ኮንችት በሃሳብ የስጠመውን ሶራን እጅዋን ዘርግታ እንዲነሳ ጠየቀችው:: ፈገግ ብላም የበሰበሰውንና ከገላው የተጣበቀውን ልብሱን በየተራ አወለቀችለት። ከዚያ እንደ ህፃን ልጅ ፎጣ አልብሳ እየመራች ወሰደችው: “ጢዝዝ…" ድንኳኑ ከፈተች። “…ጢዝዝ'
እንደገና ተዘጋች ትንሽዋ ድንኳን!
አንድ ስልፒንግ ባግ አብረው ለበሱ! ገላቸው ተነካ ራቁቷን እሱም ራቁቱን ነው... አካላቸው ተሻሸ... ስሜታቸው ተፋጨ... ሙቀት ፈጠሩ.. ያን የብርድ ጊዜ ሙቀት ተካፈሉት…
ከዚያ ትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ የሚያደርግ ሙቀት በዚያ ላይ ትግል ጀመሩ... የነዲድ ስሜት እሳት ጢስ ድንኳኗን አፈናት.. በአካባቢው
ያሉት እፅዋትና አራዊት እሳት ሊሞቁ እሳት ሊጭሩ ተጠጉ... ከትንሽዋ ድንኳን!
💫ይቀጥላል💫

👍26❤6
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ሁለት)
(ሜሪ ፈለቀ)
ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ ለደቂቃዎች ቆየሁ። ምን ያህሉን እንዳስታወስኩ ባላውቅም ደጁን እያየሁት ምስሎቹ ጭንቅላቴ ውስጥ ቅርፅ እየሰሩ ተደረደሩ። ከቤት ተንደርድሬ ስወጣ በዛ ያሉ መሳሪያ የታጠቁ ወንዶች በድል አድራጊነት እየተወጣጠሩ ጊቢያችንን አልፈው እየወጡ፣ የመጨረሻው ሰውዬ አባቴ በወደቀበት ተራምዶት ሲያልፍ ፣ ዘልዬ አጠገቡ ስደርስ የቱጋ እንደተመታ እንኳን እንዳይለይ ሆኖ ልብሱ በደም ርሶ በእጁ የያዛትን የሲጋራ መለኮሻ መጨበጥ አቅቶት እጁ ሲዝል፣ እሪሪሪ ብዬ ስጮህ እንኳን መንደርተኛው ባለመሳሪያዎቹን ፈርቶ ስለተሸሸገ ብቅ ያለልኝ ጠፍቶ ባለመሳሪያዎቹ ተመልሰው ቢደፉኝ እንኳን ግድ ሳይለኝ ድምፄ እስኪዛጋ ስጮህ እና ስሳደብ ……… የጎረቤታችን ቤት በእሳት ተያይዞ እየነደደ የእነርሱ ጩኸት ከእኔ ቢብስም ሊረዳቸው ብቅ ያለ አልነበረም። እናቴ እግሯንም ቅስሟንም እየጎተተች ከቤት ውስጥ ብቅ ስትል አባቴ ነፍሱ ወጥታ ነበር። አላለቀሰችኝም። አጠገቡ መሬቱ ላይ ቁጭ ብላ በደም የራሰ ደረቱ ላይ ተኛች። ጩኸቴን አቁሜ አየኋት። አታወራም ፣ አታለቅስም፣ ምንም ስሜት አይታይባትም። ከአባቴ ፊት ይልቅ የሞተ የሚመስለው የእርሷ ፊት ነበር። ብርግግ ብዬ ተነስቼ ወደ ቤት ውስጥ ሮጥኩ።
በቃ እዚህ ድረስ ብቻ ነበር ለጊዜው የታየኝ። ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ሀረግ ወደወረረው ቤት ውስጥ ገባሁ። ደጁ ላይ የበቀሉት አረሞች እሾህ ያላቸው ስለነበሩበት ልብሴን እየያዘኝ ነበር ያለፍኩት። ጎንጥ አንዴ ፊት ፊቴን አንዴ መንገድ መንገዱን እያየ በዝምታ ይከተለኛል። ቤቱ ውስጥ ሳሎን አሮጌ አግዳሚ ወንበር እና የተበታተኑ ቆሻሻዎች አሉ። እንደገመትኩት አንዳንዱ ሰፈርተኛ ቆሻሻውን እያመጣ እዚህ ይጥላል። በቆሻሻ እና በዓይነምድር የሞሉትን ክፍሎች እየዞርኩ ግማቱ እንኳን አልታወቀኝም። ያ ቤት ያደግኩበት ልጅነቴ መሆን አለበት። ነገር ግን አንድም ከልጅነቴ ጋር የተያያዘ ትውስታ አልመጣልኝም። የዛን ቀን የሆነው ግን አንድ በአንድ የአሁን ያህል ሰውነቴን እስኪወረኝ ታወሰኝ። ጭንቅላቴ የፈለገውን መርጦ አንዲት ክስተት ብቻ አስታውሶ ነው ወይስ ቦታው ላይ ስገኝ ሌሎቹንም ትውስታዎቼን አገኛቸዋለሁ? አልገባኝም! ከሆነም ለምን ልጅነቴን አላስታወስኩም?
ዶክተር እንዳለኝ አስፈሪ ገጠመኞቼን ከደበቀበት እያወጣ ሊሆን ይችላል ……. ጭንቅላቴ ራሱ ክፋቱ እንጂ ወይ ሙሉውን ባያስታውሰኝ አልያም እናቴ አውርታ የማትጠግበውን ደጉንም ልጅነቴን ቢያስታውሰኝ ምን ነበረበት?
የዛን ቀን ከሆነው ውስጥ ያላስታወስኩት ይኑር አይኑር የማረጋግጥበት ምንም ማመሳከሪያ የለኝም። ያስታወስኳቸው ምስሎች ግን የጎደለ የሚመስል ትዕይንት የላቸውም።
አባቴ እና እናቴ ሲጨቃጨቁ ሌላኛው ክፍል ከኪዳን ጋር ሆነን እንሰማቸዋለን። እናቴ አባቴ ላይ ትጮሃለች።
«እኔ የምልህን አንዴ ሰምተኸኝ ቢሆን ይሄ ሁሉ አይመጣም!! ያንተ ፉከራ ዛሬ ከምን እንደሚያድንህ እናያለን! እሺ ልጆቼን ምኔ ውስጥ ልደብቃቸው? ሄዳችሁ ባትተነኩሷቸው ዛሬ አሳቻ ሰዓት ጠብቀው መንደራችንን ባልወረሯት ፤ እሺ አሁን ምንድነው የምሆነው?» በበሩ አጮልቄ አያቸዋለሁ። እሷ ወገቧን ይዛ እየተንጎራደደች ነው። እሱ ትልቅዬ መሳሪያ ወደበሩ አነጣጥሮ መንደራችንን ወረሯት የተባሉትን ሰዎች በሩን አልፈው ቢገቡ ሊቀልባቸው ይመስል ይጠብቃል። እናቴ አታቆምም።
«እናንተ የእነሱን መንደር ሄዳችሁ አቃጥላችሁ <ጉሮ ወሸባዬ> እያላችሁ ስትመለሱ እጃቸውን አጣጥፈው የሚቀመጡ ነበር የመሰላችሁ?»
«አንቺ ብዙ የማይገባሽ ነገር አለ አስካል! የአያት የቅድመአያቴን መሬት ካልፈነጨሁበት ሲሉ እኔስ ኑና በላዬ ዘብጡ ብዬ ዘንባባ አንጥፌ እንድቀበላቸው ነው ምኞትሽ?» እየጮኸ ነው እሱም የሚመልስላት። ከውጪ የብዙ ወንዶች ዘፈን ይሁን ፉከራ ያልለየለት ድምፅ እየቀረበ እየቀረበ ይሰማል። በመሃል የሚያወሩት በትክክል ባይሰማም ጮክ ያሉ ድምፆች ትእዛዝ ሲያስተላልፉ ይሰማል። ደግሞ ያጨበጭባሉ። ደግሞ አንዴ ሆ ብለው የደስታ ጩኸት ይጮሃሉ። እናቴ እሮጣ መጥታ ከሽቦ አልጋው ስር እንድንገባ ታደርገናለች።
«ምንም ቢፈጠር እንዳትወጡ! ምንም ብትፈሩ ድምፅ እንዳታሰሙ!» እያለችን መሬቱ ላይ በደረቷ ተደፍታ እያየችን እጇ ይንቀጠቀጣል። ኪዳን ማልቀስ ጀምሯል። ጆሮዎቹን በእጄ ደፍኜ ይዤለት እሹሩሩ እንደማለት እየወዘወዝኩት ወደራሴ አጣብቄ ያዝኩት። ከውጪ የሚሰማው ሁከት መስኮታችን ጋር ደረሰ። እናቴ የመላእክትን ሁሉ ስም በሹክሹክታ እየጠራች ትፀልያለች። አባቴ እኛ ወዳለንበት ብቅ ብሎ
«አንቺም ከእነርሱ ጋር ተሸሸጊ! እነርሱ የሚፈልጉት እኔን ነው!» አላት በትእዛዝ
«ያንተ ሚስትኮ ነኝ አይምሩኝም! እኔን ሲፈልጉ ልጆቼን ካገኟቸው ይገድሉብኛል። እኔን ካገኙኝ ግን ልጆቼን አይፈልጓቸውም በፍፁም አልሸሸግም! የመጣ ይምጣ!» አለች እንጂ ሰውነቷ እየራደ ነው። ላቤ ከጀርባዬ ወደቂጤ ሲወርድ ይሰማኛል። የልቤ ትርታ ሁከተኞቹ ድረስ የሚሰማ ነው የሚመስለው። ብዙም አልቆየም! ድብልቅልቅ ያለ ጩኸት ፣ የበሩ መገንጠል፣ ተኩስ ድብልቅልቁ ወጣ። ሽንቴን እላዬ ላይ ለቅቄ እንዲያ ሰውነቴ የእኔ እስከማይመስለኝ በድኖብኝ ኪዳንን አልለቀቅኩትም። ድንጋጤው በዝቶበት ነው መሰለኝ ትንፋሽ እንደሌለው ሰው ዝም አለ። እናቴ ከአልጋው አጠገብ ተነስታለች ግን አትታየኝም። ፍርሃቴ ሽባ ስላደረገኝ የመነቃነቅም ድፍረቱ አልነበረኝም። ሳሎኑ ውስጥ የተፈጠረው ምን እንደሆነ ባላውቅም ድብልቅልቁ የወጣ ትዕይንት እንደሆነ ከድምፆቹ ያስታውቃል። ከሳሎን ድምፁ እየቀለለ የተወሰኑ ሰዎች ድምፅ ብቻ መሰማት ሲጀምር የእናቴ እሪታ ተከተለ። ነፍስ ከስጋዬ የተላቀቀች መሰለኝ። የሞት ሞቴን ለማየት ስሞክር መኝታ ቤቱ ውስጥ ማንም የለም።
«ሚስትና መሬቴን አለ ይሄ እንከፍ?» የሚል ድምፅ ለመኝታ ቤቱ ቀርቦ ተሰማኝ። ቁጥራቸውን መገመት የሚቸግረኝ ሌሎች ሳቅ ተከተለ። እናቴ ትለምናቸዋለች። የምትለምንበት ድምፅ ሆዴን ረበሸው። መሸነፍ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ረዳት ማጣት…….. ሆድ የሚደበላልቅ ልመና ነው። የእናቴ ልመና ፍርሃቴን አስዋጠኝ። ምን ሊፈጠር እንደሚችል የማስብበት የብስለት ልክም አልነበረኝም ይሆናል። ኪዳንን ከአልጋው ስር ወደየትም ንቅንቅ እንዳይል አስጠንቅቄው በቀስታ እየተንፏቀቅኩ ገርበብ ያለው የመኝታ ቤት በርጋ ደረስኩ። እግሬ የቆመበት ተተክሎ ቀረ። ልሳኔም የተቆለፈ መሰለኝ። ከእናቴ ጋር ተያየን። መሬቱ ላይ በጀርባዋ ወድቃ የለበሰችው ሻማ ቀሚስ እስከደረቷ ተገልቦ አንደኛው ካኪ የለበሰ ሰውዬ በማሸነፍ ስሜት ቀበቶው ተፈትቶ ወደታች ዝቅ ባለ ሱሪው ቂጡ እየታየ እላይዋ ላይ ይፈነጫል። ሌላኛው ደግሞ የመሳሪያውን አፍ ወደ እርሷ አዙሮ ነውር እያየ ሳይሆን ትክክል ነገር ዓይኑ ስር እየሆነ ይመስል እየገለፈጠ ያያቸዋል። ፊታቸው ከእኔ በተቃራኒ አቅጣጫ ስለሆነ አያዩኝም። ሌላ ማንም የለም ሳሎኑ ውስጥ። አባቴ የት ሄዶ ነው እሷ የሚደርስላት አጥታ የተዋረደችው? አትታገልም! አትንቀሳቀስም! አፉ ብቻ ነበር የሚለምነው። እኔን ስታይ እሱንም ተወችው። በሚያሳዝን አስተያየት አየችኝ። ልመና ያለበት አስተያየት። እንዳያት አልፈለገችም! ልመናዋ ዞር እንድልላት ነው። ይሄኔ ኪዳን ከየት መጣ ሳልለው አጠገቤ ደረሰ። እየሆነ ያለውን እንዳያይ አይኑን ከደንኩት። ይሄኔ ሌላ አንድ ሰው ከውጪ ገባ። ቀና ቢል ስለሚያየኝ ኪዳንን ይዤ በበሩ ተከልዬ ማጮለቅ ቀጠልኩ። ሰውየው ሲገባ

👍26
እናቴ ያቆመችውን ልመና በለቅሶ ታጅባ ቀጠለች። የሰማት አይመስልም። ቢሰማትም ግድ አልሰጠውም። ይልቅ እንደመቆጣት እያለ
« ስንት ነገር እያለብን አንተ እዚህ ወገብህን ታላቅቃለህ? ተነስ ወደዚያ!» ብሎ አምባረቀ። አለቃቸው ነገር ይመስላል።
መሳሪያውን ይዞ የቆመው ሰውዬ «መሬቱን ወስደንበታል። ሚስቱንም እንቅመስለት ብለንኮ ነው!» ብሎ አስቀያሚ ሳቅ እየሳቀ ከእናቴ ላይ መነሳት ሲጀምር ሰውየውን በልቤ አመስግኜ ሳልጨርስ እሱም የአጋንንት ሳቅ የመሰለ ቃጭል ማስካካት አስካክቶ
«እንዲያ ነው …..» ብሎ ሱሪውን መፍታት ሲጀምር ከእኔ የሚበልጥ እልህ እና መጠቃት ሰውነቴ ውስጥ ነደደ። ወዲያው ከውጪ የሆነ ሰው ተጣራ
«ሙሉሰው? ሙሉሰው?» ይሄኔ ሊፈታ የጀመረውን ሱሪ ወደቦታው እየመለሰ በተሸከመው መሳሪያ እነርሱም እንዲወጡ ምልክት አሳይቷቸው ወጣ። መሳሪያ ይዞ በመቆም ሲያጅብ የነበረው ሰውዬ ወዲያው ተከተለው። እናቴ ላይ ሆኖ ሲያሰቃያት የነበረው ግን ቆሞ አዘቅዝቆ እያያት በፀያፍ ንግግር ይዘልፋት ጀመር። እያየኋት እንደሆነ አውቃለች። ፊቷን ወደበሩ አዙራ በስቃይ ታያለች። ከየት በመጣ ጉልበቴ እንደሆነ አላውቅም ኪዳንን ሽክም አድርጌ አልጋው ላይ ወሰድኩት እና በጩኸት እኔ እስክመለስ ንቅንቅ እንዳይል አስጠነቀቅኩት። እየተንሰቀሰቀ በጭንቅላቱ እሺ አለኝ። አልጋው አጠገብ የተቀመጠውን ሳጥን ከፍቼ ከሳጥን ውስጥ አነስ ያለች ቦርሳ አነሳሁ። ጠባብ ዚፕ ኪሱ ውስጥ ያለ ቁልፍ ወስጄ አልጋው እራስጌጋ ያለውን መሳቢያ ከፈትኩ። ከፍቼው ውስጡ ያለውን ሽጉጥ ሳየው ተርበተበትኩ። በሚንቀጠቀጥ እጄ ወጥተው ተበትነው የተቀመጡ ቀለሃዎቹን ሰካክቼ ወደሳሎን ሄድኩ። አንስቼ ሊወጣ የነበረው ሰውዬ ላይ ቀስሬ ስጠጋ እናቴ ከመሬት ብድግ አለች። አልተኮስኩም። ልተኩስ የነበረ ይመስለኛል ግን እጄ እየተንቀጠቀ ያቃተኝ። ሰውየው መርበትበቴን እና ህፃንነቴን አይቶ መሰለኝ ምንም ሳይመስለው በንቀት ወደእኔ ሲመጣ እናቴ ከለለችኝ። ግንድ በሚያክል እጁ ሲገፈትራት ተንገዳግዳ ወደቀች። እጄ መንቀጥቀጡን አቁሞልኝ ልስብ ስል የወደቀችው እናቴ ከየት እንዳገኘችው ያላየሁትን የቡና ዘነዘና አንስታ ጭንቅላቱን ከኋላ መታችው። ሰውየው ተገንድሶ ደሙ እየተንዠቀዠቀ እሱን ዘወር ብላ ሳታይ ዘላ የያዝኩትን ሽጉጥ እየቀማችኝ።
«ለእድሜ ልክ የሚበቃሽን ክፋት አይተሻል። ደግሞ ነፍስ አጥፍተሽ ስትቃዢ ልትኖሪ?» ያለችው ለእራሷ እንጂ ለእኔ አይመስልም። የተቀበለችኝን ሽጉጥ ይዛ የተገነደሰው ሰውዬ አጠገብ ዘፍ አለች። ደንዝዛ በድኗ እየተንቀሳቀሰ ነው የሚመስለው። ሰውየው ደሙ መስመር እየሰራ ወደበሩ ይፈሳል። አይንቀሳቀስም። እሮጬ ወደ ውጪ የወጣሁት አባቴን ፍለጋ መሰለኝ። መሬቱ ላይ ተዘርሮ ያገኘሁት።
እናቴን የአባቴ ሬሳ ላይ ትቻት የፈረጠጥኩት <እንዳትንቀሳቀስ> ያልኩት ኪዳን ፈርቶ ወደሳሎን ቢመጣ የወደቀውን ሰውዬ አይቶ ይደነግጣል ብዬ ነው። ካስቀመጥኩት ቦታ አልተነሳም። የሄድኩት እሱን ልጠብቀው ነበር። አልጋው ላይ አስጨንቄ አቅፌው ስወዘወዝ ምን ያህል ደቂቃዎች እንዳለፉ አላውቅም። ብቻ ወተት እንደሚንጥ ሰው ከፊት ወደኋላ ስናጥ የእናቴ ወንድም እያለቀሰ ገብቶ ኪዳንን ከጀርባ እኔን ከፊት አፋፍሶ ተሸክሞን ወጣ ……… እዚህ ድረስ ያለው ምስል ምንም ብዥ ሳይል ነው ያስታወስኩት የሚቀጥለው ግን ብዥታ አለው አጎቴ እንደተሸከመን «ወየው ወንድሜን!» እያለ ድምፅ አውጥቶ እያለቀሰ የሆነ መንገድ የሄድን ይመስለኛል። ላስታውሰው ስሞክር ይጠፋብኛል።
እዛው የመኝታ ቤት ውስጥ ቆሻሻ ተሞልቶ የተቀመጠ ማዳበሪያ ላይ ጭብጥ ብዬ ተቀምጫለሁ።
«እያስጨነቅሽኝ እኮ ነው። ምንድነው ያስታወስሽው? ሰውነትሽኮ ያንቺ አይደለም!» ይለኛል ጎንጥ። ከደቂቃዎች በኋላ እሩጫ እና እርምጃ እየደባለቅኩ እናቴጋ ደረስኩ እና ተጠመጠምኩባት። ገባት! እሪሪሪ ብላ ማልቀስ ጀመረች። ስላስታወስኩ «ምንአልኩህ አምላኬ? ለልጄ አዲስ ህይወት ሰጠህልኝ ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ?» እያለች አምላኳን መውቀስ ጀመረች። የሚሰማኝን ስሜት መለየት ከበደኝ። ከነበሩኝ ጥሩ ቀኖች ተለይቶ አስፈሪ ቅዠት የመሰለ የህይወቴን ክስተት ማስታወስ ሊያሳብደኝ አልነበር የሚገባው? ቁጣ፤ ንዴት፣ ጥላቻ ፣ ፍርሃት ፣ ሀዘን ……. አልነበር ሊሰማኝ የሚገባው? የሚሰማኝ የሆነ ቅዝቅዝ ያለ ፀጥተኛ ስሜት ነው።
«ከእናቶች ሁሉ በላይ እናት ነሽ!!» አልኳት እናቴን እንዳቀፍኳት ብዙ ከቆየሁ በኋላ። አመሻሽ ለእራት ስንሰበሰብ ማስታወስ የቻልኩት ያቺን ቀን ብቻ እንደሆነ ነገርኳቸው። የነገርኳቸው የሆነ አስደንጋጭ ነገር ይመስል ገበታውን የከበበው ሁሉ ረጭ አለ። አጎቴ ሊጎርስ የጠቀለለውን እንጀራ የመወርወር ያህል ትሪው ላይ ጣለው።
«መቼም ከዚህ የባሰ የስቃይ ቀን አለ አትሉኝማ? ምንድነው?» ብዬ ስጮህ
«እንደዛ አይደለም። ለሁላችንም ከባድ የጨለማ ቀን እሱ ነበር። እንደው …… » እያለ ፊደሎቹን አፉ ውስጥ ያውደለድላቸዋል። ከብዙ ንትርክ በኋላ የተፈጠረውን ነገሩኝ።
እንደዚያ ደም ያቃባቸው ፀብ ለዘመናት የከረመ የጎሳ ፀብ ነበር። ለዘመናት ያንተ ጎሳ ገላመጠኝ ፣ ያንተ ጎሳ ድንበሬን አልፎ ሽንቱን ሸና ዓይነት ገለባ ሰበብ እየመዘዙ ሲጣሉ ነበር የኖሩት። የአባቴ ዘመን ከፀቡ ሁሉ የከፋው ነበር። ፀቡ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደረገ። የእነዛ ወገን በቁጥር የምንበልጠው እኛ ብንሆንም ሰፊ ለም መሬት የያዙት እነዛ (የአባቴ ወገኖች) በመሆናቸው የመሬት ይገባኛል ነጠላ ጥያቄ ይዞ ነበር የተነሳው። ሲቀጥል ገበያውን የኛ ሰዎች ይቆጣጠሩት ፣ ሲቀጣጠል በማእከላዊ ደረጃ በአብላጫው ስልጣን ላይ ያሉት የአባቴ ወገኖች መሆናቸው ሌላ ዘመናዊ የመሰለ የፀብ ድፍድፍ ጋገረ። ፀቡ በከረረ ቁጥር ከላይ ወታደር ይመጣል። ለቀናት ጋብ ይላል። ደግሞ ተመልሶ ይጋጋላል። አባቴ ነው አሉ የእኛን ጎሳ የሚመራው። አጓጉል ጉልበት መለካካት። የእኔ እበልጣለሁ ፉክክሩ ጦዞ ከተማ እስከማቃጠል ዘለቀ። የመጨረሻው ፀባቸው አባቴ ህይወቱን የገበረበት ነው። ራሴን እስክፈራው ድረስ ሰውነቴ ውስጥ የሞቀ ደም እንዲሮጥ ያደረገው መጨረሻው ነው። የእነዛ ጎሳዎች ሽማግሌ ላኩ። ከዚህም ወገን ሽማግሌ ተቀመጠ። ታረቁ!!
የተበደልኩ ዓይነት ስሜት ተሰማኝ። እነርሱ ተጣሉ ከዛ ታረቁ። እኔስ በአስራ ሶስት ዓመቴ አባቴ ሲሞት እናቴ ስትደፈር ያየሁት እኔስ? እኔን ይቅርታ ጠይቀውኛል? እናቴስ? በአንድ ቀን ባሏንም ክብሯንም ያጣችው እናቴስ? ስትደፈር ያየቻትን ልጇን ዓይን እያዩ መኖር ስቃይ ሆኖባት መኖሪያዋን ጥላ የጠፋችው እናቴስ? በቃ! እነሱ እንደቀልድ ታረቁ? ማንም ላጠፋው ቅጣቱን ሳይቀበል ታረቁ! በሰላም ኖሩ! ተጋቡ! ተዋለዱ! የሚባለው የሰው ነፍስ እንዴት ሲናቅ ነው? እኔ እና የዛን ቀን የህይወት ሚዛናችንን የሳትን እኩዮቼስ? ንዴቴ ይንቀለቀል ጀመር። ከነቃሁ ጀምሮ ይሄን ስሜት አላውቀውም! እናቴ ትለምነኝ ጀመር። አጎቴ የፈራው ነገር የደረሰ ዓይነት ተሳቆ ሲያየኝ ቆይቶ ያኔም ልክ እነሱ ታረቁ ተብሎ በሰላም መኖር ሲጀምሩ እንዲህ መሆኔን እና ከዛ በኋላ ህፃንዋ ሜላት ድራሽዋ ጠፍቶ አስፈሪዋ ሜላት ማደግ መጀመሯን ነገረኝ።
....................
ይቀጥላል.........
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

👍33
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ሶስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
«አባቴም እንደእነሱ መጥፎ ሰው የነበረ ቢሆንስ? የሆነችን ልጅ አባት የገደለ ቢሆንስ? የሆነኛው ሰው ሚስት ስትደፈር ቆሞ አይቶ ቢሆንስ? መቼም ከተማቸውን በእሳት ሊለኩስ ሲሄድ <የእግዜር እንግዳ> ብለው አልተቀበሉትም! ተታኩሰዋል አይደል? በተኩሱ መሃል የገደላቸው ሰዎች እነሱም የሆነች ህፃን አባት ፣ የፀቡ ግብም አላማም ያልገባት የሆነች ምስኪን ሴት ባል ይሆናሉ።» አልኳት እናቴን ከቀናት ድንዝዝና እና ማሰላሰል በኋላ የሆነ ቀን። ከአሁን አሁን ትጎፈላለች ብሎ በዓነቁረኛ የሚከታተለኝ አጎቴ ዝግንን እያለው
«ውይ በስመአብ!!! እውነትም አባትሽን ዘንግተሽዋል። ምነው ልጄ? እሱ እንደው አንዳንዴ አጓጉል ጀብደኝነቱ ከልክ ያልፋል እንጂ እንዴት ያለ ለሰው አዛኝ እና ደግ ሰው መሰለሽ? አባትሽን መጥፎ ሰው? ኸረ ተይ መንደሬው እንዳይሰማሽ? የሀገሬው ሁሉ አጉራሽ አልባሽ ነበር።» አለኝ።
«ለወገኑ ነዋ! በመሰረቱ ሁለቱም ወገኖች ለየራሳቸው ወገን መከታ ለመሆን አይደል የሌላውን ወገን ሲያጠቁ የኖሩት። እነዛም ወገኖቻቸው የሚመሰክሩላቸው ደግ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናልኮ!! ምናልባትም <ማ? የእኔ አባት? እንኳን በሰው በዝንብ ላይ እጁን አያነሳም> የሚሉላቸው ልጆች ይኖሯቸው ይሆናል። ሁሉም ሰው በራሱ እስካልደረሰ በስተቀር ምክንያታዊ እና ልክ ነው። በራሱ ሲደርስ ነው ሚዛናዊነቱን የሚያጣው። ለምሳሌ የእኛዎቹ ተደፈርን ብለው ሲያስቡ ከተማቸው ድረስ ሄደው አጥቅተው ሲመለሱ፣ የሰራነው ልክ አይደለም ብለው ለአንዴ እንኳን ተፀጽተዋል? ምናልባትም ልክ አይደላችሁም ያለ አዋቂ ይኖር ይሆን? እስቲ ለትውልድ የሚሻገር ቁርሾ ከማኖራችን በፊት ሳንጫረስ መፍትሄ እንፈልግ ያለ ይኖር ይሆን? እነዛ ተመሳሳዩን ሲያደርጉ ህመማችንን የምናየው ከእኛ ወገን ስለሆነ አውሬነታቸው እና እንስሳነታቸው ነው የታየን። » አልኩኝ። እናቴ ፈገግ አለች።
«ምነው?» አልኳት
«ኸረ ምንም አለች!» አሁንም ድካም በተጫነው ፊቷ ላይ ፈገግታ እየነገሰ።
«እንዴ አስካል እንዲህማ ፊት አትስጫት!! የአባቷንም ነፍስ መና ማድረግ ነው። ሰው ነውና ምኑንም ያህል ጥፋት ባይጠፋው፣ ህይወቱን ጭምር የገበረው ለዝህች መንደር ነው። ያ መረሳት የለበትም!!» አለ የእውነቱን እየተቆጣ!! ምናልባት ሰው የመሆን የአፈር ልውሳችን ውስጥ ያለ ነገር ይሆን? የእኛ ወገን ቢያጠፋም ( ወይም እናውቃለን አጥፍቷል) ቢሆንም የእኛ ወገን ስለሆነ ጥፋቱ እናኮስስለታለን። ከዛሳ? ከዛማ የእሱን ሀጢያት ደርምሰን የኛ ወገን ላልሆነ እንደርባለን። ከዛማ በንፅፅሮሽ የኛ ወገን ለመልዓክ የቀረበ ፃድቅ አድርገን እናርፈዋለን!! አጎቴ ሰሞኑን ከሚነግረኝ የመንደራችን ታሪክ በብዙ የተረዳሁት ያንን ነው።
«አዛኝቷን ነው የምልሽ እንዲህ ተልፈስፍሰሽስ ከማይ ከነማስጨነቅሽ የድሮዋ ሜላት ትምጣብኝ!!» ሲለኝ እናቴ በተሟጠጠ አቅሟ ልትነሳ ሁላ ቃጣት። «እረፍ ብያለሁ!» ብላ ጮኸች ፣ አጎቴ አፍንጫውን እየነፋ ወጣ!
ማለቂያ የሌለው የጥያቄ ጎርፍ ሳንፎለፉልለት ቆይቼ አጎቴ ከነገረኝ ገጣጥሜ የገባኝ እድገቴ እንዲህ ነው። ከዛን የመዓት ቀን በኋላ እናቴ የሆነችውን ለወንድሟ ነግራው አባቴ እንኳን ሳይቀበር እኛን ትታ ተሰደደች። አጎቴ ልጅም ሚስትም ያልነበረው ላጤ ስለነበር ምድር ዞሮበት እንደነበር ነገረኝ። አባቴንና በዛን ቀን በሞት ያጣናቸውን ወገኖቻችንን ቀብረን መንደሬው ማቁን እንደለበሰ ከረመ። ከዛን ቀን በኋላ ቀሚስ ጠላሁ። ስለብሳቸው ቀሚስ የሚያካክሉትን የአባቴን አላባሾች መልበስ ጀመርኩ። ቁጭ ብዬ የአባቴን ሱሪዎች ለእኔ እንዲሆኑ ቆርጬ እና ሰፍቼ መልበስ ጀመርኩ። አንድ እለት ለበዓል በጌጥ ያሸበረቀ ቀሚስ ገዝቶልኝ መጣ።
«እኔ ይሄን አልለብስም! ሴት መሆን አልፈልግም።» አልኩ። ምናልባት በሴትነት ውስጥ የእናቴን ስቃይ በወንድነት ውስጥ የአባቴን ጀግንነት ነድፌ ይሆናል እናቴን ከመሆን አባቴን ሆኜ ሞትን እንኳን ለመግጠም ራሴን መሞረድ የጀመርኩት። ሴት ሊያደርጉኝ የሚችሉ ድርጊቶችን ማጀትን ጀምሮ ሸሸሁ። አጎቴ ትምህርት ቤት ከኪዳን ጋር ቢልከንም ትምህርቴን አልቀጥልም ብዬ አሻፈረኝ አልኩ። ትኩረቴ ሁሉን ሁሉ ጉልበት እና ጡንቻ ማካበት ላይ አደረግኩ። ውሎዬ ከጎረምሳ ጋር ኳስ መራገጥ ፣ ጅራፍ ማጮህ ፣ እንደእኩዮቼ ወንዶች ጡንቻ መለካካት ፣ ከሰፈሩ ፈልፈላ ጋር ሜዳ ላይ ማን ስንት ፑሽ አፕ ይሰራል አፈሩን ስንልስ መዋል ፣ የሰፈሩን አህያና ውርንጭላ ሁላ መጋለብ ….. ሆነ። ይሄን ሲነግረኝ አጎቴ ፈገግ ብሎ
«በአዛኝቷ! እንደው ሞገደኛ ነበርሽኮ!! ቆሜ ካልሸናሁ ብለሽ ጉድ አፍልተሽ ነበርኮ!» ብሎ ክትክት ብሎ ሳቀ። ቆሞ እንደወንድ የመሽናት ሀሳቡ አብሬው እንድስቅ አደረገኝ።
በየቀኑ የምደባደበው ሰው ፈልጌ ተደባድቤ እገባለሁ። በምለብሰው የአባቴ ልብስ ሲስቁብኝ እጣላለሁ። ሁሌም አሽተው አሰባብጠው ይለቁኛል በነገታው አሁንም ነገር ፈልጌ እወቀጣለሁ። በተለይ ትልቁ ገበያ ስንሄድ ከጠላቶቻችን ወገን የሆነ ሰው ከገጠመኝ ፍፃሜዬ ደማምቶ መምጣት ቢሆንም ነገር ከመፈለግ አልቦዝንም። በዱላ ብዛት የትኛውም ድብደባ ቅም የማይለኝ ደነዝ ሆንኩ። ቁጥር አልባ ቡጢ እና ሽመል ከፈጀሁ በኋላ አንድ ቀን አሸንፌ መጣሁ። ውጤቱ ማሸነፍ ሆነ እንጂ አፍንጫ እና ጉንጬ እስኪደባለቅ ተወግሬ ነበር።
«በጭራሽ አልገባኝም ነበር። <እንደው ከዚህ ሁሉ ምናለ ድብድቡ ቢቀር? መቼም አንድ ቀን አንዱ አጉል ቡጢ የሰነዘረብሽ እንደው 32 ጥርስሽን በእጅሽ ይዘሻት መምጣትሽ ነው። እንደው ምን ባደርግሽ ይሻለኛል?> ስልሽ <ተደባድቤ ጉልበቴን ካልፈተንኩ እንደምችላቸው በምን አውቃለሁ? ድንገት ብንገጣጠም ሽመል ወይ ኮረት ፍለጋ ልዟዟር ነው?> ብለሽ መለሽልኝ። ለካንስ አጅሪት አባትሽ ከሞተ ቀን ጀምሮ የአባትሽን ገዳዮች እንዴት እንደምትበቀዪ ስታሰዪ ነው ውሎ አዳርሽ።» አለ በሰዓቱ ስላልተረዳኝ እየከፋው።
ወንድ የመሆን ትጋቴን መቼም እንደማላቆም ሲያውቅ ፣ በራሴ ልጅነት ውስጥ መኖሬን አቁሜ በአባት እና በእናቴ በደል ውስጥ እየዋኘሁ እንደሆነ ሲረዳ ለምኜው እንቢ ብሎኝ የነበረውን የሆነ ከከተማ የመጣ ልጅ የእድር ቤቱ አዳርሽ ውስጥ የሚያስተምርበት ካራቴ ቤት በ15 ዓመቴ አስመዘገበኝ። እንደዛ ቀን የተደሰትኩበትን ቀን አይቶ እንደማያውቅ ነገረኝ። ኪዳንን ትምህርት ቤት አድርሼ የምመልሰው እኔ ነበርኩ። በኮባ የተሰራ ጠብመንጃ ትከሻዬ ላይ አንግቼ ፣ እንጨት ፈቅፍቄ የሰራሁትን የእንጨት ሽጉጥ ወገቤ ላይ ሽጬ …….. ከፍተኛ ጥበቃ እያደረግኩለት እንደሆነ አስመስላለሁ። ሰውነቴ እየፈረጠመ ….. ልቤም በማንአለብኝነት እያበጠ ….. <ፀብ ሆይ ወዴት ነህ?> ብዬ እያልኩ ማሸበር ስጀምር ….. የሰፈሩ ሰው ወንድ ልጆቻቸውን እንኳን <እሷ የሴት ተፈጥሮ አልፈጠረባትም። ወንዳወንድ ናት ከእርሷ ጋር እንዳትገጥሙ> እያሉ መከልከል ሲጀምሩ ……. የጠገበ ልቤን የሚወጥር ሙገሳ ጆሮዬ ገባ። ኪዳን ከልጆች ጋር ተጣልቶ ሲያለቅስ የሰፈር ማቴ ለእኔ ሊያሳብቅ ሲሮጥ አንድ አልፎ ሂያጅ

👍25🔥1
«አሁን አንተ የአባትህ ልጅ ነህ? ያ አባትህ ቢያይህ እንዴት ይክፉው? ወንድ አይደለህ እንዴ ምን ያነፋርቅሃል? ልጅማ ወልዷል የሴት ወንድ፣ የአባቷ ልጅስ እሷ ናት።» ያለውን ኪዳን ሲነግረኝ ጥጋቤ አናቴ ላይ ወጥቶ አጎቴን አሳር አሳየሁት። እየሰነባበተ የሆነ ቀን አንድ የኛ መንደር ልጅ እና የአባቴ ገዳዮች ወገን ልጅ ገበያ መሃል በተነሳ የግል ፀብ ሲያያዙ መሃል ጥልቅ ብዬ <እጇ ላይ መሞቱ ነው> ብሎ ሰው ጠልቃ እስኪገባ ድረስ በጥላቻዬ ልክ ቀጠቀጥኩት። ከአጎቴ ውጪ ማንም የከፋው አልነበረም። ይባሱኑ መንደርተኛው «ቁርጥ አባቷን፣ የአባቷ ቢጤ አመፀኛ ፣ ይህቺማ የመንደሩ መድሃኒት ናት ፣ ቱ በሉ የአባቷን ደም ትመልሳለች። » እያለ ልክ እንዳደረግኩ ዓይነት በየቡናው እና ጠላ ቤቱ በወሬ ሲቀባበለኝ ባሰብኝ።
«እንደአባቴ ጫካ ካልገባሁ አልሽ!» ብሎ ሳቀ አሁንም ይሄን ሲያስታውስ «አንድ ቀን እርሻ ውዬ ስመለስ አጅሪት ለካ ያንቺ ቢጤ ወጠጤ ጎረምሶች ሰብስበሽ ሄደን ጠላቶቻችንን ካልገጠምን ብለሽ ልባቸውን ዝቅ አድርገሽ ልከሻቸው፣ ይሄ ውሻ ቢያሯሩጠው ሱሪው ላይ የሚንበጫበጭ ማቲ ሁላ <መሸፈቴ ስለሆነ ስንቅ አዘጋጁልኝ> ብሎ እናቱን ሲያውክ የሰፈሩ እናቶች ተሰብስበው ጠበቁኝ። <ይህችን ልጅ አደብ አስይዝልን! የልጆቻችንን ልብ ወደ ጫካ እያሸፈተች ነው።> ቢሉኝ እንደው ሳቄን መቆጣጠር ተሳነኝ ስልሽ! (አሁንም ከት ብሎ እየሳቀ) በሽመል ጦርነት ልትገጥሚ መሆኑ ነውኮ!!» እንባው እስኪወርድ ሳቀ። አጎቴ ሲያወራው ልጅነቴን ከመራራነቱ ይልቅ የተዋዛ ጨፍጋጋ ያደርገዋል። እያንዳንዷን ክስተት በቅደም ተከተል ሳይስት ሲያወራኝ ያኔ ተሰምቶኝ የነረውን ነገር ባላውቅም ዛሬ ላይ ግን ስሰማት ሜላት ምሬት ብቻ አልነበረችም።
17 ዓመት ሲሆነኝ ከአባቴ ሞት በኋላ ረጭ ብሎ የነበረው የሁለቱ ወገኖች ቁርሾ በሽመል የማይመከት የፀብ ጉርምርምታ ሆኖ ተጀመረ። ወጣቶቹ መሳሪያ ያለው በመሳሪያ የሌለው በጦር እና በጎራዴ እንዴት ጠላቶቻቸውን እንደሚመክቱ ሲመካከሩ አንደኛ የነገር ጠንሳሽ ሆኜ ተገኘው። ለካንስ ፀብ ፈጥሬ ቁምነገራቸውን ሳይቋጩ ስለምረብሻቸው ፈርተው ዝም አሉኝ እንጂ ከሴት ጋር በፀብ አውድማ መሰለፍን እንደውርደት ቆጥረውት ኖሮ ለአጎቴ መጥተው ነገሩት። ብመከር ብዘከር የ<አባቴን ገዳዮች፣ የእናቴን ደፋሪዎች የማገኝበት ብቸኛ አጋጣሚዬ ይሄ ነው። ቢከለክሉኝ ራሱ ተደብቄ እከተላቸዋለሁ።> ብዬ ፈረጠምኩ። የዛን ቀን በሩን ቆልፎብኝ የእህል ማዳበሪያ ሊቀበል ደርሶ እስኪመለስ የሳንቃውን በር ገንጥዬ ወንዶቹ የሚመካከሩበት ጫካ ሄጃለሁ። አጎቴ በጥቆማ ከቦታው ሲደርስ ከወንዶቹ መሃል ቆሜ <እኔ ነኝ ያለ ወንድ እጅ በእጅ አንድ ለአንድ ይግጠመኝ። አንዳችሁ ካሸነፋችሁኝ እቀራለሁ። አልበጠብጣችሁም። ሁላችሁንም ካሸነፍኩ ግን አብሬያችሁ እሄዳለሁ።> እያልኩ የሚጣላኝ ስጋብዝ ደረሰ። አጎቴ እንዳለኝ ከሴት ጋር ተደባድበው ቢሸነፉ ቅሌት እንደሆነ ስለገባቸው ሊደባደበኝ የደፈረ የለም። <መቼም አንቺም አንዱን ከጣልሽው በኋላ ወንድ ነኝ ያለ ደፍሮ ለመውደቅ አይመጣም ብለሽ እንጂ ያን ሁሉ ወጠምሻ እንደማትጥዪው ታውቂው ነበር።> አለኝ እንደመኩራት እያደረገው።
ከዛ በኋላ በምንም ሴትነቴ እንደማይመለስ ተስፋ ቆረጠ። እኔ እንዳላገኘው ደብቆ ያስቀመጠውን የአባቴን ሽጉጥ እና ታጣቂዎች በየቤቱ እየፈተሹ ነው ተብሎ ተቆፍሮ የተቀበረ ክላሽንኮቭ ጠመንጃውን አውጥቶ ሰጠኝ። ከመንደር አርቆ ወስዶ ኢላማ ያስለምደኝ ጀመር። አባቴ ከልጅነቴም መሰረታዊ ነገሮችን ከእናቴ ደብቆ ይዞኝ እየሄደ ያሳየኝ ስለነበር ብዙ አላስለፋሁትም። በመጨረሻም የአባቴን ገዳዮች የመጨረስ ሀሳብ ብቻውን ልቤን በሀሴት ሲሞላው ነው ሽማግሌ ልከው ፀቤ ላይ ውሃ የቸለሱበት።
ከእኔ ውጪ የቀረው ወጠምሻ መሳሪያውን ለታጣቂ አስረክቦ ጦርና ጎራዴውን ቀጥቅጦ የሽንኩርት መክተፊያ ቢላ አድርጎ ለሚስት እና ለእናቱ ሰጠ። ምንም እንዳልሆነ ሁሉ ሰላማዊ ህይወት መኖር ጀመረ። ጭራሽ ገበያ መሃል ሲገናኙ ሰላምታ መለዋወጥ ጀመሩ። ሚስቶች በመሃከላቸው ያለ የትዬለሌ ኪሎሜትር ርቀት ሳያግዳቸው ሽሮ መበዳደር ጀመሩ። እንደአጎቴ እምነት ከዚህ በኋላ ሴትነቴን ብቻ ሳይሆን ሰውነቴንም በከፊል ከዳሁ። የበቀል ጥሜን ያብርድልኝ እንጂ በመንገዴ የሚመጣ ማንም ሰው ቢሆን ከማስቀየም ወደኋላ የማልል አውሬ ሆንኩ። ቁጣዬን የምገልፅበት የማውቀው ብቸኛ መንገድ ፀብ ስለነበር <የምትጣዪው ብታጪ ከቆመ ግንድ ተጣልተሽ ትገቢ ነበር። የማደርገው ጭንቅ ጥብብ አለኝ።> ነበር ያለኝ አጎቴ። ሰላሙን የተቀበለ ሁሉ አጎቴንም ጨምሮ ጠላቴ ሆነ። መራር ሆንኩ። የቀን ተቀን የሆነ ቀን እንደምገድላቸው ነበር። አጎቴ በማያውቀው ምክንያት እንደዛ ሰፈርተኛውን እያሳቀቅኩ ግን ቆየሁ። አንድ ቀን ጭንቅህ ይብዛ ሲለው አንድ ወዳጁ ቲቪ ገዝቶ ሊያሳየን ተለማምኖ ይዞኝ እስከሄደ ቀን ድረስ። ቲቪ እንግዳ የሆነበት ብዙ መንደርተኛ ሰብሰብ ብሎ እስክሪኑ ላይ ባፈጠጠበት ያ ሰውዬ …… እናቴ ስትደፈር መጥቶ አይቶ ሱሪውን ሊፈታ ብሎ ሲጠራ የወጣው ሰውዬ አመዳም ካኪውን አውልቆ በውሃ ሰማያዊ ሱፍ ንግግር ያደርጋል። ሰውየው ሚንስትር ሆኖ ተሹሞ ብልግናውን ከአንድ ከተማ ወደ ሀገር አቀፍ የማዛመት እድል ከማግኘቱ በላይ የመንደሬው ማሽቋለጥ አንድዶኝ በጠበጥኩኝ።
«ሙሉሰውን አያችሁት? አሁንማ ጆሮው ቢቆረጥ የማይሰማ ባለስልጣን ሆነ።» እየተባባሉ ከዓመታት በፊት መንደራችንን አጋይቷት ፣ ሬሳ አስታቅፎን እየፎከረ እንደሄደ ረስተውት በኩራት ያወሩለታል። ብቻዬን የተበደልኩ አድርጌ የተሰበሰበውን ሰው ተሳድቤ ወጣሁ። በሚቀጥለው ቀን ኪዳንን አስከትዬ አጎቴ በሌለበት ቀዬውንም ለቅቄ ወጣሁ።
«ከዛስ?» አልኩኝ ተመስጬ ስሰማው ቆይቼ
«ከዛማ በእጄ ያሳደግኩሽ ልጄ ወሬሽን በእሩቅ የምሰማ ባዳዬ ሆንሽ። ብፈልግ ባስፈልግ እንዳትገኚ ስለፈለግሽ አጣሁሽ። አንቺም እንደእናትሽ ላትመለሺ መሄድሽን አምኜ ተስፋ በቆረጥኩ ሰዓት አንድ ቀን መንደርተኛው ጠላ ቤት ውስጥ ጉድ ጉድ እያለ ወሬ ሲፈጭ ደረስኩ። የምሽት የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ መታየትሽን <ልጅህ ዘንጣለች> ብለው ነገሩኝ። ምን ስታደርግ ታየች ብል <አታውቅም ኖሯል እንዴ የሚንስትሩ የሙሉሰው ሚስትም አይደለች? ከእርሱ ጎን ሆና ነው ባለፊልሙ የቀረፃት> ብለው መርዶዬን እንደምስራች ጋቱኝ።» ሲለኝ ጆሮዬም መሰለኝ።
«ሙሉ ሰው እናቴ……. » መጨረስ አንቆኝ ስንተባተብ
«ልትገያቸው ከመዘገብሻቸው ሰዎች መሃል ዋንኛውን ማግባትሽን ስሰማ የፍቅር እንዳልሆነ ጠርጥሬ ተከፋሁ። እንደባዳ ዜናሽን ከሰውም አይደል የምሰማው ? እንደፈራሁትም <ሚንስትሩ በገዛ ሚስታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።> የሚለው ዜና ሀገሪቷን ይንጣት ጀመር።» ብሎ ኩርምት ብሎ ተከዘ።
እቤት ካዝና ውስጥ ያገኘሁት የጋብቻ ሰርተፊኬት ትዝ አለኝ። ሙሉሰው!! ጠላቴን ነው ያገባሁት? ምን ምክንያት ይኖረኝስ ይሆን?
.......... አልጨረስንም ...........

👍30
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
የሐመር ታዋቂ ሽማግሌዎች ጫማ ጣዮች አንጀት አንባቢዎች... ቡስካ ላይ እንደገና ተሰባስበው ሸፈሮ ቡና ተፈልቶ
የጋራ ምርቃቱ ተዥጎደጎደ።
ጫማ ጣዮች ደልቲ ገልዲ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
ጫማቸውን እያሽከረከሩ እየወረወሩ የጫማውን አወዳደቅ ደጋግመው አዩና “ሰላም ነው፤ ወደ ኦሞ አቅጣጫ ሄዷል" አሉ፡
"አንጀት አንባቢዎች ደግሞ ትንበያቸውን ለመጀመር ሁለት ፍየሎችን አሳረዱና አንጀቱን በጥንቃቄ አነበቡት ! “አደጋ
አልደረሰበትም ሆዱ ውስጥ ግን ነገር አለ! መንገድ አሁንም እየተጓዘ ነው ወደ ፀሐይ መውደቂያ'' አሉ።
የፍየሎች ሥጋ በሐመር ደንብ መሰረት ወጠሌ ጥብስ ተጠበሰ፡ እሳቱ ከመሐል ነደደ የሥጋው ብልቶች ጫፉ በሾለ
ረጃጅም ችካል ላይ ተሰክቶ ችካሉ በሳቱ ዙሪያ ተተከለ: እሳቱ ሥጋውን አይነካውም፤ የእሳቱ ወላፈን ግን ሥጋውን ሙክክ አድርጎ አበሰለው።
ሽማግሌዎች የግማሽ ጨረቃ ክብ ሰርተው እንደ
እድሜያቸው ልዩነት ተቀመጡ። ከዚያ በሐመር ደንብ መሰረት የፍየሎቹ ፍሪንባ ለሽማግሌዎች ቀሪው ደግሞ ብልቱ እየተቆራረጠ እንደየ እድሜው ታደለ።
ሽማግሌዎች ሲመገቡ ጎረምሶችና ልጃገረዶች ራቅ ብለው ቁጭ አሉ። ከልጃገረዶች ውስጥ እንግሊዛዊቷ የስነ ሰብዕ ተመራማሪ አለች: ተመራማሪነቷ የሚያውቁት የማንቸስተር ዩንቨርስቲና ከሎ ሆራ ብቻ ናቸው፡ ሐመር ላይ ካርለት አንድ የሐመር ልጃገረድ ናት። የተገረፈችውን የጀርባ ላይ ምልክት ሳትሸፍን የፍየል ቆዳዋን ለብሳ ጭኖችዋን ጡቷን ለጎረምሶች እይታ ገልጣ ፀጉሯን አኖ
ተቀበታ ከሐመር ልጃገረዶች ጋር ወሬዋን እየሰለቀች የአባቷን
የሐመር ቀዩ በሣቋ የምታደምቅ ዝናብ ናት።
ካለ ዝናብ ጨሌ ሳር ካለ ጨሌ ሳር ከብት ካለ ከብት
ደግሞ ሐመሮች መኖር እንደማይችሉት ሁሉ በጨሌ በዛጎልና
በአምባር ያጌጡ ልጃገረዶች በሐመር ምድር ካልታዩ ሳቃቸጡ ካልተሰማ ዳንኪራቸው ካልታዬ... ሐመሮች የሉም ማለት ነው:
ካርለት አልፈርድ ከልጃገረዶች ጋር ሽማግሌዎች የሚፈፅሙትን ከቅርብ ሆና ታያለች: ጎይቲ መንደር ውስጥ ናት ከሎ ሆራ ግን የሐመር ደን (ያገባ ሙሉ ወንድ) በመሆኑ
ከሽማግሌዎች ግርጌ የተሰጠውን ያላምጣል።
ስነ-ስርዓቱ ካለቀ በኋላ ደልቲን ለመፈለጉ ከሎ ሆራና አንተነ ይመር ተመረጡና ተመርቀው አደራቸውን ከተቀበሉ በኋላ
ወደ ካርለት ሄዱ።
"መሄድ እንችላለን ካርለት"
"ምን ተባለ?”
"
“ያው እንዳየሽው ባህላዊ ትንበያው ተፈጽሟል። ወንዙን ከመሻገሩ በፊት ድረሱበት… ብለውናል" አላት።
hዚያ ተያይዘው ወደ መንደር ሄዱና ጎይቲን አገኝዋት የተባለውን ካርለት አስረዳቻት
“ጎይቲ ለብቻሽ ላናግርሽ?”
“ይእ! እሽ ምን አዲስ ነገር ገጠመሽ?"
ይኸውልሽ አሁን እንግዲህ ለፍለጋ መሄዳችን ነው::አንች
“ይእ ካርለቴ እኔ ልቀር ማለት ነው?
"አዎ አንቺ ቅሪ ከሎም ሊከፋው ይችላል አየሽ
እሱ .. "
“በይ በቃሽ እቴ አንችስ አንደኔ ሴት አደለሽ: የወለድሽው ልጅ አድጎ መልሶ አያገባሽ ግን ለምን ነው የምተወጂው
ለምን ነው ለልጅሽ
የምትሳሽው እኔ በርግጥ አግብችለሁ ግን
ያልወለድሁት ሽል ሆኖ ልቤ ውስጥ የሚኖር ሰው አለኝ ሆዴ ውስጥ ሲንከላወስ የማየው . ያ ሰው ልቤን በፍቅር መዳፍ መሃል
የያዘው በገዛ ፍላጎቴ ነበር ልቤን ከፍቼለፈት ውስጤ ገባ.. አሁን ያ ሰው ሲጠፋ ከማንም በላይ በሐዘን አንጀቱ የተመተረ ከኔ በላይ
ማንም የለም:: የፍቅር ጀግናዩ ልቤ ውስጥ የታቀፍሁትም ልጄ
ነው አውጥቼ የማልጥለው
“ይእ! እኔኮ ከንግዲህ ከእሱ ጋር የመቃበጥ እድሌ እንደ
እትብት ተቆርጧል እትብት ከመቼ ወዲህ ተመልሶ ተቀጥሎ ያውቃል ውስጤ የታቀፍኩት ግን ከገላዬ ጋር እንደተጣበቀ ነው ለልጄ ለፍቅሬ ጌታ እሳሳ እጨነቅለታለሁ ስለዚህ የሱን መጨረሻ ሳላውቅ ጎኔ አያርፍም! ልቤ አይተኛም::
እና የኔ እህት እባክሽ ሴት ሆነሽ የሴትነት ምጥ
ይሰማሽ" ብላ እንባዋን
ታወርደው ጀመር።
ሰውነቴ አረ ተይ ይብቃሽ አይንሽ ይጠፋል ምን
ይሆናል ብለሽ እንዲህ ቀን ከሌት የምታነቢው?
“ይእ ካርለትም ከሎም ደብቂው ዋሾ ሁኚ አንጀትሽ
እየከሰለ ሳቂ በእዝነ ልቦናሽ እያየሽው በአካል ግን አ
እጥፍጥፍ ብለሽ ተቀመጭ! ፍቅርሽን አውጠሽ ድፊው እያሉ ሲታከኩብኝ አታይም
ስቅ ስቅ ብላ አለቀሰች እንደገና::
"ተዋት የኔ ልጆች
የልጅነት ጨዋታዋን ዘንጊው ማለትማ ደግ አይደለም ማንስ የልጅነት ዘመኑን ዘንግቶት ያውቃል ምስጥ አለ አንተነህ ይመር: ወደ ልጅነት ዘመኑ
የኋልዮሽ እየተንደረደረ:: አየው የልጅነት ዘመን
ቡርቃውን…
“ሁሉ ነገር ሲለዋወጥ ካለበት የማይንቀሳቀስ ትዝታ ነው የልጅነት ዘመን! የወጣትነት ዘመን" ብሎ አንተነህ ይመር እንደ
ልጁ እሱም ወደ ልጅነት ትዝታው የኋልዮሽ ሮጠ ሁሉ
የሚጣፍጥበት ዘመን በራስ መተማመን ጢቅ ብሎ ሞልቶ የሚኮፈስበት ዘመን ትዝ አለው:
ተዋት አትፍረድባት አፍኝው ቻይው ምጥሽን አትናገሪ
አትበሏት ብሶቷን ታውጣው: ሐዘኗን ትግለፀው። እንዲህ ሁናስ መቼ ሰላም ይኖራታል አብራን ትሃድ፤ ተነሽ መስታዋቴ ከለ። ካርለት በተናገረችው ተፀፀተች: አንተነህ ሲናገር ህሊናዋን ሐዘን እንደቁርጥማት አኘካት። መኪናዋ አራቱን ፈላጊዎች ይዛ ወደ ኦሞ
ተንቀሳቀሰች።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የወንዝ ላይ ጉዞውን ከጀመሩ ስምንት ቀን ሞላቸው። ወገቧ ላይ ቢጫ መስመር የተሰመረባት ሰማያዊ ጀልባ በኦሞ ወንዝ ላይ እየተንሳፈፈች ኩዱማ እና ማርኩል መንደሮች አደረሰቻቸው
ኮንችት አያቷ ባስጠናት መረጃ መሰረት በየመንደሩ
እየተዘዋወረች ስታስተውል አያቷ የነገራትን ፍንጭ ባለማግኘቷ ጎዞአቸውን ቀጠሉ።
ሙርሲ ማህበረሰብ ሲደርሱ ወንዶች ፀጉር
የማይወዱ የራስ ፀጉራቸውን የወንድ ብልታቸውን ብብታቸውን
የሚላጩና ፀጉር ማሳደግ እንደ ነውር የሚቆጠርበት
የወንዱን የራሱንም ሆነ የጉያውን ፀጉር መላጨት ያለባት ሴቷ መሆኗንና
ፀጉር ቢያድግ ግን የምትወቀስ ሴቷ እንደምትሆን አዩ።
የሙርሲ ሴቶች ከሸክላ አፈር የተሰራ ክብ ገል ኸንፈራቸው ላይ ጠፍጣፋ እንጨት ጆሮአቸው ላይ ያንጠለጥላሉ: ቁጥሩ
ከአምስት ሺ የማይበልጠው የሙርሲ ማህበረሰብ የተሻለ የግጦሽ ፈና የእርሻ ቦታ በመፈለግ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር ከበርካታ አጎራባቾቹ ጋር በዚሁ የተሻለ ቦታ ለማግኘት ሲንቀሳቀስ የሚጠቃ ማህበረሰብ በመሆኑ በጥንቱ ዘመን ብዙውን ጊዜ የሙርሲ ሴቶች፡ ከብቶቹ
በግጭቱ ወቅት የሚዘርፍና ከሱዳን የሚመጡ ባርያ ፈንጋዮችም ሴቶቹን ስለሚወስዱባቸው ለዚያ መከላከያ የሙርሲ ሴቶች ከሌሎች ሴቶች የተለዩ እንዲሆኑ ገል ከንፈራቸው ላይ እንዲያስገቡ በማድረግ
የሴቶችን ዝርፊያ ማስቆሙ! ይኸ ጠቃሚ ዘዴ በማህበረሰቡ እንዲ
ለመድም ሰፋ ያለ ገል ከንፈራቸው ላይ የሰኩ ልጃገረዶች አነስ ያለ
ገል ካደረጉት ልጃገረዶች የበለጠ ጥሉሽ እንዲከፈልባቸው መደረጉ!
ያ ድርጊት ሴቶች በከንፈራቸውና ጆሮአቸው ገል እንዲሰኩ የተጀመ
ረው ተቀባይነት አግኝቶ እንዲቀጥል አሁን አሁን እንዲያውም ሰፊ
ገል hንፈር ላይ መሰካት ብዙ ጥሉሽ የሚያስገኝ በመሆኑ የቁንጅና
መለኪያ ተደርጎ በውጩ ማህበረሰብ እንደሚገመትም አወቁ።

👍23🥰1
ኮንችት ኢትዮጵያዊው አያቷ ሉካዬ ደጋግሞ የሚቀመጥ
ባትን መቀመጫ ሙይ ማራ አካባቢ ሙርሲዎች ሲጠቀሙበት ብታይም መቀመጫዋ ለፍለጋዋ የተለዬ አስተዋፅኦ እንደማታበረክትላት ተረዳች። የሙርሲ ማህበረሰብ ከብት አርቢ በመሆናቸውም የአያቷ ዘመዶች እንዳልሆኑ አመነች: ስለዚህ የፍለጋ ጉዟቸውን ከሶራ ጋር ቀጠሉ።
ኦሞ ወንዝ ስፋቱ ውበቱ… እየጪመረ ሄደ፡ ኮንችትና
ሶራ ምንም እንኳን ቀደም ሲል ባጋጠማቸው አደገኛ ፈተና ህይወታቸውን ከማጣት ለጥቂት ቢድኑም ያጋጠማቸው ችግር
በጉዞአቸው የነበረውን ምግብ የማብሰያ እቃ... በከፊል በኦሞ የተወሰደባቸው ቢሆንም ዕለት ወደ ዕለት መግባባታቸው እየጨመረ
ጨቅላው ፍቅራቸው እየጠነhረ በመሄዱ በሞራል እየተጠናከሩ ሄዱ።
“እንደምገምተው ወደ ግባችን የተቃረብን ይመስለኛል"
"ልክ ነሽ በዚህ ሁለት ሶስት ቀን ወደተመኘሽው የአያትሽ መንደር መድረሳችን አይቀርም አላት።
ሰረቅ አድርጋ አየችውና ያን ስታልመው የኖረችውን ተስፋ እንዳገኘች ሁሉ ልቧ በደስታ ሞልቶ ፈገግ አለች። ከዚያ ካሉበት ለመድረስና ጊዚአቸውን ለመጠቀም በፀጥታ መቅዘፍ ቀጠሉ።
ኮንቺት የአፍሪካ ጉዞዋን ከመጀመሯ በፊት ለጉዞዋ
የሚስልጓትን ስታሰባስብ ችግር ቢያጋጥማት ሁለትና ሶስት የመኖር ሙከራዎኝን ልታደርግባቸዉ የምትችላቸውን ጥንቃቄዎች ስታስተካክል ቆይታለች።
ጤንነቷን የመተኛ ቀረጢት! ውሃ የማይገባው ጠንካራና ተስማሚ ቀበቶ ያለው የጀርባ ሻንጣ የመጀመሪያ ህክምና መስጫ ውሃ የማያበላሸው ክብሪት ሻማ በፀሐይ ወቅት እሳት
ለማቀጣጠል የሚችስል ከጉሊ መስታዎት መርፌና ክር የአሳ ማጥመጃ መንጠቆና ሲር የአቅጣጫ መጠቆሚያ ኮምፓስ ተጣጣፊ መጋዝ ባትሪ ጩቤ አዘጋጅታለች።
በጉዞ ወቅት ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ ለመቆጣጠር
ሲጋራ አለማጨስ በፀሐይ ሙቀት ላለመጠቃት መሞከር ከሞቀ መሬት ወይንም ከጋለ ድንጋይ ላይ አለመቀመጥ በትንሹ መመገብ (በተለይ ቅባት ያላቸው ምግቦችን አለመብላት አልኮል አለመጠጣት ብዙ አለመናገርና በአፍንጫ ብቻ መተንፈስ... አስፈላጊ መሆኑን ስትለማመድ ከርማለች::
ፍራፍሬዎች ሥራስርና ቅጠላ ቅጠልን መመገብ ጡት አጥቢ እንስሳትን ተሳቢ ነፍሳትን አዕዋፍና አሶችን ማደን ከገመድ
ከእንጨትና ከመሳሰሎት የተለያዩ ነገሮች ወጥመዶች ማጋጀትን
ከዚህ ቀደም ያልተመገቡትን እፅዋት እንሳትን ከመመገብ በፊትማሽተት እግር አካባቢ
ቀስ አድርጎ የሚያቃጥል
ወይንም የሚለበልብ ስሜት እንዳለው መሞከር! በከንፈር በምላስ
እየቀማመሱ ለአስራ አምስት ደቂቃ ጠብቆ በመጠኑ አላምጦ ቀስ
እያሉ መዋጥና
የሚያስከትለው
ችግር ካለ መከታተል
እንደሚያስፈልግ ተምራለች።
ከዚህ በተረፈ
አቅጣጫን ለማወቅ
ያሉ የተፈጥሮ ክስተቶችን በተለይም ጨረቃንና ከዋክብትን በማየት
መጠቀም መቻልን ተለማምዳለች። ጨረቃ ጀንበር፡ ከመጥለቋ በፊት ከወጣች ጨለም ያለው የጨረቃ ክፍል ምዕራብ አቅጣጫን ጀንበር ከጠለቀች ከግማሽ ሌሊት በኋላ ጨረቃ ከወጣች ጨለም ያለው ክፍል
ምስራቅን እንደሚያሳይ በከዋክብት ላይ የሃሣብ መስመር ካስዮፒያ
በኦሪዎን በመሳሰሉት ሰባት ከዋክብት በማስመር የሰሜኑንና ደቡብን
ዋልታ ለይቶ ያሉበትን አቅጣጫ ማወቅ መቻሉን ወዘተ ተለማምዳለች።
ይህን ልምዷን ለሶራ ለማካፈል የሞከረች ሲሆን በምግብ እጥረቱ ሳይደናገጡ የሚመገቡትን ካለምንም ችግር ኦሞ ወንዝ ዳርና ዳር ካሉት ተክሎችና ከኦሞ ወንዝ ላይ አሳ በማጥመድ ማግኘት
በመቻላቸው ተረጋግተው ለመጓዝ አስችሏቸዋል።
ኮንችትና ሶራ በኦሞ ወንዝ ሲጓዙ በኡዱማ መርኩል
ጎዋ ኩረምና ሻንጋሮ ያሉትን የቦዲና የሙርሲ መንደሮች ካዩ በኋላ የደቡብ ሱዳንን አቅጣጫ ይጓዝ የነበረው
አቅጣጫውን ከደቡብ ወደ ምስራቅ ድንገት እጥፍ በማድረግ መጓዝ ጀመረ
በአለምአቀፍ አቅጣጫ ማስተካከየዋ ጂፒ ኤስ'
ከሳተላይቶች ጋር ግንኙነት ፈጥራ ያለችበትን የኬክሮስና ኬንትሮስ
ዲግሪ ካወቀች በኋላ ማፑን ስትመለከት በጣም ከሚጠማዘዘው የኦሞ
ወንዝ ጉዞ በኋላ የካራ የሙሩሌ ዳሰነች ማህበረሰቦችና ዝቅ ብሎ
የሚታየው የቱርካና ሐይቅ ብቻ የሚቀራቸው መሆኑን ተረዳች:
በዚህ ጊዜ ኮንችት ትልቅ ሃሣብ ላይ ወደቀች የአያቷን
ቀዬ ለማግኘት የቀራት እድል በጣም ውስን ነው
የዳሰነች ማህበረሰብ ያለው
ከቱርካና ሐይቅ ጥግ ሲሆን አያቷ ስለሃይቅ ፈፅሞ አንስቶ ስለማያውቅ የሱ ማህበረሰብ ዳሰነች ሊሆን አይችልም ስለዚህ ጥርጣሬዋ ወደ ሁለት ዝቅ አለ ከካራና ከሙረሌ
ከነዚህ አንዱ ካልሆነ ግን የአያቷን ቀዬ ለማግኘት
የምትወስደው አማራጭ
ጭልምልም ያለና ምናልባት ሌሎች ተጨማሪ አመታትን
የሚወስድ ይሆናል ስለዚህ ኮንችት ጭንቀት አንገቷን ሲያስደፋት ሶራ ችግሯ ምን እንደሆነ ገብቶት፡-
አዞይሽ ካሰብሽው ትደርሻለሽ" አላት::
ያ ሃሳብ አንዳች ውስጣዊ ሃይል ፈጠረላት አመሰግናለሁ ብላው ጉዟቸውን ቀጠሉ።

👍25🤔2👏1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ አራት)
(ሜሪ ፈለቀ)
«ከዛ ሰውዬ ጋር አብሬው ተኛሁ? ምንድነው ያደረግኩት?» መልሱን ማናቸውም እንደማያውቁት እያወቅኩ ደጋግሜ እጠይቃቸዋለሁ። እነርሱም መልሱን ጠብቄ እንዳልጠየቅኳቸው ስለልገባቸው አይመልሱልኝም። ከዚህ ቀዬ ከወጣሁ በኋላ የተፈጠረውን ነገር ካወቀ ሊያውቅ የሚችለው ኪዳን ብቻ ነው።
እናቴን ካገኘሁ በኋላ ያለፈውን ራሴን የመፈለግ ውጥረቴ ትቶኝ ነበር። አጎቴ ታሪኬን ነግሮኝ ሲያበቃ እንደአዲስ ያቅበጠብጠኝ ጀመር። ምንድነው ያደረግኩት? ምን ዓይነት አቅል መሳት ላይ ደርሼ ነው ያን ሰውዬ ያገባሁት?
«እናቴ? ስለኪዳን የነገርኩሽን የምታስታውሺውን ሁሉ እስኪ ንገሪኝ! ከተመታሁኮ ሁለት ወር አለፈ። እንዴት አይፈልገኝም? እንዴት አይደውልልኝም?»
«እኔ እንጃ ልጄ! ብዙውን ያወራሽኝ ስለመውደድሽ ፤ ጎበዝ ተማሪ ሆኖ በማዕረግ ስለመመረቁ ፣ ፈረንጅ ፍቅረኛ እንዳለችው እና ሰርጉ ሀገሩ እንዲሆን ፈልጎ አንቺ እንቢ ማለትሽን …… እንዲህ እንዲህ ያለ ነገር ነው የነገርሽኝ እንጂ የምትገናኙበትን መንገድ አላውቅም ልጄ። ከመሞቴ በፊት ባየው ብዬሽ <በህይወት መኖርሽን አያውቅም። እንዴት እንደምነግረው እንጃ ግን እነግረዋለሁ> አልሽኝ።» እያለችኝ ሌላ የምታስታውሰው ነገር መኖሩን የጭንቅላቷን ጓዳ ትበረብራለች
«ለምን እንቢ አልኩት? ማለቴ ሰርጉን?»
«አንቺን ማጥቃት የፈለገ ሰው ሊያጠቃሽ የሚችልበት ብቸኛ መንገድ እሱ በመሆኑ አንድ ነገር እንደሚያደርጉብሽ ነው የነገርሽኝ። ሁኔታውን ልትነግሪኝ አልወደድሽም እንጂ ከዚህ በፊት በእሱ እንዳገኙሽ ነግረሽኛል።»
ድፍንፍን ያለ ነገር ሆነብኝ። ወደቤቴ መመለስ ፈለግኩ። ፍለጋዬን የት እንደምጀምር ባላውቅም እዛ የሆነ ፍንጭ አላጣም መሰለኝ። ያቺ መልእክት አስቀምጣ የነበረችው እመቤትስ? ያ የደወልንለት ሰውዬ ቃሊቲ እስር ቤት ናት ያላት እመቤት! ማን ያውቃል ለእሷ የሆነ ነገር ነግሬያት ይሆናል። ግን እስር ቤቱጋ ሄጄ በደፈናው እመቤትን ነው የምለው? ምናልባት አንድ ሀገር እመቤት የሚባል ሴት ይኖራል። አላውቅም ብቻ እዚህ ተቀምጬ ሀሳብ ከማመነዥክ መሞከሩ አይከፋም!
ምናልባት ደግሞ ያ ስልባቦት የመሰለ ዳዊት የሚሉት ፍቅረኛዬ! ለእርሱስ ምንም ልነግረው አልችልም ኸረ! ማን ያውቃል ግን? ግን እንዴት ባለ ዘዴ ነው ትውስታዬን ማጣቴን ሳልነግረው ስለኪዳን የሚያውቀው ነገር መኖሩን የማወጣጣው?
እናቴ የቀሯትን ቀናት እዛው መሆን መፈለጓን እኔ እንዳይከፋኝ በማባበል በማስፈቀድ ለዛ ስትጠይቀኝ ግራ ገባኝ። በሽታዋ የማህፀን ካንሰር ነው። ምንም ማድረግ እስከማይችሉበት ሰዓት ድረስ ሀኪሞች ብዙ ትሪትመንት ሞክረውላታል። ያገኘኋት ጊዜ ሀኪም ቤት ካልወሰድኩሽ ብዬ ስነዘንዛት
«ልጄ አንቺው እኮ ነሽ ስታሳክሚኝ የቆየሽው! ከሀገር ውጪ ወጥተሽ ካልታከምሽ ብለሽኝኮ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ሀኪሞቹ ነግረውሽ ነው የተውሽው። አምላክ በታምሩ ይሄን ደስታ ቀምሰሽ ሙቺ ሲለኝ እንጂ እንዲህም መች ትቆያለች ተባልኩ?» ብላኝ ነበር። ሀኪሞቹ ከገመቱት ቀን በላይ መቆየቷ ተዓምር እንደሆነ ሁሉ ብትታከም ድጋሚ ተዓምር ሊፈጠር ይችል ይሆናል ብዬ ላሳምናት ብሞክርም <ደከመኝ> አለችኝ። ማረፍ ብቻ ነው የፈለገችው። መሞትን ሳትፈራው ቀርታ ይሁን ወይስ እንዳይታወቅባት ውጣው ለመሞት የተዘጋጀች ነው የምትመስለው። በመጣ ቀን <እንኳን ደህና መጣህ! ስጠብቅህ ነበር> ብላ የምትቀበለው።
«እሺ!» አልኳት እና ወደጎንጥ ዞሬ «አንተ ነገውኑ ባሻህ ሰዓት ተመለስ! እኔ እዚህ ከእናቴ ጋር እሆናለሁ! » አልኩት
«ማይደረገውን!! እኔ እዚህ መሆኔ ካልከበዳችሁ በቀር ወደየትም የመሄድ መሻት የለኝም!!» (አለ ወደአጎቴ እያየ)
«ኸረ ምን ከብደኸኝ? ባደረገውና እዚሁ በባጀህ! እኔማ የሚያነጋግረኝ አገኘሁ!» አለ አጎቴ።
ከመጣን ጀምሮ ጎንጥ ከዚህ በፊት የሚያውቀው ቤት እና ቤተሰብ ውስጥ የተቀላቀለ ነበር የሚመስለው። እጅጌውን ሰብሰብ አድርጎ እንጨት ለመፍለጥ ሰዓታት አልፈጀም። ሊወድቅ ያዘመመውን የከብቶቹን ቤት ያጋደለውን እንጨት እያስተካከለ ሲተክል በእንግድነት ውሎ አላደረም ነበር። ሱሪውን ሰብስቦ እንደቁምጣ አሳጥሮ የአጎቴን የጓሮ ማሳ ሲያርም …… የኖረበት …. የሚያውቀው እንደሆነ ያሳብቅበት ነበር። አጎቴ በእርሱ መገኘት ደስ መሰኘቱን ለማወቅ ብዙ ሂሳብ አያሰራም።
«እኔ እዚህ ምን እሆናለሁ? እዚህ ጠላት የለኝም ሲገባኝ። ዝምብዬ ነው የምፈራው እንጂ ምናልባትም ማንም እያደባብኝ አይደለም። የሚያስፈልግ ነገር ሲኖር ባይሆን ትመጣለህ።» አልኩት እናቴን ላገኛት የሄድኩ ቀን እንደዛ ተንበጭብጬ ምንም ያለመፈጠሩን እያሰብኩ።
«ህም!! ክፋት የከጀለ ልብ አይደለም እዝህች ሲኦል ከመውረድ የሚያግደው የለም!» አባባሉ ስለእርሱ ያለኝን ጥርጣሬ ቀሰቀሰብኝ። የሆነ ያልነገረኝ የሚያውቀው ነገርማ አለ።
«አይሆንም አንቺም እዚህ አትከርሚም!» አለች እናቴ ጠልቃ ገብታ « ….. በአካል ባልዳብሰው እንኳን የኪዳንን ድምፅ ሰምቼ አንዴ አውርቼው ባልፍ …… ይሄ ባይሆን እንኳን ለወንድምሽ ታስፈልጊዋለሽ። አግኝው!» አለችኝ አሁንም በልምምጧ። ልቤ መሃል ላይ ዋለለብኝ። እሺ የት ብዬ ነው የምፈልገው? እሱን ለማግኘት እኔ ስዳክር እናቴ ብታመልጠኝስ? ምን ያህል እንደሆነ የማላውቀውን የቀረንን ቀን ትቻት እንዴት ነው የምሄደው?
«የእኔ አበባ ? አትከፊብኝ! እዚህ አብረሽኝ ብትሆኝም ሞትን አታስመልጪኝም! ለእኔ አምላክ በእድሜዬ ማታ አንቺን መልሶልኝ ሀሴት ሰጥቶኛል። ወንድምሽን ባላገኘው እንኳን ደህና መሆኑን ማወቄ እረፍት ነው!! ስንት ቀኖች እና ስንት ለሊቶች <ልጆቼን ለየትኛው ጅብ ዳርጌያቸው ይሆን? ምን ዓይነት ህይወት እየኖሩ ይሆን? ትቻቸው ባልሄድ የተሻለ ህይወት ይሆንላቸው ነበር?> እያልኩ በፀፀት ነድጃለሁ መሰለሽ? ያንቺ እናት ስለሆንኩ እኔ እድለኛ ነኝ። ብቻ አንድ ነገር ቃል ጊቢልኝ! ያለፍሽውን ብታስታውሺም ባታስታውሺም ወደቀደመው ህይወትሽ ላትመለሺ ቃል ጊቢልኝ!! ልብሽን ያየ አምላክ ሁለተኛ እድል ሰጥቶሻል። ያለፈውን ለመድገም ሌላ አዲስ ህይወት ባላስፈለገሽ ነበር። አዲስ ህይወትን ገንቢ የእኔ አበባ! ……. » የስንብት የሚመስል ብዙ አለችኝ። ያለእርሷ የኖርኩትን ህይወት እንዴት እንደኖርኩት ባላውቅም አሁን ያለእርሱ የምኖራቸውን ቀናት ሳስብ በረደኝ።
ግማሽ ልቤን እናቴጋ ትቼ፤ ፈጣሪ ትንሽ ቀን ቢጨምርላት፣ ኪዳንን ባገኝላት እና ብትሰማው ወይ ብታየው እየለመንኩ በተከፋች ግማሽ ልቤ ከጎንጥ ጋር ወደቤት መንገዱን ተያያዝነው።
«ይገርማል! የዛን ቀን ሞቼ ቢሆን ኖሮምኮ መሞቴን እናቴም አጎቴም አይሰሙም። በዚህ አይነት ኪዳንም አይሰማም ነበር። ሊቀብረኝ ራሱ የሚመጣ ሰው ይኖር ይሆን?» አልኩኝ
« ህም የሌላውን እንጃ። እኔ የት ሄጄ ነው የማልኖር?»
«ሬሳዬን የሚሸኝ ስለማይኖር ሰብአዊነት ተሰምቶህ እንጂ መቼም <ወየው እትይ!> እያልክ አትቀብረኝም ነበር።» ስለው አይኑን ለአፍታ ከመንገዱ ወደእኔ አዙሮ ፈገግ ብሎ ዝም አለ። በሱው የፈገግታ ለዛ ቀጥዬ «ሆስፒታል እንኳን መጥተህ እየኝ ብዬ ብልክብህ <የቀጠሩኝ ደጆን እንድጠብቅ ነው > ብለህ አልላክብኝም? ዛሬ ቤቱን ጥለህ ገጠር ለገጠር አብረኸኝ ልትንከራተት?»

👍24❤2
«ህም መች ሰው ባሰበበት ይውላል?» አለ ከንፈሩን ብቻ ሸሸት አድርጎ። እኔ አንድ ሀገር አውርቼ ከአምስት ቃል ያልዘለለ ነው የሚመልስልኝ። ያለማቋረጥ መለፍለፌ ለራሴ እንኳን እንግዳ አይነት ስሜት ሰጥቶኛል። መልሼ ይሄንንም ያንንም ሳወራ ራሴን አገኘዋለሁ እንጂ። ምናልባት ከእናቴ ጋር የነበረኝ ጊዜ፣ ወይ ደግሞ ያስታወስኩት የትውስታዬ ሽራፊ፣ ወይም ትውስታዬ የመመለስ ተስፋ እንዳለው ማወቄ፣ አልያም አጎቴ ያወራልኝ የህይወቴ ክፍል …… አላውቅም! አንዳቸው ወይም ሁሉም ተደምረው ግን የሆነ ስሄድ ከነበረው ቅልል ያለ ስሜት ስመለስ እንዲኖረኝ አድርገውኛል።
«ከመመታቴ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያደረግኩት ምን ይሆን? ለመጨረሻ ያገኘሁት ሰው ማን ይሆን? ያስቀየምኩት ወይስ በጥሩ የሚያስታውሰኝ ሰው ይሆን?» ያልኩት እንዲመልስልኝ አልነበረም።
«የዚያን እለት ከቤት ወጥተሽ ብዙም ሳትቆዪ ነው የሆነው ነገር የሆነው። በመንገድሽ የገጠመሽ ካልነበረ ለመጨረሻ ያወራሽው እኔን ነው የሚሆን!» አለ ስሜቱን ለማንበብ በሚከብድ ፊት። ያልጠበቅኩት መልስ ሆኖ መሰለኝ ተስተካክዬ ተቀመጥኩ።
«ምንድነው ያወራሁህ? መጥፎ ነገር ነው? ጥሩ?»
«ያለፈውን ከኋላችን እንተወው ተባብለንም የለ?» መመለስ የማይፈልገው ነገር ሲሆን የሚያመልጥበት ዘዴው ነው።
«በናትህ? ለምንድነው ግን ያለፈውን ስጠይቅህ የምትሸሸው? ልቤ የሚነግረኝ ከነገርከኝ በላይ ብዙ የምታውቀውን ነገር እንደደበቅከኝ ነው ግን ዝም ብዬ እያመንኩህ ነው።» ….. ብዬ ጥርጣሬዬን ላስከትል ስንደረደር የሚቀጥለውን ለማስቆም በሚመስል
«ፀያፍ ነገር ነው!! እኔ አሁን የማልደግመውን ፀያፍ ነገር ብለሽኝ ነው የወጣሽ! እንደእውነቱስ አፍሽን ከፈትሽ ነው የሚባል።» አለ እንዲመልስልኝ ስላደረግኩት እየተናደደብኝ።
«እሺ በሙሉ ልቤ እንዳምንህ አስረዳኝ! እንደዛ ፀያፍ ነገር የምናገርህ ሴት ሆኜ እቤቴ ምን አቆየህ? ስራዬ ፣ እንጀራዬ ምናምን ብለህ ልትሸነግለኝ አትሞክር! እኔ የምከፍልህን ደመወዝ ብዙ እጥፍ ከፍሎ የሚያሰራህ ሰው አታጣም ባንተ ብዙ ችሎታ! ሲጀመር የአንድ ቤት ዘበኛ፣ መኪና መንዳት የሚችል፣ ሽጉጥ የታጠቀ ፣ ክብር ሀቅ እውነት እሴቶቹ የሆነ ሰው …… አፏን የምትከፍትበት ሴት ደጅ ምን ያደርጋል?»
«ውል የሌለው አድርገሽ አትቆጣጥሪውማ! ሹፍርና እሰራ እንደነበርኮ አውግቼሽ ነበር። ወታደር ቤት ስለነበርኩ መሳሪያውም አዲሴ አይደለም። ሽጉጡንም ያስታጠቅሽኝ አንቺው ነበርሽ! ይከው ነው!!» አለ
«አሁን ያልከው በሙሉ ለምን እኔጋ እንደቆየህ አያብራራም! እሺ ንገረኝ እስኪ የት ነው የተገናኘነው? ማለቴ ስራውን እንዴት አገኘኸው? ወይም እኔ እንዴት ቀጠርኩህ?»
ለማውራት አፉን ከመክፈቱ በፊት በረጅሙ ተነፈሰ። ግንባሩ ላይ ያሉት መስመሮች ብዛታቸው ጨመረ። ዞር ብሎ ሳያየኝ
«ሰው ነው ያገናኘን! አንቺ ጠባቂ እንደምትፈልጊ እኔ ስራ እንደሚያስፈልገኝ የሚያቅ ሰው!» አለ በድፍኑ። አጀማመሩ እስከነገ የማያልቅ ታሪክ ሊያወራኝ ነበርኮ የሚመስለው።
«በቃ!? ሰው?» ድምፄን ጨመርኩ።
«ቆይ እኔ የምጎዳሽ አለመሆኔን እንድታምኚ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?»
«እያወራን ካለነው ጋር ይሄ የሚያገናኘው ነገር የለም! ትጎዳኛለህ ብዬ ባስብማ አብሬህ አልገኝም!! አንተ መናገር ያልፈለግከው ወይም እየደበቅከኝ ያለ ነገር እንዳለ እየተሰማኝ ግን ምንም ሳትጠይቂ በጭፍኑ እመኚኝ ማለት አይዋጥልኝም።» አልመለሰልኝም። አሁንም በረዥሙ ተንፍሶ ዝም አለ። በዝምታችን ውስጥ ከራሴ ሳወራ ለካንስ ምንም ነገር ለእኔ የማስረዳት ግዴታም የለበትም። <የራስሽ ጉዳይ> ብሎ ጥሎኝ ቢሄድስ መብቱ አይደል? ያኔም ለምን አብሮኝ እንደቆየ አሁን ለምን አብሮኝ እንዳለ ምክንያቱን ማወቅ አልችልም። ስለእርሱ የማወቅ መብት እንዳለኝ እንዲሰማኝ ያደረገኝ ራሱ አይደል ግን?
ሀሳብ ሳዛቁል ስልኬ ጠራ። የማላውቀው ቁጥር ነው። ለምን እንደማደርገው ባላውቅም የማላውቀው ስልክ ሲደወል ጎንጥ አጠገቤ ካለ ድምፁን ስፒከር ላይ አደርገዋለሁ። ምናልባት የመጀመሪያ ቀን ስልኬ ሲከፈት ድንብርብሬ ወጥቶ ስንተባተብ እሱ ስልኩን ተቀብሎኝ ስላወራ እንደልምድ ወስጄው ይሆናል። አነስቼ ሀሎ አልኩ።
«እሺ ሜላት!! ሁልጊዜ ጀግና አይኮንም! አንድ ቀን አገኝሻለሁ ብዬሽ አልነበር?» ወፍራም ድርብ የወንድ ድምፅ ነው።
«ማን ልበል?»
«ማን እንደሆንኩማ አሳምረሽ ታውቂዋለሽ!! ዛሬውኑ እስከማታ ድረስ የምልሽን ታደርጊያለሽ!! ህም እመኚኝ ይሄ እንደሌላ ጊዜው ማስፈራሪያ አይደለም። ምንም አይነት ወጥመድ ከጀርባዬ ሸርባለሁ ብትዪ ወንድምሽን 12 ትንንሽ አድርጌ በየተራ እልክልሻለሁ። ……. » ጎንጥ መኪናዋን ሲጢጥ አድርጎ አቆማት። እየሆነ ያለው ነገር በቅጡ ሳይገባኝ ሰውየው ማውራቱን ቀጠለ « …… ልታናግሪው ከፈለግሽ አጠገቤ ነው። ቪዲዮ ላድርግልሽ ከፈለግሽ?» (እያላገጠብኝ ነው የሚያወራው) ይሄኔ ጎንጥ ከመኪናው ፊትለፊት ያለ ወረቀት አንስቶ ከኪሱ እስኪሪብቶ አውጥቶ የፃፈውን አሳየኝ። <ምንድነው የምትፈልገው? በይው።> ሰውየው ይሄን ሲሰማ እንደመደሰት አደረገው።
« የሰውን ስስ ጎን ማግኘት ደስ ሲል።አየሽ የምትሳሺለት ነገር ሲያዝብሽ እንዲህ ነው የሚያንገበግበው። ከገባሽ! አንደኛ ወለም ዘለም ሳትዪ የቪዲዮን ያሉሽን ቅጂዎች በሙሉ ካስቀመጥሽበት ሰብስበሽ ነይ የምልሽ ቦታ ይዘሽ ትመጫለሽ። ሁለተኛ አንቺን ማመን ስለማይቻል ማስተማመኛ እንዲሆነኝ እዚህ ከመጣሽ በኋላ በይ የምልሽን እያልሽ እንቀርፅሻለን። ይቅርታ እንግዲህ ባላምንሽ … ያለመታመን ልምድሽ አቻ ባይኖረው ነው።» እኔ እሱ የተናገረው ምኑም አልገባኝ እሱ ይገለፍጣል። ጎንጥ ፅፎ ያሳየኛል።
«እኮ ምንድነው እንድቀርፅልህ የምትፈልገው?»
«ቆቅ አልነበርሽ? ይህቺ ትጠፋሻለች? በማስፈራራት ያለፍሻቸውን እዚህም እዛም የሰራሻቸው ህገወጥ ነገሮች ሲሰበሰቡ እድሜ ልክ ዘብጥያ የምትበሰብሺበት ሆኖ አጊንቼዋለሁ። ብዙም እንዳትቸገሪ መረጃዎቹንም ሰብስቤልሻለሁ። አንቺ የሚጠበቅብሽ የሰራሻቸውን ወንጀሎች በመረጃ አስደግፈሽ አምነሽ ቃል መስጠት ነው። ከምታምኛቸው ውስጥ ፌክ የምስል ቅንብር እና መረጃ ሰርተሽ እኔን በማስፈራራት የግል ጥቅም ለማግኘት ያለመታከት መልፋትሽ ይካተትበታል። ያው እዝህችጋ ምንም ያህል የረቀ ሴራ ብትሰሪ እኔ ወደር የሌለኝ ለሀገሬ ታማኝ አገልጋይ መሆኔን አክለሽ ብትጠቅሽም አይከፋኝም። ሃሃሃሃሃ» እኔ ምኑም እየገባኝ ካለመሆኔ እየተነጋገሩ ያሉት ሰውየውና ጎንጥ ናቸው የሚመስሉት
«ኪዳንን አገናኘኝ? ማስረጃ እፈልጋለሁ።» ብሎ ጎንጥ የፃፈልኝን አነበብኩለት
«ምን ችግር። ቆዪማ ቪዲዮ ላድርገው?» ሲለኝ ጎንጥ ስልኩን ዘጋው እና እኔ ላይ አፈጠጠ።
«ወንድምሽን ስታዪው የተደናገጠ ሰው እንዳትመስዪ ፣ ድሮ የሚያውቋትን ሜላት መሆንሽን አሳምኛቸው። ምንም እንደማያውቅ ሰው አትምሰዪ ….. የማታውቂውን ነገር አትጠይቂ!! ምንም ቢፈጠር እንደማታስታውሺ እንዳትናገሪ ….. የምልሽን ብቻ አድርጊ!!» ብሎ በቁጣ እያስጠነቀቀኝ ስልኬን ተቀብሎኝ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ሰው ጣቱን ካመላለሰ በኋላ ከመጡለት ዝርዝሮች የሆነች ቀይ ምልክት ነገር ተጭኖ እየመለሰልኝ ስልኩ ጠራ። ድንብርብሬ ሲወጣ በሁለቱም እጆቹ ትከሻዬን በሁለቱም በኩል አጥብቆ እየያዘ « ታምኚኛለሽ?» ያለኝ ስለምን እንደሆነ ሳይገባንኝ ጭንቅላቴን ወደ ላይ ወደታች ናጥኩ!! «ተረጋጊና ያልኩሽን አድርጊ!!»

👍29🥰4❤1
«እኔኮ ኪዳንን እንኳን ላልለየው እችላለሁ?» አልኩ አፌ ውስጥ ምራቄ ደርቆብኝ ትን የሚለኝ እየመሰለኝ። ስልኩ ጠርቶ እንዳይዘጋ እየተቻኮለ ስልክ ያልያዝኩበትን እጄን ቀለብ አድርጎ ጨብጦ ከቅድሙ በተረጋጋ ድምፅ
«ትለይዋለሽ ግድ የለም!» አለኝ። የድምፁ መርገብ ይሁን የያዘኝ እጁ ያረጋጋኝ መርበትበቴን ገትቼ የያዘኝን እጄን አስለቅቄ ስልኩን ካነሳሁ በኋላ እንዲይዘው መልሼ ሰጠሁት።
………. ይቀጥላል ………..
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
«ትለይዋለሽ ግድ የለም!» አለኝ። የድምፁ መርገብ ይሁን የያዘኝ እጁ ያረጋጋኝ መርበትበቴን ገትቼ የያዘኝን እጄን አስለቅቄ ስልኩን ካነሳሁ በኋላ እንዲይዘው መልሼ ሰጠሁት።
………. ይቀጥላል ………..
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
❤12👍3
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ኮንችትና ሶራ በኦሞ ወንዝ ሲጓዙ በኡዱማ መርኩል
ጎዋ ኩረምና ሻንጋሮ ያሉትን የቦዲና የሙርሲ መንደሮች ካዩ በኋላ የደቡብ ሱዳንን አቅጣጫ ይጓዝ የነበረው
አቅጣጫውን ከደቡብ ወደ ምስራቅ ድንገት እጥፍ በማድረግ መጓዝ ጀመረ
በአለምአቀፍ አቅጣጫ ማስተካከየዋ ጂፒ ኤስ'
ከሳተላይቶች ጋር ግንኙነት ፈጥራ ያለችበትን የኬክሮስና ኬንትሮስ
ዲግሪ ካወቀች በኋላ ማፑን ስትመለከት በጣም ከሚጠማዘዘው የኦሞ
ወንዝ ጉዞ በኋላ የካራ የሙሩሌ ዳሰነች ማህበረሰቦችና ዝቅ ብሎ
የሚታየው የቱርካና ሐይቅ ብቻ የሚቀራቸው መሆኑን ተረዳች በዚህ ጊዜ ኮንችት ትልቅ ሃሣብ ላይ ወደቀች የአያቷን ቀዬ ለማግኘት የቀራት እድል በጣም ውስን ነው የዳሰነች ማህበረሰብ ያለው ከቱርካና ሐይቅ ጥግ ሲሆን አያቷ ስለሃይቅ ፈፅሞ አንስቶ ስለማያውቅ የሱ ማህበረሰብ ዳሰነች ሊሆን አይችልም ስለዚህ ጥርጣሬዋ ወደ ሁለት ዝቅ አለ ከካራና ከሙረሌ
ከነዚህ አንዱ ካልሆነ ግን የአያቷን ቀዬ ለማግኘት
የምትወስደው አማራጭ
ጭልምልም ያለና ምናልባት ሌሎች ተጨማሪ አመታትን የሚወስድ ይሆናል ስለዚህ ኮንችት ጭንቀት አንገቷን ሲያስደፋት ሶራ ችግሯ ምን እንደሆነ ገብቶት፡-
አዞይሽ ካሰብሽው ትደርሻለሽ" አላት::
ያ ሃሳብ አንዳች ውስጣዊ ሃይል ፈጠረላት አመሰግናለሁ ብላው ጉዟቸውን ቀጠሉ።
ትንሿ ድንኳናቸው ከኦሞ ወንዝ ራቅ ካለ ጉብታም ቦታ አግራር ዛፍ አቅራቢያ ተተክላለች።
ኮንችት ሁለት እግሯን እጥፍጥፍ አድርጋ ድንቁን
የተፈጥሮ ውበት የማታዋን ጀንበርና ልዩ መስህብ የተጎናፀፈውን የዳመናውን ቀለም እያየች የተፈጥሮን ሙዚቃ የአዕዋፍ ዝማሬ
የንፋሱን ሽውሽውታ... ታዳምጣለች።
ይህች አንደበት ያጣች ሃገር ምንኛ ታሳዝናለች። የሌላ
ውበት በውሸታም ካሜራ ቀርፀው ሌላውን እየኮረኮሩ ለማዬት ሲያራኮቱት ኢትዮጵያ ግን እንዲህ ትንፋሽ ቆራጭ የሆነውን
ውበቷን ቆንጥሮ ለዓለም ህዝብ የሚያሳይላት አጣች
ከጥሩው የተበላሸው የሚበዛበት አለማችን ሳታወቅ ከተበላሽው ጥሩው የሚበዛባት አፍሪካ ግን ጨለማ ዳፍንታም
አህጉር ተባለች
“የሚዲያ ልሳን ያልተፈጠረባት ምስኪን ኢትዮጵያ ስለ ውበቷ ማን የራሱን ጥሎ የእሷን ያስተዋውቅላት ታውቃለህ ሶራ ስለ አፍሪካ ዜና በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ስናይ አንበሳ ሲያገሳ ፏፏቴው ሲንፏፏ... አዕዋፍ ሲበሩ አውሬው ሲተራመስ ይታይና
ኢትዮጵያን የሚመለከት ዜና ሲመጣ ግን ሁሌ ከረጂ ድርጅቶች ዳቦ ሲታደል ማየት ብቻ የሰሃራ በርሃ አገሮች ግመላቸውና አሸዋቸው ሲታይ ኢትዮጵያ ዛፍ አይበቅልባት ፏፏቴም የላት አውሬና አዕዋፍም አይገኙባት የሚባባለው ብዙ ነው።
ለካ ኢትዮጵያ ምንም አላጣች: ሰው ግን ያላት
አይመስለኝም እንደ “ኢብንባቱታ እየዞረ እሚያስተዋውቃት
የላትም..." አለችው እያሸጋገረች አድማሱን አያዬች: ሶራ የሚላት
ጠፋው: ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ስላላቸው ነገር ማለት እንኳን አይችሉም። ብዙ ኢትዮጵያውያን በሌላው ዓለም ይኖራሉ ፧ ግን ስለ አገራቸው ትንፍሽ አይሉም በቅኝ ግዛት የማቀቁት ህዝቦች
አንገታቸውን ቀና አድርገው መዘመር ሲጀምሩ ኢትዮጵያውያን ግን
የተውሶ ካባ ከጃማይካ ተበድረው ትዮጵያዊነታቸውን ከውስጥ
ጃማይካነታቸውን ከላይ ደርበው ተደበቁ። hገሃዱ እውነት ማስመሰሉን መረጡ።' ሶራ አዕምሮው ተረበሸ።
“ተፈጥሮን አትወድም? ሶራ
እስኪ እየው ይህን ውበት?
የሰው ኪነታዊ ጥበብ ምን ብሎ ሊገልጸው ይችላል?" አለችው።
“ያምራል ኮንችት... ብቻ ምን ይሆናል እያለን ያጣን
መሆናችን ያሳዝናል። ለቤት ማስዋቢያ በየግድግዳችን የምንለጥፈው የባህር ማዶ ስዕሉችን ነው። የባር ማዶው ህዝብን ደግሞ አንች እንዳልሽው? “ለመሆኑ አገራችሁ ዛፍ ያበቅላል ወይ! ይሉናል።
“ህይወት ሳናይ ገና የናታችንን ጡት ሳንጠግብ በባህር ማዶህይወት ለሃጫችንን እያዝረበረብን እንነሆልላለን።
“ከዚያ ማነህ? ሲሉን ጸጥ ምን አለህ ሲሉን ቁልጭልጭ በመጨረሻ እነሱም ንቀው እንደ ምራቃቸው ይተፉናል!... የመጣበትን ያላወቀ የደረሰበትን ማን ይጠይቀዋል?.." ብሎ ፀጥ አለ::
ኮንችትና ሶራ እንዲህ በፀጥታ ድባብ ተውጠው ማራኪዋን ተፈጥሮ እየቃኙ የበኩላቸውን ሃሣብ ሲያንሰላስሉ የሆነ ድምፅ
ንፋሱ ይዞ መጣ: እንደገና ድምፁን ጠበቁት ተመልሶ መጣ የወፍ ዝማሬ የወንዝ ኩሉልታ የእፅዋት ሽዋሽዋቴ
አይደለም።የአራዊት ድምፅ… ከሁሉም የተፈጥሮ ቅላፄዎች የተቀነባበረ የሙዚቃ ቃና ነው: ጥዑም ዜማው ይማርካል!
ይስባል! ከተፈጥሮ ጋር ተዋህዶ ልብ ይሰርቃል። ተያዩ ኮንችትና ሶራ: ድምፁ እንደገና እየተስረቀረቀ መጣ። ተጠቃቅሰው ተነስተው ማራኪውን የሙዚቃ ቃና ወደሰሙበት አቅጣጫ ሄዱ።
“ክላሽንኮቭ” መሳሪያውን ጎኑ ያጋደመ ሰው ወይሳውን'
ይነፋል። አዕዋፍ ነፍሳቱ ፀጥ እረጭ ብለው ያዳምጡታል፤ ሶራና
ኮንችትም ከተደበቁበት ሳይወጡ የዜማው እንቅፋት ሳይሆኑ ያን ጥዑም ዜማ በፀጥታ ማዳመጥ ቀጠሉ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ካሎ ጎይቲና አንተህ ይመር ከካሮ ማህበረሰቦች
መንደር አንዷ የሆነችው ቆርጮ ዘግይተው ስለተነሱ ከመሸ በኋላ ደረሱ። ከዚያ ወደ መንደሩ ገብተው ሽማግሌዎች ከፀሐይ ቃጠሎ ከሚጠለሉበትና ከሚወያዩበት ኦሞ ወንዝ ዳር ላይ ካለው ዳስ ሄዱ
ቆርጮ ከፍ ብሎ ሜዳማ ከሆነ ቦታ ላይ ያለች መንደር በመሆኗ ለጥ ያለውን የኦሞን ወንዝ ግርጌው ሌላውን የካሮ መንደር ዱሰን ከቀኝ የሙሩሌን ሚዳ ከግራ ማዶው ደሞ የማሽላ
አዝርዕቱን በስተ ምስራቅ ለጥ ያለውን የማንጎ ፓርክ አረንጓዴን ደን ማየት ስለሚቻል ቆርጮ ቀለል ያለችና የተፈጥሮ ውብት በትርኢት መልክ የሚቀርብባት መንደር ናት።
ከሎና አንተነህ ሽማግሌዎችን መጀመርያ ተጥሎ ጎረምሶችን የሐመሩን ደልቲ ገልዲን አይተው እንደሆን ጠየቋቸው በእርግጥ ከጎረምሶች ጥቂቶቹ እንጂ ብዙዎቹ አያውቁትም የሚያውቁት አላየነውም አ
ሲሉ ሌሎቹ ግን ብዙ የሐመር ወንዶች ከከብቶቻቸው ጋር ሙርሌ ያሉ መሆናቸውን ነገሯቸው።
በእርግጥ ይህ ለአንተነህ እንግዳ አልነበረም ዝናብ ሲቀንስና የግጦሽ ሳር ሲጠፋ የሐመር ከብቶች ፍየሎችና በጎች ወደ ኦሞ ወንዝ ይመጣሉ ኦሞ ወንዝ አካባቢ ሳሩ ጥሩ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ከብቶች የሚጠጡት በቂ ውሃ ከኦሞ ያገኛሉ ስለዚህ የቆርጮ
መንደር ካሮዎች እንደነገራችው ሐመሮች ከብቶታቸው ጋር በሙርሌ ሜዳና በኦሞ ወንዝ ዳር አሉ::
“ታዲያ ምን ይሻላል? አለች ካርለት ከሎንና ጋልተንቤን
የሚሻለውማ ለአንድ ሶስት አራት ቀን እዚሁ አካባቢ
ማጠያየቅ ነው" አላት አንተነህ ይመር ረጋ ብሎ እያንዳንዱን ቃል
እየረጋገጠ፡
ጎይቲ ጆሮዋን በሁለት እጅዋ ይዛ እግሯን አጣጥፋ መሬት ላይ ቁጭ ብላለች:: ደልቲ ቆርጮ መንደር ነኝ ብሎ እንደነገራት ሁሉ ስትመጣ ባለመኖሩና ያለበትም አለመታወቁ ሆዷን አዋለለው ! ሆድ ባሳት...
“እንግዲህ ለዛሬ እዚሁ እንደር ነገና ተነገ ወዲያ ሙርሌ ወርደን እንፈልገውና ተዚያ ወደ ሌሎች የካሮ መንደሮች ዱስና ለቡክ
እንሄድና እንፈልገዋለን!" አለና ጋልታምቤ አያቸው። ሁሉም ተስማሙ፤ ጎይቲ ግን ተነጫነጨች። እሱን ሳታይ ጎኗን ማሳረፍ
አልፈለገችም: ጀግናው እየተንጓለለ እሷ እንቅልፍ እንዴት ያሸልባት? ግን ከአቅሟ በላይ በድምፅ ብልጫ ተሸነፈችና ሁለት
ድንኳናቸውን ዘርግተው ካርለትና ጎይቲ አንዱ ድንኳን ጋልታምቤና ከሎ ደግሞ ሁለተኛው ድንኳን ሊተኙ ተስማሙ።

👍14
ከያዙት ስንቅ ከተመገቡ በኋላ ወደ መንደር ሄደው ቡና ወተት ጠጥተው ተመለሱና ከድንኳናቸው ትይዩ ካለው ሣራማ ቦታ
ቁጭ ብለው ጨዋታ ሲጀምሩ! ጨዋታቸው ያልጣማት ጎይቲ ከነሱ
ፈንጠር ብላ ወደ ወንዙ ሄዳ ቁጭ ብላ መቆዘም ቀጠለች።
“ጋልታምቤ! ለምንድን ነው የሐመር ሴቶች ከወንዶች ጋር ተሰብስበው በጋራ ችግር ላይ እማይወያዩት?" አለችው ካርለት አንተነህ ይመርን ከብት ዘሎ በተጠራበት ስም ጠርታ: እሱም የሰማውን ለማስታወስ አይኖቹን ከደን ከፈት ራሱን ከፍ ዝቅ
ሲያደርግ ቆየና፡-
“አንድ ጊዜ ቦርጆ /አምላክ/ እግሮቹ ጭቃ ውስጥ
ገብተውበት ማውጣት አቅቶት ሲታገል
ቅራቅንቦአቸውን ተሸክመው ወሬያቸውን እየሰለቁ ሲጓዙ ያያቸውና ይጠራቸዋል እባካችሁ ከዚህ ማጥ አውጡኝ ይላቸዋል። ሴቶቹ
ግን ምንም ርህራሄ ሳያሳዩት ይእ!እንቸኩላለን የማነው ቀልደኛ ብለውት ይሄዳሉ። በዚያ ወቅት ቦርጆ አዝኖ ለቁምነገር አትብቁ
ዘላለም እንደቸኮላችሁና እንዳወራችሁ ኑሩ ይላቸዋል አሉ።
“ጥቂት ቆይቶ ደግሞ ወንዶች ለማር ቆረጣ የያዙት እሳት
እንዳይጠፋባቸው እየተቻኮሉ ወደ ዱር ሲሄዱ ቦርጆ ያያቸውና! እባካችሁ ኸዚህ ማጥ አውጡኝ ብሎ ይጣራል የሐመር ወንዶችም እርስ በርሳቸው ይተያዩና የተሽከሙትን አስቀምጠው
እሳቱም ጠፍቶባቸው ቦርጆን ከጭቃው ያወጡታል። በዚህ ወቅት
ቦርጆ ለማህበረሰባችሁ የምታስቡ ችግራችሁንም
የምትፈቱ አስተዋይና የረጋችሁ ሁኑ ብሎ መረቃቸው:
ስለዚህ ከዚያን ጊዜ
ወዲህ ስለ ሐመር ማሀበረሰብ የማሰብ የመወያየትና የመወሰን መብቱ የሐመር ወንዶች ብቻ ሆነ...” አላት።
ይእ! ምነው ካርለቴ ያላመመሽን ባታሺ አሁን ድፍን ዓለም የሚያውቀውን ነገር እየጠየቅሽ ከምታዳምጭ የመኪናሽን
መብራት ተግ አርገሽ አብርተሽ አያ ደልቲን ብንፈልገው ምን
ነበረበት! እንዲያው ምኑን ጨካኝ ልብ ሰጠሽ..." ብላ ጎይቲ ምርር ስትል ካርለት ፈገግ ብላ ጎይቲን አየቻት።
“አይዞሽ! አጠገቡ ደርሰናል!
ከእንግዲህ ጀግናው
አይጠፋብንም!" ብላት ተጨማሪ ጥያቄ ጠይቃ ጎይቲን ላለማስከፋት
አንተነህን ይቅርታ ጠይቃ ወደ ድንኳኗ ሄደች፡ ጎይቲም ትኩር ብላ ተመለከተቻትና፡-
“እስኪ እንዳፍሽ ያድርገው!"ብላ ተከተለቻት።

👍19👎1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
በአትኩሮት ቢያየኝ እኮ በአፌ ልትወጣ የደረሰች ልቤ ስትደልቅ የለበስኩትን ሸሚዝ እያርገበገበችው ነው። በጀርባዬ የሚንቆረቆር ላቤ ለአፍታ ሌሎች ድምፆች ረጭ ቢሉ፤ ከማጅራቴ ወደ መቀመጫዬ ሲወርድ እንደ ዝናብ <ጠብ> ሲል ይሰማ ነበር። ስክሪኑ ላይ ያለውን የራሴን ምስል ሳየው ለመኮሳተር (የማላስታውሳትን የድሮዋን ሜላት ለመምሰል) በታገልኩ ቁጥር የዞረበት ፊት እያሳየሁ እንደሆነ ገባኝ። እጄን የያዘው የጎንጥ እጅ (ገባቶት ነው መሰለኝ) እንደመጭመቅ ሲያደርገኝ ትኩረቴን ከራሴ ፊት ላይ ወደ ኪዳን መለስኩ። መስሎኝ የነበረው ከወንበር ጋር ታስሮ እየተሰቃየ የማየው ወይም ያ ድምፁን የሰማሁት ሰውዬ ግንባሩ ላይ ሽጉጥ ደግኖበት አልያም ፊቱ በድብደባ ብዛት አባብጦ እና በደም ተለውሶ ነገር የማየው ነበር የመሰለኝ። የሆነው ግን ሌላ ነው። ኪዳንና ሰውየው እየተዝናኑ እንጂ አጋች እና ታጋች በማይመስል ሁኔታ አጠገብ ላጠገብ ተቀምጠዋል። ኪዳንን ለመለየት አልተቸገርኩም። የስልኬ ስክሪን ላይ ካለው መልኩ ምንም ለውጥ የለውም። አስቀድሞም በግራ መጋባት የጦዘውን ጭንቅላቴን ልክነት ያጠራጠረኝ የኪዳን መረጋጋት ነው። የሆነ ልክ ሰላም ልንባባል የተደዋወልን አስመስሎ
«ሜልዬ! ደህና ነሽልኝኣ?» አለ። ምንድነው እየሆነ ያለው? ኪዳን አይደለም ይሆን? ሰውየው ቅድም 12 ቦታ ቀነጣጥሼ እልክልሻለሁ ሲለኝ አልሰማም ማለት ነው? አሁንም የጎንጥ እጅ አነቃኝ።
«እኔ ደህና ነኝ! አንተስ?» ይባላል ቆይ? ከአጋቹ ጋር የተቀመጠ ሰው ደህና እንደማይሆን ግልፅ አይደል? እሱ ዝንቡ እንኳን እሽ እንዳልተባለ ሰው ዘና እያለ ታዲያ ምን ልበል? ምናልባት ለእኔ ብሎ ይሆን? እኔን ለማረጋጋት?
«አታስቢ ደህና ነኝ! ከልቤ ደህና ነኝ።» እያለ ምንም ያለመጎዳቱን ሊያሳየኝ ስልኩን እያራቀ ከተቀመጠበት ተነስቶ መላ አካላቱን አሳየኝ። እያባበለኝ ነገር መሰለኝ።
«እንዴት ነው የማላስበው? መዝናኛ ቦታ …… » እኔ ባልገባኝ ምክንያት ለእርሱ ግን ልክ በመሰለ እንድናገር አልፈለገም። ወዲያው አቋርጦኝ
«ሜል እንዲሁ ተጨነቂ ስልሽ ነው። እኔኮ ደህና ነኝ አልኩሽ። » ሲለኝ ጎንጥ ምን እንዳናደደው ሳይገባኝ ተበሳጭቶ ጥርሱን ነክሶ እኔን ባልያዘው እጁ አየሩን በቦክስ ጠለዘው። እየሆነ ያለው ነገር አፍና ጭራው የጠፋኝ እኔን ብቻ ነው? እኔ ሳይገባኝ እሱ የገባው አብረን ከሰማነው የደህና ነኝ መልእክት ውጪ ውስጠ ወይራ አለው? « በኋላ እንገናኝ የለ? እስከዛ ደህና ሁኚልኝ! ደግሞ አምላክን በልመና አታድክሚ!!! የምትችውዪውን አድርጊና በተረፈው አመስግኚው። ያመሰገንሽው አምላክ የጎደለውን ይሞላልሻል።» አለኝ ጭራሽ። የድሮዋ ሜላት ፀሎተኛ እንዳልነበረች ጠፍቶት ነው? ይሄንኑ ዓረፍተ ነገር ግን ከዚህ በፊት የሆነ ሰው ብሎት ሰምቻለሁ!! የት ነው የሰማሁት?
እስካሁን ድምፁ ያልተሰማው ሰውዬ ስልኩን ተቀበለውና በአይኑ እንደመጥቀስ አድርጎኝ ዘጋው!! አፌን እንደከፈትኩ ስልኩ ላይ አፍጥጬ ቀረሁ።
«ይሄ የውሻ ልጅ አውቆታል!» አለ ጎንጥ። መኪና ውስጥ ሆነ እንጂ ሜዳ ላይ ቢሆን <ዘራፍ> የሚል ነው የሚመስለው።
«ምኑን?» አልኩኝ ከድንዛዜዬ ሳልወጣ
«እየቀረፅሽው እንደሆን !» ብሎ ስልኩን እንድሰጠው እጁን ዘረጋልኝ። ስሰጠው ስልኩ ስክሪኑ ቆልፎ ስለነበር እንድከፍትለት መልሶ ሰጠኝ። ያለኝን የምከውነው ምኑም ገብቶኝ አይደለም። ያለውም የገባኝ ነገር የለውም።
«ማን ነበርኩ? ከምን ጋር የተቆላለፈ ህይወት ነው የነበረኝ? የምን ቪዲዮ ነው የምወስድለት? ስልኬ ውስጥ ያለ ነገር ይሆን?»
«ህም! ስልክሽ ውስጥ ልታኖሪው አትችዪም!» ሲለኝ አፌን ከፍቼ ቀረሁ። ስለቪዲዮው ያውቃል!!
«ምን ይመስልሃል ቪዲዮው?»
«እሱን በምን አውቄው! ብቻ ቅሌቱን የተሸከመ ነገር ነው የሚሆን»
ድንዝዝ እንዳልኩ አይኔ ብቻ ሲንቀዋለል ስልኩ ላይ ቅድም የተጫናት ምልክት ስክሪኑን መቅጃ መሆኗን እና ሰውየው እንደመረጃ እንዳንይዝበት ኪዳንን ምንም የተለየ ምልክት እንዳይሰጥ አስጠንቅቆት እንደሆነ እርግጠኛ ሆኖ ከነገረኝ በኋላ እኔን ረስቶ የተቀዳውን ቪዲዮ እየደጋገመ ወደፊት ወደኋላ ቅርብ …. ራቅ እያደረገ ያያል። እኔ ደግሞ ዝም ብዬ እሱን አየዋለሁ።
«በስተመጨረሻ ልመና አታብዥ ያለው ነገር ያላስፈላጊ ቦታ የተዶለ አይመስልሽም? ላንቺ የሚያስታውስሽ ነገር አለ?» አለኝ አሁንም ከስክሪኑ አይኑን ሳይነቅል።
«የሆነ ሰው ሲለው የሰማው ይመስለኛል። አላውቅም!! ራሴም እለው የነበረ ነገር ይመስለኛል። ምንም መጨበጥ አልቻልኩም።» ስለው እንባዬ ዓይኔን ሞልቶታልኮ እሱ ግን አላየኝም። ቪዲዮውን ኪዳን ስለምስጋና ያነሳበት ጋር አቁሞ
«ተመልከች እዚህ!!» ብሎ ሰውየውን ጠቆመኝ « ልክ ኪዳን ሲናገር ፊቱ አንድ አፍታ ይቀየራል። ተመልከች! ያ ማለት ይህ መስመር እንዲናገር ከተፈቀደለት ውጪ ነው ማለት ነው! ሊገልጥልሽ የፈለገው አንድ መልእክት ቢኖረው ነው።»
«ጎንጥ?» አልኩት ፍስስ ባለ ድምፅ
«ወይ!» አለ አይኑን እዛው እንደሰነቀረ
«ማ ነ ህ? » አልኩት እንባዬ አብሮ ከቃላቱ ጋር ዱብ ዱብ እያለ። እዛ ነጥብ ላይ ጎንጥ ዘበኛዬ ብቻ እንዳልሆነ ገብቶኛል። የሚያስለቅሰኝ በትክክል ምን እንደሆነ እንጃ።
«ኸረ በመድሀንያለም?! » አለ ደንግጦ የሚያደርገው ጠፍቶት ። እጄን ሊይዘኝ እጁን ሲሰድ መንጭቄ ቀማሁት
«እንዳትነካኝ! ሁሉንም ነገር ታውቃለህ! ይሄን ሁሉ ጊዜ ስሰቃይ እያወቅክ ምንም እንደማያውቅ አብረህ ስታፋልገኝ ነበር። ሰውየው ያወራው ሁሉ ነገር ገብቶሃል። ንገረኝ አንተም የእነሱ ወገን ነህ? ምን ፈልገህ ነው?» እንባዬ ባይቆምልኝም ሰውነቴ ሲቆጣ ፣ ደሜ ሲሞቅ ይታወቀኛል።
«መድሀንያለም በሚያውቀው እንደሱ አይደለም!! አንች ያሰብሽውና የእኔ ድርጊት ለየቅል ነው!! ሀሳቤ ጠላትነት ከነበር ምን እጠብቅ ነበር? ከጠዋት እስከማታ እጀ ላይ አልነበርሽ?»
«አላውቅም! የሆነ የምትፈልገው ነገር ይኖራላ!!» ተነስቼ ከመኪናው ወረድኩ። ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ድረስ ንዴቴ ያጨሰኝ ጀመር። የመኪናውን ጎማ በሃይል መጠለዜን ያወቅኩት የእግሬን አውራ ጣት ሲያመኝ ነው። የሆነ ውስጤ ተኝቶ የነበረ አውሬ የነቃ ይመስል የምቦጫጭቀው ነገር ፣ ቁጣዬን የምወጣበት ነገር ፈለግኩ። እሪሪሪ ብዬ መጮህም ፈለግኩ። የመኪናውን ኮፈን በቡጢ እየነረትኩ ማቆም እፈልጋለሁ ግን እጄን የምሰነዝርበት ቁጥር በጨመረ ልክ ሰውነቴ እየረገበ ፣ ቁጣዬ እየበረደ ስለተሰማኝ አላቆምኩም። ከመኪናው ወርዶ መምጣቱን ያወቅኩት አጠገቤ መጥቶ ሁለቱን እጄን ለቀም አድርጎ ሲያስቆመኝ ነው።
«አትንካኝ አልኩኮ!! » ብዬ ከመጮሄ እኩል በምን ቅፅበት እንደሰነዘርኩት ያልተቆጣጠርኩት ለቡጢ የተጨበጠ እጄ ጉንጩ ላይ አርፏል። ያደረግኩትን ሳውቅ ደንግጬ የመታሁበትን እጄን እንደበዓድ እጅ አየሁት። ከመኪናው ኮፈን ድብደባ ይሆን ከእርሱ ጉንጭ እጄ በልዟል። ወደኋላ ዞሮ አፉ ውስጥ የሞላውን ደም ከተፋ በኋላ ወደ እኔ እየዞረ በሱ ብሶ ይጮህ ጀመር

👍27
« ከበረደልሽ ድገሚኝ!! እ? በያ!» እያለ ለፀብ ይጋብዘኛል። ትቼው ወደመኪና ልገባ ስል እየተከተለ ሆነ ብሎ ይገፋፋኛል። «ይህችን ታህል ነው የተናደድሽብኝ? ለዝህችው ነው የጎፈላሽው?» ሲለኝ እንዴት ዥው ብዬ እንደዞርኩ አላውቀውም። እጄን ስሰነዝር በሚያስደነግጥ ፍጥነት በመዳፉ ቀለበው። ያልቆጠርኩትን ያህል ጊዜ ተከላክሎ አንዴ ነው አጓጉል ያገኘሁት። ዋጥ አደረጋት!! ቁጣዬ ረጭ ማለቱን ያወቅኩት ይሄኛው የድሮዋ ሜላት ማንነት መሆኑን መገንዘብ ስጀምር ነው።
«ደግ! አሁን ከሰከንሽ እየተጓዝን ስለኪዳን እናውጋ?» አለኝ የመታሁትን ጉንጭ እያሻሸ ወደመኪናው እየገባ
«ጉንጭህን አገላብጠህ ስለሰጠኸኝ እንዳምንህ ነው የምትጠብቀው?»
«እና ምን ይሁን ነው የምትይ? እዚሁ ቁመን ይምሽ? አንዱን አካሉን እዚሁ እንዲልኩልሽ ነው ያሰብሽ?» እየጮኸብኝኮ ነው። ከቃላት ሁላ በላይ ሆነብኝ እና አፌን ከፍቼ አፍጥጬ አየው ጀመር
«አንተ ግን የምርህን ነው? ካንተም ብሶ …….. » አልጨረስኩትም እየሮጥኩ መኪና ውስጥ ገባሁና ስልኬን አነሳሁ። አጎቴጋ ደወልኩ። ተከትሎኝ ገብቶ የማደርገውን በትኩረት ያያል።
«አጎቴ እናቴን አገናኘኝ እስቲ የሆነ ሳልጠይቃት የረሳሁት ነገር ትዝ አለኝ።» አልኩት
«እናቴ ? በቀደም <አምላክን በልመና አታድክሚ!!! የምትችውዪውን አድርጊና በተረፈው አመስግኚው!! ። ያመሰገንሽው አምላክ የጎደለውን ይሞላልሻል> ብለሽኝ ነበርኣ?»
«አዎ የእኔ አበባ ምነው?»
«አጎቴንም እንደዛው ስትዪው ሰምቻለሁኣ?»
«ሁሌምኮ የምለው ነገርኮ ነው ልጄ?» አለች ግራ እየገባት።
«የተለየ ትርጉም ነገር አለው እንዴ?»
«ኸረ ምንም ቅኔ የለውም ልጄ! ምን ጉድ ነው?»
«እንዲሁ ነው የሆነ ሚስጥር የያዘ አረፍተነገር ይመስል ውስጤ ተመላለሰ። ድንገት ሌላ መልዕክት ካለው ብዬ ነው።»
«በፍፁም! ሁሌም ሰዎች እጅ እግራቸውን አጣጥፈው በቀላሉ መስራት በሚችሉት ነገር ሁሉ ሳይቀር ፈጣሪን በልመና ሲያደክሙ እንደዛ እላለሁ። »
«እሺ በቃ እናቴ» ስልኩን ዘግቼ አስባለሁ። ምንም ሳይለኝ መኪናውን መንዳት ቀጠለ።
«እኔን አይደል የሚፈልጉት? እኔ ሄድላቸዋለሁ! እኔን የሚያደርጉትን ያድርጉና ወንድሜን ይለቁታል።» አልኩኝ ለራሴ ያሰብኩትን ድምፄን አውጥቼ እየተናገርኩት
«ህእ! አንቺን ቢፈልጉ እስከዛሬ ላንቺ የሚሆን አንድ ጥይት ጠፍቷቸው ይመስልሻል? ካንቺ በላይ የያዝሽባቸውን መረጃ ይፈልጉታል።» አለ <ቂል ነሽ እንዴ?> በሚል ለዛ
«ሊገድሉኝ ሞክረው የለ?»
«እኔን ከጠየቅሽኝ በፍፁም እነሱ አይመስሉኝም!!»
«እሺ ያለውን ቪዲዮ የምናገኝበት ፍንጭ ታውቃለህ? መቼም የማታውቀው ነገር የለም!» አልኩት አፍንጫዬን እየነፋሁ።
«አላውቅም!!» አለኝ በመድከም አይነት።
«ስለዚህ እሄዳለሁ። አትከተለኝም። እውነቱን እነግራቸዋለሁ።» አልኩኝ ፍርጥም ብዬ
«የማይደረገውን!!» አለ ኮስተር ብሎ

👍13❤10
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ኮንችትና ሶራ የሰጎን ላባ የተሰካበትን የራስ ጌጥ(ጶሮ) እንደ አቦ ሸማኔ
አይን አሸጋግሮ እየተንተገተገ የሚመለከተውን አይኑን የተተለተለ ሳንቃ ደረቱን እየተመለከቱ ከንፈሩን አሞጥሙጦ የሚያሽለከልከው ትንፋሹ ከፍ ዝቅ በሚሉት ጣቶቹ እያንኳለለ የሚያጣው ስሜተ ሰላቢ ዜማውን ሳይንቀሳሱ ሲያዳምጡ ወይሳ ተጨዋቾቹ ድንገት ዜማውን ቀጥ አደረገና መሳርያውን አንስቶ ሲያቀባብል ሶራና ኮንቺት
ድንግጥ ብለው ሲመለከቱ ድው አድርጎ ሲተኩስ አመዳቸው ቡን ብሎ ነፌሴ አውጪኝ መሬት ላይ ሲንበለበሉ እንደገና ተኮሰ።
ከዚያ ለጥቂጥ ሰአታት ከመሬቷ ጋር ተላትመው ጠበቁና ቀና ብለው ሲመለከቱ ሰውየው ኦሞ ወንዝ ዳር ሄዶ ተረጋግቶ ወንዝ ዳር ሄዶ ቆሟል ኮንቺት እየተሳበች ወደ ሶራ ተጠግታ
"ለምን ተኮሰ? አለች ሶራን።
"አልገባኝም"
"አይቶን ይሆን?"
አይመስለኝም ቢያየን ወይንም ድምፅ ሰምቶረ ቢሆን ኖሮ በሁኔታው ማወቅ እንችል ነበር።
"እሱስ ልክ ነህ ቢገርመኝ እኮ ነው ተረጋግቶ መቆሙም ለጠየቅሁት ጥያቄ ፍንጭ ሰጪ አይደለም ስትለው ከኦሞ ወንዝ ማዶ ድምፅ ተሰማ ሰባቶ ጎረምሶች ናቸው። ወደ ወንዙ ሲጠጉ
"ፃሊ!” አላቸው በካሮኛ ሰላም ናችሁ ለማለት:
'ፃሊና..." አሉትና አምስቱ ወንዙ ዳር እንደቆሙ ፤ ሁለቱ ዳር ላይ የቆመች ቀጠን ብላ ረዘም ያለች የእንጨት ታንኳ ላይ
ወጡና በረጅም ዘንግ ውሃውን ቁልቁል ሲገፉት ታንኳዋ እንደ ውሃ
እናት ውሃውን ወደ ጎን እየሰነጠቀች መጣች::
ለካ የተኮሰው እነሱን ለመጥራት ነው:: ጥሪ በተኩስ አይገርምም!” ስትል ሶራ በአድናቆት ራሱን ወዘወዘ።
“እነሱ ግን እነማን ናቸው?"
"አላውቅም ኮንችት ብናነጋግራቸው ይሻላል?" ሲላት ወዲያው ከተደበቁበት ወጥተው ወደ ሰውዬው ሲጓዙ ፊቱን ዞሮ
የቆመው ሰው የሰው ዳና ሲሰማ ከመቅፅበት መሳሪያውን ከትከሻው
አውርዶ፡-
“ከጠን ማሲዲ" ብሎ መሣሪያውን አቀባብሉ ደገነባቸው።
“ኖት አሱስቴ" አለች ኮንችት በስፓኒሽ እጅዋን እያወዛወዘች ተረጋጋ ለማለት:
ባለመሣሪያው ትኩር ብሎ ሲያያቸው ቆየና “ነጋያ! አለ
ከተቀመጠበት ተነስቶ መሳሪያውን ወደ ትከሻው እየመለሰ: ሶራ ለሰላምታ አፀፋውን መለሰ። “...ሐመር አፎ ዴሲቲኒ" አለው ባለመሣሪያው ሐመርኛ ትችላለህ ለማለት።
ሶራ ፈገግ ብሎ “ሊካ ሊካ ቂንሲዲ...” (ትንሽ ትንሽ
እችላለሁ) አለው። ባለመሳሪያው ፈገግ አለ: ያኔ ነብርነቱ ተለውጦ
እንደ ድንቡሽዬ ህፃን ፈገግታው የሚማርክ ሆነ
ባለመሳሪያውና ኮንችት ከሁለቱ የታንኳዋ ቀዛፊዎች ጋር ተሻግረው ሲጠብቁ ሶራ ጀልባዋን ይዞ ሄደና በጀርባቸው አዝለው
ጀልባዋን ከአምስቱ ጎረምሶች ሁለቱ እየተሳሳቁ ተሸክመው ጫካው
ውስጥ ገቡና በመስመር ሆነው በትላልቅ የግራር የኮሶ... ዛፍ ውስጥ ለውስጥ ትንሽ እንደተጓዙ ኮንችትና ሶራ ዛፍ ላይ እንደ ጦጣ የሚንጨዋለሉ ልጆች አዩ: ቆይቶ ደግሞ በቋንቋቸው ቶሎ ቶሎ
የሚናገሩ ልጃቸውን በቆዳ ብብታቸው ስር ያዘሉ እናቶችና ሽምገል
ያሉ ወንዶችን አዩ።
ጨቅላ ህፃናት ዛፍ ላይ በቆዳ ተንጠልጥለው አንዳንዶቹ ተኝተው እየተቁለጨለጩ ሲወዛወዙ እያዩ እንደ ሄዱ ከርቀት ላይ
የወፍ ጎጆ የሚመስል የኤሊ ቅርፅ ያለው ጎጆ ቤት ተመለከቱ።
ኮንችትን ሲያዩ ህፃናት ወላጆቻቸው ጉያ እየገቡ ወደ መንደራቸው እየሮጡ አለቀሱ: ለኩዩጉ ህፃናት አስፈሪው አውሬ ቀላ ያለ ልብስ ለባሽ ሰው ነው። ከፍ ያሉት ግን የመጣው ይምጣ ብለው በቋንቋቸው ሰላም ቢሏትም ፍርሃታቸው ግን ያስታውቃል: ለጊዜው
ሰላምታቸውን ልብ ብላ አልተከታተለችም ነበር ድንገት አንድ ሽማግሌ፡-
“አሹቃ” ሲሏት አያቷ የነገራት ሰላምታ ትዝ አላት:
ኮንችት አያቷ የሚጠቀምባትን መቀመጫ የመሰለች ሁሉም
ሽማግሌዎችና ወንዶች ይዘው አየች:: ሶራን ዘወር አለችና ምን የሚባሉት ማህበረሰቦች ናቸው?" አለችው ማፕ ላይ ያየችውን ስም ለማስታወስ እየሞከረች:: ሶራ መጀመሪያ ያዩትን ባለ ዋሽንት ጠየቀው።
ሙጉጅዎች ናቸው። እነሱ ግን ራሳቸውን ኩዩጉ ነው
የሚሉት አለው ነገራት ሶራ ለኮንችት። ማፕ ላይ መጉጅም ሆነ ኩዩጉ የሚል እንዳላየች እርግጠኛ ነች: ለማረጋገጥ ግን ወዲያው
ማፕዋን ዘርግታ አየች፤ ሁሉም እሷ ላይ አፈጠጡባት። ማፑ ላይ
የሉም። ካርታው ላይ አየች የሉም፤ ይበልጥ ደነቃት።
ኦኗኗራቸውም ልዩ ነው ፤ የጫካና የወንዝ ዳር ሰዎች: ከመንደሩ እንደደረሱ ሰዉ በአድናቆት ቆሞ አያቸው: ህፃናት ራቅ ብለው ሽሽተው ያያሉ:: አንዱ 'መጡላችሁ' ሲል ሌሎች ህፃናት ደግሞ
እየተሯሯጡ በመላቀስ ይጯጯሃሉ…..
ኮንችት ከጀርባዋ ያዘለችውን ጓዟን አውርዳ ተለቅ ተለቅ ያሉ የአያቷን ፎቶ አወጣች: የዘጠኝ ሰዓት ፀሐይ አሁንም ማቃጠሏ
እንብዛም አልቀነሰም:
ፎቶውን የያዘውን እጅዋን ወደ ህዝቡ ዘረጋችው። ፈሯት፤በምልክት እንኩ' አለቻቸው: ትክ ብለው እያዩ ዝም አሏት ከዚያ ባለዋሽንቱ ውሰዱ' አላቸው በሐመርኛ።
ሶራ ደስ አለው የራሳቸውን የሆነውን ቋንቋ ሲናገሩ
አንድም ቃል ሊገባው አልቻለም ነበር ሐመርኛ ከቻሉ ግን እሱም
ሊያናግራቸው ይችላል። ኩዩጉዎች ግን ሐመርኛን ብቻ አይደለም የሚችሉት። ሙርሲኛ ኒያንጋቶምኛም ይችላሉ።ስለዚህ ሶራ
በሐመርኛ፦
“ውሰዱና እዩ ችግር የለም” አላቸው። አሁንም ዝም ብለው ኮንችትን ሲመለከቷት ቆዩና አንዱ
ሽማግሌ ሌላውን በጆሮው አናገረው ከዚያ ብድግ ብሎ መጣና ተቀበላት።
ፎቶውን ዘቅዝቆ ስለያዘው ኮንችት አስተካክላ ሰጠችው ሽማግሌው ቀረብ እራቅ አድርጎ አየውና በቋንቋው የሆነ ነገር
ተናግሮ ወደ ሀዝቡ ሲጠጋ ለማየት ህዝቡ እንደ ንብ ዙሪያውን ከበበውና ሁካታ ሆነ: ማንም ሌላውን አያዳምጥም።
ከዚያ ሁሉም እነ ኮንችትን ጥለው እንደ ድንጉላ እምም.. እያሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ተሯሯጡ: ኮንችትና ሶራ እርስ በርስ
ተያዩ ህዝቡ የሄደበትን ምክንያት ግን ከመካካላቸው ሊመልስ የቻለ አልነበረም።
አንድ ጎጆ ቤት ሲደርሱ ሁሉም ቆሙ። ከውስጥ የሆኑ ሽማግሌ አንጀታቸው ካጥንታቸው ጋር የተጣበቀ አጎንብሰው ወጡ ህዝቡ አሁንም ክብብ አደረጓቸው።
ከዚያ እንደገና ሁካታ ሆነና ጎረምሶች እየተሯሯጡ ርቀው ሄዱ። ፎቶዎችም በልጥ ታስረው ሽማግሌው ከወጡበት ጎጆ ፊት
ለፊት ተንጠለጠሉና ሴቶች ሰማይ ሰማይ እያዩ እልልታውን አቀለጡት ወንዶች እየዘለሉ ጭፈራ ጀመሩ።
ኮንችትና ሶራ እንደገና ተያዩ። ምን እየተሰራ እንደሆነ ማወቅ ተሳናቸው: ባለ ዋሽንቱን ጠየቁት፤ መልስ አጡ። ከዚያ
አራት አምስት መሳሪያ የያዙ ሽቅብ ተኮሱ።
ኮንችትና ሶራ ደነገጡ፡ “ምን እየሰሩ ነው ሶራ?" አለች
የሶራን ትክሻ እየወዘወዘች
በፍርሃት: ሶራ ትከሻው ከፍ ዝቅ አድርጎ አላውቅም አላት በምልክት። ሰው ከየጫካው ተሰባሰበ !
ጥሩንባው እየተነፋ እልል መባል ጀመረ።
ጫካ የሄዱት ጎረምሶች በሾርቃ የሆነ ነገር ይዘው
እየተሯሯጡ መጡ የደከማቸው አይመስሉም የግንባራቸው ደም
ስር ግን ውሃ እንደሽረሸረው የዋርካ ስር አበጥ አበጥ ብሎ በየአቅጣጫው ተጋድሟል። እንደ ተመለሱ ከህዝቡ መሃል ገቡ
ከሌላ ጎጆ ደግሞ ማር የያዘ ትልቅ ቅልና ውሃ ሌሎች ጎረምሶች አመጡ። ውሃውና ማሩ ተቀላቀለና በእንጨት ተማሰለ።
ከዚያ ጥሩንባው እየተነፋ እልል እየተባለ እየተጨፈረ... ሁሉም የሉካዬን ስም እየጠሩ ሰማይ እያዩ ቆዩና ከሲታ ሽማግሌውን አስቀድመው ሶራ ኮንችትና ባለወይሳው ወደ ቆሙት እያሸበሸቡ
እየዘለሉ ጡሩንባው እየተነፋ መጡ።

👍18😢2👏1
ሽማግሌው ወደ ባለወይሳው ጠጋ ብለው በትልቅ ሾርቃ የተጠሰጠውን ብርዝ ጉንጫቸው እስኪነፋ የያዙ “ፕስስ…” ብለው
ረጩበት
ህዝቡ እልል ይላል ይጨፍራል ዳንኪራ ይረግጣል…ሰማይ ሰማይ ያያል።
ሽማግሌው ወደ ኮንቺት ደግሞ ጉንጫቸውን በብርዙ
ነፍተው ተጠጉ ኮንቺት ምን እንደሚመጣ አታውቅም ግራ ተጋብታለች
ፕስስ ብለው ፊቷ ላይ ብርዙን እንደ ወጨፎ ዝናብ
ሲያረከፈክፉባት እጆችዋ ለመከላከል ዘርግታ። ወጀ ኋላዋ እያፈገፈገች የጩኸት ድምፅ አሰማች:: ህዝብ ዋ…” ብሎ ሳቀባት።
ሽማግሌጡ ወደ ሶራም ሄዱ…
ምንድን ነው ሶራ አለችው ሽማግውና ህዝቡ
እየጨፈሩ ጎጆ ላይ ወደ ተንጠለጠለው የሎካዬ ፎቶ ሲሄዱ:: ሶራ ባለ ወይሳውን ሊጠይቀው ሲሄድ በርቀት ሽማሌው በሎካዬ ፎቶ ላይ
ፕስስ…” እያሉ ብርዙን ሲያርፈክፉበት አየች:
ህዝቡ እንደገና ሽማማሌውን ተከትሎ ወደ እነ ኮንችት መጣ: ኮንችት ልትሮጥ አሰበች: የልጅ ሃሣብ ሆነባት ሃሣቧ
አታመልጥም:: እየጨፈሩ አየሳቁ... ጦራቸውን እየሰበቁ ከሚዘሉት
በታምርም አትጠፋም::
ሽማግሌው በሾርቃ ያለውን ብርዝ ለባለዋሽንቱ ሰጡት:
ስምጥጥ አድርጎ ጠጥቶ መልሶ ሰጣቸው:: ለኮንችትም አቀበሏት
በሚንቀጠቀጠው እጅዋ ተቀብላ አጮልቃ እያየች ፉት አደረገችና እየፈራች
እጅሞን ዘረጋች: ተቀብለዋት ወደ ሶራ ሄዱ.
ጭፈራው ዝላዩ ዘፈኑ… ጥሩንባው ተኩሱ ቀጠለ
ምንድነው ሶራ? ተኩሱን በሰማች ቁጥር የምትናጠውና
የምትንቀጠቀጠው ኮንችት ደግማ ጠየቀችው።
በኩዩጉ ባህል እንግዳ ሲመጣ ብርዝ ተበጥብጦ ፊቱ ላይ ይርከፈከፍና ብርዝ እንዲጠጣ ይደረጋል:: እንግዳውን እንዲህ ብርዝ
አጠጥተው ሲቀበሉት ብዙ ሽንት ይሸናል: ያ በየጫካው ያለው ቀፎአችን በማር ይሞላል ብለው ያምናል" አላት ከባለወይሳው ጠይቆ
የተረዳውን ። ይህን ሲባባሉ ኩየጉዎች ተመልሰው መጡ። ጎረምሶች ጫካ ገብተው ያመጡትን ሾርቃ ሽማግሌው ይዘዋል: ሽማግሌው ቀጥታ ወደ ኮንችት ሲመጡ ኮንችት ክው አለች: መንቀሳቀስ
ተሳናት ሽማግሌው አጠገቧ እንደደረሱ ከሾርቃው ውስጥ ካለው የጎሽ
እበት አውጥተው በፍርሃት እንሶስላ ከመሰለው ጉንጯ ላይ ሲቀቧት ነፍስና ስጋዋ እንደተለያዩ ሁሉ ሽቅብ ነጠረች እልልታ ጭፈራ ሆነ።
ሽማግሌውና ህዝቡ የአያቷ ፎቶ ወደ ተንጠለጠለበት ጎጆ ተመሰሱ። ጭፈራው ይበልጥ ደመቀ፡ “ሉካዬ.. የሚለው ጥሪ በረከተ ወደ ጫካው አቅጣጫ ተኩሱ በዛ።
ሶራ ግራ ገብቶታል! ኮንችትን ሊያረጋጋት ግን ፈልጓል። እሷ እሱ ላይ እሱ ደግሞ ባለወይሳው ላይ ቢያፈጡም በቂ መልስ
አጥቷል: ስለዚህ ወደ አንዱ ኩዩጉ ፈራ ተባ እያለ ተጠጋና አናገረው: ከዚያ ፈገግ ብሎ ወደ ኮንችት ተጠጋ: ኮንችት ሊነግራት
የፈለገው ነገር እንዳለ ገምታለች: ከህዝቡ ላይ ግን አይኗን ማንሳት አቃታት:: ፈርታለች! ስለዚህ አይኗን አሸጋግራ እንደተከለች ጆሮዋን ደቀነችለት።
“ሎካዬ ተመልሶ መጣ ይላሉ" አላት:: ሶራ ያነጋገረው ኩዩጉ ትንሽ ራቅ ብሎ በትዝብት ያያቸዋል:
“ለምን?”
"ፎቶውን አይተው"
""ፎቶውን ብቻ አይተው?"
"አዎ"
“እንዴት? ስትል አጠገባቸው ቆሞ የነበረው ጨዋታቸውን እንዳወቀ ሁሉ በክፍት ሾርቃ ውሃ ሞልቶ ወደ ኮንችት ተጠጋ
በምልክት ጠጋ በይ አለና ሾርቃው ላይ አንገቷን ጎንበስ አደረገላት:
ከዚያ ደሞ ራቅ እንድትል አድር ሳቀ: አልገባትም! ሶራን የርዳታ እይታ አየችው::
ቅድም ምን ነበር ያለኝ መሰለሽ ውሃ ዳር የቆመ ሰው ምስሉን ውሃ ውስጥ ማየት ይችላል: ሰውዬው ከሌለ ግን ምስሉም
ውሃው ላይ አይኖርም። እኔ ኦሞ ወንዝ ስለሄድኩ ውሃው ላይ ማን ምን ሊያየው ይችላል:: የሎካዬን ምስል ያየነው እሱ ሰማይ ላይ
ስላለ ነው። እሱ ሰማይ ላይ ባይኖር ምስሉ አይኖርም። ሎካዬ ሰማይ ላይ ሆኖ መልእክተኞችን እኛ ዘንድ ላካችሁ ለዘመናት ጠፍቶ ኑሮ አሁን መምጣት ሲችል ከመምጣቱ በፊት መልዕክተኛ መላክና
'ተዘጋጁ' ማለቱ የአባቱን ባህል አክባሪ በመሆኑ ነው።
“እኛም ዛሬ ምስሉን አይተን ደስ ብሎናል። በሳልስቱ ደግሞ እሱ ሰማይ ሆኖ አይቶን ከተደሰተ ይመጣል። ስለዚህ እሱን ለማስደሰት እንጨፍራለን ሴቶች እልል ይላሉ...እንዲያውም
የኩዩጉ ሽማግሌዎች ሎካዬ የጠፋውን ነጭ እባብም ይዞልን ይመጣል እያሉ ነው' አለኝ አላት ሶራ ለኮንችት:
"የምን ነጭ እባብ?” ተገርማ ጠየቀችው:
ፎቶው ላይ ሎካዬ በአንገቱ የጠመጠመውን ነጭ የአንገት መጎናፀፊያ አይተው የጠፋው ነጭ እባብ ነው ይላሉ: ነጩ እባብ የስላም ምልክታቸው ነው። እሱ ስለጠፋ የኩዩጉ ህዝብ ግጭት
እየበዛበት ሰላሙ እየደፈረሰ ነው ብሎ ነገረኝ" አላት:
“ምን የሚደንቅ ነገር ነው፡ ፒካሶ አጥፍቷላ?
“ለምን? ሶራ ግራ ተጋብቶ ጠየቃት።
“የሰላም ምልክት ነጭ እባብ የነበረውን በነጭ እርግብ የቀየረው" አለችውና እንደገና ኮስተር አለች: ህዝቡ ከፎቶው ፊት
ለፊት ይጨፍራል! እልል ይላል…..
“ሶራ እባክህ ሎካዬ ሞቷል በላቸው! ዋሾ እንዲያደርጉኝ
አልፈልግም? አለች በመማፀን እይታ እያየችው ሶራ በእሽታ አንገቱን ነቅንቆ ለዩጉው የማህረሰብ አባል ነገረው! ኩዩጉው ግን
ሶራ የሚለውን በጥሞና አዳምጦ የሆነ ነገር ተናግሮ ሲስቅ ኮንችት አየችው
ወዲያው አያቷ ሎካዬ ትዝ አላት። አየችው በእዝነ
ህሊናዋ በልጅነቷ ቃል ያስገባትንም አባባሉን ሰማቸው! “…ሞቷል
አትበያቸው ስንት ጊዜ ለኔ ይዘኑ ለኔ ያልቅሱ! አለ! በያቸው! ያላት ታወሳት:
ይህን ስታስብ ሶራ ወደሷ መጣ
“ጠየቅኸው?” አለችው በውሳኔዋ እየተፀፀተች።
“አዎ ግን ሳቀብኝ። ሎካዬ እኮ ሞቷል...ስለው የሞተ
ሰው ምስል የለውማ! ልጅ ነህ ልበል! ምስሉን እያየኸው... ብሎ
ወደ ፎቶው አመልካች ጣቱን ቀስሮ አየኝ" አላት እሱም እየሳቀ
“ሶራ የመንደሩ ስም ማነው?''
“ኩችሩ!” አላት
“ምን?"
"ኩችሩ”
"ኩችሩ አዎ! አያቴ መንደሬ ኩችሩ ነው' ብሎኛል።"
እንደገና ሎካዬ ታወሳት:
“...መጠራጠር አያውቁም የሚጠራጠር ራሱ ዋሾ ነው...ሉካዬ አልሞተም በያቸው... ቆይተሽ ደግሞ እኔ ነኝ ሎካዬ በያቸው... ያምኑሻል.. አያቷ ያላት ትዝ አላት።
“ለካ አያቴ ከኒህ የዋህ ህዝቦች መሃል ወጥቶ ነው
ከተበከለው አለም ሲደናበር የኖረው የአያቷ ሐዘን ነፍስ ዘርቶ ሲንቀሳቀስ ታያት
“በኩችሩ ጫካ ክንፍ ውስጥ እንደ ጫጩት እየተሰገሰጉ
ሙቀታቸውን እየተጋሩ ይኖራሉ..." ያላትም ተሰማት እንደገና።
ይጨፈራል፣ እልል ይባላል... ኮንችት የሚደረገውን ሁሉ
ታያለች። በህልም ዓለም እውን ወይንም በውን ዓለም ህልም ውስጥ ያለች መሆኗን ግን ማወቅ ተሳናት ተኝታ ነቃች! ነቅታ
አንቀላፋች!
እልል... ቱቱ... የኩዩጉዎች የትክሻ ላይ ክራር ዱሩሩ.."
ይላል። ደስታና ግራ መጋባት የኩችሩን መንደር ያስፈነጥዟታል።...

👍35🥰2👏1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ስድስት )
(ሜሪ ፈለቀ)
«ብዙውን አላውቅም። እየሆነ ስላለው ነገር ምንም እውቀት እንደሌለሽ ያወቁ ሰዓት ግን እንደሚገድሉሽ በአስር ጣቴ ፈርማለሁ። ስራ አቀለልሽላቸው!! አንቺም ከእነርሱ እኩል የሚፈልጉትን ማስረጃ የት እንዳለ የማታውቂ ፣ ገና እያፈላለግሽ እንደሆነ ልቦናቸው ካወቀ ምን ትሰሪላቸዋለሽ?»
«እኮ ያ ማለት ጠላታቸው አይደለሁም እኔን የሚያሳድዱበት ወንድሜንም የሚያፍኑበት ምክንያት የላቸውም!»
«አንችዬ ጅልም ነሽሳ? ያስታወስሽ ማግስት እንደገና ራስምታታቸው እንደምትሆኚ እያወቁ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልሽ! ብለው እንዲሸኙሽ ነው የምታስቢ?»
«አንተስ የሆነ ቀን ማን እንደሆንክ እንደማስታውስ ግን በሀሳብህ ሽው ብሎ ያውቃል??»
«አይከፋኝም ዓለሜ!! ያኔ ከምታውቂኝ በላይ አሁን ነውስ ምታውቂኝ !!» አለ ዘወር ብሎ አይቶኝ መልሶ «ያለፈውን ብነግርሽ ታምኚኝ ይመስልሻል?»
«ስላልነገርከኝም እያመንኩህ አይደለም። ቢያንስ አውቄው ራሴ ልወስን!! ካልሆነ ግን እንድች ብዬ እግሬን ካንተጋ የትም አላነሳም!»
«አራት አስርት ዓመት እዝህች ምድር ባጀሁኮ!! ምኑን አውግቼሽ ምኑን ትቼው እዘልቀዋለሁ? የትየለሌ ነው!!» አለ በንግግሩ ብዙዙዙ እያስመሰለው።
«እኔ የ40 ዓመት ታሪክህ ምን ያደርግልኛል? እኔ ደጅ ያደረሰህን ታሪክ ነው የምፈልገው። አንድ ዓመት ያከረመህንም!!» በረዥሙ ተነፈሰ። ሁል ጊዜ እንደሚያደርገው። ሊነግረኝ ነው ብዬ ስጠብቅ አጀማመሩን አርዝሞ የቆመ ጆሮዬን ኩም እንደሚያደርገው
«አንዱ ከሌላው ይተሳሰራል። ሁሉን ካልነገርኩሽ ቁንፅል ነው የሚሆን። እንደው በጥቅሉ ደጅሽ ያመጣኝ እንዳልኩት ሰው ነው። ደጅሽ ያቆየኝ አንድ እለት የዋልሽልኝ ውለታ ነው!» ብሎ የማንነቱን እንቆቅልሽ ሁሉ የፈታልኝ ይመስል ጭጭ አለ። ተናደድኩ።
«ኸረ? ውለታ? እያዋረድኩህ እንኳን ደጄ የነበርከው ለአንድ እለት ውለታ ነው? ትንሽ እንኳን የሚመስል ነገር ብታወራ ምን አለበት? ማስታወስ እንጂ ያቃተኝ ጡጦ የሚጠባ ህፃን እኮ አይደለሁም!!»
«ምንአለበት? የሰው ልጅ ለአንዲት ቀን በደል እድሜውን ሙሉ ቂም ይዞ ይኖር የለ? ለአንዲት ቀን በደል ለዓመታት በቀል ሲጎነጎን ይከርም የለ? ምናለበት ለአንዲት ቀን ደግነት ብዙ ዓመት ደግ ቢሆን?» ዋናውን ርዕስ እየሸሸ መሆኑ ገብቶኛል። ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ።
«ምሽት 2 ሰዓት ላይ ፒክ የሚያደርጉሽ ሰዎች በዚህ አድራሻ ይጠብቁሻል። ሰው አይደለም የሰው ጥላ ቢከተልሽ ያልኩሽን አትርሺ!! የምልክልሽን ስጦታ!!» ይላል። ምን እንደሆነ እንድነግረው ዘወር ብሎ እያየ ይጠብቃል።
«እናቴ ናት!! በአጎቴ ስልክ ደህና መግባታችንን ለማወቅ ነው መልእክት የላከችው።» አልኩት።
ለመጀመሪያ ጊዜ ዋሸሁት! ለመጀመሪያ ጊዜ ደበቅኩት። ግን ልክ ያደረግኩ መሰለኝ አልከፋኝም!! አዲስ አበባ ገብተን ለምናልባቱ የተሻለ ፍንጭ ካገኘን ቃሊቲ እየሄድን ነው። በልቤ ወስኜ ጨርሻለሁ። ከቃሊቲ መልስ ፣ መልስ ባገኝም ባላገኝም ጎንጥን የሆነ ቦታ አመልጠዋለሁ። ለሽንቴ እንኳን ስወርድ ልጠፋበት እንደምችል ጠርጥሮ መሰለኝ በቆቅ አይኖቹ ይከተለኛል። እንዴት እንደማመልጠው አላውቅም። ግን ከእርሱ ጋር የሚቀጥለውን እርምጃ አልራመድም። አሁን ላይ ማንን እና ምን እንደማምን ግራ ገባኝ። ለምኜዋለሁኮ ስላለፈው ህይወቴ የሚያውቀውን እንዲነግረኝ። ምንም እንደማያውቅ ሲነግረኝ አምኜው ምንም ሳልደብቀው በእሱ ላይ ዘጭ ብዬ እምነቴን ስጥልበት ትንሽ እንኳን አይከብደውም? የምሸሸው ምን እንደሆነ እንኳን ሳላውቅ በፍርሃት ነፍሴ ሲርድ እና ስፈራ አላሳዝነውም? እርሱን ከምንም በላይ አምኜኮ ለሳምንታት እጁን ይዤ እንቅልፌን ተኝቻለሁ። ምን ይሆን ያስብ የነበረው? በልቡ <አይ ሞኞ> ብሎኝ ይሆን?
«እመቤት በአንድ ወቅት ከእነርሱ ወገን የነበረች ጋዜጠኛ መሆኗን ሰምቻለሁ። ወዳጃምነታችሁ እምንድረስ እንደነበር የማውቀው ባይኖረኝም ለጊዜው መዘንጋትሽን ግልፅልፅ አድርገሽ ባትነግሪያት እመክርሻለሁ።» አለኝ ልንቃረብ ገደማ። አስቤ የነበረው ሁሉንም ነግሪያት የምታውቀውን መጠየቅ ስለነበር ካልጠየቅኳት የመሄዴ ትርጉም ራሱ ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ። ቢሆንም ሄድን!!
በሩ ላይ ስንደርስ የሆነ ልጅ እግር ጠባቂ «ይሄ ባሻሽ ሰዓት እየመጣሽ እገሌን ጥሩልኝ የምትዪበት የጎረቤትሽ ቤት መሰለሽ እንዴ? እስረኛ መጠየቂያ ቀንና ሰዓት አለውኮ!!» ብሎ ፊቱን ወደ ውስጥ መለሰ
«እናውቃለን! እንደው የሞት ሽረት ጉዳይ ገጥሞን ነው! እንደው ለ2 ደቂቃ!» አለ ጎንጥ
«አትሰማኝም እንዴ ሰውየው? ስራዬን ልስራበት ከዚህ ራቁ!! እንደውም እዚህ አቅራቢያም መቆም አይቻልም ዞር በሉ ብያለሁ።» ብሎ አምባረቀ። ምንም ተስፋ እንደሌለው ሲገባኝ
«እሺ የእስረኛ መጠየቂያ ቀን መቼ ነው?» አልኩ። ይሄኔ ሌላኛው በእድሜ በሰል ያለ ጠባቂ «ምንድነው? » እያለ ብቅ አለ። ልጅ እግሩ ምንም የሚለንን የማንሰማ መሆናችንን እያብራራለት ሰውየው እኔን በትኩረት ካየ በኋላ
«አጅሪት? መቼም ካንቺ ውጪ እዚህ በር ላይ ሁከት የሚፈጥር የለም!! ስትጠፊኮ ሌላ ቦታ ሸቤ ገብታ ነው ወይም ከባርች ጋር ተጣልታ! ብለን አስይዘን ነበር። ኸረ ለውጥ ቁርጠቴ በቀሚስ?» አለኝ። አወራሩ የእስር ቤት ጠባቂ ሳይሆን የሆነ የወዳጅነት ነው። ልጅ እግሩ ጠባቂ ግራ ገብቶት ያየዋል። « ከባርች ጋር ተጣልታችሁ ነው መምጣት ያቆምሽው??» ካለኝ በኋላ ወደልጅ እግሩ ጠባቂ ዞሮ « …. ቁርጠቴ የሴቶቹ ካቦ ነበረች እዚህ እያለች።» ሲል ልጅ እግሩ የሆነ ነገር እንደማስታወስ ብሎ ከላይ እስከታች ካየኝ በኋላ « ቁርጠቴ ማለት እሷ ናት? የሰማሁትን አትመስልም!» አለ
« ምን እንታዘዝ ታዲያ? መጠየቂያ ቀን አለመሆኑን ታውቂያለሽ መቼም!!» አለ በሰል ያለው ጠባቂ ወደ እኔ እየተጠጋ
«ብያለሁ አልሰማ ብለውኝ ነው። እመቤት የምትባል ነው የሚሉት?» አለ ልጅ እግሩ እኔ ሰውየው የሚጠራቸው ቅፅል ስሞች የማን እንደሆኑ ሳላውቅ ያለቦታው ሰክቼ ስህተት እንዳልሰራ ስደነባበር። ንግግሩ ያለመፍቀድ ዓይነት አይደለም። የመፍቀድም አይነት አይደለም። ግራ የገባ ነገር አለው። ይሄኔ ጎንጥ ጠጋ ብሎ እየጨበጠው
«እግዜር ይስጥልን ጌታዬ!! የሞት ሽረት ጉዳይ ባይሆን ካለቀኑ መጥተን ባላስቸገርን!!» አለው። ሰውየው ሳቅ ብሎ የጨበጠበት እጁን ከልጅ እግሩ ጠባቂ ደበቅ አድርጎ ገለጠው። ገንዘብ ነው ያቀበለው። ገንዘብ መፈለጉ እንዴት ገባው? ቆይ እሱ የማያውቀው ነገር ምንድነው? ሰውየው ዞር ብሎ ለልጅ እግሩ እመቤት ያለችበትን ምድብ ይመስለኛል የሆነ ቁጥር ነግሮት እንዲጠራ አዘዘው። ልጁ እየተነጫነጨ የተባለውን አደረገ። ምን መጠየቅ እንዳለብኝ እና እንደሌለብኝ መወሰን አቃተኝ። እንደማላስታውሳትስ መንገር አለብኝ? እሷስ የእኔ ወዳጅ ናት ወይስ እንደጎንጥ ማንነቷን የደበቀችኝ ሴት? የስራውን ይስጠው እንኳን ጠርጥርትያት ብሎ ሹክ ብሎኝ እንዲሁም ጥላዬን የምጠራጠር ጠርጣራ አድርጎኛል:: ስትደርስ ለቅሶ እና ሳቅ የተደባለቀው ነገር ሆነች። በእኔ ተመሳሳይ እድሜ የምትገኝ ዓይነት ሴት ናት። ጎንጥ ጆሮውን ቢተክል የምናወራውን ሊሰማ በሚችልበት ርቀት ቆሟል።

👍24
«በህይወት አለሽ? በህይወት እያለሽ ነው ልታዪኝ ያልፈለግሽው? ምን ሆነሽ እንደሆነ ብቻ ንገሪኝ? ደህና ሆነሽ ነው?» እያለች ማልቀስ ጀመረች። በጥይት መመታቴን ነገርኳት። መርሳቴን ግን ዘለልኩት። ደግሞ ወቀሳዋን ትታ ለእኔ ማዘን ጀመረች። ዞር ብላ ጎንጥን በ<ማንነው ?> አይነት ምልክት ሰጠችኝ። አጠያየቋ እንደምነግራት እርግጠኛ የሆነ ነው። የቀረቤታዋ ልክ ብዙ ነገር የምናወራ ሰዎች እንደነበርን ያስታውቃል።
«ጎንጥ ዘበኛዬ ነበር።» አልኳት። ለምን <ነበር> እንዳልኳት አላውቅም!
«ጎንጥ ጎንጤ? ጎንጤ ጥጋቡ? » ብላ ጮኸች። ስለጎንጥ የምታውቀው ምን እንደሆነ ባላውቅም የግርምት አጯጯኋ ስለዘበኝነቱ ብቻ እንዳልነገርኳት ያስታውቃል። ለአንድ አፍታ ሁሉንም ዝርግፍ አድርጌ ነግሬያት የምታውቀውን ብትነግረኝ ተመኘሁ።
«ኪዳንን ይዘውታል! ቪዲዮዎቹን ካልሰጠኋቸው እንደሚገድሉት ነግረውኛል።» አልኳት የማወራው ነገር አዲሷ እንደማይሆን እርግጠኛ ሆኜ።
«ኪዳን ምን ሊሰራ መጥቶ አገኙት? ሺት!! እርግጠኛ ነሽ? እኚህ አጋሰሶች!! የፈራሽው አልቀረም!! » ብላ በድንጋጤ እና በንዴት መሃል ዝም አለች።
«አዎ በቪዲዮ አይቼዋለሁ። አውርቼዋለሁም። ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ?» አልኳት ሌላ ፍንጭ ከሰጠችኝ ብዬ
«መቼም አትሰጫቸውማ? ሌላ መላ መቼም አይጠፋሽምኣ? »
«በኪዳን ነፍስ ቁማር መጫወትም አልችልም!»
«እየቀለድኩ ነው በይኝ!! ጥይቱ የዋህ አድርጎሻል ልበል? ወይስ ሚሞርሽንም ነው ያጠበልሽ?» ያለችው ለአባባል ነበር እኔ ግን አዎ ብያት ሁሉንም ብትነግረኝ ፈለግኩ። የጎንጥን ማስጠንቀቂያ ችላ ማለትም ከበደኝ። እራሱን ሳላምነው ቃሉን ለምን እንደማምን ምክንያት የለኝም። ግን መጠንቀቅ አይከፋም። እሷ ቀጠል አድርጋ
«ከዚህ በፊት ከእጃቸው ፈልቅቀሽ ወስደሽዋል። አሁንም ተረጋግተሽ አስቢ እና መላ አታጪም!!»
«ተረጋግቼ የማስብበት ጊዜ የለኝም!! የሰጡኝ ሰዓት ሊያልቅ ሶስት ሰዓት ነው የቀረው!» ስላት የሆነ ግራ ያጋባኋት አይነት በጥያቄ አስተዋለችኝ። አለባበሴን ጭምር በዓይኗ ለቀመች እና
«ምንድነው እሱ? ከመቼ ወዲህ ነው እንዲህ መልፈስፈስ ያወቅሽበት? የሆነማ ልክ ያልሆነ ነገር አለ። ደግሞ ልስጣቸውም ብትይ ሴትየዋን በ3 ሰዓታት ውስጥ አጊንተሽ አንደኛውን ኮፒ ልትቀበያት አትችዪም!! ነው ወይስ ኦልረዲ አጊንተሻታል?»
«ሴትየዋን?» ካልኩ በኋላ ሳላስበው « የአቅሜን እሞክራለኋ» አልኳት መልሼ!! መልስ የሰጠችኝ መሰለኝ። ለሰዎቹ የሰጡኝን የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ምክንያት!! የምጠይቃት ብዙ ቢኖርም!! በምን መንገድ እን,ደምጠይቃት ካለማወቄ የእሱን እንቢታ ጥሶ ሌላኛው ጠባቂ እመቤትን እንዲጠራልኝ ያስገደደው ልጅ እግር ጠባቂ ሰዓታችን ማለቁን ከግልምጫ ጋር ይነግረኛል። ለእመቤት መልሼ እንደምመጣ ነግሬያት። ወደከተማ መመለስ ጀመርን።
«ሴትየዋ ያለችሽ ማን ትሆን?» ሲለኝ ያወራነውን ሁሉ እንደለቀመ ገባኝ።
«አላውቅም! መርሳትሽን አትንገሪያት አላልክም? ማናት ብዬ እንዴት መጠየቅ እችላለሁ? ሁሉን ነገር ታውቅ የለ? ይሄ እንዴት አመለጠህ?» ብዬ ጮህኩበት
«ታዲያ ምን የሚያስቆጣ ተናገርሁ? ቃሌን ያለማመንና ሴትዮይቱን ማመንምኮ ያንቺ ድርሻ ነበር።» አለ ተረጋግቶ።
«ለማንኛውም እቤት ንዳኝ!! ተረጋግቼ የማስብበት ሰዓት እፈልጋለሁ።» አልኩኝ። ከዛ ማውራት የእሱ ተራ ዝም ማለት የእኔ ተራ ሆነ።
« አሁን እኔና አንቺ አንባጓሮ የምንፈጥርበት ሰዓት አይደለም! በአንድነት መላ ብንዘይድ አይበጅም? ከሰውየው ጠባቂዎች አንዱ ወዳጄ ነው። ኪዳን ያለበትን አድራሻ ማግኘት ከቻልን መልዕክት አኑሬለታለሁ። እስታሁን የምትመጪበትን አድራሻ አልላኩም? መላክ ነበረባቸው!! ትክክለኛ አድራሻውን እንደማይልኩልሽ ግልጥ ነው። ከሆነ ቦታ ይቀጥሩሽና ነው በራሳቸው መኪና የሚወስዱሽ!! እርግጥ አድራሻውን ከደረስንበት እነርሱ የቀጠሩሽ ቦታ ሲመጡ እኛ ቀድመናቸው ቦታው እንደርስ ነበር ….. » እሱ እቅዱን ከጅምር እስከ ፍፃሜ ሲነግረኝ እኔ ደግሞ የራሴን እቅድ ከጅምር እስከ ፍፃሜ የሌለው አቅዳለሁ። እቤት እንደደረስን እዛ መሳቢያ ውስጥ ያለውን ሽጉጥ እወስዳለሁ። ምን እንደማደርግበት የማውቀው የለኝም። በሆነ መላ ከጎንጥ እሰወራለሁ። የቀጠሩኝ ቦታ ብቻዬን እሄዳለሁ። የሚወስዱኝ ቦታ ስደርስ (ኪዳን ይኖራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ) ሁሉንም ኮፒ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስላልነበረኝ ተጨማሪ አንድ ቀን እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ። የሚፈልጉት ቪዲዮ የዚን ያህል አንገብጋቢ ከሆነ አይገድሉኝም። የጠየቅኩትን ጊዜ ይሰጡኛል። በተቃራኒው ሊሆን እንደሚችል ሳስብ ልቤ ይደልቃል:: ትልቁ ፍላጎቴ ግን ለትንሽ ደቂቃ ከወንድሜ ጋር እንዲተውኝ ማድረግ ነው። ብቸኛ ላምነው የምችለው እና ሊያውቅ የሚችል ሰው እሱ ነው። ይሄ ጎንጥ እንዳለው የጅል እቅድ ሊሆን ይችላል። እጄን አጣጥፌ እየጠረጠርኩት ያለሁትን ጎንጥን ከመከተል ውጪ ሌላ የተሻለ እቅድ ግን የለም። ያን ደግሞ አላደርግም!!
እቤት እንደደረስን ተናኜ የማያቆም ጥያቄ እና ወሬ ታከታትላለች። እንደማልሰማት እንኳን የምታስተውልበት ፋታ አትወስድም። ጎንጥ ከገባ ጀምሮ በሩ ላይ እንደተገተረ ነው። ጮክ ብዬ ጎንጥ እንዲሰማ
« አንድ ላይ የምንበላው እራት አሰናጂ!! ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም! እራት አንድ ላይ እንቋደስ!» አልኩኝ ለእሷ ግራ እንደሚያጋባት ሳልረዳ
«ምነው እትይ የት ልትሄጅ ነው?»
«የትም አልሄድ! ያልኩሽን ዝም ብለሽ አድርጊ!» አልኳት። ቅር እያላት ገባች። ለመሄድ የሚያስፈልገኝን ነገር ካሰናዳሁ በኋላ ጥርጣሬውን ለመቀነስ ልብሴን አልቀየርኩትም። እራት ሶስታችንም ቀርበን እየበላን። አስተያየቱ እንዳላመነኝ፣ ነገረ ስራዬ እንዳላማረው ያስታውቃል።
«አድራሻውን ልከውልኛል።» አልኩት
«የት ነውስ?» አለ ቀና ብሎ ስልኬን እንድሰጠው መሰለኝ እጁን እየዘረጋ። ስልኬን የለበስኩት ሹራብ ኪስ ውስጥ የከተትኩት ለራሴ እቅድ እንዲመቸኝ በመሆኑ እጁን ችላ ብዬ
«እንዳልከው ነው። ቀበና የሚባል ሰፈር የሆነ ካፌ ፊትለፊት ነው። ስልኬ መኝታ ቤት ነው አሳይሃለሁ። ከዛ ነው ከእነርሱ ጋር ሊወስዱኝ ያሰቡት! ምንድነው የምናደርገው? ወዳጅህ እስከአሁን አልመለሰልህም?።» አልኩት። ይመነኝ አይመነኝ ባላውቅም በእርሱ እቅድ እየተመራሁ እንደሆነ እንዲመስል ጣርኩ። አስተያየቱ ያመነኝ አይመስልም። ከጎሮሮዬ አልወርድ ያለውን እህል እንደምንም ካጋመስኩ በኋላ
« …… በልተሽ ስትጨርሺ እዚህ ላይ አንድ ስኒ ቡና ብታጠጪኝ ደግሞ?» አልኳት ተናኜን። ልትነሳ ሲዳዳት ተረጋግታ እንድትጨርስ ነግሪያት ወደጓዳ እጄን እንደሚታጠብ ሰው ገባሁ። እጅ መታጠቢያውን ውሃ ክፍት አድርጌ አስቀድሜ ክፍቱን በተውኳቸው በሮች የምፈልገውን ይዤ በጓዳ ወጣሁ። መጣ አልመጣ አድብቼ እየተርበተበትኩ የአጥሩን በር ከፍቼ ስወጣ ከኋላዬ የሚያባርረኝ ያለ ነበር የሚመስለው አሯሯጤ። የቤቴ በር ከአይኔ እስኪሰወር እሮጥኩ። ያገኘሁትን ታክሲ አስቁሜ ወደተላከልኝ አድራሻ እየሄድኩ።
«ማን ስለሆነ ነው ቆይ እንዲህ የምደበቀው? ያውም በገዛ ቤቴ?» እላለሁ በልቤ!!

👍34❤4
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ሰባት)
(ሜሪ ፈለቀ)
የምጣደፈው ጎንጥን ሽሽት ይሆን ኪዳንጋ ለመድረስ ተቻኩዬ ወይም በሁለቱም ምክንያት የታክሲው ሹፌር ትዕግስቱን እስኪያንጠፈጥፍ ድረስ አቻኩለው ጀመር። <ምን ያህል ቀረን?> ፤ <ትንሽ ፈጠን ማለት አትችልም?> ፤ < ሌላ ያልተዘጋጋ አማራጭ መንገድ አይኖርም?> ፤ < አሁንም ብዙ ይቀረናል?> አንድ አይነት ጥያቄ በየሁለት ደቂቃው እየደጋገምኩ ፤ ግማሽ ጎኔ ወደፊት ግማሽ ጎኔ ወደኋላ በሆነ አቀማመጥ ፤ በአንድ ዓይኔ ወደኪዳን (ወደፊት) በአንድ ዓይኔ ወደጎንጥ (ወደኋላ) ሳማትር
«ሴትዮ ካልሆነ ውረጂ እና ሌላ ታክሲ ተሳፈሪ! አይታይሽም እንዴ በማይነዳበት እየነዳሁልሽ? ሆ! ዛሬ ምኗን ነው የጣለብኝ ባካችሁ?» አለ ያለመታከት ሲመልስልኝ ቆይቶ ከትዕግስቱ በላይ ስሆንበት
«ይቅርታ በጣም ስለቸኮልኩ ነው። ይቅርታ በቃ እንደሚመችህ አድርገህ ንዳ!!» አልኩኝ። ታክሲው ውስጥ በቦርሳ የያዝኩትን የቱታ ሱሪ ከቀሚሴ ስር ለብሼ ሳበቃ ቀሚሴን አውልቄ ወደቦርሳው ከተትኩ።
እያደረግኩት ያለሁት ድፍረት ይሁን ድድብና መመዘን የምችልበት መረጋጋት ላይ አልነበርኩም። ምናልባት አለማወቅ ደፋር ያደርግ ይሆናል ወይም ደደብ!! ጎንጥ ሰዎቹን ስለሚያውቃቸው ይሆናል የሚጠነቀቀው እና የሚፈራልኝ። የማላውቀውን ሰው ወይም ልገምት የማልችለውን የሚገጥመኝን ነገር በምነኛው መጠን ልፈራ እችላለሁ? እስከገባኝ ድረስ ቢያንስ አለማወቄ ጎንጥን እስከአለመከተል ድረስ ደፋር ወይም አላዋቂ አድርጎኛል።
የተባለው ቦታ ስደርስ ለቀጠሯችን 20 ደቂቃ ይቀረኛል። ከታክሲው ከወረድኩ በኋላ እንደማንኛውም በአካባቢው እንዳለ ተንቀሳቃሽ ግለሰብ የአዘቦት ክንውን እየከወንኩ ለመምሰል ጣርኩ እንጂ እንደሌባ ዓይኖቼም አካሌም እየተቅበጠበጠ ነበር። እስከዚህ ደቂቃ ያልተሰማኝ ፍርሃት አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ይገለባበጥ ጀመር። መቆምም መራመድም መቀመጥም ሰው ይቸግረዋል? ወደላይ ትንሽ ራመድ እልና ደግሞ በተቃራኒው አቅጣጫ እመለሳለሁ። በመሃል እንደማቅለሽለሽም ያደርገኝና መሃል የእግረኛ መንገድ ላይ ቁጢጥ እላለሁ። ከመንበጭበጬ ብዛት ሽንቴን እላዬ ላይ የምለቀው መሰለኝ። ሰዓቴን በ60 ሰከንድ ውስጥ 120 ጊዜ አያለሁ። ደቂቃው ሰዓቴ መስራቱን ያቆመ ይመስል ፈቅ አይልም። ለአፍታ የጎንጥ እጅ ናፈቀኝ። ወላ ተከትሎ ደርሶብኝ በሆነና የፈራሁ ሲመስለው ሁሌም እንደሚያደርገው በዛ ሰፊ መዳፉ እጄን አፈፍ አድርጎ እጁ ውስጥ ቢደብቀው። «……. እኔ የት ሄጄ? …… ማን አባቱንስ እና ነው? » ቢለኝ። ሜላት ምንድነው ያደረግሽው?
የምጠብቀው እንዲህ ነበር። የሆነ ቀን እንዳየሁት የሆነ ፊልም። ጥቁር መኪና መጥቶ አጠገቤ ገጭ ብሎ ይቆምና ! በሩ ብርግድግድ ብሎ በተጠና ስልት ሲከፋፈት ፊታቸው የማይታዩ መሳሪያ የታጠቁ ግባብዳ ሰዎች ከመኪናው ዱብ ዱብ ብለው ያስቀመጡትን የሆነ ሻንጣ ብድግ እንደማድረግ ብድግ አድርገውኝ እየጮህኩ እግሬ አየር ላይ ተንጠልጥሎ ስፈራገጥ ምንም ሳይመስላቸው ወደመኪናው ይወረውሩኝና ልክ እንደቅድሙ በተጠና መንገድ በሩን ድው ድው አድርገው ዘጋግተው ይዘውኝ ይሄዳሉ።
የሆነው እንዲህ ነው። እግሬን ብርክ ይዞት ጉልበቴን ደገፍ ብዬ ባጎነበስኩበት አንዲት ቆንጅዬ ጅንስ ሱሪ በቲሸርት ለብሳ አጭር ጥቁር ጃኬት የደረበች ወጣት ሴት ከጀርባዬ ጠራችኝ። «ሜላት!» ለሰላምታ እጇን ዘረጋችልኝ። እነሱማ ሰላም ሊሉኝ አይችሉም ብዬ እያሰብኩ እጄን ዘረጋሁ!!
«ዝግጁ ነሽ?» ስትለኝ ማሰቢያዬ ተዛባ! ለምኑ ነው የምዘጋጀው? ለመታገት ዝግጅት? <አዎ! እጄን ለካቴና በቅባት አሸት አሸት አድርጌ አዘጋጅቸዋለሁ። ድንገት እጃችሁ ካረፈብኝ ዱላ መቻያ ደንደን እንዲል ቆዳዬን ወጠርጠር አድርጌ አለማምጄላችኋለሁ….. > እንድላት ነው ተዘጋጀሽ የምትለኝ? እሷ ቀጠል አድርጋ ከፊቴ ወደቆመ ዘናጭ ነጭ መኪና እየጠቆመችኝ ፈገግታዋ የሆነ የተንኮል ዓይነት እየሆነ « …. ግርግር አንፈልግም አይደል?» ብላ አጭሩን ጃኬቷን ከፈት አድርጋ ሽጉጧን አሳየችኝ። ለስሙማ እኔምኮ ሽጉጤን ጎኔ ላይ ሽጬዋለሁ። ምን ላደርግበት እንደሆነ ያሰብኩት ባይኖርም ለዝህች በቆንጆ ፊቷ ለሸወደችኝ ልጅ ግን ሽጉጥ ሳይሆን የመዘዝኩት እጄን ነው ለሰላምታ የዘረጋሁት።
ወዳሳየችኝ መኪና ሄድኩ። እያገተችኝ ሳይሆን የሆነ በክብር እንግድነት የተጠራሁበት ቦታ ልታደርሰኝ ነው የሚመስለው። የኋላውን በር ከፍታ ያንን ተንኮለኛ ፈገግታዋን እያሳየችኝ እንድገባ ጋበዘችኝ። በአጠገባችን የሚያልፉ ሰዎችን <ኸረ በትኩረት ለአፍታ እዩኝ እየወሰዱኝ ነው!> ብል ደስ ባለኝ። ማንም ለአፍታ እንኳን ገልመጥ አድርጎ ያየኝ የለም። በየእለት ተእለት ውሏችን ልብ ያላልናቸው ስንቶች ይሆኑ ከአይናችን ስር ብዙ የሆኑት?
መኪና ውስጥ ከኋላ ታግቼ ባይሆን « ምን ሆኖ ነው እንዲህ የቆነጀው?» የምለው የሚመስለኝ ፈርጣማ ወንድ ተቀምጧል። እንደገባሁ ቀለበኝ ማለት ይቀላል። ፓንቴ ስር መግባት እስኪቀረው እንያንቀረቀበ ሲፈትሸኝ ልጅቷ ከፊት ወንበር ሆና ሽጉጧን አስተካክላ ትጠብቀቃለች። የምራቸውን ነው? እዝህች የክብሪት ቀፎ የምታክል መኪናቸው ውስጥ ከነሹፌሩ ለሶስት ከበውኝ ታጠቃናለች ብለው ነው ሽጉጡ? ሽጉጤን ከፊት ለተቀመጠችው ሴት እንደመወርወር አድርጎ አቀብሏት በምትኩ የሆነ ጨርቅ ስትወረውርለት ነገረ እቅዴ ሁሉ ጎንጥ እንዳለው የጅል መሆኑ ገባኝ። የሰውየው መዋከብ ቶሎ የመጨረስ ውድድር ያለበት ነው የሚመስለው። በጨርቁ ዓይኔን ሲሸፍነው መኪናው መንቀሳቀስ ጀመረ። በዚያው ፍጥነት እጄ ላይ ካቴና አሰረ።
ለምን ያህል ደቂቃ እንደተጓዝን አላውቅም!! ወይ ከላይ ወይ ከታች እንዳያመልጠኝ ከሰውነቴ ጋር ግብ ግብ ላይ ነበርኩ። የእነርሱ ዝምታ ደግሞ ጭራሽ ያለሁት መኪና ውስጥ ሳይሆን ከሞት በኋላ የሰይጣን ፍርድ ዙፋን ስር ቀርቤ አስፈሪ ፍርድ ለምሳሌ እንደ < ለእሷ እሳቱ አስር እጥፍ ይጨመር!! ይሄማ ለሷ ሻወር መውሰጃዋ ነው!! ይንተክተክላት ውሃው እንጂ! > የሚል ፍርድ እየተጠባበቅኩ መሰለኝ። ከመኪናው ወርደን የበረበረኝ ሰውዬ ይመስለኛል ብብቴ ስር ገብቶ ጨምቆ ይዞኝ እየነዳኝ በእግር የሆነ ያህል እንደተጓዝን አይኔን የሸፈነኝ ጨርቅ ሲነሳ የተንጣለለ በውብ እቃዎች የተሞላ ሳሎን ራሴን አገኘሁት። ያሰረልኝ ሰውዬ ከእጄ ላይ ካቴናውን አወለቀው።

👍21
እንግድነት የሄድኩ ይመስል እንድቀመጥ ታዘዝኩ። ያ ሰውዬ በቪዲዮ ያወራሁት ሰውዬ እና አንዲት መሬቱን የነካ ጌጠኛ ቀይ ቀሚስ የለበሰች ሴት ተቀምጠዋል። ከእነርሱ በተጨማሪ ይዞኝ የገባው ሰውዬ እና ትንሽ ቁመቱ አጠር ያለ መሳሪያ የታጠቀ ሰውዬ ብቻ ናቸው ክፍሉ ውስጥ ያሉት። ሴትየዋ የጠቆመችኝ ከፊታቸው ያለ ሶፋ ላይ ለመቀመጥ ቂጤን ሳሾል «ከመጨዋወታችን በፊት እንዳው ለመተማመኑ ….. » ብላ አጠገቤ ደርሳ የለበስኩትን ሹራብ ግልብ ስታደርገው ግራ ገባኝ እና መነጨቅኳት። የቆሙትን ጠባቂዎች (መሰሉኝ) ፊታቸውን እንዲያዞሩ ምልክት ስትሰጣቸው ሶፋው ላይ ያለው ሰውዬ እራቁቴን የማየት መብት እንዳለው ሁሉ ዝም አለችው። ከንግግሯ ምናልባት የምናወራውን የምቀዳበት ነገር ሰውነቴ ላይ ደብቄ እንደሆነ እያጣራች መሆኑ ገባኝ። በፓንት እና በጡት ማስያዣ ስቀር አይኑን ከሰውነቴ ላይ ለመንቀል ምንም ሀሳብ የሌለውን ሰውዬ እያየሁ መዋረድ አንገበገበኝ። ሴትየዋ ጡቴ ስር ገብታ ስታንቀረቅበኝ ጡቶቼን የምትመዝናቸው እንጂ የሆነ መቅጃ ያለችውን ነገር እየፈለገች አይመስልም። ጥርሴን ነክሼ ዋጥኩት። ሆነ ብላ የምታደርግ ነው የሚመስለው። ጣቷ የእንትኔን ጫፍ እስኪነካው ድረስ እጇን ፓንቴ ውስጥ ስትሰድ እስኪያማት ድረስ የእጇን አልቦ ማሰሪያ ጨመደድኩት።
«ok ok » ብላ እጇን አወጣች። የያዝኳትን ስለቀው ቦታው ደም መስሏል። ፊቷ ላይ ያስታውቃል። ከመፈተሿ በላይ እኔን ማዋረዷ ተመችቷታል። እንድለብሰው ልብሴን ከመሬት አንስታ ወረወረችልኝ። ከሰውየው ጋር ተያይተው ያልገባኝን መልዕክት ተለዋወጡ። ይዤው የነበረውን ቦርሳ አንስታ አመሳቅላ በረበረችው።
«አላመንከኝም እንጄ ነግሬህ ነበር,» አለችው። ሰውየው ባለችው ነገር ሙሉ በሙሉ ያመነ አይመስልም።
«እሺ ሜላት!! የታሉ ቪዲዮዎቼ?» አለ
«ወንድሜን በአይኔ ሳላየው ምንም ነገር አልነግርህም!!» አልኩት ለመኮሳተር እና ያልፈራ ለመምሰል እየሞከርኩ።
«ሜላት ይሄ ኔትፍሊክስ ላይ ተጥደሽ ስታዪ የምትውዪው የሆሊውድ ፊልም አይደለም። አጉል ጀግና ጀግና አትጫወቺ!! የትም አትደርሺም!!» አለ ልጥጥ ብሎ እንደተቀመጠ። አልመለስኩለትም።
«እየሰማሽኝ አይደለም? ዛሬ የምጫወትበትን ጠጠር የምመርጠው እኔ ነኝ። ያልኩሽን ነው የምታደርጊው።» ብሎ አምባረቀ።
«ወንድሜን ካላየሁ ምንም የማደርገው ነገር የለም አልኩ እኮ!!» ብዬ ለመጮህ ሞከርኩ።
ለቆመው አጭሩ ጠባቂ ምልክት ነገር ሰጠው። የታመቀ ትንፋሼን በረዥሙ ለቀቅኩት። ኪዳን ሲገባ ምንም የተጎዳ ነገር ያለው አይመስልም። ሲያየኝ ፊቱ ላይ ከቃላት በላይ የሆነ ስቃይ አየሁበት።
«I am so sorry» አለኝ ገና ስንተያየኝ። አልከለከሉኝም! ሄጄ አቀፍኩት። አጥብቆ አቀፈኝ። «ይቅርታ ሜል!»
«መልሰው!!» ብሎ ጮኸ ሰውየው። አብሬው እንድቆይ ብለምንም ሊሰማኝ እንኳን ግድ አላለውም። ምንድነበር ያሰብኩት? 'ናፍቆትሽ እስኪወጣልሽ እንጠብቅሻለን ከወንድምሽ ጋር ትንሽ ተወያዩ' እንዲሉኝ ነበር? የምርም እንዴት ያለ የቂል እቅድ ነው ያወጣሁት? ኪዳን ተመልሶ ሲሄድ የተሸነፍኩ መስዬ ላለመታየት ሞከርኩ። ሰውየው ወደእኔ አፈጠጠ።
«ሁሉንም ኮፒ እንዳመጣልህ አይደል ፍላጎትህ? በሰጠኸኝ አጭር ጊዜ ላመጣልህ አልችልም!! ተጨማሪ 24 ሰዓት ስጠኝ እና የምትፈልገውን በሙሉ እሰጥሃለሁ።» ስለው ያሳቃቸው ጉዳይ አልገባኝም ሁለቱም ከጣሪያ በላይ ሳቁ።
«ብዬህ ነበርኮ! በል ብሬን ወዲህ በል!» አለችው ሰትየዋ እጇን እየዘረጋች።
«እያወቅሽኝ ካላረጋገጥኩ መች አምናለሁ?» መለሰላት። እየሆነ ያለው ሙሉው ባይገባኝም እያላገጡብኝ እንደሆነ ገብቶኛል። ከኪሱ የሆኑ ብሮች ኖት አውጥቶ አቀበላት።
«ባንቺ ቤት አቃቂለሽኝ ሞተሻል!! ካንቺ ውጪ ማንም መረጃዎችሽን የት እንደምታስቀምጪ እንደማያውቅ ገምቻለሁ። እመቤትን ነበር የጠረጠርኩት እንደገባኝ እሷም የረዳችሽ ነገር የለም። አንቺም የት እንዳስቀመጥሽ እንዳታስታውሺ ትውስታሽ ላይመለስ ከድቶሻል። ንገሪኝ እስኪ ምን ልሁን ብዬ 24 ሰዓት ልጠብቅሽ?» ሲለኝ የበለጠ ጅልነት ተሰማኝ።
ባለፈው ከደበደቡኝ ጎረምሶች የተሻለ እነዚህ ሰዎች መረጃ ከፈለጉ በቀላሉ ማግኘት አይችሉም ብዬ እንዴት አሰብኩ? ምኗ ቂል ነበርኩ? አሁን ይገድሉኛል? እሺ ኪዳንንስ? ምንድነው ያደረግኩት?
በሩ ተከፍቶ የቅድሟ ሴት በሩ ላይ ላለው ጠባቂ የሆነ ነገር አንሾካሽኳ ወጣች። ጠባቂውም የሆነ ነገር ለሰውየው አንሾካሾከ። ሰውየው በጣም የተገረመ መሰለ።
«ያንቺው ጉድ ነው!» አላት ወደሴትየዋ እያየ። ሴትየዋ ግራ የተጋባች መሰለች። በጣም በመገረም ወደበሩ እያየች።
«ምን ልሁን ነው የሚለው አስገቡት እስኪ!»
ዓይኔ የሳተው ነገር ቢኖር ነው። ጆሮዬም እንደዛው? <የሷው ጉድ> ነው ያለው ወይስ <የአንቺው ጉድ> ነው ያለው? የእኔው ጉድ ጎንጥማ የሷው ጉድ ሊሆን አይችልም። ወይም ሌላ ጎንጥ ይሆናል እንጂ የእኔው ጎንጥማ አይሆንም!! በሩን አልፎ ሲገባ ቤቱ ነው የሚመስለው!! ልክ የእናት አባቱ ቤት እራት ሊበላ እንደመጣ ነገር ዘና ብሎ ከሶፋው ተሻግሮ ያለ ወንበር ሳብ አድርጎ ተቀመጠ።
እስከአሁን የነበረው ምኑም ያየኋቸውን ፊልሞች አይመስልም ነበር። ይሄ ግን ፊልም እንጂ እውን አይመስልም።
«ምን ትሰራለህ?» ብላ ሴትየዋ ጮኸች።
«ስራዬን ነዋ!!» አለ እንደማላገጥ ብሎ
ሆድቃዎቼ ቦታ የተቀያየሩ ነገር መሰለኝ። ሆዴ ውስጥ ተለዋወሰብኝ።

👍29❤1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
የኩችሩ መንደር እንደደመቀች ናት:: ብዛት ያላቸው አሣዎች በወጣቶች በጦር ተወጉ ማጅራታቸውን በዱላ ተመቱ በመንጠቆ ተያዙ፤ ሣር በል የሆኑ አራዊት የሜዳ ፍየልና ውድንቢት ታድነው ተገደሉ ፤ ከጫካ ብዛት ያለው ማር ተቆረጠ፤ ቦቆሎና ማሸላ ኦሞ ወንዝ ተወስዶ ተወቃ.. ይበላል ይጠጣል
ይጨፈራል ይመረቃል።
ሉካዬ ሰማይ ላይ ሆኖ ምስሉ እየታዬ ቢሆንም ሶስት ቀን ሙሉ አልመጣም:
“ሎካዬ ለመምጣት ያስባል! ነጩ እባብ ግን “አልመጣም ብሎ አስቸግሮታል ደንቡን ሳናጓድል ሥርዓቱን ብናሟላ ግን ሁለቱም ይመጣሉ" ስላሉ ሽማግሌዎች፣ ሴት ወንዱ ይኳትናል ሰማይ ላይ ላሉት ለሎካዬና ለነጩ እባብ በደስታ ለመፍጠር።
ኮንችት የሎካዬ የልጅ ልጅ መሆኗን ከሰሙም በኋላ
የመንደሩ ሰው ተስብስቦ ከአያቷ ወንድም ቤት ፊት ለፊት ተቀመጡ" የሉካዬ ፎቶ ጎጆው ላይ እንደተንጠለጠለ ነው። ከሥሩሁሌም ግልገል ፍየል ከካሮ እየመጣ ታርዶ ይቀመጥለታል።
ልጃገረዶች ኮንችትን ወደ ጎጆው ቤት ውስጥ ይዘዋት
ገብተው ውስጥ ሱሪዋንና ጡት ማስያዥዋን ሳይቀር አስወለቋት::ከውጭ ይዘፈናል እልል ይባላል. ልጃገረዶች በአኖና የዱር እጣን አላቁጠው ፀጉሯን ሰውነቷን ቀብተው የፍየል ቆዳ አለበሷት: ከዚያ
ይዛው የመጣችውን ልብሷን በእጅዋ እንድታንጠለጥል ሰጧትና ከቤት ወደተሰበሰበው ህዝብ ይዘዋት ወጡ። እሳት ነዷል.
ይጨፈራል... ሁለት ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፍተው እጅና እጅዋን
ይዘው ልብሷን ወደ እሳቱ አስወረወሯትና እልልታቸውን ሲያስነኩት
የተሰበሰበው ህዝብ እንደገና ፈነጠዘ ዘለለ አቅራራ.. ጡሩንባ
እልልታ ተኩስ ድብልቅልቅ አለ:
ኮንችት የተረጋጋች አትመስልም። ቆዳዋ ግን አማረባት ጡቶችዋ ቀልተው ቆሙ ለስላሳው ጭኗ... ሁለመናዋ አጓጊ ሆኗል:
ድንጋጤው ስላልለቀቃት ግን ካንገቷ በላይ ውበቷ ቀንሷል።
ሴቱም ወንዱም እየመጣ እጅዋን እየሳመ ደስታውን
እየገለፀላት ወደ ጭፈራው ሲገባ እንደቆዬ ሰው ሰላምታ እየሰጣት
ኩዩጉነቷን አንድነታቸውን እያረጋገጠላት ከሄደ በኋላ ሶራ እየሳቀ ወደ ኮንችት ተጠግቶ አቀፋት: ሽጉጥ አለች ወደ ደረቱ እንደ
እንቦቀቅላ ህፃን፡ አይቷት እንደማያወቅ ሁሉ በሁለት እጆቹ ጡቶችዋን እንደያዘ ፈገግ ብሎ ቁልቁል አያት: ልትስመው ስትል
የሆነች ሴት መጥታ መነጨቀቻት። የኩዩጉ ሴት ወንድን በአደባባይ
አትስምማ!
“እሺ!” አለች ኮንችት
የሴትዮዋ ግሣፄ ስለገባት።
“ለምን ልብሴን አወለቁ? ለምንስ እንዳቃጥለው አደረጉ?''አለችው እሏና ሶራ ከእቅፎቻቸው ከተላቀቁ በኋላ
“የአያትሽን ባህል ረድኤት ለማካፈል! ተፈጥሮአዊ ፀጋሽን ለመመለስ ጎረምሶች ፍቅራቸውን እንደ ወለላ ማር እንዲያውጡሽ….
ለማድረግም" አላት ሶራ እየሳቀ
ባለወይሳው ኮንችትን ባህላዊ ልብስ ለብሳ ሲያያት ደስ አለው። ስለዚ ፈገግ ብሎ ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ ቀረባትና
ካርለትን አይተሻታል ወይ? ብለህ ጠይቃት" አለው ሶራን።ሶራ የነገረውን ለኮንችት ሲተረጉምላት ተኩስ ተሰማ ተኩሱ
ተደገመ።
ጎረምሶች እየተሯሯጡ ወደ ኦሞ ወንዝ ሄዱ። ጭፈራው
ግን አልቆመም። ባለወይሳው ከሌላ አካባቢ የመጣች ፀጉረ ረጅም
ልብስ ለባሽ... ሁሉ እሱ የሚያውቃትን ካርለትን ያውቃል ብሎ አምኗል።
“ካርለት! ማነች ካርለት? የአባቷስ ስም? ዜግነቷስ?”
ኮንችት በስም ብቻ አውቃለሁ፤ አላውቅም ማለት ትክክል
እንዳልሆነ ታውቃለች: በያገሩ ስንት ካርለት
ዴቪድ... ሊኖር ፥ይችላል። መጀመሪያ ስም አገር ሥራ የሚኖርበት አድራሻ...
ለማንነት መለያ ይጠቅማል: በተረፈ በደፈናው ይከብዳል።ባለወይሳው ግን “አውቃታለሁ' አለማለቷ አስከፋው:
ምን የማረጋት መሰላት ካርለት ልጃገረድ ናት!
ብታጠፋም አላገባኋት ጥሎሽ መክፈል አልጀመርሁ... እና-
አላዝባት አልቀጣት... ይህን እያወቅች መደበቋ ምን ይሉታል? ብሎ አስቦ አዘነባት በኮንችት:
በኦሞ ወንዝ ዳር ካለው ጫካ የሆኑ ሰዎች ብቅ ሲሉ ህዝቡ ተንጫጫ። ኮንችት ቀና ብላ ታይ የኩዩጉ ጎረምሶች እንግዶችን
እየመሩ ይመጣሉ። ለኩዩጉ መንደር በሩ ኦሞ ወንዝ የበሩ ደወል ተኩስ መሆኑ ኮንችትን እንዳስደነቃት ነው።
እንግዶቹ ሲጠጉ አንዷ ነጭ ናት ሁለት ወንዶችና
አንዲት ሴት አብረዋት አሉ። እነሱ ከነጭዋ አንፃር ጥቁር ናቸው።እንግዶቹ እንደቀረቡ ባለወይሳው ዘወር ብሎ አያቸውና ከመቅፅበት
አይኑን እንደ አውሬ አፍጦ አንገቱን እንደ ሰጎን መዘዘው
ሁለቱ ሴቶች ባለወይሳውን ሲያዩ ፊታቸው በደስታ ፀዳል አበራ ቸኩለው ግን ወደ እሱ አልተጠጉም።
ከዚያ ነጯ እንደቆመች ሌላዋ ሴት ቀረብ አለችና፡-
“አያ ደልቲ!'' አለችው
በሐመርኛ:ጎይ ቲ"
ረጋ ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ ላዩ ላይ ተጠመጠመችበት: እቅፍ አድርጓት ቆየና ለቀቃት:: ነጭዋንም ካርለት" ብሉ አቀፋት፤ እሷም አቀፈችው ...
የኩችሩ መንደር ኗሪ በሁኔታው ተደንቆ ጭፈራውን አቁሞ
ያያል።
ካርለት! አለች ወገቧን ወደኋላ ለጥጣ በአድናቆት አፏን እንደከፈተች ኮንችት።
ኮንችት! ካርለት ኮንችትን ከእግር ጥፍሯ እስከ ፀጉሯ
በአድናቆት እያየቻት ቆየችና
“አገኘሻቸው?" አለቻት
“አዎ ተገናኘን” ብላ ኮንችት ሳቀች ተሳሳቁ ኮንችትና
ካርለት! ህዝቡም አብሯቸው ሳቁ! መንደሯም በሣቅ ሙላት ተጥለቀለቀች
“ኮንችት እንዴት ልታገኛቸው ቻልሽ?''
“..በጀልባ ነበር እኔና ሶራ የምንጓዘው፤ እና ባጋጣሚ እዚህ ደረስን
“ማንም ሳይመራሽ?'
“ባገኘሁት ማፕም ሆነ ካርታ ኩዩጉዎች ለመኖራቸው ፍንጭ የሚሰጥ ምልክት የለም:: አያቴ የስጠኝ የአደራ ምልክቶች ግን እንደ ኮኮብ መርተውኛል ያም ሆኖ ግን ባጋጣሚ ኩዩጉዎችን
የሚፈልገው ሰው ተኩሶ እነሱ ሲመጡ ማየት ባንችልና ተጠራጥረን
አብረን ባንመጣ ልፋቴ መና ሆኖ! ስሜቴ በስለት ቢላዋ ለሁለት ተተርትሮ ወደ መጣሁበት እየቆዘምኩ እመለስ ነበር። አጋጣሚው
ግን ረዳን፤ ተገናኘን:
“እንዴት አገኘሻቸው ታዲያ?
“ደግ ሩህሩህና ተግባቢዎች ናቸው:: ኑሯቸው በኦሞ ደለል ላይ ማሸላ በማብቀል ከጫካ ማር በመቁረጥና አሣ በማጥመድ ነው።
ከብት ፍየል የላቸውም፤ ይህ ደግሞ ከብት በሚያረቡት የአጎራባች
ያስንቃቸዋል:: ቁጥራቸው
ማህበረሰቦች ማነሱ ከብት
ባለማርባታቸው የሚያጠቃቸው ብዙ ነው። ስለዚህ የሚኖሩት
በጠባቂ ሞግዚት ነው"
“በሞግዚት?”
“አዎ ካርለት! ጥንት ሞግዚታቸው ካሮ ማህበረሰብ ነበር። አሁን
ግን የካሮዎች ኃይል እየደከመ የኒያንጋቶሞች
(ቡሜዎች) ኃይል እየበረታ በመምጣቱ ኩዩጉዎች ወደ ኒያንጋቶሞች በመጠጋት ከአጎራባች ማህበረሰቦች የሚደርስባቸውን ጥቃት
ሞግዚታቸው ኒያንጋቶሞች ይከላከሉላቸዋል።
“ታዲያ ለሃያሉ ሞግዚታቸው ማር እህል ከሚሰፍሩት ሌላ ልጃገረዶቻቸውን ካለጥሎሽና ካለ አንዳች ክፍያ ኒያንጋቶሞች
በሚስትነት ይሰጣሉ። ኩዩጉዎች ግን ከኒያንጋቶሞች ካሮዎች.. ጋርዐመጋባት አይችሉም ስለሚናቁ።
“ኩዩጉዎች የሌላቸውን የማይመኙ በዚህ ኑሯቸውም ከአቅም በላይ ለሆኑ ነገሮች የማይሰጉና የማይጨነቁ ናቸው። ከሁሉም በላይ ባህላቸውን አክብረው ራሳቸውን ሆነው መኖርን ይመርጣሉ።
የሚገርምሽ በልጅነቱ ከነሱ የተለየው አያቴ እንኳን እንደ
ዘይትና ውሃ ለረጅም ጊዜ ከኖረበት ስልጣኔና ባል ጋር ሳይዋሃድ ነው ወደ መቃብሩ የወረደወ:

👍26❤1👎1🥰1