አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አውቶቡሱ እንደተንቀሳቀሰ ብዙውን መንገደኛ እንቅልፍ
ያዳፋው ጀመር: ካርለት ለመተኛት ሞከረች! አልተመቻትም፡ አጠገቧ ያለው ፂማም ግን እያንኮራፋ እንቅልፉን ይለጥጠው ጀመር፡
ካርለት ተሳቀቀች: ፂማመ ይባስ ብሎ ትከሻዋን ደገፍ ብሎ አፉን እንደ ድምፅ
ማጉያ ጆሮዋ ላይ
ደግኖ ኩርፊያውን
ያንደቀድቅባት ገባ፡፡ ልትገፋው ወይንም ቀስቅሳ እራስህን ቻል ልትለው አለበች፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ከአፉ የሚወጣው የአልኮል ሽታ ገፍትሮ የሚጥል ነው፡
ወዘወዘችው ነቀነቀችው እንኳን ሊነቃ እሽሩሩ…
እንደሚሉት ህፃን የባሰ ተመቻችቶ ተጠጋትና ዶቅዶቄውን ይነዳው
ጀመር “ክር… ክርር…" እያደረገ: እንቅልፏ ጠፋ ı ድካሟ ጥሏት ሄደ: አስቸጋሪው ሰው ከበዳት: ከአጠገቧ ከፊት ለፊትና ከኋላ ያሉት አዘኑላት። አንዱ ሊቀሰቅሰው እንዲያውም እጁን ሰደደ፡

"ሊቭ ሂም” አለች᎓ አጠገቧ ያሉት የቀኝ እጅዋን መዳፍ
ግራና ቀኝ እየወወዘች ተዉት ማለቷ እንደሆነ የተረዱት ሰዎች
ገረማቸው፡፡

“ባህሪውን ስለሚያውቅ  ሌላ ሰው ላለማስቸገር  እሱም ላለመሳቀቅ ብሎ ሁለት ትኬት ቆርጦ በተቀመጠበት ከፍላጎቱ ውጭ አብሬው እንድቀመጥ ያስገደድሁት እኔ ነኝ እሱ ምን አጠፋ” ብላ፤ ሸክሟን በፅሞና ለመሸከም ወሰነች፡፡

ሞጆ ላይ ከእንቅልፉ ነቃ: ደስ አላት:: ሸከሙ ተነሳላት
የአልኮሉ ሽታ ራቃት: የማይቆመው ሙዚቃው ነበር የአውቶቡሱ! ለእሷ ከአዲስ አበባ እስከ ሞጆ ሳታቋርጥ አንድ ዘፈን ብቻ
ነው የሰማችው ተመሳሳይ: ሌሎች ተሳፋሪዎች ደስ
እንዳላቸው ገምታለች። እንደ ሸክሙ እሱም እሚቆም ቢሆን ለተወሰነ ጊዜ ደስታዋ ነበር።

ይሀን ስታስብ የሆነ ሽታ እፍን አደረጋት:: ወደ ፂማሙ ሰው ተመለከታች። ወደ መስታወቱ  ዞር ብሎ ትንሽዋ ጀሪካን ውስጥ
ያለውን አንደቀደቀው። አረቄ ነው ሸቷታል ከዚያ ድንገት ዘወር ሲል አይን ለአይን ግጥም አሉ።

“ዱ.ዩ ወንት? አላት
ትፈልጊያለሽ ለማለት እንግሊዘኛ መቻሉ ደስ አላት ኖ ቴንኪው” አለችው  አልፈልግም አመሰግናለሁ ለማላት ለማለት።

“ደስታ ፈጣሪ በአገራችን ያለው ይሄ ነው ብሎ ወደ ጀሪካኑ እያሳያት ከት ከት ብሎ ሳቀ። አባባሉ ሳይሆን አሳሳቁ እሷንም  አሳቃት:: ወዲያው ግን ኮስተር አለች
ለጠጪው ሰው ፊት
መስጠት እንደሌለባት በመገመት። ትከሻውን ሰብቆ እጆቹን ትልቁ
ኮቱ ውስጥ ከቶ በነጭ ወረቀት የተለበደ አሮጌ መጽሐፍ አውጥቶ
ዘርግቶ ያይ ጀመር: ሰረቅ እያደረገች እያየች ዝም አለችው፡

“ተጫወቺ!” አላት በመሃል።

እያነበብክ አይደል? ልረብሽ አልፈልግም" አለችው:
እያነበብኩ እንኳ አይመስለኝም" እንደገና ፈገገ ከንፈሩ ቀይ ነው ጥርሶቹ ግን በልዘዋል:: በሲጋራ ጢስ ግን እንዳልሆነ ገመተች  ካርለት:

“እያነበብክ ካልሆነ መጽሐፉን ለምን ገልጠህ ያዝኸው?”

“አንዳንድ መጽሐፍት ታምረኞች ናቸው፤ አንች ከማንበብሽ
በፊት አይንሽን አስፈጥጠው እነሱ ያነቡሻል። ህይወትሽ ባዶ
ዓላማሽም ባዶ ለመዋሸት የተፈጠርሽ እርጉም መሆንሽን ይነግሩሻል ይህም መጽሐፍ የዚህ ባህሪ አለው" ብሏት ፂሙን
እየሞዠቀ ትከሻውን እያርገፈገፈ ሳቀ። እሷም  አላስችል ብሏት ሳቀች።
ከልቧ ከት ከት ብላ ሳቀች፡፡

እንደገና ፂማሙ ፀጥ አለ ካርለት አሁንም እየሰረቀች
ስታየው የትልቁን ጀሪካን ክዳን ደግሞ ከፍቶ ፊቱን ዞሮ አንደቀደቀው! ሸተታት ጠጅ ነው: ኢትዮጵያ ውስጥ በቆየችበት ጊዜ ጠጅና አረቄ በተለያየ አጋጣሚ
ስለቀማመስች ሽታው ለእሷ
እንግዳ አይደለም፡፡

ዞር ብሎ እንደገና አያት:: አይኗን ልትመልስ ስትል ተያዩ። ስለዚህ መዞሩን ትታ! “ትንሽዋ ጀሪካን አረቄ ትልቁ ደግሞ ጠጅ ነው አይደለም" አለችው።

"ጎበዝ እንዴት አወቅሽ?" አላት:

"በሽታው አወቅሁት" አለችው አድናቆቱን አንገቱን
እየወዘወዘ እየገለፀላት ፈገገ::

"መጠጣት ካለብህ ለምን አረቄውን ወይንም ጠጁን  አንዱን ብቻ መርጠህ አትጠጣም። ሁለቱ ሲቀላቀል አይጣላህም? ለጥያቄ ግን ይቅርታ" አለችው።

አንች ብልጥና አስተዋይ ሰው ነሽ ሪሊ” አለና እንደገና
ሳቁን ለቀቀው። ሳቁን እስኪጨርስ ጠበቀችው። እሱ ግን ዝምታን መረጠ። እሷም ልትተወው ፈልጋ ነበር፡ ምናልባት ሊያዝንባት
እንዳይችል ሰጋች: ፂማሙ ግን ደስ እንዳለው ነው: ይግረምሽ ብሎ
እንዲያውም በሰለቻት ሙዚቃ እንደ መደነስ ይቃጣው ጀመር፡

“...ሁለቱን ስትቀላቅል  አይጣላህም?" አለችው ካርለት አንገቱን

“እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፡ በሰላም አብረው እንዲኖሩ ከብርሃን ወደ ጨጎጎታሙ ጨጓራዬ ውስጥ አስገብቻቸው እነሱ ተባብረው እኔን አንደማጥቃት እርስ በርሳቸው ካልተስማሙና ከተጣሉ የከፋው ተበደልሁ ባይ በሁለት መንገድ (በጁ ምልክት እያሳያት)
ወይም በላይ ወይ በታች መውጣት ይችላል። እኔ ደድግሞ በጠየቁኝ
አቅጣጫ በሬን እከፍታለሁ" ብሎ ፈገገ፤ ካርለት ግን ሳቋን መቆጣጠርን ተሳናት፡ ወርቃማ ፀጉሯ እስኪርገፈገፍ ተሳፋሪው ሁሉ እየዞረ እስኪያያት… ሳቀች እሱ ግን ፀጥ አለ፤ እንቅልፍ እንቅልፍ አለው ተኛ! ካርለት ትከሻ ላይ፤ ወርቃማ ፀጉሯ እንደ በቆሉ ጭራ ፊቱን ሲነካካው የናቱን ጡት እንደሚጠባ ህፃን ፍርክስክስ ብሎ ተኛ
“ኩርር… ኩርርር…" እያደረገ፡፡..

💫ይቀጥላል💫
👍292
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ ከሉ ሆራ ጎይቲ አንተነህን ሐመር ካደረሳት በኋላ አስር ቀን በማይሞላ ጊዜ ተመልሶ እንደሚመጣና እሱ አዲሳባ ለተወሰኑ ቀናት ሲቆይ ካርለት ደግሞ ወደ ሐመር ለመሄድ እቅድ ነበራቸው፡፡ ከሎ ሆራ ግን የውሃ ሽታ ሆነባት፡፡ “ምን ነካው?” እያለች ብዙ አሰበች ካርለት: ደህንነታቸውንና ያጋጠመውን ችግር ግን ማወቂያ አንዳችም የመገናኛ እድል…»
የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… ክፍል ሁለት
(ሜሪ ፈለቀ)

በአጭሩ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሁለት ይከፈላል። ብዙሃኑ እኔን የማያውቀኝ እና የቀረው ጥቂቱ እኔን የሚጠላኝ።

«ይሄን ሁሉ ጥላቻ ትከሻዬ ላይ ቆልዬ እንዴት ኖርኩ? እንዴት አላጎበጠኝም? » በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ አትክልቱን የሚያጠጣውን ጎንጤን ጠየቅሁት።

« አይ እትዬ ዛሬ ሌላ ሰው ሆነው በንፁህ ልብ ስለተቀበሉት ነው የሚያጎብጥ ሸክም የሆነብዎት። ቂም ባቄመና በጠለሸ ልብ ሆነው ሲቀበሉት እንዲህ አልተሰማዎት ይሆናል።» አለኝ ከስራው ሳይስተጓጎል። እሱ 'ምንም የማውቀው የለም' ይበለኝ እንጂ በእያንዳንዱ የቃላት ምልሳችን ውስጥ ከነገረኝ በላይ ስለእኔ እንደሚያውቅ የሚያሳብቅ ንግግር ይሰነቅራል። ለጎንጥ ጥሩ ሰው የነበርኩ ሆኜ ወዶኝ አይደለም እንዲህ ቀና መልስ የሚመልስልኝ። እግሩ ስር ፈራርሼ በሽንፈቴ ነው ልቡን ያገኘሁት።

ሆስፒታል ተኝቼ ተናኜ (የቤት ሰራተኛዬ) እየተመላለሰች ስትጠይቀኝ በእያንዳንዱ ቀን ለምጠይቃት ጥያቄ በምትሰጠኝ መልስ ከአደጋው በፊት የነበረችውን ሜላት አበጃጅቼ ላውቃት ጣርኩ። ተናኜ የምታውቀው ጥቂት ነው። በሳምንት ውስጥ አብዛኛውን ቀን ጂም ሄጄ እሰራ ነበር ፣ አብዛኛውን ቀን አመሻሽ ወጥቼ ለሊት እሷ ስትተኛ ነው የምመለሰው፤ በእሷ አገላለፅ ከፈሴ የተጣላሁ ምንም የማያስደስተኝ መንቻካ ሴት ነበርኩ። ጎንጤ በዘበኝነት 1 ዓመት መስራቱን ስትነግረኝ ከሷ የተሻለ መረጃ ይኖረዋል በሚል ሆስፒታል መጥቶ እንዲያየኝ እንድትነግረው ጠየቅኳት።

«ይቅርታ ያድርጉልኝ እመቤቴ ስራዬ ደጃፎትን መጠበቅ ነው። ስራዬን ጥዬ መምጣት አይሆንልኝም። በተረፈው እግዜር ይማሮት!» ብሎ መልዕክት ሰዷል።» ብላ የእርሱን እንቢታ ስትነግረኝ በእርሱ እንቢታ ደስ ያላት ነው የምትመስለው። የሆነ 'የታባሽ' የሚል ዓይነት እምቅ! የዛን ቀን ማልቀስ አማረኝ። ወደሰማይ እያንጋጠጥኩ አምላክን ለመንኩት። ግንሳ ክፉ ሴት ከነበርኩ አምላክስ ያውቀኝ ይሆን? ህይወት በረደችኝ .......የሆነ እራቁቴን አጋልጣ አደባባይ ያሰጣችኝ ዓይነት መንዘፍዘፍ ተንዘፈዘፍኩ።

አንዳንድ ገልቱኮ 'ያለፈውን ረስተህ አዲስ ህይወት ጀምር ......' ዓይነት ምክር ይመክር ይሆናል። ሰው ያለትናንቱ ምንድነው? ይኸው እጥብ አድርጌ ትናንትን ረስቼው መች ከአዲስ መጀመር ቻልኩ? ከምን እንደምጀምር ተደናብሮብኝ ተገትሬ የለ? ትናንት የዛሬ መንደርደሪያ ይሆናል እንጂ ትናንትን እርሳው እንዴት ይባላል? ትናንት ከሌለ ዛሬ መች ይመጣል? ሰውማ ትናንቱን ነው። ዛሬውን የሚንደረደረው ከትናንት ተነስቶ ነው። እረስቶ ሳይሆን ትናንቱ ጥፋት ከሆነ ተምሮበት፣ ጥሩ መሰረት ከሆነ ደግሞ አዳብሮት ይቀጥላል።

ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን ሲደርስ ሆዴ በፍርሃት ሲላወስ ታወቀኝ። የቱ በትክክል እንዳስፈራኝ አላውቅም። እቤቴ ስሄድ ያቺ ተኛኜ የምትጠላትን ሜላት የማገኛት አይነት ስሜት ይሰማኛል። ከቤቴ ይልቅ ሆስፒታል ውስጥ የተሻለ ሰላም የማገኝ ዓይነት ስሜት ፣ ወደቤቴ ሳይሆን ወደግዞት የምሄድ ስሜት ልቤን ተጫነው። ሊገድለኝ የሞከረው ሰው ድጋሚ መጥቶ ቢጨርሰኝስ? ሆስፒታል ውስጥ አኑሩኝ ይባላል? አብሮኝ የተኛ ታካሚ ወዳጅ በተናኜ መሪነት በመኪናው እቤቴ እየሸኘን እጄ ይንቀጠቀጣል። መንገዱ ሩቅ ቢሆንና ቶሎ ባንደርስ?

«ልብስ ልደርብሎት እንዴ? እየተንቀጠቀጡ ነውኮ! » አለችኝ ተናኜ። መንቀጥቀጤን ለመደበቅ አንዱን እጄን በአንደኛው ጭምቅ አድርጌ ያዝኩት። የሆነ ጥቁርና ነጭ ቀለም የተቀባ የብረት በር ፊት ለፊት እንደቆምን የሰማይ ስባሪ የሚያህል፣ ፊቱ ላይ መጀነኑ የሚንጎማለል፣ አንገቱ ላይ ፎጣ ጣል ያደረገ ጎልማሳ ሰው በሩን ከፈተልን።

«ጎንጤ እሱ ነው?» አልኳት ወደተናኜ ዘወር ብዬ ሳላስበው። በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች። ጎንጤ ይሆናል ብዬ የሳልኩት ሰውዬ የሆነ ኮስማና ሸምገል ያለ ደካማ ነገር ነው። ያደረሰንን ሰው አመስግኜ በሩን እያለፍኩ።

«ደህና ዋልክ?» አልኩት ጎንጤን።

«እግዜሐር ይመስገን። እንኳን ለቤትዎ አበቃዎት!» ብሎኝ በሩን መዘጋጋት ያዘ።

ጊቢውን ዙርያ ገባውን አየሁት። ከቤቱ ፊትለፊት ባለ ሰፋ ያለ ቦታ አበቦች ፈክተውበታል። መለስተኛ ቪላ ቤት ነገር ነው። ከቤቱ በአንደኛው ጎን ባለ ክፍት ቦታ መኪና ቆሟል። እንደእንግዳ ዙሪያ ገባውን በአይኔ ስነቅስባቸው ግራ ተጋብተው ነው መሰለኝ። ሁለቱም ቆመው ያዩኛል። እንደተቆጡት ህፃን ብርግግ ብዬ ፈጥኜ ወደበሩ ሄድኩ። እቤት ገብቼ ምን እንደምፈልግ እርግጠኛ ባልሆንም ቤቱን መበርበር ያዝኩ። የፎቶ አልበም ፣ የትዳር ሰርተፊኬት ፣ ወይ የሆነ ደብዳቤ ብቻ አላውቅም አንድ የሆነ ነገር። ሳጎነብስ ቁስሌ እየተሰማኝ መበርበሬን ቀጠልኩ። ቤቱ ሳሎን ሶስት መኝታ ቤት እና ሰፊ ጓዳ እና መታጠቢያ ቤት ነው ያለው። መኝታ ቤቴ መሆኑን የነገረችኝ ክፍል ስገባ ሙሉውን የቁምሳጥኑን በሮች ከከደነው መስታወት ጋር ተፋጠጥኩ። ራሴን በደንብ አየሁት። ትክት ያለው ገፅታ! ክፉ ከመሆኔ ሌላ መከራ የበዛበት ህይወት ይሆን ያሳለፍኩት? የአልጋው ራስጌ ኮመዲኖ ላይ በፍሬም ያለ ፎቶ አይኔን ጠለፈኝ። አንደኛው የራሴ ምስል ነው። ወይም መሰለኝ። ከሆነ ወንድ ጋር ተቃቅፈን እየሳቅን። ከኛ ምስል ጀርባ ቁመቱ በረዛዘመ አረንጓዴ ሳር የተሸፈነ መስክ ይታያል። ቦታውን የማውቀው ዓይነት ስሜት ይሰማኛል ግን ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። አሁን ካለሁበት ድንጋይ ቤት ይልቅ ምስሉ ላይ ያለው ሜዳ የቤት ዓይነት ስሜት ሰጠኝ። የሆነ በሳሮቹ መሃል ስሮጥ እርጥበት ያለው ሳር እግሬን እየሳመኝ ዓይነት። እዛ መስክ ላይ ደስተኛ ሴት የሆንኩ የምቦርቅ ዓይነት ሽውታ ትውስታ ይሁን ቅዠት ሰውነቴን ይወረዋል። እሺ የት ነው? እሱስ ማን ነው? አባቴ አይሆንም። በእድሜ እኩያዬ ቢሆን ነው። ተጨማሪ መረጃ ካገኘሁ ብዬ ቁምሳጥኑን አተራምሰው ጀመር። አንደኛውን መሳቢያ ስቤው በድንጋጤ እሪሪሪ ብዬ ጮህኩ። ጎንጥም ተናኜም እየተሯሯጡ ሲደርሱ መሳቢያው እንደተከፈተ ራቅ ብዬ ቆሜ ደንዝዣለሁ።

«ሽጉጥ መኝታ ቤቴ ውስጥ ምን ይሰራል?» ስላቸው ግራ በመጋባት ተያዩ።

«የራስዎ ሽጉጥ ነዋ ሆ!» አለ ጎንጥ ለማይረባ ምክንያት ሮጦ በመምጣቱ እየተናደደ።

«እኮ ሽጉጥ ምን ያደርግልኛል?»

«እሱን እኔ በምን አውቃለሁ?» ብሎ አየሩን እየቀዘፈ በትክክል የማልሰማውን ነገር እያጉተመተመ ወጣ። ተናኜ ያሳዘንኳት መሰለች ወይም እኔ መሰለኝ ቆማ በግራ መጋባት ስታየኝ ቆይታ።

«እንግዲህ ጠላት ቢኖሮትም አይደል ሊገድሎት የሞከረው? ራሶትን ሊጠብቁበት ይሆናላ ያስቀመጡት።» አለች የተከፈተውን መሳቢያ መልሳ እየዘጋች።

«ገላዬን ታጥቤ የምለብሰው ንፁህ ልብስ አውጪልኝ በናትሽ።» አልኳት ለጊዜው እዛ ቁምሳጥን ውስጥ ያለ ተጨማሪ አስደንጋጭ ነገር ለመጋፈጥ በቂ አቅም አልነበረኝም።

ገላዬን እየታጠብኩ ጀርባዬን ለማሸት ስንጠራራ በመስታወቱ ውስጥ ጀርባዬን አይቼው

«በስመአብ !» ብዬ ጮህኩ። ሰካራም የሳለው ስዕል ይመስላል ጀርባዬ! ከማጅራቴ ጀምሮ የቂጤን ኳሶች ጭምር በንቅሳት የተዥጎረጎረ ነው። የንቅሳቱ ዓይነት አበዛዝ የሰው ጀርባ ሳይሆን ለህፃን ልጅ በምስል ማስተማሪያ ደብተር ነው የሚመስለው። የልብ ምስል፣ አንበሳ፣ ፈረስ የሚጋልብ ሰው ወይ መልዓክ ያለየለት ነገር በትልቁ የተፃፈ «ኪዳን» የሚል ፅሁፍ ፣ በደንብ የማይታዩኝ ብዙ ጥቃቅን ምስሎች .......
👍301
በመስታወቱ ጀርባዬን ሙሉ በሙሉ ላየው ስታገል የሆነ ማስታወስ ይሁን ያልገባኝ የሳሩ መስክ ዓይነት ስሜት ሽው አለብኝ። የሆነ የተቆራረጠ ትርጉም የለሽ ምስል። ጨለምለም ያለ ክፍል ውስጥ የሚነድ ሊያልቅ የደረሰ ሻማ ፣ ስኒከር ጫማ የተጫማ አንድ የሰው እግር እና የመጠጥ ሽታ ከ30 ደቂቃ በላይ መስታወቱ ላይ ባፈጥም የተለየ ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። ምን ዓይነት ህይወት የኖርኩ ሰው ብሆን ነው ቂጤን ንቀሱኝ ብዬ ገልቤ የሰጠሁት? ቤተሰብ አልነበረኝ ይሆን? በመሃል ደግሞ ሌላ ሀሳብ ይጠልፈኛል:: ቋንቋ የሚሞሪ አካል አይደለም ? ጭንቅላቴ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋባበት ወና ሆኖ እንዴት አማርኛ ማውራት ቻልኩ? አነበብኩኮኣ? እንዴት ማንበብ አልጠፋኝም?

«ፖሊሶቹ መጥተዋል።» አለችኝ ተናኜ እዛው እንዳፈጠጥኩ። የምሰጠው ቃል ባይኖረኝም ቃሌን ሊቀበሉ መሆኑ ነው። ለባብሼ ወደሳሎን መጣሁ። ከእኔ ያገኙት መረጃ ባይኖርም ሲጠይቁኝ ቆይተው ቦርሳ እና ስልኬን ሰጥተውኝ ሄዱ። ስልኩን ከማገላበጥ ውጪ የማደርገው ግራ ገብቶኝ ቀና ስል ተናኜ እያየችኝ ነው። አፈርኩኝ መሰለኝ እሱን ቁጭ አድርጌ ቦርሳውን መበርበር ጀመርኩ። መታወቂያ ፣ መንጃ ፈቃድ እና የብር ኖቶች ያሉበት ትንሽዬ ቦርሳ ውስጡ አለ። ምንም ፍንጭ የለውም። የሆነች ተጨማድዳ የተቀመጠች ትንሽዬ ወረቀት አገኘሁ። አገላብጬ ሳነብ የሽያጭ ሪሲት መሆኑን ተረዳሁ። ጂም ውሃ የገዛሁበት ነው። ቁስል እንዳለኝ ሁሉ ዘንግቼ መዥረጥ ብዬ ወጣሁና

«እስፖርት የምሰራበት ጂም የት እንደሆነ ታውቃለህ?» አልኩት ጎንጤን
«እ!» አለ አዎ እንደማለት ነገር። እንዲያሳየኝ ጠይቄው ታክሲ ጠርቶ አብሮኝ ሄደ::

ገብቼ ምን እንደምል እንኳን አላውቅም! 'እስኪ ካወቃችሁኝ ራሴን አፋልጉኝ ማን ነበርኩ ?' ነው የምላቸው? በሩን አልፌ እንደገባሁ ቆምኩ። ከፊትለፊቴ እስፖርት እየሰራ ያለ ሰውነቱ የተነፋፋ ወጣት ነገር በሆነ ነገር ፈላጊ አይን አፍጥጦ እያየኝ ያዝኩት። የሚያውቀኝ ሰው ቢሆን ነው ብዬ የሆነ ነገር እስኪለኝ አትኩሬ ማየት ቀጠልኩ። የለበስኩትን ፒጃማ ቅንድቡን ሰቅሎ ከገረመመ በኋላ

«ምን ታፈጫለሽ?» አባባሉ። ቢያውቀኝም በወዳጅነት የሚያውቀኝ ሰው እንዳልሆነ ያሳብቃል። ምንም ሳላስብ ወዳለበት እየተጠጋሁ።

«ይቅርታ እና ታውቀኛለህ ማለት ነው?» ስለው እየጎፈላ ከማሽኑ ላይ ወርዶ ደረቱን እየነፋፋ
«ኸረ ተይ ሴት ነሽ ብዬ ነው የታገስኩሽ ግን?» ከማለቱ የሆነኛው ከሌላ አቅጣጫ እየሮጠ መጥቶ

«እኔ ብጥብጥ አልፈልግም ሜላት አርፌ ስራዬን ልስራበት!» አለ በልመና ዓይነት። መናገርም መራመድም የጠፋውን ሚሞሪዬን ተከተሉት መሰለኝ እንደተገተርኩ ቀረሁ።

..................... ይቀጥላል ..........................

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
12👍6
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


“እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፡ በሰላም አብረው እንዲኖሩ ከብርሃን ወደ ጨጎጎታሙ ጨጓራዬ ውስጥ አስገብቻቸው እነሱ ተባብረው እኔን አንደማጥቃት እርስ በርሳቸው ካልተስማሙና ከተጣሉ የከፋው ተበደልሁ ባይ በሁለት መንገድ (በጁ ምልክት እያሳያት
ወይም በላይ ወይ በታች መውጣት ይችላል። እኔ ደድግሞ በጠየቁኝ
አቅጣጫ በሬን እከፍታለሁ" ብሎ ፈገገ፤ ካርለት ግን ሳቋን መቆጣጠርን ተሳናት፡ ወርቃማ ፀጉሯ እስኪርገፈገፍ ተሳፋሪው ሁሉ እየዞረ እስኪያያት… ሳቀች እሱ ግን ፀጥ አለ፤ እንቅልፍ እንቅልፍ አለው ተኛ! ካርለት ትከሻ ላይ፤ ወርቃማ ፀጉሯ እንደ በቆሉ ጭራ ፊቱን ሲነካካው የናቱን ጡት እንደሚጠባ ህፃን ፍርክስክስ ብሎ ተኛ
“ኩርር… ኩርርር. እያደረገ፡፡

ዝዋይ ላይ አውቶቡስ ለቁርስ ሲቆም ነቃ። ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ነው: ሰዉ ሁሉ ወረደ: ካርለት ካለፂማሙ ሰው
የምታውቀው የለም:: ስለዚሀ አብረው ወረዱ፡፡

የኢትዮጵያውያን ምግብ ለሷ አዲስ አይደለም። ግን
ለተወሰኑ ወራት እርቃው ቆይታለች፡፡

እሱ ጥሬ ክትፎ እሷ ዳቦና ሻይ አዘው ሲበሉ ቆዩና፡-

“ስለ ከቡ ነገርኩሽ" አለ ፂሞ:

“ማነች ከቡ?"

“ሚስቴi ለጋብቻ ስጠይቃት ፂማም ነህ' ብላ ናቀችኝ፡ ዝም ብዬ ጥረቴን ቀጠልሁ፡፡ ፂሙ አያስጠላሽም፤ምኑን ልትስሚው ነው' ብለው ሲያጥላሉባትም እኔ ጥረቴን እንደቀጠልሁ ነበር፡ አንድ
ቀን ታድያ ተሳካልኝ ለትዳር እንደምፈልጋት የተማርሁ መሆኔን ላዬ ሞኛ ሞኝ ቢሆንም ውስጤ ግን ዘመናዊ እንደሆነ በአለማችን ካሉ በጣት ከሚቆጠሩ ደስተኞች መካከል አንዱ መሆኔን…
እየዘረዘርሁ ሳጫውታት ቆየሁ፡፡ ምኗ ሞኝ መሰለችሽ! ቆቅ ነች:
ከምታየውና ከሰማችው ጋር እኔ ያልኋት ሁሉ ተምታታባት ከቡ!

“ሰርቲፍኬቴን ስቀበል የተነሳሁትን ፎቶ ሳሳያት ግን ውሃ ሆነች፡ ፍንጥር ፍንጥር ማለቷን ቀነሰች፡ ያኔ ጠልፎ እሚጥላትን ምላሴን እያወናጨፍሁ እግሯን አንስቼ እግሬ ላይ አደረግሁና የርግብ
አሳሳም ስሚያት ወጥቼ ስሄድ የጨው መላሾ እንደቀመሰ ከብት
እየተከተለችኝ ለምን አትመጣም መሰለሽ!" ብሎ ሳቁን ለቀቀው፡፡

ካርለት ስለ አንድ ነገር መናገር በጀመረ ቁጥር መጨረሻው አስቂኝ
መሆኑን መጠበቅ ጀምራ ስለነበር እሷም አብራው
ሳቀችና የሆነ ነገር
በህሊናዋ ትዝ አላት  እንግዳ አባባል፡

“ምንድነው የርግብ አሳሳም''

“አታውቂም? ብዙው ኧረ በጠቅላላው ሰው የሚያውቅ አይመስለኝም" አላትና ቀና አለ፡፡ “እኔ ግን የተማርሁት ከርግቦች
ነው፡፡ ቆርቆሮዬ ላይ ሲ
ሲዳሩ አይቼ፡፡
“ታያለሽ ከንፈሬ አካባቢ ያለውን ፂሜን ለመሳም ከፈለግሁ ከሴቷ አፍ ውስጥ ገብቶ ጉሮሮዋን ያንቃታል፡፡ እኔ ደግሞ ችግር
መፍጠር አልወድም፤ ለምን ብዬ! ሰው ሁሉ የሌላው ሳይጨመር የራሱ ችግር መቼ አነሰው… ስለዚህ እኔ እንደ እርግብ አፌን
ስከፍትላት ክቡ ከንፈሯን ውስጥ ትጨምረዋለች ያኔ እጠባታለሁ  ከንፈሯን: ያ ነው የእርግብ አሳሳም! ያ የርግብ አሳሳም ነው ነው
ከቡዬን እንደ ከብት  እያንደረደረ እቤቴ  ያስገባት፡፡ ፂሜ ችግር
ስለማይፈጥርባት ቅቤ እየቀባች ሽሩባ ትሰራኝ ጀመር፡፡ ከዚያ እንዲያውም ልቧ እየራራ እንደ ሰናፍጭ የሚሰነፍጥ ፍቅሯን
እየመገበች ይኸው ያየኝን ሁሉ አጠገብህ ካልተቀመጥን' እያስኘ
የሚያስጎመጅ ሰው ወጣኝ" አላትና ሳቀ ተሳሳቁ…..

አውቶብሱ እንደገና ጉዙውን ሲቀጥል ፂሞ ከያይነቱ
ጎንጨት አድርጎ ተኛ: ካርለት እንግዳ ባህሪው ገርሟታል። አጠገቡ
መቀመጧን እንዳልጠላችው አሁን ግን ከነበረው ሰው
ልትግባባው የምትችለው ከሱ የተሻለ እንዳልነበር ተሰማት።

አውቶብሱ የላንጋኖንና የሻላን ደን እያቆራረጠ ሲጓዝ ሙቀቱ እየጨመረ የዳቦ መጋገሪያ ፍም ላይ የተቀመጡ ያህል
ያተኩስ ጀመር። የአውቶብሱ መስኮትና በር ባጠቃላይ ክርችም ብሎ
ተዘግቶ ህዝቡ በላብ ሻወር ይታጠባል፡ መስኮቱን ለምን
እንደማይከፍቱት ፂሞን ጠይቃው የአውቶብስ መስኮት አትክፈቱ•
ብርድ ይመታችኋል ያለው ዶክተር ባይታወቅም ልጅ አዋቂውን ቃሉን አክብሮ በሙቀት መቀቀል መምረጡን ነግሯታል፡ ስለዚህ የለበሰችውን ጃኬት አውልቃ በነጭ ቲሸርት ሆና የሙቀት ቅጣቷን
እየተቀበለች ለማረፍ ከፊት ለፊቷ ካለው ወንበር የብረት ዘንግ ላይ ራሷን ደገፍ አደረገች፡፡

ሙዚቃው ማንቧረቁ አልቆመም፡፡ አውቶብሱ ማርሹን እየቀያየረ ይጓዛል፡ ካርለት እንደ ቀልድ እንቅልፍ ወስዷት ቆይታ የአውቶብሱ ሹፌር አህያ ድንገት ልትገባበት ስትል ፍሬኑን ያዝ
ሲያደርግ ከወንበሩ ጋር ተጋጨችና ብንን ብላ ደንግጣ ተነሳች፡፡

ፂሞ ያነባል። ብጥስጥስ ያለች መጽሐፉን፡ ትንሽ ቆይቶ ከትልቁ ኪሱ ወረቀቶች ያወጣና ያነብ ጀመር፡ ካርለት
ተደንቃ አየችው፡፡ ልታምን አልቻለችም፡፡ ማንም ሰው ያደርገዋል ብላም አትገምትም፡:

የምን ወረቀቶች ናቸው?”

“ወረቀቶቹ አያቸው ግንባሩን ሽቅብ ሰብሰብ አድርጎ፡፡

"ቁም ነገር ያላቸው ወረቀቶች ናቸው፡፡"

ላያቸው እኮ ቆሻሻ አለባቸው?”

“አዎ አይነምድር አው፡ ግን ደርቋል፡፡ ሳነሳው እንኳን ብዙም አልደረቀም ነበር፡ ይኸ ጃኬት ግን ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለመሃረቤና
ስለሚፈጥር እዚያው ደረቀ፡፡
ለወረቀቶችም ሙቀት
እስክርቢቶ አይበረክትልኝም ሙቀቱ ያገነፍለዋል፡፡"

“ወረቀቶቹን ከየት ነው ያገኘሃቸው?''።

“በየሄድሁበት መፀዳዳትም ባልፈልግ ሽንት ቤት መሄድ
አዘወትራለሁ የተፃፈውን ማንበብ ሱስ ሆኖብኛል፡ አሁን አሁን ደግሞ አንዳንድ ሽንት ቤቶች ውስጥ ያሉ ቅርጫቶች ላይ ሰው
ተፀዳድቶባቸው እማገኛቸው ወረቀቶች ሽንት ቤቶች ከመፀዳጃነት
አልፈው ወደ መፃህፍት ቤትነት እየተቀየሩ ነው
የሚያሰኝ ነው፡፡

“በአማርኛ ሆነ እንጂ ይህን ብታነቢው የወደቅሽበትን
ሳታውቂው ሶስት ቀን ተኝተሽ ትከርሚ ነበር" አላት፡፡

“ቆሻሻ ወረቀቱን አትጠየፍም?"

“እጠየፋለሁ እንጂ! ግን ጠቃሚ ነገር ኣለበት፡፡ ጠቃሚ ነገር ደግሞ ቆሻሻ አለው ተብለቀ አይጣልም፡፡ ቆሻሻ ማለት ጥቅም
የማይሰጥ ተራ ነገር ነው፡፡

“ይገርምሻል ካለ እነዚህ'' ጀሪካኖቹን ጠቁሞ አሳያት
“...ካለ እነዚህና ካለ ከቡ የረባም ጓደኛ የለኝ፡፡ ምናልባት እኔ ወይ እነሱ ቆሻሻ ስለሆን ይሆናል  ከብዙው የሥራ ጓደኞቼ ጋር
የማልግባባው ታዲያልሽ…" የትንሽዋን ጀሪካን ክዳን ከፍቶ ወደ መስታዋቱ ዞሮ አንደቀደቀና

“…ታዲያልሽ ከሽንት ቤት ቅርጫት ቆሻሻ ወረቀት አንስተህ እንዴት እኪስህ ትከታለህ ያሳዝናል! ይህን የሚፈጽም ህሊናው
የተስተካከለ ሰው የለም ካለ እብድ በቀር' ብለው አጥላሉኝ፡፡

“አንድ ቀን ታድያ ሁለት ቀያይ ብሮችን ይዥ ሽንት ቤት ገባሁና በብሩ ተፀዳጅቼ ወጣሁ፡፡ ከኔ የሚቀጥለው አላየኝም ገባ ብሎ ሲወጣ ተመልሼ ብገባ የተፀዳዳሁባቸውን የብር ኖቶች ወስዷቸዋል
ደሞ ሌላ ቦታ ሄጄ በሁለት አምስት አምስት ብሮች ተፀዳዳሁ ... ቀጥሎ የገባው ሲወጣ ብሮቹ የሉም፡፡ hዚያ ደግሞ በአንድ አንድ ብር ሞከርኩ፤ እነሱም ተወሰዱ ታዲያልሽ!ብሮቹ ከእለት ጥቅም
ሌላ ጠቃሚ አይደሉም፤ ማንም ሰው ግን ቆሽሸው ቢያገኛቸውም ወደ ኪሱ ይላቸዋል፡፡

“እና እኔ ለይወት ጠቃሚ ቁም ነገር ያለውን ቆሻሻ ወደ
ኪሴ ብል ያለፋሁበትን ገንዘብን ፈልጌ አይደል? እውቀት ጠምቶኝ
እንጂ፡፡ ስለዚህ ምኑ ያስነውራል" ከት ከት ብሎ ሳቀ፡ ካርለት አንገቷን በአድናቆት ወዘወዘች፤ አልሳቀችም፡፡

“ኢትዮጵያ ውስጥ የፍልስፍና ሰዎችም አሉ፡፡ ማህበረሰቡ ግን እንደ ቆሻሻ ያያቸዋል፧ እነሱ ግን ለአገሪቱ ጠቃሚ እሴቶች
ነበሩ…" የትልቁ ጀሪካን ክዳን እንደገና ተከፈተ፡፡ ደቅ ደቅደቅ…
👍27🥰2😁21
“አዋቂ ሰዎች የጥበብ ግምጃ ቤት ናቸው፡፡ ይወታቸው ግን ጉራማይሌ ነው" ፈገገ ፂሞ፡፡
“አርባምንጭን ታውቂዋለሽ? ደረስን"

“አመሰግናለሁ ትልቅ ትምህርት ሰጠኸኝ፡፡ ይህች አገር!…" ምስጋናዋን አላስጨረሳትም፡ ካለ ትንሽና ትልቁ ጀሪካን በስተቀር ሌላ ጓዝ የሌለው ፂሞ ቀድሟት ወርዶ ከመናኸሪያው ወጥቶ ተሰወረ፡ስሙን ባለመጠየቋ አዘነች፡ እና ስም ሰጠችው: "ኢትዮጵያዊው ስም የለሽ ፈላስፋ.." አለችው::በሃሣቧ ግን የሚስማማ
ኢትዮጵያዊ ታገኝ ይሆን?


💫ይቀጥላል💫
👍23
የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሶስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«ኸረ እኔ ብጥብጥ ፈልጌ አይደለም የመጣሁት ! እባካችሁ? አደጋ ደርሶብኝ ሚሞሪዬ በሙሉ ጠፍቷል። የማስታውሰው ነገር የለም! ካወቃችሁኝ ማን እንደነበርኩ እንድትነግሩኝ ልጠይቃችሁ ነው!» ያልኩት ምን ማለት ነው? አላውቅም! 'ማነኝ?' ብሎ መጠየቅ ምን የሚሉት የነፈዝ ጥያቄ ነው? 'ሜላት ነሽ!' ነዋ ሊሉኝ የሚችሉት አይደል? ስም ግን ማንነትን እንዴት ይገልፃል? እንዴት ነው ሰው 'ማንነህ?' ሲሉት 'እገሌ ነኝ 'የሚለው? ስሜንስ አስታውሼው ነው? ወይስ ዶክተሩ ስለነገረኝ ነው ያወቅኩት?

«ሙድ ትይዣለሽ እንዴ? ባቡር በገጨሽ! እሱማ ፀሎቴ ነበር! ይህቺ ደግሞ የሰሞኑ ሙድሽ ናት? አደጋ ትላለች እንዴ በናታችሁ?» አለ የመጀመሪያው ሰውነቱ የተነፋፋው ወጣት ስነስርዓትም ርህራሄም በሌለው ሁኔታ። ያልኩትን እንዳላመነኝ ቢገባኝም ስሜቱ ግን ቅድም ከነበረው ፍርሃት ወይ ማክበር ያልገባኝ ማመንታት አሁን ወደ ንቀት ወይ ድፍረት ያልለየሁት ስሜት ተቀየረ:: ሊገላግል የመጣው ልጅ ግን እንደመረጋጋት ብሎ በጥርጣሬ አስተውሎ እያየኝ ነበር።

«በስመአብ! ምነው ይሄን ያህል? እንዲህ አይነት ነገር በራሴ ላይ አሟርታለሁ?» አልኩኝ በልመና! እንዴት እንደማሳምነናቸው ግራ እየገባኝ

«አንቺ የምርሽን ነው እንዴ?» አለ ሊገላግል የመጣው ልጅ! ባለ ንፍፊት ሰውነታሙም ከቅድሙ አሁን ግራ የተጋባ ቢመስልም ፍርጥም ብሎ

«ሰይፊኝ ካመንኩሽ!» አለ አንገቱ ላይ በጣቱ ከቀኝ ወደግራ የመቁረጥ ምልክት ሰርቶ

«ካላመንከኝ ላሳይህ » ብዬ የተመታሁበትን ቁስሌን ላሳያቸው ከላይ የለበስኩትን ልብስ ልገልጥ ስል ጎንጤ ከየት መጣ ሳልለው ዘሎ እጄን ቀጨም አደረገ እና ልገልጥ የጀመርኩትን ልብስ ወደታች እያለበሰ

«አንተ በአግባቡ ተጠየቅክ አይደል እንዴ? በወጉ አትመልስም? የምን ኩፍ ማለት ነው?» አለው ከእግሩ እስከጭንቅላቱ በንቀት እያየው።

«አንተ ደግሞ ማነኝ ነው የምትለው?» አለ ያኛውም እየተጠጋው።

«ሰውዬ ተከበር! ነገር አትፈልገኝ!»

«ምን እንዳታመጣ?» ሁለቱም ተኮፋፍሰው ሊነካከሱ የተፋጠጡ አውሬዎች መሰሉ። ቅድም ሊገላግል የመጣው ልጅ በመሃከላቸው ገባ!

ጎንጤ እንድንሄድ በእጁ ወደበሩ እያሳየኝ በሚያስፈራ ፊት እንድቀድመው ሲጠብቀኝ ምንም ሳልል ወጣሁ። ተከትሎኝ ወጥቶ እያለፈ የነበረ ታክሲ አስቁሞ አሁንም እንድገባ በእጁ ምልክት ሰጠኝ። ምንም ቃል ሳይናገር ቁጣው ይጋረፋል። እንዲህ የሚያስፈራ ሰውዬ ሊያስተዳድረኝ ነው ላስተዳድረው የቀጠርኩት? እልህ የታጨቀበት አተነፋፈስ ቁና ቁና እየተነፈሰ ፈርቼው ምንም ሳልናገር እቤት ደረስን። ድንገት በመጣልኝ ሃሳብ

«መቼም ጎረቤቶቼ ያውቁኛል አይደል? » ብዬ ወደ ቀኝ ወዳሉ ጎረቤቶቼ በር ላመራ እግሬን ከመዘርጋቴ ወደቤት መሄዱን ሳይገታ እየተራመደ ዞርም ብሎ ሳያየኝ

«እእ (ጭንቅላቱን በተቃውሞ እየናጠ) እኔ እርሶን ብሆን አልሞክረውም!» ሲለኝ ቆምኩ።

«እህእ? ቆይ ሰላም የሆንኩት አንድ ሰው የለም?» አልኩኝ ለራሴ ይሁን ለእርሱ

«እሱን አላውቅም!»

«እሺ እነሱስ?» አልኩት በግራ በኩል ወዳለው በር እየጠቆምኩ።

«ህእ!(ፌዝ ባለበት ሽራፊ ፈገግታ) እሱኛውም ጥሩ ሃሳብ አልመሰለኝም!» እያለ በሩን ከፍቶ ክፍቱን ለእኔ ትቶት ወደጊቢ ገባ። ተከትዬው እየገባሁ።

«ይሄን ያህል ምን ዓይነት ሰው ብሆን ነው ከሰው ሁሉ ጋር የምናከስ የነበረው? መቼም ከዚህ ሁሉ ሰው ጋር ፀብ ከሆንኩ ችግሩ ሰውጋ ሳይሆን እኔጋ ነው የሚሆነው! ይሄን ያህል ክፉ ሰው ነበርኩ?» አልኩት

«እኔ አልወጣኝም!» ብሎ በሩ አጠገብ ያለ የእንጨት ወንበር ላይ ተቀምጦ እኔን ላለማየት በሚመስል አጥር አጥሩን ማየት ጀመረ።

«በአፍህ ባትልም ሁኔታህ ያስታውቃል። እሺ የሌላው ይቅር አንተ ምን አድርጌህ ነው እንዲህ የምትጠላኝ? ምን እንዳደረግኩ እንኳን በማላውቀው ጥፋቴ ስትቀጣኝ ግፍ አይሆንም?»

«ሆ! እኔ ክፉ ደግ አያናግሩኝ! እንዲህ ነው እንዲያ ነው አልወጣኝም! ከፈለጉ ሄደው ማንኳኳት ይችላሉ።»(ወደጎረቤት ጊቢ በእጁ እየጠቆመ)

«ከእነርሱ አንተ አትቀርብም? 1 ዓመት እዚህ ቤት ነበርክ! ንገረኝ ምን አይነት ሴት ነበርኩ? ምንድነው የምሰራው? ከማን ጋር ነው የምውለው? እንዴት አንድስ ወዳጅ የለኝም?»

«የማውቀው ነገር የለም። ምንም ነግረውኝ አያውቁም! ሆ! እኔ የምውለው እዚችሁ ደጅ እርሶ ከቤትዎ! ምን ያገናኘናል?» አለ አሁንም ወንበሩ ላይ እንደተኮፈሰ

«እኔ ባልነግርህም ወይ ያየኸው ወይ የሰማኸው ግን ይኖራል?»

«ወሬ ለቃቅሜ የማቀብል ባለጌ አይደለሁም። ያላየሁትን አላወራም!» አለኝ ድርቅ ብሎ

«እኮ ያየኸውን ንገረኝ! ቢያንስ ላንተ ምን ዓይነት ሰው እንደነበርኩ ንገረኝ?»

«ሆ!» ከማለት ውጪ አልመለሰልኝም! ተስፋ ቆረጥኩ። በተወሰነ መልኩ ድርቅናው አናደደኝም! ቅድም በዛ ንፍፊታም ሰውዬ ፊት ለእኔ እንደሚያስብ ዓይነት ሰው ሲሆን አልነበረ? ስራው ቤቴን መጠበቅ እንጂ እኔን መጠበቅ ነው? እየጠላኝ ግን ደግሞ ሊጠብቀኝ መሞከር አይጋጭም? ወደቤት ገብቼ የህመም ማስታገሻ ከዋጥኩ በኋላ ተኛሁ!!

«እራት አይበሉም?» ብላ ተናኜ ስትቀሰቅሰኝ ብዙ እንደተኛው ያወቅኩት። ማታ አራት ሰዓት ሆኗል። እራቴን ከበላሁ በኋላ ለመተኛት ብሞክርም አቃተኝ። ምሽቱን ፈራሁት። አይኔን መጨፈን ፈራሁ። ጨለማውን ፈራሁት። ፀጥታውን ፈራሁት። የተኛሁበትን መኝታ ቤት ፈራሁት:: የሆነ ሰው ተደብቆ እያየኝ ሁሉ መሰለኝ:: ከአልጋዬ እንኳን ተነስቼ መንቀሳቀስ ፈራሁ። 'አምላኬ ሆይ እባክህ ለሊቱን ቶሎ አንጋው' ብዬ የጅል ፀሎት ፀለይኩ:: መብራቱ እንደበራ እኔም ከአንዱ ጎን ወደሌላው እንደተገላበጥኩ ነጋ። ብርሃኑ ከክፉ ይጠብቀኝ ይመስል ብርሃን ወገግ ሲል ፍርሃቴ እየረገበ አይኔ ተከደነ። ስነቃ የመጣው ይምጣ ብዬ በሩን ከፍቼ የሚቀጥለውን ቤት በር አንኳኳሁ። የሆነ የዋህ የሚመስል ፊት ያለው አጠር ያለ ቀይ ሰው በሩን ከፈተ።

«ደህና አረፈድክ?» ከማለቴ የዋህ ፊቱ ደም መሰለ። በሩ ላይ ስላየኝ የደነገጠም የተናደደም መሰለኝ።

«ደሞ ምን ፈልገሽ ነው? እንዴ? አንቺ ትዳር የለሽም እና የሰው ትዳር ሰላም መሆን አይችልም?» ሲለኝ ህመም ተሰማኝ። ቁስሌንም ልቤንም ራሴንም አንድ ላይ ያመመኝ ነገር መሰለኝ። ዝም ብዬ ቆምኩ። አካሌ ቆመ እንጂ ውስጤ የሆነ ነገር ፈርሷል። የሆነ ራቁትነት ስሜት ተሰማኝ። በትክክል የማልገልፀው ስሜት ግን እርቃኔን በብዙ ሰዎች ፊት ቆሜ ሀፍረቴን ለመሸፈን ስቃዬን እየበላሁ ያለሁ ዓይነት ስሜት ......... የተዋረድኩ ግን ውርደቴ ለሌሎች ጌጥ የሆነ የተሸነፍኩ ግን በመሸነፌ የሚደሰት እንጂ የሚያዝንልኝ የሌለ.......... እንክትክት ብዬ የወደቅኩ ግን ሊያነሳኝ እጁን የሚዘረጋ ሳይሁን የወደቅኩበት ሁሉም እያየኝ የሚያልፍ .......

«ድንቄም ሰላም ትዳር! (የጎንጤን ድምጽ ከትከሻዬ ላይ ሰማሁት) ከነገሩ የእግዜር ሰላምታ አይቀድምም?»

ሰውየው በሩን በሃይል አጋጭቶ ዘግቶት በጣም እየጮኸ «ኤደን? አንቺ ኤደን? » እየተጣራ ከበሩ ራቀ። ስድብ የቀላቀለው በጩኸት የታጀበ ንግግር ይሰማኛል።
👍341
«አልነገረኝም እንዳይሉ ተናግሬያለሁ!» ብሎ ጎንጤ ጥሎኝ እንደትናንቱ በሩን ክፍት ትቶት ወደውስጥ ገባ። የእንፉቅቅ እርምጃ እየተራመድኩ ወደጊቢ ገባሁ። ትኩስ እንባ ጉንጬን እያራሰ ያጥበኝ ጀመር። አምላክ ግን እንዴት ባሳዝነው ነው እንዲህ የሚቀጣኝ? ልብ ይበርደዋል? እንዲህ ያለ ነገር አለ ይሆን? ልቤን በረደኝ። ያለፈውን ራሴን ማወቅ የመፈለጌን ያህል በዛው መጠን ላውቀው የምችለውን ትናንቴን ፈራሁት። እግሩ ስር ፈራርሼ በሽንፈቴ ነው ልቡን ያገኘሁት ያልኩት ይሄን ቅፅበት ነው።

«እሺ በድዬህ የነበረውን ማረኝ? ይቅርታ አድርግልኝ? የማውቀውም፣ እርዳኝ የምለውም፣ የምሄድበትም ማንም የሌለኝ ሆኜ፣ ያጋጠመኝ ሁሉ ሲያላግጥብኝ አላሳዝንህም? እንዲህ ውሉ ጠፍቶኝ ስደናበር ምንስ ክፉ የነበርኩ ቢሆን ትንሽ ልብህ አይራራም? እባክህ እንድታግዘኝ እየለመንኩህ ነው።» ብዬ በዛለ ጉልበቴ እግሩ ስር ተነጠፍኩ።

«ኸረ በመድሃንያለም!» ብሎ ደንግጦ ዘሎ አነሳኝ። « የምረዳዎት ነገር ካለ ምን ገዶኝ! ሆ! ሀጢያት ሊያስገቡኝ?» አለ ወደ ሰማይ መልከት አድርጎ እስከዛ ሰዓት ባላየሁበት እርግብ ያለ ድምፅ ..... እየተጎተትኩ በረንዳው ላይ ያለ ወንበር ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ። እንባዬ አልቆም አለኝ።

«ኸረ በድሃንያለም ይሁንብዎት ሀጢያት አያስቆጥሩብኝ? » አለ በተጨነቀ ድምፅ ፊቴ እየተንጎራደደ። መቆሟን እስከዛ ሰዓት ድረስ ያላስዋልኳት ተናኜ ሳጓን ወደ ውስጧ ስትስብ በሩ ላይ ቆማ የሹራቧን አንገትጌ ስባ በጥርሷ ነክሳ አብራኝ እያለቀሰች እንደሆነ አየሁ። ስንተያይ እንባዋን እየጠራረገች ወደ ውስጥ ገባች። ጎረቤቴ አሁንም እየጮኸ ነው። ማልቀሴን ገታ አድርጌ ለመስማት ስጥር

«ደንፍቶ ደንፍቶ ይተዋል።» አለኝ ጎንጤ። 'ማን ላይ ነው የሚደነፋው?' ብዬ መጠየቅ አሰብኩ እና ስለደከመኝ ይሁን ባይመልስልኝስ ብዬ ይሁን አላውቅም ዝም አልኩ። ትንሽ ቆይቶ

«በገባ በወጣ ቁጥር ሚስቱን መርገጥ ነበር ስራው። በነጋ በጠባ እየደቆሳት ምን ጥሎባት እንደሁ ፍቅር አለባት መሰለኝ በየቀኑ ጎረቤት እየገባ ያስታርቃቸዋል መልሳ ስሩ ነች። ከሳምንት በኃላ መልሶ ያሻታል። ይጯጯሃሉ፣ ጎረቤት ይገለግላል። በሳምንቱ መልሰው እዛው ናቸው። እንደለመደው አንድ ማታ ሲያሻት በደም ብትነከር ልጃቸው እሪሪ ብላ ትጮሃለች፣ ጎረቤት የአጥሩን በር ይደበድባል፣ ለካንስ አጅሬው የቤቱን በር ዘግቶ ነው የሚደበድባት። እርሶ 'መሰላል አቀብለኝ!' ብለው በዚህ በኩል አድርገው (ከጎረቤት የሚያዋስነንን አጥር እያመለከተ) ዘለው ገቡ። የቤቱን በር በምን እንደሰበሩት ያየ የለም። ብቻ መስታወቱ ረግፎ ነበር።» ብሎ ዝም አለ። ሽራፊ ፈገግታው በአጋጣሚው የመኩራት ዓይነት መሆኑ ግራ አጋባኝ። ወሬውን ያጠናቀቀ ያህል ዝም ሲል

«ከዛስ?» አልኩኝ አንገቴን አስግጌ

«ህም! ከዚያማ እንዴት አድርገው ቢያሹት እንደሆነ እንጃ ለብዙ ቀናት 'እገሌ ነኝ!' ካላለ በቀር ፊቱ አይለይም ነበር! እንደመሰለኝ ከሆነ ከዱላው በላይ ሽጉጥ አውጥተው እንደሚገድሉት አስፈራርተውት ስለነበር መሰለኝ ወደፖሊስም አልሄደ ወደዚህም መልሶ ዝር አላለም። ያቺ ገልቱ ሚስትየው ናት በበነጋው መጥታ እንዴት ባሌ ላይ ሽጉጥ መዘዙ ብላ የደነፋችው! ከዛ ቀን በኋላ እንዳረጀ ውሻ ያላዝናል እንጂ እጁን አንስቶባት አያውቅም!» ብሎኝ አሁንም ሽራፊ ፈገግታውን ፈገግ ብሎ ዝም አለ።

.............. ይቀጥላል ...............

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
12👍6
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አራት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«እትዬ ትናንት ሲያይዎት ሙታንቲው ላይ ቅዘኑን የሚለቅ ሽንታም ሁላ ዛሬ ዝቅ ብለው ይቅርታ ቢጠይቁት ለምህረት እቅፉን ከሚዘረጋልዎ ይልቅ በቀል የሚፈትል ይበዛል። የተዋረደ የመሰለውን ጊዜያት እርሶን በማዋረድ ሊያካክስ ይጥራል። ግድ የሎትም ይቅርታ መጠየቁ ይቆይዎት።» የሚለኝ 'ለምን ጎረቤቶቼን ይቅርታ አልጠይቃቸውም?' ብዬው ነው።

እቤቱ ገብቼ ከደበደብኩት ጎረቤቴ በተቃራኒ ካሉት ጎረቤቶቼ ጋር የፀብ መነሾዬ ምን እንደነበር ጎንጤም አያውቅም። ድንገት በር ላይ ከተገጣጠምን ግን በእርሱ ቃላት ፀያፍ ስድቦች እንለዋወጣለን።
'እስኪ ንገረኝ እንዴት ያለ ስድብ ነው የሰደብኳቸው?' ስለው። እያንገሸገሸው
'እትዬ ሲናገሩስ አፍዎ አለፍ ይላል! እኔ አልደግመውም' ነው ያለኝ። እሱን ምን አድርጌው እንደጠላኝ ስጠይቀው
' በይቅርታ አለፍነውም አይደል? ከይቅርታ በፊት እንጂ ከይቅርታ በኃላ የበደል ዝርዝር አይቀርብም።' ብሎኝ ነው ያለፈው።

«አንተ ይቅርታ አድርገህልኝ አይደል? ተናኜ ይቅርታ አድርጋልኝ አይደል? ወይስ አላደረግክልኝም? ልትበቀለኝ መች አሰብክ? ወይስ ታስባለህ?»

«ኸረ መድሃንያለም ይቅር ይበሎት! እኔ የመሰለኝን ነው የነገርክዎት። አይ አሻፈረኝ ካሉ ይሞክሩት። ኋላ የሚከተለው ምንም ቢሆን የመቋቋም አቅሙ አለኝ ካሉ ....... » ብሎ ትከሻውን በምንቸገረኝ ሰበከ። የሚያወራው ከልምድ ይመስላል፣ ከሚያውቀው ካለፈበት ልምድ፣

«ይቅርታ በመጠየቄ ከእነርሱ ይልቅ ራሴን ነፃ የማወጣው እኔ አይደለሁ? የሚሰማንን መጥፎ ስሜት ለይቅርታ ባጎነበስኩበት አራግፌ የምነሳው ራሴም አይደለሁ?»

«ከተነሱ ነዋ! ለይቅርታ ባጎነበሱበት የሚረግጥዎ ካጋጠሞትስ? በመድሃንያለም ዘንድ ይቅርታ መጠያየቅ ወደ ፍቅር መሸጋገሪያ ድልድይ ነው። ያ ግን የይቅርታ ትርጉም ለሚገባው ሰው ነው። የኛ ሰው ይቅርታ ጠያቂ የተዋረደ፣ ይቅርታ ተጠያቂ ክብር የተጎናፀፈ አድርጎ ነው ይቅርታን የሚፈታው። የኛ ሰው ለብቻው በጓዳ እግሩ ስር ወድቀው ይቅርታ ቢጠይቁት እንደማይረካ አያውቁም? ሰው በተሰበሰበበት ስህተትዎትን ማመንዎ አይደለም ይቅርታዎን ትልቅ የሚያደርግለት። በሰዎች ፊት ለእግሩ ስር መዋልዎ እንጂ ምክንያቱም በሰዎች ፊት የእሱን ልክነት እና ፅድቅ አወጁለታ። በሰዎች ፊት የእርሶን ከእርሱ እግር ስር ዝቅ ማለት አሳዩለታ። እንደዛም ሆኖ የሚረካ እንዳይመስልዎ! ከዛ ለሚቀጥለው ዘመን ሁሉ ፈቅ እንዲሉ አይፈልግም!»

አምርሮ ስለተናገረ ይሆን ስለይቅርታ ሌላ ሀሳብ መሰንዘር አልፈለግሁም። ግንስ ምን እንዳደረግኩ ሙሉውን ጥፋቴን የማላስታውሰውን በደል ይቅርታ አድርጉልኝ ማለት ልክ ነው? ከይቅርታው በፊት ሀጥያቱ ይቀድማል። እኔ ደግሞ እሱን አላስታውሰውም። ብቻ ምንም ይሆንና ብቻዬን አልሁን! ብቻ እግራቸው ስር መውደቄ ያደረግኳቸውን ነገር አስረስቶ ባይወዱኝ እንኳን ጥላቻቸውን እንዲተው ካደረገልኝ ምን አለበት? ልቤን ከሚበርደው የማወራው ሰው አጊንቼ ክብሬ ቢቀል አይሻለኝም? ክብር ያለሰው ምንድነው? ኸረ ከሰው ጋር የማይጋሩት ህይወት ምንስ በድሎት የተንቆጠቆጠ ቢሆን ትርጉም አለው?

ከዚህ በኋላ በሚቀጥሉት ቀናት ራሴን ፍለጋ ቤቴን መበርበሬም ሆነ ተናኜን እና ጎንጤን በጥያቄ ማስጨነቄ ትናንቴን ይበልጡን እንድፈራው እና እንድጠላው አደረገኝ። እያንዳንዱን ፍንጭ ሰካክቼ መረጃ ለማግኘት በቅደም ተከተል ሄድኩ። መክፈቻ ኮዱን የማላስታውሰው ዝግ ካዝና፣ 1.2 ሚሊየን ብር ተቀማጭ ያለበት የባንክ ደብተር፣ አብዛኛዎቹ ቀዳዳ የሚበዛባቸው ሰፋፊ ጅንስ ሱሪዎች ፣ ሰንሰለት እና ብልጭልጭ የሚበዛባቸው ጃኬቶች እና ኮቶች፣ የወንድ የሚመስሉ ጫማዎች፣ አልጋዬ ራስጌ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ሌሎች ፎቶዎች ፣ ሽጉጥ፣ ስልክ ፣ በንቅሳት የተዥጎረጎረ ጀርባ እና ቂጥ ያለው ሰውነቴ ፣ በአጭሩ የተቆረጠ ጥቁር ፀጉሬ ....

1. ኮዱን ያላስታወስኩት ካዝና

የተከረቸመ ነገር መቼም ሚስጥር ነው። ይሄ ዝግ ብረት የእንቆቅልሼ ሁሉ መፍቻ መሰሎኝ ነበር። ጎንጤን ካዝናውን የሚሰብርልኝ ባለሙያ እንዲያመጣልኝ አድርጌ ተሰበረ። ውስጡ ያገኘኋቸው ነገሮች የበለጠ የሚያወዛግቡኝ እንጂ ትክክለኛ መልስ የሚሆኑ አልነበሩም። ጥሬ ገንዘብ፣ የጋብቻ ቀለበቶች ፣ የቤት ካርታ እና ውል፣ የወታደር ልብስ ቀለም ያለው የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ናቸው። በመጀመሪያ እጄ ፈጥኖ ያነሳው ላይተሩን ነው።

«አጨስ ነበር እንዴ?» አልኩት ጎንጤን
«እኔ ሲያጨሱ አይቼ አላውቅም! እትዬ አስታወሱ እንዴ?» አለኝ በጣም ተጠግቶ አይኖቹን አቦዝዞ እያየኝ።

«ምኑን?» ካልኩት በኋላ ካላስታወስኩ ሲጋራ መለኮሻ መሆኑን በምን አወቅኩ? ብዬ ግራ ተጋባሁ። አገላብጬ እያየሁት አስባለሁ። የቁሶቹ ምስል ጭንቅላቴ ውስጥ አይከሰትልኝም። ልክ በዓይኔ ሳያቸው ግን ምን እንደሆኑ አውቃለሁ። ለምሳሌ ሆስፒታል ከነቃሁ በኋላ እንጀራ ለመጀመሪያ ጌዜ ሲያቀርቡልኝ ሳልጠይቅ ጠቅልዬ እንደጎረስኩት። ሾርባ ከማንኪያው ጋር ሲያቀርቡልኝ በማንኪያው ተጨልፎ እንደሚበላ ማንም እንዳላስተማረኝ፣! ይሄ እብደት ነው ወይስ ትርጉም ይሰጣል? ስለሆነ ነገር ያለን እውቀት የትውስታ አንዱ አካል አይደለም? በአይኔ ቀለበቶቹ ላይ አፍጥጫለሁ እጄ ግን የሲጋራ መለኮሻውን ማስቀመጥ አቃተው። ግማሽ ትውስታ ብሎ ነገር አለ ይሁን? ላይተሩን የሆነ ሰው እጅ ላይ የማውቀው ይመስለኛል። በደም ተጨማልቆ በከፊል የተዘረጋ እጅ መዳፍ ላይ! አይኔን ከድኜ እከፍታለሁ............. እጅ ብቻ! ላይተሩን አስቀምጬ ቀለበቶቹን አነሳኋቸው። አነስ ያለውን ጣቴ ውስጥ አስገባሁት።

«አግብቼ ነበር?» ያልኩት መልስ ባልጠበቀ አጠያየቅ ነው። ሁለቱም ዝም ሲሉ ግን የሚያውቁት ነገር እንዳለ ተሰማኝ። «አግብቼ ነበር?» ብዬ አስረግጬ ጠየቅኩ። ተናኜ ተንተባተበች።

«እኔ እዚህ ቤት በነበርኩበት ጊዜ ብቻዎትን ነበሩ!» አለ ጎንጤ ፍርጥም ብሎ እና ተናኜን በቁጣ ዓይን እያጉረጠረጠባት።
«ከዛ በፊትስ?»
«እኔ የማውቀው የለኝም!» አለ አሁንም ፍርጥም ብሎ። የሚያውቀው እንዳለ ግን ያሳብቅበታል።

የራሴ ካልሆነ የሰው ቀለበት ካዝና ውስጥ ላስቀምጥ የምችልበት ምን ምክንያት ይኖራል? ከቤቱ ካርታ ጋር ያሉትን ወረቀቶች በሙሉ ለመረዳት ሞከርኩ። ብዙው ግራ አጋባኝ። ካርታውም ውሉም ሁለት የተለያየ ነው። ያ ማለት ከዚህ ቤት በተጨማሪ ሌላ ቤት በስሜ አለ። የንግድ ቤት የሚል። ውሉ ላይ ብዙ ያልገባኝ ጥልቅ ነገር አለ። በግርድፉ ከገባኝ ግን አቶ ሙሉ ሰው መሆን አንድአርጌ ከሚባል ሰው ነው ንብረቱ በእኔ ስም በውርስ የዞረው። ውሉ የተፈረመበት ቀን 08-11-2004 ፣ የሰውየው እድሜ 40 ይላል።

«አቶ ሙሉሰው መሆን የሚባል ስም ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?» አልኳቸው

«በፍፁም!» አለች ተናኜ። የጎንጤ ዝምታ ግን ሰምቶ እንደሚያውቅ ነገረኝ።
«ምኔ ነበር?» አልኩት

«እትዬ እኔ በወሬ ብቻ የሰማሁትን ነገር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብዬ እንድነግርዎት አያስገድዱኝ። ምናልባትም ሀቁ ከዛ የራቀ ሊሆን ይችላል። እንኳን ዓመታት ያለፈው ወሬ ቀርቶ የትናንት ወሬ እንኳን ከአንዱ አፍ ወደሌላው ስታልፍ ተቀባብታ ወፍራ ነው። » አለ በልምምጥ። ምንም ይሁን ምን ወሬው ለመንገር እንደጎረቤቶቼ ፀብ ቀላል ያለመሆኑ ገባኝ።

«ምንም ይሁን የሰማኸውን ንገረኝ እና ማጣራቱን ራሴው ላጣራ! ምንድነው ወሬው»
👍383
«እትዬ አምላክ እንደአዲስ በንፁህ ልብ የመኖር እድል ሲሰጥዎ እርሱ አዋቂ አይደል? እንደው ያለፈውን ከመበርበር እንደአዲስ......... »

«ንገረኝ ምንድነው? ንገረኝ አልኩህኮ!» ብዬ ጮህኩ

«ባለቤትዎ እንደነበሩ ሲወራ ሰምቻለሁ።» ብሎ ዝም አለ
«ይሄን ሁሉ የታሸኸው ይሄን ልትነግረኝ አይደለም! ከዛስ? ምን ሆነ?»

«ሞተው ነው (እንደበረዶ የቀዘቀዙ ቃላት ) እንደሚባለው ከሆነ እርሶ በሞታቸው እጅዎ አለበት ተብሎ ታስረው ነበር።»

«ለንብረት ብለው የገደሏቸው ነው የሚባለውማ ከወሬው» አለች ተናኜ ለማውራት ሰበብ ትፈልግ ይመስል። ጎንጤ ሲያፈጥባት «እህእ ንገሩኝ ብለው አይደል?» ብላ አፈጠጠች። ያቺን ሜላት እኔ ራሴ ጠላኋት። እኔ ራሴ ባገኛት አልገላትም ነበር?

«እትዬ እውነታውን የሚያውቀውኮ አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው።» አለኝ ሊያፅናናኝ ይሁን ከልቡ አልገባኝም። ፖሊሶቹ እየደጋገሙ ሊገድለኝ የሚችል የምጠረጥረው ጠላት እንዳለኝ የማስታውስ ከሆነ ብለው ሲያደርቁኝ ይሄን ክፍል ለእኔ መንገር አልታያቸውም? የአደጋው መንስኤ ከዚህኛው ጋር የተያያዘ ነገር ይኖረው እንደው ማሰብ ተስኗቸው ነው? ወይስ አያውቁም? ወይስ እውነትም ወሬ ነው? ምኑ ነው ልክ ? ምኑ ነው ቅዠት?

እንደእብድ መዥረጥ ብዬ ተነስቼ ፖሊሶቹ የማስታውሰው ፍንጭ ካገኘሁ እንድመጣ የነገሩኝ ቢሮ ጎንጤን አስከትዬ ሄድኩ። ገና ኮሪደሩን አልፌ እየሄድኩ እኔ የማላውቀው እሱ ግን በትክክል እንደሚያውቀኝ የሚያስታውቅ ፖሊስ

«እሺ አጅሪት?» አለኝ። አጅሪት አባባሉ ስልችት ያለበት፣ ትዝብት ያለበት ፣ ፍርድ ያለበት አይነት ነው።

................ ይቀጥላል .............

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍25😱3
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሲሚንቶና ብረት የጫነው ኤንትሬ ከሌሊቱ አስር ሰዓት
ከእርባምንጭ ተነሳ፡፡ ያጓራል ያቃስታል ይንቶሰቶሳል. ጉራው
እንጂ ጎዞው የኤሊ ነው፡፡ ማዝገም… ከአርባምንጭ ቀይ አፈር ሁለት መቶ ስምንት ኪሎ ሜትር ለመጓዝ አስራ ሁለት ሰዓት ፈጀበት፡፡ሲሚንቶና ብረቱ ላይ ያሉት ተሳፋሪዎች የተሳፈሩት ተለምነው
ሳይሆን ለምነው ነው፡ ወደ ጂንካ የሚሄድ አስተማማኝ
ትራንስፖርት የለም፡፡ ወደዚያ መሄድ የፈለገ አማራጭ እንደሌለው አውቆ በአጋጣሚው መጠቀም አለበት፡፡ ካለበለዚያ ሲቀላና ሴቻ እያለ ሲንገላወድ ይከርማታል፡፡

የሚያንሰፈስፈው ውርጭ እያኮማተረው የማያተኩሰው የፀሐይ ሙቀት እያቃጠለው አይኑ ጆሮው አፍንጫው፦ አፉ አቧራ እየቃመ ከመሬት ርቆ ጭነት ላይ የወጣው ተሳፋሪ ለሁሉም
ሳይሳቀቅ ጭንቅላቱን በጨርቅ ቢጤ ጠቅልሎ በሁለቱ እጁ ካቦውን
ጥርቅም አድርጎ ይዞ እየተናጠ መጓዝ ነው፡፡ ታዲያ አቀበት ቁልቁለቱ  ጫካና ሜዳው አይጠገብም፡፡ እንደ ጥሩ ትርዒት እየተቀያየረ ያዝናናል፧ “ሣይደግስ አይጣላ" እንዲሉ!

ካርለት አልፈርድ አርባ ምንጭ መቆየት አልፈለገችም፡፡በእርግጥ በቦታ አመራረጡ ምሥራቅ አፍሪካ ወደር አይገኝለትም
ተብሎ በውጭ ዜጎች የተመሰከረለት የበቀለ ሞላ ሆቴል ሁለት ቀለማቸው የተለያዩ ሐይቆች (ጫሞና  አባያ) በርካታ የሆኑ ምንጮች በኢትዮጵያ ከሚገኙት ታላላቅ ተራሮች አንዱ ጉጂ ተራራና ከስሩ የኢኳቶሪያል የዝናብ ደን ያለው ተፈጥርው የማይሰለቻት ቢሆንም ችግሩ ሐመሮች ናፍቀዋታል።
የሐመሩን የፍዬል ቆዳዋን የሐመር ጎረምሶች የሽለሟትን የእጅ አንባር በአስሩም እጣቷ የምትጠቀምበትን ቀለበት የአንገቷን ጨሌ ስታይ የሐመር ትዝታዋ አገረሸ፡፡ መከባበሩ መተዛዘኑ አብሮ
መብላት መጠጣቱ ጫካውና መንደሩ ተራራውና ሜዳው
በተለይም የኢቫንጋዲ ጭፈራው ውልብሎ ታያት፡ ወደ ሐመር የምትሄድ ሳይሆን ከሐመር እንደምትመለስ ሁሉ! ልቧ እንደ ፅናፅል በፍርሃት ተንሿሿ፡ ፊቷ ገረጣ የሐመር ተፈጥሮአዊ ህይወት
ራባት፡፡

አጠገቧ ከኤንትሬው ጀርባ መኪናው ቆጥ ላይ ብዙ ሰው ሰፍሯል፡፡ ወታደር ተማሪ ነጋዴ ቄስ ሳይቀር አለ፡፡ ቀልዱ ጨዋታው ያስቀናል፡፡ ሰዎች ሁሌም ችግር ሲበዛባቸው ደጎች
ተዛዛኞች... መሆናቸው ያለ ነው፡ ካርለት ሁሉንም ስታጤን ቄሱ ሌላው ሲጫወት ዝም ብለው ሲያዳምጡ ይቆዩና ፈርጠም ብለው
ማሳረጊያ ሲሰጡ አስተውላቸዋለች፡፡ በእርግጥም የሚጫወቱት
አይገባትም ፤ ሆኖም ግን ይንከባከቧታል፡፡  አይናቸውን ወርወር
ያደርጉና ፈገግ ይሉላታል፡፡ እየደጋገሙ ያዩዋታል፡፡ ብታናግራቸው በወደደች ግን የቋንቋ ችግር አለ በመካከላቸው፡፡ እሳቸው ስለ እሷ እያሰቡ እንደሆን ገምታለች፡፡ ጠይቃ ሃሣባቸውን ማወቅ ባለመቻሏ ግን በተራዋ እሷም ስለ እሳቸው ማሰብ ጀመረች

ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሉባት ሃገር ነች፡ ክርስቲያኑ ሙስሊሙ… ህዝቡ የአንዱ ወይም የሌላው ተከታይ ነው በአመዛኙ፡ የአገሪቱ ታሪክና የባህል መዘክርም የሚገኙ ናቸው፡፡ ካርለት አንዴ ሰሜን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አክሱም ላሊበላ ባህርዳር ጎንደር ሄዳ ብዙ ቤተክርስቲያኖችንና መስጊዶችን ጎብኝታለች፡ በምስራቅም እንዲሁ ማየት የሚገባትን አይታለች፡፡
ግን ደብረብርሃን ስላሴ
ጎንደርን በጎበኘችበት ጊዜ
የሚባለውን ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ካየች በኋላ ከሁለት ወንድ መነኮሳት ጋር ያደረገችው የሣሣብ ልውውጥ አይረሳትም፡፡
ደርቡሾችና ግራኝ  ሞሐመድ ብዙውን የጎንደር ቤተ
መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ሲያፈርሱና ሲያቃጥሉ ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ግን ከመፍረስና ከመቃጠል ተርፏል፡ ሁሉም
አልደረሱበትም፡፡ እና ቤተክርስቲያኑ በወቅቱ
የነበረውን የአገሪቱን
የህንፃ ሥራ ጥበብ ምጥቀት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

አፀደ ግቢው በውስጡ ያሉት ሥነ ስዕላቱ በመፅሐፍ ቅዱስ
ላይ ስሟ ሰባ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰላትን ኢትዮጵያን ሃይማኖታዊ
ጥንካሬና ድንቅ የቤተ ክህነት ሥርዓት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ልጅ እግሩ መነኩሴ ለካርለትና ስአስጎብኚዋ የቤተ ክርስቲያኗን ታሪካዊነት ሲያስረዱዋቸው ከቆዩ በኋላ ከደብሩ
ከመውጣታቸው በፊት አንድ ጠና ያሉ መነኩሴ መግቢያው እድሞ
ካለው ሁለት ክፍል አንደኛው በር ላይ ዳዊታቸውን ሲደግሙ አየችና ከመነኩሴው ጋር ለመነጋገር ፎቁ ላይ ወጣች፡፡

መነኩሴው የተቀመጡት ! እሳቸውና ልጅ እግሩ
ከሚኖሩበት ክፍል
በሩ ላይ ነው፡: ከጎን ያለችው ክፍል ቢሮ ናት፡፡
ካርለትና አስጎብኝዋን ሲያዩ መነኩሴው ከተቀመጡበት
ተነሱና በትህትና ተቀበሏቸው፡፡ ወደ ውስጥ ግቡ እንዳይሉ ካርለት
ሴት ናት፡፡ ሴት ደግሞ ወደ መነኩሴ መኖሪያ ቤት አትገባም! ስለዚህ በረንዳ ላይ ቁጭ አሉ፡፡

አባ ከሰል ላይ በበራድ ውሃ ሞልተው ጣዱና ተመልሰው
ለወግ መጀመሪያ እህሣ እንደምን ናችሁ" አሉ፡ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ትግርኛ መሆኑ ከአነጋገራቸው ይታወቃል፡
“እንዴት መነኩሴ ሆኑ?" ብላ ጠየቀቻቸው ካርለት
በአስተርጋሚዋ፡፡

“በአያልቅበቱ ፈቃድ ነዋ ካለ እሱ ፈቃድ ምን የሚሆን አለ" አምላካቸውን ሽቅብ አዩ፡፡ እግዚአብሔር ከመንበሩ ላይ ተቀምጦ
ታያቸው በአይነ ህሊናቸው: ቶሎ ሰገድ ብለው አይናቸውን መለሱ፡፡

እዚህ ምን አገልግሎት ይሰጣሉ?"

እህ የእግዚአብሔርን ቤት! ቤተ ክርስቲያኒቱን አገለግላለሁ ተደብር ደብር እየሄድሁ እግዚአብሔርን ማገልገል ነው ሥራዬ፡ ሌላ
ዓለማዊውን ህይወትማ ትቸው መጥቻለሁ,," ቀና ብለው ሁለት እጆቻቸውን ዘርግተው አጮልቀው
አዩ ወደ መንበሩ

“ቤተሰብ ልጅ አልነበረዎትም? ካርለት ሌላ ጥያቂ ጠየቀቻቸው፡

“ነበረኝ እንጂ! ግና ከአንድዬ ምን የሚበልጥ አለ!-" አዩ ሽቅብ፡፡ካርለት ከመነኩሴው ጋር ብዙ ሃሣብ ተለዋወጠችና ደስ
አላት፡

መነኩሴው ሻዩን በብርጭቆ ቀዱና በቀለምሻሽ ዳቦ ቆራርሰው ሰጧቸው ለነካርለት፡፡

“አባ… ሻዩ ፈልቷል አይመጡም ወይ" ጠና ያሉት መነኩሴ ልጅ እግሩን መነኩሴ ጠሩአቸው፡፡

“…ከቤተ-ክህነት ሙያ ሌላ ምን ሙያ አላችሁ?"

“ኧረገይ ከዚህ ሌላ ደግሞ ምን ሞያ ይኖረናል! ኧረ
የለንም፡፡"

“የሃይማኖት ተከታዩ ወደ ቤተ-ክርስቲያኗ ሲመጣ ምንድን ነው የምታስተምሩት?”

“መንፈሳዊ ትምህርት  መንፈሳዊ ትምህርት ይማራል! ቅዱሳት መጽሐፍት ይነበበለታል…"

“ቤተ ክርስቲያኗን ስታገለግሉ ለእናንተ የሚያስፈልገው
መሠረታዊ ነገር ይሟላላችኋል?

“ኧረገይ! ኧረ ችግር ነው ችግሩማ እንዲህ በአጭር ጊዜ ተነስቶ አያልቅም ልጅ እግሩ መነኩሴ ተከዝ አሉ፡

"እርስዎ ሃይማኖትዎ ምንድነው? ጠና ያሉት መነኩሴ አንዴ አስተርጓሚዋን ሌላ ጊዜ እሷን እየተመለከቱ ጠየቋት፡፡

“የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ነኝ፡” ሁለቱም መነኮሳት ቀና ብለው አዩዋትናı “አሃ አሉ ባንድነት እንደ መደንገጥ ብለው፡፡

“በእኛ ሃገር መነኮሳት ከመንፈሳዊ እውቀታቸው ሌላ የሞራል ትምህርትና የሙያ ስልጠና ይሰጣቸዋል፡ ስለዚህ መነኮሳት ምዕመናኑ ወደ ቤተ ክርስትያን ሲመጡ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን
ሞራላዊ ትምህርትም ያስተምራሉ፡

“የመነኮሳት እርዳታ በመንፈሳዊና ሞራላዊ ትምህርትም ብቻ
ሳይሆን በስልጠና ባገኙት
ሙያ በህክምና. በጓሮ አትክልት በእንጨትና ብረታብረት ሥራ….. ወዘተ ህዝቡን ያገለግሉታል፡፡
ስለዚህ መነኮሳት የራሳቸው ገቢ ያላቸው፤ ህዝቡን የሚረዱ ምፅዋት
የማይጠይቁ ነገር ግን ለህብረተሰቡ መንፈሳዊና ሞራላዊ ትምህርት
እየሰጡ በሙያ ሰልጥነው ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን አገርን ወገንን… መርዳት መቻሉን አርአያን ሆነው የሚያስተምሩ አባቶች ናቸው
👍24🥰2👎1
“መንፈሳዊ እውቀት ያለው ሞራሉ በተስፋ የተገነባ ህዝብ ደግሞ ሠርቶ የመኖርን ባህል ስለሚጎናፀፍ ህይወቱ መስተጋብራዊ ውህደት ያለው በመሻሻልና በተስፋ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ
ሃይማኖቱን ቤተሰቡን ወገኑን የሚወድና አገሩን በኢኮኖሚ የሚገነባ ቀናኢነት ያለው ዜጋ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ጠንካራ መንፈሳዊ እምነት አለ፡፡ ሞራላዊ ትምርት ግን አላይም፡፡
የሃይማኖት መሪዎችም ከመንፈሳዊ ትምህርታቸው ውጭ ስርተው የሚያስተምሩ ሳይሆን ተቀምጠው ከህዝቡ ምፅዋት የሚጠብቁ
ይመስላሉ! ይህ ደግሞ ህዝቡንም እነሱንም በሃይማኖታቸው ላይ
ያላቸውን ፍቅር ቀስ በቀስ ይሽረሽረዋል፡"

“ይህ እውነት ነው፡፡ ችግሩ አለ…" አሉ በእድሜ ጠና ያሉት መነኩሴ፡፡
አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት ዘዴኮ ጥንት የናንተ የነበረ ነው፡፡ ለምንድን ነው ቤተ ክርስቲያናትና መስጊዶች በአገራችሁ የታሪክ ቅርስ ተብለው ጎብኚ የሚጎርፍላቸው በእኔ እምነት ይኸን ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ ሌሉቹ የታሪክ ቅርሶች የተነደፉት
የተቀነባቡሩት በሐይማኖት መሪዎች ይመስለኛል፡፡  የሃይማኖት መሪዎች በአርአያነት ስለሚታዩና
ህዝቡንም በሞራላዊ
ትምህርታቸው ስላስተባበሩት እኒህ ድንቅ ቅርሶች ለዚህ ትውልድ
የሚያኮሩ ሁነዋል…"

ኧረገይ አባቴ ይህች ሰውኮ የምትለው እውነት ነው!”
አሉ ልጅ እግሩ መነኩሴ የጥንቱ የቤተክርስቲያን አባቶች እየታዩዋቸው፡

የእኛ ችግር የነበረውን እየናቅን ብርሃኑን ትተን ወደ
ጨለማ መጓዛችን ነው" አሉ ጠና ያሉት መነኩሴ ሐዘን ልባቸውን ሰብሮት ካርለት ብዙ ብታጫውታቸው በወደደች  መቀደም ግን
አትሻም  በጊዜ፡፡ እና ጊዜዋን ለመጠቀም ተሰናብታቸው ሄደች፡፡

ካርለት በጭነት መኪናው እየተጓዘች ከመናኩሳቱ ጋር
ጎንደር ላይ ያደረገችውን የሃሣብ ልውውጥ አስታወሰች፡፡ እኒህ አብረዋት ከሚጓዙት ቄስ ጋር ግን መወያየት አልቻለችም፡፡ ድልድዩ
የለም  የቋንቋው፡፡

ኤንትሬው የቀይ አፈርን ዳገት አቃስቶ አቃስቶ ጨረሰው ካርለትም ከሰፈረችበት የኤንትሬው ቆጥ ላይ ወረደች፡፡...

💫ይቀጥላል💫
👍167👎1
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሦስት ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ ሲሚንቶና ብረት የጫነው ኤንትሬ ከሌሊቱ አስር ሰዓት ከእርባምንጭ ተነሳ፡፡ ያጓራል ያቃስታል ይንቶሰቶሳል. ጉራው እንጂ ጎዞው የኤሊ ነው፡፡ ማዝገም… ከአርባምንጭ ቀይ አፈር ሁለት መቶ ስምንት ኪሎ ሜትር ለመጓዝ አስራ ሁለት ሰዓት ፈጀበት፡፡ሲሚንቶና ብረቱ ላይ ያሉት ተሳፋሪዎች የተሳፈሩት ተለምነው ሳይሆን ለምነው ነው፡ ወደ ጂንካ የሚሄድ…»
#የመኖር አጋማሽ ..የመሞት ሲሶ ... መሃል መንገድ ላይ ..... (ክፍል አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

ማነኝ?
ለመርማሪ ፖሊሱ 'ነፍሰ ገዳይ' ነኝ:: እገሌ ዶክተር ነው: ኢንጅነር ነው... ምናምን እንደሚባለው... 'እ ... ሜላት? እሷኮ ነፍሰ ገዳይ ናት!' የሚል ማዕረግ ያለኝ ነኝ:: .. ድርጊት ወይም ድርጊቶች ናቸው ማንነቶቻችን?? እንደዛስ እንኳን ቢሆን እኔ የትኛዋን ነኝ?? እንደተናኜ አባባል 'አር ከማር የምትለየዋን' የአሁኗን ሜላት ወይስ ነፍሰገዳይዋን ሜላት?

"እትዬ በሰዓቱ የሆነውን ያደረጉበትን ምክኝያት: የነበሩበትን ሁናቴ እና ሌሎች አጃቢ ግብሮች ማወቅ ባልቻሉበት ሁኔታ ድርጊቱ ብቻውን የተሟላ መረጃ አይደምኮ!!" ዝም ስለው አሁንም ይቀጥላል!

ከፖሊስ ጣቢያው ከተመለስኩ ጀምሮ ለሰዓታት የማውቃቸውን ቃላት እዛ መርማሪ ፖሊስ ጠረዼዛ ላይ አስቀምጬው እንደመጣሁ ሁላ ዲዳ ሆንኩ:: ሳሎን ሶፋው ላይ እንደተጋደምኩ ተናኜ የሚለበስ አምጥታ ደረበችልኝ:: ጎንጤ ለእኔ ይሁን ለራሱ እንጃ ብቻ ነፍሰ ገዳይነቴን ማለዘቢያ ሰበብ ያስረዳኛል::

የሚለው ነገር እኮ እውነት ነው ለምሳሌ 'ሜላት ባሏን ገደለች' ከሚለው በምንም አጃቢ ምክንያት ካልታሸ ዓረፍተ ነገር:: 'ሜላት ባሏ ሊገድላት ሲል ሽጉጡን ቀምታ ገደለችው' ቢባል ራሱ ነፍሰ ገዳይነት ግን ራሷን ለመከላከል የገደለች ትንሽ የሚታዘንላት ነፍሰ ገዳይ ያደርገኛል:: ወይም 'ሜላት እህቷን ሊገድል ሽጉጥ ደግኖ የነበረውን ባሏን እህቷን ለማትረፍ ባደረገችው ትግል የባሏ ህይወት ሊያልፍ ችሏል' ያው ነፍሰ ገዳይነት ትንሽም ጀግንነት ሁሉ ይኖረዋል:: .... የእኔው አጃቢ ሁኔታኮ 'ሜላት ባሏን ገደለች' የሚለው ልዝብ ገላጩ ነው:: ... 'አጅሪት' ያለኝ መርማሪ ፖሊስ የማስታወስ ችሎታዬን ማጣቴን ከግምት አስገብቶ በማባበል ቃል መርጦ እንደነገረኝ.... እስከዛሬ በስራው እንደእኔ ዓይነት ኬዝ ገጥሞት አያውቅም!! እንደእርሱ ገለፃ ..

የሆነ ቀን ቢሮው ተቀምጦ የተለመደ ስርቆት: ድብድብ... ወንጀሎችን ሲመረምር በሩን ከፍቼ ገባሁ:: ሁለት የሰው ቆለጥ ጠረዼዛው ላይ ዱብ ሲል ነው የገባው ሰው ባልደረባው አለመሆኑን ያወቀው... በደም የተለወሰ እጄን ልብሴ ላይ እየጠራገግሁ

" ፍሬውን ማስረጃ እንዲሆንህ ነው ያመጣሁልህ! ዋናውን ከፈለግከው አጉርሼዋለሁ:: " አልኩት:: ሬሳው ያልኳቸው ቦታ እንዳልኩትም ዋናውን ጎርሶ አገኙት:: የወንድነት ንብረቱ ከፊሉ መርማሪው ጠረዼዛ ላይ ... ከፊሉ አፉ ውስጥ ከመዝረክረኩ ውጪ በጥይት ነው የተገደለው.... ምክንያቴን እንዳስረዳ ስጠየቅ 'እንዴት እንደምገድለው ለረዥም ጊዜ ሳስብ ቆይቼ ተሳካልኝ::... ለዝህችው አቅሙ ይሄ የማይረባ.. ስንት እንዳስለፋኝ::" ብቻ ነው ያልኩት... በድርጊቴ ከልኩ በላይ መርካቴ ሲደመር ሟች ለመሬት ለሰማይ የከበደ በህዝብ ዘንድ የተወደደ ባለስልጣን መሆኑ ፍርዱን የእድሜ ልክ እስራት አስፈረደብኝ::

እኔ ይሄ ነፍሰ ገዳይነት በምን ምክንያት ቢቀመም: በምን ነባራዊ ሁኔታ ቢሰነግ ነው የሚለዝበው??

ገዳይነት ብቻ አይደለም እንደሁኔታው ሊገዝፍ እና ሊቀል የሚችለው?? የሟች ነፍስም ሊገዝፍ እና ሊቀል ይችላል... እንትን አውራጃ በነበረ የእርስ በእርስ ግጭት 200 ሰው ሞተ ከሚል ዜና እና እገሌ የሚባለው እውቁ ፖለቲከኛ ተገደለ! ከሚል ዜና ሲነፃፀር ከ200 ነፍስ የአንዱ ታዋቂ ነፍስ ይገዝፋል:: ... ያው ሞት ሚዛን ይሰፈርለታል:: ....

"እኔ ምን አውቃለሁ የሳብሽውን ገመድ!! " ብሎኝ ነበር መርማሪው የእድሜ ልክ ከተፈረደብኝ እንዴት ልወጣ እንደቻልኩ ስጠይቀው::

ሰውዬው ስለነገረኝ ይሆን አስታውሼ አላውቅም:: አይኔን ለመጨፈን ስሞክር የሚታየኝ ጠረዼዛ ላይ የሚንከባለል ቆለጥ ነው::.... የምግብ ጣዕም ሁሉ ደም ደም አለኝ:: .... ከዚህ በኃላ ስላለፈው ለማወቅ መቆፈሬን ማቆም ይኑርብኝ መቀጠል ግራ ገባኝ::... ፍርሃት ብቻ ነው የሚንጠኝ:: ጎንጤ አርጅቶ ሽፋኑ የተልፈሰፈሰ መፅሃፍ ቅዱስ አምጥቶ ከተኛሁበት ራስጌ እያስቀመጠ

"ባታነቢው እንኳን ከራስጌሽ ይኑር :: ከበረታሽ ግን አንብቢው ያበረታሻል:: " ብሎኝ ብሎኝ ሲወጣ መፅሃፍ ቅዱሱን አንስቼ አገላበጥኩት:: በእርግጠኝነት የማልገልፀው የእሩቅነት ... የባይተዋርነት ስሜት ተሰማኝ:: ከመንፈሳዊነት የራቀ ህይወት እንደነበረኝ ለመረዳት ምንም ቀመር የሚያስፈልገው ሆኖ አይደለም:: እንደው ግን ቢያንስ በልጅነቴ... አንዱ የህይወቴ ቀን ላይ እንኳን ከእግዚአብሄር ደጅ ተገኝቼ አውቅ ይሆን??

"ተናኜ? ተናኜ? (በሩ ላይ ተለጥፋ እስክጠራት እየጠበቀች ይሁን ዘላ ገባች) ቤተክርስቲያን የሚለበስ ልብስ አውጪልኝ እስኪ... ይዘሽኝ ትሄጃለሽ" አልኳት... ሄዳ የሆነ የራሷን ሰፊ ጉርድ ይዛ ተመለሰች

"ይሄ ከበቃዎት ይሞክሩት እንጂ እትይ እርሶ ቀሚስ የሚመስል ነገርኮ የሎትም" አለች... ጎንጤ ብድግ ብሎ ሲከተን

"አንተ እዚሁ ሁን ችግር የለውም!" ብዬው ነበር:: አልሰማኝም!

"የማይሆነውን! በመንገድ ምን ሊገጥሞት እንደሚች ምን አውቃለሁ? አንዱ የጠገበ ቢጋጭዎትስ? ደሞ ቤተክስኪኑ ትንሽ ያስኬዳል እንደዚያ እርቀት ለመሄድ የሚያስችል አልጠነከሩም! ታክሲ ይጠራልዎ!" ብሎ ለሶስት በታክሲ ሄድን... ቤተክርስትያን ጊቢ ውስጥ አንዱን ዛፍ ደገፍ ብዬ ተቀመጥኩ... ተናኜ ትታኝ ልትፀልይ መሰለኝ ሄደች:: ጎንጤ ትንሽ ራቅ ብሎ እጁን ደረቱ ላይ መስቀልኛ አጣምሮ ያነበንባል:: .... የመጣሁት ላዋራው ነበር:: ልፀልይ: ልለምን.... ዝም ብቻ ነበር ግን ያልኩት... ምን ብዬ ነው የምለምነው?? ብዙ ደቂቃ ፀጥ ብዬ ተቀመጥኩ...

"ልጅ ሜላት" የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞርኩ!! ነጭ ነጠላ ራሳቸው ላይ የጠመጠሙ : በእድሜ ተለቅ ያሉ ሰው ናቸው::

"አንቺ ነሽ? " ብለው የተገረመ እና የመደሰት ቅልቅል ፈገግ እያሉ በትኩረት እያዩኝ.... " ያሰብሽው ሞላልሽ?" አሉ እየተጠጉኝ በጋቢያቸው ስር ደብቀው የያዙትን መስቀል አውጥተው እየተጠጉኝ..... ዝም ብዬ አያቸዋለሁ:: ከመፅሃፍ ቅዱሱ ይልቅ እኚህን ሰው ልቤ ያውቃቸዋል:: ብርድ ያንዘፈዘፈው ልቤ ባልገባኝ ምክንያት ሞቀው...

"ምነው ልጄ ደህናም አይደለሽ? ምነው አፍሽ ሰነፈብኝ?" አሉኝ ቀርበው ግራ በመጋባት እያዩኝ .... ጎንጤ ቀረብ ብሎ የሚሆነውን ይከታተላል:: .... ሳላስበው እንባዬ ይፈነቅለኝ ጀመር.... ለመጀመሪያ ጊዜ ከአደጋው ከነቃሁ ከወር ከአንድ ቀን በኃላ ... በስሜ ጠርቶ በፍቅር ያየኝ ሰው ገጠመኝ.... ድምፅ አውጥቼ እነፋረቅ ጀመር::

"እኔን ልጄ!! ምን ገጠመሽ? " ሲሉኝ ከተቀመጥኩበት ዘልዬ ተጠመጠምኩባቸው... ግራ እንደገባቸው ያስታውቃሉ:: አቀፉኝ..... እቅፋቸው ውስጥ ነፍሰ ገዳይ መሆኔን ረሳሁት.... ያየኝ ሁሉ ዓይን ውስጥ ያየሁትን ፍርድ እና ጥላቻ ረሳሁት... ግራ መጋባቴን ረሳሁት.... ባዶነቴን ረሳሁት .... ለደቂቃዎች ብዙ ነገሬን ረሳሁት... ሲያባብሉኝ ቆይተው .... እኔ ተቀምጬበት የነበረ ዛፍ አጠገብ ያለ ጉቶ ላይ አረፍ አሉ እንድቀመጥ እግራቸው ስር አስዩኝ:: .... ከሁኔታቸው ከዚህ በፊት አድርጌው የማውቀው ነገር እንደሆነ ገባኝ:: እግራቸው ስር ተዘርፍጬ ጉልበታቸውን ደገፍ ብዬ የተፈጠረውን ነገር ሆስፒታል ከነቃሁ ሰዓት ጀምሬ ነገርኳቸው:: ዝም ብለው ሲሰሙኝ ቆይተው ብርዳሙ ልቤን የሚያሞቅ ፈገግታ ፈገግ ብለው::
👍243
"ልጄ እኔ በዘመናት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ፀሎት በአንድም በሌላም መንገድ ሲመልስ አይቻለሁ:: ያንቺ ግን ይለያል! (መገረማቸው ይሰማል) የዛሬ ሁለት ወር ገደማ የገብርኤል እለት ማግስት እዝህችው ቦታ እንደዝህችው ተቀምጠሽ 'ያለፈውን ሁሉ በላዺስ ማጥፋት ቢቻል እና እንደአዲስ ሀ ብዬ መኖር ብችል?' ያልሽኝ! 'በቃሉ: በንሰሃ: በጌታችን ደም እንደአዲስ ስርየትን አጊንተሽ መኖር ትችያለሽኮ!' ብልሽ .... 'አይ አባ መች እንዲህ ቀሎ!' ነበር ያልሽኝ:: ልጄ የተመኘሽውን አዲስ ህይወትኮ ነው እግዚአብሔር የሰጠሽ!! " አሉኝ ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉ.... እዚህችው መኖር አይቻልም?? ቤት አልፈልግም... ፀሃይም ዝናብም... ክረምትም በጋም ለምን እዝህችው እግራቸው ስር ሆኜ አያልፍም?

የጠየቅኩትን አዲስ ህይወት እንድፅፍ ጭንቅላቴን ነጭ ወረቀት አድርጎ እንደሰጠኝ ቢነግሩኝም ስለራሴ የነገርኳቸው ነገር ካለ እንዲነግሩኝ ጠየቅኳቸው::

"መጀመሪያ ያገኘሁሽ ቀን ... እርግጠኛ ቀኑን አላስታውሰውም... ሰባት ስምንት ወር ቢሆን ነው... እዝህችው ጋር ቆመሽ በአምላክሽ ተቀይመሽ ጮክ ብለሽ እየተጣላሽው ነበር:: እያለፍኩ ገርመም ሳደርግሽ 'ምን ያፈጣሉ? በእግዚአብሄር የተናደደ ሰው አይተው አያውቁም? ' ብለሽኝ ነው ያስቆምሽኝ.... የዛን እለት ለብዙ ዓመታት ፈልገሽ አስፈልገሽ ያገኘሻት እናትሽ ስታገኛት በማይድን በሽታ ልትሞት ወራት እንደቀራት የሰማሽ ቀን ነበር:: ... ዝርዝሩን አልጠየቅኩሽም... ሲጠይቁሽም አትወጂም.... ከዛን ቀን በኃላ ቢያንስ በሳምንት ካልያም በሁለት ሳምንት አርብ አርብ ትመጫለሽ... ያሳለፍሽው ህይወት በዝርዝር ባትነግሪኝም ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው:: .... መጥተሽ እዚህጋ ትቀመጫለሽ... አንዳንዴ ታዋሪኛለሽ ሌላ ጊዜ በዝምታ ቆይተሽ ትሄጃለሽ.... "

"እናቴ ምን ሆነች ከዛ? የት እንደሆነች ነግሬዎታለሁ?"

"አልነገርሽኝም ልጄ! እናትሽ እኔ እስካገኘሁሽ ድረስ በህይወት ነበሩ:: ወንድም እንዳለሽ ነግረሽኛል:: ስለእናትሽ ለወንድምሽ መንገር ተጨንቀሽ ነበር:: አዝናለሁ ልጄ ከዚህ በላይ የማውቀው የለም!" አሉኝ አሁንም ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉኝ..... እናት? የት ናት? ወንድም?? ታዲያ ለምንድነው ብቻዬን የምኖረው? ለምንድነው ጎንጤም ተናኜም ፖሊሶቹም የማያውቋቸው?? እነርሱስ ቢሆን እንዴት ሊፈልጉኝ አልመጡም? ....

...........ይቀጥላል.......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍25🥰124
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ስድስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«ልጄ ዘመንሽን ሁሉ ክፉ ያደረጉብሽን ሰዎች ለመበቀል ስትዪ ነው የኖርሽው። እንደገባኝ ከሆነ ከበቀል እና ለወንድምሽ ከመኖር ውጪ ሌላ ልምድም ህልምም ስላልነበረሽ የጎዳሽን ሰው ካጠፋሽ በኋላ አንቺ የምትኖሪለት ነገር አጥተሽ ነበር። ልጄ የበደሉሽን ይቅር በይ፣ ራስሽን ይቅር በይ! ለፍቅር በፍቅር ለመኖር ራስሽን አስለምጂ! እግዚአብሄር አዲስን እድል ሰጥቶሻል።» አሉኝ ከጉልበታቸው ላይ ሳልነሳ ብዙ ደቂቃዎች ወይም ሰዓት ካለፈኝ በኋላ

«አባ ለምንድነው ብዙ የሚያውቁት ነገር ያለ ግን ያልነገሩኝ የሚመስለኝ?»

«የማይበጅሽን ብነግርሽ ምን ሊጠቅምሽ ልጄ? ስላሴ ከጭንቅላትሽ ብን አድርጎ ያጠፋው ባይጠቅምሽ አይደል? ወይም ለጊዜው ባያስፈልግሽ? »

«አባ ያለትናንት ዛሬን መኖር ይቻላል? ትናንት የሌለበትስ ዛሬ አለ? እያንዳንዱ ከሰዎች ጋር የሚያያይዘኝ ገመድ ከትናንት ጋር የተጋመደ አይደለም? ቤተሰቦቼም እኮ ትናንቴ ውስጥ የነበሩ ናቸው። እሺ ካልነገሩኝ እናቴን ወይ ወንድሜን እንዴት አገኛቸዋለሁ?»

«የሚጠቅምሽን መረጃ አልደብቅሽም ልጄ። ስለእናትሽ ብዙም አላወራሽኝ ስለወንድምሽ ግን አውርተሽ አትጠግቢም። ስሙ በየእለቱ የምደግመው ስለለሆነ አልዘነጋሁትም። ኪዳን! አዎ ኪዳን ነው።» ጀርባዬ ላይ በትልቁ የተነቀስኩት የወንድሜን ስም ነው ማለት ነው። «ጥይምናው እና ፈገግታው ያንቺው ነው።» ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጉልበታቸው ቀና አልኩ

«እንዴ አባ ያውቁታል? አብሮኝ መጥቶ ያውቅ ነበር?» አልኩኝ በጉጉት

«እንደዛ አይደለም ልጄ! በስልክሽ ነው ምስሉን ያሳየሽኝ። » ጠይም ሳቂታ .......... የአልጋዬ ኮመዲኖ ላይ ያለው ፎቶ ነው የሚሆነው

ስልኬ! ......... እንዴት እንደምከፍተው ማወቅ አቅቶኝ መሳቢያ ውስጥ ያስቀመጥኩት መስታወቱ የተሰነጣጠቀ ስልኬ! ቀና ብዬ ጎንጤን አየሁት። ከተቀመጥኩበት እየተነሳሁ

«አባ ልሂድ በቃ! ብመጣ አገኝዎታለሁ? »

«አለሁኝ ከቤቱ የት እሄዳለሁ? (ወደ ሰማይ መልከት አደረጉ) በአይንሽ ካጣሽኝ መልከፃድቅን ጥሩልኝ በይ!» የለበስኩትን እያጤኑ «ለምስጋና እንደመጣሽ አምኜ አምላኬን አመሰግናለሁ» አሉኝ። መጨረሻ ላይ የተናገሩት እንዳልገባኝ ገብቷቸው ፈገግ እያሉ። «ሁሌም ስትመጪ ሌጣሽን ያለክንብንብ ደግሞም የክፉ ነገሮች ምስል ያለበት ልብስ ለብሰሽ ነበር። አንድ እለት ከጀርባው ትልቅ የእባብ ምስል ያለበት ጃኬት አድርገሽ 'ምነው ልጄ ከጀርባሽ ፈልገሽው ነው?' ብልሽ። ' ከእግዚአብሄር የታረቅኩ ቀን ለምስጋና ስመጣ ቀሚስ ለብሼ ነጠላ ደርቤ እመጣለሁ።' ብለሽኝ ነበር።» አሉኝ።

እቤት የምደርስበት ሰዓት እርቆብኝ ከደረስኩ በኋላ ከስልኬ ጋር ተፋጥጫለሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ምስላቸው የሌሉ ነገሮችን እንኳን ስይዛቸው በደመነፍስ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቅ ነበር። ለምንድነው ስልኬን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ የገባኝ?

«ባትሪ ያለው አልመሰለኝም! እንዱለው ይሆን?» አለኝ ጎንጤ አለማወቄ ቢገባውም እንዳያሳፍረኝ በመጠንቀቅ ዓይነት። አቀበልኩት። ተቀብሎኝ ግድግዳው ላይ ተሰክቶ ገመዱ የተዝረከረከ ገመድ ብድግ ሲያደርግ የሚቀጥለው ሂደት ጫፉን ስልኩ ላይ መሰካት እንደሆነ አውቃለሁ። የሆነ አለ አይደል ሰው መንገድ ጠፍቶበት ልክ ቤቱን ሲያየው ይኸው እንደሚለው ዓይነት ነገር?

አባ 'እግዚአብሄር ጭንቅላትሽን እንደህፃን ልጅ ነጭ ወረቀት አድርጎ ሰጥቶሻል፣ የሚቀጥለውን ዘመንሽን አስተካክለሽ ፃፊበት' ይበሉኝ እንጂ እንደህፃን ነጭ ወረቀት የሆነ ጭንቅላት እንዳልቀረኝ አውቃለሁ። እንደህፃን እንዴት እንደምበላ ከ 'ሀ' አልጀመርኩም ወይም አፌ አልጠፋብኝም፣ መራመድ ለመቻል ከመዳህ አልጀመርኩም ፣ 'ኡፉ ነው' ባልባልም እሳት እንደሚፋጅ ሳየው አውቄያለሁ፣ ሽንቴን ልብሴ ላይ ይሁን ሽንት ቤት የምሸናው ሳላውቅ እላዬ ላይ አልለቀቅኩም፣ ሱሪ ለመልበስ በአንገቴ አላስገባሁም ወይም ጫማ ለማጥለቅ ግራ አልተጋባሁም፣ አልጋ ሳይ ይሄ መተኛሽ ነው ሳልባል ገልጬ ውስጥ ገብቼ ተኝቻለሁ ፣ የጥርስ ብሩሽ ሳይ ምንም ሳልጠይቅ እጄ አንስቶ ጥርሴን ቦርሿል .........

2. ስልኬ

ስልኬ ለመጀመር የሚያስችለውን ባትሪ ሲያገኝ ራሱ ከፈተ። እስክሪኑ ሲበራ ዘልዬ አጠገቡ ደረስኩ እና አነሳሁት። ያ አልጋዬ አጠገብ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ዓይኖች ያሉት ፎቶ ይታያል። ራሱ ነው! ኪዳን ነው። ትልቅ ሰው ሆኖ! ይሄን ምስል ሳየው እስከአሁን ምስሎቹን በወረቀት ሳየው ከተሰማኝ የተለየ ስሜት ተሰማኝ። የሆነ የሚያፍን ፈንጠዝያ! ልቤ ሰውነቴ ውስጥ ይነጥር ጀመር። ስልኬን በችኮላ ብነካካውም በኮድ ተዘግቷል። ተስፋ ቆርጬ መሬቱ ላይ እንደተቀመጥኩ

«እትዬ ስልኮትን በፊትዎት ነው ሲከፍቱ ያየሁት!» አለችኝ። እንዳልገባኝ አውቃ ስልኩ እጄ ላይ እንዳለ ወደ ፊቴ ስታቀርበው እውነትም የኮድ ምልክቱ ተነሳ። የሚቀጥለውን ፍለጋዬን ለማድረግ በረጅሙ ተነፈስኩ። ወዲያው ስልኩ በመደዳ የማያቆም ተደጋጋሚ ድምፅ ያሰማ ጀመር። ለምን እንደሆነ ድምፁ ረበሸኝ። የሆነ ቀጥሎ መጥፎ ክስተት ይከሰት ይመስል ጭንቅላቴን ወጠረኝ። መሬቱ ላይ አስቀመጥኩት። የሆነ ግጭት ጭንቅላቴ ውስጥ የተከሰተ መሰለኝ። የሆነ የተኩስ ድምፅ ነገር።

«ምነው እትይ? አመሞት እንዴ? » ወድያው አስከትላ «ጎንጥ! አንተ ጎንጥ» ጆሮዬ ላይ አምባርቃ ተጣራች። በረንዳው ላይ የነበረ መሰለኝ

«ምንድነው?» ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።
«እኔእንጃ የስልኩ ድምፅ ረበሸኝ።» አልኩት ስልኩን ካስቀመጥኩበት አንስቼ እያቀበልኩት።

«ደውሎ ያጣዎትን ስልክ መልእክት እየላከልዎት ነውኮ! ሌላም መልዕክቶች አሉት።»
«የሚጠቅም ነገር ካለው አንብብልኝ» አልኩት ልቤ ለምን እንደፈራ ሳላውቀው እየተርበተብኝ። ዝም ብሎ ስልኩን ሲነካካ ቆይቶ

«ሾካካ የሚባል ሰው 'ዛሬ ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ ስለሚመጡ ቤቱ ይፅዳ' የሚል መልዕክት ልኮልዎት ነበር። ኦው ብዙ መልዕክት ነው የላከው። 'ምነው ዘጋሽኝ? በሰላም ነው ስልክሽ የማይሰራው?'......... 'ኸረ ምንድነው ጉዱ አንቺ ሳይኖሪኮ ቤቱ ስርዓት አጣ! '...... »

«ተስተምረሃል እና?» አለች ተናኜ በጣም በተገረመ አባባል አገጭዋን በእጅዋ ደግፉ ጎንጤን እያየችው። እሷ ማንበብ እንደማይችል እንዴት አሰበች እኔ እንዴት እንደሚያነብ እርግጠኛ ሆንኩ? አላውቅም! እሱ ተናኜን ቁጣና ግልምጫ ደባልቆ ለግሷት ወደንባቡ ሲመለስ የሚያነብበት ስልት እና ፍጥነት ስለእርሱ ብዙ የማላውቀው ነገር እንዳለ እንድጠረጥር አደረገኝ።

« ........ 'ሜሉ መላ ሳይገባልኝኮ ሁለት ሳምንት ተቆጠረ.' ........... እእ 'መታመምሽን በወሬ ሰማሁ መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ቤትሽን የሚነግረኝ አጣሁ። ብደውል ስልክሽ አሁንም ዝግ ነው።'»
«ራሱ ሾካካው ነው?» ያልኩት አስቤው አልነበረም። ሁለቱም እኩል ሲስቁ አባባሌ ራሴንም አሳቀኝ! ጎንጤ ሳቁን ሲገታ
👍23🥰21
«አዎ ራሱ ነው!........ ' አንቺ በቅርቡ የማትመለሺ ከሆነ ለዳዊት መላዬን እንዲቆርስልኝ ንገሪልኝ ዛሬ ሄጄ ስጠይቀው የማውቅልህ ነገር የለም ብሎ አባርሮኛል።' ......... እ ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር........ ' እመቤት ነኝ ሜሉ ያለፈውን ሳምንት ስትቀሪ ባይመችሽ ነው ብዬ አለፍኩ ይሄንን ሳምንት ስትቀሪ ግን አሳሰብሽኝ። በሰላም ነው?' ........ሌላ ደግሞ ዳዊት የሚባል ሰው......... »ካለ በኋላ ድምፁን ዝግ አድርጎ «እትይ ይሄን ራስዎ ቢያነቡት ሳይሻል አይቀርም ብሎ ስልኩን ዘረጋልኝ። እትዬ ነበር የሚለኝ እሱም እንደ ተናኜ እትይ ብሎ መጥራት መጀመሩ ቁልምጫ መሆኑ ነው?
«አንብበው ችግር የለውም ኸረ!» አልኩት እስከዛሬ ከሚያውቀው የባሰ ምን ሊመጣ ይችላል ብዬ እያሰብኩ። መቼም የገዛ ባሌን ፍሬዎች የቲማቲም ወይ የብርቱካን ፍሬ ከዛፉ እንደመቀንጠስ ቀለል አድርጌ ከሰውነቱ ቆርጬ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ከመውሰድ የባሰ ጉዳይ ሊኖር አይችልም!
«አይ እትይ ግድ የልዎትም ራስዎ ያንብቡት!» አለ እያመነታ ስልኩን የዘረጋበት እጁን ሳይመልስ
«ግድ የለህም አንብበው» ስለው እያመነታ
«ካሉ እሺ!» ብሎ እስከዛሬ ያላየሁበት አይነት የማፈር ይሁን የመቅለስለስ ያልገባኝን ፊት እያሳየኝ ማንበብ ጀመረ። « የእኔ ፍቅር ስደውልልሽ አታነሺም ስትመጪ የምንጠጣውን እንዳትረሺ! በጣም ቆየሽኮ ፍቅር በሰላም ነው ስልክ የማታነሺው? ....... »
«እሺ እሱን ተወው እና ሌላ አንብብ ኪዳን የሚል መልእክት የለም?» አልኩት እኔም እንደማፈር እያደረገኝ። ፍቅረኛ ነበረኝ? ቢያንስ የእኔ ፍቅር የሚለኝ ሰው ነበረ።
«እኮ!» ብሎ ጣቱን ወደላይ እና ወደ ታች ኪዳንን ፍለጋ ይፈትለው ጀመር። «አይ እትይ ኪዳን የሚል የለም! ምናልባት በሌላ ስም ይሆናል የመዘገቡት! ስም መዝገቡም ውስጥ ኪዳን የሚል የለም!»
«እሺ እስቲ ሊሎቹን አንብብልኝ እና በሌላ ስምም ከሆነ ከመልእክቱ እንደርስበት ይሆናል።» አልኩኝ።
«ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር አሁንም 'እመቤት ነኝ ሜሉ ያስቀየምኩሽ ነገር አለ እንዴ? በባለፈው ንግግሬ ተቀይመሽኝ ይሆን? ግራ ገባኝኮ! ምንም ውስጥ ሆነሽ ቢያንስ መልእክት ትልኪብኝ ነበር። እንዲህ ጨክነሽብኝ አታውቂም! ብደውልም ስልክሽ አይሰራም። እባክሽ ቢያንስ ደህና መሆንሽን እንኳን አሳውቂኝ!»
«እናቴ ትሆን እንዴ?»
«መደወል እንችል ነበር ግን በሁለት የተለያየ ቁጥር ነው መልእክቱ የተላከው። በየትኛው እንደውል?» አለ ጎንጤ
«ምናልባት የራሷ ስልክ የላትም ይሆናል። አባ ታማለች ብለውኝ የለ? ባለፈው ሳምንት ሳትጠይቂኝ አይደል የሚለው የመጀመሪያው መልእክት?»
«ይሆን ይሆናል። ግን እትይ ለማንኛውም ለጊዜው ማን ምን እንደሆነ እስኪለይ ላገኙት ሁሉ ሰው ምንም እንደማያስታውሱ አይናገሩ! አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሊጎዳዎት የሚያስብ ሰው ሊኖር ይችላል።» አለ ሀሳብ እንደገባው ሰው።
«አንደኛው ስልክ ላይ እንደውል!» አልኩኝ። ስልኩ አድምቆ ሶስታችንም በምንሰማው መጠን ሲጠራ ቆይቶ ከወድያኛው ጫፍ ተነሳ እና የወንድ ድምፅ «ሀሎ» አለ። ቀጥሎ የምለው ግራ ገብቶኝ ሳለ ጎንጤ ስልኩን ወደራሱ አስጠግቶ
«ይቅርታ ያድርጉልኝ እና በዚህ ስልክ እመቤትን ማግኘት እችል ይሆን? ሰው መልዕክት ሰዶኝ ነው!» አለ። የሰውየው ድምፅ ያመነታ መሰለ።
«ማነህ አንተ? እመቤትን ለምንድነው የፈለግካት? ማነው የላከህስ?»
«እኔን አያውቁኝም! እንደው እመቤትን ማግኘትን ብችል ወይ የማገኝበትን ሌላ ስልክ ቢጠቁሙኝ።»
«ተሳስተሃል። እመቤት የምትባል ሴት በዚህ ስልክ የለችም!» ስልኩ ተዘጋ። መልሶ እየደወለ። «ሲወሸክት ነው! » አለኝ ለእኔ
«እመቤት የምትባል ሴት አላውቅም አልኩህ አይደል?» አለ ሰውየው እየተቆጣ
«እየዋሹ ነው እሎታለሁኝኣ! በዚሁ ስልክ ከእመቤት መልዕክት ተልኮ ነበር። እመቤትን ካላወቋቸው እመቤት ነኝ የሚል መልእክት እንዴት እዚህ ደረሰ?» አለ ጎንጤ ቆፍጠን ብሎ ሰውየው ስልኩን ሲነካካ ድምፁ ይሰማል።
«ማነው ላከኝ ያልከው?» አለ በጥርጣሬ እንደማጣራት
«ሜላት»
«ታዲያ ራሷ ሜላት ለምን አልደወለችም አንተጋ ስልኳ ምን ይሰራል?»
«ለጊዜው እትዬ ሜላት ታመዋል። እንደየትም ብለህ መልእክት አድርስልኝ ብለውኝ ነው!» ሲለው ሰውየው የጠበበው ድምጽ አሰማ።
«እ መልእክቱን ብትነግረኝ እኔ እመቤትን ሳገኛት አደርስልሃለሁ። እመቤት የት እንዳለች ሜላት ነግራሃለች?» አለ አሁንም እንደጨነቀው።
«በፍፁም! በዚህ ስልክ ደውል ብቻ ነው ያሉኝ!»
«ዌል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ናት!» አባባሉ 'እስቲ መልእክትህን እዛ ሄደህ ታደርስ እንደሆነ እናያለን!' አይነት ነው።
«እባክዎትን ካላስቸገርኩ ደውዬ እንደነበር መልእክት ያድርሱልኝ!» ብሎ ዘጋ ስልኩን። እናቴ ልትሆን አትችልም! እናቴ እስር ቤት ምን ታደርጋለች? ታማ የለ? ጎንጤ ስልኩን ሲበረብር ስልኩ እጁ ላይ ጮኸ
«እትይ ዳዊት እየደወለ ነው!» አለኝ ስልኩ ላይ አንዳች ነገር ያየ ይመስል እያፈጠጠ።
«አንሳዋ!» አልኩት መልሼ እያፈጠጥኩ
«ኸረግ! ተዚያ ምን ልለው?» ብሎ ስልኩን ክፍት አድርጎ ጆሮዬ ላይ ለጥፎልኝ ለተናኜ እንድትወጣ በዓይኑ ምልክት ሰጥቷት እሱም ወጣ!
«ኦህ ማይ ጋድ ፋይናሊ! በሀሳብ ከማለቄ በፊት! ስልክሽ መከፈቱን ቴሌ ማሳወቂያ ሲልክልኝ አይኔን ነበር ማመን ያቃተኝ! ሜሉዬ የኔ ፍቅር! ምን ባደርግሽ ነው እንዲህ የጨከንሽብኝ?» ሀሎ እንኳን ሳልለው ያለማቋረጥ ይለፈልፋል።
«ትንሽ አሞኝ ነበር» አልኩኝ ጎንጤ ያለኝን አስታውሼ
«ኦህ ማይ ጋድ! ታዲያ አትደውዪልኝም ነበር? እሺ አሁን የት ነው ያለሽው? የት ልምጣ? ኦህ አምላኬ? እሺ አሁን እንዴት ነሽ?»
የሚጠይቀኝ እንድመልስለት አይመስልም! የሆነ ልክ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማኝ አደረገኝ። እቤት እንዲመጣ ስነግረው የቤቴን አቅጣጫ አልጠየቀኝም!
«ጎንጥ ? ዳዊት የሚባል ሰው እዚህ ቤት መጥቶ ያውቃል? ሆስፒታል እያለሁ መጥቶ ጠይቆህ ከሆነ?» አልኩት ወደበረንዳ ብቅ ብዬ። እኔስ ጎንጤን ተናኜ እንደምትጠራው ጎንጥ ማለቴ ማቆላመጤ ይሆን?
«በፍፁም እትይ!»
በር በሩን እያየሁ ቆይቼ መጣ! አራት ጊዜ ባጥፈው ያለምንም መጣበብ ሰፋፊዎቹ ጅንስ ሱሪዎቼ ጎን ኪስ መሰስ ብሎ ጥልቅ የሚል፣ ቀጭን ለመባል ራሱ መወፈር ያለበት ፣ አጭር ቀይ ስጋም ቀልብ የራቀው የሆነ ጥላ ቢስ ነገር ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን ይደረጋል? መቼም ወንድ ነው ብዬ ከስር ሆኜ አልደረግለትም! ከላይ ብሆንበት ከእጥረቱ ከቅጥነቱ ፈሱ ነው የሚያመልጠው።
....................
ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍40
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


የቀይ አፈር መንደር ገና እያዛጋች ነው፡፡ ካርለት ጥቁርና ቡናማ ቀለም ያለው የፍዬል ቆዳዋን ለብሳ አንባሯን ጨሌዋን
አንገቷ ላይ ደርድራ ቀለበቶችዋን በጣቶችዋ ሰክታ ጥልፍልፍ ነጠላ
ጫማዋን ተጫምታ
እቃዋን በጀርባዋ በማዘል ከከተማው ቁልቁል
በሚወስደው መንገድ ትንሽ ሄደችና ሰፊውን የአርባምንጭ መንገድ
ትታ ወደ ግራዋ በመታጠፍ ወደ ዲመካ የሚወስደውን ጎዳና ይዛ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

በሾላ ቆንጥር ዘረማይ ሶውት• ዲሎ ጉርዶ  ሶቆላ… የተሞላውን ጫካ ግራና ቀኝ እያየች የድርጭት ጭልፊት ቁራ
አቲ ሴሌ አርክሻ… አዕዋፍ ዝማሬ እያዳመጠች ልቧ በደስታ እየዘለለ ነጎደች፡፡

የእግር ጉዞ ትወዳለች፡፡ አቀበት ወጥታ ቁልቁለት ወርዳ! ላብ በጀርባዋ ተንቆርቁሮ, ሰውነቷ ዝሎ. ካሰበችበት ስትደርስ
የአሸናፊነት ስሜት  ይሰማታል፡፡ በራሷ ትኮራለች ህይወቷ ይታደሳል፤ ልቧ በደስታ ይዘላል።

በተለያዩ ቦታዎች ተራራ ወጥታለች በበረሃ አሸዋ
ተጉዛለች በበረዶ ተንሸራታለች ስለዚህ አካሏ ብቻ ሳይሆን የህሊናዋ ጡንቻም ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ ነው።

በሰዓት በአማካይ ከአራት እስከ አምስት ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች፡፡ ከቀይ አፈር መንደር እስከ ዲመካ ያለው ርቀት ሃምሳ ስምንት ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ሃምሳውን ኪሎ ሜትር ለመጓዝ ከአስር እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ይፈጅባታል፡፡ በየመካከሉ ግን እረፍት
ማድረጓ ስለማይቀር የመድረሻ ሰዓቷ በሁለትና ሶስት ሰዓት ይጨምር ይሆናል፡፡

የለበሰችው የሐመር ባህላዊ ልብስ አምሮባታል፡ ከኋላዋ በኩል የለበሰችው ቆዳ ውን ውን የሚል ሲሆን ከፊት ለፊቷ ግን አጭር ነው፡ ጭኖችዋ ለፀሐይ እንብዛም ተጋልጠው ስላልከረሙ እንደ ፋርኖ ነጭ ሆነው ያስጎመጃሉ፡፡ አንድ ወቅት ፀሐዩ ጠብሷቸው እንሶስላ መስለው ነበር፡፡

በየመንገዱ የሚያገኝዋት መንገደኞች እንግዳነቷን ገምተው ተደንቀው ቆም ብለው ሲያይዋት

ነጋ ያ” ትላቸዋለች፡

ጋ ያኒ" ይሏታል፡፡

“ነኖኖምቤ ቀለሎምቤ
ፈያዎ…" በነጭዋ ሐመር
ይገረማሉ፡ በደስታም ፈገግ ይሉና፡“ፈያኔ! ያ ፈያዎ! ይሏታል፡ ሰላምታዋን አቅርባ ከብቶች… ደህና ብላ ስትጠይቃቸው፡፡ እነሱም የእሷን ደህንነት ሲጠይቋት፡-

“ኢንታ ፊያዋ…” ብላ መንገዷን ትቀጥላለች፡እነሱም በአይናቸው ይሸኝዋታል፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሰላምታ ከተለዋወጡ ደህንነታቸውን ከተነጋገሩ በኋላ፡

“ናቢ ናሞ አይኔ? ይሏታል ስምሽ ማነው ለማለት በሐመርኛ፡፡

“ኢንታው! ፈገግ ትላለች የእኔ  ስም በማለት፡፡ እየሳቁ
እራሳቸውን ሲወዘውዙ፡

ናሞ አይኔ ካርለት ስትላቸው ይከብዳቸዋል፡ እንደገና
እየደጋገመች የእኔ ስም ካርለት ነው፡" ትላቸውና ተጨዋውተው
ደሞ ይለያያሉ፡፡

አንዳንዶቹ እንዲያውም ከደስታቸው ብዛት ሮጠው ሄደው በለሻ ወተት ይዘውላት ይመጣሉ፡ እነሱ ዘንድ እንድትውል
እንድታድርም ይጠይቋታል፡፡ “ምነው እዚች ምድር ያለው ሁሉ እንደእናንተ ቅን በሆነ! ብቻ ግን ሁሉም እንዲህ ቢተዛዘን ምናልባት
የህይወት ጣምናውን መግለጽ ይከብድ ይሆናል" እያለች ታስባለች፡፡

ስለዚህ ደግነታቸው  አቀባበላቸው ሞራል ስለሚሆናት ስትጓዝ ድካም አይሰማትም፡፡ ላብ ብቻ፡፡ የትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ
ማለት ብቻ… ውስጧ ግን ብርቱ ነው፡፡ ብረት ሞራሏም እንደአለት ጥንካሬው እያደገ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ hብቶችን የሚጠብቁ አፍላ ጎረምሶች
ያጋጥሟታል፡፡መፉቂያቸውን አፋቸው ውስጥ ሰክተው
የሚያብለጨልጭ ጭናቸውን ሳንቃ ደረታቸው ላይ ጨሌያቸውን
ያንዠረገጉ ይቀርቧትና ሞቼ ጉምዛ ክሮጃ  መፋቂያ  ጨሌ ይሸልሟትና፡-

“እጮኛ አለ?” ይሏታል፡፡

“አዎ!” ትላቸዋለች፡፡

“ሐመር ነው?”

“ከዎ፡፡

“ማን ይባላል?"

“ደልቲ ጉልዲ…"

“ይእ- አንች ነሽ ነጭዋ ሐመር?"

“አዎ"

ካርለት የምትባይው አንቺ ነሻ?

“አዎ-” ይገረሙና
“አንችንማ በስም የማያውቅ ማን አለ! ይእ!.." ሲሏት ካርለት ደስ ይላታል፡፡

ቀኑ እንኳን መሽቶ ከጨለመ በኋላ ሲያገኝዋት ጠጋ ብለው ያነጋግሯትና ሽኝተዋት ይመለሳሉ፡፡ በዚህ በጉዞው ወቅት ቀበሮ
ጅብ… ሲጮሁ ይሰሟታል፡፡ ግን አልፈራችም፡፡ አውሬዎች የሚያጠቁት ፊሪን ነው፡፡ የዓላማ ዕፅት ያለውን ያከብሩታል፡፡

ካርለት ዲመካ ለመድረስ ወደ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲቀራት ደከመች፡፡ በሐመር ባህል ልጃገረድ በምሽትም ሆነ
በቀን ብትጓዝ የሚደፍራት እንደሌለ ጠንቅቃ ታውቃለች:: ስለዚህ
በጉዞዋ ብትቀጥል የሚያሰጋት ነገር የለም፤ ድካሙ ሲጠነክርባት ግን
አንድ በቆሎ እርሻ ውስጥ ገብታ ለወፍ: መጠበቂያ ከተዘጋጀው ማማ ላይ ወጣች ትንሽ ብስኩትና ቼኮሌት ተመግባ በኮዳ ከያዘችው ውሃ ተጎንጭታ “ስልፒንግ ባጓ" ውስጥ ገብታ ከዋክብትን እያየች,
ተወርዋሪ ኮቦችን እየቆጠረች የእንቁራሪቶችን የኮኮሮችን ዝማሬ
እያዳመጠች እንቅልፍ እያባበለ ይዟት ጭልጥ አለ

ካርለት ከእንቅልፏ ስትነቃ ለጊዜው የት እንዳለች ድንግርግር አለባት፡፡ አይኖችዋን ከድና ስታስብ ከየት ተነስታ ወዴት
እንደምትጓዝ መቼ እንደደከማትና ማማው ላይ እንዴት እንደወጣች
ትዝ አላት፡ ራቅ ብለው ጎረምሶችና ህፃናት ይጫወቱ ነበር፡፡ ከማማው
ለመውረድ ስትሞክር ግን ሁሉም ዘወር ብለው አይዋት፡፡ ሻንጣዋን
ማማው ላይ ይዛ መውጣቱ ስለከበዳት ማማው ስር ነበር ጥላው የወጣችው፡ ማማው ከመንገዱ ብዙም  ስለማይርቅ እሷንም ሆነ
እቃዋን ብዙ ተላላፊዎች እያዩ ነው ያለፉት፡፡ ሐመር ውስጥ ግን የአንዱን ንብረት ሌላው አይነካም ወድቆ እንኳን ቢያገኝ ዛፍ ላይ
አንጠልጥሎት ይሄዳል፡፡ የጠፋው ተመልሶ እንዲያገኘው

ካርለት ልጆችንና ጎረምሶችን ሰላም ስትል አንድ ልጅ እግር ከቡዱኑ ነጠል ብሉሎ ሄደና፡-

“አይቶ!  እረ ኦይቶ" ብሎ ተጣራ፡፡

“ዬ!” የሴት ድምፅ ተሰማ፡፡
“ይዘሽው ነይ እንግዳዋ ልትሄድ ነው" ሲል በሐመርኛ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ካርለት ሰንደል ጫማዋን ቆልፋ ሳትጨርስ
አንዲት ልጃገረድ በዛጎልና ጨሌ የተዋበውን ቆዳዋን እያንሿሿች በቀጭኗ መንገድ እየሮጠች መጣች፡፡ በእጅዋ የወተት መያዣ ዶላ በሾርቃ ደግሞ የማሽላ ጭብጦ ይዛለች፡፡
ካርለት ልጃገረዷ ወደ እሷ ስትመጣ በአድናቆት
ተመለከተቻት፡፡ ኦይቶ ሰላም ብላት የወተቱን ዶላ ሰጠቻት፡፡ በሐመር ባህል የቁጥ ቁጥ ስጦታ የለም ያን የምታውቀው ነጭዋ ሐመር ዶላውንና ሾርቃውን ተቀበለቻት፡ ርቧታል፡፡ የዶላውን ክዳን ደፍታ
በ“ዶንግ" የታጠነውን ትኩስ ወተት በክዳኑ ቀዳቸና አንዱን ለጥሟ ጠጣች፡ ከዚያ ጭብጦውን በወተቱ እያማገች በላችና፡-

“ባይሮ ኢሜ” እግዜር ይስጥልኝ ብላ አመስግና ዶለውንና ሾርቃውን ለልጃገረዷ መልሳ ሁሉንም ተሰናብታ አሁንም “ሁላችንም ምን ነበረ እንደ እናንተ ብንሆን! ብላ እየተመኘች ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ወፎች ይዘምራሉ እሷም ትዘምራለች ከብቶች ያገሳሉ
ተፈጥሮም እንዲሁ. የሙዚቃው  ህብረ ዜማ ተዋህዶ በሐመር
ቀዬዎች ያስተጋባሉ አይ ሕይወት! ተፈጥሮ የቃኘችው የህይወት
ለዛ.... ሳያቋርጥ እንደ ምንጭ ውሃ ከአድማስ አድማስ ይንቆረቆራል።

ምህረትየለሽ ቴክኖሉጂ አየሩን ከመበከሉ
ስግብግብነትንና ጦርነትን ከማስፋፋቱ ሌላ ተፈጥሮን ሊያዛባ አሁንም ባልተዳረሰበት ሁሉ ሃዲዱን ዘርግቶ ባህላዊ ህይወትን ሊጨፈልቅ ወደ ሐመር ሲምዘገዘግ ታያት፡፡

“አይ አፍሪካ! አለች ካርለት ከግብፅ እስከ ደቡብ አፍሪካ፧.ከኢትዮጵያ እስከ ሞሪታንያ ያሉትን የአፍሪካ አገሮች እያሰበች፡፡
👍26😱2🥰1
አፍሪካ! አፍሪካ ለአፍሪካውያን የዳቦ ቅርጫት እንዳልነበረች
ሁሉ ሰለጠን ባይ እረኞች አኗኗርን ተፈጥሮዋን
የቅራንቅቧቸው መጣያ ማረጋቸው አንሶ ጨለማ አህጉር¡ ያልሰለጠነ
ህዝብ መገኛ እያሉ ሲመፃደቁ ስትሰማ የኖረችው አቀረሻት።

“አዛኝ መሳይ የአዞ እንባ አፍሳሾች ከሰጠነው በላይ ሰጠን ብለን የምናወራ እብሪተኞች ከዘረፍነው ላይ ለመመፅዋት እንኳን
የሚንቀጠቀጥ ንፉጎች... የአፍሪካውያንን ተፈጥሯአዊ
ህይወት አጠፋንባቸው፤ ማዕድናቸውን ብቻ ሳይሆን ደስታቸውንም ዘረፍናቸው እርስ በርሳቸው አስተላለቅናቸው. እኛ በሐብት ደለብን ! እነሱ በእሪታ ተዋጡ!... ምናለ አሁንስ በቃችሁ ብንላቸው!”
ካርለት በሐዘን እየተንዘፈዘፈች የወሮን መንደር ጎዳና ተያያዘችው።

ካርለት ወሮ መንደር ስትደርስ መጀመሪያ ህፃናት አይተው ከሩቅ ለዩዋት፡፡ ከዚያ ኮረዶችና ጎረምሶች፤ ቀጥሎ የመንደሩ ሰው
ባጠቃላይ ወደ እሷ ግልብጥ ብለው እንደ ንብ ከቦቧት፡፡

ውሾች ጅራታቸውን እየቆሉ ከብቶች እምቡ-ዋ እምቡ-ዋ አሉ ናፍቆታቸውን ገለፁላት፡፡ ተናፋቂዋ የስነ ስብዕ ተመራማሪ ሰዎች እንዲህ ይናፍቁኛል ብላ አታስብም ነብር፡፡ ሁሉም ናፍቆቱን በተለያዬ ስልት ሲያበረክትላት ግን ሆዷ ታመሰ፡፡ ፍቅር ሃላፊነት
ነው ፍቅር አደራ ነው ፍቅራቸውን እንደተቀበለች እሷስ ፍቅሯን  ማከፋፈሉ ይሳናት ይሆን? ይህን ስታስብ እየሳቀች አነባች፡:
ሲለይዋቸው የሚናፍቁ ሲገናኝዋቸው የማያሰለቹት ሐመሮች ቅቤና
ጭቃ ሊቀቧት መዓዛው ከጥሪኝ ዝባድ ፈረንሳዮች ከሚቀምሙት ሽቶ
በላይ ጠረኑ ሰነፈጣት፡

ቶዮታ መኪናዋ ከከብቶች በረት ራቅ ብላ ቆማለች፡፡
መንዜው ሐመር አንተነህ ይመር ስላምታው ጋብ ሲል ጭንቅ እስኪላት አቅፎ ወዘወዛት: “ካርለት  ነጋያ ካርለት…” እሚላት
ጠፋው፡፡  ስለዚህፈ  እንደገና ጨመቃት፡፡ ደክሟታል፡፡ ላዩ ላይ
ለመለጠፍ  ግን ሃይል አላጣችም፡፡

ከሎ ሆራ ሁሉም ሰላምታቸውን ሰጥተው እስኪጨርሱ ጠብቆ ወደ እሷ መጣ፡፡ ደንግጧል
ካርለትን በምን መጣች ብሎ ይመን እንደምትጠብቀው ያውቃል
ለቀጠሮ ያላትን አክብሮት
ተለማምዶታል ግን በቀጠሮው ጊዜ አላገኘችውም፡፡ ልጆች ገና
ስሟን ሲጠሩ ከተቀመጠበት ደንግጦ የበረገገው እሱ ነው፡፡

ካርለት!

“አቤት ከሎ እንዴት ድክም ብሎኛል መሰለህ'' ብላ ላዩ
ላይ ወደቀች፡፡ አቀፋት• ደገፋት …..

“በእግርሽ መጣሽ?"

አንገቷን ወዛውዛ “አዎን" አለችው

“ወይ አምላኬ!- ከየት ጀምረሽ?"

“ከቀይ አፈር"

“ከቀይ አፈር! ይበልጥ ክው አለ፡፡ ራሱን ጠላው ህሊናው
ተበጠበጠ፡፡

“አዝናለሁ ካርለት! ጎይቲ መቋሚያ መቀመጫ አሳጣችኝ!''

“የታለች ጎይቲ?" ካርለት ቢደክማትም ጎይቲን እስካሁን ስላላየቻት አሰበች፡፡

“አለች ያቻት ወደ አንቺ እየመጣች ነው"

“ይእ! ካርለት"
“ጎይቲ " ተቃቀፋ፤ ተወዛወዙ
“ይእ!- እኔ አፈር ልብላልሽ!- በእግርሽ መጣሽ?”

“አዎ! በእግሬ መጣሁ ከቀይ አፈር ጀምሮ…" ካርለት ጎይቲን ተደግፋ ከተነጠፈላት የከብት ቆዳ ላይ ተቀመጠች፡፡

“ይእ! እኔ ነኝ ገዳይሽ ዘንድሮ ምነው ቦርጆ በኔ ጨከነ!'' ጎይቲ እንባዋ መንታ መንታ ሆኖ ወረደ፡

“ተይ አታልቅሺ ጎይቲ እንኳን ደህና ሆናችሁ። እኔስ
ድካሙ ትንሽ አሸነፈኝ እንጂ በጣም ደስ ብሎኛል፡" ጫማዋን  ፈተው እግሯን በቀዝቃዛ ውሃ ሲያስነኩላት ካርለት አቃሰተች እግሯ ውሃ ቋጥሯል፡
የከበቧት ሁሉ አዘኑላት፡፡

አንተነህ ይመር የከብት ሞራና የጋሊ ቅጠል  አምጥቶ እግሯን ሲቀባባላት ሌሉቹ ሸፈሮ ቡና  ለማፍላት እሳቱን ግር
አድርገው አንድደው እንስራውን ጣዱት

የሚለፈልፍ ጠቦት ፍየል ጎረምሶች ሰብሰብ ብለው እንደቆመ ጕሮሮው አካባቢ ብልቱን ወግተው ፀጥ ሲያደርጉት ሌሎቹ ቅጠል
ቆራርጠው አመጡና ገፈፋው ተጀመረ፡ ጫካ የሄዱት ወጣቶች
የደራረቀ እንጨት ይዘው መጡ ጥቂት ወጣቶች ደግሞ እንጨቱን
በሰንጢያቸው አሾሉና የሥጋውን ብልት እየወጉ በሳቱ ዙሪያ ተከሉት  ወጠሌ ጥብሱ ተጀመረ፡

ካርለትን እንቅልፍ ድብን አድርጎ ወሰዳት የፍየል ቆዳዋን እንደለበሰች፡፡ ጎይቲና እናቷ ከሸፈሮ ቡናው ጎን ሌላ ምድጃ ጥደው
ከብልቱ አጥንቱንና ስጋውን ጨምረው ሾርባ ቀቀሉላት፡፡

ካርለት ከመንቃቷ በፊት ሾርባውን እየሰበቁ  አረፋውን ደጋግመው አስወጡና ስትነቃ በሾርቃ አቀበሏት፡፡ ካርለት አይኗን
እንደተጠራጠረች ሁሉ ክድን ክፍት ኦሸት… እያደረገች አየች፡፡
እወ ነት ነበር የወሮ መንደር ህዝብ እንግዳዋን ለመቀበል እንደ ንብ
ሁሉም በየድርሻው ይተማል፡፡...

💫ይቀጥላል💫
20👍17🥰3
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ የቀይ አፈር መንደር ገና እያዛጋች ነው፡፡ ካርለት ጥቁርና ቡናማ ቀለም ያለው የፍዬል ቆዳዋን ለብሳ አንባሯን ጨሌዋን አንገቷ ላይ ደርድራ ቀለበቶችዋን በጣቶችዋ ሰክታ ጥልፍልፍ ነጠላ ጫማዋን ተጫምታ እቃዋን በጀርባዋ በማዘል ከከተማው ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ትንሽ ሄደችና ሰፊውን የአርባምንጭ መንገድ ትታ ወደ ግራዋ በመታጠፍ ወደ ዲመካ…»
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የንጋት ፀሐይ ከወደቀችበት ተነስታ ብርሃኗን ሐመር
ላይ ፈንጥቃለች፡ ካርለት ከወሮ መንደር ሆና ቁልቁል የሐመርን ተፈጥሮ ደኑን የልጃገረድ ጡት መስለው በሰማዩ ደረት የተሰካኩትን የአለሌ  ኤሎ ኤዲ ቢታ… ተራራዎች ስታይ
የምትሆነው ጠፋት ልብ ሰራቂው ተፈጥሮ አነሆለላት እና! ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ወደ ተፈጥሮ ሮጠች ተፈጥሮም ወደ እሷ ገሰገሰች ተቃቀፉ.. አንዱ የሌላውን ሽፋን አወለቀ… አየሩን ሳመችው... መሬቷን አቀፈቻት... ቅጠሉን ሰበሰበችው…ከወፎች ጌር
ሽቅብ ጎነች… ዳመናውን እየበረቃቀሰች በረረች የተፈጥሮ ፍቅር

የሐመር ተፈጥሮአዊ ሕይወት እንደ ቅንቡርስ በውስጧ ገብቶ በሰራ
አካላቷ ተንከላወሰባት ! እንደ እንበሶች ቦረቀች….. ፈነደቀች ከማራኪዋ ተፈጥሮ ጋር እየደጋገመች ተወሳሰበች…..

እንዲህ በደስታ ሰክራ በድካም ጥንዝል ዝርግትግት ብላ
ሳሩ ላይ እንደተንጋለለች የሰው ድምፅ ሰማች፡፡ 'ምን ነበረበት ከእንደዚያ ካለው ዓለም የማይመለሱ ቢሆን!'

ካርለት!

“አቤት" አለች ዞር ብላ እያየች ካርለት፡፡ “ጎይቲ ነይ
እስኪ አጠገቤ ቁጭ በይ"

“ይእ! ምነው እስካሁን ሳትጠይቂኝ ቀረሽ?''

“ምን ብዬ ጎይቲ?

"ይእ! አሁን እውን እሱ የሚረሳ ሆኖ ነው፡ ናፍቆትሽን ውስጥሽ ቀብረሽ ደብቀሽኝ እንጂ…" ያ ሐጫ በረዶ መሳዩን ችምችም
ያለ ጥርሷን እያሳየቻት ጠየቀቻት፡፡

“ደልቲን ነው! ምን ብዬ ልጠይቅሽ? ወሮ እንደማይኖር
አውቃለሁ፤ ዛሬ ግን ሄጀ ላየው እፈልጋለሁ  ናፍቆኛል!"

ጎይቲ ናፍቆኛል የሚለው አባባል የእሷንም እሳት
ጫረባት ወዲያው ገለባው ልቧ ቦግ ብሎ ነደደ፡

“ይእ! ካርለቴ አያ ደልቲ እኔንም ናፍቆኛል ግን የት ሄጄ ላግኘው" ብላ እንባዋ እንደ በጋ ዝናብ የመጣበት ሳይታወቅ ዥጉድጉድ ብሎ ወረደ፡፡ የሳግ ብርቅታ የውስጣዊ ስሜት
ነጎድጓድ… ጎይቲን ደፈቃት፡፡ ካርለት ደነገጠች ደስታዋ በኦንድ ጊዜ ሙሽሽ አለባት፡፡

“ጎይቲ ምን ሆነ? ካርለትን ጩሂ ጩሂ ብረሪ ብረሪ
አሰኛት፡፡ ጎይቲ ግን ካርለት የጠቀቻትን አልሰማችም! በአይነ ህሊናዎ ጀግናዋ እየተንጎማለለ ሲጓዝ አየችው፡፡ ስታየው አቅበጠበጣት ልቧ ዳንኪራ ረገጠባት… ሊርቃት ሆነ፤ መጥራት ፈለገች፡፡
ካልጠራችው እየተንጎማለላ ሄዶ ጫካው ውስጥ ገብቶ ይጠፋባታል፡፡

“አያ ደልቲ!” ተጣራች ጎይቲ ጮክ ብላ እንዲሰማት፡፡

ምን ሆነ ደልቲ" ካርለት ጎይቲን እየነቀነቀች ጠየቀቻት ጎይቲ ግን የጠራችው አንበሳዋ ዞር ብሎ የጠራውን ሰው በአይኖቹ ሲፈልግ የጡቶችዋ ጫፎች እየቆሙ ሰውነቷን እየነዘራት ወደ እሱ
ስትጓዝ ድንገት ጀግናው እየተንጎማለለ ጫካ ገባ፡፡ ሮጠች! እንቅፋቱ
መታት እሾሁ በልቧ ተሰገሰገ… ጫካው ደልቲን ሸፈነው ዋጠው
ለለቀጠው... ስለዚህ ድምጿን ከፍ አድርጋ ተጣራች፡

“አያ ደልቲ ጮኸች ጎይቲ፡፡ ካርለት ግን የምትሆነው
ጠፋት፡-

“ጎይቲ- ደልቲ ምን ሆነ?" ካርለት ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት
አቅም አነሳት• ድካሟ አገረሸ፡፡ ጎይቲ ደግማ ደጋግማ አለቀሰች
እውነተኛውን ደም መሳዩን እንባ!

ደልቲ ምን ሆነ ደ-ል-ቲ ካርለት እንባዋ ግድብን ጥሶ ወጣ› ጎይቲና ካርት ተቃቅፈው ልቅሶአቸውን አስነኩት፡፡

“አያ ደልቲ" እያሉ ጮሁ፤ የገደል ማሚቶው ግን
ድምፃቸውንም ደልቲንም ዋጠው…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ለምን አለቀስሽ?" አላት ከሎ ሆራ፡፡ ቲማቲም
የመለለ ፊቷን እያዬ:

እንዲሁ ጎይተን ምን እንደሆነ ደጋግሜ ስለጠይቃት…"አቋረጣት ከሎ፡-

“ጎይቲ ምን አለችሽ ታዲያ?

“ምንም"

“እንግዲያው ለምን አለቀስሽ?''

“እንጃ ክፉ ነገር የደረሰበት መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከማጣራቴ በፊት ግን እንደዚህ መሆን አይገባኝም ነበር ይቅርታ! አለች ካርለት፡

ከዚያ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ፡፡

“ከሎ አንተ ግን ለምን አትነግረኝም?"

“ምኑን?

“ስለ ደልቲና ስለ አጋጠመው ሁሉ፡፡"

ካርለት ምን ብዬ ልንገርሽ? ጎይቲ እንደዚያ መሄጃ
መቀመጫ አሳጥታኝ መኪናዋን አስተኛሃት! እያለች ወትውታኝ
ካለረፍት ተጉዘን እዚህ ስንደርስ ደልቲ አልነበረም

“ቡስካ ሄዷል' አሉንና እዚያ ሄደን ስንጠይቅ ዳራ የምትባል የሳላ መንደር ልጃገረድ አብራው እንደተቃበጠችና ደልቲ
መቀመጫውን ሰርቶ እንደሄደ ወይሳ እየነፋ ያም እንደነበርና በእርግጥ አልፎ አልፎ ትክዝ ይል እንደነበር ሰማን፡፡ ከዚያ የላላም
የሻንቆም የቡስካም ሰው ዳግመኛ አለማየቱን ተረዳን፡፡

“ጎይቲ ይህን ጊዜ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች መጮህና ማልቀስ ጀመረች፡፡ ዳራ በበኩሏ ጎይቲ ስታለቅስ እሷም በተራዋ ትንፈቀፈቅ
ጀመር” ብሎ ከሎ ገጠመኛቸውን ሊቀጥል ሲል፦

“ከዚያስ ተገኘ? ካርለት  ረጅሙን ታሪክ መከታተል
አልቻለችም! ሲቃ ያዛት፡፡

“ከዚያማ ጫማ ጣዮች እንዲተነብዩ ተጠየቀና “ክፉ
አልደረሰበትም፧ ራቅ ብሎ ግን ሄዷል' አሉ፡፡ አንጀት አንባቢዎችም ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ብለው የታያቸውን ተናገሩ፡፡ጎረምሶች ጫካውን ደአሰሱት መልዕክት በየአቅጣጫው ተላከ ከዚያ  በካሮ  ማህበረሰብ በኩል ያሉት የደንበላ መንደር ሰዎች አየነው ብለው መናገራቸውን ሰማን፡፡

እኔም የአንችን መኪና ይዤ በየመንደሩ ለፍለጋ ዞርሁ
አሁን ደንበላ አይተነዋል እሚለውን ስንሰማ ግን እሱን ልፈልግ ወይንስ አንቺን አዲሳባ ሄጄ ላምጣ በሚለው ከሽማግሌዎች ጋር ስማካር አንች መጣሽ?

ከወጣ  ማለቴ ከሄደ ስንት ጊዜ ሆነው?

"ሃያ ቀን በላይ ሆኖታል፡"
እሽ ለምን ነው አንዳንዴ ከፍቶታል የተባለው?"

“ጎይቲን ያፍቅራታል፡ የአንድ ቤተሰብ አባል በመሆናቸው
እንጂ አብሯት ቢኖር ደስታውን አይችለውም ነበር፡፡ ስለዚህ ከአይኑ
ስትርቅ ላይከፋው ሳይተክዝ አልቀረም። ስለ አንችም ደጋግሞ ያነሳ እንደነበር ሰምቻለሁ የእሷ መባለግ አንሶ ጎይቲንም ይዛት ሄደች!  እያለ እንደሚቆጭ ኮይታውን ከፍሉ እንደጨረሰ አንችን ሲያገባ ያንን
ለስላሳ ገላዋን እገለብጠዋለሁ' እያለም ሲፎክር እንደነበር ሰምቻለሁ" አላት ከሎ ፈገግ ብሎ።

እውነቱን ነው የሐመር ልጃገረድ ነኝ ብዬ ባህሉን
መቀበሌን አሳውቄ! ካለ ሽማግሌ ፈቃድ ያውም ከሐመር ምድር ርቂ መሄዴ በእርግጥ ሊያበሳጨው ይገባል" አለችና በሃሣብ ተውጣ ቆየች፡፡

እንዲህ ካርለትና ከሎ በሃሣብ ተውጠው እንደተቀመጡ ጎይቲ አንተነህ መጣች

“ይእ ምን ሆናችኁል?"
አለቻቸው ሁለቱንም በፍርሃት አየቻቸው ሆዷ ፈራባት “ጎይቲ ምንም አልሆነም፡፡ አንችን
ጠይቄ ልትነግሪኝ ያልቻልሽውን ስለ ደልቲ ከሎን እየጠየቅሁት ነበር"

“እሁሁ… እኔስ ደሞ ምን ሰማችሁ ብዬ የሆንሁትን
አላውቅም" አለችና ሐጫ በረዶ ጥርሶችዋን አሳይታ

“ይእ! የአያ ደልቲን የኦሞ ዳር ጥንቅሽ የቀመስን እኔና
አንች ሌላው ጣምናውን የት ያውቀዋል" ብላ በሣቅ ተፍለቀለቀችና

ነይ በይ አሁን ቡና ጠጭ እህልም ባፍሽ አድርጊ፡፡
የደንበላ ሰዎች “አይተነዋል ብለዋል እንኳን እስካሁን ደና ሆነ እንጂ ከአሁን በኋላስ ከምስጥ ዋሻ ቢገባም አያመልጠን፡፡ ይእ!

አንተስ ና እንጂ  ይኸውልሽ ከመጣን ጀምሮ አበሳውን እያሳየሁት ነው፡፡ ና በል የኔ ጌታ.." አለችውና ከሎን ሶስቱም ተያይዘው በር ወደሌለው የሐመር ጎጆ ሄዱ!
👍291👏1