አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አምስት ጅራፌን ጀርባዬ ላይ ጠጥቼ ሌሊቱን ያሳለፍሁት በሆዴ ተኝቼ ሳቃስት ነው አንዲት ኢትዮጵያዊት በወለደች በሁለተኛ ቀኗ
“ኧረ ስለነፍስ! ወገቧ ያልጠና ትኩስ አራስ አትግረፏት የፍርዷ
ውሳኔ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍላት ብንል የሚሰማን ጠፍቶ ከተፈረደባት ሃያ አምስት ጅራፍ ውስጥ አስራ ሰባቱ ብቻ አሰናበታት
ወንድዬ! በሷ ሞት ማንም ያዘነ የለም እሷም ለራሷ አላዘነችም ልጄን፥ልጄን … ብቻ እንዳለች ግልግል
ነው የሚባለውን ሞት ሞተች ልጅዋን አደራ ለማንም አልሰጠችም ሁላችንም አቅም የሌለን አደራ በላ ነን ጥሩ አደረገች  እንኳንም አደራ አላለችን አደራ ብትለን ኖሮ በመጨረሻዋ የመከራዋ መጀመሪያ ወይንም ማጠቃለያ አዝንባት ነበር
አብራን ኖራ እንዴት አቅማችንን ረሳችው' ብዬ እጠላት ነበር" ወንድማለም እምቦቀቅላዋ ከእኛ ከተገረፍነው ጋር ወህኒ ቤት ውስጥ ዐይኖቹ እንባ ተብሎ በጥቅል ስም  በሚጠራው ደም ተሞሉ" ዐይኑን ጨፍኖ: ደሙን አፍስሶ ንባቡን ቀጠለ።

ከተገረፍነው ጋር ስታለቅስ ዋለች ምርር ብለን ስናነባ
እሷም አብራን አነባች ከሁላችን ለቅሶ የዚያች ንፁህ ለቅሶ እንደ
ሬት መረረኝ እኛስ ባሳለፍነው ጥቂት ዓመታት የፈፀምነው ኃጢያት
ወይንም እርግማን ይኖርብን ይሆናል ይህች ሙጭቅላዋ ህፃን
ወንድዬ! እስኪ ምን አጠፋች? አንድ ጊዜ አንድ ፈረንሳዊ ደራሲ ያለው ትዝ አለኝ እግዜርን ማምለክና ካርታ ጨዋታ መጫወት
አንድ ነው ብሎ የፃፈው
እራስህን መድበህ ትጫወትና ከበላህ
እሰዬ ኪስህን በገንዘብ ትወጥራለህ ገንዘብ ደግሞ ኃይል ነው በራስህ እንድትተማመን እንድትኮፈስ ያደርግሃል እንደ ፅጌረዳ አበባ አይ ሲያምር ያሰኝሃል ሁሉ ወዳፍንጫው አስጠግቶ መዐዛህን ወደ ውስጥ እየሳበ ይረካብሃል ይክብሃል ይሽቆጠቆጥልሃል እንደ
በግ ገራም ሆኖ ይታከክሃል ጅራቱን እየቆላ ካንተ ያስቀድመኝ እያለ ይምልልሃል ሰው ብትበድል እንኳ የሳንቲም ሽርፍራፊ
ስለምትወረውር እሱ አፉ እንጂ ውስጡ የዋህ ነው እየተባልህ የሚማረርብህ የለም ከተበላህ ግን ያው ኪሎህ ስለሚቀንስ መሬቷ
እያንቀረቀበች ስታነፍስህ አንደበትህ ሁሉን ሲያበሳጭብህ
ሁሉ እንዳላዬ ፊቱን ሲያዞርብህ ውሾች ሊነክሱህ ሲጮሁ
በራስህ ከሌሎች ጋር ተባብረህ ኳስ አበደች እያልህ ስትጠልዘው
ህሊናህን እንደ ሽንኩርት እየላጥህ ስትጥለው ያንጊዜ እንደ አበቅ
የምትደፋበትን መፈለግ ነው እና! እግዚአብሔርን የምናመልከው
እንደ ካርታ ጨዋታው ብናተርፍ  ብለን ነው የገነትን ምቾት
ልንጎናፀፍ በለምለሙ መስክ ልንፈነጭ ካልሆነም ያው ሽ ቢታለብ በገሌ ለማለት እንጂ አንተ ወንድዬ እግዜር ካለ እውን
የረሃብና ጦርነት ምሳሌ እንዳደረገን ዘላለም ይኖራል? ዛሬ እንኳን
በቃችሁ አይለንም? ምሳሌው አይቀየርም?

"አንድ ጊዜ አዲሳባ እያለሁ አንተ አልነበርክም ብቸኝነት
እንደ ውርጭ ቤታችን ገብቶ
ገብቶ ሞላ.ውርጩ አጥንቴን ሲያኝከው ህቅ ብዬ አለቀስሁ በልጅነቴ ገነት ማለት የተዋበ
ልምላሜ የተሞላበት ይመስለኝ ነበር የኔ ጅል ከዚህ ውጭ ገነትን
የሚያስበው ማን አለ' አትበለኝ እንጂ" ገሃነም ግን አስጠሊታ ሆኖ ነበር የሚሰማኝ" ታዲያ የዛን ቀን ፀሐይ እንደ በዛበት ዋልካ መሬት ፊቴ የተሰነጣጠቀ እስኪመስለኝ ካለቀስሁ በሃዘን ኩምትርትሬ ከወጣ
በኋላ በኃሳቤ ወደ ሆነ ቦታ ተነጠቅሁ ገሃነም ውስጥ! ከማዶ ገነት አለ  እንዳሰብሁት ግን ሰፊ አልነበረም ጠባብ ነው ግን ያምራል እኔ ግን እንዲያ ዐይኔ እስኪፈርጥ  አልቅሼ: አልቅሼ የሄድሁት
ገሃነም ነው አይገርምም
ወንድማለም! ከዚያ የሚዘገንን ቆሻሻ ክምር ላይ በጭንቀት እንደቆምሁ ድንገት ትናንሽ አበቦች
ከትንሽነታቸው በስተቀር
ግን የሚያምሩ አየሁ
ወንድዬ! አሁን ሳስበው እነዚያ ትናንሽ አበቦች ተስፋ ናቸው ጥሩውን ብንመኝም
የምናገኘው ግን ያልተመኘነውን ነው ያልተመኘነው መጥፎ
ህይወት ላይ ግን ትንሽም ቢሆን የሚያምር ነገር አለ እና! እግዜርን ያን ትንሽ ነገር እንኳን አታሳጣኝ እያሉ መለመኑ አይሻልም ለዚህ
ለዚህ ወዲያ ውሰደው ብሎ ሐይሉ ዲካ የለውም ከሚባለው አምላክ ጋር
ከመጣላት ደግሞ
ነው!… ብሎ እንደ ጠረጴዛ
ኳስ ቢያድቦለቡለኝስ፣ መጫወቻ ሆኜ ተሰባብሬ  መቅረቴ አይደል!
ወንድማለም!- እግዜር ግን ምነው ዝምታው ይበዛል? እስኪ የእኛስ ይቅር ይህች
የዶሮ እግር የመሳሰሉ እግሮችዋን እጆችዋን
እያወናጨፈች እየተንቀጠቀጠች
በምታለቅሰው ጨቅላ ለምን
ጨከነባት? በናቷ ሃጢያት ይሆን? እሷማ አጠፋሽ” ለተባለችው ቅጣቷን ተቀብላ  አስራ ሰባት ጅራፏን ቀምሳ የለ! የቀራትን
ስምንት ጅራፍ በህፃኗ ላይ ለመጨረስ ካልሆነ? እዚህ የሚቀጣው እዛም ይቀጣ ይሆን! ወንድዬ ቢጨንቀኝ እኮ ነው መቀባጠሬ! ይልቅ
የሆነውን ልጨርስልህ

"ህፃኗ  ልቅሶዋ ሲቀጥል አንጀቴ አልችል  ብሎኝ  እኔም ከማለቅስበት እየተንፏቀኩ ሄጄ አቀፍኳት ትንሽ ናት ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታህል' እጅ እግር: ዐይን  ሁሉም የሰው ልጅ
ያለው አካል ሁሉ እጅግ ቢያንስም አላት ወደ ጡቴ አስጠግቼ እሹሩሩ
እያልሁ ልቅሶዬን ቀጠልሁ ትንሽዬ አፏን አሞጥሙጣ
የሚጠባ ነገር ፈለገች, እኔ ደግሞ ያለኝ ደም ነው የግርፋቱ" ካለነው
ውስጥ ካለደም ወተት ያለው ጡት አልነበረምህፃኗ እንደማልረዳት
ስታውቀው እሪታዋን ለቀቀችው ኣጀብናት
እኛም በር
በማይከፍተው ልቅሷችን ወተት በማይሆነው እንባችን: ክፍሉን
አጥለቀለቅነው በእንባ: በምሬት: ከዚያ ልረዳት ያልቻልኋትን
ህፃን ካነሳሁበት አንጋለልኋትና ተንፏቅቄ ራቅሁ ይኸውልህ! ከተኛሁበት ስነቃ ሁሉም የእስር ቤት ጓደኞቼ ተኝተዋል ወንድማለም!-
ሚሚም‥ ተስቤ ሄጄ አየኋት
እውነተኛውን እንቅልፍ አፏን
እንዳሞጠሞጠች
እንደ ራባት ...አንቀላፍታለች
ለምን ተፈጠረች?
ለምንስ እሷን ለመፍጠር ብዙ ተደከመ  ወንድዬ! ላትኖር ተሸክማ ዘጠኝ ወር ካለ አዛኝ: ካለ እረፍት
ስትማስን የኖረችው እናቷስ
ለምን በምጥ አቃሰተች? ለምን ደሟ ፈሰሰ: ለምንስ ነጭ ላብ አነባች?
አቤት የመከራችን ዓይነት ቢመዙት ቢመዙት መርዘሙ
እንደ ውቅያኖስ የተንጣለለው እንባችን ሐዘን በሸነቆረው አካላችን
ፈሶ ፈሶ አለማለቁ ... ወንድዬ! የጠዋት ቁርሴ በለቅሶ የተጣፈጠ ቅስም ሰባሪ ሀዘን ሆነ ..." አባቷ ስቅስቅ ብሎ አልቅሶ ማስታወሻዋን ከደነው" ከዚያ በላይ  ማንበብ አልቻለም ከዚያ በላይ
አልቻለም ከዚያ በላይ መቆም አልቻለም ከዚያ በላይ የመከራ ሬት መጠጣት አልቻለም! ዐይኖቹ ተጨፈኑ አካሉ ተጨመታተረ ደሙ ዐይኖቹን እንደ ቀይ ጃኖ እያለበሰ በጉንጮቹ ቁልቁል ተንኳለለ ግን ለምን? ልጆች እንዲህ
ከማይችሉት የመከራ
ውቅያኖስ በጮርቃ እድሜያቸው ይነከራሉ? እኮ ምን ጠፍቶ? ማነው የሚወቀሰው! የላይኛው ወይንስ የምድሮቹ ንጉሶች! የማይመለሰው ጥያቄ እንደ አቧራ እየተበተነ ከአየሩ ተደባለቀ!

💫ይቀጥላል💫
👍26👏4😢1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ ሶስት)
(ሜሪ ፈለቀ)


ኪዳን የመጠጥ ውሃ የሞላው ብርጭቆ ይዞ ወደሳሎን ብቅ ሲል ልቤ ወደቦታዋ ተመለሰች። እዚህ ድረስ ያለውን በድል ተወጥቼዋለሁ!! ብርጭቆውን ተቀብዬው ለደሳለኝ ከወገቤ ጎንበስ ብዬ በሁለት እጄ ሳቀብለው ጭራሽ የሚያወራው ተወነባበደበት። ጋዜጠኛው በሚሆነው ትርምስ ትዕግስቱ ነው ያለቀው። ኪዳን እየሆነ ያለው ነገር ግር ብሎት አይኑን ከወድያ ወዲህ ያንቀዋልላል። ወደጆሮው ጠጋ ብዬ «አምላክን በልመና አታድክም!! » አልኩት እና ጠቀስኩት።  ፈገግ ብሎ ደረቱን እንደመንፋት አድርጎ ጎምለል እያየ ዙሪያውን መቃኘት ጀመረ። አተኩሮ ላየው የሆነ ቁራጭ የፊልም ትወና እየከወነ ነው የሚመስለው። ሁሌም እንዲህ ነው! ከልጅነታችን ጀምሮ ከልጆች ጋር ተደባድቤ እኔ ከሆንኩ ያሸነፍኩት የፀቡ መሃል ሜዳ ይገባና ደረቱን ነፍቶ ይንቀባረራል። «ማን መሰለችህ? የእኔ እህት እኮ ናት!!» ይላል እየተጀነነ።

•  * * * * * * * * * * * * *

ድሮ ልጅ እያለን አባቴ እናቴ ላይ ሙድ የሚይዝበት መላው ነበር አሁን እኔ እና ኪዳን የምንግባባበት ኮድ። እናቴ ብር እጇ ላይ ቢኖርም ባይኖርም አለኝ አትለውም!! ብር ጨርሰሻል ወይ ብሎ ቀጥታ ከጠየቃት መልሷ ሁሌም አዎን ነው። በአቋራጭ ነው የሚያጣራው

«አስካል እንደው ከአባወራዎቹ ልደብለቅበት እስኪ መቀነትሽን ፈትሽልኝ!» ይላታል

«አይ እንግዲህ እንኳን ላንተ አምቡላህን መጋቻ ለልጆቼም የሚቀምሱትን ማሰናዳበት አልሞላልኝ» ትለዋለች

«ውይ በሞትኩት እናቴን! አያ ተካን አበድረኝ ልበለው ይሆን? እንደው ቸሩ መድሃንያለም ለልጆቼ የምሰጠው አታሳጣኝ» ይላል ወደላይ እንደማንጋጠጥ ብሎ በአንድ አይኑ እሷን አጮልቆ እያየ እና እያስተዛዘነ (ልበደራቸው የሚላቸው ሰዎች ስም ይቀያየራል)

«አይ እንግዲህ አምላክን በልመና ማድከም ደግም አይደል!! የምንችለውን እናደራርግና በተረፈው ማመስገን ነው። ያመሰገንነው አምላክ የጎደለውን ይሞላል!» ትለዋለች ልትወጣ ነጠላዋን እላይዋ ላይ እያደረገች። አለኝም እንዳትለው ለእሱ መጠጫ መስጠት አትፈልግም። የለኝም እንዳትለው ባሏ የሰው ፊት ሊያይባት ሲሆን በዘዴ አድበስብሳ! አባቴ እሷ ዞር ስትል ጠብቆ እየሳቀ

«እም! መች አጣኋት እናታችሁን? አላት ማለት ነው! አሁን ዘንቢል ሙሉ ሸምታ ትመጣ የለ? ምንአለ በሉኝ!» ይላል። እንዳለውም ከገበያ መዓት ነገር ሸማምታ ስትመጣ አባቴ ያላትን አንነግራትም ተያይዘን እንስቃለን!!

የእውነትም እጇ ላይ ብር ከሌላት መልሷ ይለያል። የአባዬ ጥያቄ ስሞቹንና አጠያየቁን ቀይሮ ያው ነው። የመጨረሻው <ለልጆቼ የምሰጠው አታሳጣኝ> የሚልበት ጋር ሲደርስ

«እንግዲህ አንድዬ ያውቃል!! እርሱ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድር!!» ካለች አባቴ አሁንም እሷ ዞር ስትል ጠብቆ

«አሁን የእውነቷን ነው የላትም ማለት ነው!!» ብሎ ከኛ ፊቱን አዙሮ ብር ይቆጥር እና « ገበያ ውረጅበት ብሎሻል! ብላችሁ ስጧት» ብሎ ለአንዳችን ያቀብለናል። ለምን እራሱ እንደማይሰጣት አሁንም ድረስ አይገባኝም!! ምናልባት ለእኛ ማስተማር የፈለገው ነገር ይኖር ይሆን ነበር። ሁሌም መልሷ እንዲሁ ነው። ሁሌም የእርሱ አጠያየቅ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው። ገና እሱ ሲጠይቃት በተለይ እኔ ሳቄ ይመጣል። ለእማዬ <እየፈተነሽ ነው!> አልላትም!! ለትንሿ ልቤ የእነርሱ የፍቅር ቋንቋቸው መሆኑ ገብቷት ነው መሰለኝ በተለይ የሌላት ጊዜ እሱ ሲያዝንላት ልቤ በሙቀት ቅልጥ ትላለች።

ከኪዳን ጋር ልጆች ሆነን እናታችንን የምናስታውስበት አንዱ ጨዋታችን ነበር። አድገን የህይወት ውጥንቅጥ ውስጥ የተነከርን ጊዜ ደግሞ ምልክት መሰጣጫችን ሆነ። ያለንበት ሁኔታ ተስፋ ያለው፣ መውጫ ያለው ፣ ደህንነታችን ጥሩ ሁኔታ ላይ ከሆነ። «አምላክን በልመና አታድክሚ….. » የምትለዋ! ለምሳሌ ባለፈው ኪዳን እንዳለኝ « ደህና ነኝ አታስቢ! አልጎዱኝም!! ተረጋግተሽ መላውን ፈልጊ!»  እንደማለት ነው!! ወይም ደግሞ « አንድዬ ያውቃል» ብዬ መልዕክት ካደረስኩት «እንዳትደውልልኝ፣ በምንም መንገድ ልታገኘን አትሞክር! ያለሁበት ሁኔታ ሲሪየስ ነው!!» እንደማለት ነው። እንደገባንበት ማጥ መልእክቱ ይለያያል። እኔ እና እሱ እንግባባበታለን!! በደፈናው ያለንበትን ሁኔታ አስከፊነት የምንለዋወጥበት ነው።

•                   
•  * * * * * * * * *

ጋዜጠኛው ከዚህ በኋላ ላይቭ እንዳለ ሊቆይ የሚችለው ከ2 ደቂቃ አይበልጥም!! እንደየትም ብሎ ቢያራዝምልኝ ሊጨምርልኝ የሚችለው 1 ደቂቃ ነው። በዛ 2 ደቂቃ ደግሞ መኪናችን ጋር መድረስ አለብን። ለጋዜጠኛው ተጨማሪ ደቂቃ ማስረዘም ከቻለ ምልክት ሰጠሁት። ትከሻውን ሰበቀ። እሞክራለሁ እንደማለት ነገር።

«አንቺ እስከበሩ ትሸኝናለሽ እኮ!!» አልኳት ሚስትየውን። ባሏ አፉ እዛ ይለፍልፍ እንጂ አይኑም ቀልቡም እኛጋ ነው። ባይገባትም እየመራችን ወጣች። በፍጥነት ወደአጥሩ በር እየተጓዝኩ

«ልትከተሉኝ ብታስቡ! መንገዴ ላይ የሆነ ነገር ልትፈጥሩ ብትሞክሩ ውርድ ከራሴ!! ወጥተሽ ጋዜጠኞቹ መኪና ውስጥ ገብተሽ ማረጋገጥ ትችያለሽ!! አሁን ላይቭ እየተላለፈ ያለው የባልሽ ቃለመጠይቅ ብቻ ነው። አንዲት ዝንፍ ያለች ነገር አደርጋለሁ ብላችሁ ብትሞክሩ እዛ መኪና ውስጥ ያሉት ባለሞያዎች አንድ በተን ብቻ ነው መጫን የሚጠበቅባቸው። ቤትሽ እያንዳንዱ ክፍል ካሜራ አስቀምጫለሁ!! እየሆነ ያለው ነገር አሁን እኔና አንቺ የምናወራውም ምስል ሳይቀር ሪከርድድ ነው። መኪናዬ በስህተት ጎማዋ ቢቀንስ አልኩሽ ሁሉንም ምስል ገጣጥሞ ዜና ማዋቀር አይከብድምኣ? ቻው! መልካም እድል በይልኝ ባልሽን!! እም ጷ» በእጄ የመሳም ምልክት አሳይቻት ራሷ ለዘበኞቹ እንዲያሳልፉኝ ምልክት ሰጠቻቸው እና እኛ ስንወጣ

«ቱ » ብላ በንዴት እና በጥላቻ ምራቋን ስትተፋ እሰማታለሁ። እኔና ኪዳን በሩጫ መኪናችን ውስጥ ስንገባ ጋዜጠኛው የላይቭ ስርጭቱን ጨርሷል። ከአካባቢው እስክርቅ ድረስ በማይነዳ ፍጥነት እየነዳሁ ምንም ቃል ሳልተነፍስ ሸመጠጥኩት። ብዙ እርቀን እንኳን እንዳልተረጋጋሁ ያወቅኩት ኪዳን

«ሜል በፍፁም እዚህ ድረስ ሊከተሉሽ አይችሉምኮ!» ሲለኝ ነው።

«አይችሉም ብሎ ተዘናግቶ ወጥመዳቸው ውስጥ ከመውደቅ ሊሞክሩ ይችላሉ ብሎ መጠንቀቅ ነው የሚያዋጣው!! አታውቃቸውም እስከምን ጥግ መሄድ የሚያስችል ጭካኔ እንዳላቸው።» እጁን ሰዶ ትከሻዬን ዳሰስ ዳሰስ ሲያደርገኝ ዞሬ አየሁት። የናፍቆቴ መጠን እየሆኑ በነበሩት ክስተቶች ተከድኖ እንጂ ገደቡን የጣሰ እንደነበር የገባኝ ዓይኖቹን ሳያቸው ነው። መኪናዬን ጥጉን አስያዝኩት እና አቀፍኩት!!

«ለምን መጣህ? በዝህች ዓለም ያለኝ ብቸኛ ነገሬ አንተ መሆንህን አታውቅም? የሆነ ነገር ሆነህብኝስ ቢሆን? ሰው እንደማልሆን አታውቅም?» ቁጣም ፍቅርም እንባም ሳግም ያንቀረቅቡኝ ጀመር። ያውቀዋል ስስቴን!! ሁሌም እየተቆጣሁት ወይ እየጮህኩበት ሳለቅስ አይመልስልኝም። ስረጋጋ ነው ምክንያቱን የሚነግረኝ!!

«ይቅርታ ሜል! ይቅርታ እሺ!» አለኝ ከእኔ በላይ አጥብቆ አቅፎኝ እያባበለኝ!! መረጋጋቴን ሲያይ!!
👍241
«ብዙ ጠበቅኩሽኮ ሜል! አንድም ሶሻል ሚዲያ አካውንትሽ አክቲቭ አይደለም!! ካንቺ ሳልሰማ ብዙ የቆየሁበት ቀን 12 ቀን ነው መጀመሪያ የታሰርሽ ጊዜ!! ቢያንስ እንዳላስብ በሰው ትልኪብኝ ነበርኮ!! ቢቸግረኝ መልዕክት ላኩልሽኮ (ትዝ አለኝ! ቁጥሩ ከማይታይ ላኪ ላመስግን ወይስ ልፀልይ? የሚል መልዕክት ስልኬ ነበረው! ስላልገባኝ እንጂ!! ምንም ቢፈጠር የምደውልለት እኔ ነኝ እንጂ እሱ እንዳይደውል ህግ አለን!! ስልኩን በቃሌ ነው የማውቀው እንጂ ሴቭ አላደርገውም!!)

…… በእኔ አስችሎሽ በጤናሽ ሁለት ወር እንደማትቆዪ አውቃለሁ። እኔስ አንቺን ባጣ ሰው እንደማልሆን አታውቂም? ከዛ በላይ መጠበቅ አልችልም ነበር ትኬቴን ቆርጬ መጣሁ!! የያዝኩትን ሻንጣ የያዝኩት ሆቴል ክፍል ወርውሬ ልብሴን እንኳን ሳልቀይር ማንን መጠየቅ እንደነበረብኝ እርግጠኛ ስላልነበርኩ እቤት መሄዱ አደገኛ ሊሆን ስለሚችል ብዬ ክለቡጋ ሄድኩ!! መምጣቴንም እዛ መሆኔንም ማን እንደነገራቸው አላውቅም!! ከዛ ወጥቼ ታክሲ ልይዝ ስጠብቅ መጥተው በመኪናቸው ከበቡኝ!!»

«ቆይ ቆይ ቆይ (ከእቅፉ ወጣሁ!) ክለብ ማንን አገኘህ? ማንን አናገርክ? ስንት ሰዓት ነው የሄድከውስ?»

«አመሻሽ ነገር 11 ወይ 12 ሰዓት ገደማ!! ብዙ ሰው ነበርኮ እኔእንጃ!» አለኝ ግራ እየገባው።

«ከበር ጀምሮ ያናገርከውን ሰው አንድ በአንድ ንገረኝ!! ለማስታወስ ሞክር!» እያልኩት መኪናውን አስነስቼ መንዳት ጀመርኩ።

«ጋርዶቹን? መግባት አይቻልም ሰዓት ገና ነው ብለው እንቢ አሉኝ መጀመሪያ እ ….. ከዛ አንቺን ፈልጌ እንደሆነ ከካናዳ የተላከ ዕቃ ላደርስ እንደሆነ ነገርኳቸው እና ከውስጥ የሆነ ሰው ጠርተው አገናኙኝ። ከዛ ለእነርሱ የነገርኳቸውን ስነግረው ሄደሽ እንደማታውቂ …. አንድ ቀን ብቅ ብለሽ እንደነበር ነገረኝ። የግድ ማድረስ ያለብኝ እቃ አለ ስለው እሱም ገብቶ ዳዊት የሚባል ሰው ጠራልኝ። ፍቅረኛሽ መሆኑን ነገረኝ (እዚህጋ የአይመስለኝም ሽርደዳ ያለበት ፈገግታ ፈገግ ብሎ በቁም ነገር የሚያወራውን እየተከታተልኩ እንደሆነ ሲያውቅ ወደ ቁምነገሩ ተመለሰ።) እሱ ወደ ውስጥ እንድገባ ጋበዘኝ እና ከዛ በቃ ያልታወቀ ሰው በሽጉጥ መትቶሽ እንደነበር ከዛም ድጋሚ ከሰዎች ጋር ተጣልተሽ እስከሆስፒታል የሚያደርስ ጉዳት ደርሶብሽ እንደነበር እና እቤት እንደማገኝሽ ነገረኝ።»

« ከኤርፖርት ሆቴልህ? ከሆቴልህ ክለብ? በመሃል የሄድክበት ቦታ አለ? አስታውስ? ያናገርከው ሰው? ሁለቴ የገጠመህ ሰው?»

«ሜል? እኔን ታውቂኝ የለ? ጀርባዬን እያየሁ የምሄድ ሰውኮ አይደለሁም!! ግን ማንንም አላገኘሁም!! ከዛ ውጪ የትም አልሄድኩም! ያናገረኝም ያናገርኩትም ሰው የለም ከሪሴፕሽኖቹ ውጪ!!» አለኝ ተጨንቆ

«ክለብ ውስጥ ሌላ ማን ነበር?»
«የሚሰሩ ሰዎች ነበሩ!! ቤቱን እያስተካከሉ ምናምን የነበሩ እኔ እንጃ በደንብ አላስተዋልኩም ግን ሴቶችም ነበሩ!!»

«ስምህን የነገርከው ወይም የእኔ ወንድም መሆንህን የነገርከው ሰው አለ?»
«ለዳዊት! ስሜን ነግሬዋለሁ ግን ያንቺ ወንድም መሆኔን አልነገርኩትም!! ዳዊት እባላለሁ ሲለኝ ኪዳን! ብዬዋለሁ!!»

«ምን ያህል ይሆናል ውስጥ የቆየኸው?»
«እኔ እንጃ አንድ ሰዓት!! የሚጠጣ ጋብዞኝ አንድ አንድ ብርጭቆ ይዘን ነው የሆነውን የነገረኝ!! ይኸው ጀመረሽ ነገር ስትቀምሪ መሃል ቤት እኔን የምታጦዥኝ ነገርሽ!»

«ጥርጣሬ እንጂ ያረጋገጥኩት ነገር ስለሌለ ልነግርህ አልችልምኮ ኪዳንዬ! መጠጡን የጋበዘህ እሱ ነው? አልጠጣም ብለኸው ነበር? እንድትጠጣ ወተዋተህ?»

«አይ እውነትም ፍቅረኛሽ ነበር በሚገባ ነው የምታውቂው!! አዎ አልጠጣም እቸኩላለሁ ስለው። <እዚህ ድረስ መጥተህ ሳላስተናግድህ መሄድህን ሜሉ ብትሰማ ትቀየመኛለች፤ አንድ ብርጭቆ ይዘን የሆነውን ላውራህ አለኝ!!»

«ይሄ የውሻ ልጅ!! እውነት ባይሆን ነው የሚሻለው እንጂ አልለቀውም! (ይሄ ጤነኛ ንዴት ይሆን አልገባኝም! ጭንቅላቴ ከውስጥ የተወጠረ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ የሆነ ሊፈነዳ የቀረበ ነገር። ደረቴ ላይ እልህ እና ቁጣ ከትንፋሼ ጋር እኔ ልውጣ እኔ ልቅደም ግብ ግብ የገጠሙ አይነት ስሜት) ይሄ ሙት እሱም ሰው ሆኖ መሆኑ ነው?» ኪዳን እየሆነ ያለው ግራ ገብቶት

«ሜል? እሱ ደውሎላቸው ነው የመጡት ብለሽ ነው የምታስቢው? ከአጠገቤኮ ለአፍታም ዞር አላለም ነበር። ኸረ በፍፁም እንዲህ የሚያደርግ ሰው አይመስልም! ግማሹን ሰዓትኮ እንዴት እንደሚወድሽ ነው ሲነግረኝ የነበረው። ደግሞ ፍቅሩ አይኑ ላይ ያስታውቃል። ምንም ከማድረግሽ በፊት አጣሪ እህትዬ በእኔ ሞት? እ?»

«ሌባ አይኑ እና ቅቤ ምላሱ አይሸውድህ!! በእርግብ ላባ ያጌጠ እባብ ነው!! ታውቀኛለህ ደግሞ ባልተረጋገጠ ነገር ምንም አላደርግም!!» እያልኩት ስልኬን አውጥቼ ደወልኩ!!

«ሻለቃ! ሜላት ነኝ!!»
«ሜላት ሜላት?»
«አውቀኸኛል ባክህ! እንዴት አስታውሳ ደወለች ብለህ ከሆነ ግራ የተጋባኸው አዎ አስታውሼ ነው!! አደጋ የደረሰብኝ ቀን ለኤግዝቢትነት በሚል የወሰዳችሁትን ስልኬን መረጃውን ከውስጡ አፅድታችሁ እንደመለሳችሁልኝም ጭምር ነው ያስታወስኩት! ለሶስተኛ ወገን አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ ማለቴ ሸጣችሁ የግሌን መረጃ እንደነገዳችሁበትም ጭምር!! ልቀጥል?»

«ምን እንደምታወሪ ታውቂዋለሽ? ወይስ ጥይቱ ሚሞሪሽን ብቻ ሳይሆን ማሰቢያሽንም ነው የወሰደው?»

«ምን እንደማወራ አሳምረህ ታውቃለህ!! ፌስቡኬ የእኔ መሆኑን ሰይጣን እንኳን አይደርስበትም። ድንገት እኔ በተመታሁ በነጋታው 10 ዓመት ሙሉ ማን መሆኔ ሳይታወቅ የተጠቀምኩበት አካውንት በአስማት ታወቀና ዘጉት ነው የምትለኝ ያለኸው? ኦው ለምን ስልኬን እንደሚፈልጉት አልነገሩህም ማለት ነው?» ዝም አለ ለአፍታ

«የውልህ! በጣም በተቻለኝ አቅም ጥሩ ሴት ልሆን እየሞከርኩ ያለሁበት ሰዓት ላይ በመሆኑ ፈጣሪህን አመስግን!! ከናንተ ጋር አውጫጭኝ የምጫወትበት ጊዜ የለኝም!! አንድ መረጃ ብቻ ነው የምፈልገው!! የመታኝን ሰው ማወቅ ነው የምፈልገው!! መሃል ከተማ ነው! አመለጠ ምናምን በሚል ተረት ተረት እኔን አትሸውደኝም!! ግማሽ መንገድ ላግዝህ?  ጥቁር ጃጓር መኪና የጎማው ቸርኬ ወርቅማ ፣ ከኋላው መስታወት በቀኝ በኩል ጠርዝ ላይ ትንሽዬ ቀይ ስቲከር ያለበት፣ ታርጋ ቁጥሩ የመጨረሻ ሁለት ቁጥር 52 ነው!! እኔ ሁለት ጥይት መትቶኝ ይሄን ሁሉ መረጃ ስቶር ማድረግ ከቻልኩ ምርመራውን የያዘው ወይም ይዞ የለቀቀው ባልደረባህ በአንድ ሰዓት ውስጥ ሙሉ መረጃውን ጠረጴዛህ ላይ ማኖር አይቸግረውም!! ሌላው ደግሞ ሴት ናት!! ወንድ ለመምሰል የሞከረች ሴት ናት!! መኪናው በማን ስም እንደተመዘገበ እና ሴትየዋ ማን እንደሆነች ብቻ ነው ማወቅ የምፈልገው። ከአንድ ሰዓት በኋላ እደውልልሃለሁ! ከዛ ቀድመህ አሁንም ቢሆን የምትነግረኝ ነገር ካለህ ግን ዝግጁ ነኝ!!» ዝም አለኝ። ስልኩን ዘጋሁት!! እና ወደኪዳን ዞሬ

«ያረፍክበት ሆቴል ደውል እና ሻንጣህን መውሰድ እንደምትችል አረጋግጥ!! የምታርፍበት ሌላ ቦታ እንፈልጋለን። ለጊዜው እኔም ወደቤት መሄድ ያለብኝ አይመስለኝም!!»


«በእንዲህ ዓይነት ሰዓትኮ ሌላ የማላውቃት ሴት ነው የምትሆኝብኝ!! ውስጥሽ ሁለት ሴት ያለች ነው የሚመስለኝ! የእኔ ሜል እና የሌላ ሰው ሜላት! የእኔዋ እናት፣ እህት፣ ስስ ፣ የምታለቅስ ፣ የምታቅፍ ፣ የምታባብል ፣ ቀድማኝ የምትሞትልኝ …….. ያችኛዋ አያድርስ ነው!! » አለ ኪዳን በመገረም ሲያየኝ ቆይቶ!!
👍13🥰2
«መሸነፊያዬም መጀገኛዬም አንተ መሆንህን አታውቅም? ባንተ ሲመጡብኝ ነው እጅ የምሰጠውም አውሬ የምሆነውም! ያን ታውቃለህ አይደል?»

«አውቃለሁ ሜል። ግን አሁንኮ ትልቅ ሰውዬ ነኝ!! ሚስትኮ ላገባ እየተሰናዳሁ ያለው ግብዳ ሰውዬ ነኝ! እስከመቼ ነው የምትጠብቂኝ? (ዞር ብዬ ያለፉትን ቀናት እንደማስታወስ ሳየው) ይሄ የተለየ situation ነው። እንዲህ ያለ አጋጣሚ ከተፈጠረማ በድዴም ቀርቼ እንደምትደርሺልኝ አውቃለሁ። ገብቶሻል ምን ማለት እንደፈለግኩ!! መቼ ነው አንቺ የራስሽ የሆነ ህይወት የሚኖርሽ? ለእኔ ብለሽ ፣ ለአባዬ ብለሽ ወይም ለእማዬ ብለሽ የማትኖሪው። ለሜላት ብለሽ የምትኖሪው ቀን መቼ ነው? (ይሄን ሲለኝ ስለእማዬ ለካ መንገር አለብኝ። ምን ብዬ ነው የምነግረው? የሞተችዋ እናታችን ከሞት ተነሳች! ነው የምለው?)  ደግሞ አባት ልሆንልሽ ነው!» ሲለኝ ስለእማዬ ያሰብኩት ጠፋብኝ። መኪናውን አቆምኩ።

«ሊንዳ እርጉዝ ናት? ስንት ወሯ ነው?» እያልኩት እሺ የአሁኑ እንባ ምን የሚሉት ነው? እንደትናንት በሚመስለኝ የቀናት ርዝመት ውስጥ እግሬ ላይ ተጠምጥሞ ትተሽኝ አትሂጂ ብሎ የሚያለቅስ ትንሽዬ ልጅ ነበርኮ!! አባቱ የሞተበት እናቱ ትታው የሄደች ቀንኮ <አባዬ ዳቦ ገዝቶ ሲመጣ ዳቦ በሻይ ነው የምበላው እንጀራ አልበላም!> ብሎ ያለቀሰ የአባቱ ሳጥን ውስጥ መቆለፍ ያልገባው ሚጢጢ ነበረ።

«ስድስት ወር ሆናት! ሴት ናት!» አለኝ እንደመኩራትም እያደረገው። ዝም አልኩ!! ዝምታዬ ውስጥ ግን ብዙ ጩኸት ነበረ። ደስ የሚል ከዛ ደግሞ የሚከፋ ስሜት እንዴት ተብሎ ይብራራል? የእኔ ኪዳን ፣ ልጄ ፣ ታናሼ ፣ ዓለሜ ፣ ብቸኛ የዓይን ማረፊያዬ አደገልኝ!! እሱ አድጎ ልጅ ሊያሳድግ ነው!! እንዲኖረው የተመኘሁለትን እና የተመኘውን ሁሉ አንድም ሳይጎድልበት አግኝቷል። በህይወቴ ትልቁ ድሌ እና ስኬቴ እኮ እሱ ነው!! ከዛ ግን ለምን የመከፋት ስሜት ተሰማኝ? ለእሱ ደስ አለኝ ለእኔ ግን ከፋኝ። የሆነ እዝህች ምድር ላይ ለመኖር የመጣሁበትን ዓላማ የጨረስኩ ፤ የምኖርለት ምክንያት ምንም ያልቀረኝ ፤ ከዚህ በኋላ እኔ የማላስፈልገው ፤ የራቀኝ ዓይነት ስሜት ተሰማኝ። ይሄን ግን ለእርሱ ልነግረው አልፈለግኩም። ደስታው ትንሽ እንኳን እንዲደበዝዝበት አልፈልግም!! አቅፌው እንባዬን እየጠረግኩ ደስ እንዳለኝ ነግሬው መኪናዬን መንዳት ጀመርኩ። ሆቴሉ ደውለን ሪሴፕሽን እቃውን እንዲያስቀምጡልን አድርገን። የሚከፋፈለውን ከፍለን ሻንጣውን ወሰድን። ለአፍታም ቢሆን ከእኔ እይታ ዘወር እንዲል ስላልፈለግኩ ሆቴል ከመያዛችን በፊት ጎንጥን ለማየት ወደሆስፒታል ነዳሁ።

«የእኔ ኪዳን? አውቃለሁ ታጥበህ ልብስ ለመቀየር እንደቸኩልክ!! ለትንሽ ደቂቃ ሆስፒታል የሆነ ሰው ጠይቀን እንመለስ እና ደግሞም የምነግርህ ትልቅ ነገር አለ።» አልኩት በመንገዳችን።

«ምንድነው እሱ? የምነግርህ ትልቅ ነገር ስትዪ ሁሌም የሚከተለው ደስ የማይል ነው!! ምንድነው እሱ? ምን ልታደርጊ ነው? ደህና ነሽ አንቺኣ?»

«ኸረ ጭራሽ እንደሱ አይነት ነገር አይደለም!! እንደውም ደስ የሚል ነው መሰለኝ! ቢያንስ በግማሽ!»

ጎንጥ የተኛበት ክፍል ስንገባ ትንፋሹን ሰብስቦ የሆነ መርዶ እየጠበቀ ያለ ይመስል ነበር። ከሆዱ ድረስ ትንፋሹን ስቦ በረጅሙ የመገላገል ዓይነት ተነፈሰ እና ፈገግ አለ።

«ነፍሴን እኮ አወክሻት ዓለሜ? ከቤቱ ወጣች ካሉኝ ቆየ!! ስትዘገዪ ከመንገድ ምን አገኘሽ ብዬ ነፍሴ ከስጋዬ ልትለይ?» አለ የመጨረሻውን ዓረፍተ ነገር መልስ ባልጠበቀ ጥያቄ ዓይነት አስረዝሞ!! ማለት የፈለግኩት የነበረው <ልቤንኮ በረደኝ! እጄን ያዘኝ! ጦሽ ብዬ ላልቅስና! ኸረ በመድሃንያለም ነፍሴን አታስጨንቂያት! እያልክ አባብለኝ!> ነው። ያልኩት ግን «የኪዳንን ሻንጣ ልናመጣ በዛው ሄድን! ይቅርታ ቢያንስ መልዕክት እንኳን መላክ ነበረብኝ!»

ኪዳን አንዴ እኔን አንዴ እሱን <እየሆነ ያለውን ነገር አንዳችሁ ትነግሩኝ> በሚል አስተያየት ያየናል።

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍275
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አምስት

////

አሁን ወደ ቤቴ ልሄድ ወሰንኩና ወደ እሷ ዞርኩ ...እና አሁንም በድጋሜ ከፊል  እርቃኗን ስመለከት እርብድብድ አልኩና"አይ በዚህ ሰአት ዘበኞቹ ሰለሚተኙ ግቢውን አይከፍቱልኝ ይሆን እያልኩ እያሰብኩ ነው።››

"ነውእንዴ? ታዲያ እዚህ እደራ!!"ብላ ዘጭ ያለው ሞራሌን መልሳ ሰማይ ሰቀለችው..፡፡እያንቀጠቀጠኝ የነበረው የውስጥ ቅዝቃዜ ከውስጤ እየተወገደ በምትኩ ሙቀት ሲራወጥ ታወቀኝ፡፡

"ይሻላል?"

"አዎ ..ችግር የለውም...፡፡አለችና አንሶላውን እና ብርድ ልብሱን ገልጣ ከውስጥ ገባች...፡፡እኔም በአፌ ምራቅ እየሞላ ጫማዬን ማውለቅ ጀመርኩ፤ ሸሚዜን አወለቅኩ፤ፓክ አውቴንም አልተውኩ አወለቅኩ፤ በመጨረሻ ሱሪዬን አወለቅኩና ልክ እንደእሷ በፓንት ብቻ ወደ አልጋ ላይ እየተስገበገብኩ ወጣሁ።..እያየኋት ብርድልብሱን  ወደእኔ ገፋችና  በአንሶላና አልጋልብሱ ተጠቅልላ አንደኛውን ጠርዝ ይዛ ተኛች ..

"ብርድልብሱን ልበስ..ደህና እደር"ብላኝ መብራቱን አጠፋችና ለሽ...፡፡

"እንደተባልኩት በብርድ ልብሱ እርቃኔን ጠቅልዬ ለመተኛት ሞከርኩ...፡፡ምን አይነቱ እንከፍ ነኝ እስኪ ደህና እደር እንዳለችኝ ያልሆነ ነገር ከምቀባጥር በክብር ፈጠን ብዬ ይሄን ክፍል ለቅቄ ብወጣስ?...እሷ እያንኮራፍች ነው፤እኔ ግን ..?እኔማ በሁለት እጇቼ እንትኔን አፍኜ ይዤ እየተገለባጥኩ ነው።በግድ ጉብ ልበልባት ይሆን ?አይ ይሄ  አይሆንም ጓደኞቼ በፓለቲካ ምክንያት ታስረው ጀግና ሲባሉ እኔ በአስገድዶ ደፈራ ሀያ አመት ....አይ መታገስ መልካም ነው፡፡እኔ ደግሞ በትግስት አልታማም ..በእፅዋት ሳይንስ ከሀረማያ በዲግሪ ተመርቄ አዲስአበባ ላይ በአስተናጋጅነት ተቀጥሬ በመስራት ኑሮዬን እየገፋሁ ያለው ትሁት ትዕግስተኛ። ከዚህ በላይ ትግስት ምን አለ...?በተወለድኩባት አዲስአበባ ከተማ  በተማርኩበት ሞያ ስራ ለማግኘት ከአመት በላይ በየመስሪያ ቤቱ  ተንከራተትኩ ..ምንም ጠብ ያለልኝ ነገር የለም...አንድ መስሪያ ቤት ጋምቤላ ልላክህ ይላል...ሌላው ጋ ስሄድ የበጋ ስንዴ ፕሮጀክት አርሲ ላይ አለን እዛ እንላክህ ይለኛል።"ምነው ውትድርና የሰለጠንኩ መሠላቸሁ እንዴ? "ብዬ በእነሱ ይሁን በራሴ እያላገጥኩ አላውቅም ሁሉንም እርግፍ አድርጌ  ያለሞያዬ ስባክን ይሄው ይሄን የመሠለ ፈተና…..

የባጥ የቆጡን ሳስብ ምንጊዜ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም፡፡ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስደኝ፡፡ ….....የበር መንኳኳት ነበር ከእንቅልፍ አለም መዞ ያወጣኝ
‹‹...ማነው? ምንድነው ?››በርግጌ ተነሳው፡፡

"ፅዳት ነው ሰዓት ደርሷል"

"ፅዳት "ዙሪያ ገባውን ቀኘሁ፡፡ነግቷል፡፡ክፍሉ ባዶ ነው.፡፡.ልጅቷ የለችም...፡፡ልብሷቾም ሆነ ዕቃዋቾ የሉም...፡፡ጠረኗ ብቻ ነው ያለው...፡፡ሄዳለች ማለት ነው..፡፡.ምኑ እንክርፍፍ ነገር ነኝ በፈጣሪ...?ምን አለ በጥዋት ተነስቼ ቢያንስ ለመጨረሻ ጊዜ እነዛን አይኗቾን ማለቴ መቀመጫዋን አይቼ በተሰናበትኳት...፡፡በንዴት ከላዬ ላይ ብርድ ልብሱን አሽቀንጥሬ  ከላዬ ላይ ወረወርኩ፡፡ ...ከአልጋው ወረድኩ… ጠረጴዛ ላይ ያለውን ልብሴን ሳነሳ የሆኑ ባለመቶ ብር ድፍን ብሮች  እና ብጣሽ ወረቀት ድብ ብሎ ወለል ላይ ወደቀ...ብሩን ተውኩና ወረቀቱን አነሳሁት አነበብኩት።

‹‹ደህና ሁን ቆንጇ...ቁርስ በእኔ ነው"ይላል ...
ብሩን አነሳሁና ቆጠርኩት 500 ብር ነው፡፡
‹‹እኔን ብሎ ቆንጆ›› አልኩና በቅጡ እንኳን ልብሴን አስተካክዬ ሳለብስ  በንዴት ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ፡፡

ከውስጤ እየተንቀለቀለ ያለው ንዴት በቀላሉ ሊበርድልኝ ስላልቻለ እቤቴ ስደርስ እንኳን የበራፍ አከፋፈቴና አዘጋጌ ኃይል የተቀላቀለበት ነበር ፡፡

‹‹አንተ ቀልማዳ….››

‹‹አቤት አያቴ››

‹‹የትአባህ ነው ያደርከው…?ሰው ያስባል አትልም እንዴ…?ከአሁን አሁን መጣ እያልኩ ቁጭ ብዬ እኮ ነው ያደርኩት››

‹‹ውይ በጣም ይቅርታ ..ጋሼ ስራ አዞኝ እስከ 9 ሰዓት ስሰራ ስለነበር ደከመኝና እዛው ተኛሁ፡፡››

‹‹እና ሮጥ ብለህ አንድ አፍታ መጥተህ ላድር ነው ብትል የትኛውን ድንበር ስታቆርጥ ነው››ጠንከር ባለ የንዴት ቃና ሲቆጡኝ እንባዬ በአይኔ ሞላ ..ተበሳጫቼ  አይደለም..፡፡ይሄን ያህል የሚያስብልኝ ሰው ይኖረል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበረ…፡፡
‹ሁለተኛ አይለመደኝም››ቃል ገባሁ፡፡
‹ፍፅምዐእንዳይለመድህ .
ትደግመውናትጣላኛለህ
.በል አሁን እንደደካከመህ ድምፅህ  ያስታውቃል ትንሽ ተኛ፡፡››

‹‹እሺ አያቴ›አልኩና አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ፡፡

‹‹ዜና ወርቅ… ›
›.‹‹የዜናወርቅ አዎ እንደዛ ብላ ነበር ስሟን  የነገረችኝ…ለዛም ይመስለኛል የዜናወርቅ የሚለው ስም ከእምሮዬ ሞልቶ እየፈሰሰ ያለው….
‹‹ወይ ጉድ ፍቅር ስለሚለው ቃል እራሱ ያሰብኩት ከስንት ጊዜ በኃላ መሆኑ ነው…?አዎ ከስድስት ረጂም አመት በኃላ …፡፡ ፍቅርን እርም ብዬ ነበር…፡፡ልክ እየደጋገሙ እየተንበገበገ ባለ እሳት እጣቱን ከተው እስኪቆስልና ቆዳወ እስኪገሸለጥ ድረስ እያቃጠሉ እንዳስፈራሩት ልጅ አይነት ነበርኩ፡፡.አዎ ፍቅርን የምፈራው ልክ ያ ህፃን ልጅ እድሜ ልኩን እሳትን በሚፈራበት መጠን ነው፡፡እና ጊዜያዊ ስሜቴን ማስወገድ አለብኝ.››.አስቤ አስቤ ሲደክመኝ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡

‹‹ወይ ዝም ብዬህ ቻው እንኳን  ሳልልህ ሄድኩ አይደል?››

‹‹አዎ…ግራ አጋባሺኝ እኮ››

‹‹አይ አስቸኮይ ነገር ስላጋጠመኝ ነው .ይቅርታ››

‹‹አይ ምንም አይደል…ግን እቤቴን ማን አሳየሽ? ››

‹‹አለቃህ…ማለቴ የሆቴሉ ባለቤት ለመነኩትና ከአንድ ጩጬ ጋ ላከኝ፡፡››

‹‹እሺ የቤቱን በራፍስ ማን ከፈተልሽ...?እኔ ተኝቼ ነበር››

‹እሱን ተወው .በመምጣቴ አልተደሰትክም እንዴ?››

‹‹አረ በጣም ተደስቼያለሁ…ነገሮች ድንገተኛ ስለሆኑብኝ ግራ ተጋብቼ ነው››

‹እንደዛ ከሆነ እቀፈኝ››

‹‹እሺ…ይሄው….ወደራሴ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት…››

‹‹እዬብዬ.›በተሰባበረ እና በሚያቃትት ድምፅ ጠራችኝ፡፡

‹‹ወዬ ዜናዬ.››

‹በጣም ሞቀኝ…ልብሴን ላውልቅ››

‹አዎ አውልቂ…. እንደውም እኔም ላውልቅ.››አልኩና እኩል እየተረዳዳን  ልብሳችንን አወለቅንና እርቃናችንን ተመልሰን እቅፍቅፍ ብለን ተጋደምን….፡፡እርቃናችን ሲፋተግ እሳት ፈጠረ..ነደድኩ… ከንፈሯ ላይ ተጣበቅኩባት…ጭኗን ፈለቀቅኩና ሰርስሬ ከመሀል ገባሁ….ቃተተች…‹‹ወይ የእኔ ጀግና ጎዳኸኝ….ቀስ በል..አመመኝ›››
በእጆቼ አፏን አፈንኳት..እንደዛ ያደረኩት የዜናወርቅን የመቃተት ጩኸት አያቴ እንዳይሰሙንና እንዳይረበሹ ስለፈራሁ ነው፡፡እንኳን እንዲህ የምትቃትት ሴት ይቅርና ጮክ ብሎ የሚያወራ ወንድ ጓደኛ  እዚህ ቤት ይዤ መጥቼ አላውቅም፡ተጨነቅኩ፡፡ ስላፈንኳት እሷ ተንፈራገጠች…፡፡ግራ ገባኝ፤ ልልቀቃትና መጮኸን ትቀጥል ወይስ እንዳፈንኳት ልቀጥል …?ብትሞትብኝስ..?፡፡ከመጨነቄ  የተነሳ ላቤ መንጠባጠብ ጀመረ …ተስፈንጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁ፤መኝታዬ ባዶ ክፍሉም ኦና  ነበር…ዜናወርቅ ሀሳብ ብቻ ነበረች.፡፡ምኞት የፈጠራት ህልም››
‹‹ተመስገን›አልኩ፡፡
‹‹ተመስገን ያልኩት ዜናወርቅ ቤቴ ስላልመጣችና ስላልተዋሰብን ተደስቼ አይደለም..ይልቁንስ የእውነት ሆኖ ጋሽ ሙሉአለም ስላረበሽኳቸውና ስላላስቀየምኳቸው ተደስቼ ነው ተመስጌን ማለቴ..አንዳንዴ ግን ህልም ባይኖር በምኞታችን እና  በምናገኘው ነገር መካከል ያለውን ክፍተት በምን እንሞላው ነበር?››

ይቀጥላል
👍722👏2
አትሮኖስ pinned «#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ ፡ ፡ #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት //// አሁን ወደ ቤቴ ልሄድ ወሰንኩና ወደ እሷ ዞርኩ ...እና አሁንም በድጋሜ ከፊል  እርቃኗን ስመለከት እርብድብድ አልኩና"አይ በዚህ ሰአት ዘበኞቹ ሰለሚተኙ ግቢውን አይከፍቱልኝ ይሆን እያልኩ እያሰብኩ ነው።›› "ነውእንዴ? ታዲያ እዚህ እደራ!!"ብላ ዘጭ ያለው ሞራሌን መልሳ ሰማይ ሰቀለችው..፡፡እያንቀጠቀጠኝ የነበረው…»
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ሁለት


የወሮ መንደር ሽማግሎች ከሁለቱ መንደሮች መሃል ካለችው ትንሽ ሜዳ ግማሽ ክብ ሰርተው በርኮታቸው ላይ ተቀምጠዋል" ባለ
ጴሮው፥ ሹልሹላው፥ የሰጎን ላባ ፀጉሩ ላይ የሰካው ሁሉም በተመስጦ ስብሰባው እስኪጀምር ለውይይቱ ህሊናቸውን ይሳስላሉ  ህፃናት ከሽማግሎች ርቀው
እንቧይ እየተቀባበሉ
ይጫወታሉ ጋልታምቤ ከቤቱ ወደ ሜዳው በምትወስደው ቀጭን ጎዳና ሄዶ ከሽማግሎች ጋር ተቀላቀለ ሌሎችም ከያቅጣጫው እየመጡ
ተደባለቁ„

ረጅም ጦር የያዙት የመንደሩ አለቃ (ዘርሲ) ከተቀመጡበት
ተነሱና ከወገባቸው ከታጠቁት ዝናር ጩቤ አውጥተው ጎረምሶች
የያዙትን ለፍላፊ ፍየል በቁሙ ጉሮሮው ላይ ወጉትና ፍየሉ ሲወድቅ
ከደሙ ጦራቸው ላይ ከፈርሱ ደግሞ ባታቸውን ቀባ-ቀባ አድርገው
ሄድ መለስ: ሄድ መለስ ብለው ንግግር ጀመሩ

"ጥሩ ነው! ዝናቡ መጥቷል መሬቷ ሳር አብቅላለች፥
ተራሮች እንደ ልጃገረድ አጊጠዋል ድንጉላ ቢራቢሮዎች፥ ወፎች
ይበራሉ" ንቦች አበባቸውን እየቀሰሙ ወደ ቀፎቻችን ይተማሉ፥ ውሃ የጠማት ምድር እምትጠጣው አግኝታለች እኛም የምንጠጣውን  ከስኬ ይሰጠናል አሸዋውን ስንጭረው ውሃ መሬቷን በጧር  ስንወጋት ማሽላ እናገኛለን ዳመናውን ሰርስራ
በምትወጣው ጨረቃም ልጆቻችን ይደሰታሉ
እንግዲህ ተቀያችን: ከዚች
አባቶቻችን ካቆዩን ምድር ምን ጎደለ!" ብለው ዝም አሉ የሽማግሎች
አለቃ" እንደገና ሄድ መለስ እያሉ ሁሉንም በዐይናቸው እየቃኙ

ብዙዎቹ ተሰብሳቢዎች ዐይናቸው ያለው ሌላ ቦታ ነው ሐመር ላይ ነገር በዐይን አይገባም' ነገር የሚደመጠው በልቦና ነው፤
ልቦና ያያል ልቦና ይሰማል
ልቦና ይመራመራል ልቦና
ይወስናል" በልቦና ለማየትና ለመስማት ግን ፀጥታ ያስፈልጋል ውስጣዊ እርጋታ የሃሳብ ማዕበል የሌለበት መተራመስ የተረጋጋበት ሊሆን ይገባል" ሐመር ላይ ሽበት ብቻ
ለሽምግልና አያበቃም፤
ጀግንነት ብቻ አያስከብርም
ማህበራዊ ችግርን ለመፍታት በጥንቃቄ ውሉን ፈልጎ አግኝቶ ትብትቡን
የሚፈታ ህሊናው ቀልጣፋ ከጀግንነቱም ከፍርድ አዋቂነቱም ሁለገብ ችሎታ ያለው መሆን ያሻል  ለሽምግልና ለመታጨት

"ጥሩ ነው! የአባቶቻችን መንፈስ ከእኛ ጋር አለ እንዳንራብ መከራ እንዳይበዛብን ዝንጉ እንዳንሆን የነሱ መንፈስ እንደ ዛፍ ጥላ ከለላ ይሆነናል ይሁን እንጂ በአባቶቻችን የነበረው ችግር አሁንም
አለ አሁንም የአባት ጠላት አለን አሁንም የአባት ጠላቶች እያዘናጉ የከብቶቻችንን ጅራት ሊጎትቱ የሚስቶቻችንን እጅ ሊስቡ፥ የላሞቻችንን ጡት ሊያልቡ ይፈልጋሉ ተናጋሪው  ንግግራቸውን ገተው ዙሪያ ገቡን እያዩ ፀጥ አሉ የኦሞ ወንዝ ቆሞ ያውቃል? ውሃ ታግዶ ይቆማል? ያባት
ደንብም እንዲሁ ነው፤ ሁሌም ከልጅ ወደ ልጅ ግድቡ በሽማግሎች
እየተከፈተ ከላይ እየወረደ የመጣው ወደሚቀጥለው
ትውልድ እየቶንዶለዶለ
ይፈሳል" ለዚህ ነው ከስኬ ሲጫር ውሃ: የእኛ ልብ
ሲቆፈር ደግሞ ያባት ደንብና ባህል የሚፈልቀው፤ ከእኛ መሃል ልቡ ሲቆፈር የአባት ደንብና ባህል የማያፈልቅ ደረቅ ካለ ግን ከጠላት
የተወረወረብን ድንጋይ ስለሆነ አምዘግዝገን መወርወር፥ ካካባቢያችን
ማጥፋት ይኖርብናል" ተናጋሪው ሽማግሌ ንግግራቸውን ገትተው
የተናገሩትን እንደገና በህሊናቸው አጣጣሙት።

"ወንድሞቼ የአባቶቻችን መንፈስ ከእኛ ጋር ነው
የምንሰራውን እነሱ ካቆዩን ደንብ ጋር ካላመዛዘነው እንደ ዱር ጉንዳን ማን እንደቆመብን ሳይታወቅ፤ ምንነታችንም ሳይጠየቅ አውራ እንደሌለው የሚያስተባብረው እንዳጣ ንብ በየጢሻው እንበተናለን
እንጨት ቆርጠን ሳር አጭደን ለንብ ቀፎ እየሰራን: እኛ ግን ተሰርቶ የቆየንን የአባት ደንብ ደህንነቱን
በመጠበቅ ለልጅ ልጆቻችን ማስተላለፍን ዘንግተናል" ከጉንዳን: ከንብ አንሰን የአባት ደንብ እየሻርን ነው: ትብብራችን እየላላ ነው፥ ወኔያችን ተሸንቁሮ
ንፋስ እየገባው ነው." እንደገና ቃኙት ተሰብሳቢውን  በዝምታ።

"አውሬ ይሁን ወፍ የማይታወቅ ጉድ በአራት እግሩ መንደራችን እየመጣ ሲቆም በሰፊው ሆዱ  ሴቶቻችንን እየሸፋፈኑ
እያቀፈ ሲወስድና ሲመልስ
ሴት ልጅ ወንድ የዘራውን ማብቀል  ሲሳናት እኛ አልተቃወምንም! ኧረ ተው! የተቀበልነውን የማናቀብል ጅብ አንሁን ጅብ የሚኖረውና የሚሞተውም ለሆዱ ነው የአባት ደንብ የለው ለልጄ ማለት አያውቅ አፍንጫው ጥንብ እንዳሸተተ: ሆዱ ለመብላት እንደተስገበገበ
ኖሮ ይሞታል ለልጄ ሳይል ደንብ ሳይኖረው ጥንብ እንደ አማተረ ይሞታል ለሆዱ! የተናጋሪውን ሃሳብ ከሚያዳምጡት መካከል አንዱ ሽማግሌ
የዘርሲዎች አለቃ በተናገሩ ቁጥር "ህም ህም… "አሉ በሐመር የስብሰባ ደንብ አንዱ ሲናገር ሌላው ህም ህም ካለ ልቀጥል ልናገር ማለት ስለሆነ የሽማግሎች አለቃ የንግግር እድሉንና
ተናጋሪው የሚይዘውን ጦር አቀበሉ  ተረኛው ሽማግሌ ጦሩን በቀኛቸው ይዘው ከፍየሉ ፈርስ ባታቸውንና ግንባራቸው ቀባ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ሽማግሎችን: ህፃናትን: መንደሩን: ዙሪያ
ገቡን ቃኙት ጦሩ እጃቸውን ነዘረው ስሜታቸውን በሙቀቱ አጋጋለው፤ ወኔያቸውን እንደ ብረቱ ጫፍ አጠነከረው  የአያት
የአባቶቻቸው መንፈስ ከጦሩ ተነስቶ ወደ ልቦናቸው ተስለከለከ

ጥሩ ነው! የቀጋ ፍሬ ከሾላ ዛፍ የለቀመ ማነው ሾላና
ቀጋን ደባልቆ የሚበላ ግን አስተዋይ ነው ይህ ሰው የተፈጠረው ደግሞ እዚሁ እኛ ዘንድ ቡስካ ተራራ ላይ ነው ያ ሰው እሳት
አንድዶ የሚፈልጋቸውን መልካም መልካም ሰዎች በእሳት ብርሃን
ከያካባቢው ጠራቸው
እንግዲህ አያቶቻችን የባንኪሞሮን እሳት
እያዩ ከያቅጣጫው የተሰባሰቡ ናቸው እኒያን ፍሬዎች  ቀጋና ሾላዎች ባንኪሞሮ ደባልቆ በሐመር ምድር በተናቸው"
አያቶቻችንና አባቶቻችን በቀሉ ከእኒያ ብሩክ ፍሬዎች ደግሞ እኛ በቅለን እህ! በተራችን እንድናፈራ ላደረጉን አባቶቻችን ውለታችን ምንድነው?" ብለው ዝም አሉ ሽማግሌው በጠየቁት ጥያቄ አንጀታቸው እየተላወሰ መልሱን ግን ፀጥታው ዋጠው"

"ወንድሞቼ የአባቶቻችን መልካም ሥራ የሚመለሰው ባህልና.ደንባቸውን በመጠበቅ ነው" ተዚህ ታፈነገጥን የሚያድነው እንሰሳ ላይ ማነጣጠር እንዳልቻለ አነር መሮጥ እንጂ የምንይዘው አይኖርም ሁሉም ያምረናል፤ አረንጓዴ ሁሉ ይበላል? ኮሽም: ዶቅማ ይሆናል?- የእኛ ህይወት የአባቶቻችንን ፈለግ በመከተል የሚመራ
ነው፤ እነሱ ያዩትን ዓለምና ደስታ ለማግኘት ከዱካቸው ዝንፍ ማለት የለብንም ተዚያ ታፈነገጥን ግን እሾህ አለ እንቅፋት አለ… ዳመና
ከሰማዩ ላይ ይጠፋል ከብትና ምድሯ ይነጥፋሉ በሽታ ይበዛል ከዚያ ያኔ ቀያችን አጥንት ሰላማችን ቆምጭሮ ሁከት
ይከመርበታል እፅዋት መብቀል ያቆማሉ፤  ባንኪሞሮ  የአነደደው
እሳት ይጠፋና ጥንት እንደነበረው ቀያችንን ዳፍንት ይውጠዋል
ባዶ ይሆናል! እና ተልባችን እንምከር ወንድሞቼ!" ብለው እጃቸውን
አወራጭተው ጦሩን ስመው ዝም አሉ ሌሎች ሽማግሎችም እንዲሁ
የሚሰማቸውን ሲናገሩ ቆዩና ጥፋቶች በመጀመሪያው
ተናጋሪ ተዘረዘሩ።

በአካል ለዘለዓለም
ለተለዩን በርቲና ቃላ መደረግ የሚገባው ደንብ አልተሰራላቸውም "አሉ” እንዳንል የሉም የሉም
እንዳንል ደግሞ ደንቡን የምትጠብቀው ነፍሳቸው አንዴ በወፍ ሌላ ጊዜ በአሞራ ወይንም በንፋስ … መልክ እየመጣች ከእኛ ጋር ናት ንግግራቸውን ገተው የሽማግሎችን የመንደሯን የአካባቢውን ትንፋሽ አዳመጡና

ነጯ ሐመር ይዛው የመጣችብን ስም የለሽ: ጢስ ተፊ አውሬም እዚሁ ከእኛ ጋር እየኖረ ነው ሲበላ ባናየውም ሲጋት ግን
በዐይናችን በብረቱ አይተነዋል ከዚያ እንደ ጅብ አጉረምርሞ ዐይናችን እያዬ ግማቱን ለቆብን ይሄዳል "
👍18
"ደልቲስ ነጯን ሐመር እጮኛ ላርግሽ ብሎ በሽማግሌ ጠይቆ
ጥሎሹን መክፈል መጀመር ሲገባው ነጯ ሐመር ጥሎሽ እኔ ልስጥህ
አለችኝ ብሎ በሴት አባባል አኩርፎ የሽማግሌ ውሳኔ መጣሱ እውን ዝምታ የሚገባው ነው!

"ከሎና ጎይቲም
ሽማግሌው ወደ አንተነህ  ጋልታምቤ ሰረቅ አድርገው ተመልክተው፤ "… ከሎና ጎይቲም ተተጋቡ ሁለት
ዓመት አለፋቸው" ከኋላው ያገቡት ሁሉ ለፍሬ ሲበቁ ከሎ የዘራውን ግን የጎይቲ ማህፀን ይኸው አላፈራም ሽማግሌው ንግግራቸውን
ቀጠሉ

"ጎረምሶች ከጎረምሳ ተራራ እየሄዱ ኢላማ ተኩስ
መለማመዳቸውም ቁሟል . ጠላት ሲመጣ የዝሆን ቀንድ አይነፋም ሳይጠበቅ ይመጣል ሳይታጠቁ አጥቅቶ ይሄዳል የኛ ጎረምሶች ደግሞ መሳሪያ መሸከም እንጂ ቃታ መሳብ የሚገባው ጣታቸው እንደ
መዥገር የልጃገረድ ጡት ነክሶ ይውላል እንግዲህ እነዚህን ችግሮች መፍታት አለብን" ብለው፥ የሽማግሎች አለቃ ንግግራቸውን አቆሙ።

💫ይቀጥላል💫
👍13😁1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ክፍል_ስድስት



#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

ከሀያ ቀን በኃላ ፤ስለእሷ ማሰብ ካቆምኩ በኃላ ...ኦልሞስት ከረሳኋት በኃላ  ድንገት ተከሰተች። እለቱ ቅዳሜ ነው ፤ቅዳሜ ለአብዛኛው ሰራተኛ የደመቀች ቀን ነች። ፈገግታ የሚፈስባት ..ሙዚቃ የሚንቆረቆርባት..የዳንስ ጥበብ  የሚጠበብባት ወሲብ የሚወሰብባት በስራ ሳይሆን በመዝናናት ብዛት የሚደከምባት...በወጪ ብዛት ኪስ የሚታጠብባት አዲስ ፍቅረኛ የሚጠባበስባት ክንድ ላይ ያለ ፍቅረኛ ድንገት ሾልኮ የሚሰወርበት… የታሪክ መፃፊያ ቀን ነች።
ከቅዳሜው የተትረፈረፈው ወደ እሁድ ይዘዋወራል።

ያው ከላይ በገለፅኩላችሁ ምክንያት ለእኛ ለአስተናጋጆች ዋና የስራ ቀናችን ነው።እና በዛው ልክ ወከባ አለ፡፡ ከአንዱ ወደሌላው  ጠረጴዛ መስፈንጠር ..ከአንዱ ተስተናጋጅ ትዕዛዝ ወደሌላው...ብቻ ከባድ ግን ደግሞ ወሳኝ ቀን ነች።ከባድ ያልኩት የስራውን ጫና ፤ የተስተናጋጆቹ ወከባ፤ የትዕዛዝ መደበላለቅ፤ የሰከራሙ ትንኮሳ፤የሂሳብ መጉደል የመሳሰሉትን ጫና አስቤ ነው። ወሳኝ ያልኩት ሳምንቱን ሙሉ የማናገኘውን ቲፕ እና መሠል ተጨማሪ ገቢ የምናገኝበት ቀን ስለሆነ ነው።ዛሬም እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት እንደወትሮ የተለመደ ስራዬን እየሠራሁ ሳለ ጋሼ አስጠረኝ።

‹‹አቤት ጋሼ፡፡››

‹‹ወንበርህን ለሌሎቹ አስረክብና    ቪ.አይ.ፒ ቁጥር 4 ያሉትን እንግዶች አስተናግድ"

ፈጠን ብዬ ‹‹እሺ ጋሼ "አልኩና በደቂቃ ውስጥ ወንበሬን ለጓደኞቼ አስረክቤ ወደታዘዝኩት ቦታ ሄድኩ ፡፡  በእኛ ሆቴል ስድስት የቪ.አይ.ፒ ቦታዎች አሉ።ልክ እንደትያትር ቤት በሆቴሉ ሰፊ አዳራሽ አራቱ ኮርነሮች ላይ  ከፍ ብሎ የተገነብ ሲሆን ወደ እዛ የሚወጣው ከሆቴሉ ሳይገባ በውጭ በኩል ባለ እስቴር ነው።የሁሉም መግቢያ ለየብቻ ሲሆን ቀጥታ በጓሮ በር ገብቶ መልሶ በጎሮ መውጣት ያስችላል..የቤቱ ዙሪያ በጠንካራ ኮንክሪት ግድግዳ የተገነባ ሲሆን አንድ ጎን ማለት ወደሆቴሉ ያለው ጥይት በማይበሳው  መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ነው ..፡፡መስታወቱ እታች ሆቴል ያለውን እንቅስቃሴ ጭፈራውንና እያንዳንድን እድምተኛ ቁልጭ አድርጎ ሲያሳይ ከሆቴል ወደላይ ግን ድፍን ጥቁር መስታወት ግድግዳ ብቻ ነው የሚታየው።ክፍሉ በጣም ዘመናዊ፤ ምቹ ሶፋዋች እና እንደ አማራጭ የባለጌ ወንበሮች ከምቹ ባልኮኒ ጋር ተገጥሞላቸዋል
መብራቶቹም በምርጫ የሚቀያየሩ  ተደርገው የተሠሩ ሲሆን ሙዚቃን በተመለከተ ቀጥታ እታች የሚለቀቀው በጥራት የሚመጣበት ወይም ያንን ዘግቶ እዛው የራሳቸውን የተመረጠ ሙዚቃ የሚጠቀሙበት አማራጭ አለው። እዛ ክፍል …ተጠቃሚዎች ወይ በራፍ ላይ  ቆሞ ወይ ውስጥ ተቀምጧ የሚያስተናግዳቸው  የብቻቸው አስተናጋጅ ይመደብላቸዋል። የተለየ ፕራይቬሲ ከፈለጉ ደግሞ  አስተናጋጅ ከክፍሉ ውጭ  ይሆንና ልክ መጥሪያውን ተጭነው ከመድገማቸው በፊት ተስፈንጥሮ በመግባት ትዛዛቸውን ተቀብሎ የሚፈልጉትን ያመጣላቸዋል።

ይህን  ክፍል የሚጠቀሙት ለደህንነታቸው ወይም ለስማቸው አብዝተው የሚጨነቁ ትላልቅ የቢዝነስ ሰዎች፤ዝነኞችና እና ባለስልጣኖች ናቸው። ቢሆንም ለሁሉም አገልግሎቶች ከመደበኛው  ከአራት እጥፍ በላይ ያስከፋላል ።አስተናጋጅም ብዙን ጊዜ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያገኛል።እናም ሁሉም እዚህ ቦታ ሲመደብ በደስታና  በፈንጠዝያ ነው የሚቀበለው።

ደረስኩ ..በራፋን እንደመቆርቆር አደረኩና ገፋ አድርጌ ስከፍት ደነገጥኩ...፡፡እንደጠበቅኩት ቀለል ያሉ ሰዎች አይደሉም የገጠሙኝ። እርግጥ ሴቲቷ ጀርባዎን ሰጥታኝ የተቀመጠች በመሆኑ ፊቷ አይታየኝም፡፡ግን ዝንጥ ብላለች።ደማቅ ሰማያዊ ረጅም ቀሚስ፤ መካከለኛ ታኮ ካለው ሰማያዊ ጫማ ጋር አስማምታ ለብሳለች። ፀጉሯ የእውነት የእሷ ከሆነ ውብ መሆኑን  በቀላሉ መናገር ይቻላል ፤ወገቧ ላይ ተበትኖ  ይታያል .፡፡

.ሰውዬው ከእኔ ፊት ለፊት ናቸው ያሉት ፤ትልቅ ሰው ናቸው።ቆፍጣና ፤ኮስታራና አስፈሪ  ..ፀጉራቸው ገብስማ ነው..፡፡ሙሉ ዠንጉርጉር የመከላከያ ልብስ ለብሰዋል።ትከሻቸው ላይ አራት ኮከብ ወደጎን ተደርድሯል።መቼስ በዚህ አለባበስ የሆነ ስብሰባ ላይ ወይም ወሳኝ ሀገራዊ ተልዕኮ ላይ አምሽተው ከጊዜ መጣበብ የተነሳ ወደቤታቸው ጎራ ብለው ለመቀየር ሳይችሉ ቀጥታ መተው ነው እንጂ ይሄ የክብር ልብስ ቦታው አይመስለኝም"በውስጤ አጉረመረምኩ ...

እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ወደፊት የተወሰነ እርምጃ ጠጋ አልኩና ‹‹ጌታዬ የጎደለ ነገር አለ?››ብዬ ጠየቅኳቸው፡

"ሚበላ ምን አላችሁ?"ጎርናና እና ሻካራ ድምፅ...እኚ ጄኔራልማ እቤታቸው ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውን አስቀምጠው ነው ከዚህች ኮረዳ ጋር የሚማግጡት› በሆዴ አማኋቸው፡፡እስቲ አሁን ምን አውቄ ነው ለሰከንድ ያየኋቸውን ሰዎዬ ወደማማትና መፈረጅ የገባሁት ብዬ እራሴን ወቀስኩ።

"ጌታዬ ሜኑ ላምጣ"

"አይ አንድ ክትፎ አምጣልን...ክትፎቸው አሪፍ ነው" አለች ሴቲቱ...አሁንም  በደበዘዘው ብርሀን ከእኔ በተቃራኒ የዞረ ፊቷ እየታየኝ አይደለም ።ድምፆ ግን የሚነዝር ኃይል ነበረው። የሚያደነዝዝ...በምን ምክንያት ነዘረኝ...?ስለምንስ ውስጤ ተናጠ... ?

"በቃ ጎረምሳው እንዳለችህ አድርግ"አሉኝ ጄኔራሉ ..ንግግራቸው  ብቻውን ምሽግ የሚንድ አይነት ነው፤ተስፈንጥሬ ወጣሁ።በተቻለ ፍጥነት በልዩ ሁኔታ ክትፎውን አሰርቼ ይዤ ተመለስኩ።

"የእጅ ውሀ እዚሁ ልታመጣልን ትችላለህ?"ሴቲቱ ነች ጠያቂዋ፡

"ይቻላል እመቤቴ.. አሁን አመጣለሁ"አልኩና በደቂቃ ውስጥ የእጅ ውሀ ይዤ መጣሁ። ተንደርድሬ ሄጄ በክብር ጎንበስ ብዬ ልክ እማማ ኢትዬጰያን እያስታጠብኩ እንደሆነ ኩራት እየተሠማኝ ጄኔራሉን አስታጠብኩና ወደ ሴቲቱ ዞር ስል ፊት ለፊት አይን ለአይን ግጥም ...ምን ተአምር ነው?...ልደሰት ወይስ ልዘን? ላልቅስ ወይስ ልሳቅ ?

ጎንበስ ብዬ እያስታጠብኳት ቢሆንም ግን በደመነፍስ ነው። ድምፅ አውጥቼ ላወራት አልቻልኩም  ? አውቅሻለሁ... ጋብዘሺኛል.. እርቃን ገላሽን በዓይኖቼ አይቻለሁ...በጣቶቼ ዳብሼሻለሁ ልላት ፈፅሞ አልቻልኩም።

‹‹አይ የጎረምሳ ነገር....ውሀውን ደፍተህ ጨረስከው እኮ"አሉኝ ጀኔራሉ እንደመሳቅ ብለው። ለካ እሷ መታጠብን ጨርሳ እጇን ብትሰበስብም እኔ ግን አይኔን አይኖቾ ላይ እንደተከልኩ ፈዝዤ ውሀውን ማንጮርጮሬን ቀጥያለሁ...በጄኔራሉ ንግግር ባነንኩና ተስፈንጥሬ ከስራቸው ወደበሩ መራመድ ጀመርኩ።

"በራፋ አካባቢ ነኝ፤ ስትፈልጉኝ መጥሪያውን ተጫኑ ››አልኩና  ክፍሉን ዘግቼላቸው  ወጣሁ።የእጅ ማስታጠቢያውን አስቀምጬ በረንዳው ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተሸከረከርኩ መብሰልሰል ጀመርኩ፡፡

"ፍፅም እንደማታውቀኝ እኮ ነው የሆነችው...ምን አይነቷ ባለጌ ነች?" ከንፈሬን በብስጭት ነከስኩ ..‹‹አንድ ለሊትም ቢሆን እኮ እንዲህ በቀላሉ የሚረሳ ነገር  አልነበረንም ያሳለፍነው..? ነው ወይስ ውሽማዋን ፈርታ ነው?››

"ብትፈራ ይፈረድባታል .. ጄኔራሉ እኮ እንኳን በጎናቸው የሸጎጡት ሽጉጥ ተጨምሮበት ይቅርና እንዲሁ ያን ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ሲያደርጉት ያርበደብዳሉ...እኔስ ሀይ ሰላም ነሽ የሚል አጭር ሰላምታ እንኳን ለመስጠት ድፍረት ያጣሁት እሳቸውን ከመፍራት አይደል?።ግን ውሽማዎ ናቸው ነው ያልኳችሁ ..?ያንን በምን አወቅኩ ?አልነገሩኝ...ሲሳሳሙ እንኳን አላየሁም"

የመጥሪያው መንጣረር ከሀሳቤ አናጠበኝ። ፈጥኜ ወደውስጥ ገባሁና መሽቆጥቆጤን ሳልቀንስ "አቤት ጌታዬ"አልኩኝ፡፡
👍562👎2👏1
"ጥሩ ምግብ ነበር ከፍ ይበል አሉኝ "ቶሎ ብዬ ምግብን አነሳሁ እጃቸውን አስታጠብኩ፡፡ ጠረጰዛቸውን አፀዳዳሁና ወጥቼ  ወደበረንዳዬ ሄድኩ።እነሱም በጠርሙስ ያዘዙትን ውስኪያቸውን መጋት  ቀጠሉ...በሆነ ምክንያት ወጣ ብትል ስል ተመኘሁ...ለምን ፈለኳት ግን...?.እንዳረሳችኝ ለማረጋገጥ?ወይስ ሳስብሽ ነበር የከረምኩት ብዬ ለመናዘዝ ይሆን?ብቻ ለደቂቃዎችም ቢሆን  ብቻዎን ባገኛት  ቢያንስ ስልክ ቁጥሯን  እጠይቃታለሁ። ›› እያልኩ ስብሰለሠል መጥሪያው ተንጣረረ ..ተንደርድሬ ስገባ ሁለቱም ቆመው ለመውጣት እየተዘገጃጅ ነው ።

"እንዴ ምን አስቸኳላችሁ?"የሚለው ቃል ከአንደበቴ አዳልጧኝ ሊወጣ ለጥቂት ነው የተረፍኩት።

"ሂሳብ ተዘግቷል"አሉኝ ጄኔራሉ፡

"እሺ ጌታዬ ችግር የለም" አልኩ፡፡

መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ እሷ እጅ መዳፌን አፈፍ አድርጋ የሆነ ጥቅል አስቀመጠችና ተከተለቻቸው ...ጄኔራሉ ያደረገችውን በቆረጣ ቢያዩም እንዳላዩ በራፉን አልፈው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ ከኃላ ተከተለቻቸው..  እኔ ባዶ ክፍል ውስጥ ቀረሁ።

አሁን ወዴት ነው ይዘዋት የሚሄድት..?ወደቤርጎ .?.እዚህ ነው ቤርጎ የያዙት...?እንደዛ ከሆነ ክፍሉን ማወቅ አለብኝ፡፡ የሰጠችኝን ጥቅል ኪሴ ከትቼ ተንደረደርኩ፡፡ ሳይሰወሩብኝ ልከተላቸው ..ወደ ሆቴል ጊቢ አይደለም ወደውጭ በጓሮ በኩል ነው የሄድት፡፡ ተሹለክልኬ ተከተልኳቸው። ሁለት የወታደር ጂፕ መኪኖች አሉ፤ስድስት የሚሆኑ እስከአፍንጫቸው መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮች ይተረማመሳሉ..ጄኔራሉ ፊት ለፊት ባለው መኪና ሲገብ የእኔዋ የኃለኛው ውስጥ ገባች። አራቱ ወታደሮች በጄኔራሉ  መኪና ሲሳፈሩ ሁለቱ የሆለኛው ውስጥ ከእሷ ጋር ገብ።የታደለ እንዲ ነው በመንግስት መኪና በአጃቢ ይሸኛል ስል ተንጨረጨርኩ ። ወደነበርኩበት ክፍል ተመስኩ፤ሳይጨርሱ የተውትን ውስኪ ከእነጠርሙሱ እያንደቀደቅኩ ከታች ያለውን ዳንስና ግርግር በተተረማመሰ ስሜቴ ማየት ጀመርኩ።ድንገት አስጨብጣኝ የሄደችው ትዝ አለኝ።ስንት ብር ነው የሰጠችኝ?የክፍሉን ደማቅ መብራት አበራሁና እጄን ወደኪሴ ሰደድኩ ..ጥቅሉን አወጣሁት ።አንድ የ200ብር ኖትና ብጣሽ ወረቀት ነው፤ብሩን ወደኪሴ መልሼ ወረቀቱን  ተረተርኩት፤ሁለት ቃል ተፅፎበታል፡፡

   "ምነው ቀናህ እንዴ?"ይላል፡፡

ዘለልኩ፤ ጮህኩ፡፡

ይቀጥላል
👍457
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ አራት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«ጓደኛዬ ነው!! ትናንት አንተን ትተን ስንወጣ ተከትለውን ነበር።» ብዬ ሆስፒታል የመተኛቱን ሚስጥር አብራራሁ ጎንጥን ምኔ ነው ብዬ ማስተዋወቅ እንዳለብኝ ግራ ሲገባኝ ማቅረቤ ይሁን ማራቄ ልኬቱን እንጃ!! ወዲያው ግን ስም ሲለዋወጡ በስሙ ያውቀዋል እና ኪዳን ዞሮ አየኝ! <ጎንጥ ይሄ እኔ የማውቀው ጎንጤ?> ዓይነት አስተያየት! ምንም እንዳይጠይቀኝ በልምምጥ ሳየው እኔን ተወኝ! ከዛ ግን ወንበር ስቦ ጎንጥ ፊት ተቀምጦ አንዱን ጥያቄ ከሌላው እያስከተለ ይደራርብ ጀመር።

«ቤተሰብ አለህ? ማለቴ የራስህ ሚስትና ልጆች? አዲስአበባ ከመጣህ ቆየህ? ሜልጋ ሳትሰራ በፊት ምንድነበር የምትሰራው? ሴት ጓደኞችህን ሁሉ <ዓለሜ> ብለህ አትጠራም መቼም አይደል? ስራህ ስለሆነ ነው ወይስ ሜል ስለሆነች ነው (በአገጩ የተመታውን ጠቆመው) ከዳንክ በኋላ ….. »

«ኪዳን?» አልኩኝ በልመና መጠየቁን እንዲያቆም ….. በአንድ በኩል ግን መልሳቸውን ልሰማቸው የምፈልጋቸው ጥያቄዎች መሆናቸው ለጎንጥ መልስ እንድጓጓ አደረገኝ። የእውነት ከዳነ በኋላስ?

«ሴት ልጅ አለችኝ!» የሚለውን ብቻ ነው ከዚህ ሁሉ ጥያቄ ፈገግ እያለ መርጦ የመለሰው። ኪዳን ሌላውን ጥያቄ እንዲመልስለት አንገቱን አስግጎ ጠብቆ ዝም ሲለው

«come on!» አለ

«መሽቶም የለ? ሂዱና ጎናችሁን አሳርፉ!! » ሲል ነው ጎኔ አልጋ ከነካ 48 ሰዓት እንዳለፈው ትዝ ያለኝ።

«እርግጠኛ ነህ ብቻህን ምንም አትሆንም?»

«ምንም አልሆን አልኩሽ እኮ!!» ያለበት ድምፅ <ዓለሜ> እንደሚለው ያለ ማባበል አለው ነገር? ወይም መስሎኝ ነው 48 ሰዓት ያልተኛ ሰው ብዙ ያልተባለ ነገር የመስማት እድሉ ከፍተኛ ነው።

ይሄን ካለ በኋላ ለሆነ ደቂቃ የሆነ ያልተለመደ ዓይነት ዝምታ ተፈጠረ። ቻው ብዬው መውጣት እፈልጋለሁ ግን የአልጋው ግርጌጋ እንደተገተርኩ ነው። ልቤና እግሬ ተጣሉብኝ!! እንድሄድ እየጠበቀ ነው ግን በዓይኖቹ እንድቆይለት እያባበለኝ ነው ወይም መሰለኝ። በእንደዛ ዓይነት ፖዝ ፎቶ አንሺ ያስቆመኝ ነው የምመስለው።

«እኔ የምለው? እኔኮ ብቻዬን ማደር እችላለሁ! አንቺ ለምን እዚህ አትቆዪም?» የሚለው የኪዳን ንግግር ነው እኩል ሁለታችንንም እንደመባነን ያደረገን

«አይሆንም!» አልን ሁለታችንም በአንድ ድምፅ ግንኮ አሁንም ኪዳንን ያየው የለም እኔና እሱ ዓይናችን አልተፋታም! ከዛ ደግሞ ራሴው አይሆንም ያልኩትን እሱም አይሆንም ማለቱ ለምን ከፋኝ?

«እህእ? ወይ ሶስታችንም እዚሁ እንደር?» አለ ኪዳን ሳቅ እያፈነው። አሁን ሁለታችንም አየነው። ስንወጣ ሲያበሽቀኝ እንደሚያድር አውቃለሁ።

«ደግ! በሉ ቸር እደሩ!! ትከሻሽን መገላመጥ አትዘንጊ!» አለ በቃ ተሰናብቼሻለሁ ሂጂ እንደማለት ነገር ከነበረበት በቀስታ ዘወር እያለ።

«የምትባባሉትን ተባባሉ በሩጋ ነኝ!» ብሎ ኪዳን ወጣ!! ምን እንደሚባል የማውቀው የለኝም!! ማለት የምፈልገው መኖሩንም እንጃ! ካለሁበት ተንቀሳቅሼ ልቀርበው ፈልጌ ማፈር ነው ግራ መጋባት የማላውቀው ስሜት ጨመደደኝ። ጭንቅላቴም ልቤም ሰውነቴም ተባብረውብኝ ማድረግ የምሻው ብቸኛ ነገርኮ እሱን መንካት ነው። እንዲህ ሆኖ የሚያውቅ ሰው ኖሮ ያውቅ ይሆን አላውቅም! ገብቶት ነው መሰለኝ ወይም እሱም እንደእኔ አካላቶቹ አምፀውበት ሊነካኝ ፈልጎ እጁን እንድይዘው ዘረጋልኝ። ከረሜላ አይቶ ሲቁለጨለጭ ምራቁ አፉ ውስጥ ሞልቶ ወደ ጎሮሮው ሲደፍቅበት ቆይቶ ከረሜላውን እንደሰጡት ህፃን በአንድ እርምጃ ዘልዬ እጁን ያዝኩት። እጁን እጄ ላይ ከማጫወቱ ውጪ በቃላት አላወራኝም። በዓይኖቹ የሚያወራው ደግሞ ትርጉሙ እኔ እንደምፈታው ይሆን ሌላ እየገባኝ አይደለም። <የዓይን ቋንቋ እንደፈቺው ነው!>

«ከዳንክ በኋላስ?» አልኩት ለሚመልስልኝ መልስ ሳልዘጋጅ

«አላውቅም!» አለኝ ከአይኔ ውስጥ ቆፍሮ የሚያወጣው ስሜት ያለ ይመስል በአይኑ አይኔ ውስጥ እየቆፈረ። መልሱ ምን ሊሆን እንደሚችል የጠበቅኩት ነገር ስላልነበረ አልከፋኝም! እሙ እንዳለችው ከመጃጃልም በላይ እየሆንኩ እንደሆነ የገባኝ ከ<አላውቅም> አስከትሎ <ዓለሜ> አለማለቱ ከፋኝ! አንዴ አለሜ በለኝ ብለው ሆዱን ይዞ አይስቅብኝም? ይባላልስ?

«አንቺ ምንድነው የምትፈልጊው?» አለኝ

«አላውቅም! ምን እንደምፈልግ አላውቅም!» አለ አፌ! የምፈልግ የነበረው ግን ዓለሜ እንዲለኝ ፣ የምፈልግ የነበረው እንደቀኑ የእጄን መዳፍ መሃሉን እንዲስምልኝ፣ እምፈልግ የነበረውማ ለአንዴ በህይወቴ ጀግና ጀግና የማልጫወትበት ሰው እንዲሆነኝ ……. ለአንዴ ብቻ ፍርሃቴን ፣ ድክመቴን ፣ ማፈሬን ፣ ሽንፈቴን ፣ …. ከእንባዬ ጋር ለውሼ ደረቱ ላይ እንድተነፍሰው በክንዱ ደግፎ ደረቱ ላይ እንዲያቅፈኝ ….. እፈልግ የነበረውማ ይሄ ያልኩት ሁሉ ሲሆን ዘመናት ቢቆጠሩ ነበር። ቀጥዬ ያልኩት ግን

«ኪዳን አባት ሊሆን ነው!» የሚለውን ነው! ሳልፈልግ ድምፄ ውስጥ መከፋቴ ተሰማብኝ። የያዘውን እጄን ስቦ ወደደረቱ አስጠግቶ ደረቱ ላይ አጥብቆ ያዘው። ይሄ ሰውዬማ ከእጄጋር የሆነ ነገር አለው! ነውስ እጄና ልቤ የሚያገናኛቸው ነገር አለ እጄን የሆነ ነገር ሲያደርገኝ ልቤ አብሮ የሚያሸበሽበው?


«ዳር የተተውሽ መሰለሽ?» ሲለኝ እንባዬ ታገለኝ!! ነግሬዋለሁ? አልነገርኩትም! የተሰማኝን በልከኛው ቃል እንዴት ማስቀመጥ ቻለበት? አንዲት ፊደል ከአፌ ቢወጣ እንባዬ እንደሚያጅበው ስለገባኝ ዓይኖቹን ሸሽቼ ዝም አልኩ። ደረቱ ላይ የያዘውን እጄን እዛው ትቶት በእጁ አገጬን ደግፎ ዓይኖቹን እንዳያቸው አደረገኝ።

«መቼም ቢሆን በምንም የማይተካሽ እህቱ ነሽ!! ሚሽትና ልጁ ያንቺን ቦታ አይጋፉም!! ኪዳንን በዚህ ሁሉ መዓት ፍቅር ስትወጂ ልብሽ ጠቦሽ አባትሽን አስወጥተሻል? ወይሳ እናትሽን? እኔን ወደልብሽ ስታስገቢስ ልብሽ አልበቃ ብሎ ከኪዳን ፍቅር አጎደልሽ? የእርሱን ቦታ ቀነስሽ?»

«አይ!!» ብዬ ጭንቅላቴን በአሉታ ከነቀነቅኩ በኋላ ነውኮ መጨረሻ ላይ ያለውን ለራሴ ደግሜ ስሰማው ዓይኔን የማሳርፍበት የጠፋኝ። ጥሩ እየሰማሁት ነበርኮ ከመጨረሻው እሱን ልቤ ካስገባበት ዓረፍተ ነገር በፊት! <አይ> ያልኩት ምንድነው ቆይ? የኪዳንን ፍቅር ሳታጎድል ነው ልቤ የገባኸው ነው አይደል ያልኩት? የጥያቄው መልስ እንደተመለሰለት ፈገግ ብሎ አገጬ ላይ አውራ ጣቱን አሸት አሸት ነገር አድርጎ እጁን ደረቱ ላይ ወደተወው እጄ መልሶ እንደቅድሙ አጥብቆ ደረቱ ላይ ያዘው።

«ያልኩት ሀቅ አለው?» ብሎ አወነባበደብኝ። ምናለ ዝም ቢለኝ ገብቶት የለ?
«ምኑ?»
«ከልብሽ ገብቻለሁ?»
«አዎ! መሰለኝ! እኔ እንጃ አላውቅም! በምን አውቃለሁ?» በዚህ ነፋሻማ አየር እንዲህ ሊሞቀኝ ይገባ ነበር? ስፈራ ጉልበቴን እንደቁርጥማት እንደሚያደርገኝ ነገር አሁን ሊሰማኝ ይገባ ነበር? ሳቅ እንደማለት ነገር ብሎ
👍34😁2
«በይ ተነሽ ሂጅ አሁን እየጠበቀሽ ነው!!» ብሎ እጄን አንስቶ አገላብጦ ይስመው ጀመር!! አንዴ ሁለቴ ሶስቴ ….. ሁለቴ አይበሉባውን አንዴ ወይም ሶስቴ መሃል እጄን….. እኔ እንጃ አንድ አራቴ ጎኑን ….. ጣቶቼን …… ከመጀመሪያው በኋላ እንኳን ቁጥሩን ላውቀው እንደባለፈው ራሴንም አለመዘንጋቴ በቸርነቱ ነው። ከዛ ነገና ዛሬዬን ከደባለቀብኝ በኋላማ ምንም እንዳልሆነ ነገር እጄን መለሰልኝ። ማድረግ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበር። ግን ለመሄድ ተነሳሁ እና ወደበሩ መንገድ ጀመርኩ። ልቤማ ደረቴ ውስጥ የለችም! እንጂ ሰውነቴ እንዲህ ወደኋላ ባልጎተተኝ። በሩጋ ደርሼ ዘወር አልኩና

«ነገ እኮ እማዬጋ ልሄድ እችል ይሆናል።» አልኩት ለምን እንዳልኩት ሁሉ እኔ እንጃ! ምናልባት አንድ ደቂቃ እሱጋ መቆያ ምክንያት እየፈለግኩ መሰለኝ።

«ደግ!!» ብቻ ነው ያለው!! እንዴ? ምንድነው ሰው ማግዶ እሪሪሪ እስኪሉ መጠበቅ? ኮስተር እንዳልኩ ለራሴ እየታወቀኝ በሩን ይዤ ቆምኩ!

«ምነው ዓለሜ? የምትነግሪኝ አለሽ እንዴ?» ሲል ከንፈሬ ሳላዘው ሸሽቶ ያለኝ ጥርስ ሁሉ ንፋስ ዳበሰው

«ምንም የለም! ደህና እደር በቃ!» ብዬው ወጣሁ። መኪናው ጋር እስክንደርስ ከኪዳን ጋር ምንም ቃል አልተለዋወጥንም! መጣሁ መጣሁ እያለ እየተናነቀው እንደሆነ ያስታውቅበታል።

«ትከሻሽን መገላመጡን አትርሽ ዓለሜ!» አለ መጨረሻ ላይ ከት ብሎ እየሳቀ

«አፍህን ዝጋ እሺ!! አንድ ነገር እንዳትለኝ!» አልኩት ሳቅም ማፈርም በደባለቀው ቁጣ

«ጀግና ነው ግን ሜል ሙች!! ይፈርምልኝ! ጠባቂ ሆኖ ገብቶ ጠብ ያድርግልኝ? ሜል ገና ስታይው ፍስስ እኮ ነው ያልሽው!»

«ኪዳን ተወኝ አልኩ እኮ!»

«አንዴማ ጨብጬው ልምጣ ሜል ሙች» ብሎ ወደኋላው እንደመመለስ አለ

«ባክህ አርፈህ መኪና ውስጥ ግባ አትጨማለቅ!!»

የማውቀው ገስትሀውስ ደውዬ አልጋ ያዝኩ። መንገዱን ሁሉ ሲያበሽቀኝ እና ሲገረም ዘለቅነው «ምን አባቱ አድርጎሽ ነው ግን ስንቱን ወንድ ያሸና ልብሽን ዘጭ ያደረገው? ፣ እኔንኮ እዛ እንደሌለሁ ረሳችሁኝ ሆ! ፣ እድሜ ደጉ ሜል ስትሽኮረመም ያሳየኝ? ፣ ፍቅር በሀገርኛ ግን ጆሮ ላይ ደስ ይላል አንቺ? ነፍሴን አወክሻትኮ ዓለሜ! ነው ያለው? > አያቆምም ይለፈልፋል። በመሃል

«ሜል ሻምበሉጋ ከአንድ ሰዓት በኋላ እደውላለሁ ካልሽው ሁለት ሰዓት አለፈ!» ሲለኝ ሰዓቴን አየሁት። መርሳቴ እኔንም ኪዳንንም ገረመን!! አንድ ሰው እንዲህ የሰውን ሀሳብ መቆጣጠር ይችላል?

«እኩለለሊት ሊሆን ነው!! ጠዋት ብደውል ይሻላል!!» ስለው ኪዳን አይኑን ጎልጎሎ አውጥቶ አፈጠጠብኝ

«you know am happy for you!! ሜል ነገር አሳደረች? ያውም ሊገድላት የሚከረ ሰው ? ፍቅር ግን ደስ ሲል!!»

«ለምንድነው ግን አፍህን የማትዘጋው?»

ለሁለት ደቂቃ ዝም ይልና ደግሞ ይጀምረኛል። ማረፊያችን ደርሰን የምናወራው ቁምነገር መኖሩን ተኮሳትሬ እስክነግረው ማብሸቁን አላቆመም!!

«አሁን የምር አስጨነቅሽኝ! ምንድነው ንገሪኝ!!» አለኝ አጠገቤ አልጋው ላይ እየተቀመጠ አንድ እጁን እንደማቀፍ ትከሻዬ ላይ ጣል እያደረገ

«እማዬ አልሞተችም! በህይወት አለች!! እና ልታይህ ትፈልጋለች!»

«ማለት?» ብሎ እጁን ከትከሻዬ ላይ አነሳው

«በሰዓቱ ላንተ እውነቱን መንገር ከምትሸከመው በላይ ስለሚሆንብህ ነው ከአጎቴ ጋር ተነጋግረን እንደሞተች የነገርንህ! ታዲያ የታለች ብትለን ኖሮ መልስ አልነበረንም!»

«እና የት ነበረች?» ብሎ ስፈራው እና ስሸሸው የኖርኩትን ጥያቄ ጠየቀኝ። እንዴት ብዬ እንደምነግረው ስጨነቅ

«ሜል ያኔ ህፃን ስለነበርኩ ነው የዋሸሽኝ አሁን ግን ትልቅ ሰው ነኝ ንገሪኝ!!» ብሎ ሲሆን አይቼ እንደማላውቀው ተኮሳተረ። የዛን ቀን ያየሁትን ነገር በሙሉ ነገርኩት። እየጠበቅኩ የነበረው የሚናደድ ወይ ሌላ ጥያቄ የሚያስከትል ነበር። እሱ ግን መጥቶ እያቀፈኝ

«አንቺምኮ ይሄን ሁሉ ብቻሽን የምትሸከሚበት እድሜ ላይ አልነበርሽም!!» አለኝ። ቀጥሎ ግን «አንቺ ትታን ስለሄደች አላዘንሽባትምኣ?» ብሎ ያላሰብኩትን ጥያቄ ጠየቀኝ።

«አላውቅም የኔ ኪዳን! ልጅ እያለን ብዙ ጊዜ ተናድጄባት አውቃለሁ። የምናደደው ግን ትታኝ ከመሄዷ በላይ ካየሁት ነገር በላይ እናትነቷን እንደማይላት እንዴት አልተረዳችልኝም ብዬ ነው! ከውርደቷ በላይ ፍቅሯ እንደሚገዝፍብኝ እንዴት ማሰብ አትችልም ብዬ ነው። ከዛ ግን የዛን ቀን ዓይኗ ውስጥ ያየሁት ህመሟ ከምናደድበት ይበልጥብኝና አንድ ቀን አጊንቻት ባቅፋት ነበር የምመኝ የነበረው»

«እሺ አገኛታለሁ!! ላገኛት ፈልጋለሁ!!» አለኝ።

«ታማለች ኪዳንዬ" አልኩት!እናቱን የማግኘት ተስፋ እንደሰጠሁት ትዝ ሲለኝ ብዙ ከማለሙ በፊት እየተሽቀዳደምኩ ይመስል ተቅለብልቤ

«ታማለች ማለት? የከፋ?»

«አዎን!! ታውቃለህ ለበደሌ እየቀጣኝ ሁሉ መስሎ ተሰምቶኝ ያውቃል! ዓይኗን ደግሜ ባየው ብዬ ዘመኔን የተመኘሁላት እናቴን በመጨረሻ ሳገኛት ለሞቷ ቀናት እየቆጠረች ሆነ።» ከዚህ በኋላ ለረዥም ሰዓት ዝም ተባባልን!! በቃ ዝም! የዛለው ሰውነቴ የተቀመጥኩበት ወደቀ። እግሬን ወደላይ ሰብስቤ ተጋደምኩ።


የነቃሁት የቧንቧ ውሃ ሲወርድ ሰምቼ ነው። ኪዳን ቀድሞኝ ነቅቷል ወይም አልተኛም! አልጋው ጫፍ ላይ እንቅልፍ እንደወሰደኝ ልብስ ደርቦልኛል። ምናልባት እንቅልፍ አልወስድ ብሎት የነበረ ይሆን ብዬ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። በደቂቃዎች ውስጥ እናትህ አለችም ልትሞትም ነው የሚል መርዶ አርድቼው እኔ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ። እናቴን አግኝቻት ልትሞት መሆኑን ሳውቅ ለወራት መቀበል አቅቶኝ የሆንኩትን መሆን አስቤ ያጠፋሁ መሰለኝ። ብቅ ሲል

«ይቅርታ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?» አለኝ

«ነግቶ የለ! ምነው እንቅልፍ አልወሰደህም እንዴ?»

«አይ ተኝቻለሁ!» ይበለኝ እንጄ የእኔን ኪዳን መች አጣሁት እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነው ያደረው። አስር ጊዜ <ደህና ነህ> እለዋለሁ። <ደህና ነኝ> ይለኛል።

«ማውራት ትፈልጋለህ ኪዳንዬ?»

«አልፈልግም! ዝም ብለን እንሂድ!» አለኝ።

ከመሄዴ በፊት ብዙ ማድረግ የምፈልጋቸው ነገሮች ነበሩኝ። ሆስፒታል ሄጄ ጎንጥን ማየት። ሻለቃው ጋር መደወል፣ ሴትየዋ ማን መሆኗን አውቄ ማግኘት….. ብዙ!! ከኪዳን የሚበልጥ ነገር የለኝም አይደል? እሱ እንዲህ በዝምታ ተለጉሞ የሚሰማውን እንኳን ሳላውቅ ራሴን ማስቀደም አልሆንልሽ አለኝ!! ክፍላችን የመጣውን ቁርስ እንደነገሩ እየለኳኮፍን መኪና ስፈልግ የሚያዘጋጅልኝ ሰው ጋር ደውዬ መኪና እንዲያመጣልኝ ካደረግኩ በኋላ የዳዊትን መኪና ሌላ ቦታ ወስዶ እንዲያቆምልኝ አደረግኩ። ለዳዊት ደውዬ መኪናውን ከቆመበት እንዲወስድ ስነግረው ምንም እንዳልጠረጠርኩ ለመምሰል ከራሴ ታገልኩ። መንገድ ከጀመርን በኋላ ሻንበሉ ደወለ። የመኪናው ባለቤት እና ልትገድለኝ የሞከረችው ሴት የተለያዩ ናቸው። ግን ሁለቱም በስማቸው የማውቃቸው አይደሉም!!

«ቢሮ ብቅ ካልሽ የሁለቱንም ፎቶ ላሳይሽ እችላለሁ!!» ብሎ ስልኩን ዘጋው!! መልዕክቱ አንድም ለመላክ አላምንሽም ነው ሁለትም ፎቶውን ለማየት ተጨማሪ ዋጋ አለው ነው። ስልኩን ዘግቼ ዝም አልኩ! ኪዳንም ምንም አልጠየቀኝም!! ዝምታው አስጨነቀኝ!! ልቤ ድንጋይ የተጫነበት እስኪመስለን ድረስ እንደከበደኝ ተጉዘን ከሰዓታት በኋላ እነእማዬጋ ደረስን!! አጎቴ ከበር እንደተቀበለን ኪዳንን እያገላበጠ ስሞ አልጠግብ አለው!!
👍26👏1
«አቤት አንተ መድሃንያለም ምን ይሳንሃል!! አስካል ልጅሽ መጣልሽ!» እያላት ወደ ውስጥ ገባ!! እማዬ ለመነሳት በዛለ ጉልበቷ ተፍጨረጨረች። ከሁለት ቀን በፊት ካየኋት በላይ ገርጥታለች። ይብሱን የከሳችም መሰለኝ። ዝም እንዳባባሉ ፣ እንደማታው አጠያየቁ ከኪዳን ጋር ሲተያዩ አሁን የሚሆኑትን የሚሆኑ አይመስልም ነበር። ጉልበቷን አቅፎ ተንሰቀሰቀ። ፀጉሩን እየደባበሰች ተንፈቀፈቀች። እኔና አጎቴ የሁለቱን መሆን እያየን ስንነፋረቅ ቆይተን! አጎቴ ፊቱ ላይ የተዝረከረከ እንባውን ጠራርጎ ሲያበቃ ደግሞ እንዳላለቀሰ ሰው ኮስተር ብሎ

«አይ ደግም አይደል የምን ለቅሶ ነው?» አላለም?

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍172
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ሦስት

ካርለት መሳተፍ የማትችለውን የሽማግሎች ስብሰባ በርቀት
እየተመለከተች አልፎ አልፎም የካሜራ ችፕስ  በተደረገበት ባለዙም ካሜራዋ ፎቶ ስታነሳ ቆይታ ጎይቲን ፍለጋ ወደ መንደር
ተመለሰች

"ካርለት ነጋያ ... ነጋያ ... ያ ፈያው" አሉ ህፃናት የካርለትን ነጭ እጅ ለመያዝ እየተሽቀዳደሙ "ነጋያኒ  ጎይቲ ዳ! ደህና ነኝ
ጎይቲ አለች ብላ ጠየቀቻቸው በሐመርኛ

"እእ  ዳኒ" አለች አንዷ ህፃን ራሷን ዝቅ አድርጋ ሽቅብ
በመናጥ አለች ለማለት ካርለት  መዝጊያ ወደሌለው መግቢያ ጎንበስ ብላ በጠባቧ በር ወደ ውስጥ ስታይ ምርግ በሌለው የእንጨት መከታ መሐል ለመሐል በሚገባው ብርሃን ጎይቲ በርከክ ብላ እጆችደ
ከወፍጮው መጅ ላይ ሳይነሱ ራሷን ብቻ ወደ በሩ መልሳ አየቻትደ ካርለት የጎይቲን ማራኪ ፈገግታና የምትወደውን ጥርሷን ስታይ የደስታ ስሜት ውርር አድርጓት እሷም ሳቀች  ተሳሳቁ"

"አርዳ?" አለች ጎይቲ በአንገቷ እንደምትስባት ሁሉ አገጯን ወደ ታች እየሰበቀች ካርለት ፈገግ እንዳለች እሷን፥ ከኋላዋ
የተንጠለጠሉትን የቁርበት ልብሶች ግርግሙ ላይ የተንጠለጠሉትን
ዶላዎች (የወተት መያዣዎች) ግልጥጥ ያለውን የምድጃ ፍም:
በቀበቶው ጉጥ ላይ ቁልቁል የተንጠለጠለውን ክላሽንኮቭ ጠመንጃ
ልጆች አመዱን በውሃ በጥብጠው መግቢያው ጥግ ባለው የግድግዳ
ልጥፍ ላይ ያዩትን ለመሳል ያደረጉትን ጥረት ... በዐይኗ ስትቃኝ.

"አርዳ!" አለች ጎይቲ ደግማ አትገቢም! ለማለት ቃሉን ረገጥ አድርጋ።

"ፈያኔ" ብላ ካርለት እንደ ጅራት ከኋላዋ የተንጠለጠለውን
የፍዬል ቆዳዋን በግራ እጅዋ ወደ እግሮችዋ መሐል አስገብታ ቀኝ
እግሯን በማስቀደም በጠባቧ በር ሹልክ ብላ ገባች የሐመር ቤት
መዝጊያ የለውም  ቀንም ሆነ ማታ እንግዳ የአባት ሙት መንፈስ ከመጣ ሁሌም ሳይጠብቅ: ደጅ ሳይጠና ሰተት ብሎ መግባት አለበት ትንሽዋ በር ደፍዋ ከፍ ያለ በመሆኑ ለከብትም ሆነ ለአውሬ
ለመግባት አታመችም ቤት ለሐመሮች መቀመጫና መተኛ እንጂ መቆሚያ  አይደለም"  ሁሉም ነገር ትርጉም  ሊኖረው ይገባል
ስለሆነም ካለ ህፃናት በስተቀር በጣም አጭር ሰው እንኳ ጎንበስ ብሎ
ካልሆነ መቆም አይችልም ይህ የሆነው ደግሞ እንጨት ጠፍቶ ቦታ
ጠቦ ሳይሆን ለትርጉሙ ነው"

"ጎይቲ?"

"ዬ!"

ምነው ዛሬስ ስትፈጭ መዝፈን: ማንጎራጎሩን ተውሽው?" ብላ ጠይቃት ካርለት ፈገግ ብላ ጎይቲን ሳመቻት እንደ
ሐመር ሴቶች የልብ ሰላምታ ጎይቲ ካርለት ለጠየቀቻት መልስ  ሳትሰጥ አንገቷን ደፍታ እጅዋ ወፍጮው
መጅ ላይ እንዳለ በተመስጦ ስታስብ ቆይታ በቀኝ እጅዋ ማሽላውን ግራና ቀኝ ሰብስባ  ወደ ወፍጮው ጥርስ አስገብታ
ወገቧን ወደ ኋላና ወደ ፊት
እያረገረገች "ሸርደም: ሸርደም አድርጋ ፈጨችውና ብርኩማዋ ላይ ተቀመጠች
ከዚያ እኒያን ሐጫ በረዶ የመሳሰሉ ጥርሶችዋን
ገልጣ ለዓመል ያህል ፈርጠም አለችና

"ይእ!ካርለቴ ኧረ አሁን ሳንጎራጉር ነበር መቼ
እንጉርጉሮዬን እንደ አቆምኩት ግን እንጃ! አዝኜ እንኳን ቢሆን ሁልጊዜ መፍጨት ስጀምር እህሉ ከታች ሲደቅ እኔ ከላይ ትዝታዬን እየጨመርሁ እንጉርጉሮዬን አቀልጠው ነበር አሁን እኮ ኮቶ እግሯ
ወጣ ከማለቱ ነው አንች የመጣሽ ከኮቶ ጋር እየተከራከርን ሁላ እዘፍን ነበር  በኋላ ግን ኮቶ ለመሄድ ስትቁነጠነጥ እያወራች እንድትቆይ ብዙ
ክርክር ገጠምኋት
ታውቂያታለሽ ተከራክራ ተከራክራ ካልረታች እንደ ፍየል ልዋጋ ስትል ታስቀኛለች ስለዚህ ጥላኝ ከምትሄድ ብዬ ነገር ጀመርኋት

"ኮቶ ከተማ አትሄጅም?" ስላት

"ይእ! ኧረ ምን አልሁሽ እቴ እኔስ ያገሬ ጅብ ይብላኝ
አለችኝ ትንሽ ላስለፍልፋት ብዬ እኔ ግን መበላቴ ታልቀረ የጅብ ዘመድ አልመርጥም አልኋት አይምሰልሽ ጅሊት! ያገርሽ ጅብ ገሎ ነው የሚበላሽ  የሰው አገር ጅብ ግን እየበላ ነው የሚገልሽ ስትለኝ ይእ! አንች ምነው ታልጠፋ አውሬ ጅብን እንዲህ ዘመድ
አዋቂ አደረግሽው?
አልኳት‥ ይሄ እንኳ ምሳሌ ነው ስትለኝ ሞጥሟጤ  ምሳሌሽን ቀይሪያ!ታለበለዚያ ካለ
ጥንባቸው ሌላ
የማያውቁትን ጅቦች ካለስማቸው
ስም ሰጥተሽ ቅዱስ አድርገሽ ታውሬው ሁሉ አታቀያይሚያቸው" ብላት ወገቤን ደቅታኝ ሹልክ ብላ ሄደች ከዚያ ማንጎራጎር ጀምሬ ነበር ወዲያው ግን ድምፄ ለከት የለሽ ሆኖ ልቤ ግንድ የሚያመሽክ ምስጥ ይርመሰመስበት ጀመር

"ምን ሆነሽ ነው ጎይቲ የምን ጭንቀት ነው?"

"ወደው አይስቁ አለ ያገሬ ሰው ..." ብላ ጎይቲ ከትከት ብላ ስቃ።

"ይእ! ምነው እንዳንች ጅል ሆኜ እድሜ ልኬን ስጠይቅ
በኖርሁ" ስትላት ተያይዘው እንደገና ተሳሳቁ

"ካርለቴ! እውን ሴት ልጅ እግርና እጅዋ የሚያጥረው፥
ቀትረ ቀላል ሆና ድምጿ የሚሰለው ... ለምን እንደሆን አታውቂም?

"አላውቅም ጎይቲ ለምንድን ነው?"

"ይእ! እንግዲያ ዝናብ እንደበዛበት ማሽላ ታለ ፍሬ መለል ብለሽ ያደግሽ አገዳ ነሻ! ሙች አንችስ ተህፃን አትሻይም አንቺ እኮ! ተንግዲህ ወዲያ ትልቅ ሰው ነሽ! ጉያሽና ልብሽ ላይ የትዝታ ምሰሶ የተተከለ
ፈጭተሽ የምታበይ ጭሮሽ ውሃ ቀድተሽ ለጥም
መቁረጫ የምታጠጭ
የወንድ ልብ ሲጎመራ ጫካ መሃል ገብተሽ የምትካፈይ
ፍቅርሽን እንደ ህፃን ልጅሽ የምትግች ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?" ትልቅ ሴት እኮ ነሽ?"

"ጎይቲ የባሰ ግራ ገባኝ?"

"ይእ! እንዲያ ይሻላል! ቁም ነገር አታውቂም ብዬ ተመንገር ሌላ እህ ላሳይሽ?"  ብላ ጎይቲ በአድናቆት ጨብጨብ ጨብጨብ አድርጋ በሣቅ ተፍለቀለቀች

ካርለት ከተቀመጠችበት
ፈገግ ብላ ተነስታ ጎይቲን ገፋ አድርጋት የወፍጮውን መጅ በግራ እጅዋ ይዛ ከሾርቃው በቀኝ
እጅዋ ማሽላውን አፍሳ ጨምራ

"እሽ እኔ እፈጫለሁ አንች ንገሪኝ?" አለቻት

"ይእ! እውነት ታላወቅሽውማ እነግርሻለሁ  እንጂ ብላ እግሯን ዘርግታ ቁርበቱ ላይ ቁጭ አለች ጎይቲ ወደ ቁምነገር
ስትመለስ የሚያስጨንቃትን
ለመናገር ስትዘጋጅ ውስጧን የሚጎማምደው ችግሯ የፈገግታ ፀዳሏን እየቸለሰ አከሰመው ደሟ
እንደቀትር ማዕበል ደረቱን ገልብጦ እየዘለለ በመፍረጥ አረፋ ደፈቀ
ታወከ
"ሐመር ላይ ሴት ልጅ የግል ችግር የለባትም እምትበላውን መሬቷ እምትጠጣውን ላሞች: ፍቅርን ደግሞ የሐመር ወንዶች እንደ ማሽላ ገንፎ እያድበለበሉ ያውጧታል ሴት ልጅ ወንዝ
ብትሄድ እንጨት ለቀማ ጫካ ብትገባ እህል ልታቀና ገበያ ብትወጣ ብቻዋን አትሆንም ሰው ከብቶች: ዛፎች አሉላት ሴት ብቻዋን ችግር የሚገጥማት የማትወልድ ስትሆን ነው መሐንነት ትታይሻለች ያች ፀሐይ " ዝቅ ብላ በግርግዳው ቀዳዳ ጮራዋን ፈንጥቃ የምትንቦገቦገውን የረፋድ ፀሐይ እያሳየቻት

"ይኸውልሽ መሐንነት ያችን በሙቀት የምትነድ እሳት ዘላለም እንደ ጨቅላ ህፃን ደረትሽ ላይ ታቅፈሽ መኖር: ታቅፈሽ መሞት ነው" ተዚያ እድሜ ልክሽን መቃጠል: መንደድ ነው"

"መሐንነቱ የመጣብሽ ሳታስቢው የሴት ብልትሽን ውሃ ነክቶት ይሆናል ሆን ብለሽ ባታደርጊውም ትዕዛዝ ነውና ቅጣቱ ቃጠሎው ወደ ገለብ ብትሮጭም አታመልጭውም ስትቃጠይ ደግሞ ሰው የሻጉራ እያዬ ይሸሽሻል ባይሆን ከቃጠሎሽ  ባይጠቅምሽም
ለእነሱም ባይጠቅማቸውም ለአባትሽ ለእናትሽ ለእህትሽ
ለዘመዶችሽ ታካፍያቸዋለሽ የተረገመ ቤተሰብ እያሰኘሽ" ብላ ዝም አለች ጎይቲ  እንደተላጠ ጣውላ ሰውነቷ ሟሾ

ግዙፍነት ለካ በአጥንትና ስጋ ብቻ አይደለምና  መጠንም በህሊና ይወሰናል ውበትና ቁመና ህሊና በሚፈጥረው መተማመን ተገዥ ነውና! እያለች ካርለት ጎይቲን እያየች ስታስብ
👍19👎1
"ሐመር ላይ ሴት ልጅ ማህፀኗ ባዶ ከሆነ አፏ አለብላቢት እንደበላች ፍየል ሰውን ይረብሻል ቅስም ሰባሪ ተስቦ በሽታዋ ሁሉንም ተአጠገቧ ያርቀዋል ከዚያ ተከብቱም ተሰውም በረት ርቃ
ብቻዋን ሆና እህል የማያበቅል እማይጠጣ እንደ በረዶ እየቀዘቀዘ
በመንዠቅዠቅ የማያባራ
ዝናም ላይዋ ላይ እየወረደ ጥርሷን እያፋጨች ስትንቀጠቀጥ እናቷ እንኳ አትደርስላትም"

መከራዋን ስታዳምጥ
ማንጎራጎሩን ከልቦናዋ ትረሳዋለች የኢቫንጋዲ ዳንሱ ትዝታ ሙልጭ ብሎ ይጠፋል . ያን ጊዜ ካርለቴ
የኩራት ክብሩ ቀርቶ ሆደ ባሻነት እንደ ሰንበሌጥ ሣር በውስጥሽ በቅሎ በቅሎ ይውጥሻል" ለሐመር ሴት እውነተኛው ለቅሶ እንደ
አባቷ መፎከሪያ በሬ እየተፎገራች ግረፉኝ ስትል እየተንጠራራ ጎረምሳ በባራዛ አርጩሜ ጀርባዋን ሲሸነቁጣት ሰንበሩ እንደ እባብ ጀርባዋ ላይ ተጋድሞ: ደም ፍጭጭ ሲል ከዐይኗ የሚፈሰው እንባ አይደለም ያማ ስቃይሽን እንዲያጠፋ በአባትሽ ደንብ ከተሞላው
ልብሽ የሚደፋ የሥቃይ ማጥፊያ ውሃ እንጂ ለቅሶ አይደለም ካርለቴ! የኔ እህት  ለቅሶ ማለት የውስጥ ቃጠሎ ነው" ውስጥሽ
የሚንቀለቀልን እሳት ማጥፋት ሲቸግርሽ ነው ወደ እሳቱ የምትደፊው የእንባ ውሃ ስታጭ ነው ..." ሳግ ተናነቃት ጎይቲ
ውስጧ ጤሶ ተቀጣጠለ ካርለት ደነገጠች

"ኦ! ጎይቲ ካርለት ጎይቲ እንዲህ አዝና ተስፋ ቆርጣ አይታት አታውቅም
ሃዘኗ አሸበራት ፊቷ እንደ በሰለ ቲማቲም ቀላ አንጀቷ በኃዘን ተላወሰ ጎይቲ ንፍጧን ተናፍጣ እንባዋን
በአይበሉባዋ ጠርጋ

"እንዲያ ታያ ደልቲና ተጎረምሶች ጋር በየጫካው ስቃበጥ ጓደኞቼ ማህፀናችንን እንፈትሸው' ሲሉ እኔ ውበቴ ጠላት ሆኖኝ
ጨረቃን እያየሁ: እየተጠነቀቅሁ መቅበጥ እንጂ ልቤን ደፍኖኝ
ለማርገዝ አልሞከርኩም ነበር ... ስትል ካርለት ንግግሯን አቋርጣት,

"ጎይቲ ምንድን ነው ደግሞ ማህፀን መፈተሽ'? አለቻት
ጎይቲ ወዘናው በቀነሰ ፈገግታ ፈገግ ብላ "ይእ  አንች ሰው! ምኒቱ
ልብ አድርቅ ነሽ እቴ! ይህን ይህን ታላወቅሽ እህ እሱን ጭሮሽሽን አስደፍኝና ቦርጆን እንዳሁላ
አብቅልልኝ ብለሽ ሳዳጎራሽን አገልድመሽ ተወንዶች ጋራ አደን ውረጂያ!"

"አትሰልችኝ ጎይቲ! ስለማላውቀው እኮ ነው  የምጠይቅሽ?" አለች ካርለት ለጥናቷም ትልቅ ፍንጭ በማግኘቷ ባንድ በኩል ደስ እያላት

"ይእ! አታምርሪ የኔ ሸጋ  ጨዋታየን እንጂ እንኳን ይህን አያ ደልቲና አንች ጫካ ስትገቡ … ብለሽስ
ጠይቀሽኝ መልሸልሽ
የለ ላላወቀ ደግሞ መመለሱ ምኑ ያሰለቻል
ደንብ ነው!" ብላ

"ማህፀን መፈተሽ ማለት ማርገዝ  ማለት ነው በሐመር ልጃገረድ ቀብጣ ስታረግዝ አትጠነቀቅም
ነበር ተብላ ላይ ላዩን
ብትወቀስም ማርገዟ ግን ጥቅም አለው
አባቷንም የሚያስደስት
ፅንሱን ብታስወርድም ማህፀኗ የተቀደሰ ነው' ትባላለች ባልም
እጮኛ ሊያረጋት ይሽሎኮሎካል ያን ጊዜ አባቷ ጥሎሹን ጨምሮ
ይጠይቅባታል፤ ጥሎሽ ከፋዩም ማህፀኗ የተቀደሰ ስለሆነ ይሁን ብሎ ይስማማል" ያን ነው ልጃገረዶች ማህፀን መፈተሽ የሚሉት" ብላ
እሷ ያን ባለማድረጓ መበሳጨቷን እጅዋን በእጅዋ እየደበደበች
አሳየች ካርለት ዐይን ዐይኗን ስታያት ቆይታ

"ጎይቲ መሃን ሴት በምን ትታወቃለች?" አለቻት"

"ይእ! በቀንዷ!" ብላ ጎይቲ ቀለደችና ስትስቅ  ካርለትም
አብራት ሳቀች

"ጎይቲ እየቀለድሽብኝ ነው?"

"ይእ! እህ ምናባቴ ላርግ ካርለቴ  ሴቱ ሁሉ የሚያውቀውን
አንች አዲስ ሆነሽ ስትጠይቂኝ መቀለድሽ አይደለ?"

"የለም ጎይቲ  አልቀለድሁም ቁም ነገር እየተጫወትን
አልቀልድም "

"ይእ! ምን ነበር እቴ የጠየቅሽኝ?"

"መሃን ሴት በምን ትታወቃለች?"

"… በጥንት ጊዜ ቦርጆ እዚሁ እቅርብ ተሐመሮች ጋር ነበር አሉ የሚኖረው" ታዲያልሽ አንድ ጊዜ ከአንዲት ሴት ጋር ይጣሉና
ሴቷ ቦርጆን በጋሊ አርጩሜ ትደበድበዋለች እና በጥፋቷ ያዘነው
ቦርጆ መሐን ሁኝ ብሎ ረገማትና የሐመር ወንዶችን ሰብስቦ  አብሬያችሁ በመኖሬ እየተናናቅን ነው
ዝናብ ስትፈልጉ
ተሰብስባችሁ ጥሩኝ እርስ በርሳችሁ አትጣሉ
ከተጣላችሁ ደግሞ
ሽማግሎች ያስታርቋችሁ
በቡድን ሁናችሁ አትጣሉ
ያገኛችሁትን ተካፍላችሁ እንድትበሉ በራችሁ ቀን ከሌሊት አይዘጋ ካለበለዚያ
ዝናብ አልሰጣችሁም"
ሁሉም ሴቶቻችሁ አይወልዱም
ከብቶቻችሁም አይራቡም በሽታም እልክባችኋለሁ  ብሎ ነው አሉ ርቆ ሰማይ ላይ የወጣው" እና  መሐን ሴት ቦርጆን : ደብድባ
የተረገመች ናት ስትሞት እንኳ ነፍሷ መጀመሪያ እሳት ውስጥ ተዚያ ተተከማቸ ትል ውስጥ ነው አሉ ስትባዝን የምትኖረው ንግግሯን አቋርጣ  ጎይቲ | ስቅስቅ  ብላ  አለቀሰች ካርለት  ጎይቲ ባለችው ባታምንም
“እምነቷ ምን ያህል
እንደረበሻትና ባለመውለዷም የሚጠብቃትን ጣጣ አስታውሳ ለእሷና ለሌሎችም መሐኖች አዘነች" ካርለት   የምታውቀውን ለጎይቲ እንዴት እንደምታስረዳት ስታስብ ቆየችና

"ጎይቲ መሐንነት የትም አገር አልፎ አልፎ አለ ችግሩ ግን
ከሴቷ ብቻ ሳይሆን ከወንዱም ሊመጣ ይችላልኮ" ስትላት ጎይቲ
ቅንድቧን ሽቅብ ሸብሽባ

"ይእ! የባሰው መጣ!
ኧረ ዝም በይ ያገር መሳቂያ
እንዳትሆኝ. የዘራሽው እህል
ባይበቅል ችግሩ ተመሬቱ
ነውዐኸዘሪው?  አንች እውነትም ዝናብ በዝቶበት ፍሬ ያልያዘ ማሽላ ነሽ"
አለቻት" ካርለት በምን ዘዴ እንደምታስረዳት ጨንቋት መላ ፍለጋ መሬቷ ላይ አፈጠጠች

💫ይቀጥላል💫
👍26
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ አራት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«ጓደኛዬ ነው!! ትናንት አንተን ትተን ስንወጣ ተከትለውን ነበር።» ብዬ ሆስፒታል የመተኛቱን ሚስጥር አብራራሁ ጎንጥን ምኔ ነው ብዬ ማስተዋወቅ እንዳለብኝ ግራ ሲገባኝ ማቅረቤ ይሁን ማራቄ ልኬቱን እንጃ!! ወዲያው ግን ስም ሲለዋወጡ በስሙ ያውቀዋል እና ኪዳን ዞሮ አየኝ! <ጎንጥ ይሄ እኔ የማውቀው ጎንጤ?> ዓይነት አስተያየት! ምንም እንዳይጠይቀኝ በልምምጥ ሳየው እኔን ተወኝ! ከዛ ግን ወንበር ስቦ ጎንጥ ፊት ተቀምጦ አንዱን ጥያቄ ከሌላው እያስከተለ ይደራርብ ጀመር።

«ቤተሰብ አለህ? ማለቴ የራስህ ሚስትና ልጆች? አዲስአበባ ከመጣህ ቆየህ? ሜልጋ ሳትሰራ በፊት ምንድነበር የምትሰራው? ሴት ጓደኞችህን ሁሉ <ዓለሜ> ብለህ አትጠራም መቼም አይደል? ስራህ ስለሆነ ነው ወይስ ሜል ስለሆነች ነው (በአገጩ የተመታውን ጠቆመው) ከዳንክ በኋላ ….. »

«ኪዳን?» አልኩኝ በልመና መጠየቁን እንዲያቆም ….. በአንድ በኩል ግን መልሳቸውን ልሰማቸው የምፈልጋቸው ጥያቄዎች መሆናቸው ለጎንጥ መልስ እንድጓጓ አደረገኝ። የእውነት ከዳነ በኋላስ?

«ሴት ልጅ አለችኝ!» የሚለውን ብቻ ነው ከዚህ ሁሉ ጥያቄ ፈገግ እያለ መርጦ የመለሰው። ኪዳን ሌላውን ጥያቄ እንዲመልስለት አንገቱን አስግጎ ጠብቆ ዝም ሲለው

«come on!» አለ

«መሽቶም የለ? ሂዱና ጎናችሁን አሳርፉ!! » ሲል ነው ጎኔ አልጋ ከነካ 48 ሰዓት እንዳለፈው ትዝ ያለኝ።

«እርግጠኛ ነህ ብቻህን ምንም አትሆንም?»

«ምንም አልሆን አልኩሽ እኮ!!» ያለበት ድምፅ <ዓለሜ> እንደሚለው ያለ ማባበል አለው ነገር? ወይም መስሎኝ ነው 48 ሰዓት ያልተኛ ሰው ብዙ ያልተባለ ነገር የመስማት እድሉ ከፍተኛ ነው።

ይሄን ካለ በኋላ ለሆነ ደቂቃ የሆነ ያልተለመደ ዓይነት ዝምታ ተፈጠረ። ቻው ብዬው መውጣት እፈልጋለሁ ግን የአልጋው ግርጌጋ እንደተገተርኩ ነው። ልቤና እግሬ ተጣሉብኝ!! እንድሄድ እየጠበቀ ነው ግን በዓይኖቹ እንድቆይለት እያባበለኝ ነው ወይም መሰለኝ። በእንደዛ ዓይነት ፖዝ ፎቶ አንሺ ያስቆመኝ ነው የምመስለው።

«እኔ የምለው? እኔኮ ብቻዬን ማደር እችላለሁ! አንቺ ለምን እዚህ አትቆዪም?» የሚለው የኪዳን ንግግር ነው እኩል ሁለታችንንም እንደመባነን ያደረገን

«አይሆንም!» አልን ሁለታችንም በአንድ ድምፅ ግንኮ አሁንም ኪዳንን ያየው የለም እኔና እሱ ዓይናችን አልተፋታም! ከዛ ደግሞ ራሴው አይሆንም ያልኩትን እሱም አይሆንም ማለቱ ለምን ከፋኝ?

«እህእ? ወይ ሶስታችንም እዚሁ እንደር?» አለ ኪዳን ሳቅ እያፈነው። አሁን ሁለታችንም አየነው። ስንወጣ ሲያበሽቀኝ እንደሚያድር አውቃለሁ።

«ደግ! በሉ ቸር እደሩ!! ትከሻሽን መገላመጥ አትዘንጊ!» አለ በቃ ተሰናብቼሻለሁ ሂጂ እንደማለት ነገር ከነበረበት በቀስታ ዘወር እያለ።

«የምትባባሉትን ተባባሉ በሩጋ ነኝ!» ብሎ ኪዳን ወጣ!! ምን እንደሚባል የማውቀው የለኝም!! ማለት የምፈልገው መኖሩንም እንጃ! ካለሁበት ተንቀሳቅሼ ልቀርበው ፈልጌ ማፈር ነው ግራ መጋባት የማላውቀው ስሜት ጨመደደኝ። ጭንቅላቴም ልቤም ሰውነቴም ተባብረውብኝ ማድረግ የምሻው ብቸኛ ነገርኮ እሱን መንካት ነው። እንዲህ ሆኖ የሚያውቅ ሰው ኖሮ ያውቅ ይሆን አላውቅም! ገብቶት ነው መሰለኝ ወይም እሱም እንደእኔ አካላቶቹ አምፀውበት ሊነካኝ ፈልጎ እጁን እንድይዘው ዘረጋልኝ። ከረሜላ አይቶ ሲቁለጨለጭ ምራቁ አፉ ውስጥ ሞልቶ ወደ ጎሮሮው ሲደፍቅበት ቆይቶ ከረሜላውን እንደሰጡት ህፃን በአንድ እርምጃ ዘልዬ እጁን ያዝኩት። እጁን እጄ ላይ ከማጫወቱ ውጪ በቃላት አላወራኝም። በዓይኖቹ የሚያወራው ደግሞ ትርጉሙ እኔ እንደምፈታው ይሆን ሌላ እየገባኝ አይደለም። <የዓይን ቋንቋ እንደፈቺው ነው!>

«ከዳንክ በኋላስ?» አልኩት ለሚመልስልኝ መልስ ሳልዘጋጅ

«አላውቅም!» አለኝ ከአይኔ ውስጥ ቆፍሮ የሚያወጣው ስሜት ያለ ይመስል በአይኑ አይኔ ውስጥ እየቆፈረ። መልሱ ምን ሊሆን እንደሚችል የጠበቅኩት ነገር ስላልነበረ አልከፋኝም! እሙ እንዳለችው ከመጃጃልም በላይ እየሆንኩ እንደሆነ የገባኝ ከ<አላውቅም> አስከትሎ <ዓለሜ> አለማለቱ ከፋኝ! አንዴ አለሜ በለኝ ብለው ሆዱን ይዞ አይስቅብኝም? ይባላልስ?

«አንቺ ምንድነው የምትፈልጊው?» አለኝ

«አላውቅም! ምን እንደምፈልግ አላውቅም!» አለ አፌ! የምፈልግ የነበረው ግን ዓለሜ እንዲለኝ ፣ የምፈልግ የነበረው እንደቀኑ የእጄን መዳፍ መሃሉን እንዲስምልኝ፣ እምፈልግ የነበረውማ ለአንዴ በህይወቴ ጀግና ጀግና የማልጫወትበት ሰው እንዲሆነኝ ……. ለአንዴ ብቻ ፍርሃቴን ፣ ድክመቴን ፣ ማፈሬን ፣ ሽንፈቴን ፣ …. ከእንባዬ ጋር ለውሼ ደረቱ ላይ እንድተነፍሰው በክንዱ ደግፎ ደረቱ ላይ እንዲያቅፈኝ ….. እፈልግ የነበረውማ ይሄ ያልኩት ሁሉ ሲሆን ዘመናት ቢቆጠሩ ነበር። ቀጥዬ ያልኩት ግን

«ኪዳን አባት ሊሆን ነው!» የሚለውን ነው! ሳልፈልግ ድምፄ ውስጥ መከፋቴ ተሰማብኝ። የያዘውን እጄን ስቦ ወደደረቱ አስጠግቶ ደረቱ ላይ አጥብቆ ያዘው። ይሄ ሰውዬማ ከእጄጋር የሆነ ነገር አለው! ነውስ እጄና ልቤ የሚያገናኛቸው ነገር አለ እጄን የሆነ ነገር ሲያደርገኝ ልቤ አብሮ የሚያሸበሽበው?
👍14👏1
«ዳር የተተውሽ መሰለሽ?» ሲለኝ እንባዬ ታገለኝ!! ነግሬዋለሁ? አልነገርኩትም! የተሰማኝን በልከኛው ቃል እንዴት ማስቀመጥ ቻለበት? አንዲት ፊደል ከአፌ ቢወጣ እንባዬ እንደሚያጅበው ስለገባኝ ዓይኖቹን ሸሽቼ ዝም አልኩ። ደረቱ ላይ የያዘውን እጄን እዛው ትቶት በእጁ አገጬን ደግፎ ዓይኖቹን እንዳያቸው አደረገኝ።

«መቼም ቢሆን በምንም የማይተካሽ እህቱ ነሽ!! ሚሽትና ልጁ ያንቺን ቦታ አይጋፉም!! ኪዳንን በዚህ ሁሉ መዓት ፍቅር ስትወጂ ልብሽ ጠቦሽ አባትሽን አስወጥተሻል? ወይሳ እናትሽን? እኔን ወደልብሽ ስታስገቢስ ልብሽ አልበቃ ብሎ ከኪዳን ፍቅር አጎደልሽ? የእርሱን ቦታ ቀነስሽ?»

«አይ!!» ብዬ ጭንቅላቴን በአሉታ ከነቀነቅኩ በኋላ ነውኮ መጨረሻ ላይ ያለውን ለራሴ ደግሜ ስሰማው ዓይኔን የማሳርፍበት የጠፋኝ። ጥሩ እየሰማሁት ነበርኮ ከመጨረሻው እሱን ልቤ ካስገባበት ዓረፍተ ነገር በፊት! <አይ> ያልኩት ምንድነው ቆይ? የኪዳንን ፍቅር ሳታጎድል ነው ልቤ የገባኸው ነው አይደል ያልኩት? የጥያቄው መልስ እንደተመለሰለት ፈገግ ብሎ አገጬ ላይ አውራ ጣቱን አሸት አሸት ነገር አድርጎ እጁን ደረቱ ላይ ወደተወው እጄ መልሶ እንደቅድሙ አጥብቆ ደረቱ ላይ ያዘው።

«ያልኩት ሀቅ አለው?» ብሎ አወነባበደብኝ። ምናለ ዝም ቢለኝ ገብቶት የለ?
«ምኑ?»
«ከልብሽ ገብቻለሁ?»
«አዎ! መሰለኝ! እኔ እንጃ አላውቅም! በምን አውቃለሁ?» በዚህ ነፋሻማ አየር እንዲህ ሊሞቀኝ ይገባ ነበር? ስፈራ ጉልበቴን እንደቁርጥማት እንደሚያደርገኝ ነገር አሁን ሊሰማኝ ይገባ ነበር? ሳቅ እንደማለት ነገር ብሎ

«በይ ተነሽ ሂጅ አሁን እየጠበቀሽ ነው!!» ብሎ እጄን አንስቶ አገላብጦ ይስመው ጀመር!! አንዴ ሁለቴ ሶስቴ ….. ሁለቴ አይበሉባውን አንዴ ወይም ሶስቴ መሃል እጄን….. እኔ እንጃ አንድ አራቴ ጎኑን ….. ጣቶቼን …… ከመጀመሪያው በኋላ እንኳን ቁጥሩን ላውቀው እንደባለፈው ራሴንም አለመዘንጋቴ በቸርነቱ ነው። ከዛ ነገና ዛሬዬን ከደባለቀብኝ በኋላማ ምንም እንዳልሆነ ነገር እጄን መለሰልኝ። ማድረግ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበር። ግን ለመሄድ ተነሳሁ እና ወደበሩ መንገድ ጀመርኩ። ልቤማ ደረቴ ውስጥ የለችም! እንጂ ሰውነቴ እንዲህ ወደኋላ ባልጎተተኝ። በሩጋ ደርሼ ዘወር አልኩና

«ነገ እኮ እማዬጋ ልሄድ እችል ይሆናል።» አልኩት ለምን እንዳልኩት ሁሉ እኔ እንጃ! ምናልባት አንድ ደቂቃ እሱጋ መቆያ ምክንያት እየፈለግኩ መሰለኝ።

«ደግ!!» ብቻ ነው ያለው!! እንዴ? ምንድነው ሰው ማግዶ እሪሪሪ እስኪሉ መጠበቅ? ኮስተር እንዳልኩ ለራሴ እየታወቀኝ በሩን ይዤ ቆምኩ!

«ምነው ዓለሜ? የምትነግሪኝ አለሽ እንዴ?» ሲል ከንፈሬ ሳላዘው ሸሽቶ ያለኝ ጥርስ ሁሉ ንፋስ ዳበሰው

«ምንም የለም! ደህና እደር በቃ!» ብዬው ወጣሁ። መኪናው ጋር እስክንደርስ ከኪዳን ጋር ምንም ቃል አልተለዋወጥንም! መጣሁ መጣሁ እያለ እየተናነቀው እንደሆነ ያስታውቅበታል።

«ትከሻሽን መገላመጡን አትርሽ ዓለሜ!» አለ መጨረሻ ላይ ከት ብሎ እየሳቀ

«አፍህን ዝጋ እሺ!! አንድ ነገር እንዳትለኝ!» አልኩት ሳቅም ማፈርም በደባለቀው ቁጣ

«ጀግና ነው ግን ሜል ሙች!! ይፈርምልኝ! ጠባቂ ሆኖ ገብቶ ጠብ ያድርግልኝ? ሜል ገና ስታይው ፍስስ እኮ ነው ያልሽው!»

«ኪዳን ተወኝ አልኩ እኮ!»

«አንዴማ ጨብጬው ልምጣ ሜል ሙች» ብሎ ወደኋላው እንደመመለስ አለ

«ባክህ አርፈህ መኪና ውስጥ ግባ አትጨማለቅ!!»

የማውቀው ገስትሀውስ ደውዬ አልጋ ያዝኩ። መንገዱን ሁሉ ሲያበሽቀኝ እና ሲገረም ዘለቅነው «ምን አባቱ አድርጎሽ ነው ግን ስንቱን ወንድ ያሸና ልብሽን ዘጭ ያደረገው? ፣ እኔንኮ እዛ እንደሌለሁ ረሳችሁኝ ሆ! ፣ እድሜ ደጉ ሜል ስትሽኮረመም ያሳየኝ? ፣ ፍቅር በሀገርኛ ግን ጆሮ ላይ ደስ ይላል አንቺ? ነፍሴን አወክሻትኮ ዓለሜ! ነው ያለው? > አያቆምም ይለፈልፋል። በመሃል

«ሜል ሻምበሉጋ ከአንድ ሰዓት በኋላ እደውላለሁ ካልሽው ሁለት ሰዓት አለፈ!» ሲለኝ ሰዓቴን አየሁት። መርሳቴ እኔንም ኪዳንንም ገረመን!! አንድ ሰው እንዲህ የሰውን ሀሳብ መቆጣጠር ይችላል?

«እኩለለሊት ሊሆን ነው!! ጠዋት ብደውል ይሻላል!!» ስለው ኪዳን አይኑን ጎልጎሎ አውጥቶ አፈጠጠብኝ

«you know am happy for you!! ሜል ነገር አሳደረች? ያውም ሊገድላት የሚከረ ሰው ? ፍቅር ግን ደስ ሲል!!»

«ለምንድነው ግን አፍህን የማትዘጋው?»

ለሁለት ደቂቃ ዝም ይልና ደግሞ ይጀምረኛል። ማረፊያችን ደርሰን የምናወራው ቁምነገር መኖሩን ተኮሳትሬ እስክነግረው ማብሸቁን አላቆመም!!

«አሁን የምር አስጨነቅሽኝ! ምንድነው ንገሪኝ!!» አለኝ አጠገቤ አልጋው ላይ እየተቀመጠ አንድ እጁን እንደማቀፍ ትከሻዬ ላይ ጣል እያደረገ

«እማዬ አልሞተችም! በህይወት አለች!! እና ልታይህ ትፈልጋለች!»

«ማለት?» ብሎ እጁን ከትከሻዬ ላይ አነሳው

«በሰዓቱ ላንተ እውነቱን መንገር ከምትሸከመው በላይ ስለሚሆንብህ ነው ከአጎቴ ጋር ተነጋግረን እንደሞተች የነገርንህ! ታዲያ የታለች ብትለን ኖሮ መልስ አልነበረንም!»

«እና የት ነበረች?» ብሎ ስፈራው እና ስሸሸው የኖርኩትን ጥያቄ ጠየቀኝ። እንዴት ብዬ እንደምነግረው ስጨነቅ

«ሜል ያኔ ህፃን ስለነበርኩ ነው የዋሸሽኝ አሁን ግን ትልቅ ሰው ነኝ ንገሪኝ!!» ብሎ ሲሆን አይቼ እንደማላውቀው ተኮሳተረ። የዛን ቀን ያየሁትን ነገር በሙሉ ነገርኩት። እየጠበቅኩ የነበረው የሚናደድ ወይ ሌላ ጥያቄ የሚያስከትል ነበር። እሱ ግን መጥቶ እያቀፈኝ

«አንቺምኮ ይሄን ሁሉ ብቻሽን የምትሸከሚበት እድሜ ላይ አልነበርሽም!!» አለኝ። ቀጥሎ ግን «አንቺ ትታን ስለሄደች አላዘንሽባትምኣ?» ብሎ ያላሰብኩትን ጥያቄ ጠየቀኝ።

«አላውቅም የኔ ኪዳን! ልጅ እያለን ብዙ ጊዜ ተናድጄባት አውቃለሁ። የምናደደው ግን ትታኝ ከመሄዷ በላይ ካየሁት ነገር በላይ እናትነቷን እንደማይላት እንዴት አልተረዳችልኝም ብዬ ነው! ከውርደቷ በላይ ፍቅሯ እንደሚገዝፍብኝ እንዴት ማሰብ አትችልም ብዬ ነው። ከዛ ግን የዛን ቀን ዓይኗ ውስጥ ያየሁት ህመሟ ከምናደድበት ይበልጥብኝና አንድ ቀን አጊንቻት ባቅፋት ነበር የምመኝ የነበረው»

«እሺ አገኛታለሁ!! ላገኛት ፈልጋለሁ!!» አለኝ።

«ታማለች ኪዳንዬ" አልኩት!እናቱን የማግኘት ተስፋ እንደሰጠሁት ትዝ ሲለኝ ብዙ ከማለሙ በፊት እየተሽቀዳደምኩ ይመስል ተቅለብልቤ

«ታማለች ማለት? የከፋ?»

«አዎን!! ታውቃለህ ለበደሌ እየቀጣኝ ሁሉ መስሎ ተሰምቶኝ ያውቃል! ዓይኗን ደግሜ ባየው ብዬ ዘመኔን የተመኘሁላት እናቴን በመጨረሻ ሳገኛት ለሞቷ ቀናት እየቆጠረች ሆነ።» ከዚህ በኋላ ለረዥም ሰዓት ዝም ተባባልን!! በቃ ዝም! የዛለው ሰውነቴ የተቀመጥኩበት ወደቀ። እግሬን ወደላይ ሰብስቤ ተጋደምኩ።
👍11
የነቃሁት የቧንቧ ውሃ ሲወርድ ሰምቼ ነው። ኪዳን ቀድሞኝ ነቅቷል ወይም አልተኛም! አልጋው ጫፍ ላይ እንቅልፍ እንደወሰደኝ ልብስ ደርቦልኛል። ምናልባት እንቅልፍ አልወስድ ብሎት የነበረ ይሆን ብዬ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። በደቂቃዎች ውስጥ እናትህ አለችም ልትሞትም ነው የሚል መርዶ አርድቼው እኔ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ። እናቴን አግኝቻት ልትሞት መሆኑን ሳውቅ ለወራት መቀበል አቅቶኝ የሆንኩትን መሆን አስቤ ያጠፋሁ መሰለኝ። ብቅ ሲል

«ይቅርታ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?» አለኝ

«ነግቶ የለ! ምነው እንቅልፍ አልወሰደህም እንዴ?»

«አይ ተኝቻለሁ!» ይበለኝ እንጄ የእኔን ኪዳን መች አጣሁት እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነው ያደረው። አስር ጊዜ <ደህና ነህ> እለዋለሁ። <ደህና ነኝ> ይለኛል።

«ማውራት ትፈልጋለህ ኪዳንዬ?»

«አልፈልግም! ዝም ብለን እንሂድ!» አለኝ።

ከመሄዴ በፊት ብዙ ማድረግ የምፈልጋቸው ነገሮች ነበሩኝ። ሆስፒታል ሄጄ ጎንጥን ማየት። ሻለቃው ጋር መደወል፣ ሴትየዋ ማን መሆኗን አውቄ ማግኘት….. ብዙ!! ከኪዳን የሚበልጥ ነገር የለኝም አይደል? እሱ እንዲህ በዝምታ ተለጉሞ የሚሰማውን እንኳን ሳላውቅ ራሴን ማስቀደም አልሆንልሽ አለኝ!! ክፍላችን የመጣውን ቁርስ እንደነገሩ እየለኳኮፍን መኪና ስፈልግ የሚያዘጋጅልኝ ሰው ጋር ደውዬ መኪና እንዲያመጣልኝ ካደረግኩ በኋላ የዳዊትን መኪና ሌላ ቦታ ወስዶ እንዲያቆምልኝ አደረግኩ። ለዳዊት ደውዬ መኪናውን ከቆመበት እንዲወስድ ስነግረው ምንም እንዳልጠረጠርኩ ለመምሰል ከራሴ ታገልኩ። መንገድ ከጀመርን በኋላ ሻንበሉ ደወለ። የመኪናው ባለቤት እና ልትገድለኝ የሞከረችው ሴት የተለያዩ ናቸው። ግን ሁለቱም በስማቸው የማውቃቸው አይደሉም!!

«ቢሮ ብቅ ካልሽ የሁለቱንም ፎቶ ላሳይሽ እችላለሁ!!» ብሎ ስልኩን ዘጋው!! መልዕክቱ አንድም ለመላክ አላምንሽም ነው ሁለትም ፎቶውን ለማየት ተጨማሪ ዋጋ አለው ነው። ስልኩን ዘግቼ ዝም አልኩ! ኪዳንም ምንም አልጠየቀኝም!! ዝምታው አስጨነቀኝ!! ልቤ ድንጋይ የተጫነበት እስኪመስለን ድረስ እንደከበደኝ ተጉዘን ከሰዓታት በኋላ እነእማዬጋ ደረስን!! አጎቴ ከበር እንደተቀበለን ኪዳንን እያገላበጠ ስሞ አልጠግብ አለው!!

«አቤት አንተ መድሃንያለም ምን ይሳንሃል!! አስካል ልጅሽ መጣልሽ!» እያላት ወደ ውስጥ ገባ!! እማዬ ለመነሳት በዛለ ጉልበቷ ተፍጨረጨረች። ከሁለት ቀን በፊት ካየኋት በላይ ገርጥታለች። ይብሱን የከሳችም መሰለኝ። ዝም እንዳባባሉ ፣ እንደማታው አጠያየቁ ከኪዳን ጋር ሲተያዩ አሁን የሚሆኑትን የሚሆኑ አይመስልም ነበር። ጉልበቷን አቅፎ ተንሰቀሰቀ። ፀጉሩን እየደባበሰች ተንፈቀፈቀች። እኔና አጎቴ የሁለቱን መሆን እያየን ስንነፋረቅ ቆይተን! አጎቴ ፊቱ ላይ የተዝረከረከ እንባውን ጠራርጎ ሲያበቃ ደግሞ እንዳላለቀሰ ሰው ኮስተር ብሎ

«አይ ደግም አይደል የምን ለቅሶ ነው?» አላለም?

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍182🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሰባት

...በሙዚቃው ደነስኩ.. ውልቅልቅ እስክል ውስኪውን አንጠፍጥፌ ጠጣሁ"..አዎ አውቃኛለች... ፈፅሞ አልረሳችኝም...ከሁሉም ያስደሰተኝ ደግሞ ‹‹ቀናህ!!!›› የምትለዋ ቃል ነች...ምክንያቱም ቅናት እነጠቃለሁ ብሎ ከመፍራት ጋር ወይም ከመሠሠት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስሜት ነው።ፍርሀትም ስስትም ምንጫቸው ፍቅር ነው...እርግጠኝነት ከጎደለው ፍቅር።እና ታፈቅረኛለህ እያለችኝ ነው?ግን እንዳዛ ስላሰበች ለምንድነው እንደዚህ የፈነጠዝኩት? የእውነት እያፈቀርኳት ይሆን እንዴ ? እንዴ ከነጠላ ስሞ ሌላ ስለእሷ ምንም የማላውቃትን ሴት እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? ግን እኮ ፍቅር የኋላ ታሪክን አጥንቶ የወደፊት መድረሻን ገምቶ አሁን የቋሙበትን ድልዳል በሚዛን መዝኖ የሚገባበት  የምክንያትና ውጤት ቁርኝት ማሳያ አይደለም..?ፍቅር ጨርቁን እንደጣለ ዕብድ ነገረ ስራው ቅፅበታዊና ተአምራዊ ነው።ስለዚህ ሳላቃትም በፍቅሯ ብወድቅ የሚደንቅ አይደለም!ግን ዕድሜዋ ጉዳይስ? ቢያንስ 10 አመት ትበልጠኛለች? እርግጥ በዕድሜ ሰላሳም ሀምሳም የምትበልጠውን እንስት ማፍቀር የተለመደ ነው?ቢሆንም ግን ቢገለበጥ ነበር የሚያምረው ..እኔ 10 አመት ብበልጣት።

ወየጉድ አሁንኮ ነገረ ስራዬን ላየ የመጀመሪያ የፍቅር አይነጥላዬን ገና እየገለጥኩ ያለው  ጀማሪ አፍቃሪ ነው የምመስለው ፤ግን እኔ ቢያንስ አምስት አጫጭር ጣፍጭ ለወግ የሚበቁ እና አንድ ረጅም የተወሳሰበ  ልቤንም ቅስሜንም  አብሮ እንቅሽቅሽ አድርጎ የሠበረ.. በአለንጋ ተደጋግሞ በመገረፍ የተነሳ ትላልቅ ተጠላላፊ ሰንበር እንደተጋደመበት ጀርባ የእኔም ልብ በዛ ፍቅር ምክንያት ዙሪያ ጥምጥም የዞረበት ጠባሳ የተጋደመበት ሆኗል...
"ያ ፍቅር ህይወትን አስተምሮኛል ?ያ ፍቅር  ደስታን አሳይቶኛል...?ያ ፍቅር ዘመዶቼን አሳጥቶ የከተማ ስደተኛና ምፅተኛ  አድርጎኛል...ያ ፍቅር በራስ መታመኔን እንቅሽቅሽ አድርጎ  የህይወት መስመሬን ከላይ ወደታች ገለባብጦታል…ያ ፍቅር ዛሬ ቢቋረጥም ግን ትዝታ ብቻ ሆኖ የቀረ እንደይመስላችሁ፡፡ ዛሬም ጣጣው እያደነኝ ነው...፡፡

እስከህይወቴ ፍፃሜ እንደተጣባኝ የሚዘልቅ ይመስለኛል። ...ይሄው ስድስት አመት ሞላኝ ባዶ ሆኜ መኖር ከጀመርኩ ...እና አሁን የማፍቀር ስሜት ሲሰማኝ የተገረምኩት ለዛ ነው።እውነት እርቃን ገላዋን ስላሳየችኝ ...ተዳፍኖ የኖረው የወሲብ ስሜቴ ስለተወጣጠረ ነው የተምታታብኝ። ግን አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከለል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል፤ ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን  ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ...የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር  እስከ እርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች ስለሆን ይሆናል።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል..ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር ከቃላት ልውውጥ እና ከአይን መሠራረቅ  ላያልፍ ይችላል፤ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቋረጥ ይችላል..እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ አለ?።

ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ ስላለቀ ነው ብለን መደምደም አንችልም... አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው  ጉዞቸውን  በተለያየ ጎዳና  ሊቀጥሉ የሚገደዱባቸው አያሌ አጋጣሚዎች አሉ። ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።

ወይ ጉድ ..በዚህች እንግዳ ሴት የተነሳ የፍቅር ኤክሰፐርት መሆን ዳዳኝ እኮ….ጠርሙሶ ውስጥ ያለችውን መጠጥ እያወዛወዝኩ ከሆቴል ወጣሁና በእኩለ ለሊት ወደቤቴ ገባሁ፡፡በፀጥታ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ….፡፡ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ፡፡
ጥዋት
..ከእንቅልፌ ባንኜ አይኖቼን ብገልጥም ቀልጠፍ ብዬ ከአልጋዬ መውረድ አልቻልኩም። ብነሳም ምን አልባት ምሳዬን ሰርቼ ከመብላት ውጭ ሌላ የምሄድበት ቦታ የለም ።ምሳ ደግሞ አላሰኘኝም፡፡ ምን አልባት ቁርሴን ከጋሽ ሙሉአለም የተሠጠኝን ቋንጣ ፈርፍር በደንብ ስለበላሁ ይሆናል። ተንጠራራሁና ከኮመዲኖዬ ላይ rich Dad poor Dad የሚለውን መፅሀፍ አነሳሁና ማንበብ ጀመርኩ .. አንድንም አባት የሌለው ሰው ሁለት አባቶች ያሉት ሰው የፃፈውን መፅሀፍ ለማንበብ መቋመጡ የሚገርም ነው። ብቻ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሁለት ገፅ ሳላነብ ስልኬ ጠራ አነሳሁና አየሁት..፡፡

የማላውቀው ቁጥር ነው ፡፡ላንሳው ልተወው ተወዛገብኩ።በስተመጨረሻ አነሳሁት

‹‹ሄሎ»

"ሄ...ሎ"ጥፍጥ ያለ የህፃን ድምፅ...ደነገጥኩ፡፡

‹‹ሄሎ..ሄሎ ..ማን ልበል?"

«ተአምል...ነኝ»

"ተአምር"የተኛሁበት የእንጨት አልጋ ከስር እርብራብ ተቀንጥሶ ይዞኝ ወደታች እየሰመጠ መሠለኝ...፡፡ስልክ ባልያዘው ቀኝ እጄ ፍራሹን ጨምድጄ ያዝኩ....፡፡እለተ መፅአት የፊታችን እሁድ መሆኑን ተረጋገጠ የሚል አዎጅን አስከትሎ የነጋሪት ጉሰማ ብሰማ ራሱ እንዲህ ሰማይ ምድሩ አይዞርብኝ፡፡

ልጅቷ ኩልትፍትፍ ባለ ድምፅ ንግግሯን ቀጠለች
"አዎ ተአምል...ል..ጅህ"
ይሄ መቼስ ተአምር ነው....፡፡ ተአምር አሁን ስምንት አመቷ ነው።በአካል ከተያየን 6 አመት አልፎናል።ማለቴ ቀጥታ በአካል ያየዋት አቅፌ የሳምኮት :ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ስታለቅስ ያባበልኮት የዛሬ ስድስት አመት ገና ክፉና ደጉን በቅጡ መለየት ባልቻለችበት ጊዜ ነው። ለዛውም እንደአባትና እንደልጅ እኮ አይደለም እንደ እህቴ ልጅ...እንደአጎቷ ሆኜ..፡፡ለምን እንደዛ ሆነ የእውነትም አጎቷ ስለሆንኩ፤ እንደዛም ስለመሰለኝ...፡፡ከዛ ወላጆቾ የውጭ ፕሮሰስ ጀምረው ስለነበር  ተአምር ዲ.ኤን. ኤ ምርመራ ማድረግ ግዴታ ሆነ …ተመረመረች...ውጤቱ  ለቤተሠብ በሀይለኛ መብረቅ የመመታት ያህል ድብ እዳና አስደንጋጭ ነበር... ልጅቱ የእህቴ ባል አይደለችም?
‹‹እንዴት ሆኗ...?"የህግ ሚስቱ እኮ ነች…፡፡››
"በተክሊል ነው እኮ የተጋብት"ብዙ ብዙ ተባለ... እኔ የምገባበት ጠፋኝ..ጠጋ አልኩና
በወቅቱ"ምስር ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ?››ብዬ ጠየቅኳት።
"አንተም እንደሌላው እንዴት ሆነ ብለህ ትጠይቀኛለህ?"
‹‹ምን ማለት ነው ?እንዴት አልጠይቅሽም?"
‹‹ያደረከውን ታውቃለህ ብዬ ነዋ ?››
👍56😁2😱1
"እና ተአምር የእኔ ልጅ ነች?"
"መቼሰ ከአንተና ከባሌ ውጭ ከሌላ ወንድ ተኝታለች ብለህ አታስብም..ነው ወይስ ታስባለህ?እንደዛ ከሆነ ያው አንተም ዲኤን.ኤ አሰርተህ ማረጋገጥ ትችላለህ።›› አለቺኝ እየተውረገረገች
"ኸረ እንደዛ ማለቴ አይደለም ...በፈጣሪ ምንድነው የምታወሪው?አሁን እቴቴ  ስሰማ ምንድነው የምትለው?››እቴቴ ማለት ለእሷ የስጋ እናቷ ለእኔ ደግሞ አሳዳጊ እናቴና አክስቴ (የእናቴ ታናሽ እህት)ነች።

"ለጊዜው ዝርዝሩን ለማንም መንገሩ አስፈላጊ አይደለም?››
"እንዴት ታደርጊያለሽ ?ሁሉም እኮ እውነቱን እስክትነግሪያቸው አይተውሽም።"
"ግድ የለም ለእኔ አታስብ..ጫናውን እችለዋለሁ....በዛ ላይ ወደአሜሪካ ለመብረር ሁለት ወር ነው የቀረኝ ...ሁለት ወር ምን ያደርጉኛል..ስጋዬን ዘልዝለው አይበሉት"
"የመስፍኔስ ጉዳይ..."
"በደፈናው ተነጋግረናል  ..ሁለቱንም ልጆች ይዞ የመሄድን ሀሳብ ለጊዜው ትተነዋል"
ደነገጥኩ ‹‹ምን ማለትሽ ነው ?ተአምርን የት ጥለሽ ልትሄጂ?"
ፈገግ አለችና‹‹ እንዴ ላንተ ለአባቷ ነዋ...አባቷ እያለ ለሌላ ለማን ጥያት እሄዳለሁ?"
"ባክሽ በዚህ በጭንቅ ጊዜ ትቀልጂያለሽ እንዴ?"አልኳት፡፡ እውነቴን ነው፡፡ በወቅቱ የዪኒሸርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ነበርኩ ይሄ ሁሉ ጉድ የተፈጠረው ክረምት ላይ እረፍት ሆኖ ቤተሠቤ ጋር ብዬ በመጣሁበት ቅፅበት ነው።እና እብድ ካልሆነች እንደዚህ አይነት ቀሺም ሀሳብ እንደማታስብ እርግጠኛ ነኝ።

"ለእቴቴ ጥያት እሄዳለሁ"
"አቤልንም?"አቤል ማለት ገና ከተወለደ ስድስት ወር ያላለፈው ወንድ ልጇ ነው፡፡
‹‹አይ እሱን ለእናቱ ሊሰጣቸው ነው"
‹‹እና  ልጆቹን ተከፋፈላችሁ ማለት ነው?"
"አዎ ...ጋብቻው ለጊዜው አሜሪካ እስክንገባ ባለበት ይቀጥላል...ከዛ እንፋታና በየፊናችን ህይወታችንን መምራት እንቀጥላለን።››
"ግን ከልጆች ተለይቶ መኖር አይከብድም?"
"አይ ከልጆች ይልቅ ከአንተ ተለይቶ መኖር ነው የሚከብደኝ ...ልክ ትምህርትህን እንደጨረስክ ሁኔታውን አመቻችና ተአምርን ይዘህ ትመጣለህ ..ከዛ ከዚህ ወግ አጥባቂ አፋም ህዝብ ተገላግለን  በነፃነት ሀገር የራሳችንን ነፃ ህይወት እንኖራለን"
"እንዴት ነው አሜሪካ እህትና ወንድም እንዲጋቡ ይፈቀዳል እንዴ?"
‹‹አትቀልድ .... ››
..ከምስር ጋር በዛ ተለያየን፡፡ ነገሮች ፍርጥርጥ ብለው ቅሌቴን እስክከናነብ እጄን አጣጥፌ ቁጭ ብዬ መጠበቅ አልቻልኩም፡፡ማድረግ የቻልኩት አንድ ነገር ነበር…፡፡  በማግስቱ ጨርቄን ማቄን ሳልል ስልኬን አጥፍቼ ደብረብርሀን ለቅቄ አዲስአበባ ገባሁ፡፡ትምህርት  ወደምማርበት አለማያ አልሄድኩም ።አዲስአባ ነው የመሸግኩት ።ይህን ያደረኩበት ዋና ምክንያት ምን አልባት ልፈልግ ብለው ቢሄድ እንዳያገኙኝ ነው።አዲስአበባ  የቀን ስራም መላላክም እየሠራው አንድ ወሩን አሳለፍኩና መስከረም ሲጠባ ወደ ዪኒሸርሲቲ አመራሁ..፡፡ዩኒቨርስቲ እንደረስኩ በፊት ይላክልኝ የነበረው ብር ያለማቆረጥ በባንክ ደብተሬ ይገባልኝ ስለነበር በወጪ ችግር አልነበረብኝም፡፡ከዛ ወጭ ግን ይሄው ስድስት አመት ከማንም ጋር ተገናኝቼ አላውቅም፤ የወሬ ወሬ ምስርም ወዲያው ወደአሜሪካ እንደሄደች ሰምቼያለሁ..፡፡ ቤተሠብ ሁሉ እውነቱን እንዳወቀና በተለይ አክስቴ እጅግ በጣም እንዳዘነች እና ትዳሯንም እንደፈታች ሰማሁ። እንግዲህ በእኔ በደደብ ቀሺም ስህተት ሁለት ትዳር ፈረሰ ማለት ነው..የባንክ ደብተሬንም ቢሆን ልክ ከተመረቅኩበት ወር ጀምሮ አዘጋሁት.. እንደዛ ያደረኩት እቴቴ ብር  መላኳን አንድታቆም ነው፡፡እንደውም ለምረቃ ሁለት ወር ሲቀረው…ባንክ ደብተሬ ውስጥ ከ20 ሺብር በላይ ነበር ያስገባችልኝ፡፡ያው ምረቃ ላይ ወጪ ስለሚበዛ  ለሱፍ ምናምን አስባ እንደሆነ ገባኝ…እኔ ግን ሱፉንም አልገዛሁ ምረቃ ላይም አልተገኘሁ ወረቀቴን ተቀብዬ ወደአዲሳባ ሸመጠጥኩ ብሩን ሰራ እስካገኝ ተጠቀምኩበት፡፡. ለማንኛውም ለጊዜው ትዝታዬን ላቁምና ወደእንግዳዬ ልመለሠ፡፡
////
"ሠላም ነሽ ታአምር?"
"ሠላም ነኝ አባዬ...ድምፅህን ስለሠማው ደስ ብሎኛል"

ይቀጥላል
👍447🤔3🥰1🤩1
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_አራት

ዘርሲዎች ግማሽ ክብ ሰርተው ከመንደሩ ራቅ ብላ ዙሪያ ገቡን ከምታሳየው
የግራር ዛፍ ስርቁጭ ብለዋል ጩሉሌዎች
አንገታቸውን ቁልቁል ደፋ አድርገው በዛ ዙሪያ ያንዣብባሉ: ነፋሱ
ቅጠሎችን ጎንበስ ቀና እያደረገ ይነፍሳል 
ከፊት ለፊታቸው ርጥብ
ቅጠል ተነጥፏል  መሃል ላይ ጎረምሶች የተጠበሰውን የፍየል ስጋ እየቆራረጡ የፍሪንባውን ሥጋ በእድሜ ለገፉትና በጀግንነታደው ለሚታወቁት ለሌሎች ደግሞ ከተለያየውደ የስጋ አይነት እፊት ለፊታቸው ካለው ቅጠል አስቀመጡ" ህፃናት ጨዋታቸውን አቁመው ራቅ ብለው ሲቁለጨለጩ ቆይተው እደላው አልቆ መብሉ ሲጀመር ወደየአባቶቻቸው ጉያ ተሸጉጠው ዳረጎታቸውን እየተቀበሉ ከአጥንት ጋር መታገል ጀመሩ በመጨረሻ የሚበላው ከተበላ: ቀሪውን ደግሞ ጎረምሶቹ ካቀለጣጠፉት በኋላ ወጣቶቹ ቅጠሉን ሰብስበው ጥለው
ከስብሰባው አካባቢ ርቀው ሄዱ።

የሽማግሎች አለቃ ጦራቸውን ይዘው ከተቀመጡበት ተነስተው
ከፈርሱ እግራቸውን ቀባ አድርገው ወዲህ ወዲያ ወዲያ ወዲህ አሉና፣
"የአባት ደንብ ጥሩ ነው" በልክ መብላት የአባቶቻችን ባህል ነው አባቶቻችን የራበውና የጠገበ ትክክል ፍርድ አይሰጥም ይሉ
ነበር" የጠገበ ወንድ ሴት ማለት ነው መሳቅ ቧልት ይወዳል ከብቶችን አይፈቅድም ጫካውን አይቃኝም ከጓደኞቹ ጋር
አይመክርም መዝለል አይችልም መቀመጥና ማንጎላጀት ይወዳል
ትክክለኛ ፍርድ በዚህ ምክንያት አይሰጥም ይሉ ነበር አባቶቻችን" ሽማግሌው እቱፍ: እቱፍ
ብለው የጦሩን ዘንግ በምራቃቸው ቀባ ቀባ እያደረጉ ሽማግሎችን:
የአባታቸውን አገር አድማስ እየተዟዟሩ አይተው

አባቶቼ የራበውም ከጠገበ አይሻልም ይሉ ነበር የራበው ሰው ሰነፍ ነው
ሲኖረው አያውቅበትም
የወደቀችው ጀንበር:
የጠፋችው ጨረቃ ተመልሰው  የሚመጡ
አይመስሉትም እንደ
አጋሰስ ፈረስ ዘመዶቹ ለመቋቋሚያ የሰጡትን ፍየሉንም፥ በጉንም
ከብቱንም: እህሉንም ብቻውን እየበላ ነገን ዘንግቶ: ልጆቼ: የአባቴ
ምክር ሳይል ሁሉን ያሟጥጥና የሚያልበው ሲያጣ የሚበላው
ሲቸግረው ሰውን: መሬቷን: ቦርጆን: አባቶቹን ይራገማል" ሆዱን
ለመሙላት ይቀማል ይዋሻል … ፍቅር አያውቅም ዘመድ ወገን አይለይም
አያስተውልም፤ ጨካኝ ነው
በዚህ ምክንያት
አባቶቻችን የራበው ሰው ትክክል አይፈርድም ይሉ ነበር አባቶቻችን ትክክል ናቸው ወንድሞቼ ጥጋብ ልቦናን ያዛባል ረሃብ ደግሞ ተስፋ መቁረጥንና ጥላቻን ያመጣል ከሁሉም የሚከፋው ደግሞ ሁለቱም ያስዋሻሉ" ብለው በርኮታቸው ላይ ቁጭ አሉ
ዝምታው ቀጠለ ሐመር ላይ ተረትን ሽማግሌ ለሌላው ማስታወስ እንጂ አይጨርሰውም የሰሙት እኩል: የፈፀሙት እኩል … ስለሆነ ተረት ጨራሽ አዳማጭ የለውም"

"በሉ ተናገሩ?" አሉ ሽማግሌው ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጥሩ ነው! ከወደ መሃል አንዱ ድምፅ አሰሙ ገልመጥ ብሎ ያዬ የለም ሁሉም ግን አባባላቸውን በጆሮው ቀልቧል።

"ጥሩ ነው!- በአካል ተለይተውን ነፍሶቻቸው ደንቡን ጥበቃ አብረውን ላሉት ወንድሞቻችን ተገቢው ደንብ የሚሰራበት
ቀን ይመረጥ ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው በየበረሃው የአሉትን ተባት በግና ፍየሎች ከብቶችን ያስመጡ" በየመንደሩ ለሚኖሩት ዘመድ ጓደኞችም ጥሪ ይላክ ለዚያ ደሞ ዛሬ ቀኑ ተቆርጦ ቋጠሮ ይዘጋጅ አሉ።

የሽማግሎች አለቃ ሌላ ኃሳብ አለመኖሩን በዝምታደ ጠበቁና አንድ ጎረምሳ ጠርተው ልጥ አምጣ አንተ" አሉት ልጡ መጣ
"ስንት ላይ ይቋጠር?"

"መከን ተቢ" አሉ አንድ ሽማግሌ በስተግራ በኩል
ከተቀመጡት ሰላሳ ለማለት ልጡ ሰላሳ ላይ ተቋጥሮ ለሟቹ ታናሽ ወንድም
ተሰጠው" የሽማግሎች አለቃ አንዱን ችግር
በመቋጨታቸው
"ባይሮ ኢሜ" አሉ ሽማግሎችን እግዜር
ይስጣችሁ ለማለት

"በሉ ቀጥሉ?" አሉ የስብሰባው መሪ

"ጥሩ ነው!" አለ ልጅ እግሩና የአባቱን ጠላት ገሎ በቅርቡ
ከሽማግሌዎች ጋር ለመቀመጥ እድል ያገኘው ሰለምቤ፤ "ጥሩ ነው!
ታለውሻ በቀር አባቶቻችን ከአውሬ ጋር አልኖሩም እና ካርለቴ ይዛብን የመጣችውን አውሬ በጥይት አጉኖ ራቅ አድርጎ መቅበር ነው "አለ ገና የጎረምሳነት ባህሪው ሙሉ በሙሉ ያልቀዘቀዘለት ወጣቱ ሽማግሌ አለመብሰሉ በአነጋገሩ ፍጥጥ ብሎ እየታየበት።

"ጥሩ ነው! አውሬ ማለት ከብት የሚበላ ችግር የሚፈጥር ነው የነጯ ሐመር  የካርለቴ አራት እግር አውሬ ሳይሆን መሂና
ነው የሚባል አባቶቻችን ደሞ መሂና የሚባል አውሬ አለ አላሉንም ደሞስ የካርለቴ መሂና እንደ ፈረስ እየጫነን ገበያ እያመላለሰን ነው እና መኖሩ ምን ጎዳ! አሉ ግራሯን የተደገፉት አንድ ዐይና

የአባት ደንብ እየሻርን ያ ይጎዳል ይሄ ይጠቅማል
ካልንማ ይህች አገርና ይህ ህዝብ መዓት ይመጣበታል" በነሱ ጊዜ ያልነበረ አውሬ አሁንም መኖር የለበትም " አሉ አገጫቸውን በግራ
እጃቸው ደግፈው የቆዩት ሽማግሌ ከዚያ ክርክሩ ከተለያዬ አቅጣጫ
መቅረቡ ቀጠለ

በአባቶቻችን ደንብ ፍየል ቢመጣ ፍየል ጋጥ: ከብት
ቢመጣ ከብቶች በረት ሰው ቢመጣ  ወደ ሰዎች መኖሪያ ጎጆ ይገባል እህ እንዲህ እስተሆነ ድረስ የካርለቴ መሂና የሚገባ
ፍየሎች ጋጥ ነው? ከከብቶች በረት ነው? ወይንስ ከሰዎች ጋር ጎጆ
ውስጥ! መቼም ተውሾች ጋር እየተሯሯጠ አውሬና ጠላት ይከላከላል
አይባል ይኑር ከተባለ ወገኑ ከማን ነው?  ተከብቶቹ ወይንስ ከእኛ! አሉ ከወደመሀል መፋቂያቸውን ሲያኝኩ የቆዩት ሽማግሌ

"ጥሩ ነው የሁላችሁም አስተያየት አዲስ ነገር መምጣቱ ይኸው ሁለት ሶስት ቦታ ከፋፍሎ አጨቃጨቀን ያልነበረ ነገር
ሲመጣ ያልነበረ ችግር ይፈጥራል ነጯ ሐመር የእኛ የሆነች እንግዳ ናት መሂና ያለችውን አውሬ ዱካውን ለማጥፋት በጥይትና ጦር
ደብድበን እንቅበረው ብንል እሷን እናሳዝናት ይሆናል"
ባይሆን አውሬሽን ካመጣሽበት ጫካ ጥለሽ ነይ ብንላት አይሻልም
ወንድሞቼ!" አሉ። አንተነህ ይመር  ጋልታምቤ ጎን የተቀመጡት ሽማግሌ

ተው! ተው! ይህችን ሰው ተማበራችን አታውጧት! እሷ
ሐመር ናት  የሐመር  ልጃገረድ ተቀብላማ እንደ እህቶችዋ የፍየል ቆዳ ለብሳ ለዘመዷ ለከሎ ከብት
የአባቷን ትክክለኛ ደንብ
ዝላይ ተገርፋ … እንዴት እንዴት ነው  እንደውጭ ሰው ይከፋታል ማለት! ከአባትሽ ባህልና ደንብ ውጭ ያመጣሽው አውሬ ቦርጆን ያስከፋል የአባቶቻችንንም ነፍስ ያሳዝናል እነሱ ተቆጥተው ዝናብ ከሚያጠፉብን በሽታ ከሚልኩብን አውሬሽን ቀብረነው እንረፍ
ብንላት በፍጡም አይከፋትም  ወዲያውስ ከሽማግሌ ቃል ወጥታ የት ልትደርስ ኧረ አይከፋትም!" አሉ የዘርሲዎች አለቃ ከዚያ ለረጅም ጊዜ ዝምታ ሰፍኖ ቆየ

"ጥሩ ነው! እንዳላችሁትም
ነጯ ሐመር የእኛ ናት, የእኛ
ያልሆነውን ግን ዝም ብለን ብንለቀው ምን እንደሚያመጣ አናውቅም ሲቆይ ልጆቻችንን  እሷን ጨምሮ: እኛን ይተናኮስ
አይተናኮስ ሳናውቅ እናጥፋው እስከተባባልን
ድረስ በኋላ ለቀን
ከምናሳድድ እዚሁ ገራም መስሎ አጠገባችን እንዳለ አድብቶ በጥይት ማጎን ነው የሚበጀው ካለበለዚያ
እኮ አስተውላችሁት እንደሁ
አላውቅም እንጂ አጉረምርሞ አጉረምርሞ ሰውነቱ የጋለ እንደሆን
እንደ ጥይት ከተፈተለከ
ድንጋይ አይል ውሃ ... ማን ጀግና   ያቆመዋል! ስለዚህ ሳይደነብር አዋዝተው ጎረምሶች በክላሽ ጥይት
ሆድቃውን እንዲነድሉት ማድረግ ነው"" እንዳሉ

"ይህስ እውነት ነው! በቀደም ሳላየው ሩም … ብሎ ባጠገቤ ቢያልፍ የድምፁ ወላፈን እንዴት አሽቀንጥሮ ወረወረኝ መሰላችሁ ተዚያ ንዴቱ ይሁን ድንጋጤው ሰማይ እሆን ምድር ጠፋኝ!" አሉ ሌላው አዛውንት
👍21