#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሮፕላን እያጉረመረመ ከለንደኑ ሒትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ የለንደኑን ዳመና በአፍንጫው
እየበረቃቀሰ አቅጣጫውን ካስተካከለ በኋላ ካርለት ከሎና ጎይቲ እንደ ሌሎቹ መንገደኞች ሣቅ ጨዋታ አላበዙም።
ካርለትና ጎይቲ እየቆዩ ጫን ጫን ይተነፍሳሉ። ሶስቱም
የተቀመጡት በአሮፕላኑ መካከል ባሉት መቀመጫዎች ጎን ለጎን
ሲሆን ከፊት ለፊታቸውና ከኋላቸው ነጮችአሉ በስተቀኝ በኩል
አንድ ኢትዮጵያዊና አንድ ነጭ፤ በስተግራ በኩል ደግሞ የንጉሥ
ኃይለስላሴን ምስል ደረታቸው ላይ ያንጠለጠሉ ፀጉራቸውን እንደ ባህታዊ ጎንጉነው የኢትዮጵያ ባንዲራ የጠመጠሙ ጃማይካውያን
ተቀምጠዋል።
ካርለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚታተመውን “ሰላምታ" መጽሔት እያነበበች ሳለች።
“ይቅርታ” የሚል ድምፅ ሰምታ ቀና ስትል የአሮፕላኑ
አስተናጋጅ ፈገግ ብላ የምግብ ማስቀመጫውን እንዲዘረጉ ጠይቃ
ለሶስቱም የሚሆነውን ምግብ በፊታቸው አስቀመጠች።
በአጭር ጊዜ ውስጥ በኤሮፕላኑ ውስጥ ያለው ተሳፋሪ መመገብ ጀመረ: ጎይቲ ልትበላ አልፈለገችም: ካርለት ግን፡-
“ጎይቲ እባክሽ ትንሽ ለመብላት ሞክሪ?" አለቻት፡
“ካርለት እህል መች ራበኝ። ይልቅንስ አንች ብይ" አለቻት ፈርጠም ብላ ጎይቲ።
ባይሆን ይሄ ደረቅ ስለሆነ ብስኩቱን ብይ እስፕራይቱንም
ጠጪ" ስትላት።
“ይእ! አቤት! የምግባችሁ ስሙ ብዛቱ። አፍ ላይ
ይጣፍጥና ውስጥ ሲገባ እንደ ነፍሰ ጡር ማቅለሽለሽ። አሁንስ ወደ
አገሬ እሄድሁ ነው:: ለኔ ያደግሁበት ኩርኩፋ ትኩስ ወተቴ ይሻለኛል፡" ጎይቲ ኮስተር አለች።
ከሎና ካርለት ተያዩ: ጎይቲ አንዴ ከወሰነች ውሳኔዋን
እንደማታጥፍ ስላወቁ የየበኩላቸውን መመገብ ጀመሩ::
ጎይቲ ወዲያ ወዲህ ሄድ መለስ የሚሉትን እያየች ቆየችና፡-
“ፈረንጅና ህፃን ልጅ አንድ ነው፡ አንድ ጊዜ እስኪጠግብ አይበላ! አሁንም አሁንም መለካከፍ! ሁሉን መላስ ብቻ አንዴ
ጥሩ አርጎ አይጎርስ አይ ደንብ እቴ: ይእ! - ደግሞ የልብሳቸወ ብዛት:: ልብስን ቢያበዙት ትርፍ የለው: ከብት ቢገዙት ይራባል
በረት ይሞላል፤ ተዚያ ወተቱ ስጋው ይጠቅማል። ለዘመድ ወገን ቢሸልሙት ደስ ይላል።
“እነሱ ቤታቸውን ኮሮጆአቸውን የሞላው የሚያልቅ ቅራቅንቦ ብቻ! እና እኒህ ከህፃን በምን ይሻላሉ። እንደ ቀበሮ
የሚፈልጉትን እየተሯሯጡ ሲያነፈነፉ ይውሉና በዚያ ተግቶ በሚውለው ዋሻቸው ገብተው ማድፈጥ: እርስ በርስ አይዋደዱ አንዱ ሌላው ዘንድ አይደርስ ሲጫወቱ ለከት የላቸው:: ጆሮ እሚያደነቁር ነገር ይከፍቱና ዛር እንደያዘው ሰው አንዱ ከመሬት
መፈጥፈጥ ሌላው እንደ ጠገበ እንቦሳ መዝለል... ወንድና ሴቱ ደግሞ አይታወቅ ሁለቱም እቤት ውስጥ ተከተው አንድ አልጋ
ላይ ወጥተው መተኛት። ሴት ወንድን እንደህፃን ልጅ አቅፋ ተኝታ ሲያንኮራፋ ማየት።
“ደሞ የዚህ የኔው ጉድ የከሎ ይባስ እንጂ! ወዷቸው ሊሞት! ሳያርፍ ደሞ መኖርስ እዚህ ነበር' ይበለኝ፡ መጨከኑ
እንደ ዶሮ ሲጠጡ ማንጋጠጥ ሲበሉ አንገት መድፋት ከዚያ መሮጥ እንደ እብድ እየተገፋፉ መክላፍለፍ ተመልሶ ዋሻን ዘግቶ መቀመጥ ይህ የቀበሮ ኑሮ ምን ይወደዳል? ይእ! እነ አያ ደልቲ! ሐመሮች እዚህ ውስጥ መኖሬን ብነግራቸው እውን ሰው ያረጉኛል።ዳሩ እኒስ ምን ጥሩ አለው ብዬ አወራቸዋለሁ። ብቻ እንድረስ!"ጎይቲ ስለ ነጮች አኗኗር ማሰቧም ዘገነናት።
ጎይቲ አይኖችዋ ቡዝዝ ብለው ቢከፈቱም አያዩም: እሷ የምታየው የሐመር ተራራን ሜዳን... የጀግኖችን ቁንጮ ደልቲ ገልዲን ነው::
ቱር እያሉ የሚበሩ አዕዋፍ በነፋስ ጎንበስ ቀና የሚሉት
እዕዋት... ሳራቸውን የሚያመነዥኩ ከብቶች በጎችና ፍየሎች በጨረቃ ብርሃን ተቃቅፈው የሚጨፍሩት ልጃገረዶችና ጎረምሶች በአይነ ህሊናዋ ይመጡባታል፧ ይታይዋታል::
ደልቲን ለዳንስ ስትጋብዘው አየሩን እየቀዘፈ የወተት አረፋ የመሰለ ጥርሱን በጨረቃዋ ብርሃን እያብለጨለጨ ሲመጣ ከወገቧ እየረገረገች ጡቶችዋን እያስነጠረች ስልቱ ባልተዘበራረቀ እንቅስቃሴ መሬት እስኪጨንቃት እየረገጠ ሲጠጋትና ስትሾር... እንደ ብረት የጠነከሩት እጆቹ ትከሻዋን ሲደገፉ እንደ ባልጩት የሚለሰልሰው
ጭኑ ወደ ጭኗ ሲዘልቅ የብልቷ በር ደጋግሞ ሲንኳኳ... ከዚያ ወደ
ተፈጥሮ መኝታ ቤት ወደ ጫካው ሲገቡ በሩ ተከፍቶ ጋ ተደርጎ ሲቀረቀር የፍቅር ማራቸውን ሲላላሱ እንዳይሰላቹ ተሰነባብተው
እሷ ወደ ጎጆዋ እሱ ወደ ማማው ሲያመሩ ታያት።
ይህን ጊዜ ጎይቲ
ካርለት! ምነው ይኸ ነገር ቆመ፤ ምነው የሰው ጭንቀት ቢገባው ፤ምናለ! ከሐመር ቀዬ ቶሎ በሮ ቢያደርሰኝ!... አለቻት
መሳሳቋን ሳትደብቅ።
“እንደ ወፍ እየበረርን ነው'ኮ ጎይቲ! አይዞሽ ወደ ናፈቅሽው ቶሎ ትደርሻለሽ: ከሎን አታየውም? አለቻት እንድትረጋጋ በማሰብ
“ይእ! እሱማ ለማዳ ነው። ታቦቱ ደንብ የወረሰው የለም ለኔ የጨነቀኝ ለሱ ደስታ ፈጥሮለታል። ብቻ ተይኝ! እንዲያው እሚሰሙሽ ከሆነ ይኸ ነገሩ በቋራጭ በአቋራጭ አድርጎ ከሐመር
hእባቴ ተራራ ከቡስካ እንዲጥለኝ ንገሪው:: ከዚያስ ወዲያ ችግር
ቀናም ብዬ ሳላየው እየቦረቅሁ ተቀየዬ
ከዘመዶቼ ከጀግናዬ ጋር እገናኛለሁ፡ እና! እስቲ ንገሪቸው? አለች ጎይቲ፡
ካርለት ሳቅ ብላ፦
“ኤሮፕላኑ የራሱ የተወሰነ ፍጥነት ኦለው..." ስትል ጎይቲ አቋረጣት።
"አቤት! የደንባችሁ ብዛቱ። አቤት ስትፈራሩ… በይ ተይው እኔስ እንግዲህ ለአንድ ጊዜ እችለዋለሁ። መጥኔ ለናንተ! አለቻትና
ወደ ህልሟ ገባች። ከሎ ከጃማይካዎች ጋር ይጫወታል ይከራhራል...ይሳሳቃል።
የጎይቲ አስተያየት
ካርለት እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ አስገረማት። የጎይቲን ገሀዳዊ ህይወት አይታዋለች: ሐመሮች
በጥቁር ቆዳ የተሸፈነ አልማዝ ጥቅማ ጥቅም ያልበከለው ንፁህ ህሊና ያልተበከለ ባህል ካለ ዘመናዊ ህግና ፖሊሲ ተስማምተው
የሚኖሩ ተፈጥሮን የማይቃረኑ ህዝቦች መሆናቸውን አብራቸው
ኖራ አይታለች።
ሐመር ውስጥ ስሜት በህሊና እንጂ ሰዎች ባወጡት ህግ
አልተለጎመም: እውነት ራቁቷን ናት! እነሱም ራቁታቸውን ናቸው!
ተፈጥሮም አልተበከለችም! መሬት የፈለገችውን እፅዋት ታበቅላለች!የተጠጓትን አውሬዎች ደስ ብሉአቸው እንዲኖሩ ታረጋለች
የተፈጥሮ አበባ አካባቢውን እንዳስዋበው ነው። ሰማዩ ግን በአይሮፕላን ጢስ እየቆሸሸ መኪናው አራዊትን እያስበረገገ ነው።ስልጣኔ የተፈጥሮ ሚዛንን ለማዛባት ኬላውን ለመጣስ እየጣረ ነው ያኔ በራስ መተማመን በራሱ ይቆማል! ህክምና አልባው የመምስል
በሽታ ይጠናወታል! ማንነት ይጠፋል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የመስኮቱ መጋረጃ እንደተዘጋ ነው: የመኝታ ክፍሉ ግን በማለዳ ፀሐይ ብርሃን ደምቋል። ካርለት ተንጠራርታ አይኖችዋን
ስትከፍት ነጭ ቀለም የተቀባውን የመኝታ ክፍል ከጣራው እስከ ወለሉ የሚደርሰውን ሰፊ ቁምሳጥን ሰፊውን አልጋ.. ቃኝታ ዘወር ስትል ከስቲቭ ጋር ተያዩ::
ተንጠራርታ ወደሱ ጠጋ አለችና በፀጉር ከተሸፈነው ደረቱ ላይ ተለጥፋ አቀፈችው። እሱም ያቀፈበትን ክንዱን ሳብ ሳብ አድርጎ በግራ እጁ ፀጉሯን ዳበሰላት።
መቀሽቀሻ ስዓቷ ዲሪሪን… ዲሪሪን.ዲሪሪን' ስትል ስቲቭ ቀና ብሎ ድምፅ ሲያሰማት ፀጥ አለች እነሱም ሙቀታቸውን
እየተጋሩ ተቃቅፈው ፀጥ አሉ።
መቀሽቀሻ ሰዓቷ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ደግማ ዲሪሪን…..ዲሪሪን...' ስትል ካርለት የስቲቭን ከንፈር ሳም አድርጋ ቢጃማዋን
ሳትለብስ እርቃኗን መታጠቢያ ክፍል ገባች።

👍31👏1
ከተደረደረው የገላ መታጠቢያ ሻምፖ “ፋ” የሚለውን አንስታ ከታጠበች በኋላ በፎጣ ፀጉሯን ጠቅልላ ጥርሶችዋን
በመቦረሽ ልብሷን ለማምጣት ከመታጠቢያ ክፍሉ ወጣች።
ስቲቭ እንደተኛ ነው: ሁሌም መኝታውን ለመልቀቅ
ለረጅም ደቂቃዎች አልጋው ውስጥ አመድ ላይ እንደሚንከባለል አህያ ግራና ቀኝ መዟዟር አለባት: ካርለት ደግሞ ጠዋት መነሳትና የአዕዋፍን ዝማሬ እያዳመጠች ስራ እንኳን ባይኖራት መንጎዳጎዱን
ትመርጣለች። የዛን ቀን ግን ብርቱ ጉዳይ ነበራት።
“ስቲቭ?" አለችው ወደ አልጋው ጠርዝ ጠጋ ብላ:
“እህ!” አላት በድካም መንፈስ። ጎንበስ ብላ ከንፈሩን ስማው ቀና ስትል መዓዛውን የያዘውን አየር ባፍንጫው ሳበና “ዋው..” ብሎ ፈገግ አለ።
“ስቲቭ ስማ! ከሎና ጎይቲ ዛሬ ወደ ሐመር መሄድ
አለባቸው:: ጎይቲ አዲስ በበባ ውስጥ ማደር መዋል አትፈልግም::ናፍቆቷ ከልክ አልፏል። ፍላጎቷን ለማሳካት ደግሞ መሄድ አለባት::
ከሎ ግን ጥቂት ቀናት አዲስ አበባ ለመቆየት ፈልጎ ነበር። እሱ አዚህ
እንዳይቆይ ደግሞ እኔም የግድ ወደ ዩንቨርሊቲ መሄድና ከአንዳንድ
ሰዎች ጋር መገናኘት ምግቦችን... መገዛዛት አለብኝ።
“በተጨማሪም አያቷ ኢትዮጵያዊ የሆነች ስፔናዊት የአያቷን ትውልድ ቦታና ዘመዶችዋን ማየት እንደምትፈልግ እረፍት ስፔን
በቆየሁበት ጊዜ አጫውታኝ ኢትዮጵያ ብትመጣ በመፈለጉ ላይ ልተባበራት እንደምችል ቃል ገብቼላታለሁ: ስለዚህ ከከሎ ይልቅ የኔ እዚህ መቆየት የግድ ነው" ስትለው
“ጥሩ ነው!” አላት ስቲቭ። ቀጥላ ግን
“የመኪናው ባትሪ የት ነው? አለችው።
“ትናንት መልሰው እንዲያሰሩት ስለነገርኳቸው አስረውታል።ዘይት በመቀየር የሚፈትሽውን ሁሉ በመፈተሽ መኪናውን
ሞክረውት ለጉዞ ዝግጁ መሆኑን የኛ መካኒኮች አረጋግጠውልኛል!
ቁልፉ እሳሎን ተንጠልጥሏል"
“አመሰግናለሁ ስቲቭ"
“ለምኑ?” አለ ፈገግ ብሉ።
“ላስቆጠርከው መልካም ሥራ ሁሉ” አለችና እንደገና ስማው ወጣች።
💫ይቀጥላል💫

👍22
‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ16
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
/
የዳይመንድ ኢንተርናሺናል ሆስፒታል ዋና መግቢያ በራፍ በአድማ በታኝ ፖሊሶች ታጥሯል…በሆስፒታሉ ቀደም ብለው በውስጡ ተኝተው ከሚታከሙት ታካሚዎች ውጭ አዲስ ታካሚ መቀበል ካቆመ ሁለት ቀን አልፎታል፡፡ ወደሆስፒታሉ የሚያስገባው የአስፓልት መንገድና በአከባቢው የሚገኘው አደባባይ ጠቅላላ በሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች ተጨናንቆል፡፡በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የሚሰሙ መፈክሮች ውስጥ ጥቂቱ
‹‹ፍትህ ለዶ/ር ሰጵራ››
‹‹የዚህ ወንጀል ማስተር ማይንድ ፕሮፌሰሩ ነው››
‹‹ፖሊሶች ስራችሁን ስሩ››
‹‹ፈትህ ኩላሊታችውና ልባቸው ለተዘረፉ ዜጎች ››
‹‹ከዚህ ጀርባ ያላችሁ ባለስልጣን ወየሁላችሁ››
‹‹ፕሮፌሰሩ አጭበርባሪ ነው››
ይሄ ሁሉ ግርግራና ሰላማዊ ሰልፈ ሊወጣ የቻለው አብዬት በተሰባበሩ ነፍሶች የፌስብክ ገፅ ዶክተሯ መታፈኗንና ያፈኗት የፕሮፌሰሩ ሰዎች ከሆኑ ወንጀላቸውን እንዳታጋልጥበቸው እስከአሁን ገድለዋት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳለው መረጃውን ከለቀቀ ብኃላ ነው፡፡
ከዛ ደግሞ አንድ የግል የቴሌቬዝን ጣቢያ(እርግጥ ለጣቢያው ጋዘጠኛ አብዬት ከፍሎታል)ጎንደር ድረስ ሄዶ ታግተው የነበሩ እናቷንና እህቷን ኤንተርቨው አድርጎ አየር ላይ ካዋለው ብኃላ የዶ/ሯ ጉዳይ ሀገራዊ ችግር ሆነ..ትላልቅ ባለስልጣኖች ጉዳዩ ምንድነው ?ብለው መጠየቅ ሲጀምሩ ጉዳዩ ውስጥ የነበሩበት ባለስልጣኖች ደግሞ የሚይዙት የሚጨብጡት ጠፍቶቸው መተረማመስ ጀመሩ፡፡
..
ግፊት እነ ጫና ሲበዛበት ፖሊስ መግለጫ ሰጠ
ዶ/ር ሰጳራን ያገቷትን ሰዎችን በማደን ላይ አንደሆነና በአሁኑ ጊዜ ፕሮፌሰሩና ሙሉ የተባለው የፕሮፌሰሩ አጋር መሰወራቸውንና ከሀገር ለመውጣት እቅድ እንደነበራቸው መረጃው ስለደረሰው በየትኛውም መንገድ ከሀገር እንዳይወጡ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆ ገልፀው ከህብረተሰብም ውስጥ ፕሮፌሰሩንና አጋራቸውን ያሉበን የሚያውቅ ካለ በመጠቆም እንዲተባበር አሳወቁ
//
ዶ/ር ሰጳራና ካሳ በምቹ የሆቴል ክፍል ውስጥ ከታገቱ ሶስት ቀን ሆኗቸዋል፡፡በዚህ ሶስት ቀን ውስጥ ማንም ሰው እኔ ነኝ ያገትኮችሁ ብሎ ያናገራቸው የለም፡፡ግን በራፍቸው ላይ በተጠንቅ 24 ሰዓት የሚጠበብቆቸው ጠባቂዎቻቸው የፈለጉትን ነገሮች ሁሉ ከጥቂት የተከለከሉ እንደሞባይል ያሉ እቃዎች በስተቀር በፍጥነትና ያለማቅማማት ያቀርቡላቸዋል፡፡፡ዶ/ር ምንም እንኳን በመጀመሪያው ቀናቶች የቤተሰቦቾ ነገሮች በጣም እያሳሳባት ስለነበረ እሷ እርፍት አጠጥታ ጠባቂዎቹን በጭቅጭቅ እርፍት ነስታቸው የነበር ቢሆንም ከትናንትና ጀምሮ ግን ቤተሰቦቾ መለቃቸውን እንደውም እናቷንና እህቷን ስለደረሰባቸው ጉዳይ ሲያስረዱ ቀጥታ በቴሊቪዝን ካየች ቡኃላ በጣም ተረጋግታለች፡:፡ካሳ ደግሞ ከመጀመሪያ ቀን አንስቶ እጅግ ደስተኛ ሆኗል፡እንደውም ከከተማ ወጣ ብሎ ሳባና ቢች አካባቢ ባለ ቤርጎ ዘና እያለ ነው ሚመስለው፡፡
ካሳ ከፊት ለፊቷ ተቀምጦ አይን አይኗን እያያት‹‹ዶ/ር እነዚህ ሰዎች ምን ያህል የተባረኩ ናቸው?››አላት
‹‹የእኔ ጅል …የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እኮ መገደልህ አይቀርም››
‹‹እንዴ ልገደላ …ሞት እኮ መቼም አይቀርልንም…..ግን ይሄው ካንቺ ጋር የሶስት ቀን ገነታዊ የሆነ የጫጉላ ጊዜ እንዳሳልፍ እረድተውኛል...ለእኔ በጣም ባለውለታዬ ናቸው…››
‹‹የጫጉላ ጊዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙንም አታውቅም እንዴ?››
‹‹ቀላል ነው ከሚወዶት ሴት ጋር ለብቻ ተገልሎ የብቻ የሆነ ደስታ ጊዜ ማሳለፍ ማለት ነው››
‹‹በቃ››
‹‹አዎ በቃ… ከዛ በላይ ምን አለ?››
‹‹አለ ጂሉ....ለብቻቸው ተገልላው፤ የብቻ ጊዜ ማሳለፋቸው ብቻ ሳይሆን እንዴት እየሳለፉ ነው የሚለውም ወሳኝ ጉዳይ ነው..የጫጉላ ጊዜ ብዙ መሳሳም አለ…መተቃቀፍ አለ..መተሻሸት አለ ፤መዋሰብ አለ..ልጅ መስራት አለ››ከገባው ብላ ዘረዘረቸለት
‹‹በቃ?›አላት በተራው
‹‹ምነው? ልጨምር››
እነዚህን የዘረዘርሻቸው እኮ የፍቅር ማስዋቢያዎች ናቸው...እኔ ደግሞ ፍቅርን በሌሎች ነገሮች መኳኳል አልፈልግም..
እና አሁን እሺ ብዬህ ብንጋባም ምንም አንፈፅምም ማለት ነው?››
‹‹እኔ ብዙም አልፈልግም..ግን አንቺ ምትፈልጊ ከሆነ ችግር የለውም…ወሲብም ሆነ መሳሳሙን ላንቺ ስል አደረገዋለሁ››አላት፤ከእሱ የጠበቀችውን መልስ ነበር ያገኘችው፡፡
‹‹ስለዚህ ይሄንን የጫጉል ጊዜ ላመቻቹልህ ተወዳጆቹ አጋቾችህ ህይወትህን ብትሰጣቸውም ቅር አይልህም ማለት ነው?›አለቺው፡፡
‹‹በትክክል…በተለይ ቆይታችንን ለአንድ ሳማንት ቢያራዝሙልን››
ኣንድ ሰምንት››ዘገነናት…ከዛሬ ነገ ሊገድሉኝ ነው እያሉ የገዛ መሞቻ ጊዜን እየጠበቁ ለአንድ ሳምንት መጠበቅ ከባድ ነው፡፡
‹‹የሆንክ ዊርድ ነገር እኮ ነህ…..ከአንድ ሰው ጋር ዝም ብሎ ለሳምንት ተፋጦ መቀመጠ አያስጨንቅህም?››
‹‹አዎ በጣም ደባሪ ነገር ነው...ከአንድ ሰው ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ለአንድ ቀን እንኳን ተዘግቶብኝ ቢሆን በንዴት እራሴን ላጠፋ ሁሉ እችል ነበር..ችግሩ አንቺ ሌላ ሰው አይደለቺም…..አንቺ ማለት እራሴው ነሽ…ከራሴው ጋ ደግሞ ለዘላለም ብቀመጥ ችግር የለውም››
‹‹አይ አንተ… ጅል አፍቃሪ ነህ እኮ….››አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉንጩን ሳመችው…..ዞር ብላ ወደ መቀመጫዋ ልትመለስ ስትል አይኞቾ ቴሊቭዝኑ ላይ አረፉ… ሪሞቱን አነሳችን ድምፅን ጨምራበት አጠገቧ ያለው ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ማየት ጀመረች…ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ስለእነሱ የሚያወራ ስለሆነ ነው ቀልቧን የሳባት፡፡ የሆስፒታላቸው ዋና ባለሼር የሆኑት ሼክ ጠሀ ፊታቸው ለተደረደሩት በቁጥር አምስት ለሚሆኑ ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡
ክብርን የአትዬጵያ ህዝቦች በሆስፒታላችን ላይ በተከሰተው ጊዜያው ቀውስ በጣም እናዝናለን፡፡ግን እመኑኝ በአጭር ቀናት ውስጥ ከፖሊሶች ጋር በመተባበር በሆስፒታላችን ስም ጀርባ ተሸጉጠው ለአመታት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩትን ሰዎች በማደን በህግ ተይዘው ፍትህ እንዲሰጣቸው ማድረግ ብቻ ሳይሆን ካለጥፋታቸው በወንጀለኞቹ አሻጥር ሲሳደዱ የነበሩትን ባለደረቦቻችንን ደግሞ በሰላም ወደቤታው እንዲመለሱ ማድረግ ዋና ስራችን ይሆናል፡፡
አንድ ጋዜጠና ማይኩን ወደራሱ አስጠጋና ጥያቄውን ማቅማረብ ጀመረ‹‹ፓሊስ በሰጠው መግለጫ ከሆስፒታሉ ዋና ዋና ባለአክሲዬኖች መካከል ሁለቱ ማለቴ ፕሮፌሰሩና አቶ ሙሉ የተባሉት ግለሰቦች ተሰውረዋል…ታግተዋል የሚሉ ጭምጭምታዎችም አሉ…በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አሎት?›
መመለስ ጀመሩ‹‹ፕሮፌሰሩ እና አቶ ሙሉ የሆስፒታሉ ባለአክሲዎኖች ብቻ ሳይሆኑ ሆስፒታሉንም ዋናና ምክትል ሆነው ለአመታት ሲያስተዳድሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው.፡፡በሆስፒታሉ የምትከወን እያንዳንዶ ጥቃቅን ነገር ሳትቀር ከእነዚህ ሰዎች እውቅን ውጭ አትከወንም….እና እንደእኔ ግመት እነዚህን ሰዎች ታግተው ሳይሆን ተሸሽገው ወይንም ከሀገር ለመውጣት ሙከራ ላይ ያሉ ይመስለኛል…..ዶ/ር ሰጵራንም አግተዋት ከሆነ በጣም ደጎች ከሆኑ(ፕሮፌሰሩ እጮኛው እንደሆነች ከግምት በማስገባት)ይዘዋት ሊወጡ ይችላሉ…..ካልሆነም አላህ ቸሩን ያሰማን ብቻ……..ግን ፕሮፌሰሩና ግብረ አበሩ ሰሞኑን ከየወዳጆቻቸው ዶላር እየጠየቁ እንደነበር መስማት ችለናል……እቤታቸውም በፖሊስ ሲፈተሸ..ዋና ዋና እቃቸውን በሻንጣ ሞልተው ከቤት እንደወጡ ማወቅ ተችሏል፡፡የሚታገት ሰው ደግሞ እንደዚህ አይደለም›

👍45❤1👎1
ሌላ ጋዜጠኛ‹‹እርሶ የሆስፒታል ትልቅ ባለድርሻ ኖት…ታዲያ ይሄ ሁሉ ውስብስብና አሳዛኝ ወንጀል ሲሰራ እንዴት ዝም ሊሉ ቻሉ?››ሲል መሰረታዊ ሚባል ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡ዶ/ር ሰጳራ በታገተችበት ክፍል ሆና ሼኪው ለዚህ ጥያቄ ምን አይነት መልስ እንደሚመልሱ በጉጉት እየጠበቀች ነው፡፡
ሼኪው መልስ መስጠት ጀመሩ‹‹አይ ልጄ እኔ እንደምታየኝ የዘጠና አምስት አመት ሽማጊሌ ነኝ…ሆስፒታሉን ከባለሞያዎች ጋር ብሬን አውጥቼ ሳቋቁም በመጨረሻ የህይወት ምዕራፌ ለሀገሬና ለህዝቤ መልካም ስራ ለመስራት ካለኝ ፍላጎትና በተጨማሪ ደግሞ ለልጆቼና ለልጅ ልጆቼ ቋሚ ቅርስ ጥያላቸው ለማለፍ ብዬ ነው….አውቃለሁ የሆስፒታሉ ትልቁ ባለድርሻ እኔ ነኝ…ግን ሆስፒታሉ አስተዳደር ላይም ሆነ ሌሎች ስራዎች ላይ ምንም አይነት የቀጥታ ተሳትፎ የለኝም…..ስለሆስፒታሉ መረጃ የማገኘው ከሆስፒታሉ በየሶስት ወሩ እቤቴ ድረስ ከሚልኩልኝ ሪፖርት ነው..ከዛ በስተቀር ያው አዛውንት እንደመሆኔ በሽታ በየጊዜው ነው ሚጎበኘኝ እና እንደማንኛውም ታካሚ ለመታከም እመላለሳለሁ፡፡
‹‹በመጨረሻ የሚያስተላልፉት ነገር አለ?››
አዎ ፕሮፌሰሩና አቶ ሙሉ ተይዘው በህግ ፊት በመቅረብ ለአጠፉት ጠቅላላ ጥፋት መጠየቅ አለባቸው.እነሱን እንድናገኘኝ ለተባበረን ወይም ለፖሊስ ትክክለኛ ጥቆማ ለጠቆመ ሰው 5 ሚሊየን ብር እንሸልማለን…ሌላው የሆስፒተላችን እውቋ ባለሞያ የሆነችውን ዶ/ር ሰጵራን በሰላም እንድትገኝና ከተለጠፈባት የሀሰት ክስ እራሷን ተከላና ጀግና ሰው መሆኗን በህግ ፊት ለመላው ህዝብ አረጋግጣ ወደስራዎ እንድትመለስ እፈልጋለሁ…አዎ እሷ ጠንካራና ብልህ ሴት ስለሆነች በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ አልፋ ለድል እንደምትበቃ እተማመንባታለሁ…ለዚህም አንዲረዳ እኔ በግሌ እሷን በማግኘቱ ለረዳንና ለጠቆመን ሰው ሌላ የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አዘጋጅቼያለሁ፡፡.በሉ ለዛሬው ይብቃን ሽማግሌ ነኝ ከዚህ በላይ መቀመጡም ይከብደኛል፡››
መግለጫው አለቀ…..ቴሌቪዥን ጣቢያው ቀጥታ አሁናዊው ሁኔታን ማሳየት ጀመረ…. ሰላማዊ ሰልፉ፤ መፈክሩ ተደበላልቆ ይታያል፡፡
ካሳ ሁኔታውን አብሮ ስያይና ሲታዘብ ከቆየ ቡኃላ ‹‹እንዲህ ታወቂ ከሆንሽ ብኃላ ልትገደይ መሆኑ ያሳዝናል፡››አለ
‹‹ እኔ ታዋቂ መሆኔ ሳየሆን የገረመኝ የዚህ ሼኪ እንደዚህ እራሱን ለማንፃት የሄደብት እርቀት ነው ነው ››
‹‹ሰውዬውን ወድጄያቸዋለሁ….ካንቺው ፕሮፌሰር የተሻሉ አራዳ ናቸው›አላት ካሳ
‹‹አንተ ደግሞ በቃ ሁሌ ተቃራኒ ሆኖ ሰውን ማብሸቅ ምኑ ነው የሚያስደስትህ?፡፡
በዚህ መካከል በራፍ ሲጢጢ እያለ መከፈት ጀመረ..ሁለቱም አይናቸውን ወደ በራፉ ወረወሩ፡፡
ካሳ መናገር ጀመረ‹‹አራዳው ሽማጊሌ አሁን ቴሌቪዥን ውስጥ አልነበሩም እንዴ? በየት በየት ዞሮው እኛ ጋር መጡ?››ሲል ጠየቀ፡፡
ዶክተሯም በድንጋጤ እጇን በመዳፎ ላይ አድርጋ‹‹እርሶ እዚህ እንዴት? ››ስትል ተየቀች.
አዛውንቱ አብረቅራቂ ወርቅ ቅብ ከዘራቻን ተደግፈው ወደ ውስጥ የገቡተው በቅርባቸው ያገኙት ወንበር ላይ ተቀመጡና መናገር ጀመሩ‹‹ዶክተር ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ የእኔ ሰዎች እንክብካቤ እንዳላጎደሉባችሁ እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና እርሶ ኖት ያሳገቱን?››
‹‹ዶክተር አንዴት እንደምወድሽና እንዴት እንደማከብርሽ ታውቂያለሽ….መታገት የሚል ከባድ ቃል ስትጠቀሚ ስሰማ ይከፋኛል…እኔ ሊገድልሽ ከነበረ የገዛ እጮኛሽ ነው ያዳንኩሽ…እዚህም ከጓደኞችሽ ጋር ያመጣሁሽ ና ያቆየሁሽ ከአደጋ ነፃ መሆንሽን እርግጠኛ አስከምሆን ነው፡፡እጮኛሽም ሆነ በፖሊሶች እጅ እንዳትገቢ አንቺን ለመጠበቅ ያደረኩት ነው››
‹‹ምንም አይደል፡፡››
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

👍29🥰7😁2❤1🤔1
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ_17
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
""""
ካሳና ዶ/ር ሶፊያ በታገቱበት ቢት ሼኪው ተከስተዋል፡፡
"ሼኪ እሶን አይስሞት ...በእውነቱ ድንቅ መስተንግዶ ነው የተደረገልን ...እንደው ካላስቸገርኮት አንድ ወር ወይም አንድ ሳምንት በተመሳሳይ ሁኔታ ብንቆይ ውለታዋትን አንረሳውም።"አለ ካሳ፡፡
የካሳን እጅ እግር የሌለው ወሬ ችላ ብላ"ቆይ ያ አውሬ እቤተሠቦቼን እንዴት ሊለቃቸው ቻለ?"ስትል ጠየቀች።
"ተገዶ"አሏት በአጭሩ
"አልገባኝም...እርሷ ኖት ያስገደድት?ምን ለማግኘት ብለው?"
"እኔ አይደለሁም .....ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር ...በአንቺ ዘንድ ሌላ ውለታ ሆኖ ይመዘገብልኝ ነበር"
"እና ሌላ ማን ነው?የህዝብን ጩኸትና ሠላማዊ ሰልፍን ፈርቶ"
‹‹አሁን ያንቺ ሰውዬ ነው የህዝብ ጩኸት ፈርቶ እንደዚህ አይነት ነገር የሚያደርገው ደግሞስ እንደምታውቂው ይሄ ህዝብ ዝምብ ነው..አንዳንዴ የሰማውን ነገር እንኳን ለምን ብሎ ሳያጣራ ግር ብሎ መጥቶ አካባቢሽን ሲወረው ..እሽ ብለሽ ታባርሪዋለሽ…አልሰማ ሲልሽና ትንሽ ሲያበሳጭሽ..እጅሽን አስወንጭፈሽ በአየር ላይ ቀጨም ታደርጊውና በመዳፍሽ ውስጥ አፍነሽ ትጨፈልቂዋለሽ…..በቃ ጭፍልቅ…፡፡ከዛ የተጨበጠ የእጅ መዳፍሽን ታላቅቂና እሬሳውን ከእጅሽ ላይ አራግፈሽ ወደቆሻሸ ማጠራቀሚያ ትጨምሪዋለሽ…እጅሽን በንፅህ ውሀና በሳሙና ፈትገሽ በማታጠብ እራስሽን ታፀጂና የተለመደ ተግባርሽን መከወንሽን ትቀጥያለሽ፡፡አዎ ህዝብ እና ዝንብ አንድ ናቸው፡፡
‹‹እና እርሶም እንደዛ ነው የሚያስቡት››
‹‹አዎ በዚህ ጉዳይ እንኳን ከፕሮፌሰሩ ጋር ልዩነት የለኝ››
‹‹እኔ እስከማውቀው ግን በሌሎችም ጉዳዬች ላይ ከእሱ ጋር ልዩነት ሲኖራችሁ አይቼ አላውቅም….ጥሩ አባትና ልጅ ነው የምትመስሉት..ሁለታችሁም የዳቢሎስ ልብ ነው ያላችሁ››
‹‹ተይ እንጂ ዶክተር…..እኔን ከእጮኛሽ ጋር በጭካኔ ማነፃፀር ምን አይነት ፍርደ ገምድልነት ነው?››
"አሁን እሱን ተውትና የጠየቅኮትን ይመልሱልኝ፤ ቤተሰቦቼን ለምን እንደለቀቃቸው ምክንያቱን አያውቁም ማለት ነው?።"
"አውቃለሁ የራስሽ ልጅ ነው?"
"አልገባኝም"
"አቢዬት"
"እንዴት አድርጓ ?የት አግኝቶት? ማለት መሠወሩን በዜና ሰምቼ ነበር"
"ተሠውሮ አይደለም ታግቶ ነው...ያንቺ አብዬት አንቺው በታገትሽበት ምሽት ነው አግቶ ቤተሰቦችሽን እንዲለቅ ያደረገው...እሱን ብቻ ሳይሆን ሙሉንም አግቶታል። ምን አልባት እኔንም ሞክሮ ሳይሳካለት ቀርቶ ሊሆን ይችላል.....አሁን ሁለቱም በእሱ እጅ ናቸው።"
"የእኔ ጀግና"እንባዎ በጉንጮቾ ተንኳለለ።
"ያ አውሬ ተሣካለት…አሁን ሁለት ተፎካካሪዎቼ አንድ ቤት ናቸው...እንደው ሼኪ እሷን እዚህ አስቀርተው እኔን ቢለቁኝና ብቀላቀላቸው።"አለ ካሳ በሰማው ነገር ተበሳጭቶ...የዶተሯ አዳኝ ጀግና ከእሱ ውጭ ሌላ ሰው እንዲሆን አይፈልግም።በተለይ አፍቃሪዎቾ እንዲሆኑ።
ሼኪው የሚናገረው ስላልገባቸው "የምን ተፎካካሪ?"ሲሉ ጠየቁት
"ሦስታችንም የእሷ ፍቅር ተጠቂዎች ነን...እርስ በርስ ደግሞ ጣውንታሞች።
"እ እንደዛ ነው"
ዶ/ሯ ትግስቷ አልቆ ‹‹ሼኪ አሁን በዚህ ሰዓት ከእሱ ጋር ያወራሉ ...እሺ አሁን የእርሷ ዕቅድ ምንድነው?ምን ሊያደርጉን ነው ያሰብት?"
"አመጣጤ እኮ ስለዛው ልነግርሽ ነበር?"ብለው በከዘራቸው በመረዳት ከመቀመጫቸው ተነስተው ቆሙና"ዶ/ር ስለእናንተ ጉዳይ ከአብዬት ጋር እየተደራደርን ነው ...ቁርጥ ያለ ስምምነት ላይ ስንደርስ እንድታውቂው ይደረጋል።"
"በምንድነው የምትደራደሩት ፤እነዛን አራጅ ወንጀለኞችን ለማስለቀቅ?እነሡ ተለቀው ከተጠያቂነት ከሚያመልጡ እኔ አዚሁ የሆንኩትን ብሆን ይሻለኛል"
ፊታቸውን ዞረው እግራቸውን እየጎተቱ ወደ መውጫው መጓዝ ጀመሩ
"ጥያቄዬን መልሱልኝ እንጂ"
"ነገርኩሽ ዶ/ር ...ስምምነቱ ሲጠናቀቅ እንድታውቂው ይደረጋል" አሉና በራፋን ቆረቆሩ ፤ከውጭ ያለው ጠባቂ ከፈተላቸው።ወጥተው ሄድ።
እሷ በቆመችበት ተንገዳገደች...እራሷን ለመቆጣጠር ብትሞክርም አልቻለችም....ተዝለፍልፍ ወደቀች።
"እንዴ ዶክተር ደስታ ነው ወይስ ዋቴ ሰርተሽ እንዲለቁሽ እየሞከርሽ ነሽ።"አለ ካሳ ሁኔታዋ ግራ አጋብቶት።
መልስ ሲያጣ ከመቀመጫው ተነሳና ተጠጋት.. ቁጢጥ አለና ወዘወዛት ..አትንቀሳቀስም ሰቅስቋ በማቀፍ አልጋ ላይ አስተኛትና በሩን ሄዶ በሀይል አንኳኳ ።ጠባቂው መጥቶ ከፈተ
"ምን ተፈጠረ.?"
"ራሷን ሳተች"
"ራሳን ስተች ማለት?" ሁለቱም ተጠ ጓት.... ጠባቂው ዝቅ ብሎ ትንፋሿን አዳመጠ...ፈጠን ብሎ ጠረጰዛ ላይ ያለ የውሀ ጆግ አነሳና በጨርቅ እየነከረ ያቀዘቅዝላት ጀመር ...ከሶስት ደቂቃ ብኃላ ነቃች
"ምን ሆኜ ነው?"
"በደስታ እራስሽን ስተሽ"ካሳ ነው የመለሰላት፡፡
"ምንድነው የምትቀባዠረው?የምን ደስታ ነው"ጮኸችበት።
ጠበቂው"ዶ/ር ተረጋጊ ...ስለተጨናነቅሽ ይሆናል እራስሽን የሳትሽው።"
"የሄንን ሁሉ ትህትና ይዘህ የወንጀለኛ ጉዳይ አስፈፃሚ መሆን አይከብድም?"አለችው፤ ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እያሳያቸው በነበረው ትህትናና ስርአት ያለው መስተንግዶ ተገርማ፡፡
"ዶ/ር ህይወት ከበድ እንደሆነች መቼስ ለአንቺ አልነግርሽም...አንዳንዴ ገነት ያደርሰኛል ብለሽ የጀመርሽው መንገድ በየት አዙሩ ሲኦል እንደሚጥልሽ አታውቂም።"አለና ከተቀመጠበት ተነሳና ቆመ..
"እንደው አንድ ነገር ላስቸግርህ?"
"ምችለው ከሆነ ችግር የለም"
"አንድ ቦታ ለመደወል ስልክ ፈልጌ ነበር"
"በራሴ እንደዛ ማድረግ አልችልም..ታውቂያለሽ በራፍ ላይ ሁኔታዎችን የሚቆጣጠር ሌላ ጠባቂ አለ..ማድረግ የምችለው ሀለቃዬ ጋር ደውዬ ሀኪም እንደሚያስፈልግሽና ስልክም እንደጠየቅሺኝ ነግራቸዋለሁ..ከዛ መልሱን አሳውቅሻለሁ።"ብሎ ወጥቶ ሊሄድ በራፍ አቅራቢያ ሲደርስ ቆይ አንዴ ብላ አስቆመችው።
ኮመዲኖ ላይ ካለው ማስታወሻ አንድ ሉክ ቀደደችና
አብዬት እኔን ለማስለቀቅ ከሼኪው ጋር እየተደራደርክ መሆኑን አውቃለሁ። በምንም አይነት እኔን ለማዳን ብለህ እነዣ ሰው በላ ጭራቆች እንዲያመልጡና ነፃ እንዲወጡ እንዳታደርግ..እኔን ባለሁበት ተወኝ...እነሱ በአደባባይ እንዲሰቀሉና ሰማንያ ቦታ እንዲቆራረጡ ነው የምፈልገው።ደግሞ ቤተሠቦቼን በሰላም ወደቤታቸው እንዲመለሡ ስላደረክ አመሠግናለሁ።በጣም ነው የምወድህ።"
ስልክ.ቁ 091205....ፅፋ ከጨረሰች ብኃላ።
በዚህ ቁጥር ደውልና ለሚያነሳው ሰው ይሄንን መልዕክት ንገርልኝ።አውቃለሁ ትልቅ ውለታ እየጠየኩህ ነው...እባክህ "
እሺም እንቢም ሳይል ወረቀቱን ተቀብሏት ኪሱ ውስጥ ጨመረና በራፍን በላያቸው ላይ መልሶ ከውጭ በመቆለፍ ሄደ።
"አይገርምሽም ዶ/ር እነዚህን ሠዎች በጣም ነው የወደድኳቸው..."ካሳ ነው ተናጋሪው፡፡
"ሂድና ሳማቸዋ"
"እኔ የወደድኩትን ስስም አይተሽ ታውቂያለሽ? ለምሳሌ አንቺን ስሜሽ አውቃለሁ?"
ምንም አልመለሠችለትም… ከላይ ያለበሰችውን አልጋልብስ ወደላይ ሳበችና ሙሉ በሙሉ ፊቷን ሸፍነች። እንቅልፏ መጥቶ አልነበረም። በፀጥታ በካሳ አንጀት አድብን ንግግሮች ሳትረበሽ ለማሰብ እንጂ"
እሱም ወደሌላው አልጋ ሄዶ ከእነጫማው ወጣና ተዘርሮ ተኛ...በደቂቃ ውስጥ ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰደው።
////
አብት ከአቶ ሙሉ ፊት ለፊት ቁጭ ብሎ እየተደራደረው ነው፡፡
<<አቶ ሙሉ የነገርኩህን ነገር አሰብክበት?››
‹አዎ አሰቤበታለሁ… .ግን ምን መሰለህ እባክህ ከዚህ ጉድ አውጣኝ..ወደውጭ እንድወጣ ከረዳሀኝ ግማሽ ሀብቴን ላስተላልፍልህ እችላለሁ››
‹‹ግማሽ ሀብትህ ምን ያህል ይሆናል?››
‹‹እስከ 20 ሚሊዬን››

👍32
‹‹እና 20 ሚሊዬን ልትሰጠኝ?››
እንደነገርከኝ ከሆነ እስከአሁን የ205 ሰዎች ኩላሊት በጥቂት ገንዘብ እየገዛችሁ አንዳንዱንም በአደጋ ሆስፐታል ከገብና ከሞቱ ሰዎች ሰርቃችሁ ሸጣችሆል፡፡የ52 ሰዎች ልብ ሸጣችኋል፡..ሌላም ብዙ ብዙ የሚዘገንኑ ወንጀሎች››
‹‹አዎ.ብዙ ጊዜ እኮ ያልካቸውን ወንጀሎች መፈፀማችንን ነግሬሀለው››
‹‹ምነው ታዲያ ስትፈፅሙት ያልደከማችሁ አሁን ስታወራው አንገሸገሸህ፤ስማኝ ከጠቀስክልኝ ወንጀሎች ውስጥ ቢያንስ ግማሹ በእናንተ ታፍነው ልባቸውና በመዝረፍ እንዲሞቱና ሰውነታቸው በአሲድ ቀልጦ ለቀብር እንኳን እንዳይበቁ የተደረጉ ናቸወ፡..እና 20ሚሊዬን ሳይሆን 20 ቢሊዬን ብር ቢኖርህና እንኳን አያድንህም››
‹‹ግን የዚህ ሀሳብ ጠንሳሽም ዋናው አድራጊ ፈጣሪ እኮ ፕሮፌሰሩ ነው፡፡የእኔና የሺኪው ድርሻ ትንሽ ነው››በማለት እራሱን ለመከላከል ሚያደርገውን ጥረት ቀጠለበት፡፡
በንግግሩ አብዬት ተንቀጠቀጠ‹‹ግን ምን አይነት ህሊና ቢስ ሰው ነህ?እንዚህን ቃላቶች ከአንደበትህ ስታወጣ ትንሽ አያደናቅፍህም?ስማ እኔ የእድሜዬን ግማሽ ማጅራት መቺ ሆኜ አሳልፌያለሁ ፡፡በዚህ ሂደት በስህተት አንድ ሰው በእጄ ላይ አልፎል እና ከዛን ቀን ጀምሮ ንፅህ እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም… እናንተ ያን ሁሉ ሰው እንዲህ ጨፈጭፋችሁ እንዴት ነው በሰላም መተንፈስ የምትችሉት..ምን አይት አውሬነት ነው በውስጣችሁ ያለው?፡፡አሁን ዝም ብለህ ስማኝ …እኔ እናንተን ለመንግስት አሳልፌ ሰጥቼ በ ፍርድ ቤት እስክትዳኙ መጠበቅ እልችልም፡፡ምን አልባትም የሞት ፍርድም ቢፈረድባችሁ አንኳን አያረካኝም››
‹‹እሸ እንዲሆን የምትፈልገውን ንገረኝ?››
‹‹ኩላሊታቸው ለተዘረፉ 35 ሰዎችን ማግኘት ችለናል.እንሱ አንድ ላይ ሆነው ጠበቃ ገዝተው ሆስፒታላችሁን ከሰዋል፡፡እርግጠኛነኝ ፍርድቤቱ ተገቢውን ካሳ ስለሚበይንላቸው የሚከፈለው ከአንተና ከፕሮፌሰሩ ሼር ተቀንሶ ነው፡፡
‹እንዴ ሼኪውስ…ከዚህ ጉዳይ ከተገኘ አያንዳንዱ ትርፍ ተካፋይ ነበሩ እኮ…››
‹‹ጥሩ .ለጊዜው ግን እሳቸውና ዶዬ እዚህ ወንጀል ውስጥ አይካቱም.. ለአንተ ቤተሰብ የሚሰጠውን ብር ከእሳቸው ነው የምቀበለው….በዛ ላይ ዶክተሯና ጓደኛዬ በእሳቸው እጅ ነው ያሉት..ግን እመነኝ ቀኑ ሲደርስ እራሴው ለሰሩት ወንጀል በደንብ አስከፍላቸዋለው ለዛ ቃል ገባልሀለሁ፡፡አንተ ግን ስለሆስፒታሉ ሼር እርሳው.ምንም አይኖርህም፡፡››
‹‹ቤተሰቦቼ እዚህ ወንጀል ውስጥ የሉበትም.ሚስቴ በጣም ሀይማኖተኛ ና ፈርሀ እግዚያብሄር ያላት ሴት ነች .እና በእኔ ሀጥያት እነሱ መቀጣት የለባቸውም.እንድ ያላቸው መተዳደሪያ ደግሞ ይሄ ሆስፒታል የሚገኝ ገቢ ነው››
‹‹እሱን እኮ አየሁ… ሚስትህንም ልጆችህንም አነጋግሬያቸዋለሁ….ስለአንተ በሚዲያም በሰሙት ነገር ተሳቀውና ተሸማቀው ነው ያሉት…..ብትሞት እራሱ ያን ያህል አያዝኑም…እንዴት አንተን የመሰለ የሰይጣን ታናሽ ወንድም እዛ ቤተሰብ ውስጥ ሊኖር እንደቻላ ማሰብ እንኳን አልቻልኩም፡፡
‹‹አዝናለሁ››
‹‹አይ አንተማ ሀዘኔታ የሚባል ነገር ውስጥህ የለም..ይልቅ አሁን ስማኝ…ለቤተሰብ 20 ሚሊየን ጥሬ በር እንዲደርሰቸው አደርጋለው፡ያንን በስልክ እንድታረጋግጥ ይደረጋል፤ከዛ ቡኃላ ግን ያልከሀውን ታደርጋለህ›
በመጀመሪያ የእያንዳንዱን ሰው ወንጀል በዝርዝር .ምን እንደሰራችሁ ..የእያንዳንዱ ወንጀለኛ ድርሻ ምን እደነበረ፤ በተለይ ፕሮፌሰሩና ባለስልጣኖቹ ላይ አተኩረህ ትተነትናለህ.ያንን በቪዲዬ ይቀረፃል…የራስህንም ወንጀል ሳትረሳ ማለት ነው..ኑዛዜ በለው፡፡››
‹‹ያልከኸውን ማለቴ 20 ሚሊዬን ብር ለበተሰቤ የእውነት እንዲያገኙ ካደረክ ያልከኸውን በደስታ አደረጋለሁ፡››
‹‹ለዛ አትጠራጠር. ቀረፃውን የምታረግው ብሩን እንዳገኙ ካረጋገጥክ ቡኃላ ነው፡፡ግን ከዛ ቡኃላ ደግሞ ሌላ አንድ ነገር ይጠበቅቅሀል፡፡››
‹‹ምንድነው?››
‹‹እኛ በመረጥነው ቦታ ላይ አንተ በመረጥከው መንገድ እራስህን ታጠፋለህ፡፡ ››
‹‹ምን?››
‹‹አዎ .ይሄ እኮ ለአንተ አይነቱ ጭራቅ ትልቅ እድል ነው ….እንደ ወንጀልህ ቢሆን እያንዳንዶን የሰውነትህን ብልት እየተቆረጠ ሞትን እስክትለምን መቃተት ነበረብህ ..እና ግን ያው በአንት ልክ አውሬነት ውስጣችን ስሌለ ምህረት አድርገንልህ ነው እንዲህ አይነት የክብር ሞት አማራጭ የቀረበልህ..እራስህን በራስህ እንድታጠፋ ልንተባበርህ ወስነናል፡፡እንዳልኩህ የመሞቻ ዘዴውን ግድ የለም እራስህ መምረጥ ትችላለህ.ከፈለክ በሽጉጥ ፣ከፈለክ በመርዝ ፣ከፈለክ ደግሞ ተንጠልጥለህ…እኛ የመረጥከውን መሳሪያ ያለምንም ክፍያ እናመቻችልሀለን፤እ ምን ተትላለህ?
‹‹ሌላ ምርጫ የለም..››
‹‹አለ››
‹‹ምን ?››አለ በጉጉትና ፡፡
ኩላሊታቸው ተዘረፈባቸው ያልኩህ 35 ሰዎችን በአንድ አዳራሽ ውስጥ እንዲሰበሰቡ አመቻችና እጅ እግርህን በማሰር መሀከላቸው እንጥልሀለን ፤ከዛ የሚሆነውን ማየት እንችላለን››
‹‹እሺ ፕሮፌሰሩስ እንደእኔ ነው ሚሆነው.እንደእኔ አራሱን እንዲያጠፋ ልታደርጉት ነው?፡፡››
‹‹አይ በፍፅም……እሱ አንተ ያገኘሀውን እድል አያገኝም….በእጆቼ ቀስ በቀስ ነው የምገድለው፡፡ምን አልባት አንድ ወር ሊፈጅብኝ ይችላል.ለማንኛውም ማሰቢያ አንድ ቀን አለህ.ነገ በዚህን ሰዓት ተመልሼ እመጣለሁ..የዛን ጊዜ የመጨረሻ ውሳኔህን ታሳሳቀኛለህ፡››ብሎ በራፉን ዘግቶበት ወጥቶ ሄደ

👍38❤7
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሦስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ሶራ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዓመተ ምህረት ነው። ከዚያም በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና በረጂ ድርጅቶች ሰርቷል። ሥራ መቀያየሩ ግን ሆዱን እንደ እንቁራሪት ሆድ ከማሳበጥ በስተቀር ያገኘው የሕይወት እርካታ
የለም። የት ቢሄድ ምን
ቢሆን የህሊና እርካታ እንደሚያገኝ
አያውቅም ዩኒቨርስቲ ውስጥ እያለ ኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንትን የመረጠው በጓደኞቹ ምክርና ግፊት ነው።
"...አትሞኝ! ጥሩ ደመወዝ ለማግኘት አዲሳባ ለመመደብ ዕድልተህ እንዲሰፋ ከፈለግህ" እያሉ የሰማይ ጥገት የሚመኙ ጓደኞቹ እየነዱ ወደ አልተመኘው ዲፓርትመንት
ሃሳቡን አኮላሽተው
አስገቡት።
ከአደገበት· ቀዬ ከተንቦራቸበት የኤርቦሬ ምድርም ዳግመኛ ሳይመለስ የውሃ ሽታ ሆኖ ወደ መጣበት ተመልሶ መግባት የማይታሰብ ገደል ሆነበት። በልጅነቱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ሊሄድ
ጥብቆ ሲለብስ
ሽማግሌዎችም ሲመርቁት
“…እንደ ጅብ በነጋበት የምትቀር አትሁን። የአያት የቅድመ አያቶችህን ደንብ አክባሪ ለወገንህ ተቆርቋሪ መሆንህን የምታስመሰክር ሁን ብትጠፋ እንኳ የእነሱ ዘር ነው የሚያሰኝህን
ኤርቦሬነትህን አታጥፋ።
ኤርቦሬ ውስጥ ሪስ ፋርቶ ሃልዝጋለች አልሞቅ ሩፍ ህፀንቴ ኤቡሬ ጋሮራ
ጋራንጉዶ ጋርሌ ዲሳ የሚባል ዘር አለ ወደምትሄድበት አገር ስትደርስ የከብት ጆሮ
አበሳሳችሁ እንዴት ነው? ህፃን ልጅ እንደ ተወለደስ መጀመሪያ የምታቀምሱት ምንድን ነው?ብዙ ጊዜ የምትጋቡትስ ከማን
ከማን ጋር ነው?..." ብለህ ጠይቅ።
“...የአንተ ዘር የከብት ጆሮ አበሳስ ታችኛውን የጆሮ ክፍል ከውስጥ ወደ ውጭ በመብሳት ሲሆን! ህፃን ልጅ እንደተወለደ የቡና
ፍሬ ማሽላ የከብት ጥፍር ከህፃኑ ልጅ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ ይሰጠዋል። ብዙ ጊዜ ጋብቻ ከቦረናና ፀማይ ጋር ነው። ስለዚህ
ይህን በሄድህበት ሁሉ እየነገርህ ዘርህን ብትጠይቅ ካለጥርጥር
ታገኛቸዋለህ: ከዚያ የቤተስባችሁ አባል ከሌላ አገር ስለመጣ ተቀበሉት ብለው ከዘሮችህ ያደባልቁሃል:
ወደ ሌላ አገር የሄደና የሞተ አንድ ነው እስካልታዩ ድረስ:: ልዩነቱ ያልሞተ ከሄደበት ይመለሳል ! ያኔ ወደ ቤተሰቡ ከመቀላቀሉ በፊት የመንደሩ ሰዎች ማንም ሰው ጠጥቶበት
በማያውቅ ቅል ውሃ ሞልተው ይይዙና ከፊት ለፊቱ ውሃውን እየደፉ መሬቱን በማርጠብ እርጥቡን እግር" ከቤተሰቡ ጋር ይደባልቁታል! ካለበለዚያ ግን ማንም የቤተሰቡ አባል ቢያየውም
ሰላም አይለውም:: እና! አንተም ክሄድክበት ስትመለስ ይኸ ደንብ
እንደሚሰራልህ አትርሳ: ከደንቡ በኋላ ከኤርቦሬ ወንድሞችህ ጋር ጫካ ትወርድና ያገኘኸውን አውሬ ገለህ ስትመጣ ከወላጆችህ በር ፊት ለፊት የእድሜ ጓደኞችህ "ዘውትር ምሽት እየዘፈኑ እያቅራሩ አንዱ የሌላውን ጀርባ ሸፍኖ እየተቀመጠ የአባትህ ቤት የጀግና ቤት መሆኑን እያወደሱ ሲያደምቁት ይሰነብታሉ… ከዚያ ተድረህ ወልደህ ከብደህ ጋንደሩባ ኡላም ሙራል ወይም እጉዴ ትኖራለህ።
“ ኤርቦሬ በአሁኑ ጊዜ ስልጣን የያዘው የኦጌልሻ ሄር ሲሆን ኦጌልሻ ሄር ስልጣነን የተረከበው ከሜልባሳ ሄር ነው።
“በአባትህ ባህል በአርባ ዓመት አንድ ጊዜ አሮጌው ገዥ ሄር በአዲሱ ገዥ ሄር ይተካል:: ይህም ኦቤርሻ ጂም ጊድማ ጂም
ማሮሌ ጂምና ዋተኛ ጂም ሲሆን የመጀመሪያው ጂም ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ሲሆኑ ኦቤርሻ ጂም ይባላሉ: ከዚያ ከጨቅላነት እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት ህፃናት
አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት አመት ሲሞላቸው ጊድማ ጂም ይሆናሉ። ያም ማለት ከኦቤርሻ ጂም እስከ ጊድማ ጂም ዘጠኝ ዓመት
ይሆናል ቀጥሎ ደግሞ ከጊድማ ጂም በታች ካሉት ጨቅላዎች እስከ ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር አመት እስከ አስራ ስምንት ዓመት ሲሞላቸው ማሮሌ ጂምን ይመሰርታሉ።
ይህም ዘጠኝ ዓመት
ይፈጃል። ከማሮሌ በታች ያሉት ከጨቅላነት እስከ "ዘጠኝ ዓመት ያሉት አድገው ከአስር እስከ አስራ ስምንት ዓመት ሲሞላቸው ደግሞ ዋተኛ ጂም ይባላሉ።
“ስለዚህ ኦቤርሻ ጂም ዘጠኝ ጊዴማ ጅም ዘጠኝ ማርሌና የአራቱን ጂም
ዋተኛ ጂም እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ዘጠኝ ስለሚቆዩ
ለመፈፀም ሰላሳ ስድስት አመት የሚፈጅ ሲሆን አሮጌውን የገዥ ሄር
ከተለያዩ እድሜ ከሴትና ወንድ በእኩል የተሰባሰበውን አዲስ ሄር
አጠቃላይ የኤርቦራ ማህበረሰብ በተሰበሰበበት በተለያዩ ባህላዊ ስነስርዓቶች ስልጣን ከአሮጌው ሄር ይረከብና በጋንደሩባ ኩላም
ሙራልና እጉዴ አንዳንድ ከርነት (ጠቅላይ ሚኒስቴር) ይመረጣል። ከርነት ሆኖ የተመረጠው ሰው ካለ ግልድም በስተቀር ልብስ
አይለብስም። ባህሪውም የተመሰገነ ትሁት... መሆን ይገባዋል። ይህ ሰው የአባት ደንብና አሁን ያለው የኤርቦሬ ህዝብ የአደራ ቀንበር የሚጫንበት በሬ ነው: ጎረምሶችም የራሳቸውን የጦርነት ጊዜ
አዝማች 'መሪናኔት' መርጠው የነብር ቆዳ ያለብሱታል: ይህም ሰው
በጦርነት ጊዜ ስልት አውጭና ደረቱን ለጦር ሰጥቶ ለህዝቡ መከታ
የሚሆን ነው።
“ከዚያ የፖለቲካ መሪ የሚሆኑት አራቱ ከርነቶች
ከመንፈሳዊ መሪዎች (ቃውቶች) የአገር ሽማግሌዎች (ጃላቦች) ጋር
ስልጣናቸውን ለሚቀጥለው ወጣት ሄር ያስረክባሉ። ስለዚህ አንተ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኦጌልሻ ሄር አባል በመሆንህ ቶሎ ተመልሰህ
ማህበረሰብህን መርዳትህን አትዘንጋ: እስከዚያው ግን
ወገኖችህ ፀሐይ ወጥታ እስክትገባ ሳንሰለች እንጠብቅሃለን፡፡ ይህ ኸሊናህ ሳይጎድፍ ተመልሰህ ናና ከማህበረሰብህ ተቀላቀል...” ብለውት ነበር።
አካሉ እያደገ ህሊናው እየበሰለ ሲሄድ ግን ከዘመዶቹ አደራ በላይ የአገሩ የአህጉሩ ባጠቃላይ የሰው ልጆችን የመርዳት አደራ ፕላኔቷን የመጠበቅ ግዴታ... እንዳለበት እንኳን ተረድቶ ነበር። በጎ
አስተሳሰቡን ግን ውሃ በላው። አፍንጫው ጥቅም ውስጥ እየተሰነቀረ
ሆዱ ለእለት ደስታ እየተነጠፈ አስቸገረው መቆፈሪያ አንስቶ
የድህነት ተራራ ለመናድ የማንዴላ እናት አምጣ እንድትወልደው ኃይልን እንድታቀብለው ፈለገ እየቆየ ግን አንድ ሃሣብ በህሊናው
ማውጣት ማውረድ ጀመረ።: ቢያንስ በግሉ አንድ ሆዝብን ሊረዳ
ድርጅት መክፈት። ለዚህም ደግሞ ገንዘብ ያሻዋል። ገንዘብ ያላቸው ሰዎች መዳፍ ገብቶ እንደ ቆሎ እያሹ ጉልበቱን ቆረጣጥመው ምስጥ
እንደበላው ግንድ ገንድሰው እንዲጥሉት ግን አልፈለገም
ነፃ መሆንን መረጠ፡
ለዚህ ግን አልታደለም። ያለበት ዘመን ህይወት በገንዘብ የሚተመንበት የገንዘብ ኃይል ነጋሪት እየተጎሰመ በሚለፈፍበት ጊዜ ነው። ዓላማውን ለማሳካት ግን አንድ አማራጭ አለው: ሰርቶ
የማግኛ ስደት: "ስደት ግን ሽሽት ነው" ብሎ ያምን ነበር: ከዚህ ህዝብ ጋር የበላውን በልቶ የጠጣውን ጠጥቶ ከንፈር እየመጠጡ
ማስተዛኑም ደግሞ ድፍረት እንዳልሆነ ተረዳ። ኤርቦሬ አደራ ይዞ ወጣ፤ አልተመለሰም እና! አደራውን በላ: ከአገሩ ሰርቶ
ለማግኘት ብሎ ሄዶ ፍርፋሬ ቢጥመውስ፤ አዲስ ምኞት ህሊናው ቢያረግዝስ እንደገና ክህደት ሊፈፅም? ስለዚህ ለመወሰን ብዙ
አማጠ ከወሰነ በኋላም ህልሙን እውን ለማድረግ ብዙ ጣረ፤ ግን ተሳካለት። እንደ ደረቀ እንጨት የተለዬ ሆነ እንጂ።

👍21
“ኤርቦሬ" የሚለውን ስያሜ ያወጡት ሐመሮች ናቸው።
በሐመርኛ ቋንቋ “ኤር' ማለት ህዝብ “ቦሬ" ደግሞ ቦረና ማለት ነው።
ኤር ቦሬ' በቋንቋው ጥቅል ትርጉም “ከቦረና የመጣ ህዝብ" ማለት ነው
ኤርቦሬዎች ከኤሎ የተራራ ሰንሰለት በስተ ምስራቅ ከቦረና በስተምዕራብ በደቡብ ምስራቅ ከሐመር በደቡብ ከኬንያ ድንበር
ተዋስነው በረባዳማው የወይጦ ሜዳ የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው:
በጆግራፊያዊ አቀማመጡ ሰበብ ማህበረሰቡ ለሁለት የተከፈለ ሲሆን በስተሰሜን ያለው ኤርቦሮ በጋንዱሩባና ኩሳም፤ ማርሌ በመባል በሙራልና በእጉዴ መንደር የሚኖሩ ናቸው።
በአርባ አመት አንዴ በሚደረገው የስልጣን ሽግግር አጠቃላይ የማህበረሰቡ አባል ሴት ወንድ ህፃን ሳይል በየቤቱ
ውስጥ የነበረውን እሳት አጥፍቶ ይወጣና በአንድ ላይ ይሰባሰባል፤
አዲስ እሳት በሰበቃ ይቀጣጠላል ፤ ከብት ይታረዳል። ጎረምሶችና
ጎልማሶችም በሰልፍ ሆነው የከብቱን ደም በጣታቸው ግንባራቸው ላይ እየቀቡ ወደ ህዝቡ እንዲቀላቀሉ ይደረጋል ቃል ኪዳን ነው::
በኤርቦሬ ባህል ልጃገረድን ካለፈቃዷ የደፈረ የተወገዘ
በመሆኑ ከወንዶች መካከል ይህን የፈፀመ ወንጀለኛ ካለ በጣቱ የከብቱን ደም ነክቶ ግንባሩን አይቀባም ጓደኛው ደም ነክቶ ፊቱን ሳይዞር ጣቱ ላይ ይቀባለታል ማህበረሰቡ በጥላቻ ያየዋል ቃል ኪዳን አፍራሹን ድርጊቱም በሁሉም ይወገዛል። ደንብ ጣሹም በመጥፎ ተግባሩ ተደናግጦ እንደ ተቆረጠ ቅጠል ሲጠወልግ ሲወይብ ይታያል። ማህበረሰቡ እውነት በእጁ ነች: የዋሸ የደበቀ ያታለለ የሰውነቱ ቆዳ እስኪገለበጥ እየተገረፈ አይቀጡ ቅጣት
ይቀጣል። ጥፋቱን ካመነና ሲሸማቀቅ ከታዬ ግን ከህሊና ቅጣት በላይ ቅጣት አይሰጠውም: የማህበረሰቡ የዝምታ ሳማ ህሊናውን የለበለበው ግን ሁለተኛ ጥፋቱን አይደግምም።
በበዓሉ ይበላል ይጠጣል ይጨፈራል። ከዚያ አሮጌው
የገዥ ሄር ስልጣኑን ለአዲሱ ገዥ ሄር ትውልድ በሰላም ያዙኝ ልቀቁኝ ሳይል ያስረክባል። አዲሱ ገዥ ሄርም የራሱን ጠቅላይ
እና ሽማግሌዎች ይመርጥና ሚኒስተሮች የጦር መሪዎች
ከሃይማኖታዊ ንጉሶች ጋር ተባብረው ለመስራት ቃል ኪዳን ይገባሉ፡
ይህ ትውልድ ካለፈው ትውልድ የተቀበለውን ኃላፊነት እስኪወጣ
ከፀሐይ መውጫ ወደ ፀሐይ መግቢያ በረድፍ ጎጆ ቤት የሚሰራ ሲሆን በእድሜ በጣም አነስተኛው በፀሐይ መውጫ በኩል ይሆንና እንደ ዕድሜው ደረጃ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ይደረደሩና ከመሪው ትውልድ በእድሜ ከፍተኛው በፀሐይ መግቢያው ያለው ጎጆ ይገባል።
ይህም ወጣቱ ለማህበረሰቡ ለረጅም ጊዜ ማገልገል የመቻሉን ተስፋና ሃላፊነቱን የመግለጫ ዘዴ ሲሆን ሽማግሌም
የህይወት ጮራው እስክትጠልቅበት ድረስ ማህበረሰቡን ባለው አቅም
አገልግሉ ማለፍ እንዳለበትና ፊትና ኋላ ሆኖ ማለፍ የማይቀር የማይፈሩት የተፈጥሮ ክስተት መሆኑን እየተረዳ ከሞቱ በፊት ቀና
ተግባራትን የመፈፀሙን አርአያነት የሚያሳይ ነው።
ስለዚህ የእድሜ ባለፀጋው የበኩሉን እየፈፀመ ሲሞት ሌላው እየተሸጋሸገ የዚያ ትውልድ የገዥነት ዘመን ሲደርስ አዲስ ምርጫ
ይደረጋል: ያኔ አሮጌው እሳት ይጠፋል። አዲስ እሳት ለማህበረሰቡ
ይለኮሳል... አዲሱ ትውልድም የራሱን ትውልድ መሪዎች መርጦ
ማህበረሰቡን ያገለግላል።

👍34
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-18
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
//
አቢዬት ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እቤቱን የድግስ ቤት አስመስሎትል።ያልተገዛ መጠጥና ያልተሰናዳ የምግብ አይነት የለም።ይሄ ሁሉ ስርጉድ ዶ/ር ሰጲራን ለመቀበል ነው።አዎ ዛሬ ማታ ከሼክ ጠኸ ሰዎች እጅ ይረከባታል።በህይወቱ በዚህ መጠን ሰው ናፍቆት አያውቅም፡፡ ከፍቅረኛው ጋር ያለው ቀጠሮ እስኪደርስ አላስችል እንዳለው አዲስ አፍቃሪ አስሬ ሞባይሉን እያወጣ ሰዓቱን ያያል።ካሳ ከ10 ሰዓት በፊት የተለቀቀው ።እንደዛ የሆነበት ምክንያት የአቶ ሙሉን የመጨረሻና ወሳኝ ውሳኔ እንዲቀርፅ ከሼክ ጠሀ ጋር በተደረገ ስምምነት ነው።አብዬት ካሳን ሲረከብ አብሮ ሀያ ሚሊዬን ብር ተቀብሎ ለአቶ ሙሉ ቤተሠብ ሚስጥሩ በተጠበቀ ሁኔታ አስረክቦ አቶ ሙሉ እንድያረጋግጥ ከባለቤቱ ጋር በስልክ አገናኝቶት ነበር።
በወቅቱ የባለቤቱ ስሜት ቅስም ሰባሪ ነበር
"ሙሉ አሁን ለእኛ ገንዘብ ምን ያረግልናል ...የሀገር ሁሉ ብር ብትልክልን እኮ ከደረሰብን ውርደት አያወጣንም...ሙሉ ስለአንተ ከሰማሁ በኃላ ቤተክርስቲያን ሄጄ አላውቅም ፡፡ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? እግዜር ፊት መቅረብ አፈርኩ...ስለባሌ ቢጠይቀኝ ምን ብዬ መልስለታለሁ...?እኚንና መሠል ስሜት የሚያደፈርሱ ንግግሮችን ከማያባራ እንባ አጅባ ተናገረች፡፡
ከዛ ብኃላ አቶ ሙሉ በስምምነታቸው መሠረት እራሱ የሠራውን...የኘሮፌሰሩን..እና የባለስልጣኖችን... እያንዳንድ የፈፀሙትን የወንጀል አይነትና ያገኙትን ብር በመዘርዘር እና ለእያንዳንድም ያለውን ማስረጃ በማቅረብ ተቀረፀ...ከአብዬት ጋር በገባው ውል መሠረት የሼኪውንና የዶዬን ስም አላነሳም።ግን የአቶ ሙሉን የቪዲዬ ኑዛዜና መረጃ ካየ ብኃላ ፓሊስ ምርመራ መጀመሩና ወደእነዶዬ መቅረብ ስለማይቀር..ከአሁኑ ከውስጣቸው ሁለቱ እራሳቸውን ለፓሊስ አሳልፈው በመስጠት በፕሮፌሰሩ የሚታዘዙትን ወንጀሎች ሁሉ እነሱ ብቻ እንደፈፀሙ እንዲናዘዙ ተመቻችቶል።ያው ልጆቹ የእውነትም በእያንዳንድ ወንጀል ስለነበሩበት የሚሰጡት ቃል ከአቶ ሙሉ ቪዲዬ ጋር እንደማይጣረዝ ታምኖል....ከዛ ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን ብኃላ ዶክተር ሰጲራ ከፕሮፌሰሩ እጅ እንዳመለጠች ተደርጎ ከጠበቃዋ ጋር ሆና እጆን ትሰጣለች...በተቻለ መጠን መረጃዎች ሁሉ የእሷን ነፃ መሆን ሲለሚረጋገጥ እስር ቤት ሳታድር በዋስ እንድትለቀቅ የተቻለውን ለማድረግ ውሳኔ ላይ ደርሷ ስለዝርዝር ጉዳዩ ከህግ ሰዎች ጋር ከአሁኑ እየተነጋገሩበት ነው።
አብዬት ከካሳ ጋር ዶክተር ሰጲራን ለመቀበል የተቀጠሩበት ቦታ ደርሰው መኪናቸው አቁመው ገቢና ውስጥ ቁጭ ብለው እስኪያመጡላቸው እየጠበቁ ነው።
አቢዬተት"ግን አሞት ነበር ብለኸኝ ነበር አይደል?"በሰላም አላገኛት ይሆን እንዴ የሚል ጥርጣሬ ውስጡን ስላመሠው ካሳን ጠየቀው።
"ካሳ "አይ አሞታል አላልኩህም ግን ፌንት በልታ ነበር "
"ሰው ሳይታመም ፌንት ይበላል እንዴ"
"አዎ በደስታም ሊያረገው ይችላል"
"ግን ሀኪም አላያትም?"
"አንድ ሀኪም መጥቶ አይቶት ሆስፒታል ሄዳ ተጨማሪ ምርመራ ታድርግ ብሎ ኪኒና ሰጥቷት ሄደ...ግን አሁን ስለእሱ እርሳና አሁን ስትመጣ ቀድሞ አቅፎ የሚስማት ማን ነው?"
"ምን ማለት ነው ከማና ከማ?››
"ከእኔና ከአንተ ነዋ?"
"አንተ ደግሞ ለምንድነው የምታቅፋት"
"እንደ አንተ ሰለማፈቅራት ነዋ"
"አይ አንተ ከስሯ የመጣሀው ዛሬ ነው.. ከእኔ ግን ከ5 አስጨናቂና እረፍት የለሽ ቀናት ብኃላ ነው የማገኛት እና የማቅፍትም የምስማትም እኔው ነኝ"አለው ፡፡ምንም እንኳን ንግግሩ ለካሳ ግራ አጋቢ ንግግር የቀልድ መልስ መስጠት ይምሰል እንጂ በእውነትም ማድረግ የሚፈልገውን ትክክለኛ ስሜቱን ነው ያንፀባረቀው
"ንግግሩን እንዳገባደደ አንድ ማርቼዲስ መኪና እየከነፈች መጣችና አጠገባቸው ቆመች ።አብዬት ሽጉጡን በቀኝ እጅ ያዘና ፈጠን ብሎ ገቢናውን ለቆ ወረደ...የመኪናዋ ገቢና ተከፈተ ዳክተሯን አወረዶትና መኪናዋ ተስፈንጥራ ከአካባቢው ተሠወረች ።አብዬት ሽጉጡን ጎኑ ሻጠና ተንደርድሮ ወደእሷ ሮጠ..እንደደረሰ ሙሉ በሙሉ እጆቹን በወገቦ ዙሪያ ጠመጠመና በአየር ላይ አንስቶ አሽከረከራት።እንደተሸከማት ወደመኪናው ይዛት ሄደ..
"አረ አውርደኝ እከብድሀለው"
"አረ በጣም ቀላል ነሽ...ምግብ አይሰጡሽም ነበር እንዴ?"
"አይ ምግብ ነው ሚያወፍረው ብለህ ነው"
መኪናው ጋር ሲደርስ አወረዳት..ካሳ ገቢና እንደተቀመጠ ነው...አልተንቀሳቀሰም።ስታየው ደነገጠች"
"እንዴ ካሳ መጥተሀል እንዴ"
"መምጣት እንኳን መጥቼ ነበር…ይሄ አውሬ እንዳትወርድ..እንዳትስማት ብሎ አስፈራራኝ እንጂ"አለ በቅሬታ
‹‹ማሙሽ ገቢናውን ልቀቅላትና ከኃላ ግባ አለው ››አብዬት ጣልቃ ገብቶ አዘዘው።
አረ ተወው እኃላ ሆናለው ብላ ከፍታ ገባች..አቢዬትም ገባና መኪናዋን አንቀሳቀሰ
"አብዬት በእስፓኪዬ ወደኃላ አየተመለከታት ነው።ከስታለች..መክሳት ብቻ ሳይሆን ገርጥታለች አይኖቾ ጉድጉድ ከማለታቸው በላይ ቁዝዝ ብለዋል...ለቀናት የረባ እንቅልፍ እንዳልተኛች ያስታውቃል...የጤናዋም ሁኔታ አሳስቦታል።
"እንዴ ወደቤት አይደለ እንዴ የምንሄደው ?ነው ወይስ አድራሻ ቀየራችሁ?"ስትል ጠየቀች።የዚህ ጥያቄ መነሻ አብዬት መኪናዋን እየነዳበት ያለው አቅጣጫ ከቤታቸው አቅጣጫ ጋር ስላልገጠመላት ነው።
"አይ እዛው ነን...እግረ መንገዳችንን እዚህ ሰፈር ጉዳይ ቢጤ ስላለችኝ ነው።አያቆየንም።"
"ጉዳይ ካለህ ታዲያ እኛ ምን አገባን ..አውርደን እና በታክሲ እንሄዳለን"አለ ካሳ ተበሳጭቶ
ዶ/ሯ ደነገጠችና "አረ ችግር የለም..እቤትስ ሄደን ምን እንሰራለን ..እንደውም በዚህ ምሽት ነፍሻማ አየር ከተማውን መዞር አስደሳች ነው...በዛ ላይ አንድ ክፍል ውስጥ ታፍኜ መሠንበቴን አትርሳ"
"ላንቺው ብዬ ነው"
"ለእሷ ብለህ ምን...?"
"ይሄንን ያንተን አስቀያሚ ፊት ለረጂም ሰዓት እያየች እንዳትፈራ ብዬ ነው...ይሄንን ፊት ይዘህ ስታፈቅራት ግን ትንሽ አታሳዝንህም?"
በካሳ ሰቅጣጭ ንግግር ዶክተሯ የምትገባበት ጠፋት.. የአብዬትን ንዴት ለማየት አይኖቾን በፈራ ተባ ወደእሱ ስትልካቸውእሱ በካሳ ንግግር እየሳቀ ነው..መኪናውን አቆመ ፡፡
"ሆስፒታል ደግሞ ምን እንሰራለን?"አሁንን በንጭንጭ ቃና ጥያቄውን የሰነዘረው ካሳ ነው
"አስቀያሚ ፊቴን እንዲያስተካክሉልኝ"
ከእግሩ ስር የነበረ ጥቁር ፔስታል አነሳና ለዶክተር ወደኃላ አቀበላት
"ምንድነው...?››
‹‹ወደ ውስጥ አብረን ስለምንገባ እራስሺን ቀይሪ››
ፔስታሉን ውስጥ ያሉ ቁሳቁሶችን ጎኗ ካለ ወንበር ላይ ዘረገፈችና በየተራ አየቻቸው።
"አንተ እነዚ ዕቃዎች አሁንም አሉ?"
"ከዚህ መከራ ሙሉ በሙሉ እስክንወጣ ያስፈልጉናል ብዬ አስቀምጬቸው ነበር ይሄው ዛሬ አስፈለጉን..››እቃዎቹን
ስታይ ከገዳዬቾ ሽሽት እንዴት እሱ እጅ እንደገባቸ እነዚህን እራስን መቀየሪያ የገዛላት ጊዜ ተሠምቶት የነበረው ስሜት ሁሉም ፊቷ ላይ ድቅን አለ..ፀጉሩን አጠለቀች...መነፅሯን ሰካች...በአንገቷ ዙሪያ ሻርፗን ጠመጠመችና አጠናቀቀች
አቢዬትም ከገቢናውን ለቆ ወረደና የዶ/ሯን በራፍ ከፈተ
‹‹ውረጂ ዶክተር››
ወረደች..
ካሳ "እኔም ልምጣ እንዴ..?"
"ቦሮጫህን ቀደው እንዲያስወግድልህ ከፈለክ ና"
"አይ እንደውም ትቼዋለው.. የመድሀኒት ሽታ በጣም ነው የሚያስጠላኝ።
ትተውት ጎን ለጎን ሆነው ወደውስጥ መጓዝ ጀመሩ
"ለምንድነው ግን ወደእዚህ የመጣነው?"ጠየቀችው
"ታመሽና እራስሽን ስተሽ እንደነበር ሰምቼያለው ምክንያቱን ማወቅ አለብን።››
"እና ነገ ተነገ ወዲያ አይደርስም ነበር?"

👍22❤3🥰3😁1
"አይ ...የጤና ጉዳይ ለነገ አይባልም...አሁኑኑ መመርመር አለብሽ"
"ታውቃለህ አይደል ...በጣም ምርጥ ሰው ነህ"
"መስሎሽ ነው...ምርጥ መሆን ፈልጌ አይምሰልሽ ..ፈርዶብኝ እንጂ"
‹‹ማለት?›› አለችው የሚለው ስላልገባት
"አይ ምንም እንዲሁ ነው"
በዚህ ጊዜ ካርድ የምትቆርጠዋ ልጅ ፊት ለፋት ደርሰው ነበረ
"ካርድ ፈልገን ነበር"
"ላንተነው ለእሷ"
"ለእሷ"
"እስኪሪፕቶዋን ካርድ ላይ ቀስራ ለመፃፍ እየተዘጋጀች ‹‹ስም ስትል ጠየቀች "
ዶክተሯ ስሟን ለመናገር አፎን ስትከፍት
"እፅብ."ብሎ ነገራት አብዬት
ዶክተሯ በገረሜታ ቀና ብላ አየችው
"እፅብ ማ.."
"እፅብ አብዬት"ካርዳቸውን ተቀብለው እየተስሳሳቁ ወደተዘጋጀው ተራ ወደመጠበቂያ ወንበር ሄደው ጎን ለጎን ተቀመጡ
"እፅብ ማነች አለቺው?"
"እፅብ ልጄ"
"እንዴ ልጅ አለህ እንዴ ?"
"አይ ለአሁኑ የለኝም...ወደፊት ከኖረኝ ብዬ ነው ቀድሜ ስም ያወጣሁላት"
በዚህ ጊዜ ስሞ ተጠራና ለምርመራ ገባች..አጠቃላይ ምርመራው 40 ደቂቃ ፈጀ ጨርሳ ስትወጣ ግን ...ጎብጣ ነበር...እንባዋ ከቁጥጥሯ ወጭ ይረግፋል...አብዬት ሁኔታዋን ሲያይ በጣም ደነገጠ..እንደምንም ደግፎ መኪናው ጋር ወሰደና ወደ ውስጥ አስገባት...ተከትሎት ገባና ከጎኖ ቁጭ አለ፡፡
"እዛ ከጎኖ የተለጠፍከው መኪናውን ማን እንዲነዳልህ ነው?"አለው ካሳ
‹‹ችላ አለውና"አረ ባክሽ ዶክተር ምንድነው የተፈጠረው?"
ደረቱ ላይ ተለጥፋ መንሰቅሰቅ ጀመረች።ካሳ እንዴ አንተ ምን አድርገሀት"እያለ ገቢናውን ለቆ ወረደና እነሱ ወዳሉበት የኃላ ወንበር ገባ ።መሀከል አደረጎት
‹‹ዶክተር ምን አይነት በሽታ ቢሉሽ ነው እንዲህ በአንዴ ማቅ የለበሽው...?ይሄውልሽ አንቺ በዚህ አስራአምስት ቀን ውስጥ ከስንት ወጥመድ ከስንት ሞት አምልጠሻል ...እና ምን አዲስ ነገር መጣ ? እነዛ ጭራቆችን ያሸነፍሽ በሽታ ማሸነፍ ያቅትሻል?››
"ደግሞ ከአሁን ወዲያ እኛም ከጎንሽ ነን ...መቼም ቢሆን መቼ ብቻሽን አንተውሽም..."
"አዎ አንተውሽም ..እንዲ እንደአሁኑ በግራና በቀኝ ደግፈን አስከመጨረሻው እንንከባከብሻለን"ካሳ ቃል ገባ፡፡
"ከጎኔ እንደሆናችሁ አውቃለው..ግን ያልገባችሁ ነገር አለ"
"እኮ እንዲገባን ንገሪና እየለመንሽ እኮ ነው?"አብዬት ነው በጭንቀት የጠየቃት
"አርግዤለሁ"
"አርግዤለሁ ማለት ..?ማርገዝ ምንድነው..?ከእኔ ጋር አድርገን ነበር እንዴ..?.ነው ከእኔ ተደብቃችሁ አደረጋችው...ካሳ አብዬት ላይ አፈጠጠበት
‹አብዬት ተናደደ‹‹እስቲ አሁን እንኳን ቢሆን ዝም በል …ዶ/ር አልገባኝም›
‹እኔም አልገባኝም..የ7 ሰማንት እርጉዝ ነኝ…የዛን አውሬ ልጅ በሆዴ ተሸክሜለሁ››
‹‹የፈጣሪ ያለህ››አለ አብዬት ለ30 ደቂቃ ሁሉም እርስ በርስ እንደተጣበቁ በመቀመጥ ከመተከዝና ከመብሰልሰል ውጭ የተነጋገሩት ነገር አልነበረም፡፡

👍29❤4😁1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ቀኑ ቅዳሜ ነው። ሴቬሊያ ከተማ ላይ አንዣቦ የከረመው ዳመና ተበታትኖ ሰማያዊው ሰማይ በፀሐይ ብርሃን ተጥለቅልቆ ኗሪው በደስታ ሲንቀሳቀስ ይታያል።
ሶራ ከመኝው የተነሳው ዘግየት ብሎ ሲሆን ከመኝታው ተነስቶ ሳሎኑ ሲገባ አብረውት የሚኖሩት ሁለቱ የክፍል ጓደኞቹ
ሞዛምቢካዊው ኢናሲዬ እና ሴኔጋላው ዲያንካ ሲከራከሩ አገኛቸው:
“...አየህ የኛ የአፍሪካውያን ችግር በእለት ችግሮቻችን ላይ ካልሆነ በህልማችን በሐሳባችን... ላይ በትዕግስት መወያየት
መከራከር አንችልም: በግልፍተኝነት ስለ ዛሬ እናወራለን ዛሬ በምንፈፅመው እናዝናለን ወይንም እንረካለን።
ዛሬን ከትናንትና ከነገ ጋር ማነፃፀር ስለማንችል መቻቻሉም ያቅተናል: እና እኛ አፍሪውያን ከጊዜ የቁም እስር እራሳችንን ነፃ
አድርገን ጊዜን መጠቀም ስንጀምር! ሽንፈትና ድልን ልዩነቱን ስናውቅ በቅድሚያ ችግሮቻችንን እንፈታለን…” አለ ሞዛምቢካዊው
ኢናሲዬ:
“…በሃሣብህ እኮ እስማማለሁ፡ ችግሩ ግን እንደ ቡችላ ያለው አይናችንን ለመክፈት ገና ስናስብ የሰለጠኑት ህዝቦች ባለፉት ጊዜያት ከተጠቀሙበት መሳሪያ በተሻለና በረከሰ የረቀቀ መረብ እየጠለፉ ይጥሉናል: ለዚህ መፍትሄው ምን
ይሁን ነው? እኛ ፊደል እንዴት እንቁጠር ስንል አንዱ እርስ በራሳችን እንማማር ሌላው የሰለጠኑት ህዝቦች እንዲያስተምሩን
እንለምን... ሲል ጊዜያት ከነፉ፤ የጥቁር ህዝብ ህልም እንደ
ኪሊማንጃሮ ተራራ ቢከመር ጠብታ ተግባር ካልወጣው! አንዱ ሌላውን ወንድሙን ገሉ ማቅራራቱንና መፎከሩን ካላቆምንና ራሳችንን መግዛት ካቃተን ጥሩ ተገዥ መሆን ይሻለናል” ብሎ
የምፀት ሳቁን ሳቀ ሁለቱም ተሳሳቁ፡
“ጥሩ! ማን በማን ላይ እንደሳቀ ዳኝነቱን ወደፊት
እስከገልፅ አንዴ ይቅርታ ይደረግልኝ..."
“ሶራ! ሁለቱም እንደተመካከሩ ሀሉ በአድናቆት ዞረው
ጠሩትና
ዛሬ ምነው ምሽግን አለቅም ብለህ ዋልህ? ያች ኢትዬ
ስፔናዊት የምትሰራው የቤት ስራም ሰጥታህ
ነበር መሰል ሞዛምቢካዊው ኢናሊዬ የጓደኛውን ጉልበት መታ አድርጎ ቤቱን
ለሁለት በሣቅ አነቃነቁት።
ከባድ የቤት ሥራ ነበር የሰጠችኝ፡ ጥያቄዋን ሽ ጊዜ አነበብኩት በቃሌ አነበብኩት! መልሱ ግን ጠፋኝ። ጥያቄዋን
ካለእሷ ሊመልሰው የሚችል የለም:"
“ስለዚህ መልሱን ከመምህርት ኢትዮ ስፔናዊት ለማግኘት
ልትሄድ ነዋ!” ነዋ!
ቶሉ መሄድ! የጠፋኝን ቶሉ ማወቅ ከዚያ ጎበዝ
ደቀ መዝሙሯ መሆን እፈልጋለሁ።” የሁለቱንም ትከሻ መታ መ+ አድርጎ። ወደ ውስጥ ገብቶ ለባብሶ ወጣና፡-
“አጭርና ያልተንዛዛ አስተያየት አላማረብኝም አላቸዎሸ በየተራ እያያቸው።
“መልሱን ካለ አንድ ሰው አይመልሰውም" ሲል ዲያንካ
“እሷም መምህርት ኢትዮ ስፔናዊት ብቻ ናት..." አለ ኢናልዬ
“ትክክል!'' ብሎ የኢናሲዬን ትከሻ መታ መታ አድርጎ በሩን ከፍቶ ሲወጣ ሳቃቸው ከኋላው ተከተለው
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሶራና ኮንችት ከተዋወቁ በኋላ ኮንችት ቤት ማድሪድ
በሚገኘው ፒካሶ ሆቴል... ደጋግመው ተገናኝተዋል። ኮንችት በሶራ ግልፅነት በጎደለው ይሉኝታ በተበተበው ባህሪው ብዙ ጊዜ ትበሽቃለች።
ሶራ መብላት ትፈልጋለህ?" ስትለው
“አንችስ?” ሲላት በብስጭት
"እፈልጋለሁ! ወይንም አልፈልግም። ስለእኔ እኔ ስለአንተ ደግሞ አንተ መመለስ በቃ። የአንተ መፈለግ አለመፈለግ ከእኔ ጋር ምን አገናኘው" ትለዋለች
“የዛሬ ግብዣ የኔ ነው"
“ጥሩ ስለግብዣ ሃሳብህ አመሰግንሃለሁ። የት ነው የምትጋብዘኝ?
“የት ልጋብዝሽ?”
“ኦ! - አምላኬ!” በንዴት ትጦፍና፦
“ሰውን ልትጋብዝ ስትፈልግ በቅድሚያ የት ምን
እንደምትጋብዘው አስብ እሽ ፊቷ በንዴት እንደቀላ ትነግረዋለች
“ምነው ዝም አልሽ?
“ለምን ጠየቅከኝ?
“ስለማትጫወቺ ስለማትስቂ...”
"ሰው ቤት ከመሄድህ በፊት ልትገናኙ መቻል አለመቻላችሁን ደውለህ ፈቃድ ጠይቅ ! እኛ ሰዎች ለስራ ለጨዋታ
ለእረፍት... የምንመድበው ጊዜ አለ:: ሰዎችን በፕርግራማቸው
እንዳይጠቀሙ እንቅፋት መሆን ትልቅ ሃጢያት ነው: ገባህ!” ትለዋለች።
“የያዝሽውን እቃ ልያዝልሽ?
“ለምን?
“ይከብድሻል…”
“ፖልፋቮር /ይቅርታ/ እኔ ጡጦ የምታጠባው ህፃን ልጅህ አይደለሁም የሚከብደኝን መጀመሪያውንም አልይዝም።እሺ
በንዴት ትንጨረጨርበታለች ሶራ ባህሪዋ ሙልጭልጭ ይልበታል ሲያዝንላት ሲንከባከባት ሲሞክርና እንዲቀራረቡ ጥረት ሲያደርግ? አባባሉን በተቃራኒ ተረድታ በግሳፄ የህሊና ድዱን በርግጫ
ታወልቀዋለች:
እሱ ግን ይችላታል: ሆዱ እየተቀየመ አንደበቱ ግን
ያልፋታል።
“ዲስኮ ዳንስ ቤት ብዙ መቆየት አልወድም"
“ሶራ! ከኔ ጋር ግን'ኮ አብረህ…"
“ላስከፋሽ ስላልፈለግሁ"
“እብድ ነህ! የማትፈልገውን ለኔ ብለህ የምታደርግ?”
“ብቻሽን ትቼሽ መሄድ ስላልፈለግሁ"
“በቃህ አንተ ኖርህ አልኖር ለኔ ለውጥ የለውም 7
ገባህ! መዝናናት ስፈልግ ዘበኛ አላስከትልም: ማንንም ካለፍላጎቱ እንደ
ከዘራ ቆልምሜ የኔ ምርኩዝ ማድረግ አልሻም.." ታፈጥበታለች።
አብሯት ለመሆን እንደሚጓጓው ሁሉ ከሷ መለየቱንም ይፈልገዋል: ልዩነታቸው ብዙ ነው።
ኮንችት ባህሪው ግልፅ
ነው ሣቋን አንደ ጥሩ ሙዚቃ በስሜት ይደንስበታል: ችግሩ ድንገት እሳት ወዲያው ውሃ
ትሆንበታለች:: እሳት ስትሆን ሊሸሻት ይፈልጋል! ውሃ ስትሆን ደግሞ እንደ ፀበል በጨዋታዋ ይጠመቃል!
ሶራ ሜዳ ይሁን ገደል ስሜቱ በደመ ነፍሱ ሲጋልብም እሷ
ለሁሉም ነገር ምክንያት ትፈልጋለች: እየተሞላቀቀች
ጭኖችዋን ፓንቷን.. ስታሳየውና ጉሮሮውን ስታስጮህበት ስሜቱን
ስታስነጥስበት ትቆይና መላውን ሳትለው ድንገት
“መተኛት እፈልጋለሁ" ትለዋለች።
ትንሽ አንጫወትም?"
...የሰው ፍላጎት ሊገባህ ይገባል እሽ?" ቀልቡን ገፋበት መኝታ ቤቷ ትገባለች። እሱም ወጥቶ ይሄዳል። ቤቱ ሲሄድ ግን
ህሊናው እረፍት ሲነሳው ሰውነቱ እንደ እሳት ሲቀጣጠልበት
መታጠቢያ ቤት ይገባና ቀዝቃዛ ሻወር ገላው ላይ ያፈሳል፡ ለአያቷ
አገር ለኢትዮጵያ ያላት ናፍቆት ግልፅነቷ ሳቋ… ተክለ ቁመናዋ
እያወዛወዘው ሲያንጨዋልለው ፍላጎቱ ለእሷ ያለው ቀረቤታ
ከጓደኝነት ያለፈ ይሆንበታል።
ኮንችት ደጋግማ
የነገረችው ስሜትህንና ፍላጎትህን አትደብቅ ነው። ስለዚህ እየዋለ ባደረ ቁጥር ናፍቆቱ ጤና ሲነሳው
ስሜቱን ሊገልፅላት አሰበ: ድፍረቱና አጋጣሚው ጠፍቶ ለቀናት ተሰቃዩ:: አንድ ቀን ግን ደፈረ:
“ኮንችት?”
“አቤት" ያ እንደ ንስር አይን ተልቆ የሚበረበረው አይኗ
ከመናገሩ በፊት እየበሳሳው ውስጠ ሚስጥሩን አየበት።
“አፈቅርሻለሁ አላት ባጭሩ። ኮንችት ግን ይህን ስሜቱንና አባባሉን ቀደም ብላ እንደተረዳች ሀሉ፡
“ለምን አፈቀርኸኝ? በአባባሉ ሳትደነቅ ጠየቀችው
ተቁነጠነጠ! ግልጽ ሁን ብላ ወትውታ ግልፅ ሲሆን ደግሞ ዓለምን ያስጨነቀ ጥያቄ “ለምን?" እያለች በማስቸገሯ ተማረረባት።
ለምን አፈቀርኝ? ደግማ ጠየቀችው
“አስተሳሰብሽ ደስ ይለኛል” አንገቱ ላይ እንደቆሙበት ውሻ አይኑ እየተቁለጨለጨ መለሰላት።
“አስተሳሰቤን ገና መች ተረዳኸው። እኔ የማስበው ለአንተ እንግዳ ነው: የአንተ ደግሞ ለእኔ እንዲሁ አይገባኝም። ታዲያ
ሳንግባባ እንዴት አስተሳሰቤን አውቀህ አፈቀርኸኝ:"
“የምልሽ ፀባይሽም ደስ ይለኛል"
“ፀባዬ ምን አይነት ነው?"
“ግልፅ
“ፀባዬን እንዳልወደድኸው ግን ብዙ ምልክቶች አይቸብሃለሁ
"ቁመናሽ ደስ ይለኛል..."
“አንድን ሰው በማፍቀርና በመፈለግ መካከል ያለውን ልይነት ግን ታውቃለህ?"

👍27👎1
“እሱን'ኳ በሚገባ አውቃለሁ።"
“አይመስለኝም፤ ቁመናዬን ወደኸዋል። ባህሪዬንና
አስተሳሰቤን ግን ለአንተ ብዙው እንግዳ ነው እና ቢያንስ አትናፍቀውም::
አንተ ከአገርህ ከለመድኸው ባህል ርቀህ ስለመጣህ ብቸኝነትን ይሰማሃል: በአጋጣሚ ደግሞ ብቸኝነትህን የሚቀንስልህ
የሚጋራህና ደስታ የሚፈጥርልህ ሰው ስትፈልግ እኔን አገኘህ። ደስ
አለህ እና እኔን ትፈልገኛለህ እንጂ አታፈቅረኝም: ፍቅር የሚገዛው በህሊና ነው። ወሲባዊ የስሜት ፍላጎት ቢሆን እንኳን በስሜት
ቅፅበታዊ ደስታን ለማግኘት እስከሆነ ድረስ የፍቅር ምልክት ሊሆን
አይችልም::
"...በህይወቴ አፈቀርሁሽ ከመባል ሌላ እሚያስደስተኝ ነገር የሚኖር አይመስለኝም: ጓደኞቼ አንተን አፈቅርሻለሁ ስትለኝ ቢሰሙ ምን አይነት የመንፈስ ቅናት ውስጥ ይዘፈቁ ይሆን!?
እኔ ግን አባባልህን ለቀበለው አልችልም: በባህሪ አልተግባባን ስሜት ፍላጎታችንን አልተፈታተሽን ሚስጥራችንን አልተወያየን... ታዲያ ፍቅር እንደ ህብሰተ- መና ከየት ወረደ?
“አንዱ የሌላውን እገዛ አይዞህ ባይነት ለማግኘት ሲባል የሚደረግ ቀረቤታ ሁሉ ካለአግባቡ በሜዳ የፍቅር ዘውድ ቢጭን
ንጉሥነቱን ማን አምኖ ሊቀበል ይችላል!
“ሶራ አንተ እኔን ስለማፈቅርህ እውን እርግጠኛ ነህ?
“በእርግጥ አንተ ደግ ሩህሩና አሳቢዬ ነህ እንደ
አባቴ የምፈልገውን የልጅነት ፍቅር በመጠኑ ሰጥቶኛል: ያ የአባትና ልጅ ቀረቤታ ግን አልፏል። አሁን የአባቴን ተመሳሳይ ፍቅር
የሚለግሰኝን እጄን ዘርግቼ አልቀበለውም። እንደ እንቁላል ሽፍን ፍቅር አልሻም: አፍርጬ ማየት መቅመስ ማጣጣም እፈልጋለሁ።
“ስለዚህ ከተገናኘን ወዲህ ለአንተ መጠነኛ የሆነ ስሜት አለኝ። ፍቅር ግን አይደለም: አንተን ማጣት ለኔ ትልቅ ውድቀት
ቢሆንም በፍቅር ያልተመሰረተ ግንኙነት ፈጥሬ ልሸሽህ በዚያ ሳቢያ
ልጎዳህና ልጨክንብህ ስለማልፈልግ ስሜቴን እያጠናሁት ነው።
እስከዚያው ግን ግንኙነታችን እንዲለወጥ አልፈልግም:
“ነገ ማታ እደውልልሃለሁ በመጭው ሦስት ቀናት
አልኖርም:: ጓደኛዬን ለመጠየቅና እግረ መንገዴን ለመሰናበት ባርሴሉና እሄዳለሁ... መልካም ጊዜ ለማሳለፍ ሞክር አሁን
መተኛት እፈልጋለሁ ኦርቫ" ብላው ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች:....

ምዕራፍ-19
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
‹‹ስጋዬ ነው ነፍሴን በውስጡ አቅፎ የሚዞረው ወይስ ነፍሴ ነች ስጋዬን አዝላ ምትዞረው…?ነፍሴ ባትኖር ስጋዬ እራሱን መሸከም ይችላል?፡፡አይ በመሬት ስበት በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ተሸንፎ ዝልፍልፍ በሎ ከመሬት እንደሚዘረር ጥርጣሬ የለኝም፡፡ አሁን እኔ 56 ኪሎ ነኝ ሰላሳ ኪሎ የሚመዝን እቃ ትከሻዬ ላይ ቢጭኑ አጎብድጄ ልወድቅ እደርሳለሁ፡፡ግን ደግሞ አስቡት እግሬ ከቁርጭምጭሚቴ በታች ስንት ኪሎ ይሆናል? ሰባት ኪሎ ይሆናል ብዬ ባስብ ከላይ ያለውን 50 ኪሎ ሲያረፍበት እንዴት ቅንጥስ ብሎ አልወደቀም…?እንዴት ከበላይ ያለውን ቅጥልጥል ስጋ መሸከም ብቻ ሳይሆን ያለምንም ጫናና መዳከም ይዞ ያለማቋረጥ በኪሎ ሜትሮች ርዝመት ወደተራራው ጫፍ ይዞት ወጥቶ መልሶ ወደሸለቆው ይዞት የሚወርደው?
ለካ በጣም የሚፈልጉት ነገርም ቢሆን በተገቢው ጊዜ ቦታና ሁኔታ በእጅ ካልገባ ደስታው ሙሉ አይሆንም።ይሄን ልጅ ትፈልገዋለች።በጣም ትፈልገው ነበር።ጋብቻን 70 ፐርሰንት ትፈልግ የነበረው እንደቢጤዎቹ ዘመናዊ ሴቶች ለፍቅር ሳይሆን ለልጆች ነበር፡፡ጋብቻም ብቻ ሳይሆን ሀብታም መሆን የምፈልገውና ለዛም ቀንና ሌት ስትባክን ኖራ ያሳካችው ሳትሳቀቅ እስከቻለችው በቂ ልጅ መውለድ እንድትችል ነው።ከፕሮፌሰሩም ጋር ከጋብቻ በፊት ተደጋጋሚ ወሲብ የፈፀመችው ስሜቷን መቆጣጠር አቅቶቷት ወይም እሱን አቅሏን እስክትስት ስለምታፈቅረው ሳይሆን በምትወልዳቸው የልጆች ቁጥር ላይ በጊዜ ካልጀመረች ችግር ያመጣብኛል ብላ ስለሰጋች ነበር።ይሄ ችግር ከመከሰቱ በፊት አረገዝኩ አላረገዝኩ ብላ ብዙ ጊዜ ቼክ ታደርግ ነበር..በዛም ለብዙ ቀናት ተሳቃለች ...ብዙ ቀንም አልቅሳለች ..ተጠራጥራም የመሀንነት ምርመራ ሁሉ አድርጋ ነበር ። አሁን ይህ ችግር ከተፈጠረ በኃላ ግን ስለእንደዚህ አይነት ነገር ማሰብ ቅንጦት ከመሆኑም በላይ ጊዜ ማባከን ስለሆነ አድርጋውም አስባውም አታውቅም፡፡ግን ማርገዞን አሁን ሰማች?
‹‹ ሊያጠፋኝ ከሚያሳድደኝ ሰው እና ልገድለው ቃታውን ብቻ መሳብ ከሚቀረኝ ሰው ልጅ አርግዤያለሁ ።ይሄ ፅንስ የወላጆቹን ስራ እያየ ምን እያለ ይሆን።?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡
ይህንን እያሰበች ያለችው ከሆስፒታል ወደቤት እየሄደች መንገድ ላይ ሆና ነው፡፡አሁን በዚህ ወቅት ከአደጋ መጠበቅና ከሞት የመትራፍ ፍላጎት አይደልም ያላት..እንደው በሆነ ተአምር ብን ብሎ የመጥፋት…ቢቻል በአስማት ቢሆንም የመሰወር …ወይ ደግማ አቧራ ሆኖ በመላው ምድር የመበትን ፍላጎት ነው ያላት፡፡.ልጅ በጣም ትፈልጋለች፡፡መውለድም ለረጅም ጊዜ ስታልመው የቆየችው ነገር ነው፡፡ሌላው ይቅር ከፕሮፈሰሩ ልጅ እንዲኖራት ስለት እስከመሳል ሁሉ ደርሳ ነበር…..ግን በዛ በምትለምንና በምትሳልበት ጊዜ ሳትፀንስ ለምን አሁን? ››ያ ነው እንቆቅልሽ የሆነባት፡፡፡
እቤት ደርሰው ስለነበረ አብዬት የመኪናውን ጡሩንባ ተጫነው.. ብዙም አላስጠበቋቸውም ..የውጪን በራፍ ከፈቱላቸው፡፡ገብቶ አቆመና …ተሎ ብሎ ከገቢና በመውረድ የእሷን በራፍ ከፈተላት፡፡እንዳለ የቤቱ ሰው እሷን ለመቀበል በረንዳውን ሞልተውታል፡፡የሰብለ ልጅ በእድሉ ድክ ድክ እያለ ከበረንዳ ሮጠና ተጠመጠመባት….ጎንበስ ብላ ጉንጮቹን እያገላበጠች ሳመችው….ሌሎቹም ከበረናዳው እየወረድ በደስታ ከበቧት…በመጠኑም ቢሆን የጨፈገጋት ስሜት እየበረደ ሲሄድ ተሰማት….የእሷ መጥፋት ይሄን ያህል ያስጨንቃቸዋል መፈታቶ ደግሞ ያስደስታቸዋል ብላ ግምት አልነበራም…እሷን ከፊት አስቀድመው ተከትለዋት ሳሎን ስትገባ ማመን አልቻለችም…በቃ አግብታ ወላጆቾ ቤት መልስ የተጠራች ነው የመሰላት..ሳሎኑ በተለያ ድሚ መብራቶችና ዶኮሬሽኖች ደምቆል፡፡ጠረጳዛው በምግብና በመጠጦች ተሞልቶል….ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ በትልቁ
ደ/ር በሰላም ወደቤትሽ ስለተመለሽ ደስ ብሎናል፡፡
እንወድሻለን፡፡ይላል…፡
ቆማ አነበበችና
‹‹በእውነት በጣም አመስጋናሁ… እኔም በጣም ነው የምወዳችሁ…››ሳግ ተናነቃት..ድሮም በቋፍ ነች ..ስቅስቅ ብላ አለቀሰች..በድሉና የእሷ ሰራተኛ ተከተለዋት በለቅሶ አገዞት...አብዬት አንገቱን አቀረቀረ..ሌሎቹ ትከሻዋን መታ መታ እያደረጉ ያፅናኗት ጀመሩ…ወደ መቀመጫዋ ይዘዋት ሄድና የእራት ፕሮግራሙ ተከናወነ ፣ከአብዬት ከካሳና ከዶክተሯ በስተቀር ሎሎቹ በደስታ ወደመጠጡ ተሸጋገሩ…
. ዶክተር ‹‹በጣም ስለደከማኝ ባርፍ ቅር ይላችኋል?››ስትል ሁሉንም በትህትና ፍቃድ ጠየቀች፡፡
‹ችግር የለም..አሁን ነፃ ነሽ ነገም ተነገ ወዲያም አብረን ነን.. ተነሽ ተኚ…››ፈቀዱላት፡፡
በዚህ ጊዜ ከሳ ለንቦጩን እንደጣለ ወደመኝታው ቀድሞ ተንቀሳቀ..ሆስፒታል ዝም ያለ እስከአሁን አንድ ነጠላ ቃል እንኳን አልተናገረም.እንደዛ በመሆኑ አብዬት አስደስቶታል ፡እራት ፕሮግራሙ ላይ የሆነ ነገር ዘባርቆ የልጆቹን ስሜት ልክ እንደነሱ ያደፈራርሰው ይሆን? በሚል ስጋት ሲሳቀቅ ነበር ያመሸው….ዶክተሯ ከኃላ ተከተለችው..፡፡
አብዬትም ‹‹እመጣለሁ ተጫወቱ ››አለና ዶ/ሯን ከኃላ ተከተላት፡፡መኝታ ክፍላቸው ከሚገኝበት አንደኛ ፎቅ ላይ እንደደረሱ ቆማ ጠበቀችውና‹‹አቢ አንድ ነገር ፈልጋለሁ ››አለችው፡፡
‹‹ምንድነው ?ጠይቂኝ ምን ላድርግልሽ?››ተንሰፈሰፈ
‹‹ላናጋረው ፈልጋለሁ››
‹‹ማንን..?ማለት መቼ?››
‹‹አሁን››
‹‹እርግጠኛ ነሽ?››
‹‹አዎ››
ዝም ብሏት ቀድሟት ተራመደ… ከኃላው ተከተለችው…መጫረሻ ከሚገኙት ክፍሎች መካከል አንድን ከፈተና ‹‹አብሬሽ እንድገባ ትፈልጊያለሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ግድ የለም ብቻዬን ብሆን ይሻለኛል፡፡››
‹‹በቃ እዚሁ ኮሪደር ላይ ነው ያለሁት ..ስትፈልጊኝ ጥሪኝ› አላትና የበራፉን መግቢያ ለቀቀላት፤ አልፋ ወደውስጥ ገባች፡፡
ፌት ለፊቷ የምታየው ሰው እሱ መሆኑን ማመን አልቻለችም…ከግድግዳ ጋር ተበይዶ በተያያዘ ግዙፍ ብረት ጋር እጆቹ በሰንሰለት ወዲህና ወዲያ ተሰትረው ተንጠልለዋል፡፡ እግሮቹ ከተቀመጠበት ወንበር ጋር በተመሳሳይ ሰለንሰለት ተጠፍንጎ ስለታሰረ መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ፊቱ በቦቅስና በጥፊዎች ብዛት ቆሳስሎና ተቦዳድሶ ሌላ መልክ ሰጥቶታል፡፡እላዬ ላይ የለበሰው ነጭ ሸሚዝ በደም ከመጨማለቁም በላይ ተቦተራርፎ ሲታይ ይቀፋል፡፡እሱ አንገቱን ድፍት አድርጎ ያንጎላጅጃል…፡.
ክፍል ውስጥ ያገኘችውን ባዶ ወንበር ወደእሱ አስጠጋችና በአንድ ሜትር እርቀት ላይ አስቀምጣ ተቀመጠችበት፡፡
‹እሺ….ፕሮፌሰር!!››
ድምፆን ሲሰማ ከገባበት ሰመመን እንደመበርገግ ብሎ ነቃአለና አይኖቹን ከፈተ….
‹‹አለሽ?››በሰለለና በደከመ ድምፅ ጠየቀት፡፡
ፐሮፌሰሩ ዶ/ራን እንዳያት ተገርሞልም ተደስቷልም፡እዚህ ቤት ታግቶ ከመጣበት ደቂቃ ጀምሮ እሷን ከአሁን አሁን ትመጣለች ብሎ ሲጠብቅ ነበር…እሱ ሊገድላት ወስኖ እያሳደዳት የነበረ ቢሆንም በሌላ ሰው ተገደለች ሚለውን ዜና ለመስማት ፈፅሞ ዝግጁ አልነበረም.ደግሞ ነገሮች እንዲህ ዝብርቅርቅ ብለው እሱም በገዳዬች እጅ ከገባ በኃላ የእሷ መገደል ለእሱ ምንም የሚያስገኝለት ፋይዳ እንደሌለ ገብቶታል፡፡ቢሆንም የእሷ የመታገት ዜና ውሎ ሲያድር ተስፋ ቆርጦ ነበር.ገድለው የሆነ ጥሻ ውስጥ እንደቀበሯት እርግጠኛ መሆን ጀምሮ ነበር.፡፡

አሁን ሲያያት አላመነም…እሱም እንዲህ በተአምር ከእዚህ እስር ወጥቶ ነፃ የሚሆንበት እድል እንዳለው ተሰማው.አዎ እሷ እድሉ ነች.፡፡ብቸኛ እድሉ.፡፡ቢያንስ ላሳለፍት በርካታ ጣፋጭ የፍቅር ጊዜያቶች ስትል ከእዚህ ጉድ ታወጣዋለች፡፡በዚህ አመነ፡፡እሷንም ሊያሳምናት ወሰነ፡፡ እንደምንም ተዳክሞና ተንጠፍፍፎ የነበረውን የውስጥ ኃይሉን አበረታ.
‹ይመስገነው እንደአንተ ሳይሆን እንደእግዚያብሄር አለሁ›››አለችው፡፡
‹‹በሰላም ስለተመለሽ ደስ ብሎኛል…አንቺንም እንደእኔ አድርገውሽ ይሆን? ብዬ ሳስብ ነበር››አላት .የተናገረው ከአንጀቱ ነው.እሷ ግን እንደማላጋጥ ነው የወሰደችው፡፡
‹‹አይ ፕሮፌሰር ፤በዚህ አይነት ቅጥፈትህ እኮ ለዘመናት ስታታልለኝና ስትጫወትብኝ ነበር፡፡ቢያንስ አሁን በዚህ ለመሞት ሳዕታት በቀረህ ቅፅበት አውነቱን ተናገር…እኔ እንደሆነ ምንም አይሰማኝም..እንዴት ትጠላኝ እንደነበር፣….ምን አይነት ርካሽ አሻንጉሊትህ እንደነበርኩ.. አዎ ጢባ ጢቢ መጫወቻህ እንደነበርኩና….በደደብነቴ ስትስቅብኝ እንደኖርክ ንገረኝ››
‹‹አረ ተይ…እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ….እውነት ነው ምልሽ ከእነዚህ ሰዎች በሆነ መንገድ ካዳንሺኝ የእድሜ ልክ ባርያሽ ነው የምሆነው››
እሱ የሚያወራውን ችላ አለችና የራሷን ወሬ ማውራት ጀመረች‹‹ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት አሞኝ ስለነበር አብዬት በግድ ሆስፒታል ወሰደኝ…ተመረመርኩ…ምን እንደተከሰተ እስኪ ገምት….?የሰባት ሳምንት እርጉዝ ነኝ…፡፡የሰባት ሳምንት ፅንስ በሆዴ አለ…ከማ ያው ከማን ይሆናል ታውቀዋለህ ካንተ..ያዛሬ15 ቀን በዛ አጋጣሚ ኤልያስ አስጠነንቅቆኝ ከእጃችሁ ባላመልጣችሁና ብትገድለኝ ኖሮ እኔና የአመስት ሳምንት ልጅህን ነበር የምትገድለው..››
ያለቸውን ሲሰማ በፊት እሷን ሲያይ ከነቃው በላይ አሁን ነቃ…..ይሄ ልጅ ለእሱ ተስፋውና ከዚህ ከገባበት ድቅድቅ ጨለማ የሚወጣበት ብቸኛ እድሉ እንደሆነ ተማመነበት…በውስጡ ፈነጠዘ፡፡
እሷ ንግግሮን ቀጠለች‹‹ሰሞኑን በታገትኩባቸው ቀናቶች እዛ የብቸኝነት ጉድጓድ ውስጥ ተወሽቄ ምን እየሠራው ያሰለፍኩ ይመስልሀል?።ስለበቀል ነበር የማስበው።አንተን ስለመበቀል። አዎ ስለአንተ ያለኝ ንዴት ልክ እንደነቀርሳ ሰውነቴን በልቶ ሊጨርሰው ነው። ቀድሞ ከወደድኩህ በላይ አምርሬ ጠልችሀለው።አየህ እድሜ ላንተ ይሁንና ጥላቻ ከፍቅር በላይ ጉልበታምና አስፈሪ መሆኑን ሰሞኑን በደንብ ተረድቼያለሁ። ስመጣ በእንቅፍ ውስጥ ገብተህ እያንጎላጅክ ነበር፡፡ እኔ አንተን ብሆን እንቅልፍ ለመተኛት አይኖቼን አልጨፍንም...በማንኛውም ሰዓት ድንገት ባለህበት ቦታ ደርሰው አንገትህን ቀንጥሰው እስከወዲያኛው ሊገላግሉህ የሚችሉ እኔን መሠል በርካታ ጠላቶች እያሉህ እንዴት ደፍረህ ልተኛ ትችላለህ?እንደሰው እንኳን ነፍሴን ለፈጣሪዬ አደራ ሰጥቼ ነው የማሸልበው አትለኝም፤ ምክንያቱም ከሚያሳድዱህ ሰዎች በፊት ያስቀየምከውና ያሳዘንከው አምላክህን ነው።በዛ የተነሳ አምላክህ ምንም እንኳን ልክ እንደኛ ሊያጠፍህ ባያሳድድህም ልናጠፍህ ስንንቀሳቀስ ግን ጣልቃ ገብቶ እንደማይታደግህ እርግጠኛ ነኝ።
እሱም የእሷን የምሬት ንግግር ችላ ብሎ የራሱን ማውራት ጀመረ፡፡‹‹ይሄ የእግዚያብሄር ተአምር ነው….እኔና እንቺ ለአመታት እንዴት ልጅ መውለድ እንፈልግ እንደነበር ትዝ ይልሻል አይደል፡፡… እኔም በጣም አብዝቼው ነበር..አየሽ ልጅ የተፀነሰው እግዚያብሄር ይቅር ሊለኝ ሲፈልግ ነው፡፡ በቃ አሁን እንደምንም እንዚህን ሰዎች አዘናጊና ከዚህ ይዘሺኝ ውጪ ፡፡ከዛ ይሄን ሀገር ጥለን እንጠፋለን፡፡ከዚህ ሁሉ ግርግር ተገልለን የፈለግሺው ሀገር ልጃችንን በሰላም እናሳድጋለን፡፡ደግሞ አትስጊ ሆስፒታሉ ቢወረስ እንኳን ግቢዬ ውስጥ የቀበርኩት መአት ገንዘብ አለኝ…አረ ገና ሌሎች ብዙ ልጆችም እንወልዳለን፡፡››
‹‹ግን ስንት ልጆች ነው መውለድ ምትፈልገው..?ማለት ከእኔ?››
‹‹ስድስት ልጅ….ገና አምስት ልጅ ይቀረናል፡፡››በራሱ መልስ ፈገግ ለማለት ቢሞክርም የቆሳሰለ ፊቱና ያበባጠ ከንፈሩ የፈለገውን ይህል እንዲፈግ አላደረገውም፡፡
‹‹እና ከእኔ ስድስት ልጅ መውለድ ትፈልጋለህ?››
‹‹አዎ…ከፈለግሽም እንጨምራለን፡፡››
ንዴቷን መቆጣጠር ተሳናት…አንገቱን አንቃው እስከወዲያኛው ልታሰናብተው ፈለገች..‹‹አይ እሱማ እሱን መተባበር ነው..ከመሞቱ በፊትማ በደንብ መሰቃየት አለበት…ይሄ እንዲህ የመጨረሻ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንኳን ሳለማታለል እና ማጭበርበር ብቻ የሚያስብ ሰው ሊታዘንለት አይገባም››ስትል ወሰነችና ድንገት ከመቀመጫዋ ተነሳች… ወደበራፉ ተራመደች..ከፍታ ወጣች..በረንዳ ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሰ ሲጠብቃት የነበረው አብዬት ሮጦ ስሮ ደረሰ›፡፡
‹‹ጨረሽ በቃ…?ልቆልፈውና እንሂድ?››
‹‹አይ የሆኑ እቃዎች ፈለጌ ነበር፡፡››
‹‹ምን ልስጥሽ?››
‹‹ፒንሳ አገኛለሁ?››
‹‹ለምን….?››አለ አብዬት ግራ ገብቶት.. ‹‹ሰንሰለቱን ልትበጥስለት ፈልጋ ይሆን እንዴ…?.የልጇ አባት መሆኑን ስታውቅ አሳዘናት ይሆን….?›ስል በውስጡ አሰበ ከእሷ መልስ ሳይጠብቅ‹‹ቆይ ላምጣልሽ ጠብቂኝ››አለና እዛው ከጎኗ የሚገኘው መሳሪያ ማስቀመጫ ክፍላቸው ውስጥ ገባ… አንድ መለስተኛ ፒንሳ አምጥቶ ሰጣት…ምንም ብታደርግ ምንም በውሳኔዋ ጣልቃ ላለመግባት ለራሱ ቃል ገብቶል፡፡አሁን ፈታው በፊት ለፊቱ ብትለቀው ወይም ተከትላው ብትሄድ እንኳን..በሀዘኔታ ከመመልከት በስተቀር ሊያስቆማት በፍፅም አይሞክርም፡፡ይሄንን ወስኗል፡
ያመጣላትን ፒንሳ ተቀበለችውና ‹‹ይቅርታ ..መቀስ አገኛለሁ?›› ብላ ጠየቀችው፡፡አሁንም ተመልሶ ሄደና ይዞላት መጣ፡፡
አመሰግናለሁ፡፡ብላ ወደውስጥ ገባችና በራፉን ከውስጥ ቀረቀረችው፡፡ከላይ የለበሰችውን ሻርፕ ከላዬ ገፈፈችና ቀጥታ ወደፕሮፌሰሩ በመቅረብ አፉ ውስጥ ጠቀጠቀችው….ምን ልታደርግ እንዳሰበች ግራ ስለገባው ተወራጨ ….ግን ደግሞ እራሱን መከላከል የሚችልበት ምንም አይነት እድል የለውም፡፡ ፀጉሯን ጠቅልላ የሰረችበትን ጨርቅ አነሳችና የጠቀጠቀችውን ሻርፕ ተንሸራቶ እንዳይወድቅ በጭንቅላቱ ዙሪያ አዙር አንድ ላይ አሰረችው፡፡ አሁን ቢጮህም ድምፅ ከዚህ ግቢ አልፎ እንደማይሰማ እርግጠኛ ሆነች፡፡፡

👍36❤1
የተሰባበሩ ነፍሶች
ምዕራፍ-20
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
//
አፉን በትክክል ድምፅ እንዳያወጣ እንዳደረገች እርግጠኛ ሆነች፡፡ ከዛ እግሩ የታሰረባቸውን ሰንሰለት ፈታችና አንድ ላይ ተቆራኝተው ተስረው የነበሩ እግሮቹን ለየብቻ ለይታ ወደግራና ወደቀኝ በለቃቅጣ ለየብቻ መልሳ አጥብቃ አሰረችው፡፡
ፕሮፌሰሩ አይኖች ፈጠው እንደህፃን ልጅ እንባ እያረገፉ ነው፡፡
እሷ ነገሬም ሳትለው…ወለል ላይ ያሰቀመጠችውን መቀስ አነሳችና አስተካክላ ወደ እሱ ቀረበች፡፡ በእግርና እግሩ መሀከል ገባች፡፡ ብልቱ አካባቢ ያለውን ሱሪውን በመቀሱ ተረተረችው፡፡ ሙሉ በሙሉ እስኪለያይና የውስጥ ፓንቱ እስኪታይ ድረስ ..ከዛ ፓንቱን ወደታች ጎተተችና ከላይ ጀምራ መሉ በሙሉ ወደታች ተረተረችውና ብልቱ እስከነፍሬው ወደውጭ ተዘርግፎ መውጣቱን ስታረጋጥ መቀሱን መልሳ ወንበሩ ላይ አስቀመጠችና ፒንሳውን ይዛ ቆመች፡፡እና ማውራት ጀመረች
‹ፕሮፌሰር ይሄንን ነገር ለማድረግ ፈፅሞ አላሰብኩም ነበር…. እንዴትስ ላስብ እችላለሁ?..እንደእዚህ አይነት ስራዎች እኮ በእኔ ሳይሆን በአንተ ተፈጥሮ ውስጥ ነው የሚገኙት..ግን አየህ አይደል..?እንዴት እንደቀየርከኝ..?እንዴት እኔንም ጭምረህ አውሬ እንዳደረከኝ…?አሁን ከእዚህ ቁጭ ብዬ ከአንተ ንግግረር እያደማጥኩ ሳለ ይሄንን ማድረግ አለብሽ የሚል ድምፅ በጆሮዬ ሹክ አለኝ..ምን አልባት አንተ ያስቀየምከው ያንተው ወዳጅ የሆነ ሰይጣን ይሆናል እንደዛ ያደረገው…..አንተ እንደዚህ ህይወቴን አመሰቃቀለህ….ስሜን፤ ስራዬን ገደል ከተህ…እናቴንና እህቴን እንደዛ አሰቃይተህ ካበቃህ በኃላም ከእኔ ስድስት ልጅ መውለድ ትፈልጋለህ?፡፡ያማ አይሆንም፡፡ነገ ወይም ተነገ ወዲያ የሚገድሉህ ይመስለኛል፡፡ግን ከእነሙሉ ዘርህ ወደመቃብር መውረድ የለብህም..አንተ በቁም መመክን አለብህ..እንደአንተ አይነት አውሬ በሰው ልጆች መካከል ዳግም እንዳይፈጠር ያንተ ዘር መምከን የግድ ነው፡፡››
አብዬት በጣም ከመጨነቁ የተነሳ ጆሮውን በራፍ ላይ ለጥፎ ያዳምጣል….ፕሮፌሰሩን በሰንሰለት ያሰረው እራሱ ባይሆን እንዲህ ተማምኖ ይሄን ሁሉ ሰአት አይቆይም ነበረ…የእሷ ድምፅ ብቻ ይሰማዋል…ለማንኳኳት ፈለገና የተወሰነ ደቂቃዎች ለመተገስ እራሱን አሰመነ፡፡
//
ዶክተር ፒንሳውን ቀስራ ወዲህና ወዲያ ተበለቃቅጠው በታሰሩ እግሮቹ መካከል ቁጭ አለች..ከአዚህ በፊት ብዙ ጊዜ በእግሮቹ መሀከል እንዲህ ተቀምጣ ታውቃለች..ግን ፍቅር ለመስራት ነበር፤ ደስታና እራካታ ፍለጋ፡፡አሁን ግን ድንበር በጣሰ የሲኦል ጥላቻ ነው በቦታው የተገኘችው፡፡ፒንሳውን በለቀጠችና በብልቱ ፍሬ መካከል አስተካክላ ያዘች፤ሰይጣን ባዋሳት ሀይል አንድ ላይ ጨምቃ ያዘችውና ወደግራና ወደቀኝ እየጠመዘዘች አሸችው፤ ለተወሰኑ ደቂቆች የኤሌክትሪክ ወንበር ላይ እንደተቀመጠ ሟች ፍርደኛ ተንሰዘረዘረ ተንዘረዘረና እራሱን ስቶ ዝርግትግት በማለት አንገቱና ደፋ፡፡
የቆለጡ ቆዳ ተሞሽልቆ ሲነሳ እጇ በደም ተሞላ.. እጇን እያነከረፈፈችና እንደእብድ እየተወራጨች ከአካሉ የተቦጨቀ ቆዳ የያዘውን ፒንሳ ወለል ላይ ወርውራ ወደ በራፍ ሄዳ ከፈተችና አብዬት ደረት ላይ ተደገፈች..በእጇ የሞላውን ደም ሲያይ ደነገጠ …የሆነ ነገር የሆነቸ ነው መሰለው፡፡
‹‹ምን ሆነሻል ፣ምን አደረገሽ?››
እጇን በማራገፍ ደሙን ወለሉ ላይ እየረጨች ከጥልቅ ማለክለክ ጋር ‹‹ምንም አለደረገኝ ..እኔ ነኝ ያደረኩት››አለችና ሸርተት ብላ እዛው በራፉ ጋር ከውጭ በኩል ግድግዳ ተደግፋ ተቀመጠች..
አብዬት የሆነውን ሊያጣራ ወደውስጥ ገባ..ፐሮፌሰሩን ዝርግትግት ብሎ ፤አንገቱን ደፍቶ፤ አፍ ታሽጎ፤ ልብሱ ተበጣጥቆ በደም ተጨማልቆ ሲያገኘው‹‹..በቃ ገደለችው?››ሲል አሰበ፡፡ ተንደርድሮ ተጠጋውና ጣቶቹን ወደ አንገቱ ልኮ ሲያረጋገጥ ነፍሱ አለች..ቶሎ ብሎ አፍ ላይ የተጠቀጠቀውን ጨርቅ አላቀቀና አየር እንዲያገኝ አደረገ ..የእጅ ሰንሰለቱን ከተንጠለተለበት አላቀቀ….ከወንበሩ አወረደና መሬት ወለል ላይ አስተኛው፡፡ከክፍሉ በመውጣት መልሶ ከውጭ ቆለፈውና እሷን ደግፎ ከተቀመጠችበት አነሳትና ወደክፍሏ ይዞት ሄደ ….፡፡
ገፋ አድርጎ ሲገባ…አልጋዋ እንደተነጠፈ፤ መኝታ ቤቷም እንደፀዳ ነው..ይሄን እራሱነው የመምጣቷ ነገር እርግጠኛ ሲሆን ቀን ያዘዘውና በትክክል መሰራቱን ያረጋገጠው፡፡አሁን ያልጠበቀው ነገር ያጋጠመው ከአልጋው በታች ወለል ላይ ግዙፍ ፍራሽ ተዘርግቶሎ እላዩ ላይ ተጠቅልሎ የተኛ ግዙፍ ሰው ማየቱ ነው›
እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ምንድነው ይሄ?››አብዬት ተበሳጨ...እሷን ደግፎ አልጋዋ ጠርዝ ላይ እንድትቀመጥ ካደረገ በኃላ ወደተጋደመው ሰው ሄዶ የተጠቀለለበትን አልጋ ልብስ ከላዩ ላይ ገፎ ሲያየው ካሳ ነው
‹‹ወይ..!!እንዴት ሳላስበው?..ከዚህ ንክ ውጭ እንዲህ የሚያደርግ ሌላ ሰው ከየት ይገኛል?..አንተ ተነስ ››ቀሰቀሰው፡፡
አይኑን እያሸ ተነሰና‹‹ምን ያስጮህሀል››
‹‹ምን ትሰራለህ እዚህ….መኝታ ቤትህ ምን ሆነ?ጉንዳን ወይስ አይጥ ነው ያባረህ?››
‹‹ከአንተ በላይ አይጥ አለ እንዴ?እሷ ያለችበት ክፍል መተኛት ጥሩ ህልም ለማለም ጥቅም እንዳለው እዛ አብረን በነበርንበት ግዜ ተረድቼለሁ..››
‹‹አና››አለው አብየት ተገርሞ፡፡
‹‹እናማ..ከዛሬ ጀመሮ ከእሷ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ በዚህ አይነት ሁኔታ ነው የምተኛው…ለዛ ነው ፍራሼን ወደእዚህ አምጥቼ የዘረጋሁት፡፡››
‹‹ጅሎ እዚህ ከአንድ ሳምንት በኃላ አንኖርም..ሁላችንም በየቤታችን እንበታተናለን፡፡››
‹‹እናንተ ቅጥረኛ አሽከሮች ሰለነበራችሁ አዎ ጥቅማችሁ ስላበቃ በካልቾ ቂጣችሁ እየተጠለዘ ወደበፊት ድርዬነታችሁ ትበተናላችሁ.. እኔ ግን ከእሷ ጋር እሷ ቤት ነው የምሄደው… ከልሆነም እኔ ቤት ወስዳትና አኔ ክፍል አብረን እንተኛለን፡፡››
በጣም በተናደደበትና ግራ በተገባበት ወቅት ባይሆን አሁን እያየ እና እየሰማው ያለውን ነገር በጣም ያስቀው ነበር…
ዶ/ር በሁሉ ነገር የተሰላቸ በሚመስስ ስሜት‹‹አቢ ተወው ይተኛ››አለችው…
‹‹ይሄው ሰማሀት አይደል.?.ተወኝ አንተ ቀፋፊ….ደግሞ ልብህን መንቅራ አውጥታልህ ነው እንዴ እንዲህ እጇ ደም በደም የሆነው?›› አለና ሌላ መልስ ሳይጠብቅ የተገፈፈውን አልጋ ልብስ መልሶ ሙሉ በሙሉ ተጠቀለለና ወደእንቅልፉ ተመለሰ፡
አብዬትም ለካሳ መልስ መስጡን ችላ ብሎ ወደእሷ ዞረና ‹‹አሁን ግቢና ሻወር ውሰጂ›››እኔ ሰውዬውን አይቼው ልምጣ…በእንዲህ አይነት ሁኔታ መሞት የለበትም››አላትና ወጥቶ ሄደ፡፡
እሷም ቀጥታ ወደ ሻወር ቤት ገባችና ተስተካክላ ቆመች…. የሻወሩን ቀዝቃዛ ውሀ ከፈተችው ከነልብሷ ያረሰርሳት ጀመር… ወደታች በእግሮቾ እየተንኳለለ የሚወርደው ውሀ በደም የተበረዘና የደፈረሰ ነው..ቅፍፍ አላት፡፡

👍24❤2😢1
አቢዬት ከእሷ እንደተመለሰ ቀጥታ ወደታች ወርደ ..ሁሉም እየጠጡና እየተጫወቱ ፈንጠዚያ ላይ ናቸው፡፡ ሊረብሻቸው አልፈልገም፡፡ ፈንጠር ብሎ የተቀምጦ የሚቆዝመውን ቶላን በምልክት ጠራው ።ያንን የሠማይ ስባሪ የሚያህል ሰውነቱን ይዞ ሲቆም የሳሎኑን ኮርኒስ በጭንቅላቱ ሊነካ ጥቂት ነው የቀረው አብዬት ፊቱን አዞረና ደረጃውን ወደ ላይ መውጣት ጀመረ...ቶላ ከኃላ ተከተለው..ፕሮፌሰሩ ያለበት ክፍል ደረሱት ከፍተው ወደውስጥ ገብ...ዝርግትግት ብሎ በደም እንደተጨመላለቀ እረሱ ስቶ ወለል ላይ እንደተዘረረ ነው።"አብዬት ጎንበስ አለና እግሩን የታሰረበትን ሰንሰለት ቁልፉን በማላቀቅ ፈታለትና እግሮቹን ነፃ አደረጋቸው።የእጆቹን ሰንሰለት ቅድም ነው የፈታለት ።ቶላ የክፍሉ መአከላዊ ስፍራ እንደቆመ ቁልቁል አዘቅዝቆ እራሱን የሳተውን ፕሮፌሰር ያለምንም የስሜት ለውጥ እያየው ነው።በእሱ ቦታ ማንሞ ቢሆን፤ ምን ሆኖ ነው?ለምንድነው በደም የተሸፈነው? ለምንድነው እራሱን የሳተው ?የሚሉ አያሌ ጥያቄዎችን ያቀርብ ነበር..እሱ ግን እንደዚ አይዳዳውም ፡፡ በማይመለከተው ነገር አይገባ።ካልጠየቁት አይመልስም። እንደውም ጠይቀውት እራሱ ብዙ ጊዜ አይመልስም።በዚህም ባህሪው አብዬት በጣም ይወደዋል።
‹‹ወደእኔ ክፍል እንድንወስደው ፈልጌ ነው"
ስሩ ተንበረከከና እንደሚታቀፍ ህፃን ልጅ እጆቹን በጀርባው ሰቅስቆ ለማስገባት መሞከር ጀመረ‹‹ ምን እያደረክ ነው?"
"እራሱን ስቶ የለ ላቅፈው ነዋ።››
"አይ እንደዛ አይደለም ..እግሩ መሀከል ስለቆሰለ ይበልጥ እንዳይጎዳ አብረን ነው የምንይዘው"
"እሺ"አለና ወደ ጭንቅላቱ ሄደና ግራና ቀኝ ብብቱ ውስጥ ግዙፍ የእጅ መዳፎቹን አስገባና ያዘው።አብዬት ሁለት እግሮቹን እርስ በረስ እንዳይፍተጉ እየተጠነቀቀ ያዘው ፡፡ወደላይ አንጠለጠሉትና ከክፍል ይዘውት ወጡ፡፡ወደአብዬት ክፍል አመሩ ፡፡ደሙ በመንገዳቸው ሁሉ እየተንጠባጠበ የቤቱ ወለል ላይ የራሱ መስመር ሰርቶ ነበር፡፡እንደደረሱ ከፍ አደረጉና አስተካክለው ምቹው አልጋ መሀከል ላይ አስቀመጡት።
አሁን የአንተ ሀላፊነት ይሄን ሰው እስኪነጋ መጠበቅ ነው አለው አብዬት ለቶላ
"ችግር የለም"አለና መግቢያው ጋር ካለች አንድ ደረቅ ወንበር ሄዶ ተቀመጠ.፡፡. አብዬት ስልኩን አወጣና እየደወለ ወጣ።
‹‹ሄሎ ዶክተር..."
"እባክህ ሆስፒታል መውሰድ የማልችለው አንድ የተጎዳ ሰው እጄ ላይ እራሱን ሳተ"
"አዎ አሁን ልወስድህ እየመጣሁ ነው"
"አዎ እራሴ ነኝ የምመጣው...በሀያ ደቂቃ ውስጥ እቤትህ በራፍ ጋ እደርሳለሁ።
"አመሠግናለሁ ዶክተር..."ዘጋውና መኪና ውስጥ ገብቶ ግቢውን ለቆ ወጣ፡፡ ይሄን ዶክተር የረጂም ጊዜ ወዳጅ ስለሆነ ለእንደ እዚህ አይነት ጉዳይ በሚስጥር ጠባቂነቱ የሚተማመንበት ብቸኛው ሰው ነው።

👍19❤1🔥1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
“ነገ ማታ እደውልልሃለሁ በመጭው ሦስት ቀናት
አልኖርም:: ጓደኛዬን ለመጠየቅና እግረ መንገዴን ለመሰናበት ባርሴሉና እሄዳለሁ... መልካም ጊዜ ለማሳለፍ ሞክር አሁን
መተኛት እፈልጋለሁ ኦርቫ" ብላው ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች:
በተቀመጠበት ህሊናው የስሜት ግጭት ተንቆራቆሰበት...
የሐሳብ ልዩነት.. ውሃና እሳት ትኩሳትና ብርድ... የስሜት
ጩሕት... የማይታኘክ ጉርሻ..
ከጥቁርና ነጭ ቀለም የተውጣጣው የቀይ ዳማ ቀለሟ ዞማ ፀጉሯ ከለግላጋ ቁመናዋ ጋር ፈጣን አስተሳሰቧ ሁሌም ጎልታ
እንድትታይ ያደርጋታል።
መርከበኛው አባቷ ፍራንሲስኮ ፔሶ ቤኒ በስራው ምክንያት
ከናቷ ከሎካዬ ጋር ለብዙ ወራት ተለያይቶ ሲቆይ ከህፃንነቷ ጀምሮ ናፍቆት ቢንጣትም እንኳን የተሟላው ኑሯቸው
ጨዋታ ወዳዱ አባቷ በየመዝናኛው ከናቷ ጋር ይዟት ስለሚዞር አብሯት
ስለሚቦርቅ ደስተኛ ሆና ለማደግ አስችሏታል።
በተማሪነቷ የስካውት አባል የነበረችውና በስካውትነቷ ብዙ ጉዞዎችን ከእድሜ እኮዮችዋ ጋር ያደረገችው ቅርፀ ማራኪዋ ኮንችት
ጊታር መጫወትን በጋራ ማዜምንና ከእስፔናውያን ባህላዊ ዳንስ በተጨማሪ የምዕራባውያንን ውዝዋዜ በስልት አጣጥማ የማቅረብ
ተሰጥኦዋ ተደጋጋሚ አድናቆትን ስላተረፉላት ከዘጠኝ ዓመት እድሜዋ ጀምሮ ጊዜዋ “የፋሽን ሾው" ስራ እየሰራች የራሷ ገቢ
እስከማግኘት አስችሏት ነበር።
አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከፈፀመች በኋላ በባልትና ሳይንስ ትምህርት ሰልጥና ከሙያዋ ይልቅ በሞዴሊስትነት
ሥራ በመሰማራት በጂምናዚዬም አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ
ለሚስስ ካታሉንያነት ሁለት ጊዜ ተወዳድራ በሶስተኛው ሚስስ ካታሉንያ በመባል የቁንጅና ዘውዷን ደፍታለች።
ኮንችት በህፃንነት ያየችው አፍሪካዊ አያቷ ኤድዋርድ ሎካዬ ብቸኝነቱ ዝምታውና ደስታ አልባ ሆኖ ኖሮ ከሚናፍቃቸው ዘመዶቹ
ተገናኝቶ ያሰበው ሳይሳካለት ማለፉ እንደ እግር እሳት ሁሌም
ያቃጥላታል። አይቶት በማያውቀው እንደ ሰማይ በተዘረጋ ውቅያኖስ ላይ ጭነው ፖርቶሪኮ ውስጥ ኗሪ ለነበረው ለኤድዋርድ ጃኒፌር የተሸጠው አያቷ ከአንዱ አለም ወደ ሌላ ዓለም ከተወሰደ በኋላ
በቋንቋም በአስተሳሰብም ልዩ ሆኖ ፖርቶሪኮ ውስጥ በተነሳው የርስ በርስ ጦርነት እንደ አባቱ የሚቆጥረው ጌታው ኤድዋርድ ጃኒፈር
ወደ አሜሪካ ሜሪላንድ ሸሽቶ በመሄዱ እንግሊዘኛና እስፓኒሽ ቋንቋ
አፍንጫውን ተይዞ ተምሮ የዕለት ፍላጎቱን ለማርካት የታክሲ ሾፌር ሆነ።
ከዚያ ከኮንችት ሴት አያት ከራሚሬዝ ኦርኔዝ አኜስ ጋር
በአጋጣሚ ተገናኝተው የኮንችት አያት አኜስና ሉካያ እናቷን ከሪናን በመውለድ ስፔን ውስጥ አ ብረው መኖሩ ጀመሩ። ሎካዬ በተለያየ ጊዜ በአፍሪካ ጉብኝት አድርጎ ዘመዶቹን ፈልጎ ለማግኘት ቢሞክርም
ሊሳካለት አልቻለም ነበር:
በስተ እርጅናው ጣልያን ሮም ላይ የተደረገውን የማራቶን ውድድር ለመመልከት ሄዶ ግን ባጋጣሚ የአገሩ ፍንጭ ቢታወቅም ሽምግልናውና ጤና ማጣቱ ተዳምረው
ምኞቱን አሰናከለባት።
ኮንችት አያቷ ለመሞት ቀናት ሲቀሩት ጠርቷት ወደ
አታክልቱ ቦታ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ወስዷት ትክ ብሎ እያያት።
“ለሰባት ዓመት ልጅ አደራ መተው ምንኛ ይከብዳል
መሰለሽ” አለና አፉን በመሀረብ ይዞ ሲስል ቆይቶ፡
“አሁ ካንች ሌላ ማንስ አደራዬን ሊቀበል ይችላል-" ሲል ኮንችት የሚለውን ነገር ስላልገባት ግራ ገብቷት ስትቁለጨለጭ፡-
“የዘመዶቼን አገር አላውቅም ነበር። ጠንካራነቴ አሁን
የነበረውን ፍንጭ የዛኔ ቢኖረኝ ኖሮ ምን ነበረበት ግን አልሆነም
የኔ ልጅ ይህች ትንሽ ባንዲራ በልጅነቴ አሁን ስሙን ከማላውቀው
የገጠር ከተማ ከአባቴ ጋር ሄጄ አይቻት ነበር። በህፃንነት ልቦናዬ ያን
ጊዜ ስትውለበለብ ያየኋት ባንዲራ ሮም ላይ ሯጩ ይዟት አየኋት እና እንኪ ያዣት በጥንቃቄም አስቀምጫት! ሲሆንልሽ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ | ባንዲራ ወደ አለባት ኢትዮጵያ ወደሚሏት
ሃገር ሂጂ።
"ይህም መቀመጫ ስንተራሳት ስቀመጥባት ምንድናት?' እያልሽ የምትጠይቂኝ መቀመጫዬም 'በርኮቶ' ትባላለች በኮዬጉዎች።
“ምን?” አለች ኮንችት
ኩዬጕ ኩዬጉዎች… የኔ ዘመዶች የሚቀመጡባት
መቀመጫ ናት" ሳሉ እንደገና አሳለው ላቡ በግንባሩ ተንቆረቆረ
ወደ ሰማይ ቀና ብሎ፦
“ልዑል እግዚአብሔር! እባክህ ትንሽ ትንሽ ጊዜ ስጠኝ አለና እግዚአብሔርን ተማፅኖ፣ “አጠገባቸው ትልቅ ወንዝ አለ::
ሱርማዎች ኦሞ ይሉታል: ከወንዙ ተሻግረሽ ትንሽ ስትሄጂ ኩችሩ የሚባል መንደር አለ፡፡
ሰላም ሲሉ አሹቃ ይላሉ። አሳ አጥማጆች አትክልተኞች ከዱር ማር ሰብሳቢዎች ናቸው" እንደገና ሳለ፤ ቀና ብሉ ሰማዩን ተመለhተ።
ኮንችት የሚለው አልገባትም በጨቅላ ህሊናዋ ግን ስቃዩ
አሳዝኗታል።
“ሁሉንም ፅፌልሻለሁ ባንዲራዋን ከዘነጋኋት ዘመዶቼም ከመኖሪያቸው ለቀው ከሆነ ልፋትሽ መና ይቀራል። ወለላዬ እስቲ
እነዚያ ቆንጂዬ ጣቶችሽ? አላት ድንገት:: ሁለቱንም እጆችዋን ዘረጋችለት:: ጊዜ አልነበረውም መጣደፍ ነበረበት፡፡
ጳ..ጳ አርጎ በጥቁሩ ከንፈሩ በየተራ ሳማቸው: ጉንጯን
ሊስማት ፈለገ¦ ግን ፈራ ሳሉ ቢተላለፍባትስ:
“እንኪ በላስቲኩ
አሮጌ ካርቶን ውስጥ ይኸው ከትቼልሻለሁ። የኔ ልጅ እኒያን ዘመዶቼን ቀንቶሽ ካገኘሻቸው
እዘኝላቸው እንዳንች ንፁሆች ናቸው፡፡ ሎካዬ ናፍቋችኋል ሰላም
ብሏችኋል! በያቸው: ሞቷል አትበያቸው: ስንት ጊዜ በእኔ ይዘኑ ለእኔ ያልቅሱ አለ በያቸው ሲረጋጉ ደግሞ እኔ ነኝ ሎካዬ በያቸው እንደ ህፃን ያምኑሻል መጠራጠር አያውቁም ፤የሚጠራጠር ራሱ ሌባ ነው ይባል የለ! እነሱ ግን እንደ ዶሮ እየጫሩ
ተዛዝነው ያገኙትን ሲለቅሙ ይውሉና የኩችሩ ጫካ ክንፍ ውስጥ እንደ ጫጩት እየተሰገሰጉ ሙቀታቸውን እየተጋሩ ይተኛሉ…"
አሳለው! ሰውነቱ ራደ ላቡ ወረደ።
በይ ሄጂ ተጫወቺ እ..ኔ
ደ.ግ.ሞ እ ..ሁ ልረፍ” አላት ተስፋ በቆረጠ አስተያየት እያያት የአደራ ካርቶኗን ታቅፋ ስትሄድ ፈገግ ብሎ ከኋላዋ ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከታት።

👍20
እሷ ስትሮጥ እሱ መሄድ አቃተው:? የህይወት ጉዞው
ሊያከትም ይሆን? ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፤ ጉልበቱ ራደ ቀዝቃዛ ላብ ሰውነቱን አራሰው። ጠንካራው ሎካዬ እንደ ሰከረ ሰው ዝልፍልፍ
ብሎ ወደቀ፤ሰማዩን አየው፤ እራቀበት… ዘመዶቹ ይንጫጫሉ…ኦሞ ወንዝ ቦዩን ጥሶ ወደ ውጭ ይፈሳል… ቀስተ ደመናዋ ግን ግራና ቀኝ እግሮችዋን ተራሮች ላይ አንቧትራ ቆማለች። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማቷን ለአመል ያህል አያቸው. ጨለማ ግን ወደሷ ይገሰግሳል። ፍርሃቱ ሉካዬን ናጠው ፍርግጥግጥ አለ፡፡ እውነትም እንዳለው ሰማይ ሰማይ እያዬ ለዘላለሙ አይኖቹን አፍጥጦ ፀጥ
አለ፡ አረፈ!....

👍16