አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ስምንት)
(ሜሪ ፈለቀ)

መቼም ሰው <ልቤ ዝቅ አለብኝ> የሚለው አሁን እኔ እንደሚሰማኝ ልቤ አቃፊዋን ለቃ የወጣች የሚመስል ስሜት ሲሰማ ነው የሚሆነው። የኔዋማ ዝቅ ከማለትዋም እነ ሳንባ ጉበትን <ዞር በሉ በናታችሁ> ብላ ገፋ ገፋ አድርጋ አንጀቴ ላይ ዛል ብላ ጋደም ያለች ይመስለኛል። አጅሬው እኔን ድዳና ሽባ አድርጎ በድንጋጤ አደንዝዞኝ እሱ እቴ በሙሉ አይኑ እንኳን አላየኝምኮ!!

ለመሆኑ ስሙስ የምር ጎንጥ ነው? የሚያወራው የሀገርኛ ለዛውስ ዘበኛ ለመምሰል ያስመሰለው ይሆን? ቅድም እንዴት ነበር ያወራው? ንፋስ ሲሆን ትከሻው ላይ ጣል የሚያደርጋት ፎጣውስ የትወናው አካል ትሆን? ዘበኛም ሆኖ አንዳንዴ ስንወጣ የሚለብሰውን ዓይነት ጅንስ በሸሚዝ ስለለበሰ የአለባበሱን ትወና መለየት ይቸግራል።

«ስራህንማ በአግባቡ ተወጣህ!» አለችው ሴትየዋ። ሙገሳ አይደለም! የሆነ ለበጣ ያለበት ነገር ነው! ቀጥላ የሆነ በእኔ ፊት ወይም በሰውየው ፊት መናገር ያልፈለገችውን ነገር ለብቻቸው እንዲያወሩ መሰለኝ። « ….. እኔ እና አንተ ብዙ የምናወራርደው ነገር አለ።» ብላ እጁን መንጨቅ አድርጋ ይዛው ልትሄድ ስትሞክር ከተቀመጠበት ሳይነሳ እጁን መነጨቃት። አስከትሎ ከእግሯ እስከ አናቷ በግልምጫ ካበጠራት በኋላ ራሱ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቀድማው ከሳሎኑ እንድትወጣ ምልክት አሳያት። (እንደለመደው ነዳት ብል ይቀላል) በተጫማችው ሂል ጫማ እንደዝግዛግ ያለ አረማመድ እየረገጠች ሳሎኑን ለቃ ስትወጣ ተከትሏት እየተቆለለ ወጣ!! ከትውውቅ አልፈው መደነቋቋል ላይ የደረሱ ወዳጃማሞች መሆናቸውን ለማወቅ ምንም ሂሳብ አያስፈልግም!!

< ሄሎ!! እዚህ ነኝ! ሜላት! አስታወስከኝ? ከአንድ ቀን በፊት እመኚኝ ብለህ እንደወፍጮ ቤት እህል አየር ላይ ያንቀረቀብከኝ? አልታይህም?> ይላል ውስጤኮ አፌን ቃል ማን ያበድረው? ከሳሎኑ ከወጡ በኋላ የሚያወሩት ባይሰማኝም ጭቅጭቅ ላይ መሆናቸው ከድምፃቸው ያስታውቃል። ጎንጥ እንዲህ ይጮሃል እንዴ ሲያወራ? እኔ ንግግሩን ሳልሰማ ድምፁ እንዲህ ያስደነገጠኝ እሷ እዛች ሚጢጥዬ ፊቷ ላይ ሲጮህባት ወትሮም ያነሰች ፊቷ አለመትነኗ!!

የሁለቱ ሁኔታ ግራ የገባው ከመሰለው ሰውዬ ጋር ተፋጠን ሁለታችንም ከማይሰማው የሁለቱ ጭቅጭቅ ቃላት ለመልቀም ጆሯችንን አሹለን እንቃርማለን!! ፀጥ ያሉ መሰለ ወይም ድምፃቸው ለኛ መሰማቱን አቆመ።

«ለመሆኑ እኔ ማን እንደሆንኩ ታውቂያለሽ?» አለኝ ሰውየው በተፈጠረው ክፍተት። የሆነ ተራ ጥያቄ የጠየቀኝ አስመስዬ አፍንጫዬን ነፍቼ ለማለፍ ሞከርኩ።

«ጊዜ ግን ሲገርም!! በተሰቀለው!! ምንም ምንም አታስታውሺም?» ብሎ ሊገለፍጥ ዳዳው « መቼም ግፍሽ ነው!! በቁጥር እኮ አይደለም አንቺ የህዝብ ግፍ ነው ያለብሽ!! ሃሃሃሃ ሰውኮ የዘራውን ነው የሚያጭደው ሃሃሃ ስንቱን እንዳልከዳሽ የራስሽ ጭንቅላት ይክዳሽ? እረስታለች ሲሉኝ ማመን ያቃተኝ ቀጥ ብለሽ ስትመጪ ነው። ምንም የምታውቂው እና የምታስታውሺው ሳይኖር …… » ብሎ ሲጨርስ

«እኔ እንዳልረሳው አይጠፋህምሳ መቼም!» እያለ ገባ ጎንጥ!! ሴትየዋ ትንሽ ቀይ ፊቷ ሚጥሚጣ የተነፋበት ሰሃን መስሎ ተበሳጭታ ተከትላው ገባች።

«እሷ ትሄዳለች። ወንድምየው እኛጋ ይቆያል።» አለች በኮሳሳ ድምፅ ትዕዛዝም ሀሳብ ማቅረብም በመሰለ አነጋገር - ለሰውየው። ሰውየው ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲደነፋ እና ሲጯጯሁ «ኪዳንን ትቼ አልሄድም!» ያልኩትን የሰማኝ የለም!! ጎንጥ አጠገቤ ደርሶ ቁጢጥ እንደማለት አለ እና

«እባክሽ እንዳታስቸግሪኝ (ይሄኛው ልመና ነገር ነበር) የምልሽን አድርጊ! ካለበለዚያ ያንቺንም የእኔንም የኪዳንንም ህይወት ነው እሳት ምትሰጅበት (ትዕዛዝ ነገር ሆነ) ለዛሬ! ለዝህች ደቂቃ ልታምኝኝ ይቻልሻል? (ልምምጥ ነገር ሆነ)» አልመለስኩለትም!! ሰውየውና ሴትየዋ በጥፍራቸው ቆመው ይጨቃጨቃሉ።

«ታምኚኛለሽ?» ሲል ግን በፍጥነት
«አላምንህም!!» አልኩት። ይህችን ለመተንፈስ ሰዓት እየጠበቅሁ ይመስል ተቅለብልቤ

«ሜላት እኔና አንቺ የምንነታረክበት ጊዜ የለንም! ስትፈልጊ አትመኚኝ ያልኩሽን ካልሰማሽ ሙት ነሽ!! (ይሄ ድብን ያለ ቁጣ ነው!!) እኔ እና አንቺ አሁን ወጥተን እንሄዳለን!! አንቺን እንጂ ኪዳንን አይፈልጉትም!! በምትወጅው ኪዳን ይሁንብሽ ለአንዴ እመኝኝማ! (እዚህጋ እኔን ማስረዳት የደከመው መሰለ) ኪዳን ምንም አይሆንም!! (ድምፁን ቀነስ አድርጎ) ኪስሽው ውስጥ አሁን እንዳታስታውቂ ! ኪዳን መልዕክት አኑሮልሻል!! ከዚህ ከወጣን በኋላ ታይዋለሽ!! አሁን እንሂድ? (ይሄ እባክሽ እንቢ እንዳትዪኝ የሚል ማባበል ነው።)።» ምላሴን ምን ያዘብኝ? እሺም እንቢም ማለት ጠፋኝ!! ሰዎቹ ጭቅጭቃቸውን ማቆማቸውን ያወቅኩት

« I knew it!! ወደሃት ነዋ!» ብላ እግሬ ስር ቁጢጥ ያለውን ጎንጥ በትንግርት እያየችው የሆነ ግኝት የተገለጠላት ዓይነት አስመስላ ስትጮህ ነው። ጎንጥ አቀማመጡን ገና አሁን ያስተዋለው ይመስል ተመንጭቆ ተነስቶ ክምር ተራራ አክሎ ተገተረ። ሴትየዋ አላቆመችም። እንደንቀትም፣ እንደ መገረምም ፣ እንደመናደድም …… እንደብዙ ነገር በሆነ ድምፅ እና እይታ « ጎንጥ ለዝህች? (በአይኗ አቅልላ የጤፍ ፍሬ አሳከለችኝ) ማን ያምናል? በምን አገኘችህ በናትህ?»

«አፍሽ ሲያልፍኮ አይታወቅሽም!! እረፊ ብያለሁ!» ብሎ ተቆጣ።

ቆይ እዚህጋ የትኛውን ሀሳብ አስቀድሜ የትኛውን አስከትዬ የቱን ምኑጋ ሰካክቼ ልከኛውን ምስል ላግኝ? ሰው ሀሳብ ይበዛበታል አይሉም በአንዴ ራሱን ጎንጥን የሚያካክል መአት ሀሳብ ወርውረውብኝ እዛ እንደተቀመጥኩ የሚዘነጉት? ኸረ ቆይ ጎንጥ ወዶኝ ነው የሚለውን ላስቀድም? ኸረ አይደለም! <ይህችን?> ብላ ምላሷ ላይ ያሟሸሸችኝ እኔ አስቀያሚ ነኝ እንዴ? አይደለም ኸረ ቆይ ጎንጥ ሴትየዋን ምን ቢላት ነው እኔን ይዞ እንዲሄድ የተስማማች? ኸረ ሌላው ደሞ እሱስ <ወድጃት አይደለም> ከማለት ይልቅ የሚደነፋው ወዶኝ ነበር ማለት ነው? አይ እነዚህ ሁሉ ይቅሩ እንዴት አምኜው ነው ኪዳንን ትቼው የምሄደው? ግን ምርጫስ አለኝ? ኸረ ኪዳን በምን ቅፅበት ነው መልዕክት ያስቀመጠልኝ? ምን ይሆን የሚለውስ? ደሞ ሌላ አለ እንጂ ቆይ ጎንጥ እኔን ቢወደኝ እሷ ምን እንዲህ ይንጣታል?

በአይኑ ከተቀመጥኩበት እንድነሳ ምልክት ሰጠኝ። በአይኑ አስነሳኝ። እጁን ሰጠኝ ወይም እጄን ተቀበለኝ እኔእንጃ ብቻ እጄን ያዘው እና ወደበሩ መራመድ ጀመረ። ጠባቂዎቹ ትዕዛዝ የሚጠብቁ ይመስላል ከበሩ አልተንቀሳቀሱም!! ሰውየው በአገጩ የሆነ ምልክት ሰጣቸው!! ከበሩ ገለል አሉ!! ሴትየዋ መናጥዋ በረታባት!!
👍241🔥1
«እመነኝ ጎኔ ይህችን አታልፋትም!! አስከፍልሃለሁ!! እመነኝ ትከፍላታለህ!!» አለች እየጮኸች። <ጎኔ> ብላ ነው ያቆላጰሰችው? ዛሬማ የሆነኛው ፊልም ተዋናይት ሆኛለሁ እንጂ እየሆነ ያለው እውን በእኔ ህይወት እየሆነ ያለ አይደለም!! እንዲህ አፍና ጭራው ያልተለየ እውነተኛ ህይወት ሊኖር አይችልም።
በሩን አልፈን እንደወጣን የቅድሟ ሴት ተቀበለችን። ስመጣ ያሰሩልኝን ጨርቅ ይዛ ስትቀርበኝ የያዘኝን እጁን ለቅቄ በጥያቄ አየሁት!! የታከትኩት መሰለ እና በቁጣ ጮኸ « እየገባሽ አይደለም አንቺን መምረጤ? ከዚህ በላይ ምን ባደርግ ነው የምታምኝኝ በይ? ያለፈውን ካላወቅኩ ነው? አንድም ሳይቀር አወጋሻለሁ! እዝህችው ቆመን 19 መቶ ብዬ እንዳወጋሽ አይደለማ ሀሳብሽ?» ቅድም ሴትየዋ ላይ እንደጮኸው ነው የጮኸው!! ጨርቁን እንድትሰጠው ለልጅቷ እጁን ሲዘረጋ ልጅቷ እንደማቅማማት አለች። ጮክ ብሎ ሲያፈጥባት የመወርወር ያህል እጁ ላይ ጣለችው። ከሁኔታዋ ከዚህ በፊት የሚተዋወቁ የምትፈራው ሰው መሆኑ ያስታውቃል። ምናልባት አለቃዋ ነበር? ዛሬማ የሆነ ፊልም ገፀ ባህሪ ሆኛለሁ።

ከሴትየዋ እጅ ተቀብሎ እሱ እያሰረልኝ እንደዛ እንዳልጮኸ ልስልስ ብሎ ነገር «መግቢያ መውጫቸውን እያየሽ እንድትሄጂ በጀ አይሉሽም!! ለዛሬ የምልሽን እሽ በይ በሞቴ?» አለ። ማደንዠዣ እንደወጉት በሽተኛ ፍዝዝ ድንግዝ አልኩ። ጨርቁን ካሰረልኝ በኋላ እጄን አጥብቆ ይዞ መራመድ ጀመረ። የምረግጠው ምን እንደሆነ ሳላውቅ እግሬን እያነሳሁ ተከተልኩት። መኪና ውስጥ ገባን!! ባላይም መኪናው ውስጥ ከእኔና ከእርሱ በተጨማሪ ያቺ እንደጥላ የምታጅበኝ ሴት እና ሹፌር እንዳሉ አውቂያለሁ። እኔእና እሱ መጓዝ ጀምረን የያዘኝ እጁ መያዝ ብቻ ሳይሆን መዳበስ ነገር ያደርገኛል። ልቤ የምን አጃቢ ናት አብራ የምትቀልጠው? ትንፋሹ እንዳልተረጋጋ ያስታውቅበታል። አካሉም ይቅበጠበጣል። ከእርሱ ሁኔታ በመነሳት አሁንም እርግጠኛ የሆነ ማምለጥ አለማምለጤን ጠረጠርኩ። ቆይ እራሱ የሆነ ቦታ አግቶ ይዞኝ እየሄደ ቢሆንስ? እሱንስ እንዴት አመንኩት?

«ሴትየዋ ማናት? ምንህ ናት?» አልኩት ከዛ ሁሉ አናቴን ከወጠረው ጥያቄ ይሄን ለምን እንዳስቀደምኩ አላውቅም!! በረዥሙ ተንፍሶ

«የልጄ እናት ናት!! ምሽቴ ነበረች» አላለኝም? ከዚህ በላይ ከእውነታ የራቀ ቀን አለ እሺ?
«እ?» የምትለዋ ፊደል ከየትኛው ቃል አምልጣ በአፌ እንደሾለከች አላውቅም!! ብቻ ለምሳሌ <እንደ> ከሚለው ቃል ቢሆን ተጣልተው የፈረጠጠችው …… <ን> ን እና <ደ>ን ትርጉም አልባ አድርጋ ጥላቸው ብቻዋን ስትፈረጥጥ …… ተንደርድራ አምልጣ መሆኑ የሚያስታውቀው አፌ ፊደሏን ሊያስወጣ እንደተበረገደ አልተከደነም!!

«ባሏ ነው!!» አለ አክሎ። ሰውየውን መሆኑ ገባኝ ግን ጭንቅላቴ ውስጥ ሀሳቦቹ ተጠላለፉ ነገር። የሰውየው የአሁን ሚስት የጎንጥ የድሮ ሚስት የልጁ እናት! ከዛ ግን ዛሬም ውሉን ያልጨበጥኩትን ስራ (እገታ እና ስለላ ማለት ይቀላል) አብረው የሚሰሩ? ነው ወይስ ያልገባኝ ነገር አለ? ይሄ ቢገባኝም እንኳን በ2 ወር ከአስር ቀኔ እንደምንም ያጠራቀምኩትን አዲስ ትውስታ ሁላ ነው የሚያጠፋብኝ።


መኪናው ቆመ። ከአይኔ ላይ ጨርቁ ሲነሳ መኪናዋ የቆመችው ከከተማ የራቀ ጭር ያለ ቦታ መሆኑን አስተዋልኩ። በቅርብ ርቀት የእኔ መኪና ቆማለች። እዚህ ደቂቃ ላይ ማመንም መጠራጠርም አይደለም የተሰማኝ። ምንም ነው!! ጎንጥ ግን የሆነ ነገር እንዳላማረው ያስታውቃል። ዙሪያ ገባውን ከቃኘ በኋላ እስከአሁንም ያልለቀቀውን እጄን አፈፍ አድርጎ ወደመኪናችን እየሄድን።

«ከአይናችን ተሰወሩ ማለት የሉም ማለት አደለም!! አሁን አንቺን ማጥፋት ቀላሉ መፍትሄያቸው ስለሆነ ማስታወስ ችለሽ ከምትፈጃቸው በፊት የአቅማቸውን ይሞክራሉ።» እያለኝ እኔን ባልያዘው እጁ ወገቡ ላይ ያለ ሽጉጡን ጨብጦ ወደኋላ እና ወደጎን እየተገለማመጠ መሬቱን በረጃጅም እርምጃው ይመትረው ጀመር። ያደረሰችን መኪና ከኛ በተቃራኒ አቅጣጫ ሄደች። ከአይናችን ስትሰወር መኪናችንጋ ደርሰናል። ስንቀርብ የመኪናችን ጎማ መተኛቱን አይቶ ጎንጥ ጎማውን በእግሩ ሲነርተው አየሁ።

ከየት መጣ ሳይባል አንድ ፒካፕ መኪና እየበረረ ፒስታውን መንገድ አቧራ እያጨሰ መጣ። እየሆነ ያለው ነገር ከመፈጣጠኑ የተነሳ ውዥብርብር አለብኝ። በቅፅበት የተኩስ ድምፅ ተሰማ!! ማናቸው ቀድመው እንደተኮሱ እንኳን አላውቅም ምክንያቱም ጎንጥም እየተኮሰ ነው። በየትኛው ቅፅበት ሽጉጡን እንዳወጣ እንኳን አላየሁም!! የትኛው ቅፅበት ላይ እጄን እንደለቀቀኝም አላውቅም! ማየት እስኪያቅተን የበዛ አቧራ እያቦነነ እና እየተኮሰ አልፎን የሄደው መኪና በሄደበት ፍጥነት አዙሮ ተመልሶ ወደእኛ ሲመጣ በአንድ እጁ የመኪናውን በር ከፍቶ

«ግቢ!! ገብተሽ ወደታች ዝቅ በይ!!!! ከወለሉ ተኝ!» ብሎ ጮኸ! ምንድነው እግሬን ከመሬቱ የሰፋው? እኔ የድርጊቱ አካል ያልሆንኩ ይመስል ዓይኔ አንዴ ጎንጥን አንዴ በፍጥነት እየመጣ ያለውን መኪና ያያል። በሩን ከፍቶበት በነበረው እጁ ከጎኑ ወደጀርባው ገፈተረኝ። አፈሰኝ ማለት ይገልፀዋል። እኔንም ራሱን መከላከል የማይችልበት አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተትኩት ገብቶኛል ግን በምን በኩል ሰውነቴን ልዘዘው? ዓይኔ ስር ፊልም እየተሰራ ያለ ዓይነት ስሜት ነው ያለው። እኔን ወደጀርባው በደበቀኝ ቅፅበት ለጊዜው ምኑጋ እንደሆነ ያልለየሁት ቦታ እሱ ተመታ። እኔ የተመታሁ ዓይነት መሰለኝ። ጭንቅላቴ ለቅፅበት ያን ቦታ ትቶ ሄደ። ቅፅበት ናት ግን ድንዝዝዝ ያለ..... ብዥዥዥ ያለ ቅፅበት .... ጎንጥ የተመታበትን ቦታ በአንድ እጁ ይዞ

«ወዳጄ ይደርሳል። ከእርሱ ጋር ሂጂ!! እቤት እንዳትሄጅ!! » ይለኛል ጮክ ብሎ!!

«ትቼህማ አልሄድም!!» ዓይኔ ከፒካፑ መኪና ጀርባ እየመጣ ያለ መኪና በአቧራው ውስጥ ቢያይም ጭንቅላቴ ግን እዛው ገትሮኝ ሄዷል። አንድ ጥይት በጎኔ አልፎ መኪናውን ደነቆለው:: ሰውነቴ አይታዘዝም!! ደንዝዟል::

"ዝቅ በይ!" እያለ ይጮሃል ጎንጥ በከፊል ዘወር ሲል ከጎኑ የሚፈስ ደሙን እያየሁ ሀሳቤ ሄደ .... እዛ ቀን ላይ!!

ጥይቱ የተከፈተ የመኪናዬን መስኮት አልፎ ጡቴ ስር ሲመታኝ!! የመጀመሪያውን ህመም በቅጡ አስተናግጄ ሳልጨርስ ሁለተኛው ተመሳሳይ ቦታ ሲያገኘኝ። - የተመታሁ ቀን!! አንድ በአንድ ቁልጭ ብሎ ስዕሉ ጭንቅላቴ ውስጥ መጣ!! የማደርገው እና የማስበው በአንድ እኩል ቅፅበት ነበር። እጄን ማዘዜን አላስታውስም ብቻ ከጎንጥ እጅ ላይ ሽጉጡን እንደቀማው አውቃለሁ። ክፍቱን በተተወው የመኪና በር ግማሽ ሰውነቴን ከልዬ ሳደርገው የኖርኩት ልምዴ መሆኑን እርግጠኛ የሆንኩበትን ድርጊት እከውናለሁ። ከኋላ የመጣው መኪና በእኛና በፒካፑ መሃል ገብቶ ቆመ።

« ሂጅ እኮ አልኩ!!» ብሎ አምባረቀብኝ። በእጁ ጎኑን ደግፎ መሬቱ ላይ ተቀምጦ የመኪናውን ጎማ እንደተደገፈ።

«ደፋር እየሸሸ አይሞትም! እየተዋጋ እንጂ!» ስለው በህመሙ መሃል በስቃይ የታጀበ ፈገግታ አሳየኝ። ትውስታዬ ሳይከዳኝ በፊት አዘውትሬ የምለው አባባል ስለነበር ገባው። ጭንቀቱ የቀለለው መሰለ እና ህመሙን ማድመጥ ጀመረ። ፒካፕዋ መኪና ከአይኔ ራቀች። ወዳጄ ነው ያለው ሰውም ከመኪናው ወርዶ ወደኛ መጣ!! ሁለት ቦታ ነው የተመታው። አንዱ ከትከሻው ዝቅ ብሎ ሌላኛው ጎኑ ላይ የጎድን አጥንቶቹ መሃል ……. የለበስኩትን ሹራብ አውልቄ የሚንዥቀዥቅ ደሙን ለማቆም ከአንዱ ቁስል ወደ አንዱ እላለሁ።
👍28👎1
« ሁሉንም?» ይለኛል አይኑን ላለመክደን እየታገለ።
« ምኑን ነው ሁሉንም?»
«ያስታወሽው?»
«መሰለኝ!!» አልኩት። ሁሉንም ላስታውስ የጎደለ ይኑረው በምን አውቃለሁ?

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍246👏1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“አፈርሁኝ በራሴ ከሎ!

“ሃፍረት ልብሳችን ሆኗል፡ በተለይ ከዚች ሃገር ወጣ ብለህ ስትመለስ የት ነን? ማን ይዞ አስቀረን?... ሺ ጥያቄ በህሊናሀ ይደረደራል። መልሱን ግን አታገኘውም! የሚመልስልህም የለም::

“መጽሐፍ ስታነብ ያለፉትን የኪነ ጥበብ ስራዎች ስታይ
በታላላቆቻችንና በኛ መካከል ያለው ግሉህ ልዩነት ያፈጥብሃል
ጠልፎ እሚጥል ! ጉቶ ይመስል እንቅፋት ሆኖ ለመስራት የሚፍጨረጨሩትን የሚያደናቅፍ ምክንያት ይኖራል! ደግሞ አለ!
ነበረም።

“ይህ ግን በእንቅልፍ ለመደበቅ በቂ ምክንያት አይደለም ችግር ሲበዛ መፍትሄውም ከውስጡ ይፈለፈላል። ለመሻሻል ምንጩ ችግር እርካታ ማጣት ነው:

“እኛ ግን ብዙ አጥተን ብዙ ነገር ካላቸው በላይ ቆመን
እናናውዛለን። ብቸኛ ሆነን አጠገባችን ያሉትን እናኮርፋለን እንኮንናለን
ከመሃከላችን ለመውጣትና እኛኑ ለመሳብ
የሚንቀሳቀሰውን ሞራል እየስጠን ከማደፋፈር ይልቅ ተጋግዘን በጠረባ እንዘርረዋለን። የኛ ደስታ የሚታየው በወደቀው ስንስቅ ነው ሌሎቹ ደግሞ በእኛ በወደቅነው ይሳለቁብናል።

“ሰው ሆነን ተፈጥረን ሰው ሆነን ከመከበር ራሳችንን
አራቅን ያለንን አናውቅም! ሌላው ቀርቶ ባለንም አኮራም፡ ከዚያ ይልቅ በተውሶ አልባሳትና ቅራቅንቦ የማስመሰል ተውኔት በባለቤቶቹና በእኛው ህዝብ ፊት እንሰራለን፡ ሁለቱም ግን ረክተው አያጨበጭቡልንም! ከሁለት ያጣ ጎመን' ነን…”
ሶራ በከሎ ሃሳብ መመሰጡና መስማማቱ በሚተናነቀው እልህ ያስታውቃል።

“ሳይጠባበቁ ለስራ መነሳት አስፈላጊ ነው" ብሎ ሶራ ትንሽ አሰብ አደረገና፡-

“ይህችን ሃገር ግን አቅጣጫዋ ወዴት ይሆን የሚለውን ለመመለስ ይከብዳል፤ ወደ ተፈጥሯዊ ሕይወት ወይንስ ወደ ዘመናዊ ኑሮን ሔ? ይህ ሃሳብ በህዝቡ ሲመለስ ህዝቡ ያሰበው ጋ ለመድረስ
መጣጣር ይጀምራል፡ አሁን ግን ያለው ነገር ዝብርቅርቁ የወጣ ነው እስኪ አስበው ጉዟችን እውነት ወዴት ነው? አለና ሃሳቡን ገቶ ከሎን አየው: ሁለቱም ጆሮ ላይ የሚያላዝን ውሻ ጩኸት
የመሰለ ኦምቧረቀ።

“ግን አንድ እውነት አለ፡ አንድ ወቅት የቀደምናቸው
አገሮች አሁን ጥለውን ተፈትልከዋል። እነሱ  ዘንድ ለመድረስ ቀጥሎም ለማለፍ በእልህ የታገዘ ጥረት ያስፈልጋል! ከኋላችን
ተነስተው አሁን ከፊት የሚገኙት ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑን ይገባል::
መላና ዘዴ ሳንቀይስ፤ የምንነሳበትንና የምንደርስበትን... ሳናውቅ ግን በለመድናት ጠባብ ጎዳና እንጓዝ ካልን አንዱ መሄጃችን ላይ ገብቶ
ሲሰነቀር ሌላው እንደተለመደው ቆሞ ይቀራል። ለዚህ ሁሉ ግን
ከየት እንጀምር?'' አለ ሶራ ጥያቄ እያቀረበ መልሱን ራሱ ለመመለስ።

“ከራሳችን ከራሳችን መጀመር አለብን" በስሜት ያቀረበው ሃሳብ እንደ ጦር ጎኑን ወጋው። ባዶ ምኞት ወይንስ በተግባር የሚውል ህልም... ፍቅሯ ልቡን እንደ ክትፎ የበላበት ኮንችትስ?
ከሎና ሶራ አንዱ ሌላውን ይበልጥ ለማወቅ፤ ተረዳድተው የአገራቸው አለኝታ ለመሆን ህሊናቸው ቋምጧል: የውጪ ዓለም
ልምዳቸው በራስ መተማመናቸውን ብትንትኑን ቢያወጣቸውም ማንነታቸውን ግን እንደ መስታዋት ቁልጭ አድርጎ አሳይቷቸዋል።
በዚህ የአድቬንቼር ዘመን በትርኪ ምርኪው የግደለሽነት ሕይወት መኖር እንደ አበቅ አንጓሉ አንጓሉ የሐፍረት ቆሻሻ ላይ
እንደሚጥል ተረድተዋል ከሌላው መማር እንጂ እንደ ተውሳክ ጥገኛ መሆን አይንን ጨፍኖ መለመን... በቁም ከመሞት በሞራል
ከመላሸቅ በቀር የሚያመጣው ህሊናዊ ጥጋብ አለመኖሩን ከሕይወት ገጠመኞቻቸው አንፃር አንስተው ብዙ ጊዜ ተጨዋውተዋል::

በህዳሩ የመኸር ወቅት ጨረቃ እንደ ቡሄ ዳቦ ክብ ሆና ገና የብርሃን ወጋገኗን በኒያንጋቶም ተራሮች ወደ ኩዩጉ መንደር ወደ
ኩችሩ ስትፈነጥቅ ከሎና ሶራ እንደተለመደው ሃሳብ ሲለዋወጡ እንደ ቆዩ በመካከላቸው ዝምታ ሰፈነና በእዝነ ሊናቸው ሰማዩ ላይ ጎላ ብሎ የተፃፈ ነገር ተመለከቱ ያን ፅሑፍ ሁለቱም ቀና ብለው አዩት።

“የህይወት ጀልባ ከማዕበል ጋር እየታገለች በውቅያኖሶች ጉያ
አካሏን ነክራ ትንሳፈፋለች ሞት ችግር መከራ ... ያደፍቋታል፤ ደስታ እርካታ ፍቅር. እንደ እንዝርት እያሾሩ ይፈትሏታል እና ጀልባዋ በሁለቱ እጣ ፈንታ ሚዛኗን ጠብቃı የተኙትን የሚስሩት
እየረጋገጧቸው ትሰሩለች:

“በእርገጥ የጎደለው ይተካል ያጣው ያገኛል! ያፈቀረ ይጠላል! የተለጣለ ያነሳል፤የሄደ ይመጣል... በተቃራኒዎች የተወጠረችው ጀልባ የሚፈራረቁባትን ችላ ትጓዛለች።

“አቅጣጫዋ መነሻ መድረሻዋ አይታወቅም:: ጀልባዋ አልቆላታል ትባል እንጂ ከጉዞዋ ከቶ ተገታ አታውቅም: አንድ ቀን
ግን ሥቃይና ሰቆቃ፤ እብሪትና ግፍ የበዛባት ጀልባ ብልሽት
ይገጥማት ይሆናል ያኔ ተሳፋሪዎችዋን ይዛ ትዘቅጣለች  ቁልቁል!
“እሪታ ሰማዩን ያቀልጠዋል የቀስተ ዳመና ቀለሞች በሺ
ተባዝተው ሰማዩን ያስውቡታል ከዋክብት ከነበሩበት በታች ዝቅ
ብለው ብርሃናቸውን ያንተገትጋሉ ገነትና መንግሥተ ሰማያት
ይጣመራሉ።

“ሟቹ ያን ውብ ሰማይ ርቆት ሲሄድ እማይጠገብ
ይሆንበታል! ጀልባዋ ስትዘቅጥ ተስፋ የቆረጠ ያለቅሳል... ሰሚና
ጯሂ እንዲሆ በአንድ ጀልባ ሆነው ዋይ ዋይ' ሲሉ ስቃይ እንደ ቅርጫት ላያቸው ላይ ሲከደንባቸው ይወርዳል።

“በዚያ ሰዓት ቅድስት ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ ሰማይ ትዘረጋለች አምላኳም ድምጿን ሰምቶ ህዝቧን ስለ ስንፍናው አምርሮ ይገስፀዋል።

“እጆቻችሁ ስለምን ሽባ ሆኑ! ስለምንስ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅን መረጣችሁ... ሆድ ብቻ. ጥቅምን ማነፍነፍ ብቻ... ብሎ አዝኖ ውቅያኖሱን ሜዳ ያደርገዋል ድህነትም በምድር ይወርዳል….ልብ ያለው ልብ ይበል" ይላል ሶራና ከሎ አይናቸውን ጨፍነው ያነበቡት።

በጥቁር የሰማይ ሰሌዳ የተፃፈውን ታምር 'ሁለቱም
እየደጋገሙ አነበቡት:
እንግዳው አጋጣሚ
አስገረማቸው አስፈራቸው ... ያ አጉራሽ የለመደው ህሊናቸው ግን ትርጉሙን በጊዜው ሊያቀርብላቸው አልቻለም።

“የምን ጽሑፍ ነው?... ማንስ ፃፈው?...በየግል የፍች "ቀመሩን ለማግኘት ዳንኪራ ረጋጭ ህሊናቸውን አስጨፈሩት። አንዱ
ለሌላው ያየውን ሚስጥር ግን አላወጣም።

ችግርን ለመናድ ማነስ የሚያመጣውን የአዕምሮ ሰንካላነት ለማስቀረት በራስ የመተማመንን ተፈጥሯዊ ፀጋ ጠብቆ ልጅ የልጅ
ልጆችን ከሃፍረት ለማዳን ሆዳምነትን አስወግዶ በእጅና አዕምሮ መጠቀም... ጀልባዋ ሳትሰጥም ደካማ ጎንን ማስተካከል እንደሚገባ
ዘግይተውም ቢሆን የተረዱ ይመስላል።

በዚያች ሰዓት ከሎና ሶራ ተያዩ! ኤርቦሬና ሐመሩ
ሁለቱ አፍሪካውያን ሊግባቡ
ሞከሩ! ሃይላቸውን ለማስተባበር ተቃቀፉደ
ፍቅራቸው ስህተታቸው ቁጭታቸው... ያስፈነደቃት ጨረቃም አላማቸውን ለማጠንhር ብርሃኗን እያሰፋች ፍጥነቷን በመጨር ጥቁሩን ሰማይ እየገለጠች ወደ እነሱ ገሠገሠች።

ከዚያ ያ ኩሩው ድፍርሱ ሚሊዮን ነፍሳትን በውስጡ
አጭቆ ቁልቁል ይሁን ሽቅብ መፍሰሱ ሳይታወቅ በፀጥታ የሚጓዘው ኦሞ ወንዝ በቁጭት አፍ አውጥቶ ሲናገር! እንደ ውሻ ሲጮህ ተሰማ።

"ኢትዮጵያ ፈላስፎቿን ተመራማሪዎቿን የንብ ተምሳሌት ታታሪ ምሁሮቿን, ማቀፍ እርስ በርሳቸው በጡንቻ ሳይሆን
👍18👏1🤔1
በአዕምሮ በምላስ ሳይሆን በሥራ ማታገል አለባት፡ዠ ሥራ ባህሉ የሆነው ህዝብ የሚመክረው የሚመራው ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ
ልማትን ለማምጣት መቻቻል ያስፈልጋል፡ ከዚያ ይህች የጥቁር ምድር የልጆችዋን አዕምሮ ተመርኩዛ ሽቅብ ከፍ ትላለች፤ የመርፌ ማምረቻዎች
ይመሰረታሉ….. ያኔ ሁላችንም ከሃፍረት
ነፃ እንሆናለን... እንደ ፋሲካ ሙክት አህጉራችንን ሊያርዷት የሚያደልቧትን እንነቃባቸዋለን.. ስንፍና መናቆር ይብቃን! ኦሞ እንደ ማርቲን ሉተርኪንግ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ! ተራሮች እንደ ተቆጣ አንበሳ አገሱ፧ ምድሪቱ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፤ ማንዴላ! ያ የአፍሪካ የበኩር ልጅ የማሳረጊያውን ድምፅ ጮክ ብሎ አሰማ፡

“...ቂም በቀል በእኛ ዘመን ይቁም፤ አምላክ አፍሪካን
ይባርክ! አለ። አፍሪካም የአትላንቲክ የህንድ ውቅያኖሶች ፤የሜዲትራንያን ባህር. ማዕበል እያደፈቃት የአንድዬ ልጅዋን ድምፅ
እንደ ገደል ማሚቶ ከጫፍ ጫፍ አስተጋባችለት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የኩችሩ መንደር የጨረቃ ዳንስ ደርቷል። ጭብጨባው ዝማሬው. ሽቅብ እየጎነ ከሰማይ ይጋጫል! ከተራሮች ደረት ጋር ይላተማል፤ በየሰዉ የደም ስር ይስለከለካል ... በድሪያ የጣፈጠው
የምሽት ዳንስ የተፈጥሮ ህይወት ኗሪ ወጣቶችን ያስፈነድቃል።

ፈገግታ ዝማሬ ድሪያ እንደ
ሰነፍ ቆሎ ታሽተው
የሚያወጡትን
የፍቅር ፍሬ ወጣቶቹ ይቅማሉ፤ ልጃገረዶች
ጎረምሶች ያን የማይጠገብ ማዕድ ከበው እየበሉ ያበላሉ እየሰጡ
ይወስዳሉ እየነኩ ይነካሉ… እያረኩ ይረካሉ። በዚህ መሃል ካርለት ጀግናዋን ፈለገችው ! ደልቲስ?' ጠየቀች ራሷን። የት ሄዶ ይሆን?' ስለ ሐመሩ
ቀብራራ አሰበች: ዝምታው ናፈቃት፤ ዝምታው ውስጥ ያለውን ወንድነት ፍቅር ናፍቆት በሰመመን አመነዥከችው:: የደልቲ ዝምታ ፍላጎቱን የሚያሳይ መስታዋት ነው። እርጋታው ሽፋን ነው ውጫዊ ቆዳ፤ ውስጡ ግን በያቅጣጫው እየፈለቀ የሚንዶሉዶል
የፍቅር ስሜት አለ የሚሞቅ የሚስብ ሲገጭ እያመመ ደስታን የሚፈጥር አካልን ዘረጋግቶ ሲወጥር የሚያረካ….

ካርለት ከዳንሱ ቦታ ራቅ ብላ ጀግናዋን በአይኖቿ
ስትፈልገው በጆሮዋ ስልምልም የሚያደርግ የሙዚቃ ቃና ሰማች።
እንግዳ ነው ያ ሙዚቃ ለጆሮዋ! ሳባት ሙዚቃው
ተጎተተችለት: ቃናው ጆሮዋን እየላሳት ወደ ውስጧ ዘለቀ የህሊናዋን ጓዳ! የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው። አሻት፤ ዳሰሳት…..እሷም
አንኳኳ የሆሊናዋን ጓዳ የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው አሻት፤ ዳሰሳት
ሁለመናዋን ነካካው
አንሸራተታት ደመቅ
ደመቅመቅ... የሚለው ዜማ ፍል ውኃ ውስጥ እንደገባች ሁሉ ቁልቁል እየፈሰሰ ሰውነቷን አጋላት ደስ አላት ሰውነቷ ሲግል‥. ጡቶችዋ ግን ተቆጥተው ቆሙ፤ ዳሌዋ አኩሩፎ አበጠ ፤ ጭኗ አዝኖ ለሰለሰ… ሙዚቃና ልብ ወለድ ጽሑፍ ካለ እሳት ሰውነቷን ሲያጋግሉት ደስ ይላታል... የረሳችው ስሜት
ፈረሰኛው አረፋ እንደሚያስደፍቀው ወራጅ ወንዝ ሞተሯን አሽከረከረው፤ አቃሰተች ያኔም ስርቅርቁ ዜማ በጆሮዋ መግባቱን
አላቆመም

እየቀረበች ስትሄድ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ወይሳውን እየነፋ ጥዑም ዜማ የሚያወጣውን ጀግና አየችው። የሙዚቃው
ቅላፄ እንደ “ቤቶሆቨን ሞዛርት ሲንፎኒ" ቃናው እየቆዬ ጣማት።እሰይ እሱ ነው ብላ አጉተመተመች...

💫ይቀጥላል💫
👍242
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ዘጠኝ)
(ሜሪ ፈለቀ)

እንዲህ ነው የሚመስለኝ :- የራሴን ህይወት ራሴው ኖሬው እና ሌላ ሰው ሆኜ ደግሞ ከውጪ ሳየው!! ራሴን ሌላ ሰው ሆኜ ባየው ምን አይነት ሰው ነኝ ብሎ አስቦ የሚያውቅ ሰው ይኖራል? እድሉ ተሰጥቶትስ ራሱን ከውጪ ቢያየው ስንት ሰው ራሱን ይወደዋል? ወይስ ይፀየፈዋል?

እንግዲህ መታደል ይሁን መረገም እኔ የደረሰኝ ይህ እጣ ነው!! እንደ ሌላ ሰው ከውጪ ያየኋትን የድሮዋን ሜላት ድጋሚ መኖር ወይም ሌላ ሜላትን መፍጠር ደግሞ ከፊቴ ያሉ ምርጫዎች ናቸው። ሁለቱም አስፈሪ ምርጫ ነው!!!

በደም በተለወሰ ልብሴ ደሙ እጅና ፊቴ ላይ ደርቆ የሆስፒታሉ መጠበቂያ ቦታ ለሰዓታት ከአንዱ ቦታ ወደሌላው እንደፌንጣ እየዘለልኩ ነው ይሄን የማስበው። ስንት ሰዓት እንደጠበቅን ከማላውቀው ጊዜ በኋላ ከዛ ውጥንቅጥ ቦታ ይዞን የመጣው የጎንጥ ወዳጅ ወንበሩ ላይ ከነበረው ሰውነት በግማሽ ያነሰ መስሎ ተኮራምቶ እንደተቀመጠ

«መታጠቢያ እኮ አለ ቢያንስ ደሙን ከሰውነትሽ ታጠቢ!! ወይ መቀየሪያ ልብስ ላምጣልሽ?» ያለኝ እሱም እንደእኔ ሰውነቱ በደም መቅለሙን ሳያውቀው ይሆን እንጃ!! <አንተምኮ ደም ብቻ ነህ!> ማለት እፈልጋለሁ ግን አፌ ተለጉሟል። አውልቄ የጎንጥን ደም ለማስቆም ቁስሉ ላይ ይዤው የነበረውን ሹራቤን ይዞት ነው የተቀመጠው። - የኪዳን መልዕክት!! ዘልዬ ተነስቼ ሹራቡን ስወስድበት ብርግግ ብሎ አፈጠጠብኝ!!

«ሜል ይቅርታ እሺ!! ብዙ የምፅፍበት ጊዜ እና ሁኔታ ላይ አይደለሁም!! ማስታወስ እንደማትችዪ ሲያወሩ ሰምቻለሁ። ነገሮችን ስገጣጥማቸው ገባኝ!! እመቤትን እመኛት!! ያለችሽ ብቸኛ ጓደኛ እሷ ብቻ ናት!! ሌላው እኔ ማን እንደሆነች ብዙ ያልገባኝ አምነሽ ቪዲዮዎቹን ኮፒ ያስቀመጥሽባት ሴት አሁን ከእነርሱ ጋር ናት!! በቢዲዮዎቹ እየተደራደረች ነው!! እንዳታምኛት!! ታውቂ የለ እወድሽ የለ?»

«ይህቺ ከንቱ!» አልኩኝ ሳላስበው!! ወትሮም ጓደኛዬ አይደለችም!! ጥቅም ነው ያገናኘን!! እኔ ለጥቅሟ የምደምርላት ነገር እንደሌለ ባወቀች ቅፅበት ልትቀብራቸው ጉድጓድ ስትምስ የኖረችባቸው ሰዎች ጋር ሌላ የጥቅም ወጥመድ የዘረጋችበት ፍጥነት ……. ድሮም ትርፍ ካገኘችበት የገዛ ባሏን ከመሸጥ የማትመለስ ነጋዴ መሆኗን አውቃለሁ። የከንቲባው ሚስት ናት!! ባሏ ከንቲባ ከመሆኑ በፊት ከደሳለኝ (ኪዳንን ያገተው ሰውዬ) ጋር ወዳጃሞች ነበሩ!! ለአንድ ቦታ ለመመረጥ ፉክክር እስከጀመሩባት ጊዜ አንዳቸው ከሌላቸው ቤት የማይጠፉ፣ ልጆቻቸው እንደእህትና ወንድም የተቋለፉ ፣ ሚስቶቻቸው ከፀጉር ቤት እስከ ትልልቅ የህዝብ መድረክ ተቆላልፈው የሚተያዩ ዓይነት ነበሩ። ከንቲባው ሞተሩ ሚስቱ ናት እንደፈለገች በቀን ሙዷ የምታሾረው እንጂ የዋህ ቢጤ ነው። ደሳለኝ በገዛ ፍቃዱ ከውድድሩ ራሱን እንዲያገል ያን መረጃ ከእኔ ጋር በልዋጭ ጥቅም ተደራድራ ነው!! ተማምነን አይደለም የጠላቴ ጠላት በሚለው ተወዳጅተን እንጂ!! እከኪልኝ ልከክልሽ ተባብለን ነገር ……. እኔ አደጋ ላይ ብወድቅ እሷጋ ያለው ቅጂ ማስያዣ እንዲሆን ፤ እሷ አደጋ ላይ ብትወድቅ እኔ ጋር ያለው ቅጂ መገበያያ እንዲሆን ነበር ውላችን!! ድንገት በአንድ ቀን ጀንበር ያለድካም የተገነባ መተማመንም አልነበረም!! ከአንዲት 10 ሺህ ህዝብ ከሚኖርባት መንደር ወጥቼ ስልጣኑና አቅሙ አለን ከሚሉት ወንበዴዎች ጋር ለመግባት ለመውጣትስ የተጓዝኩት ጉዞ ቢሆን በቀላል ድካምና ላብ የተገነባ መች ነበር?

«የአቶ ጎንጥ ቤተሰቦች?»

ዘልዬ ተነሳሁ!! ዶክተሩ ከማውራቱ በፊት ነገረ አካላቴን በሀዘኔታ እያየ ነው ቀዶ ጥገናውን በስኬት መጨረሱን የነገረን።

«እስኪነቃ ድረስ እቤት ሄደሽ ተጣጥበሽ ልብስሽን ቀይረሽ መምጣት ትችያለሽ!!» አለኝ የጎንጥ ወዳጅ!! አልሄድኩም!! ተናኜጋ ደውዬ የምቀይረው ልብስ እንድታመጣልኝ አደረግኩ። ስልኩን ስዘጋ ተናኜ መርሳቴን አስታክካ የተቀበለችውን ደሞዝ ድጋሚ እንደተቀበለችኝ አስታውሼ ፈገግ አልኩ። የጎንጥን መመታት ስነግራት ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቷስ? የአባቷን ለቅሶ የተረዳች አስመስላ አረፈችው። ልብሴን ቀያይሬ እንድትረጋጋ ላሳያት የተኛበት ክፍል ይዣት ብገባ ተኝቶ ስታየው ያን ለቅሶዋን አመጣችው። የልብሷን አንገትጌ በእጇ ጨምድዳ ይዛ ወደአፏ አስገብታ ንክስ አድርጋ…… <ህእእ > እያለች ሳጎን ወደ ውስጥ እየሳበች ተነፋረቀች።

«ምን ልሁን ነው ምትይ?» ሲል ነው መንቃቱን ያየነው። ይሄኔ ግራ የገባው ስሜት ተሰማኝ። የሆነኛው ልቤ (የሁለት ወሯ ሜላት ልብ ይመስለኛል) ስለነቃልኝ መፈንጠዝ ፣ አጠገቡ ሄጄ መነካካት ያምረዋል። የሆነኛው ልቤ (የድሮዋ ሜላት ልብ ይመስለኛል) ቆጠብ ማለት ፣ ኮስተር ማለት ያምረዋል። አጠገቡ ደረስኩ ግን እጁን ሊይዘው የተዘረጋ እጄ መንገድ እንደሳተ ነገር የአልጋውን ጫፍ ጨበጠ። ቅድም ሁለት ምርጫ አለኝ አላልኳችሁም? ወይ አሮጌዋን መሆን ወይ አዲስ መሆን? ሁለቱንም መሆን እንደማልችል እዚህ ጋር ገባኝ!! ቢያንስ በጎንጥ ጉዳይ!! ልቤ እና ሰውነቴ እንዳልተስማሙ ገብቶታል መሰለኝ ተናኜም ወዳጁም እግራቸው እንደወጣ ጠብቆ

«ተቀይመሽኝ ነው እንዴ?» ሲለኝ እስካሁን ስለማንነቱ፣ ስለዋሸኝ ዘበኝነቱ …… ተያያዥ ነገር ጭራሽ አለማሰቤ ገረመኝ። እዛ መኪናው ጋር ራሱን ከፊቴ አድርጎ የእኔን ሞት የተጋፈጠልኝ ሰዓት መቀየሜን ተውኩት? እዛጋ የበደለኝን አጣፋሁት?

«ቅያሜ አይደለም ያለኝ ጥያቄ ነው» አልኩት። ፈገግ ብሎ <ጠይቂኝ> እንደማለት በእጁ ወዲህ በይው ዓይነት ምልክት ሰራ። ወንበሩን ስቤ ከፊቱ እየተቀመጥኩ። <እዝህችው ቆመን 19 መቶ ብዬ እንዳወጋሽ አይደለማ ሀሳብሽ?> ብሎ የጮኸብኝ ትዝ ብሎኝ

«ገና ከመንቃትህ 19 መቶ ዓመተምህረት ብለህ ልታወጋኝ አይደለምኣ ሀሳብህ? (ፈገግ አለ) አንተ ጥለኸኝ የመጥፋት ሀሳቡ ከሌለህ በቀር እኔ የትም አልሄድም ያንተ እና የእኔ ጉዳይ ይደርሳል። ኪዳንን ጭረት ሳይነካው ዛሬውኑ ከዛ ቤት እንዲወጣልኝ ማድረግ አለብኝ።» አልኩት።

******

ልጅነቴ አጎቴ እንዳለው በጀግንነት እና ጀብድ ብቻ የተሞላ አልነበረም። ያ እነሱን ሆነው ሲያዩት የገባቻቸው ሜላት ናት። አባቴ የሞተበት ቦታ እየሄድኩ ሬሳው የነበረበት ቦታ ተቀምጬ በለቅሶ የምደነዝዝባቸውን የትዬለሌ ሰዓታት እሱ አያውቅም!! እናቴን የደፈራት ሰውዬ ፊት ለዓመታት በህልሜ እኔኑ ሲደፍረኝ እያየሁ በላብ ተጠምቄ ስንቀጠቀጥ የነጉትን ቁጥር አልባ ለሊቶች እሱ አያውቅም። ከሞቱ በፊት የነበረው የአባቴ ፊት ጠፍቶብኝ አባቴን ሳስብ የማስታውሰው የዛን ቀን ያየሁትን ፊቱን እየሆነብኝ ተሰቃይቼ ፎቶውን አቅፌ ማደሬን አያውቅም!! እናቴ ተመልሳ ትመጣ ይሆናል ብዬ ስንት ቀን እንደጠበቅኩ አያውቅም። አባቴን የገደሉብኝን ሰዎች ኮቲያቸውን ልኬት ሳይቀር በጭንቅላቴ ውስጥ ስዬ እንዳስቀመጥኩ አያውቅም!! ብዙ አያውቅም !! ብዙውን አልተናገርኩም!!
👍364🔥1👏1
የማይቆጠር ጊዜ ቀዬውን ጥዬ ልሄድ አስቤ አውቃለሁ። አንድ ቀን ኪዳን ከትምህርት ቤት ሲመጣ እኔ እቤት አልነበርኩም!! እያለቀሰ ስሜን እየተጣራ ሲፈልገኝ አገኘሁት
«ምን ያስለቅስሃል? ማን መታህ?» ነበር እንዳየሁት ያልኩት
«እ እ…. አንቺም እንደእማዬ ትተሽኝ አትሂጂ !! እንደአባዬ አትሙቺብኝ!» ብሎ ሲንሰቀሰቅ መቼም እንደማልተወው ለራሴ ቃል ገባሁ። በጊዜው እኔ ራሱ የሚያባብለኝ የሚያስፈልገኝ እንጭጭ ብሆንም ከእድሜዬ በላይ ሀላፊነትን ለራሴ ሰጠሁት። ከዛ በኋላ ነው ትምህርት ቤት ራሴ አድርሼ እመልሰው የጀመርኩት። ሁሌ ለሊት ተኝቶ ሲነቃ መጀመሪያ የሚያረጋግጠው የእኔን አልጋዬ ላይ መኖር ነው። ድንገት ቀድሜው ተነስቼ ካጣኝ በማጣት ሰቀቀን ሲፈልገኝ አገኘዋለሁ። የትም ጥየው እንደማልሄድ እንዲያምነኝ ብዙ ለሊት አቅፌው ካደርኩ በኋላ ነው ያመነኝ። የአባቴን ገዳዮች ከጠላኋቸው በላይ ጠላኋቸው።

በሽምግልና የታረቁ ጊዜ የተሰማኝ አጎቴ እንዳለው ቁጣ ብቻ አይደለም። መከዳት ነው የተሰማኝ!! የራሴን ወገኖችም ነው የተቀየምኩት። የእኔ እና የኪዳን ህመም ያላመማቸው ፣ እኔን አግልለው እነሱ የደስታ ጠቦት ጥለው የተቃቀፉ ……

አልገባቸውም!! አድጋ የአባቷን ደም ትበቀላለች ብለው ያጀገኑት ልቤ ውስጥ የበቀል ጥንስሴን እርሾ አድርገውበት ልቤ ልትፈነዳ እንደደረሰች። አልገባቸውም እሷማ ይሄን መንደር ታስከብራለች እያሉ ባሽሞነሙኑኝ ቃላት በጭንቅላቴ ውስጥ ያሉ ሌሎች የሰው ልጅ የመኖር መሰረታዊ ፍላጎቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ በበቀል እንደተካሁ። አይዞሽ፣ በርቺ ብለው እጄን ይዘው ከድልድዩ ካደረሱኝ በኋላ እነርሱ ከጠላቶቼ ጋር ተመሳጥረው ቺርስ የተባባሉብኝ ዓይነት ስሜት ነው የተሰማኝ።

የአባቴ ገዳዮች ላደረጉት ነገር ሊቀጡ ሲገባቸው ግፋቸው ጭራሽ ክብር ሆኗቸው ስልጣን ሲሾማቸው የእኔው ወገን ሲያጨበጭብላቸው ብቸኝነት አጥንቴን ሰረሰረኝ። ብቻዬን የቀረሁ። ያውም ከነበቀል ጥማቴ!!

ባገኘሁት ሰው ላይ ሁሉ ከመደንፋት እና ከመደባደብ ውጪ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ስላላወቅኩ የማደርገው ጠፍቶኝ ሳለ ነበር አንድ ቀን ለክረምት ለክረምት አዲስ አበባ የሚሄደው ካራቴ አሰልጣኛችን በጉራ ሰውመሆንና የእሱ ቤተሰቦች አዲስ አበባ የሚጠያየቁ ወዳጃሞች መሆናቸውን ሲያወራ የሰማሁት ……. የዛን ቀን እንቅልፍ አልወሰደኝም!!! ከብዙ ጊዜ በኋላ የበቀል እቅዴን የማሳከበት መንገድ ጭላንጭል የታየኝ ስለመሰለኝ ሳቅኩኝ።

አዲስ አበባ መሄድ የሚለውን ሳስብ ደግሞ ከዚህ መንደር መራቅን አብዝቼ ሻትኩ። አዲስ ህይወት መጀመር የሚል ሀሳብ ልቤን በሀሴት ሞላው። አዲስ ያልኩት ህይወት መሰረቱ በቀል መሆኑ ካለፈው ህይወት ጋር እያመላለሰ እንደሚያላትመኝ የምረዳበት የአዕምሮ ብስለት አልነበረኝም!! ጭራሽም ከበቀል እና ከጥላቻ የተረፈ አዕምሮም አልነበረኝም!! የሚጠረጥርበት ምንም ፍንጭ ያልነበረው አሰልጣኝ አዲስአበባ ለክረምት መሄድ ማሰቤን እና ከተማውን እንዲያስለምደኝ ስጠይቀው ደስ ብሎት ነው የተስማማልኝ። ሰዎችን መጠቀሚያ ማድረግ የጀመርኩበት የመጀመሪያ ቀን መሆኑ ነው። ደሜ ውስጥ ከሚንቀለቀል በቀል ውጪ የሚሰማኝ የህሊና ደውል ስላልነበረ ያደረግኩት ብልጠት እንጂ ክፉት አልነበረም!! እንድደውልለት ስልክ ፅፎ ሰጠኝ።

«ኪዳንዬ ለሆነ ጉዳይ አዲስአበባ ደርሼ እመጣለሁ። ከዛ ግን መጥቼ እወስድህና አብረን እንኖራለን» አልኩት በራችን ላይ ቆሜ እሱ ከትምህርት ቤት መጥቶ እግሩን እየታጠበ ነበር። ያሰብኩት የነበረው ብቻዬን ሄጄ ከሸክም ጀምሮ ምንም ብሰራ ፣ ከዛ የተወሰነ ፍራንክ አጠራቅምና ኪዳንን አዲስ አበባ አምጥቼ አስተምረዋለሁ። ነው። የያዘውን ጆክ በቁሙ ለቀቀው እና እኔጋ መጥቶ እግሬ ላይ ተጠመጠመ። 15 ዓመቱ ነበር። ሁለቱንም እግሬን እንዳልፈናፈን አንድ ላይ ጨምቆ ይዞ

«የትም ትቼህ አልሄድም! ብለሽኝ አልነበር? ለምንድነው ይዘሽኝ የማትሄጂው? በዛው ልትቀሪ ነውኣ? አብሬሽ እሄዳለሁ!!» አለኝ እየጎረመሰ ባለ ድምፁ። አያለቅስም ግን ድምፁ ውስጥ ከለቅሶ የከበደ ሀዘን አለው።

«ኪዳንዬ አሁን ወስጄህ ምን አደርግሃለሁ? የምናድርበት ባይደላን ምን በወጣህ ውጪ ታድራለህ? የምንበላው ባይመቻች በምን እዳህ ትራባለህ? አንተ ገና ልጅ ነህ!! እኔ ይሰናከልብኛል የምለው የለኝም። አንተ ከትምህርትህ ለምን ትሰናከልብኛለህ?»

«ይኸው ትተሽኝ ሄደሽ ላትመለሽ ነው እንዲህ የምትዪኝ» አለ እግሬን ሳይለቅ

«እሺ በቃ ትቼህ አልሄድም!! አብረን እንሄዳለን!» ስል ራሴን ሰማሁት!! እዛው ላይ እንዴትም ብዬ ገንዘብ ማግኘት አለብኝ የሚለውንም አሰብኩ።

አስቤው አቅጄው ተለማምጄው ያደረግኩት ነገር አይደለም። 19 ዓመት እስኪሆነኝ ድረስ መግደልን እንጂ መስረቅን ለዓፍታም አስቤው አላውቅም!! ለመግደል ለራሴ በቂ ምክንያት ስለሰጠሁት ከመግደል ይልቅ መስረቅ ፀያፍ መሆኑን ነው ህሊናዬ የመዘገበው። በዛው ሳምንት ከአጎቴ ጋር እህል ልንሸጥ ትልቁ ገበያ አጅቤው ሄድኩ። አጎቴ እህሉን እያስረከበ አይኔ ተሻግሮ ከብት የሚገበያዩት ጋር ቀላወጠ። ነጋዴው ምን ያህል ከብት ቢሸጥ ነው እጁን ሞልቶ የተረፈ ገንዘብ የያዘው ብዬ እያሰብኩ ጭንቅላቴ ወዲያው ይሄ ሁሉ ብር ቢኖረኝ ኪዳንን ይዤ አዲስ አበባ የምኖረው ህይወት ታየኝ። ሰውየውን አየሁት አየኝ። ራሴን ገሰፅኩ!!

መረኑ ሀሳቤ <ያውም ጠላትሽ ነው> አለኝ። ለምሰራው ከእነርሱ ለባሰ ክፋት እና በቀሌ የምሰጠው ምክንያት ያ ነው። ድክመቴ!! እናት እና አባት ያሳጡኝ ሰዎች ናቸው!! ከሰውየው አይን ተሰውሬ ገበያውን ለቆ ሲወጣ ተከተልኩት። መውጫው ላይ ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ገጥመው ወደቀያቸው የሚወስዳቸውን መንገድ ተያያዙት። አድብቼ ተከተልኳቸው። አስር ወንድ ገጥሜ የማልፈራዋ ሴት እግሬ ተልፈሰፈሰብኝ!! እጄ አላበው!! በጥሻው አልፌ ከፊታቸው ብቅ አልኩ

«ልጎዳችሁ አልፈልግም!! እንደዛ እንዳደርግ አታስገድዱኝ!! ብር ነው የምፈልገው ብራችሁን ብቻ አውጥታችሁ እዚጋ አስቀምጡና ሂዱ!» አልኳቸው። እኔ መሆኔን ሲያውቁ ገና ብርክ ያዛቸው ….. ሽጉጥ መያዜን ሲያዩ በያዙት ሽመል ተስፋ ቆረጡ። አንደኛው ግን ወንድነቱ አነቀው። ሁለቱ ብራቸውን አስቀምጠውት መንገድ ሲጀምሩ እሱ ካልገጠምኩሽ አለ። አልምታህ ብዬ ለመንኩት።

«ግደይኝ» አለ። ቶሎ ካልሄድኩ መንገደኛ መጥቶ ሌላ አምባጓሮ ሊፈጠር እና ፖሊስ ሊመጣ ሆነ። በቆመበት ጉልበቱን ወደጎን ስረግጠው ህመሙ የእኔ ጉልበት እስኪመስለኝ ታወቀኝ። ብሩን አንስቼ ጢሻው ገባሁ። ለዘመናት ያላነባሁትን እንባ እያነባሁ ወደቤት ሮጥኩ። ሰውነትንም ከእንባዬጋ አብሬ አጥቤ ከሰውነቴ አስወጣሁት።

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍4413😱2😢2🥰1😁1
#አኩርፈሻል_መሰል

ግራ እጄን አመመኝ…
ከበረዶ በልጦ ይሄው ቀዘቀዘ
መራመድ አቃተው…
ለእርምጃ ሰነፈ ቀኝ እግሬም ተያዘ
የጎረስኩት ሁሉ…
አልጣፍጥህ አለኝ ጣእም ጣ'ሙን አጣ
የመሬት መንቀጥቀጥ…
የሚያስነሳ ንዝረት አናቴ ላይ ወጣ
ሁሉም ፉርሽ ሆነ
ህዝበ አዳም ተቀጣ ሕዝበ አዳም ተቆጣ
አኩርፈሻል መሰል…

ካልጋዬ ተኝቼ..
የምሰማው ዜማ እንቅልፍ እንዲወስደኝ
የነካውን እንጃ …
ባላሰብኩት ቅጽበት እንቅልፌን ነጠቀኝ
ለሽራፊ ጊዜ…
ዜማው አልዘመመም ቅኝቱ አልፈረሰም
ልክ እንደ ጥንቱ ነው የጎደለው የለም
የሆነው ሆኖ ግን…
እንዳረጀ ወንበር…
የሚንቋቋ ሆኖ ለኔ ይሰማኛል
በጨቀየ መንገድ…
ፍሬን እንደያዘ የመኪና ጎማ
ድምጹ እንደሚረብሽ
ልብስ እንደሚያበላሽ
ሰባት አይነት ዘፈን…
እንደለቀቁበት የገበያ አዳራሽ
እንደ ቆራሌው ድምጽ…
እንደ ልዋጭ ጥሪ እንደ ፍራሽ አዳሽ
እንደ ደፈኑት ቦይ …
እንደ አጥር ምሰሶ እንደ ግንቡ ፍራሽ
እንደ ጉቶ ጥላ…
እንደ ጫካ መንገድ እንደ ነገር ብላሽ
እንደ…እንደ…እንደ…እንደ
እንዲያ ይሰማኛል
አኩርፈሻል መሰል…

የቀየዷት በቅሎ …
የጎፈላ በሬ ያልተገራ ፈረስ
መስኮት የሌለው ዳስ…
በር የሌለው ድንኳን የጨበራ ድግስ
ምስክር የፈራው…
ማህላ የረሳ ሰው ናፋቂ መቅደስ
ከራስ የተጣላ…
ሩሁን የሳተ ጥምጣም የጣለ ቄስ
መምጫው ያልታወቀ…
መሄጃው የጠፋ ከባድ አውሎ ንፋስ
እንዲያ እንዲያ…እንዲያ እንዲያ
እንዲያ ይሰማኛል እንዲያ ይታየኛል
አኩርፈሻል መሰል…

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍394
#እህቴ_በባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ፡፡
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_አንድ
///

ይሄን ታሪክ እንደባዬግራፊ ውሰዱት፡፡ በነገራችን ላይ ባዬግራፊ ማንበብ ደስ ይለኛል፡፡ግለ-ታሪክ በጥልቅ ሳንሱር የተደረገ፤ የተስተካከለ እና የተሞረደ የግለሰብ ፍፅማዊ ታሪክ ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡
ግለ-ታሪክ በተለየ መለኩ  ታዳጊዎችን ለመቅረፅና ሞዴል ኖሯቸው የወደፊቱን ህይወታቸውን  መስመር  እንዲያሲዙትና ጉዞቸውን ከመዝረክረክ፤ እራሳቸውንም ካላአስፈላጊ ውጤት አልባ መስዋዕትነት ለመታደግ  ጥረት እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ግን ያው ሄዶ ሄዶ ህይወታቸው መዝረክረኩ፤ በየሂደቱም ለማይረቡ ነገሮች መሰዋዕትነት መክፈላቸው የማይቀርላቸው የህይወት ዕዳ ነው፡፡ ቢሆንም ጥረታቸው  የመዝረክረክ መጠኑ ላይ ልዩነት ያመጣል፡፡

ሌላው አዎ ግለ-ታሪክ ግለሰቦችን ብራንድና፤ ሪብራንድ የማድረጊያ ውጤታማ ዘዴ ነው፡፡ የማይሰበረው፤ሰውዬው፤የታፋኙ ማስታወሻ፤የበጋው  መብረቅ፤ የህይወቴ ጉዞና የፖለቲካ ህይወቴ  ፤የመንግስቱ ትዝታዎች ፤የመለስ ዜናዊ የህይወትና ትግል ታሪክ ፤ዳኛው ማን ነው?፤ ማማ በሰማይ ወዘተ…..
ቢሆንም ይሄን የእኔ ታሪክ ከእነዚህ ከላይ ከዘረዘርኳቸው ግለ-ታሪኮች የሚለየው ድንግል በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ድንግል ግለ-ታሪክ ግን ምን አይነት ነው? ፡፡ለማለት የፈለኩት ስለባለታሪኩ ከዚህ በፊት በየትኛውም የመገናኛ  ዘዴ ፤በመፅሀፍ፤ በሬዲዬ ሆነ በጋዜጣ  አልሰማችሁም ፤አላነበባችሁም ማለቴ ነው፡፡

ከእኔና በዙሪያዬ ካሉ ጥቂት ሰዎች በስተቀር ማንም የማያውቀኝ ተራ ግለሰብ ነኝ፡፡ያው አናንተም እንደእኔ ተራ ከሆናችሁ ከላይ ከዘረዘርኳቸው ግለ-ታሪኮች ይልቅ የሚመጥናችሁም የሚያስተምራችሁም ይህ የእኔ የተራው ሰው ተራ ታሪክ ነው፡፡ምክንያቱም እኔ ራሴን ብራንድም፤ ሪብራንድም የማድረግ  ዓላማ የለኝም፤ምን ሊረባኝ..?እኔ መተንፈስ ብቻ ነው የምፈልገው፤ እናንተም አድማጭ እንድትሆኑኝ ብቻ ነው የምጠይቀው…በቃ ይሄው ነው፡፡

ከደብረብርሀን ወደአለማያ ዩኒቨርሲቲ ..ከአለማያ ደግሞ ወደአዲስ አበባ ከገባሁ ሁለት አመት ሆነኝ።  የተመረቅኩት በእፅዋት ሳይንስ ሲሆን ስራ ፍለጋ ከአንድ አመት በላይ የኳተንኩት ግን አዲስአበባ ነው። እርግጥ ወደ እድገት ከተማዬ ደብረብርሀን  ተመልሼ ቢሆን ኖሮ በቀላሉ በሁለት እና ሶስት ወር ውስጥ በተማርኩበት ትምህርት የሚገባኝን ወይንም ደግሞ ለጊዜውም ቢሆን የሚያኖረኝን ስራ አገኝ እንደነበረ እርግጠኛ ነኝ፤ግን እኔ ያንን ማድረግ አልቻልኩም… አልችልምም።
ለጊዜው ሰው እንደጉንዳን በሚርመሰመስባት  ፤ የህንፃ ጫካ የተጥለቀለቀባት  አዲስአበባ ምርጫዬ ሆናለች? ለምን? እራሴን ልደብቅባት፡፡ለምን ?ከሚያውቁኝ ዘመድ ወዳጅ አብሮ አደጎቼ መሠወር የምችልባት አስተማማኝ  ዋሻ አድርጌ ስለወሰድኳት።ለምን ?ባላድግባትም እትብቴ የተቀበረባት የትውልድ ከተማዬ ስለሆነች፤ ስለምወዳት፡፡የእኔ አዱ ገነት፤የእኔ ሸገር፡፡

እውነት እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በዚህ ዘመን በኢትዬጵያ ዘመድ ወይም ወገን የምትለው ሰው በዙሪያህ ከሌለ ከዛም አለፍ ብሎ ባለጎሳና ባለ ብሄር ካልሆንክ መኖር የምትችለበት ቦታ እየጠፋ ነው…፡፡እንደእኔ ነጠላና መለመለውን ያለ ግለሰብማ ከሸገር ውጭ ለመኖር መወሰን አይደለም ማሰብ እራሱ አደጋ  ነው፡፡በዚህ ምክንያትም ይመስለኛል ሰዉ ከአራቱም አቅጣጫ በየምክንያቱ ጓዜን ማቄን ሳይል መጥቶ እየተጠቀጠቀባት ይሄው አሁን ሞልታ የሰውን ልጅ እንደ ውሻ ቡችሎች በየጎዳናው እና ስርቻው እያዝረከረከች ያለችው፡
ያው እንደነገርኳችሁ ብቸኛ ነኝ፡፡ ዋናዎቹ ቤተሠቦቼ ማለት እናትና አባቴ በህይወት የሉም።ልጅ ሆኜ ነው በድንገተኛ አደጋ ተያይዘው የሞቱት ።እህትና ወንድምም በፊቱንም የለኝም፡፡ያሳደገችኝ የእናቴ ታናሽ እህት አክስቴ ነች። አክስቴ ከእኔ ውጭ የራሷ ሶስት ልጆች አሏት ፡፡ሶስት ሴቶች  እኔ አራተኛ ልጅ ነኝ።ምን አልባት ብቸኛ ወንድ ልጅ ስለሆንኩ  ወይንም የሙት  ልጅ  ስለሆንኩ አላውቅም  ልክ እንደ ስለት ልጅ በልዩ በእንክብካቤና በሀዘኔታ ነው ያደኩት።

አሁን ግን አድጌ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ከተመረቅኩ በኃላ ከዘመዶቼ በመቆራረጤ አየር ላይ ቀርቼያለሁ፤ወደዛ ቤተሠብ ፊቴን ማዞር የማልችልበት ሁኔታ ውስጥ ከገባው አመታት አልፏኛል።እንዴት? ቤተሠብን አፍርሻለሁ፡፡ እከሌ ከእከሌ ሳይባል ቤተሰቦቼ ምላቸውን የሁሉንም ልብ ሰብሬያለሁ..የዚህ ሁሉ መጥፎ ስራ ውጤት ደግሞ በድምሩ ወደራሴው ተመልሶ ሙሉውን የህይወት ተስፋዬን ደረማምሶ አፍራርሶብኝል፡፡ዓላማ ቢስ …ምንም ተስፋ የሌለው ተንቀሳቃሽ ሬሳ ሆኜያለሁ፡፡ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ ከመነሻ ታሪኩ አንስቶ ተርክላችኋለሁ፡፡
///

እንደነገርኳችሁ እንዲህ ሆናለሁ ወይም እዚህ ቦታ ደርሳለሁ የሚል እንጥፍጣፊ ምኞትና እቅድ ውስጤ የለም…ተስፋዬ ከፈረሰ ቆይቷል.. ቢሆንም ዝም ብሎ  ለመኖር ብቻ ቢሆንም እንኳን መብላት ያስፈልገኛል።ለዛውም በቀን ሁለቴ እና ሶስቴ ። እናም ያንን ለማሟላት ደግሞ በየቀኑ መስራት የግድ ይላል።አዎ ወይ መብላት ማቆም አለብኝ ወይ ደግሞ ስራ መስራትና ገንዘብ መስራት አለብኝ። ግን ምንድነው የምሰራው?ምን ችሎታ ወይም ሞያ አለኝ?ስራ ለመፈለግ ስነሳ ይሄንን ጥያቄ  ነው እራሴን የጠየቅኩት፡፡

ከአለማያ ወደአዲስ አበባ እንደገባው እጄ ላይ አጠራቅሚያት የነበረችውን ጥቂት ሳንቲም እስክታልቅ ስራ በመፈግ በመኳተን አራት ድፍን ወራቶች አሳልፌያለሁ፡፡በስተመጨረሻ ተስፋ ከቆረጥኩና ኪሴ መራቆቱ እርግጥ ከሆነ በኃላ ያገኘሁትን ማንኛውንም ስራ ለመስራት ወሰንኩ፡፡ ,…ለሁለት ወራት በኮንስትራክሽን ድርጅቶች በቀን ስራ ለመስራት ሞክሬ ነበር….ግን በእውነት በጣም ወገብ ቆራጭ ብቻ ሳይሆን ተስፋ አስቆራጭ ስራ  ነው የሆነብኝ…በፊቱኑም የሌለ ተስፋ ሲቆረጥ ይታያችሁ፡፡ዕድሜውን ሙሉ በቤቱ ምንም አይነት የጉልበት ስራ የመስራት ልምድ ለሌለው ሰው ይቅርና ልምድ ላለውም ጉልበተኛ አርማታ መግፋትን መሸከምን የመሰለ ሌላ ፈታኝ  ስራ መኖሩን እጠራጠራለሁ…ምን አልባት የምድር ውስጥ የመአድን ቁፋሮ ሊበልጠው ይችላል፡፡ ስራው እኮ በተለይ ከሰዓት በኃላ ሲሆን ምላስ ታጥፋ ጉሮሮው ውስጥ ነው የምትወተፈው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ለመስራት የሞከርኩት የፓርኪንግ ስራ ነው…፡፡ከቀን ስራው ቢሻልም ገቢው ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም…፡፡ቢሆንም የፓርኪንግ ስራው ወደሌላ ስራ መሸጋገሪያ ድልድይ ሆነኝ….፡፡የፓርኪንግ ስራ የምሰራበት ቦታ በሁለት ቀንም ሆነ በሶስት ቀን እየመጣ ከሚጠቀም ሰው ጋር ቀስ በቀስ ተግባባን፡፡እንዲሁ ያለምክንያት ሲመጣ ደስ ይለኛል....፡፡ከሌላው የተለየ ፈገግታ እና መሽቆጥቆጥ አስተናግደዋለሁ..፡፡እሱም ቲፕ አስጨብጦኝ ይሄዳል፤ሳይመጣ አራት አምስት ቀን ካሳለፈ ቅር ይለኛል፤ለቲፑ አይደለም…እንዲሁ ለመልካምነቱ…፡፡
አንድ ቀን ታዲያ እንደወትሮ መጥቶ ፓርኪንግ ተጠቀሞ ሊሄድ ሂስብ እየተቀባበልን ሳለ ድንገት ወሬ ጀመርን፡፡
‹‹እዬብ እንዴት ነው ስራ?››
‹‹ጋሼ ሰሎሞን  ሰሪው ነው እንጂ ስራ ምን ይሆናል  ብለህ ነው?››አልኩት(ይህቺን ንግግር ከሆነ ጓደኛዬ ነው የሰማሁት)
👍914🥰3😁2👏1🤔1
‹‹አይ እዬብ እውነትህን ነው…ስለ ሰሪውን ነው መጠየቅ፤እሺ ሰሪው እንዴት ነው?››
‹‹ይመስገነው..››በአጭሩ መለስኩለት፡፡
‹‹ምነው? ችግር አለ እንዴ?››
‹አይ የለም..ያው ትንሽ ስራው እዛው ሞላ እዛው ፈላ ነገር ሆነብን እንጂ ሌላው ነገር አሪፍ ነው፡፡››
‹‹አዎ ይገባኛል …ግን ከበረታህ የማይቀየር ነገር የለም፤.ለመሆኑ ትማራለህ?››
‹‹ጋሼ ከረጅም ግዜ በፊት የሰማኋትን አንድ ቀልድ ልንገርህ…  አንዱ ዲያስፖራ ኢትዬጵያ ውስጥ መጣና በየመስሪያ ቤቱ እየዞረ እንዲቀጥሩት ማስረጃውን ይዞ ዞረ ዞረ ሁሉም ቦታ የለንም እያሉ መለሱት ..፡፡ከዛ በቃ ወደመጣሁበት ሀገር መመለስ አለብኝ ብሎ ዝግጅት ጀመረ..‹አንደኛህን አልነበረ እንዴ የመጣኸው ምነው?ለምን ትመለሳለህ ?››ሲሉ ጓደኞቹ ጠየቁት ‹አይ መሮኛል ይህቺ አገር ድሮም ለተማረ ሰው አትሆንም ..ከምድረ አሜሪካ ማስተርስ ድረስ ተምሬና ተመራምሬ  መጥቼ ስራ ተነፈገኝ?›ብሎ አማረረ…ሰዎቹም እውነትም ይህ ሰው ተበድሏል ብለው ቁጭት ውስጥ ገቡና ይበልጥ ለማጣራት ..‹ ለመሆኑ በምን ሞያ ነበር የተመረቅከው.. ?ብለው ይጠይቁታል ‹‹በበረዶ ሸርተቴ›ብሎ እርፍ››
አቤት የሳቁት ሳቅ…እንባቸው እስኪንጠባጠብ ድረስ ነው ሆዳቸውን ይዘው እየተንፈቀፈቀቁ የሳቁት ….ደስ አለኝ፡፡.ቀልድ የሚገባው ሰው ደስ ይለኛል…አዕምሮ ንቁና ፈጣን የሆነ ሰው ነው ለቀልድ ፈጣን ምላሽ የሚሰጠው ብዬ አምናለሁ፡፡
‹‹ቆይ ቆይ ቀልዱ እውነት ይሆን ፈጠራ አስቆኛል..ግን  ከጠየቅኩህ ጋር ምን አገናኘው?››
አላልኳችሁም ሰውዬው ነቄ ነው ፤ ወደዋናው ቁምነገር ጫወታውን አዞረልኝ፡፡
‹‹ጋሼ ሰው እንዳይሰማን  ቀስ ብዬ ልንገሮት.. እኔም  ከአለማያ ዩኒቨርሲቲ በእፅዋት ሳይንስ በዲግሪ ተመርቄያለሁ…እና ስራ ፍለጋ የተሰማራሁት ግን አዲስ አበባ ነው……እና እንደዲያስፖራው ይህቺ ሀገር ድሮም ለተማረ ሰው አትሆንም እያልኩ እራሴን እያፅናናሁ ነው፡፡›.
‹‹እውነትህን ነው?››
‹‹አዎ እውነቴን ነው››
‹‹እንግዲያው…›› አሉና ከጃኬት ኪሳቸው ውስጥ ቢዝነስ ካርዳቸውን አውጥተው እየሰጡኝ…..ቢያንስ ከዚህ ትንሽ የተሻለ ስራ ልሰጥህ የምችል ይመስለኛል፤ነገ ተነገ ወዲያ ሲመችህ ደውልልኝ›› ብለውኝ እንደፈዘዝኩ መኪናቸውን አስነስተው ተፈተለኩ ....ከዛ ያለ ዋስ የለምንም አንጃ ግራንጃ ሁለት ስራ ተሰጠኝ፡፡የመጀመሪያው ስራ አስተናጋጅ ሆኜ እንድሰራ ሲሆን ሁለተኛው ስራ  የሆቴሉን ንብረት መቆጣጠር ነው፡፡የተሰበረ ካለ ማስጠገን፤የጠፋ ካለ  ሪፖርት ማድረግ፤የጎደለ ካለ እንዲገዛ ማድረግ ወዘተ..ለሁለቱም ስራዬ በተናጠል ደሞዝ ይከፈለኛል፡፡በዛ ላይ የአስተናጋጅነት ስራ ከደሞዙ በላይ ቲፑ አስደሳች ነው፡፡....

ይቀጥላል
👍59😁2👏1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ)
(ሜሪ ፈለቀ)

እነዛ ጫማ ያልለበሱ እግሮቻቸው ፣ የከብት ሽታ የሚሸት አዳፋ ልብሳቸው ፣ ያለፉበት መከራ የተፃፈበት የግንባራቸው መስመር ፣ ዘመናቸው ድሎት እንዳልጎበኘው የሚያሳብቁት ሻካራ እጆቻቸው ፣ ብራቸውን ስወስድባቸው እንድራራላቸው የሚለማመጡ ከርታታ ዓይኖቻቸው …….. ከአጠገባቸው ርቄ እንኳን አልራቀኝም!! የስንት ቀን የልጆቻቸው ምሳና እራት ይሆን? ምናልባት የሚያፈስ ቤታቸውን ሊያድሱ ይሆናል! ምናልባት የሚከፍሉት እዳ ይኖርባቸዋል! …… ብዙ ርቄያቸው ከሄድኩ በኋላ በጉልበቴ መሬቱ ላይ ዘጭ አልኩ!! አባቴ <ጀግና አያለቅስም!> ብሎ ቢያሳድገኝም ዛሬ መጀገን አቃተኝ! ለአፍታ ተመልሼ ሄጄ ብሩን ሰጥቻቸው የመምጣት ሀሳብ ሁላ ሽው ብሎብኝ ነበር። ይሄ ምስላቸው ለዓመታት ስቃዬ ነበር። ከበደሉኝ ሰዎች እኩል የበደልኳቸው ሰዎች ፊት እንቅልፍ የማያስተኛ ቅዠቴ ነበር። ለደቂቃዎች እዛው በጉልበቴ ከተንበረከኩበት የመጨረሻዋን አውቶቡስ ተሳፍረን አሁኑኑ ካልወጣን ፖሊሶቹ እኛ ቤት ለመድረስ ምንም የምርመራ ሂደት እንደማይፈጅባቸው ሳስታውስ ተነሳሁ::

እንባዬን ጠራርጌ ሮጥኩ!! ያገኘሁትን የእኔን እና የኪዳንን ልብስ በፔስታል ጨመርኩ። ያለችንን አንድ ለእናቱ ጫማ ተጫምተን ወደመነሃሪያ እጁን ይዤ መሮጥ ጀመርኩ። መነሃርያው አካባቢ ስንደርስ ከኋላዬ ሁለት በእድሜ ጠና ያሉ የኛ አካባቢ የማይመስሉ ሰዎች ሲያወሩ ወሬያቸው ጆሮዬን ጠለፈው።

«የወዲያ ቀዬ ሰዎችን ዛሬ ሽፍታ ዘረፋቸው የሚሉትን ወሬ ሰማህ?»

«ኸረ አልሰማሁም!! ወደየት ግድም?»

«ከገበያው ጫፍ ትንሽ ቢርቁ ነው አሉ!! አንደኛው ይሄ በሬ ሻጩ አያልነህን አታውቀውም?»

«አያልነህ? አያልነህ?»

«ይሄ ሲያወራ ምራቁን እንትፍ የሚለው? ይህ እንኳን ወንድ ወልዳለሁ ብሎ ሲተኛ ስድስት ሴት ያሳደገው? በመጨረሻ ሚስቱ ወንድ ልጅ ሰጥታው እንዴየውም ደግሶ ያበላ ጊዜ አቅልህን እስክትስት ጠጥተሃልይ!!»

«እንዴ? እንዴ? አያልነህ በሬ ሻጩ?»
«ኤድያ እንዴት ያለው እንከፍ ነው? ምን እያልኩት ምን ይላል?»

ፍጥነቴን አቀዝቅዤ ወሬያቸውን ከሰማሁ በኋላ ድጋሚ መፍጠን ጀመርኩ። <አያልነህ> የሚለው ስም ጭንቅላቴ ውስጥ ልክ እንደዛ የአባቴን ሬሳ ተራምዶት እንዳለፈው ሰውዬ ኮቴ ታተመ።

«ሜል? ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው?» ብሎ ኪዳን ዓይን ዓይኔን እያየ ሲቁለጨለጭ ነው እንባዬ እየወረደ መሆኑን ያወቅኩት።

«ምንም አልሆንኩም!!»
«ምንም ሳትሆኚ ታዲያ እንባሽ ይፈሳል? እኔ ይዘሽኝ ካልሄድሽ ብዬ ስላስጨነቅኩሽ ነው?»

«ይሄ ደግሞ! ለምን አርፈህ አትሄድም? እኔ አስጨንቀኸኛል አልኩህ?» እየተነጫነጭኩ እንባዬን ጠርጌ ትኬታችንን ቆርጠን አውቶብስ ውስጥ ገባን!! ከከተማዋ እየወጣሁ በአውቶብሱ መስኮት ወደኋላዬ የሚያልፈውን ተወልጄ ያደግኩበት መንደር ሸኘሁት። ድብልቅልቁ የወጣ ስሜት ተሰማኝ። ትቼው ስሄድ ሀዘን ካጠላበት ጊዜያቶች ይልቅ የታሰበኝ

የአባቴ ትከሻ ላይ እሽኮኮ ተደርጌ ከጫካው እስከ ጠላ ቤት ግርግሩ ስዞር ጠላ ቤት እግሩ ላይ አስቀምጦኝ በሰዓቱ የማይገቡኝን ወሬዎች እየቀደደ ጠላውን ሲጠጣ እናቴ ከሩቅ እየተራገመች መጥታ «ልጅቱን ጭራሽ አምቡላችሁ መሃል ይዘሃት ትመጣ?» ብላ ከእግሩ አንስታኝ የምትሄደው

አባቴ ገበያ መሃል ጠብመንጃውን እንዳነገተ ሲያልፍ አላፊ አግዳሚ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ ከልብ በሆነ አክብሮት ሰላምታ ሲያቀርብለት ትከሻው ላይ ሆኜ የተቆነንኩት

ከወዳጆቹጋ ሰብሰብ ብሎ ዳማ ከሚጫወትበት አብሬያቸው ሳነግስ እማዬ ትመጣና <ልጄን በቃ ወንዲላ አድርገህ ባልም ልታሳጣብኝ ነው!> ብላ ገና በ10 እና በ11 ዓመቴ ሀሳብ የሚገባት የነበረው

አንድ ቀን አባቴ ሽጉጡን አስይዞኝ ስታይ ለቅሶ እንደተረዳች ጭንቅላቷን ይዛ እሪሪሪሪሪሪ ብላ ጮሃ ጎረቤት አሰብስባ «ይሄን ሰው አንድ በሉኝ» እያለች ወገቧን ይዛ የተንጎራደደችው

እናቴ ከምትሸጠው ፍራፍሬ ላይ ከገበያ ስትመለስ ለምድረማቲ ትሰጥና እኛ ቤት ደጅ ላይ የተሰጠንን እየበላን የምንዘለው

ከትምህርት ቤት ስንመለስ ከቤተሰብ ተደብቀን ወንዝ ወርደን እየተንቦጫረቅን ባልተገረዘው ልጅ ወ*ላ ንፍር ብለን የምንስቀው

ክረምት ላይ እማዬ ቡና እያፈላች የተቀቀለ በቆሎ እየጋጥን እጣኑን ስትሞጅረው <አስካል ጥይት ያልገደለኝን ጀግና በጭስ ልትገይኝ ነው ሀሳብሽ?> ሲላት ከተናገረው ውጪ እሷ ምን እንደገባት ሳይገባን እንደመሽኮርመም እያደረጋት <እንደው ወሬ ስታሳምር ቅም!> እያለች ጭሱን በተን በተን ስታደርግለት የነገሩ ውል ምን እንደሆነ ባይገባንም እኔና ኪዳንም አብረናቸው የምንሽኮረመመው

<አስካል ነይ እስኪ ጀርባዬን ዳበስ ዳበስ አድርጊኝ በሞቴ!!> ሁሌም መምጣቷ ላይቀር ጓዳ ሆና <እስኪ ስራ አታስፈታኝ አንተ ሰውዬ> ስትል <ተይዋ ነይማ አምሳሌ!> ይለኛል እንደመጥቀስ እያደረገኝ። እጇን እያደራረቀች እያጉረመረመች መጥታ ትከሻውን ጀርባውን የምታሸው

እንዲህ እንዲህ ዓይነቱን ቀን ነው ያስታወስኩት! አስታውሼም በአውቶብሱ መስኮት የሸኘሁት!! አባቴ የሞተ ቀን ይሄ ሁሉ አብሮ ከአባቴ ጋር የተቀበረ ሳይሆን ልቤ ያን ንፁህ የልጅነት ጊዜም ልብም ዳግም ላላገኘው ልክ የዛን እለት የተሰናበትኩት ያህል አንሰፈሰፈው ……. ሁሉም ነገር ልክ የዛን ቀን የተሰናበትኩት ያህል….. የሚገጥመው አቀበት ታውቆት ነበር መሰለኝ! የአብቶብሱ መቀመጫ ላይ አጠገቤ የተቀመጠውን ኪዳን ጭምቅ አድርጌ አቅፌ
👍213
«አንተ አብረኸኝ ስላለህ ደስ ነው ያለኝ!! የማለቅሰው አጎቴ ስለሚናፍቀኝ ነው!! ሰፈሩ ስለሚናፍቀኝ ነው!! ባንተ አይደለም እሺ!!» እያልኩት ተደጋግፈን እንቅልፍ ወሰደን!!

አዲስ አበባ

አዲስ አበባ <እንኳን ደህና መጣችሁ!> ብላ አልተቀበለችንም!! አውቶብስ ተራ እንደወረድኩ ነው ይሄ ከእኔ ዓለም በምንም የማይገጣጠም ውቅያኖስ እንደሆነ የገባኝ!! አዲስ አበቤዎች ሲያወሩ እንኳን የሚደማመጡ አይመስሉም። ሁሉም ያወራል፣ ሁሉም ይራወጣል፣ የተረጋጋ የለም! የት ሊሄዱ እንደሚቸኩሉ እንጃ ቸኩለው እያወሩ ቸኩለው እየተገጫጩ ይተላለፋሉ። ከራሱ መንገድ ውጪ ማንም በአካባቢው ያለውን አያስተውልም። በጩኸቱ ጆሮዬ ዛለ። ኪዳንን በአንድ እጄ ጥፍንግ አድርጌ ይዤ በሌላ እጄ ልብሳችን ያለበትን ፔስታል ይዤ <አልጋ> የሚሉ ልጆችን ተከትዬ የዛን ቀን የትኋን እራት ሆነን አደርን!! አዲስአበባ ቀማኛው ብዙ ነው ሲሉ ስለሰማሁ ምግብ ልንበላ በገባንበት ሁሉ የማየውን በጥንቃቄ እከታተላለሁ። በሀገሬ ባለፍኩ ባገደምኩበት ሰው የሚጎነበስልኝ ፣ ሁሉ የሚያውቀኝ ነበርኩ:: ….. እዚህ ባዳነት ተሰማኝ። እዚህ ማንም ነኝ!! ከኪዳን ውጪ የሚያነጋግረኝ እንኳን የሌለ ማንም ነኝ!!

በበነጋታው ስልክ መደወያ ቦታ ፈልጌ አሰልጣኙጋ ስልክ ደወልኩ እና ያለንበት መጣ!!! የምንከራየው ቤት እስካገኝ እቤቱ ይወስደኛል መቼም የእግዜር እንግዳ ዝም አይባልም ብዬ ስጠብቅ እሱ እቴ!! የዛኑ ቀን በእጁ በያዛት ስልክ ለደላሎች ደውሎ ቤት እንዲፈልጉ ነግሮልኝ የማላውቅበት ምድረ ገበያ ህዝብ የሚተራመስበት ሰፈር አልጋ አስይዞን ሄደ። አሁን ብቻዬን እንደሆንኩ አወቅኩ!! አባት እና እናቴ የሉም! አጎቴ የለም! አሁን ለኪዳን እነሱን መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ ለካ!!

አንዲት ትንሽዬ የጭቃ ቤት በአስጠኚው በኩል አጊንተን ተከራየን!! የምንተኛበት እና የምናበስልበት ዕቃ ገዛን!! ኑሮ ተጀመረ!! መጀመሪያ አካባቢ መኪና ማጠብ ስራ አገኘሁ። አምስት መኪና በነፃ ካጠብኩ በኋላ ነው የቀጠሩኝ። ሰፈሩን መውጫ መግቢያ ተሽሎክልኬ አወቅኩት። የሆነ ቀን ጠዋት ከኪዳን ጋር ዳቦ በሻያችንን በልተን ከቤት ልወጣ ስል

«ሜል?»
«ወዬ»
«እንዳትቆጭኝ! አልቆጣህም አባባ ይሙት በይ!» አለኝ ከዓመታት በኋላም የሞተውን አባቴን እየገደልን ነው የምንምለው።
«አባባ ይሙት አልቆጣህም ምንድነው?»
«እኔምኮ ትልቅ ልጅ ሆኛለሁ!! ስራ ፈልጌ የማልሰራው ለምንድነው?» አለኝ እንዳልቆጣው እየተሳቀቀ

«አባባ ይሙት እቆጣሃለሁ!! ሁለተኛ እንዲህ እንዳትለኝ!! አንተ አርፈህ ተቀመጥ ከወር በኋላ ትምህርት ሲጀመር ትምህርትህን ወጥረህ ትማራለህ!! ስራህ ትምህርትህ ነው!! ተግባባን?» ብዬ እንደፈራውም ጮህኩበት

«አዎ» ሲለኝ ስቅቅ ብሎ አሳዘነኝ እና አቀፍኩት።

«ላንተ ብዬኮ ነው!! ታውቅ የለ እንደምወድህ? አንተ ተምረህ ስራ ስትይዝ ያኔ አንተ ትሰራለህ እኔ እቤት እቀመጣለሁ!! አሁን ግን እኔ ታላቅህ አይደለሁ? እኔ እሰራለሁ አንተ ትማራለህ!!» ስለው ጭንቅላቱን ነቀነቀ። እናት መሆን ፣ ልጅ ማሳደግ : እናት መቼ እንደምትቆጣ: መች እንደምታባብል : መች እንደምትቀጣ ... ምኑም በቅጡ ሳይገባኝ ለካ እናትም የመሆን ሀላፊነትን ወስጃለሁ።

የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት አንዱ በጉልቤነቱ የሚፈሩት ጥጋበኛ ሴት ሆኜ ከወንዶቹጋ መኪና ማጠቤን ሊያፌዝበት ሞከረ። ያልፈጠረብኝን አይ አለመተዋወቅ ብዬ ታገስኩት። በሌላኛው ቀን መጥቶ ግን ከኋላ ቂጤን ሲመታኝ መታገስ የምችልበት ልብ አጣሁ እና አፍንጫውን አልኩት። በቦታው የነበረው ሁሉ ደንግጦ ብድግ አለ። ልጁ ያልጠበቀው ቡጢ ስለጠጣ መጀመሪያ ተደናግጦ የደማ አፍንጫውን መጠራረግ ጀመረ። ቀጥሎ ግን ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ሊገለግሉት የያዙትን ሁሉ እየተወራጨ ደነፋ!! እኔ በናታችሁ ልቀቁት ስል ፣ እሱ ከወድያ ልቀቁኝ ሲል …. አንድ በአንድ ሰው እየተሰበሰበ የፈሪ ድብድብ ሆነ። ድንገት ለቀቁት እና እኔና እሱ ተያይዝን። ለካስ ሲገላግሉ የነበሩት ልጆች የሸሹት ፖሊሶች መምጣታቸውን አይተው ነው። ፖሊሶቹ ማናችንንም ምንም የጠየቁትም ያጣሩትም የለም! አፋፍሰው ብቻ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱን።

<እባካችሁ ትንሽ ወንድሜ ብቻውን ነው> ብል ማን ይስማኝ? ጀርባዬ ላይ ካሳረፈው ጥቁር ዱላ ህመም በላይ የተሰማኝ የኪዳን ብቻውን በፍርሃት መራድ ነው። ትቼው የጠፋሁ ይመስለዋል? ሊፈልገኝ ወጥቶ መንገድ ይጠፋበት እና የማያውቀው መንደር መንገድ ላይ ሲያለቅስ ታየኝ። ብዙ ክፉ ነገር ታየኝ። ተንዘፈዘፍኩ። ደቂቃ ባለፈ ቁጥር ፍርሃት ከአንጀቴ ይተራመሳል። ሰዓቱ አይሄድም!! ማልቀስ እፈልጋለሁ ግን እንባ አይወጣኝም።

<ጥጋባቸው በርዶላቸዋል> ብለው በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ሲለቁን እግሬ መሮጥ አቅቶት ተንቀጠቀጠ። የቤቱን በር አልፌ ስገባ ኪዳን ባይኖር የት ብዬ ነው የምፈልገው? ራሴን ረገምኩ! ደህና ተደላድሎ ከሚኖርበት ቤት ይዤው የወጣውበትን ቀን ረገምኩ። ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ በሩን ከፍቼ ስገባ ኪዳን ኩርምት ብሎ ፍራሹ ላይ ተቀምጧል። ሲያየኝ ዘሎ እላዬ ላይ ተሰቅሎ እንደህፃን ድምፅ አውጥቶ ማልቀስ ጀመረ። የሱ መርበትበት ይብስ አርበተበተኝ እና አብሬው እዬዬ ማለት ጀመርኩ። እህል ሳይበላ ከአሁን አሁን መጣች ብሎ ኩርምት ብሎ በር በሩን ሲያይ ነው ያደረው።

ፈሪ ሆንኩ! ለኪዳን ስል ፈሪ ሆንኩ!! ለእሱ ስል ብቻዬን ብሆን የማልውጠውን ብዙ መናቅ ዋጥኩ። ለእሱ ስል የማላልፈውን ውርደት አለፍኩ። አንገቴን ደፋሁለት!!! ከብዙ ስራ ቅየራ በኋላ …… ኪዳንም ትምህርቱን ብዙ ቀን ከተማረ በኋላ ….. ብዙ ጥጋበኛ አንገቴን ደፍቼ ካሳለፍኩ በኋላ …..….. በራሴው ሰውንም ከተማውንም መልመድ ከጀመርኩ በኋላ……. የከተማ ሚኒባስ ወያላ ሆኜ እቁብ መጣል ከጀመርኩ በኋላ …… አንድ ቀን ተሰብስበን ተራ የምንጠብቅበት ቦታ ኪዳን መጥቶ ሲፈልገኝ በእድሜ በጣም ከሚበልጠው ልጅ ጋር ነገር ተፈላለጉና ኪዳንን በቁመቱ አንስቶ በጠረባ ጣለው። ደርሼ ልጁን ሳንጠለጥለው ከሚፈላው ደሜ ውጪ የሚሰማኝ ነገር አልነበረም። ምን እንዳደረግኩ አላውቅም!

«ሜል!» ብሎ ኪዳን ሲለምነኝ ነው ጆሮዬ ድምፅ መስማት የቻለው። ፖሊስ ከመቼ መጥቶ ብዬ ስሳቀቅ ግርግሩ ሰክኖ የሆነ ሰውዬ ተጠጋኝ እና

«ስራ ልስጥሽ! እዚህ ከተሳፋሪ ፍራንክ እየለቃቀምሽ ፀሃይ እና ዝናብ እየተፈራረቀብሽ ከምታገኝው እልፍ እጥፍ ደመወዝ የሚከፈልሽ ስራ ላስቀጥርሽ! » አለኝ

«እንዴ ምንድነው ስራው ?» አልኩት

«ደውዪልኝ» ብሎ ስልኩ ያለበት ቢዝነስ ካርድ ሰጥቶኝ ሄደ። ተሰብስቦ የነበረውን ወሬኛ አላስተዋልኩትም ነበር።

«ኸረ በለው! በአንድ ቦክስኮ ስሙን ሁሉ ነው ያስረሳሽው!! መሬት ሲደርስ ኦልሬዲ ቤተሰቡን ዘንግቷል!!» እያሉ ትከሻዬን አቅፈው ማውራት ጀመሩ። ሊያዋራኝ ይኮራ የነበረ ሁላ ጓደኛዬ ሊሆን ሰበብ ይፈልግ ጀመር።

.ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍49
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት 


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ካርለት ከዳንሱ ቦታ ራቅ ብላ ጀግናዋን በአይኖቿ
ስትፈልገው በጆሮዋ ስልምልም የሚያደርግ የሙዚቃ ቃና ሰማች።
እንግዳ ነው ያ ሙዚቃ ለጆሮዋ! ሳባት ሙዚቃው
ተጎተተችለት: ቃናው ጆሮዋን እየላሳት ወደ ውስጧ ዘለቀ የህሊናዋን ጓዳ! የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው። አሻት፤ ዳሰሳት…..እሷም
አንኳኳ የሆሊናዋን ጓዳ የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው አሻት፤ ዳሰሳት
ሁለመናዋን ነካካው
አንሸራተታት ደመቅ
ደመቅመቅ... የሚለው ዜማ ፍል ውኃ ውስጥ እንደገባች ሁሉ ቁልቁል እየፈሰሰ ሰውነቷን አጋላት ደስ አላት ሰውነቷ ሲግል‥. ጡቶችዋ ግን ተቆጥተው ቆሙ፤ ዳሌዋ አኩሩፎ አበጠ ፤ ጭኗ አዝኖ ለሰለሰ… ሙዚቃና ልብ ወለድ ጽሑፍ ካለ እሳት ሰውነቷን ሲያጋግሉት ደስ ይላታል... የረሳችው ስሜት
ፈረሰኛው አረፋ እንደሚያስደፍቀው ወራጅ ወንዝ ሞተሯን አሽከረከረው፤ አቃሰተች ያኔም ስርቅርቁ ዜማ በጆሮዋ መግባቱን
አላቆመም:

እየቀረበች ስትሄድ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ወይሳውን እየነፋ ጥዑም ዜማ የሚያወጣውን ጀግና አየችው። የሙዚቃው
ቅላፄ እንደ “ቤቶሆቨን ሞዛርት ሲንፎኒ" ቃናው እየቆዬ ጣማት።እሰይ እሱ ነው ብላ አጉተመተመች..

ከዚያ ዱካዋን አጥፍታ በሙዚቃው ስልት እርምጃዋን አስተካክላ ተጠጋችው፡
ባለወይሳው አይኖቹ ከጨረቃና ከዋክብቱ ጋር ይጫወታሉ ቅላፄው
ወዲያና ወዲህ ይመላለሳል። ሙዚቃው እንኳን ሌላውን ራሱንም
መስጦታል። እውነተኛ የኪነ ጥበብ ሥራ ውጤት ስቃይና ደስታዋ፤ሐዘንና ትካዜዋ. እፍታውን ቀማሹ ጣዕሙን አስተካካዩና ፈጣሪው
ያኔው ነውና ወይሳው ደልቲን መስጦታል! ወጥሮታል...

ካርለት ደልቲን በሚጫወተው የሙዚቃ ቃና ተመስጦ በማየቷ ይበልጥ ወደደችው፡ ደልቲ
ለስሜቱ ታማኝ ነው አይቀጥፍም አያስመስልም...
ስርቅርቁ የሙዚቃ ቃና
የሚንቆረቆረው ለህሊናው እርካታ ነው::

ካርለትን የሙዚቃው ስልት አቅም አሳነሳት: ሁለመናዋ
እንቅስቃሴ ፍጥነቱን ስለጨመረ ደካከመች: ስሜቷን አፋጭቶ
ሃይሏን መልሶ ለመሳል አጋዥ ያስፈልጋታል
ባለወይሳው ያን ሰው አጥታው ከርማለች! አሁን ግን አጠገቧ ነው።

እጆችዋ ትከሻው ላይ አረፉ። ባለወይሳው ስርቅርቅ ዜማውን አቁሞ ቀና ብሎ አያት። ቆዳዋ ተገልቧል፣ ከርቀት ጠቆር
ብለ የታየው አካሏ ቁልቁል ወደሱ ሲመጣ እየጎላ ታየው። የራቀው
ሽለቆ ቀረበው።

ንጥት ያለው ገላዋ  በተለይም ጭኗን ትክ ብሎ እያዬ፡ “ካርለትት አላትና አይኖቹ ሳቁ። ሃይል ያጣችው ካርለት
የተሸበሸበ ርጥብ ከንፈሯን ለጠጥ አርጋ ደካማ ፈግታዋን አሳየችው።

ባለወይሳው አስተውሎ አያት ውስጧንም አየው
የተቀጣጠለውን ስሜቷን ነካው፡

ጭኖቹ ላይ ያለውን ወይሳ አንስቶ ለጨረቃ ሰጣት!
ጨረቃም ወይሳውን ተቀብላ እየነፋች ጥዑም ዜማዋን ማንቆርቆር ጀመረች። በጨረቃ የሙዚቃ ቃና ደልቲ ቀኝ እጁ እየተንከላወሰ ወደ
ነጩ ጭኗ ገባ። ነዘራት
በሽተኛዋን! “በሽታውን የደበቀ..." እንዲሉ እሷም ሃኪሟን ረዳችው የሚያቃጥላትን የሚቆረጥማትን እጁን
በእጅዋ ይዛ አሳየችው።
ጆሮ ግንዱን ፀጉሩን
ማጅራቱን...እየደባበሰች የእርዳኝ ጥሪዋን አሰማችው። ሀኪሟ በስሜቷ እሱም ተሽፈነ። ለጋራ በሽታቸው ግን የሚበጀውን ያውቃል። ስለዚህ ማገገሚያ ቀንዱን አቁሞ ይዞ ከተቀመጠበት ተነሳ።

ሙዚቃው ይስረቀረቃል! ዳንሱ ጦፏል... ጨረቃ
ታዜማለች ! ቅጠሉ እስክስታ ይወርዳል! ነፋሱ አታሞውን
ይደልቃል... ጥቁርና ነጭ ቀለሙ ማራኪ ዜብራም ያናፋል...

ኮንችት ጭፈራውን በጉጉት እያየች እንደቆየች ስለ ነገው
ጉዟቸው ካርለትን ለመጠየቅ ፈልጋ አጣቻት የኩችሩ መንደር ኗሪ
ጥበቃውን አላቆመም። ነጩ እባብና ሎካዬ ግን አልመጡም። ኮንችት
በየዋህነታቸው ብታዝንም ማድረግ የምትችለው ባለመኖሩ በዝምታ
ሁኔታውን ስትከታተል ሰነበተች። የመቆያ ፈቃዷ  እያለቀ ነው:: ስፔን ስትመለስ ብዙ ልትሰራ አስባለች በተለይ ስለ ኢትዮጵያ  ስለ ኩጉዩ፡ ከመሄዷ በፊት ግን ሐመርን ኤርቦሬን ከካርለት ጋር በሷ
መኪና ለማየት ተስማምታለች ጉዞዋን በተመለከተ ግን ከካርለት
ጋር መነጋገር ያለባት ቁም ነገር ነበር።

ኮንቺት ካርለትን ስታጣት ደልቲን በጨረቀዋ ብርሃን  ፈለገችው የለም:

ካርለት የሄደችው እሱ ዘንድ ይሆን?' አብረው ሆነው
ለማየት ጓጓች: ፍቅር ሲለዋወጡ እንዴት ይሆን?' ለማስብ ሞከረች:: መልሳ ደግሞ ሃጢያት እንደሰራች ሁሉ አስበችው አፈረች። ሆኖም ግን አልቻለችም ጉጉቷ ጨመረ።

በዚህ መካከል ድክምክም ያለውን የወይሳውን ድምፅ
ኮንችት ከርቀት ሰማችው። በድፍረት ሄደች  ወደ ጫካው! ድንገት ግን ክው ኦለች ! ባለበት የሚሰግር
ዜብራ አየች ፈራችው
ዜብራውን ይጋልባል ... በስሜት ተውጣ አይኖችዋን ጨፈነች:
"...የፍቅር እንጥሌን ሌሎች ተንጠራርተው ሲያጡት የነካው እሱ ብቻ ነው" ኮንችትን የነገረቻት ትዝ አላት።

“ዋው! ጎመጀች በዜብራው
ግልቢያውን አሰጋገሩን
አደነቀችው። ወደደችው ያን ስሜት ሰላቢ ጥዑም ዜማ... ፈውስ ሰጭ ዳንኪራ… ንፁህ የጫካ ፍቅር... ማራኪ ተፈጥሮ ተጋግዘው እንግዳዋን መልሀቋን አስጥለው በጉጉት ገተሯት!  ተጣራች በሲቃ ሶራ ግን አልሰማትም! ኤጭ! ብላ ከንፈሯን ጣለች። ጎደሎነት
ተሰማት ያማራትን የዜብራ ግልቢያ ግን የሚያቀምሳት አጣች.የጎመጀችለትን ያጣችው ኮንችት አዘነች። ...ዛፉ ቅጠሉም አዘነላት ላልተጠራችው ተመልካች!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

“እ. እ..." አቃሰቱ እምቡዋ እ. እ" ሳግ ተናነቃቸው
ህፃናት ወጣቶች አዛውንቶች ኦሞ ወንዝ ዳር ጫካ ተሰባስበው እንግዶች በእንጨቷ ታንኳ ኦሞን ሲያቋርጡ አያቸው።

ኮንችት እጅዋን አውለበለበችላቸው “ቻው... ባባይ... አለቻቸው። ዝም አሉ ኩዩጉዎች የነሱ የጥልቅ ፍቅር መግለጫቸው ዝምታ ነው። ሳግ ያበት “እ... እ..." እሚያሰኝ ከጥጃዋ በሃይል እንደተነጠለች ላም የሚያንሰፈስፍ ዝምታ! “እ. እ. እምቡዋ.. እያሰኘ የማይፈስ እንባ የሚያስነባ, የማይገልፁት ግን የሚታይ
የሚነካ... የመለየት ጭንቀት የሚታይበት ስሜት..

“እወዳችኋለሁ! ከናንተ በመለየቴ አዝናለሁ. ምንጊዜም አልረሳችሁም..." ኮንችት በስፓኒሽ ለመግለፅ ለፈለፈች¦ ምላሽ ግን
አልነበረም። “ፀጥታ ብቻ! ለኩዩጉዎች የመለየትን መጥፎነት የሚገልፅ ቋንቋ የላቸውም ካለ ዝምታ በቀር።

ኮንችት አነባች::
የካርለትን ትከሻ ተደግፋ አነባች አለቀለች  ሌሎች ግን ዝም ረጭ ብለዋል  እንደ ሌሎች ወንዞች
የማይጮኸው የማይደነፋው.
የኩዩጉዎች ህይወት የመልክ ማያ መስታዋታቸው የሆነው የኦሞ ወንዝም በዝምታ ድባብ እንደ ተዋጠ
ነው: ወፎች ግን ይበራሉ ያዜማሉ! እዕዋት ያሽበሽባሉ...

“እሷ ሄደች በሉ
ሉካዬንና የሰላም አድባራችን
የነበረውን ነጩን እባብ እንጠብቅ ! ተከፍተን ታዩን መምጣቱን እንዳይተዉት እንዝፈን እንጫወት.."
ሽማግሌዎች ለኩችሩ መንደር ህዝባችው ተናገሩ ኮንችት ካርለት ከሎ ሶራ… ኦሞን ከተሻገሩ በኋላ ዞር ብለው አዩ: ኩዩጉዎች የሉም!.ሲደልቁ ግን ይሰማል ለዚህች ተለዋዋጭ ዓለም ለረጅም ጊዜ አልቅሶና አዝኖስ መኖር እንዴት ይቻላል!
👍263👎1🥰1😁1
"አዝናለሁ ካርለት: »አንችና ደልቲ ፍቅር ስትሰሩ
እየኋችሁ ከዚያ እሱን ተመኘሁት አለምሁት... እና
የተስገበገብሁትን ከጨረቃዋ ግርጌ ጫካው መሃል አቀፍሁት የተስገበገብኩትን አይቶ
አይቶ እሱም እስክጠግብ በአፍ ባፌ አጎረሰኝ ይቅርታ ካርለት ፈገግ አለች ካርለት ቀጥላ ከት ከት ብላ ሳቀችና “አንችኮ ያላገባሽ ልጃገረድ ነሽ ደልቲም ወንድ ነው ካሻው ልጃረድ ጋ
ፍቅር መስራት ይችላል! በሐመር ባህል የሁለታችሁ ግንኙት ነውርነትም የለውም እዚህ ስንሆን እንደ ሐመሮች አስበን ይህን
እውነት መቀበል አለብን" አለችና ካርላት ደግማ ሳቀች

ኮንችት ከካርለት ጋር የተነጋገሩትን
ኤርቦሬዎችን ሐመሮችን እያሰበች! ደስታና ድንጋጤዋን እያለመች
ወደ ማድሪድ ባቀናው ኤሮፕላን ጭንቅላቷን በመቀመጨዋ ትራስ አጋደመች።ይጥማል ህልሟ! ውስጡ ግና አደራና ቃል ኪዳን ቋጥራል::

“አልረሳችሁም አካሌ ቢርቅም መንፈሴ ከናንቱ ጋር ነው ያሰብሁትም ይሆናል” እያለች እንቅልፍ አሸለበች ኤሮፕላኑ ግን
በረረ  ወደ ማድሪድ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የእንቁላል ቅርፅ ካለው አዳራሽ “ቀጭ ቋ… ቀጭ ... ቋ‥" የሚል ኮቲ ደጋግሞ ተሰማ: ኮቴው ቀስ በቀስ እየቀነሰ ሄደ
በርካታ ህዝብ ጓጉቶ የዝግጅቱን መጀመር ይጠብቃል።

በስፔን ፈረንሳይ እንግሊዝ ካናዳ , ታይቶ በተለያየ
ጋዜጦች የራዲዮና ቴሌቪዥን ፕርግራሞች
ብርሃን ያልደረሰባት በሰው ሰራሽ ግንብ የተከለለች ሃገር በሚ ርዕስ ብዙ የዘገቡበት ዝግጅት በሲውዘርላንድ ጄኔቭ ይቀርባል ሲባል
መግቢያ ትኬቱን ለማግኘት የተራኮተው ብዙ ነው ተመልካቹ ካለምንም ኮሽታ የዝግጅቱን መጀመሪያ ሰዓት ይጠባበቃል።

“የስልጣኔ ምሳሌ የነፃነት ምድር የአባይ የአባይ ወንዝ ምንጭ የዓለም የባሀል ቅርስ ሙዚዬም... ኢትዮጵያ አስተ ጋባ ድምፅ ማጉያው የአዳራሹ መብራት ጎላ እያለ መድረኩን በብርሃን
አጥለቀለቀው ::

የሐመር የኩዩጉ የወላይታ የኤርቦሬ የዶርዜ የአፋር•
የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ልብሶችን የአማራ የኦሮሞ የትግሬ የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ልብሶችን የዓለም ዕውቅ የፋሽን ሞዴሊስት ለብሰው ውበታቸውን ሊያሳዩ ተመልካቹ ትናንትና ዛሬን በምሳሌነትዠ የሚቀርብለትን ትዕይንት እያዩ በደስታ ጮኸ  የባህል ብዛት የዐገር ውበት ነው... ኢትዮጵያ ድምፅ ማጉያው ያችን የሰው ልጅ መገኛ ለአለም ህዝብ አበሰራት:

“እናቴ ኢትዮጵያ ውቢቷ ሃገሬ” የተስፋዩ ገብሬ
ሙዚቃ አስተጋባ ቀጥሎ እውቅ የኢትዮጵያ ዘፋኞችና ዳንኪረኞች የየብሔረሰቡን ጭፈራ አሳዩ: ዳንhራው ውዝዋዜ እስክስታው….
ወረደ እልልታው ደመቀ አፍሪካ ኋላ የቀረችባትን የበኩር ልጇን ኢትዮጵያን አቀፈቻት እንባና ሳቅ ሳቅና
እንባ  በሃፍረት አንገታቸውን የደፉትን ልጆችዋን ተናነቃቸው።

ለሳምንት በቆየው 'ኢትዮጵያን እንወቃት' ሳምንት የየብሔረሰቡ ቤት አሰራር ስለ ብራና መፃህፍት ስለ ባህላዊ አስተዳደር ስልት ስለ ምግብ አይነት
. ሁሉም በየአይነቱ ቀረበ
ኢትዮጵያ እንደ አልማዝ ፈርጥ አንፀባረቀች እልልታው ቀለጠ

መምሰሉን ትተን ባለን እንኩራ ማድነቁን ትተን ለመደነቅ እንስራ አገራችንና አህጉራችንን የሚያሳፍር ሳይሆን ስማቸውን የሚያስጠራ ድል እናጎናፅፋቸው ሃይሌ ገብረስላሴ በእያንዳንዱ
“ኢትዮጵያዊ ጆሮ አምርሮ ተናገረ።

ኢትዮትጵያ ተራሮች ሜዳዋ
ሸንተረሩ እንደ በቄላ አሹቅ
ሀፍረታቸውን እያወለቁ ወረወሩ።

የዝግጅቱ አቀነባባሪ ፔሶ ቢኒ ኮንቺት ካርለት አልፈርድ  ከሎና ሶራ የመጀመሪያው ምኞታቸው ሲሰምር ፈነደቁ ኩዩጎዎች
ሐመሮች ኤርቦሬዎች በመገናኛ ድልድይ ማንነታቸው  ታውቀ ክራሩ እምቢልታው ማሲንቆ ዋሽንቱ ቶም ቶም  በገናው
ወይሳው ጥዑም ዜማቸውን አሰሙ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኮንቺት በመጨረ  ያሰብነው ተሳካ  ሁለት ዓመታት በፈጀው ውጤታችን ረክቻለሁ ሶራ ደስታው ፍንቅል እያደረገው
ቡድኑ ወደ ሩቅ ምስራቅ ከማቅናቱ በፊት።

ረክቻለሁ  ኮንቺት
ሶራ የተነገረውን አጣጣማችው።

ሶራ ምን ሰራንና ረካህ መርካት ማለት እኮ ከባድ አባባል ነው።በሩን ከፍተነው እንጂ መቼ ጓራችን ለማ የመስኖ ምርቱ መቼ አደገ... ያለውን አሳየን እንጂ መች የነበረው ተሻሽሎ ተበልቶ
የተረፈው ጎተራ ተከተተ። ለውጥ ሳናመጣ እርካታ ሺ ኪሎ ሜትር የውድድር ጉዞ ከፊት በመቅረባችንና ማንነታችን በመገለፁ እርካታ ኮንቺት እልህ ሲተናነቃት ሶራ ሽምቅቅ አለ።

“አሁን ይበልጥ ለመስራት እልህ ያስፈልጋል የዓለም
ህዝብ ከአመት በኋላ ˚
በነበርንበት ሊያገኘን  አይፈልግም: ለውጥ
ይፈልጋል አዲስ ነገር  ይጠብቃል! እና አንተም ሆንክ ሌላው ወጣት አፍሪካዊ ግቡ መታወቅ መሆን የለበትም
ማሸነፍ. መቅደም ውጤቱን አሻሽሎ  ክብረ ወሰኑን መጨበጥ አለበት
ፍቅራችንን ለጊዜው እርሳው፧ አቅመ ቢስ ነኝ ብለህ የምታስበውን
ከአዕምሮህ አውጥተህ ወርውረው….. ደካማ፤
ካልጎተቱት የማይሄድ፤ ካለነጭ ፍርፋሪ የማይኖር...” መባሉ ይብቃ!
እልህ ይታይ፤ የመስራት የመፍጠር  ሰው  የመሆን
ይመስከር እንጂ ሳይጀምሩ የምን እርካታ አመጣህ!" ኦለችው ኮንችት

ሶራ ስሜቱ ጭምትርትር ሲል ኮስተር  ብሎ  አይኖቹን አድማሱ ላይ ሰካ ንስር አሞራ ሰማዩ ላይ ይበራል፤ ደኑ ሸንተረሩ
ሜዳው ተራራው... ተፈጥሮ አምራ ሰው ትጠብቃለች! ህሊና ያለው፤ መስራት የሚችል ትፈልጋለች፦

“ኢትዮጵያ እውን በስልጣኔና እድገቷ የአፍሪካ ቀንዲል
መሆኗ ተመልሶ እውን ይሆን?" ግራ እጁን ጉንጩ ላይ አስደግፎ
አዝኖ አጉተመተመ የመለሰለት ግን የለም ካለ ተግባር ይህን የተተበተበ ውል የሚፈታ አይኖርም
በአፍሪካዊነት
በኢትዮጵያዊነት ለመኩራት ጥረት ያስፈልጋል! ያላሰለሰ  ተስፋ የማያስቆርጥ እልህ የተሞላበት... ጥረት!... ያኔ ውጤት ሲገኝ ጨረቃን ተንተርሶ የፀሐይን ሙቀት እየኮመኮሙ በአባትነት ወግ
ዛሬን ለነገ ልጆች ማስረከብ ይቻላል። እውን ግን ያች ቀን ትመጣ ይሆን!

💫ተፈፀመ💫 ሌላው ይቀጥላል

አስተያየታችሁን እጠብቃለው ድርሰቱም ላይ እንዲሁም በሌላ
👍31
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስድስት  ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ ካርለት ከዳንሱ ቦታ ራቅ ብላ ጀግናዋን በአይኖቿ ስትፈልገው በጆሮዋ ስልምልም የሚያደርግ የሙዚቃ ቃና ሰማች። እንግዳ ነው ያ ሙዚቃ ለጆሮዋ! ሳባት ሙዚቃው ተጎተተችለት: ቃናው ጆሮዋን እየላሳት ወደ ውስጧ ዘለቀ የህሊናዋን ጓዳ! የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው። አሻት፤ ዳሰሳት…..እሷም አንኳኳ የሆሊናዋን ጓዳ የስርቆሽ በሯን ከፍታ…»
🕯አሳዛኝ ዜና

በኢትዮጵያ የፊልሙ ኢንደስትሪ ትልቅ ድርሻ የነበረው አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጆቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።

ነብስ ይማር 🙏
😢68👍5
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሁለት

///
    እሁድ ነው በዛ ላይ ክረምት፡፡አየሩ ጨላማና ጭጋጋማ ነበር፤በዛም የተነሳ ከመኝታዬ መውጣት አልቻልኩም..ሞቆኛል ብርድልብሴን ተከናንቤ የሀሳብ ድር እያደራሁ የምኞት ሸማ እየሸመንኩ ነው፡፡እኔ እየብ ነኘ፤ማለት ስሜ እዬብ ነው፤ ህይወቴም ልክ እንደመፅሀፍ ቅዱሱ እዬብ ከምቾትና ከድሎት ህይወት በተአምራዊ ሁኔታ የተፋታ  ወደ ድህነት አዘቅት ተሸቀንጥሮ የተጣለ ነው፡፡

ልዩነቱ የዛኛው እዬብ መከራ የመጣበት በሰይጣንና በእግዚያብሄር መካከል በተፈጠረ ቁማረ መሰለ ክርክር በማያውቀው ጉዳይና የእሱ ባልሆነ ስህትት የአለምን ቅጣት ሁሉ እንዲቀጣ የተደረገ ነው..በእኔ ምልከታ እሱ ላይ የተደረገበት ግፍ ነው፤ አረ እንደውም ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች እንደሚጠቀሙበት ሚስኪን አይጥ ነው ያደረጉት፡፡

   የእኔ ጉዳይ ግን እንደዛ አይደለም...እያንዳንዷን ያሳልፍኳት መከራ እያንዳንዷ የገጠመኝ ጨለማ ችግርና የብቸኝነት ስቃይ ከገዛ ራሴ ጥፋት የተመዘዙ ፤ወድጄና ፈቅጄ በምርጫዬ ወደ ህይወቴ ያመጣኋቸው የድክመቶቼ ውጤቶች ናቸው…እንደውም ሳስበው ከሚገባኝ በታች የተቀጣው ሰው ነኝ፡፡ስለዚህ ታላቄ እዮብ በማይገባው ስቃይ ተሰቃይቶ እንኳን እግዜሐብሄርን ሲያመሰግን ከኖረ እኔ ግን ከሚገባኝ በታች  እየተቀጣሁ እያለሁ እንኳን ሁሉ ግዜ ከምስጋና ይልቅ ንጭንጬ ለምን  አንደበቴን እንደሚቆጣጠረው ግራ ይገባኛል፡፡

ለአለፉት ሁለት አመት   የዘወትር ጸሎቴ፤ ስነሰና ስተኛ  መፅሀፍ ቅዱሴን ገልጬ መፅሀፈ-እዮብ ላይ ሄደና የእዬብን ምሬት ልክ ከራሴ ምናብ እንደመነጨ በመቁጠር  አንበለብል  ነበር ፡፡

..ያ የተወለድኩበት ቀን ይጥፋ...ያም ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ለሊት።ያ  ቀን ጨለማ ይሁን፣ እግዚሐብሄር ከላይ አይመልከተው፣ብርሀንም አይብራበት።ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፣ደመናም ይረፍበት።የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።ያን ሌሊት ጪለማ ይያዘው።በአመቶች ቀኖች መካከል ደስ አይበለው።በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቆጠር።እንሆ ያ ሌሊት መካን ይሁን።እልልታ አይግባበት።...........ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት። አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፣........በመሀፀን ሳለሁ ለምን አልምትሁም?ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም?ጉልበቾች ስለምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለምን ጠባሁ።አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፣አንቀላፍቼ ባረፋሁ ነበር።

     አሁን ግን ይህንን የምሬት እንጉርጉሮ ማላዘን ካቆምኩ ሰነባበትኩ፤ ምክንያቱም በጥቂቱም ቢሆን ጭል ጭል የምትል ሻማ በህይወቴ የሆነ ጫፍ ላይ ተለኩሳ ማብራት የጀመረች ይመስለኛል.. ፡፡እንደነገርኳችሁ አቶ ሰሎሞን   ሆቴል ስራ ካገኘሁ ከአንድ ወር በኃላ የምኖርበትንም ቤት አገኘሁ፡፡የምኖርበት ግቢ ከሆቴሉ ተያያዥ ወይም ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ሰፊና በዛፎች የተሞላ ነው፡፡በግቢው ውስጥ አንድ ኪችን፤ አንድ ሳሎን እና አንድ ሻወር ቤት ያለው መለስተኛ ቢላ አለ፡፡ይሄ ቤት የፊት ለፊቱ ሳሎን ከሌሎቹ ክፍሎች ጋር የሚያገናኘው በራፍ ታሸጎል፡፡ እኔ ሳሎኑ ውስጥ እኖራለሁ፤የተቀረውን ክፍል ነጋሽ’ዩ ሙሉአለም ይኖሩበታል፡፡ለዚህ ለምኖርበት ቤት በቀጥታ ኪራይ አልከፍልም፤ በምትኩ ግን የተወሰኑ አገልግሎቶችን ለቤቱ ባለቤት እሰጣለሁ፡፡
እኚህ እቤት የሚጋሩኝ ሰውዬ ማለቴ አቶ ሙሉአለም የአለቃዬ ማለት የሆቴሉ ባለቤት የአቶ ሰሎሞን አባት ናቸው፡፡

አዛውንቱ አቶ ሙሉዓለም የሚገርም ባህሪ አላቸው ፡፡ከቤት መውጣት ካቆሙ ሶስተኛ አመታቸውን ሊጨርሱ ነው፡፡በኮሮና ሰሞን በጣም የሚወዷት የእድሜ ዘመን ባለቤታቸው በዚህ በሽታ ተይዛ ሞተችባቸው...ከዛ እሳቸውም በፍራቻ እራሳቸውን ኳረንቲን አስገቡ፡፡ ይሄ በዛን ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገር ደረጃ በአዎጅ ሁሉም ዜጋ ባለበት እንቅስቃሴውን ገቶ እንዲቀመጥ ታዞ ስለነበር የእሳቸውም የተለየ አልነበረም…፡፡ግን ከወራት በኃላ አዎጁም ተነሳ ሁሉም ሰው ቀስ በቀስ ማስክ እያደረገ ከቤት መውጣት ፤ከዛም በሂደት ያለማስክስ ልክ እንደበፊቱ መተረማመስ ጀመረ፤ እሳቸው ግን ከቤታቸው ደጃፍ መውጣት አምቢኝ አሉ..፡፡ፀሀዮም ትቅርብኝ ጨረቃም አትናፍቀኝም አሉ፡፡ልክ እድሜ ልክ ተፈርዶበት ከርቸሌ እንደገባ ሰው በክፍላቸው ተከተቱ፡፡
ልጃቸው እራሱ በሳምንት አንድ ቀን መስኮታቸውን ይከፍቱና ከመስታወት ወዲያ ማዶ ሆኖ ያያቸዋል .እዛው በሶስት ሜትር ርቀት ሆነው አይን አይኑን  እያዩት  የሚያወሩትን ያወሩትና ይለያያሉ..ከቤታቸው ደጃፍ ለመሻገር ፍቃደኛ አይደሉም…ከማንም ሰው ጋር ለመነካካት አይፈልጉም፡፡

እና አኔ አንደኛ በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ከሆቴል አሰራና አምጥቼ  በራፍ  ስር  በማስቀመጥ …‹‹አያቴ ምግብ አምጠቻለሁ ያስገቡት፡፡›› እላቸዋለሁ፡

‹እሺ ዞረ በል›› ይሉኛል፡፡

‹‹እሺ ››ብዬ ዞሬ ወደ ክፍሌ ገባለሁ..እሳቸው ቀስ ብለው በራፉን ከፈት አድርገው መጋኛ እንዳያጠናግራቸው የፈሩ ይመስል ግራና ቀኛቸውን ገልመጥ ገልመጥ ያደርጉና የመመንጨቅ ያህል የምግብ ሰሀኑን በማንሳት ወደ ውስጥ ተመልሰው በመግባት በራፉን መልሰው ጠርቅመው ይዘጉታል፡፡
እና ሌላ የሚፈልጉት   ነገር ካለ ይነግሩኛል…ብዙውን ጊዜ በሳምንት አንድ ጠርሙስ ውሰኪና  መፅሀፍ ነው የሚጠይቁት፤ አልፎ አልፎ የራስ ምታት መድሀኒት ያዙኛል፡፡በአጠቃላይ ከውጭ የሚፈልጉት ነገር በጣም ጥቂት ቢሆንም ያንኑ ጥቂቱን  ካለበት ፈልጌ  የማቅረብ ኃላፊነቱ የእኔ ነው፡፡

በተጨማሪ  ከስራ ሰዓት ውጭ  እቤት ስሆን እኔም ሳሎኔ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ፤እሳቸውም ወይ ተቀምጠው ውስኪቸውን እየተጎነጩ ወይ አልጋቸው ላይ ተጋድመው ይደሰኩሩልኛል ፡፡እኔም የጣሙኝንም ያላጣሙኝንም ወሬዎች በማዳነቅ እና በተመስጦ አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አልፎ አልፎም ስለውጩ ዓለም ወቅታዊ ሁኔታ የተወሰነ ወሬዎች እነግራቸዋለሁ..ያው ድምፅን ትንሽ ከፍ አድርጎ ማውራት ይጠይቃል እንጂ ከግድግዳ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ በደንብ ለመደማመጥ ተቸግረን አናውቅም፡፡
ከእኔ በፊት ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት መአት ሴትና ወንዶች እዚህ ቤት ገብተው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ግን ከአንድ እና ሁለት ወር በላይ መቆየት አልቻሉም ነበር..አብዛኞቹን አቶ ሙሉ አለም አልፈላጓቸውምና እንዲለቁ ተደረጉ ፤ የተወሰኑት ደግሞ ጠቅላላ ሁኔታውና የእሳቸውን ዲስኩርና ወሬ  በግድ ማድመጥ ሰልችቶቸው በራሳቸው ለቀው ይሄው ዛሬ እኔ ጋር ደረሰ..ለእኔ ግን ይሄው 11 ወር ሆኖኛል.እሳቸውም እስከዛሬ ከምስጋና ውጭ ስሞታ አቅርበውብኝ አያቀውቁም፤ እኔም ከቀን ወደቀን ከእሳቸው ጋር ያለኝ ትስስር እየጠነከረ እና እንደውም አያቴ እየመሰሉኝ መቸገሬን ስገልፅ እየተገረምኩ ነው፡፡አሁን ስገምት እንደውም ባሉካው እራሱ እየወደደኝ እና እያመነኝ የመጣበት ዋናው ምክንያት ከእሳቸው በሚያገኘው ተደራራቢ ሙገሳና ምሳጋና የተነሳ ይመስለኛል፡፡

ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን እስከአሁን ጋሽ ሙሉአለም በአካል አይቻቸው አላውቅም…ልጃቸው እንኳን እንደሚያደርጉት በመስታወት አሻግሬ በሩቅ ለማየት እኔም ሞክሬ አላውቅም እሳቸውም አበረታተውኝ አያውቁም አንድ ቀን ጋሼ ‹‹መልኮት እኮ ናፈቀኝ ››አልኳቸው፡፡

‹‹ምነው ሳታውቀው እንዴት ሊናፍቅህ ቻለ….?

«የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም ሲሉ አልሰማህም?››

‹‹እኔ ግን እኮ በደንብ  አውቆታለሁ….እንደውም የማላውቀውን አያቴን ነው የሚመስሉኝ…..››
👍764🔥1🥰1😁1🎉1
‹‹አንተ ወሽካታ..አንጀቴን መብላትህ ነው..››.አሉና አንድ የድሮ ፎታቸውን በበር ሰር አሾልከው ወረወሩልኝና…‹‹ያው አያትህ ሙሉአለም ማለት ያ ነው››አሉኝ፡፡
እና ለመጀመሪያ ጊዜ አቶ ሙሉአለም ምን እንደሚመስሉ በፎቶ አየኋቸው….ያምራሉ ፡፡ትንሽ ወፈርና ደንደን ከማለታቸው በስተቀር  ጋሽ ስብሀት ገበረእግዚያብሄርን  ነው የሚመስሉት፡፡ጠይም መላአክ፤ዘለግ ያለ ቁመትና፤የሚስብ ግርማ ሞገደስ አላቸው ፡፡ ፎቶቸውን ካየሁ በኃላ እንደውም ይበልጥ በአካል ፊት ለፊታቸው ቁጭ ብዬ እጃቸውን ትከሻዬ ላይ ጣል እያደረጉ ወይንም ጨበሬ ፀጉሬን እየዳበሱ እንዲያወሩኝ እጓጓ ጀመር….እሳቸው ግን ከአቋማቸው መቼም ንቅንቅ የሚሉ አይነት አይደሉም፡፡

ይቀጥላል
👍46
ካቻምናን ብንከሰው: ቆመን ካምና ደጅ
መቼ ፈረደልን? ፈረደብን አንጂ!
አምናንም ብንረግመው: ቆመን ከዘንድሮ
አልደረሰበትም ደረሰብን ዞሮ
ከእንግዲህስ ይብቃን…
ሂያጆቹን ለመጡት ማማቱን ትተናል
እኛ ስንተዋቸው ይተውን ይሆናል!

🔘ረድኤት🔘
👏33👍2210
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሦስት

አስተናጋጅ ሆኜ ከተቀጠርኩ አንድ አመት  አለፈኝ።በሲቪዬ ላይ የስራ ልምድ በሚለው ርዕስ ስር የንብረት ክፍል ተቆጣጣሪ እና የሆቴል አስተናጋጅነት የአንድ አመት የስራ ልምድ የሚለውን አስገብቼ መፃፍ እችላለሁ፤አዎ ይሄ ቀላል ነገር አይደለም።እያንዳንዱን የሠው ትዕዛዝ በትሪ ይዤ አቀርብና በዛው ትሪ ባህሪያቸውን  ያስረክቡኛል። ትሁቱ... ቁጡ.. ጉረኛ... ጋግርታም... እርብትብት... ለጋስ...ንፉግና ተነጫናጭ...በየቀኑ ፀባዩ የሚገለባበጥ ሙልጭልጭ በቃ እኔ ትምህርት ሚኒስቴርን ብሆን ኖሮ ሳይኮሎጂ እና ሶሾሎጂ ለሚያጠኑ  ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ቢያንስ ለስድስት ወር እንደዚህ አይነት ቦታ አፓረንት እንዲወጡ አደርጋቸው ነበር..ሆቴል ማለት የሠው ባህሪ በብፌ መልክ የሚቀርብበት ቦታ እኮ   ነው።

አሁን ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል ፡፡ባሩ ውስጥ አንድ ተስተናጋጅ ብቻ ነው ያለው፡፡ ለዛውም ሴት ደንበኛ...፡፡ይሄንን ብላክ ሌብል  ትጋተዋለች ።አሁን አሷ ብትወጣልን ሌላ የቀረን ስራ ስለሌለን ወደየቤታችን እንሄድና አረፍ እንል  ነበር ስል አሰብኩ ስናስተናግድ ከነበረነው  ስምንት ሴትና አራት ወንድ አስተናጋጆች መካከል አምስቱ ሴት ቀድመው መውጫ ቆርጠው ሄደዋል?ምን? መውጫ ምንድነው ?አላችሁኝ... መውጫ ማለት አንድ ሴት አብሯት የሚያድር ሰው አግኝታ የስራ ሰዓቷ ከመጠናቀቁ በፊት መውጣትና ከደንበኛዋ ጋር መሄድ ከፈለገች እንደሰዓቱ እየታየ ከምታገኘው ላይ እንድትከፍል ይደረጋል...ያው ግብር በሉት ።
ብዙውን ጊዜ በኢትዬጵያ የቡና ቤት ሴቶች ግብር አይከፍሉም ይባላል..እኔም እንደዛ አምን ነበር፡፡ አሁን ግን እንዲህ ተጠግቼ ሳይ አመት እስከ አመት እንደውም እንደእነሱ የሚከፍል የለም? ያው ግብር ማለት ከደሀው  መቀነት  ተቀንሶ  ለኃያላኑ ጡንቻ ማፈርጠሚያ  በግዳጅም ይሁን በይሁንታ የሚሰጥ መባ ነው።ኃያሉ መንግስት ሊሆን ይችላል..ባለሀብት ሊሆን ይችላል...የሠፈር አስተዳዳሪ ባለጡንቻ ሊሆን ይችላል...፡፡  ሁሉም በሚስኪኑ ደሀ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ ከርሱን የሚሞላ  ብልጉ አውሬ ነው...ውይ በማሪያም አለቃዬን ነው ከሌላው ባለጉልበት ጨምሬ እንዲህ የጨፈጨፍኩት .አምላክ ሰምቶ ውለታ ቢስ ብሎ እንዳይቀየመኝ፡፡

አሁን ሆቴል ውስጥ የቀረነው ሁለት ወንድ  አስተናጋጆች እና አንድ ሴት አስተናጋጅ እና ደግሞ የእለቱን የተሰራ ሂሳብ ተረክቦ   እየደመረ ያለው ባሉካ ብቻ ነኝ...ሽኩክ ብዬ ወደእሱ ሄድኩና ፡፡
"ጋሼ እንዴት ነው?"

"ስለምኑ ነው የምትጠይቀኝ ጎረምሳው?"

‹‹ስድስት ሰዓት ሊሆን ነው...ተስተናጋጇን ልንዘጋ ነው ልበላት እንዴ?"

"አይ አይሆንም...ትልቅ ደንበኛችን ነች ..ቅር እንዲላት አልፈልግም.."

"አይ ለእሷም ቢሆን ይመሽባታል ብዬ እኮ ነው፡፡"

"የእኔ አሳቢ አይመሽባትም... ከተቀመጠችበት ተነስትታ አስር እርምጃ ከተራመደች የተከራየችበት ቤርጎ ትደርሳለች"

"ኦ ረስቼው… ለካ እዚህ ነው አልጋ የያዘችው"

"አዎ ባይሆን ልጇቹ ይግቡ ..ንገራቸው፡፡"

"እሺ ግን ጋሼ እሷ እስክትሄድ ብቻህን ልትሆን ነው?"

"አይ እኔ አይደለሁም ቀርቼ የማስተናግዳት ...አንተነህ.፡፡..በራሷ  ጊዜ በቅቷት ስትሄድ ቆላልፍና ሂድ...እኔ ሚስቴ ትጠብቀኛለች ...አንተ ከአይጥ ጋር ድብብቆሽ ለመጫወት ምን አስቸኮለህ?››

‹‹እንዴ ጋሼ ከጓደኞቼ ጋር የማወራው ነገር ተደብቆ ይሰማል እንዴ...?"ስል በውስጤ አልጎመጎምኩ፡፡ከሶስት ቀን በፊት ነበር ለሴቶቹ አንድ አይጥ አላስተኛ እንዳለቺኝና ልክ ስተኛ ጆሮዬን እየቀረጠፈች፤ ከንፈሬን እየነከሰች  አስቸገረችኝ ብዬ ያወራኋቸው...እነሱ ደግሞ አፍቅራህ ነው እያሉ ሲያሾፍብኝ ነበር..ይሄው አሁን ጋሼም ተቀላቀላቸው...
ጋሼ ሂሳቡን ሰርቶ ጨርሶ ለመሄድ ተነሳ፡፡

"ጋሼ ለመቆየቱ ግን ካሌብ አይሻልም?"

"ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?...መልካም አዳር"ብሎኝ ጥሎኝ ወጣ...፡፡እኔም ሌሎቹ እንዲሄዱ ተናግሬ በዛ ውድቅት ለሊት ከአንድ እንስት ተስተናጋጅ ጋር ተፋጥጬ ተቀመጥኩ...፡፡
እኔም እንደሌሎች በዚህ ሰአት ክፍሌ ገብቼ አረፍ ባለማለቴ ከፍቶኛል ..ግን ደግሞ ጋሼ የተናገራት ነገር ልቤ ላይ አሪፍ  ደስታና ኩራትን አርከፋክፋብኛለች "ጓረምሳው ንብረቴን ለማን አምኜ ጥዬ እንደምሄድ የመወሰኑ መብት የእኔ መሰለኝ?ነበር ያለኝ አይደል?፡፡ "በእውነት መታመን ያስደስታል" ለዛውም አንድ አመት ባልበለጠው ጊዜ ውስጥ ይህን መሳይ ክብር ማግኘት ተስፋው ለፈረሰበት ሰውም ቢሆን  በህይወቱ ጥቂት መነቃቃትን ይፈጥራል፡፡

ጠረጴዛው ተንኳኳ ከነበርኩበት ባንኮኒ ውስጥ ፡ሮጬ ወጣሁና  ወደ ተጠራሁበት ቀርቤ፤ እጇቼን ወደኃላዬ አጣምሬ፤ ከጉልበቴ ሸብረክ ፤ ከአንገቴ ጎንበስ ብዬ"አቤት ምን ጎደለ ? ምን ላምጣ?"አልኩ፡፡

"እ ..ምንድነበር..?."በፈጣሪ ሰክራለች መሠለኝ ..?ለምን እንደጠራችኝ እንኳን  አታውቅም፡፡
"አዎ..ሙዚቃውን በጣም ቀንሰው እናም አንድ ብርጭቆ አምጣልኝ"
ወይ ፈጣሪዬ ሴትዬዋ ገና መጠጣት ልትጀምር ነው..ለዛውም በሁለት ብርጭቆ…. እንዳለችኝ የሙዚቃውን ድምፅ  ቀነስኩና ብርጭቆውን አጣጥቤ ይዤላት ሄጄ ጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጥኩላትና ልመለስ ስል "ተቀመጥ"አለችኝ...
ተቀመጥ በሚለው ቃሏ ውስጥ ምንም አይነት ትህትናም ሆነ ሀዘኔታ አይነበብም፡፡.

"ምን አልሺኝ እመቤቴ?"

"ቁጭ በል..ንግግሬ አይሰማም እንዴ?"

"ኸረ በደንብ ይሰማል"ብዬ ትዕዛዟን በማክበር ሽኩክ ብዬ ቁጭ አልኩ..ፊቷ የተቀመጠውን  የተጋመሰ ብላክ ሌብል ጠርሙስ አነሳችና አዲስ ያመጣሁት ብርጭቆ ውስጥ አንደቀደቀችው፤ስትጨርስ  ወደፊት ለፊቴ አሽከርክራ አሰጠጋችው።

"ኸረ ይሄ ነገር ለእኔ አይሆንም?"

"ባክህ አትንጠባረር ..ዝም ብለህ ጠጣ "ብላኝ እርፍ...
አሁን ይሄ ግብዠ ነው አስገድዷ ደፈራ፡፡ፈራኋት መሠለኝ አነስሁና አንዴ ጎንጨት አልኩለት...
.፡፡‹‹እራት መቼ ነበር የበላሁት?›› ስል እራሴን ጠየቅኩ፡፡ አዎ 12፡30 አካባቢ....‹‹ምንድ ነበር የበላሁት?›› ዳቦ በሙዝ ...፡፡.ሶስት ሙዝና ሁለት ዶቦ....፡፡‹‹አሁን ከስድስት ሰዓት በኃላ ምን እየጠጣሁ ነው›› ውስኪ፡፡...‹‹ይህቺ ጋባዤ አራት ሰዓት አካባቢ ምንድነበር ያዘዘችው..?››ለማስታወስ ሞከርኩ...አዎ ክትፎ ነበረ ያዘዘችው እናም ግማሹን በልታ ግማሹ እንደተመለሠ አይቼያለሁ....አሁን ኪችን ብገባ ግማሹን ትራፊ አገኝ ይሆን?

"እዚህ ሀገር ለስራ መጥተሽ ነው?"ጥያቄውን መጠየቅ ፈልጌ ሳይሆን ዝም ብሎ መቀመጥ ስለጨነቀኝ ነው የቀባጠርኩት። ቢዝነስ የሚሰሩ ሴት  አስተናጋጆች ግን  እንዴት ብለው ነው ከማያውቁት ሰው ፊት ለፊት ተቀምጠው ዘና ብለው የሚጠጡት...ከዛም አልፎ የሚስቁት፤ የሚጫወቱት?ለዛውም በየቀኑ…፡፡ጥያቄዬን ሰምታ ሲጋራዋን ለኮሰች ...እናም ጭሱን አትጎልጉላ እላዬ ላይ በተነችብኝ ፡፡...ልክ እንደቤተመቅደስ ማዕጠንት ዝም ብዬ በፀጋ ተቀበልኩና ወደውስጤ ማግኩት?

"ምሽቱ ደስ ይላል..."ሌላ የማይረባ አስተያየት ከአንደበቴ ድንገት ሾለከ፡፡

"ምሽቱ አንተን ነው የሚመስለው?"አለችኝ፡፡
👍522👎1👏1
‹‹በፈጣሪ ምን ለማለት ፈልጋ ነው?እኔ ምን እመስላለሁ? ምሽቱስ ምን ይመስላል? በእኔና በምሽቱ መካከል ያለው መመሳሰልስ እንዴት ነው ሊመሳጠር የሚችለው?መቼስ ይህቺ ሴትዬ እዚህ መቀመጫ ላይ ከተቀመጠች ሰዓት አንስቶ መጠጧን ከመገልበጥ እና ሲጋራዎን ከማቡነን ሌላ  ፊቷ ሲፈታም ሆነ ጥርሶቾ ለሳቅ ሲገለጡ አላየሁም ...፡፡.ያ ማለት ደግሞ ምሽቱ ለእሷ ደባሪ ነበር የሚለው ድምዳሜ ላይ ያደርሰኛል ..ያ ከሆነ ደግሞ አንተ ደባሪ ነህ እያለችኝ ነው? እሺ ምኔ ነው ደባሪ ? መልኬ ነው?ቁመናዬ ነው?ወሬዬ ነው?
"ምን ትንጠባርብኛለች..እስከጋበዝኩህ ድረስ እንደፈለኩ ልሰድብህ እችላለሁ እያለች ነው እኮ?...ሴቶቹ የስራ ባለደረቦቼ በየቀኑ ከሚጋበዙአቸው ሰዎች  እንደዚህ አይነት ንቀትና መንቀባረር የሚያጋጥማቸው ከሆነ ለትዕግስታቸው ታላቅ አክብሮት አለኝ››ይህንን ሀሳብ በውስጤ ነው እያመነዥግኩ ያለሁት፡፡
"ድንገት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ጠረጴዛው ላይ የነበረውን ፓኮ ሮዝማን ሲጋራዎን እና ላይተሯን ይዛ ብድግ ብላ ተነሳች።
በመሄዷ እፎይታ እየተሠማኝ ፈጠን ብዬ"ልትሄጂ ነው… ደህና እደሪ"አልኳት፡፡
"አዎ ልሄድ ነው ..ክፍሌ 104 ቁጥር ነው...መጠጡን ይዘህልኝ ና"ብላኝ እርፍ፡፡

"እሺ ግን ሰው ስለሌለ እስክዘጋጋ እቆይብሻለሁ.."ሰበብ መደርደሬ ነው፡:፡

"እንደፈለክ…ለሊቱ ገና ረጅም ነው…. የትም እልሄድም፤ እጠብቅሀለሁ"ብላኝ የሚያርድ መቀመጫዎን እያማታች ቀጥ ብላ ወጥታ ሄደች..፡፡

እንዳትሰማኝ ድምፄን ዝቅ አድርግ ‹‹የእውነት አድናቂሽ ነኝ"አልኩ..እውነቴን ነው ግማሽ ጠርሙስ ውስኪ ብቻዋን ገልብጣ ገድገድ ሳትል ...እኔ ገና በግማሽ ብርጭቆ ጉልበቴ  እየተብረከረከ ነው።

ይቀጥላል
👍411👎1👏1