አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
«ህም መች ሰው ባሰበበት ይውላል?» አለ ከንፈሩን ብቻ ሸሸት አድርጎ። እኔ አንድ ሀገር አውርቼ ከአምስት ቃል ያልዘለለ ነው የሚመልስልኝ። ያለማቋረጥ መለፍለፌ ለራሴ እንኳን እንግዳ አይነት ስሜት ሰጥቶኛል። መልሼ ይሄንንም ያንንም ሳወራ ራሴን አገኘዋለሁ እንጂ። ምናልባት ከእናቴ ጋር የነበረኝ ጊዜ፣ ወይ ደግሞ ያስታወስኩት የትውስታዬ ሽራፊ፣ ወይም ትውስታዬ የመመለስ ተስፋ እንዳለው ማወቄ፣ አልያም አጎቴ ያወራልኝ የህይወቴ ክፍል …… አላውቅም! አንዳቸው ወይም ሁሉም ተደምረው ግን የሆነ ስሄድ ከነበረው ቅልል ያለ ስሜት ስመለስ እንዲኖረኝ አድርገውኛል።

«ከመመታቴ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያደረግኩት ምን ይሆን? ለመጨረሻ ያገኘሁት ሰው ማን ይሆን? ያስቀየምኩት ወይስ በጥሩ የሚያስታውሰኝ ሰው ይሆን?» ያልኩት እንዲመልስልኝ አልነበረም።

«የዚያን እለት ከቤት ወጥተሽ ብዙም ሳትቆዪ ነው የሆነው ነገር የሆነው። በመንገድሽ የገጠመሽ ካልነበረ ለመጨረሻ ያወራሽው እኔን ነው የሚሆን!» አለ ስሜቱን ለማንበብ በሚከብድ ፊት። ያልጠበቅኩት መልስ ሆኖ መሰለኝ ተስተካክዬ ተቀመጥኩ።

«ምንድነው ያወራሁህ? መጥፎ ነገር ነው? ጥሩ?»
«ያለፈውን ከኋላችን እንተወው ተባብለንም የለ?» መመለስ የማይፈልገው ነገር ሲሆን የሚያመልጥበት ዘዴው ነው።
«በናትህ? ለምንድነው ግን ያለፈውን ስጠይቅህ የምትሸሸው? ልቤ የሚነግረኝ ከነገርከኝ በላይ ብዙ የምታውቀውን ነገር እንደደበቅከኝ ነው ግን ዝም ብዬ እያመንኩህ ነው።» ….. ብዬ ጥርጣሬዬን ላስከትል ስንደረደር የሚቀጥለውን ለማስቆም በሚመስል

«ፀያፍ ነገር ነው!! እኔ አሁን የማልደግመውን ፀያፍ ነገር ብለሽኝ ነው የወጣሽ! እንደእውነቱስ አፍሽን ከፈትሽ ነው የሚባል።» አለ እንዲመልስልኝ ስላደረግኩት እየተናደደብኝ።

«እሺ በሙሉ ልቤ እንዳምንህ አስረዳኝ! እንደዛ ፀያፍ ነገር የምናገርህ ሴት ሆኜ እቤቴ ምን አቆየህ? ስራዬ ፣ እንጀራዬ ምናምን ብለህ ልትሸነግለኝ አትሞክር! እኔ የምከፍልህን ደመወዝ ብዙ እጥፍ ከፍሎ የሚያሰራህ ሰው አታጣም ባንተ ብዙ ችሎታ! ሲጀመር የአንድ ቤት ዘበኛ፣ መኪና መንዳት የሚችል፣ ሽጉጥ የታጠቀ ፣ ክብር ሀቅ እውነት እሴቶቹ የሆነ ሰው …… አፏን የምትከፍትበት ሴት ደጅ ምን ያደርጋል?»

«ውል የሌለው አድርገሽ አትቆጣጥሪውማ! ሹፍርና እሰራ እንደነበርኮ አውግቼሽ ነበር። ወታደር ቤት ስለነበርኩ መሳሪያውም አዲሴ አይደለም። ሽጉጡንም ያስታጠቅሽኝ አንቺው ነበርሽ! ይከው ነው!!» አለ

«አሁን ያልከው በሙሉ ለምን እኔጋ እንደቆየህ አያብራራም! እሺ ንገረኝ እስኪ የት ነው የተገናኘነው? ማለቴ ስራውን እንዴት አገኘኸው? ወይም እኔ እንዴት ቀጠርኩህ?»

ለማውራት አፉን ከመክፈቱ በፊት በረጅሙ ተነፈሰ። ግንባሩ ላይ ያሉት መስመሮች ብዛታቸው ጨመረ። ዞር ብሎ ሳያየኝ

«ሰው ነው ያገናኘን! አንቺ ጠባቂ እንደምትፈልጊ እኔ ስራ እንደሚያስፈልገኝ የሚያቅ ሰው!» አለ በድፍኑ። አጀማመሩ እስከነገ የማያልቅ ታሪክ ሊያወራኝ ነበርኮ የሚመስለው።

«በቃ!? ሰው?» ድምፄን ጨመርኩ።
«ቆይ እኔ የምጎዳሽ አለመሆኔን እንድታምኚ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?»
«እያወራን ካለነው ጋር ይሄ የሚያገናኘው ነገር የለም! ትጎዳኛለህ ብዬ ባስብማ አብሬህ አልገኝም!! አንተ መናገር ያልፈለግከው ወይም እየደበቅከኝ ያለ ነገር እንዳለ እየተሰማኝ ግን ምንም ሳትጠይቂ በጭፍኑ እመኚኝ ማለት አይዋጥልኝም።» አልመለሰልኝም። አሁንም በረዥሙ ተንፍሶ ዝም አለ። በዝምታችን ውስጥ ከራሴ ሳወራ ለካንስ ምንም ነገር ለእኔ የማስረዳት ግዴታም የለበትም። <የራስሽ ጉዳይ> ብሎ ጥሎኝ ቢሄድስ መብቱ አይደል? ያኔም ለምን አብሮኝ እንደቆየ አሁን ለምን አብሮኝ እንዳለ ምክንያቱን ማወቅ አልችልም። ስለእርሱ የማወቅ መብት እንዳለኝ እንዲሰማኝ ያደረገኝ ራሱ አይደል ግን?

ሀሳብ ሳዛቁል ስልኬ ጠራ። የማላውቀው ቁጥር ነው። ለምን እንደማደርገው ባላውቅም የማላውቀው ስልክ ሲደወል ጎንጥ አጠገቤ ካለ ድምፁን ስፒከር ላይ አደርገዋለሁ። ምናልባት የመጀመሪያ ቀን ስልኬ ሲከፈት ድንብርብሬ ወጥቶ ስንተባተብ እሱ ስልኩን ተቀብሎኝ ስላወራ እንደልምድ ወስጄው ይሆናል። አነስቼ ሀሎ አልኩ።

«እሺ ሜላት!! ሁልጊዜ ጀግና አይኮንም! አንድ ቀን አገኝሻለሁ ብዬሽ አልነበር?» ወፍራም ድርብ የወንድ ድምፅ ነው።
«ማን ልበል?»
«ማን እንደሆንኩማ አሳምረሽ ታውቂዋለሽ!! ዛሬውኑ እስከማታ ድረስ የምልሽን ታደርጊያለሽ!! ህም እመኚኝ ይሄ እንደሌላ ጊዜው ማስፈራሪያ አይደለም። ምንም አይነት ወጥመድ ከጀርባዬ ሸርባለሁ ብትዪ ወንድምሽን 12 ትንንሽ አድርጌ በየተራ እልክልሻለሁ። ……. » ጎንጥ መኪናዋን ሲጢጥ አድርጎ አቆማት። እየሆነ ያለው ነገር በቅጡ ሳይገባኝ ሰውየው ማውራቱን ቀጠለ « …… ልታናግሪው ከፈለግሽ አጠገቤ ነው። ቪዲዮ ላድርግልሽ ከፈለግሽ?» (እያላገጠብኝ ነው የሚያወራው) ይሄኔ ጎንጥ ከመኪናው ፊትለፊት ያለ ወረቀት አንስቶ ከኪሱ እስኪሪብቶ አውጥቶ የፃፈውን አሳየኝ። <ምንድነው የምትፈልገው? በይው።> ሰውየው ይሄን ሲሰማ እንደመደሰት አደረገው።

« የሰውን ስስ ጎን ማግኘት ደስ ሲል።አየሽ የምትሳሺለት ነገር ሲያዝብሽ እንዲህ ነው የሚያንገበግበው። ከገባሽ! አንደኛ ወለም ዘለም ሳትዪ የቪዲዮን ያሉሽን ቅጂዎች በሙሉ ካስቀመጥሽበት ሰብስበሽ ነይ የምልሽ ቦታ ይዘሽ ትመጫለሽ። ሁለተኛ አንቺን ማመን ስለማይቻል ማስተማመኛ እንዲሆነኝ እዚህ ከመጣሽ በኋላ በይ የምልሽን እያልሽ እንቀርፅሻለን። ይቅርታ እንግዲህ ባላምንሽ … ያለመታመን ልምድሽ አቻ ባይኖረው ነው።» እኔ እሱ የተናገረው ምኑም አልገባኝ እሱ ይገለፍጣል። ጎንጥ ፅፎ ያሳየኛል።

«እኮ ምንድነው እንድቀርፅልህ የምትፈልገው?»
«ቆቅ አልነበርሽ? ይህቺ ትጠፋሻለች? በማስፈራራት ያለፍሻቸውን እዚህም እዛም የሰራሻቸው ህገወጥ ነገሮች ሲሰበሰቡ እድሜ ልክ ዘብጥያ የምትበሰብሺበት ሆኖ አጊንቼዋለሁ። ብዙም እንዳትቸገሪ መረጃዎቹንም ሰብስቤልሻለሁ። አንቺ የሚጠበቅብሽ የሰራሻቸውን ወንጀሎች በመረጃ አስደግፈሽ አምነሽ ቃል መስጠት ነው። ከምታምኛቸው ውስጥ ፌክ የምስል ቅንብር እና መረጃ ሰርተሽ እኔን በማስፈራራት የግል ጥቅም ለማግኘት ያለመታከት መልፋትሽ ይካተትበታል። ያው እዝህችጋ ምንም ያህል የረቀ ሴራ ብትሰሪ እኔ ወደር የሌለኝ ለሀገሬ ታማኝ አገልጋይ መሆኔን አክለሽ ብትጠቅሽም አይከፋኝም። ሃሃሃሃሃ» እኔ ምኑም እየገባኝ ካለመሆኔ እየተነጋገሩ ያሉት ሰውየውና ጎንጥ ናቸው የሚመስሉት

«ኪዳንን አገናኘኝ? ማስረጃ እፈልጋለሁ።» ብሎ ጎንጥ የፃፈልኝን አነበብኩለት

«ምን ችግር። ቆዪማ ቪዲዮ ላድርገው?» ሲለኝ ጎንጥ ስልኩን ዘጋው እና እኔ ላይ አፈጠጠ።

«ወንድምሽን ስታዪው የተደናገጠ ሰው እንዳትመስዪ ፣ ድሮ የሚያውቋትን ሜላት መሆንሽን አሳምኛቸው። ምንም እንደማያውቅ ሰው አትምሰዪ ….. የማታውቂውን ነገር አትጠይቂ!! ምንም ቢፈጠር እንደማታስታውሺ እንዳትናገሪ ….. የምልሽን ብቻ አድርጊ!!» ብሎ በቁጣ እያስጠነቀቀኝ ስልኬን ተቀብሎኝ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ሰው ጣቱን ካመላለሰ በኋላ ከመጡለት ዝርዝሮች የሆነች ቀይ ምልክት ነገር ተጭኖ እየመለሰልኝ ስልኩ ጠራ። ድንብርብሬ ሲወጣ በሁለቱም እጆቹ ትከሻዬን በሁለቱም በኩል አጥብቆ እየያዘ « ታምኚኛለሽ?» ያለኝ ስለምን እንደሆነ ሳይገባንኝ ጭንቅላቴን ወደ ላይ ወደታች ናጥኩ!! «ተረጋጊና ያልኩሽን አድርጊ!!»
👍29🥰41
«እኔኮ ኪዳንን እንኳን ላልለየው እችላለሁ?» አልኩ አፌ ውስጥ ምራቄ ደርቆብኝ ትን የሚለኝ እየመሰለኝ። ስልኩ ጠርቶ እንዳይዘጋ እየተቻኮለ ስልክ ያልያዝኩበትን እጄን ቀለብ አድርጎ ጨብጦ ከቅድሙ በተረጋጋ ድምፅ

«ትለይዋለሽ ግድ የለም!» አለኝ። የድምፁ መርገብ ይሁን የያዘኝ እጁ ያረጋጋኝ መርበትበቴን ገትቼ የያዘኝን እጄን አስለቅቄ ስልኩን ካነሳሁ በኋላ እንዲይዘው መልሼ ሰጠሁት።

………. ይቀጥላል ………..

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
12👍3
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ኮንችትና ሶራ በኦሞ ወንዝ ሲጓዙ በኡዱማ መርኩል
ጎዋ ኩረምና ሻንጋሮ ያሉትን የቦዲና የሙርሲ መንደሮች ካዩ በኋላ የደቡብ ሱዳንን አቅጣጫ  ይጓዝ የነበረው
አቅጣጫውን ከደቡብ ወደ ምስራቅ ድንገት እጥፍ በማድረግ መጓዝ ጀመረ

በአለምአቀፍ አቅጣጫ ማስተካከየዋ ጂፒ ኤስ'
ከሳተላይቶች ጋር ግንኙነት ፈጥራ ያለችበትን የኬክሮስና ኬንትሮስ
ዲግሪ ካወቀች በኋላ ማፑን ስትመለከት በጣም ከሚጠማዘዘው የኦሞ
ወንዝ ጉዞ በኋላ የካራ የሙሩሌ ዳሰነች ማህበረሰቦችና ዝቅ ብሎ
የሚታየው የቱርካና ሐይቅ ብቻ የሚቀራቸው መሆኑን ተረዳች በዚህ ጊዜ ኮንችት ትልቅ ሃሣብ ላይ ወደቀች የአያቷን ቀዬ ለማግኘት የቀራት እድል በጣም ውስን ነው  የዳሰነች ማህበረሰብ ያለው  ከቱርካና ሐይቅ ጥግ ሲሆን አያቷ ስለሃይቅ ፈፅሞ አንስቶ ስለማያውቅ የሱ ማህበረሰብ ዳሰነች ሊሆን አይችልም ስለዚህ ጥርጣሬዋ ወደ ሁለት ዝቅ አለ ከካራና ከሙረሌ
ከነዚህ አንዱ ካልሆነ ግን የአያቷን ቀዬ ለማግኘት
የምትወስደው አማራጭ
ጭልምልም ያለና  ምናልባት ሌሎች ተጨማሪ አመታትን የሚወስድ ይሆናል ስለዚህ ኮንችት ጭንቀት አንገቷን ሲያስደፋት ሶራ ችግሯ ምን እንደሆነ ገብቶት፡-

አዞይሽ ካሰብሽው ትደርሻለሽ" አላት::

ያ ሃሳብ አንዳች ውስጣዊ ሃይል ፈጠረላት አመሰግናለሁ ብላው ጉዟቸውን ቀጠሉ።

ትንሿ ድንኳናቸው ከኦሞ ወንዝ ራቅ ካለ ጉብታም ቦታ አግራር ዛፍ አቅራቢያ ተተክላለች።

ኮንችት ሁለት እግሯን እጥፍጥፍ አድርጋ ድንቁን
የተፈጥሮ ውበት የማታዋን ጀንበርና ልዩ መስህብ የተጎናፀፈውን የዳመናውን ቀለም እያየች የተፈጥሮን ሙዚቃ የአዕዋፍ ዝማሬ
የንፋሱን ሽውሽውታ... ታዳምጣለች።

ይህች አንደበት ያጣች ሃገር ምንኛ ታሳዝናለች። የሌላ
ውበት በውሸታም ካሜራ ቀርፀው ሌላውን እየኮረኮሩ ለማዬት ሲያራኮቱት ኢትዮጵያ ግን እንዲህ ትንፋሽ ቆራጭ የሆነውን
ውበቷን ቆንጥሮ ለዓለም ህዝብ የሚያሳይላት አጣች

ከጥሩው የተበላሸው  የሚበዛበት አለማችን ሳታወቅ ከተበላሽው ጥሩው የሚበዛባት አፍሪካ ግን ጨለማ ዳፍንታም
አህጉር ተባለች

“የሚዲያ ልሳን ያልተፈጠረባት ምስኪን ኢትዮጵያ ስለ ውበቷ ማን የራሱን ጥሎ የእሷን ያስተዋውቅላት ታውቃለህ ሶራ ስለ አፍሪካ ዜና በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ስናይ አንበሳ ሲያገሳ ፏፏቴው ሲንፏፏ... አዕዋፍ ሲበሩ አውሬው ሲተራመስ ይታይና
ኢትዮጵያን የሚመለከት ዜና ሲመጣ ግን ሁሌ ከረጂ ድርጅቶች ዳቦ ሲታደል ማየት ብቻ የሰሃራ በርሃ አገሮች ግመላቸውና አሸዋቸው ሲታይ ኢትዮጵያ ዛፍ አይበቅልባት ፏፏቴም የላት አውሬና አዕዋፍም አይገኙባት የሚባባለው ብዙ ነው።

ለካ ኢትዮጵያ ምንም አላጣች: ሰው ግን ያላት
አይመስለኝም እንደ “ኢብንባቱታ እየዞረ እሚያስተዋውቃት
የላትም..." አለችው እያሸጋገረች አድማሱን አያዬች: ሶራ የሚላት
ጠፋው: ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ስላላቸው ነገር ማለት እንኳን አይችሉም። ብዙ ኢትዮጵያውያን በሌላው ዓለም ይኖራሉ ፧ ግን ስለ አገራቸው ትንፍሽ አይሉም በቅኝ ግዛት የማቀቁት ህዝቦች
አንገታቸውን ቀና አድርገው መዘመር ሲጀምሩ ኢትዮጵያውያን ግን
የተውሶ ካባ ከጃማይካ ተበድረው ትዮጵያዊነታቸውን ከውስጥ
ጃማይካነታቸውን ከላይ ደርበው ተደበቁ። hገሃዱ እውነት ማስመሰሉን መረጡ።' ሶራ አዕምሮው ተረበሸ።

“ተፈጥሮን አትወድም? ሶራ
እስኪ እየው ይህን ውበት?
የሰው ኪነታዊ ጥበብ ምን ብሎ ሊገልጸው ይችላል?" አለችው።

“ያምራል ኮንችት... ብቻ ምን ይሆናል እያለን ያጣን
መሆናችን ያሳዝናል። ለቤት ማስዋቢያ በየግድግዳችን የምንለጥፈው የባህር ማዶ ስዕሉችን ነው። የባር ማዶው ህዝብን ደግሞ አንች እንዳልሽው? “ለመሆኑ አገራችሁ ዛፍ ያበቅላል ወይ! ይሉናል።

“ህይወት ሳናይ ገና የናታችንን ጡት ሳንጠግብ በባህር ማዶህይወት ለሃጫችንን እያዝረበረብን እንነሆልላለን።

“ከዚያ ማነህ? ሲሉን  ጸጥ ምን አለህ ሲሉን ቁልጭልጭ በመጨረሻ እነሱም ንቀው እንደ ምራቃቸው ይተፉናል!... የመጣበትን ያላወቀ የደረሰበትን ማን ይጠይቀዋል?.." ብሎ ፀጥ አለ::

ኮንችትና ሶራ እንዲህ በፀጥታ ድባብ ተውጠው ማራኪዋን ተፈጥሮ እየቃኙ የበኩላቸውን ሃሣብ ሲያንሰላስሉ የሆነ ድምፅ
ንፋሱ ይዞ መጣ: እንደገና ድምፁን ጠበቁት  ተመልሶ መጣ የወፍ ዝማሬ የወንዝ ኩሉልታ የእፅዋት ሽዋሽዋቴ
አይደለም።የአራዊት ድምፅ… ከሁሉም የተፈጥሮ ቅላፄዎች የተቀነባበረ የሙዚቃ ቃና ነው: ጥዑም ዜማው ይማርካል!
ይስባል! ከተፈጥሮ ጋር ተዋህዶ ልብ ይሰርቃል። ተያዩ ኮንችትና ሶራ: ድምፁ እንደገና እየተስረቀረቀ መጣ። ተጠቃቅሰው ተነስተው ማራኪውን የሙዚቃ ቃና ወደሰሙበት አቅጣጫ ሄዱ።

“ክላሽንኮቭ” መሳሪያውን ጎኑ ያጋደመ ሰው ወይሳውን'
ይነፋል። አዕዋፍ ነፍሳቱ ፀጥ እረጭ ብለው ያዳምጡታል፤ ሶራና
ኮንችትም ከተደበቁበት ሳይወጡ የዜማው እንቅፋት ሳይሆኑ ያን ጥዑም ዜማ በፀጥታ ማዳመጥ ቀጠሉ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ካሎ ጎይቲና አንተህ ይመር ከካሮ ማህበረሰቦች
መንደር አንዷ የሆነችው ቆርጮ ዘግይተው ስለተነሱ ከመሸ በኋላ ደረሱ። ከዚያ ወደ መንደሩ ገብተው ሽማግሌዎች ከፀሐይ ቃጠሎ ከሚጠለሉበትና ከሚወያዩበት ኦሞ ወንዝ ዳር ላይ ካለው ዳስ ሄዱ

ቆርጮ ከፍ ብሎ ሜዳማ ከሆነ ቦታ  ላይ ያለች መንደር በመሆኗ ለጥ ያለውን የኦሞን ወንዝ ግርጌው ሌላውን የካሮ መንደር ዱሰን ከቀኝ የሙሩሌን ሚዳ ከግራ ማዶው ደሞ የማሽላ
አዝርዕቱን በስተ ምስራቅ ለጥ ያለውን የማንጎ ፓርክ አረንጓዴን ደን ማየት ስለሚቻል ቆርጮ ቀለል ያለችና የተፈጥሮ ውብት በትርኢት መልክ የሚቀርብባት መንደር ናት።

ከሎና አንተነህ ሽማግሌዎችን መጀመርያ ተጥሎ ጎረምሶችን የሐመሩን ደልቲ ገልዲን አይተው እንደሆን ጠየቋቸው በእርግጥ ከጎረምሶች ጥቂቶቹ እንጂ ብዙዎቹ አያውቁትም  የሚያውቁት አላየነውም አ
ሲሉ ሌሎቹ ግን ብዙ የሐመር ወንዶች ከከብቶቻቸው ጋር ሙርሌ ያሉ መሆናቸውን ነገሯቸው።

በእርግጥ ይህ ለአንተነህ  እንግዳ አልነበረም ዝናብ ሲቀንስና የግጦሽ ሳር ሲጠፋ የሐመር ከብቶች ፍየሎችና በጎች ወደ ኦሞ ወንዝ  ይመጣሉ ኦሞ ወንዝ አካባቢ ሳሩ ጥሩ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ከብቶች የሚጠጡት በቂ ውሃ ከኦሞ ያገኛሉ ስለዚህ የቆርጮ
መንደር ካሮዎች እንደነገራችው ሐመሮች ከብቶታቸው ጋር በሙርሌ ሜዳና በኦሞ ወንዝ ዳር አሉ::

“ታዲያ ምን ይሻላል? አለች ካርለት ከሎንና ጋልተንቤን

የሚሻለውማ ለአንድ ሶስት አራት ቀን እዚሁ አካባቢ
ማጠያየቅ ነው" አላት አንተነህ ይመር ረጋ ብሎ እያንዳንዱን ቃል
እየረጋገጠ፡

ጎይቲ ጆሮዋን በሁለት እጅዋ ይዛ እግሯን አጣጥፋ መሬት ላይ ቁጭ ብላለች:: ደልቲ ቆርጮ መንደር ነኝ ብሎ እንደነገራት ሁሉ ስትመጣ ባለመኖሩና ያለበትም አለመታወቁ ሆዷን አዋለለው ! ሆድ ባሳት...

“እንግዲህ ለዛሬ እዚሁ እንደር ነገና ተነገ ወዲያ ሙርሌ ወርደን እንፈልገውና ተዚያ ወደ ሌሎች የካሮ መንደሮች ዱስና ለቡክ
እንሄድና እንፈልገዋለን!" አለና ጋልታምቤ አያቸው። ሁሉም ተስማሙ፤ ጎይቲ ግን ተነጫነጨች። እሱን ሳታይ ጎኗን ማሳረፍ
አልፈለገችም: ጀግናው እየተንጓለለ እሷ እንቅልፍ እንዴት ያሸልባት? ግን ከአቅሟ በላይ በድምፅ ብልጫ ተሸነፈችና ሁለት
ድንኳናቸውን ዘርግተው ካርለትና ጎይቲ አንዱ ድንኳን ጋልታምቤና ከሎ ደግሞ ሁለተኛው ድንኳን ሊተኙ ተስማሙ።
👍14
ከያዙት ስንቅ ከተመገቡ በኋላ ወደ መንደር ሄደው ቡና ወተት ጠጥተው ተመለሱና ከድንኳናቸው ትይዩ ካለው ሣራማ ቦታ
ቁጭ ብለው ጨዋታ ሲጀምሩ! ጨዋታቸው ያልጣማት ጎይቲ ከነሱ
ፈንጠር ብላ ወደ ወንዙ ሄዳ ቁጭ ብላ መቆዘም ቀጠለች።

“ጋልታምቤ! ለምንድን ነው የሐመር ሴቶች ከወንዶች ጋር ተሰብስበው በጋራ ችግር ላይ እማይወያዩት?" አለችው ካርለት አንተነህ ይመርን ከብት ዘሎ በተጠራበት ስም ጠርታ: እሱም የሰማውን ለማስታወስ አይኖቹን ከደን ከፈት ራሱን ከፍ ዝቅ
ሲያደርግ ቆየና፡-

“አንድ ጊዜ ቦርጆ /አምላክ/ እግሮቹ ጭቃ ውስጥ
ገብተውበት ማውጣት አቅቶት ሲታገል
ቅራቅንቦአቸውን ተሸክመው ወሬያቸውን እየሰለቁ ሲጓዙ ያያቸውና ይጠራቸዋል እባካችሁ ከዚህ ማጥ አውጡኝ ይላቸዋል። ሴቶቹ
ግን ምንም ርህራሄ ሳያሳዩት ይእ!እንቸኩላለን የማነው ቀልደኛ ብለውት ይሄዳሉ። በዚያ ወቅት ቦርጆ አዝኖ ለቁምነገር አትብቁ
ዘላለም እንደቸኮላችሁና እንዳወራችሁ ኑሩ ይላቸዋል አሉ።

“ጥቂት ቆይቶ ደግሞ ወንዶች ለማር ቆረጣ የያዙት እሳት
እንዳይጠፋባቸው እየተቻኮሉ ወደ ዱር ሲሄዱ ቦርጆ ያያቸውና! እባካችሁ ኸዚህ ማጥ አውጡኝ ብሎ ይጣራል የሐመር ወንዶችም እርስ በርሳቸው ይተያዩና የተሽከሙትን አስቀምጠው
እሳቱም ጠፍቶባቸው ቦርጆን ከጭቃው ያወጡታል። በዚህ ወቅት
ቦርጆ ለማህበረሰባችሁ የምታስቡ ችግራችሁንም
የምትፈቱ አስተዋይና የረጋችሁ ሁኑ ብሎ መረቃቸው:

ስለዚህ ከዚያን ጊዜ
ወዲህ ስለ ሐመር ማሀበረሰብ የማሰብ የመወያየትና የመወሰን መብቱ የሐመር ወንዶች ብቻ ሆነ...” አላት።

ይእ!  ምነው ካርለቴ ያላመመሽን ባታሺ  አሁን ድፍን ዓለም የሚያውቀውን ነገር እየጠየቅሽ ከምታዳምጭ የመኪናሽን
መብራት ተግ አርገሽ አብርተሽ አያ ደልቲን ብንፈልገው ምን
ነበረበት! እንዲያው ምኑን ጨካኝ ልብ ሰጠሽ..." ብላ ጎይቲ ምርር ስትል ካርለት ፈገግ ብላ ጎይቲን አየቻት።

“አይዞሽ! አጠገቡ ደርሰናል!
ከእንግዲህ ጀግናው
አይጠፋብንም!" ብላት ተጨማሪ ጥያቄ ጠይቃ ጎይቲን ላለማስከፋት
አንተነህን ይቅርታ ጠይቃ ወደ ድንኳኗ ሄደች፡ ጎይቲም ትኩር ብላ ተመለከተቻትና፡-

“እስኪ እንዳፍሽ ያድርገው!"ብላ ተከተለቻት።

💫ይቀጥላል💫
👍19👎1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

በአትኩሮት ቢያየኝ እኮ በአፌ ልትወጣ የደረሰች ልቤ ስትደልቅ የለበስኩትን ሸሚዝ እያርገበገበችው ነው። በጀርባዬ የሚንቆረቆር ላቤ ለአፍታ ሌሎች ድምፆች ረጭ ቢሉ፤ ከማጅራቴ ወደ መቀመጫዬ ሲወርድ እንደ ዝናብ <ጠብ> ሲል ይሰማ ነበር። ስክሪኑ ላይ ያለውን የራሴን ምስል ሳየው ለመኮሳተር (የማላስታውሳትን የድሮዋን ሜላት ለመምሰል) በታገልኩ ቁጥር የዞረበት ፊት እያሳየሁ እንደሆነ ገባኝ። እጄን የያዘው የጎንጥ እጅ (ገባቶት ነው መሰለኝ) እንደመጭመቅ ሲያደርገኝ ትኩረቴን ከራሴ ፊት ላይ ወደ ኪዳን መለስኩ። መስሎኝ የነበረው ከወንበር ጋር ታስሮ እየተሰቃየ የማየው ወይም ያ ድምፁን የሰማሁት ሰውዬ ግንባሩ ላይ ሽጉጥ ደግኖበት አልያም ፊቱ በድብደባ ብዛት አባብጦ እና በደም ተለውሶ ነገር የማየው ነበር የመሰለኝ። የሆነው ግን ሌላ ነው። ኪዳንና ሰውየው እየተዝናኑ እንጂ አጋች እና ታጋች በማይመስል ሁኔታ አጠገብ ላጠገብ ተቀምጠዋል። ኪዳንን ለመለየት አልተቸገርኩም። የስልኬ ስክሪን ላይ ካለው መልኩ ምንም ለውጥ የለውም። አስቀድሞም በግራ መጋባት የጦዘውን ጭንቅላቴን ልክነት ያጠራጠረኝ የኪዳን መረጋጋት ነው። የሆነ ልክ ሰላም ልንባባል የተደዋወልን አስመስሎ

«ሜልዬ! ደህና ነሽልኝኣ?» አለ። ምንድነው እየሆነ ያለው? ኪዳን አይደለም ይሆን? ሰውየው ቅድም 12 ቦታ ቀነጣጥሼ እልክልሻለሁ ሲለኝ አልሰማም ማለት ነው? አሁንም የጎንጥ እጅ አነቃኝ።

«እኔ ደህና ነኝ! አንተስ?» ይባላል ቆይ? ከአጋቹ ጋር የተቀመጠ ሰው ደህና እንደማይሆን ግልፅ አይደል? እሱ ዝንቡ እንኳን እሽ እንዳልተባለ ሰው ዘና እያለ ታዲያ ምን ልበል? ምናልባት ለእኔ ብሎ ይሆን? እኔን ለማረጋጋት?

«አታስቢ ደህና ነኝ! ከልቤ ደህና ነኝ።» እያለ ምንም ያለመጎዳቱን ሊያሳየኝ ስልኩን እያራቀ ከተቀመጠበት ተነስቶ መላ አካላቱን አሳየኝ። እያባበለኝ ነገር መሰለኝ።

«እንዴት ነው የማላስበው? መዝናኛ ቦታ …… » እኔ ባልገባኝ ምክንያት ለእርሱ ግን ልክ በመሰለ እንድናገር አልፈለገም። ወዲያው አቋርጦኝ

«ሜል እንዲሁ ተጨነቂ ስልሽ ነው። እኔኮ ደህና ነኝ አልኩሽ። » ሲለኝ ጎንጥ ምን እንዳናደደው ሳይገባኝ ተበሳጭቶ ጥርሱን ነክሶ እኔን ባልያዘው እጁ አየሩን በቦክስ ጠለዘው። እየሆነ ያለው ነገር አፍና ጭራው የጠፋኝ እኔን ብቻ ነው? እኔ ሳይገባኝ እሱ የገባው አብረን ከሰማነው የደህና ነኝ መልእክት ውጪ ውስጠ ወይራ አለው? « በኋላ እንገናኝ የለ? እስከዛ ደህና ሁኚልኝ! ደግሞ አምላክን በልመና አታድክሚ!!! የምትችውዪውን አድርጊና በተረፈው አመስግኚው። ያመሰገንሽው አምላክ የጎደለውን ይሞላልሻል።» አለኝ ጭራሽ። የድሮዋ ሜላት ፀሎተኛ እንዳልነበረች ጠፍቶት ነው? ይሄንኑ ዓረፍተ ነገር ግን ከዚህ በፊት የሆነ ሰው ብሎት ሰምቻለሁ!! የት ነው የሰማሁት?

እስካሁን ድምፁ ያልተሰማው ሰውዬ ስልኩን ተቀበለውና በአይኑ እንደመጥቀስ አድርጎኝ ዘጋው!! አፌን እንደከፈትኩ ስልኩ ላይ አፍጥጬ ቀረሁ።

«ይሄ የውሻ ልጅ አውቆታል!» አለ ጎንጥ። መኪና ውስጥ ሆነ እንጂ ሜዳ ላይ ቢሆን <ዘራፍ> የሚል ነው የሚመስለው።
«ምኑን?» አልኩኝ ከድንዛዜዬ ሳልወጣ

«እየቀረፅሽው እንደሆን !» ብሎ ስልኩን እንድሰጠው እጁን ዘረጋልኝ። ስሰጠው ስልኩ ስክሪኑ ቆልፎ ስለነበር እንድከፍትለት መልሶ ሰጠኝ። ያለኝን የምከውነው ምኑም ገብቶኝ አይደለም። ያለውም የገባኝ ነገር የለውም።

«ማን ነበርኩ? ከምን ጋር የተቆላለፈ ህይወት ነው የነበረኝ? የምን ቪዲዮ ነው የምወስድለት? ስልኬ ውስጥ ያለ ነገር ይሆን?»

«ህም! ስልክሽ ውስጥ ልታኖሪው አትችዪም!» ሲለኝ አፌን ከፍቼ ቀረሁ። ስለቪዲዮው ያውቃል!!

«ምን ይመስልሃል ቪዲዮው?»

«እሱን በምን አውቄው! ብቻ ቅሌቱን የተሸከመ ነገር ነው የሚሆን»

ድንዝዝ እንዳልኩ አይኔ ብቻ ሲንቀዋለል ስልኩ ላይ ቅድም የተጫናት ምልክት ስክሪኑን መቅጃ መሆኗን እና ሰውየው እንደመረጃ እንዳንይዝበት ኪዳንን ምንም የተለየ ምልክት እንዳይሰጥ አስጠንቅቆት እንደሆነ እርግጠኛ ሆኖ ከነገረኝ በኋላ እኔን ረስቶ የተቀዳውን ቪዲዮ እየደጋገመ ወደፊት ወደኋላ ቅርብ …. ራቅ እያደረገ ያያል። እኔ ደግሞ ዝም ብዬ እሱን አየዋለሁ።

«በስተመጨረሻ ልመና አታብዥ ያለው ነገር ያላስፈላጊ ቦታ የተዶለ አይመስልሽም? ላንቺ የሚያስታውስሽ ነገር አለ?» አለኝ አሁንም ከስክሪኑ አይኑን ሳይነቅል።

«የሆነ ሰው ሲለው የሰማው ይመስለኛል። አላውቅም!! ራሴም እለው የነበረ ነገር ይመስለኛል። ምንም መጨበጥ አልቻልኩም።» ስለው እንባዬ ዓይኔን ሞልቶታልኮ እሱ ግን አላየኝም። ቪዲዮውን ኪዳን ስለምስጋና ያነሳበት ጋር አቁሞ

«ተመልከች እዚህ!!» ብሎ ሰውየውን ጠቆመኝ « ልክ ኪዳን ሲናገር ፊቱ አንድ አፍታ ይቀየራል። ተመልከች! ያ ማለት ይህ መስመር እንዲናገር ከተፈቀደለት ውጪ ነው ማለት ነው! ሊገልጥልሽ የፈለገው አንድ መልእክት ቢኖረው ነው።»


«ጎንጥ?» አልኩት ፍስስ ባለ ድምፅ

«ወይ!» አለ አይኑን እዛው እንደሰነቀረ

«ማ ነ ህ? » አልኩት እንባዬ አብሮ ከቃላቱ ጋር ዱብ ዱብ እያለ። እዛ ነጥብ ላይ ጎንጥ ዘበኛዬ ብቻ እንዳልሆነ ገብቶኛል። የሚያስለቅሰኝ በትክክል ምን እንደሆነ እንጃ።

«ኸረ በመድሀንያለም?! » አለ ደንግጦ የሚያደርገው ጠፍቶት ። እጄን ሊይዘኝ እጁን ሲሰድ መንጭቄ ቀማሁት

«እንዳትነካኝ! ሁሉንም ነገር ታውቃለህ! ይሄን ሁሉ ጊዜ ስሰቃይ እያወቅክ ምንም እንደማያውቅ አብረህ ስታፋልገኝ ነበር። ሰውየው ያወራው ሁሉ ነገር ገብቶሃል። ንገረኝ አንተም የእነሱ ወገን ነህ? ምን ፈልገህ ነው?» እንባዬ ባይቆምልኝም ሰውነቴ ሲቆጣ ፣ ደሜ ሲሞቅ ይታወቀኛል።

«መድሀንያለም በሚያውቀው እንደሱ አይደለም!! አንች ያሰብሽውና የእኔ ድርጊት ለየቅል ነው!! ሀሳቤ ጠላትነት ከነበር ምን እጠብቅ ነበር? ከጠዋት እስከማታ እጀ ላይ አልነበርሽ?»

«አላውቅም! የሆነ የምትፈልገው ነገር ይኖራላ!!» ተነስቼ ከመኪናው ወረድኩ። ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ድረስ ንዴቴ ያጨሰኝ ጀመር። የመኪናውን ጎማ በሃይል መጠለዜን ያወቅኩት የእግሬን አውራ ጣት ሲያመኝ ነው። የሆነ ውስጤ ተኝቶ የነበረ አውሬ የነቃ ይመስል የምቦጫጭቀው ነገር ፣ ቁጣዬን የምወጣበት ነገር ፈለግኩ። እሪሪሪ ብዬ መጮህም ፈለግኩ። የመኪናውን ኮፈን በቡጢ እየነረትኩ ማቆም እፈልጋለሁ ግን እጄን የምሰነዝርበት ቁጥር በጨመረ ልክ ሰውነቴ እየረገበ ፣ ቁጣዬ እየበረደ ስለተሰማኝ አላቆምኩም። ከመኪናው ወርዶ መምጣቱን ያወቅኩት አጠገቤ መጥቶ ሁለቱን እጄን ለቀም አድርጎ ሲያስቆመኝ ነው።

«አትንካኝ አልኩኮ!! » ብዬ ከመጮሄ እኩል በምን ቅፅበት እንደሰነዘርኩት ያልተቆጣጠርኩት ለቡጢ የተጨበጠ እጄ ጉንጩ ላይ አርፏል። ያደረግኩትን ሳውቅ ደንግጬ የመታሁበትን እጄን እንደበዓድ እጅ አየሁት። ከመኪናው ኮፈን ድብደባ ይሆን ከእርሱ ጉንጭ እጄ በልዟል። ወደኋላ ዞሮ አፉ ውስጥ የሞላውን ደም ከተፋ በኋላ ወደ እኔ እየዞረ በሱ ብሶ ይጮህ ጀመር
👍27
« ከበረደልሽ ድገሚኝ!! እ? በያ!» እያለ ለፀብ ይጋብዘኛል። ትቼው ወደመኪና ልገባ ስል እየተከተለ ሆነ ብሎ ይገፋፋኛል። «ይህችን ታህል ነው የተናደድሽብኝ? ለዝህችው ነው የጎፈላሽው?» ሲለኝ እንዴት ዥው ብዬ እንደዞርኩ አላውቀውም። እጄን ስሰነዝር በሚያስደነግጥ ፍጥነት በመዳፉ ቀለበው። ያልቆጠርኩትን ያህል ጊዜ ተከላክሎ አንዴ ነው አጓጉል ያገኘሁት። ዋጥ አደረጋት!! ቁጣዬ ረጭ ማለቱን ያወቅኩት ይሄኛው የድሮዋ ሜላት ማንነት መሆኑን መገንዘብ ስጀምር ነው።

«ደግ! አሁን ከሰከንሽ እየተጓዝን ስለኪዳን እናውጋ?» አለኝ የመታሁትን ጉንጭ እያሻሸ ወደመኪናው እየገባ
«ጉንጭህን አገላብጠህ ስለሰጠኸኝ እንዳምንህ ነው የምትጠብቀው?»
«እና ምን ይሁን ነው የምትይ? እዚሁ ቁመን ይምሽ? አንዱን አካሉን እዚሁ እንዲልኩልሽ ነው ያሰብሽ?» እየጮኸብኝኮ ነው። ከቃላት ሁላ በላይ ሆነብኝ እና አፌን ከፍቼ አፍጥጬ አየው ጀመር

«አንተ ግን የምርህን ነው? ካንተም ብሶ …….. » አልጨረስኩትም እየሮጥኩ መኪና ውስጥ ገባሁና ስልኬን አነሳሁ። አጎቴጋ ደወልኩ። ተከትሎኝ ገብቶ የማደርገውን በትኩረት ያያል።

«አጎቴ እናቴን አገናኘኝ እስቲ የሆነ ሳልጠይቃት የረሳሁት ነገር ትዝ አለኝ።» አልኩት

«እናቴ ? በቀደም <አምላክን በልመና አታድክሚ!!! የምትችውዪውን አድርጊና በተረፈው አመስግኚው!! ። ያመሰገንሽው አምላክ የጎደለውን ይሞላልሻል> ብለሽኝ ነበርኣ?»

«አዎ የእኔ አበባ ምነው?»

«አጎቴንም እንደዛው ስትዪው ሰምቻለሁኣ?»

«ሁሌምኮ የምለው ነገርኮ ነው ልጄ?» አለች ግራ እየገባት።

«የተለየ ትርጉም ነገር አለው እንዴ?»
«ኸረ ምንም ቅኔ የለውም ልጄ! ምን ጉድ ነው?»
«እንዲሁ ነው የሆነ ሚስጥር የያዘ አረፍተነገር ይመስል ውስጤ ተመላለሰ። ድንገት ሌላ መልዕክት ካለው ብዬ ነው።»
«በፍፁም! ሁሌም ሰዎች እጅ እግራቸውን አጣጥፈው በቀላሉ መስራት በሚችሉት ነገር ሁሉ ሳይቀር ፈጣሪን በልመና ሲያደክሙ እንደዛ እላለሁ። »

«እሺ በቃ እናቴ» ስልኩን ዘግቼ አስባለሁ። ምንም ሳይለኝ መኪናውን መንዳት ቀጠለ።

«እኔን አይደል የሚፈልጉት? እኔ ሄድላቸዋለሁ! እኔን የሚያደርጉትን ያድርጉና ወንድሜን ይለቁታል።» አልኩኝ ለራሴ ያሰብኩትን ድምፄን አውጥቼ እየተናገርኩት

«ህእ! አንቺን ቢፈልጉ እስከዛሬ ላንቺ የሚሆን አንድ ጥይት ጠፍቷቸው ይመስልሻል? ካንቺ በላይ የያዝሽባቸውን መረጃ ይፈልጉታል።» አለ <ቂል ነሽ እንዴ?> በሚል ለዛ

«ሊገድሉኝ ሞክረው የለ?»
«እኔን ከጠየቅሽኝ በፍፁም እነሱ አይመስሉኝም!!»

«እሺ ያለውን ቪዲዮ የምናገኝበት ፍንጭ ታውቃለህ? መቼም የማታውቀው ነገር የለም!» አልኩት አፍንጫዬን እየነፋሁ።
«አላውቅም!!» አለኝ በመድከም አይነት።

«ስለዚህ እሄዳለሁ። አትከተለኝም። እውነቱን እነግራቸዋለሁ።» አልኩኝ ፍርጥም ብዬ
«የማይደረገውን!!» አለ ኮስተር ብሎ

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍1310
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ኮንችትና ሶራ የሰጎን ላባ የተሰካበትን የራስ ጌጥ(ጶሮ) እንደ አቦ ሸማኔ
አይን አሸጋግሮ  እየተንተገተገ የሚመለከተውን አይኑን የተተለተለ ሳንቃ ደረቱን እየተመለከቱ  ከንፈሩን አሞጥሙጦ የሚያሽለከልከው ትንፋሹ ከፍ ዝቅ በሚሉት ጣቶቹ እያንኳለለ የሚያጣው ስሜተ ሰላቢ ዜማውን ሳይንቀሳሱ ሲያዳምጡ  ወይሳ ተጨዋቾቹ ድንገት ዜማውን ቀጥ አደረገና መሳርያውን አንስቶ ሲያቀባብል ሶራና ኮንቺት
ድንግጥ ብለው ሲመለከቱ ድው አድርጎ ሲተኩስ አመዳቸው ቡን ብሎ ነፌሴ አውጪኝ መሬት ላይ ሲንበለበሉ እንደገና ተኮሰ።

ከዚያ ለጥቂጥ ሰአታት ከመሬቷ ጋር ተላትመው ጠበቁና ቀና ብለው ሲመለከቱ   ሰውየው ኦሞ ወንዝ ዳር ሄዶ ተረጋግቶ ወንዝ ዳር ሄዶ ቆሟል ኮንቺት እየተሳበች ወደ ሶራ ተጠግታ

"ለምን ተኮሰ? አለች ሶራን።

"አልገባኝም"

"አይቶን ይሆን?"

አይመስለኝም ቢያየን ወይንም ድምፅ ሰምቶረ ቢሆን ኖሮ በሁኔታው ማወቅ እንችል ነበር።

"እሱስ ልክ ነህ ቢገርመኝ እኮ ነው ተረጋግቶ መቆሙም ለጠየቅሁት ጥያቄ ፍንጭ ሰጪ አይደለም ስትለው ከኦሞ ወንዝ ማዶ ድምፅ ተሰማ ሰባቶ ጎረምሶች ናቸው። ወደ ወንዙ ሲጠጉ

"ፃሊ!” አላቸው በካሮኛ  ሰላም ናችሁ ለማለት:

'ፃሊና..." አሉትና አምስቱ ወንዙ ዳር እንደቆሙ ፤ ሁለቱ ዳር ላይ የቆመች ቀጠን ብላ ረዘም ያለች የእንጨት ታንኳ ላይ
ወጡና በረጅም ዘንግ ውሃውን ቁልቁል ሲገፉት ታንኳዋ እንደ ውሃ
እናት ውሃውን ወደ ጎን እየሰነጠቀች መጣች::

ለካ የተኮሰው እነሱን ለመጥራት ነው:: ጥሪ በተኩስ አይገርምም!” ስትል ሶራ በአድናቆት ራሱን ወዘወዘ።

“እነሱ ግን እነማን ናቸው?"

"አላውቅም ኮንችት  ብናነጋግራቸው ይሻላል?" ሲላት ወዲያው ከተደበቁበት ወጥተው ወደ ሰውዬው ሲጓዙ ፊቱን ዞሮ
የቆመው ሰው የሰው ዳና ሲሰማ ከመቅፅበት መሳሪያውን ከትከሻው
አውርዶ፡-

“ከጠን ማሲዲ" ብሎ መሣሪያውን አቀባብሉ ደገነባቸው።

“ኖት አሱስቴ" አለች ኮንችት በስፓኒሽ እጅዋን እያወዛወዘች ተረጋጋ ለማለት:

ባለመሣሪያው ትኩር ብሎ ሲያያቸው ቆየና “ነጋያ! አለ
ከተቀመጠበት ተነስቶ መሳሪያውን ወደ ትከሻው እየመለሰ: ሶራ ለሰላምታ አፀፋውን መለሰ። “...ሐመር አፎ ዴሲቲኒ"  አለው ባለመሣሪያው ሐመርኛ ትችላለህ ለማለት።

ሶራ ፈገግ ብሎ “ሊካ ሊካ ቂንሲዲ...” (ትንሽ ትንሽ
እችላለሁ) አለው። ባለመሳሪያው ፈገግ አለ: ያኔ ነብርነቱ ተለውጦ
እንደ ድንቡሽዬ ህፃን ፈገግታው የሚማርክ ሆነ

ባለመሳሪያውና ኮንችት ከሁለቱ የታንኳዋ ቀዛፊዎች ጋር ተሻግረው ሲጠብቁ ሶራ ጀልባዋን ይዞ ሄደና በጀርባቸው አዝለው
ጀልባዋን ከአምስቱ ጎረምሶች ሁለቱ እየተሳሳቁ ተሸክመው ጫካው
ውስጥ ገቡና በመስመር ሆነው በትላልቅ የግራር የኮሶ... ዛፍ ውስጥ ለውስጥ ትንሽ እንደተጓዙ ኮንችትና ሶራ ዛፍ ላይ እንደ ጦጣ የሚንጨዋለሉ ልጆች አዩ: ቆይቶ ደግሞ በቋንቋቸው ቶሎ ቶሎ
የሚናገሩ ልጃቸውን በቆዳ ብብታቸው ስር ያዘሉ እናቶችና ሽምገል
ያሉ ወንዶችን አዩ።

ጨቅላ ህፃናት ዛፍ ላይ በቆዳ ተንጠልጥለው አንዳንዶቹ ተኝተው እየተቁለጨለጩ ሲወዛወዙ እያዩ እንደ ሄዱ ከርቀት ላይ
የወፍ ጎጆ የሚመስል የኤሊ ቅርፅ ያለው ጎጆ ቤት ተመለከቱ።

ኮንችትን ሲያዩ ህፃናት  ወላጆቻቸው ጉያ እየገቡ ወደ መንደራቸው እየሮጡ አለቀሱ: ለኩዩጉ ህፃናት አስፈሪው አውሬ ቀላ ያለ ልብስ ለባሽ ሰው ነው። ከፍ ያሉት ግን የመጣው ይምጣ ብለው በቋንቋቸው ሰላም ቢሏትም ፍርሃታቸው ግን ያስታውቃል: ለጊዜው
ሰላምታቸውን ልብ ብላ አልተከታተለችም ነበር ድንገት አንድ ሽማግሌ፡-

“አሹቃ” ሲሏት አያቷ የነገራት ሰላምታ ትዝ አላት:
ኮንችት አያቷ የሚጠቀምባትን መቀመጫ የመሰለች ሁሉም
ሽማግሌዎችና ወንዶች ይዘው አየች:: ሶራን ዘወር አለችና ምን የሚባሉት ማህበረሰቦች ናቸው?" አለችው ማፕ ላይ ያየችውን ስም ለማስታወስ እየሞከረች:: ሶራ መጀመሪያ ያዩትን ባለ ዋሽንት ጠየቀው።

ሙጉጅዎች ናቸው። እነሱ ግን ራሳቸውን ኩዩጉ ነው
የሚሉት አለው ነገራት ሶራ  ለኮንችት። ማፕ ላይ መጉጅም ሆነ ኩዩጉ የሚል እንዳላየች እርግጠኛ ነች: ለማረጋገጥ ግን ወዲያው
ማፕዋን ዘርግታ አየች፤ ሁሉም እሷ ላይ አፈጠጡባት። ማፑ ላይ
የሉም። ካርታው ላይ አየች የሉም፤ ይበልጥ ደነቃት።
ኦኗኗራቸውም ልዩ ነው ፤ የጫካና የወንዝ ዳር ሰዎች: ከመንደሩ እንደደረሱ ሰዉ በአድናቆት ቆሞ አያቸው: ህፃናት ራቅ ብለው ሽሽተው ያያሉ:: አንዱ 'መጡላችሁ' ሲል ሌሎች ህፃናት ደግሞ
እየተሯሯጡ በመላቀስ ይጯጯሃሉ…..

ኮንችት ከጀርባዋ ያዘለችውን ጓዟን አውርዳ ተለቅ ተለቅ ያሉ የአያቷን ፎቶ አወጣች: የዘጠኝ ሰዓት ፀሐይ አሁንም ማቃጠሏ
እንብዛም አልቀነሰም:

ፎቶውን የያዘውን እጅዋን ወደ ህዝቡ ዘረጋችው። ፈሯት፤በምልክት እንኩ' አለቻቸው: ትክ ብለው እያዩ ዝም አሏት ከዚያ ባለዋሽንቱ ውሰዱ' አላቸው በሐመርኛ።

ሶራ ደስ አለው የራሳቸውን የሆነውን ቋንቋ ሲናገሩ
አንድም ቃል ሊገባው አልቻለም ነበር ሐመርኛ ከቻሉ ግን እሱም
ሊያናግራቸው ይችላል። ኩዩጉዎች ግን ሐመርኛን ብቻ አይደለም የሚችሉት። ሙርሲኛ ኒያንጋቶምኛም ይችላሉ።ስለዚህ ሶራ
በሐመርኛ፦

“ውሰዱና እዩ ችግር የለም” አላቸው። አሁንም ዝም ብለው ኮንችትን ሲመለከቷት ቆዩና አንዱ
ሽማግሌ ሌላውን በጆሮው አናገረው ከዚያ ብድግ ብሎ መጣና ተቀበላት።

ፎቶውን ዘቅዝቆ ስለያዘው ኮንችት አስተካክላ ሰጠችው ሽማግሌው ቀረብ እራቅ አድርጎ አየውና በቋንቋው የሆነ ነገር
ተናግሮ ወደ ሀዝቡ ሲጠጋ ለማየት ህዝቡ እንደ ንብ ዙሪያውን ከበበውና ሁካታ ሆነ: ማንም ሌላውን አያዳምጥም።

ከዚያ ሁሉም እነ ኮንችትን ጥለው እንደ ድንጉላ እምም.. እያሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ተሯሯጡ: ኮንችትና ሶራ እርስ በርስ
ተያዩ ህዝቡ የሄደበትን ምክንያት ግን ከመካካላቸው ሊመልስ የቻለ አልነበረም።

አንድ ጎጆ ቤት ሲደርሱ ሁሉም ቆሙ። ከውስጥ የሆኑ ሽማግሌ አንጀታቸው ካጥንታቸው ጋር የተጣበቀ አጎንብሰው ወጡ ህዝቡ አሁንም ክብብ አደረጓቸው።
ከዚያ እንደገና ሁካታ ሆነና ጎረምሶች እየተሯሯጡ ርቀው ሄዱ። ፎቶዎችም በልጥ ታስረው ሽማግሌው ከወጡበት ጎጆ ፊት
ለፊት ተንጠለጠሉና ሴቶች ሰማይ ሰማይ እያዩ እልልታውን አቀለጡት ወንዶች እየዘለሉ ጭፈራ ጀመሩ።

ኮንችትና ሶራ እንደገና ተያዩ። ምን እየተሰራ እንደሆነ ማወቅ ተሳናቸው: ባለ ዋሽንቱን ጠየቁት፤ መልስ አጡ። ከዚያ
አራት አምስት መሳሪያ የያዙ ሽቅብ ተኮሱ።

ኮንችትና ሶራ ደነገጡ፡ “ምን እየሰሩ ነው ሶራ?" አለች
የሶራን ትክሻ እየወዘወዘች
በፍርሃት: ሶራ ትከሻው ከፍ ዝቅ አድርጎ አላውቅም አላት በምልክት።  ሰው ከየጫካው ተሰባሰበ !
ጥሩንባው እየተነፋ እልል መባል ጀመረ።

ጫካ የሄዱት ጎረምሶች በሾርቃ የሆነ ነገር ይዘው
እየተሯሯጡ መጡ የደከማቸው አይመስሉም የግንባራቸው ደም
ስር ግን ውሃ እንደሽረሸረው የዋርካ ስር አበጥ አበጥ ብሎ በየአቅጣጫው ተጋድሟል። እንደ ተመለሱ ከህዝቡ መሃል ገቡ
ከሌላ ጎጆ ደግሞ ማር የያዘ ትልቅ ቅልና ውሃ ሌሎች ጎረምሶች አመጡ። ውሃውና ማሩ ተቀላቀለና በእንጨት ተማሰለ።

ከዚያ ጥሩንባው እየተነፋ እልል እየተባለ እየተጨፈረ... ሁሉም የሉካዬን ስም እየጠሩ ሰማይ እያዩ ቆዩና ከሲታ ሽማግሌውን አስቀድመው ሶራ ኮንችትና ባለወይሳው ወደ ቆሙት እያሸበሸቡ
እየዘለሉ ጡሩንባው እየተነፋ መጡ።
👍18😢2👏1
ሽማግሌው ወደ ባለወይሳው ጠጋ ብለው በትልቅ ሾርቃ የተጠሰጠውን ብርዝ ጉንጫቸው እስኪነፋ የያዙ “ፕስስ…” ብለው
ረጩበት

ህዝቡ  እልል ይላል ይጨፍራል ዳንኪራ ይረግጣል…ሰማይ ሰማይ ያያል።

ሽማግሌው ወደ ኮንቺት ደግሞ ጉንጫቸውን በብርዙ
ነፍተው  ተጠጉ ኮንቺት ምን እንደሚመጣ አታውቅም ግራ ተጋብታለች

ፕስስ ብለው ፊቷ ላይ ብርዙን እንደ ወጨፎ ዝናብ
ሲያረከፈክፉባት እጆችዋ ለመከላከል ዘርግታ። ወጀ ኋላዋ  እያፈገፈገች የጩኸት ድምፅ አሰማች:: ህዝብ ዋ…” ብሎ ሳቀባት።
ሽማግሌጡ ወደ ሶራም ሄዱ…

ምንድን ነው ሶራ አለችው ሽማግውና ህዝቡ
እየጨፈሩ ጎጆ ላይ ወደ ተንጠለጠለው የሎካዬ ፎቶ ሲሄዱ:: ሶራ ባለ ወይሳውን ሊጠይቀው ሲሄድ በርቀት ሽማሌው በሎካዬ ፎቶ ላይ
ፕስስ…” እያሉ ብርዙን ሲያርፈክፉበት አየች:

ህዝቡ እንደገና ሽማማሌውን ተከትሎ ወደ እነ ኮንችት መጣ: ኮንችት ልትሮጥ አሰበች: የልጅ ሃሣብ ሆነባት ሃሣቧ
አታመልጥም:: እየጨፈሩ አየሳቁ... ጦራቸውን እየሰበቁ ከሚዘሉት
በታምርም አትጠፋም::

ሽማግሌው በሾርቃ ያለውን ብርዝ ለባለዋሽንቱ ሰጡት:
ስምጥጥ አድርጎ ጠጥቶ መልሶ ሰጣቸው:: ለኮንችትም አቀበሏት
በሚንቀጠቀጠው እጅዋ ተቀብላ አጮልቃ እያየች ፉት አደረገችና እየፈራች
እጅሞን ዘረጋች: ተቀብለዋት ወደ ሶራ ሄዱ.

ጭፈራው ዝላዩ ዘፈኑ… ጥሩንባው ተኩሱ ቀጠለ

ምንድነው ሶራ? ተኩሱን በሰማች ቁጥር የምትናጠውና
የምትንቀጠቀጠው ኮንችት ደግማ ጠየቀችው።

በኩዩጉ ባህል እንግዳ ሲመጣ ብርዝ ተበጥብጦ ፊቱ ላይ ይርከፈከፍና ብርዝ እንዲጠጣ ይደረጋል:: እንግዳውን እንዲህ ብርዝ
አጠጥተው ሲቀበሉት ብዙ ሽንት ይሸናል: ያ በየጫካው ያለው ቀፎአችን በማር ይሞላል ብለው ያምናል" አላት ከባለወይሳው ጠይቆ
የተረዳውን ። ይህን ሲባባሉ ኩየጉዎች ተመልሰው መጡ። ጎረምሶች ጫካ ገብተው ያመጡትን ሾርቃ ሽማግሌው ይዘዋል: ሽማግሌው ቀጥታ ወደ ኮንችት ሲመጡ ኮንችት ክው  አለች: መንቀሳቀስ
ተሳናት ሽማግሌው አጠገቧ እንደደረሱ ከሾርቃው ውስጥ ካለው የጎሽ
እበት አውጥተው በፍርሃት እንሶስላ ከመሰለው ጉንጯ ላይ ሲቀቧት ነፍስና  ስጋዋ እንደተለያዩ ሁሉ ሽቅብ ነጠረች እልልታ ጭፈራ ሆነ።

ሽማግሌውና ህዝቡ የአያቷ ፎቶ ወደ ተንጠለጠለበት ጎጆ ተመሰሱ። ጭፈራው ይበልጥ ደመቀ፡ “ሉካዬ.. የሚለው ጥሪ በረከተ ወደ ጫካው አቅጣጫ ተኩሱ በዛ።

ሶራ ግራ ገብቶታል! ኮንችትን ሊያረጋጋት ግን ፈልጓል። እሷ እሱ ላይ እሱ ደግሞ ባለወይሳው ላይ ቢያፈጡም በቂ መልስ
አጥቷል: ስለዚህ ወደ አንዱ ኩዩጉ ፈራ ተባ እያለ  ተጠጋና አናገረው: ከዚያ ፈገግ ብሎ ወደ ኮንችት ተጠጋ: ኮንችት ሊነግራት
የፈለገው ነገር እንዳለ ገምታለች: ከህዝቡ ላይ ግን አይኗን ማንሳት አቃታት:: ፈርታለች!  ስለዚህ አይኗን አሸጋግራ እንደተከለች ጆሮዋን ደቀነችለት።

“ሎካዬ ተመልሶ መጣ ይላሉ" አላት:: ሶራ ያነጋገረው ኩዩጉ ትንሽ ራቅ ብሎ በትዝብት ያያቸዋል:

“ለምን?”

"ፎቶውን አይተው"

""ፎቶውን ብቻ አይተው?"

"አዎ"

“እንዴት? ስትል አጠገባቸው ቆሞ የነበረው ጨዋታቸውን እንዳወቀ ሁሉ በክፍት ሾርቃ ውሃ ሞልቶ ወደ ኮንችት ተጠጋ
በምልክት ጠጋ በይ አለና ሾርቃው ላይ አንገቷን ጎንበስ አደረገላት:
ከዚያ ደሞ ራቅ እንድትል አድር ሳቀ: አልገባትም! ሶራን የርዳታ እይታ አየችው::

ቅድም ምን ነበር ያለኝ መሰለሽ ውሃ ዳር የቆመ ሰው ምስሉን ውሃ ውስጥ ማየት ይችላል: ሰውዬው ከሌለ ግን ምስሉም
ውሃው ላይ አይኖርም። እኔ ኦሞ ወንዝ ስለሄድኩ ውሃው ላይ ማን ምን ሊያየው ይችላል:: የሎካዬን ምስል ያየነው እሱ ሰማይ ላይ
ስላለ ነው። እሱ ሰማይ ላይ ባይኖር ምስሉ አይኖርም። ሎካዬ ሰማይ ላይ ሆኖ መልእክተኞችን እኛ ዘንድ ላካችሁ ለዘመናት ጠፍቶ ኑሮ አሁን መምጣት ሲችል ከመምጣቱ በፊት መልዕክተኛ መላክና
'ተዘጋጁ' ማለቱ የአባቱን ባህል አክባሪ በመሆኑ ነው።

“እኛም ዛሬ ምስሉን አይተን ደስ ብሎናል። በሳልስቱ ደግሞ እሱ ሰማይ ሆኖ አይቶን ከተደሰተ ይመጣል። ስለዚህ እሱን  ለማስደሰት እንጨፍራለን ሴቶች እልል  ይላሉ...እንዲያውም
የኩዩጉ ሽማግሌዎች ሎካዬ የጠፋውን ነጭ እባብም ይዞልን ይመጣል እያሉ ነው' አለኝ አላት ሶራ ለኮንችት:

"የምን ነጭ እባብ?” ተገርማ ጠየቀችው:

ፎቶው ላይ ሎካዬ በአንገቱ የጠመጠመውን ነጭ የአንገት መጎናፀፊያ አይተው የጠፋው ነጭ እባብ ነው ይላሉ: ነጩ እባብ የስላም ምልክታቸው ነው። እሱ ስለጠፋ  የኩዩጉ ህዝብ ግጭት
እየበዛበት ሰላሙ እየደፈረሰ ነው ብሎ ነገረኝ" አላት:

“ምን የሚደንቅ ነገር ነው፡ ፒካሶ አጥፍቷላ?

“ለምን? ሶራ ግራ ተጋብቶ ጠየቃት።

“የሰላም  ምልክት ነጭ እባብ የነበረውን በነጭ እርግብ የቀየረው" አለችውና እንደገና ኮስተር አለች: ህዝቡ ከፎቶው ፊት
ለፊት ይጨፍራል! እልል ይላል…..

“ሶራ እባክህ ሎካዬ ሞቷል በላቸው! ዋሾ እንዲያደርጉኝ
አልፈልግም? አለች በመማፀን እይታ እያየችው ሶራ በእሽታ አንገቱን ነቅንቆ ለዩጉው የማህረሰብ አባል ነገረው! ኩዩጉው ግን
ሶራ የሚለውን በጥሞና አዳምጦ የሆነ ነገር ተናግሮ ሲስቅ ኮንችት አየችው

ወዲያው አያቷ  ሎካዬ ትዝ አላት። አየችው በእዝነ
ህሊናዋ በልጅነቷ ቃል ያስገባትንም አባባሉን ሰማቸው! “…ሞቷል
አትበያቸው ስንት ጊዜ ለኔ ይዘኑ ለኔ ያልቅሱ! አለ! በያቸው! ያላት ታወሳት:

ይህን ስታስብ ሶራ ወደሷ መጣ
“ጠየቅኸው?” አለችው በውሳኔዋ እየተፀፀተች።
“አዎ ግን ሳቀብኝ። ሎካዬ እኮ ሞቷል...ስለው የሞተ
ሰው ምስል የለውማ! ልጅ ነህ ልበል! ምስሉን እያየኸው... ብሎ
ወደ ፎቶው አመልካች ጣቱን ቀስሮ አየኝ" አላት እሱም እየሳቀ

“ሶራ የመንደሩ ስም ማነው?''

“ኩችሩ!” አላት

“ምን?"

"ኩችሩ”

"ኩችሩ አዎ! አያቴ መንደሬ ኩችሩ ነው' ብሎኛል።"
እንደገና ሎካዬ ታወሳት:

“...መጠራጠር አያውቁም የሚጠራጠር ራሱ ዋሾ ነው...ሉካዬ አልሞተም በያቸው... ቆይተሽ ደግሞ እኔ ነኝ ሎካዬ በያቸው... ያምኑሻል.. አያቷ ያላት ትዝ አላት።

“ለካ አያቴ ከኒህ የዋህ ህዝቦች መሃል ወጥቶ ነው
ከተበከለው አለም ሲደናበር የኖረው የአያቷ ሐዘን ነፍስ ዘርቶ ሲንቀሳቀስ ታያት
“በኩችሩ ጫካ ክንፍ ውስጥ እንደ ጫጩት እየተሰገሰጉ
ሙቀታቸውን እየተጋሩ ይኖራሉ..." ያላትም ተሰማት እንደገና።

ይጨፈራል፣ እልል ይባላል... ኮንችት የሚደረገውን ሁሉ
ታያለች። በህልም ዓለም እውን ወይንም በውን ዓለም ህልም ውስጥ ያለች መሆኗን ግን ማወቅ ተሳናት ተኝታ ነቃች! ነቅታ
አንቀላፋች!

እልል... ቱቱ... የኩዩጉዎች የትክሻ ላይ ክራር ዱሩሩ.."
ይላል። ደስታና ግራ መጋባት የኩችሩን መንደር ያስፈነጥዟታል።...


💫ይቀጥላል💫
👍35🥰2👏1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ስድስት )
(ሜሪ ፈለቀ)

«ብዙውን አላውቅም። እየሆነ ስላለው ነገር ምንም እውቀት እንደሌለሽ ያወቁ ሰዓት ግን እንደሚገድሉሽ በአስር ጣቴ ፈርማለሁ። ስራ አቀለልሽላቸው!! አንቺም ከእነርሱ እኩል የሚፈልጉትን ማስረጃ የት እንዳለ የማታውቂ ፣ ገና እያፈላለግሽ እንደሆነ ልቦናቸው ካወቀ ምን ትሰሪላቸዋለሽ?»

«እኮ ያ ማለት ጠላታቸው አይደለሁም እኔን የሚያሳድዱበት ወንድሜንም የሚያፍኑበት ምክንያት የላቸውም!»

«አንችዬ ጅልም ነሽሳ? ያስታወስሽ ማግስት እንደገና ራስምታታቸው እንደምትሆኚ እያወቁ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልሽ! ብለው እንዲሸኙሽ ነው የምታስቢ?»

«አንተስ የሆነ ቀን ማን እንደሆንክ እንደማስታውስ ግን በሀሳብህ ሽው ብሎ ያውቃል??»

«አይከፋኝም ዓለሜ!! ያኔ ከምታውቂኝ በላይ አሁን ነውስ ምታውቂኝ !!» አለ ዘወር ብሎ አይቶኝ መልሶ «ያለፈውን ብነግርሽ ታምኚኝ ይመስልሻል?»

«ስላልነገርከኝም እያመንኩህ አይደለም። ቢያንስ አውቄው ራሴ ልወስን!! ካልሆነ ግን እንድች ብዬ እግሬን ካንተጋ የትም አላነሳም!»

«አራት አስርት ዓመት እዝህች ምድር ባጀሁኮ!! ምኑን አውግቼሽ ምኑን ትቼው እዘልቀዋለሁ? የትየለሌ ነው!!» አለ በንግግሩ ብዙዙዙ እያስመሰለው።

«እኔ የ40 ዓመት ታሪክህ ምን ያደርግልኛል? እኔ ደጅ ያደረሰህን ታሪክ ነው የምፈልገው። አንድ ዓመት ያከረመህንም!!» በረዥሙ ተነፈሰ። ሁል ጊዜ እንደሚያደርገው። ሊነግረኝ ነው ብዬ ስጠብቅ አጀማመሩን አርዝሞ የቆመ ጆሮዬን ኩም እንደሚያደርገው

«አንዱ ከሌላው ይተሳሰራል። ሁሉን ካልነገርኩሽ ቁንፅል ነው የሚሆን። እንደው በጥቅሉ ደጅሽ ያመጣኝ እንዳልኩት ሰው ነው። ደጅሽ ያቆየኝ አንድ እለት የዋልሽልኝ ውለታ ነው!» ብሎ የማንነቱን እንቆቅልሽ ሁሉ የፈታልኝ ይመስል ጭጭ አለ። ተናደድኩ።

«ኸረ? ውለታ? እያዋረድኩህ እንኳን ደጄ የነበርከው ለአንድ እለት ውለታ ነው? ትንሽ እንኳን የሚመስል ነገር ብታወራ ምን አለበት? ማስታወስ እንጂ ያቃተኝ ጡጦ የሚጠባ ህፃን እኮ አይደለሁም!!»

«ምንአለበት? የሰው ልጅ ለአንዲት ቀን በደል እድሜውን ሙሉ ቂም ይዞ ይኖር የለ? ለአንዲት ቀን በደል ለዓመታት በቀል ሲጎነጎን ይከርም የለ? ምናለበት ለአንዲት ቀን ደግነት ብዙ ዓመት ደግ ቢሆን?» ዋናውን ርዕስ እየሸሸ መሆኑ ገብቶኛል። ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ።

«ምሽት 2 ሰዓት ላይ ፒክ የሚያደርጉሽ ሰዎች በዚህ አድራሻ ይጠብቁሻል። ሰው አይደለም የሰው ጥላ ቢከተልሽ ያልኩሽን አትርሺ!! የምልክልሽን ስጦታ!!» ይላል። ምን እንደሆነ እንድነግረው ዘወር ብሎ እያየ ይጠብቃል።

«እናቴ ናት!! በአጎቴ ስልክ ደህና መግባታችንን ለማወቅ ነው መልእክት የላከችው።» አልኩት።

ለመጀመሪያ ጊዜ ዋሸሁት! ለመጀመሪያ ጊዜ ደበቅኩት። ግን ልክ ያደረግኩ መሰለኝ አልከፋኝም!! አዲስ አበባ ገብተን ለምናልባቱ የተሻለ ፍንጭ ካገኘን ቃሊቲ እየሄድን ነው። በልቤ ወስኜ ጨርሻለሁ። ከቃሊቲ መልስ ፣ መልስ ባገኝም ባላገኝም ጎንጥን የሆነ ቦታ አመልጠዋለሁ። ለሽንቴ እንኳን ስወርድ ልጠፋበት እንደምችል ጠርጥሮ መሰለኝ በቆቅ አይኖቹ ይከተለኛል። እንዴት እንደማመልጠው አላውቅም። ግን ከእርሱ ጋር የሚቀጥለውን እርምጃ አልራመድም። አሁን ላይ ማንን እና ምን እንደማምን ግራ ገባኝ። ለምኜዋለሁኮ ስላለፈው ህይወቴ የሚያውቀውን እንዲነግረኝ። ምንም እንደማያውቅ ሲነግረኝ አምኜው ምንም ሳልደብቀው በእሱ ላይ ዘጭ ብዬ እምነቴን ስጥልበት ትንሽ እንኳን አይከብደውም? የምሸሸው ምን እንደሆነ እንኳን ሳላውቅ በፍርሃት ነፍሴ ሲርድ እና ስፈራ አላሳዝነውም? እርሱን ከምንም በላይ አምኜኮ ለሳምንታት እጁን ይዤ እንቅልፌን ተኝቻለሁ። ምን ይሆን ያስብ የነበረው? በልቡ <አይ ሞኞ> ብሎኝ ይሆን?

«እመቤት በአንድ ወቅት ከእነርሱ ወገን የነበረች ጋዜጠኛ መሆኗን ሰምቻለሁ። ወዳጃምነታችሁ እምንድረስ እንደነበር የማውቀው ባይኖረኝም ለጊዜው መዘንጋትሽን ግልፅልፅ አድርገሽ ባትነግሪያት እመክርሻለሁ።» አለኝ ልንቃረብ ገደማ። አስቤ የነበረው ሁሉንም ነግሪያት የምታውቀውን መጠየቅ ስለነበር ካልጠየቅኳት የመሄዴ ትርጉም ራሱ ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ። ቢሆንም ሄድን!!


በሩ ላይ ስንደርስ የሆነ ልጅ እግር ጠባቂ «ይሄ ባሻሽ ሰዓት እየመጣሽ እገሌን ጥሩልኝ የምትዪበት የጎረቤትሽ ቤት መሰለሽ እንዴ? እስረኛ መጠየቂያ ቀንና ሰዓት አለውኮ!!» ብሎ ፊቱን ወደ ውስጥ መለሰ
«እናውቃለን! እንደው የሞት ሽረት ጉዳይ ገጥሞን ነው! እንደው ለ2 ደቂቃ!» አለ ጎንጥ
«አትሰማኝም እንዴ ሰውየው? ስራዬን ልስራበት ከዚህ ራቁ!! እንደውም እዚህ አቅራቢያም መቆም አይቻልም ዞር በሉ ብያለሁ።» ብሎ አምባረቀ። ምንም ተስፋ እንደሌለው ሲገባኝ

«እሺ የእስረኛ መጠየቂያ ቀን መቼ ነው?» አልኩ። ይሄኔ ሌላኛው በእድሜ በሰል ያለ ጠባቂ «ምንድነው? » እያለ ብቅ አለ። ልጅ እግሩ ምንም የሚለንን የማንሰማ መሆናችንን እያብራራለት ሰውየው እኔን በትኩረት ካየ በኋላ

«አጅሪት? መቼም ካንቺ ውጪ እዚህ በር ላይ ሁከት የሚፈጥር የለም!! ስትጠፊኮ ሌላ ቦታ ሸቤ ገብታ ነው ወይም ከባርች ጋር ተጣልታ! ብለን አስይዘን ነበር። ኸረ ለውጥ ቁርጠቴ በቀሚስ?» አለኝ። አወራሩ የእስር ቤት ጠባቂ ሳይሆን የሆነ የወዳጅነት ነው። ልጅ እግሩ ጠባቂ ግራ ገብቶት ያየዋል። « ከባርች ጋር ተጣልታችሁ ነው መምጣት ያቆምሽው??» ካለኝ በኋላ ወደልጅ እግሩ ጠባቂ ዞሮ « …. ቁርጠቴ የሴቶቹ ካቦ ነበረች እዚህ እያለች።» ሲል ልጅ እግሩ የሆነ ነገር እንደማስታወስ ብሎ ከላይ እስከታች ካየኝ በኋላ « ቁርጠቴ ማለት እሷ ናት? የሰማሁትን አትመስልም!» አለ

« ምን እንታዘዝ ታዲያ? መጠየቂያ ቀን አለመሆኑን ታውቂያለሽ መቼም!!» አለ በሰል ያለው ጠባቂ ወደ እኔ እየተጠጋ
«ብያለሁ አልሰማ ብለውኝ ነው። እመቤት የምትባል ነው የሚሉት?» አለ ልጅ እግሩ እኔ ሰውየው የሚጠራቸው ቅፅል ስሞች የማን እንደሆኑ ሳላውቅ ያለቦታው ሰክቼ ስህተት እንዳልሰራ ስደነባበር። ንግግሩ ያለመፍቀድ ዓይነት አይደለም። የመፍቀድም አይነት አይደለም። ግራ የገባ ነገር አለው። ይሄኔ ጎንጥ ጠጋ ብሎ እየጨበጠው

«እግዜር ይስጥልን ጌታዬ!! የሞት ሽረት ጉዳይ ባይሆን ካለቀኑ መጥተን ባላስቸገርን!!» አለው። ሰውየው ሳቅ ብሎ የጨበጠበት እጁን ከልጅ እግሩ ጠባቂ ደበቅ አድርጎ ገለጠው። ገንዘብ ነው ያቀበለው። ገንዘብ መፈለጉ እንዴት ገባው? ቆይ እሱ የማያውቀው ነገር ምንድነው? ሰውየው ዞር ብሎ ለልጅ እግሩ እመቤት ያለችበትን ምድብ ይመስለኛል የሆነ ቁጥር ነግሮት እንዲጠራ አዘዘው። ልጁ እየተነጫነጨ የተባለውን አደረገ። ምን መጠየቅ እንዳለብኝ እና እንደሌለብኝ መወሰን አቃተኝ። እንደማላስታውሳትስ መንገር አለብኝ? እሷስ የእኔ ወዳጅ ናት ወይስ እንደጎንጥ ማንነቷን የደበቀችኝ ሴት? የስራውን ይስጠው እንኳን ጠርጥርትያት ብሎ ሹክ ብሎኝ እንዲሁም ጥላዬን የምጠራጠር ጠርጣራ አድርጎኛል:: ስትደርስ ለቅሶ እና ሳቅ የተደባለቀው ነገር ሆነች። በእኔ ተመሳሳይ እድሜ የምትገኝ ዓይነት ሴት ናት። ጎንጥ ጆሮውን ቢተክል የምናወራውን ሊሰማ በሚችልበት ርቀት ቆሟል።
👍24
«በህይወት አለሽ? በህይወት እያለሽ ነው ልታዪኝ ያልፈለግሽው? ምን ሆነሽ እንደሆነ ብቻ ንገሪኝ? ደህና ሆነሽ ነው?» እያለች ማልቀስ ጀመረች። በጥይት መመታቴን ነገርኳት። መርሳቴን ግን ዘለልኩት። ደግሞ ወቀሳዋን ትታ ለእኔ ማዘን ጀመረች። ዞር ብላ ጎንጥን በ<ማንነው ?> አይነት ምልክት ሰጠችኝ። አጠያየቋ እንደምነግራት እርግጠኛ የሆነ ነው። የቀረቤታዋ ልክ ብዙ ነገር የምናወራ ሰዎች እንደነበርን ያስታውቃል።

«ጎንጥ ዘበኛዬ ነበር።» አልኳት። ለምን <ነበር> እንዳልኳት አላውቅም!
«ጎንጥ ጎንጤ? ጎንጤ ጥጋቡ? » ብላ ጮኸች። ስለጎንጥ የምታውቀው ምን እንደሆነ ባላውቅም የግርምት አጯጯኋ ስለዘበኝነቱ ብቻ እንዳልነገርኳት ያስታውቃል። ለአንድ አፍታ ሁሉንም ዝርግፍ አድርጌ ነግሬያት የምታውቀውን ብትነግረኝ ተመኘሁ።

«ኪዳንን ይዘውታል! ቪዲዮዎቹን ካልሰጠኋቸው እንደሚገድሉት ነግረውኛል።» አልኳት የማወራው ነገር አዲሷ እንደማይሆን እርግጠኛ ሆኜ።

«ኪዳን ምን ሊሰራ መጥቶ አገኙት? ሺት!! እርግጠኛ ነሽ? እኚህ አጋሰሶች!! የፈራሽው አልቀረም!! » ብላ በድንጋጤ እና በንዴት መሃል ዝም አለች።
«አዎ በቪዲዮ አይቼዋለሁ። አውርቼዋለሁም። ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ?» አልኳት ሌላ ፍንጭ ከሰጠችኝ ብዬ
«መቼም አትሰጫቸውማ? ሌላ መላ መቼም አይጠፋሽምኣ? »
«በኪዳን ነፍስ ቁማር መጫወትም አልችልም!»
«እየቀለድኩ ነው በይኝ!! ጥይቱ የዋህ አድርጎሻል ልበል? ወይስ ሚሞርሽንም ነው ያጠበልሽ?» ያለችው ለአባባል ነበር እኔ ግን አዎ ብያት ሁሉንም ብትነግረኝ ፈለግኩ። የጎንጥን ማስጠንቀቂያ ችላ ማለትም ከበደኝ። እራሱን ሳላምነው ቃሉን ለምን እንደማምን ምክንያት የለኝም። ግን መጠንቀቅ አይከፋም። እሷ ቀጠል አድርጋ

«ከዚህ በፊት ከእጃቸው ፈልቅቀሽ ወስደሽዋል። አሁንም ተረጋግተሽ አስቢ እና መላ አታጪም!!»
«ተረጋግቼ የማስብበት ጊዜ የለኝም!! የሰጡኝ ሰዓት ሊያልቅ ሶስት ሰዓት ነው የቀረው!» ስላት የሆነ ግራ ያጋባኋት አይነት በጥያቄ አስተዋለችኝ። አለባበሴን ጭምር በዓይኗ ለቀመች እና
«ምንድነው እሱ? ከመቼ ወዲህ ነው እንዲህ መልፈስፈስ ያወቅሽበት? የሆነማ ልክ ያልሆነ ነገር አለ። ደግሞ ልስጣቸውም ብትይ ሴትየዋን በ3 ሰዓታት ውስጥ አጊንተሽ አንደኛውን ኮፒ ልትቀበያት አትችዪም!! ነው ወይስ ኦልረዲ አጊንተሻታል?»

«ሴትየዋን?» ካልኩ በኋላ ሳላስበው « የአቅሜን እሞክራለኋ» አልኳት መልሼ!! መልስ የሰጠችኝ መሰለኝ። ለሰዎቹ የሰጡኝን የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ምክንያት!! የምጠይቃት ብዙ ቢኖርም!! በምን መንገድ እን,ደምጠይቃት ካለማወቄ የእሱን እንቢታ ጥሶ ሌላኛው ጠባቂ እመቤትን እንዲጠራልኝ ያስገደደው ልጅ እግር ጠባቂ ሰዓታችን ማለቁን ከግልምጫ ጋር ይነግረኛል። ለእመቤት መልሼ እንደምመጣ ነግሬያት። ወደከተማ መመለስ ጀመርን።

«ሴትየዋ ያለችሽ ማን ትሆን?» ሲለኝ ያወራነውን ሁሉ እንደለቀመ ገባኝ።
«አላውቅም! መርሳትሽን አትንገሪያት አላልክም? ማናት ብዬ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ? ሁሉን ነገር ታውቅ የለ? ይሄ እንዴት አመለጠህ?» ብዬ ጮህኩበት

«ታዲያ ምን የሚያስቆጣ ተናገርሁ? ቃሌን ያለማመንና ሴትዮይቱን ማመንምኮ ያንቺ ድርሻ ነበር።» አለ ተረጋግቶ።

«ለማንኛውም እቤት ንዳኝ!! ተረጋግቼ የማስብበት ሰዓት እፈልጋለሁ።» አልኩኝ። ከዛ ማውራት የእሱ ተራ ዝም ማለት የእኔ ተራ ሆነ።

« አሁን እኔና አንቺ አንባጓሮ የምንፈጥርበት ሰዓት አይደለም! በአንድነት መላ ብንዘይድ አይበጅም? ከሰውየው ጠባቂዎች አንዱ ወዳጄ ነው። ኪዳን ያለበትን አድራሻ ማግኘት ከቻልን መልዕክት አኑሬለታለሁ። እስታሁን የምትመጪበትን አድራሻ አልላኩም? መላክ ነበረባቸው!! ትክክለኛ አድራሻውን እንደማይልኩልሽ ግልጥ ነው። ከሆነ ቦታ ይቀጥሩሽና ነው በራሳቸው መኪና የሚወስዱሽ!! እርግጥ አድራሻውን ከደረስንበት እነርሱ የቀጠሩሽ ቦታ ሲመጡ እኛ ቀድመናቸው ቦታው እንደርስ ነበር ….. » እሱ እቅዱን ከጅምር እስከ ፍፃሜ ሲነግረኝ እኔ ደግሞ የራሴን እቅድ ከጅምር እስከ ፍፃሜ የሌለው አቅዳለሁ። እቤት እንደደረስን እዛ መሳቢያ ውስጥ ያለውን ሽጉጥ እወስዳለሁ። ምን እንደማደርግበት የማውቀው የለኝም። በሆነ መላ ከጎንጥ እሰወራለሁ። የቀጠሩኝ ቦታ ብቻዬን እሄዳለሁ። የሚወስዱኝ ቦታ ስደርስ (ኪዳን ይኖራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ) ሁሉንም ኮፒ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስላልነበረኝ ተጨማሪ አንድ ቀን እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ። የሚፈልጉት ቪዲዮ የዚን ያህል አንገብጋቢ ከሆነ አይገድሉኝም። የጠየቅኩትን ጊዜ ይሰጡኛል። በተቃራኒው ሊሆን እንደሚችል ሳስብ ልቤ ይደልቃል:: ትልቁ ፍላጎቴ ግን ለትንሽ ደቂቃ ከወንድሜ ጋር እንዲተውኝ ማድረግ ነው። ብቸኛ ላምነው የምችለው እና ሊያውቅ የሚችል ሰው እሱ ነው። ይሄ ጎንጥ እንዳለው የጅል እቅድ ሊሆን ይችላል። እጄን አጣጥፌ እየጠረጠርኩት ያለሁትን ጎንጥን ከመከተል ውጪ ሌላ የተሻለ እቅድ ግን የለም። ያን ደግሞ አላደርግም!!

እቤት እንደደረስን ተናኜ የማያቆም ጥያቄ እና ወሬ ታከታትላለች። እንደማልሰማት እንኳን የምታስተውልበት ፋታ አትወስድም። ጎንጥ ከገባ ጀምሮ በሩ ላይ እንደተገተረ ነው። ጮክ ብዬ ጎንጥ እንዲሰማ

« አንድ ላይ የምንበላው እራት አሰናጂ!! ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም! እራት አንድ ላይ እንቋደስ!» አልኩኝ ለእሷ ግራ እንደሚያጋባት ሳልረዳ

«ምነው እትይ የት ልትሄጅ ነው?»
«የትም አልሄድ! ያልኩሽን ዝም ብለሽ አድርጊ!» አልኳት። ቅር እያላት ገባች። ለመሄድ የሚያስፈልገኝን ነገር ካሰናዳሁ በኋላ ጥርጣሬውን ለመቀነስ ልብሴን አልቀየርኩትም። እራት ሶስታችንም ቀርበን እየበላን። አስተያየቱ እንዳላመነኝ፣ ነገረ ስራዬ እንዳላማረው ያስታውቃል።

«አድራሻውን ልከውልኛል።» አልኩት
«የት ነውስ?» አለ ቀና ብሎ ስልኬን እንድሰጠው መሰለኝ እጁን እየዘረጋ። ስልኬን የለበስኩት ሹራብ ኪስ ውስጥ የከተትኩት ለራሴ እቅድ እንዲመቸኝ በመሆኑ እጁን ችላ ብዬ

«እንዳልከው ነው። ቀበና የሚባል ሰፈር የሆነ ካፌ ፊትለፊት ነው። ስልኬ መኝታ ቤት ነው አሳይሃለሁ። ከዛ ነው ከእነርሱ ጋር ሊወስዱኝ ያሰቡት! ምንድነው የምናደርገው? ወዳጅህ እስከአሁን አልመለሰልህም?።» አልኩት። ይመነኝ አይመነኝ ባላውቅም በእርሱ እቅድ እየተመራሁ እንደሆነ እንዲመስል ጣርኩ። አስተያየቱ ያመነኝ አይመስልም። ከጎሮሮዬ አልወርድ ያለውን እህል እንደምንም ካጋመስኩ በኋላ

« …… በልተሽ ስትጨርሺ እዚህ ላይ አንድ ስኒ ቡና ብታጠጪኝ ደግሞ?» አልኳት ተናኜን። ልትነሳ ሲዳዳት ተረጋግታ እንድትጨርስ ነግሪያት ወደጓዳ እጄን እንደሚታጠብ ሰው ገባሁ። እጅ መታጠቢያውን ውሃ ክፍት አድርጌ አስቀድሜ ክፍቱን በተውኳቸው በሮች የምፈልገውን ይዤ በጓዳ ወጣሁ። መጣ አልመጣ አድብቼ እየተርበተበትኩ የአጥሩን በር ከፍቼ ስወጣ ከኋላዬ የሚያባርረኝ ያለ ነበር የሚመስለው አሯሯጤ። የቤቴ በር ከአይኔ እስኪሰወር እሮጥኩ። ያገኘሁትን ታክሲ አስቁሜ ወደተላከልኝ አድራሻ እየሄድኩ።

«ማን ስለሆነ ነው ቆይ እንዲህ የምደበቀው? ያውም በገዛ ቤቴ?» እላለሁ በልቤ!!

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍344
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ሰባት)
(ሜሪ ፈለቀ)

የምጣደፈው ጎንጥን ሽሽት ይሆን ኪዳንጋ ለመድረስ ተቻኩዬ ወይም በሁለቱም ምክንያት የታክሲው ሹፌር ትዕግስቱን እስኪያንጠፈጥፍ ድረስ አቻኩለው ጀመር። <ምን ያህል ቀረን?> ፤ <ትንሽ ፈጠን ማለት አትችልም?> ፤ < ሌላ ያልተዘጋጋ አማራጭ መንገድ አይኖርም?> ፤ < አሁንም ብዙ ይቀረናል?> አንድ አይነት ጥያቄ በየሁለት ደቂቃው እየደጋገምኩ ፤ ግማሽ ጎኔ ወደፊት ግማሽ ጎኔ ወደኋላ በሆነ አቀማመጥ ፤ በአንድ ዓይኔ ወደኪዳን (ወደፊት) በአንድ ዓይኔ ወደጎንጥ (ወደኋላ) ሳማትር

«ሴትዮ ካልሆነ ውረጂ እና ሌላ ታክሲ ተሳፈሪ! አይታይሽም እንዴ በማይነዳበት እየነዳሁልሽ? ሆ! ዛሬ ምኗን ነው የጣለብኝ ባካችሁ?» አለ ያለመታከት ሲመልስልኝ ቆይቶ ከትዕግስቱ በላይ ስሆንበት

«ይቅርታ በጣም ስለቸኮልኩ ነው። ይቅርታ በቃ እንደሚመችህ አድርገህ ንዳ!!» አልኩኝ። ታክሲው ውስጥ በቦርሳ የያዝኩትን የቱታ ሱሪ ከቀሚሴ ስር ለብሼ ሳበቃ ቀሚሴን አውልቄ ወደቦርሳው ከተትኩ።

እያደረግኩት ያለሁት ድፍረት ይሁን ድድብና መመዘን የምችልበት መረጋጋት ላይ አልነበርኩም። ምናልባት አለማወቅ ደፋር ያደርግ ይሆናል ወይም ደደብ!! ጎንጥ ሰዎቹን ስለሚያውቃቸው ይሆናል የሚጠነቀቀው እና የሚፈራልኝ። የማላውቀውን ሰው ወይም ልገምት የማልችለውን የሚገጥመኝን ነገር በምነኛው መጠን ልፈራ እችላለሁ? እስከገባኝ ድረስ ቢያንስ አለማወቄ ጎንጥን እስከአለመከተል ድረስ ደፋር ወይም አላዋቂ አድርጎኛል።

የተባለው ቦታ ስደርስ ለቀጠሯችን 20 ደቂቃ ይቀረኛል። ከታክሲው ከወረድኩ በኋላ እንደማንኛውም በአካባቢው እንዳለ ተንቀሳቃሽ ግለሰብ የአዘቦት ክንውን እየከወንኩ ለመምሰል ጣርኩ እንጂ እንደሌባ ዓይኖቼም አካሌም እየተቅበጠበጠ ነበር። እስከዚህ ደቂቃ ያልተሰማኝ ፍርሃት አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ይገለባበጥ ጀመር። መቆምም መራመድም መቀመጥም ሰው ይቸግረዋል? ወደላይ ትንሽ ራመድ እልና ደግሞ በተቃራኒው አቅጣጫ እመለሳለሁ። በመሃል እንደማቅለሽለሽም ያደርገኝና መሃል የእግረኛ መንገድ ላይ ቁጢጥ እላለሁ። ከመንበጭበጬ ብዛት ሽንቴን እላዬ ላይ የምለቀው መሰለኝ። ሰዓቴን በ60 ሰከንድ ውስጥ 120 ጊዜ አያለሁ። ደቂቃው ሰዓቴ መስራቱን ያቆመ ይመስል ፈቅ አይልም። ለአፍታ የጎንጥ እጅ ናፈቀኝ። ወላ ተከትሎ ደርሶብኝ በሆነና የፈራሁ ሲመስለው ሁሌም እንደሚያደርገው በዛ ሰፊ መዳፉ እጄን አፈፍ አድርጎ እጁ ውስጥ ቢደብቀው። «……. እኔ የት ሄጄ? …… ማን አባቱንስ እና ነው? » ቢለኝ። ሜላት ምንድነው ያደረግሽው?

የምጠብቀው እንዲህ ነበር። የሆነ ቀን እንዳየሁት የሆነ ፊልም። ጥቁር መኪና መጥቶ አጠገቤ ገጭ ብሎ ይቆምና ! በሩ ብርግድግድ ብሎ በተጠና ስልት ሲከፋፈት ፊታቸው የማይታዩ መሳሪያ የታጠቁ ግባብዳ ሰዎች ከመኪናው ዱብ ዱብ ብለው ያስቀመጡትን የሆነ ሻንጣ ብድግ እንደማድረግ ብድግ አድርገውኝ እየጮህኩ እግሬ አየር ላይ ተንጠልጥሎ ስፈራገጥ ምንም ሳይመስላቸው ወደመኪናው ይወረውሩኝና ልክ እንደቅድሙ በተጠና መንገድ በሩን ድው ድው አድርገው ዘጋግተው ይዘውኝ ይሄዳሉ።

የሆነው እንዲህ ነው። እግሬን ብርክ ይዞት ጉልበቴን ደገፍ ብዬ ባጎነበስኩበት አንዲት ቆንጅዬ ጅንስ ሱሪ በቲሸርት ለብሳ አጭር ጥቁር ጃኬት የደረበች ወጣት ሴት ከጀርባዬ ጠራችኝ። «ሜላት!» ለሰላምታ እጇን ዘረጋችልኝ። እነሱማ ሰላም ሊሉኝ አይችሉም ብዬ እያሰብኩ እጄን ዘረጋሁ!!

«ዝግጁ ነሽ?» ስትለኝ ማሰቢያዬ ተዛባ! ለምኑ ነው የምዘጋጀው? ለመታገት ዝግጅት? <አዎ! እጄን ለካቴና በቅባት አሸት አሸት አድርጌ አዘጋጅቸዋለሁ። ድንገት እጃችሁ ካረፈብኝ ዱላ መቻያ ደንደን እንዲል ቆዳዬን ወጠርጠር አድርጌ አለማምጄላችኋለሁ….. > እንድላት ነው ተዘጋጀሽ የምትለኝ? እሷ ቀጠል አድርጋ ከፊቴ ወደቆመ ዘናጭ ነጭ መኪና እየጠቆመችኝ ፈገግታዋ የሆነ የተንኮል ዓይነት እየሆነ « …. ግርግር አንፈልግም አይደል?» ብላ አጭሩን ጃኬቷን ከፈት አድርጋ ሽጉጧን አሳየችኝ። ለስሙማ እኔምኮ ሽጉጤን ጎኔ ላይ ሽጬዋለሁ። ምን ላደርግበት እንደሆነ ያሰብኩት ባይኖርም ለዝህች በቆንጆ ፊቷ ለሸወደችኝ ልጅ ግን ሽጉጥ ሳይሆን የመዘዝኩት እጄን ነው ለሰላምታ የዘረጋሁት።

ወዳሳየችኝ መኪና ሄድኩ። እያገተችኝ ሳይሆን የሆነ በክብር እንግድነት የተጠራሁበት ቦታ ልታደርሰኝ ነው የሚመስለው። የኋላውን በር ከፍታ ያንን ተንኮለኛ ፈገግታዋን እያሳየችኝ እንድገባ ጋበዘችኝ። በአጠገባችን የሚያልፉ ሰዎችን <ኸረ በትኩረት ለአፍታ እዩኝ እየወሰዱኝ ነው!> ብል ደስ ባለኝ። ማንም ለአፍታ እንኳን ገልመጥ አድርጎ ያየኝ የለም። በየእለት ተእለት ውሏችን ልብ ያላልናቸው ስንቶች ይሆኑ ከአይናችን ስር ብዙ የሆኑት?

መኪና ውስጥ ከኋላ ታግቼ ባይሆን « ምን ሆኖ ነው እንዲህ የቆነጀው?» የምለው የሚመስለኝ ፈርጣማ ወንድ ተቀምጧል። እንደገባሁ ቀለበኝ ማለት ይቀላል። ፓንቴ ስር መግባት እስኪቀረው እንያንቀረቀበ ሲፈትሸኝ ልጅቷ ከፊት ወንበር ሆና ሽጉጧን አስተካክላ ትጠብቀቃለች። የምራቸውን ነው? እዝህች የክብሪት ቀፎ የምታክል መኪናቸው ውስጥ ከነሹፌሩ ለሶስት ከበውኝ ታጠቃናለች ብለው ነው ሽጉጡ? ሽጉጤን ከፊት ለተቀመጠችው ሴት እንደመወርወር አድርጎ አቀብሏት በምትኩ የሆነ ጨርቅ ስትወረውርለት ነገረ እቅዴ ሁሉ ጎንጥ እንዳለው የጅል መሆኑ ገባኝ። የሰውየው መዋከብ ቶሎ የመጨረስ ውድድር ያለበት ነው የሚመስለው። በጨርቁ ዓይኔን ሲሸፍነው መኪናው መንቀሳቀስ ጀመረ። በዚያው ፍጥነት እጄ ላይ ካቴና አሰረ።

ለምን ያህል ደቂቃ እንደተጓዝን አላውቅም!! ወይ ከላይ ወይ ከታች እንዳያመልጠኝ ከሰውነቴ ጋር ግብ ግብ ላይ ነበርኩ። የእነርሱ ዝምታ ደግሞ ጭራሽ ያለሁት መኪና ውስጥ ሳይሆን ከሞት በኋላ የሰይጣን ፍርድ ዙፋን ስር ቀርቤ አስፈሪ ፍርድ ለምሳሌ እንደ < ለእሷ እሳቱ አስር እጥፍ ይጨመር!! ይሄማ ለሷ ሻወር መውሰጃዋ ነው!! ይንተክተክላት ውሃው እንጂ! > የሚል ፍርድ እየተጠባበቅኩ መሰለኝ። ከመኪናው ወርደን የበረበረኝ ሰውዬ ይመስለኛል ብብቴ ስር ገብቶ ጨምቆ ይዞኝ እየነዳኝ በእግር የሆነ ያህል እንደተጓዝን አይኔን የሸፈነኝ ጨርቅ ሲነሳ የተንጣለለ በውብ እቃዎች የተሞላ ሳሎን ራሴን አገኘሁት። ያሰረልኝ ሰውዬ ከእጄ ላይ ካቴናውን አወለቀው።
👍21
እንግድነት የሄድኩ ይመስል እንድቀመጥ ታዘዝኩ። ያ ሰውዬ በቪዲዮ ያወራሁት ሰውዬ እና አንዲት መሬቱን የነካ ጌጠኛ ቀይ ቀሚስ የለበሰች ሴት ተቀምጠዋል። ከእነርሱ በተጨማሪ ይዞኝ የገባው ሰውዬ እና ትንሽ ቁመቱ አጠር ያለ መሳሪያ የታጠቀ ሰውዬ ብቻ ናቸው ክፍሉ ውስጥ ያሉት። ሴትየዋ የጠቆመችኝ ከፊታቸው ያለ ሶፋ ላይ ለመቀመጥ ቂጤን ሳሾል «ከመጨዋወታችን በፊት እንዳው ለመተማመኑ ….. » ብላ አጠገቤ ደርሳ የለበስኩትን ሹራብ ግልብ ስታደርገው ግራ ገባኝ እና መነጨቅኳት። የቆሙትን ጠባቂዎች (መሰሉኝ) ፊታቸውን እንዲያዞሩ ምልክት ስትሰጣቸው ሶፋው ላይ ያለው ሰውዬ እራቁቴን የማየት መብት እንዳለው ሁሉ ዝም አለችው። ከንግግሯ ምናልባት የምናወራውን የምቀዳበት ነገር ሰውነቴ ላይ ደብቄ እንደሆነ እያጣራች መሆኑ ገባኝ። በፓንት እና በጡት ማስያዣ ስቀር አይኑን ከሰውነቴ ላይ ለመንቀል ምንም ሀሳብ የሌለውን ሰውዬ እያየሁ መዋረድ አንገበገበኝ። ሴትየዋ ጡቴ ስር ገብታ ስታንቀረቅበኝ ጡቶቼን የምትመዝናቸው እንጂ የሆነ መቅጃ ያለችውን ነገር እየፈለገች አይመስልም። ጥርሴን ነክሼ ዋጥኩት። ሆነ ብላ የምታደርግ ነው የሚመስለው። ጣቷ የእንትኔን ጫፍ እስኪነካው ድረስ እጇን ፓንቴ ውስጥ ስትሰድ እስኪያማት ድረስ የእጇን አልቦ ማሰሪያ ጨመደድኩት።

«ok ok » ብላ እጇን አወጣች። የያዝኳትን ስለቀው ቦታው ደም መስሏል። ፊቷ ላይ ያስታውቃል። ከመፈተሿ በላይ እኔን ማዋረዷ ተመችቷታል። እንድለብሰው ልብሴን ከመሬት አንስታ ወረወረችልኝ። ከሰውየው ጋር ተያይተው ያልገባኝን መልዕክት ተለዋወጡ። ይዤው የነበረውን ቦርሳ አንስታ አመሳቅላ በረበረችው።

«አላመንከኝም እንጄ ነግሬህ ነበር,» አለችው። ሰውየው ባለችው ነገር ሙሉ በሙሉ ያመነ አይመስልም።

«እሺ ሜላት!! የታሉ ቪዲዮዎቼ?» አለ

«ወንድሜን በአይኔ ሳላየው ምንም ነገር አልነግርህም!!» አልኩት ለመኮሳተር እና ያልፈራ ለመምሰል እየሞከርኩ።

«ሜላት ይሄ ኔትፍሊክስ ላይ ተጥደሽ ስታዪ የምትውዪው የሆሊውድ ፊልም አይደለም። አጉል ጀግና ጀግና አትጫወቺ!! የትም አትደርሺም!!» አለ ልጥጥ ብሎ እንደተቀመጠ። አልመለስኩለትም።

«እየሰማሽኝ አይደለም? ዛሬ የምጫወትበትን ጠጠር የምመርጠው እኔ ነኝ። ያልኩሽን ነው የምታደርጊው።» ብሎ አምባረቀ።

«ወንድሜን ካላየሁ ምንም የማደርገው ነገር የለም አልኩ እኮ!!» ብዬ ለመጮህ ሞከርኩ።
ለቆመው አጭሩ ጠባቂ ምልክት ነገር ሰጠው። የታመቀ ትንፋሼን በረዥሙ ለቀቅኩት። ኪዳን ሲገባ ምንም የተጎዳ ነገር ያለው አይመስልም። ሲያየኝ ፊቱ ላይ ከቃላት በላይ የሆነ ስቃይ አየሁበት።

«I am so sorry» አለኝ ገና ስንተያየኝ። አልከለከሉኝም! ሄጄ አቀፍኩት። አጥብቆ አቀፈኝ። «ይቅርታ ሜል!»

«መልሰው!!» ብሎ ጮኸ ሰውየው። አብሬው እንድቆይ ብለምንም ሊሰማኝ እንኳን ግድ አላለውም። ምንድነበር ያሰብኩት? 'ናፍቆትሽ እስኪወጣልሽ እንጠብቅሻለን ከወንድምሽ ጋር ትንሽ ተወያዩ' እንዲሉኝ ነበር? የምርም እንዴት ያለ የቂል እቅድ ነው ያወጣሁት? ኪዳን ተመልሶ ሲሄድ የተሸነፍኩ መስዬ ላለመታየት ሞከርኩ። ሰውየው ወደእኔ አፈጠጠ።

«ሁሉንም ኮፒ እንዳመጣልህ አይደል ፍላጎትህ? በሰጠኸኝ አጭር ጊዜ ላመጣልህ አልችልም!! ተጨማሪ 24 ሰዓት ስጠኝ እና የምትፈልገውን በሙሉ እሰጥሃለሁ።» ስለው ያሳቃቸው ጉዳይ አልገባኝም ሁለቱም ከጣሪያ በላይ ሳቁ።

«ብዬህ ነበርኮ! በል ብሬን ወዲህ በል!» አለችው ሰትየዋ እጇን እየዘረጋች።

«እያወቅሽኝ ካላረጋገጥኩ መች አምናለሁ?» መለሰላት። እየሆነ ያለው ሙሉው ባይገባኝም እያላገጡብኝ እንደሆነ ገብቶኛል። ከኪሱ የሆኑ ብሮች ኖት አውጥቶ አቀበላት።

«ባንቺ ቤት አቃቂለሽኝ ሞተሻል!! ካንቺ ውጪ ማንም መረጃዎችሽን የት እንደምታስቀምጪ እንደማያውቅ ገምቻለሁ። እመቤትን ነበር የጠረጠርኩት እንደገባኝ እሷም የረዳችሽ ነገር የለም። አንቺም የት እንዳስቀመጥሽ እንዳታስታውሺ ትውስታሽ ላይመለስ ከድቶሻል። ንገሪኝ እስኪ ምን ልሁን ብዬ 24 ሰዓት ልጠብቅሽ?» ሲለኝ የበለጠ ጅልነት ተሰማኝ።

ባለፈው ከደበደቡኝ ጎረምሶች የተሻለ እነዚህ ሰዎች መረጃ ከፈለጉ በቀላሉ ማግኘት አይችሉም ብዬ እንዴት አሰብኩ? ምኗ ቂል ነበርኩ? አሁን ይገድሉኛል? እሺ ኪዳንንስ? ምንድነው ያደረግኩት?

በሩ ተከፍቶ የቅድሟ ሴት በሩ ላይ ላለው ጠባቂ የሆነ ነገር አንሾካሽኳ ወጣች። ጠባቂውም የሆነ ነገር ለሰውየው አንሾካሾከ። ሰውየው በጣም የተገረመ መሰለ።

«ያንቺው ጉድ ነው!» አላት ወደሴትየዋ እያየ። ሴትየዋ ግራ የተጋባች መሰለች። በጣም በመገረም ወደበሩ እያየች።
«ምን ልሁን ነው የሚለው አስገቡት እስኪ!»

ዓይኔ የሳተው ነገር ቢኖር ነው። ጆሮዬም እንደዛው? <የሷው ጉድ> ነው ያለው ወይስ <የአንቺው ጉድ> ነው ያለው? የእኔው ጉድ ጎንጥማ የሷው ጉድ ሊሆን አይችልም። ወይም ሌላ ጎንጥ ይሆናል እንጂ የእኔው ጎንጥማ አይሆንም!! በሩን አልፎ ሲገባ ቤቱ ነው የሚመስለው!! ልክ የእናት አባቱ ቤት እራት ሊበላ እንደመጣ ነገር ዘና ብሎ ከሶፋው ተሻግሮ ያለ ወንበር ሳብ አድርጎ ተቀመጠ።

እስከአሁን የነበረው ምኑም ያየኋቸውን ፊልሞች አይመስልም ነበር። ይሄ ግን ፊልም እንጂ እውን አይመስልም።

«ምን ትሰራለህ?» ብላ ሴትየዋ ጮኸች።

«ስራዬን ነዋ!!» አለ እንደማላገጥ ብሎ

ሆድቃዎቼ ቦታ የተቀያየሩ ነገር መሰለኝ። ሆዴ ውስጥ ተለዋወሰብኝ።

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍291
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የኩችሩ መንደር እንደደመቀች ናት:: ብዛት ያላቸው አሣዎች በወጣቶች በጦር ተወጉ ማጅራታቸውን በዱላ ተመቱ በመንጠቆ ተያዙ፤ ሣር በል የሆኑ አራዊት የሜዳ ፍየልና ውድንቢት ታድነው ተገደሉ ፤ ከጫካ ብዛት ያለው ማር ተቆረጠ፤ ቦቆሎና ማሸላ ኦሞ ወንዝ ተወስዶ ተወቃ.. ይበላል ይጠጣል
ይጨፈራል ይመረቃል።

ሉካዬ ሰማይ ላይ ሆኖ ምስሉ እየታዬ ቢሆንም ሶስት ቀን ሙሉ አልመጣም:

“ሎካዬ ለመምጣት ያስባል! ነጩ እባብ ግን “አልመጣም ብሎ አስቸግሮታል ደንቡን ሳናጓድል ሥርዓቱን ብናሟላ ግን ሁለቱም ይመጣሉ" ስላሉ ሽማግሌዎች፣ ሴት ወንዱ ይኳትናል ሰማይ ላይ ላሉት  ለሎካዬና ለነጩ እባብ በደስታ ለመፍጠር።

ኮንችት የሎካዬ የልጅ ልጅ መሆኗን ከሰሙም በኋላ
የመንደሩ ሰው ተስብስቦ ከአያቷ ወንድም ቤት ፊት ለፊት ተቀመጡ" የሉካዬ ፎቶ ጎጆው ላይ እንደተንጠለጠለ ነው። ከሥሩሁሌም ግልገል ፍየል ከካሮ እየመጣ ታርዶ ይቀመጥለታል።

ልጃገረዶች ኮንችትን ወደ ጎጆው ቤት ውስጥ ይዘዋት
ገብተው ውስጥ ሱሪዋንና ጡት ማስያዥዋን ሳይቀር አስወለቋት::ከውጭ ይዘፈናል እልል ይባላል. ልጃገረዶች በአኖና የዱር እጣን አላቁጠው ፀጉሯን ሰውነቷን ቀብተው የፍየል ቆዳ አለበሷት: ከዚያ
ይዛው የመጣችውን ልብሷን በእጅዋ እንድታንጠለጥል ሰጧትና ከቤት ወደተሰበሰበው ህዝብ ይዘዋት ወጡ። እሳት ነዷል.
ይጨፈራል... ሁለት ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፍተው እጅና እጅዋን
ይዘው ልብሷን ወደ እሳቱ አስወረወሯትና እልልታቸውን ሲያስነኩት
የተሰበሰበው ህዝብ እንደገና ፈነጠዘ ዘለለ  አቅራራ.. ጡሩንባ
እልልታ ተኩስ ድብልቅልቅ አለ:

ኮንችት የተረጋጋች አትመስልም። ቆዳዋ ግን አማረባት ጡቶችዋ ቀልተው ቆሙ ለስላሳው ጭኗ... ሁለመናዋ አጓጊ ሆኗል:
ድንጋጤው ስላልለቀቃት ግን ካንገቷ በላይ ውበቷ ቀንሷል።

ሴቱም ወንዱም እየመጣ እጅዋን እየሳመ ደስታውን
እየገለፀላት ወደ ጭፈራው ሲገባ እንደቆዬ ሰው ሰላምታ እየሰጣት
ኩዩጉነቷን አንድነታቸውን እያረጋገጠላት ከሄደ በኋላ ሶራ እየሳቀ ወደ ኮንችት ተጠግቶ አቀፋት: ሽጉጥ አለች ወደ ደረቱ እንደ
እንቦቀቅላ  ህፃን፡ አይቷት እንደማያወቅ ሁሉ በሁለት እጆቹ ጡቶችዋን እንደያዘ ፈገግ ብሎ ቁልቁል አያት: ልትስመው ስትል
የሆነች ሴት መጥታ መነጨቀቻት። የኩዩጉ ሴት ወንድን በአደባባይ
አትስምማ!

“እሺ!” አለች ኮንችት
የሴትዮዋ ግሣፄ ስለገባት።

“ለምን ልብሴን አወለቁ?  ለምንስ እንዳቃጥለው አደረጉ?''አለችው እሏና ሶራ ከእቅፎቻቸው ከተላቀቁ በኋላ

“የአያትሽን ባህል ረድኤት ለማካፈል! ተፈጥሮአዊ ፀጋሽን ለመመለስ ጎረምሶች ፍቅራቸውን እንደ ወለላ ማር እንዲያውጡሽ….
ለማድረግም" አላት ሶራ እየሳቀ
ባለወይሳው ኮንችትን ባህላዊ ልብስ ለብሳ ሲያያት ደስ አለው። ስለዚ ፈገግ ብሎ ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ ቀረባትና

ካርለትን አይተሻታል ወይ? ብለህ ጠይቃት" አለው ሶራን።ሶራ የነገረውን ለኮንችት ሲተረጉምላት ተኩስ ተሰማ ተኩሱ
ተደገመ።

ጎረምሶች እየተሯሯጡ ወደ ኦሞ ወንዝ ሄዱ። ጭፈራው
ግን አልቆመም። ባለወይሳው ከሌላ አካባቢ የመጣች ፀጉረ ረጅም
ልብስ ለባሽ... ሁሉ እሱ የሚያውቃትን ካርለትን ያውቃል ብሎ አምኗል።

“ካርለት! ማነች ካርለት? የአባቷስ ስም? ዜግነቷስ?”
ኮንችት በስም ብቻ አውቃለሁ፤ አላውቅም  ማለት ትክክል
እንዳልሆነ ታውቃለች: በያገሩ ስንት  ካርለት
ዴቪድ... ሊኖር ፥ይችላል። መጀመሪያ ስም  አገር ሥራ የሚኖርበት አድራሻ...
ለማንነት መለያ ይጠቅማል: በተረፈ በደፈናው ይከብዳል።ባለወይሳው ግን “አውቃታለሁ' አለማለቷ አስከፋው:

ምን የማረጋት መሰላት ካርለት ልጃገረድ ናት!
ብታጠፋም አላገባኋት ጥሎሽ መክፈል አልጀመርሁ... እና-
አላዝባት አልቀጣት... ይህን እያወቅች መደበቋ ምን ይሉታል? ብሎ አስቦ አዘነባት በኮንችት:

በኦሞ ወንዝ ዳር ካለው ጫካ የሆኑ ሰዎች ብቅ ሲሉ ህዝቡ ተንጫጫ። ኮንችት ቀና ብላ ታይ የኩዩጉ ጎረምሶች እንግዶችን
እየመሩ ይመጣሉ። ለኩዩጉ መንደር በሩ ኦሞ ወንዝ የበሩ ደወል ተኩስ መሆኑ ኮንችትን እንዳስደነቃት ነው።

እንግዶቹ ሲጠጉ አንዷ ነጭ ናት ሁለት ወንዶችና
አንዲት ሴት አብረዋት አሉ። እነሱ ከነጭዋ አንፃር ጥቁር ናቸው።እንግዶቹ እንደቀረቡ ባለወይሳው ዘወር ብሎ አያቸውና ከመቅፅበት
አይኑን እንደ አውሬ አፍጦ አንገቱን እንደ ሰጎን መዘዘው
ሁለቱ ሴቶች ባለወይሳውን ሲያዩ ፊታቸው በደስታ ፀዳል አበራ ቸኩለው ግን ወደ እሱ አልተጠጉም።
ከዚያ ነጯ እንደቆመች ሌላዋ ሴት ቀረብ አለችና፡-

“አያ ደልቲ!'' አለችው
በሐመርኛ:ጎይ ቲ"

ረጋ ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ ላዩ ላይ ተጠመጠመችበት: እቅፍ አድርጓት ቆየና ለቀቃት:: ነጭዋንም ካርለት" ብሉ አቀፋት፤ እሷም አቀፈችው ...

የኩችሩ መንደር ኗሪ በሁኔታው ተደንቆ ጭፈራውን አቁሞ
ያያል።

ካርለት! አለች ወገቧን ወደኋላ ለጥጣ በአድናቆት አፏን እንደከፈተች ኮንችት።

ኮንችት! ካርለት ኮንችትን ከእግር ጥፍሯ እስከ ፀጉሯ
በአድናቆት እያየቻት ቆየችና

“አገኘሻቸው?" አለቻት

“አዎ ተገናኘን” ብላ ኮንችት ሳቀች ተሳሳቁ ኮንችትና
ካርለት! ህዝቡም አብሯቸው ሳቁ! መንደሯም በሣቅ ሙላት ተጥለቀለቀች

“ኮንችት እንዴት ልታገኛቸው ቻልሽ?''

“..በጀልባ ነበር እኔና ሶራ የምንጓዘው፤ እና ባጋጣሚ እዚህ ደረስን

“ማንም ሳይመራሽ?'

“ባገኘሁት ማፕም ሆነ ካርታ ኩዩጉዎች ለመኖራቸው ፍንጭ የሚሰጥ ምልክት የለም:: አያቴ የስጠኝ የአደራ ምልክቶች ግን እንደ ኮኮብ መርተውኛል ያም ሆኖ ግን ባጋጣሚ ኩዩጉዎችን
የሚፈልገው ሰው ተኩሶ እነሱ ሲመጡ ማየት ባንችልና ተጠራጥረን
አብረን ባንመጣ ልፋቴ መና ሆኖ! ስሜቴ በስለት ቢላዋ ለሁለት ተተርትሮ ወደ መጣሁበት እየቆዘምኩ እመለስ ነበር። አጋጣሚው
ግን ረዳን፤ ተገናኘን:

“እንዴት አገኘሻቸው ታዲያ?

“ደግ ሩህሩህና ተግባቢዎች ናቸው:: ኑሯቸው በኦሞ ደለል ላይ ማሸላ በማብቀል ከጫካ ማር በመቁረጥና አሣ በማጥመድ ነው።
ከብት ፍየል የላቸውም፤ ይህ ደግሞ ከብት በሚያረቡት የአጎራባች
ያስንቃቸዋል:: ቁጥራቸው
ማህበረሰቦች ማነሱ ከብት
ባለማርባታቸው የሚያጠቃቸው ብዙ ነው። ስለዚህ የሚኖሩት
በጠባቂ ሞግዚት ነው"

“በሞግዚት?”

“አዎ ካርለት!  ጥንት ሞግዚታቸው ካሮ ማህበረሰብ ነበር። አሁን
ግን የካሮዎች ኃይል እየደከመ የኒያንጋቶሞች
(ቡሜዎች) ኃይል እየበረታ በመምጣቱ ኩዩጉዎች ወደ ኒያንጋቶሞች በመጠጋት ከአጎራባች ማህበረሰቦች የሚደርስባቸውን ጥቃት
ሞግዚታቸው ኒያንጋቶሞች ይከላከሉላቸዋል።

“ታዲያ ለሃያሉ ሞግዚታቸው ማር እህል  ከሚሰፍሩት ሌላ ልጃገረዶቻቸውን ካለጥሎሽና ካለ አንዳች ክፍያ ኒያንጋቶሞች
በሚስትነት ይሰጣሉ። ኩዩጉዎች ግን ከኒያንጋቶሞች ካሮዎች.. ጋርዐመጋባት አይችሉም ስለሚናቁ።

“ኩዩጉዎች የሌላቸውን የማይመኙ በዚህ ኑሯቸውም ከአቅም በላይ ለሆኑ ነገሮች የማይሰጉና የማይጨነቁ ናቸው። ከሁሉም በላይ ባህላቸውን አክብረው ራሳቸውን ሆነው መኖርን ይመርጣሉ።
የሚገርምሽ በልጅነቱ ከነሱ የተለየው አያቴ እንኳን እንደ
ዘይትና ውሃ ለረጅም ጊዜ ከኖረበት ስልጣኔና ባል ጋር ሳይዋሃድ ነው ወደ መቃብሩ የወረደወ:
👍261👎1🥰1
በዚህች ዓለም ላይ ቁጥራቸው አምስት መቶ የማይሞሉት ኩዩጉዎች ስላም ወዳድ ስለሆኑ አምርተው ከዱር ፍሬ ለቅመው ከጫካ ማር ቆርጠው አሳ አጥምደው... በደስታ ተፋቅረው የሚኖሩ
ሲሆን ትልቁ አሣ ትንሹን እንደሚውጠው ሁሉ ከጥቃት ለመራቅ
የተወሰኑት ከሌሉች ማህበረሰቦች ጋር በጥገኝነት ሲኖሩ ቀሪው ግን እዚሁ ጫካ ቤቴ' ብሎ ኩችሩ ውስጥ የሚኖር ነው:"

“እሚደንቅ ነው። ታዲያ አሁን ምን አሰብሽ?"

“ለጊዜው ወደ ስፔን እመለሳለሁ! ልርቃቸው ግን
አልፈልግም: ቀደም ሲል የአያቴ  አደራ  አሁን ደግሞ ሃዘን ህሊናዬን አሸማቆታል። እንዴት ልረዳቸው እንደምችል አላውቅም።
ይህ ረጋ ብዬ ወደፊት የማስብበት ይሆናል::

“ስለ ኢትዮጵያ የአለም ህዝብ እስካሁን የሚያውቀውን ግልባጭ ግን ለማሳወቅ አንደበቴን ከፍቼ ለመጮህ እፈልጋለሁ።እኒህ ንፁህ ማህበረሰቦችም  ሳይረበሹና ሳይደናገጡ የምርት መሣሪያዎቻቸውን በማሳደግ ትምህርት በማስተማር ሰው
መሆናቸው ተረጋግጦ ቀስ በቀስ የተሻለ ሕይወት እንዲያገኙ በሚደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ተሰላፊ እሆናለሁ:

“የኦኗኗር ስልታቸው ማህበራዊ ሯቸው ለሰው ልጅ ያላቸው አጠቃላይ ፍቅር... አፍሪካውያን በቅጅ ህይወት የተነከሩ ብቻ
ሳይሆኑ ማራኪ ማህበራዊ ህይወት የነበራቸውና ካለ ምንም እገዛና ቅራቅንቦ የሚበሉትን ራሳቸው በሰሩት መሣሪያ አምርተው
የራሳቸውን ልብስ ሰፍተው በባህላቸው የጋራ ችግሮቻቸውን ፈተው
በመቻቻል! ተደስተው... ለዘመናት መኖራቸውን ስለሚያረጋግጥ ባህሉንና ወጉን ላለውና ለሚቀጥለው አፍሪካዊ ትውልድ ማቆየቱ
የምዕራባውያንን ጉንጭ አልፋ የእብሪት ጎሜ ሰማስቆም  ይረዳል
ብዬም እገምታለሁ" አለች ኮንችት ፈገግ ብላ።

“ጥሩ አስበሻል ኮንችት። የስነ ሰብዕ ምርምርም ይህንኑ የሚያጠነከር ነው: ማንነትን መጠበቅና በራስ መተማመን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ መብቱ ነው ሊሽራረፍ የማይችል! ጥቁር ነጭ...የተለያዬ ባህል ይችን ዓለም አሳምሯት ኖሯል:: ይህ ውበቷ
መጠበቅ እንጂ አንዱ ከሌላው የተሻለ ሆኖ ይህ ሲጠፋ ያ ማደግ
የለበትም። ተረዳድቶ ተግባብቶ ተጋዞ ተከባብሮ መኖር ለሁሉም ይበጀዋል።

“ንቀት የደካማነት መስፈሪያ ቁና ሆኗል: ዘመንሁ ባዬ
ህብረተሰብ በዚህ የንቀት ቁና ተንቀርቅቦ እበቅ ሆኖ ከመደፋቱ በፊት በእርጋታ ተፈጥሮአዊ  እውነትን ሊመለከት ይገባዎል።  በጥቅም የተሸነታተረው ህይወቱ የሚጠገንበትንም ማወቅ አለበት: ካለበለዚያ
በሰራው ዘመናዊ ሙቀጫ እየተወቀጠ ይደቃል።

“የሰው ልጅ ተፈጥሮን እየተቃረነ በስልጣኔ የሚጓዘው ፈጣን ጉዞ ጭው ካለው ገደል ይጨምረዋል:: የዓለማችን ብክለት
የሰላም መጥፋት ጦሱ ይኸው የኋላውን ሳያስተውሉ ፊት ለፊት
እያዩ የመሮጥ ስህተት ነው᎓ ሐመሮች ኩዩጉዎች. ከስለጠነው ዓለም ከሚፈልጉት ይልቅ 'ስልጡኑ' ህዝብ ከነሱ የሚያገኘው ጥቅም
ይበዛል። የሰለጠነው ዓለም የአፍሪካውያንን ባህል ቁጭ ብሉ መማር አለበት። ካለ ኤሌክትሪክሲቲና ኒኵሌየር ሃይል... በጨረቃ ብርሃን መኖር መቻሉን እንደገና ማወቅ አለበት።

“በዘመነው ዓለም የጥቅም ቁማር አፍሪካውያንን በጦርነት እሳት መማገዱ ውሎ አድሮ ሰደዱ እጉያው እንደሚገባም ሊዘነጋው
አይገባም... ስለዚህ እኔም የዘመነው ዓለም የናቃትን አፍሪካ ሐመሮችን የሚያይበትንና ኑሮአቸውን የሚያደንቅበት መላ
ለማምጣት ያወቅሁትን በዓለም አቀፍ መድረኮች አትሮኖስ ላይ ቆሜ
እለፍፋለሁ..." አለችና ካርለት ፈገግ አለች ኮንችት ካርላትን በስሜት ስታያት  ካርለት ድምጿን ለስለስ
አድርጋ ንግግሯን በመቀጠል አፍሪካ ከማዕድናቷ ይልቅ ማህበራዊ ህይወቷ ታላቅ
ጥራ ሃብት ነው ለዘመነው ህዝብ ስትል ሁለቱም በስሜት ተቃቀፉ።

💫ይቀጥላል💫
👍271
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“ይህ ክላሲካል ዋሽንት ተጫዋች ማነው?"

ሐመሩ የፍቅር ጓደኛዬ ነው ዋሽንት ግን መጫወት
ይችላል?

“ያውም ልብን በሚሰልብ ቅላፄ ነዋ የአጨዋወት ስልቱ ልብሽን የሚሰውርበት አካልሽን የሚያንሳፍፍበት... አንዳች ኃይል አለው:: ከርቀት የሚቀሰቅስሽ የሚንጥሽ…"

“እንኳን ደስ አለሽ በይኛ!በፍቅር ክንዱ አፍቃሪዎቹን
በተራ ያሰለፈን ጀግና በሙዚቃ አርቱም የምንተኛበትንና
የምንነቃበትን ፕሮግራም ያወጣልናላ ደልቲ ገልዲ…

ምን

የሱ ታሪክ ብዙ ነው ኮንችት: በርቀት ስታይው የፍልፈል
አፈር! እየተጠጋሽ ሄደሽ ውስጡ ስትገቢ ግን እንደ ተራራ እየገዘፈ፤ወደላይ እየተከመረ የሚሄድ የሚስጥር ዓለም ነው።''

“እውነትሽን ነው"

“አዎ  ኮንችት"

ኮንችት ደነቃት ገረማት ፍቅራቸውን ልታየው ሞከረች አንዴ ካርለትን
ተመልሳ ደልቲን… አየችው አጠጋጋቻቸው አሰተቃቀፈቻቸው
አሳሳመቻቸው… በሃሳቧ ምራቋን እየዋጠች፡፡

“ምነው ኮንችት? ካርለት ኮንችትበብ ጭልጥ ስል
እየሳቀች ቀስቅሳ ጠየቀቻት።

“እንጃ! ግን." ኮንችት ሃሣቧን ገደበችው ዋጠችው ካርለት እንደገና ሳቀች። ሳቋ ደልቲን ጎሻሸመው። ዞር ብሎ ፈገግ
ሲል የኮንችት አይኖች ጥርሶቹ ላይ ተሰኩ! እንደ በረዶ ጥርሱ ነጭ ነው።

“ታፈቅሪዋለሽ?” ሞኝ ሆነች ኮንችት

"አዎ የፍቅር እንጥሌን ሌሎቹ ተንጠራርተው ሲያጡት ተቀምጦ የነካው እሱ ብቻ ነው ተሳሳቁ ካርለትና ኮንችት::

'እንጥሌን እምም...” ኮንችት እንደገና ምራቋን ዋጠች።

“እሱም ያፈቅርሻል?”

“እኔ እንጃ... ቢሆንም አይላኝም እኔ ለእሱ ገና
ያልተገራሁ ባዝራ ነኝ: ስለዚህ ከኔ ይልቅ እሷን ይወዳታል:"

ካርለት በአገጯ ጎይቲን ለኮንችት አሳየቻት
ኮንችት ጎይቲን እስከ አሁን ለምን እንዳላስተዋለቻት
ገረማት የጠይም ቆንጀ እግሮችዋና ወገቧ የሚያምር ችምችም
ያሉት የወተት አረፋ ጥርሶችዋ የሚያስጎመጁ ሆነባት።

ኮንችት ጎይቲን ስታያት እንደቆየች ስለ ውበት አሰበች።ስለ ሰው ልጆች የራቁት ውበት ልብስ ስላልሸፈነው ተፈጥሮአዊ ገላ አለመች:: ሰው ሁሉ በተፈጥሮው ማራኪ ነው ያምራል ይስባል...

“አሁን ግን እሷ አግብታለች ስለዚህ የደልቲን ፍቅር እንደ
ማንጎ እየጋጥሁ እረካባታለሁ ስል ጀግናው ሌላ ቆንጆ በፍቅሩ ግዳይ
ጥሎ ቆንጀዋ ልቡን ሰብራ ልትገባ ስትፈልጠው ደረስሁ... ሳቀች

ካርለት: ሳቋ ኮንችትን ስለውበት ከምታልምበት የፍልስፍና ዓለም ቀሰቀሳት።

"እሷ ደግሞ ማን ናት?"

“ዳራ ትባላለች ሐመር ናት: ልቅም ያለች ቆንጆ!...”

ካርለትና ኮንችት እንዲህ ሲጨዋወቱ ጎይቲ አንተነህ
የምታየው የምትሰማው የምትነካው የምታልመው... አንድ ሰው ነው:: ከፊት ለፊቷ የተቀመጠውን የፍቅር ጀግናዋን ትኩር ብላ
ስታስተውለው ቆይታ ወደ እሱ ሄደች።

በእጇዋ ጨሌ
አንጠልጥላለች መለሎ
አንገቱ ላይ አጠለቀችለት! ቀና ብሎ አያት እሷም ዝቅ ብላ አየችው።

አልተቀየረም  እሷም
አልተቀየረችም ትንፋሻቸው ይጥማል። የጫካ ነፃነታቸው ግን የለም ጭኗቿ አይታቀፏትም ደረቱ ላይ አትተኛም፤እሱም ዳሌዋን አያቅፍም
ጡቶችዋ እንደ እንቧይ ደረቱ ላይ አይነጥሩም...

“ይእ! እንኳን ደና ሆነህልኝ እንጂ..." ብላው እንባዋ
በአይኗ ዙሪያ ተኮለኮለ

“ምን ይሆን ብለሽ ነው አንች..." እሱም መናገሩ
አቃተው: ይህን ሲል ጎይቲ የፍቅር ትዝታው ጠቅ አድርጎ ወጋት ስለዚህ ሃዘን የሰራ አካላቷን በጨካኝ ስለቱ አብጠለጠለው። ያኔ ልቧ፣ ሲኮማተር አይኗ ዙሪያ የተኮለኮለው እንባዋ ኩልል ብሎ ወረደ።

“ይእ ባይሆን አልጣህ- አይንህን ልየው ፍቅርህ ልቤ ውስጥ ሲንፈራገጥ አንተ ሳትኖር እንደ ምጥ ያስጮኸኛል ጤና ይነሳኛል። እንኳንም ግን ፍቅርህ ተሆዴ አይወጣ! እንኳንም
አልገላገለው! እሚወለድ ቢሆን ሲያድግ ብቻዬን ጥሎኝ ይሄድ ነበር.." ትክዝ አለች እይታዋን የከለከለውን እንባዋን ጭምቅ አድርጋ
አፍስሳ።

ስሜቷ ጭምትርትር ያለውን ጎይቲን ሲያይ ደልቲም የሆነ
ነገር እሱም ሆድ እንደጉማሬ ሲገላበጥ በዓይነ ህሊናው ታየው።

“ተይው የኔ እህት! ተይው እርሽው ተንግዲህ ተሱ
ምሰይ: የአባት ደንብ ተሁሉም ይቦልጣል  ተፍቅርም!! ስለዚህ
ጉም መቼስ አይዘገን.." ብሎ የባሰ የሐዘን ቦይዋን ከፍቶ ለቀቀባት
የሚያጉረመርም ሳግ ቀጥሎ የህሊና ብራቅ ከዚያ እንባዋ አጨቀያት:
ጎይቲ እንገቷን ደፋች: እሱን ማጣቷ እውነት ነው! እውነትም የሱ የመሆን
እድሏ አክትሟል፤
አክትሟል፤እውነትም
የፍቅር ጥገታቸው
ነጥፋለች...

ጎይቲ እንባዋ ቦዩን ይዞ ፈሰሰ፣ እንባ የጠማት መሬት ደግሞ የፍቅር እንባዋን እያጣጣመች ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው::መሬት ሰዎች ሲፋቀሩ የሚተርፋት እርግጫቸው ነው ሲያዝኑ ግን ፀሐይ ያቃጠው ጉሮሮዋን ጨዋማ እንባቸው ጥሟን ያረሰርስላታል ጥሟን ይቆርጥላታል ጣፋጩ የሰው ልጅ እንባ የጎይቲን እንባም መሬቷ አፏን ከፍታ ጠጣችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

' ...ይእ ተወኝ አንተ ሰው! መች አንተ ለእኔ አነስከኝ።
የአንተ መሆኔን ነጋሪ አልሻም ሰው መቼስ ካሉት በረት ሙሉ ከብቶች የሚቆረቆረውና የሚቆጨው አውሬ የበላበትን ጫካ
ያስቀረበትን ከብት አይደል! እንደማያገኘው ልቦናው ያውቀዋል ቢኖርም ለእሱ እስካላለው ድረስ በሽታ ይገለው ይሆናል: ይህን ግን
አያስብም። ዘወትር ቁጭት ብቻ ወይኔ ብቻ. እሮሮ ብቻ

“አያ ደልቲ የኔ አይደለም:: ከእንግዲህ በሴትነት መላዬ
ጀግናውን እየመራሁ ወስጄ ልቤ ውስጥ አላስተኛውም ሙቀቱን አልጋሪውም... ያች የፍቅር ጨረቃ አሁን የማይወለደውን ጨቅላ
አቅፌ እሽሩሩ….' የምልባት ብርሃን ናት: የፍቅሩን ትዝታ!
የጀግናውን ገድል፤ የማይጎረምስ ፍቅሩን፤ ጠረኑ የማይለውጥ
ፍቅሩን... የማልምባት ናት ጨረቃ!

"በእጅ ያረጉት አንባር ከእንጨት ይቆጤራል' እንዲሉ ለአያ ደልቲ ስንሰፈሰፍ ልብህ ቢከፋው አይደንቀኝም!በድየሃለሁ
"ዘንግቼሃለሁ... ግን ወድጄ አይደለም። ስቆምበት ልብህ እንደ ደረቀ
እንጨት ሲሰባበር ይሰማኛል። ወንድነትህን ብታሳዬኝ ሸንቆጥ
ብታደርገኝ አብያው ልቤ አደብ ገዝቶ ትዝታዬን እያረሰ ገለባብጦ የአንተን የፍትር ቡቃያ ያበቅለው ነበር: አንተ ግን ወኔ ከወንድነቱ
ይልቅ ወደ ሴትነቱ ያደላል፡ እንደ ወንዶች አታገሳም አትፎገራምI አትዋጋም አሯሩጠህ አትጥልም! አትጀነንምI የተከደነውን በሃይል አትከፍትም...

“እና ልቤ ሃይ ባይ አጣ ትዝታዬን የሚሽር ትዝታ
አጣሁ ይእ! አይ ልፋቴ አንተ እቅፍ ውስጥ ሆኜ ከተራራው ማዶ ሰው ፍለጋ ስንጠራራ! 'አሁንም ትወጂዋለሽ... እያልህ ከምትለኝ በወንድነት በልቤ ውስጥ የሚዋኘውን ጀግና አጥምደውና ሃሣቤን
ቆልምመው: ለእኔስ አያ ደልቲ እንዳለኝ ተአባቴ ደንብ ውጭ እሱን ማሰብ 'ጉም መዝገን' አይደል!

“አንተና እኔ ሰውነታችን እንጂ አበቃቀላችን ለየቅል ነው።መስሎህ እንጂ ማንም ትሁን ማን የደረሰ ቡቃያዋን አሽቶ ያቃማትን ሐመር አትረሳም:: ያውም ያያ ደልቲን የፋና ወጊውን የጀግናውን አንበሳ ቀጭኔ... ከገደለው እቅፍ የገባችውን... 'ተይ' ተብላ ፍቅሩን ከልቦናዋ አውጥታ ልትወረውረው ይህ የሚቻላት ሐመር የለችም።

“እኔ የኔ ጌታ በቃልህ ተይ ዘንጊው... አትበለኝ: ቅጣትህ ይሻለኛል! ልመናህ ግን ያብሰኛል.." ጎይቲ አይኖችዋን አድማሱ ላይ
ሰንቅራ ሃሳቧን ሳትጨርሰው ፀጥ አለች።
👍281
ከሎ የሚላት ጠፋው! ቢጪንቀው ጠጋ ብሎ አቀፋት ተቆጥታ ገፋችው! ምርር አለችበት ከዚያ ወንድነቱ መጣበት ቆጣ
አለ! ቀኑ ጨልሟል እጆችዋን ጠበቅ አድርጎ ጎትቶ ይዟት ወደ ኩችሩ ጫካ ገባ። ጫካው ውስጥ አያያዙን ሳያላላ ወደ እሱ በሃይል አስጠጋት አልታየወም እንጂ ሃጫ በረዶ ጥርሶችዋ በደስታ
ተገልጠው ወደ የሰውነቱ ተላጠቀች

ጨረቃዋ አካባቢውን
በብርሃኗ አጥለቅልቃዋለች።
ኩዩጉዎች ሎካዬንና ነጩን እባብ ስምንት ቀን ሙሉ ቢጠብቁም ከሰማይ ሳይወርዱላቸው ቀሩ: ተስፋ አልቆረጡም የተስፋ መቁረጥ ስሩ መጠራጠር
ነው: ኩዩጉዎች ግን መጠራጠር አያውቁም !
ስለዚህ ሎካዬ የሰላም ምልክታቸው የሆነውን ነጩን እባብ ይዞ አንድ
ቀን ከማህበረሰቡ ጋር ይቀላቀላል ብለው እየጠበቁት ነው:

ጭፈራው አልተቋረጠምI ኩዩጉዎች ባለ ብዙ ቋንቋ
ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በተለያዬ ስልት ጥሩ ደናሾችም ናቸው::
አቅመ ደካማነታቸው ለዚህ ችሎታ አብቅቷቸዋል:: ኒያንጋቶሞኛ ካሮኛ ሙርሱኛና ሐመርኛ ጭፈራ ይችላሉ:

አንድ ቀን ታዲያ የኩዩጉ
ልጃገረዶችና ጎረምሶች
ሰውነታቸውን በአኖ አሰማምረው ለኢቫንጋዲ ጭፈራ ሲዘገጃጁ ዋሉ:
አይደርስ የለም ከተበላ h
ከተጠጣ በኋላ የጭፈራው ስዓት ደረሰ።

ሁለት የምሽት ጭፈራ መሐንዲሶች ጎይቲና ደልቲ
ቢኖሩም ጎይቲ ግን ያገባች በመሆኗ በምሽቱ ጭፈራ አንጀቷ እያረረ ተመልካች ሆነች። ደልቲ ጭፈራው እንደተጀመረ  በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ እያሸጋገረ ጎይቲን ያያል:

የኢቫንጋዲ እንዝርቷን አስታወሳት። አቤት ጊዜ
የነበረውን ሲቀይር እንዴት ያውቅበታል ጎይቲ የኢቫንጋዲ ጭፈራ
ተመልካች ሆነች! እንደ እናቷ ከጭፈራው ቦታ ራቀች? ከጎረምሳ ጋራ መፋተግ መተሻሸት... አቆመች: ጭፈራውን ስትሰማ
የጎረሰችውን ተፍታ የምትሮጠው ቆንጆ የዳንሱን መድረክ የምትሞላው አበባ ባህል ጠወለግሽ አላት

ደልቲ ያያታል! መሬቱ ላይ በግዴለሽነት ዝርፍጥ ብላ
አይኖችዋ ያያሉ! ህሊናዋ ግን የት እንዳለ አይታወቅም፡

“እውን አንች ጨረቃ የትናንቷ ነሽ? እናንተ ከዋክብትስ እውነት ቦታችሁ እዚሁ ነበር...  ምነው እናንተን ባረገኝ
ከጭፈራውስ ባልርቅ ጥሩ ነበር..." የተናገረችው፧ አባባሏ ይብስ እንደ
ሐምሌ ውርጭ አቀዘቀዛት።

ጭፈራው ድሪያው ፍትጊያው ደርቷል። እሷ ግን
ትዝታ ያንጎላጃታል
“ጎይቲ ተብርዱ ብትሄጂ አይሻልሽም! ከንቱ ላትጫወች እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?''

“ይእ ልያችሁ እንጂ! አይን መቼም አይከለከል። አንተ
ምነው አትጫወት…”

“ይቅርብኝ አንች ሳትኖሪ ይሻለኛል እንጂ..."

“ልሂድልሃ”

“ለምን? እኔ እሄዳለሁ።"

“ወዴየት?”

“አልርቅም፤ ወደዚያ ወደ ጫካው ቆየት ብዪ እመለሳለሁ

“አንተ ከሄድህማ እኔስ ምን እሰራለሁ ተኝቼ በህልሜ
ልይህ!" ደልቲ ትኩር ብሎ አይቷት ሄደ ከአይኗ እስኪሰወር አየችውና ከተቀመጠችበት ተነስታ ሄደች። ጨዋታው ግን ሞቋል፤ልጃገረዶች ይሣሣቃሉ…

💫ይቀጥላል💫
👍19👏1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ስምንት)
(ሜሪ ፈለቀ)

መቼም ሰው <ልቤ ዝቅ አለብኝ> የሚለው አሁን እኔ እንደሚሰማኝ ልቤ አቃፊዋን ለቃ የወጣች የሚመስል ስሜት ሲሰማ ነው የሚሆነው። የኔዋማ ዝቅ ከማለትዋም እነ ሳንባ ጉበትን <ዞር በሉ በናታችሁ> ብላ ገፋ ገፋ አድርጋ አንጀቴ ላይ ዛል ብላ ጋደም ያለች ይመስለኛል። አጅሬው እኔን ድዳና ሽባ አድርጎ በድንጋጤ አደንዝዞኝ እሱ እቴ በሙሉ አይኑ እንኳን አላየኝምኮ!!

ለመሆኑ ስሙስ የምር ጎንጥ ነው? የሚያወራው የሀገርኛ ለዛውስ ዘበኛ ለመምሰል ያስመሰለው ይሆን? ቅድም እንዴት ነበር ያወራው? ንፋስ ሲሆን ትከሻው ላይ ጣል የሚያደርጋት ፎጣውስ የትወናው አካል ትሆን? ዘበኛም ሆኖ አንዳንዴ ስንወጣ የሚለብሰውን ዓይነት ጅንስ በሸሚዝ ስለለበሰ የአለባበሱን ትወና መለየት ይቸግራል።

«ስራህንማ በአግባቡ ተወጣህ!» አለችው ሴትየዋ። ሙገሳ አይደለም! የሆነ ለበጣ ያለበት ነገር ነው! ቀጥላ የሆነ በእኔ ፊት ወይም በሰውየው ፊት መናገር ያልፈለገችውን ነገር ለብቻቸው እንዲያወሩ መሰለኝ። « ….. እኔ እና አንተ ብዙ የምናወራርደው ነገር አለ።» ብላ እጁን መንጨቅ አድርጋ ይዛው ልትሄድ ስትሞክር ከተቀመጠበት ሳይነሳ እጁን መነጨቃት። አስከትሎ ከእግሯ እስከ አናቷ በግልምጫ ካበጠራት በኋላ ራሱ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቀድማው ከሳሎኑ እንድትወጣ ምልክት አሳያት። (እንደለመደው ነዳት ብል ይቀላል) በተጫማችው ሂል ጫማ እንደዝግዛግ ያለ አረማመድ እየረገጠች ሳሎኑን ለቃ ስትወጣ ተከትሏት እየተቆለለ ወጣ!! ከትውውቅ አልፈው መደነቋቋል ላይ የደረሱ ወዳጃማሞች መሆናቸውን ለማወቅ ምንም ሂሳብ አያስፈልግም!!

< ሄሎ!! እዚህ ነኝ! ሜላት! አስታወስከኝ? ከአንድ ቀን በፊት እመኚኝ ብለህ እንደወፍጮ ቤት እህል አየር ላይ ያንቀረቀብከኝ? አልታይህም?> ይላል ውስጤኮ አፌን ቃል ማን ያበድረው? ከሳሎኑ ከወጡ በኋላ የሚያወሩት ባይሰማኝም ጭቅጭቅ ላይ መሆናቸው ከድምፃቸው ያስታውቃል። ጎንጥ እንዲህ ይጮሃል እንዴ ሲያወራ? እኔ ንግግሩን ሳልሰማ ድምፁ እንዲህ ያስደነገጠኝ እሷ እዛች ሚጢጥዬ ፊቷ ላይ ሲጮህባት ወትሮም ያነሰች ፊቷ አለመትነኗ!!

የሁለቱ ሁኔታ ግራ የገባው ከመሰለው ሰውዬ ጋር ተፋጠን ሁለታችንም ከማይሰማው የሁለቱ ጭቅጭቅ ቃላት ለመልቀም ጆሯችንን አሹለን እንቃርማለን!! ፀጥ ያሉ መሰለ ወይም ድምፃቸው ለኛ መሰማቱን አቆመ።

«ለመሆኑ እኔ ማን እንደሆንኩ ታውቂያለሽ?» አለኝ ሰውየው በተፈጠረው ክፍተት። የሆነ ተራ ጥያቄ የጠየቀኝ አስመስዬ አፍንጫዬን ነፍቼ ለማለፍ ሞከርኩ።

«ጊዜ ግን ሲገርም!! በተሰቀለው!! ምንም ምንም አታስታውሺም?» ብሎ ሊገለፍጥ ዳዳው « መቼም ግፍሽ ነው!! በቁጥር እኮ አይደለም አንቺ የህዝብ ግፍ ነው ያለብሽ!! ሃሃሃሃ ሰውኮ የዘራውን ነው የሚያጭደው ሃሃሃ ስንቱን እንዳልከዳሽ የራስሽ ጭንቅላት ይክዳሽ? እረስታለች ሲሉኝ ማመን ያቃተኝ ቀጥ ብለሽ ስትመጪ ነው። ምንም የምታውቂው እና የምታስታውሺው ሳይኖር …… » ብሎ ሲጨርስ

«እኔ እንዳልረሳው አይጠፋህምሳ መቼም!» እያለ ገባ ጎንጥ!! ሴትየዋ ትንሽ ቀይ ፊቷ ሚጥሚጣ የተነፋበት ሰሃን መስሎ ተበሳጭታ ተከትላው ገባች።

«እሷ ትሄዳለች። ወንድምየው እኛጋ ይቆያል።» አለች በኮሳሳ ድምፅ ትዕዛዝም ሀሳብ ማቅረብም በመሰለ አነጋገር - ለሰውየው። ሰውየው ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲደነፋ እና ሲጯጯሁ «ኪዳንን ትቼ አልሄድም!» ያልኩትን የሰማኝ የለም!! ጎንጥ አጠገቤ ደርሶ ቁጢጥ እንደማለት አለ እና

«እባክሽ እንዳታስቸግሪኝ (ይሄኛው ልመና ነገር ነበር) የምልሽን አድርጊ! ካለበለዚያ ያንቺንም የእኔንም የኪዳንንም ህይወት ነው እሳት ምትሰጅበት (ትዕዛዝ ነገር ሆነ) ለዛሬ! ለዝህች ደቂቃ ልታምኝኝ ይቻልሻል? (ልምምጥ ነገር ሆነ)» አልመለስኩለትም!! ሰውየውና ሴትየዋ በጥፍራቸው ቆመው ይጨቃጨቃሉ።

«ታምኚኛለሽ?» ሲል ግን በፍጥነት
«አላምንህም!!» አልኩት። ይህችን ለመተንፈስ ሰዓት እየጠበቅሁ ይመስል ተቅለብልቤ

«ሜላት እኔና አንቺ የምንነታረክበት ጊዜ የለንም! ስትፈልጊ አትመኚኝ ያልኩሽን ካልሰማሽ ሙት ነሽ!! (ይሄ ድብን ያለ ቁጣ ነው!!) እኔ እና አንቺ አሁን ወጥተን እንሄዳለን!! አንቺን እንጂ ኪዳንን አይፈልጉትም!! በምትወጅው ኪዳን ይሁንብሽ ለአንዴ እመኝኝማ! (እዚህጋ እኔን ማስረዳት የደከመው መሰለ) ኪዳን ምንም አይሆንም!! (ድምፁን ቀነስ አድርጎ) ኪስሽው ውስጥ አሁን እንዳታስታውቂ ! ኪዳን መልዕክት አኑሮልሻል!! ከዚህ ከወጣን በኋላ ታይዋለሽ!! አሁን እንሂድ? (ይሄ እባክሽ እንቢ እንዳትዪኝ የሚል ማባበል ነው።)።» ምላሴን ምን ያዘብኝ? እሺም እንቢም ማለት ጠፋኝ!! ሰዎቹ ጭቅጭቃቸውን ማቆማቸውን ያወቅኩት

« I knew it!! ወደሃት ነዋ!» ብላ እግሬ ስር ቁጢጥ ያለውን ጎንጥ በትንግርት እያየችው የሆነ ግኝት የተገለጠላት ዓይነት አስመስላ ስትጮህ ነው። ጎንጥ አቀማመጡን ገና አሁን ያስተዋለው ይመስል ተመንጭቆ ተነስቶ ክምር ተራራ አክሎ ተገተረ። ሴትየዋ አላቆመችም። እንደንቀትም፣ እንደ መገረምም ፣ እንደመናደድም …… እንደብዙ ነገር በሆነ ድምፅ እና እይታ « ጎንጥ ለዝህች? (በአይኗ አቅልላ የጤፍ ፍሬ አሳከለችኝ) ማን ያምናል? በምን አገኘችህ በናትህ?»

«አፍሽ ሲያልፍኮ አይታወቅሽም!! እረፊ ብያለሁ!» ብሎ ተቆጣ።

ቆይ እዚህጋ የትኛውን ሀሳብ አስቀድሜ የትኛውን አስከትዬ የቱን ምኑጋ ሰካክቼ ልከኛውን ምስል ላግኝ? ሰው ሀሳብ ይበዛበታል አይሉም በአንዴ ራሱን ጎንጥን የሚያካክል መአት ሀሳብ ወርውረውብኝ እዛ እንደተቀመጥኩ የሚዘነጉት? ኸረ ቆይ ጎንጥ ወዶኝ ነው የሚለውን ላስቀድም? ኸረ አይደለም! <ይህችን?> ብላ ምላሷ ላይ ያሟሸሸችኝ እኔ አስቀያሚ ነኝ እንዴ? አይደለም ኸረ ቆይ ጎንጥ ሴትየዋን ምን ቢላት ነው እኔን ይዞ እንዲሄድ የተስማማች? ኸረ ሌላው ደሞ እሱስ <ወድጃት አይደለም> ከማለት ይልቅ የሚደነፋው ወዶኝ ነበር ማለት ነው? አይ እነዚህ ሁሉ ይቅሩ እንዴት አምኜው ነው ኪዳንን ትቼው የምሄደው? ግን ምርጫስ አለኝ? ኸረ ኪዳን በምን ቅፅበት ነው መልዕክት ያስቀመጠልኝ? ምን ይሆን የሚለውስ? ደሞ ሌላ አለ እንጂ ቆይ ጎንጥ እኔን ቢወደኝ እሷ ምን እንዲህ ይንጣታል?

በአይኑ ከተቀመጥኩበት እንድነሳ ምልክት ሰጠኝ። በአይኑ አስነሳኝ። እጁን ሰጠኝ ወይም እጄን ተቀበለኝ እኔእንጃ ብቻ እጄን ያዘው እና ወደበሩ መራመድ ጀመረ። ጠባቂዎቹ ትዕዛዝ የሚጠብቁ ይመስላል ከበሩ አልተንቀሳቀሱም!! ሰውየው በአገጩ የሆነ ምልክት ሰጣቸው!! ከበሩ ገለል አሉ!! ሴትየዋ መናጥዋ በረታባት!!
👍241🔥1
«እመነኝ ጎኔ ይህችን አታልፋትም!! አስከፍልሃለሁ!! እመነኝ ትከፍላታለህ!!» አለች እየጮኸች። <ጎኔ> ብላ ነው ያቆላጰሰችው? ዛሬማ የሆነኛው ፊልም ተዋናይት ሆኛለሁ እንጂ እየሆነ ያለው እውን በእኔ ህይወት እየሆነ ያለ አይደለም!! እንዲህ አፍና ጭራው ያልተለየ እውነተኛ ህይወት ሊኖር አይችልም።
በሩን አልፈን እንደወጣን የቅድሟ ሴት ተቀበለችን። ስመጣ ያሰሩልኝን ጨርቅ ይዛ ስትቀርበኝ የያዘኝን እጁን ለቅቄ በጥያቄ አየሁት!! የታከትኩት መሰለ እና በቁጣ ጮኸ « እየገባሽ አይደለም አንቺን መምረጤ? ከዚህ በላይ ምን ባደርግ ነው የምታምኝኝ በይ? ያለፈውን ካላወቅኩ ነው? አንድም ሳይቀር አወጋሻለሁ! እዝህችው ቆመን 19 መቶ ብዬ እንዳወጋሽ አይደለማ ሀሳብሽ?» ቅድም ሴትየዋ ላይ እንደጮኸው ነው የጮኸው!! ጨርቁን እንድትሰጠው ለልጅቷ እጁን ሲዘረጋ ልጅቷ እንደማቅማማት አለች። ጮክ ብሎ ሲያፈጥባት የመወርወር ያህል እጁ ላይ ጣለችው። ከሁኔታዋ ከዚህ በፊት የሚተዋወቁ የምትፈራው ሰው መሆኑ ያስታውቃል። ምናልባት አለቃዋ ነበር? ዛሬማ የሆነ ፊልም ገፀ ባህሪ ሆኛለሁ።

ከሴትየዋ እጅ ተቀብሎ እሱ እያሰረልኝ እንደዛ እንዳልጮኸ ልስልስ ብሎ ነገር «መግቢያ መውጫቸውን እያየሽ እንድትሄጂ በጀ አይሉሽም!! ለዛሬ የምልሽን እሽ በይ በሞቴ?» አለ። ማደንዠዣ እንደወጉት በሽተኛ ፍዝዝ ድንግዝ አልኩ። ጨርቁን ካሰረልኝ በኋላ እጄን አጥብቆ ይዞ መራመድ ጀመረ። የምረግጠው ምን እንደሆነ ሳላውቅ እግሬን እያነሳሁ ተከተልኩት። መኪና ውስጥ ገባን!! ባላይም መኪናው ውስጥ ከእኔና ከእርሱ በተጨማሪ ያቺ እንደጥላ የምታጅበኝ ሴት እና ሹፌር እንዳሉ አውቂያለሁ። እኔእና እሱ መጓዝ ጀምረን የያዘኝ እጁ መያዝ ብቻ ሳይሆን መዳበስ ነገር ያደርገኛል። ልቤ የምን አጃቢ ናት አብራ የምትቀልጠው? ትንፋሹ እንዳልተረጋጋ ያስታውቅበታል። አካሉም ይቅበጠበጣል። ከእርሱ ሁኔታ በመነሳት አሁንም እርግጠኛ የሆነ ማምለጥ አለማምለጤን ጠረጠርኩ። ቆይ እራሱ የሆነ ቦታ አግቶ ይዞኝ እየሄደ ቢሆንስ? እሱንስ እንዴት አመንኩት?

«ሴትየዋ ማናት? ምንህ ናት?» አልኩት ከዛ ሁሉ አናቴን ከወጠረው ጥያቄ ይሄን ለምን እንዳስቀደምኩ አላውቅም!! በረዥሙ ተንፍሶ

«የልጄ እናት ናት!! ምሽቴ ነበረች» አላለኝም? ከዚህ በላይ ከእውነታ የራቀ ቀን አለ እሺ?
«እ?» የምትለዋ ፊደል ከየትኛው ቃል አምልጣ በአፌ እንደሾለከች አላውቅም!! ብቻ ለምሳሌ <እንደ> ከሚለው ቃል ቢሆን ተጣልተው የፈረጠጠችው …… <ን> ን እና <ደ>ን ትርጉም አልባ አድርጋ ጥላቸው ብቻዋን ስትፈረጥጥ …… ተንደርድራ አምልጣ መሆኑ የሚያስታውቀው አፌ ፊደሏን ሊያስወጣ እንደተበረገደ አልተከደነም!!

«ባሏ ነው!!» አለ አክሎ። ሰውየውን መሆኑ ገባኝ ግን ጭንቅላቴ ውስጥ ሀሳቦቹ ተጠላለፉ ነገር። የሰውየው የአሁን ሚስት የጎንጥ የድሮ ሚስት የልጁ እናት! ከዛ ግን ዛሬም ውሉን ያልጨበጥኩትን ስራ (እገታ እና ስለላ ማለት ይቀላል) አብረው የሚሰሩ? ነው ወይስ ያልገባኝ ነገር አለ? ይሄ ቢገባኝም እንኳን በ2 ወር ከአስር ቀኔ እንደምንም ያጠራቀምኩትን አዲስ ትውስታ ሁላ ነው የሚያጠፋብኝ።


መኪናው ቆመ። ከአይኔ ላይ ጨርቁ ሲነሳ መኪናዋ የቆመችው ከከተማ የራቀ ጭር ያለ ቦታ መሆኑን አስተዋልኩ። በቅርብ ርቀት የእኔ መኪና ቆማለች። እዚህ ደቂቃ ላይ ማመንም መጠራጠርም አይደለም የተሰማኝ። ምንም ነው!! ጎንጥ ግን የሆነ ነገር እንዳላማረው ያስታውቃል። ዙሪያ ገባውን ከቃኘ በኋላ እስከአሁንም ያልለቀቀውን እጄን አፈፍ አድርጎ ወደመኪናችን እየሄድን።

«ከአይናችን ተሰወሩ ማለት የሉም ማለት አደለም!! አሁን አንቺን ማጥፋት ቀላሉ መፍትሄያቸው ስለሆነ ማስታወስ ችለሽ ከምትፈጃቸው በፊት የአቅማቸውን ይሞክራሉ።» እያለኝ እኔን ባልያዘው እጁ ወገቡ ላይ ያለ ሽጉጡን ጨብጦ ወደኋላ እና ወደጎን እየተገለማመጠ መሬቱን በረጃጅም እርምጃው ይመትረው ጀመር። ያደረሰችን መኪና ከኛ በተቃራኒ አቅጣጫ ሄደች። ከአይናችን ስትሰወር መኪናችንጋ ደርሰናል። ስንቀርብ የመኪናችን ጎማ መተኛቱን አይቶ ጎንጥ ጎማውን በእግሩ ሲነርተው አየሁ።

ከየት መጣ ሳይባል አንድ ፒካፕ መኪና እየበረረ ፒስታውን መንገድ አቧራ እያጨሰ መጣ። እየሆነ ያለው ነገር ከመፈጣጠኑ የተነሳ ውዥብርብር አለብኝ። በቅፅበት የተኩስ ድምፅ ተሰማ!! ማናቸው ቀድመው እንደተኮሱ እንኳን አላውቅም ምክንያቱም ጎንጥም እየተኮሰ ነው። በየትኛው ቅፅበት ሽጉጡን እንዳወጣ እንኳን አላየሁም!! የትኛው ቅፅበት ላይ እጄን እንደለቀቀኝም አላውቅም! ማየት እስኪያቅተን የበዛ አቧራ እያቦነነ እና እየተኮሰ አልፎን የሄደው መኪና በሄደበት ፍጥነት አዙሮ ተመልሶ ወደእኛ ሲመጣ በአንድ እጁ የመኪናውን በር ከፍቶ

«ግቢ!! ገብተሽ ወደታች ዝቅ በይ!!!! ከወለሉ ተኝ!» ብሎ ጮኸ! ምንድነው እግሬን ከመሬቱ የሰፋው? እኔ የድርጊቱ አካል ያልሆንኩ ይመስል ዓይኔ አንዴ ጎንጥን አንዴ በፍጥነት እየመጣ ያለውን መኪና ያያል። በሩን ከፍቶበት በነበረው እጁ ከጎኑ ወደጀርባው ገፈተረኝ። አፈሰኝ ማለት ይገልፀዋል። እኔንም ራሱን መከላከል የማይችልበት አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተትኩት ገብቶኛል ግን በምን በኩል ሰውነቴን ልዘዘው? ዓይኔ ስር ፊልም እየተሰራ ያለ ዓይነት ስሜት ነው ያለው። እኔን ወደጀርባው በደበቀኝ ቅፅበት ለጊዜው ምኑጋ እንደሆነ ያልለየሁት ቦታ እሱ ተመታ። እኔ የተመታሁ ዓይነት መሰለኝ። ጭንቅላቴ ለቅፅበት ያን ቦታ ትቶ ሄደ። ቅፅበት ናት ግን ድንዝዝዝ ያለ..... ብዥዥዥ ያለ ቅፅበት .... ጎንጥ የተመታበትን ቦታ በአንድ እጁ ይዞ

«ወዳጄ ይደርሳል። ከእርሱ ጋር ሂጂ!! እቤት እንዳትሄጅ!! » ይለኛል ጮክ ብሎ!!

«ትቼህማ አልሄድም!!» ዓይኔ ከፒካፑ መኪና ጀርባ እየመጣ ያለ መኪና በአቧራው ውስጥ ቢያይም ጭንቅላቴ ግን እዛው ገትሮኝ ሄዷል። አንድ ጥይት በጎኔ አልፎ መኪናውን ደነቆለው:: ሰውነቴ አይታዘዝም!! ደንዝዟል::

"ዝቅ በይ!" እያለ ይጮሃል ጎንጥ በከፊል ዘወር ሲል ከጎኑ የሚፈስ ደሙን እያየሁ ሀሳቤ ሄደ .... እዛ ቀን ላይ!!

ጥይቱ የተከፈተ የመኪናዬን መስኮት አልፎ ጡቴ ስር ሲመታኝ!! የመጀመሪያውን ህመም በቅጡ አስተናግጄ ሳልጨርስ ሁለተኛው ተመሳሳይ ቦታ ሲያገኘኝ። - የተመታሁ ቀን!! አንድ በአንድ ቁልጭ ብሎ ስዕሉ ጭንቅላቴ ውስጥ መጣ!! የማደርገው እና የማስበው በአንድ እኩል ቅፅበት ነበር። እጄን ማዘዜን አላስታውስም ብቻ ከጎንጥ እጅ ላይ ሽጉጡን እንደቀማው አውቃለሁ። ክፍቱን በተተወው የመኪና በር ግማሽ ሰውነቴን ከልዬ ሳደርገው የኖርኩት ልምዴ መሆኑን እርግጠኛ የሆንኩበትን ድርጊት እከውናለሁ። ከኋላ የመጣው መኪና በእኛና በፒካፑ መሃል ገብቶ ቆመ።

« ሂጅ እኮ አልኩ!!» ብሎ አምባረቀብኝ። በእጁ ጎኑን ደግፎ መሬቱ ላይ ተቀምጦ የመኪናውን ጎማ እንደተደገፈ።

«ደፋር እየሸሸ አይሞትም! እየተዋጋ እንጂ!» ስለው በህመሙ መሃል በስቃይ የታጀበ ፈገግታ አሳየኝ። ትውስታዬ ሳይከዳኝ በፊት አዘውትሬ የምለው አባባል ስለነበር ገባው። ጭንቀቱ የቀለለው መሰለ እና ህመሙን ማድመጥ ጀመረ። ፒካፕዋ መኪና ከአይኔ ራቀች። ወዳጄ ነው ያለው ሰውም ከመኪናው ወርዶ ወደኛ መጣ!! ሁለት ቦታ ነው የተመታው። አንዱ ከትከሻው ዝቅ ብሎ ሌላኛው ጎኑ ላይ የጎድን አጥንቶቹ መሃል ……. የለበስኩትን ሹራብ አውልቄ የሚንዥቀዥቅ ደሙን ለማቆም ከአንዱ ቁስል ወደ አንዱ እላለሁ።
👍28👎1
« ሁሉንም?» ይለኛል አይኑን ላለመክደን እየታገለ።
« ምኑን ነው ሁሉንም?»
«ያስታወሽው?»
«መሰለኝ!!» አልኩት። ሁሉንም ላስታውስ የጎደለ ይኑረው በምን አውቃለሁ?

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍246👏1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“አፈርሁኝ በራሴ ከሎ!

“ሃፍረት ልብሳችን ሆኗል፡ በተለይ ከዚች ሃገር ወጣ ብለህ ስትመለስ የት ነን? ማን ይዞ አስቀረን?... ሺ ጥያቄ በህሊናሀ ይደረደራል። መልሱን ግን አታገኘውም! የሚመልስልህም የለም::

“መጽሐፍ ስታነብ ያለፉትን የኪነ ጥበብ ስራዎች ስታይ
በታላላቆቻችንና በኛ መካከል ያለው ግሉህ ልዩነት ያፈጥብሃል
ጠልፎ እሚጥል ! ጉቶ ይመስል እንቅፋት ሆኖ ለመስራት የሚፍጨረጨሩትን የሚያደናቅፍ ምክንያት ይኖራል! ደግሞ አለ!
ነበረም።

“ይህ ግን በእንቅልፍ ለመደበቅ በቂ ምክንያት አይደለም ችግር ሲበዛ መፍትሄውም ከውስጡ ይፈለፈላል። ለመሻሻል ምንጩ ችግር እርካታ ማጣት ነው:

“እኛ ግን ብዙ አጥተን ብዙ ነገር ካላቸው በላይ ቆመን
እናናውዛለን። ብቸኛ ሆነን አጠገባችን ያሉትን እናኮርፋለን እንኮንናለን
ከመሃከላችን ለመውጣትና እኛኑ ለመሳብ
የሚንቀሳቀሰውን ሞራል እየስጠን ከማደፋፈር ይልቅ ተጋግዘን በጠረባ እንዘርረዋለን። የኛ ደስታ የሚታየው በወደቀው ስንስቅ ነው ሌሎቹ ደግሞ በእኛ በወደቅነው ይሳለቁብናል።

“ሰው ሆነን ተፈጥረን ሰው ሆነን ከመከበር ራሳችንን
አራቅን ያለንን አናውቅም! ሌላው ቀርቶ ባለንም አኮራም፡ ከዚያ ይልቅ በተውሶ አልባሳትና ቅራቅንቦ የማስመሰል ተውኔት በባለቤቶቹና በእኛው ህዝብ ፊት እንሰራለን፡ ሁለቱም ግን ረክተው አያጨበጭቡልንም! ከሁለት ያጣ ጎመን' ነን…”
ሶራ በከሎ ሃሳብ መመሰጡና መስማማቱ በሚተናነቀው እልህ ያስታውቃል።

“ሳይጠባበቁ ለስራ መነሳት አስፈላጊ ነው" ብሎ ሶራ ትንሽ አሰብ አደረገና፡-

“ይህችን ሃገር ግን አቅጣጫዋ ወዴት ይሆን የሚለውን ለመመለስ ይከብዳል፤ ወደ ተፈጥሯዊ ሕይወት ወይንስ ወደ ዘመናዊ ኑሮን ሔ? ይህ ሃሳብ በህዝቡ ሲመለስ ህዝቡ ያሰበው ጋ ለመድረስ
መጣጣር ይጀምራል፡ አሁን ግን ያለው ነገር ዝብርቅርቁ የወጣ ነው እስኪ አስበው ጉዟችን እውነት ወዴት ነው? አለና ሃሳቡን ገቶ ከሎን አየው: ሁለቱም ጆሮ ላይ የሚያላዝን ውሻ ጩኸት
የመሰለ ኦምቧረቀ።

“ግን አንድ እውነት አለ፡ አንድ ወቅት የቀደምናቸው
አገሮች አሁን ጥለውን ተፈትልከዋል። እነሱ  ዘንድ ለመድረስ ቀጥሎም ለማለፍ በእልህ የታገዘ ጥረት ያስፈልጋል! ከኋላችን
ተነስተው አሁን ከፊት የሚገኙት ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑን ይገባል::
መላና ዘዴ ሳንቀይስ፤ የምንነሳበትንና የምንደርስበትን... ሳናውቅ ግን በለመድናት ጠባብ ጎዳና እንጓዝ ካልን አንዱ መሄጃችን ላይ ገብቶ
ሲሰነቀር ሌላው እንደተለመደው ቆሞ ይቀራል። ለዚህ ሁሉ ግን
ከየት እንጀምር?'' አለ ሶራ ጥያቄ እያቀረበ መልሱን ራሱ ለመመለስ።

“ከራሳችን ከራሳችን መጀመር አለብን" በስሜት ያቀረበው ሃሳብ እንደ ጦር ጎኑን ወጋው። ባዶ ምኞት ወይንስ በተግባር የሚውል ህልም... ፍቅሯ ልቡን እንደ ክትፎ የበላበት ኮንችትስ?
ከሎና ሶራ አንዱ ሌላውን ይበልጥ ለማወቅ፤ ተረዳድተው የአገራቸው አለኝታ ለመሆን ህሊናቸው ቋምጧል: የውጪ ዓለም
ልምዳቸው በራስ መተማመናቸውን ብትንትኑን ቢያወጣቸውም ማንነታቸውን ግን እንደ መስታዋት ቁልጭ አድርጎ አሳይቷቸዋል።
በዚህ የአድቬንቼር ዘመን በትርኪ ምርኪው የግደለሽነት ሕይወት መኖር እንደ አበቅ አንጓሉ አንጓሉ የሐፍረት ቆሻሻ ላይ
እንደሚጥል ተረድተዋል ከሌላው መማር እንጂ እንደ ተውሳክ ጥገኛ መሆን አይንን ጨፍኖ መለመን... በቁም ከመሞት በሞራል
ከመላሸቅ በቀር የሚያመጣው ህሊናዊ ጥጋብ አለመኖሩን ከሕይወት ገጠመኞቻቸው አንፃር አንስተው ብዙ ጊዜ ተጨዋውተዋል::

በህዳሩ የመኸር ወቅት ጨረቃ እንደ ቡሄ ዳቦ ክብ ሆና ገና የብርሃን ወጋገኗን በኒያንጋቶም ተራሮች ወደ ኩዩጉ መንደር ወደ
ኩችሩ ስትፈነጥቅ ከሎና ሶራ እንደተለመደው ሃሳብ ሲለዋወጡ እንደ ቆዩ በመካከላቸው ዝምታ ሰፈነና በእዝነ ሊናቸው ሰማዩ ላይ ጎላ ብሎ የተፃፈ ነገር ተመለከቱ ያን ፅሑፍ ሁለቱም ቀና ብለው አዩት።

“የህይወት ጀልባ ከማዕበል ጋር እየታገለች በውቅያኖሶች ጉያ
አካሏን ነክራ ትንሳፈፋለች ሞት ችግር መከራ ... ያደፍቋታል፤ ደስታ እርካታ ፍቅር. እንደ እንዝርት እያሾሩ ይፈትሏታል እና ጀልባዋ በሁለቱ እጣ ፈንታ ሚዛኗን ጠብቃı የተኙትን የሚስሩት
እየረጋገጧቸው ትሰሩለች:

“በእርገጥ የጎደለው ይተካል ያጣው ያገኛል! ያፈቀረ ይጠላል! የተለጣለ ያነሳል፤የሄደ ይመጣል... በተቃራኒዎች የተወጠረችው ጀልባ የሚፈራረቁባትን ችላ ትጓዛለች።

“አቅጣጫዋ መነሻ መድረሻዋ አይታወቅም:: ጀልባዋ አልቆላታል ትባል እንጂ ከጉዞዋ ከቶ ተገታ አታውቅም: አንድ ቀን
ግን ሥቃይና ሰቆቃ፤ እብሪትና ግፍ የበዛባት ጀልባ ብልሽት
ይገጥማት ይሆናል ያኔ ተሳፋሪዎችዋን ይዛ ትዘቅጣለች  ቁልቁል!
“እሪታ ሰማዩን ያቀልጠዋል የቀስተ ዳመና ቀለሞች በሺ
ተባዝተው ሰማዩን ያስውቡታል ከዋክብት ከነበሩበት በታች ዝቅ
ብለው ብርሃናቸውን ያንተገትጋሉ ገነትና መንግሥተ ሰማያት
ይጣመራሉ።

“ሟቹ ያን ውብ ሰማይ ርቆት ሲሄድ እማይጠገብ
ይሆንበታል! ጀልባዋ ስትዘቅጥ ተስፋ የቆረጠ ያለቅሳል... ሰሚና
ጯሂ እንዲሆ በአንድ ጀልባ ሆነው ዋይ ዋይ' ሲሉ ስቃይ እንደ ቅርጫት ላያቸው ላይ ሲከደንባቸው ይወርዳል።

“በዚያ ሰዓት ቅድስት ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ ሰማይ ትዘረጋለች አምላኳም ድምጿን ሰምቶ ህዝቧን ስለ ስንፍናው አምርሮ ይገስፀዋል።

“እጆቻችሁ ስለምን ሽባ ሆኑ! ስለምንስ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅን መረጣችሁ... ሆድ ብቻ. ጥቅምን ማነፍነፍ ብቻ... ብሎ አዝኖ ውቅያኖሱን ሜዳ ያደርገዋል ድህነትም በምድር ይወርዳል….ልብ ያለው ልብ ይበል" ይላል ሶራና ከሎ አይናቸውን ጨፍነው ያነበቡት።

በጥቁር የሰማይ ሰሌዳ የተፃፈውን ታምር 'ሁለቱም
እየደጋገሙ አነበቡት:
እንግዳው አጋጣሚ
አስገረማቸው አስፈራቸው ... ያ አጉራሽ የለመደው ህሊናቸው ግን ትርጉሙን በጊዜው ሊያቀርብላቸው አልቻለም።

“የምን ጽሑፍ ነው?... ማንስ ፃፈው?...በየግል የፍች "ቀመሩን ለማግኘት ዳንኪራ ረጋጭ ህሊናቸውን አስጨፈሩት። አንዱ
ለሌላው ያየውን ሚስጥር ግን አላወጣም።

ችግርን ለመናድ ማነስ የሚያመጣውን የአዕምሮ ሰንካላነት ለማስቀረት በራስ የመተማመንን ተፈጥሯዊ ፀጋ ጠብቆ ልጅ የልጅ
ልጆችን ከሃፍረት ለማዳን ሆዳምነትን አስወግዶ በእጅና አዕምሮ መጠቀም... ጀልባዋ ሳትሰጥም ደካማ ጎንን ማስተካከል እንደሚገባ
ዘግይተውም ቢሆን የተረዱ ይመስላል።

በዚያች ሰዓት ከሎና ሶራ ተያዩ! ኤርቦሬና ሐመሩ
ሁለቱ አፍሪካውያን ሊግባቡ
ሞከሩ! ሃይላቸውን ለማስተባበር ተቃቀፉደ
ፍቅራቸው ስህተታቸው ቁጭታቸው... ያስፈነደቃት ጨረቃም አላማቸውን ለማጠንhር ብርሃኗን እያሰፋች ፍጥነቷን በመጨር ጥቁሩን ሰማይ እየገለጠች ወደ እነሱ ገሠገሠች።

ከዚያ ያ ኩሩው ድፍርሱ ሚሊዮን ነፍሳትን በውስጡ
አጭቆ ቁልቁል ይሁን ሽቅብ መፍሰሱ ሳይታወቅ በፀጥታ የሚጓዘው ኦሞ ወንዝ በቁጭት አፍ አውጥቶ ሲናገር! እንደ ውሻ ሲጮህ ተሰማ።

"ኢትዮጵያ ፈላስፎቿን ተመራማሪዎቿን የንብ ተምሳሌት ታታሪ ምሁሮቿን, ማቀፍ እርስ በርሳቸው በጡንቻ ሳይሆን
👍18👏1🤔1
በአዕምሮ በምላስ ሳይሆን በሥራ ማታገል አለባት፡ዠ ሥራ ባህሉ የሆነው ህዝብ የሚመክረው የሚመራው ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ
ልማትን ለማምጣት መቻቻል ያስፈልጋል፡ ከዚያ ይህች የጥቁር ምድር የልጆችዋን አዕምሮ ተመርኩዛ ሽቅብ ከፍ ትላለች፤ የመርፌ ማምረቻዎች
ይመሰረታሉ….. ያኔ ሁላችንም ከሃፍረት
ነፃ እንሆናለን... እንደ ፋሲካ ሙክት አህጉራችንን ሊያርዷት የሚያደልቧትን እንነቃባቸዋለን.. ስንፍና መናቆር ይብቃን! ኦሞ እንደ ማርቲን ሉተርኪንግ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ! ተራሮች እንደ ተቆጣ አንበሳ አገሱ፧ ምድሪቱ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፤ ማንዴላ! ያ የአፍሪካ የበኩር ልጅ የማሳረጊያውን ድምፅ ጮክ ብሎ አሰማ፡

“...ቂም በቀል በእኛ ዘመን ይቁም፤ አምላክ አፍሪካን
ይባርክ! አለ። አፍሪካም የአትላንቲክ የህንድ ውቅያኖሶች ፤የሜዲትራንያን ባህር. ማዕበል እያደፈቃት የአንድዬ ልጅዋን ድምፅ
እንደ ገደል ማሚቶ ከጫፍ ጫፍ አስተጋባችለት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የኩችሩ መንደር የጨረቃ ዳንስ ደርቷል። ጭብጨባው ዝማሬው. ሽቅብ እየጎነ ከሰማይ ይጋጫል! ከተራሮች ደረት ጋር ይላተማል፤ በየሰዉ የደም ስር ይስለከለካል ... በድሪያ የጣፈጠው
የምሽት ዳንስ የተፈጥሮ ህይወት ኗሪ ወጣቶችን ያስፈነድቃል።

ፈገግታ ዝማሬ ድሪያ እንደ
ሰነፍ ቆሎ ታሽተው
የሚያወጡትን
የፍቅር ፍሬ ወጣቶቹ ይቅማሉ፤ ልጃገረዶች
ጎረምሶች ያን የማይጠገብ ማዕድ ከበው እየበሉ ያበላሉ እየሰጡ
ይወስዳሉ እየነኩ ይነካሉ… እያረኩ ይረካሉ። በዚህ መሃል ካርለት ጀግናዋን ፈለገችው ! ደልቲስ?' ጠየቀች ራሷን። የት ሄዶ ይሆን?' ስለ ሐመሩ
ቀብራራ አሰበች: ዝምታው ናፈቃት፤ ዝምታው ውስጥ ያለውን ወንድነት ፍቅር ናፍቆት በሰመመን አመነዥከችው:: የደልቲ ዝምታ ፍላጎቱን የሚያሳይ መስታዋት ነው። እርጋታው ሽፋን ነው ውጫዊ ቆዳ፤ ውስጡ ግን በያቅጣጫው እየፈለቀ የሚንዶሉዶል
የፍቅር ስሜት አለ የሚሞቅ የሚስብ ሲገጭ እያመመ ደስታን የሚፈጥር አካልን ዘረጋግቶ ሲወጥር የሚያረካ….

ካርለት ከዳንሱ ቦታ ራቅ ብላ ጀግናዋን በአይኖቿ
ስትፈልገው በጆሮዋ ስልምልም የሚያደርግ የሙዚቃ ቃና ሰማች።
እንግዳ ነው ያ ሙዚቃ ለጆሮዋ! ሳባት ሙዚቃው
ተጎተተችለት: ቃናው ጆሮዋን እየላሳት ወደ ውስጧ ዘለቀ የህሊናዋን ጓዳ! የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው። አሻት፤ ዳሰሳት…..እሷም
አንኳኳ የሆሊናዋን ጓዳ የስርቆሽ በሯን ከፍታ አስገባችው አሻት፤ ዳሰሳት
ሁለመናዋን ነካካው
አንሸራተታት ደመቅ
ደመቅመቅ... የሚለው ዜማ ፍል ውኃ ውስጥ እንደገባች ሁሉ ቁልቁል እየፈሰሰ ሰውነቷን አጋላት ደስ አላት ሰውነቷ ሲግል‥. ጡቶችዋ ግን ተቆጥተው ቆሙ፤ ዳሌዋ አኩሩፎ አበጠ ፤ ጭኗ አዝኖ ለሰለሰ… ሙዚቃና ልብ ወለድ ጽሑፍ ካለ እሳት ሰውነቷን ሲያጋግሉት ደስ ይላታል... የረሳችው ስሜት
ፈረሰኛው አረፋ እንደሚያስደፍቀው ወራጅ ወንዝ ሞተሯን አሽከረከረው፤ አቃሰተች ያኔም ስርቅርቁ ዜማ በጆሮዋ መግባቱን
አላቆመም

እየቀረበች ስትሄድ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ወይሳውን እየነፋ ጥዑም ዜማ የሚያወጣውን ጀግና አየችው። የሙዚቃው
ቅላፄ እንደ “ቤቶሆቨን ሞዛርት ሲንፎኒ" ቃናው እየቆዬ ጣማት።እሰይ እሱ ነው ብላ አጉተመተመች...

💫ይቀጥላል💫
👍242