አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስድስት  ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ ካርለት ከዳንሱ ቦታ ራቅ ብላ ጀግናዋን በአይኖቿ ስትፈልገው በጆሮዋ ስልምልም የሚያደርግ የሙዚቃ ቃና ሰማች። እንግዳ ነው ያ ሙዚቃ ለጆሮዋ! ሳባት ሙዚቃው ተጎተተችለት: ቃናው ጆሮዋን እየላሳት ወደ ውስጧ ዘለቀ የህሊናዋን ጓዳ! የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው። አሻት፤ ዳሰሳት…..እሷም አንኳኳ የሆሊናዋን ጓዳ የስርቆሽ በሯን ከፍታ…»
🕯አሳዛኝ ዜና

በኢትዮጵያ የፊልሙ ኢንደስትሪ ትልቅ ድርሻ የነበረው አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጆቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።

ነብስ ይማር 🙏
😢68👍5
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሁለት

///
    እሁድ ነው በዛ ላይ ክረምት፡፡አየሩ ጨላማና ጭጋጋማ ነበር፤በዛም የተነሳ ከመኝታዬ መውጣት አልቻልኩም..ሞቆኛል ብርድልብሴን ተከናንቤ የሀሳብ ድር እያደራሁ የምኞት ሸማ እየሸመንኩ ነው፡፡እኔ እየብ ነኘ፤ማለት ስሜ እዬብ ነው፤ ህይወቴም ልክ እንደመፅሀፍ ቅዱሱ እዬብ ከምቾትና ከድሎት ህይወት በተአምራዊ ሁኔታ የተፋታ  ወደ ድህነት አዘቅት ተሸቀንጥሮ የተጣለ ነው፡፡

ልዩነቱ የዛኛው እዬብ መከራ የመጣበት በሰይጣንና በእግዚያብሄር መካከል በተፈጠረ ቁማረ መሰለ ክርክር በማያውቀው ጉዳይና የእሱ ባልሆነ ስህትት የአለምን ቅጣት ሁሉ እንዲቀጣ የተደረገ ነው..በእኔ ምልከታ እሱ ላይ የተደረገበት ግፍ ነው፤ አረ እንደውም ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች እንደሚጠቀሙበት ሚስኪን አይጥ ነው ያደረጉት፡፡

   የእኔ ጉዳይ ግን እንደዛ አይደለም...እያንዳንዷን ያሳልፍኳት መከራ እያንዳንዷ የገጠመኝ ጨለማ ችግርና የብቸኝነት ስቃይ ከገዛ ራሴ ጥፋት የተመዘዙ ፤ወድጄና ፈቅጄ በምርጫዬ ወደ ህይወቴ ያመጣኋቸው የድክመቶቼ ውጤቶች ናቸው…እንደውም ሳስበው ከሚገባኝ በታች የተቀጣው ሰው ነኝ፡፡ስለዚህ ታላቄ እዮብ በማይገባው ስቃይ ተሰቃይቶ እንኳን እግዜሐብሄርን ሲያመሰግን ከኖረ እኔ ግን ከሚገባኝ በታች  እየተቀጣሁ እያለሁ እንኳን ሁሉ ግዜ ከምስጋና ይልቅ ንጭንጬ ለምን  አንደበቴን እንደሚቆጣጠረው ግራ ይገባኛል፡፡

ለአለፉት ሁለት አመት   የዘወትር ጸሎቴ፤ ስነሰና ስተኛ  መፅሀፍ ቅዱሴን ገልጬ መፅሀፈ-እዮብ ላይ ሄደና የእዬብን ምሬት ልክ ከራሴ ምናብ እንደመነጨ በመቁጠር  አንበለብል  ነበር ፡፡

..ያ የተወለድኩበት ቀን ይጥፋ...ያም ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ለሊት።ያ  ቀን ጨለማ ይሁን፣ እግዚሐብሄር ከላይ አይመልከተው፣ብርሀንም አይብራበት።ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፣ደመናም ይረፍበት።የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።ያን ሌሊት ጪለማ ይያዘው።በአመቶች ቀኖች መካከል ደስ አይበለው።በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቆጠር።እንሆ ያ ሌሊት መካን ይሁን።እልልታ አይግባበት።...........ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት። አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፣........በመሀፀን ሳለሁ ለምን አልምትሁም?ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም?ጉልበቾች ስለምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለምን ጠባሁ።አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፣አንቀላፍቼ ባረፋሁ ነበር።

     አሁን ግን ይህንን የምሬት እንጉርጉሮ ማላዘን ካቆምኩ ሰነባበትኩ፤ ምክንያቱም በጥቂቱም ቢሆን ጭል ጭል የምትል ሻማ በህይወቴ የሆነ ጫፍ ላይ ተለኩሳ ማብራት የጀመረች ይመስለኛል.. ፡፡እንደነገርኳችሁ አቶ ሰሎሞን   ሆቴል ስራ ካገኘሁ ከአንድ ወር በኃላ የምኖርበትንም ቤት አገኘሁ፡፡የምኖርበት ግቢ ከሆቴሉ ተያያዥ ወይም ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ሰፊና በዛፎች የተሞላ ነው፡፡በግቢው ውስጥ አንድ ኪችን፤ አንድ ሳሎን እና አንድ ሻወር ቤት ያለው መለስተኛ ቢላ አለ፡፡ይሄ ቤት የፊት ለፊቱ ሳሎን ከሌሎቹ ክፍሎች ጋር የሚያገናኘው በራፍ ታሸጎል፡፡ እኔ ሳሎኑ ውስጥ እኖራለሁ፤የተቀረውን ክፍል ነጋሽ’ዩ ሙሉአለም ይኖሩበታል፡፡ለዚህ ለምኖርበት ቤት በቀጥታ ኪራይ አልከፍልም፤ በምትኩ ግን የተወሰኑ አገልግሎቶችን ለቤቱ ባለቤት እሰጣለሁ፡፡
እኚህ እቤት የሚጋሩኝ ሰውዬ ማለቴ አቶ ሙሉአለም የአለቃዬ ማለት የሆቴሉ ባለቤት የአቶ ሰሎሞን አባት ናቸው፡፡

አዛውንቱ አቶ ሙሉዓለም የሚገርም ባህሪ አላቸው ፡፡ከቤት መውጣት ካቆሙ ሶስተኛ አመታቸውን ሊጨርሱ ነው፡፡በኮሮና ሰሞን በጣም የሚወዷት የእድሜ ዘመን ባለቤታቸው በዚህ በሽታ ተይዛ ሞተችባቸው...ከዛ እሳቸውም በፍራቻ እራሳቸውን ኳረንቲን አስገቡ፡፡ ይሄ በዛን ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገር ደረጃ በአዎጅ ሁሉም ዜጋ ባለበት እንቅስቃሴውን ገቶ እንዲቀመጥ ታዞ ስለነበር የእሳቸውም የተለየ አልነበረም…፡፡ግን ከወራት በኃላ አዎጁም ተነሳ ሁሉም ሰው ቀስ በቀስ ማስክ እያደረገ ከቤት መውጣት ፤ከዛም በሂደት ያለማስክስ ልክ እንደበፊቱ መተረማመስ ጀመረ፤ እሳቸው ግን ከቤታቸው ደጃፍ መውጣት አምቢኝ አሉ..፡፡ፀሀዮም ትቅርብኝ ጨረቃም አትናፍቀኝም አሉ፡፡ልክ እድሜ ልክ ተፈርዶበት ከርቸሌ እንደገባ ሰው በክፍላቸው ተከተቱ፡፡
ልጃቸው እራሱ በሳምንት አንድ ቀን መስኮታቸውን ይከፍቱና ከመስታወት ወዲያ ማዶ ሆኖ ያያቸዋል .እዛው በሶስት ሜትር ርቀት ሆነው አይን አይኑን  እያዩት  የሚያወሩትን ያወሩትና ይለያያሉ..ከቤታቸው ደጃፍ ለመሻገር ፍቃደኛ አይደሉም…ከማንም ሰው ጋር ለመነካካት አይፈልጉም፡፡

እና አኔ አንደኛ በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ከሆቴል አሰራና አምጥቼ  በራፍ  ስር  በማስቀመጥ …‹‹አያቴ ምግብ አምጠቻለሁ ያስገቡት፡፡›› እላቸዋለሁ፡

‹እሺ ዞረ በል›› ይሉኛል፡፡

‹‹እሺ ››ብዬ ዞሬ ወደ ክፍሌ ገባለሁ..እሳቸው ቀስ ብለው በራፉን ከፈት አድርገው መጋኛ እንዳያጠናግራቸው የፈሩ ይመስል ግራና ቀኛቸውን ገልመጥ ገልመጥ ያደርጉና የመመንጨቅ ያህል የምግብ ሰሀኑን በማንሳት ወደ ውስጥ ተመልሰው በመግባት በራፉን መልሰው ጠርቅመው ይዘጉታል፡፡
እና ሌላ የሚፈልጉት   ነገር ካለ ይነግሩኛል…ብዙውን ጊዜ በሳምንት አንድ ጠርሙስ ውሰኪና  መፅሀፍ ነው የሚጠይቁት፤ አልፎ አልፎ የራስ ምታት መድሀኒት ያዙኛል፡፡በአጠቃላይ ከውጭ የሚፈልጉት ነገር በጣም ጥቂት ቢሆንም ያንኑ ጥቂቱን  ካለበት ፈልጌ  የማቅረብ ኃላፊነቱ የእኔ ነው፡፡

በተጨማሪ  ከስራ ሰዓት ውጭ  እቤት ስሆን እኔም ሳሎኔ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ፤እሳቸውም ወይ ተቀምጠው ውስኪቸውን እየተጎነጩ ወይ አልጋቸው ላይ ተጋድመው ይደሰኩሩልኛል ፡፡እኔም የጣሙኝንም ያላጣሙኝንም ወሬዎች በማዳነቅ እና በተመስጦ አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አልፎ አልፎም ስለውጩ ዓለም ወቅታዊ ሁኔታ የተወሰነ ወሬዎች እነግራቸዋለሁ..ያው ድምፅን ትንሽ ከፍ አድርጎ ማውራት ይጠይቃል እንጂ ከግድግዳ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ በደንብ ለመደማመጥ ተቸግረን አናውቅም፡፡
ከእኔ በፊት ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት መአት ሴትና ወንዶች እዚህ ቤት ገብተው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ግን ከአንድ እና ሁለት ወር በላይ መቆየት አልቻሉም ነበር..አብዛኞቹን አቶ ሙሉ አለም አልፈላጓቸውምና እንዲለቁ ተደረጉ ፤ የተወሰኑት ደግሞ ጠቅላላ ሁኔታውና የእሳቸውን ዲስኩርና ወሬ  በግድ ማድመጥ ሰልችቶቸው በራሳቸው ለቀው ይሄው ዛሬ እኔ ጋር ደረሰ..ለእኔ ግን ይሄው 11 ወር ሆኖኛል.እሳቸውም እስከዛሬ ከምስጋና ውጭ ስሞታ አቅርበውብኝ አያቀውቁም፤ እኔም ከቀን ወደቀን ከእሳቸው ጋር ያለኝ ትስስር እየጠነከረ እና እንደውም አያቴ እየመሰሉኝ መቸገሬን ስገልፅ እየተገረምኩ ነው፡፡አሁን ስገምት እንደውም ባሉካው እራሱ እየወደደኝ እና እያመነኝ የመጣበት ዋናው ምክንያት ከእሳቸው በሚያገኘው ተደራራቢ ሙገሳና ምሳጋና የተነሳ ይመስለኛል፡፡

ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን እስከአሁን ጋሽ ሙሉአለም በአካል አይቻቸው አላውቅም…ልጃቸው እንኳን እንደሚያደርጉት በመስታወት አሻግሬ በሩቅ ለማየት እኔም ሞክሬ አላውቅም እሳቸውም አበረታተውኝ አያውቁም አንድ ቀን ጋሼ ‹‹መልኮት እኮ ናፈቀኝ ››አልኳቸው፡፡

‹‹ምነው ሳታውቀው እንዴት ሊናፍቅህ ቻለ….?

«የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም ሲሉ አልሰማህም?››

‹‹እኔ ግን እኮ በደንብ  አውቆታለሁ….እንደውም የማላውቀውን አያቴን ነው የሚመስሉኝ…..››
👍764🔥1🥰1😁1🎉1
‹‹አንተ ወሽካታ..አንጀቴን መብላትህ ነው..››.አሉና አንድ የድሮ ፎታቸውን በበር ሰር አሾልከው ወረወሩልኝና…‹‹ያው አያትህ ሙሉአለም ማለት ያ ነው››አሉኝ፡፡
እና ለመጀመሪያ ጊዜ አቶ ሙሉአለም ምን እንደሚመስሉ በፎቶ አየኋቸው….ያምራሉ ፡፡ትንሽ ወፈርና ደንደን ከማለታቸው በስተቀር  ጋሽ ስብሀት ገበረእግዚያብሄርን  ነው የሚመስሉት፡፡ጠይም መላአክ፤ዘለግ ያለ ቁመትና፤የሚስብ ግርማ ሞገደስ አላቸው ፡፡ ፎቶቸውን ካየሁ በኃላ እንደውም ይበልጥ በአካል ፊት ለፊታቸው ቁጭ ብዬ እጃቸውን ትከሻዬ ላይ ጣል እያደረጉ ወይንም ጨበሬ ፀጉሬን እየዳበሱ እንዲያወሩኝ እጓጓ ጀመር….እሳቸው ግን ከአቋማቸው መቼም ንቅንቅ የሚሉ አይነት አይደሉም፡፡

ይቀጥላል
👍46
ካቻምናን ብንከሰው: ቆመን ካምና ደጅ
መቼ ፈረደልን? ፈረደብን አንጂ!
አምናንም ብንረግመው: ቆመን ከዘንድሮ
አልደረሰበትም ደረሰብን ዞሮ
ከእንግዲህስ ይብቃን…
ሂያጆቹን ለመጡት ማማቱን ትተናል
እኛ ስንተዋቸው ይተውን ይሆናል!

🔘ረድኤት🔘
👏33👍2210
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሦስት

አስተናጋጅ ሆኜ ከተቀጠርኩ አንድ አመት  አለፈኝ።በሲቪዬ ላይ የስራ ልምድ በሚለው ርዕስ ስር የንብረት ክፍል ተቆጣጣሪ እና የሆቴል አስተናጋጅነት የአንድ አመት የስራ ልምድ የሚለውን አስገብቼ መፃፍ እችላለሁ፤አዎ ይሄ ቀላል ነገር አይደለም።እያንዳንዱን የሠው ትዕዛዝ በትሪ ይዤ አቀርብና በዛው ትሪ ባህሪያቸውን  ያስረክቡኛል። ትሁቱ... ቁጡ.. ጉረኛ... ጋግርታም... እርብትብት... ለጋስ...ንፉግና ተነጫናጭ...በየቀኑ ፀባዩ የሚገለባበጥ ሙልጭልጭ በቃ እኔ ትምህርት ሚኒስቴርን ብሆን ኖሮ ሳይኮሎጂ እና ሶሾሎጂ ለሚያጠኑ  ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ቢያንስ ለስድስት ወር እንደዚህ አይነት ቦታ አፓረንት እንዲወጡ አደርጋቸው ነበር..ሆቴል ማለት የሠው ባህሪ በብፌ መልክ የሚቀርብበት ቦታ እኮ   ነው።

አሁን ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል ፡፡ባሩ ውስጥ አንድ ተስተናጋጅ ብቻ ነው ያለው፡፡ ለዛውም ሴት ደንበኛ...፡፡ይሄንን ብላክ ሌብል  ትጋተዋለች ።አሁን አሷ ብትወጣልን ሌላ የቀረን ስራ ስለሌለን ወደየቤታችን እንሄድና አረፍ እንል  ነበር ስል አሰብኩ ስናስተናግድ ከነበረነው  ስምንት ሴትና አራት ወንድ አስተናጋጆች መካከል አምስቱ ሴት ቀድመው መውጫ ቆርጠው ሄደዋል?ምን? መውጫ ምንድነው ?አላችሁኝ... መውጫ ማለት አንድ ሴት አብሯት የሚያድር ሰው አግኝታ የስራ ሰዓቷ ከመጠናቀቁ በፊት መውጣትና ከደንበኛዋ ጋር መሄድ ከፈለገች እንደሰዓቱ እየታየ ከምታገኘው ላይ እንድትከፍል ይደረጋል...ያው ግብር በሉት ።
ብዙውን ጊዜ በኢትዬጵያ የቡና ቤት ሴቶች ግብር አይከፍሉም ይባላል..እኔም እንደዛ አምን ነበር፡፡ አሁን ግን እንዲህ ተጠግቼ ሳይ አመት እስከ አመት እንደውም እንደእነሱ የሚከፍል የለም? ያው ግብር ማለት ከደሀው  መቀነት  ተቀንሶ  ለኃያላኑ ጡንቻ ማፈርጠሚያ  በግዳጅም ይሁን በይሁንታ የሚሰጥ መባ ነው።ኃያሉ መንግስት ሊሆን ይችላል..ባለሀብት ሊሆን ይችላል...የሠፈር አስተዳዳሪ ባለጡንቻ ሊሆን ይችላል...፡፡  ሁሉም በሚስኪኑ ደሀ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ ከርሱን የሚሞላ  ብልጉ አውሬ ነው...ውይ በማሪያም አለቃዬን ነው ከሌላው ባለጉልበት ጨምሬ እንዲህ የጨፈጨፍኩት .አምላክ ሰምቶ ውለታ ቢስ ብሎ እንዳይቀየመኝ፡፡

አሁን ሆቴል ውስጥ የቀረነው ሁለት ወንድ  አስተናጋጆች እና አንድ ሴት አስተናጋጅ እና ደግሞ የእለቱን የተሰራ ሂሳብ ተረክቦ   እየደመረ ያለው ባሉካ ብቻ ነኝ...ሽኩክ ብዬ ወደእሱ ሄድኩና ፡፡
"ጋሼ እንዴት ነው?"

"ስለምኑ ነው የምትጠይቀኝ ጎረምሳው?"

‹‹ስድስት ሰዓት ሊሆን ነው...ተስተናጋጇን ልንዘጋ ነው ልበላት እንዴ?"

"አይ አይሆንም...ትልቅ ደንበኛችን ነች ..ቅር እንዲላት አልፈልግም.."

"አይ ለእሷም ቢሆን ይመሽባታል ብዬ እኮ ነው፡፡"

"የእኔ አሳቢ አይመሽባትም... ከተቀመጠችበት ተነስትታ አስር እርምጃ ከተራመደች የተከራየችበት ቤርጎ ትደርሳለች"

"ኦ ረስቼው… ለካ እዚህ ነው አልጋ የያዘችው"

"አዎ ባይሆን ልጇቹ ይግቡ ..ንገራቸው፡፡"

"እሺ ግን ጋሼ እሷ እስክትሄድ ብቻህን ልትሆን ነው?"

"አይ እኔ አይደለሁም ቀርቼ የማስተናግዳት ...አንተነህ.፡፡..በራሷ  ጊዜ በቅቷት ስትሄድ ቆላልፍና ሂድ...እኔ ሚስቴ ትጠብቀኛለች ...አንተ ከአይጥ ጋር ድብብቆሽ ለመጫወት ምን አስቸኮለህ?››

‹‹እንዴ ጋሼ ከጓደኞቼ ጋር የማወራው ነገር ተደብቆ ይሰማል እንዴ...?"ስል በውስጤ አልጎመጎምኩ፡፡ከሶስት ቀን በፊት ነበር ለሴቶቹ አንድ አይጥ አላስተኛ እንዳለቺኝና ልክ ስተኛ ጆሮዬን እየቀረጠፈች፤ ከንፈሬን እየነከሰች  አስቸገረችኝ ብዬ ያወራኋቸው...እነሱ ደግሞ አፍቅራህ ነው እያሉ ሲያሾፍብኝ ነበር..ይሄው አሁን ጋሼም ተቀላቀላቸው...
ጋሼ ሂሳቡን ሰርቶ ጨርሶ ለመሄድ ተነሳ፡፡

"ጋሼ ለመቆየቱ ግን ካሌብ አይሻልም?"

"ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?...መልካም አዳር"ብሎኝ ጥሎኝ ወጣ...፡፡እኔም ሌሎቹ እንዲሄዱ ተናግሬ በዛ ውድቅት ለሊት ከአንድ እንስት ተስተናጋጅ ጋር ተፋጥጬ ተቀመጥኩ...፡፡
እኔም እንደሌሎች በዚህ ሰአት ክፍሌ ገብቼ አረፍ ባለማለቴ ከፍቶኛል ..ግን ደግሞ ጋሼ የተናገራት ነገር ልቤ ላይ አሪፍ  ደስታና ኩራትን አርከፋክፋብኛለች "ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?ነበር ያለኝ አይደል?፡፡ "በእውነት መታመን ያስደስታል" ለዛውም አንድ አመት ባልበለጠው ጊዜ ውስጥ ይህን መሳይ ክብር ማግኘት ተስፋው ለፈረሰበት ሰውም ቢሆን  በህይወቱ ጥቂት መነቃቃትን ይፈጥራል፡፡

ጠረጴዛው ተንኳኳ ከነበርኩበት ባንኮኒ ውስጥ ፡ሮጬ ወጣሁና  ወደ ተጠራሁበት ቀርቤ፤ እጇቼን ወደኃላዬ አጣምሬ፤ ከጉልበቴ ሸብረክ ፤ ከአንገቴ ጎንበስ ብዬ"አቤት ምን ጎደለ ? ምን ላምጣ?"አልኩ፡፡

"እ ..ምንድነበር..?."በፈጣሪ ሰክራለች መሠለኝ ..?ለምን እንደጠራችኝ እንኳን  አታውቅም፡፡
"አዎ..ሙዚቃውን በጣም ቀንሰው እናም አንድ ብርጭቆ አምጣልኝ"
ወይ ፈጣሪዬ ሴትዬዋ ገና መጠጣት ልትጀምር ነው..ለዛውም በሁለት ብርጭቆ…. እንዳለችኝ የሙዚቃውን ድምፅ  ቀነስኩና ብርጭቆውን አጣጥቤ ይዤላት ሄጄ ጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጥኩላትና ልመለስ ስል "ተቀመጥ"አለችኝ...
ተቀመጥ በሚለው ቃሏ ውስጥ ምንም አይነት ትህትናም ሆነ ሀዘኔታ አይነበብም፡፡.

"ምን አልሺኝ እመቤቴ?"

"ቁጭ በል..ንግግሬ አይሰማም እንዴ?"

"ኸረ በደንብ ይሰማል"ብዬ ትዕዛዟን በማክበር ሽኩክ ብዬ ቁጭ አልኩ..ፊቷ የተቀመጠውን  የተጋመሰ ብላክ ሌብል ጠርሙስ አነሳችና አዲስ ያመጣሁት ብርጭቆ ውስጥ አንደቀደቀችው፤ስትጨርስ  ወደፊት ለፊቴ አሽከርክራ አሰጠጋችው።

"ኸረ ይሄ ነገር ለእኔ አይሆንም?"

"ባክህ አትንጠባረር ..ዝም ብለህ ጠጣ "ብላኝ እርፍ...
አሁን ይሄ ግብዠ ነው አስገድዷ ደፈራ፡፡ፈራኋት መሠለኝ አነስሁና አንዴ ጎንጨት አልኩለት...
.፡፡‹‹እራት መቼ ነበር የበላሁት?›› ስል እራሴን ጠየቅኩ፡፡ አዎ 12፡30 አካባቢ....‹‹ምንድ ነበር የበላሁት?›› ዳቦ በሙዝ ...፡፡.ሶስት ሙዝና ሁለት ዶቦ....፡፡‹‹አሁን ከስድስት ሰዓት በኃላ ምን እየጠጣሁ ነው›› ውስኪ፡፡...‹‹ይህቺ ጋባዤ አራት ሰዓት አካባቢ ምንድነበር ያዘዘችው..?››ለማስታወስ ሞከርኩ...አዎ ክትፎ ነበረ ያዘዘችው እናም ግማሹን በልታ ግማሹ እንደተመለሠ አይቼያለሁ....አሁን ኪችን ብገባ ግማሹን ትራፊ አገኝ ይሆን?

"እዚህ ሀገር ለስራ መጥተሽ ነው?"ጥያቄውን መጠየቅ ፈልጌ ሳይሆን ዝም ብሎ መቀመጥ ስለጨነቀኝ ነው የቀባጠርኩት። ቢዝነስ የሚሰሩ ሴት  አስተናጋጆች ግን  እንዴት ብለው ነው ከማያውቁት ሰው ፊት ለፊት ተቀምጠው ዘና ብለው የሚጠጡት...ከዛም አልፎ የሚስቁት፤ የሚጫወቱት?ለዛውም በየቀኑ…፡፡ጥያቄዬን ሰምታ ሲጋራዋን ለኮሰች ...እናም ጭሱን አትጎልጉላ እላዬ ላይ በተነችብኝ ፡፡...ልክ እንደቤተመቅደስ ማዕጠንት ዝም ብዬ በፀጋ ተቀበልኩና ወደውስጤ ማግኩት?

"ምሽቱ ደስ ይላል..."ሌላ የማይረባ አስተያየት ከአንደበቴ ድንገት ሾለከ፡፡

"ምሽቱ አንተን ነው የሚመስለው?"አለችኝ፡፡
👍522👎1👏1
‹‹በፈጣሪ ምን ለማለት ፈልጋ ነው?እኔ ምን እመስላለሁ? ምሽቱስ ምን ይመስላል? በእኔና በምሽቱ መካከል ያለው መመሳሰልስ እንዴት ነው ሊመሳጠር የሚችለው?መቼስ ይህቺ ሴትዬ እዚህ መቀመጫ ላይ ከተቀመጠች ሰዓት አንስቶ መጠጧን ከመገልበጥ እና ሲጋራዎን ከማቡነን ሌላ  ፊቷ ሲፈታም ሆነ ጥርሶቾ ለሳቅ ሲገለጡ አላየሁም ...፡፡.ያ ማለት ደግሞ ምሽቱ ለእሷ ደባሪ ነበር የሚለው ድምዳሜ ላይ ያደርሰኛል ..ያ ከሆነ ደግሞ አንተ ደባሪ ነህ እያለችኝ ነው? እሺ ምኔ ነው ደባሪ ? መልኬ ነው?ቁመናዬ ነው?ወሬዬ ነው?
"ምን ትንጠባርብኛለች..እስከጋበዝኩህ ድረስ እንደፈለኩ ልሰድብህ እችላለሁ እያለች ነው እኮ?...ሴቶቹ የስራ ባለደረቦቼ በየቀኑ ከሚጋበዙአቸው ሰዎች  እንደዚህ አይነት ንቀትና መንቀባረር የሚያጋጥማቸው ከሆነ ለትዕግስታቸው ታላቅ አክብሮት አለኝ››ይህንን ሀሳብ በውስጤ ነው እያመነዥግኩ ያለሁት፡፡
"ድንገት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ጠረጴዛው ላይ የነበረውን ፓኮ ሮዝማን ሲጋራዎን እና ላይተሯን ይዛ ብድግ ብላ ተነሳች።
በመሄዷ እፎይታ እየተሠማኝ ፈጠን ብዬ"ልትሄጂ ነው… ደህና እደሪ"አልኳት፡፡
"አዎ ልሄድ ነው ..ክፍሌ 104 ቁጥር ነው...መጠጡን ይዘህልኝ ና"ብላኝ እርፍ፡፡

"እሺ ግን ሰው ስለሌለ እስክዘጋጋ እቆይብሻለሁ.."ሰበብ መደርደሬ ነው፡:፡

"እንደፈለክ…ለሊቱ ገና ረጅም ነው…. የትም እልሄድም፤ እጠብቅሀለሁ"ብላኝ የሚያርድ መቀመጫዎን እያማታች ቀጥ ብላ ወጥታ ሄደች..፡፡

እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርግ ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ  እየተብረከረከ ነው።

ይቀጥላል
👍411👎1👏1
አትሮኖስ pinned «#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፡ ፡ #ክፍል_ሦስት አስተናጋጅ ሆኜ ከተቀጠርኩ አንድ አመት  አለፈኝ።በሲቪዬ ላይ የስራ ልምድ በሚለው ርዕስ ስር የንብረት ክፍል ተቆጣጣሪ እና የሆቴል አስተናጋጅነት የአንድ አመት የስራ ልምድ የሚለውን አስገብቼ መፃፍ እችላለሁ፤አዎ ይሄ ቀላል ነገር አይደለም።እያንዳንዱን የሠው ትዕዛዝ በትሪ ይዤ አቀርብና በዛው ትሪ ባህሪያቸውን  ያስረክቡኛል።…»
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ አንድ)
(ሜሪ ፈለቀ)

« የበፊቷን ሴት መሆን አልፈልግም!!!» አልኩት ኪዳንን እንዴት እንደምናስወጣው የሚያቀርበው አማራጭ ሁሉ የሆነን ሰው ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ሲሆንብኝ

«ይሆንልሻል ?» አለ ማደንዘዣው እየለቀቀው የቁስሉ ህመም እየተሰማው ሲያወራም ጭምር እየተሰቃየ ።
«ውስጥ ያለህ ሰው ካሜራ መግጠም የሚያስችል ቅርበት አለው?»
«ይመስለኛል!! ምን አስበሽ ነው? ስልኬን ከኪሴ ውስጥ ወዲህ በይውማ እርግጡን ልንገርሽ! በቅድሚያ ግን ያሰብሽውን ልስማው?»

አመነታሁ! ከራሴ ውጪ ማንንም ሰው አምኜ የማውቅ ሰው አልነበርኩም! አለማመን በደሜ ውስጥ ያለ ነገር ነው። በሁለት ወር ከምናምን ጊዜ ሙልጭ ብሎ ሊጠራ አይችልም። የብዙ ዓመት ልምዴ ሁሌም ጀርባ እና ፊቴን ራሴው ስጠብቅ ፣ በመንገዴ የተደገፍኳቸው ሲንሸራተቱብኝ ፣ ከጎኔ ናቸው ያልኳቸው ጎኔን ሲወጉኝ ….. ነው። አውቃለሁ እኮ ደረቱን ለጥይት ሰጥቶልኛል። በማንም ሰው ሚዛን ከዚህ በላይ ከእኔ ጎን መሆኑን ሊያሳይለት የሚችል ምንም ማረጋገጫ አይኖርም። በቃ ግን የዛች ሜላት ልብ አመነታ። ለአፍታ ዝም ስል ገብቶታል።

«አሁንም እምነትሽን አላገኘሁም ማለት ነው?? እንዲያው ምን ባደርግልሽ ነው የምታምኝኝ ዓለሜ?» የጎንጥ ድምፅ አይመስልም። ሳላምነው እንኳን የሚቆጣኝ ድምፅ ሳይሆን ምንም ማድረግ የማይችል በጣም የተከፋ ድምፅ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ <ዓለሜ> ብሎ እንደጠራኝ ያላስተዋልኩ መስዬ አለፍኩ።

«እሺ ይሁን!! ዝርዝሩን አትንገሪኝ!! እንዲሆን የምትፈልጊውን ብቻ ንገሪኝ!!» አለ በዛው በከፋው ድምፁ

«ውስጥ ያለህን ሰው ምን ያህል ታምነዋለህ?»
«በመድሃንያለም!! አንች የምታውቂያቸውን ሰዎች አላውቅም!! እኔ የማውቃቸው ግን እስከህይወት የሚታመኑኝ ሰዎች አሉኝ!!»

ለእኔ የማመን ትርጉም እርሱ ካለው ይለያል። አመኔታ ከሚታመነው ሰው ይልቅ የሚያምነው ሰው ላይ ይመስለኛል ጫናው። ማንንም ሰው <እገሌ በፍፁም አይከዳኝም! በፍፁም ፊቱን አያዞርብኝም!> ብሎ መቶ ፐርሰንት ሰውየው ላይ መዘርፈጥ የዋህነትም ጅልነትም ነው። ምክንያቱም ማንም ሰው በማይደራደረው ነገር ከመጡበት አሳልፎ ይሰጥሃል። እኔ እገሌን አምነዋለሁ ስል ፍፁም አይከዳኝም ማለቴ ሳይሆን ቢከዳኝ ወይ ፊቱን ቢያዞርብኝ እንኳን ያለበቂ ምክንያት አልከዳኝም ብሎ ምክንያቱን ለማወቅ ክፍት እስከመሆን የሚደርስ ልብ አለኝ ማለት ነው። ከበቀል በፊት <ለምን?> ብዬ መጠየቅ የምችልበት ልብ ካለኝ ያን ሰው አምኜዋለሁ ማለት ነው።

ሰዎች በፍቅር ለወደቁለት ሰው <አምንሃለሁ> ወይም <አምንሻለሁ> ብለው ልባቸውን ሲሰጡ ያን የወደዱትን ሰው <በፍፁም ልቤን እንደማትሰብረው አውቃለሁ!> እያሉት ነው እንዴ? እኔ አይመስለኝም። <ብትሰብረው እንኳን ልሰጥህ ዝግጁ ነኝ! ብትሰብረው እንኳን ህመሙን እስከመቀበል ድረስ ነው ፍቅሬ!> እያሉት እንጂ!


«አትፍረድብኝ! የመጣሁበት መንገድ ከሚታመኑት ይልቅ የማይታመኑት የበዙበት ነው! በዛ ላይ አንዲት ስህተት ብሰራ አደጋ ላይ ያለው ኪዳን ነው! በሱ ጉዳይ ማንም ላይ ባልታመን ተረዳኝ!! ደግሞም እኮ ጎንጥ ለልጅህ …… » ብዬ ነገሩን መጨረስ ይቅር ያላልኩት ያስመስልብኛል ብዬ ተውኩት

«ላውጋሽ ሁሉንም ከስር መሰረቱ አልኩሽ እኮ ዓለሜ? ስሚኝና ቅያሜሽን ያዥው ካሻሽ!»
«ቅያሜ አይደለምኮ! ግን እረስቼዋለሁ ብልህ ውሸቴን ነው!»

እውነታው ይቅርታ ማድረግ እና መርሳት ይለያያል። ይቅር ብዬዋለሁ ማለት ከዛ በኋላ ያደረገኝን ነገር ሳስታውስ ቁጣ ወይም በቀል ወይም ጥላቻ ሳይሰማኝ አልፈዋለሁ ማለት ነው እንጂ ድርጊቱን ረስቼዋለሁ ማለት አይደለም!! ይቅር ብያለሁ ማለት የበደለኝን ሰው ሳየው ለቡጢ የሚዘረጋው እጄ ለማቀፍ መዘርጋት ይችላል ማለት እንጂ ያ ሰው በዛው ወጥመድ እንደማይጥለኝ አምኜ (መጃጃል ብለው ይቀለኛል) መጠንቀቅ እተዋለሁ ማለት አይደለም!! በኔ ልምድና ፍቺ ይቅርታ ይህ ይመስለኛል። ሀይማኖተኛም ባልሆን ከሰማኋቸው ጥቂት የመፅሃፍ ቅዱስ ስብከቶች በመነሳት እራሱ እግዚአብሄርም ይቅር ብዬሃለሁ ሲል በጥፋትህ አልቀጣህም ምህረት አጊንተህበታል ማለቱ እንጂ ስራህን ረስቸዋለሁ ማለቱ አይመስለኝም። ቢሆን ኖሮ እስራኤሎችን አንድ ሺህ አንድ ጊዜ ይቅር ካላቸው በኋላ አንድ ሺህ ሁለተኛ ጊዜ ባዕድ ሲያመልኩ ከግብፅ ካወጣቸው ጀምሮ የበደሉትን ባልዘረዘረላቸው ነበር።
ጎንጥ እኔጋ መስራት ከጀመረ ከተወሰነ ወር በኋላ ልጁ ታማበት ነበር። ለሳምንት አስፈቅዶኝ ጠፍቶ ተመልሶ ሲመጣ ልቡ ተሰብሮ ልጁ ኩላሊቷ መቀየር እንዳለበት እና የሱ ኩላሊት ማች እንዳላደረገ ሲነግረኝ ምክንያቴ ለሷ ማዘን ይሆን ለሱ ወይም በደም የጨቀየ ህይወቴን በደል መቀነስ ለማላውቃት ህፃን ኩላሊቴን ልሰጥለት ፈቃደኛ ነበርኩ። ሄጄ ምርመራውን አድርጌላት ነበር።

የዛን ቀን ለእመቤት ይገርማታል ብዬ ለጎንጥ ልጅ ላደርግ ያሰብኩትን ስነግራት እሷ ግን በሚያሳዝን አይን እያየችኝ
«ሜልዬ? የመረጥሽውን ህይወት ድጋሚ የማስተካከል እድል ቢኖርሽ ምርጫሽ ይለይ ነበር?» አለችኝ

«አላውቅም! አስቤው አላውቅም! ምናልባት እንደማንኛውም ሰው ዓይነት ህይወት ኖሮኝ ቢሆን ምን እንደምመርጥ አላውቅም!! ግን ማንኛዋም ህፃን እኔ ያለፍኩበትን መንገድ አላለፈችም!! ማንኛዋም ህፃን እኔ ያየሁትን አላየችም!!»

«እኔ ግን ሲመስለኝ እንደማንኛዋም ሴት ሚስት መሆን እናት መሆን ….. ስስ መሆን …. ማፍቀር …. ባፈቀሩት ሰው ልብ መሰበር ….. ማለቃቀስ ….. እነዚህን ሁሉ የማድረግ ፍላጎት ልትሰሚው ስለማትፈልጊ እንጂ የሆነ ልብሽ ጥግ ተደብቆ ያለ ይመስለኛል።» አለችኝ። ጋዜጠኛ አይደለች? ወሬ ማዳመቅ ትችልበታለች።

«ሌላውስ ይሁን ልብ ተሰብሮ ማልቀስ መፈለግ የጤና ነው?» አልኳት ወሬው ሲኮሳተር ራሴን እፈልግ ይሆን አልፈልግ መጠየቅ ሽሽት። አፍቅሬ አላውቅም ወይም ፍቅር ይሉት ነገር በእኔ የህይወት ጉዞ ገደቡን ያለፈ ቅብጠት ነው። ከቅፅበት ስጋዊ መንደድ አልፎ አቅሉን ስቶ በፍቅሬ የነሆለለ ወንድም አላስታውስም!! ጭራሹኑ ከልብሴ ስር የሴት ገላ መኖሩ ትዝ የሚለው ወንድ ልብሴን አውልቄ ያየኝ ብቻ ይመስለኛል።

«እሱ ራሱ ጣዕም እንዳለው ብታውቂ? አፍቅረሽ ጧ ብለሽ! ከሌላ ሴት ጋር አየሁት ብለሽ ግንባርሽ ላይ ሻሽ ሸብ አድርገሽ ትኩስ ነገር የሞላው ኩባያ ይዘሽ ለጓደኛሽ ማውራት ……. »

«በይ እናቴ ያንቺ የጤና ፍቅር አይደለም! ታየኝኮ ማግ ይዤ ለወንድ ስንሰቀሰቅ!» ብያት ስቄ ከደንኩት።

የጎንጥን ልጅ ሆስፒታል ሄጄ ሳያት ተስፋ ባዘሉ የልጅነት ዓይኖቿ ውስጥ የራሴን ልጅነት አየሁት። ኩላሊቴ ሊያድናት እንደሚችል ሲነገረኝ የነበረኝን የደስታ ስሜት የዛሬን ያህል አስታውሰዋለሁ። ከዛን ቀን በፊት ሆስፒታል የመተኛት ከፍተኛ ፍርሃት ነበረብኝ። በተለይ ማደንዘዣ የሚያስወስድ ነገር ከሆነ። ራሴን ባላወቅኩበት ቅፅበት የሆነ ሰው የሆነ ነገር ያደርገኛል ብዬ እፈራለሁ። በጥይት ተመትቼ ሀኪም አምኜ ሆስፒታል የማልተኛ ሴት በገዛ ፈቃዴ ቅደዱና ኩላሊቴን አውጡ ብዬ የሆስፒታል አልጋ ላይ ልተኛ ዝግጁ ነበርኩ። ማንም ምንም ቢያደርገኝ ይሁን ከዛች ህፃን አይበልጥም ራሴን አስቱኝ ብዬ ፍርሃቴን ልውጥ ዝግጁ ነበርኩ። መኪናዋን ጊቢ እስካስገባ እንኳን አቅበጥብጦኝ

«እንኳን ደስ አለህ!!» ስለው ፊቱን ወደሌላ ቦታ አዙሮ እየተገማሸረ
👍341😁1
«በአምላክዎት! ግን ሀሳቤን አንስቻለሁ!! ከዚህ ወድያ የእርሶ እርዳታ አያሻኝም!» አለ ሁኔታው ንቀት ወይ ፅያፌ በሚመስል ሁኔታ እየጎፈላ !! የተሰማኝ ስሜት ልሰጠው የነበረውን ኩላሊት አልፈልግም የተባልኩ ሳይሆን ሊሰጠኝ የነበረ ኩላሊት ተከልክዬ ሞቴ የፈጠነ አይነት ነገር ነበር። ምክንያቱን ደጋግሜ ብጠይቀውም መልሱ

«ራሴን እንዳብራራ አያስገድዱኝ!! ሌላ ሰው ተገኝቷል!» ብቻ ነው። የሆነ የማላውቀው ተስፋ ልበለው ደስታ አላውቅም የተነነ! የሆነ ነገሬን የቀማኝ መሰለኝ። ያበሳጨኝ ደግሞ ንግግሩ ትህትና እንኳን ያልነበረው መሆኑ ነው። የሆነ በድክመቴ ያገኘኝ ነገር መሰለኝ።

«ድሮምኮ የሰው ልጅ ያለቦታው ክብር ሲሰጡት ሽቅብ ካልሸናሁ ይላል።» አልኩት ብስጭት እያልኩ

«እትዬ ይልቅ እላፊ አንነጋገር!! ስራዬን መልቀቅ ስለምሻ ሌላ ዘበኛ ቢፈልጉ ጥሩ ነው!» ሲለኝ የተናደድኩበት ምክንያት የቱ እንደሆነ ሳይገባኝ ጨስኩ!

«ለአንድ አመት ነው ልትሰራ የፈረምከው!! ኮንትራትህን ሳትጨርስ ወዴትም አትሄድም! ሞክረኝና ታያታለህ!» ብዬው ገባው።

በነጋታው ለራሴ ራሱ በማይገባኝ ምክንያት ልጁ ደህና መሆኗን ማወቅ ፈለግኩ። አላውቅም ብቻ እጇን ይዤ <አይዞሽ> ማለት አማረኝ። ምናልባት እሙ እንዳለችው የከደንኩት እናት የመሆን ስሜት ይኖር ይሆናል። እልሄን ውጬ ልጁን ላያት እንደምፈልግ ስነግረው።

«ይቅርታ ያድርጉልኝ እትዬ ለጊዜው ከቤተሰብ ውጪ ማንም እንዲያያት አልፈቅድም!! በሌላ አይዩብኝ ልነግሮት በማልችለው ምክንያት ነው!! " አለኝ። የፈረደባት እመቤት ጋር ሄጄ

«ይሄ የማይረባ! ሌላ ሰው ስለተገኘ አያስፈልግም አይለኝም? ቱ! » እያልኩ ስደነፋ እንባዋ እስኪፈስ እየሳቀች

«እንዲህ ያበሳጨሽ ለምን ኩላሊቴ አልወጣም ነው ወይስ ለምን እሱ እንደሌሎች በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች እቴጌ እመቤቴ አላለኝም አልተሽቆጠቆጠልኝም ነው? ይሄ ሰውዬማ ከገባ ጀምሮ ነርቭሽን ነክቶታል።»

«ባክሽን አንቺ ደግሞ! ጭራሽ ስራዬን እለቃለሁ ይበለኝ?» እኔ እበሳጫለሁ እሷ ትስቃለች። «ምኑ ነው አሁን ይሄ የሚያስቀው?»

«ለማንም ሰውኮ እንዲህ ቦታ ሰጥተሽ አታውቂም! ያውም ለዘበኛሽ? ጥጋቡ ነው የሚያንተከትክሽ ወይስ ሌላ ነገር አለ?» አለችኝ መሳቋን ሳታቆም። ከዛን ቀን በኋላ ስለጎንጥ ስናወራ < ጎንጤ ጥጋቡ> ነበር የምትለው።

ከቀናት በኋላ እሙ እንዳለችው የመንተክተኬ ምክንያቱ አልገባ ሲለኝ። ስራውን መልቀቅ እንደሚችል ሌላ ዘበኛ እንዳገኘው ስነግረው ደግሞ

«ሀሳቤን አንስቻለሁ! ኮንትራቴን ሳልጨርስ ወየትም ፍንክች አልልም» ብሎ አናቴን በብስጭት አዞሮው።

«እኔ ነኝና ሜላት! ሰውዬ ስትፈልግ እወጣለሁ ስትፈልግ እገባለሁ እያልክ እንደፈለግክ ሀሳብህን የምታነሳ የምትጥልበት የሰፈርህ ጠጅ ቤት አይደለም ይሄ! የቀጠርኩህ እኔ ነኝ! ስፈልግ ደግሞ በቃኝ ብዬ የማባርርህም እኔ ነኝ! ከነገ ጀምሮ ላይህ አልፈልግም!»

«ተናገርኩኮ ፍርማዬን ሳልጨርስ አልሄድም!» ብሎ እያወራሁት ትቶኝ ሌላ ስራ መስራቱን ቀጠለ።

አሁን ሲመስለኝ ያልጨረሰው ስራ ስለነበረ ነው የቆየው። ከዛ ቀን በኋላ የሰላም ቃላት ተለዋውጠን አናውቅም ነበር። አሁን ልለው የነበረው። <ለልጅህ ስልኮ እዛ አልጋ ላይ ተኝቼ ልደነዝዝ ዝግጁ ነበርኩ። ያ እንኳን ለጠላቶቼ ከመስራት አላገደህም!> ልለው ነበር። ይቅር አልኩት እንጂ አልረሳሁትም።

*******


ያቀበልኩትን ስልኩን ባልተመታበት ጎን እጁ እየነካካ ያልኩትን እንዳልሰማ ዝም ብሎ አልፎ!!
«ማንም ሰው እንዳልተከተለሽ እርግጠኛ ሆነሽ እዚህ ቦታ ሂጂ! የምትፈልጊውን ንገሪው።» ብሎ የምንገናኝበትን አድራሻ ሰውየው የሚለብሰው ልብስ እና ኮፍያ ቀለም። የምንግባባበት ኮድ ፣ የምንገናኝበትን ሰዓት እና የሰውየውን ፎቶ በጭንቅላቴ መያዝ እስክችል አስደጋገመኝ።

«እሺ ግን አንተ እርግጠኛ ነህ ምንም አትሆንም?»

«አታስቢ! ለጊዜው እኔን ለማጥቃት ሆስፒታል ድረስ የሚያስመጣ ምክንያት ያለው ጠላት የለኝም!» አለ እንድሄድ መውጫውን እየጠቆመኝ። ተነሳሁ ግን እግሬ አልተራመደም! ቆሜ ግራ በገባው ስሜት ዘቅዝቄ እያየሁት ቆየሁ። እጄን በሚይዘኝ አያያዙ ያዘኝ እና

« ድንገት ካንቺ አቅም በላይ የሆነ ነገር ቢፈጠር ቢያንስ ምንም ምርጫ ከጠፋሽ የምትደውይለት የመጀመሪያ ሰው እንደሆንኩ ቃል ጊቢልኝ!» አለኝ

«ብደውልልህስ? ቀና ማለት እንኳን የማትችል ሰው ምን እንድታደርግ ነው?»
«ብቻ ደውይልኝ! ምልክት ስጭኝ! ያን እንደምታደርጊ ቃልሽን ስጭኝ!!» እያለኝ ስልኩን ወደ ስልኬ ደወለ። «ስልክሽ ፊት ለፊት የኔ ቁጥር ይኑር!»

«እሺ በራሴ የማልወጣው ነገር ከገጠመኝ እደውላለሁ።» አልኩት እጄን አልለቀቀኝም። ላስለቅቀውም አልቸኮልኩም። በእጁ የአውራ ጣት እንደመደባበስ ካደረገው በኋላ አንስቶ ወደ ከንፈሩ አስጠጋው። የእጄን አይበሉባ ሳይሆን ገልብጦ መዳፌን የውስጥ እጄን መሃሉን በከንፈሩ በስሱ ሳመው። ሳመው ወይ ዳሰሰው ወይ ተጫነው። የሆነ ነገር …….. የእጅ ውስጥ ተስሞ ሰው እንዲህ እንደመስከርም እንደመጦዝም ያለ ስሜት ይሰማዋል?

«…. ተደናበርኩልሽ ጥይት እንደሳተው!» ያለው ዘፋኙ እንዲህ ተሰምቶት ነው የሚሆነው።

.ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍344
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አራት
////

እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርጌ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ  ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ  እየተብረከረከ ነው።

ተነሳሁና የተከፈቱ መስኮቶችን መዘጋጋት ጀመርኩ..ማብራቶችን አጠፍሁ፡፡ የሴትዬዎን ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ይዤ ወጣሁና የሆቴሉን በራፍ ቆልፌ ቁልፉን በጥንቃቄ ሚስጥር ኪሴ ውስጥ ሽጉጬ  ወደ አልጋ ክፍል አመራሁ...አቀብያት በዛው ወደ ቤቴ ሄዳለሁ ሞባይሌን አውጥቼ ሰዓት ሳይ 7፡40 ይላል።
ደረስኩና አንኳኳሁ...

‹‹ግባ ክፍት ነው››

የሚል ድምፅ ስሰማ ቀስ ብዬ በራፍን ወደ ውስጥ ገፋ አደረኩትና  ውስኪ ጠርሙስ የያዘ እጄን አስቀድሜ አንገቴን አሰገግኩ፡ መሀል ወለል ላይ ቆማ ተበትኖ ጀርባዋ ላይ የተኛውን ፀጉሯን አንድ ላይ ጠቅልላ እያሰረችው ነው..ቅድም ለብሳ የነበረውን ጅንስ ሱሪ አውልቃ ስስ የለሊት ቢጃማ ቀሚስ ለብሳለች...፡፡ ቢጃማው ሮዝ ቀለም ሲኖረው አጭር እና በቀላሉ አይን ውስጥ የሚመሰግ ነው...አስተውሎ ላየው ቀሚስ ሳይሆን ቁምጣ ነው የሚመስለው..እና ያ የሚንቀጠቀጥ እና ሊፈርጥ የደረሰ ዳሌዋ በከፊል እርቃን ነው...፡፡

"በራፍ ላይ ተገትረህ ታድራለህ ወይስ ትገባለህ ?"

"እ እሺ ገባለሁ ››አልኩና ወደውስጥ ገብቼ ጠርሙሱን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጬ ለመውጣት ዞር ስል  እሷ ከቦታዋ ተንቀሳቅሳ ወደበራፍ እያመራች ነው፡፡

‹‹...ብርድ አስመታሀኝ ››"በሚል ሰበብ  ክፍት ጥዬ የመጣሁትን በራፍ ዘጋችና ቆለፈችው፡፡

"ቆይ እኔ ሳልወጣ?"አልኩ ደንግጬ፡፡

"ትንሽ አጣጣኝ እና ትሄዳለህ.. ያውልህ ብርጭቆ…

"ቅዳልኝ" የንግግሯ ቃና ወደ ትዕዛዝ ያዘነበለ ነው.፡፡
ግራ በመጋባትና በመርበትበት  እንዳለቺኝ አደረኩና እዛው ጠረጴዛ ጎን ያለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ..፡፡እሷም ወደእኔ መጣችና ብርጭቆዋን አንስታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች ...፡፡አቀማመጧ በእኔ ትክክል ነው...፡፡አይኔ ወደታች ወደተጋለጠው ጭኗ እየተንሸራተተ አስቸገረኝ ፡፡...እሷ የእኔን ሁኔታ ከቁብም የቆጠረች አይመስልም፡፡ጭኗ እንደሴቶች ጭን ልል እና ለስላሳ አይደለም…፡፡እንደስፖርተኛ የዳበረ እና ፈርጣማ ነው፡፡ሲነኩት ትንቡክ የሚል አይነት ሳይሆን ሲነካ ጭፍልቅ  የሚያደርግ አይነት፡፡

"አሁን ጋሼ እንዲህ ከእንግዳ ጋር በውድቅት ለሊት ቤርጎ ውስጥ  ገብቼ ዘና ስል  ቢያየኝ ምን ይለኛል? ጓደኞቼስ ቢያዩ ተረባቸውን እችለዋለሁ?››

በዝምታ ውስጥ ሆና የቀዳሁላትን  ጠጥታ  ጨረሰችና ከተቀመጠችበት ተነስታ እራሷ ለራሷ ቀዳች ፡፡..ልትቀዳ ስትል ታከከቺኝ..እናም ደግሞ የተቀባችው ሽቶ ያለፍላጎቴ በአፍንጫዬ ሰርጎ ገባ...እና እየጠጣሁ ካለሁት መጠጥ ጋር ተጋግዞ አነቃቃኝ...፡፡

ወደቦታዋ ተመልሳ ተቀመጠች ፡፡አቀማመጧ ግን እንደቅድሙ እግሮቿን አጣምራ ሳይሆን ፈርክክ አድርጋ ከፍታ ነው፡፡ ...እና በክፍተቱ አይንን ሚያጥበረብር ቀይ ፓንት አየሁ..፡፡ለምን አየህ ?ብላ ተነስታ የምታንቀኝ መስሎኝ  ከመርበትበቴ የተነሳ ብርጭቆ ውስጥ ያለችውን መጠጥ በአንድ ትንፍሽ ገርገጭ አድርጌ አጋባኋት፡፡

"በቃ እግዜር ይስጥልኝ አሁን  መሸብኝ ልሂድ..›› ለማለት አስቤ ገና አፌን ሳልከፋት ከተቀመጠችበት ተነስታ በድጋሚ ቀዳችልኝ፡፡ ..ለመናገር የተከፈተ አፌን ቀስ ብዬ ዘጋሁትና  አንዴ መጠጡን አንዴ እሷን እያፈራረቅኩ ማየት ጀመርኩ።"አሁን ብዥ እያለብኝ ነው..፡፡ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓት ተመለከትኩ...8:18 ይላል።

"ምነው መሸብህ እንዴ?"

"አይ አንቺን እንቅልፍ ነሳሁሽ ብዬ ነው"

"ጥሩ አስመሳይ ነህ"አለችኝ.፡፡

‹‹እስቲ በጌታ አሁን እንዲህ ይባላል?››አንገቴን በእፍረት ከማቀርቀር ውጭ ምንም መልስ አልሰጠኋትም፡፡ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደሻንጣዋ በመሄድ መጎርጎር ጀመረች‹‹...ምን ልትሰጠኝ ነው?"ብዬ ሳሰላስል  ክሬም ቅባት አወጣችና አልጋ ላይ ወረወረች..መቀመጫዋን ወደ እኔ ፊቷን በተቃራኒው ወደግድግዳው አዞረችና በቆመችበት አጭሩን የለሊት ቀሚሷን ሞሽልቃ አወለቀች።አይኖቼን ጨፈንኩ..ገለጥኩ...መልሼ ጨፈንኩ...ቅድም በስሱ ካየሁት  ቀይ  ፓንት በስተቀር ምንም የጨርቅ ዘር በሰውነቷ አልቀረም....፡፡ጡቶቾ እንደሩሲያ አስፈሪ ሚሳዬሎች ጫፋቸውን ወደእኔ   ቀስረው ልቤን አራዷት ብላችሁ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን እየታዩኝ አይደለም፡፡ፐ!! ከኃላዋ የሚታየው የሰውነቷ  ቅርፅ  ግን ከአንገቷ በላይ ያለውን መልኳን በሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጣል።

ዘለህ ተጠምጠምባት የሚል ስሜት  ከሁሉም የስሜት ህዎሳቶቼ ተሰባስቦ ጉሮሮዬ ላይ ተወተፈብኝ... እጇቼ ገላዋን ለመዳሰስ አይኖቼ ከግራ ወደቀኝ እያገላበጠ  መላ ሰውነቷን በምስጠት ለመመልከት፤ አፍንጫዬ አንገቷ ስር ተደፍቶ ጠረኗን ወደውስጥ መማግ፤ጆሮዎቼ አፍ አካባቢ ተለጥፈው ከአንደበቷ የሚወጣውን ሹክሹክታ በፅሞና ለማዳመጥ እና እንትኔ ደግሞ ጭኖቾን ፈልቅቆ ወደ ውስጠቷ መስመጥ ፈለገ(ውይ እንትኔ ለካ የስሜት ህዋሳቴ አይደለም...ነው እንዴ?)

ዘፍ ብላ በሆዷ አልጋው ላይ ተኛች...አሁን በህይወቴ በአካልም በፊልምም ጭምር ካየኋቸው ባለ እርቃን ሴቶች ሁሉ ተወዳዳሪ የሌላት ፍፅም አማላይ ሆና ታየችኝ፡፡.. ፀጉሯ ብትን ብሎ ከፊል ጀርባዋን እና የተንተራሰችበትን ትራስ ሸፍኖታል..፡፡ከዛ ወረድ ስንል ልምጥ  ብሎ የሚታየው ወገቧ  የሩብ ጨረቃን ቅርፅ ይዞ አይንን ያፈዛል ፡፡..ከዛ ሽቅብ ወደላይ ስንወጣ መቀመጫዋ ቀይ ፅጌረዳ አበባ የሸፈናቸው ግዙፍ መንታ ተራሮች ይመስላሉ፡፡..ከዛ በመነሳት ለሁለት ተከፍለው የተዘረጉት እግሮቾ ለምለም መስክ ላይ የተዘረጋ የአክሱም ሀውልትን ይመስላሉ...እጣቶቾ ደግሞ....

"ትንሽ እሸኝና ትሄዳለህ.."የሚለው ንግግሯ ስለውበቷ ተቀኝቼ ሳልጨርስ ከሀሳቤ አናጠበኝ።

" ሎሺኑን ተጠቀምና እሸኝ.."ደገመችልኝ።

"እሸኝ ማለት ምን ማለት ነው..?እንዴት ነው የማሻት..?የሚታሽና የማይታሽ የሠውነት ክፍል ይኖራት  ይሆን ?ካሸዋትስ በኃላ የሚከተል ነገር ይኖራል..?በሰከንድ ውስጥ በምናቤ  ብልጭ ድርግም ያሉ  ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው..፡፡እጆቼን ሰበሰብኩና ወደአልጋው ተራመድኩ፡፡ ጠርዝ ላይ ተመቻችቼ ተቀመጥኩ..፡፡ጃርባዋን ያለበሰውን ፀጉሯን ሰበሰብኩና ወደትራሱ አሻገርኩት...እና ሎሺኑን አነሳሁና ጨመቅ ጨመቅ አድርጌ እጄ ላይ አፈሰስኩና   ከትከሻዋ ጀመርኩ...፡፡ይህ ሰውነት ከዚህ በፊት እንደማውቃቸው የሴት ገላዎች የሀር ጨርቅ አይነት ልስላሴ የለውም..፡፡በዳበሩ ጡንቻዎች የተገነባና በጠንካራ ቆዳ የተሸፈነ ልዩ አይነት ሰውነት ነው፡፡ቢሆንም ሲያሹት እጅን ሙልጭ ሙልጭ እያደረገ ቢፈታተንም ደስ ይላል፡፡ ‹‹ አዎ ትግስት ካለኝ  ተገልብጣ በጀርባዋ ስትተኛና ከፊት ለፊቷ ያለውን የሰውነት ክፍሏን እንዳሻት ስትመቻችልኝ ቀስ ብዬ ልክ እንደዚህ ሎሺን ጡቶቾን አሸት አሸት እያደረኩ ከውስጣቸው ፍቅር እንዲያመነጩ አስገድዳቸዋለሁ፡፡›› ስል በአይነ ህሊናዬ በመሳል ጎመዣሁ..ምራቄን ገርገጭ እያደረግኩ ዋጥኩ ።
👍541
እጆቼን ከትከሻዋ ወደ ጀርባዋ..ከጀርባዋ ወደ ወገቧ እያንሸራተትኩ በንቃትና በትጋት ስራዬን ቀጠልኩ...፡፡ከስካሩ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ ሙቀት በሰውነቴ እየተራወጠ ነው...፡፡በረሀብ ምክንያት ይገላባበጥ የነበረው አንጀቴ አሁን አደብ ገዝቶ ፋታ ሲሰጠኝ ወሲብ በተመለከተ የሚመለከታቸው የሰውነቴ ክፍሎች ግን በተቃራኒው እንደ ጃርት እሾህ በያሉበት ቀጥ ብለው  ወጣጥረውኛል....፡፡

"ኸረ ትንሽ ታገሱ ...ግብዣው ሙሉ በሙሉ  ከእሷ እስኪመጣ አደብ ግዙ...ያው የክብር ጉዳይ ነው››"እያልኩ የገዛ ብልቶቼን ለመምከር ብሞክርም ብዙም ሊሰሙኝ ፍቃደኞች አይደሉም፡፡...ግን ሙሉ ፍቃድ እስኪያገኙ ከመጠበቅ ውጭ ሌላ ምርጫ አልሰጠኋቸውም፡፡...አሁን ከወገቧ እስከአንገቷ በችሎታዬ ልክ በደንብ አሽቼያታለሁ...ቀስ ብዬ ወደታች ወረድኩና ቀኝ እጄን በመቀመጫዋና በፓንቷ መካከል ሰንቅሬ በማሸት ሙድ ጨመቅ ጨመቅ  ማድረግ   ስጀምር ለመጀመሪያ ጊዜ ቀኝ እጇን አንቀሳቀሳችና እጄን ክርኔ አካባቢ አፈፍ አድርጋ ይዛ በቀስታ መዛ አወጣችና ‹‹..እንደዛ ብፈልግ ቀድሞውኑ ፓንቴን አወልቅ ነበር"አሁን ወደ ቤትህ መሄድ ትችላለህ...ለሁሉም አመሰግናለሁ...የተረፈውን ውስኪ ይዘህ ሂድ"አለችኝ

አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ... ኩምሽሽ ነው ያልኩት..ስኳር ሲሰርቅ በወላጆቹ የተያዘ ህፃን ልጅ በሉኝ" ከተቀመጥኩበት ሹክክ ብዬ ተነሳሁ እና በቀሰስተኛ እርምጃ ወደ በራፍ መራመድ ጀመርኩ

አውልቃ የነበረውን ቢጃማ ጡቶቾን እና ሆዷን ሸፍና ከተጋደመችበት ተነሳችና "ምነው ቅር ያለህ ትመስላለህ? ሌላ ነገር ጠብቀህ ነበር እንዴ?"ብላኝ እርፍ..

በፈጣሪ እስኪ አስቡት… የማላውቃት ሴት በውድቅት ለሊት ጋብዛኝ..ጎትታ ክፋሏ አስገብታኝ፤ አጠጥታኝ..  ፊት ለፊቴ ልብሷን አውልቃ እርቃኗን አስጎብኝታኝ...በጣቶቼ ከፊል ሰውነቷን  እንድነካና እንድዳስስ ፈቅዳልኝ "ሌላ ነገር ባስብ ይፈረድብኛል"እንኳን እንደእኔ ደመ ሙቅ ወጣትና  ሙሉ ብልቱ ጤነኛ የሆነ ሠው ይቅርና ጃነደረባስ ቢሆን   በዚህ አይነት  ሁኔታ ውስጥ አልፎ ሌላ ነገር ማሰብ ይቀራል...?

ይቀጥላል
👍421
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ ሁለት)
(ሜሪ ፈለቀ)

የሳመውን እጄን ተቀብዬው ከሆስፒታሉ ወጥቼኮ ታክሲ ተሳፍሬ ወደቃሊቲ መንገድ ከጀመርኩ ቆይቻለሁ። እጄን ተቀብዬው አልኩኝ እንጂ እየተሰማኝ ያለው ወይ ከንፈሩ እጄ ላይ የቀረ ወይ ደግሞ እጄ እዛው እሱጋ ከንፈሩ ላይ የቀረ አይነት ስሜት ነው። የሳመኝን እጄን የሳመኝን ቦታ አንዳች የእግዜር ተአምር የፈለቀበት ነገር ይመስል እየደጋገምኩ አየዋለሁ። ደግሞ እየደጋገምኩ እሱ እንደሳመው እስመዋለሁ። ቀስ ብሎ ልስልስ ያለ …… እርጥበት ያለው ግን የሚሞቅ …….. ከዛ ደግሞ ከእግሬ ጥፍር ድረስ እስከ አናቴ እንደኤሌክትሪክ ሞገድ ጥዝዝዝ ብሎ በደምስሬ ውስጥ ይሆን የተጓዘው ፣ ከጅማቶቼ  ጎን ለጎን ባገኘው ክፍት ቦታ ይሆን እየተሽሎከለከ የተጓዘው ባልገባኝ አካሄድ የናጠኝ …… የሆነ መለኮታዊ የሆነ መሳም ነገር …..

ስሳም የመጀመሪያዬ ሆኖ አይደለም። በትግል ፣ ኑሮን ለማሸነፍ በመጋጋጥ ፣ ኪዳንን ትልቅ ቦታ እንዲደርስ በመታተር ፣ በበቀል ፣ ሴራ በመጎንጎን ፣ ገንዘብ እና ጉልበትን በማካበት …… እና ሌሎች ብዙ ለሌላው ሰው ስሜት የማይሰጡ ነገሮችን በማድረግ ውስጥ ከወንድ ጋር የሚደራረጉ አልባሌ ነገሮችን ከማድረግ አልታቀብኩም። እንደእውነቱ ከሆነ ብዙ አድርጌያለሁ። አብሮ በመግባት እና በመውጣት እንደፍቅረኛ ወግ ያሳለፍኩት ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ከዳዊት ጋር ነበር። ዳዊት በከተማችን ውስጥ አለ የሚባል ባለሃብት ልጅ ነው። አባቱ በገንዘቡ ባለስልጣናትን የሚሾፍር ተፅዕኖ ፈጣሪ ነው። የእድሜ ልክ እስራት ፍርዴን በ6 ዓመት ያቀለለልኝ እሱ ነው። ውለታ ውሎልኝ አይደለም! በልዋጩ ሶስት ነገር ሰጥቼዋለሁ። አንድ የነበረኝን 48% የሚሸፍን የአንድ ባንክ አክስዮን (እሱ 20% ስለነበረው የእኔን ሲጨምር በባንኩ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ያደርገዋል።) ሁለት የራቁት ዳንስ ቤቱን ግማሽ ልሸጥለት (ዳዊት የገባው በዛ ነው) ሶስተኛው እና ዋነኛው (ሌሎቹ ተጨማሪ ናቸው) የአንድ እሱ የሚፈልገው ከፍተኛ ባለስልጣን ሚስጥር (ለምን እንደፈለገው አልገባኝም ምክንያቱም እስካሁን አልተጠቀመበትም። ወይም እያስፈራራበት እየተጠቀመበት ይሆናል አላውቅም! ሰውየው ግን እስካሁን ስልጣኑ ላይ ነው።)

አንዲት ከትንሽ መንደር መጥታ ኑሮን ለመግፋት ትፍጨረጨር የነበረች ሴት የባለስልጣናት ሚስጥር እጇ ላይ እንዴት ወደቀ? ይሄ ሁሉ ሀብትስ እንዴት ተቆለለ? የሚሆን አይመስልም አይደል? ሆኗል!!

እዚህ ሀገር አንድ የገባኝን ነገር ልንገራችሁ! በተለይ  እላይኛው የኑሮ መደብ እና ስልጣን ላይ የተፈናጠጡት ሰዎቻችን ዘንድ ….. በገንዘብ አቅም የማይሆን ምንም ነገር የለም። የሚለያየው የገንዘቡ መጠን ብቻ ነው። በመቶ ሺህዎች <ሀቀኝነቴን ፣ እምነቴን ፣ ህሊናዬን > ሲል የነበረ ለሚሊየኖች እጅ ይሰጣል። ለሚሊየኖች <ቤተሰቤን ፣ አምላኬን ፣ ቃሌን ፣ ህዝቤን > ያለው ደግሞ ለቢሊየን ወድቆ ይሰግዳል። ገንዘቡን የምታቀርብለት ሰው ወይም ድርጅት የሌለውን ያህል ወይም በቀላሉ ሊያገኝ የማይችለውን ያህል ገንዘብ መጠን አቅርብለት! የምትፈልገውን ይሸጥልሃል። ለምን ሚስቱ አትሆንም!!! በስህተት አምልጦ የሾለከ <በገንዘብ የማልሸጠው ህሊና አለኝ> ያለ ጎርባጭ ከተገኘ …… በነዛኛዎቹ ይሰለቀጣል። <ህዝብን በተገቢ ሁኔታ ባለማገልገል፣ የህዝብን ጥቅም ባለማስቀደም > ምናምን ምናምን የሚባሉ ፖለቲካዊ ሀቅ የሚመስሉ ውስልትናዎች ተለጥፈውበት እንደ እድሉ አርፎ የማይቀመጥ ቅብጥብጥ ከሆነ ወደ እስር ቤት ……. ለቤተሰቤ አንገቴን ልድፋ ያለ የቤተሰብ ሰው ከሆነ ደግሞ ወደቤት ይላካል።

እንግዲህ ከዳዊት ጋር አብረን መስራት የጀመርነው ከእስር ቤት ከወጣሁ በኋላ መሆኑ ነው። ወድጄው አይደለም! ማለቴ እንደፍቅረኛ! እንደስራ ባልደረባ ጭንቅላቱ ለቢዝነስ የተፈጠረ፣ ለተንኮል እና ሴራ እኔን የተስተካከለ ፈጥኖ አሳቢ ፣ አባቱ ስለሚንቀው ለአባቱ የሆነ ጀብድ ሰርቶ ራሱን ማስመስከር አብዝቶ የሚሻ ሰው ነው። ከምለብሳቸው የወሮበላ ልብሶች ውስጥ ያለ የሴት ገላዬን ራቁቱን ሳያየው የተመኘ ብቸኛ ወንድ ይመስለኛል። ባለገንዘብ ፣ ባለጉልበት ፣ ባለሀይል ከሆንኩ በኋላ ለአመታት በዙሪያዬ ያለ ሰው ሁሉ እንደአለቃ የሚፈራኝ ፣ እንደሰው የሚያከብረኝ ፣ በዛ ካለ ትንሽ የሚቀርቡኝ እንደወዳጅ የሚያዩኝ ሴት ነበርኩ እንጂ ማንም በሴትነቴ የተመኘኝ አላስታውስም። ሴት መሆኔ ትዝ የሚላቸውም አይመስለኝም። እሱ ግን እንደስራ ባልደረባው ሳይሆን እንደሴት አየኝ!! የሚጋረፍ ፊቴ ሳያግደው ለወራት አበባ አመላለሰልኝ (እያየ ፊቱ ላይ አበባውን በጫጭቄ እበትነዋለሁ) ። <ደነዝ ነህ ወይ አትሰማም? አንተ ምኔም መሆን አትችልም!> እያልኩት በየቀኑ ቆንጆ መሆኔን ነገረኝ። በግልፅ <አይደለም ፍቅረኛዬ ልትሆን ለአንድ ቀን ተሳስቼ አብሬህ ብተኛ የምፀፀትብህ አይነት ሰው ነህ!> እያልኩት እንኳን በየቀኑ ሳይደክመው እንደሚወደኝ እየነገረኝ ዓመት ተቆጠረ። አንድ ቀን ከአባቱ ጋር ተጣልቶ ቢሮ ተቀምጦ እንደ ትንሽዬ ሴት ልጅ ሲንሰቀሰቅ ደረስኩ። ምን እንደሆነ ስጠይቀው እንባውን ከንፍጡ እየደባለቀ ማልቀሱን ሳያቆም በአባቱ ፊት ሁል ጊዜ ትንሽ መሆኑን ነገረኝ። አሳዘነኝኮ ግን ከማልወደው ነገሩ አንዱ ይሄ ልፍስፍስ ሴታ ሴት ነገሩ ነው። የዛን ቀን ግን

«ዛሬ እራት ልጋብዝህ?» አልኩት። እንባው ጥሎት ጠፋ! ከዛ በኋላ እንደፍቅረኞች የሚፈፃፀመውን ነገር ሁሉ እንፈፃፅማለን። አልጋ ላይ ሲያዩት ስልባቦት እንደሚመስለው ገላው አይደለም ወይም እንደሴታሴት አኳኋኑ። ስለዚህ ሴታዊ ፍላጎቴን ለማግኘት የማላውቀው ሰው ጋር ከምሄድ ጥሩ ቅብብሎሽ ነበር። አንዳንዴ ምንችክ ሲልብኝ እዘጋዋለሁ። ደግሞ መልሰን እንጀምራለን። ስለእውነቱ ግንኙነታችን ምን እንደሆነ ወይም ወዴት እንደሚሄድ እንኳን ውልም ስምም የለውም ነበር። እንኳን እጄን ስሞኝ የስሜቴ የመጨረሻ ጡዘት ጠርዝ ላይ እንኳን እንዲህ ዛሬ ጎንጥ እጄን ሲስመኝ እንደተሰማኝ  አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም!! ኸረ እንኳን ሊሰማኝ መኖሩንም አላውቅም!! ፊልም ላይ እንኳን ትኩረታቸው ከንፈር እንጂ እጅ እና ከንፈር ሲገናኝ እንዲህ አስማታዊ ስሜት እንዳለው መች ይነግሩናል?
ቃሊቲ በሩ ላይ እንደደረስኩ ዘበኛው ሲያየኝ እንደተለመደው በወዳጅነት  «ቁርጠትዬ እስቲ ዛሬ ደህና ጊቢልኝ ታውቂ የለ ሚስትየው ስታላምጠኝ ነው የምትከርመው?» አለኝ።

«ይገባልሃል! ሂድ ባርችን ጥራልኝ!! እዚህ ስትቅለሰለስ እኮ እኔን አማክረህ አራት የወለድክ ነው የምትመስለው!»

«እሱማ ይጠራልሻል!! ግን ሰሞኑን ምርጫ ደርሷል ብለው የሌለ ህግ እያጠበቁ ነው!!»

«በቃ እሱ ታሳቢ ተደርጎ ይገባልሃል! መርዶ ሊነገራት ነው …. ወንድሟ ራሱን አጥፍቶ ነው …. መዓተኛ አይደለህ? አንዱን ቀባጥርና ጥራልኝ» ብዬ ከኪሴ ብር አውጥቼ አቀበልኩት። እሱ ወደ ውስጥ ሲገባ እየሆነ ያለውን ባላየ ዝም ብሎ የተቀመጠውን ሌላ ጠባቂ ብር በያዘ እጄ ጨበጥኩት። እየወተወተ አመሰገነኝ!!

«ያልጠየቅሽኝን እያካካስሽ ነው በየቀኑ?» አለች እሙ ገና ከመድረሷ «ጎንጤ ጥጋቡስ ዛሬ የለም?»

« ሁሉንም ነገር ላስረዳሽ ጊዜ አይበቃኝም!! እርዳታሽን ፈልጌ ነው የመጣሁት!! ከዛ ደግሞ በአጭሩ ትናንት ላይሽ የመጣሁ ጊዜ የማውቀው ታሪክ አልነበረም። የተመታሁ ጊዜ ሚሞሪዬን እንዳለ አጥቼ ነበር።»

«እና አሁን?» ብላ ግራ ገብቷት ከላይ እስከታች አስተዋለችኝ።
👍214
«ከትናንት እስከአሁን በ24 ሰዓታት ያልተፈጠረ ነገር የለም ብልሽ ይቀላል። አንድ ቀን ሳይሆን አንድ ዓመት የሆነ ነው የሚመስለው። ኪዳንን ላስለቅቅ በነበረ ሂደት የተኩስ ልውውጥ ነበር። በዛ መሃል ሲመስለኝ የሽጉጥ ተውሱ ትውስታዬን የወሰደብኝ ተኩስ አደጋን አስታወሰ እና ትውስታዬን ቀሰቀሰው። አላውቅም የተከሰተውን ብቻ አስታወስኩ ሁሉንም!!»

«wait a minute …. It’s too much information eko (ጭንቅላቷን የሆነ ከደነዘዘበት እንደማባነን፣ እንደማንቃት ያለ እየወዘወዘች) እሺ የትውስታ መሄድ መምጣቱ ይቆየኝ! ኪዳን safe ሆነ? ሆ! አይገርምሽም?  I felt it ደግሞ እኮ……. Something was off » አለች አሁንም ዓይኗ እላዬ ላይ መርመስመሱን ሳታቆም!

«አልሆነም!! አሁንም እነሱጋ ነው ለዛ ነው እርዳታሽን የምፈልገው!!»
«ምንም እየገባኝ አይደለም! ተኩስ ነበር አላልሽኝም? አንቺ ታዲያ እንዴት እዚህ ተገኘሽ?»
«እሙዬ እመኚኝ ስናወራ ውለን ብናድር አይገባሽም!! ጎንጥ ከነርሱ አንዱ ነው። እኔ በሱ ምክንያት ነው እዚህ ያለሁት! እሱ ደግሞ ሆስፒታል ነው ተመትቶ!! (ይበልጥ ሲዞርባት አየሁ) ሌላ ቀን እነግርሻለሁ እሱን!!»

«ጎንጤ ጥጋቡ የእነሱ? እኮ ዘበኛሽ ሰላይ? እመኚኝ አመትም ብትነግሪኝ ይሄ ነገር አይገባኝም!!»
«እኔም ብዙ አልገባኝም ኪዳኔን ቅድሚያ ልስጥ ብዬ እንጂ!!»
«እሺ ምንድነው እንዳደርግልሽ የምትፈልጊው?»
«እናንተ ቴሌቭዥን ጣቢያ አሁን በምርጫው ዙሪያ እየሰራ ያለ ጋዜጠኛ እንዲተባበረኝ እንድታደርጊልኝ እፈልጋለሁ። እና ደግሞ ዛሬ የሁለት ሰዓቱን ዜና የሚያነበውን ሰው!»

«እሺ አገኘሁልሽ! ምን አስበሽ ነው?» አለች ጭራሽ ግራ ተጋብታ!!
«የምርጫው ዜና ሲተላለፍ አቶ ደሳለኝም አንዱ እጩ ተወዳዳሪ እንደመሆናቸው አንዱ ጋዜጠኛችሁ እቤታቸው ተገኝተው ላይቭ አጭር ቃለመጠይቅ ያደርጉላቸዋል። የምታደርጉትን አድርጉ ስትፈልጉ ሙሉውን ቃለመጠይቅ ከዜና በኋላ ያቅርቡት። እኔ የምፈልገው ከእኔጋ በተቀናጀ ሰዓት ላይቭ መግባታቸውን ነው።»

«እየገባኝ አይደለም!! የማስበውን እያሰብሽ ከሆነ በጣም ሪስክ አለው!»
«አውቃለሁ ግን ከዚህ የተሻለ ደም ሳይፈስ፣ ህይወት ሳይጠፋ ኪዳንን ላገኝ የምችልበት ምንም አማራጭ አልታየኝም!! ብቻ አንቺ ይሄን ማድረግ ትችዪ እንደው ንገሪኝ?»

«ወይ ጉድ! እስኪ ስልክሽን ስጪኝ ልደዋውል!!»

«እሺ በስልኬ ግን ምንም አይነት መረጃ እንዳትቀያየሪ! ከእኔ ጋር እንዲገናኑ ብቻ በሆነ መላ ንገሪያቸው። ምናልባት አላውቅም!! ስልኬን ሲሰጡኝ ውስጡ የነበረ ብዙ ነገር አፅድተው ነው የሰጡኝ። ሁሉንም ሶሻል ሚዲያዎቼን አዘግተውታል። መቼም የማላስታውስ ነበር የመሰላቸው መሰለኝ ወይም ከማስታወሴ በፊት እንደሚደፉኝ እርግጠኞች ነበሩ።»

«እንደዛ ከሆነ መደወሉ በራሱ ሪስክ አለው!! (ዘወር ብላ ወደ ጠባቂው) ሼባው? ዛሬ ለሚስትህ ዓመትበዓል ማስመሰል አላማረህም? ስልክህን ለ5 ደቂቃ ልደውልበት ?» አለችው። የጠባቂውን ስልክ ተቀብላ ሁለት ቦታ ስልክ ደዋወለች። ስልኮቹንም ለእኔ እንድመዘግብ ነገረችኝ። እኔ በምፈልገው መንገድ አዘጋጀችልኝ። መልሳ ለጠባቂው ከሰጠኋት ብር ጋር ስልኩን እየሰጠችው

«ሳመኝኮ!» የሚለው ቃል አፌን አምልጦ ሲወጣ እኔው ራሴ ስሰማው እና እሷ ጆሮ ጠልቆ ሽው ብላ ዞራ ስታፈጥብኝ አንድ ቅፅበት ነው።

«ጎንጥ! ከንፈሬን አይደለም ደግሞ እጄን ነው! እዚህጋ! » ብያት የሳመኝን እጄን እንደሌላ ሰው ባዕድ እጅ ሳየው አይታ

«እርፍ መጃጃል!! እጅሽን ስሞሽ ድንግልናዋን ዛሬ እንደሰጠች ልጃገረድ እንዲህ የተሽኮረመምሽ ሌላ ነገር ቢያደርግሽ ክንፍ አውጥተሽ ልትበሪ ነው?» ብላ መሳሜን ስላቀለለችብኝ ተናደድኩ። እንዲህ ያለ መሳም ተስማ ባታውቅ ነው ያልገባት። ወዲያው ቀጥላ  «እንዴ ደግሞ ቆይ አሁን ከደቂቃዎች በፊት የእነርሱ ወገን ነው አላልሽኝም? አንቺ ሴት ዛሬ ግራ ያልተጋባ ምንም ወሬ ያለሽ አልመሰለኝም!»


«እንዳልሽው ነው ሁሉም ነገር ግራ የተጋባ ነው!! እጄን የሳመኝ ግን ግራ አያጋባም ሃሃሃሃሃሃ ኩልልል ብሎ ጥርት ያለ ነው።» ብያት ዝርዝሩን ከሰሞኑ መጥቼ ልነግራት ተስማምተን ተለያየን።

ተመልሼ ወደከተማ እየሄድኩ ተናኜጋ ደውዬ የተወሰነ ጥሬ ብር እና ለእንዲህ አይነት ጊዜ ለመጠቀም ገዝቼ አስቀምጫቸው ከነበሩ ሲሞች አንዱን እንድታመጣ ቦታውን ነገርኳት። በመንገዴ አዲስ የስልክ ቀፎ ገዛሁ። ዳዊትጋ ስልክ ደውዬ መኪናዬ ስለተበላሸች አሁኑኑ የእርሱን እንዲያውሰኝ ስጠይቀው በዛ ጭንቅንቅ መንገድ ነድቶ ሳይሆን በአየር ላይ በሮ በሚመስል ፍጥነት ያልኩት ቦታ ደረሰ። መኪናዋን ልነዳ ከተቀመጥኩ በኋላ ምንም እንኳን ሁሉም ትውስታዬ ቢመለስ ለሰከንዶች መንዳት መቻሌን እርግጠኛ አልሆንኩም ነበር። ወይም ፍርሃት ተሰምቶኝ ነበር።

ሁሉንም ነገር ባቀድኩት መሰረት ማስተካከሌን ለመቶኛ ጊዜ ካረጋገጥኩ በኋላ መፀለይ አሰብኩ። ሰዓቱ ገና ስለነበር የቀረበኝ ቤተክርስቲያን ገባሁ እና በሩ አካባቢ ቆምኩ። ከዛ ግራ ተጋባሁ!!! ላለፈው በደሌ ሁሉ አንድም ቀን መጥቼ ንሰሃ አልገባሁም!! በደም የተነከረ እጄን ወደ እርሱ መዘርጋት ድፍረትም ሆነብኝ!! ከዛ ደግሞ ያለፈውን ሁ,ለት ወር ከምናምንኮ ፀልዬ ነበር!! ሰምቶኝ ይሆን ወይስ አያውቀኝ ይሆን? ወይስ ባኮረፈ ፊቱ ነው ሲያየኝ የነበረው? ደግሞ መልሼ ከሰማኝ ይስማኝ ብዬ መፀለይ ጀመርኩ።

«አምላክ ሆይ ታውቀኛለህ ብዬ አስባለሁ። ካላወቅከኝ ሜላት ነኝ። ያለፈውን ሀጥያቴን ሁሉ ብናዘዝ መሽቶ ይነጋል። ከዛ በፊት ግን ያንተን እርዳታ እሻለሁ ተለመነኝ!! አሁንም የምሰራው ባንተ ዘንድ ልክ ይሆን ስህተት አላውቅም! ግን የተሻለ የመጨረሻ አማራጭ የምለውን ነው የመረጥኩት። እኔም ራሴ የድሮዋን ሜላት መሆን አልፈልግም! አንተም እንደማትወዳት ነው የማስበው!! ያለፈውን ሁሉ ማረኝ እና ለእኔ ስትል ሳይሆን ለወንድሜ ስትል፣ ለዛች ደጅህ ለማትጠፋ ምስኪን እናቴ ስትል ….. ወንድሜን ይዤው እንድመለስ እርዳኝ!! እባክህ እ? ከፈለግክ አትማረኝ! ከፈለግክም ቅጣኝ ግን በወንድሜ አትቅጣኝ!! እ? » የሆነ ከሰማይ <እሺ> የሚል ድምፅ እሰማ ይመስል አንጋጥጬ ቆየሁ!!

መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ኪዳን ወዳለበት ቦታ መንዳት ጀመርኩ። ትናንት ከነበረበት ቤት ቀይረውታል። ከምሽቱ 3 ሰዓት የሚፈልገውን ይዤለት እንደምመጣ ስለነገርኩት እኔን ለመጠበቅ በጊዜ ከሚስትየው ጋር ወደዛው መሄዳቸውን አረጋግጫለሁ። የእሱ እቅድ ያው እንደተለመደው የራሱን ሰዎች እና መኪና ልኮ ይዘውኝ ልሄዱ ነው። እኔ ቀድሜ እዛው እንደምደርስ የሚጠረጥርበት ምንም ፍንጭ የለውም። በገዛሁት ስልክ እቤቱ ውስጥ የተጠመዱትን ካሜራዎች መቆጣጠር እችላለሁ። ሳሎኑን በሁለት አንግል፣ ኮሪደሩን እና ኪዳን ያለበትን ክፍል። ኪዳን አልጋው ላይ ኩርምት ብሎ ከመጋደሙ ውጪ ምኑም ታግቶ ያለ አይመስልም። ደጁ ላይ ጠብደል ጠባቂ ቆሟል። ለአፍታ ጎንጥን አሰብኩ> አሁን በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ ሆኜ የእሱን አሳሳም ማሰብ ነበረብኝ? አስቤስ እጄን መሳም ነበረብኝ?
👍314👏3🎉1
አቅራቢያው ስደርስ የጋዜጠኛው ቡድን እኩል ደረሰ። ስልኬ ላይ የማየውን እቤት ያሉት ካሜራዎች እይታ አቀበልኳቸው። እነርሱ በኮምፒውተር ፣ በተለያዩ ገመዶች ፣ ማይክራፎኖች  እና ሌሎች ነገሮች በሞላው የመኪናቸው ጀርባ የሚሰካካውን ሰካክተው ዝግጁ መሆናቸውን ሲነግሩኝ መኪናችንን የአጥር በሩጋ አስጠግተን አቁመን እኔ እና አንድ ማይክራፎን የያዘ ጋዜጠኛ እና ሌሎች ሁለት ካሜራ እና ካሜራ ረዳት ወርደን ስንጠጋ ጠባቂው የያዘውን መሳሪያ ወደፊት አስቀድሞ ወደእኛ ቀረበ።

«ጋዜጠኞች ነን!! ላይቭ ነው! አቶ ደሳለኝ ስለምርጫው ትንሽ እንዲሉልን ነው!» አለው አብሮኝ ያለው ጋዜጠኛ። ጠባቂው ምኑም አልተመቸውም። ለሌላኛው ጠባቂ መልዕክቱን ለአቶ ደሳለኝ እንዲያስተላልፍ ጮክ ብሎ ተናግሮ እኛን እንድንጠብቅ አዘዘን። ሌላኛው ጠባቂ ከደቂቃዎች በኋላ አቶ ደሳለኝን አስከትሎ ብቅ አለ።

«እኔ ከምንም ዓይነት ጋዜጠኛ ጋር ቀጠሮ አልያዝኩም!! ምን አይነት ጣጣ ነው! ሰው ማረፍ አይችልም? ደግሞ ይሄን ቤት ማን አሳያችሁ?» እያለ እየተነጫነጨ ቀና ሲል ከእኔ ጋር ተያየን። ሊቀየር ሲዳዳው አብሮኝ ያለው ጋዜጠኛ ለካሜራ ማኑ እንዲጀምር ምልክት ሰጠው። ቀጥሎም የቴሌቭዥን ጣቢያውን ፈቃድ እያቀበለው

« አቶ ደሳለኝ ላይቭ የኢትዮጵያ ህዝብ እየተከታተሎት ነው። በዚህ ምርጫ ለየት ባለ የምርጫ ቅስቀሳዎ የህዝብን ቀልብ የሳቡ ይመስላል። ወደ ውስጥ ገብተን አንድ ሁለት ነገር ቢሉን? » አለው። ግራ ተጋባ እና እየተወነባበደ ሳቅ አይሉት ስላቅ ያልለየለት ፈገግታ ፈገግ እያለ ወደውስጥ ጋበዘን። ይሄኔ ፅፌ አዘጋጅቼው የነበረውን መልዕክት ኪዳን ያለበትን ክፍል ጨምሮ ካሜራ የተገጠመባቸውን ክፍሎች ምስል ከሚያሳየው ምስልጋ ላኩለት። ስልኩ መልዕክት መቀበሉን ቢሰማም አላየውም።

«አቶ ደሳለኝ መልዕክቱ የሚያስፈልጎ መልዕክት ይመስለኛል።» አልኩት ጠጋ ብዬው። በጥፍሮቹ ቢቦጫጭረኝ ደስ እንደሚለው እያስታወቀበት የግዱን ፈገግ ብሎ ወደሳሎን እየመራን መልዕክቱን አነበበው።

« ቴሌቭዥንህን ክፈተው ካላመንከኝ ላይቭ ነህ!! ኪዳን ያለበት ክፍል ጨምሮ ኮሪደርህ እና ሳሎንህ በድብቅ ካሜራ እይታ ውስጥ ነው። የምስሉ መዳረሻ መቼም ይገባሃል የኢትዮጵያ ህዝብ አይን ነው። አርፈህ በቀጣፊ ምላስህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለህን ፍቅር እና ብትመረጥ የማታደርገውን የውሸት ቃልህን ላይቭ ዘብዝበህ የምርጫ ቅስቀሳህን ብታደርግ ይሻልሃል ወይስ ዜናውን ከምርጫ ቅስቀሳ ወደአፈና ወንጀል ብንቀይረው? ምርጫው ያንተ ነው!! ከጋዜጠኞቹ ጋር እያወራህ ወንድሜን ሳሎን አስመጣልኝ። ምንም ግርግር ሳንፈጥር ከጋዜጠኞቹ ቀደም ብዬ ውልቅ ብዬ እወጣልሃለሁ!! አይ ካልክ ግን እዚሁ ላይቭ ወንድሜን እንዳገትከው ከነምስሉ ለጋዜጠኛው ሹክ እለዋለሁ። እዛው ላይቭ ጮማ ዜና አይመስልህም? በዛ ላይ ያን የቪዲዮ ቅጂ እመርቅላቸዋለሁ።!!» እያነበበ ጋዜጠኛው ደጋግሞ ስሙን ይጠራዋል። አልሰማውም!! እንደመባነን ብሎ

«እ እ!! የሆነ ትንሽ አስቸኳይ መልዕክት ደርሶኝኮ እ!!» ተንተባተበ።
«አዝናለሁ መጥፎ ዜና ነው?» አለው ጋዜጠኛው።
«አይ እንደው ትንሽ ነገር ነው። እኔ የምልህ እና አሁን ይሄም ላይቭ እየተላለፈ ነው?» ብሎ የቴሌቭዥኑን ሪሞት አንስቶ እየከፈተ  የሆነች ተንኮል ያለበት አስተያየት ወደእኔ አየ። ልቤ በመጠኑም ቢሆን መደለቅ ጀመረ። ደቂቃ እንኳን ዝንፍ ያለ ክፍተት ከተፈጠረ ሰውየው እዛ ያለነውን በሙሉ ጭጭ አድርጎ የቀደመ እቅዱን ለማሳካት የጋዜጠኞቹ ብዛትም ማንነትም የሚያሳስበው ሰው አይደለም። ጋዜጠኛው ነውም አይደለምም ሳይለው (ምክንያቱም እስከዛ ደቂቃ ድረስ ላይቭ አልነበረም) ቀጠለ። በቴሌቭዥኑ ዜና የምታቀርበዋ ሴት ስለአቶ ደሳለኝ አውርታ ስታበቃ ባልደረባዋን ጋበዘችው። ጋዜጠኛው ጥያቄውን ቀጠለ። መልሱም መላ ቅጡ የጠፋበት ወሬ ከመሆኑ በተጨማሪ በተቀመጠበት ላብ ያጠምቀው ጀመር። እየተንተባተበ ጥቂት እንዳወራ ሚስትየው ብቅ እንዳለች እየሆነ ባለው ነገር ግራ ተጋብታ ፍሬን ያዘች። በሚቀባጥረው ወሬ መሃል ወደሚስቱ ዞሮ «እስቲ ኪዳንን የሚጠጣ ውሃ እንዲያመጣ አድርጊልኝ! ቡናም ሻይም ሳልላችሁ በሞቴ ለእናንተስ ምን ይምጣላችሁ?» አለው ጋዜጠኛውን! ጋዜጠኛው ቀጥታ በዜና መሃል እየተላለፈ ያለ ፕሮግራም ላይ መዘለባበዱ እያናደደው ግን በጨዋ ደንብ ቀጠለ።

«በእውነቱ አቶ ደሳለኝ በዚህ አጋጣሚ ሳይዘጋጁ የመጣንቦት ቢሆንም እንግዳ ተቀባይነትዎ እና ልግስናዎ አልተለየንም። ከልብ እናመሰግናለን!! ባልደረባዬ የቀሩትን ዜናዎች ለማቅረብ እየተጠባበቀች ስለሆነ ለህዝቤ ማለት አለብኝ የሚሉት መልዕክት ካለ እድሉን ልስጦት!! »

ጋዜጠኛውን በቅጡ የሰማው አይመስልም። ሚስቱ እንደጅብራ መገተሯ አሳስቦት በግንባሩ መልዕክት ሊያስተላልፍላት እየሞከረ ነው። እያመነታች ከሳሎኑ ስትወጣ ልቤ መደለቋን ቀጠለች። እሱም ለዚህ የፈረደበት የኢትዮጵያ ህዝብ ላቡንና ወሬውን በቲቪ ማስተላለፉን ቀጠለ። ኪዳን የመጠጥ ውሃ የሞላው ብርጭቆ ይዙ ወደሳሎን ብቅ ሲል ልቤ ወደቦታዋ ተመለሰች። እዚህ ድረስ ያለውን በድል ተወጥቼዋለሁ!!

.ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍236👏1
አትሮኖስ pinned «#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ ፡ ፡ #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፡ ፡ #ክፍል_አራት //// እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርጌ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ  ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ  እየተብረከረከ ነው። ተነሳሁና የተከፈቱ መስኮቶችን መዘጋጋት ጀመርኩ..ማብራቶችን አጠፍሁ፡፡ የሴትዬዎን ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ይዤ ወጣሁና የሆቴሉን…»
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#ክፍል_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከእንቅልፉ ረፋዱ ላይ ነቃ ክፍሉ በብርሃን ተሞልቷል
እንደተጋደመ ማሰብ ጀመረ ተስፋ ያለው ነገር አልታየውም እዚች
አገር ከመኝታው ሲነቃ ፍንድቅድቅ የሚል የእናቱን ጡት የሚጠባ ህፃን ብቻ ነው" ሌላው ግን ህሊናውን እያከከ ምን ሰርቶ እንደሚበላ ያስባል፤ ምን ሰርቶ እንደሚኖር ያልማል ትንሹ በትልቁ ህሊና
ገብቶ መሞትን ይመኛል ሞት የሌለበትን አሸናፊነት ለማግኘት ይማስናል እና ከመኝታው ሲነሳ ጭንቀትንና ተስፋ መቁረጥን ያዛጋል

ምነው አገሬ ጭንጫ ምድር በሆነች ኖሮ ለፋን ለፋን
ምርት ግን ጠፋ ብለን እናመሃኝ ነበር ምነው ከርሰ-ምድሯ በደረቀ
ኖሮ ካለውሃ መቼስ ምን መስራት ይቻላል እንልም ነበር ካላት የከርሰ-ምድር ውሃ አስር ፐርሰንት እንኳ አለመጠቀሟን ባናውቅ
ምነው የሰው ኃይልስ ባልኖረ ምን ይደረግ
የአለንን ለመጠቀም
ሰው ያስፈልጋል እንልም ነበር የሰው ኃይል ባልኖረ ኖሮ ይህች አገር ግን ሁሉም  አላት  ልምላሜ ታሪክ ውበት እህ!.. የጭንቀታችን ምንጭ የሆነው ህምታ ከየት መጣ?" የእኛ ትውልድ የወሲብ  የጦርነት የዝርፊያ ፊልም ማየት በቃው? እኮ ምን አለፋን በፊልም የሌለንን እናያለን በፊልም የማንኖረውን እንኖራለን ..."  ብሎ ሲፈላሰፍ ቆይቶ
ከመኝታው አፈፍ ብሎ ተነሳና ወደ ተናኘ መኝታ ክፍል ሄደ  ተናኘ በጠዋቱ የለችም እሱ ግን ወደ አልጋዋ ተጠጋና ጠርዙ ላይ ቁጭ አለ ራስጌዋ ካለችው ትንሽ ኮመዲኖ ላይ የእለት ውሎዋን የምትፅፍበትን ማስታወሻ አየው" ላንሳው አላንሳው ከህሊናው ጋር
ተሟገተ እረፍ  እረፍና ተነስ! ህሊናው አዘዘው"

እንጃባህ! በልጄ …'

"ኦሆሆ! ጅል አትሁን  አንተ አባት ማስታወሻ ደግሞ
ምሥጢር ተቀባይና አስቀማጭ ነው" አንተን አያውቅም ለአንተም
አይታዘዝም ጌታው እሷ ናት ገላጯ ፀሐፊዋ  ልጅህ ናት
ለአንተ የሚሆነውን ከእሷ ጠይቅ ከእሷ ህሊና አንብብ

"ማንም ሰው ሊገልፀው የማይፈልግ የምሥጢር መቃብር ህሊናው ውስጥ አለ በሐዘን ብቻውን እንደ ጥጥ ተባዝቶ አስከፊ
መቃብሩን ተሸክሞ በፍርሃት እየራደ ከአፅም ጋር እየተፋጠጠ እጣ ፋንታው የሆነውን ዘግናኝ ህይወቱን የሚኖር አለ! ... የህሊና ውስጥ ሞት ሃዘንተኛ የማይጠይቅበት የመቃብር ሐውልት የማይታነፅበት
በየግላችን ያጣነውን መልካምም ሆነ መጥፎ የህይወት እጣ በሙሚ
ቀባብተን ሳይበሰብስ የምንቀብርበት ብቸኛው የመቃብር ሥፍራ
ህሊናችን ነው" ሁለተኛ የመቃብር ሥፍራ ደግሞ የግል ማስታወሻ
ነው" ማንም ሊያየው፥ ሊመራመርበት ሊጎበኘው ... አይችልም
ካለባለቤቱ በስተቀር ለሌላ ሰው ዝግ ነው  ስለዚህ ማስታወሻዋን
አትንካው ! በሃጢያት ደም ህሊናህን አትበክለው ...'
አያገባህም፤ ለልጄ ከኔ የበለጠ ምሥጢር ጠባቂ የላትም ይህን ሲያስብ ሰቀጠጠው፤

"እሽ ልጄ የራሷ የህይወት ምሥጢር ይኖራት ይሆናል
ማወቅም አይገባኝ ይሆናል ማስታወሻዋን ማንበቤም ትልቅ የህሊና ወቀሳ ያመጣል" ግን እሷን ደግሞ ማወቅ አለብኝ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ አስፈልጋታለሁ  አለሁልሽ የማልላትን ልጄን እውነተኛ
እሷነቷን በመጠየቅ አላገኘውም የማነበው ልቆጣጠራት አይደለም
ለዚያማ ህሊናዋ የት ሄዶ የምታነበው መጽሐፍ መች አንሷት እሳትና ውኃ
ለልጄ ማወቅ ያለባትን  ማሳወቅ የነበረብኝንም እሳትና ውኀ
አሳይቻታለሁ እንዴት እንደምትጠጣና እንደምታበስል ግን እያየች፥
እያነበበች እየሞከረች
ተማረች አባት ልጁን ዘለዓለም የሚያስተምር መምህር አይደለም ትምህርት አያቆምም አባትና የክፍል አስተማሪ ግን የማስተማሩ እድላቸው የሆነ ደረጃ ላይ ያቆማል ከዚያ መማማር በመጨረሻ ደግሞ ይማራሉ" እና!- ከልጄ የህይወት ፈተና ልማር ተወኝ" ብሎ ህሊናውን መንጭቆት
ማስታወሻዋን ከኮሞዲኖው ላይ አነሳው

ሰርቶ መብላት ምን ነውር አለው መሰደድስ ቢሆን
ወንድማለም! ከቸገረህ ምን ያሳፍራል? እውነቴን'ኮ ነው በሃብት ደልበዋል የተባሉትስ አሜሪካኖችና አውሮፓውያን ተሰደው ለአረብ አሽከር ሆነው ብራቸውን አፍሰው አገራቸው ይገቡ የለ ..." የሚለውን የራስ ማፅናኛ አባባል አንብቦ ሌላ ገፅ ገለጠ።

"ወንድማለም! ወገቤ እስኪቆረጥ ለሰዓታት ስማስን ቀኑ ነጉዶ
ለሊቱ ጭላጭ ሰዓት እየቀረው ነው ምስጋና የሌለበት ባዶ ህይወት!
“ለገንዘብሽ ነው ስትቆይ ያው መጥገብሽ አይቀርም ፀባይሽ ካላማረ ኮንትራትሽን ሰርዞ መተካት ነው ተሰልፎ ከሚለምነው አንዱን
እየተባልህ የዕቃ ክብር ተነፍጎህ በዘመናዊ ባርነት መኖር ወንድማለም ደከመኝ እባክህ ልተኛ! ልተኛ ማን አስተኝቶኝ ባለቤቷ እንቅልፍ ስታጣ የኔን መኝታ በር አንኳኩታ ቀስቅሳኝ
ተመልሳ መተኛት ልማዷ ነው" አንዳንዴ ሳስበው እኔ ሰራተኛዋ ብቻ ሳልሆን የእንቅልፍ ማስወሰጃ እንክብሏም ነኝ እላለሁ  በል
ለሁሉም ጎኔን ላሳርፈው ማለቱ ይሻለኛል የሚለውንም አንብቦ ሌላ
ገፅ ገለጠ።

"አይ ወንድማለም!  ይሄንስ እድሜ ልክህን ባታስበው
ይሻላል" ለአንተ እኔ ሁሌ ህፃን ነኝ አይደል?  ግንኮ ህፃን ከሆንኩ ሁለት አስርተ ዓመታት አለፉ ግን አንተ ስለጎረምሳነት ዘመንህ
ለምንድን ነው የማታወራው?  የምትወደድ ሰው ነበርህ?  ወይንስ
ጨካኝ: ዋሾ! ... ሁሉንም ሁን ለምን እንደሆንህ አላውቅምና ጭፍን
ያለ የተሳሳተ ፍርድ ሰጥቼ ልወቅስህ አልሻም ያ አይነት ፍርድ መስጠት ካቆምሁ ደግሞ ቀናት ተቆጠሩ።

"ወንድዬ! የጀመርሁትን ሳልነገርህ  ምን ዙሪያ ጥምጥም አዞረኝ? ማስታወሻዬን ነው አታነበው፤ግን ፈራሁህ ስፅፍ  እያሰብሁህ ነው" በዚህ ዓለም የምታምኝው?'
ብባል የለኝም
የምትቀርቢው? ከተባልሁ
ግን ወንድማለምን
ነው የምለው"ይከፋህ ይሆን? ይክፋህ እንጂ የምወድህ
ስለማላምንህ ስንት የደበቅሁህ ጉድ አለ መሰለህ አንተ መቼም እንደ
አባቴ ብትሆንም
ብዙ አባቶች ድፍን ፍቅርን የምትሻ ግብዝ አባት አትመስለኝም ሁሉም ልክ እንዳለው ታውቃለህ  አይደል?"

"ፍቅሬ አገረሼ ወንድዬ! አንድ ጊዜ በየሄድሁበት እያስነጠሰ የሚያሳጣ ፍቅር ይዞኝ ነበር" ያ የፍቅር ገጠመኝ አሁን ተረት ነው
የነ ጦጢትና አንበሳ ተረት የዓረብ ቤት እያፀዳሁ ግን ያ የተረት ስሜቴን ፏጨረው፤ አንዴ ይቆረጥመኛል ሌላ ጊዜ ይለበልበኛል እንደ ቁርጠት ቀስፎ አላስቆም አላስቀምጥ ይለኛል
ያንጠራራኛል እንደ ምጥ ገፍቶ ሲመጣ ደግሞ ሲቃ ነው፡ ውለጂው ነው
አንተ ወንድማለም! አሁን አሁን ሳስበው ከሱስ ነፃ ነኝ!' እያልሁ ስመፃደቅ ለካ ማፍረሻ የሌለው ሱስ ሱሰኛ ነኝ  እህህህ በሱስ መጠመድ ቢሉህ መጠመድ ነው ያውም በቅርብ ባላረከው
ወደፊትም በቅርቡ በማታገኘው ሱስ የሚፋጨው የስሜት ስለት
ህሊናህን ሲበሳሳው፤ እየወጠረ ሲያከረው ነፍስህ ረፍት አጣ ውጪ
ነፍስ ግቢ ነፍስ ብትሰቃይ ምን ይሰማህ ይሆን?" ፈገግ አለ ጥያቄዋ
አፈፍ አድርጎ ተሸክሞት ወደ ኋላው ከነፈ አልፎት ወደመጣው የወጣትነት ህይወት የልጁን ምስጢር ከዚያ በላይ አንብቦ ማወቅ
ግን አልፈለገም እሷ ግን ማስታወሻዋ ላይ ስሜቷን: ውጥረቷን ረሃቧን ጥማቷን ... ዘክዝካው ነበር"

"... ወንድማለም የአለሁት ወህኒ ቤት ነው ትናንት ሃያ
👍29
አምስት ጅራፌን ጀርባዬ ላይ ጠጥቼ ሌሊቱን ያሳለፍሁት በሆዴ ተኝቼ ሳቃስት ነው አንዲት ኢትዮጵያዊት በወለደች በሁለተኛ ቀኗ
“ኧረ ስለነፍስ! ወገቧ ያልጠና ትኩስ አራስ አትግረፏት የፍርዷ
ውሳኔ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍላት ብንል የሚሰማን ጠፍቶ ከተፈረደባት ሃያ አምስት ጅራፍ ውስጥ አስራ ሰባቱ ብቻ አሰናበታት
ወንድዬ! በሷ ሞት ማንም ያዘነ የለም እሷም ለራሷ አላዘነችም ልጄን፥ልጄን … ብቻ እንዳለች ግልግል
ነው የሚባለውን ሞት ሞተች ልጅዋን አደራ ለማንም አልሰጠችም ሁላችንም አቅም የሌለን አደራ በላ ነን ጥሩ አደረገች  እንኳንም አደራ አላለችን አደራ ብትለን ኖሮ በመጨረሻዋ የመከራዋ መጀመሪያ ወይንም ማጠቃለያ አዝንባት ነበር
አብራን ኖራ እንዴት አቅማችንን ረሳችው' ብዬ እጠላት ነበር" ወንድማለም እምቦቀቅላዋ ከእኛ ከተገረፍነው ጋር ወህኒ ቤት ውስጥ ዐይኖቹ እንባ ተብሎ በጥቅል ስም  በሚጠራው ደም ተሞሉ" ዐይኑን ጨፍኖ: ደሙን አፍስሶ ንባቡን ቀጠለ።

ከተገረፍነው ጋር ስታለቅስ ዋለች ምርር ብለን ስናነባ
እሷም አብራን አነባች ከሁላችን ለቅሶ የዚያች ንፁህ ለቅሶ እንደ
ሬት መረረኝ እኛስ ባሳለፍነው ጥቂት ዓመታት የፈፀምነው ኃጢያት
ወይንም እርግማን ይኖርብን ይሆናል ይህች ሙጭቅላዋ ህፃን
ወንድዬ! እስኪ ምን አጠፋች? አንድ ጊዜ አንድ ፈረንሳዊ ደራሲ ያለው ትዝ አለኝ እግዜርን ማምለክና ካርታ ጨዋታ መጫወት
አንድ ነው ብሎ የፃፈው
እራስህን መድበህ ትጫወትና ከበላህ
እሰዬ ኪስህን በገንዘብ ትወጥራለህ ገንዘብ ደግሞ ኃይል ነው በራስህ እንድትተማመን እንድትኮፈስ ያደርግሃል እንደ ፅጌረዳ አበባ አይ ሲያምር ያሰኝሃል ሁሉ ወዳፍንጫው አስጠግቶ መዐዛህን ወደ ውስጥ እየሳበ ይረካብሃል ይክብሃል ይሽቆጠቆጥልሃል እንደ
በግ ገራም ሆኖ ይታከክሃል ጅራቱን እየቆላ ካንተ ያስቀድመኝ እያለ ይምልልሃል ሰው ብትበድል እንኳ የሳንቲም ሽርፍራፊ
ስለምትወረውር እሱ አፉ እንጂ ውስጡ የዋህ ነው እየተባልህ የሚማረርብህ የለም ከተበላህ ግን ያው ኪሎህ ስለሚቀንስ መሬቷ
እያንቀረቀበች ስታነፍስህ አንደበትህ ሁሉን ሲያበሳጭብህ
ሁሉ እንዳላዬ ፊቱን ሲያዞርብህ ውሾች ሊነክሱህ ሲጮሁ
በራስህ ከሌሎች ጋር ተባብረህ ኳስ አበደች እያልህ ስትጠልዘው
ህሊናህን እንደ ሽንኩርት እየላጥህ ስትጥለው ያንጊዜ እንደ አበቅ
የምትደፋበትን መፈለግ ነው እና! እግዚአብሔርን የምናመልከው
እንደ ካርታ ጨዋታው ብናተርፍ  ብለን ነው የገነትን ምቾት
ልንጎናፀፍ በለምለሙ መስክ ልንፈነጭ ካልሆነም ያው ሽ ቢታለብ በገሌ ለማለት እንጂ አንተ ወንድዬ እግዜር ካለ እውን
የረሃብና ጦርነት ምሳሌ እንዳደረገን ዘላለም ይኖራል? ዛሬ እንኳን
በቃችሁ አይለንም? ምሳሌው አይቀየርም?

"አንድ ጊዜ አዲሳባ እያለሁ አንተ አልነበርክም ብቸኝነት
እንደ ውርጭ ቤታችን ገብቶ
ገብቶ ሞላ.ውርጩ አጥንቴን ሲያኝከው ህቅ ብዬ አለቀስሁ በልጅነቴ ገነት ማለት የተዋበ
ልምላሜ የተሞላበት ይመስለኝ ነበር የኔ ጅል ከዚህ ውጭ ገነትን
የሚያስበው ማን አለ' አትበለኝ እንጂ" ገሃነም ግን አስጠሊታ ሆኖ ነበር የሚሰማኝ" ታዲያ የዛን ቀን ፀሐይ እንደ በዛበት ዋልካ መሬት ፊቴ የተሰነጣጠቀ እስኪመስለኝ ካለቀስሁ በሃዘን ኩምትርትሬ ከወጣ
በኋላ በኃሳቤ ወደ ሆነ ቦታ ተነጠቅሁ ገሃነም ውስጥ! ከማዶ ገነት አለ  እንዳሰብሁት ግን ሰፊ አልነበረም ጠባብ ነው ግን ያምራል እኔ ግን እንዲያ ዐይኔ እስኪፈርጥ  አልቅሼ: አልቅሼ የሄድሁት
ገሃነም ነው አይገርምም
ወንድማለም! ከዚያ የሚዘገንን ቆሻሻ ክምር ላይ በጭንቀት እንደቆምሁ ድንገት ትናንሽ አበቦች
ከትንሽነታቸው በስተቀር
ግን የሚያምሩ አየሁ
ወንድዬ! አሁን ሳስበው እነዚያ ትናንሽ አበቦች ተስፋ ናቸው ጥሩውን ብንመኝም
የምናገኘው ግን ያልተመኘነውን ነው ያልተመኘነው መጥፎ
ህይወት ላይ ግን ትንሽም ቢሆን የሚያምር ነገር አለ እና! እግዜርን ያን ትንሽ ነገር እንኳን አታሳጣኝ እያሉ መለመኑ አይሻልም ለዚህ
ለዚህ ወዲያ ውሰደው ብሎ ሐይሉ ዲካ የለውም ከሚባለው አምላክ ጋር
ከመጣላት ደግሞ
ነው!… ብሎ እንደ ጠረጴዛ
ኳስ ቢያድቦለቡለኝስ፣ መጫወቻ ሆኜ ተሰባብሬ  መቅረቴ አይደል!
ወንድማለም!- እግዜር ግን ምነው ዝምታው ይበዛል? እስኪ የእኛስ ይቅር ይህች
የዶሮ እግር የመሳሰሉ እግሮችዋን እጆችዋን
እያወናጨፈች እየተንቀጠቀጠች
በምታለቅሰው ጨቅላ ለምን
ጨከነባት? በናቷ ሃጢያት ይሆን? እሷማ አጠፋሽ” ለተባለችው ቅጣቷን ተቀብላ  አስራ ሰባት ጅራፏን ቀምሳ የለ! የቀራትን
ስምንት ጅራፍ በህፃኗ ላይ ለመጨረስ ካልሆነ? እዚህ የሚቀጣው እዛም ይቀጣ ይሆን! ወንድዬ ቢጨንቀኝ እኮ ነው መቀባጠሬ! ይልቅ
የሆነውን ልጨርስልህ

"ህፃኗ  ልቅሶዋ ሲቀጥል አንጀቴ አልችል  ብሎኝ  እኔም ከማለቅስበት እየተንፏቀኩ ሄጄ አቀፍኳት ትንሽ ናት ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታህል' እጅ እግር: ዐይን  ሁሉም የሰው ልጅ
ያለው አካል ሁሉ እጅግ ቢያንስም አላት ወደ ጡቴ አስጠግቼ እሹሩሩ
እያልሁ ልቅሶዬን ቀጠልሁ ትንሽዬ አፏን አሞጥሙጣ
የሚጠባ ነገር ፈለገች, እኔ ደግሞ ያለኝ ደም ነው የግርፋቱ" ካለነው
ውስጥ ካለደም ወተት ያለው ጡት አልነበረምህፃኗ እንደማልረዳት
ስታውቀው እሪታዋን ለቀቀችው ኣጀብናት
እኛም በር
በማይከፍተው ልቅሷችን ወተት በማይሆነው እንባችን: ክፍሉን
አጥለቀለቅነው በእንባ: በምሬት: ከዚያ ልረዳት ያልቻልኋትን
ህፃን ካነሳሁበት አንጋለልኋትና ተንፏቅቄ ራቅሁ ይኸውልህ! ከተኛሁበት ስነቃ ሁሉም የእስር ቤት ጓደኞቼ ተኝተዋል ወንድማለም!-
ሚሚም‥ ተስቤ ሄጄ አየኋት
እውነተኛውን እንቅልፍ አፏን
እንዳሞጠሞጠች
እንደ ራባት ...አንቀላፍታለች
ለምን ተፈጠረች?
ለምንስ እሷን ለመፍጠር ብዙ ተደከመ  ወንድዬ! ላትኖር ተሸክማ ዘጠኝ ወር ካለ አዛኝ: ካለ እረፍት
ስትማስን የኖረችው እናቷስ
ለምን በምጥ አቃሰተች? ለምን ደሟ ፈሰሰ: ለምንስ ነጭ ላብ አነባች?
አቤት የመከራችን ዓይነት ቢመዙት ቢመዙት መርዘሙ
እንደ ውቅያኖስ የተንጣለለው እንባችን ሐዘን በሸነቆረው አካላችን
ፈሶ ፈሶ አለማለቁ ... ወንድዬ! የጠዋት ቁርሴ በለቅሶ የተጣፈጠ ቅስም ሰባሪ ሀዘን ሆነ ..." አባቷ ስቅስቅ ብሎ አልቅሶ ማስታወሻዋን ከደነው" ከዚያ በላይ  ማንበብ አልቻለም ከዚያ በላይ
አልቻለም ከዚያ በላይ መቆም አልቻለም ከዚያ በላይ የመከራ ሬት መጠጣት አልቻለም! ዐይኖቹ ተጨፈኑ አካሉ ተጨመታተረ ደሙ ዐይኖቹን እንደ ቀይ ጃኖ እያለበሰ በጉንጮቹ ቁልቁል ተንኳለለ ግን ለምን? ልጆች እንዲህ
ከማይችሉት የመከራ
ውቅያኖስ በጮርቃ እድሜያቸው ይነከራሉ? እኮ ምን ጠፍቶ? ማነው የሚወቀሰው! የላይኛው ወይንስ የምድሮቹ ንጉሶች! የማይመለሰው ጥያቄ እንደ አቧራ እየተበተነ ከአየሩ ተደባለቀ!

💫ይቀጥላል💫
👍26👏4😢1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ ሶስት)
(ሜሪ ፈለቀ)


ኪዳን የመጠጥ ውሃ የሞላው ብርጭቆ ይዞ ወደሳሎን ብቅ ሲል ልቤ ወደቦታዋ ተመለሰች። እዚህ ድረስ ያለውን በድል ተወጥቼዋለሁ!! ብርጭቆውን ተቀብዬው ለደሳለኝ ከወገቤ ጎንበስ ብዬ በሁለት እጄ ሳቀብለው ጭራሽ የሚያወራው ተወነባበደበት። ጋዜጠኛው በሚሆነው ትርምስ ትዕግስቱ ነው ያለቀው። ኪዳን እየሆነ ያለው ነገር ግር ብሎት አይኑን ከወድያ ወዲህ ያንቀዋልላል። ወደጆሮው ጠጋ ብዬ «አምላክን በልመና አታድክም!! » አልኩት እና ጠቀስኩት።  ፈገግ ብሎ ደረቱን እንደመንፋት አድርጎ ጎምለል እያየ ዙሪያውን መቃኘት ጀመረ። አተኩሮ ላየው የሆነ ቁራጭ የፊልም ትወና እየከወነ ነው የሚመስለው። ሁሌም እንዲህ ነው! ከልጅነታችን ጀምሮ ከልጆች ጋር ተደባድቤ እኔ ከሆንኩ ያሸነፍኩት የፀቡ መሃል ሜዳ ይገባና ደረቱን ነፍቶ ይንቀባረራል። «ማን መሰለችህ? የእኔ እህት እኮ ናት!!» ይላል እየተጀነነ።

•  * * * * * * * * * * * * *

ድሮ ልጅ እያለን አባቴ እናቴ ላይ ሙድ የሚይዝበት መላው ነበር አሁን እኔ እና ኪዳን የምንግባባበት ኮድ። እናቴ ብር እጇ ላይ ቢኖርም ባይኖርም አለኝ አትለውም!! ብር ጨርሰሻል ወይ ብሎ ቀጥታ ከጠየቃት መልሷ ሁሌም አዎን ነው። በአቋራጭ ነው የሚያጣራው

«አስካል እንደው ከአባወራዎቹ ልደብለቅበት እስኪ መቀነትሽን ፈትሽልኝ!» ይላታል

«አይ እንግዲህ እንኳን ላንተ አምቡላህን መጋቻ ለልጆቼም የሚቀምሱትን ማሰናዳበት አልሞላልኝ» ትለዋለች

«ውይ በሞትኩት እናቴን! አያ ተካን አበድረኝ ልበለው ይሆን? እንደው ቸሩ መድሃንያለም ለልጆቼ የምሰጠው አታሳጣኝ» ይላል ወደላይ እንደማንጋጠጥ ብሎ በአንድ አይኑ እሷን አጮልቆ እያየ እና እያስተዛዘነ (ልበደራቸው የሚላቸው ሰዎች ስም ይቀያየራል)

«አይ እንግዲህ አምላክን በልመና ማድከም ደግም አይደል!! የምንችለውን እናደራርግና በተረፈው ማመስገን ነው። ያመሰገንነው አምላክ የጎደለውን ይሞላል!» ትለዋለች ልትወጣ ነጠላዋን እላይዋ ላይ እያደረገች። አለኝም እንዳትለው ለእሱ መጠጫ መስጠት አትፈልግም። የለኝም እንዳትለው ባሏ የሰው ፊት ሊያይባት ሲሆን በዘዴ አድበስብሳ! አባቴ እሷ ዞር ስትል ጠብቆ እየሳቀ

«እም! መች አጣኋት እናታችሁን? አላት ማለት ነው! አሁን ዘንቢል ሙሉ ሸምታ ትመጣ የለ? ምንአለ በሉኝ!» ይላል። እንዳለውም ከገበያ መዓት ነገር ሸማምታ ስትመጣ አባቴ ያላትን አንነግራትም ተያይዘን እንስቃለን!!

የእውነትም እጇ ላይ ብር ከሌላት መልሷ ይለያል። የአባዬ ጥያቄ ስሞቹንና አጠያየቁን ቀይሮ ያው ነው። የመጨረሻው <ለልጆቼ የምሰጠው አታሳጣኝ> የሚልበት ጋር ሲደርስ

«እንግዲህ አንድዬ ያውቃል!! እርሱ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድር!!» ካለች አባቴ አሁንም እሷ ዞር ስትል ጠብቆ

«አሁን የእውነቷን ነው የላትም ማለት ነው!!» ብሎ ከኛ ፊቱን አዙሮ ብር ይቆጥር እና « ገበያ ውረጅበት ብሎሻል! ብላችሁ ስጧት» ብሎ ለአንዳችን ያቀብለናል። ለምን እራሱ እንደማይሰጣት አሁንም ድረስ አይገባኝም!! ምናልባት ለእኛ ማስተማር የፈለገው ነገር ይኖር ይሆን ነበር። ሁሌም መልሷ እንዲሁ ነው። ሁሌም የእርሱ አጠያየቅ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው። ገና እሱ ሲጠይቃት በተለይ እኔ ሳቄ ይመጣል። ለእማዬ <እየፈተነሽ ነው!> አልላትም!! ለትንሿ ልቤ የእነርሱ የፍቅር ቋንቋቸው መሆኑ ገብቷት ነው መሰለኝ በተለይ የሌላት ጊዜ እሱ ሲያዝንላት ልቤ በሙቀት ቅልጥ ትላለች።

ከኪዳን ጋር ልጆች ሆነን እናታችንን የምናስታውስበት አንዱ ጨዋታችን ነበር። አድገን የህይወት ውጥንቅጥ ውስጥ የተነከርን ጊዜ ደግሞ ምልክት መሰጣጫችን ሆነ። ያለንበት ሁኔታ ተስፋ ያለው፣ መውጫ ያለው ፣ ደህንነታችን ጥሩ ሁኔታ ላይ ከሆነ። «አምላክን በልመና አታድክሚ….. » የምትለዋ! ለምሳሌ ባለፈው ኪዳን እንዳለኝ « ደህና ነኝ አታስቢ! አልጎዱኝም!! ተረጋግተሽ መላውን ፈልጊ!»  እንደማለት ነው!! ወይም ደግሞ « አንድዬ ያውቃል» ብዬ መልዕክት ካደረስኩት «እንዳትደውልልኝ፣ በምንም መንገድ ልታገኘን አትሞክር! ያለሁበት ሁኔታ ሲሪየስ ነው!!» እንደማለት ነው። እንደገባንበት ማጥ መልእክቱ ይለያያል። እኔ እና እሱ እንግባባበታለን!! በደፈናው ያለንበትን ሁኔታ አስከፊነት የምንለዋወጥበት ነው።

•                   
•  * * * * * * * * *

ጋዜጠኛው ከዚህ በኋላ ላይቭ እንዳለ ሊቆይ የሚችለው ከ2 ደቂቃ አይበልጥም!! እንደየትም ብሎ ቢያራዝምልኝ ሊጨምርልኝ የሚችለው 1 ደቂቃ ነው። በዛ 2 ደቂቃ ደግሞ መኪናችን ጋር መድረስ አለብን። ለጋዜጠኛው ተጨማሪ ደቂቃ ማስረዘም ከቻለ ምልክት ሰጠሁት። ትከሻውን ሰበቀ። እሞክራለሁ እንደማለት ነገር።

«አንቺ እስከበሩ ትሸኝናለሽ እኮ!!» አልኳት ሚስትየውን። ባሏ አፉ እዛ ይለፍልፍ እንጂ አይኑም ቀልቡም እኛጋ ነው። ባይገባትም እየመራችን ወጣች። በፍጥነት ወደአጥሩ በር እየተጓዝኩ

«ልትከተሉኝ ብታስቡ! መንገዴ ላይ የሆነ ነገር ልትፈጥሩ ብትሞክሩ ውርድ ከራሴ!! ወጥተሽ ጋዜጠኞቹ መኪና ውስጥ ገብተሽ ማረጋገጥ ትችያለሽ!! አሁን ላይቭ እየተላለፈ ያለው የባልሽ ቃለመጠይቅ ብቻ ነው። አንዲት ዝንፍ ያለች ነገር አደርጋለሁ ብላችሁ ብትሞክሩ እዛ መኪና ውስጥ ያሉት ባለሞያዎች አንድ በተን ብቻ ነው መጫን የሚጠበቅባቸው። ቤትሽ እያንዳንዱ ክፍል ካሜራ አስቀምጫለሁ!! እየሆነ ያለው ነገር አሁን እኔና አንቺ የምናወራውም ምስል ሳይቀር ሪከርድድ ነው። መኪናዬ በስህተት ጎማዋ ቢቀንስ አልኩሽ ሁሉንም ምስል ገጣጥሞ ዜና ማዋቀር አይከብድምኣ? ቻው! መልካም እድል በይልኝ ባልሽን!! እም ጷ» በእጄ የመሳም ምልክት አሳይቻት ራሷ ለዘበኞቹ እንዲያሳልፉኝ ምልክት ሰጠቻቸው እና እኛ ስንወጣ

«ቱ » ብላ በንዴት እና በጥላቻ ምራቋን ስትተፋ እሰማታለሁ። እኔና ኪዳን በሩጫ መኪናችን ውስጥ ስንገባ ጋዜጠኛው የላይቭ ስርጭቱን ጨርሷል። ከአካባቢው እስክርቅ ድረስ በማይነዳ ፍጥነት እየነዳሁ ምንም ቃል ሳልተነፍስ ሸመጠጥኩት። ብዙ እርቀን እንኳን እንዳልተረጋጋሁ ያወቅኩት ኪዳን

«ሜል በፍፁም እዚህ ድረስ ሊከተሉሽ አይችሉምኮ!» ሲለኝ ነው።

«አይችሉም ብሎ ተዘናግቶ ወጥመዳቸው ውስጥ ከመውደቅ ሊሞክሩ ይችላሉ ብሎ መጠንቀቅ ነው የሚያዋጣው!! አታውቃቸውም እስከምን ጥግ መሄድ የሚያስችል ጭካኔ እንዳላቸው።» እጁን ሰዶ ትከሻዬን ዳሰስ ዳሰስ ሲያደርገኝ ዞሬ አየሁት። የናፍቆቴ መጠን እየሆኑ በነበሩት ክስተቶች ተከድኖ እንጂ ገደቡን የጣሰ እንደነበር የገባኝ ዓይኖቹን ሳያቸው ነው። መኪናዬን ጥጉን አስያዝኩት እና አቀፍኩት!!

«ለምን መጣህ? በዝህች ዓለም ያለኝ ብቸኛ ነገሬ አንተ መሆንህን አታውቅም? የሆነ ነገር ሆነህብኝስ ቢሆን? ሰው እንደማልሆን አታውቅም?» ቁጣም ፍቅርም እንባም ሳግም ያንቀረቅቡኝ ጀመር። ያውቀዋል ስስቴን!! ሁሌም እየተቆጣሁት ወይ እየጮህኩበት ሳለቅስ አይመልስልኝም። ስረጋጋ ነው ምክንያቱን የሚነግረኝ!!

«ይቅርታ ሜል! ይቅርታ እሺ!» አለኝ ከእኔ በላይ አጥብቆ አቅፎኝ እያባበለኝ!! መረጋጋቴን ሲያይ!!
👍241
«ብዙ ጠበቅኩሽኮ ሜል! አንድም ሶሻል ሚዲያ አካውንትሽ አክቲቭ አይደለም!! ካንቺ ሳልሰማ ብዙ የቆየሁበት ቀን 12 ቀን ነው መጀመሪያ የታሰርሽ ጊዜ!! ቢያንስ እንዳላስብ በሰው ትልኪብኝ ነበርኮ!! ቢቸግረኝ መልዕክት ላኩልሽኮ (ትዝ አለኝ! ቁጥሩ ከማይታይ ላኪ ላመስግን ወይስ ልፀልይ? የሚል መልዕክት ስልኬ ነበረው! ስላልገባኝ እንጂ!! ምንም ቢፈጠር የምደውልለት እኔ ነኝ እንጂ እሱ እንዳይደውል ህግ አለን!! ስልኩን በቃሌ ነው የማውቀው እንጂ ሴቭ አላደርገውም!!)

…… በእኔ አስችሎሽ በጤናሽ ሁለት ወር እንደማትቆዪ አውቃለሁ። እኔስ አንቺን ባጣ ሰው እንደማልሆን አታውቂም? ከዛ በላይ መጠበቅ አልችልም ነበር ትኬቴን ቆርጬ መጣሁ!! የያዝኩትን ሻንጣ የያዝኩት ሆቴል ክፍል ወርውሬ ልብሴን እንኳን ሳልቀይር ማንን መጠየቅ እንደነበረብኝ እርግጠኛ ስላልነበርኩ እቤት መሄዱ አደገኛ ሊሆን ስለሚችል ብዬ ክለቡጋ ሄድኩ!! መምጣቴንም እዛ መሆኔንም ማን እንደነገራቸው አላውቅም!! ከዛ ወጥቼ ታክሲ ልይዝ ስጠብቅ መጥተው በመኪናቸው ከበቡኝ!!»

«ቆይ ቆይ ቆይ (ከእቅፉ ወጣሁ!) ክለብ ማንን አገኘህ? ማንን አናገርክ? ስንት ሰዓት ነው የሄድከውስ?»

«አመሻሽ ነገር 11 ወይ 12 ሰዓት ገደማ!! ብዙ ሰው ነበርኮ እኔእንጃ!» አለኝ ግራ እየገባው።

«ከበር ጀምሮ ያናገርከውን ሰው አንድ በአንድ ንገረኝ!! ለማስታወስ ሞክር!» እያልኩት መኪናውን አስነስቼ መንዳት ጀመርኩ።

«ጋርዶቹን? መግባት አይቻልም ሰዓት ገና ነው ብለው እንቢ አሉኝ መጀመሪያ እ ….. ከዛ አንቺን ፈልጌ እንደሆነ ከካናዳ የተላከ ዕቃ ላደርስ እንደሆነ ነገርኳቸው እና ከውስጥ የሆነ ሰው ጠርተው አገናኙኝ። ከዛ ለእነርሱ የነገርኳቸውን ስነግረው ሄደሽ እንደማታውቂ …. አንድ ቀን ብቅ ብለሽ እንደነበር ነገረኝ። የግድ ማድረስ ያለብኝ እቃ አለ ስለው እሱም ገብቶ ዳዊት የሚባል ሰው ጠራልኝ። ፍቅረኛሽ መሆኑን ነገረኝ (እዚህጋ የአይመስለኝም ሽርደዳ ያለበት ፈገግታ ፈገግ ብሎ በቁም ነገር የሚያወራውን እየተከታተልኩ እንደሆነ ሲያውቅ ወደ ቁምነገሩ ተመለሰ።) እሱ ወደ ውስጥ እንድገባ ጋበዘኝ እና ከዛ በቃ ያልታወቀ ሰው በሽጉጥ መትቶሽ እንደነበር ከዛም ድጋሚ ከሰዎች ጋር ተጣልተሽ እስከሆስፒታል የሚያደርስ ጉዳት ደርሶብሽ እንደነበር እና እቤት እንደማገኝሽ ነገረኝ።»

« ከኤርፖርት ሆቴልህ? ከሆቴልህ ክለብ? በመሃል የሄድክበት ቦታ አለ? አስታውስ? ያናገርከው ሰው? ሁለቴ የገጠመህ ሰው?»

«ሜል? እኔን ታውቂኝ የለ? ጀርባዬን እያየሁ የምሄድ ሰውኮ አይደለሁም!! ግን ማንንም አላገኘሁም!! ከዛ ውጪ የትም አልሄድኩም! ያናገረኝም ያናገርኩትም ሰው የለም ከሪሴፕሽኖቹ ውጪ!!» አለኝ ተጨንቆ

«ክለብ ውስጥ ሌላ ማን ነበር?»
«የሚሰሩ ሰዎች ነበሩ!! ቤቱን እያስተካከሉ ምናምን የነበሩ እኔ እንጃ በደንብ አላስተዋልኩም ግን ሴቶችም ነበሩ!!»

«ስምህን የነገርከው ወይም የእኔ ወንድም መሆንህን የነገርከው ሰው አለ?»
«ለዳዊት! ስሜን ነግሬዋለሁ ግን ያንቺ ወንድም መሆኔን አልነገርኩትም!! ዳዊት እባላለሁ ሲለኝ ኪዳን! ብዬዋለሁ!!»

«ምን ያህል ይሆናል ውስጥ የቆየኸው?»
«እኔ እንጃ አንድ ሰዓት!! የሚጠጣ ጋብዞኝ አንድ አንድ ብርጭቆ ይዘን ነው የሆነውን የነገረኝ!! ይኸው ጀመረሽ ነገር ስትቀምሪ መሃል ቤት እኔን የምታጦዥኝ ነገርሽ!»

«ጥርጣሬ እንጂ ያረጋገጥኩት ነገር ስለሌለ ልነግርህ አልችልምኮ ኪዳንዬ! መጠጡን የጋበዘህ እሱ ነው? አልጠጣም ብለኸው ነበር? እንድትጠጣ ወተዋተህ?»

«አይ እውነትም ፍቅረኛሽ ነበር በሚገባ ነው የምታውቂው!! አዎ አልጠጣም እቸኩላለሁ ስለው። <እዚህ ድረስ መጥተህ ሳላስተናግድህ መሄድህን ሜሉ ብትሰማ ትቀየመኛለች፤ አንድ ብርጭቆ ይዘን የሆነውን ላውራህ አለኝ!!»

«ይሄ የውሻ ልጅ!! እውነት ባይሆን ነው የሚሻለው እንጂ አልለቀውም! (ይሄ ጤነኛ ንዴት ይሆን አልገባኝም! ጭንቅላቴ ከውስጥ የተወጠረ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ የሆነ ሊፈነዳ የቀረበ ነገር። ደረቴ ላይ እልህ እና ቁጣ ከትንፋሼ ጋር እኔ ልውጣ እኔ ልቅደም ግብ ግብ የገጠሙ አይነት ስሜት) ይሄ ሙት እሱም ሰው ሆኖ መሆኑ ነው?» ኪዳን እየሆነ ያለው ግራ ገብቶት

«ሜል? እሱ ደውሎላቸው ነው የመጡት ብለሽ ነው የምታስቢው? ከአጠገቤኮ ለአፍታም ዞር አላለም ነበር። ኸረ በፍፁም እንዲህ የሚያደርግ ሰው አይመስልም! ግማሹን ሰዓትኮ እንዴት እንደሚወድሽ ነው ሲነግረኝ የነበረው። ደግሞ ፍቅሩ አይኑ ላይ ያስታውቃል። ምንም ከማድረግሽ በፊት አጣሪ እህትዬ በእኔ ሞት? እ?»

«ሌባ አይኑ እና ቅቤ ምላሱ አይሸውድህ!! በእርግብ ላባ ያጌጠ እባብ ነው!! ታውቀኛለህ ደግሞ ባልተረጋገጠ ነገር ምንም አላደርግም!!» እያልኩት ስልኬን አውጥቼ ደወልኩ!!

«ሻለቃ! ሜላት ነኝ!!»
«ሜላት ሜላት?»
«አውቀኸኛል ባክህ! እንዴት አስታውሳ ደወለች ብለህ ከሆነ ግራ የተጋባኸው አዎ አስታውሼ ነው!! አደጋ የደረሰብኝ ቀን ለኤግዝቢትነት በሚል የወሰዳችሁትን ስልኬን መረጃውን ከውስጡ አፅድታችሁ እንደመለሳችሁልኝም ጭምር ነው ያስታወስኩት! ለሶስተኛ ወገን አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ ማለቴ ሸጣችሁ የግሌን መረጃ እንደነገዳችሁበትም ጭምር!! ልቀጥል?»

«ምን እንደምታወሪ ታውቂዋለሽ? ወይስ ጥይቱ ሚሞሪሽን ብቻ ሳይሆን ማሰቢያሽንም ነው የወሰደው?»

«ምን እንደማወራ አሳምረህ ታውቃለህ!! ፌስቡኬ የእኔ መሆኑን ሰይጣን እንኳን አይደርስበትም። ድንገት እኔ በተመታሁ በነጋታው 10 ዓመት ሙሉ ማን መሆኔ ሳይታወቅ የተጠቀምኩበት አካውንት በአስማት ታወቀና ዘጉት ነው የምትለኝ ያለኸው? ኦው ለምን ስልኬን እንደሚፈልጉት አልነገሩህም ማለት ነው?» ዝም አለ ለአፍታ

«የውልህ! በጣም በተቻለኝ አቅም ጥሩ ሴት ልሆን እየሞከርኩ ያለሁበት ሰዓት ላይ በመሆኑ ፈጣሪህን አመስግን!! ከናንተ ጋር አውጫጭኝ የምጫወትበት ጊዜ የለኝም!! አንድ መረጃ ብቻ ነው የምፈልገው!! የመታኝን ሰው ማወቅ ነው የምፈልገው!! መሃል ከተማ ነው! አመለጠ ምናምን በሚል ተረት ተረት እኔን አትሸውደኝም!! ግማሽ መንገድ ላግዝህ?  ጥቁር ጃጓር መኪና የጎማው ቸርኬ ወርቅማ ፣ ከኋላው መስታወት በቀኝ በኩል ጠርዝ ላይ ትንሽዬ ቀይ ስቲከር ያለበት፣ ታርጋ ቁጥሩ የመጨረሻ ሁለት ቁጥር 52 ነው!! እኔ ሁለት ጥይት መትቶኝ ይሄን ሁሉ መረጃ ስቶር ማድረግ ከቻልኩ ምርመራውን የያዘው ወይም ይዞ የለቀቀው ባልደረባህ በአንድ ሰዓት ውስጥ ሙሉ መረጃውን ጠረጴዛህ ላይ ማኖር አይቸግረውም!! ሌላው ደግሞ ሴት ናት!! ወንድ ለመምሰል የሞከረች ሴት ናት!! መኪናው በማን ስም እንደተመዘገበ እና ሴትየዋ ማን እንደሆነች ብቻ ነው ማወቅ የምፈልገው። ከአንድ ሰዓት በኋላ እደውልልሃለሁ! ከዛ ቀድመህ አሁንም ቢሆን የምትነግረኝ ነገር ካለህ ግን ዝግጁ ነኝ!!» ዝም አለኝ። ስልኩን ዘጋሁት!! እና ወደኪዳን ዞሬ

«ያረፍክበት ሆቴል ደውል እና ሻንጣህን መውሰድ እንደምትችል አረጋግጥ!! የምታርፍበት ሌላ ቦታ እንፈልጋለን። ለጊዜው እኔም ወደቤት መሄድ ያለብኝ አይመስለኝም!!»


«በእንዲህ ዓይነት ሰዓትኮ ሌላ የማላውቃት ሴት ነው የምትሆኝብኝ!! ውስጥሽ ሁለት ሴት ያለች ነው የሚመስለኝ! የእኔ ሜል እና የሌላ ሰው ሜላት! የእኔዋ እናት፣ እህት፣ ስስ ፣ የምታለቅስ ፣ የምታቅፍ ፣ የምታባብል ፣ ቀድማኝ የምትሞትልኝ …….. ያችኛዋ አያድርስ ነው!! » አለ ኪዳን በመገረም ሲያየኝ ቆይቶ!!
👍13🥰2
«መሸነፊያዬም መጀገኛዬም አንተ መሆንህን አታውቅም? ባንተ ሲመጡብኝ ነው እጅ የምሰጠውም አውሬ የምሆነውም! ያን ታውቃለህ አይደል?»

«አውቃለሁ ሜል። ግን አሁንኮ ትልቅ ሰውዬ ነኝ!! ሚስትኮ ላገባ እየተሰናዳሁ ያለው ግብዳ ሰውዬ ነኝ! እስከመቼ ነው የምትጠብቂኝ? (ዞር ብዬ ያለፉትን ቀናት እንደማስታወስ ሳየው) ይሄ የተለየ situation ነው። እንዲህ ያለ አጋጣሚ ከተፈጠረማ በድዴም ቀርቼ እንደምትደርሺልኝ አውቃለሁ። ገብቶሻል ምን ማለት እንደፈለግኩ!! መቼ ነው አንቺ የራስሽ የሆነ ህይወት የሚኖርሽ? ለእኔ ብለሽ ፣ ለአባዬ ብለሽ ወይም ለእማዬ ብለሽ የማትኖሪው። ለሜላት ብለሽ የምትኖሪው ቀን መቼ ነው? (ይሄን ሲለኝ ስለእማዬ ለካ መንገር አለብኝ። ምን ብዬ ነው የምነግረው? የሞተችዋ እናታችን ከሞት ተነሳች! ነው የምለው?)  ደግሞ አባት ልሆንልሽ ነው!» ሲለኝ ስለእማዬ ያሰብኩት ጠፋብኝ። መኪናውን አቆምኩ።

«ሊንዳ እርጉዝ ናት? ስንት ወሯ ነው?» እያልኩት እሺ የአሁኑ እንባ ምን የሚሉት ነው? እንደትናንት በሚመስለኝ የቀናት ርዝመት ውስጥ እግሬ ላይ ተጠምጥሞ ትተሽኝ አትሂጂ ብሎ የሚያለቅስ ትንሽዬ ልጅ ነበርኮ!! አባቱ የሞተበት እናቱ ትታው የሄደች ቀንኮ <አባዬ ዳቦ ገዝቶ ሲመጣ ዳቦ በሻይ ነው የምበላው እንጀራ አልበላም!> ብሎ ያለቀሰ የአባቱ ሳጥን ውስጥ መቆለፍ ያልገባው ሚጢጢ ነበረ።

«ስድስት ወር ሆናት! ሴት ናት!» አለኝ እንደመኩራትም እያደረገው። ዝም አልኩ!! ዝምታዬ ውስጥ ግን ብዙ ጩኸት ነበረ። ደስ የሚል ከዛ ደግሞ የሚከፋ ስሜት እንዴት ተብሎ ይብራራል? የእኔ ኪዳን ፣ ልጄ ፣ ታናሼ ፣ ዓለሜ ፣ ብቸኛ የዓይን ማረፊያዬ አደገልኝ!! እሱ አድጎ ልጅ ሊያሳድግ ነው!! እንዲኖረው የተመኘሁለትን እና የተመኘውን ሁሉ አንድም ሳይጎድልበት አግኝቷል። በህይወቴ ትልቁ ድሌ እና ስኬቴ እኮ እሱ ነው!! ከዛ ግን ለምን የመከፋት ስሜት ተሰማኝ? ለእሱ ደስ አለኝ ለእኔ ግን ከፋኝ። የሆነ እዝህች ምድር ላይ ለመኖር የመጣሁበትን ዓላማ የጨረስኩ ፤ የምኖርለት ምክንያት ምንም ያልቀረኝ ፤ ከዚህ በኋላ እኔ የማላስፈልገው ፤ የራቀኝ ዓይነት ስሜት ተሰማኝ። ይሄን ግን ለእርሱ ልነግረው አልፈለግኩም። ደስታው ትንሽ እንኳን እንዲደበዝዝበት አልፈልግም!! አቅፌው እንባዬን እየጠረግኩ ደስ እንዳለኝ ነግሬው መኪናዬን መንዳት ጀመርኩ። ሆቴሉ ደውለን ሪሴፕሽን እቃውን እንዲያስቀምጡልን አድርገን። የሚከፋፈለውን ከፍለን ሻንጣውን ወሰድን። ለአፍታም ቢሆን ከእኔ እይታ ዘወር እንዲል ስላልፈለግኩ ሆቴል ከመያዛችን በፊት ጎንጥን ለማየት ወደሆስፒታል ነዳሁ።

«የእኔ ኪዳን? አውቃለሁ ታጥበህ ልብስ ለመቀየር እንደቸኩልክ!! ለትንሽ ደቂቃ ሆስፒታል የሆነ ሰው ጠይቀን እንመለስ እና ደግሞም የምነግርህ ትልቅ ነገር አለ።» አልኩት በመንገዳችን።

«ምንድነው እሱ? የምነግርህ ትልቅ ነገር ስትዪ ሁሌም የሚከተለው ደስ የማይል ነው!! ምንድነው እሱ? ምን ልታደርጊ ነው? ደህና ነሽ አንቺኣ?»

«ኸረ ጭራሽ እንደሱ አይነት ነገር አይደለም!! እንደውም ደስ የሚል ነው መሰለኝ! ቢያንስ በግማሽ!»

ጎንጥ የተኛበት ክፍል ስንገባ ትንፋሹን ሰብስቦ የሆነ መርዶ እየጠበቀ ያለ ይመስል ነበር። ከሆዱ ድረስ ትንፋሹን ስቦ በረጅሙ የመገላገል ዓይነት ተነፈሰ እና ፈገግ አለ።

«ነፍሴን እኮ አወክሻት ዓለሜ? ከቤቱ ወጣች ካሉኝ ቆየ!! ስትዘገዪ ከመንገድ ምን አገኘሽ ብዬ ነፍሴ ከስጋዬ ልትለይ?» አለ የመጨረሻውን ዓረፍተ ነገር መልስ ባልጠበቀ ጥያቄ ዓይነት አስረዝሞ!! ማለት የፈለግኩት የነበረው <ልቤንኮ በረደኝ! እጄን ያዘኝ! ጦሽ ብዬ ላልቅስና! ኸረ በመድሃንያለም ነፍሴን አታስጨንቂያት! እያልክ አባብለኝ!> ነው። ያልኩት ግን «የኪዳንን ሻንጣ ልናመጣ በዛው ሄድን! ይቅርታ ቢያንስ መልዕክት እንኳን መላክ ነበረብኝ!»

ኪዳን አንዴ እኔን አንዴ እሱን <እየሆነ ያለውን ነገር አንዳችሁ ትነግሩኝ> በሚል አስተያየት ያየናል።

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍275