"ሐመር ላይ ሴት ልጅ ማህፀኗ ባዶ ከሆነ አፏ አለብላቢት እንደበላች ፍየል ሰውን ይረብሻል ቅስም ሰባሪ ተስቦ በሽታዋ ሁሉንም ተአጠገቧ ያርቀዋል ከዚያ ተከብቱም ተሰውም በረት ርቃ
ብቻዋን ሆና እህል የማያበቅል እማይጠጣ እንደ በረዶ እየቀዘቀዘ
በመንዠቅዠቅ የማያባራ
ዝናም ላይዋ ላይ እየወረደ ጥርሷን እያፋጨች ስትንቀጠቀጥ እናቷ እንኳ አትደርስላትም"
መከራዋን ስታዳምጥ
ማንጎራጎሩን ከልቦናዋ ትረሳዋለች የኢቫንጋዲ ዳንሱ ትዝታ ሙልጭ ብሎ ይጠፋል . ያን ጊዜ ካርለቴ
የኩራት ክብሩ ቀርቶ ሆደ ባሻነት እንደ ሰንበሌጥ ሣር በውስጥሽ በቅሎ በቅሎ ይውጥሻል" ለሐመር ሴት እውነተኛው ለቅሶ እንደ
አባቷ መፎከሪያ በሬ እየተፎገራች ግረፉኝ ስትል እየተንጠራራ ጎረምሳ በባራዛ አርጩሜ ጀርባዋን ሲሸነቁጣት ሰንበሩ እንደ እባብ ጀርባዋ ላይ ተጋድሞ: ደም ፍጭጭ ሲል ከዐይኗ የሚፈሰው እንባ አይደለም ያማ ስቃይሽን እንዲያጠፋ በአባትሽ ደንብ ከተሞላው
ልብሽ የሚደፋ የሥቃይ ማጥፊያ ውሃ እንጂ ለቅሶ አይደለም ካርለቴ! የኔ እህት ለቅሶ ማለት የውስጥ ቃጠሎ ነው" ውስጥሽ
የሚንቀለቀልን እሳት ማጥፋት ሲቸግርሽ ነው ወደ እሳቱ የምትደፊው የእንባ ውሃ ስታጭ ነው ..." ሳግ ተናነቃት ጎይቲ
ውስጧ ጤሶ ተቀጣጠለ ካርለት ደነገጠች
"ኦ! ጎይቲ ካርለት ጎይቲ እንዲህ አዝና ተስፋ ቆርጣ አይታት አታውቅም
ሃዘኗ አሸበራት ፊቷ እንደ በሰለ ቲማቲም ቀላ አንጀቷ በኃዘን ተላወሰ ጎይቲ ንፍጧን ተናፍጣ እንባዋን
በአይበሉባዋ ጠርጋ
"እንዲያ ታያ ደልቲና ተጎረምሶች ጋር በየጫካው ስቃበጥ ጓደኞቼ ማህፀናችንን እንፈትሸው' ሲሉ እኔ ውበቴ ጠላት ሆኖኝ
ጨረቃን እያየሁ: እየተጠነቀቅሁ መቅበጥ እንጂ ልቤን ደፍኖኝ
ለማርገዝ አልሞከርኩም ነበር ... ስትል ካርለት ንግግሯን አቋርጣት,
"ጎይቲ ምንድን ነው ደግሞ ማህፀን መፈተሽ'? አለቻት
ጎይቲ ወዘናው በቀነሰ ፈገግታ ፈገግ ብላ "ይእ አንች ሰው! ምኒቱ
ልብ አድርቅ ነሽ እቴ! ይህን ይህን ታላወቅሽ እህ እሱን ጭሮሽሽን አስደፍኝና ቦርጆን እንዳሁላ
አብቅልልኝ ብለሽ ሳዳጎራሽን አገልድመሽ ተወንዶች ጋራ አደን ውረጂያ!"
"አትሰልችኝ ጎይቲ! ስለማላውቀው እኮ ነው የምጠይቅሽ?" አለች ካርለት ለጥናቷም ትልቅ ፍንጭ በማግኘቷ ባንድ በኩል ደስ እያላት
"ይእ! አታምርሪ የኔ ሸጋ ጨዋታየን እንጂ እንኳን ይህን አያ ደልቲና አንች ጫካ ስትገቡ … ብለሽስ
ጠይቀሽኝ መልሸልሽ
የለ ላላወቀ ደግሞ መመለሱ ምኑ ያሰለቻል
ደንብ ነው!" ብላ
"ማህፀን መፈተሽ ማለት ማርገዝ ማለት ነው በሐመር ልጃገረድ ቀብጣ ስታረግዝ አትጠነቀቅም
ነበር ተብላ ላይ ላዩን
ብትወቀስም ማርገዟ ግን ጥቅም አለው
አባቷንም የሚያስደስት
ፅንሱን ብታስወርድም ማህፀኗ የተቀደሰ ነው' ትባላለች ባልም
እጮኛ ሊያረጋት ይሽሎኮሎካል ያን ጊዜ አባቷ ጥሎሹን ጨምሮ
ይጠይቅባታል፤ ጥሎሽ ከፋዩም ማህፀኗ የተቀደሰ ስለሆነ ይሁን ብሎ ይስማማል" ያን ነው ልጃገረዶች ማህፀን መፈተሽ የሚሉት" ብላ
እሷ ያን ባለማድረጓ መበሳጨቷን እጅዋን በእጅዋ እየደበደበች
አሳየች ካርለት ዐይን ዐይኗን ስታያት ቆይታ
"ጎይቲ መሃን ሴት በምን ትታወቃለች?" አለቻት"
"ይእ! በቀንዷ!" ብላ ጎይቲ ቀለደችና ስትስቅ ካርለትም
አብራት ሳቀች
"ጎይቲ እየቀለድሽብኝ ነው?"
"ይእ! እህ ምናባቴ ላርግ ካርለቴ ሴቱ ሁሉ የሚያውቀውን
አንች አዲስ ሆነሽ ስትጠይቂኝ መቀለድሽ አይደለ?"
"የለም ጎይቲ አልቀለድሁም ቁም ነገር እየተጫወትን
አልቀልድም "
"ይእ! ምን ነበር እቴ የጠየቅሽኝ?"
"መሃን ሴት በምን ትታወቃለች?"
"… በጥንት ጊዜ ቦርጆ እዚሁ እቅርብ ተሐመሮች ጋር ነበር አሉ የሚኖረው" ታዲያልሽ አንድ ጊዜ ከአንዲት ሴት ጋር ይጣሉና
ሴቷ ቦርጆን በጋሊ አርጩሜ ትደበድበዋለች እና በጥፋቷ ያዘነው
ቦርጆ መሐን ሁኝ ብሎ ረገማትና የሐመር ወንዶችን ሰብስቦ አብሬያችሁ በመኖሬ እየተናናቅን ነው
ዝናብ ስትፈልጉ
ተሰብስባችሁ ጥሩኝ እርስ በርሳችሁ አትጣሉ
ከተጣላችሁ ደግሞ
ሽማግሎች ያስታርቋችሁ
በቡድን ሁናችሁ አትጣሉ
ያገኛችሁትን ተካፍላችሁ እንድትበሉ በራችሁ ቀን ከሌሊት አይዘጋ ካለበለዚያ
ዝናብ አልሰጣችሁም"
ሁሉም ሴቶቻችሁ አይወልዱም
ከብቶቻችሁም አይራቡም በሽታም እልክባችኋለሁ ብሎ ነው አሉ ርቆ ሰማይ ላይ የወጣው" እና መሐን ሴት ቦርጆን : ደብድባ
የተረገመች ናት ስትሞት እንኳ ነፍሷ መጀመሪያ እሳት ውስጥ ተዚያ ተተከማቸ ትል ውስጥ ነው አሉ ስትባዝን የምትኖረው ንግግሯን አቋርጣ ጎይቲ | ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ካርለት ጎይቲ ባለችው ባታምንም
“እምነቷ ምን ያህል
እንደረበሻትና ባለመውለዷም የሚጠብቃትን ጣጣ አስታውሳ ለእሷና ለሌሎችም መሐኖች አዘነች" ካርለት የምታውቀውን ለጎይቲ እንዴት እንደምታስረዳት ስታስብ ቆየችና
"ጎይቲ መሐንነት የትም አገር አልፎ አልፎ አለ ችግሩ ግን
ከሴቷ ብቻ ሳይሆን ከወንዱም ሊመጣ ይችላልኮ" ስትላት ጎይቲ
ቅንድቧን ሽቅብ ሸብሽባ
"ይእ! የባሰው መጣ!
ኧረ ዝም በይ ያገር መሳቂያ
እንዳትሆኝ. የዘራሽው እህል
ባይበቅል ችግሩ ተመሬቱ
ነውዐኸዘሪው? አንች እውነትም ዝናብ በዝቶበት ፍሬ ያልያዘ ማሽላ ነሽ"
አለቻት" ካርለት በምን ዘዴ እንደምታስረዳት ጨንቋት መላ ፍለጋ መሬቷ ላይ አፈጠጠች
💫ይቀጥላል💫

👍26
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ አራት)
(ሜሪ ፈለቀ)
«ጓደኛዬ ነው!! ትናንት አንተን ትተን ስንወጣ ተከትለውን ነበር።» ብዬ ሆስፒታል የመተኛቱን ሚስጥር አብራራሁ ጎንጥን ምኔ ነው ብዬ ማስተዋወቅ እንዳለብኝ ግራ ሲገባኝ ማቅረቤ ይሁን ማራቄ ልኬቱን እንጃ!! ወዲያው ግን ስም ሲለዋወጡ በስሙ ያውቀዋል እና ኪዳን ዞሮ አየኝ! <ጎንጥ ይሄ እኔ የማውቀው ጎንጤ?> ዓይነት አስተያየት! ምንም እንዳይጠይቀኝ በልምምጥ ሳየው እኔን ተወኝ! ከዛ ግን ወንበር ስቦ ጎንጥ ፊት ተቀምጦ አንዱን ጥያቄ ከሌላው እያስከተለ ይደራርብ ጀመር።
«ቤተሰብ አለህ? ማለቴ የራስህ ሚስትና ልጆች? አዲስአበባ ከመጣህ ቆየህ? ሜልጋ ሳትሰራ በፊት ምንድነበር የምትሰራው? ሴት ጓደኞችህን ሁሉ <ዓለሜ> ብለህ አትጠራም መቼም አይደል? ስራህ ስለሆነ ነው ወይስ ሜል ስለሆነች ነው (በአገጩ የተመታውን ጠቆመው) ከዳንክ በኋላ ….. »
«ኪዳን?» አልኩኝ በልመና መጠየቁን እንዲያቆም ….. በአንድ በኩል ግን መልሳቸውን ልሰማቸው የምፈልጋቸው ጥያቄዎች መሆናቸው ለጎንጥ መልስ እንድጓጓ አደረገኝ። የእውነት ከዳነ በኋላስ?
«ሴት ልጅ አለችኝ!» የሚለውን ብቻ ነው ከዚህ ሁሉ ጥያቄ ፈገግ እያለ መርጦ የመለሰው። ኪዳን ሌላውን ጥያቄ እንዲመልስለት አንገቱን አስግጎ ጠብቆ ዝም ሲለው
«come on!» አለ
«መሽቶም የለ? ሂዱና ጎናችሁን አሳርፉ!! » ሲል ነው ጎኔ አልጋ ከነካ 48 ሰዓት እንዳለፈው ትዝ ያለኝ።
«እርግጠኛ ነህ ብቻህን ምንም አትሆንም?»
«ምንም አልሆን አልኩሽ እኮ!!» ያለበት ድምፅ <ዓለሜ> እንደሚለው ያለ ማባበል አለው ነገር? ወይም መስሎኝ ነው 48 ሰዓት ያልተኛ ሰው ብዙ ያልተባለ ነገር የመስማት እድሉ ከፍተኛ ነው።
ይሄን ካለ በኋላ ለሆነ ደቂቃ የሆነ ያልተለመደ ዓይነት ዝምታ ተፈጠረ። ቻው ብዬው መውጣት እፈልጋለሁ ግን የአልጋው ግርጌጋ እንደተገተርኩ ነው። ልቤና እግሬ ተጣሉብኝ!! እንድሄድ እየጠበቀ ነው ግን በዓይኖቹ እንድቆይለት እያባበለኝ ነው ወይም መሰለኝ። በእንደዛ ዓይነት ፖዝ ፎቶ አንሺ ያስቆመኝ ነው የምመስለው።
«እኔ የምለው? እኔኮ ብቻዬን ማደር እችላለሁ! አንቺ ለምን እዚህ አትቆዪም?» የሚለው የኪዳን ንግግር ነው እኩል ሁለታችንንም እንደመባነን ያደረገን
«አይሆንም!» አልን ሁለታችንም በአንድ ድምፅ ግንኮ አሁንም ኪዳንን ያየው የለም እኔና እሱ ዓይናችን አልተፋታም! ከዛ ደግሞ ራሴው አይሆንም ያልኩትን እሱም አይሆንም ማለቱ ለምን ከፋኝ?
«እህእ? ወይ ሶስታችንም እዚሁ እንደር?» አለ ኪዳን ሳቅ እያፈነው። አሁን ሁለታችንም አየነው። ስንወጣ ሲያበሽቀኝ እንደሚያድር አውቃለሁ።
«ደግ! በሉ ቸር እደሩ!! ትከሻሽን መገላመጥ አትዘንጊ!» አለ በቃ ተሰናብቼሻለሁ ሂጂ እንደማለት ነገር ከነበረበት በቀስታ ዘወር እያለ።
«የምትባባሉትን ተባባሉ በሩጋ ነኝ!» ብሎ ኪዳን ወጣ!! ምን እንደሚባል የማውቀው የለኝም!! ማለት የምፈልገው መኖሩንም እንጃ! ካለሁበት ተንቀሳቅሼ ልቀርበው ፈልጌ ማፈር ነው ግራ መጋባት የማላውቀው ስሜት ጨመደደኝ። ጭንቅላቴም ልቤም ሰውነቴም ተባብረውብኝ ማድረግ የምሻው ብቸኛ ነገርኮ እሱን መንካት ነው። እንዲህ ሆኖ የሚያውቅ ሰው ኖሮ ያውቅ ይሆን አላውቅም! ገብቶት ነው መሰለኝ ወይም እሱም እንደእኔ አካላቶቹ አምፀውበት ሊነካኝ ፈልጎ እጁን እንድይዘው ዘረጋልኝ። ከረሜላ አይቶ ሲቁለጨለጭ ምራቁ አፉ ውስጥ ሞልቶ ወደ ጎሮሮው ሲደፍቅበት ቆይቶ ከረሜላውን እንደሰጡት ህፃን በአንድ እርምጃ ዘልዬ እጁን ያዝኩት። እጁን እጄ ላይ ከማጫወቱ ውጪ በቃላት አላወራኝም። በዓይኖቹ የሚያወራው ደግሞ ትርጉሙ እኔ እንደምፈታው ይሆን ሌላ እየገባኝ አይደለም። <የዓይን ቋንቋ እንደፈቺው ነው!>
«ከዳንክ በኋላስ?» አልኩት ለሚመልስልኝ መልስ ሳልዘጋጅ
«አላውቅም!» አለኝ ከአይኔ ውስጥ ቆፍሮ የሚያወጣው ስሜት ያለ ይመስል በአይኑ አይኔ ውስጥ እየቆፈረ። መልሱ ምን ሊሆን እንደሚችል የጠበቅኩት ነገር ስላልነበረ አልከፋኝም! እሙ እንዳለችው ከመጃጃልም በላይ እየሆንኩ እንደሆነ የገባኝ ከ<አላውቅም> አስከትሎ <ዓለሜ> አለማለቱ ከፋኝ! አንዴ አለሜ በለኝ ብለው ሆዱን ይዞ አይስቅብኝም? ይባላልስ?
«አንቺ ምንድነው የምትፈልጊው?» አለኝ
«አላውቅም! ምን እንደምፈልግ አላውቅም!» አለ አፌ! የምፈልግ የነበረው ግን ዓለሜ እንዲለኝ ፣ የምፈልግ የነበረው እንደቀኑ የእጄን መዳፍ መሃሉን እንዲስምልኝ፣ እምፈልግ የነበረውማ ለአንዴ በህይወቴ ጀግና ጀግና የማልጫወትበት ሰው እንዲሆነኝ ……. ለአንዴ ብቻ ፍርሃቴን ፣ ድክመቴን ፣ ማፈሬን ፣ ሽንፈቴን ፣ …. ከእንባዬ ጋር ለውሼ ደረቱ ላይ እንድተነፍሰው በክንዱ ደግፎ ደረቱ ላይ እንዲያቅፈኝ ….. እፈልግ የነበረውማ ይሄ ያልኩት ሁሉ ሲሆን ዘመናት ቢቆጠሩ ነበር። ቀጥዬ ያልኩት ግን
«ኪዳን አባት ሊሆን ነው!» የሚለውን ነው! ሳልፈልግ ድምፄ ውስጥ መከፋቴ ተሰማብኝ። የያዘውን እጄን ስቦ ወደደረቱ አስጠግቶ ደረቱ ላይ አጥብቆ ያዘው። ይሄ ሰውዬማ ከእጄጋር የሆነ ነገር አለው! ነውስ እጄና ልቤ የሚያገናኛቸው ነገር አለ እጄን የሆነ ነገር ሲያደርገኝ ልቤ አብሮ የሚያሸበሽበው?

👍14👏1
«ዳር የተተውሽ መሰለሽ?» ሲለኝ እንባዬ ታገለኝ!! ነግሬዋለሁ? አልነገርኩትም! የተሰማኝን በልከኛው ቃል እንዴት ማስቀመጥ ቻለበት? አንዲት ፊደል ከአፌ ቢወጣ እንባዬ እንደሚያጅበው ስለገባኝ ዓይኖቹን ሸሽቼ ዝም አልኩ። ደረቱ ላይ የያዘውን እጄን እዛው ትቶት በእጁ አገጬን ደግፎ ዓይኖቹን እንዳያቸው አደረገኝ።
«መቼም ቢሆን በምንም የማይተካሽ እህቱ ነሽ!! ሚሽትና ልጁ ያንቺን ቦታ አይጋፉም!! ኪዳንን በዚህ ሁሉ መዓት ፍቅር ስትወጂ ልብሽ ጠቦሽ አባትሽን አስወጥተሻል? ወይሳ እናትሽን? እኔን ወደልብሽ ስታስገቢስ ልብሽ አልበቃ ብሎ ከኪዳን ፍቅር አጎደልሽ? የእርሱን ቦታ ቀነስሽ?»
«አይ!!» ብዬ ጭንቅላቴን በአሉታ ከነቀነቅኩ በኋላ ነውኮ መጨረሻ ላይ ያለውን ለራሴ ደግሜ ስሰማው ዓይኔን የማሳርፍበት የጠፋኝ። ጥሩ እየሰማሁት ነበርኮ ከመጨረሻው እሱን ልቤ ካስገባበት ዓረፍተ ነገር በፊት! <አይ> ያልኩት ምንድነው ቆይ? የኪዳንን ፍቅር ሳታጎድል ነው ልቤ የገባኸው ነው አይደል ያልኩት? የጥያቄው መልስ እንደተመለሰለት ፈገግ ብሎ አገጬ ላይ አውራ ጣቱን አሸት አሸት ነገር አድርጎ እጁን ደረቱ ላይ ወደተወው እጄ መልሶ እንደቅድሙ አጥብቆ ደረቱ ላይ ያዘው።
«ያልኩት ሀቅ አለው?» ብሎ አወነባበደብኝ። ምናለ ዝም ቢለኝ ገብቶት የለ?
«ምኑ?»
«ከልብሽ ገብቻለሁ?»
«አዎ! መሰለኝ! እኔ እንጃ አላውቅም! በምን አውቃለሁ?» በዚህ ነፋሻማ አየር እንዲህ ሊሞቀኝ ይገባ ነበር? ስፈራ ጉልበቴን እንደቁርጥማት እንደሚያደርገኝ ነገር አሁን ሊሰማኝ ይገባ ነበር? ሳቅ እንደማለት ነገር ብሎ
«በይ ተነሽ ሂጅ አሁን እየጠበቀሽ ነው!!» ብሎ እጄን አንስቶ አገላብጦ ይስመው ጀመር!! አንዴ ሁለቴ ሶስቴ ….. ሁለቴ አይበሉባውን አንዴ ወይም ሶስቴ መሃል እጄን….. እኔ እንጃ አንድ አራቴ ጎኑን ….. ጣቶቼን …… ከመጀመሪያው በኋላ እንኳን ቁጥሩን ላውቀው እንደባለፈው ራሴንም አለመዘንጋቴ በቸርነቱ ነው። ከዛ ነገና ዛሬዬን ከደባለቀብኝ በኋላማ ምንም እንዳልሆነ ነገር እጄን መለሰልኝ። ማድረግ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበር። ግን ለመሄድ ተነሳሁ እና ወደበሩ መንገድ ጀመርኩ። ልቤማ ደረቴ ውስጥ የለችም! እንጂ ሰውነቴ እንዲህ ወደኋላ ባልጎተተኝ። በሩጋ ደርሼ ዘወር አልኩና
«ነገ እኮ እማዬጋ ልሄድ እችል ይሆናል።» አልኩት ለምን እንዳልኩት ሁሉ እኔ እንጃ! ምናልባት አንድ ደቂቃ እሱጋ መቆያ ምክንያት እየፈለግኩ መሰለኝ።
«ደግ!!» ብቻ ነው ያለው!! እንዴ? ምንድነው ሰው ማግዶ እሪሪሪ እስኪሉ መጠበቅ? ኮስተር እንዳልኩ ለራሴ እየታወቀኝ በሩን ይዤ ቆምኩ!
«ምነው ዓለሜ? የምትነግሪኝ አለሽ እንዴ?» ሲል ከንፈሬ ሳላዘው ሸሽቶ ያለኝ ጥርስ ሁሉ ንፋስ ዳበሰው
«ምንም የለም! ደህና እደር በቃ!» ብዬው ወጣሁ። መኪናው ጋር እስክንደርስ ከኪዳን ጋር ምንም ቃል አልተለዋወጥንም! መጣሁ መጣሁ እያለ እየተናነቀው እንደሆነ ያስታውቅበታል።
«ትከሻሽን መገላመጡን አትርሽ ዓለሜ!» አለ መጨረሻ ላይ ከት ብሎ እየሳቀ
«አፍህን ዝጋ እሺ!! አንድ ነገር እንዳትለኝ!» አልኩት ሳቅም ማፈርም በደባለቀው ቁጣ
«ጀግና ነው ግን ሜል ሙች!! ይፈርምልኝ! ጠባቂ ሆኖ ገብቶ ጠብ ያድርግልኝ? ሜል ገና ስታይው ፍስስ እኮ ነው ያልሽው!»
«ኪዳን ተወኝ አልኩ እኮ!»
«አንዴማ ጨብጬው ልምጣ ሜል ሙች» ብሎ ወደኋላው እንደመመለስ አለ
«ባክህ አርፈህ መኪና ውስጥ ግባ አትጨማለቅ!!»
የማውቀው ገስትሀውስ ደውዬ አልጋ ያዝኩ። መንገዱን ሁሉ ሲያበሽቀኝ እና ሲገረም ዘለቅነው «ምን አባቱ አድርጎሽ ነው ግን ስንቱን ወንድ ያሸና ልብሽን ዘጭ ያደረገው? ፣ እኔንኮ እዛ እንደሌለሁ ረሳችሁኝ ሆ! ፣ እድሜ ደጉ ሜል ስትሽኮረመም ያሳየኝ? ፣ ፍቅር በሀገርኛ ግን ጆሮ ላይ ደስ ይላል አንቺ? ነፍሴን አወክሻትኮ ዓለሜ! ነው ያለው? > አያቆምም ይለፈልፋል። በመሃል
«ሜል ሻምበሉጋ ከአንድ ሰዓት በኋላ እደውላለሁ ካልሽው ሁለት ሰዓት አለፈ!» ሲለኝ ሰዓቴን አየሁት። መርሳቴ እኔንም ኪዳንንም ገረመን!! አንድ ሰው እንዲህ የሰውን ሀሳብ መቆጣጠር ይችላል?
«እኩለለሊት ሊሆን ነው!! ጠዋት ብደውል ይሻላል!!» ስለው ኪዳን አይኑን ጎልጎሎ አውጥቶ አፈጠጠብኝ
«you know am happy for you!! ሜል ነገር አሳደረች? ያውም ሊገድላት የሚከረ ሰው ? ፍቅር ግን ደስ ሲል!!»
«ለምንድነው ግን አፍህን የማትዘጋው?»
ለሁለት ደቂቃ ዝም ይልና ደግሞ ይጀምረኛል። ማረፊያችን ደርሰን የምናወራው ቁምነገር መኖሩን ተኮሳትሬ እስክነግረው ማብሸቁን አላቆመም!!
«አሁን የምር አስጨነቅሽኝ! ምንድነው ንገሪኝ!!» አለኝ አጠገቤ አልጋው ላይ እየተቀመጠ አንድ እጁን እንደማቀፍ ትከሻዬ ላይ ጣል እያደረገ
«እማዬ አልሞተችም! በህይወት አለች!! እና ልታይህ ትፈልጋለች!»
«ማለት?» ብሎ እጁን ከትከሻዬ ላይ አነሳው
«በሰዓቱ ላንተ እውነቱን መንገር ከምትሸከመው በላይ ስለሚሆንብህ ነው ከአጎቴ ጋር ተነጋግረን እንደሞተች የነገርንህ! ታዲያ የታለች ብትለን ኖሮ መልስ አልነበረንም!»
«እና የት ነበረች?» ብሎ ስፈራው እና ስሸሸው የኖርኩትን ጥያቄ ጠየቀኝ። እንዴት ብዬ እንደምነግረው ስጨነቅ
«ሜል ያኔ ህፃን ስለነበርኩ ነው የዋሸሽኝ አሁን ግን ትልቅ ሰው ነኝ ንገሪኝ!!» ብሎ ሲሆን አይቼ እንደማላውቀው ተኮሳተረ። የዛን ቀን ያየሁትን ነገር በሙሉ ነገርኩት። እየጠበቅኩ የነበረው የሚናደድ ወይ ሌላ ጥያቄ የሚያስከትል ነበር። እሱ ግን መጥቶ እያቀፈኝ
«አንቺምኮ ይሄን ሁሉ ብቻሽን የምትሸከሚበት እድሜ ላይ አልነበርሽም!!» አለኝ። ቀጥሎ ግን «አንቺ ትታን ስለሄደች አላዘንሽባትምኣ?» ብሎ ያላሰብኩትን ጥያቄ ጠየቀኝ።
«አላውቅም የኔ ኪዳን! ልጅ እያለን ብዙ ጊዜ ተናድጄባት አውቃለሁ። የምናደደው ግን ትታኝ ከመሄዷ በላይ ካየሁት ነገር በላይ እናትነቷን እንደማይላት እንዴት አልተረዳችልኝም ብዬ ነው! ከውርደቷ በላይ ፍቅሯ እንደሚገዝፍብኝ እንዴት ማሰብ አትችልም ብዬ ነው። ከዛ ግን የዛን ቀን ዓይኗ ውስጥ ያየሁት ህመሟ ከምናደድበት ይበልጥብኝና አንድ ቀን አጊንቻት ባቅፋት ነበር የምመኝ የነበረው»
«እሺ አገኛታለሁ!! ላገኛት ፈልጋለሁ!!» አለኝ።
«ታማለች ኪዳንዬ" አልኩት!እናቱን የማግኘት ተስፋ እንደሰጠሁት ትዝ ሲለኝ ብዙ ከማለሙ በፊት እየተሽቀዳደምኩ ይመስል ተቅለብልቤ
«ታማለች ማለት? የከፋ?»
«አዎን!! ታውቃለህ ለበደሌ እየቀጣኝ ሁሉ መስሎ ተሰምቶኝ ያውቃል! ዓይኗን ደግሜ ባየው ብዬ ዘመኔን የተመኘሁላት እናቴን በመጨረሻ ሳገኛት ለሞቷ ቀናት እየቆጠረች ሆነ።» ከዚህ በኋላ ለረዥም ሰዓት ዝም ተባባልን!! በቃ ዝም! የዛለው ሰውነቴ የተቀመጥኩበት ወደቀ። እግሬን ወደላይ ሰብስቤ ተጋደምኩ።

👍11
የነቃሁት የቧንቧ ውሃ ሲወርድ ሰምቼ ነው። ኪዳን ቀድሞኝ ነቅቷል ወይም አልተኛም! አልጋው ጫፍ ላይ እንቅልፍ እንደወሰደኝ ልብስ ደርቦልኛል። ምናልባት እንቅልፍ አልወስድ ብሎት የነበረ ይሆን ብዬ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። በደቂቃዎች ውስጥ እናትህ አለችም ልትሞትም ነው የሚል መርዶ አርድቼው እኔ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ። እናቴን አግኝቻት ልትሞት መሆኑን ሳውቅ ለወራት መቀበል አቅቶኝ የሆንኩትን መሆን አስቤ ያጠፋሁ መሰለኝ። ብቅ ሲል
«ይቅርታ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?» አለኝ
«ነግቶ የለ! ምነው እንቅልፍ አልወሰደህም እንዴ?»
«አይ ተኝቻለሁ!» ይበለኝ እንጄ የእኔን ኪዳን መች አጣሁት እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነው ያደረው። አስር ጊዜ <ደህና ነህ> እለዋለሁ። <ደህና ነኝ> ይለኛል።
«ማውራት ትፈልጋለህ ኪዳንዬ?»
«አልፈልግም! ዝም ብለን እንሂድ!» አለኝ።
ከመሄዴ በፊት ብዙ ማድረግ የምፈልጋቸው ነገሮች ነበሩኝ። ሆስፒታል ሄጄ ጎንጥን ማየት። ሻለቃው ጋር መደወል፣ ሴትየዋ ማን መሆኗን አውቄ ማግኘት….. ብዙ!! ከኪዳን የሚበልጥ ነገር የለኝም አይደል? እሱ እንዲህ በዝምታ ተለጉሞ የሚሰማውን እንኳን ሳላውቅ ራሴን ማስቀደም አልሆንልሽ አለኝ!! ክፍላችን የመጣውን ቁርስ እንደነገሩ እየለኳኮፍን መኪና ስፈልግ የሚያዘጋጅልኝ ሰው ጋር ደውዬ መኪና እንዲያመጣልኝ ካደረግኩ በኋላ የዳዊትን መኪና ሌላ ቦታ ወስዶ እንዲያቆምልኝ አደረግኩ። ለዳዊት ደውዬ መኪናውን ከቆመበት እንዲወስድ ስነግረው ምንም እንዳልጠረጠርኩ ለመምሰል ከራሴ ታገልኩ። መንገድ ከጀመርን በኋላ ሻንበሉ ደወለ። የመኪናው ባለቤት እና ልትገድለኝ የሞከረችው ሴት የተለያዩ ናቸው። ግን ሁለቱም በስማቸው የማውቃቸው አይደሉም!!
«ቢሮ ብቅ ካልሽ የሁለቱንም ፎቶ ላሳይሽ እችላለሁ!!» ብሎ ስልኩን ዘጋው!! መልዕክቱ አንድም ለመላክ አላምንሽም ነው ሁለትም ፎቶውን ለማየት ተጨማሪ ዋጋ አለው ነው። ስልኩን ዘግቼ ዝም አልኩ! ኪዳንም ምንም አልጠየቀኝም!! ዝምታው አስጨነቀኝ!! ልቤ ድንጋይ የተጫነበት እስኪመስለን ድረስ እንደከበደኝ ተጉዘን ከሰዓታት በኋላ እነእማዬጋ ደረስን!! አጎቴ ከበር እንደተቀበለን ኪዳንን እያገላበጠ ስሞ አልጠግብ አለው!!
«አቤት አንተ መድሃንያለም ምን ይሳንሃል!! አስካል ልጅሽ መጣልሽ!» እያላት ወደ ውስጥ ገባ!! እማዬ ለመነሳት በዛለ ጉልበቷ ተፍጨረጨረች። ከሁለት ቀን በፊት ካየኋት በላይ ገርጥታለች። ይብሱን የከሳችም መሰለኝ። ዝም እንዳባባሉ ፣ እንደማታው አጠያየቁ ከኪዳን ጋር ሲተያዩ አሁን የሚሆኑትን የሚሆኑ አይመስልም ነበር። ጉልበቷን አቅፎ ተንሰቀሰቀ። ፀጉሩን እየደባበሰች ተንፈቀፈቀች። እኔና አጎቴ የሁለቱን መሆን እያየን ስንነፋረቅ ቆይተን! አጎቴ ፊቱ ላይ የተዝረከረከ እንባውን ጠራርጎ ሲያበቃ ደግሞ እንዳላለቀሰ ሰው ኮስተር ብሎ
«አይ ደግም አይደል የምን ለቅሶ ነው?» አላለም?
ይቀጥላል.........
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

👍18❤2🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
...በሙዚቃው ደነስኩ.. ውልቅልቅ እስክል ውስኪውን አንጠፍጥፌ ጠጣሁ"..አዎ አውቃኛለች... ፈፅሞ አልረሳችኝም...ከሁሉም ያስደሰተኝ ደግሞ ‹‹ቀናህ!!!›› የምትለዋ ቃል ነች...ምክንያቱም ቅናት እነጠቃለሁ ብሎ ከመፍራት ጋር ወይም ከመሠሠት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስሜት ነው።ፍርሀትም ስስትም ምንጫቸው ፍቅር ነው...እርግጠኝነት ከጎደለው ፍቅር።እና ታፈቅረኛለህ እያለችኝ ነው?ግን እንዳዛ ስላሰበች ለምንድነው እንደዚህ የፈነጠዝኩት? የእውነት እያፈቀርኳት ይሆን እንዴ ? እንዴ ከነጠላ ስሞ ሌላ ስለእሷ ምንም የማላውቃትን ሴት እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? ግን እኮ ፍቅር የኋላ ታሪክን አጥንቶ የወደፊት መድረሻን ገምቶ አሁን የቋሙበትን ድልዳል በሚዛን መዝኖ የሚገባበት የምክንያትና ውጤት ቁርኝት ማሳያ አይደለም..?ፍቅር ጨርቁን እንደጣለ ዕብድ ነገረ ስራው ቅፅበታዊና ተአምራዊ ነው።ስለዚህ ሳላቃትም በፍቅሯ ብወድቅ የሚደንቅ አይደለም!ግን ዕድሜዋ ጉዳይስ? ቢያንስ 10 አመት ትበልጠኛለች? እርግጥ በዕድሜ ሰላሳም ሀምሳም የምትበልጠውን እንስት ማፍቀር የተለመደ ነው?ቢሆንም ግን ቢገለበጥ ነበር የሚያምረው ..እኔ 10 አመት ብበልጣት።
ወየጉድ አሁንኮ ነገረ ስራዬን ላየ የመጀመሪያ የፍቅር አይነጥላዬን ገና እየገለጥኩ ያለው ጀማሪ አፍቃሪ ነው የምመስለው ፤ግን እኔ ቢያንስ አምስት አጫጭር ጣፍጭ ለወግ የሚበቁ እና አንድ ረጅም የተወሳሰበ ልቤንም ቅስሜንም አብሮ እንቅሽቅሽ አድርጎ የሠበረ.. በአለንጋ ተደጋግሞ በመገረፍ የተነሳ ትላልቅ ተጠላላፊ ሰንበር እንደተጋደመበት ጀርባ የእኔም ልብ በዛ ፍቅር ምክንያት ዙሪያ ጥምጥም የዞረበት ጠባሳ የተጋደመበት ሆኗል...
"ያ ፍቅር ህይወትን አስተምሮኛል ?ያ ፍቅር ደስታን አሳይቶኛል...?ያ ፍቅር ዘመዶቼን አሳጥቶ የከተማ ስደተኛና ምፅተኛ አድርጎኛል...ያ ፍቅር በራስ መታመኔን እንቅሽቅሽ አድርጎ የህይወት መስመሬን ከላይ ወደታች ገለባብጦታል…ያ ፍቅር ዛሬ ቢቋረጥም ግን ትዝታ ብቻ ሆኖ የቀረ እንደይመስላችሁ፡፡ ዛሬም ጣጣው እያደነኝ ነው...፡፡
እስከህይወቴ ፍፃሜ እንደተጣባኝ የሚዘልቅ ይመስለኛል። ...ይሄው ስድስት አመት ሞላኝ ባዶ ሆኜ መኖር ከጀመርኩ ...እና አሁን የማፍቀር ስሜት ሲሰማኝ የተገረምኩት ለዛ ነው።እውነት እርቃን ገላዋን ስላሳየችኝ ...ተዳፍኖ የኖረው የወሲብ ስሜቴ ስለተወጣጠረ ነው የተምታታብኝ። ግን አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከለል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል፤ ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ...የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር እስከ እርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች ስለሆን ይሆናል።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል..ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር ከቃላት ልውውጥ እና ከአይን መሠራረቅ ላያልፍ ይችላል፤ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቋረጥ ይችላል..እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ አለ?።
ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ ስላለቀ ነው ብለን መደምደም አንችልም... አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው ጉዞቸውን በተለያየ ጎዳና ሊቀጥሉ የሚገደዱባቸው አያሌ አጋጣሚዎች አሉ። ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።
ወይ ጉድ ..በዚህች እንግዳ ሴት የተነሳ የፍቅር ኤክሰፐርት መሆን ዳዳኝ እኮ….ጠርሙሶ ውስጥ ያለችውን መጠጥ እያወዛወዝኩ ከሆቴል ወጣሁና በእኩለ ለሊት ወደቤቴ ገባሁ፡፡በፀጥታ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ….፡፡ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ፡፡
ጥዋት
..ከእንቅልፌ ባንኜ አይኖቼን ብገልጥም ቀልጠፍ ብዬ ከአልጋዬ መውረድ አልቻልኩም። ብነሳም ምን አልባት ምሳዬን ሰርቼ ከመብላት ውጭ ሌላ የምሄድበት ቦታ የለም ።ምሳ ደግሞ አላሰኘኝም፡፡ ምን አልባት ቁርሴን ከጋሽ ሙሉአለም የተሠጠኝን ቋንጣ ፈርፍር በደንብ ስለበላሁ ይሆናል። ተንጠራራሁና ከኮመዲኖዬ ላይ rich Dad poor Dad የሚለውን መፅሀፍ አነሳሁና ማንበብ ጀመርኩ .. አንድንም አባት የሌለው ሰው ሁለት አባቶች ያሉት ሰው የፃፈውን መፅሀፍ ለማንበብ መቋመጡ የሚገርም ነው። ብቻ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሁለት ገፅ ሳላነብ ስልኬ ጠራ አነሳሁና አየሁት..፡፡
የማላውቀው ቁጥር ነው ፡፡ላንሳው ልተወው ተወዛገብኩ።በስተመጨረሻ አነሳሁት
‹‹ሄሎ»
"ሄ...ሎ"ጥፍጥ ያለ የህፃን ድምፅ...ደነገጥኩ፡፡
‹‹ሄሎ..ሄሎ ..ማን ልበል?"
«ተአምል...ነኝ»
"ተአምር"የተኛሁበት የእንጨት አልጋ ከስር እርብራብ ተቀንጥሶ ይዞኝ ወደታች እየሰመጠ መሠለኝ...፡፡ስልክ ባልያዘው ቀኝ እጄ ፍራሹን ጨምድጄ ያዝኩ....፡፡እለተ መፅአት የፊታችን እሁድ መሆኑን ተረጋገጠ የሚል አዎጅን አስከትሎ የነጋሪት ጉሰማ ብሰማ ራሱ እንዲህ ሰማይ ምድሩ አይዞርብኝ፡፡
ልጅቷ ኩልትፍትፍ ባለ ድምፅ ንግግሯን ቀጠለች
"አዎ ተአምል...ል..ጅህ"
ይሄ መቼስ ተአምር ነው....፡፡ ተአምር አሁን ስምንት አመቷ ነው።በአካል ከተያየን 6 አመት አልፎናል።ማለቴ ቀጥታ በአካል ያየዋት አቅፌ የሳምኮት :ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ስታለቅስ ያባበልኮት የዛሬ ስድስት አመት ገና ክፉና ደጉን በቅጡ መለየት ባልቻለችበት ጊዜ ነው። ለዛውም እንደአባትና እንደልጅ እኮ አይደለም እንደ እህቴ ልጅ...እንደአጎቷ ሆኜ..፡፡ለምን እንደዛ ሆነ የእውነትም አጎቷ ስለሆንኩ፤ እንደዛም ስለመሰለኝ...፡፡ከዛ ወላጆቾ የውጭ ፕሮሰስ ጀምረው ስለነበር ተአምር ዲ.ኤን. ኤ ምርመራ ማድረግ ግዴታ ሆነ …ተመረመረች...ውጤቱ ለቤተሠብ በሀይለኛ መብረቅ የመመታት ያህል ድብ እዳና አስደንጋጭ ነበር... ልጅቱ የእህቴ ባል አይደለችም?
‹‹እንዴት ሆኗ...?"የህግ ሚስቱ እኮ ነች…፡፡››
"በተክሊል ነው እኮ የተጋብት"ብዙ ብዙ ተባለ... እኔ የምገባበት ጠፋኝ..ጠጋ አልኩና
በወቅቱ"ምስር ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ?››ብዬ ጠየቅኳት።
"አንተም እንደሌላው እንዴት ሆነ ብለህ ትጠይቀኛለህ?"
‹‹ምን ማለት ነው ?እንዴት አልጠይቅሽም?"
‹‹ያደረከውን ታውቃለህ ብዬ ነዋ ?››

👍56😁2😱1
"እና ተአምር የእኔ ልጅ ነች?"
"መቼሰ ከአንተና ከባሌ ውጭ ከሌላ ወንድ ተኝታለች ብለህ አታስብም..ነው ወይስ ታስባለህ?እንደዛ ከሆነ ያው አንተም ዲኤን.ኤ አሰርተህ ማረጋገጥ ትችላለህ።›› አለቺኝ እየተውረገረገች
"ኸረ እንደዛ ማለቴ አይደለም ...በፈጣሪ ምንድነው የምታወሪው?አሁን እቴቴ ስሰማ ምንድነው የምትለው?››እቴቴ ማለት ለእሷ የስጋ እናቷ ለእኔ ደግሞ አሳዳጊ እናቴና አክስቴ (የእናቴ ታናሽ እህት)ነች።
"ለጊዜው ዝርዝሩን ለማንም መንገሩ አስፈላጊ አይደለም?››
"እንዴት ታደርጊያለሽ ?ሁሉም እኮ እውነቱን እስክትነግሪያቸው አይተውሽም።"
"ግድ የለም ለእኔ አታስብ..ጫናውን እችለዋለሁ....በዛ ላይ ወደአሜሪካ ለመብረር ሁለት ወር ነው የቀረኝ ...ሁለት ወር ምን ያደርጉኛል..ስጋዬን ዘልዝለው አይበሉት"
"የመስፍኔስ ጉዳይ..."
"በደፈናው ተነጋግረናል ..ሁለቱንም ልጆች ይዞ የመሄድን ሀሳብ ለጊዜው ትተነዋል"
ደነገጥኩ ‹‹ምን ማለትሽ ነው ?ተአምርን የት ጥለሽ ልትሄጂ?"
ፈገግ አለችና‹‹ እንዴ ላንተ ለአባቷ ነዋ...አባቷ እያለ ለሌላ ለማን ጥያት እሄዳለሁ?"
"ባክሽ በዚህ በጭንቅ ጊዜ ትቀልጂያለሽ እንዴ?"አልኳት፡፡ እውነቴን ነው፡፡ በወቅቱ የዪኒሸርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ነበርኩ ይሄ ሁሉ ጉድ የተፈጠረው ክረምት ላይ እረፍት ሆኖ ቤተሠቤ ጋር ብዬ በመጣሁበት ቅፅበት ነው።እና እብድ ካልሆነች እንደዚህ አይነት ቀሺም ሀሳብ እንደማታስብ እርግጠኛ ነኝ።
"ለእቴቴ ጥያት እሄዳለሁ"
"አቤልንም?"አቤል ማለት ገና ከተወለደ ስድስት ወር ያላለፈው ወንድ ልጇ ነው፡፡
‹‹አይ እሱን ለእናቱ ሊሰጣቸው ነው"
‹‹እና ልጆቹን ተከፋፈላችሁ ማለት ነው?"
"አዎ ...ጋብቻው ለጊዜው አሜሪካ እስክንገባ ባለበት ይቀጥላል...ከዛ እንፋታና በየፊናችን ህይወታችንን መምራት እንቀጥላለን።››
"ግን ከልጆች ተለይቶ መኖር አይከብድም?"
"አይ ከልጆች ይልቅ ከአንተ ተለይቶ መኖር ነው የሚከብደኝ ...ልክ ትምህርትህን እንደጨረስክ ሁኔታውን አመቻችና ተአምርን ይዘህ ትመጣለህ ..ከዛ ከዚህ ወግ አጥባቂ አፋም ህዝብ ተገላግለን በነፃነት ሀገር የራሳችንን ነፃ ህይወት እንኖራለን"
"እንዴት ነው አሜሪካ እህትና ወንድም እንዲጋቡ ይፈቀዳል እንዴ?"
‹‹አትቀልድ .... ››
..ከምስር ጋር በዛ ተለያየን፡፡ ነገሮች ፍርጥርጥ ብለው ቅሌቴን እስክከናነብ እጄን አጣጥፌ ቁጭ ብዬ መጠበቅ አልቻልኩም፡፡ማድረግ የቻልኩት አንድ ነገር ነበር…፡፡ በማግስቱ ጨርቄን ማቄን ሳልል ስልኬን አጥፍቼ ደብረብርሀን ለቅቄ አዲስአበባ ገባሁ፡፡ትምህርት ወደምማርበት አለማያ አልሄድኩም ።አዲስአባ ነው የመሸግኩት ።ይህን ያደረኩበት ዋና ምክንያት ምን አልባት ልፈልግ ብለው ቢሄድ እንዳያገኙኝ ነው።አዲስአበባ የቀን ስራም መላላክም እየሠራው አንድ ወሩን አሳለፍኩና መስከረም ሲጠባ ወደ ዪኒሸርሲቲ አመራሁ..፡፡ዩኒቨርስቲ እንደረስኩ በፊት ይላክልኝ የነበረው ብር ያለማቆረጥ በባንክ ደብተሬ ይገባልኝ ስለነበር በወጪ ችግር አልነበረብኝም፡፡ከዛ ወጭ ግን ይሄው ስድስት አመት ከማንም ጋር ተገናኝቼ አላውቅም፤ የወሬ ወሬ ምስርም ወዲያው ወደአሜሪካ እንደሄደች ሰምቼያለሁ..፡፡ ቤተሠብ ሁሉ እውነቱን እንዳወቀና በተለይ አክስቴ እጅግ በጣም እንዳዘነች እና ትዳሯንም እንደፈታች ሰማሁ። እንግዲህ በእኔ በደደብ ቀሺም ስህተት ሁለት ትዳር ፈረሰ ማለት ነው..የባንክ ደብተሬንም ቢሆን ልክ ከተመረቅኩበት ወር ጀምሮ አዘጋሁት.. እንደዛ ያደረኩት እቴቴ ብር መላኳን አንድታቆም ነው፡፡እንደውም ለምረቃ ሁለት ወር ሲቀረው…ባንክ ደብተሬ ውስጥ ከ20 ሺብር በላይ ነበር ያስገባችልኝ፡፡ያው ምረቃ ላይ ወጪ ስለሚበዛ ለሱፍ ምናምን አስባ እንደሆነ ገባኝ…እኔ ግን ሱፉንም አልገዛሁ ምረቃ ላይም አልተገኘሁ ወረቀቴን ተቀብዬ ወደአዲሳባ ሸመጠጥኩ ብሩን ሰራ እስካገኝ ተጠቀምኩበት፡፡. ለማንኛውም ለጊዜው ትዝታዬን ላቁምና ወደእንግዳዬ ልመለሠ፡፡
////
"ሠላም ነሽ ታአምር?"
"ሠላም ነኝ አባዬ...ድምፅህን ስለሠማው ደስ ብሎኛል"
✨ይቀጥላል✨

👍44❤7🤔3🥰1🤩1
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
፡
፡
#ክፍል_አራት
ዘርሲዎች ግማሽ ክብ ሰርተው ከመንደሩ ራቅ ብላ ዙሪያ ገቡን ከምታሳየው
የግራር ዛፍ ስርቁጭ ብለዋል ጩሉሌዎች
አንገታቸውን ቁልቁል ደፋ አድርገው በዛ ዙሪያ ያንዣብባሉ: ነፋሱ
ቅጠሎችን ጎንበስ ቀና እያደረገ ይነፍሳል
ከፊት ለፊታቸው ርጥብ
ቅጠል ተነጥፏል መሃል ላይ ጎረምሶች የተጠበሰውን የፍየል ስጋ እየቆራረጡ የፍሪንባውን ሥጋ በእድሜ ለገፉትና በጀግንነታደው ለሚታወቁት ለሌሎች ደግሞ ከተለያየውደ የስጋ አይነት እፊት ለፊታቸው ካለው ቅጠል አስቀመጡ" ህፃናት ጨዋታቸውን አቁመው ራቅ ብለው ሲቁለጨለጩ ቆይተው እደላው አልቆ መብሉ ሲጀመር ወደየአባቶቻቸው ጉያ ተሸጉጠው ዳረጎታቸውን እየተቀበሉ ከአጥንት ጋር መታገል ጀመሩ በመጨረሻ የሚበላው ከተበላ: ቀሪውን ደግሞ ጎረምሶቹ ካቀለጣጠፉት በኋላ ወጣቶቹ ቅጠሉን ሰብስበው ጥለው
ከስብሰባው አካባቢ ርቀው ሄዱ።
የሽማግሎች አለቃ ጦራቸውን ይዘው ከተቀመጡበት ተነስተው
ከፈርሱ እግራቸውን ቀባ አድርገው ወዲህ ወዲያ ወዲያ ወዲህ አሉና፣
"የአባት ደንብ ጥሩ ነው" በልክ መብላት የአባቶቻችን ባህል ነው አባቶቻችን የራበውና የጠገበ ትክክል ፍርድ አይሰጥም ይሉ
ነበር" የጠገበ ወንድ ሴት ማለት ነው መሳቅ ቧልት ይወዳል ከብቶችን አይፈቅድም ጫካውን አይቃኝም ከጓደኞቹ ጋር
አይመክርም መዝለል አይችልም መቀመጥና ማንጎላጀት ይወዳል
ትክክለኛ ፍርድ በዚህ ምክንያት አይሰጥም ይሉ ነበር አባቶቻችን" ሽማግሌው እቱፍ: እቱፍ
ብለው የጦሩን ዘንግ በምራቃቸው ቀባ ቀባ እያደረጉ ሽማግሎችን:
የአባታቸውን አገር አድማስ እየተዟዟሩ አይተው
አባቶቼ የራበውም ከጠገበ አይሻልም ይሉ ነበር የራበው ሰው ሰነፍ ነው
ሲኖረው አያውቅበትም
የወደቀችው ጀንበር:
የጠፋችው ጨረቃ ተመልሰው የሚመጡ
አይመስሉትም እንደ
አጋሰስ ፈረስ ዘመዶቹ ለመቋቋሚያ የሰጡትን ፍየሉንም፥ በጉንም
ከብቱንም: እህሉንም ብቻውን እየበላ ነገን ዘንግቶ: ልጆቼ: የአባቴ
ምክር ሳይል ሁሉን ያሟጥጥና የሚያልበው ሲያጣ የሚበላው
ሲቸግረው ሰውን: መሬቷን: ቦርጆን: አባቶቹን ይራገማል" ሆዱን
ለመሙላት ይቀማል ይዋሻል … ፍቅር አያውቅም ዘመድ ወገን አይለይም
አያስተውልም፤ ጨካኝ ነው
በዚህ ምክንያት
አባቶቻችን የራበው ሰው ትክክል አይፈርድም ይሉ ነበር አባቶቻችን ትክክል ናቸው ወንድሞቼ ጥጋብ ልቦናን ያዛባል ረሃብ ደግሞ ተስፋ መቁረጥንና ጥላቻን ያመጣል ከሁሉም የሚከፋው ደግሞ ሁለቱም ያስዋሻሉ" ብለው በርኮታቸው ላይ ቁጭ አሉ
ዝምታው ቀጠለ ሐመር ላይ ተረትን ሽማግሌ ለሌላው ማስታወስ እንጂ አይጨርሰውም የሰሙት እኩል: የፈፀሙት እኩል … ስለሆነ ተረት ጨራሽ አዳማጭ የለውም"
"በሉ ተናገሩ?" አሉ ሽማግሌው ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጥሩ ነው! ከወደ መሃል አንዱ ድምፅ አሰሙ ገልመጥ ብሎ ያዬ የለም ሁሉም ግን አባባላቸውን በጆሮው ቀልቧል።
"ጥሩ ነው!- በአካል ተለይተውን ነፍሶቻቸው ደንቡን ጥበቃ አብረውን ላሉት ወንድሞቻችን ተገቢው ደንብ የሚሰራበት
ቀን ይመረጥ ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው በየበረሃው የአሉትን ተባት በግና ፍየሎች ከብቶችን ያስመጡ" በየመንደሩ ለሚኖሩት ዘመድ ጓደኞችም ጥሪ ይላክ ለዚያ ደሞ ዛሬ ቀኑ ተቆርጦ ቋጠሮ ይዘጋጅ አሉ።
የሽማግሎች አለቃ ሌላ ኃሳብ አለመኖሩን በዝምታደ ጠበቁና አንድ ጎረምሳ ጠርተው ልጥ አምጣ አንተ" አሉት ልጡ መጣ
"ስንት ላይ ይቋጠር?"
"መከን ተቢ" አሉ አንድ ሽማግሌ በስተግራ በኩል
ከተቀመጡት ሰላሳ ለማለት ልጡ ሰላሳ ላይ ተቋጥሮ ለሟቹ ታናሽ ወንድም
ተሰጠው" የሽማግሎች አለቃ አንዱን ችግር
በመቋጨታቸው
"ባይሮ ኢሜ" አሉ ሽማግሎችን እግዜር
ይስጣችሁ ለማለት
"በሉ ቀጥሉ?" አሉ የስብሰባው መሪ
"ጥሩ ነው!" አለ ልጅ እግሩና የአባቱን ጠላት ገሎ በቅርቡ
ከሽማግሌዎች ጋር ለመቀመጥ እድል ያገኘው ሰለምቤ፤ "ጥሩ ነው!
ታለውሻ በቀር አባቶቻችን ከአውሬ ጋር አልኖሩም እና ካርለቴ ይዛብን የመጣችውን አውሬ በጥይት አጉኖ ራቅ አድርጎ መቅበር ነው "አለ ገና የጎረምሳነት ባህሪው ሙሉ በሙሉ ያልቀዘቀዘለት ወጣቱ ሽማግሌ አለመብሰሉ በአነጋገሩ ፍጥጥ ብሎ እየታየበት።
"ጥሩ ነው! አውሬ ማለት ከብት የሚበላ ችግር የሚፈጥር ነው የነጯ ሐመር የካርለቴ አራት እግር አውሬ ሳይሆን መሂና
ነው የሚባል አባቶቻችን ደሞ መሂና የሚባል አውሬ አለ አላሉንም ደሞስ የካርለቴ መሂና እንደ ፈረስ እየጫነን ገበያ እያመላለሰን ነው እና መኖሩ ምን ጎዳ! አሉ ግራሯን የተደገፉት አንድ ዐይና
የአባት ደንብ እየሻርን ያ ይጎዳል ይሄ ይጠቅማል
ካልንማ ይህች አገርና ይህ ህዝብ መዓት ይመጣበታል" በነሱ ጊዜ ያልነበረ አውሬ አሁንም መኖር የለበትም " አሉ አገጫቸውን በግራ
እጃቸው ደግፈው የቆዩት ሽማግሌ ከዚያ ክርክሩ ከተለያዬ አቅጣጫ
መቅረቡ ቀጠለ
በአባቶቻችን ደንብ ፍየል ቢመጣ ፍየል ጋጥ: ከብት
ቢመጣ ከብቶች በረት ሰው ቢመጣ ወደ ሰዎች መኖሪያ ጎጆ ይገባል እህ እንዲህ እስተሆነ ድረስ የካርለቴ መሂና የሚገባ
ፍየሎች ጋጥ ነው? ከከብቶች በረት ነው? ወይንስ ከሰዎች ጋር ጎጆ
ውስጥ! መቼም ተውሾች ጋር እየተሯሯጠ አውሬና ጠላት ይከላከላል
አይባል ይኑር ከተባለ ወገኑ ከማን ነው? ተከብቶቹ ወይንስ ከእኛ! አሉ ከወደመሀል መፋቂያቸውን ሲያኝኩ የቆዩት ሽማግሌ
"ጥሩ ነው የሁላችሁም አስተያየት አዲስ ነገር መምጣቱ ይኸው ሁለት ሶስት ቦታ ከፋፍሎ አጨቃጨቀን ያልነበረ ነገር
ሲመጣ ያልነበረ ችግር ይፈጥራል ነጯ ሐመር የእኛ የሆነች እንግዳ ናት መሂና ያለችውን አውሬ ዱካውን ለማጥፋት በጥይትና ጦር
ደብድበን እንቅበረው ብንል እሷን እናሳዝናት ይሆናል"
ባይሆን አውሬሽን ካመጣሽበት ጫካ ጥለሽ ነይ ብንላት አይሻልም
ወንድሞቼ!" አሉ። አንተነህ ይመር ጋልታምቤ ጎን የተቀመጡት ሽማግሌ
ተው! ተው! ይህችን ሰው ተማበራችን አታውጧት! እሷ
ሐመር ናት የሐመር ልጃገረድ ተቀብላማ እንደ እህቶችዋ የፍየል ቆዳ ለብሳ ለዘመዷ ለከሎ ከብት
የአባቷን ትክክለኛ ደንብ
ዝላይ ተገርፋ … እንዴት እንዴት ነው እንደውጭ ሰው ይከፋታል ማለት! ከአባትሽ ባህልና ደንብ ውጭ ያመጣሽው አውሬ ቦርጆን ያስከፋል የአባቶቻችንንም ነፍስ ያሳዝናል እነሱ ተቆጥተው ዝናብ ከሚያጠፉብን በሽታ ከሚልኩብን አውሬሽን ቀብረነው እንረፍ
ብንላት በፍጡም አይከፋትም ወዲያውስ ከሽማግሌ ቃል ወጥታ የት ልትደርስ ኧረ አይከፋትም!" አሉ የዘርሲዎች አለቃ ከዚያ ለረጅም ጊዜ ዝምታ ሰፍኖ ቆየ
"ጥሩ ነው! እንዳላችሁትም
ነጯ ሐመር የእኛ ናት, የእኛ
ያልሆነውን ግን ዝም ብለን ብንለቀው ምን እንደሚያመጣ አናውቅም ሲቆይ ልጆቻችንን እሷን ጨምሮ: እኛን ይተናኮስ
አይተናኮስ ሳናውቅ እናጥፋው እስከተባባልን
ድረስ በኋላ ለቀን
ከምናሳድድ እዚሁ ገራም መስሎ አጠገባችን እንዳለ አድብቶ በጥይት ማጎን ነው የሚበጀው ካለበለዚያ
እኮ አስተውላችሁት እንደሁ
አላውቅም እንጂ አጉረምርሞ አጉረምርሞ ሰውነቱ የጋለ እንደሆን
እንደ ጥይት ከተፈተለከ
ድንጋይ አይል ውሃ ... ማን ጀግና ያቆመዋል! ስለዚህ ሳይደነብር አዋዝተው ጎረምሶች በክላሽ ጥይት
ሆድቃውን እንዲነድሉት ማድረግ ነው"" እንዳሉ
"ይህስ እውነት ነው! በቀደም ሳላየው ሩም … ብሎ ባጠገቤ ቢያልፍ የድምፁ ወላፈን እንዴት አሽቀንጥሮ ወረወረኝ መሰላችሁ ተዚያ ንዴቱ ይሁን ድንጋጤው ሰማይ እሆን ምድር ጠፋኝ!" አሉ ሌላው አዛውንት

👍21
... ኧረ አንተ ተርፈሃል! በዚያን ሰሞን ምን የመሰለውን ጎበዝ ከበሸዳ የመጣ ሐመር ሌላ መሂና መሃል መንገድ
ተንደርድሮ ሄዶ እንደ ተዋጊ ወይፈን ከስሩ ቢያነሳው እንደ ቅንቡርስ ጥቅልል ብሎ አልተነሳም አሉ በዚያው ቀረ! እና እንዲህ እያደቡ መጨረስ ነው እንጂ ገራም መስሎ አንድ አንዳችንን እየለቀመ
ሊፈጀን እማይደል!" ብለው አንድ ዐይናው ሽማግሌ ተናግረው ሲጨርሱ ያን የሰሙት ሽማግሎች አንገታቸውን ከፍና ዝቅ እያደረጉ አዘኑና እነማን በጥይት እንደሚደበድቡትና
እንደሚቀብሩት ተመካክረው የጎረምሶቹ ቡድን ተመረጠደ።
"ቶሎ ቶሎ እንበል'ንጂ ከብቱ መምጫው ደርሷል?" አለ ጋልታምቤ ልቡ በፍርሃት ትር ትር እያለችበት
"ጥሩ ነው!" በእጃቸው ሰበቅ የያዙት ሽማግሌ ከበስተኋላ ድምፅ አሰሙ
"ጥሩ ነው! ደልቲ ጀግና ነው
ጀግና! ግን አንድ
ራሱን ነው እስቲ እዩት የአባቶቻችንን ዱር"
ብዙ ዛፍ በመኖሩ
አይደለም ለማገዶ እንጨት ለእኛ የምንበላው ፍሬ የሚሰጠን አንድ ግዙፍ የሾላ ዛፍ ብቻ ቢኖር ምን ዋጋ አለው" አንዱ ሲደርቅና
ሲረግፍ ሌላው ካለመለመ አንዱ ፍሬው ወዳድቆ ሲበሰብስ ሌላው
ካላፈራ ይህን ጊዜ የት እንደርስ ነበር ቢያመን የምንጠቀመው ስርና
ቅጠልስ ዱር ውስጥ ብዙ ዛፍ በመኖሩ የምናገኘው አይደለም! አንድ ዛፍ ብቻ ስንቱን ይሆናል? ማገዶ የቤትና በረት መስሪያ: ጥላ
አንድ ጀግና ማለትም አንድ ግዙፍ ዛፍ ማለት ነው አንድ ዛፍ ደግሞ ስንቱን ይሆናል? ለእኛም ትልቁ አለኝታ ጀግና ሳይሆን ጀግኖች
ናቸው ጀግኖች ለድንበራችን
ትልልቆቹ ጀግኖች አባቶቻችን ናቸው
ለህልውናችን አለኝታዎች ነን እየሞቱ መልካም ነገር
ያቆዩን ልጆቻቸው የነሱን ጀግንነት ወራሽ ነን።
አደራችንን ደግሞ በትዕግሥት መፈፀም አለብን እንጂ ደንብ አፍራሽ
መሆን አይገባንም
ልበ ሙሉ አንበሳ ከሚሮጠው ቁጭ ብሎ የሚያስበው ይበዛል
አከርካሪ ሰብሬያለሁ እያለ ድንበሩን እየተወ እንደሮጠ አይኖርም፥ የአውሬነቱን የአባቱን ደንብ ሽሮ ካሮዎች ተወንዝ የወጣ አሳ
አቅም የለውም ይላሉ
አያችሁት አባባላቸው ማማሩን! ደልቲም እንደ እያንዳዳችን የአባቱ ወራሽ ባላደራ እንጂ ሥራዬ
በቃኝ ባይ ደንብ አጉዳይ ባሻው ሯጭ ሊሆን አይችልም የሽማግሌ ልጓም አላ! አፈንጋጭን አጋድመው የሚገርፉ ጀግኖች አሉዋ! ስለዚህ ጥሎሹን እስታሁን ባለመጀመሩ ቅጣት ይገባዋል " ብለው ንግግራቸውን ጨረሱ„
ደልቲ ጥፋተኛ ነው" ሴት እንዲህ አለችኝ ብሎ ማለት
ራሱ ትልቅ ነውር ነው
ነውር! አባት ብላ ካርለት ከመረጠችው ከእኛ ከሽማግሎች ጋር መመካከር ይገባ ነበር እንጂ ራሱ ወስኖ ጭጭ
ማለቱ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ስለዚህ ደልቲ ለጥፋቱ ከብት ይውጋና ጥሎሹን ነገ ዛሬ ሳይል ይጀምር ተቅጣቱ ሌላ" አሉ
በዝምታ ሲያዳምጡ የቆዩት ሽማግሌ
"ተው! አንቸኩል ነገር ከስሩ ውሃን ከጥሩው ይባል የለም
ያቀደው ስትባልግ: ስርዓት ስታጣ ደልቲ ካርለትን ለማግባት ቢያያት ሥርዓት ሊያሲዛት: አደብ ሊያስገዛት አስቦ ነው ልጃገረዷ
ሙሉ ሰውነቷን ስትታጠብ የኖረች መሆኗን
ግን እንደ ወንድ
የአየነው ነገር ነው" ስለዚህ ደልቲ ጥሎሽ ከፍሎ ካርለቴን አግብቶ
ፍሬ ባታፈራ የትኛዋን እህቷን ቀይሮ ሊወስድ ነው አባቴ ብላ የመረጠችው እንደሁ ያለችው አንድ ሴት ልጅ ናት እሷም
አግብታለች እስቲ በፊት በዚህ እንነጋገር ለቅጣት ከመቸኮላችን በፊት" አሉ አልፎ አልፎ የሚስሉት ሽማግሌ።
"እንዴት እንዴት ነው አያ ላሎምቤ ሃሣብህ?- አንድ ላም በረት ሙሉ ከብቶችን ሞልታ ያየን መስሎኝ የካርለት አባት ሚስትስ ብትሆን ስንትና ስንት የልጃገረድ ዘመዶች አሏት ረሳኸው ወንድሜ! በቅድሚያ ካርለቴ በና ሂዳ ከተመረቀችና ለጥፋቷ ደንቡ
ከተሰራላት ደግሞ ለምን አታፈራ ታፈራለች ይልቅ ደልቲ ለተፈፀመው ጥፋት እንደተባለው ከብት ወግቶ ጥሎሹን ይጀምር" አሉ
አንጀት የማንበብ ችሎታ ያላቸው ሽማግሌ
እሺ አጥፍቻለው
የቦርጆን ታምር እውነትስ ማን አውቆ አታፈራም ታፈራለች ይባላል" አንዴ ሊያገባ ጠይቋል እንግዲህ
ዕድሉ ይታይና ችግር ከመጣ ሽማግሌደ የማይፈታውስ ምን ኣለ
ቅድሚያ ማሟረትም ለካርለቴ ደግ አይደለም" እንደተባለውም ደልቲ
ከብት ወግቶ ጥሎሹን ይጀምር" አሉና ሲያበቁ ፀጥታ ሰፍኖ ቆዬ።
"እህ! ከብት የሚወጋበት ቀን በቋጠሮ ይሰጠዋ ማነህ ና ልጥ አምጣ" አሉ የሽማግሎች አለቃ ከዚያ ልጡ መጣና አስራ
አምስት ቦታ ላይ ተቋጠረ
"ጥሩ ነው!" አሉ ከበስተኋላ የተቀመጡት ሽማግሌ ለበቃቸውን እየወዘወዙ
"ጥሩ ነው! ሴት ልጅ ብሩክ መሬት ናት ተወንዱ
የተቀበለችውን ዘር ፍሬ አድርጋ ቤተሰቡን ታበዛዋለች ጀግናን ትወልዳለች ቆንጆን ትተካለች ያለሴት ጀግና የለም ቆንጆ የለም የጋዲ ዳንስ የለም ... ሴት የቦርጃ ባላደራ ናት ሽማግሌው
ንግግራቸውን ገታ አደረጉ አንተነህ ይመር መንደርደሪያ ሐሳባቸውን ሲሰማ የፈራው በመምጣቱ በድንጋጤ ክው ብሎ ቃዠ
ጨነቀው የሃሳብ ማጥ ውስጥ ተነከረ
ሴት የቦርጆ ባላደራ ናት ይሁን እንጂ ሁሉም መሬት
አንድ አይደለም‥ በጦር ወጋ ወጋ አድርገው ጥቂት ፍሬ የበተኑለት ቅዱስ መሬት ታፍሶ የማያልቅ ምርት የሚሰጥ እንዳለ ሁሉ ጭንጫ መሬትም አለ ዘሩን አበስብሶ የሚያስቀር" አንዳንድ ሴትም አለች
ማህፀኗ የተረገመ ይህች ሴት ማህፀኗ ጀግናና ቆንጆ አያፈራም ታቀዘቅዘዋለች የባሏን በረት ባዶ ታደርግበታለች ቤተሰቧን ታሳፍራለች ለዚህ ደግሞ የአባት ደንባችን መፍትሄ
አለው" ብለው ንግግራቸውን አቆሙ
ጎይቲ እንዲያው ተሳስታ ብልቷን ውሃ ማስነካቷ ይኸው ለዚህ ችግር ዳርጓታል በሷ ስህተት
መቼም ደንባችን አይሻር
የከሎም ዕድል አይነፈግ
ስለዚህ በእሷ ምትክ ከናቷ ዘመድ ልጃገረዶች አንዷ ትለወጥለታ!" አሉ የሽማግሎች አለቃ
በሉ መቼም ይሄ ነገር እንዲህ በዛሬ ምሽት የሚያልቅ አይደለም
ከብቶችም መጥተዋል: ሌላ ቀን ደግሞ አስበን እንምከርበታ አሉ ከወደመሐል በዚህ
ተመራርቀው በርኮታቸውን እያንጠለጠሉ ሁሉም ተስማሙና ወደ መንደራቸው ሄዱ።
የማታዋ ጀምበር ሰማዩን በቢጫና ቀይ ቀለማት አስውባ የቡሜን
ተራራ እየታከከች ወረደች የከብቶች ቃጭል ይቅጨለጨላል
ከብቶች ያገሳሉ: እምቧ ይላሉ መንደሯ ታዜማለች

👍18
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
ብዙ ነገር አጥቼ እንደነበር የተሰማኝ አሁን ላይ ነው። የእማዬን አልጋ ከበን ቡና ተፈልቶ ቆሎ እየቆረጠምን አንዱን ወሬ ስናነሳ አንዱን ስንጥል በብዙ ሳቅ እና ደግሞ በደስታ ለቅሶ የታጀበ ቀን እየዋልን ያለፉ አመታቴን አስቤ ብዙ እንደጎደለኝ ገባኝ።
ደግሞ በዚህ ሁሉ የቤተሰብ ፍቅር ታቅፌ ልቤ ክንፍ አውጥታ ጎንጥ ጋር ስትሄድ፣ የያዘኝን አያያዝ ፣ የሳመኝን መሳም ፣ የጠራኝን መጥራት አሰብ አድርጌ ብቻዬን ፈገግ ስል ባለፉት ዓመታቶቼ ብዙ እንዳለፈኝ ገባኝ። ብዙ እንዳልኖርኩ ገባኝ!!
«እትዬ ዛሬ ሌላ ሰው ሆነው በንፁህ ልብ ስለተቀበሉት ነው የሚያጎብጥ ሸክም የሆነብዎት። ቂም ባቄመና በጠለሸ ልብ ሆነው ሲቀበሉት እንዲህ አልተሰማዎት ይሆናል።» ነበር ያለው ጎንጥ እንዴት ይሄን ሁሉ ጥላቻ ተሸክሜ ኖርኩ ስለው?
በንፁህ ልብ አይደለም። በፍቅር ልብ ሳየው ነው ዓለምን እና ዙሪያዬን የማይበት መነፅር የተቀየረው። በፍቅር ዓይን!! ሁሉ እንዳለኝ የተሰማኝ፣ መኖር ደስ የሚል ነገር መሆኑን ማሰብ የጀመርኩት በፍቅር ልቤ ማየት ስጀምር ነው።
እናቴን አቀፍኳት፣ ኪዳንዬ አለኝ፣ አጎቴን አለኝ፣ ጎንጥ ይኑረኝ አይኑረኝ ባላውቅም አዎ በልቤ ውስጥ ግን ከነጥጋቡ አለኝ!! ምን እጠይቃለሁ ሌላ? አጎቴ እናታችን ስለደከመች ካጠገቧ ባንርቅ መልካም መሆኑን ስለነገረን በአካሌ ላለመሄድ ወሰንኩ። ግን ልትሞት ቀናት የቀራት እናቴን አቅፌ ልቤ አዲስአበባ መሸምጠጡ ራስወዳድነት ነው? እንደዛ እየተሰማኝኮ ራሴን እገስፃለሁ። ልቤ አልሰማኝ አለኝ እንጂ!!
የገባን ቀን ማታ ምናልባት ለጥንቃቄ በሚል። በኪዳን ስልክ ዋትሳፕ መልዕክት ላኩለት። ሁለት መስመር ለመፃፍ ከ20 ደቂቃ በላይ ፈጀብኝ። ለኪዳን ካልሆነ በቀር ፅፌ የማውቀው ማስፈራሪያ ወይ ቢዝነስ ነክ ነገር አልያም የሆነ መልእክት እንጂ ፍቅር ነክ ነገር እንዴት እንደሚፃፍ አላውቅም። ምን ተብሎ ነው የሚጀመረውስ? ሀይ ጎንጥ? ስሙ ደግሞ ሲጠራ ምንም የፍቅር ቅላፄ የለውም!! እንዴት ዋልክ ዓለሜ? ልበለው? አይሆንም እሱ ሲል ነው እንደሱ የሚያምርበት! ሀኒ ልበለው? ሆ ጎንጥን ሀኒ? ራሴኑ አሳቀኝ!! ያቺ የድሮ ሚስቱ እንደጠራችው ጎኔ ልበለው? ኡፍፍፍ
«ሰላም ዋልክ? እኔ ነኝ!! በጠዋት ላይህ ሳልችል ቀርቼ እማዬጋ መጥቻለሁ!! ደህና አድረህ ዋልክ?» በቃ መፃፍ የቻልኩት ይሄን ብቻ ነው። ምን አይነቷ ነፈዝ ነኝ በፈጣሪ!! ከዛማ ስልኩን አቅፌ የፃፍኩለት መልዕክት ሰማያዊ የራይት ምልክት እስኪያሳየኝ ስልኩ ላይ አፍጥጬ ቀረሁ።
«ዓለሜ ናፈቀሽ እንዴ?» ይለኛል ኪዳን ሲያበሽቀኝ
«ለምን ግን አታርፍም?» እላለሁ
«ጎንጤን ነው?» ይላል አጎቴ
«እንዴ? እኔ ብቻ ነኝ የማላውቀው ማለት ነው? አንደኛውን ሽማግሌ ልኳል አትይኝም እንዴ?»
«እዚህ ከርሞ አይደል እንዴ የሄደው? ዓይነውሃው ያስታውቃልኮ ፍቅር እንዳለበት! መች አይኑን ከርሷ ላይ አንስቶ! <ጎንጤ እርሻ ወረድ ብለን እንምጣ ?> ብለው <አይ ጋሼ ከርሷ ባልርቅ ነው የሚሻል። ደህና መሆኗን ማየት አለብኝ> ይለኛል። <እንደው ታች ሰፈር ደረስ ብለን ብንመጣስ?> ብለው <ይቅርታ ጋሼ ዛሬ ልክም አይደለች ርቄ አልሄድ> ይለኛል። ኋላማ <እኔ የምለው ጎንጤ? ትከጅላታለህ እንዴ?> እለዋለሁ ቆጣ ብሎ <ምን ማለቶት ነው!> አለኛ» እናቴን ጨምሮ ሁሉም ይስቃሉ። እንደኮረዳ እሽኮረመማለሁ።
ስልኩ መልዕክት መቀበሉን የሚገልፅ ድምፅ ሲያሰማ ከመቀመጫዬ እንደመዝለል ሁሉ ሲያደርገኝ ቡና የምታፈላው ትንሽዬ ዘመዳችን ሳትቀር በአንድ ላይ አውካኩብኝ። የትልቅ ሰው ያልሆነ ማፈር አፍሬ መልዕክቱን ለማየት ሁሉ ስግደረደር ቆየሁ።
<እኔ ደግ ነኝ! የሚቻልሽ ከሆነ ድምፅሽን ታሰሚኛለሽ?> ነው የሚለው መልዕክቱ! አሁን ይሄ እሺ ምኑ ነው የሚያስቦርቀው? በፍቅርሽ ሞቻለሁ የተባለች ኮረዳ እንኳን እኔ የምሆነውን መሆን አትሆንምኮ! ትቻቸው ወደበር ወጣሁ እና ደወልኩለት። ቶሎ አውርተሽ መጨረስ አለብሽ የተባልኩ ይመስል የተፈጠረውን ለምን ሳላየው እንደመጣሁ እማዬ ስለደከመች ወደከተማ እንደማልመለስ በጥድፊያ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ አውርቼ ሳበቃ ሳቅ ብሎ
«ለመዝጋት ተቻኮልሽ እንዴ?» አለኝ
«አይ!» እያልኩ በቆምኩበት በጫማዬ መሬቱን እየቆፈርኩ መሆኑን አየሁ
«ደግ! ያሻሽን ያህል ጊዜ ቆይ!! » አለኝ
«አንተስ?»
«እኔ ምን እሆናለሁ?» አለኝ እኔ ማወቅ የፈለግኩት ከዛስ የሚለውን….. እኔ ያሻኝን ያህል ጊዜ እዚህ ስቆይ እሱስ? ከሆስፒታል ሲወጣ ቤት ሄዶ ይጠብቀኛል? ወይስ ያለሁበት ይመጣልኛል? ወይስ እኔ ወደማላውቀው ቤቱ ይሄድብኛል?
ያናደደኝን ወይ የተጣላኝን ሰው በጉልበት እንዴት እንደማግተው አውቅ ነበርኮ! የወደድኩትን ሰው እንዴት አባቴ አድርጌ ነው የራሴ የማደርገው? እሱን አልችልበትም!! በጉልበት ባገቱት ሰው ላይ ሙሉ ስልጣን ማራመድ ይቻላል። በፍቅር የወደቁለትን ሰው ራሱ ፈቅዶ ወደእኔ ካልቀረበ ምንድነው የማደርገው? ዝም አልኩ!!
«ዝም አልሽኝ እኮ ዓለሜ?» አለኝ ጠብቆ
«ምን እንደምል አላውቅበትም!! ያለፍከውን አላውቅም! ወደፊት ምን እንደምታስብ አላውቅም! ነገ ምን እንደምንሆን አላውቅም! አሁንም ምን እንደሆንን አላውቅም!! አላውቅህምኮ ጭራሽ! እኔ ግን እዚህ ልትሞት ያለች እናቴን አቅፌ ካንተ ሌላ ሀሳብ የለኝም!! ይሄ እንዴት ያለ መሸነፍ ነው ቆይ?» አልኩት።
«የት እሄድብሻለሁ? አለሁ አደል? ሁሉን ትደርሽበት የለ? አንች ብቻ የተሸነፍሽ አታድርጊው እንጅ!!» ብሎ ግማሽ መልስ ምን ግማሽ እሩብ መልስ ይመልስልኛል።
«እንዲህ እንድትለኝ አይደለም የምፈልገው!» ስለው እየሳቀ
«እንዴት እንድልሽ ነው የምትፈልጊ? ቁጣው የምንድነው ታዲያ?» ሲለኝ ነው እየተቆጣሁ እንደሆነ ያስተዋልኩት
«እንደምትወደኝ ነው ማወቅ የምፈልገው!! እንዳልነሳ ሆኜ በፍቅርህ ከመውደቄ በፊት እየተሰማኝ ያለው ስሜት የእኔ ብቻ እንዳልሆነ ነው ማወቅ የምፈልገው! አይሆኑ አሸናነፍ ከመሸነፌ በፊት እንደማላጣህ እርግጠኛ መሆን ነው የምፈልገው? እ?» ስለው መሳቁን ሳያቆም
«ፍቅርሽም ቁጣ ነው? እንደምወድሽማ ታውቂያለሽ! መስማቱን ከሆነ የፈለግሽ እወድሻለሁኮ ዓለሜ!! ነገ ምን እንደሚሆን ከፈጣሪ ጋር እናበጀዋለን!! ዛሬን ልውደድሽ ዓለሜ ዛሬን ውደጂኝ!!»
እንኳን ፊት ሰጥቶኝ ዘጭ ለማለት እየተንደረደረ የነበረ ልቤ ዝርፍጥ ብሎ በፍቅር ነሆለለ። ከዛን ቀን በኋላ በየቀኑ ተደዋወልን!! በየቀኑ እንደሚወደኝ ነገረኝ። በየቀኑ ደጋግሜ ተሸነፍኩ። በየቀኑ ከእማዬጋ ሳቅን። በየቀኑ ድሮ ያጣነውን እቅፏን ናፍቆት መሬት ላይ አንጥፈን ለሶስት እቅፏ ውስጥ አደርን። በየቀኑ ደስ አላት!! በአስራ ሶስተኛው ቀን ጠዋት እኔና ኪዳን በቀኝና በግራዋ ሙቀቷን እየሞቅን እማዬ ዝም አለች።
እማዬን ስላጣኋት ከፋኝ። አግኝቻት ስለሞተች ደግሞ አመሰገንኩ። ኪዳንም ተመሳሳይ ስሜት ነበር የተሰማው ግን ከእኔ በላይ የእርሱ ሃዘን በረታ!! ምናልባት እኔ ለእርሱ ለመሆን ስታትር ዘመኔን ስለኖርኩ አጎደልኩበት ብዬ እንዳላስብ ዝም ብሎኝ እንጂ ሁሌም የእናቱ ናፍቆት ያንገበግበው ነበር ይሆናል። በኖረችልኝ ብሎ ሲመኝ ይሆናል የኖረው። እኔና አጎቴ ከእርሱ በርትተን እሱን ማበርታት ጀመርን።
የቀብሯ ቀን ሬሳዋ ከቤት ሲወጣ አይኖቼን ደጋግሜ አሸሁ ያየሁትን ሰው ለማጣራት። አቶ አያልነህ! ፈገግ አልኩ! ይቅር ብለውኛል ማለት ነው።

👍30👏2
አዲስ አበባ ከገባሁ ከአመታት በኋላ ባለገንዘብ የሆንኩ ጊዜ ወደእሳቸው መንደር ላገኛቸው ተመልሼ ነበር። አፈላልጌ በጥቆማ እቤታቸውን ፈልጌ ሳገኝ እኔ አወቅኳቸው። ከዘራ ይዘው እያነከሱ ከበራቸው ወደቤት እየገቡ። እሳቸው ግን አላወቁኝም ነበር። ከአመታት በፊት ካየኋቸው አርጅተው። ተጎሳቁለው ነበር። ሰላም ካልኳቸው በኋላ ከከተማ መምጣቴን ስነግራቸው ወደቤታቸው ጋበዙኝ።
«ያስታውሱኝ ይሆን?» አልኳቸው
«ዓይኔ እያስቸገረኝ ነው ልጄ አላስታወስኩሽም! የማን ልጅ ነሽ?»
«ማን እንደሆንኩ እነግሮታለሁ! መጀመሪያ ግን ማንነቴን ስነግርዎት የምለውን ሰምተው እንደሚያስጨርሱኝ ቃል ይግቡልኝ!!»
«ልጄ እያስጨነቅሽኝኮ ነው!!»
«ቃል ይግቡልኝ!! የምለውን ሁሉ ይሰሙኛል?»
«እሽ ቃሌ ነው!!»
«ከብዙ ዓመት በፊት ከገበያ ሲመለሱ አንዲት ሴት እንደዘረፈችዎት አይጠፋዎትም መቼስ!»
«እንዴት ይጠፋኛል! ቤቴን እኮ ነው ያፈረሰችው! » ብለው በደንብ አዩኝና « አምሳል ነኝ እንዳትይኝና እዚህ ደም እንዳንፋሰስ!!»
«እስከመጨረሻው እሰማሻለሁ ብለው ቃል ገብተውልኝ የለ?»
«በይ ልስማዋ!!»
እግራቸው ላይ ወደቅኩ!! «ከዛን ቀን በኋላ ሳላስቦት የዋልኩ ያደርኩበት ቀን የለም! አንዲት ቀን እንኳን ፀፀት ሳይፈጀኝ አልፎ አያውቅም!! ይቅር አይበሉኝ! ግን ከዚህ በላይ አይቅጡኝ!! የምሰጦትን ገንዘብ ይቀበሉኝ!» አልኳቸው
ተነስተው በፍፁም አሉ!! ሚስታቸው ከጓዳ ትሰማ ነበር እና
«ደግም አይደል አያል! ይህች ልጅ ተጠጥታ መጣችም አይደል? እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አቤቱ በደላችንን ይቅር በል ብለንም አይደል የምንጠልይ? ተነሽ ይበሏት በቃ!» አሉ። ከስንት ልምምጥ በኋላ እንዳኩረፉ ያመጣሁላቸውን ገንዘብ ተቀበሉኝ። አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች አንደኛው ማረፋቸውን ነገሩኝ! ሌላኛውን እቤታቸው ሄጄ ስላላገኘኋቸው መልዕክቴን ከገንዘቡ ጋር አስቀምጬ ተመልሼ ለአቶ አያልነህ ይቅርታዬን እንዲነግሩልኝ ለምኜ ልወጣ ስል እንዲህ አሉኝ
«ጨርሶ ይቅር ያልኩሽ እንዳይመስልሽ!! ድህነት አይኑ ይጥፋ ዛሬም ለልጆቼ ፍራንካው ስለሚያስፈልግ እንጂ ለራሴ ቢሆን እመቤቴ ምስክሬ ናት ፍንክች አላደርገውም!!» ብለውኝ ነበር። ከዓመታት በኋላ ለቅሶዬን ሊደርሱኝ የመጡት በልባቸው ይቅር የሚሉበት ፍቅር አጊንተው ቢሆን አይደል? ይቅር መባል እንዲህ ደስ እንደሚል ባውቅ ስንት ይቅርታ የምጠይቀው ነበረኝ!!

👍16❤4🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
:
:
#ክፍል_ስምንት
////
"ሠላም ነሽ ታአምር?"
"ሠላም ነኝ"
" አባዬ...ድምፅህን ስለሠማው ደስ ብሎኛል"
"እኔም ደስ ብሎኛል የእኔ ጣፋጭ...ግን ስልኬን እንዴት አገኘሽ?"
"የጓደኛዬ የቢጡ አባት ነው አባቴን ባገኝ ደስ ይለኛል እያልኩ ሳለቅስ አሳዘንኩትና ..ከፌስብክ ላይ ፈልጎ ባንተ ስም የሚመሳሰል ሶስት ቁጥር ሰጠኝና …ሞክሬ …ሞክሬ.. ከዛ አገኘውህ...እናም ደስ አለኝ"
"ውዴ..እስከዛሬ ፈልጌ ስላላገኘውሽ በጣም ይቅርታ...እቴቴን ስላስቀየምኳት ፈርቼ እኮ ነው"
ዕድሜ ልኬን ከብዙ ሰዎች ጋር በክፉም በደጉም ብዙ ንግግር ተነጋግሬያለሁ... እንደዛሬው ግን የምይዘው የምጨብጠው ጠፍቶኝ አያውቅም...ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፊት ብቀርብ እራሱ እንዲህ አልርበተበትም።
"አባዬ"
አልተቀየምኩህም..እቴቴም ደግሞ ሰው ሳያያት ክፍሏ ውስጥ ትደበቅና ያንተን ፎቶ እና የእናትህን ፎቶ እያየች "የእህቴን አደራ በላሁ›› እያለች ታለቅሳለች ..፡፡
"እውነትሽን ነው..?"
"አዎ አባዬ እውነቴን ነው"
""ታአምሬ"
"ወዬ አባዬ"
"ስልኩ..ማለት የደወልሽልኝ በማን ስልክ ነው?"
"ስልኩ የራሴ ነው...እማዬ ከአሜሪካ ስትደውል በራሴ ስልክ እንዳናግራት ልካልኝ ነው"
"እና በዚህ ብደውል አገኝሻለሁ?"
"አዎ ግን..ማለቴ አንተን እንዳገኘሁህ እቴቴ ስለማታውቅ ፈርቼ ነው"
"ችግር የለም"
ሲመችሽ..እንዳወራሽ ስትፈልጊ ሚስኮል አድርጊልኝ"
"እሺ አባዬ"
"ቻው...እወድሀለሁ"
"እኔም በጣም ወድሻለሁ..ቻው"ስልኩ ተዘጋ፡፡
ስልኩን ከዘጋሁ በኃላ እንኳን እንባዬንም ስሜቴንም መቆጣጠር አልቻልኩም.፡፡ አልጋውን ለቅቄ በመውረድ ቤት ውስጥ ከላይ ወደ ታች እየተመላለስኩ ወለሉ ላይ የተዝረከረከኩትን ዕቃዎች እየረገጥኩ ዘለልኩ ..፡፡በቃ እብድ ነው የሆንኩት ። የማልረባ ነኝ...፡፡እኔ ሰው አይደለሁም፡፡መኖር ፈፅሞ አይገባኝም…
ከብዙ ቆይታና መታገስ በኋላ ጋሽ ሙሉአለም ድምፅ አውጥተው ተናገሩ ...፡፡ ውስጤ መተራመሱ ብሶ ቤቱን በማተራመሴ እሳቸውንም እየረበሸኩ መሆኑን እስከአሁን ልብ አላልኩም ነበር።
"ልጄ ምን ገጠመህ?"
‹‹አያቴ ጉድ ሆኜሎታለሁ? ..እኔ እኮ ሰው አይደለሁም?
‹‹ሠው አይደለሁም ስትል?
"በስህተት እና ሀጥያት የተጨማለቅኩ እርኩስ ነኝ።
"እንደዛማ ከሆነማ እንደውም ኦርጅናሌ ሰው ነህ...››
‹‹አያቴ ትክክል ኖት ..ግን ይሄን ታሪክ ብነግሮት ቀጥታ ይጠሉኛል...ዛሬውኑ ነው ቤቱን ለቀህ ውጣልኝ የሚሉኝ "
"ይበልጥ አጓጓኸኝ..‹.ምን ሰራው ቢለኝ ነው ይሄንን ልጅ የምጠላው?›እያልኩ ውስጤን እየጠየቅኩ ነው?...እስቲ ንገረኝና የትዕግስቴንና ይቅር የማለት ችሎታዬን ልክ ልፈትሽበት።››
"ልጄ ደወለችልኝ"
"ልጄ ..?.›
‹‹አዩ አያቴ ገና ከመጀመሪያው ደነገጡ አይደል?"
"ሂድ ከዚህ…. ቀላማጅ፡፡ እኔ አልደነገጥኩም...ይልቅ ቅድምአያት ስላደረከኝ ተደስቼ ነው"
‹‹ይሁን እሺ….ልጅቷን የወለድኩት ካሳደገችኝ ከአክስቴ ልጅ መሆኑን ስነግሮትስ ምን ይሰማዎታል....? 40 ለሚሆን ደቂቃ ከመጀመሪያው አንስቼ አወራሁላቸው...በፅሞና አዳመጡኝ።
"የማልረባ ሰው ነኝ አይደል?"እንዲጮሁብኝ …እንዲረግሙኝ ፈልጌለሁ፡፡
.እሳቸው ግን ለስለስ ብለው ሀዘኔታ ባጠቃው አነጋገር"የማትረባም ብትሆንም ልጄ ያው ሰው ነህ… ዋናው እሱ ነው።ሰው ደግሞ በማንኛውም ጊዜና አጋጣሚ አውቆም ሆነ ሳያውቅ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ስህተት ይሰራል!ምክንያቱም ሰው እንደዛ ስለሆነ?ልዩነቱ አንዳንድ የሰራውን ስህተት ለመሸፈን ሌላ ስህተት ሲጨምር አጠቃላይ ሁኔታውን ጭምልቅልቅ አድርጎ እስከወዲያኛው ያበላሸዋል..፡፡ሌላው ደግሞ ስህተቱን በማረምና ያስከፋቸውን ሰዎች በመካስ ቀሪ ህይወቱን ያስተካክላል..፡፡.ደግሞ ያንተ የሚገርም ነው..፡፡ልጅ አለችህ..ልጅቷ ደግሞ ስህተት ልትሆን አትችልም..፡፡.እሷ ንፁህ እውነት ነች...፡፡ስህተቱ እሷ የተገኘችበት መንገድ ነው...፡፡እሱም ቢሆን አንዴ የተዘረጋ መንገድ ነው... በመንገድ ዙሪያ ያለውን ገደል ማስተካከል ነው የምትችለው፡፡ መንገድን ለሁለት በመክፈል የለያዩት ገደሎች ድልድይ መስራት ነው የምትችለው፤ድልድዩ ደግሞ በይቅርታ ብረትና በፍቅር አርማታ ነው የሚገነባው... ፡፡
‹‹እንደሚሉት ቀላል አይደለም››
‹‹አትሞኝ ልጄ ፤የሰው ልጅ ከባባድ ነገሮችን ለመስራት ብዙም አይቸግረውም …ብዙ ጊዜ እንዝላል የሚሆነው ጥቃቅን ነገሮችን ለመስራት ነው፡፡ያው ዞሮ ዞሮ ጥቃቅን ነገሮች ተደምረው ነው ከባድ ችግሮችን የሚፈጥሩት ፡፡አሁን የነገርከኝን ታሪክ ስትሰራ በአንድ ቅፅበትና በአንድ ቀን አይደለም..ቀስ በቀስ፣አንድን በአንዱ ላይ እየደረብክ….በአመታት ውስጥ ነው የሆነው፡፡ለማጥፋት እንደዛ ከሆነ ያንን የጠፋውንም ለማደስ እንደዛው ቀስ በቀስ ምን አልባት የአራት እና በአምስት አመታት ጥረትና ልፋት ይጠይቅ ይሆናል..ግን በየእለቱ የምትችለውን ስራ.››
‹‹እንዴት አድርጌ አያቴ?››
‹‹ይው እኮ አስበህበትም ባይሆን ዛሬ ጀመርክ፡፡››
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹ያው ከልጅህ ጋር አወራህ፣ድምፆን ሰማህ፤ምን ያህል አንተን እየናፈቀች እንደሆነ እና በአንተም ምንም ቅሬታ እንደሌላት ከአንደበቷ አረጋገጥክ፡፡››
‹‹አዎ አያቴ እሱን እንኳን እውነቶትን ነው፡፡››
‹‹አዎ እውነቴን ነው፤ አሁን ማድረግ ያለብህ ከጭንቀትና ትካዜ እራስህን ሙሉ በሙሉ አላቅና ከልጅህ ጋር ያለህን ግንኙነት በጥበብ በጣም ሳታግለበልበው ፤በጣም ሳታደፋነው በሚገባው ልክ ይዘህ አስቀጥለው››
‹‹ማግለብለብ ማለት?››
‹‹ለምሳሌ የሚቀጥለው እሁድ ብር ብለህ ደብረብርሀን ሄደህ ላግኝሽ ብትላት ቤተሰቦቾ ሳይዛጁበት ይሰሙና ልጃችንን ይዞብን ሊጠፋ ነው ብለው ፈፅሞ እንዳታያትና እንዳታናግራት በሊያደርጉ ይችላሉ.. ወይም እናቷ ጋ አሜሪክ ሊልኳት ይችላሉ….ስለዚህ መጀመሪያ በስልክ ግንኙነትህን በደንብ አጠንክር..ስለቤተሰቦችህ አሁናዊ ሁኔታ ቀስ በቀስ ከልጅህ እየጠየቅክ ተረዳ..፡፡ታዲያ ስትጠይቃት በጥበብ ማለቴ ድንገት በወሬ በወሬ ትዝ ብሎህ እንዳነሳህ እያስመሰልክ መሆን አለበት..፡፡የዛሬ ልጆች ቀላሎች አይደሉም…..እሷን ስለዘመዶችህ መረጃ ለማግኘት እየተጠቀምክባት እንደሆነ ከተሰማት ልትቀየምህ ትችላለች፡፡ከዛ አጠቃላይ ሁኔታውን ከተረዳ በኃላ ምን አይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብህ ትወስናለህ…፡፡ችግሮችሀን በደረጃ ከፋፍላቸው…ከዛ እያንዳንዱን በተናጠል ስታየው መፍትሄ ለማበጀት ያን ያህል ከባድ አይደለም…..፡፡
ለምሳሌ የልጅህን በአካል ማግኘት፤ከልጅህ እናት መታረቅ፤የአክስትህን ልጆች ይቅርታ መጠየቅ፤ የአክስትህን ባል ይቅር እንዲልህ መማፀን፤ የእራስህን ህይወት ለልጅህ በሚመጥን መልኩ ማስተካከል፡ እነዚህን ሁሉ ኮተት ችግሮች በአንድ ኩንታል ውስጥ ጠቅጥቀህ ካየሀቸው ዘላለም በጫንቃህ ተሸክመህ ስታላዝን ትኖራለህ እንጂ መቼም አትፈታቸውም፤ግን እያንዳንዱን በፔስታል ለየብቻ አድርገህ ያዛቸው ቅደም ተከተል ስትሰጣቸው በአንድ ጊዜ አንዱ ፔስታል ብቻ ተሸክመህ መዞር ቀላል ስለሆነ ሳትጨናነቅ በተወሰነ ጥረትና መስዋዕትነት ትፈታዋለህ፡፡ እሱን መፍታትህ ለሁለተኛው ፔስታል ውስጥ ላለው ችግርህ መፍቻ መንደርደሪያ ይሆናል.እንደዛ ነው ልጄ››

👍71❤2
‹‹እሞክራለሁ አያቴ››
‹‹አዎ በደንብ ሞክር …ከኃላ ታሪክህ ካልታረቅክ የፊትህን ታሪክ ማሳመር አትችልም፡፡አውቀህም ቢሆን ሰታውቅ የብዙ ሰው ልብ ሰብረሀል…የብዙ ሰው ደስታ አክስመሀል፤ ለዚህ ደግሞ ያለምንም ማቅማማት ኃላፊነቱን መውሰድ አለብህ፡፡
‹‹ኸረ እወስዳለው…በደንብ ነው ምወስደው.. ሌላወ ይቅር አክስቴን ያሳዘንኳት እራሱ ቀላል ነው.?.››
‹‹አዎ ገብቶሀል ማለት ነው…አክስትህ ለአንተ እናትህ ነች….በፍቅርና በርህራሄ ልክ ከማህፀኗ እንደወጣ ልጇ አድርጋ አሳድጋሀለች..የአንድ እናት የመጨረሻ ደግነት የሚለካው ከሌላ ሰው ማህፀን የወጣን ልጅ ከራስ ማህፀን ፈልቅቆ ከስጋዋ ቦጭቀውና ከአጥንቷ ቀንሰው ከተፈጠሩ ልጆች እኩል በማየት ነው….ያንተ አክስት በዛም አላበቃች፤ የአንተ ኃላፊነት የሆነችውን ልጅህን መልሳ እያሳደገች ነው…ይህ ለእሷ ምን ያህል በየቀኑ የሚንጠባጠብ የልብ ድማት እንደሚያስከትልባት ታውቃለህ….?ልጅህን ባቀፈች ቁጥር አንተን ሆነ እናቷን ታስታውሳለች….
እነዚህ ልጆች ሳሳድግ ምን ላይ ይሆን የተሳሳትኩት? እያለች አብዝታ እራሷን ትወቅሳለች…እንዲህ ባላደረኩ ኖሮ….እንዲህ ማድረግ ነበረብኝ…..መአት ነገር እያሰበች እራሷን ትቀጣለች፡፡››
‹‹ጋሼ ይሄም እውነት አይደለም…ለእኛ ሉጋም የለቀቀ ስህተት እሷ ቅንጣት ኀላፊነት የለባትም …ሁሉም ጥፋት የእኛ ነው….፡፡››
‹‹በዛ እኔም አልከራከርህ….ጥፋቱ ሁሉ የሁለታችሁ ነው….፡፡ አክስትህ ግን እርግጠኛ ነኝ እንደዛ አታስብም፡፡ልጄ ምን አልባት አባት መሆንህን አውቃለሁ…በስም አባት መሆንና እና ልጅ ማሳደግ ግን ፍፅም የሚገናኝ ነገር አይደለም፡፡ለዘመናት አባይ የእኛ ነው እያልን ስንዘፍንና ስናቅራራ ኖረናል ግብፆችም እንደዛው አባይ የእኛ ነው ይላሉ፡፡አንድ ኢትዬጵያዊ መንገድ ላይ አቁመህ አባይ የማነው ብትለው አረገኝ ይሄ ምን የሚሉት ጥያቄ ነው አባይማ ከእኛው ጎጃም ምድር ከሰከላ መንጭቶ አያሌ ወንዞቻችንን እያስገበረ የሚንፎላፎል የገዛ ወንዛችን ነው ይልሀል፡፡››
አዎ በቲኦሪ ደረጃ ትክክል ነው…እውነታው ግን አባይ የግብጽች ነው፡፡ምክንያቱም እንሱ ተንከባከብውታል ….በላዩ ላይ ዘርተው ሙዝ ገምጠዋል፤ ብርቱካን ልጠው ውጠዋል፡፡፡ግድብ ገድበውበት ህዝባቸውን በሰው ሰራሽ ብርሀን እንድያሸበርቅ አድርገዋል፡፡ስንዴ በገፍ ዘርተውበት ህዝባቸውን መግበውበታል ፤ በየቀኑ ይበሉታለ በየቀኑ ይጠጡታል፤ በየቀኑ ይንከባከቡታል፤ እና የእኛ ነውር ሲሉ ቃሉ ከከንፈራቸው በዘልማድ አይደለም የሚወጣው ከጥልቅ ልባቸው በፍቅርና በስስት ነው የሚፈሰው፡፡ ምን አልባት እኛም ከአሁን ወዲያ ልከ እንደነሱ ወግ ይደርሰን ይሆናል…እና ልጅም ወልዶ ማሳደግ ቀላል አይደለም፡፡››
‹‹እሱማ በትንሹም ቢሆን ይገባኛል››
‹አዎ..አንድ ልጅ ወልዶ ለማሳደግ ትልቁ ጣጣ ልጁ ሚያስፈልገውን ምግብ፤ ልብስ የመሳሰሉትን ማሟላት አይደለም፡፡ከዛ ይልቅ የልጁን ማንነት መስራት ነው ከባዱ ጉዳይ፡ብዙው ወላጅ ሳያሳከው የሚቀረውና ፌል የሚያደርገውም እዚህ ላይ ነው፡፡ልጅን በየትኛው መንገድ መምራት ነው ተክክል ፡እያንዳንዱን አታካችና ድንበር አልባ የልጅ ጥያቄዎችንስ በምን አይነት ዘዴና ብቃት መመለስም ይቻላል?፡፡ልጅን ማቅረብ ነው ማራቅ ጥሩ?፡፡ሲያጠፋ መግረፍ ወይስ ዝም ብሎ ማየት? ወይስ ምከር መለገስ…?ምክሩ ማያርቀው ሆኖስ ሲገኝ?፡፡እነዚህ የመሳሰሉት አያሌ የህይወት መንገዶች ውጤታቸውም የራሱ የሆነ ጥሩና መጥፎ ጎን ያላቸውና በትክክልም አስቀድመው የማይተነበዩ ናቸው፡፡፡፡እና ቀድመን የራሳችን ህይወት መስመር ተቆጣጥረን መምራት ያልቻልን በህይወት ኪሳራ ውስጥ ምንዳክር ወላጆች እንዴት ባለ ታአምር ነው ስኬታማ ልጅ የመቀረፅን እጅግ ረጅምና አታካች ፕሮጀክት በብቃት እና በስኬት ልንወጣ ምንችለው?፡፡በዛ ላይ የሀይማኖት ተቋማት ተፅዕኖ አለ፤ .የማህበረሰብ ተፅዕኖ አለ.፤የቴክኖሎጂ ተፅዕኖ አለ..የጓደኛ እና የትምህርት ቤት ተፅዕኖ አለ…ከነዚህ መካከል የአንዱ የተጣመመ ተፅዕኖ ለዕድሜያችንን እኩሌታ የለፋንበትን የልጃችንን ህልውና ድምጥማጡን ላለማጥፋቱስ ምን ዋስትና አለን?፡፡
‹‹አያቴ››
‹‹አቤት ልጄ››
‹‹እርሶ ከጎኔ ባይኖሩልኝ ምን ይውጠኝ ነበር….?››
‹‹አንተ ቀልማዳ….በል ተነስ አሁን ወደስራ ሂድ ..ስትንቀሳቀሰ ቀለል ይልሀል……እዚህ ካበቃለት ሽማግሌ ጋ ነገር በመፍተል ጊዜህን አትፍጅ››
‹‹እሺ»
እሄዳለሁ..አመሰግናለሁ ብዬ ልብሴን ቀያየርኩና ወደሆቴል ሄድኩ፡፡

👍55❤4🥰3👏3😁2
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ ስድስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
የእማዬ ቀብር ላይ የአባቴ ገዳዮች ዘመድ አዝማድ እና ልጆች ሁሉ ሊቀብሯት ሲያጅቧት ፤ አንዳንዱም ሲያለቅሱላት እያየሁ የተሳከረ ስሜት ወረረኝ። የዛን እለት ከአቶ አያልነህ ጋር የነበሩት ሰውም አረፋፍደው ተቀላቀሉ። የኛም ወገን የእነሱም ወገን የተፈጠረውን እልቂት ይቅር ተባብለው ተሻግረውት እኔ ብቻ ነበርኩ በጥላቻ የሰከርኩት? አይደለም! እዚህ ያሉት ናቸው በይቅርታ የተሻገሩት!! ጥላቻ እና ቂማችንን ይዘን ከተማ የገባን እኔና መሰሎቼ በየሶሻል ሚዲያው በቃላት ተዋግተናል፣ ካለመንደራችን በተገናኘንበት ተጠማምደን ተጠላልፈናል፣ የደማችንን ምንጭ ተጠያይቀን ለአባቶቻችንን ፀብ እኛ ተሰነካክለናለን ተጫርሰናል፣ እኛ እንደአባቶቻችን በጥይት ተጫርሰን ባናሳያቸውም ለወለድናቸው ልጆቻችንን እና ታናናሾቻችን ጥላቻችንን አጋብተናል። እነርሱ ግን እረስተውትም እንኳን ባይሆን አልፈውት የአንዳቸውን ለቅሶ ይላቀሳሉ። እኔ ግን ከወራት በፊት እንኳን የእነእርሱን የልጅ ልጅ እንኳን ባገኝ በማያውቀው የአያቱ በደል ጥላቻዬ ውስጤ ይፈላ ነበር።
ከቀብር መልስ ሰው እየተሰናበተን ሲወጣ አቶ አያልነህ ከሚስታቸው ጋር ተሰናብተው ሊወጡ ሲሉ እጄን ያዝ አድርገው።
«እግዜሃር ያፅናሽ!» ሲሉኝ እጃቸውን በደንብ ጨብጬ ይዤ
«ዛሬ ነው የፈቱኝ!! እስከዛሬ የእርሶ እስረኛ ነበርኩ።» ስላቸው ቁጥብ ያለ ፈገግታ ፈገግ ብለው
«እኔ ይቅር ብያለሁ እርሱ ጨርሶ ይቅር ይበልሽ!! በርቱ!!» ብለውኝ ወጡ!!
በኋላ ላይም ወዳጃቸው የተቀመጡበት ሄጄ እጃቸውን ያዝ አድርጌ (በአካል ስላላገኘኋቸው ሁሌ ይከነክነኝ ነበር) «የማይገባኝን ይቅርታ ስለሰጡኝ አመሰግናለሁ!!» አልኳቸው። እሳቸው ከአቶ አያልነህ በላይ በተፈታ መንፈስ
«እግዜር ያፅናሽ ልጄ!! እቤቴ በተውሽው መልዕክት የልጆቼን ህይወት ነው የቀየርሽው!! ልብሽ ቀና ነው የእኔ ልጅ ቂምና ጥላቻ ለማንም አይበጅ! ለአባትሽም ለእኛም አልሆነን!! ልብሽን ከክፉ ጠብቂው!» ብለው ጭራሽ እኔኑ አበረቱኝ።
የቀብር ቀን ማታ ፍራሽ ላይ ተቀምጠን ሊያማሽ የመጣውን ለቀስተኛ እየተቀበልን ስንሸኝ በሚገባ እና በሚወጣው ሰው መሃል ጎንጥ በሞላ ሞገሱ ጎንበስ ብሎ ድንኳኑን ሲዘልቅ ሳየው የእማዬን መሞት አሁን የተረዳሁ ይመስል ድንኳኑን በለቅሶ ደበላለቅኩት። እስከአሁን ሲገባ ሲወጣ ከነበረው ሰው የበለጠ ፣ እስከአሁን ሊያፅናናኝ ከሞከረው ህዝብ በበለጠ ፣ እንደነፍሴ ከምወደው ኪዳኔ እንኳን የበለጠ ፣ ከአጎቴም የበለጠ ……. እሱ ብቻ የበለጠ ህመሜ የሚገባው ዓይነት ነው የመሰለኝ። ድንኳኑ እንደአዲስ በለቅሶ ተናጠ። ሌላ ሰው መኖሩን ረሳሁ!! ዘልዬ እቅፉ ውስጥ ገባሁ!! አላባበለኝም አብሮኝ አለቀሰ። ሽማግሌዎች <ከመሸ እንዲህ አይለቀስም> ብለው ሊያረጋጉ ሲሞክሩ አጎቴ ከውጭ ብቅ ሲል ጎንጥን ሲያየው ከእኔ ብሶ አረፈው። ልክ የሆነ ታናሽ ወንድሙን ያገኘ ወይ ታላቅ ልጁን አልያም የብዙ ጊዜ ወዳጁን ያገኘ ይመስል
«አመለጠችኝኮ! አትከብጅኝም ትንሽ ቆይ እያልኳት አሻፈረኝ ብላ ሄደች! እንብኝ አለች! ናፍቆቴ አልወጣልኝም እያልኳት ተሸነፍኩ አለች!» እያለ ሲያለቅስ ድንኳኑ ተተራመሰ። ጭራሽ ሁለቱ ተቃቅፈው ሲላቀሱ የተወሰኑ ቀናት አብረው ያሳለፉ ሳይሆን ሳይነጋገሩ የሚግባቡ ቤተሰቦች ነው የሚመስሉት። እኔስ ስለወደድኩት ወይ ይወደኛል ብዬ ስላሰብኩ ለልቤ አቅርቤው መሰለኝ ሳየው ሀዘኔ የፈነቀለኝ። አጎቴስ? ምናልባት እኔ ያልሰማኋቸውን ቅፅበት የልብ የልባቸውን አውግተውበት ተናበው ይሆን? ወይስ ለልብ ለመቅረብ የተለየ ነፍስ ያለው ሰው አለ?
ለቅሶው ሲበርድ አጠገቤ መጥቶ ፍራሽ ላይ ተቀመጠ። ለቀስተኛው ማን ስለመሆኑ ግራ እየተጋባ ሲጠያየቅ አጎቴ «ቤተሰብ ነው!» እያለ ይመልሳል። አንድ ዘመዳችን
«የአባትሽ ቤተሰብ ነው? የእነርሱ ደም ይመስላል!» ስትለኝ በደንብ አስተዋልኩት። በጭንቅላቴ ውስጥ ሊጠፋ የደበዘዘ የአባቴን መልክ ለማነፃፀር እየታገልኩ ….. ቁመቱ ፣ ትከሻው ፣ ግርማ ሞገሱ ፣ ጥይምናው ፣ ጅንንነቱ …… ከአባቴ ጋር ይመሳሰላል። ለአፍታ <የተሸነፍኩት ሳላውቀው አባቴን እሱ ውስጥ ስላገኘሁ ይሆን?> ብዬ አሰብኩ። ሳይታወቀኝ አፍጥጬ እያየሁት ስለነበር
«ምን አስፈልጎሽ ነው?» አለኝ
«ምንም! ስለመጣህ ደስ ብሎኛል።» አልኩት
«እንዴት ይቀራል ብለሽ አሰብሽ?» ብሎ ወደትከሻው አጥብቆ ከያዘኝ በኋላ የህመም ትንፋሽ ተነፈሰ። ከሆስፒታል የሚወጣበት ቀን ቀናት እንደሚቀሩት እያወቅኩ እሱን አለማሰቤ አሳፈረኝ። እሱ አጠገቤ መሆኑን እንጂ የእርሱን ቁስል አላሰብኩለትም።
«ውይ! ይቅርታ!» ብዬ ከትከሻው ቀና ስል መልሶ ከቅድሙ በላላ ሁኔታ ትከሻው ላይ አስደግፎኝ
«ደህና ነኝ!!» አለኝ
«ሆስፒታል መቆየት ነበረብሃ?»
«አንድ ሁለት ተጨማሪ ቀን ነበረብኝ! የእኔ ሀሳብ አይግባሽ!! ደህና ነኝ አልኩሽ እኮ ዓለሜ? አንች መድሃኒቴ አይደለሽ? ሆስፒታል ምናባቱ?» ብሎ ከደቂቃዎች በፊት ስንሰቀሰቅ የነበርኩትን ሴት ያሽኮረምመኛል? እያየኝ ያለ ሰው መኖሩን ለማረጋገጥ አይኔን የተቀመጠው ለቀስተኛ ላይ አንቀዋለልኩ።
እናቴ የሞተችብኝ እኔ ከዛ ደግሞ የተሽኮረመምኩትም እኔ …… ለሰው የሀዘኔን ጥልቀት አሳይቼ መሽኮርመሜን መደበቅ ያለብኝም እኔው!! ምክንያቱም ምንም እንኳን ሊያፅናኑ ቢመጡም ስፅናና እንደሚዳኙኝ አውቃለሁ። <የእናቷ ለቅሶ ላይ ተሽኮረመመች፣ የእናቷ ለቅሶ ላይ ስታስካካ ነበር ፣ ምን እሷ ምንም አልመሰላት ኸረ አላያችኋትም እንዴ እናቷን መቅበሯን ረስታ ከወንድ ጋር ስትለፋደድ?> እንደሚሉኝ አውቃለሁ። ግራ የሚገባኝ ሊያፅናኑኝ የሚሞክሩት የውሸት ነው ማለት ነው? ሀዘን ማብዛት ጥሩ አይደለም የሚሉት ስለሚባል ነው ማለት ነው? ስፅናና ወይ ስስቅ ታዲያ ለምን ይከፋቸዋል? <በደንብ አላለቀሰችም!> ሁሉ እንደሚባል አውቃለሁ!!
ስለዚህ ተሰብስቤ ተቀመጥኩ። እኔ ትቼው የምሄደው ህዝብ እና መንደር ቢሆንም ለአጎቴ ወሬ ትቼለት መሄድ አልፈለግኩም!! በሁለተኛው ቀን ጎንጥ የምጨራርሰው ጉዳይ አለኝ ብሎ ወደከተማ ተመለሰ።
ከእማዬ ቀብር በኋላ ቤቱ ውስጥ የሚተራመሰው ዘመድ አዝማድ እና ጎረቤት እየተመናመነ ሄዶ ድንኳኑ ከተነሳ በኋላም ኪዳን መሄድ የፈለገ አይመስልም። «ትንሽ ቀን እንቆይ!» ሲል ብዙ ቆየን። ሁሉም ወደቤቱ ገብቶ ሶስታችን ብቻ የቀረን ቀን ማታ ሀዘናችን በረታ እና እንደአዲስ መላቀስ ያዝን። ኪዳን ከሁለታችን ብሶ «ምናለ ትንሽ ቀን ብትሰጣት? ፣ ምናለ ትንሽ ቀን ብጠግባት? ፣» እያለ ከአምላኩ ጋር ሲሟገት አንጀቴ ልውስ ብሎብኝ ተንሰፈሰፍኩ። አጎቴ እንደልማዱ «እህቴ ፤ ክፋዬ ፣ አንድ ደሜ …. » እያለ እንዳልተነፋረቀ እንባውን በፎጣው አደራርቆ
«ተው ደግም አይደል። የፈጣሪን አይን አትውጉ! ሳናያት ሳናውቅ አልፋስ ቢሆን? የልጆቿን ዓይን ዓይታ ፤ ጠረናችሁን ስባ በትውልድ ቀዬዋ ሀገሬው ቤቱን ነቅሎ ወጥቶ በፍቅር የሸኛት እሰቡት አምላክ እንዴት ቸር እንደሆነ? ደግም አይደል?» ብሎ ተቆጥቶ አረጋጋን!! እንባችንን አቆምን እንጂ ለሚቀጥሉት ቀናት እንደተኳረፈ ሰው በመሃከላችን ብዙም የቃላት ልውውጥ አልነበረም። የሆነ ቀን ውጪ ሳሩ ላይ ተቀምጠን
«የኔ ኪዳን? አሁንም ከዚህ በላይ መቆየት ትፈልጋለህ?» አልኩት
«እኔ እንጃ ሜል! ወደ አዲስአበባ መመለስ ከፈለግሽ እንመለስ! እኔ አሁን ምን እንደምፈልግ ራሱ አላውቅም!!» አለኝ።

👍31❤2👏1
«አዲስአበባ ከሄድን እዛ አንድ ቀን እንኳን እንድታድር አልፈልግም!! ሳይውል ሳያድር እንድትወጣልኝ ነው የምፈልገው ምን ያደርጉብኝ ይሆን ብዬ ማሰብ አልፈልም!!»
«አውቃለሁ!! ግን አንቺስ?»
«እኔ ምን? እኔ ራሴን መጠበቅ አያቅተኝም!!»
«ሜል ብዙ ነገር ተቀይሯል። ምን ያህል እንዳስተዋልሽው አላውቅም እንጂ አንቺም ራሱ ፍፁም ተቀይረሻል። ወደኋላ ተመልሰሽ ያለፈ ህይወትሽን መኖር የምትችዪ አይመስለኝም! እሱን ነው የምታስቢው? ምንድነው የምታስቢው?» አጠያየቁ የእኔ ኪዳን አይመስልም በጣም ተኮሳትሮ እንደታላቅ ነው የሚያወራው
«አላውቅም! ራሴ እንደተቀየርኩ አውቃለሁ ነገር ግን ያለፈውን ህይወቴን ሙሉ ለሙሉ ተፋትቼ መኖር እችል እንደሆነ አላውቅም! ምክንያቱም እኔ ብቻ እንጂ የተቀየርኩት በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችም ሁኔታዎችም እንዳሉ ናቸው። የቱን ጥዬ የቱን ይዤ እንደምቀጥል አላውቅም!»
«ለምን ከሀገር መውጣትን አታስቢበትም? ሁሌ ጀርባሽን መጠበቅ ሳይኖርብሽ አዲስ ህይወት አዲስ ማንነት ትገነቢያለሽ!»
«እኔእንጃ የኔ ኪዳን!!»
«በጎንጥ ምክንያት ነው? የነገ አብሮነታችሁ ምን ሊሆን እንደሚችል ተነጋግራችኋል?»
«አይደለም! ስለነገም ያወራነው የለም! ስለምንም ያወራነው የለም!»
«ሜልዬ እስኪ ዛሬ እንደ ትንሹ ወንድምሽ ሳይሆን እንደ 31 ዓመት ትልቅ ሰው አውሪኝ! እንደምትዋደዱ ግልፅ ነው!! እኔ ሳውቅሽ ለማንም ሆነሽ የማታውቂውን ነው ለሱ እየሆንሽ ያለሽው! ማንንም ሰው ባላቀረብሽው ልክ ነው እሱን ያቀረብሽው! ወደፊትሽን ስታስቢ እሱ አለበት? ያወራችሁት አይኑር! አንቺ ምንድነው የምታስቢው?»
«እኔ እንጃ ኪዳንዬ የእውነቴን እኮ ነው እኔንጃ የምልህ!! ታውቃለህ እኔ ፍቅር አላውቅም!! ፀብ ቢሉኝ አውቃለሁ፣ በቀል ቢሉኝ አውቃለሁ ……. ፍቅር ግን አዲሴ ነው!! ስምጥ ብዬ ከዋኘሁ በኋላ ነውኮ እንደወደድኩት እንኳን የነቃሁት! ደግሞ እኔ ብቻ የማስበው ምን ይፈይዳል? እኔ ስላሰብኩህ ና ወደፊቴ ውስጥ ላካትህ ይባላል?»
«ጠይቂዋ!»
«ምን ብዬ?»
«ምንድነው ስለወደፊት የምታስበው? አብሮነታችን ምን ድረስ ነው የሚዘልቀው? ብለሽ ነዋ!»
«እህ እሱ አይደል እንዴ ወንዱ! ይሄን መጠየቅ ያለበት እሱ አይደለም? በግድ እየገፋፋሁት ቢመስልብኝስ?» ስለው ከቀናት በፊት ሲስቅ የሰማሁትን ሳቅ ሳቀ።
«አይመስልም ዓለሜ (ልክ ጎንጥ በሚልበት ለዛ) ዘመኑ ተቀይሯል!! ሴት ተንበርክካ አግባኝ የምትልበት ዘመን ላይ ነን!»
« ምንስ ፍቅር ብርቄ ቢሆን ጥንቅር ይላታል እንጂ ተንበርክኬማ አግባኝ አልለውም! ጭራሽ? ለተሸነፍኩትም መደበቅ ቢቻለኝ በዋጥኩት! እንቢ እያለኝ እያመለጠኝ እንጂ!!» ተሳሳቅን!!
በሚቀጥለው ቀን ኦንላይን ትኬቱን ቆርጦ አጎቴን ተሰናብተን (ስንብቱ በእንባ የታጀበ ነበር።) ወደ አዲስ አበባ መጣን!! የዛኑ ቀን በረራው ነበረ። ስንሰነባበት
«ሜል አስብበታለሁ በይኝ ከሀገር መውጣቱን?»
«አስብበታለሁ ሙት!!»
«ለዓለሜ እንደምትዪው <የእህቴን ልብ ብትሰብር ውርድ ከራሴ!! ጦርነት በራስህ ላይ እንዳወጅክ ቁጠረው አንላቀቅም!!> ብሎሃል በይልኝ። የምሬን ነው ንገሪው!»
«ሂድ አሁን አርፈህ!! እነግርልሃለሁ!!»
እሱን ሸኝቼው ስመለስ ህይወቴን ካቆምኩበት መቀጠል እንደማልችል ገባኝ። ቤቴ እንኳን ያለስጋት መሄድ እንደማልችል ሳውቅ መኪናውን መንገድ ዳር አቁሜ ውስጥ እንደተቀመጥኩ ብዙ ቆየሁ። የእውነት ምንድነው አሁን የማደርገው? እንደድሮው ባር ሄጄ ወገበ ቀጫጭን ሴቶች የቆመ ፖል ላይ ሲውረገረጉ ፣ ለፍዳዳ ሰካራሞች ለሀጫቸውን እያዝረከረኩ ብራቸውን ሲረጩ …. .፣ አቅላቸውን የሳቱ ሱሰኞች ሀሺሺን ከሺሻው እያደባለቁ ሲያጨሱ …… እያየሁ እየተዘዋወርኩ ብሉልኝ ፣ ጠጡልኝ ፣ አጭሱልኝ ፣ ተዝናኑልኝ እያልኩ ብሬን መምታት ይቻለኛል?
ከአንድ ሰዓት በላይ ከቆምኩ በኋላ የሆነኛው ገስት ሀውስ ይዤ ለዛሬ እርፍ ብዬ መተኛት ፈለግኩና ከዛ በፊት የጎንጥን ድምፅ መስማት ፈለግኩ። አንዱ ሱቅ ገብቼ ደወልኩ። ስልኩ ዝግ ነው። ገስትሀውስ ገብቼ ለማረፍ ሞከርኩ እና ተገላበጥኩ። ራሴን አሁንም ወጥቼ የሱቅ ስልክ ላይ ስደውል አገኘሁት። ዝግ ነው!! ተመልሼ ገብቼ ለጥ ብዬ አድራለሁ ያልኩትን ለሊት ስገላበጥ አደርኩ። ይሄኛው ስሜት ደስ አይልም!! ስልኩን ባይከፍተው የት ብዬ ነው የማገኘው? የድሮ ሚስቱ ቤት ሄጄ <እየገደልሽኝ ሳለ እግረመንገድሽን ጎኔ የት እንዳለ ብቻ ንገሪኝ> ነው የምላት? ደግሞ ለራሴ <ማታ አይደል ያዋራሁት? ይሄኔ ባትሪ ዘግቶበት ነው!> እላለሁ። ዛሬ እንደምመጣ እያወቀ ስልኩን የዘጋው ሊያገኘኝ ስላልፈለገ ቢሆንስ? ምን እየሆንኩ ነው ስንት ሀሳብ እያለብኝ ስለእርሱ ብቻ የማስበው? ……. ስወራጭ ቆይቼ ሊነጋ ሲቃረብ እንቅልፍ ወሰደኝ!!
እንደነቃሁ ተጣጥቤ ስልኩን ሞከርኩ። አሁንም ዝግ ነው። ወደሰፈሬ ነዳሁ እና ተናኜን ቅያሪ ልብሶች ተቀብያት ጎንጥ ብቅ ብሎ እንደው ስጠይቃት አለመምጣቱን ነገረችኝ። ልብሴን እዛው መኪና ውስጥ ቀይሬ ሻለቃው ቢሮ ሄድኩ። የሰዎቹን ፎቶ ከተገበያየሁ በኋላ እንደማላውቃቸው ሳውቅ መረጃ የሚያቀብለኝ ሰው ጋር ደወልኩ።
«ኢሜል የማደርግልህን ፎቶ ተመልከተውና መረጃ አቀብለኝ» ካልኩት በኋላ የሁለቱን ሰዎች ፎቶ እየላኩለት ልክ እንዳልሆነ የማውቀው ሀሳብ ጭንቅላቴን ወጠረኝ። ላለማድረግ ከራሴ ጋር ታገልኩ። ግን አቃተኝ!! ከስልኬ ውስጥ ጎንጥን ስቀጥረው ይዤው የነበረውን ፎቶ አብሬ ላኩለት። መልሶ ደወለልኝ እና
«ይሄን ሰውዬኮ ከዚህ በፊት ጠይቀሽኝ ነበር።»
«አውቃለሁ!! ተጨማሪ መረጃ ፈልግ!! በጓሮ ሂድ!» አልኩት (ሰውየው በግልፅ ከተመዘገበው መረጃ በላይ የተደበቀ መረጃ አለው ለማለት ነው በጓሮ ሂድ የምንባባለው)
ስልኩን ዘግቼው ኮምፒውተር ቤቱ ውስጥ ፍዝዝ ብዬ ቀረሁ!!!

👍26❤3
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
ካለወትሮው እያከታተለ የሚወርደው ዝናብ የሐመርን ምድር:
የወሮን መንደር የብርሃን ጥላ አልብሷታል" ሰማዩ ላይ በጨርቅ እንደተጠቀለለ ህፃን ዳመናው እየተገለባበጠ
ምርር ብሎ እየጮኸ
ብልጭታው በሁሉም አቅጣጫ ይፈነጣጠቃል
ከክቧ የሐመሮች ጎጆ የሚትጎለጎለው
ከሚጥመለመለው ጥቁር ዳመና ጋር እየተደባለቀ ይጠፋል ፍየሎች በጎች ጥጆች ገና ከበረታቸው አልወጡም በከብቶች አንገት የተንጠለጠለው የኤሊ ድንጋይ ከብቶቹ በተንቀሳቀሱ ቁጥር
ቋቋ ቋቋ እያለ ይሰማል" መንደሯ ልብ ብለው ሲያዳምጧት ትንፋሽዋ እንደወትሮዋ ነው፤ ማነጠሱ፥ ጨዋታው፥ እንጉርጉሮው: ቀልዱ ወፍጮው፥ የወፎቹ ዝማሬ ሁሉም ከዘመናት በፊት
እንደተቃኘው ነው
የናት ጉያ ሙቀት የናፈቃቸው ሆዳቸውን የሞረሞራቸው ጥጆች ግን ከናታችን አራክቡን በሚል ሆድን በሚያላውስ ቅላፄ እ-
ም--ዋ … እም-ቡ-ዋ እያሉ የጌቶቻቸውን ጆሮና ቀልብ ለመሳብ ረሃብና ናፍቆታቸውን በለሆስታ ዜማ አለዝበው ያንጎራጉራሉ" ላሞች እንደሌሎች ከብቶች ማመንዠካቸውን አቁመው ፊታቸውን ወደ ጥጆቻቸው አዙረው ዐይናቸውን እያቁለጨለጩ: ሳጋቸውን እያሰሙ የጥጆችን ከለላ በአፍንጫቸው እያሸተቱና
እየነካኩ የናትነት አንጀታቸው ረፍት ነስቶ ያንሰፈስፋቸዋል አንተነህ ይመር ከምድጃው ጎን ካለችው ትንሽ መደብ ላይ
በቦርኮታው የቀኝ ጭኑን አስደግፎ፥ ጎኑን እሳቱን እያሞቀ እሱም
የማይሰማ ውስጡ ፈልቶ እዚያው ተኖ የሚቀረውን ሳጉን ራሱ ለራሱ ይሰማል
ባለቤቱ እሳቱን እየቆሰቆሰች ሻላው (ቆጡ) ላይ ባሰረችው ጠፍር የአንጠለጠለችውን እርጎ በቀኝ እጅዋ ወደ ፊትና ኋላ
ትንጣለች ቅቤ ለማውጣት ነጭና ጥቁር መልክ ያለው ቁርበት ከበስተ ኋላዋ ተነጥፏል ዳሚ ሰረቅ እያደረገች ስታየው ቆይታ
"ይእ! ምን ሆነሃል የኔ ጌታ?" አለችው
ቢጨንቃት" እሱ ግን ዝም አላት ዝም እየተነፈሰ ጭጭ
"ተቡኑ ልስጥህ?"
ጋልታምቤ መልስ ሳይሰጣት ውጭውን
አየው በጠባቧ በር በግድግዳው ቀዳዳ አየሩ ክርስስ ያለ ነው ቀዝቃዛ የሱም ልብ ቀዝቅዛለች
በሐመር ባህል የተጠየቀ ሁሉ ወዲያው የመመለስ ግዴታ የለበትም አዋቂ አስተሳሰቡ የበሰለ ከመናገሩ በፊት ልቡን ዐይኑ ላይ ማውጣት አለበት በልቦናው የሚያይ ሐሳቡ ሚዛናዊ ሆነ ክፉና ደግ ለመለየት በቃ ሃላፊነት ለመቀበል ደረሰ ማለት ነው" ጋልታምቤም በዚህ መላ
የሚስቱን ጥያቄና ጭጋጋማውን ቀን በልቦናው አየው" ልቦናው ግን ምንም እንዲል አልፈቀደለትም
ዝምታ ደግሞ በራሱ ቋንቋ ነው ዝምታና ዐይን ዝምታና ጥርስ ዝምታና ዝም በአይነቱ የተለያዬ ትርጉም አላቸው በቢጫው በሬ ምድር በሐመር።
ዳሚ የጋልታምቤን ዝምታና ዐይን አይታ የሚያሳስበው ነገር እንዳለ አውጥቶ ሊነግራት ግን እንዳልፈለገ ተረዳች ያን ጊዜ።
ይእ! ምን ሆነ? እንግዲ ተሱ ይምጣ'ንጂ እኔ ምናባቴ
ላርግለት ብላ እሷም ዝም አለች ዝም ተባባሉ እሱና እሷ እሱና እሱ: እሱና ተፈጥሮ ተዘጋጉ"
ጋልታምቤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሰረቅ አድርጎ አያት ልቧን ከንፈሯ ላይ ተቀምጦ አየው ፍርሃት ነፋ ልትት፤ ነፋ ልትት
ሲያደርገው ሲገፋፋው ሲያንቀጠቅጠው ሲያወዛውዘው ተመለከተው
ዳሚ ከበስተግራዋ ተሰካክተው ከተቀመጡት በጨሌ ያጌጠውን
ሾርቃ አንስታ ጠረግ ጠረግ በማድረግ ከተወዘተው እንስራ በቅል ጭልፋ ሸፈሮ ቡና ቀድታ አቀበለችው
ጋልታምቤ እግሩን አንፈራጦ ተቀበላትና ግራ ቀኝ ፊትና ኋላ ጎለል ጎለል አድርጎ አበረደው ከዚያ እፉት ብሎ ፕስስ አድርጎ አማተበ ሸፈሮ ቡና የቦርጆ ፍሬ ሽፋን ነው ደስታን ያመጣል ራስን ለማየት ከራስ ጋር ለመምከር የቆሸሸ ህሊናን
ፈውስን ለማጽዳት የሚፋጅ የሚያቃጥል ነገር ሲያጋጥም ነቅነቅ ወዝወዝ
እያደረጉ ለማብረድ ለማቀዝቀዝ ጥሩ ነው
ይህ ሐይል ያለው
ሸፈሮ የተወጠረውን ስሜት ሲያላላው፥ የታመቀ
የጋልታምቤን ትንፋሹን እያንቦለቦለ አስወጥቶ እሁ! አለ ዳሚ አየችው የደሙ
ዝውውር ተረጋግቶ ይሽከረከራል: ገፅታው ጠይቂኝ ይላል"
"ዛሬ ቀን ምን ሆነሃል?" ስትለው ትክ ብሎ አያትና ዐይኖቹን ከላይዋ ላይ አንስቶ ከራሱ ጋር ሙግት ገጠመ" ይህች ሰው
ባትሰማው ይሻል ይሆን? ይህማ የማይቀር እዳዋ ነው ከሌላ ከምትሰማው እኔ ብነግራት አይሻልም አአይ ይቅርባት ትጨነቃለች ችግሩ ደግሞ ወደሷ እየገሰገሰ ነው መከራዋን በቀስ እየደራረበች ብትሸከመው አይሻልም … ብሎ ፊቱን ወደ ዳሚ
መለሰው
"ዳሚ!"
"ዬ!" አለችው ዐይኖችዋን ከዐይኑ ነቅላ እሳት እሳቱን እያየች አይን አፋርነቷ
ትልቁ ውበቷ ነው" ሁሌም ሲጠራት ዐይኗ
ይንከራተትና የሆነ ቦታ ገብቶ ውሽቅ ይላል" የምታየው ግን እሱን ነው።
"ዳሚ!" አላት ደግሞ
"ዬ!" አለችው ድምጿን ከረር አድርጋ እየሰማሁህ ነው'
ለማለት።
"ያች ልጅ መንጠፏ ነው ይሆን?" አላት የሃሣብ ሸክሙን በጥሶ ላይዋ ላይ በትኖ ዳሚ ጥያቄውን ስትሰማ ህሊናዋ አስደንጋጭ ነጎድጓድ ባረቀበት ክው ብላ ደነገጠች አልጮኸችም መልስም አልሰጠችም ውስጧ ግን ባንዴ ባዶ ሆነ ቀፎ ዐይኖችዋን እሳቱ ላይ ለረጅም ጊዜ ተክላ ቆየች
ጥያቄው በቀፎው ሰውነቷ
እየተንጎዳጎደ ነዘራት አመማት እንደ ሚጥሚጣ ለበለባት ... እሳቱ
ላይ የተሰካው ዐይኗ ሙቀቱ እንዳቀለጠው ሁሉ በፈሳሽ ተሞላ በእንባ በምሬት የዐይኗ ኳስ ሲንቀሳቀስ ግን እንባዋ ፈሰሰ እንባዋን ንፍጧ ጠርቶት ቁልቁል ወረደ እንባዋ ንፍጧን ተከተለው አያት ጋልታምቤ እንደገና በዐይነ-ህሊናው ራሱን አየው፤ እንደ
ከስኬ ወንዝ ወደ ውስጡ የሚሰርገው እንባው ስለማይፈስ መውጫ
ስለሌለው የሰራ አካላቱ ላይ የእንባ ጎርፍ ተኝቶበታል"
"ሁለት ዓመት ሙሉ ይኸው ወልዳ ለመሳም አልታደለችም የሐመር ሽማግሎችም ተነጠፈች በሐመር ደንብ መሰረት ለከሎ ወይ ምትክ ይሰጠው ካለበለዚያም ጥሎሹ ይመለስ እያሉ ነው" አላትና
መሬቷን ተመለከታት ዳሚ የሚለውን አልሰማችውም ከፊት ለፊቱ ተቀምጣ እሷ ግን የለችም አትንቀሳቀስም:
ጋልታምቤ ከውስጥ የዳሚ ከውጭ የላሞች ሳግ ተሰማው የጥጆች ጥሪ የጎይቲ ሰቆቃ
መሀን ሴት በሐመር ልቧ እንደ አሮጌ ቅል የተጠረማመሰ ምስጥ እንዳነካከተው ግንድ ተስፋዋ ፍርክስክስ ያለ ከዚህ መከራዋ በተጨማሪም ቤተሰቧን የመጥፎ ቤተሰብ የምታሰኝ እሷ የመጣችበትን መንገድ ለሌላው ግን የምትከለክል
እርጉም ተብላ
ከማህበራዊው ቡድን ተነጥላ ተወርውራ የምትጣል የቤተሰቧን ጎጆ
በጨለማ የምትሸፍን ናት
"የፈራሁት ደረሰ! ብላ ዳሚ የእንባዋን ውታፍ ከፈተችው
ልቧን ነደለችው ሆን ብላ ያዳፈነችውን የጭንቀት እሳት እፍ አለችው የእንባ ፈሳሽ ያገኘው ስሜቷ እንደ ደረቀ ቅጠል በውስጧ
ሲንቀለቀል ናጣት አርገፈገፋት አስቃሰታት
ስለዚህ ጋልታምቤ ጭንቀቷን ተቀምጦ ማየት ሰቀጠጠው
ከተቀመጠበት ተነስቶ ጥጆችን ከእናታቸው ያራክባቸዋል ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አንዱ ጠብቶ ሌላው
ሊያራክባቸው ወጣ ጥጆችን
አጥብቶ ጥጋብ ይሆንና የመለያየቱ ምልክት ድራሹ ጠፍቶ መላላስና
መቦረቅ ይመጣል አንተነህ ይመር ለጎይቲ ምኑን አጥብቶ ከጭንቀቷ
ይገላግላታል! አለኝታው፡ መስታዋቱ ደስታውን እንዳያይባት መከራ

👍30
ዳመና ፈጥሮ ላይዋ ላይ እያዠ ዘላለም ልታነባ ነው በእሷ ያገኘውን ደስታ በእሷው መከራ ሊነጠቅ ነው"
ጋልታምቤ የጥጆችን በረት ሲከፍተው ጂናቸውን አቁመው እናታቸው ጉያ ገቡ እናቶቻቸው የልጆቻቸውን ሰውነት ላሱ፤ እሱ
ግን ለጎይቲ የሚያደርግላት የለም ከረሰሰው ስሜቱን … ራሱን ወደ ሰማይ ቀና ሲያደርግ ጎይቲን በጭጋጋማው ሰማይ አያት አንገቷን ደፍታ ስታነባ ከሰዎች በረት ወጥታ ወደ ጨለማ ስታዘግም ውበቷ
ውሃ አንዳጣ አበባ ሲጠወልግ አያት ያኔ ህይወቱ ጎመዘዘው
መኖሩ እንደእርጥብ ጌሾ መረረው፤ ልጁ አክ እንትፍ ተብላ ስትተፋ በእዝነ ህሊናው አይቶ ተሸማቆ ዐይኖቹን ጨፈነ ግን አልተኛም ግን አላንቀላፋም እረፍት አላገኘም ሳጉ ይሰማዋል … ምን ነበረበት ዐይንን መጨፈን ማለት መተኛት ሁሉንም መርሳት በሆነ!

👍12
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው፡፡የምሰራበት ሆቴል ቤርጎ ይዛለች፡፡ስራ እንደጨረስክ ና ብላኝ ስለነበረ ስራዬን ጨርሼ ወደእሷ ለመሄድ እየተዘጋጀው ነው፡፡ስደርስ በረንዳ ላይ ባለ ወንበር ላይ ኩርምት ብላ ቁጭ ብላለች አይኖቾን ሰማይ ላይ ሰክታ ፈዛለች፡፡ከጎኗ ቁጭ አልኩና‹‹ጨረቃን እያየኋት ነው እንዳትይኝ?››አልኳት፡፡
‹‹አልኩህ››
‹‹እራስሽን ምን አሳየሽ?››
‹‹ማለት? ››
‹‹ያው እንቺም ጨረቃ ነሽ ብዬ ነዋ...››
‹‹ጨረቃ ነሽ ስትል በቀጥታ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››
"ከዚህ ንግግሬ ምን የማይገባ ነገር አገኘሽበት... ጨረቃ ነሽ ስል አደንዛዥ የሆነ ውበት ባለቤት ነሽ ማለቴ ነዋ።"
‹‹ጨረቃ እውነትም እንደምትለው አደንዛዥ ውበት አላት ?››
" የላትም እንዴ?"
‹‹እኔ ምን አውቄ እንደዛ ስላልከኝ ነው..ይህቺን አባባል ሁሉም ሰው ይጠቀማታል …ግን በትክክል በምሽት ስራዬ ብሎ የቤቱን በራፍ ከፍቶ በረንዳ ላይ ወጥቶ አንገቱን ወደ ሰማይ አንጋጦ፤ አይኖቹን ጨረቃ ላይ ተክሎ፤ ውበቷን ያስተዋለ ድምቀቷን ያጣጣመ.. ከመቶ ሺ አንድ ሠው ይገኝ ይመስልኸል...ግን ዝም ብሎ ስለሚባል ብቻ ትክክል ይሁን አይሁን ሳያውቅ ሁሉም ይደሰኩራል....
"እና ማጠቃለያሽ ጨረቃ ቆንጆ አይደለችም ነው?›
"አይ ነችምም አይደለችምም..ለምሳሌ እኔ ቆንጆ ነኝ?"
"ግጥም አድርጎ ...በጣም ውብ ነሽ"
"ከዚህ በፊት ሁለት ሰዎች ቀጥታ አሁን አንተ እንደቆምከው ፊቴ ቆመው ምንሽም የማያምር አስቀያሚ ሴት ነሽ ብለውኝ ያውቃሉ።እንደውም እንደዛ አይደለም.አስቀያሚ ወንዳወንድ ነገር ነሽ ነው ያሉኝ፡፡››
"እና ማንኛችንን አመንሽ?"
"ሁለታችሁኑም"
"ሁለታችንንማ ልታምኚ አትችይም ..አንቺ ወይ ቆንጆ ወይ አስቀያማሚ ነሽ.."
"አይ እንደየሁኔታው ቆንጆም አስቀያሚም ልሆን እችላለሁ...ውበት እንደየተመልካቹ ነው በሚለው ንግግር አምናለሁ...ለዚህ ነው ቆንጇ ነሽ ሲሉኝ ብዙ የማልፈነጥዘው አሰቀያሚም ሲሉኝ አንገቴን የማልደፋው።"
‹‹እና ማየቴን ላቁም?››
‹‹እንዳሰኘህ…ግን ጨረቃ በትከክልም ምን ግዜ ውብ እንደምትሆን ታውቃለህ?››
‹‹አላውቅም ንገሪኝ ››
ጦር ሜዳ ፊት ለፊት ግምባር ላይ እያለህ የሆነ ግዳጅ ተሰጥቶህ ከጓደኞችህ ጋር ድቅድቅ ባለ ጨለማ እየተጓዝክ መንገድ ጠፍቶህ ከጠላት ምሽግ ሰተት ብዬ ገባሁ ወይስ የጠላት ደጋፊ ከሆኑ ህብረተሰብ እጅ ወደቅኩ እያልክ አቅጣጫህን እንዴት እደምታስተካክል ግራ ገብቶህ እያለ ድንገት ብልጭ ብላ ስትወጣ…ከዛ እየደመቀች ስትሄድ….በቃ ውብ መሆኗ የሚገባህ የዛን ጊዜ ነው፡፡ምክንያም ህይወትህ የምታድንበት ጭላንጭል እድል ሰጥታሀለችና፡፡
‹‹ወይም ደግሞ›› ብዬ እኔ ቀጠልኩላት
‹‹ወይ ደግሞ.. በጣም የምትወጃትን ማለቴ የምታፈቅሪያት ልጅ አባትዬው ከእቅፍሽ ነጥቀው ለሌላ ሊድሩብሽ መሆኑን ስትሰሚ እሷን በጠፍ ጨረቃ ከቤት አስኮብልለሻት በየጫካው ይዘሻት ስትጠፊ በዛን አስደሳችና ጭንቀት በተቀላቀለበት ወሳኝ ሰዓት ለመንገድሽ ብርሀን ሆና ከፊት ለፊትሽ ቦግ ስትል .. በዛን በክፉና በደስታ ቀን የመንገድሽ አጃቢና መሪ ብሎም ለፍቅርሽም ድምቀት ስትሆን…አዎ የዛን ቀን ነው ጨረቃ ከውብም ውብ መሆኗን በደንብ የሚገባሽ››
‹‹አየህ ጨረቃን እንደየልምዳችን ነው ለውበቷ ትርጉም የሰጠነው..››
‹‹እንደልምዳችን ማለት?አንቺ ወታደር ነሽ እንዴ?››ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት፡፡
‹‹አይ ማለቴ ጓደኛዬ ወታደር ነው….ታውቃለህ አይደል?››
‹‹አዎ የበቀደምለታው ጄኔራል አይደል?››
‹‹አዎ ..እሱ ነው››
‹‹ግን…እንዲህ ከሌላ ሰው ጋር በምትሆኚበት ጊዜ ችግር አይፈጥርብሽም?››
አይኖቾ በንዴት ግልብጥብጥ አሉ….‹‹እንደዚህ ከማን ጋር ስሆን አይተኸኛል?›አፋጠጠችኝ፡፡
‹‹አረ አረጋጊው…ከእኔ ጋ ለማለት ፈልጌ ነው›
‹‹ካንተ ጋርስ ምን አድረግናል?››
‹የባሰ አለ ሀገርህን አትልቀቅ› ይላል የሀገሬ ሰው..ድንብርብሬ ወጣ…ምን ብዬ በንዴት ወደላይ የተመነጠቀ ስሜቷን ልመልሰው?‹‹ምንም አለማድረጋችንን እኮ የምናውቀው እኔና አንቺ ብቻ ነን…ቢያንስ ሁለት ቀን አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ አድረናል…››
‹እ..እሱስ እውነትን ነው….ግን ያ ምንም ችግር የለውም..እሱም አመቱን ሙሉ ከሚስቱ ጋ ሲተኛ እኔ ምንም ብዬው አላውቅም፡፡››
‹‹ሚስቱ?›
‹‹አዎ ሚስቱ….ሚስትና ሶስት ልጆች አሉት››
‹‹ከባድ ነው››
‹‹አዎ ፍቅር ምን ጊዜም ቀላል ሆኖ አያውቅም››
‹‹ግን ምንድነው ስራሽ..?››
‹‹እሱን ማፍቀር?››
‹‹አይ ስራ መትተዳደሪበትን ነው የጠየቅኩሽ..?››
‹‹ነገርኩህ ስራዬ እሱን ማፍቀር ነው….ገንዘብ ማገኝበትን ከሆነ የጠየቅከኝ ሌላ ጊዜ ነግሀለሁ…ግን ለራሴ የሚበቃ በቂ ገቢ አለኝ፡፡››
‹‹አይ ጥሩ ነው‹‹
‹‹ጥሩ ባይሆንስ ምን ምርጫ አለኝ....በል አሁን ይብቃን ገብተን እንተኛ››
‹‹አዎ ተነሽ.. ግን እኔ ወደቤቴ ልሂድ››
ፈገግ አለች‹‹ምነው ምን አሳቀሽ?››
‹‹አይ ወደቤት ልሂድ አባባልህ እራሱ ያስቃል..ምነው የጄኔራሉ ሽጉጥ ፊትህ ላይ ሲደቀንብህ በምናብህ አየህ እንዴ ››
‹‹ቀላል…ትቀልጂያለሽ እንዴ…?ገና በቅጡ እንኳን ያላየኋት እና ያላሰደኳት ልጅ አለችኝ..ድፍት ቢያደርገኝ ምን እላለሁ፡?፡››
ከተቀመጠችበት ተነስታ እጄን ይዛ ወደክፍሏ እያመረን ነው.. በራፍ አካባቢ ስንደርስ ነው ስለልጄ የነገርኳትን …ስትሰማ በድንጋጤ እጄን ለቀቀችና ባለችበት በመቆም አፍጥጣ አየችኝ፡፡
‹‹አንተ የእውነትን እንዳይሆን?››
‹‹ግራ ገባኝ ..ስለፍቅረኛዬ እያወራኋት ቢሆን ልሸመጥጣት እችል ነበር ..የልጅ ነገር ግን እንዴት አድርጌ…?መጀመሪያ አዳልጦኝ የተናገርኩ ቢሆን ወደኃላ ልመልሰው ግን እልፈለኩም …ቀጠልኩበት፡፡
‹‹አዎ ልጅ..አለቺኝ..የ7 አመት ልጅ..ተአምር ትባላለች››
‹‹ከዚህ በፊት ግን ፍቅረኛም ሚስትም እንደሌለህ የነገርከኝ መሰለኝ››
ይሄን ደግሞ መች ይሆን የቀባጠርኩላት…ማስታወስ አልቻልኩም፡፡አሁን ወደፊት ተንቀሳቅሰን በራፍ ጋር ደርሰናል….በእጇ ያንጠለጠለችውን ቁልፍ በማስተካከል በራፉን እየከፈተች ነው‹‹አዎ አሁንም ሚስትም ፍቅረኛም የለኝም ….እውነቴን ነው››
ወደውስጥ ገባች…ሄዳለሁ ያልኩት ሰውዬ ተከትያት ወደውስጥ ገባሁ ..መልሳ በራፉን ከውስጥ ቆለፈችው፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡ከጎኗ ተቀመጥኩና ወሬዬን ቀጠልኩ፡፡
‹‹ነገሩ ውስብስብ እና የድሮ ታሪክ ነው… ሀይስኩል ተማሪ እያለው ነው የልጅ አባት የሆንኩት››
‹‹ታድለህ….ምን አለ እኔም ከእናቴ ቤት ሳልወጣ አንድ ዲቃላም ቢሆን ወልጄ በሆነ››
‹‹እውነትሽን ነው?፡፡››
‹አዎ..እውነቴን ነው…..የህይወቴ አንዱ ህመም የልጅ እናት ካለመሆኔ ጋ የተያያዘ ነው…››አይኖቾ በእንባ ተሞሉ…አረ ዘረገፈችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ አሁንም ይቻላል.. ገናነው አልረፈደም…ሶስትም አራትም ልጅ መውለድ ትችያለሽ››
ኩስትርትር ብላ‹‹መቻሌን በምን አወቅክ?››በሚል ጥያቄ አስበረገገችኝ፡፡

👍53❤2😢2🤔1
‹‹ያው ገና ልጅ ነሽ ብዬ ነዋ››
‹‹አንዳንድ ነገሮችን እኛ በቀላል ስላደረግናቸውና ስላገኘናቸው ለሌላውም እንደዛው በቀላሉ ይገኛሉ ማለት አይደለም….ያሉን ነገሮች ዋጋ በመገመት ላይ ቀሺሞች ምንሆነው ለዛ ነው…..በል አሁን እንተኛ አለችና ከነልብሶ አልጋ ላይ ወጥታ ከውስጥ ገልጣ ጥጓን ይዛ ጥቅል ብላ ተኛች፡፡እኔም ጃኬቴን አውልቄ ሱሪዬንና ቲሸርቴን እንዳለ በመተው ልክ እሷ እንዳደረገችው ከውስጥ ገባሁና ተቃራኒውን ጠርዝ ይዤ ተጠቅልዬ ተኛሁ…፡፡ቢያንስ ከዚህ ቀደሙ የሚለየው ብርድልብሱን ወርውረልኝ በአልጋ ልብስ ተጠቅልላ አልተኘችም፡፡አንድ አንሶላ ለሁለት አንድ ብርድልብስ ለሁለት ተጋርተናል..ይህ ጥሩ እድገት ነው፡፡ስለዚህ ተመስጌን ብዬ ተኛሁ…ተኛሁ ማለት እንቅልፍ ወሰደኝ ማለቴ አይደለም፡፡እንደውም የሀሳብ ትብታብ ውስጥ ነው የተሰነቀርኩት፡፡
ሄዳለሁ ብዬ አልነበረ እንዴ…?ለምን ታዲያ..? እንዳልሄድ እንኳን ያን ያህል ሳትለምነኝ ተከትያት ገባሁ……ምን ፈልጌ ነው…?.የምታፈቅረው ሰው እንዳለ በግልፅና በማያሻማ ቋንቋ ነግራኛለች፤ለዛውም ጄኔራል….አይደለም አራት ኮከብ የደረደረ ጅኔራል ይቅርና የቀበሌያችን ታጣቂዎች ኃላፊ ልጅ ስጀነጅን ብገኝ ሌላ ሰበብ ተፈጥሮልኝ ከርቸሌ ልወረወርበት በምችለበት ሀገር እንዴት ነው እንዲ ያቃለልኩት….?ነው ወይስ እሷ እንዳለችው ፍቅር መቼም ቀላል ሆኖ አያውቅም ይሆን? ..እሺ አባባሉ እውነት ይሁን ግን እኔ እንዳዛ የሚያስብል አይነት ፍቅር ከእሷ ይዞኛል እንዴ…?አረ ቆይ እስኪ ከዚህ በፊት የጀመርኩትን እና ህይወቴን እንዲሀ ብትትኑን ያወጣውንስ ፍቅር እልባት መች አበጀሁለት..?እንዴ እልባት ማለት ወደኃላም መመለስ ያምረኛል እንዴ?…በራሴ የእብደት ሀሳብ ተገረምኩ…፡፡ሴትዬዋ እኮ የገዛ ልጆቾን እራሱ ጥላ አሜሪካ ከገባች 6 አመት ሞላት…በዚህ ስድስት አመት ውስጥ አንድ ቃል አልተለዋወጥንም፤ስለእሷ ምንም ሰምቼ አላውቅም፤ ስለእኔም እርግጠኛ ነኝ ምንም ሰምታ አታውቅም ፡፡ታዲያ ምንድነው የማወራው…?የመገለባበጥ ድምፅ ሰማሁና ሀሳቤን ለጊዜውም ቢሆን ገደብኩት…ወደእኔ ዞረችና ክፍተቱን አጠበበችው…መታ ተለጠፈችብኝና አቀፈችኝ…እኔም በፀጥታ አቀፍኳት፡፡

👍58❤9👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
እራሴን አመም ስላደረገኝ አስፈቅጄ ወደቤት ስገባ ሶስት ሰዓትም አልሆነም።..ሹክክ ብዬ ገብቼ አልጋዬ ላይ "በመውጣት አረፍ እንዳልኩ ስልኬ ጠራ...አሁን ማንንም ቢሆን አንስቶ የማናገር ፍላጎት የለኝም የዜና ወርቅም ብትሆን እንኳን፡፡ስልኩ መጥራቱን ቀጥሏል ማንም ቢሆን ላለማንሳት ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ ማንነቱንም ማየት አስፈላጊ አልነበረም ..እኔ ግን እጄን ሰድጄ ስልኬን አነሳሁ፡፡ እስክሪኑን ወደአይኔ አስጠጋሁ..ተፈናጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁና ቁጭ አልኩ..እንዳይዘጋብኝ እየተስገበገብኩ አነሳሁት..
‹‹ሄሎ የእኔ ውድ..?
"ሄሎ አባዬ እንዴት ነህ?
"አለሁልሽ ..በጣም ሰላም ነኝ..አልተኛሽም እንዴ?"
"አይ ገና ልተኛ እየተዘጋጀሁ ነው...አባዬ የእኔ ክላስ የትኛው እንደሆነ ታውቃለህ አይደል?"
በምናብ ወደ አደኩበት ቤት ፈረጠጥኩ..ሁሉንም ክፍሎች በሀሳቤ ቃኘሁ ከእነቴቴ መኝታ ቤት ቀጥሎ ያለችው ክፍል ነች አይደል?"ግምቴ መቼስ የቤቱ ትንሽዬ ህፃን ስለሆነች ለቁጥጥርም ለሊት ተነስቶ ደህንነቷን ለማየትም ቅርብ ያለው ክፍል ነው የሚመረጠው ብዬ ነው...፡፡
"አይደለም..እዛ ህፃን ሆኜ ነበር አሁን ትልቅ ስሆን የአንተና የእማዬ የነበረውን ክፍል ወሰድኩት
ደነገጥኩ"በእውነት እሱ ክፍል መኖሩ ትዝ አላለኝም ነበር፡፡ እንደዛ ያልኩት ከዛ ሁሉ ዝብርቅርቅ ክስተት በኃላ እቴቴ ክፍሉን ምንቅርቅር አድርጋ የአንድን ሳይድ ግድግዳ በመደርመስ ከሌላው ጋር በመቀላቀል ክፍሉ ለታሪክነትም እንዳይታወስ የምታደርገው ነበር የሚመስለኝ ..ለዛ ነው ያንን አይነት ጥያቄ የጠየቅኳት"
"ልጄ ሳይገኝ ያ ክፍል አይከፈትም ብላ ከእነዕቃው አሽጋበት ነበር...ከዛ እኔ አክስቴ ትልቋን ለመንኩና እሷ በሌለችበት አስከፈቼ ገባሁበት፡፡"
"ታዲያ አልተቆጣችሽም?"
"አይ ምንም አላለቺኝም ግን አለቀሰች፡፡"
እኔም አሁን አለቀስኩ የሚቆጠቁጥ እምባ በቀኝ ጉንጬ ረገፈ"የእኔ ማር እናትሽ ለእቴቴ ትደውልላታለች አይደል?"ድንገት በእምሮዬ ብልጭ ያልኝን ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡
"ትደውልላታለች...እቴቴ ግን ትሰማታለች እንጂ አታናግራትም፡፡"
"ለምን?"
‹‹"እኔ እንጃ አባዬ...የሙት እህቴን ቃል እንድበላ አደረጋኛለች..ልጄን ወይ በህይወት አልያም ሞቶ ከሆነ ሬሳውን አግኝቼ እርሜን ሳላወጣ ከእሷ ጋር ባወራ እግዜር ይቀየመኛል ትላለች...ግን አባዬ እርም ማውጣት ማለት ምን ማለት ነው?።››
"ቁርጥ ማወቅ ማለት ነው የእኔ ልጅ"ቀላል ነው ብዬ ባልኩት ቃል ገለፅኩላት።
"አባዬ"
"ወዬ የእኔ ልጅ"
"እቃችሁን ስጎለጉል የእማዬ ማስታወሻ ደብተር አገኘሁት..ሁል ጊዜ አነበዋለሁ.. ደስ ይላል..።"
"እናትሽ ማስታወሻ ደብተር ነበራት እንዴ? እኔ አላውቅም..."
"አዎ አላት ..ትልቅ ሰማያዊ ደብተር....እና ደግሞ ስላንተ ብቻ ነው የፃፈችው...ትንሽ ትንሽ አንብቤው ስላልገባኝ ተውኩት.. ››
የእውነትም በጣም ተገርሜ "በእውነት ይገርማል .!"አልኩ ፡፡
በድንገት ማስታወሻው ላይ ያለውን ሀሳብ ለማወቅ የሚቀስፍ አይነት የጉጉት ስሜት ተሰማኝ..ልጄ የውስጤን እንዴት ማንበብ እንደቻለች አላውቅም"አባዬ ከፈለክ ትንሽ ትንሽ ፎቶ እያነሳው ልልክልህ እችላለሁ"ደ
ተነቃቃሁ"እንዴት አድርገሽ?"
"ቴሌግላም መጠቀም እኮ በጣም እችላለሁ...ለእማዬ ፎቶዬንና የፈተና ውጤቴን እያነሳሁ ሁሌ ነው የምልክላት"
"በጣም ደስ ይለኛል የእኔ ማር...በይ አሁን ተኚ"
"እሺ አባቢ ..ደህና እደር...እወድሀለሁ"
"እኔም እወድሻለሁ"
ስልኩ ተዘጋ...እራስ ምታት የሚባል ነገር ከጭንቅላቴ ተጠራርጎ ወዴት ጥርግ እንዳለ እኔ እንጃ።ልጅ መድሀኒት ነው የሚባለው ለካ ዝም ብሎ አባባል አይደለም፡፡
ስልኬ ተንጣጣ...ሚሴጅ ነው..ከልጄ ነው ከፈትኩት
‹‹ልኬያለሁ›› ይላል ወዲያው ዳታ አበራሁና ቴሌግራም ከፈትኩ .ተአምር እዬብ ሁለት ፋይል ልካልኛለች...የእኔ ቅመም ልጅ...፡፡ዳውን ሎድ አደረኩትና ከፈትኩት ፡፡ እውነትም ልምድ አላት ፡፡ፍይሉ በጥራት የሚነበብ በጥንቃቄ ተነስቶ የተላከ ነው።የእናቷን የእጅ ፅሁፍ ሳየው ሰውነቴን ነዘረኝ ፅሁፍና ምስሏ በአእምሮዬ እየተፈራረቀ ትዝታ ውስጥ ጨመረኝ...ምን አለ እህቴ ባትሆኚ።ትራሴን አስተካክዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩና ማንበብ ጀመርኩ።
ግንቦት 5/2008 ከምሽቱ 5 ሰዓት
እቤታችን ሲመጣ 9 አመቱ ነበር ።የመጣበትን ቀን በደንብ ነው የማስታውሰው እማዬና አባዬ ለቅሷ ብለው ወደ አዲስአባ ከሄዱ ከሳምንት በሀላ ነው ጥቁር በጥቁር ለብሰው ፊታቸው ጨልሞና ከፍቶቸው ሌላ የከፋው ፤ለንቦጩን የጣለና ግራ የገባው ልጅ ይዘው የመጡት፡፡ልጁን ቀድሞውንም አውቀዋለሁ፤ ያውቀኛል፡፡ አዲስአባ ያለችው የአክስቴ ልጅ ነው።የአሁኑ አመጣጡ ግን እንደከዚህ ቀደሙ ቦርቆና ፈንድቆ ከእኔና ከእህቶቼ ጋር ለአራት ለአምስት ቀን እቃ እቃ ተጫውቶ ለመመለስ እንዳልሆነ ገብቶኛል።
ትላልቅ ሰዎች አክስቴም ባሏም በድንገተኛ አደጋ ዘእንደሞቱ ሲያወሩ ሰምቼያለሁ ..ግን ይሄ ድንገተኛ አደጋ የተባለው ሰውን የሚገድል አውሬ ምን አይነት ነው?ስል በወቅቱ በነበረኝ የልጅነት አዕምሮዬ አሰብኩና በጣም ተበሳጨሁ። አክስቴን በተመለከተ ጣፋጭና የማይሳሳ አይነት ትዝታ ነው ያለኝ።በሶስት ወር ሆነ በስድስት ወር ልትጠይቀን ስትመጣ ..ኬክ፤ቸኮሌት፤ እና ልብስ ቀሚስ፤ ቲሸርት ጫማ ብቻ አንድ ነገር ይዛልን ትመጣ ነበር።
ትምህርት ቤት ሲዘጋ ደግሞ አዲስአባ እንሄዳለን...ያንን ቢሄድ ማለቂያ የሌለውን ከተማ በፈንጠዝያ ስንዝናናበት ቆይተን ሽክ ብለን በአዳዲስ ልብስ አሸብርቀን እንመለሳለን..አመቱን ሙሉ ከደብረብርሀን ወጥተው ለማያውቁ ጓደኞቻችን ስለአዲስአባ ተረት መሰል ታሪኮችን እየተረክን ስንጎርርባቸው እንከርማለን ለእኔ የአክስቴ ሞት ትርጉም በዛ የጨቅላነት ዕድሜዬ እንኳን በደንብ ነበር የገባኝ...ከአሁን በሀላ ከአዲስ አበባ የሚመጣልኝ ምንም ኬክ ሆነ ቸኮሌት እንደማይኖር ገባኝ..ዘናጭና ፍሽን ቀሚሶችም ከአክስቴ እንደማይበረከቱልኝ ከሁሉም በላይ ግን ክረምት መጥቶ ት/ቤት በተዘጋ ቁጥር አዲስአበባ ሄዶ መዝናናት የማይቻል መሆኑን ምን አልባትም ትልቅ ሰው እስክሆን አዲስአበባን እንደማላያት ተረዳሁ..
እና እዬቤን እማዬ ከሌሎች ሀዘንተኞች ጋር ይዛው ስትመጣ እላዩ ላይ ተጠምጥሜ አንገቱን አቅፌ አለቀስኩ..ቢያባብሉኝ እራሱ ላቆም አልቻልኩም... በወቅቱ እንደዛ ማለቀሴ አክስቴን አስታውሼ ነበር. የምታመጣልኝ ኬክና ቸኮሌትም ስላማራኝ ነበር...እናም አዲስአባም መሄድ ስለፈለኩ ግን ደግሞ እንደማልችል ስለገባኝ ነበር.፡
.ታላላቆቼ በድርጊቴ ግራ ቢጋቡም እኔ ግን በጣም አዝኜ ነበር..እና ለእዬቤ የራሱ አልጋ ከአዲስአባ እስኪመጣለት አልጋዬን አጋራሁት..እርግጥ አብዛኛውን ጊዜ እማዬ እያለ ሲቃዠና ሲንፈራገጥ እማዬ እየመጣች ወደራሷ መኝታ ቤት ትወስደውና ከማዬና አባዬ መሀል ይተኛ ነበር...እንደዛ ሲያደርግ እኔም ምን አለ አብሬው ሄጄ መሀከላቸው በተኛሁ እላለሁ፡፡እኛ ልጆቻቸው እንደው ፍርጥ እንላታለን እንጂ ከእነሱ ጋር የመተኛት እድል አናገኝም።እና በዚህ አይነት ሁኔታ እዬቤ ወንድማችን ሆነ፡፡ እቃቸው ከአዲስአባ መጣና ከእኛ ቤት እቃ ጋር ተቀላቀለ..ቤታቸውም እንደተከራየ እማዬ ስታወራ ሰምቼያለሁ። አልጋውም መጣለትና ከእኔ አልጋ ጎን ቦታ ተመቻቸለት።ግን ስንላፋና ስንጫወት ቆይተን ሳናስበው ወይ እሱ አልጋ ላይ ጥቅልል ብለን ተቃቅፈን

👍67❤3👎1🥰1
እንተኛለን ወይም እኔ አልጋ ላይ ተኝተን እንገኛለን።ሁል ጊዜ አንደኛው አልጋ ባዶውን ነው የሚያድረው..በኃላ እማዬ ለምን ማትጠቀሙበት ከሆነ ክፍሉ ይጨናነቃል አለችና የሁለታችንንም አልጋ አውጥታ አንድ ባለሜትር ከሀያ አልጋ አስገባችልን።
…
አንብቤ ጨረስኩ….የሚነዝር የልጅነት ትዝታ ውስጥ ነው ወደኃላ ተስቤ እድዘፈቅ ያደረገችኝ…እንዴ ልጅቷ ይህን ያህል ሀሳብን አቀናብሮና አሳምሮ የመፃፍ ችሎታ ነበራት እንዴ…?እርግጠኛ ነኝ ይሄንን ማስታወሻ መፃፍ የጀመረችው እኔ ከጠፋው በኃላ አሜሪካ ለመሄድ በዝግጅት ላይ በነበረችበት አጭር ጊዜ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም….ግን እንደዛ ከሆነ ለምን ጥላው ሄደች…?.መልስ ላገኝለት ያልቻልኩት ጥየቄ ነው…ልጄ ቀጣዩን ክፍል መቼ ይሆን የምትልክልኝ…?የሚያስጨንቅ ጉጉት አደረብኝ፡፡

👍36❤9