አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ስምንት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡ አራቱም ሞተሮች በአንድ ጊዜ ሲጠፉ የኤዲም ዕጣ ፈንታ አብሮ ተዘጋ። ችግር ከመከሰቱ በፊት ሃሳቡን ቢለውጥ ኖሮ ይሄ ችግር አይመጣም፡፡ ሃሳቡ በውጥን ላይ ብቻ ቢቀር…»
😘  #ቃል  😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሁለት (42)

ልክ እወደቡ ደርሳ የካሜራ መትከያውን ባለሶስት እግር  መቋሚያ እንዳስተካከለች አንድ ሰዉ ቀጥ ብሎ ወደ እሷ ሲመጣ ታያት ። አማመዱ ወደሷ መሆኑ አጠያየቃት፡፡  ማን እንደሆ አወቀች፤ ቆይታ ።
ማይክል !ጣጣ ነው ፤አለች በሀሳቧ።
«አንድ ነገር ልነግርሽ ነው የመጣሁት» አለ እፊቷ ተገትሮ። «መስማት አልፈልግም» አለችው ቀና ሳትል። «እሱ እንኳ ያስቸግራል ። ምክንያቱም ፈቀድሽም ቀረ እነግርሻለሁ ። እና ብታስቢበት ይሻላል ስለግል ሕይወቴ የሆነ ያልሆነ ነገር እየጎረጎርሽ ሀሳብ የመስጠት መብት የለሽም ። እንዲህ ያለህ ሰው ነህ እንዲህ አይነት ፍጡር ነህ ልትይኝ አትችይም። አታውቂኝም ፤ አላውቅሽም ። ይህን ለማለት ምን መብት አለሽ !?» አለ።

ትናንት የተናገረችው ቃል ሌሊቱን ሙሉ እንደጥርስ ህመም ሲጠዘጥዘው ነው ያደረው። «ስለኔ ስነምግባር አስተያየትም ሆነ ፍርድ ለመስጠት የሾመሽ ማን ይሆን ? የኛ ዳኛ ምን መብትስ አለሽ» ጦፈ ። «ምንም» አለች ረጋ እንዳለች ። « ግን ደግሞ የማየው ነገር ደስ አላለኝም » ይህን ስትል ቀና ብላ አላየችውም ። የካሜራ ሌንስ ትቀይር ነበር ። «ያየሽው ነገር ምን ይሆን እባክሽ ?»
«ዛጎል ። ቀንዳውጣው የሞተ በድን ቅርፊት ። ልቡ ፍቅርን የተራቆተ፤ ስራ ስራ ብቻ የሚል ሰው። ስለማንም ደንታ የሌለው ማንንም የማይወድ፤ ምንም የማይሰጥ ፤ ምንም ያልሆነ ባዶ ሰዉ ይህንን ነው ያየሁት ። »
«አንች ውሻ |! አንች ማን ሆነሽ፤ ምን አውቀሽ ነው ደሞ ስለኔ የውስጥ ስሜት ይህን ያህል እምታወሪው ! ለመሆኑ አንችን ሁሉን አዋቂ ያደረገሽ ማነው በይ!» አለ። ዝም ብላ ካሜራዋን አዙራ የአሸዋ ኮረብታ ላይ አነጣጠረች። «አንችን እኮ ነው እማናግረው! ሰሚኝ !» አለ ካሜራዋን ሊይዝ እየሞከረ ። ቀደም ብላ ፊት ለፊቱ ቆመችና አፈጠጠችበት። ከዚያም እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ «ለምን አትተወኝም ። ለምን እሰው ኑሮ ውስጥ ገብተህ የሰው ሰላም ትነሳለህ ?» አለችው ። «ማ ? እኔ ? እኔ አንች ኑሮ ውስጥ አልገባሁም ። እኔ ጥቂት ፎቶግራፎችን መግዛት ብቻ ነው እምፈልገው በቃ ። በተረፈ ያንቺን ኑሮም ፤ያንችን አስተያዬት አልሻም ። ፎቶግራፍ ! በቃ!» በንዴት መንቀጥቀጥ ጀመረ። እሷ ግን አልመለሰችለትም ። እንደቆመ ትታው ሄደች። አንድ ብርድ ልብስ ላይ የተቀመጠ የወረቀት መያዣ ቦርሳ አነሳች ፤ ዚፑን ከፍታ ከውስጡ አንድ የታጠበ ፎቶግራፍ አወጣች እና ፎቶ ግራፍ ነው የምትፈልገው አደል? ይኽውልህ ። ይኽን ወስደህ የፈለገህን ነገር አድርገው ። እኔን ግን ተወት አርገኝ። እሺ» ብላ ሰጠችው ። ተቀበላት ። አላነጋገራትም ። ሄደ ዞራ አላየችውም። ስራዋን ቀጠለች። ስራ ፤ ስራ ፤ሰራ። ጸሐይ ብርሃኗን ስትነሳ ካሜራው መስራት ሲሳነው ስራዋን አቆመች።

እቤቷ እንደደረሰች እንቁላል ጠብሳ በልታ ቡና አፍልታ ጠጣች በኋላ ወደ ፎቶግራፍ ማጠቢያ ክፍሏ ገባች። ያንለት የተኛችው ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ሲሆን ነበር ። ጧት በሁለት ሰዓት ለመነሳት ወስና ባለዶወል ሰዓቷን አስተካክላ ተኛች። ባለችው ሰዓት ነቃች። ደወሉ ቀሰቀሳት ። ሰውነቷን ታጥባ ፣ ልብሷን ለባብሳ፤ ቡናዋን እየጠጣች ጋዜጣዋን እንብባ ከቤቷ ስትወጣ ልክ ማታ ባቀደችው መሰረት ለሶስት ሰዓት ጥቂት ደቂቃ ይቀር ነበር ። ደረጃውን ስትወርድ ሁሉ የምታስበው ስለቀኑ ስራዋ ነበር። ፍሬድ ኋላ ኋላዋ ቱስ ቱስ እያለ እሷ እያሰበች ከቤት ወጡ፡፡ የውጪውን ደረጃ በመውረድ ላይ እንዳለች አንድ ደረጃ ሲቅራት ቀና ብላ ተመለከተች ። ከመንገድ ማዶ ማይክል ሂልያርድን ቆሞ አየችው። እጁን አውለበለበላት ። አጠገቡ ባለው የጭነት መኪና ላይ በትልቅ ሰሌዳ የተለጠፈ ስእል አየች ። ተመለከተችው ። ትናንት ጧት የሰጠችው ፎቶ ግራፍ ነበር ። ወስዶ በትልቁ ኦጉልቶ አሳጥቦ አንዳች በሚያህል ሰሌዳ ላይ ለጥፎ ይዞት መጥቷል ። ድንገት ሳቋ መጣ ። እደረጃው ላይ ቁጭ ብላ ትንከተከት ጀመር ። ፊቱ በፈገግታ በርቶ ሰውነቱ በደስታ ተሞልቶ ወደ ተቀመጠችበት መጣ፡። አጠገቧ ሲደርስ በፈገግታ እንደበራ በደስታ እንደተሞላ እደረጃው ላይ እጎኗ ተቀመጠ። «ቆንጆ ነው? ወደደሺው ?» ሲል ጠየቃት። «አንተ ግን የምትገርም ሰው ነህ!» አለችው ። «ልክ ብለሻል ። ግን እንዴት ነው? ደስ አይልም?» ሲል አሁንም ደግሞ ጠየቃት። ደስ ይላል ብትለው እንዴት አድርጎ ይደሰት። «እይው እስኪ፤ አሪፍ አሪፎቹን ፎቶግራፎች መርጠን ከፊሉን እንዲህ በትልቁ አሳጥበን እህክምና ማእከሉ አናት ላይ ብንሰቅላቸው ጉድ አይደለም ? » አላት ። ጉድስ ራስህ ነህ… ስትል አሰበች።፡ ደስ እንዳላት ሲያይ በጣም ደስ አለው ። ስለዚህም ነፃ ሆነ «አሁን እዚህ ምን ጎለተን? ተነሺና አንድ ቦታ ሄደን ቁርሳችንን እንብላ» አላት ።

ዛሬ ቆርጦ ተነስቷል ። እሺ ሳያስኛት ይች ቀን አታልፍም። ለዚህ ሲል ከሰዓት በፊት ያለውን ጊዜ በጠቅላላ ምንም ቀጠሮ አልያዘበትም ። እሷም ብትሆን ይህንን ውሳኔውን ከሁኔታው ተረድታለች። ውሣኔው ልቧን ነክቷታል ፤ አስደንቋታል ። በዚህም ላይ ጭቅጭቅ መፍጠሩን ስሜቷ አልተቀበለውም ። «እንሂድ» አላት ። «እምቢ ማለት ነበሪብኝ። ግን አልልህም» አለች፡፡ «ጥሩ ዘይደሻል ። አብረን እንሂድ?» ሲል ጠየቃት ። «በምን? በዚያ?» አለችው የጭነት መኪናውን እያሳየችው። ነገሩ አስቂኝ ሆነባት ። «ምናለበት ይሄዳል እኮ » አስተስማማች ።

አሳ አጥማጆች ወደሚመገቡት ሆቴል አመሩ ። መኪናውን እበሩ ላይ አቆሙት ። በዚያ አካባቢ የጭነት መኪና አዲስ አልነበረምና ማንም ጉዳዬ ብሎ አላያቸውም ። ገትረውት ወደቁርስ ገቡ። ማንም ያን ያህል ፎቶግራፍ አንስቶ ይወስዳል የሚል ፍርሀት አልነበረባቸውምና ጠባቂ አልፈለጉም ። ያንለት ቁርሱ ሳይቀር በሚያስገርም ሁኔታ ድንቅ ሆነላቸው። ቡናቸውን ጠጥተው እስኪጨርሱ ድረስ በመካከላቸፅ- ጭቅጭት አልተነሳም ። ያኔ… «አሁን ተስማማሽ አይደለም?» ሲል ጠየቀ ። ነገሩን በጥያቄ ያቅርበው እንጂ በፊቱ ላይ የሚታየው ፈገግታ ርግጠኛነትና ኩራት አረፍተ ነገሩን «አሸነፍኩሽ» የሚል ስሜት ስጥተውት ነበር ። «በፍጹም አልተስማማሁም። ሆኖም ደስ የሜል ቁርስ በላሁ ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍኩ» አለችው ። «ትንሽ ውለታ ሲውሉልኝ ውለታ አነሰ ብዬ በጥፊ የምመታ ሰው አደለሁም ። ሆኖም ያ ሙሉ መንገዴ አይደለም»
«ሙሉው ምንድ ነው? እስኪ ንገረኝ»
«አሃ! ስለኔ አንች መናገርሽን ፤ መፍረድሽን አቁመሽ እኔ ራሴ እንድናገር ፈቀድሽልኝ ማለት ነው?» ነገሩን እንደቀልድ ቢለውም በውስጡ ሽሙጥ ነበረበት ። «ባለፈው ቀን ያልሽው በመጠኑም ቢሆን እውነትነት አለው ። ለስራዬ ብዙ እጨነቃለሁ» አላት ። «ሌሳ የምታስብለት ምንም ነገር የለህም? ።»
«በእውነት ከሆነ ሌሳው ነገር ለኔ ይህን ያህልም አደለም። ምናልባትም ብዙዎቹ በኑሮ ተስተካክለዋል የምንላቸው ሰዎች ካለስራ ሌላ ሕይወት የላቸው ይሆናል ። ጊዜም ቦታም አይገኝ ?››
👍18🥰1
«ታዲያ ይኸ ጅልነት ነው። በጣም ትልቅ ጅልነት ። ስራህን ለማሳካት ኑሮህን መስዋእት ማድረግ የለብህም ። ካልካቸው ትልልቅ ሰዎች መካከል ደግሞ ኑሮንም እየኖሩ ስራቸውን በሚገባ የሚያካሂዱ ይኖራሉ»
«ካንቿ እንነሳ። ሁለቱንም አጣምረሽ ማድረግ ትችያለሽ ?»
«አሁን አልችልም ። ወደፊት ግን አይቀርም። ቻልኩም፤ቀረም ቢያንስ እንደሚቻል ግን አውቃለሁ»
«ምናልባትም እንዳልሺው ይሆን ይሆናል ። እኔም ዱሮ እንደማስበው አላስብ ይሆናል » ይህን ሲላት አዘነች። ልቧ ለሰለሰ

«ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ሕይወቴ እጅጉን ተለውጧል ። በፊት ያቀድኩት ነገር ሁሉ ከልቡናዬ ጠፍቷል፡፡ መልሼ ያን ለማሰብ ደግሞ አቅም የለኝም። አልሞክርም። በጭራሽ የሆነ ሆኖ አልተጎዳሁም ። መተኪያ የሚሆን መላ አግኝቻለሁ›› አለ፡፡ ለምሣሌ የኮተር ሂልያርድ ፕሬዚዳንት መሆንን የመሰለ ሲል በሀሳቡ ጨመረ ። ለመናገር ግን እፈረ ። «አሃ ገባኝ። አላገባህም ማለት ነው» አለች፡፡ «እንዲያውም ። ጊዜም የለኝ ፤ ፍላጎትም » አለ ። እንዲያ ነው? አለች በሀሳቧ። እንዲያ ከሆነ ባደጋ ተመካኝቶ የቀረው ጋብቻ እንኳን የቀረ ። «ኑሮን ተቆርጦ የደረቀ ቅጠል አደረግከው ኮ» አለች ። «ለጊዜው ለኔ እንዲያ ንው። አንችስ እንዴት ነው ?»
«እኔም አላገባሁም››
«ይገርምሻል ፤ እንዲያው የኔን የአኗኗር ዘዬ ታረካክሽዋለሽ እንጂ ያንችንም ሕይወት ከኔ በምንም ሁኔታ የተለዬ ሆኖ አላገኘሁትም ። እንደኔ በስራ የተጠመድሽ ነሽ ። እንደእኔ ብቸኛ ነሽ ። እንደ እኔ በግልሽ ትንሽ አለም ውስጥ ተቀብረሽ ነው የምትኖሪው፤ ያው ነሽ ። ታዲያ እንዲህ ሆነሽ ሳለ አጉል ፍርድ ትሰነዝሪብኛለሽ? ደግ ነገር አይመስለኝም» ይህን ሲናገር ድምፁ ለስላሳ ቢሆንም ወቀሳ ያዘለም ነበር ። ስለዚህም ተሰማት ። «ይቅርታ አድርግልኝ ። ምናልባትም ልክ አይደለሁም ይሆናል» እለች።

ይህን ብላ ቀና አለች እየችው ። ማይክል ነው ። የተሰበረው ማይክል ። የተሰበረች እሷ ። የተጣጡ ሁለት ። ያኔ ደስ እሚላት ማልቀስ ብትችል ፣ ብታነባ ፣ እሪ ብትል ነበር አየችው ። ተለያይተዋል ። መንገዳቸው ለየብቻ ሆኗል፡፡ በሕይወት እያለህ አልለይህም ፣ ደህና ሁን. . . አልለይህም… ቃል ኪዳናቸው ትዝ አላት ። ይህ ግን ፤ መለያየታቸውን ፣ መንገዳቸው ለየብቻ መሆኑን ማወቋ ግን ፣ ደህና ሁን እንደማለት ነው ። «ብሄድ ይሻላል መሰለኝ… ወደ ሥራ» አለች ሰዓቷን አየት አድርጋ ። «ወደ ይቻላል ተቃረብኩ ይሆን… ለድርጅታችን ትሠሪያለሽ ለሚለው ጥያቄዬ? »
«አይመስለኝም… አይቻልም» አለች ።


ይህን ሲሰማ ካሁን በኋላ የፈለገውን ቢያደርግ እሺ ሊያሰኛት እንደማይችል ገባው ። እስከዛሬ የለፋው ልፋት ሁሉ ከንቱ እንደነበረ ተገነዘበ ። በጣም ጠንካራ የሆነች ሴት ናት ። ግን ደግሞ ወዷታል ። ሁሉን ነገር ትታ ሰው ስትሆን ፤ ስትሸነፍ ምን ዓይነት ልብ እንዳላት ሲያስብ ተደነቀ ። የልቧን ንጽሕና፤ ገርነትዋን ፤ ውስጡዋን ሲያይ ይህን ያህል ጊዜ ማንም ሰው መስጦት ስቦት የማያውቀውን ያህል እንዳቀረበችው ተገነዘበ ።»

«አንድ ቀን ራት አብረን እንድንበላ ብጠይቅሽ እሺ የምትይ ይመስልሻል ሜሪ ? ማለት እንዳሸነፍሽኝ ተረድቻለሁ ። ለማጽናናት ያህል እሺ አትይኝም?» አለ ። ፊቱ ላይ የነበረውን ነገር አይታ በለሆሳስ ሳቀች ። ከዚያም እጁን በአይዞህ አትዘን ማጽናናት መንገድ ቸብ ቸብ ካደረገችው በኋላ «እኔም ደስ ይለኛል ። ግን አሁን አይሆንም ። በቅርብ ከከተማ መውጣቴ አይቀርም» አለች፡፡ ምን ዓይነት የተገረመ ነገር ነው አሁንም አልቻለም ። ዙሪያ ገባውን መሸነፍ በመሸነፍ ሆነ ማለት ነው አሰበ ።

«ወዴት ነው ለመሄድ ያሰብሽው? »
«ወደ ምሥራቅ ልመለስ አስቤአለሁ ። ለጥቂት ቀን ለግል ጉዳዬ » ይህን የወሰነችው ድንገት ነበር ። ከማይክል ጋር እየተነጋገሩ ሳለ ። ከግማሽ ሰዓት ባፊት ። ቀድሞ ማድረግ እንደሚገባት አልወሰነችም ። አሁን ግን ወስናለች ። ፒተር እንዳላት ለማድረግ አስባለች ። ያለፈውን ቁስል መሸፋፈን ሳይሆን ገልጦ ምን ያህል እንዳመረቀዘ ፤ እንደተመረዘ ማዬት ። ፒተር ልክ ነው ባንድ በኩል ስትል ነበር ። አሁን ግን ልክ እንደነበረ በሚገባ አረጋግጣለች ። ገልጣ ማዳን አለባት ። ገልጣ አይታ ማከም ይገባታል ። እሱ ፒተር እንዳለው ። «በሚቀጥለው ጊዜ ሳንፍራንሲስኮ ስመጣ ስልክ እደውልልሻለሁ ወይም መጥቼ እጠይቅሻለሁ ። ያኔ ከዚህ የተሻለ ዕድል እንደሚገጥመኝ ተስፋ አደርጋለሁ » ምናልባት አለች በሐሳቧ ። ምናልባትም ያኔ የፒተር ግሬግስን ባለቤት ሆኜ ታገኘኝ ይሆናል ። ምናልባትም ያኔ ከበሸታዬ ተፈውሼ አልፈልግህ ይሆናል ።

ጸጥ ብለው መኪናው ወደቆመበት ሄዱ ፤ ጐን ለጐን ። ቤቷ በር ላይ አወረዳት ። ያኔም ሆነ እመንገድ ላይ ብዙ ንግግር አልተለዋወጡም ። ከመኪናው ስትወርድም ብዙ አልተናገረችም ። ቁርስ ስለጋበዛት አመሰገነችው ጨበጠችው ሄደች ። አለቀለት ተሸነፈ ። ይህን እያሰበ ወደ ቤቷ ስትሄድ አያት ። መጠን የሌለው ኀዘን ሲወድቅበት ፤ ልቡን ሲያስጨንቃት ተሰማው ። አንድ ልዩ የሆነ ፤ ካለው ነገር ሁሉ የላቀ ነገር እንዳጣ ፤ እንደጠፋበት ሆኖ ተሰማው ። ምን እንደሆነ ግን ፈጽሞ አላወቀውም ። የሥራ ውል? ተወዳጅ ሴት ወይስ ጥሩ ጓደኛ ? እንጃ ። አንድ ነገር ግን ከእጁ ሾልኮ ጠፍቶበታል ። በዚህ በረጅም ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ መጠንህ የማይባል ብቸኝነት ተጫነው ። መኪናውን አስነስቶ ወደ ሆቴሉ ፈረጠጠ ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍413🔥2
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹እሺ›› አለ ቪንቺኒ ወደ ጀልባዋ ፊቱን አዞረና ‹‹ጆ መጀመሪያ አንተ ና
ቀጥሎ ትንሹ ልጅ በመጨረሻ የኤዲ ሚስት፡፡›› ወደ ውስጥ ሲያዩ ካፒቴኑ ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ሲሄድ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ቪንቺኒ ሽጉጡን
መዘዘና ‹‹አንተ ባለህበት ቁም›› ሲል አዘዘው ቤከርን፡፡
ኤዲም ካፒቴን እንደሚልህ አድርግ እባክህ እነዚህ ሰዎች ቀልድ አያውቁም›› አለ ቤከር ባለበት ቆመና እጁን ወደ ላይ አነሳ፡፡

ጆ የተባለው ወሮበላ ‹‹እዚህ ውስጥ ብወድቅ መዋኘት አልችልም›› አለ
ከጀልባው ወደ አይሮፕላኑ መዝለል ፈርቶ፡፡

‹‹መዋኘት አያስፈልግም›› አለ ኤዲ እጁን ዘረጋለት፡፡

ጆም እንደምንም ዘለለና አይሮፕላኑ ውስጥ ገባ፡፡
ከእሱ በፊት ሁለት ሰዎች በደህና መዝለላቸውን አይቶ ትንሹ ልጅ ኮራ ብሎ ዘለለ፤ ነገር ግን ሲዘል ሚዛኑን ሳተና ወደኋላው ሊወድቅ ሲል ኤዲ የልጁን ቀበቶ ይዞ አዳነው ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ልጁ፡፡

አሁን የካሮል አን ተራ ደረሰ ለመዝለል ፈርታ የኤዲን አይን አይን ታያለች በተፈጥሮዋ ፈሪ ሆና ሳይሆን ከእሷ በፊት ትንሹ ልጅ ተንገዳግዶ ባህር ውስጥ ሊገባ ሲል ስላየች ነው የፈራችው፡፡ ኤዲም ፈገግ አለና
‹‹እንደነሱ ዝለይ ማርዬ›› አለ ‹‹አይዞሽ ውሃ ውስጥ አትወድቂም::››

ኤዲ በፍርሃት ልቡ እየደለቀ በጉጉት ጠበቀ ሚስቱ እስክትዘል፡፡ ካሮል
አን መዝለል መቻሏን ተጠራጠረች፡፡ ‹‹ተዘጋጂና ዝለይ!›› አላት እሱም የእሷ
ፍርሃት ተጋብቶበት፡፡

ካሮል አን ጥርሷን ነክሳ እንደ ምንም ዘለለች፤ ነገር ግን ግማሽ አካሏ ባህሩ ውስጥ ሆኖ ገመዱን ለመያዝ ተፍጨረጨረች፤ ‹‹ገመዱን አጥብቀሽ
ያዥ አይዞሽ›› አለ ወደ ባህሩ የምትወድቅ ከሆነ ለመዝለል ተዘጋጅቶ
ኤዲ ተንበረከከና እጇን ለመያዝ እጁን ሰደደ፤ ሆኖም ሚዛኑን ሳተና ወደ
ባህሩ ሲወድቅ እጇን መያዝ አልቻለም፤ የባህሩ ሞገድ ጎትቶ ውሃ ውስጥ
ሲያስቀራት በተስፋ መቁረጥ ጮኸች፡፡

ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ወደ ኤዲ እየዋኘች ተጠጋች፤ ኤዲ ጥርሷ
ሊንገጫገጭ አየ፧ እንደ ምንም ብሎ እግሯን ያዘ፤ ሆኖም የባህሩ ሞገድ
ሃይለኛ በመሆኑ ከእጁ አፈተለከችና እንደገና ባህሩ ላይ ወደቀች፤ ካሮል አን
እየሰመጠች ነው እሱም እጁን ሰደደና ወገቧን ያዘ፡፡

‹‹አይዞሽ የኔ ማር ይዤሻለሁ›› አለና እንደምንም ተሸክሞ ወደ
አይሮፕላኑ አስገባት፡፡ ካሮል አን ባሏ  እቅፍ ውስጥ ገብታ ማንባቷን ቀጠለች፡፡ እምባ ቢተናነቀውም እንደምንም ዋጥ አደረገው፡፡የምትንቀጠቀጠውን
ሚስቱን ለማረጋጋት አጥብቆ ደረቱ ላይ ለጠፋት
‹‹ደህና ነሽ የኔ ማር? እነዚህ ሰዎች አንገላቱሽ?›› ሲል ጠየቃት

‹‹ደህና ነኝ›› አለች ጥርሷ እየተንገጫገጨ፡፡

የካፒቴኑን ዓይን ለማየት ፈርቶ እየሰረቀ ያየዋል፡፡ ቤከር ወደ ካሮል
አን አማተረና
‹‹ያደረግኸው ሁሉ ለምን እንደሆነ አሁን እየገባኝ መጣ›› አለ፡፡
‹‹ይበቃል የምንሰራው ስራ አለን›› አለ ቪንቺኒም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን ለቀቃትና ‹‹እሺ ወደምትፈልጉት ሰው እወስዳችኋለሁ››
‹‹እሺ›› አለ የወሮበሎቹ መሪ፡
‹‹ተከተሉኝ›› አላቸውና ወደ ውስጥ ገቡ፡ ሰራተኞቹ ምንም ነገር ለማድረግ እንዳይሞክሩ ኤዲ አስጠነቀቃቸው:
‹‹ሁላችሁም አደብ ግዙ፡፡ እነዚህ ሰዎች አድርጉ የሚሏችሁን ማድረግ
ብቻ ነው ያለባችሁ አለበለዚያ በጥይት ከመግደል ወደ ኋላ የሚሉ ሰዎች አይደሉም፡ ሰው እንዲጎዳ አልፈልግም፡ ካፒቴኑም ይህንኑ ነው የሚላችሁ አለ ኤዲ፡

‹‹ትክክል ነው›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ጎበዝ! እነዚህ ሰዎች መሳሪያ የያዙ ናቸው፤ ብትወራጩ በጥይት ነው የሚሏችሁ ››
ኤዲ ወደ ቪንቺኒ ዞረና ‹‹እንሂድ እንግዲህ፤ ካፒቴን ተሳፋሪዎቹን ማረጋጋት ይኖርብሃል›› አለ፡፡

ቪንቺኒ በኤዲ አባባል መስማማቱን በራሱ ንቅናቄ አሳየ፡
‹‹ካሮል አን ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች ጋር ሁኚ፧ እሺ›› አላት፡፡

ኤዲ ሚስቱ ከወሮበሎቹ ጥይት መራቋን ወዶታል፡ በተጨማሪም ባሏ
ለምን እነዚህን ሰዎች ሊተባበር እንደወሰነ ለተሳፋሪዎቹ ታስረዳለታለች፡
ኤዲ ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ጠመንጃህን ከተሳፋሪዎች ብታርቅልኝ፧ ይፈራሉ››
‹‹ተነፋ!›› አለ ቪንቺኒ ‹‹እንሂድ›› ሲል አዘዘ ጓደኞቹን፡ ኤዲ ትከሻውን
በንዴት ነቀነቀ፡፡ ሁሉም ቦታ ቦታቸው ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡ ሁለቱ አስተናጋጆች ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
ኤዲ አይሮፕላኑ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያይ መብል ክፍሉ ትርምስምስ
ብሏል፡፡ ወለሉ በሸክላ እና በብርጭቆ ስብርባሪ ተሸፍኗል። ምግብ ተበልቶ
ስላለቀና ተሳፋሪዎች እየጠጡ ስለሆነ የተደፋፋ ነገር አይታይም፡:
ተሳፋሪዎቹ የቪንቺኒን ሽጉጥ ሲያዩ በፍርሃት ድምጻቸውን አጠፉ፡፡ ካፒቴን
ቤከር ወደ ፊት መጣና ‹‹ክቡራንና ክቡራት ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ
እጠይቃለሁ፡ ከመቀመጫችሁ እንዳትነሱ፡ አሁን ያለው ችግር ከተወሰነ
ደቂቃ በኋላ መፍትሄ ያገኛል›› አለ፡፡

ኦሊስ ፊልድና ፍራንኪ ጎርዲኖ አብረው ቁጭ ብለዋል አሁን ነፍሰ
ገዳይ እንዲያመልጥ ላደርግ ነው አለ ኤዲ ለራሱ፡ ወደ ጎርዲኖም ጣቱን እየጠቆመ ‹‹ያውልህ ሰውዬህ ውሰደው›› አለ፡፡
ኦሊስ ፊልድ ከተቀመጠበት ተነሳና ‹‹ይሄ የኤፍ ቢ አይ መርማሪ ቶሚ ማክ አርድል ነው›› አለ ‹‹ፍራንኪ ጎርዲኖ ትላንት በመርከብ ኒውዮርክ ደርሶ ወህኒ ገብቷል››
‹‹የአምላክ ያለህ!›› ሲል ኤዲ በግርምት ጮኸ፡፡ ይህን ሁሉ እኩይ ተግባር ሲፈጽም የነበረው ለአስመሳይ ሰው ነው?!

‹‹እኛ ከፍራንኪ ጉዳይ የለንም፡፡ ጀርመናዊው ሳይንቲስት የታለ?›› አለ ቬኒቺኒ

ኤዲ ተገርሞ ቪንቺኒ ላይ አፈጠጠ፡፡ ጎርዲኖን አይፈልጉትም፡፡ ታዲያ
ማንን ነው የሚፈልጉት?ተ

የቶም ሉተር ድምፅ ተሰማ ‹‹እዚህ ነው ያለው፤ በእኔ ቁጥጥር ስር  ነው›› አለ ሉተር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን እየደገነ፡፡ተ

ኤዲ የበለጠ እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡ የፓትሪያርካ ማፊያ ቡድን ለምንድን ነው ካርል ሃርትማንን ማገት የፈለገው?› ‹‹ሳይንቲስቱን ለምንድን ነው የምትፈልጉት?› ሲል ጠየቀ፡፡

ቀበል አድርጎ ‹‹ተራ ሳይንቲስት እንዳይመስልህ የኒኩሊየር ፊዚስት
ነው›› አለ ሉተር፡

‹‹እናንተ ናዚ ናችሁ?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡

‹‹አይደለንም፧ እኛ ዲሞክራቶች ነን፡፡ እነሱ ሳይንቲስቱን አግተን
እንድንሰጣቸው ስራ አዘውን ነው፡ ረብጣ ገንዘብ ይከፍሉናል›› አለና ቪንቺኒ
ተንከተከተ፡

ሉተርም ‹‹እኔ ዲሞክራት አይደለሁም፡፡ የጀርመን አሜሪካን ትብብር
ማህበር አባል ነኝ፡፡ ይህ ማህበር በናዚ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ
የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው፡፡ ሂትለር ራሱ ነው ከአገር አምልጦ የወጣውን
ሳይንቲስት አፍኜ ወደ ጀርመን እንዳመጣው ያዘዘኝ›› አለ፡፡ ሉተር ይህን
ሲናገር በኩራት ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ሰዎች ከፍዬ የማሰራቸው እኔ ነኝ፡፡ ስለዚህ ዶክተር ፕሮፌሰር ሃርትማንን ወደ ጀርመን መልሼ እወስደዋለሁ፡
ሳይንቲስቱ እዚያ በጣም ይፈለጋል›› አለ፡

ኤዲ ከሃርትማን ጋር ዓይን ላይን ግጥም አለ፡፡ ሰውዬው ፍርሃት
ጨምድዷቸዋል፡ ኤዲ ወዲያው ፀፀት ገባው፡፡ ሳይንቲስቱ ወደ ጀርመን
ሊመለሱ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የኤዲ ጥፋት ነው፡፡

‹‹ምን ላድርግ ባለቤቴን ስላገቱብኝ ነው የተባበርኳቸው›› አለ፡፡

የሃርትማን አስተያየት ተለወጠ ‹‹ይገባኛል›› አሉ ሳይንቲስቱ ‹‹እንደዚህ
አይነት ክህደቶችን ጀርመን ውስጥ ለምደናቸዋል፡ አንዱን ለማዳን ስትል
ሌላውን አሳልፈህ ትሰጣለህ፡ ምንም ምርጫ አልነበረህም፡፡ በዚህ ራስህን አትውቀስ›› አሉት፡፡
👍12
ኤዲ ሳይንቲስቱ በዚህ ወቅት ሊያጽናኑት በመሞከራቸው ተገርሟል፡

ኤዲ ወደ ኦሊስ ፊልድ ዞሮ ‹‹ለምንድነው አስመሳይ ሰው አይሮፕላን ውስጥ ያሳፈራችሁት?››

‹‹ጎርዲኖ ለፖሊስ መረጃ እንዳይሰጥ ሊገድሉት እንደሆነ መረጃ ደረሰን፡፡ አሜሪካ እንደደረሰ ይመቱታል፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖ በዚህ አይሮፕላን
እንደሚሄድ የሀሰት መረጃ ለማፊያዎቹ አቀበልናቸውና እሱን አስቀድመን
በመርከብ ላክነው፡፡ ጎርዲኖ እስር ቤት መግባቱን የማፊያ ቡድኑ ሲሰማ
መሸወዱን ያውቃል››

‹ለምንድን ነው ለካርል ሃርትማን ጥበቃ ያላደረጋችሁላቸው?,,

እሳቸው በዚህ አይሮፕላን ላይ እንደሚሳፈሩ አናውቅም፡፡ የነገረን
ሰው የለም፡፡››

ጆ የሚባለው ወሮበላ በአንድ እጁ ሽጉጡን በሌላ እጁ የሻምፓኝ ጠርሙስ ይዞ ‹‹እዚህ ያሉት ተሳፋሪዎች በፍርሃት ረጭ ብለዋል፡ ስለዚህ
ትንሹ ልጅ እነሱን መቆጣጠር ይችላል›› አለው ቪንቺኒን፡፡

ቪንቺኒም ‹‹የታለ የባህር ጠላቂው መርከብ?›› ሲል ሉተርን ጠየቀው፡

‹‹በጥቂት ጊዜ ውስጥ እዚህ ይደርሳል›› አለ ሉተር፡

‹‹በል እንግዲህ ሉተር ስራችንን ጨርሰናል ገንዘቡን ስጠን›› አለ ቪንቺኒ፡፡

ሉተር ሳምሶናይት ቦርሳ አወጣና ለቪንቺኒ አቀበለው: ቪንቺኒ
ቦርሳውን ሲከፍተው ረብጣ ገንዘብ አለበት፡፡

‹‹አንድ መቶ ሺህ ዶላር ነው›› አለው ሉተር፡፡

‹‹እስቲ ቼክ ላድርግ›› አለና ቪንቺኒ ሽጉጡን አስቀምጦ ቦርሳውን ጉልበቱ ላይ አኖረና ገንዘቡን መቁጠር ጀመረ፡፡ ሉተርም ሲቆጥር አይቶ
‹‹ይሄን ሁሉ ለመቁጠር ብዙ ሰዓት ይወስድብሃል›› አለው

ሁሉም ሰው ቪንቺኒን ገንዘቡን ሲቆጥር አፍጦ ያየዋል፡፡ ጆ ተዋናይዋን
ሉሉ ቤልን አወቃትና ‹‹አንቺ የፊልም ተዋናይ  አይደለሽም?›› ሲል
ጠየቃት፡፡ ሉሉ ፊቷን አዞረች፡፡ ጆ ከጠርሙሱ ላይ መጠጡን ተጎነጨና
ዳያና ላቭሴይን ‹‹ጠጪ›› ብሎ ጠርሙሱን አቀረበላት፡፡ እሷ በጥላቻ ፈንጠር አለች፡፡ ‹‹አዎ ይሄ ያሰክርሻል›› ብሎ ቀሚሷ ላይ መጠጡን ሲደፋው ዳያና ጮኸችና እጁን ገፋ አደረገች፡፡ በመጠጥ የራሰው ቀሚሷ ሰውነቷ ላይ
ተጣብቆ ገላዋን በግልጽ ያሳያል፡፡

እንዲህ አይነት ነገር ጠብ ሊያጭር መቻሉን ኤዲ ተገነዘበና ‹‹ተው››
ሲል ተቆጣ፡፡ ወሮበላው የኤዲ ቁጣ ምንም አልመሰለውም፡፡ ጠርሙሱን
ጣለና ጡቷን ያዝ ሲያደርገው ዳያና ጮኸች፡፡
ወዳጇ ማርክ ‹‹ተዋት አንተ ወንበዴ!›› ሲል ተሳደበ በመቀመጫ ቀበቶው ታስሮ እንደተቀመጠ፡ ወሮበላው ታዲያ ቀልጠፍ አለና ማርክን በሽጉጡ አፉን ሲለው ደሙ ተንፎለፎለ፡፡
ኤዲም ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ተው በላቸው›› ሲል ለመነው፡፡

‹‹እንደዚህ ያለች ሴት ከዚህ ቀደም ጡቷን አልተዳሰሰች ከሆነ የመዳበሻ ጊዜዋ አሁን ነው›› አለ ቪንቺኒ፡፡
ጆ በዳያና ቀሚስ ስር እጁን ሲሰድ እጁን ለማስጣል ታገለች፡፡ ነገር ግን
እሷም ወንበሯ ላይ በመቀመጫ ቀበቶ ታስራ ስለነበር እጁን ማስጣል
አልቻለችም::

ማርክ የመቀመጫ ቀበቶውን ፈታና ሲነሳ ሰውዬው እንደገና አይኑን
መታው፡፡ ቀጠለና ሆዱንና ፊቱን በሽጉጡ እጀታ እየደጋገመ ሲመታው
ማርክም በሚፈሰው ደም ዓይኑ ስለተጋረደ ማየት አቃተው፡፡ ሴቶቹ
ይጮሃሉ፡

ኤዲ የደረሰው ሁኔታ አስደንግጦታል፡ ምንም ደም ሳይፈስ የእገታው
ድራማ እንዲጠናቀቅ ነው የሚፈልገው፡፡ ከዚህ በላይ ግን መታገስ አልቻለም: ጆ እንደገና ማርክን ሊመታ ሲል ኤዲ ህይወቱን ሸጦ
ወሮበላውን እጁን ለቀም አድርጎ ያዘው፡፡

ጆ ራሱን ለማስለቀቅና ሽጉጡን ኤዲ ላይ ለመደገን ቢሞክርም ኤዲ አጥብቆ እጁን ስለያዘው መፈናፈን አልቻለም፡፡ በዚህ ጊዜ ጆ የሽጉጡን ምላጭ ሳበው የጥይቱ ጨኸት ጆሮ ይሰነጥቃል፡ ነገር ግን ሽጉጡ የያዘውን
የጆን እጅ ታግሎ ወደ ታች ስለያዘው የወጣው ጥይት ወለሉን በሳው የመጀመሪያ ጥይት ሲተኮስ ሁኔታው ከእጅ እየወጣ መሆኑ ኤዲ
ታወቀው፡፡ እዚህ ላይ ካልቆመ ደም መፋሰስ ይከተላል በመጨረሻም ቪንቺኒ ጣልቃ መግባት ግድ ሆነበትና ‹‹ጆ ይበቃሃል
አቁም!›› ሲል ጮኸ፡
ጆ ትግሉን ሲያቆም ኤዲም ለቀቀው፡

ጆ በጥላቻ ኤዲን አየው ነገር ግን ምንም አላለም፡

ቪንቺኒም ‹‹መሄድ እንችላለን ገንዘቡን ተቀብለናል›› አለ፡፡

ኤዲ ተስፋው ለመለመ:፡ አሁን ከሄዱ ደም መፋሰስ አይኖርም› አለ
በሆዱ፡ቪንቺኒ ቀጠለና ‹‹ጆ ሴትዬዋን ከፈለካት አምጣት እኔም ልነፋት እፈልጋለሁ፡፡ ከኢንጂነሩ ሰናና ሚስት እሷ ትሻላለች›› አለና ተነሳ፡፡

ዳያና ጮኸች ‹‹እባካችሁ ተዉኝ!››

ጆ የዳያናን የመቀመጫ ቀበቶ ፈታና ፀጉሯን ጎትቶ አነሳት፡ ዳያና የአቅሟን ያህል ታገለች ማርክ ደሙን ከዓይኑ ላይ እየጠራረገ ለጠብ ሲነሳ ኤዲ አየና ‹‹ይገሉሃል›› አለው በለሆሳስ፡፡ ‹‹አይዞ ችግር አይኖርም፡››የባህር ኃይሉ መርከብ እየመጣ መሆኑን እንደሚደርስላቸው ሊነግረው ፈልጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ቪንቺኒ ሊሰማ ይችላል ብሎ ተወው፡

ጆም ቀጠለና ማርክ ላይ ሽጉጡን ደግኖ ዳያናን ‹‹አንቺን እንወስድሻለን፧ አለበለዚያ ወዳጅሽ ዓይን ላይ ጥይት እንለቅበታለን›› አለ ዳያና በድንጋጤ ቆመችና ማልቀስ ጀመረች፡
‹‹እኔ ከእናንተ ጋር እመጣለሁ፡፡ የባህር ጠላቂው መርከብ መምጣት ያስቸግረዋል››
አለ ሉተር

ቪንቺኒ ስለ ጠላቂ መርከብ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ምናልባትም ጠላቂው መርከብ ያልመጣው የስቲቭ አፕልባይን የጦር መርከብ አይቶ ሊሆን ይችላል፡ ስለዚህ ጀልባው ራቅ ብሎ እስኪሄድ ሊጠብቅ ይችላል፡

‹‹አንሂድ›› አለ ቪንቺኒ፡፡ ‹‹በመጀመሪያ እኔ እወጣለሁ፡፡ ቀጥሎ ኤዲ፡፡
በመጨረሻ ጆ ከቆንጆዋ ጋር ትወጣለህ፡፡››

ማርክ ኦልደር ከኤዲ እጅ ለማምለጥ ይታገላል፡፡ ቪንቺኒም ቀጠለና
ሌላውን መርማሪ ‹‹ይህን ሰው አደብ እንዲገዛ
ኦሊስ ፊልድንና ታደርጉታላችሁ ወይስ ጆ በጥይት ይበለው?›› ሲል ጠየቀ፡፡ እነሱም ማርክን
እንዳይንቀሳቀስ አድርገው አጥብቀው ያዙት
ኤዲ ቪንቺኒን ተከትሎ ሲሄድ ሚስተር መምበሪ ሽጉጡን መዞ

‹‹ቁም!›› አለና ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን ደገነ፡፡ ‹‹ወሮበላ ሁሉ ጸጥ በይ!
አለበለዚያ አለቃሽን በጥይት እደፋዋለሁ›› አለ፡ ቪንቺኒም ይህን ሲያይ
ደንግጦ ‹‹ሁላችሁም እንዳትንቀሳቀሱ!›› ሲል ጓደኞቹን አዘዘ፡፡ ነገር ግን
ትንሹ ልጅ የሚባለው ሰውዬ ፈንጠር አለና ሁለት ጊዜ ሲተኩስ መምበሪ
ወደቀ፡ ቪንቺኒም ትንሹ ላይ ጮኸ ‹‹አንተ የማትረባ! ሰውዬው ሊገለኝ
ይችል ነበር እኮ!›› አለው፡
‹‹አነጋገሩን አልሰማኸውም?›› ሲል ትንሹ ልጅ መለሰ ‹‹እንግሊዛዊ እኮ
ነው››
‹‹ታዲያ ቢሆንስ?›› ሲል ቪንቺኒ አምባረቀ፡፡

‹‹በርካታ ፊልም አይቻለሁ ነገር ግን በእንግሊዛዊ ጥይት የተመታ ሰው
የለም፡፡››

ኤዲ መምበሪ አጠገብ ተምበርክኮ ሲያይ ጥይቶቹ ደረቱን በስተው
ገብተዋል፡፡ ደሙ እየተንፎለፎለ ነው ‹‹ማነህ አንተ?›› ሲል ጠየቀው
መምበሪን፡፡

‹‹የእንግሊዝ ልዩ ፖሊስ አባል ነኝ›› አለ መምበሪ በደከመ ድምፅ፡፡‹‹ሳይንቲስቱን ሃርትማንን ለመጠበቅ ነው የተመደብኩት አልሆነልኝም››
አለና አይኑን ዘጋ፤ ትንፋሹም ቆመ:፡

ኤዲ አንድ ሰው ሳይሞት ወሮበሎቹ ከአይሮፕላኑ እንዲወጡ ፈልጎ
ነበር፡ ያሰበው ሊሳካለትም ትንሽ ነበር የቀረው፡፡ ነገር ግን ይሄው አንድ ፖሊስ ተገደለ፡ በትዕግስት ሊታለፍ ይችል ነበር፡፡ ለሰው ህይወት መጥፊያ
የሆነው ደግሞ እሱ ነው፡፡

የእነ ቪንቺኒ ጀልባ ነጂ ሲሮጥ መጣና ‹‹የሬዲዮ መልእክት መጥቷል››
አለው፡:

የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ለአስቸኳይ ጉዳይ ካልሆነ መገናኛ እንዳይጠቀም
ነግሬው አልነበረም?›› አለ ቪንቺኒ፡፡
‹ይሄ በጣም አስቸኳይ ነው፡፡ አንድ የባህር ኃይል መርከብ እየመጣ ነው።
👍19
የኤዲ ልብ ሊቆም ምንም አልቀረውም፡፡ የወሮበላው ቡድን መልዕክት አስተላለፊ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቪንቺኒ ወጥመድ ውስጥ እንደወደቁ አውቋል፡

‹‹ከዳኸኝ›› አለ ቪንቺኒ ኤዲን፡፡ ‹‹ለዚህ ክህደትህ ደግሞ እገልሃለሁ››

ኤዲ የካፒቴኑን ዓይን ሰረቅ አድርጎ ሲያይ ካፒቴኑ ጥረቱን እንደተረዳለትና ባደረገው አክብሮት እንዳለው ከካፒቴኑ አይን ላይ አነበበ፡

ቪንቺኒ ኤዲ ላይ ሽጉጡን ደገነ፡፡

‹‹የቻልኩትን ያህል እንዳደረኩ ሁሉም አውቆልኛል፡ አሁን ብሞትም
አይቆጨኝም›› አለ ኤዲ፡
ሉተርም ለጠቀና ቪንቺኒን ‹‹አንድ ድምጽ  አይሰማህም?›› ሲል
ጠየቀው፡

ሁሉም ጸጥ አለ፡፡ የሌላ አይሮፕላን ድምጽ ነው፡፡

ሉተር በመስኮቱ አሻግሮ ሲመለከት ባህር ላይ የሚያርፍ አይሮፕላን
መሆኑን አወቀ፡ አጠገባቸው ሊያርፍ ነው፡

ቪንቺኒ ሽጉጡን ወደ ታች አደረገ፤ ኤዲ ጉልበቱ ተብረከረከ፡፡ ‹‹ቢሆንስ
አናስኬድም ካሉን በጥይት ነው የምንረፈርፋቸው›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ሌላ ነገር አይታይም›› አለ ሉተር በደስታ በዚህ አይሮፕላን ከባህር ሀይሉ መርከብ በላይ በረን እናመልጣለን›› አለ፡፡

ቪንቺኒ በመስማማት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ጥሩ አስበሃል እንደዚያ ነው የምናደርገው›› አለ፡

ይቀጥላል
👍104
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሶስት (43)


ሜሪ ስልክ በመደወል ላይ ነበረች፡፡ ለፒተር ግሬግሰን ። «መቼ አልሺኝ? ዛሬ» አለ ፒተር ግሬግሰን ‹‹ውዴ ዛሬ ስብሰባ አለብኝ »
«እንዲያ ከሆነ ስብሰባውን እንደጨረስክ እፈልግሃለሁ ። በጣም እፈልግሃለሁ ። ነገ መሄዴ ነው»
«የት ? ወዴት ? ለስንት ጊዜ!»
«ስትመጣ እነግርሃለሁ ። ዛሬውኑ ና ። ማታ»
«እሺ...ይሁን ። እሺ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ። ግን ስብሰባውን… የቂል ሥራ መሰለኝ ። ሊዘገይ አይችልም»
«በፍጹም አይቻልም» አለች ። ሁለት ዓመት ሙሉ ቆይቷል ። ያን ያህል ጊዜ ማቆየቱም ራሱን የቻለ ቂልነት ነበር እብደት አለች በሐሳቧ ። «እሺ እንግዲህ እመጣለሁ » ዘጋ ። ወዲያው ወደ አየር መንገድ ቢሮ ደወለች ፤ቲኬት እንዲይዙላት ። ቀጥላም ወደ እንስሳት ሐኪም ደወለች ፤ ለፍሬድ ማቆያ እንዲያዘጋጅላት...

ያንለት ከሰዓት በኋላ ሜሪ ፌ አሊሰንን ለማነጋገር መደ መሥሪያ ቤቷ ሄደች ። ሜሪ ወደ ፌ መሥሪያ ቤት ከሄደች ወራት አልፈው ነበረና ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል ስትገባ ምንም እንዳልተቀየረና እንደ ተለመደው ምቹ እንደሆነ ተገነዘበች። እምቹው ወንበር ላይ ተቀምጣ እግሯን ፊት ለፊት ዘርግታ ጣቶቿን እየተመለከተች ቀስ በቀስ ሐሳብ ውስጥ ገባች ። ሐሳቡ ጭልጥ አድርጐ ወሰዷት ነበርና ፌ ስትግባ አልሰማቻትም ። «እንቅልፍ እየታገለሽ ነው ወይስ እጸጥታ ቁዘማ ላይ ነሽ ?» የፌ አሊሰን ድምጽ ከሐሳቧ የመለሳት ሜሪ ፈገግ ብላ ፊት ለፊቷ በሚገኘው ወንበር ላይ የምትቀመጠው ፌን በጸጥታ ተመለከተቻት ። «እንቅልፍም ቁዘማም አይደለም። ዝም ብሎ ሐሳብ ነው» አለች ሜሪ ። ፌ «ደግ» በሚል አስተያየት እያየቻት ፈገግታዋን መለሰችላት ። ሜሪ ፌን ስታይ ደስ አላት ይህንንም፡፡ «ናፍቀሽኝ ኖሯል ባክሽ ፤ ሳይሽ በጣም ደስ አለኝ» ስትል ገለጸችላት ። «ድንቅ ነገር ሆነሻል ልበልሽ ወይስ ከዚያም ከዚያም ስለምትሰሚው ሰልችቶሻል ?» አለች ፌ አሊሰን በፈገግታ በርታ። በፌ አሊሰን ፊት ላይ ያየችው ደስታ ተጋባባትና ሜሪም መሳቅ ጀመረች ። ቀጥላም «ድንቅ ነሽ መባል ምኑ ይሰለቻል ብለሽ» ስትል ተናገረች ። ይህን ስትል ደስ አላት ። ለፌ አሊሰን ባይሆን ይህን እውነት እንኳ ለመናገር አስቸጋሪ እንደነበር ታውቀዋለች ። «ዛሬ ደርሼ ዱብ ስል ለምን መጣች ? የሚል ጥያቄ እንደሚመጣብሽ መቼም የታወቀ ነው» አለች ሜሪ አዳምሰን ። «ጥያቄው ብልጭ ብሎብኝ ነበር» ፌ ግምቷን አረጋገጠችላት ። ፊት ለፊት ፤ ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ ። ቦግ ድርግም ፈገግታ ተለዋወጡ ። ከዚያም ሜሪን ሐሳብ ጠለፋትና ወደ ቁዘማዋ ገባች ። ስለተወሰነ ጊዜ ጸጥታ ሆነ ። ከዚያም ሜሪ ድንገት ቀና ብላ በቦዛዛ ድምጽ ማይክልን አገኘሁት'ኮ» ስትል ተናገረች ። «ሊፈልግሽ መጣ ? »
«መልሱ አዎም ሊሆን ይችላል አልመጣምም ሊሆን ይችላል ። ነገሩንኳ የፈለገው ያገኘውም ሜሪ አዳምሰንን ነው» ቀጥላም ማይክል ለምን እንደፈለጋት ባጭሩ ነገረቻት ። «ሦስቱም ሰዎች ይህን ያህል ለመኑሽ »
«ሽንጣቸውን ገትረው»
«ደህና ምልክት ይመስላል ። በነገራችን ላይ. . . ከሦስቱ አንዱም እንኳ ማን መሆንሽን አላጤነም'!? »
«ሁለቱ ወንዶች አላወቁም ። ማሪዮን ግን አውቃለች ። እንዲያውም ማይክልን የላከችውም አውቃ ነው የሚል ግምት አለኝ» ለተወሰነ ጊዜ ጸጥ አሉ
‹‹ስትገናኙ ምን ስሜት ተሰማሽ ? »
«ከማን ጋር ? »
«ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር»
«አስቀያሚ ፤ አስቀያሚ ስሜት ነበረ የተሰማኝ ። ልክ እንዳየኋት ያደረሰችብኝ ስቃይ ሁሉ ፍንትው ብሎ ታየኝ ። ጦላኋት››
‹‹እሺ››
«ምን ልበልሽ ? ያላሰብኩት ነገር አልነበረም የናቴ ምትክ እንድትሆን የተመኘኋት ፤ ብትወደኝ ብዬ ያለምኩዋት የማይክል ሚስት ለመሆን እምበቃ መሆኔን እንድትቀበል የጓጓሁት ። ያ ሁሉ ነገር ትዝ አለኝ»
«አሁንም የማይክል ሚስት ለመሆን አትበቂም እምትል ይመስልሻል ?»
«ያሁኑን አላውቅም ። ብቻ እንጃ ። አየሽ ያንለት እንዳየኋት ብዙው ነገሯ ተለውጦአል ። እንደመሰለኝ የፈጸመችው በደል ከብዷታል ። የተጸጸተችበት ይመስለኛል ። ለኔ ሳይሆ ለልጅዋ ይሆናል ። እንደገመትኩት ከሆነ ማይክልም የሚመስለውን ያህል ደስተኛ አይደለም»
«ደስተኛ አሊመሆኑ ሲሰማሽ ልብሽ ምን አለ ?»
«ቀለል አለኛ»

ሆኖም ለማጋነን የፈለገችውን ያህል አላጋነነላችም ቀለል ማለቱ ። እንዲያውም በኀዘን የተሰበረ ድምጽ ነበረ። ለተወሰነ ጊዜ ጸጥታ ሆነ ። «ቆይቼ ሳስበው ግን» አለች ሜሪ ጸጥታውን እየገሰሰች ፤ «ቆይቼ ሳስበው ግን ፤ እሱን ደላው ከፋው ለኔ ያው እንደሆነ ገባኝ ። የኔና የሱ ነገር ያበቃ ነገር ነው ፌ። ዛሬ እሱም አያውቀኝ እኔም አላውቀው ። ሁለታችንም በጣም ተለውጠናል ። ማን መሆኔን ቢያውቅ ሥራዬ ብሎንኳ ሊያነጋግረኝ አይፈልግ ይሆናል ። እኔ ናንሲ ማክአሊስተር ያልሆንኩትን ያህል እሱም ማይክል ሂልያርድ አይደለም »
«ያን ያህል እንደተለወጠ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ!»
«አየሁታ ! መራራ ፤ ጥድፍድፍ ሰው ሆኗል ። ልቡ ቀዝቅዞ ሰብአዊ ስሜቱ ሞቷል ።እዚሀ ሁሉ ውስጥ ምን እንዳለ እንጃ…. ያየሁት ባህርይ ግን አብዛኛው አዲስ ነው»
«የፈለጉት የማጣት ፤ ተስፋ የመቁረጥ ፤ የጥልቅ ሀዘን ስሜት አይታይበትም ?››
«የለም አልታየኝም ። ይልቅ እኔን ስለመክዳቱ ፣ ስለመምጣቱስ ምን ይሰማሻል ? ልትይኝ የፈለግሽ መሰለኝ ። ቁም ነገሩ ይህ አይመስልሽም ?››
«እኔ እንጃ ። እኔ እንኳ ይህን አላሰብኩም። ግን እስካሁን ይህ አይነቱ ስሜት አለብሽ ማለት ነው? በትለይም እንደከዳሽ ነው እሁንም የቆጠርሽው ? »
‹‹እንደከዳኝ እንጂ እንደሌላ ልቆጥረው እችላለሁ ? » አለች ከረር በለ ድምፅ « ፌ፣ ማይክልን እንዴት መሰለሽ እምጠላው ! ››
ያን የህል እጠላዋለሁ ብለሽ ካሰብሽ አሁንም ሀሳብሽ ሙሉ በሙሉ እሱ ላይ ነው ማለት ነው»

ናንሲ ይህ እውነት እንዳልሆነ ሽንጧን ገትራ ትከራከረች ። ምን ያህል እንደምትጠላው እምርራ ተናገረች ። ይህን እያደረገች ሳለችተም እንባዋ ተናነቃት ። አለቀሰች። ፌ አሊሰን ይህን ስታይ ነገሩን ለማለስለስ ፣ ሜሪን ላማፅናናት አልሞከረችም ። ይልቁንም የተነሳውን ነገር ፍርጥ ለማድረግ «ናንሲ ፤ ንገሪኝ ። ማይክልን ታፈቅሪዋለሽ ወይስ ፍቅርሽን ጨርሰሻል ? » ስትል ጠየቀቻች ። ናንሲ ብላ የጠራቻት አውቃ ነበር ። ናንሲ የፌ አሊሰንን ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ ፈጀባት ። ስትመልስም ጣራ ጣራውን እያየች ሲሆን ድምጺም ደከም ያለ ነበረ ። « ናንሲ አሁንም ታፈቅረው ይሁናል ። መቼም የናንሲ ርዝራዥ ከውሰጧ አይጠፋም ። እሷ ትወደው ይሆናል ። ሜሪ ግን ማይክልን አትወደውም ። ሜሪ ማለት እኔ ነኝ ፣ፌ ። አዲስ ህይወት፤ አዲስ ዓለም ያለኝ ሰው ነኝ ። ልወደው አልችልም ማይክልን!»
«ለምን እትችይም ?››
«ምክንያቱም እይወደኝም ። እርሉን መርሳት ኣለብኝ፣ ፌ ፈጽሞ መርሳት አለብኝ ።ይህን ወስኛለሁ ፣ አውቀዋለሁ ። ስለዚህ ይህን ላማክርሽ ፣፡ ስለማይክል ፍቅር አንስቼ ኣንገትሽ ስር ተወሽቄ ላለቅስ አይደለም የዛሬው አመጣጤ ። የተሰማኝን ነገር ላንድ ስው መንገር እንዳለብኝ በመግመት ነው። ለፒትር ብነግረው ጥሩ ነበር፡፡ ግን ይህን ለሱ መንገር ደግሞ የማይቻል መስሎ ታየኝ ። መንፈሱን ይረብሻዋል ብዬ ገመትኩ ። ለለዚህ ቀለል እንዲለኝ ላንቺ መንገር እንዳለብኝ ገባኝ ። ሙጣሁ»
👍16
‹‹መምጣትሽም ፤ መንገርሽም ጥሩ ነው። ደለ ብሎኛል ግን እልብ ውስጥ የሰረፀን ነገር እንዲህ በቀላሉ በቃኝ ፤ ተውኩት በማለት ብቻ ማራገፍ የሚቻል እይመስለኝም።. . . ያን ያህል ቀላል እይደለም»
«የተራገፈውኮ የዛሬ ሁለት አመት ነው ። እኔ ሙጭጭ ብዬ ነው እንጂ ። ሙጭጭ ማለቴን ደግሞ ስክድ ነበር ። አሁን ግን ግልፅ ሆኖልኛል ። እና….. ›› ንግግሯን ድንገት አቋረጠችና ቆና ብላ ተቀመጠች ። ከዚያም ፌ አሊሰንን እየተመለከተች…. «ነገ ለጉዳይ ወደ ቦስተን መሄዴ ነው» ስትል ተናገረች
«ለምን ጉዳይ ?»
«ሁሉን ነገር የማራገፍ ጉዳይ ። እኔና ማይክ ኣንድ ላይ በነበርንበት ጊዜ በጋራ የአደረግናቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ ። እስከዛሬ ድረስ ማይክል ይመለሳል ፣ ያስበኛል ፤፣ ይፈልገኛል እያልኩ የተውኳቸውን ነገሮች ማለቴ ነው ። ለፍቅራችን ሀውልት እንዲሆኑ ብዬ ነበር የተውኳቸው ። አሁን በቃ ። ሄጄ አንድ ነገር ላደርግ ወስኛለሁ»
«እምትችይ ይመስልሻል ?»
«በሚገባ» አለች ፌ እሊሰንን እንኳ ቆራጥ መስሎ በተሰማት ድምፅ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍14🥰1
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ ሶስት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
ሰዓቱ ዘጠኝ ሰኣት ከ20 ሆኗል..ፕሮፌሰሩ ሳሎን ውስጥ ከወዲህ-ወዲያ እየተወራጨ ይሽከረከራል….ግማሽ መላጣው ፊቱን ጨምሮ በላብ ተዝፍቋል…በዚህ ቀዝቃና ነፋሻማ ለሊት እንዲህ አይነት ላብ ከከፍተኝ ንዳድ ካለበት በሽታ እንጂ ከጭንቀትና ንዴት የተነሳ ሆነ ቢባል ማን ያምናል፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ
‹‹እ..እስከአሁን አላገኛችሆትም….?››በቁጣ ድምፅ ጠየቀ
‹‹አላገኘሁትም….በሶስት የተለያየ መኪና በከተማዋ መንገዶች እያሰስናት ነው፡፡››
‹‹ግን ምን አይነት ዝርክርኮች ናችሁ በፈጣሪ….ፕሮፌሽናል ነን ..ምንጥቅርሴ እያላችሁ ያንን ሁሉ ብር ስትጠይቁ እኮ እንኳን አንድ እራሷን በቅጡ መከላከል የማትችል ሴት ይቅርና ጠቅላይ ሚኒስቴሩን እኮ ከቤተመንግስት ገብታችሁ መግደል የምትችሉ ነው ምታስመስሉት››
ወቀሳውን መከላከል በሚያስችል ጠንከር ያለ ንግግር፡፡‹‹ፕሮፌሰር …ችሎታችንን በተመለከተ እስከምን ጥግ እደሚሄድ በዚህ ከተማ ከአንተ በላይ ምስክር ያለ አይመስለኝም…እንግዲህ በማንኛውም ስራ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ስሀትት ይፈጠራል››ሲል መለሰለት
‹‹ስለትናንት ጀብዶችሁ ማውራት ምን ይረባል…?ትሰማኛለህ..አንዳንድ ስራዎች ፍፅምናን ይጠይቃሉ….እንደእዚህ አይነት ስራዎች ለስህተት ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆን አለባቸው….ከስህተታቸው ጀርባ እኮ ታላቅ ውድቀትነው የሚያስከትሉት…ድምጥማጥን የሚያጠፋ ውርድት….ወለል ብሎ የተከፈተ እስርቤት…አሁን ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ አመልክታስ ከሆነ ማን አወቀ?››
‹‹አይ እሱን በአካባቢውና በቅርብ ርቀት ባሉ ፖሊስ ጣያዎች ሁሉ ዝር እንዳላለች በየጣቢያው ባሉ የእኛ ሰዎች አማካይነት አረጋግጠናል››
‹‹እሺ እሱም አንድ ነገር ነው….ለመሆኑ ያንን ኤሌያስ ተብዬውንስ ሄዳችሁ አረጋገጣችሁ?››
‹‹‹አዎ መልሰን ሰው ልከን ነበር….እንደውም ሰለእሱ ጉዳይ ልደውልልህ ስል ነው ቀድመህ የደወልክልኝ..››
‹‹ምን አዲስ ነገር አለ እንዴ?›› በስጋትና ጥርጣሬ ጠየቀ
‹‹እራሱን ስቶ ቤተሰቦቹ አግኝተውት ወደ ሆስፒታል ወስደውታል››
ጭንቅላቱን ያዘ‹‹ወደሆስፒታል? ያንተ ያለህ..አልቆልናል በለኛ››
‹‹አይ አላለቀልንም..ቤተሰቦቹም ይመስለኛል ምንም የጠረጠሩት ነገር ስለሌለ ወደእናንተው ሆስፒታል ነው የወሰድት››
‹እሱም አንድ ነገር ነው….ግን እስከአሁን ለሆነ ሰው የሆነ ነገር ብሎ ከሆነስ?››
‹‹አይመስለኝም….አሁን ሆሰፒታል ደውዬ ማጣራት እንደቻልኩት ሰውዬው እራሱን ስቷል፡፡ አሁን ቀዶ ጥገና ሊያደርጉለት ማደንዘዣ ሰጥተውታል…..እንደሰማሁት ከሆነ ቀዶ ጥገናው ቢያንስ ሶስት ሰአት ይፈጃል..ስለዚህ አስበን የሆነ ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ ያለን ይመስለኛ፡፡››
‹‹በቃ እሺ ..ደግሞ በየደረሳችሁበት አሻራ ምናምን እንዳታዝረከርኩ…ምን ላድርግ ይሄንንን ልንገራችሁ እንጂ..በል አሁን ከፈለክ ሳማይ ውጣ..ከልሆነም መቀመቅ ግባ..ይቺ ለሊት ከመንጋቷ በፊት ያቺን ሴት አግኝተህ አጥፋልኝ…፡፡ይህንን ካሳካችሁ ከተነጋገረንው እጥፍ ክፍያ ይጠብቃችሆል..ካልተሳካላችሁ ግን አብረን እንጠፋታለን፡፡የኤልያስን ጉዳይ ምን ማድረግ እንደምችል አስብበት እና ደውልላችሆለው››
‹‹እሺ ጌታዬ››
ስልኩን ዘጋውና ወደጠረጳዛው ሄደ፡፡ ውስኪ ያያዘውን ጠርሙስ አነሳ ፡፡አፉ ላይ ደቅኖ ገርገጭ ገርገጭ አድርጎ ጠጣለት….፡፡አዎ ስሜቱን ቢያስተካክልለት …አይኖቹን ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ገዝፎ ከሚታየው ከእጮኛው ፎቶ ላይ ሰካ…..ዶ/ር ሰጲራ…በጣም ነው የማፈቅርሽ..በጣም..››አለና በእጁ ይዞ የነበረው ጠርሙስ ልክ እንደ ዲስከስ ፉር አድርጎ ወረወረው ….ተምዘግዝጎ ከፎቶ በታች ካለ ግድግዳ ጋር ተላተመና ፍርክስስ ብሎ ተበተነ…በአቅራቢያው ያለ የሳሎን ወለል በጠርሙስ ስብርባሪ እና በውስኪ ፈሳሽ ፍንጥቅጣቂ ተሞላ
ድጋሚ ስልኩን ካስቀመጠበት ጠረጳዛ አነሳና ደወለ….ጥሪው ሰልችቶት ሊዘጋ ሲል ተነሳለት
‹‹ሄሎ ….ሼኪ ››
‹‹ሄሎ ማን ልበል…››ጎርናና...ያልተሞሸ የለሊት ድምጽ
‹‹ጭራሽ ማን ልበል?››እሱ ለሊቱን ሙሉ ነፍስ ግቢ ነፍስውጪ መከራውን ያያል የሆስፒታሉ ትልቁ ባለድርሻ ሀገር ሰላም ብለው እንቅልፋቸውን መለጠጣቸው አበሳጭቶታል፡፡
‹‹እ..ፕሮፌሰር..ምነው በለሊት?
‹‹በለሊት…አስር ሰዓት እየተቃረበ እኮ ነው››
‹‹ለ85 ዓመት ሽማግሌ 10 ሰዓት ለሊት አይመስልህም?››
‹‹አይመስለኝም ..ለ85 ዓመት ሽማጊሌ ቢያንስ ሌላው ይቅር ለፀሎት በዚህን ሰዓት ንቁ መሆን የለበትም…?››
‹‹ፕሮፌሰር ምነው እንደምታስተምራቸው ተማሪዎች ወረድክብኝ..በሰላም ነው?››
‹‹ምን ሰላም አለ…ነገሮች ምስቅልቅላቸው ወጥቷል…››
‹‹ተረጋጋ የነገሮች መመሰቃቀል ሳይሆን አደገኛው የገዛ አይምሮህ መመሰቃቀል መሆኑን መቼም ለአንተ አልነግህም…መጀመሪያ የተመሰቃቀለውን አዕምሮህን አረጋጋው …ከዛ ሌላውን ለማስተካከል መንገዱ ይገለጽልሀል››
‹‹ወይ እርሶ …ነገሩ እንዲህ ቀላል አደረጉት እንዴ?››
‹‹ቀላል እዳልሆነማ በዚህ ሰዓት ደውለህ መአት ስታወራ መገመት ችያለሁ››
ያንን በቀደም ያማከርኮትን ነገር ዛሬ ማታ ለማድረግ ተንቀሳቅሰን ነበር.. አንደኛውን ማድረግ ብንሞክርም ሁለተኛው ግን እስከአሁን ማሳካት አልቻልንም….፡፡››
‹‹እስኪ ልገምት..ያንተዋን ነው አይደል ያለተሳካላችሁ?››
‹‹አዎ በምን አወቁ ?ኤልያስ ልክ እንደተመታ እራሱን ከመሳቱ በፊት ደውሎ አስጠንቅቋት ስለነበረ በለሊት ከቤቷ ወጥታ ተሰውራለች.እስከአሁን ልጆቹ እያሰሶት ቢሆንም እልተሳካላቸውም፡፡››
‹‹አይ.. የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ…መጀመሪያ በዲፕሎማሲ እስከመጨረሻ ሞክር ብዬህ ነበር እኮ››
‹‹ያልሞከርኩ ይመስሎታል ..እምቢ አለች …ደጋሜ ሞከርኩ ለመንኳት አስፈራራዋት እምቢ አለች››
‹‹ምነው ወደፊት ይህችን ሀገር መምራት ፈልጋለሁ ትል የለ እንዴ? ታዲያ የገዛ ፍቅረኛህን ማሳማን ሳትችል ይሄንን ውስብስብና ሙልጭልጭ ህዝብ እንዴት አድርገህ ልታሳምን ነው?››
‹‹እርሶ ደግሞ…አሁን ለዚህ አይነት ተራባ አሁን ጊዜው ነው››
‹‹አይደለም አፉ በለኝ..ለመሆኑ ያኛውስ በትክክል ተጠናቋል..ማለት የኤልያስ?››
‹‹ያበሳጨኝ እሱ አይደል…እሱም ክፍኛ ቆስሎ እራሱን ቢስትም እስከአሁን አልሞተም›››
‹‹እና››
‹‹እናማ..ቤተሰቦቹ ወደ ሆስፒታል አምጥተውት ዶክተሮች ቀዶ ጥገና እያደረጉለት ነው››
‹‹አይ ፕሮፌሰር..ዛሬ ሁሉን ነገር አጨመላልቀኸዋል››
‹‹አውቃለው..እሱን እራሴ እንደምንም አስተካክለዋለሁ…..አሁን የደወልኩሎት አንድ ሰዓት ቢሮ እንድንገናኝ ነው….ለአቶ ንገሩት››
‹‹አንድ ሰዓት ቢሮ..ትቀልዳለህ….?ከባለደረባችን አንዱ በቤቱ ተተኩሶበት ለህይወቱ እያጣጣረ ሌላዋ ያለችበት ሳይታወቅ እኛ በግልጽ ሰው እያየን ቢሮ ለዛውም ባልተመደ ሰዓት…?››
‹‹እና የተለየ ሀሳብ አሎት?፡፡››
‹‹መልሼ እደውልልሀለው…እከዛው እራስህን አረጋጋ››
ስልኩን ዘጋና የኤልያስን ጉዳይ ከኮማው ከመንቃቱ በፊት እንዴት አድርጎ እልባት እንዲሚያበጅለት ማሰላሰል ጀመረ….
//////
ዶክተር ሰጵራ የገባችበትን ክፍል ዙሪያ ገባ በደንብ ካተመለከተች ቡኃላ አጠገቧ ያገኘችው የፕላስቲክ ወንበር ላይ ተቀመጠች….
👍27
አጋቾ በራፍን ዘግቶ ከዛው አካባቢ ሳይንቀሳቀስ ግድግዳውን ተደግፎ ቆሟል…..ሲጋራውን እና ላይተሩን ከቀኝ ኪሱ አወጣ… ለኮሰ…ጪሱን በጥልቀት ወደውስጡ እየሳበ ለሰከንዶች አቆይቶ ይለቀዋል..እየተትጎለጎለና ክብ እየሰራ አየሩን ይሞላዋል… በዛ ክብ ውስጥ አሻግሮ እሷን ይመለከታታል… ያለብዥታ..ያለምንም የአይን እርግብግብታ….፡፡‹.ይህቺ ሴት ከእሱ ሴት ጋር በጣም ትመሳሰላለች….››ሲል አሰበ በውስጡ፡፡ከከዳችውና እያፈቀራት ጥላው ከተሰደደችው ፍቅረኛው ጋር..የገዛ ጓደኛውን ተከትላ ከሄደችው ፍቅሩ ጋር.. ከውስጡ ሊቆጣጠረው የማይችለው ቁጣ ሲቀጣጠል ይታወቀዋል‹‹….አብዬት እቺ እሷ አደለችም..እራስህን ተቆጣጠር…እንዳትጎዳት፡፡››እራሱን ለመገሰፅ የሚቻለውን መጣር ጀመረ….እጁን ወደግራ ኪሱ ሰደደና የአረቄ ብልቃጥ ይዞ ወጣ.. አንደቀደቀው፡፡
ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ዶክተር በጣም ፈራችው..እያየችው ስሜቱ እየተቀያየረ ነው….ዛሬ በቃ ሙቺ ተብሎ ከእግዚያብሄር ትዕዛዝ ተላልፎብኛል እያለች በማሰላሰል ላይ ሳለች…በእጁ የቀረችውን የሲጋራ ትርኮሽ የጣውላ ወለል ላይ ጥሎ በእግሩ ጭፍልቅልቅ አደረጋትና ከአረቄው አንዴ ተጎንጭቶ ብልቃጦን በግራ እጁ እንዳንጠለጠለ ወደ እሷ ተጠጋ …፡፡በተቀመጠችበት መነሳት ባትችልም እራሷን ወደኃላ ለጥጣ ከፕላስቲክ ወንበሩ ጋር በመለጠፍ ለመሸሽ የማይሆን ሙከራ ሞከረች ፡፡ ጨምድዶ ያዛትና ወደ ላይ ጎትቶ አስነሳት….አረቄ የያዘ እጁ በወጋቧ አዙሮ ያዛትና ወደ እሱ ስቦ ከሰፊ ደረቱ ጋር አጣበቃት…፡፡ጡቶቹ ከጠናካራ ደረቱ ጋር ሲጋጩ የመጨፍለቅና የህመም ስሜት ተሰማት….ከእሱ ትንፋሽ ወደእሷ የሚደርሰው ሽታ ከቅድሙ በላይ አስጠሊታ ሆነባት…
‹‹ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹ምነው ትንፋሼ አንገሸገሸሽ..እንቺ ይሄን ስትጠጪ ይተውሻል›› ብሎ በግድ ህጻን ልጅ ጡጦ እደሚግት አፏን ፈልቅቆ አረቄውን በጉሮሮዋ አንደቀደቀው….፡፡
እንዳዛ ያደረገው ሳትዘጋጅ ስለሆነ ሁለቴ ወደውስጥ እንዳስገባች ትን አላት..ከአፎ አላቀቀውና ብልቃጡን ወረወረው….ከዛ ነፃ በሆኑ ሁለት እጆቹ ሙሉ በሙሉ ተሸከማትና አልጋው ላይ ወረወራት…
‹‹ምን እያደረክ ነው..?እጮሀለው….ተወኝ›››
‹‹አምቦርቂው…..ግን ልንገርሽ ጉሮሮሽ ይሰነጠቃል እንጂ ማንም ደፍሮ ወደእዚህ አይመጣልሽም..ምን አልባት አሳዳጆችሽ ሰምተው ሊመጡ ይችሉ ይሆናል ››
‹‹በፈጠረህ….በምትወደው››
‹‹ምንም የምወደው የለም›› አለና….ከላይ ለብሳው ነበረውን ካፖርት ጫፍን ያዘና ሞሽልቆ ከላዬ ላይ አወለቀው…፡፡እጇ የተገነጠለባት መሳለትና ድምፅ አውጥታ ጮኸች፡፡ አፎን በአስፈሪ መዳፉ አፈናት በቀኝ እጁ የለበሰችውን የጨርቅ ሱሪ ከላይ ይዞ ወደላይ ጎተተው….እግሮቾን አንድ ላይ አጣምራ ያሰበውን እዳያደርግ ለመከላከል ሞከረች…አፎ ላይ የከደነውን እጁን አነሳና በሁለት እጆቹ የሱሪዋን ጠርዝ ግራና ቀኝ ይዞ ወደታች ሸረከተው……በግራ በኩል ተመሳሳዩን አደረገ..ከዛ ሞሽልቆ ከላዬ ላይ ሙሉ በሙሉ አንሰቶ ጣለው..፡፡
በዚህ ጊዜ ወሰነች….ተስፋ ከመቁረጥ ተመዘዘ ውሳኔ.. በቃ ከዚህ በላይ መታገል ይበልጥ ለመጎዳትና በራስ ላይ ስቃይን መጨመር ነው እንጂ ሌላ የምታተርፈው ነገር እንደሌለ አሰበች..ይኅን የህክምና ሰው ስለሆነች በልምድ ታውቀዋለች….ቡዙ ግዚ ሴቶች በመደፈር ታሪክ ውስጥ በጣም ጉዳት የሚደርስባቸው ከግንኙነቱ በላይ በትግልና እራሳቸውን ለማትረፍ በሚያደርጉት መፋተግ ነው..እርግጥ ለራሳቸው ክብር ሲሉ እስከመጨረሻው ህቅታ ለሚፋለሙ ሴቷች ክብር አላት…አሁን ግን እሷ ያንን ማድረግ አትችልም…አራሷን ከትግል ሙሉ በሙሉ አላቀቀች…፡፡ከላይ የለበሰችውን ልብስ ወደ ላይ ሞሽልቆ ሲያወጣ በፍቃደኝነት ተባበረችው……ጡት ማስያዣዋን ሳይቀር አወለቀ…እሷ እየለዘበች ስትመጣ የእሱም የንዴትና የእልህ ስሜቱ እየረገበ መጣ፡፡
እንዳጋጣሚ ከቤት ስትወጣ ፓንት አላደረገችም ነበርና፡፡እንዳጋጣሚ ማታ ስትተኛ ፓንት አውልቆ ቢጃማ ብቻ አድርጎ የመተኛት ልምድ ነበራት …እና ለሊት ኤልያስ ሲደውልላት ከመደናገጧ የተነሳ ቢጃማዋን አውልቃ ሱሪዋን ከመልበስ ውጭ ስለፓንት አስፈላጊነት በወቅቱ አልተገለፀላትም ነበር…እና አሁን ሱሪዋን ቀዳዶ ሲጥለው..ቀጥታ እርቃኖን ነበር ቀረችው...እርቃኖን ካስቀራት ቡኃላ ወለሉ ላይ በሁለተ እግሮች ቆሞ ቁልቁል ያያት ጀመር..እሷ አይኖቾን ጨፍና በቀጣይ የሚሆነውን እየጠበቀች ነው….አዎ አሁን ልብሱን አውልቆ መጥቶ ሊጫወተብኝ ነው……ግን ምን ምርጫ አለኝ…አምላኬ ሆይ አንተ ካልክ ይሁን ››ብላ ስታሰላስል
.እሱ ጎንበስ ብሎ አንደ እጅን እግሯን በሌላ እጁ አንገቷ አካባቢ በመያዝ ሰቅስቆ እንደህፃን ልጅ ወደላይ አቀፈት…..
‹‹‹አረ..እሺ በስርአቱ አድርገው..በፈጠረህ››መልሳ መወራጨት ጀመረች ፡፡እሷ ያሰበችው ወዳ ላይ ሲያቅፋትና ሰያነሳት በፊልም የወሲብ ፊልም ሚሰሩ ፈረንጆች እንደሚፈፅሙት አይነት እሷም ያለመደችውን አይነት ወሲብ ሊፈፅምና ሊያበለሻሻት መስሎት ነበር፡፡ እሱ ግን እንዳቀፋት ጎንበስ አለና አልጋ ልብሱንና ብርደልብሱን ገፎ ከውስጥ አንሶላው ላይ አስተኛት..ከዛ እንሶላውንና ብርድ ልብሱን አልብሶት አልጋ ልብሱን ከላይ ገፈፈና ወደፊት ለፊት ተራመደ …ከዛ አይኖቾን በስሱ ገልጣ እያየችው በራፉን ከፍቶ ወጣና መልሶ ዘጋው..፡፡ባዶ ከፍል ብቻዋን ስትቀር ቅድም ከፈራችው በላይ አሁን ይበልጥ ፈራች…..፡፡
ሊያደርግ የፈለገውን ሳያደርግ ሀሳቡን ቀይሮ መልሶ መውጣቱን አሁንም አላመነችም..አሁንም መላ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው..አረ ውስጧም ጭምር እየተንዘፈዘፈ ነው..፡፡‹‹ገና የእውነት ሀሳቡን ቀይሮ ነው ወይስ የቡድን ወሲብ እንደሚሉት ጎደኞቹን ጠርቶ ሊመጣ ይሆን?›› የሚል ሀሳብ በአእምሮዋ ተፈበረከ፡፡ ብድግ ብላ ከመኝታዋ ተነሳችና እርቃኖን ወለሉ ላይ ቆመች.. ካፖርቷን ከመሬት አነሳችና ለበሰች….ቅስ ብላ ወደ በራፉ ሄደችና ቆለፈችው…. ከዛ ደግሞ ሀሳቧን ቀይራ ከፈተችው..እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ከፈተችው ..እንገቷን አስግጋ ወደ ውጭ ስትመለከት እዛው በራፍ ስር በረንዳ ላይ እልጋ ልብሱን ተከናንቦ ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ አይቹን ሰማይ ላይ የተሰቀለችው ጨረቃ ላይ ተክሎ ሲጋራውን እያቧነነ ነበር፡፡መልሳ ወደ ውስጥ ገባች..፡፡
‹‹አሁን ዝም ብዬ ሳልቀረቅረው ልተኛ.?...ለሊት ላይ የወንድነት ስሜቱ ዳግም አገርሽቶበት መጥቶ ቢከመርብኝስ?አይ መቆለፍ አለብኝ..››አለችና ቆለፈችው፡፡ ሁለት እርምጃ ከሄደች ቡኃላ ደግሞ ሌላ ተቀያሪ ሀሳብ መጣባት..‹‹እንዴ የሰው ሰው በገዛ ቤቱ ውጭ አሳድርሬ እንዴት ይሆናል…ምን አልባት ለሊት ላይ ብርዱን መቋቋም አቅቶት ወደ ውስጥ መግባት ቢፈልግስ….?የራሱ ጉዳይ›› አለችና ተመልሳ የቆለፈችውን ቁልፍ ከፋታ ወደመኝታዋ ሄዳ ተኛች…እንቅልፍ የወሰዳት ግን ምን አልባት ከሳዕታት መገለባበጥ ቡኃላ ነው… ለዛውም በቅዠትና የተሞላ አስጠሊታ እንቅልፍ፡፡

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍241
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ከሎ ሆራ ጥሩ ጥሩ የባራዝ አርጩሜ ይዞ እሱና ጎይቲ በሚዞሩበት መንደር ሲጓዙ በየምክንያቱ ጎይቲ አንተነህን በአርጩሜ
ይገርፋታል” ለሽንት ስትቆም ለምን ቆምሽ፣ እንቅፋት ሲመታት ለምን መታሽ፣ ደክሟት ቁጭ ስትል ለምን ቁጭ አልሽ እያለ
በየምክንያቱ እንዲገርፍ ባህሉ ያስገድዳል" ሴት ልጅ በኋላ ከቁጥጥር ውጭ ሆና እንዳታስቸግር፣ ባሏ እየገረፈ በማሽቆጥቆጥ ቅን ታዛዥ ሽር ያለች አገልጋይ እንድትሆን ያደርጋል"

ካርለት አልፈርድ ማስታወሻ፣ ካሜራ፣ ድንኳኗን በጨርቅ
ከረጢት ይዛ፣ የፍየል ቆዳዋን በመልበስ አብራቸው እየተጓዘች ከሎ
ጎይቲ የሚያደርጉትን ትቃኛለች የከሎ ዘመዶች ለከሎ የሚያደርጉለትን ስጦታም ትመለከታለች"

ከሎ ሆራ እናቱ ዘንድ ስጦታ ለመቀበል ላላ መንደር ሲሄድ፣ ካርለት እጅግ በጣም አዘነች" ከሎም በጣም ተሰማው። እናትዬዋ
እንዳዩት አቅፈው፣ አንገቱን ሲያሻሹ ቆዩና ካርለትና ሚስቱን ሰላም ብለው ትክዝ ብለው ቁጭ አሉ" ለልጃቸው ምን እንደሚያደርጉለት ጨነቃቸው። ለሱ ስጦታ ያዘጋጁለት መካከለኛ መጠን ያለው ሁለት
ቅል ቅቤና አንድ ቅል ማር ብቻ ነው ከሎ የእናቱን ሁኔታ አይቶ ኃዘን ተሰምቶት ዘወር ሲል፣ ካርለት ተጠጋቻቸው"

«ለምን ያለቅሳሉ?» አለች ትንሽ ዐረፍ ካለች በኋላ።

«ይእ! ልጄ የሚያስፈልገውን ያህል ስጦታ አላገኘማ።»

«እርስዎ ለልጅዎ የሚሰጡት ከብት፣ ፍየል... የለዎትም?»

«የለኝም»

«ለምን?»

«ይእ! እኔ ከብት፣ ፍየል... ኖሮኝም አያውቅም ወደፊትም አይኖረኝም" በልጃገረድነቴ ከብቶች፣ ፍየሎች፣ በጎች የአባቴ
ነበሩ" ባል ሳገባ ደግሞ፣ የባሌ ነበሩ። አሁን ባሌ ሞቷል፤ የከሎ አባት ቢኖር ለልጄ ብዙ ሀብት ይሰጠው ነበር።»

«የባልዎትን ሀብት አልወረሱም?

ይእ! ሚስት እንዴት የባሏን ሀብት ትወርሳለች? ባሏ ሲሞት ለወንድሙ በውርስ ትተላለፍና ወንድሙ ሌላውን ሀብት እንደ ወረሰ
እሷንም ይወርሳል። እኔም፣ ለባሌ ታናሽ ወንድም እያገለገልኩ እኖራለሁ"» አሁንም ባልቴቷ ፍዝዝ እንዳሉ ናቸው"

«ባልዎ የሞቱ ጊዜ መቼም እንዳሁኑ የበለተቱ አይመስለኝም፤ከታናሽ ወንድምየው ጋር ይቃበጡ ነበር?»

«ይ..እ ይሄማ ይጠየቃል፤ ባሌ እያለም ቢሆን ከታናሽ
ወንድምየው ጋር እንጨዋወታለን። እንዲያውም ከሎን የወለድኩት ከሆራ ሼላ ታናሽ ወንድም ነው።» ባልቴቷ ፈርጠም አሉ፣ የሞጨሞጨውን አይናቸውን ወደ ካርለት እየመለሱ።

«ምን? ማለቴ የከሎ ወላጅ አባት ሆራ ሼላ አይደለም ነው የሚሉኝ? የሚጠራው እኮ ከሎ ሆራ ተብሎ ነው።» ካርለት መልሱን ለመስማት ጓጓች።

«ይ..እ! በኛ ባህል አንድ ሴት ከባሏ ታናሽ ወንድም ልጅ ብትወልድ የልጇ አባት የሚሆነው ባሏ ነው። ባሏ እንኳ ሞቶ ከሌላ ወንድ ብትወልድ የልጇ አባት ስም በሟቹ ባሏ ስም ነው
ሚሆነው;»

«እና የከሎ እውነተኛ ወላጅ አባት በሕይወት አለ?»

«አዎን አለ።»

«አሁን እርስዎን የሚጦርዎ ማነው? »

«እሱና ልጆቼ።» ካርለት ይህ ለሷ እስከ አሁን ያልሰማችው አዲስ ነገር ነው" ከሎ ሆራም ስለ ወላጅ አባቱ የሚያውቅ አልመሰላትም" ምክንያቱም የግል ታሪኩን ሲነግራት አባቴ ሞቷል ብሎ ነበር።
ካርለት ወደ ከሎ ሄዳ ጉዳዩን ስትነግረው በጣም ተገረመ። ይህን ምሥጢር እሱ ቀደም ብሎ አያውቅም። ወደፊትም ለማወቅ የሚችል
አልመሰለውም።

«ካርለት አሁን የምትነግሪኝ ሁሉ ለኔ አዲስ ነገር ነውኮ፤
በጥረትሽ ወላጅ አባቴን እንዳውቅና እንዳገኝ እያደረግሽኝ እኮ ነው»
አላት ከሎ።

ካርለት፣ «ምንም አይደለም፣ ይልቁንስ አባትክን ማግኘ;
ይኖርብናል» አለችው።
።።።።።።፡፡።።።።።።።።።።።።
ጂሚ ሼላ ብዙ አላረጀም።  ሰውነቱ ስላለው ጠንካራ ቢሆንም ዕድሜውን ከ60 በላይ ነው። ካርለትና ከሎ ሆራ እሱ ዘንድ ሲመጡ ከጎጆው ፊት ለፊት በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ ፀሐይ እየሞቀ አገኙት። ካርለት ጂሚን ስታየው ደንገጥ ብላ ከሎን ዞራ አየችው ከሎ ሆራና ጂሚ ሼላ በጣም ይመሳሰላሉ። ካርለት ጂሚን እንዳየች
ከሎ ሆራ አርጅቶ ከፊት ለፊት የተቀመጠ መስሏት ነበር"

ጂሚ ሼላ ከሎ ሆራን ለመጠየቅ ሻንቆ መንደር ሄዶ ሳለ ካርለትን
አይቷታል። ስለዚህ እንዳያቸው አወቃቸው" እነሱም ሄደው አጠገቡ
ቁጭ አሉና በሐመር ባህል መሠረት ዕረፍት ከወሰዱ በኋላ፣

«እንዴት ነዎት?» አሉት።

«ደህና ነኝ" እናንተስ እንዴት ናችሁ?» አለ ጂሚ ሼላ።

«ከሎ ለእርስዎ ምንዎ ነው?»

«የወንድሜ ልጅ ነው"» ጂሚ ካርለትን በተመስጦ
ተመለከታት።

«መልኩ ግን ቁርጥ እርስዎን ነው የሚመስለው?»

«ሆራ ሼላና እኔም እንመሳሰል ነበር እኮ።»

«ከሎ የእርስዎ ልጅ እንደሆነ ሰምቻለሁ" እንዴት ነው?»

ካርለት ዋናው ነጥብ ላይ ዘላ ጥቡልቅ አለች።

«እንዴት ተደርጎ?» ጂሚ ሼላ መልሶ ጠየቃት"

«እርስዎ ከከሎ እናት ጋር... ያረጉ አልነበረም? »

«ያማ ባህል ነው።»

«እና እንዴት ከሎ የማን ልጅ እንደሆነ ያጡታል?»

«ይሕ! በሐመር ባህል ልጅ ከወንድም ተወለደም፣ ከውሽማ በአባትነት የሚታወቀው ባል ነው። እኔም ከከሎ እናት ጋር ወንድሜ እያለም ሆነ፣ ከዚያን ወዲህ ግንኙነት ቢኖረኝም ከሎ ከማንኛችን
እንደ ተወለደ የምታውቀው እናቱ ብቻ ናት"»

ካርለት ነገሩ ገባት። «በሐመር ማኅበረሰብ የልጇን ትክክለኛ ወላጅ አባት የምታውቀው እናት ብቻ ናት ለካ!» ብላ፣ ተደንቃ
ቆየችና፣ «ለምን ስምዎ ጂሚ ተባለ?» አለችው፣ ጂሚ ሼላን።

«አንድ ጂሚ የሚባል ፈረንጅ እዚህ መጥቶ፣ ከአባቴ ጋር ተዋውቆ ነበር። እንዳጋጣሚ እናቴ እሱ ከዚህ ሳይሄድ እኔን ወለደችኝ በሐመር ባህል እንግዳ መጥቶ በአጋጣሚ ልጅ ቢወለድ ስሙ
በዚያው ሰው ስም ነው የሚጠራው።»

ካርለት ነገሩ ወዲያው ገባት" ምክንያቱም በዚህ መልክ በሷ ስም የሚጠሩ ሁለት ሕፃናት ታውቃለች
«የከሎ ሆራ እናት፣ የከሎን ትክክለኛ አባት ጠይቄያቸው እርስዎ እንደሆኑ ነገሩኝ» ስትለው፣ ጂሚ ምንም መልስ ሳይሰጣት ከሎ
ሆራን ዓይን ዓይኑን ሲያይ ቆየና እጁን ጎተት አድርጎ ያዘው" ከሎ የወላጅ አባቱ ጣቶች እጁን ሲነኩት፣ ደስታ አይሉት ኃዘን ቅጡ የጠፋ ስሜት በመላ አካሉ ተስለከለከበት" ትንሽ ቆይተው አባትና
ልጅ ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው ተቃቀፉ። የወላጅና ልጅ ፍቅር
በመካከላቸው ታየ ካርለትም የደስታ እንባ አነባች የሐመር ፀሐይ
ግን ወደ መሠወሪያዋ ወደቀች"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከሎ ሆራ በፈቃድ ከዩኒቨርሲቲው በተገለለ በሁለተኛ ዓመቱ
ትምህርቱን ለማጠናቀቅ አዲስ አበባ ሄደ። ከሎ አዲሳባ ዩኒቨርሲቲ
ገብቶ ትምህርቱን ከጀመረ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለስቲቭ ደወለለት። ቀጠሮ ተሰጣጡና እሑድ ዕለት ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ከሎ
ከስቲቭ ቀድሞ በቀጠሮው ቦታ ተገኘ። ስቲቭ ልክ በሰዓቱ ሲገባ፣ከሎ ገና ከበሩ ወደ ቀኝ ሲታጠፍ ተመለከተው። ስቲቭ፣ የሆነ ፖስታ ይዞ የመሮጥ ያህል ሲራመድ፣ ከሆቴሉ ማዕዘን ላይ ካለው ሶፋ ላይ ነጫጭ ጥርሶቹን የሚያብለጨልጨውን ከሎን ተመለከተው። ስቲቭ
በማስብበት ወቅት ላገኝህ በመቻሌ በጣም ተደስቻለሁ» አለ ስቲቭ፣
የፈገግታውን መጠን እየጨመረ።
👍34🥰2
«እኔም እንደገና ላገኝህ በመቻሌ ደስ ብሎኛል» አለ ከሎ በተራው። በመካከሉ የሆቴሉ አስተናጋጅ በትሕትና ቀርቦ፣ «ምን
ልታዘዝ?» አለ። ስቲቭ ማኪያቶ አዘዘና፣ «ከሎ ይህ ፖስታ ለአንተ ከኢንግላንድ የተላከ ነው» ብሎ ሰጠው።
«ለእኔ?» ብሎ፣ ከሎ ስቲቭን በመደነቅ ተመለከተውና የታሸገውን ካኪ ፖስታ ከፈተው። ከሎ ይሆናል ብሎ ባይገምትም ከካርለት ጋር ተመካክሮ ለእንግሊዝ አገር የአፍሪካ ቀንድ አንትሮፖሎጂስቶች
ፕሮጀክት ያጭር ጊዜ የትምህርት ዕድል ሐሳብ አቅርቦ ነበር።

«ይገርማል! የአፍሪካ ቀንድ አንትሮፖሎጂስቶች ፕሮጀክት የስድስት ወር የሙያ ማሻሻያ የትምህርት ዕድል ማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዳገኘሁ የሚገልጽ ነው» አለ ከሎ ስቲቭን ፈገግ
ብሎ እያየ።
«አዎ! አውቄያለሁ። ባለፈው ካርለትና እኔ በአንተ የትምህርት ዕድልና በባለቤትህ የኢንግላንድ ጕብኝት ብዙ አስበንበት ነበር" ሆኖም ግን ስለ መሳካቱ እርግጠኞች አልነበርንም" አሁን ግን ሊሳካ ችሏል።» ብሎ፣ ስቲቭ የእንግሊዝ ቪዛ የተመታበትን ፓስፖርት ሰጠውና የባለቤትህ ፓስፖርት ዘግየት ቢልም ይደርሳል አለው።

«ጎይቲ የኖረችበት ዓለም ወደፊት ከምታየው ዓለም የተለየ ነው። ላጭር ጊዜ ቀሪውን ዓለም እንድታይ ማድረጉ ባስተሳሰቧ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ይኖራል። ጎይቲ በመማር ለማኅበረሰቧ ጠቃሚና
የሌሎች እኅቶቿ አርአያ መሆን አለባት» ብሎ ከሎ በተመስጦ ሲያስብ፣ ስቲቭ በጥሞና እየተመለከተው ማኪያቶውን ጠጣና በሌላ
ጊዜ ለመገናኘት ስልክ እንደሚደዋወሉ ተነጋግረው ተለያዩ።

ከሎ ሆራ፣ መልሱን በማያውቀው ጥያቄ ለዓመታት በሐሳብ
ዥዋዥዌ ሲጫወት፣ አቅሉን ስቶ የወደቀ ሲመስለው፣ በፍርሃትና መራራ ጥላቻ ሲነከር ኖሯል" ጊዜ የምሥጢሮች ሁሉ ቁልፍ
በመሆኑ፣ የጠወለጉት እምነቶቹ በሕሊናው ትክክለኛ ፍርድ እየተጠረጉ ሲወጡ፣ በጊዜ የለመለሙ ሐሳቦቹ በሕሊናው ውስጥ
ስፍራ ስፍራቸውን ያዙ። ጊዜ ደካማ ሐሳቦቹን ጠገነለት፤ አደሰለት፤ዐወለወለለት፤ አጸዳለት። እራሱን የደበቀውን ከሎን ከመሸገበት የተሳሳተ ምሽግ እንዲመለስ የተጋፈጠው እውነት አስተዋጽኦ አደረገለት። ዛሬ ከሎ የተደበቀ እውነት በማያሰልስ ብርቱ ጥረትና ፍለጋ ከተቀበረበት
ማውጣት የሚቻልበትን ልምድ አግኝቷል።

(ጥቁርን ጥቁር› ከሚሉት ይልቅ (ጥቁሩን ነጭ ብንልስ የሚሉት
እውነት ላይ ለመድረስ የተሻሉ እንደሆኑና እነዚህኞቹ ከእነዚያኞቹ
የማወቅ ዕድላቸው የሰፋ መሆኑን ተገንዝቧል።
ዓለማችን እሾህ እንደ ቄጠማ የተጎዘጎዘባት አይደለችም። እሾህ
ግን አለባት። እሾሁ ለሰው ልጆች ችግር እንዲያስከትል አልተፈጠረም። ባጋጣሚና በራስ ጥፋት ግን ችግር ሊያደርስ ይችላል።ዋናው ቁም ነገር ግን የሾሁን ጉዳትና ጥቅም በሚገባ ማወቅና ሊጠቅም የሚችልበትን ዘዴ መፈለጉ ነው። ከነአባባሉስ፣ እሾህን በሾህ አይደል የሚባለው ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን በሕይወት ቅንጣቢ ላይ
በደረሰ ጥፋት ከጓደኛ፣ ከዘመድ፣ ከሰው፣ ከአገርና ከዓለም ለመሸሽ መሞከር፣ ሕዝብን መናቅ እርካታ ወደማይገኝበት ያዘቅት
ሕይወት መንሸራተት ይሆናል"

ከሎ አሁን ልብሱ ሳዳጎራ (ግልድም) ነው፤ የሚጓዘው ካለጫማ፣ የሚተኛው ቆዳ ላይ ነው። ሕሊናው ግን ብስለትን፣ ማስተዋልን፣
መቻልን ተለማምዶ ስለ ደነደነ ደስተኛ ነው። ደስታ የቁስ ውጤት ሳይሆን የሕሊና ትርጕም መሆኑን ከሎ በራሱ ላይ አረጋግጧል

የእናትን ጡት እየጠቡ ዕድሜ ልክ የማይኖርባት ዓለማችን ለእኛ ብዙ ሽፍንፍን ገፀ በረከት ታድለናለች" ሽፍንፍኑን ከመፍታታችን በፊት ግን አንድ ልናስተውለው የሚገባ የሕሊና ፍርድ መኖር አለበት። ሽፍንፍኑ ውስጥ የምንፈልገው ወይንም የማንፈልገው በረከት ሊኖር እንደሚችል ማወቅና የማንፈልገው ከደረሰን
ሕሊናችን እስኪደማ ድረስ ላለመማረር ራሳችን ለራሳችን ቃል መግባት አለብን። ያገኙትን የሕይወት ዕጣ ለማሻሻል ሁሌም መጣር፣ መድከም ግን ይጠበቅብናል።

ካርለትና ከሎ ሆራ አንዱ ከሌላው ብዙ ተምረዋል። ሁለቱም ለሐመር ሕዝብ ልዩ ፍቅር አድሮባቸዋል። አብሮ መኖር፣ የሕዝብን ሥነ ሕይወታዊ ቀመር ረዳት ፍቅርን ማስከተሉ የማይቀር ሲሆን (መወለድ ቋንቋ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የከሎ ሆራ የመመረቂያ ቀን ሦስት ቀን ሲቀረው ካርለት ጎይቲን ይዛ አዲስ አበባ መጣች። ጎይቲ አዲስ አበባ እንደ መጣች ከሎ ስቲቭ
መኖሪያ ቤት ሄዶ ተገናኙ። ጎይቲ ጕድጓድ ውስጥ እንደ ኖረ ውሻ በምታየው ነገር ሁሉ በርገግ በርገግ ማለቷን ሰውነቷ ሲርበተበት
አይቶ ቢረዳም፣ ከሎ አንድ ነገር በሕሊናው ተመላለሰ።

«ሐመር ላይ ልብስ የለበሰ ሰው የደረቀ ዛፍ ይመስል ከርቀት እንደሚታየው ሁሉ፣ አዲሳባም ለየት ያለ አለባበስ ለብሶ መታየት
እንዳሻንጉሊት ያስቆጥራል» ብሎ ከሎ አሰበ" ጎይቲ ደግሞ እንዲያ እንድትሆን ፈቃዱ አልሆነም። ስለዚህ ጉዳይ ከካርለት ጋር ተመካክሮ፣ በሐሳቡ ከተስማሙ በኋላ፣ «የከተማ ሰዎች የሚለብሱትን አይተሽ የለ? አንቺም የዚያ ዓይነት ልብስ ልበሽ፤ ወደ ሐመር ስንመለስ ግን የራስሽን ልብስ ትለብሺያለሽ» ብሎ ጠየቃት ጎይቲን።

«ይእ! ለማን ብዬ፣ ያባቴን የወግ ልብስ ትቼ የከተማ ጨርቅ ለምን እለብሳለሁ?» አለችው።

«ለተወሰነ ጊዜ እኮ ነው እንጂ እኛስ ብንሆን ሐመር
የምንለብሰውን አይተሽው የለም! እዚህ ከከተማው ሰው ለየት ያለ ልብስ ከለበስሽ የሰው ሁሉ ዓይን አንቺ ላይ ስለሚያርፍ ያሳፍርሻል ብለን ነው» አላት ከሎ ለማግባባት ያህል ምክንያቱን ዘርዝሮ።

«ይእ! እንዴት ነው ያሳፍርሻል? እነሱ ቢያጠፉ፣ እኔም ልሳሳት፤ እኔ በአባቴ ደንብ ሰው አየኝ ብዬ የማፍር አይደለሁም። በገላዬ የሚያስቀይም ነገር ስለሌለኝ በጨርቅ አልሸፈንም» አለች ጎይቲ
ኰስተር ብላ።

ከሎና ካርለት ጎይቲ ባቀረበችው ምክንያት ተቀጥቶ አፍህን ያዝ
የተባለ ሕፃን ሆኑ። ጎይቲ፣ ከሎና ካርለትን የኃፍረት ምንጩ ራሱ የተሳሳተ የሕሊና ማነስ ትርጕም ውጤት መሆኑን አስተማረቻቸው።
ስለዚህ፣ ሁለቱም ጥያቄያቸውን አነሡ።

ጎይቲ፣ ካርለትና ስቲቭ በከሎ ምረቃ ከተገኙ በኋላ የማስታወሻ ፎቶ ተነሡ። ከዚያም ስቲቭ ቤት ፊት ለፊት ካለው ለምለም ሣር
ላይ ቁጭ ብለው ከሎና ስቲቭ ቢራ፣ ካርለትና ጎይቲ ሚሪንዳ እየተጎነጩ፣ የተጠበሰ የከብት ሥጋ ከመጥበሻው ላይ እያነሡ
ሲመገቡ እንደ ቆዩ ስቲቭ ወደ ቤቱ ገባና ሲመለስ፣ ለከሎና ካርለት አዲስ ዜና አበሠራቸው"
«ጎይቲ በቱሪስት መልክ ወደ እንግሊዝ አገር እንድትሄ
በፓስፖርቷ ላይ የእንግሊዝ ቪዛ አስመትቻለሁ» ብሎ ፓስፖርቱን ለከሎ አቀብሎ፣ በግራ እጁ የያዘውን ሻምፓኝ ከፈተ"

ካርለት ከመቀመጫዋ ተነሥታ ትዊስት እየደነሰች
ሳቋን ለቀቀችው" ከሎም ለስድስት ወር አጠገቡ በመሆኗ ፊቱ በደስታ
‹የቀለጠ ኑግ መስሎ አንፀባረቀ። ጎይቲ ግን በሷ ጕዞ የሚፈነድቁትን ግራ ገብቷት እየተመለከተች ፈገግ አለች ከዚያ ካርለት ጎይቲን ጠራቻትና፣ «ጎይቲ ከኔ ጋር ለንደን ትሄጃለሽ?» አለቻት

«እናንተ አሁንስ ብላችሁ ብላችሁ ባህሌን ልታስፈርሱኝ ነው
እኔ በራሴ ፈቃድ የትም የትም አልሄድም፤ እሱን ጠይቂው» አለቻት
ጎይቲ አንተነህ፣ ፊቷን ቅጭም አድርጋ።

ከሎ ሆራ፣ «ጎይቲ ፈቅጄልሻለሁ፣ ሂጂ» አላት።

«ይእ! እሱስ አይሄድም? እኔ ብቻ ነኝ የምሄደው? » አለች
በድንጋጤ ትከሻዋን ሰብቃ።

«ጎይቲ ከሎን ታፈቅሪዋለሽ?

«ይእ! አዎና ከእንግዲህ ካለሱ ማን አለኝ» አለች፣ ጎይቲ አንገቷን ቀበር አድርጋ ከሎን ሰርቃ እያየች
👍27
«ደስ ይበልሽ፣ ሦስታችንም አብረን እንሄዳለን» አለቻት" ከሎ ሆራ ሳይታወቀው በሐሳብ ጀት ገብቶ ተሳፈረ። ወዲያው ሦስቱም ስቲቭን ተሰናብተው በመኪናቸው ወደ ሐመር በረሩ" አዕዋፍ
ሲዘምሩ፣ ንቦች አበባ ሲቀስሙ፣ ኮርማዎች ሲያገሱ ሦስቱ ጓደኛሞችም የተፈጥሮው ትርዒት ዕድምተኛ ሆነው ተቀላቀሉ።

💫ይቀጥላል💫
🥰23👍8
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ



ናንሲ ሌኔሃን በተከራየችው አይሮፕላን በካናዳ ጠረፍ ላይ ስትበር ለችግሯ መፍትሄ ታያት፡ ወንድሟን መርታት ብቻ ሳይሆን አባቷ
ካስቀመጡላት የህይወት መርህ መውጣት ትፈልጋለች፡ ከመርቪን ጋር
መሆንም ትፈልጋለች፡ ሆኖም የጫማ ፋብሪካውን ትታ መርቪንን ተከትላ
እንግሊዝ ሃገር ሄዳ ብትኖር እንደ ዳያና የባሏን እጅ መጠበቅ የሰለቻት
ሚስት መሆኗ ነው፡

ናት ሪጅዌይ ኩባንያውን በተሻለ ዋጋ እንደሚገዛና በጄኔራል ቴክስታይል ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ እንደሚሰጣት ነግሯታል፡ ጄኔራል ቴክስታይልስ ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ባብዛኛው በተለይም እንግሊዝ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች አለው፡፡ ናት ሪጅዌይ ደግሞ ጦርነቱ ካላበቃ ፋብሪካዎቹን መጎብኘት አይችልም፡፡ ስለዚህ እሷ የፋብሪካ
ዎቹን የአውሮፓ የበላይ ሀላፊነት ቦታ ይሰጣታል፡፡ ይህ ደግሞ በራሱ
ከመርቪን ጋር ለመሆንና ስራ መስራት የሚያስችላት በመሆኑ ጥሩ ነው፡

መፍትሄው ጥሩ ይመስላል፡፡ አንድ የሚያስፈራ ነገር አውሮፓ ጦርነት ውስጥ ስላለች ልትሞት ትችላለች፡፡ ናንሲ ይህን ስታወጣና ስታወርድ
መርቪን ባህሩ ላይ የቆመውን አይሮፕላናቸውን አሳያት፡፡
መርቪን ከአይሮፕላኑ ጋር በሬዲዮ መገናኛ ለመገናኘት ቢሞክርም ምንም ምላሽ አላገኘም፡፡ ናንሲ አይሮፕላኗ ስታንዣብብ አዕምሮዋ ውስጥ የሚመላለሰውን ነገር ተወችው፡፡ ምንድን
ምንድን ነው የተፈጠረው?
አይሮፕላኑ ውስጥ አሉ? አይሮፕላኑ ሲታይ ምንም አልተጎዳም፡፡ ሆኖም
የሰው ዘር ያለበት አይመስልም፡፡

መርቪን ‹‹ምናልባትም ችግር ደርሶባቸው ከሆነ አርፈን ብናያቸው›› አለ፡፡ ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡

‹‹የመቀመጫ ቀበቶሽን በደምብ እሰሪ፡፡ ባህሩ ማዕበል ያለበት ስለሆነ
ስናርፍ ይንገጫገጫል፡››
ፓይለታቸው እንደ ፈረስ የሚጋልበው ባህር ላይ አይሮፕላናቸውን
አሳረፈ፡ ናንሲ እንደገመተችው ማዕበሉ አስቸጋሪ አልነበረም፡፡
አንድ የሞተር ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር ታስሯል፡፡ ትልቁ አይሮፕላን በር ላይ አንድ ሰው እጁን ያውለበልባል። ከዚያም እነ መርቪን አይሮፕላናቸውን ከግዙፉ አይሮፕላን ጋር አሰሩት፡፡

ኔድ ‹‹እኔ አይሮፕላኔ ውስጥ እቆያችኋለሁ›› አለ ‹‹እናንተ ውጡ አይሮፕላኑ ምን ችግር እንደደረሰበት አጣሩ›› አላቸው፡፡

‹‹እኔም እመጣለሁ›› አለች ናንሲ፡፡

መርቪን መጀመሪያ ወደ አይሮፕላኑ ዘለለና ለናንሲ እጁን ዘረጋላት፡

በሩ ላይ የቆመውን ሰው ‹‹ምንድን ነው የተፈጠረው?›› ሲል ጠየቀው፡

‹‹ነዳጅ ስላለቀባቸው ነው ባህሩ ላይ ያረፉት›› ሲል መለሰ፡፡

‹‹በሬዲዮ መገናኛ ላገኛቸው ሞክሬ ነበር፡፡

ሰውዬውም ‹‹ወደ ውስጥ ግባ›› አለው፡

መርቪን ከገባ በኋላ ‹‹ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አይሮፕላኑ ድንገት ነው ያረፈው›› አለ ወጣቱ ሰው ‹‹እኛ አሳ አጥማጆች ነን ስለዚህ ችግሩን ለማጣራት መጥተን ነው››

‹ካፒቴኑን እጠይቀዋለሁ›› አለ መርቪን፡፡

ወጣቱ ሰው በአለባበሱ አሳ አጥማጅ አይመስልም፡፡ ክራቫት አድርጓል፡፡
ናንሲ ሁኔታው አሳቃት፡፡

ወደ ውስጥ ገብተው ሲመለከቱ መምበሪ በደም ተለውሶ ወለሉ ላይ
ተዘርግቷል፡፡ አፏን ያዘች በድንጋጤ
‹ወይ አምላኬ! ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል መርቪን ጠየቀ ከኋላቸው ያለው ወጣቱ ሰው ‹‹ቀጥሉ ወደፊት›› አለ በቁጣ፡

ናንሲ ዞር ብላ ስታየው ሰውዬው ሽጉጥ ደግኗል፡፡ ‹‹አንተ ነህ እንዲህ ያደረከው?›› ስትል ጠየቀች
‹‹አፍሽን ዝጊና ቀጥ ብለሽ ሂጂ›› አላት፡፡

መብል ክፍል ውስጥ ገቡ፡፡
ሌሎች ሶስት ሽጉጥ የያዙ ሰዎች አሉ፡፡ አዛዣቸው የሚመስል አራተኛ
ሰው ቆሟል፡፡ ትንሹ ልጅ ከመርቪን ሚስት ኋላ ቆሞ ጡቷን ይጎነትላል፡
መርቪን ይህንን ሲያይ ተናደደ፡፡ ሶስተኛው ሰው የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ
የሆነው ሉተር ሲሆን በፕሮፌሰር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡
ካፒቴኑና የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ዓይናቸውን
ያቁለጨልጫሉ፡ በርካታ ተሳፋሪዎች ወምበራቸው ላይ እንደተቀመጡ
ሲሆን ወለሉ ላይ የብርጭቆና የሰሃን ስብርባሪ ይታያል፡፡ ናንሲ ዙሪያውን ስታማትር በፍርሃት የተዋጠችው ማርጋሬት አይኗ ገባች፡፡
‹‹ላቭሴይ አምላክ ፊቱን አዙሯል፡፡ አይሮፕላን በምንፈልግበት ጊዜ
ደርሰህልናል፡ እኔን ቪንቺኒንና የእሱን ሰዎች በአይሮፕላን ይዘኸን ትሄዳለህ፡ ኤዲ ዲኪንማ ፖሊስ እጅ ሊጥለን ወጥመድ ሲያሰናዳልን ነው
የከረመው›› አለ ሉተር፡
መርቪን ከመገላመጥ በስተቀር ምንም መልስ አልሰጠውም፡፡

ባለመስመር ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰው ‹‹የባህር ኃይል ወታደሮች
መጥተው ችግር ከመፍጠራቸው በፊት እንሂድ፡፡ ትንሹ ልጅ አንተ ላቭሌይን ይዘህ ና፡፡ ገርል ፍሬንዱ እዚሁ ትቆይ›› አለ፡፡
‹‹እሺ ቪኒ›› አለ ትንሹ ልጅ፡፡
ናንሲ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ባታውቅም ወደኋላ መቅረት ግን አልፈለገችም፡፡ መርቪን ችግር ውስጥ የሚገባ ከሆነ ከጎኑ ትሆናለች፡፡

ቪንቺኒ ሌላ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ‹‹ሉተር አንተ ሳይንቲስቱን ይዘህ ና፡›› ወደ ጆ ዞር አለና ‹‹በመጨረሻ ቆንጆዋን ሴት ይዘህ ና›› ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ሰውየው ዳያና ላቭሴይ ላይ ሽጉጡን ደግኖ ‹‹እንሂድ›› አላት እሷ ግን ከቦታዋ ንቅንቅ አልልም አለች፡፡ ናንሲ ሌላ ጥያቄ ጭንቅላቷ ውስጥ አጫረ፡ ዳያናን ለምንድን ነው የሚወስዷት? በኋላ ግን መልሱ ተከሰተላት
ጆ ቀጠለና በሽጉጡ አፈሙዝ የዳያናን ጡት ወጋ ሲያደርገው ጮኸች፡፡

‹‹ቆይ እስቲ›› አለ መርቪን፡፡

ሁሉም እሱ ላይ አፈጠጡ፡፡

‹ሁላችሁንም በአይሮፕላን እወስዳችኋለሁ። ነገር ግን አንድ ነገር ማሟላት አለባችሁ›› አላቸው

ቪንቺኒም ‹‹አፍህን
ዝጋና ተንቀሳቀስ፡፡ ምንም ቅድመ  ሁኔታ ማስቀመጥ አትችልም›› አለው፡፡

መርቪን እጁን ዘረጋና ‹‹እንግዲያውስ ግደሉኝ›› አለ፡፡

ናንሲ በፍርሃት ጮኸች፡
እነዚህ ሰዎች የሚዳፈራቸውን ሰው
ከመግደል ወደኋላ የሚሉ አይደሉም መርቪን  አላወቃቸውም አለች በሆዷ

‹‹ምንድነው ቅድመ ሁኔታው?›› ሲል ጠየቀ ሉተር

መርቪን ወደ ዳያና
አመለከተና ‹‹እሷ እዚሁ ትቆይ›› አለ ጆ በንዴት መርቪን ላይ አፈጠጠ፡፡

‹‹አንፈልግህም ብዙ የፓን አሜሪን ፓይለቶች ሞልተዋል፡፡ እነሱም
እንዳንተ ማብረር ይችላሉ›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ሁሉም እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ›› አለ መርቪን፡፡
‹‹ጠይቋቸው ጊዜ ካላችሁ፡፡›› ወሮበሎቹ እነሱን ያመጣው ፓይለት መኖሩን እንዳላወቁ ተገንዝቧል፡

‹‹ሴትዬዋን ተዋት›› አለ ሉተር፡፡

ጆ በንዴት ፊቱ ቀላ፡፡

‹‹ለምን?››

‹‹እሷን ተዋት›› ሲል ጮኸ ሉተር፡፡ ‹‹እኔ ገንዘብ የከፈልኩህ ሃርትማንን እንድታፍንልኝ ነው እንጂ ሴት እንድትደፍርልኝ ነው እንዴ››

‹‹ሉተር ልክ ነው ጆ፡ በኋላ ሌላ ሴት ታገኛለህ›› አለው ቪንቺኒም:

‹‹እሺ›› አለ ጆ፡

ዳያና በእፎይታ አለቀሰች።

‹‹ጊዜ የለንም ከዚህ እንውጣ›› ሲል ቪንቺኒ አዘዘ፡፡

ናንሲ ‹መርቪንን ዳግመኛ አየው ይሆን?› አለች በሃሳቧ
ከውጭ ክላክስ ተሰማ፡፡ የጀልባው ነጂ ነው ክላክስ ያደረገው።
👍192
ትንሹ ልጅ ‹‹አለቃ እስቲ በመስኮት ተመልከት›› አለው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሄሪ ማርክስ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ለማረፍ ከውሃ ጋር ስለተጋጨ ወደ
አንድ ጎን ወድቆ ነበር፡ በመጀመሪያ ተወርውሮ ከሻንጣዎቹ ጋር ተጋጨ፡
እንደገና ለመነሳት ሲሞክር ከአይሮፕላኑ ግድግዳ ጋር ተጋጨና ራሱን ሳተ፡
ሲነቃ ምንድን ነው የሆነው? አለ በሆዱ፡ ፖርት ዋሽንግተን እንዳልደረሱ
አውቋል፡፡ ገና ከሚቀራቸው የአምስት ሰዓት በረራ ሁለቱን ሰዓት ብቻ ነው
የተጓዙት፡፡ ስለዚህ ይሄ ከፕሮግራሙ ውጭ
ይሄ ከፕሮግራሙ ውጭ የተደረገ ቆይታ ነው፡፡
ምናልባትም አይሮፕላኑ ችግር ገጥሞት ድንገት ይሆናል ያረፈው::
አሁን ተመቻችቶ ቁጭ
ሲል ቁስሉ ተሰማው፡፡  አይሮፕላኖች የመቀመጫ ቀበቶ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው የተረዳው አሁን ነው
አፍንጫው እየደማ ነው፡፡ ራሱን ይፈልጠዋል፡፡ ሰውነቱን ሁሉ ቁስል
ይሰማዋል፡፡ እጅ እግሩ ግን ደህና ነው፡፡ አፍንጫውን በመሀረብ ጠረገና
ለመትረፉ አምላኩን አመሰገነ፡፡

የአይሮፕላኑ ሻንጣ ማስቀመጫ ክፍል መስኮት ስለሌለው ውጭ ምን
እንደተፈጠረ ማየት አልቻለም፡፡ በጸጥታ ቁጭ አለና ሲያዳምጥ የአይሮፕላኑ ሞተር ጠፍቷል፡ ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል፡፡

ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፡፡

የሽጉጥ ተኩስ ካለ ወሮበሎቹ አሉ ማለት ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ
ካሉ ደግሞ ጎርዲኖን ነው የሚፈልጉት፡፡ ሌላም ነገር አለ፡፡ የሽጉጥ ተኩስ
ካለ ግርግር ስለሚኖር በዚያ መሀል ሾልኮ ለመውጣት ይመቻል፡፡ ስለዚ, ከሻንጣ ክፍል ወጥቶ ለማየት ወሰነ፡፡

በሩን ትንሽ ከፈት አደረገና አየ፡፡ ምንም የሚታይ ነገር የለም

ኮሪደሩ ላይ ወጣና ወደ አይሮፕላኑ መንጃ ክፍል ሄደ፡ ከዚያም በሩ
ጋር ተለጥፎ ድምፅ ይሰማ እንደሆነ ጠበቀ፡፡ ምንም የለም፡ ከዚያ ቀስ ብሎ
በሩን ከፈተና አጮልቆ አየ፡፡
የአይሮፕላኑ መንጃ ክፍል ውስጥ የሰው ዘር አይታይም፡፡ ከዚያም ወደ
ፊት ሲሄድ ሰዎች ሲጨቃጨቁ ሰማ፡፡ ምን እንደሚሉ አይሰማውም፡ በአይሮፕላኑ መስኮት አሻግሮ ሲመለከት አንድ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር ታስሮ አየ፡፡ አንድ ሰው ይታየዋል፡፡ ለማምለጥ ትንሽ እንደቀረው ሄሪ ተገነዘበ፡፡
ውጭ ሰው ወደሌለበት የባህሩ ዳርቻ የሚወስደው ጀልባ አለ፤ አንድ ሰው ብቻ ስለሆነ ሰውዬውን አባሮ ጀልባውን መውስድ ይችላል።

ከኋላው የጫማ ኮቴ ሰማ፡፡ ልቡ እየደለቀ ዞረ፡ ከኋላው የመጣው ፔርሲ ኦክሰንፎርድ ነው፡፡ ልጁ በፍርሃት ተውጧል።

‹‹የት ነው የተደበቅኸው?›› ሲል ፔርሲ ጠየቀው

‹‹ተወው እሱን›› አለ ‹‹ይልቅ እዚያ ምን እንደተፈጠረ ንገረኝ›› ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ሚስተር ሉተር የናዚ ደጋፊ ነው፡፡ ፕሮፌሰር ሃርትማንን መልሶ ወደ ጀርመን ሊወስዳቸው ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ስራው በመቶ ሺህ ዶላር ወሮበሎችን ቀጥሮል
ሻንጣ ሙሉ ገንዘብም ሰጥቷቸዋል ወሮበሎቹ መምበሪን ገደሉት፡ ከእንግሊዝ ፖሊስ መምሪያ ሃርትማንን ሊጠብቅ
የተመደበ ፖሊስ ነበር››

‹‹እህትህ ደህና ነች?››

‹‹እስካሁን ደህና ነች፡፡ ሚስስ ላቭሴይ ቆንጆ ስለሆነች ሊወስዷት ነው፡፡
ማርጋሬትን ከሰውም አይቆጥሯት!›› አለ ፔርሲ ‹‹ተደብቄ ሰው ሳያየኝ ነው
ወደዚህ የመጣሁት››

‹‹ለምን?››

‹‹የኦሊስ ፊልድን ሽጉጥ ለመውሰድ፡፡ ካፒቴን ቤከር ከሚስተር ፊልድ ነጥቆ እዚህ ጠረጴዛ ኪስ ውስጥ ሲያስቀምጥ አይቻለሁ›› አለና ሽጉጡን አንስቶ ያዘ።

‹‹ሄሪ አንተ ልጅ ነህ ሽጉጥ መያዝ የለብህም፧ ባርቆብህ ሊመታህ ይችላል›› አለና ሽጉጡን ነጥቆ የጠረጴዛ ኪስ ውስጥ ከተተና መሳቢያውን ዘጋው፡:

እውጭ የሚያስገመግም ድምጽ ሰሙ፤ በመስኮቱ ሲመለከቱ የእነሱን
አይሮፕላን ከላይ ሆኖ የሚዞር አይሮፕላን አዩ አይሮፕላኑም ትንሽ
ሲያንዣብብ ቆይቶ ለማረፍ መውረድ ጀመረ ከዚያም ባህሩ ላይ አረፈና
ወደ እነሱ አይሮፕላን እንደ ጀልባ እየተነዳ መጣ:፡

‹‹አሁን ምን እናድርግ?›› አለና ፊቱን ወደ ፔርሲ ሲያዞር እሱ የለም፧
የጠረጴዛው መሳቢያም ተከፍቷል፡ ሽጉጡም የለም፡፡

ጊዜ ሳያጠፋ ከሻንጣ መያዣ ክፍሉ ወጥቶ ሄደና ሌላ ክፍል ዳር ተለጥፎ አየ፡፡ ፔርሲን አሁን ማስቆም አልቻለም ጥሎት ሄዷል፡
ማርጋሬት ሁሉም ቤተሰቡ  በሙሉ ሽጉጥ መተኮስ እንደሚችል የነገረችው ትዝ አለው፡፡ ልጁ ግን ስለማፊያዎች የሚያውቀው ነገር የለም፧ ሊያስቆማቸው ከሞከረ ደመ ከልብ ይሆናል፡፡

ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ገብቶ ወደ ውጭ ሲያይ አሁን ያረፈው አይሮፕላን ከእነሱ አይሮፕላን ጋር በገመድ ሲታሰር አየ፡ ወደ
አይሮፕላኑ ጭራ አካባቢ ድረስ ሄዶ በሩን ትንሽ ከፈት አድርጎ ምን እየተደረገ እንደሆነ ለማወቅ ፈለገ፡፡
የአንድ ሰው ኮቴ ይሰማዋል፡፡ ሌሎች ሁለት ሰዎች ሲመጡ ኮቴ ሰማ፤
አልፈው መሄዳቸውን አረጋገጠና ወጣ፡፡
ማፊያዎችን የሚይዝ የፖሊስ ሀይል መጣ ይሆን?› ሄሪ የሚነግረው
አጣ ቀስ እያለ ኮቴውን ሳያሰማ ወደ ፊት ሄደ፡፡ በመሀል በመሀሉ ቆም
ይልና ያዳምጣል፡፡ አሁን ድምጽ በደምብ ይሰማዋል፡፡ የቶም ሉተር ድምጽ እንደሆነ አወቀ፡ አነጋገሩ ትንሽ የአውሮፓ ቅላጼ ያለው የጨዋ አሜሪካዊ አነጋገር ነው፡፡

ወሮበሎቹ ሲጨነቁበት የነበረው የማምለጥ ጉዳይ አሁን መፍትሄ አግኝቷል፡፡ በመጣው አይሮፕላን ሚስተር ሃርትማንን ይዘው ሊጠፉ ነው፡

ሄሪ በእግሩ እየዳኸ ቀረበ
ምስኪኑን ሳይንቲስት ለናዚዎች አሳልፎ
መስጠት በእርግጥም ልብ ይሰብራል፡፡ መቼም ለሳይንቲስቱ ብሎ አንገቱን
ለካራ አይሰጥም፡፡ ሆኖም ፔርሲ አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል፡፡ እሱ ደግሞ
እንዲሞት አይፈልግም፡፡ ለማርጋሬት ሲል አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡
ከሄሪ ቀድሞ በመገኘት ወሮበሎቹን እርምጃ እንዳይወስዱ ለማደነጋገር
ወይም ሊሰሩት በተዘጋጁት ላይ ጋሬጣ በመፍጠር ሊያዘናጋ ነው፡፡
በአይሮፕላኑ በኩል ወጣና
ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ጋር
🙄፡£የታሰረችበትን ገመድ ፈታው፡ ነገር ግን ጀልባዋ በሌላ ገመድ ከአይሮፕላኑ
ተናደደ፡፡
ስለዚህ
ገመዱን ለመፍታት ወደ
ጋር መታሰሯን ሲያይ
አይሮፕላኑ መግቢያ መሄድ ሊኖርበት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ አንዱ
ያየዋል፡ ሆነም ቀረ የመጣው ይምጣ ብሎ አንድ ነገር ማድረጉ አይቀርም ጊዜም ስለሌለው ቶሎ ማድረግ አለበት፡፡

ሁለተኛውንም ገመድ ፈታና ጣለው፡፡

ጀልባው ውስጥ ያለው ሰው ‹‹አንተ ምን እያደረግህ ነው?›› ሲል ጠየቀው ሄሪን፡፡

ፊቱን አዙሮ ሲያይ የጀልባው ነጂ ነው ያናገረው። መሳሪያ
አልታጠቀም ሰውዬው ገመዱን ለማሰር ሲጎትት ከእጁ አመለጠውና ባህሩ
ውስጥ ገባ፡፡ የጀልባው ነጂ ወደ ውስጥ ገባና ሞተሩን አስነሳ፡ በዚህ ጊዜ
ወሮበሎቹ ጀልባው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ማየታቸው አይቀርም፡፡ ጉዳዩም አስገራሚም አስደንጋጭም ይሆንባቸዋል፡፡ ሄሪ ወደ አይሮፕላኑ ተመልሶ
ገብቶ የሻንጣ መያዣ ክፍል ውስጥ ገብቶ ተደበቀ።

ከማፊያዎቹ ጋር እሰጣ እገባ ውስጥ መግባት አደገኛ መሆኑን ያውቃል፡ ከያዙት ምን እንደሚያደርጉት ሲያስበው ፍርሃት ይወረዋል
ሄሪ ተደብቆ አንድ ነገር ይፈጠራል ብሎ ጠበቀ፡፡

በመጨረሻ ወደ አይሮፕላን መንጂያው ክፍል የሚሄድ የተቻኮለ የእግር ኮቴ ተሰማው፡ በኮቴው ድምጽ ሁለት ሰዎች እንደመጡ አውቋል፡ እሱ ከሁለት ሰዎች ጋር ሊጋፈጥ እንደሚችል አልገመተም::
ትንሽ ራቅ ብለው ሄደዋል ብሎ በመገመት በሩን ከፈት አድርጎ ሲያይ ምንም ሰው የለም፡፡ ትንሽ ወደፊት ሄዶ ሲመለከት ሁለት ሰዎች ሽጉጥ ያልያዙ ቢሆንም ዓይን የሚስቡ ልብሶች በመልበሳቸው ብቻ ማፊያዎች መሆናቸውን መገመት ችሏል፡ አንዱ አስቀያሚና ክፉ መልክ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጣም ወጣት ነው፤ ምናልባትም ከ18 ዓመት የማይበልጥ ጎረምሳ፡፡
👍11
ተመልሼ ልደበቅ ይሆን› ሲል አሰበ፡፡

ሁለቱ ወሮበሎች ጀልባውን ከአይሮፕላኑ ጋር ለማሰር እንደገና ትግል ጀምረዋል፡ ለማሰር ደግሞ የግድ ሽጉጦቻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው ሄሪም መሳሪያቸውን እስኪያስቀምጡ ጠበቃቸው፡፡

ሁለቱ ሰዎች ሽጉጦቻቸውን በኪሳቸው ከተቱና ወደ ውጭ ወጡ የጀልባው ነጂ የሚወረውርላቸውን ገመድ ለመያዝ ትግል እያደረጉ ስለሆነ በመጀመሪያ ሄሪን አላዩትም ነበር፡፡

አንደኛው ማለትም ወጣቱ ገመዱን ሲይዝ ሁለተኛው ሰው ዞር ሲል ሄሪን አየው፡፡ ልክ ሄሪ ሲደርስበት ሽጉጡን ከኪሱ አወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ሄሪ ሞቱ እንደቀረበ ስለተረዳ ጊዜ ሳያጠፋ የሰውየውን እግር ለቀም አድርጎ ጎተተው፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ ጥይት ጮኸች ሰውዬው ሲንገዳገድ ሽጉጡ
ቢወድቅበትም ላለመውደቅ ብሎ ጓደኛውን ያዘው፡፡ ወጣቱ ሰው ሚዛኑን ሳተና ገመዱ ከእጁ ወጣ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ አንዱ አንዱን ለመያዝ ወዲያ ወዲህ ተንጠራወዙ፡፡ ሄሪ የአንደኛውን ሰው እግር ይዞ እንደገና ጎተተው፡፡
በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች በማዕበል በሚጋልበው ውሃ ውስጥ ወደቁ፡፡ ሁለቱ ስዎች አንዴ ውሃ ውስጥ እየጠለቁ አንዴ ወደ ጠለሉ እየወጡ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ይጣጣራሉ፡፡ ሄሪ ከሁኔታቸው ዋና እንደማይችሉ አውቋል፡

‹‹ይህን የማደርገው የክላይቭ መምበሪን ደም ለመበቀል ነው›› አላቸው ሄሪ፡፡ ከዚያ በኋላ ይሙቱ ይዳኑ አያውቅም፡፡ ቢሞቱም ግድ አልነበረውም ከዚያም ኮቴ ሳያሰማ በፍጥነት ወደ አይሮፕላኑ ተመለሰ።

ማርጋሬት የራሷ ልብ ድውድውታ ይሰማታል፡፡ ልቧ ልክ እሳት ላይ
እንደተጣደ ጀበና ይንደቀደቃል፡፡ ያለማቋረጥ በጣም ስለሚመታ አጠገቧ ያሉ ሰዎች የሚሰሙ መሰላት፡፡

በህይወቷ እንደዚህ ፈርታ ስለማታውቅ ፍርሃቷን ሌሎች ያውቁብኝ ይሆናል ብላ ሰግታለች።
የፍርሃቷ ምንጭ እንዲሁ የመጣ አይደለም፡፡ አይሮፕላኑ ድንገት
መሃል ባህር ላይ ማረፉ፣ ፍራንኪ ጎርዲኖ፣ ሚስተር ሉተርና የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ ዲከን እየሰሩ ያሉት ስራ፣ ሱፍ የለበሱ ማፊያዎች ድንገት ከዚህም ከዚያም ብቅ  ብለው የአይሮፕላኑን ህብረተሰብ ቁም ስቅል ማሳየታቸውና ሚስተር መምበሪ በጥይት ተመትቶ ወለሉ ላይ መዘረሩ ተደማምሮ ፍርሃቷን ጣራ አድርሶታል፡

ለዓመታት ፋሺዝምን እንዴት እንደምትታገል ስትናገር ኖራለች፡፡ አሁን ዕድሉ በሯ ድረስ መጥቷል፡ የፋሺስት ቡድኑ ሳይንቲስቱን ካርል
ሃርትማንን ወደ ጀርመን አፍኖ ለመመለስ እየተውተረተረ ነው፡፡ እሷ ደግሞ በፍርሃት እጅ እግሯ ስለተሳሰረ ምንም ማድረግ አትችልም፡፡ ነገር ግን
መሞከር ይኖርባታል። ምክንያቱም እሷም ፋሺዝምን ለመዋጋት
የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝና በሞት የተነጠቀችውን ኢያንን
ለማስታወስ ስትል ትግል መግጠም እንዳለባት ታስባለች፡፡

ጀግና ነኝ እያለች ስታስመስል አባቷ የስድብ ናዳ እሷ ላይ ማውረዳቸው
ትክክል ነው፡፡ እሷም ይህን ታውቃለች፡ ጀግንነት በአፍ ብቻ ነው፡፡ በጦር ሜዳ በሞተር ሳይክል እየተመላለሰች ለጦሩ ዕቃ አጓጉዛለሁ ማለቷ ህልም
ነው፡ አንድ ጥይት ቢተኮስ የሆነ ነገር ውስጥ መወሸቋ አይቀርም፡፡ ከባድ ጥቃት ከተፈጸመማ ዋጋ አይኖራትም፡፡

ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡

ይቀጥላል
👍26
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ስሞንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ካርለት የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የሥራ ፈቃዷን ልትጨርስ የቀራት አንድ ሳምንት ብቻ ነው ከዚህ በፊት ከአንድም ሁለት ጊዜ፡
የጥናት ፈቃዷን አራዝማለች" ዘመናዊው ሕይወቷን በመዘንጋት ለሐመሩ ንጹሕ ሕይወት ረክታለች" ዛሬ የሐመር ሕዝብ ለሷ የለንደን
ሕዝብ ነው።
ከእንግዲህ ወዲያ ካርለት ኢትዮጵያዊት ነች" ለንደን
የሥጋ ዘመዶቿ፣ ሐመር ደግሞ የመንፈስ ወዳጆቿ የሚገኙበት ነው" በዚህ ቀን ካርለት ከከሎ ጋር ስለ ማኅበረሰቡ የወደፊት ዕጣ
ተነጋግረው ነበርu ካርለት፣ «ሐመሮች በእርግጥ የሚያውቁት ራሳቸውን ነው ከነሱ ውጭ ያለው ዓለም ምን እንደሚመስል
አያውቁም። ይሁን እንጂ ከዓለማችን ውጭ በራሳቸው ደሴት
ተጠልለው ዝንተ ዓለም መኖር አይችሉም" ተወደደም ተጠላ
በክልላቸው ሳይንስ የፈጠራቸው ተሽከርካሪዎችና በራሪዎች
ያልፋሉ። ስለ እነሱ ሌላው ሲያውቅ፣ እነሱም ስለ ሌላው ለማወቅ መቻል አለባቸው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ድልድይ የሐመር ወጣቶች ሲሆኑ፣ የዘመኑን ትምህርት መቅሰም መቻል አለባቸው» ብላ ነገራዋለች" ከሎም ሐሳቧ የሱም እምነት እንደሆነ አረጋግጦላታል"

ካርለት፣ ሐመርን ለመልቀቅ የተወሰኑ ቀናት ሲቀራት ሆዷ
ተሸበረ ተጨነቀች" የገርሲ፣ ፌጦ፣ ኩንኩሮ፣ ጨዋንዛ፣ ግራር ዘንባባ፣ አጋም፣ ጠዬ፣ አንቃ፣ ሌሊሚ፣ ጨውሊምባ፣ ሾላ፣ ዋንዛ፣
እንኮይ...ደኑ የአሰሌ፣ የካራ ሰንሰለታማ ተራራ፣ የላላ፣ የሻንቆ፣የወሮ…መንደር፤ የሐመር ልጃገረድ፣ ጐረምሳ፣ አዛውንት፣
ሽማግሌ፣ ባልቴት ቀብራራው ደልቲ ገልዲ በአእምሮዋ እንደ
ፔንዱለም ባለማቋረጥ እየተመላለሱ (ጨክነሽ ጥለሽን ልትሄጂ እያሉ፣ ልቧን አንጠለጠሉባት።
ካርለት ቀሪውን ጊዜዋን ከብቱን፣ ሰውን፣ ጫካውን ፎቶ ስታነሣ ሰነበተች። ልቧ ግን እንደ ታረደ ዶሮ እየተነሣ ፈረጠባት ስትመጣ
ዳር ዳር ቆመው የተመለከቷት ሐመሮች የጕዞዋን ዜና ሲሰሙ
ሕሊናቸው ኩምሽሽ ብሎ ዓይናቸው በእንባ ሲሞላ ተመለከተች ስትቀርባቸው ሊወጓት ቀንዳቸውን ያዞሩባት የነበሩት ከብቶች
ጠረኗን እየፈለጉ ተጠግተው እጆቿን ላሷት።

ካርለት በሕይወቷ እንዲህ ልብ ሰራቂ የሆነ የሰውና የተፈጥሮ ፍቅር አጋጥሟት አያውቅም። ስለዚህ፣ ልቧ ደረቷን ሲረግጥ፣
ሕሊናዋ አነባ! ዓይኖቿም አለቀሱ።

ካርለት ሐመርን ልትለቅ አንድ ቀን ሲቀራት የኢቫንጋዲ ጭፈራውን ለመካፈል አሸዋማ፣ ገላጣና ዙሪያውን በለመለሙ የሐመር እፅዋት ተከቦ ፍቅር እየተቦካ ወደሚጋገርበት፣ ንብ አበባ
ወደምትቀስምበት፣ አዕዋፍና ሰዎች ጥዑም ዜማቸውን ወደሚያዜሙበት፣ የእፅዋት፣ የአራዊት፣ የአዕዋፍ፣ የሰው ዳንኪራ
ወደሚረገጥበት ስፍራ ተጓዘች።

ካርለት በኢቫንጋዲ ጭፈራ ወቅት ሁሌም እንደምታደርገው
ጀግናውን በዓይኖቿ አማተረች" ጀግናው እየዘለሉ አየሩን ከሚቀዝፉት ጐረምሶች መካከል የለም ካርለት፣ «አምላኬ!» ብላ፣
እንደ መኪና ጎማ ተነፈሰች" በጭንቀት ዓይኖቿ ሲቅበዘበዙ ግን ደልቲ ገልዲ ካለወትሮው ተክዞ፣ ራቅ ብሎ ቆሞ አየችው" ጀግናውን ተክዞ አይታው አታውቅም። ቀጭኔ፣ አንበሳ...የገደሉት አነጣጣሪ
ዓይኖቹ ቦዘው ስታይ ሰውነቷ ተዝለፈለፈባት። ጭንቀት ያዘለው ዶፍ
ዝናብ ሊያለብሳት መጣሁ ወረድሁ እያለ አጕረመረመባት። ካርለት
በደመ ነፍስ ወደ እሱ እየተንቀሳቀሰች፣ «ምን ሆኖ ይሆን?» ብላ ራሷን ጠይቃ ፊት ለፊቱ ሄዳ ቆመች።

«ካርለት» አላትና ዝም ብሎ ዓይን ዓይኗን ተመለከተ

«ምን ሆንክ ደልቲ?» ብላ ጠየቀችው።

ዝም ብሎ ዓይኖቹን ከሷ ላይ አንሥቶ ወደ ጨረቃዋ ወረወራቸው" ካርለት ዘለሽ እቀፊው እቀፊው አሰኛት።
ካርለት» አለ ደልቲ ዓይኖቹን ሳያወርድ።
«አቤት» አለችው:
ደልቲ ገልዲ ግን ዝም አለ ተመልሶ።

እንደ ባልጩት ድንጋይ እያብለጨለጨ የተከፋፈለው የጭኑና
አጁ ጡንቻ፣ ሣንቃው ደረቱ፣ የሚንቦገቦጉት ትናንሽ ዓይኖቹ በጨረቀዋ ብርሃን ካርለት ስታይ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት
መላ አካሏ እሳት ላይ የወደቀ ቋንጣ ይመስል ኩምትርትሩ ወጣ"

«ወይ አምላኬ፣ ምናለ የልቡን በነገረኝ፤ ምናልባት
መለያየታችን አስጨንቆት ይሆን? መቼም ማለት የፈለገው ነገር አለ
ከአንደበቱ እንዳያወጣው ግን እየተናነቀው ነው» ብላ አሰበች"

ይህን ስታስብ፣ «ካርለት መሄድሽ ነው?» የሚል ከደልቲ ጕሮሮ አፈትልኮ ወጣ"

«አዎ መሄዴ ነው» አለች ካርለት፣ «ምን ሊለኝ ይሆን አምላኬ» ብላ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተችው» ደልቲ ግን አሁንም ጸጥ አላት።

«ትወደኝ ነበር?» ብላ የሞኝ ጥያቄ ጠየቀችው ደልቲ ግን ትክ ብሎ አይቷት፣ «አይ» አላት፣ በምፀት" ካርለት መልሱ ከልቡ እንዳልሆነ በሚገባ ተረዳች" ካርለት ያኔስ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆነች ጀግናው እንደገና ጣላት። ስለዚህ፣ እጇን ሰዳ እጁን ያዘችውና ወደ
ሰንበሌጡ ይዛው ገባች“ ከዚያ ጭፈራው በዓይነት በዓይነት ቀጠለ ዳንኪራው ተመታ። አሁንም እንደ ባለፈው ተመልካች በሌለበት የተፈጥሮ አዳራሽ ትርዒታቸውን ለራሳቸው አሳዩ። ዳንኪራው ግን
እንዳለፈው ተስፋ ሰጪ ሳይሆን ለየት ያለ፣ የሰቀቀን፣ የኃዘን፣
የህምታ ውዝዋዜ ሆነ።

በነጋታው ፀሐይ ከወደቀችበት ተነሥታ ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ ካርለት ዕቃዎቿን በስቴሽን ዋገን መኪናዋ ላይ ከከሎ ጋር አስተካክለው ጭነው እንደ ጨረሱ ሐመሮች ከየመንደሩ ተሰባስበው

ሴቶቹ ደረታቸውን እየደቁ ሲያለቅሱ፣ ወንዶቹ በርኮታቸው ተቀምጠው ተከዙ። ካርለት ዓይኗ በእንባ ሊጠፋ ተቃረበ" የሁለት
ዓለም ዘመዳሞች ሲለያዩ አምርረው አዘኑ"

ካርለት፣ ከሎ ሆራና ጎይቲ በሽማግሎች ተመርቀው፣ ጀርባቸው በከብት እበት ከተቀባ በኋላ ሦስቱም መኪና ውስጥ ገብተው መኪናዋ ተንቀሳቅሳ አቧራው ሲነሣ የሐመር ጭንቅላቶች ወደ መሬት
አቀረቀሩ" ካርለት ትንሽ ከተጓዘች በኋላ ኢቫንጋዲ የጨፈረችበትንና
የቦረቀችበትን የሐመር ጫካ ለመሰናበት መኪናዋን አቁማ ስትወርድ፣ ከሎና ጎይቲም አብረው ወረዱና እንባቸውን አወረዱ..
ወፎች ግን እየዘመሩ፣ ቱር እያሉ እየበረሩ፣ እየተዳሩ ምግባቸውን መፈለጋቸውን አላቆሙም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዋናው የመኸር ወቅት የሐመር የተፈጥሮ ውበትና ልምላሜ የክቱን አውጥቶታል" እፅዋት ለምልመው አብበዋል የከስኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ሆኖ ይፈሳል። የቡስካ ተራራ አሁንም ከቦታው ሳይንቀሳቀስ የሐመሮች የታሪክ ሐውልት ሆኖ ፈገግታውን በልምላሜ ያሳያል"

ከአሰሌ ሰንሰለታማ ተራራዎች እስከ ኬንያ ጠረፍ፣ ከኤርቦ እስከ አሪ ማኅበረሰብ የሐመሮች ዘፈንና ዳንኪራ አሁንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ያስተጋባል። የሐመር ተፈጥሮ ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ከድንቢጥ ወፍ እስከ ጥንብ አንሳ ጆፌ አሞራ፣ ከትል እስከ ተሳቢው
ዘንዶ ከከብት እስከ ሚዳቋና ድኩላ ይፈነጭበታል"

ሁሉም የተፈጥሮ ድምፁን ባሰማ፣ እንቅስቃሴ ባደረገ ቁጥር ውብ የሙዚቃ ቅማሬ ከጋራ ጋራ፣ ከቋጥኝ ቋጥኝ ይስተጋባል" የሐመር ምድር ለሚመጡትም ለሚሄዱትም ሁሌም ያው ነው" መለምለም፣ ማበብ፣ መጠውለግ፣መድረቅ..ተልሶ ደግሞ መለምለም።

ደልቲ ገልዲን መኪናዋ የሚወዳቸውን ጭና በአራት እግሯ ከቡስካ በስተጀርባ ተሠውራበታለች መዝናኛዎቹ፣ መደሰቻዎቹን
ሌባዋ ይዛ በአቧራ ደመና ገብታ ጠፍታበታለች" ደልቲ አሁን ሁለት እግር ያለው ከሌላ ፍጡር ያልተለየ መሆኑን ሳይረዳ አልቀረም
የጎሽን ጀርባ በአንድ ምት ብቻ አከርካሪውን አድቅቆ
የሚያንበረክከው አንበሳ መጨረሻ የዝንብ መዝናኛ መሆኑ የማይቀር እውነት መሆኑን ደልቲ የግድ ሊመለከተው፣ ሊደርስበት ነው"
👍283
ያ ከቀጭኔ እይታ ውጭ አልፎ ብብት ስር የሚገባ ፈጣን ሯጭ ፍቅረኞቹን ለመያዝ አቅም አነሰው" ሲሄዱ አላይም ብሎ ከስኬ
አሸዋ ገብቶ ተሠወረ። ደልቲ የመለየትን መጥፎ ዕጣ ተጋተ"

ደልቲ አሁን የሚወደውን የማጣት ዕጣ ደርሶት የትካዜ አባዜን
እያስተናገደ ነው። እነሱ ጥለውት ሄዱ፤ እሱ ግን ያለው እዚያው ነው" ነገ ልጃገረዶች ለሱ የዘፈኑለት የዘፈን ዜማና ግጥም ለሌላ አዲስ ጀግና ሲተላለፍ ህምታ ሰፍኖበት መቆዘሙ ላይቀር ነው"

አይ ሕይወት! የሞላ መስሎ ይቆይና መፍሰስ ይጀምራል" ፍቅር
ሲጀምሩት የጥቅምት ማር ይሆንና ሲያልቅ ግን ይመራል ያስከፋል ያስደምማል" ጀግናው ደልቲ ላይ እንኳን የወደዱትን
የማጣት አባዜ እየተንቦራቸ እየተጠጋ ነው።

ሁለቱ ፍቅረኞቹ ሲያዩት እንደ በሰለ ድንች በፍቅር ትርክክ ብለውለት ነበር እቀፈኝ፣ ጠበቅ አድርገህ ወደ ሰውነትህ ለጥፈኝ
እያሉ አዝናንተውታል ከዚያና ከዚህ እየተቀባበሉ ዘፍነው፣
በጭፈራ ልባቸው ጠፍቶ፣ ልቡን አጥፍተውታል" አሁን ግን እነሱ የሉም" አሁን ተራው የሌላ ነው" ለዛሬ ትናንት ትዝታ ነው በትናንት እሱ ተውቧል፤ ዛሬ የትዝታው ቀን ናት ነገስ የማን ትሆን?

ደልቲ ገልዲና አንተነህ ይመር ከሐመር አለኝታ፣ ከሐመሮች ሕይወትና ተስፋ "ከስኬ ወንዝ ዳር ተጋድመዋል" ሁለቱም ከተስፋ ይልቅ በትዝታ ይንቦጫረቃሉ።....

💫ይቀጥላል💫
👍245
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ማርጋሬት መጮኋን ሰምቶ ሉተር በመስኮት ተመለከተና ‹‹ባህሩ ውስጥ ወድቀዋል››› ሲል ጮኸ በጭንቀት፡፡

‹‹እነማ ናቸው?›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ጎረምሳውና ጆ›› አለ ሉተር፡

የጀልባው ነጂ ገመድ ቢወረውርላቸውም ሁለቱ ሰዎች አላዩትም፡፡ እነሱ
የሚይዙትን አጥተው በፍርሃት ውሃ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ሲሆን ጆ
ጎረምሳውን ልጅ ወደ ባህሩ ውስጥ እየደፈቀው ነው፡፡

‹‹እባክህ እርዳቸው›› አለ ሉተር እሱም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ፡፡

‹‹ምን?›› አለቪንቺኒ ‹‹ምንም ልንረዳቸው የምንችለው ነገር ያለ
አይመስለኝም፡ እነሱም ራሳቸውን ለማዳን አቅም የላቸውም፡፡›› በመጨረሻም
ሁለቱን ሰዎች ጨካኙ ባህር ሰለቀጣቸው፡

‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር ‹‹በመጀመሪያ ውሃ ውስጥዐእንዴት ሊወድቁ ቻሉ?››

‹‹ምናልባት የሆነ ሰው ገፍቷቸው ይሆናል›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ማን?››

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የሆነ ሌላ ሰው ይሆናል፡›› ማርጋሬት የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስትሰማ ስለነበር ሄሪ ሊሆን ይችላል› ስትል
ገመተች፡ ሄሪ ጀልባው ውስጥ ይኖር ይሆን?
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን
ሲፈትሹ እሱ የሆነ ቦታ ተደብቆ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ሲያርፍ ከተደበቀበት
ወጥቶ ይሆን? ሁለቱን ወሮበሎች ውሃ ውስጥ ገፍቶ የጨመራቸው እሱ
ይሆን? እያለች መልስ የሌለው ጥያቄ በአዕምሮዋ ተጉላላ፡፡

በኋላ ደግሞ ወንድሟ ትዝ አላት ፔርሲ የወሮበሎቹ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር በሚታሰርበት ጊዜ ነው የጠፋው፡፡ ‹ምናልባትም መጸዳጃ ቤት ሄዶ ግርግሩ እስኪያልቅ እዚያው ሊቆይ አስቦ ይሆናል› አለች በሆዷ፡
እሱ ደግሞ እንዲህ አይነት ባህሪ የለውም፡፡ እሱ እንደውም ሁሉን ነገር
ለማወቅ ስለሚፈልግ ችግር አይፈራም፡፡

ሉተር ‹‹ሁሉ ነገር ከእጃችን እየወጣ ነው ምን ብናደርግ ይሻላል?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አሁን በመጣችው አይሮፕላን እንሄዳለን እንዳቀድነው፡፡ አንተ፣ እኔና
ሳይንቲስቱ›› አለ ቪንቺኒ፡ ‹‹መንገዳችንን ሊያሰናክል የሚሞክር ሰው ካለ
በሆዱ ጥይት ልቀቅበት፡ አሁን ረጋ ብለን እንውጣ፡፡››
ማርጋሬት ወሮበሎቹ ፔርሲን ደረጃው ላይ ያገኙትና በሆዱ ጥይት
ይለቁበታል ብላ ሰጋች፡
ሶስቱ ሰዎች ከምግብ ቤቱ ሲወጡ የፔርሲ ድምጽ ከበስተኋላቸው
ተሰማ፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ ‹‹እንዳትነቃነቁ!›› አለ፡፡
ፔርሲ ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን መደገኑን ስታይ ማርጋሬት ዓይኗን ማመን አቃታት፡፡ የሽጉጡን አፈሙዝ አይታ ካፒቴኑ ከኤፍ.ቢ.አዩ ሰውዬ
ላይ የነጠቀው መሆኑን ገመተች፡

ቪንቺኒ ቀስ ብሎ ወደ ፔርሲ ዞረ፡፡

ማርጋሬት የወንድሟ ህይወት አደጋ ላይ ቢሆንም በፔርሲ ኮራች፡፡

የመብል ክፍሉ በሰው
ተሞልቷል፡፡ ከቪንቺኒ ኋላ ማርጋሬት ከተቀመጠችበት አጠገብ ሉተር በሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡ በሌላኛው በኩል ናንሲ፣ መርቪን፣ ዳያና፣ ኤዲ እና ካፒቴኑ ቆመዋል ቪንቺኒ ፔርሲን ዘለግ ላለ ጊዜ አየውና ‹‹ልጅ ከዚህ ጥፋ›› አለው፡፡

‹‹ሽጉጥህን ጣል!›› ሲል ፔርሲ አዘዘ፡፡

በመሃል አንድ ጥይት ጮኸች፡፡ የጥይቱ ድምጽ ጆሮ ያደነቁራል፡
ማርጋሬት ጩኸቷን አቀለጠችው: ማን ማን ላይ እንደተኮሰ አላወቀችም:: ፔርሲ ምንም አልሆነም፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቪንቺኒ ከደረቱ ላይ ደም እየተንፎለፎለ ተንገዳገደና መሬት ዘፍ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦርሳው
ሲወድቅ ተበረገደና ብሮቹ በደም ታጠቡ፡

ፔርሲ ቪንቺኒን ሲያይ ሽጉጡን ጣለ፡፡ ደንግጧል፡
ሁሉም ሰው ሽጉጥ የያዘው የመጨረሻው ወሮበላ ላይ አፍጧል፡

ካርል ሃርትማን በተፈጠረው
ሁኔታ ከተዘናጋው ሉተር መንጭቀው ራሳቸውን ነጻ አደረጉና መሬት ያዙ ማርጋሬት ሳይንቲስቱን ይገድላቸዋል ብላ ሰግታለች ፔርሲንም እንዲሁ፡ ነገር ግን ወዲያው የሆነው ግን
አስደንግጧታል፡፡

ሉተር አፈፍ አድርጎ ያዛት፡ ከወንበሯ ጎትቶ አነሳትና ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጡን ደገነባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በድንጋጤ በድን ሆኑ።

ማርጋሬት ፍርሃት ስለገባት መንቀሳቀስ መጮህ አልቻለችም፡ የሉተር
ሽጉጭ ጭንቅላቷን እየወጋት ነው፡ ሉተር ራሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ ከዚያም
ሳይንቲስቱን ‹‹ውጣና ጀልባ ውስጥ ግባ፡፡ ትዕዛዜን ካልፈጸምክ ልጅቷ
ጭንቅላት ላይ ጥይት እቀረቅርበታለሁ›› አለ፡፡
ወዲያው ፍርሃቷ ሲለቃት ታወቃት፡፡ ሉተር  ብልህ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ ሽጉጡን ሃርትማን ላይ ደግኖ ቢሆን ኖሮ ሃርትማን ግደለኝ ጀርመን አገር ከምመለስ ሞቴን እመርጣለሁ› እንደሚሉ እርግጠኛ ሆኗል፡ አሁን ግን የእሷ ህይወት አደጋ ላይ ነው፡ ሃርትማን ምናልባት
ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ይሆኑ ይሆናል፡፡

ሃርትማን ቀስ ብለው ተነስተው ቆሙ፡፡

ሁሉም ነገር በማርጋሬት ላይ የተጣለ ነበር፡ ራሷን ሰውታ ማዳን ትችላለች፡ ሆኖም ይህ አድራጎት ጥሩ አይደለም፡፡ እሷም ይህን አደርጋለሁ ብላ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህ ራሴን አላዘጋጀሁም፡፡ ማድረግ አልችልም› አለች
በሆዷ፡
ከአባቷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ አባቷ በጣም ደንግጠዋል ሲያበሻቅጧት እንደኖሩ ምን ያህል
አቅመቢስ እንደሆነች ጦሩንም ተቀላቅላ አንድ ቀን እንኳን እንደማትቆይ
የነገሯት ሁሉ ትዝ አላት፡፡
አባቴ ያለው እውነት ይሆን?› አለች ለራሷ፡
ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ሉተር ሊገላት ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት ሌሎች ሰዎች ዘለው ይረባረቡበታል ጊዜው እየሄደ ነው፤ አንድ ነገር ማድረግ አያቅተኝም, አለች በሆዷ፡

ከዚያም ‹‹ሁላችሁም ደህና ሁኑ›› አለች፡፡ አፍታም ሳይቆይ የሄሪን ድምጽ ከኋላዋ ሰማች፡፡

‹‹ሚስተር ሉተር ጠላቂው መርከብህ ደርሷል›› አለ፡፡

ሁሉም ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት ተመለከተ፡፡ ማርጋሬት ሄሪ በተናገረው ነገር ሉተር ልቡ መወሰዱን አወቀች፡፡ ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፤ እሷ ግን ምንም አልሆነችም፡፡ ሁሉም አንድ ጊዜ ተንቀሳቀሰ፡፡ ኤዲ ዘለለና እንደ ተቆረጠ ዛፍ ሉተር ላይ ወደቀበት፡፡ ሄሪ የሉተርን ሽጉጥ
መንጭቆ ወሰደ፡፡

ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ሄደና አቀፈችው፡፡ ‹‹አንተ ግን ደህና ነህ?››ቸ ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ ይመስለኛል››
‹‹በጣም ጎበዝ ነህ››
‹‹አንቺም እንዲሁ››
‹አዎ እኔ ጎበዝ ነኝ አለች ለራሷ፡
ፀጥ ብሎ የቆየው ተሳፋሪ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተንጫጫ፡፡ በዚህ ጊዜ
ካፒቴኑ ‹‹ፀጥታ እባካችሁ ዝም በሉ›› አለ፡፡
ማርጋሬት ዙሪያውን ቃኘች፡፡
ሉተር ኤዲ እና ሄሪ ላዩ ላይ ወጥተውበት ከመሬቱ ላይ እንደተደፋ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ያንዣበበው አደጋ ተወግዷል፡ ሃርትማንና
ሉተርን ሊወስድ የመጣው ጠላቂ መርከብ ተንሳፎ ይታያል፡

ካፒቴኑም የባህር ኃይል መርከብ በቅርብ ርቀት ይታያል፡ ‹‹ጠላቂ
መርከብ እዚህ እንዳለ የሬዲዮ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡››
‹‹ቤን›› ሲል ተጣራ፡
‹‹አቤት ጌታዬ›› አለ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹የጠላቂው መርከብ አዛዥ
ሬዲዮ መልእክት ማስተላለፋችንን ካወቀ ወደ እኛ ሊተኩስ እንደሚችል
ተገንዝበኸዋል?›› አለ ቤን፡፡

‹‹ደህና ይቅር›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ተሳፋሪዎቻችን እስካሁን የደረሰባቸው መከራ
ይበቃል፡››
ጠላቂው መርከብ መግቢያው እንደተዘጋ ነው አዛዡ  አንድ ነገር
ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ነው፡፡

‹‹ቤከር አንድ ያልተያዘ ወሮበላ  ይቀረናል፡ እዚህ እንዲመጣ እፈልጋለሁ፡፡ የጀልባዋ ነጂ፡ ኤዲ ሂድና ቪንቺኒ እንደሚፈልገው ንገረው አለው
👍192🔥2🥰2🤔1
ኤዲ ሉተርን ለቀቀና ወጥቶ ሄደ፡

ካፒቴኑ ናቪጌተሩን ጠራና ‹‹እነዚህን ሽጉጦች ሰብስብና ጥይቶቹን
አውጥተህ አስቀምጥ›› ሲል አዘዘ፡፡

ካፒቴኑ ሉተርን በጫማው ወጋ አደረገውና ሌላውን የአይሮፕላኑ ሰራተኛ የሆነውን ጆኒን ‹‹ይህን ወንበዴ ውሰድና አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፍበት ጠብቀው›› ሲል አዘዘው፡
ሄሪ ሉተርን ለቀቀውና ጆኒ ይዞት ሄደ፡

ሄሪና ማርጋሬት ተያዩ፡
ሄሪ ትቶኝ ሄዷል ብላ ደምድማ ነበር፡፡ እስከወዲያኛው ዓይኑን
አላየውም ብላ ነበር ያሰበችው: ህይወቴ ይተርፋልም ብላ አልገመተችም፡ ሆኖም ግን በአምላክ ቸርነት በህይወት መገናኘታቸው ደንቋታል፡
ማርጋሬት ሮጠችና እቅፉ ውስጥ ገባች፡፡ አንድ ሰው እስኪመስሉ ድረስ
ተጣበቁ፡፡

ትንሽ ቆይቶ ‹‹ወደ ውጭ ተመልከች›› አላት፡፡
ጠላቂው መርከብ ቀስ እያለ እየሰመጠ ነበር፡፡
ማርጋሬት ፈገግ አለችና ሄሪን ከንፈሩን መጠመጠችው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሁሉ ነገር ካበቃ በኋላ ካሮል አን ባሏ ጫፌን አይነካኝም ብላ መሸሽ ጀምራለች፡ አስተናጋጁ ዴቪ ያፈላላትን ማኪያቶ እየጠጣች ነው፡ ፊቷ ገርጥቷል፡፡ ሰውነቷ አሁንም ይንቀጠቀጣል፡፡ ኤዲ ባለፈ ባገደመ ቁጥር
ሲነካት ድንግጥ ትላለች፡፡

አጠገቧ ቁጭ ብሎ ያያታል፡፡ እሷ ግን የባሏን ዓይን ትሸሻለች፡፡ ምን
እንደተፈጠረ ያወራሉ፡፡ ሰዎቹ በሩን በርግደው ገብተው ወደ መኪናቸው
እየጎተቱ እንደወሰዷት ደጋግማ ትነግረዋለች ታሪኩ ይሄ ብቻ እንደሆነ
ሁሉ፡፡

‹‹አሁን ክፉው ነገር ሁሉ አልፏል›› ይላታል ኤዲ ደጋግሞ፧ እሷም ራሷን ትነቀንቃለች ነገር ግን እሷ ከዚህ በሰላም እስካልወጣች ድረስ
አታምንም::
በመጨረሻ እንደምንም ብላ ቀና ብላ አየችውና ‹‹በሚቀጥለው ጊዜ መቹ
ነው የምትበረው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

ጥያቄዋ ገባው፡፡ እሱም ‹‹የበረራ ስራ አቆማለሁ›› አላት ‹አሁኑኑ ስራዬን እለቃለሁ፡ እኔም ስራዬን ባልለቅ እነሱ ማባረራቸው አይቀርም::የተሳፋሪዎቹን ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ ድንገት አይሮፕላን ባህር ላይ እንዲያርፍ የሚያደርግ እንደ እኔ ያለ አይቆይም፡፡››

ካፒቴን ባልና ሚስቱ የሚነጋገሩትን ሰምቶ ኖሮ
‹‹አንድ ነገር ልነግርህ
ወደድኩ፡፡ ያደረከው ነገር በሙሉ አሁን ገብቶኛል፤ የገጠመህን ችግር በድል
ለመወጣት የምትችለውን አድርገሃል፡፡ አንተ ካደረግኸው የተሻለ ነገሩን
የሚያስኬድ ሰው አለ ብዬ አላምንም፧ በጣም ጎበዝ ስለሆንክ ከአንተ ጋር
መብረሩ ያኮራኛል›› አለ፡፡

‹‹አመሰግናለሁ አለቃ›› አለ ኤዲ፡፡ ኤዲ በካፒቴኑ አነጋገር ልቡ ተነካና ሳግ ጉሮሮውን ተናነቀው፤ ‹‹ያልከው ነገር ምን ያህል ችግሬን እንዳቀለለልኝ
መናገር ያቅተኛል›› አለ፡ ዞር ብሎ በድንጋጤ የተሸማቀቀውን ፔርሲን
ተመለከተና ‹‹ጌታዬ ወጣቱ ፔርሲን ማመስገን ይገባናል፤ እሱ ነው ከጉድ
ያወጣን›› አለ

‹‹ጥሩ ብለሃል›› አለ ካፒቴኑ የኤዲን ጀርባ በአድናቆት ቸበቸበና፡ ወደ ፔርሲም ሄዶ

‹‹አንተ ጎበዝ ልጅ ነህ ፔርሲ›› አለና ጨበጠው፡፡
ፔርሲም ወዲያው ድንጋጤው ለቀቀውና ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ፡
ካሮል አን ‹‹መብረር የምታቆም ከሆነ ምን አይነት ስራ ልትሰራ
አስበሃል?›› ስትል ጠየቀችው ኤዲን፡፡

‹‹የተነጋገርነውን ስራ እጀምራለሁ፡››

ዓይኗ ላይ ተስፋ አነበበ፤ ነገር ግን ለማመን ስለቸገራት ‹‹እንችላለን?››
ስትል ጠየቀችው፡

‹‹አየር ማረፊያውን ለመግዛት የሚያስችለኝን ገንዘብ ባንክ አስቀምጫለሁ። ቀሪውን ከባንክ እበደራለሁ፡፡››

ካሮል አን ወዲያውኑ በደስታ ዓይኗ በራና ‹‹አብረን እንሰራለና›› አለች
‹‹አንተ ለጥገና ወይም ነዳጅ ለመሙላት ስትሄድ እኔ ሂሳብ እሰራልሃለሁ
የስልክ ጥሪም እቀበላለሁ፡››
ኤዲም ፈገግ አለና ‹‹ልጅ እስከምትወልጂ ድረስ›› አለ፡፡

እጁን ሰደደና እጇን ለቀም አደረገው:፡ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ ድንብር
አላለችም፡፡ እንደውም እሷ አጥብቃ እጁን ያዘች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ናንሲ መርቪንን እንቅ አድርጋ ስትይዘው ዳያና ልታናግረው ፈልጋ
ጀርባውን ነካ አደረገችው፡፡

ናንሲ የእሷና የምትወደው ሰው ህይወት መትረፍ በፈጠረላት ደስታ
ተውጣለች፡ ዳያና በዚህ ጊዜ የመጣላትን ደስታ እንዳትነጥቅባት ተመኘች፡፡
ዳያና ከባሏ ለመለየት እስካሁን ቁርጥ ውሳኔ ላይ አልደረሰችም ነበር፡ አንዴ
መጣ አንዴ ሸሸት ስትል ነበር እስካሁን የቆየችው የእሷን ህይወት ለማትረፍ ከወረበሎች ጋር መደራደሩ እስካሁን ለእሷ ያለውን ፍቅር ያሳያል፡፡ ‹ታዲያ መልሰህ ውሰደኝ ትለው ይሆን?,

መርቪን ወደ ሚስቱ ዞር አለና ‹‹አቤት ዳያና›› አላት፡፡ ዓይኗ በእምባ የተሞላ ቢሆንም ውሳኔ ላይ እንደደረሰች ያስታውቃል፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ታናግረኛለህ?›› አለች

ዳያና ያለችው ለናንሲ ግልፅ አልሆነላትም፡፡ የመርቪን ሆድ አልቆርጥ ማለቱም ወደ እሷ ይመለሳል የሚል ጥርጣሬ አጭሮባታል፡

እሱም እጇን ለመጨበጥ እጁን ዘረጋና ‹‹በሚገባ›› አላት፡፡

ዳያና በሁለት እጇ እጁን አጥብቃ ያዘችው አሁንም ታነባለች፡፡

ናንሲ ይህን ስታይ ዳያና ‹ወደቤት እመለሳለሁ› ትላለች ብላ ጠበቀች
የተገላቢጦሽ ግን ‹‹መልካም ዕድል ይግጠምህ መርቪን፡፡ ቀሪው ህይወት በደስታ የተሞላ እንዲሆን እመኝልሃለሁ›› አለች፡፡

መርቪን ፊቱን እንደከፋው ‹‹አመሰግናለሁ ዳያና፤ እኔም እንደዚሁ መልካም ዕድል እንዲገጥምሽ እመኝልሻለሁ›› አለ፡፡

ናንሲ ሁለቱም ለሆነው ነገር ይቅር ሊባባሉ እንደሆነ ገባት መለያየታቸው አይቀርም፧ ሆኖም የሚለያዩት ቂም በሆዳቸው ቋጥረው አይደለም፡፡

በደመነፍስ ናንሲ ጣውንቷን ‹‹መጨባበጥ እንችላለን?›› አለቻት፡

ዳያናም ‹‹አዎ›› አለችና ተጨባበጡ ‹‹መልካም ዕድል ይግጠምሽ››
አለቻት፡፡

‹‹አንቺም እንዲሁ›› አለች ናንሲ፡፡

ዳያና ዞረችና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች፡፡
መርቪንም ‹‹እንዴት ነው የወደፊት አኗኗራችን?›› ሲል ናንሲን ጠየቃት፡፡

ናንሲ ጊዜ አግኝታ ያሰበችውን አለመንገሯን ተገነዘበች፡፡ ‹‹የናት
ሪጅዌይ ኩባንያ የአውሮፓ ሀላፊ ሆኜ እሰራለሁ››
መርቪን አባባሏ ገረመውና ‹‹ይህን ኃላፊነት የሰጠሽ መቼ ነው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡

‹‹አልሰጠኝም ነገር ግን ይሰጠኛል›› አለችና በደስታ ተፍነከነከች፡

ትንሽ ቆየና የሞተር ጩኸት ተሰማ፡፡ ይህ ድምጽ ግን የግዙፉ አይሮፕላናቸው ድምጽ እንዳልሆነ ይታወቃል፡ የባህር ኃይሎች የመጡ መስሏት ናንሲ በመስኮት አየች፡፡

የወሮበሎቹ ጀልባ ከትልቁ
አይሮፕላን ጋር የታሰረበት ገመድ መፈታቱንና ጀልባው ሊሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን አየች፡:

ታዲያ ጀልባውን ማነው የሚነዳው?

ማርጋሬት በፍጥነት ጀልባውን ነዳችው፡፡

ንፋሱ ጸጉሯን ወደ ኋላ ይገፋዋል፡፡

በደስታ ‹‹አሁን ነፃ! ነፃ!›› አለች፡፡

እሷና ሄሪ ይህ ሀሳብ የመጣላቸው ሳይነጋገሩ ነው፡

‹ወደፊት እንዴት ነው የምንኖረው?› እያሉ በየግላቸው ሲያስቡ ኤዲ
ወሮበሎቹን ይዞ የመጣውን ጀልባ ነጂ አግቶ ሲያመጣው ጀልባውን ይዞ
መጥፋት የሚባል ሀሳብ መጣላቸው፡፡

ተሳፋሪዎቹ ከሞት አደጋ ስለተረፉ እርስ በእርሳቸው ‹‹እንኳን ደስ ያለህ ደስ ያለሽ›› ሲባባሉ ሄሪና ማርጋሬት ሾልከው ወጥተው ነው ጀልባው
ላይ የወጡት፡፡ የጀልባው ሞተር አልጠፋም ነበር፡ ሄሪ ጀልባው ከትልቁ አይሮፕላን ጋር የታሰረበትን ገመድ ሲፈታ ማርጋሬት በበኩሏ የሞተሩን ማንቀሳቀሻ መሳሪያዎች እንዴት እንደሚሰሩ እየቃኘች ነበር፡ ጀልባው ደግሞ ከአባቷ ጀልባ ጋር ብዙ ልዩነት የለውም፡፡
👍12
ከኋላቸው ማንም እንደማይከተላቸው ገምታለች፡ የባህር ኃይሉ
መርከብ የጀርመኑን ጠላቂ መርከብ እያሳደደ ስለሆነ ለንደን ላይ የተወሰኑ
የወርቅ አምባሮች የሰረቀ ሰውን የሚፈልግበት ምክንያት የለም፡ ፖሊስ
አይሮፕላኑ ጋ ሲመጣ ደግሞ የግድያ፣ የአፈና እና የባህር ላይ ውንብድና
ወንጀሎች በማጣራት ላይ ይጠመዳል፡ ሄሪን ምናልባት የሚያስታውሱት
ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው
ሄሪ የጀልባዋን ኪሶች ሲበረብር ማፕ አገኘ፡፡ ማፑን በደምብ ሲያይ
ቆየና ‹‹እዚያ የሚታየውን ጠረፍ አላማ አድርገን ብንጓዝ አቅጣጫችንን
አንስትም አመሻሽ ላይ ጠረፉ ጋር እንደርሳለን›› አለ፡

ማርጋሬት ፈገግ አለች፡
ማፑን አስቀመጠና አፍጥጦ ተመለከታት፡
‹‹ምን እንደዚህ አፍጥጠህ ታየኛለህ?›› ስትል ጠየቀችው
‹‹በጣም ቆንጆ ነሽ›› አለ ‹‹እኔን ደሞ ትወጂኛለሽ››
ማርጋሬት በሳቅ ፈነዳች፡፡ ‹‹ከአንተ ጋር የተቀራረበ ሁሉ ይወድሃል” አለችው:
እጁን ሰዶ ወገቧን አቀፈና ‹‹እንዳንቺ ካለች ልጅ ጋር በጀልባ መጓዝ
ምንኛ ደስ ይላል፡፡ አሮጊቷ እናቴ ሁልጊዜ አንተ እድለኛ ነህ ትለኝ ነበር፡ ልክ ናት አይደለችም?›› አላት፡፡ተ

‹‹ጠረፍ ስንደርስ ምንድን ነው የምናደርገው?›› አለች፡፡

‹‹ጀልባውን አንድ ጥግ አቁመን ወደ ከተማ ሄደን ቤርጎ እንይዝና
አድረን በጠዋት በባቡር ተሳፍረን እንሄዳለን››
‹‹ገንዘብ እንዴት እንደምናገኝ አላውቅም›› አለች ማርጋሬት ፊቷ ላይ
ጭንቀት እየተነበበ፡፡ ‹‹አሁን ችግሬ ገንዘብ ነው፡፡ ትንሽ ገንዘብ ነው ያለኝ
ይህን ገንዘብ ለቤርጎ እንከፍላለን፡፡ ቲኬትና ልብስ እንገዛበታለን፡፡ ቦርሳዬን
እንደ አንተ አምጥቼ ቢሆን ጥሩ ነበር›› አለች፡፡
‹‹ይሄ የኔ ሻንጣ አይደለም›› አለ ‹‹የሚስተር ሉተር ነው››
‹‹ለምን የእሱን ቦርሳ ይዘህ መጣህ?››
‹‹ምክንያቱም መቶ ሺህ ዶላር እውስጡ ስላለበት ነዋ›› አለና አስካካ፡...

ተፈፀመ
👍27👏6