#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሦስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ሲሚንቶና ብረት የጫነው ኤንትሬ ከሌሊቱ አስር ሰዓት
ከእርባምንጭ ተነሳ፡፡ ያጓራል ያቃስታል ይንቶሰቶሳል. ጉራው
እንጂ ጎዞው የኤሊ ነው፡፡ ማዝገም… ከአርባምንጭ ቀይ አፈር ሁለት መቶ ስምንት ኪሎ ሜትር ለመጓዝ አስራ ሁለት ሰዓት ፈጀበት፡፡ሲሚንቶና ብረቱ ላይ ያሉት ተሳፋሪዎች የተሳፈሩት ተለምነው
ሳይሆን ለምነው ነው፡ ወደ ጂንካ የሚሄድ አስተማማኝ
ትራንስፖርት የለም፡፡ ወደዚያ መሄድ የፈለገ አማራጭ እንደሌለው አውቆ በአጋጣሚው መጠቀም አለበት፡፡ ካለበለዚያ ሲቀላና ሴቻ እያለ ሲንገላወድ ይከርማታል፡፡
የሚያንሰፈስፈው ውርጭ እያኮማተረው የማያተኩሰው የፀሐይ ሙቀት እያቃጠለው አይኑ ጆሮው አፍንጫው፦ አፉ አቧራ እየቃመ ከመሬት ርቆ ጭነት ላይ የወጣው ተሳፋሪ ለሁሉም
ሳይሳቀቅ ጭንቅላቱን በጨርቅ ቢጤ ጠቅልሎ በሁለቱ እጁ ካቦውን
ጥርቅም አድርጎ ይዞ እየተናጠ መጓዝ ነው፡፡ ታዲያ አቀበት ቁልቁለቱ ጫካና ሜዳው አይጠገብም፡፡ እንደ ጥሩ ትርዒት እየተቀያየረ ያዝናናል፧ “ሣይደግስ አይጣላ" እንዲሉ!
ካርለት አልፈርድ አርባ ምንጭ መቆየት አልፈለገችም፡፡በእርግጥ በቦታ አመራረጡ ምሥራቅ አፍሪካ ወደር አይገኝለትም
ተብሎ በውጭ ዜጎች የተመሰከረለት የበቀለ ሞላ ሆቴል ሁለት ቀለማቸው የተለያዩ ሐይቆች (ጫሞና አባያ) በርካታ የሆኑ ምንጮች በኢትዮጵያ ከሚገኙት ታላላቅ ተራሮች አንዱ ጉጂ ተራራና ከስሩ የኢኳቶሪያል የዝናብ ደን ያለው ተፈጥርው የማይሰለቻት ቢሆንም ችግሩ ሐመሮች ናፍቀዋታል።
የሐመሩን የፍዬል ቆዳዋን የሐመር ጎረምሶች የሽለሟትን የእጅ አንባር በአስሩም እጣቷ የምትጠቀምበትን ቀለበት የአንገቷን ጨሌ ስታይ የሐመር ትዝታዋ አገረሸ፡፡ መከባበሩ መተዛዘኑ አብሮ
መብላት መጠጣቱ ጫካውና መንደሩ ተራራውና ሜዳው
በተለይም የኢቫንጋዲ ጭፈራው ውልብሎ ታያት፡ ወደ ሐመር የምትሄድ ሳይሆን ከሐመር እንደምትመለስ ሁሉ! ልቧ እንደ ፅናፅል በፍርሃት ተንሿሿ፡ ፊቷ ገረጣ የሐመር ተፈጥሮአዊ ህይወት
ራባት፡፡
አጠገቧ ከኤንትሬው ጀርባ መኪናው ቆጥ ላይ ብዙ ሰው ሰፍሯል፡፡ ወታደር ተማሪ ነጋዴ ቄስ ሳይቀር አለ፡፡ ቀልዱ ጨዋታው ያስቀናል፡፡ ሰዎች ሁሌም ችግር ሲበዛባቸው ደጎች
ተዛዛኞች... መሆናቸው ያለ ነው፡ ካርለት ሁሉንም ስታጤን ቄሱ ሌላው ሲጫወት ዝም ብለው ሲያዳምጡ ይቆዩና ፈርጠም ብለው
ማሳረጊያ ሲሰጡ አስተውላቸዋለች፡፡ በእርግጥም የሚጫወቱት
አይገባትም ፤ ሆኖም ግን ይንከባከቧታል፡፡ አይናቸውን ወርወር
ያደርጉና ፈገግ ይሉላታል፡፡ እየደጋገሙ ያዩዋታል፡፡ ብታናግራቸው በወደደች ግን የቋንቋ ችግር አለ በመካከላቸው፡፡ እሳቸው ስለ እሷ እያሰቡ እንደሆን ገምታለች፡፡ ጠይቃ ሃሣባቸውን ማወቅ ባለመቻሏ ግን በተራዋ እሷም ስለ እሳቸው ማሰብ ጀመረች
ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሉባት ሃገር ነች፡ ክርስቲያኑ ሙስሊሙ… ህዝቡ የአንዱ ወይም የሌላው ተከታይ ነው በአመዛኙ፡ የአገሪቱ ታሪክና የባህል መዘክርም የሚገኙ ናቸው፡፡ ካርለት አንዴ ሰሜን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አክሱም ላሊበላ ባህርዳር ጎንደር ሄዳ ብዙ ቤተክርስቲያኖችንና መስጊዶችን ጎብኝታለች፡ በምስራቅም እንዲሁ ማየት የሚገባትን አይታለች፡፡
ግን ደብረብርሃን ስላሴ
ጎንደርን በጎበኘችበት ጊዜ
የሚባለውን ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ካየች በኋላ ከሁለት ወንድ መነኮሳት ጋር ያደረገችው የሣሣብ ልውውጥ አይረሳትም፡፡
ደርቡሾችና ግራኝ ሞሐመድ ብዙውን የጎንደር ቤተ
መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ሲያፈርሱና ሲያቃጥሉ ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ግን ከመፍረስና ከመቃጠል ተርፏል፡ ሁሉም
አልደረሱበትም፡፡ እና ቤተክርስቲያኑ በወቅቱ
የነበረውን የአገሪቱን
የህንፃ ሥራ ጥበብ ምጥቀት የሚያረጋግጥ ነው፡፡
አፀደ ግቢው በውስጡ ያሉት ሥነ ስዕላቱ በመፅሐፍ ቅዱስ
ላይ ስሟ ሰባ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰላትን ኢትዮጵያን ሃይማኖታዊ
ጥንካሬና ድንቅ የቤተ ክህነት ሥርዓት የሚያረጋግጥ ነው፡፡
ልጅ እግሩ መነኩሴ ለካርለትና ስአስጎብኚዋ የቤተ ክርስቲያኗን ታሪካዊነት ሲያስረዱዋቸው ከቆዩ በኋላ ከደብሩ
ከመውጣታቸው በፊት አንድ ጠና ያሉ መነኩሴ መግቢያው እድሞ
ካለው ሁለት ክፍል አንደኛው በር ላይ ዳዊታቸውን ሲደግሙ አየችና ከመነኩሴው ጋር ለመነጋገር ፎቁ ላይ ወጣች፡፡
መነኩሴው የተቀመጡት ! እሳቸውና ልጅ እግሩ
ከሚኖሩበት ክፍል
በሩ ላይ ነው፡: ከጎን ያለችው ክፍል ቢሮ ናት፡፡
ካርለትና አስጎብኝዋን ሲያዩ መነኩሴው ከተቀመጡበት
ተነሱና በትህትና ተቀበሏቸው፡፡ ወደ ውስጥ ግቡ እንዳይሉ ካርለት
ሴት ናት፡፡ ሴት ደግሞ ወደ መነኩሴ መኖሪያ ቤት አትገባም! ስለዚህ በረንዳ ላይ ቁጭ አሉ፡፡
አባ ከሰል ላይ በበራድ ውሃ ሞልተው ጣዱና ተመልሰው
ለወግ መጀመሪያ እህሣ እንደምን ናችሁ" አሉ፡ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ትግርኛ መሆኑ ከአነጋገራቸው ይታወቃል፡
“እንዴት መነኩሴ ሆኑ?" ብላ ጠየቀቻቸው ካርለት
በአስተርጋሚዋ፡፡
“በአያልቅበቱ ፈቃድ ነዋ ካለ እሱ ፈቃድ ምን የሚሆን አለ" አምላካቸውን ሽቅብ አዩ፡፡ እግዚአብሔር ከመንበሩ ላይ ተቀምጦ
ታያቸው በአይነ ህሊናቸው: ቶሎ ሰገድ ብለው አይናቸውን መለሱ፡፡
እዚህ ምን አገልግሎት ይሰጣሉ?"
እህ የእግዚአብሔርን ቤት! ቤተ ክርስቲያኒቱን አገለግላለሁ ተደብር ደብር እየሄድሁ እግዚአብሔርን ማገልገል ነው ሥራዬ፡ ሌላ
ዓለማዊውን ህይወትማ ትቸው መጥቻለሁ,," ቀና ብለው ሁለት እጆቻቸውን ዘርግተው አጮልቀው
አዩ ወደ መንበሩ
“ቤተሰብ ልጅ አልነበረዎትም? ካርለት ሌላ ጥያቂ ጠየቀቻቸው፡
“ነበረኝ እንጂ! ግና ከአንድዬ ምን የሚበልጥ አለ!-" አዩ ሽቅብ፡፡ካርለት ከመነኩሴው ጋር ብዙ ሃሣብ ተለዋወጠችና ደስ
አላት፡
መነኩሴው ሻዩን በብርጭቆ ቀዱና በቀለምሻሽ ዳቦ ቆራርሰው ሰጧቸው ለነካርለት፡፡
“አባ… ሻዩ ፈልቷል አይመጡም ወይ" ጠና ያሉት መነኩሴ ልጅ እግሩን መነኩሴ ጠሩአቸው፡፡
“…ከቤተ-ክህነት ሙያ ሌላ ምን ሙያ አላችሁ?"
“ኧረገይ ከዚህ ሌላ ደግሞ ምን ሞያ ይኖረናል! ኧረ
የለንም፡፡"
“የሃይማኖት ተከታዩ ወደ ቤተ-ክርስቲያኗ ሲመጣ ምንድን ነው የምታስተምሩት?”
“መንፈሳዊ ትምህርት መንፈሳዊ ትምህርት ይማራል! ቅዱሳት መጽሐፍት ይነበበለታል…"
“ቤተ ክርስቲያኗን ስታገለግሉ ለእናንተ የሚያስፈልገው
መሠረታዊ ነገር ይሟላላችኋል?
“ኧረገይ! ኧረ ችግር ነው ችግሩማ እንዲህ በአጭር ጊዜ ተነስቶ አያልቅም ልጅ እግሩ መነኩሴ ተከዝ አሉ፡
"እርስዎ ሃይማኖትዎ ምንድነው? ጠና ያሉት መነኩሴ አንዴ አስተርጓሚዋን ሌላ ጊዜ እሷን እየተመለከቱ ጠየቋት፡፡
“የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ነኝ፡” ሁለቱም መነኮሳት ቀና ብለው አዩዋትናı “አሃ አሉ ባንድነት እንደ መደንገጥ ብለው፡፡
“በእኛ ሃገር መነኮሳት ከመንፈሳዊ እውቀታቸው ሌላ የሞራል ትምህርትና የሙያ ስልጠና ይሰጣቸዋል፡ ስለዚህ መነኮሳት ምዕመናኑ ወደ ቤተ ክርስትያን ሲመጡ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን
ሞራላዊ ትምህርትም ያስተምራሉ፡
“የመነኮሳት እርዳታ በመንፈሳዊና ሞራላዊ ትምህርትም ብቻ
ሳይሆን በስልጠና ባገኙት
ሙያ በህክምና. በጓሮ አትክልት በእንጨትና ብረታብረት ሥራ….. ወዘተ ህዝቡን ያገለግሉታል፡፡
ስለዚህ መነኮሳት የራሳቸው ገቢ ያላቸው፤ ህዝቡን የሚረዱ ምፅዋት
የማይጠይቁ ነገር ግን ለህብረተሰቡ መንፈሳዊና ሞራላዊ ትምህርት
እየሰጡ በሙያ ሰልጥነው ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን አገርን ወገንን… መርዳት መቻሉን አርአያን ሆነው የሚያስተምሩ አባቶች ናቸው

👍24🥰2👎1
“መንፈሳዊ እውቀት ያለው ሞራሉ በተስፋ የተገነባ ህዝብ ደግሞ ሠርቶ የመኖርን ባህል ስለሚጎናፀፍ ህይወቱ መስተጋብራዊ ውህደት ያለው በመሻሻልና በተስፋ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ
ሃይማኖቱን ቤተሰቡን ወገኑን የሚወድና አገሩን በኢኮኖሚ የሚገነባ ቀናኢነት ያለው ዜጋ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጠንካራ መንፈሳዊ እምነት አለ፡፡ ሞራላዊ ትምርት ግን አላይም፡፡
የሃይማኖት መሪዎችም ከመንፈሳዊ ትምህርታቸው ውጭ ስርተው የሚያስተምሩ ሳይሆን ተቀምጠው ከህዝቡ ምፅዋት የሚጠብቁ
ይመስላሉ! ይህ ደግሞ ህዝቡንም እነሱንም በሃይማኖታቸው ላይ
ያላቸውን ፍቅር ቀስ በቀስ ይሽረሽረዋል፡"
“ይህ እውነት ነው፡፡ ችግሩ አለ…" አሉ በእድሜ ጠና ያሉት መነኩሴ፡፡
አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት ዘዴኮ ጥንት የናንተ የነበረ ነው፡፡ ለምንድን ነው ቤተ ክርስቲያናትና መስጊዶች በአገራችሁ የታሪክ ቅርስ ተብለው ጎብኚ የሚጎርፍላቸው በእኔ እምነት ይኸን ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ ሌሉቹ የታሪክ ቅርሶች የተነደፉት
የተቀነባቡሩት በሐይማኖት መሪዎች ይመስለኛል፡፡ የሃይማኖት መሪዎች በአርአያነት ስለሚታዩና
ህዝቡንም በሞራላዊ
ትምህርታቸው ስላስተባበሩት እኒህ ድንቅ ቅርሶች ለዚህ ትውልድ
የሚያኮሩ ሁነዋል…"
ኧረገይ አባቴ ይህች ሰውኮ የምትለው እውነት ነው!”
አሉ ልጅ እግሩ መነኩሴ የጥንቱ የቤተክርስቲያን አባቶች እየታዩዋቸው፡
የእኛ ችግር የነበረውን እየናቅን ብርሃኑን ትተን ወደ
ጨለማ መጓዛችን ነው" አሉ ጠና ያሉት መነኩሴ ሐዘን ልባቸውን ሰብሮት ካርለት ብዙ ብታጫውታቸው በወደደች መቀደም ግን
አትሻም በጊዜ፡፡ እና ጊዜዋን ለመጠቀም ተሰናብታቸው ሄደች፡፡
ካርለት በጭነት መኪናው እየተጓዘች ከመናኩሳቱ ጋር
ጎንደር ላይ ያደረገችውን የሃሣብ ልውውጥ አስታወሰች፡፡ እኒህ አብረዋት ከሚጓዙት ቄስ ጋር ግን መወያየት አልቻለችም፡፡ ድልድዩ
የለም የቋንቋው፡፡
ኤንትሬው የቀይ አፈርን ዳገት አቃስቶ አቃስቶ ጨረሰው ካርለትም ከሰፈረችበት የኤንትሬው ቆጥ ላይ ወረደች፡፡...
💫ይቀጥላል💫

👍16❤7👎1
#የመኖር አጋማሽ ..የመሞት ሲሶ ... መሃል መንገድ ላይ ..... (ክፍል አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
ማነኝ?
ለመርማሪ ፖሊሱ 'ነፍሰ ገዳይ' ነኝ:: እገሌ ዶክተር ነው: ኢንጅነር ነው... ምናምን እንደሚባለው... 'እ ... ሜላት? እሷኮ ነፍሰ ገዳይ ናት!' የሚል ማዕረግ ያለኝ ነኝ:: .. ድርጊት ወይም ድርጊቶች ናቸው ማንነቶቻችን?? እንደዛስ እንኳን ቢሆን እኔ የትኛዋን ነኝ?? እንደተናኜ አባባል 'አር ከማር የምትለየዋን' የአሁኗን ሜላት ወይስ ነፍሰገዳይዋን ሜላት?
"እትዬ በሰዓቱ የሆነውን ያደረጉበትን ምክኝያት: የነበሩበትን ሁናቴ እና ሌሎች አጃቢ ግብሮች ማወቅ ባልቻሉበት ሁኔታ ድርጊቱ ብቻውን የተሟላ መረጃ አይደምኮ!!" ዝም ስለው አሁንም ይቀጥላል!
ከፖሊስ ጣቢያው ከተመለስኩ ጀምሮ ለሰዓታት የማውቃቸውን ቃላት እዛ መርማሪ ፖሊስ ጠረዼዛ ላይ አስቀምጬው እንደመጣሁ ሁላ ዲዳ ሆንኩ:: ሳሎን ሶፋው ላይ እንደተጋደምኩ ተናኜ የሚለበስ አምጥታ ደረበችልኝ:: ጎንጤ ለእኔ ይሁን ለራሱ እንጃ ብቻ ነፍሰ ገዳይነቴን ማለዘቢያ ሰበብ ያስረዳኛል::
የሚለው ነገር እኮ እውነት ነው ለምሳሌ 'ሜላት ባሏን ገደለች' ከሚለው በምንም አጃቢ ምክንያት ካልታሸ ዓረፍተ ነገር:: 'ሜላት ባሏ ሊገድላት ሲል ሽጉጡን ቀምታ ገደለችው' ቢባል ራሱ ነፍሰ ገዳይነት ግን ራሷን ለመከላከል የገደለች ትንሽ የሚታዘንላት ነፍሰ ገዳይ ያደርገኛል:: ወይም 'ሜላት እህቷን ሊገድል ሽጉጥ ደግኖ የነበረውን ባሏን እህቷን ለማትረፍ ባደረገችው ትግል የባሏ ህይወት ሊያልፍ ችሏል' ያው ነፍሰ ገዳይነት ትንሽም ጀግንነት ሁሉ ይኖረዋል:: .... የእኔው አጃቢ ሁኔታኮ 'ሜላት ባሏን ገደለች' የሚለው ልዝብ ገላጩ ነው:: ... 'አጅሪት' ያለኝ መርማሪ ፖሊስ የማስታወስ ችሎታዬን ማጣቴን ከግምት አስገብቶ በማባበል ቃል መርጦ እንደነገረኝ.... እስከዛሬ በስራው እንደእኔ ዓይነት ኬዝ ገጥሞት አያውቅም!! እንደእርሱ ገለፃ ..
የሆነ ቀን ቢሮው ተቀምጦ የተለመደ ስርቆት: ድብድብ... ወንጀሎችን ሲመረምር በሩን ከፍቼ ገባሁ:: ሁለት የሰው ቆለጥ ጠረዼዛው ላይ ዱብ ሲል ነው የገባው ሰው ባልደረባው አለመሆኑን ያወቀው... በደም የተለወሰ እጄን ልብሴ ላይ እየጠራገግሁ
" ፍሬውን ማስረጃ እንዲሆንህ ነው ያመጣሁልህ! ዋናውን ከፈለግከው አጉርሼዋለሁ:: " አልኩት:: ሬሳው ያልኳቸው ቦታ እንዳልኩትም ዋናውን ጎርሶ አገኙት:: የወንድነት ንብረቱ ከፊሉ መርማሪው ጠረዼዛ ላይ ... ከፊሉ አፉ ውስጥ ከመዝረክረኩ ውጪ በጥይት ነው የተገደለው.... ምክንያቴን እንዳስረዳ ስጠየቅ 'እንዴት እንደምገድለው ለረዥም ጊዜ ሳስብ ቆይቼ ተሳካልኝ::... ለዝህችው አቅሙ ይሄ የማይረባ.. ስንት እንዳስለፋኝ::" ብቻ ነው ያልኩት... በድርጊቴ ከልኩ በላይ መርካቴ ሲደመር ሟች ለመሬት ለሰማይ የከበደ በህዝብ ዘንድ የተወደደ ባለስልጣን መሆኑ ፍርዱን የእድሜ ልክ እስራት አስፈረደብኝ::
እኔ ይሄ ነፍሰ ገዳይነት በምን ምክንያት ቢቀመም: በምን ነባራዊ ሁኔታ ቢሰነግ ነው የሚለዝበው??
ገዳይነት ብቻ አይደለም እንደሁኔታው ሊገዝፍ እና ሊቀል የሚችለው?? የሟች ነፍስም ሊገዝፍ እና ሊቀል ይችላል... እንትን አውራጃ በነበረ የእርስ በእርስ ግጭት 200 ሰው ሞተ ከሚል ዜና እና እገሌ የሚባለው እውቁ ፖለቲከኛ ተገደለ! ከሚል ዜና ሲነፃፀር ከ200 ነፍስ የአንዱ ታዋቂ ነፍስ ይገዝፋል:: ... ያው ሞት ሚዛን ይሰፈርለታል:: ....
"እኔ ምን አውቃለሁ የሳብሽውን ገመድ!! " ብሎኝ ነበር መርማሪው የእድሜ ልክ ከተፈረደብኝ እንዴት ልወጣ እንደቻልኩ ስጠይቀው::
ሰውዬው ስለነገረኝ ይሆን አስታውሼ አላውቅም:: አይኔን ለመጨፈን ስሞክር የሚታየኝ ጠረዼዛ ላይ የሚንከባለል ቆለጥ ነው::.... የምግብ ጣዕም ሁሉ ደም ደም አለኝ:: .... ከዚህ በኃላ ስላለፈው ለማወቅ መቆፈሬን ማቆም ይኑርብኝ መቀጠል ግራ ገባኝ::... ፍርሃት ብቻ ነው የሚንጠኝ:: ጎንጤ አርጅቶ ሽፋኑ የተልፈሰፈሰ መፅሃፍ ቅዱስ አምጥቶ ከተኛሁበት ራስጌ እያስቀመጠ
"ባታነቢው እንኳን ከራስጌሽ ይኑር :: ከበረታሽ ግን አንብቢው ያበረታሻል:: " ብሎኝ ብሎኝ ሲወጣ መፅሃፍ ቅዱሱን አንስቼ አገላበጥኩት:: በእርግጠኝነት የማልገልፀው የእሩቅነት ... የባይተዋርነት ስሜት ተሰማኝ:: ከመንፈሳዊነት የራቀ ህይወት እንደነበረኝ ለመረዳት ምንም ቀመር የሚያስፈልገው ሆኖ አይደለም:: እንደው ግን ቢያንስ በልጅነቴ... አንዱ የህይወቴ ቀን ላይ እንኳን ከእግዚአብሄር ደጅ ተገኝቼ አውቅ ይሆን??
"ተናኜ? ተናኜ? (በሩ ላይ ተለጥፋ እስክጠራት እየጠበቀች ይሁን ዘላ ገባች) ቤተክርስቲያን የሚለበስ ልብስ አውጪልኝ እስኪ... ይዘሽኝ ትሄጃለሽ" አልኳት... ሄዳ የሆነ የራሷን ሰፊ ጉርድ ይዛ ተመለሰች
"ይሄ ከበቃዎት ይሞክሩት እንጂ እትይ እርሶ ቀሚስ የሚመስል ነገርኮ የሎትም" አለች... ጎንጤ ብድግ ብሎ ሲከተን
"አንተ እዚሁ ሁን ችግር የለውም!" ብዬው ነበር:: አልሰማኝም!
"የማይሆነውን! በመንገድ ምን ሊገጥሞት እንደሚች ምን አውቃለሁ? አንዱ የጠገበ ቢጋጭዎትስ? ደሞ ቤተክስኪኑ ትንሽ ያስኬዳል እንደዚያ እርቀት ለመሄድ የሚያስችል አልጠነከሩም! ታክሲ ይጠራልዎ!" ብሎ ለሶስት በታክሲ ሄድን... ቤተክርስትያን ጊቢ ውስጥ አንዱን ዛፍ ደገፍ ብዬ ተቀመጥኩ... ተናኜ ትታኝ ልትፀልይ መሰለኝ ሄደች:: ጎንጤ ትንሽ ራቅ ብሎ እጁን ደረቱ ላይ መስቀልኛ አጣምሮ ያነበንባል:: .... የመጣሁት ላዋራው ነበር:: ልፀልይ: ልለምን.... ዝም ብቻ ነበር ግን ያልኩት... ምን ብዬ ነው የምለምነው?? ብዙ ደቂቃ ፀጥ ብዬ ተቀመጥኩ...
"ልጅ ሜላት" የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞርኩ!! ነጭ ነጠላ ራሳቸው ላይ የጠመጠሙ : በእድሜ ተለቅ ያሉ ሰው ናቸው::
"አንቺ ነሽ? " ብለው የተገረመ እና የመደሰት ቅልቅል ፈገግ እያሉ በትኩረት እያዩኝ.... " ያሰብሽው ሞላልሽ?" አሉ እየተጠጉኝ በጋቢያቸው ስር ደብቀው የያዙትን መስቀል አውጥተው እየተጠጉኝ..... ዝም ብዬ አያቸዋለሁ:: ከመፅሃፍ ቅዱሱ ይልቅ እኚህን ሰው ልቤ ያውቃቸዋል:: ብርድ ያንዘፈዘፈው ልቤ ባልገባኝ ምክንያት ሞቀው...
"ምነው ልጄ ደህናም አይደለሽ? ምነው አፍሽ ሰነፈብኝ?" አሉኝ ቀርበው ግራ በመጋባት እያዩኝ .... ጎንጤ ቀረብ ብሎ የሚሆነውን ይከታተላል:: .... ሳላስበው እንባዬ ይፈነቅለኝ ጀመር.... ለመጀመሪያ ጊዜ ከአደጋው ከነቃሁ ከወር ከአንድ ቀን በኃላ ... በስሜ ጠርቶ በፍቅር ያየኝ ሰው ገጠመኝ.... ድምፅ አውጥቼ እነፋረቅ ጀመር::
"እኔን ልጄ!! ምን ገጠመሽ? " ሲሉኝ ከተቀመጥኩበት ዘልዬ ተጠመጠምኩባቸው... ግራ እንደገባቸው ያስታውቃሉ:: አቀፉኝ..... እቅፋቸው ውስጥ ነፍሰ ገዳይ መሆኔን ረሳሁት.... ያየኝ ሁሉ ዓይን ውስጥ ያየሁትን ፍርድ እና ጥላቻ ረሳሁት... ግራ መጋባቴን ረሳሁት.... ባዶነቴን ረሳሁት .... ለደቂቃዎች ብዙ ነገሬን ረሳሁት... ሲያባብሉኝ ቆይተው .... እኔ ተቀምጬበት የነበረ ዛፍ አጠገብ ያለ ጉቶ ላይ አረፍ አሉ እንድቀመጥ እግራቸው ስር አስዩኝ:: .... ከሁኔታቸው ከዚህ በፊት አድርጌው የማውቀው ነገር እንደሆነ ገባኝ:: እግራቸው ስር ተዘርፍጬ ጉልበታቸውን ደገፍ ብዬ የተፈጠረውን ነገር ሆስፒታል ከነቃሁ ሰዓት ጀምሬ ነገርኳቸው:: ዝም ብለው ሲሰሙኝ ቆይተው ብርዳሙ ልቤን የሚያሞቅ ፈገግታ ፈገግ ብለው::

👍24❤3
"ልጄ እኔ በዘመናት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ፀሎት በአንድም በሌላም መንገድ ሲመልስ አይቻለሁ:: ያንቺ ግን ይለያል! (መገረማቸው ይሰማል) የዛሬ ሁለት ወር ገደማ የገብርኤል እለት ማግስት እዝህችው ቦታ እንደዝህችው ተቀምጠሽ 'ያለፈውን ሁሉ በላዺስ ማጥፋት ቢቻል እና እንደአዲስ ሀ ብዬ መኖር ብችል?' ያልሽኝ! 'በቃሉ: በንሰሃ: በጌታችን ደም እንደአዲስ ስርየትን አጊንተሽ መኖር ትችያለሽኮ!' ብልሽ .... 'አይ አባ መች እንዲህ ቀሎ!' ነበር ያልሽኝ:: ልጄ የተመኘሽውን አዲስ ህይወትኮ ነው እግዚአብሔር የሰጠሽ!! " አሉኝ ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉ.... እዚህችው መኖር አይቻልም?? ቤት አልፈልግም... ፀሃይም ዝናብም... ክረምትም በጋም ለምን እዝህችው እግራቸው ስር ሆኜ አያልፍም?
የጠየቅኩትን አዲስ ህይወት እንድፅፍ ጭንቅላቴን ነጭ ወረቀት አድርጎ እንደሰጠኝ ቢነግሩኝም ስለራሴ የነገርኳቸው ነገር ካለ እንዲነግሩኝ ጠየቅኳቸው::
"መጀመሪያ ያገኘሁሽ ቀን ... እርግጠኛ ቀኑን አላስታውሰውም... ሰባት ስምንት ወር ቢሆን ነው... እዝህችው ጋር ቆመሽ በአምላክሽ ተቀይመሽ ጮክ ብለሽ እየተጣላሽው ነበር:: እያለፍኩ ገርመም ሳደርግሽ 'ምን ያፈጣሉ? በእግዚአብሄር የተናደደ ሰው አይተው አያውቁም? ' ብለሽኝ ነው ያስቆምሽኝ.... የዛን እለት ለብዙ ዓመታት ፈልገሽ አስፈልገሽ ያገኘሻት እናትሽ ስታገኛት በማይድን በሽታ ልትሞት ወራት እንደቀራት የሰማሽ ቀን ነበር:: ... ዝርዝሩን አልጠየቅኩሽም... ሲጠይቁሽም አትወጂም.... ከዛን ቀን በኃላ ቢያንስ በሳምንት ካልያም በሁለት ሳምንት አርብ አርብ ትመጫለሽ... ያሳለፍሽው ህይወት በዝርዝር ባትነግሪኝም ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው:: .... መጥተሽ እዚህጋ ትቀመጫለሽ... አንዳንዴ ታዋሪኛለሽ ሌላ ጊዜ በዝምታ ቆይተሽ ትሄጃለሽ.... "
"እናቴ ምን ሆነች ከዛ? የት እንደሆነች ነግሬዎታለሁ?"
"አልነገርሽኝም ልጄ! እናትሽ እኔ እስካገኘሁሽ ድረስ በህይወት ነበሩ:: ወንድም እንዳለሽ ነግረሽኛል:: ስለእናትሽ ለወንድምሽ መንገር ተጨንቀሽ ነበር:: አዝናለሁ ልጄ ከዚህ በላይ የማውቀው የለም!" አሉኝ አሁንም ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉኝ..... እናት? የት ናት? ወንድም?? ታዲያ ለምንድነው ብቻዬን የምኖረው? ለምንድነው ጎንጤም ተናኜም ፖሊሶቹም የማያውቋቸው?? እነርሱስ ቢሆን እንዴት ሊፈልጉኝ አልመጡም? ....
...........ይቀጥላል.......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

👍25🥰12❤4
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ስድስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
«ልጄ ዘመንሽን ሁሉ ክፉ ያደረጉብሽን ሰዎች ለመበቀል ስትዪ ነው የኖርሽው። እንደገባኝ ከሆነ ከበቀል እና ለወንድምሽ ከመኖር ውጪ ሌላ ልምድም ህልምም ስላልነበረሽ የጎዳሽን ሰው ካጠፋሽ በኋላ አንቺ የምትኖሪለት ነገር አጥተሽ ነበር። ልጄ የበደሉሽን ይቅር በይ፣ ራስሽን ይቅር በይ! ለፍቅር በፍቅር ለመኖር ራስሽን አስለምጂ! እግዚአብሄር አዲስን እድል ሰጥቶሻል።» አሉኝ ከጉልበታቸው ላይ ሳልነሳ ብዙ ደቂቃዎች ወይም ሰዓት ካለፈኝ በኋላ
«አባ ለምንድነው ብዙ የሚያውቁት ነገር ያለ ግን ያልነገሩኝ የሚመስለኝ?»
«የማይበጅሽን ብነግርሽ ምን ሊጠቅምሽ ልጄ? ስላሴ ከጭንቅላትሽ ብን አድርጎ ያጠፋው ባይጠቅምሽ አይደል? ወይም ለጊዜው ባያስፈልግሽ? »
«አባ ያለትናንት ዛሬን መኖር ይቻላል? ትናንት የሌለበትስ ዛሬ አለ? እያንዳንዱ ከሰዎች ጋር የሚያያይዘኝ ገመድ ከትናንት ጋር የተጋመደ አይደለም? ቤተሰቦቼም እኮ ትናንቴ ውስጥ የነበሩ ናቸው። እሺ ካልነገሩኝ እናቴን ወይ ወንድሜን እንዴት አገኛቸዋለሁ?»
«የሚጠቅምሽን መረጃ አልደብቅሽም ልጄ። ስለእናትሽ ብዙም አላወራሽኝ ስለወንድምሽ ግን አውርተሽ አትጠግቢም። ስሙ በየእለቱ የምደግመው ስለለሆነ አልዘነጋሁትም። ኪዳን! አዎ ኪዳን ነው።» ጀርባዬ ላይ በትልቁ የተነቀስኩት የወንድሜን ስም ነው ማለት ነው። «ጥይምናው እና ፈገግታው ያንቺው ነው።» ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጉልበታቸው ቀና አልኩ
«እንዴ አባ ያውቁታል? አብሮኝ መጥቶ ያውቅ ነበር?» አልኩኝ በጉጉት
«እንደዛ አይደለም ልጄ! በስልክሽ ነው ምስሉን ያሳየሽኝ። » ጠይም ሳቂታ .......... የአልጋዬ ኮመዲኖ ላይ ያለው ፎቶ ነው የሚሆነው
ስልኬ! ......... እንዴት እንደምከፍተው ማወቅ አቅቶኝ መሳቢያ ውስጥ ያስቀመጥኩት መስታወቱ የተሰነጣጠቀ ስልኬ! ቀና ብዬ ጎንጤን አየሁት። ከተቀመጥኩበት እየተነሳሁ
«አባ ልሂድ በቃ! ብመጣ አገኝዎታለሁ? »
«አለሁኝ ከቤቱ የት እሄዳለሁ? (ወደ ሰማይ መልከት አደረጉ) በአይንሽ ካጣሽኝ መልከፃድቅን ጥሩልኝ በይ!» የለበስኩትን እያጤኑ «ለምስጋና እንደመጣሽ አምኜ አምላኬን አመሰግናለሁ» አሉኝ። መጨረሻ ላይ የተናገሩት እንዳልገባኝ ገብቷቸው ፈገግ እያሉ። «ሁሌም ስትመጪ ሌጣሽን ያለክንብንብ ደግሞም የክፉ ነገሮች ምስል ያለበት ልብስ ለብሰሽ ነበር። አንድ እለት ከጀርባው ትልቅ የእባብ ምስል ያለበት ጃኬት አድርገሽ 'ምነው ልጄ ከጀርባሽ ፈልገሽው ነው?' ብልሽ። ' ከእግዚአብሄር የታረቅኩ ቀን ለምስጋና ስመጣ ቀሚስ ለብሼ ነጠላ ደርቤ እመጣለሁ።' ብለሽኝ ነበር።» አሉኝ።
እቤት የምደርስበት ሰዓት እርቆብኝ ከደረስኩ በኋላ ከስልኬ ጋር ተፋጥጫለሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ምስላቸው የሌሉ ነገሮችን እንኳን ስይዛቸው በደመነፍስ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቅ ነበር። ለምንድነው ስልኬን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ የገባኝ?
«ባትሪ ያለው አልመሰለኝም! እንዱለው ይሆን?» አለኝ ጎንጤ አለማወቄ ቢገባውም እንዳያሳፍረኝ በመጠንቀቅ ዓይነት። አቀበልኩት። ተቀብሎኝ ግድግዳው ላይ ተሰክቶ ገመዱ የተዝረከረከ ገመድ ብድግ ሲያደርግ የሚቀጥለው ሂደት ጫፉን ስልኩ ላይ መሰካት እንደሆነ አውቃለሁ። የሆነ አለ አይደል ሰው መንገድ ጠፍቶበት ልክ ቤቱን ሲያየው ይኸው እንደሚለው ዓይነት ነገር?
አባ 'እግዚአብሄር ጭንቅላትሽን እንደህፃን ልጅ ነጭ ወረቀት አድርጎ ሰጥቶሻል፣ የሚቀጥለውን ዘመንሽን አስተካክለሽ ፃፊበት' ይበሉኝ እንጂ እንደህፃን ነጭ ወረቀት የሆነ ጭንቅላት እንዳልቀረኝ አውቃለሁ። እንደህፃን እንዴት እንደምበላ ከ 'ሀ' አልጀመርኩም ወይም አፌ አልጠፋብኝም፣ መራመድ ለመቻል ከመዳህ አልጀመርኩም ፣ 'ኡፉ ነው' ባልባልም እሳት እንደሚፋጅ ሳየው አውቄያለሁ፣ ሽንቴን ልብሴ ላይ ይሁን ሽንት ቤት የምሸናው ሳላውቅ እላዬ ላይ አልለቀቅኩም፣ ሱሪ ለመልበስ በአንገቴ አላስገባሁም ወይም ጫማ ለማጥለቅ ግራ አልተጋባሁም፣ አልጋ ሳይ ይሄ መተኛሽ ነው ሳልባል ገልጬ ውስጥ ገብቼ ተኝቻለሁ ፣ የጥርስ ብሩሽ ሳይ ምንም ሳልጠይቅ እጄ አንስቶ ጥርሴን ቦርሿል .........
2. ስልኬ
ስልኬ ለመጀመር የሚያስችለውን ባትሪ ሲያገኝ ራሱ ከፈተ። እስክሪኑ ሲበራ ዘልዬ አጠገቡ ደረስኩ እና አነሳሁት። ያ አልጋዬ አጠገብ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ዓይኖች ያሉት ፎቶ ይታያል። ራሱ ነው! ኪዳን ነው። ትልቅ ሰው ሆኖ! ይሄን ምስል ሳየው እስከአሁን ምስሎቹን በወረቀት ሳየው ከተሰማኝ የተለየ ስሜት ተሰማኝ። የሆነ የሚያፍን ፈንጠዝያ! ልቤ ሰውነቴ ውስጥ ይነጥር ጀመር። ስልኬን በችኮላ ብነካካውም በኮድ ተዘግቷል። ተስፋ ቆርጬ መሬቱ ላይ እንደተቀመጥኩ
«እትዬ ስልኮትን በፊትዎት ነው ሲከፍቱ ያየሁት!» አለችኝ። እንዳልገባኝ አውቃ ስልኩ እጄ ላይ እንዳለ ወደ ፊቴ ስታቀርበው እውነትም የኮድ ምልክቱ ተነሳ። የሚቀጥለውን ፍለጋዬን ለማድረግ በረጅሙ ተነፈስኩ። ወዲያው ስልኩ በመደዳ የማያቆም ተደጋጋሚ ድምፅ ያሰማ ጀመር። ለምን እንደሆነ ድምፁ ረበሸኝ። የሆነ ቀጥሎ መጥፎ ክስተት ይከሰት ይመስል ጭንቅላቴን ወጠረኝ። መሬቱ ላይ አስቀመጥኩት። የሆነ ግጭት ጭንቅላቴ ውስጥ የተከሰተ መሰለኝ። የሆነ የተኩስ ድምፅ ነገር።
«ምነው እትይ? አመሞት እንዴ? » ወድያው አስከትላ «ጎንጥ! አንተ ጎንጥ» ጆሮዬ ላይ አምባርቃ ተጣራች። በረንዳው ላይ የነበረ መሰለኝ
«ምንድነው?» ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።
«እኔእንጃ የስልኩ ድምፅ ረበሸኝ።» አልኩት ስልኩን ካስቀመጥኩበት አንስቼ እያቀበልኩት።
«ደውሎ ያጣዎትን ስልክ መልእክት እየላከልዎት ነውኮ! ሌላም መልዕክቶች አሉት።»
«የሚጠቅም ነገር ካለው አንብብልኝ» አልኩት ልቤ ለምን እንደፈራ ሳላውቀው እየተርበተብኝ። ዝም ብሎ ስልኩን ሲነካካ ቆይቶ
«ሾካካ የሚባል ሰው 'ዛሬ ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ ስለሚመጡ ቤቱ ይፅዳ' የሚል መልዕክት ልኮልዎት ነበር። ኦው ብዙ መልዕክት ነው የላከው። 'ምነው ዘጋሽኝ? በሰላም ነው ስልክሽ የማይሰራው?'......... 'ኸረ ምንድነው ጉዱ አንቺ ሳይኖሪኮ ቤቱ ስርዓት አጣ! '...... »
«ተስተምረሃል እና?» አለች ተናኜ በጣም በተገረመ አባባል አገጭዋን በእጅዋ ደግፉ ጎንጤን እያየችው። እሷ ማንበብ እንደማይችል እንዴት አሰበች እኔ እንዴት እንደሚያነብ እርግጠኛ ሆንኩ? አላውቅም! እሱ ተናኜን ቁጣና ግልምጫ ደባልቆ ለግሷት ወደንባቡ ሲመለስ የሚያነብበት ስልት እና ፍጥነት ስለእርሱ ብዙ የማላውቀው ነገር እንዳለ እንድጠረጥር አደረገኝ።
« ........ 'ሜሉ መላ ሳይገባልኝኮ ሁለት ሳምንት ተቆጠረ.' ........... እእ 'መታመምሽን በወሬ ሰማሁ መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ቤትሽን የሚነግረኝ አጣሁ። ብደውል ስልክሽ አሁንም ዝግ ነው።'»
«ራሱ ሾካካው ነው?» ያልኩት አስቤው አልነበረም። ሁለቱም እኩል ሲስቁ አባባሌ ራሴንም አሳቀኝ! ጎንጤ ሳቁን ሲገታ

👍23🥰2❤1
«አዎ ራሱ ነው!........ ' አንቺ በቅርቡ የማትመለሺ ከሆነ ለዳዊት መላዬን እንዲቆርስልኝ ንገሪልኝ ዛሬ ሄጄ ስጠይቀው የማውቅልህ ነገር የለም ብሎ አባርሮኛል።' ......... እ ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር........ ' እመቤት ነኝ ሜሉ ያለፈውን ሳምንት ስትቀሪ ባይመችሽ ነው ብዬ አለፍኩ ይሄንን ሳምንት ስትቀሪ ግን አሳሰብሽኝ። በሰላም ነው?' ........ሌላ ደግሞ ዳዊት የሚባል ሰው......... »ካለ በኋላ ድምፁን ዝግ አድርጎ «እትይ ይሄን ራስዎ ቢያነቡት ሳይሻል አይቀርም ብሎ ስልኩን ዘረጋልኝ። እትዬ ነበር የሚለኝ እሱም እንደ ተናኜ እትይ ብሎ መጥራት መጀመሩ ቁልምጫ መሆኑ ነው?
«አንብበው ችግር የለውም ኸረ!» አልኩት እስከዛሬ ከሚያውቀው የባሰ ምን ሊመጣ ይችላል ብዬ እያሰብኩ። መቼም የገዛ ባሌን ፍሬዎች የቲማቲም ወይ የብርቱካን ፍሬ ከዛፉ እንደመቀንጠስ ቀለል አድርጌ ከሰውነቱ ቆርጬ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ከመውሰድ የባሰ ጉዳይ ሊኖር አይችልም!
«አይ እትይ ግድ የልዎትም ራስዎ ያንብቡት!» አለ እያመነታ ስልኩን የዘረጋበት እጁን ሳይመልስ
«ግድ የለህም አንብበው» ስለው እያመነታ
«ካሉ እሺ!» ብሎ እስከዛሬ ያላየሁበት አይነት የማፈር ይሁን የመቅለስለስ ያልገባኝን ፊት እያሳየኝ ማንበብ ጀመረ። « የእኔ ፍቅር ስደውልልሽ አታነሺም ስትመጪ የምንጠጣውን እንዳትረሺ! በጣም ቆየሽኮ ፍቅር በሰላም ነው ስልክ የማታነሺው? ....... »
«እሺ እሱን ተወው እና ሌላ አንብብ ኪዳን የሚል መልእክት የለም?» አልኩት እኔም እንደማፈር እያደረገኝ። ፍቅረኛ ነበረኝ? ቢያንስ የእኔ ፍቅር የሚለኝ ሰው ነበረ።
«እኮ!» ብሎ ጣቱን ወደላይ እና ወደ ታች ኪዳንን ፍለጋ ይፈትለው ጀመር። «አይ እትይ ኪዳን የሚል የለም! ምናልባት በሌላ ስም ይሆናል የመዘገቡት! ስም መዝገቡም ውስጥ ኪዳን የሚል የለም!»
«እሺ እስቲ ሊሎቹን አንብብልኝ እና በሌላ ስምም ከሆነ ከመልእክቱ እንደርስበት ይሆናል።» አልኩኝ።
«ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር አሁንም 'እመቤት ነኝ ሜሉ ያስቀየምኩሽ ነገር አለ እንዴ? በባለፈው ንግግሬ ተቀይመሽኝ ይሆን? ግራ ገባኝኮ! ምንም ውስጥ ሆነሽ ቢያንስ መልእክት ትልኪብኝ ነበር። እንዲህ ጨክነሽብኝ አታውቂም! ብደውልም ስልክሽ አይሰራም። እባክሽ ቢያንስ ደህና መሆንሽን እንኳን አሳውቂኝ!»
«እናቴ ትሆን እንዴ?»
«መደወል እንችል ነበር ግን በሁለት የተለያየ ቁጥር ነው መልእክቱ የተላከው። በየትኛው እንደውል?» አለ ጎንጤ
«ምናልባት የራሷ ስልክ የላትም ይሆናል። አባ ታማለች ብለውኝ የለ? ባለፈው ሳምንት ሳትጠይቂኝ አይደል የሚለው የመጀመሪያው መልእክት?»
«ይሆን ይሆናል። ግን እትይ ለማንኛውም ለጊዜው ማን ምን እንደሆነ እስኪለይ ላገኙት ሁሉ ሰው ምንም እንደማያስታውሱ አይናገሩ! አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሊጎዳዎት የሚያስብ ሰው ሊኖር ይችላል።» አለ ሀሳብ እንደገባው ሰው።
«አንደኛው ስልክ ላይ እንደውል!» አልኩኝ። ስልኩ አድምቆ ሶስታችንም በምንሰማው መጠን ሲጠራ ቆይቶ ከወድያኛው ጫፍ ተነሳ እና የወንድ ድምፅ «ሀሎ» አለ። ቀጥሎ የምለው ግራ ገብቶኝ ሳለ ጎንጤ ስልኩን ወደራሱ አስጠግቶ
«ይቅርታ ያድርጉልኝ እና በዚህ ስልክ እመቤትን ማግኘት እችል ይሆን? ሰው መልዕክት ሰዶኝ ነው!» አለ። የሰውየው ድምፅ ያመነታ መሰለ።
«ማነህ አንተ? እመቤትን ለምንድነው የፈለግካት? ማነው የላከህስ?»
«እኔን አያውቁኝም! እንደው እመቤትን ማግኘትን ብችል ወይ የማገኝበትን ሌላ ስልክ ቢጠቁሙኝ።»
«ተሳስተሃል። እመቤት የምትባል ሴት በዚህ ስልክ የለችም!» ስልኩ ተዘጋ። መልሶ እየደወለ። «ሲወሸክት ነው! » አለኝ ለእኔ
«እመቤት የምትባል ሴት አላውቅም አልኩህ አይደል?» አለ ሰውየው እየተቆጣ
«እየዋሹ ነው እሎታለሁኝኣ! በዚሁ ስልክ ከእመቤት መልዕክት ተልኮ ነበር። እመቤትን ካላወቋቸው እመቤት ነኝ የሚል መልእክት እንዴት እዚህ ደረሰ?» አለ ጎንጤ ቆፍጠን ብሎ ሰውየው ስልኩን ሲነካካ ድምፁ ይሰማል።
«ማነው ላከኝ ያልከው?» አለ በጥርጣሬ እንደማጣራት
«ሜላት»
«ታዲያ ራሷ ሜላት ለምን አልደወለችም አንተጋ ስልኳ ምን ይሰራል?»
«ለጊዜው እትዬ ሜላት ታመዋል። እንደየትም ብለህ መልእክት አድርስልኝ ብለውኝ ነው!» ሲለው ሰውየው የጠበበው ድምጽ አሰማ።
«እ መልእክቱን ብትነግረኝ እኔ እመቤትን ሳገኛት አደርስልሃለሁ። እመቤት የት እንዳለች ሜላት ነግራሃለች?» አለ አሁንም እንደጨነቀው።
«በፍፁም! በዚህ ስልክ ደውል ብቻ ነው ያሉኝ!»
«ዌል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ናት!» አባባሉ 'እስቲ መልእክትህን እዛ ሄደህ ታደርስ እንደሆነ እናያለን!' አይነት ነው።
«እባክዎትን ካላስቸገርኩ ደውዬ እንደነበር መልእክት ያድርሱልኝ!» ብሎ ዘጋ ስልኩን። እናቴ ልትሆን አትችልም! እናቴ እስር ቤት ምን ታደርጋለች? ታማ የለ? ጎንጤ ስልኩን ሲበረብር ስልኩ እጁ ላይ ጮኸ
«እትይ ዳዊት እየደወለ ነው!» አለኝ ስልኩ ላይ አንዳች ነገር ያየ ይመስል እያፈጠጠ።
«አንሳዋ!» አልኩት መልሼ እያፈጠጥኩ
«ኸረግ! ተዚያ ምን ልለው?» ብሎ ስልኩን ክፍት አድርጎ ጆሮዬ ላይ ለጥፎልኝ ለተናኜ እንድትወጣ በዓይኑ ምልክት ሰጥቷት እሱም ወጣ!
«ኦህ ማይ ጋድ ፋይናሊ! በሀሳብ ከማለቄ በፊት! ስልክሽ መከፈቱን ቴሌ ማሳወቂያ ሲልክልኝ አይኔን ነበር ማመን ያቃተኝ! ሜሉዬ የኔ ፍቅር! ምን ባደርግሽ ነው እንዲህ የጨከንሽብኝ?» ሀሎ እንኳን ሳልለው ያለማቋረጥ ይለፈልፋል።
«ትንሽ አሞኝ ነበር» አልኩኝ ጎንጤ ያለኝን አስታውሼ
«ኦህ ማይ ጋድ! ታዲያ አትደውዪልኝም ነበር? እሺ አሁን የት ነው ያለሽው? የት ልምጣ? ኦህ አምላኬ? እሺ አሁን እንዴት ነሽ?»
የሚጠይቀኝ እንድመልስለት አይመስልም! የሆነ ልክ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማኝ አደረገኝ። እቤት እንዲመጣ ስነግረው የቤቴን አቅጣጫ አልጠየቀኝም!
«ጎንጥ ? ዳዊት የሚባል ሰው እዚህ ቤት መጥቶ ያውቃል? ሆስፒታል እያለሁ መጥቶ ጠይቆህ ከሆነ?» አልኩት ወደበረንዳ ብቅ ብዬ። እኔስ ጎንጤን ተናኜ እንደምትጠራው ጎንጥ ማለቴ ማቆላመጤ ይሆን?
«በፍፁም እትይ!»
በር በሩን እያየሁ ቆይቼ መጣ! አራት ጊዜ ባጥፈው ያለምንም መጣበብ ሰፋፊዎቹ ጅንስ ሱሪዎቼ ጎን ኪስ መሰስ ብሎ ጥልቅ የሚል፣ ቀጭን ለመባል ራሱ መወፈር ያለበት ፣ አጭር ቀይ ስጋም ቀልብ የራቀው የሆነ ጥላ ቢስ ነገር ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን ይደረጋል? መቼም ወንድ ነው ብዬ ከስር ሆኜ አልደረግለትም! ከላይ ብሆንበት ከእጥረቱ ከቅጥነቱ ፈሱ ነው የሚያመልጠው።
....................
ይቀጥላል.........

👍40
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
የቀይ አፈር መንደር ገና እያዛጋች ነው፡፡ ካርለት ጥቁርና ቡናማ ቀለም ያለው የፍዬል ቆዳዋን ለብሳ አንባሯን ጨሌዋን
አንገቷ ላይ ደርድራ ቀለበቶችዋን በጣቶችዋ ሰክታ ጥልፍልፍ ነጠላ
ጫማዋን ተጫምታ
እቃዋን በጀርባዋ በማዘል ከከተማው ቁልቁል
በሚወስደው መንገድ ትንሽ ሄደችና ሰፊውን የአርባምንጭ መንገድ
ትታ ወደ ግራዋ በመታጠፍ ወደ ዲመካ የሚወስደውን ጎዳና ይዛ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
በሾላ ቆንጥር ዘረማይ ሶውት• ዲሎ ጉርዶ ሶቆላ… የተሞላውን ጫካ ግራና ቀኝ እያየች የድርጭት ጭልፊት ቁራ
አቲ ሴሌ አርክሻ… አዕዋፍ ዝማሬ እያዳመጠች ልቧ በደስታ እየዘለለ ነጎደች፡፡
የእግር ጉዞ ትወዳለች፡፡ አቀበት ወጥታ ቁልቁለት ወርዳ! ላብ በጀርባዋ ተንቆርቁሮ, ሰውነቷ ዝሎ. ካሰበችበት ስትደርስ
የአሸናፊነት ስሜት ይሰማታል፡፡ በራሷ ትኮራለች ህይወቷ ይታደሳል፤ ልቧ በደስታ ይዘላል።
በተለያዩ ቦታዎች ተራራ ወጥታለች በበረሃ አሸዋ
ተጉዛለች በበረዶ ተንሸራታለች ስለዚህ አካሏ ብቻ ሳይሆን የህሊናዋ ጡንቻም ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ ነው።
በሰዓት በአማካይ ከአራት እስከ አምስት ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች፡፡ ከቀይ አፈር መንደር እስከ ዲመካ ያለው ርቀት ሃምሳ ስምንት ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ሃምሳውን ኪሎ ሜትር ለመጓዝ ከአስር እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ይፈጅባታል፡፡ በየመካከሉ ግን እረፍት
ማድረጓ ስለማይቀር የመድረሻ ሰዓቷ በሁለትና ሶስት ሰዓት ይጨምር ይሆናል፡፡
የለበሰችው የሐመር ባህላዊ ልብስ አምሮባታል፡ ከኋላዋ በኩል የለበሰችው ቆዳ ውን ውን የሚል ሲሆን ከፊት ለፊቷ ግን አጭር ነው፡ ጭኖችዋ ለፀሐይ እንብዛም ተጋልጠው ስላልከረሙ እንደ ፋርኖ ነጭ ሆነው ያስጎመጃሉ፡፡ አንድ ወቅት ፀሐዩ ጠብሷቸው እንሶስላ መስለው ነበር፡፡
በየመንገዱ የሚያገኝዋት መንገደኞች እንግዳነቷን ገምተው ተደንቀው ቆም ብለው ሲያይዋት
ነጋ ያ” ትላቸዋለች፡
ጋ ያኒ" ይሏታል፡፡
“ነኖኖምቤ ቀለሎምቤ
ፈያዎ…" በነጭዋ ሐመር
ይገረማሉ፡ በደስታም ፈገግ ይሉና፡“ፈያኔ! ያ ፈያዎ! ይሏታል፡ ሰላምታዋን አቅርባ ከብቶች… ደህና ብላ ስትጠይቃቸው፡፡ እነሱም የእሷን ደህንነት ሲጠይቋት፡-
“ኢንታ ፊያዋ…” ብላ መንገዷን ትቀጥላለች፡እነሱም በአይናቸው ይሸኝዋታል፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሰላምታ ከተለዋወጡ ደህንነታቸውን ከተነጋገሩ በኋላ፡
“ናቢ ናሞ አይኔ? ይሏታል ስምሽ ማነው ለማለት በሐመርኛ፡፡
“ኢንታው! ፈገግ ትላለች የእኔ ስም በማለት፡፡ እየሳቁ
እራሳቸውን ሲወዘውዙ፡
ናሞ አይኔ ካርለት ስትላቸው ይከብዳቸዋል፡ እንደገና
እየደጋገመች የእኔ ስም ካርለት ነው፡" ትላቸውና ተጨዋውተው
ደሞ ይለያያሉ፡፡
አንዳንዶቹ እንዲያውም ከደስታቸው ብዛት ሮጠው ሄደው በለሻ ወተት ይዘውላት ይመጣሉ፡ እነሱ ዘንድ እንድትውል
እንድታድርም ይጠይቋታል፡፡ “ምነው እዚች ምድር ያለው ሁሉ እንደእናንተ ቅን በሆነ! ብቻ ግን ሁሉም እንዲህ ቢተዛዘን ምናልባት
የህይወት ጣምናውን መግለጽ ይከብድ ይሆናል" እያለች ታስባለች፡፡
ስለዚህ ደግነታቸው አቀባበላቸው ሞራል ስለሚሆናት ስትጓዝ ድካም አይሰማትም፡፡ ላብ ብቻ፡፡ የትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ
ማለት ብቻ… ውስጧ ግን ብርቱ ነው፡፡ ብረት ሞራሏም እንደአለት ጥንካሬው እያደገ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ hብቶችን የሚጠብቁ አፍላ ጎረምሶች
ያጋጥሟታል፡፡መፉቂያቸውን አፋቸው ውስጥ ሰክተው
የሚያብለጨልጭ ጭናቸውን ሳንቃ ደረታቸው ላይ ጨሌያቸውን
ያንዠረገጉ ይቀርቧትና ሞቼ ጉምዛ ክሮጃ መፋቂያ ጨሌ ይሸልሟትና፡-
“እጮኛ አለ?” ይሏታል፡፡
“አዎ!” ትላቸዋለች፡፡
“ሐመር ነው?”
“ከዎ፡፡
“ማን ይባላል?"
“ደልቲ ጉልዲ…"
“ይእ- አንች ነሽ ነጭዋ ሐመር?"
“አዎ"
ካርለት የምትባይው አንቺ ነሻ?
“አዎ-” ይገረሙና
“አንችንማ በስም የማያውቅ ማን አለ! ይእ!.." ሲሏት ካርለት ደስ ይላታል፡፡
ቀኑ እንኳን መሽቶ ከጨለመ በኋላ ሲያገኝዋት ጠጋ ብለው ያነጋግሯትና ሽኝተዋት ይመለሳሉ፡፡ በዚህ በጉዞው ወቅት ቀበሮ
ጅብ… ሲጮሁ ይሰሟታል፡፡ ግን አልፈራችም፡፡ አውሬዎች የሚያጠቁት ፊሪን ነው፡፡ የዓላማ ዕፅት ያለውን ያከብሩታል፡፡
ካርለት ዲመካ ለመድረስ ወደ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲቀራት ደከመች፡፡ በሐመር ባህል ልጃገረድ በምሽትም ሆነ
በቀን ብትጓዝ የሚደፍራት እንደሌለ ጠንቅቃ ታውቃለች:: ስለዚህ
በጉዞዋ ብትቀጥል የሚያሰጋት ነገር የለም፤ ድካሙ ሲጠነክርባት ግን
አንድ በቆሎ እርሻ ውስጥ ገብታ ለወፍ: መጠበቂያ ከተዘጋጀው ማማ ላይ ወጣች ትንሽ ብስኩትና ቼኮሌት ተመግባ በኮዳ ከያዘችው ውሃ ተጎንጭታ “ስልፒንግ ባጓ" ውስጥ ገብታ ከዋክብትን እያየች,
ተወርዋሪ ኮቦችን እየቆጠረች የእንቁራሪቶችን የኮኮሮችን ዝማሬ
እያዳመጠች እንቅልፍ እያባበለ ይዟት ጭልጥ አለ
ካርለት ከእንቅልፏ ስትነቃ ለጊዜው የት እንዳለች ድንግርግር አለባት፡፡ አይኖችዋን ከድና ስታስብ ከየት ተነስታ ወዴት
እንደምትጓዝ መቼ እንደደከማትና ማማው ላይ እንዴት እንደወጣች
ትዝ አላት፡ ራቅ ብለው ጎረምሶችና ህፃናት ይጫወቱ ነበር፡፡ ከማማው
ለመውረድ ስትሞክር ግን ሁሉም ዘወር ብለው አይዋት፡፡ ሻንጣዋን
ማማው ላይ ይዛ መውጣቱ ስለከበዳት ማማው ስር ነበር ጥላው የወጣችው፡ ማማው ከመንገዱ ብዙም ስለማይርቅ እሷንም ሆነ
እቃዋን ብዙ ተላላፊዎች እያዩ ነው ያለፉት፡፡ ሐመር ውስጥ ግን የአንዱን ንብረት ሌላው አይነካም ወድቆ እንኳን ቢያገኝ ዛፍ ላይ
አንጠልጥሎት ይሄዳል፡፡ የጠፋው ተመልሶ እንዲያገኘው
ካርለት ልጆችንና ጎረምሶችን ሰላም ስትል አንድ ልጅ እግር ከቡዱኑ ነጠል ብሉሎ ሄደና፡-
“አይቶ! እረ ኦይቶ" ብሎ ተጣራ፡፡
“ዬ!” የሴት ድምፅ ተሰማ፡፡
“ይዘሽው ነይ እንግዳዋ ልትሄድ ነው" ሲል በሐመርኛ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ካርለት ሰንደል ጫማዋን ቆልፋ ሳትጨርስ
አንዲት ልጃገረድ በዛጎልና ጨሌ የተዋበውን ቆዳዋን እያንሿሿች በቀጭኗ መንገድ እየሮጠች መጣች፡፡ በእጅዋ የወተት መያዣ ዶላ በሾርቃ ደግሞ የማሽላ ጭብጦ ይዛለች፡፡
ካርለት ልጃገረዷ ወደ እሷ ስትመጣ በአድናቆት
ተመለከተቻት፡፡ ኦይቶ ሰላም ብላት የወተቱን ዶላ ሰጠቻት፡፡ በሐመር ባህል የቁጥ ቁጥ ስጦታ የለም ያን የምታውቀው ነጭዋ ሐመር ዶላውንና ሾርቃውን ተቀበለቻት፡ ርቧታል፡፡ የዶላውን ክዳን ደፍታ
በ“ዶንግ" የታጠነውን ትኩስ ወተት በክዳኑ ቀዳቸና አንዱን ለጥሟ ጠጣች፡ ከዚያ ጭብጦውን በወተቱ እያማገች በላችና፡-
“ባይሮ ኢሜ” እግዜር ይስጥልኝ ብላ አመስግና ዶለውንና ሾርቃውን ለልጃገረዷ መልሳ ሁሉንም ተሰናብታ አሁንም “ሁላችንም ምን ነበረ እንደ እናንተ ብንሆን! ብላ እየተመኘች ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
ወፎች ይዘምራሉ እሷም ትዘምራለች ከብቶች ያገሳሉ
ተፈጥሮም እንዲሁ. የሙዚቃው ህብረ ዜማ ተዋህዶ በሐመር
ቀዬዎች ያስተጋባሉ አይ ሕይወት! ተፈጥሮ የቃኘችው የህይወት
ለዛ.... ሳያቋርጥ እንደ ምንጭ ውሃ ከአድማስ አድማስ ይንቆረቆራል።
ምህረትየለሽ ቴክኖሉጂ አየሩን ከመበከሉ
ስግብግብነትንና ጦርነትን ከማስፋፋቱ ሌላ ተፈጥሮን ሊያዛባ አሁንም ባልተዳረሰበት ሁሉ ሃዲዱን ዘርግቶ ባህላዊ ህይወትን ሊጨፈልቅ ወደ ሐመር ሲምዘገዘግ ታያት፡፡
“አይ አፍሪካ! አለች ካርለት ከግብፅ እስከ ደቡብ አፍሪካ፧.ከኢትዮጵያ እስከ ሞሪታንያ ያሉትን የአፍሪካ አገሮች እያሰበች፡፡

👍26😱2🥰1
አፍሪካ! አፍሪካ ለአፍሪካውያን የዳቦ ቅርጫት እንዳልነበረች
ሁሉ ሰለጠን ባይ እረኞች አኗኗርን ተፈጥሮዋን
የቅራንቅቧቸው መጣያ ማረጋቸው አንሶ ጨለማ አህጉር¡ ያልሰለጠነ
ህዝብ መገኛ እያሉ ሲመፃደቁ ስትሰማ የኖረችው አቀረሻት።
“አዛኝ መሳይ የአዞ እንባ አፍሳሾች ከሰጠነው በላይ ሰጠን ብለን የምናወራ እብሪተኞች ከዘረፍነው ላይ ለመመፅዋት እንኳን
የሚንቀጠቀጥ ንፉጎች... የአፍሪካውያንን ተፈጥሯአዊ
ህይወት አጠፋንባቸው፤ ማዕድናቸውን ብቻ ሳይሆን ደስታቸውንም ዘረፍናቸው እርስ በርሳቸው አስተላለቅናቸው. እኛ በሐብት ደለብን ! እነሱ በእሪታ ተዋጡ!... ምናለ አሁንስ በቃችሁ ብንላቸው!”
ካርለት በሐዘን እየተንዘፈዘፈች የወሮን መንደር ጎዳና ተያያዘችው።
ካርለት ወሮ መንደር ስትደርስ መጀመሪያ ህፃናት አይተው ከሩቅ ለዩዋት፡፡ ከዚያ ኮረዶችና ጎረምሶች፤ ቀጥሎ የመንደሩ ሰው
ባጠቃላይ ወደ እሷ ግልብጥ ብለው እንደ ንብ ከቦቧት፡፡
ውሾች ጅራታቸውን እየቆሉ ከብቶች እምቡ-ዋ እምቡ-ዋ አሉ ናፍቆታቸውን ገለፁላት፡፡ ተናፋቂዋ የስነ ስብዕ ተመራማሪ ሰዎች እንዲህ ይናፍቁኛል ብላ አታስብም ነብር፡፡ ሁሉም ናፍቆቱን በተለያዬ ስልት ሲያበረክትላት ግን ሆዷ ታመሰ፡፡ ፍቅር ሃላፊነት
ነው ፍቅር አደራ ነው ፍቅራቸውን እንደተቀበለች እሷስ ፍቅሯን ማከፋፈሉ ይሳናት ይሆን? ይህን ስታስብ እየሳቀች አነባች፡:
ሲለይዋቸው የሚናፍቁ ሲገናኝዋቸው የማያሰለቹት ሐመሮች ቅቤና
ጭቃ ሊቀቧት መዓዛው ከጥሪኝ ዝባድ ፈረንሳዮች ከሚቀምሙት ሽቶ
በላይ ጠረኑ ሰነፈጣት፡
ቶዮታ መኪናዋ ከከብቶች በረት ራቅ ብላ ቆማለች፡፡
መንዜው ሐመር አንተነህ ይመር ስላምታው ጋብ ሲል ጭንቅ እስኪላት አቅፎ ወዘወዛት: “ካርለት ነጋያ ካርለት…” እሚላት
ጠፋው፡፡ ስለዚህፈ እንደገና ጨመቃት፡፡ ደክሟታል፡፡ ላዩ ላይ
ለመለጠፍ ግን ሃይል አላጣችም፡፡
ከሎ ሆራ ሁሉም ሰላምታቸውን ሰጥተው እስኪጨርሱ ጠብቆ ወደ እሷ መጣ፡፡ ደንግጧል
ካርለትን በምን መጣች ብሎ ይመን እንደምትጠብቀው ያውቃል
ለቀጠሮ ያላትን አክብሮት
ተለማምዶታል ግን በቀጠሮው ጊዜ አላገኘችውም፡፡ ልጆች ገና
ስሟን ሲጠሩ ከተቀመጠበት ደንግጦ የበረገገው እሱ ነው፡፡
ካርለት!
“አቤት ከሎ እንዴት ድክም ብሎኛል መሰለህ'' ብላ ላዩ
ላይ ወደቀች፡፡ አቀፋት• ደገፋት …..
“በእግርሽ መጣሽ?"
አንገቷን ወዛውዛ “አዎን" አለችው
“ወይ አምላኬ!- ከየት ጀምረሽ?"
“ከቀይ አፈር"
“ከቀይ አፈር! ይበልጥ ክው አለ፡፡ ራሱን ጠላው ህሊናው
ተበጠበጠ፡፡
“አዝናለሁ ካርለት! ጎይቲ መቋሚያ መቀመጫ አሳጣችኝ!''
“የታለች ጎይቲ?" ካርለት ቢደክማትም ጎይቲን እስካሁን ስላላየቻት አሰበች፡፡
“አለች ያቻት ወደ አንቺ እየመጣች ነው"
“ይእ! ካርለት"
“ጎይቲ " ተቃቀፋ፤ ተወዛወዙ
“ይእ!- እኔ አፈር ልብላልሽ!- በእግርሽ መጣሽ?”
“አዎ! በእግሬ መጣሁ ከቀይ አፈር ጀምሮ…" ካርለት ጎይቲን ተደግፋ ከተነጠፈላት የከብት ቆዳ ላይ ተቀመጠች፡፡
“ይእ! እኔ ነኝ ገዳይሽ ዘንድሮ ምነው ቦርጆ በኔ ጨከነ!'' ጎይቲ እንባዋ መንታ መንታ ሆኖ ወረደ፡
“ተይ አታልቅሺ ጎይቲ እንኳን ደህና ሆናችሁ። እኔስ
ድካሙ ትንሽ አሸነፈኝ እንጂ በጣም ደስ ብሎኛል፡" ጫማዋን ፈተው እግሯን በቀዝቃዛ ውሃ ሲያስነኩላት ካርለት አቃሰተች እግሯ ውሃ ቋጥሯል፡
የከበቧት ሁሉ አዘኑላት፡፡
አንተነህ ይመር የከብት ሞራና የጋሊ ቅጠል አምጥቶ እግሯን ሲቀባባላት ሌሉቹ ሸፈሮ ቡና ለማፍላት እሳቱን ግር
አድርገው አንድደው እንስራውን ጣዱት
የሚለፈልፍ ጠቦት ፍየል ጎረምሶች ሰብሰብ ብለው እንደቆመ ጕሮሮው አካባቢ ብልቱን ወግተው ፀጥ ሲያደርጉት ሌሎቹ ቅጠል
ቆራርጠው አመጡና ገፈፋው ተጀመረ፡ ጫካ የሄዱት ወጣቶች
የደራረቀ እንጨት ይዘው መጡ ጥቂት ወጣቶች ደግሞ እንጨቱን
በሰንጢያቸው አሾሉና የሥጋውን ብልት እየወጉ በሳቱ ዙሪያ ተከሉት ወጠሌ ጥብሱ ተጀመረ፡
ካርለትን እንቅልፍ ድብን አድርጎ ወሰዳት የፍየል ቆዳዋን እንደለበሰች፡፡ ጎይቲና እናቷ ከሸፈሮ ቡናው ጎን ሌላ ምድጃ ጥደው
ከብልቱ አጥንቱንና ስጋውን ጨምረው ሾርባ ቀቀሉላት፡፡
ካርለት ከመንቃቷ በፊት ሾርባውን እየሰበቁ አረፋውን ደጋግመው አስወጡና ስትነቃ በሾርቃ አቀበሏት፡፡ ካርለት አይኗን
እንደተጠራጠረች ሁሉ ክድን ክፍት ኦሸት… እያደረገች አየች፡፡
እወ ነት ነበር የወሮ መንደር ህዝብ እንግዳዋን ለመቀበል እንደ ንብ
ሁሉም በየድርሻው ይተማል፡፡...

❤20👍17🥰3
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
የንጋት ፀሐይ ከወደቀችበት ተነስታ ብርሃኗን ሐመር
ላይ ፈንጥቃለች፡ ካርለት ከወሮ መንደር ሆና ቁልቁል የሐመርን ተፈጥሮ ደኑን የልጃገረድ ጡት መስለው በሰማዩ ደረት የተሰካኩትን የአለሌ ኤሎ ኤዲ ቢታ… ተራራዎች ስታይ
የምትሆነው ጠፋት ልብ ሰራቂው ተፈጥሮ አነሆለላት እና! ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ወደ ተፈጥሮ ሮጠች ተፈጥሮም ወደ እሷ ገሰገሰች ተቃቀፉ.. አንዱ የሌላውን ሽፋን አወለቀ… አየሩን ሳመችው... መሬቷን አቀፈቻት... ቅጠሉን ሰበሰበችው…ከወፎች ጌር
ሽቅብ ጎነች… ዳመናውን እየበረቃቀሰች በረረች የተፈጥሮ ፍቅር
የሐመር ተፈጥሮአዊ ሕይወት እንደ ቅንቡርስ በውስጧ ገብቶ በሰራ
አካላቷ ተንከላወሰባት ! እንደ እንበሶች ቦረቀች….. ፈነደቀች ከማራኪዋ ተፈጥሮ ጋር እየደጋገመች ተወሳሰበች…..
እንዲህ በደስታ ሰክራ በድካም ጥንዝል ዝርግትግት ብላ
ሳሩ ላይ እንደተንጋለለች የሰው ድምፅ ሰማች፡፡ 'ምን ነበረበት ከእንደዚያ ካለው ዓለም የማይመለሱ ቢሆን!'
ካርለት!
“አቤት" አለች ዞር ብላ እያየች ካርለት፡፡ “ጎይቲ ነይ
እስኪ አጠገቤ ቁጭ በይ"
“ይእ! ምነው እስካሁን ሳትጠይቂኝ ቀረሽ?''
“ምን ብዬ ጎይቲ?
"ይእ! አሁን እውን እሱ የሚረሳ ሆኖ ነው፡ ናፍቆትሽን ውስጥሽ ቀብረሽ ደብቀሽኝ እንጂ…" ያ ሐጫ በረዶ መሳዩን ችምችም
ያለ ጥርሷን እያሳየቻት ጠየቀቻት፡፡
“ደልቲን ነው! ምን ብዬ ልጠይቅሽ? ወሮ እንደማይኖር
አውቃለሁ፤ ዛሬ ግን ሄጀ ላየው እፈልጋለሁ ናፍቆኛል!"
ጎይቲ ናፍቆኛል የሚለው አባባል የእሷንም እሳት
ጫረባት ወዲያው ገለባው ልቧ ቦግ ብሎ ነደደ፡
“ይእ! ካርለቴ አያ ደልቲ እኔንም ናፍቆኛል ግን የት ሄጄ ላግኘው" ብላ እንባዋ እንደ በጋ ዝናብ የመጣበት ሳይታወቅ ዥጉድጉድ ብሎ ወረደ፡፡ የሳግ ብርቅታ የውስጣዊ ስሜት
ነጎድጓድ… ጎይቲን ደፈቃት፡፡ ካርለት ደነገጠች ደስታዋ በኦንድ ጊዜ ሙሽሽ አለባት፡፡
“ጎይቲ ምን ሆነ? ካርለትን ጩሂ ጩሂ ብረሪ ብረሪ
አሰኛት፡፡ ጎይቲ ግን ካርለት የጠቀቻትን አልሰማችም! በአይነ ህሊናዎ ጀግናዋ እየተንጎማለለ ሲጓዝ አየችው፡፡ ስታየው አቅበጠበጣት ልቧ ዳንኪራ ረገጠባት… ሊርቃት ሆነ፤ መጥራት ፈለገች፡፡
ካልጠራችው እየተንጎማለላ ሄዶ ጫካው ውስጥ ገብቶ ይጠፋባታል፡፡
“አያ ደልቲ!” ተጣራች ጎይቲ ጮክ ብላ እንዲሰማት፡፡
ምን ሆነ ደልቲ" ካርለት ጎይቲን እየነቀነቀች ጠየቀቻት ጎይቲ ግን የጠራችው አንበሳዋ ዞር ብሎ የጠራውን ሰው በአይኖቹ ሲፈልግ የጡቶችዋ ጫፎች እየቆሙ ሰውነቷን እየነዘራት ወደ እሱ
ስትጓዝ ድንገት ጀግናው እየተንጎማለለ ጫካ ገባ፡፡ ሮጠች! እንቅፋቱ
መታት እሾሁ በልቧ ተሰገሰገ… ጫካው ደልቲን ሸፈነው ዋጠው
ለለቀጠው... ስለዚህ ድምጿን ከፍ አድርጋ ተጣራች፡
“አያ ደልቲ ጮኸች ጎይቲ፡፡ ካርለት ግን የምትሆነው
ጠፋት፡-
“ጎይቲ- ደልቲ ምን ሆነ?" ካርለት ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት
አቅም አነሳት• ድካሟ አገረሸ፡፡ ጎይቲ ደግማ ደጋግማ አለቀሰች
እውነተኛውን ደም መሳዩን እንባ!
ደልቲ ምን ሆነ ደ-ል-ቲ ካርለት እንባዋ ግድብን ጥሶ ወጣ› ጎይቲና ካርት ተቃቅፈው ልቅሶአቸውን አስነኩት፡፡
“አያ ደልቲ" እያሉ ጮሁ፤ የገደል ማሚቶው ግን
ድምፃቸውንም ደልቲንም ዋጠው…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ለምን አለቀስሽ?" አላት ከሎ ሆራ፡፡ ቲማቲም
የመለለ ፊቷን እያዬ:
እንዲሁ ጎይተን ምን እንደሆነ ደጋግሜ ስለጠይቃት…"አቋረጣት ከሎ፡-
“ጎይቲ ምን አለችሽ ታዲያ?
“ምንም"
“እንግዲያው ለምን አለቀስሽ?''
“እንጃ ክፉ ነገር የደረሰበት መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከማጣራቴ በፊት ግን እንደዚህ መሆን አይገባኝም ነበር ይቅርታ! አለች ካርለት፡
ከዚያ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ፡፡
“ከሎ አንተ ግን ለምን አትነግረኝም?"
“ምኑን?
“ስለ ደልቲና ስለ አጋጠመው ሁሉ፡፡"
ካርለት ምን ብዬ ልንገርሽ? ጎይቲ እንደዚያ መሄጃ
መቀመጫ አሳጥታኝ መኪናዋን አስተኛሃት! እያለች ወትውታኝ
ካለረፍት ተጉዘን እዚህ ስንደርስ ደልቲ አልነበረም
“ቡስካ ሄዷል' አሉንና እዚያ ሄደን ስንጠይቅ ዳራ የምትባል የሳላ መንደር ልጃገረድ አብራው እንደተቃበጠችና ደልቲ
መቀመጫውን ሰርቶ እንደሄደ ወይሳ እየነፋ ያም እንደነበርና በእርግጥ አልፎ አልፎ ትክዝ ይል እንደነበር ሰማን፡፡ ከዚያ የላላም
የሻንቆም የቡስካም ሰው ዳግመኛ አለማየቱን ተረዳን፡፡
“ጎይቲ ይህን ጊዜ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች መጮህና ማልቀስ ጀመረች፡፡ ዳራ በበኩሏ ጎይቲ ስታለቅስ እሷም በተራዋ ትንፈቀፈቅ
ጀመር” ብሎ ከሎ ገጠመኛቸውን ሊቀጥል ሲል፦
“ከዚያስ ተገኘ? ካርለት ረጅሙን ታሪክ መከታተል
አልቻለችም! ሲቃ ያዛት፡፡
“ከዚያማ ጫማ ጣዮች እንዲተነብዩ ተጠየቀና “ክፉ
አልደረሰበትም፧ ራቅ ብሎ ግን ሄዷል' አሉ፡፡ አንጀት አንባቢዎችም ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ብለው የታያቸውን ተናገሩ፡፡ጎረምሶች ጫካውን ደአሰሱት መልዕክት በየአቅጣጫው ተላከ ከዚያ በካሮ ማህበረሰብ በኩል ያሉት የደንበላ መንደር ሰዎች አየነው ብለው መናገራቸውን ሰማን፡፡
እኔም የአንችን መኪና ይዤ በየመንደሩ ለፍለጋ ዞርሁ
አሁን ደንበላ አይተነዋል እሚለውን ስንሰማ ግን እሱን ልፈልግ ወይንስ አንቺን አዲሳባ ሄጄ ላምጣ በሚለው ከሽማግሌዎች ጋር ስማካር አንች መጣሽ?
ከወጣ ማለቴ ከሄደ ስንት ጊዜ ሆነው?
"ሃያ ቀን በላይ ሆኖታል፡"
እሽ ለምን ነው አንዳንዴ ከፍቶታል የተባለው?"
“ጎይቲን ያፍቅራታል፡ የአንድ ቤተሰብ አባል በመሆናቸው
እንጂ አብሯት ቢኖር ደስታውን አይችለውም ነበር፡፡ ስለዚህ ከአይኑ
ስትርቅ ላይከፋው ሳይተክዝ አልቀረም። ስለ አንችም ደጋግሞ ያነሳ እንደነበር ሰምቻለሁ የእሷ መባለግ አንሶ ጎይቲንም ይዛት ሄደች! እያለ እንደሚቆጭ ኮይታውን ከፍሉ እንደጨረሰ አንችን ሲያገባ ያንን
ለስላሳ ገላዋን እገለብጠዋለሁ' እያለም ሲፎክር እንደነበር ሰምቻለሁ" አላት ከሎ ፈገግ ብሎ።
እውነቱን ነው የሐመር ልጃገረድ ነኝ ብዬ ባህሉን
መቀበሌን አሳውቄ! ካለ ሽማግሌ ፈቃድ ያውም ከሐመር ምድር ርቂ መሄዴ በእርግጥ ሊያበሳጨው ይገባል" አለችና በሃሣብ ተውጣ ቆየች፡፡
እንዲህ ካርለትና ከሎ በሃሣብ ተውጠው እንደተቀመጡ ጎይቲ አንተነህ መጣች
“ይእ ምን ሆናችኁል?"
አለቻቸው ሁለቱንም በፍርሃት አየቻቸው ሆዷ ፈራባት “ጎይቲ ምንም አልሆነም፡፡ አንችን
ጠይቄ ልትነግሪኝ ያልቻልሽውን ስለ ደልቲ ከሎን እየጠየቅሁት ነበር"
“እሁሁ… እኔስ ደሞ ምን ሰማችሁ ብዬ የሆንሁትን
አላውቅም" አለችና ሐጫ በረዶ ጥርሶችዋን አሳይታ
“ይእ! የአያ ደልቲን የኦሞ ዳር ጥንቅሽ የቀመስን እኔና
አንች ሌላው ጣምናውን የት ያውቀዋል" ብላ በሣቅ ተፍለቀለቀችና
ነይ በይ አሁን ቡና ጠጭ እህልም ባፍሽ አድርጊ፡፡
የደንበላ ሰዎች “አይተነዋል ብለዋል እንኳን እስካሁን ደና ሆነ እንጂ ከአሁን በኋላስ ከምስጥ ዋሻ ቢገባም አያመልጠን፡፡ ይእ!
አንተስ ና እንጂ ይኸውልሽ ከመጣን ጀምሮ አበሳውን እያሳየሁት ነው፡፡ ና በል የኔ ጌታ.." አለችውና ከሎን ሶስቱም ተያይዘው በር ወደሌለው የሐመር ጎጆ ሄዱ!

👍29❤1👏1
ቆርበቱ ተነጣጥፏል፡፡ ወንዱ ሴቱ ጎጆዋ ውስጥ
ተጠቅጥቋል፡፡ እንስራው ዘመም ብሎ ከታች የሚነደው እሳት ቂጡን
አግሞታል፡፡ ከየቤቱ የመጣው የወተት መያዣ ዶላ ተደርድሯል ለእንግዳዋ ለካርለት ጭብጦው በሾርቃ ወተት በዶላ ለካርለትና ለሆራ ቀረበላቸው፡፡ ከዚያ ሸፈሮ ቡናው በሾርቃ መቀዳት ጀመረ። ከቅል የሚሰራው ሾርቃ ለሐመሮች መብያ ሣህናቸው መጠጫ
ብርጭቆና ሰነያቸው ነው፡፡
አንተነህ ይመር ፕስስ ፕስስ ፕስስ" ብሎ ሶስት ጊዜ
አማትቦ “የአባቴ ሰማይ ዝናብ ይጣል በሽታዎች ይጥፉ…" ብሎ መረቀና ጨዋታና ቀልዱ ተጀመረ፡፡
“ይእ! አያ ደልቲ እንደሆን መኖሩ ተሰምቷል፤ ጨረቃም አለች… እህ ዛሬ ማታ ልጃገረዷን ጋዲ አጫውቷት እንጂ፡፡ እኔስ…"
አዘን ብላ ፀጥ አለች ጎይቲ፡፡ የአገባች ሴት በሐመር የምሽት ጭፈራ
እንደማትካፈል የሚያውቁት ፀጥ አሉ፡፡ ካርለት ግን ለጎይቲ አዘነችላት፡፡ እንዲያ በኢቫንጋዲ ጭፈራ እንደማትሾር ሁሉ ትዳር
አጥር አስደግፎ ተመልካች አደረጋት…ብላ ተከዘች፡፡
ጎረምሳና ኮረዳዎች ግን የእለት ስራቸውን ሰራርተው በአኖ ጭቃ ሰውነታቸውን አዦጎርጉረዉ በጨረቃ ብርሃን ለመጨፈርና ለመዳራት ቀኑ እንዲያጥር እየተመኙ በየአቅጣጫው ተበታተኑ ጎይቲ የካርለትን ፀጉር በእጣን በአሰሌ አፈር አሏቁጣ እየተቀባች ለኢቫንጋዲ ጭፈራ አሰማመረቻት ካለ ደልቲ ግን ዳንሱና ጭፈራው ያረካት ይሆን? ማን ይህን ሊመልስ ይቻለዋል።

👍23❤2👎1👏1
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ-ሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሰባት)
(ሜሪ ፈለቀ)
በር በሩን እያየሁ ቆይቼ መጣ! አራት ጊዜ ባጥፈው ያለምንም መጣበብ ሰፋፊዎቹ ጅንስ ሱሪዎቼ ጎን ኪስ መሰስ ብሎ ጥልቅ የሚል፣ ቀጭን ለመባል ራሱ መወፈር ስጋ መጨመር ያለበት ፣ አጭር ቀይ……….. ስጋም ቀልብም የራቀው የሆነ ጥላ ቢስ ነገር ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን ይደረጋል? መቼም ወንድ ነው ብዬ ከስር ሆኜ አልተደረግኩለትም አይደል?! ከላይ ብሆንበት ከእጥረቱ ከቅጥነቱ ፈሱ ነው የሚያመልጠው ነውኮ የሚመስለው። ኸረ እንደው በፈጣሪ ምኑ ደስ ብሎኝ ይሆን አብሬው የነበርኩት? ምናልባት ሌላ በፍቅር የሚፈልገኝ ወንድ ጠፋቶ ምርጫ አጥቼ ይሆናል።
ዓይኖቹ የሌባ ዓይኖች ናቸው…….. ቅብዝብዝ የሚሉ ከይሲ ዓይኖች……. ሲያወራ ሁሉም የሰውነቱ አካል ይሳተፋል። በእግሮቹ ጥፍር እንደመቆም፣ ጫማውን መሬቱ ላይ እንደመሳብ፣ ጉልበት እና ጉልበቱን እንደማጋጨት፣ ከወገቡም ሰበርበር እንደማለት፣ የእጁቹን ጣቶች እንደማፍተልተል ነገር ፣ መዳፍ እና መዳፉን እንደማሻሸት፣ ትከሻውን እንደመስበቅ፣ አንገቱን ከወሬው ስልት ጋር እንደመወዝወዝ ፣ ከንፈሩን እንደመንከስ፣ አፍንጫውን እንደመንፋት፣ ዓይኖቹ ከወዲያ ወዲህ እንደመቅበዝበዝ፣ በቄንጥ ያበጠረው ሉጫ ፀጉሩ እንደመንቀጥቀጥ…………. ብቻ ከወሬው ጋር የማይሾር አካል የለውም።
ምንም ከማላስታውሰው ከእኔ በላይ እሱ ግራ ገባው! እንደመነካካካት እንደማቀፍ እንደመሳም ሁሉንም ቅጥ በሌለው ሁኔታ ለኮፍ ለኮፍ አድርጎ ከወነ። አንድ ነገር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ይፈራኛል! እንዲህ አገጩ እስኪዝረበረብ እየፈራኝ ምን ሆኖ ነው «የእኔ ፍቅር » የሚለኝ? አስገድጄው ወይ በቦክስ አላግቼው ይሆን እንዴ ፍቅረኛዬ ያደረግኩት? ጎንጥ ባያስጠነቅቀኝ ምንም እንደማላስታውስ ነግሬው ምን ሲሆን አብሮኝ እንደሆነ ባወቅኩ! ………
«በቀናችን ስትቀሪ እና ስልክ ሳታነሺ ስትቀሪ መጀመሪያ ያው break ፈልገሽ መስሎኝ ነበር። በኋላ ስታመሪ ግራ ገባኝ! በዛ ላይ ስልክሽ ዝግ ሲሆን በቃ ከአንዱ ተጣልታ አንዱ ሸቤ ናት ብዬ አስቤ ሳጣራ መታመምሽን ሰማሁ! ማለቴ መመታትሽን! ያው መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ያው አንቺ ነሽ!» ያሄን ሁሉ የሚያወራው እዛው ደጅ እንደቆመ ነው። ጎንጥ እንዳልወደደው ያስታውቃል። በአይኑ ቂጥ በጥርጣሬ እና ባለመደሰት ሲያየው ቆይቶ እኔ ወደ ቤት እንዲገባ ስጋብዘው እሱ ደጅ ቀረ። ‘ያው አንቺ ነሽ!’ ማለት ምን ማለት ነው? መጠየቅ አትወጂም ነው? አትፈልጊም ነው? ምን ማለት ነው? ምንም ነገር ብናገር ከትውስታ ነፃ መሆኔን ላቃጥር ስለምችል እኔ ብዙ ዝም ማለት መረጥኩ። ያለማቋረጥ ከለፈለፈው ብዙ ነገር ገጣጥሜ የተረዳሁት እኔ እና እሱ የምንጋራው ምን እንደሆነ በግልፅ ያላወቅኩት ንግድ ቤት አለን። ስለመጠጥ፣ ሙዚቃ እና ሴቶች የሆነ የሆነ ነገር አውርቷል። ……ብቻ በወሬው መሃል ጣል ጣል ካደረገው የሚያያዝ ነገር በመነሳት ለመገመት ብሞክርም ከስልኬ ካገኘሁት መልእክት ጋር ተደምሮ ብዙ አልገባኝም። ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ የሚመጡት ምን ዓይነት ንግድ ቢሆን ነው?
«….. ብቻ ብዙ ነገር በአንድ ወር ተመሳቅሏል። ያ ሾካካ ደግሞ ገንዘብ አልተሰጠኝም ብሎ ሊያስፈራራኝ አልዳዳው መሰለሽ? ቃልኪዳን በጣም ስለጠገበች አባርሪያታለሁ። በወሬ አላድክምሽ ስትመለሺ ሁሉንም ትደርሺበት የለ! ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? የመታሽ ሰው ማንነት ታወቀ? …… »
«ዛሬውኑ መመለስ እፈልጋለሁ። ለምን አሁኑኑ አብሬህ ሄጄ ፊቴን አሳይቼ አልመለስም?» አልኩኝ ሄጄ የምገባው ምን ውስጥ እንደሆነ ባላውቅም ማወቅ እያጓጓኝ
«አሁን ይሻላል? የምልሽ አሁን ምን እንሰራለን ወይ አንደኛሽን በኋላ ሁሉም ሲገቡ ብትመጪ አይሻልም?» ፊቱ ላይ ግራ የመጋባት እና ጥርጣሬ ነገር ነገሰ። የሆነ ነገር እንደተሳሳትኩ ገባኝ
«ይሁን ሁሉም ባይኖሩም ቤቱ ያለበትን ሁኔታ ቃኘት አድርጌ እመለሳለሁ።» አልኩኝ እሱ ሲያወራ «ቤቱ» እያለ ሲያወራ ከሰማሁት ኮርጄ
«ካልሽ እሺ! ወስጄ እመልስሻለሁ!» አለኝ የሆነ ያልተዋጠለት ነገር እንዳለ እያስታወቀበት።
መኝታ ቤት ገብቼ ተናኜን ጠራኋት እና በፊት እንደምለብሰው አለባበስ ልብስ መርጣ እንድትሰጠኝ አደረግኩ። ምንድነው ብዬ ነው ይሆን እንደዚህ እለብስ የነበረው? መለወጤን ለማንም በቃልም በተግባርም ማሳየት ስላልነበረብኝ ያወጣችልኝን ልብሶች ለባብሼ ከዳዊት ጋር ለመሄድ ተነሳሁ።
«እትይ አንዴ ለብቻዎ ላናግሮት?» አለኝ ጎንጥ ወደ ውጪ ብቅ ስንል። ወደጓሮ ዘወር ብለን ድምፁን ዝግ አድርጎ በሹክሹክታ
«ይቅርታ ያድርጉልኝ እትይ ከዚህ ሰውዬ ጋር ብቻዎትን መሄድዎን አልወደድኩትም። የት እንደሚሄዱስ ያውቃሉ? ልከተልዎት!» አለ ፍርጥም ብሎ
«ግድ የለህም ጎንጥ ምንም አልሆንም! እስከመቼ እንደህፃን ልጅ ትጠብቀኛለህ? የከፋ ነገር እንኳን ቢመጣ ምንም የበፊቷን ሜላት መሆን ባልችል ይሄን አንድ ጭብጥ ሰውዬ መገንበር ያቅተኛል? » ስለው ፈገግ ነገር ብሎ
«ብቻውን ከሆነስ ቆርጥመው ይበሉታል። የት እንደሚወስድዎ ነው ያሳሰበኝ።»
«ግድ የለህም አጠራጣሪ እና ሰው የሌለበት ቦታ ከሆነ እጠነቀቃለሁ።»
«ግድ የሎትም ልከተልዎት?»
«ግድ የለህም ይሄን ብቻዬን ልወጣው! ይልቅ አንቱ የምትለኝን ነገር ተው!»

👍19❤1
እንደጠበቅኩትም መኪናውን እየነዳ ያለማቋረጥ እየለፈለፈ ፣ እንዳልጠበቅኩትም አልፎ አልፎ አንድ እጁን እየሰደደ ወይ ትከሻዬን አልያም ጭኔን እንደመዳበስ እያደረገኝ (በጣም ደስ የማይል ስሜት አለው። በተለይ ጭኔ ላይ እጁን ሲያሳርፍ! መጀመሪያ ሲነካኝ ከመቀመጫዬ እንደመዝለልም አድርጎኝ ነበር። ) መንገዱን ተያያዝነው። የምንሄድበትን መንገድ በጭንቅላቴ ለመመዝገብ ፣ የማያቸውን ፅሁፎች ጭንቅላቴ ውስጥ ለማስቀረት እሞክራለሁ። አንዳንዶቹን በትልልቅ የተፃፉ ጽሁፎች የማውቃቸው የማውቃቸው ይመስለኛል። ይመስለኛል እንጂ ከምስሉ ተያይዞ የማስታውሰው ነገር የለም። ይሄ በጣም የሚያስጨንቅ ስሜት አለው። ትውስታ ይሆን ጭንቅላቴ የሚፈጥረው ስሜት ይሆን አለመለየት ፣ የቱ የነበረ የቱ አዲስ መሆኑን አለመለየት ከመርሳቱ በላይ ጭንቅላት ይወጥራል። ለምሳሌ መንገዱን አላውቀውም ነገር ግን መታጠፊያ ጋር ስንደርስ በዛ መታጠፊያ እንደሚታጠፍ ገምቼ ይሁን አውቄ አላውቅም። ግን ልክ መኪናውን እየነዳሁ ያለሁት እኔ ብሆን ልክ እዛ መታጠፊያ ጋር ስደርስ ማንም ሳይነግረኝ መሪውን የማዞር ይመስለኛል። ከትውስታዬ ማህደር ከሆነ መንገዱን ሳላውቀው እንዴት መታጠፊያዎቹን ብቻ አስታውሳለሁ? የሆነ ቀን ለክትትል ሀኪም ቤት ስሄድ ለሀኪሙ የሚሰማኝን መቀዣበር ስነግረው
«በህይወትሽ ውስጥ በተደጋጋሚ ታደርጊያቸው የነበሩትን ነገሮች በደመነፍስ ሰውነትሽ ሲያደርጋቸው ልታገኚ ትችያለሽ። ሳታውቂው ታዘወትሪበት የነበረ ቦታ መገኘት፣ ቋንቋ ድንገት ሰዎች ሲያወሩ መረዳት ወይ መንገር ፣ በፊት ትወጃቸው ከነበሩ ነገሮች ጋር መቆራኘት፣ ትጠያቸው የነበሩ ነገሮችን መጥላት …….. የመሳሰሉ ነገሮች የሚከሰቱ ናቸው። ከነገሮች ጋር ተያይዞ ጭንቅላትሽ የሚከስተው ምስል ካለ ግን ያ የትውስታሽ አካል ነው። ምናልባት እቦታው ላይ ብትገኚ ክስተቱን የማስታወስ እድልሽ ሰፊ ሊሆን ይችላል።» ብሎኝ ነበር። በእርግጥ የአዕምሮ ክፍላችንን የሚያሳይ ምስል አስቀምጦ ብዙ የተወሳሰበ ነገር ሊያስረዳኝ ሞክሯል። አልገቡኝም እንጂ! ቤተ ክርስቲያን ሄጄ እቀመጥበት ከነበረበት ቦታ እና ከወንድሜ መልክ የቱ ነበር ለስሜቴ መቅረብ የነበረበት? የጎንጥን ፊት ሳላስታውስ እንዴት ሽጉጥን ማስታወስ አወቅሁበት? ዋናውን መንገድ ወይም መዳረሻዬን ሳላውቅ እንዴት ኩርባዎቹን አወቅሁ?
አንድ የሆነ ትልቅ ህንፃ ጋር ደርሰን መኪናውን ካቆመ በኋላ ሰባተኛው ወለል ላይ እየመራ አደረሰኝ እና የሆነ በር ከፍተን ገባን። የማያቸውን ነገሮች የማውቃቸው ወይም አዲስ እንዳልሆነብኝ ለማስመሰል የማደርገው ሂደት ምን ያህል ይሳካልኝ አላውቅም! ሁለት ሴቶች ወለሉን እያፀዱ ነው። እዚህም እዚያም ወለሉ መሃል ዘርዘር ብለው የተቀመጡት ጠረጴዛዎች ላይ ወንበሮች ተደፋፍተውባቸዋል። ጥግጥጉን በቀይ ገመድ የታጠሩ ጥቋቁር ሶፋዎች አሉ፣ አንደኛውን ግድግዳ ሙሉ በተለያዩ ጠርሙሶችና ሌሎች ነገሮች የተሞላ መደርደሪያ ሸፍኖታል። ከመደርደሪያው እና ከፊቱ ካለው ከፍ ያለ እግራቸው ረዣዥም ወንበሮች ከተደፋበት መደገፊያ ነገር መሃል ሁለት ወንዶች እየተቀባበሉ ብርጭቆ እያደረቁ ይደረድራሉ። መግባቴን ሲያዩ ሁለቱ ወንዶች ስራቸውን ትተው ቆሙ። አንደኛው ወገቡጋ የሚደርሰውን መደገፊያ ነገር ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።
«ውይ ሜሉዬ እንኳን እግዚአብሄር ለዚህ አበቃሽ! » ጭንቅ አድርጎ እያቀፈኝ በጆሮዬ እንደማንሾካሾክ ነገር «ቤቱ በአፍ ጢሙ ተደፍቶ ስራ አጥ ከመሆኔ በፊት ለጥቂት ነው የደረሽልኝ» ብሎ ለቀቀኝ። ፈገግ ብቻ አልኩ። የበፊቷ ሜላት እንዲህ ያለ አስጨናቂ መታቀፍ ሲደርስባት በጥፊ ትለፈው በፈገግታ መገመት ባልችልም……. እየተቀባበሉ እንኳን ደህና መጣሽ ይበሉኝ እንጂ መጀመሪያ ካቀፈኝ ሰው ውጪ የጨበጠኝም ያቀፈኝም የለም። ልክ እንደሚያውቅ ሰው የሽንት ቤት ምልክት ከሚታይበት ተቃራኒ ያለውን ቀጣዩን በር አልፌ ወደ ውስጥ ገባሁ። ሰፊ ኮሪደር እና የተለያዩ ክፍሎች አሉ። እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ሶፋ እና መሃሉ ላይ የብረት ዘንግ ያለበት ከፍ ያለ በቆዳ የተለበጠ ክብ አልጋ መሳይ ነገር አለ። የመጨረሻውን ክፍል ከፍቼ ስገባ አንዲት ቢነኳት ቆዳዋ ተሰርጉዶ የሚቀር የምትመስል ቆንጅዬ ወጣት በፓንት እና በጡት ማስያዣ እዛው አልጋ መሳዩ ቦታ ላይ ተኝታለች። በሩን ከፍቼ ስገባ ብንን ብላ ነቃች እና እንደመደንገጥ ብላ
«ማታ በጣም ዝዬ ስለነበር እዛ ድረስ ከምሄድ ብዬ እዚሁ ተኝቼ ነውኮ! እ? አሁኑኑ ተጣጥቤ ፏ እላለሁ። ይቅርታ በጣም» እያለች ተለማመጠችኝ። ለምን ይቅርታ እንደጠየቀችኝም፤ ስራዋ ምን እንደሆነም፤ ለምን እርቃኗን እንዳለችም ……. ምኑም በእርግጠኝነት ስላልገባኝ በአጠገቤ አልፋ ልትወጣ ስትል ትከሻዋን በአይዞሽ ዓይነት መታ መታ አደረግኳት። ልምምጧ ያሳዝናል። እንዴት ባሳቅቃት ነው ይህችን የመሰለች ልጅ ስታየኝ እንዲህ የምትርመጠመጠው?
እንደገባኝ ከሆነ እቤቱ ውስጥ የሚከወነውን ለማየት ሲመሽ መምጣት አለብኝ። ስር ስሬ ሲከተለኝ የነበረው ዳዊት ወደ ቤት እየመለሰኝ አስብ የነበረው ……. ስንት ዓይነት ሰው ነኝ? ወይም ነበርኩ የሚለውን ነበር። አንደኛው መጥቶ የሚጠመጠምብኝ፣ ሌላኛዋ ስታየኝ ሽንቷ ሊያመልጣት የሚዳዳ ፣ ለዳዊት የሚፈራን ግን የእኔ ፍቅር የሚለኝ …….. አባ እንደልጃቸው ፀጉሬን የሚደባብሱኝ ፣ ጎረቤቶቼ የሚጠሉኝ ፣ ጎንጥ እና ተናኜም ቢሆኑ እንደክፉ ሴት የሚያዩኝ …….. ትክክለኛዋ ሜላት የትኛዋ ነበርኩ? ወይስ ሁሉንም ነኝ? ለማናቸው ነው ትክክለኛ ማንነቴን የገለፅኩት? ለማናቸውስ ነው ያስመሰልኩት? ዝም ብዬ ሳስበው ለምሳሌ ልጅ ቢኖረኝ ፍቅረኛዬ ወይ ባሌ በሚያውቀኝ መልኩ ሊያውቀኝ አይችልም። ምናልባት ባስታውሰው ወላጆቼም ጓደኞቼ በሚያውቁኝ መንገድ አያውቁኝም። የምወደው ጓደኛ ኖሮኝ ቢያውቅ ለእሷ የምሆነውን መሆን ቅድም ብርጭቆ ሲያፀዳ ለነበረው ልጅ አልሆንም። ምናልባት እያስመሰልኩ አይደል ይሆናል። እኔ እንደልጅ፣ እኔ እንደሚስት፣ እኔ እንደጓደኛ፣ እኔው እንደእናት፣ እኔው እንደአለቃ …… እንደብዙ ነገር እንደብዙ የምኖር የእነዚህ ሁሉ ስብጥሮች እሆን ይሆናል።
በር ላይ አድርሶኝ ስንሰነባበት ከንፈሬን ሊስመኝ ሲጠጋኝ ሳላስበው ገፋሁት። ካደረግኩት በኋላ እሱ ፊት ላይ የነበረው ምላሽ እንድፀፀት አደረገኝ።
«ይቅርታ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ ነው!»
«እረዳሻለሁ የኔ ፍቅር!» ብሎ ወደመኪናው ገባ!
እቤት ከገባሁ በኋላ ቅድም አስቀምጬው የነበረውን ስልክ መበርበር ጀመርኩ። ብቻ የሆነ ፍንጭ! የሆነ መረጃ! ያልነካሁት ያልፈተሽኩት ምልክት የለም። ከፎቶዎቹ ውጪ ለኪዳን የተጠጋጋ ስምም ሆነ መልእክት የለም። ሌሎች የማላውቃቸው ሰዎች ብቻቸውንም አንዳንዱ ከእኔ ጋር ፎቶ አይቻለሁ። የሆነ ነገር ካስታወስኩ ብዬ ፎቶዎቹን እየደጋገምኩ ባይም ጠብ የሚል ነገር የለም። እናቴ ልትሆን ትችላለች ብዬ የጠረጠርኳት አንዲት ሴት ጋር ተደጋጋሚ ፎቶ አለን። አልጋ ላይ ተኝታ አጠገቧ ተጋድሜ፣ አልጋ ላይ ተኝታ ጉሉኮስ ተሰክቶላት አልጋዋ አጠገብ ተንበርክኬ፣ የሆነ በረንዳ ላይ የሚመስል ቦታ ምግብ እየበላን ፣ ደግሞ ብቻዋን ፈገግ ብላ ……… አንዳቸውም የት ላገኛት እንደምችል መላ አልሰጡኝም።
«እትይ ይሄ መኪና ለምን ጋራዥ አይገባም? በታክሲ ከሚመላለሱም ሰው ከሚያስቸግሩም ይሻልዎታል!» አለኝ ጎንጥ አመሻሽ ላይ ብቅ ብሎ አንድ ጎኗ የተጋጨ እና የጥይት ብስ ያለባት መኪናዬ ወደቆመችበት አቅጣጫ በአገጩ እየጠቆመ።

👍19❤1🥰1
«ማን ሊነዳው?»
«እሷ ትሰራና መንዳቱስ አይጠፋዎትም! ካልሆነም …… ብሎ አቅማማ
«መኪና መንዳት ትችላለህ እንዴ?» አልኩት ደገፍ ብዬ ከተቀመጥኩበት እየሰገግኩ
« እንዲያ ነገር! ለአንዱ ዲታ ሹፌር ሆኜ 7 ዓመት ሾፍሬያለሁ።» አለ በማጣጣል አይነት።
«ታዲያ ለምን አልነገርከኝም እስከዛሬ? ደግሞ አንቱ አትበለኝ አላልኩህም?»
«አይ እትይ አፌ አይለምድልኝም አንች ማለቱን! ልምድ እንዲህ መች ቶሎ ይለቃል?»
«ሞክረው! መኪናዋን ነገ ውሰዳት ጋራዥ እኔ በታክሲ ደርሼ እመጣለሁ።» ካልኩት በኋላ ነው ስለቤቱ ያየሁትንም ያሰብኩትንም እንዳልነገርኩት ያስታወስኩት።
«እንዲህ ከመሸ ወዲያ መሄድ ደግ ነው ታዲያ? ወይ ልከተሎት!» ብሎ ይተገትገኝ ጀመር። «እትይ ዘንግተውት እንጂ ብዙ ጠላት ያሎት ሰው ኖት!» አሁንም ትንሽ ይቆይና «ባይሆን ከደጅ እጠብቆታለሁ! መንገዱን ላካሂዶት!»
«አንቱ አትበለኝ አልኩህኮ!»
«ይሁን እሺ እኔ ምኑም አላማረኝ እትይ!»
«እህእ!»
«ኸረግ እትይ እንዳትለኝማ አይበሉኝ!»
ባያሳምነውም ታክሲ ጠርቶ ሸኘኝ። የህንፃውን ስም ስነግረው ባለታክሲው አወቀው። እየሄድን የሆነ ጭር ያለ መንገድ ላይ የሆነ መኪና መጥቶ መንገድ ዘጋብን። ባለታክሲው እየተሳደበ መኪናውን አቆመ። ከቆመው መኪና ውስጥ ሁለት የገዛዘፍ ወንዶች ወርደው ደረታቸውን አሳብጠው እየተራመዱ ወደእኛ ቀረቡ!!
............. ይቀጥላል.......

👍19❤2😢2
#የመኖር አጋማሽ ..የመ: ሞ : ት ሲሶ ... መንገድ መሃል ..... (ክፍል ስምንት)
(ሜሪ ፈለቀ)
'ማናችሁ? ምን ፈለጋችሁ?' ከማለቴ በፊት ከታክሲው ኃላ መቀመጫ ጎትተው አስወጥተው ያበጥሩኝ ጀመር:: .... 'ምን አድርጌያችሁ ነው?' ማለት አፌ ይፈልጋል... በየትኛው ትንፋሽ?... እንኳን የማወራበት... የምተነፍስበት ፋታ ሳይሰጡ ተቀባበሉኝ.... ባለታክሲው ሁለት ቡጢውን ሲያጣጥም መፍጨርጨሩንም ተወው:: ... ሶስተኛ ሲሰልሱት እንዲተውኝ መለመኑንም ተወው! መሬቱ ላይ ወድቄ 'እንካ በእርግጫ' ተባባሉብኝ.... የምቱ ቁጥር ሲጨምር የህመሙ መጠን ቀነሰ... ሰውነቴ የደነዘዘ መሰለኝ.... አንደኛው በጫማው ደሬቴን ሲለኝ... ቁስሌ የተቀደደ አይነት ስሜት ተሰማኝ... ሳያስፈቅደኝ ልቤ ክድት ... ጭልጥ ይልብኝ እና ምቱ ያነቃኛል.... በስልምልምታ ከሩቅ እየቀረበ የመጣ የመኪና ድምፅ እና መብራት የተፈራረቁብኝ ይመስለኛል::..... የሚደልቁኝ ጫማዎች በፍጥነት ጥለውኝ ሲሄዱ ነገር.... ... ልቤ ቅልጥ ብሎ ጥፍት አለብኝ....
የሆነ በርቀት ነገር "እትይ! እትይ!" ... የሚል ጥሪ ይሰማኛል:: ... አይኖቼን ልገልጥ ስሞክር የአይኖቼ ቆቦች ህመማቸው ያሰቃየኛል:: ... ያልታመመ የሰውነት አካል የለኝም:: ... ሀኪም ቤት ተኝቻለሁ::.... ጎንጥ የአልጋዬን ጠርዝ ይዞራል:: ያልተጠቀለለ የሰውነት አካል የለኝም::.... አይኔን መግለጤን ሲያይ
"እትይ ነቁ? ክብር ምስጋና ይግባህ አምላከ ስላሴ!" ብሎ ወደ ሰማይ አየ.... ፊቴ ላይ ሳይቀር በፋሻ ተጠቅልያለሁ!.... እንባዬ ሲወርድ ወደ ጆሮዬ እየሄደ የሚያልፍበት ቆዳ ሁሉ አልኮል እንደተደፋበት ቁስል ያቃጥለኛል::... አንገቴ ቀስሮ በሚይዝ መደገፊያ ተደግፎ ስለታሰረ አይኔን እንጂ አንገቴን ማዞር አልችልም:: አፌን ላንቀሳቅስ ብሞክር የተሰነጠቀ ከንፈሬ ስቃይ ውስጥ ይጥደኛል::...
"እትይ! ግድ የለም እነዚህን ሽንታሞች አገኛቸዋለሁ!!" ይለኛል ጎንጥ እሳት በሚተፋ የንዴት እና የእልህ ትንፋሽ .... በቁጭት አንዱን እጁን በቡጢ ጨብጦ ሌላኛውን ይመታል::
በጥይት ተመትቼ ስነቃ እንዲህ በህመም አልተሰቃየሁም ነበር::.... ተኛኜ እና ጎንጥ እየተፈራረቁ እያስታመሙኝ ሆስፒታል ከረምኩ::.... ከሳምንታት በኃላ የተሰበረ አፍንጫዬ አገገመ.... የተሰነጠቀ ከንፈሬ ቁስል ሻረ... የተሰባበሩት የጎድን አጥንቶቼ ተደጋገፋ... የበለዙ ስጋዎቼ ፈዘዙ..... አንገቴ ያለ ድጋፍ ዞረ.... የዞረ ክንዴ ቦታው ሰገበ... ወደ አንጀቴ የፈሰሰ ደሜ ተቀዳ..... የተቀደደ ቁስሌ ተሰፋ......
"ተሻለሽ?" ሲሉኝ .... "ደህና ነኝ!" እላለሁ! ... የጠየቁኝ የስጋ ቁስሌን እንደሆነ ስለማውቅ...
እኔ ግን አልተሻለኝም!! ደህና አይደለሁም!! ጭራሽ ለደህና የቀረበ ነገር አይደለሁም!! ... ጎንጥ አጠገቤ ሆኖ እጄን ካልያዘኝ እንቅልፍ የማይወስደኝ ፈሪ ሆኛለሁ:: ኮሽ ባለ ቁጥር ከአልጋዬ የማልዘለው እሱ እየጠበቀኝ እንደሆነ ሳውቅ ብቻ ነው:: .... ካለበለዚያ ኮቴ ያስደነግጠኛል:: .... የትንኝ ጥዝታታታ እንኳን ጩሂ ጩሂ ይለኛል:: መጠየቅም መመለስም ተውኩ:: መሞትም መኖርም ፈራሁ!! ... ተናኜ አብራኝ ስትውል.... የቆጥ የባጡን ስትለፈክፍ አልመልስ ስላት!!
"ኸረ እትይ በማርያም እንዲህ አይሁኑ!" ትለኛለች:: ጭንቅ ጥብብ ሲላት ደግሞ
"እትይ? ካልሆነ እብስ ብለው ለምን የሆነ ሀገር አይሄዱም?" ትለኛለች::
"እትይ? እስኪ ትንሽ ነገር ደግሞ ይቅመሱ በማርያም?"
..... አግጯን ደገፍ ታደርግና "ምፅ!" ብላ እንባዋን ትለቀዋለች:: ...
"ምን ልሁን ነው የምትይ?" ይላታል ጎንጥ ማልቀሷን ሲያውቅ:: ....
የዛን ቀን ሹፌሩ የመኪና ታርጋቸውን መዝግቦ ስለነበር ለፖሊስ መረጃ ብንሰጥም ፖሊሶቹ የእኔ ጉዳይ ግድ የሚሰጣቸው አልመሰሉም:: ጎንጥ ብስጭት ብሎ
"በነጋ በጠባ 'ያላሰለሰ ጥረት እያደረግን ነው! ' ይሉኛል:: ጠብ የሚል ነገር የለም! እንዴት ያለ ህግ ነው?" አለኝ የሆነ ቀን.... አልመለስኩለትም!! .... ቀን ቀን ተናኜ ትውልልኛለች:: ማታ ማታ እሱ ያድራል:: ... ዳዊት አንድ ሁለቴ ሊጠይቀኝ መጥቶ ነበር:: እንዳይመጣ ስለነገርኩት ቀረ!! ....
"እትይ ? ዛሬ ጎንጥ ስለማይመጣ ምሽቱንም እኔ ነኝ የማስተዳድሮት.... እቤት ደረስ ብዬ እራት አበሳስዬ ላምጣ?" አለች በጨነቀው ልምምጥ....
"ለምንድነው ጎንጥ የማይመጣው? " አልኩኝ የወላለቀ ሰውነቴን እየጎተትኩ ተቀምጬ
"አላውቅም እትይ!! የምፈጣጥመው ነገር አለኝ ! ነው ያለው!"
"እሺ ትተሽኝ አትሂጂ.... ከካፍቴሪያ የሆነ ነገር ግዢ" ብያት (የሆስፒታሉ ጊቢ ውስጥ ያለ ካፍቴሪያ ነው) እሷ ልታመጣ ስትሄድ ከፋኝ!! እንደህፃን ልጅ አለቀስኩ:: .... ሆስፒታል ማደር ደክሞት ይሆን??? እኔን መጠበቅ ከነአካቴው ደክሞት ይሆን?? ጠልቶኝ ይሆን?? .... ላይመለስ ትቶኝ ቢሄድ ምንድነው የምሆነው?? ከእርሱና ከተናኜ ውጪ ማንንም እንደማላውቅ እያወቀ ትቶኝ ይሄድ ይሆን?? ይቅር ይበለኝ እና ብር አምጣ ብዬ ከካዝናው ውስጥ ያወጣሁት ብር የት እንዳለ ነግሬዋለሁኮ .... ብሩን ይዞ እኔን ትቶኝ ሄዶ ቢሆንስ? እኔ በወር የምከፍለውን ደመወዝ ከ20 ዓመት በላይ የሚከፍለው ብር ነው..... በስመአብ !! ኸረ እንደሱ አያደርግም!!!
ለሊቱ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ!! ተናኜ ሳለቅስ ካየችኝ ከእኔ ብሳ ታርፈዋለች:: አልጋዬ ስር ፍራሿን ዘርግታ እንቅልፍ እስኪወስዳት ጠብቄ ..... ብዙ አልቅሼ እንባዬ ሁላ ያለቀ መሰለኝ!! ፍርሃት ሆዴን አላወሰው!!! የበር ድምፅ በሰማሁ ቁጥር ልቤ ይርዳል:: ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል::.... ነግቶ ብርሃን ሲሆን እንቅልፍ ጣለኝ:: .... ብርሃን ከክፋት የሚጠብቀኝ ይመስል ሲፈካ ልቤ ይረጋጋል:: ከእንቅልፌ ስነቃ አይኔን ሳልገልጥ በፊት እጄን የያዘኝን እጅ ጨበጥኩ.... አይኖቼን ስገልጣቸው ጎንጥ ለሊት ሲያድር እንደሚያደርገው ወንበር ላይ ተቀምጦ እጄን ይዞኝ ... አንገቱን አልጋው ላይ ደፍቶ ተኝቷል:: .... ደስታ ይሁን መከፋት የማላውቀው ስሜት ናጠኝ::: ህቅታዬ እንዳይረብሸው እየታገልኩ ተንሰቀሰቅኩ:: ... ከደቂቃዎች በኃላ ግን ልያዘውም ብል ፈንቅሎኝ የወጣ ህቅታዬ ቀሰቀሰው.... እንደነቃ ሳየው ይብስ ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩ:: ....
"መድሃንያለም! እትይ? ምን ሆነው ነው?? ኸረ በመድሃንያለም ነፍስያዬን አያስጨንቋት?? " የሚያደርገው ግር ብሎት እጄን ባልጨበጠ እጁ እንባዬን ሊጠርግ ይታገላል::
"የሄ.... ድክ ... መስሎኝ..." ብዬ መጨረስ አቃተኝ:: ህቅ ማለት ቀጠልኩ:: ክፉ ነገር እንደነገርኩት ሁሉ ... ዝግንን ብሎት እጄን እንደጨበጠ ከተቀመጠበት እየተነሳ
"መሄድ ሲሉ?? መሄድ ! መሄድ!? ... ይቅር ይበሎት! ምኑን አሰቡት? እንዲህ ያለ ሁኔታ ላይ እንዴት ትቼዎት እሄዳለሁ?? እንዴት ያለ ሰው ነው ብለው ነው የሚያስቡኝ?" አለ ቁጣም በቀላቀለው አነጋገር!!
"ይቅርታ አድርግልኝ!! እኔ አላውቅም!! ምን እንደማስብ... ግራ የገባኝ ሰው ነኝ! ካንተ እና ከተናኜ ውጪ ማን ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም!! አንተ ብትሄድ..." ብዬ መጨረስ ቸገረኝ:: ተመልሶ እየተቀመጠ በሚለማመጥ ድምፅ
"የትም አልሄድም! እርሶ አልፈልግህም ብለው እስካላበረሩኝ ድረስ እኔ የትም አልሄድም!!" አለኝ:: ...

👍43❤1🥰1👏1
በአንድ አፍታ በእጄ የያዘኝን እጁን አጥብቄ ስይዘው እና ዓይኖቼ የበለዘ አይኑን ሲያዩ እኩል ሆነ... አጥብቄ ያያዝኩት እጄ ህመም እንደሰጠው ፊቱ ላይ ስቃዩ ታየ:: እያየሁት እንደሆነ ሲያስተውል ህመሙን ለመዋጥ ታገለ:: እጁን ስቤ አየሁት:: እንደማበጥም እንደመቁሰልም ብሏል::
"አምላክ ሆይ!! ምን ሆነህ ነው?" ብዬ ጮህኩ:: እሱ ከአፉ ቃል ሳይወጣ የሆነው ነገር ከእኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገባኝ::
"ምንም አልሆንኩ! እንዲያው ዝም ብሎ ነገር ነው!" ይለኛል ደጋግሜም ብጠይቀው:: ቅስስስ ብዬ ተነስቼ እየተቀመጥኩ አገጬን በእጆቼ ወደራሴ እያዞርኩ ፊቱን አየሁት....
"እሺ የተፈጠረውን አትንገረኝ!! ተጎድተሃል?? ሌላ ቦታ ተመትተሃል?"
"ምንም አይደልኮ ትንሽ ነገር ነው!" ይበለኝ እንጂ ትልቅ ነገር እንደሆነ ሆዴ ነግሮኛል:: የዛን ቀን ከሰዓታት በኃላ ያላሰብኩት እንግዳ ጎበኘኝ..... ማንነቱ የገባኝ ከደቂቃዎች በኃላ ነው:: ... የዛን ምሽት ከደበደቡኝ ውስጥ አንዱ ነው:: ..... ጎንጥ አጠገቤ ቆሞ እንኳን ፍርሃት ልቤን ከደረቴ ጎትቶ ሊያስወጣት ታገለኝ:: ... ሳይታወቀኝ አይኔን ከድኜ እግሬን ሰብስቤ ጉልበቴን አቅፌ ጥቅልል አልኩ:: ....
.......... ይቀጥላል........
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
"አምላክ ሆይ!! ምን ሆነህ ነው?" ብዬ ጮህኩ:: እሱ ከአፉ ቃል ሳይወጣ የሆነው ነገር ከእኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገባኝ::
"ምንም አልሆንኩ! እንዲያው ዝም ብሎ ነገር ነው!" ይለኛል ደጋግሜም ብጠይቀው:: ቅስስስ ብዬ ተነስቼ እየተቀመጥኩ አገጬን በእጆቼ ወደራሴ እያዞርኩ ፊቱን አየሁት....
"እሺ የተፈጠረውን አትንገረኝ!! ተጎድተሃል?? ሌላ ቦታ ተመትተሃል?"
"ምንም አይደልኮ ትንሽ ነገር ነው!" ይበለኝ እንጂ ትልቅ ነገር እንደሆነ ሆዴ ነግሮኛል:: የዛን ቀን ከሰዓታት በኃላ ያላሰብኩት እንግዳ ጎበኘኝ..... ማንነቱ የገባኝ ከደቂቃዎች በኃላ ነው:: ... የዛን ምሽት ከደበደቡኝ ውስጥ አንዱ ነው:: ..... ጎንጥ አጠገቤ ቆሞ እንኳን ፍርሃት ልቤን ከደረቴ ጎትቶ ሊያስወጣት ታገለኝ:: ... ሳይታወቀኝ አይኔን ከድኜ እግሬን ሰብስቤ ጉልበቴን አቅፌ ጥቅልል አልኩ:: ....
.......... ይቀጥላል........
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
❤27👍8👏1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ብላንክ ፓሎማ' ይሉታል ስፔኖች! ነጭ እርግብ ማለት ነው፡ የዚህ የስፔኑ ተወላጅ እውቁ ሰዓሊ ፓውሉ ፒካሶ ደግሞ ነጭ
እርግብን የሰላም ምልክት አድርጎ ለአለም ህዝብ አበርከቷል፡
ብላንካ ፓሎማ ሮሲ በተባለ ቦታ በዓመት አንዴ የሚከበር ከኢትዮጵያውያን ጥምቀት ጋር የሚመሳሰል በዓል ነው፡፡ ስፔናውያን
እየደነሱና እየጨፈሩ የአለፈውን ዘመን አመስግነው መጭውን
ደግሞ ሰላም የሰፈነበት የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው አምላክን የሚያመሰግኑበትና የሚለምኑበት ክብረ በዓል ነው ብላንካ ፓሎማ።
በዓሉን ለማክበር ከተለያየ ቦታ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ እንዲሉ ሴቶቹ ከወገባቸው ጠቡብ ብሎ ከታች ቦለል በማለት መሬት
የሚነካውን ቀሚሳቸውን ወደ ላይ በጣታቸው ሰብሰብ ያርጉና
አንቧለሌ እየዘሩ ጣቶቻቸውን እንደ ኮብራ አንገት እያሟለሉ ወንዶች ደግሞ የተተፈተፈ የቆዳ ሱሪና ሰደርያ ነጭ ሸሚዝ ሰፊ ባርኔጣ ይለብሱና ብብቱ ውስጥ ዝንብ እንደገባበት ፈረስ ባለ በሌለ ኃይላቸው መሬቱን እየደለቁ እጆቸውን እየሰበቁ እንደ አውራ ዶሮ በሴቷ ክብ ሲዞሩ ጭብጨባው ዝማሬው ፉጨቱና ጨኸቱ
ይቀልጣል፡፡ አሸነፈችው! አሸንፏታል! እየተባለ አቧራው ይጤሳል።
በብላንክ ፓሎማ በዓል
ዘመናዊ ተሽከርካሪ አይኬድም ዘመናዊ ነገር ፈጽሞ እንዲታይም አይፈለግም ወደ በዓሉ ቦታ
የሚጓዘው ሰው በፈረስና በቅሎ በሚሳቡ ባህላዊ ጋሪዎች የሚበላ የሚጠጣው ይጫንና ህፃናትና አዋቂን በባህል ልብሳቸው አሸብርቀው አልፎ አልፎ ወንዶቹ በሚገባ በተቀለበ ጠብደል ፈረሰና በቅሎ ሆነው ሶምሶማ እየረገጡ እንደ አባቶቻቸው ወግና ባህል በዓሉ ወደ ሚከበርበት ሮሲ ሲጓዙ በየከተማው ህዝቡ እየወጣ እያጨበጨበና
አብሮ እየጨፈረ ይሽኛቸዋል፡፡
በግብርና ምርቷ በመላው አውሮፖ በይበልጥ የምትታወቀው
ስፔን ህዝቧ በደስታ ፍንድቅድቅ እያለ የአለፈ ወግና ልማዱን በዓመት በዓመት እየተከተሉ አምላኩን ሲያመሰግን ሮሲ ሲሰባሰብ ደስታውን ለመክፈል ፈገግተኛና ደስተኛውን የበዓል አክባሪ አይቶ ለመርካት በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ከፈረንሳይ ከፖርቹጋል ከሌሎችም የአውሮፓ አገሮች ወደ ሮሲ ይጎርፋል፡፡
ብላንክ ፓሉማን ለማክበር የሚሰባሰበው ሁሉ ዓላማው በሰላም መዝናናት ነው፡፡ በቡድን በቡድን ጨዋታና ጭፈራው
ይቀልጣል ፍቅር እየታጨደ ይወቃል ደስታ እንደ ብርቱካን እየተላጠ ይበላል.. በብላንካ ፓሉማ
ኮንችትና ሶራን ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸው በፊት እዚህ ባህላዊ በዓል ላይ እንዲካፈል ጋበዘችው፡፡ ሶራ ሆራ ብላንካ ፓሎማን
ለማክበር የተሰባስበው ህዝብ ለበዓሉ የሚሰጠው ግምት ሲያይ የባህል የማንነት መለያነት ጥቅሙ የመገናኛ ድልድይ መሆኑ
የፍቅር ማጠናከሪያነቱ… ወለል ብhሎ ታየው።
ስዉ ይጨፍራል ይተቃቀፋል በአንድ ጠርሙስ እየተቀባበለ ይጎነጫል እየተሸማ ይበላል... ደስ አለው ሶራን፡፡
እሱንም እየነካኩ እያጨዋወቱ የስፓኛን ወይን እያቀማመሱ… በህዝቡ መስመር አሰለፉት፡፡ የችሎታውን አጨበጨበ ጨፈረ “ኢትዮጵያዬ' እያለም ጮኸ፡፡ የጥቁሩም የነጩም ፈጣሪ ወደ ሆነው
አምላኩም ምስጋናውን በማህሌተ ዜማው አሰማ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከጎኑ ጽናጽሉን እያንሿሿ ያዜም ቀሳውስት ሲወርቡ የአማራው የጉራጌው የወላይታው. የሲዳማው የኦሮሞው
የኤርቦሬ..ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ባህላዊ ጭፈራ ታየው፡፡ እና ዘለለ!
ብቻውን ሳይሆን ምናቡ ከአመጣቸው ወገኖች ጋር ከዚያ ውብ አፍሪካዊ ጋር ከብላንካ ፓሎማ በዓል አክባሪ ጋር ዘለለ ነጭ
እርግቦች ሰማዩን ሞልተውታል፡
“ብረሩ ሂዱ አፍሪካንም ሙሏት..." ጠራቸው ነጫጭ
እርግቦችን፡፡ እርግቦቹ ይስሙት አይስሙት ግን አያውቅም፡፡
ኮንችት አረንጋዴ ሆኖ ዳር ዳሩ በቀይ ሪባን የተከፈፈ
ቀሚሷን ለብሳ ዞማ ፀጉሯን ጎንጉና አናቷ ላይ በቀይ ሮዝ የፀጉር ማስያዣ አስይዛ የሙቀት ማራገቢያዋን በቄንጥ በመያዝ እንደ አበባ
ፈክታ ወንዶች እንደ ንብ ዙሪያዋን እየበረሩ፤ መሬቱን እየደለቁ ጣታቸውን እየሰበቁ… በዚያ እንደማግኔት በሚስበው ፈገግታቸው እያሽኮረመሟት ሲያይ ኮንችት ልዩ ፍጥረት ሆነችበት፡፡ ጠይሟ
ለግላጋዋ... ኮንችት ደሙን ተክታ በውስጡ ተሰራጨች፡
ብላንካ ፓሎማ… ብላንካ ፓሎማ… ሶራ በሺ የሚቆጠረው ህዝብ ተረሳው፡፡ ሌሎችን ዘነጋቸው. ኮንችት ብቻ ታየችው ኢትዮጵያዊዋ ውብ የጠይም ቆንጆዋ የቁንጅና ልዕልቷ…
“በብላንካ ፓሎማ ስጦታ አበረክትልሀለሁ" ብላዋለች፡፡
“ምን ይሆን ስጦታዋ! ጎመዠ፡፡ እስካሁን ልትሰጠው ስላሰበችው ስጦታዋ አለማሰቡ አስገረመው፡ አያት ከርቀት
ትደንሳለች፡፡ ቼኮሌቷ ጠይም እንቁዋ! በአይኑ ነካት በአይኑ ቀመሳት ጣፈጠችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እኩለ ለሊት አካባቢ ሰዉ ተዳከመ፡፡ ሁሉም ወደ
የማደሪያው ተበታተነ… ኮንችት ገላዋን ታጥባ ስስ የሌሊት ገዋኗን ለብሳ ስትወጣ ከድንኳኑ ትይዩ ሶራ ያቀጣጠለውን እሳት አየች፡፡
ከሐር የተሰራ ሰፊ ስጋጃ ተነጥፏል አንድ ጠርሙስ ወይንና ሁለት ብርጭቆ ይዛለች
እሳቱ አስቸግሮህ ነደደ" አለችው ስጋጃው ላይ
ቁጭ እያለች።
የት ያመልጣል ብሎ ሲያያት የሆነ ነገር ተመለከተ ነጭ ፓንት ተምታታበት፡ አንዳች ሀይል ከውስጡ አንገጫገጨው
"ብላንካ ፓሉማን ወደድከው?"
ቆንጆ በዓል ነው፡ ስሙ ራሱ ነጭ…" እንደገና ወደ እሷ
ተመለከተ ነጩንም ...አየው
ኮንችት ከላይ ገዋኗን ከታች ነጭ ፓንቷን ትልበስ እንጂ
እንደ ሎሚ ሁለት ቦታ ጉች ጉች ያሉት ጡቶችዋ ሰርጓዳ ወገቧ ለስላሳው ጭኗ ካለመከላከያ ይታየዋል፡
ሶራ ጫን ጫን ተነፈሰ ልቡ ፈራ ስሜቱ ተረበሸ ይባስ ብሎ ተንጫጫ።
ኮንችት በሁለቱ
ብርጭቆዎች ለብላንካ ፓሎማ የሚዘጋጀውን ምርጥ ወይን ቀዳችና የዚህ ዓይነት ወይን ከዚህ
በፊት እርግጠኛ ነኝ የቀመስህ አይመስልኝም፡፡ ውድ ነው! እኔ ግን
የምወደው በውድነቱ ወይንም በቃናው ሳይሆን በመልኩ ነው፡፡
ፀሐይ ላይ ወይን ጠጀ በጨረቃ ብርሃን ደግሞ ወርቃማ ይሇናል ና አዚህ ጋ ቁጭ በልና ተጎንጨው" አለችው፡፡
ሄዶ ከሷ ፈንጠር ብሎ ቁጭ አለ መዓዛዋ ግን
አልራቀውም ለጤናችን ለስጦታዬ" ብላ አየችው፡ ተጎነጫጨለት፡፡
ለስጦታዬ አሰበ ሶራ
እንዳንጋጠጠ ወይኑ መሆኑ
ነው ስጦታዋ .. ውዱ በጨረቃና በፀሐይ ብርሃን እንደ እስስት ቀለሙን የሚቀያይረው
ጣምናውን ለማወቅ እንደገና ጎንጭ አድርጎ አጣጣመው ወደ አፍንጫው ጠጋ አድርጎ አሽተተው ቀና አድርጎ በጨረቃ ብርሃን ተመለከተው… ወርቃማ ነው!
“ወደድከው አይደል?" የኮንችት አነጋገር እንደ ከላሲካል ሙዚቃ የጆሮውን ታንቡር እየዳሰሰው በሰራ አካላቱ ሰረገ፡፡
“አዎ ጥሩ ነው" ዝም ተባባሉ እሳቱ ይነዳል፡፡ የእሳቱ ብርሃን እነሱ ላይም ተንፀባርቆ ከርቀት ለሚያያቸው እነሱም የሳት
ላንቃ መስለዋል፡፡ ሶራ በጀርባው ስጋጃው ላይ ተኛ እሷ ደግሞ ወደ እሱ ዙራ በጎኗ ተኛች፡፡ የሆነ ነገር እየወዛወዘ እያት እያት አሰኘው ግን ፈራ፡፡
ዛሬስ ገና ስሜቷን እያዳመጠችው ይሆን? ጠየቀ ራሱን ዞር ብሎ ሊያያት አሰበ፡፡ የሆነው ነገር ወዘወዘው እንደገና ቀስ ብሎ ዞር ብሎ አያት አይኗ ነው የወዘወዘው ፍዝዝ ብሏል አይኗ ከንፈሯ እንደ እንቡጥ ፅጌሬዳ አሞጥሙጧል አይኑን ፈጠጥ አድርጎ አያት፡፡ አየችው እሷም በፈዘዙ አይኖችዋ፤ የእሳቱ ብርሃን
ግን በመካከላቸው አለ፡፡ ጡቷ ወገቧ ነጩ ፓንት. ታዩት የገዛ ምራቁ ሊያንቀው
ተቃረበ፡፡ ዘወዲያው ልቡ አይኑን ስልብ ስልምልም… አደረገበት፡፡

👍27👎2
በሚስለመለመው አይኑ ኮንችትን አያት ፧ ትመጣለች ወደ እሱ እሱም እየተሳበ ወደ እሷ ሄደ‥ ፓሎማ ፒካሶ ዘመናዊ ሽቶዋ አወደው! ተጠጋ መጣች እሷምI የሞቀው ከንፈሩ ላይ ቀስ ብሎ አረፈ፡፡ ወዲያው ሁለቱም ተስገብግበው ተጎራረሱ… ኮንችት ሸሚዙን
ገለጥ አድርጋ ፀጉራም ደረቱ ላይ ጡቶችዋን አስጠጋችለት፡፡ እጆቹ
እየተንቀጠቀጡ ወደ እሱ ስቦ አቀቄፋት፡፡ ብሎኑ ለመግጠም መዞር
ጀመረ እሳቱ አሁንም በመካከላቸው አለ ስሰዚህ እሳቱን ከመካከላቸው ለማውጣት እግሮቹ እግሯ ውስጥ ዘለቁ… እንደቶን
ለመጨረሻ ጊዜ ተንቀለቀለ ተንቦገቦ
ብላንካ ፓሎማ…
የስፔኑ አይቤርያ ኤርፕሌን ግግር የዳመና ባዘቶዎችን
አልፎ ከማድሪድ ወደ ሮማ የሚወስደውን የጉዞ መስመር እንዳስተካከለ በስፓንሽ የበረራ ከፍታው የሚጓዝበትን የጉዞ
መስመር የንፋሱ ግፊት… ሮማ ከስንት ሰዓት በረራ በኋላ እንደ ሚደርስ ተነገረ በኋላ ካፒቴኑና ረዳቶቹ ለተሳፋሪው መልካም ጉዞ
ተመኙ ከቢዝነስ ክፍል ያሉት መንገኞች አይታዩም፡፡ የኢኮኖሚ ክፍሉ ግን በሰው “ተሞልቷል። መስተንግዶ ልዩ ነው…
"የፍቅር ግንኙነታችን የዓላማዬ እንቅፋት እንደማይሆን ተስፉ አለኝ"
"በዚያ በኩል እንኳን ብዙ አታስቢ ከራሴ በላይ…"
ቃል ኪዳን አታብዛ እሺ ካልኸው ብታጎድልብኝ ስሜቴ በቀላሉ እንደሚሰበር መስታዋት ይንከሻከሻል፡ የምልህ ትክክለኛ
ባህሪህንና ስሜትህን አትደብቀኝ እሚሰማህን ሁሉ አካፍለኝ፡፡ስሜትህን ማወቅ ለኔና ላንተ ግንኙነት ትልቅ ትርጉም አለው"
አለችው ኮንችት አይኖቹን እያየች፡፡
እሺ አላት፡፡
“እየህ! እኔ ለብዙ ጊዜ ብቻዬን ነው የኖርኩት፡፡ ከዚያ ሕይወቴ ወጥቼ አዲስ ህይወት ባንዴ መላመዱ ይከብደኛል፡
ግንኙነታችን ቀስ በቀስ እንዲያድግ ነው የምፈልገው ከዚህ ቀደም
እንደነገርኩህ?
“እሺ"
ግንነታችን የባልና ሚስት ግንኙነት አይሆንም፡፡ እንደ
ሴትና ወንድ ጓደኛ እንዲሆን እፈልጋለሁ…."
"እሽ!”
ሶራ አንተን ገና በደንብ አላውቅህም፡" ልጎዳህ አልሻም እንድትጎዳኝም አልፈልግም”
“አፈቅርሻለሁ የሚያፈቅሩትን ደግሞ በጥንቃቄ መያዝ እንደሚገባ አውቃለሁ
“በእርግጥ ፍቅራችን እኩል ነው ብዬ አላምንም፡ መውደዴ ውሎ ሲያደር ወደ ፍቅር ሊያደግ ይችል ይሆናል! ለሁሉም ግን
ነፃነቴን መቀነስ ወይም ማጣት አልፈልግም፡ ለእኔ ነፃነቴ እህልና አየር ማለት ነው የምልህ ግን ይገባሃል?
“ይገባኛል፡፡ በእርግጥ ስሜታዊና በስሜቴ የምመራ አድርገሽ
ገምተሽኝ ይሆናል! ግን
ያሰብሽው እንዳልሆነና
የፈራሽው እንደማይደርስ አምናለሁ፡
“እኄ ግን ሶራ! ስሜታዊና በስሜቴ የምመራ ነኝ ብዙ
ጊዜ፡፡ በእንደዚ ዓይነቱ ግንኙነት ስሜቴ የፈለገውን መስጠትና እንዳይራብ የጠየቀኝን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ በባህላችን ለወንድና ሴት ግንኙነት ይህን ያህል ቦታ አንሰጠውም፡፡
“በሁለታችን መካከል እርግጠኛ ነኝ ብዙ የባሕል ልዩነቶች ይፈጠራሉ፡ ማፍቀርና እለታዊ ግንኙነት መፈለግም ይለያያሉ፡፡
ሁሉም ነገር ቀርቶ የኔና የአንተ ግንኙነት ገና ከመጀመሪያው ለስሜቴ ማርኪያ ላውለውና አለመግባባቱ ሲመጣ ደግሞ ልንለያይ እንችል ነበር፡ አንተን ግን ማጣት አልፈልግም፡፡ ቢያንስ በነፃ
ጓደኝነት፡፡
“ስለዚህ እባክህ ግንኙነታችንን የህይወት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ አድርገህ አትውሰደው፡ ካለበለዚያ ትከብደኛለህ እና
ልሸሽህ እገደዳለሁ…." አለችው፡፡ እውነትም ሰፊ የባሆል ልዩነት
በመካከላቸው እንዳለ ገመተ፡
“የዘመነው ህዝብ ለምን ይሆን ፍቅርን መሸከም የሚጠላው? ለምንስ ነው ኸሃላፊነት መሸሽ የሚመርጠው?.." ኮንችትን
ሊጠይቃት ፈለገ ግን ፈራ፡፡ እንዳለችውም ገና ከመጀመሩ የተሰማውን ደበቃት…

👍23❤1
እንጀራ የበላ ፈውስ የተቀበለ
ፀሐይ ቆልቆል ሲል አንድ እንኳ የታለ
የሰው አለኝታነት ዘለቄታ የለው
በሆሳዕና ማግስት "ስቀለው ስቀለው"
🔘ታምራቶ ሀይሌ🔘
ፀሐይ ቆልቆል ሲል አንድ እንኳ የታለ
የሰው አለኝታነት ዘለቄታ የለው
በሆሳዕና ማግስት "ስቀለው ስቀለው"
🔘ታምራቶ ሀይሌ🔘
👍25❤8👏6
#እሳት_ያልገባው_ልብ
ሚሚዬን ጠየቅኳት፣
ሁልጊዜ አረንጓዴ ለምለም ፍቅር አለ?
ትወጃለሽ ሚሚ ይህን የመሰለ?
ወይስ ያዝ ለቀቅ፣ጭልጥ አንዴ መጥቶ
አፍ ጠራርጎ መሄድ ያገኙትን በልቶ?
ሚሚዬ እንዲህ አለች
ሳስቃ መለሰች፣
“የምን እኝኝ ነው፣ እድሜ ልክ አንድ ሰው
ቋሚ ፍቅር ይቅር፣ ለብ ለብ እናርገው”
ክትፎዋም ለብ ለብ
ፍቅሯም ለብ ለብ
ኑሮዋም ለብ ለብ
ዕውቀቷም ለብ ለብ
ነገር አለሟ ግልብ
እንዴት ይበስል ይሆን፣ እሳት ያልገባው ልብ?
(ላልበሰሉቱ)
🔘ነቢይ መኮንን🔘
ሚሚዬን ጠየቅኳት፣
ሁልጊዜ አረንጓዴ ለምለም ፍቅር አለ?
ትወጃለሽ ሚሚ ይህን የመሰለ?
ወይስ ያዝ ለቀቅ፣ጭልጥ አንዴ መጥቶ
አፍ ጠራርጎ መሄድ ያገኙትን በልቶ?
ሚሚዬ እንዲህ አለች
ሳስቃ መለሰች፣
“የምን እኝኝ ነው፣ እድሜ ልክ አንድ ሰው
ቋሚ ፍቅር ይቅር፣ ለብ ለብ እናርገው”
ክትፎዋም ለብ ለብ
ፍቅሯም ለብ ለብ
ኑሮዋም ለብ ለብ
ዕውቀቷም ለብ ለብ
ነገር አለሟ ግልብ
እንዴት ይበስል ይሆን፣ እሳት ያልገባው ልብ?
(ላልበሰሉቱ)
🔘ነቢይ መኮንን🔘
👍41❤14👏4😁4👎2🔥2