳት የእውነትም ተገርሜ፡፡
ትራስ አስቀምጣ የነበረውን ሽጉጥ አነሳችና የጃኬቷን የውስጠኛ ኪስ ውስጥ አስቀመጠች፡፡..እኔም ለብሼ ጨርሼ ስለነበረ .ተያይዘን ወጣን….ወደሆቴሉ የመኪና ማቆሚያ ፓርክ ነው የወሰደችኝ፡፡
.አንድ አይጣማ ቪታራ ጋር ስትደርስ ቁልፉን ከኪሷ አወጣችና ከፈተች.፡፡መኪና ይዛለች ብዬ ስላላሰብኩ ታክሲ ለመጥራት ስልኬን አውጥቼ ስልክ ቁጥር እየፈለኩ ነበር…ፈገግ አልኩና ገቢና ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ከመንቀሳቀሳችን በፊት ግን ስልኬ ጠራ…ጋሼ ሰለሞን ነው የደወልኝ፡፡ አነሳሁት፡፡
‹‹ሄሎ ጋሼ››
‹‹እዬብ የት ነህ?››ኮስተር ያለ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ሆቴል ነኝ››
‹‹ቶሎ እቤት ና.. ፈልግሀለሁ›
‹‹እቤት ማለት.?››.ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ፡፡
‹‹.አንተ ቤት.. አባዬ አሞታል መሰለኝ››
‹‹መጣጣሁ መጣሁ›ስልኩን ዘጋሁት
‹‹ምነው ችግር አለ?…››
‹‹አያቴ ማለት ጋሽ ሙሉአለም አሞቸዋል መሰለኝ .›መሄድ አለብኝ ይቅርታ››
‹‹…ላድርስህ?››
‹‹ምን ታደርሺኛለሽ…..ከዚህ ገቢ ቀጥሎ እኮ ነው ቤታችን..ደውልልሻለሁ›ተንጠራርቼ ጉንጯን ሳምኳት፡፡
‹‹በቃ ቸው›
ገቢናውን በር ከፍቼ ወጣሁ‹‹..ቁርሱ ደግሞ ለሌላ ቀን ይዘዋወርልኝ.››
‹‹በተመቸህ ጊዜ ደስ ይለኛል.. ነገም ተነገ ወዲያም.. ደውልልኝ…መጥቼ ወስድሀለሁ…፡፡››
እየሮጥኩ ወደቤት ሄድኩ፡፡
//
አያት መድሀኒት ከወሰደና ቀኑን ሙሉ ስንከባከበው ከዋልኩ በኃላ አሁን ከመሸ ተሸሎታል፡፡በአካል ስሩ ባልሆንም ከግድግዳ ማዶ ሆኜ ደህንነቱን እንድከታተል በሀለቃዬ በአቶ ሰለሞን ተነግሮኝ የስራ ፍቃድም ተሰጥቶኝ ስራ አልገባሁም፡፡አሁን ከፍሌ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከእንቅልፌ ጋር እየታገልኩ አያቴም በክፍሉ ውስጥ በተኛበት የልጅና የአባት ወሬ እያወራን ነው፡፡
‹‹አያቴ እርሶ እኮ ፃድቅ ኖት››ድንገት ነው ይሄ አረፍተነገር ከአፌ ሾልኮ የወጣው..ግን ደግሞ ለሽርደዳ ወይም ለማስመሰል አይደለም..የእውነትም ከልቤ እንደዛ ነው የማምነው፡፡

👍42👏2❤1
‹‹ተው ሰው ፃድቅ አይባልም…የሰው መልካም ስራ ሆነ ክፉ ስራ ዘላቂ ሊሆን አይችልም…››
‹‹ማለት?››
‹‹ሰው የክፋትና ፤መልካምነት..የደግነትና፤ ንፍገት …የብርሀን እና የጨለማ ቅይጥ ስሪት ነው፡፡ አሁን ብርሀን ጎኑን ያሳይህና ከሁለት ቀን በኃላ ጨለማ ወርሶት ታገኛለህ፡፡ሰኞ ደሙን ከሰውነቱ ቀድቶ ከሞት ያድንህና እሁድ ላይ አልጋህ ላይ ከሚስትህ ተኝቶ ልታገኘው ትችላለህ…፡፡እንደሰው ግራ አጋቢ የማይጨበጥና የማይተነበይ ፍጥረት መኖሩን እጠራጠራለሁ››
‹‹ያው ጥቂት ይሁኑ እንጂ ልከ እንደእርሶ ቅን እና መልካም ሰዎች እዚህም እዛም አይጠፉም፡፡››
‹‹አይምሰልህ… የትኛውንም ሰው በተመለከተ ስለወቅታዊ ድርጊቱ በነጠላ መናገር እና መመስከር ትችላለህ እንጂ በአጠቃላይ እከሌ እንዲህ ነው ብለህ መደምደም በኃላ መሸማቀቅን ነው የሚያስከትልብህ፡፡ስንት ሰዎች በቆሰሉለት የፓለቲካ መሪ አፍረዋል….?ስንቱ ሰው ባከበራቸው የሀይማኖት አባቶች ተሸማቋል…?.ስንቱ ሰው የማምለክ ያህል በሚወደው አርቲስት ምግባር ልቡ ተሰበሯል?››
‹‹አያቴ ትክክል ኖት…፡፡ ግን ሰውን ሁሉ ሲጠራጠሩ መኖር አይከብድም?››
‹‹ልጄ በሀይማኖት ተቋማት እንኳን ለአንድ ሰው የሠማዕትነት ማዕረግ ለመስጠት አንድ መስፈርታቸው ታውቃለህ?የሰውዬው መሞት ነው ።..ለምን ይመስልሀል?"
‹‹እኔ እንጃ አያቴ››
"በህይወት ያለ ሠው በቀጣይ ምን እንደሚሰራ እና ምን እንደሚያጠፍ ፍፅም መተንበይ ስለማይቻል ነው።ይህ ግለሠብ በእኛ ሀይማኖት ዶግማና ቅኖና መሠረት እንከን አልባና በቅድስናው የተመሰከረለት ብለው አክሊል ከደፉለት በኃላ አንድ አመት እንኳን ሳይጠብቅ ‹‹አይ የእናንተ ሀይማኖት ግድፈት አለበት እስከአሁን በተሳሳተ ጓዳና ነበር ስጓዝ የነበረው በሉ ደህና ሁኑ›› ቢል ወይም በእግዚያብሄር ማመን አቁሜያለሁ ብሎ ቢያውጅ ምን ይፈጠራል? ።እንዲህ አይነት ጥፋት ደግሞ በመሸማቀቅ ብቻ አያበቃም… ተራ በሚባሉ አማኞ ዘንድ ውዠንብር ይፈጥራል…ጥያቄ ያስነሳል...ጥርጣሬ ያጭራል።ታዲያ ይሄንን የሚረድት የሀይማኖት ተቋሞች የፈለገ ክንፍ አብቅለህ በአየር ብትንሳፈፍ እንኳን ሞተህ ከአፈር በታች ቀብረው እስኪያረጋግጡ ድረስ ፃድቅ ነው ብለው አያውጅልህም፤ ሰማዕታችን ነው ብለው በመዝገባቸው አያሰፍሩህም ፡፡
‹‹አያቴ…አሁን አሁን እየተረዳሁት ያለሁት ሰው በጣም ውስብስብ ፍጡር እንደሆነ ነው፡፡››
‹‹ትክክል ነህ…እግዜር ሰውን እንደመልካችን በአምሳላችን እንፍጠር ብሎ አይደል የፈጠረን..ውስብስብነቱን ከእሱ ከባለቤቱ የወረስን ይመስለኛል..በል አንተ ቀልማዳ አሁን ተኛ ፡፡››
እሺ አያቴ ደህና ይደሩ››
‹‹ደህና እደር››

👍57❤5🥰3👏3🔥1😁1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
‹‹አያቴ ዛሬ በጣም አዝኛለሁ…››
‹አይ አንተ ልጅ ..መቼ ነው ዛሬ ተደስቼያለሁ የምትለው….ደግሞ ምን ሆንክ?››
‹‹ስለልጅቷ ነግሬዎታለሁ አይደል?›
‹‹ሥለየቷ… ስለልጅህ እናት››
‹‹እማይደል… እኛ ሆቴል ስለምትመጣው››
‹‹እ. ጄኔራል ውሽማ አላት ያልከኝ››
‹‹አዎ…›
‹‹ምነው? ተተናኮላት እንዴ?››
‹‹አይ ነገሩ ወዲህ ነው…›
‹‹እንዴት..››
‹‹በቀደም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕረግ እድገት ከሰጣቸው ጀኔራሎች መካከል አንዷ እሷ ነበረች››
‹‹ምን?››
‹‹አዎ ወታደር መሆኗን ሳላውቅ ..ጄኔራል ሆና አገኘኋት››
‹‹እርግጠኛ ነህ..በመልክ መመሳሰል ወይም መንታ እህት ኖሯት ይሆናል››
‹‹አይ አያቴ እንደዛ አይደለም..ማታ እቤት ከገባኁ ቡኃላ ሳይሰሙኝ ቀስ ብዬ ወጥቼ ወደሆቴል ሂጄ ነበር›
‹‹አንተ ቀልማዳ ምን ለመፍጠር…›
‹‹ቤርጎ ይዛ ስለነበረ አግኝቼ ልጠይቃት..እና እውነት መሆኑን አረጋጣልኛለች፡፡››
‹‹ታዲያ ይሄ ይደንቃል እንጂ ምኑ ያሳዝናል….እርግጥ ይገባኛል…አንተ የምታስበው ፍቅር እውን የመሆን እድል የለውም ብለህ ልታስብ ትችላለህ..እንደዘ ብታስብ አይገርምም፡፡ ማንም ባንተ ቦታ ቢሆን በተለየ መልኩ ሊያስብ አይችልም..ግን ማወቅ ያለብህ መቼም ቢሆን ፍቅር ምክንያታዊ ሆኖ አለማወቁን ነው፡፡እና በፍቅርና በጦርነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው›› የሚባለው ለምን ይመስልሀል፡፡ምንም ያልተገመተ እና ያልታቀደ ነገር መከሰት በፍቅርና በጦርነት ውስጥ ተደጋሞ የሚስተዋል እውነት ስለሆነ ነው፡፡
‹‹አያቴ ትክክል ኗት፤ እሱ እንዳለ ሆኖ እኔ ያዘንኩት ግን በአሁኑ ጦርነት ክፉኛ ተጎድታ ለሶስት ወር ሆስፒታል እንደነበረች ነገረችኝ…..››
‹‹ያሳዝናል….ድሮስ ከጦርነት ምን መልካም ዜና ይሰማል.››
‹‹አዎ እንደነገረችን ከሆነ ለአንድ ወር ሙሉ እራሷን አታውቅም ነበር..ከተንቤን በረሀ ተጭና አዲስ አበባ እስክትመጣ ..ኦፕራሲዬን ሲሰራላት ሁሉንም አታስተውስም…ጓደኞቾ እንደነገሯት አንጃቷ ሙሉ በሙሉ ተዘርገፎ ከተዝረከረከበት ተፋሶ ወደውስጥ ተመልሶ ነው ልትተርፍ የቻለችው …
ጠባሳዋ ከእንብርቷ ከፍ ብሎ ወደታች ከ20 ሴ.ሜትር በላይ ይረዝማል…እንደተነገራት ከሆነ ማህፀኗም ተቆርጦ ስለወጣ ከአሁን ወዲህ መውለድ አትችለም….. ለሀገሯ ደሞን ማፍስ ብቻ ሳይሆን …..››
‹‹በቃ በቃ ልጄ…በህይወት መትረፎም አንድ ተአምር ነው….ሌላው በሂደት የሚታይ ነው፡፡››
‹‹አያቴ እንዲህ መስዋዕት የሚከፈልላት ሀገር የምትባለው ጣኦት ግን ማን ናት?;›
ይህቺን ጥያቄ ለእሷ ብታቀርብላት እርግጠና ነኝ በእንባ ባቀረሩ አይነቾ በሞቀና በደመቀ ስሜት የሚያንሳፍፍ አይነት መልስ ልትሰጥህ ትችል ነበር፡፡እኔ ግን የተለመደው አይነት ቀና መልስ ልሰጥህ አልችልም ፡፡፡ልጄ እንደእኔ ሀገር ሀሳብ ወለድ ፅንሰ ሀሳብ ነው።ቋሚ እውነት አይደለም..ይጠባል ይሰፋል...ይለማል ፤ይፈርሳል ። ቢሆንም ከስነልቧናችን ጋር ስር የሰደደ ትስስር አለው፤ምክንያቱም ዘሬ ምንለውን መንጋ ህዝብ አዝሎ የሚያኖርልን .. ሀይማኖቴ የምንለውን መንፈሳዊ ተቋም የሚያቅፍልን ...መከታዬ ብለን የምንመካበትን ወታደርና ፓሊስ የሚያስገኝልን ….ተወልደን ያደግንበት ስፍራ ብቻ ሳይሆን ወልደንም የምናሳድግበት. .ዘርተን የምናጭድበት…ሞተንም የምንቀበርበት፤መታወቂያ እንጂ ፓስፖርት የማንጠየቅበት ስፍራ ነው፡፡
ሀገር በህይወት ጉዞችን በኑሮ ውጣ ውረዳችን ቀላል ትርጉም የለውም።ከሀገር በላይ ለእውነት የቀረበው እቤታችን ነው..፡፡ .አዎ ሚስታችን የምታስተዳድረው...ልጇቻችን የሚያደምቁት .. የልባችን የመጨረሻ ማረፊያ የአካላችን የየእለት መገኛ ..አዎ ሀገርን እንደ እንቁላል ውሰዷት ...ቅርፊቱ የአገር የመጨረሻው ድንበር ማለት ነው ...፡፡ጠላት በቀላሉ የሚበረቅሰው የመጀመሪያው ከለላ...ከዛ የመሀሉ ነጭ ክፍል የመሀል ሀገር ..ወይም ዋና ከተማ በለው...አስኳሉ ግን እቤትህ ነው ...ሚስትና ልጇችህ ወይም እናትና አባትህ እናም ቤተሠብህ የሚኖርበት ቢላ ቤትም ሆነ ደሳሳ ጎጇ።ግን አጥቂ ጠላት ሲመጣ ገና ከሩቅ ቅርፊቱን እንዳይሸነቁር ነፍስህን አሲዘህ ትፋለማለህ...ደምህን ታፈሳለህ ከዛም ከጨከነ ህይወትህንም ትሰጣለህ...ምክንያቱም ከቅርፊት መሸንቆር በኃላ እንቁላሉ ነጭ ክፍል መዝረክረኩ አስኳሉም መፍረሱ አይቀሬ ነውና...እና ለሀገሬ ብለን ስንፍለም አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የምንለፋበት ዋናው ምክንያት ለገዛ ቤታችን ደህንነት ነው...ለሚስታችንና ልጆቻችንን ለመታደግ ነው።
እስቲ የሀግርህን ሰው ተመልከት ቤት የሚሰራበት መሬት ሲመራ ቀድሞ አጥር ነው የሚያጥረው፡፡ ይህን የሚያደርገው በቀላሉ ሰው ያለእሱ ፍቃድ አልፎ የማይገባበትን..እንስሳ ሳይቀሩ የማይደፍሩትን የግል ይዞታን ለመፍጠር ነው፡፡እቤቱ ቀስ ብሎ ይደርሳል ዋናው ግን ግዛትን ማስከበር ነው የሚል ሳያውቀው በውርስ ያዳበረው እውነት አለው፡፡
ተረታችን እንኳን ባለቤቱን ካናቁ አጥሩን አይነቀንቁ፡፡››የአንድን ኢትዬጵያዊ ግለሰብ አጥር ሄደህ መነቅነቅ ቀጥታ ሰውዬውን በዱላ ከመዠለጥ የተለየ ትርጉም አይሰጠውም…ህግ የመጣስ ሳይሆን የክብር ጉዳይ ነው፡፡እና የሀገር ስሜት እንዲህ ከማንነታችን የተጋመደና የተወሳሰበ እሳቤ ነው፡፡እውነት ሆነ ሀሰባ ወለድ እሱ ብዙም ትርጉም የለውም፡፡ምክንያቱም አብዛኛው የሰው ልጅ የህይወት ፍልስፍና የተቃኘው በእውነት ላይ ሳይሆን በሚያማልሉ አፈታሪኮች ላይ ነው፡፡
‹‹ጋሼ…እሷም ከዚህ በላይ አታስረዳኝም…ግን ዋናው አሁን ምን ላድርግ ?አሳዝናኛለች››
‹‹አይ ልጄ…..ፍታ ያልኩህን ችግሮች ሳትፈታ ሌላ የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ተጎትተህ እየገባህ ነው፡፡ቢሆንም ይቅርብህ አደጋ ስላለው ሸሽተህ አምልጥ አልልህም….ህይወትን በመጋፈጠ እንጂ ሸሽቶ በማምለጥ ምንም የምታተርፈው ነገር የለም…ግን አንድ ነገር ልመክርህ እችላለሁ፡፡
‹‹ምን አያቴ …?››
‹‹ስራህ ቀይር››
‹‹ምን አያቴ?››
‹‹አዎ ከዚህ በላይ አስተኛጋጅ ሆነህ መቀጠልህ ህይወትህን ማባከን ነው የሚሆነው..ደግሞም አስተናጋጅ ሆነህ በቀጣይ እየመጣብህ ያለውን የህይወት ፈተና ተታግለህ ለማሸነፍ ትቸገራለህ፡፡›
‹‹ትክክል ነህ አያቴ..ግን?››
‹‹ግን ምን?››
‹‹ሁለት ችግር አለብኝ..አንድ የሂሳብ ደብተሬ ውስጥ ያለው 70 ሺ ብር ብቻ ነው..በዛ ብር ደግሞ እራሴን ችዬ ምን አይነት ስራ መጀመር እንደምችል አላውቅም…?››.
‹‹ሁለተኛውስ?››
‹‹ሁለተኛውም..ጋሼ ነው….ጋሼ ለእኔ በጣም ባለውለታዬ ነው….እሱ ጎትቶ ባያወጣኝ ዛሬም እዛ ጎዳና ትኬት መኪና ላይ እየለጠፍኩ ነበር ምገኘው…በዛ ላይ አያቴ ከእርሶ መለየትም ዝግጁ አይደለሁም…››
‹‹እኔም ካንተ ለመለየት ዝግጁ አይደለሁም…ለዛውስ ስራ ቀይር አልኩህ እንጂ እቤቱን ለቀህ ወጥተህ ተንዘላዘል ወጣኝ….?.››
‹‹አይ ማለቴ?››
ይሄውልህ ስማኝ..ጋሼ ውለታ ምናምን የምትለውን እርሳው እኔ ነገረዋለሁ…ማለቴ ካለፍላጎትህ እንድትለቅ የፈለኩት እኔ እንደሆንኩ እነግረዋለው…ይሄውልህ ስማኝ እኔ እንደምታየኝ ሽማግሌ ነኝ…ለዛውም የከተማ ባህታዊ ሆኜ ባህት የዘጋሁ…ምን ለማለት ነው ምንም ስራ የመስራት ፍላጎት የለኝም…ግን የተወሰነ ብር ደብተሬ ውስጥ አለ…እና አንተ ደስ የሚልህን ቢዝነስ አጥናና አምጣ እኔ ገንዘብ እሰጥሀለሁ…የጋራ ቢዝነስ እንመስርታለን ማለት ነው፡፡›

👍65👏3😁3🔥1
‹‹እውነቶትን ነው አያቴ?››
‹‹አንተ ቀላማጅ…ስዋሽ አይተሀኝ ታውቃለህ?››
‹‹አይ ለዛሬ እንኳን በራፍን ቢከፍቱልኝ ጉንጮትን አገለባብጪ ብስም እንዴት ደስተኛ እሆን ነበር መሰሎት?››
‹‹ብልጡ ይቅርብኝ ግዴለም…..ግድግዳውን ሳም››
‹አያቴ በጣም ነው ማመሰግነው….እኔ ጋር እንደነገርኮት 70 ሺ ብር አለ.. ደሞዜን ስቀበል 75 ሺ ብር አካባቢ ይሆንልኛል...እንደምንም እርሶ ጋር የተወሰነ ከተገኘ የሆነ ነገር መጀመር እንችላለን..በእውነት በጣም ነው የተደሰትኩት፡
‹‹ልጄ ››
‹አቤት አያቴ››ደንግጬያለሁ…ያን ያህል ብር ከየት አመጣለሁ ሊሉኝ ነው የመሰለኝ…ቢዝነሱ የጋራ ከሆነ እኩል እኩል ብር ማወጣት አለብን ..በዛ ላይ ምንም እንኳን የደሀ ጉልበት ሂሳብ ውስጥ አይገባም እንጂ ቢገባማ ስራውን የምሰራው እኔ ነኝ›› ስል በውስጤ አጉረመረመኩ…አያቴ ግን ተአምራዊ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
‹‹ያንተን ብር ቢዝነሱን ለማጥናት ተጠቀማት..እኔ አንድ ሚሊዬን ብር እሰጥሀለሁ››
ትን አለኝ..ምራቄ ስርኔ ውስጥ ተወተፈ‹‹ምን አሉ አያቴ?››
‹‹ሰምተሀል››
‹‹ይሄማ አይሆንም …ይህ ሁሉ ብር. በዛ ላይ እርሶ እሺ ቢሉ እንኳን ጋሼ አይፈቅድሎትም… ››ጥርጣሬዬን ነው የተናገርኩት፡፡
‹‹አንተ ቀልማዳ..መቼ ነው የምፈልግ ነገር ለማድረግ የአንተን ጋሼ ሳስፈቅድ ያየሀው…ወለድኩት እንጂ አልወለደኝም እኮ››
‹‹ቢሆንም…እንደዛ አይነት ብር ደፍሬ ልቀበል አልችለም››
‹ከችግርሀ ለመውጣት ፍላጎት ካለህ ትቀበላለህ..አየህ እያንዳንዱ ስኬታማ ሰው ቆም ብለህ ብትጠይቀው በአየር ላይ ተንሳፎ አሁን የደረሰበት ቦታ አልደረሰም..እንዲህ አሁን አንተ እንዳጋጠመህ አይት ቅጽበታዊ እድል አጋጥሞት ያንን በምስጋና ተቀብሎ በጥረት አሳድጎና አበርክቶ ነው፡፡አሁን ይሄን እድል ከገፋህ ምን አልባት የዛሬ ሃያ አመትም ተመሳሳይ እድል አታገኝም፡፡
ባለህ እውቀት፤ በቀናነት እና በፅናት ስራህን ስራ፡፡ ከዛ ውጭ ከቁጥጥርሀ ውጭ በሆነ ሁኔታ ብትከስር እኔ ግድ የለኝም..ከእኔ በላይ ከሳሪው አንተ ነህ ብታተርፍም ከእኔ በላይ ተጠቃሚው አንተ ነህ፡፡፡ምክንያቱም እደምታዬኝ በትርፉ ልጃገረድ አላገባበትም….በኪሳራውም እራሴን አላጠፋም፡፡ደግሞ ዝም ብዬ ስለምወድህ ብቻ አይደለም ይሄንን ብር የምሰጥህ በብዙ መንገድ ነገሮችህን ገምግሜና አይቼ ነው..ጓደኛ አታግተለትልም….ወደቤት መግባት ባለብህ ሰዓተ ተቆጪ አለኝ ወይም የለኝም ሳትል ታደርገዋልህ…ስራህ ሰው አየኝ አላየኝ ሳትል በታማኝነት ትሰራለህ… ስላለህ ብቻ ገንዘብህን አትረጭም…..የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሳይሆን በጣም የሚያስልጉህን ነገሮች በመጠቀም በመጠን እና በልክ የመኖር ልዩ ችሎታ አለህ…….ይሄ ደግሞ ብትከስር እንኳን በአንተ ጥፋትና እንዝላልነት እንደማይሆን እንዳማይሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹አያቴ ካሉ ደስ ይለኛል፡፡
‹‹እንግዲህ ተዘጋጅ…. ለጋሼህ ሰሞኑን እነግረዋለሁ..ከዚህ ወር በኃላ አስተናጋጅ ስለማትሆን በድንብ አጣጥመው››
‹‹አያቴ ››
‹‹አሁን ደግሞ ምን ቀረህ?››
‹‹ጥዋት እቤትህ ውሰደኝ ብላ ለምናኝ ነበር….አያቴን እንረብሸዋለን ብዬ እምቢ አልኳት፡፡›
‹‹አይ እንደውም ላወራት እፈልጋለሁ››
‹‹ማለት ከክፍሎት ይወጣሉ? ››
‹‹አንተ ቀልማዳ….የእኔን ወደውጭ መውጣት እንዴት እንዲህ ፈለከው..?እንድኖር አትፈልግ ማለት ነው..?ቢያንስ እስኪ ቃል የገባሁልህ ብር በእጅህ አስገባ››
‹‹አያቴ እርሶ ከሌሉ ብሩ ምን ያደርግልኛል ..ስለሚናፍቁኝ እኮ ነው ….. ደግሞ ይደብራቸው ይሆን እያልኩ እጨነቃለሁ›››
‹‹በል ወሬውን ተውና ይዘሀት ና…ግን ስለአለው ሁኔታ አስረዳት...ልክ ካንተ ጋር እንደማወራው አወራታለሁ..አጫውትታታለሁ፡፡›
‹‹እሺ አያቴ አመሰግናለሁ››
‹ደግሞ ልምድ ስለሌለህ በተዝረከረከ ቤት ዝም ብለህ ጎትተህ እንዳታመጣት፡፡ ለክብሯ በሚመጥን ዝግጅት ነው መምጣት ያላባት.፡፡.ሴት ነች..በዛ ላይ ወታደር ሴት፡፡እና ሀገርህን ወደቤትህ እንደጋበዝክ ቆጥረህ ተዘጋጅ››ብለው ጭንቅላት የሚበላ የቤት ስራ ሰጡኝ፡፡

👍88❤13🥰6🔥5🤔4
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
እንደተለመደው እቤቴ አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ በመተኛት ጣፋጮና ተወዳጇ ልጄ በቴሌግራም የላከችልኝን የእናቷን ዲያሪ በከፍተኛ ተመስጦና ውስጥን በሚሸረካክት የልብ ድማት ያለፈ ታሪኬን እያነበብኩ ነው፡፡
////
ማትሪክ በተቀበልን በአንድ ወር ውስጥ ለሰርግ ሽር ጉድ ተጀመረ..፡፡ለሠርጉ 15 ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ..፡፡በረሽ ጥፊ ጥፊ..ወይም እራስሽን አጥፊ የሚል ስሜት ይተናነቀኝ ጀመር...፡፡እስቲ በፈረሰኛው በግድ ካላገባሽ እቆራርጥሻለሁ ብሎ ያስፈራራኝ ሰው የለ... ሁሉንም ያደረኩት በራሴ ፍቃድና ምርጫ ነው። እንደውም ቤተሠቦቼ በዚህ ሀሳብ እንዲስማሙ ለማሳመን ብዙ ነገር ቀባጥሬ ነበር...እና ታዲያ ?የቁርጡ ቀን ሲመጣ ምነውሳ...?ዋናው ጉዳይ ከእዬቤ እንዴት አድርጌ የምር እለያለሁ ?የሚለው ሀሳብ ነው እረፍት የነሳኝ....፡፡ እርግጥ አውቃለሁ ወደ ጋብቻው የገባሁበት ዋና አላማ ከእዬብ ለመራቅ ከአምላክ የተላከ ልዩና ረቂቅ ዘዴ አድርጌ በደፈናው ተቀብዬው ነበር እንጂ ዝርዝር ጉዳዬች ላይ በደንብ ያሰብኩባቸው አልነበረም። ይታያችሁ ባል ካገባው እኮ አብሮ ማደር ከዛም ያለፈ ነገር ማድረግ የግድ ነው ፡፡ በህልሜም ሆነ በእውኔ ከእዬብ ገላ ውጭ የወንድ ገላ ታስቦኝ በፍፁም አያውቅም።የሚገርመው እናትና አባቴን ጨምሮ የቤቱ ሰው ሁሉ በደስታ ሰክሮ ለድግሱ መሳካት ጠብ እርግፍ ሲል እዬቤ ግን ልክ እንደእኔ በተመሳሳይ ሁኔታ ድባቴ ውስጥ ገብቶ ነበር።አሳዘነኝ።እሱም እንደ እኔ ያፈቅረኝ ይሆን እንዴ?ለመጀመሪያ ጊዜ በአእምሮዬ የተሠነቀረ አስደሳች ጥርጣሬ ነበር ፡፡
ለማንኛውም የሰርጉ ቀን ደረሰ በተክሊል ስለምንጋባ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለሊት ስምንት ሰዓት ነው ቤተክርስቲያን የሄድነው። ግን በተክሊል እንዴት ልንጋባ ወሰንን? እርግጥ ሀሳብን ቀድሞ ያቀረበው መስፋን ነው።ግን እኔም ያለምንም ማቅማማት ነበር እሺ ያልኩት ፡፡ለዚህም ምክንያቴ በዋናነት ሁለት ነው። አንደኛው በተክሊል መጋባት ጋብቻውን ጥብቅ ስለሚያደርገው ወለም ዘለም የሚለውን ልቤን ያቃናልኛል ወይም መስመር ያስገባልኛል ብዬ ስላመንኩ ነው።ሁለተኛው ብዙ የሠንበት ት/ቤት ጓደኞቼ በተክሊል ሲያገቡ ሚዜም ሆነ አጃቢ ሆኚ አይቼ ስለነበረ እኔም አንድ ቀን እንደዚህ አገባ ይሆን የሚል የተደበቀ ምኞት በውስጤ ስለነበረ ያንን ምኞቴን ለማሳካት ያገኘሁትን እድል ለመጠቀም ነበር።
ስርዓቱም ከቅዳሴው ጥዋት ሶስት ሰዓት ተጠናቀቀ።በሰንበት ት/ቤት መዘምራን የሠርግ መዝሙር በመታጀብ ወደ የቤታችን ሄድን።እንግዲህ ምሳ ሰዓት ላይ ሙሽራው ከሚዜዎቹና አጃቢዎቹ ጋር መጥተው እስኪወስድን የተወሰነ ለማረፍና ለመዘገጃጀት የሚሆን ጊዜ ይኖረናል ብዬ ነው።እቤት ከገባን በኃላ ትንሽ ለማረፍ ሞከርኩ እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ ተነሳሁና እየተኳኳሉና እየተቆነጃጅ ካሉት ሚዜዎቼ ጋር ተቀላቀልኩ።እኔም መዘገጃጀት ስላለብኝ ያሳምሩኝ ጀመር...፡፡ሁሉም ደስተኛ ይመስላል... የተከፈተ ጥርስ..የፈገገ ፊት...በማይክራፎን የተለቀቀ መዝሙር እኔ ግን ቅር እንዳለኝ ነው ።ከቤተ ክርስቲያን መልስ ጀምሮ እዬቤን አላየሁትም።የት ገባ?ከአሁኑ በጣም ነው የናፈቀኝ።እህቴን ጠራኋትና ጠየቅኳት..እንዳላየችው ነገረችኝ።ሌላ የምትሰራውን ስራ ሁሉ ትታ እሱን ፈልጋ እንድትጠራልኝ ጠየቅኳት...ሌላ ቀን ቢሆን የራስሽ ጉዳይ ነበር የምትለኝ።በእለቱ ግን ያው የቤቱ ንግስት ነኝና ጥያቄዬን በእሺታ ተቀብላ ልትፈልገው ወጣች።
15 ከሚሆኑ ደቂቃዎች በኃላ ይመስለኛል እየተጎተተ በግድ የፈገገ ግን ደግሞ የዳመነ ፊቱን ይዞ መጣ..ሴቶች የሞሉበትን ክፍል በራፍ ላይ ቆሞ አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ ‹‹ሪች ፈለግሺኝ" ሲል ጠየቀ….ገና ድምፁ ጆሮዬ ከመድረሱ ሰውነቴ በጠቅላላ ነዘረኝ፡፡
‹‹አዎ ግባ››
‹‹ወዴት ልግባ..?››
‹‹ጥፋሬን ቀለም እየተቀባሁ ስለሆነ እኮ ነው..ግባ የማታውቀው ሰው የለም "ብዬ አደፋፈርኩት፡፡ገባና ወደእኔ ቀረበ..እንዲቀመጥ ኩርሲ ከጎኔ አስቀመጥኩለት እያቅማማ ተቀመጠ።እዛች ክፍል ውስጥ የተጠቀጠቁት ሴቶች ጆሮና አይን በጠቅላላ እኛ ላይ እንደሰፈረ አውቃለሁ። ቢሆንም ምርጫ የለኝም።ድምፄን ቀነስ አድርጌ በሹክሹክታ መጠን
"የት ጠፍተህ ነው? ናፈቅከኝ እኮ"አልኩት
"ደክሞኝ ተኝቼ ነበር"
"የት?"ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩት የእኔና የእሱን የጋራ ክፍል አሁን እያተረማመሰነው ስለሆነ ብዬ ነው፡፡
"እቴቴ ክፍል"
"አይንህ ግን ምንም የተኛ ሰው አይን አይመስልም"
እንደዛ ያልኩት አይኑ በርበሬ ይመስላል እንደሚባለው ቀይ ሆኖ ስለደፈራረሰ ነው።
"ተኝቼ ነበር እኮ አልኩሽ...አሁን ለምን ፈለግሺኝ?"ቆጣ አለ፡፡
"አትቆጣኛ"
"አልተቆጣሁሽም"
"አብረኸን ትሄዳለህ አይደል?"
ደንግጦ"የት?"
ለእሱ መልስ ከመመለሴ በፊት ‹‹ተነሡ ተነሱ ሰርገኛው ደረሰ ተዘጋጅ ..››የሚል የማንቂያ ድምፅ ከውጭ ተሰማ…ትርምስምስ ተፈጠረ... የእሱን አደነጋገጥ እስከዛሬም በፊቴ ላይ አለ።በርግጎ ተነስቶ ፊቴ ተገተረ...እኔም ተነስቼ ቆምኩ።ተጠመጠምኩበት..ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ።እንባዬን ዘረገፍኩት እሱም ተንሰቅስቆ ማልቀስ ጀመረ።ሊያላቅቁን መሀላችን ገቡ።
‹‹አረ ቆርበሽ እንዴት ታለቅሺያለሽ?››
"አገባች እንጂ አልሞተች… የምን ሟርት ነው?።››
"አረ ተው ነውር ነው።››
ሁሉም የመሰለውን ተንጣጣ...አላቀቁን ።እዬቤ ተስፈንጥሮ ክፍሉን ለቆ ተፈተለከ።ከፋኝ ።በጣም ከፋኝ።ፈፅሞ ጥሎኝ እንዲሄድ አልፈለኩም ነበር።እጥፍጥፍ አድርጌ ጡቶቼ መሀከል ከትቼ በየሄድኩበት ይዤው ብሄድ ደስተኛ ነበርኩ።..የምሳ ፕሮግራሙ ሲካሄድም ሆነ እኛ ቤት የነበረው ዝግጅት ተጠናቆ ከእኛ ቤት ወጥተን ስንሄድ አይኔ ቢንከራተትም እዬቤን ዳግመኛ ሳላየው ነበር የእናትና አባቴን ቤት ለዘላለም በሚመስል መንገድ ለቅቄ በቅርብ ከተዋወቅኩት እና በቅጡ እንኳን ያለመድኩትን ሰው ተከትዬ የሄድኩት።
ሙሽራው ሙሽሪት..እንኳን ደስ ያላችሁ
የአብርሀም የሳራ-ይሁን ጋብቻችሁ።
እንደዛ እንደዛ እያለ ሰርጉ ተጠናቀቀ ..መሸ ጫጉላ ቤት ገባን ..እግዚያብሄር ይመስገን ፡፡ በተክሊል ስለተጋባንና በእለቱም ስለቆረብኩ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም ነበርና አንድ አልጋ ላይ ብንተኛም ሰውነታችንን እንኳን ሳናነካካ ተራርቀን ተኛን ፡፡የሁለት ቀን የተጠራቀመ እንቅልፍ ስለነበረብኝ የት እንዳደርኩ አላውቅም ነበረ ።የሚገርመው ጥዋት እንደነቃሁ በእጆቼ የሞጨሞጩ አይኖቼን እያሻሸው"እዬብ ነጋ እንዴ?"ብዬ ነበር ጠየቅኩት ።ደግነቱ ክፍል ውስጥ ማንም ስላልነበረ የሰማኝ ሰው አልነበረም። እንደምንም አልጋዬን ለቅቄ በመውረድ ልብሴን እየለበሰኩ ሳለ በሩ ተከፈተና መስፍኔ ገባ፡
"እንዴ ተነሳሽ እንዴ?"ዝም አልኩት።
"ምነው አመመሽ እንዴ?"አለኝ ወደእኔ እየተጠጋ።
ጭራሽ እየታገልኩት የነበረውን ስሜቴን ነቅንቆ አደፈራረሠው...እንባዬን ዘረገፍኩት።
"እንዴ ምነው?ምን ተፈጠረ?"
"እዬቤ"
"እዬቤ ምን ሆነ?››

👍76❤8🥰1😢1
"ናፈቀኝ"አሁን ሳስበው እንደዚህ ማለቴን ማመን ይከብደኛል።ሰው እንዴት እናቱ ሳትናፍቀው..አባቱ ሳይናፍቀው ..እህቶቹ ሳይናፍቁት የአክስቱ ልጅ ይናፍቀዋል..መስፍኔ ነገር የሚበላ ሰው ቢሆን ወዲያውኑ ምን ነበር ሊያስብ የሚችለው?።እሱ ግን አባበለኝ... መጥቶ እንዲያየኝ መልእክት እንደሚልክበት ቃል ገባልኝ ..በዛ ተደስቼ ለመጀመሪያ ጊዜ ጉንጩን ሳምኩት...ደስ አለው።
ቀኑን እንዲህም እንዳም እያለ አልፎ ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ ሆነ። ድንኳኑ በቅርብ ሰዎችና በመስፍኔ ቤተዘመድ እና በጋራ ጓደኞቻችን ተሞልቷል።እኛ ከሚዜዎቻችን እና ከነፍስ አባታችን ጋር መድረኩ ላይ በግዙፍ ጠረጳዛ ዙሪያ ከበን በደመቀ ጫወታ አድምቀነዎል።ይበላል ይጠጣል...ይሳቃል ። እኔ ወሰድ መለስ እያደረገኝ ነው .፡፡.ለሆነ ሀያ ሰላሳ ደቂቃዎች ጋል ባለ ስሜት በጫወታው እሳተፍና ድንገት ሁሉን ነገር ጣጥዬ በድኔን እዛው ጎልቼ ወደወላጆቼ ቤት በራለሁ...
ክፍሌ ትዝ ይለኛል ፤እዬቤ ይናፍቀኛል።በዚህ የተቀባዠረ ስሜት ላይ እያለሁ ድንገት እኛ ባለንበት በጎን በኩል ድንኳኑ ገለጥ ሲደረግ አየሁ "የትኛው እብድ ነው የተንቦረቀቀ በር ከፊት ለፊት እያለለት ባልተገባ ቦታ ለመግባት የሚታገል...? ሰርስሮ አንገቱን ብቅ ሲያደርግ ግን ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለች።እዬቤ ነው...የእኔ ማር...
"እዬቤ"
ድንኳን ውስጥ ያሉ አይኖች ሁሉ እሱ ላይ ተሰኩ ..ሙሉ በሙሉ ወደ ድንኳኑ ገባ።በአብዛኛው ስለሚያውቁት በሞቀ ሰላምታ ነው የተቀበሉት.፡ከእኔ ጎን ተቀምጣ የነበረችው ሚዜዬ መቀመጫውን ለቀቀችለት ..ከጎኔ ተቀመጠ..በአንድ ቀን በጣም ከስቶ ታየኝ..በፈገግታ ለማውራትና በሳቅ ለመድመቅ ይጥራል ..ግን ውስጡ ሀዘን እንደተጠራቀመና የተተራመሰ ስሜት ላይ እንደሆነ በቀላሉ ማወቅ ችያለሁ.. ይሄ ሁሉ የእኔ ጥፋት ነው...እዛ ሁሉ ሰው መሀል እንባዬን ለቀቅኩት፡፡ የድንኳን ሁሉ ድባብ ተቀየረ...በቀኜ ያተቀመጠው መስፍን እና በግራዬ የተቀመጠው እዬቤ ተከሻዬን እየዳበሱ ጉንጬን እያበሱ ያባብሉኝ ጀመር...(ግን ቆይ በግራዬ መቀመጥ የነበረበት ማን ነበር?።)..መጨረሻም በጓደኞቼ ውትወታና በቄሱ ግዝት እንደምንም ተረጋጋሁ።እዬቤም ብዙም ሳይቆይ እንዳመጣጡ ሹልክ ብሎ ሄደ... ስለመጣና ስላየሁት በጣም ብደሰትም ተመልሷ ሲሄድ ግን ሀሉን ነገር ጣጥለሽ ተከትለሽው ሂጂ የሚል መጥፎ ስሜት ነበር የተፈታተነኝ።እራሴን አመመኝ ...መቀመጥ ሁሉ ነው ያቃተኝ።ሁለት ሰዓት ሳይሞላ ወደመኝተ ቤቴ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ፡፡መስፍኔም ቆያይቶ ቢመጣም ሊነካካኝ ሳይሞክር ርቀቱን ጠብቆ ለሁለተኛ ቀን አደብ ገዝቶ ተኛ፡፡

👍55❤8👏2
#እህቴ_በባትሆኚ_አገባ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል። ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ... የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር እስከእርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች እንሆናለን ።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል.. ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር በቃላት ልውውጥ እና በአይን መሠራረቅ ላያልፍ ይችላል።ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቆረጥ ይችላል ወይም እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ "የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ የለንም?።ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ አልቆ ብቻ አይደለም...አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው ጉዞቸውን በተለያየ ጎዳና ይቀጥላሉ።ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።
እንዲህ ስለፍቅር የምፈላሰፈው ከጄኔራሏ ጋር ወደ ቤቷ እየሄድኩ ባለሁበት ጊዜ ነው፡፡በራሷ መኪና ሰፈር ድረስ መጥታ ነው የወሰደችኝ፡፡ …ከ20 ደቂቃ በኃላ ፍፀም ያልጠበቅኩት ሰፈር ይዛኝ ገባች…፡፡አደነጋገጤን አትጠይቁኝ፡፡ይሄነው ቤቴ ብላ የመኪናውን አፍንጫ ወደአንድ ቢላ ቤት በራፍ አዙራ በማስጠጋት የመኪናዋን ጡሩንባ አስጮኸች፡፡
እኔ በራፉ ከመከፈቱ በፊት የመኪናውን በራፍ ከፍቼ ወረድኩና ፊቴና ወደማዶ አዙሬ ፈዝዤ ቆምኩ፡፡.ይሄ እንዴት አጋጣሚ ሊሆን ይችላል..?ከጄኔራሏ ቤት ፊት ለፊት የሚታየው የድሮ ስሪት ቢላ ቤት እትብቴ የተቀበረበት ቤት ነው.. የወላጆቼ ላብ ጉልበት የፈሰበት ጥሪት ሀብታቸው ነው፡፡እዚህ ቤት ውስጥ ነው ደግሰው የተጋቡት፤እዚህ ቤት ውስጥ ነው ተፋቅረው ኖረው ልጅ የወለዱት፤ ከእዚህ ግቢ ውስጥ ነው እሬሳቸው ወጥቶ የተቀበረው….፡፡የዚህ ቤት ወራሽ አሁን እኔ ነኝ፡፡ግን በሞግዚትነት ስታስተዳድረው የነበረችው እቴቴ ማለት አክስቴ ስለነበረች አሁንም በእሷ እጅ እንዳለ ነው፡፡የእሷን አይን ለማየት ድፍረት በማጣቴ ምክንያት ይሄንን ንብረቴን መረከብ አልቻልኩም፡፡በአሁኑ የአዲስአባ ገበያ ባዶ መሬቱ ብቻ ቢያንስ 10 ሚሊዬን ብር ያወጣል.፤አቤቱ ሲጨመርበት ገምቱት..አዎ አሁን እኔ ባልጠቀምበትም ወደፊት ለልጄ ይሆናል ስል ተፅናናሁ፡፡
‹ኸረ ግባ በራፉ ተከፍቷል…ምንድነው እንዲህ ያፈዘዘህ..?››
‹‹እ እሺ ›ብዬ ከደነዘዝኩበት እንደመባነን አልኩና ወደውስጥ ገባሁ፡፡
እሷም መኪናዋን ወደግቢው ውስጥ አስገብታ አቆመችና ወረደች፡፡ለዘበኛው ሰላምታ ሰጠችውና ወደ ውስጥ ገባን ፡፡ግቢው ማህል ላይ እድሜ ጠገብ ትልቅ ቢላ ቤት ያለ ሲሆን ወደ አንድ ጥግ ደግሞ በግምት ሶስት ወይም አራት ክፍል ያለው አዲስ ህንፃ ይታያል…ወደ አዲሱ ህንፃ በረንዳ ላይ ሁለት ህፃናት ይጫወታሉ…
.‹‹ያንን አከራይቼው ነው››፡፡ብላ ወደ አሮጌው ቤት ይዛኝ ገባች፡፡
የድሮ መኳንንት መኖሪያ የመሰለ ባለብዙ ክፍል ቤት ነው፡፡ሙሉ ቤቱ የባለሞያ ጥበብ ያረፈበት ባለግርማ ሞገስ ሲሆን በጥንታዊና ዘመናዊ እቃዎች ስብጥር ተሞልቷል፡፡ለምሳሌ ከወደቀኝ ኮርነር አካባቢ ዘመናዊ የሆነ ባለነጭ ልባስ ሶፋ ሲታይ፤ ከእሱ ፊት ለፊት ፍፅም ባህላዊና ከጠፍርና ከእንጨት የተሰራ ልዩ መቀመጫዎች ይታያሉ፡፡ብቻ ቤቱ መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚዬም ነው የሚመስለው፡፡
‹‹ደህና አደራችሁ?››ብዬ ገባሁ
‹‹ቁልፍ ከፍቼ እየገባሁ እያየህ ደህና አደራችሁ ትላለህ እንዴ?፡፡››
‹‹ምን ላድርግ ይሄንን የሚያህል ግዙፍ ቤት ሰው አልባ አይሆንም ብዬ ነዋ››
‹‹በጊዜውማ ልጇች ትላለህ የልጅ ልጆች ሲተረማመሱበት ነበር.. ቁጭ በል
ቁጭ አልኩ‹አሁንስ?››
‹አሁን ግማሹ የራሱን ቤት እየመሰረተ ወጣ…ሌላው አውሮፓ..የተቀረው አሜሪካ ገብቷል…እኔና ቤቴ ግን ይሄው አለን››
‹‹ወላጆችሽስ?.››
‹›አባቴ ሞቷል ፤ እናቴ ትንሽ የጤና እክል ስላለባት አሜሪካ እህቶቼ ጋር ነው የምትኖረው….መጣሁ ዘና በል…››ብላኝ ወደኪችን መሰለኝ ገባች፡፡
‹‹ለዚህ ቤት አዲስነት አልተሰማኝም..ምንድነው ፊልም ተሰርቶበት እዛ ላይ አይቼው ይሆን እንዴ…?.››ሪሞት አነሳሁና ፊት ለፊት ያለውን ቴሊቭዝን ከፈትኩ..ጄኔራሏ ከነማዕረጎ የተነሳችው ፎቶ በትልቁ ፊተ ለፊት ግድግዳ ላይ ገጭ ብሏል፡፡ በሙሉ አይን ማየት ፈራሁና አንገቴን አቀረቀርኩ…፡፡የሙሉ ቤተሰቡ ፎቶ እዚህና እዛ በተናጠልና በጋራ የተነሱት ቤቱን ሞልቶታል፡፡ሲታዩ የደላቸው ቤተሰብ መሆናቸው ያስታውቃል፡፡ድንገት የተቀመጥኩበት ጠረጴዛ ስር የፎቶ አልበም አየሁ፡፡ መቼስ አልበም ፊት ለፊት እንግዳ ሲመጣ የሚቀመጥበት ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጠው…የመጣው ሁሉ እንዲያየው ነው ብዬ አወጣሁና ማየት ጀመርኩ…፡፡አብዛኛውን ስለማላውቃቸው ብዙም ስሜት አይሰጠኝም፡፡ ቤዛወርቅ ያለችበትን የህፃንነቷን ቲኔጀር ሆና የተነሳችው ….የሚገርመው ከልጅነቷም ስፖርተኛና ተቦቃሽ ነገር ነች..እንዴ ምንድነው..?ይሄ ፎቶ እዚህ ምን ይሰራል…..?ፎቶውን እንደያዝኩ ከመቀመጫዬ ተነሳውና ወደኪችን ተንደረደርኩ፡፡
‹‹…ቤዝ.ቤ..ዝ….››እያለከለኩ ቅድም ስትገባ ወደያኋት ክፍል ገባሁ
‹‹ምነው ምን ተፈጠረ ..?ቢላዋ በእጇ እንደያዘች ጥሪዬን ሰምታ ስትወጣ በራፍ ላይ ተገጣጠምን …..አልበሙን ወደ እሷ ዘርግቼ‹‹ይህቺ ማነች…?ይህቺኛዋስ?›
‹‹ጤና ትባላለች…በሚያሳዝን ሁኔታ አሁን በህይወት የለችም…..?ምነው ከሰው ጋር ተመሳሰለችብህ እንዴ?››
‹ጤናዬ ማለት? ጤናዬ አስረስ…የበሪሶ አያና ሚስት፡፡››
‹‹አዎ ጋሼ በሪሶ..የት ነው የምታውቃቸው….?››በገረሜታ ጠየቀችኝ፡፡
ፊቴን አዞርኩና ወደሳሎን ተመለስኩ…ሶፋው ላይ ዝርፍጥ አልኩና ጭንቅላቴን ያዝኩ፡፡
ቤዛ ሁሉ ነገር ግራ ገባትና ከኃላዬ ተከትላኝ መጣች ‹‹ቆይ ቆይ እነሱ እኮ ከሞቱ ቢያንስ 20 አመታት አልፏቸዋል….ቅድም ስንመጣ ከመኪና ወርደህ እቤታቸው ላይ ስታፈጥ ነገሩ ምድነው ብዬ ግራ ተጋበቼ ነበር››
‹‹ለመሆኑ አንቺ ታስታውሺያቸዋለሽ…?››
‹‹አዎ ሲሞቱ የደረስኩ ወጣትና 12ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ ሁሉን ነገር ነበር የማስታውሰው…ቤተሰብ ነበርን…አንድ ልጅ ነበራቸው..የሚያምር ወንድ ልጅ… ክርስትና ያነሳው አባቴ ነበር.አበልጆች ነበርን..?አይ እዬብ ይሄኔ አድጎ ትልቅ ሰው ሆኗል….ስሙ እዬብ ነበር…፡፡››
‹አዎ ስሜ እዬብ ነው፡፡››
‹‹ምን ?አንተ…!!!እኔ አላምንም..፡፡እዬቤ ነህ…፡፡ቆይ ቆይ…. ››አልበሙን ነጠቀችና ገለጥ ገለጥ አድርጋ እኔ ያለሁበትን ፎቶዎች አወጠች…፡፡ እሷ አቅፋኝ የተነሳሁት..አባቷ ታቅፈውኝ የተነሳሁት..አራት የሚሆኑ ፎቶዎችን አሳየችኝ….ከዛ በኃላ ቁርሱም ተረሳ.፡፡
✨ይቀጥላል ✨

👍70😱9❤7😁5
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
፡
፡
#ክፍል_አስር
ሽማግሌዎች ከዘርሲዎች አለቃ ጎጆ ፊት ለፊት ቁርበት
ተነጥፎላቸው ሲያወሩ እንደቆዩ ኮቶ ቡና የያዘ ሾርቃ አደለቻቸው"
ካርለት ጎጆው ውስጥ ሆና በቀዳዳ ታያቸዋለች ዘግይታ የወጣችው የጨረቃ ብርሃን ምሽቱን ፍንትው አድርጋ አስውባዋለች ካርለት
በልጅነቷም ሆነ በአፍላ ወጣትነቷ ብዙ ስነ ግጥሞች ስለጨረቃ
ውበት፥ ስለጨረቃ ፍቅር: ስለጨረቃ ስደት ... ተፅፈው አንብባለች
የሰለጠነው ዓለም ግን ፀሐይን እንጂ የጨረቃን ውበት ራሱ በፈበረከው የኤሌክትሪክ ብርሃን ተነጥቋል የጨረቃ ውስጠ ሚስጥር ትዝታውም ተረስቷል ሐመር ላይ ግን ጨረቃ እንደ ጥንቱ ዘመን ሙሉ አቅም: ጥንካሬ ውበት
አላት
ሽማግሎች በጨረቃ ብርሃን ምረቃ ጀመሩ፤ ምኞታቸው
ፍላጎታቸው የጋራ ነው" ሐመሮች አምላካቸውን አያስቸግሩም አንዱ ጤንነት ሌላው ንዋይ ፍቅር . ... እየተመኘ አምላኩን የሚይዘው የሚጨብጠውን
እያሳጣ ግራ አያጋባውም
ሐመሮች ዝናብና ጤንነት
ሁሌም የሚለምኑት ሁለት ነገር ነው ውስን
ብቻ ዝናብ ካለ ሳር አለ ሣር ካለ ከብቶች አሉ ከብቶች ካሉ ይኖራሉ" ሐመር ላይ ቦርጫም ምኞት የለም
የህይወት ልዩነት እንዲኖር የሚፈልግ ወይንም የሚመኝ የለም በእኩልነት እንጂ በልጦ ለመኖር የሚያስብ የለም የቤቱ ቅርፅ አንድ መልክ የቤቱ ዕቃ አንድ አለባበሱ አንድ
ሁሉም አንድ መልክ አለው ሐመር ላይ የተለዬ ያፍራል እንጂ አይኮራም፤ በመለየቱ
ይወቀሳል እንጂ አይከበርም
ሽማግሎች ቡናቸውን እንዲህ ተመራርቀው ከጠጡ በኋላ ወደ
መደነሻው ገላጣ ሜዳ ሄዱ ከተሰባሰበው የመንደሯ ሰው አቅራቢያ ተይዞ የቆመው በሬ ጂራቱን እያጠማዘዘ: ወገቡን እየለመጠ፥አንገቱን እየቀበረ ለማምለጥ ቢሞክርም ቀንድና ቀንዱን፥ ጅራቱን
የያዙት ጎረምሶች ሊያንቀሳቅሱት አልቻሉም
ሽማግሎች ከመረቁና ደልቲን የአባቱን ደንብ በማክበሩ ፕስስ እያሉ ትንፋሻቸውን ካርከፈከፉበት በኋላ የአመጣውን የቅጣት
ከብት ጉሮሮ ከወገቡ ባወጣው ጩቤ ወጋው፤ ደሙ በሾርቃ ተጠራቅሞ
የተወጋውን ከብት ጎረምሶቹ ለቀቁትና ወድቆ ተፈራገጠ ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ ብልቱ እየወጣ ጥብሱ ተጀመረ የተዘጋጀው ከተበላ በኋላ ዳንሱ ቀጠለ ሽማግሎች ከጎረምሶችና
ልጃገረዶች ጋር ሲደንሱና ሲፎክሩ ቆይተው እኩለ ሌሊት አካባቢ
ተጠራርተው የዳንሱን ቦታ ለጎረምሶችና ልጃገረዶች ለቀው ሄዱ ልጃገረዶች በጨሌና ዛጎል የተዋበውን የፍየል ቆዳቸውን እያወናወኑ: አንባራቸውን እያፋጩ ፊታቸው ላይ የተቀቡት የአኖ ቀለም ከጨረቃዋ ብርሃን ጋር እንደ ከብቶች እያንፀባረቀ ሳቃቸው እንደ ከርሰ ምድር የእንፋሎት ውሃ ቡልቅ ፍልቅልቅ ሽቅብ ወደ ወንዶች ጆሮ እየፈሰሰ ጭፈራው ደመቀ
ጎረምሶች ረጋ ብሎ ሲፈስ የነበረውን ዳንስ ሲለውጡት
መአበሉን ሊያስነሱት ፍቅር
በጥቅማ ጥቅም የጠቦት ስብ ያልሆነበትን የፍቅር ገበያ እንዲደራ በአይነት ሰጦ ለመቀበል እንዲቻል
የቦዮን ጎዳና ሊከፍቱት
ዳንስ ሊለውጡት የወንድን ጭን ከሴት ጭን ጋር እያፏጩ የፍቅር
አረፋ ሊያስደፍቁት በማዕበሉ እየተወረወሩ
ነፍሳቸው የመጨረሻውን እርካታ ለቅፅበት ወደምታገኝበት ጫካ
ለመግባት የሚያስችላቸውን ቅላፄ ጀመሩት።
… አንች ከርታታ ከልቡ የሚያስተናግድሽ በአልኮል ፈረስ ሳይጋልብ በጥቅም
ዓይኑ ሳይታወር በምኞት ህሊናው ሳይበሰብስ
በመምሰል ቀሳፊ በሽታ ሳይጠመድ፥ በራስ መተማመኑን አኝኮ
ሳይውጥ ደስታ ሆይ! ከልቡ የሚቀበልሽ ስላለሽ ደስ ይበልሽ' እግዚኦ! በስንቱ አገር: በስንቱ ሰው ሰራሽ አበባ ለማስጌጥ በተሞከረ
ውብ ስፍራ' እየተጠራሽ ዝክር ጠይቀሽ አዝነሽ ተመለሽ! እግዚኦ!
ስንቱ በውሸት ሊያገኝሽ ተንጠራራ አንች ምስኪን ከርታታ ክብርት ደስታ ሆይ! ደስ ይበልሽ እግዚኦ! ... የሚል የመላእክት ማህሌተ
ቡራኬ በዳንሱ አካባቢ
ተሰማት ካርለት
ከርከር ከርከር ዳሌ ወዝወዝ ወገብና አንገት ሰበቅ
ሰበቅ ... እጥፍ እጥፍ፥ ዘርጋ ዘርጋ ዳሌ ወዝወዝ: ሣቅ ሣቅ ሆኖ አሀሀ-ሎሜ!
መባል ተጀመረ ተሟሟቀ የወንዶችና የልጃገረዶች
ሰውነት ልጃገረዶች የሚፈልጉትን ወንድ
እየተወረወሩ እየሄዱ ጋብዘው ወዲያ ወዲህ ሽርር ሽርር … እያሉ
ሲጠብቁ የተመረጡት ወንዶች ወገብ ለወገብ ከጓደኞቻቸው ጋር
ከተያያዙበት እየተላቀቁ እንደ ጎራዴ ምዝዝ: መሬቷን ድልቅ፥ ሸብሸብ ደሞ ዝልል
እያሉ ወደ ጋባዦቻቸው ተጠጉና ወገብ ለወገብ እየተያያዙ ገቡ ባልጩቱ
ተጠልፎ እንደ ኤሌክትሪክ ገመድ ጫፍ ተገናኘ ሞገዱ ተለቀቀ የጡት ጫፍ ሊወርድ እንደተቃረበ ጀት ጎማ ከተጣጠፈበት እየተዘረጋጋ ቆመ ተሳሳለ ቢላዋና ሞረዱ ስለቱ የፍቅር ጮማውን ቆርጦ ወደ የአፋቸው አስጠጋው አላመጡት: አደቀቁት አልመው ዋጡት ያን ምርጥ የሐመር ሰንጋ የፍቅር ጮማ ልብ ቦታውን
እየለቀቀች ዘለለች ህሊና ትዕዛዝ ሰጠ ደስታ ሆይ አንቺ ከርታታ ምስኪን ሆይ ደስ ይበልሽ! ማህሌቱ አላቆመም ካርለት
ይህን ሰማያዊና ምድራዊ የተጣጣመ ትርዒት ፈዛ ስትመለከት ለረጅም ጊዜ ቆየች ኮቶ ከኋላዋ መጥታ ባትነካትማ የምትነቃ
አትመስልም ቅዠት የሌለበት ህልም ... ፍርሃት የሌለበት ደስታ።
"ኮቶ ልትደንሽ ወደ ዳንሱ ገብተሽ ከኋላዬ የምትመጭው ከየት
ነው?" አለቻት ካርለት ዐይን ዐይኖችዋን እያየች
"ይእ! ጥጆችን ሳራክብ እሁ አለፉኝ ሲራከቡ!" ብላ
የካርለትን ትከሻ ተደገፈች "ነው!" ካርለት ገባት የቆየችበት የኮቶ ሰውነት ዛል ብሏል ሰውነቷ እንደ እንቦሳ ሰውነት ያረግዳል
የእርካታ ትንፋሽዋ በመላ ሰውነቷ ይትጎለጎላል
"ኮቶ ደልቲን ልጋብዘው?"
"ይእ! ኧረ ተይ ከእጮኛ ጋርማ አይደነስም እሱ ከፈለገ መጥቶ ሲጠራሽ ባይሆን አጠገቡ ትሄጃለሽ ከዚያ እያወጋችሁ ቀስ
በቀስ ከዳንሱ ቦታ ፈንጠር፥ ፈንጠር ... እያላችሁ በመጨረሻ ጨረቃዋን እፍ' ብላችሁ አሹፋችሁባት ትጠፋላችሁ እሷም ቀልድ
ስለምትወድ እየሳቀች ትከተላችኋለች ካለ ጨረቃ የወንድና ልጃገረድን ፍቅር ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ የሚያውቀው
የለም!"
"የመንደራችን ጎረምሶች ግን ተእንግዲህ ትቀመስ ማለታቸው አይቀርም የአባትሽ ዘመዶች (እንደናሶችም) እንደ እኛ ይገርፉሻል"በይ እቴ ወሬው ይብቃ እንጫወት" ብላ በቆሙበት መወዛወዝ
ጀመሩ"
ደልቲ ከዳንሱ ወጥቶ ካርለት አባት ብላ የመረጠችውን ዘመድ
ረምሳ ጠራውና በርኮታው ላይ ተቀመጠ" ጎረምሳው
ጥሪውን ተቀብሎ አጠገቡ ሄዶ ቁጭ አለ
"ሚሶ!" አለው ደልቲ
"ሚሶ!" አለ ጎረምሳው"
"...ይህችን ልጅ የአባት ወጓን አስተምሯት እንጂ?"
"እእ! - ካርለቴን ነው?"
"አዎ! ከብትና ፍዬል ትጠብቅ ቀፎም ትስቀል ዳንሱ ላይም ግረፏት እንጂ. አሁን ታልሰባች በኋላ እኔ ስንቱን ላርማት ነው?"
"እእ! እሽ ኧረ እኛም ስንመክርበት ነበር እንዳልኸውስ ተሌሎች እህቶቻችን ነጥለን ለምን እናያታለን! ትንሽ
እሚያሰቃጥጠው እንኳን ተገርፋ ሌሎቹ ሲገረፉ ስታይ ንዳድ
እንደያዘው ሰው እየተንቀጠቀጠች መግቢያው ነው የሚጠፋት,,
"አይቻታለሁ ባትለምደው ነው! ግዴለም አስለምዷት
ተዚያ እሷው ያምራታል እሷ እኮ ህፃን ማለት ናት ህፃንን
ብትመታው ያለቅሳል
ሴቷ ግን እድሜ ለአባቷ
ለመንደሯ ጎረምሶች እያደገች ስትሄድ እያየች ትማርና በኋላ በተግባር ደሞ ቀስ በቀስ ትለምዳለች, ትፈራለች ብላችሁ አትተዋት
የኖረችበትን መገመቱ ይከብዳል! እነሱ በድለዋታልና እኛም ግን
ደግመን ልንበድላት አይገባም የዱላን ፍቅር አሳይዋት እሷም ተተወሰነ ጊዜ በኋላ ፍርሃቱ ይወጣላታል!"
"እእ!- እሽ ዛሬስ እኛም አስበናታል ና እንጂ አንተስ
ተጫዋት?"

👍29❤2😢2
አለሁ የት እሄዳለሁ አዳሬ ተዚሁ ነው" ብሎ ደልቲ
ከበርኮታው ላይ ተነሳ ጎረምሳው ደግሞ የባራዛ አርጩሜውን ወደ
ደበቁበት ጉቶ ሄዶ ሶስት ለበቆችን አነሳ ደልቲም ከወንዶች ግማሽ ክብ ሰልፍ ገብቶ ወገብ ለወገብ ተያያዘ
.

👍15👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ከጋሽ ሙሉ አለም ጋር ከተነጋገርን በኃላ አዎጪ ስራ ለመምረጥ ያልበረበርኩት ዌብ ሳይት ያላማከርኩት የቢዝነስ ሰው...በሰበብ አስባብ ያልጎበኘሁት የንግድ ተቋም የለም።ምንም ግን ልቤን እርግጥ አድርጎ ሞልቶ በቃ ይሄንን ነው ብዬ እንድወስን የሚያደርገኝ ስራ በቀላሉ ማግኘት አልቻልኩም። ሰው ደግሞ አላውቅም የሚለው ነገር የለውም፡፡ ትንሽ መንገድ ካሳዪት በማንኛውም ነገር ከኤክስፐርት በልጦ ይቦተረፈዋል።
"እኔነኝ ያለ አሪፍ ቡቲክ ብትከፍት በጣም ትርፋማ ነው የምትሆነው...በተለይ የሴቶች ካረከው ትርፍህ ባለሁለት ስለት ነው የሚሆነው..እነዚህ የሀብታም ቺኮችን ገንዘባቸውንም ውበታቸውንም እጥብ ነው የምታደርገው...››እንደዚህ የመከረኝ ጎረምሳ ነጋዴ እንዳይመስላቹሁ የአምስት ልጆች አባትና ባለሁለት ቀለም ፀጉር ባለቤት የሆነ አዛውንት ነው።
"ለምን ማሳጅ ቤት አትከፍትም›› ያለኝ ሰውም አለ...
"በአሁኑ ጊዜ አዎጪው ስራ ድለላ ነው፡፡ ፍቃድ አውጣና የውጭ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ብትሆን አሪፍ ትሸቅላለህ..በጎንም ቤት መደለል ፤:መኪና መደለል ፤ሴት መደለል አይነት አዋጪ ስራዎችን ትሰራለህ
የሪል እስቴትና የባንክ ቤት ኤጀንቶችም "ከሰርኩ አልከሰርኩ እያልክ ምን አጨናነቀህ፡፡ በገንዘብህ አክሲዬን ግዛበት.፡፡ አንተ ዘና ብለህ በየአመቱ በምትዝቀው የትርፍ ድርሻ ብቻ ዘና ብለህ መኖሮ ነው››ብለውኛል
"በአጠቃላይ በሰሞኑ ውጣ ውረዴ የተረዳሁት አንድ ነገር ቢኖር ከዚህ በፊት ስራ ለመጀመር ትልቁ መስፈርት መነሻ ካፒታል ማግኘት ብቻ ነበር የሚመስለኝ፤ለካ መጀመሪያ አውጥተን አውርደን ይሄንን ስራ በዚህ አይነት ሁኔታ እንሰራለን የሚል ቢያንስ መነሻ የሚሆን ሀሳብ በውስጣችን ከሌለን ገንዘቡ ቢኖር እንኳን ትልቅ እራስ ምታት ውስጥ ነው የምንወድቀው ?
ስዞር ውዬ ደክሞኝ ወደቤት ገባሁና አልጋዬ ላይ በቁሜ ወደቅኩበት ...ተንሳጠጠ፡፡
"ጎረምሳው ቀስ..."
"አያቴ...ደክሞኛል"
""የትኛውን ተራራ ወጥተህ ነው ይሄ ሁሉ ማለክለክ?"
"አረ ተራራ መውጣት ይሻላል...ሰው የሚሰራበት ገንዘብ ለማግኘት ይባክናል እኔ የምሰራው ስራ ማሰብ ና መወሰን ያቅተኝ።አረ ምን አይነት ቀሺም ነኝ?››
"እንኳንም አቃተህ"
"እንዴት አያቴ?"
"አየህ ተጨንቀህ ተጠበህ ያፈለቅከው ሀሳብ ጥልቀትም ውጤትም ይኖረዋል።"
"አይ አያቴ እስከአሁን ምንሞ የረባ ሀሳብ ላይ አልደረስኩም እኮ...የማማክረው ሰው ሁሉ ሺ ሀሳብ ነው የሚሰጠኝ...አንድ አሪፍ ነው ይሄን ስራ ጀምር ብሎኝ አሳምኖኝ ዞር ስል ሌላው ደግሞ ያንን ስራ ተሳስተህም ቢሆን እንዳትጀምረው አገርምድሩ የከሰረበት ስራ ነው ብሎ ኩም ያደርገኛል።
"እንደዛ ከሆነ ከማንም ምክር መጠየቅ አቁም.."
"ማለት?"
"ስለቢዝነስ መሠረታዊ ግንዛቤ ለማግኘት ይሄው በዚህ 15 ቀን ውስጥ የጠየቅካቸውና ያማከሩህ ሰዎች ከዩቲዩቨ እያወረድክ ያየሀቸው ቨዲዬዎች በቂ ናቸው"
"እና ምን ላድርግ?"
"እየሠማሀኝ አይደለም እንዴ ..?ምክር መጠየቅ አቁም እያልኩህ እኮ ነው"
"አያቴ ደግሞ… እርሷ እኮ ሌላ ሰው አይደሉም የቢዝነስ ፓርትነሬ ኗት"
"ቢሆንም ስራአስኪያጅና ፈላጭ ቆራጩ አንተ ነህ"
"አያቴ ደግሞ..እሺ የመጨረሻ ምክር ከእርሶ ልወሰድና ከዛ ያሉኝን አደርጋለሁ።››
"እንደዛ ከሆነ ሶስት ምክር ልስጥህ "
‹‹ደስ ይለኛል"
"1 አንተ የተሻለ ግንዛቤ ወይም እውቀት ባለህ የስራ ዘርፍ ብትሰማራ ተመራጭ ነው።ቀጥረህ የምታሠራው ስራ ቢሆን እንኳን ለመቆጣጠር የተወሰነ ግንዛቤና እውቀት ሲኖርህ ውጤታማ ይሆናል፡፡
2/የምትወደውና የምትደሰትበት...ትርጉም የሚሰጥህ ስራ ቢሆን የግድ ባይሆንም የተሻለ ነው"..ኢንጂነር ኮንትራክተር እንደሚሆነው...የህክምና ዶክተር ክሊኒክ እንደሚከፍተው ማለት ነው
3/ኪሳራ የሚባል ነገር ከአዕምሮህ አውጣ...ፍፅም ኪሳራ የሚባል ነገር በህይወት የለም ..ይህ የመጀመሪያ የቢዝነስ ስራህ ነው፤ አሁን የምትጀምረውን ስራ ለሁለት አመት ከሰራህ በኃላ ከስረህ ብትዘጋው ያጣሀው ገንዘብ ነው ግን ከፍተኛ ልምድ ታካብትበታለህ… ቀጣይ ስራ ሀ ብለህ ለመጀመር እንደአሁኑ ድንብርብርህ አይወጣም...በል አሁን ተኝተህ አስብ››
"እሺ አያቴ አመሰግናለሁ "
ይሄንን ከተነጋገርን ከአራት ቀን በኋላ የሚገርም አጋጣሚ ተከሰተ፡፡ አንድ አለማያ አብረን የተማርን የቢሾፍቱ ልጅ ነበር..ከዛ እንደወጣ ወላጆቹ የችግኝ ስራ ይሰሩ ስለነበር እሱም ተቀላቀላቸውና መስራት ጀመረ..ሞያው ስለሆነ በሁለት አመት የሚገርም ለውጥ አመጣ ፡በሶስተኛው አመት 2 ሺ ካሬ መሬት ተከራይቶ ...የተለያዩ የአበባ አይነቶች ፤ለግቢ ውበት ማስጌጫ ተክሎች፤ ለምግብ የሚሆኑ አትክልቶች መንጎ፤ፓፓያ ፤አቡካዶ በስፋት አምርቶ ማቅረብ ጀመረ…
የዘንድሮውን ምርትም ለገበያ ለማቅረብ ሁለት ወር ሲቀረው የውጭ እድል አገኘና ጠቅላላ ልማቱን ባለበት ለመሸጥ ገዢ በማፈላለግ ላይ እንደሆነ ሰማሁና ደወለኩለት ..፡፡እርግጥ ከአንድ ሰው ጋር ተነጋግሬና ተስማምቼ ነበር፤ ቢሆንም.እኔ ስራውን ለሚያውቅና ለማውቀው ሰው መሸጤ ነው በጣም የሚያስደስተኝ…የአትክልት የማልማት ስራ ልጅ ከማሳደግ ጋር የሚያመሳስል ነገር አለው…ዝም ብሎ ብር የማግኛ ስራ ብቻ አይደለም…የተቀዳደደ እና የተቦተራረፈውን የተፈጥሮ ልብስ በጥንቃቄ የመስፋትና የማደስ ፤ እፍረቷንም የመሸፈን ስራ ነው፡፡ ..ግን ትንሽ ተወደደብኝ ካላልክ.. እርግጥ ከሁለት ወር በኃላ ብሸጥ አገኘዎለሁ ካልኩት ብር ከግማሽ በላይ ቀንሼ ነው የምሸጠው አለኝ
"መጀመሪያ ልየው አልኩት፡፡በፈለከው ሰአት ቢሾፍቱ ናና ደውልልኝ አለኝ..ጊዜ ሳልፈጅ እየበረርኩ ሄድኩና አየሁት ..ከገመትኩት በላይ በጣም ማራኪና አስደማሚ ሆኖ አገኘሁት ...እሱም በቦታው ላይ ስራ ከሁለት አመት በፊት ሰራ ሲጀምር እንደዚህ አይስፋ እንጂ የተወሰነውን ባለበት ከሰው ገዝቶ እንዳስፍፍው አስረዳኝ ..በተቻለኝ መጠን ፎቶም ቪዲዬም አነሳሁ።አንዳንድ ብቻውን በመኪና ተጭኖ ሄዶ ሲተከል መለስተኛ ዛፍ የሚሆንና ከ10 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ በርከት ያሉ ዛፎች ያሉበት ነው። ዎጋውን የአምስት ወር ከተከፈለበት የመሬት ኪራይ ጋር 350 ሺ ብር አለኝ። ከሸሪኬ ጋር ተማክሬ በአንድ ቀን ውስጥ አሳውቅሀለሁ ብየው ወደአዲሳባዬ ተመለስኩ።
እቤት እንደደረስኩ .."አያቴ"
"አቤት መጣህ..የት ጠፍተህ ነበር?"
"የሆነ ቦታ ሄጄ ነበር፡፡ ቀላል እቃዎችን በምንቀባበልበት ስንጥቅ እጄን አሸልኬ""እንኩ ይቀበሉኝ"
"ምንድነው...?ሞባይልህን ምን ላድርገው?።››
"አሁን ትክክለኛ የምንሰራውን ስራ ያገኘው ይመስለኛል...እስኪ ቪዲዬውንም ፎቶዎችንም ይዩት"
"ከተቀበሉኝ በኃላ..ለ15 ደቂቃ ንግግር አልነበረም... ዝም ማለታቸው ያልጣማቸው ነገር ስለአለ ነው ብዬ ደነገጥኩ .. ፈራሁም።ምክንያቱም ስራውን በጣም ከልቤ ነው የፈለኩት.ደግሞም በሙሉ የራስ መተማመንና በዕውቀት የምሰራው ስራ ነው….ይሄ ግን ለእሷቸው ካልተገለፀላቸው የእኔ መሻት ብቻ ዋጋ የለውም፡
"ለዚህ እኮ ነው የምወድህ?"
"ምን አሉኝ አያቴ?"
"ውብ የሆነ ስራ መርጠሀል"
"ወደዱት..ልጁ ጓደኛዬ ነው ማለት አለማያ አብረን ነው የተማርነው ..አሜሪካ የመሄድ እድል ስላገኘ ባለበት ሊሸጠው ነው የፈለገው። ሌላ ሰው ሊገዛው ጠይቆታል እሱ ግን ሰውዬው የሰጠኝን ምትከፍለኝ ከሆነ ላንተነው መሸጥ የምፈልገው ብሎኛል››

👍73❤5👏1
"እና አንተ ምን አልክ?"
"እኔማ ከአያቴ ጋር ተማክሬ መልሱን እስከነገ እነግርሀለሁ ነው ያልኩት"
‹ስንት ነው የጠየቀህ?"
"ሁለት ሺ ካሬ ሜትር ነው፡፤ የመሬቱ የአምስት ወር ኪራይ ተከፍሎበታል ፡፡350 ሺ ብር ይላል"
"እና ነገ ድረስ ምን አስጠበቀህ ..ዛሬውኑ ንገረው"
"ምን ልበለው...?››
‹‹ነገ ብሩን ይዤልህ እመጣለሁ ..ውልና አስፈላጊ መረጃዎችን አዘጋጅተህ ጠብቀኝ በለው"
"እና ልንገዛው መሆኑ ነው"
‹‹"ይልቅ እዚህም ከዛ እያመጣህ የምታከፋፍልበት መቶ ወይም ሁለት መቶ ካሬ የምትሰፍ ቦታ ፈልግ...ከዛ እየመጣ እዚህ ቢሸጥ አሪፍ ይሆናል"
ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ዘለልኩ፤ ጨፈርኩ ‹...አያቴ በጣም ነው የምወዶት ...››
"ቤቱን አፈረስከው ..በል እንካ ስልክህን ..››
እየጨፈርኩ ወደስንጥቁ ሄድኩና ተቀበልኩ..ከስልኩ ጋር ወረቀት አለ‹‹
ምንድነው?›› ከፈትኩት ቼክ ነው"1 እና ስድስት ዜሮ ይታየኛል"
"ምንድነው አያቴ?"
"በል ሂድና ወደ ደብተርህ አዘዋውር፡፡ ከዛ እንደአስፈላጊነቱ እያወጣህ ለአስፈላጊው ነገር አውል...በቃ አሁን ስራ ተጀመረ እኮ›
አለቀስኩ ..ልክ ወላጆቼ ዛሬ እንደሞቱብኝና መርዶ እንደተረዳ ሰው ወለል ላይ ተዘርፍጬ አለቀስኩ... ሲደክመኝ ፊቴን ታጠብኩና ቼኬን ይዤ ወጣሁ... መንገድ ላይ ሆኜ ለልጁ ደወልኩለት....እንደተስማማሁና ነገ ስለምመጣ ተዘጋጅህ ጠብቀኝ አልኩት...፡፡ደስ አለው። እንዲህ በቀላሉ ስምምነት ላይ የምንደርስ እንዳልመሰለው ከሁኔታው ያስታውቅበታል..፡፡ባክህ ትንሽ ቀንስልኝ...እቺን ያህል ብር ጎደለችኝ እያልኩ የማስቸግረው መስሎት ነበር..ያው የባንክ ውጣ ውረድ አልፌ ብሩን ወደ ባንክ ደብተሬ አስገባሁ..ምንም የሚያስፈነጥዝ ነገር እየተሠማኝ አይደለም...ሸክሜ ነው የጨመረው..ትከሻዬ ነው በኃላፊነት የጎበጠው..
ቤዛ ወርቅ ጋር ደወልኩላት
"የት ነሽ?"
"ዝም ብዬ ልደታ አካባቢ ካፌ ቁጭ ብያለሁ"
"መኪና ከያዝሽ ስቴዲዬም ትመጫለሽ?"
"እችላለሁ ፡፡ ምነው ናፈቅኩህ እንዴ?"
"አዎ..ግን በጣም የተቀዣበረ ስሜት ላይ ነው ያለሁት ..ብዠ ብሎብኛል ፡፡ብቻዬን ስንገላወድ የሰው የመኪና ጎማ እንዳላበላሽ ስለፈራሁ ነው የደወልኩልሽ።
"ምነው አሞሀል እንዴ?"ደነገጠች
‹አይ ደህና ነኝ ግን ሰው ያስፈልገኛል"
"መጣሁ መጣሁ ባለህበት ሆነህ ጠብቀኝ"አለችና ስልኩን ዘጋችው፡፡
..ሰባት ወይሞ ስምንት ደቂቃ ነው ያስጠበቀችኝ፡፡ ስሬ መኪናዋን አቆመችና የገቢናውን በራፍ ከፈተችልኝ ...ገባሁ"ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳምን .
‹‹..አንተ ሠውነትህ ሁሉ ይግላል...አሞሀል ሀኪም ቤት ልውሰድህ...››
"አይ ህመም አይደለም"
"እና ምንድነው?"
"ድንጋጤ መሠለኝ"
"አልገባኝም"
የባንክ ደብተሬን ከኪሴ አወጣሁና ሰጠኋት፡፡

👍57🥰8❤7
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ልጄ ስልክ ደውላልኝ እያወራኋት ነው፡፡
‹‹አባዬ እንዴት ነህ?››
"አለው የእኔ ማር ትምህርት እንዴት ነው?።››
"ትምርት ጨርሰናል አላልኩህም..እሁድ የወላጆች በአል ነው..ካርድ ይሰጠናል።››
‹‹በእውነት ደስ ሲል.."
"አዎ !!ቲቸር ደግሞ ተሸላሚ ስለሆንሽ ወላጆችሽ እንዳይቀሩ አለችኝ...ለእቴቴ ስነግራት ‹ጎበዝ ልክ እንደአባትሽ ብሩህ ጭንቅላት ነው ያለሽ› አለችኝና አለቀሰች።"
እንባዬን መቆጣጠር ተሳነኝ...ያለፍቃዴ እየተንጠባጠበ ነው።
"አባዬ ምነው ዝም አልከኝ ?"
"ልጄ ደስ ብለኸኝ እኮ ነው ... እና ማነው አብሮሽ የሚሄደው...?››
"እቴቴና አክስቴ ትልቆ አብረንሽ እንሄዳለን ብለውኛል...ደግሞ እቴቴ ቆንጆ ቀሚስና ጫማ ገዝታልኛለች ..."
"አሪፍ ነው ...እናትሽ ጀግና ልጅ እንዳላት ሰምታለች?"
"አዎ ….በቀደም በእስካይ ፒ ስናወራ ነገርኳትና ..ከሀይስኩል በኃላ እዚህ አሜሪካ ነው ምትማሪው አለችኝ"
"እና ምን አልሻት ..?.ደስ አለሽ?"
"አይ አላለኝም..እኔ አባቴን ፈልጌ ሳላገኘው አንቺ ጋር መምጣት አልፈልግም .. ከፈለግሽ አንቺ ነይ አልኳት..."
ደንግጬ"እና ምን አለችሽ?"
"ከየት አባሽ ነው ፈልገሽ የምታገኚው...?በህይወት መኖሩን እራሱ እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚችል ሰው የለም ።"አለችኝ
እኔ ደግሞ‹‹ እኔ ልጅ ስለሆንኩ ይታወቀኛል በቅርቤ አለ...በጣም እንደሚወደኝም አውቃለሁ›› ስላት ተበሳጨችና ዘጋችብኝ።››
"አትቀየሚያት …እኔ ዝም ብያት ስለጠፋሁ እስከአሁን እንደተናደደችብኝ ነው።››
"አይ አውቃለሁ.. ከዛ እኮ ቆይታ ደውላ ይቅርታ ጠይቃኛለች ..ወደፊት እመጣና አብረን እንፈልገዋለን አለችኝ"
"የእውነትሽን ነው ..አራሷ እንደዛ አለቺሽ?"
"አዎ …ቃል ገብታልኛለች...ሁኔታዎችን አመቻችቼ ረጅም ፍቃድ ወስጄ እመጣና እንፈልገዋለን …በህይወት ካለ እናገኘዋለን..››አለችኝ፡፡
‹‹አና አንቺ ምን አልሻት?››
"እማዬ አንቺ ብቻ ነይ እንጂ ፈልገን አናገኘዎለን...በልቤ ይታወቀኛል።"አልኳት፡፡
‹‹ልጄ በጣም ነው የምኮራብሽ...እና ለሚመጣው አመት እንደአሁኑ ተሸላሚ ከሆንሽ እንደምንም ብዬ ከጎንሽ እገኛለሁ!››
"አባዬ ›
ወዬ ልጄ..?
‹‹ቻው እማዬ የላከችልኝን ፎቶዋን በቴሌግራም ልኬልሀለሁ.. ከናፈቀችህ ብዬ ነው"
‹‹እሺ የእኔ ልጅ አመሠግናለሁ..ሰሞኑን ደውይልኝ።››
"እም ጶ… የእኔ ውድ አባት እወድሀለሁ።"ስልኩ ተዘጋ፡፡ የእኔም አንደበት ተዘጋ..
."የፈጣሪ ያለህ!!እኔ ምን አይነት እድለኛ ሰው ነኝ...፡፡ምን አይነት እንደስሟ ተአምር የሆነች ልጅ ነው የሠጠኝ?።እሷ በመወለዷ ምክንያት ህይወቴ ተሠነካከለ ብዬ ለረጅም ጊዜ በማሰብ ሳማርር ቆይቼ ነበር ..፡፡ግን አሁን ለዚህች በረከት ለሆነች ልጅ ከዚህ በላይ መከራና ስቃይ ቢቀበሉላት የማታስቆጭ ልጅ ሆና በማግኘቴ ደስተኛ ሰው ሆኜያለሁ።
✨ይቀጥላል..✨

👍81❤17🥰11👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
ስበሳጭ ጀርባዬን ይበላኛል...የበላኝን ቦታ ለማከክ እጄን በወገቤ አዙሬ አሽከረክራለሁ፤ ግን ደግሞ አልደርስበትም.. በትከሻዬ በኩል አጠማዝዤ ሞክራለሁ፤ ትርፉ ድካም ነው። ከእከኬ ስቃይ እራሴን ለማስታገስ እገዛ መፈለጌ ያበሳጨኛል ደካማነቴንና ማድረግ የማልችላቸው ነገሮች ብዛት ያስጨንቀኛል...ጀርባዬን በላኝ እከኩልኝ ብዬ የሰው እገዛ ላለመጠየቅ ልብሴን አወልቅና ከሻካራ ግድግዳ ጋር እራሴን አፋትጋለሁ... ቢያቆስለኝም ያስተነፋሰኛል። ቢያንስ ገበናዬ ጠብቄያለሁ፡፡
አለመቻሌንም በሚስጥር በውስጤ አፍኜ ይዘዋለሁ፡፡አዎ አንዳንዴ ህይወት በዛ መጠን ትጨክንብኛለች በዛ መጠንም ታሰቃየኛለች፡፡
ዛሬ እርግጥ አልተበሳጨሁም ፤ግን ደግሞ በጣም ተጨንቄያለሁ፡፡ ጊዜው ጨለምለም ብሎል...አንድ ሰአት ከሩብ አካባቢ ነው›፡፡ ጀማሪ ማፊያ ይመስል ተጀባብኜ ወደሰፈር ተጠጋሁ...፡፡
እየተንቀጠቀጥኩ ነው ፡፡መቼስ ብርድ ብቻ አይመስለኝም እንደዚህ ውስጤ ገብቶ እያንቀጠቀጠኝ ያለው ።ኳስ እንጫወትበት የነበረው ሜዳ ባለአራት ፎቅ ህንፃ ተገማሽሮ ቆሞበታል። መቼስ ደፍረው ጠጠርና አሸዋ አምጥተው የሠፈሩ ሰው እያየ ሲሚንቶ አውርደው ፤ቀስበቀስ የገነቡት ሳይሆን ድንገት ከእለታት በአንድ ቀን ሁሉም የሰፈር ጎረምሳ ሆነ አሮጊት መተኛታቸውን አረጋግጠው ከሆነ ቦታ ጭነው መተው የተከተሉት ነው የሚመስለው። ወደቤታችን አየተቃረብኩ ስመጣ እግሬ እየተሳሰረ አስቸገረኝ፤ መራመድ ሁሉ አቃተኝ።
የውጩ ፍሬንች ዶር በአዲስ ከመቀየሩ ውጭ ቤታችን ከውጭ ያለው እይታ በፊት እንዳነበረ ነው።አለፍ ብዬ ሄድኩና ኮርነር ጋር ስደርስ ጨለማን ተገን አድርጌ ቆምኩ፡፡ ፊቴን ወደ በራፋችን አነጣጠርኩ
፡፡ ...ምንድነው የምጠብቀው..?.ማን እንዲወጣ ወይ ማን እንዲገባ ነው ? ልጄን አሁን የማየት እድል አለኝ ይሆን?በዚህ ጨለማ ምን ልትሰራ ትወጣለች...?ምን አልባት አክስቴ...አዎ ምንአልባት እሷን ነው ላይ የምችለው...፡፡ባላናግራትም ላያት ምኞቴ ነው፡፡ ሶስት ሰአት ድረስ እዛው በቆምኩበት ደንዝዤለሁ… የጨው ሀውልት እንደሆነችው ልክ እንደ ሎጥ ሚስት እኔም የበረዶ ሀውልት ከመሆኔ በፊት ወደ ሆቴሌ ልመለስ ወስኜ እግሬን ሳንቀሳቅስ ስልኬ ተንጫረረ ።በደነዘዘ እጄ አወጣሁና አየሁት ..የደዋዪን ማንነት ሳይ ከሰውነቴ ላይ በረዶ የሠራው ቅዝቃዜ በቅፅበት የረገፈ ይመስል ሙቀት ተሠማኝ ።ልጄ ነች።እንዴ አይታኝ ይሆን እንዴ? ዙሪያ ገባዬን ተገላምጬ ተመለከትኩ።ምንም የለም፡፡ስልኩን አነሳሁት
"ሄሎ የእኔ ልዕልት"
"አባዬ እንዴት ነህ..?ምን እየሠራህ ነው?"
"ስለአንቺ እያሰብኩ"
"ታድዬ" ታድዬ አባባሏ ልቤን ስንጥቅ አድርጎ ቃላቱ በስንጥቁ እየተንጠባጠበ ወደውስጤ ሲዘልቅ ተሠማኝ።
"ምን እየሠራሽ ነው...?ነገ ዝግጅት ስላለብሽ በጊዜ አትተኚም እንዴ?
"እነቴቴ እንደዛ ብለው አጠፋፍተው በጊዜ ተኙ።እኔ ግን ክፍሌ ከገባሁ ብኃላ ከመተኛቴ በፊት መስኮቴን ከፍቼ ጨረቃን ሳያት አንተ ትዝ አልከኝ...እና ደወልኩልህ"
ቀና ብዬ ምትላትን ጨረቃ አያየኋት… ግማሽ ቅርፅ፤ግማሽ ውበት፡፡
"ልጄ እውነትሽን ነው ..ታምራለች"
"ማን ነች የምታምረው አባዬ"
"ያልሻት ጨረቃ ነቻ..አይኖቼን አንጋጥጬ እያየኋት ነው… ግማሽ ብትሆንም ልክ እንደአንቺ ታምራለች"
"አባዬ ዛሬ ከጎኔ ሆነህ እቅፍ አድርጌህ ብተኛ ደስ ይለኝ ነበር"
"እንግዲያው መስኮቱን ክፍት አድርጊና ለጥ በይ ..እኔ በርሬ እመጣና በመስኮት ክፍልሽ ገብቼ እቅፍ አደርግሻለሁ..ግን ከተኛሽ በኃላ ነው የምመጣው"
"አባዬ ደስ የሚል ጫወታ ነው ...በቃ ሳልዘጋው ነው የምተኛው..ነገ ከዝግጅቱ በኃላ ደውልልሀለሁ.ወድሀለሁ።››
"እኔም ወድሻለሁ "ስልኩ ተዘጋ..
የእኔም ወደሆቴሌ የመመለስ አፒታይቴም አብሮ ተዘጋ፤
"ምን ላድርግ?"ከሀያ ደቂቃ በላይ ባለሁበት ቦታ ተገትሬ ማሰብ እንኳን አቅቶኝ ደንዝዤ ቆየሁ።ወደጓሮ ሄድኩ ..፡፡.ካልተቀየረች አንድ ወደጊቢ ዘሎ መግቢያ ምቹ ቦታ ነበረች..አዎ አገኘኋት።ዙሪያ ገባውን ዞር ዞር ብዬ ሰው አለመኖሩ አረጋገጥኩና እንደምንም ተንጠላጥዬ ዘልዬ ግቢውስጥ ገባሁ። ድሮ የሀይእስኩል ተማሪ እያለሁ በተለያየ ምክንያት ውጭ ሳመሽና በራፍ ሲዘጋብኝ በዚህ ዘዴ ነበር ወደ ውስጥ የምገባው..፡፡ይሄው የዛን ጊዜው ልምድ ለዛሬ ረዳኝ።
የውጭ መብራት ስለጠፍ ግቢው በፀጥታና በጭለማ ተውጧል።ኮቴዬን ሳላሰማ ቀስ ብዬ ወደልጄ ክፍል ማለት ወደእኔ የድሮ ክፍል አመራሁ...፡፡ወይ የእኔ ማር እንዳልኳት መስኮቱን ከፍታ ነው የተኛችው። እንደምንም ተንጠላጠልኩና መስኮቱ ላይ ወጣሁ ..ደግነቱ መስኮቱ አጠር ስለሚል በተለይ ከእኔ ቁመት አንፃር አልተቸገርኩም፡፡ በቀላሉ ወደላይ ወጣሁና እግሬን አሽከርክሬ ወደውስጥ ገባሁ፡፡ ልጄን እንዳላስደነግጣት ተጠንቅቄ ወደማብሪያ ማጥፊያው አመራሁ..፡፡አብዛኛውን ዕድሜዬን የኖርኩበት ቤት መሆኑ ነገሮች የት የት እንደሆኑ በቀላሉ ለመለየት ረድቶኛል ። መብራቱን አበራሁ።ልጄ እንዴት አድጋለች..ደግሞ አተኛኞ ልክ እንደናቷ ዝርግትግት ብላ ነው።በቅርቤ ያገኘኋት ኩርሲ መቀመጫ ወደአልጋዎ አስጠጋሁና ቁጭ አልኩ ...፡፡ጭንቅላቴን ሸፍኜበት የነበረውን ኮፍያ ከላዬ ላይ ገፍፌ ጣልኩት።አይኔ ላይ ሰክቼ የነበረውን መነፅር አወለቅኩና በአቅራቢዬ ያለ ትንሽ ጠረጰዛ ላይ አስቀመጥኩ። ሙሉ ትኩረቴን ወደልጄ ሰበሰብኩ።እጆቼን በእርጋታ ወደጭንቅላቷ ሰደድኩ .."ቀስ ብዬ ስዳብሳት አይኖቾን ገለጠች...፡፡ደነገጥኩና እጄን ሰበሰብኩ...እሪ ብላ የምትጮህ መሠሎኝ ፈራሁ። ምን ላድርግ...?ፈጠን ብዬ ዘልዬ እንደአመጣጤ ልውጣ እንዴ?ብዙ ነገር አስቤ አንድንም ሳላደርግ
"አባዬ....ህልም አይደለም አይደል..?"አለችኝ፡፡
"አይደለም የእኔ ማር ...››በተኛችበት ጉንጮቾን ሞጨሞጭኳት...እሷም እጇቾን በአንገቴ ዙሪያ ጠመጠመችና ግንባሬን፤ጉንጬን ፤አገጬን ምንም የቀራት ቦታ የለም...ሙሉ በሙሉ ንቁ ሆና አልጋዎ መካከል ቁጭ አለች።
"አባዬ እኔ እኮ እመጣለሁ ስትለኝ በህልሜ መስሎኝ ነው ቶሎ የተኛሁት።
"በጣም ስለናፈቅሺኝና ..ነገ የደረጃ ተማሪ ሆነሽ ልትሸለሚ ስለሆነ እኔ አባትሽ በጣም ኩራት ስለተሰማኝ እንዴ ተደብቄም ቢሆን በዚህ ቀን ልጄን ካላየኋት እኔ ምን አይነት አባት ነኝ ?ብዬ ነው በዚህ ለሊት ሹልክ ብዬ ክፍልሽ የተገኘሁት።
"አባቴ ውድድድ ነው የማደርግህ...አሁን አቅፍቅፍ ብለን እንተኛ"
"ግን አቴቴ ለሊት ልታይሽ ብትመጣስ?"
"አትመጣም ..ደግሞ እኮ ከውስጥ ተቀርቅሯል ..ብትመጣም ገና ስታንኳኳ ቶሎ ብለህ በመስኮት ትሄዳለህ"
"ምን አይነት ብልጥ ልጅ ነው ያለኝ"አልኩና ከላይ የለበስኩትን ጃኬት በማውለቅ ጠረጳዛ ላይ አኑሬ አልጋ ላይ ወጣሁ..ይሄ አልጋ የእኔና የእናትሽ እንደነበር ታውቂያለሽ?"
"አዎ …ለዛ እኮነው ክፍሌንም አልጋዬንም የምወደው"

👍56❤4