አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ-12
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
ሰዓቱ ከምሽቱ 7፡23 ቢሆንም አብዬትና ዶክተር ሰጳራ እሷ መኝታ ቤት ናቸው ፡፡ከጎኑ ቁጭ ብላ በስሜት እያወራችው ነው..እሱም በስጋውም በነፍሱም እያዳመጣት ነው
‹‹…ይሄውልህ ስማኝ ፤የምረግጠው ቦታ ሁሉ እየከዳኝ ነው...ደረቅ መሬት መስሎኝ በሙሉ ክብደቴ ስጫነው ያዳልጠኝና ሰማይ ደርሼ መሬት እፈርጣለሁ።መሬት ሳርፍ የእጆቼን ቆዳ ጠጠርና አሸዋው ገሽልጦ ያቆሳስላቸዋል።ወገቤ ለሁለት ይከፈላል።ቢሆንም በወደቅኩበት እየተንከባለልኩ ማላዘን አይሆንልኝም። እንደምንም እራሴን አበርትቼ እነሳለሁ ።የጀርባዬ ህመም ጥዝጣዜው እስኪያቅለሸልሸኝ ድረስ ቢያመኝም ከአቋቋሜ ሽብርክ አልልም ..ፊቴንም አልቋጥርም....ወደፊትም ከመራመድ አልሰንፍም።የራሴን ህመም ለራሴው በሚስጥር ይዘዋለሁ።እኔ እንዲህ ነኝ።ውስጤ እየተሠባበረ ውጬ ፈክቶ ከሩቅ ብርሀን የሚረጭ...የህይወቴን ስንጥቅ ነፍስ አባቴ እንኳን እንዲያዩት የማልፈቅድ ከሸክላ የተሠራሁ አልማዝ ቅብ ጉራማይሌ ሰው፤የተሰባበረ ነፍሴን ከተበታተነበት እየሰበሰብኩ በአኩፋዳ በመሸከፋ መንገዴን የምቀጥል ብርቱ መሳይ ተሰባሪ ..አዎ እኔ እንደዛ ነኝ።
ንግግሯ ልቡ ድረስ ዘልቆ ተሰምቶታል..ምን ብሎ እንደሚያፅናናት ግራ ገባው..ቢሆንም ለስለስ ባለ አንደበት የመጣለትን መናገር ጀመረ"ብቻሽን አይደለሽም… በዚህ ዘመን ያልተሰባበረ ነፍስ ያለው ሰው ማግኘት ቀላል ይመስልሻል?ልዩነቱ አንቺ በጊዜ ነቅተሸ ወደውስጥሽ ተመልክተሽ የነፍስሽን መሰባበር ማየት መቻልሽ ነው።ስለተሰባበረችው ነፍስሽ በጊዜ አይተሸ ማወቅሽ ደግሞ ራሰሽው እንዳልሽው ስብርባሪዎቹን ከወዳደቁበት እየሰበሰብሽ በአኩፋዳሽ እንድታጠራቅሚ እድል ፈጥሮልሻል፡፡ወደፊት ምን አልባት (ወደፊት የሚባል ቀን ካለ )ነፍስሽን ለመጠገን ምቹ የሆነ ብርሀናዊ ቀን ህይወት ታመቻችልሽ ይሆናል...አዎ የዛን ጊዜ አኩፋዳሽን መክፈትና ያጠረቀምሻቸውን የነፍስሽን ስብርባሪዎች በየባታቸው አስተካክለሽ በጥንቃቄ በመሰካካት አንድ ላይ እንደአዲስ ማጣበቅ ነው።…አየሽ ከእንደገና ለማገገም እድል አለሽ….››
ከቁዘማዋ ሳትወጣ መልስ መስጠት ጀመረች "ባጣብቀውስ? ስንጥቁ እንዴት ሊጠፋ ይችላል?››
አብዬት መለሰላት‹‹ስንጥቁማ ስንጥቅ ነው...ዘላለም ከአንቺ ጋር የሚኖር ህመምሽና ትዝታሽ ነው።ያንን ደግሞ አትጥይው ፡፡ሰው የመሆንሽ ማንቂያ፤ በህይወት ኖረሽ እየተነፈሰሽ መሆኑን ማስገንዘቢያ አላርትሽ ነው።››
‹‹ምን አለ አንተ ልብ ውስጥ ያለው አንፀባራቂ ተስፋ ወደእኔም ልብ ሰንጥቆ ቢገባና ለጨለማው እኔነቴ ብርሀን ቢረጭልኝ…››ብላ ደረቱ ላይ ደገፍ አለች..እሱም ቀኝ እጁን በተከሻዋ አዙሮ አቀፋት ፡፡
በዚህ ቅፅበት ነበር የመኝታ ቤቱ በራፍ የተበረገደው..ሁለቱም ደነገጡና ከተጣበቁበት ተላቀቁ..ካሳ ነው ፡፡ካምፒተሩን በእጆቹ እንዳንከረፈፈ በራፍ ላይ ቆሞ እያለከለከ ነው..
‹‹ምን ተፈጠረ?››ዶክተሯ ጠየቀችው
‹‹እናንተ እዚህ ፍቅር ፍቅር ትጫወታላችሁ ነገሮች ተመሰቃቅለዋል;;››
‹‹ምንድነው የምታወራው?››አለው አብዬት
አንተማ ምን ቸገረህ..ደረትህ ላይ አስተኝተህ አስለቅሳት….አንቺ ግን መቼ ነው ትክክለኛ ምርጫ የምትመርጪው ?አሁን ይሄ ደረት የሚታኛበት ሆኖ ነው….?ሌላው ይቅር እንዲህ እንደሰነፍ ገበሬ መሬት ዝግዛግ የታረሰው ፊቱ አያስፈራሽም?›
‹‹አሁን ስለእሱ ፊት ልታወራነው የመጣሀው ወይስ ሌላ የምትነግረኝ ነገር አለ;?››
‹‹አይ በመምጣቴ ከእሱ በላይ አንቺ የተከፋሽ መሰለኝ..በቃ ወደአቆረጣችሁት መላላስ ተመለሱ፣አለና በርግዶ የከፈተውን በራፍ ፊቱን አዙሮ በመውጣት ዘጋውንና መሄድ ጀመረ
‹በጣም እኮ ነው የሚያፈቅርሽ..ቀንቶ ነው?››አለ አብዬት በድርጌቱ ተገርሞ
‹‹ምን እሱን የሚያስቀናው ነገር ሰራን…?.ደግሞ እኔም እኮ ወደዋለው..ግን እንደምታውቀወ አሁን ስለእዛ ማሰቢያ ጊዜ ላይ …››ንግግሯን ሳትጨርስ አሁንም በራፉ ተበርግዶ ተከፈተ
‹‹አሁን ደግሞ ምንድነው?››አለችው
‹‹ልነግርሽ ያለኩትን ረስቼው ሄድኩ››
‹‹እኮ ምንድነበር..ንገረኝ››ትዕግስቷን ተፈታተነው፡፡
‹‹ያ እጮኛሽ የነበረው እኔ የምጠላው ሰውዬ መልዕክት ልኮልሻል››
‹‹ምን….?››ሁለቱም ደነገጡ
‹‹ምነው? ይህቺ ያህል ብቻ ነው እንዴ የምደነግጡት?››
‹‹ምንድነው የምትቀባጥረው?›› ከተቀመጠችበት ተነሳችና ተንደርድራ ሄዳ ላፕቶፑን ከእጁ ነጠቀችና ሊያሳያት መጣውን ነገር ማየት ጀመረች…..ዥው አለበት…..እናቷ ና እህቷና እጃቸው ወደኃላ ተጠፍሮ፤ አፋቸው በጨርቅ ታሽጎ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ ብለዋል…የእህቷ ህፃን ልጅ በፍራቻ ትናንሽ አይኖቹን እያቁለጨለጨ የታሰረች እናቱ ጉያ ውስጥ ተሸጉጧል…ሶስት ወጠምሻ ጠባቂዎች ሽጉጥና ጩቤ በእጃቸው ጨብጠው ከእናቷና ከእህቷ ግራናና ቀኝ ቆመው ይታያሉ….አጋቾቹ ጭንብል ቢለብሱም አውቀቸዋለች..እሷን ለመግደል እቤቷ ድረስ ከመጡት መካከል ናቸው፡፡፡
ዥው አለባት…እጆጆቾ ከመንቀጥቀጣቸው የተነሳ ላፕቶፑን ማያዝ አልቻለችም.. ለቀቀችው፡፡ ወደታች ሲምዘገዘግ መሬት አርፎ ከመከስከሱ በፊት አብዮት ተንደርድሮ ቀለበው…ካሳ አፋን በድንጋጤ ከፍቶ ቀረ…. ላፕቶፑ መትረፉን ሲያውቅ ከቆመበት ተንደርድሮ ሄደና ከአብዬት ላይ ነጠቀው..‹‹ላፕቶፔ ምን አደረገ..?ባገለገለሽ…?እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ..ድሮም አንቺ ከልቡ የሚያገለግልሽን ነገር እንደቀልድ ወርውረሽ መስበር ልማድሽ ነው››
አብዬት በጣም ተበሳጭቶበት‹‹ዝም በል››በማለት ከፊት ለፊቱ ገፍትሮ ገለል እንዲል አደረገና ወደእሷ ተጠግቶ ክንዶቾን በመያዝ ደገፋና ከመውደቋ በፊት አልጋዋ ላይ አስቀመጣት፡፡
ለአስር ደቂቃ በቤቱ ዝምታ ሰፈነ..አብዬት ከጎኖ ተቀምጦል….ካሳም ዝም በል እንደተባለ ኮሚፒተሩን በደረቱ እንዳቀፈ ፊት ለፊታቸው ካያለውን ወንበር በግዙፍ ሰውነቱ ሞልቶት ተቀምጦ ይተክዛል፡፡
ዋጋ ከፍዬ ለዘመናት የገነባሁትን ህይወት ምሰሶዬ ይሆናል ባልኩት ሰው ተሠረቅኩ ።እንዲህ አይነት ክደህት ልብ ያደክማል።ልብን ማድከም ብቻ አይደለም ነፍስንም ጭምር ይሰባብራል።ስጋን ብቻ ሳይሆን ነፍስንም ጭምር ባስረከብት ሰው ነፍስ ሲሰባበር ማየት ለማዘን እራሱ አይቻልም።ምን ቀረና በምን ይታዘናል?እኔንስ እሼ እንደፈለገ ያድርግ እንዴት እናቴንና እህቴን ለዛውም ከነልጆ ያግዳል…ኣናቴ መንኩሳ የመሞቻ ግዜዋን በፀሎትና በምስጋና ውስጥ ሆና የምትጠብቅ አሮጌት ነች….እህቴ ገና ህይወትን አህዱ ብላ መኖር ከጀመረች አመት አልሆናትም…እኔስ በገዛ እጄ ነወ እነሱን ለምን እዚህ ውስጥ ያስገባቸዋል››
‹‹አይዞሽ ተረጋጊ….የሚሆነውን እናደርጋለን፡፡››
‹‹በቃ አሁን ደክኛል…ልተኛ››
‹‹እሺ…ከፈለግሺኝ በማንኛውም ሰዓት ደውይልኝ››
‹‹ችግር የለም፡፡››
‹‹ለእኔ ግን ባትደውይልኝ ችግር የለውም..ስትፈልጊኝ ስለሚሰማኝ ፈጥኜ መጣለሁ››በዚህ ሁሉ ጭንቅ ውስጥ ሆና እንኳን ፈገግ አስባላት፡፡
ተያይዘው በሯን ዘግተውላት ወጡ….
አሁን መኝታዬ ላይ ተኝቼ በመነፍረቅ ምንም የማመጣው ነገር የለም ስትል አሰበች…ተነሳችና የለበሰችውን ቢጃማ አውልቃ….ጥቁር ጂንስ ሱሪ ለበሰች፡፡ ከላይ ወፈር ያለ ጥቁር ሹራብ ለበሰች ፡፡ከዛ ኮፊያ ያለው ጃኬት ደረበችበት፡፡መሳቢያዋን ከፈተችና ማስታወሻዋን አወጣችና መፃፍ ጀመረች፡፡
///
👍32
አብዬት ይሄንን ነገር ከዚህ በላይ መኝታ ቤቴ ውስጥ ዘግቼ በመቀመጥ የእናቴንና የእህቴን የግድያ መርዶ አሰስክሰማ መጠበቅ አልችልም…የእኔ ነገር ያበቃለት ነው…..፡፡ለዛ አውሬ ሄጄ እጄን እሰጣለሁ..፡፡እርግጠኛ ነኝ ደቂቃዎች ሳያባክን ያስወግደኛል….፡፡ግን ከዛ ቡኃላ ቤተሰቦቼን ምንም ስላማያደርጉለት ይለቃቸዋል የሚል ተስፋ አለኝ…እና ከአንተ አንድ ነገር እፈልጋለሁ…..የጀመርነውን ነገር ከግብ አንድታደርስ…፡፡.አዎ አነሱ መቀመቅ ገብተው የእኔ ከወንጀል ነፃ መሆን ከተረጋገጠ አና በእነሱ ወንጀል ምክንያት የጠፉ የብዙ ነፍሶች የተዳፈነ እውነት ከዋጣ.. የዛኔ እኔም አልሞቱኩም ማለት ነው..እስከዛው ድረሰ ግን ነፍሴ ወደ ሲኦልም ሆነ ወደገነት አትሄድም..ይልቅስ እዚሁ በአንተ ዙሪያ እየተንሳፈፈች እቅዳችንን ከግብ እስክታደርስ በፀሎት ታግዝሀለች….ሚሽኑ በድል በተጠናቀቀበት ቀን ደግሞ በሰላም ወደምትሄድበት አንተን አመሰግና ትሄዳለች፡፡
ደግሞ ነገሮች ከተስተካከሉ ቡኃላ ቤተሰቦቼነ አደራ ተንከባከብልኝ…ካሳንም እንደወንድምህ እየው…በነገራችን ላይ በህይወቴ ካሳን ባንተ መጠን የተረዳው ሰው አላውቅም..እኔ እንኳን እንደአንተ ልረዳው ብችል ኖሮ ምን አልባት አሁን ህይወቴ የተለየ መልክ ነበር የሚኖረው….ለማንኛውም አሁን ሁሉ ነገር አክትሞላታል፡፡ይሄው ከዚህ መስታወሻ ጋር አንድ ፍለሽና አንድ ቁልፍ ትቼልሀለው፡፡ፍላሹ ስለፕሮፌሰሩና ስለግብረአበሮቹ የማውቀውን ሁሉ መራጃ የሰፈረበት ነው..ከካሳ ጋር እየተማከራችሁ የሚሆነውን አድርጉ…ቁልፉ ፖስታ ሳጥኔ ነው….ሳሙኤል ለሚባል የፖስታ ቤቱ ምክትል ሀላፊ ንግሬዋለው…ችግር ካለ እሱ ያግዝሀል..እዛ ፓስታ ሳጥን ውስጥ ሁለት የታሸገ ፖስታ አለ…..አንዱ ዶላር ሲሆን ሌላው ፓውንድ ነው..አውጣና ተጠቀምበት ፡፡በል ቸው…ለእኔ በህይወቴ በጣም ጥሩ ከሆኑልኝ ጥቂት ሰዎች መካከል አንተ አንዱ ነህ፡፡ ብሞትም አረሳህም..፡፡ቸው…..ደግሞ ወንጀለኞችን ካጠፋህ ቡኃላ አንተም መልሰህ ወንጀለኛ እንዳማትሆን ሙሉ ተስፋ አለኝ….ካለበለዚያ የሙት መንፈሴ እየመጣ ይረብሽሀል፡፡
//
ጽፋ ከጨረሰች ቡኃላ መልሳ እንኳን ሳታናበው አልጋዋ መሀከላ አስቀመጠችና በላዩ ላይ ቁልፉን እና ፍላሹኑ አኑራበት ቀስ ብላ በራፉን ከፍታ ወጣች፡፡ኮሪደሩ በደመቀ የአምፑል ብርሀን ቦግ ያለ ቢሆንም ማንም የለም …የተጫማችው ፍላት ሸራ ጫማ ስለሆነ ድምፅ ሳያሰሙ ለመራመድ ምቹ ነው….ጥግ ላይ ወዳለች አነስተኛ ክፍል ነው ያመራችው….፡፡ቁልፉን ከኪሷ አወጣችና ወደውስጥ ገባች፣መልሳ ዘጋችውና መብራቱን አበራች….ክፍሏ ውስጥ አንድ ግዙፍ ጠረጳዛ አለ ፡፡ጠረጳዛው ሙሉ በክላሽ፤ በሽጉጥ፤ በጥይቶች በጩቤና በመሳሰሉት የጦር መሳሪያዎች የተሞላ ነው….፡፡በአይኗ ከዳር እስከዳር ካየች ቡኃላ ቀላልና በኪስ ሸጎጥ ለማድረግ የምትመች አነስተኛ ሽጉጥ አነሳች፣ ውስ ስድስት ጥይቶች አሉ….በጃኬት ኪሷ ውስጥ ከተተች፣አንድ አነስተኛ ጩቤም ከጩቤዎች መካከል አነሳችና በእጇ ያዘች…መብራቱን አጠፋችና በራፉን ዘግታ ወጣች…ወደመኝታ ክፍሎ አልተመለሰችም፡፡ፎቁ መውረጃ ደረጃ ይዛ ቁልቁል ወደታች ተንደረደረች…. መኪናውን አስነስታ መሄድ አትችልም…ሞተር ስታስነሳ ንቁ የሆነው አብዬት በደቂቃ ውስጥ ነው ወደታች ወርዶ አንቆ የሚመልሳት…ስለዚህ በእግሯ ግቢውን ለቃ ወጣች…ሞባይሏን አወጣችና ራይድ ታክሲ ጋር ደወለች..ከአስር ደቂቃ ቡኃላ መጥተው ጫኗት….የፕሮፌሰሩ ሰፈር አድርሻ ለሹፌሩ ሰጠችው፡፡በሰላሳ ደቂቃ ውስጥ አደረሳት…ለማንኛውም በማለት ራቅ ብላ ወረደች….ለሹፌሩ ሳብን ከጉርሻ ጋር ከፈለችውና ሸኘችው…ወጥታ ወደፕሮፌሰሩ ቤት አመራች፡፡ለምን እሰከአሁን እንዳስቀመጠችው ባታውቅም እስከአሁን የቤቱ ቁልፍ አላት….የውጩን በራፍ አንኳኳች..ዘበኛው ሰምቶ ይከፍትልኛል ብላ ነበር..ግን ደምፅ የሚባል ነገር ከውስጥ አይሰማም….ሰዓቱ ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ስላለፈ እንቅልፍ ጥሎት እንደሚሆን ገመተችና ቁፉን ከጃኬት ከኪሷ አወጣችና ከፈተች..ወደ ውስጥ ገባች፣፣ጩቤዋን ጎንበስ አለችና የካልሲው በውስጥ ሸጎጠችና ሽጉጧን በእጇ አስተካክላ በመደቀን የዘበኛውን ቤት እየገላመጠች ወደውስጥ ዘለቀች…የሳሎኑን በራፍ ቀስ ብላ ከፈተችና ወደውስጥ ገባች፣ሳሎኑ ባዶ ነው…..ወደመኝታ ቤት ሄደች….ማንም ሰው የለም…አልጋው አልተነጠፈም ክፍሉ ጠቅላላ እንደተዝረከረከ ነው….ካዝናው ክፍት ነው…..ወደቁምሳጥኑ ፊቷን አዞረችና ቀረበችና ከፈተችው….ግማሽ ሚሆን ልብስ ተንስቶለታል….፡፡
‹‹ብሽቅ አለች….ቦታ ቀይሮል ማለት ነው..ይሄ ፈሪ..››
ያገኘችው ወንበር ላይ ቁጭ አለችና..ስልኩን ደወለች፣፣አይሰራም…..በጣም ተበሳጨች..እና ገና እሱ እስኪያገኘኝን እጄን አጣጥፌ ልጠብቅ ነው…?የተለየ ሀሰብ መጣላት..ሞባይሏን ከእንደገና አነሳችና ፌስቡኳን ከፈተች…..የእሱን ፈለገችና
እቤትህ መጥቼ የለህም…የት ነህ..?
እኔን ውሰድና እቤተሰቦቼን ልቀቃቸው..አሁኑኑ››
ብላ በመጸፍ ላከችለት ፡፡አይኖቾን ሚሴጃ ቦክሰ ላይ ተክላ መጠበቅ ጀመረች..ከ20 ደቃቃ ጥበቃ ቡኃላ በዚህ ስልክ ደውይልኝ የሚል ቁጥር ተላከላት..ወዲያው አነሳችው...ደወለች፡፡
‹‹እሺ የእኔ ውድና ተፈቃሪ እጮኛዬ››
‹ድምፅ እንዲህ ቀፋፊ ነበር እንዴ?› ስትል በውስጧ አሰበች‹‹በጣም ነው የምታስጣላኝ››መለሰችለት፡
‹‹ተይ እንጂ የእኔ ውድ ..እኔ እኮ የወደፊት ባልሽና የልጆችሽ አባት ነኝ..ለእኔ ጥላቻ አይገባኝም;;››
‹ካንተ ጋር ማውራት እራሱ በጣም ነው የሚያቅለሸልሸኝ››
‹‹እና ተስገብግበሽ ለምን ደወልሽ…?››
‹‹የት ነህ ልምጣ….››
‹በጣም ናፍቄሻለው አይደል….እኔም በጣም ናፍቀሺኛል..አሪፍ የፍቅር ምሽት እንደምናሳልፍ እርግጠኛ ነኝ››
‹‹ቤተሰቦቼን አሁኑኑ ልቀቃቸው››
‹‹ምን አስቸኮለሽ… መጀመሪያ እንገናኝ..ከዛ አብረን ሆነን እንዲለቆቸውና ተንከባክበው ይቅርታ ጠይቀው እቤታቸው ድርስ እንዲያደርሳቸው እንነጋራቸዋለን…እና ደግሞ ከመሞተሽ በፊት ሁለት ነገሮችን እንሰራለን አንደኛውና የመጀመሪያው ጣፋጭ የሆነ የመጨረሻ ፍቅር እንሰራለን….ያው የመጨረሻ እራት እንደሚባለው ማለት ነው….ከዛ ያው እኔ ችግር አስገድገዶኝ እንጂ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ላረጋግጥልሽ ስለምፈልግ ቤተሰቦችሽ እቤታቸው መመለሳቸውን አረጋግጥልሻለው…ማለት በስልክ ታወሪያቸዋለሽ.ከዛ እስከመጨረሻው እንሰነባበታለን….››
‹‹እሺ አሁን የት ልምጣ?››
‹‹አይ የትም አትምጪ.. እዛው ጠብቂኝ ፡፡አሁን መኪናና ሰው እልካለሁ....ግን ማንንም ሰው አለማስከትልሽንና የሆነ ተንኮል አለማሰብሽን እርግጠኛ ሁኚ… ካለበለዚያ በእናትሽም ሆነ በተቀሩት ላይ ቀጥታ ቃታ ስበሽ እንደገደልሻቸው እወቂ…››
‹‹ባክህ ሁሉም ሰው እንደአንተ ሸረኛ እና ተንኮለኛ ይመስልሀል አይደል.?አንተ እኮ የዳቢሎስ የበኩር ልጅ ስለሆንክ ነው.. …በል አሽከሮችህን ላካቸው ፡፡ስልኩ ዘጋችው..ትንፋሽ አጠራት….በፍራቻ ብርድ እየተንዘፈዘፈች ወደመታረጃዋ የሚወስዳት ሰው እስኪደርስ መጠበቁን ተያያዘችው፡ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍26😢91🥰1
ለአንድ ሆድ
         መሸዋዎድ

ለአንድ እንጀራ
                በገጀራ

ላይባርከን
          መጨካከን

ላያፀድቀን
        ጉሮሮ አንቀን
👍4216
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ


ከአዲስ አበባ ፍልውሃ በታች ከማህተማ ጋንዲ መንገድ መስመር ከብሔራዊ ስታዲዬም ብዙም ሳይርቅ ከግዮን
ከኢትዮጵያ ከሒልተን
ሆቴል... ለሚመጡ እንግዶች አመች የሆነው የ“ጎጆ” ምግብ ቤት ግቢው በመኪና ተጣቧል።

ቢኤም ደብሊው መኪና በዘበኛው መሪነት ቦታዋን ይዛ እንደቆመች ሁለቱ እንግሊዛውያን ወደ ምግብ ቤቱ አመሩ። እሷ ቀደም እሱ ደግሞ ከኋላዋ ተከትሏት ሲገባ እንደ ቀልድ ቁመናዋን አስተዋለ: ፀጉሯ አጠር ከማለቱ ሌላ ስትሄድ የሚደንሰው ዳሌዋ አለ
'' የለም' »አስኝቶ የሚያወራርደው ወገቧ
ያው ነው።ስትጠመጠም እንደ ላስቲክ እየተሳሳበ በሰራ አካላቱ የሚስለከለከው አካሏ ለውጥ የለውም። ልክ እንደ ዛሬ ሁለት ዓመት ከስድስት ወሩ ነው ጥቁር ቲሽርት እንደ ወትሮው ሁሉ ጂንስ ሱሪ ለባብሳለች።ወገቧና አንገቷ ልብሷ አልደረሰበትም:

የሴት እምብርት ሲያይ ጎሮሮውን እንዳነቁት ሁሉ አይኑ የሚፈጠው ስቲቭ አጎጠጎጤ ጡቷን ደረቱ ላይ አስደግፋ ለጠጥ ብላ
ሽቅብ ተስባ ስትስመው እንደ ህፃን ልጅ በእቅፉ አልሞላ ስትለው እቅፉን ጠበቅ አድርጎ እንደ ቄጤማ አካሉ ላይ የለጠፉት ትዝ
አለው።

ገባ ብለው ክፍት ቦታ ሲያማትሩ አስተናጋጁ በስተግራ በኩል ግድግዳው ጥግ ባዶ ቦታ አሳያቸው።

የሲሊን ዲዮን ዜማ በለሆስታ ይሰማል ካርለት ድምፀ መረዋ ካናዳዊት አቀንቃኝ ስሊን ዲዮን ኒወርክ “ብራንድ ዌይ
ዳንሰሮች ጋር አይኖቿዋን እያስለመለመች, እግሮችዋን መሬት
ለመሬት እየሳበች ወለሉ ላይ እየተኛች...በለበሰችው ጃፖኒ እርቃን የሆነውን ትከሻዋን እየላሰች ስትዘፍን ስላየቻት ይበልጥ ወዳታለች::

እና! ገና "ከመግባታቸው በፊት የምትወደውን ዜማ ስትሰማ የደስታ ስሜት ተሰምቷታል።

አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ይዞላቸው መጣ: ሁለቱም
ዝርዝሩን ተቀበሉና በፀጥታ አንብበው ካዘዙ በኋላ ጨዋታቸውን ሊጀምሩ ሲሉ

“የሚጠጣስ?” አይኖቹን ግራና ቀኝ እያዟዟረ  ጠየቀ
አስተናጋጁ።

“ማርቲኒ” አለችው ካርለት

“ነጭ ወይንስ ቀይ ማርቲኒ” የሾለ ፊቱን ወደ ፊት አስግጎ ጠየቃት።

ነጭ ይሁንልኝ አለችው። አስተናጋጁ ለጨዋታ
መጣደፋቸውን ተረድቶ ይቅርታ በሚጠይቅ አስተያየት ስቲቭን
እያየ አገጩን ሽቅብ ሰበቀ።

“ብሳክ ሌብል” አለው።

ካርለት ቦርሳዋን ወንበሩ ላይ አንጠልጥላ ፈገግ እያለች።

“እሺ ስቲቭ! ስትለው ስቲቭም ወንበሩ ላይ ጠረዼዛው እያስጠጋ ፈገግ ብሎ አንገቱን ወዘወዘ ደህና ነኝ ለማለት።

“…ኢንግላንድ መልም ጊዜ አሳለፍሽ?

“ከናቴ ከጓደኞቺ ጋር በመገናኘቴ ደስ ብሎኛል። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ግን ደስተኞች አይደሉም:: ሁሉም ያለሙትን ህይወት
መኖር የቻሉ አልመሰለኝም። ከጎይቲና  ከከሎ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜም ባመዛኙ እንግዳ ለሆነባቸው ስልጣኔ እያንዳንዷ እንደ ህፃን
ልጅ ማስረዳቱ አድካሚ ቢሆንም ወድጄዋለሁ:

“ጥናቴን በተመለከተ ማንቸስተር ያቀረብሁት ዝግጅት ለአማሪዬና ስብሰባ ተሳታፊዎቼ ጥሩ ስሜት የፈጠረ በመሆኑ ደስ ብሉኛል። ከዚህ ተጨማሪ ከማንቸስተር ዩንቨርስቲ አዳራሽ ስንወጣ ብዛት ያላቸው የ" ጋርዲያን የሄራልድ ትሪቡን…
ጋዜጠኞች ለኔ ለጎይቲና ለከሎ ያቀረቡልን ጥያቄ የሰጠነው መልስ  በቤቱ ውስጥ የነበረው የመግባባትና የማድነቅ እንድምታ ስቃይን እሚያስረሳ ነበር። “በተለይም ሴቶችን አስገድዶ መድፈርና
የወሲብ ብዝበዛ በሐመር ምድር የተወገዘና የማይፈፀም ፀያፍ ጉዳይ
መሆኑን ላስረዳቸውና ጎይቲ “ሴትን ያለፍቃዷ ማን ያስቸግራታል ደሞ." ያለችው ስሜታዊ አባባል ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው ውስጥ
ዋናው ነበር።

“በተረፈ ለአንድ ሳምንት ስፔን ለአንድ ሳምንት ደግሞ
ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሄጄ ነበር: እንደ ማይክል ጃክሰን በዚች ፕላኔት ካለው ወፈ ሰማያት ህዝብ መሀከል የማደንቀው ሁለት ሰው ነው:: ማንዴላንና ማር ትሬዛን ብዬ ባልደመድምም በደረጃ ከማይክል አስተያየት የማላርቀውን ማንዴላንና የሱን አመራር
በቅርብ ለማየት እድል ለማግኘቴ የተደሰተሁ ሲሆን በጆሀንስበርግ ሰሜን ማዕክል ብራምፎንቴን በሚገኘው ዊትስ ዩንቨርስቲ የአባቴ ስራዎች በመታሰቢያነት ሲቀርቡ ንግግር ማድረግ መቻሌሞ ጥሩ አባት ሞቶም የደስታ ምንጭ እንደሚሆን ለማመን ችያለሁ።

የነፃነት ረጅም ጉዞ በሚል
ርዕስ በ1994 ዓ.ም
በማክዶናልድ አሳታሚ ኩባንያ በኔልስን ማንዴላ የታተመው የ ባለ 617 ገጽ መጽሐፍም በመርፌ ቀዳዳ የሚታይን ብርሃን ተከትሎ
ከፀሐይ አካል መድረስ መቻሉን የተማርኩበት ነበረ።

“የፍቅር ህይወቴን በተመለከተ ግን እግሮቼ ሁለት መሰላል ላይ ናቸው:: ባል የማግቢያዬ ልጅ የመውለጃዬ ጊዜ እያለፈ
መሆኑን ሳስብ አንጀቴ በሃዘን መኮራመቱ ባይቀርም የሰለጠነው
ዓለም ለፍቅር ቀረቤታ ያለው አነስተኛ ግምት የመመዘኛ ዝባንዝንኬው በተፈጥሮው ዓለም ደግሞ ህይወቱን ላልኖረው ሰው
ያለው አስቸጋሪነትና የፍቅር  አለመጣጣም... ለጊዜው መምረጥ ከሚያስቸግር ሁኔታ ላይ እንደጣለኝ ነው የምረዳው።

“እዚህ  ላይ ግን ልገልፅልህ የምወደው እንደማንኛውም
ሰው መጭው ህይወቴ ምን መምሰል እንዳለበት ሳስብ ብዥ ብዥ እያለ የሚታየኝ ህልም አስጨናቂና አሳሳቢ ቢሆንም ከምንም በላይ
የምፈልገው በአባቴ የሰው ልጅ ሕይወት ምርምር ጎዳና መጓዝንና ለሙያዬ መሉ መስዋዕትን መክፈል ስለሆነ መፅናኛዬ ሚዛኍን
የደፋ ነው፡፡ ስለዚህ ደስተኛነቴ አሁንም ከቁጥጥሬ አልወጣም ብላ
ፈገግ አለች::

ስቲቭ ሃሣቧን ያዝኩት ሲል ወዲያ ስታላጋው ወዲህ
ስታጋጨወ ቆይታ እንደ ጥሩ ተውኔት ጨዋታውን ባላሰበው መንገድ ደመደመችበት።

ለጥቂት ጊዜ ሁለቱም በየግል ሃሣባቸው ተውጠው እንደቆዩ ፈጣኗ ካርለት ከነበረችበት የሃሣብ ግልቢያ ድንገት ልጓሟን ስባ የስቲቭን ቀኝ እጅ በቀኝ እጅዋ ቀስ ብላ ጫን አድርጋ
ሳታስደነግጠው ሳታሽብረው ሃሣቡን ሳታምታታበት ትክ ብላ
መረጋጋቱን ካስተዋለች በኋላ፡-

“ስቲቭ! አንተስ ከተለያዬን በኋላ ጥሩ ጊዜ አሳሰፍክ?"
አለችው።

ዘናና ፈገግ ብሎ  “በስራዪ ብዙም ውጥረት አልነበረኝም የዲፕሎማት ትልቁ ሥራ ግንኙነት መፍጠር፤ የአገሪቱን
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አዝማሚያ መከታተል፤ ተስፋን መመገብ ገደብ አልባ የሆነ ቃል ኪዳን መግባት በመሆኑ በፈቀደልኝ የጉዞ ፍጥነት እያሽከረከርኩ ስራዬን ለመወጣት ሞክሬያለሁ፡ የኢትዮጵያ ኑሮ ግን ከብዶኛል" አላት

እንዴት? የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ!" አለችው ውስጡን
ጠልቃ ለመመልከት አይኖቹን እየፈለገች።

ካርለት የሰዎችን አይን በማየት ስለ ሁኔታዎች ምንነት ለማወቅ እንደሚቻል በስነ ልቦናዊ ትምህርቷ ታውቃለች። አንድ ሰው ያስጨነቀው ነገር ትዝታውን• ፍቅሩን ጥላቻውን... ሲገልፅ
የአይኖቹ ኳሶች የት እንደሚሆኑ ወዴት እንደሚዞሩ ከስነ አዕምሮ
ባለሙያዋ እናቷ ተምራለች። ሌላው ቀርቶ እውነትና ውሸት አባባልን የአይንን እንቅስቃሴ አይታ በከፊል መግለጽ ትችላለች።
ከዚህ በተጨማሪም የአንድ ሰው አመለካከቱ በመስማት ወይንም በማየት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ከአገላለፁ በመረዳት አይኑና ሃሣቡ  ከሚሰጣት ግንዛቤ ግንኙነቷን ለመመዘንና ለመለካት
አትቸገርም። ለዚህም ካርለት ስቲቭ ሲያወራት አይኖቹን ትፈልግ ነበር: ኋላ ግን አይኑን በአይኗ ያዘችው እንቅስቃሴዋንም
አስተከለችና፡-

"...የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ? አለችው ደግማ ስቲቭ
በአፍንጫው ጫን አድርጎ ተነፈሰና፡-
👍22
ይህች አገር አዲስ ነገር የሚጠበቅባት አይደለችም፡
መምሸት መንጋቱ ያለመቆሙም የተፈጥሮ ስጦታ በመሆኑ ሊገዛ
ስለማይችል ነው። ምን መሰለሽ! ህዝቡ አባቶቹ የሰሩለትን ታሪክ ብርድ ልብስ ተሸፋፍኖ እንደ ህፃን የተኛ ነው ቢበርደው
እንደተኛ ማልቀስ! ቢቆረቁረው እየተገላበጠ እዚያው መዟዟር!
ተባይ ቢበላው ማከክ እንጂ. ከተኛበት ተነስቶ ምሬቱን የሚገልፅ አይደለም። መለወጥ የሚሻ አይደለም። እንቅልፍ ስንፍና ምቀኝነት የደበተው ነው።


(እንግዲህ ተመልከቱ የዛሬ 20 ዓመት የተፃፈ መፅሀፍ ነው አሁንም ግን የተለወጥን አይመስለኝም 😏)


"ጎኑ ለም መሬት ከጓሮው ወንዝ እየፈስሰ ለልመና
የሚዘረጉ እጆች ቁጥር ግን በአፍሪካ ለምነት ያንሳቸዋል ከሚባሉት ከቡርኪናፋሶ እጅግ የበዛ ነው" ሲል የአዘዙት ምግብ መጣ።

አስተናጋጁ ምግቡን ካቀራረበላቸው በኋላ ፈገግ ብሎ “መልካም ራት አለ።

“ቴንኪው” አለችው ካርለት እሷም ፈገግ ብላ ከዚያ
በፀጥታ ሲመገቡ ካርለት ገልመጥ ገልመጥ እያለች ምግብ ቤቱ ውስጥ ያሉትን አማተረችና

“ኢትዮጵያውያን ሴቶችና የውጭ ወንዶች የተጣጣሙ ይመስላል: ልክ ነኝ?" አለችው ፈገግ በማለት ራሷን ለዓመል ወደ
ግራ ሰበቅ አድርጋ በግራ እጅዋ ወደ ፊቷ የመጣውን ፀጉር እየመለሰች። እሱም ያየችውን በአይኖቹ አማትሮ አፉን በናፕኪን እየጠረገ፡-

ልክ ነሽ ብሎ የኮረኮሩትን ያህል በተቀመጠበት
እየተርገፈገፈ ሳቀና “ብዙው የውጭ ዜጋ በተለይ ወንዱ ቼኮሌት ከመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር መውጣትና እንደ አይስክሬም እየላሱ ጣምናቸውን ማጣጣሙን ይወዳል:

“ችግሩ ግን አንች ለስሜት እርካታ ስትቀርቢያቸው እነሱ ግንኙነቱን ክብደት ይሰጡትና አፈቀርሁ' እያሉ ሲሟዘዙ ብዙው
በድርጊታቸው ግራ ይጋባል። እየደወሉ ጤና ይነሳሉ::

“ቆንጅት! ትናንት ጥሩ ትዝታ አሳልፈናል:: ዛሬ ደግሞ
የራሱ ትዝታ ይፈልጋል: መረብን ጥሉ አዲስ የሚፈራገጥ አሳ ይዞ ትዝታን በትዝታ ማነባበሩ ወደ ፊት አካል ሲደክም የሚነበብ ጥሩ ህሊናዊ መጽሐፍ ይወጣዋል። ስለዚህ የትናንቱን ትዝታ
በህሊናሽ ጓዳ በጥንቃቄ አስቀምጭውና ዛሬን ደግሞ ለመዝናናትና
ለእርካታ አውይው፤ ያለፈ ነገር ስታስቢ ዛሬ እያዘነብሽ አይንጎድ…ስትያቸው በዚያ ትላልቅ አይናቸው እንባቸውን ያፈሱታል:

“ቶሉ ያፈቅራሉ ማለት ነው?”

“አይደለም በስተጀርባው ሚስጥር  አለው ከንፈርሽን
ይስሙና ከገንዘብ ቦርሳሽ ውስጥ አንጥፈው መተኛት ይፈልጋሉ፡ ከዚያ ቀፎው እንደተነካ ንብ ዘመድ አዝማዷ ይከብሻል: አንዱ
ገንዘብ ሌላው ውጭ አውጭኝ... ባዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃ
መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣሻል እዚች ሃገር መዝናናቱ ፍቅሩ ጋብቻው በጋራ ነው::ግላዊ ህይወት እንኳን ልታይ ብትናገሪ
ብትናገሪ  እሚረዳሽ የለም
ኢትዮጵያውያን የአምስት ሣንቲምን እንጂ የአንድ ደቂቃን ጥቅም አያውቁም:: ስለዚህ የደስታ ጊዜሽን እንዳይሻሙሽ ቋሚ አድራሻሽን ሳትገልጭ ዛሬ የተጠቀምሽበትን ሸሚዝ ጥለሽ ነገ ራቅ ብለሽ ሌላ
መሽመት ሆኗል የውጪው እንግዳ ምርጫ" አለና ንግግሩን ገታ አድርጎ ፈገግ በማለት ትኩር ብሎ አያት።

"እኔ ግን የነገርኸኝን ሁሉ መቀበሉ ይከብደኛል። በእርግጥ እድል ቀንቷቸው በበለፀጉ አገሮች የተወለዱ ወንዶች የአገራቸውን
ሴት በፍቅር ካልሆነ በጥቅም እንዳልንሽ ሁኝልን ቢሏት ከሃፍረት
በስተቀር ሰሚ ጆሮ ስለማያገኙ ጋጠ ወጥ ፍላጎታቸውን በሦስተኛው
ዓለም አገር ሴቶች ላይ መፈፀሙ የተለመደ በመሆኑ ድርጊቱ
ቢያሳፍረኝና ቢያሳዝነኝም ሁኔታው አዲስ አይደለም።

“ያልገባኝ ግን መጀመሪያ በቋንቋ ችግር ምክንያት ከህዝቡ ጋር ልትቀራረብ አለመቻልህን ገለፅህልኝ፡ ቀጥለህም ስለ አዲሳባ
ሴቶች ባህሪ  ምናልባትም በህይወት አስገዳጅነት በሽርሙጥና ሙያ
የተሰማሩትን ባህሪ ገለፅክልኝ። እና ኢትዮጵያ ማለት አዲሳባ ማለት
ነው? እውን ይህ የሴቶች ባህሪስ የአዲሳባ ሴቶች ባህሪ ነው? እንዲህ አይነቱ ገጠመኝ የሌለበትስ አገር አለ? ከሌለስ ኢትዮጵያን
ከሌሎች ምን ለይቷት እዚች አገር መኖር አስጠላህ?" አለችው፡

“ይህን እንኳ ያነሳሁት ስለ ኢትዮጵያ ሴቶችና ስለ ውጭ ዜጎች ግንኙነት ስለጠየቅሽኝ እንጂ እዚች አገር ለመኖር የከበዱኝ
ምክንያቶች ብዙ ናቸው" ብሎ ጨዋታቸውን ሊዘጋው ፈለገ።

“ማንኛውም ህዝብ ቋንቋውን ካወቁ ከተግባቡት ውስጣዊ ውበቱን ማግኘት እንደሚቻል በቋንቋ ድልድይነት መገናኘት
ካልቻሉ ግን አለመቀራረብና አለመተዋወቅ ስለሚኖር  መግባባት መጥፋቱና ሆድና ጀርባ መሆኑ ያለ ነው።
“የህይወት ልምድ ልዩነት በአስተሳሰብ በአኗኗር ዘይቤ በአቀራረብ... የሚኖረው ተፅዕኖ ባይቀርም ቋንቋ ግን በመካከል ያለን ቁስል ያክማል

“ኢትዮጵያ ደግሞ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ
ባህሏም የዛኑ ያህል የተለያየ ግን ተዋሀዶ ጥሩ ቀለም የፈጠረ ነውና አንድ የውጭ ዜጋ ስለ ግለሰቦች ባህሪ እያወራ
“ኢትዮጵያውያን' በሚል ሊደመድም አይገባም ኢንግላድ የግብረሰዶማዊ አገር እንደማትባለው ሁሉ የዚች አገርም ግላዊ
ባህሪ በጥቅል ሳይሆን በግላዊ አመለካከት መቅረብ አለበት:"

“ይቅርታ!  የስነ ሰብዕ ተመራማሪዎች ጓዳዩን የምታውቁ እናንተ ስለሆናችሁ ለስሜታዊ አባባሌ በግል ካልሆነ ለሚዲያ ሃሳብ ስለማላቀርብ ጨዋታችንን ለጊዜው እዚህ እንግታውና ለምን አንድ ሃሳብ አላቀርብም:: የጃዝ ሙዚቃ ለማየት ኢምፔሪያል ሆቴል መሄድ ወደ ወቅቱ የአዲሳባ መዝናኛ? አላት መልሷን
ለመስማት አቆብቁቦ::

“ጃዝ ሙዚቃ መስማት ለነፍሴ ሐሴትን ይፈጥርላታል::
አዲስ ነገር ደግሞ ሁሌም ቆንጆ ነው..” ብላው ወጡ ቢ ኤም ደብሊዋ ወደ አዲስ አበባው አለም አቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ አቅጣጫ
ተሽከረከረች:.

💫ይቀጥላል💫
👍24
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ 13
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ከመኝታ ቤት ወደሳሎን እየተመላለስች በናፈቆት መጠበቅ ጀመረች፡፡.‹‹ሰው እንዴት ወደ መታረጃ ቄራው ወስዶ ሊያርደው የሚመጣን ሰው በናፍቅት ይጠብቃል?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡‹.በቃ ሰልችቶኝ ነው….ነገሮች ሁሉ በፍጥነት እንዲጠናቀቁና ሁሉ ነገር እንዳልነበረ እንዲሆን ስለምፈልግ ነው››ስትል መልስ ሰጠች፡፡‹‹ቤተሰቦቼን ማለት እናቴንና፤ እህቴን ወደቤታቸው በሰላም እንዲመለሱ ማድረግ ከቻልኩ ቡኃላ እኔ እስከወዲያኛው መሄድ እፈልገለሁ…›ልክ የሆነ አድማጭ እቤት ውስጥ ኖሮ ለእሱ የምታወራ ነው የሚመስለው፡፡
እቅዷ ጠላቶጮ ከወሰዷት ቡሃላ ወላጆቾን አስለቅቃ ዝም ብሎ በፀጥታ መሞት አይደለም…ከመሞቷ በፊት በተቻለት መጠን እንደምንም ብላ ዋነውን ጠላቷን ….(እውነቷን እና ህልሞን የቀማትን ሰው )ህይወቱን ለመንጠቅ ቆርጠለች...፡፡ለዛ ነው ከቤት ስትነሳ ሽጉጥም ጩቤም የያዘችው…አንዱ ባይመቻት በሌላው ለመሞከር..የያዘችውን ጩቤና ሽጉጥ እሱ ጋር ከመድረሷ በፊት በፍተሻ አግኝተውባት ቢነጥቋት እንኳን በጥርሷም ቢሆን አንገቱ ላይ ተጣብቃ ጉሮሮውን በመበጠስ ሳትገለው ላለሞት ወስናለች…..፡፡
ለዘህ ደግሞ አሁን እሱ ሲደውልላት አንቺን ከመግደሌ በፊት የመጨረሻ ፍቅር አብሬሽ መስራት እፈልጋለው ብሎታል…(እንዲህ አይነት ቆሻሻ ወሲብ መፈፀምም ጭምር ልክ እንደሌላው ፍቅር መስራት ተብሎ ለምን እንደሚገለፅ አይገባትም….)እሷም ብትሆን እሱን በተገኘው አጋጣሚ ለመግደል ወሲብ የመፈፀሙን ሀሳቡ በጣም ወዳዋለች…፡፡
ሰው በወሲብ ፍላጎት ላይ ሲሆን በአካባቢው ስለሚከናወኑ ሌሎች ነገሮች የሚሰጠው ትኩረት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስለሚጠፋ ….እሷ ንቁ ሆና እሱን ለማስወገድ የሚያግዛትን አጋጣሚዎች ታገኛለች፤ለዛ ነው ሀሳቡን የወደደችው፡፡ይሄንን ክፍት በደንብ ልትጠቀምበት ወስናለች…‹‹.አዎ አልጋ ላይ ይዤው ወጣና ለዛላለሙ ተኝቶ እንዲቀር አደርገዋለሁ››ስትል ወሰነችና …አዎ ያንን ካደረገች በህይወቷ ምንም የሚቆጫት ነገር አንደማይኖር ተስምቷታል…ያው እሷ እንደዛ አሰበቸ እንጂ ሰው ከሞተ ብኃላ ወደኃላ ተመልሶ የሚቆጭበት እድልም ፍላጎትም እንደማይኖረው የታወቀ ነው፡፡
መጠበቁ ደከማት…መልሳ ለፕሮፌሰሩ ልትደውልለት አሰበች….‹‹ድውዬ ምንድነው የምለው? ሰዎችህ ፈጠን ብለው መጥተው አይወስዱኝም እንዴ እስከአሁን አልደረሰሱም….ፍጠኑ በላቸው›› ነው የምለው..ብላ አሰበችን ፈገግ አለች፡፡ሰው በእንደዚህ አይነት የመጨረሻ ጭንቀት ላይ ሆኖም ፈገግ ማለት መቻሉ አስገረማት…..ቆይ ትንሽ ልታገስ አለችና .ወደ በረንዳ ወጣች…ወደበረንዳ የወጣችው አየር ስላጠራት ነው…ግን እንደወጣች ወደፊት ለፊቷ ስታይ የውጩ በራፍ ወለል ብሎ ተከፍቷል…
‹‹ማነው እንዲህ በልቅጦ ከፍቶ የተወው?››ስትል ጠየቀችና ወዲያው እራሷ ቅድም ከፍታ ስትገባ መልሳ እንዳልዘጋችው ትዝ አላት፡፡: …‹‹ሄጄ ልዝጋው›› በማለት መራመድ ከጀመረች ቡኃላ ልታደረግ ያሰበችው ነገር ትርጉመ ቢስ እንደሆነ ስለተረዳች ተወችው፡፡
‹‹….ምነው ይሁንልኝ ብዬ ነው በራፉን ምዘጋው…?እንደውም እንዲህ ተበልቅጦ መከፈቱ የሚወስዱኝ ሰዎች ሲመጡ ገና ከማንኳኳት ቀጥታ ገባ ብለው ክንዴን ይዘው በማንጠልጠል መኪናቸው ውስጥ ወርውረውኝ ይዘውኝ እንዲሄዱ ቀላል ይሆንላቸዋል›› በማለት አስባ ወደኃላዋ ልትመለስ ስትል ከውጭ በራፍ በቀኝ በኩል ብቅ ጥልቅ የሚል የሰው አንገት ያየች መሰላት….‹‹እርግጥ የእውነት አይቼያለሁ ወይስ ተመሳስሎብኝ ነው?››እራሷን ጠየቀች፡፡
ለአንድ ሰከንድ ያህል እንደመጥፋት አለና መልሶ አንገቱን አሰገገ…
‹‹ምን አይነት ፈሪ ሰው ነው የላከው…እራሴ ልሂድለት›› አለችና በእግሬ ካልሲ ውስጥ የሸጎጠቻውን አነስተኛ ጩቤ እና በወገቧ የሻጠችውን ሽጉጥ በትክክል ቦታቸው መኖራቸውን አረጋገተችና በረንዳውን ለቃ ያለምንም ፍራቻ ወደውጭ ተንቀሳቀሰች…ለካ ፍራቻ ተስፋ ሲኖረን ነው ውስጠችንን በማራድ እስክንንቀጠቀጥ ድረስ ሚቆጣጠረን?››በማለት አሰበችና የፍራቻ ስሜት ስላልተሰማት በጣም ተገረመች፡
በራፍ ላይ ደረሰች…‹‹ማነህ ?የምን ድብብቆሽ ነው….?ና ውጣና… ወደምትወስደኝ ቦታ ውሰደን..››ብላ ከበረፉ አልፋ ወደውጭ ሙሉ በሙሉ ወጣች….ድብብቀሽ ከሚጫወተው ሰውዬ ጋር ፊት ለፊት ተላተመች….ግዙፍና ዝርጥርጥ ነገር ነው.. በደንብ ተጠግታው በትኩረት ስታየው ማንነቱን አወቀች…እናም ከውስጧ ተሟጦ ጠፍቶ የነበረው ፍራቻ ከየት ተለቃቅሞ እንደመጣ ሳታውቅ ሰውነቷን በመላ ወረራት..፡፡
..ተንደርድራ አንገቱን አንቃ ጎተተችና ወደ ጊቢው ውስጥ አስገባችው…አንገቷን ወደውጭ አስግጋ ግራና ቀኝ በመገለማመጥ እንደዛ ሰታደርግ ማንም እንዳላያ ለማረጋገጥ ተመለከተች….በግራም ሆነ በቀኝ ያለው መንገድ እንቅስቃሴ አላባና ጭር ያለ ነው… በራፉን ጠርቅማ ዘጋችው፡፡
‹‹ምን እየሰራህ ነው…?ከየት መጣህ .?እንዴት መጣህ……..?››አንገቱን እንዳነቀች ሰውነቱን በንዴት በማርገፍገፍ የጥያቄ ናዳ አወረደችበት፡፡
‹‹ነግሬሽ ነበር እኮ…በፈለግሺኝ ጊዜ ባትደውይልኝም ከጎንሽ እገኛለሁ ብዬሽ ነበር››አላት ካሳ ባደረገው ነገር በመኩራት፡፡
‹‹አይ ካሳ…እኔ መች ፈለኩህ…?ለዛውም በዚህ ወቅት… እዚህ ቦታ እንዴት አንተን ልፈልግ እችላለሁ?›
‹‹እና አብዬትን ነው የምፈትፈልጊው?››
‹አትቀባጥር…እኔ ይሄንን ጉዳይ በራሴ ነው መፍታት የምፈልገው….አሁን እዚህ ከእኔ ጋር ሲገኙህ ስመውና ጋብዘው የሚለቁህ መስሎ ነው….?ከእኔ ጋር አንድ ላይ ነው ሚገድሉህ››
‹‹እሱንማ አውቄ ነው የመጣሁት?›
‹‹…ሞት እኮ ተኝቶ መነሳት አይደለም››
‹‹አውቃለሁ ሞት ተኝቶ መነሳት ሳይሆን ተኝቶ መቅረት ነው››
‹‹እና ከእኔ ጋር ለመሞት…›አረፍተነገሩን መጨረስ ከበዳት
‹አዎ ካንቺ ጋር መኖር ቢያቅተኝ መሞት ያቅተኛል?››
‹‹ለመሆኑ እንዴት መጣህ? እንዴትስ አገኘኸኝ?››
‹‹ከቤት ሹክክ ቡለሽ ስትወጪ… ተከተልኩሽ….ተክሲ ስትጠሪ እኔም ታክሲ ጠራሁና ከኃላ ተከተልኩሽ..እናም እዚህ ቤት እንደገባሽ አየሁ››
‹‹ለምን እንደዛ አደረክ…..?እየጎተች ወደቤት ይዛው ገባችና የሳሎኑን በራፍ ዘጋችና..ወደማያልቅ ጥያቄዋ ተመለሰች…
‹‹ለመሆኑ ስትወጣ አብዬት አላየህም?››
‹‹አይ ያንቺ ጀግና ጠባቂ ዛሬ ተሸውዶል….አንቺ ሸውደሽዋል….እኔም ሸውጄዋለው…ይሄ ማለት የምታስቢውን ያህል ጀግና ልዑል አልነበረም ማለት ነው…?ይሄኔ መሸወዱን አውቆ ያንን ከንኪ ፀጉሩን በንዴት እየነጨ ነው…..ንዴቱን እያየሁ ብዝናና ደስ ይለኝ ነበር፡፡››
‹‹አሁን የእሱ መሸወድና መበሳጨት ነው የሚያሳስብህ...ወይስ ያንተ ጅልነት ነው››
‹‹ጅልነት ስትይ››ለንቦጩን በኩርፊያ መልክ ወደፊት ዘርግፎ ጠየቃት
‹‹መቼስ ብልጥ ብትሆን እኔን ተከትለህ ቀጥታ እዚህ ድረስ ህይትህን ለማጣት አትመጣም ነበር››
‹‹ቀሺም ነሽ››አላት እስከአሁን እያደረገ ያለውን ነገር የእውነት ስላልተረዳችው ተበሳጭቶ
‹‹ማለት?››
‹‹ሞትን ይሄን ያህል ትፈሪያለሽ ማለት ነው?›
‹‹እኔማ መፍራት አቁሜያለሁ...ለመሞት በቁርጠኝነት ነው የመጣሁት…አይገባህም እንዴ አሁን ስለአንተ ነው እየፈራው ያለውት››
‹‹ስለእኔ አትፍሪ..አብሬሽ ለመሞት ለዘመናት ስፀልይ ነበር….እንደውም ጥሩ የፍቅር ድምዳሜ ነው››
‹‹የእውነት ይሄን ያህል ታፈቅረኛለህ ማለት ነው
👍323
‹‹ሀይ እስኩል እያለን ማለቴ አንቺን ማፍቀር የጀመርኩ ሰሞን ስለመልክሽ አብዝቼ አስብ ነበር።አፍንጫዋ ቀጥ ያለ ነው...አይኖቾ ትንሽ ደፍረስ ያሉ ናቸው..ትንሽ ውፍረቷን ብትቀንስ መልካም ነበር...የቀኝ ጡቷ ለምን ከግራው ተለቀ...እኚህንና መሠል ጥያቄዎች ደጋግሜ ጠይቅ ነበር።እየዋለ እያደረ ግን ጥያቄዎቼ እየቀነሱ እያነሱ መጡና በስተመጨረሻ ከነጭራሹ ጠፉ።አሁን መልክሽና መልኬ ሁሉ ይምታታብኛል።ተኝቼ ስለእኛ ሳስብ የትኛው መልክ የእኔ የትኛው ደግሞ የአንቺ እንደሆነ ይወሳሰብብኛል።አንቺ በጊዜያቶች ቆይታ ሌለኛዋ እኔ ሆነሻል። ስትስቂ እንኳን ለሁለታችንም እየሳቅሽ ያለሽ ነው የሚመስለኝ።አይኖችሽ ላይ ጉድፍ ስመለከት የራሴን አይን ዳብሳለሁ ጉድፉን ላነሳልሽ ኦኮ ነው።እራሴን የማፈቅረውን ያህል አፈቅርሻለሁ።አጠገቤ ብትሆኚም ወይንም ከእኔ በኪሎ ሜትሮች እርቀሽ በሌላ ሰው ክንድ ውስጥ ብትሆኚም እኔ ለአንቺ ባለኝ የፍቅር ስሜት ላይ ለውጥ የለውም…ያው ስትኖሪ ከኖርኩ..ስትሞቺም መሞት አለብኝ..ለዛ ነው››አላት በፍፅም መመሰጥ፡፡
የእንባ ነጠብጣብ በጉንጮቾ ላይ ተንኳለለ….ይሄንን የመሰለ ህልማዊ የፍቅር እድል ማባከን እንዳልነበረባት ተሰማት…..‹‹እስከዛሬ ከሰማዋቸው ድንቅ የፍቅር ውዳሴዎች መካከለ ከእዚህ ሚስተካከል የለም…በእውነት ይሄ ለእኔ የመጨረሻ ስንቄ ነው…..በጣም ተፈቃሪ ሰው እንደነበርኩ እያሰብኩ እንድሞት ስላደረከኝ አመሰግናለሁ››አለቺው፡፡
‹‹አዎ አብረን ነው የምንሄደው ምንም መሰነባበት አያስፈልግም..….እዛም ከሄድን ቡኃላ ብዙ ብዙ ስለአንቺ የሚሰሙኝን ነገሮች በግልፅ ነግርሻለሁ..እንዲህ በደስታ የሚያስለቅስሽ ከሆነ ምንም የምደብቅሽ ነገር አይኖርም…ለዛ ቃል እገባልሻለው፡፡እንደውም እኮ እኔ እድለኛ ነኝ..ከፕሮፌሰሩም ሆነ ከአዲሱ አፍቃሪሽ አብዬት ይሄው በጥበብ ነጥቄሽ ለዘላለም ይዤሽ ልሄድ ነው..በጣም ደስ የሚል ነገር ነው››አላት በመፍለቅለቅ፡፡
ትኩር ብላ አየችው ‹‹ለመሆኑ ምኔን ነው የምትወድልኝ?››ስትል መልሱን ለመስማትበመጎጎት ጠየቀችው
‹‹በእውነት ይሄንን ከዚህ ብዬ የማበላልጠው ነገር የለም…ምንም ያማልወድልሽ ነገር የለም….ይልቅ ስለእኔ ምኔን ነው ምትጠላው ካልሺኝ ምን አልባት ልመልስልሽ እችላለሁ?››
‹‹ያው እኮ ነው…..እሺ ስለእኔ ምኔን ነው ምትጠላው?››ጥያቄውን በሚፈልገው መልኩ አስተካከለችለት፡፡
‹‹ኩርፊያሽን ወይም ዝምታሽን››
ያልጠበቀችው መልስ ነው‹‹ምን ማለት ነው…?››እንዲያብራራት ፈለገች
‹‹ምን መሰለሽ…ከድሮም ጀምሮ ጩኸትሽ አያስደነግጠኝም...ቁጣሽ አያስፈራኝም...ለቅሶሽም አንጀቴን አያላውሰውም...ብዙ ጊዜ ግን ዝምታሽ ጥልቅ ስለሆነ ውስጤን ያርደዋል...ዝም ስትይ የምሸሸግበት ጥጋት አጣለሁ...ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሁሉ ግራ ይገባኛል...ጌታ ሆይ አንበቷን ክፈት ከፅሞናዋም መንጭቀህ አውጣት ብዬ ሁሉ ፀልያለሁ። አዎ ነቅታ እንድትረብሸኝ..በነገር እየሸነቆቋጠች እንድታበሳጨኝ እፈልጋለሁ….ወይንም ሌላ ወንድ አቅፋ ፊቴ ቁጭ ብላ እያስካካች እንድታበሳጨኝ እፈልጋለሁ እላለሁ…አዎ ያንኛውን ጎንሽን እመርጣለሁ።እሱኛውን እሷን መልስልኝ ብዬ የአምላክ ስር ተደፍቼ እግሮቹን በእንባዬ እያጠብኩ እማፀናለው፡፡
‹‹የምታወራቸውን ነገሮች እውነትንት እኮ አምኖ መቀበል ይከብደኛል››
‹‹እኔም እኮ ስለጠየቅሺኝ እንጂ እንድታምኒኝ አይደለም እየተናገርኩ ያለሁት››
ስልኳ ተደወለ…..ፕሮፌሰሩ ነው…….ሰው መላኩን ተውኩት ሊላት መስሏት ተርበተበተች…የሌባ ጣቷን ከንፈሯ ላይ በማስቀመጥ ዝም በል የሚል ምልክት ለካሳ አሳየችውና ስልኩን አነሳች
‹‹እ ምነው ሰዎችህ ቀሩ? ፈራህ እንዴ?››
‹‹የእኛ ደፋር እስኪ ይሄ ጀግንነት ወኔሽ እሰከመቼ በዚህ መጠን እንደሚቀጥል እናያለን..አሁን በራፌን ገንጥለው ይግቡ ወይስ ወጥተሸ ከፍተሸ እጅሽን በሰላም ታስረክብያቸዋለሽ…?››
‹፣ደርሰዋል እንዴⵏ››
‹‹አዎ ከግቢው ውጭ ጥቁር መኪና አቁመው እየጠበቁሽ ነው…ያው ጥቁር ያደረኩት በምክንያት ነው….ወደመቀበሪያሽ እየመጣሽ አይደል?››‹‹
‹‹እሺ ጥ አደረክ… በቃ ወጣሁ››ስልኩን ዘጋች፡፡‹‹ምን አልባት የሁለታችንም ቀበር በዛሬዋ ለሊት ይፈፀም ይሆናል››ስትል በውስጧ አሰበች፡፡
ይሄውልህ እዚሁ አንድ ሀያ ደቂቃ ታሳለፍና ልክ እንደአመጣጥህ ተመልሰህ ወደ ቤት ትሄዳለህ‹‹..እንካ ይሄን ሞባይል…ምን አልባት አሁን እየደወለልኝ ያለው ስልክ ይሄ ነው ..በዚህ ተከታትላችሁ ያለበትን አድራሻ ልትደርሱበት ትችላላችሁ…ከደረሳችሁበት ቡኃላ ደግሞ ምን አልባት….እኔን የማዳን እድል ልታገኙ ወይንም ያ ባይሳካ እንኳን ፕሮፌሰሩን አድራሻውን ሙሉ ለሙሉ እስከወዲያናው አጥፍቶ ከመሰወሩ በፊት ደርሳችሁበት የመጨረሻውን ፍርድ እንዲያገኝ በማድረግ ትበቀሉልኛላችሁ፡፡
‹‹እኔ እኮ አንቺን የማዳን ተልዕኮ ይዤ እየተንቀሳቀስኩ አይደለም…….እኔ አብሬሽ ለመሞት ነው ፍላጎቴ….ፕሮፌሰሩ ተያዘ አልተያዘ ጉዳዬ አይደለም…››ሲል መለሰላት..
ንግግሩ አናዳጅ ብቻ ሳይሆን ተስፋ አስቆራጨም ነው የሆነባት ‹‹እንግዲያው ስማኝ..››አለችና ጎኗ የሻጠችውን ሽጉጥ አወጣች… አቀባበለች..ያለምንም የስሜት መለዋወጥ ፍርጥም ብሎ እያያት ነው…፡፡
‹‹ሽጉጡን ግንባሯ ላይ ደቀነች…..ይሄውልህ ምላጩን ስብና እዚሁ እራሴን አጠፋለሁ…››
‹‹እና አሪፍ ነዋ..ተዝለፍልፈሽ ስትወድቂ በክንዶቼ አቅፍሽና ወስጄ በክብር እዛ ሶፋ ላይ አስተኝቼሽ እኔም ያንችኑ ሽጉጥ አንስቼ እዛው ሶፋ ላይ አብሬሽ ተስተካክዬ እተኛና በቀረው ጥይት እንዳደረግሽው አደርጋለው....ከዛ ምን አልባት የሚቀብሩን ሰዎችም ተቃቅፈን ከሞትንበት መለያየቱ ሀጥያት መስሎ ስለሚታያቸው..እንዳለነው ጠቅልለው በአንድ ሳጥን በመክተት አንድ ጉድጓድ ውስጥ ይቀብሩን ይሆናል፡፡››
‹‹ጥሩ እንደዛ ሊያደርጉ ይችላሉ…አሁን ሁለታችንም እዚህ ተያይዘን ሞትን ማለት ምን አልባት ፕሮፌሰሩን እናበሳጨውና እጁ ውስጥ ያሉትን እናትና እህቴን በንዴት ሊገድላቸው ይችል ይሆናል..እንደዛ ከሆነ ደግሞ በጣም ነው ምበሳጭብህ…እስከመቼም ይቅር አልልህም..በሄድንበት ማለቴ ገነትም ገባን ሲኦል ለዘላለም አላናግርህም….አንተን ብቻ ሳይሆን ማንንም አላናግረም….ዝም እላለው ለዘላለም ፀጥ….››
‹‹እ ትስማማለህ…ምላጩን ልሳበው…?››
ድክመቱን እንዳገኘች እርግጠኛ ነች….እንደመተከዝ አለ…..አንገቱን አቀረቀረ..‹‹ለዘላለም አይደለም ለሳዕታት ዝም እንድትይኝ አልፈልግም….እንዳልሺኝ አደርጋለሁ..በቃ ሞባይልሽን ስጪኝና ሄጂ..ግን ያ ፕሮፌሰር አይገድልሽም ….ጥለሺኝ እንድትሄጂ ስለማልፈልግ አድንሻለው››አላት
ስላሳመነችው ደስ ብሎት ሽጉጡን ከግንባሯ ላይ አነሳችና በፊት በነበረበት ጎኖ ላይ ሻጠች… ሞባይሉን አቀብላው ወደራሷ ጥብቅ አድርጋ አቀፈችውና እንደ ሙልሙሉ ዳቦ ወፈር ያሉ ከንፈሮችን አንዴ በረጂሙና በጥልቀት መጠጠቻቸው….ይህ መሳም በሁለቱ የፍቅር ታሪክ የመጀማሪያው ነው …ምን አልባትም የመጨረሻው እንደሚሆን ይታመናል..ግን ለሁለቱም በቂና ዘላለማዊ ጣዕም ነበረው፣ካሳ ደንዝዞ እይኖቹን በጨፈነበት ትታው ልትወጣ ወደ በራፉ መጓዝ እንደጀመረች ድንገት መብራቱ ጅም ብሎ ጠፋና እቤቱ በጭለማ ተዋጠ..ወዴያው ጠንካራና ፈርጣማ ክንድ ትከሻዋ ላይ አረፈ……
👍30😱1
‹‹እንዴ ምንድነው..?ይ ሁሉ ግርግር አያስፈልግም..?እየመጣሁ አይደለ እንዴ…;;?እንዳትናገር አፎን በመዳፉ አፈናትና ጨርቅ በጭንቅላቷ አጠለቀላት….ከዛ አንጠልጥሎ ወደላይ ተሸከማት…..ሲያርገፈግፋት ሹጉጦ ከጎኖ ተንሸራቶ መሬት ወደቀ…..ጎንበስ ብሎ ያነነሳው የለም
ይሄ ድርጊት ካሳ ላይም በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የተከወነው..ሁለቱንም ድፍን አይሩፍ መኪና ውስጥ ከተቷቸውና ከአካባቢው ተፈተለኩ…..
ዳክተር ሰጵራ ባጋጠማት ያልተጠበቀ ነገር በጣም ነው የተበሳጨችው….የተበሳጨችበት ምክንያት በዚህ መልክ ስላፈኗት እና ስላንገላቶት አልነበረም…ካሳንም ከእሷ ጋር አብረው ስለያዙት እንጂ..ፈፅሞ ካሳ ላይ ምንም አይነት አደጋ እንዲደርስበት አትፈልግም…እንደእዛ ከሆነ እራሷን ይቅር ሳትል ነው ምትሞተው ፡፡
አይሩፋ ቦታውን ለቃ ስትበር ፕሮፌሰሩ የላካት ጥቁሯ የቀብር ማስፈፀሚያ ምትመስለው መኪና ግን ከመንገድ ባሻገር እንደቆመች ነበረች…….
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍171
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ጠበብ ብሎ ዘመናዊነትን የተላበሰው ክፍል በእንግዶች ተጣቧል። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መሃል ፈንድሻ በቆሎና የተለኮሰ
ሻማ ተቀምጧል። በአመዛኙ ተስተናጋጁ የሚጠጣው ውስኪ ነው ::

የጃዝ ሙዚቃውን ስልት ተከትለው እየነጎዱ እጃቸው
ከሰው ጉያ ውስጥ ዘው ብሎ ሲገባ ከንፈር ከከንፈር ሲላተም...ነፍሳቸውን የሚያውቁ የማይመስሉ ፍቅረኞች ጥግ ጥግ ይዘው
ይታያሉ።

ታዲያ ተመልካችና የሚታይ ተናጋሪና ታዛቢ... ያለ
አይመስልም፤ ክፍሉ ውስጥ ሁሉም እንደተመቸው ይዝናናል።

የደረታቸውና የእጃቸው ጡንቻ ያበጠ የሰማይ ስባሪ
የሚያካክሉ “ቦዲ ጋርድ" መሳዮች ባንኮኒውን ከበው ከጃዙ ሙዚቃ በላይ አልፎ አልፎ ድምፃቸው እስኪሰማ ድረስ ያውካካሉ።

ዓለም አቀፍ የአየር ሜዳ ጠቆር ብሎ ከጥቁሩ ሰማይ ጋር የተመሳሰለው ተራራ  ሌሎችም የአዲሳባ መንገዶችና ቤቶች
ተሰበጣጥረው በሚበሩት አንፖሎች ብርሃን የጃዝ ሙዚቃው ከሚንቆርቆርበት ኢምፔሪያል ሆቴል ሰባተኛው ፎቅ ላይ ሆኖ
ይታያል።

ቀኑ የሥራ መጨረሻው ሳምንት አርብ በመሆኑ ብዙው ጠጥቶና ደንሶ ጥቂቱም ጠንብዞ ቅዳሜን ተኝቶ ለማሳለፍ
ተዘጋጅቶ መምጣቱ ያስታውቃል።

“ይህ እንግዲህ አዲሱ ሆቴል ነው" አለ ስቲቭ እሱ
ውስኪውን እሷ ማርቲኒን “ችርስ ብለው አጋጭተው ከተጎነጩ በኋላ።

“ዘመናዊ ነው። እንዲህ አይነት ሆቴል አዲሳባ ያለህ
እያስመስልህም አለችውና እየተዟዟረች ውጭውን በርቀት ተመልክታ

“አዲሳባ በዘመናዊነቷ ሳይሆን በተፈጥሮ አቀማመጧ በአመቺው የአየር ፀባይዋ... በተለይም ድሃና ሃብታም ተሰበጣጥሮ
የሚኖርባት ብቸኛ ከተማ መሆኗ ያረካኛል ስትለው ስቲቭ አንገቱን
በመወዝወዝ አባባሏን ተቀበሎ፡-

“ወደ ኢትዮጵያ እንዲህ ቶሉ እንደምትመለሽ አላውቅም
ነበር። እንዴት ቶሎ
ተመለስሽ? አላት
“ይህን ለመግለጽ ይከብደኛልስቲቭ።
ምናልባት ሙያዬን
ስለምወድ። ከዚህ ውጭ ግን ለረጅምጊዜ ፍቅር ምን እንደሆነ ለመረዳት ባለመቻሌ ካለበለዚያ ያገኘሁትን አዲስ የህይወት ልምድ ይበልጥ ቀርቤ ለማወቅ... ብቻ በትክክል መግለጽ ይከብደኛል”
አለችው። ማርቲኒ የያዘ ብርጭቆዋን እያሽከረከረች።

“ፍቅር ምን እንደሆነ አታውቂም?

“የፍቅር ደራሲውም ተዋናዩም እየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እንጂ ፍቅር ምን እንደሆነ አላውቅም” አለችው ፈገግ ብላ

“በእርግጥ ማንም አውቀዋለሁ ለማለት ይከብደዋል" ሲል

“አፈቅርሁሽ ሲሉኝ በጣም እደነግጣለሁ። ምክንያቱም
ትልቅ ሃላፊነት እንደመሸከም እቆጥረዋለሁ: ለምን በምን
እንዴት... እኔን አፈቀረ ለሚለው ጥያቄ መመለስም ያቅተኛል መፈቀሬን ከተቀበልኩ ከራሴ በላይ የምሽከመው ሰው አለ ማለት ነው። ይህ ደሞ ሕይወቴን ያከብድብኛል ነፃነቴን ይነፍገኛል!
ሌላውን ለማግኘት· · ብጎመጅም ያሰብሁትን ካገኘሁ በኋላ ይሰለቸኛል:: አብሮ መዋል መኖሩ ያስጠላኛል። ብቸኝነት ደግሞ አልወድም

“ይሁን እንጂ ብቸኝነቴን የምመርጥበት ጊዜ ይበልጣል በልጅነቴ  ደጋግሜ ያነበብሁት ትንሹ  ልዑል መጽሐፍ ላይ
እንዳለችው ቀበሮ ሌውን ለመልመድ ትዕግስትና ተራርቆ መኖርን እመርጣለሁ:: ፍቅር  እራስን  አሳልፎ መስጠት ነው ሲሉም እሰማለሁ  እውነት ግን አይመስለኝም።  ብዙዎች እራሳችንን
አሳልፈን ሰጠን ይሉና በኋላ ሌላውን እያስለቀሱ  እሪሳቸውን ይወስዳሉ።

የሰጠውን መውሰድ እንደሌለበት ሃላፊነት የሚሰማው ሰው ይኖራል ብዬ አልገምትም። በጊዜያዊ ስሜትና በፍቅር መካከል ያለው ልዩነት አይገባኝም። ከፍተኛ መካከለኛና አነስተኛ ስሜት
ይኖራል። ከፍተኛውን ስሜት እንደ ፍቅር እንቆጥረዋለን። ፍቅር ግን ሊሆን አይችልም። ፍቅር መስዋዕትነት መስጠት  መከራን መቀበል  ነው... በበደል በንዋይ የሚፈታ በጊዜ የሚኮሰምን
አይደለም፡ የምናየውና መሆን የነበረበት ፈፅሞ ይለያያል። ስለዚህ
ለሌላ ፍቅር አለ ብዬ ራሴን በመደለል የጥቅም ቁማር መጫወት አልፈልግም ውስጣዊ እሳት ሲበዛ ስሜት ሊገነፍል ሲቃረብ
መቃበጥ ! በተረፈ የሚያምኑበትን መልካም ሥራ በትጋት መስራት: ፍቅርን ከሥራ ጋር እንጂ!...” አይኖችዋን ሽቅብ በልጥጣ
የግንባሯን ቆዳ ሸበሸበችው።

ስቲቭ በዚህ ርዕስ ላይ ብዙ ሊሞግታት የሚያስችለው
ሀሣብ አጣ ሰዎች ከገሃዱ አለም እንከን የሌለው ፍቅር ቀርቶ ለምሣሌ የሚበቃ ፍቅር በማጣታቸው ስለ ፍቅር በተነሳ ቁጥር
የሚያነሱት ሸክስፒር  በምናቡ ስለፈጠረው  “የሮሚዎና ዡሌት”
ፍቅር መሆኑን ስለሚያውቅ ፍቅር ለጋራ ጥቅም እንጂ አንዱ ለሌላው መስዋዕት ለመሆን አለመሆኑንም ሲያስብ፤ ካርለት የጃዙን
መዚቃ  ተመስጣ እያዳመጠች ቆየችና፡

“ልንደንስ ብንችል ምንኛ ደስ ይለኝ ነበር'' አለችው

“ጥሩ ሃሣብ'' ብሉ በተራው ሂሣቡን ዘጋ

መብራቱ የሙዚቃውን ስልት ተከትሎ ብልጭ ድርግም ብልጭ ድርግም ይላል
በዳንሱ መድረክ ላይ ደጋግመው። በዳንሱ
ከሚውረገረጉት መካከል ካርለትና ስቲቭ ይገኙበታል።

የብሬክ የቫልስ የብራዚል ዳንስ ሳምባ ሳይቀር ካርለት
እየደነስች የስቲቭን ወሲባዊ ስሜት አጦዘችው:: ከዳሌዋ ግራና ቀኝ
ነቅነቅ ነቅነቅ ብላ ወደፊት ከወገቧ በታች ስትናጥ፤ ወገቧን ለአመል ያህል ይዞ በሚሽከረከረው ዳሌዋ ሲደነቅ ምራቁን ሲውጥ እንደቆዩ ረጋ ያለው ይህች ዓለም ትቀየር የሚላው የኤሪክ ክላፕተን ሙዚቃ
ጀመረ: ካርለት ከሰውነቱ ተጣብቃ እንደ እባብ እየተጥመለመለች
ዳሌዋን እያንቀሳቀሰች, በትንፋሽዋ ደረቱን ስታተራምስው የመውደቅ
ያህል ላዩዋ ላይ ዘፍ አለባት

እሷም አቅሙ እያነሳት ስሜቷ እየገፈተራት መጣና “ስቲቭ እንሃድ" አለችው፡ ተከትሏት ወጣ። መኪናቸው ውስጥ እንደገቡ
ከንፈሩ ከከንፈሯ ገጠመ: ተንቀሳቀሱ... ፓንቷ ቁልቁል ሲንሽራተት ጭኖችዋም ተከፈቱ…..

“የወሲብ ፈውስ" የሚለው የማርቪን ጌይ ሙዚቃ ዜማ
በርቀት ተሰማት፡ ካርለት ዓለሟን ቀየረች... ለመፈወስ ነጎደች...
ሙዚቃው ይስረቀረቃል... ደስ የሚለው ሙዚቃ  እየራቀችም ተከተላት... ከፈተችለት ጆሮዋን አይኗን ልቧን. ሙዚቃውም
እንደ ምንጭ ውሃ ኩልል እያለ እየሰረሰራት ወደ ውስጧ ፈሰሰ።

💫ይቀጥላል💫
👍30😁21👎1
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ -14
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
አብዬት የዶ/ሯ ደህንነት ስላሳሳበው ሁኔታዋን ሊያይ ወደ ክፍሏ ሄዶ ሲያንኳኳ አይከፈተም.ቀስ ብሎ ገፋ ሲያደርገው ተከፈተለት .ክፍሉ ባዶ ነው፡፡ መጀመሪያ ወደሳሎን ፊልም ለማየት የሄደች መስሎት ተንደርድሮ ወደታች ወረደ….ባዶ ነው፡፡ተመልሷ የአንደኛ ፎቅ በረንዳ ጋ ቁጭ ብላ ከጨረቃ ጋር ብቻዋን እያወራች ይሆናል ብሎ ስለተጠራጠረ ወደ እዛው ሄደ. ቦታው ባዶ ነው፡፡ ሰው የለበትም…. ወደክፍሏ ዳግመኛ ተመልሶ ለማየት ወደእዛው እየተንቀሳቀሰ ሳላ የከሳ ክፍል ገርብ በሎ ተለመለከተ…‹‹ምን አልባት ካሳ ጋር ሄዳ ይሆን ?››ሲል አሰበና አይምሮ ሌላ ነገር ስላሳሰበው የማያውቀው ነገር ሰውነቱን ወረረው
‹….እየቀናሁ ብቻ እንዳይሆን?›ሲል እራሱን ጠየቀ…
‹ያ ንክ ታፈቅራታለህ ያለኝ እውነቱን ይሆን እንዴ?›>
‹‹የምን ፍቅር?››በቃ የጀመሩትን ይጨርሱ ብሎ ወደክፍሉ መሄድ ከጀመረ ብኃላ የሚያስበው ሀሳቡ የማይመስል እንደሆነ ተሰማው. .የሚያስበውን እየፈፀሙ ከሆነ በራፉን አይዘጉትም ለምን ገርብ ማድረግ አስፈለጋቸው?››
እግሩን ወደካሳ ቤት መለሳና ተጠጋ.. ጆሮውን ቀሰረ….ከውስጥ የሚሰማ ምንም አይነት ድምፅ ሆነ የሰው ትንፋሽ የለም…በደንብ ተጠጋ… በራፉን በእጁ ገፋ አደረገው.. እንገቱን ወደውስጥ አሰገጎ ተመለከተ.ክፍሉ .ባዶ ነው..አሁን በጣም ደነገጠ፡፡
‹‹…እነዚህ ሰዎች የት ሄደው ነው….?ያሰበው ነገር እውነት እንዳይሆነ በውስጡ ፀለየ….ይሄ ንክ እናትሽንን አስለቅቅልሻለው ብሎ ገፋፍቶ ይዞተ ሄዶ እንዳይሆን ››አለና በፍጥነት ወደ ዶክተሯ ክፍል ተመልሶ ገባ…ወደየት እንደሄደች የሚጠቁም ነገር ለማግኘት ክፍሉን መመነቃቀር ሲጀምር አይኑ ባዶው አልጋ ላይ አረፈ..ጥላለት የሄደችውን ወረቀት ፍላሽና ቁልፍ አገኘ….ሌሎቹን ባሉበት ተወና ወረቀቱን አንስቶ ማንበብ ጀመረ….የእነዚህ የዶክተሮች የእጅ ፅሁፍ ደግሞ ለምንድነው እንዲህ የሚያጨመላለቀው አለ..ቢሆንም እንደምንም ገጣጥሞ የተወችለትን መልእክት አንብቦ ተረዳ…ፍላሹንና ቁልፉን ኪሱ ከተተና ስልኩን አውጥቶ እየደወለ ክፍሉ ለቆ ወጣ ..እየተንደረደረ ወደመሳሪያ ማከማቻ ክፍላቸው ገባ፡፡
///
ፕሮፌሰሩ የዶክታሯን ድምፅ ከሰማ ጀምሮ ፈንጠዝያ ላይ ነው….ምን አልባትም በቅርብ ጊዜያቶች ይሄን የመሰለ ፈንጠዝያ ተሰምቶት አያውቅም፡፡ነገሮች እዲህ ልክክ ብለው በእቅዱ መሰረት ተግባራዊ ሲሆኑ በማየታቸው በሰላ እምሮው ብቃት በጣም ተደሰተ…ይሄ ጭንቅላት እኮ ሀገር ለመምራት ነበር የተፈጠረው››አለ….አዲሱ የተደበቀበት ቤት በረጅም ግንብ አጥር ሆኖ አደገኛ አጥር የዞረበት...ለጥበቃ ምቹ የሆነ ባለሶስት ክፍል ዘመናዊ ቢላ ቤት ነው…አብረውት የቤቱ ጠባቂ ዘበኛ እና ሌሎች ሁለት ፕሮፌሽናል ጠባቂዎች አሉ…እዚህ ቤት መመሸጉን ከእሱና ከእነዚህ ሰዎች በስተቀር ሌላ ማንምአያውቅም…
ለጊዚው ከእይታ እራሱን መሰወር እንዳለበት ከሼኪው ጋር ከተመካከረና ከተስማሙ ቡኃላ እሳቸው ቤታቸው እንዲመሽግ በመነጋገር ተስማምተው የነበረ ቢሆንም..ለሊት ላይ ሲያስበው ግን እሳቸው ቤት ገባ ማለት በእሳቸው ቁጥጥር ስር ገባ ማለት ነው…እሱ ደግሞ ማንም ቁጥጥር ስር መግባት አይፈልግም…እራሱን ከሁሉም ሰውሮ በሪሞት ሌሎቹን መቆጣጠር ነው አላማው፡፡እና እንዳሰበውም ከምንም ነገር ጋር ንክኪ በሌላቸው ሰዎች…ለዛውም እራሱን ለእይታ ሳያጋልጥ እቤቱን መከራየት ቻለ…የሚፈልጋቸውን እቃዎችንና ዘበኛውን ይዞ ገባበት.. ከዛ ከእነዶዬ ጋር ፈፅሞ የማይተዋወቁ ከቀድሞ ታሪኩ ጋርም ምንም ግንኙነት የሌላቸው..(ከእነዶዬም ጭምር የሚጠብቁት) አራት ጠባቂዎች በብዙ ብር ቀጠረ …. እና ይሄንን ትናንትና ማታ አሰበ ዛሬ ተግባራዊ አደረገ
…‹‹.የሚገርመው እቤቱ ገዳም ነው›› አለ ይህንን ሊል የቻለበት ምክንያት ይሄው አሁን ዶ/ር ናና ውሰደኝ ብላለችው ነው፡.አዎ ከጠባቂዎቹ አንዱን እንዲያመጣት ልኮል..እና ስትመጣ ምን አይነት አቀባበል እንደሚያደርግላት እየሰበ እና እየተዘጋጀ ነው፡፡አዎ እያንዳንዶ ላሳጣችው ዶላር…ለእያንዳንዷ ለቆሸሸችው ስሜ…ለእያንደንዱ እሷን ለመፈለግ ለተሰቃየውባቸውና እንቅልፍ ላጣጣባቸው ቀናት እያንዳንዱን የሰውነቷን ክፍል ለየብቻ እየቆራረጥኩ አሳከፍላተለው..እባክህ ግደለኝ ብላ ብትማፀነኝ እንኳን በቀላሉ አልገድላትም..ምን አልባት በስቃይ ቃታ እስክትሞት ሳምንት ሊፈጅ ይችላል አለ›…አንድ ክፍል መረጠና ባዶ እንዲያደርጉት ለሰራተኞቹ አዛቸው…
በ15 ደቂቃ ውስጥ ባዶ አደረጉለት፡፡ አንድ መለስተኛ ጠረጳዛና ፤አንደ የብረት ወንበር አንዲገባ ተደረገ …የግቢው ውሻ ይታሰርበት የነበረ ሰንሰለት ከቦታው ተፈቶ እንዲመጣ አደረገ…..አቤቱ ውስጥ ያሉ ቢላዋዎች መከትከቻዎችና ሹል ብረቶች… ሁሉ ኪችን ገብቶ ኪችን ካቢኔቱን በመክፈትበእየንዳንዱ መሳቢያ ውስጥ ያሉትን ብረት ነክ ነገሮች ሰበሰበና ወደአዘጋጀው ክፍል በማስመጣት ጠረጳዛ ላይ ቆለለው…በመሀፀን የሚገቡ ቱቦዎችና ብረቶች አልቀሩም…
‹‹.ዶ/ር ሰጲራ አሁን መምጣት ትችያለሽ…አንቺን ለመቀበል ከልብ በመነጨ የፍቅር ስሜተ የመጨረሻውን ምርጥ ድግስ ደግሼ እየጠበቅኩሽ ነው፡፡›በማለት የእርካታ ትንፋሽ በረጂሙ ተነፈሰና ከፍሉን ለመጨረሻ ጊዜ ቃኝቶ በእርካታ ስሜት ወደክፍሉ እየተመለሰ ሳለ….ስልኩ ጠራ አወጣና አየው .የተላከው ጠባቂው ቁጥር ነው….በደስታ ዘለለ.ደርሰዋል ማለት ነው…
///
በጭንቅቷ ተጠልቆ አንገቷ ጋር በሚደርስ ጨርቅ እንዳፈኗት መኪና ውስጥ ሲወረውሯት ያልተሰማት ንዴት በተመሳሳይ ከጎኗ የተወረወረው ካሳ መሆኑን ስታውቅ በህይወቷ ከተናደዳቸው ንዴቶች የመጨረሻውን ንዴት ነው በውስጦ የተቀጣጠለው..የተናደደችው ደግሞ በራሷም ፤በካሳም፤ በፕሮፌሰሩም በእግዚያብሄርም ጭምር ነው፡፡
‹‹እኔ ራሴ ህይወት ለሚያስከፍል ይሄን መሰል ተልእኮ ስወጣ እንዴት በዚህ መጠን እንዝላል እሆናለሁ?…...እንዴት ግራና ቀኜን መቃኘት ያቅተኛል….››አለች..አዎ እንደእዛ አድርጋ ቢሆን ኖሮ ካሳ እንደተከተላት ልታውቅ እንደምትችል አሰበች….እንደተከተላት አውቃ ቢሆን ኖሮ እንደምንም ብላ ታስመልሰዋለች..ወይ ደግሞ በከተማው ቅያሶች በመሹለክለክ ትጠፋበት ነበር…
‹‹ደግሞስ እሱስ ቢሆን ምን አይነት ጅልነት ነው ገና ህይወትን በቅጡ ሳይኖር በእንዲህ አይነት ሁኔታ ወደሞት ሰተት ብሎ የሚገባው…?››.እራሷን ሆነ ሌላውን መውቀሱን ደከማት
‹‹ስሙ ሰዎች ፕሮፌሰሩን ማናገር እፈልጋለሁ››ስትል ለማታያቸው ግን ደግሞ መኖራቸውን እርግጠኛ ለሆነችበት ሰዎች አቀረበች
‹‹ምነው ናፈቀሽ እንዴ ?ወደእሱ እየሄድሽ አደል በአከል ስታገኚው የምትፈልጊውን ነገር ትጠይቂያቸዋለሽ››አላት ካሳ እንደእሰዋ በጭንብል በተከለለበት በተነፋነፈ ድምፅ
‹‹አንተ ዝም በል…ይሄው ጅልነትህ እዚህ ላይ አድርሶህ ህይወትህን ሊያሳጣህ ነው››
‹‹ፍቅርን ጅልነት አልሽው ..አረ ይሄ ክብረቢስነት ነው››
‹‹‹ዝም በል ደግሞ አትቀባጥር…እናንተ አጋቾቹ ትሰማላችሁ …አሁኑኑ ከፕሮፌሰሩ ጋር በስልክ አገናኙኝ››
መኪናዋ ትበራለች..መልስ ሚሰጣት የለም፡፡
‹‹ዱዳ ሰዎችን ነው የላከብን እንዴ?››አለች…ያለችውን ነገር አንዱንም እንደማያደርጉ ስለተሰማተ እሷም ዝም ብላ የሀሳብ መናወዝ ውስጥ ገባች፡፡
👍281
ይህቺ አለም ለምን እንዲህ ፍትህ የሌለባት የወንበዴዎች መፈንጫ ልትሆን እንደቻለች እራሷን ጠየቀች፡፡ከፍም ለማም በዚህ አለም ላይ ፍርድ ስንሰጥ ነው የምንኖረው፡፡...ገንዘብ ለመዝረፍ ወይም ንብረቱን ለመቀማት የጓደኛውን ህይወት በግፍ ያስወገደ ሰው ታሪክ ስንሰማ ከእግር ጥፍራችን እስከራስ ፀጉራችን ይሰቀጥጠናል ...ከዛ ከዚህ ከሰማነው ጨለማ ሀሳብ እራሳችንን ለማረጋጋት ወደጓሮችን እንገባለን ከዘራነው ሰላጣና ቆስጣ መደብ ላይ አረም ያልናቸውን አያሌ ለጋ ተክሎች በደመነፍስ ወሳኔ እየነቀልን እንጥላለን።የትኛው ተክል ማደግ የትኛው ተክል በእንጭጭነቱ መቀጨት እንዳለበት እንወስናለን ..በወሰነው መሰረትም እንተገብራለን።እቤታችን የሚቀመስ ፍለጋ ጎራ የሚሉትን ሁለትና ሶስት አይጦች ወይ በወጥመድ አልያም በመርዝ ማስወገድ ምንም ክፋት የሌለው መደበኛ የተለመደ ተግባር ነው።ለእኛ ምቾት የማይሰጡን ፍጡራን የመኖር መብት መንጠቅ ተፈጥሮችን ነው።ፍሲካ ወይም ሞሊድ ሲመጣ እቤታችን ካረባናቸው በርካታ በጎች መካከል የትኛውን እንረድ ?ቀዩን ወይስ ጥቁሩን? ብለን አማርጠን እንደቀልድ ምድር ላይ ዘርረን አንገቱን ስንቀነጥስ በውስጣችን የደስታ እንጂ የፀፀት ስሜት አይሰማንም።በአጠቃላይ እኛ የሰው ልጆች ገዳዬች ነን..ገና ከእናታችን ሆድ ከወጣንበት ቀን አንስቶ መግደልን በተለያየ መንገድ ትንሽ በትንሽ እየተለማመድን ነው ምናድገው….ለዚህ ነው የተማርን ሆንን መሀይም ..ፕሮፌሰር ሆንን ዘበኛ..ወታደር ሆንን ቄስ……ሴት ሆንን ወንድ….አጋጣሚውን ሲናገኝ በቀላሉ ገዳይ የምንሆነው…..በዚህ ጉዳይ አንዳችን ካንዳችን ቡዙም የተሻልን አይደለንም.. በዝርዝር ባሰላሰለችው ፍልስፍናዊ ሃሳቦ ድምዳሜ ላይ እንደደረሰች መኪናዋ መዳረሻዋ መድረሷን የሚያመለክቱ ነገሮችን አስተዋለች …..
የመኪናዋ ፍጥነቷን መቀነስ ….የባራፍ መከፈት ድምፅ…ከዛ ሚኪናዋ ትንሽ ተንቀሰቀሰችና ቆመች…ገቢናው ተከፈተና በፈርጣማ ክንድ እየተጎተቱ ወጡ…እየጎተቱ እንዲራመዱ አስገደዶቸው..ከዛ በራፍ ሲከፈት ሰማች…ፕሮፌሰሩን አግኝታ ምራቋን እስክትተፋበት…በጥርሶቾ እስክተቦጫጭቀውና..ደግሞ ካልሲዋ ውስጥ በሻጠችው ጩቤ ጉሮሮውን እስክትበጥስለት ቸኩላለች፡፡ከዛ የተጠለቀላቸው ጭንብል በየተራ ከላያቸው ላይ ተነሳ…ብርሀኑን ተለማምደው ዙሪያ ገባቸውን በደንብ ለማየት የተወሰኑ ሰከንዶች አባከኑ…
የገቡበት ክፍል የሆቴል መኝታ ክፍል የሚመስል ነው፡፡ውስጡ ግዙፍና ውብ ሁለት አልጋዎች ፤አንድ መለስተኛ ሶፋ፤ ቴሌቪዥን ፤ፍሪጅ ሁለት ወንበርና አንድ ጠረጵዛ አለበት፡፡ ክፍሉ የራሰ የሆነ መታጠቢያ ክፍል አለው….የምግብ ጠረጳዛው በምግብና በፍሩት ተሞልቷል፡፡
ጋርዱ ከፊት ለፊታቸው ቆሞላ..ዶክተር ያሳበችውና የመጣችበት ቦታ ሊገጥምላት አልቻለም‹‹..በል ጌታህን ጥራው…..እቤተሰቦቼን አሁኑኑ እንዲለቃቸው እፈልጋለው››
‹‹እሺ ሰዓቱ ሲደርስ ነግራቸዋለው…የምትፈልጉት ምግብ ጠረጳዛ ላይ አለ ..መጠጥም ከፈለጋሁ ፍሪጁ ሙሉ ነው…..ፊልምም ማየት ከፈለጋችሁ ያው ሪሞቱ ጠረጳዛው ላይ ነው..እኔ እዚሁ በረንዳ ላይ ነው ያለሁት…የምትፈልጉት ነገር ካላ ይህቺን መጥሪያ ደውሉ……ሀለቃዬ ምንም ነገር እንዳይጎድልባቸው ብለው አስጠንቅቀውኛል››
በዚህ ጊዜ ካሳ ልክ ለጫጉላ ሽርሽር ፍቅረኛውን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ይዞ እንደገባ አዲስ ሙሽራ እያንዳንዱን ዕቃ በመደነቅና በአግራሞት እየነካካ በመፈተሸ ላይ ነው፡፡
‹‹ቀልድ በለው….ይ ሁሉ ምቾት …ይ ሁሉ እንክብካቤ ከሰዓታ ቡኃላ ለምትገድሉት ሰው ምን የሚረባው ይመስላችዎል..››
‹‹የእኔ እመቤት የምን ግድያ ነው..?ጌታዬ እንኳን ሰው ዝንብ የሚገድል አንጀት የላቸውም….ለማንኛውም እስከ ጥዋት እራሳችሁን ዘና አድርጉ …ጌታዬ ጥዋት ሁለት ሰዓት ይመጡና ሁሉን ነገር ያብራራላችሆል››
‹‹አሁኑኑ ና በለው ..አሁኑኑ ሁሉ ነገር በፍጥነት እዲጠናቀቅ ነው የሚፈልገው››
‹‹አረ ተይ ሰጵራ…ማምሻም እድሜ ነው ሲባል አልሰማሽም…እንደውም የድሮ እጮኛሽን ሀሰብ በጣም ነው የወደድኩት…እስኪ ዘና እንበል..ይሄንን ምግብ እንብላ… ከፍሩቱም እንግመጥ..ከወይኑም እንንጓጭ…ከዛ ለአንድ ሰዓትም ቢሆን በዚህ አልጋ ላይ ፈልሰስ እንበልበትና እንደተባለው ሲነጋ ሻወራችንን ወስደን ንፅህና ንቁ ሆነን ዳይ ወደ መንገዳችን፡፡
እህቴ እሱ እንዳለው ዘና በሉ..ደግሞም ግድያ ፤ሞት የምትሉትን ነገር ከአእምሮችሁ አውጡ… አዝናለሁ ፣..ሀለቃዬን ግን ከመንጋቱ በፊት የማገኘንበት ምንም አይነት እድል የለም…..በሉ እንዳልኮችሁ የምትፈልጉት ነገር ካለ በረንዳ ላይ ነኝ››በማለት በራፉን ከወፍቶ ወጣና ከውጭ ቆልፎባቸው ድምፅን አጠፋ፡፡
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍24🥰3
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ጊዜው የበጋ ወቅት እንደመሆኑ መጠን የሁዌልቫ አየር እጅግ ማራኪ ነበር።

ሁዌልቫ ሶራ ከወር በፊት ብርዳማው የክረምት ወቅት
ከመውጣቱ አስቀድሞ ካፖርቱን ከጥጥ የተሰራ የአንገት መጎናፀፊያውንና የሱፍ ቆቡን እያደረገ ወደ “ኢስላእ ክርስቲናእ"
ወደብ በመሄድ የአሳ ማጥመጃ ጀልባዎች በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ
ሲንሳፈፉ ዲካ አልባውንም የአትላንቲክ ውቅያኖስ አድማስ... ማየት
የመኪናውን ሙቀት መስጫ እንደከፈተም ከኮሎምበስ ሐውልት ስር ከተደረደሩትና የፍቅር አላማቸውን ከሚቀጩት ስፔናውያን ጎን
አቁሞ እያሸጋገረ የጠፋው ነገር እንዳለ ሁሉ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ማፍጠጥ ያዘወትር ነበር።

የአገሩን አፈር የአገሩን ባንዲራ ከኮለምበስ ሐውልት ሙዚየም ውስጥ አይቷል። ያ ጠንካራው የውሀ ጀግና ከዘመናት
በፊት ዘግኖ ያመጣውን የአገሩን አፈር ከግዙፉ ሐውልት ስር ካለው
ሙዚየም መስታዋት ውስጥ ተመልክቷል: አፈሩ ከወርቅና እንቁ
በላይ እንደሆነ ሁሉ አፍሶ ቢያሸተው ዘግኖ ቢጨብጠው እንደስኳር
ቢቅመው ተመኝቷል: ግን አልቻለም:: በመካከላቸው ጠንካራ መስታዋት አለ: የአፈሩን ጠረን ባፍንጫው ማሽተት እንኳን
ተመኝቶ አልተሳካለትም።

የአገሩ ባንዲራ የአቢሲኒያ ባንዲራ" ይላል አንጂ ቀለሙ ለቋል: ትክ ብሎ ሲመለከተው ግን ያ የቀስተ ዳመና ቀለም ያ ከህፃንነቱ ጀምሮ “የማሪያም መቀነት ለኔ..." እያለ ጮቤ የረገጠለት
ትምህርት ሲማር እንደገባ በጮርቃ አስተሳሰቡ በእንቦቀቅላነቱ.
አንጋጦ እያየ ያዜመለት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ባንዲራው ታየው ያኔ እጆቹን ዘርግቶ እንባው ከአይኖቹ እየፈሰሰ መስታዋቱ
ላይ ተደፋ።

“መለያዬ መታወቂያዬ...
የጥቁርነቴ አርማ... የነፃነቴ
ምልክት” ብሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለው ባንዲራ ንፋሱ “ጧ" እያደረገው "ሰማዩ ላይ ሲውለበለብ
ታየውና ሆድ ባሰው ባይተዋርነት ተሰማው ማንነቱን ያጣ ሆነ
ብቸኝነት ስለት ጥፍሩን አሹሎ መላ አካሉን ቧጠጠው: ውስጡ
ደማ በብሶቱ ህሊናው ደረቀ ስሩ እንደተቆረጠ እፅዋት ሲጠወልግ ሲወይብ እራሱን ተመለከተው: ስለዚህ ብሶቱን በእንባው ለውሶ
ወፍራሙ እንባው እንደጎርፍ የተሰበረ ልቡን እየሸረሸረው ወደ ውጭ ተደፋ። ማንነቱን ከአጣ ቆይቷል። ከርሱ ቢሞላም ህሊናው ግን
በፍርፋሪ ማንነት ሊጠግብ አልቻለም: እየሄደ ይቆማል እየሰራ ይቃዣል ሲስቅ እንባው ከየት መጣ ሳይባል በአይኖቹ ይሞላል...
“ማነህ?” ሲሉት እውነት ማን ነኝ! የማንነቴስ መለያ ምንድን ነው?  ለምንስ ዓላማ እኖራለሁ? ቅዠቴስ ለምን በረከተ? እውን የምበላውን የሚያፈራ አፈር የለኝም? የሚለበስ በታሪኩ
የሚያኮራ ባንዲራስ የለኝም..." ይልና በሃዘን ይንዘፈዘፋል።

ከወር በፊትም ያጋጠመው ይኸው ነው: የማንነት ረሃቡ
አይሎ ብቸኝነት በዚያ ስለታም አካፋው ህሊናውን እየሰቀሰቀ አንጎሉን ሲያቦካበት ህመሙ እየለበለበ ሲያቃጥለው ልቡ ሲደማ መስታዋቱ ላይ ተደፍቶ ኮሎምበስ ከዘመናት በፊት ያመጣውን
የአገሩን አፈርና ባንዲራ ተማፀነ።

“ምነው አምላኬ መግባባትንና መቻቻሉን ነፈግኸን። ምነው
የርሃብተኞች ምሳሌ አደረግኸን...” ሳግ ተናነቀው እንባው እንደ
ዶፍ ዝናብ ወረደ ንፍጡ ተዝረከረከ፡ በዚህ አጋጣሚ የሆነ ሰው ከተደፋበት ቀስ አድርጎ ቀና አደረገው: ሶራ ከሙዚየሙ ክፍል
ወጥቶ የአትላንቲክ ውቅያኖስ የማዕበል ነፋስ አካሉን ሲዳስሰው
የተለያየ ሃሳብ ተፈራረቀበት።
ከተደፋበት ያቃናው ግን ማን እንደሆነ ለምንስ ከሐዘኑ  እንዳናጠበው ለምን አብሮት
እንደሚራመድ አሰበ
ነፋሱ እየበረታበት ሀሊናው እየተስተካከለ ማሰብ ሲጀምር የያዘውን ሰው
ማንነት ለማየት ሞከረ።

ወፍራም ሰማያዊ ሹራብ
የፈረንሳዮችን ቡትስ ጫማ
የተጫማች ካፖርት ለብሳ ፀጉሯን በሱፍ ኮፍያ ብትሸፍንም በእንቢታ  ያፈነገጡ ፀጉሮችዋ ፊቷ ላይ ብን ብን እያሉ በሚያምረው ጠይም የፊት ቅርጿ ላይ የሚራወጡ፣ በግራ ትከሻው በኩል ወገቡን በእጆችዋ አቅፋው ተመለከተ።

ጡቷ ብብቱን ሊነካካው
ተገርሞ ትክ ብሉ አያት: ፈገግ አለችና አይኗን ሰበር አደረገች። በእርግጥ እርዳታዋ ራሱን መቆጣር እስከሚችልበት ድረስ በመሆኑ እስኪረጋጋ ጠበቀችው። ከዚያ

“ግራሊያስ” አላት በስፓንሽ አመሰግናለሁ ለማለት።

“ዴናዳ...” አለች ምንም አይደል ለማለት። ለቀቅ አድርጋው! አሁን የተረጋጋህ ይመስለኛል። ስለዚህ ብሄድ ይከፋሃል?" አለችው።
በዚህ ግላዊ ህይወት ጥልቅ መሰረት ያለው ፎቅ እየሰራ ባለበት ዓለም አፓርታማው ውስጥ የሚኖረውን ኗሪ በግል ህይወቱ ገብተው
“ለምን  ሳቅህ?... እያሉ መጠየቅ የግል ነፃነቱን እንደመዳፈር ስለሚቆጠር መርዳትና መተባበር የሚችሉትን ፈፅሞ ሌላውን ጣጣ ለባለቤቱ ትቶ ዘወር ማለት ተገቢ በመሆኑ ልጅቷ ካለምንም ጥያቄ፡-

“ደህና ሁን” ብላው ስትሄድ ከወገቡ በፊት እጥፍ ብሎ
አጆቹን ዘርግቶ እጅዋን ያዛት: በግርምታ ዘወር ብላ አየችው አያት እሱም: ወዲያው ሃፍረት ተሰማው ወንጀለኝነት ስሜት አደረበት።የያዛት እጁ እጅዋን አለቀቀም። እሷም ለማስለቀቅ አልሞከረችም።
እጁ ግን ሲንቀጠቀጥ ይሰማታል። ስሜቱም ሲለዋወጥ ተመልክታዋለች። ስለዚህ ልታፈጥበት ልትገስፀው አልፈለገችም:

“አዝናለሁ" አላት ፈገግ
ለማለት ቢሞክርም ቅንድቡ
እየተንቀጠቀጠ እያሳጣው።

“ለምን?” አለችው በፅሞና።

“ትንሽ እንድትቆይ መጠየቅ በመፈልጌ..." አላት ቀስ ብሎ እየተጠጋ።

“ማዘን አያስፈልግህም! ቶሎ መሄድ ስላሰብኝ ግን አሁኑኑ መሄድ አለብኝ።" እጆቹን ኪሱ ከተተና አድራሻውን የያዘውን ካርድ
እየሰጣት “ብትችይ ደውይልኝ አላት በትህትና።

“አዝናለሁ” ትከሻዋን ሽቅብ ሰበቅ አድርጋ “ወደ አፍሪካ
መሄድ ስለምፈልግ ጊዜ የለኝም።''

“አፍሪካ...” ከነበረበት ቅዠት ሙሉ ለሙሉ ነቃ።

“አፍሪካ የት?" አላት ፊቱ ላይ ደስታ እየታዩ፡

“አያቴ አገር... ኢትዮጲያ”  ስትለው  አለከለከ: ድንጋጤ
አይሉት ደስታ ላብ እስኪያሰምጠው ድረስ ተሸበረ:

“ኢትዮጵያ!... ኢትዮጵያ... ኦ! አምላኬ እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ። የሃዘኔም ጦስ ናፍቆት ነው..." ሲል ልጅቷ አይኖችዋን አጥብ
ተመለከተችውና

“ኮንችት”

“ምን?”

“ፔሶ ቤኒ ኮንቺት እባላለሁ። ነገ በአስር ሰዓት እዚሁ እንገናኝ አለችውና ሄደች።
በግርምታ ከአይኑ እስክትጠፋ ተመለከታት።

“…አያቴ አገር ኢትዮጲያ... ያለችው እንደገና ጆሮው
ላይ አቃጨለበት ደስ አለው። ስለ ኢትዮጵያ አብሮት የሚያወራ
አግኝቷል፡ ከጉጉቱ የተነሳ ግን ነገ ራቀበት: ያን ሩቁን ነገ እንግዳውን ነገ. መጠበቅ ግን ግዴታው ነበር።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሶራ መኪናው ውስጥ ሆኖ በሃሣብ ፈረስ ከርቀት ደረቱን እንደ ጎረምሳ ገልብጦ ከሚመጣው የአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዕበል ይገባና አብሮ ብቅ ጥልቅ እያለ እየሰጠመ እየተንሳፈፈ ወደ ዳር
ይመጣና ካለው የሲሚንቶ ግንብ ጋር እየተጋጨ እንደ ጥይት ጮሆ.አረፋ ሲደፍቅ... እራሱን እያዬ መሪው ላይ ተደፍቶ ሲጨነቅ ተመልሶ ደግሞ አይኖቹን ውቅያኖሱ ላይ ተክሎ በሃሣብ ለረጅም ጊዜ ሲንቦራጨቅ በምናቡ አለም መግቢያ ጠፍቶት ሲዛክር ቆዬ:

ቶዮታ ኮሮላ መኪና ቀስ እያለች አልፋ ክፍቱ የመኪና
ማቆሚያ ላይ ተስተካክላ ቆመችና ሞተሯ ጠፋ: ለተወሰነ ጊዜ ፀጥታው እንደገና ሰፈነ። ከዚያ የአስር ሰዓት ደወል ተሰማ።
👍23🔥2👎1🤔1
ታኮ ጫማ አጭር ስከርት ላዩ ላይ ቁልፎቹ ያልተቆለፉ
ካፖርት አንገቷ ላይ የአንገት መጎናፀፊያ የደረበች ሴት የቶዮታ መኪናዋን በር ከፍታ ወጣች: የመኪናዋን በር ገፋ አድርጋ ዘጋችና
ቁልፏን በጣቶችዋ እንዳንጠለጠለች ግራ ቀኝ ከይታ ፈጠን ብላ
ጠባቧን መንገድ ተሻግራ ወደ ሶራ አሮጌ ፊያት መኪና ተጠጋች።

ሶራ አይኖቹ እንደቦዙ በሃሣብ ጭልጥ ብሏል። የመኪናውን መስታዋት አንኳኩታ እጅዋን እያውለበለበች ፈገግ አለች። አላያትም! አልሰማትም:: ከፊት ለፊቱ ያለውን መስታዋት በእጆችዋ ስትጠበጥብ ድንገት ሲፀዳዳ የሽንት ቤት በር እንደከፈቱበት ሰው
ደንግጦ አያት: አዎ እሷ ናት: እንደአመታት ለረዘመ ስዓታት የጠበቃት እሷን ነው:: የመኪናውን በር
ከፍቶ ወጣ እጇን ዘረጋችለት ተጨባበጡ።
“እኔ ቤት ብንሄድ ምን ይመስልሃል?” ኮስተር ብላ በትህትና ጠየቀችው። እሽ በላት ቶሎ በል እሽ በል ስሜቱ አጣደፈው።

"ይቻላል” አለ ግራ ትከሻው ከፍ የግራ አይኑን ጨንቆር
አድርጎ።

“የምኖረው ሁዌልቫ ሳይሆን ሴቪልያ ነው፡ ስለዚህ
በየግላችን ዘጠና ኪሎሜትር መጓዝ  አለብን: ምናልባት አርባ አምስት ደቂቃ ይፈጅብን ይሆናል። ተከታትለን ልንጓዝ እንችላለን
ብንጠፋፋ ግን ሴቪልያ ድልድዩን ካለፍህ በኋላ ኤክስፖ  92 ከተካሄደበት ከመድረስህ በፊት ወደ ግራ ትታጠፍና በጎዳና ቁጥር...
አፓርታማው ስር እጠብቅሃለሁ" ብላው ወደ መኪናዋ ሄደች::

“ሴፍቲ ቤልቱን አስሮ መኪናውን ካስነሳ በኋላ የሷን መኪና ተከትሎ ፍጥነቱን እየጨማመረ አሽከረከረ:
።።።።።።።።።።።።።።።።።

“ኦባቴ ኢትዮጵያዊ ነበር አልሽኝ?" አላት እሱ ሶፋው ላይ እሷ ደግሞ የሙዚቃ ዲስኬት እየመረጠች ከተሽከርካሪው ባለ
መስታዋት መደርደሪያ ፊት ለፊት እንደቆመች።

“አባቴ ሳይሆን አያቴ" አለችው ከወገቧ በላይ በቄንጠኛ አዟዟር ዞራ: ፈገግ ብሎ እራሱን በአዎንታ ወዘወዘና ዝም አለ። ገና
ጨዋታ ከመጀመሩ መሳሳቱ አሳዘነው: ቤቱ ውስጥ ሁለት ትላልቅ ፎቶ አለ: አንዱ የወንድ ሌላው የሴት
የወንዱ ፎቶ የአባቷ ወይም የአያቷ መሆን አለበት።
“ያ ፎቶ የአንች ነው ወይንስ የአባትሽ?
“የቱ" አለችው በተለመደው መልክ ዞራ። ጠቁሞ አሳያት
ከመመለሷ በፊት ግን፡

ምን ነበር የጠየቅከኝ?” አለችው::

ያ ፎቶ የአንች ነው ወይንስ
የአባትሽ?” አላት
እንደመቁነጥነጥ ብሎ: ኪሊሊ… ብላ ሳቀችና “ወንድና ሌት መለየት
አትችልም? ስትለው ደነገጠ።

ምነው! ምን ብዬ ጠየቅሁሽ? ፈገግ ለማለት እየሞከረ ያ ፎቶ የአንች ነው ወይንስ የአባትሽ ነውኮ ያልከኝ" አሁንም ሳቀች።

“የአባትሽ ነው ወይንስ የያትሽ ለማለት ፈልጎ ነው"
“ለነገሩ ገብቶኛል:: ጥያቄህ ግን በተለይ ስትደግመው
አሳቀኝ ይቅርታ እሽ የአያቴ ፎቶ ነው፡"

ምን ነካኝ፤ መረጋጋት አለብኝ፧ ካለበለዚያ ሴት ነሽ ወንድ' ብዬ መጠየቄ አይቀርም... ትዕግስት ያስፈልገኛል:: ደግሞ ዝም
ብልስ! ምን አስቀባጠረኝ። ፋይዳ ለሌለው ጥያቄ ግምት ውስጥ መግባት የለብኝም ... ሲል የመረጠችው ፊላሚንኮ ባህላዊ የስፔን ሙዚቃ መሰማት ጀመረ:: መሬቱን በቀኝ እግሯ መታ መታ
እጆችዋን ወደ ላይ አቁማ ጣቶችዋን እያዞረችና እያሽከረከረች...ስትደንስ ፈዞ ተመለከታት: ያምርባታል!

“ፊላሚንኮ ዳንስ ነው  ትችላለህ? አላችው ቆም ብላ።

“አልችልም'' አላት

ሁስተኛው ፎቶ ላይ አይኖቹን አፈጠጠ: የዋና ፓንት የለበስች ከግራ ትከሻዋ ወዳ ዳሌዋ የወረደ ሪቫን በእጆችዋ የቁንጅና
በትረ ውበት የያዘች ቀኝ እግሯን ወደ ፊት ከወገቧ ትንሽ ወደኋላ ለጠጥ ብላ የቆመች ሴት ተመለከተ
ማናት?' ጠየቀ ራሱን።
ማንም ትሁን። ለምን ማወቅ ያስፈልገኛል: ኮንችት
የምታደንቃት የስፔን ውብ
በቃ! ሊረሳት ሞከረ:

ጠይቆ ማወቅ ምን ነውር  አለው? ይልቅ ጠይቃት ፧
እየተሳሳቱ መጠየቅን መቀጠል እንዲያውም የጥንካሬ መለኪያ
ነው... ሁለተኛው ሃሣቡ አሸነፈ:

“ያች ደግሞ ማን የምትባል የስፔን ቆንጆ ናት? ጠየቃት
ጨከን ብሎ። አጠያየቁን ወደደው።

“ኮንችት  ፔሶ ቤኒ ኮንችት” አለችው፡ ግራ ገባው: የእሷን
ስም ፔሶ ቤኒ ኮንችት እንዳለችው ያስታውሳል: ግን ደግሞ እሷ ትሆናለች የሚል ግምት አልነበረውም።

"በስም አንድ ናችሁ" በአጠያየቁ ኮራ:: ስሟን እንዳልረሳው
እግረ መንገዱን አስታወቃት።

“በስምም, በአካልም በመንፈስም አንድ ነን" አለችው ወደ ሌላ ክፍል ለመሄድ እያዘገመች። ጨነቀው እንደገና

“አንች ነሽ እንዴ?”

“አዎ እኔ ነኝ: በተለያዩ ጊዜያት የቁንጅና ውድድር
ተካፍያለሁ: ይሄ ያሸነፍኩበትና ሚስስ ካታሎንያ የተባልኩበት ነው።

ስራዬም እኮ ሞዴሊስትነት ነው'

አፉን በአድናቆት ከፈተ: መራጮችን አደነቃቸው: “ጎበዞች ቆንጆ ያውቃሉ" አለ ሳያስበው ከት ብላ ስትስቅበት ቅዠት ላይ
መሆኑን አወቀ: እየሳቀች ወደ ውስጥ ገባች

አራት በሮች ክፍሉ  ውስጥ አሉ። አንዱ የገባበት ነው:
ሌሎችን አላወቀም፡

በአጋጣሚው እንደገና ተገረመ፤ በበታችነት ስሜት ስሜቱ እጁን ሲያጥፍ ተሰማው፡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም አደረበት በሃሣቡ ራሱን ብቸኝነትን ፈንቅዬ ወጣሁ ወዳለበት ጉድጓድ ተመልሶ ሲገባ አየው።

ኮንችት በሩን ከፍታ ገባች።

“አያቴ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የደረሰበት ከብዙ ልፋትና
ድካም በኋላ ቢሆንም በአፍለኛ የወጣትነት ዘመኑ አፍሪካዊ መሆኑን
በሚገባ ያውቅ ነበር: ኋላ ግን በግል ጥረቱ የአፍሪካን ምድር ከቱኒሲያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ከዚያም ከፊል ጥርጣሬው አይሉ
ወደነበረበት ወደ  ምዕራብ  አፍሪካ  ቢጓዝም  እንዳሰበው በልጅነቱ
ጥሎት የወጣውን የአባቱን አገር ማወቅ አልቻለም ነበር" አለችና፡

“እንዴ ይቅርታ ወደ ጓዳ ገባ ልበልና የሚበላላውን
ላዘጋጅ:: ከዚህ በፊት ግን ቺቫስ ሪጋል ሬሚ ማርቲን፤ ጆኒ ወከር! ብላክ ሌብል ሄግ ውስኪ የሚጠጣ አለልህ፤ ቤንሰን ማርልቦሮ
ዊንስተን ሲጋራዎች እኒሁልህ: ፍሪጅ ውስጥ ለስላሳ  ቢራ በረዶም... አለ ሙዚቃው የእኔ ምርጫ በመሆኑ ይቅርታ እሱንም
ካሉኝ ዲስኬቶች መርጠህ ያሻህን ማዳመጥ ትችላለህ ቤተኛ ሁን እሽ ብላ ፈገግታዋን አፍስሳበት ገባች:

ሶራ ፈገግ ብሎ ለምስጋናው ምላሽ አቅርቦ ወደ ውስጥ
ስትጀባ የሰውነት ቅርጿን ትኩር ብሎ ተመለከተ: የለበሰችው አጭር
ቀሚስ ወልቆ ስስ ጋዋን ስትለብስ የሰውነቷን ቅርፅ እንደ አጉሊ መነፅር አጉልቶ የሚያሳይ እስኪመስለው ጠባብ ትከሻዋ ስርጓዳ
ወገቧ የሚያማምሩት እግሮችዋ... ቁልጭ ብለው ታዩት።

ነጩ ፓንቷ የሴትነት ብልቷ… እራቁቷን እንኳ ብትሆን
ያን ሁሉ የሚያይ አልመሰለውም:

ከገባች በኋላም ቅርጿን ለማስታወስ ፈለገ።

'ለምን? ጊዜ አለኝ። የዚችን ቆንጆ ምስል ህሊናዩ
በሚፈጥረው ቅርፅ እያሰብሁ ማበላሽት የለብኝም አለና የቺቫዝ
ሪጋሉን ጠርሙዝ አንስቶ በብርጭቆ ጨመረና ከፍሪጁ በረዶ አውጥቶ ሁለት እንክብል ጨምሮ ነቅነቅ በማድረግና ወደ ከንፈሩ አስጠጋው። ከዚያም ወደ መስቱ ጠጋ ብሉ በነጩ መጋረጃ ቁልቁል ተመለከተ። መንገዱ ላይ ሰዎች ተሽከርካሪዎች... ይርመሰመሳሉ። ህፃናት ከመንገዱ ማዶ ዥዋ ዥዌ ኳስ በሮለር ብሌድ መንሸራተቻ ይጫወታሉ።

ሶራ ውስኪ የያዘ ብርጭቆውን አስቀምጦ የሲጋራ ፓኮውን ሲያነሳ “ጠሽ ጠሽ" የሚል ድምፅ ቀጥሎ የምግብ ሽታ አወደው። ያኔ ረሃብ ተሰማው፡ በሆዱ ፍላጎት የተስማማ  አይመስልም::
ህሊናው በራበው ግን ተስማምቷል። ያን ሊገልፁት የሚከብድ ገላ እንደገና ማየት…..

💫ይቀጥላል💫
👍371
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ- 15
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
እሺ ጀግናው.አመጣህልኝ››
አይ ጌታዬ ችግረ ተፈጥሮለል››የጋለ ሰውነቱ ሲቀዘቅዝ ተሰማው
ይሄውልህ አንድ ግዜ በእንቤታ በተንፈራገጥሽ ቁጥር በእጄ ከሉት ዘመዶቾ አንዱን እንደምገድ ነገራት ሁለተኘውን ስትደግም ደግሞ ሌለኛውን..››
እንደዛ ከሆነ ጥሩ
‹‹እሺ ጀግናው…አመጣህልኝ?››
‹‹አይ ጌታዬ ችግር ተፈጥሮል››የጋለ ሰውነቱ ሲቀዘቅዝ ተሰማው
‹ይሄውልህ አንድ ግዜ በእንቢታ በተንፈራገጥሽ ቁጥር በእጄ ከሉት ዘመዶቾ አንዱን እንደምገድ ንገራት ሁለተኛውን ስትደግም ደግሞ ሌለኛውን..እንደውም ስልኩን ጆሮዋ ላይ ለጥፍልኝ››
‹‹ጌታዬ እንደዛ አይደለም፡፡ ከእኔ በፊት አራት ሰዎች ቀድመው ደርሰው አፍነዋታል፡፡አብሮትም አንድ ሰው ነበር ፤ሁለቱንም ነው ያፈኗቸው፡፡››
ምን እያልከኝ ነው… ማን ሊሆን ይችላል?›
‹‹አላወቅኩም . .ጌታዬ….››
‹‹የመንግስት ሰው ናቸው .ማለቴ ፖሊሶች ናቸው?›
‹አይ ፖሊሶች እንኳን አይደሉም..ማለቴ የፖሊስ ለብስ አለበሱም››
‹‹በቃ ደህንነቶች ይሆናሉ›እንግዲያው ቀስ ብለህ ከኃላህ ተከተላቸውና የት እንደሚወስዷት አጣራ…ጓደኖችህን አሁን ልካቸዋለው፡፡››
ስልኩን ዘጋና እጁን ወደፊት በቡጢ ሰነዘረ ፊት ለፊቱ ያለው ደግሞ የመስተወት መስኮት ነበር.. ተፈረካከሰ ፡፡የእጁን ጣት ሸረከተው..ደሙ መንጠባጠብ ጀመረ…ግድም አልሰጠውም፡፡
‹ስልኩን አነሰሳና አቶ ሙላ ጋር ደወለ.›
‹ስማ አንተ…እነዛ ባለስልጣኖች ምን እየሰሩ ነው?››
‹‹ምን ሰሩ?››
‹‹ይሄው የሴትዬዋን ቤተሰቦች አግቼ በእቅዴ መሰረት መልዕቱ እንዲደርሳት አድርጌ ነበር…እሷም ሁለት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ነበር እየሮጠች እቤቴ የመጣቸው
‹‹እቤቴ ደስ ሲል እና ነገሩ አለቀ በለኛ! ከጉድ ወጠን ማለት ነው…እና ገደልካት?›አለ አቶ ሙሉ በሚፈነጥዝ ድምፀ
‹‹እስኪ መቀባጠርህን አቁመህ አድመጠኝ››
‹እያዳመጥኩህ ነው .ምን ተፈጠረ?››
‹‹ከእኔ ቤት ወደአለሁበት ቦታ የሚያመጣት ሰው ልኬ ነበር.. ልጁ እዛ ሲደርስ ግን ሌላ ሀይል ቀድሞ ደርሶ አፍኖ ወደ ሆነ ቦታ እየወሰዶት ነው ››.
‹‹ማን ነው እንደዛ የሚያደርገው…?››
ማን ይሆናል .እንደዛ የማድረግ ኃይል ያላቸው እነዛ ባለስልጣናት ብቻ ናቸው…እና አሁን የእኔ ሰው እየተከተላቸው ነው…. አሁን ደውልና መኪናቸወን አቁመው ልጅቷን አስረክበውን ወደሚሔዱበት እንዲሄዱ ንገራቸው፡ ካልሆነ ከ30 ደቂቃ ቡኃላ ጉዳቸውን ለመለው አለም ነው የምነዛው››
‹‹አረ ፕሮፌሰር ተረጋጋ..እነሱ ምን ለማትረፍ እንዲህ ያደርጋሉ.በችኮላ የማይሆን ነገር አድርገህ ሁላችንንም ገደል እንዳትከተን››ሲል ፋራቸውን ገለፀለት፡
ምን ሊያገኙ አልክ…አሁን እኮ እሷ ማለት ለሁላችንም ትልቅ መጫወቻ ካርድ ነች….እሷን ያገኘ እራሱን ማዳን ብቻ ሳይሆን ጠላቴ ነው አያስፈልገኝም ያለውን ሰውም ያጠፋበታል.››
‹‹እና አንተ እጅህ ብትገባ እንደዛ የማድረግ እቅድ ነበረህ ››
‹‹አዎ ነበረኝ ግን.አንተ ከጠላቶቼ መካከል አይደለህም…ምነው ነህ እነዴ?›
ተርበተበተ‹‹ፕሮፌሰር የምን ጠላት አመጣህብኝ..በቃ አሁን ደውልላቸዋለው››
ስልኩ ተዘጋ…የእጁ ደም አሁንም እየተነጠባተበ ነወ..ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ የመጋረጃን ጨርቅ ከጨጫፍ ይዞ ሸረከተና ጠቀለለው፡ከዛ ስልኩን አነሳና ደወለ…ከብዙ ጥሪ ብኃላ ተነሳለት
አንተ ሰው እኔ እኮ ሽማጊሌ ነኝ በውድቅት ሊት አትደወውልልኝ ብልህ አልሰመ አልከኝ››በወቀሳ ተቀበሉት
ሼኪ ይቀልዳሉ እንዴ.መቼሰ በጣም አስቸጋሪ ነገር ባይፈጠር በዚህ ሰዓት አልደውልም›
ነገርኩህ እኮ ጥዋት ይደርሳል..ደግሞ ምንም ቢከሰት ትወጠጣዋለህ.›
‹ያሾፋሉ አይደል…አሺ እንዳለሉት እወጣዋለው.. አሁን በቀደም እዘጋጁ ያልኮትን ዶላር ነገ ያቀብሉኛል..ከሳይውል ሳያድር ከሀገር መውጣጣት አለብኝ፡፡
እ..እስኪ ፈልጋለው..አለ ያልኩህን ሌጄ ለእኔ ሳሳነግር ለጉዳይ ተጠቅሞበታል.እስኪ ሰሞኑን ከዚህም ከዛም እንፈልጋለን›
በሼኪወው ንግግር እምሮውን ሊስት ትንሽ ነው የቀረው‹ሴኪ ያለንበት ስቺዌሽን ግልፅ ሆነሎት አይመስለኝም..ከገባን ሁለቻንም ንነ ን መቀመቅ ውጥ የምንገባው…..ለሁላችንም የምለፋው እኮ እርሶ ትልቅ ሰው ኖት በዚሀህ እድሜየት መንገላታት የለቦትም ብዬ ነው.እረሶ ግን
‹ስማ ፕሮፌሰር በል አሁ ተኛ ቸው›ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጉበት፡፡
ማመን አልቻለም…እኚ ሰውዬ ማን ነው አይዞችሁ ያላቸው…እንዴት ነው እንዲህ ሊንቀባሩብኝ የቻሉት፡፡ወይ እምሮቸውን ስተዋል…ወይ ተስፋ ቆርጠዋል ወይ ደግሞ የሆነ እኔ ያልደረስኩበት ሚስጠጥር በእጃቸው ገብቷል..ደከመውና እዛው በቆመበት ሸርት ብሎ ወል ላይ ጠቀመጠ
ታዲያ ጉዳዩን እራስህ በጥነንቃቄ ምራው..ምንም ችግር እንዲፈተረር አልፈልግም.እናም ደግመ ማንኛቸውም እንዳይጎዱ›
የፕሮፌሰሩ መልዕክተኛ ከፕሮፌሰሩu ጋር አያወራ የነበረው ከመኪናው ወጥ ገቢናውን ተደግፎ ነበር..አውርቶ ከጨረሰ ብሃላ እንደታዘው መኪናዋን ለመከተል ወደመኪናው ሊገባ ሲል ከኃላው ማጀራቱ ላይ ቀዝቀቃዛ ብረት አረፈ..ሊዞር ሲል
‹‹ቀጥ ብለህ ባለህበት ቁም››የሚል ድምፅ አስጠነቀቀው…እንደተባለው አደረገ፡፡.ትዘዛዙን አክብሮ ገባና የሹፌሩን ቦታ ያዘ..ሌለኛው ዞሮ ገባና ከጎኑ ተቀመጠ…ሽጉጥ የደቀነው በጥንቃቄ የሃላውን በራፍ ከፍቶ ገባ…ሽጉጡን በጭንቅላቱ አስተካክሎ አንደቀነበት ነው፡ገቢና ከጎኑ ያለው ዘና ብሎ ስልክ አውጥቶ ደወለ..
‹ሄሎ ስንደርስ ይዛዋት ሄደዋል .ግን አንድ የእነሱን ሰው ከነመኪናው ይዘነዋ… ምን እናድርገው?፡፡›ታጋቹ እንዲሰማው ሞባይሉን ላውድ ላይ አደረገ…
‹‹ከፈለጋችሁ ሰባብሩት..ካልሆነም ቆራርጡትና ቀጥታ ወደ ወሰዷት ቦታ እንዲመራችሁ አድርጉ፡፡እነአቤሎም ወደ እናተ እንዲመጡ አ,እና እንዲያግዛችሁ አደርጋለው … እኔም መጣሁ››ስልኩ ተዘጋ፡
‹ሀለቃችን ያለውን ሰምተሀል አይደል?፡፡›
‹አዎ ሰምቼያለው…..››
‹‹ስለዚህ እነደማይ አንተም እንደ እኛ ባለሞያ ነህ… ስለዚህ ከአንተ ጠብ የለንም…ጓደኞችህ ወደየት ነው የወሰዶቸው?››
‹‹አልገባችሁም..ሰዎቹ ጎደኞቼ አይደሉም…በእርግጥ እኔ ፕሮፌሰሩ ሂድና አምጣት ብሎኝ ነበር የመጣሁት…እራሷ ደውላ ውሰደኝ ስላለችው ኃይል ና ግርግር ስለማያስፈልግ ብቻዬን ነበር የመጣሁት፡፡ ስደርስ ግን አራት የታጠቁና የተደራጁ አፋኞች መኪናዋ ውስጥ ሲከቷት ደረስኩ፡፡ለሀለቃዬ ደውዬ ስነግረው ተከተላቸውና የገቡበትን እይ ብሎኝ ነበር..›
‹‹እናስ?›
‹‹እናማ እናንተ አሰናከላችሁኝ ..››
‹እስኪ ፍጠን ሞተሩን አስነሳው..በየት ነው የሄዱት፣በፊት ለፊት ሄደው ማደያው ጋ ሲደርሱ ወደግራ ነው የታጠፉት…››
‹ንዳው.ንዳው›ጮኸበት፡፡
መዳው.. ወደግራ ታጠፉ ፡፡አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ዙሪያ ገባቸውን እቃኙ ቢበሩም የተባለችውን መኪና ሊያገኞት አልቻሉም…
መልሶ ደወለለት…ለአብዬት…ያለውን ነገረው..፡፡
‹‹እወነቱን ከሆነ ፕሮፌሰሩ ጋር ይውሰዳችሁ….አሳልፎ ይስጣችሁ እሱን ይዛችሁልኝ ኑ..››
‹‹እሺ››
‹‹ነግሬሀለው ስህተት አልፈልግም..ወይ ዶክተሯንና ካሳን ወይም ደግሞ ፕሮፌሰሩን አሁኑኑ ፈልጋለው..››ስልኩ ተዘጋ
‹‹ያው የስራውን አካሄድ ምታውቅው ነው…አንተ ላይ ብጢ መሰንዘር ወይ ደግሞ ተኩሶ ተፋህን መበርቀስ አልፈልግም…..ካልሆነ ግን
‹‹ጓደኛዬ ላይም ሆነ እኔ ላይ ምንም አደጋ እንዲደርስ አልፈልግም››መለሰ
‹‹ነገርኩህ እኮ..እንደው ቀልል እንዲል ካደረጋችሁ ለሀለቃችን በማስረዳ ከዚህ ያጣችሁትን ስራ እኛ ጋር እንድታገኙ ማድረግ እንችላለን፡፡
👍29
‹‹ችግር የለውም…ከሰውዬው ጋ እኮ ገና ዛሬ ነው ስራ የጀመርነው…››
ስለዚህ ወደእዛው ንዳው…ላስጠንቅቅህ.ምንም አይንት የማታል ወይ የማጭበርበር ሙከራ ለሞከር እንደታስብ››
ተስማማና ወደፕሮፌሰሩ ቤት መንዳት ጀመረ. . መንገድ ላይ ሌላ ሁለት ጓደኞቻቸውን ጨምረው አራት ሆነው ፕሮፌሰሩ የተደበቀበት ቤት ደረሱ….ጠቅላላ ኦፕሬሽኑ 15 ደቂቃ ነው የፈጀው….ሲደርሱ ጠባቂዎቹ ዶክተሯን የወሰደውን መኪና ለማግኘት ተሰማርተው ስለነበረ ከዘበኛው በስተቀር ሌላ ጠባቂ አልነበረውም..ዘበኛውን ደግሞ ሰብለ በአንድ ጥፊ ነው ዝም እንዲል ያደረገችው ፡፡ ከቤቱ አውጥተው መኪናቸው ውስጥ ጨመረው ይዘውት እየሄዱ ነው፡፡
ፕሮፌሰሩ መንገዱን ሙሉ እየለፈለፈፈ ነበር‹‹ለባለስልጣኖቹ ሀለቆቻችሁ ንገሯቸው…ካለቀልኝ ያልቅላቸዋል..እኔን ማሳፈን ቀላል እንዳልሆነ አልገባቸውም›› ስላስቸገራቸው በአፉ ጨርቅ ጠቅጥቀው አሰሩት፡፡
እንደደረሰ ሰሎን አስገብተው አብዬት ፊት ሲያቆሙት ደነገጠ…በፍፅም ያልጠረጠረው ተአምር ነው..ይንን ሰው በፎቶ እነዶዬ አሳይተውታል…ዶክተሯን ይረዳታል የተባለው ሰውዬ ነው…በአካል ሲያየው በዝና ከሰማውና በፎቶ ባየው ጊዜ ከፈራው በላይ ፈራ፡፡አብዬት ፐሮፌሰሩን አንገቱን አንቆ ወደፎቅ ይዞት ወጣና አንድ ባዶ ክፍል ውስጥ ወረወረው፡፡በራፉን በላው ላይ በመዝጋት ቀርቅሮበት ወደ መሳሪያ ማከማቻ ክፍል ሄደና ሚፈልጋቸውን መሳሪያዎች ሰበሰቦ ተመለሰ.. ፕሮፌሰሩን ወደአስቀመጠበት ክፍል ገባና ፊቱ ለፊቱ ደረደራቸው….፡፡
‹‹የት ነች ያለችው?››
‹‹በእውነት በፈለከው ነገር እምልልሀለው የት እንዳች አላውቅም፡፡››ፕሮፌሰሩ የወላጆቹን ዱላ ፈርቶ እንደሚሽቆጠቆጥ ህፃን ልጅ ተርበተበተ
‹‹አንተን ልታገኝ ነበር የመጣችው…››
‹አዎ ደውላልኝ ካንተ ጋር ማውራት ፈልጋለሁ አለቺኝ….እሺ ብዬ መኪናና ሺፌር ላኩላት…ሹፌሩ ሲደርስ የሆኑ ሰዎች እያፈኗት ነበር….ሹፌሩ ሲነግረኝ.ተከተልና አድናት ብዬው ነበር….ከዛ ብኃላ የሆነውን አላውቅም.››…
አይዞህ እንድታውቅ አደርጋለው..አለና ከጩቤዎች መካከል አንዱን መዘዘና እያገለባበጠ ወደእሱ ተጠጋ..ፕሮፌሰሩ አይኖቹን አጉረጠረጠ…. አብዬት ድንገት ወደምድር ቁጢጥ አለና ጩቤውን ግራ እግሩ ላይ ሰካው…ጩቤው በጫማው አልፎ እግሩ ላይ ተሰነቀረ….ፕሮፌሰሩ አጓራና መሬት ላይ ተዘረረ…
‹‹ምን እያደረክ ነው…?ምትፈልገውን ነገር በሰላም አትጠይቀኝም….?ምን አይነት ጭካኔ ነው?››ለሀጩን እያዝረከረከ ለፈለፈ.
‹‹እሺ አሁን እራስህን ታረጋጋለህ ወይስ ልድገመው…?››
‹‹አረ በፈጠረህ፣ግፍ አትፈራም…?››
‹‹እሺ እንግዲህ እንድደግመው ካልፈለክ….አሁን እራስህን አረጋጋና ዶዬህ ጋ ደውል››
‹‹ዶዬ ማን ነው?››
‹‹ነው ልድገመው ማለት ነው›› አለና ሲጠጋ
‹‹አይ ማለቴ ዶዬ እዚህ የለም ብዬ ነው››
‹‹እኮ እኔም እኮ አለ አላልኩም..ደውልለትና የዶክተሯን ቤተሰቦች እቤታቸው በክብር ተንከባክቦ ይመልሳቸውና ቀጥታ በቪዲዬ ያረጋግጥልኝ፡፡
‹‹ስልኬን እቤት ጥዬ ነው የመጣሁት....ቁጥሩን አላውቅም››
‹‹ግድ የለም….››ስልኩን አወጣና ደወለ…ለፕሮፌሰሩ አቀበለው..የተባውን መልዕክት ያለምንም ዝንፈት ፈፀመ ….
‹‹አብዬት ለዶዬ ደወለለት..››
‹‹አቤት አብዬት››
‹‹ጦርነቱ ከእናንተ ጋር አይደለም፡፡››
‹ነው እንጂ…ፕሮፌሰሩ ለህግ ፊት ከቀረበ እኛን አሳልፎ የማይሰጠን ይመስልሀል››
‹‹ስለዚህ አግዙኝ ላግዛችሁ››
‹‹ምንድነው ምናግዝገህ?››
እንደምታውቁት እኔ ፕሮፌሰሩን ይዤዋለው..ሙሉ የሚባለውንም አጋሩን በእጄ ገብቶ አሁን ይዘውት እየመጡ ነው…..ዶክተሯን እና አንድ ጓደኛችንን ደግሞ ማን እንደጠለፋቸው አናውቅም….እንሱን እንዳገኝ ከረዳችሁኝ..እኔም ወደእናንተ ሚጠቁም ማንኛውንም የማገኘውን መረጃ ላጠፋላችሁ ቃል እገባለው፡፡
‹‹በቃ አሁን ወደአዲስ አበባ ለመምጣ ከጎንደር ከተማ እየወጣን ነው..ነገ እንደገባን እንገናኝና በጉዳዩ እንወያይ››
‹‹ዶዬ…ታውቀኛለህ እኔ አብዬት ነኝ….በአካል አንገናኝም….በስልክ እስከፈለከው እናወራለን..ደግሞ የገባሁትን ቃል መቼም እንደማላጥፍ ታውቃላችሁ..እናንተም እንደምታከብሩ አውቃለሁ….ጓደኞቼን እንዳገኝ እርዱኝ እኔም እንዳልኩት አደርጋለሁ››
‹‹እሺ አቢ…እንዳልክ ይሆናል እናመሰግናለን…..››
‹‹ምንም አይደል፡፡››
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍405
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

ከፖርት ፕሪንስ በስተ ምስራቅ ፓርቶሪኮ ሳንጁአን ውስጥ የግል እርሻ የጀመረው አሌክስ ቀደም  ሲል የስፔን ፋሽዝም
አራማጅና የጦር አባል ከነበረው ስመ ጥር አባቱ ጋር ወደ ፓርቶሪ
በተደጋጋሚ ከሄደ በኋላ ሳንጁአን ለመኖር እንዲወስን ተፈጥሮአዊ
ፍቅሩ አደፋፈረው፡

የሻምበልነት ማዕረግ የነበረው አባቱ ልጁ በእርሻ ትምህርት ሰልጥኖ ህይወቱ በእርሻ ምርት ላይ ቢመሰረት የወደፊት ዕድሉ
የተቃና ደስተኛና ሃብታም ሊሆን እንደሚችል በመከረው መሰረት
አሴክስ የአባቱን ህልም የእራሱ በማድረግ ህልሙን ለማሳካት የሚያስችለውን ጥረት ፈጽሞ በመጨረሻ ተሳካለት፡

አሌክስ ደጋግሞ ስለ እርሻ ዘመናዊ እርሻ ስለሚያስገኘው
ብልፅግና ስለ ተሻሉ የምርት ውጤቶች ማውራት እንጂ በፍቅሩ ተረትታ
እንደነፍስ ጡር ለምትብረከረከው
ፍቅረኛው ቁብ
አልነበረውም ሌላው ቀርቶ እግሩ ስር እንደምትታከከውና "ፔሙስ" ብሎ እንደሚጠራት ድመቱ ሲገናኙ እጁን ሰዶ ዳብሷት ካልያም እጆችዋን ስቦ ወደ ደረቱ አስጠግቷት አያውቅም አይብዛ እንጂ
አንድ ወቅት የፍቅር አባባሎችን ይለዋወጡ አብረውም እየተሻሹ
ጊዜያቸውን በደስታ ያሳልፉ የነበረ ቢሆንም! ያ የስሜት መመሳሰል ግን ከጠለቀ ብዙ ወራቶች ተቆጠሩ።

ይህ የቸልተኝነት ባህሪው ሸበላ ቁመናው የታከታት ደረቅ የአጨዋወት ስልቱ ሳይቀር አኜስን ለአሌክስ ያላትን ስሜት ከእለት
ወደ እለት እንዲያድግ አደረገው። አንዳንዴ እንዲያውም፡-
“አሌክስ! እባክህ ለፍቅራችን የሚሆን ጊዜ ይኑርህ? እባክህ በፍቅር
ስሜቴ አትጫወትበት!...” በማለት ምርር ብላ ስትነግረው፡-

“እባክሽ አኜስ ታገሽ!
ትዕግስት ይኑርሽ! ልትረጅኝ
ሞክሪ! በአሁኑ ሰዓት የፍቅር ስሜቴ በወደፊት ዓላማዬ እንደ ጉም ተሸፍኗል። አንድ ወቅት ግን ጉሙ ይበተናል፤ በሰማያዊው ሰማይ
ከምስራቅ ወደ ምዕራብ እንደምትጓዝ ፀሐይ የፍቅር ብርሃን ፍንትው ብሎ ይፈነጥቃል...'' ይላታል:

“አሌክስ! እኔ'ኮ ብዙ ላሳስብህ አልሻም። በሳምንት ቢያንስ
ለተወሰነ ደቂቃ እንኳ ፍቅር እንድንለዋወጥ ለማድረግ ሞክር ፧እየተጎዳሁ ነው” ስትለው፡-

“እስኪ እሞክራለሁ አንች ግን ጠንከር በይ: በህልሜ
ልትደሰች ሞክሪ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በተከበበችው ሳን ጁን
ውስጥ የሚኖረው ቡቃያ ንፋሱ ጎንበስ ቀና ሲያደርገው ይታይሽ!
አዲዎስ ብሏት ይሄዳል።

አንድ ቀን ግን አሌክስ በጅፕ መኪናው መኖሪያዋ ድረስ መጥቶ ድንገት “ለሽርሽር እንሂድ? አላት።

“የት?” አለችው አኜስ ግራ ተጋብታ።

“ሱ..” አለ አፉን በቀኝ እጁ አመልካች ጣት እየጠበጠበ።

“አሌክስ የት እንደምንሄድ መንገሩን ባትፈልግ እንኳን ወጣ እንደምንል ቀደም ብለህ ፍንጭ መስጠት ነበረብህ: ከሰዓታት
ወይንም ከቀናት በፊት ወጣ እንደምንል ነግረኸኝ ቢሆን ኖሮ ነፍሴ በደስታ ከመዝለሏም በተጨማሪ ስሜቴ በጉጉት ተበረጋግዶ በናፍቆት ይጠብቅህ ነበር: አሁን ግን ልቤ በሐዘን ቀዝቅዛለች። ስሜቴም በድን
ነው። እኔም ስላልተዘጋጀሁ የትም መሄድ አልፈልግም” አሰችው።

ያልተለመደ ፈገግታ አሳይቶ ባልጠበቀችው መልክ የግራ እጅዋን ብድግ አድርጎ ጣቶችዋን ሳም ሳም አደረጋት፤ ጉንጯን በቀኝ
እጅ አመልካች ጣቱ ደባበሰላት: ሽቅብ አንስቶም ከንፈሯን በከንፈሩ
ደባበሰላት።

ወዲያው ልቧ ጋለች ሰውነቷ በሙቀት ተጥለቀለቀ፡
የፍቅር ሃይሏ ከየስርቻው ተሰባሰበ ስለዚህ! “ማሬ!
እንሂድ" አለችው::ሃሳቡን እንዳይለወጥ እየሰጋች: አሌክስ መኪናውን እያሽከረከረ ጭኖችዋን በቀኝ እጁ እየደባበሰ የምትሆነውን አሳጣት: ያ ጨካኙ አሌክስ ሳይሆን የፍቅር መልአክ ሆነባት…

“አሌክስ አልቻልሁም አለችው እየተስለመለመች
ጥቂት ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ።

“ትዕግስት ጥሩ ነው..."

“ኡፍ ስብከትህን አቁም። በሰዎች ሙያ ጣልቃ አትግባ መኪናዋን ይልቁንስ አቁም አለችው በትዕዛዝ መልክ፡ መኪናዋ ወደ
ዳር ወጥታ ቆመች ሞተሯ ጠፋ።

ከተቀመጠችበት ዞር ብላ እጆችዋን ዘርግታ የአሌክስን
አንገት አቀፈችው። ተገናኙ
ረሃብተኛዋ ከንፈሩን ጎረሰቸው እፅዋት በነፋሱ ጎንበስ ቀና ይላሉ ከርቤው እየጤሰ  መላዕክት
እያጀቧቸው ሽቅብ በፍቅር ስረገላ አረጉ።

“አሌክስ! እኔ አላምንም... እንዴት ደስ አለኝ ለካ እንዲህ የደስታ ምንጭ ነህ እሰይ እንኳን ታገስኩህ እንኳን ቻልኩህ እንግዲህ ዳግመኛ ከፍቅር ሠረገላችን አንወርድም አይደል! ከምድር ላይ ይልቅ እዚህ ነፍስ ነህ..." እያለች ላዩ ላይ ተንከባለለችበት

የአትላንቲክ ውቅያኖስ ማዕበል በርቀት ከቆሙት መርከቦችና አጠገባቸው ካለው የድንጋይ ግንብ ጋር እየተላተመ አረፋ ሲደፍቅ
ከኮሎምበስ መታሰቢያ ግዙፍ ሃውልት ትይዩ የሚነፍሰው ጤሮ ንፋስ በጆሮ ግንዷ እያፋጨ ሲያልፍ ግን አይኗን ገልጣ ከገነት ወደ ምድር ተመለሰች። ምድሯን ውቅያኖሱን ስታይ አስጠሏት፡ አሌክስ
አሁንም አብሯት አለ ያ ሲያደርጉ የነበረውና አሁን አጠገቧ ባለው አሌክስ መካከል ግን ልዩነት ያለ መሰላት፤ ተጠራጠረችው።

“ማሬ የት ነው ያለነው?" ከሰመመኗ እንደነቃች ጠየቀችው።

“ሁዌልቫ ነን! ለስንብት አመች በመሆኗ የምሄድበትንም ከርቀት ላሳይሽ ስለምችል  ሁዌልቫን መርጨልሻለሁ" አላት ሳብ አድርጎ ወርቃማ ዞማ ፀጉሯን ስሞ፡

“ሁዌልቫ” ይህ ስም ምድር ላይ ያውም ስፔን ውስጥ
የምታውቃት ከተማ ስም ነው:

“ለምን ግን እዚህ አመጣኸኝ?” ተሸበረች:

“ለስንብት አልሁሽ እኮ! አላት ወደ እሱ ጠጋ አድርጎ
እያቀፋት ሰውነቱ ሰውነቷን ሲነካት እየዘገነናት

“የምን ስንብት?... ደግሞ እንዴት ጨካኝ ነህ?... በአንዴ ከደስታ ወደ መከራ ትመልሰኝ..." አለችና ልሳኗ ተዘጋ: አሌክስ ሲስማት ከንፈሯ እንደ በረዶ ቀዘቀዛት።

ዙሪያቸውን እንደ እንቦቀቅላ ህፃን ድክ ድክ የሚሉት
እርግቦች አንዳች ነገር እንደመጣባቸው ሁሉ ድንገት ግር ብለው ወደ
ሃይቁ አቅጣጫ በረሩ።
አኜስ የአሌክስን እጆች ወርውራ እርግቦችን
ተመለከታቸው።

እጥፍ ብለው እንደገና ሽቅብ ጎነው በረሩ: አሌክስ ፊቷን ወደ እሱ አዙሮ
“ሰርቶ መበልፀግ ስመኘው የኖርሁትን እድል በማግኘቴ
ረክቻለሁ። ፍቅራችን ከብልፅግና ማግስት.. ጆሮዋ ደነቆረ: ከዚያ በኋላ የሚለውን አልሰማችውም።
ፍቅር ከብልፅግና
ማግስት…" አባባሉ በአእምሮዋ አስተጋባ:
ዛሬን አበላሽቶ ነገን ማስዋብ ፍቅርን ገፍትሮ ጥቅምን ማቀፍ
ተምታታባት እሪ ብለሽ ጩሂ አሰኛት… መጮህ ግን ተሳናት::ለመጮሀም ኃይል ያስፈልጋል።

አሌክስን ጠላችው 1
ገፋችው... ከዚያ እርግቦቹ ወደ ሄዱበት አቅጣጫ በረረች “አዕዋፍ ለካ ወደው ከምድር ርቀው አይበሩም ብላ በአየር ላይ ለመብረር ወደ ሰማዬ ሰማያት ለመጎን ሞከረች ትናንሽ ፍጡራን የፈፀሙትን ግን መፈፀም ተሳናት።

ይህ ከሆነና ከአሌክስ በተለየች በአምስት ዓመቷ “አሽቀንጥሬ ጣልሁት ያለችው የከንፈር ወዳጅዋ አንደገና ራባት። ፍቅሩ አገርሽቶ ጤና አሳጣት ስለዚህ ፓርቶሪኮን ለመጎብኘት በሚል ሽፋን ወደ ሳንጁአን ሄደች።

ሳን ጁአን እንደደረስችም አሌክስ በሰጣት የእርሻ ጣቢያ ማዕከል አዳራሻ ሄዳ አሌክስን እንዲያገናኝዋት ጠየቀች። በእርግጥ
👍28
በእእምሮዋ ብዙ ነገር ተፈራረቀባት። ፍቅሩ ጭካኔው. ግዴለሽነቱ
ወንዳወንድነቱ ስሜቷን አምታቱባት ናፍቀዋለች፤ ግን ፍቅሯን  አንኮሻክሻ ሰባብሮታል: ለብዙ ጊዜ ልትረሳው ሞክራለች ድንገት ግን ፍቅሩ ያቃዣታል
የስራ ባልደረቦቹ ማንነቷንና ያላቸውን ግንኙነት ከጠየቋት በኋላ እንድትጠነክር በመምከር “ አሌክስ ለሽርሽር ይዟት በወጣው ጀልባ የአደጋው መንስኤ ባይታወቅም አደጋ ደርሶበት በህክምና
ሊፈወስ ባለመቻሉ አረፈ..." ብለው አረዷት።

ከዚያ ማንን ለማምለጥ መሆኑ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ በመጣችበት አቅጣጫ ሮጠች:: ለዚያች ውብ ከማዘን በስተቀር
የተከተላት ግን አልነበረም: ሃዘኗን አንጂ የአጣችው ፍቅር ምን ያህል ባዶ ብቸኛ አድርጎ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደዶላት የተረዳ
የለም: ይህ ስሜት አይተው የሚረዱት አይደለም ከርቀት ሲያዩት ገለባ ነው ቀላል።
እንደ ቋጥኝ ድንጋይ እየተንከባለለ መጥቶ አከርካሪው የደቀቀበት ያፈቀረውን ያጣ በሽተኛ
ግን ስቃዩን ህመሙን
ስለሚያውቀው ያዝን ይሆናል። አኜስ ግን በጊዜው አዛኝ አላገችም:
ስለዚህ ከመከራዋ
እንደምታመልጥ ሁሉ
ሮጠች።ከግቢው እንደወጣች ቀጥታ ይዟት ወደ መጣው ታክሲ
ውስጥ ገባች። ገራገሩ ሾፌር፦

“ሲኞሪታ! የተከበሩ እመቤቴ! ወዴት ይዥዎት ልሂድ? ሲላት እንደ በሰለ ቲማቲም ፊቷ ቀልቶ አስተዋለ።

“ክብር አልፈልግም
ገባህ? አኜስ ብለህ ጥራኝ: ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ወደ ፈለከው ይዘኸኝ ልትሄድ ትችላለህ: እኔ ደግሞ
የጠየቅኸኝን ሒሳብህን እh
እከፍልሃለሁ" አለችው።
ግር ያለው የታhሲ ሾፌር እንደገና ዘወር ብሎ አያት::
ከእሱ አንፃር ወጣት ናት። ከአቅሟ በላይ የሆነ መረበሽ ግን ያትነከነክናታል። ችግሯን ባይረዳውም አዘነላት:: ሰዎች ሲረበሹ ፀሐይ ወጥታ የምትገባ አይመስላቸውም። ይች ዓለም ለዝንተ ዓለም
በጨለማ ተውጣ የምትቀር ስለሚመስላቸው የሚሰሩትን አያውቁም'
ብሉ አሰበና! “እባክሽን
ለመረጋጋት ሞክሪንና
ከዚያ መሄድ ወደምትፈልጊው
አደርስሻለሁ" አላት ፍፁም በኃዘኔታ ስሜት:

“ማረፍ እፈልጋለሁ መሸሽ እፈልጋለሁ... መኪናህን
አስነሳና ይዘኸኝ ሂድ" አለችው።

“ወዴት ልውስድሽ?" ብሎ እንዳዘዘችው የመኪናውን ሞተር ሲያስነሳ።

“ወደምትኖርበት ወደምትፈልገው ይዘኸኝ ሂድ" አለችው።

ጤና ያጣች መሰለው፡ ይበልጥም አዘነላት። ወደ ሆስፒታል ሊወስዳት ቢጠይቃት ጆሮ ግንዱ ላይ ጮኸችበት።

እኔ ያጣሁ የነጣሁ አፍሪካዊ ነኝ፡ ከኔ ጋር ያሰብሽው ፍፁም እብድነት ነው" ሲላት ደግማ አንቧረቀችበትና፡

ጤነኛ ነኝ! ጤነኛ ነኝ! ስቃዩ ሰዎች በሽታ ከሚሉት
ዝርዝር ውስጥ የለም... አሁን ወደምትወስደኝ ውሰደኝ አለችው:

ሾፌሩ ጉዞውን ጀመረና ወደ ጥቁሮች ሰፈር ይዟት ገባ።
ከዛ... የኮንችት እናት ከሪና ተፀነሰች የከሪና መወለድ ደግሞ አኜስና አፍሪካዊው ሉካዬ ስፔን ውስጥ አብረው እንዲኖሩ ምክንያት
ሆናችው..

💫ይቀጥላል💫
👍32
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ ከፖርት ፕሪንስ በስተ ምስራቅ ፓርቶሪኮ ሳንጁአን ውስጥ የግል እርሻ የጀመረው አሌክስ ቀደም  ሲል የስፔን ፋሽዝም አራማጅና የጦር አባል ከነበረው ስመ ጥር አባቱ ጋር ወደ ፓርቶሪ በተደጋጋሚ ከሄደ በኋላ ሳንጁአን ለመኖር እንዲወስን ተፈጥሮአዊ ፍቅሩ አደፋፈረው፡ የሻምበልነት ማዕረግ የነበረው አባቱ ልጁ በእርሻ ትምህርት ሰልጥኖ ህይወቱ በእርሻ…»
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ


ጆሮዎቹ ላይ ሉቲ አንጠልጥሏል ጥቁር ቆዳው ላይ አልፎ
አልፎ ቡግር መሣይ ነጠብጣቦች ይታያሉ: አገጩ ጠበብ ብሎ
ቁጥርጥር ያሉት ፂሙ ፀጉሮቹ አልፎ አልፎ ጉች ጉች ብለዋል።

አይኖቹ ቦዘዝ ብለው የጭካኔ የእንቢተኝነት... እይታ ይታይባቸዋል። ሶራ የኮንችትን አያት ፎቶ ግራፍ ሲመለከት ቆይቶ ሲጋራውን አቀጣጥሎ ወደ መቀመጫው ተመለሰ።

ኮንችት ከወደ ውስጥ በሩን ከፍታ ብቅ ስትል ቤቱ በምግብ ሽታ ታፈነ። ከዚያ የተጣጠፉ የጠረዼዛ ልብሶችን እያነጣጠፈች
ሰሃን ማንኪያ ሹካ እየደረደረች።

“ወንድ አያቴ ሴት አያቴን በፍቅር ልቧን ጠምዝዞ የጣላት እንዴት እንደሆነ ልንገርህ" አለችው ሙሉ ለሙሉ በፈገግታ ወደ
እሱ ዞራ።

የጡቶችዋ ጎንና ጎኖች ታዩት፡ ጫፋቸው ደግሞ ጋዋኗን ወጠር አድርጎት ተመለከተ። ሰርጓዳ እምብርቷን አይቶ ዝቅ ሲል
ደግሞ ነጭ ፓንቷን አየ የታባክ ተመለስ እንደተባለ ሁሉ እንደመርበትበት ብሎ

“ምን አልሽኝ?" አላት:

“ሴት አያቴ በወንዱ አያቴ ፍቅር እንዴት እንደወደቀች
ልንገርህ"

“እሽ በምናቸው ነው?''

በዝምታው ነው” አለችው።

“ዝምታው!” ተደንቆ አያት:

አዎ!

ዝምታው” አለችውና ቀኝ እግሯን አንዱ ወንበር
ላይ አስቀምጣ ሙሉ ለሙሉ ለስላሳ ጭኗን እያሳየችው ስታየው፡-

“አልገባኝም” አላት ግራ ትከሻውን ሰብቆ። እሷም ጠረጴዛው ላይ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ማዘጋጀቷን እያረጋገጠች፡-

“አዝናለሁ! እይታ እንጂ ማብራሪያ ሊገልፀው አይችልም:: ዝምታ ግን የሴት አያቴን የፍቅር ልብ ማሸነፉ እውነት ነው"
ብላው ወደ ጓዳ ገባች::

ሶራ ምክንያቷን ለመስማት ጆሮዎቹን እንዳቆመ ጠበቃት።የበሰሉና  የቆርቆሮ ምግቦችን እየደረደረች በመካከሉ ቀና ብላ አይታው፡-

“እዚህ ገባ ስትል መታጠቢያና መፀዳጃ ታገኛለህ። በኔ በኩል
አስፈላጊውን ሁሉ እዘጋጅቼ የጨረስሁ ይመስለኛል" ብላ አንድ የቲማቲም ቁራጭ በሹካዋ አንስታ ዋጠች።

ሶራ ወደ ጠቆመችው ክፍል ገብቶ ተጣጥቦ ወጣ፡

የስፔን ባህላዊ ምግብ ጃፓሾ ፒላ... ክሪም በእንቁላል ከወይን ጋር ጠረዼዛው ላይ ተደርድሯል።

“ቦና ፔቲ" አለችው ኮንችት እንብላ ለማለት በፈረንሳይኛ።

"ሳቅ ብሎ “ሜርሲ” አላት: ፈረንሳይኛ, እንግሊዘኛ መቻሏ አስተሳሰቧ በአመለካከቷ አድማስ መጨመር የሚኖረው ጠቀሜታ ታየው:: የአስተሳሰብ ብስለት ከሚያመጡ ምክንያቶች አንዱ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ መሆንና ሌላውን ለማንበብ መቻል እንደሆነ ያውቃል።

ይህን እያሰበ የሚፈልገውን ከአነሳ በኋላ አንገቱን አቀርቅሮ ሲበላ ቆየና ቀና ሲል እሷ ሰሃን ላይ ምንም ምግብ የለም።

“አትበይም?'' አላት ወደ ምግቡ በቢላዋው እየጠቆመ፡

አይኖችቿን በልጠጥ አድርጋ አመሠግናለሁ: ደስ ሲለኝ ብዙ አልበላም" አለችው።

“ለቅርፅሽ እንዳይሆን ፈገግ ብሉ ጠቃት:

“ለዚያ ቢሆን ከልቤ ነው የምጨነቀው:"

“ለምን?”

“ቅጥነት ውበት መሆኑን ገና በመዋለ ህናት እያለሁ
ስለማውቅ" ፈገግ አለች
ጭኖቹ ላይ ያስቀመጠውን “ናፕኪን' አንስቶ አፉን እያበሰ፤

“አዎ! ሴት ልጅ ቀጠን ስትል ውበቷ ይፈካል" ሲል
አቋረጠችውና፡-

“ወንድም ቢሆን ዘርጠጥ ከሚል ከወደ ሆዱ ሰብሰብ ሲልና ትከሻው ሲሰፋ ለሴት ልጅ የደረት ላይ ዋና አመች ይሆናል" ብላ ፈገግ ስትል ሶራ ደነገጠ። ከደረቱ ይልቅ ሆዱ አብጧል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሆን
ኖር እንዴት አማረብህ?”
የሚያሰኘው ውፍረቱ ያኔ አሳፈረው፡

ሆዱ ወደ ውስጥ ሊሸልገው ሞከረ:: ህሊናው ግን “ዘገየህ”ብሎ አሾፈበት: ቅርዑን ጠላው።

መብላቱንም አቆመ።

“ምነው?” አለችው ኮንችት በመገረም እያየችው።

ምኑ?" አላት ስሜቱን ለመደበቅ እየጣረ።

“ሀሳብ የያዘህ ትመስላለህ?"

ደህና ነኝ" አለና ዘና ብሎ ቁጭ አለ።

ኮንችት ከተቀመጠችበት ተነስታ ሶፋው ላይ እግሮችዋን አጣጥፋ ቁጭ ስትል ተነስቶ ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ገባ።

ውሃውን ከፍቶ ጎረድ  ያለ  አፍንጫውን ቦግ ቦግ ያሉ
አይኖቹንን ጠይም ፊቱን ተመልክቶ ጎንበስ ብሎ ሆዱን አየው:በሁለት እጁ ሆዱን ከፍሉ የተከመረውን ትርፍ በጥላቻ ተመልከቶ
"ቆርጦ መጣል ነበር ብሎ ተመኘና ፊቱን በውሃ አበስ አበስ አድርጎ ወጣ።

“ሆዴን እንዴት ጠላሁት መሰለሽ አላት ወደ መቀመጫው እየሄደ።

“ዘገየህ” አለችው ዘና ብላ፡

“ለምኑ? አላት ፈገግ ብሎ።

“ግልፅነት ይጎድልሃል አንደ የሚያስጨንቅህ ነገር
እንደነበር ስለተረዳሁ ስጠይቅህ ደበቅኸኝ፡ አሁን ግን ሳልጠይቅህ
ነገርኸኝ... ደካማነት ነው" አለችውና፡-

“ሆድህን ግን ለምን ጠላኸው?''

“...ለዋና ስለማይመች" አላት።

“ባለህ እንኳ የምትኮራ መሆን አለብህ። ለውበትና ለጤንነት መስተካከል ሽንቃጣነት ምርጫህ ካልሆነ ለሴት ብለህ አካላዊ ለውጥ መፈለግ የለብህም: ሴት ልጅ በባህር ውስጥ ጠልቃ የፍቅር ሉል

ማውጣት በአስተሳሰብ በስለት ወይንም በሌሎች የራሷ ምክንያት
የምትፈልገውን ለመምረጥ እምትቸግር አይደለችም ግን አንድ ነገር አትጣ” ስትለው

“ምን?” አላት ፈጠን ብሎ።

"ለሴት ልጅ ቅርፅ ብቻ ወሳኝ አይደለም፡ ህሊናዊ ይዘትንም የመፈተሽ ተፈጥሮአዊ ፀጋ አላት። ብቻ የሚፈቀር ነገር አትጣ።
ይዘቱም ቅርፁም ባዶ ከሆነባት እንደ ሎጥ ሚስት ገትራህ ፊቷን ሳታዞር ትሄዳለች አለችና ራሷን ሶፋው ላይ አስተኝታ ሳቀች::
ክሊሊሊ..ሊ እያለ የሚያስተጋባው ሳቋ በውስጡ አንዳች ስሜት
ፈጠረበት:: ሳቋ የተለመደ አይነት አይደለም። ግን የሚያውቀው
እንዲያውም ሲያዳምጣቸው ስሜቱን ከሚያዝናኑት ሙዚቃዎች እንደ አንዱ ቆጠረው:

“እኔ እንደምገምተው" ብላ እግሮችዋን ፈርከክ አድርጋ
የእግሮችዋን ጣቶች በእጆችዋ ጣቶች እየደባበሰች ሳለች ነጩን ፓንት እንደገና አየው።

“በአዳምና ሔዋን ዘመን ፍቅርን የጀመረችና የሰጠች ሔዋን ናት: አዳም በእግዚአብሔር ስም ዳቦዋን ቆረሰው፤እና አብረው ተካፍለው በሉት፤ አጣጣሙት:: ከዚያን ጊዜ ወዲሆ ሴት ልጅ
በወንድ አካል ጠልቃ የፍቅር ሉል ለማውጣት የምትፈልገው አንድ
ነገር ብቻ ነው” አለችው።

“ምን?” ሲላት ኮንችት ፈገግ ብላ፦

ጊዜ አነስተኛ ጊዜ" አለችው።

“እንዳባባልሽ እንግዲህ ፍቅርን የፈጠረች ሴት ናት ማለት ነው ሲል።

“የፈጠረች የሚለውን የጀመረች ካልነው እውነተኛው  መላምት ይህ ይመስለኛል" አለችው

"ወንዶችስ?”

ወንዶችማ ሲበዛ ስሜታዊ ናችሁ: ወደ ስር ለመጥለቅና የፍቅር ሉል ለማግኘት የዋና ስልት የላችሁም:: ላይ ለላይ ያዝ ለቀቅ ማረጉን ትመርጣላችሁ: ይህ ደግሞ የተፈጥሮ ችግራችሁ ነው:
ጥልቁን የፍቅር ሉል የምትፈልጉት በሆዳችሁ እንጂ በልባችሁ
አይደለም

ሶራ ፀጥ ብሎ ማሰቡን መረጠ፡

'ውብ... ለስላሳ... አስተሳስብ በሳል. ሞልቃቃ...' እያለ ስለሷ
ሲያስብ በተከፈተው ጭኗ እንደገና አየው። ነጭ ፓንቷን…

💫ይቀጥላል💫
👍461🔥1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሮፕላን እያጉረመረመ ከለንደኑ ሒትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ የለንደኑን ዳመና በአፍንጫው
እየበረቃቀሰ አቅጣጫውን ካስተካከለ በኋላ ካርለት ከሎና ጎይቲ እንደ ሌሎቹ መንገደኞች ሣቅ ጨዋታ አላበዙም።

ካርለትና ጎይቲ እየቆዩ ጫን ጫን ይተነፍሳሉ። ሶስቱም
የተቀመጡት በአሮፕላኑ መካከል ባሉት መቀመጫዎች ጎን ለጎን
ሲሆን ከፊት ለፊታቸውና ከኋላቸው ነጮችአሉ በስተቀኝ በኩል
አንድ ኢትዮጵያዊና አንድ ነጭ፤ በስተግራ በኩል ደግሞ የንጉሥ
ኃይለስላሴን ምስል ደረታቸው ላይ ያንጠለጠሉ ፀጉራቸውን እንደ ባህታዊ ጎንጉነው የኢትዮጵያ ባንዲራ የጠመጠሙ ጃማይካውያን
ተቀምጠዋል።

ካርለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚታተመውን “ሰላምታ" መጽሔት እያነበበች ሳለች።

“ይቅርታ” የሚል ድምፅ ሰምታ ቀና ስትል የአሮፕላኑ
አስተናጋጅ ፈገግ ብላ የምግብ ማስቀመጫውን እንዲዘረጉ ጠይቃ
ለሶስቱም የሚሆነውን ምግብ በፊታቸው አስቀመጠች።

በአጭር ጊዜ ውስጥ በኤሮፕላኑ ውስጥ ያለው ተሳፋሪ መመገብ ጀመረ: ጎይቲ ልትበላ አልፈለገችም: ካርለት ግን፡-

“ጎይቲ እባክሽ ትንሽ ለመብላት ሞክሪ?" አለቻት፡

“ካርለት እህል መች ራበኝ። ይልቅንስ አንች ብይ" አለቻት ፈርጠም ብላ  ጎይቲ።

ባይሆን ይሄ ደረቅ ስለሆነ ብስኩቱን ብይ እስፕራይቱንም
ጠጪ" ስትላት።

“ይእ! አቤት! የምግባችሁ ስሙ ብዛቱ። አፍ ላይ
ይጣፍጥና ውስጥ ሲገባ እንደ ነፍሰ ጡር ማቅለሽለሽ። አሁንስ ወደ
አገሬ እሄድሁ ነው:: ለኔ ያደግሁበት ኩርኩፋ ትኩስ ወተቴ ይሻለኛል፡" ጎይቲ ኮስተር አለች።

ከሎና ካርለት ተያዩ: ጎይቲ አንዴ ከወሰነች ውሳኔዋን
እንደማታጥፍ ስላወቁ የየበኩላቸውን መመገብ ጀመሩ::

ጎይቲ ወዲያ ወዲህ ሄድ መለስ የሚሉትን እያየች ቆየችና፡-

“ፈረንጅና ህፃን ልጅ አንድ ነው፡ አንድ ጊዜ እስኪጠግብ አይበላ! አሁንም አሁንም መለካከፍ! ሁሉን መላስ ብቻ አንዴ
ጥሩ አርጎ አይጎርስ  አይ ደንብ እቴ: ይእ! - ደግሞ የልብሳቸወ ብዛት:: ልብስን ቢያበዙት ትርፍ የለው: ከብት ቢገዙት ይራባል
በረት ይሞላል፤ ተዚያ ወተቱ ስጋው ይጠቅማል። ለዘመድ ወገን ቢሸልሙት ደስ ይላል።

“እነሱ ቤታቸውን ኮሮጆአቸውን የሞላው የሚያልቅ ቅራቅንቦ ብቻ! እና እኒህ ከህፃን በምን ይሻላሉ። እንደ ቀበሮ
የሚፈልጉትን እየተሯሯጡ ሲያነፈነፉ ይውሉና በዚያ ተግቶ በሚውለው ዋሻቸው ገብተው ማድፈጥ: እርስ በርስ አይዋደዱ አንዱ ሌላው ዘንድ አይደርስ ሲጫወቱ ለከት የላቸው:: ጆሮ እሚያደነቁር ነገር ይከፍቱና ዛር እንደያዘው ሰው አንዱ ከመሬት
መፈጥፈጥ ሌላው እንደ ጠገበ እንቦሳ መዝለል... ወንድና ሴቱ ደግሞ አይታወቅ ሁለቱም እቤት ውስጥ ተከተው አንድ አልጋ
ላይ ወጥተው መተኛት። ሴት ወንድን እንደህፃን ልጅ አቅፋ ተኝታ ሲያንኮራፋ ማየት።

“ደሞ የዚህ የኔው ጉድ የከሎ ይባስ እንጂ! ወዷቸው ሊሞት! ሳያርፍ ደሞ መኖርስ እዚህ ነበር' ይበለኝ፡ መጨከኑ
እንደ ዶሮ ሲጠጡ ማንጋጠጥ ሲበሉ አንገት መድፋት ከዚያ መሮጥ እንደ እብድ እየተገፋፉ መክላፍለፍ ተመልሶ ዋሻን ዘግቶ መቀመጥ ይህ የቀበሮ ኑሮ ምን ይወደዳል? ይእ! እነ አያ ደልቲ!  ሐመሮች እዚህ ውስጥ መኖሬን ብነግራቸው እውን ሰው ያረጉኛል።ዳሩ እኒስ ምን ጥሩ አለው ብዬ አወራቸዋለሁ። ብቻ እንድረስ!"ጎይቲ ስለ ነጮች አኗኗር ማሰቧም ዘገነናት።

ጎይቲ አይኖችዋ ቡዝዝ ብለው ቢከፈቱም አያዩም: እሷ የምታየው የሐመር ተራራን ሜዳን... የጀግኖችን ቁንጮ ደልቲ ገልዲን ነው::

ቱር እያሉ የሚበሩ አዕዋፍ በነፋስ ጎንበስ ቀና የሚሉት
እዕዋት... ሳራቸውን የሚያመነዥኩ ከብቶች በጎችና ፍየሎች በጨረቃ ብርሃን ተቃቅፈው የሚጨፍሩት ልጃገረዶችና ጎረምሶች በአይነ ህሊናዋ ይመጡባታል፧ ይታይዋታል::
ደልቲን ለዳንስ ስትጋብዘው አየሩን እየቀዘፈ የወተት አረፋ የመሰለ ጥርሱን በጨረቃዋ ብርሃን እያብለጨለጨ ሲመጣ ከወገቧ እየረገረገች ጡቶችዋን እያስነጠረች ስልቱ ባልተዘበራረቀ እንቅስቃሴ መሬት እስኪጨንቃት እየረገጠ ሲጠጋትና ስትሾር... እንደ ብረት የጠነከሩት እጆቹ ትከሻዋን ሲደገፉ እንደ ባልጩት የሚለሰልሰው
ጭኑ ወደ ጭኗ ሲዘልቅ የብልቷ በር ደጋግሞ ሲንኳኳ... ከዚያ ወደ
ተፈጥሮ መኝታ ቤት ወደ ጫካው ሲገቡ በሩ ተከፍቶ ጋ ተደርጎ ሲቀረቀር የፍቅር ማራቸውን ሲላላሱ እንዳይሰላቹ ተሰነባብተው
እሷ ወደ ጎጆዋ እሱ ወደ ማማው ሲያመሩ ታያት።

ይህን ጊዜ ጎይቲ

ካርለት! ምነው ይኸ ነገር ቆመ፤ ምነው የሰው ጭንቀት ቢገባው ፤ምናለ! ከሐመር ቀዬ ቶሎ በሮ ቢያደርሰኝ!... አለቻት
መሳሳቋን ሳትደብቅ።

“እንደ ወፍ እየበረርን ነው'ኮ ጎይቲ! አይዞሽ ወደ ናፈቅሽው ቶሎ ትደርሻለሽ: ከሎን አታየውም? አለቻት እንድትረጋጋ በማሰብ

“ይእ! እሱማ ለማዳ ነው። ታቦቱ ደንብ የወረሰው የለም ለኔ የጨነቀኝ ለሱ ደስታ ፈጥሮለታል። ብቻ ተይኝ! እንዲያው እሚሰሙሽ ከሆነ ይኸ ነገሩ በቋራጭ በአቋራጭ አድርጎ ከሐመር
hእባቴ ተራራ ከቡስካ እንዲጥለኝ ንገሪው:: ከዚያስ ወዲያ ችግር
ቀናም ብዬ ሳላየው እየቦረቅሁ  ተቀየዬ
ከዘመዶቼ ከጀግናዬ ጋር እገናኛለሁ፡ እና! እስቲ ንገሪቸው? አለች ጎይቲ፡
ካርለት ሳቅ ብላ፦

“ኤሮፕላኑ የራሱ የተወሰነ ፍጥነት ኦለው..." ስትል ጎይቲ አቋረጣት።

"አቤት! የደንባችሁ ብዛቱ። አቤት ስትፈራሩ… በይ ተይው እኔስ እንግዲህ ለአንድ ጊዜ እችለዋለሁ። መጥኔ ለናንተ! አለቻትና
ወደ ህልሟ ገባች። ከሎ ከጃማይካዎች ጋር ይጫወታል ይከራhራል...ይሳሳቃል።

የጎይቲ አስተያየት
ካርለት እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ አስገረማት። የጎይቲን ገሀዳዊ ህይወት አይታዋለች: ሐመሮች
በጥቁር ቆዳ የተሸፈነ አልማዝ ጥቅማ ጥቅም ያልበከለው ንፁህ ህሊና ያልተበከለ ባህል ካለ ዘመናዊ ህግና ፖሊሲ ተስማምተው
የሚኖሩ ተፈጥሮን የማይቃረኑ ህዝቦች መሆናቸውን አብራቸው
ኖራ አይታለች።

ሐመር ውስጥ ስሜት በህሊና እንጂ ሰዎች ባወጡት ህግ
አልተለጎመም: እውነት ራቁቷን ናት! እነሱም ራቁታቸውን ናቸው!
ተፈጥሮም አልተበከለችም! መሬት የፈለገችውን እፅዋት ታበቅላለች!የተጠጓትን አውሬዎች ደስ ብሉአቸው እንዲኖሩ ታረጋለች
የተፈጥሮ አበባ አካባቢውን እንዳስዋበው ነው። ሰማዩ ግን በአይሮፕላን ጢስ እየቆሸሸ መኪናው አራዊትን እያስበረገገ ነው።ስልጣኔ የተፈጥሮ ሚዛንን ለማዛባት ኬላውን ለመጣስ እየጣረ ነው ያኔ በራስ መተማመን በራሱ ይቆማል! ህክምና አልባው የመምስል
በሽታ ይጠናወታል! ማንነት ይጠፋል።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የመስኮቱ መጋረጃ እንደተዘጋ ነው: የመኝታ ክፍሉ ግን በማለዳ ፀሐይ ብርሃን ደምቋል። ካርለት ተንጠራርታ አይኖችዋን
ስትከፍት ነጭ ቀለም የተቀባውን የመኝታ ክፍል  ከጣራው እስከ ወለሉ የሚደርሰውን ሰፊ ቁምሳጥን ሰፊውን አልጋ.. ቃኝታ ዘወር ስትል ከስቲቭ ጋር ተያዩ::

ተንጠራርታ ወደሱ ጠጋ አለችና በፀጉር ከተሸፈነው ደረቱ ላይ ተለጥፋ አቀፈችው። እሱም ያቀፈበትን ክንዱን ሳብ ሳብ አድርጎ በግራ እጁ ፀጉሯን ዳበሰላት።

መቀሽቀሻ ስዓቷ ዲሪሪን… ዲሪሪን.ዲሪሪን' ስትል ስቲቭ ቀና ብሎ ድምፅ ሲያሰማት ፀጥ አለች እነሱም ሙቀታቸውን
እየተጋሩ ተቃቅፈው ፀጥ አሉ።

መቀሽቀሻ ሰዓቷ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ደግማ ዲሪሪን…..ዲሪሪን...' ስትል ካርለት የስቲቭን ከንፈር ሳም አድርጋ ቢጃማዋን
ሳትለብስ እርቃኗን መታጠቢያ ክፍል ገባች።
👍31👏1
ከተደረደረው የገላ መታጠቢያ ሻምፖ “ፋ” የሚለውን አንስታ ከታጠበች በኋላ በፎጣ ፀጉሯን ጠቅልላ ጥርሶችዋን
በመቦረሽ ልብሷን ለማምጣት ከመታጠቢያ ክፍሉ ወጣች።

ስቲቭ እንደተኛ ነው: ሁሌም መኝታውን ለመልቀቅ
ለረጅም ደቂቃዎች አልጋው ውስጥ አመድ ላይ እንደሚንከባለል አህያ ግራና ቀኝ መዟዟር አለባት: ካርለት ደግሞ ጠዋት መነሳትና የአዕዋፍን ዝማሬ እያዳመጠች ስራ እንኳን ባይኖራት መንጎዳጎዱን
ትመርጣለች። የዛን ቀን ግን ብርቱ ጉዳይ ነበራት።

“ስቲቭ?" አለችው ወደ አልጋው ጠርዝ ጠጋ ብላ:

“እህ!” አላት በድካም መንፈስ። ጎንበስ ብላ ከንፈሩን ስማው ቀና ስትል መዓዛውን የያዘውን አየር ባፍንጫው ሳበና “ዋው..” ብሎ  ፈገግ አለ።

“ስቲቭ ስማ! ከሎና ጎይቲ ዛሬ ወደ  ሐመር መሄድ
አለባቸው:: ጎይቲ አዲስ በበባ ውስጥ ማደር መዋል አትፈልግም::ናፍቆቷ ከልክ አልፏል። ፍላጎቷን ለማሳካት ደግሞ መሄድ አለባት::
ከሎ ግን ጥቂት ቀናት አዲስ አበባ ለመቆየት ፈልጎ ነበር። እሱ አዚህ
እንዳይቆይ ደግሞ እኔም የግድ ወደ ዩንቨርሊቲ መሄድና ከአንዳንድ
ሰዎች ጋር መገናኘት ምግቦችን... መገዛዛት አለብኝ።

“በተጨማሪም አያቷ ኢትዮጵያዊ የሆነች ስፔናዊት የአያቷን ትውልድ ቦታና ዘመዶችዋን ማየት እንደምትፈልግ እረፍት ስፔን
በቆየሁበት ጊዜ አጫውታኝ ኢትዮጵያ ብትመጣ በመፈለጉ ላይ ልተባበራት እንደምችል ቃል ገብቼላታለሁ: ስለዚህ ከከሎ ይልቅ የኔ እዚህ መቆየት የግድ ነው" ስትለው

“ጥሩ ነው!” አላት ስቲቭ። ቀጥላ ግን

“የመኪናው ባትሪ የት ነው? አለችው።

“ትናንት መልሰው እንዲያሰሩት ስለነገርኳቸው አስረውታል።ዘይት በመቀየር የሚፈትሽውን ሁሉ በመፈተሽ መኪናውን
ሞክረውት ለጉዞ ዝግጁ መሆኑን የኛ መካኒኮች አረጋግጠውልኛል!
ቁልፉ እሳሎን ተንጠልጥሏል"

“አመሰግናለሁ ስቲቭ"

“ለምኑ?” አለ ፈገግ ብሉ።

“ላስቆጠርከው መልካም ሥራ ሁሉ” አለችና እንደገና ስማው  ወጣች።

💫ይቀጥላል💫
👍22