አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ትንሹ ልጅ ‹‹አለቃ እስቲ በመስኮት ተመልከት›› አለው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሄሪ ማርክስ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ለማረፍ ከውሃ ጋር ስለተጋጨ ወደ
አንድ ጎን ወድቆ ነበር፡ በመጀመሪያ ተወርውሮ ከሻንጣዎቹ ጋር ተጋጨ፡
እንደገና ለመነሳት ሲሞክር ከአይሮፕላኑ ግድግዳ ጋር ተጋጨና ራሱን ሳተ፡
ሲነቃ ምንድን ነው የሆነው? አለ በሆዱ፡ ፖርት ዋሽንግተን እንዳልደረሱ
አውቋል፡፡ ገና ከሚቀራቸው የአምስት ሰዓት በረራ ሁለቱን ሰዓት ብቻ ነው
የተጓዙት፡፡ ስለዚህ ይሄ ከፕሮግራሙ ውጭ
ይሄ ከፕሮግራሙ ውጭ የተደረገ ቆይታ ነው፡፡
ምናልባትም አይሮፕላኑ ችግር ገጥሞት ድንገት ይሆናል ያረፈው::
አሁን ተመቻችቶ ቁጭ
ሲል ቁስሉ ተሰማው፡፡  አይሮፕላኖች የመቀመጫ ቀበቶ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው የተረዳው አሁን ነው
አፍንጫው እየደማ ነው፡፡ ራሱን ይፈልጠዋል፡፡ ሰውነቱን ሁሉ ቁስል
ይሰማዋል፡፡ እጅ እግሩ ግን ደህና ነው፡፡ አፍንጫውን በመሀረብ ጠረገና
ለመትረፉ አምላኩን አመሰገነ፡፡

የአይሮፕላኑ ሻንጣ ማስቀመጫ ክፍል መስኮት ስለሌለው ውጭ ምን
እንደተፈጠረ ማየት አልቻለም፡፡ በጸጥታ ቁጭ አለና ሲያዳምጥ የአይሮፕላኑ ሞተር ጠፍቷል፡ ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል፡፡

ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፡፡

የሽጉጥ ተኩስ ካለ ወሮበሎቹ አሉ ማለት ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ
ካሉ ደግሞ ጎርዲኖን ነው የሚፈልጉት፡፡ ሌላም ነገር አለ፡፡ የሽጉጥ ተኩስ
ካለ ግርግር ስለሚኖር በዚያ መሀል ሾልኮ ለመውጣት ይመቻል፡፡ ስለዚ, ከሻንጣ ክፍል ወጥቶ ለማየት ወሰነ፡፡

በሩን ትንሽ ከፈት አደረገና አየ፡፡ ምንም የሚታይ ነገር የለም

ኮሪደሩ ላይ ወጣና ወደ አይሮፕላኑ መንጃ ክፍል ሄደ፡ ከዚያም በሩ
ጋር ተለጥፎ ድምፅ ይሰማ እንደሆነ ጠበቀ፡፡ ምንም የለም፡ ከዚያ ቀስ ብሎ
በሩን ከፈተና አጮልቆ አየ፡፡
የአይሮፕላኑ መንጃ ክፍል ውስጥ የሰው ዘር አይታይም፡፡ ከዚያም ወደ
ፊት ሲሄድ ሰዎች ሲጨቃጨቁ ሰማ፡፡ ምን እንደሚሉ አይሰማውም፡ በአይሮፕላኑ መስኮት አሻግሮ ሲመለከት አንድ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር ታስሮ አየ፡፡ አንድ ሰው ይታየዋል፡፡ ለማምለጥ ትንሽ እንደቀረው ሄሪ ተገነዘበ፡፡
ውጭ ሰው ወደሌለበት የባህሩ ዳርቻ የሚወስደው ጀልባ አለ፤ አንድ ሰው ብቻ ስለሆነ ሰውዬውን አባሮ ጀልባውን መውስድ ይችላል።

ከኋላው የጫማ ኮቴ ሰማ፡፡ ልቡ እየደለቀ ዞረ፡ ከኋላው የመጣው ፔርሲ ኦክሰንፎርድ ነው፡፡ ልጁ በፍርሃት ተውጧል።

‹‹የት ነው የተደበቅኸው?›› ሲል ፔርሲ ጠየቀው

‹‹ተወው እሱን›› አለ ‹‹ይልቅ እዚያ ምን እንደተፈጠረ ንገረኝ›› ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ሚስተር ሉተር የናዚ ደጋፊ ነው፡፡ ፕሮፌሰር ሃርትማንን መልሶ ወደ ጀርመን ሊወስዳቸው ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ስራው በመቶ ሺህ ዶላር ወሮበሎችን ቀጥሮል
ሻንጣ ሙሉ ገንዘብም ሰጥቷቸዋል ወሮበሎቹ መምበሪን ገደሉት፡ ከእንግሊዝ ፖሊስ መምሪያ ሃርትማንን ሊጠብቅ
የተመደበ ፖሊስ ነበር››

‹‹እህትህ ደህና ነች?››

‹‹እስካሁን ደህና ነች፡፡ ሚስስ ላቭሴይ ቆንጆ ስለሆነች ሊወስዷት ነው፡፡
ማርጋሬትን ከሰውም አይቆጥሯት!›› አለ ፔርሲ ‹‹ተደብቄ ሰው ሳያየኝ ነው
ወደዚህ የመጣሁት››

‹‹ለምን?››

‹‹የኦሊስ ፊልድን ሽጉጥ ለመውሰድ፡፡ ካፒቴን ቤከር ከሚስተር ፊልድ ነጥቆ እዚህ ጠረጴዛ ኪስ ውስጥ ሲያስቀምጥ አይቻለሁ›› አለና ሽጉጡን አንስቶ ያዘ።

‹‹ሄሪ አንተ ልጅ ነህ ሽጉጥ መያዝ የለብህም፧ ባርቆብህ ሊመታህ ይችላል›› አለና ሽጉጡን ነጥቆ የጠረጴዛ ኪስ ውስጥ ከተተና መሳቢያውን ዘጋው፡:

እውጭ የሚያስገመግም ድምጽ ሰሙ፤ በመስኮቱ ሲመለከቱ የእነሱን
አይሮፕላን ከላይ ሆኖ የሚዞር አይሮፕላን አዩ አይሮፕላኑም ትንሽ
ሲያንዣብብ ቆይቶ ለማረፍ መውረድ ጀመረ ከዚያም ባህሩ ላይ አረፈና
ወደ እነሱ አይሮፕላን እንደ ጀልባ እየተነዳ መጣ:፡

‹‹አሁን ምን እናድርግ?›› አለና ፊቱን ወደ ፔርሲ ሲያዞር እሱ የለም፧
የጠረጴዛው መሳቢያም ተከፍቷል፡ ሽጉጡም የለም፡፡

ጊዜ ሳያጠፋ ከሻንጣ መያዣ ክፍሉ ወጥቶ ሄደና ሌላ ክፍል ዳር ተለጥፎ አየ፡፡ ፔርሲን አሁን ማስቆም አልቻለም ጥሎት ሄዷል፡
ማርጋሬት ሁሉም ቤተሰቡ  በሙሉ ሽጉጥ መተኮስ እንደሚችል የነገረችው ትዝ አለው፡፡ ልጁ ግን ስለማፊያዎች የሚያውቀው ነገር የለም፧ ሊያስቆማቸው ከሞከረ ደመ ከልብ ይሆናል፡፡

ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ገብቶ ወደ ውጭ ሲያይ አሁን ያረፈው አይሮፕላን ከእነሱ አይሮፕላን ጋር በገመድ ሲታሰር አየ፡ ወደ
አይሮፕላኑ ጭራ አካባቢ ድረስ ሄዶ በሩን ትንሽ ከፈት አድርጎ ምን እየተደረገ እንደሆነ ለማወቅ ፈለገ፡፡
የአንድ ሰው ኮቴ ይሰማዋል፡፡ ሌሎች ሁለት ሰዎች ሲመጡ ኮቴ ሰማ፤
አልፈው መሄዳቸውን አረጋገጠና ወጣ፡፡
ማፊያዎችን የሚይዝ የፖሊስ ሀይል መጣ ይሆን?› ሄሪ የሚነግረው
አጣ ቀስ እያለ ኮቴውን ሳያሰማ ወደ ፊት ሄደ፡፡ በመሀል በመሀሉ ቆም
ይልና ያዳምጣል፡፡ አሁን ድምጽ በደምብ ይሰማዋል፡፡ የቶም ሉተር ድምጽ እንደሆነ አወቀ፡ አነጋገሩ ትንሽ የአውሮፓ ቅላጼ ያለው የጨዋ አሜሪካዊ አነጋገር ነው፡፡

ወሮበሎቹ ሲጨነቁበት የነበረው የማምለጥ ጉዳይ አሁን መፍትሄ አግኝቷል፡፡ በመጣው አይሮፕላን ሚስተር ሃርትማንን ይዘው ሊጠፉ ነው፡

ሄሪ በእግሩ እየዳኸ ቀረበ
ምስኪኑን ሳይንቲስት ለናዚዎች አሳልፎ
መስጠት በእርግጥም ልብ ይሰብራል፡፡ መቼም ለሳይንቲስቱ ብሎ አንገቱን
ለካራ አይሰጥም፡፡ ሆኖም ፔርሲ አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል፡፡ እሱ ደግሞ
እንዲሞት አይፈልግም፡፡ ለማርጋሬት ሲል አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡
ከሄሪ ቀድሞ በመገኘት ወሮበሎቹን እርምጃ እንዳይወስዱ ለማደነጋገር
ወይም ሊሰሩት በተዘጋጁት ላይ ጋሬጣ በመፍጠር ሊያዘናጋ ነው፡፡
በአይሮፕላኑ በኩል ወጣና
ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ጋር
🙄፡£የታሰረችበትን ገመድ ፈታው፡ ነገር ግን ጀልባዋ በሌላ ገመድ ከአይሮፕላኑ
ተናደደ፡፡
ስለዚህ
ገመዱን ለመፍታት ወደ
ጋር መታሰሯን ሲያይ
አይሮፕላኑ መግቢያ መሄድ ሊኖርበት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ አንዱ
ያየዋል፡ ሆነም ቀረ የመጣው ይምጣ ብሎ አንድ ነገር ማድረጉ አይቀርም ጊዜም ስለሌለው ቶሎ ማድረግ አለበት፡፡

ሁለተኛውንም ገመድ ፈታና ጣለው፡፡

ጀልባው ውስጥ ያለው ሰው ‹‹አንተ ምን እያደረግህ ነው?›› ሲል ጠየቀው ሄሪን፡፡

ፊቱን አዙሮ ሲያይ የጀልባው ነጂ ነው ያናገረው። መሳሪያ
አልታጠቀም ሰውዬው ገመዱን ለማሰር ሲጎትት ከእጁ አመለጠውና ባህሩ
ውስጥ ገባ፡፡ የጀልባው ነጂ ወደ ውስጥ ገባና ሞተሩን አስነሳ፡ በዚህ ጊዜ
ወሮበሎቹ ጀልባው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ማየታቸው አይቀርም፡፡ ጉዳዩም አስገራሚም አስደንጋጭም ይሆንባቸዋል፡፡ ሄሪ ወደ አይሮፕላኑ ተመልሶ
ገብቶ የሻንጣ መያዣ ክፍል ውስጥ ገብቶ ተደበቀ።

ከማፊያዎቹ ጋር እሰጣ እገባ ውስጥ መግባት አደገኛ መሆኑን ያውቃል፡ ከያዙት ምን እንደሚያደርጉት ሲያስበው ፍርሃት ይወረዋል
ሄሪ ተደብቆ አንድ ነገር ይፈጠራል ብሎ ጠበቀ፡፡

በመጨረሻ ወደ አይሮፕላን መንጂያው ክፍል የሚሄድ የተቻኮለ የእግር ኮቴ ተሰማው፡ በኮቴው ድምጽ ሁለት ሰዎች እንደመጡ አውቋል፡ እሱ ከሁለት ሰዎች ጋር ሊጋፈጥ እንደሚችል አልገመተም::
ትንሽ ራቅ ብለው ሄደዋል ብሎ በመገመት በሩን ከፈት አድርጎ ሲያይ ምንም ሰው የለም፡፡ ትንሽ ወደፊት ሄዶ ሲመለከት ሁለት ሰዎች ሽጉጥ ያልያዙ ቢሆንም ዓይን የሚስቡ ልብሶች በመልበሳቸው ብቻ ማፊያዎች መሆናቸውን መገመት ችሏል፡ አንዱ አስቀያሚና ክፉ መልክ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጣም ወጣት ነው፤ ምናልባትም ከ18 ዓመት የማይበልጥ ጎረምሳ፡፡
👍11
ተመልሼ ልደበቅ ይሆን› ሲል አሰበ፡፡

ሁለቱ ወሮበሎች ጀልባውን ከአይሮፕላኑ ጋር ለማሰር እንደገና ትግል ጀምረዋል፡ ለማሰር ደግሞ የግድ ሽጉጦቻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው ሄሪም መሳሪያቸውን እስኪያስቀምጡ ጠበቃቸው፡፡

ሁለቱ ሰዎች ሽጉጦቻቸውን በኪሳቸው ከተቱና ወደ ውጭ ወጡ የጀልባው ነጂ የሚወረውርላቸውን ገመድ ለመያዝ ትግል እያደረጉ ስለሆነ በመጀመሪያ ሄሪን አላዩትም ነበር፡፡

አንደኛው ማለትም ወጣቱ ገመዱን ሲይዝ ሁለተኛው ሰው ዞር ሲል ሄሪን አየው፡፡ ልክ ሄሪ ሲደርስበት ሽጉጡን ከኪሱ አወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ሄሪ ሞቱ እንደቀረበ ስለተረዳ ጊዜ ሳያጠፋ የሰውየውን እግር ለቀም አድርጎ ጎተተው፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ ጥይት ጮኸች ሰውዬው ሲንገዳገድ ሽጉጡ
ቢወድቅበትም ላለመውደቅ ብሎ ጓደኛውን ያዘው፡፡ ወጣቱ ሰው ሚዛኑን ሳተና ገመዱ ከእጁ ወጣ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ አንዱ አንዱን ለመያዝ ወዲያ ወዲህ ተንጠራወዙ፡፡ ሄሪ የአንደኛውን ሰው እግር ይዞ እንደገና ጎተተው፡፡
በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች በማዕበል በሚጋልበው ውሃ ውስጥ ወደቁ፡፡ ሁለቱ ስዎች አንዴ ውሃ ውስጥ እየጠለቁ አንዴ ወደ ጠለሉ እየወጡ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ይጣጣራሉ፡፡ ሄሪ ከሁኔታቸው ዋና እንደማይችሉ አውቋል፡

‹‹ይህን የማደርገው የክላይቭ መምበሪን ደም ለመበቀል ነው›› አላቸው ሄሪ፡፡ ከዚያ በኋላ ይሙቱ ይዳኑ አያውቅም፡፡ ቢሞቱም ግድ አልነበረውም ከዚያም ኮቴ ሳያሰማ በፍጥነት ወደ አይሮፕላኑ ተመለሰ።

ማርጋሬት የራሷ ልብ ድውድውታ ይሰማታል፡፡ ልቧ ልክ እሳት ላይ
እንደተጣደ ጀበና ይንደቀደቃል፡፡ ያለማቋረጥ በጣም ስለሚመታ አጠገቧ ያሉ ሰዎች የሚሰሙ መሰላት፡፡

በህይወቷ እንደዚህ ፈርታ ስለማታውቅ ፍርሃቷን ሌሎች ያውቁብኝ ይሆናል ብላ ሰግታለች።
የፍርሃቷ ምንጭ እንዲሁ የመጣ አይደለም፡፡ አይሮፕላኑ ድንገት
መሃል ባህር ላይ ማረፉ፣ ፍራንኪ ጎርዲኖ፣ ሚስተር ሉተርና የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ ዲከን እየሰሩ ያሉት ስራ፣ ሱፍ የለበሱ ማፊያዎች ድንገት ከዚህም ከዚያም ብቅ  ብለው የአይሮፕላኑን ህብረተሰብ ቁም ስቅል ማሳየታቸውና ሚስተር መምበሪ በጥይት ተመትቶ ወለሉ ላይ መዘረሩ ተደማምሮ ፍርሃቷን ጣራ አድርሶታል፡

ለዓመታት ፋሺዝምን እንዴት እንደምትታገል ስትናገር ኖራለች፡፡ አሁን ዕድሉ በሯ ድረስ መጥቷል፡ የፋሺስት ቡድኑ ሳይንቲስቱን ካርል
ሃርትማንን ወደ ጀርመን አፍኖ ለመመለስ እየተውተረተረ ነው፡፡ እሷ ደግሞ በፍርሃት እጅ እግሯ ስለተሳሰረ ምንም ማድረግ አትችልም፡፡ ነገር ግን
መሞከር ይኖርባታል። ምክንያቱም እሷም ፋሺዝምን ለመዋጋት
የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝና በሞት የተነጠቀችውን ኢያንን
ለማስታወስ ስትል ትግል መግጠም እንዳለባት ታስባለች፡፡

ጀግና ነኝ እያለች ስታስመስል አባቷ የስድብ ናዳ እሷ ላይ ማውረዳቸው
ትክክል ነው፡፡ እሷም ይህን ታውቃለች፡ ጀግንነት በአፍ ብቻ ነው፡፡ በጦር ሜዳ በሞተር ሳይክል እየተመላለሰች ለጦሩ ዕቃ አጓጉዛለሁ ማለቷ ህልም
ነው፡ አንድ ጥይት ቢተኮስ የሆነ ነገር ውስጥ መወሸቋ አይቀርም፡፡ ከባድ ጥቃት ከተፈጸመማ ዋጋ አይኖራትም፡፡

ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡

ይቀጥላል
👍26
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ስሞንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ካርለት የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የሥራ ፈቃዷን ልትጨርስ የቀራት አንድ ሳምንት ብቻ ነው ከዚህ በፊት ከአንድም ሁለት ጊዜ፡
የጥናት ፈቃዷን አራዝማለች" ዘመናዊው ሕይወቷን በመዘንጋት ለሐመሩ ንጹሕ ሕይወት ረክታለች" ዛሬ የሐመር ሕዝብ ለሷ የለንደን
ሕዝብ ነው።
ከእንግዲህ ወዲያ ካርለት ኢትዮጵያዊት ነች" ለንደን
የሥጋ ዘመዶቿ፣ ሐመር ደግሞ የመንፈስ ወዳጆቿ የሚገኙበት ነው" በዚህ ቀን ካርለት ከከሎ ጋር ስለ ማኅበረሰቡ የወደፊት ዕጣ
ተነጋግረው ነበርu ካርለት፣ «ሐመሮች በእርግጥ የሚያውቁት ራሳቸውን ነው ከነሱ ውጭ ያለው ዓለም ምን እንደሚመስል
አያውቁም። ይሁን እንጂ ከዓለማችን ውጭ በራሳቸው ደሴት
ተጠልለው ዝንተ ዓለም መኖር አይችሉም" ተወደደም ተጠላ
በክልላቸው ሳይንስ የፈጠራቸው ተሽከርካሪዎችና በራሪዎች
ያልፋሉ። ስለ እነሱ ሌላው ሲያውቅ፣ እነሱም ስለ ሌላው ለማወቅ መቻል አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ድልድይ የሐመር ወጣቶች ሲሆኑ፣ የዘመኑን ትምህርት መቅሰም መቻል አለባቸው» ብላ ነገራዋለች" ከሎም ሐሳቧ የሱም እምነት እንደሆነ አረጋግጦላታል"

ካርለት፣ ሐመርን ለመልቀቅ የተወሰኑ ቀናት ሲቀራት ሆዷ
ተሸበረ ተጨነቀች" የገርሲ፣ ፌጦ፣ ኩንኩሮ፣ ጨዋንዛ፣ ግራር ዘንባባ፣ አጋም፣ ጠዬ፣ አንቃ፣ ሌሊሚ፣ ጨውሊምባ፣ ሾላ፣ ዋንዛ፣
እንኮይ...ደኑ የአሰሌ፣ የካራ ሰንሰለታማ ተራራ፣ የላላ፣ የሻንቆ፣የወሮ…መንደር፤ የሐመር ልጃገረድ፣ ጐረምሳ፣ አዛውንት፣
ሽማግሌ፣ ባልቴት ቀብራራው ደልቲ ገልዲ በአእምሮዋ እንደ
ፔንዱለም ባለማቋረጥ እየተመላለሱ (ጨክነሽ ጥለሽን ልትሄጂ እያሉ፣ ልቧን አንጠለጠሉባት።
ካርለት ቀሪውን ጊዜዋን ከብቱን፣ ሰውን፣ ጫካውን ፎቶ ስታነሣ ሰነበተች። ልቧ ግን እንደ ታረደ ዶሮ እየተነሣ ፈረጠባት ስትመጣ
ዳር ዳር ቆመው የተመለከቷት ሐመሮች የጕዞዋን ዜና ሲሰሙ
ሕሊናቸው ኩምሽሽ ብሎ ዓይናቸው በእንባ ሲሞላ ተመለከተች ስትቀርባቸው ሊወጓት ቀንዳቸውን ያዞሩባት የነበሩት ከብቶች
ጠረኗን እየፈለጉ ተጠግተው እጆቿን ላሷት።

ካርለት በሕይወቷ እንዲህ ልብ ሰራቂ የሆነ የሰውና የተፈጥሮ ፍቅር አጋጥሟት አያውቅም። ስለዚህ፣ ልቧ ደረቷን ሲረግጥ፣
ሕሊናዋ አነባ! ዓይኖቿም አለቀሱ።

ካርለት ሐመርን ልትለቅ አንድ ቀን ሲቀራት የኢቫንጋዲ ጭፈራውን ለመካፈል አሸዋማ፣ ገላጣና ዙሪያውን በለመለሙ የሐመር እፅዋት ተከቦ ፍቅር እየተቦካ ወደሚጋገርበት፣ ንብ አበባ
ወደምትቀስምበት፣ አዕዋፍና ሰዎች ጥዑም ዜማቸውን ወደሚያዜሙበት፣ የእፅዋት፣ የአራዊት፣ የአዕዋፍ፣ የሰው ዳንኪራ
ወደሚረገጥበት ስፍራ ተጓዘች።

ካርለት በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት ሁሌም እንደምታደርገው
ጀግናውን በዓይኖቿ አማተረች" ጀግናው እየዘለሉ አየሩን ከሚቀዝፉት ጐረምሶች መካከል የለም ካርለት፣ «አምላኬ!» ብላ፣
እንደ መኪና ጎማ ተነፈሰች" በጭንቀት ዓይኖቿ ሲቅበዘበዙ ግን ደልቲ ገልዲ ካለወትሮው ተክዞ፣ ራቅ ብሎ ቆሞ አየችው" ጀግናውን ተክዞ አይታው አታውቅም። ቀጭኔ፣ አንበሳ...የገደሉት አነጣጣሪ
ዓይኖቹ ቦዘው ስታይ ሰውነቷ ተዝለፈለፈባት። ጭንቀት ያዘለው ዶፍ
ዝናብ ሊያለብሳት መጣሁ ወረድሁ እያለ አጕረመረመባት። ካርለት
በደመ ነፍስ ወደ እሱ እየተንቀሳቀሰች፣ «ምን ሆኖ ይሆን?» ብላ ራሷን ጠይቃ ፊት ለፊቱ ሄዳ ቆመች።

«ካርለት» አላትና ዝም ብሎ ዓይን ዓይኗን ተመለከተ

«ምን ሆንክ ደልቲ?» ብላ ጠየቀችው።

ዝም ብሎ ዓይኖቹን ከሷ ላይ አንሥቶ ወደ ጨረቃዋ ወረወራቸው" ካርለት ዘለሽ እቀፊው እቀፊው አሰኛት።
ካርለት» አለ ደልቲ ዓይኖቹን ሳያወርድ።
«አቤት» አለችው:
ደልቲ ገልዲ ግን ዝም አለ ተመልሶ።

እንደ ባልጩት ድንጋይ እያብለጨለጨ የተከፋፈለው የጭኑና
አጁ ጡንቻ፣ ሣንቃው ደረቱ፣ የሚንቦገቦጉት ትናንሽ ዓይኖቹ በጨረቀዋ ብርሃን ካርለት ስታይ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት
መላ አካሏ እሳት ላይ የወደቀ ቋንጣ ይመስል ኩምትርትሩ ወጣ"

«ወይ አምላኬ፣ ምናለ የልቡን በነገረኝ፤ ምናልባት
መለያየታችን አስጨንቆት ይሆን? መቼም ማለት የፈለገው ነገር አለ
ከአንደበቱ እንዳያወጣው ግን እየተናነቀው ነው» ብላ አሰበች"

ይህን ስታስብ፣ «ካርለት መሄድሽ ነው?» የሚል ከደልቲ ጕሮሮ አፈትልኮ ወጣ"

«አዎ መሄዴ ነው» አለች ካርለት፣ «ምን ሊለኝ ይሆን አምላኬ» ብላ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተችው» ደልቲ ግን አሁንም ጸጥ አላት።

«ትወደኝ ነበር?» ብላ የሞኝ ጥያቄ ጠየቀችው ደልቲ ግን ትክ ብሎ አይቷት፣ «አይ» አላት፣ በምፀት" ካርለት መልሱ ከልቡ እንዳልሆነ በሚገባ ተረዳች" ካርለት ያኔስ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆነች ጀግናው እንደገና ጣላት። ስለዚህ፣ እጇን ሰዳ እጁን ያዘችውና ወደ
ሰንበሌጡ ይዛው ገባች“ ከዚያ ጭፈራው በዓይነት በዓይነት ቀጠለ ዳንኪራው ተመታ። አሁንም እንደ ባለፈው ተመልካች በሌለበት የተፈጥሮ አዳራሽ ትርዒታቸውን ለራሳቸው አሳዩ። ዳንኪራው ግን
እንዳለፈው ተስፋ ሰጪ ሳይሆን ለየት ያለ፣ የሰቀቀን፣ የኃዘን፣
የህምታ ውዝዋዜ ሆነ።

በነጋታው ፀሐይ ከወደቀችበት ተነሥታ ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ ካርለት ዕቃዎቿን በስቴሽን ዋገን መኪናዋ ላይ ከከሎ ጋር አስተካክለው ጭነው እንደ ጨረሱ ሐመሮች ከየመንደሩ ተሰባስበው

ሴቶቹ ደረታቸውን እየደቁ ሲያለቅሱ፣ ወንዶቹ በርኮታቸው ተቀምጠው ተከዙ። ካርለት ዓይኗ በእንባ ሊጠፋ ተቃረበ" የሁለት
ዓለም ዘመዳሞች ሲለያዩ አምርረው አዘኑ"

ካርለት፣ ከሎ ሆራና ጎይቲ በሽማግሎች ተመርቀው፣ ጀርባቸው በከብት እበት ከተቀባ በኋላ ሦስቱም መኪና ውስጥ ገብተው መኪናዋ ተንቀሳቅሳ አቧራው ሲነሣ የሐመር ጭንቅላቶች ወደ መሬት
አቀረቀሩ" ካርለት ትንሽ ከተጓዘች በኋላ ኢቫንጋዲ የጨፈረችበትንና
የቦረቀችበትን የሐመር ጫካ ለመሰናበት መኪናዋን አቁማ ስትወርድ፣ ከሎና ጎይቲም አብረው ወረዱና እንባቸውን አወረዱ..
ወፎች ግን እየዘመሩ፣ ቱር እያሉ እየበረሩ፣ እየተዳሩ ምግባቸውን መፈለጋቸውን አላቆሙም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዋናው የመኸር ወቅት የሐመር የተፈጥሮ ውበትና ልምላሜ የክቱን አውጥቶታል" እፅዋት ለምልመው አብበዋል የከስኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ሆኖ ይፈሳል። የቡስካ ተራራ አሁንም ከቦታው ሳይንቀሳቀስ የሐመሮች የታሪክ ሐውልት ሆኖ ፈገግታውን በልምላሜ ያሳያል"

ከአሰሌ ሰንሰለታማ ተራራዎች እስከ ኬንያ ጠረፍ፣ ከኤርቦ እስከ አሪ ማኅበረሰብ የሐመሮች ዘፈንና ዳንኪራ አሁንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ያስተጋባል። የሐመር ተፈጥሮ ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ከድንቢጥ ወፍ እስከ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ፣ ከትል እስከ ተሳቢው
ዘንዶ ከከብት እስከ ሚዳቋና ድኩላ ይፈነጭበታል"

ሁሉም የተፈጥሮ ድምፁን ባሰማ፣ እንቅስቃሴ ባደረገ ቁጥር ውብ የሙዚቃ ቅማሬ ከጋራ ጋራ፣ ከቋጥኝ ቋጥኝ ይስተጋባል" የሐመር ምድር ለሚመጡትም ለሚሄዱትም ሁሌም ያው ነው" መለምለም፣ ማበብ፣ መጠውለግ፣መድረቅ..ተልሶ ደግሞ መለምለም።

ደልቲ ገልዲን መኪናዋ የሚወዳቸውን ጭና በአራት እግሯ ከቡስካ በስተጀርባ ተሠውራበታለች መዝናኛዎቹ፣ መደሰቻዎቹን
ሌባዋ ይዛ በአቧራ ደመና ገብታ ጠፍታበታለች" ደልቲ አሁን ሁለት እግር ያለው ከሌላ ፍጡር ያልተለየ መሆኑን ሳይረዳ አልቀረም
የጎሽን ጀርባ በአንድ ምት ብቻ አከርካሪውን አድቅቆ
የሚያንበረክከው አንበሳ መጨረሻ የዝንብ መዝናኛ መሆኑ የማይቀር እውነት መሆኑን ደልቲ የግድ ሊመለከተው፣ ሊደርስበት ነው"
👍283
ያ ከቀጭኔ እይታ ውጭ አልፎ ብብት ስር የሚገባ ፈጣን ሯጭ ፍቅረኞቹን ለመያዝ አቅም አነሰው" ሲሄዱ አላይም ብሎ ከስኬ
አሸዋ ገብቶ ተሠወረ። ደልቲ የመለየትን መጥፎ ዕጣ ተጋተ"

ደልቲ አሁን የሚወደውን የማጣት ዕጣ ደርሶት የትካዜ አባዜን
እያስተናገደ ነው። እነሱ ጥለውት ሄዱ፤ እሱ ግን ያለው እዚያው ነው" ነገ ልጃገረዶች ለሱ የዘፈኑለት የዘፈን ዜማና ግጥም ለሌላ አዲስ ጀግና ሲተላለፍ ህምታ ሰፍኖበት መቆዘሙ ላይቀር ነው"

አይ ሕይወት! የሞላ መስሎ ይቆይና መፍሰስ ይጀምራል" ፍቅር
ሲጀምሩት የጥቅምት ማር ይሆንና ሲያልቅ ግን ይመራል ያስከፋል ያስደምማል" ጀግናው ደልቲ ላይ እንኳን የወደዱትን
የማጣት አባዜ እየተንቦራቸ እየተጠጋ ነው።

ሁለቱ ፍቅረኞቹ ሲያዩት እንደ በሰለ ድንች በፍቅር ትርክክ ብለውለት ነበር እቀፈኝ፣ ጠበቅ አድርገህ ወደ ሰውነትህ ለጥፈኝ
እያሉ አዝናንተውታል ከዚያና ከዚህ እየተቀባበሉ ዘፍነው፣
በጭፈራ ልባቸው ጠፍቶ፣ ልቡን አጥፍተውታል" አሁን ግን እነሱ የሉም" አሁን ተራው የሌላ ነው" ለዛሬ ትናንት ትዝታ ነው በትናንት እሱ ተውቧል፤ ዛሬ የትዝታው ቀን ናት ነገስ የማን ትሆን?

ደልቲ ገልዲና አንተነህ ይመር ከሐመር አለኝታ፣ ከሐመሮች ሕይወትና ተስፋ "ከስኬ ወንዝ ዳር ተጋድመዋል" ሁለቱም ከተስፋ ይልቅ በትዝታ ይንቦጫረቃሉ።....

💫ይቀጥላል💫
👍245
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ማርጋሬት መጮኋን ሰምቶ ሉተር በመስኮት ተመለከተና ‹‹ባህሩ ውስጥ ወድቀዋል››› ሲል ጮኸ በጭንቀት፡፡

‹‹እነማ ናቸው?›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ጎረምሳውና ጆ›› አለ ሉተር፡

የጀልባው ነጂ ገመድ ቢወረውርላቸውም ሁለቱ ሰዎች አላዩትም፡፡ እነሱ
የሚይዙትን አጥተው በፍርሃት ውሃ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ሲሆን ጆ
ጎረምሳውን ልጅ ወደ ባህሩ ውስጥ እየደፈቀው ነው፡፡

‹‹እባክህ እርዳቸው›› አለ ሉተር እሱም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ፡፡

‹‹ምን?›› አለቪንቺኒ ‹‹ምንም ልንረዳቸው የምንችለው ነገር ያለ
አይመስለኝም፡ እነሱም ራሳቸውን ለማዳን አቅም የላቸውም፡፡›› በመጨረሻም
ሁለቱን ሰዎች ጨካኙ ባህር ሰለቀጣቸው፡

‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር ‹‹በመጀመሪያ ውሃ ውስጥዐእንዴት ሊወድቁ ቻሉ?››

‹‹ምናልባት የሆነ ሰው ገፍቷቸው ይሆናል›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ማን?››

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የሆነ ሌላ ሰው ይሆናል፡›› ማርጋሬት የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስትሰማ ስለነበር ሄሪ ሊሆን ይችላል› ስትል
ገመተች፡ ሄሪ ጀልባው ውስጥ ይኖር ይሆን?
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን
ሲፈትሹ እሱ የሆነ ቦታ ተደብቆ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ሲያርፍ ከተደበቀበት
ወጥቶ ይሆን? ሁለቱን ወሮበሎች ውሃ ውስጥ ገፍቶ የጨመራቸው እሱ
ይሆን? እያለች መልስ የሌለው ጥያቄ በአዕምሮዋ ተጉላላ፡፡

በኋላ ደግሞ ወንድሟ ትዝ አላት ፔርሲ የወሮበሎቹ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር በሚታሰርበት ጊዜ ነው የጠፋው፡፡ ‹ምናልባትም መጸዳጃ ቤት ሄዶ ግርግሩ እስኪያልቅ እዚያው ሊቆይ አስቦ ይሆናል› አለች በሆዷ፡
እሱ ደግሞ እንዲህ አይነት ባህሪ የለውም፡፡ እሱ እንደውም ሁሉን ነገር
ለማወቅ ስለሚፈልግ ችግር አይፈራም፡፡

ሉተር ‹‹ሁሉ ነገር ከእጃችን እየወጣ ነው ምን ብናደርግ ይሻላል?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አሁን በመጣችው አይሮፕላን እንሄዳለን እንዳቀድነው፡፡ አንተ፣ እኔና
ሳይንቲስቱ›› አለ ቪንቺኒ፡ ‹‹መንገዳችንን ሊያሰናክል የሚሞክር ሰው ካለ
በሆዱ ጥይት ልቀቅበት፡ አሁን ረጋ ብለን እንውጣ፡፡››
ማርጋሬት ወሮበሎቹ ፔርሲን ደረጃው ላይ ያገኙትና በሆዱ ጥይት
ይለቁበታል ብላ ሰጋች፡
ሶስቱ ሰዎች ከምግብ ቤቱ ሲወጡ የፔርሲ ድምጽ ከበስተኋላቸው
ተሰማ፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ ‹‹እንዳትነቃነቁ!›› አለ፡፡
ፔርሲ ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን መደገኑን ስታይ ማርጋሬት ዓይኗን ማመን አቃታት፡፡ የሽጉጡን አፈሙዝ አይታ ካፒቴኑ ከኤፍ.ቢ.አዩ ሰውዬ
ላይ የነጠቀው መሆኑን ገመተች፡

ቪንቺኒ ቀስ ብሎ ወደ ፔርሲ ዞረ፡፡

ማርጋሬት የወንድሟ ህይወት አደጋ ላይ ቢሆንም በፔርሲ ኮራች፡፡

የመብል ክፍሉ በሰው
ተሞልቷል፡፡ ከቪንቺኒ ኋላ ማርጋሬት ከተቀመጠችበት አጠገብ ሉተር በሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡ በሌላኛው በኩል ናንሲ፣ መርቪን፣ ዳያና፣ ኤዲ እና ካፒቴኑ ቆመዋል ቪንቺኒ ፔርሲን ዘለግ ላለ ጊዜ አየውና ‹‹ልጅ ከዚህ ጥፋ›› አለው፡፡

‹‹ሽጉጥህን ጣል!›› ሲል ፔርሲ አዘዘ፡፡

በመሃል አንድ ጥይት ጮኸች፡፡ የጥይቱ ድምጽ ጆሮ ያደነቁራል፡
ማርጋሬት ጩኸቷን አቀለጠችው: ማን ማን ላይ እንደተኮሰ አላወቀችም:: ፔርሲ ምንም አልሆነም፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቪንቺኒ ከደረቱ ላይ ደም እየተንፎለፎለ ተንገዳገደና መሬት ዘፍ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦርሳው
ሲወድቅ ተበረገደና ብሮቹ በደም ታጠቡ፡

ፔርሲ ቪንቺኒን ሲያይ ሽጉጡን ጣለ፡፡ ደንግጧል፡
ሁሉም ሰው ሽጉጥ የያዘው የመጨረሻው ወሮበላ ላይ አፍጧል፡

ካርል ሃርትማን በተፈጠረው
ሁኔታ ከተዘናጋው ሉተር መንጭቀው ራሳቸውን ነጻ አደረጉና መሬት ያዙ ማርጋሬት ሳይንቲስቱን ይገድላቸዋል ብላ ሰግታለች ፔርሲንም እንዲሁ፡ ነገር ግን ወዲያው የሆነው ግን
አስደንግጧታል፡፡

ሉተር አፈፍ አድርጎ ያዛት፡ ከወንበሯ ጎትቶ አነሳትና ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጡን ደገነባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በድንጋጤ በድን ሆኑ።

ማርጋሬት ፍርሃት ስለገባት መንቀሳቀስ መጮህ አልቻለችም፡ የሉተር
ሽጉጭ ጭንቅላቷን እየወጋት ነው፡ ሉተር ራሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ ከዚያም
ሳይንቲስቱን ‹‹ውጣና ጀልባ ውስጥ ግባ፡፡ ትዕዛዜን ካልፈጸምክ ልጅቷ
ጭንቅላት ላይ ጥይት እቀረቅርበታለሁ›› አለ፡፡
ወዲያው ፍርሃቷ ሲለቃት ታወቃት፡፡ ሉተር  ብልህ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ ሽጉጡን ሃርትማን ላይ ደግኖ ቢሆን ኖሮ ሃርትማን ግደለኝ ጀርመን አገር ከምመለስ ሞቴን እመርጣለሁ› እንደሚሉ እርግጠኛ ሆኗል፡ አሁን ግን የእሷ ህይወት አደጋ ላይ ነው፡ ሃርትማን ምናልባት
ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ይሆኑ ይሆናል፡፡

ሃርትማን ቀስ ብለው ተነስተው ቆሙ፡፡

ሁሉም ነገር በማርጋሬት ላይ የተጣለ ነበር፡ ራሷን ሰውታ ማዳን ትችላለች፡ ሆኖም ይህ አድራጎት ጥሩ አይደለም፡፡ እሷም ይህን አደርጋለሁ ብላ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህ ራሴን አላዘጋጀሁም፡፡ ማድረግ አልችልም› አለች
በሆዷ፡
ከአባቷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ አባቷ በጣም ደንግጠዋል ሲያበሻቅጧት እንደኖሩ ምን ያህል
አቅመቢስ እንደሆነች ጦሩንም ተቀላቅላ አንድ ቀን እንኳን እንደማትቆይ
የነገሯት ሁሉ ትዝ አላት፡፡
አባቴ ያለው እውነት ይሆን?› አለች ለራሷ፡
ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ሉተር ሊገላት ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት ሌሎች ሰዎች ዘለው ይረባረቡበታል ጊዜው እየሄደ ነው፤ አንድ ነገር ማድረግ አያቅተኝም, አለች በሆዷ፡

ከዚያም ‹‹ሁላችሁም ደህና ሁኑ›› አለች፡፡ አፍታም ሳይቆይ የሄሪን ድምጽ ከኋላዋ ሰማች፡፡

‹‹ሚስተር ሉተር ጠላቂው መርከብህ ደርሷል›› አለ፡፡

ሁሉም ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት ተመለከተ፡፡ ማርጋሬት ሄሪ በተናገረው ነገር ሉተር ልቡ መወሰዱን አወቀች፡፡ ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፤ እሷ ግን ምንም አልሆነችም፡፡ ሁሉም አንድ ጊዜ ተንቀሳቀሰ፡፡ ኤዲ ዘለለና እንደ ተቆረጠ ዛፍ ሉተር ላይ ወደቀበት፡፡ ሄሪ የሉተርን ሽጉጥ
መንጭቆ ወሰደ፡፡

ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ሄደና አቀፈችው፡፡ ‹‹አንተ ግን ደህና ነህ?››ቸ ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ ይመስለኛል››
‹‹በጣም ጎበዝ ነህ››
‹‹አንቺም እንዲሁ››
‹አዎ እኔ ጎበዝ ነኝ አለች ለራሷ፡
ፀጥ ብሎ የቆየው ተሳፋሪ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተንጫጫ፡፡ በዚህ ጊዜ
ካፒቴኑ ‹‹ፀጥታ እባካችሁ ዝም በሉ›› አለ፡፡
ማርጋሬት ዙሪያውን ቃኘች፡፡
ሉተር ኤዲ እና ሄሪ ላዩ ላይ ወጥተውበት ከመሬቱ ላይ እንደተደፋ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ያንዣበበው አደጋ ተወግዷል፡ ሃርትማንና
ሉተርን ሊወስድ የመጣው ጠላቂ መርከብ ተንሳፎ ይታያል፡

ካፒቴኑም የባህር ኃይል መርከብ በቅርብ ርቀት ይታያል፡ ‹‹ጠላቂ
መርከብ እዚህ እንዳለ የሬዲዮ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡››
‹‹ቤን›› ሲል ተጣራ፡
‹‹አቤት ጌታዬ›› አለ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹የጠላቂው መርከብ አዛዥ
ሬዲዮ መልእክት ማስተላለፋችንን ካወቀ ወደ እኛ ሊተኩስ እንደሚችል
ተገንዝበኸዋል?›› አለ ቤን፡፡

‹‹ደህና ይቅር›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ተሳፋሪዎቻችን እስካሁን የደረሰባቸው መከራ
ይበቃል፡››
ጠላቂው መርከብ መግቢያው እንደተዘጋ ነው አዛዡ  አንድ ነገር
ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ነው፡፡

‹‹ቤከር አንድ ያልተያዘ ወሮበላ  ይቀረናል፡ እዚህ እንዲመጣ እፈልጋለሁ፡፡ የጀልባዋ ነጂ፡ ኤዲ ሂድና ቪንቺኒ እንደሚፈልገው ንገረው አለው
👍192🔥2🥰2🤔1
ኤዲ ሉተርን ለቀቀና ወጥቶ ሄደ፡

ካፒቴኑ ናቪጌተሩን ጠራና ‹‹እነዚህን ሽጉጦች ሰብስብና ጥይቶቹን
አውጥተህ አስቀምጥ›› ሲል አዘዘ፡፡

ካፒቴኑ ሉተርን በጫማው ወጋ አደረገውና ሌላውን የአይሮፕላኑ ሰራተኛ የሆነውን ጆኒን ‹‹ይህን ወንበዴ ውሰድና አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፍበት ጠብቀው›› ሲል አዘዘው፡
ሄሪ ሉተርን ለቀቀውና ጆኒ ይዞት ሄደ፡

ሄሪና ማርጋሬት ተያዩ፡
ሄሪ ትቶኝ ሄዷል ብላ ደምድማ ነበር፡፡ እስከወዲያኛው ዓይኑን
አላየውም ብላ ነበር ያሰበችው: ህይወቴ ይተርፋልም ብላ አልገመተችም፡ ሆኖም ግን በአምላክ ቸርነት በህይወት መገናኘታቸው ደንቋታል፡
ማርጋሬት ሮጠችና እቅፉ ውስጥ ገባች፡፡ አንድ ሰው እስኪመስሉ ድረስ
ተጣበቁ፡፡

ትንሽ ቆይቶ ‹‹ወደ ውጭ ተመልከች›› አላት፡፡
ጠላቂው መርከብ ቀስ እያለ እየሰመጠ ነበር፡፡
ማርጋሬት ፈገግ አለችና ሄሪን ከንፈሩን መጠመጠችው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሁሉ ነገር ካበቃ በኋላ ካሮል አን ባሏ ጫፌን አይነካኝም ብላ መሸሽ ጀምራለች፡ አስተናጋጁ ዴቪ ያፈላላትን ማኪያቶ እየጠጣች ነው፡ ፊቷ ገርጥቷል፡፡ ሰውነቷ አሁንም ይንቀጠቀጣል፡፡ ኤዲ ባለፈ ባገደመ ቁጥር
ሲነካት ድንግጥ ትላለች፡፡

አጠገቧ ቁጭ ብሎ ያያታል፡፡ እሷ ግን የባሏን ዓይን ትሸሻለች፡፡ ምን
እንደተፈጠረ ያወራሉ፡፡ ሰዎቹ በሩን በርግደው ገብተው ወደ መኪናቸው
እየጎተቱ እንደወሰዷት ደጋግማ ትነግረዋለች ታሪኩ ይሄ ብቻ እንደሆነ
ሁሉ፡፡

‹‹አሁን ክፉው ነገር ሁሉ አልፏል›› ይላታል ኤዲ ደጋግሞ፧ እሷም ራሷን ትነቀንቃለች ነገር ግን እሷ ከዚህ በሰላም እስካልወጣች ድረስ
አታምንም::
በመጨረሻ እንደምንም ብላ ቀና ብላ አየችውና ‹‹በሚቀጥለው ጊዜ መቹ
ነው የምትበረው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

ጥያቄዋ ገባው፡፡ እሱም ‹‹የበረራ ስራ አቆማለሁ›› አላት ‹አሁኑኑ ስራዬን እለቃለሁ፡ እኔም ስራዬን ባልለቅ እነሱ ማባረራቸው አይቀርም::የተሳፋሪዎቹን ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ ድንገት አይሮፕላን ባህር ላይ እንዲያርፍ የሚያደርግ እንደ እኔ ያለ አይቆይም፡፡››

ካፒቴን ባልና ሚስቱ የሚነጋገሩትን ሰምቶ ኖሮ
‹‹አንድ ነገር ልነግርህ
ወደድኩ፡፡ ያደረከው ነገር በሙሉ አሁን ገብቶኛል፤ የገጠመህን ችግር በድል
ለመወጣት የምትችለውን አድርገሃል፡፡ አንተ ካደረግኸው የተሻለ ነገሩን
የሚያስኬድ ሰው አለ ብዬ አላምንም፧ በጣም ጎበዝ ስለሆንክ ከአንተ ጋር
መብረሩ ያኮራኛል›› አለ፡፡

‹‹አመሰግናለሁ አለቃ›› አለ ኤዲ፡፡ ኤዲ በካፒቴኑ አነጋገር ልቡ ተነካና ሳግ ጉሮሮውን ተናነቀው፤ ‹‹ያልከው ነገር ምን ያህል ችግሬን እንዳቀለለልኝ
መናገር ያቅተኛል›› አለ፡ ዞር ብሎ በድንጋጤ የተሸማቀቀውን ፔርሲን
ተመለከተና ‹‹ጌታዬ ወጣቱ ፔርሲን ማመስገን ይገባናል፤ እሱ ነው ከጉድ
ያወጣን›› አለ

‹‹ጥሩ ብለሃል›› አለ ካፒቴኑ የኤዲን ጀርባ በአድናቆት ቸበቸበና፡ ወደ ፔርሲም ሄዶ

‹‹አንተ ጎበዝ ልጅ ነህ ፔርሲ›› አለና ጨበጠው፡፡
ፔርሲም ወዲያው ድንጋጤው ለቀቀውና ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ፡
ካሮል አን ‹‹መብረር የምታቆም ከሆነ ምን አይነት ስራ ልትሰራ
አስበሃል?›› ስትል ጠየቀችው ኤዲን፡፡

‹‹የተነጋገርነውን ስራ እጀምራለሁ፡››

ዓይኗ ላይ ተስፋ አነበበ፤ ነገር ግን ለማመን ስለቸገራት ‹‹እንችላለን?››
ስትል ጠየቀችው፡

‹‹አየር ማረፊያውን ለመግዛት የሚያስችለኝን ገንዘብ ባንክ አስቀምጫለሁ። ቀሪውን ከባንክ እበደራለሁ፡፡››

ካሮል አን ወዲያውኑ በደስታ ዓይኗ በራና ‹‹አብረን እንሰራለና›› አለች
‹‹አንተ ለጥገና ወይም ነዳጅ ለመሙላት ስትሄድ እኔ ሂሳብ እሰራልሃለሁ
የስልክ ጥሪም እቀበላለሁ፡››
ኤዲም ፈገግ አለና ‹‹ልጅ እስከምትወልጂ ድረስ›› አለ፡፡

እጁን ሰደደና እጇን ለቀም አደረገው:፡ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ ድንብር
አላለችም፡፡ እንደውም እሷ አጥብቃ እጁን ያዘች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ናንሲ መርቪንን እንቅ አድርጋ ስትይዘው ዳያና ልታናግረው ፈልጋ
ጀርባውን ነካ አደረገችው፡፡

ናንሲ የእሷና የምትወደው ሰው ህይወት መትረፍ በፈጠረላት ደስታ
ተውጣለች፡ ዳያና በዚህ ጊዜ የመጣላትን ደስታ እንዳትነጥቅባት ተመኘች፡፡
ዳያና ከባሏ ለመለየት እስካሁን ቁርጥ ውሳኔ ላይ አልደረሰችም ነበር፡ አንዴ
መጣ አንዴ ሸሸት ስትል ነበር እስካሁን የቆየችው የእሷን ህይወት ለማትረፍ ከወረበሎች ጋር መደራደሩ እስካሁን ለእሷ ያለውን ፍቅር ያሳያል፡፡ ‹ታዲያ መልሰህ ውሰደኝ ትለው ይሆን?,

መርቪን ወደ ሚስቱ ዞር አለና ‹‹አቤት ዳያና›› አላት፡፡ ዓይኗ በእምባ የተሞላ ቢሆንም ውሳኔ ላይ እንደደረሰች ያስታውቃል፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ታናግረኛለህ?›› አለች

ዳያና ያለችው ለናንሲ ግልፅ አልሆነላትም፡፡ የመርቪን ሆድ አልቆርጥ ማለቱም ወደ እሷ ይመለሳል የሚል ጥርጣሬ አጭሮባታል፡

እሱም እጇን ለመጨበጥ እጁን ዘረጋና ‹‹በሚገባ›› አላት፡፡

ዳያና በሁለት እጇ እጁን አጥብቃ ያዘችው አሁንም ታነባለች፡፡

ናንሲ ይህን ስታይ ዳያና ‹ወደቤት እመለሳለሁ› ትላለች ብላ ጠበቀች
የተገላቢጦሽ ግን ‹‹መልካም ዕድል ይግጠምህ መርቪን፡፡ ቀሪው ህይወት በደስታ የተሞላ እንዲሆን እመኝልሃለሁ›› አለች፡፡

መርቪን ፊቱን እንደከፋው ‹‹አመሰግናለሁ ዳያና፤ እኔም እንደዚሁ መልካም ዕድል እንዲገጥምሽ እመኝልሻለሁ›› አለ፡፡

ናንሲ ሁለቱም ለሆነው ነገር ይቅር ሊባባሉ እንደሆነ ገባት መለያየታቸው አይቀርም፧ ሆኖም የሚለያዩት ቂም በሆዳቸው ቋጥረው አይደለም፡፡

በደመነፍስ ናንሲ ጣውንቷን ‹‹መጨባበጥ እንችላለን?›› አለቻት፡

ዳያናም ‹‹አዎ›› አለችና ተጨባበጡ ‹‹መልካም ዕድል ይግጠምሽ››
አለቻት፡፡

‹‹አንቺም እንዲሁ›› አለች ናንሲ፡፡

ዳያና ዞረችና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች፡፡
መርቪንም ‹‹እንዴት ነው የወደፊት አኗኗራችን?›› ሲል ናንሲን ጠየቃት፡፡

ናንሲ ጊዜ አግኝታ ያሰበችውን አለመንገሯን ተገነዘበች፡፡ ‹‹የናት
ሪጅዌይ ኩባንያ የአውሮፓ ሀላፊ ሆኜ እሰራለሁ››
መርቪን አባባሏ ገረመውና ‹‹ይህን ኃላፊነት የሰጠሽ መቼ ነው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡

‹‹አልሰጠኝም ነገር ግን ይሰጠኛል›› አለችና በደስታ ተፍነከነከች፡

ትንሽ ቆየና የሞተር ጩኸት ተሰማ፡፡ ይህ ድምጽ ግን የግዙፉ አይሮፕላናቸው ድምጽ እንዳልሆነ ይታወቃል፡ የባህር ኃይሎች የመጡ መስሏት ናንሲ በመስኮት አየች፡፡

የወሮበሎቹ ጀልባ ከትልቁ
አይሮፕላን ጋር የታሰረበት ገመድ መፈታቱንና ጀልባው ሊሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን አየች፡:

ታዲያ ጀልባውን ማነው የሚነዳው?

ማርጋሬት በፍጥነት ጀልባውን ነዳችው፡፡

ንፋሱ ጸጉሯን ወደ ኋላ ይገፋዋል፡፡

በደስታ ‹‹አሁን ነፃ! ነፃ!›› አለች፡፡

እሷና ሄሪ ይህ ሀሳብ የመጣላቸው ሳይነጋገሩ ነው፡

‹ወደፊት እንዴት ነው የምንኖረው?› እያሉ በየግላቸው ሲያስቡ ኤዲ
ወሮበሎቹን ይዞ የመጣውን ጀልባ ነጂ አግቶ ሲያመጣው ጀልባውን ይዞ
መጥፋት የሚባል ሀሳብ መጣላቸው፡፡

ተሳፋሪዎቹ ከሞት አደጋ ስለተረፉ እርስ በእርሳቸው ‹‹እንኳን ደስ ያለህ ደስ ያለሽ›› ሲባባሉ ሄሪና ማርጋሬት ሾልከው ወጥተው ነው ጀልባው
ላይ የወጡት፡፡ የጀልባው ሞተር አልጠፋም ነበር፡ ሄሪ ጀልባው ከትልቁ አይሮፕላን ጋር የታሰረበትን ገመድ ሲፈታ ማርጋሬት በበኩሏ የሞተሩን ማንቀሳቀሻ መሳሪያዎች እንዴት እንደሚሰሩ እየቃኘች ነበር፡ ጀልባው ደግሞ ከአባቷ ጀልባ ጋር ብዙ ልዩነት የለውም፡፡
👍12
ከኋላቸው ማንም እንደማይከተላቸው ገምታለች፡ የባህር ኃይሉ
መርከብ የጀርመኑን ጠላቂ መርከብ እያሳደደ ስለሆነ ለንደን ላይ የተወሰኑ
የወርቅ አምባሮች የሰረቀ ሰውን የሚፈልግበት ምክንያት የለም፡ ፖሊስ
አይሮፕላኑ ጋ ሲመጣ ደግሞ የግድያ፣ የአፈና እና የባህር ላይ ውንብድና
ወንጀሎች በማጣራት ላይ ይጠመዳል፡ ሄሪን ምናልባት የሚያስታውሱት
ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው
ሄሪ የጀልባዋን ኪሶች ሲበረብር ማፕ አገኘ፡፡ ማፑን በደምብ ሲያይ
ቆየና ‹‹እዚያ የሚታየውን ጠረፍ አላማ አድርገን ብንጓዝ አቅጣጫችንን
አንስትም አመሻሽ ላይ ጠረፉ ጋር እንደርሳለን›› አለ፡

ማርጋሬት ፈገግ አለች፡
ማፑን አስቀመጠና አፍጥጦ ተመለከታት፡
‹‹ምን እንደዚህ አፍጥጠህ ታየኛለህ?›› ስትል ጠየቀችው
‹‹በጣም ቆንጆ ነሽ›› አለ ‹‹እኔን ደሞ ትወጂኛለሽ››
ማርጋሬት በሳቅ ፈነዳች፡፡ ‹‹ከአንተ ጋር የተቀራረበ ሁሉ ይወድሃል” አለችው:
እጁን ሰዶ ወገቧን አቀፈና ‹‹እንዳንቺ ካለች ልጅ ጋር በጀልባ መጓዝ
ምንኛ ደስ ይላል፡፡ አሮጊቷ እናቴ ሁልጊዜ አንተ እድለኛ ነህ ትለኝ ነበር፡ ልክ ናት አይደለችም?›› አላት፡፡ተ

‹‹ጠረፍ ስንደርስ ምንድን ነው የምናደርገው?›› አለች፡፡

‹‹ጀልባውን አንድ ጥግ አቁመን ወደ ከተማ ሄደን ቤርጎ እንይዝና
አድረን በጠዋት በባቡር ተሳፍረን እንሄዳለን››
‹‹ገንዘብ እንዴት እንደምናገኝ አላውቅም›› አለች ማርጋሬት ፊቷ ላይ
ጭንቀት እየተነበበ፡፡ ‹‹አሁን ችግሬ ገንዘብ ነው፡፡ ትንሽ ገንዘብ ነው ያለኝ
ይህን ገንዘብ ለቤርጎ እንከፍላለን፡፡ ቲኬትና ልብስ እንገዛበታለን፡፡ ቦርሳዬን
እንደ አንተ አምጥቼ ቢሆን ጥሩ ነበር›› አለች፡፡
‹‹ይሄ የኔ ሻንጣ አይደለም›› አለ ‹‹የሚስተር ሉተር ነው››
‹‹ለምን የእሱን ቦርሳ ይዘህ መጣህ?››
‹‹ምክንያቱም መቶ ሺህ ዶላር እውስጡ ስላለበት ነዋ›› አለና አስካካ፡...

ተፈፀመ
👍27👏6
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ አራት (44)


«ሁሉን ነገር የማራገፍ ጉዳይ ። እኔና ማይክ ኣንድ ላይ በነበርንበት ጊዜ በጋራ የአደረግናቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ ። እስከዛሬ ድረስ ማይክል ይመለሳል ፣ ያስበኛል ፤፣ ይፈልገኛል እያልኩ የተውኳቸውን ነገሮች ማለቴ ነው ። ለፍቅራችን ሀውልት እንዲሆኑ ብዬ ነበር የተውኳቸው ። አሁን በቃ ። ሄጄ አንድ ነገር ላደርግ ወስኛለሁ»
«እምትችይ ይመስልሻል ?»
«በሚገባ» አለች ፌ እሊሰንን እንኳ ቆራጥ መስሎ በተሰማት ድምፅ።
«ከዚህ ሁሉ በፊት ማን እንደሆንሽ ፤ ማን እንደነበርሽ ለማይክል መንገር አትፈልጊም ? »
«ፍጹም የማይሞከር ነገር ነው» አለች እያንገፈገፋት «አለቀ ደቀቀ ፤ አልኩሽኮ በቃ ። በዚያም ላይ ይህን ባደርግ ለፒተርም መልካም አይሆንም» አለች የሀዘን ትንፋሽ በረጂሙ ተንፍሳ ። ቀጥላም… ‹‹ፌ» አለች ። «ፌ ፣! ፒተርን ላስቀይመው አልፈልግም። ፒተር ጥሩ ሰው ነው ። የዋለልኝ ውለታ ተቆጥሮ እሚያልቅ እይደለም «ያም ሆነ ያ አታፈቅሪውም» አለች ፌ አሊሰን ። «አይምሰልሽ እወደዋለሁ»
«ታዲያ ቃል ለመግባት እወድሀለሁ ብሎ ለመንገር ችግሩ ምንድነው!!?»
‹‹ማይክል ይመስለኛል ። ማይክል በመካከላችን ገብቶ ድንቅር ይል ስለነበረ ነው ብዬ አምናለሁ»
«እሱ ቀላል ነገር ነውኮ ሜሪ ። ስሜትን መሸፈኛ ካልሆነ በስተቀር እሱ ነገር አልቆለታል ብለናል ገና ዱሮ»
«ብቻ እንጃ» አለችና ንግግሯን አቋረጠች ፤ ‹‹ብቻ አንድ ነገር አለ ፤ ለፒተር ቃል እንዳልገባ የሚገረግረኝ ፤ ተይ የሚለኝ ። አንድ የጎደለ ነገር አለ ።ምናልባት... ብቻ ማይክልን ተውኩት ብልም ከልቤ አላወጣሁትም ነበር ። ከፊል ልቤ ይመጣል የሚል ተስፋ ላይ ሙጭጭ ብሎ ተጣብቆ ይሆናል... . ብቻ እንጃ አንድ ልክ ያልሆነ ነገር ቢኖር ይሆናል ። ምናልባትም እኔው ራሴ እሆናለሁ»
«ልክ ያልሆነ ነገር ይኖር ይሆናል ብለሽ እንድታስቢ የሚያደርግሽ ምን ይመስልሻል ? »
«ይህንንም በቅጡ አላውቀውም ። ምናልባት ፒተር ይወደኛል እንጂ አያውቀኝም የሟል ሀሳብ ሳይኖር አይቀርም በኔ በኩል።... ፒተር ያውቀኛል ፤እኔን ሜሪ አዳምሰንን ማለቴ ነው ግን ያለፈ ህይወቴን አያውቀውም ። ባለፈ ህይወቴ የምወዳቸውን ነገሮች አያውቅም»
«አትነግሪውም ? ማለት እንዲያውቅ ማድረግ አትችይም ?»
«ምናልባት እችል ይሆናል ። ግን ደግሞ ማወቅ እሚፈልግም ኦይመስለኝም ። መፈቀሬን እንዳውቅ ሊያደርግ ሲሞክር አየዋለሁ። ግን ደግሞ ሙሉ እኔነቴን እንዳልሆነም እጠራጠራለሁ»
«ያን ካነሳን ብዙ ነገር ሊመጣ ይችላል»
«ልክ ነሽ ።ያም ሆኖ ግን ፒተር ደህና ሰው ነው። በፈለግኩት መንገድ ብሞክር ጉዳዩ የማይሳካበት ምክንያት አይታየኝም»
«ሊሳካ የሚችለው ካፈቀርሺው ብቻ ነው»
«አፈቅረዋለሁና»
«በሱም ካመንሽበት ደህና ። ዘና ብለሽ የሚሆነው እስኪሆን ጠብቂ ። ከፈለግሺም እንዲህ እንደዛሬው ጎራ እያልሽ ልንማግከርበት እንችላለን… ወደሬት ። ለዛሬ ግን ስለማይክል ምን ፤ ምን እንደሚሰማሽ ተነጋግረን መጨረሻውን ማየቱ ነው ደጉ»
«ይህን የቦስተን ጉዞዬን ላድርግና ሁሉን ነገር ላራግፍ ። ከዚያ በኋላ ነፃ እሆናለሁ»
«መልካም ። ስትመለሺ ጎራ በይና ጠይቂኝ ። እንዲያ ማድረጉ ጥሩ አይመስልሽም ?»
«በጣም እንጂ !» ሜሪ አዳምሰን ሁሉ ነገር ቀለል ያላት ሆና ታየች ።

ፌ አሊሰን ሰዓቷን አይታ ዩኒቨርስቲ ማስተማር ስላለባት ልትለያት መሆኑን በማሰብ የመከፋት መልክ ታየባት ። ከዚያም «እንግዲህ እንዴት ነው እምናደርገው ? ከቦስተን እንደተመሽ ደውለሽ ቀጠሮ ብንይዝ አይሻልም ?» ስትል ጠየቀቻት ። ‹‹ልክ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ »
«መልካም ። እና ደሞ ራስሽን ጠብቂ፣ እሺ? ያለፈ ነገር እያስታወሱ በትዝታ መናበዝ አያስፈልግም ። ቦስተንም ሆነ የት ችግር ካጋጠመሸ ደውዬልኝ ።» ፌ አሊሰን ይህን ስትላት ሜሪ ተደሰተች ።እገሌ አለኝ ብሎ ማሰቡ ራሱ ትልቅ ነገር እንደሆነ ገባት ።

ያንለት ከፌ አሊሰን ጋር ተነጋግራ ስትመለስ ሰሞኑን ከብዷት የነበረው ነገር ሁሉ ቀላል ሆኖ ታያት ። ስሜቷም ፈካ ። የዛሬው የፌ አሊሰንና የሷ ንግግር የሚሰማትን ነገር ለፒተር ግሬግሰን ለመግለፅ መንገድ እንደጠረገላት ፤ ውሳኔዋንም ለመንገር ቀላል እንዳደረገላት ተገነዘበት ።
👍15
ያንለት ማታ ሜሪ አዳምሰን ለፒተር ግሬግሰን ወደ ቦስትን ለመሄድ እንዳሰበች ነገረችው ። «ቦስተን? ለምን? ምን ልትፈጥሪ ፤ ሜሪ? የምትይው ነገር ፈጽሞ አልገባኝም» አለ ፒትር። ያንለት ፒተር ያለወትሮው ሰልችትችት ብሎት ነበር ። እንዲሁም አነጋገሩ የቁጣ ይመስል ነበር ። በመሰላቸቱም ቁጣ ቁጣ ስላለውም ሜሪ አልከፋትም። የዚህ አዲስ ባህሪ ምክንያቱ ገብቷታል ። ሰሞኑን አላረፈም ። በተለይም ያንለት ቀኑን በሙሉ ተወጥሮ እንደዋለ ታውቃለች ። አሰልቺ ስብሰባዎች ፤ ይኸ ወይም ያ ነገር ። አዲስ ስለሚሰራው የህክምና ማዕከል ለመነጋገር ደግሞ ነገ ከአርክቴክቶች ጋር ቀጠሮ እለው ፤በጧት ። ጣጣ ነው። ያን ሁሉ ችሎ የዋለ ሰው ገና ነገም እንደማያርፍ ሲረዳ ቢደክም ቢሰለች በተለይም ያላሰበውን ነገር ሲሰማ ቁጣ ቁጣ ቢለው ይፈረድበታል ? ለፒተርም ሆነ ለሜሪ ያልገባቸው ነገር የፒተር እዚያ ኮሚቴ ውስጥ መግባት ነው። ምን ሊሰራ ገባ? የተሻለ ሥራ ሊሠራ ሲችል ጊዜውን ለምን ያባክናል? ግልፅ አይደለም ። «ከመሬት ተነስተሽ ልሂድ ስትይ በጠቅላላ እብድ መሰልሽኝ» አለ ፒተር «እብደት ነው»
«እብድም አይደለሁም ፤ አብደትም አይደለም ። መሄድ ስላለብኝ ነው። ስለሆነም ይኽው ወስኘ ጨርሻለሁ።. .. ፒተር በፊት በሕይወቴ የነበረውን ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ አራግፌ ጨርሻለሁ ። አንድም ትዝታ ሳይቀር››
«እኮ እየነው አደል! ... ምንም ትዝታ ሳይቀር ስላራገፍሽው አይደለም ትላንትና ያልደረሰ የመኪና አደጋ ያን ያሀል ያስደነገጠሽና ነፍስሽን ለመግዛት ካንድ ሰዓት በላይ የወሰደብሽ! ሜሪ አንደባበቅ። ሙሉ በሙሉ አላራገፍሽውም።ያለፈ ትዝታሽን ማለቴ ነው»
«አመነኝ አንድም ችግር አይኖርም ። አንድ ነገር አለ! ካለፈው ችዝታ የተረፈ ። ያንን እንደሚሆን ካደረግኩ በኋላ በቃ ነፃ ነኝ። ከነገ ወዲያ ነፃ ሆኘ እመለሳለሁ››
«እብዶት ነው አልኩሽ!»
«በፍጹም አይደለም አልኩህ!» ይህን ያለችው በሙሉ ልብና በትረጋጋ ድምፅ ነበረና ፒተር ግሬግሰንን ገታው። ፒተር እወንበሩ ላይ ወደ ኋላው ተለጥጦ ተቀመጠ። በመሰልቸት በረጂሙ ተነፈሰ ። ምናልባትም እውነቷን ሊሆን ይችላል ። አውጥታ አውርዳ የወሰነችው ነገር ሊሆን ይችላል ፤ ሲል አሳበ ። «ካልሽ እንግዲህ ደግ። ግን ምኑም አልገባኝም። ምናልባት አስበሽበት ይሆናል ። እንዲያ እንደሚሆንም እምኛለሁ ። ግን ቦስተን ስችሄጂ የምትፈሪው ምንም ነገር የለም?»
«ምን ይነካኛል ምንም አልሆንም ። እመነኝ››
«አምንሻለሁ የኔ እመቤት ። እንዲህ እሚያሰኘኝ ስላላመንኩሽ ሳይሆን ... ፤ያ ሳይሆን ... እንዲያው አንድ ነገር... ብቻ እንጃ ክፉ ነገር እንዲደርስብሽ አልፈልግም ። አየሽ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? ግን . . ጥያቄው ሙሉ በሙሉ የጅል ጥያቄ ሊሆን ይችላል?» ክርስቶስ አውጣኝ ! አለች ሜሪ በሀሳቧ ። ያን ጥያቄ ባልጠየቀኝ ። ዛሬ ልመልስለት አልችልም ። እሺ ወይም ፍርጥ እድርገሽ ንገሪኝ ቢለኝ ምን ልመልስለት ነው? እሷ ይህን እያሰበች ትጨነቅ እንጂ እሱ ያሰበው ደግሞ ሌላ ነበር። «ጠይቀኝ» አለች ። ቶሎ መልስ አልሰጣትም ። ማለትም ጥያቄውን ወዲያው አልጠየቃትም ።እፕራሲዮን ለመሆን የምትጠባበቅ መሰላት ጨነቃት። «ማይክል ሂልያርድ እዚህ ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ እንደሚገኝ ታውቂያ ለሽ?»
‹‹እዎ» እለች ረጋ ባላ ድምፅ ።
«ተገናኝታችኋል?»
«አዎ ። ኤግዚብሽን አዳራሽ መጥቶ ተገናኘን ። ለህክምና ማዕከሉ ፕሮጄክት የውስጥ ማስጌጫ ፎቶግራፎች እንድሰራለት ጠየቀኝ ። አይቻልም ስል መለስኩለት»
‹‹ማንነትሽን እውቋል?»
«አላወቅም»
«ለምን አልነገርሺውም?» እስከ ዛሬ ያልነገረችውን ፤ ከማይክል እናት ጋር ያደረገችውን ስምምነት ለመንገር አመቺው ጊዜ አሁን እንደሆነ ተገነዘበች። ግን ደግሞ እስከ ዛሬ አቆይታ ዛሬ ብትነግረው ፋይዳ የለውም ። ያለቀለት ነገር ነው ። «ብነግረው ባልነግረው ምንም ልዩነት እንደማያመጣ ስለገባኝ አልነገርኩትም ። ያለፈ ነገር ፤ ያለቀ ነገር ሆኗል» አለች ። «እዚህ ነገር ላይ ... ማለት እንዲህ ስትይ ... ርግጠኛ ነሽ!»
«ርግጠኛ ነኝ ። ስለሆንኩም ነው ወደ ቦስተን እምሄደው»
«እንዲያ ከሆነ እኔም ደስ አለኝ» ይህን ብሎ ለጥቂች ጊዜ ዝም አለ ። ገጽታው ላይ ጭንቀት ይነበብ ነበር «ጉዞው ከማይክል ጋር የተያያዘ ነገር አለው?» አለ ቆጥሎ። «በፍጹም እንደሱ ብለሀ አታስብ ። ማይክልና እኔ አፍም የለን ፣ ትውውቅም የለን ። ዛሬ ለየብቻ ነን ። የምሄደው . ካለፈው ኑሮዬ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ስላለኝ ነው ፤ ከኔ ኑሮ ጋር ብቻ። ከዚህ በላይ ለመናገር ግን አልፈልግም»
«እኔም ንገሪኝ አልልም ። እንደፍላጎትሽ ብታደርጊ ነው ይበልጥ ደስ የሚለኝና ነው»
«እግዜር ይስጥልኝ»

ይህን ከተነጋገሩ በኋላ ፒተር ከሜሪ ጋር አልቆየም ። ብቻዋን መሆን የምትፈልግ መሰለው ። ስለዚህም ደህና እደሪ ብሎ ስሟት ፣ መለስ ብሎ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሄደ። ያን ለት ሜሪ መንፈሷ ሁሉ ተረጋግቶ ነበር ። ስለዚህም ሌሊቱም ሰላማዊና በፀጥታ የተሞላ ሆነ ። ጧት ተነስታ ወደ እንሰሳት መጠበቂያው ፍሬድን ወሰዳ ባደራ ስታስረክብ ሁሉ መልካም እንቅልፍ መተኛት ይሰማት ነበር ። ወደ ቤቷ ኣልተመለሰችም ። በቀጥታ ወደ አየር ማረፊያ ሄዴች ። ተዝናንታ ጉዞዋን ቀጠለች ።

ቦስተን ከተማ የደረሰችው ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ነበር ። ቢመሽም ያኑለት ማታ ጉዳይዋን ወደምታከናውንበት ቦታ ለመሄድ አሰበች ። ግን ደግሞ ትንሽ እንዳበዛችውም ገባት ። ያለወግ መቻኮሏ ወለል ብሎ ታያት ። ስለዚህም ጉዞዋን ሲነጋ በጠዋቱ ማድረግ እንዳለባት ወስና መኪና ተከራይታ አደረች ። ቦስተን የኖረችበች ከተማ ሲሆን የምታውቃቸው ሰዎች አሉ። ሆኖም ለማንኛቸውም ስልክ ልትደውል አልፈለገችም ማንንም ሄዳ ልትጠይቅ አላማራትም ። ከተማውን ተዘዋውራ ለማየት እንኳ ኣልከጀለችም ። ያመጣት ጉዳይ አንድ ነው ። ጧት ተነስታ ትሄዳለች « ጉዳይዋን ፈጽማ ትመለሳለች ። የመጨረሻውን አውሮፕላንም ቢሆን ተሳፍራ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ትመለሳለች ። ሌላ ነገር የለም ። ራሷን አንድ ቅዱስ ተልኮ ያላት ሴት አድርጋ ቆጠረች ። ወዲያ ወዲህ ሳትል እሆቴሏ ውስጥ ተቀመጠች ። ሰው የለም ። የምታውቀው ነገር የለም ። እንዲያውም እሷ ራሷም ቦስተን ውስጥ አይደለም ያለችው። ይህ እሚሆነው ሁሉ ህልም ነው። ሁለት አመት ሙሉ ሳያቋርጥ ያየችው ህልም ነው ። ካሁን በኋላ ያ ህልም አይኖርም ፤ በገሃድ ። አንድ ጊዜ ብቻ ነገ ብቻ ታየዋለች።


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍32
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ልክ በስድስተኛ ወሩ እንግሊዝ አገር ውስጥ በሚገኘው የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ሁለት ቆዳ ለባሽ ሴቶች፣ አንድ
ሳዳጎራ ያገለደመ ወጣት፣ ተቃቅፈው በመግባት ቦታቸውን ይዘዋል"
አፉን ከፍቶ የነበረው አዳራሽ ቀስ በቀስ ሞልቶ ተጨናነቀ" የዕለቱ
አንትሮፖሎጂካዊ ጥናት አቅራቢ የአፍሪካ ውስጥ ምርምሯን ይዛ ወደ መድረክ ወጣች።

«…ክቡራትና ክቡራን፣ በተመራማሪነቴ የሠለጠነው ዓለም
ከረሳው ተፈጥሮና ሕዝብ መካከል ተገኝቼ፣ ለዘመናት የዳበረ ባህልና ጥበብ ያለውን ክልል ለማየትና ሕይወቱንም ለመኖር ችዬ እኔ ያገኘሁትን ዕውቀት ለቀሪው ዓለም ሕዝብ ለመግለጽ በመብቃቴ
ደስታዩ ወደር የለውም።

«የሐመር ተፈጥሮ፣ ሰው ሠራሽ ብክለት ያልተጠናወተው ንጹሕ
ተፈጥሮ ነው። በዓለማችን ፍጹም ደስታ ያለው ሕዝብ አለ የሚል እምነት የለኝም" ደስተኛ ሕዝብ አለ ከተባለ ግን ከሐመር ሕዝብ
የበለጠ ደስተኛ፣ ግልጽ፣ በመካከሉ ጠንካራ መፈቃቀር ያለው ያለ
አይመስለኝም።

«በዘመናችን እንደ ብርቅ የሚታየው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሐመሮች ለብዙ ዘመናት የሕልውናቸው የማዕዘን ድንጋይ አድርገውት ኖረዋል" ከዚህ በተጨማሪም፣ የሐመሮች የዳበረ የከብት አረባብ ዘዴ፣ የአመጋገብ ሥርዓት፣ ብሒሎችና ትውፊቶች ወዘተ.ዝብርቅርቁ የወጣውን የዘመነውን ዓለም ዓይነ ልቦና የሚስብ
እንደሆነ አምናለሁ።
«...ለማጠቃለል
ያህል፣ እኔ የምናገረው የማውቀውን ብቻ
ሳይሆን የሚሰማኝንም ጭምር ነው" በእርግጥ ሐመር ላይ ሊሻሻሉ፣
ሊያድጉና እገዛ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ቁም ነገሮች እንዳሉ
አምናለሁ" ሆኖም ግን ከሠለጠነው ዓለም የአካባቢ ብክለት ችግር፣
የበሽታ መስፋፋት፣ ተፈጥሮአዊ ካልሆነ የአኗኗር ሥርዓት ችግር አንፃር የሐመር ተፈጥሮ ማራኪ ነው" ሕዝቡም ንጹሕ ሕሊና፣የዳበረ የአኗኗር ልምድ፣ ተፈጥሮአዊ ፍቅርና በራሱ የሚተማመን
ሕዝብ መሆኑን ሳረጋግጥ በዓለማችን እውነቱን በመመስከር ከታወቁት ምስክሮች ራሴን እንደ አንዱ እቈጥረዋለሁ።

«..ቀሪው ዓለም አፍሪቃውያንን መርዳት ብቻ ሳይሆን፣አሁንም ከአፍሪቃውያን ብዙ የሚማረው እንዳለ ማወቂያው ጊዜ
አሁን ነው» የሚለው፣ በጽሑፍና በተንቀሳቃሽ ሥዕል የተደገፈው
ጥናቷ ተመልካቿን ከመቀመጫው ናጠው።
ተመራማሪዋ በባዶ እግሯ፣ ቆዳዋን እንደ ለበሰች ጥናቷን ስታቀርብ ቆይታ ስታጠቃልል ያችን ችግርና ሰቆቃ ተቋቁማ፣ የሁለቱን ዓለም ልዩነትና አለመግባባት አስወግዳ፣ እውነተኛ ሰብአዊ ፍቅርንና ሕይወትን ያሳየች ተመራማሪ የአድናቆት ጭብጨባና ጩኸት ለደቂቃዎች በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ
በማይታወቅ መልክ ቀረበላት። ካርለት አልፈርድ ተባባሪዋንና ጓደኞቿን ይዛ ወደ መድረክ ስትወጣ ጭብጨባው ይበልጥ ጋለ"
ከሎና ጎይቲም ሕሊናቸው በደስታ ረካ።

ሦስቱም ጓደኛሞች በሐመር ደን መካከል እንዳደረጉት ሁሉ፣በማንቸስተሩ የጉባኤ አዳራሽም ተቃቅፈው አነቡ እየሣቁ አለቀሱ።
በአውሮፓ ሕይወት ከሎ ብዙውን ጊዜውን በትምህርት አሳለፈ
ጎይቲ ግን ከካርለት ቤተሰቦች ጋር ተቀመጠች" ጎይቲ በዓይን ማየት
ቀርቶ በወሬ እንኳን በአሳለፈችው ሕይወት ያልሰማችው ጉድ ውስጥ
ስትገባ በእውኗ መቃዠት አበዛች።

ከካርለትና ከከሎ ጋር መጀመሪያ ከሐመር ሲነሡ የመኪናው ጕዞ ደስ ብሏት ነበር" ከካርለት ጋር በመኪና መካ፣ ቱርሚ፣ ጂንካም
ሄዳ ስለነበር እንደ ልማዷ መኪናዋ ስትጓዝ የሐመር ሰዎችና እፅዋት ወደ ኋላ ሲሮጡ እሷ በሣቅ ፍርስ ብላለች" አንዴ ወደፊት፣ አንዴ ወደኋላ ስታይ እንደ ቆየች ግን የሆነ ነገር ሆዷን አሸበራት" ወዲያው
ለካርለትና ለከሎ፣ «ይእ! አያችሁልኝ የኔን ነገር አገሩን ሁሉ ስሰናበት አያ ደልቲን ግን ሳልሰናበተው ስመጣ? ምናለ እናንተዬ
ብትመልሱኝ? አሁን ባል በማግባቴ አንጀቱ የተኰማተረው አንሶት
መሄዴን ሲሰማ ሆዱ መንቦጫቦጩ ቀረ! ጀግና ሰው ልቡ ቶሎ
ይቀየማል» አለች።

«ጎይቲ አሁንማ ብዙ ርቀን መጥተናል" ቀደም ብለሽ አስበሽው ቢሆን ኖሮ ብንመለስም አይከብድም ነበር" አሁን ግን ብዙ ርቀናል" አንቺስ አያ ደልቲ የሚገኘው ከስኬ ወንዝ አሸዋ ላይ ተጋድሞ
መሆኑን እያወቅሽ ለምን ሄደሽ ሳትሰናበችው ቀረሽ?» አላት ከሎ
«ይእ! እናንተ ልቤን አጠፋችሁታ" እንዲህ አሁን ሆዴን ሊያጥወለውለኝ እዚች መኪናይቱ ላይ መውጣቱም አጓጓኝና
እረሳሁት እንጂ ምነው እናንተዬ ኧረ ኃዘኑ ቅስሙን ይሰብረዋል"ጀግና ሰው ዕድሜው አጭር ነውI መርቀኝ፣ ላገርሽ ያብቃሽ በለኝ ሳልለው ወጥቼ ስመለስ ባጣው ጸጸቱ ዕድሜ ልኬን ይወጣልኛል?» አለች"

«ጎይቲ አያ ደልቲን አሁንም ታልሚዋለሽ ማለት ነው። ድሮ የተቃበጣችሁት አይበቃም?» አላት ከሎ ፈርጠም ብሎ"

«ይእ! ኧረ እይልኝ የአያ ደልቲ ጨዋታ እንደ ከተማ ልብስ የሚወልቅና
የሚታጠብ መሰለህ! ሆድ ዕቃ ውስጥ ነው የሚቀመጥ ያ ደልቲ አንፈራጦ ብቻውን ይዞት የነበረውን ስፍራ አንተ ገብተህ እሱን ወደ ጥግ ወሰድከው እንጂ ከሆድ
አልጣልከው" እኔና እሱ የአንድ ጎሳ ልጅ መሆናችንና አንተ ባዕድ ሆንህ እኔና አንተን አገናኘን እንጂ የዚያ ጀግና ሎሌ ሆኜ ብኖር
ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር» ብላ በሣቅ ስትፍለቀለቅ፣ ካርለትና ከሎአብረው አጀቧት።

ካርለት ጎይቲ በሐመርኛ ቋንቋ የተናገረችውን ካዳመጠች በኋላ፣
«ምነው ሰው ሁሉ እንዳንቺ ግልጽ በሆነ፣ እውነተኛ ስሜቱን ባልደበቀ እዚህ ወርቅ መሳይ ብልጭልጭ ዓለም እውነተኛው ወርቅ
ሕይወት ሐመር ላይ አለ ቢሉት ማን ጆሮውን ይሰጣል" መተማመን
ቀርቶ መጠራጠር ዘውድ በጫነበት በዚህ የውሸት ዓለም እስከ መቼ መኖር ይቻላል?» ብላ፣ ስታስብ ካይኖቿ ስር መጀመሪያ ጉም መሰለ ነገር፣ በኋላ ተከታትሎ እየተስረገረገ የሚንኳለል ትኵስ እንባ
ዓይኗን ሲሞላ፣ መኪናዋን አቁማ መሪው ላይ ተደፍታ መንሰቅሰ ጀመረች።

ጎይቲ መጀመሪያ ካርለት እየሣቀች መስሏት ነበር" የቀላው? ፊቷንና የራሰውን ዓይኗን ስታይ ግን ልቧ በኃዘን ተሰብሮ ቆየችና፣
“ይእ! ምነው አይደክማት እሷ ብቸዋን ደፋ ቀና እያለች እኛ ዝም አልናት። በይ አንቺስ ከምታለቅሺ ዕርዱኝ አትይም? እንደ እርፍ
ወዲያ ወዲህ የምታማስይውን እንደሁ አያቅተኝም። መዘወሩንም
ቢሆን አላጣውም» አለቻት

«ጎይቲዬ አመሰግናለሁ" መንዳቱ ለአንቺ እንኳ ይhብድሻል ባይሆን መኪናውን ከሎ ያሽከርክር፣ ወደፊት ግን አንቺም
ታሽከረከሪያለሽ» ብላ ቦታዋን ለቀቀችለት"

ጎይቲ አንተነህ ደስ ያላት ጕ" እያንገሸገሻት ሄደ" አንገቷ
ደፍታ የማታውቀው ጎይቲ ሆዷን አቅፋ፣ አንገቷን አዘነበለች
ጎይቲ በአውሮፕላኑ ጕዞም ሆነ በአውሮፓው ሕይወት ቋንቋውን ገጽታውን የማታውቀው ትያትር ተመልካች ሆና ሁሉም ነገር
ታከታት። ኵሩው አረማመዷ ስብር ስብር አለ ጥርሶቿ በከንፈሮቿ በጥብቅ ተጋረዱ" የሐመሯን ሸጋ ህምታ ሰፈነባት" ፀሐይ ከእሷ በጣም ርቃ ሙቀቷ ሳይሰማትና ብርሃኗ ሳያስደስታት ወጥታ ገባች
ጨረቃን ከናካቴው ከሰማይ ላይ አጣቻት" ሲያዩት የሚያብለጨልጨውና የሚያምረው ሰው ሠራሽ ውበት፣ እየቆዩ በሄዱ ቁጥር
እያፈናት መጣ" መለምለም፣ ጠውልጎ መድረቅ፣ ተልሶ
መለምለም የማያውቀው የተፈጥሮ ቅመም የጎደለው የቴክኖሎጂው
ዓለም ለውጥ አልባ በመሆኑ እጅ እጅ አላቸው። ንጹሕ አየር፣ ተለዋዋጩ የተፈጥሮ ውበትና የሚያውደው መዓዛ፣ የአዕዋፍ ዝማሬና
የአውሬዎች ጩኸትና ግሳት፣ የጨረቃ ወቅት ዳንስና ጣፋጩ የጫካ
ውስጥ ፍቅር በእዝነ ሕሊናቸው ውል እያለ አስቈዘማቸው"
👍29😁1
ካርለት በሐመር ሕዝብ ግልጽነትና እሷ በምታውቀው
የተጠራጣሪነት ድብቅ ዓለም ያለው ልዩነት ሰፋባት" አንደበት
እምነትን የማይገልጽበት፣ ስሜት በቃላት ሾኬ ተመትቶ የሚልወሰወስበትን፣ ችሎታ በፍቅረ ንዋይ ተተብትቦ የሚንቦራችበትን
ዓለም ታዘበችው። የድብብቆሽ ሕይወት፣ ገሐዳዊ እምነት የጎደለው
ተፈጥሮአዊ ቅኝቱ ያልተጣጣመና ዝብርቅርቁ የወጣ ሕይወት
መሆኑን አረጋገጠች።

የአውሮፓ ሕይወት የተፈጥሮ መሥመሩን የሳተ፣ ሰዎች ተፈጥሮን ለማዛባት የሚፍጨረጨሩበት ጨው አልባ ሕይወት ሆነባት ስለዚህ ካርለት ጠባይዋ ቀጠነ፣ መነጫነጭ አበዛች የድሮ ጓደኞቿም አላረካሽ አሏት ከእሱ ፍቅር ሳይዘኝ አይቀርም ያለችው
ሰልካካ አፍንጫ፣ የሚያማምሩ ዓይኖችና መካከለኛ ቁመና ያለው
ዴቪድ ጋር እንኳ ፍቅሯ ከሥሩ እንደ ተነቀለ ፅጌረዳ ቀን በቀን እየጠወለገ መምጣቱን አስተዋለች።

አንድ ቀን እንዲያውም ካርለትና ዴቪድ በመዝናኛ ክፍላቸው ውስጥ ሲጨዋወቱ፣ «ፍቅሬ ለምን
ሽቅርቅር ማለቱን ተውሽው?» አላት።

«ተፈጥሮ የምታምረው ራቁቷን፣ የሰው ልጅ ባዶ ሙገሳ ጣልቃ
ሳይገባባት መሆኑን በመረዳቴ ይሆናላ» ብላ መለሰችለት" ዴቪድ
በስስ ከንሮቹ ጆሮግንዷን፣ ጸጕሯን እየሳመ ቆየና የግራ እጁን ጣቶች በቀኝ እጇ ጣቶች አስገብቶ፣ በቀኝ እጁ ጆሮግንዷን እየዳሰሰ፣ በከንፈሮቹ ከንፈሯን፣ ጉንን፣ ዓይኗን፣ ጡቷን...እየሳመ
ውስጥ ሱሪዋን ወደ ታች ሲጎትት፣ ካርለት አጠገቧ ሳይሆን ሐመር ትታው የመጣችው ሰው ታወሳት" አዎ! ደልቲ እያሻሸ፣ እያባበለ፣ ውስጥ ሱሪዋን በማውለቅ ወደ ፍቅር ዓለም አይዶላትም የሷ ስሜት
ሲግል፣ የሱም ስሜት ሲግል አንዱ ሌላውን እንደ ሕፃን ሳያባብል፣
አንዱ እየተኛ ሌላውን ለማስተኛት ሳይሞክር፣ አንዱ አውላቂ ሌላው
አጥላቂ ሳይሆን፣ የጋራ በሆነ ቅኝት የፍቅር ዳንኪራው ከተፈጥሮው
የሙዚቃ ቃና ጋር ተዋሕዶ እየተስረቀረቀ ይቆረቆራል“ የፍቅር ምላሳቸው ላይ ጠብ ጠብ ይላል። ካርለት ያ የሐመሩ ማር ናፈቃት።
ስለዚህ ዴቪድን ገፍተር አድርጋ ፊቷን ዞረችበት"

«ዴቪድ አዝናለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቁልፍ አስገብቶ ሞቶሬን
በማስነሣት እንደ መኪና የሚያሽከረክረኝ ሾፌር አልሻም። የጋራ ቁልፍ፣ እኩል የስሜት ምልክትና እርካታ ነው የምሻው" ስለ
ጠላሁህ ይቅርታ አድርግልኝ የፍቅር ሚዛኑ የተስተካከለውን
ስሜቴን ከእንግዲህ ማዛባት አልሻም።»

«ፍቅሬ፣ አበድሽ ልበል! ዴቭ ነኝኮ! lፍቅሬ ተይዘሽ፣ እኔንም ወደ ፍቅር ዓለም የዘፈቅሽኝ እኮ አንቺ ነሽ እኔኮ ፍቅርሽን ስራብ
ነው የኖርኩት“ ትዳር ይዘን፣ ተደጋግፈን፣ ገቢያችንን በማዳበር ጥሩ ሕይወት እንኖራለን እያልኩ የማልም ፍቅረኛሽ ነኝ» አላት ዴቪድ፣
በቀዘቀዘና አንጀት በሚበላ አንደበቱ።

«ፍቅረኛሽ ነኝ አልከኝ ዴቪድ፤ ትዳር እንመሠርታለን ብዬ
የማልም ነኝ አልከኝ፤ ይህን ያሰብነውና ያለምነው ትናንት መሆኑን
እርግጠኛ ነኝ  ትናንት ደግሞ ለእኔ በሕይወቴ ይ የተዛባ ፍርድ ስበይንበት የነበረበት ወቅት ነው። ትናንት ዙ ባለ አንበሳ የረካሁበት ጊዜ ነው። ዛሬ ግን ስሜቴ ለዚህ ቁሳዊ ዓለም፣ የሽንገላ ሕይወት
እየተማረከ እንዲያሸልብ አልፈልግም" ሐቀኛውን ሕይወትና የጫካውን አንበሳ ከነግርማ ሞገሱ ለማየት በቅቻለሁ" ዴቪድ! ፍቅር
ያለው በጫካ ከሚኖሩት ወፎች ነው» አለችው።

«ካርለት የምትዪኝ አይገባኝም»

«ስላልገባህ እኔም አልገረምም"»

«እስኪ በፈጠረሽ ታዲያ አፍቃሪሽን—እኔን እንዴት ግፍ ትሠሪብኛለሽ? »

«ዴቭ! ፍቅር ከፋብሪካ የተፈበረከ ሸቀጥ አይደለም" ፍቅር
ከላይ የሚለበስ ሳይሆን ከውስጣችን አብቦ የሚፈካ ነው" ስለዚህ ውስጣዊ ስሜቴን ስገልጽልህ ለምን የፍቅር ግፍ ፈጻሚ አድርገህ፣ፍቅር አልባ ስሜቴን ለመቀበል ትፈልጋለህ?»

ሐሳቧን ከመጨረሷ በፊት ዴቭ ፊቱ ደም መስሎ፣ የደም ሥሩ ተገታተረና የግራ እጁን በቀኝ እጁ በቦክስ አንዴ ነርቶ፣ በሩን በርግጾ
አጩሆ በላይዋ ላይ ዘግቶባት ሄደ ካርለት ጆሮዋን ይዛ፣ አንገቷን
ወደ ታች ዘንበል አደረገች።

ጊዜው እየተጎተተ ሰባት ወራት ሞሳቸው። የካርለትን እምነት ቤተሰቦቿ፣ ፍቅረኛዋና ምቾት ያለው ዘመናዊ ሕይወቷ ሊያስቀ
ለብሷት አልቻሉም።

የለንደን ሰማይ በጉም ተሸፍኖ፣ በረዶው በስሱ ያካፋል" የለንደን ኗሪም እንደ ልማዱ በየአቅጣጫው ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት፣ ከለንደኑ ሒትሮ አይሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን እያጕረመረመ፣ የለንደኑን ዳመና በአፍንጫው እየሰቀሰቀ ወደ ኢትዮጵያ ሲያቀና ካርለት፣ ጎይቲና ከሎ በሐሳብ ወደነደልቲ ቀዬ ወደ ፊት ቀድመው ተጓዙ – ሐመር...


💫ተ.ፈ.ፀ.መ💫

ተከታዪን መፅሀፍ በቅርብ ይዤ እመለሳለሁ እስቲ የሐመር አኗኗራቸውን እንዴት አያችሁት አስተያየት እፈልጋለው መልካም ምሽት።
👍4412🎉3
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ አምስት (45)

ጧት ወደ ቢሮው እንደገባ አውሮፕላን ጣቢያ ደውሎ ሜሪ አዳምሰንን በስልክ አነጋገራት ። መሄድ ከፈለገች መቸስ ምን ማድረግ ይቻላል በማለት እንጂ የሜሪ ወደ ቦስተን መሄድ ደስ አላሰኘውም ። እንዲያውም ምንነቱን አይወቀው እንጂ ደስ የማይል ስሜትም አሳድሮበታል ። አስጨንቆታል ። «ዶክተር ግሬግሰን» አለች ጸሐፊው «አቤት» አለ ፒተር ግሬግሰን ፤ ከሐሳቡ እየባነነ እና ቀና ብሎ እያያት ። «ማይክል ሂልያርድ እባላለሁ የሚል ሰው ቀጠሮ አለኝ ይላል ላስገባው?»
«አዎ አስገቢው»
«ሌሎች ሶስት ሰዎችም አብረውት አሉ»
«ሁሉንም አስገቢያቸው» ጸሐፊዋ ስትወጣ ፒተር ማይክል ሂልያርድን ማየት እንደሚፈልግ ተረዳ ። ገና ባይኑ ሳያየው ስለ ለማይክል ከጋዜጣ ባነበበው እና በግምት ከተረዳው በመነሳት ማይክል ገና ወጣት እንደሆነ ያውቃል ። ፒተር ሊወልደው ይችላል ። ምን ዓይነት ሐሳብ ነው ! ሜሪ ይህን የመሰለ ነገር አስባ ታውቅ ይሆን ? አራቱ እንግዶች ወዶ ፒተር ግሬግሰን ቢሮ ገቡ ። ተጨባበጡ ። ተዋወቁ ። ጊዜ አላባከኑም ። ወዲያው የመጡበትን ጉዳይ ጀመሩ ። የኮተር ሂልያርድ ግዙፍ ድርጅት በሳንፍራንሲስኮ ለሚሠራው የሕክምና ማዕከል በተለያዬ መንገድ የሚረዱትን የሕክምና ባለሙያዎችን በማስተባበር ላይ ሲገኝ ፒተር ግሬግሰንም በዚህ የባለሙያዎች ቡድን ውስጥ እንዲገባ ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማስረዳት ነበር የመጡት ። በሳንፍራንሲስኮ ከሚገኙት በርካታ በርካታ የህክምና ባለሙያዎች መካከል ዚህ በፊት አስራ አምስቱን አነጋግረው የአዎንታ መልስ እንዳጥኙና ቡድኑም ሥራውን እንደጀመረም አስረዱት ።

ይህን ሁሉ ከሰማ በኋላ ፒተር ግሬግሰን አሉታዊ መልስ ሊሰጥ አዳጋች ሆነበት ። ዳሩ ሲጀመርም አሉታውን መልስ አላሰበውም ። ስብሰባውን የሚከታተለው አስቀድሞ ባሰበበት መሠረት ስለነበረ ብዙም አልተመሰጠበትም ። እሱን የመሰጠው ማይክል ሂልያርድ ነበር ።
ማይክል ሂልያርድ ።
የሚያስፈራ ጠላት አይደለም ። ወጣት ነው ። ቆንጆ ነው። በራሱ የሚተማመን ሰው መሆኑ በግልጽ ይታያል ። ግን ክፉ ሰው አይደለም ። እንደ ጠላት አያስፈራም ።
ማይክል ሂልያርድ ።
ራሷ ሜሪን ነው። ልክ ነው። ብዙ የሚመሳሰሉበት ነገር አላቸው ። ድፍረታቸው ቆራጥነታቸው በራሳቸው መተማመናቸው ቀልዳቸው አዎ ቀልዳቸው ሳይቀር ተመሳሳይ ነው ፣ አዎ። ፒተር ማሬግሰን ይህን ሲረዳ ደነገጠ ። ሁሉ ነገር ድፍንፍን አለበት ። ጸጥ ብሎ ዓይኑን እማይክል ሂልያርድ ላይ ተክሎ ተቀመጠ ። ስብሰባው… አዎ ስብሰባው በመካሄድ ላይ ነበር ግን... ግን ፒተር ግሬግሰን አዲስ ቃል አልሰማም የሁለቱን ፤ የማይክልንና የሜሪን ተመሳሳይነት ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ቀስ እያለ ፤ ራሱን እያለማመደ ፤ ልቡን እያዋዛ እውነቱን ሊጋፈጠው ሲሸሸው የነበረውን ነገር ሁሉ ሊመረምረው ቆሪጠ ።

ቦስተን… ሜሪ ቦስተን የሄደችው ለምንድነው ? ትዝታዋን ለመቅበር ለማራገፍ ወይስ ለማክበር ለመሳለም ?... ግን እኔ ማነኝ ? ምንድነኝ?-... . አሰበ ። ልቡ ሜሪን መከጀል አልፎም ማፍቀር እስከደረሰበት ጊዜ ራሱን ጠይቆት የማያውቀውን ጥያቄ ጠየቀ ። ለመሆኑ እኔ ምንድን ነኝ? ማነኝ ?! አለ። የሆነው ሆነና በኒህ ሁለት ፍቅረኞች መካከል መግባት አለብኝ ? ፍቅራቸውን የማበላሸት መብት ማን ሰጠኝ? አለ። እንዲህ እያለ ማይክን አየው። ሜሪ… ማይክል። ማይክል ሂልያርድ የሜሪ አዳምሰን ክፋይ ነው። ሌላዋ ሜሪ ነው። ፒተር ግሬግሰን የሚያውቃት ሜሪን ነው። ያችን ሜሪ ፒተር አያውቃትም። ብቻ ያች አደጋው ከመድረሱ በፊት የነበረችው ሜሪ ፣ ሜሪ አልነበረችም ። ናንሲ ማክአሊስተር ነበረች ። ፒተር ግሬግሰን ደግሞ ናንሲ ማክአሊስተርን አያውቃትም ። ላውቃት አልፈለግኩም፤ እለ በሐሳቡ ። አዎ ፡ እሱ ሜሪን እንጂ ናንሲን ማወቅ አይፈልግም ። ሜሪ ከፊል ፍጡሩ ናት። ያችን ያለፈ ሕይወት ያላትን ያችን የሚጥም ትዝታ ፤ የሚመር ትውስታ ያላትን ናንሲን አያውቃትም። ሊያውቃት አይፈልግም ። እንኳን እሱ ሊያውቃት መፈለግ፤ እሷም እንድትረሳት፤ ሜሪም ሜሪን እንጂ ናንሲ ማክአሊስተርን እንደሌለች ፤ እንዳልነበረች እንድትቆጥራት ይፈልጋል ። ግን ይህ ሁሉ ከንቱ ነበር። ከሜሪ አዳምሰን ሌላ፤ በሜሪ ውስጥ ናንሲም ትኖራለች። ፒተር አይኑን ጨፍኖ የለችም እያለ ቢኖር እንጂ ለካ ናንሲን ሁልጊዜ ያያት ነበር… በሜሪ ውስጥ ። ናንሲን ባየ ቁጥር ፤ ናንሲ መሆኗን መመርመርን ስለሚሸሽ ለራሱ እንኳ አንዳንዴ ጠባይዋ እንቆቅልሽ ይሆናል ብሉ ነበር የሚነግረው ። እንጂ ናንሲስ ሁልጊዜም በሜሪ ውስጥ ትኖር ኖሯል ። አሁን ግልፅ ሆኖ ታየው ። ተስፋ ቆረጠ ። የማይዋጉትን ጦርነት ነበር ስዋጋ የኖርኩት ሲል አሰበ ። ሜሪን ሲፈጥራት ፒተር አንድ ነገር ሞክሯል ። ስለዚህ ሜሪ አዲስ ሰው ነበረች። ከመቃብር ሊያወጣት የፈለጋት ሴት ነበረች በመጠኑ የዚያች ሴት ደም ነበራት ። እሷ ነች እያለ እያሰባት። ሟችቷ ፍቅረኛው እየመሰለችው ።

ሊቪያ… የሊቪያን ደም ከገፅታዋ ላይ ስሎ። ምናልባትም ይህን ማድረግ አልነበረበትም ይሆናል ። ይሆን ማድረግ ተገቢ አልነበረም ይሆናል ። ከዚህ በፊት እንዲህ ልጓሙን ለቆ ሙያውን በፈለገው መንገድ የጋለበበት ጊዜ እልነበረም ። በሽተኛው እንደፈለገው ወይም የበሸተኛው ቤተሰብ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ነበር የሚሠራው ። ሜሪ ግን ... ሜሪ ግን፤ ያለሱ ያለፒተር ግሬግሰን ማንም አልነበራትም። ይህ ደግሞ የፈለገውን እንዲሆን ነፃነት ሰጠው ። የፈለገውን እንዲሆን ነፃነት ሰጥቶት ቆዬ ። አሁን ግን ያ ነፃነት ምኞት፤ ተስፋ ሆኖ ታየው።
ማይክልን ሲመለከት ...
አዎ እኔ ለካ ለሜሪ የአባት ያህል ነበርኩ ነኝ ። አባቷ ነኝ አለ፤ በሀሳቡ። ሜሪ ይህን ላታውቅ ትችላለች፡፡ ሆኖም ትደርስበታለች። ይዘገያል እንጂ ትደርስበታለች። አራቱ ሰዎች ጉዳያቸውን ፈፅመው ተነሱ። ስብሰባው ተፈፀመ ከማይክል ጋር የመጡት ሶስት ረዳቶቹ ፒተርን ተሰናብተው። ማይክል ግን ወደ ኋላ ቀርቶ ነበረና ሶስቱ ረዳቶች እንግዳ ማረፈያ ክፍል ውስጥ ሆነው ይጠብቁት ነበር ።

ማይክል ወደኋላ የቀረው የተለየ በቆይታ የሚነጋገርበት ነገር ስለነበረም አልነበረም ። ከፒተር ግሬግሰን ጋር ይበልጥ ለመግባባት እንዲረዳው ቀልዳ ቀልድ ፤ ገራ ገር ነገር ለመነጋገር ነበር፤ ሆነ። ፒተርና ማይክል ቆመው ገራገሩን ሲያወሩ፡፤ ሲሳሳቁ ሳለ ድንገት አንድ ነገር ተፈጠረ። ገራ ገሩ ቀልዳ ቀልዱ ወሬ ቀጥ ብሎ ቆመ። ይህን ያመጣው የማይክል ሂልያርድ አይን ነበር። ከፒተር ጋር እየተጨዋወቱ ሲሳቁ አይኑ በፒተር ትከሻ ዘሎ አልፎ አንድ ነገር ላይ አረፈ። አንድ ቅብ ስእል ላይ። ሁሉ ነገር ፀጥ አለ።

ያን ስእል ማይክል ያውቀዋል። የሷ ነው። የናንሲ ነው ። ስትስለው፣፤ ስትጀምረው አይቶታል ። እነዚያ ነርሶች ... ወደ ቦስተን አፓርትማዋ ሄዶ እቃዋ ሁሉ እንደተወሰደ አይቶ ሲጠይቅ ሁለት ነርሶች መጥተው የሳለቻቸውን ስእሎችና አንዳንድ እቃዎቿን እንደወሰዱ ተነግሮት ነበር ። ይህን ስእል ማይክል አይረሳውም ። በሐሳቡ « እንዴት ልርሳው ! ሰሰርግህ በስጦታ መልክ አበረክትልሀለሁ ብላኝ ነበር» አለ ። ደነዘዘ። የሚያደርገውን የሚሰራውን አያውቅም ነበር ። ስእሉ አልቋል ። ማን ጨረሰው?
👍21🥰1
እንድ ኃይል እየጎተተ ስእሉ ወደተሰቀለበት ወሰደው ። ፒተርም ደንግጦ ነበርና ሊያቆመው አልሞከረም ። ሊያቆመው ቢሞክርም የማይቻል ነገር ነበረ ። ሊያቆመው የሚችል ኃይል ከቶ ሊኖር አይችልም ። የሰአሊውን ፊርማ ሊያይ ተጠጋ ። እንዲያው ነው እንጂ ማን ሊሆን እንደሚችል ስሜቱ ነግሮታል ። ልቡ አውቆታል ። ሜሪ አዳምሰን ይላል ፊርማው ። «ኦ! ጸምላኬ ምንድነው ? አምላኬ ሆይ!» አለ ። ግሬግሰን ትኩር ብሎ ይመለከተዋል ። ማይክል ከዚህ በላይ ለማለት የማይችል ሆኖ ታየው ለፒተር። «ቆይ፤ እንዴት ? ኦ አምላኬ ምነው !እንዴት አንድም ሰው ይህን ጉድ አልነገረኝም ? ለምን... ኮ... ማን...›› እዚህ ላይ ጸጥ አለ። ቅድም ስሜቱ የነገረው ፣ ልቡ ያወቀው አሁን ተስተካክሎ ፤ጥርት ብሎ ታየው ። ልክ ነው ናንሲ አልሞተችም ። ናንሲ በሕይወት አለች ። ግን ተለውጣለች ‹‹ሌላ መስላለች ። ግን በሕይወት አለች ። እስዋ ናት።ለካ. . . ለካ እንደዚያ አድርጋ የጠላችኝ ! ልትጠላኝ ይገባታል። ግን እሱ ምንም ጥርጣሬ አልነበረበትም ። ግን ፎቶ ግራፎቹን ሲያይ… ለካ ወደ ሆነ እማያውቀው የአስማት አገር የሚሄደው ለዚያ ነው። ይህ ሁሉ በሃሳቡ እንደ ጐርፍ ተዥጐደጐደ ።
ለካ !

ዓይኑን የእንባ ጭጋግ ሸፈነው ። እንባውን ዱብ ዱብ እያደረገ ወደፒተር ግሬግስን ዞረ ። ፒተር ግሬግሰን ማይክልን ሲያይ ፈራው ። ፊት ለፊት ለማየትም አልሆነለትም ። «ተዋት ። ለስዋ ሁሉም ነገር ተረት ሆኖአል ። ቁስሏን አትንካባት ። ካሁን ቀደም የተሰቃየችው ይበቃታል» አለ ፒተር ። ፒተር ይህን ያለው ከልቡ አልነበረም ። ድምጹም ይሀን እውነት ቁልጭ አድርጐ ያሳይ ነበረ ። ማይክልን ካየበት ጊዜ ጀምሮ የሆነውን ነገር ሁሉ ልክ እንዳይደለ ተገንዝቧል ። እንዲያውም የት እንዳለች ልንገረው ወይስ አልንገረው የሚለው ሃሳብም ረብሾታል ። «ሰው ሁሉ ዋሸኝ ግሬግሰን ። ሁሉም ሰው ውሸቱን ሞታለች አለኝ» አለ ማይክል ።
አሁን እንባው ይወርዳል ።
«ሁለት ዓመት ሙሉ! ስሜትን ተራቁቼ አለምን ረስቼ ፤ እንደሰው ሳይሆን እንደሞተር ሌትና ቀን በሥራ ተጠምጄ... ብረሳት ብዬኮ ነው! አልቻልኩም ። ሁለት ዓመት ሙሉ እግዜርን ምነው እኔን በገደልከኝ፤ እስዋን ባተረፍካት እያልኩ ስነተርከው እና ይህን ያህል ጊዜ...›› አይኑ በእንባ ይታጠባል ። ሳጉ ንግግሩን እቋረጠው ። «ያን ያህል ጊዜ ስመኛት ኑሬ ሳገኛት አጣኋት። አላወቅኳትም።» ቀጠለ «ደግሜ ገደልኳት ። ደግሜ ሳሰቃያት ሰነበትኩ ። ልትጠላኝ ይገባል ። መጠላት ያለብኝ ሰው ነኝ። ጠላሁት ብላ ነግራሃለች?»
«አልነገረችኝም ። አልጠላችህምም ። ልትል ትሞክራለች ግን ሽሽት ነው። ለመርሳት መሞከር ነው ። ያን ማድረግ ደሞ ያለባት ይመስለኛል ፤ ለመኖር» አሊ ፒተር ። በሀሳቡም እኔም የራሴ የማድረግ መብት አለኝ ሲል ጨመረ ። ይህን ሃሳብ ማይክል ያነበበው ይመስል ፤ «አንተ እዚህ ውስጥ ምን ጥልቅ አድርጐህ መርሳት ይገባታል ፣ይህን ማድረግ አለባት ብለህ ትፈተፍታለህ? » አለ ማይክል ፒተር ግሬግሰንን በኮቱ ኮሌታ እያነቀው ። ማይክልን ያናደደው የፒተር ንግግር ሳይሆን ከዚህ ቀደም ስለሜሪ አዳምሰን የሰማው ነገር ነበር ። ሜሪ አንድ ዶክተር ወኪል እንዳላት ሰምቶ ነበር ። የሰማው ነገር ትዝ ሲለው ከደረሰባት ብስጭት ሁለት ዓመት ሙሉ ታፍኖ ከቆየ መብሰልሰል ጋር ተዳምሮ ቱግ እንዲል አደረገው ።
«አረ ሊመሆኑ ይኽን ሁሉ እንዴት ልታውቅ ቻልክ? በኔና በስዋ መካከል ምን እንዳለ ማን ነገረህ ? ይህ ለኔና ለስዋ ምን ማለት መሆኑን እንዴት አድርገህ አወቅክ !» ንዴቱ እየናረ ሲሄድ ነገሩ ልክ እየመሰለው ሄዶ ። «ንገረኝ አትንገራት አልከኝ ? ! እኔ ጸጥ ስልልህ አንተ እንደፈለግክ እንድታደርጋት እንዲያመችህ ነው አይደል ? የለም ዶክተር ፤ ይህ አይቻልም ። በሕይወቴ ልትጫወትበት የፈለግክ ትመስላለህ ! አይቻልም ። እንደመሰለኝ ብዙ ሰዎች እስከ ዛሬ ተጫውተውብኛል ፤ ይበቃል ። አንተ ሌላ አሻንጉሊት ፈልግ። ልቀቃት አልከኝ ። በቃኝ ብላ ራሷ ትንገረኝ። ሌላ ማንም አያገባውም››
‹‹እሷማ ነግራሃለችኮ ተወኝ ብላሃለችኮ» ፒተር ረጋ ባለ ድምፅ ነበር ይህን የተናገረው… ማይክልን ፊት ለፊት በጠንካራ አስተያዬት እያየ። ማይክል ይህን ሲሰማ ደነገጠ ። ሳያስበው ወደኋላ አፈገፈገ።
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍27🥰5
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ አራት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ
"""
ከእንቅልፎ ባና እጇን እዚህና እዛ ወጣጥራ ተንጠራራችና አይኖቾን ገለጠች።ልክ እቤቷ ከመኝታ ክፍሏና ከገዛ አልጋዋ የምትነሳ ነበር የመሰላት። አይኖቾን በልጥጣ ከፍታ የቤቱን መለየትና ከፊቷ ተቀምጧ በመገረም ያፈጠጠባትን ጎልማሳም ስታይ በርግጋ ተነሳችና ቁጭ አለች።እርቃን መሆኗን ስታይ ቶሎ ብላ ብርድልብሱን ወደላይ ጎተተችና ከጡቶቾ በታች ያለውን የሰውነቷን ክፍል ሸፈነች፡፡
ከዛ ሁሉ ስቃይና የመደፈር ሙከራ ቡኃላ እንደዚህ አይነት እንቅልፍ መተኛት መቻሏ ለራሷም በጣም አስገረማት፡፡
"የቤቱ እማወራ እንኳን እንዲህ ዘና ብላ ስተኛ አይቻት አላውቅም"
"ይቅርታ ሳላስበው ነው እንቅልፍ የወሰደኝ...ግን ሚስት ከለችህ እንዴት?"
"ማለት?ሚስት እያለችህ እንዴት ልትደፍረኝ ሞከርክ ለማለት ነው …?ጠጥቼ ስለነበር ከእሷ ጋር ተምታተሸብኝ ነው…..?"አላት፡፡
"አረ እንደዛ ማለቴ አይደለም...ችግር እንዳልፈጥርብህ ፈርቼ ነው?።"
"ትቀልጂያለሽ አይደል...?አሁን በዚህን ሰዓት ከሚስቴ ጋር ባንቺ የተነሳ የሚገጥመኝ ችግር ነው ያሳሰበሽ?"ምን ለማለት እንደፈለገ አልገባትም"
‹‹ሌላ ደግሞ ምን አለ?"
"እዚህ ቤቴ ሸሽጌ እንዳሳደርኩሽ አሳዳጆችሽ ቢደርሱበት መጥተው አንቺን ብቻ ደፍተውሽ የሚሄድ ይመስልሻል...የወንበዴዎቹ ህግ እንደዛ አይደለም የሚሰራው። በመንገዳቸው እንቅፍት የሚሆንባቸውንም ለሌላው መቀጣጫ እንዲሆን አብረው ደፍተውት ነው የሚሄድት"
"ወይኔ በፈጣሪ...በቃ አሁን ወጥቼ ልሂድልህ… " አለችና ልትነሳ ካለች ቡኃላ እርቃኗን እንደሆነች ለሁለተኛ ጊዜ ስታስታውስ ግራ በመጋባት መልሳ ባለችበት ቀረች ፡፡
‹‹ምነው ዝም አለሽ….?››
‹‹ሱሪዬን እኮ ብትንትን አድረገኸዋል››አለች በአይኗ ወለሉ ላይ ተቀዳዶ የተጣለውን ሱሪዋን እየተመለከተች፡፡
‹‹እና እየወቀሺኝ ነው?››
‹‹አረ በፍፅም..አንተ በጣም ጥሩ ሰው ባትሆን እኮ እደዛ በቀላሉ ወደህሊናህ ተመልሰህ አትተወኝም ነበር…››ከአንጀቷ የተሰማትን ነው የተናገረችው፡፡
‹‹ጥሩ ሰው?››የለበጣ ሳቅ ሳቀ፡፡
‹‹ኣዎ ከአንጀቴ ነው..በመከራ ላይ ሌላ መከራ ስላልጨመርክብኝ አመሰግናለሁ››
‹‹በይ አሁን በዛ ድቅድቅ ለሊት እዚህ ሰፈር ለምን እንደተገኘሽና? አሳዳጆችሽ ለምን እንደሚያሳድዱሽ ንገሪኝ፡፡››
‹‹መነሻው የስራ አለመግባባት ነው››
‹‹የስራ አለመግባባት ለግድያ?››
‹‹ማለቴ ቀላል አለመግባባት አይደለም... ብዙ መቶ ሚሊዬን ብሮችን የማግኘትና ያማጣት ጉዳይ ነው ….ከአሳዳጆቼ ጋር በጋራ በመሰረትነው ድርጅት የሚሰራ አፀያፊ ወንጀልን ለመከላከል ስለሞከርኩ ነው፡፡አሳዳጆቼ የሚፈልጉት ብር የሚገኘው በሰው ደም እጅን በመታጠብ ነው…..በተጨመላለቀ ወንጀል››
‹‹እስኪ ትንሽ አብራሪልኝ።››
‹‹ የማወራህ ስለዳይመንድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ነው››
‹‹እና አንቺ የዛ ግዙፍ ሆስፒታል ባለቤት ነኝ እያልሽ ነው››
‹‹አይ አላልኩም ፡፡22 ፐርሰንት ሼር አለኝ፡፡በአጠቃላይ ሆስፒታሉ አርባ የሰዎች ንብረት ሲሆን 35 ሰዎች ግን በጣም ጥቂት ድርሻ ነው ያላቸው..በአጠቃላይ 11 ፐርሰንት ብቻ፡፡ቀሪው 89 ፐርሰንት የአምስት ሰዎች ነው…››
‹‹እሺ እጮኛዬ ያልሺውስ እሱ ነው አይደል ትልቅ ድርሻ ያለው?…››
‹‹.አይ እሱ 16 ፐርሰንት ነው ያለው፡፡ ሼክ ጠሀ የሚባሉት ባለሀብት ናቸው 45 ፐርሰንት ድርሻ ይዘው ትልቁ ስልጣን የያዙት ፡፡አሁን ይሙት ይትረፍ ያላወቅኩት ለሊት ደውሎ አስጠነቀቀኝ ያልኩህ ኤልያስ 10 ፐርሰንት ድርሻ ሲኖረው የተቀረውን አቶ ሙሉ የተባሉ ግለሰብ ይይዙታል፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነው ያ ስሙ ከየቴሌቪዥን ማስተወቂያና ጋዜጦች ላይ የማይጠፋው ግዙፍ የህክምና ተቆም ከወንጀል ጋር ተገናኘ የምትይኝ?››
‹‹በሰዎች ኦርጋን ህግ ወጥ ንግድ ላይ እስከአንገታቸው ተዘፍቀዋል፡፡በአረመኒያዊ መንገድ ከአንዱ የሆነ ነገር እየነቀሉ ለሌላው መትከል ብቻ ሳይሆን ውጭ ሀገር ድረስ እየወሰዱ መሸጥንም ያጠቃልላል፡፡››
‹‹አልገባኝም››
‹‹አንድ ልብ እንዲቀየርለት የሚፈልግ ሚሊዬን ብሮችን መክፈል የሚችል ባለሀብት በቀጥታ ለእሱ ልብ የሚለግሰው ሰው ባይኖር እንኳን በእኛ ሆስፒታል ዋና ሰዎች ይቀርብለታል ማለት ነው፡፡››
‹‹እንዴት ተደርጎ..አርቴፌሻል ማለት ነው…?››
‹‹አይ በትክክል…ከሰው››
‹‹እንዴት አድርገው?››የምትናገረው ቶሎ ሊገባው ስላልቻለ ተበሳጨ፡፡
‹‹እንግዲህ ያጣላን ይሄ ጉዳይ ነው፣ባደረግነው መጠነኛ ክትትል የተለያየ መንገድ ነው የሚጠቀሙት…. ከእነሱ ጋር የሚሰራ በጣም ብዛትም ጥልቅነትም ያለው ብድን አለ..ደላሎችን ..ገዳዬችን ..ፖሊሶችን እና ባለስልጣኖችን ያካተተ ነው፡፡
‹‹ይሄ ሁሉ?››
‹‹አዎ እንደውም ይሄ እኛ የደረስንበት ነው..ከዚህም በላይ ውስብስብ ይሆናል ብዬ ገምታለሁ?››
‹‹አሺ እንዴት ነው የሚያደርጉት?››
‹‹ከተቻለ ለምሳሌ እንደኩላሊት አይነቱን ከጎዳና ተዳዳሪዎች ፤ከቸገራቸው የተለያዩ ሰዎቸ ጋር በገንዘብ በመደራደር..አንዳንዴ በመጠጥና በሀሺስ አደንዝዞ በመስረቅ…ከዛም ከፍ ሲል በተለያ መንገድ በመኪና በመግጨት ማጅራት በመምታት ፤ ቤተሰብ የሌላቸውና አድራሻቸው በቀላሉ መገኘት የማይችል ከቤተሰብ ተነጥለው በከተማዋ የሚገዋለሉ ባይተዋሮችን በማፈን፤በመግደል ወዘተ
‹‹በምታወሪው ግን እርግጠኛ ነሽ..እኔ እኮ ሌባና ማጅራት መቺ ነኝ…የምውለውም ከብዙ መሰሎቼ ጋር ነው..በዚህ ከተማ የተደረገች የተወራችና የተፈሳች ሁሉ አያመልጠኝም ብዬ የማሲዝ ሰው ነኝ››
‹‹እንግዲያው ተሸውደሀል…ለነገሩ ይሄ በከፍተኛ ሚስጥር የሚሰራ ስራና በዚህ የወንጀል ሰንሰለት ውስጥ ያለበት ሰው ስለአንድ ነጠላ ክስተት እንኳን ለገዛ ሚስቱ መንገሩ ከተረጋገጠ ያለምንም ማቅማማት እሱንም መላ ቤተሰቡንም በማግስቱ እንደሚገደሉ አውቆና ምሎ ነው ወደ ብድኑ የሚገባው፡፡››
‹‹እኚማ ደንበኛ አሸባሪ ናቸው በይኛ?
‹‹ትክክል….እኔ እንደውም ያልገባኝ በፍቃደኝት አካላቸውን ስለሚቸበችቡት ሰዎች ነው ..ሰው እንዴት አካሉን አውጥቶ በብር ይቀይራል?››እስከዛሬ በአእምሮዋ ሚመላለሰውን ጥያቄ ነው አሁንም ደግማ ለእሱ ያነሳችው፡፡
‹‹ሰው ሲቸገር ምንም ነገር ለመሞከር ይደፍራል..አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ የትኛውንም የተነገረውን ነገር ያምናል.. የትኛውንም መጥፎ የተባለ ስምምነት ይፈርማል… የትኛውንም የሚወደውን ነገር አሳልፎ ይሰጣል፤አዎ ችግር እንደዛ ያደርጋል፡፡ለነገር አንቺ ችግር ባለፈበት አልፈሽ የምታውቂ አትመስይም..ስለዚህም እንዲህ አይነት ነገር ሊገባሽ አይችልም..እሱን ተይውና አሁን ምን ለማድረግ አሰብሽ?››
"ምን አስባለሁ ...መች የማሰቢያ ጊዜ አገኘሁና ላስብ?"
"ሊገሉሽ የተቀጠሩትን ሰዎች ግን አውቃቸዎለሁ..ማለት በተለያየ አጋጣሚም አብሬያቸው ሰርቼም አውቃለሁ...በጣም አደገኞችና ለመስራት ተስማምተው የወሰድትን ስራ ሳይፈፅሙ ወደኃላ የማይሉ..ለስራቸው ትልቅ ክብር ያላቸው ቆራጦች ናቸው።››
ገላመጠችው...ምንም እንኳ ነፍሷ በእሱ እጅ እንዳለች ብታውቅም ንግግሩን ልትቆጣጠረው የማትችል አብሻቂ ሆኖ ነው ያገኘው፡፡
"ምነው?"አላት ያንን የተቦጫጨቀ ፊቱን አጨማዶ
"ለስራቸው ክብር አላቸው የምትለው መግደል ስራ ነው እንዴ?"
ፈገግ አለ..."አልገባሽም እንዴ? ይህቺ አለም እኮ የተመሠረተችው በመግደልና በመሞት ነው።ለጊዜው ትገያለሽ ጊዜ ሲጥልሽ ደግሞ በሌላ ገዳይ እጅ ትወድቂና ትገደያለሽ።እንስሳ ሆንሽ ተክል ሆንሽ የሠው ልጅ ህጉ ተመሳሳይ ነው።"
👍261
"መገዳደል የአውሬዎች ተግባር ነው"
"አረ ባክሽ?..እኔ ግን በህይወት ልምዴ የማውቀው አደገኛው አውሬ ይሄ ሰው የምትይው ቀፋፊ ፍጡር እንደሆነ ነው።ቆይ ቆይ አሁን አንቺን እያሳደደ ያለው አንበሳ ነው ነብር?"አላገጠባት ፡፡ምትመልስለት መልስ አልነበራትም።
‹‹በይ ተመልሰሽ ተኚ…እኔ ወጥቼ ሁኔታዎችን አጣርቼ ልምጣ።ደግሞ ስልክሽን እንዳትከፍቺ ።እስከዛ ወዴየት እንደምትሄጂ …?ምን እንደምታደርጊ... ?እንዴት ነፍስሽን እንደምታተርፊ ?እያሰላሰልሽ ጠብቂኝ ።››አለና ስለምትለብሰው ልብስ ምንም ነገር ሳይናገር ከመቀመጫው ተነሳቶ ወደበራፍ ተጓዘ ።በራፉን ከፈተና መልሶ ዘግቶላት ሄደ…..፡፡
አልተኛችም ፡፡ከአልጋዋ ተነሳችና እርቃኗን ወለሉ ላይ ቆመች ፡፡ጠረጵዛው ላይ ያለውን ካፖርቷን አንሳችና ለበሰችው… ማሰብ ጀመረች…ምን አይነት ብሽቅ ነኝ ? ስትል እራሷን ወቀሰች…..አዎ ልብስ ገዝቶላት እንዲመጣ ብር ልትሰጠው ይገባ ነበር….የሆነ ሀሳብ መጣላት ወደ እሱ ቁምሳጥን ሄደችና ከፈተችው፡፡ቁምሳጥኑ ሙሉው በልብስ የተጠቀጠቀ ነው..ክፋቱ ግን መጣናቸው ከእሱ ጋር በጣም ስለሚራራቅ ለእሷ የሚሆን ልብስ ለማግኘት አልቻለችም..ድንገት የሆነ የማታውቀው ስሜት ገፋፋት እና የታችኛውን መሳቢያ ከፈተችው…በስነ-ስርአት ተጣጥፈው የተቀመጡ አንድ አምስት የሚሆኑ ቀሚሶች ፤የሴት ሱሪዎች፤ ፓንቶችና፤ ጡት መሳያዣዎች፤ ኮስሞቲኮች ጭምር አሉ‹‹….የሚስቱ ነው ?የት ሄዳ ይሆን …?ምን የት ሄዳ እላለሁ..እቤቱ እኮ ምኑም የባለ ትዳር ቤት አይመስልም››አለች..ይሄንን ልትል የቻለችው የቤቱን ዙሪያ ገባ ስትቃኝ አንድ ክፍል ከመሆኑም በላይ ምንም አይነት የማብሰያ ዕቃዎች ባለመኖራቸው ነው፡፡››
ከመሀሉ ዓይኗን የሳባትን አንድን መካከለኛ ቁመት ያለው ቀሚስ መረጠችና ለበሰች…..ለራሷ ተለክቶ የተሰበፋ ይመስል እላዬ ላይ ልክክ አለ፡፡
ከዛ በላዩ ላይ ካፖርን ደረበችበትና ዝግጁ ሆና መምጣቱን ትጠባበቅ ጀመር..‹‹አዎ ፓንት ደግሞ ስወጣ ገዛና ወደ ሆነ ሆቴል ሬስት ሩም ጎራ ብዬ አደርጋለሁ› በማለት በአዕምሮዋ እቅዷን አቅዳ ጨረሰች፡፡
ከ40 ደቂቃ ጥበቃ ቡኃላ በራፉ ገፋ ገፋ ተደረገና አልከፈት ሲል ተንኳኳ
እሱ መሆኑን ስላወቀች ተንደርድራ ሄዳ ከፈተች
‹‹በራፌን ምነው ቀረቀርሺው?››
" ምነው አጠፋው?"
"አይ እቤቴ መቆለፍም መቀርቀርም አለመደበትም›› ብሎ …ንግግሩን ሳይጨርስ አይኖቹን እሷ ላይ እንደተከለ ባለበት ፈዞ ቆመ..በእጁ አንጠልጥሎ ነበረው በቀይ ፔስታል የሞላ እቃ ወለሉ ላይ ጣል አደረገው፡፡
እሷን ሳይሆን በለበሰችው ቀሚስ ሌላ ሰው አሻግሮ እየተመለከተ እንደሆነ ተረዳች…እና መልበስ አልነበረብኝም ይሆን እንዴ? ስትል በውስጧ አሰበችን …ፍራች ..
ከዛ ከደነዘዘበት እንደመባነን አለና ምንም ሳይናገር ወደውስጥ በመዝለቅ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡
..ልክ ረጅም አመት እንደምታውቀው ፍቅረኛዋ ከጎኑ ሄዳ አልጋ ላይ ቁጭ አለችና ‹‹ ..ምን የሰማሀው አዲስ ነገር አለ?››ጠየቀችው
‹‹አዲስ ነገር ትያለሽ እንዴ….?መፈንቅለ መንግስት እንኳን ቢደረግ ይሄን ያህል ከተማዋ አትተረማመስም…ከተማዋን መነቃቅረው እያሰሱስሽ ነው…እና ደግሞ ብቻቸውንም አይደሉም የመንግስት ሰዎች አብረዋቸው አሉ ያልሽው ትክክል ነሽ...እንዳንድ ፖሊሶችና ፤ ትራፊከ ፖሊሶች በየተመደቡበት ድንገት ካዩሽ እንዲያሳውቁ ተነግሮቸው ፎቶሽ ተሰጥቷቸዋል….››
በመላ ሰውነቷ ፍራቻ ለቀቀባት‹‹እየቀለድክ እንዳይሆን…?››
ያንን አስፈሪ ፊሉን ይበልጥ አጨመዶ ‹‹አሁን በዚህ ፊት ቀልድ የሚያምረኝ ሰው እመስልሻለሁ?››አላት
‹‹እና ምን ይሻለኛል….?››
‹‹እሱን አምላክሽን ጠይቂ እኔ ምን አውቃለሁ?››
///
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
25👍18
​​ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ ስለፈረንሳይ ለቅሶ ስነ ስርአት በፒያሣ ልጅ መፅሐፋቸው ላይ ከከተቡት.


የፈረንሳይ የለቅሶ ሥነ ሥርዓት ከኛ በጣም የተለየ ነው አንድ ሰው ሲያርፍ ለቅርብ ቤተሰብ ይነገራል፡: ጣጣ የማይፈልገው ቤተሰብ በቤተክርስቲያን ፀሎት ካደረሰ በኋላ ወስዶ ይቀብራል ከዚያም እገሌ በዚህን ቀን አርፎ፣ በዚህን ቀን ተቀብሯል በማለት የመላው
ቤተሰብ ስም ያለበትን የሐዘን መግለጫ ደብዳቤ
ለሚያውቁአቸው በሙሉ ይልካሉ:: ለቅሶ መድረስ ብሎ ነገር የለም:
ግፋ ቢል ስልክ ደውሎ ወይም በደብዳቤ የሐዘኑ ተካፋይ መሆንን
መግለጽ ነው:: ሬሳን ማሳየትና ለትንሽ ቀናት ማቆየት የተለመደ
ነው: አንዳንዱ ፀሎት የሚካሄድበትን ቤተ ክርስቲያን አዳራሽና የመቃብሩን ሥፍራ ያሳውቃል: የቅርብ ወዳጅ የሆነ በሁለቱም ሥነ ሥርዓት ላይ ተግኝቶ ይሰናበታል።

አንዳንድ ቤተሰቦች በቀብሩ ላይ ከሟቹ ዘመዶች በቀር ሌላ አይፈልጉም። ግራም ነፈሰ ቀኝ እንደኛ አገር ሦስት ቀን
ለለቅሶ ደራሽ ድንኳን ተክለው አይደግሱም፡ ከዚያም አርባ፣ ሰማንያ እያሉ ሲያበሉና ሲያጠጡ አይከርሙም: ከስድስት ወር በኋላም ለቅሶ የሚደርስ አለ፡ የሞተውን ማስነሳት እስካልተቻለ መቸገርና ማስቸገር ለምንድን ነው? አንዱ፣ «እገሌ ሞቶ ዛሬ ነው ቀብሩ
ትሄዳለህ ወይ?» ብሎ ቢጠይቀው፣ «ምን ላደርግ እሄዳለሁ፤ እኔ
ስሞት መጥቶ ላይቀብረኝ» በማለት መልሶለታል: «አሁንማ አዲስ
አበባ ሰው የሚያሰባስበው፣ ድግስ የሚደገሰው ለቅሶ ቤት ነው»
የሚል የባቡር መንገድ ወሬ ሰምቻለሁ:: ለማንኛውም እኔ
የምሞትበትን ቀንና የምቀበርበትንም ሥፍራ በእርግጥ ባላውቅም፣ ወዳጆቼ የሆናችሁ ሁሉ ሥራ ፈታችሁ፣ ለቀብርም ለለቅሶም እንዳትመጡ፡፡ አዲስ አበባ ከሆነ ደሃ ዘመዶቼን እንዳታስቸግሩ፤ አውሮፓ ከሆነ ችግር የለም፡፡

ልጄ እንዳባቱ ጣጣ አይወድም፡ ልክ እንደ ሦስተኛ ፖሊስ
ጣቢያ ምርመራ አታብዙ: «መቼ አረፈ! ምን ሆኖ ሞተ!ታሞ ነበር
ወይ! ሲጃራ ቀንስ ብዬው ነበር! ሕክምናህን ችላ አትበል ብዬ
ነግሬዋለሁ! ከቅባቱም ቀንስ፤ መጠጥም አቁም፤ተብሎ ነበር»
በማለት ውትወታ ይቅር፡ አልፋችሁ ተርፋችሁ ክቡር ዶክተር
እንዳትሉኝ፡፡ ይልቁንስ «አዬ ፍቅርሻ! እንዳሾፈ ሞተ። ዓለምን ዞሯል፡ ያላየው ነገር የለም» በማለት ፉት እያላችሁ ማውራት ነው: «ምን ሠራ?» ቢሉዋችሁ «ብቻውን ሆኖ ልጁን አሳደገ ከጉለሌ ተነስቶ ከዓለም ውስጥ በቆንጆይቷ ከተማ በፓሪ ፒያሣ ውስጥ እያፏጨ ኖሯል ብላችሁ መልሱ: ሊያስታውሰኝ የሚፈልግ የጥንት ወሬ ማውራት ይችላል፡ ይሄ ሁሉ ዝባዝንኬ ተረት
የፈረንጆች ለቅሶ ሥነ ሥርዓት ጥሩ
መሆኑን ለማስረዳትና
የሚስማማኝ መሆኑን ለመግለጽ ነው: ለማንኛውም የሰው ልጅ
የተወለደ ዕለት ነው የሞት ፍርድ የተቀበለው በማለት ተፅናኑ፡...


ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ ነብስ ይማር።
👍314
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሰድስት (46) ‹‹እሷማ ነግራሃለችኮ ተወኝ ብላሃለችኮ» ፒተር ረጋ ባለ ድምፅ ነበር ይህን የተናገረው… ማይክልን ፊት ለፊት በጠንካራ አስተያዬት እያየ። ማይክል ይህን ሲሰማ ደነገጠ ። ሳያስበው ወደኋላ አፈገፈገ።
ደነገጦ እንጂ በአይኑ ውስጥ ተስፋ ይነበብ ነበር ። አይኑም ገፅታውም ተስፋውን ድንጋጤውንና ግራ መጋባቱን ያሳዩ ነበር፡፡ ከሁለት አመት በኋላ ነፍስ ዘርተው ። «ግሬግሰን አትሳሳት ። ተወኝ ያለችኝ ሜሪ አዳምሰን ናት ። ናንሲ ማክአሊስተርን አላነጋገርኳትም ። ሁሉንም ከሷ መስማት እፈልጋለሁ። ያ ብቻ አይደለም ። ብዙ ምርመራም አለባት። ሁለት አመት ሙሉ ለምን አልነገረችኝም? ለምን በሕይወት መኖሯን አልገፃለፀችልኝም ? ሞተች ብለው የነገሩኝ፤ ፈቅዳላቸው ነው ወይስ ... የሌላ ሰው ሀሳብ ነው ? ይኸ ሁሉ አለ ። ትጠየቃለች ። ይኽ ሁሉ ሆኖ ግን ...› አለና ንግግሩን አቋረጠ ። ጥያቄውን ከመጠየቁ በፊት መልሱን አወቀው። ቢሆንም ርግጠኛ መሆን አለበት ስለዚህ ጠየቀው ፤ «ማነው ለህክምናው የከፈለላት ?»
«ብዙ ጥያቄዎች አቀረብክልኝ ።የሁሉንም መልስ እማውቅ አይመስለኝም ፤ ባውቅም... እንደልቤ መልስ ለመስጠት የሚያስቸግሩኝ ናቸው »
«ተው ። እንዲያ ብለህ አት ....» ማይክል ይህን ብሎ ወደ ፒተር ተንደረደረ ፤ ሊያንቀው ።
ሆኖም ፒተር ብልህ ስለሆነ በቃ የሚል ምልክትና ማረጋጊያ አሳየው ፤ መዳፉን በማንሳት ። «ለቀዶ ጥገናው ሕክምናና ለመኖሪያዋ የሚሆነውን ገንዘብ የከፈለቸው እናትህ ናት ። በጣም ከፍተኛ ልግስና አድርጋለች ›› ማይክል የፈራው መልስ ይህን ነበር። ግን ያሰበውን ያህል አላስደነገጠውም ፤ አልሰቀጠጠውም። ይህን ሁሉ ሲያስበው ካጠነጠናቸው ነገሮች ጋር ይገጥማል ። አትጠቅመውም ብላ ይሆናል፡፡ መሳሳት ልማዷ ነው ማሪዮን… ማይክልን በሚመለከት ጉዳይ ላይ አሁን ደግሞ ወደ ሜሪ የላከችው እንዲገናኙ ፈልጋ ሊሆን ይች ይህን አሰበ ማይክል ። «ያንተስ ? ማለት ያንተና የናንሲ ግንኙነት ምንድነው ግልዕ አድርገህ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ »
«ያን እነኳ አንተን የሚያገባህ አልመሰለኝም »
«ስማ ጋግርት…» እንደገና በኮሌታው እንቅ አደረገው ። ፒተር እጁን አነሳ መሸነፉን ለመግለፅ ። እና «እኔና አንተ ይህን ነገር ብንተወው ምናለበት ? ሜሪ አለች አይደለም ? መልስሀን ሁሉ ከራሷ ታገኛለህ ። ጥያቄህን ሁሉ እሷኑ ጠይቃት» አለና ተቀመጠ ። «እኔ እንደሆንኩ አባቷ እሆናለሁ ። እንደኔ እንደኔ ከኔም ካንተም እሷ የተሻለውን መርጣ ታደርጋለች»
«ምናልባት ይሆናል ። ግን ይህንም ቢሆን ከሷው መስማት ነው እምፈልገው ። እንዲያውም አሁኑኑ እጠይቃታለሁ ፤እቤቷ ድረስ ሄጄ »
«ወደ ቤቷ መሄድህ እንኳ ዋጋ የለውም»
«ለምን ?»
«የለችም ። አታገኛትም» ማይክል ግራ በመጋባት ይመለከተው ጀመር ።
«እናንተ እቢሮዬ የገባችሁት ከአየር ማረፊያ ስልክ ደውላልኝ ተነጋግረን እንደዘጋሁት ነው»
«የት ሄደች ? ወዴት ሄደች ደሞ አሁን » ፒተር ለጥቂት ጊዜ ያህል ዝም ብሎ ቆዬ ። ልንገረው አልንገረው አለ ። መንገር የለበትም። ምንም ነገር መንገር አልነበረበትም። « ወደ ቦስተን ነው የሄደችው»

ይህን ሲሰማ ማይክል ለቅፅበት ያህል አይኑን በፒተር ላይ አሳረፈ ። ፈገግታ ቢጤ ፈቱን ዳሰሰውና አለፈ ። ወደበሩ የሄደው በሩጫ ነበር ። በሩን ከፍቶ ሊወጣ አሰበና ቆመ ። ዞረ ። እንዳበባ በፈካ ፈገግታ ለፒተር ስንብቱን አቀረበ ። እና… «አመሰግንሃለሁ» አለ ።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ጐሀ ሲቀድ ከመኝታዋ ተነሳች ። ድቅስቃሱ ሁሉ ለቅቋት ሙሉ በሙሉ ሕያው ሆና ። ዝንተ ዓለም ያልተሰማት መልካም ሰሜት ተሰማት ። አሁን ነፃ ናት ። ነፃ የሆነች ያህል ነው ። ተቃርባለች ። ከሁለት ሦስት ሰዓት በኋላ ሙሉ በሙሉ ነፃ ትሆናለች ። ከታሰረችበት ትፈታለች ። ያ የልጅነት ቃል ኪዳን ያ የሕፃን ጨዋታ ይህን ያህል ጊዜ ይሠራል ! ፈቀደችለታ ። የዚያ ቃል የማሰር ኃይሉ ፤ እሷ ፈቅዳ የለጠፈችበት ኃይል ብቻ ኖሯል ለካ ። ቁርስ በመብላት እንኳ ልትዘገይ ፤ ልትቸገር አልፈለገችም ። በቁርስ ፋንታ ሁለት ሲኒ ቡና ጠጣች ። ከዚያም እተከራየችው መኪና ውስጥ ገብታ ጉዞዋን ቀጠለች ። መንገዱ ሁለት በዓት ያሀል ቢፈጅባት ነው ፤ ከቦስተን እስከ ጉዳይዋ ያለው መንገድ ። አራት ሰዓት አካባቢ ትደርሳለች ። ቀትር ላይ ተመልሳ ቦስተን ትደርሳለች ። ወዲያው ወደ አየር ማረፊያ መሄድ ነው ። ወደ ሳንፍራንሲስኮ የሚጓዝ አውሮፕላን ብታገኝ . . . መሸትሸት ሲል ሳንፍራንሲስኮ ከች ነው ። ከቀናትማ ፒተር ከቢሮው ሳይወጣም ልትደርስ ትችላለች ። ያ ከሆነ ደግሞ በቀጥታ ወደ ፒተር ቢሮ ሄዳ ሳያስበው ዱብ ብላ ልታስደምመውም ትችላለች ። ምስኪን ፒተር ፤ እሄዳለሁ ስለው እኮ በጣም ተጨንቋል ። ግን ታገሰ፡፡
👍22
መንገድ ላይ ሁሉ አሁንም ሐሳቧ ወደ ፒተር ይሄድ ነበር፡፡ ስለዚህም ከከተማው ወጥታ ገጠሩን ስትያያዘው ያለ አንድም ነገር ትዝ አይላትም ። ስለፒተር ስታስብ አሳዘናት ይወዳታል ። ብዙ ውሎላታል ። እሷ ግን ምንም አላደረገችለትም ። ብትችል ብዙ ብትውልለት ደሰ ይላት ነበር። ምናልባት ከዛሬ በኋላ ሁሉ ነገር ይለወጥ ይሆናል። ያሰበውን ለመፈጸም እችል ይሆናል ። ወይስ ከዚህ በኋላም ይህን ሐሳብ ጠላችው ። እስከ መጨረሻው ለማሰብ እንኳ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም አለች ። ፒተርን እኮ አፈቅረዋለሁ ይኸ ጥርጥር የለውም ። ዋናው ነገር ግን ይህ አይደለም ። ወደ ውጭ ስትመለከት የኒው ኢንግላንድ የገጠር ምድር ግራጫ ጥቁር ሆኖ ታያት ። ክረምቱ ቢወጣም በረዶው ቢሟሟም ዕፅዋት ገና አልለመለሙም ፣ ሣር አልበቀለበትም ። ይህን ሁለት ዓመት እሷ ብቻ ሳትሆን የገጠሩ ምድር ውበት ተቀብሮ ያሳለፈ ይመስል ። ሪቨር ቢች አካባቢ ስትደርስ አንድ ጊዜ ባዛር ተዘጋጅቶበት የነበረውን ቦታ አየችው ። ስታስታውሰው አንድ ስሜት የሠራ አካላቷን አናወጻት ። በወደቡ ዳር ዳር የሚያስኬድ አንድ ያልተጠገነ የመኪና መንገድ ተከትላ መንገድ ጀመረች ። እምትፈልገው ቦታ ስትደርስ ከመኪናዋ ወረች ። ሁለመናዋን አንድ ነገር ጨምድዷት ነበር እንጂ ድካም አልነበረባትም ። መንፈሷም ይሸበር ፤ ይረበሽ ነበር ። አሁን ወደኋላ የለም ። ይህ ነገር መከናወን አለበት ። ማድረግ አለባት…. ያ ዛፍ ታያት ። ባለችበት ላይ ቆማ ለረጂም ጊዜ ትኩር ብላ ተመለከተችው ፣ የሚያውቃት ፣ ምሥጢሯን ሁሉ የሰማ ምስክር ይመስል ። ታሪኳን የሚያውቅና እንደምትመለስ ስለሚያውቅ እሷኑ ሊጠብቅ የቆመ ይመስል ። ቀስ እያለች ወደዚያ ዛፍ ሄደች ። ልክ አንድ የምታውቀውን የናፈቃችን ጓደኛዋን እንደምትገናኝ እየተሰማት ። ግን ያ ዛፍ ጓዶኛዋ መሆኑ ቀርቷል ።. ያኔ የወደደችውን ነገር ሁሉ ስትተው እሱም ቀርቷል ፤ ትታዋለች ። እንግዳ ነው ፤ ለሷ። ከዚያም ካለፈ በናንሲ ማክአሊስተር መቃብር ላይ ከተተከሉ ምልክቶች አንዱ ነው። እዛፉ አጠገብ ስትደርስ ቆመች ። እንደገና ተራመደች ወደ ትልቁ ድንጋይ ። ያኔ እንደነበረ አሁንም አለ ። ኦልተንቀሳቀሰም ። ሁሉም ነርገ እንዳለ ነው። ከሷና ከማይክል በስተቀር ። እሷና ማይክል ግን ወዶ ተቃራኒ አቅጣጫ ተጉዞዋል፡፡ ላይገናኙ ተለያይተዋል ። ረዘም ላለ ጊዜ እድንጋዩ አጠገብ ቆመች፡፡ ሀይል ከማጠራቀም የፈለገች ይመስል ። በመጨረሻ ጎንበስ ብላ ድንጋዩን ለማንሳት መታገል ጀመረች። ድንጋዩ ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ ጀመረ ። የነበረበትን ቦታ በእንጨት ቶሎ ቶሎ ጫረች ። አለ ብላ ያሰበችውን እዚህ ድረስ ያመጣትን ነገር ለማግኘት ። አንድም ነዢ አልነበረም ። ድንጋዩን ለቀቀችው ። ወደ ቦታው ተመለሰ ። ተስፋ አልቆረጠችም። በእልህና ባዲስ ጉልበት ብድግ አደረገቺው ይኸኔ ግን በጣም ስላነሳችው የፈለገችው ነገር የነበረበት ቦታ ባዶ ሆኖ ታያት ። አንድ ሰው ወስዶታል ። እኒያን የአንገት ጌጥ መቁጠሪያዎች አንድ ሌላ ሰው ወስዷቸዋል ። ድንጋዩን ስትለቀውና ቦታውን ሲይዝ ሰማች ፤ ድምጹን ።

« ያንችን ያልሆነ ነገር ለመውሰድ መሞከር የለብሽም ። ጌጦቹ የሌላ ሰው ናቸው ። እኔ አፈቅራት የነበረች ልረሳት ያልተቻለኝ … የሷ ናቸው » አየችው ። ማይክል ነበር ። ዓይኖቹ በእንባ ረጥበዋል

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
30👍12😁1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አንድ


#ከፍቅረ_ማርቆስ_ደስታ

...የልጃገረድ ጡት የመሰለው የሐመር ተራራ አፈዘዘው እና! ያን ማራኪ ተራራ በአይኑ ጠባው... በህሊና አኘከው... ጳ...
እኝ... ጳ... እያደረገ አጣጣመው።

hቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የሐመርን ምድርና ቀዬ ከአድማስ ወዲህ የአስሌንና የቡሜን ተራራ በየኮረብታው ላይ የሚታዩትን የሐመር መኖሪያ ቀዬዎች እየተጠማዘዘ ከቡስካ ተራራ ስር ጀምሮ ቁልቁል ወደ ኦሞ ወንዝ የሚጓዘውን የከስኬን ወንዝ... በአረንጓዴ
ልምላሜ የተዋበውን የሐመርን ጫካ ሲቃኝ የከብቶችን ግሣት
ሲያዳምጥ ስሜቱ ዋለለ፡፡

ደልቲ ውስጡ እንደዚያ በደስታ ቢተራመስም ውጫዊ እርጋታው ያው እንደወትሮው ነው:: ዝም!  ጅንን፡

አካባቢው በአዕዋፍ ድምፅ በሽምልማል ንፋስ ሽውሽውታ ከዛፍ እየተንጨዋለሉ በሚቦርቁት ጉሬዛና ጦጣዎች... ደምቋልዘ

ደልቲ ገልዲ ዝግባ ጥድ ግራር ካስዋበው የቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የአባቱን ምድር የሐመር ውብ ተፈጥሮ ሲቃኝ ቆይቶ
ከቆመበት ቦታ በስተግራ በኩል ካለችው ውብ የግራር ዛፍ ስር ሄዶ
በርኮታው ላይ ቁጭ አለ፡፡

ገሃዱ ዓለም ላይ ዋና ሥራ ጉዞ ፍቅር ጥላቻ... ይሆንና
በህሊና ቀረጢት ደግሞ ትዝታ ይከማቻል፡  ህልም ትዝታ...ማንም ከዚ ከስተት ሊያመልጥ አይችልም:: በገሃዱ የፈፀመውን
በትዝታ ምስል ያየዋል ከዚያ ይፍነከነካል ወይ ይቆዝማል! ይቅበጠበጣል ወይ ይሽማቀቃል! አልያም ይስቃል ወይ ያነባል...
ትዝታ! የተዳፈነውን እውነት እየጫረ ስሜትን ይለዋውጣል…

ደልቲም እንዲያ ከተዋበው ሥፍራ ሆኖ ዛሬን ከዛሬ ተቋድሶ ትናንትን አለማት ህልሟ  ትናንት ደግሞ የትናንት ግሣንግሷን
ይዛለት ከፊት ለፊቱ ተደቀነች፡ ጨዋታ ጭፈራ ጀግንነት ፍቅር...
አንዱ በሌላው ላይ እየተነባበረ ታየው፡፡ ገሃዱን ዓለም ከምናባዊ ትውስታው ጋር አንዳንዴ እየተጋጨ ሌላ ጊዜ እየተዋሃደ ተመለከተው የህይወት ኡደት የተፈጥሮ ባህሪ አንዱ ሌላውን እየተካ ብቅ ጥልቅ እያለ ሲያልፍ ህሊናው የትናንት ትዝታን ወደኋላ
ሲያነጠጥን ለማየት ተከተለው፡

ጦጣና ጉሬዛዎች ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ ሲቦርቁ አዕዋፍ ሽቅብ እየጓኑ ቁልቁል ሲወረወሩ... የደልቲ የቦዙ አይኖች የሚያዩት
ትናንትን ነው:: የትናንት ትዝታ ከሁሉም ገዝፎ በህሊናው ተንሰራፍቷል።

በዚህ የትዝታ ማጥ እንደተዘፈቀ የቦዙ አይኖቹ እንግዳ ነገር ተመለከተ
አይኑ የሚንቦገቦግ ቀንዱ የሾለ ሰውነቱ
የሚያንፀባርቅ... ግን የደነበረ አውሬ ሰውነቱ የሚንቀጠቀጥ መሸሽ
ደግሞ ያቃተው አውሬ::

ደልቲ ከትዝታ ማጡ ያለ የሌለ ሃይሉን አስተባብሮ
በመውጣት የያዘውን ክላሽንኮቭ በአውሬው ግንባር ላይ አነጣጥሮ
አመልካች ጣቱን ቃታውን ከመሳቧ በፊት ስሜቱ ሲጣራ ወስፋቱ ሲጮህ ሰማው፡፡ የተጠበሰ ስጋ ወጠሌ ጥብስ ትዝ አለው  ጎመጀ።የራበው ሰው የሚበላ ሲመጣ አይገፋም፡ ያውም ካውሬም የድኩላ
ምራቁ በአፉ ሞላ፡፡

ድኩላውን ከማሰናበቱ በፊት በመሣሪያው የማነጣጠሪያ
ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከተው። ተሸብሯል! ፍርሃትም ያንዘፈዝፈዋል! “ለማምለጥ መሞከር ሲገባው ለምን ተገትሮ ቀረ?
አይኖቹስ ለምን ይማፀኑኛል?..” አለ በማይሰማ ድምፅ

ደልቲ ግራ ገባው፡፡ ቀጭኔ ጎሽ አንበሳ... ሲገል
እየተሯሯጠ አንዱ ለማምለጥ ሌላው ለማስቀረት እየተጣጣረ...
እየወደቀ.. እየተነሳ... ነበር: ዱኩላው ግን አልተንቀሳቀሰምI
አልሮጠም ታዲያ ደልቲ እንዴት ደንግጦ የቆመ እንስሳ ይገላል!
እንዴትስ ለሆዱ  ብሎ ተሸብሮ ከፊት ለፊቱ እንደ በግ ቆሞ የሚማፀነውን አውሬ ገድሎ የአባቱን የጀግንነት ባህልና ታሪኩን
ያበላሻል።

ዘገነነው! የራሱ የሆኑት ፍየሉች በጎችና, ከብቶች
ታሰቡት። የሥጋ አምሮት የአባት ባህል... እስሜትና እህሊና ትግል ውስጥ ከተቱት። ስሜቱ በሰውና ጥብስ ብላ አለው: ሀሊናው
“ፈርቶ ደንብሮ ጉያ ውስጥ የገባን አውሬ ተኩሶ መግደል የጀግና ሞያ አይደለም። የመልካም ስም የደግነት ሥራ ጠላቱ ከርስ ነው። ሆዳምነት! እና ተወው" አለው።

ደልቲ ይህን እያስበ ዓይኖቹን ከድኖ ሲከፍት ደነገጠ:: ተምታታበት ደኩላው ከፊት ለፊቱ የለም በሱ ቦታ የተተካውን
ማመን አቃተው አይኖቹን ጨፍኖ እንደገና ከፈታቸው: ለውጥ የለም: ድኩላው የለም: እሱን የተካው ግን ከፊት ለፊቱ ቆሟል።

ምን ጉድ ነው!" ደልቲ ተሸበረ። የሚያየውን ማመን
ተሳነው። አይኖቹን ደጋግሞ እየከደነ ከፈታቸው: አዎ! ቅዠት አይደለም እውነት ነው ከፊት ለፊቱ የቆመው ሰው ነው  ልጃገረድ... ያውም የደም ገንቦ ..

ድኵላ. ልጃገረድ… ድኩላ ልጃገረድ… ህሊናው እውነቱን ለማጣራት ሞከረ።

"ለምን መጣች? ምን ጉዳይ ይኖራት ይሆን ድኩላውስ
ለምን ቆመ? ለምን ደነገጠ? የትስ ሄደ ?  ለምን በሱ ቦታ እሷ ተተካች..." ራሱን ለማሳመን ማጠፊው አጠረበት።
ልጃገረዷን  የደም ገንቦዋን አውቋታል: የወሮ መንደር
ቆንጆ ናት ግን እሷ ስለመሆኗ ማን ማረጋገጫ ይስጠው: በህሊናው
መልስ አልባ ጥያቄዎች ተደረደሩ'

“ይእ! ከመሞት እንደሁ የሚያመልጥ የለ። ነገ ወይንም ተዚያ በኋላ በወባ ሞተች... የከስኬ ውሃ በላት… ከብት ወግቷት
ሞተች... ከምባል ደልቲ ገደላት I አፍቅራው ሄዳ ፍቅሯን ሳይረዳ
ጭንቀቷን ሳይካፈላት ራቧን ሳይራብ ሙቀቷን ሳይጋራት...ጀግናው ገደላት ቢባል ምናለ!" ልጃገረዷ ከቆመችበት ሳትንቀሳቀስ
አጉተመተመች።

እሏ ያስደነበረችው ድኩላ እሷን ፈርቶ ሮጦ ደልቲን ሲያይ ከፊት ለፊቱ ቆመ: እሷም የስንት ጎረምሳ ልብ ተነጥፎላት እየረጋገጠች አልፋ በፍቅር ልቡ ርሷል ለተባለው ጀግና ፍቅሯን
ልታበረከትለት ከደስታ ፈጣሪ ደረቱ ላይ ለመጋደም ተራራውን ወጥታ ከፊት ለፊቱ ተገተረች።

“ ደልቲ ድኩላውን ለምን ሳይገለው ቀረ? የቆመ
የተሽበረ አልገልም ብሎ እንጂ ከሰማይ ወፍ የሚያወርድ ጀግና ነው፡፡
ይእ እንዲህ ነው እንጂ ጎበዝ! ምግባሩን ለአባቱ ለባንኪሞሮ ትዕዛዝ
ያስገዛ  ለሆዱ ያላደረ... ለዚህ ጀግና ፍቅር ተራራ ቢወጡ እንደ ቅንቡርስ መሬት ለመሬት ቢልወሰወሱ እንደ ኩይሳ ከፊት ለፊቱ
ተገትረው ቢኖሩ ነፍስና ስጋን ቢሰጡት ምን ይቆረቁራል

“አይ እርጋታ! ደሞ ዛሬ እንደ አንበሳ ግርማ ሞገሱ እንዴት ያምራል? እውነት ከእሱ እቅፍ ገብታ ዓለሟን ያየች ሴት ጨረቃና
ከዋክብት በሌሉበት ድቅድቅ ጨለማ ብትጓዝ ትደናቀፍ ይሆን!"ፍቅሩ ውስጧን እያመሳት ቀባጠረች

ደልቲ ከንፈሯ ሲንቀላቀስ አይቷል። የምትለውን ግን
አልሰማም፡ ልጃገረዷ አንገቷ ላይ ከደረደረቻቸው ጨሌዎች ሦስቱን
አወጣች፡፡ ትንባሆ የያዘ ትንሽ የፍየል ቀንድ በቆዳዋ ጫፍ ቋጠረችበት ፈታች። ደልቲ በትዕግሥት ይመለከታታል፡

ልጃገረዷ አይኖችዋን ሳትሰብር በፍቅር አይን አይኑን እያየች ስትመጣ ደልቲ ትዝታው እንደአውሎ ነፋስ ወደ ኋላው ነጥቆት
ነጎደ። ወደ ትናንት ወደ ድሮ: ያኔ የትናንቱ ድሮ ጎይቲ አንተነና እሱ መጀመሪያ ከዲመካ ገበያ ተያይተው በአይን ተጠቃቅስው
በልቦናቸው ተስማምተው በፍቅር መሪነት ጫካ ገብተው ያ ያዜመችለት የወንዶች አውራ ጭን ላይ ቁጭ ብላ አእዋፍና ነፋሱ
እያጀቧት የድምጿን ቅኝት
👍663
በሚጥመው ድምጽ ቃኝታ
በሚስረቀረቀው ድምጿ ስታሞካሸው ምርጫዋ ተፈቃሪው በትክክል
እሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ከጭኖቹ ላይ ተነስታ ከፊት ለፊቱ ቆማ ስትመለከተው! እሱም በፍቅር እመቤቱ ትዝታን እንደሚጫወት
አዝማሪ ኩሩው ዳሌዋን በጉንጮቹ ተንተርሶ የአንባር ማስገቢያ የመሰለ ወገቧን አቅፎ በተፈጥሮ መኝታ ቤት ተያይዘው ላይና ታች
ሲሆኑ በዝነ ህሊናው እንደገና እየተጓዘ ውበቷን እየበረቃቀሰ ሲጎመጅ ... ጎይቲ ደግሞ ያ ጎሽን የሰበረ አንበሳ ያ ቀጭኔን
የቀለመጠው አይበገሬ አጓርቶ የተወረወረን አንበሳ ያንበረከከውዐየሐመር አንበሳ እሷንም የፍቅር አከርካሪዋን አድቅቆ ለፍቅሩ
ያልወሰወሳት ጀግናና ቀብራራው ደልቲ መሆኑን አረጋግጣ የፍቅር ምሷን ወስዳ አምሮቷን ለመወጣት የቀለጠ ልቧን ወደ ደልቲ ገላ ለማፍሰስ ወደ ከንፈሮቹ ዝቅ ስትል... እያዬ ያን ደግ ትናንት ሲያልም እንግዳዋ ልጃገረድ በእጆችዋ የያዘችውን ጨሌ ሽልማት
በአንገቱ አጥልቃ ትምባሆውን ልታቀብለው ስትጠጋ ጎይቲን እንዳገኘ
ሁሉ በሰመመን ወደ እሱ ሳባት፡፡

ልጃገረዷ የደስታ እንባ
አይኖችዋን ሞላው፡፡ለካ
የተመኙትን ለማግኘት አስፈላጊው የቡስካ ተራራን መውጣት ነው:"
ልቧ እየደለቀ ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያሉ ከደልቲ ጠንካራ ጣቶች ከመሸሽ ይልቅ ወደ ጎመጀችለት ገላ ቀድማ በሃሣቧ ወደቀች። እቅፉ ሞቃት ደረቱ እንደ ኦሞ ደለል ተመቻት ገላው ደላት በደስታ ሰከረች፡

“ጎይቲ…” ብሎ  ደልቲ በቅዠት ዓለም እንደ ሰመጠ
ልጃገረዷን ወደ እሱ ይበልጥ ሳባት ልጃገረዷም በስሟ እንዳልጠራት
በሰመመን ውስጥ ሆና ብትሰማውም አካሏን ዘና አድርጋ ወደ እሱ ጉዞዋን አጣደፈች።

“ይእ! ባሻው ስም ይጥራኝ እኔ ምን ተዳዬ! ይልቅ ይኸዋ እንደ ትኩስ ወተት የሚያውደው የጀግናው ጠረን አወደኝ እቅፉ ውስጥ ገባሁ ከእንግዲህ ከዚህ ሰው ምን የምደብቀው ሚስጥር አለኝ? ምንስ የምነፍገው ነገር ይኖረኛል። ሁሉንም ይንካው እንደ
አባቴ ቁርበት አንጥፎ ይንከባላልብኝ... እንደ ጭሮሽ ወሃ የማመነጭለትን ፍቅር በእፍኙ እያፈሰ ይጠጣው" ብላ ከአካሉ ተጣበቀች።

የወፎች ድሪያ ተጀመረ: ጡቷ ደረቱን ነክሶ ያወ እጆችዋ አንገቱ ላይ እንደ ሃረግ ተጠመጠሙ የጋራ ሙቀታቸው እንደ እቶን የሚንቀለቀል እሳት ፈጠረ... ደልቲ ስርጓዳ ወገቧን እንደ ችቦ ጨምቆ ሲስባት እየተለጠጠች ወደሱ ስትጓዝ ቀንዱ ወጋት ያኔ
ከእግር እስከ ራሷ ነዘራት  ከማፈግፈግ ይልቅ…..

“አዎ! ከዚህ ደስታ በኋላ ሺ ሞት ይምጣ! የመጨረሻዋ ቀኔ ዛሬ ትሁን የአባቴ ጨረቃና ከዋክባት ብርሃናቸው ይጥፉ
የሚመስሰኝ መንገድ ሰውና ከብት የማይጓዝበት ገደል ይሁን..."እያለች ተጓች።

ነፋሱ ያገኘውን እየጠራረገ ሽቅብ ያጓነ እፅዋትን ጎንበስ
ቀና እያደረገ... ይነፍሳል። የፍቅራቸው እሳት ግን ወደ እነሱ ሊያስጠጋው አልቻለም።

ቡስካ ላይ በዚያ ለዘመናት በተገተረ ጥድ ስር... ፍቅር
ተተክሎ አደገ። አበባ ሆኖ ከመቅፅበት አፈራ ንቦች ከአባው ሊቀስሙ ወፎች ከፍሬው ሊለቅሙ አንዣበቡ ... ልባዊ የፍቅር
ጨዋታው አካባቢውን በመልካም መዓዛው አወደው: በመዓዛው አራዊት ቦረቁ አዕዋፍ ድምፃቸውን  ከፍ አድርገው ማህሌት ዜማቸውን አንቆረቆሩ ፀሐይ ዳመና ውስጥ ገብታ ሙቀቷን ቀነስች ዛፏ ጥላዋን አሰፋች... ለፍቅር ሊባል ሁሉም የየአቅሙን አደረገ።...

💫ይቀጥላል💫
👍5014🔥5🥰2👎1
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ከፍቅረ_ማርቆስ_ደስታ ...የልጃገረድ ጡት የመሰለው የሐመር ተራራ አፈዘዘው እና! ያን ማራኪ ተራራ በአይኑ ጠባው... በህሊና አኘከው... ጳ... እኝ... ጳ... እያደረገ አጣጣመው። hቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የሐመርን ምድርና ቀዬ ከአድማስ ወዲህ የአስሌንና የቡሜን ተራራ በየኮረብታው ላይ የሚታዩትን የሐመር መኖሪያ ቀዬዎች እየተጠማዘዘ ከቡስካ ተራራ ስር ጀምሮ…»