"በፍፅም፤እኔ ዳግመኛ ወደእዛ ሆስፒታል አልመለስም...አእምሮዬ ንፅህ ሆኖ በተረጋጋ መንፈስ በሽተኞችን ማከም የምችል አይመስለኝም።እና ደግሞ ከዛ ሽማግሌ ጋርም የጋራ ቢዝነስ እንዲኖሰኝ አልፈልግም..ሙሉ ያለኝን የአኪሲዬን ድርሻ እሽጥና የእኛ የራሳችን ድርጅት እንከፍታለን።
"ስለእሱ ለማሰብ በቂ ጊዜ አለን …አሁን የሠዎቹ ጉዳይ ነው አሳሳቢው።"
"ምን እናርጋቸው?"
"ውሳኔው ያንቺው ነው ..እናስወግዳቸው የምትይ ከሆነም ችግር የለውም..ለህግ ተላልፈው ይሰጡ የምትይ ከሆነም"
"ግራ ገባኝ እኮ...እነሱን ለህግ አሳልፎ መስጠትም ለእነሱ ድል ነው፤እነሱን መግደልም ያው ከእነሱ ጋር አንድ መሆን ነው››
‹‹እኔ በፍቃደኝነት እራሳቸውን እንዲያጠፍ ነበር እቅዴ ...አሁን ግን ያ ሚሰራ አይመስለኝም… በተለይ ለኘሮፌሰሩ››
"ለምን?››
‹‹ አንደኛ የፅንሱ ጉዳይ አለ (ምንም ቢሆን የልጅሽ አባት ነው) ወደፊት ለልጅሽ ምን ብለሽ ትነግሪዋለሽ።ሌላው እኛም ትንሽ ደብድበነዋል አንቺ ደግሞ አቆሳስለሽዋል..በዚህ አይነት ሁኔታ እራሱን አጥፍቶ ሬሳው ቢገኝ ምርመራ መደረጉ አይቀርም፤ምንም እንኳን የበሰበሰ ወንጀለኛ ቢሆንም በግለሰብ እጅ በዚህ መጠን እንዲሰቃይ ህግ ስለማይፈቅድ ዞሮ ዞሮ መጠየቃችን አይቀርም።"
"ሙሉስ?"
"እሱ እንኳን ጥፊም አላረፈበትም ... "
"እንግዲያው አንተ የመሠለህን አድርግ...እኔ በአንተ ውሳኔ እስማማለሁ…አሁን ደክሞኛል ትንሽ ልረፍ"
"አዎ ተነሽ እረፊ..."
///
አይገርምም ግን አንዳንዴ የእግዜር ስውር እጆች ሳስብ እደነቃለሁ።ጠላቴን ለማጥፍት ቀስቴን አዘጋጅቼ ነበር ። የቀስቴንም ጫፍ ከበረሀ እባብ የተቀመመ በሁለት ደቂቃ ውስጥ አፍርጦ የሚገድለው መርዝ በጥንቃቄ ጫፍን ቀብቼ አነጣጥሬ ኢላማዬ ውስጥ እስኪገባ በእጆቼ ወጥሬ በአይኖቼ አጨንቁሬ እየጠበቅኩት ነበር...ግን ድንገት ደመና በሌለበት ዶፍ ዝናብ ዘነበና መርዙን ከጫፉ አጠበው ..አሁን ምን ላድርግ ?። ተረጋግቼ ማሰብ አለብኝ እቅዴን መከለስ አለብኝ።ይሄንን እያሰበች ያለችው ክፍሏ ቁጭ ብላ ነበር ..ከዛ ከበቡሽ እቤቷ ሄዳ ያመጣችላትን ቦርሳ አነሳችና ከፈተች…ውስጡ ያሉትን እቃዎች በጠቅላላ ውስጡ ተወችና አንድ ኪኒን ብቻ ከመሀከሉ አንስታ መኝታ ከፍሏን ለቃ ወጣች፡፡ቀጥታ ፕሮፌሰሩ ወደሚገኝበት የአብዬት ክፍል ነው ያመራችው፤ገፋ አድርጋ ገባች፤ፕሮፌሰሩ እግሮቹን ወዲህና ወዲያ ማዶ አንፈርክኮ አይኖቹን ወዲህና ወዲያ በፍረቻ የያወራጫ ተጋድሞል....ቶላ በራፉ ጋር ባለ ወንበር ቁጭ ብሎ እየጠበቀው ነው፡፡
‹‹ቶላ አንዴ ይሄንን ሰውዬ ማናገር እፈልጋለሁ ውጭ ትጠብቀኛለህ››አለችው
.ምን አልተናገረም…ብድግ ብሎ ወጣና በረንዳው ላይ ከውጨ በኩል ቆመ፤ እሷ ከውስጥ በራፉን ቆለፈችው … .አልጋው ላይ የተሰተረው ፕሮፌሰር ተስፋ ቆረጠ…. በቃ ልትጨርሰው እንደመጣች እርግጠኛ ሆነ…፡፡
‹‹እሺ ፕሮፌሰር ተሸለህ..?ወንበሩን ይዛ ወደእሱ ተጠጋችና በሁለት ሜትር እርቀት አስቀመጠችው.ረጋ ብላ ተቀመጠችበት
‹‹አረ በፈጠረሽ..አሁን ደግሞ ምን ልታደረጊኝ ነው?››
ምን አደርግሀለሁ.. አሁን ኮ ጥቅም የሌለህ ሙትቻና እሬሳ ሆነሀል…ከወር በፊት በዚህ ሀገር በጣም የተከበረክ ሙሁር….እጅግ የተሳከለት የቢዝነስ ሰው….ሙሉ ጤና የነበረህ ውብና ሽቅርቅር ሰው ነበርክ..ግን ዛሬ ተመልከት… መሁርነትህ መክኖ፤ ዝናህ ተኖ፤ ጤናህ ታውኮ ፤ውበትህ ይሄው እንደማየው ከስሞ አልባሌና ተራ ሰው ሆነሀል…ይሄም ሊሆን የቻለው በማን ነው በአንተው ስግገብግብነት..
አየህ አንዳንዴ የሰላ ጭንቅለትና አሰላሳይ አዕምሮ ስላለን ልዩ ሰዎች ነን ማለት አይደለም..ስለምንድነው የምናሰላስለው ?ችሎታችንን ለምን ጉዳይ እየተጠቀምንበት ነው….?ብለን ቆም ብለን አስበን እንደው በጊዜያዊ ፍላጎታች ተገፋፍተን መንገድ ስተን እንኳን ከሆነ ወዲያው እራሳችንን ገምግመን ወደትክክለኛው መንገድ በጊዜ መመለስ ካልቻልን የእኛ ምሁርነት የእኛ አዋቂነት ምንደነው እርባናው…?
ሰው ያለውን እውቀት ፤ዝናና ስልጣን በአግባቡ ካልተገለገለበት…ፕሮፌሰር ሆነ ሚኒስቴር ፤ሼኪ ሆነ ቄስ….ጀኔራል ሆነ ካፒቴን ያው ሄዶ ሄዶ ለውርደት ተዳርጎ ተራ ሰው ሆኖ እንዲህ እንደአንተ ተልከ ስክሶ መቅረቱ አይቀርም..እነዛ ሰሞች አነዛ ማዕረጎች በሚገባ ለሚጠቀምባቸውና በምስጋና ለሚያገለግልባቸው ብቻ ነው እስከመጨረሻው በክብር አብረውት የሚቆዩት፡፡ዳሩ ይሄንን ሁሉ ለአንተ መለፍለፉ ምን ይረባል….በዛ በሰላሙ ጊዜ በፍቅር እያነባው ከድርጊትህ እንድትታቀብ ስማፀንሀ ጥቂት እንኳን ሰምተሀኝ ቢሆን ዛሬ ባንተም ሆነ በእኔ ላይ ይሄ ሁሉ ጥፋትና ውድመት አይፈጠርም ነበር፡
ፕሮፌሰሩ የደ/ሯ ንግግሯን የደከመ መንፈሱን እየሰባበረው ነው…ምንም ትክክል ያልሆነ ንግግር አልተናገረችም፡፡
‹‹ትክክል ነሸ ..ላደረኩት ነገር ሁሉ በጣም አዝናለሁ…መኝታ ቤቴ አልጋዬ ያለበት ቦታ ላይ ወለሉ የሚነሳ ነው.. እዛ የተቀበረ መቶ ሚሊዬን የሚጠጋ ብር አለ…አንድ ነገር ከሆንኩ አስቆፍረሽ ውሰጂው…እቤቱም ያለው ባንቺ ስም ነው…ለሰርጋችን ስጦታ ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ነበር ባንቺ ስም ያዘዋወርኩት…እና እቤቱም ሆነ ብሩ ለልጄ ይሁንልኝ፡፡
‹‹ልጅህ …››በእጇ የያዘችወን መድሀኒት አሳየችው….አይኑን አፍጦ… .‹‹ምንድ ነው?›› አለት..ከእይታው .ሰለራቀ መለየት አልቻለም፡፡ችግሩን ስለተረዳች ወደ እሱ በደንብ አስጠጋችለት››
የኪኒኑን ምንነት ሲረዳ ሰውነቱ ተንዘረዘረ‹‹አይሆንም…እንዳታደርጊው በፈጠረሽ››
ድምፅንና ጉልበቱን ከየት እንዳመጣው አያውቅም..አጓራ..ተማፀናት፡፡
እሷ ግን በእሱ መቃተት እየተደሰተች… ኪኒኖቹን ከእሽጉ ማውጣት ጀመረች..
‹‹አይሆንም ...በፈጠረሽ..››አልጋው ላይ እንዳለ እጅን ዘርግቶ መድሀኒቱን ሊነጥቃት ቢሞክርም ሊደርስባት አልቻለም… መንጠራራቱን ሲጨምር ከአልጋው ላይ ተንደባለና ወደቀ ..የብልቱን ቁስል በእግሮቹ ስለተጨፈለቀ በስቃይ ድምፅ አጎራ…
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

👍31
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
“…ሶራ- የባህል ትንሽ ትልቅ አለው ብዬ ላነፃፀር
አልሻም። ልምዴና እውቀቴ ገና ውስን ነው: የባህል ልዩነት ግን አኗኗር ልዩነት እንደሚያመጣ አውቃለሁ፡፡
“ሁሉም ሰው ያለበትን አካባቢ ከሌላው በተሻለ ያውቃል! ይጠቀማል አያቴም ከለመደው ባህል ወጥቶ ካለፍላጎቱ ወደ
አለመደው ባህል ከመጣ በኋላ አስተሳሰቡ ከዘመነው ህብረተሰብ አንፃር ያነሰ ቢሆንም ከዚህኛው ህብረተሰብ የተሻለ ትዕግስትና ጨዋነት የነበረው ከዚህኛው የነበረው በመሆኑ ሴት አያቴን አስባውና
አልማው ያልነበረውን በጥቁር ፍቅር እንድትንቦራችና አያቴ ከዚህ
ዓለም በሞት ከተለየ በኋላም ፍቅሩ ጥቁር ድመት አቅፋ እንድትውል አድርጓታል፡
“ወንድ አያትሽን በመልክ ታውቂያቸዋለሽ? ሶራ ጠየቃት:
“ልጅ ነበርኩ እንጂ አስታውሰዋለሁ። ከእንጨት ጠርቦ የሰራት ትንሽና ልዩ በርጩማው ላይ ቁጭ አንዳንዴም ጋደም ብሎ
ይንተራስና ሽቅብ ሽቅብ እያየ ሰማዩ ላይ ማፍጠጥ ይወዳል:
“እኔም ከሌሎች ጋር ስሆን መዝለልና መጫወት
እንደማልወድ ሁሉ እሱ ደረት ወይ ትከሻ ላይ ሆኜ ግን ለረጅም ጊዜ
ከሚቆዝመው ጥቁርና ልዩው አያቴ ጋር ፀጥ ስለምል ሴት አያቴ፡-
“ሎካዬ! ካንተ ጋር ስትሆን ለምን ዝም እንደምትል
ታውቃለህ?" ስትለው ዘወር ብሎ ወይም አይኖቹን ከሰማዩ ላይ መልሶ ያያታል።
“ስለምትፈራህ ነው አንተ ስ
ለህፃንም ለአዋቂም ዝግ ነህ አዕምሮህ የዕድሜ ልዩነትን አይገምትም! መሣቅ መጫወት ለልጆች
ምን ያህል ጠቃሚ መሆኑን አታስብም…” ትለውና ለመውሲድ እጅዋን ስትዘረጋልኝ በእንቢታ ደረቱ ውስጥ ድብቅ እላለሁ፡
“ወለላዬ! ሂጂ፤ አብረሽኝ መሆንሽን እየዘነጋሁ በዝምታ እኔ የምፈራው አንሶኝ አንችንም አስፈራሁሽ ውሰጃት :ኜስ
ላጫውታት አልታደልሁም" ይላታል። ያን ጊዜ በትናንሽ እጆቼና እግሮቼ ቁልፍ አድርጌ እይዘውና “አልሄድም' እላለሁ
“ያኔ ሴት አያቴ ትኩር ብላ ታየንና ቀስ ብላ መጥታ
ትከሻውን ተደግፋ! …ሎካዬ ለምን ደስተኛ አትሆንም እወድሃለሁ እኮ መሣቅ መጫወት ግን ልትለምድልኝ አልቻልክም: ለምን
ታሳቅቀናለህ! ስትለው ዝም ብሏት ይቆይና፡-
"አኜስ እባክሽ ተይኝ" ይላታል:
ከኔ በላይ የሚቀርብህ ማን ሊመጣ ይችላል፡፡ ጭንቀትህ ውስጣዊ ብሶትህ ጊዜ የማይሽረው ዝምታህ ምንድነው?” ስትለው፡-
“የአባቴ ልማድና ወግ ከብቶቼ…"ሃሳቡን ሳይጨርስ
አይኖቹን ይጨፍናል
“የአንተ አገር ከብቶች ከኛ ይለያሉ?"
“እንዴታ! ይለያሉ እንጂ።"
“በምን?”
“በማእረግ ፧ አኜስ! ከብት ከስጋና ወተቱ ይልቅ ቅሩ
ያጠግባል። በምላሱ ሲልስሽ በሽንቱ ስትታጠቢ እነሱ እያገሱ አንች
እያንጎራጎርሽ ስትከተያቸው
ስትውይ የሆዳቸውን
ጩኸት እያዳመጥሽ
ትንፋሻቸውን እየሞቅሽ
አብረሻቸው ስትተኝ…
የህይወት ቁርኝቱ የተፈጥሮ ሰንሰለቱ በፍቅር የተገመደ ነውር ።
“እዚህ ግን ከብቶችና እኔ አረም ነን። የምግብ ክምር
ይሰጠንና ታስረን የምንውል ማግሳትና ማንጎራጎር የማንችል…"ሲላት ሴት አያቴ በወንድ አዬቴና ላይ ያለ የሌለ እርግማን ታወርድበታለች፡፡
“ምንም ሳይመልስላት አይኖቹን አድማስ ላይ ይተክላል። የእጅ ጣቶቹ ግን የሰራ አካላቴን ሳይታክቱ
ስለሚደባብሱኝ የመጨረሻውን ሳላውቅ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ይወስደኛል፡፡
“እና! የሴት አያቴ ዘመዶች ሴት አያቴን፡
“አፍሪካዊው ሎካዬን በማግባቷ ብዙ ነር ጎድሏታል እያሉ
ኢያቴን ለምን አብራው እንደምትኖር ሲጠይቋት-
ዝምታው ልቤን በፍቅር የባህር ጨው አድርጎታል::
የፍቅር ነፃነቴም ያስደስተኛል ሎካዬን እንለያይ ብለው እሺ እህትና ወንድም እንሁን 'እንዳልሽ' ከማለት ሌላ ታቃውሞ ግዴታዬ መለማመጥ ፍርሃት ስለማላይበት ከእሱ መለየት የማይታሰብ ነው ብላ አፋቸውን ታሲዛቸዋለች:
“ወንድ አያቴ ሎካዬ በግር መጓዝም ይወዳል! በተለይ
በረፍት ቀኑ ከተማው መሃል ካለው መናፈሻ የተወራረደ ሰው ሄዶ አያጣውም እፅዋት ስር ይገባና አላፊ
አግዳሚውን ሳያይ እንደ ስነ
ፍጥረት ተመራማሪ አይኑን ሰማዩ ላይ ሰክቶ በርጋታ ለብዙ ጊዜ ይቀመጣል።
ሶራ ወንድ አያቴ ማንም ሊረዳው ከሚችለው በላይ ውስጡ ናፍቆት ትዝታ የቦረቦረው ነበር ዘመናዊነት ደስታን ሊፈጥርለት አልቻለም በረጅሙ ህይወቱ ካገኘው ልምድ ይልቅ
የልጅነት ዘመነ ትዝታ እሱነቱን ሽፍኖለታል: ድሮ ስለ አያቴ ባሰብኩ ቁጥር የሱን ትውልድ ቦታ እንደ ገነት እቆጥረው ነበር።
እናቴ ግን አፍሪካ ድህነት ችግር….የተከመረባት ሰዎቹም እርስ በርሳቸው የሚበላሉ እንደሆኑና ሲኦል እንጂ ገነት እንደሊለባት
ስትነግረኝ ሌላ ሃሳብ በአእምሮዬ መፈጠር ጀምሮ ነበር። ይህች አለም ጥቁርና ነጭ አምላክ ያላት ሁለት ገነት የሚገኝባት ሆና
አንዱ የሌላው ጠላት እንደሆነ ይስማኝ ነበር፡፡
"አያቴ ስለ ወንድ አያቴ ሁለት ተቃራኒ እምነቶች ነበሯት በአንድ በኩል ዝምታውንና ጅንነቱን የምትወድለት ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ አብረው ለመዝናናት ለመወያየት ስለማይችሉ ፀጉሯን እየነጨች ትበሳጫለች ያም ሆኖ ግን እናቴ እንደነገረችኝ ከሆነ
አያቴ ለወንድ አያቴ በተደጋጋሚ በፍቅር ስትናዘዝለት ሰምታታስች
ለምሳሌ እንድ ቀን አያቴ ከሁዌልቫ በስተምእራብ አስራ አምስት ኪሎሜትር ላይ ከሚገኘው የብርቱካን ማሳቸው አያቴን ይዛት
ትሄዳለች እዚያ ሲደርሱ ግን ወንድ አያቴ አልነበረም፡
“ስለዚህ እናቴ ከሪና ሁሌም እንደምታደርገው ወደ ብርቱካን ማሳው ገባ ብላ ብርቱኳን እየላጠች ስትበላ የቀሚሷ ጫፍ እየያዘች
ስትዘፍንና ስትዝናና ቆይታ አያቴን ወደተለየችበት ቦታ ስትመጣ አያቴን ታጣታለች።
“ደጋግማ ተጣርታ ወይ የሚላት ሲጠፋ የትም አትሄድም በሚል እራሷን አረጋግታ አያቴን አኜስን ስትፈልጋት እመስኖው
ውሃ ቦይ ትደርስና ውስጡ
ገብታ እየተንቦጫረቀች ስትሄድ የመስኖውን ውሃ ከሚስበው ሞተር ቤት ደረሰች፡፡
የሰው ድምፅ የሰማች መስሏት ፀጥ ስትል ድምፁ
ጠፋባት፡ ልትጣራ ፈለገች
ከመጣራቷ በፊት ግን ቀርቦ የራቃት ድምጽ ተመልሶ መጣ! ከሞተሩ ቤት የሚመጣውን ድምጽ በጆሮዋ ያዘችው። የሚያቃስት ሰው ድምጽ ነው የእናቷ! ደነገጠች ወደ
ሞተሩ ቤት ሄዳ በፍርሃት በጭላንጭል አየች እናቴን ከእግር ጥፍሯ እስከ ጸጉሯ አንዳች ነገር ነዘራት፡፡ ድምፁ እንደገና ቀሰቀሳት
አያቴ አኜስ ናት! ድምፅዋ ቁርጥርጥ እንደሚቀጣ ህፃን ትንፋሽዋን በሲቃ ውጥር ይልና ደሞ ይጠፋባታል፤
በመጨረሻ ድምፁ
መጠኑን ጨምሮ መጣ
የሁለት ሰው ድምፅ የሉካዬና አኜስ ጨመረ ድምፁ እናቴ ተጨነቀች። ልትሮጥ ዘወር ስትል
የፎይታ ድምጽ ሰማች። ከዚያ አያቴ ተረጋግታ ስትናገር ሰማቻት፡
“አመሰግናለሁ ሎካዬ የልቤን ነው ያደረስከው ከከሪና ጋር ወደ አንተ ስገሰግስ እንዲህ አንጀቴን እንደምታርሰው እርግጠኛ
ነበርሁ። የውጭ በግ…
የልጋ ላይ ግን አንበሳ ነህ. ብላ ስትናዘዝላት እናቴ አያቴን ሰምታታለች።
“ይህ ደግሞ ሴት አያቴ
ወንድ አያቴን የምታፈቅረው
በዲፕሎማሲያዊ አነጋገር በዝምታው ነው ትበል እንጂ ጌታውን እንዳዬ ውሻ እግሩ ስር የሚያልወሰውሳት ሚስጥሩ ሴላ ነው፡፡
ሶራ የሚገርምህ ግን እናቴ ያችን ቀን ፆታዬን
ያወቅሁበትና ረሃቤን ለማዳመጥ ትእግስት የጎደለኝና የተመኘሁትን
ያጣሁበት ቀን ናት' ብላ ታስታውሳለች፡፡
ይህ በሆነ ከአምስት ዓመት በኋላ ግን እናቴ ከአባቴ
ከፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ ጋር ከሁዌልቫ ወደ ሊዝበን ለጉብኝት ስትሄድ
ተዋውቀው ግንኙነታቸውና መግባባታቸው እየጨመረ ሲሄድ የብርቱካን ማሳቸውን ልታሳየው ቀጠረችው፡፡

👍32
“በቀጠርው ቀን እጁን ይዛ በብርቱካን ማሳው ውስጥ
ስትዘዋወር ብርቱካን እየላጡ እየተከፋፈሉ በመጎራረስ ሊጨዋወቱ
በመጀመሪያው የመስኖ ውሃውን ቀጥላ ደግሞ የሞተር ቤቱን አየችው: ወዲያው አምስት ዓመት ወደኋላ በትዝታ ተጓዘች:
ፊልሙ መጣባት ድምፁን ሰማችው ፧ ፔሶ ቤኒ በትዝታ የቦዘውን አይኗን እያዬ ምን እንደሆነች ጠየቃት! አይኗ ስልምልም አካሏ ዝልፍልፍ ሲል ጠጋ ብሉ ደገፋት፡
“የኔ ቆንጆ ምነው?" አላት ተጨንቆ እቅፍ አድርጎ ወደ
ደረቱ እያስጠጋት
“እዚያ…” አለች::
“ምን?'' አላት ወደ ሞተሩ ቤት እያዬ።
“እዚያ እንሂድ" አለችው እንደተባለው ይዟት ሄደ
ከአምስት ዓመት በፊት ፊልሙ ከተሰራበት ስፍራ ሄደው ተቃቀፉ ፊልሙ ጀመረ፤ ድምፁ ተሰማ ከተዋናዩ በቀር ተመልካች የሌለው ድንቅ ፊልም ታዬ፡"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአያቷን አደራ ለመፈፀም ቆርጣ የተነሳችው ኮንችት ስለ ኢትዮጵያ የማወቅ ፍላጎቷ ጨምሯል ሶራ ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ
እንዲያሳውቃት እስከአሁን እድል አልሰጠችውም ከአለም ካርታ ላይ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በስተ ምስራቅ እሷ ካለችበት ስፔን ደግሞ በስተ ደቡብ ምስራቅ እንደምትገኝ አውቃለች፡፡
በዓለም ካርታ ላይ የጣና ሐይቅና አባይን ሸበሌን አዋሽን ኦሞን ወንዞችን 4620 ከፍታ ያለውን የራስ ዳሸንን ተራራ 4200
ከፍታ ያለውን የጉጂን ተራራ አይታለች፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራውን ከጀመረ አርባ አምስት አመት እንደሞላው የመጀመሪያውን አገር ውስጥ በረራ እ.ኤ.አ
1946 ዓ.ም እንዳደረገ በዚያው አመት አለማቀፍ በረራውን ከርእሰ ከተማው አዲስ አበባ ወደ ካይሮ በመብረር አሀዱ እንዳለ! በአገር ውስጥ 30 የበረራ ጣቢያዎች በ.ኤቲ.አር 42 ዲ.ኤች 5 ዲ.ኤች ሲ 6 እንደሚጠቀምና ከአገር ውጭ ደግሞ ከ35 ሀገሮች በላይ እንደሚበር ዘመናዊ የሚባሉት የቦይንግ 757 እና 767 ኤሮፕላኖች
ባለቤት መሆኑንም አውቃለች፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ 13 ወራት ፀሐይ የማይለያት ክረምትና በጋ በሚባሉ ወራቶችዋ በሁለት የተከፈለች የአየር ፀባይዋ
ደጋ ወይናደጋና ቆላ ተብሎ የተከፋፈለ 1.112.000.00 ስኩየር
ኪሉ ሜትር የቆዳ ስፋት ያላት የአለም ህዝብ የሚወደው የቡና ምርት መገኛ አርኬዎሉጂ ጥናት 4.3 ሚሊዮን ዓመት የቆዬ
ቅሬተ አፅም የተገኘባት ከኮሊያሊስቶች ወረራ በጀግኖችዋ ተጋድሎ
ራሷን ጠብቃ ነፃ ሁና የኖረች ታሪካዊ አገር መሆኗን አጥንታለች
በመናዊነቷ ስሟ የማይጠቀሰው ኢትዮጵ
በታሪካዊ ቅርሷ በተፈጥሮዋ በእንግዳ አክባሪው ህዝቧ በታሪክ ተመራማሪዎች በቱሪስቶችና በአንዳንድ ፀሐፍት የተሰጣትን መልካም ሙገሳም
አንብባለች፡፡
ከዚህ ውጭ ግን ኮንችት ከሶራ ብዙ ነገሮችን ማወቅ
ስለምትፈልግ አንድ ቀን ማስታወሻዋን አውጥታ
“ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ክፍለ ሃገራት ወይም መንግስታት አሉ? አለችው።
“ወደ አስራ አራት አካባቢ" አላት እየተጠራጠረ።
"ከነዚህ ውስጥ ስንቱን ታውቃለህ?"
“ሶስቱን።"
“ማን ማንን?"
“ጋሞጎፋን ሸዋን ሲዳሞን"
"አገራችሁ ውስጥ ስንት ታሪካዊ ቦታዎች አሉ?
“በቁጥር አላውቃቸውም። ጎንደር ላሊበላ ሶፍ ኡመር,
አክሱም…"
“ከነሱ ውስጥ የቱን የቱን አይተሃል"
“ሁሉንም አላየሁም:"
“ለምን?
“ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ባህል አይደለም።“
“ታዲያ ታሪካዊ ቦታዎችን ካላየህ በየቦታው ያለውን
ተፈጥሮ ካልጎበኘህ ኢትዮጵያዊነትህን አፍሪካዊነትህን እንዴት
ማፍቀርና ማክበር ትችላለህ" በትዝብት አየችውና “በረፍት ጊዜ
ምን ታደርጋለህ?"
ቤት መዋል መጽሓፍ ማንበብ በግር መንቀሳቀስ''
አቋረጠችው:
በሣምንት ስንት መጽሐፍት ታነባለህ? ሳቅ አለና፦በወር አድርጊልኝ?” አላት
እሽ" ፈገግ አለችና እሺ በወር ስንት መፅሐፍ
ታነባለህ
ቢበዛ ሁለት ሶራ በራሱ አፈረ በወር በወር ሁለት
መጽሀፍት ያነበበት ጊዜ ግን የለም:
“ሁለት ብቻ”
“አዎ!”
የሥራ ሰዓት ስንት ነው ኢትዮጵያ?
“ስምንት”
ስምንት ሰዓት ትሰራለህ ስምንት ለዓት ትተኛለህ
ቀሪውን ስምንት ሰዓት በየቀኑ እንዴት ታሳልፈዋለሀ ኮንችት አዘነችበት:: “ሁሉም እንዳንተ ነው?"
“አዎ! እንዲያውም ብዙው ከኔ የባሰ ነው። በአመት አንድ መጽሐፍ እንኳ የሚያነብ ከመንደሩ የማይርቅ" አላት:
ማንበብ እኮ ነው ሰውን አዋቂ ያደረገው:: አገራችሁ
የውጭ ቱሪስቶች ለምን እንደሚመጡ ታውቃለህ?"
"ለመዝናናት"
“ሌላስ?”
“ዋናው ለመዝናናት ነው" አላት ትከሻውን ሰብቆ።
“በማህበራዊ ህይወትና በተፈጥሮ ላይ ያላቸውን እውቀት ለማሳደግ ነው፡፡ እውቀት ደግሞ ከመዝናናት ጋር ይጥማል፡፡ የምዕራቡ ዓለም ጊዜን በቁጥጥሩ ስር ከማዋል አልፎ እያስገበረው
ነው እናንተ ደግሞ ለጊዜ
ጊዜያችሁን ከሚገመተው በላይ ትገብራላችሁ፡፡ ጊዜ ከአፍሪካ የተረፈውን ታክስ ለምዕራቡ ዓለም በብዙ እጥፍ ጨምሮ ይከፍላል ማለት ነው፡" ኮንችት አንገቷን ደፋች፡ ሶራ ደግሞ ስለጊዜ ማሰብ ጀመረ!
💫ይቀጥላል💫

👍15❤5
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-22
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
የሻወር ቤቱ በር ተከፈተ..አብዬት ከውስጡ ወጣ…
.ዶ/ር ማንም እቤት ውስጥ ይኖራል ብላ አልጠበቀችም ነበር..ፕሮፌሰሩም ተኝቶ ስለነበረ አብዬት ምን ጊዜ ወደ ሻወር ቤት እንደገባ አያውቅም…ሻወር ቤቱ ተከፍቶ ከውስጥ ሲወጣ ሲመለከተው .. አምላክ መላዐክ እንደላከለት ነው የተሰማው፡፡
አብዬት ሻወር ቤት ለመታጠብ ገብቶ ልክ ጨርሶ ልብሱን እየለበሳ ሳለ ነበር የዶክተሯን ድምፅ የሰማው..ከዛ ወጥቶ ሊረብሻት ስላልፈለገ እዛው መቆየትን ወስኖ ነበር የዘገየው...አሁን ግን ጪኸትና ማጎራት ሲሰማ ሰውየውን የጨረሰችው መስሎት ከሻወር ቤት ወጣ
‹‹ምንድነው? ምን ተፈጠረ…?ተንደርድሮ ፕሮፌሰሩን ለማገዝ ወለሉ ላይ ተንበረከከ…
‹‹እባክህ እኔን ተውና ከእሷ መድሀኒቱን ተቀበላለት?›
‹‹የምን መድሀኒት ነው?›
‹‹ዝም ብለህ ተቀበላት…››ተንደርድሮ ተነሳና ስሯ ደረሰ ..መዳፏ መካከል የኖረቻቸውን አራት ፍሬ ኪኒኖች ለመዋጥ አጆን አየር ላይ አንዳንጠለጠለች ተሸከረከረና እጇን በካራቴ ሲጠልዘው ኪኒኖች ቤቱ ጥጋ ጥግ ተበታተኑ…እሷ ክው ብላ ደነገጠች..እጇን በጣም አመማትና እንዳንከረፈፈች ከመቀመጫዋ ተነስተታ ቆመች
‹‹ምን እየሰራሽ ነው?ለዚህ አውሬ ብለሽ እራስሽን ልታጠፊ ነው?››
‹‹ለማን ብዬ?››
‹‹ታዲያ ኪኒኑ ምንደነው?››
‹‹የእሱን ልጅ የሚገድል ነበር…ፅንስ ለማስወረድ የሚያግዙ መድሀኒቶች ናቸው››
‹‹አንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ…?.ነይ በይ አግዢኝ.. ሰውዬውን እናንሳው.››
ተጋግዘው ወደ አልጋው መለሱት
በንዴት ‹‹ቁጭ በይ…›ብሎ ወንበሩ ላይ ተመልሳ እንድትቀመጥ.አደረገና እሱ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ..
‹‹ዶ/ር በጣም እያበሳጨሺኝ ነው…አሁን አንድ ነገር ብትሆኚስ? ደግሞ ልጅ ምን ባጠፋ ነው እንዲህ አይነት ቅጣት ሚደርስበት…?ይሄ ልጅ ይወለዳል…ሰምተሺኛል አይደል ይወለዳል… በቃ ይሄ የእኔ ውሳኔ ነው…ይሄ ሰውዬንም ሆነ ሙሉን ዛሬ ማታ ለህግ አሳልፈን እንሰጣቸዋለን፡፡››
‹‹ምን?›› አሉ ሁለቱም፡፡
‹‹አዎ ..ባንተ ውሳኔ እስማማለሁ አላልሺኝም?››
‹‹አዎ ብየሀለው….ግን እንዲህ ቆሳስሎ ፖሊሶች ሲያገኙት ምን ይላሉ..እራስህ እኮ ነህ እንደሚያስጠይቀን የነገርከኝ?›
አዎ ግን ለዚህ መፍትሄ አለው ..እሺ ፕሮፌሰር ምን ትላለህ…?ልጅህ እንዳታስወርደው ከልፈለክ …ይሄ የደረሰብህ ነገር ሁሉ ከዶክተሯ ጋርም ሆነ ከእኛ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ቃልህን ለመስጠት ትስማማለህ?››
‹አዎ.እኔ ልጅ መውለድ ምን ያህል እንደምፈልግ እሷ ታውቃለች…እኔ በዚህ ምድር ብቸኛ ሰው ነኝ…..ወላጆቼንም ዘመዶቼንም አላውቅም… በዘንቢል መንገድ ዳር ተጥዬ የተገኘው..ከዛም በማደጎ ቤት ብዙ ስቃይና ችግር እያየው ያደኩ ሰው ነኝ…በዛም የተነሳ ብዙ ልጆችና ትልቅ ቤተሰብ የመመስረት ከፈተኛ ፍላጎት ነበረኝ….ይመሰለኛል ለዛም ነው እንዲ ስግብግባና ማልጠግብ የሆንኩት..ለማንኛውም ለዚህ ልጅ ስል አደርግ ያላችሁኝኝን ሁሉ ያለማቅማማት አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ሰማሽ አይደል…በቃ በዘርዝር ምን እንደምናደርግ ደግሞ እኔ እቅዱን ጨርሰና ለሁለታችሁም አሳውቃችኋለው….አሁን ተነሽ ከእዚህ አንውጣ ››ብሎ ይዞት ወጣ፡፡ክፍሏ አስገባትና..አሁን እራስሽን አጠንክሪና ተዘጋጅተሸ ጠብቂኝ..1፡30 ሰዓት ላይ የመጨረሻውን ተልዕኮ ለመፈፀም እንንቀሳቀሳለን ብሎት ተለይቶት ሄደ
///
ሰዓቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ሆኖል -አብዬት አቶ ሙሉ ፊት ለፊት ተቀምጦል።
‹‹እሺ ትናንት የተነጋገርነውን አሰብክበት?››
‹‹አዎ እንዳላችሁት አደርጋለሁ"
"ማለት››
‹‹ እራሴን አጠፍለሁ"
"ጥሩ.. በእውነት የጀግና ውሳኔ ነው..ታዲያ በምን ይሁንልህ?"
ትንሽ እንደማቅማማት አለና "በሽጉጥ ይሻለኛል...በሽጉጥ"
"ጥሩ ምርጫ ነው...ምንም ሳትሰቃይ ከዚህ ሁሉ ጣጣ ትገላገላለህ ማለት ነው...ተነስ በል እንሂድ"
"ወደ የት?"
"እንዴ እራሴን ማጥፋት ፈልጋለሁ አላልክም ? ...እዚህ እኛው ቤት ካደረከውማ እኛን ያለስራችን ይጠረጥሩናል...ስለዚህ ሌላ የተመቻቸ ቦታ እንፈልግልሀለን ።
‹‹እና ዛሬውኑ ነው የምትገሉኝ?"
"አንተ ደግሞ.. አሁን እንግደልህ ወጣን ..?.እራስህ ነህ ለመሞት የመረጥከው...መሞትህ ካልቀረ ደግሞ የምን ዛሬ ነገ እያሉ ጊዜ መፍጀት ነው"
ቀድሞት ክፍሉን ለቀቀና ሽጉጥ በጎኑ ጩቤ በእጅ ይዞ በራፍ ላይ ወደሚጠብቀው ቶላ.‹‹.ይሄን ሰውዬ ይዘህ ወደ መኪና ውሰድልኝ መጣሁ›› አለና ወደዶክተር ክፍል አመራ ..ዝግጅ ሆና ስትጠብቀው ነበር።
"ዶክተር እንሂድ"ምንም መያዝ ስይጠበቅባት ብድግ ብላ ለመሄድ ዝግጅ ሆነች።ካሳ ሻንጣውን ይዞ ተከተላት
"እንዴ ወዴት ነው?"አብዬት ጠየቀው
"ልንታገት አይደል?"
"እና ለመታገት ይሄን ያህል መስገብገብ"
"አዎ ከእሷ ጋር አይደለ እንዴ ..?."
"አብሽ ዛሬ ተራው የእኔ ነው ።አንተ ዛሬ እዚሁ ዘና ብለህ እደርና ነገ በጥዋት ተነስተህ ወደቀድሞ ስራህ?ስራ አለህ እኮ እረሳሀው እንዴ?"
‹‹አረሳሁትም...የሦስት ቀን ፍቃድ ይቀረኛል..ሶስት ቀን መታገት እችላለሁ"
"አረ ባክህ ትችላለህ...?።ዶ/ር መሀከል ገብታ ታስረዳው ጀመር..."ይሄ ጉዳይ ለዛሬ ለሊት ብቻ ነው።ነገ ጥዎት እኔ ቤት እንገናኛለን።ብላ ተጠጋችውና ጉንጩን ሳመችው።
ምንም ሳይናገር ሻንጣውን ትከሻው ላይ እንዳንጠለጠለ ወደ ክፍሉ መራመድ ጀመረ...ዶ/ርና አብዬት ጎን ለጎን ሆነው ወደታች ወረድና እቤቱን ለቀው ወጡ።መኪናዋ ጋር ሲደርሱ ቶሌ አቶ ሙሉን መኪና ውስጥ አስገብቶ እሱ ከጎኑ ቁጭ ብሎ ለማምለጥም ሆነ ለመንፈራገጥ እንዳይሞክር ጩቤውን ጎኑ ላይ ሽጦበት በተጠንቀቅ ሲጠብቀው ደረሱ።ሁለቱም ገቢና ገብና በአብዬት ሹፌርነት ከጊቢው ወጥተው መጓዝ ጀመሩ።
///
ቀጥታ የሄድት አቃቂ ድልድዩ አካባቢ 500ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኝ አንድ አዲስ የሚሰራ ቤት ውስጥ ነው።ቤቱ ከቀለም መልስ ያሉ ግንባታዎች ያተጠናቀቁበት ቢሆንም ...ባለቤቶቹ አልገብበትም።እቤቱን ከዘበኛው ጋር በመነጋገር ሁለት ቀን ሊጠቀሙበትና 5000ብር እንደሚከፍሉት ነግረውት 3 ሺ ብር ቅድሚያ ተቀብሎ በደስታ ፈቅዶላቸዋል። ባለቤቶቹ የክፍለሀገር ሰዎች ስለሆኑ ከወር ወደእዚ እንደማይመጡ ተረጋግጦል።
አቶ ሙሉ ይሄ ሁሉ መጓዝና ይሄ ሁሉ ግርግር ለምን እንደሆነ አልገባውም‹‹ ..እዚሁ መንገድ ላይ አውርዳችሁ ሽጉጡን ብትሰጡኝ እኮ.. ግልግል ነው"አለ
‹‹እዚህ መሞት ይሻልሀል?"አብዬት ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ"
"እኛ እኮ የተሻለ ቦታ ...በጥሩ ሴርሞኒ ብታደርገው ይሻላል ብለን ነው።››
"የምን ሴርሞኒ እያሾፋችሁብኝ ነው?..ባካችሁ እዚሁ ልገላገል.. መኪውን አቁሙት››
"እሺ እንዳልክ"አለና ቤት ሆነ የሠው እንቅስቃሴ የሌለበለት ቦታ ሲደርስ መኪናዋን ጠርዝ አሲይዞ አቆመ...የውስጥ መብራቱን አበራ ..ዶ/ር አብዬት ምን እየሠራ እንደሆነ ስላልገባት ግራ ገባት፡፡
"ምን እያደረክ ነው ..የእውነት እሱን ሰምተህ እያቆምክ ነው?።"ስትል ጠየቀችው፡፡
"አዎ ለመሞት እንዲህ ከቸኮለ ለምን እናዘገየዋለን...አለና ከጎኑ ሽጦ የነበረውን ሽጉጥ መዠርጦ አወጣ…
"በሽጉጥ ነበር አይደለ መሞት ፈልጋለሁ ያልከው?››ወደኃላ ዞረና ...በመንጠራራት ሽጉጡን በእጅ አስጨበጠው"
ዶ/ር አብዬት አሁን እያደረገ ያለው ነገር እየገባት ስላልሆነ ተደነጋግራለች ..እንዲህ አልነበረም ንግግራቸው።
"እና ምን ትጠብቃለህ ?አድርገዋ"
"እዚሁ?"

👍30❤1🔥1
"አዎ እዚሁ …ቶሌ ደሙ ተፈነጣጥቆ ልብስህን እንዳያበላሽ ራቅ በለው ..ጥግህን ያዝ።››ቶላ እጅ ላይ የነበረውን ጩቤ እያገለባበጠ የታዘዘውን አደረገ።አቶ ሙሉ ሽጉጡን አቀባበለና መሀል ጭንቅላቱ ላይ ደቀነ...ዶክተር በፍራቻ እየተንቀጠቀጠች የሚንጣጣ የሽጉጥ ድምፅ ላለመስማትና የሚበረቀስ የራስ ቅል ላለማየት አይኖቾን ጨፍና ጆሮዎቾን በመዳፏ ሸፈነች።
"ስንት ጥይት አለው?"ሲል ጠየቀ
"አታስብ ይበቃሀል ...እንደውም ትርፍ ነው ..6 ጥይት አለው ..ሁለቱን ከተጠቀም ሌላውን አታባክንብን ጓደኛህም በዚሁ ካንተ በተረፈው ነው እራሱን የሚያሰናብተው።››
አቶ ሙሉ አእምሮውን ማሰራት ጀመረ...‹‹አዎ እድሉን መሞከር አለብኝ፤ ከፈጠንኩ ሊሳካልኛል ይችላል...ቀድሜ ይሄ የሠማይ ስባሪ የሚያህለው ጠረንገሎ ጭንቅላት ላይ ሁለት ጥይት ብለቅበት …ከዛ ያኛው ሌላ መሣራያ ከማውጣቱ በፊት የተቀረውን በጀርባውም በጭንቅላቱም ባንጣጣበት አበቃ ማለት ነው.. ዶ/ሯን በእጄም አያቅተኝ ።ከዛ የሶስቱንም እሬሳ እዚሁ ቅርብ ድልድይ ስር ገልብጬ.. በዚህችው መኪና ወደቤት ሄድና በቀደም ለሚስቴ ከሰጦት ብር ቢያንስ 10ሚሊዬንን ይዤ ከእዚህ አገር ላጥ..በሰከንዶች የጊዜ ልኬት ሁስጥ የወራት እቅድ አውጥቶ ጨረሰ..
"ሰውዬ ፈራህ እንዴ,.?.እየጠበቅንህ እኮ ነው?"አለው አብዬት፡፡
አቶ ሙሉ በጥልቀት ተነፈሰ እራሱን ከዘጋጀ...በህይወቱ ሙሉ ፈጥኖ ከሚያውቀው ፍጥነት በተለየ ሽጉጥ የጨበጠው እጁን ቶላ ጭንቅላት ላይ ቀሰረና ቃታውን ደጋግሞ ሳበ.ቃ... ቃ.. ደገመው"ቃ..ቃ"ምንም የፈነዳ ድምፅ የለም...ምንም ተፈናጥሮ የወደቀ ቀለሀም የለም ..የተፈረከሰ ጭንቅላትም አይታይም፤ አብዬት እየተንከተከተ ተንጠራራና ሽጉጡን ከእጅ መንጭቆ ተቀበለው...
"እንደማስብህ ከርፋፋ ሰው አይደለህም"ብሎ መኪናዋን አንቀሳቀሰ..ዶ/ር ቀስ ብላ አይኖቾንም ገለጠችና የተፈጠረውን ለማየት ወደኃላ ዞረች ሁሉ ነገር ሰላም ነው ..አቶ ሙሉ አይኖቹን በፍራቻ ቁልጭ ቁልጭ እያደረገ ነው።መዳፎን ከጆሮዋ አነሳች። "ምን ተፈጠረ?"አብዬትን ጠየቀችው።
"ሙሉ የሚባለው ሰውዬሽ ገና ለመሞት ዝግጅ አይደለም"
"እና? "
"እናማ ...ቶላ ላይ ደቀነና ቃታውን ሳበ...በጣም ጥሩ ገዳይ መሆኑን በደንብ አረጋገጠልን፡፡"
"እንዴ ቶሌ ተጎዳህ?"መልሳ ባለማመኖ ጠየቀችው..ቶላ እየተደረገ ያለውን ነገር ሁሉ እሱ የማይሳተፍበት ቀሺም ፊልም እንደሚያይ ሰው ነው በቸልተኝነት እየታዘበ ያለው።ሽጉጥ ሲደቀንበትና ቃታ ሲሳብበት እንኳን የስሜት ለውጥ፤ የመፍራት ፤የመደንገጥ ሁኔታ በፊቱ ላይ አልታየም።
"እድሜ ለእኔ ከቤት ስንወጣ ዘንግቼው ሽጉጡ ውስጥ ጥይት አልጨመርኩበትም ነበር...ለዝንጉነቴ ይቅርታ አቶ ሙሉ"አሾፈበት።
"አንተ ክፉ ሰው ነህ ባዶ ሽጉጥ ሰጥተሀው ነው እንዲህ የምታጨናንቀኝ...እርጉዝ እኮ ነኝ "ደነጠ"ውይ ይቅርታ ...ፈፅሞ እንደዛ አላሰብኩም"
"አረ ስቀልድ ነው… የክፉ ሰው ፅንስ እንዲህ በቀላሉ ይሸበራል ብለህ ነው?።ደረሱ ቶሌ ክንድን ጨምድዶ ጎትቶ አወጣው
ቶሌ ቆይ አለና ቅድም ከአቶ ሙሉ እጅ የነጠቀውን ሽጉጥ አወጣ …ኪሱ ገባና ጥይቶች በማውጣት ሞላበት ...
"አሁን ልስጥህ እንደ?"የቀዘቀዘው ና የደነዘዘው አቶ ሙሉ ፀጥ እንዳለ ነው፡፡ቶሌ እሱን ለእኔ ተውልኝ አንተ እዚሁ ቦታህን ያዝና እስክደውልልህ ጠብቅ….ደክተር ተከተይኝ..››አለ
ዶክተሮ ፈራ ተባ ስትል ያያት አብዬት ወደዶክተሯ ጠጋ አለና
‹‹አይዞሽ ዶክተር ችግር የለውም ..ይሄውልሽ እዛ ጥግ ሰብለ ክላሽ ደቅና ገቢ ወጪውን እየጠበቀች ነው ..በተቃራኒው እዛ ደግሞ አቤል እስናይፐሩን ሰትሮ እየጠበቀ ነው እዛ ፊት ለፊት ደግሞ ዛፍ ተከልሎ ባርቾ ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ ነው።ቶላም አሁን ቦታን ይይዛል/..ችግር ከተፈጠረ ወዲያው አንቺን ከዚህ ያስወጡሻል"
"አንተ ከጎኔ ካለህ አልፈራም ..››አለችው
‹‹አቶ ሙሉ ቀጥል"መራመድ ጀመረ...ግቢ ውስጥ ተከታትለው ገቡ ...እቤቱ በረንዳ ላይ ባለ አግዳሚ ወንበር ላይ የዶዬ 3 ሰዎች ተኮልኩለው ተቀምጠዋል።
አቶ ሙሉ ግራ ተጋባ ..እነዚህን ሰዎች ያውቃቸዋል ..ለረጅም ጊዜ ለእነሱ ሲሰሩ የነበሩ የዶዬ ሰዎች ናቸው።‹‹እዚህ ምን እየሰሩ ነው?"››እራሱን ጠየቀ ‹‹ከመጀመሪያውም ከእኛ በተቃራኒ ሆነው እየሠሩ ነበር እንዴ?"ጥያቄውን እርግፍ አድርጎ ተወው...አሁን ምንም ሆነ ምንም ለእሱ የሚጠቅመው ነገር የለም ። የእሱ ጉዳይ አብቅቶለታል …ልጆቹ የአብዬትን መሞጣት ሲያዩ ከተቀመጡበት ተነስተው ቆም...አብዬት ምንም ሳይላቸው ሰውዬውን በሽጉጡ አፈሙዝ እየገፋ ወደቤቱ ውስጥ ይዞት ገባ..ዶክተሯ ሁኔታውን እየቃኘች ከኃላቸው ተከትላለች፡፡
ሳሎኑ ውስጥ ሁለት ወንበር፣ አንድ ጠረጰዛ ፣ ምንጣፍ፣ ምንጣፍ ላይ የተዘረጋ ፍራሽ፣ አንሶላና ብርድ ልብስ ፣እሽግ ውሀ በደርዘን.. በቃ ይሄ ነው ያለው...
አብዬት ማውራት ጀመረ‹‹ስማኝ።አንተ ማንም አላገተህም። እስከዛሬ ለአንድ ሳምንት እዚህ ነበርክ...የምትተኛው እዚህ ፍራሽ ነው ፤ውሀውም እነዛ ኩኪሶችና ቆሎዎች ለአንተ የተዘጋጅ ናቸው። ፍራሹን ገለጥ አደረገና አሳየው..አየህ 500 ሺ ብር ነው ..እርግጥ 50 ሺ ብር አካባቢ ተነስቶለታል ..ያንተ ነው።ስትያዝ የተወሰነ ብር በእጅህ መገኘት አለበት ከለዛ አያሳምንም፡፡ በራፍ ላይ ያየሀቸው ካንተ ጋር የሚሰሩ አንተ የቀጠርካቸው ናቸው።እነሱን ስትቀጥር ዶዬም ሆነ ሼኪው አያውቅም። አንተና ፕሮፌሰሩ ብቻ ናችሁ የምታውቁት፡፡ከዶዬ በብር ኃይል ለእነሱ መቶ ሺ ብር ከፍላችሁ ነው ያስኮበለልካቸው።በስምህ በየአካውንታቸው መቶ መቶ ሺ ብር ገብቶላቸዋል፡፡››
ፍዝዝ ሲልበት።"ሰውዬ የምለውን እየሠማኸኝ ነው አይደል?
"አዎ በደንብ እየሠማውህ ነው..ግን አልገባኝም"
"ቆያ ትንሽ ታገስ እያስረዳውህ ያለውት እኮ እንዲገባህ ነው። ከሳሎኑ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ከፈተው ..."ዶ/ር ነይ ግቢ፤ እዛ ወንበር ላይ ቁጭ በይ ...ቁጭ አለች..ተጠጋትና ፀጉሯን ያሰረችበትን ፀጉር ማስያዣ ፈታችውና ፀጉሯን ብትንትን አደረገው...፡፡
‹‹ምን እያደረክ ነው?››አለች ግራ ገብቶት፡፡
"ትንሽ መጎሳቆል አለብሽ ...››አለና ከላይ የለበሰችውን ቲሸርት እንድታወልቀው አደረገ፡፡ ወለል ላይ ጥሎ በእግሮቹ በማሻሸት እንዲቆሽሽ ካደረገ በሀላ አንስቶ የለበሰችው ሱሪዋ ላይ አራገፈው.. ሽሮ መልክ ያለው ሱሪዋ በቀላሉ ቆሸሸ… ሸሚዙን ሶስት ቦታ ቀደድ ቀደድ አደረገና መልሶ አለበሳት
"ትናንት ገዝተህልኝ ዛሬ ስትቀደው ትንሽ አያሳዝንህም? አለችው
‹‹አይ የገዛሁበት ብር ያንቺ ስለሆነ አያሳዝነኝም"
እጇን በገመድ አንድ ላይ ጠፍሮ አሰራት...‹‹በጣም አሳመምከኝ .."
‹‹በደንብ መምሰል አለበት እንደውም ክርክር ቢያወጣ ወይም ቢደማ አሪፍ ነው..››.ጎንበስ ብሎ እግሯንም ከወንበሩ እግር ጋር አሰረኸው..ግድግዳውን ተደግፏ ፈዞ ለሚያየው አቶ ሙሉ ..።‹‹ስማኝ አሁን በህይወት ላተርፍህ እየጣርኩ ነው። እድሜ ለዶ/ር በል …እኛ እንደ እነሱ ገዳይ አንሆንም ስላለች ...እጃችሁን ለመንግስት እንድትሰጡ እያመቻቸን ነው።ህግ ፊት ደግሞ የሞት ፍርድ ቢወሰኖብህ እራሱ ገና መረጃ ተሠብስቦ ፤ስንት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶ፤ ክስ ቀርቦ፤ የምስክሮች ቃል ተሠምቶ፤የቅጣት ውሳኔ ተላልፎ ፍርድ ታውቆ ፕሬዘዳንቷ ፈርማ እስኪባል ቢያንስ አምስት አመት በህይወት ትኖራለህ..አስርና ሀያ አመትም ልትኖር ትችላለህ።እ ምን ትላለህ?።
‹‹አረ በጣም ነው የማመሰግነው ...እውነት ዶ/ር ላደረግሺልኝ ምህረት አመሠግናለው"አለ

👍28❤1😢1
እንግዲያው የምልህን በደንብ አስተውለህ ስማኝ…..በቪዲዬ ተቀርፀሀ የለቀቅከውን እያንዳንዱን መረጃ እንዳትዘነጋ ..ና ተከተለኝ አለና ዶ/ሮን እዛው ተዋትና ቀጣዩ ክፍል ይዞት ገባ…እዛ ክፍል በተነጠፈ አልጋ ላይ ፕሮፌሰሩ ዝርግትግት ብሎ ተኝቶ ያቃስታል…እነሱ እዚህ ከመድረሳቸው ከ30 ደቂቃ በፊት ነው ከቤት አምጥተው እዚህ ያስተኙት፡፡ከፍተኛ ስቃይ ላይ ቢሆንም ግን ንቁ ነው….ክፍል ውስጥ ሙሉንና አብዬትን ሲያይ ማቃሰቱን ቀነስ አደረገና ትኩረቱን ወደእነሱ አዞረ
‹‹እሺ ፕሮፌሰር ወዳጅህን ይዤልህ መጥቼያለው…..››
አቶ ሙሉ የፕሮፌሰሩን ሁኔታ ሲያይ ዝግንን አለው..ያ ኩሩ ቀብራራ..ያ ሽቅርቅር መሬት አይንካኝ ብሎ በአየር ላይ የሚበር ግለሰብ እንዲህ ተገጣጥቦና ጠቋቁሮ፤ ዝሎና ደክሞ፤ልክ በሰመመን አድክሞ አልጋ ላይ አስተኝቶ እንደሚቀዳቸው በሽተኞቹ እሱም ተሰትሮ ሲያየው የሰው ልጅ ከንቱነት ፍንትው ብሎ ተገለፀለት..እሱን ስላላሰቃዩት በውስጡ አመሰገናቸው፡፡
‹‹አሁን ሁለታችሁም ሱሙኝ….እንደተለመደው..ይሄን ቦታ ከዘበኛው በሌላ ሰው አማካይነት ተከራይታችሁ ነው፡፡ የተከለከራያቸሁት 5 ሺ ብር ሲሆን 3 ሺብር ከፍላችኋል፡፡እዚህ ሳምንት ተቀምጣችኋል….ዶክተሯንና አግታችሁ ሁኔታዎችን እየተከታተላችሁ ነበር….አንተ አቶ ሙሉ ስሜታዊ ሆነህ እራስህን እንደምታጠፋ ገልፀህ የንዛዜ ቪዲዬውን የለቀቅከው…በጎደኛህ እንዲህ መሆን ተስፋ ቆርጠህ ነበር…ምክንያም ፕሮፌሰሩን ከሁለት ቀን በፊት ማታ አራት ሰዓት ላይ ወደከተማ ደርሼ ልምጣ ብሎ ወጥቶ ሲመለስ ጨለማ ተገን አድርገው እዚህ መግቢያ ላይ ጠብቀው ነው እንዲህ አበለሻሽተው ጥለውት የሄዱት፡፡አንተ ስትገማት እንዲህ ያደረጉት ሰዎች ምክንያታቸው ደግሞ ፕሮፌሰሩ ቀድሞ ከሰራቸው ስራዎች ጋር በተያያዘ ቂም የያዙበት ሰዎች እንደሆኑ ጥርጣሬው ፡፡እነዚህ የህክምና ቁሳቁሶች ይታዩሀል እነሱን ከፋርማሲ ገዝተህ በእናንተ እገታ ስር ያለችውን ዶክተር በግድ እንድታከመው አስገድዳችሁ ከሞት እንዲተርፍ አድርገሀል…ገባህ››
‹‹አዎ የገባኝ መሰለኝ››
‹‹ጥያቄ አላችሁ?››
አቶ ሙሉ ጠየቀ‹‹የመሞት ሀሳብህን ለምን ቀየርክ ካሉኝስ?››
‹‹ያው ፈሪ ስለሆንኩ በላቸዋ››
‹‹ፕሮፌሰሩ በሚርገበገብ ድምፅ‹‹ልጄስ?›ሲል ጠየቀ
‹ፕሮፌሰር እንደውም አስታወስከኝ.. ዶ/ሯን ሳትገድላት እስከአሁን ያቆሀት ልጅህን ማርገዞን ስላወቅክ እንደሆነ ብትናገር በጣም አሳማኝ ምክንያት ነው››
‹‹እሺ አደርገዋለሁ አታስብ…ልጄን ብቻ እዳታስወርደው ተከታተልልኝ…ውለታህን አልዘናጋውም››
‹‹ላንተ ውለታ የመዋል ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም.. ግን ለእሷ ስል ልጆንም ሆነ እሷን እጠብቃቸዋለሁ፡፡››
‹‹እኔም የምፈልገው ያንን ነው….አመሰግናለሁ››
‹‹እንግዲያው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ልንገራችሁ….በምንም አይነት ሁኔታ ዶ/ሯን ለአንድ ቀን እንኳን እስር ቤት የሚያስገባትን መረጃ አሳልፋችሁ ብትሰጡና ከስምምነታችን ውጭ ብትንቀሳቀሱ እስር ቤት ሆናችሁ የትም አንድ ቀን አታድሩም፤ምንም አላዝንላችሁም፡፡አንተ ሙሉ ተብዬው…. ቅድም መኪና ውስጥ እንዳደረከው ብልጥ ልሁን ብትል መጀመሪያ ልጆችህን ከዛ ሚስትህን ጨርስና ወደአንተ መጣለሁ… አሁን በሉ ፖሊሶቹ ጥቆማ ይደርሳቸዋል…በሀያ ደቂቃ ውስጥ መጥተው ይከቦችኋል፡፡ በረንዳ ላይ ከእናንተ ጋ እጃቸውን ለመስጠት የተዘጋጁ ጠባቂዎች አሉ፡፡ወጭ ደግሞ የእኔ ልጆች ችግር ከተፈጠረ ..ማለቴ ለማምለጥ የምትሞክሩ ወይም አልማረክም ብላችሁ ፖሊሶችን የምታስቸግሩ ከሆነ በእስናይፐራቸው ይቀልቡና ይገላግላችኋል፡፡በሉ መልካም የእስር ዘመን በጣም ትናፍቁኛላችሁ››ብሎ ወጣና ወደ ዶ/ር ክፍል ተመለሰ፡፡
ዶ/ር እንግዲህ ሰዓቱ ደርሶል፡፡በቃ ልሂድና ፖሊቹን ይዣቸው ልምጣ››
‹‹እንዴ እራስህ ነህ እንዴ የምትጠቁመው››
‹‹አዎ…እንዚህን ወንጀለኞች በመጠቆም እራሴንም ከተጠርጣሪነት ነፃ ማውጣት አለብኝ..በዛ ላይ የሼኪው 5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አለ››
‹‹ትቀልዳለህ አይደል?››
‹‹በይ..ደግሞ ሰውዬሽን እንደዛ ደብድበውና አኮላሽተው እዚ ባራፍ ላይ ጥለውት ሲሄዱ አቶ ሙሉና ጠባቂዎቹ በግድ አስገድደው እንድታክሚው አድርገውሻል..አንቺ ነሽ ያከምሽው››
ዝግንን አላት
‹‹በይ…አልቆይም ፖሊስ ይዤ መጥቼ አድንሻለሁ፡፡››ብሎ ወጣ፡፡

👍31❤1👎1🔥1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ትልቁ የሮማ ስታዲዬም በተመልካቾች ተጨናንቋል፡፡
መንገዶች ተጣበዋል
ለተሽከርካሪ ዝግ በሆነው መንገድ ላይ ህዝቡ
እንደ ጉንዳን ይርመሰመሳል፡ ሳቅ ጨዋታ, ዳንኪራ ሁሉም እንደየግል ዝንባሌው ያሻውን ይፈፅማል። ከዘመናዊው ስታዲዬም
በጣልያንኛ በእንግሊዝኛ• በፈረንሳይኛ… ስለውድድሩ ታላቅነት ስለ ውድድሩ አጀማመር ተወዳዳሪዎች ምርጥነት ስለ ያሸንፋሉ
ተብለው ስለሚገመቱ አትሌቶች በተለያየ ቋንቋ ይተነበያል።
አኜስ ሎካዬን ወደ ሮማ እንዲሄድና ውድድሩን እንዲያይ ያግባባቸው ከብዘ ልፋትና ድካም በኋላ ነው፡፡
“…ሉካዬ ውድድሩን ማዬት መቻል አለብን!” ስትለው:
"አኜስ አንች ሂጂ እኔ ግን እዚሁ መቆየት እፈልጋለሁ።
ምናልባት አንቺ ከተመለሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ሄጄ ዘመዶቼን ብፈልግ ደስ ይለኛል"
“ሎካዬ አብረኸኝ እንድትሆን እፈልጋለሁ: ጣልያን ውስጥ ጥሩ የመዝናናት እድል ይኖረናል። ወንድሜና ሴት ጓደኛው አብረን እንድንሆን ይፈልጋሉ ልጃችንም ክሪናም ከሁለታችን ጋር መሆኑን
እንደምትመርጥ ነግራኛለች፡፡
“ሊሆን ይችላል አኜስ ከእነሱ ይልቅ አንች እኔን በሚገባ ታውቂኛለሽ፡ ሮማ በመሄድ ደስተኛ ይሆናል ብለሽ እንደማትገምች
ነው የማስበው፡ እዚህ ብሆን ግን ቢያንስ የልጅነት ጊዜዬን እያሰብኩ
በፀጥታው ልዝናና እችላለሁ: ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስም በመሄድ
በማዕበሉ ውሃ እግሮቼን እየነከርሁ ለመደሰት እሞክራለሁ: ሮም ሄጄ ግን ጎንና ጎኔ ጨዋታ ወዳድና ደስተኛ ሰዎች ይቀመጡና
እየጎነታተሉ እንድጫወት ተፅዕኖ ያደርጉብኛል፡፡ እየቆየ ግን ዝምታዬ እየከበዳቸው ሲመጣ ይሸሹኛል። ያኔ ጩኸቱ በሚያስበረግግ
ፀጥታ እዋጥና አዕምሮዬ ይረበሻል። ስለዚህ አኜስ! እባክሽን እኔን እንሂድ ማለትሽን ተይኝና ከሌሉች ጋር ሄደሽ ተዝናንተሽ ተመለሽ አላት ረጋ ብሎ
“ኦ አምላኬ! ለምን ይኸን ቅዠትህን አታቆምም። ስግብግብ አትሁን እሽ! ለሌሎች ደስታ ማሰብ መቻል ኦለብህ፡ ግትርነትህንና
የገነተረ አስተሳሰብህን አለዝበው" አፈጠጠችበት፡፡
…ለሌሎች ደስታ ማሰብ መቻል አለብህ አባባሏ ውስጡን ረበሸው፡ ሉካዩ ራሱን አይወድም ሌሎች ደስ ሲላቸው ማየት
ያረካዋል። እራሱን ግን ለማዝናናት እንዳይችል በልጅነቱ ከወላጆቹና
ከዘመዶቹ ካደገበት ቀዬ ነጥቀው በጭንቀት በሃዘን… እያለቀሰ!
ማንነታቸውን የማያውቃቸው ሰዎች እንደ
አውሬ ደስታውን
ገነጣጥለው በልተውበታል፡ ተስፋውን አምክነውበታል፧ ስሜቱን ጭምትርትር አድርገው አኮራምተውበታል፡፡ እድሜው እየጨመረ
በሄደ ቁጥር ከጠባሳው በታች ሊድን የማይችል የቁስሉ ጎሚ እየበረታበት መጣ። ራሱን ሊያክም ሞከረ ውስጡ ግን እያመረቀዘ በሰራ አካላቱ የስቃይ መርዙ ተሰራጨ፡
“አኜስ! ለምን ስቃዬን አትረጅልኝም ሁሌ ለሞን አሸናፊነት ትመርጫለሽ!"
“ሎካዬ! ተው እንዲህ ምርር አትበል ልለይህ አለመፈለጌ
ላንተ ካለማሰብ የመጣ ነው ብለህ ታስባለህ? እንደዚያማ ላለማሰብ
ሞክር" ብላ አንገቷን ሰበር ስታደርግ ሎካዬ ጠጋ ብሎ ፀጉሯን ደባበሰና፡-
“ይቅር በይኝ እሽ አብረን እንሄዳለን" ሲል ቀና ብላ
አይታው እንባዋ ከአይኖችዋ ረገፉ:: ሎካዬ ግን እንባዋን ማየቱ
ከብዶት ፀጉሯን ስሞ ወጣ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በተለያየ ቀለማት ያሸበረቁ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሜዳውን ሞልተው እክሮባት ሲያሳዩ እንደቆዩ እውቁ ጣሊያናዊ አቀንቃኝ
ከሙዚቃው ጋር አጣጥሞ ድምፁ ሲያስረቀርቀው በስቴዲየሙ ውስጥ
ያለው ህዝብ አድናቆቱን በጭብጨባ በፉጨት በጩኸት በጥሩንባ በከበሮ
ሲገልፅ ድምፃዊው አሳ እንደሚውጥ ትልቅ አሳ ፉን
ከፍቶ ሲዘፍን በስታዲየሙ ዙሪያ የተደገኑት ማጉያዎች ድምፁን አስተጋቡት:: አሁንም ጭብጨባ ጩኸት ደስታ ሁካታ ሆነ፤
ጭፈራው ቀለጠ፡ ርችት ተለኮሰ፡፡
ከዚያ ከያገሩ የመጡት ሯጮች ወደ መወዳደሪያው ቦታ ሲወጡ ተመልካቹ
ቆሞ በጭብጨባ
ተቀበላቸው፡፡ ከያገሩ
ስለተወከሉት ተወዳዳሪዎች ማንነት ጋዜጠኞች በየቋንቋው መዘርዘር
ቀጠሉ፡
አኜስ ሎካዬ ከሪናና የአኜስ ወንድም ከሴት ጓደኛው ጋር
ሮም ስታዲዬም ናቸው: ከሎካዬ በስተቀር ሁሉም ያጨበጭባሉ ብድግ ቁጭ ይላሉ ይለፈልፋሉ… ሎካዬ ግን በብዙ ሺ ህዝብ መሀል ሆኖ ያልማል የልጅነቱን ህይወት የወላጆቹን ቀዬ...
ተወዳዳሪዎች ተደረደሩ፤ ችቦው ተለኮሰ፤ ማራቶን የሮማ ማራቶን ተጀመረ፡
ከዚያ በስቴዲየሙ ውስጥ የጥቂት አትሌቶች ገድልና
በዛኔው ውድድርም ያሸንፉ ይሆናል የሚለው ግምት ተለፈፈ፡፡አውሮፓውያን አሜሪካውያን ሩቀ ምስራቆች የአሰለፏቸው
አትሌቶች መጠን በ ውድድር አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎችም በተወሰኑ አትሌቶች መወከላቸው ተነገረ፡፡
ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራት መቶ ዘጠና በፔርሽያና አቴና በተፈጠረው ድንገተኛ የጦር ወረራ ትንኮሳ የተደናገጡት
አቴናውያን ፊዲፒደስ የተባለውን ጀግና ስፖርት ላኩት: ፊዲፒደስም
ለሃምሳ ሰዓታት ካለ ምግብና መጠጥ ሩጦ መልዕክቱን አድርሶ
በመመለሱ ውጊያው ተጀመረ፡፡
የአምባገነኑ የፔርሺያ ኃይል
ግን የማታ ማታ ሟሾ የውጊያው ድል ፎክሮ ጦር አውድማ ከሄደው ከፔርሽያው መሪ
ከዳሪዮስ እጅ ወጥቶ አቴናውያን እጅ ገባ፡፡
የአቴና ፍቅር ያማለለው ጀግናው ሯጭና ተዋጊ
ፌዲፒደስም ያንን ያገሩን ታላቅ ድል ሲያይ ደስታ
ፈንቅሎት አቅጠበጠው ስለዚህ ያንን ታላቅ ድል ለወገኑ ለማብሰር ቂጤማ
የያዘች እርግቡን ህሊናው ቆጥ ላይ አስፍሮ ሀያ ሁለት ማይልስ ካለ እረፍት የተነሳውን ክቡር ቃል ሊያደርስ ሮጠ፡፡
ፊዲፒደስ ከተማ
ሲደርስ አካሉ ደክሞ ! ሕይወቱ የተንጠለጠለችው ጠንካራ ሞራሉ ላይ ነበርና ወገን ሊያገኝ ያን
እንደ አልማዝ የሚያንፀባርቅ ቃል እያከለከለከ “ቪክትሪ" ብሉ ቃሏን ብቻ አሰምቶ ህዝቡ ሲደሰት እሱ ግን ሕይወቱን ለአገሩ ድል ሰዋ እየሳቀ አንቀላፋ!
መልካም ሥራና እውነት
ግን ውሎ አድሮ ከትቢያ
መነሳታቸው የክብር ሥፍራቸውን መያዛቸው አይቀርምና በአስራ
ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት ግሪኮች የፊዲፒደስን ውለታ ለመክፈልተ ተስማሙ፡፡ መልካሙ ስሙን ከመቃብር ውጭ ሊያውለበልቡት
አቀዱ! ስለዚህ ባምላካቸው መሪ በዜውስ ስም ሰይመው የኦለምፒክ
ማራቶን ጀመሩ… ያ የመልካም ስራ ሽቶ መዓዛም አለማችንን
አወዳት፡፡ ከዚያ የማራቶን ሩጫ ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንና በምዕራባውያን አገሮች በተለይ ሩጫን ዘመናዊ
ለማድረግ ሳይንሳዊ አሰለጣጠን ዘዴዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን አትሌቶች ከህፃንነታቸው ጀምሮ እየተመለመሉ ድንቅ
ተወዳዳሪዎችን ማፍራት መቻሉም ተናገረ፡፡
ሚዲያዎች ተወዳዳሪዎች የደረሱበትን ማን እየመራ
እንደሆነ ገለፁ፡፡የሚመራው አፍሪካዊ' ነው ሲባል ስለ ዘመናዊ የሩጫ አሰለጣጠን ዘዴ የሰማው ተመልካች ግራ የገባው መሰለ፡፡ብዙዎች ግን በማራቶን እሩጫ ትልቁ ዘዴ ትንፋሽን መጠበቅና ሃይልን እየቆጠቡ ቆይቶ የተወስነ ርቀት ሲቀር አፈትልኮ እንደ
ቀስት መወርወር ነው፡፡ ሲጀመር አካባቢ የቀደመ በስተመጨረሻ አትሌቶችን እየተሰናበተ ውራ ይወጣል' እየተባባሉ ተሳለቁ፡፡
ህዝቡን ከሚያዝናና ዝግጅቶች ጣልቃ ላይ የማራቶን ተወዳዳሪዎች ደረጃ እንደገና ተጠቀሰ:: አሁንም “አፍሪካዊው

👍25🥰2👏2❤1🔥1😁1
ይመራል" ተባለ። ተመልካቹ እርስ በርሱ ተያዩ: “አፍሪካውያን ድሮም መጀመሪያ ላይ ይቀድማሉ፡ ጉልበት እንጂ ብልጠት
ከለሌላቸው ግን በኋላ መጨረሻነቱን ይረከባሉ። ስልት የላቸውም!ጥበብ ይጎድላቸዋል! አዕምሮአቸው ዝንጉ ስለሆነ በስተመጨረሻ መወዳደራቸውንም ይረሳሉ
ያንጎላቻሉ…"ባዬች
በዕብሪት አስተያየታቸው ተመልካቹን ሊያረጋጉ ሞከሩ። ተመልካቹ በብዙ ሺ
የሚቆጠር ለስላሳዎችን ሣንዱቾችን… እየበላና እየጠጣ የአሸናፊነቱን
ክብር በሳይንሳዊ ስልት በሰለጠኑ አትሌቶቹ ተጎናፅፎ እልልታ
ሆታውን አያቅለጠ ለመሄድ ቋምጧል፡፡
አጋጣሚና ዕድል ያጋጠመቻቸው በደጋፊነት ስም በዝንባሌ መመሳሰል
ባለሰባበስ ውበት… እንዲያው በአንዱ ምክንያት
ይቀራረቡና ሁሉንም ዘንግተው መሳሳሙን ያጦፉታል:: ተመልካች
ከጎናቸው ይዘላል ያጨበጭባል ይቀባጥራል…
የማራቶን ሯጮች ዜና እንደገና ተሰማ “ሯጮች አንዱ ሌላውን ለማሸነፍ ፍጥነት እየጨመሩ ነው፡፡ ቅልጥማሙ አፍሪካዊ
ግን አሁንም ይመራል… ተወዳዳዎች ሰላሳ አምስት ኪሎ ሜትር እስከ አሁን ሮጠዋል፡"
ተመልካቹ በከፊል ግራ ተጋባ “ሰላሳ አምስት ኪሎ ሜትር ድረስ እንዴት አፍሪካዊው ሊመራ ይችላል? እነ እከሌ እነ እከሌ…አሁን መሳብ አለባቸው: መድረስ፤ ጥለውት ማለፍ! ሰዓት
አሻሽለው የክብረወሰን ባለቤት መሆን" አስተያየቱ ጭንቀቱ ጨመረ፡ የሚበላ የሚጠጣው ቀነሰ፡ ሮም ስታዲየም ላይ ዳመና
አንዣበበ ዳመናው ጠቆረ የውሃ እንክብል አዝሎ ሊያነባ ተቃረበ፡፡
ቅልጥማሙ አፍሪካዊ ኢትዮጵያን የወከለ ሲሆን ጃፓን ቶኪዮ በተካሄው ዓለማቀፍ ማራቶን ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣት ያሸነፈ ነው:: ህዝቡ ሚዲያዎችን መውቀስ ጀመረ፡ ከዚህ ቀደም የማራቶን አሸናፊዎች ሲዘረዘሩ እንዴት ስለ እሱ እንዳልተተቀሰ
ብዙዎቹን አስገረመ፡፡
“ኢትዮጵያዊው አትሌት በባዶ እግሩ ትንሽ ፀጥታ ሆነ ጋጠኛው ለጥቂት ጊዜ ሊታመን የማይችለውን ጉድ ከመናገር ይልቅ ዝምታን መረጠ፡፡ ከዚያ አትሌቱ በባዶ እግሩ እየሮጠ እዚህ ይደርሳል ያለ አልነበረም…" የስታዲዬሙ ህዝብ አንዴ ከዳር እስከዳር የመገረም ድምፅ አሰማ፡፡
ለተለያዩ ትርዒቶች ሜዳ ውስጥ የነበሩት በፍጥነት ሜዳውን መልቀቅ ጀመሩ፡
አፍሪካዊው… በባዶ እግሩ…
ሊታመን የሚከብድ... ድንቅ
ታምር… እንዴት… ሳይንሳዊው ስልጠናስ… ከህፃንነት ጀምሮ በእንክብካቤ ያደጉት አትሌቶችስ
የማራቶን ሯጮች ዜና እንደገና ተሰማ የቀራቸው...
እሯጮቹ አምስት ኪሉ ሜትር ብቻ ነው፡፡ ያ ቅልጥማም አሁንም
በባዶ እግሩ እየመራ ነው፡፡ ሊደርስበት የቻለ የለም! እሱ እንደ አቦ ሽማኔ ፍጥነቱን በመጨመር በሚያስደንቅ ፍጥነት ወደ ስታዲየሙ
እየተወረወረ ነው" አሉ ሲቃ የያዛቸው የሚዲያ ዘጋቢዎች፡፡
“አፍሪካዊው ሯጭ… ኢትዮጵያዊው… በቂላ አበበ ይባላል፡ እሚደንቅ ነው! በባዶ እግሩ… ከኔ ድምፅ ቀድሞ ሁለቱን ኪሎ
ሜትር ላስ አርጎ ጨረሰ... የቀረው ሶስት ኪሎ ሜትር ብቻ ነው"በተለያየ ቋንቋ አፍሪካ ኢትዮጵያ በቂላ ብቻ ሆነ የሚሰማው፡፡
ብዙው ተመልካች! ተአምረኛውን አትሌት ማድነቅና መናፈቅ ጀመረ፡፡ “በመምራት ጀምሮ በመምራት የሚጨርስ ያውም በባዶ እግሩ…" ግርምታው ሁሉንም አዳረሰ፡፡
የማራቶን ሯጮች ዜና “...አንድ ኪሎ ሜትር ብቻ ቀረ ኢትዮጵያዊው በቂላ" ማንም ሳይጠይቀው ህዝቡ
በስሜት ከመቀመጫው
ተነስቶ ጭብጨባውን ጩኸቱን…ፉጨቱን አቀለጠው፡ ስታዲየሙ ደመቀ ሯጩ ተጠጋ
ቀረበ ወደ ስታዲየሙ ገባ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ ስማይ አነሳች" ልጅዋ
ብቻውን ነው! የተከተለው የለም! ረጃጅም እግሮቹ ይወረወራሉ ሽበላ ነው፡፡ ህዝቡ እንደ ህፃን ልጅ ደለቀ
“ፍሪካዊው….ኢትዮጵያዊው ቢቂላ ተፎካካሪዎቹን ጥሎ በባዶ እግሩ…" ጋዜጠኛው መናገር አቃተው፡፡ በየቋንቋው ስሙ ደጋግሞ ተነሳ፡፡
አበበ ፍጥነቱን ጨመረ ፉክሩ ከራሱ ጋር ነበር፡ ጀግናው ኢትዮጵያዊ ገመዱን በጥሶ ለአገሩ ሶስተኛውን ድል አጎናፀፋት
የአፍሪካው ጥቁር አንበሳ በመላው ስቴዲዬም ድሉን ለማብሰር ደጋግሞ አገሳ፡
..የማራቶኑ ጀግና የአህጉሩን የአገሩን የጥቁሩን የህዝብ
የድል ባለቤትነት አረጋገጠ፡፡ አልወደቀም አልተልፈሰፈሰም ይልቁንስ ከአሰልጣኙ ባንዲራ ተቀብሎ እያውለበለበ
በደስታ የሰከረውን ህዝብ እየተዟዟረ ሲያመሰግን
ሉካዬ ከነበረበት ነቃ፡ ትኩር ብሎ አየው አትሌቱን፤ ከዚያ እንደ ሚዳቋ እየዘለለ ያገኘውን ሰው እየገፋ ወደ ጀግናው አትሌት ሮጠ፡፡ ልሎቹ ከበቡት
አኜስ ከተቀመጠችበት ተነስታ
“ሉካዬ… ሎካዬ… ሎካዬ…" እያለች እየጠራች ተከተለችው: እሱ ይዘላል! ወደፊት ወደ አትሌቱ፡፡ ከፊት ለፊቱ ቆመጥ የያዙ ወታደሮች መጡበት ገፈታትሮ ጥሏቸው ሮጠ፡፡
ሌሎች ከበቡት:፡ ያዙት። ከላይ ከላይ ያቃትታል፡፡ ወታደሮቹን አምልጦ ለመሄድ ታገላቸው፡፡ አለከለከ፤ እንባው ፈሰለ፧ ለመጀመሪያ ጊዜ አይኑ በሙቅ እንባ ረጠበ ግን ደስ ብሎታል፡
አኜስ አጠገቡ ደረሰች፡፡ ለጊዜው መናገር አቃታት፡፡ ቀስ ብላ ተጠጋችው፡ ወታደሮቹ ማንነቷን ጠየቋት፡፡ “ባለቤቱ ነኝ ባሌ ነው".ብላ መልሳቸውን ሳትጠብቅ “ሎካዬ… ሎካዬ…" ጠራችው፡፡ ወይ
አላላትም፡ ሩቅ ሄዷል። ሩቅ ወደ ልጅነቱ… ወደ ኩችሩ…
አኜስ እንደገና ደግማ ደጋግማ እየጠራች ስትወዘውዘው ነቃ: አትሌቱ ብዙም ሳይርቅ ለሚያደንቀው ህዝብ ባንዲራውን እያውለበለበ
ፈገግታውን ይለግሳል።
የሉካዬ ጣቶች ወደ አትሌቱ አመለከቱ፡፡ አኜስ አትሌቱን
አየችው። ሉካዬ ለስፖርት ደንታ እንደሌለው ታውቃለች፡፡
“ምንድነው?” አለችው።ዝም አላት ወዘወዘችው፡ እንደገና
ነቃ ባንዲራዋ አውቃታለሁ." አላት: አኜስ ግራ ገባት
“አገሬ ያችን ባንዲራ አውቃታለሁ፡፡እርግጠኛ ነኝ
አውቃታለሁ፡ ይችን ባንዲራ እስከዛሬ ቀስተዳመናው ላይ ካልሆነ አይቻት አላውቅም:፡ ሁሌ ሰማይ ሳይ ሳያት ከለማይ የመጣሁ ይመስልኝ ነበር
ያች ባንዲራ…" እንደ እብድ ቀበጣጠረ፡፡ የያዙት
ፖሊሶች ጤንነቱን ተጠራጠሩ፡፡ አዘኑለት እሱ ግን ደስ ብሎታል፡
ዘመዶቹን ባንዲራው ውስጥ አያቸው! ከብቶቹ ሲጮሁ ተሰሙት! አሳ ሊያጠምዱ ዘመዶቹ ታዩት ደስ አለው አኜስም ደስ አላት
ሎካዩን እንዲህ ደስ ብሎት አይታው አታውቅም፡፡ እንዲህ ልቡ ሲቦርቅ ከዚህ ቀደም አላየችውም፡፡
አኜስ አፏን ከፍታ ሳቅ አይሉት ልቅሶ የስሜት መምታታት እየታየባት ወደ ሎካዬ ልብ ጠጋ አለች፡፡ ልቡ ጆሮዋን ደለቃት፡
ይበልጥ ተጠጋችው እጆችዋ ወገቡ ላይ ተጠመጠሙ። እሱም
አቀፋት:: ባንዲራዋን እያዬ ፀጉሯን “ጳ" አድርጎ ሳማት፡
“ከሃገሩ ስም ይልቅ የአገሩን
ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ" ብላ ሽቅብ ሽቅብ እምባ በሞሉ አይኖቹዋ ስታየው ፈገግ ፈገግ እያለ አትሌቱን ባንዲራዋን አየና ሳቁን
ለቀቀው ድል አደረገ፡፡ ብቻውን ማንነቱን ሳያውቅ ኖሮ በመጨረሻ
ግን መሰረቱን አገኘ…

👍27❤3
የመጨረሻ ክፍል
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-23
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
ደ/ር ሰጵራ ከሁሉ ነገር ነፃ ሆኖ እቤቷ ከገባች አንድ ወር ሆኗታል፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ያለምንም እንከንነና የአካል ጉዳት የነፃነት አየር እተነፋሳለሁ የሚል ግምት ፍፅም አልነበራትም..ተስፋ ቆርጣ ነበር፡፡አሁን ማዕበሉ ሁሉ እንዲህ ፀጥ ብሎ ወጀብና መናወጹ ቆሞ ሁሉ ነገር ሰላማዊ ሆነ ማየቷ ማመን ነው ያቃታት፡፡
ወደቤቷ ስትመለስ ሶስት ሰዎች አብረዋት ተመልሰው ከእሷ ጋር እየኖሩ ነው፡፡የመጀመሪያው የቀድሞ ተመላላሽ ሰራተኛዋ የሆነችው ከበብሽ አሁን በቆሚነት ለብቻዋ ከኃላ ያለ አንድ ሰርቢስ ክፍል ተሰጥቶት እዛው እየኖረች የቀድሞ ስራዋን እንድትቀጥል ተደርጎል፡ሁለተኛው ከእሷ ጋር መኖር የጀመረው ሰው ካሳ ነው፡፡ ከፖሊስ ጣቢያ በነፃ ተለቃ እቤቷ በገባች ከሶስት ቀን በኃላ በፒካፕ መኪና ጠቅላላ እቃውን ጭኖ መጣና ግቢው ውስጥ ዘረገፈው... እንደዚህ ያደረገው ለእሷ ምንም ሳይነግራት ምንም ሳያማክራት ነው፡፡ አልከፋትም፤ እንደውም በተቃራኒው ደስታ ነው የተሰማት፡፡ ቤቷ ካለው ሶስት መኝታ ክፍሎች መካከል አንድን ሰጠችው.ከዕቃዎቹ መሀከል ያቻለለትን ያህል ወደክፍሉ እንዲያስገባ ካተደረገ በኃላ የቀሩት ዕቃዎች ታሽገው ወደእቃ ማከማቸ መጋዘን እንዲገቡ ተደረገ፡፡የመጨረሻውን ሶስተኛው አብሮት ለመኖር የመጣውና እሰከአሁን የራሱ መኝታ ቤት ስላልተዘጋጀለት ከእሷው ጋር ጉያዋ ውስጥ ገብቶ እየተኛ የሚገኘው ህፃኑ በድሉ ነው፡፡ይሄ የሆነው ዶ/ር ህጻኑን በተመለከተ ከእናቱ ጋር ከተነጋገረች በሃላ ልታሳድገው ተስማምታ ወደቤቷ ስላመጣችው ነው፡፡በአንድ ጊዜ የሁለት ልጆች እናት ልትሆን በመሆኗ ጥልቅ ደስታ ነው የተሰማት፡፡ የበድሉ እናት ልጇን ማየት በፈለገች በማንኛውም ሰዓት መጥታ ማየትና ልታዝናናውም በፈለገች ጊዜ ወደፈለገችበት ቦታ ወስዳ መመለስ እንደምትችል ተስማምተው በሁለቱም ፍቃድ ነው እንደዛ የሆነው፡
ከአስር ቅን በፊት ጎንደር ሄዳ ለሁለት ቀን በማደር እናቷንና ቀሪ ቤተሰቦቾን ጠይቃና አረጋግታ ነው የመጣችው፡፡
በዚህ አንድ ወር ውስጥ እራሳቸው ለህግ አሳለፈው አንዲሰጡ የተደረጉት ፐሮፌሰሩ፤ አቶ ሙሉና ሶስቱ ጠባቂዎች በአንድ መዝገብ በተከፈታቸው ክስ በከፍኛ የፀጥታ ጥበቃ እስከአሁን ሶስት ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል..እያንዳንዱ የፍርድ ቤት ውሎቸው በሀገሪቱ ሚዲያዎች ሆነ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ ትኩረት የሚያገኝ ትኩስ ዜና ሆኗል…በተለይ ከእነሱ ጋር ንክኪ ባላቸው ባለስልጣንና የፖሊስ አባላት አብሮ መታሰር እና በወንጀሉ ተጠያቂ መሆን ለጉዳዩ ተጨማሪ ድምቀት ፈጥሮለታል፡፡ የፓለቲካ ተቃዋሚሆችም ነገሩን በማራገብ መንግስትንና ባለስልጣኖቹን አንዲያጥላሉበት መንገድ ከፍቶላቸዋል፡፡
ሌላው በፍርድ ቤት ውሰኔ የሆስፒታሉን ህልውና ለመጠበቅና የግለሰቦቹ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱ የህክምና አገልግሎት ላይ የማይናቅ ድርሻ ሰላለው እና በዚህም የተነሳ የህዝብ ሀብት ጭምር መሆኑን ከግምት በማስገባት ሆስፒታሉ ሰሙን አድሶ እንደአዲስ ሰራውን እንዲቀጥል በመንግስትም ሆነ በፍርድቤት በኩል ከፍተኛ አርብርብ ተደርጎ ውጤት ተገኝቷል፡፡
በዚህም የተነሳ የዶክተሯን ለፍትህ ያደረገችውን ከፍተኛ ተጋድሎና አስተዋፅኦ ከግምት በማስገባት..የፕሮፌሰሩንና የአቶ ሙሉን የአክሲዬን ድርሻ ለእሷ እንዲተላለፍና እሷ ደግሞ በወንጀለኛቹ ምክንያት ጥቃትና የአካል ዘረፋ ለደረሰባቸው በአካል ቀርበው ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት ተጨባጭ መስረጃ ላቀረብ 78 ግለሰቦች እንደጉዳታቸው መጠን የሚከፈል ካሳ 30 ሚ ብር እንድትከፍል ተወሰነ፡፡
በዚህ ውሳኔ ወንጀለኞቹ ፕሮፌሰሩና አቶ ሙሉም ስለተስማሙ የሀግ ሂደቱ ያለምንም እንከን ነው የተከናወነው፡፡.እሷም ሚፈለግባትን ብር እጇ ላይ ያላውን ብር በመሰብሰብ የጎደላትን ከባንክ በመበደር ወዲያው ለተወሰነላቸው ተጠቂዎች እንዲውል ለፍርድ ቤቱ አስረከበች….፡፡
በዚህ ምክንያት የሆስፒታሉ 23ፐርሰንት የራሶ 16 ፐርሰንት የፕሮፌሰሩና 5 ፐርሰንት የአቶ ሙሉ በአጠቃላይ 44 ፐርሰንት ባለድርሻ ሆነች፡፡፡ 10 ፐርሰንት የሞቹ የአቶ ኤልያስ ሲሆን ለቤተሰቦቹ እንዲተላለፍ ተደርጎል…..ግን ከቤቱ ስራውን ለመስራት የደረሰ ልጅ ስላልነበረና ባለቤቱም ለስራ ፍቃደኛ ስላልሆነች…ውክልናዋን ለዶ/ሯ በመስጠቷ ደክተሯ ከሌሎቸ ፅቃቅን ባለአክሲዬኖች ከሰጧት ድምፅ ጋር ተዳምሮ ከ60 ፐርሰንት በላይ በሆነ ድምፅ ሆስፒታሉን የማስተዳደሩን ኃላፊነት ተረከበች፡፡ቀሪው 35 ፐርሰንቱ ደግሞ ቀጥታ የአቶ ጠሀ ድርሻ ሲሆን ሌሎች 5 ፐርሰንት ድርሻ ያላቸው የእሳቸው ደጋፊዎች አሉ ፡፡እርግጥ በምንም አይነት መንገድ እሷቸው ባለንብረት በሆኑበት ሆስፒታል ዳግም እደማትመለስ ድርሻዋንም እንደምትሸጥ ምላ ነበር፡አሁንም ማሀላዋን አላፈረስችም፡እቤቷ በተመለሰች በሶስተኛው ቀን ነበረ ሼክ ጠሀ በልብ ድካም በሽታ ሆስፒታል መግባታቸው የሰማችው፡፡ ወዲያው ከ3 ሰዓት በኃላ ሌላ ስልክ ተደውሎ መሞታቸውን ሰማች፡፡ በማግስቱ ቀብራቸው ላይ ከአብዬት ጋር ተገኘች፡፡እዛው ወደ ግብአተ-መሬታቸው በሚገቡበት ጊዜ ነበር‹‹አንተ ነህ ወይስ እግዜር ነው የወሰዳቸው››ብላ አብዬትን የጠየቀችው፡፡›
እሱም ‹ተጋግዘን ነው›ብሎ መለሰላት፡፡.እንዴት አድርጎ ሀኪሞች እንኳን መለየት በማይችሉበት ሁኔታ እንደመረዛቸው ዝርዝሩን አልጠየቀችውም፤እሱም ሊነግራት ፍቃደኛ አልነበረም፤ግን እንዳለው ቃሉን ጠብቋል፡፡
ከዛ በሃላ ፍፅም የእሳቸው ልጅ የማይመስል መሀመድ የሚባል ከድሮም ጀምሮ የምትወደው የ50 ዓመት ጎልማሳ የተማረና በስነ-ምግባር የታነፀ ልጃቸው የቤተሰቦቻቸውን ሙሉ ፍቃድና ውክልና አግኝቶ ቦታውን ተረክቦ ከእሷ ጋር ለመስራት መጣ…እሷም ከዛ በኃላ ነው የመጣላትን ሁሉ እድል ተጠቅማ 55 ፐርሰንት ድርሻ ወስዳ ሆስፒታሉና በመረከብ ወደቀድሞ ስራዋ በአዲስ ሞራል የተመለሰችው፡፡
///
ዛሬ ይሄ ሁሉ ከሆነ አንድ ወር በላይ ሆኖታል፤ለዚህ ያበቁአትን ሰዎች ለማመስገን ቤቷ የትረፈረፈ ድግስ በማዘጋጀት አቢዬትንና ልጆቹን ጠርታለች ፡፡ምሳ ተበልቶ …ብና ተፈልቶ፤ተጠጥቶ ካበቃ በኃላ ሁሉም ፊቱ የሚፈልጉትን መጠጥ አስቀምጠው እየጠጡ መጫወት እና መሳቃቅ ጀመሩ… ዶክተር ሁሉም እየተደሰቱና እየተፍነከነኩ ስታይ ደስ አላት፡፡
..እና ንግግር ለማድረግ ፈለገች… ትኩረት እንዲሰጧት አጇን በማጨብጨብ በተቀመጠችበት ሆና መውራት ጀመረች፡፡
ዛሬ ይሄን የምሳ ግብዣ ያዘጋጀሁት ሁላችሁንም አመሰግናለሁ ለማለት ነው፡፡እናንተ ለእኔ ነፍሴን መልሳችሁ ሰጥታችሁኛል፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፋችሁ ከገባሁበት የህይወት ማጥ ጎትታችሁ ታድጋችሁኛል..በኢትየጳያ ህዝብ ዘንድ ጀግና ተብዬ በየመንገዱ እንድከበር እድሉን አመቻችታችሁልኛል፡፡ሆስፒታሌን በ44 ፐርሰንት ድርሻ እና በ60 ፐርሰንት የድጋፍ ድምፅ መልሼ እንድቆጣጠር የሆነው በእናንተ ቀና ድጋፍ ነው፡፡
በአሁኑ ሰአት በጣም ሀብታም፤ስኬታማና ዝነኛ ሴት ሆኜያለሁ.. እናንተ እኔን ማዳን ብቻ ሳይሆን እነዚህ ሰዎች በተደላደለ ሁኔታ ቢቀጥሉ ኖሮ አጉል የሚያደርጎቸውን በሺ ሚቆጠሩ ንፅሀንን ከሚደርስባቸው አሰቃቂ የአካል ዘረፋን ህይወት ማጣት አድናችኋል…ስለዚህ ልትኮሩ ይገባል.እኔም በጣም ነው የምኮራባችው፡፡

👍44❤1
ግን አሁን ይሄንን የመሰለ የፅድቅና የጀግንነት ስራ ከሰራችሁ በኃላ መልሳችሁ ወደድሮ ህይወታችሁ የምትመለሱ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም፡፡እናንተ ከአሁን በኃላ ልዩ ሰው መሆን አለባችሁ.. በዚሁ ንፅሀንን ምትታደጉ፤ ስውር ወንጀለኞን የምታጋልጡ፤ ለተግፉት ዋስትና …ለተረገጡት ድምፅ የምትሆኑና መቀጣት ያለበትንም ለህግም እያሳለፈችሁ የምትሰጡ ስውር የነፃነትና የፍትህ አርበኞች መሆን አለባችሁ፡፡ዝርዝር ጥናቱ ገና እኔ አበዬትና ካሳ እያዘጋጀነው ሲሆን ሁሉ ነገረ ካለቀ ለእናተ እንድታውቁት ይደረጋል፡፡
ግን ከአሁን ወዲህ ሁላችሁም የአብዬት ሰራተኞች እንደሆናችሁና በየወሩ የራሳችሁ የሆነ ደሞዝ እንዳላችሁ ስናገር ደስ እያለኝ ነው፡፡እቤቱን በጭብጨባ አናጉት
አብዬት ተራውን መናገር ጀመረ‹‹አዎ .ደ/ር እንዳለችው ከአሁን በኃላ ከመካከላችን ማንም የበፊቱን ስራ የሚሰራ አይኖርም...መስረቅ ፤ማጅራት መምታት ወዘተ መሰል ስራዎች አይፈቀዱም..ይሄንን ለማድረግ ሁላችሁም ቃል እንድትገቡልኝ እፈልገላው..››
‹‹ቀለል እንገባለን .ቃል እንገባለን…››
እንግዲህ ዶክተር እንዳለችው ለሁላችሁም በዳይመንድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ውስጥ ቆሚ ስራ ይሰጣችኋል….ማለቴ የጥበቃ ክፍል ፤ጉዳይ አስፈፃሚ የመሳሰለው፡፡ግን ከዛም በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የምንሰራው ሰራ ይኖረናል….ዶ/ር ቅድም ለመነካካት እንደሞከረችው.ልክ እሷ እንዳጋጠማት አይነትቸ ችግር ውስጥ ያሉትን የተገፍትን በወንጀለኞችና ባለስልጣን በደል ደርሶባቸው ከቤታቸው ከንብረታቸው የተፈናቀሉትን ማንኛውንም ግለሰብ ሳንመርጥ በአቅማችን እንረዳለን፤እራሳችንን ሳናጋልጥ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እንደርጋለን፡፡.ሌላው ጠቅላላ የስራችን ይዘት ምንድነው የሚለውን ግን በዘርዝር በቅርብ እንነጋገርበታለን፡፡ ከዚህ አፈንግጦ ወደበፊት ህይወቴ እመለሳለው ሚል ግን የሁላችንም ጠለት ስለሚሆን እኛም አሳልፈን እንሰጠዋለን… እንደማንኛውም ሌላ ወንጀለኛ ጠላታችን አድርገን እንፋለመዋለን፡፡
ካሳ እጁን አወጣ
‹‹እሺ ካሳ››አለው አብዬት የሚናገረውን ነገር ለመስማት በመጓጓት
‹‹ይህ ፊትህ ላይ ያለውን ጠባሳ ሰርጀሪ ተሰራው.. ከቂጥህ ላይ ቦጨቀው ይለጥፉና ያጠፉልሀል.የህክምና ወጪውን እኔ እሸፍናለሁ››አለው፡፡
በተናገረው ነገር ሁሉም ግራ ተጋቡ‹‹ያን ያህል ምን አሳሰበህ?››
‹‹ለአንተ አስቤልህ አይደለም.ለራሴ ብዬ ነው›
‹‹አልገባኝም››
‹‹ያው ከአሁን በኃላም አብረን የምንሰራና ደጋግመን የምንገናኝ ከሆነ ይህንን ፊትህን እያየሁ መፍራትና መሳቅ አልፈልግም››
‹‹እሺ ከፈለክ አሰራዋለሁ..ሌላ የምትለው ነገር አለህ?›አለው እየሳቀ
‹‹አዎ እዚህ ቤት የተጠራቀሙ የተሰባበሩ ነፍሶች በጣም ነው አንጀቴን የሚበሉኝ .አሁን ምን አልባት ቀስ በቀስ እየተጠገኑና እየተስተከካከሉ ይሄዳሉ ብዬ አስባለሁ.እዚህ ቤት ካሉ ነፍሶች ውስጥ የእኔዋ ነፍስ ብቻ ያልተሰባበረች በመሆኗ ኩራት ይሰማኛል፡፡›አለ
አብዬት ፈገግ አለና‹‹አይ ካሳ ብዙም አትኩራራ…የራስ ነፍስ መሰበር እኮ ለራስ አይታይም፤እኔ አሁን ያንተን ነፍስ ሳያት ስንጥቅጥቅ ብላ ነው የምትታየኝ ››አለው፡፡
ዶክተር መሀከል ገባችና‹‹በሉ እንግዲህ እቤታችሁ ነው ..ብሉ ጠጡ፤ ሙዚቃውን ሞቅ አድርጉትና ጨፍሩ.. ተዝናኑ ዛሬ ሁላችንም እዚሁ ነው የምታድሩት…ለሁላችሁም መኝታ ተዘጋጅቷል፤የጎደለ ነገር ካለ ጠይቁ›አለቻቸው ሁሉም በጭብጨባ መስማማታቸቸውን ገለፅ
በዚህ ጊዜ ከእንቅልፍ የተነሳው ህፃኑ በድሎ ፈንደስ ፈንደስ እያለ መጣና ጉያዋ ተሸጎጠ….ዶ/ር አንስታ አቀፈችው…ከወንዶቹ መካከል ሆና ቢራዋን እየላፈች የነበረችው እናቱ በቆረጣ የልጇን እና የዶ/ርን ሀኔታ አየችና በደስታ ፈገግ አለች፡፡
//
ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ዶክተር ሰጵራ ንፋስ ለመቀበል ወደበረንዳ ስትወጣ አብዬት ከኃላው ተከተላት
‹‹ምነው ደ/ር እንደ እኔ ሰከርሽ እንዴ?››አላት
‹‹ምነው አንተ ሰክረሀል እንዴ….?ብዙ ስትጠጣ እንኳን አላየውህም፡፡››
‹‹መጠጥ ብቻ መሰለሽ ደስታም እኮ ያሰክራል፡፡››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…እንደዛ ከሆነማ እኔም ሰክሬላሁ፡››
‹‹ልጅሽስ?››
‹‹ማለት? ሆዴ ውስጥ ነዋ!!››
‹‹አይ ..አሱን አይደለም የጠየቅኩሽ…ታላቅዬውን… በድሉን ››
‹‹እ ..እናቱ ይዛው ተኝታለች.. ከእሷ ጋር ነው፡፡››
‹እ ..ዛሬ ብቻሽን ነዋ የምታድሪው ››አላት
‹‹ብቻዬን…?አዎ ምነው የተገናኘን ቀን የጀመርከውን ልትጨርሰው ፈለክ እንዴ?›››አለችው
በእፍረት አንገቱን አቀረቀረ…ዶክተር ሁልጊዜ ስለዛች ቀኗ ድርጊቴ ሳስብ ትንሽነት ነው የሚሰማኝ..እባክሽ ይቅርታ አድረግልኝና ሁለተኛ መልሰሽ አታንሺብኘ››
‹‹አይ አንተ..እኔ ደግሞ ስለእዛች ቀን ሳስብ ያንተን ትልቅነት እና ስሜትን የመቆጣጠር ችሎታ እያሰብኩ ነው…ምደነቅብህ….››
‹‹ተይ እንጂ ዶክተር››
‹‹እውነቴን ነው..እንደውም የዛን ቀን የጀመርከውን መጨረስ አለብህ…ና›› ብላ ክንዱን ያዘችና ያለምንም ይሉኝታ ሳሎን ውስጥ እየጨፈሩ ባሉት ጓደኞቻቸው መካከል ሰንጥቃ ወደመኝታ ቤቷ ይዛወ ሄደች…ሲደርሱ ካሳ በራፍ ጋር ተገትሮ..ለንቦጩን ጥሎ እየጠበቃቸው ነበር…አብዬት እርር አለ፡፡ ተ ፈ ፀ መ ::

👍35🥰14😁10👏1😢1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታረ
“ሶራ ልታስብበት ይገባል" አለችው በጥሞና እያየችው፡
"ወደ ኢትዮጵያ አብሬሽ ልሂድና የአያትሽን የትውልድ ቦታ ላፈላልግሽ እፈልጋለሁ፡፡ ያሳየሽኝ መቀመጫ ታችኛው የኦሞ ወንዝ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ማህበረሰቦች በሙሉ ይጠቀሙበታል። ኤርቦሬ
ሐመር በና ካሮ መቀመጫው በእርግጥም የኦሞ ህዝቦች ብቻ
እንደሆነ አምናላሁ" አላት።
ጥሩ! እኔ የተዘጋጀሁት ለአንድ ሰው በሚበቃ ባጀት ነው" በግልፅ ችግሯን ገለፀችለት፡
“እኔ ደግሞ የራሴን እችላለሁ በዚያ በኩል አታስቢ"
አመሠግናለሁ ሶራ በእውነት አንተን ማግኘቴ ያላሰብሁት
እድል ነው" ብላ ፈገግ አለችለት::
ሶራና ኮንችት በዚህ መልክ ለአፍሪካ ጉዞዋቸው
መሰናዶአቸውን አብረው ቀጠሉ፡፡
ከሁዌልቫ ሊዝበን በመርከብ የሚፈጀወ ጊዜ ግማሽ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከጅበላርታር ለንደን በሚወስደው የጉዞ መስመር መርከቡ
አቅጣጫውን ካስተካከለ በኋላ ተጓዡ እንደየግል ፍላጎቱ ተሰማራ፡፡
ኮንችትና ሶራ በመርhቡ ግራ ጎን ባለው ማማ ላይ ወጥተው በርቀት የተዘረጋውን የአትላንቲክ ውቅያኖስ እያዩ ተቀምጠዋል፡፡
ኮንችትና ሶራ የለበሱት ነጭ ቲሸርት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል የአለባበስ ልዩነቱ ኮንችት ነጭ አጭር ቀሚስ በሰፊ ቀበቶ ሶራ
ደግሞ ቡላ ሲልክ ሱሪ መልበሳቸው ነው፡፡ ሁለቱም ጥቁር የፀሐይ መነፅር አድርገዋል። ቀኑ ሞቃታማና ፀሐያማ ነው፡፡
ወደ ሊዝበን የመሄዱን ሐሳብ ያመጣችው ኮንችት ናት ሶራን የተለያዩ ቦታዎችን ሙዚዬሞችን ታሪካዊ ቦታዎችን መዝናኛዎችን… እንዲያይ ብዙ ጊዜ እየጋበዘች ወስዳዋለች፡፡
ስለ ፖርቹጋሎች ምን ታውቃለህ?" አለችው አንድ ቀን በማድሪድ ከተማ መናፈሻ ውስጥ እንደተቀመጡ፡፡
“ባህረተኞችና ቅኝ ገዥዎች እንደነበሩ"
“አዎ! ፖርቹጋሎች ማንም እሚያውቃቸው በባህር ላይ
ህይወታቸውና ለቅኝ ገዥነት በብዙው የዓለም ክፍል በተለይም በአፍሪካና በላቲን አሜሪካ ያደርጉት የነበረውን ቅኝት ነው፡ ይህ ጥንት ሌላው ስለእነሱ ያውቅ የነበረው እውቀት ነው በአሁን ሰዓት ግን ፖርቹጋል ብዙ ቱሪስት የሚስተናገድባት አገር ናት።
“ሙዚየሞቻቸው የዓለምን ቅርስ የያዙ ናቸው ይባላል።
ስለ ዓለም ይበልጥ ማወቅ የማፈልገው ይህ ትውልድ ደግሞ ቅርሶች አሉ የተባለበት መጉረፉ የተለመደ ነው፡፡
“አፍሪካ የራሷ ካሏት ቅርሶች ይልቅ በአውሮፓ ያሏት ቅርሶች ይበልጣሉ፡ የሚያሳዝነው ግን አፍሪካ ለቅርሷ የባለቤትነት
መብት የላትም፡፡ በኮለኒያሊስቶች የተዘረፈችው ቅርስ አሁንም የእነሱ ኪስ ማድለቢያ ነው፡፡
“ከኢትዮጵያ የመጡ
ቅርሶች ከዚህ በፊት ፈረንሳይ እንግሊዝ ጣሊያን… ሄጄ አይቻለሁ፡፡ ፖርቹጋልም እንደዚሁ ብዙ
የሃይማኖት መጽሐፍትና የታሪክ ቅርሶች አሉ: አንዳንዴ ሳስበው እንዲያውም ኢትዮጵያውያን
የታሪክ የባህል ተመራማሪዎች ወደ ፊት በአገራቸው ታሪክና ባህል ላይ ምርምር ማድረግ ቢፈልጉ ዋቢ ቅርሶችን ለማየት ወደ አውሮፓ ብቅ ማለታቸው የግድ
ይመስለኛል
“አውሮፖና በሌላው የሰለጠነው ዓለም አንድ ወቅት የቅርስ ዝርፊያ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በስምምነት አንዱ ዘንድ ያለው ወደ ሌላው እየተመለሰ ነው። ባይመለስ እንኳን የዛ ቅርስ ባለቤት
የሚሆነው በመጀመሪያ ባለቤት የነበረው አገር ነው፡፡ ለዚህ ውጤት
ግን ብዙዎች ልሳናቸው እስኪዘጋ እየጮሁ ታግለዋል፡፡ ግዞት ስደት
እስራትም ደርሶባቸዋል: አሁን ግን ቀስ በቀስ ህልማቸው እውን
እየሆነ ነው:
ሶራ አንተም ፖርቹጋል ያሉትን ሙዚየሞች ስታይ
እርግጠኛ ነኝ ብዙ የአገርህን ቅርሶች ታያለህ የኢትዮጵያ ቅርሶች
የሚል ጽሁፍ ግን አይታይባቸውም፡፡ አንድ እውነት ግን በህሊናህ
ይመጣል! ቅርስ ለአንድ ሀገር ህዝብ ማንነት ምን ያህል አስፈላጊ
መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡
የአውሮፓውያን ስልጣኔ ባሰባሰቡት ቅርስ ላይ የተመስረተ ነው ለቅርሶች ልዩ ከበሬታ መስጠትም የአንድ ሃገር ስልጣኔያዊ
ብስለት መለኪያ ነው፡
“ሶራ ስለ! ሌላውን ለማወቅ ከሌላው ለመማር ራስሀን
ለማነፃዐር ያጣኸውን ለመፈለግ… ጉብኝት አስፈላጊ ነው" አለችው፡፡
ልክ ነሽ ኮንችት ለምን ለጊዜው ፖርቹጋልን አብረን
አናይም?” አላት፡
“በደስታ! ሶራ" ብላ ሳቋን ለቀቀችው: ኪሊሊ... የሚለውን ሳቋን ሰማው: ናፍቆት ነበር ሣቋ::
“ሳቅሽ ደስ ይለኛል አላት ፈገግ ብሎ፡፡
“አመለግናለሁ” አለችው። ኪሊሊ ብላ እየሳቀች:: እያያት አሰበ: ሌላውን ማወቅ ነው….. የተናገረችውን አስታወሰ፡
አውሮፓውያን ስልጣኔ ባሰባሰቡት ቅርስ ላይ የተመሰተ ነው ገረመው: በልተህ በልተህ ወደ አገርህ አንጋጥ ተሪቱማ እሱም
አገር አለ፡፡ ተግባሩ ግን ጠፋ፡፡ ሌላው እስኪጀምረው መጠበቅ አንዱ የአፍሪካውያን ችግር ነው። እና የሚጠቅመውን ሁሉ ለአገሩ ጆሮ
ለማድረስ ለአገሩ ሕዝብ ለማሳየት የተማረውን ዜጋ ህሊና ለማንኳኪያ ከእንቅልፍ ለመቀስቀሻ ሊጠቀምበት እንደሚገባ ቃል ገባ: እራሱን ግን ተጠራጠረው “ፍርፋሬ ያዘናጋኝ ይሆን?” አለ።
ኮንችት ያለውን አልሰማችም፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሁለቱ መንገደኞች መርከቡ ጉዞ ከጀመረ በኋላ
ጨዋታቸውን ጀመሩ፡፡
“…ለወላጆቼ የመጀመሪያ ነኝ፡ ከኔ በታች ሁለት ታናናሽ
ወንድሞች አሉኝ፡ በተለይ ከኔ ተከታይ ጋር በሰፊ አልጋ አብረን ነበር የምንተኛው።
አባቴ ፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ ለወደፊቱ መፃኢ እድላችን
ስለሚያስብ ገንዘብ ለማስቀመጥ ቢጥርም ግማሽ ኢትዮጵያዊቷ እናቱ
ካሪና ግን ለግል ውበቷ ብቻ የምትጪነቅ አባካኝ በመሆኗ አባቴ
እንዳሰበው ገንዘብ የማስቀመጥ ህልሙ አልሳካ ሲለው በእናቴና
በአባቴ መካከል አለመጣጣሙ እየበዛ በመምጣቱ ተለያዩ በዚህ
ሳቢያ አባቴ ወደ ቤታችን የሚመጣው በጣም እየቆዬ ሆነ፡ እኔ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኔ መጠን የአባቴን ፍቅር በምሻበት
ወቅት ላገኘው ባለመቻሌ ከልቤ ጠላሁት ስለዚህ ከአባቴ ይልቅ ለኢትዮያዊው አያቴ ለሎካዬ ሆነ ፍቅሬ” ብላ ክሊሊ… ብላ ሳቀች
እሱም ፈገግ አለ ጉሮሮዋን ለማራስ የቆርቆሮ ቢራዋን ለመክፈት ዘወር ስትል የቢራው ቆርቆሮ ወደቀባት ለማንሳት ጎንበስ ስትል
አየው ጥቁር ፓንቷን
አፈር አለና ፊቱን ወደ አትላንቲክ ውቂያኖስ አዙሮ
ሲመለከት hርቀት የሆነ ብረት አዬ
ኮንችት ተመልከች ያ ምንድው?” አላት።
መርከብ ነው የመሬት ክብነትን ስትማር ስለዚህ
አልተማርህም..."
አዎ አሁን ትዝ አለኝ: ሳታይ የተማርሽው ቶሎ
ይዘነጋል እሽ ጨዋታሽን ቀጥይ? አላት አንጋጣ አንዴ ጉንጯን ሞልታ ተጎነጨችና
"ኧህ ብላ ጨዋታዋን ያቆመችበትን አሰብ በማድረግ
ቸበርቻቻ ወዳጅዋን እናቴን ግን እወዳት ነበር በፊት
እንነገርሁህ በቁመናዬ ሳቢያ በትርፍ ጊዜዬ የግል ገቢ ማግኘት የጀመርሁት ገና በህፃንነቴ ቢሆንም እናቴ እናደ ሌሉች ልጆች
አስባ ልብስ ስለማትገልኝና ከሷ የምጠብቀውን አንድም ቀን "ቆንጆ ብላኝ ስለማታውቅ ለእሷ የነበረኝ ፍቅር እየሟሽሽ የጥላቻ
ስሜት ህሊናዬን ይተናነቀው ጀመር አንድ ቀን እንዲያውም አባቴ ጠፍቶ ከርሞ በመጣበት አጋጣሚ
እናቴና አባቴ አንድ ላይ በሚገኙበት ወቅት ጠባቂ በነበረኝ ገንዘብ ላይ ስጦታ ገዝቼ አልጋቸው ላይ አስቀመጥኩላቸ
ንግግሯን ሳትጨርስ ሶራ
አቋረጣትና
ይቅታ ስላቋረጥኩሽ የዚያን ጊዜ የስንት ዓመት ልጅ ነበረሽ።
ምናልባት የአስራ አራት ዓመት ከዚያ አይበልጠኝም
አለችው።
እሽ ቀጥይ አላት ሶራ

👍21
“እናቴም አባቴም ስለዚያ የልጅነት ስጦታዬ ትንፍሽ ሳይሉኝ ስጦታውን ግን እየተቀባበሉ ሲያዩት አይቻቸዋለሁ ይህ ደሞ አይወዱኝም ማት ነው የሚል ስሜት ፈጠረብኝና
ያልደነደነችው ልቤ ሐዘን እንደ ደሰቀ ዳቦ ነካከተች ከዚያን ቀን በኋላ ከነሱ የምለይበትን ቀን ማሰላሶል ጀመርሁ

👍10
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
“እናቴም አባቴም ስለዚያ የልጅነት ስጦታዬ ትንፍሽ ሳይሉኝ ስጦታውን ግን እየተቀባበሉ ሲያዩት አይቻቸዋለሁ ይህ ደሞ አይወዱኝም ማት ነው የሚል ስሜት ፈጠረብኝና
ያልደነደነችው ልቤ ሐዘን እንደ ደሰቀ ዳቦ ነካከተች ከዚያን ቀን በኋላ ከነሱ የምለይበትን ቀን ማሰላሰል ጀመርሁ
“በየቀኑም ከነሱ ለመራቅና እነሱን ለመርሳት ስል የወንድ ጓደኛ ያዝሁ
የያዝኋቸውን የወንድ ጓደኞቼን እንድርቃቸው ተገደድሁ።
“እናቴ እንደነገርሁ የስነ አዕምሮ ትምህርት እውቀት
አላት ይሄ እከሌ የሚባለው የወንድ ጓደኛዬ ነው ስላት፡-
የጨካኝ ሰው መልክ ነው ያለው፡፡ ወንጀል ለመሥራት ወደ ኋላ አይልም…” ትለዋለች ወይም ደግሞ፡-ዠ
“ይኸ ጅላጅል ነው: የታወረ አዕምሮ ያለው ነው፡፡ እና
እሱን ስትመሪ መኖር ትፈልጊያሽ" ትለኛለች፡፡ ሌላውን ሳስተዋውቃት
ደግሞ፡-
ይኸ ጭልፋ አፍንጫ አንድ ቀን አይንሽን ያወጣዋል: እንደ ጣውላ የተላገ የሚመስል የወንድ ቅርፅ የሌለው... እኔ አንችን
ብሆን ኖሮ ከሱ ጋር በሆንሁ ቁጥር በጥላቻ አስመልስ ነበር….እያለች ስታጥላላብኝ ከያዝኋቸው የወንድ ጓደኞቼ በሙሉ ራቅሁ: በኋላ ግን ወደ ቤታችን አልፎ አልፎ ብቅ ከሚለው የእናቴ ጓደኛ
ልጅ ጋር ግንኙነት ጀመርሁ፡
ፔድሮ ይባላል፡ ሙልቅቅ ያለ ባህሪው መያዣ መጨበጫ የሌለው ነው፡፡ ከፍቅር ይልቅ የጦርነት ታሪክ ማውራት ይወዳል:
ህዝብ ከተጨናነቀበት መዝናኛ መሃል ይወስደኝና ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ እየጮኸ ጩኸትና ሁካታ አልወድም' ይለኛል ማን
ለምኖህ መጣህ? ደሞ ማንስ ጩኸት ይወዳል እንዳንተ ካለው ደደብ
በስተቀር' እልና በሃሳቤ እነቂው እነቂው ያሰኘኛል፡፡ አማራጭ ግን አልነበረኝም፡፡ ወላጆቼን ለመርሳት ስል በሄደበት ሁሉ እንደ ግል
ውሻው ካለሰንሰለት እየተሳብሁ እሄድለታለሁ! ሁኝ ያለኝንም እሆንለት ጀመር፡፡ እናቴም ከእሱ ጋር መሆን ደገፈችልኝ
የማላይበትን ውበት እየደረደረች አይታይሽም፧ እስኪ ተመልከች
እያለች እራሴን አይነ ስውር እንደሆንሁ እስክቆጥር ድረስ ግራ አጋባችኝ፡፡ ስለዚህ ፔድሮን በእናቴ ግፊት ልወደው ሞከርኩ፡
“የግንኙነቴን ጥልቀትና እንደ እንቁላል ተጠንቅቄ
እንደያዝሁት የተገነዘበው
ፔድሮ ግን ልቡ እያበጠ
ለፍቅር የዘረጋሁሉትን ልቤን ይጠብሰው ጀመር! እየቆየም በመጥፎ ባህሪው እየወጋጋ ማድማቱን ቀጠለ፡፡ ከእሱ ከተለየሁ ብቸኝነቱን ስለማልችለውግን
ስቃዬን አምቂ በትዕግስት እየተለማመጥሁ
የሞዴሊስነት ፍላጎቴን ገትቼ ለሶስት ዓመታት የመከራ ጊዜ አሳለፍሁ?።
“ሶራ! የሚገርምህ ደግሞ ያ የጭራቅ ልጅ አንድም ቀን "ቆንጆ ነሽ" ብሎኝ አያውቅም፡፡እንደወላጆቼ እሱም አሞካሽቶኝ
አለማወቁ ደግሞ ፍርሃት ለቀቀብኝ፡፡ ከውጪ ሰው ይልቅ እነሱ ቆንጆ ነሽ ቢሉኝ ደስተኛ እሆን ነበር፡ ይህን ባለማለታቸው ግን
እራሴን ለማወቅ ወደ ሞዴሊስትነቱ ሞያ ተመለስሁ፡፡ ጅምናዚዬም
መሄድ አዘወተርሁ፡ በቁንጅና ውድድር ከተመረጡት አንዷ ብሆንም
ማሸነፍ ባለመቻሌ በገንሁ፡፡ ፔድሮ ያኔም ይጀነንንብኝ ነበር በመጨረሻ በቁንጅና ውድድሩ ባሽነፍሁበት እለት እናቴ አበባ አበረከተችልኝ፤ እሱ ግን ሳይመጣ ቀረ፡፡
“የሚገርምህ ያን ጭራቅ እንዲያ አንጀቴን እየበጣጠሰ ሲጥለው ልርቀው አልቻልሁም፡፡ ስለዚህ ከስፔን ውጭ ሄዶ ሥራ መስራት ማስታወቂያ ሲወጣ ከቤተሰቦቼ ለመራቅና እፎይታን
ለማግኘት አመች በመሆኑ እሱም እንዲወዳደርና አብረን እንድንሄድ
ጠየኩት፡፡
“ምን እንዳለኝ ታውቃለህ? ማራኪዋን አገሬን ጥዬ የትም አልሄድም አለኝ፡፡ የዚያን ቀን ብቻ ደፍሬ ገሃነም ግባ ብየው
በማስታወቂያው መሰረት ሄጄ አፍሪካ በተለይም አያቴ አገር ኢትዮጵያ እንዲመድቡኝ ጠየኳቸው፡፡ ሆኖም አላሰመረም፡ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች እንጂ ኢትዮጵያ ከዝርዝሩ
ውስጥ እንደሌለችበት ሲነግረኝ እጢዬ ዱብ አለች፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ምርጫዬ አስፈላጊ ስላልነበረ የትም መድቡኝ ስላቸው ቡርኪናፋሶ
መደቡኝ፡፡
ሶራ የሚሳዝንህ ፔድሮ ውጭ አገር እንደማይሄድ
እንዳልነገረኝ ሁሉ ሃሣቤን ቀይሬ ተወዳድሬ ላቲን አሜሪካ ብራዚልን አግኝቻለሁና አብረን እንሃድ' አለኝ፡፡
የዛኑ እለት እኔጋ የነበረውን የአፓርታማችንን ቁልፍ
ወርውሬለት ሁለተኛ አጠገቤ እንዳይደርስ አስጠንቅቄው ሄድሁ፡፡ ከሱ
ከተለየሁ በኋላ ግን አይኔ የፈረጠ እስኪመስለኝ ድረስ ሳለቅስ አደርሁ: ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ ትክክለኛ ውሳኔ መወስኔን በመረዳቴ ትልቅ እፎይታ ተሰማኝ፡፡
“በልጅነቴ የወላጅ.
ከአደግሁ በኋላ ደግሞ የፍቅረኛዬ 'አፈቅርሻለሁ' አለማለት የማልወደድ
ቢያደርገኝም ወደ አፍሪካ ከመሄዴ ሦስት ወራት በፊት
የተዋወኳቸው የተለያዩ ወንዶች ግን ውበቴን እያዩ የተንጠለጠለ ሥጋ እንዳየ ድመት እየተቁለለጩ ሲያላዝኑ ስሰማና በተለይም
በጓደኝነት የያዝሁት ፎራንችስኮ መላ ሰውነቴን እየላሰ “ቆንጆ ነሽ…
ውሸት ነው!.." እያለ ደርቆ የነበረውን ሞራሌን በፍቅር ዜማ ሲያረሰርሰው ድርቆሹ ሞራሌ እንደገና ለመለመ፤ እንደገና ታነፀ….አፍሪካ ሄጄ ስመለስ ግን የቁንጅናን ትልቁን ትርጉም አወቅሁት‥
አካላዊ ሳይሆን ህሊናዊ መሆኑን….
“ሶራ! ይታይሃል ከፊት ለፊታችን ሊዝበን ናት
የፖርቹጋል ዋና ከተማ፡፡ ወደ ጕብኝት ቦታችን እየደረስን ነው" ብላው ከመርከቡ መቀመጫ ተነሳችና ሄድ ብላ ወገቧን ለማንቀሳቀስ ከወገቧ እጥፍ ብላ ስፖርት ስትሰራ አየው ጥቁር ፓንቷን…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
"ሔሉ… ሔሉ… ካርለት አልፈርድ ነኝ ከአዲስ አበባ"
"ሃይ ካርለት! ደህና ነሽ? ስፖንሽኛውን ስታቀላጥፈው
ገረመኝ እኮ"
“እውነትሽን አመሰግናለሁ፡፡
አዲሳባ ከመጣሁ
አምስተኛ ቀኔ ነው፡፡ ወደ ሐመር ከአንድ ሣምንት በኋላ እሄዳለሁ፡፡ መቼ ልትመጭ አስሰሻል?"
“አዝናለሁ ላገኝሽ የምችል አይመስለኝም፤ ምክንያቱም እኔ ከማድሪድ ወደ ሮም ከዚያ ወደ አዲሳባ የምበረው የዛሬ አስራ
አምስት ቀን ነው፡፡ ባገኝሽ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
“አልችልም ኮንችት ቶሉ መሄድ አለብኝ፡፡ ምናልባት…" ካርለት ፀጥ ብላ አሰበችናi “ምናልባት አዲሳባ ስትመጭ የሚቀበልሽ ሰው ላስተዋውትሽ እችላለሁ፡፡ ሔሎ! …”
“አመሰግናለሁ ካርለት፡፡ አንችን ማግኘት ካልቻልኩ ለጊዜው ችግር የሚያጋጥመኝ አይመስለኝም፧ አብሮኝ የሚመጣ ኢትዮጵያዊ
አለ ሔሎ!"
“ሔሎ ኢትዮጵያዊ!” ካርለት አዕምሮዋ ደነሰባት፡፡
“ጥሩI እንግዲያው እዚህ ከመጣሽ በኋላ" ተቀጣጠሩና ካርለት ስልኩን ዘጋችው፡፡ በአይነህሊናዋ ኮንችትን ልታስታውሳት
ሞከረች ረጅም ሸንቀጥ ያለች ውብ ጠይም! ካርለት ከንፈሯን እንደ ጡጦ ጠብታ እራሷን ወዘወዘች፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::
ካርለት ዋና የለመደችበትን
ጊዜ አታስታውሰውም፡
ምናልባት በእናቷ ሆድ ካለበለዚያም ገና ጨቅላ እያለች፡ ቁም ነገር
ብሎ የነገራት የለም፡፡ ጥሩ ዋናተኛ ሆና ነው ራሷን የምታውቀው፡
ግዮን ሆቴል የሄደችውም ለመዋኘት ነው፡፡ ብቅ ጥልቅ, ብቅ ጥልቅ
ውሃው ውስጥ ግልብጥ እያለች የግዮንን ሆቴል መዋኛ በቁመትና በወርዱ እየዋኘች አሳ ሆና ለመቆየት፡፡ ከዚያ ፎጣዋን አንጥፋ ገላዋን

👍20🥰1
ለፀሐይ ሰጥታ ጥቁር መነፅሯን በመሰካት መቅረት የሌለበትን
የሆሊና ሳንዱችዋን ትወስዳለች ንባቧን፡፡ አመሻሽ ላይ ከንባቧ
ወጥታ አካባቢውን የምታየው ፀሐይ ማተኮሷን ስትቀንስ ቅዝቃዜ
ገላዋን መላስ ሲጀምር ነው፡፡
ደ
ካርለት በእንደዚህ ዓይነቱ ግላዊ የመዝናኛ ሰዓቷ መናገር ትጠላለች፡ ፀጥታን እንደ አየር እየሳበች ገላዋን ውሃ ውስጥ መንከር ከዚያ ፀጥታዋን እንደለበሰች ወደ ንባቧ አዕምሮዋን ከፍታ
መግባት… ይህ ነበር የዘወትር ልማዷ፡ አንድ ቀን ግን ቀኑ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ነው፡፡ ብዙ ዋናተኛ የለም፡፡ የግዮን የዋና ገንዳ
በውሃው ውስጥ ሽል ብቅ… ሽል ብቅ እያለች ስትዋኝ አንድ እድሜው በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ መዋኛውን በወርዱ
እያቋረጠ አርፎ ይቆይና ደሞ ሲዋኝ አየችው፡፡ ዋና ገና እየለመደ ነው፡፡ ገረማት ዘግይቷል፡ ካርለት እየዋኘች አጠገቡ ሄደች።
አላያትም ወይንም ሊያያት አልፈለገም፧ ማዶ ማዶ ብቻ ያያል
“ሃይ?” አለችው፡፡
“ሃይ" አላትና ፀጥ አለ፡፡
ወዲያው ወደ ውሃው ገባ። ዋናው ያስቃል፧ ሰውነቱን ዘና ሳያደርግ እግሩና እጁን ቶሎ ቶሎ እያንቀሳቀለ ውሃውን ያንቦራጭቃል፡፡ ካርለት በእንቅስቃሴ ብዛት ቶሉ እንደሚደክም ገመተች።መሃል ሊደርስ ሲል የገዳውን ግድግዳ በእግሯ በሃይል ረግጣ
በውሃው ውስጥ ለውስጥ ቀዝፋ ብቅ ብላ ከፊት ለፊቷ ራሷን ግራና ቀኝ ነቅንቃ አየችው የለም፡ ዘወር ብላ አየችው ይታገላል።
እንዳቅሙ እየተፈራገጠ ይዋኛል¦ ሰላሳ መጀመሪያዎቹ የውሃ ላይ
ህፃን
ዳር ወጥታ ጠበቀችው: ጥርሱን ነክሶ ወደ ዳር ሄደና እጁን ዘርግቶ የመዋኛ ግድግዳውን ብረት ያዝሁት ሲል አልደረሰበትም ነበርና ለጠም ብሎ ውሃ ጠጣ፡፡ ደንግጦ ተወራጨና ብረቱን
እንደምንም ብሎ ያዘ፡፡ ንፍጡ ተዝክርኳል፡፡ በውሃው አፍንጫውን
አፀዳና ሳለ፡፡
“በቅርቡ ነው የለመድህ" ፈገግ ብላ ጠየቀችው፡፡
አዎ!
“ዋና ለመልመድ እንዴት ዘገየህ?” ቀና ብሉ አያት፡፡
“ውሃ ስለምፈራ” ካርለት መልሱ ሳባት፡፡
“በልጅነትህ ብትለምድ ኖሮ…”
“አንች በልጅነትሽ ነበር የለመድሽው?"
“ከልጅነትም ነፍስ ሳላውቅ ነው"
ነፍስ ሳላውቅማ እኔም መዋኘት እችል ነበር"
እንዴት ጠፋህ?”
“ከብት ስጠብቅ” ግራ በመጋባት አየችው፡፡
“ከብት አልጠበቅሽም?" አንገቷን ወዘወዘችው አልጠበቅሁም ለማለት
“በልጅነትሽ መልመድ ነበረብሽ"
“ምን ለማለት እንደፈለግህ አልገባኝም?"
“አንች ለምታቀላጥፊው እንግዳ ብሆንም እኔም የራሴ የሆነ የምችለው የህይወት ልምድ አለኝ" ብሏት መልሷን ሳይጠብቅ
እየተወራጨ ደሞ ሊያቋርጥ ወደውሃው ገባ፡፡
ካርለት ባህሪው ግራ አጋባት፡፡ የተለየ ባህሪ ያላቸው ደግሞ
እራሳቸው ውሃ ናቸው፡፡ የሚዋኝባቸው
መጽሐፍት ናቸው
የሚነበቡ፡፡ እንደቆመች በመከራ አቋርጦ
ገላውን እያለከለከ
ለመታጠብ ከመዋኛ ገንዳው ወጥቶ ወደ ሻወሩ አመራ፡፡ እሷም ወደ
ሴቶቹ ሻወር ሄደች፡፡ ገላውን ሲያደራርቅ እሷ ታጥባ ጨረሰች፡ እሱ ግን ጊዜ አልሰጣትም ልብሱን ወዲያው መልበስ ቀጠለ፡
ርጥብ ፎጣዋን እንደለበሰች ወደ እሱ ገሰገሰች፡
“ይቅርታ ብንተዋወቅ ደስ ይለኛል?"
“አልዘገየሽም? ተዋውቀንማ የህይወት
ልምዳችንን ተለዋውጠን" ብሏት ልብሶቹን ወደ ቦርሳው መክተቱን ጀመረ፡
“ጥሩ! ጊዜ ካለህ አብረን ሻይ ቡና ልንል እንችላለን፡”
“አመሰግናለሁ! ግን
ሥራ አለኝ፡፡" ጨነቃት ካርለት በሽቃታም የአዲሳባ ወንዶች ብዙዎቹ ነጭ ሲያዩ እንደማንኛዋም ሴት ሳይሆን ልዩ ፍጥረት እንደሆነች ሁሉ ማፍጠጥ መቅለስለስ ለማናገር መጣር… ነበር ፍላጎታቸው፡፡ ይህ ስው ግን እንግዳ
ሆነባት፡፡ የሚነበበውን የሚዋኝበትን ሰው ማጣት ለሷ ትልቅ ሽንፈት ነው፡፡ ቦርሳዋ ውስጥ ደግሞ “ራይዚንግ ሰን የሚለው
የሚካኤል ክሪሽቶን መጽሐፍ አላት፡፡
በፍጥነት ሁለቱን
አወዳደረቻቸው፡፡ ህይወት ያለው መጽሐፍ ይሻላታል፡፡ ስለዚህ ቶሎ ወሰነችና፡-
“ዛሬ እንኳን ባይመችም ሌላ ቀን ብንገናኝ?”
ለምን ፈለግሽ?" አላት በመደፍረስ ላይ ያለውን ስሜቱን ሳይደብቅ።
“ለጨዋታ!” ትከሻዋን ሰበቀች፡፡ እንዲህ መናገር የሌለባት መሰላት:
ለእኔ ቆንጂዬ ጥቁር የፍቅር ጓደኛ አለችኝ፡፡ ስለዚህ ተይኝ
“የለም! አስተሳሰቤን የተረዳኸው አይመስለኝም፡ የፈለግሁት ያሰብኸው ጨዋታ አይነት አይደለም፡''
እንደዚያ ካልሆነ ይቅርታ- አንዳንድ ነጭ ሴቶች ግማሽ
ሰው ግማሽ አውሬ' የሚሉትን አፍሪካዊ ዛሬም በዚያ በዘረኝነት
እምነታቸው የወሲብ መጠቀሚያ የሚያደርጉት መሆኑን ስለማውቅ
ነው፡፡
“በብዙ የአፍሪካና የካሪቢያን አገሮች የሴት እህቶቻችን የሽርሙጥና ህይወት የምናጠፋበት መፍትሄ አጥተን ለቀናትና
ለሳምንታት የጥቁር ገላ የናፈቃቸው ነጭ ሴቶች “አውሬ' የሚሉትን
አፍሪካዊ ወንድ ገንዘብ እየከፈሉ በፈለጉት መልክ ወሲብ በመፈፀም
ለአህጉራችን አዲስ የወንድ ሸርመጡች ችግር እያስታቀፉን በመሆኑ…” ቀና ብሎ አያት፡
“ልክ ነህ! ያን አውቃለሁ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
እንዲሁ በአፍሪካውያንና በካሪቢያን ወንዶች በታይዋንና ታይላንድ…
ሌቶች የሚፈፀመውን የወሲብ ግፍ አውጋዥ ነኝ ስትለው ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቱ ፈገግ ብሎ አያትና፡-
“የኮሉኒያሊስት እምነት አራማጆች ከመልካም ነገር ይልቅ በዚህ ምስኪን የአፍሪካ ህዝብ ላይ ጦር ሰብቀው መወርወሩን
አሁንም አላቆሙም፡፡ ምላሳቸው ደግሞ ደሙን ያብሳል፡፡ እና!የነሱ ወንጀል አሻራ የሌለው ከህግ ተሰውሮ ዘላለም የሚኖር ነው፡
ነጭ በመሆንሽ ግን ጥላቻ የለኝም፡፡ ለሻይና ለጨዋታ
ለመማማር ፈቃደኛ ነኝ አላት፡፡
ቴንኪው!” ደስ አላት ካርለት። እንግዳ ባህሪ ስላለው ግልፅ
ኢትዮጵያዊው እያሰበች፡፡ ልብሷን ለመቀየር ከመሄዷ በፊት ግን ከአምስት ደቂቃ በኋላ እዚህ ነኝ" አለችው ከአክብሮት ይቅርታ
ጋር።

👍34🤔2
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ሰማዩ ከአድማስ እስከ
አድማስ ዙሪያውን በከዋክብት ተጥለቅልቋል፡፡ አንዳንዶቹ ብርሃናቸው ደመቅ የሌሎቹ ደግሞ ፈዘዝ ቢልም ሁሉም ይብለጨለጫሉ፡ ብልጭ ድርግም፤ ብልጭ ድርግም
እያሉ፡ ጨረቃ የለችም ዳመናም የለም። ሰማዩ ግን ተውቧል፡፡ጨለማው
ለትናንሾቹ ከዋክብት ጠቅሟቸዋል። ውበታቸውን
የምትነፍጋቸው ጨረቃ፤ መኖራቸውን ጭራሽ የምታጠፋው ፀሐይ
የለችም።
“በህይወቴ እንዲህ እልፍ
አዕላፍ ከዋክብት አይቼ
አላውቅም፡፡ ለካ ሰማዩ ለእግር መቋሚያ የሌለው በከዋክብት የተጠቀጠቀ ነው!” አለና ወደ ሰማዩ አንጋጠጠ፡፡ ከዋክብቱ በድቅድቅ ጨለማው እየፈነደቁ ብርሃናቸውን ቦግ እልም ያደርጋሉ፡
“ድንቅ ነው ታምር፧ የጨለማ ውበት!” አለች ለምለሙ ሳር ላይበጀርባዋ
እንደተንጋለለች፡፡ ሁለቱም ግን አንዱ ሌላው ያለውን አልሰማም።
የጉደር ፏፏቴ ይንፏፏል፡፡ የጉደር ወንዝ ለሁለት ተከፍሎ አንዱ ከደልዳላው መሬት ላይ ተወርውሮ ድንጋይ ላይ ይፈጠፈጥና
ለሰዎች አይን የሚማርክ ነጭ አረፋ ፈጥሮ ህሊናን አርክቶ ሲፈስ ፧ በስተግራ ያለው ደግሞ አክሮባቱን ሳያሳይ በኩራት ቁልቁል እየፈሰሰ ከፏፏቴው ጋር ተመልሶ ይገናኛል፡፡ ወንዝ ሆኖ ለመፍሰስ… ትዝ
አለው ስዩምን ወንዙ፡፡
“ድንጋዩ ላይ ተፈጥፍጦ አረፋ የደፈቀው ውሃና በሰላም የተጓዘው ውሃ እንደገና ሲገናኙ ልዩነት አይኖራቸው ይሆን? የቱ
ይሆን እድሉን የሚያማርረው? ከድንጋይ ላይ ተላትሞ አረፋ
የደፈቀው ወይንስ ጓደኛው ያስቀናው ሰዎችን መማረክ ያልቻለው ውሃ ሆኖ ተፈጥሮ ከጎኑ የተለየው ውሃ እየተንፏፏ አረፋውን
ሲደፍቅ ሰዎች እጅ ወደ እሱ ሳይሆን ወደ ፏፏቴው ተቀስሮ እያዩ ወይ ነዶ እኔም
በውስጤ ያለውን አረፋ ደፍቄ አሳያቸው ነበር፡ ምን ያረጋል ውሃ መሆኔን ያኔ ያውቁ ነበር። እርጉም ጊዜ ግን እሱን ተመልካች
አጎረፈለት፤ እኔን አይቶ አድናቂ አሳጣኝ' ይል ይሆን! ብሎ አሰበ፡፡
ሁለቱም ፀጥታን ወዳጆች ናቸው በዚ ደግሞ
ተግባብተዋል፡ ጸጥታን የሚፈራ የራስ መተማመን የጎደለው ፈሪ
ነው፡፡ አካባቢውን የማያውቅ ጨቅላ አስተሳሰብ ያለው… ፀጥ ካላሉ የቅጠል ሹዋሹዋቴ አይሰማም የጨለማ ውበት አይታይም! የጽልመት ብርሃን የውበት ሚስጥር አይገለጥም… ፀጥታ የግዑዙ ዓለም ቁልፍ ነው የሚስጥራት መክፈቻ…
ይህን የተረዱት ጥቁሩና ነጯ ግንኙነታቸው ገና ያልጠበቀ ቢሆንም በፀጥታ ቋንቋ ተግባብተዋል፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው ውበት
አላቸው ከቀለማቸው ጀምሮ።
ፏፏቴው ይንፏፏል የሌሊት ወፍ እንደ ንጋት ወፍ
የችሎታዋን እየዘመረች በጨለማው ትበራለች… ሁለቱም በየግላቸው
በፀጥታ የሙከራ መስሪያ ህሊናቸው ውስጥ እንደየአቅማቸው
ይመራመራሉ፡ ይቀንሳሉ ይደምራሉ አንዱ ሌላውን ያስባል፡፡
የጋዝ ምድጃው ላይ በብረት ድስት የጣዱት ፓስታ ክዳኑን
ሽቅብ እየገፋ ሲንፈቀፈቅ ግን ሁለቱም ከዚያ የፀጥታ ዓለማቸው ተመለሱ፡፡
ስዩም ከተቀመጠበት ተነስቶ ባትሪውን አብርቶ የብረት ድስቱን ክዳን ከፈተና ፓስታው መብሰል አለመብሰሉን አረጋገጠ
በስሏል… ለምግብነት ያመጡትን አቀራረቡ የጉደር ወይኑንም ዷ አድርገው ከፈቱ፡፡
"መልካም ራት!” አለችው፡፡
“ለአንችም” አላትና መብላት ጀመሩ
"ተወርዋሪ ኮከብ! ፈነደቀች፡፡
“ለብዙ ጊዜ ተወርዋሪ ኮከብ ስጠበቅ ነበር አሁን ግን አየሁ ዘግይቶም ቢሆን ያሰብሁት ይሳካል፡፡ አውሮፓ ውስጥ እንዲሁ ዓይነት እምነት አለ" አለችው፡፡ ስዩም ፈገግ ብሎ ራሱን ወዘወዘ ለአባባሏ እንግዳ አይመስልም፡፡
በሰባት ሰዓት ተኩል
ከአዲስ አበባ ተነስተው ገነት አዲሳለም ጊንጭ አምቦን እያዩ ጉደር የደረሱት ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡ አምቦ ኢትዮጵያ ሆቴል ትልቁ ዋርካ ስር
ቁጭ ብለው ማራኪውን አትክልት ቦታ እያዩ ቆዩ፡
"ጥሩ አገር አለቻችሁ፡፡ ከአዲሳባ እዚህ ድረስ ትንፋሽ ቆራጩ ተፈጥሮ በደስታ እንዴት እንዳረካኝ ልገልፅልህ አልችልም”
አለችው።
"ገና ይቀርሻል: ጉደር ስንደርስ የጉደርን ተፈጥሮ ስታይ የማድነቂያ ቃል እንዳታጭ” አላት፡ በፈገግታ ግንባሯን ሰበሰበች፡፡
ከአምቦ አንድ አስር ኪሉ ሜትር እንደተጓዙ ጉደር ከተማ ገቡ፡ በከተማው መሃል አለፉ፡፡ ወደ ግራ ታጥፈው አልባሌ መዝጊያ
ያለው በር ላይ ቆሙ፡፡ ትህትና ያለው ዘበኛ እየሮጠ መጥቶ በሩን ከፈተላቸው፡፡ አናገሩት፡፡
ፏፏቴው ይንፎለፎላል፤ ድምፁን እየሰሙ ቁልቁል ወረዱና ብብቱ ስር ገቡ። ስዩም ካርለትን አያት “ዋው!” ብላ አፏን ከፍታ
አይኖችዋን ወረወረቻቸው አረፋው ላይ ለምለሙ ጫካ ላይ የበልግ እፀዋት ላይ… የመጨረሻዋ ማድነቂያ አባባሏ ሁለት ፊደል ሆነ “ዋው! ብቻ፡፡
ሁለቱም በልተው ጨረሱ
የጉደር ፏፏቴ ይሰማል
ካርለት የጉደርን ወይን በሁለት ብርጭቆ ቀድታ አንዱን ለስዩም ሰጠችው። “ለጤናችን ለኢትዮጰያውያን አዲስ ዓመት" አለችው:
በየመንገዱ ያየችው ቢጫ አበባ ከለምለም ቄጠማ ጋር በየሰዎች እቅፍ ላይ የነበረው አበባ፤ የኢትዮጵያ የአዲስ ዘመን አብሳሪ አደይ
አበባ እንደ ህፃንነቷ ከአረንጓዴው ለምለም መስክ እየቀነጠሰች
ችቦዋን ሞልታ መዓዛውን ባፍንጫዋ የሳበችው የአደይ አበባ ሽታ
መጣባት፡
ፏፏቴው ከብቶቹ ህፃናት… ቃናቸው ተዋህዶ “አደይ
አደይ አበባ…" እያሉ ያዜማሉ፡፡ ስዩም “ችቦው ተለኮሰ' አላት፡፡
“የምኑ” አለችው፡፡
“የአዲሱ ዓመት የአዲስ
ዘመን... የነገ ፈገግ አሉ
አንጋጠው ተጎነጩት ጉደሩን፡፡ ፀጥ አሉ እንደገና አዲሱን ነገ ህልሙን ነገ፤ ሽፍንፍኑን መጭ አመት እያዩ፡፡ ከዚያ ካርለት
ለመናገር ስትቁነጠነጥ አያት፡፡
“አመሰግናለሁ፡ በዚህ የደስታ ቀንህ አብሬህ እንድሆን ስለመረጥኸኝ" አለቸው:
“ምስጋና አያስፈልገኝም: ሌላ አብሮኝ ሊመጣ የሚችል ባለመኖሩ ነው" አላት፡፡
“ለምን?” አለችው ካርለት፡፡
“በአዲስ ዓመት ዋዜማ የአዲሳባን ሰው ወደ ገጠር ወጣ እንበል ብትይው ፀበል ይወስድሽና በመስቀል እያስደበደበ ሰባት ቀን
ቤት ያዘጋብሻል እብድ ነሽ ብሎ" አላት: በቀልድ አዘል አባባሉ ፈገግ አለችለት፡ ከጥርሷ ይልቅ ቀይ ከንፈሯን በከዋክብት የብርሃን ወጋገን አየው፡
ካርለት፧ እንግዳ ባህሪው
የሚገርማት ኢትዮጵያዊ
ዮትያትሪካል አርት ምሩቅ መሆኑን እንጂ የግል ህይወቱን አልዘረዘረላትም፡፡ የሴት ጓደኛ አለኝ ብሏት የነበረውም ትዝ አላት።
የሴት ጓደኛህስ ፍላጎትህን አትወድልህም?"
“እሷማ ሁሌም አብራኝ ነች፡፡ በውኔ ቀርቶ በህልሜም"
“አልገባኝም?" አለች ካርለት፡፡
"በገሃድ የሚሆነኝን አላገኘሁም !በምናቤ ግን
ፍቅርኛ አለችኝ
“ለምን?''
"የፈጠራ ሰዎች ግላዊ እምነታቸውን በተከተሉ ቁጥር ከህብረተሰቡ ጋር የነበራቸው የመግባባት ቅኝት እንደተበላሽ የሚገምተው ይበዛል። እነሱም የብቸኝነት ጥዑም ዜማው ያረካቸዋል፡፡ ስለዚv
ሌለች የሚወዱት ሙዚቃ ለእነሱ ጩኸት ይሆንባቸዋል፡፡
በምናቤ ግን ፍቅረኛ
“ቁም ነገሩ ግን ግላዊ ዓለማቸውም ውስጥ ሆነው
የህብረተሰቡን ህይወትና ቅላፄ ምንነት ለመረዳት ህሊናቸውን ወደ
ዱ ዓለም እየዶሉ እርቀው ይቀርባሉ፤ ከህዝቡ ጋር ይሆናሱ፤

👍21👎1😁1
ህብረተሰቡ ከተቀመጠበት ቆሻሻም አፍንጫቸውም ይሰካሉ…
“ህብረተሰቡ የሉም ሲላቸው ግን በፈጠራ ስራቸው ከውስጡ ገብተው ህሊናውን ሲቆነጥጡት ብብቱን ሲኮረኩሩት ስሜቱን እንደ
“ፔንዱለም ሲያወዛውዙት ሲያስተክዙት ወይ ሲያስቁት ፤ሲቀሰቅሱት ሲጎነትሉት….. እነሱን ግን አያያቸውም አይቀርባቸውም
ስራቸውን አቅፎ እነሱን ይገፋቸዋል፧ ከዚያ ይሸሻሉ፤ ፍቅራቸው ህሊናቸው ከፈጠረው ጋር ይሆናል፡፡
"ስለዚህ ብቸኛ ነኝ፤ ፍቅረኛ የለኝም ብለው አያምኑም፡፡
ቆንጆ ሆሊናቸው ውስጥ አለ! እንደማንኛውም ሰው ይተቃቀፋሉ ይሳሳማሉ ይዳራሉ… እና እኔም የምወዳት ቆንጅዬ ፍቅረኛ አለችኝ፡፡ውስጤ! ጎኔ ግን የለችም…" አላት፡፡
ሌላ ሰው ቢሆን እየተንፏቀቀ ጤንነቱን ተጠራጥሮ በራቀው፡፡ ቃዥኮ፤ ንክ ቢጤ ነው' ብሎ በሸሸው፤ ሴትዬዋ ግን
ካርለት ናት፡፡ ካርለት አልፈርድ፡፡ የሐመሮችን ድብቅ ውበት ለእይታ
ያበቃች ዘላን' የሚባሉትን ድንቅ ስርዓታዊ አኗኗር እንዳላቸው ያሳወቀች፡፡
የእግር አውራ ጣቷን እየላሱ የሰሙትን የፍቅር ዜማ
የሚቀኙላትን የፋብሪካ እቃ መሳይ ሰዎች ረግጣ ከባለ ግርማ ሞገሱ የጫካ አንበሳ በድፍረት የቀረበች በድፍረት የኖረች በጋራ አግስታ ተፈጥሮ ህይወት ዘመንሁ ብሎ ኋላ ቀር ለሆነው ህብረተሰብ ያሳየች ካርለት ናትና ስዩምን ተረዳችው።
“የፈጠራ ሰው ነህ?"
“አዎ!”
የምን?”
“እንጃ! ግን እዚህ ይቆረጥመኛል ጨጓራዬን

ያቃጥለኛል እንደምንለው እኔንም የፈጠራ ሰው ስሜት
ያመኛል" አላትና መረዳት አለመረዳቷን ለማወቅ በጨለማው ብርሃን አያት
“ይገባኛል" አለችውና እንደገና በመካከላቸው ፀጥታ ሰፍኖ ቆየና።
“ሙያህንስ ትወደዋለህ?"
“የተመረቅሁበትን? መች ሰራሁበትና መውደዴን መጥላቴን ልወቀው: የተማርሁት ሌላ፤ የሚሰራው ሌላ፡፡ ገሃድ እውነት የሚቀርብበት መድረክ ባዶ ነው: ባለመያዎች እራሳችን ከህዝቡ በስተኋላ የተቀመጥን ተመልካቾች ነን፡፡
“መድረኩ ላይ የሚታየው የማስታወቂያ ሰሌዳ ነው: ድንቅ ተውኔት የሚቀርብ መሆኑ የመግቢያ ዋጋው ተመልካቹም 'ምን አየሁ ብሎ የሚበሳጭ አይደለም: ቁጭ ብሎ ትርፉን የሚያስላ መንገድ ለመንገድ መንገላወድ የሰለቸውና እግሩን ሰቅሎ የሚተኛ ፍቅረኛሞች ደግሞ ለመተሻሸት… ነው የሚገቡት፡
"ታዲያ ይኸ ተመልካች እንዳይከፋው አልፎ አልፎ ቀሚሷን የምትገልብ ሴት ጋቢ ለብሶ አፉን እያጣመመ ምላሱን የሚያወጣ ወንድ ካገኘ እየሳቀ ተውኔት ብሎ ዝም ነው' እያለ እያጨበጨበ ወደ ነበረበት ይመለሳል። ስለዚህ እኔም hሥራ ባልደረቦቼ ጋር የምቀመጥ
ከኋላ ተራዬ ሲደርስ ጋቢዬን ለብሼ ምላሴን ማውጣት ብቻ…..ታዲያ ሙያዬን ልውደደው አልውደደው በምን አጋጣሚ, ልወቅ!
“አሁን አሁን እንዲያውም ከሰፈሬ ካለው ጎሚስታ መቀጠር እያማረኝ ነው: የተነፈሰ ጎማ ሲመጣ ቡኮውን ፈልጎ… ቀዳዳውን
ለጥፎ ነፍቶ ስራና ውጤትን አይቶ ያገኙትን በልቶ ተችና ተተቺ ሳይኖር ህሊናና ተግባር ሳይቃረን. ሰላማዊ ህይወት መኖር አይሻልም!" አላት፡፡
“ስዩም! ሰላም በትግል እንጂ በመሸሽ እኮ አይመጣም።ይኸማ እውነትን ማነቅ ነው። እልህ የለሽ ደካማ መሆን ነው:: ካለኪነ ጥበብ ህይወት ንብ የሌላት ቀፎ ናት፡፡ ዓለማችን እኮ በደቦ የሚኖርባት እንጂ በደቦ አዲስ ነገ የተገኘባት አይደለችም፡፡
“ደንቆሮው ኤደሰን እውሩ ሆሜር… ጆሮና አይናቸውን
አጥተው እንኳን በብዙ ሺ የሚቆጠር ሙከራና ጥረት ሲያደርጉ ተስፋ መቼ ቆረጡ፡፡ ከአስር ሺ ሙከራ በኋላ ኤድሰን ዓለምን
በኤሌክትሪክ ብርሃን አጥለቀለቀ። ሆሜር 'ኢልያድ' በተባለው የስነ
ፅሁፍ ገፀ በረከቱ ዓይናማውን የዓለምን ህዝብ አስደምሞ ገሃዱን
የትያትር መድረክ በጥልቅ መሰረት ላይ ገነባት፡፡
“ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የፈጠራ ሰዎች የደቦ ለውጥ
እየጠበቃችሁ ይመስላል፡፡ የግላችሁን ጥረት ሳታደርጉ የምትኮናነኑ ከሆነ ሺ ጊዜ ሳይሞክሩ ግላዊ ጥረት ከመከነ የጥበብ የፈጠራ
ዓለም ታዝንባችኋለች: አጉራሽ ሳይጠብቁ ሙያን መወጣት እንጂ
በሙያ መሸነፍማ አንገትን የሚያስደፋ አስነዋሪ ተግባር ነው! አለችው፡፡
ፏፏቴው ያኔም ይንፎፎላል ከዋክብትም ይብለጨለጫሉ...
ካርለት የጨለማውን ውበት በህሊናዋ ለመበርበር ቀና ስትል ስዩም ወደ ውስጡ ጉድፉን ሊያይ ህሊናውን ሊያፀዳ የላላውን ሞራሉን ሊወጥር… ሄደ፡፡
“…ካርለት እንግሊዛዊ በመሆንሽ ልትኮሪ ይገባል፡ በአለም ላይ ሃብታም ከሚባሉ በጣት ከሚቆጠሩት ትንሽ አገሮች አንዷ የአንች አገር ናት፡፡"
“እንግሊዛዊነቴን ጠላሁት ወይም አፈርሁበት መች ወጣኝ?
“ደረጃሽን እየዘነጋሽው ነው። ፍቅርሽ እየተሽቆለቆለ
መሰለኝ። በዓለም ላይ ይህችን ድሃ አገር ብቻሽን በመውደድሽ የምታመጭው ለውጥ የለም: የአገርሽን ዝና በሄድሽበት ሁሉ
መጠበቅ የዜግነት ግዴታሽ…"
“በቃህ በቃህ ብዙው የአገሬ ህዝብ እንዳንተ ቢያስብ ኖሮ
እዚያች አገር መፈጠሬን እረግመው ነበር፡፡ ግን ብዙዎች እንግሊዛውያን ከእንዲህ ዓይነቱ ትምክህተኛ አስተሳሰብ የራቁ ናቸው።
“አንተ ይህችን ዓለም ይህችን ትንሽ ፕላኔት በህሊናህ ሰንጢ ቆራርጠህ ትንሽና ትልቅ ብልት ፈጠርህላት። ድሃና ሃብታም
ብለህ ከፋፈልካት የዘመናችን ጠበብትና እያደገ ያለው ሳይንስ ግን
እሚያስጨንቀው ይህችን ትንሽዬ ፕላኔት እየበከልናት ነው! እየጠበበችብን ነው በርቀት ሲያያት የምታሳዝነው ትንሽዬ
ፕላኔታችንን እንዴት እንጠብቃት እንዴት ከጥቃት እንከላከላት… እያሉ የሚጨነቁ ናቸው፡
“እኛም የአለም አካል ነን' የሚለውን ሙዚቃ አካልህ
ይደንስበታል። ህሊናህ ግን ሚስጥሩ አይገባውም፡፡ የአዕምሮ ብስለት
ያለው ሰው ልዩነትን ሳይሆን ቅድሚያ የሚሰጠው መመሳሰሉን ነው፡፡ ነጭና ጥቁሩን ያለያየው ምንድን ነው? አንዱ ጆሮ ሲኖረው
ሌላው ጆሮ የለውም! አንዱ ልብ ሲኖረው ሌላው ልብ ይጎለዋል… ይኸ ነው ልዩነትን ማምጣት ያለበት በዚህ የሚለያይ ካለ የብልት መብዛትና ማነስ ከመጣ ያኔ ልዩነት አለ ማለት ነው፡ በቀለም
በስልጣኔና በሃብት ከሆነ ግን ልዩነቱ ያ የጆግራፊያዊ አቀማመጥና የአኗኗር ልዩነት ነው፡፡ በሰዎች መካከል ያለ ልዩነት አይደለም፡፡ለዚያም ቢሆን በቂ ምክንያት አለው:

👍11
“ሌላው ማወቅ ያለብህ እግዜር ሰማይና ምድርን ሲፈጥር ድንበር ፈጥሮ አጥር አጥሮ አይደለም:: ድንበሮች ሰው የከለላቸው,
ልዩነቱንም ሰው የፈጠረው ነው። የኔ እምነት መነሻም ይኸው ነው የስነ-ሰብዕ ተመራማሪ የስራው የምርምሩ መጀመሪያ ይህ ሃቅ ነው፡፡
“ካርለት! በህልም ዓለም ያለሽ ገና ከመኝታሽ ያልነቃሽ ነሽ"አላት ከመቀመጫው እየተነሳ፡፡
“እኔ በእርግጥ በህልም ዓለም ያለሁ፧ ገና ህልሜን
ለመፍታት ብዙ የሚቀረኝ፤ ለብዙ እውቀቶች ያልታደልሁ የዓለም
ሚስጥር ያልተገለጠችልኝ ነኝ አንተ ግን ህልም የሌለህ ቅዠታም" ነህ አለችው፡፡
“እሽ! ያም ሆነ ይህ ወደ ሐመር የመሄጃ ጊዜሽን
አዘግይው። ውለን ስናድር የአንች እምነት ለኔ ወይንም የኔ እምነት ለአንች ይገለጽልን ይሆናል ስለዚህ…" አያት ሊያግባባ በሚችል ፈገግታ።
“አንግሊዝ ኤምባሲ ከዲፕሉማቲክ ሰራተኛ ጋር ለመኖር ለመቅበጥ ይመስልሃል ኢትዮጰያ የመጣሁት: አዝናለሁ ስቲቭ!
ዓላማዬን አልተረዳኸውም: ካለ ወንድ ምርኩዝነት ራሴን ችዬ ዓላማዬን ለማሳካት የምችል ሴት እንዳልሆንኩ አድርገህ የገመትኸኝ
ይመስለኛል፡፡ ያ ያንተ ድክመት ነው፡ እኔ ግን ዓላማኣለኝ። የስነ ሰብዕ ተመራማሪ ነኝ፡፡ መኖሪያዬ ኤምባሲ ግቢ አይደለም ከህዞብ ከተፈጥሮ ጋር ነው፡
“ስቲቭ! ላደረግልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ፡ በአለፉት ጊዜያት የነበረን ግንኙነት እርሳው። ጥሩ የፍቅር ጓደኛ ልሆንህ አልችልም።
ጥሩ እህትህ ግን ልሆን ፈቃደኛ ነኝ።" ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
“መልካም የሥራ ጊዜ እመኝልሃለሁ ከመናገርህ በፊት ግን ሰዎችን ላለመጉዳት ጥንቃቄ አድርግ ቻው ስቲቭ! ስትለው ስቲቭ
በደመ-ነፍስ እጁን ዘረጋላትና ወደ ሰፊው መስኮት ሄዶ ትላልቅ
የባህር ዛፎችንና ቅርፊታቸውን ተመሰከተ:
የታሰረውን ጥቁር ውሻውንም አየው። ያላዝናል! ምግብ ግን
ከፊት ለፊቱ አለ: ስቲቭ ምን ጎደለበት!' ብሉ አሰበ። ረጅሙን ሰንሰለቱን ግን አላየለትም…

የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........ part 1
(ሜሪ ፈለቀ)
ዓይኖቼን በቦዛዛው ስከፍት መጀመሪያ ያየሁት የጨለማ በር የመሰለ ሁለት ቀዳዳ ነበር። ቀዳዳው ውስጥ ጥቋቁር ሰበዝ የመሰሉ ነገሮች እጅብ ብለው ነገር……… እይታዬ እየጠራ ሲመጣ ነው የሰው አፍንጫ መሆኑን ያወቅኩት። የፊቴ ደፍ ላይ ይሄን የሚያህል አፍንጫ ምን ያደርጋል? ምን ሊሆን ነው እንዲህ የተጠጋኝ?
«ሜላት ትሰሚኛለሽ? የምለው ከተሰማሽ ዓይኖችሽን በጣቴ አቅጣጫ አንቀሳቅሺልኝ» ባለአፍንጫው ሰውዬ ፊቱን አሸሽቶ የሌባ ጣቱን ከአንዱ አቅጣጫ ወደሌላው ያወዛውዘዋል። ትንፋሹ የሚሰማኝ ቅርበት ላይ ሆኜ ምን ያስጮኸዋል? በአይኖቼ ጣቱን እየተከተልኩ ከቆየሁ በኋላ ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁ። ሀኪም ቤት አልጋ ላይ ነኝ። ባለአፍንጫው ሰውዬ እና አጠገቡ የቆመችው በዓይኖቿ የምትስቅ ወጣት ሴት ከደረቡት ነጭ ጋውን በመነሳት ዶክተር ወይ ነርስ እንደሆኑ ገመትኩ። ዓይኔን ከጣቱ ጋር ስላዳከርኩት ደስ ያላቸው ይመስላሉ። ሴቷ ሰውነቴ ላይ እየተርመሰመሰች እንደሆነ ይታወቀኛል ግን የገዛ ሰውነቴ እንደባዕድ ነገር ነው የሚሰማኝ። ሽባ ሆኜ ነው? ለምንድነው ሰውነቴን የማልሰማው? አፌ ላይ የነበረውን የሆነ ፕላስቲክ ነገር ፈልቅቃ አንዳች የሚያህል ቱቦ ከአፌ ውስጥ እየመዘዘች ስትስብ የት ድረስ ዘልቆ እንደነበር ያልገባኝ ቱቦ ጉሮሮዬን እየፋቀው ሲወጣ ይታወቀኛል።
«ዌልካም ባክ ሜላት። ዶክተር ሀይሌ እባላለሁ። በቀስታ ለማውራት ሞክሪ እስኪ……. ዝምብሎ አንድ ቃል! የመጣልሽን» አለኝ በማባበል።
«ምን ሆኜ ነው ሀኪም ቤት የመጣሁት?» አልኩኝ ስሰማው የራሴ ባልሆነ ቀሰስተኛ ድምፅ። ፈገግ አለ የሆነ ግልግል አይነት ስሜት በቋጠረ ፊት…………. ሴቷ ከግርጌዬ ዞራ የእግሬን መሃል በጣቷ እየነካካች።
«ጣቴ ከተሰማሽ እግርሽን አንቀሳቅሺልኝ እስቲ» አለችኝ። ጣቴን ይሁን ያንቀሳቀስኩት ሙሉ እግሬን ብቻ አንቀሳቀስኩላት። ተያይተው ያልገባኝን መልዕክት በግንባራቸው ተለዋወጡ። በደመነፍስ እጄ ይሰራ እንደሆነ ለማረጋገጥ ሳይጠይቁኝ እጄን አዘዝኩት። ይታዘዛል። ሰውየው የሆነች አንድ ቂጥ በአግባቡ የማታስቀምጥ መቀመጫ ነገር ስቦ በግራ ጎኔ አልጋው አጠገብ ተቀመጠ።
«ወይዘሪት ሜላት? አደጋ ደርሶብሽ ነው ወደዚህ የመጣሽው። ከደረትሽ ዝቅ ብሎ ሁለት ቦታ በመሳሪያ ተመትተሽ ነው። (እሱ እያወራ በእጄ ለመዳበስ ሞከርኩ።) ስለተፈጠረው ነገር የምታስታውሺው ነገር አለ?» በጭንቅላቴ ንቅናቄ እንደማላስታውስ ነገርኩት።
«እድለኛ ነሽ ጥይቱ ጉበትሽን ለጨረፍታ ነው የሳተው። በቀዶ ጥገና ወቅት ትንሽ ኮምፕልኬሽን ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ቀዶ ጥገናው ስኬታማ ነበር። ነገር ግን ወደአዕምሮሽ ክፍል የሚሄደው ኦክስጅን ተቋረጦ ስለነበር የተወሰነው የእዕምሮሽን ክፍል ጎድቶታል። የዚህ ጉዳት ዋነኛው አካል ሜሞሪ ሎስ ነው።» ያለው ይግባኝ አይግባኝ እንጃ ብቻ በጭንቅላቴ የማስታውሰውን ነገር መበርበር ጀመርኩ። እሱ ማብራራቱን ቀጥሏል። ሀባ ምናምኒት ነገር ጭንቅላቴ ጓዳ የለም። አይ በደንብ ስላልነቃሁ ይሆናል፣ ድንጋጤ ላይ ስለሆንኩ ይሆናል፣ የሰጡኝ ማደንዘዣ አለቀቀኝ ይሆናል፣ ......... ምንም ምክንያት ይሁን ብቻ የሆነ ነገር ይሆናል እንጂ ዜሮ ዘጭ የሆነ ጭንቅላትማ አይኖረኝም።
«ጥያቄ አለሽ?» አለኝ ግማሹን ያልሰማሁትን ማብራሪያ ሲጨርስ።
«ማነው የተኮሰብኝ? ምን አድርጌያቸው ነው?» የሚለው ጥያቄ ከአፌ ወጣ!
«አልታወቀም። ማንም ይሁን ማን የተኮሰብሽ ሰው ፖሊሶች እቦታው ከመድረሳቸው በፊት አምልጧል። ዝግጁ ስትሆኚ ፖሊሶች ቃልሽን ሊቀበሉ ይመጣሉ። ምናልባት አገግመሽ ወደቤት ስትገቢ ፍንጭ የሚሰጥሽ ነገር ታገኚ ይሆናል።» ሲለኝ ቤቴን ለማሰብ ሞከርኩ።
«ቤት አለኝ? ቤቴ የት ነው? የሚያውቀኝ ሰው፣ ሊጠይቀኝ የመጣ ሰው የለም?»
«የቤት ሰራተኛዋ ነኝ ያለች ሴት ጠዋት መጥታ ነበር። ስልክ አስቀምጣ ነው የሄደችው። ደውለን እንደነቃሽ እናሳውቃታለን። አደጋው በደረሰብሽ ሰዓት መኪናሽ ውስጥ የእጅ ቦርሳሽ ተገኝቷል። ፖሊሶች በኤግዝቢትነት ይዘውት ነው። መታወቂያሽ ላይ ያለው አድራሻ አሁንም ድረስ የምትጠቀሚበት ከሆነ አራዳ ክፍለከተማ ነው የሚለው።» አለኝ ከተቀመጠበት እየተነሳ። የቤት ሰራተኛ ያለኝ ሴት ነኝ? እናት እና አባቴስ? አግብቼ ወልጄ ይሆን? ስንት ዓመቴ ነው? በወና ጭንቅላቴ ውስጥ መዓት ጥያቄዎች ሚሞሪ በሌለው ሰፊ ቦታ ተንቀዠቀዡበት።
«መቼ ነው አደጋው የደረሰብኝ?» አልኩኝ
«ከ27 ሰዓታት በፊት»
«ካላስቸገርኩኝ ትንሽዬ መስታወት ነገር ማግኘት እችል ይሆን? ፊቴ ምን እንደሚመስል ማስታወስ አልቻልኩም።» ስለው ግር በተሰኘ ሁናቴ ሲያየኝ እስከዛ ሰዓት እጇን ቆላልፋ ቆማ የነበረችው ሴቷ ሀኪም ፈጠን ብላ
«ቆይ ቦርሳዬ ውስጥ አለ» ብላ ወጣች። እንኳን የዘነጉትን ፊት አንድ ዓይን አጉልታ የማታሳይ ትንሽዬ መስታወት ይዛ ተመለሰች። መስታወቷን ቀረብ ራቅ እያደረግሁ ራሴን ላይ ሞከርኩ። ፊቴን አውቀዋለሁ። የሆነ 'የት እንደማውቀው ጠፋኝ እንጂ ይሄን ሰው አውቀዋለሁ' እንደሚሉት የሌላ ሰው ፊት አይነት እውቂያ ፊቴን አውቀዋለሁ። የሆነ ነገሩ የተቀየረም ይመስለኛል። ብቻ አላውቅም ቢዚ የሚያደርገው ሚሞሪ የሌለው ወና ጭንቅላቴ የፈጠረብኝ ቅዥብር ይሆናል። ያበጠ ከሚመስለው ዓይኔ ውጪ የተሸበሸበ ቆዳ ፊቴ ላይ የለም። አሮጊት አይደለሁም ማለት ነው።
«እድሜዬን መታወቂያዬ ላይ አግኝታችሁታል?»
«የትውልድ ዘመን 1980 ነው የሚለው።» ካለ በኋላ ያለንበትን ጊዜ ላላስታውስ እንደምችል አውቆ መሰለኝ «አሁን 2015 ላይ ነን!» አለ ቀጥሎ።
«እስከመቼ ነው ምንም የማላስታውሰው?» አልኩት ባወራሁ ቁጥር ሲደክመኝ እየታወቀኝ።
«አዝናለሁ! በእዚህ ጊዜ ብሎ ማለት አይቻልም። ወደኖርማል የበፊት እንቅስቃሴሽ ስትመለሺ ትውስታሽ በራሱ ጊዜ ሊነቃ ይችላል። ምናልባት እስከወዲያኛውም ላይመለስ ይችላል። ምናልባት ደግሞ የተወሰነ ትውስታሽ ተመልሶ የተቀረው ላይመለስ ይችላል። ቁስልሽ ድኖ ስትበረቺ የተለያዩ ቴራፒዎች እንድትሞክሪ እናደርጋለን። አዝናለሁ። » አለኝ አዝኖ ሳይሆን ማለት ስላለበት የስራ ግዴታው በሚመስል አነጋገር። ከዛ በኋላ ለረዥም ሰዓታት ዝም አልኩ። ብቻዬን ከተኛሁበት ክፍል በህመም ሲቃ በሚያዜሙ ታካሚዎች በተከበበ ክፍል ስድስተኛ ሆኜ ተደመርኩ። ሁሉም ታካሚዎች አስታማሚ አላቸው። የሚያጎርስ፣ የሚያገላብጥ፣ ምጽ ምፅ የሚል፣ ሲከፋም የሚያለቅስ፣ ሲበረታ አምላኩን የሚለማመንለት ብቻ ከጎናቸው ሰው አለ። ቀኑ የማላውቀውን የሰዓት ዙረት ቁጥር ዞሮ ምሽት እስኪሆን እኔን ብሎ የመጣ ሰው የለም። አደጋ እንደደረሰብኝ አልሰሙ ይሆን? ብቻዬን ይሆን የምኖረው? እሺ ይሁን ያቺ የቤት ሰራተኛ ነኝ ያለችውስ የት ገባች? ደውላ ለቤተሰቤ ወይ ለጓደኞቼ አትናገርም? ከአንዱ ሀሳብ ወደሌላው ስዘል፣ አናቴ ላይ የተንጠለጠለው ጉሉኮስ ሲያልቅ ሲቀየር ፣ በየመሃሉ መድሃኒት በክንዴ ሲሰጡኝ፣ ሳንቀላፋ ስነቃ ምሽቶ ነግቶ አረፋፈዱ ላይ የቤት ሰራተኛዋ ነኝ ያለችው ሴት በዶክተሩ እየተመራች መጣች። በትንሽዬ ዘንቢል የያዘችውን የምግብ ሰሃን እና ፔርሙዝ እያወጣጣች ከልብ ባልሆነ አጠያየቅ

👍28❤1
«እንዴት ኖት እትዬ? ተሻሎት?» አለችኝ ባመጣችው ኩባያ ከፔርሙዙ እየቀዳች። ዓይኔን እንኳን አላየችንም። ዓይኖቼን ሽሽቷ የሀፍረት፤ የማክበር ወይም የፍራቻ አይደለም። የጥላቻ እንጂ! ሞቼም ቢሆን ግድ እንደማይሰጣት ታስታውቃለች። ወይኔ አምላኬ ክፉ ሴት ነበርኩ ማለት ነው?
«እቤት ሌላ ሰው የለም?» አልኳት ምን ብዬ መጠየቅ እንዳለብኝ ግራ እየገባኝ
«እ ሀኪሙ ገና መለመላውን ወደምድር እንደመጣ ህጣን ማር ከአር እንደማይለዪ ነገረኝ። አጠያየቅዎ ቤተሰብ እንዳሎት ከሆነ አይድከሙ። ብቻዎትን ነው የሚኖሩት። እኔና የበር ጠባቂው ጎንጥ ብቻ ነን!» አባባሏ ምንም የሰብዓዊነት ርህራሄ ያለው አይደለም። እንዴት ያለ ክፉ አሰሪ ብሆንባት ነው ?
«አብሮኝ የሚኖር ሰው እንኳን ባይኖር ሌላ ቦታ የሚኖር » ብዬ ሳልጨርስ
«እኔ እርሶ ቤት ከገባሁ ገና ሶስት ወሬ ነው። እርሶን ብሎ የመጣ ሰውም አላውቅም። እርሶም ፈልገውት የሄዱት ወዳጅ ይኑሮት የማውቀው የለኝም።»
«መቼም የምሰራበት ቦታ ባልደረቦች ይኖሩኛል። ምንድነው ስራዬ? የምሰራበትን ቦታ ታውቂዋለሽ?» እንደሁኔታዋ ብታውቅም የምትነግረኝ አትመስልም።
«እርፍ ወግ! እኔ አላውቅም እትዬ!! ከቀጠሩኝ ቀን ጀምሮ ሰው ብለው ያናገሩኝ ዛሬ ነው። እንዴት አውቄው? በወጉ እንደሰርቶ አዳሪው በጠዋት ተነስተው ስራ ሲገቡ አይቼዎት አላውቅም። እንደው ያሎት ቀን ውልብ ብለው ከቤት ይጠፋሉ። ለሊት በጭፍራው ሰዓት ወደቤት ይመለሳሉ። ብቻ ቤትዎ ከሳምንት እስከሳምንት ሙሉ ነው።» ቃላቶችዋ ውስጥ ያልተፋቻቸው ሌሎች ቃላት ይሰማሉ። በስመአብ!! ስራዬ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ይሆን እንዴ? ብዙ ነገር ልጠይቃት ቅደም ተከተሉን እየሰካካሁ ፤ ምን ዓይነት ሴት ብሆን ነው እንዲህ ሆስፒታል አልጋ ላይ ተኮራምቼ እያየችኝ የማላሳዝናት እያልኩ አስባለሁ።
............. ይቀጥላል...................

👍28❤2👏1