ምንም ጥፋት ባጠፋ አንገቱ ይቀነጠሳል እንጂ እኔን ለማንም አሳልፎ አይሰጠኝም..ትምህርትን በተመለከተ ግን ለማዬም ሆነ ለአባቴ ሁሌ እንዳቃጠረብኝና እንዳስቆጣኝ ነው"...እኔ ግን ምንም መሻሻል የማሳይ ሰው አይደለሁም።ደግሞ የሚገርመው በፈተና ቀን እንደምንም ብሎ ከእኔ ርቆ ለመቀመጥ ነው ጥረቱ...እንደምንም ተጣብቄበት ከጎኑ ብቀመጥ እንኳን ለሌሎች ልጆች ሲያስኮርጅ እኔ ብረግጠው ብጎነትለው እንደው ተሳስቶ አንድ ጥያቄ አያቀምሰኝም።አንዳንድ ጊዜ የሚገርመው ከእሱ ከምኮረጅ ልጆች ለምኜ ኮርጃለው።ከዛ ስንወጣ አኮርፈዋለሁ...ሲያናግረኝ እንባዬ እርግፋ እርግፋ ይላል፡፡
"አሁን እንዲህ ተጨንቆ ከማልቀስ..በክብር እናጥና እያልኩ ስለምንሽ ብታጠኚ አይሻልም ነበር?"
"አላጠናም...እኔ እኮ ክፋትህ ነው የሚያበሳጨኝ..ከእኔ ከልክለህ ለእነሱ ማስኮረጅህ… ካንቺ እነሱ ይበልጡብኛል ማለትህ ነው..?"
እንደትልቅ ሰው ደረቱን ነፍቶ፡"አይ ለማለት የፈለኩት ከእነሱ ጋር በፍፅም አትወዳደሪም ነው..እነሱ ደነዝ ሆኑ ሌባ ከፈለጉ ማጅራት መቺ አያገባኝም..እህቴን በተመለከተ ግን ጉዳዩ ይለያል...ከአሁኑ ኩረጃ ለመድሽ ማለት ነገ ስታድጊ ሌባ..አጭበርባሪ እና ሙሰኛ የመሆን እድልሽ ከፍተኛ ነው...እንደዛ እንዲሆን ደግሞ አልፈቅድም"ይለኛል ፡፡
"ሙሰኛ ማለት ደግሞ ምን ማለት ነው?"የማላውቀውን የፓለቲከኞች ቃል ትርጉም እንዲያብራራልኝ ጠይቀዋለው።
"የተሠጠውን ኃላፊነት ተገን አድርጎ ከሀብታሙም ከደሀውም የማይገባውን ገንዘብ ወይም መማለጃ የሚቀበል ሰው ማለት ነው...ይሄንን የሚያስረዳኝ 6 ተኛ ክፍል ሆነን ነው።ከዛ በወሬው መደመም ብቻ ሳይሆን በማብራሪያውም እኮራበታለሁ፡፡ ንዴቴ ይጠፋና እስቅለታለሁ... ሁሉን እረሳለትና እላፍው እጀምራለሁ...ከዛ በማግስቱ ነይ በይ እናጥና ይለኛል፡፡ እሺ ብዬ ጎኑ እቀመጣለሁ ...ወዲያው ግን የተለመደው መሠላቸት ውስጥ እገባለሁ... ይበሳጭብኛል...በቃ መጨረሻሽ የቤት እመቤት እና ልጅ አሳዳጊ ሆኖ መቅረት ነው?ይለኛል
"የወደፊቴን የምትወስነው አንተ ማን ስለሆንክ ነው..ለሁሉም ሰው እጣ ፋንታውን የሚደለድለው እግዚያብሄር ነው"እለዋለሁ፡
"እግዚያብሄር አንዴ ፈጥሮን ምድርና በውስጧ ያሉትን ሁሉ እንድንገዛ ሰጥቶናል..ነጋችንን የምንወስነው ዛሬ በምንሰራው ስራ ነው...እጣፋንታችንን በገዛ መዳፋችን . ነው የምንፅፈው...ዛሬ በጥረታችንና በላባችን የምንገነባው መሠረት ላይ ነው ነገ ግድግዳና ጣሪያውን የምንሰራው..አሁን የምንሰራው መሠረት የማይረባና ጥልቀት የሌለው ከሆነ ነገ ምን አልባት እላዩ ላይ ጎጇ ቤት ብቻ ነው ልንገነባ የምንችለው...ፎቅ ካሰብን እኛንም ይዞ እስከወዲያኛው ይሰምጣል›› ንግግሩ ሁሉ የበሰለና የትልቅ ሰው ስለሆነ እፈራዋለሁ ..እና ሁል ጊዜ እንዳሰማነኝና በሀሳብ እንደተስማማው ነው..እንደዛ በመሆኑ ደግምሞ እፍረት ይሰማኛል፡፡ እንደዚህ ለምን ይሆናል? አልፎ አልፎም ቢሆን የማላሸንፈው ለምንድነው?ስለምወደው ማሸነፍ በምችልበት ቀንም ጭምር አውቄ እየተሸነፍኩለት ነው ?ወይስ ሴት ስለሆንኩ ደካማ ሆኜ ነው..እንደዛ አይነት ድምዳሜ ላይ እንዳልደርስ ደግሞ ከእሱ በብዙ አመት የሚበልጠውን አባቴን ብዙ ጊዜ ተከራክሬ አሸንፌው አቃለሁ ..ብቻ ግራ ይገባኛል።
ሌላው ትዝ የሚለኝ እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ ሁሌ እሁድ እሁድ ታላቅ እህታችን ሁለታችንም አንድ ላይ ሻወር ቤት አስገብታ በየተራ እያፈራረቀች ታጥበናለች። እሷን እያበሳጨንና እያስጮህናት እርስ በርስ እንጎነታተላለን ፡፡እርስበርስ ውሀ እንረጫጫለን።እህቴ አውቃም ይሁን ወይንም ከእኔ በላይ ስለምትወደው አላውቅም እኔን ለማሸት ከምታጠፋው ጊዜ በላይ እሱ ላይ የምታጠፍው ጊዜ ይበልጣል።ታጥበን ጨርሰን የለበስነውን ፓንት አውልቀን ፎጣ ከለበስን በኃላ እኔ ፓንቴን አጥቤ እዛው አስጥቼ የመውጣት ግዴታ አለብኝ እሱ ግን አውልቆ እዛው ወለል ላይ ጥሎ መውጣት ነው የሚጠበቅበት..ከዛ እህቴ በስነ-ስርአት አጥባ ታሰጣለታለች"ብዙውን ጊዜ ከንክኖኝ ለምን ?ብዬ ጠይቄ ነበር"
"ደግሞ ከእሱ ልትፎካከሪ ነው ...ሴት እኮ ነሽ ከአሁኑ እንደዚህ አይነት ስራዎችን በራስሽ መስራት መማር አለብሽ"እባላለሁ..ቅሬታዬን ለእናቴ ሳቀርብላት"የእኔ ጎረምሳ በይ ሰው እንዳይሰማሽ"ብላ ኩም ታደርገኛለች..ለእኔ ግን መልሳቸውም ድርጊታቸው መቼም ተውጦልኝ አያውቅም።ከዛ እልክ ያዘኝና ልብስ ማጠብን በፍቅር አደርገው ጀመር ።ከአምስተኛ ክፍል ጀምሮ የራሴን ልብስ ሆነ ሰውነት በራሴ የመከወኑን ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ተረከብኩ ..ስድስተኛ ክፍል ስንደርስ የእዬቤንም ልብሷች እኔነኝ የማጥበው ብዬ አብዬት አስነሳሁ.. እህቶቼ እጅ ሊሠጡ አልቻሉም..ቢሆንም እየተናጠቅኩም ቢሆን የተወሰነውን ልብሷቹን ከልብሴ ጋር እየደባለቅኩ ማጠብ ጀመርኩ ፡፡እንደዛ ማድረግ በመቻሌ አቤት የተሰማኝ ኩራት ፡፡እዬቤ የወደፊቱን እንዴት እንደሚሆን አላውቅም እንጂ ዩኒሸርሲቲ እስኪገባ አንድ ቀን ካልሲና ፓንቱን እንኳን አጥቦ አያውቅም ነበር..እኔና ሁለቱ እህቶቼ እየተሻማንና እየተናጠቅን እናጥብለታለን....በዚህ ሁኔታ ጠቅመነው ይሁን ጎድተነው ወደፊት ጊዜ ነው የሚታወቀው።
//
አንብቤ ጨረስኩ..እሷ ግን በጣም ናፈቀችኝ..ህፃንና ቀጫጫ ሆና እርቃኗን ፊቴ ከወዲህ ወዲያ ስትቅበጠበጥ..አዘናግቼ ቂጦን በእጄ መዳፍ ጧ.. አድርጌ ሳስደነግጣትና ሳስለቅሳት ትዝ አለኝና ፈገግ አልኩ፡፡
እያንዳንድን ፁሁፎቾን ባነበብኩ ቁጥር አርቄ ጥልቅ ልቤ ውስጥ የሸሸኮቸውን ትዝታዎቼን ይቀሰቀሱብኝና ጥዝጣዜው በነሀሴ ወር እንደተነሳ ሀይለኛ የጥርስ በሽታ እየነዘነዘ የምገባበት ያሳጣኛል...ትዝታው ብቻ አይደለም ናፍቆቴንም ነው የሚቀሰቅስብኝ....በተለይ ‹በዚሁ ከቀጠልሽ ወደፊት የቤት እመቤትና ልጆች አሳዳጊ ሆነሽ ነው ምትቀሪው›› ብዬ የጎረርኩባትን አሁን ባለንበት ሁኔታ ስንመዝነው ማን ትክክል አንደሆነ እዩት...ህይወት በጣም ውስብስብ እና በማይተነበይ እጣ ፋንታ የሚሾር መሆኑን ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም…ብቻ አሁን ሁሉ ነገር ነው የናፈቀኝ፡፡ እቴቴ ትናፍቀኛለች ...እህቶቼ ሁሉም ይናፍቁኛል .. የአክስቴ ባል ጋሼ ይናፍቀኛል..እቤታችን ይናፍቀኛል..ሆያ..ሆዬ አብሬ የምጨፍራቸው የሠፈሬ ልጇች ይናፍቁኛል....
ሩትን በተመለከተ ግን ከሁሉም በላይ የማደንቅላት የማስታወት ችሎታዋን ነው...ፈፅመው ወደአእምሮዬ ጎራ ብለው የማያውቁ መአት ነገሮችን ትዝ እንዲሉኝ አድርጋለች። ታሪኩን ከስር ከስር በተከወነበት ጊዜ ፅፋው ቢሆን እሺ አሁን ግን እሷም አግብታ ከወለደች እኔም የኒቨርሲቲ ከገባሁ በኃላ በመሆኑ የሚገርም ነው።
ስልኬን አስቀመጥኩና ኩርምትምት ብዬ ተኛው….እንቅልፍ ግን በቀላሉ ሊወስደኝ አልቻለም፡፡ለአስራ ሁለት አመት እኮ እሷን አቅፌ ነበር የተኛሁት….ዛሬ ግን ይሄው ትራሴን አቅፌ ተኝቻለሁ፡፡
✨ይቀጥላል✨

👍78❤5🥰3
የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........ ክፍል ሀያ ዘጠኝ
(ሜሪ ፈለቀ)
ሰውነቴን ያጋራሁት ወንድ ሊያስገድለኝ ከመሞከሩ በላይ የተሸነፍኩለት ሰው ስልኩን ዘጋግቶ መጥፋቱ ልቤን ሊያበድነው ይገባ ነበር? ክህደት ያውም ለመግደል እስከመሞከር የደረሰ ክህደት ይበልጣል ወይስ መተው? ጭፈራ ቤቱ እስክደርስ በዳዊት ከምናደደው እኩል በጎንጥም እየተናደድኩ ነበር የምነዳው! እንደደረስኩ በሩን በረጋግጄ ስገባ ለወትሮው የሚውልበት ቢሮው ዳዊት የለም። እሱ እስኪመጣ እየጠበቅኩ ቤቱን እየተዘዋወርኩ ማየት ጀመርኩ። ገና ረፋድ ስለሆነ ከሚያፀዱት ሰዎች ውጪ ማንም የለም!! ምንድነው የማደርገው አሁን? መቼም እንደድሮው ስራ ብዬ አልቀጥልበትም! ወይም ቢያንስ የአገልግሎቱን ዝርዝር ማስተካከል ይኖርብኛል!! ከዋናው ጭፈራ ቤት ይልቅ ከሀያ እጥፍ በላይ ገቢ የሚያስገኙት ባለሀብቱ እና ባለስልጣናቱ የሚያዘወትሯቸው በድብቅ የሚከወኑት የሴቶቹ ገላ እና የሚሸጡት አደንዛዥ እፆች ናቸው!! እነዚህ አገልግሎቶች ከተቀነሱ እንደማንኛውም የከተማዋ ጭፈራ ቤቶች ሰካራም የሚራገጥበት ወለል ብቻ ነው የሚቀረው!
እዚህ ቤት ስንቷ ወጣት የሀብታም እና የባለሀብት መዝናኛ ሆናለች!! (ስንቷ ክብሯን ሸጣ ሆዷን ሞልታለች! ወይም እናቷን አሳክማለች።) እዚህ ቤት ስንቱ ወጣት የማይወጣበት ሱስ ውስጥ ተዘፍቋል! (VIP ደንበኛ የሚባሉት ኮኬይን የሚገዙት ናቸው!! ሺሻ እንዲሰራላቸው ያዛሉ ኮኬይን ተደባልቆ ያጨሱታል። ኪሳቸውም ጤናቸውም አብሮ ይጨሳል።) እዚህ ቤት ስንቱ ባለጌ በሚስቱ ላይ ማግጧል (ስንቷ ምስኪን ሚስት እቤቷ ልጆቿን አቅፋ አልቅሳለች) ፣ እዚሁ ቤት ስንቱን ብልግና ማየት ተለማምጄ እንደ ጤንነት ቆጥሬዋለሁ!
ከሙሉሰው ጋር ተጋብተን ትንሽ እንደቆየን ፣ እንግዳ ወይ ጓደኞቹ እቤቱ ሲመጡ እቤቱ ሄጄ እንደሚስት ስብር ቅንጥስ ብሉልኝ ጠጡልኝ ማለት የለመድኩ ጊዜ ፣ እኔ ጠባቂ መሆኔ ቀርቶ በጠባቂ መታጀብ የጀመርኩኝ ጊዜ (አስፈላጊ ሆኖ አልነበረም! ለምን ጠባቂ እንደሚያጅበውም አይገባኝም!! ታይታ ካልሆነ በቀር) ፣ በቴሌቭዥን እንኳን ለማየት ወራት ከምንጠብቃቸው ባለስልጣናት ጋር የተለያዩ ክስተት እና ድግሶች ላይ የባሌን እጅ ቆልፌ መታየት የለመድኩ ጊዜ ፣ አንቱ የምለው ባለስልጣን ሚስት ባሏን ስታማልኝ የለመድኩ ጊዜ ፣ ራሴን ከእነርሱ እንደአንዳቸው ስቆጥር ያልታየ ድግስ ደግሼ እቤት እንዲታደሙልኝ ማድረግ የጀመርኩ ጊዜ፣ ………. ያኔ ጭፈራ ቤቱን በእኔ ስም እንዲያዞርልኝ አስደረግኩት። (እንደ ዓረፍተነገሩ እጥረት ሂደቱ ቀላል አልነበረም!! ትልቁ የገቢ ምንጩ ነው!! ባለስልጣናቱ የሚመጡት እሱን ስለሚያምኑት ነው!! )
ሌላው ጭንቅላቱን የምዘውርበት ጉድፉ ጭፈራ ቤቱ ነው! <ሌላውን ነውርህን ተወውና በወጣት ሴቶች ገላ እንደምትነግድ ፣ እፅ እንደምትነግድ ቢያውቅ እንደቅዱስ መልዓክ የሚያይህ ህዝብ ይቅር የሚልህ ይመስልሃል? > ራስምታት የሚቀሰቅስበት ርዕስ ነው።) ስራውን ለመልመድ ትንሽ ወራት ፈጀብኝ ግን ስለምደው ከእርሱ በተሻለ ያዝኩት ምክንያቱም እኔ ሙሉ ሀይሌን ተጠቅሜ እንጂ እንደእሱ ድብብቆሽ እየተጫወትኩ እና በትርፍ ጊዜዬ አልነበረም የምሰራው። ወደአካውንቴ ከሚያስገባልኝ ጠርቀም ያለ ገንዘብ በተጨማሪ ቁጭ ብዬ ራሴን የምሰማበት ጊዜ ስለማይሰጠኝ ወደድኩት።
እቅዴ በምፈልገው መንገድ እየሄደ ያልሞላልኝ ያን እናቴ ስትሞት መሳሪያ ዘቅዝቆ ይዞባት ተራ ሲጠብቅ የነበረ ደመኛዬን መድፋት ነበር። የሚኖረው አዲስአበባ ቢሆንም እዚህ ግባ የሚባል ማዕረግም ሀብትም ያለው ሰው አልነበረም!! ከሙሉሰው ጋር ግን በየእለቱ የሚገናኙ ሰዎች ባይሆኑም ቢያንስ የአንዳቸውን ፌስቡክ ፖስት አንዳቸው ሼር የሚደራረጉ ወዳጃሞች ናቸው!! እቅዴ ግልፅ ነበር ለሁለታችንም!! አንድ ቅዳሜ <ኸረ ተጠፋፋን ለምን ምሳ አንበላም?> ብሎ ሙሉሰው እንዲቀጥረው፣ ከዛ ሲገናኙ እኔ ባለሁበት ምሳ ልንበላ! (የመጨረሻዋን ምሳ) ስንጨርስ መኪናውን እኔ ልሾፍር ፣ ከዛማ ከከተማ አርቄ ወስጃቸው ትክክለኛ ማንነቴን ነግሬው ሬሳውን ለጅብ ጥዬ መምጣት ነበር እቅዴ!! ይሄን ከ10 ጊዜ በላይ ለሙሉሰው ነግሬዋለሁ!!
የዚህን ወቅት ከእኔ የሚያመልጥበት መንገድ መሞከሩን ተስፋ አልቆረጠበትም ነበር። በእቅዱ መሰረት መጥተን ከምሳ ወጥተን ወደመኪናችን ስንሄድ ሙሉሰው ለሰውየው እኔ ያልሰማሁትን ግን ሲመስለኝ እራሱን እንዲከላከል ወይ ልገድለው እንደሆነ አልያም ማን እንደሆንኩ ብቻ አላውቅም የነገረው መልዕክት አደባባይ ላይ ሽጉጥ አስመዝዞታል!! (ሙሉሰው አስቦበት ያደረገው ነገር መሆኑ በሚያቃጥርበት መልኩ ሰውየው መሳሪያ ስላልታጠቀ የሱን ሽጉጥ መውሰድ የሚችልበት አቋቋም ላይ ኮቱን ገልጦለት ነበር የቆመው) ሀሳቡ እሱ ማድረግ ያልቻለውን ሰውየው እኔን እንዲገድልለት ነበር። ተቀደመ እና ሰውየው እዛው ሞተ። በሰውየው ሞት ከማዘን በእኔ አለመሞት ሲበሳጭ ላየው ግራ ያጋባ ነበር። አደባባይ ላይ ስለነበር የሆነው ሁሉ የሆነው ታሰርኩ!! የዚህን ጊዜ ነው እስር ቤት ከእሙጋ የተዋወቅነው። ነገር የማትፋታ ጋዜጠኛ ነበረች። ያልሆነ ነገር እያነፈነፈች አላፈናፍን ስትላቸው ነው እረፍት እንድታደርግ ያስገቧት!! እሷ እስር ቤቱን ለምዳዋለች። ሲፈቷት ደግሞ ሲያስሯት፣ ደግሞ የሆነ ነገር ትቆፍራለች ደግሞ ይከቷታል። ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወቴ ሳይከብደኝ ያወራኋት ፣ ሳልደብቅ ያጫወትኳት ፣ ሳትፈርድብኝ የሰማችኝ ፣ ውርደት እና ክፋቴን እንኳን የተረዳችኝ የመጀመሪያ ጓደኛዬ ሆነች። ከሶስት ወር በኋላ ምርጫ ስላልነበረው ሙሉሰው በሚኬደው ሄዶ እራሱ አስፈታኝ። እሙም ከወራት በኋላ ተፈትታ ከእስር ቤት ውጪ ጓደኝነታችን ቀጥሎ ነበር።

👍25❤1
ወጥቼ ብዙም ሳይቆይ አንድ ባንክ ውስጥ በራሱ ፣ በእህቱ ፣ በአንድ የሩቅ ዘመዱ …… ደማምሮ የያዘውን 48% አክሲዮን ተቀበልኩት። እኔም በራሴ ፣ በኪዳን እና በእሙ ስም አደረግኩት!! የዚህን ጊዜ <እንደውም መልቀቂያ አስገብቼ ስልጣኔን እለቃለሁ!! ከዛ ምን ይመጣል?> ብሎ ፎክሮ ነበር። እንደባለስልጣን ሳይሆን እንደተራ መናኛ ሰው ራሱ የሚጠብቀው ነገር ቅሌት መሆኑን እየደጋገምኩ ማስታወስ ነበረብኝ። ይፎክራል እንጂ እንደማያደርገው አውቃለሁ። የስልጣን ፍቅሩ ነፍሱን እስከመገበር የሚያደርሰው ነው። ቀስ በቀስ ሀብቱን ስቀበለው። <አይኔ እያየ አትበያትም! ገድዬሽ ከሀገር እጠፋለሁ!> የሚልበት ቀን ብዙ ነበር!!
ከዚህ በኋላ ግን ሁሉም ሲኖረኝ ፣ ከህፃንነቴ ጀምሮ የኖርኩለትን ጠላቶቼን የመግደል ህልም ሳሳካ ፣ ካሰብኩት በላይ ገንዘብ እና አቅም ሲኖረኝ ………. ሁሉም ቀስ በቀስ ጣዕሙን እያጣብኝ መጣ!!! የምኖርበት ህልም አጣሁ!! ለራሴ ስል የምለው ምንም ነገር ጠፋኝ!! ለካንስ በበቀል ስካሬ ውስጥ ወጣትነቴን ሰውቼዋለሁ፣ ሴትነቴን ሰውቼዋለሁ፣ እናት የመሆን እድሌን ቀርጥፌዋለሁ ፣ ሚስት የመሆን መንገዴን ዘግቼዋለሁ ፣ ከሁሉ በላይ ግን ሰው መሆንን ገብሬ ከሰውነት ወርጃለሁ!! ………… ከዛማ በህይወቴ ከኪዳን እና በጥቂቱ ከእሙ ውጪ ምንም ነገር ፈገግ የማያስብለኝ ፣ ልኩን ከስህተቱ ያደበላለቅኩ ፣ ባህልን ከዘመናዊነት ያቀላቀልኩ ፣ ብልግናን ከጨዋነት ያጣረስኩ ፣ ምን ለምን እንደማደርግ የተወናበደብኝ ሆንኩ!! ሲረጥቡ መበስበስ ለምጄ የለ? ተበሳበስኩት!!
ሙሉሰውም ጭንቅላቱ የተዛባ እስኪመስለኝ ድረስ የሚሰራው ሁሉ የሚበላሽበት ፣ ከቀን ወደቀን የደጋፊዎቹ መወድስ እየቀነሰ የሚተቸው ሰው ቁጥር እየበዛ ጭራሹኑ አስተካክሎ የሚከውነው ነገር ጠፋው!! እዚህ ነጥብ ላይ እየፈራሁት መጥቼ ነበር። የሆነ ቀን ገድሎኝ ራሱን ሊገድል ይችላል ብዬ ማሰብ ጀምሬ ነበር። ግን ለምንድነው የማልረካው? እሱን በቁሙ ገድዬው ሌሎቹን ጨርሼ አሁንም የተሸነፍኩ ዓይነት ስሜት የሚሰማኝ ለምንድነው? ያ ሁሉ ቁስል እነርሱን ስበቀል የሚድን መስሎኝ አልነበር? ለምን አሁንም እንደድሮ ያመኛል? ያደረግኩት ክፋት እና በቀል ጥያቄዬን እንዳልመለሰ ወይም ህመሜን እንዳልፈወሰ እያወቅኩም በክፋት መቆመሬን ቀጠልኩበት።
ገንዘብ ካለ ሲደመር ስልጣኑ ያለው ሰው ካወቅኩ የማላገኘው ነገር ጥቂት መሆኑን ስረዳ የማይጣሱ ብዙ መስመሮች ጣስኩ። ከአንድ ባልደረባው ጋር በአንድ ውሳኔ ሳይግባቡ ቀርተው እራሱ ስንቴ መጥቶ የባለገበትን ቤት እንደማስፈራሪያ ተጠቅሞ የሙሉ ሰውን እጅ ጠመዘዘው። ሙሉሰው አይደለም የማይፈልገውን ውሳኔ መወሰን ቢሞት ራሱኮ ግድ አይሰጠኝም ግን ሰው መበቀል እና ክፋት ደሜ ውስጥ ያለ ነገር መሰለኝ። ሰውየው ሲባልግ በድብቅ ቀረፅኩት። የተከበረ ባለትዳር እና የልጆች አባት ስለሆነ የቀረፅኩትን ቪዲዮ ሳሳየው ሽንቱን ሱሪው ላይ ሊሸናው ምንም አልቀረውም። የሚገርመው ግን <ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ?> ብሎ ይሆን አልገባኝም። እየመጣ መባለጉን አላቆመም!! በድብቅ ካሜራ እንደቀረፅኩት ለአንድ ሰው ትንፍሽ ቢልና አንድ ደንበኛ ባጣ በራሱ እንዲፈርድ አስጠንቅቄዋለሁ። እውነትም ለማንም ትንፍሽ ሳይል ቀርቶ ይሆን ወይም የነገራቸውም ሰዎች እንደእርሱ ሱሳቸው በልጦባቸው አላውቅም የቀረ የለም። ለምናልባቱ የምፈልጋቸውን ሰዎች የፖርን ፊልም ማስቀመጤ አልቀረም። አስፈልጎኝ የምጠቀምበት ቀን እስኪመጣ ድረስ
የሙሉ ሰውን ከቀልቡ አለመሆን ተከትሎ ህዝቡ በሱ ላይ እንዲነሳ አጋጋይ በዛ!! ጨዋ ናቸው የሚባሉት እንኳን እሱን ለመጣል ተወለካከፉ!! ጨዋታው ስላዝናናኝ ብቻ ቆሻሻቸውን እየፈለጉ ሲሸነፉ ማየት የበላይነት ስሜት ስለሚሰጠኝ ወደድኩት። ለእኔ ቀላል ጨዋታ እንደሆነው ለእነሱ አልነበረም እና ከሙሉሰው ጀርባ ነገር የምቀምረው እኔ መሆኔን ሲያውቁ ሁለት ተቃራኒ ጠላቶች አፈራሁ። የተወሰኑት ሊያጠፉኝ የሚያደቡ ሲሆኑ የተቀሩት መዝራት የፈለጉትን ክፋታቸውን እና ወጥመዳቸውን በእኔ ተከልለው መከወን የሚፈልጉ ጥቅመኞች (አጋጣሚውን ካገኙ በራሴው ወጥመድ የሚያጠምዱኝ ሴረኞች ናቸው።) ሁለቱም ወገን በአይነቁረኛ የሚፈራኝ እና የሚጠላኝ ሰውም ሆንኩ። ባሎች ለሚስቶቻቸው ስለእኔ አሙላቸው። ሚስቶች ተሰብስበው ስጋዬን በሉት። በውስጣቸው ግን እነርሱ በባላቸው ላይ የሌላቸው ስልጣን እኔ ስላለኝ ቀኑ!! ተሰብስባ በመንገሽገሽ ስሜን የምትጠራ ለብቻዋ ስትሆን ልታገኘኝ ትፈልጋለች።
እኔም ሲሰለቸኝ እሱም ሲታክተው አንድ ቀን ቤቱ ሄድኩ!! ባልገድልህም ሞተሃል ይበቃሃል ልለው ነበርኮ አካሄዴ! ከልቤ በቅቶኝ በቃህ ካሁን በኋላ የምፈልገውን አግኝቻለሁ እና በቀሌ በቅቶኛል!! ትቼሃለሁ!! ልለው ነበርኮ!!
ሞትን ራሱ በዓይኑ ያየ የሚመስል ህፃን እያባበለ ደረስኩ!! በፊት እቤቱ የነበረው ዘመዱ እኛ መረጃ ከያዝንበት በኋላ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲያስገባው ያስገደድኩት እኔ ነበርኩ። የህፃኑን መንሰፍሰፍ ሳይ ዘንግቼው የነበረው ያኔ ሱሪውን ዝቅ አድርጎ የመለሰው መጣብኝ። ሲያየኝ ከመደንገጡ፣ መቀበጣጠሩ፣ ውክቢያው፣ ህፃኑ እንዲሄድ ማካለቡ ……. የሆነው ነገር ያልገባኝ መስዬ ተረጋጋሁ!! ህፃኑ የጎረቤት ልጅ መሆኑን አረጋግጬ ልጁን አባብዬ ወደቤቱ መልሼ ምንም እንዳልተፈጠረ ወይም እንዳልገባኝ መሰልኩ። እስኪረጋጋ እና ድንጋጤው እስኪለቀው ጠበቅኩት። ስመጣ አስቤው የመጣሁትን ነገርኩት።
«እውነትሽን ነው? በምን አምንሻለሁ? ቪዲዮዎቹን ካልሰጠሽኝ በምን አምናለሁ? የሆነ ቀን ሀሳብሽን ብትቀይሪስ?» አለኝ
«ከቃሌ ውጪ ምንም ማስተማመኛ የለህም!! ግን ሁሉንም ነገር ወስጄብሃለሁ ከዚህ በኋላ ምን ቀረኝ ብዬ ካንተጋ አኩኩሉ እጫወታለሁ? ግን እኔስ በምን አምንሃለሁ? ማረችኝ ብለህ ልትገድለኝ ብትሞክርስ? ማረችኝ ብለህ አሁንም የሌላ ለጋ ህፃን ህይወት እንደማታበላሽ በምን አውቃለሁ?» ስለው ከተቀመጠበት ዘሎ ተነሳ!! የዚህ ቀን ነው እንደአጓጉል አድርጌ ገድዬው እጄን ለፖሊስ የሰጠሁት!!!
* * * * * * * * *
ዳዊት በሩን አልፎ ሲገባ ዋናው የጭፈራ ወለል መሃል ቆሜ ቤቱን እየቃኘሁ ነበር። ሌባ አይኖቹ እየተቁለጨለጩ ወደኋላም ወደፊትም ከማለቱ በፊት ፊቴን ማጥናት ያዘ።
«አለቃ የለብኝም ብለህ በፈለግክ ሰዓት ነውኣ የምትገባ የምትወጣው?» አልኩት ሊገድለኝ የድሮ ፍቅረኛውን እንደላከብኝ ምንም ፍንጭ እንደሌለኝ መስዬ
«የኔፍቅር አትደውይልኝም ነበር? መጥቼ እጠብቅሽ ነበርኮ» ብሎ በመገላገል እየተነፈሰ ሊያቅፈኝ ተጠጋኝ!! አንገቱን አንቄ ወደላይ አንጠለጠልኩት እና እግሩ አየር ላይ ሲወራጭ ፣ የግንባሩ ደምስር ሲፈጥ እያፀዱ የነበሩት ሁለት ሴቶች መሄድም መቆምም ተወዛግቦባቸው ሲያዩኝ ቆይተው አንዷ መጥታ እግሬ ስር ወድቃ ትለምነኝ ጀመር።

👍26❤1
«ተነሺ ከእግሬ ላይ!!» ብዬ ጮህኩባት
«በእመቤቴ ይዤዎታለሁ!! እንደው በሚወዱት ይሁንብዎ!! እጆት ላይ ይሞታል!! ኸረ እንኳን አንጠልጥለውት በአንድ ጥፍ ባህር የሚሻገር ነፍሰ ቀጭን ሰበብ ይሆንብዎታል።»
«ተነሺ ከእግሬ ላይ አልኩኮ!! እንዲሞት አይደል እንዴ ታዲያ!» ጮህኩኝ ድጋሚ
«እኔንም እንደፈለጉ ያድርጉኝ ከፈለጉ አልነሳም!!» ብላ አንድ እግሬ ላይ ተጠመጠመች። ሌላን ሰው ለመታደግ መሬት መንበርከኳ ገረመኝ። ትንፋሽ አጥሮት ሲልሞሰሞስ እያየሁት አሰብኩ!! ንዴት ላይ ሆኜ በፍፁም የማስብ ሰው አልነበርኩምኮ!! የድሮዋ እኔ ብሆን እጄ ላይ ይህችን ደቂቃ አይቆይም! ገና ሲመጣ ዘግቼው ነበር። ሆኖልኝ ቆይቶ እንኳን ቢሆን እግሬ ስር የተደፋችውን ሴት ታግሼ ተነሺ አትነሺ ግብ ግብ አልገጥምም! ይሄኔ ገንብሬ ጥያት ነበር!! አሁን ተቀይሬያለሁ ወይም ለመቀየር እየሞከርኩ ነው! መሬቱ ላይ ለቀቅኩት!! ሴትየዋ ከእግሬ ላይ ተነሳች። እየተንከባለለ አስሎ ሲያበቃ! መሬቱ ላይ ቁጢጥ ብዬ
«ለምን? ለምን እንዳደረግከው ብቻ እውነቱን ንገረኝ!! ከዋሸኸኝ ኪዳንን ይንሳኝ እጨርስሃለሁ!!» አልኩት! ለገንዘብ ብሎ እንደማያደርገው አውቃለሁ። የገንዘብ ችግር የለበትም!!
« ግልፅ አይደል እንዴ? ስለምጠላሽ!» አለኝ እስከዛሬ አናግሮኝ በማያውቀው ጥላቻ እና ድፍረት። ደነገጥኩ። ወዲያው ከአፌ ቃል አልወጣም!!
«ልትገድለኝ እስከሞከርክ ቀን ድረስ እወድሻለሁ ስትለኝ አልነበር? እየጠላኸኝ ነው አብረኸኝ የነበርከው? ደግሞስ ምን አድርጌህ ነው እስከመግደል የምትጠላኝ?» ስለው ተነስቶ እዛው መሬቱ ላይ ተቀመጠ እና ቆመው ሲያዩን የነበሩትን ሴቶች አያቸው። እየተሯሯጡ ወደ ውስጥ ገቡ።
«ከአባቴ ቀጥሎ እንዳንቺ ያዋረደኝ ፣ ትንሽ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ፣ ራሴን እንድጠላ ያደረገኝ ሰው የለም። ከዛሬ ነገ ትወጂኛለሽ፣ በፍቅርሽ እፈወሳለሁ ብዬ ጠበቅኩሽ። በየቀኑ ናቅሽኝ!! ለፍቅሬ ምላሽሽ ሁሌም እንደበረዶ የቀዘቀዘ ቃላት ነው የምትወረውሪልኝ። <አንተም ወንድ ሆነህ?> ያላልሽኝን ቀን ብቆጥረው ከእጄ ጣት አይበልጥም!! ለአባቴ እንደልጅ እንደሰው ነው የከሸፍኩበት። አንቺ ግን ወንድነቴንም ነው የቀማሽኝ!! አብሬሽ ባሳለፍኩት እያንዳንዱ ቀን ትንሽ በትንሽ በራስ መተማመኔን እየሸረፍሽ ካንቺ ሌላ ሴት እንደወንድ እንኳን የማትቆጥረኝ እየመሰለኝ አብሬሽ ቆየሁ። ምክንያትሽን ሳትነግሪኝ ለወራት ስትዘጊኝ እጠብቃለሁ። ምክንያትሽን ሳትነግሪኝ ስትመለሺ እቀበልሻለሁ። ላንቺ ምንም ነኝ!! በፈለግሽ ሰዓት ሄደሽ ስትመለሺ የምታገኚኝ እቃሽ ነኝ!! እኩል ድርሻ ባለን ቤት ላይ እንኳን ፈላጭ ቆራጯ አንቺ ነሽ!! አንቺ አለቃ እኔ ባሪያሽ ነኝ!! ንገሪኝ ለመጥላት በቂ ምክንያት አይደለም?»
አልመለስኩለትም። ቁጢጥ ካልኩበት ተነሳሁ!!!! ቆሜ ምን እንደማስብ አላውቅም ግን ፈዝዣለሁ። እሱ ከአሁን አሁን ምን ታደርገኛለች ብሎ በሰቀቀን እየጠበቀኝ ነው።
«ይቅርታ!!! ይሄ ሁሉ አይገባህም ነበር። እንዲህ እንዲሰማህ ማድረጌንም አላውቅም ነበር። ስቀህ ማለፍህ ልክ የሆንኩ እንዲመስለኝ አድርጎኛል። ይቅርታ አድርግልኝ!! ከልቤ ነው አንተ ጥሩ ሰው ነህ!! ቢያንስ ለእኔ ጥሩ ሰው ነበርክ!! አይገባህም ያልኩህ የእውነቴን ነው። » አልኩት። ሞቶ መንግስተሰማያት ደርሶ ይሁን በእውኑ እዚህ ምድር ላይ ሆኖ ይሄን ከእኔ አፍ መስማቱ እያወዛገበው አይኑን ጎልጉሎ ያየኛል።
«ሙከራህን ብትደግመው የምምርህ እንዳይመስልህ!! ቤቱን ልሸጠው እፈልጋለሁ!! ህገወጥ ስራውን የምታቆም ከሆነ የእኔን ድርሻ ልሽጥልህና የቤት ኪራይ እየከፈልክ ስራበት። አይ ካልክ ግን ቤቱን ለቀህ ትወጣለህ!! እኔ ጨርሻለሁ!!» ብዬው ወጣሁ።
ከወጣሁ በኋላ ያ ስሜት ተሰማኝ!! ባዶ የሆነ ስሜት!! ጣዕም አልባ ስሜት!! የምሄድበትን ሳላውቅ እየነዳሁ ስዞር ቆይቼ አመሻሽ ላይ አባ መልከፃዲቅ ያሉበት ቤተክርስቲያን ሄድኩ!! እግራቸው ላይ ተደፍቼ ማልቀስ ፈልጌ ነው።ኮቴን ክለብ እረስቼው የለበስኩት እጁ የተጋለጠ ነገር ስለነበረ ሱቅ ገብቼ ነጠላ እና ሹራብ ደርቤ ቀጠልኩ።
በሩን አልፌ ቦታዬጋ ስደርስ አይኔ ከቆቡ ውስጥ ተጎልጉሎ ሊወጣ ደረሰ። አባ የሚቀመጡባት ጉቷቸው ላይ ተቀምጠው ጎንጥ እኔ በምቀመጥበት ቦታ እግራቸው ስር ተቀምጦ ያወራሉ። እግሬ ተወለካከፈብኝና ቆምኩ። አየኝ!! ምንም ቀን እንዳልዘጋኝ!! ልቤ በመከፋት ተኮማትራ ከእጄ ጭብጥ እንዳላሳነሳት፣ መከፋት እና ተስፋ መቁረጥ እንዳላሸከመኝ ሁሉ ፈገግ አለ
ይቀጥላል.........
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️

👍30
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
///
እንደተለመደው ከሳምንት በኃላ ወደሆቴል መጥታ እኔም ስራዬን ስሰራ አሷም ስትዝናን አምሽተን እኩለ ለሊት ላይ ተያይዘን ወደተከራየችው ሆቴል በመግባት ተቃቅፈን ተኝተን እያወራን ነው፡፡እንዴት እንደሆነ አለወቅም ወሬው ደግሞ እንደወትሮው ፍቅር ፍቅር ሚሸት ሳይሆን ኮምጠጥ ያለ ሀገራዊ ጉዳይ ነው..፡፡ዛሬ እንኳን እሷን የሚመጥናትን ጫወታ ልጫወት ብዬ መሰለኝ በገዛ ጥያቄዬ ውስብስብ ወሬ ውስጥ እነንድንገባ መንገዱን የከፈትኩት
‹‹መቼስ ወታደር ነሽ…ለዛውም ባለትልቅ ማአረግ….የሀገሪቱን ችግር ለማከምና ከመከራዋ እንድትወጣ ለማገዝ በደምና በላብ ዋጋ ከፍለሻል…ግን አሁን ስታስቢው መስዋዕትነቴ ባክኗል….ደሜም ያለውጤት ፈሷል ብለሽ ታስቢያለሽ፡፡?››ስል ጠየቅኳት፡፡
እስኪ ምን ሚሉት ጥያቄ ነወ….ይሄንን ጥያቄ አንድን የተከበረች ጄኔራል ስጠይቅ የሀገሪቱ ደህንንት ቢሮ ጆሮ ቢገባ የትኛው ተቃዋሚ አካል ነው አስርጎ ያስገባህ ብሎ ቢያፍነኝ ይፈረድበታል?
እሷ ግን ተረጋግታ መመለስ ጀመረች‹‹ፈፅሞ አላስብም…አርግጥ እኔ እንዲሆን እያሰብኩና እያለምኩ እንደነበረው የተከወነ ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ውጤቱ ከግምቴ በጣም ዝቅ ያለ ወይንም ሙሉ በሙሉ ተቃራኒ ሊሆን ይችላል…እንደዛም ነው የሆነው፡፡ግን እኔ ነገሮችን ለማስተካከል በተሰጠኝ ኃላፊነትና ሪሶርስ በአግባቡ በመጠቀም በቀናነት እናም በሙሉ ችሎታዬ ተንቀሳቅሼለሁ ወይ ?ብዬ ነው የምጠይቀው…መልሱ አዎ ከሆነ በቂ ነው፡
ነገሮችን ሁሉ በውጤታቸው ብቻ ከለካህ መጨረሻው ጥሩ አይሆንም… ወደፊትም አያስኬድህም፡፡
‹‹እስቲ አብራሪልኝ››
‹‹ስራዎችን ከመከወንህ በፊት ስለስራው ሞያዊ ጥናት ታርጋለህ፡ ውጤታማ የሚደርግህን እቅድ ትነድፋለህ ፡ከዛ ወደተግባር ትገባለህ…. .በእኔ አረዳድ እቅድ በወረቀት በሰፈረው መሰረት ተግባራዊ የሚሆነው ከ50 ፐርሰንት በታች ነው..ማንኛውም እቅድ ማለቴ ነው..የጦርነት እቅድ ሲሆን ደግሞ የተለየ ይሆናል….ግን ደግሞ እቅድ አስፈላጊና በጥንቃቄ መሰራት የሚገባው ጉዳይ ነው..ቢያንስ ነገሮችን ለመጀመር መነሻ ይሆንሀል፡: በሂደት ለሚያጋጥሙህ እዲስ ክስተቶች የሚሆን የሚሳራ ቅፅበታዊ እቅደም ለማቀድ መነሻ ፍንጭ ይሰጥሀል…በአጠቃላይ ለማለት የፈለኩት እንኳን እንደኛ የተወሳሰበና የተጨመላለቀ የችግር ትብታብ ያለባት ሀገር ይቅርና ባደጉት ሀገሮች የማስፈፀም ብቃት እንኳን ነገሮች እንደሀሳብ አይሄዱም..ምሳሌ አሜሪካ ኢራቅን ሰትወር የስንት ቀን ኦፕሬሽን ብላ ገባች? ስንት አመትስ ፈጀባት…?ራሺያ ዩክሬንን ላይ ለሳምንት ብላ የጀመረችው ጦርነት ምን ያህል ጊዜ ፈጀባት ?
ይሄ የወታደራዊ ፤ አመራሩ ችግር፤የፖለቲካኛው ችግር ፤የቦታው ነባራዊ ሁኔታ..የተፋላሚህ አቅድህን ለማበላሸት የሚነድፈው ሌላ እቅድ…የተፋላሚህ ወዳጆች ተፅዕኖ፤የአንተ ጠላቶች በሁኔታው ለመጠቀም የሚያደርጉት ጥረት፤ ጠላትም ወዳጅም ሳይሉ ከነገሩ ገቢያቸውን ለማደለብ የሚዳክሩ ሚዲያዎች፤ነጋዴዎች፤ ደላላዎች….ምኑ ቅጡ…የአንተ ዕቅድ በእግዚያሄር ካልተዘጋጀ በስተቀር የእንዚህን ሁሉ ተዋናይ ትርምስ ከግምት አስገብቶና በትክክል ተንብዮ የሚሰራ እቅድ ሊያዘጋጅልህ አይችልም…..እና መጀመሪያ ይሆናል ተብሎ ተነገሮህ አንተም ያንን አምነህ ወደጦርነት ትገባለህ..እንዳልከው ላብህም ይንጠባጠባል ፤ ደምህም ይረጫል …አካልህም እየተቦደደሰ ይበራል…..ነፍስህም ልትሰናበት ችላለች…. ውጤቱ ደግሞ ከታሰበው ተቃራኒ ወይንም በጎን የልታሰበ ሽንቁር ከፍተት እየተስገመገመ ወዳልታወቀ መዳረሻ የሚያደርስ ሊሆን ይችላል፡፡
፤የዛን ጊዜ ልትደነግጥ ትችላለህ…ሊከፋህ ይችላል…ግን በምንም አይነት ተስፋ አትቆርጥም…ተስፋ መቆረጥ ከሁሉም ጠባሳዎችህ እንዳታገግም እና ሁለተኛ እድል እንዳሞክር እስከወዲያኛው ነው የሚያደቅህ….ሀገር ደግሞ ቢያንስ ህልውናዋ ማስጠበቅ የምትችለው ሁል ጊዜ ተስፋ በማድረግና ከነመዝረክረኩም ቢሆን ወደፊት በመጎዝ ነው፡፡በምንም አይነት ሁኔታ በሀገርህ ላይ ያለህ ተስፋ በውስጥህ እንዲፈርስ ልትፈቅድ አይገባም፡፡በተለይ በዚህ የኢንፎርሜሽን ዘመን ጦርነት በጣም የማይተነበይ እና የሸረሪት ድር አይነት የተወሳሰበ ሆኗል፡፡
ከሌላ አካል ተልኮ ተሰጥቶት እንደሚጠይቅ እንደ ችኮ ጋዜጠኛ ሙግቴን ቀጠልኩ‹‹ግን የእኛ ሀገር ዋና ችግር ምን ይመስልሻል…?ድህነታችን መሆኑን አውቃለሁ…. ቢሆንም እንደወታደር በሀገሪቱ ፍፅም ሰለም እንዳትሆን ዋናው እንቅፋት ምንድነው?፡፡
‹‹ትክክል ነህ እኮ.. በግራም ዞርክ በቀኝ ለእኛ ሀገር ዋነው ችግራችን ድህነታችን ነው፡፡፡ሚያናጥቀንም ሚያላትመንም እሱ ነው፡፡ግን ከድህታችን በመለስ ዋናው ችግር ምንድነው ካልከኝ ፅንፈኝነት ነው…ፅንፈኝነት ማለት አይነ ልቦናል ጨፍኖ በደመነፍስ ማሰብ ነው፡፡ያ ማለት በውድቅት ለሊት የቤቱን መብራት ሁሉ አጥፍቶ የጠፋብንን መርፌ ለማግኘት የመዳከር ያህል ነው፡፡ቀንቶህ መርፌውን በዳበሳ መጨበጥ ብትችል እንኳን መወጋትህና መድማትህ አይቀርም፡፡
ፅንፈኝነት የራስን ፍላጎት ጥቅምና ስሜት ብቻ መሰረት አድርጎ ብይን መስጠት ለዛም ብይን ደምሳሽና ጨፍላቂ ውሳኔን መውሰድ ማለት ነው፡፡
አክራሪነት በብዙ ዘርፍ አለ....የብሄር አክራሪነት፤ የሀይማኖት አክራሪነት ፤የፆታ አክራሪነት ፤የፖለቲካ አክራሪነት…የሀገር አክራሪነት ወዘተ፡፡ፅንፈኝነት ነገሮችን ከአንድ የተቸነከረ ፖይንት ኦፍ ቪው ብቻ መመልከትና ፍርድ መስጠት ማለት ነው፡፡ወደአንዱ ፅንፍ በጣም ተለጥፈን ስንቆም ከሌላኛው ፅንፍ ያለን ርቀት በጣም ሰፊ ይሆናል…ከእይታችንም ይጠፋል፡፡
ፅንፈኞች መቼም የእኛ ነገር የመጀመሪያው ይሁን…የእኛ ነገር ይሰማ …የእኛ ነገር ይቀመስ ፤ የእኛ ነገር ይበላ….ባይ ናቸው፡፡ማመቻመች የሚባል ነገር ፈፅሞ አልፈጠረባቸውም…. የጋራ በሆነ ነገር ላይ ደግሞ የእኔ ብቻ አይሰራም…፡፡
እና እንደአንድ ወታደር የትኛውንም ሀይማኖት ተከታይ ብትሆን ችግር የለብኝም.፤የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ብትሆን እኔን አይመለከተኝም…አህዳዊ ብትሆንም ፌዴራሊስት ብትሆንም ግድ አይሰጠኝም….ግን ሁሉም ውስጥ ሆነህ ፅንፈኛ ከሆንክ የዛን ጊዜ ችግር አለ..አንዳንድ ሰው አክራሪነት ላይ የተሳሳተ የትርጉም ስህተት ሲፈፅም አያለሁ….አንድ ሰው የራሱን ሀይማኖት ይዞ የሀይማቱን ዶግማዊና ቅኖናዊ ህግጋን ሳያፋለስ በፍፅም መሰጠትና ትኩረት ተግባራዊ በማድረጉ አክራሪ ሀይማተኛ ነው ልንለው እንችላለን…አክራሪነቱ ግን የሌላው ሀይማኖት አማኝ ላይ ድንጋይ እስካልወረወረ እና የሌላውን አማኝ ማምለኪ ቦታ ላጥቃና ላውድም እስካላለ ድረሰ በክፍትም በስህተትም ሊወሰድ አይገባም….፡፡በብሄርም ስትመጣ እንደዛው…አንድ የኦሮሞ ብሄር ተከታይ በኦሮሚኛ ቋንቋ ማውራቱ..በእየእለቱ የኦሮሞ ባላዊ ልብስ መልበሱና ገንፎና፤አንጮቴ እና ወተት የእየለት ምግቡ ማድረጉ በፍፅም ችግር የለውም…..ችግሩ በአካባቢዬ ያለው ስው ሁሉ ከአንጮቴ ውጭ ሌላ ምግብ እንዳይቀምስ ካለና በጆሮዬ ከኦሮምኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ አንዳይሰማ በማለት ከሌላው ብሄር ጋር ባለው መስተጋብር ችግር መፍጠር ከጀመረ ነው፡፡

👍33❤7🔥2🥰2👏2😁1
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ እኔም አክራሪነትን በጣም መፀየፍ ከጀምርኩ ቆየሁ፡፡በሀይማኖት አክራሪዎች ምክንያት ሀይማኖት የሚባል ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ…በብሄር አክራሪዎች ምክንያት ለብሄሬ ያለኝ ትርጉምና ፍላጎት ተንጠፍጥፎ ባደ ስለሆነ ብሄር አልባ አድርገውኛል፡፡፡የሀገር አክራሪዎች ደግሞ ሀገሬን ሊያሳጡኝ ጫፍ ላይ ናቸው፡፡ ›› የሚል ማብራሪያ ሰጠዋት፡፡
‹‹አየህ ጥሩ ገልፀኸዋል ፡፡የአክራሪዎቹን ዋና አላማ ምንም የማይጠይቁ አባላትን ከጎናቸው ማሰለፍ እናም ከመሀከል ይሉትን ገፍተውና ተስፋ አስቆርጠው ከጫወታው ውጭ ማድረግ ነው..ከዛ ማን ይቀራል እንሱ ከነጭፍን ደጋፊዎቻው፡፡ …ተቃራኒዎቻቸውም በተመሳሳይ የጫወታ ህግ ከነጭፍን ደጋፊዎቻቸው በዛኛው ጫፍ ይቆማሉ…..ከዛ ጦር መወራወሩና መሳሪያ መተኳኮሱ ቀላል ይሆናል…፡
.በዚሀ መሀል ሀገር ይበጠበጣል…ወታደሩ ባረባ ነገር ከአንዱ ጫፍ ወደሌላ ጫፍ እየተስፈነጠረ ሁኔታዎችን ለማስተካክል መስዋዕት መክፈሉን ይቀጥላል….ደግሞ የሚገርመው እኮ የፅንፈኞች አሰላለፍ እንደሁኔታዎች መከረባበቱ ነው፡፡አሁን በብሄራቸው መመሳሰል ምክንያት የአንድ ቡድን ማሊያ ለብሰው ለአንድ አላማ ሲፋለሙ የቆዩ ጓደኛሞች..የጫወታው ግጥሚያ አይነት ወደሀይማኖት ሲቀየር ጭራሽ እንደማይተዋወቅ በተለያየ ቡደን ተሰለፈው እርስ በርስ ይጠዛጠዛሉ፡፡አክራሪዎች አንድ የጋራ ፀባያቸው ፀረ እኩልነት መሆናቸው ነው…በአፋቸው ቢያንበለብሉም ፈፅሞ ከሌላው ጋር እኩል መሆንን አይቀበሉም፡፡የእነሱ ሀይማኖት የሀገሪቱ የመጀመሪያ እንዲሆን ፤የእነሱ ብሄር የሀገሪቱ የበላይ እንዲሆን ወዘተ..ብቻ ነው የቀንና ሊት ህልማቸው፡፡
‹‹መፍትሄው ግን ይኖረው ይመስልሻል፡፡››
‹‹መፍሄውማ መሀከል ላይ ያሉት አንዳንተ በእነሱ ድብቅ ሴራ በሂደቱ ተስፋ ቆርጠው ከመድረኩ እራሳቸውን ያገለሉ ወይም ጆሮቸውን ደፍነው የተኙትን ማንቃትና እነሱን ማብዛት ሲቻል ነው፡፡ ››
‹‹መንግስትስ ?››
‹‹እኛ ስለመንግስት የማስፈፀምና የመቆጣጠር አቅም ያለን ግንዛቤ ከእውነታው ጋር ፍፅም የተምታታ ነው።ምን አልባትም ለሺ ምናምን አመታት በነገስታት ሲገዛ የኖረ ማህበረሰብ ነገስታት ደግሞ ስልጣናቸው ከላይ የተፈቀደ የሚመርጣቸውም የሚቀባቸውም አምላክ እንደሆነ እየታመነ ሁሉን አድራጊነትንና ሁሉን አዎቂነትን ገንዘባቸው እንደሆነ ሲወርድ ሲፈረድ በመጣ የክብርና የፍርሀት ስሜት ሲተዳደር የኖረ ማህበረሰብም ዛሬም መንግስት ማለት የመጨረሻውን ወንበር የያዘው ሰውዬ እንደሆነ በደመነፍስ ማመን በሀገሪቱ ለመጣው ስኬትም ጠቅልሎ ለእሱ መስጠት ውድቀቱንም እንደዛው ጠቅልሎ በእሱ ማሳበብ ። ሁሉን ማድረግ ይችላል ብሎ በሌለው አቅምና ችሎታ ላይ መተማመንና ተስፋ ማድረግ...ሳይፈፀም ሲገኝ ስላልቸለና አቅም አጥሮት ሳይሆን ሆነብሎ በተንኮልና በዳተኝነት ነው ብሎ በመውሰድ መማረርና እራስን መጉዳት…ምሳሌ የምንኖርበት ከተማ ስፋቱ ምን ያህል ነው።ስንት ቀበሌ አለው?ስንት ህዝብ ይኖርበታል..?ያን ህዝብ የየእለት ደህንነት ለመጠበቅ ስንት ፓሊስ ጣቢያና ምን ያህል ፓሊስ አለ? በከተማዋ 50 የተለያየ ቦታ በአስር ደቂቃ ልዩነት አደጋ ቢደርስ እና ፓሊስ ሪፓርት ቢደረግለት ስንቱ ጋር ከምን ያህል ጊዜ በኃላ መድረስ ይችላል?የተረኛ ፓሊስ እጥረት፤የትራንስፓርት እጥረት-የተመደብት ፓሊሶች ዳተኝነት፤የአደጋዎቹ ቦታዎች ከንዑስ ፓሊስ ጣቢያዎች ያላቸው እርቀት..?
እና ፀጥታችንን የሚጠብቀው መንግስት ነው? ደህንነታችንን እያስከበረ ያለው መንግስት ነው?አይደለም፡፡ እዚህ ላይ የመንግስት ቀጥተኛ ሚና ኢምንት ነው።ግን ደግሞ እንደማህበረሰብ በውስጣችን ያዳበርነው መንግስትን የመፍራት…የማስፈፀም አቅሙን አጋኖ የማሰብ ባህሪያችን እርስ በርስ እንድንከባበር አድርጎናል.. የወጡትን ህጎች የማክበር አቅማችንም በንፅፅር ሲታይ ከፍተኛ ነው።እውነታው ግን መንግስት ህግን ለማውጣት ያለውን ብቃት ያህል እነዛ ህጎች እንዳይጣሱ ቀድሞ የመከላከል እና ሲጣሱም ተከታትሎ የመቅጣት አቅሙ ውሱን ነው።እግዚያብሄር ይመስገን ይህንን እውነት በልኩ የሚረዳ የማህበረስብ አካል ከ2 ፐርሰንት የማይበልጥ በመሆኑ መንግስት እንደሰፈር ጎረምሳ እየተኮሳተረ እና እያስፈራራ ብቻ እራሱን አስከብሮ ለረጅም ጊዜ እንዲኖር እረድቶታል፡፡
‹‹እና ማጠቃለያሽ ምንድነው;?››
‹‹ማጠቃለያውማ….ምን ጊዜም እራስህ በራስህ ለመጠበቅ ትጋ…ከመንግስት የምትጠብቀውን ነገር በተለይ እንደግለሰብ መንግስት ለእኔ ማድረግ አለበት ብለህ የምታስበውን ነገር በተቻለህ መጠን ለዜሮ የተጠጋ ይሁን…ያን ጊዜ ከራስህም አልፈህ ሌሎች የእኔ የምትላቸወን ሰዎች ለመጠበቅና ለመታደግ ብቃት ይኖርሀል …በተቃራኒው መንግስት እንዲህ አደረገ...መንግስት ለምን እንዲህ አያደርግም? እያልክ በየቀኑ ስትነጫጭና ስታማርር ምትውል ከሆነ በስተመጨረሻ የጨጓራ በሽተኛ ሆነህ ታርፈዋለህ እንጂ በህይወትህ ምንም ለውጥ አታመጣም፡›
‹አምርሮ ማማረር እኮ ወደአምርሮ መጥላት ያድጋል ...አምርሮ መጥላት ደግሞ መንግስትን ለማስወገደ እና በሌላ ለመተካት እርምጃ ለመውሰድ ይገፋፋል ፡፡››አልኳት ፈራ ተባ እያልኩ….
‹‹ችግሩ እሱ አይደል?››
‹‹እንዴት?››
‹‹በአንተ እድሜ እንኳን ስንት መንግስት ተቀየረ…?እና መንግስት በመቀያየሩ በአንተ ህይወት ላይ ያመጣው ለውጥ ምድነው..?በሀገሪቱስ..?አንዱ መንግስት ሲመጣ በዛኛው መንግስት የነበረ ሰህተትን ያስተካክል ይሆናል ግን ደግሞ ውሎ ሳያድር ተመጣጣኝ የሆነ ሌላ የራሱ ችግር ይፈጥራል..በተለይ አፍሪካ ውስጥ መንግስት መቀየር ማለት በአጠቃላይ የችግር አይነትን መቀየር ማለት ነው..››
‹‹ውይ ይብቃን የፓለቲካ መድረክ አደረግነው እኮ..››
‹‹እሺ እንደውም ደክሞኛል.ማለቴ እንቅልፌ መጥቷል እንተኛ…››
‹‹እሺ ጓደኛዬ እውነትሽን ነው እንተኛ››ተንጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁና ልክ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አዳሮች አይነት አተኛኘት ተኛን፡፡

👍48👎1🥰1
የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........ ክፍል ሰላሳ (የመጨረሻ ክፍል)
(ሜሪ ፈለቀ)
ብዙ ጥያቄዎች ስለእርሱ እያብሰለሰልኩ አልነበር? ቅድም ተበሳጭቼበት ባገኘው የምጮህበት ሲመስለኝ አልነበር? ታዲያ ገና ሳየው እንኳን ልቆጣ የማወራውም የማስበውም ጠፍቶኝ አባን ጉልበት ስሜ እሱን እጁን ጨብጬ ተቀመጥኩ። እየመላለስኩ <ደህና ኖት> ስል ቆየሁ አባን!!
«ተገናኛችሁም አይደል? እኔ የምፈፅማት ጉዳይ አለችኝ!» ብለው ተነሱ። እሳቸው ከአጠገባችን ከራቁ ከደቂቃዎች በኋላ እንኳን ዝም ተባብለናል። የሆነ በነዚህ ባልተገናኘንባቸው ቀናት በመሃከላችን መራራቅ የተፈጠረ ዓይነት ስሜት አለው።
«ቸር ባጀሽ?» አለኝ እኔ ቀድሜ እንዳወራ ሲጠብቅ ቆይቶ! ቸር ነው የባጀሁት? እሱ ምን ሆኖ እንደዘጋኝ የሀሳብ ካብ ስከምር እና ስንድ እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ የተሰቃየሁት ፣ እወድሻለሁ እያለ አንሶላ አብሮኝ ሲጋፈፍ የነበረው ሰው ከምድረገፅ ሊያጠፋኝ እስኪሻ አምርሮ የሚጠላኝ ሰው ሆኖ ማግኘቴ ፣ አሁን ወደዚህ እየመጣሁ በብዙ ባዶነት መዋጤ …… ይሄ ቸር ከተባለ አዎ ቸር ነው የባጀሁት!!
«መሄድ ነበረብኝ!!» አለኝ እኔ ምንም ሳልጠይቀው! ዝም አልኩ!
«አናግሪኝ እንጅ ዓለሜ?» ሲለኝ ኩርፊያዬን ትቼ <እቀፈኝ> ማለት ነበር ያሰኘኝ ደጀ ሰላም ሆንኩ እንጂ!!
«ምን ልበል? መሄድ ኖሮብኝ ነው አልከኝ አይደል? <የት? ለምን ሄድክብኝ? > የማለት መብት አለኝ? ከመሄድህ በፊት ልታሳውቀኝ እንኳን ግድ ያልሰጠህ አያገባትም ብለህ አይደል? ያስኬደህ ነገር ከእኔ በላይ ያንተን ትኩረት የሚሻ ነገር ቢሆን አይደል ሀሳብ አሳቅፈኸኝ የጠፋኸው? ዝም ከማለት ውጪ ምን አቅም አለኝ?» ስለው በጣም ስፍስፍ ባለ አስተያየት አይቶኝ ከተቀመጠበት ተነሳ
«ተነሽ እንሂድ?» አለኝ
«የት?»
«እኔእንጃ! ቁጭ ብለን የምናወጋበት ቦታ!!» ሲለኝ ለምንድነው ከተናገረው ዓረፍተ ነገር የተለየ የገባኝ? ማውጋቱንማ እያወጋን አይደል? እየነካሁሽ፣ እያቀፍኩሽ እየሳምኩሽ የማወጋሽ ቦታ እንዳለ ነው የሰማሁት። ተነሳሁ!! ደጁን ስመን ወጣን እና መኪናዬን ወዳቆምኩበት ልሄድ ስል ታክሲ ይዘን እንሂድ ሲል ለምን ብዬ አልጠየቅኩም!!
«አባጋ እንደምመጣ በምን አወቅህ?»
«ጭንቅ ጥብብ ሲልሽ የምትመጭ እዚሁ አይደል? ደሞ አርብ አይደል? አርብ አርብኮ ለወትሮም አባጋ ታዘወትሪ ነበር!»
ከዋናው መንገድ ደርሰን ከቆሙት ላዳዎች አንዱን ወደሱሉልታ ይዞን እንዲሄድ አናግሮት ከኋላ ወንበር ገባን። መንገድ ስንጀምር እጁን በትከሻዬ አሳልፎ አመልጠው ይመስል ተሽቀዳድሞ ስብስብ አድርጎ ደረቱ ላይ አደረሰኝና ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ።
«እኔ ላይ ሙሉ መብት አለሽ!! የልቤ አዛዡ አንቺ አይደለሽ? ያንቺን ያህል እኔ እንኳን መች በገዛ ልቤ አዝበታለሁ? አያገባሽም ብዬ አይደለም ሳልነግርሽ የጠፋሁ።» አለኝ። ካቀፈኝ በኋላ ምክንያቱን ቢነግረኝም ባይነግረኝም ግድ አልነበረኝም። ተናድጄ የነበረውን ፣ ከፍቶኝ የነበረውን ፣ ተቆጥቼ የነበረውን ፣ መጠየቅ እፈልግ የነበረውን ……… ሁሉንም ረሳሁት!! እጄን በሆዱ ላይ አሳልፌ ወገቡን አቀፍኩትና በቃ ዝም አልኩ!! እንደዚህ ታቅፌ አላውቅማ!! ደረት ከዝህች ዓለም ውጥንቅጥ መጠለያ ቤት መሆኑን አላውቅማ!! የሰው ልብ ማዘዝ እንደሚቻል አላውቅም ነበራ!! ብዙዙዙዙ ከፍቅር ጎድዬ ነበራ!! ሲጠፋብኝ ሳቄንም ሀሳቤንም ይዞብኝ የጠፋ ፣ ሲመጣልኝ ዓለምን ያስጨበጠኝ ሰው ኖሮኝ አያውቅማ!! በዚሁ ሱሉልታ አይደለም ከሀገር ይዞኝ ቢጠፋ ፣ እንዲሁ ደረቱ ላይ በክንዱ ታቅፌ ብቻ ብዙ ዓመት መሽቶ በነጋ!! ያለፈው ዘመኔ ፍቅር ያልጎበኘው ምነኛ ባዶ ነበር? ፀጉሬን ሳም አድርጎ
«እየተከተሉሽ ነበር!! …… » ብሎ ሊቀጥል ሲል
«ዝም ብለህ እቀፈኝ!! በኋላ ትነግረኛለህ!! አሁን ዝም በለኝ!!» አልኩት ከእርሱ ፍቅር ውጪ ቢያንስ ሱሉልታ እስክንደርስ መስማት የፈለግኩት ነገር የለም!! ክትትል ፣ ፀብ ፣ በቀል ፣ ሴራ ….. የት ይሄድብኛል ሲሆንብኝና ሳደርገው የኖርኩት አይደል? እንዲህ የታቀፍኩት ግን ዛሬ ብቻ ነው! እንዲህ ልቆይና የሱን የልብ ምት የእኔን የልብ ፈንጠዝያ ልስማ!! ከዛ በኋላ የሚከተሉኝ ሰዎች እንኳን አጊንተው ቢገድሉኝ ታቅፌ ነበር ፣ የእናትን ሞት በሚያስረሳ እቅፍ ታቅፌ ነበር፣ የበረደው ልብ በሚያሞቅ እቅፍ ታቅፌ ነበር፣ መኖር ጀምሬ ነበር።
«እሽ» ብሎ ባላቀፈኝ እጁም ደርቦ አቅፎኝ አንዴ ጨመቅ አንዴ ላላ ሲያደርገኝ ፣ አሁንም አሁንም ፀጉሬን ሲስመኝ ደረስን። ልጁን መንገድ እንደሚያሻግር አባት እጄን ይዞኝ የገባው ሪዞርት ውስጥ ካሉት ትንንሽ ጎጆ ቤት መሳይ አንደኛው ጋር ገብተን ፊት ለፊት ለፊት ለፊት ተቀመጥን። ጎጆ ቤትዋ ውስጥ እኛ ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ በተጨማሪ ሌላ አንድ ጠረጴዛ ቢኖርም ሰው የለውም ነበር እና እኔና እሱ ብቻ ነበርን። አስተናጋጁ የሚታዘዘውን ጨራርሶ እንዲሄድልን አጣድፈን አዘን ሸኘነው። መብት አለሽ ተብዬ የለ? ሁለቱንም እጄን ጠረጴዛው ላይ ዘርግቼ እንዲይዘኝ ሰጠሁት። በሁለቱም እጆቹ ያዘኝ።
«እሺ አሁን ንገረኝ!!» አልኩት በስስት የሚያዩኝን አይኖቹን(መሰለኝ) እያየሁት
«ከወየት ልጀምር?»
«እኔ እንጃ!! ማነህ? ምንም ሳይቀር ስላንተ ማወቅ እፈልጋለሁ!» ስለው ዓይኖቹ ውስጥ መከፋት ነገር ያየሁ መሰለኝ ወይም ፍርሃት እኔንጃ
«እሽ! ምንም ሳላስተርፍ አወጋሻለሁ!! ግና የቱ ነው ማን መሆኔን የሚገልጥልሽ? ያለፈ ህይወቴ? የመጣሁበት ብሄር ጎሳዬ? አባት አያት ቅድመአያቴ? እምነቴ? የእስከዛሬ በጎ ምግባሬ ወይስ ሀጥያቴ? ወይሳ አሁን የሆንኩት እኔ? በየትኛው ነው አንት ይህ ነህ ብለሽ ምትቀበይኝ?» አለኝ ያለፈው ህይወት አድካሚ እንደነበር በሚያሳብቅ መልኩ።
«ሁሉም መሰለኝ!! የሁሉም ድምር መሰለኝ አንተን አንተ የሚያደርግህ!! ሁሉንም ልወቀው!!»
«ደግ!! ከማን ጎሳ መገኘቴ ፍቅርሽን ያሳሳብኛል?» አለኝ ሲሆን አይቼው እንደማላውቅ ሽንፍ ብሎ በልምምጥ
«የእነሱ ወገን አትሁን እንጂ ….. » ብዬ የአባቴን ገዳዮች ጎሳ ከመጥራቴ መልሱን ፊቱ ላይ አገኘሁት!! ማድረጌን ሳላውቀው እጄን ቀማሁት። ልቤ ድው ድው ማለቱን ያቆመ መሰለኝ። ከዛች የተረገመች ቀን ጀምሮ እድሜዬን ሙሉ ስጠላቸው ኖሪያለሁ። ያለፉትን ወራት ግን ልቤን የሞላው የሱ ፍቅር ጥላቻዬን ከድኖት ክፋትን እየሸሸሁ ፣ በቀልን እና ጥላቻን ከልቤ እያስወጣሁ ሌላ ሰው ልሆን እየሞከርኩ አልነበር? ለምን እንዲህ ተሰማኝ ታዲያ? የሱ ፍቅር ሌላው ላይ ያለኝን ጥላቻ እንጂ ማጥፋት የሚችለው እሱ የምጠላውን ሆኖ ሲመጣ ፍቅሩ አያሻግረኝ ይሆን? ዝም ብዬ መሬት መሬቱን ሳይ አስተናጋጁ የታዘዘውን ይዞ መጥቶ ጠረጴዛው ላይ መዋከብ ጀመረ። ቀና ብዬ አየሁት። እያየኝ ነው። ዓይኔን በዓይኑ ሲይዘው በሚለምን አስተያየት አየኝ!!
«እሺ አንድ ነገር ንገረኝ? እኔጋ መስራት መጀመርህ የእነሱ ወገን ከመሆንህ ጋር ተያያዥነት አለው?»
«የለውም ዓለሜ!!» አለኝ እንደተጨነቀ እያስታወቀበት።

👍39❤1👏1
«አባቴንኮ የገደሉብኝ ያንተ ወገኖች ናቸው፤ ማን ያውቃል ወይ አጎትህ ወይ አባትህም ሊሆን ይችላል፤ እናቴን መሳሪያ ይዘው የደፈሩብኝኮ እነዛው ያንተ ወገኞች ናቸው፤ ልጅነቴን ፣ወጣትነቴን ፣ ጉልምስናዬን ያመሳቀሉብኝኮ ያንተ ወገኖች ናቸው ፤ አምርሬ ስጠላቸው እና ላጠፋቸው ስመኝኮ ነው የኖርኩት። በህይወቴ አንድ ጥሩ ነገር ቢከሰት ፣ አንዴ ፍቅርን ባገኝ ፣ አንዴ ብሸነፍ …… እሱም የእነሱ ወገን ይሁን?» እያልኩት ውስጤኮ ቁጭት ነው የሞላው ቃላቶቹ ከአፌ ሲወጡ ግን እንባዬን አስከትለው ሀዘን የተሸከሙ ነበሩ።
«አንዴ ሁሉን ስሚና ፍረጅኝ!! ሰምተሽ አሻፈረኝ ከአሁን ፍቅሬ ያለፈ በደሌ ይበልጣል ካልሽ ምን ማድረግ ይቻለኛል? ልብሽ ያለሽን አድርጊ!! እ? እ ዓለሜ?» ከፊት ለፊቴ ተነስቶ አጠገቤ ወንበር አድርጎ ተቀመጠ። እንዳያቅፈኝም እንዳይነካኝም የቸገረው መሰለ። እንዳየው በዓይኖቼ ዓይኖቼን ያሳድዳል።
«እሺ ንገረኝ! ሁሉንም ልስማህ!! የእነሱ ወገን መሆንህን ግን የትኛው ታሪክ ይቀይረዋል?»
«ፍቅር! ፍቅር ይቀይረዋል! ፍቅር ጎሳ ብሄር ሀገር የለውምኮ ዓለሜ? እኔስ አስቤ እና አቅጄ በፍቅርሽ የወደቅኩ ይመስልሻል? ላንች እስከተንንበረከኩባት ሰዓት ድረስ እኔምኮ ያንቺን ጎሳ እንገሸገሸው ነበር። ሁሉም ቤትኮ እሳት አለ ዓለሜ!? ከጥላቻዬ አስበልጬ ወድጄሽ ነው! ከቂሜ አስበልጬ ወድጄሽ ነው፣ ፍቅርሽ ልቤ ሲሞላ መበደሌን ይቅር ብዬ ነውይ!» ብሎ ጀርባዬ ላይ አንድ እጁን ደገፍ አደረገ።
«የአባትን ሞት ያህል በደል አልተበደልክማ! የእናትን መደፈር ያህል ቂም አልያዝክማ! እድሜህን ሁሉ የቀማህ ጥላቻ አልጠላህማ!!» አልኩት ማልቀሴን ሳላቆም! ከተቀመጠበት ተነስቶ እንደገና ወደነበረበት ተመልሶ
«ህም!!» አለ እና በረዥሙ ተንፍሶ ቀጠለ። « እኮ የእኔ ህመም ይተናነስ እንደው ሰምተሽ ፍረጅኛ!! አብይ ህፃን ሳለሁ ነው የሞተው!! እንደመጎርመስ ብዬ ድምጤ የሻከረ ጊዜ እምይ ታማ ካልጋ ዋለች። ህመሟ እንዲህ ነው ሳይባል ወሰድ መለስ እያደረጋት እድሜ ቆጠርን!! እኔ እና ትልቅ ወንድሜ ነበርን እርሻውኑም ከብቱንም ብለን እምዬን የምናኖራት። ትልቄ እንደታላቅነቱ ሀላፊነት አለብኝ ብሎ ትምህርቱን ተወው!! እኔ በቀለሙ ትንሽ ፈጠን ያልኩ ስለነበርኩ እኔን ከትምህርት እንዳልጎድል አገደኝ። 10 ክፍል ስማር ሳለሁ አንድ እለት ተማሪ ቤት እየተማርን ሳለ ከተማው በጩኸት ሰከረ። በላይ በላያችን እየተረጋገጥን ብቅ ስንል ከተማው ይንቦለቦላል። ያልነደደ ቤት ያለ አይመስልም ነበር። ሁሉም የራሱን ቤተኞች ደህንነት ሊያጣራ ሲሮጥ መደሚጤሰው ከተማ ገባ። የምማርበትን ደብተር በትኜ ስበር ወደቤት ሄድኩ። በመንገዴ ከከተማው ግማሽ የሚያህለው ቤት እየነደደ መሆኑን ሳይ አልጋ ላይ የዋለች እምዬን እሳት በላብኝ ብዬ ነፍሴ ስትጨነቅ ደረስኩ። ቤታችን ሲነድ ደረስኩ። እምይ በደረቷ ስትሳብ ከበሩ ደርሳ ነበር።» ብሎኝ ፊቱ በሀዘን ተውጦ ከንፈሩን ነከሰ።
« እሳት የጀመረው ቀሚሷን አፈር በትኜ አጥፍቼ እሷን በክንዴ ላይ አቅፌ ከጎረቤት የነበረ እሳት ያላገኘው የወንድሟ ቤት አስቀምጫት ለወንድሜ ሚስት ሀደራ ብዬ እንዲህ ካለ ግርግር መሃል አይጠፋም እና አንዳች ነገር እንዳይሆንብኝ ብዬ ወንድሜን ፍለጋ ወጣሁ። ሰፈርተኛው እሳቱ የባሰ እንዳይዛመት ሊያጠፋ ደፋ ቀና ይላል። ደመኞቻችን እጃቸው የደረሰውን ታህል ቤት አንድደው ፣ የደረሰው እህል ላይ እሳት ለቀውበት ወደገበያ መሃል መግባታቸውን ከመንገድ ስሰማ በአሳላጭ ቅያስ በርሬ ደረስኩ። (ክብድ ያለው ትንፋሽ ግንባሩን አኮሳትሮ ተነፈሰ እና ቀጠለ) ያንች ዘመዶች ገበያው ዳር የተፋለሟቸውን የከተሜውን ወንዶች ሬሳ አጋድመው ሲጨፍሩ ደረስኩ። ትልቄ ለስራ ከለበሰው ቡት ጫማውጋር በእጁ የአብዬን ጠብመንጃ እንደያዘ ተዘርግቷል።» ሲለኝ ሳላስበው
«ሞተ?» አልኩኝ
«እህ!! (ጭንቅላቱን ወደላይ እና ወደታች እየነቀነቀ) እንደዋዛ ድፍት ብሎ ሞተ። አድብተው እንደሌባ አጥቅተውን እንደጀግና እየጨፈሩ መሪያቸውን ትከሻቸው ላይ ተሸክመው በሽለላ እያወደሱት ያጋደሙትን ሬሳ ሲዞሩ ቆይተው ከተማውን ለቀው ወጡ!! ድምፃቸው ከጆሮዬ ብዙ ጊዜ ዋለ - የወንድ ዋርካ የጀግና አድባር
የአምሳል አባት ባለዝናር …… » እሱ ድሮ በልጅነቴ ለአባቴ ሲገጠም የማውቀውን ግጥም በቃሉ ወረደልኝ። እኔ ግን የአምሳል አባት ከሚለው በኋላ ያለውን አልሰማሁትም!! ሰውነቴ ቀዘቀዘ። ሁሉም ቤት እሳት አለ ያለኝ ይሄን ነበር? ታዲያ ይሄን እረስቶ ወዶኝ ነው? ሊበቀለኝ ፈልጎ እንጂ!!!
«እኔጋ መቀጠርህ ከቀዬህ ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም አላልከኝም?» አልኩት ሳላስበው
«የሚያያይዘው የለም!! ያ ሰው አባትሽ መሆኑን ያወቅሁት ራሱ አንቺጋ ከገባሁ ከወራት በኋላ ነው!!» አለኝ ረጋ እንዳለ። ዝም አልኩኝ!!
«ታምኚኛለሽ? እንድዋሽሽ የሚያደርግ አንዳች ምክንያት የለኝም! አለመንገር እችል አልነበር? የምፈልገው በቀል ከነበር እጄ ላይ ነበርሽኮ ዓለሜ!! በብዙ መንገድ ላደርገው እችል ነበር። ለእነደሳለኝ መረጃውን እስኪያገኝ ነው ያልተበቀለኝ ብለሽ ታስቢ ከሆነ ልንገርሽ!! ሁሉንም አውቃለሁ!! ባንክ ያስቀመጥሽውን ኮፒ ፣ እሙጋ ያስቀመጥሽውን ፣ ሴትየዋጋ ያለውን!! እቤትሽ መታጠቢያ ቤት መስታወት ጀርባ ያለ ድብቅ ካዝናሽ ውስጥ ያሉ መረጃዎችሽን፣ ኮዱን ልነግርሽ እችላለሁ። የቀረኝ አለ? ሁሉን ደርሼበታለሁ!!! በቀል ከነበር ዓላማዬ እጄ ላይ ነበርሽ!! ታምኚኛለሽ? እርግጥ ነው ብዙ ጥላቻ እና ቂም ነበረኝ ግን የበቀል ሰው አልነበርኩም!!» ሲለኝ የማስበው ተምታቶብኝ የነገረኝን ትርጉም ልሰጠው እታገላለሁ!! ይሄን ሁሉ ካወቀ ምንድነበር የሚሰራው በሬ ላይ? ያሰብኩትን ያወቀ ይመስል
«አላውቅም!! ለምን እንደቆየሁ አላውቅም!! መች በፍቅር እንዳየሁሽ አላውቅም!! ብቻ አንቺን መጠበቁን ወደድኩት!! የዚያን ቀን መሄዴ ነው ስልሽ ከልቤ ነበር!! ወረቀት አኑሬልሽ ልሄድ ነበር። እውነታውን ፅፌ አኑሬልሽ ልሄድ ነበር። እንደማይባል እንደማይባል ብለሽ ታች ላይ አድርሰሽ ሰድበሽኝ ወጣሽ!! ስዘገጃጅ ፖሊስ በሩን አንኳክቶ መመታትሽን ነገረኝ!! ልቤ ሁለት ሆነ። ከሆስፒታል እስክትወጪ ታግሼ እቤትሽ ስትገቢ ጠብቄ ልሂድ ብዬ ጠበቅኩ!! ስትመጭ ጭራሽ ሌላ ሰው ነበርሽና ትቼሽ መሄድ አልቻልኩም!!» (የዛን ቀን ያለውን ቀን እኔ እየከተለኝ የነበረ መኪና አስተውዬ <የሆነ ሰው እየተከተለኝ ነው!! የተለየ ነገር አስተውለሃል? በንቃት ተከታተልልኝ> ልለው ስወጣ ነበር ስራዬን መልቀቄ ነው ያለኝ። ምን እንደዛ እንዳናደደኝም አላውቅም!! እሱ ክብሩ ከሚነካ ሞቱ እንደሆነ አውቃለሁ ግን ተናገርኩት!! ስወጣ <ጥርግ በል! ያንተ ቢጤ 10 አመጣለሁ> ማለቴን አስታውሳለሁ።

👍22
«እሺ ታዲያ እንዴት ከእነርሱ ጋር መስራት ጀመርክ?» አልኩት የነገሩን ጅማሬ ውል እየፈለግኩ
«ተዚያማ ትልቄ ሲሞት እምዬን ማስተዳደር በኔ ላይ ወደቀ። ያሸተ እህላችንን በእሳት ስላጋዩት ለከርሞ የሚቀመስ አልነበረም!! ቀዬው በጠኔ ደቀቀ። ይህኔ እምዬን ለወንድሟ አደራ ብዬ ወታደር ቤት ገባሁ!! ከዛ በምልክላቸው ፍራንክ እንደሆነው እንደሆነው አድርገው ከራረሙ።ወታደር ቤት ዓመታት ከቆየሁ ኋላ ወደቀዬ ተመልሼ መኖሪያዬን ቀለስኩ!! ምሽት አገባሁ ልጄን ወለድኩ!! ሚሽቴ ከ9 አቁማ የነበረውን የቀለም ትምህርት የመቀጠል እና በትምህርቷ ከፍ ያለ ቦታ የመድረስ ምኞቷ ትልቅ ስለነበር ከተጋባን ኋላ አስተምራት ነበር። የ12 ክፍል ትምህርቷን ስትጨርስ ሸጋ ውጤት አመጣች!! አዲስአበባ ዩንቨርስቲ ለትምህርት ተመደበች እና የ6 ዓመት ጨቅላ ልጃችንን ትታ መምጣት ግድ ሆነ!! ገና ከወራት ግን የልጇ ናፍቆት አቅቷት ተመልሳ መጣች። እሷ ከህልሟ አጓጉል ከምትሆን ምናባቱ ያገኘሁትን ሰርቼ እኖራለሁ ብዬ ልጄን ምሽቴን ይዤ አዲስአበባ ገባሁ!! ስራውንም ሳላማርጥ እየሰራሁ ባጀሁና ትንሽ ስደላደል እምዬንም አመጣኋት እኔጋ!! እንዳያልፍ የለም መቼም እንዴትም እንዴትም እሷ ተመረቀች። ይሄኔ እሷ ናት ይሄን ስራ በሰው አገኘሁልህ ብላ ደሳለኝጋ ያገናኘችኝ። እሷ ተመርቃ ከፍ ያለ ስራ ይዛ ከፍ ካሉ ሰዎች ጋር መዋል ስትጀምር ከእኔጋ መኖሩን እየተጠየፈችው መጣች። የምለብሰው አይጥማት ፣ አካሄዴ አይጥማት ፣ የማወራው አይጥማት …… ትምህርት ሚሽቴን ቀየራት ….. ትምህርት ሚሽቴን ነጠቀኝ!!» አለ ከደረቱ ቀና እንደማለት ብሎ በቁጭት ነገር የሆነ መፅሃፍ ትረካ ነገር በሬድዮ እየሰማሁ ያለሁ ነው እየመሰለኝ ያለው።
«ኋላማ ትዳራችን እንደማይሆን ሆነ። አቶ ደሳለኝ ጋር በጥበቃ ሰርቼ የማገኛት ገንዘብ ለሚስቴ ከራሷ ደመወዝ ጋር ተደምሮላትም የሚበቃትን ኑሮ አላኖር አለኝ። ኋላ ላይ አቶ ደሳለኝ በሷ ጥቆማ የግሉ ጠባቂ አደረገኝ። መድሃንያለም በሚያውቀው የዚህን ጊዜ ሁለቱ የሆነ ነገር ይኑራቸው የማውቀው የለኝም!! አይኔ ስር የሚሰሩትን ቆሻሻ ስራ አያለሁ!! ንፁህ ሰው አግተው ሲዝናኑ አያለሁ!! ቤቴን አቆም ብዬ አንገቴን ደፋሁ። ሰውየው <ልዩ ጠባቂዎቼ > የሚላቸው አሉት!! ስራው ጥበቃ አይደለም! ቆሻሻ ስራዎችን መስራት ነው!! የሚፈልገውን ሰው ከመሰለል እስከማገት ፣ መረጃ መስረቅ ፣ …… እነርሱን ተቀላቀል ሲለኝ አሻፈረኝ አልኩ። ሚሽቴ ብዙ ብር የሚያስገኝልኝን ስራ እንቢ ማለቴን ደሳለኝ እንደነገራት ነግራኝ ስትቆጣ የዚያኔ እምነቴ ሙሉ ስለነበር አልጠረጠርኳትም!! ብሩ ቢያስፈልጋት ነው ብዬ ስራውን ተቀበልኩ!! እሷን ካስደሰተልኝ እና በሷ ፊት ሞገስ ከሆነኝ ምናባቱ ብዬ ገባሁ!! ብዙ ወዳጅ አፈራሁ!! ስለከተማ ሰው ብዙ አወቅኩ!! እንዲያ ህሊናዬን አቆሽሼ ብዙ ብር ባመጣላትም ሚሽቴን አላቆየልኝም!! ፍታኝ አለችኝ!! በግድ ይዤ ላቆያት አልችል ለቀቅኳት።»
«ትወዳት ነበር!»
«ሚሽቴ አይደለች እንዴ? ቤቴ እኮ ናት የልጄ እናት! እንዴት አልወዳት?» አለኝ እንደመቆጣት ብሎ
«አይ እንዴት ሆነልህ ብዬ ነው! ባለፈው ሳያችሁ የሌላ ሴት ሚስት ሆና ምንም የመሰለህ አትመስልም ነበር።»
«ያልፋልኮ! ያልፋል! ቅናቱም ፣ ህመሙም ፣ እህህ ማለቱም ያልፋል!»
«እና ደሳለኝን ካገባችው በኋላ እሷን እያየህ ስራ እዛው እንዴት ቀጠልክ?»
«እኔና እሷ ከተፋታን ኋላ ትንሽ ቆይቶ እምይ በጠና ታመመችብኝና ለህክምና 10 ዓመት ብሰራ የማላገኘው ፍራንክ ተጠየቅሁ!! አቶ ደሳለኝ ብሩን ሊያበድረኝ እና በምትኩ ለ3 ዓመት የታዘዝኩትን ልሰራ ያቀረበልኝን ሀሳብ ለማለፍ ምርጫዬ የእምዬ ህይወት ነበርና ፈርሜ ገባሁበት!! እምዬን አዳንኩበት እኔ የማልወጣው ሀጥያት ውስጥ በየቀኑ ሰመጥኩ እንጅ!! ከዚያማ የልጄ እናት የአለቃዬ ሚስት ሆና መጣች። ትቼ አልሄድ ቃሌ ፣ ፊርማዬ ….. አልቀመጥ ሽንፈት ፣ ቅናት ፣ መከዳት ፣ መታለል ፣ መዋረድ አንገበገበኝ። ያልፋል አልኩሽ አይደል? አለፈ። እሷን ወይ አብራኝ እያለች አላውቃት ይሆን ወይ ከትምህርቱ በኋላ ተቀይራ : ጭራሽ የማላውቃት ሰይጣን ሴት መሆኗን አለቃዬ ስትሆን አወቅኩ። ለእኔ እንዲያ ብትሆንም ለልጄ ወደር የሌላት እናት ናት!! ልጄ በቋሚነት እኔጋ ብትሆንም ከአርብ እስከእሁድ እሷጋ ትሆናለች። አብረሽኝ ሁኝ ብትላት ልጄ እኔን መረጠች» አለ ኮራ ብሎ በፈገግታ ቀጥሎ
«አንቺጋ ስቀጠር ያገናኘን ሰውዬ ያንቺ ወዳጅ ቢሆንም በድብቅ የእነርሱ ወዳጅ ነው!! ያው ዘበኝነት ገብቼ የፈለጉትን መረጃ እንዳመጣ ነበር። ልጄ የታመመች ጊዜ » ብሎ ጊዜውን በማስታወስ ነገር ፍዝዝ አለ። «ልክ ያሁን ያህል አስታውሳለሁ። በረንዳው ላይ ተቀምጠሽ!
«ቤተሰብ ነኝ ብዬ ከቀበሌ የሆነ ወረቀት እናሰራ እና የእኔ ከሆናት የኔን ኩላሊት እሰጣታለሁ!» ስትይ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ እንደስራዬ ሳይሆን እንደሰው ያየሁሽ!! የዚያኔ ነው ለምን እንደሆን እንጃ ስላንች ማወቅ ናፈቅኩ። እናቷ ያንች ኩላሊት መስማማቱን ስነግራት አይሆንም አለች። ፈጣሪ ደግ ነው ሌላ ሰው ተገኘና ልጄ ዳነችልኝ! በሰው በሰው ሳጠራ ማን እንደሆንሽ ደረስኩበት። ስራዬን ልልቀቅ ካልኩሽ በኋላ ለእነርሱም ሄጄ ሌላ ስራ እንዲቀይሩልኝ ጠየቅኳቸው። በእኔ ምትክ እንዲገባ አናግረሽው የነበረውን ሰውዬ እነርሱ ናቸው የላኩልሽ!! የሰው ተፈጥሮ ያልፈጠረበት የሰይጣን ቁራጭ አረመኔ ነው!! ምንም እንኳን የምጠላው ጎሳ ፣የወንድሜ ገዳዮች ልጅ ብትሆኝም ለልጄ ስትይ አካልሽን ልትሰጭኝ ስስት አልነበረብሽም እና ለዚያ አውሬ አሳልፌ ልሰጥሽ አልሆነልኝም!! መልሼ ሀሳቤን አንስቻለሁ እሰራለሁ በቃ ብዬ ተመለስሁ!!» ብሎ ነግሮኝ እንደጨረሰ ነገር ዝም አለ።

👍23❤2
«ከዚያስ!»
«ከዚያማ ምን የማታውቂው ቀረ?»
«ይቀራል እንጂ! መች ነው የወደድከኝ? የተመታሁ ቀንኮ ግን ትተኸኝ ልትሄድ ነበር ለነሱ ትተኸኝ!»
«መች እንደወደድኩሽ ምኑን አውቄው? ስገቢ ስትወጭ ስትገለምጭ ስትሰድቢኝ!! አንዳንዴ ነገረ ስራሽ አፍሽ እንጅ የከፋ ልብሽ ደግ መሆኑን ሲነግረኝ አላውቅም!! እነርሱ የሚፈልጉትን መረጃ ሁላ አግኝቼ ለእነርሱ አሳልፌ ልሰጥሽ አቃተኝ!! ጥላሽን የማታምኝ ሴት እኔን ግን ከነጭርሱ አለመጠርጠርሽ አሳዘነኝ!! እንጃ ካስታወሽ የሆነ ቀን ለሊት ገብተሽ በር ስከፍትልሽ <አንተ ግን ደስተኛ ነህ?> አልሽኝ።»
ብሎ ፈገግ አለ። አስታወስኩት።
ትንሽም ቢሆን ደስታዬ የነበረው ከእሙጋ በማሳልፈው ጊዜ የነበረ ጊዜ እሷ የማያገባት ነገር የመቆስቆስ ሱሷ አላስቀምጥ ብሏት ለአምስተኛ ጊዜ የታሰረች ቀን ነው። (እኔ እስር ቤት ለ6 ዓመት እያለሁ እሷ ሁለቴ ገብታ ወጥታለች። ስትገባ አብረን ጊቢውን እናምሳለን። ከጋዜጠኝነቷ ባሻግር ታቱ መስራት በልምድ ተምራለች። እስር ቤት ውስጥ እንኳን ዘመናዊ ንቅሳት ልትነቀስ ፀጉሯን ከሁለት ጉንጉን የዘለለ የማትሰራ የገጠር ልጅ ሁላ ሳትቀር በጋዜጠኛ ምላሷ አዋክባ አሳምና ትነቅሳታለች። የጀርባዬን እና የቂጤን ንቅሳት ግማሹን መጀመሪያ የገባች ጊዜ የተቀረውን ቀለም ያልደረሰው ቦታ እየፈለገች ሁለተኛ ስትመለስ የነቀሰችኝ እሷ ናት።) የዛን ቀን መታሰሯን ሰምቼ የበረደው ልቤን ይዤ ስባዝን አምሽቼ ስገባ ጎንጥ ከእንቅልፉ ነቅቶ በር ከፈተልኝ። በረንዳው ጠርዝ ላይ ተቀምጬ እያየሁት በህይወቱ ምንም ግድ የሚሰጠው አይመስልም ነበር።
«አንተ ግን ደስተኛ ነህ?» አልኩት በመገረም እያየሁት! እንደገመትኩትም ቁልል ብሎ
«ፈጣሪ ይመስገን!!» አለኝ
«ምን ማለት ነው ፈጣሪ ይመስገን? መልስኮ አልሰጠኸኝም!! ነህ አይደለህም? ነው ጥያቄው ! ነኝ ወይም አይደለሁም! ነው መልሱ»
«ምን ለየው!! ፈጣሪ ይመስገን ማለቴ ደስተኛ በመሆኔም አይደል?» ብሎ አሁንም መልስ ያልሆነ መልስ ይመልስልኛል።
«አንተ ግን መቼ ነው ቀጥተኛ ወሬ የምታወራው? ምናለ አሁን ነኝ ወይ አይደለሁም ብትል!! ምንህ ይቀነሳል?»
«እሽ ካሻዎት! አዎን ደስተኛ ነኝ!! ምነው? እርሶ ደስተኛ አይደሉም እንዴ?» አለኝ መልሴ የጨነቀው አይመስልም። እኔ ግን ውስጤ መከፋቴ ሞልቶ ስለነበር መተንፈስ ለማልፈልገው ሰው ገነፈለብኝ።
«ደስታ ምን እንደሚመስል ስለማላውቅ ደስ ቢለኝም ማወቄን እንጃ!! አላውቅም!! ደስታ ማለት መሳቅ ከሆነ ስቄኮ አውቃለሁ። በህይወት ውስጥ ምን ያህሉን ፐርሰንት ደስተኛ ስትሆን ነው ደስተኛ ነኝ የሚባለው? እኔእንጃ! አላውቅም ደስተኛ ሆኜ ማወቄን! ሰው የሚፈልገው ሁሉ ኖሮት እንዴት ደስታ አይኖረውም አይደል?» አልኩት እና ጎንጥ መሆኑን ሳስብ ትቼው ገባሁ!!
«የዚህን ቀን አንጀቴን አላወስሽው!!» አለኝ አሁን ሳቅ ብሎ! «ከዛ ወዲህ ያለውን አላውቅም በጣም ብዙውን ቀን ታናድጅኛለሽ ለራሴ በቃ እተዋለሁ ይህን ስራ እላለሁ መልሼ ግን ያቅተኛል። የልጄ እናት በደንብ ስለምታውቀኝ ጠረጠረች። እየለገመ ነው እንጂ ይህን ያህል ጊዜ ምንም ፍንጭ ሳያገኝ ቀርቶ አይደለም ብላ ሰው ልትቀይር ነበር። ከዛ በላይ ምክንያት ደርድሬ ብቆይም አንች ፍቅሬን የምታይበት ልብ አልነበረሽም እና ደጅሽ መክረሜ ትርጉም አጣብኝ ለዛ ነው ልሄድ የነበር!! እንደው ጥሎብሽ ስታይኝ ትበሰጫለሽኮ!! ምን በድዬ ነው ግን እንዲያ የምትጠይኝ?»
«ኸረ አልጠላህም!! አላውቅም!! እሙ ስለምትወጂው ነው እንደዛ የምትሆኝው ነው ያለችኝ!» ስለው አይኑን አፍጥጦ ሲያየኝ አብራራሁ «ከፀብ ውጪ የምታውቂው ፍቅር ስለሌለ ፍቅርሽን የምትገልጪበት መንገድ ነው የምትናደጂውና የምትቆጭው አለችኝ! እሷ ናት ያለችኝ!» አልኩኝ!! ሳቅ ብሎ ዝም ተባብለን እንደቆየን እህሉ ሳንነካው መቀዝቀዙን አየን!! ሁለታችንም የመብላት ፍላጎት አልነበረንም!! እኔ የምበላው መዓት ነገር አቀብሎኝ እንዴት ነው እህል የማስብ የነበረው። ልክ እንደቅድሙ አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ እና አገጬን ከፍ አድርጎ አይኖቼን እያየኝ።
«መድሃንያለም ምስክሬ ነው! የደበቅኩሽ የለኝም!! ከፍቅርሽ ውጪ አንቺጋ ያኖረኝ ምንም ሰበብ የለም!! አሁን ሁሉን አውቀሻል!! አልሻህም እሄዳለሁ ካልሽኝም በግዴ የእኔ አላደርግሽም!! ብትተይኝም ከአፌ የሚወጣ ሚስጥር የለም!! በልጄ እምልልሻለሁ!! እ? ዓለሜ? ፍቅሬ ከጥላቻሽ ከበለጠ ንገሪኝ!! እሽ በይኝና የኔ ሁኝ በደልሽን በፍቅር እንድትረሽ አደርግሻለሁ!!» ሲለኝ ለተወሰነ ደቂቃ የእነሱ ወገን እንደሆነ ረስቼው እንደነበር አስታወስኩ። አባቴ ከወንድሙ ገዳዮች አንዱ ወይም አዛዡ እንደነበር አውቆ እንዴት ቻለበት ማፍቀሩን!
«ስትጠፋብኝ ስላንተ መረጃ እንዲያቀብሉኝ አድርጌ ነበርኮ!!» አልኩት የተጠየቅኩት ሌላ የምመልሰው ሌላ እንደሆነ እየገባኝ
« እየተከተሉሽ ነበር። ከኪዳን ጋር ከተማ ስትገቡ እንዴት እንደሆነ መረጃ ደርሷቸው ነበር። ኪዳን በሰላም እንዲወጣ እኔ ጣልቃ መግባት ነበረብኝ!! (ፍጥጥ ብዬ ሳየው) ምንም አልሆንኩም!! » አለኝ እጁን ከአገጬ አውርዶ
«ምንድነው ያደረግከው?» አልኩት
«ብዙም አይደል! ዋናው ኪዳን መውጣቱ ነበር ያንቺ እዳው ገብስ ነው!!» አለኝ
«ይሁን ንገረኝ ምንድነው ያደረግከው?» ብዬ ጮህኩ
«ከረፈደ ነው መኪና እንደተመደበባችሁ የሰማሁት!! ምንም ማድረግ የምችለው ስላልነበር መኪናውን ተጋጨሁት!! ምንም አልሆንኩም!! ማንም አልተጎዳም!! ትራፊክ መጥቶ ስንጨቃጨቅ እናንተ ተሰውራችኋል። እኔን ተከትለው ሊደርሱብሽ ስለሚችሉ ካንቺ አካባቢ መጥፋት ነበረብኝ! ለጊዜው የሚያቆሙ ይመስለኛል። ሌላ መላ እስኪያገኙ!! አንቺን መከተል ካላቆመች ለልጄ ማንነቷን እንደምነግራት ነግሪያታለሁ!! መረጃዎች እንዳሉኝ ስለምታውቅ ለጊዜው አትሞክረውም!! ስጋታቸው አሁን ለምርጫው የሆነ ነገር ታደርጊያለሽ ብለው ፈርተው ነው!! የምታደርጊውን እስክታስቢ ፋታ ይኖርሻል!! (ትንሽ ፋታ ወስዶ)መች ነው ግን አንቺ የምታምኝኝ? ምን ባደርግ ነው ትቶኝ ይሄዳል ወይ ይከዳኛል ብለሽ የምታስቢውን የምታቆሚው?» አለኝ
«አላውቅም!! እኔ እንዲህ የምወደው ነገር ኖሮኝ አያውቅም! እንዲህ የተሸነፍኩለት ነገር ኖሮኝ አያውቅም!! እንዲህ የተንሰፈሰፍኩለት ሰው ኖሮኝ አያውቅም!! ባጣው የምሞት መስሎ የተሰማኝ ሰው ኖሮኝ አያውቅም!! የምወደውን ስጠብቅ የኖርኩት በመጠራጠር እና በጉልበት ነው!! ማመን እንዴት እንደሆነ አላውቅማ!!» አልኩት አስቤ የተናገርኩት አልነበረም!!
ፈገግ ብሎ ፊቱን አዞረ እና መልሶ በተመስጦ ሲያየኝ ቆይቶ ሁለቱን እጆቹን በአንገቴ ዙሪያ ልኮ አንገቴን እንደመደገፍ ፣ ከአገጬ ቀና እንደማድረግ አድርጎ ከንፈሩን ከንፈሬ ላይ አሳረፈው። ስሞኝ እጆቹ እዛው እንዳሉ ከመልሴ በኋላ መልሶ እንደሚስመኝ ነገር
«ያ ማለት ምን ማለት ነው? አለሽልኝ ማለት ነው? እ? ንገሪኛ?» ከንፈሩ ከንፈሬን ከነካው በኃላ እንኳን ዘሩን ያለሁበትን የማላስታውስበት ስካር ውስጥ ከቶኝ ነው የሚጠይቀኝ? በጭንቅላቴ ንቅናቄ አዎ!! አልኩት!! ከንፈሩን እቦታው መለሰው!!
......... አሁን ጨርሰናል!!..........

👍75❤12🥰10
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_አስራ_አራት
/////
እለተ እሁድ ነው፡፡ረፋድ ላይ ቁርሴን ከበላሁ በኃላ ወደአልገዬ ተመልሼ ልጄ የላከችልኝን የእናቷን ማስታወሻ በተመስጦ እያነበብኩ ነው፡፡ይሄ ታሪክ የአፈላነት ጊዜ ታሪካችን ነው፡፡ትኩስ ወጣት ሆነን የኖርነው፡፡ወጣትነት ውስጥ የሚንፎለፎል ኃይል አለ።"ልክ የኒዩክሌር ኃይል አይነት።ወደማብራት ኃይል ተቀይሮ ልማትን ሚያሳልጥ...ወደአውዳሚ ቦንብ ተቀይሮ ለጦርነት ውሎ ከተማን የሚያፈርስ ወጣትነት ከተራራ የሚገዝፍ ነገሮችን የማድረግ ጉጉት እና ሳይታክቱ የመሞከር ትጋት ..ቢወድቁ በፍጥነት ተነስቶ የመቆም ፅናት፡፡ አዎ ከሰው ልጅ የዕድሜ እርከኖች ጎልደን ኤጅ የሚባለው ነው ወጣትነት፡፡ ህፃንነትና ታዳጊነት ከኃላው ትቶ ጎልማሳነትና አዛውንትነትን ከፊቱ አስቀምጦ ከህይወት ዘንግ የመሀል አንጓ ላይ ያለ በዕንቁ ያሸበረበቀ ጌጥ ነው።
ወጣትነት ውበት በመጨረሻው እንጥፍጣፊ አቅሙ የሚጎመራበት ስሜት ክላይማክሱን ገጭቶ የሚንፎለልበት የአበባነት እድሜ ነው።የፍቅር ኮንሰርት ቢዘጋጅ የዳንሱን መድረክ የሚሞላው ወጣት ነው...የጦርነት ነጋሪት ቢመታ ለመስዋዕትነት ግር ብሎ የጦር ካንፑን የሚያጨናንቀው ወጣት ነው።አብዬት አንስቶ ከተማውን በድንጋይ አጥሮ አስፓልቱን በጎማ ጭስ የሚያጥነው ወጣት ነው....ለድጋፍ ሰልፍ ቲሸርትና ኬፕ ገድግዶ ጎዳናውን በመፈክርና በባንዲራ የሚያጣብበውም ያው ወጣት ነው። በቀደድለት ቦይ የሚፈስ ፤ባሳዩት መንገድ የሚነጉድ ወጣት ነው።ቤተ እምነቱ የሚሻማው ቤተመንግስቱም የሚፈራው ያው ወጣት ነው...፡፡ ወጣት ሆነህ ጥበብ ቀድሞ ከበራልህ ቤተእምነትም ሆነ ቤተመንግስት አያታልሉህም....፡፡ፓለቲከኛው በስሜትህ ጢባጢብ አይጫወትብህም ...፡፡አዎ የነቃህ ወጣት ከሆንክ ለእሱ ወደስልጣን ማማ መስፈንጠሪያ እስፕሪንጉ ለመሆን በምንም አይነት ሁኔታ ፍቃደኛ ልትሆን አትችልም" ግን ወጣትነት በብዙ ችኮላ ፤ፋታ በማይሰጥ ጉጉት፤ ስር ባልሰደደ ዕውቀትና ልምድ የሚጓዝ በመሆኑ ከስህተት ሊፀዳ አይችልም፡፡እርግጥ ሙሉ የሰው ልጅ ከስህተት ጋር የእድሜ ልክ ትስስር አለው…ወጣትነት ላይ ግን ይለያል..እኔም እንደአብዛኛው ሰው ህይወቴን ያጨመላለቅኩት በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ በሰራሁት ስህተት ነው፡፡ውይ እስቲ መዘበራረቁን
ገታ አድርጌ እጄ ላይ አንከርፍፌ የያዝኩትን ከሪች ማስታወሻ ፎቶ ተንስቶ በልጄ አማካይነት በቴሌግራም የተላከልኝን ቀጣይ ታሪክ ላንብብላችሁ፡፡
ሰኔ 5 2008 ዓ.ም
11 ኛ ክፍል ሆነን ነው፡፡ማታ 11 ሰዓት ሆኖ ከትምህርት ቤት ከገባን በኃላ በምን ሰዓት በየት እንደሄደ ሳላውቅ እዬብ ከቤት ወጥቶ ጠፋ..ሰፈር ዞር ዞር ብዬ ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም.ግራ ገባኝ…ማታ እራት ሰአት ላይም ተመልሶ አልመጣም.. እነእማዬ ሲጠይቁኝ ጓዳኛዬ ጋ አብረን እናጠናለን ሲል ሰምቼለሁ ብዬ ዋሸሁ…የቤቱ ሰው ሁሉ ከተኛ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ የክፍላችን መስኮት ከፈትኩለት.ዘሎ ገባ፡፡
‹‹እስከአሁን አልተኛሽም እንዴ?››
‹አፈር ብላ…ዝም ብለህ ከቤት ወጥተህ እስከእዚህን ሰዓት ድረስ ትቆያለህ?››
‹‹የእኔ ውድ እህት …አሳስብኩሽ እንዴ ..?
ድንገተኛ በረከት አጋጥሞኝ ነው፡፡››
‹‹የምን በረከት ነው?››
‹‹ባክሽ ሶፊያ ጋር ነበርኩ››
አቤት የደነገጥኩት
ድንጋጤ‹‹ሶፊያ የት? .ለምን?.ከእሷ ጋር ምን አባህ ትሰራለህ?››
ተንሰረዘረኩበት ፤አዎ ሶፊያን በደንብ አውቃታለሁ...አረ እንደውም. የክፍላችን ልጅና ለእኔም ጓደኛዬ ነች..የተበሳጨሁበት ጉዳይ ግን ወደጎን ነው፡፡ሶፊያ እዬብዬን በጣም እንደምትወደው አውቃለሁ፡፡.ማለት እንደምታፈቅረው አውቃለሁ….ብዙ ጊዜ ደጋግማ ‹ወንድምሽን አፈቅረዋለሁ› …ብላ ነግራኝ ፊት ነስቻታለሁ፡፡እንደዛ ስትለኝ የማቀርብላት ምክንያት ‹ወንድሜ ጎበዝ ተማሪ ነው..ያለጊዜው ፍቅር ምናምን እያልሽ እንድታዘናጊው አልፈልግም› የሚል ነበር››ዋናው ምክንያቴ ግን ያ አልነበረም…እዬብን ፍቅረኛም ሆነ ጓደኛ በሚል የብእር ስም አንድ ሴት መሀከላችን ገብታ እንድትሻማኝ አልፈልግም፡፡
‹‹እረጋ በይ እቤቷ ነበርን››አለኝ.በሚያበሳጭ የድምፅ ቃና..
‹ለመሆኑ እስከዚህን ሰአት እቤቷ ጎረምሳ ስታቆይ እቤተሰቦቾ ምንም አይሏትም?››
‹‹አታስቢ የእኔ እህት… ብቻዋን ነበረች››
‹‹ብቻዋን?››
‹‹አዎ ምነው ደነገጥሽ…ገጠር ሄደዋል… ብቻዋን ስለምታድር ነው የጠራቺኝ››
‹‹እና ምነው ብቻዋን ጥለኸት መጣህ ..የሆነ ነገር ቢያስደነግጣትስ…?አብረሀት አታድርም ነበር?››
‹‹እንኳን አድሬ ላመሸሁትም ሞቼልሻለሁ…አንቺ ጓደኛሽ እንዳንቺ መሰለችሽ.. አስጮኸችኝ እኮ››
‹እስጮኸችኝ ማለት…?መታህ ነው
አስደንግጣህ?››
‹‹አይ አንቺ ልጅ በቀላሉ አይገባሽም…ወሲብ ፈፀምን ….ወሲብ እንደዚህ እንደሚጥም ዛሬ በእሷ አወቅኩ፡፡››
‹ወሲብ .ወይኔ እቴትዬ…ወይ እግዚያብሄር ድረስ..ከተቀመጥኩበት አልጋ ተነሳሁ .እንባዬ አራት መስመር ሰርቶ በጉንጮቼ ላይ መፍሰስ ጀመረ…ወለሉ ላይ ተዘርፍጬ መሬቱን አሰስኩት..እዬቤ ያላሰበው ዱብ እዳ ነው የገጠመው...በጣም ግራ ገባውም በጣምም ደነገጠ.
‹‹አንዴ ምን ሆነሻል.?አረ ደምፅሽን ቀንሺ.እነቴቴ አንዲሰሙ ተፈልጊያለሽ እንዴ?›
‹‹አንተ እንዴት እንዲህ ትሰራለህ…?ምን ነክቶህ ነው?››
‹‹ምን ችግር አለው ?ይሄ እኮ ማንም ወጣት የሚሰራው ኖርማል ነገር ነው›
‹አይደለም እኔስ ወጣት አይደለሁ ለምን ሳልሰራሁም…?ለምን ቆይ?
‹‹እሱን እግዲህ እራስሽን መጠየቅ ነው››
‹‹አይደለም..በሽታውስ እንዴት እንዲህ እንዝላል ትሆናለህ.?.በዛ ላይ ብታረግዝብህስ…?ምን አባህ ልታደርግ ነው…ደግሞ ቤተክረስቲያን ይሄን ሁሉ ዘመን የተመላለስከው ለዚህ ነው፡፡ይሄ እኮ ዝሙት ነው..››
‹‹አረ በፈጠረሽ..እኔ ፀፀት እንዲሰማኝ ለማድረግ የሚያስቸልሽን አንድም ምክንያት እኮ አልቀረሽም..እኔ እኮ አስቤበት አልነበረም አሷ ጋር የሄድኩት..ድንገት ነው ሳናስበው ወደወሲብ የገባነው….ጥሩነቱ ግን እሷ ሁሉንም አዘጋጅታ ነበር የጠበቀችኝ.››
‹‹ሁሉንም ማለት?››
‹ኮንደም ነበራት..ልታረግዝ አትችልም አትፍሪ... በሽታውም እንደዛው…››
‹‹እሷማ አዎ እንደዛ ታደርጋለች …ልምድ ያላት ሸርሙጣ ነች፡፡እሺ የእግዚያብሄር ቃልን መጣሱስ? ዝሙቱስ?›
‹እሱን አንግዲህ አንዴ ተሳሳትኩ ወደኃላ መልሼ አልውጠው…ማድረግ የምችለው ንሰሀ መግባት ነው…እሱን አስብበታለሁ…አሁን እንተኛ ደክሞኛል አለኝና ልብሱን ፊቴ አወላልቆ ከውስጥ ገባና ከጭቅጭቄ ለማምለጥም ጭምር መሰለኝ ጥቅልል ብሎ ተኛ፡፡
‹‹እኔማ ከሻርሙጣ ጋር አብሬ አልተኛም›› አልኩና አልጋ ልብሱን ከላዩ ገፍፌው ትራሴን ወሰድኩና ምንጣፍን ወለሉ ላይ ዘርግቼ ተኛሁ…ተነስቶ እንዲለምነኝ ፤ጉንጬን፤ ግንባሬን እየሳመ ይቅርታ እንዲጠየቀኝ…እቅፍ አድርጎ ፀጉሬን እያሻሸ ሁለተኛ አልመለስበትም ብሎ በስሜ እየማለ ቃል እንዲገባልኝ ፈልጌ ነበር….እሱ እቴ ዝም አለኝ….ደረቅ ወለል ላይ ብገላበጥ..እህህ ብል ምንም ጭራሽ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብቶ ማንኮራፋት ጀመረ..

👍37
ምን ላድርግ ግራ ሲገባኝ ቀስ ብዬ ከወለሉ ተነሳሁና ወደአልጋዬ ተመለስኩ፡፡ ብርድልብሰን ገልጬ ሰርስሬ ከውስጥ ገባሁና ጉያው ውስጥ ተሸጎጥኩ…የእሱ ያልሆነ አስጠሊታ ጠረን በአፍንጫዬ እየማግኩ ፤በለቅሶ እያታጠብኩና በንዴት እተንጨረጨርኩ እንቅልፍ ወሰደኝ..እንግዲህ በዛን ቀን ነው ሴይጣን እንኳን የማያስበውን ምኞት በውስጤ የተፀነሰው‹‹…እዬብ ባሌ እንጂ ወንድሜ መሆን አልነበረበትም….በዚህ ጉዳይ እግዚያብሄር ስህተት ሰርቶል›› ብዬ ሙግት መግጠም ጀመርኩ….ከዛን ቀን በኃላ ትምህርት ቤት ከእኩዬቼ ጋር ፃታዊ ስለሆነ ጉዳይ በሹክሽክታ ስናወራ እነሱ ልባቸውን ስላስደነገጠው ወንድ ማንነት አንስተው ሲያወሩልኝ በእኔ ምናብ ድንቅር ብሎ እቅሌን እስክስት የሚያስጨንቀኝ የእዬብ ምስልና ማንነት ሆነ….ከማንም ጋር ሰሙን አንስቼ መናገር የማልችለው የውስጥ እምቅ ብሶቴ…የሚጠዘጠጥዝ የብቻ ህመሜ ፡፡
////
ይቺን ቀን አዎ በደንብ አስታውሳታለሁ፡፡ከጓደኛዋ ጋር ያሳለፍኩትን የፍቅር ታሪክ ሳልደብቅ በጉጉትና በመደነቅ የነገርኳት ያለምንም መሸማቀቅ በኩራት ነበር፡፡በጣም የምወዳት እህቴ ብቻ ሳትሆን ብቸኛዋ የልብ ጓደኛዬ ጭምር ስለሆነች እንዲህ አይነት አዲስ ልምድና አስደማሚ የወጣትነት ገጠመኜን ከእሷ ውጭ ለማን ልንገር እችላለሁ?፡፡ያገኘሁት ግብረ መልስ ግን ከጠበቅኩት ፍፁም ተቃራኒ እና አብሻቂ ነበር፡ለእቴቴ ብነግራት እራሱ የዛን ያህል አንባጎሮ አታስነሳም ነበር፡፡በጣም ነበር የበሸቅኩባት…ይህቺ ልጅ የእኔ መደሰት አያስደስታትም እንዴ? ስል አሰብኩ እንጂ ስለምታፈቅረኝ ቀንታ ነው የሚል ሀሳብ ፈፅሞ በምናቤ አልመጣም ነበር፤እንዴት ሆኖ?፡፡እንደውም በዚህ ድርጊቷ ቂም ይዤባት የዛን ሰሞን የፈፀምኳቸውን ሁለት ተመሳሳይ ታሪኮች ሚስጥር አድርጌ ሳልነገራት ደብቄያታለሁ፡እስቲ ቀጣዩን ላንብብ
ሰኔ 14-2008 ዓ.ም
ለሊት ተነስቼ ጊዬርጊስ ቤ.ክርስቲያን ሄደኩ ። ‹‹እባክህ ያሳደከኝ ፈረሰኛው ጊዬርጊስ በእእምሮዬ የተሰነቀረብኝን መጥፎ ሀሳብ ከውስጤ እጠብልኝ። …አባክሽ እመብርሀን እኔ ሀጥያተኛ ልጅሽን ተመልከችኝ .. ምንድነው በውስጤ የበቀለው ጨለማ ሀሳብ? ምንድነው አእምሮዬን እየበላው ያለው ሀጥያት?›› በጥልቅ ሀዘን አንገቴን ደፍቼ ከዚህ ከገባሁበት እንድወጣ አምላክ እንዲረዳኝ ሠማዕቱ ቅድስ ጊዬርጊስ እንዲያማልደኝ...እናቱ ድክመቴን አይታ ምርኩዝ እንድትሆነኝ ፀለይኩ...
ሳስበው ግን ፀሎቴ ከልቤ የመነጫ አልመሰለኝም… ምክንያቱም እለት በእለት ይሄን መጥፎ ሀሳብ ከምናቤ አውጣልኝ ብዬ በተማፀንኩ ቁጥር ይባስኑ ሀሳብ ልክ እንደክፉ የነቀርሳ በሽታ በመላ አከላቴ እየተሰራጨ ጭራሽ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረኝ።በቃ ከእሱ ውጭ በዚህ ምድር ምን አለኝ ብዬ እስካስብ ድረስ...በአጋጣሚ በእዛን ጊዜ ከመስፍን ጋር ተቀራረብን ።
መስፍን አስተማሪ ነው።የተዋወቅነው ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ስናገለግል ነው።ሁለታችንም የፍቅር ተጣማሪ ሆነን የምንሰራበት መንፈሳዊ ድራማ ላይ ተመደብን። ድራማው ለሰንበት ት/ቤቱ ገቢ ለማስገኘት በትልቅ ደረጃ ለህዝብ በክፍያ እንዲታይ የታሰበ ስለነበረ ልምምድ ጠንከር ያለና በየቀኑ ለሁለት ወር በተከታታይ የሚደረግ ነበር...እንግዲህ ይህ የድራማ ልምምድም አልቆ ድራማውም ለህዝብ ከቀረበ በኃላ እንደበፊቱ የመገናኘት አጋጣሚው ተቋረጠ...በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ቀን ብቻ መገናኘት ሆነ...ለእኔ ሁኔታው ምንም የተለየ ነገር አልነበረውም... ::ለመስፍን ግን የተለየ የሆነበት ይመስለኛል፡፡ከተለያየን በኃለ፤ ናፍቆት ያስቸግረው እንደጀመር ደጋግሞ ነግሮኛል...እንዳፈቀረኝ እንደዛው" እስኪደነግጥ ጮህኩበት..አለቀስኩ ...በተገተረበት ጥዬው ወደቤቴ ገባሁ...፡፡እስቲ ምን እንደዛ ያደርገኛል?በጨዋ ደንብ ነው አፍቅሬሻለሁ ያለኝ።እኔም መመለስ የሚገባኝ በተመሳሳይ መንገድ ነበር?በራሴ አፈርኩም ተበሳጨሁም።
"አፍቅሬሻለሁ ሲለኝ ወዲያው በአእምሮዬ የመጣው ለእዬቤ ያለኝ ፍቅር ነው።ከእሱ ጉያ መንጭቄ ልውሰድሽና የራሴ ላድርግሽ ያለኝ አድርጌ ነው የወሰድኩት። አሁን ግን ተረጋግቼ ሳስበው እሱ በእኔ ልብ ስለበቀለው ሴጣናዊ ሀሳብ በምን መንገድ ሊያውቅ ይችላል?። ቢያውቅማ እንኳን ለፍቅር ሊጠይቀኝ በጓደኝነትም ከጎኔ ሆኖ ለማውራት ያፍርብኝ ነበር።እንዲሁ በነገሩ ስብሰለሰል አንድ ወር አሳለፍኩ ..ድንገት ግን አንድ ነገር በአእምሮዬ ብልጭ አለልኝ...ለፀሎቴና ለለቅሷዬ እግዚያብሄር የላከልኝ መልስ ቢሆንስ?።ከእዚ በልቤ ከበቀለው ክፍ ሀሳብ ሾልኬ የማመልጥበት የድህነት መንገዴ ቢሆንስ...?አዎ የመስፍኔን ጥያቄ መቀበል አለብኝ"ስል ወዲያውኑ ወሰንኩ።ወዲያው አእምሮዬ"ሪች ግን እኮ አታፈቅሪውም ?"ብሎ አስጠንቅቆኝ ነበር።የሰጠሁት መልስ ግን"አይ ግድ የለም የማፈቅረው ወንድሜ ጋር ያልሆነ ነገር ውስጥ ገብቼ ዘላለሜን ስፀፀት ከመኖር ለጊዜውም ቢሆን የማላፈቅረውን ሰው አግብቼ እድሌን ልሞክር"አልኩት።ከዛም ብዙም ጊዜ ሳላጠፋ ውሳኔዬን ለመስፍኔ ነገርኩት።ውሳኔዬን በደስታ ተቀብሎ ሽማግሌ ለቤተሠቦቼ ለመላክ ዝግጅት ጀመረ፡፡ይሄንን ጉዳይ ለእዬቤ የነገርኩበት ቀን ትዝ ይለኛል።ማታ ነው።ክፍላችን ገብተን ልብሳችንን አወላልቀን አልጋችን ላይ ወጥተን ጋደም ካልን በኃላ ነበር።
"እዬቤ"
"ወዬ ሪች"
"አንድ ነገር ልነግርህ ፈልጌ ነበር"
"ንገሪኛ..ቶሎ በይ እንቅልፍ ሳያሸንፈኝ"
"ማለቴ እንትን..?"
"እንትን ምን?"
"ማለቴ……››ጨነቀኝ…እኔ እራሴ ውስጤ ያላመነበትን ነገር እንዴት አድርጌ በቀላሉ ልነግረው እችላለሁ?
"ሴትዬ ጤነኛ ነሽ...የሆነ በፍቅር ጠብ ያደረገሽን ወጣት የፍቅር ጥያቄ ልትጠይቂ እኮ ነው የምትመስይው።
"ላገባ ነው"አፈረጥኩት፡፡
"ምን ?ምን?
አልሰማሁሽም"
"ላገባ ነው"
"ማግባት ማግባት….ባል ማለትሽ ነው....?"ከተኛበት ተነሳና ቁጭ አለ...ወደታች አይኔን እያየ አፈጠጠብኝ።
‹‹ የፈራሁት ደረሰ›› አልኩ በውስጤ...፡፡
"ምነው ከሁለት ወር በኃላ እኮ 18 ዓመት ይሞላኛል።"
"እና 18 ዓመት ሞላሽ ማለት ለማግባት ብቁ ሆንሽ ማለት ነው?"
"አዎ"
"ያምሻል እንዴ?ለመሆኑ ይሄ ባል ከየትኛው ፕላኔት ነው እንዲህ ድንገት ድብ ያለው።"
"ከዚሁ"
"ማነው ሰውዬው?"
"መስፍን"
"መስፍን? መስፍን ?አውቀዋለሁ፡፡"
"አዎ...አስተማሪው..ሰንበት ትምርት ቤት…››
"እንዴ!! መስፍን ዘገየ እንዳይሆን?"
"አዎ ነው"
"እኔ ይሄንን እንዲህ በቀላሉ ላምን አልችልም...?ብሎ መልሶ ጥቅልል ብሎ ተኛ ።
"እዬቤ›› "
"በቃ ደህና እደሪ…. አሁን ምንም ማለት አልችልም፡፡"
‹‹የዛን ቀን ነገሮች በዚህ ሁኔታ አለፉ...አምኖ ለመቀበል አንድ ወር አካባቢ ፈጀበት..፡፡ከዛ በድርድር ተስማማን...፡፡ትምህርቴን ሳልጨርስ እንዳላገባና ማትሪክ ከመጣልኝ ዪኒቨርሲት ገብቼ ለመማር መስፍን ፍቃደኛ መሆኑን አረጋግጪ አለኝ።ለመስፋን ነገርኩት ፤እስማማለሁ አለ።በቃ ሰላም ወረደ።ሽማግሌም ተላከ...፡፡ቀለበት አሰረልኝ።ይፍዊ እጮኛው ሆንኩ።ቀስ በቀስ በእኔ ምክንያት እዬቤና መስፍኔ እየተቀራረብ መጡ። ስንኮራረፍ የሚያስታርቀን ስንጨቃጨቅ የሚያግባባንን ሀሳብ የሚያፈልቅ የነገር አባታችን ሆኖ እርፍ አለ…እናም እንደዛ በመሆኑ አንድአንዴ ይከፋኛል አንዳንዴም ያበሳጨኛል።

👍47🔥1🥰1😁1
///
አንብቤ ስጨርስ ስቅስቅ ብዬ እያለቀስኩ ነበር በእውነት ይሄን ያህል እንደተሰቃየች በፍፅም አላውቅም ነበር…መስፍንንም ያገባችው ወዳው እንጂ ከእኔ ፍቅር መሸሻ እንዲሆናት እንደሆነ ለአንዲትም ደቂቃ ተጠራጥሬ አላውቅም፡እንደዛ አይነት ትንሽ ትርጣሬ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ መስፍንን እንድታገባው ፍፅም አልፈቅድላትም ነበር፡የእሷ ውሳኔ እኮ ማስተዋል የጎደለውና ከድጡ ወደማጡ የሚባል አይነት ነው፡፡አንድ ሰው ወደ ጋብቻ ሲገባ በፍፅም ልቡ ፈቅዶ በፍፅም ነፍሱም አፍቅሮ መሆን አለበት …በተለይ ጋብቻው ሀይማኖታዊ ሲሆንና እሷ እንዳደረገችው በተክሊል ሲሆን ደግሞ ፍፅም በእውነት ላይ የተመሰረት…በፍፅም ፍቃደኝነት ላይ መስረት ያደረገ መሆን አለበት …የእሷ ወሳኔ ግን በመንፈሳዊ አይን አይደለም በስጋዊ አይን እራሱ ሊያደርጉት የማይገባ የማይረባ ውሳኔ ነበር፡እና ለዚህም እኔም ከእሷ እኩል በደለኛ ነኝ….ለዚህም ይሄው እሰከዛሬ እየከፈልኩበት ነው..፡

👍28❤1👏1
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
"ይእ!ጥሩ ነው እንጂ ካርለቴ ባልሽ በመታሽ ቁጥር የፍቅር ጥገትሽ ይጨምራል ለባልሽ የሚያስገሳውን ፍቅር ትሰጭዋለሽ እሱም እንደ ክረምት ዝናብ በፍቅሩ ያርስሻል ያን ጊዜ ይበልጥ
ትቀራረባላችሁ
በሐመር ሴት ሁለት ሶስት እስት ትወልድ ድረስ ባሏ
እንዲመታት ሰበብ ትፈጥራለች ልጃገረድ እያለሽ በኢቫንጋዲ
ላይ ዘመድሽ አብረሽኝ አልደነስሽም ብሎ ወይ ሌላ ምክንያት ፈጥሮ ይገርፍሻል" ዝምድናውን ለማጥበቅና አንድትግባቡ መፈለጉን ስለምታውቂ አትቀየሚውም ዘመድሽ ካልገረፈሽ ጠልቶሻል ወይንም ተቀይሞሻል ማለት ነው" ችግር ቢመጣ አይደርስልሽም
"ዘመድሽ ከብት ሲዘል እየፎከርሽ የምትገረፊውም የእሱን ዝምድና ለመግለፅ ሲሆን ያን አይቶ መከታሽ ይሆናል" ባልሽ ዘንድ
ስትሄጂም እንዲቀርብሽ:
ዘመድ እንዲሆንሽ
እንዲመታሽ ታደርጊያለሽ ያኔ ይመታሽ ይመታሽና
የኔ ሸጋ ... የኔ ወለላ
አርጊ ያልኸኝን ከአሁን ጀምሮ አንተን
አደርጋለሁ ስጭኝ ያልኸኝን እሰጥሃለሁ ማስደሰትና ልጅ መውለድ ይሆናል ስራዬ ስትይው እንደ ማሽላ
ዱቄት አፍሶ ደረቱ ላይ ነስንሶሽ ጫካ ውስጥ ይገባል አንች ደግሞ
እንደ አለቅት ደረቱን እየበሳሽ ሙቅ ልቡ ወስጥ ትገቢና ጎዝጉዘሽ
ትተኛለሽ ልቡ ውስጥ ሆነሽ ጡትሽን ሲዳስሰው ሁለመናሽን ሲያሸው
ለሴት ልጅ ከዚህ የበለጠ ምን ደስታና ጣእም ያለው ህይወት ይኖራታል!" አለች ጎይቲ ያቆመችውን ፀጉር መስራት ለመጀመር ካርለትን ወደ ጉያዋ ሳብ እያደረገቻት።
"ጎይቲ ታዲያ ዱላ ለሐመር ሴት የፍቅር መግለጫ ነው?"
"ይእ! ልጃገረድ ሆነሽ ዳንስ ቦታ የለመድሽው ፍቅር ባልሽ ዘንድ ስትሄጂም የሚጠብቅሽ ፍቅር ዱላ ነው"
"እናንተ አገር የፍቅር መግለጫችሁ ምንድን ነው?"
"መተሳሰብ: መሳሳም …"
"ይእ! ታለ ግርፊያ መተሳሰብ የተኮመታተረው ስሜትሽ ተመታቶ ሳይፍታታ መሳሳም በአፍንጫዬ ይውጣ! ምን ኑሮ ነው
እቴ!"
"ስላለመድሽው እንጂ …"
"ይእ! በይ ዝምበይ
እኔ የሌሎችን ነገርሁሽ እንጂ እኔማ ልምዴን ተገፍፌ እንደ ምትታለብ ላም ዳሌየንና ጡት ስሬን
የሚያሽ ባል አግብቻለሁ" እንዲያው ግን ካርለቴ ከሎ የልምዴን ሰጥቶኝ እንዲህ ማህፀኔ ቢደርቅ እኮ አይከፋኝም ነበር, ከዛሬ ነገ
ወንድ ወንድ ይሸተኛል ስል ከዛሬ ነገ የወንዶችን ለበቅ ያነሳል ስል ዕጣ ፋንታዬ እንዲህ ይክፋ ካርለቴ!" ብላ ምርር ብላ አዘነች
"አዝናለሁ ጎይቲ
ግርፊያ ለሐመር ልጃገረድ እንዲህ እንደ ውቅያኖስ ወለል የጠለቀ ትርጉም ያለው አይመስለኝም ነበር!
ስትላት ጎይቲ ውቅያኖስ ያለችው ባይገባትም
"ይእ! የአባት ደንብ አይደል ካርለቴ እናትሽ ባልሽ ዘንድ
ከመሄድሽ በፊት ባልሽ ሲመታሽ አታልቅሽ የባልሽ ጓደኞች ወደ ቤትሽ ሲመጡ ከጎሽ ቆዳ የተሰራ ጫማቸውን ጠመንጃቸውን ተቀብለሽ ተቀብለሽ ቤት አስገቢ ቀጥለሽ ከውጭ ቁርበት አንጥፈሽ ሸፈሮ ቡና አፍይላቸው" የባልሽን የአደን ጓደኛ ሚሶ'
የዝላይ ወቅት ጓደኛውን ባርግያ በይ በባራዛ አርጩሜ ገርፈው
ምን ተሰማሽ? ሲሉሽ ፈገግ ብለሽ ምንም በያቸው ያን ጊዜ በማርና ወተት ያደገች ተጨዋች ናት ብለው ይግባቡሻል" ለባልሽም
አንችን አሞጋግሰው ስለሚነግሩት ይቀርብሻል"
"ሲመቱሽ ካለቀስሽና አንገትሽን ከደፋሽ ግን ከብትና ፍየል አልጠበቀችም ቀፎ አልሰቀለችም ድሀ አደግ ጨዋታ የማታውቅ
እንደ አነር ቁጡና ክፉ ናት ብለው ይጠሉሻል" ያን ሲሰማ ደግሞ ባልሽም ይጠላሻል ይርቅሻል ውሎው ከሌላ ሴት ጋር ይሆናል እያሉ ዘመዶችሽ መክረውሽ አለት ድንጋይ ልብሽ ውስጥ ጨምረሽ
ጠንካራ እሆናለሁ ብለሽ ባልሽ ዘንድ ሄደሽ የጠበቅሽውን ሁሉ
ስታጭው ምነው አትራቢ ምነው አታዝኝ!" ብላ ጎይቲ እንባዋን ፀጥ ብሎ እንዲፈስ ከፈተችው
ካርለትም ዐይኖችዋ በእንባ እንዳቀረዘዙ ጎይቲን እያባበለች አንድ ቃል በህሊናዋ ብልጭ ብሎ ድርግም አለ ፈለገችው
ያን ቃል ፈረንሳዮች ፍላጀላሲዬን ይሉታል እንግሊዞች ደሞ
ፍላጄሌሽን ደስ አላት ህሊናዋ ከትውስታው ክፍል ጀባ ያላትን ቃል ወደ ኖረበት ተመልሶ ሳይገባ አፈፍ አድርጋ ስለያዘችው
ፍላጀላሲዬን ስርዓት ባለው ወይንም ሃይል በተሞላበት
መንገድ በሃይማኖት ተከታዮች የሚፈፀም ግርፊያ ነው" በብዙ
የሃይማኖት ተቋማት ፍላጀላሲዬን በመባል የሚታወቀው ግርፊያ
የርኩስ መንፈስ የማስወጫ ስልትና መፈወሻ ዘዴ ተደርጎ ይቆጠራል"በጥንት "ዘመን የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በግርፊያ መሰቃየትን እንደ
አምልኮዋዊ ፀጋ ይቆጥሩት ነበር በነዚህ ህዝቦች እምነት መገረፍ ወይን በአካላዊ ጉዳት መሰቃየት ከሃጢያታቸው መንፃታቸውን፥ከመቅሰፍት
መዳናቸውን የሚያረጋግጡበት
ሆኖ ሲታመንበት ቆይቷል
በሰሜን አሜሪካ ህንዶች: በስፖርታዎችና በሮማውያን
ግርፊያ የአማልክትን ወይንም የቅድመ አያቶችን
ምስል ጭንብል
ባጠለቀ ገራፊ የሚፈፀም ነበር" ይህ ድርጊት በአስራ ሶስተኛው ክፍለ
ዘመን አጋማሽና በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመንም ቀጥሎ እንደ ጀርመን: ሆላንድ በመሣሰሉት አገሮችም ተስፋፍቶ ቆይቷል በብዙ አገሮች በበዓላት ቀን ወንዶች ጀርባቸውንና ደረታቸውን በአለንጋ
ይገረፋሉ።
ይህ አምልኮዋዊ እምነት እ.ኤ.አ. በ1349 ዓ.ም እንደነበሩት ፓትሪያርክ ክሌመንት በመሳሰሉ የሃይማኖት አባቶች ከረር ያለ ተቃውሞ ግርፊያ እየቀነሰ ቢመጣም በአሁኑ ዘመንም በደቡብ
የአውሮፓ ሀገሮች በላቲን አሜሪካውያንና በመካከለኛውና ሩቅ
ምስራቅ አገሮች የተለመደ ነው ለምሳሌ በታይዋን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በየአመቱ በስቅለት ቀን እንደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መገረፍ: መሰቃየት: እጅና እግርን በሚስማር መቸንከር
የእየሱስ ክርስቶስን ፍቅር እንደ ማግኘት ምድራዊ ሃጢያትን እንደ መቀነስና ለሰማያዊው ህይወት በክብር መዝገብ እንደመመዝገብ
ይቆጠራል
ከዚህ ውጭ ግን ዘመንሁ በሚለው ህብረተሰብ በሁለቱም ፆታ ግርፊያ በብዙ ግለሰቦች የወሲብ ስሜት መቀስቀሻ ወይንም የወሲብ ስሜት ማርኪያ ስልት እንደሆነና የገራፊ ልብሶችና የመግረፊያ
አለንጋዎች የሚሸጡባቸው የወሲብ ሱቆች
በርካታ እየሆኑ
መጥተዋል እኒህ ግርፊያን እንደ ወሲባዊ የችግር መፍትሔ የሚቆጥሩ
ሰዎችን የስነ አዕምሮ ጠቢባን የስነ-አዕምሮ
ችግር ያለባቸው እንደሆኑ በመቁጠር ብዙ መላ ምቶችን እየደረደሩ ቢሆንም
የመገረፍ ፍላጎት ወይንም ሱስ ግን አንድም የተፈጥሮ ባህሪ ውጤት ወይንም እምነት የፈጠረው ፍላጎት ስለመሆኑ አያጠራጥርም ብላ አሰበችና የሐመሩ ግርፊያም ባህላዊ እምነት የፈጠረው የህሊናና
የአካል ዝግጁነት ውጤት ነው ብላ ደመደመች።
እየጨለመ ሲመጣ የእሳቱ ወጋገን ይበልጥ እየጎላ እየጎላ መጣ ወጣቶች ለስነ-ስርዓቱ ከሰበሰቡት እንጨት በተጨማሪ ከጫካ
ግንዲላውን: ጭራሮውን እየተሸከሙ እያመጡ ይከምራሉ ጥቂት ጎረምሶች ደግሞ ለወጠሌ ጥብስ የሚሆነውን ችካል በጩቤያቸው ይጠርባሉ ሌሎች የእድሜ ጓደኛ ጎረምሶች ደግሞ ከሳቱ ርቀው ተሰብስበው ያወጋሉ፤ አንዳንዴም
በተቀቡት ዥንጉርጉር የአኖ ቀለም ከሹልሹላቸው
ለዳንሱ ዝግጅት
የሰጎን ላባ ሰክተው
ጨሌያቸውን አንገታቸው
ላይ ደርድረው ግንባራቸው ላይ የጨሌ ገመድ
ቋጥረው ዳንሱንና ድሪያውን ናፍቀው ውስጥ ለውስጥ ይቋምጣሉ አልደርስ ብሏቸው"
"ሚሶ!" አለ አንዱ
አለ አንዱ ከመሀላቸው የአደን ጓደኞቹን የሰአት ማሳለፍያ ጨዋታ ሊያወጋቸው።

👍25
ሚሶ አሉት እነሱም እንደደንቡ የአደን ጓደኞቹ ሲጠራሩም ሆነ ሲጨዋወቱ ስም አይጠራሩም ቀረቤታቸውን መግባባታቸውን ጓደኝነታቸውን የምትገልፀው ቃል ሚሶ የምትለው ቃል ናት።
የወኛርኪ መንደር ጎረምሶች አደን ወርደው ሁለት አንበሳ
ገለው መመለሳቸውን ሰምታችኋል?"
"ኧረ የለም! ከማን ሰማህ አንተ?"
"እኔማ ትናንት ሌሊት ሽማግሎች ልከውኝ ሄጀ ነበር
"እነማን ገዳይ ተባሉ እህ?" ሁሉም የሚለውን
አቆበቆቡ
"አይኬና ቦዳ ናቸው" አለ ረጋ ብሎ
"ቀንቷቸዋላ! እኛ ነን እንጂ አሸዋ ላይ ስንተኛ ቀኑ ነጎደ
ምናለ ወንድነቱ እንዲደርሰን
እኛስ ብንሄድ?" አለ አንዱ
ከመካከላቸው
"እኔ በበኩሌ ልቤ ተነስቷል እንኳን ይኸን ሰምቼ" አለ ሌላውም።
"በፊት ቆይ አስኪ ያየሁትን ላውጋችሁ የሰው ጨዋታ
አታቆርፍዱ!" አለ መጀመሪያ የተናገረው ጎረምሳ
"እስቲ አውጋን?"
"ዛሬ ረፋዱ ላይ ከብት ልፈቅድ ስሄድ አይ የአየሁት ነገር!"
"ምን አየህ?" ጓጉ ጓደኞቹ ለመስማት
"እኔ ሳያቸው መጀመሪያ ደነገጥሁ ተዚያ ልቤን ድንገት ነሸጥ አደረገኝ እንዲያው ምን ልበላችሁ አቁነጠነጠኝ
"እ! አትናገርም ምን እንዳየህ?" ጓደኞቹ የመስማት ጉጉታቸው ይበልጥ ጨመረ።
"እእ! ጎዳናውን ለቅቄ ሽንቴን ልከፍል በዛፎች ከለል ስል
ኮሽታ ሰማሁ ያች መናጢ ቀበሮ መስላኝ ወደል ድንጋይ አማትሬ
አንስቼ አድፍጬ ዛሬ በጠዋት እጄ ላይ ጣለሽ አንች መናጢ! እያልሁ ቅጠሉን ከለላ አድርጌ ስሳብ የሰው ድምፅ ሰማሁ እነማን ይሆኑ ደግሞ ብዬ በቅጠሎች ተከልዬ አጮልቄ ሳይ ሴትና ወንድ
ናቸው።
ማንና ማን ይሆኑ? እያልሁ አፍጥጬ ሳይ ኮቶ ናት
የእኛዋ አጠገቧ ቦዳ አለ የገደለውን አንበሳ ጎፈር
ደፍቶ ኮቶ የወሰደችለትን በለሻ በወተት እያማገ
ይውጣል" እሷ አንዴ በጀርባው አንድ ጊዜ ደግሞ ከፊት ለፊቱ እንደ ድመት
በዳሌዋ እየታከከች ጨሌውን ታስተካክላለች
ጎፈሩን ትነካካለች
እሱ ግን በለሻውን እንደ ኮንሶ ልቃቂት እያዥሞለሞለ እየጎረሰ ወተቱን በላዩ ላይ እየሰመጠጠ ያላምጣል እእ! ያን ሳይ እህል
ቀምሼ የማላውቅ ይመስል ወስፋቴ እሪ! አለ
ትናንት ወኛርኪ ሄጄ አይቸው ተምኔው እዚህ መጣ? ኮቶንስ እንዴት አገኛት? አይ የሐመር ልጃገረድ ገዳይ ስታነፈንፍ ማን ይስተካከላታል! እያልሁ ሳስብ እኔን ቅጠል አልብሰው ገትረውኝ አፍ ላፍ ገጠሙላችኋ! ገጠሙ ገጠሙ.. ለካ ሴትና ወንድ አፍ ላፍ ሲገጠሙ ለተመልካቹ የሚነካከሱ ነውና የሚመስሉት! አንገቷን ቆልምሞ ሲነክሳት ሲጨባብጣት ኮቶ
ታሁን አሁን ጮኸች ብትጮህ ምናባቴ ነው የማደርግ ልገላግል
ብሄድ በጥርሷ ነው የምትዘለዝለኝ ስል ኧረ እሷ እቴ! ከቅንቡርስ
እንደምትታገል ጉንዳን
ግብግብ ስትገጥመው ብታዩ ይደንቃችኋል አይ ጥንካሬ! ጅማት ናት ጅማት! እንኳን ልትጮህ ድምጿ ይሰማልጀ መሰላችሁ
ስትሞጨሙጨው!
ቁልቁል ሆና ሽቅብ
ያን ሳይ እኔ ምንም የማላውቅ የእቅፍ ጨቅላ
ሆኜ ቁጭ!" ብሎ ዝም አለ
"እእ! በለው ..." እያሉ አውካኩ ጓደኞቹ
ኧረ ይገርማችኋል ታሁን አሁን ተላቀቁ ስል እነሱ
እየተተካኩ: ላይና ታች እየሆኑ ሲናከሱ ፈዝዥ እንዳለሁz
"እእ! ሲሰሙት ዘላለም የሚጥም ጉድ እሽ ተዚያ በኋላስ? ኧረ ባክህ ቶሎ ጨርሰው ." አለ አንዱ ጎረምሳ አቋርጦት
"እየነገርኳችሁ
ተዚያማ ለእነሱ እኔ ፈርቼ ድንገት የሐመር መንገደኛ ቢመጣ ምን ይውጣቸዋል ብዬ ዞር ብዬ ቃኝቼ
አንገቴን እስትመልስ ጠላታችሁ ጥፍት ይበል' ኮቶ ጠፋችብኝ ምኑ
ይክተታት ምኑ ጥፍት አለችብኝ ሄደች እንዳልል ድምጿ ይሰማኛል አለች እንዳልል አትታየኝም
ለካስ አጅሪት " ብሎ
ዝም ሲል ጓደኞቹ በግድ ጎትጉተው የሆነውን ሰሙ"
"ሚሶ!" አለ ሌላው ደግሞ
"ሚሶ!" አሉት"
"ኧረባካችሁ አደን እንውረድ ተው ቀናችን አይለፍ?"
"እኔ በበኩሌ ፈቃደኛ ነኝ
የማይመቸው አለ?"
"ተመቼን አልተመቼን ጠፍተንም ቢሆን መሄድ ነው እንጂ
"መቼ እንውረድ እህ?" ተባብለው አስራ ሰባት ላይ ልጥ ቋጠሩ ለቀጠሮው ቋጠሮ በየቀኑ ቋጠሮውን በመፍታት በተስማሙበት
ትክክለኛ ቀን ለመሄድ
"ሚሶ!"
"ሚሶ!"
"ካርለቴን ደልቲ ሊያገባት ነው አሉ እንግዲህ ዝም ልንላት ነው?
"እእ! ይኸውላችሁ ጨዋታችንን ሊያቆረፍደው ነው ድፍን አገር የሚያውቀውን ነገር ምን አዲስ ጨዋታ አለው ብለህ ነው፤ አዲሷ ተእንግዲህ በዘመዶችዋ መጎንተሏ የት ይቀራል" ብለው አፍ
አፉን አሉትና ተሳሳቁ
"እእ! ምንድነው ጊዜው ረዘመ'ሳ!"
"አይዞህ! ሌሊቱ ብዙ ነው
አንላቀቅም "
"ባራዛ አርጩሜ ቆርጣችኋል?" ብሎ ጠየቀ ከመሃላቸው አንዱ።
"እእ! እሱ መቁረጣቸው ለመግለፅ ሌሎች ከዚህ ሌላ ጨዋታ ጀመሩ የምሽቱ ጭፈራ እስኪጀመር"
💫ይቀጥላል💫

👍29🔥2👎1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
///
ከጄኔራሏ ጋር የነበረን የጋለ የፍቅር መሳሳብ ቀስ በቀስ እየተዳፈነ የጓደኝነት ቁርኝታችን እየጠነከረ መጥቶል፡፡ይሄን አይነት የስሜት ለወጥ በመከሰቱ ልደሰት ወይስ ይክፋኝ እስከአሁን መለየት አልቻልኩም፡፡ ነግቶ ከእንቅልፌ ስባንን እሷ ከጎኔ ተኝታለች..እስክትነቃ ጠበቅኩና
"ደህና አደርሽ?" በሚል በአክብሮት በታሸ ለስላሳ ንግግር ተቀበልኳት፡፡
"አዎ ..ደህና አድሬያለሁ..ነጋ እንዴ?"
አዎ ነግቷል.. አታይውም እንዴ? በክፍላችን ብርሀን ተጥለቅልቆ ደሰ ሲል፡›
‹‹ብርሀን ብቻ ነው እንዴ ደስ ሚለው?››.
‹‹ጨለማማ ያው ጨለማ ነው ምኑ ደስ ይላል?››
ጨለማ ያን ያህል አስፈሪ አይደለም።በድፍረት ላጣጣመው ጨለማ የራሱ ውበት አለው።ጨለማ ደግሞ ከብርሀን በላይ ፈጣን ነው።ሁል ጊዜ ብርሀን በጨለማ ቀድሞ የተያዘውን ግዛት አስለቅቆ ነው አለሁ እዚህ ነኝ የሚለው።እኛም ወረተኛና ፍርደ ገምድል ስለሆን ኃላ ስላየነው አንፀባራቂና ደማቁ ብርሀን አጋነን እናወራለን እንጂ ቀድሞ ቦታው ላይ የነበረውን ጨለማ ትዝ አይለንም፡፡
ከእሱ ማምለጥ ባንችልም መሞከራችን አይቀርም።ደግሞ እኮ የብርሀኑ ውበትና ድምቀት ሙሉ ሆኖ የሚታየው በድቅድቁ ጨለማ ሰንጥቀን ማለፍ ሲችል ነው።ደግሞ ወታደር ብትሆን ለጨለማ ያለህ እይታ ይቀየር ነበር፡፡
‹‹እንዴት?››
‹‹ጨለማ ወሳኝ ወዳጅህ የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚዎች ይኖራሉ...ከጠላት አይታ ከልሎ ህይወትህን ያተርፍልሀል….ከብርሀን በተሻለ መረጋጋተትና ትንፋሽ መውሰጃ ሰላማዊ እረፍት ዕድሎችን ያመቻችልሀል…ኦ እኔ ጨለማ ወዳለሁ…በተለይ ድቅድቅ ጨለማ፡፡
‹‹በስመአብ በይ››
‹‹አልኩ.. አሁን ስንት ሰዓት ሆነ?››
"ሁለት ሰዓት ሆኗል"
"ስራ ትገባለህ እንዴ?"
"ማታ አስራሁለት ሰዓት ነዎ..አንችስ?"
"እኔኮ ስራ የለኝም.?."
"አንድ ጄኔራል ለዛውም በዚህ ጊዜ..."
እጄን ያዘችና ወደ ሆዷ ወሰደችኝ፡፡ ያሳረፈችኝን ቦታ ዳበስኩት፡፡ የታረሰ ቦይ መስሎ ያስታውቃል፡፡ ...ብርድልብስን ከነአንሶላው ገለጥኩና አየሁት እንብርቷን ከፍ ብሎ ወደታች በመውረድ ፓንቷ ውስጥ ድረስ የሚዘልቅ አስፈሪና ሰፊ ጠባሳ አለ፡፡
.‹‹..እስከዛሬ እንዴት ሳላየው?"
"አይኖችህ መቀመጫዬ ላይ ነበር የሚንከባለሉት..ለዛነው ያላየኸው"
"እውነቴን ነው ..ማታ እንኳን እርቃንሽን ሆነሽ ከስሬ ቆመሽ ነበር"
"ባክህ እንዳታየው በዘዴ ስለጋረድኩት ነው"
"ምን ሆነሽ ነው?"
"ቆስዬ ፡፡በጦርነቱ ላይ ቅስዬ ላለፍት ሶስት ወራት በከፍተኛ የህክምና ክትትል ጦርሀይሎች ተኝቼ ነበር...፡፡ገና ከወጣሁ አንድ ወር አይሆነኝም..፡፡.አሁንም ከሆስፒታል ወጣው እንጂ ህክምናውን ሙሉ በሙሉ አላጠናቀቅኩም ...በሳምንት አንድ ቀን ቼክአኘ አለኝ፡፡..እና በአጠቃላይ ከስራ ውጭ ነኝ፡፡
‹‹ስትድኚ ትመለሺያለሽ አይደል?››
‹‹ከዚህ በፊት እኮ ነግሬህ ነበር..መመለስ እንደማልችል ሀኪሞቹ ተስማምተው ፅፈውልኛል...መጀመሪያ ከፍቶኝ ነበር...ቆይቼ ሳስበው ግን ውሳኔውን በፀጋ ተቀብዬዋለሁ።››
"ይገርማል.. ታዲያ እንደዚህ ከፍተኛ ህክምና ላይ እያለሽ ነው እንደዛ አልኮል ስትጠቀሚ የነበረው ።››
‹‹አንድ ቀን ነው የጠጣሁት.. እሡኑም ቦርድ መውጣቴን የሠማው ቀን ..››..
"አረ ተይ...ከሰውዬሽ ጋር የመጣሽ ቀንስ..?"
"እ በቃ..የወታደር ነገር አንዳንዴ እንዲህ ነው...አየህ ከተወረወረ ቦንብ መሀል አምልጠህ የሚንጣጣ መትረየስ ሸውደህ፤ ታንክና ድሽቃ ሳይገልህ በህይወት ተርፈህ አሁን አልኮል በብርጭቆ ስለጠጣሁ ይገለኛል ብለህ ለማመን ይከብድሀል...እና መጠጣት እንደሌለብህ ብታምን እንኳን ትንሽ ከተበሳጨህ ወይም ድብርት ውስጥ ከገባህ እኔ እንዳደረኩት ታደርጋለህ...፡፡
"አሁን ቁርስ ልጋብዝሽ"
"የት እቤትህ ወስደህ"
"አረ እዚሁ ሆቴል"
"እቤትህ ስልህ ምነው ደነገጥክ...ሴትየዋ አለች እንዴ?"
‹‹አይ የለችም"ብዬ ስለጋሽ ሙሉአለም ታሪክ ስነግራት ማመን ነው ያቃታት።
"እሺ እኔ ቤት ሄደን እንዋላ"
"እኔ ቤት ...እዚህ አዲስ አባ ቤት አለሽ"
"አዎ ብዙም ባልጠቀምበትም ቤት አለኝ››
‹‹ታዲያ ቁርስ በልተን እንሂድ?..›
‹‹ምነው ቁርስ መስራት እትችልም አሉህ እንዴ?››
‹‹እስከዛ ይርብሻል ብዬ ነዋ;››
‹‹ለራስህ አስብ ..አንተ ወታደር እኮ ነኝ..አስርና ሀያ ቀን ያለምግብ ያሳለፍኩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ...በል ተነስ ››አለችና …አልጋዋን ለቃ በመውረድ ልብሷን መለባበስ ጀመረች፡፡.
‹‹አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ››
‹‹ጠይቀኝ››
‹‹ስንት አመትሽ ነው?››
‹‹ምን?››ደንግጣ
‹‹አይ ለሌላ እኮ አይደለም….በዚህ ዕድሜሽ እንዴት ይሄ ሁሉ ብዬ ነው፡፡››
‹‹እስኪ ገምት ስንት እሆናለሁ?››
‹‹35››
‹‹ብዙም አልተሳሳትክም…10 ብቻ ጨምርበት፡፡››
‹‹የእውነትሽን ብቻ እንዳይሆን?››
‹‹ምነው አረጀሁብህ?››
‹‹አረ አቋምሽና ጠቀሽወ እድሜ ፈፅሞ አይመሳሰልም››አልኳት የእውነትም ተገርሜ፡፡
ትራስ አስቀምጣ የነበረውን ሽጉጥ አነሳችና የጃኬቷን የውስጠኛ ኪስ ውስጥ አስቀመጠች፡፡..እኔም ለብሼ ጨርሼ ስለነበረ .ተያይዘን ወጣን….ወደሆቴሉ የመኪና ማቆሚያ ፓርክ ነው የወሰደችኝ፡፡
.አንድ አይጣማ ቪታራ ጋር ስትደርስ ቁልፉን ከኪሷ አወጣችና ከፈተች.፡፡መኪና ይዛለች ብዬ ስላላሰብኩ ታክሲ ለመጥራት ስልኬን አውጥቼ ስልክ ቁጥር እየፈለኩ ነበር…ፈገግ አልኩና ገቢና ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ከመንቀሳቀሳችን በፊት ግን ስልኬ ጠራ…ጋሼ ሰለሞን ነው የደወልኝ፡፡ አነሳሁት፡፡
‹‹ሄሎ ጋሼ››
‹‹እዬብ የት ነህ?››ኮስተር ያለ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ሆቴል ነኝ››
‹‹ቶሎ እቤት ና.. ፈልግሀለሁ›
‹‹እቤት ማለት.?››.ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ፡፡
‹‹.አንተ ቤት.. አባዬ አሞታል መሰለኝ››
‹‹መጣጣሁ መጣሁ›ስልኩን ዘጋሁት
‹‹ምነው ችግር አለ?…››
‹‹አያቴ ማለት ጋሽ ሙሉአለም አሞቸዋል መሰለኝ .›መሄድ አለብኝ ይቅርታ››
‹‹…ላድርስህ?››
‹‹ምን ታደርሺኛለሽ…..ከዚህ ገቢ ቀጥሎ እኮ ነው ቤታችን..ደውልልሻለሁ›ተንጠራርቼ ጉንጯን ሳምኳት፡፡
‹‹በቃ ቸው›
ገቢናውን በር ከፍቼ ወጣሁ‹‹..ቁርሱ ደግሞ ለሌላ ቀን ይዘዋወርልኝ.››
‹‹በተመቸህ ጊዜ ደስ ይለኛል.. ነገም ተነገ ወዲያም.. ደውልልኝ…መጥቼ ወስድሀለሁ…፡፡››
እየሮጥኩ ወደቤት ሄድኩ፡፡
//
አያት መድሀኒት ከወሰደና ቀኑን ሙሉ ስንከባከበው ከዋልኩ በኃላ አሁን ከመሸ ተሸሎታል፡፡በአካል ስሩ ባልሆንም ከግድግዳ ማዶ ሆኜ ደህንነቱን እንድከታተል በሀለቃዬ በአቶ ሰለሞን ተነግሮኝ የስራ ፍቃድም ተሰጥቶኝ ስራ አልገባሁም፡፡አሁን ከፍሌ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከእንቅልፌ ጋር እየታገልኩ አያቴም በክፍሉ ውስጥ በተኛበት የልጅና የአባት ወሬ እያወራን ነው፡፡
‹‹አያቴ እርሶ እኮ ፃድቅ ኖት››ድንገት ነው ይሄ አረፍተነገር ከአፌ ሾልኮ የወጣው..ግን ደግሞ ለሽርደዳ ወይም ለማስመሰል አይደለም..የእውነትም ከልቤ እንደዛ ነው የማምነው፡፡

👍42👏2❤1
‹‹ተው ሰው ፃድቅ አይባልም…የሰው መልካም ስራ ሆነ ክፉ ስራ ዘላቂ ሊሆን አይችልም…››
‹‹ማለት?››
‹‹ሰው የክፋትና ፤መልካምነት..የደግነትና፤ ንፍገት …የብርሀን እና የጨለማ ቅይጥ ስሪት ነው፡፡ አሁን ብርሀን ጎኑን ያሳይህና ከሁለት ቀን በኃላ ጨለማ ወርሶት ታገኛለህ፡፡ሰኞ ደሙን ከሰውነቱ ቀድቶ ከሞት ያድንህና እሁድ ላይ አልጋህ ላይ ከሚስትህ ተኝቶ ልታገኘው ትችላለህ…፡፡እንደሰው ግራ አጋቢ የማይጨበጥና የማይተነበይ ፍጥረት መኖሩን እጠራጠራለሁ››
‹‹ያው ጥቂት ይሁኑ እንጂ ልከ እንደእርሶ ቅን እና መልካም ሰዎች እዚህም እዛም አይጠፉም፡፡››
‹‹አይምሰልህ… የትኛውንም ሰው በተመለከተ ስለወቅታዊ ድርጊቱ በነጠላ መናገር እና መመስከር ትችላለህ እንጂ በአጠቃላይ እከሌ እንዲህ ነው ብለህ መደምደም በኃላ መሸማቀቅን ነው የሚያስከትልብህ፡፡ስንት ሰዎች በቆሰሉለት የፓለቲካ መሪ አፍረዋል….?ስንቱ ሰው ባከበራቸው የሀይማኖት አባቶች ተሸማቋል…?.ስንቱ ሰው የማምለክ ያህል በሚወደው አርቲስት ምግባር ልቡ ተሰበሯል?››
‹‹አያቴ ትክክል ኖት…፡፡ ግን ሰውን ሁሉ ሲጠራጠሩ መኖር አይከብድም?››
‹‹ልጄ በሀይማኖት ተቋማት እንኳን ለአንድ ሰው የሠማዕትነት ማዕረግ ለመስጠት አንድ መስፈርታቸው ታውቃለህ?የሰውዬው መሞት ነው ።..ለምን ይመስልሀል?"
‹‹እኔ እንጃ አያቴ››
"በህይወት ያለ ሠው በቀጣይ ምን እንደሚሰራ እና ምን እንደሚያጠፍ ፍፅም መተንበይ ስለማይቻል ነው።ይህ ግለሠብ በእኛ ሀይማኖት ዶግማና ቅኖና መሠረት እንከን አልባና በቅድስናው የተመሰከረለት ብለው አክሊል ከደፉለት በኃላ አንድ አመት እንኳን ሳይጠብቅ ‹‹አይ የእናንተ ሀይማኖት ግድፈት አለበት እስከአሁን በተሳሳተ ጓዳና ነበር ስጓዝ የነበረው በሉ ደህና ሁኑ›› ቢል ወይም በእግዚያብሄር ማመን አቁሜያለሁ ብሎ ቢያውጅ ምን ይፈጠራል? ።እንዲህ አይነት ጥፋት ደግሞ በመሸማቀቅ ብቻ አያበቃም… ተራ በሚባሉ አማኞ ዘንድ ውዠንብር ይፈጥራል…ጥያቄ ያስነሳል...ጥርጣሬ ያጭራል።ታዲያ ይሄንን የሚረድት የሀይማኖት ተቋሞች የፈለገ ክንፍ አብቅለህ በአየር ብትንሳፈፍ እንኳን ሞተህ ከአፈር በታች ቀብረው እስኪያረጋግጡ ድረስ ፃድቅ ነው ብለው አያውጅልህም፤ ሰማዕታችን ነው ብለው በመዝገባቸው አያሰፍሩህም ፡፡
‹‹አያቴ…አሁን አሁን እየተረዳሁት ያለሁት ሰው በጣም ውስብስብ ፍጡር እንደሆነ ነው፡፡››
‹‹ትክክል ነህ…እግዜር ሰውን እንደመልካችን በአምሳላችን እንፍጠር ብሎ አይደል የፈጠረን..ውስብስብነቱን ከእሱ ከባለቤቱ የወረስን ይመስለኛል..በል አንተ ቀልማዳ አሁን ተኛ ፡፡››
እሺ አያቴ ደህና ይደሩ››
‹‹ደህና እደር››

👍57❤5🥰3👏3🔥1😁1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
‹‹አያቴ ዛሬ በጣም አዝኛለሁ…››
‹አይ አንተ ልጅ ..መቼ ነው ዛሬ ተደስቼያለሁ የምትለው….ደግሞ ምን ሆንክ?››
‹‹ስለልጅቷ ነግሬዎታለሁ አይደል?›
‹‹ሥለየቷ… ስለልጅህ እናት››
‹‹እማይደል… እኛ ሆቴል ስለምትመጣው››
‹‹እ. ጄኔራል ውሽማ አላት ያልከኝ››
‹‹አዎ…›
‹‹ምነው? ተተናኮላት እንዴ?››
‹‹አይ ነገሩ ወዲህ ነው…›
‹‹እንዴት..››
‹‹በቀደም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕረግ እድገት ከሰጣቸው ጀኔራሎች መካከል አንዷ እሷ ነበረች››
‹‹ምን?››
‹‹አዎ ወታደር መሆኗን ሳላውቅ ..ጄኔራል ሆና አገኘኋት››
‹‹እርግጠኛ ነህ..በመልክ መመሳሰል ወይም መንታ እህት ኖሯት ይሆናል››
‹‹አይ አያቴ እንደዛ አይደለም..ማታ እቤት ከገባኁ ቡኃላ ሳይሰሙኝ ቀስ ብዬ ወጥቼ ወደሆቴል ሂጄ ነበር›
‹‹አንተ ቀልማዳ ምን ለመፍጠር…›
‹‹ቤርጎ ይዛ ስለነበረ አግኝቼ ልጠይቃት..እና እውነት መሆኑን አረጋጣልኛለች፡፡››
‹‹ታዲያ ይሄ ይደንቃል እንጂ ምኑ ያሳዝናል….እርግጥ ይገባኛል…አንተ የምታስበው ፍቅር እውን የመሆን እድል የለውም ብለህ ልታስብ ትችላለህ..እንደዘ ብታስብ አይገርምም፡፡ ማንም ባንተ ቦታ ቢሆን በተለየ መልኩ ሊያስብ አይችልም..ግን ማወቅ ያለብህ መቼም ቢሆን ፍቅር ምክንያታዊ ሆኖ አለማወቁን ነው፡፡እና በፍቅርና በጦርነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው›› የሚባለው ለምን ይመስልሀል፡፡ምንም ያልተገመተ እና ያልታቀደ ነገር መከሰት በፍቅርና በጦርነት ውስጥ ተደጋሞ የሚስተዋል እውነት ስለሆነ ነው፡፡
‹‹አያቴ ትክክል ኗት፤ እሱ እንዳለ ሆኖ እኔ ያዘንኩት ግን በአሁኑ ጦርነት ክፉኛ ተጎድታ ለሶስት ወር ሆስፒታል እንደነበረች ነገረችኝ…..››
‹‹ያሳዝናል….ድሮስ ከጦርነት ምን መልካም ዜና ይሰማል.››
‹‹አዎ እንደነገረችን ከሆነ ለአንድ ወር ሙሉ እራሷን አታውቅም ነበር..ከተንቤን በረሀ ተጭና አዲስ አበባ እስክትመጣ ..ኦፕራሲዬን ሲሰራላት ሁሉንም አታስተውስም…ጓደኞቾ እንደነገሯት አንጃቷ ሙሉ በሙሉ ተዘርገፎ ከተዝረከረከበት ተፋሶ ወደውስጥ ተመልሶ ነው ልትተርፍ የቻለችው …
ጠባሳዋ ከእንብርቷ ከፍ ብሎ ወደታች ከ20 ሴ.ሜትር በላይ ይረዝማል…እንደተነገራት ከሆነ ማህፀኗም ተቆርጦ ስለወጣ ከአሁን ወዲህ መውለድ አትችለም….. ለሀገሯ ደሞን ማፍስ ብቻ ሳይሆን …..››
‹‹በቃ በቃ ልጄ…በህይወት መትረፎም አንድ ተአምር ነው….ሌላው በሂደት የሚታይ ነው፡፡››
‹‹አያቴ እንዲህ መስዋዕት የሚከፈልላት ሀገር የምትባለው ጣኦት ግን ማን ናት?;›
ይህቺን ጥያቄ ለእሷ ብታቀርብላት እርግጠና ነኝ በእንባ ባቀረሩ አይነቾ በሞቀና በደመቀ ስሜት የሚያንሳፍፍ አይነት መልስ ልትሰጥህ ትችል ነበር፡፡እኔ ግን የተለመደው አይነት ቀና መልስ ልሰጥህ አልችልም ፡፡፡ልጄ እንደእኔ ሀገር ሀሳብ ወለድ ፅንሰ ሀሳብ ነው።ቋሚ እውነት አይደለም..ይጠባል ይሰፋል...ይለማል ፤ይፈርሳል ። ቢሆንም ከስነልቧናችን ጋር ስር የሰደደ ትስስር አለው፤ምክንያቱም ዘሬ ምንለውን መንጋ ህዝብ አዝሎ የሚያኖርልን .. ሀይማኖቴ የምንለውን መንፈሳዊ ተቋም የሚያቅፍልን ...መከታዬ ብለን የምንመካበትን ወታደርና ፓሊስ የሚያስገኝልን ….ተወልደን ያደግንበት ስፍራ ብቻ ሳይሆን ወልደንም የምናሳድግበት. .ዘርተን የምናጭድበት…ሞተንም የምንቀበርበት፤መታወቂያ እንጂ ፓስፖርት የማንጠየቅበት ስፍራ ነው፡፡
ሀገር በህይወት ጉዞችን በኑሮ ውጣ ውረዳችን ቀላል ትርጉም የለውም።ከሀገር በላይ ለእውነት የቀረበው እቤታችን ነው..፡፡ .አዎ ሚስታችን የምታስተዳድረው...ልጇቻችን የሚያደምቁት .. የልባችን የመጨረሻ ማረፊያ የአካላችን የየእለት መገኛ ..አዎ ሀገርን እንደ እንቁላል ውሰዷት ...ቅርፊቱ የአገር የመጨረሻው ድንበር ማለት ነው ...፡፡ጠላት በቀላሉ የሚበረቅሰው የመጀመሪያው ከለላ...ከዛ የመሀሉ ነጭ ክፍል የመሀል ሀገር ..ወይም ዋና ከተማ በለው...አስኳሉ ግን እቤትህ ነው ...ሚስትና ልጇችህ ወይም እናትና አባትህ እናም ቤተሠብህ የሚኖርበት ቢላ ቤትም ሆነ ደሳሳ ጎጇ።ግን አጥቂ ጠላት ሲመጣ ገና ከሩቅ ቅርፊቱን እንዳይሸነቁር ነፍስህን አሲዘህ ትፋለማለህ...ደምህን ታፈሳለህ ከዛም ከጨከነ ህይወትህንም ትሰጣለህ...ምክንያቱም ከቅርፊት መሸንቆር በኃላ እንቁላሉ ነጭ ክፍል መዝረክረኩ አስኳሉም መፍረሱ አይቀሬ ነውና...እና ለሀገሬ ብለን ስንፍለም አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የምንለፋበት ዋናው ምክንያት ለገዛ ቤታችን ደህንነት ነው...ለሚስታችንና ልጆቻችንን ለመታደግ ነው።
እስቲ የሀግርህን ሰው ተመልከት ቤት የሚሰራበት መሬት ሲመራ ቀድሞ አጥር ነው የሚያጥረው፡፡ ይህን የሚያደርገው በቀላሉ ሰው ያለእሱ ፍቃድ አልፎ የማይገባበትን..እንስሳ ሳይቀሩ የማይደፍሩትን የግል ይዞታን ለመፍጠር ነው፡፡እቤቱ ቀስ ብሎ ይደርሳል ዋናው ግን ግዛትን ማስከበር ነው የሚል ሳያውቀው በውርስ ያዳበረው እውነት አለው፡፡
ተረታችን እንኳን ባለቤቱን ካናቁ አጥሩን አይነቀንቁ፡፡››የአንድን ኢትዬጵያዊ ግለሰብ አጥር ሄደህ መነቅነቅ ቀጥታ ሰውዬውን በዱላ ከመዠለጥ የተለየ ትርጉም አይሰጠውም…ህግ የመጣስ ሳይሆን የክብር ጉዳይ ነው፡፡እና የሀገር ስሜት እንዲህ ከማንነታችን የተጋመደና የተወሳሰበ እሳቤ ነው፡፡እውነት ሆነ ሀሰባ ወለድ እሱ ብዙም ትርጉም የለውም፡፡ምክንያቱም አብዛኛው የሰው ልጅ የህይወት ፍልስፍና የተቃኘው በእውነት ላይ ሳይሆን በሚያማልሉ አፈታሪኮች ላይ ነው፡፡
‹‹ጋሼ…እሷም ከዚህ በላይ አታስረዳኝም…ግን ዋናው አሁን ምን ላድርግ ?አሳዝናኛለች››
‹‹አይ ልጄ…..ፍታ ያልኩህን ችግሮች ሳትፈታ ሌላ የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ተጎትተህ እየገባህ ነው፡፡ቢሆንም ይቅርብህ አደጋ ስላለው ሸሽተህ አምልጥ አልልህም….ህይወትን በመጋፈጠ እንጂ ሸሽቶ በማምለጥ ምንም የምታተርፈው ነገር የለም…ግን አንድ ነገር ልመክርህ እችላለሁ፡፡
‹‹ምን አያቴ …?››
‹‹ስራህ ቀይር››
‹‹ምን አያቴ?››
‹‹አዎ ከዚህ በላይ አስተኛጋጅ ሆነህ መቀጠልህ ህይወትህን ማባከን ነው የሚሆነው..ደግሞም አስተናጋጅ ሆነህ በቀጣይ እየመጣብህ ያለውን የህይወት ፈተና ተታግለህ ለማሸነፍ ትቸገራለህ፡፡›
‹‹ትክክል ነህ አያቴ..ግን?››
‹‹ግን ምን?››
‹‹ሁለት ችግር አለብኝ..አንድ የሂሳብ ደብተሬ ውስጥ ያለው 70 ሺ ብር ብቻ ነው..በዛ ብር ደግሞ እራሴን ችዬ ምን አይነት ስራ መጀመር እንደምችል አላውቅም…?››.
‹‹ሁለተኛውስ?››
‹‹ሁለተኛውም..ጋሼ ነው….ጋሼ ለእኔ በጣም ባለውለታዬ ነው….እሱ ጎትቶ ባያወጣኝ ዛሬም እዛ ጎዳና ትኬት መኪና ላይ እየለጠፍኩ ነበር ምገኘው…በዛ ላይ አያቴ ከእርሶ መለየትም ዝግጁ አይደለሁም…››
‹‹እኔም ካንተ ለመለየት ዝግጁ አይደለሁም…ለዛውስ ስራ ቀይር አልኩህ እንጂ እቤቱን ለቀህ ወጥተህ ተንዘላዘል ወጣኝ….?.››
‹‹አይ ማለቴ?››
ይሄውልህ ስማኝ..ጋሼ ውለታ ምናምን የምትለውን እርሳው እኔ ነገረዋለሁ…ማለቴ ካለፍላጎትህ እንድትለቅ የፈለኩት እኔ እንደሆንኩ እነግረዋለው…ይሄውልህ ስማኝ እኔ እንደምታየኝ ሽማግሌ ነኝ…ለዛውም የከተማ ባህታዊ ሆኜ ባህት የዘጋሁ…ምን ለማለት ነው ምንም ስራ የመስራት ፍላጎት የለኝም…ግን የተወሰነ ብር ደብተሬ ውስጥ አለ…እና አንተ ደስ የሚልህን ቢዝነስ አጥናና አምጣ እኔ ገንዘብ እሰጥሀለሁ…የጋራ ቢዝነስ እንመስርታለን ማለት ነው፡፡›

👍65👏3😁3🔥1
‹‹እውነቶትን ነው አያቴ?››
‹‹አንተ ቀላማጅ…ስዋሽ አይተሀኝ ታውቃለህ?››
‹‹አይ ለዛሬ እንኳን በራፍን ቢከፍቱልኝ ጉንጮትን አገለባብጪ ብስም እንዴት ደስተኛ እሆን ነበር መሰሎት?››
‹‹ብልጡ ይቅርብኝ ግዴለም…..ግድግዳውን ሳም››
‹አያቴ በጣም ነው ማመሰግነው….እኔ ጋር እንደነገርኮት 70 ሺ ብር አለ.. ደሞዜን ስቀበል 75 ሺ ብር አካባቢ ይሆንልኛል...እንደምንም እርሶ ጋር የተወሰነ ከተገኘ የሆነ ነገር መጀመር እንችላለን..በእውነት በጣም ነው የተደሰትኩት፡
‹‹ልጄ ››
‹አቤት አያቴ››ደንግጬያለሁ…ያን ያህል ብር ከየት አመጣለሁ ሊሉኝ ነው የመሰለኝ…ቢዝነሱ የጋራ ከሆነ እኩል እኩል ብር ማወጣት አለብን ..በዛ ላይ ምንም እንኳን የደሀ ጉልበት ሂሳብ ውስጥ አይገባም እንጂ ቢገባማ ስራውን የምሰራው እኔ ነኝ›› ስል በውስጤ አጉረመረመኩ…አያቴ ግን ተአምራዊ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
‹‹ያንተን ብር ቢዝነሱን ለማጥናት ተጠቀማት..እኔ አንድ ሚሊዬን ብር እሰጥሀለሁ››
ትን አለኝ..ምራቄ ስርኔ ውስጥ ተወተፈ‹‹ምን አሉ አያቴ?››
‹‹ሰምተሀል››
‹‹ይሄማ አይሆንም …ይህ ሁሉ ብር. በዛ ላይ እርሶ እሺ ቢሉ እንኳን ጋሼ አይፈቅድሎትም… ››ጥርጣሬዬን ነው የተናገርኩት፡፡
‹‹አንተ ቀልማዳ..መቼ ነው የምፈልግ ነገር ለማድረግ የአንተን ጋሼ ሳስፈቅድ ያየሀው…ወለድኩት እንጂ አልወለደኝም እኮ››
‹‹ቢሆንም…እንደዛ አይነት ብር ደፍሬ ልቀበል አልችለም››
‹ከችግርሀ ለመውጣት ፍላጎት ካለህ ትቀበላለህ..አየህ እያንዳንዱ ስኬታማ ሰው ቆም ብለህ ብትጠይቀው በአየር ላይ ተንሳፎ አሁን የደረሰበት ቦታ አልደረሰም..እንዲህ አሁን አንተ እንዳጋጠመህ አይት ቅጽበታዊ እድል አጋጥሞት ያንን በምስጋና ተቀብሎ በጥረት አሳድጎና አበርክቶ ነው፡፡አሁን ይሄን እድል ከገፋህ ምን አልባት የዛሬ ሃያ አመትም ተመሳሳይ እድል አታገኝም፡፡
ባለህ እውቀት፤ በቀናነት እና በፅናት ስራህን ስራ፡፡ ከዛ ውጭ ከቁጥጥርሀ ውጭ በሆነ ሁኔታ ብትከስር እኔ ግድ የለኝም..ከእኔ በላይ ከሳሪው አንተ ነህ ብታተርፍም ከእኔ በላይ ተጠቃሚው አንተ ነህ፡፡፡ምክንያቱም እደምታዬኝ በትርፉ ልጃገረድ አላገባበትም….በኪሳራውም እራሴን አላጠፋም፡፡ደግሞ ዝም ብዬ ስለምወድህ ብቻ አይደለም ይሄንን ብር የምሰጥህ በብዙ መንገድ ነገሮችህን ገምግሜና አይቼ ነው..ጓደኛ አታግተለትልም….ወደቤት መግባት ባለብህ ሰዓተ ተቆጪ አለኝ ወይም የለኝም ሳትል ታደርገዋልህ…ስራህ ሰው አየኝ አላየኝ ሳትል በታማኝነት ትሰራለህ… ስላለህ ብቻ ገንዘብህን አትረጭም…..የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሳይሆን በጣም የሚያስልጉህን ነገሮች በመጠቀም በመጠን እና በልክ የመኖር ልዩ ችሎታ አለህ…….ይሄ ደግሞ ብትከስር እንኳን በአንተ ጥፋትና እንዝላልነት እንደማይሆን እንዳማይሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹አያቴ ካሉ ደስ ይለኛል፡፡
‹‹እንግዲህ ተዘጋጅ…. ለጋሼህ ሰሞኑን እነግረዋለሁ..ከዚህ ወር በኃላ አስተናጋጅ ስለማትሆን በድንብ አጣጥመው››
‹‹አያቴ ››
‹‹አሁን ደግሞ ምን ቀረህ?››
‹‹ጥዋት እቤትህ ውሰደኝ ብላ ለምናኝ ነበር….አያቴን እንረብሸዋለን ብዬ እምቢ አልኳት፡፡›
‹‹አይ እንደውም ላወራት እፈልጋለሁ››
‹‹ማለት ከክፍሎት ይወጣሉ? ››
‹‹አንተ ቀልማዳ….የእኔን ወደውጭ መውጣት እንዴት እንዲህ ፈለከው..?እንድኖር አትፈልግ ማለት ነው..?ቢያንስ እስኪ ቃል የገባሁልህ ብር በእጅህ አስገባ››
‹‹አያቴ እርሶ ከሌሉ ብሩ ምን ያደርግልኛል ..ስለሚናፍቁኝ እኮ ነው ….. ደግሞ ይደብራቸው ይሆን እያልኩ እጨነቃለሁ›››
‹‹በል ወሬውን ተውና ይዘሀት ና…ግን ስለአለው ሁኔታ አስረዳት...ልክ ካንተ ጋር እንደማወራው አወራታለሁ..አጫውትታታለሁ፡፡›
‹‹እሺ አያቴ አመሰግናለሁ››
‹ደግሞ ልምድ ስለሌለህ በተዝረከረከ ቤት ዝም ብለህ ጎትተህ እንዳታመጣት፡፡ ለክብሯ በሚመጥን ዝግጅት ነው መምጣት ያላባት.፡፡.ሴት ነች..በዛ ላይ ወታደር ሴት፡፡እና ሀገርህን ወደቤትህ እንደጋበዝክ ቆጥረህ ተዘጋጅ››ብለው ጭንቅላት የሚበላ የቤት ስራ ሰጡኝ፡፡

👍88❤13🥰6🔥5🤔4
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
እንደተለመደው እቤቴ አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተዘርሬ በመተኛት ጣፋጮና ተወዳጇ ልጄ በቴሌግራም የላከችልኝን የእናቷን ዲያሪ በከፍተኛ ተመስጦና ውስጥን በሚሸረካክት የልብ ድማት ያለፈ ታሪኬን እያነበብኩ ነው፡፡
////
ማትሪክ በተቀበልን በአንድ ወር ውስጥ ለሰርግ ሽር ጉድ ተጀመረ..፡፡ለሠርጉ 15 ቀን ሲቀረው ጨነቀኝ..፡፡በረሽ ጥፊ ጥፊ..ወይም እራስሽን አጥፊ የሚል ስሜት ይተናነቀኝ ጀመር...፡፡እስቲ በፈረሰኛው በግድ ካላገባሽ እቆራርጥሻለሁ ብሎ ያስፈራራኝ ሰው የለ... ሁሉንም ያደረኩት በራሴ ፍቃድና ምርጫ ነው። እንደውም ቤተሠቦቼ በዚህ ሀሳብ እንዲስማሙ ለማሳመን ብዙ ነገር ቀባጥሬ ነበር...እና ታዲያ ?የቁርጡ ቀን ሲመጣ ምነውሳ...?ዋናው ጉዳይ ከእዬቤ እንዴት አድርጌ የምር እለያለሁ ?የሚለው ሀሳብ ነው እረፍት የነሳኝ....፡፡ እርግጥ አውቃለሁ ወደ ጋብቻው የገባሁበት ዋና አላማ ከእዬብ ለመራቅ ከአምላክ የተላከ ልዩና ረቂቅ ዘዴ አድርጌ በደፈናው ተቀብዬው ነበር እንጂ ዝርዝር ጉዳዬች ላይ በደንብ ያሰብኩባቸው አልነበረም። ይታያችሁ ባል ካገባው እኮ አብሮ ማደር ከዛም ያለፈ ነገር ማድረግ የግድ ነው ፡፡ በህልሜም ሆነ በእውኔ ከእዬብ ገላ ውጭ የወንድ ገላ ታስቦኝ በፍፁም አያውቅም።የሚገርመው እናትና አባቴን ጨምሮ የቤቱ ሰው ሁሉ በደስታ ሰክሮ ለድግሱ መሳካት ጠብ እርግፍ ሲል እዬቤ ግን ልክ እንደእኔ በተመሳሳይ ሁኔታ ድባቴ ውስጥ ገብቶ ነበር።አሳዘነኝ።እሱም እንደ እኔ ያፈቅረኝ ይሆን እንዴ?ለመጀመሪያ ጊዜ በአእምሮዬ የተሠነቀረ አስደሳች ጥርጣሬ ነበር ፡፡
ለማንኛውም የሰርጉ ቀን ደረሰ በተክሊል ስለምንጋባ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለሊት ስምንት ሰዓት ነው ቤተክርስቲያን የሄድነው። ግን በተክሊል እንዴት ልንጋባ ወሰንን? እርግጥ ሀሳብን ቀድሞ ያቀረበው መስፋን ነው።ግን እኔም ያለምንም ማቅማማት ነበር እሺ ያልኩት ፡፡ለዚህም ምክንያቴ በዋናነት ሁለት ነው። አንደኛው በተክሊል መጋባት ጋብቻውን ጥብቅ ስለሚያደርገው ወለም ዘለም የሚለውን ልቤን ያቃናልኛል ወይም መስመር ያስገባልኛል ብዬ ስላመንኩ ነው።ሁለተኛው ብዙ የሠንበት ት/ቤት ጓደኞቼ በተክሊል ሲያገቡ ሚዜም ሆነ አጃቢ ሆኚ አይቼ ስለነበረ እኔም አንድ ቀን እንደዚህ አገባ ይሆን የሚል የተደበቀ ምኞት በውስጤ ስለነበረ ያንን ምኞቴን ለማሳካት ያገኘሁትን እድል ለመጠቀም ነበር።
ስርዓቱም ከቅዳሴው ጥዋት ሶስት ሰዓት ተጠናቀቀ።በሰንበት ት/ቤት መዘምራን የሠርግ መዝሙር በመታጀብ ወደ የቤታችን ሄድን።እንግዲህ ምሳ ሰዓት ላይ ሙሽራው ከሚዜዎቹና አጃቢዎቹ ጋር መጥተው እስኪወስድን የተወሰነ ለማረፍና ለመዘገጃጀት የሚሆን ጊዜ ይኖረናል ብዬ ነው።እቤት ከገባን በኃላ ትንሽ ለማረፍ ሞከርኩ እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ ተነሳሁና እየተኳኳሉና እየተቆነጃጅ ካሉት ሚዜዎቼ ጋር ተቀላቀልኩ።እኔም መዘገጃጀት ስላለብኝ ያሳምሩኝ ጀመር...፡፡ሁሉም ደስተኛ ይመስላል... የተከፈተ ጥርስ..የፈገገ ፊት...በማይክራፎን የተለቀቀ መዝሙር እኔ ግን ቅር እንዳለኝ ነው ።ከቤተ ክርስቲያን መልስ ጀምሮ እዬቤን አላየሁትም።የት ገባ?ከአሁኑ በጣም ነው የናፈቀኝ።እህቴን ጠራኋትና ጠየቅኳት..እንዳላየችው ነገረችኝ።ሌላ የምትሰራውን ስራ ሁሉ ትታ እሱን ፈልጋ እንድትጠራልኝ ጠየቅኳት...ሌላ ቀን ቢሆን የራስሽ ጉዳይ ነበር የምትለኝ።በእለቱ ግን ያው የቤቱ ንግስት ነኝና ጥያቄዬን በእሺታ ተቀብላ ልትፈልገው ወጣች።
15 ከሚሆኑ ደቂቃዎች በኃላ ይመስለኛል እየተጎተተ በግድ የፈገገ ግን ደግሞ የዳመነ ፊቱን ይዞ መጣ..ሴቶች የሞሉበትን ክፍል በራፍ ላይ ቆሞ አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ ‹‹ሪች ፈለግሺኝ" ሲል ጠየቀ….ገና ድምፁ ጆሮዬ ከመድረሱ ሰውነቴ በጠቅላላ ነዘረኝ፡፡
‹‹አዎ ግባ››
‹‹ወዴት ልግባ..?››
‹‹ጥፋሬን ቀለም እየተቀባሁ ስለሆነ እኮ ነው..ግባ የማታውቀው ሰው የለም "ብዬ አደፋፈርኩት፡፡ገባና ወደእኔ ቀረበ..እንዲቀመጥ ኩርሲ ከጎኔ አስቀመጥኩለት እያቅማማ ተቀመጠ።እዛች ክፍል ውስጥ የተጠቀጠቁት ሴቶች ጆሮና አይን በጠቅላላ እኛ ላይ እንደሰፈረ አውቃለሁ። ቢሆንም ምርጫ የለኝም።ድምፄን ቀነስ አድርጌ በሹክሹክታ መጠን
"የት ጠፍተህ ነው? ናፈቅከኝ እኮ"አልኩት
"ደክሞኝ ተኝቼ ነበር"
"የት?"ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩት የእኔና የእሱን የጋራ ክፍል አሁን እያተረማመሰነው ስለሆነ ብዬ ነው፡፡
"እቴቴ ክፍል"
"አይንህ ግን ምንም የተኛ ሰው አይን አይመስልም"
እንደዛ ያልኩት አይኑ በርበሬ ይመስላል እንደሚባለው ቀይ ሆኖ ስለደፈራረሰ ነው።
"ተኝቼ ነበር እኮ አልኩሽ...አሁን ለምን ፈለግሺኝ?"ቆጣ አለ፡፡
"አትቆጣኛ"
"አልተቆጣሁሽም"
"አብረኸን ትሄዳለህ አይደል?"
ደንግጦ"የት?"
ለእሱ መልስ ከመመለሴ በፊት ‹‹ተነሡ ተነሱ ሰርገኛው ደረሰ ተዘጋጅ ..››የሚል የማንቂያ ድምፅ ከውጭ ተሰማ…ትርምስምስ ተፈጠረ... የእሱን አደነጋገጥ እስከዛሬም በፊቴ ላይ አለ።በርግጎ ተነስቶ ፊቴ ተገተረ...እኔም ተነስቼ ቆምኩ።ተጠመጠምኩበት..ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ።እንባዬን ዘረገፍኩት እሱም ተንሰቅስቆ ማልቀስ ጀመረ።ሊያላቅቁን መሀላችን ገቡ።
‹‹አረ ቆርበሽ እንዴት ታለቅሺያለሽ?››
"አገባች እንጂ አልሞተች… የምን ሟርት ነው?።››
"አረ ተው ነውር ነው።››
ሁሉም የመሰለውን ተንጣጣ...አላቀቁን ።እዬቤ ተስፈንጥሮ ክፍሉን ለቆ ተፈተለከ።ከፋኝ ።በጣም ከፋኝ።ፈፅሞ ጥሎኝ እንዲሄድ አልፈለኩም ነበር።እጥፍጥፍ አድርጌ ጡቶቼ መሀከል ከትቼ በየሄድኩበት ይዤው ብሄድ ደስተኛ ነበርኩ።..የምሳ ፕሮግራሙ ሲካሄድም ሆነ እኛ ቤት የነበረው ዝግጅት ተጠናቆ ከእኛ ቤት ወጥተን ስንሄድ አይኔ ቢንከራተትም እዬቤን ዳግመኛ ሳላየው ነበር የእናትና አባቴን ቤት ለዘላለም በሚመስል መንገድ ለቅቄ በቅርብ ከተዋወቅኩት እና በቅጡ እንኳን ያለመድኩትን ሰው ተከትዬ የሄድኩት።
ሙሽራው ሙሽሪት..እንኳን ደስ ያላችሁ
የአብርሀም የሳራ-ይሁን ጋብቻችሁ።
እንደዛ እንደዛ እያለ ሰርጉ ተጠናቀቀ ..መሸ ጫጉላ ቤት ገባን ..እግዚያብሄር ይመስገን ፡፡ በተክሊል ስለተጋባንና በእለቱም ስለቆረብኩ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም ነበርና አንድ አልጋ ላይ ብንተኛም ሰውነታችንን እንኳን ሳናነካካ ተራርቀን ተኛን ፡፡የሁለት ቀን የተጠራቀመ እንቅልፍ ስለነበረብኝ የት እንዳደርኩ አላውቅም ነበረ ።የሚገርመው ጥዋት እንደነቃሁ በእጆቼ የሞጨሞጩ አይኖቼን እያሻሸው"እዬብ ነጋ እንዴ?"ብዬ ነበር ጠየቅኩት ።ደግነቱ ክፍል ውስጥ ማንም ስላልነበረ የሰማኝ ሰው አልነበረም። እንደምንም አልጋዬን ለቅቄ በመውረድ ልብሴን እየለበሰኩ ሳለ በሩ ተከፈተና መስፍኔ ገባ፡
"እንዴ ተነሳሽ እንዴ?"ዝም አልኩት።
"ምነው አመመሽ እንዴ?"አለኝ ወደእኔ እየተጠጋ።
ጭራሽ እየታገልኩት የነበረውን ስሜቴን ነቅንቆ አደፈራረሠው...እንባዬን ዘረገፍኩት።
"እንዴ ምነው?ምን ተፈጠረ?"
"እዬቤ"
"እዬቤ ምን ሆነ?››

👍76❤8🥰1😢1