አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ጎይቲና ሌሎች እንግዶች ሲወጡ፣ ጋልታምቤና ሁለቱ እንግዶች ብቻ ቀሩ። ካርለትና ከሎ ይህ ሰው ለየት የሚል ሆኖ አግኝተውታል ስለዚህ፣ ሊጠይቁት የፈለጉት በመጀመሪያ ማንነቱንና ሕይወቱን በተመለከተ ነው። ሰውየውም እንዲያውም ከሚረካበት ትልቁ ነገር
ስላለፈው ሕይወቱ ማውራት ስለነበር፣ ጕሮሮውን ጠራርጎ ጨዋታውን ጀመረ። «ስሜ አንተነህ ይመር ይባላል። ትውልዴ መንዝ ነው። የመጣሁት ለአደን ነበር። አውሬ ገድሎ ጀግና
ለመባል...ሁሉም ቀረና ጓደኞቼ ሞቱ…በጦርነቱ ወቅት ከሐመሮች
ወግኜ ተዋጋሁ" የሐመሮችን ወንድምነት፣ ፍቅርና እምነት ወደድኩት። ከዚያ ወደ ትውልድ ቦታዬ መመለሱ ከበደኝ።

«ባህላዊ ደንቡን አሟልቼ ሐመር አገባሁ" ሴት ልጅም
ወለድሁ። እስካሁን በኑሮዬ ደስተኛ ነኝ» አላቸው። በረጅሙና አስገራሚ ታሪኩ ተደነቁ። እንዲያውም ካርለት፣ ስለ ሰውዬው ሁኔታ
በጥልቅ አሰበች፤ ሰውዬው በሐመሮች ኑሮ ደስተኛ ነኝ ብሏታል ስለዚህ፣ ምናልባት በሰውዬውና በሐመሮች ባህል መካከል የባህል
ልዩነት ሊኖር ይችላል። ልዩነቱ ግን እንደኔ የማይገናኝ ላይሆን ይችላል» በማለት አሰበች።
ሰውዬው ከሐመሮች ጋር ለመኖርና ለመጋባት የቻለበት የራሱ ምክንያት ቢኖረውም፣ አብሮ በመኖሩና ጋብቻ በመፍጠሩ ደስተኛ ሆኗል። እሷም ለዓላማዋ ስኬት ስትል አብራ መኖርና መጋባት
እንዳለባት ወስናለች ስለሆነም በዚህ ተመሳሳይነት አላቸው።

ሌላው ያጓጓት ነገር ግን በከሎና በልጃገረዷ መካከል ሊኖር የሚችለው ግንኙነት ነው። ከሎም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ከማንም በላይ መባዘኑ አልቀረም።ከሎ፣ የሚያስበው የተወሳሰበ የፍቅር ድራማ ነው ተዋናዮች ገና ተግባብተው መከወን ያልጀመሩት ካርለት ግን፣ ግንኙነቱ
የሚሳካበትን እያወጣች እያወረደች ሳለ፣ አንድ ቁለፍ ጥያቄ እንደሚቀር ተገንዝባለች።

በሐመር ባህል ደንብ መሠረት፣ አንድ ወንድ ከብት ከዘለለ፣.ጨርቆሴ ማዘ ከሆነ በኋላ ከሽያው (ሚዜው) ጋር ደም፣ ወተትና ማር እየተመገበ በየመንደሩ እጮኛ ፍለጋ ይዞራል።

በየመንደሩ የሚኖሩት ልጃገረዶች ደግሞ ከማይፈለግ ቤተሰብ
ጋብቻ እንዳይፈጠር በወንድሞቻቸው ስለሚጠበቁ፣ እጮኛ
ፈላጊዎች ውኃ ልትቀዳ፣ እንጨት ልትለቅም ወይምንም በሌላ ምክንያት ወደ ኋላ የቀረች ልጃገረድ ሮጠው ሄደው ይይዙና እጮኛ ፈላጊው ልጃገረዷ ፊት ለፊት ላይ «ተሪ» (ዲክዲክ) ቆዳ
የተተለተለ ጠፍር መሳይ ነገር ያጋድማል" ከዚያም ይዞት ከሚዞረው ኩርኩፋ (ከማሽላ የተሠራ) ያጐርሳታል" ይህን ካደረጉ በኋላ አጮኛ ፈላጊና ሚዜው፣ ወደ ጫካ ይፈተለካሉ" ልጅቷ ታለቅሳለች፣ ትጮሃለች ሁኔታውን የሰማ አባት፣ ወንድም፣ ዘመድ መሣሪያውን እየያዘ ለፍለጋ ይሰማራል። ከአንድና ከሁለት ቀን በኋላ ሽማግሌው ከወንድ ወገን ይመጣና አስፈቅዶ፣ ኮይታ (ጥሎሹን) በማስወሰን
ከፍያው ይጀመራል። አንድ ልጃገረድ የተሪ ቆዳ ፊት ለፊቷ መሬት ላይ ከተጋደመና ኩርኩፋ ከጐረሰች፣ ከዚያ ካጐረሳት ሰው ውጭ ሌላ አታገባም» ብለው ሽማግሎች ያጫወቷት ካርለትን ትዝ
ብሏታል"

ስለሆነም፣ አንተነህ ይመርን (ጋልታምቤን)፣ «ጎይቲ እጮኛ አላት ወይ?» ብላ ጠየቀችው። ከሎ ውስጥ ለውስጥ ይጨነቅበት
የነበረው ጥያቄ በመጠየቁ ደስ ብሎት መልሱን ከአንተነህ ለመስማት
ጓጓ" «መቼም ልጅቱ ንቁ ናት፤ በዚያ ላይ የእናቷ ዘመድ የሆኑት ጐረምሶች ሲጠብቋት ነበር» ሲል፣ ከሎ ፊቱ ወደ አመድነት
ተቀየረ ካርለት እንኳን ደልቲ ገልዲን ማታ ስትነጥቃት የነበረችውን ጎይቲን ከሎ እንዲያጣት ስለማትፈልግ እሷም የጭንቀት መልክ
ታየባት» አንተነህ ይመር ነገሩን በመቀጠል፣ «.እስካሁን እንግዲህ
ኩርኩፋ ያጐረሳት የለም" ይህ ግን መቼም የሚቀርላት አይደለም»ሲል፣ ከሎና ካርለት ሁለቱም እፎይታ ተሰማቸው"

ከሎ ሆራ፣ መሠረታዊው ጥያቆ ከተመለሰለት በኋላ፣ ስሜቱ መጋለብ ጀመረ «ጎይቲን ለማግኘት ሁለት መንገድ ይኖረዋል
አንደኛው በባህላዊ ደንቡ መሠረት፣ ካሊያም በአቋራጭ ከአባቷ
ተስማምቶ፣ ከባህላዊ ደንቡ ውጭ ጋብቻ መፈጸም ነው" ለእኔ ሁለተኛው ሐሳብ የተሻለ ይመስለኛል ሁለተኛውን አማራጭ
ለመከተል ግን አቶ አንተነህ ይመርን ማግባባት አለብኝ" ልጁ እንድትማርለትና እንድትሻሻልለት ስለሚፈልግ፣ ሁኔታው አመቺ ሊሆንልኝ ስለሚችል ብጠይቀውስ» ብሎ ከሎ አሰበ" መፍራቱ ግን
አልቀረም" ከሎ ከብዙ የሕሊና ጭንቀት በኋላ አንተነህን ሲጠይቅ
ያገኘው መልስ የጠበቀው አልሆነም።

«መወለድ ወሬ ነው ወሳኙ አብሮ ተቻችሎ መኖሩ ነው።»ሐመሮች ወንድሞቼ፣ እኅቶቼ ሆነው ተንከባክበው፣ ልዩነት ሳያደርጉ፣ ድረውና ኩለው፣ ሸልመው፣ ለትዳርና ለንብረት አብቅተውኛል" ተስፋ የቈረጥሁትንና በሞት ጥርስ የተያዝኩትን፣ ከሞት
አፍ ፈልቅቀው ተስፋዬን አድሰው ከዚህ አድርሰውኛል"

«እኔ አሁን ሐመር ነኝ" ባህሌና ቋንቋዩ ሐመር ነው" ስለዚህ ልጄን የምድራት በባህሌ ነው" በሐመር ባህል ደንብ ልታገባና
ለተሻለ ሕይወት ወደ ከተማ ይዘሃት ልትሄድ ትችላለህ" ይህ የእኔ ትብብር ይሆናል። የባህል ደንቡን ካላሟላህ ግን ቃሌንና ባህሌን
አልጥስም» አለ አንተነህ ይመር ኰስተር ብሎ። ከሎም ራሱን ቀብሮ
ሲያስብ ቆየና ውቢቱን ልጃገረድ የራሱ ለማድረግ የባህላዊ ደንቡን
ለመፈጸም መስማማቱን አስታወቀ ግን ከብት ዘሎ ቀሪውን ባህላዊ ደንብ እስኪፈጽም ጎይቲ ትጠብቀው ይሆን?

ከሎ ሆራ የአንተነህ ይመርን (ጋልታምቤን) ልጅ ለማግባት ሽማግሌ ከመላኩ በፊት አንድ ባህላዊ ደንብ መፈጸም ነበረበት"ይኸውም በልጅነቱ ወድቆ ጥርሱ በመውለቁ ሚንጊ (ገፊ) ተብሎ ተጥሉ ነበር" አሁን ግን ከሞት ተርፎ አድጎ ወደ ቤተሰቡና አካባቢው
በሥራ ምክንያት ተመልሷል" ያ ሐመር አይደለህም ተብሎ
የተጣለው ሕፃን ዛሬ ሐመር ነህ ለመባል ዝም ብሎ እንደ ከብት አይቀላቀልም

ለዚህም ከሎ ሽማግሎችን አማክሮ ከብት ታርዶ በደምና ፈርስ እንዲታጠብ ተደረገና ወደ ሐመር ማኅበረሰብ መቀላቀሉ ተበሠረ"
ከዚያ ቀጥሎ ትንሽ እራፊ ቆዳ በመልበስ «ኡhሊ» ሆኖ በየዘመዶቹ ለመዞር የወንድ ብልት መሳዩን አጭር ከእንጨት የተጠረበ «ቦኮ» ያዘ“ ከዚያም በሐመር ቆላማና ደጋማ አካባቢ በእግሩ መዞር ጀመረ" ኡከሊ ማለት በሐመርኛ አህያ ማለት ሲሆን፣ ኡክሊ የተባለው
ወጣት ለሴት ያልደረሰ ማለት እንደሆነ ይታመናል ከሎ ሆራ ቦኮውን ይዞ በየዘመዶቹ ሲዞር በመጀመሪያ «ዳውስ» ይላል ሠርጉ መድረሱን ለማብሠር" በሦስተኛው ቀን የሠርጉ (ከብት መዝለያው)
እንደተቃረበ ለመግለጽ። ቀጥሎ «ከርከሴ» ይላል" አሁንም ሠርጉ ቀን የቀረውን ጊዜ የሚያሳውቅ ቋጠሮ ለዘመዶቹ ይሰጣል" አምስት
ቋጠሮ አምስት ቀን፣ አራት ቋጠሮ አራት ቀን፣ አንድ ቋጠሮ አንድ ቀን ይሆንና ቀጠሮውን በቋጠሮ ያበሥራል" ዳውስ፣ ከርከሴ፣ የተቋጠረ ልጥ ይዞ ሲዞር የሚበላውንና የሚጠጣውን ዘመዶቹ
ያዘጋጁለታል። እናቱና ዘመዶቹም ከብት በሚዘልበት ቦታ (ራፂ) ለሚሰበሰበው ዘመድና የአገር ሰው፣ የሚጠጣ ቦርዴ፣ ምግብ አዘጋጁ" በዚህ በኩል ካርለት ወጪውን አሟላች ሚስቱ ገና ሳትታጭ፣ ሠርጉ ተደገሰ ማለት ነው።

ከብት ከሚዘልልበት ቦታ
(ራፂ) ዳስ ቢጤ ተዘጋጅቷል ሰፋፊ ቅጠልም እየተቈረጠ ከላዩ ተረብርቦበታልI እንደናሱ (እናት ሚዜው)፣ ሽያው (አንደኛ ሚዜው) ጋር፣ ስም የሚሠየምባት ትንሽ ጥጃ፣ ዘመዶቹና እንግዶች ተሰብስበዋል።

ልጃገረዶች ከብት ለሚዘለው ዘመዳቸው ለግርፊያ እየተዘጋጁ
ሲሆን «ፀንጋዞች» (ባዕዳን) የተባሉት ገራፊዎችም «ስሌንት» የተባለውን ቦታቸውን ይዘዋል።
👍231👏1
ከልጃገረዱ መካከል በመልኳ ለየት ያለችውና በፍርሃት ሰውነቷ
እየተንቀጠቀጠ ያስቸገራት ሴት አለች። ሁሉም ልጃገረዶች አምናና
ታች አምና ለወንድ ዘመዶቻቸው ከብት ሲዘሉ ተገርፈው በግርፋት
ቻይነታቸው እንደሚወደሱት ሴቶች ለውደሳ ለመብቃት ስሌንት ወደ ተባለው ቦታ እየሄዱ ፀንጋዞች (ባዕዳን) የሚባሉትን በነገር
ይተነኳኲሳሉ፣ ግርፊያውን ለምን አትጀምሩም" ፈራችሁ እንዴ መግረፍ የማትችሉ ከሆነ፣ ልበ ሙሉ ለሆኑት ወንዶች ስጧቸው እያሉ ገራፊዎችን መጥተው እንዲገርፏቸው ያደፋፍራሉ
መልኳ ለየት ያለችው ልጃገረድ ግን የሚሉት ቢገባትም በምትሠራው ድርጊት ራሷን «አውቆ አበድ መሆን አለብኝ...»እያለች፣ አብራ ትመላለሳለች በባዶ እግሯ ላይ ታች ስትል፣ የቈሰለ እግሯ ሕመም በጣም እየተሰማት ነው ለልጃገረዶች እንደሚሰፋ
ሁሉ ዙሪያውን ዛጐልና ጨሌ ክፍከፍ ያለበት ጥቁር የፍየል ቆዳ ከወገቧ በታች ለብሳ፣ ከለበሰችው ቆዳ ውጭ ያለው ጭኗና ከወገቧ በላይ ራቁት የሆነው ሰውነቷ ለጋ ጥብስ መስሏል" አንገቷ ላይ ጨሌ
እጆቿ ላይ ደግሞ አምባር ደርድራለች" ጸጕሯ አጠር ብሎ ቅቤና የአሰሌ አፈር በስሱ ተቀብታ፣ በፀሖይ ሙቀት የሚቀልጠው
ጆሮግንዷ ላይ ሲወርድ ይታያል። በበዓሉ ቦታ ከተሰበሰቡት ሰዎች
ሁሉ በፍርሃትና በድንጋጤ የተዋጠችው ይችው ሰው ብቻ ነበረች የሚያሳዝነው ጭንቀቷ ብቻ ሳይሆን ከዚያ ሁሉ ሰው ውስጥ ጭንቀቷን ካለ አንድ ሰው በስተቀር የሚያውቅላት አለመኖሩ ነው ያ ሰውም የዕለቱ ከብት ዘላይ እሱ በመሆኑና ልምምዱም አጭር
በመሆኑ በራሱ ችግር እየተዋጠ ይዘነጋታል"
ይህች ለየት ያለች ሰው ትናንት በሥልጣኔ ሕዋ ውስጥ ከተሰቀሩት ምዕራባውያን አባል የነበረች በቅምጥልና በድሎት ያደገች፣
ተንከባካቢ ቤተሰቦቿ አሁንም ድረስ የሚሳሱላት ናት" ዓላማዋ ግን
የማታውቀውን እያስቦካት ነው።

ከጫማ ጫማ አማርጦ የሚጫማ እግር ለእንቅፋትና እሾሀ፣
ለጋሬጣና ለቃጠሎ ተጋልጦ ደም ያዣል" ከአገር አገር፣ ከፋሽን ፋሽን ተመርጦ ዘመናዊና ውድ ልብስ የሚሸፈነው ገላ በቀላሉ በእጅ በተውሰበሰበ የፍየል ቆዳ ሩቡ ተሸፍኖ ሦስት አራተኛውን ውርጭና
ሙቀት የደረቀ ባሕር ዛፍ ቅርፊት አስመስሎታል" ይህም ብቻ አይደለም፣ በለስሳ እጆች በጥንቃቄ የሚዳሰሰው ጀርባ ለግርፋት ተዘጋጅቷል ፤ የሐር ነዶ የመሰለው ጸጕር፣ በአፈርና ቅቤ ተለውሷል።

ይህች ለየት ያለችው ልዩ ፍጡር ካርለት አልፈርድ፣ እንግሊዛዊቷ ተመራማሪ ነበረች" እናት ሚዚው፣ ማዞች (በአለፈው ዓመት
የዘለሉት)፣ የሚጨፍረው ሕዝብ፣ ልጃገረዶች፣ ወደሚጕርፍበት
ሲሄድ ፀንጋዞች (ባዕዳን) የሚባሉት ገራፊዎች መግረፊያቸውን ባራዛ አርጩሜውን እየያዙ ተጠጉ አርጩሜው   ረጃጅም ከመሆኑ አልፎ ከመሰበር ይልቅ ገላ ላይ እንዲጠመጠም ተቀብሮ የቆየውን ዘንጋዞች እያንዳንዳቸው በብዛት ይዘዋል" አንድ አርጩሜ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን፣ ገራፊው ተንጠራርቶ ሲገርፍ አርጩሜው ተጠቅልሎ ስምበር ከፊትና ጓላ ማውጣት አለበት
ካርለት ልጃገረዶች ግረፉን እያሉ ፀንጋዞችን እያናናቁ ሲፎክሩ፣ የሷ ሰውነት በላብ ራሰ የምትራመደው እየተንሻፈፈች ነው ቁሱሏን ሣር በነካው ቍጥር ስፍስፍ ትላለች፤ ጠዋት ብርዱ አሁን ደግሞ ልትገረፍ ነው። ጩሂ ጩሂ አሰኛት" ከዚህ ሁሉ የሚያድናት ሰው የለም" ስለዚህ፣ «አምላኬ የዛሬን ከመከራ አውጣኝ» ብላ ተማጸነች።

እንዲህ ስትብረከረክ ግርፋቱ ተጀመረ ከሎ ሆራ ለካርለት ከልቡ አዘነላት እሱም ጭንቀት ላይ ነበር" ሦስት ጥንድ በከብት ጀርባ ሳይወድቅ መሮጥ አለበት" ከወደቀ ለእሱም ለዘመዶቹም ውርደት ነው" ምልምል ራቁቱን ሆኖ እናት ሚዚው በልጥ መሳይ ነገር ሰውነቱ ላይ በሁለት ወገን አሰር አድርጎ፣ በእበት ሰውነቱን ቀባ ቀባ አደረገች እሱም እበት በመሃል እግሮቹ ነካ ነካ አድርጎ መሬት ላይ አሸት አሸት አደረገና ከአንደኛው ሚዜው በስተኋላ በመሆን
ከሚዘልባቸው ከብቶች መሃል ገባ።

ማዝ የተባሉት በከብቶች ዙሪያ በርከክ ብለው አማተቡና እየዘለሉ
የከብቶችን ጅራትና ቀንድ ይዘው በአንድ ረድፍ ደረደሯቸው።

ካርለት በባራዛ አርጩሜ ገና አንድ ጊዜ በፀንጋዛው ስትገረፍ፣ ነፍሷ ከሥጋዋ የተለየች መሰላት አርጩው ሥጋዋን ይዞ ሄዶ፣
ደም በጀርባዋና በጡቷ አካባቢ ፍጭጭ አለ" ወደ ላይ ዘለለች ከላይ ስትመለስ ደግሞ ሣሩ የእግሯን ቍስል ነካባት ቁጭ ስትል የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ሣቅ በሣቅ ሆነ" ነፍሷን ስታውቅ መላ
ስውነቷን ጠዘጠዛት በሁኔታዋ ሐፍረትም ተሰማት ምከንያቱንም
ሳታውቅ ከተቀመጠችበት ተነሣች፣ ግርፋቱ እየቀጠለ ሲሄድ ካርለት ራሷን ሳተች" ሰውነቷ ደም በደም ሆነ አብረዋት የተገረፉት
ልጃገረዶች እንደሷ ባይሆንም ደም በደም ሆነዋል" የሁሉም ሰምበሩ
ያስፈራል፤ የሷ ግን ልዩ ነው። ከግርፋቱ በኋሳ ራሷን ስታ ብትወድቅም ልብ ያላት አልነበረም፤ ሁሉም በዕላቱ ከብት ወደሚዘለልበት ቦታ ሄዱ" ከሎ ሆራ መንደርደር እንዲያስችለው ራቅ ብሎ አሁንም ምልምል ራቁቱን
ከአንደኛ ሚዜው በስተጀረባ ቆሟል። እናቱ፣ ወንድሙ፣ ዘመዶቹ ለምለም ቅጠል ቈርጠው ይዘው፣ «ይቅናህ፣ አይዞህ እያሉ መልካም ዕድል እንዲገጥመውና ክውርደት እንዲድኑ ይመኛሉ"።

ሁሉም ዝግጁ መሆኑን እናት ሚዜው ሲረዳና ምልከት ሲያሳየው
ከብት ዘላዩ ከአንደኛ ሚዜው ጀርባ ወጣ ብሎ ወደፊት ተንደረደረና ጋር
በምትባለው ትንሿ ጥጃ ላይ ዘሎ ወጥቶ በተደረደሩት ከብቶች
ጀርባ ሮጠ። መሃል አካባቢ ሚዛኑን ለመጠበቅ ቢንገዳገድም እንደምንም ብሎ መሬት አረፈ" እንደገና ዘሎ ወጥቶ አሁንም በከብቶች ጀርባ ሮጠ፤ ሦስት ጥንድ ሮጦ ሊጨርስ ሲል ከብት ዘላዩን እናት
ሚዜው ጠበቀውI ከሎ ዝላዩን ሊጨርስ እንደ ተቃረበ ወደ እናት
ሚዜው በአየር ላይ ሲዘል፣ እናት ሚዜው ከአየር ላይ ቀለበው ደንብ ነዋ!

ከሎ ሆራ ዝላዩን በሚገባ ሲፈጽም ዕልልታው፣ ደስታው! ፈንጠዝያውና ዘፈኑ ቀጠለ" ጸጥ ብሎ የነበረው አካባቢ በጩኸት
ድብልቅልቅ ሲል ካርለት ከነበረችበት ነቃች" ሰውነቷ በደም ተበከሏል። ከዚህም በተጨማሪ ሰውነቷን ማንከላወስ ተሳናት እንደ
ምንም ብላ ከተኛችበት ስትነሣ አንዲት ልጃገረድ ጀርባዋን ለጋ ቅቤ ቀባችላት ቀና ብላ ስታያት ጎይቲ አንተነህ ናት" ጎባኗ» ካርለት
ጎይቲን አመስግና እንደ ምንም እንድትደግፋት ነገረቻትና ለእህል ውኃ ወደ ዳሱ ከሚገባው ሰው ራቅ ብላ ዛፍ ስር ተኛች" ዝንቦቹም ትኵስ ደም ከቍስሏ ላይ በመምጠጥ ቁም ስቅሏን አሳይዋት“
በዚህ ወቅት hሎ ሆራ ካለምንም ልብስ ብልቱን እያማታ ወደ እሷ መጣ" ልትሥቅ ሞከረች «እንኳን ደስ አለህ!» ብላ እጇን
ልትዘረጋለት ብታስብም እጇን ማዘዝ ተሳናት። እሱም እንዳያት በሁኔታዋ ድንግጥ ብሎ አዘጋጅታ ያመጣችውን አልኮልና ጂቪ
እያቃሰተች ቁስሏን ጠራረገላትና ቀና ሲል ጎይቲ አንተነህ ኰራ ብላ ስታየው ተመለከታት” ዘወር ሲልም ደልቲ ገልዲን አየው። ጎንበስ ሲል የካርለትና የከሎ ሆራ ዓይኖች ተገናኙ"
ሁለቱም የተግባቡ ይመስላሉ" የሚፈልጉትን ለማግኘት አስፈላጊውን ሁሉ መፈጻም እንደሚያስፈልግ አንዱ ለሌላው መንገር
አላሻቸውም" ለዚህ ምሳሌዎች ናቸዋ!....

💫ይቀጥላል💫
👍33
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ከእንቅልፏ  ስትነቃ ሃሳብ ውስጥ ገባች፡: ዛሬ ለአባቴ ቁርጡን እነግረዋለሁ  አለች በሆዷ አሜሪካ ሲደርሱ ከእነሱ ጋር
እንደማትኖር ከቤት ወጥታ ቤት ተከራይታ እና ስራ ይዛ ልትኖር እንደሆነ
ትነግራቸዋለች፡፡ መቼም አባቷ ይህን ሲሰሙ ኮረንቲ ይጨብጣሉ፡፡

ማርጋሬት ነገሩን ባሰበችው ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማታል አባቷን ለመቃወም ስትነሳ የሚሰማት ይኸው ነው፡፡ አሁን አስራ ዘጠኝ ዓመቴ ነው፡፡ አሁን ልጅ አይደለሁም፡፡ ትናንት ከድንቅ ሰው ጋር ወሲብ
ፈጽሜያለሁ፡፡ ታዲያ ለምንድነው የምፈራው? ስትል ታስባለች፡

ለምን አባቷ ሁልጊዜ እንደ አውሬ በግርግም ውስጥ እንደሚዘጉባት አይገባትም፡ ኤልሳቤትንም እንዲሁ ነበር የሚያደርጓት፡፡ ፔርሱን ግን ለቀቅ አድርገውታል፡፡ ሴት ልጆቻቸውን እንደ ጌጣጌጥ ነው የሚቆጥሯቸው: አንድ
የሆነ ስራ እንስራ ብለው የተነሱ እንደሆን ቁጣቸው ለጉድ ነው፡፡ ለምሳሌ
ዋና እንዋኝ ወይም ብስክሌት እንንዳ ብለው ቢነሱ በቃ አለቀላቸው፡
ልብስ የፈለጉትን ያህል ቢያወጡ ምንም የማይሉትን ያህል መጽሐፍ
እንግዛ ቢሉ ጸጉራቸው ይቆማል፡

ማርጋሬት ይህን ባሰበች ቁጥር ሽንፈቷ አይደለም የሚያሳምማት፡፡አባቷ የእሷን ሀሳብ ውድቅ ለማድረግ የሚያወርዱባት የስድብ ውርጅብኝና
የፌዝ ጋጋታ እንጂ፡

ብዙ ጊዜ አባቷን ለማታለል ሞክራለች፡ የተሳካላት ግን ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ሁልጊዜም ከአባቷ ትዕዛዝ ውጭ የምትፈጽመው በሌሎች እርዳታ
ነው:: ስለወሲብ ያስተማረቻት ዘመዷ ሞኒካ ናት፡፡ ፔርሲ ተኩስ አስተምሯታል፡፡ ሹፌራቸው መኪና መንዳት አስለምዷታል አሁን ደግሞ
ሄሪና ናንሲ ሌኔሃን ነጻነቷን እንድትቀዳጅ ይረዷት ይሆናል።

አሁን ለየት ያለ ስሜት እየተሰማት ነው፡፡ መኝታዋ ላይ ተጋድማ መላ አካላቷን ደባበሰችው፡፡ ከዚህ ቀደም ጸጉሯ የተንጨፈረረ ቅርጿ ደግሞ የማያምር አድርጋ ትገምት ነበር፡፡ አሁን ግን ገላዋን እየወደደችው
መጥታለች፡ ሄሪ ‹‹ቅርጽሽ ያምራል›› ብሏታል
አይሮፕላኑ ውስጥ የሰዎች ሹክሹክታና የዕቃ ኳኳታ ይሰማታል ተጓዦች ከመኝታቸው እየተነሱ ነው መጋረጃውን ገለጥ አድርጋ ስታይ ዱባው አስተናጋጅ ኒኪ የእናትና የአባቷን መኝታዎች ወደ መቀመጫነት እየቀየረ ነው፡፡ ሄሪ ሙሉ ልብሱን ለብሶ ቁጭ ብሎ በተመስጦ በመስኮት ወደ ውጭ ይመለከታል፡፡
እሱን ስታይ አፈረችና ሳያያት ወዲያው መጋረጃውን ዘጋችው::ከጥቂት ሰዓት በፊት በወሲብ ሲያብዱ ቢቆዩም አሁን ግን ሁኔታው
አሳፈራት።

ሌሎቹ ሰዎች የት ሄደው ይሆን?› ስትል አሰበች፡፡ ፔርሲና አባቷ ውጭ ወጥተው ይሆናል፡ አባቷ ለወትሮው በጧት ነው የሚነሱት፡ እናቷ
ግን በጧት መነሳት አይሆንላቸውም፡፡ ምናልባትም መታጠቢያ ቤት ይሆናሉ፡ ሚስተር መምበሪም በቦታው የለም፡፡

ማርጋሬት በመስኮት ስትመለከት ነግቷል፡፡ የሰማይ በራሪው አይሮፕላን
አንድ ትንሽ የወደብ ከተማ ዳርቻ ላይ ታስሮ ቆሟል፡ እንደገና መኝታዋ ላይ
ጋደም አለች፡፡ የለሊቱ ሁኔታ በዓይነ ህሊናዋ ድቅን አለ፡፡ የትናንቱ ቀን ድንግልናዋ የተወሰደበት ቀን አድርጋ ነው የቆጠረችው፡፡ ከኢያን  ጋር ስትፈጽም የነበረው ወሲብ ችግር ያልተለየውና ጥድፍ ጥድፍ ያለ ነበር፡
ከእሱ ጋር ወሲብ ከፈጸመች በኋላ ሁልጊዜ በእፍረት ትሸማቀቃለች፡ትናንት ከሄሪ ጋር ያደረገችው ግን አስደስቷታል፡፡ እያንዳንዱ የስውነት ክፍሏ እየተቆጠረና እየተዳበሰ የተፈጸመ ወሲብ ነበር፡፡ ምንም እፍረት ያልነበረበት፡፡ እንደ ሴት ራሷን የቆጠረችበት ወቅት ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ወሲብ ከሄሪ ጋር በተደጋጋሚ መፈጸም አለብኝ አለች ለራሷ፡ የትናንት ማታው ትዝታ የወሲብ ፍላጎቷን ቀሰቀሰባትና ሰውነቷን አወራጨች።

ሄሪ የክት ልብሱን ለብሶ መስኮቱ ጋ ተቀምጦ በተመስጦ ሲያይ ሰርቃ
አየችው:፡ የሆነ ነገር እያሰላሰለ መሆኑን መልከ መልካም ፊቱ ነገራት::
ልትስመው ዳዳት፡፡ መጋረጃውን ገለጥ አደረገችና ‹‹እንደምን አደርክ ሄሪ አለችው፡፡

ድንገት የሰማው ድምጽ ሲሰርቅ እንደተያዘ ሰው አስደነገጠውና ደንብሮ
ዞር አለ፡፡ ሲያያት አየችውና ፈገግታ ተለዋወጡ፡፡ እንደ ጅል ለረጅም ጊዜ ሲሳሳቁ ቆዩ፡፡ በኋላም ማርጋሬት አይኗን ሰበረችና ተነሳች።

አስተናጋጁ የእናቷን መቀመጫ ከሚያዘጋጅበት ቀና ብሎ ‹‹ደህና አደርሽ እመቤት ማርጋሬት ቡና ላምጣልሽ?›› አላት፡

‹‹ኒኪ ይቅርብኝ አመሰግናለሁ›› አለችው ሁኔታ እንደ ጭራቅ ለራሷ
አስፈራት፡፡ ጸጉሯ ተንጨፍርሯል፡፡ ልብስም በቅጡ አልለበሰችም፡፡ ሄሪ ግን ጢሙን ተላጭቶና ዘንጦ አዲስ ሳንቲም መስሏል

ብትስመው በወደደች፡፡

ነጠላ ጫማዋን እግሯ ላይ ሰካች፤ ሌሊት ለወሲብ ስትቻኮል ሄሪ አልጋ
ስር እንዴት እንደተወችውና አባቷ ሳያይዋት እንዴት አድርጋ አንስታ አልጋው ውስጥ እንደከተተችው እየታወሳት፡፡

የሌሊት ልብሷን ስትለብስ እርቃኗን ስለነበረች ሄሪ ጡቶቿ ላይ ዓይኑን
ተከለ፡፡ ቢያያትም ምንም አልመሰላትም፡፡ ሄሪ ጡቷን ሲያይ ደስ አላት፡ የሌሊት ልብሷን መቀነት ጠበቅ አደረገችና ጸጉሯን አሻሸች፡፡
ኒክ ስራውን ጨረሰ፡፡ ሄሪን መሳም ስለፈለገች ኒኪ ከዚያ ቦታ ቶሎ እንዲ ሄድላት ፈለገች፡፡ ኒኪ ግን የልቧን ፍላጎት ስላላወቀ መቀመጫውን ላዘጋጅልሽ?›› አላት

እሺ›› አለች ውስጧ በንዴት እየጨሰ፡፡ ሄሪን ድጋሚ የምትስምበት ጊዜ እንደሰማይ ራቃት፡፡ የመታጠቢያ ዕቃዎቿን የያዘችበትን ቦርሳዋን
አነሳችና ሄሪ በሀዘኔታ እያያት ተነስታ ሄደች፡፡

ሌላው አስተናጋጅ ዴቪ መብል ክፍሉ ውስጥ ምግብ እየደረደረ ነው፡፡
እግረ መንገዷን አንድ የእንጆሪ ፍሬ ሰርቃ አፏ ላይ አደረገች፡ ስትሄድ
ብዙዎቹ መኝታዎች
ወደ መቀመጫነት ተለውጠዋል አንዳንዶቹ
ተሳፋሪዎች ቡና እየጠጡ ነው፡ ሚስተር መምበሪ ከሳይንቲስቱና ከባሮን
ጋቦን ጋር ወሬ ይዟል፡፡

መታጠቢያ ክፍሉ ውስጥ ስትገባ እናቷ መስታወት ፊት ቁጭ ብለው ይዋባሉ፡፡ እሳቸውን ስታይ እፍረት ተሰማት፡ ‹እናቴ ካለችበት አንድ ሁለት ርምጃ ርቀት ላይ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር አደርጋለሁ? አለች በሆዷ፡
ጉንጮቿ በእፍረት በርበሬ መስለዋል፡፡ ‹‹እንዴት አደርሽ እማማ›› አለች

‹‹ምን ሆነሽ ነው ፊትሽ እንደዚህ የቀላው? እንቅልፍ አልተኛሽም እንዴ?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹ኧረ በደምብ ተኝቻለሁ›› አለች ማርጋሬት፡፡ ‹‹አንዲት ፍሬ እንጆሪ ከጠረጴዛ ላይ አንስቼ ስለበላሁ ነው›› አለችና መጸዳጃ ቤት ጥልቅ አለች ከዚያም መታጠቢያው ላይ ውሃ ሞላችና ፊቷን ታጠበች፡:

ትናንት የለበሰችውን ልብስ ዛሬም በመልበሷ ደስ አላላትም፡፡ የታጠበ
ልብስ ብትለውጥ በወደደች: አንገቷ ስርና ጡቶቿ ውስጥ ሽቶ
አርከፈከፈች፡፡ ሽቶ ለይቶ የሚያውቅ ያየችው ወንድ ሄሪን ብቻ ነው፡፡

ረጅም ጊዜ ፈጅታ ጸጉሯን አበጠረች፡፡ ያላት ውበቷ ጸጉሯ ስለሆነ ለጸጉሯ የማትሆነው የለም፡፡ መልኬን ለማሳመር ስል ማድረግ ያለብኝ ሁሉ
አደርጋለሁ አለች ለራሷ፡ እስካሁን ስለመልኳ ተጨንቃ አታውቅም፡፡ ዛሬ ግን አስተሳሰቧ ተለውጧል፡፡ ገላዬን ልቅም አድርጎ የሚያሳይና ረጅም ታኮ
ጫማ ያስፈልገኛል፡፡ ከገላዬና ከጸጉሬ ከለር ጋር የሚሄድ ልብስ መምረጥ
አለብኝ፡፡› አሁን የለበሰችው ልብስ እንደ ሽክላ ቀይ ነው፡፡ እንዲያው ዝም ብሎ የወረደና ቅርጸ ቢስ መሆኑን በመስታወት አይታ ትከሻውጋ ቀጥ ያለና
ወገቡ ጋ በመቀነት ሸብ የሚደረግ ቢሆን ጥሩ ነበር ስትል ተመኘች።ሜክአፕ ባትቀባባም ያላት መልክ በቂ ነው፡ ጥርሶቿም አያሳጡም፡፡

‹‹ከሚስተር ቫንዴርፖስት ጋር ለመጫወት ልትሄጂ ነው አይደለም?››
አሉ እናት፡፡
👍231🥰1
‹‹አዎ እሱ ጋ ነው የምሄደው፡፡ ሌላማ ማን አለ፡፡ አንቺም እየተኳኳልሽ ነው።

‹‹እንደ ጀማሪ እጅሽን አትስጪ፡፡ ይህ ልጅ ይሁዳዊ ይመስላል፡፡››
አፏ አምልጧት ሄሪ አልተገረዘም› ልትል ብላ ከአፏ መለሰችው፡፡ ነገር
ግን ምንም ቃል ሳትተነፍስ ስቃ አሳለፈችው::

እናት ተናደዱና ‹‹ምንም የሚያስቅ ነገር የለም፡፡ ከዚህ አይሮፕላን ከወረድን በኋላ ከዚህ ልጅ ጋር እንዳላይሽ!›› አሏት

‹‹ከዚህ በኋላ ለእናንተ ግድ እንደሌለኝ እንድታውቂ እፈልጋለሁ›› አለች ማርጋሬት ‹‹እውነቴን ነው›› ወላጆቿን ጥላ ልትሄድ ስለሆነ ፈቀዱ አልፈቀዱ ለውጥ የለውም፡፡

እናት ጥርጣሬ ገባቸውና ‹‹እውነትሽን ነው?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹ጨቋኞች ማንንም አያምኑም›› አለች ማርጋሬት፡፡ ይህን ካልኩ
ይበቃል ብላ ማርጋሬት ወደ በሩ ስታመራ ጠሯትና ቆም አለች

‹‹እባክሽ አትሂጂ፡ አንዴ አናግሪኝ የኔ ማር›› አሉ እናት ዓይናቸው እምባ እንዳረገዘ፡

ማርጋሬት ምን እንዳሰበች እናት ጠርጥረው ይሆናል፡፡ እናት የወደፊቱን መገመት እንደሚችሉ ታውቃለች፡
ማርጋሬት መልስ
አልሰጠችም።

‹‹ኤልሳቤት ጥላኝ ሄደች፤ አንቺንም እንዳላጣ እፈራለሁ››
‹‹አባባ ነው ጥላን እንድትሄድ ያደረገው›› አለችና ጧ ብላ አለቀሰች::
ኡኡ ለማለት ዳዳት ‹‹እንዲህ ሲሆን ለምንድነው ተው የማትይው?,,
‹‹ሳልሞክር የቀረሁ ይመስልሻል?››

ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ደነገጠች፡፡ እናት አንድም ቀን አባቷ ተሳስተዋል ሲሉ ሰምታ አታውቅም፡፡ ‹‹እሱ እንግዲህ ይህን ባህሪውን
ካልተወ ምንም ማድረግ አልችልም›› አለች ብስጭቷ ገንፍሎ፡፡
‹‹ምናለ ባታበሳጪው?›› አሉ እናት፡
‹‹ስለዚህ ሁልጊዜ የሚለውን ሁሉ ተቀባይ እያልሽኝ ነው?››
‹‹አዎ አግብተሽ እስክትወጪ ድረስ››
‹‹አንቺ እስከዛሬ ዝም ባትይው ኖሮ እንዲህ አይሆንም ነበር››
እናትም ራሳቸውን ነቀነቁና ‹‹ባሌ ስለሆነ ካንቺ ጋር አታካሮ ሲገጥም እኔ ላንቺ ማገዝ የለብኝም››

‹‹እሱ ግን የሚሰራው ሁሌ ትክክል አይደለም››

‹‹ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ባል ስታገቢ ነው ነገሩ የሚገባሽ››
‹‹በእውነት ይሄ ጥሩ አይደለም›› አለች ማርጋሬት፡
‹‹እንዲህ እንደሆነ እኮ አይቀጥልም፡፡ ትንሽ እንድትታገሺው ነው
የምለምንሽ፡፡ ሃያ አንድ አመት  ከሞላሽ በኋላ ምንም ማድረግ አይችልም፡
ባል አገባሽም አላገባሽም የእሱ ባህሪ እንደሆን እንደማይለወጥ አውቃለሁ
እንደ ኤልሳቤት ብር ብለሽ እንድትሄጂ አልፈልግም፡››
እናት ከቤተሰቡ እንዳትለይ የሚፈልጉትን ያህል እሷም ተለይታ መሄዱ ደስ አይላትም:፡ ‹‹እኔም እኮ ይህን ፈልጌ አይደለም!›› አለችና ወደ እናቷ ስትጠጋ እናቷ እቅፍ አደረጓት፡፡
‹‹ ከአባትሽ ጋር ከዚህ በኋላ እንደማትጣዪ ቃል ግቢልኝ›› አሉ እናት፡

ማርጋሬት ለእናቷ ከልቧ ቃል መግባት ብትፈልግም ውስጧ ግን ‹‹ተይ ተይ›› ይላታል፡፡ ‹‹አባቴን ላለማበሳጨት እሞክራለሁ›› አለች፡፡
እናትም ‹‹እግዚአብሔር ይባርክሽ›› አሉ ከዚያም ማርጋሬት ወጥታ ሄደች፡፡
ሄሪ ወዳለበት ስትገባ ተነስቶ ተቀበላት፡፡ በጣም ከፍቷት ስለነበር
ዙሪያዋ ምን እንዳለ ሳትጨነቅ ጥምጥም አለችበት፡፡ እሱም የሰው ዓይን እየገረፈው እቅፍ አድርጎ ግንባሯን ሲስማት ትንሽ ቀለል አላት፡

አይኗን ከፈት ስታደርግ ሚስተር መምበሪ በአግራሞት ያያቸዋል
መምበሪ ማየቱ ግድ ባይሰጣትም ከሄሪ እቅፍ ውስጥ ወጣችና ተራርቀው
ተቀመጡ።

የወደፊት እንቅስቃሴያችንን በጥንቃቄ ማቀድ አለብን›› አለ ሄሪ፡
‹‹ብቻችንን ለመነጋገር ደግሞ ያለን ጊዜ ይህ ብቻ ነው››
‹‹ማርጋሬት ቤተሰቦቿ በማንኛውም ጊዜ ሊመጡ ስለሚችሉ እንደልባቸው መነጋገር የሚችሉት አሁን እንደሆነ ተገንዝባለች፡ አሜሪካ ሲደርሱ ሊለያዩ እንደሚችሉ ስታስበው ሰቀጠጣት፡፡

‹‹አሜሪካ እንዴት ነው የምንገናኘው? ቶሎ ንገረኝ›› አለች፡
‹‹እኔ ምን አውቄ፡፡ ያሰብኩት ነገር የለም፡፡ ግን ብዙ አትጨነቂ እኔ ፈልጌ አገኝሻለሁ፡ የት ሆቴል ነው አልጋ የምትይዙት?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ኒውዮርክ ዋልዶርፍ አስቶሪያ ሆቴል ነው፡፡ ዛሬ ማታ ሆቴል ትደውልልኛለህ?››

‹‹ተረጋጊ እደውልልሻለሁ። ሚስተር ማርክ ነኝ እላለሁ ምልክት እንዲሆንሽ፡፡››

‹‹አንተስ የት ሆቴል ነው አልጋ የምትይዘው?››
‹‹እኔ ረከስ ያለ ሆቴል ነው የምይዘው››
አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላትና ‹‹ማታ ሹልክ ብለህ ወደኔ መኝታ ክፍል
ትመጣለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
ፈገግ አለና ‹‹ከምርሽ ነው? ታውቂኛለሽ እንደምመጣ››

በዚህ አባባሉ ደስ አላት፡ ‹‹እህቴ ብትኖር ኖሮ አብረን ነበር የምንተኛው:፡ አሁን ግን ብቻዬን ነኝ፡፡››

‹‹ወይኔ እንዴት ደስ ይላል! ምነው አሁን በሆነ!›› አላት፡፡
የባለጸጋ አኗኗር እንደሚወድ ታውቃለች፡፡ ‹‹አልቤርጓችን ቁጭ ብለን እንቁላል ጥብስና ሻምፓኝ እናዛለን›› አለችው::

‹‹ለዘላለም አንቺ ጋር መሆን ነው የምፈልገው››

ቤት ተከራይቼ መኖር እፈልጋለሁ›› ቤተሰቦቼ ኮኔክቲከት ውስጥ አያቴ ቤት ይሄዳሉ፡፡ እኔ ግን የራሴን

‹‹የሚከራይ ቤት እኔ እፈልግልሻለሁ፡ ከቀናን አንድ ፎቅ ላይ ቤት
‹‹በእውነት!›› አለች በደስታ ሲቃ፡ አንድ ህንጻ ላይ መኖር፡ እሷም ይህን ነበር ስታስብ የነበረው፡፡ ቢሆንም በአንድ በኩል ላግባሽ ብሎ
እንደሚጠይቃት ብታስብም በሌላ በኩል ደግሞ ዓይኗን ማየት አይፈልግ
ይሆናል ብላ ትገምታለች፡፡ ነገር ግን በችኮላ እዚህ ድምዳሜ ላይ ከመድረሷ
እንከራይ ይሆናል››
በፊት ከእሱ መራቅ አልፈለገችም፡፡

‹‹ሆኖም አንድ ያልተፈታ ችግር አለ፡ ናንሲ ሌኔሃን እቀጥርሻለሁ ስላለችኝ ቦስተን ሳልሄድ አልቀርም›› አለች፡፡

‹‹እኔም ቦስተን መምጣት እችላለሁ››
‹‹ትመጣለህ?!›› ስትል ጠየቀች ያለውን ማመን አቅቷት፡፡
‹‹ቦስተን የት ነው የሚገኘው?››

‹‹ኒው ኢንግላንድ፡ እንደ እንግሊዝ አገር ነው››
‹‹እዚያም ያሉ ሰዎች ሰው ይንቃሉ፡፡ ደማቸው ከእንግሊዝ የተቀዳ
ነው››

‹‹ስንት ክፍል ቤት ነው? ምን ዓይነት ቤት ነው የምንከራየው?›› ስትል
ጠየቀችው።

ሄሪ ፈገግ አለና ‹‹ካንድ ክፍል በላይ ሊኖረን አይችልም፡፡ የአንድ ክፍል
ቤት ኪራይ ለመክፈልም ብዙ ትግል ይጠይቃል፡፡ ኑሮ እንደ አገራችን ከሆነ
ረከስ ያለ የቤት ዕቃ እንገዛለን፡፡ ዕድለኛ ከሆንን ደግሞ የኤሌክትሪክ ወይም
የጋዝ ምድጃ ይኖረን ይሆናል፡፡ መጸዳጃ ቤት ግን የጋራ ነው የሚሆነው›

‹‹ኩሽናስ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

ራሱን ነቀነቀና ‹‹ኩሽና ያለው ቤት መከራየት አቅማችን የሚፈቅድ
አይመስለኝም፡››
ምናልባትም ራስን ችለው ሲወጡ ሊገጥም የሚችለውን ኑሮ ካሁኑ
እንድታውቅ እያለማመዳት ሳይሆን አይቀርም፡ እሷ ግን የሚነግራትን
በሙሉ ጥሩ ነው ብላ ተቀብላለች፡፡ በራስህ ቤት ውስጥ በምትፈልገው ጊዜ
የምትፈልገውን ምግብ እያዘጋጀህ መብላት፡ ተቆጪና ተቆጣጣሪ በሌለበት በነጻነት መኖርና የምትቆጣውና የሚያጉረመርም የቤት ሰራተኛ የሌለበት ኑሮ፡፡ ይህማ ጽድቅ ማለት ነው፡፡ ‹‹ግን የቤቱ ባለቤቶች እዚያው ህንጻ ላይ
ነው የሚኖሩት?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አንዳንድ ጊዜ አዎ፡፡ ህንጻው ውስጥ አብረው ቢኖሩ ጥሩ ነው፡፡
ሀንጻውን በደምብ ስለሚንከባከቡት በግል ህይወትሽ መግባታቸው ከፋ እንጂ ሌላ ቦታ የሚኖሩ ከሆነ ግን ህንጻው ቢፈራርስ፣ መስታወት ቢሰበር፣ ቧንቧ ቢፈነዳ፣ ቀለም ቢረግፍና ጣሪያው ቢያፈስ፣ ወዘተ ዞር ብሎ
የሚያየው ሰው የለም፡፡››
👍16
ማርጋሬት ገና ብዙ መማር ያለባት ነገር እንዳለ ተገነዘበች፡፡ ሄሪ ልትጠይቀው ስትል እውጭ ወጥተው የነበሩት ተሳፋሪዎች ተመልሰው መጡ፡፡ እናትም በዚሁ ጊዜ ከመታጠቢያ ቤት ተመለሱ፡ ፊታቸው ቢገረጣም ውበታቸው እንዳለ ነው፡፡ ማርጋሬት እናቷን ስታይ በደስታ ተሞልቶ የነበረው ልቧ ተነፈሰ፡፡ ይህም ከሄሪ ጋር ልትጠፋ ያሰበችው ነገር
የሚሰጣትን ደስታ ሳይበርዝባት አልቀረም፡፡

ጧት ጧት የምግብ ፍላጎት የላትም፡፡ ዛሬ ግን ጅብ አድርጓታል፡ እስቲ
‹‹ሞርቶዴላና እንቁላል አምጣልኝ በርከት አድርገህ›› አለችው አስተናጋጁን፡፡

ሄሪ ትኩር ብሎ ያያታል እንዲህ የራባት ከእሱ ጋር ሌሊቱን በሙሉ የአልጋ ጨዋታ ሲያደርጉ ስላደሩ ነው፡፡ ፈገግ ስትል እሱም ገባውና ቶሎ ፊቱን ዞር አደረገ፡፡

አይሮፕላኑ ትንሽ ቆይቶ ተነሳ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ መነሳቱ ቢሆንም
አሁንም በአይሮፕላን መብረር ደስታ ይሰጣታል፡፡ አሁን መፍራት ትታለች፡፡
ከሄሪ ጋር ያወራችውን ሁሉ መልሳ መላልሳ አሰላሰለችው ሄሪ ከእሷ
ጋር ቦስተን ሊሄድ ነው፡፡ መልከ መልካምና ፎልፏላ በመሆኑ ሴቶች በቀላሉ
ልባቸው የሚቀልጥለት ቢሆንም እሷን ግን ወዷታል፡፡ ምንም እንኳን
ከተዋወቁ ጥቂት ጊዜ ቢሆንም ደስ የሚል ፍቅር ጀምረዋል፡፡ እሱም ጉረኛ
ባለመሆኑ የማይፈጸም ቃል አይገባላትም፡፡ ከእሷ ጋር መሆን ግን ይፈልጋል፡፡

ከእሱ ያገኘችው ፍቅር ደግሞ ጥርጣሬዋን ፍቆላታል፡ እስካሁን ከሄሪ
ጋር የወደፊት ኑሮዋን ለማቆራኘት አስባ አታውቅም፡፡ አሁን ግን እሱን
ማመን ጀምራለች፡፡ የምትፈልገውን ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እርግጠኛ ሆናለች  ነጻነትና ፍቅር፡፡

አይሮፕላኑ አየር ላይ ወጥቶ ቀጥ ብሎ መጓዝ ሲጀምር ለቁርስ የተዘጋጀላቸውን ቡፌ እንዲያነሱ ሲነገራቸው ማርጋሬት አግበስብሳ አነሳች፡ ሁሉም እንጆሪና ክሬም ሲያነሱ ፔርሲ ፈንድሻ አነሳ፡ አባት ሻምፓኝና እንጆሪ ሲያነሱ ማርጋሬት የዳቦ ቅቤና ዳቦ ጨምራ አነሳች፡፡ ማርጋሬት
ከመብል ክፍሉ ልትመለስ ስትል የቀረበላትን አጃ ያለ ምህረት ከምትውጠው
ናንሲ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ ናንሲ ሌላ ልብስ ለብሳ እንደ ምን
ጊዜውም አምሮባታል፡፡ ማርጋሬትን በጥቅሻ ጠራቻትና ድምጿን ዝቅ አድርጋ ‹‹ቦትውድ ላይ ህይወቴን ሊለውጥ የሚችል አንድ መልእክት ደርሶኛል፡፡ ዛሬ አሜሪካ ስገባ ድሉ የኔ ስለሚሆን ያልኩሽን ስራ እንዳገኘሽ ቁጠሪው፡››
ማርጋሬት ፊቷ በደስታ ፈካ፡፡ ‹‹አመሰግናለሁ ናንሲዬ›› አለች፡፡

ናንሲ የስልክ ቁጥሯ
የተፃፈበትን ካርድ በዳቦ ሳህኗ ላይ አስቀመጠችላትና ‹‹ለስራው ዝግጁ ስትሆኚ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውይልኝ›› አለች::

‹‹እደውላለሁ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ እደውላለሁ ደግሜ ደጋግሜ አመሰግናለሁ›› አለች፡፡
ማርጋሬት ወደ መቀመጫዋ የተመለሰችው በደስታ ባህር እየዋኘች
ነው፡፡ አባቷ ናንሲ የሰጠቻትን የስልክና የአድራሻ ካርድ ባያዩ ደስታዋ ነው፡:
ብዙ ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ ምግቡ ላይ ትኩረት ስላደረጉ ነው ያላዩት፡

አባቷ አንድ ቀን ከቤተሰቡ ተለይታ የምትሄድ መሆኑ ሊነገራቸው እንደሚገባ አምናለች፡፡ ከአባቷ ጋር ምንም ዓይነት ጠብ ውስጥ እንዳትገባ እናቷ ቢያስጠነቅቋትም፣ ዞሮ ዞሮ ለአባቷ ቁርጡ ይነገራቸዋል
ጊዜው ሲደርስ፡፡ ባለፈው ጊዜ ጠፍታ ነበር ባይሳካላትም፡፡ አሁን ግን ትታቸው እንደምትሄድ
በግልጽ ለመንገር ቆርጣለች
ይለይለት  ብላ፡፡ በምስጢር
ማድረግ የለባትም ፖሊስም መጥራት የለባትም፡፡ የምትኖርበት ቤትና
የሚያስጠጓት ሰዎች እንዳገኘች ትነግራቸዋለች፡፡

አባቷን ደግሞ ሙግት ልትገጥማቸው የምትችልበት ዓይነተኛው ቦታ ይህ አይሮፕላን ብቻ ነው፡ ኤልሳቤትም የገጠመቻቸው ባቡር ላይ ነበር፡ ይህም ሰርቶላታል፡ ምክንያቱም አባት ባቡር ላይ ምንም ሊያደርጓት
ስለማይችሉ፡ አሜሪካ ከደረሱ በኋላ ሆቴል ውስጥ የፈለጉትን ማድረግ
ይችላሉ፡

መቼ ትንገራቸው፡፡ ቶሎ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡
ፔርሲ ብድግ አለና ‹‹ፈንዲሻ ልጨምር እስቲ›› አለ፡፡
‹‹ቁጭ በል›› አሉ አባት በቁጣ ‹‹ሞርቶዴላ እየመጣ ነው፡፡ ግብስብሱን
ሁላ አትብላ፡›› አባት ጥሎባቸው ፈንድሻ አይወዱም፡፡

‹‹እኔ አልጠገብኩም›› አለና ትዕዛዛቸውን ረግጦ ሄደ፡ ማርጋሬት የፔርሲ አድራጎት ገርሟታል፡
አባት በድንጋጤ አፋቸው ተሳሰረ፡፡

ፔርሲ ከዚህ በፊት አባቱን እንዲህ ፊት ለፊት ትዕዛዛቸውን አልቀበልም ብሎ አያውቅም፡፡

እናትም አይናቸው  ፈጧል፡ ሁሉም  ፔርሲ የአባቱን ትዕዛዝ እንዲፈጽም ነበር ፍላጎታቸው፡፡ እሱ ግን ሰሃን ሙሉ ፈንድሻ ይዞ ተመለስና
ቁጭ ብሎ መብላቱን ቀጠለ፡፡
‹‹ይሄን ፈንድሻ ተው አላልኩህም?›› አሉ አባት፡፡

‹‹በኔ ሆድ አያገባህም›› አላቸውና ፔርሲ መብላቱን ቀጠለ፡፡
አባት ተነስተው ፔርሲን ሊመቱ ሲሉ አስተናጋጁ ኒኪ ቋሊማ፣ ሞርቶዴላና ቅቅል  እንቁላል ይዞ መጣና ፊታቸው አስቀመጠላቸው፡
ማርጋሬት ካሁን አሁን ሰሃኑን አንስተው ፔርሲ ላይ ወረወሩት ብላ ጠብቃ
ነበር፡ እሳቸው ርቧቸው ስለነበር ቢላና ሹካቸውን አነሱና ‹ሰናፍጭ
አምጣልኝ›› አሉት ኒኪን፡፡
‹‹ይቅርታ ሰናፍጭ አንይዝም ጌታዬ፡››
‹‹ሰናፍጭ የለም?›› ሲሉ አባት ጠየቁ ግስላ ሆነው ‹‹ታዲያ እንዴት አድርጌ ነው ያለ ሰናፍጭ የምበላው?››
ኒኪም ድንግጥ አለና ‹‹ይቅርታ ጌታዬ ከዚህ ቀደም ሰናፍጭ የሚጠይቅ
ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም:: በሚቀጥለው በረራ በእርግጠኛነት ሰናፍጭ
ይዘን እንቀርባለን›› አለ፡፡
እኔ የፈለኩት አሁን ነው፡፡ ሌላ ጊዜ አመጣለሁ ያልከው አሁን ምን
ሊረባኝ››
‹‹ ውነት ነው ይህን ማለት ለአሁኑ ምንም አይጠቅምም ይቅርታ
ጌታዬ፡››
አባት እያልጎመጎሙ ምግባቸውን በሹካ እየወጉ ይወቁት ጀመር
ንዴታቸውንም በኒኪ ላይ ስለተወጡ ፔርሲ ከቁጣ አምልጧል፡ አንድ ነገር
ከያዙ እንደማይለቁ ስለምታውቅ አባቷ በዝምታ ስላለፉት ማርጋሬት
ገርሟታል፡፡

ማርጋሬት፣ ኒኪ ያመጣላትን ሞርቶዴላና እንቁላል ጣፍጧት ስልቅጥ
አደረገችው: አባባ በስተመጨረሻ መለሳለስ ጀመረ እንዴ? እንዲህ
ያቀዘቀዛቸው በፖለቲካው መስክ ተሰሚነት በማጣታቸው፣ የጦርነቱ
መጀመር፣ ስደቱና የመጀመሪያ ልጃቸው ትዕዛዛቸውን ጥሳ መኮብለሏዐሳይሆን አይቀርም፡፡

ማርጋሬት የተብሰለሰለችበትን ነገር ለመናገር ከዚህ የተሻለ ጊዜ
እንደሌለ አወቀች፡፡
ቁርሷን አጣጥማ ጨረሰችና ሌሎች እስኪጨርሱ ጠበቀች፡ ከዚያም
ኒኪ የተበላባቸውን ሳህኖች እስኪያነሳና ቡና እስኪጠጣ ጠበቀች፡ የማታ ማታ በጭንቀት የወጠራት ጉዳይ የሚፈነዳበት ጊዜ መድረሱ አልቀረም ደረሰ፡
እናም አባቷ ከተቀመጡበት ትይዩ ተቀመጠችና ትንፋሿን በረጅሙ ለቃ
‹‹አባባ አንድ የማናግርህ ነገር ስላለኝ እንዳትቆጣኝ›› አለች፡፡
እናት ‹‹አሁን ተይ እባክሽ›› ሲሉ አጉረመረሙ:
‹‹ምንድነው አሁን?›› ሲሉ አባት ሚስታቸውን ጠየቁ፡፡

‹‹አስራ ዘጠኝ ዓመት ሞልቶኛል ነገር ግን የፈሰሰ ውሃ እንኳን አቅንቼ አላውቅም አሁን ስራ መስራት ይኖርብኛል›› አለች
ለምን የኔ ማር?›› እናት ጠየቁ፡፡
‹‹ብቻዬን መሆን ስለምፈልግ፡፡››
‹‹አንቺ የምትኖሪውን ኑሮ ታገኛላችሁ ቢባሉ ዓይናቸውን ጠንቁለው
ለማውጣት ፈቃደኛ የሚሆኑ በየፋብሪካውና በየቢሮው የሚሰሩ ስንትና ስንት ሴቶች አሉ መሰለሽ›› አሉ እናት፡፡

‹‹አውቃለሁ እማ›› አለች፡፡ እናቷ ከእሷ መከራከሩን የመረጡት ከአባቷ
ጋር አታካሮ እንዳትገጥም ብለው መሆኑን አውቃለች፡ ቢሆንም አባቷን
ግምባር ለግምባር መግጠሟ እንደሆን አይቀርም::

እናት ባንድ ጊዜ እጃቸውን መስጠታቸው ገርሟታል፡፡ ‹‹ከኛ ተለይተሽ መኖር የምትፈልጊ ከሆነ አያትሽ አብሮሽ የሚኖር ሰው ይፈልግልሻል››
አሉ፡
👍20😱1
‹‹ስራ አግኝቻለሁ እርዳታ አልፈልግም››

እናት ይህን ሲሰሙ ተገረሙ: ‹‹አሜሪካ ውስጥ? እንዴት››

ማርጋሬት ስለናንሲ ሌኔሃን ልትነግራቸው አትፈልግም:፡ ስራ የምትሰጣት ናንሲ መሆንዋን ካወቁ ከእሷ ጋር ተነጋግረው ሁሉንም ነገር
ያበላሹባታል፡ ‹‹ሁሉም ነገር አልቋል›› አለች በደፈናው፡፡
‹‹ምንድነው ያገኘሽው ስራ?›› እናት ጠየቁ፡፡
‹‹በጫማ ፋብሪካ ውስጥ የሽያጭ ረዳትነት››
‹‹ወይ አምላኬ! አበድሽ ይህን አይነት ስራ የምትሰሪው?››
ማርጋሬት በንዴት ከንፈሯን ነከሰች፡፡ ለምንድነው እናቷ ስራ እንዲህ የሚንቁት? ‹‹እኔ አላበድኩም እንደውም በዚህ አስተሳሰቤ እኮራለሁ›› አለች ማርጋሬት፡

‹‹ፋብሪካው የት ነው የሚገኘው?››
‹‹ፋብሪካ ውስጥ እንደሆነ አትሰሪም፤ በቃ!›› ሲሉ አባት ለመጀመሪያ
ጊዜ ተናገሩ፡

‹‹በሽያጭ ክፍል ውስጥ ነው የምሰራው፧ ፋብሪካ ውስጥ አይደለም፡፡
ደግሞም ቦስተን ውስጥ ስለሆነ ችግር የለም›› አለች ማርጋሬት፡
‹‹ያ ከሆነ ጥሩ ነው›› አሉ እናት፡ ‹‹የምትኖሪው ግን ስታንፎርድ ነው
እንጂ ቦስተን ውስጥ አይደለም››
‹‹አይሆንም እማ ቦስተን ነው የምኖረው፡፡ ትቼያችሁ ወደ ቦስተን ልሄድ መሆኑን እወቁት ነው የምለው፡፡ እዚያ ቤት ተከራይቼ ነው
የምኖረው››

‹‹ይሄ የማይሆን ነው›› አሉ እናት፡፡

ማርጋሬት በንዴት ተንጨረጨረች
አታጣጥዪ እማ›› አለች ከጣራ በላይ እየጮኸች፡፡ እሷ ስትጮህ እናቷ ስለደነገጡ ጸጸት ተሰማት፡ ‹‹በኔ ዕድሜ ወጣት ሴቶች የሚያደርጉትን ነው እኔ የማደርገው›› ስትል አከለች ቀስ ብላ።

አዎ በአንቺ ዕድሜ ያሉ ወጣቶች እንዲህ ነው የሚያደርጉት፡ እንዳንቺ ያሉ የጌታ ልጆች ግን አይሞክሩትም›› አሉ እናት፡፡

‹‹ታዲያ እኔ ከሌሎቹ በምን እለያለሁ?››
ብሳምንት አምስት ዶላር እየተከፈለሽ ለምትሰሪው ስራ አባትሽ መቶ
ዶላር የሚከፍልበት ምክንያት የለም››

‹‹አባባ ለቤት ኪራይ እንዲከፍልልኝ አልፈልግም››

‹‹ታዲያ የት ልትኖሪ ነው?››
‹‹ኪራይ ቤት ውስጥ አልኩሽ እኮ እማ››
‹‹የድሆች መኖሪያ ውስጥ! ግን ምን ታተርፊያለሽ?››
‹‹ወደ አገሬ መመለሻ ገንዘብ እስኪሞላልኝ ድረስ ገንዘብ አስቀምጣለሁ፡፡
ከዚያም ጦሩን እቀላቀላለሁ›› አለች ማርጋሬት፡
‹‹ስለምትናገሪው ምንም የምታውቂው ነገር የለም›› አሉ አባት፡፡
ማርጋሬት ንዴት ጠቅ አደረጋትና ‹‹ምንድነው የማላውቀው ነገር
አባባ?›› ስትል ጠየቀች:
እናት ጣልቃ ገቡና ‹‹አዎ የምታውቂው ነገር የለም›› አሉ፡

ማርጋት የእናቷን ንግግር አቋረጠችና ‹‹ቢሮ ውስጥ መላላክ፣ ቡና ማፍላትና ስልክ ማገናኘት አያቅተኝም፡፡ አንድ ክፍል ውስጥ እንደምኖር፣
መጸዳጃ ቤት ከሌሎች ጋር በጋራ እንደምጠቀም አውቃለሁ ደሃ መሆን
ባልፈልግም ነጻ ሆኜ መኖር ግን ያስደስተኛል›› አለች፡፡

‹‹ምንም የምታውቂው ነገር እኮ የለም›› አሉ አባት በንቀት ‹‹ነጻነት?
አንቺ? ከማጎሪያ እንደተለቀቀች ጥንቸል ነው የምትሆኚው ልጅት! ዕድሜሽን ሙሉ ተሞላቀሽ ስላደግሽ ብልሹ ልጅ  ሆነሻል፡ ትምህርት እንኳን
አልተማርሽም›› አሉ፡፡ አባቷ በመጨረሻ የተናገሩት ነገር እንዴት ወደ ኋላ
እንዳስቀራት ስላስታወሳት በንዴት ‹‹እኔ መማር እፈልግ ነበር አንተ ነህ
ከትምህርቴ አስቀርተህ እንደዚህ መሀይም ያደርግኸኝ›› አለች፡፡

‹‹ልብስሽ እየታጠበልሽ፣ ምግብሽ እየተዘጋጀልሽ፣ የምትሄጅበት ቦታ
ሁሉ ሾፌር እያመላለሰሽ፣ ሌላው ቢቀር ከቤት እንዳትወጪ ሲባል የጎረቤት
ልጆች እየመጡ እያጫወቱሽ ነው ያደግሽው፡፡ ይሄ  ሁሉ እንዴት እንደሚደረግልሽ እንኳን ሳታውቂ ነው ያደግሽው፡ አንድ ዳቦ ስንት
እንደሚያወጣ እንኳን ሳታውቂ ብቻዬን ልኖር ነው ትችያለሽ›› አሉ አባት
ምርር ብለው፡፡

‹‹ብቻዬን ስኖር ይህን ሁሉ በሂደት ማወቅ እችላለሁ››
‹‹ፓንትሽን እንኳን ማጠብ አትችይም፡፡ በአውቶብስ ተሳፍረሽ አታውቂም፡፡ አንድ ቤት ውስጥ ለብቻሽ ተኝተሽ አታውቂም፡፡ የመቀስቀሻ ሰዓት እንዴት እንደሚሞላ፣ ወጥመድ እንዴት እንደሚጠመድ፣ሰሃን
ማጠብ፣ እንቁላል መጥበስ አታውቂም››

‹‹ታዲያ ይሄ የማን ጥፋት ነው? ይሄን ሁሉ እንዳላውቅ ያደረግኸኝ አንት አይደለህም ወይ?›› አለች ማርጋሬት እያለቀሰች፡
አባት ፊታቸውን እንዳቀጨሙ ‹‹ቢሮ ውስጥስ ምን ልትጠቅሚ
ትችያለሽ? ሻይ ማፍላት እንኳን አታውቂ፤ ከጧቱ ሶስት ሰዓት እስከ አስር
ሰዓት ድረስ ቆመሽ መስራት አትችይ ይግረምሽና  ሳምንት እንኳን
አትቆይም፧ ጥለሽው ትወጫለሽ፡፡››

ማርጋሬት ሲያስጨንቃት የነበረውን ነገር አባቷ ሲነግሯት ሆዷ በብስጭት ታመሰ፡፡ አባቷ ያሉት እውነት መሆኑን ስታስበው ፍርሃት
ፍርሃት አላት፡ ብቻዋን መኖር ሳያስጨንቃት አልቀረም: አንድ ስህተት
ሰርታ ወይም መስራት አቅቷት ከስራዋ ልትባረር ትችላለች፡፡ አባቷ በምሬት
የተናገሩት ነገር ወደፊት ሊሆን እንደሚችል ሳትገምት አልቀረችም:
የወደፊት ራዕይዋን የሚንድባት መሰላት፡፡
እምባዋን በጉንጮቿ
እየተንዥቀዥቀ አነባች፡:

አባቷ ጣታቸውን እያወዛወዙና ከጣራ በላይ እየጮሁ ‹‹ቦስተን ከተማ
እንደ ኦክሰንፎርድ መንደር እንዳይመስልሽ፡፡ እዚያ ብትነሺ ብትፈርጪ
የሚረዳሽ የለም፡ በዘረቢሶች ልትመረዢ ትቺያለሽ፡፡ ይሁዳውያን ቤት
በረንዳ አዳሪ ኔግሮዎች አስገድደው ይደፍሩሻል፡፡ ጦሩን እቀላቀላለሁ ላልሺው.›› ሲሉ አቋረጠቻቸውና፣

‹‹በሺህ የሚቆጠሩ እንደኔ ያሉ ወጣት ሴቶች ጦሩን ተቀላቅለዋል›› አለች ማርጋሬት እምባ በተናነቀው ድምጽ።

‹‹ታዲያ እነሱ አንዳንቺ ያሉ ሴቶች አይደሉም፡፡ እነሱ ጠንካራ ሴቶች ናቸው፡፡ እነሱ በጧት ተነስተው የጉልበት ስራ መስራት የሚችሉ ናቸው እንጂ እንዳንቺ ተሞላቀው ያደጉ ልፍስፍሶች አይደሉም፡፡  እግዜር አያድርገውና አንድ ችግር ቢደርስብሽ ዋጋ የለሽም›› አሉ አባት፡

ማርጋሬት ባለፈው ከቤት ጠፍታ የሄደች ጊዜ እንዴት እግሯ እንደተሳሰረ፣ ምን ያህል እንደፈራችና አቅመቢስ እንደነበረች ስታስታውስ በእፍረት ትሸማቀቃለች፡፡ በአንድ በኩል አባቷ እውነታቸውን ነው፡፡

አባቷ ጣታቸውን ወደ እሷ እየቀሰሩ ዓይናቸው ተጎልጉሎ የወጣ
እስኪመስል ድረስ አፍጥጠው ‹‹በቢሮ ስራውም ሆነ በጦሩ ውስጥ ሳምንት እንኳን ከቆየሽ ከምላሴ ጠጉር ይነቀል፤ ልፍስፍስ ነሽ›› አሉና በተናገሩት
ረክተው ቁጭ አሉ፡
ከዚያም ሄሪ ከየት መጣ ሳይባል ‹‹ይበቃል!›› ሲል ተሰማ፡ ይሄ የእሷና
የአባቷ ጉዳይ ቢሆንም ፍቅረኛው ስትሰደብ አላስችለው ብሎ ከጎኗ ሊቆም ደረሰላት፡፡ ሄሪ አጠገቧ መጥቶ ቁጭ አለና መሃረቡን አውጥቶ በእምባ
የረጠቡ ጉንጮቿን አበሰላት፡
አባትም ‹‹አንተ ወጠጤ · ›› ብለው ለመናገር ያሰቡትን ተናግረው ሳይጨርሱ ሄሪ ከመቀመጫው ተነሳና ‹‹እኔ ሴት ወይም ልጅ አይደለሁም፧ ከዚህ በኋላ ቢሰድቡኝ በቡጢ ነው የማንገጫግጮት›› አላቸው፡

አባት በዚህ ጊዜ አደብ ገዙ፡:

ሄሪ ተመልሶ ማርጋሬት ጎን ቁጭ አለ፡፡

ማርጋሬት ብትደናደድም በሆዷ ድል እንዳደረገች ይሰማታል፡፡ ትታቸው
እንደምትሄድ ነግራቸዋለች፡ ምንም እንኳን ቢቆጧትም፣ ቢያፌዙባትም፣
ቢያስለቅሷትም ከአቋሟ ንቅንቅ አላደረጓትም፡፡ ለመሄድ ቆርጣለች፡፡
👍15
ይህም ሆኖ ጥርጣሬ ውስጥ ሳይከቷት አልቀረም፡፡ ምናልባትም
በመጨረሻው ሰዓት ላይ ያሰበችውን እንዳታደርግ ሽባ ሊያደርጋት የሚችል
ሽብር ሳይለቁባት አልቀረም፡፡ ለረጅም ሰዓት ያወረዱባት የስድብ ውርጅብኝና ፌዝ በራሷ መቆም እንደማትችል አድርጋ እንድትገምት አድርጓታል፡በህይወቷ በድፍረት ያደረገችው አንድም ነገር የለም፡ ታዲያ አሁን ታደርገው ይሆን? አዎ  አደርገዋለሁ አለች በሆዷ እኔ ልፍስፍስ አይደለሁም፧ አለመሆኔንም በተግባር አሳያለሁ፡፡›

አባቷ ተስፋ ለማስቆረጥ ብዙ ቢጥሩም አልተሳካላቸውም፡ ነገር ግን
ጉዳዩን እንዳልተዉት እርግጥ ሆኗል፡ ወደ ሄሪ ፊቷን አዞረች፡፡ በአባቷ ፊት
ላይ የበቀል ስሜት ይነበባል፡፡ ኤልሳቤት ትዕዛዛቸውን ጥሳ ጥላቸው
ስለሄደች ልጅነቷን ክደዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ቤተሰብ አለኝ ብላ መመለስ አትችልም፡

ለማርጋሬትስ ምን አስበውላታል?

ይቀጥላል
👍10
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ሰባት (37) «ማሪዮን» አለ። አየችው ፤ አቤት እንደማለት ። «ማሪዮን ያለፈው ኣልፏል ። ላሁኑ ሁለቱ የሚገናኙበትን መንገድ ቀይሺ ። የሚቻልሽን ሞክሪ ። ከዚያ በኋላ የሁለቱ ጉዳይ ነው። አንቺ ምንም ማድረግ አትችይም ። እኔና አንቺ ብዙ እድሜ አልትረፈንም ። ያችኮ ያለችዋን የተቻለንን ያህል እንድንደሰትባት እፈልጋለሁ እንጋባ ። አንድ ላይ እንኑር ፤ በሰላም ። እኔም እስከ ዛሬ የናፈቅሁት ፣ አንቺም ሠራሁት በምትይው ሀጢአት እስከ ዛሬ የተቀጣሽው በቂ ነው ። እኛም'ኮ በደስታ የመኖር ድርሻ አለን» አለ ጆርጅ ። ‹‹ድርሻው ይሁን ፣ ግን እኔ የመደሰት መብት ያለኝ ይመሰልሀል ጆርጅ ?» አለች ማሪዮን ቅዝዝ ብላ ፤ ከልቧ። ይህን ስትል ቅዝዝ እንዳለች ቁልቁል ሲያያት ገና ለግላጋ ወጣት ሆና ታየችው ፤ ለጆርጅ ኮሎዌ ። «በደንብ ነዋ |» አላት «የመኖር መብትሽን ማን ሊነሳሽ ፍቅሬ ?» ከዚያም ፀፀቷን ሁሉ እንድትረሳ ፤ ሀጢአት የምትለው ነገር ከንቱ ሀሳብ መሆኑንና ለወደፊቱ የሚቻለውን ካደረገች በኋላ ደስታቸውን እየተላበሱ በሰላም መኖር እንዳለባቸው ደግሞ ነገራት። ቀጥሎም… «ላሁኑ ግን ማረፍ አለብሽ ለጥ በቃ ። ለእንደዚህ ያለው በሽታ መድሐኒቱ እረፍት ነው። እሺ ?» አለ ወደ ላይ እያየችው ፍንድቅ ብላ ሳቀችና «ጆርጅ ኮሎዌ እወድሀለሁ» አለችው፡፡ «መውደድሽ ደግ ሆነ ። ምክንያቱም ወደድሽም ጠላሽ አንችኑ ማግባቴ አይቀርም ነበር ። የመጣው ቢመጣ። ገባሽ?»
«አዎና» ሁለቱም በደስታ ግለው በፈገግታ ይንቦገቦጉ ጀመር።

አንድ ነርስ በሩን ቀስ ብላ ከፍታ ሀኪሙ ለማሪዮን በደንብ መተኛት እንዳለባት መግለፃቸውንና ሌሊቱ እየተገባደደ መሆኑን እስክትነግራቸው ሁሉንም ረስተው በፍቅር ተተብትበው አንድ ላይ ቆዩ ። ጆርጅ ኮሎዌ እንደወጣ ማሪዮን ሂልያርድ ወደ ኒው ዮርክ ስልክ ደወለች… ከሳንፍራንሲስኮ ማለት ነው ። ጊዜው (ኒውዮርክ ውስጥ) አነጋጉ ላይ ቢሆንም ማይክል ስልኩን ቶሎ አላነሳውም ። ጠበቀች ፤ ማሪዮን። «ሃሎ?» አለ ፤እንቅልፍ የተጫጫነው የማይክል ድምፅ «የኔ ሸጋ ፤እኔ ነኝ » አለች ማሪዮን። «እማዬ ነሽ ? ደህና ነሽ ? ተሻለሽ? » ጥያቄውን አዥጎደጎደው። «ደህና ነኝ ። አይዞህ አትስጋ ። ይልቅስ አንድ ነገር ልነግርህ ስለፈለኩ ነው የደወልኩልህ »
« ገባኝ ። ጆርጅ ነግሮኛል » አለ እያዛጋ «እንዴት ነው እሺታ ወይስ እምቢታ?»
«እምቢታ የለም ። ሁሉንም ተቀብያለሁ » አለች ። «አሁን የጠራሁህ ለሌላ ጉዳይ ነበር» አለች ። መልስ አልሰጣትም ። ትንሽ እንደማጉረምረም ብቻ አለ ። «ስለዚያች ልጅ ጉዳይ» አለች ማሪዮን ። «የቷ ልጅ?» ማይክ እየተደናገረ ጠየቀ ። «ፎቶግራፍ አንሺዋ... ማይክል ገና አልነቃህም”ንዴ
«ገባኝ። እሺ።ምን ትሁን!»
«ታስፈልገናለች»
«ያን ያህል››
«በጣም ። ሆኖም እንደምታውቀው እንግዲህ እኔ የጆርጅ ሰው ነኝ። ልጀቷን ማደኑ ያንተ ሥራ መሆኑ ነው»
«ትቀልጃለሽ እማዬ ? እኔ ያለብኝን የሥራ ውጥረት እያወቅሺው ። ቤን ይከታተል የሷን ጉዳይ»
‹‹ቤንንማ አፍንጫህን ላስ አለችውኮ ። ይልቅ ስማ ። ልጅቷ ዘመናዊ ከመሆኗም በላይ የታረመችና በእውቀቷም የምትተማመን ሰው ናት ። ከማንም ኩታራ ጋር ለመነጋገር የምትፈቅድ አይመስለኝም… ከተቀጣሪዎች ጋር ማለቴ ነው»
«ገባኝ ። ግን የመቀመጫ እሾህ መስላ ነው ለኔ የታየችኝ››
«እሷ ሳትሆን አንተ ነህ እንዲያ የሆንክብኝ ። በምን መንገድ ልታግባባት እንደምትሞክር አላውቅም ። በሆነው ፣ በመሰለህ ሁሉ ብትቀርባት ደንታዬ አይደለም ። ግን እንፈልጋታለን። ለኔ ስትልም ቢሆን ይህን ነገር ዳር እንድታደርገው እፈልጋለሁ››
«የለም ፤ የለም ዛሬ ደህና አይደለሽም ። ጊዜ እንደሌለኝ እያወቅሽ እንዲህ ስትይ» አለ። «ይልቅ ይህን ጉዳይ ብቻ አንቺ ጨርሺ በቃ።»
«አላደርገውም ማይክ ፤ ደግሞ ይህን ጉዳይ አልፈፅምም የምትል ከሆነ ገና እኮ ነው ፤ሥራውን አልለቀኩምኮ !››
«ይህን ካላደረግክ አንደኛ ሥራዬን አልለቅም ፤ እዚያው እቢሮዬ ውስጥ እሞታለሁ ። ሁለተኛ…»
«በቃ በቃ!» አለ ማይክል አቋርጧት «እንዳልሽው ይሆናል »
«ልባርግ ! ቀልድ አይደለም ። ቃል ፤ ቃል ነው ። ቃልህን ከሻርክ ቃሌን እሽራለሁ ።»
« አረ በእግዜር |! እሺ አልኩሽኮ አሁን ትተኛለሽ ወይስ ?»
«እተኛለሁ ግን ይኸ ጉዳይ ነገ ዛሬ እንደሌለው እወቅ ። ገባህ?»
«ገባኝ ስሟን ማን ነበር ያልሺኝ ››
‹‹ሜሪ አዳምሰን»
«ሜሪ አዳምሰን ። በቃ ከነገ ጀምሮ የማገኝበትን መንገድ እፈልጋለሁ»
«ደግ... እግዜር ያክብርህ የኔ ቆንጆ»
«ደህና ደሪ የኔ አሮጊት ።... ቆይ... ቆይ እንኳን ለፍጥምጥሙ አበቃን ። ወሬውን ላናፍሰው ? ሙሽራው ማን እንደሆነ ልናገር ?»
«ምን ይጠየቃል ? ከጆርጅ የተሻለ ማንን ላገኝ ? አላፍርበትም» ሁለቱም ዘጉ ።

ማይክልንና ሜሪን ካገናኘች ፤ሁለቱ ተዋውቀው አንድ ነገር ከመሰረቱ አእምሮዋ ሰላም ያገኛል ። ማይክ የሠራችውን ሁሉ ሲሰማ ምን ይላት ? ሆኖም ፍቅሩን የማግኘቱ ደስታ ለሷ የሚኖረውን ጥላቻ ሊቀንሰው ይችላል። በኋላ ተፀፅታ የሠራችውን ሲያይ ይቅር ይላታል ። እንቅልፍ እያንሸራተተ……

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
14👍11
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ሁለት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ማርጋሬት ከእንቅልፏ  ስትነቃ ሃሳብ ውስጥ ገባች፡: ዛሬ ለአባቴ ቁርጡን እነግረዋለሁ  አለች በሆዷ አሜሪካ ሲደርሱ ከእነሱ ጋር እንደማትኖር ከቤት ወጥታ ቤት ተከራይታ እና ስራ ይዛ ልትኖር እንደሆነ ትነግራቸዋለች፡፡ መቼም አባቷ ይህን ሲሰሙ ኮረንቲ ይጨብጣሉ፡፡ ማርጋሬት ነገሩን ባሰበችው ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ስምንት (38) ጆርጅ ኮሎዌ በፍቅር ሲስማት ለስላሳው ሙዚቃ እንደገና ጀመረ ። የሠርጉ ሥነ ሥርዓት የተከናወነው በማሪዮን ሂልያርድ ቤት ሲሆን እሷም ለዚሁ የሠርጓ ቀን ሶስት ሙዚቀኞች ቀጥራ ነበር ። ለሠርጉ የታደሙት አንድ ሰባ የሚሆኑ ሰዎች ሲሆኑ ፤ የምግብ ቤቱ ክፍልም እንደ የዳንስ አዳራሽ ሆኖ ተዘጋጅቷል ። የቡፌ ግብዣው የሚከናወነው ደግሞ በዚሁ መኖሪያ ቤተ መፃሕፍት ውስጥ ነው ። ዝግጅቱ የተከናወነ ፤ቀኑም ተስማሚ ነበር። የየካቲት የመጨረሻው ቀን ። ይህ ቀን ጥርት ያለ ፤ ነፋሻና ሳንካ አልባ የሆነ የኒውዮርክ ቀን ሆኗል ። ማሪዮን ሳንፍራንሲስኮ የደረሰባትን ነገር እንደመርሳት ያለች ይመስላል ። ደሟ ግጥም ብሎ ሞልቷል ። ጆርጅ በደስታ ፈነድቋል፡፡

ጋዜጠኞችም በዚሁ ሠርግ ላይ ተገኝተዋል ። ታይም የተባለው ታዋቂ መጽሔት ፎቶ አንሺ ማይክልንና ማሪዮንን ፤ ባሏ ጆርጅን ፎቶ አነሳቸው። ማሪዮን በባለቤቷና በልጅዋ ታጅባ ነበር የተነሳችው ። ማይክል ሂልያርድ እናቱን ዳረ ። ማሪዮን ሂልያርድ ካሁን ጀምሮ ፤ ማሪዮን ኮሎዊ ትባላለች ፤ የጆርጅ ኮሎዌ ባለቤት ። ማይክል ሂልያርድ ከዚህ ጊዜ ጄምሮ የኮተር ሂልያርድ ባለቤት ነው ። የአንድ ግዙፍ ድርጅት (የኮተር ሂልያርድን ያክል ግዙፍ ድርጅት) ፕሬዚዳንት መሆን ! ለማይክል የተሰማው ስሜት . . . ሆኖም ይህም ስሜት ቢሰማውም . . . ይህን ስሜቱን ደግሞ ማይክል ሊደብቅ አይሻም ። ፕሬዚዳንት ፣ በዚህ እድሜው ባለቤት ! በማግስቱ ታይም የተባለው በመላው ዓለም የሚሰራጭ መጽሔት የማይክልን ፎቶ በሽፋኑ ይዞ ወጣ ። ድንቅ ተባል ። በዚህ እድሜ የኮተር ሂልያርድ ፕሬዚዳንት !. . የማሪዮንና የጆርጅ ኮሎዌ ሠርግ እለት የዛ ለት ማይክል ወደእናቱ ቀረብ ብሎ፣ «ሚስዝ ኮሎዌ ! » አለ አዲሱን የጋብቻ ስሟን እየተጠቀመና ለቀሰስተኛው ዳንስ እየጋበዛት ። «አዲሱን ስም እናክብረው ጋብቻውን እናክብረው» አለ ። አዲሱን ስም እናክብረው ሲል ናንሲ ትዝ አለችው ። እንዳለው ሆነ ። አከበሩት ፤ ጆርጅና ማሪዮን ኩሎዌ በጋብቻ ተሳሰሩ ። ሁለቱም ለረጅም ጊዜ ተሰቃይተዋል ። ደስ ይበላቸው ፤ ደስታ ይገባቸዋል ። ደስታ ያስፈልጋቸዋል ። ጋብቻቸውን ምክንያት በማድረግ ወደ አውሮፓ ሔደው ሽርሽር ይላሉ። ደስ ይሰኛሉ ። « በጣም ቆንጆ ነህ የኔ ሸጋ » አለች ማሪዮን ፡ ማይክልን በፍቅር እየተመለከተች ። «ያንቺን አላየሽ ። አሸብርቀሻል ፤ ተውበሻል » አለ ማይክ ከልቡ። «ቤቱ ሳይቀር እንደ አዲስ ያበራል ፤ አምሯል » እለ ። «በጣም አሸብርቋል አደል ? » አለች ማሪዮን ። ማይክ ከልቡ ተደስቶ ማሪዮንን ተመለከታት ። እናቱ ነችኮ። ይህቺ ሙሽሪት እናቱ ነች ። ሙሽራ ትመስላለች ፤ የእውነት ሁኔታዋ ሁሉ የሙሽራ . . . የልጃገረድ ሙሽራ ሆኖ ታየው ። «ሚስተር ሂልያርድ » የሚል ድምዕ ቀሰቀሰው ። « ማይክል ሂልያርድ በጣም ደስ ያለህ ትመስላለህ ዛሬ » ዌንዲ ነበረች ። ሲያያት እንደወትሮው አላፈረም ። ዓይኑ አልሸሻትም ። ይህ ቀርቷል። ዛሬ ቤን አቭሪና ዌንዲ ሊጋቡ ተጫጭተዋል ። የማጫ ቀለበቷ (ዕንቁ ያለበት ቀለበቷ ) እቀለበት ጣቷ ላይ ያበራል ። ሊጋቡ ወስነዋል ። ማይክል ሂልያርድም ዋና ሚዜ ሆኖ ተመርጧል ። ተስማምቷልም ።

«ደስ አትልም?» አለ ማይክ እናቱን ለዌንዲ እያሳያት ዌንዲ አንገቷን በአዎንታ ነቅንቃ በደስታ ፈገግ አሰች ። ደስ ብሎት ስላየችው ደስ እላት ። እንዲህ ደስ የሚለው መስሏት አያውቅም ። ብቻ ነገሩ ሁሉ አይገባትም ። ገባት አልገባት ደሞ ደንታዋ አይደለም ። ለሷ እንደሆነ ቤን አለላት ። የቤንን ያህል በፍቅር ደስ ያሰኛት ወንድ የለም ። «እንቺም በሚቀጥለው በጋ እንዲህ ቆንጆ ሆነሽ ማየት አለብኝ ። ሙሽራ ቁንጅት ሲል የሠራ አከላቴ በደስታ ይሞላል » አለ ማይክል ዊንዲን በደስታ እያየ ። ደስ አላት ። ዛሬ ጓደኛዋ ነው። ትወደዋለች ። አትመኘውም ለጓደኛ የሚገባውን ሁሉ ግን ትመኝለታለች ። «አሀ የኛ ጀግና ፤ የሰው እጮኛ ለማማገጥ ነዋ ?» ቤን አቭሪ ነበር እንዲህ ያለው ። ቤን ሶስት መለኪያ ሻምፓኝ ይዞ ነበር የመጣው ። «በሉ ተቀመጡ። ይኸው ! ሁለት መለኪያ የናንተ ነው አንሱና ጠጡ» አለ ቤን በደስታ ፈክቶ ። ቀጥሎም ፣ «በነገራችን ላይ ማይክ ምን እንደሚሻለኝ እንጃ እንጂ ፍቅር ይዞኛል ፤ ከማሪዮን ጋር » አለ ። «ቀለጥክ… ዛሬ ጠዋት ላንድ ጎረምሳ ዳርኳት» አለ ማይክ ። ቤን ወይኔ በሚል ሁኔታ ጣትና ጣቱን አጩሆ ደንግጦ ቀረ። በዚህም ነገር ሶስቱም ከልባቸው ሳቁ። ሙዚቃው የተጀመረው ገና ስቀው ሳያበቁ ነበር ። በዚህ ጊዜ ማይክ « ሙዚቃው ጀመረ። መሔድና እናቴን ለዳንስ መጋበዝ አለብኝ ። ደንቡ እንደሚለው እኔና እሷ ዳንሱን እንከፍታለን ። ጆርጅ ይቅርታ ጠይቆ ይነጥቀኛል።» ይህን ብሎ ወደ ዳንሱ አዳራሽ ከገባ በኋላ ነበር እናቱን ባዲሱ የጋብቻ ስሟ ጠርቶ የጋበዛት ።

« ዛሬ በጣም ደስ ያለው ይመስላል » አለች ዌንዲ ማይክ እንደተለያቸው ። «እንዲህ አንዳንድ ቀን እንኳ ደስ ብሎት እንየው እንጂ » አለ ቤን ፊቱ በተመስጦ ተሞልቶ። ከዚያም ድንገት ተመስጦን ነጥቆ ወጥቶና ከልቡ ፈገግ ብሎ «አንቺም ዛሬ በጣም ደስ ብሎሻል » አላት «ደሞ እኔ መቼ ከፍቶኝ ያውቃል? ዕድሜ ላንተ እንጂ›› አለች ከልቧ ። ለጥቂት ጊዜ ፀጥታ ሆነ ። ከዚያ በኋላ « በነገራችን ላይ ፤ እጠይቅሀለሁ እያልኩ እየረሳሁት «ያችን ፍቶ ግራፍ አንሺ አነጋገርካት ወይስ እንዴት አደረግክ?» ስትል ጠየቀችው ፡፡ «አላነጋገርኳትም » አለ ቤን ራሱን በአሉታ እየነቀነቀ «ማይክ ሊያነጋግራት አስቧል » አልመስልሽ አላት « ማይክ ጊዜ አግኝቶ ? » አለች ጥያቄዋ መደነቅም ነበር ። «ጊዜ እንኳን የለውም ። ግን ማይክ ለሥራ ጊዜ ያጣል ብለሽ ነው እንደምንም ያብቃቃዋል ።. ለዚህም ለሌላ ሌላ ሺህ ጉዳይም በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሳንፍራንሲስኮ ይሔዳል » አለ ቤን ። ፀጥታ ሆነ ። ዌንዲ ማሰብ ቀጠለች ።
👍15
የለም ማይክ አላውቀውም ፤ ሁል ጊዜ አዲስ ነው ። ብቻም አይመስለኝም ። ማይክ ምን እንደሆነ የሚያውቀው ያለኔ ምናልባት ቤን ። ቤንም ቢሆን እንጃ ። ምናልባት ያውቀው ነበር ማለት ይቻላል ፤ በፊት ። ግን አሁንስ ያውቀዋል ? አረ በፊትስ ቢሆን ያውቀው ነበር ? አስቸጋሪ ነገር ነው። «መደነስ ትፈልጊያለሽ ? » አለ ቤን መለኪያውን እጠረጴዛው ላይ እያኖረና እያቀፋት ። «መፈለግ ነው ! » አለች ደስ እያላት ። ተያይዘው ወደ ዳንሱ አዳራሽ ገቡ ። ትንሽ እንደደነሰ… ቢያንስ ለነሱ ትንሽ የደነሱ ነው የመሰላቸው ማይክል በመካከቸው ሊገባ እየሞከረ ። ‹‹ተራ ይድረሰኝ እንጂ »
«እንዲህ ነኝና ፤ ምናለ ይደርስሀል …» አለ ቤን «ሰውየው ደህናም አይደለህ ? ለመሆኑ ከእናትህ ጋር ልትደሰት እልነበረም እንዴ ትተኸን የሔድከው ? »
« ጆርጅን ስታይ እኔን ፈንግጣኝ ሔደች » ሶስቱም ሳቁ ። «ደግ አደረገች። አዋቂ ይሉሀል እንዲሀ ነው» አለ ቤን እየሳቀ ። ቤንም ወለሉን አልለቀቀ ፤ ማይክልም አልተመለሰ ። ሶስቱም ባንድነት መደነስ ጀመሩ ። መንገላወድ ልበለው ? ይህ የተሰማት ዌንዲ በሳቅ መንከትከት ጀመረች ። ቤንና ማይክ ያን ያህል ሲደሰቱ ስታይ አደጋው ከመድረሱ በፊት የነበረው ሁኔታ በዓይነ ኅሊናዋ ታያት ። እንዲህ ነበር ማለት ነው የሚደሰቱት ስትል አሰበች ። ዛሬ ይህ በመመለሱ ደስ አላት ። መሳቅ ጀመረች። በመካከሉ ማይክ ቤንን በትያትራዊ ቁጣ እየተመለከተ «ስማ አቭሪ !ከዚህ ጥፋ ብያለሁ ጥፋ ። ከእጮኛህ ጋር ለብቻየ መደነስ እፈልጋለሁ ማለት ይግባህ » ሲል አስጠነቀቀው። «አልሔድም ፣ አይቻልም ብል ምን ሊመጣ !» አለ ቤን «ሶስታችንም ከዳንሱ ወለል ተጠርገን እንድንጣል ታዛለች እናቴ ። ያ ደሞ ጥሩ አይመስለኝም » በዚህ ሁኔታ ከቆዩ በኋላ !

« ስሙ » አለ ማይክ «ለምን ሔደን ኬክ አንበላም? » ተስማሙ ። ኬክ ወዳለበት ሲሔዱ ቤን አቭሪ የጫማውን ሶል አየት ካደረገ በኋላ ሳታየው ዌንዲን በአውራጣቱ እያሳየና አትሰማም አሉ በሚል ሁኔታና ትያትራዊ ሹክሹክታ ፣ «ዳንስ አትችልም ይቺ ሴት ። ጫማዬን ታያለህ ? » አለው። ማይክም «የኔንም ተመልከተው! » ሲል አጋነነ ። «የናንተን አሳያችሁ እኔ ደሞ ነገ በእግሬ መሔዴ እማይቀር ነው » አለች ዌንዲ በማኩረፍ ። በዚህ እየተሳሳቁ እኬኩ ዘንድ ደረሱ። ኬኩን አንስተው እየገመጡ ዳንሱን መመልከት ጀመሩ ። የተጠሩት ሀብታሞች ነበሩ ፤ሁሉም ። በሀብታም ጋለሞቶች አንገት ላይ የተንጠለጠሉት የእንቁና የሉል ጌጦች ያበራሉ። ልጃገረዶችም አበባ መስለዋል፡፡ «ትንሽ ቀደም ብሎ ይህን ባይ ኖሮ » አለ ቤን በውሸት የፀፀት ድምጽ ልጃገረዶቹን ኢያየ ። «እህሳ !» አለ ማይክ ቀልዱን እየተክተለ ።

«እሀህ ... ወደ መፀዳጃ ቤት ብቅ ብዬ የአፍንጫዬን ላብ በፑደር ላስተካክል አስቤ ነበር ። አሁን ግን እናንተ ሰዎች የምትታመኑ ሆናችሁ አልታያችሁኝም ። ይቅርብኝ » አለች ዌንዲ ። «አይ ለዚህስ አታስቢ ። እጠብቅልሻለሁ » አለ ቤን። «ምን ጊዜ ኖሮህ ጌታዬ ! አንተንም የሚጠብቅ በተገኘ ፤ እንኳን አንተ ሰው ልትጠብቅ » ቤን አቭሪ « ግድየለሽም » ብሎ ብርጭቆዋን ተቀብሎ እንደማባረር አደረጋት ። ዌንዲ ወደ ወይዛዝርት ክፍል ስትሔድ ። «ሴት ብሎ ዝም ናት ፤ አይደል ?» አለው ማይክን ። ማይክም አድናቆቱን ከልቡ ገለጸ ። ከዚህ ቀጥሎ ቤን ማይክን በደንብ እየተመለከተ «ሁሌ ሳስበው ምንኛ ታድያለሁ እላለሁ ። ማይክ ያኔ ስነግርህ አለመቆጣትህ…. ስለኔና ስለሷ የነገርኩህ እለት… » አለ። «ለምን እቆጣለሁ!?. . . ደሞም'ኮ አየህ እኔ ለእንደዚህ ዓይነቱ ነገር ጊዜ የለኝም »
« ለወደፊቱ ግን ጊዜ እንደሚኖርህ አልጠራጠርም››
‹‹ምናልባት። ሆኖም ለጊዜው እናንተ ፡ እናንተ ሂዱ፤አግቡ ተጋቡ። እኔ ልጄ ከባድ ሥራ ፤ ከባድ ኃላፊነት አለብኝ » ማይክ ይህን ያህል ቢልም ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ነገር እንደሚያስከፋው አልተከፋም ። ፈገግታ በፊቱ ላይ እንዳለ ነበር እንዲሁ ፈገግ እንዳለ መለኪያውን ተመለከተ ። ከዚያም ለጤናችን በሚል ቅኝት ብድግ አድርጐ «ለሁላችን ! » አለ ሁለቱም ግጥም አድርገው ጠጡ።

•••••••••••••••••••••••••

ማይክል የእጅ ሻንጣውን ጧ እድርጎ ሲዘጋ አውሮፕላኑ የሳንፍራንሲስኮ ማረፊያውን አስፋልት ያዘ ። በመንገድ ላይም እያለ አላረፈም ነበር ። በሳንፍራንሲስኮ ውስጥ በሚቆይበት ጊዜ ብዙ ስራ መስራት አለበት ። ብዙ ስብሰባዎች ይጠብቁታል ። የተለያዩ ሐኪሞችን ማነጋገር ፣ ጥያቄዎችን መመለስ ፡ የተለያዩ ስራዎችን መመልከት አርኪቴክቶችን ማነጋገር፤ ማደራጀት ፤ መመሪያ መስጠት ። በዚያ ላይ ደሞ... ያችን ፎቶ ግራፍ እንሺም ማነጋገር፤ ማግባባት ማለቂያ የለውም ። ሆኖም እንደምንም ይወጣዋል፤ ለምዶታል ። ወይ የምግብ ሳዓቱን በማሳለፍ ወይ የመኝታ ሰዓቱን በመቅነስ ወይም ሌላ። በቻ... ይወጣዋል ። ይህን እያሰበ በአንደኛ ደረጃ የበረራ ክፍል ከተቀመጠበት ወንበር በላይ ባለው ርብራብ ላይ ኣጥፎ ያስቅመጠውን ካፖርት ሲያወርድ ሆስቴስዋ አይኗን እንደጣለችበት ተገንዝቦ ፊት እልሰጣትም ። እንደሁልጊዜው ፀጥ ብሎ ወደ ውጭው በር አመራ። ሲያዩት እንዲህ አድርጎ ትቷቸው መሄዱንም እንደስራው ሁሉ ለምዶታል ። ሰዓቱን አየ ። ከቀትር በኋላ መሆኑን ትገነዘበ። አውሮፕላን ማረፊያው ድረስ መጥቶ የሚጠብቀው መኪና እንዳለ ያውቃል ። ምናልባትም ዛሬውኑ ስብሰባዎች ማካሄድ ይኖርበታል ። ነገ ጧት ቁርስ ላይም ስብሰባ አለው ። ከአንድ ሰዓት ጀምሮ ። የማይክል ሂልያርድ ሕይወት ይኸው ሆኗል ። ማይክል ሂልያርድ ሰለ ስራ እንጂ ስለሌላ ነገር አያስብም ። በርግጥ ያስባል ። ሰለእናቱ ያስባል ። ስለጆርጅ ኮሎዊ ያስባል ። ስለቤንና ስለዌንዲም ያስባል ። እናቱና ጆርጅ ግን የሉም ። ማጆርካ ውስጥ የሙሽርና ወቅት እያሳለፉ አለማቸውን ይቀጫሉ ። ቤንም በዌንዲ እቅፍ ውስጥ በሰላም ኒውዮርክ ውስጥ ይምነሽነሻል ። ሁሉም ተከባካቢ አላቸው። ስለነሱ መጨነቅ አያስፈልግም ። እሱንም ቢሆን የሳንፍራንሲስኮ ሕክምና ማእከል እያቀማጠለ ያኖረዋል ። ይሰራል ከዚህ የበለጠ ምን አለ ? ስራ ሰላም ነው ለማይክል ሂልያርድ ።

እንዳሰበው ሆነ። መኪና ይጠብቀዋል ። ትሳፍሮ ወደ ታላቁ ፌይርሞንት ሆቴል አመራ ። ተይዘዋል የተባሉች ሁለቱም ልዩ ክፍሎች በትክክል እንደተጠበቁ ሆነው እገኛቸው። ሁለቱም ክፍሎች የራሳቸው ሳሎንና መኝታ ያላቸው የትሟሉ ክፍሎች ሲሆኑ ለማይክል እንዱ ክፍል በቂ እንደሆነ ግልፅ ነው። ሁለተኛውን ልዩ ክፍል የተከራየው ሰስብሰባ ሲል ነበር ። ሲያስበው በሁለቱም ውስጥ ሰብሰባዎችን ማካሄድ እንደሚችልም ገሙተ፤ ባንዴ። እቃው ተራግፎ ክፍሉ ውስጥ ከገባ በኋላ ጣመኑ በሚገባ ሳይለቀው ስራ ጀመረ፡። ያን ለት የመጨረሻውን ጉዳይ ተነጋግሮ ሲጨርስ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ሆኖ ነበር ። ሌላ ጉዳይ ሊጨምር አልቻለም። ደከመው፡ ራበው። ይበቃዋል ።
👍15
እዚያው እክፍሉ ውስጥ እንዳለ ስልክ ደውሎ ብስቴካ እንዲያመጡለት እዘዘ ። ብስቴካው እሰኪመጣለት አልጋው ላይ ተንጋሎ እግሩን ቡና ማቅረቢያው ጠረጴዛ ላይ ዘርግቶ ትዘረረ ። ወዲያው «አነጋገርካት ?!» የሚል ድምዕ የሰማ መሰለው። በርግጥ ድምጹን ሰምቶታል ። ግን ግዙፍ ድምፅ አልነበረም ። ድምጹን የሰማው በሀሳቡ ነበር ። ድምጹም የእናቱ ድምፅ ነበር ። ያን ያህል ጉልህ ሆኖ በመሰማቱ ገረመው ። ቀና አለ ። ክፍሉ ከሰዎች ጋር በነበረበች ጊዜ በተጨሰው የሲጋራ ጭሰና በዊስኪ ሽታ ታፍኗል። እንዲያም እለ በሀሳቡ ፤ የምበላውን ነገር እስኢያመጡልኝ ልደውልላት ። እኔንም እንዳልተኛ ይረዳኛል ።

ደወለ ።

«ሄሎ» አለች ሶስት እራቴ ስልኩ ከጮኸ በኋላ ። «እንደምን አመሸሸ ሚሰ አዳምስን። ማይክል ሂልያርድ እባላለሁ» አለ ። ባለችበት ላይ ደንዝዛ ቀረች ። ልትጮህ ቃጣት…..
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍15
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ አንድ
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
ከለሊቱ 8.15 ሞባይሏ ተንጣረረ… በግማሽ መንቃት ተንጠራርታ አጠፋችውና ወደእንቅልፏ ተመለሠች።ከ3 ደቂቃ ብኃላ የቤቷን መደበኛ ስልክ አንቃጨለ...ድምፁ እየሠመጠችበት ካለ የእንቅልፍ ማዕበል ዳግመኛ መንጭቆ አወጣት :: እያጎረመረመች ተነሳችና በዳበሳ መብራቱን አበራችው።እና መቆም በተሳናቸው እግሮቾ እየተንገዳገደች ስልኩ ወዳለበት ቦታ ሄደችና እጀታውን አንስታ ጆሮዋ ላይ ለጠፈች።
‹‹ሄሎ...ማን ል...በል?"
"ዶ/ር አምልጪ...ሊ...ገድ..ሉሽ ...እየ...መጡ ..ነው" ጭል ጭል እያለች ልጥፋ አልጥፋ በማለት ከንፋስ ጋር ትግል እንደገጠመች ቁራጭ ሻማ ለህይወቱ የሚታገል የተቆራረጠ እና እጅጉን የተዳከመ የወንድ ድምፅ..ማንነቱን ወዲያው አወቀችው፡፡
"ኤልያስ..?"
"እባ...ክሽ ፍጠ..ኚ"
‹‹ኤልያስ አንተ ደህና ነህ..?ጎድተውሀል እንዴ?"መልስ ሳይሆን የእቃ መንጓጓትና ድምፅ ነው የተሠማት ..ያንን ተከትሎ ከውጭ ተንጋግቶ የሚገባ ሚመስል የእግር ኮቴ፤ ጩኸትና ጫጫታ ጆሮዋ ላይ ለጥፋ በያዘችው ስልክ ውስጥ እየተሰማት ነው፡፡
‹‹አባዬ ..ምንድነው…?….ቶሎ በሉ አንብላንስ ጋር ደውሉ…››ብዙ ብዙ ድምፅ እየተደራረበ ወደ ጆሮዋ ይገባል፡፡
‹‹ሄሎ ኤልያስ...ሄሎ አናግረኝ…ሌላ ሰው አለ..ባካችሁ አነጋግሩኝ"
ስልኩ አልተዘጋም…ረዘም ላለ ደቂቃ ብትታገስም የሚያናግራት ሰውም አላገኘችም፡፡ ተስፋ ቆርጣ ስልኩን ዘጋችው..የእንቅልፍ ስሜት ተሟጦ ከውስጧ በኖ ስለጠፋ ፍፅም ንቁ ሆናለች።ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው።
"ምንድነው የተፈጠረው?"….ቢጃማዋን አውልቃ ሌላ ልብስ እየለበሰች መልስ የማታገኝላቸውን ጥያቄዎችን እየጠየቀች ነው።
"ግድያን ምን አመጣው? "
የሆነ የመንጎጎት ድምፅ ከውጭ የሠማች መሠላት "ቀስ ብላ ወደመስኮት ተጠጋችና መጋረጃውን በጥቂቱ ገለጥ አድርጋ አይኖቾን ወደውጭ አጨነቆረች።ምንም የሚታያት የተለየ ነገር የለም።
"ውይ ከፍራቻዬ የተነሳ በሀሳቤ የፈጠርኩት ነገር ነው"አለችና ዝግጅቷን ቀጠለች..በለበሰችው ልብስ ላይ ረዘም ያለ ብኒ ቀለም ያለው ባለኮፍያ ኮፓርት ደረበች...ኮመዲኖዎን ከፈተችና ውስጡ የነበረውን ብር በማውጣት ወደ ቦርሳዎ ከተተች።መታወቂያ እና ፓስፓርቷን፤ ኤት.ኤም ካርዶን መረጃ የምታከማችበትን 64 ጂቢ ፍላሽ ያዘችና እቤቷን ወደኃላም ሳታይ ግቢዎንም ለቃ ወጣች።
የተረገመ አጋጣሚ መኪናዋ ግቢዋ ውስጥ የለችም፡፡ የተወሰነ ያልተለመደ ድምጽ ስላሰማቻት ማታ ወደቤት ስትገባ ነበር ደንበኞቾ የሆኑ ጋራዥ ጋር ጎራ ብላ ለጥዋት እንዲያደርሱላት ጥላላቸው በኮንትራት ታኪሲ ወደቤቷ የገባችው…..ስለዚህ አሁን ያላት ምርጫ በእግር ማምለጥ ነው፡፡
ከቤቷ የውጨኛው በር 20 ሜትር ሳትርቅ ከሩቅ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ሰማች፡፡ በደመነፍስ ቅፅበታዊ ውሳኔ ወሰነች...፡፡ዘላ ከመንገድ ወጣችና በጨለማ የተጋረደ መሸሸጊያ በመፈለግ እራሷን አጣጥፍ በመወሸቅ የሚሆነውን ለማየት እይታዋን ወደመንገድ አስተካከለች ።አልተሳሳተችም አንድ የቀብር አስፈፃሚዎች ድርጅት ንብረት የምትመስል ጥቁር ጨለማ ሚኒባስ እየተክለፈለፈች መጣችና ከእሷ ቤት በራፍ ጋር ስትደርስ ቀጥ ብላ ቆመች። ወዲያው የኃላው በራፍ ተንሸራቶ ተከፈተና ሶስት የሆሊውድ አክሽን ፊልም ላይ የሚተውኑ ሚመስሉ የተወጣጠሩ ወጠምሻ ሰዎች ድብ ድብ እያሉ ወረድ።.
"እኚ ሁሉ ለአንድ ሴት ?"ስትል በውስጧ ጠየቀች
"አሁን በዚህ ሰውነታቸው ይሄን በአደገኛ ሽቦ የታጠረ ግዙፍ ግንብ አጥር እንዴት አድርገው ዘለው ሊገቡ ነው?›› እያለች ስታሰላስል ይግረምሽ ብለው ቀጥታ እንደቤቱ አባወራ ወደበራፍ ተጉዘው በተዝናና ሁኔታ ቁልፍ ከኪሳቸው አውጥተው በመክፈት ወደውስጥ ሲገብ ባለማመን ተመለከተች።ይሄ እንዴት ሆነ የቤቷ ቁልፍ እሷና ፕሮፌሰሩ ጋር ነበር ያለው፡፡ከዛን በላይ በዛ አካባቢ መቆየት እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ነው ብላ ስላመነች ሚኒባሱ ውስጥ የቀረው ሹፌር እንዳያያት ተጠንቅቃ ከተወሸቀችበት ወጥታ ጥግ ጥጉን እየታከከች ከሰፈሯ ርቃ ወጣች።
አሁን ካለችበት መኖሪያ ቤቷ ከሚገኝበት ወሎ ሰፈር ወደብዙ አቅጣጫ ሚወስዱ መንገዶች አሉ..ወደቦሌ መሄድ ትችላለች….በአቋራጭ ወደላንቻ መሄድ ትችላለች..እሷ ግን የያዘችው ወደጎተራ የሚመራውን መስመር ነው….…ጎተራ ማሳለጫው ጋር ስትደርስ ለተወሰነ ደቂቃ ቆመችና ለሰከንድ አሰላሰለች …ከፊት ለፊቷ ሌላ ሶስት ምርጫ አጋጠማት ፡፡ወደግራዋ ታጥፋ ወደ ሳሪስ መሄድ ወደ ቀኞ ታጥፋ ወደ ላንቻና ስቴዲዬም መጎዝ ወይም የፊት ለፊቱን አስፓልት ይዛ ወደቄራ መሸምጠጥ….
ያለምንም ደጋፊ ምክንያት የፊት ለፊቱን መርጣ ጉዞዋን ቀጠለች…...አስር ደቂቃ ከተጓዘች ቡኃላ ከሰፈሯ በጣም መራቋንና አዳኞቾም በቀላሉ ሊያገኞት በሚችሉባት አቅጣጫና ስፍራ ላይ አለመሆኗን ስትረዳ እራሷን ገታ ተረጋግታ ማሰብ ጀመረች ፡፡
‹‹ከኃላ ከሚያሳድደኝ ሞት ሳመልጥ ፊት ለፊቴ ያልታሰበበት ሞት እንዳይገጥመኝ"አለችና ዙሪያዎን አማተረች….…ከጭፈራ ቤቶች የሚወጣ ድምፅ እንኳን አይሰማትም ወይም ከመሸታ ቤት ወጥቶ ወደቤቱ እየተወለጋገደ ሚሄድ ሰካራም በስፍራው አይታይም……ብቻ የተወሰኑ መቶ ሜትሮች ወደፊት ጠጋ ብሎ የቄራው አጥር አካባቢ የሚልከሰከሱ የተወሰኑ ውሾች ይታዬታል..በተረፈ አካባቢው ፍፅም ጭር ብሏል... መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለችው… ከፊት ለፊቷ በአንድ ሜትር ርቀት የትራፊክ መብራት አለ……ትንሽ ሳብ ብሎ ወደሚታየው የባስ ፌርማታ አመራችና ጥጎን ይዛ ቁጭ አለች።
‹‹ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ ላመልክት?›› የሚል ሀሳብ መጣላት፡፡ግን ነገሩ ፖሊስ ጆሮ አንዴ ከገባ ወደኃላ የሚመለስ ነገር አይኖርም…ሄዶ ሄዶ ወንጀሉ በግለሰቦች ደረጃ ታጥሮ አይቀርም ወደ ሆስፒታላቸውም መዛመቱ አይቀርም…ያ ሆስፒታል ደግሞ የእሷም ሀብት ነው……ጠቅላላ ልፋቷንና ህልሞን ያዘለ ተቋም ነው….የእሱ መውደም እሷንም ቀጥታ ያወድማታል….ይሄንን ሁሉ በታትና አሰበችና ‹‹የነገሩን ጭራ በደንብ ሳልይዝ ለጊዜውም ቢሆን ፖሊስ ጋ አልሄድም ››ብላ ሀሳቧን ሰረዘችው፡፡
‹‹እሺ ሌላ ምን ማድረግ እችላለሁ..?››በቀጣይ እራሷን የጠየቀችው ጥያቄ ነው፡፡አሁን ምን ላድርግ..?ማን ጋር ልደውል?ስትል ፕሮፌሰሩ ወደ አእምሮዋ መጣ፡፡
…እዚህ ጉዳይ ላይ ፕሮፌሰሩ አለበት?"ስትል ህሊናን አዙሮ የሚደፋ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች።
ኘሮፌሰር ማለት የስራ ባለደረባዋ ነው...ፕሮፌሰር ማለት የረጅም ጊዜ የቅርብ ጓደኛዋ ነው...ፕሮፌሰር ማለት የሶስት አመት ፍቅረኛዋ ነው...ኘሮፌሰር ማለት ከአራት ወራት ብኃላ ልታገባው ሽር ጉድ ያለችለት ያለ የወደፊት ባሏ እና የልጇቾ አባት ለመሆን ጫፍ ላይ ያለ ሰው ነው....
ፕሮፌሰር ብዙ የውጭና የሀገር ውስጥ ዪኒቨርሲቲዎች ለሁለት አስር አመታት ያስተማረ በአለም አቀፍ የምርምር ጆርናሎች አያሌ የጥናት ስራዎቹን ያሳተመ የአደባባይ ምሁር ነው.....በዚህ ላይ ሀገሪቱ ከለቻቸው ከአንድ እጣት ከማይበልጡ የልብ ቀዶ ህክምና ሀኪሞች አንዱ ነው፡፡ታዲያ እንዴት ነው ይሄ ሰው የእሷን የትሙት በቃ ውሳኔ ከሌሎች ገዳይና ማጅራት መቺዎቾ ጋር በማበር ሊፈርም የሚችለው?እሷ ስለሆነች አይደለም ሌላ ማንስ ቢሆን እንዴት እንዲህ ያደርጋል? ይሄ ሰው እኮ ለእንስሳት ነፍስ ሁሉ አንጀቱ ከመንሰፍሰፍ የተነሳ ቬጂቴሪያል የሆነ ሰው ነው?..ምንም ሊዋጥላት አልቻለም፡፡
👍281
‹‹አዎ ኤሊያስን ያጠቁትም እሷን ለማስወገድ እቤቷ ድረስ የሚገድላት ሰው የላኩት ሌሎች የኮሚቴ አባላት ናቸው ፡፡በተለይ ሼክ ጠሀ እና አቶ ከፍያለው?አዎ እነሱ ናቸው ወንጀላቸውን ለማዳፈን ከፕሮፌሰሩ ጀርባ ገዳይ እስኮድ ያሰማሩት"ስትል ድምዳሜ ላይ ደረሰች።
"ግን የቤቴን መክፈቻ ቁልፍ ፕሮፌሰሩ ብቻ ነው ያለው እሱ ካልሰጣቸው ማን ሊሰጣቸው ይችላል?››አስጠሊታ ስሜት የሚያጭር ጥያቄ በምናቧ ተሠነቀበረ..ነው ወይስ ትናንት አባቴ ሞቶል ብሎ ድንገት ስራውን ጥሎ ወደክፍለሀገር የሄደው የቤቷ ዘበኛ ስራ ይሆን
."አዎ ወይ ዘበኛውን በብር ኃይል አታለውት እንዲተባበራቸው አድርገዋል…ወይ ደግሞ ከፕሮፈሰሩ ቁልፉን ሰርቀውት ይሆናል...አዎ እንደዛ ነው የሚሆነው"እርግጠኛ ሆነች።
ስልኳን አነሳችና ደወለችለት ፡፡ዘጠኝ ሰዓት እየተቃረበ ነው፡፡በሁለት ጥሪ ተነሳ፡፡
"ፕሮፌሰር እንዴት ነህ?"
"ደህና ነኝ …ምነው ደህና አይደለሽም እንዴ?"
‹‹ሰላም ነኝ››
‹‹የት ነሽ?"
"እንዴት የት ነሽ እቤቴ ነኛ"ኮስተር ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እቤት የት..ማለቴ እንዴት...?"የሚርገበገብ የተሰባሀረ እና ድንብርብሩ የወጣ ድምፅ
"እንዴት ማለት..?."
"ማለቴ በዚህ ሰአት በሰላም ልትደውይልኝ አትችይም ብዬ ነው ፡፡ሰዓቱን አይተሽዋል...?ምነው አመመሽ እንዴ?"
ልንገረው አልንገረው ...አለበት ?የለበትም ? ከፍተኛ ሙግት ከራሷ ጋር ገጠመች፡፡
"አረ አናግሪኝ...ካልሆነ ልምጣ እንዴ?"
"የት"
"እንዴት የት? እቤቴ ነኝ አላልሺኝም እንዴ?"
"አይ እቤት አይደለሁም..."
"አረ ግራ አታጋቢኝ ?የሆንሺውን ነገር ነገሪኝ"
‹‹መቼስ ያን የሚያህል ሰውዬ በዚህ መጠን አያስመስልም››አለችና እውነቱን መናገር ጀመረ…
‹‹የሆኑ ሰዎች ሊያጠቁኝ እቤቴ ድረስ መጥተው ነበር...››
"በፈጣሪ ሊያጠቁኝ ማለት ?›› ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍18
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከሎ ሆራ ጨርቆሉ ማዝ ሆኖ ደም፣ ወተት፣ ሥጋና ማር እየተቀለበ፣ ከሰልና ቅቤ ተቀላቅሎ ፊቱንና የተላጨውን ራሱን
ተቀብቶ፣ ከሚዜው ጋር ውሎው ጫካ ነው። ከሎ የወገኖቹን ባህላዊ
የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ለመጀመር ምክንያቱ አንድ ነበር ፍቅር። ሥነ ሥርዓቱን እያሟላ ሲመጣ ግን፣ አዲስ ስሜት አእምሮው ማፍለቅ ጀመረ።

ወገኖቹ የሆኑት ሐመሮች በአንድ ወቅት ከማኅበረሰባቸው
አግልለውት ነበር" ያውም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ፣ እንዲሞት ተደርጎ ተጥሏል። ከሚወዳቸው ወላጆቹና እኅት ወንድሞቹ፣ ከሚያፈቅረው የፍየልና ጥጃ ጥበቃው፣ ከቦረቀበትና ከተጫወተበት ማራኪ
የሐመር ምድር ተጎትቶ ተወስዶ፣ በጦር ተወግቶ፣ ወደ ገደልም ተገፍቶ፣ የሞትን ጽዋ ጕድጓድ ውስጥ እንዲቀምስ ተደርጎ ነበር።

የሕፃንና የወጣትነት አእምሮው ይህን የደረሰበትን መራራ ጽዋ
ጠንጥኖ በገዛ አእምሮው የዛን ጊዜውን መሪ ተዋናይ ሲያስታውሰው አፉን ደም ደም ይለዋልI ልሳኑ ይዘጋበታል ሕይወቱ የላሸቀ፣ የተበላሸ እንቍላል ሆኖ ባለመጥቀሙ ተሽቀንጥሮ የተወረወረ
ይመስለዋል።

የዛኔው የቍስል ስሜት ምልክት ጥሎ ካለፈ ዓመታት ቢቈጠሩም
ሁሌም አጋጣሚውን ባስታወሰ ቍጥር ሥቃዩ ይጀምረዋል" ሞት
ጒሮሮው ላይ ቆሞ ስለታም ሰይፉን ጕሮሮው ውስጥ ሊቀረቅርበት ሲመጣ ይታየውና ይባባል፤ መሸሻ፣ መደበቂያ፣ ማምለጫ መንገድ ያጣል። ከራስ ሕሊና የሚፈጠር አስፈሪ ነገር በምን አንቀጽ
ይከሰሳል! ምን ዓይነት ጠንካራ በር ያግደዋል?

«እኮ ለምን? ምን ባደረኳቸው በእንቦቀቅላነቴ ወቅት ልሸከመው
የማልችለውን ሞትና ፍርሃት አሸከሙኝ ምን ባደረኳቸው ከእናት  ጉያ ነጥለው፣ አብሬአቸው ከምዘላቸው ጓደኞቼ ለይተው ለመከራ
ዳረጉኝ?» ባለፈው ሕይወቱ ከሎ ሆራ ራሱን በራሱ እየጠየቀ መልስ ያጣበት ጉዳይ ነው" ለብዙ ዓመታት የዕለት ተዕለት ትዕይንት ሆኖ የሚቀርበውን የቆየ ትዝታ ባስታወሰ ቍጥር የመጨረሻውን ረድፍ
ይዘው የሚደረደሩት ጥያቄዎች ከላይ የተዘረዘሩት ሲሆኑ መልሳቸው ግን ሰው ወይንም መዝገበ ቃላት ሳይመልሰው እስከ ዛሬ አብረውት ዘልቀዋል"

ከሎ ሆራ በሕይወቱ ሙሉ ያምንበት የነበረው አሁን ግን እንደ አጉም እየበነነ አልጨበጥልህ ይለው ጀምሯል" ወደ ወገኖቹ ብቻ
ሳይሆን ወደ ሐመር ምድር ለመመለስ አልሞም አያውቅም። የኖረው
እነሱን ሲረግምና ሲሸሽ ነው። አሥራ ሁለተኛ ክፍል እንደ ጨረሰ በአገር አቀፍ የመሠረተ ትምህርት ዘመቻውም ወቅት፣ ከዘመቻው መቅረት ወይንም መለወጥ አልቻልህ ብሎት እንጂ እግሩንም
ለማንሣት አያስብም ነበር" የዛኔም ቢሆን ደግሞ፣ «ጌታዋን የተማመነች በግ...» እንዲሉ፣ መንግሥትን ተማምኖ እንጂ እንኳን የከፍተኛ ትምህርት ዕድሉ ሌላው ሁሉ ነገር ቢቀር ወደ ሐመር
ተመልሶ ለመምጣት አያስብም። በቆይታውም አይጥና ድመት ሆነው
ቆዩ እንጂ አልተቀራረቡም።

አሁን ግን ከሎ ሆራ አይጡም ድመቱም እሱ እንደሆነ በመቁጠር ወደ ቤቱና ወደ ባለቤቶቹ መመለስ ይከጃጅለዋል"

ከሎ ሆራ በእርግጥ አሁን ያለው ሐመር ነው" ሐመሮች በተለይም ዘመዶቹ ባዩት ቍጥር ይሳሱለታል" ወላጅ እናቱ ልክ እንደ ልጅነቱ እጆቹን እያፍተለተሉ እንባቸውን ያፈሱለታል ያላቸውንና
ቤት ያፈራውን ጎጆው ድረስ ተሸከመው ያመጡለታል፤ ከብት ለመዝለል በየዘመዶቹ ቤት ሲዞር እንደ ብርቅ ስመው አስተናግደውታል ከብት በሚዘለልበትም ወቅት ዘመዶቹ ዝግጅቱን በማሟላትና በለምለም ቅጠል መልካም ዕድልን በመመኘት አብረውት
ተጨንቀዋል ልጃገረድ ዘመዶቹም የዝምናድ ምልክት የሆነውን
ግርፋት በወኔና በፍላጎት ተገርፈውለታል።
ከሎ ሆራ ይህን ሁሉ ካመዛዘነ በኋላ ለዘመናት በአእምሮው ተቀብረው
የኖሩትን ጥያቄዎች ከመቃብራቸው እያወጣ መጣል ጀምሯል እናቱ እንደ ብርቅዬ ልጃቸው፣ ወንድምና እኅቶቹ እንደ
ተወዳጅ ወንድማቸው አድርገው ይቈጥሩታል“ ታዲያ ማንን ይጥላ?
ለሥቃዩ ሁሉ ተጠያቂው ማን ሊሆን? ለምንስ እንዲሞት አድርገው
ጣሉት?

ከሎ ሆራ አእምሮው ለጥያቄዎቹ መልስ አገኘ" ለመጣል ያበቃው ባህል ነው። እሱን ለመጉዳት፣ ከእናቱ ጉያ ለመነጠል የደፈሩት የአገር ሽማግሎች አንኳን ለሱ ከሜዳ ተነሥተው hፉ አላሰቡም”

የሐመር ሕዝብ ባህሉን አክባሪ፣ ካለ ዘመናዊ ሕግና ደምብ በባህላዊ ደምቦችና ሥርዓቶች የሚመራ፣ ተፋቅሮና ተዛዝኖ የሚኖር
ማኅበረሰብ ነው። ማንንም የማያገል፣ ባህሉን ከመከተል ዝንፍ
የማይል ሕዝብ መሆኑን አረጋግጧል። «ታዲያ ወገኖቼ በእኔ ላይ
ብቻ ልዩ ቅጣት አልፈጸሙብኝማ። ባህላዊው ደንብ መሟላት
ነበረበትና ተገደልኩ፤ ከሙትነት ተነሥቼ ስመጣ ግን ተቀበሉኝ" አሁን የተቀበሉኝ ስለ ተማርሁ፣ ከእነሱ የተለየ ሕይወት ስላየሁ አይደለም ባህሉ ስለሚፈቅድ ብቻ ነው ታዲያ ባህል ባመጣው ጦስ ወገኖቼን መጥላት አለብኝ?» ጨርቆሌ ማዝ ተብሎ ጫካ ለጫካ
የሚዞረው ከሎ ሆራ ዕድሜ ልኩን አእምሮውን ሰንገው ይዘው ያስጨንቁት የነበሩትን ጥያቄዎች መመለስ ጀመረ።
።።።።።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ሰው ራሱን ማስተማር የሚችል ታላቅ ፍጡር ነው" በተለይም ታታሪ ሰዎች ከአምላክ የተሰጠውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ
እየተጣጣሩ ናቸው። እየተሳካላቸውም ነው

በምርምር እንደ እብድ ያልለፈለፈ ፈላስፋ፣ ቀንና ሌሊት በምርምርና በሙከራ እልሁን ያልጨረሰ ሳይንቲስት፣ እንደ
ሚፈጥራቸው ገጸባሕርያት ስቅስቅ ብሎ ያላዘነ አሊያም በደስታ ያልተፍነከነከ ደራሲ፣ የሚሥለውን ሥዕል የተዋጣ ለማድረግ
ረቂቁን የተፈጥሮ ምሥጢር ለማወቅ በመጣጣር ያልዳከረ ሠዓሊ
l ሊኖር አይችልም" ካለም ከነሆድ አምላኩ ወገን የሆነ አስመሳይ መሆኑ ነው"

ካርለት የሐመር ሴቶችን ሕይወትና ማኅበራዊ ተሳትፎ የምታጠና
ወጣት አንትሮፖሎጂስት ናት ያለችበት ዘመን ሳይንስና ተክኖሎጂ የመጠቀበት፣ የሰው ልጆች በአዲስ ግኝቶች የሚንበሸበሹበት ወቅት ነው„

«እንደ ዱሮው ዘመን ይህን  ይህን ማድረግ ያስቸግራል የሚል አዳማጭም ሆነ ተመልካች አያገኝም" መሆን አለበት ብዬ ብዙ
ሞከርኩኝ ፈተናና ሥቃይም ገጠመኝ፤ በመጨረሻ ግን ተሳካልኝ ሲባል አድናቆታዊው ጭብጨባ መቅለጡን አውቃለሁ። የሰው ልጅ በውኃ ውስጥ በባቡር መጓዝ በቻለበት፣ ሕዋ ላይ ከተማ በከተመበት፣አይጥና ድመት አብረው እንዲጫወቱ በተደረገበት ወቅት እኔስ
ሰውነቴ ቢቈስል፣ የአእምሮ ጭንቀት ቢደርስብኝ፣ ብገረፍ፣ ባል ባገባ ምኑ አዲስ ነገር ነው። ከዚህስ የቀለለ የዓላማ መሥዋዕትነት ምን
ሊኖር ይችላል?» ካርለት መኝታዋ ላይ ተጋድማ የምታስበው ነበር
ካርለት ለአንድ ወር ያክል በከብት ዝላይ ወቅት የተገረፈችው ቁስል አሠቃያት ጫማ የለመደውን እግሯንም እንቅፋቱና እሾሁ
እየተተካካ አንሰፈሰፋት" እየቆየ ሲመጣ ግን ይህ ሁሉ ሥቃይ እየታገሠ፣ ቍስሉም እየደረቀ፣ እግሯም እየደነደነ መጣ ካርለት በቃን በማይሉት ማስታወሻዎቿ የየዕለት ገጠመኞቿን
እያሰፈረች፣ በካሜራዋ እይታዋን እያጠናከረች፣ በድንኳኗ አካባቢ
አገገመች ካርለት አልፈርድ ልብሶቿን በሻንጣዋ ቆልፋ፣ ቆዳዋን በመልበስ፣ በባዶ እግሯ በጨሌና አንባር አጊጣ ስትወጣ ብዙ አዲስ
👍22
ሁኔታ አጋጠማት። የሐመር ልጃገረዶችና ሴቶች ከልብ ቀረቧት ጐረምሶች ያሽኰረምሟት ጀመር። እነሱ የእኛ ናት፣ እሷ ደግሞ
የእነሱ ነኝ የሚል ስሜት ፈጠሩና ከልብ መቀራረብ ጀማመሩ"ለካርለት አዲሱ ቍልፍ በሩን ከፈተላት።
በተለይም ካርለት እንጨት ለመልቀም ወደ ጫካ ስትሄድ እንቅፋቱም፣ እሾሁም የለቀመችው እንጨት ክብደትም፣ ስቅስቅ
ብላ እስከማልቀስ ቢያደርሳትም ከልጃገረዶችና ካገቡ ሴቶች ጋር በኩንኩሮ፣ አጋም፣ ጨውሊንባ፣ እንኮይ፣ ሾላ፣ ዋንዛ ተሞላው ጬካ በሄደች ቍጥር የሚያወሩት፣ የሚዘፍኑት፣ ምሥጢራቸውን የሚያካፍሏት ሁሉ ማር ሆኖላታል ጣፋጭ!

«ባልሽን ትወጅዋለሽ?» ካርለት አንድ ጊዜ አንዷን ባለትዳር ነጠል ብለው እንጨት ሲለቅሙ ጠጋ ብላ ጠየቀቻት"

«ይእ!» በሣቅ እየተፍለቀለቀች ራሷን በአወንታ አወዛወዘች"

«...ይገርፍሻል?»

«ይእ!ባል ሆኖ እህ ላይገርፈኝ ነው!» በካርለት ጥያቄ እየተገረመች መለሰችላት"

«ለምንድነው የሚገርፍሽ?» ሌላው የካርለት ጥያቄ ነበር።

«ሳጠፋl በትክክል እንድሠራ፤ እሱ ካልመታኝማ አጠፋለሁu»
የታፈነ ሣቋን ለቀቀችው።

«ሲመታሽ አትጠይውም?»
«ይእ! ለምን? ወንድ ሆኖ ሴትን ካልምታት ታዲያ ስታጠፋ እያየ ዝም ሊል ነው?»

«ከባልሽ ወንድም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ትፈጽሚያለሽ? »

«ይእ! ታዲያ ሊቀር ነው! ከባለቤቴ ታናሽ ወንድም ጋር።» ሣቋ ቀደማት።

ይህንና ይህን መሰሉን ውይይት ካርለት ከባለትዳር ሴቶች ጋር ባደረገች ቍጥር መልሳቸው ተመሳሳይ ይሆንባታል" ካርለት ከልጃገረዶች ጋር ስትጨዋወት ደግሞ ለየት ያሉ ነገሮችን ትሰማለች።
«ዕድሜሽ ስንት ነው?» ካርለት ልጃገረዷን ጠየቀቻት

«ይእ!» በአሉታ አንገቷን ግራና ቀኝ አወዛወዘችላት።

«እጮኛ አለሽ?»

«እ!» በአወንታ አንገቷን ላይና ታች አወዛወዘች

«እጮኛሽን ታውቂዋለሽ?» ካርለት ጠየቀቻት።

«እ!» ልጃገረዷ የካርለት ጥያቄ ግር አላት።

«ከእጮኛሽ ጋር ተገናኝታችሁ ታውቃላችሁ?» ልጃገረዷ በአሉታ አንገቷን ወዘወዘች።

«ከወንድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጀምረሻል?»

«ይእ! ያማ ይጠየቃል፤ በደንብ ነዋ» በሣቅ ፍርስ አለች።ተጠያቂዋ ልጃገረድ" ልጃገረዷ በካርለት የሞኛሞኝ ጥያቄ ስትሥቅ
ውላ ብታድርም አይወጣላትም። ሆኖም ካርለትን ባለማወቋ ብቻ
ስሜቷን ካለገደብ ለቃ ልታሳቅቃት አልፈለገችም።

«ግንኙነት ስታደርጊ እንዴት ነው?» ካርለት ጥያቄዋን
ቀጠለች" ልጅቷ ያን ግዜስ ሣቋን ልትቈጣጠር ተስኗት ከርቀት ያሉ ጓደኞቿ እስኪደነግጡ ድረስ በሣቅ ተፍለቀለቀችና የፍየል ቆዳዋን ከኋላ በኩል ለዐመል ያህል ከፍ አድርጋ፣ ጎንበስ በማለት ያደራረግ
ስልቷን አሳየቻት።

«እስh አሁን ከስንት ወንድ ጋር ቀበጥሽ?» ቍጥር አለማወቋን ካርለት ዘነጋች።

«ይእብዙ ነዋ!» መለሰች ልጃገረዷ።
«ካገባችና ካላገባች ልጃገረድ የየትኛውን ኑሮ ትወጃለሽ?»
«ሁለቱም ጥሩ ነው" ልጃገረድነት እንደ ልብ ለመጫወትና ከጐረምሳ ጋር ለመዳራት፤ ባል ማግባትም ልጅ ስለሚወለድ ደስ
ይላል» ብላ መለሰች ልጃገረዷ።

ካርለት፣ ልጃገረዶች ሆኑ ያገቡ ሴቶች በባህላቸው የሚረኩI ባህላቸውን የሚያከብሩና የሚወዱ ሆነው አገኘቻቸው። ካለሐፍረትና መሳቀቅ ከልባቸው የቀረቧት ሴቶች ከጓደኛ የሚደብቁት ምሥጢር የሚባል ነገር እንደሌላቸውም በተግባር አረጋገጡላት።
ካርለት እንደ ክልሉ ኗሪ ሕዝብ ባህል ራሷን ለማኖር በገባችው የራስ በራስ እምነት መሠረት ቆዳ እንደ መልበሱ፣ በባዶ እግር እንደ
መሄዱ፣ እንጨት እንደ መልቀሙ ሁሉ ለማረስም ሞካከረች"ስለዚህ እርፍን የሚጨብጡ የእጇ ጣቶችና መዳፏ ለስላሳና ገና
ያልገበረ በመሆኑ፣ መላጡ ወደ እጇ ተሸጋገረ" በዚያ ላይ ከብቶች ወዲያና ወዲህ ሲያላጓት አቅመ ቢስ በመሆኗ መውደቅ፣ መነሣት
ቀጠለች።

ያም ሆኖ ግን፣ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ እጆቿ ጠነከሩl የአካል ጥንካሬዋም ዳበረ። ሌላው ያስቸገራት ልምድ ደግሞ ላሞችን ማለቡ ነበር" በሐመር ባህል የምታርስ፣ ከብት የምታልብ ልጃገረዷ ናት"ካርለትም መጀመሪያ ማለብ ስትሞክር መልኳና ወዟ አዲስ የሆነባቸው ከብቶች አላስጠጋሽ አሏት" ይባስ ብለውም በቀንዳቸው
ይደስቋት ጀመር።

አንድ ጊዜ እንዲያውም የጎን አጥንቷን አንዷ ላም ወግታት ለሁለት ሳምንት ያህል ውጋት እያጣደፋት ታማ ቆየች" ሲሻላት
ደግሞ ሙከራዋን እንደ ምንም ቀጥላ ከብቶችን በመላመድ ላሞችን
ማለብ ጀመረች።

💫ይቀጥላል💫
👍193
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ዳያና ላቭሴይ እውነተኛ ፍቅር በአጭር ጊዜ እንደማይለቅ በሃዘን
አስታወሰች፡፡ መርቪን በፍቅሯ የተነደፈ ጊዜ የጠየቀችውን ነገር ሁሉ
በፍጥነት ለማድረግ ደስተኛ ነበር፡፡ አንድ ነገር ከፈለገች በመኪና በመሄድ ያመጣላት ነበር፡፡ ሲኒማ አምሮኛል ካለች ከስራውም ቀርቶም ቢሆን ይዟት ይገባ ነበር፡፡ ከባሰም ለጉብኝት ፓሪስ ይወስዳት ነበር፡ የፈለገችው ሻርፕ እስኪገኝ ድረስ በማንቼስተር ሱቆች እግሩ እስኪቀጥን እየዞረ ሲያስስ ቢውል አይደክመውም፡፡ ቴአትር ቤት ገብተው በመሃል ደበረኝ ካለችው ሳይጨርሱ ቢወጡ ቅር አይለውም፡፡ ታዲያ ይሄ ታዛዥነት ከተጋቡ በኋላ ቀስ በቀስእንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡ ከዚያ በኋላ የጠየቀችውን ባይነሳትም ያደርግ የነበረው
ግን በዳተኝነት ነበር፡፡ ግድ የለም ልታገስ ብሎ እንጂ እንደ በፊቱ በፍቅር
ማድረጉን እየተወ መጣ፡፡ በመጨረሻ እንደውም ትዕግስት እያጣ ሲመጣ
ሚስቱን ጭራሹን ‹‹ዞር በይ›› ማለት አመጣ፡፡
ታዲያ ማርክም እንዲህ ሊያደርገኝ ይችላል የሚል ፍርሃት አጫረባት፡

ማርክ እንግሊዝ አገር በቆየበት ጊዜ ባሪያዋ ሆኖ ነው የስነበተው
በጠፉ በሁለተኛው ቀን ተጣልተው መኝታ ለይተውነበር፡ ሆኖም እኩለ
ሌሊት ላይ እውጭ ያለው ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ አይሮፕላኑን እንዳልተገራ
ፈረስ ሲያሰግረው ዳያና በጣም ፈራችና ዓይኗን በጨው አጥባና ክብሯን ሽጣ ወደ ማርክ መኝታ ሄደች፡፡ እንደዚያም ሆኖ ውጤቱ አላማረም፡፡ በኋላ ወደ እኔ ይመጣል ብላ ብትጠብቅም እሱም ኩራት ልቡን ነፍቶት ሳይመጣ
በመቅረቱ በንዴት ኤሌክትሪክ ልትጨብጥ ምንም አልቀራትም:

ዛሬ ጧት ምንም አልተነጋገሩም ማለት ይቻላል፡፡ ጧት ከእንቅልፏ
የነቃችው አይሮፕላኑ ቦትውድ ሲያርፍ ሲሆን ከአልጋዋ ስትነሳ ማርክ
ወጥቶ መሄዱን አወቀች፡፡ ጧት ቁርስ ላይ መሳ ለመሳ ተቀምጠው በሃሳብ
ተውጠው ምግባቸውን ሲቆነጣጥሩ ነበር፡፡
ዳያናን መርቪን ከናንሲ ጋር የሙሽሮች ክፍልን ተጋርተው ማደራቸው
ለምን እንደዚህ እንዳናደዳት አልገባትም፡ ማርክ በዚህ ረገድ ቢያግዛት
በወደደች። በተቃራኒ አሁንም መርቪንን ትወጂዋለሽ እንዴ?ሲል
ጠይቋታል፡፡ ትዳሯንና ቤት ንብረቷን ትታ ከእሱ ጋር መኮብለሏን እያወቀ
ማርክ እንዲህ ማለቱ አናዷታል፡፡

ዙሪያዋን ስትመለከት በቀኝዋ የተቀመጡት ልዕልት ላቪኒያና ሉሉ ቤል
የቆጡን የባጡን ያወራሉ፡፡ ሁለቱም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ ስላደረ እንቅልፍ
ባይናቸው ሳይዞር ስለነጋባቸው ተዳክመዋል፡፡ በግራ በኩል የኤፍ.ቢ.አዩ ሰው ኦሊስ ፊልድና እስረኛው ፍራንኪ ጎርዲኖ በጸጥታ ምግባቸውን ይበላሉ።

የጎርዲኖ እግር በእግረ ሙቅ ከመቀመጫው ጋር ተጠፍሯል፡ሁሉም
በድካም የዛሉና ነጭናጫ ሆነዋል፡፡ እንዲህ ያለ አለቅጥ የረዘመ ሌሊት
ገጥሟቸው አያውቅም፡፡
አስተናጋጁ ዴቪ ቁርስ የተበላባቸውን ሰሃኖችና ቁሳቁሶች እየሰበሰበ
ነው፡፡ ልዕልት ላቪኒያ ‹‹እንቁላሉ አልበሰለም ሞርቶዴላው ደግሞ በጣም
ሙክክ ብሏል›› በማለት ስሞታ ያሰማሉ፡ ዴቪ ቡና ቢያመጣም ዳያና
አልጠጣችም::

ማርክን ሰረቅ አድርጋ አይታ ፈገግ ስትል እሱም በፈገግታ ተቀበላት
‹‹ከነጋ አንዴ እንኳን አላናገርከኝም›› አለችው፡፡
‹‹ምክንያቱም ከኔ ይልቅ ለመርቪን ልብሽ መጥፋቱን ስላወቅሁ ነው›
ወዲያው ጸጸት ገባት፡፡ መቅናቱ ትክክል ነው፡ ‹‹ይቅር በለኝ ማርክዬ›
አለች ‹‹ልቤ ያለው ካንተጋ ብቻ ነው እውነቴን ነው››
እጁን ሰዶ እጇን ያዝ አደረገና ‹‹እውነትሽን ነው?››
‹‹እውነቴን ነው፡፡ ትናንት ምን እንደነካኝ አላውቅም››

‹‹እሺ›› አለ ማርክ፡፡
ሁለቱም አፍቃሪዎቿ አፍጥጠውባታል፡፡ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ
እንዳለባት አውቃለች፡ ከመርቪን ጋር ብቻዋን ብትነጋገር ማርክን
አስከፋዋለሁ ብላ ገምታለች፡፡ አሁን መርቪንን ትቼ ከማርክ ጋር ነው
ያለሁት ስለዚህ ማርክን ነው መደገፍ ያለብኝ ስትል አሰበች፡፡

ልቧ  ከበሮ  እየደለቀ ‹‹ማርክ ፊት የማታናግረኝ ከሆነ ልሰማው አልፈልግም›› አለችው፡:

መርቪን ደንገጥ አለና ‹‹እሺ›› አለ በብስጭት፡፡ ወዲያው ራሱን አረጋጋና ‹‹ከዚህ በፊት ያልሺኝን ተገንዝቤያለሁ፤ምን ያህል ቀዝቃዛ እንደነበርኩ አንቺም ምን ያህል ብቸኝነት ይሰማሽ እንደነበር…›› ንግግሩንቆም አደረገ፤ ዳያና ምንም መልስ አልሰጠችም፡፡ ይቅርታ ማለት ወይም መጸጸትን መግለጽ የመርቪን ባህሪ አይደለም፡፡ ምን ሊል ነው?› አለች ዳያና በሆዷ።

‹‹እስካሁን ላደረግሁት ሁሉ ይቅር በይኝ›› አለ መርቪን፡ ዳያና የመርቪን አባባል ቢገርማትም እውነቱን መናገሩን አውቃለች፡ ‹ይህ ሁሉ ለውጥ ከየት መጣ?›

መርቪን ቀጠለና ‹‹የተዋወቅን ሰሞን አንቺን ለማስደሰት ጥረት አደርግ
ነበር፡፡ እንዲከፋሽ አልፈልግም ነበር፡፡ አሁን ኑሮሽን ጨለማ ማድረጌ
ተሰምቶኛል፡ ደስታ ማግኘት መብትሽ ነው፡፡ የሰው ሁሉ ዓይን ማረፊያ እንደሆንሽ አውቃለሁ፡››

ዳያና ይህን ስትሰማ እምባዋ በዓይኗ ሞላ፡፡ የወንዶችን ዓይን መሳቧ
እውነት ነው፡፡

‹‹አንቺን ማሳዘኔ ሀጢያት ነው›› አለ መርቪን፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ አንቺን ለማስደሰት እጥራለሁ፡››

ከዚህ በኋላ ጥሩ እሆናለሁ› ማለቱ ፍርሃት ለቀቀባት፡ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ እሷ ግን እንዲጠይቃት እንኳን
አትፈልግም፡፡ ‹‹ወደ አንተ ተመልሼ አልመጣም›› አለች ዳያና፡

‹‹ከማርክ ጋር ደስተኛ ህይወት የምትኖሪ ይመስልሻል?››

ዳያና ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች፡፡

‹‹ያስብልኛል ብለሽ ታምኛለሽ?››

‹‹አዎ ያስብልኛል››

ማርክ ጣልቃ ገባና ‹‹እኔን እንደ እቃ ቆጥራችሁ ስለኔ ትናገራላችሁ? አለ፡፡

ዳያና የማርክን እጅ ለቀም አድርጋ ያዘችና ‹‹እንዋደዳለን›› አለችው:
‹‹አይ!›› አለ መርቪን፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ፊቱ ላይ የለበጣ ፈገግታ
ተነበበ ‹‹ትዋደዳላችሁ›› አለ፡፡
መርቪን የተለሳለሰ መሰለ፡፡ ይሄ የእሱ ባህሪ አይደለም፡፡
ወይዘሮ ሌኔሃን ሄደህ ከሚስትህ ጋር ተነጋገር አለችህ እንዴ?›› አለች ዳያና ተጠራጥራ።
አላለችም፡፡ ሆኖም ልናገር እንደምችል ታውቃለች››
‹‹ታዲያ ፈጠን ብለህ ተናገረውና ይውጣልህ›› አለ ማርክ፡፡
መርቪን ማርክን ገላመጠውና ‹ጎረምሳው አንተን እዚህ ነገር ውስጥ
የሚያገባህ ነገር የለም፤ ዳያና እኮ አሁንም ባለቤቴ ናት›› አለ፡፡

ማርክ ፍቅረኛውን ለማገዝ ‹‹ተው እባክህ!  ከዚህ በኋላ ከእጅህ ወጥታለች፤ ደግሞ ጎረምሳው አትበለኝ ሽ
ሽሜ›› አለው መርቪንን፡፡

‹‹መርቪን እዚህ አምባጓሮ ማንሳት አትችልም የምትለው ካለህ
አውጣና ተናገረው፤ አለበለዚያ አንድ ዓይነት ኃይል ያለህ አታስመስል››
አለችው ዳያና፡፡
‹‹ደህና፧ ነገሩ እንዲህ ነው›› ትንፋሹን ዋጥ አደረገና ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፤ ወደ ቤትሽ እንድትመለሺ ስጠይቅሽ ‹ምን ሲደረግ ብለሻል፧ ይሄ ሰው እኔ ማድረግ የማልችለውን አድርጎ ከሆነና ከእሱ ጋር
መኖር ደስታ የሚሰጥሽ ከሆነ መልካም እድል ይግጠማችሁ፡፡ መልካሙን
እመኝላችኋለሁ ይሄው ነው›› አለ፡፡ ከዚያም ጸጥታ ነገሰ፡

ማርክ ሊናገር ሲል ዳያና አቋረጠችውና ‹‹አንተ የተረገምክ እምነተ ቢስ
የሆንክ ሰው!›› አለች ‹‹እንዴት ያለኸው ደፋር ነህ!›› አለችና ምራቋን ጢቅ
አደረገች፡፡

መርቪን አባባሏ ግራ አጋባውና ‹‹ምነው?›› አላት፡፡
👍223🥰1
‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ እያልክ የማይረባ ነገር ለምን
እንደምትናገር አልገባኝም፡፡ መርቪን ላቭሴይ አንድን ነገር የምትተወው
የማትፈልገው ሲሆን እንደሆነ አሳምሬ አውቃለሁ›› ሰው ሁሉ ጆሮውን ቀስሮ የሚያዳምጥ መሆኑ ግድም አልሰጣትም፡፡ ‹‹ምን እንደፈለክ አውቃለሁ፡፡ ትናንት ማታ ከዚያች ጋለሞታ ጋር የልብህን ስታደርስ ነው
ያደርከው አይደለም?››

‹‹አይደለም››

‹‹አይደለም?!›› አለችና አፍጣ አየችው፡፡ እውነቱን እየተናገረ መሆኑን ገምታለች አለዚያም በጣም ተቀራርባችኋል  አይደለም? ልብህን ወስዳዋለች እሷም  ወዳሃለች  አሁን እኔን አትፈልገኝም፧ እውነት
አይደለም? እመን!››

‹‹ምንም የማምነው ነገር የለም››

‹‹እምነተ ቢስ ስለሆንክ ነዋ፡፡ እኔ አውቄብሃለሁ፤ አይሮፕላኑ ውስጥ
ያለው ሰው ሁሉ የሚጠረጥረውም ይህንኑ ነው፡፡ መርቪን በጣም
አዝኜብሃለሁ፡ ሃሞተ ኮስታራ ትመስለኝ ነበር፡፡››
ሃሞተ ኮስታራ! ይህ ቃል ጠቅ አደረገው::
‹‹እውነቴን ነው እንደፈለግሁ መሆን እንደምችል አሳዛኝ ወሬ ፈጥረህ ታወራለህ፡፡ በጣም ተለሳልሰሃል፤ እኔ ጣቱን የሚጠባ ህጻን አይደለሁም ልታታልለኝ አትችልም›› አለች፡፡

‹‹ደህና›› አለ መርቪን ‹‹ሰላማዊ ድርድር እንድናደርግ  ብጠይቅሽ
አልተቀበልሽም፤ እንደፈለግሽ ሁኚ›› አለና ተነሳ ‹‹አነጋገርሽን የሰማ ሰው ከውሽማዬ ጋር አገር ጥዬ የምጠፋው እኔ እመስለዋለሁ›› ወደበሩ አመራና

ተ‹‹ስትጋቡ አሳውቂኝ›› አለና ሄደ፡፡

‹‹ደህና!›› አለች ዳያና ደሟ እየተንተከተከ፡፡ አካባቢውን ስትቃኝ ልዕልት ላቪኒያ ገልመጥ አደረጓት፤ ሉሉ ቤል ፈገግ አለች፤ ኦሊስ ፊልድ አባባሏን
ባለመውደድ ሲኮሳተር ፍራንክ ጎርዲኖ ደግሞ ወንድ ነሽ ሲል አደነቃት፡

በመጨረሻም የመርቪንን ሁኔታና በንዴት መገንፈል አይቶ ‹ማርክ ምን
ይል ይሆን› ብላ ስትመለከተው ጥርስ በጥርስ ሆኗል፡፡ እሷም የእሱ ሳቅ ተጋብቶባት ትስቃለች፡፡

‹ምንድነው የሚያስቅህ? አለችው እየሳቀች
‹‹ልክ ልኩን ነው የነገርሽው›› አለ ‹‹ኮርቼብሻለሁ፤ ደስም ብሎኛል።
‹‹ለምን ተደሰትክ?››
‹‹በህይወትሽ መርቪንን ስትጋተሪው የመጀመሪያሽ ነው?››
‹‹ሳይሆን አይቀርም››
‹‹ከዚህ በኋላ አትፈሪውም አይደል?››
‹‹አልፈራውም››
‹‹አትወጂውም ማለት እኮ ነው ይሄ››
‹‹ይሆን?›› አለች ሃሳብ ገብቷት፡፡ ለብዙ ጊዜ መርቪንን አልወደውም
ብላ ስታስብ ነበር፧ አሁን ግን ልቧ የሚነግራት ሌላ ነው ባለፉት ወራት
ከሱ እየተደበቀች ስትማግጥ እንኳን ለእሱ ያላት ፍቅር እንዳለ መሆኑን
አውቃለች፡፡ ትታው ሄዳ እንኳን ልቧ ከእሱ ጋር ነው፤ አሁን ደግሞ አይሮፕላን ውስጥ ጸጸት ጠቅ እያደረገ ሲያስቸግራት እግሩ ላይ ውደቂ ውደቂ ይላታል፡ ይህም ሆኖ ወደ እሱ መመለስ የማይታሰብ ነው፡፡

ማርክም ‹‹ከዚያች ጋለሞታ ሴትዮ ጋር ቢሄድ ምንድነው የሚሰማሽ?»ሲል ጠየቃት

«ግድ የለኝም» አለች ወዲያውኑ ‹‹አንተ ልክ ብለሃል፡ ከዚህ በኋላ
ወደ ኋላ መመለስ የለም፡፡››

ይቀጥላል
👍17
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ዘጠኝ (39) «ሄሎ» አለች ሶስት እራቴ ስልኩ ከጮኸ በኋላ ። «እንደምን አመሸሸ ሚሰ አዳምስን። ማይክል ሂልያርድ እባላለሁ» አለ ። ባለችበት ላይ ደንዝዛ ቀረች ። ልትጮህ ቃጣት…..
። ሆኖም እንደምንም ብላ ተቆጣጠረቸው ። ትንፋሽዋንም ዋጥ አደረገች ። ይህን ሁሉ ካደረገች በኋላ «ነው? ሳንፍራንሲስኮ መጥተሃል ማለት ነው" አለች፡፡ ይህን የተናገረችው በመጠኑ በሚቆራረጥና በጎረና ድምፅ ነበር ። ያን ድምፅ የሰማው ማይክል የተቆጣች መሰለው ። ምን አስቆጣት ? አለ በሀሳቡ ። ምናልባት በሌላ ነገር ትበሳጭታ ይሆናል ። ወይም እቤቷ ሲደውሉላት አትወድ ይሆናል ። ብቻ የሰው ጠባይ ብዙ ነው ። ያም ሆነ ያ ማይክል ደንታው አይደልም ። «አዎ። ሳንፍራንሲስኮ ነው ያለሁት ። እና ተገናኝቶን አንዳንድ ነገር ብንወያይ ብዬ ነበር» አለ ማይክ «የለም የለም ። ምንም የምንነጋገረው ነገር የለም ። ለእናትህ ግልጹን የተናገርኩ መስሎኝ ነበርኮ» አለች። አልቅሺ አላት። ሰውነቷ በመላ ተንቀጠቀጠ ፤ የስልኩን እጀታ እንደያዘች ። «አልነገረችኝም ። ምናልባትም ረስታው ይሆናል» አለ ። የሱም ድምፅ እንደ እሷ ድምዕ ሙጥረት ይሰማበት ጀመረ። «ካንች ጋር እንደተለያያችው ቅለል ያለ የልብ ድካም በሽታ ስለተነሳባት ከህመሙ በኋላ ረሰታው ይሆናል ፣ ያው ልትረጂው እንደምትችይ…››

‹‹አመሣት ?» አለችና ዝም አለች « ግን ወዲያው… «አሁንስ እንዴት ነው ተሻላት?» ስትል ጠየቀች። «አሁን ደህና ናት ። ከዚያም አልፎ ባለፈው ሳምንት ባል አግብታ አሁን ማጆርካ ውስጥ ትገኛለች» አለ ማይክ ። አንድ ነገር መጥቶ እጉሮሮዋ ላይ ተሰነቅረ ። ውሻ! የኔን ሕይወት ብልሽትሽቱን አውጥታ ስታበቃ እሷ ተሰርጋ ትምነሽነሽ እንጂ ! እለች ፤ በሀሳቧ ። ጥርሷን ማንቀራጨጭም አማራት ። ስልኩን እጆሮው ላይ ድርግም ማድረግም አሰኛት። «ይህ እንኳ ከቁም ነገራችን ውጭ ነው» ኣለ የማይክል ድምዕ «እና መቼ እንገናኝ ትያለሽ ? »
«አንችልም ብዬ ነገርኩህኮ » ይህን ያለችው በፍጥነት ነበር ፤እንትፍ ያለችበትን ያህል ። ጉዳዩ አስደንግጦት ወይም አስገርሞት ኣይኑን ገርበብ አደረገ ግን ብዙም አልተጨነቀም ። ጉልበት አልነበረውም፤ ደክሞት ነበረና ። «እሺ ይሁን፤ተሸነፍኩ ። ላሁኑ ማለቴ ነው። ምናልባት ሀሳብሽን ከቆየርሽ ፌይርሞንት ሆቴል ነኝ። ደውይልኝ»
«አልደውልም»
«ደግ»
«ደህና ደር፤ ሚስተር ሂልያርድ»
«ደህና ደሪ፤ ሜሪ አዳምሰን» እንዴት ባንዴ ነገሩን ቁርጥ አደረገው! ደሞም ፈፅሞ ማይክልን የመሰለ ነገር የለውም! የደከመ፤ ሁሉ ነገር ገደል ይግባ ብሎ የተወ ይመስላል ። በነዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ ምን ደርሶበት ይሆን? ምን አጋጥሞት ይሆን? ስልኩን ከዘጋች በኋላ ለረጂም ጊዜ ስለማይክል ብዙ ጥያቄዎች ጠየቶች። ስለማይክል ባያሌው ኣሰበች።

•••••••••••••••••••••••••

«ውዴ ዛሬ በጣም ፀጥ ብለሻል። ቅር የተሰኘሽበት ነገር አለ ?› አለ ፒተር ግሬግሰን ምሳ የሚበሉበትን ጠረጴዛ አሻግሮ እያየ ። ሜሪ ምንም አልሆንኩም በሚል መንገድ ራሷን ነቅንቃ ወይን የተቀዳበትን መለኪያ እያሽከረከረች «ምንም አልሆንኩም» አለች «ምንም አልሆንኩም ። ቅር ያለኝ ነገርም የለም ። እያሰብኩ ነው… ስለምጀምረው አዲስ ስራ። አዲስ ፕሮጀክት ሳስብ ሁሌም እንዲህ ያደርገኛል ። ከአእምሮዬ ማውጣት አልችልም » ይህን ያለችው ስታብል ነበር ።ይህን ደግሞ እሷም ታውቅዋለቸ፤ ፒተርም ያውቀዋል ። ነገሩ ሌላ ነበር። ከትናንት በስቲያ ምሽት ማይክል ከደወለ ጊዜ ጀምሮ ናንሲ ዛሬን መኖር አልቻለችም ወደ ትናንት እየተጠለፈች ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የሆነውን ሁሉ ታሰባለች ። የምታስበው ሁሉ የመጨረሻዋን ቀን ነበር።... ቢስክሌቶቻቸውን ሲነዱ፤ ወደ ባዛሩ ሲገቡ ፎቶ ግራፍ ሲነሱ ካንዲ ፍሎስ ስትልስ… ሰማያዊዎቹን መቁጠሪያዎች በባህሩ ዳርቻ ላይ ስትቀብራቸው፡፤ የገቡት ቃል... ያን ለት ማታ የለበሰችው ቀሚስ፤ማይክልን ልታገባ ስትወጣ እና .. እና በመጨረሻ የማይክል እናት ድምፅ . . እሷ በፋሻ ትደግልላ ያነጋገረቻት ።

ይኸ ሁሉ ልክ እንደፊልም ባይኗ ላይ ጎልቶ ይታያት ነበር። ስንቴ ሌላ ነገር ልታስብ ሞከረች ግን አልቻለችም ። ከዚህ ሀሳብ ልታመልጥ ከቶ አልቻለችም ። «ውዴ ግን. .ግን . . ደህና ነሽ?» አለ ፒተር በመጨነቅ ። «ምን ትሆናለች ብለህ ነው? አይዞህ አትጨነቅ ። ደህና ነኝ በእውነት ደህና ነኝ ። ይቅርታ ዛሬ መቼም አሰጨነቅኩህ ። ምናልባትም ደክሞኝ ይሆናል ፤ በቃ» አለች ሆኖም አላመናትም ። አይቷላ የተጠናወተው የሚመስል ገፅታዋን ። የተከፋ ፈቷን ፤ በዓይኖቹዋ መካከል የተቋጠረ ግንባሩዋን አይቷል ። «ከፌ ጋር በቅርብ ተገናኝታችሁ ነበር?» አለ ፒተር። «አልተገናኘንም ። አንድ ቀን ምሳ እጋብዛታለሁ እያልኩ አልቻልኩም። ኤግዚብሽኑ ከተከፈተ ወዲህ ስራ በዛ» አለች ። ኤግዚብሽኑን ሰታነሳ ውለታውን በሚነግር ድምፅ ነበር የተናገረችው ፈገግ ብላ ። ከዚያም አከታትላ «ምን! እንደምታየው ከፎቶ ግራፍ ማጠቢያ ክፍል ወጥቼ አላውቅም» አለች። «እንዲህ በጓደኝነት ማለቴ ሳይሆን እንደሐኪም አነጋግራሽ ታውቃለች ወይ? ማለቴ ነበር» ኣለ ። «እንዲያውም ። አልነገርኩህም እንዴ ከገና በአል በፊት ያን ጉዳይ ጨረሰን ብዬ?»
«ግን እኮ ማን እንደሆነ ውሣኔውን የሰጠው አልነገርሽኝም ። አንቺ ትሆኝ ፤እሷ »
«የወሰንኩት እኔ ነኝ ። ግን ስነግራት አልተቃወመችም »። አለች

ፒተር የአእምሮ ሕክምና እንደሚያስፈልጋት በመጠቆሙ ናንሲ ትንሽ ቅር አላት ። ስለዚህም ሕክምናው እንደማያስፈልጋት በተዘዋዋሪ እንዲህ ስትል ልትነግረው ሞከረች ። «ፒተር ምንም የመረበሽ ስሜት የለብኝም ። ድካም ብቻ ነው። ደሞ እሱ ይለቀኛል »
«ይሆናል ። ግን ልቤ ይጠራጠራል ምክንያቱም አየሽ እፊትሽ ላይ የሆነ ነገር ይታየኛል ። . . . ማለት ከሁለት ዓመት በፈት የነበረው ነገር የሆነው ሁሉ እየመጣ የሚያስጨንቅሽ ይመስለኛል » ይህን ሲል እየተጨነቀና ሁኔታዋን እያጤነ ነበር ። ሰምታው ሽምቅቅ ስትል ሲያይ ደነገጠ ። ራሱን ጠላ ። «የምን ያለፈ ነገር?» አለች ሜሪ « የማይረባ ነገር አታምጣ››
👍17
«ያ ሆነ ማለት እኮ አእምሮሽኮ ትክክል አይደለም ማለት አይደለም። ያለ ነው። ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ነገር ቶሎ አይለቅም ። ቁስሉ እንዲህ በቀላሉ አይሽርም ። እስከ አስር ዓመት እስከ ሃያ አመት የሚሰቃዩ ሰዎች አሉ ፤ አደጋ ከደረሰባቸው በኋላ። ውስጥሽ ሁሌም ያስታውሳል ። ሀሳቡን አዘውትረሽ ገሸሽ ካላደረግሽው አይለቅሽም »
«አድርጌዋለሁ ፤ ለቆኛልም»
«እሱን እንግዲህ በሚገባ እምታውቂው አንቺ ነሽ ። ሆኖም አትዘናጊለት። ልትደብቂው አትሞክሪ ። ያ ከሆነ በትንሽ በትንሹ ውስጥ ለውስጥ ይጎዳሽና ሕይወትሽን ይሰነክለዋል። ችሎታሽንም ውሱን አድርጎ ያስቀረዋል ። እኔ እንኳ ይህን ያህል መናገርም እያስፈልገኝም ። ግን አንቺ መጠንቀቅ ይኖርብሻል ። ከፌ አሊሰን ጋር ያለውን ግንኙነትም ለተወሰነ ጊዜ ብትቀጥይው የሚበጅ ይመስለኛል» ይህን ሁሉ ሲል ጉዳዩ እንዳስጨነቀው ይታወቅበት ነበር ። ይህን ብሎም ትክዝ አለ ። «ከፌ ጋር መቀጠሉ እንኳ አያስፈልገኝም» አለች ሜሪ።

ይህን ካለች በኋላ መልስ ሊሰጣት አልፈለገም ። መከራከር የለበትም ። ዝም ብሎ እጅዋን ይዞ ተይው እንደማለት ያህል መታ መታ አደረገው። ጉዳዩን ስላነሳና ስለረበሻት ግን ይቅርታ አልጠየቅም ። ሁኔታዋ ሁሉ ነገሩ አሳሳቢ እንደሆነ በግልፅ እንዲያይ አድርጎአታል ። በዚህ ሁኔታ ትንሽ እንደቆዩ «እሺ እንግዲህ። አሁን ብንሄድ ምን ይመስልሻል?» አለ ። ይህን ሲል ከልቡ ፈገግ እያለ ነበረና አፀፋውን ልትመልስለት ሞከረች። ግን አልቻለችም ። ልታምንለት አትፈልግም እንጂ ግምቱ ልክ እንደሆነ ገብቷታል ። ዋሽታዋለችና ፈገግታው እንቢ አላት። ከምግብ ቤቱ እንደወጡ ፤ «ቤት ላድርስሽ? ሲል ጠየቃት ። «አያስፈልግም ፤ ወደ ኤግዚብሽኑ አዳራሽ ጎራ ብዬ ጃክን ላነጋግረው አስቤአለሁ። የምናዘጋጃቸው ነገሮች አሉ» አለች። «ደግ» አለ ፒተር። እጁን እትከሻዋ ላይ ጣል ኦድርጎ ወደ ፀደዩ የፀሐይ ብር ገቡ። ጧት መሬቱን ሸፍኖ የነበረው ጉም በኖ ጠፍቶ ቀኑ ብሩህ ሆኗል ። የምግብ ቤቱ የቆሙ መኪናዎች አስተናባሪ የፒተርን ጥቁር አውቶሞቢል ነድቶ እመንገዱ አስገብቶ ሲያቆማት ፒተር የእንግዳ መቀመጫውን ጋቢና በር ለናንሲ ከፈተላት ። ገብታ ተቀመጠች ከዚያም በወዲያኛው በር ዞሮ እነጂው መቀመጫ ወንበር ላይ ተቀምጦ መሪውን ሲይዝ ቀሚሷን እያስተካከለች ፈገግ አለች። በሀሳብ ተውጣ ። ምን ያህል እንደሚያስብላት፤ የቱን ያህል እንደሚጨነቅላት ይገባታል ። ሆኖም ለምን እንደሚያፈቅራት አይገባትም ። ትጠራጠራለች። ለምን ? ትላለች። ስለፈጠረኝ ፍቅሩን ለፍጡሩ ሊሰጥ የሚገባው ዓይነት ፍቅር ይሆን ? ወይስ ፊት ስለምነሳው አላገኛትም ብሎ ስለሚያስብ ? እንጃ ። ሆኖም ሁልጊዜም መንገድ እምትዘጋ እሷ ናት ። ይህ ሀሳብ ስላለባት ይሆናል… ነፃ አትሆንም፤ ከፒተር ጋር ስትሆን። እሱ ግን ደግ ነው። ሁሉ ነገር ነው። ጥሩ ሰው አይደለሁም ማለት ነው የሚል ሃሳብ መጣባት ። ግን እንዴት ነፃ ትሁን? ፍርሃት አልባ ሁለተኛ አደጋ እንደሚደርስባት የሚያሳስብ ነገር አለባት ። ባለፈው የደረሰባት አደጋ ጥሎት ያለፈ ጠባሳ ቢኖር ነው። ምናልባትም ፌ አሊሰንን (የአእምሮ ሕክምና ጠቢቧን) ማነጋገር ሊኖርባት ይሆናል….»

«ዛሬ ዝምታ በዝምታ ሆነሻል፤ የኔ ፍቅር ። አሁንም ያንኑ አዲስ ፕሮጀክት እያሰብሽ ነው?» አለ ፒተር ሃሳቧን እያናጠባት። እራሷን በአዎንታ ነቅንቃ የእፍረት ፈገግታ ፈገግ እንዳለች እማጅራቱ አካባቢ በለሆሳስ ዳሰስ አደረገችው። እና ፤ «ግን ለምንድነው ይህን ያሀል እምትጨነቀው » ስትል ጠየቀችው።
«ምክንያቱም ሜሪ አንች ለኔ ወደር የሌለሽ ልዩ ፍጡር ስለሆንሽ ነው» አላት «እና ደግሞ ይህን የምልሽ ከልቤ መሆኑን ብታውቂልኝ ደስ ይለኝ ነበር» ግን ለምን? ይህን ያህል ለምን ? ምናልባት ፊቴን በፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሲያክም ያቺን የሚወዳትን ሴት አስመስሎ ሰርቶኝ ይሆን እንዴ? እሷን እየመሰልኩት ይሆን እንዴ? ዝም ብሎ ሀሳብ ነበር ።

ሀሳቧን ፀጥ ለማድረግ ፤ አእምሮዋን ለማሳረፍ ወደ ኋላ ተለጥጣ ራሷን እሶፋው ላይ ጥላ አይኗን ከደነች። ሆኖም በዚያ ሁኔታ ብዙ አልቆየችም ። የጥይት መሰሏን መኪና መሪ አንድ መታጠፊያ ላይ ሲያዞረው አይኗን በግድ ገለጠች። አይኗን ገልጣ ስትመለከት፤ አንድ መናጢ ቀይ ጃጉዋር ኦቶሞቢል በሷ በኩል ከፊት ለፊት እየተፈተለከ ሲመጣ አየች። ጃጉዋሩ መንገዱን ለቆ ካሉበት አውቶሞቢል ፊት ለፊት እንዲመጣ ያደረገው እንድ እመንገዱ ዳር የቆመ የጭነት መኪና ነበር ፤ መንገዱን ስለያዘበትና ያንን ደርቦ ለማለፍ ሲሞክር ። ይህ ጃጓር ፍጥነቱንም አልቀነሰም ። መንገዱን ስቶ ፊት ለፊት መጣ። ፈረፋንጎውና የፒተር መኪና ፈረፋንጎ የተሳሳሙ እስኪመስል ድረስ ቀርቦ ታያት ። ያበደው የጃጓር ነጂ ፊት ለፊት ሲመጣ ፒተር እንደምንም ብሎ መንገዱን ለቀቀለትና ቀይ መብራት ጥሶ ወደፊት ተፈተለከ ። ጃጓሩን ተደንቆ ዞሮ አየው ሜሪ ግን የለችም ። ባለችበት ላይ ደርቃ ቀርታለች። የጨው አመድ ሆናለች። እፊት ለፊት ያለውን የእቃ ማስቀሙጫ መድራ ይዛ፤ አይኗ ፈጥጦ፡፤ የሰራ አካላቷ እየራደ ፤ ጥርሷ እየተንገጫገጨ አእምሮዋ ከዚህ በፊት እደረሰ አንድ አሰፈሪ ነገር ላይ ተተክሎ በጠቅላላ ጠፍታለች ።

የሜሪን ሁኔታ ያየው ፒተር ምን እንደታሰባት ፤ አሁን እምን ውስጥ እንዳለች ለማጤን ጊዜ አልፈጀበትም ። ስለዚህም የመንገዱን ዳር ካስያዘ በኋላ መኪናውን አቁሞ ሜሪን ንፋስ እንዲነካት ከመኪናው ሊያወጣት ሲይዛት ድርቅ ብላለች። ጎተት ሲያደርጋት በድንገት መኪናውን በጩኸት ሞላችው ። ከነፍስ ጠሊቅ ፍርሃት ወጥቶ ሀይለኛ ጩኽት ሆነ ። ዝም ለማሰኘት ማቀፍ ፤ መወዝወዝ፤ ጥብቅ አድርጎ መያዝ. . . ይህን ሁሉ ማድረግ ነበረበት ። ይህን ሁሉ አድርጎም በቶሎ ዝም አላለችም ። «ዝም በይ.. በቃ ዝም በይ… የለም እኮ አለፈ ። የለም ውሽት ነው። ያ ሁለተኛ አይደገምም ። እሰይ የኔመቤት ። በቃ በቃ ዝም በይ….

ይህን ሁሉ ብሎ ዝም አሰኛት ። ይህን ለማድረግ ግን ግማሽ ሰዓት ያህል ወሰደበት ። ቀስ እያለች ፀጥ አለች። ከዚያም ጉልበቷ ሁሉ ተሟጥጦ ተዝለፈለፈች። አቅሏን ግን አልሳተችም ። ቀስ ኢያለ እየደባበሰ አረጋጋት ። ይልቁንም ፊቷ ምንም እንዳልሆነ እንድ ትረዳ እጅዋን አንስቶ ፊቷን እየዳሰሳት «ይኸው ደህና ነሽ እኮ ! ምንም አልሆንሽም እኮ!
👍12
አየሽው!» አላት ። ፒተር ባየውና በሆነው ነገር ሁሉ እጅግ ተረበሸ ። የገመተው ነገር እውነት እንደሆነ በሚገባ ተገነዘበ። በጣም መለስ ስትል ለስለስ ባለ፤ ግን ውሣኔ ባጠነክረው ድምፅ ‹‹የለም የለም፣ የፌ አሊሰንን ሕክምና መከታተል አለብሽ የገመትሽውን ያህል ቁስሉ አልዳነም ። ቆርጠሽ ካልተጋፈጥሽው ደሞ ሊድን አይችልም» አለ። አይኗን ክድና አዳመጠችው ግን እንዴት አድርጋ ትጋፈጠው? ምን ብላ ትጋፈጠው? ብትጋፈጠውስ የሚድነው ነገር ምንድነው ያለፈው ነገር ማለት ማይክ ማለትእኮ ነው ። ለማይክ ያላትን ፍቅር ደግሞ ምንስ ብላ እንዴትስ አድርጋ ልትረሳው ትችላለች? ማይክ ስልክ እንደደወለላት፣ ድምጹን ስትሰማ እቅፍ አድርጋ ልትስመው ምን ያህል እንደጓጓች እንዴት አድርጋ ትንገረው ለፒተር ? ቢያቅፋት የተመኘችውን ፣ማይክን ያለመችውን ምን ጉልበት አግኝታ ብታስረዳው ይገባዋል ?
ይቀጥላል...... ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
9👍3