ተቸገረ፡ የሻንጣ መያዣው ክፍል ውስጥ ማሞቂያ ስለሌለ ሄሪ ብርዱን
አልቻለውም: ሻንጣዎቹ በበረራ ጊዜ እንዳይወዳድቁ የታሰሩበትን ገመድ
ለመፍታት ሲታገል እጆቹ እየተንቀጠቀጡ አስቸገሩት፡፡ ያየውን ሻንጣ መልሶ እንዳነፈያይ አንድ በአንድ ማየቱን ተያያዘው፡፡ ከሻንጣዎቹ መካከል
የኦክሰንፎርድን ሻንጣ ግን ማግኘት አልቻለም፡፡ ከሃያ ደቂቃ በኋላ የሁሉንም
ሻንጣዎች ስሞች ማየት አጠናቀቀ፡፡ ስለዚህ የኦክሰንፎርዶች ሻንጣዎች
በሚቀጥለው ክፍል ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ ዕድሉን ረገመ፡
የፈታውን ገመድ መልሶ አሰረና ምንም አሻራ አለመተዉን ለማረጋገጥ
በጥንቃቄ ቦታውን ቃኘ፡፡
የሚቀጥለው የሻንጣ ክፍል ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ፍተሻውን ማድረግ ይኖርበታል፡ በሩን ከፍቶ ሲወጣ አንድ ሰው ‹‹ማነህ!?›› ሲል
በቁጣ ጠየቀ፡
ሄሪ ቢደነግጥም ቶሎ ድንጋጤውን ዋጥ አደረገና በሩን ዘግቶ ‹‹ሄሪ
ቫንዴርፖስት ነኝ›› አለ፡፡ ‹‹አንተስ ማነህ?›› ሲል ጠየቀ፡
‹‹ሚኪ ፊን እባላለሁ፡፡ የበረራ መሀንዲሱ ነኝ፡፡ ጌታዬ እዚህ ቦታ
መገኘት አይጠበቅብህም፡፡ እዚህ መግባትህ ገርሞኛል፡፡ በመቆጣቴ ይቅርታ ለመሆኑ እዚህ ምን ታደርጋለህ?›› ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ሻንጣዬን እየፈለኩ ነው›› አለ ሄሪ ‹‹ምላጭ ላወጣ ነው››
‹‹አይሮፕላን ውስጥ ከተገባ በኋላ በማንኛውም ሁኔታ ሻንጣ ያለበት
ቦታ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው››
‹‹አይ እኔ ምንም ችግር የለውም ብዬ ነው የመጣሁት››
‹‹ይቅርታ እዚህ መግባት አይፈቀድም፡፡ እኔ የራሴን ምላጭ ልሰጥህ
እችላለሁ››
‹አመሰግናለሁ ለችሮታህ እኔ ግን የራሴን ምላጭ ነው የምፈልገው ማግኘት ከቻልኩ››
‹‹የምትፈልገውን ባደርግልህ በወደድኩ
ጌታዬ እዚህ መግባት
ስለማይቻል ነው፡ ካፒቴኑ ሲመጣ ልትጠይቀው ትችላለህ፡፡ እኔ ያልኩህን
ነው የሚልህ››
ሄሪ እየቆጨው ሽንፈቱን መቀበል ሊኖርበት ነው፡፡ ካልሆነ ያንተን ምላጭ እወስዳለሁ አመሰግናለሁ የኔ ወንድም፡፡››
ሚኪ ፊን በሩን ከፍቶ ያዘለትና ሄሪ ወጥቶ ሄደ፡፡ ምን አይነት ክፉ እድል ነው› አለ በሆዱ፡፡ ‹ትንሽ ጊዜ አግኝቼ ቢሆን ኖሮ ሁለተኛውን የሻንጣ
ክፍል እበረብር ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት እድል አገኝ እንደሆን
እንጃ አለ በሆዱ ያመለጠው ዕድል እያንገበገበው፡፡
ሚኪ ፊን ወደ አይሮፕላኑ ሰራተኞች ክፍል ሄደና አዲስ ምላጭ ከሳሙናና ከውሃ ጋር ይዞለት መጣ፡፡ ሄሪ ተቀበለና አመስግኖ ይዞ ሄደ ስለጌጣጌጡ እያሰበ መታጠቢያ ክፍል ጥልቅ ሲል ሳይንቲስቱን ካርል
ሃርትማንን አገኛቸው፡ ሄሪ ሚኪ በሰጠው ምላጭ ጢሙን ሙልጭ አድርጎ
ተላጨ፡፡ ‹‹ትናንት ማታ ጉዞው በጣም መጥፎ ነበር›› አለ ወሬ ለመጫር፡
‹‹ለኔ ደግሞ የበለጠ መጥፎ ነበር›› አሉ ሃርትማን፡፡
ሄሪ የሳይንቲስቱን የከሳ ሰውነት ሲያይ ተደነቀ፡፡
‹‹አዎ እውነት ነው ለእርስዎ በጣም መጥፎ ምሽት ነበር›› አለ፡
ከዚህ በላይ ያወሩት ነገር የለም፡፡ ሃርትማን ወሬ የሚወዱ ሰው አይነት አይመስሉም፡፡ ሄሪ ደግሞ ልቡ ያለው ጌጣጌጡ ላይ ነው ሄሪ ጢሙን ከተላጨ በኋላ አዲስ የገዛውን ሰማያዊ ሽሚዝ ለበሰና
ከሸሚዙ ጋ የሚሄድ ክራቫት አሰረ፡፡
ወደ መቀመጫው ሲመለስ የማርጋሬት መጋረጃ መዘጋቱን አየ::ጸጉሯን ትራሱ ላይ በትና እንቅልፏን ተኝታ ታየችውና ፈገግ አለ፡፡ ምግብ ቤቱ ክፍል ውስጥ አስተናጋጆች ምግብ እያቀረቡ አየና አፉን ምራቅ ሞላው:
የሚኪን የጢም መላጫ ዕቃዎች ይዞ ደረጃውን ወጣና የበረራ ክፍል
አካባቢ ተመልሶ ሄደ፧ ዕድሉን እንደገና ለመሞከር፡፡
ሚኪ እዚያ የለም፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ቁጭ ብሎ ስሌት ሲሰራ አገኘ፡፡ ሰውየው ቀና አለና በፈገግታ ‹‹ጤና ይስጥልኝ ምን ትሻለህ የኔ ወንድም?›› አለው፡፡
‹‹ሚኪን ነው የምፈልገው፤ ምላጩን ልመልስለት››
‹‹ቁጥር አንድ ክፍል ውስጥ ታገኘዋለህ››
‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ሄሪ፡፡ ይህን ሰውዬ አልፎ መሄድ ሊኖርበት ነው፡፡
ግን እንዴት?
‹‹ሌላ የፈለግኸው ነገር አለ?›› ሲል ጠየቀ ሰውየው ፈገግታ ሳይለየው፡፡
‹‹ይሄ የበረራ ክፍል
የሚገርም ነው›› አለ ሄሪ ‹‹ቢሮ ነው የሚመስለው››
‹‹ይደንቃል፡ አይገርምም?››
‹‹በአይሮፕላን ላይ መስራት ትወዳለህ?››
‹‹እወዳለሁ። አየህ ካንተ ጋር ባወራ ደስ ይለኝ ነበር፧ ነገር ግን አይሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት ስሌቱን መጨረስ አለብኝ›› አለ፡
ሄሪ ወሽመጡ ቁርጥ አለ፡፡ ወደ ሻንጣዎቹ ክፍል መሄድ አይቻልም ማለት ነው› አለ በሆዱ፡ ወደዚህ ክፍል ለመግባት የሚያስችለው ምንም ምክንያት አይኖርም፡ ንዴቱን ዋጠና ‹‹ይቅርታ›› አለ ‹‹እሺ እመለሳለሁ፡››
ወትሮው ከተሳፋሪዎች ጋር እናወራለን፡፡ ብዙ ዓይነት ሰዎች በበረራ ወቅት ይገጥሙናል፡፡ አሁን ግን ጊዜ የለኝም፡››
እኔ ነኝ ጥፋተኛው በዚህ ሰዓት መምጣቴ›› አለና ዕድሉን እየረገመ በደረጃው ወርዶ ሄደ ለሁለተኛ ጊዜ ዕድሉ እንደተበላሸ አየ፡
የተዋሰውን ምላጭ ለሚኪ መለሰና ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡
ማርጋሬት ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷታል፡፡ ሄሪ ወደ ውጭ ሲወጣ
ቀዝቃዛ አየር ተቀበለው፡፡ በህይወት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገጥም ወርቃማ
ዕድል አመለጠኝ አለ በሆዱ፡፡ እሱ ካለበት ቦታ ጥቂት ራቅ ብሎ የሚገኘውን ውድ ጌጥ ሲያስበው እጁን በላው፡ግን
ግን ተስፋው ገና አልተሟጠጠም፡ ከዚህ በላይ አሜሪካ ከመድረሳቸው በፊት አይሮፕላኑ የመጨረሻ ማረፊያ ላይ ዕድሉን ይሞክራል፧ ሼዲያክ ላይ።፡፡
✨ይቀጥላል✨

👍24😁1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ
ምዕራፍ ሰላሳ ስድስት (36) ትዝ ካለህ ያንለት ልክ እንተ ስትገባ እሱ ወጥቶ አልሄደም ? እየተቆጣ ? ያንለት የመጣው ልጅቷን እንደሚያገባት ሊነግረኝ ነበር ። እኔ ደግሞ ስለቤተሰቧ ያሠራሁትን ሪፖርት ሰጠሁት » ልትቀጥል አልቻለችም ። የለም ጆርጅ በሀሳቡ ። ምንም ደህና አይደለችም ፤ አለ «ማሪዮን ውዴ ፤ ታዲያኮ ያችን ልጅ ዛሬ ልታገኛት አይልሽም ። ማለት ልጅቷ እኮ ያኔ ነው... ያለፈችው»
«አይ ጆርጅ ። ሞኝ ነህ ። ብዙ እማታውቀው ነገር አለ ፣ ስለኔም ስለብዙ ነገርም ። አልሞተችም እኔ ነኝ ሞተች ብዬ የነገርኳችሁ ። አደጋው ደረሰ ። ፊቷ ብቻ ሲጎዳ ፣ ሲበላሽ ልበልህ ? ሌላው አካሏ ምንም አልሆነም ነበር….. ፊቷ ግን ከአይኗ በቀር አልነበረም» ጆርጅ ማዳመጥ ጀመረ ። ማሪዮን የሆነውን ከዳር እስከዳር ገለፀችለት ። «ማይክልን ለማግኘት ካልሞከረች ፊቷን በፕላስቲክ ሰርጄሪ ለማስጠገን ገንዘቡን እንደምከፍልላት ቃል ገባሁላት» አለች ማሪዮን ።
«ተስማማች?»
«ተስማማች»
«እንዲያ ከሆነ ማይክልን አትወደውም ነበር ማለት ነው። ስለዚህ ለህክምናው ስለከፈልሽላት እንዲያውም በጎ አድራጊ እንጂ ክፉ አይደለሽም ። እንዲያውም እሱም ያን ያሀል ቢወዳት እሷም ያን ያህል ብትወደው በዚህ ጉዳይ ተስማምተው ቁጭ አይሉም ነበር»
«የለም የለም ። ያልገባህ ነገር አለ ፤ ጆርጅ ። አየህ ዋሽቻቸዋለሁ ። እሷ የተስማማችበት ምክንያት ፤ ምን ተባለ ምን ማይክል የሷንና የኔን ስምምነት እንደማይቀበል ፤ መኖሯን እንዳወቀ የፈለገውን ነገር ጥሶ እንደሚያገባት በመገመት ነው ። ለማይክል ደሞ ሞታለች ብለን ነግረነዋል ። የሚያውቀው መሞቷን ነው።
ባይሆን ኖሮ ደሞ ርግጠኛ ነኝ ማይክል የፈለገው ቢሆን ውርስ ብነሳው እንኳ ትቶልኝ እሷን ያገባ እንደነበር ቁልጭ ብሎ ይታየኛል » ጆርጅ ይህን ሲሰማ አዘነ ። ማሪዮን የዓለም ሰው መሆኗን ያውቃል ። ምንም አይነት ውሣኔ የምትወስነው ለሷ ቅርብ የሆነውን ነገር ለማዳን ነው። ይህን ሁሉ ያደረገችው ደግሞ በልጅቷ ላይ ክፉ ለማድረግ ሳይሆን የማይክልን ክብር ለመጠበቅ ስትል እንደሆነ ይገባዋል ። ሆኖም ነገሩ ማይክልን እንዳልጠቀመው ግልፅ ነው። በህይወቱ የመጣ ነገር ነበረና ብዙ ጎድቶታል። ይህ ደግሞ ለማሪዮን የማይሽር ቁስል ሆኗል ። ነገርን ቢያባብሱት ዋጋ የለውም ። ይልቅ ቁስሏ ይሽር እንደሆነ የሚቀባ መድሐኒት መሞከር ይሻላል አለና አሰበ ። እና… «ግን ይህ ስለሆነ ማይክል ምንም ያህል አልተጎዳም። ወደ መጀመሪያው ላይ በርግጥ… !» ሲል አቋርጣው «የለም ፣ ዛሬም የማይክል ቁስል አልሻረም ። ርግጥ ነው ማይክል እንደመጀመሪያው ሲያዝን ፡ ሲተክዝ ፤ ሲበሳጭ ፡ ሲጠጣ አይታይም ። ያን ያህል እኔም ሳልገነዘብ አልቀረሁም ሆኖም እንዳየኽው ሌት ተቀን ሥራ ሥራ ሥራ ነው። በሥራ ተጠምዶ ይውላል ፤ በዚያው ያድራል ። በሱ እድሜ እንደሚገኝ ወጣት አይደሰትም ። የሱን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው እኩዮቹ አይጨፍርም ። ሽሽት ነው። ይኸ ሁሉ ኑሮን መተው ነው። ቁስሉ ውስጥ ውስጡን እያሰቃየው. . . የሱ ኑሮ ይሄ ነው። ከማንም ሰው ይበልጥ ይህን እማውቅለት እኔ ነኝ። እናቱ ነኝ። ግን….» አለች።
«ግንኮ ይህን ያህል ጊዜ ተለያይተዋል ማሪዮን ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ደሞ ሁለቱም ተለውጠዋል ። ስለዚህ ዛሬ ቢገናኙ እንኳ ፍቅራቸው እንደዚያ ጊዜው ላይሆን ይችላል ። ላይፈቃቀዱ ይችላሉ» አለ ጆርጅ ቁስሏን የማከም ሙከራውን በመቀጠል ። «ይገባኛል ። አሁን ያልከውንም አስቤዋለሁ ። ግን እንጃ ማይክ ሁሉን ማድረግ ሲችል ሁሉን ትቶ ሥራ፣ ሥራ እያለ ከመኖር ሸሽቶ ኑሮውን ይገፋል። እሷም ብትሆን…. እሷም የሷም…» ንግግሯን አቋርጣ በሀሳብ ጭልጥ ብላ ጠፋች ። በአይነ ኅሊናዋ ሜሪን በማየት ላይ ነበረች ። «እሷም» አለች በሀሳብ እንደሰመጠች «በርግጥ ቆንጆ ሆናለች ። አለባበሷ አቋሟ ይኽ ቀረሽ የማትባል ቆንጆ ሆናለች ። ናትግን ቁጡ ፤መራራ ስሜት ያላትና በጥላቻ የተሞላች ሰው እንደወጣትም በግልፅ አይቻለሁ ። ቢጋቡ እንዴት አይነት ድንቅ ባልና ሚስት ይወጣቸው ነበር»
«አሁን ያ ሁሉ እንዳይሆን መሰናክሏ እኔ ነኝ ነው እምትይው ?»
«ይህን ሁሉ ከነገርኩህ ፤ይህን ያህል ስለሁኔታው ካወቅህ በኋላ አንተስ ቢሆን ጥፋተኛ ናት ቢሉህ እትስማማም?...›› «
‹‹... ጆርጅ እውነቱን መሸሽ አያሻም ። ጥፋተኛ ነኝ ። በሁለት ፍቅረኞች መካከል መግባት አልነበረብኝም ። »
«ሳይታሰብ በደል ተፈፅሟል እንበል ። ግን ደግሞ የሁለቱ ነገር የሚሆን ከሆነ አሁንም ነገሩ የሚስተካከልበት መንገድ ይኖር ይሆናል ። ከተስተካከለ ደግሞ ያ ባይሳካ እንኳ ለልጅቷ የዋልሽላት ውለታ ቀላል አይደለም። ገላዋን መልሰሽላታል እኮ... ምናልባትም የተሻለ ኑሮ እንድትኖርም ረድተሻታል»
«ይህን ሁሉ አደረግሺልኝ አላለችም ፤ እሷ እንዲያውም በጣም ትጠላኛለች»
«ይህን እያወቀች የምትጠላሽ ከሆነ ዋጋ የላትም ። ጅል ናት ማለት ነው»
«የለም ጆርጅ ጅል አይደለችም ። መጥላቷም ትክክል ነው። ልብ ቢኖረኝ ኖሮ ደሞ ለማይክል እነግረው ነበር የሆነውን ሁሉ።»
«አሁንማ መንገር ምን ዋጋ አለው? አሁንስ ባትነግሪው ይመረጣል ውዴ» አለ ጆርጅ የማይክልን ቁጣ እያሰበ ።«አትንገሪው እሺ ?»
«አይዞህ ፣፤ ጀርጅ» አለች ማሪዮን በሀዘን ፈገግ ብላ «ያን ያህል ደፋር አልምሰልህ። ይህን ለሱ ለመንገር ያህል ልብ የለ። ሆኖም ማወቁ አይቀርም ። ጊዜ ይወስዳል እንጂ ማወቁ የማይቀር ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ እኔም እረዳዋለሁ ጥፋቴን ለመዘርዘር አቅምም ድፍረትም የለኝም ። ከተገናኙ በኋላ እሚስማሙ ከሆነ እሷው ትንገረው ። ያኔ ምናልባት ይቅርታ ያደርግልኝ ይሆናል»
«ተወኝ ብላ እምታስብ ከሆነ እሺ ብላ እምትቀበለው ይመስልሻል ?››
«እሱን እንጃ ፤እሱ እኔንም ያጠራጥረኛል ። ግን እኔ የተቻለኝን ያሀል እንዲገናኙ ማድረግ አለብኝ»
«እንዴት ያለው ጣጣ ...»
«እዎ እንደተበተብኩት ማፍታታት አላብኝ ። ውሉ ላይገኝ ያሰብኩት ላይሳካ ይችላል ። ቢሆንም መሞከር አለብኝ»
«ይገርማል።... ይህን ያሀል ጊዜ ሁለት አመት መሆኑ ነው... ይህን ያሀል ጊዜ በሆነ መንገድ ከልጅቷ ጋር ግንኙነት ታደርጊ ነበር ?»
«እንዲያ በፋሻ ተደግልላ ካነጋገርኳት በኋላ አይቻት እላውቅም ነበር ። ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት ዛሬ ነው»
«ገባኝ ፤ ዛሬስ እንዴት ልትገናኙ ቻላችሁ ?››
«የቀጠርኳትም እንድንነጋገር ያቀድኩትም ራሴ ነበርኩ ። ቤን ስለፎቶግራፍ አንሺዋ አርቲስት ሲነግረኝ ልቤ ጠረጠረ ። ጥርጣሬ እንጂ ርግጠኛንኳ አልነበርኩም»
«አብራችሁ ያሳለፋችሁት ጊዜ ጭንቅ የበዛበት ሳይሆን እይቀርም»
«ከዚያ የባሰ ሊሆንም ይችል ነበር» አለች ድምጺ በሀዘን ለስልሶና አይኗ ላይ እንባዋ ተንቀርዝዞ «የባሰ ነገር ሊመጣም ይችል ነበር ግን እልሆነም ። ምን ያህል እንደትሳሳትኩ ፤ ሁለት ህይወት እንዳበላሸሁ ፤ ወንጀለኛ እንደሆንኩ ብቻ ነው የተረዳሁት ። ያ ብቻ ነው...»

👍17
«ተይ እንጂ እንዲያ አትበይ ። አንዳቸውንም አልጎዳሻቸውም'ኮ ። በደንብ ብታስቢበት እኮ ማይክልን የበረራ መሀንዲስና የተዋጣለት ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን አደረግሽው እሷም የተሟላ እካል ያላት የታወቀች ፎቶግራፍ አንሺ ነው የሆነችው ። በምንም መንገድ ይህን ሊሰጣት የሚችል ሰው አልነበረም»
«ምኑን ነው ማንም ሊሰጣት የማይችለው ? ተስፋ መቁረጥን? ሀዘንን ? ግራ መጋባትን ? ምኑን ?»
«አንቺ የሰጠሻት ይህን ከመሰላት ደህና ሰው አይደለችም ። ማለቴ ውለታ ቢስ ናት ማለት ነው። ሙሉ አካልን ያህል ነገር ሰጠሻት ። የሰጠሻት አዲስ ሕይወትስ ? አዲስ ዓለምስ ይኸ ሁሉ አይቆጠርም ? ።»
«እዲስ ሕይወት ። ዓዲስ አለም። ይኸ ሁሉ ለኔ እንደሚመስለኝ ለሷ ምንም ጣእም የለሰውም። ህያው አይደለም። ምናልባት ከዚሀ አላት ካልከው ነገር ሁሉ ያለው ሥራዋ ብቻ ይመስለኛል ። በዚሀ በኩል ደግምሞ የሷም የማይክም ስሜት ተመሳሳይ ነው »
«እንዲያ ከሆነም ማለትም አንድ አይነት ከሆኑም ጥሩ ። አሁን ፈቅደሻል ። ሰለዚህ ተገናኝተው አንድ ነገር ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል ። ገና ልጆች ናቸው ሁለቱም ። የራሳቸውን መንገድ ይቀይሱ። ስለነሱ እያሰብን የኛን ጭላንጭል ኑሮ አናበላሻት » ይህን ብሎ ጎንበስ ብሎ ከሳማት በኋላ…. «ማሪዮን» አለ ፤ «ማሪዮን እወድሻሰሁ» አየችው ። እንደገና በፍቅርና በተሰቃይተሻል አይን እያያት «ማሪዮን ፤ ፀፀቱን ችለሽ ሙቆየትሽም ይገርማል ። ምነው ቀደም ብለሽ ብትነግሪኝ ? ሀሳብ'ኮ ለሰው ሲነግሩት ይከፈላል»
«ብነግርህ ፤ ይህንም ታደርጋለች ? ብለህ ትጠላኝ ነበር» ኣለች ማሪዮን ሂልያርድ ። ‹‹ማ? እኔ? አንችን? ፍጹም የማይሆን ሀሳብ ። ያኔም ሆነ ዛሬ ኣንችን መውደድ እንጂ መጥላት አልችልም። አለና ችንሽ አሰበ ። ቀጥሎ
«ማሪዮን» አለ። አየችው ፤ አቤት እንደማለት ። «ማሪዮን ያለፈው ኣልፏል ። ላሁኑ ሁለቱ የሚገናኙበትን መንገድ ቀይሺ ። የሚቻልሽን ሞክሪ ።
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️

👍10
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ከሻንቆና ከላላ የተሰባሰቡት ሽማግሎች በደልቲ ገልዲና በካርለት ጋብቻ ላይ ሸንጎ ከመቀመጣቸው በፊት በኅብረተሰቡ አጋጣሚ ላይ
ትንበያ መስጠት ይችላሉ የተባሉት፣ «ጫማ ጣዮች» ደጋግመው ጫማ በመጣል ጋብቻው ስለ መሥመሩ አስተያየታቸውን ሰጡ"
ከጫማ ጣዮቹ ቀጥሎ ደግሞ ፍየል ታርዶ «ለአንጀት አይታዎች» ቀርቦ ጋብቻውን በተመለከተ እነሱም አስተያየት እንዲሰጡ ተጠየቁ። እነሱም ተጋቢዎቹ ልጅ ስለ መውለድ አለመውለዳቸው
ሊታያቸው ባለመቻሉ ሦስት ፍየል ከታረደ በኋላ፣ «ጋብቻው ቀና ነው» በሚል ብቻ አድበስብሰው ተውት"
በእርግጥ፣ ይህ ጉዳይ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ያወያየ ሲሆን፣ በተለይም በሽማግሎቹ ዘንድ ጋብቻውን በመጠራጠር በቀጠሮ በተለያየ ጊዜያት ለመወያየት አስቻላቸው"
ካርለት አንጀት አይታዎች በሰጡት አስተያየት መደናገጧና መደነቋ አልቀረም" በሐመር ማኅበረሰብ መካን ሴት ፈላጊ እንደ ሌላት ታውቃለች" አንድ ሴት ለአባቷ ጥሎሽ ተከፍሎ ባሏ ዘንድ ከሄደች በኋላ ልጅ ሳትወልድ ብትቀር ባሏ እሷን መልሶ ታናሿን፣
ካለበለዚያም ቅርብ ዘመዷን ያገባል" ያም ሆኖ ካልተሳካለት፣ ልጅ
መውለድ ካልቻለች ላባቷ የከፈለውን ጥሎሽ ያስመልሳል ሴቷም፣
«መካን የሆነችው በውኃ ብልቷን ታጥባ ይሆናል» ተብላ ትጠረጠራለች» መካን ሴት የተገኘችበት ቤተሰብም እንደ መጥፎ
ቤተሰብ ስለሚቈጠር ጋብቻ የሚፈልገው ሁሉ ይሸሻል" ይህ ደግሞ አባት በልጆቹ ጥሎሽ ያገኘው የነበረውን ከብት፣ ፍየል፣ በግ፣ ማር
ያስቀርበታል" ከዚያም ተጨማሪ፣ ምናልባት አባትየው ሦስት ሴት
ልጆች ቢኖሩት የመጀመሪያ ልጁን ጥሎሽ ተቀብሎ ቢድርና መካን ብትሆን ሁለተኛዋን፣ ሁለተኛዋም መካን ከሆነች ሦስተኛዋን! |
ሦስተኛዋ መካን ከሆነች የዘመድ ልጅ...በመስጠት ሞክሮ ካልተቻለ ግን የተቀበለውን ጥሎሽ ይመልሳል"
«ስለዚህ አንደኛ ነገር እኔ በውኃ ስተጣጠብ ስለሚያዩ መካን ትሆናለች የሚል ግምት መጀመሪያውንም ነበራቸው" ሁለተኛ ደግሞ
አንጀት አይታዎችና ጫማ ጣይዎች ልጅ ልወልድ አለመቻሌን ለማኅበረሰቡ አስታውቀዋል። ሌላው ግን የኔው የራሴ ጉዳይ ነው
ለጥንቃቄ እንዳላረግዝ የሕክምና መከላከያ አለኝ" ስለዚህ ልወልድ
አለመቻሌን አውቀዋለሁ" እነሱም ባለመውለዴ እጅግ በጣም አምነዋል" ግንኮ እንዴት? የፍየል አንጀት ከኔ ጋር ምን አገናኘው ካርለት፣ ራሷ ለራሷ ሐሳቧን አካፍላ ራሷን ጠየቀች።
ካርለት በእውነቱ ከሆነ ጥሎሽ ከደልቲ ገልዲ ማግኘት አትሻም
ጥሎሽ አያስፈልግም ብትል ግን የሱ የግል ንብረትነቷ ማረጋገጫ አጣ ማለት ነው" ጋብቻው ከዚህ ሁሉ ቢቀርስ እንዳይባል ደግሞ እሷ ባህላዊ ግድቡን ጥሳ ጥናቷን ለማካሄድ፣ ደልቲ ደግሞ ባለጌዋን እንግዳ የራሱ አድርጎ በግርፋት ሥነ ሥርዓትንሊያስትምራት
ቈርጧል።
በግልና በተናጠል የላላና ሻንቆ ኗሪ ሲመክርና ለሽማግሎቹ
የመሰለውን አስተያየት ሲሰጥ ሰንብቶ በመጨረሻ ሽማግሎቹ በጥልቅ ከተመካከሩ በኋላ
«እንግዳዋ ምንም እንኳ በመልክና በቋንቋዋ ከእኛ ብትለይም የቦርጆ (የአምላካችን) ፍጡር ናት። እኛን ብላ፣ እኛን መርጣ መጣች እንጂ ማሌ፣ በና፣ ዳሳነች፣ ሙርሲ...ምድር ልትሄድ ይቻላት ነበር።
በእውነት ከሆነ ብልግናዋ የበዛ ነው" ይህ ደግሞ የሷ ስሕተት ሳይሆን፣ ያባቷ ስሕተት ነው» ብለው ጋብቻውን ለመቀበል ወሰኑ።
በመቀጠልም፣ «ይህች እንግዳ አባቷ በቅርብ ባለመኖሩ ደልቲ ገልዲ የሚከፍለውን ጥሎሽ የሚቀበል አባትና ጥሎሹን የሚወስን ሰው የላትም" ስለዚህ እሷ የፈለገችውን ሰው በአባትነት ትምረጥ።
ከእንግዲህ በኋሳ የምትለብሰው፣ ጠረኗ እንደ ሐመር ልጃገረዶች
እንዲሆንና እስከ አሁን የፈጸመችውን ስሕተት እሷም ራሷ ስለምታውቅ ለወደፊት የፍየል ቆዳ ለፍቶና ተሰፍቶ እንድትለብስ፣በጨሌና አንባር በማጌጥም ጸጕሯን አጠር አድርጋ አስቈርጣ ሹርባ እንድትሠራና በእግሯ እንድትሄድ» ብለው ተስማሙ"
«ባባቷ በባንኪ ሞሮ ደንብ መሠረትም ጥሩ ሴት ለመባል አባት ብላ ለምትመርጠው ወንድ ልጅ ወይም በዘመዱ ወንድ ልጅ የከብትጨዝላይ ወቅት በባራዛ አርጩሜ ዱላ ቻይ መሆኗን ለማስመስከር
ላትሸማቀቅ ፀንጋዞች (ባዕዳን) በሚባሉት ጐረምሶች እንድትገረፍና
ጀርባዋ ላይ የሚቀረው የግርፋት ምልክት ለሽማግሎችና ለአካባቢው ሰው እንዲታይ በግልጽ እንድትተወውና እንድታጌጥበት»
ተባብለው ተማመኑ።
ከሎ ሆራ የሽማግሎችን ሁኔታና አጠቃላይ ውሳኔያቸውን ለካርለት ሲነግራት ጥርሷ እስኪፋጭ ድረስ ተንቀጠቀጠች" መናገር †ሳናት" በእውነቱ ለተመለከታት የማንኛውንም ሰው አንጀት የምትበላ ሲሆን፣ በሌላ በኩልም ጋብቻ ለመፈጸም ማሰብ የግብዝነት ተግባር ነው ሊያሰኝ የሚችል ነበር።
ካርለት ከከሎ ተለይታ ሰቀላዋ ውስጥ ገብታ ምን እያደረገችና ወደፊትስ ምን ሊያጋጥማት እንደሚችል ስታስብ፣ እንባዋ
እየተንፎለፎለ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ከዚህ ቀደም የኖረችበት ዓለም
እውነት አሁን ባለችበት መሬት ላይ ሳይሆን ከሌላ ፈለክ (ፕላኔት) የመጣች እንግዳ ፍጡር የሆነች መሰላት" ሽማግሎቹ ካቀረቡላት ቅድመ ሁኔታና ባህላዊ የውጣ ውረድ ይልቅ በትንሿ የመርፌ
ቀዳዳ ሾልኮ ማለፍ እንደሚሻል ገመተች"
እሷ የምታውቀው ሕይወትና አሁን ያለችበት ዓለም የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል ተብሎ በርቀት ልዩነት ብቻ የሚለካ
ሳይሆን፣ ፈጽሞ ሊተያይ የማይችል ሆድና ጀርባ ሆነባት"
ግርፊያ.ቆዳ መልበስ…በባዶ እግር መሄድ ...አለመታጠብ ልት
ረዳው፣ልታምነው፣
ልትሰማማው የማትፈልገው ጉዳይ ነው።ስለሆነም ይህን ፈጽሚ ማለት፣ በሷ ላይ ትልቅ ችግር መፍጠር ብቻ ሳይሆን ይቅር የማይባል ግፍ እንደ መፈጸም ያክል ነው" አባባሉን እንኳን በተግባር በቃል ልትሰማው ከበዳት።
ታላቁ የሴቶች እንቅስቃሴ ለመላው አውሮፓ ሴቶች ያጎናጸፈው መብት ብናኙ እንኳን ወደማይገኝበት መጥታ መገኘቷ፣ ከመላ ሴቶች ጎን ተነጥላ ወደ ዘንዶ አፍ የመወርወር ያህል ሆኖ ተሰማት ስለዚህ ለምን ወደዚህ ጣጣ ራሷን እንደዶለች ማሰላሰል
ጀመረች ካርለት ፍዝዝ፣ ትክዝ እያለች ቀስ በቀስ አንገቷን ወደ ሰማይ በማስገግ ወደ አውሮፓ በሐሳብ ተጓዘች።
እናቷ ሚስስ አልፈርድ፣ ታናሽ እኅቷ ሴሻ አጠገቧ ቢኖሩላት ኖሮ ጭንቀቷን ገልጻላቸው ተያይዘው ያለቅሱ ነበር። ግን ምንስ ብላ ልትገልጽላቸው ነው?
«እኔ እራሴ እንኳ ሁኔታዎች ከቍጥጥሬ ውጭ ሆነውብኝ መላ ብዬ የፈጠርኩት እንጂ እነሱማ መጀመሪያውንስ እንዴት ሊረዱኝ ይችላሉ? እናቴና እኅቴ እንዳፈቅር ገፋፍተውኛል" ለታናሽ እኅቴም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ምን ዓይነት የደስታ ስሜት እንደሚፈጥር
የነገርኳት እኔ ነኝ” ጋብቻ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ከባድ ነገር መሆኑን እንደሆነ የእንግሊዝ አገር ወጣት በየትምህርት ቤቱ፣ በቲያትርና ሲኒማው የሚያውቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው።
«የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፍቅር ዋነኛው ቅመም ቢሆንም በራሱ ግን ፍቅር አይሆንም" ያልተፈለፈለ፣ እዶሮ እቅፍ ውስጥ ያለ እን
ቍላል እንደ ማለት ነው እንቍላሉ ነፍስ ሆኖ ከመፈጠሩ በፊት እን
ስቷ ዶሮና አውራው መገናኘት አለባቸው" የሰዎች ግንኙነት ደግሞ
ከዚህ በላይ ነው" በሐሳብ መጣጣምና መግባባት ያስፈልጋቸዋል"።

«የደልቲ ገልዲ ጥንካሬው ከግንኙነቱ ላይ ነው" እንደ እንግሊዝ አገር ወንዶች ሳይልፈሰፈስ በጥንካሬ ጀምሮ በጥንካሬ ይጨርሳል"ሆኖም ግን ያ ብቻውን ለእኔ በቂ አይደለም። ልዘረዝረው የማልፈልገው ሚሊዮን ፍላጎት ይቀርብኛል። የሕፃንነት ዘመኔ በመፈጸሙ
በአሻንጉሊት ልረካ የምችልበት ጊዜ አልፏል" ሦስት እግር የሌለው
በሬ በአንድ ጠንካራ እግር ብቻ መንቀሳቀስ አይችልም። ስለዚህ
እኔም ወደማላውቀው የሕይወት አዘቅት ውስጥ መግባት የለብኝም"
እስከምችለው ጥናቴን ለማከናወን እጥራለሁ" ከአቅሜ በላይ የሆነውን ደግሞ መተው እንጂ ከአቅሜ በላይ ወደሆነ ችግር ከተዘፈቅሁ፣ ከገባሁበት ተመልሼ መውጣት ይሳነኝና በዚያው
እቀራለሁ። ለእኔ ደግሞ ይህ የሞት ሞቴ ነው» ካርለት ድርጊቷን
አማረረች።
«አንድ አንትሮፖሎጂስት ጥናቱን ለማከናወን የባህል
ለውጦችን፣ ችግሮችን የመቋቋም ኃይል ሊኖረው ይገባል። ወደ ጥናቱ መስክ የተሰማራ ባለሙያ ከማንኛውም ነገር ሁሉ በላይ መወሰን የሚችል መሆን አለበት። የዘወትር እምነቱም «ሊሆን
የማይችል ነገር የለም» የሚለውን ከልብ መቀበል ነው። ከዚያ በኋላ
ልምዱንና ፍላጎቱን በማረቅ ሊያጠናው የፈለገውን መስሎ ሳይሆን፣
ሆኖ መኖርን የማወቅ ክህሎት ሊኖረው ይገባል።» ከአባቷና ከሌሎችም ምሑራን የሰማችውን አስታወሰች።
የአንድ አንትሮፖሎጂስት ጥናት ጠዋት ተጀምሮ ቀትር ላይ የሚጠናቀቅ ሳይሆን፣ የረጅም ጊዜ ልፋትን፣ ችግርን፣ ሥቃይን
የሚጠይቅ አቀበት ቁልቁለት የሚያስኬድ፣ በአዞ ጀርባ የሚያንከባልል በመርፌ ቀዳዳ የሚያሾልከ፣ አልፎም እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት የሚከፈልበት ሙያ ነው።
ጥናታቸውን ከግብ ለማድረስ ስንቶች የሕይወት መሥዋዕትነት የከፈሉለት፣ የእባብ አንገት እስከ መጨበጥ፣ ከጎሪላ ጋር እስከ መጎዳኘት፣ ጭው ባለ በረሃ እስከ መኖር፣ አካለ ስንኩል እስከ መሆን ድረስ
የበቁበት ሙያ ነው ካርለትም ሁለት መንገድ ቀርቦላታል። ጥናትን
ማካሄድ ወይንም መተው።
ጥናቷን ከተወች በሕይወቷ ሊመለስ የማይችል ሽንፈት በፍላጎቷ መቀበሏ ነው። ከዚህ በኋላ ስለ እነሱ
ማውራት እንጂ እሷ የተናቀች፣ የተዋረደች መሆኗ ነው ስለ እነሱ
እያወሩ ኖሮ ማለፍ ደግሞ ትልቁ የሞት ሞት መሆኑን ታምናለች።
ጥናቷን ለመቀጠል ካሰበች ደግሞ ለዓላማዋ ስኬታማነት የሚቀርቡላትን ጥያቄዎች መመለስ፣ ችግሮችንም መፍታት አለባት" የሐመርን ባህል ጥሳ ገብታ፣ ድብቁን፣ ሽሽጉን ሕይወት ገሐድ
ማውጣትና ሴቶች ከወንዶች፣ ማኅበረሰብ ከቤተሰብ ቀረቤታና የነሱን ሚና ሕሊናዋ በሚቀበለው እውነታ ለፀሐይ ለማብቃት ፆታዋ የፈጠረባትን ገደል ድልድይ ሠርታ መድረስ አለባት።
ለዚህ ችግር መፍትሔው ደግሞ ዓላማዋን ከግብ ለማድረስ ራሷን ለመሥዋዕትነት መሠዊያው ላይ ማጋደም መቻል አለባት
ይህም ብቻ ነው ሁለተኛው ዕድሏ"
«ይሆናል ያልተባሉት ነገሮች ሆነው የሰው ልጆትን እርካታ
አጐናጽፈዋል። እንደ «አይቻልም» በዚህ ዓለም ላይ የቀለለ የለም" እኔስ ይቻላልን አስቤ ለምን በአይቻልም እሳቤ ተሸናፊ
እሆናለሁ" እውነትስ ሰው ሊሆነውና ሊፈጽመው የማይችል ነገር ምን ሊኖር ይችላል? እኔ መበርታት ያለብኝ መሞከሩ ላይ ነው
በፍላጎቴ ወደ አድካሚው ውድድር ከገባሁ በአሸንፋለሁ መወዳደር ይጠበቅብኛል” የዘወትር እምነቴም ይኸው ነው"
ቆዳ ለመልበስ፣ በእግር ለመሄድ፣ ለመገረፍ ዝግጁ መሆን አለብኝ
ብላ፣ ከራሷ ጋር ቃል ኪዳን ገባች።
💫ይቀጥላል💫

👍28😁5🤔2👏1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
hቦትውድ ወደ ሼዲያክ
ኤዲ ዲኪን የበረራ ባልደረቦቹ ወደ ጀልባው ሲገቡ ሲያይ ሊፈጽመው
ያሰበው ክህደት በዓይነ ህሊናው ድቅን አለበት፡ መቼም ሊያደርግ ያሰበውን
ቢያውቁ ዓይንህን ላፈር እንደሚሉት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ነዳጁ ባዶ መሆኑን እያወቀ አይሮፕላኑ ባህር ውስጥ ገብቶ ሁሉም እንዲያልቅ ሊያደርግ እንደነበር ያወቁበት መሰለው፡፡
የነዳጅ መጠኑን መቆጣጠር የበረራ መሀንዲሱ ስራ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው በዚህ ምክንያት ቢያልቅ ተጠያቂ እሱ ነው፡፡
ሰሞኑን ያሳይ የነበረውን እንግዳ ባህሪ ቢያውቁ ምን ይላሉ? እነሱ በማያውቁት ነገር አዕምሮው ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ ትናንት ማታ ራት ላይ ቶም ሉተርን ሲያስፈራራው ነው ያመሸው፡፡ የወንዶች መፀዳጃ ቤት ውስጥ
መስኮት ሲሰበር እሱ
እዚያው ነበር፡፡ ስለዚህ ኤዲን ቢጠረጥሩ
አይፈረድባቸውም፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ቢታወቅ ወሬው በአንድ ጊዜ ነው
አይሮፕላኑ ውስጥ የሚዛመተው፡፡
የስራ ባልደረቦቹ በእሱ ላይ ከእንግዲህ እምነት ሊጥሉ እንደማይችሉ ማወቁ በራሱ የኮሶ መድኃኒት እንደመዋጥ ነው የሆነበት፡፡ ከሁሉም
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አቋመ ጽኑ መሆኑ ያኮራው ነበር፡ የሌሎችን ስህተት በቀላሉ ማለፍ ስለማይችል አንዳንዴ ሰዎች በግል ችግራቸው ምክንያት ግዴታቸውን መወጣት ሲያቅታቸው የሚሳደብበት ጊዜ አለ፡፡በይቅርታ ሊታለፍ አይችልም ይላቸዋል ስህተት ሲፈጽሙ ከተገኙ፡፡ አሁን ግን እሱ ራሱ የሚታመን ሰው አልሆነም፡፡
አሁን ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ የሚጨነቅበት ጊዜ አይደለም፡፡ ሚስቱን
ለማዳን የማይፈነቅለው ድንጋይ የማይምሰው ጉድጓድ የለም፡፡ ስለዚህ
ሚስጥሩን በሆዱ ይዞ ለብቻው ሊፈጽም ቆርጦ ተነስቷል፡ ስለሌሎች ስሜት
አሁን መጨነቅ የለበትም፡፡ ሆነም ቀረ ህይወታቸውን አንዴ አደጋ ላይ ጥሏል፡፡ ውጤቱም እንዳሰበው ሊሆን ነው፡ አቋመ ጽኑው መሀንዲሱ ዲኪን
ወደማይታመነው ዲኪን መቀየሩ ነው፡፡
በርካታ ተሳፋሪዎች ትንሽ እንቅልፍ ብናገኝ ብለው አይሮፕላኑ ውስጥ
ቀርተዋል፡ የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድና እስረኛው ፍራንክ ጎርዲኖም ከአይሮፕላኑ አልወረዱም፡፡ ቶም ሉተር ባለጸጉራም ጃኬቱን ለብሶና ቆቡን አናቱ ላይ ደፍቶ ጀልባው ላይ። ወጣ፡፡ ኤዲም ከኋላው መጣና ጠጋ ብሎ
‹‹የአየር መንገዱ ህንጻ ጋ ሂድና ስልኩ ያለበት ቦታ እወስድሃለሁ›› አለው፡
ቦትውድ ከእንጨት የተሰሩ ቤቶች የተገጠገጡባት ትንሽ ከተማ ስትሆን
የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በየሱቁ ብዙም የሚገዛ ነገር አላገኙም፡፡ መንደሪቱ
የስልክ አገልግሎት አላት፡፡ ኒውፋውንድ ላንድ አሁንም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ስለሆነች መኪኖች የሚሄዱት ግራቸውን ይዘው ነው፡፡
ተሳፋሪዎቹ ወደ ፓን አሜሪካ አየር መንገድ ህንጻ ሄዱ፡፡ ኤዲ ከቦትውድ ሰላሳ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ አየር ማረፊያ ላይ ካረፈ አይሮፕላን በሬዲዮ የተላከ የአየር ጠባይ መረጃ አነበበ፡፡ ከዚያም ለሚቀጥለው ጉዞ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ስሌት ሰራ፡
ሲሰራ አፉን ደም ደም አለው፡፡ ከዚህ በኋላ የበረራ መሀንዲስ አይሆንም።
ካፒቴኑ የኤዲን የነዳጅ ፍላጎት መጠን ስሌት አምኖ መቀበል ይኖርበታል፡፡ የሰራው ስራ እንዲታመንለት ስሌቱን ሁለት ጊዜ ቼክ አደረገና
‹‹ሌላ ሰው ቢያጣራው እወድ ነበር›› ብሎ ለካፒቴኑ ሰጠው።
‹‹ችግር የለውም›› አለ ካፒቴኑ ለነገሩ ትኩረት ባለመስጠት፡ ‹‹እስቲ
ተናፍሼ ልምጣ›› አለና ወጥቶ ሄደ፡ ኤዲም ካፒቴኑን ተከትሎ ወጣና ቶም ሉተርን ፓን አሜሪካን ህንጻ አጠገብ ሁለት እጁን ኪሱ ከቶ አገኘው፡፡ ‹‹ወደ ስልኩ እንሂድና ከጓደኞችህ
ጋር እንድትነጋገር አድርጌ ቶሎ ወደ ስራዬ እመለሳለሁ›› አለው፡ ሉተር
በመጀመሪያ ጎተት እያለ ነበር የሚሄደው፡፡ በኋላ ግን የትናንት ማታውን
ግብግብ አስታወሰና ቶሎ ቶሎ መራመድ ጀመረ፡፡ ኤዲን እንደገና ማናደዱ
ትርፉ ራስን መጉዳት መሆኑን ተረድቷል፡፡
በመንገዳቸው ላይ መርቪንና ናንሲን አገኙና የአንገት ሰላምታ
ሰጥተዋቸው አለፉ፡፡ ሁለቱም አንድ ላይ በመሆናቸው የተደሰቱ ይመስላሉ፡ሰዎች እሱና ካሮል አን አንድ ላይ ሲሆኑ እንደሚያስቀኑ ይነግሩት ነበር፡ እሷን ሲያስታውስ ብስጭቱ እንደገና ተቀሰቀሰበት፡፡
ስልክ ቤት ገቡና ሉተር የስልክ ቁጥሩን በብጣሽ ወረቀት ጽፎ ለስልከኛው ሰጠው:፡ ኤዲ የሚናገረውን እንዲሰማ አልፈለገም፡፡ ኦፕሬተሩ እስኪያገናኛቸው ድረስ የስልክ መደወያው ክፍል ውስጥ ገብተው ጠበቁ ማለዳ በመሆኑ ብዙ ስልክ ደዋይ የለም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍበት ቦታ ድረስ ይዘዋት እንዲመጡ ሉተር እንደሚነግራቸው ገምቷል።
ካሮል አንን በእጁ ካስገባ
በኋላ ደግሞ ሌላ ያሰበውን ነገር ለመስራት ነጻነት ያገኛል ነገር ግን ምን
ሊያደርግ ነው ያሰበው? ወዲያው ለፖሊስ ማሳወቅ? ሉተር ከጠረጠረ ድረስ ደግሞ ዝም ብሎ መጠበቅ የግድ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሬዲዮ መገናኛውን ከመስበር አይመለስም፡፡ የፖሊስ እርዳታ እስኪደርስ
ጎርዲኖና ሉተር ከአይሮፕላኑ ወጥተው በመኪና ያመልጡና አንዱ ጋ
ይሸጎጣሉ፡፡ ካናዳ ይግቡ አሜሪካ ማንም የሚያውቅ አይኖርም፡፡ ኤዲ
እንዳያመልጡ አስቀድሞ ለፖሊስ ቢነግር ደግሞ ከፖሊሶች ጋር ሲታኮሱ
የካሮል አን ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ኤዲ እንዲህ እንዲሆን
አይፈልግም::
ስልኩ ሲጮህ ሉተር አነሳና ‹‹እኔ ነኝ የዕቅድ ለውጥ መኖሩን ልነግራችሁ የደወልኩት፡፡ ሴትየዋን በጀልባ አይሮፕላኑ ድረስ ካላመጣችሁ የምትፈልጉትን አልፈጽምም ብሏል ሰውየው፡፡ እኔ በበኩሌ ያለውን አምኜ
ተቀብያለሁ፡ ስለዚህ ይዛችኋት እንድትመጡ›› አለና መልሳቸውን ጠበቀ፡፡
ከዚያም ‹‹ሊያናግሩህ ይፈልጋሉ›› አለው ኤዲን፡፡
ሉተር በመጀመሪያ ትዕዛዝ ሲሰጠው ልክ የወሮበሎቹ መሪ መስሎ ነበር የሚታየው፡፡ ካነጋገሩ ግን ካሮል አንን ወደ መገናኛቸው ቦታ እንዲያመጣለት
ለማዘዝ ስልጣን የሌለው ሆኖ ታየው፡፡
‹‹ሊያናግረኝ የሚፈልገው አለቃችሁ ነው?››
‹‹እኔ ነኝ አለቃ›› አለ ሉተር እየከበደው ‹‹ነገር ግን ግብረ አበሮች አሉኝ››
የሉተር ግብረ አበሮች ካሮል አንን ቦታው ድረስ ማምጣት እንደማይፈልጉ ይታወቃል፡፡ ከእነሱ ጋር መነጋገሩ የሚፈይድለት ነገር አለ? የለም፡፡ ካሮል አንን ስልኩጋ ያመጡና አስለቅሰው የመንፈስ ጽናቱን ይፈታተኑታል፡፡ ‹‹ስትፈልጉ ገደል ግቡ በላቸው›› አለ ጮክ ብሎ
እንዲሰሙት፡፡
ሉተር የኤዲ አነጋገር አስደንግጦት እነዚህን ሰዎች እንዲህ ልትናገራቸው አትችልም›› አለ እሱም ጮክ ብሎ፡፡
ሉተር የወሮበሎቹ መሪ ከሆነ ምን አስፈራው? አሁን የሉተርን ስልጣን መገምገም አይረባውም፡፡ ዕቅዱን ማሳካት ነው ያለበት፡፡ ሉተርም ‹‹ወይ አናግራቸዋለሁ ወይም አላናግራቸውም በል›› አለው ኤዲን፡፡
ላናግራቸው እንደማልፈልግ ንገራቸው ለእነዚህ ድንጋይ ራሶች አለው።
አይ አምላኬ አለና ሉተር የስልኩን እጀታ አንስቶ ‹‹አላናግራችሁም
ብሏል፡፡ ሰውየው አስቸጋሪ ነው:›› ንግግሩን ቆም አደረገና ‹‹ጥሩ ሃሳብ ነው እነግረዋለሁ››ብሎ የስልኩን እጀታ እንደያዘ
‹‹ሚስትህ ቀርባለች
ታናግራታለህ?›› አለው ኤዲን፡፡
ኤዲ ስልኩን ሊቀበል እጁን ዘረጋና መልሶ ተወው፡፡ ከእሷ ጋር ከተነጋገረ ምህረት ጠያቂ ሊሆን ነው ነገር ግን ድምጿን ቢሰማ አይጠላም እንደማያነጋግራት በራስ ንቅናቄ ለሉተር አመለከተው፡፡
ሉተር ኤዲ ላይ አፈጠጠና ‹‹አላናግርሽም ብሏል ባልሽ፡፡ ዞር በይ አንቺ
ሸርሙጣ!›› አላት ካሮል አንን፡፡

👍14❤1
ድንገት ኤዲ ተወረወረና ሉተርን ጉሮሮውን ሲያንቀው ስልኩ ከእጁ ላይ ወደቀ፡፡ ኤዲ የጉሮሮ ፍጥረቃውን እያጠበቀ ሲሄድ ሉተር ‹‹እባክህ ተወኝ›› ሲል ለመነ በሰለለ ድምጽ፡፡
ኤዲ ንዴቱ ጋብ እያለ ሲመጣ በእጁ ነፍስ ሊጠፋ መሆኑን ተገነዘበና
እጁን ትንሽ አላላ፡፡ ‹‹ትሰማኛለህ›› አለ ‹‹ባለቤቴን በአክብሮት ሚስስ ዲኪን በላት›› አለው የሉተርን ማንቁርት ሳይለቅ፡፡
‹‹እሺ እሺ›› አለ ሉተር ድምጹ እንደታፈነ ‹‹እባክህ ስለክርስቶስ ብለህ
ልቀቀኝ
ኤዲ ለቀቀው፡
ሉተር እያለከለከ ጉሮሮውን አሻሸና የስልኩን እጀታ አንስቶ ‹‹ቪንቺኒ ሰውየው
ሚስቱን በመሳደቤ ጉሮሮዬን አንቆ ሊገለኝ ምንም አልቀረውም::
ሊገለኝ ነበር ያልኩህን መቀበል አለብህ፡፡ እንግዲህ ፊልሙን ላሳይህ
አልችልም፡፡ ሰውየው ሰው ከመግደል ወደ ኋላ የሚል አይደለም፡ እኔ ከሱ
አንሼ አይደለም፡፡ እኔ ከእሱጋ ብደባደብ ሁሉም ነገር ይበላሻል፡ ሰዎች
ስንደባደብ ቢያዩ ምን ይላሉ?›› አለና የእነሱን መልስ በጸጥታ ጠበቀ፡ ትንሽ ቆይቶ ‹‹ጥሩ እነግረዋለሁ፡ ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰነው፡፡ ትንሽ ጠብቁኝ›› አለና ወደ ኤዲ ዞሮ ‹‹ጥያቄህን ተቀብለዋል፡ በጀልባ ይዘናት እንመጣለን ብለዋል›› አለው፡
ኤዲ ያዘዛቸውን ሊፈጽሙ በመስማማታቸው ያገኘውን የመንፈስ እርካታ ሉተር ከፊቱ እንዳያነብ ተጠነቀቀ፡
‹‹ሉተርም አንድ የሆነ ደባ እፈጽማለሁ ብትል ባለቤትህን በጥይት
እንደሚሏት እንዳትዘነጋ›› አለው ኤዲን፡፡
ኤዲም የስልኩን እጀታ ከሉተር ላይ መነጨቀና ‹‹ቪንቺኒ አዳምጥ!
አንደኛ የአይሮፕላኑ በር ከመከፈቱ በፊት ባለቤቴን በጀልባው ላይ መኖሯን
ማየት አለብኝ፡፡ ሁለተኛ ካንተ ጋር አይሮፕላኑ ድረስ መምጣት አለባት፡፡
ሶስተኛ አንድ ጉዳት ደርሶባት ባይ በባዶ እጄ ነው መጥቼ የምገድልህ
ያልኩህን በአዕምሮህ ያዝ›› አለና ሰውየው መልስ ሳይሰጠው ስልኩን ጆሮው
ላይ ዘጋበት፡፡
ሉተር ኤዲ ስልኩን ድንገት ስለዘጋው ተናደደ፡ ‹‹ለምንድነው ስልኩን
የዘጋኸው?›› አንስቶ ‹‹ሃሎ ሃሎ›› አለና ራሱን ነቅንቆ እጀታውን ቦታው መለሰው፡፡ በንዴትም በመደነቅም ኤዲ ላይ አፈጠጠበት፡፡ ‹‹አንገትህ ላይ እባብ እየጠመጠምክ ነው›› አለው ኤዲን፡፡
‹‹የስልኩን ወጪ ክፈል›› አለው ኤዲ፡፡
ሉተር እጁን ኪሱ ውስጥ ሰደደና በርካታ የተጠቀለለ ዶላር አውጥቶ ስማኝ›› አለ ‹‹ያንተ እንደዚህ መናደድ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡
የጠየቅኸውን አግኝተሃል፡፡ ያንተም የእኛም እቅድ እንዲሳካ ተጋግዘን መስራት አለብን ለሁለታችንም ሲባል፡፡ ለምንድነው የማንስማማው? ይህ
ጉዳይ አጋሮች አድርጎናል እኮ›› አለው፡፡
‹‹ተነፋ ድንጋይ ራስ›› አለና ኤዲ ወጥቶ ሄደ፡፡
መንገዱን ይዞ ሲሄድ ንዴት አልለቀቀውም፡፡ ሉተር አጋሮች ሆነናል ብሎ ያለው ሌላ ንዴት ቀሰቀሰበት፡፡ ኤዲ ሚስቱን ለማስለቀቅ ሲል ሴቶችን አስገድዶ የሚደፍረውን ጎርዲኖን ከህግ ወንጀለኛውንና
እንዲያመልጥ ሊያግዝ ነው፡፡ ይህን የሚያደርገው ሳይወድ በግድ ቢሆንም
ይህን ከፈጸመም በኋላ ራሱን ቀና አድርጎ መሄድ እንደማይችል አውቋል
መንገዱን ይዞ ሲሄድ አይሮፕላናቸው በወደቡ ላይ በኩራት ጉብ ብሎ
ይታያል፡ ኤዲ ከዚህ በኋላ አይሮፕላን ላይ ሊሰራ እንደማይችል ሲያውቀው
ተበሳጨ፡ ወደቡ ላይ ሁለት የጦር መርከቦችና ጥቂት የዓሳ ማጥመጃ ጀልባዎች ይታያሉ፡፡ አንድ የአሜሪካ ባህር ኃይል የጥበቃ ጀልባም ወደቡ ዳር ታስሮ ቆሟል፡፡ ኤዲ ይህ ጀልባ ለምን እዚህ መጣ?› አለ በሆዱ ምናልባትም በጦርነቱ ምክንያት ይሆናል የቆመው፡፡ የባህር ኃይል መርከብ ሲያይ የጥንቱን አስታወሰው፡፡
ኤዲ ፓን አሜሪካ አየር መንገድ ህንጻ ውስጥ ገባ፡፡ አንድ ምናልባትም ከባህር ኃይሉ ጀልባ የመጣ የመቶ አለቃ ዩኒፎርም የለበሰ ሰው ጀርባውን ሰጥቶ ቆሟል፡ ኤዲ ወደ ህንጻው ሲገባ ሰውየው ዞር አለ፡፡ ኤዲ በግርምትና በደስታ ሰውየውን ያየዋል፡፡ ዓይኑን ማመን አቅቶታል፡ ‹‹ስቲቭ!...... አንተ
ነህ?›› ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹እንዴት ነህ ኤዲ››
‹‹እንዴት እዚህ መጣህ?››
ሰውየው ኤዲ ከእንግሊዝ ጀምሮ ስልክ እየደወለ ሲፈልገው የነበረው ስቲቭ አፕልባይ ነው: ስቲቭ ማለት በክፉ ጊዜ አብሮት እንዲሆን የሚፈልገው አብሮ አደግ ጓደኛው ነው፡ እሱን በዓይነ ስጋ በማግኘቱ
አምላኩን አመሰገነ፡፡ ሁለቱ ሰዎች ተቃቅፈው ጀርባ ለጀርባ ተጠባጠቡ፡
ኤዲም ‹‹በአሁኑ ጊዜ ሃምፕሻየር አይደለህም እንዴ መሆን ያለብህ?
እንዴት እዚህ መጣህ?››
‹‹ስልኩን ያነሳችው ኔላ ችግር ላይ እንደወደቅህና ጭንቀት ላይ እንደሆንክ ነገረችኝ፡፡ ችግር ሲገጥምህ እንኳን ልትንበረከክ ትንሽም ፍርሃት እንደማይገባህ ነው የማውቅህ ጓደኛዬ፡፡ አንተ እኮ እንደ አለት ጠንካራ ነህ፡፡
አሁን ግን አንድ ከባድ ችግር እንደገጠመህ ሰውነቴ ነገረኝ›› አለ ስቲቭ፡
‹‹አዎ ከባድ ችግር ላይ ወድቄያለሁ…›› አለ ሳግ እየተናነቀው፡ ኤዲ
ሆደ ባሻነት ተሰማው፡ ለሃያ ሰዓት ያክል የደረሰበትን ችግር ለማንም ሳይተነፍስ በሆዱ ሲያብሰለስል ቆይቶ አሁን ሊፈነዳ ምንም አልቀረውም ታዲያ ባልንጀራው እሱን ለመታደግ የዓለምን ግማሽ አካሎ ስለደረሰለት ልቡ ተነካ፡ ‹‹ጓደኛዬ ችግር ላይ ወድቄያለሁ›› ብሎ ንግግሩን ሊጀምር ሲል
እምባው ቀደመው፡፡ ጉሮሮውም በሲቃ በመዘጋቱ መናገር አቃተው ከዚያም ወጥቶ ሲሄድ ስቲቭ ተከተለው ለመነጋገር
እንዲመቻቸው ሰው የማያያቸው ቦታ ሄዱ፡
‹‹እዚህ ለመምጣት ሰዎችን ምን ያህል ውለታ እንደጠየቅሁ እኔ ነኝ
የማውቀው፡፡ ስምንት ዓመት ሙሉ ባህር ኃይል ስሰራ ብዙ ሰዎች ውለታ
ጠይቀውኝ ውዬላቸዋለሁ፡ ዛሬ ግን ሁሉም የዋልኩላቸውን ውለታ በእጥፍ ስለመለሱልኝ አሁን የዋሉልኝ ውለታ ተጫነኝ፡፡ ስለዚህ ውለታዬን
ለማውረድ ሌላ ስምንት ዓመት ሳይፈጅብኝ አይቀርም›› አለ ስቲቭ
ኤዲ በመረዳት ራሱን ነቀነቀ፡፡ ስቲቭ የመደራደርና ተናግሮ የማሳመን
ተፈጥሯዊ ባህሪ አለው፡ የባህር ኃይሉ ዋና ችግር ፈቺ ሰው ነው፡ ኤዲ
ጓደኛው ላደረገለት ነገር አመሰግናለሁ ለማለት ቢፈልግም እንባው አልቆም
አለ፡፡
ስቲቭ የጓደኛውን እምባ ሲያይ ሆዱ ተንቦጫቦጨና ‹‹ምንድነው የገጠመህ ችግር?›› ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ካሮል አንን አግተውብኛል›› አለ ኤዲ እንደምንም፡፡
‹‹ማን ነው ያገታት?››
‹‹የፓትሪያርካ ወሮበላ ቡድን››
ስቲቭ ተገረመ ‹‹ሬ ፓትሪያርካ ማፊያው?››
‹‹አዎ እሱ ነው ያገታት››
‹‹ወይ አምላኬ! ለምን?››
‹‹አይሮፕላኑን አንድ ቦታ እንዳሳርፍላቸው ይፈልጋሉ››
‹‹ለምን?››
ኤዲ እንባውን በእጅጌው ጠረገና ራሱን ለማረጋጋት ሞከረ፡፡
‹‹ፍራንክ ጎርዲኖ የሚባል ወሮበላ እስረኛ ይዞ የሚሄድ በአይሮፕላኑ
ላይ የተሳፈረ የኤፍ.ቢ.አይ ሰው አለ፡፡ እንደገባኝ ፓትሪያርካ ጎርዲኖን
ለማስለቀቅ ይፈልጋል፡ የእኛ ተሳፋሪ የሆነ ቶም ሉተር የሚባል ሰው አይሮፕላኑን ሜይን ስቴት ጠረፍ ላይ ካናዳ አጠገብ እንዳሳርፍ አዞኛል አንድ ፈጣን ጀልባ ጠረፉ ላይ እንደሚጠብቅና ካሮል አንም ጀልባው ላይ
መኖር እንዳለባት ተስማምተናል፡፡››
ስቲቭ በመረዳት ራሱን ነቀነቀ፡፡ ‹‹ስለዚህ አንተን ለዚህ ስራ እንድትተባበራቸው ለማድረግ ያለው መንገድ ካሮል አንን ማፈን መሆኑን
ሉተር ገብቶታል›› አለ፡፡
‹‹አዎ››
‹‹እነዚህ ወንበዴዎች!›› አለ ስቲቭ ጥርሱን ነክሶ በንዴት፡
‹‹እነዚህን ሰዎች በህይወት እፈልጋቸዋለሁ፡ ባገኛቸው እሰቅላቸዋለሁ።
በውነት!›› አለ ኤዲ፡፡
ስቲቭ ራሱን ነቀነቀ ‹‹ግን ምን ለማድረግ አሰብክ?›› አለው፡

👍9🥰1
‹‹አላውቅም ለዚህ ነው ግራ ሲገባኝ ለአንተ የደወልኩት››
‹‹ለእነሱ የአደጋው ጊዜ አይሮፕላኑ ላይ ሲወጡ ጀምሮ መኪናቸው ጋ
እስኪገቡ ድረስ ነው፡፡ ምናልባትም ፖሊስ አድፍጦ አደጋ ሊጥልባቸው
ይችል ይሆናል›› አለ ስቲቭ፡፡
ኤዲ ጥርጣሬ ገባውና ‹‹ፖሊስ መኪናቸውን እንዴት ሊለይ ይችላል?
ምናልባትም መኪናቸው ባህሩ ዳርቻ ላይ ይጠብቅ ይሆናል›› አለ፡፡
‹‹እስቲ ማድረግ የምንችለውን ለማድረግ እንሞክር››
‹‹እኔ ለፖሊስ ማመልከቱን አልወደድኩትም›› አለ ኤዲ ‹‹በፖሊሶችና በወሮበሎቹ መካከል ተኩስ ቢከፈት ካሮል አን የጥይት ራት ትሆናለች፡››
ስቲቭ በመስማማት ራሱን ነቀነቀና ‹‹መኪናቸው ወይ በካናዳ ወይ በአሜሪካ በኩል ድንበሩ ላይ ሊቆም ስለሚችል ለካናዳ ፖሊስ መንገሩ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡ ፖሊስ ካወቀው ግን ባንድ ጊዜ ሚስጥሩ አፈትልኮ
ለወሮበሎቹ ሊደርስ ይችላል፡፡ ስለዚህ መንገር አያስፈልግም፡፡ ፖሊስ
መምሪያ ውስጥ ለማፍያ የሚሰራ ሰው አይጠፋም፡፡ ስለዚህ ያለን ብቸኛ አማራጭ የአሜሪካ ባህር ኃይል ወይም ጠረፍ ጠባቂ ኃይል ብቻ ነው›› አለ፡፡
ኤዲ ስለደረሰበት ዱብእዳ ለአንድ ሰው መንገር በመቻሉ ጭንቀቱ ቀሎታል፡፡ ‹‹እስቲ ስለባህር ኃይል እንነጋገር›› አለ፡፡
‹‹እሺ፡ ጎርዲኖና ሉተር ጀልባቸው ላይ እንዳሉ አጥቂ የጥበቃ ጀልባ
ባዘጋጅስ?›› አለ ስቲቭ፡፡
‹‹ይህ ሊሆን ይችላል›› አለ ኤዲ፡፡ ተስፋ አጫረበትና ‹‹ግን ጀልባውን ማግኘት ትችላለህ? የባህር ኃይል ጀልባዎችን ከእዛቸው ውጭ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ይቻላል?›› አለ፡፡
‹‹ማድረግ እችላለሁ፡ ጀልባዎቹ ሆነም ቀረ ልምምድ ላይ ናቸው
ያሉት፡ ምናልባት ናዚዎች ፖላንድን ከወረሩ በኋላ ወደ አሜሪካ ሊዞሩ ይችላሉ ተብሎ ይፈራል፡፡ ስለዚህ የምንሰራው ስራ አንዷን ጀልባ አቅጣጫ
አስቀይሮ ወደ ቦታው መውሰድ ነው፡፡ ይህን ማድረግ የሚችለው ሰው ደግሞ የሳይመን ግሪን ቦርን አባት ነው፡፡ ሳይመንን አስታወስከው?››
‹‹አዎ አስታውሰዋለሁ፡፡ አለ ኤዲ ቀልደኛውና ቢራ ገልባጩ ሳይመን ትዝ ብሎት፡፡ ሳይመን ምንጊዜም ችግር አያጣውም፡፡ ነገር ግን አባቱ የባህር ኃይል አዛዥ ስለሆነ ከችግር ያመልጣል፡
ስቲቭ ቀጠለና ‹‹ሳይመን አንድ ምሽት አንድ ቡና ቤት ላይ የጫረው እሳት የተወሰኑ ህንጻዎችን ያቃጥላል፡ ታሪኩን ለማሳጠር ከእስር እንዲወጣ ዋስ ስለሆንኩት አባቱ ከውለታ ቆጥሮ እስካሁን ያመሰግነኛል፡፡ ስለዚህ አሁን ውለታውን የሚመልስበት ጊዜ መጥቷል፡››
ኤዲ ስቲቭ የመጣበትን ጀልባ አየው፡፡ ጀልባው ሃያ ዓመት ያስቆጠረ
ባህር ጠላቂ መርከብ ማሳደጃ ነው፡፡ ጀልባው መድፍ ታጥቋል፡፡ በፈጣን
ጀልባ ላይ ያሉ ከተሜ ማፊያዎችን ለማስደንበር ይሄ ጀልባ ከበቂ በላይ
ነው፡፡ ጀልባው ግን ከሩቅ ስለሚታይ እነዚህ ማፊያዎች ሊጠረጥሩ ይችላሉ፡
‹‹ይሄ ጀልባ አደጋ ጠሪ ነው ስቲቭ፡፡ ስለዚህ የባህር ኃይል ጀልባ ካዩ ጎርዲኖን የማስጣሉን ስራ እርግፍ አድርገው ሊተዉት ይችላሉ›› አለ፡፡
ስቲቭ ሊከራከር
ቢፈልግም በሰው ቁስል
እንጨት ስደድበት
እንዳይሆንበት ፈርቶ መናገሩን ተወው፡፡ ‹‹አዎ እውነት ነው፡፡ አንድ ነገር
ሊፈጠር ይችላል፡፡ አንተ ነህ እንግዲህ እናርገው ወይም ይቅር ብለህ
መወሰን ያለብህ›› አለ፡፡
‹‹የፈራሁ እመስላለሁ ስቲቭ?››
‹‹አዎ መፍራትም ይገባሃል›› አለ ስቲቭ፡፡
ኤዲ ሰዓቱን አየና ‹‹ወደ አይሮፕላን መመለሻዬ ሰዓት ደረሰ›› አለ:
አሁን መወሰን አለበት፡ ስቲቭ አንድ ሃሳብ አቅርቦለታል፡ የመቀበል ወይም የመተው ውሳኔ የእሱ ነው፡፡ ስቲቭም አንድ ያላሰበው ነገር ትዝ አለውና፣ ‹‹እነዚህ ሰዎች ሃሳብህን
የተቀበሉ መስለው ሊሸውዱህ እንደሚችሉ ገምተሃል?›› አለው።
‹‹እንዴት?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡
‹‹እኔ እንጃ አንድ ጊዜ አይሮፕላን ላይ ከወጡ ከእነሱ ጋር መነታረክ
አይቻልም፡፡ ጎርዲኖንም ካሮል አንንም ሊወስዱ ይችላሉ›› አለ፡፡
‹‹ለምን እንዲህ ያደርጋሉ?››
‹‹አንተ ለፖሊስ እንዳትጠቁም››
‹‹ይሄም አለ ለካ›› አለ ኤዲ፡፡ ሌላም ምክንያት እንዳላቸው ተገነዘበ፡፡
እነዚህን ሰዎች በስልክ ሙልጭ አድርጎ ሰድቧቸዋል፡ አንድ ትምህርት ለእሱ ለመስጠት ሌላ ዕቅድ ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡
ኤዲ ምን እንደሚወስን ጨነቀው፡ ስቲቭ ባቀረበው ሃሳብ መሰረትም መፈጸም እንዳለበት አመነ፡፡ ሌላ ምርጫ የለም፡፡
‹‹እሺ አንተ እንዳልከው ይሁን›› አለው ኤዲ፡፡....

👍19
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ
ከሎ ሆራ ልቡን የሰረቀችውን የሐመር ውብ ለማግኘት ብዙ መድከሙ
አልቀረም።ካርለትም ብትሆን የሐሳቡን መናወጥ
ስላጤነችና ለጥናቷም እገዛ ይኖረዋል ከሚል እምነት በመነሣት ያችን ውብ ኮረዳ ማፈላለጉ ላይ አልሰነፈችም ሻንቆና ላላ መንደር
አለመኖሯን ግን ሁለቱም በየፊናቸው አረጋግጠዋል።
እንደ ተለመደው ከሎ ሆራና ካረለት በየመንደሩ በመዞር
ለማጠናከር ሲንቀሳቀሱ፣ ከዲመካ ከተማ ወደ አምስት ኪሎ ሜትር
እራቅ ብላ ከምትገኘው ኮረብታማ መንደር ወሮ ሄዱ"ከዚያ እንደ ደረሱ ወንዶች ወደ ወንዝ፣ ሴቶችም እርሻና ማሳ ጥበቃ ሄደው ስለነበር፣ መንደሯ ውስጥ ያገኙት የሚያላዝኑ ውሾችንና አሮጊቶች
ብቻ ነበር። መሸትሸት ሲል ግን ከብትና ኗሪው ከየውሎው ወደ
መንደሯ መጠረቃቀም ጀመረ።
ይህ ትዕይንት ለካርለት እንግዳ አልነበረምና ከመንደሯ ወጣ ብለው የአካባቢውን ውበት ሲቃኙ፣ ከሎ ደንገጥ ብሎ ዓይኑን ወደ አንድ አቀጣጫ ደገነ" አንዲት ልጃገረድ ስታርስበት የዋለችበትን ሞፈርና ቀንበር ከበሬዎች ጫንቃ ስታላቅቅ፣ ከበስተኋላ ተመለከቱ"።
እግርቿ ግጥም፣ ዳሌዎ ኮራ ከወገቧ ሰርጎድ ያለችውን ኮረዳ ሁለቱም ከበስተኋላዋ በማየት ብቻ ማንነቷን አወቁ" ልጅቷ በሬዎቹን
ፈትታ ዘወር ስትል፣ ሁለቱም ዓይናቸው እሷ ላይ ነው" ኮረዳዋ አንዳችም የመደነጋገር ሁኔታ ሳታሳይ ፈገግ ብላ በዚያ ኰራ ባለው አረማመዷ ወደነሱ ሄደች"።
ከሎ ምራቁን ቶሎ ቶሎ ከማንጐራጐጭ በስተቀር የሚመለከተው ልጅቷን ነው" ካርለት ደግሞ በተመስጦ የምትከታተለው እሱን ነው"
በልጅነቷ ወንድና ሴት ተቃቅፈው አልጋ ላይ ሲተኙ የሚያደርጉትን ለማወቅና ብዙ ጊዜ ለማየት ትጓጓ ነበር" ነፍስ ካወቀች
ጊዜ ጀምሮ የምትተኛው በግል መኝታ ቤቷ ሲሆን፣ አንድ ቀን ታዲያ የናቷ ጓደኛና ባሏ በእንግድነት እቤታቸው ይመጣሉ" እንዳጋጣሚ ሆኖ ለእንግዳ የተዘጋጀው የመኝታ ከፍል ተይዞ ስለነበር እንግዶች
ካርለት መኝታ ክፍል እንዲያድሩ ተደረጉ፣ እሷ ከወላጆቿ መኝታ ቤት ካለው ትንሽ ክፍል እንድትተኛ ይደረጋል" ካርለት ግን
እንቅልፍ ከመተኛት ይልቅ አንድ ለብዙ ጊዜ ለማወቅ ትጓጓ የነበረውን ሁኔታ ለመፈጸም አሰበች" እናም፣ የቆየ የልጅነት ፍላጎቷን ለማሟላት እንግዶች እሷ ከምትተኛበት ክፍል ገብተው ከመተኛታቸው በፊት አልጋው ሥር ገብታ ተደበቀች" ባልና ሚስቱ
በመጠጥ ኃይል ሞቅ ብሏቸው ነበርና እየተሣሣቁ ተደጋግፈው ገብተው አልጋ ላይ እንደ ወጡ ተያያዙ"
ካርለት የአልጋ ላይ ጨዋታቸውን ሁሉ ልቅም አድርጋ ሰማች"ከዚያ በኋላ ሰዎቹ ሲተኙ፣ ወላጅ እናቷ ካርለት ከተኛችበት ከፍል
ልታያት ስትገባ ድንግጥ አለች ቀስ አድርጋ እጇን ልጇ አልጋ ላይ ስትጭን ጨርቅ ብቻ ሆነባት በድንጋጤ ጮኸች። አባት፣ እንግዶች
ሳይቀሩ እየተሯሯጡ ሲመጡ የለችም ቤቱ ቢታሰስ፣ ብትፈለግ
በቀላሉ ልትገኝ አልቻለችም" በጨረሻ ግን አልጋ ስር እንደ ውሻ ተጠቅልላ ተገኘች" እና ዛሬም እንደ የዛኔው እንዲታወቅባት
ስላልፈለገች የኮረዳዋንና የከሎን ሁኔታ በጥንቃቄ መከታተል ቀጠለች።
ከሎና ካርለት ከልጅቱ ጋር ፊትና ኋላ ወደ መንደሩ እንደ ደረሱ፣ከልጅቷ መኖሪያ ቤት ትይዩ ድንኳን ለመትከል እንደ ፈለገች ለከሎ
ሆራ ሆነ ብላ አማከረችው «ኢህ» ብሎ ፈቃደኛነቱን ገለጸላት ለነገሩማ እንሂድ ብትለውስ መቼ በጄ ይል ነበር።
ከሎ፣ ስለ ብዙ ነገር እንዳላወጣ እንዳላወረደ አሁን የሚፈልገውና የሚያየው ውብ ልጅ ነው የሐመሯን ኮረዳ" አጠገቧ
ካለው ድንኳን ውስጥ ሆኖ እሩቅ ያለች ይመስል አለማት" ከሎ ሴት
አያውቅም ለማለት አይቻልም" በተለይ በገንዘብ የሚገኘውን የስሜት እርካታ በሚገባ ያውቀዋል" የሴት ጓደኛም ለመያዝ ብዙ
ሞካሮ ነበር" ግን፣ ከሙሉ ስሜቱ እንዲህ እንደ አሁኑ ነፍሱ ምንጥቅ እስክትል ወዶ አያውቅም"
ልጃገረዷ ደግሞ በሕይወቷ እንደ ወንድ ጓደኛ ግንኙነት
የጠገበችው የለም። ከሚጠይቋት ወንዶች ውስጥ ከመረጠቻቸው ጋር
ብቻ ተዝናንታለችI ዕድሜ ለሐመር ደንና ጫካ።
እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ልጃገረዷ ወላጆቿን በሥራ በመርዳት ስታገለግል ቆይታ ለምሽት ጭፈራው መሰናዳት ጀመረች"የጐረምሶችን ጩኸት እንደ ሰማች ከጓደኞቿ ጋር ለመደነስ ስትሄድ፣እነ ከሎ ተመለከቷት" አባቷ እንዳያገኛት ተጠንቅቃ አለፈች።
ልጃገረድ በኢቫንጋዲ (የምሽት ጭፈራ) መካፈሏን ባህሉ የሚፈቅድ ቢሆንም ወደ ጭፈራ ቦታ ስትሄድ ግን አባትየው ሳያይ
ሲሆን፣ ከጐረምሳ ጋር ስትዳራ ካገኘም አባት ተኵሶ ጐረምሳውን
እስከመግደል ድረስ መብት አለው" ይህ መብት እንጂ ያደርጋል ማለት ግን አይደለም። ስለዚህ፣ ለደንቡ ያህል ጭፈራውም ሆነ
ድሪያው አባት በማያየው መንግድ እንዲሆን ልጃገረዶች የራሳቸውን
ጥናቃቄ ይወስዳሉ"
በአጋጣሚ ግን እሷ ባህሉ ያደገችበት ሆነና ብትጠነቀቅም፣ አባቷ
ግን ከሌሎች የሐመር ወንዶች ለየት ያለ ነው።
በኢቫንጋዲ ጭፈራ ልጃገረዷ ኮከብ ደናሽ ስትሆን፣ የክልሉ ጎረምሶች
በፍቅር ሲያጫውቷትና ወደ ጫካ ሄድ መለስ ስትል ከሎን ግን ለዳንስ ሳትጋብዘው ቀረች። ወደ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የወንዶች ድምፅ ተሰማ። በመንገድ ላይ የሚያልፉ
ገበያተኞች እግረ መንገዳቸውን ለጭፈራ ሲመጡ የተለመደ ነበርና
ጨዋታው ቀጠለ። ካርለት አሁንም ክትትሏን እንደ ቀጠለች ነው" ጭፈራው ደመቀ፣ ውዝዋዚው ጦፈ፣ ከዚያ የመጨረሻው የዳንስ
ስልት ጊዜ እነ ካርለት የሚከታተሏት ኮረዳ ከአንድ መልከ መልካም ሸበላ ጋር መርፌና ክር ሆኑ ካርለት ያ ሰው ማን እንደሆነ ለመገመት ጊዜ አልፈጀባትም። መጀመሪያ እዳልነበረ እርግጠኛ ነች። ከገበያ ከተመለሱ መንገደኞች ጋር እንደ መጣ አወቀች" ደልቲና ኮረዳዋ
ወደ ጫካው ሲሠወሩ፣ ከሎና ካርለት ተፋጠጡ።
ውቢቷ ልጃገረድ ጎይቲ አንተነህ ትባላለች። በሐመርኛ ጎይቲ ማለት መንገድ ሲሆን፣ የስሟ ትርጓሜ ከመንገደኛ የተወለደች ለማለት ነው" ካርለትና ከሎ የሐመርኛ ቋንቋ አቀላጥፎ የሚናገ
ረውንና በአኗኗሩም ሆነ በአለባበሱ ሐመር የሆነው የጎይቲ ወላጅ አባት ጠዋት ከከብቶች በረት ሲመለስ፣ እንግዶች ከቤቱ ፊት ለፊት
ድንኳን ተክለው አየ አንተነህ (ጋልታምቤ) እንግዶቹን አንዳየ በጨዋ መልክ ሰላምታ ከሰጠ በኋላ፣ ጨዋታ ቢጤ ጀማመሩ።
የመጡበትን ጉዳይና ማንነታቸውን ከገለጸለት በኋላ፣ «ሸፈሮ ቡና
እንጠጣ» ብሎ፣ ወደ ቤቱ ይዟቸው ገባ።
ቡናውን ያፈላችውና የምትቀዳው ውቧ ልጃገረድ ጎይቲ አንተነህ ከአባቷ ፊት በጣም ጨዋና ረጋ ያለች ናት ካርለትና ከሎ በጣም
ጠባብ ወደ ሆነው የጎጆው በር በየተራ ገብተው ከተነጠፈው ቁርበት
ላይ እንደ ተቀመጡ፣ ጎይቲ በሾርቃ ሞልታ ሸፈሮ ቡናውን ለካርለት
አቀበለቻት ቀጥላ ለከሎ ስትሰጠው በአጋጣሚ እሷን እሷን እያየ ነበር እሷ ደግሞ ሾርቃውን የያዘ መስሏት ስትለቅለት ከመሬት
ወርዶ ተሰበረ። ሁለቱም በጣም ደነገጡ" ካርለት ድንገተኛ ሣቅ አፈናት፤ የልጃገረዷ አባትና ሌሎች ሁለቱ ሐመሮች ግን ጸጥ ብለው ሁኔታውን አረጋጉ።
ቡናው የውኃ ጥምን ስለሚከላከል ማንኛውም ሐመር በየመንደሩ
ቡና በእንስራ ተጥዶ፣ ሁለትና ከሁለት በላይ ሾርቃ ሳይጠጣ ከመንደሩ የሚርቅ የለም" አንተነህ ይመር ጎይቲ (ሴት ልጁ) ቡናውን
አጠጥታ ስትጨርስ፣ «ረሃብ፣ ችግር ከሐመር ምድር ይራቅ ከብቶች ይጥገቡ፤ ንቦች አበባ ይቅሰሙ፤ ሰማዩ ውኃ ያውረድ ፍቅር ሰላም ለሐመር ሕዝብ ቦርጆ ያውርድ አንቺም ተባረኪ የተባረh ባልና ትዳር ይስጥሽ፤ ሁላችሁም ተባረኩ» ብሎ ሸፈሮ ቡናውን ወደ አራቱም አቅጣጫና ወደ ጎይቲ፣ «ፕስስ...» አለና አማተበ።

👍17❤1
ጎይቲና ሌሎች እንግዶች ሲወጡ፣ ጋልታምቤና ሁለቱ እንግዶች ብቻ ቀሩ። ካርለትና ከሎ ይህ ሰው ለየት የሚል ሆኖ አግኝተውታል ስለዚህ፣ ሊጠይቁት የፈለጉት በመጀመሪያ ማንነቱንና ሕይወቱን በተመለከተ ነው። ሰውየውም እንዲያውም ከሚረካበት ትልቁ ነገር
ስላለፈው ሕይወቱ ማውራት ስለነበር፣ ጕሮሮውን ጠራርጎ ጨዋታውን ጀመረ። «ስሜ አንተነህ ይመር ይባላል። ትውልዴ መንዝ ነው። የመጣሁት ለአደን ነበር። አውሬ ገድሎ ጀግና
ለመባል...ሁሉም ቀረና ጓደኞቼ ሞቱ…በጦርነቱ ወቅት ከሐመሮች
ወግኜ ተዋጋሁ" የሐመሮችን ወንድምነት፣ ፍቅርና እምነት ወደድኩት። ከዚያ ወደ ትውልድ ቦታዬ መመለሱ ከበደኝ።
«ባህላዊ ደንቡን አሟልቼ ሐመር አገባሁ" ሴት ልጅም
ወለድሁ። እስካሁን በኑሮዬ ደስተኛ ነኝ» አላቸው። በረጅሙና አስገራሚ ታሪኩ ተደነቁ። እንዲያውም ካርለት፣ ስለ ሰውዬው ሁኔታ
በጥልቅ አሰበች፤ ሰውዬው በሐመሮች ኑሮ ደስተኛ ነኝ ብሏታል ስለዚህ፣ ምናልባት በሰውዬውና በሐመሮች ባህል መካከል የባህል
ልዩነት ሊኖር ይችላል። ልዩነቱ ግን እንደኔ የማይገናኝ ላይሆን ይችላል» በማለት አሰበች።
ሰውዬው ከሐመሮች ጋር ለመኖርና ለመጋባት የቻለበት የራሱ ምክንያት ቢኖረውም፣ አብሮ በመኖሩና ጋብቻ በመፍጠሩ ደስተኛ ሆኗል። እሷም ለዓላማዋ ስኬት ስትል አብራ መኖርና መጋባት
እንዳለባት ወስናለች ስለሆነም በዚህ ተመሳሳይነት አላቸው።
ሌላው ያጓጓት ነገር ግን በከሎና በልጃገረዷ መካከል ሊኖር የሚችለው ግንኙነት ነው። ከሎም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ከማንም በላይ መባዘኑ አልቀረም።ከሎ፣ የሚያስበው የተወሳሰበ የፍቅር ድራማ ነው ተዋናዮች ገና ተግባብተው መከወን ያልጀመሩት ካርለት ግን፣ ግንኙነቱ
የሚሳካበትን እያወጣች እያወረደች ሳለ፣ አንድ ቁለፍ ጥያቄ እንደሚቀር ተገንዝባለች።
በሐመር ባህል ደንብ መሠረት፣ አንድ ወንድ ከብት ከዘለለ፣.ጨርቆሴ ማዘ ከሆነ በኋላ ከሽያው (ሚዜው) ጋር ደም፣ ወተትና ማር እየተመገበ በየመንደሩ እጮኛ ፍለጋ ይዞራል።
በየመንደሩ የሚኖሩት ልጃገረዶች ደግሞ ከማይፈለግ ቤተሰብ
ጋብቻ እንዳይፈጠር በወንድሞቻቸው ስለሚጠበቁ፣ እጮኛ
ፈላጊዎች ውኃ ልትቀዳ፣ እንጨት ልትለቅም ወይምንም በሌላ ምክንያት ወደ ኋላ የቀረች ልጃገረድ ሮጠው ሄደው ይይዙና እጮኛ ፈላጊው ልጃገረዷ ፊት ለፊት ላይ «ተሪ» (ዲክዲክ) ቆዳ
የተተለተለ ጠፍር መሳይ ነገር ያጋድማል" ከዚያም ይዞት ከሚዞረው ኩርኩፋ (ከማሽላ የተሠራ) ያጐርሳታል" ይህን ካደረጉ በኋላ አጮኛ ፈላጊና ሚዜው፣ ወደ ጫካ ይፈተለካሉ" ልጅቷ ታለቅሳለች፣ ትጮሃለች ሁኔታውን የሰማ አባት፣ ወንድም፣ ዘመድ መሣሪያውን እየያዘ ለፍለጋ ይሰማራል። ከአንድና ከሁለት ቀን በኋላ ሽማግሌው ከወንድ ወገን ይመጣና አስፈቅዶ፣ ኮይታ (ጥሎሹን) በማስወሰን
ከፍያው ይጀመራል። አንድ ልጃገረድ የተሪ ቆዳ ፊት ለፊቷ መሬት ላይ ከተጋደመና ኩርኩፋ ከጐረሰች፣ ከዚያ ካጐረሳት ሰው ውጭ ሌላ አታገባም» ብለው ሽማግሎች ያጫወቷት ካርለትን ትዝ
ብሏታል"
ስለሆነም፣ አንተነህ ይመርን (ጋልታምቤን)፣ «ጎይቲ እጮኛ አላት ወይ?» ብላ ጠየቀችው። ከሎ ውስጥ ለውስጥ ይጨነቅበት
የነበረው ጥያቄ በመጠየቁ ደስ ብሎት መልሱን ከአንተነህ ለመስማት
ጓጓ" «መቼም ልጅቱ ንቁ ናት፤ በዚያ ላይ የእናቷ ዘመድ የሆኑት ጐረምሶች ሲጠብቋት ነበር» ሲል፣ ከሎ ፊቱ ወደ አመድነት
ተቀየረ ካርለት እንኳን ደልቲ ገልዲን ማታ ስትነጥቃት የነበረችውን ጎይቲን ከሎ እንዲያጣት ስለማትፈልግ እሷም የጭንቀት መልክ
ታየባት» አንተነህ ይመር ነገሩን በመቀጠል፣ «.እስካሁን እንግዲህ
ኩርኩፋ ያጐረሳት የለም" ይህ ግን መቼም የሚቀርላት አይደለም»ሲል፣ ከሎና ካርለት ሁለቱም እፎይታ ተሰማቸው"
ከሎ ሆራ፣ መሠረታዊው ጥያቆ ከተመለሰለት በኋላ፣ ስሜቱ መጋለብ ጀመረ «ጎይቲን ለማግኘት ሁለት መንገድ ይኖረዋል
አንደኛው በባህላዊ ደንቡ መሠረት፣ ካሊያም በአቋራጭ ከአባቷ
ተስማምቶ፣ ከባህላዊ ደንቡ ውጭ ጋብቻ መፈጸም ነው" ለእኔ ሁለተኛው ሐሳብ የተሻለ ይመስለኛል ሁለተኛውን አማራጭ
ለመከተል ግን አቶ አንተነህ ይመርን ማግባባት አለብኝ" ልጁ እንድትማርለትና እንድትሻሻልለት ስለሚፈልግ፣ ሁኔታው አመቺ ሊሆንልኝ ስለሚችል ብጠይቀውስ» ብሎ ከሎ አሰበ" መፍራቱ ግን
አልቀረም" ከሎ ከብዙ የሕሊና ጭንቀት በኋላ አንተነህን ሲጠይቅ
ያገኘው መልስ የጠበቀው አልሆነም።
«መወለድ ወሬ ነው ወሳኙ አብሮ ተቻችሎ መኖሩ ነው።»ሐመሮች ወንድሞቼ፣ እኅቶቼ ሆነው ተንከባክበው፣ ልዩነት ሳያደርጉ፣ ድረውና ኩለው፣ ሸልመው፣ ለትዳርና ለንብረት አብቅተውኛል" ተስፋ የቈረጥሁትንና በሞት ጥርስ የተያዝኩትን፣ ከሞት
አፍ ፈልቅቀው ተስፋዬን አድሰው ከዚህ አድርሰውኛል"
«እኔ አሁን ሐመር ነኝ" ባህሌና ቋንቋዩ ሐመር ነው" ስለዚህ ልጄን የምድራት በባህሌ ነው" በሐመር ባህል ደንብ ልታገባና
ለተሻለ ሕይወት ወደ ከተማ ይዘሃት ልትሄድ ትችላለህ" ይህ የእኔ ትብብር ይሆናል። የባህል ደንቡን ካላሟላህ ግን ቃሌንና ባህሌን
አልጥስም» አለ አንተነህ ይመር ኰስተር ብሎ። ከሎም ራሱን ቀብሮ
ሲያስብ ቆየና ውቢቱን ልጃገረድ የራሱ ለማድረግ የባህላዊ ደንቡን
ለመፈጸም መስማማቱን አስታወቀ ግን ከብት ዘሎ ቀሪውን ባህላዊ ደንብ እስኪፈጽም ጎይቲ ትጠብቀው ይሆን?
ከሎ ሆራ የአንተነህ ይመርን (ጋልታምቤን) ልጅ ለማግባት ሽማግሌ ከመላኩ በፊት አንድ ባህላዊ ደንብ መፈጸም ነበረበት"ይኸውም በልጅነቱ ወድቆ ጥርሱ በመውለቁ ሚንጊ (ገፊ) ተብሎ ተጥሉ ነበር" አሁን ግን ከሞት ተርፎ አድጎ ወደ ቤተሰቡና አካባቢው
በሥራ ምክንያት ተመልሷል" ያ ሐመር አይደለህም ተብሎ
የተጣለው ሕፃን ዛሬ ሐመር ነህ ለመባል ዝም ብሎ እንደ ከብት አይቀላቀልም
ለዚህም ከሎ ሽማግሎችን አማክሮ ከብት ታርዶ በደምና ፈርስ እንዲታጠብ ተደረገና ወደ ሐመር ማኅበረሰብ መቀላቀሉ ተበሠረ"
ከዚያ ቀጥሎ ትንሽ እራፊ ቆዳ በመልበስ «ኡhሊ» ሆኖ በየዘመዶቹ ለመዞር የወንድ ብልት መሳዩን አጭር ከእንጨት የተጠረበ «ቦኮ» ያዘ“ ከዚያም በሐመር ቆላማና ደጋማ አካባቢ በእግሩ መዞር ጀመረ" ኡከሊ ማለት በሐመርኛ አህያ ማለት ሲሆን፣ ኡክሊ የተባለው
ወጣት ለሴት ያልደረሰ ማለት እንደሆነ ይታመናል ከሎ ሆራ ቦኮውን ይዞ በየዘመዶቹ ሲዞር በመጀመሪያ «ዳውስ» ይላል ሠርጉ መድረሱን ለማብሠር" በሦስተኛው ቀን የሠርጉ (ከብት መዝለያው)
እንደተቃረበ ለመግለጽ። ቀጥሎ «ከርከሴ» ይላል" አሁንም ሠርጉ ቀን የቀረውን ጊዜ የሚያሳውቅ ቋጠሮ ለዘመዶቹ ይሰጣል" አምስት
ቋጠሮ አምስት ቀን፣ አራት ቋጠሮ አራት ቀን፣ አንድ ቋጠሮ አንድ ቀን ይሆንና ቀጠሮውን በቋጠሮ ያበሥራል" ዳውስ፣ ከርከሴ፣ የተቋጠረ ልጥ ይዞ ሲዞር የሚበላውንና የሚጠጣውን ዘመዶቹ
ያዘጋጁለታል። እናቱና ዘመዶቹም ከብት በሚዘልበት ቦታ (ራፂ) ለሚሰበሰበው ዘመድና የአገር ሰው፣ የሚጠጣ ቦርዴ፣ ምግብ አዘጋጁ" በዚህ በኩል ካርለት ወጪውን አሟላች ሚስቱ ገና ሳትታጭ፣ ሠርጉ ተደገሰ ማለት ነው።
ከብት ከሚዘልልበት ቦታ
(ራፂ) ዳስ ቢጤ ተዘጋጅቷል ሰፋፊ ቅጠልም እየተቈረጠ ከላዩ ተረብርቦበታልI እንደናሱ (እናት ሚዜው)፣ ሽያው (አንደኛ ሚዜው) ጋር፣ ስም የሚሠየምባት ትንሽ ጥጃ፣ ዘመዶቹና እንግዶች ተሰብስበዋል።
ልጃገረዶች ከብት ለሚዘለው ዘመዳቸው ለግርፊያ እየተዘጋጁ
ሲሆን «ፀንጋዞች» (ባዕዳን) የተባሉት ገራፊዎችም «ስሌንት» የተባለውን ቦታቸውን ይዘዋል።

👍23❤1👏1
ከልጃገረዱ መካከል በመልኳ ለየት ያለችውና በፍርሃት ሰውነቷ
እየተንቀጠቀጠ ያስቸገራት ሴት አለች። ሁሉም ልጃገረዶች አምናና
ታች አምና ለወንድ ዘመዶቻቸው ከብት ሲዘሉ ተገርፈው በግርፋት
ቻይነታቸው እንደሚወደሱት ሴቶች ለውደሳ ለመብቃት ስሌንት ወደ ተባለው ቦታ እየሄዱ ፀንጋዞች (ባዕዳን) የሚባሉትን በነገር
ይተነኳኲሳሉ፣ ግርፊያውን ለምን አትጀምሩም" ፈራችሁ እንዴ መግረፍ የማትችሉ ከሆነ፣ ልበ ሙሉ ለሆኑት ወንዶች ስጧቸው እያሉ ገራፊዎችን መጥተው እንዲገርፏቸው ያደፋፍራሉ
መልኳ ለየት ያለችው ልጃገረድ ግን የሚሉት ቢገባትም በምትሠራው ድርጊት ራሷን «አውቆ አበድ መሆን አለብኝ...»እያለች፣ አብራ ትመላለሳለች በባዶ እግሯ ላይ ታች ስትል፣ የቈሰለ እግሯ ሕመም በጣም እየተሰማት ነው ለልጃገረዶች እንደሚሰፋ
ሁሉ ዙሪያውን ዛጐልና ጨሌ ክፍከፍ ያለበት ጥቁር የፍየል ቆዳ ከወገቧ በታች ለብሳ፣ ከለበሰችው ቆዳ ውጭ ያለው ጭኗና ከወገቧ በላይ ራቁት የሆነው ሰውነቷ ለጋ ጥብስ መስሏል" አንገቷ ላይ ጨሌ
እጆቿ ላይ ደግሞ አምባር ደርድራለች" ጸጕሯ አጠር ብሎ ቅቤና የአሰሌ አፈር በስሱ ተቀብታ፣ በፀሖይ ሙቀት የሚቀልጠው
ጆሮግንዷ ላይ ሲወርድ ይታያል። በበዓሉ ቦታ ከተሰበሰቡት ሰዎች
ሁሉ በፍርሃትና በድንጋጤ የተዋጠችው ይችው ሰው ብቻ ነበረች የሚያሳዝነው ጭንቀቷ ብቻ ሳይሆን ከዚያ ሁሉ ሰው ውስጥ ጭንቀቷን ካለ አንድ ሰው በስተቀር የሚያውቅላት አለመኖሩ ነው ያ ሰውም የዕለቱ ከብት ዘላይ እሱ በመሆኑና ልምምዱም አጭር
በመሆኑ በራሱ ችግር እየተዋጠ ይዘነጋታል"
ይህች ለየት ያለች ሰው ትናንት በሥልጣኔ ሕዋ ውስጥ ከተሰቀሩት ምዕራባውያን አባል የነበረች በቅምጥልና በድሎት ያደገች፣
ተንከባካቢ ቤተሰቦቿ አሁንም ድረስ የሚሳሱላት ናት" ዓላማዋ ግን
የማታውቀውን እያስቦካት ነው።
ከጫማ ጫማ አማርጦ የሚጫማ እግር ለእንቅፋትና እሾሀ፣
ለጋሬጣና ለቃጠሎ ተጋልጦ ደም ያዣል" ከአገር አገር፣ ከፋሽን ፋሽን ተመርጦ ዘመናዊና ውድ ልብስ የሚሸፈነው ገላ በቀላሉ በእጅ በተውሰበሰበ የፍየል ቆዳ ሩቡ ተሸፍኖ ሦስት አራተኛውን ውርጭና
ሙቀት የደረቀ ባሕር ዛፍ ቅርፊት አስመስሎታል" ይህም ብቻ አይደለም፣ በለስሳ እጆች በጥንቃቄ የሚዳሰሰው ጀርባ ለግርፋት ተዘጋጅቷል ፤ የሐር ነዶ የመሰለው ጸጕር፣ በአፈርና ቅቤ ተለውሷል።
ይህች ለየት ያለችው ልዩ ፍጡር ካርለት አልፈርድ፣ እንግሊዛዊቷ ተመራማሪ ነበረች" እናት ሚዚው፣ ማዞች (በአለፈው ዓመት
የዘለሉት)፣ የሚጨፍረው ሕዝብ፣ ልጃገረዶች፣ ወደሚጕርፍበት
ሲሄድ ፀንጋዞች (ባዕዳን) የሚባሉት ገራፊዎች መግረፊያቸውን ባራዛ አርጩሜውን እየያዙ ተጠጉ አርጩሜው ረጃጅም ከመሆኑ አልፎ ከመሰበር ይልቅ ገላ ላይ እንዲጠመጠም ተቀብሮ የቆየውን ዘንጋዞች እያንዳንዳቸው በብዛት ይዘዋል" አንድ አርጩሜ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን፣ ገራፊው ተንጠራርቶ ሲገርፍ አርጩሜው ተጠቅልሎ ስምበር ከፊትና ጓላ ማውጣት አለበት
ካርለት ልጃገረዶች ግረፉን እያሉ ፀንጋዞችን እያናናቁ ሲፎክሩ፣ የሷ ሰውነት በላብ ራሰ የምትራመደው እየተንሻፈፈች ነው ቁሱሏን ሣር በነካው ቍጥር ስፍስፍ ትላለች፤ ጠዋት ብርዱ አሁን ደግሞ ልትገረፍ ነው። ጩሂ ጩሂ አሰኛት" ከዚህ ሁሉ የሚያድናት ሰው የለም" ስለዚህ፣ «አምላኬ የዛሬን ከመከራ አውጣኝ» ብላ ተማጸነች።
እንዲህ ስትብረከረክ ግርፋቱ ተጀመረ ከሎ ሆራ ለካርለት ከልቡ አዘነላት እሱም ጭንቀት ላይ ነበር" ሦስት ጥንድ በከብት ጀርባ ሳይወድቅ መሮጥ አለበት" ከወደቀ ለእሱም ለዘመዶቹም ውርደት ነው" ምልምል ራቁቱን ሆኖ እናት ሚዚው በልጥ መሳይ ነገር ሰውነቱ ላይ በሁለት ወገን አሰር አድርጎ፣ በእበት ሰውነቱን ቀባ ቀባ አደረገች እሱም እበት በመሃል እግሮቹ ነካ ነካ አድርጎ መሬት ላይ አሸት አሸት አደረገና ከአንደኛው ሚዜው በስተኋላ በመሆን
ከሚዘልባቸው ከብቶች መሃል ገባ።
ማዝ የተባሉት በከብቶች ዙሪያ በርከክ ብለው አማተቡና እየዘለሉ
የከብቶችን ጅራትና ቀንድ ይዘው በአንድ ረድፍ ደረደሯቸው።
ካርለት በባራዛ አርጩሜ ገና አንድ ጊዜ በፀንጋዛው ስትገረፍ፣ ነፍሷ ከሥጋዋ የተለየች መሰላት አርጩው ሥጋዋን ይዞ ሄዶ፣
ደም በጀርባዋና በጡቷ አካባቢ ፍጭጭ አለ" ወደ ላይ ዘለለች ከላይ ስትመለስ ደግሞ ሣሩ የእግሯን ቍስል ነካባት ቁጭ ስትል የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ሣቅ በሣቅ ሆነ" ነፍሷን ስታውቅ መላ
ስውነቷን ጠዘጠዛት በሁኔታዋ ሐፍረትም ተሰማት ምከንያቱንም
ሳታውቅ ከተቀመጠችበት ተነሣች፣ ግርፋቱ እየቀጠለ ሲሄድ ካርለት ራሷን ሳተች" ሰውነቷ ደም በደም ሆነ አብረዋት የተገረፉት
ልጃገረዶች እንደሷ ባይሆንም ደም በደም ሆነዋል" የሁሉም ሰምበሩ
ያስፈራል፤ የሷ ግን ልዩ ነው። ከግርፋቱ በኋሳ ራሷን ስታ ብትወድቅም ልብ ያላት አልነበረም፤ ሁሉም በዕላቱ ከብት ወደሚዘለልበት ቦታ ሄዱ" ከሎ ሆራ መንደርደር እንዲያስችለው ራቅ ብሎ አሁንም ምልምል ራቁቱን
ከአንደኛ ሚዜው በስተጀረባ ቆሟል። እናቱ፣ ወንድሙ፣ ዘመዶቹ ለምለም ቅጠል ቈርጠው ይዘው፣ «ይቅናህ፣ አይዞህ እያሉ መልካም ዕድል እንዲገጥመውና ክውርደት እንዲድኑ ይመኛሉ"።
ሁሉም ዝግጁ መሆኑን እናት ሚዜው ሲረዳና ምልከት ሲያሳየው
ከብት ዘላዩ ከአንደኛ ሚዜው ጀርባ ወጣ ብሎ ወደፊት ተንደረደረና ጋር
በምትባለው ትንሿ ጥጃ ላይ ዘሎ ወጥቶ በተደረደሩት ከብቶች
ጀርባ ሮጠ። መሃል አካባቢ ሚዛኑን ለመጠበቅ ቢንገዳገድም እንደምንም ብሎ መሬት አረፈ" እንደገና ዘሎ ወጥቶ አሁንም በከብቶች ጀርባ ሮጠ፤ ሦስት ጥንድ ሮጦ ሊጨርስ ሲል ከብት ዘላዩን እናት
ሚዜው ጠበቀውI ከሎ ዝላዩን ሊጨርስ እንደ ተቃረበ ወደ እናት
ሚዜው በአየር ላይ ሲዘል፣ እናት ሚዜው ከአየር ላይ ቀለበው ደንብ ነዋ!
ከሎ ሆራ ዝላዩን በሚገባ ሲፈጽም ዕልልታው፣ ደስታው! ፈንጠዝያውና ዘፈኑ ቀጠለ" ጸጥ ብሎ የነበረው አካባቢ በጩኸት
ድብልቅልቅ ሲል ካርለት ከነበረችበት ነቃች" ሰውነቷ በደም ተበከሏል። ከዚህም በተጨማሪ ሰውነቷን ማንከላወስ ተሳናት እንደ
ምንም ብላ ከተኛችበት ስትነሣ አንዲት ልጃገረድ ጀርባዋን ለጋ ቅቤ ቀባችላት ቀና ብላ ስታያት ጎይቲ አንተነህ ናት" ጎባኗ» ካርለት
ጎይቲን አመስግና እንደ ምንም እንድትደግፋት ነገረቻትና ለእህል ውኃ ወደ ዳሱ ከሚገባው ሰው ራቅ ብላ ዛፍ ስር ተኛች" ዝንቦቹም ትኵስ ደም ከቍስሏ ላይ በመምጠጥ ቁም ስቅሏን አሳይዋት“
በዚህ ወቅት hሎ ሆራ ካለምንም ልብስ ብልቱን እያማታ ወደ እሷ መጣ" ልትሥቅ ሞከረች «እንኳን ደስ አለህ!» ብላ እጇን
ልትዘረጋለት ብታስብም እጇን ማዘዝ ተሳናት። እሱም እንዳያት በሁኔታዋ ድንግጥ ብሎ አዘጋጅታ ያመጣችውን አልኮልና ጂቪ
እያቃሰተች ቁስሏን ጠራረገላትና ቀና ሲል ጎይቲ አንተነህ ኰራ ብላ ስታየው ተመለከታት” ዘወር ሲልም ደልቲ ገልዲን አየው። ጎንበስ ሲል የካርለትና የከሎ ሆራ ዓይኖች ተገናኙ"
ሁለቱም የተግባቡ ይመስላሉ" የሚፈልጉትን ለማግኘት አስፈላጊውን ሁሉ መፈጻም እንደሚያስፈልግ አንዱ ለሌላው መንገር
አላሻቸውም" ለዚህ ምሳሌዎች ናቸዋ!....

👍33
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሁለት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ማርጋሬት ከእንቅልፏ ስትነቃ ሃሳብ ውስጥ ገባች፡: ዛሬ ለአባቴ ቁርጡን እነግረዋለሁ አለች በሆዷ አሜሪካ ሲደርሱ ከእነሱ ጋር
እንደማትኖር ከቤት ወጥታ ቤት ተከራይታ እና ስራ ይዛ ልትኖር እንደሆነ
ትነግራቸዋለች፡፡ መቼም አባቷ ይህን ሲሰሙ ኮረንቲ ይጨብጣሉ፡፡
ማርጋሬት ነገሩን ባሰበችው ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማታል አባቷን ለመቃወም ስትነሳ የሚሰማት ይኸው ነው፡፡ አሁን አስራ ዘጠኝ ዓመቴ ነው፡፡ አሁን ልጅ አይደለሁም፡፡ ትናንት ከድንቅ ሰው ጋር ወሲብ
ፈጽሜያለሁ፡፡ ታዲያ ለምንድነው የምፈራው? ስትል ታስባለች፡
ለምን አባቷ ሁልጊዜ እንደ አውሬ በግርግም ውስጥ እንደሚዘጉባት አይገባትም፡ ኤልሳቤትንም እንዲሁ ነበር የሚያደርጓት፡፡ ፔርሱን ግን ለቀቅ አድርገውታል፡፡ ሴት ልጆቻቸውን እንደ ጌጣጌጥ ነው የሚቆጥሯቸው: አንድ
የሆነ ስራ እንስራ ብለው የተነሱ እንደሆን ቁጣቸው ለጉድ ነው፡፡ ለምሳሌ
ዋና እንዋኝ ወይም ብስክሌት እንንዳ ብለው ቢነሱ በቃ አለቀላቸው፡
ልብስ የፈለጉትን ያህል ቢያወጡ ምንም የማይሉትን ያህል መጽሐፍ
እንግዛ ቢሉ ጸጉራቸው ይቆማል፡
ማርጋሬት ይህን ባሰበች ቁጥር ሽንፈቷ አይደለም የሚያሳምማት፡፡አባቷ የእሷን ሀሳብ ውድቅ ለማድረግ የሚያወርዱባት የስድብ ውርጅብኝና
የፌዝ ጋጋታ እንጂ፡
ብዙ ጊዜ አባቷን ለማታለል ሞክራለች፡ የተሳካላት ግን ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
ሁልጊዜም ከአባቷ ትዕዛዝ ውጭ የምትፈጽመው በሌሎች እርዳታ
ነው:: ስለወሲብ ያስተማረቻት ዘመዷ ሞኒካ ናት፡፡ ፔርሲ ተኩስ አስተምሯታል፡፡ ሹፌራቸው መኪና መንዳት አስለምዷታል አሁን ደግሞ
ሄሪና ናንሲ ሌኔሃን ነጻነቷን እንድትቀዳጅ ይረዷት ይሆናል።
አሁን ለየት ያለ ስሜት እየተሰማት ነው፡፡ መኝታዋ ላይ ተጋድማ መላ አካላቷን ደባበሰችው፡፡ ከዚህ ቀደም ጸጉሯ የተንጨፈረረ ቅርጿ ደግሞ የማያምር አድርጋ ትገምት ነበር፡፡ አሁን ግን ገላዋን እየወደደችው
መጥታለች፡ ሄሪ ‹‹ቅርጽሽ ያምራል›› ብሏታል
አይሮፕላኑ ውስጥ የሰዎች ሹክሹክታና የዕቃ ኳኳታ ይሰማታል ተጓዦች ከመኝታቸው እየተነሱ ነው መጋረጃውን ገለጥ አድርጋ ስታይ ዱባው አስተናጋጅ ኒኪ የእናትና የአባቷን መኝታዎች ወደ መቀመጫነት እየቀየረ ነው፡፡ ሄሪ ሙሉ ልብሱን ለብሶ ቁጭ ብሎ በተመስጦ በመስኮት ወደ ውጭ ይመለከታል፡፡
እሱን ስታይ አፈረችና ሳያያት ወዲያው መጋረጃውን ዘጋችው::ከጥቂት ሰዓት በፊት በወሲብ ሲያብዱ ቢቆዩም አሁን ግን ሁኔታው
አሳፈራት።
ሌሎቹ ሰዎች የት ሄደው ይሆን?› ስትል አሰበች፡፡ ፔርሲና አባቷ ውጭ ወጥተው ይሆናል፡ አባቷ ለወትሮው በጧት ነው የሚነሱት፡ እናቷ
ግን በጧት መነሳት አይሆንላቸውም፡፡ ምናልባትም መታጠቢያ ቤት ይሆናሉ፡ ሚስተር መምበሪም በቦታው የለም፡፡
ማርጋሬት በመስኮት ስትመለከት ነግቷል፡፡ የሰማይ በራሪው አይሮፕላን
አንድ ትንሽ የወደብ ከተማ ዳርቻ ላይ ታስሮ ቆሟል፡ እንደገና መኝታዋ ላይ
ጋደም አለች፡፡ የለሊቱ ሁኔታ በዓይነ ህሊናዋ ድቅን አለ፡፡ የትናንቱ ቀን ድንግልናዋ የተወሰደበት ቀን አድርጋ ነው የቆጠረችው፡፡ ከኢያን ጋር ስትፈጽም የነበረው ወሲብ ችግር ያልተለየውና ጥድፍ ጥድፍ ያለ ነበር፡
ከእሱ ጋር ወሲብ ከፈጸመች በኋላ ሁልጊዜ በእፍረት ትሸማቀቃለች፡ትናንት ከሄሪ ጋር ያደረገችው ግን አስደስቷታል፡፡ እያንዳንዱ የስውነት ክፍሏ እየተቆጠረና እየተዳበሰ የተፈጸመ ወሲብ ነበር፡፡ ምንም እፍረት ያልነበረበት፡፡ እንደ ሴት ራሷን የቆጠረችበት ወቅት ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ወሲብ ከሄሪ ጋር በተደጋጋሚ መፈጸም አለብኝ አለች ለራሷ፡ የትናንት ማታው ትዝታ የወሲብ ፍላጎቷን ቀሰቀሰባትና ሰውነቷን አወራጨች።
ሄሪ የክት ልብሱን ለብሶ መስኮቱ ጋ ተቀምጦ በተመስጦ ሲያይ ሰርቃ
አየችው:፡ የሆነ ነገር እያሰላሰለ መሆኑን መልከ መልካም ፊቱ ነገራት::
ልትስመው ዳዳት፡፡ መጋረጃውን ገለጥ አደረገችና ‹‹እንደምን አደርክ ሄሪ አለችው፡፡
ድንገት የሰማው ድምጽ ሲሰርቅ እንደተያዘ ሰው አስደነገጠውና ደንብሮ
ዞር አለ፡፡ ሲያያት አየችውና ፈገግታ ተለዋወጡ፡፡ እንደ ጅል ለረጅም ጊዜ ሲሳሳቁ ቆዩ፡፡ በኋላም ማርጋሬት አይኗን ሰበረችና ተነሳች።
አስተናጋጁ የእናቷን መቀመጫ ከሚያዘጋጅበት ቀና ብሎ ‹‹ደህና አደርሽ እመቤት ማርጋሬት ቡና ላምጣልሽ?›› አላት፡
‹‹ኒኪ ይቅርብኝ አመሰግናለሁ›› አለችው ሁኔታ እንደ ጭራቅ ለራሷ
አስፈራት፡፡ ጸጉሯ ተንጨፍርሯል፡፡ ልብስም በቅጡ አልለበሰችም፡፡ ሄሪ ግን ጢሙን ተላጭቶና ዘንጦ አዲስ ሳንቲም መስሏል
ብትስመው በወደደች፡፡
ነጠላ ጫማዋን እግሯ ላይ ሰካች፤ ሌሊት ለወሲብ ስትቻኮል ሄሪ አልጋ
ስር እንዴት እንደተወችውና አባቷ ሳያይዋት እንዴት አድርጋ አንስታ አልጋው ውስጥ እንደከተተችው እየታወሳት፡፡
የሌሊት ልብሷን ስትለብስ እርቃኗን ስለነበረች ሄሪ ጡቶቿ ላይ ዓይኑን
ተከለ፡፡ ቢያያትም ምንም አልመሰላትም፡፡ ሄሪ ጡቷን ሲያይ ደስ አላት፡ የሌሊት ልብሷን መቀነት ጠበቅ አደረገችና ጸጉሯን አሻሸች፡፡
ኒክ ስራውን ጨረሰ፡፡ ሄሪን መሳም ስለፈለገች ኒኪ ከዚያ ቦታ ቶሎ እንዲ ሄድላት ፈለገች፡፡ ኒኪ ግን የልቧን ፍላጎት ስላላወቀ መቀመጫውን ላዘጋጅልሽ?›› አላት
እሺ›› አለች ውስጧ በንዴት እየጨሰ፡፡ ሄሪን ድጋሚ የምትስምበት ጊዜ እንደሰማይ ራቃት፡፡ የመታጠቢያ ዕቃዎቿን የያዘችበትን ቦርሳዋን
አነሳችና ሄሪ በሀዘኔታ እያያት ተነስታ ሄደች፡፡
ሌላው አስተናጋጅ ዴቪ መብል ክፍሉ ውስጥ ምግብ እየደረደረ ነው፡፡
እግረ መንገዷን አንድ የእንጆሪ ፍሬ ሰርቃ አፏ ላይ አደረገች፡ ስትሄድ
ብዙዎቹ መኝታዎች
ወደ መቀመጫነት ተለውጠዋል አንዳንዶቹ
ተሳፋሪዎች ቡና እየጠጡ ነው፡ ሚስተር መምበሪ ከሳይንቲስቱና ከባሮን
ጋቦን ጋር ወሬ ይዟል፡፡
መታጠቢያ ክፍሉ ውስጥ ስትገባ እናቷ መስታወት ፊት ቁጭ ብለው ይዋባሉ፡፡ እሳቸውን ስታይ እፍረት ተሰማት፡ ‹እናቴ ካለችበት አንድ ሁለት ርምጃ ርቀት ላይ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር አደርጋለሁ? አለች በሆዷ፡
ጉንጮቿ በእፍረት በርበሬ መስለዋል፡፡ ‹‹እንዴት አደርሽ እማማ›› አለች
‹‹ምን ሆነሽ ነው ፊትሽ እንደዚህ የቀላው? እንቅልፍ አልተኛሽም እንዴ?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡
‹‹ኧረ በደምብ ተኝቻለሁ›› አለች ማርጋሬት፡፡ ‹‹አንዲት ፍሬ እንጆሪ ከጠረጴዛ ላይ አንስቼ ስለበላሁ ነው›› አለችና መጸዳጃ ቤት ጥልቅ አለች ከዚያም መታጠቢያው ላይ ውሃ ሞላችና ፊቷን ታጠበች፡:
ትናንት የለበሰችውን ልብስ ዛሬም በመልበሷ ደስ አላላትም፡፡ የታጠበ
ልብስ ብትለውጥ በወደደች: አንገቷ ስርና ጡቶቿ ውስጥ ሽቶ
አርከፈከፈች፡፡ ሽቶ ለይቶ የሚያውቅ ያየችው ወንድ ሄሪን ብቻ ነው፡፡
ረጅም ጊዜ ፈጅታ ጸጉሯን አበጠረች፡፡ ያላት ውበቷ ጸጉሯ ስለሆነ ለጸጉሯ የማትሆነው የለም፡፡ መልኬን ለማሳመር ስል ማድረግ ያለብኝ ሁሉ
አደርጋለሁ አለች ለራሷ፡ እስካሁን ስለመልኳ ተጨንቃ አታውቅም፡፡ ዛሬ ግን አስተሳሰቧ ተለውጧል፡፡ ገላዬን ልቅም አድርጎ የሚያሳይና ረጅም ታኮ
ጫማ ያስፈልገኛል፡፡ ከገላዬና ከጸጉሬ ከለር ጋር የሚሄድ ልብስ መምረጥ
አለብኝ፡፡› አሁን የለበሰችው ልብስ እንደ ሽክላ ቀይ ነው፡፡ እንዲያው ዝም ብሎ የወረደና ቅርጸ ቢስ መሆኑን በመስታወት አይታ ትከሻውጋ ቀጥ ያለና
ወገቡ ጋ በመቀነት ሸብ የሚደረግ ቢሆን ጥሩ ነበር ስትል ተመኘች።ሜክአፕ ባትቀባባም ያላት መልክ በቂ ነው፡ ጥርሶቿም አያሳጡም፡፡
‹‹ከሚስተር ቫንዴርፖስት ጋር ለመጫወት ልትሄጂ ነው አይደለም?››
አሉ እናት፡፡

👍23❤1🥰1
‹‹አዎ እሱ ጋ ነው የምሄደው፡፡ ሌላማ ማን አለ፡፡ አንቺም እየተኳኳልሽ ነው።
‹‹እንደ ጀማሪ እጅሽን አትስጪ፡፡ ይህ ልጅ ይሁዳዊ ይመስላል፡፡››
አፏ አምልጧት ሄሪ አልተገረዘም› ልትል ብላ ከአፏ መለሰችው፡፡ ነገር
ግን ምንም ቃል ሳትተነፍስ ስቃ አሳለፈችው::
እናት ተናደዱና ‹‹ምንም የሚያስቅ ነገር የለም፡፡ ከዚህ አይሮፕላን ከወረድን በኋላ ከዚህ ልጅ ጋር እንዳላይሽ!›› አሏት
‹‹ከዚህ በኋላ ለእናንተ ግድ እንደሌለኝ እንድታውቂ እፈልጋለሁ›› አለች ማርጋሬት ‹‹እውነቴን ነው›› ወላጆቿን ጥላ ልትሄድ ስለሆነ ፈቀዱ አልፈቀዱ ለውጥ የለውም፡፡
እናት ጥርጣሬ ገባቸውና ‹‹እውነትሽን ነው?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡
‹‹ጨቋኞች ማንንም አያምኑም›› አለች ማርጋሬት፡፡ ይህን ካልኩ
ይበቃል ብላ ማርጋሬት ወደ በሩ ስታመራ ጠሯትና ቆም አለች
‹‹እባክሽ አትሂጂ፡ አንዴ አናግሪኝ የኔ ማር›› አሉ እናት ዓይናቸው እምባ እንዳረገዘ፡
ማርጋሬት ምን እንዳሰበች እናት ጠርጥረው ይሆናል፡፡ እናት የወደፊቱን መገመት እንደሚችሉ ታውቃለች፡
ማርጋሬት መልስ
አልሰጠችም።
‹‹ኤልሳቤት ጥላኝ ሄደች፤ አንቺንም እንዳላጣ እፈራለሁ››
‹‹አባባ ነው ጥላን እንድትሄድ ያደረገው›› አለችና ጧ ብላ አለቀሰች::
ኡኡ ለማለት ዳዳት ‹‹እንዲህ ሲሆን ለምንድነው ተው የማትይው?,,
‹‹ሳልሞክር የቀረሁ ይመስልሻል?››
ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ደነገጠች፡፡ እናት አንድም ቀን አባቷ ተሳስተዋል ሲሉ ሰምታ አታውቅም፡፡ ‹‹እሱ እንግዲህ ይህን ባህሪውን
ካልተወ ምንም ማድረግ አልችልም›› አለች ብስጭቷ ገንፍሎ፡፡
‹‹ምናለ ባታበሳጪው?›› አሉ እናት፡
‹‹ስለዚህ ሁልጊዜ የሚለውን ሁሉ ተቀባይ እያልሽኝ ነው?››
‹‹አዎ አግብተሽ እስክትወጪ ድረስ››
‹‹አንቺ እስከዛሬ ዝም ባትይው ኖሮ እንዲህ አይሆንም ነበር››
እናትም ራሳቸውን ነቀነቁና ‹‹ባሌ ስለሆነ ካንቺ ጋር አታካሮ ሲገጥም እኔ ላንቺ ማገዝ የለብኝም››
‹‹እሱ ግን የሚሰራው ሁሌ ትክክል አይደለም››
‹‹ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ባል ስታገቢ ነው ነገሩ የሚገባሽ››
‹‹በእውነት ይሄ ጥሩ አይደለም›› አለች ማርጋሬት፡
‹‹እንዲህ እንደሆነ እኮ አይቀጥልም፡፡ ትንሽ እንድትታገሺው ነው
የምለምንሽ፡፡ ሃያ አንድ አመት ከሞላሽ በኋላ ምንም ማድረግ አይችልም፡
ባል አገባሽም አላገባሽም የእሱ ባህሪ እንደሆን እንደማይለወጥ አውቃለሁ
እንደ ኤልሳቤት ብር ብለሽ እንድትሄጂ አልፈልግም፡››
እናት ከቤተሰቡ እንዳትለይ የሚፈልጉትን ያህል እሷም ተለይታ መሄዱ ደስ አይላትም:፡ ‹‹እኔም እኮ ይህን ፈልጌ አይደለም!›› አለችና ወደ እናቷ ስትጠጋ እናቷ እቅፍ አደረጓት፡፡
‹‹ ከአባትሽ ጋር ከዚህ በኋላ እንደማትጣዪ ቃል ግቢልኝ›› አሉ እናት፡
ማርጋሬት ለእናቷ ከልቧ ቃል መግባት ብትፈልግም ውስጧ ግን ‹‹ተይ ተይ›› ይላታል፡፡ ‹‹አባቴን ላለማበሳጨት እሞክራለሁ›› አለች፡፡
እናትም ‹‹እግዚአብሔር ይባርክሽ›› አሉ ከዚያም ማርጋሬት ወጥታ ሄደች፡፡
ሄሪ ወዳለበት ስትገባ ተነስቶ ተቀበላት፡፡ በጣም ከፍቷት ስለነበር
ዙሪያዋ ምን እንዳለ ሳትጨነቅ ጥምጥም አለችበት፡፡ እሱም የሰው ዓይን እየገረፈው እቅፍ አድርጎ ግንባሯን ሲስማት ትንሽ ቀለል አላት፡
አይኗን ከፈት ስታደርግ ሚስተር መምበሪ በአግራሞት ያያቸዋል
መምበሪ ማየቱ ግድ ባይሰጣትም ከሄሪ እቅፍ ውስጥ ወጣችና ተራርቀው
ተቀመጡ።
የወደፊት እንቅስቃሴያችንን በጥንቃቄ ማቀድ አለብን›› አለ ሄሪ፡
‹‹ብቻችንን ለመነጋገር ደግሞ ያለን ጊዜ ይህ ብቻ ነው››
‹‹ማርጋሬት ቤተሰቦቿ በማንኛውም ጊዜ ሊመጡ ስለሚችሉ እንደልባቸው መነጋገር የሚችሉት አሁን እንደሆነ ተገንዝባለች፡ አሜሪካ ሲደርሱ ሊለያዩ እንደሚችሉ ስታስበው ሰቀጠጣት፡፡
‹‹አሜሪካ እንዴት ነው የምንገናኘው? ቶሎ ንገረኝ›› አለች፡
‹‹እኔ ምን አውቄ፡፡ ያሰብኩት ነገር የለም፡፡ ግን ብዙ አትጨነቂ እኔ ፈልጌ አገኝሻለሁ፡ የት ሆቴል ነው አልጋ የምትይዙት?›› ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ኒውዮርክ ዋልዶርፍ አስቶሪያ ሆቴል ነው፡፡ ዛሬ ማታ ሆቴል ትደውልልኛለህ?››
‹‹ተረጋጊ እደውልልሻለሁ። ሚስተር ማርክ ነኝ እላለሁ ምልክት እንዲሆንሽ፡፡››
‹‹አንተስ የት ሆቴል ነው አልጋ የምትይዘው?››
‹‹እኔ ረከስ ያለ ሆቴል ነው የምይዘው››
አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላትና ‹‹ማታ ሹልክ ብለህ ወደኔ መኝታ ክፍል
ትመጣለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
ፈገግ አለና ‹‹ከምርሽ ነው? ታውቂኛለሽ እንደምመጣ››
በዚህ አባባሉ ደስ አላት፡ ‹‹እህቴ ብትኖር ኖሮ አብረን ነበር የምንተኛው:፡ አሁን ግን ብቻዬን ነኝ፡፡››
‹‹ወይኔ እንዴት ደስ ይላል! ምነው አሁን በሆነ!›› አላት፡፡
የባለጸጋ አኗኗር እንደሚወድ ታውቃለች፡፡ ‹‹አልቤርጓችን ቁጭ ብለን እንቁላል ጥብስና ሻምፓኝ እናዛለን›› አለችው::
‹‹ለዘላለም አንቺ ጋር መሆን ነው የምፈልገው››
ቤት ተከራይቼ መኖር እፈልጋለሁ›› ቤተሰቦቼ ኮኔክቲከት ውስጥ አያቴ ቤት ይሄዳሉ፡፡ እኔ ግን የራሴን
‹‹የሚከራይ ቤት እኔ እፈልግልሻለሁ፡ ከቀናን አንድ ፎቅ ላይ ቤት
‹‹በእውነት!›› አለች በደስታ ሲቃ፡ አንድ ህንጻ ላይ መኖር፡ እሷም ይህን ነበር ስታስብ የነበረው፡፡ ቢሆንም በአንድ በኩል ላግባሽ ብሎ
እንደሚጠይቃት ብታስብም በሌላ በኩል ደግሞ ዓይኗን ማየት አይፈልግ
ይሆናል ብላ ትገምታለች፡፡ ነገር ግን በችኮላ እዚህ ድምዳሜ ላይ ከመድረሷ
እንከራይ ይሆናል››
በፊት ከእሱ መራቅ አልፈለገችም፡፡
‹‹ሆኖም አንድ ያልተፈታ ችግር አለ፡ ናንሲ ሌኔሃን እቀጥርሻለሁ ስላለችኝ ቦስተን ሳልሄድ አልቀርም›› አለች፡፡
‹‹እኔም ቦስተን መምጣት እችላለሁ››
‹‹ትመጣለህ?!›› ስትል ጠየቀች ያለውን ማመን አቅቷት፡፡
‹‹ቦስተን የት ነው የሚገኘው?››
‹‹ኒው ኢንግላንድ፡ እንደ እንግሊዝ አገር ነው››
‹‹እዚያም ያሉ ሰዎች ሰው ይንቃሉ፡፡ ደማቸው ከእንግሊዝ የተቀዳ
ነው››
‹‹ስንት ክፍል ቤት ነው? ምን ዓይነት ቤት ነው የምንከራየው?›› ስትል
ጠየቀችው።
ሄሪ ፈገግ አለና ‹‹ካንድ ክፍል በላይ ሊኖረን አይችልም፡፡ የአንድ ክፍል
ቤት ኪራይ ለመክፈልም ብዙ ትግል ይጠይቃል፡፡ ኑሮ እንደ አገራችን ከሆነ
ረከስ ያለ የቤት ዕቃ እንገዛለን፡፡ ዕድለኛ ከሆንን ደግሞ የኤሌክትሪክ ወይም
የጋዝ ምድጃ ይኖረን ይሆናል፡፡ መጸዳጃ ቤት ግን የጋራ ነው የሚሆነው›
‹‹ኩሽናስ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
ራሱን ነቀነቀና ‹‹ኩሽና ያለው ቤት መከራየት አቅማችን የሚፈቅድ
አይመስለኝም፡››
ምናልባትም ራስን ችለው ሲወጡ ሊገጥም የሚችለውን ኑሮ ካሁኑ
እንድታውቅ እያለማመዳት ሳይሆን አይቀርም፡ እሷ ግን የሚነግራትን
በሙሉ ጥሩ ነው ብላ ተቀብላለች፡፡ በራስህ ቤት ውስጥ በምትፈልገው ጊዜ
የምትፈልገውን ምግብ እያዘጋጀህ መብላት፡ ተቆጪና ተቆጣጣሪ በሌለበት በነጻነት መኖርና የምትቆጣውና የሚያጉረመርም የቤት ሰራተኛ የሌለበት ኑሮ፡፡ ይህማ ጽድቅ ማለት ነው፡፡ ‹‹ግን የቤቱ ባለቤቶች እዚያው ህንጻ ላይ
ነው የሚኖሩት?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አንዳንድ ጊዜ አዎ፡፡ ህንጻው ውስጥ አብረው ቢኖሩ ጥሩ ነው፡፡
ሀንጻውን በደምብ ስለሚንከባከቡት በግል ህይወትሽ መግባታቸው ከፋ እንጂ ሌላ ቦታ የሚኖሩ ከሆነ ግን ህንጻው ቢፈራርስ፣ መስታወት ቢሰበር፣ ቧንቧ ቢፈነዳ፣ ቀለም ቢረግፍና ጣሪያው ቢያፈስ፣ ወዘተ ዞር ብሎ
የሚያየው ሰው የለም፡፡››

👍16
ማርጋሬት ገና ብዙ መማር ያለባት ነገር እንዳለ ተገነዘበች፡፡ ሄሪ ልትጠይቀው ስትል እውጭ ወጥተው የነበሩት ተሳፋሪዎች ተመልሰው መጡ፡፡ እናትም በዚሁ ጊዜ ከመታጠቢያ ቤት ተመለሱ፡ ፊታቸው ቢገረጣም ውበታቸው እንዳለ ነው፡፡ ማርጋሬት እናቷን ስታይ በደስታ ተሞልቶ የነበረው ልቧ ተነፈሰ፡፡ ይህም ከሄሪ ጋር ልትጠፋ ያሰበችው ነገር
የሚሰጣትን ደስታ ሳይበርዝባት አልቀረም፡፡
ጧት ጧት የምግብ ፍላጎት የላትም፡፡ ዛሬ ግን ጅብ አድርጓታል፡ እስቲ
‹‹ሞርቶዴላና እንቁላል አምጣልኝ በርከት አድርገህ›› አለችው አስተናጋጁን፡፡
ሄሪ ትኩር ብሎ ያያታል እንዲህ የራባት ከእሱ ጋር ሌሊቱን በሙሉ የአልጋ ጨዋታ ሲያደርጉ ስላደሩ ነው፡፡ ፈገግ ስትል እሱም ገባውና ቶሎ ፊቱን ዞር አደረገ፡፡
አይሮፕላኑ ትንሽ ቆይቶ ተነሳ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ መነሳቱ ቢሆንም
አሁንም በአይሮፕላን መብረር ደስታ ይሰጣታል፡፡ አሁን መፍራት ትታለች፡፡
ከሄሪ ጋር ያወራችውን ሁሉ መልሳ መላልሳ አሰላሰለችው ሄሪ ከእሷ
ጋር ቦስተን ሊሄድ ነው፡፡ መልከ መልካምና ፎልፏላ በመሆኑ ሴቶች በቀላሉ
ልባቸው የሚቀልጥለት ቢሆንም እሷን ግን ወዷታል፡፡ ምንም እንኳን
ከተዋወቁ ጥቂት ጊዜ ቢሆንም ደስ የሚል ፍቅር ጀምረዋል፡፡ እሱም ጉረኛ
ባለመሆኑ የማይፈጸም ቃል አይገባላትም፡፡ ከእሷ ጋር መሆን ግን ይፈልጋል፡፡
ከእሱ ያገኘችው ፍቅር ደግሞ ጥርጣሬዋን ፍቆላታል፡ እስካሁን ከሄሪ
ጋር የወደፊት ኑሮዋን ለማቆራኘት አስባ አታውቅም፡፡ አሁን ግን እሱን
ማመን ጀምራለች፡፡ የምትፈልገውን ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እርግጠኛ ሆናለች ነጻነትና ፍቅር፡፡
አይሮፕላኑ አየር ላይ ወጥቶ ቀጥ ብሎ መጓዝ ሲጀምር ለቁርስ የተዘጋጀላቸውን ቡፌ እንዲያነሱ ሲነገራቸው ማርጋሬት አግበስብሳ አነሳች፡ ሁሉም እንጆሪና ክሬም ሲያነሱ ፔርሲ ፈንድሻ አነሳ፡ አባት ሻምፓኝና እንጆሪ ሲያነሱ ማርጋሬት የዳቦ ቅቤና ዳቦ ጨምራ አነሳች፡፡ ማርጋሬት
ከመብል ክፍሉ ልትመለስ ስትል የቀረበላትን አጃ ያለ ምህረት ከምትውጠው
ናንሲ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ ናንሲ ሌላ ልብስ ለብሳ እንደ ምን
ጊዜውም አምሮባታል፡፡ ማርጋሬትን በጥቅሻ ጠራቻትና ድምጿን ዝቅ አድርጋ ‹‹ቦትውድ ላይ ህይወቴን ሊለውጥ የሚችል አንድ መልእክት ደርሶኛል፡፡ ዛሬ አሜሪካ ስገባ ድሉ የኔ ስለሚሆን ያልኩሽን ስራ እንዳገኘሽ ቁጠሪው፡››
ማርጋሬት ፊቷ በደስታ ፈካ፡፡ ‹‹አመሰግናለሁ ናንሲዬ›› አለች፡፡
ናንሲ የስልክ ቁጥሯ
የተፃፈበትን ካርድ በዳቦ ሳህኗ ላይ አስቀመጠችላትና ‹‹ለስራው ዝግጁ ስትሆኚ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውይልኝ›› አለች::
‹‹እደውላለሁ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ እደውላለሁ ደግሜ ደጋግሜ አመሰግናለሁ›› አለች፡፡
ማርጋሬት ወደ መቀመጫዋ የተመለሰችው በደስታ ባህር እየዋኘች
ነው፡፡ አባቷ ናንሲ የሰጠቻትን የስልክና የአድራሻ ካርድ ባያዩ ደስታዋ ነው፡:
ብዙ ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ ምግቡ ላይ ትኩረት ስላደረጉ ነው ያላዩት፡
አባቷ አንድ ቀን ከቤተሰቡ ተለይታ የምትሄድ መሆኑ ሊነገራቸው እንደሚገባ አምናለች፡፡ ከአባቷ ጋር ምንም ዓይነት ጠብ ውስጥ እንዳትገባ እናቷ ቢያስጠነቅቋትም፣ ዞሮ ዞሮ ለአባቷ ቁርጡ ይነገራቸዋል
ጊዜው ሲደርስ፡፡ ባለፈው ጊዜ ጠፍታ ነበር ባይሳካላትም፡፡ አሁን ግን ትታቸው እንደምትሄድ
በግልጽ ለመንገር ቆርጣለች
ይለይለት ብላ፡፡ በምስጢር
ማድረግ የለባትም ፖሊስም መጥራት የለባትም፡፡ የምትኖርበት ቤትና
የሚያስጠጓት ሰዎች እንዳገኘች ትነግራቸዋለች፡፡
አባቷን ደግሞ ሙግት ልትገጥማቸው የምትችልበት ዓይነተኛው ቦታ ይህ አይሮፕላን ብቻ ነው፡ ኤልሳቤትም የገጠመቻቸው ባቡር ላይ ነበር፡ ይህም ሰርቶላታል፡ ምክንያቱም አባት ባቡር ላይ ምንም ሊያደርጓት
ስለማይችሉ፡ አሜሪካ ከደረሱ በኋላ ሆቴል ውስጥ የፈለጉትን ማድረግ
ይችላሉ፡
መቼ ትንገራቸው፡፡ ቶሎ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡
ፔርሲ ብድግ አለና ‹‹ፈንዲሻ ልጨምር እስቲ›› አለ፡፡
‹‹ቁጭ በል›› አሉ አባት በቁጣ ‹‹ሞርቶዴላ እየመጣ ነው፡፡ ግብስብሱን
ሁላ አትብላ፡›› አባት ጥሎባቸው ፈንድሻ አይወዱም፡፡
‹‹እኔ አልጠገብኩም›› አለና ትዕዛዛቸውን ረግጦ ሄደ፡ ማርጋሬት የፔርሲ አድራጎት ገርሟታል፡
አባት በድንጋጤ አፋቸው ተሳሰረ፡፡
ፔርሲ ከዚህ በፊት አባቱን እንዲህ ፊት ለፊት ትዕዛዛቸውን አልቀበልም ብሎ አያውቅም፡፡
እናትም አይናቸው ፈጧል፡ ሁሉም ፔርሲ የአባቱን ትዕዛዝ እንዲፈጽም ነበር ፍላጎታቸው፡፡ እሱ ግን ሰሃን ሙሉ ፈንድሻ ይዞ ተመለስና
ቁጭ ብሎ መብላቱን ቀጠለ፡፡
‹‹ይሄን ፈንድሻ ተው አላልኩህም?›› አሉ አባት፡፡
‹‹በኔ ሆድ አያገባህም›› አላቸውና ፔርሲ መብላቱን ቀጠለ፡፡
አባት ተነስተው ፔርሲን ሊመቱ ሲሉ አስተናጋጁ ኒኪ ቋሊማ፣ ሞርቶዴላና ቅቅል እንቁላል ይዞ መጣና ፊታቸው አስቀመጠላቸው፡
ማርጋሬት ካሁን አሁን ሰሃኑን አንስተው ፔርሲ ላይ ወረወሩት ብላ ጠብቃ
ነበር፡ እሳቸው ርቧቸው ስለነበር ቢላና ሹካቸውን አነሱና ‹ሰናፍጭ
አምጣልኝ›› አሉት ኒኪን፡፡
‹‹ይቅርታ ሰናፍጭ አንይዝም ጌታዬ፡››
‹‹ሰናፍጭ የለም?›› ሲሉ አባት ጠየቁ ግስላ ሆነው ‹‹ታዲያ እንዴት አድርጌ ነው ያለ ሰናፍጭ የምበላው?››
ኒኪም ድንግጥ አለና ‹‹ይቅርታ ጌታዬ ከዚህ ቀደም ሰናፍጭ የሚጠይቅ
ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም:: በሚቀጥለው በረራ በእርግጠኛነት ሰናፍጭ
ይዘን እንቀርባለን›› አለ፡፡
እኔ የፈለኩት አሁን ነው፡፡ ሌላ ጊዜ አመጣለሁ ያልከው አሁን ምን
ሊረባኝ››
‹‹ ውነት ነው ይህን ማለት ለአሁኑ ምንም አይጠቅምም ይቅርታ
ጌታዬ፡››
አባት እያልጎመጎሙ ምግባቸውን በሹካ እየወጉ ይወቁት ጀመር
ንዴታቸውንም በኒኪ ላይ ስለተወጡ ፔርሲ ከቁጣ አምልጧል፡ አንድ ነገር
ከያዙ እንደማይለቁ ስለምታውቅ አባቷ በዝምታ ስላለፉት ማርጋሬት
ገርሟታል፡፡
ማርጋሬት፣ ኒኪ ያመጣላትን ሞርቶዴላና እንቁላል ጣፍጧት ስልቅጥ
አደረገችው: አባባ በስተመጨረሻ መለሳለስ ጀመረ እንዴ? እንዲህ
ያቀዘቀዛቸው በፖለቲካው መስክ ተሰሚነት በማጣታቸው፣ የጦርነቱ
መጀመር፣ ስደቱና የመጀመሪያ ልጃቸው ትዕዛዛቸውን ጥሳ መኮብለሏዐሳይሆን አይቀርም፡፡
ማርጋሬት የተብሰለሰለችበትን ነገር ለመናገር ከዚህ የተሻለ ጊዜ
እንደሌለ አወቀች፡፡
ቁርሷን አጣጥማ ጨረሰችና ሌሎች እስኪጨርሱ ጠበቀች፡ ከዚያም
ኒኪ የተበላባቸውን ሳህኖች እስኪያነሳና ቡና እስኪጠጣ ጠበቀች፡ የማታ ማታ በጭንቀት የወጠራት ጉዳይ የሚፈነዳበት ጊዜ መድረሱ አልቀረም ደረሰ፡
እናም አባቷ ከተቀመጡበት ትይዩ ተቀመጠችና ትንፋሿን በረጅሙ ለቃ
‹‹አባባ አንድ የማናግርህ ነገር ስላለኝ እንዳትቆጣኝ›› አለች፡፡
እናት ‹‹አሁን ተይ እባክሽ›› ሲሉ አጉረመረሙ:
‹‹ምንድነው አሁን?›› ሲሉ አባት ሚስታቸውን ጠየቁ፡፡
‹‹አስራ ዘጠኝ ዓመት ሞልቶኛል ነገር ግን የፈሰሰ ውሃ እንኳን አቅንቼ አላውቅም አሁን ስራ መስራት ይኖርብኛል›› አለች
ለምን የኔ ማር?›› እናት ጠየቁ፡፡
‹‹ብቻዬን መሆን ስለምፈልግ፡፡››
‹‹አንቺ የምትኖሪውን ኑሮ ታገኛላችሁ ቢባሉ ዓይናቸውን ጠንቁለው
ለማውጣት ፈቃደኛ የሚሆኑ በየፋብሪካውና በየቢሮው የሚሰሩ ስንትና ስንት ሴቶች አሉ መሰለሽ›› አሉ እናት፡፡
‹‹አውቃለሁ እማ›› አለች፡፡ እናቷ ከእሷ መከራከሩን የመረጡት ከአባቷ
ጋር አታካሮ እንዳትገጥም ብለው መሆኑን አውቃለች፡ ቢሆንም አባቷን
ግምባር ለግምባር መግጠሟ እንደሆን አይቀርም::
እናት ባንድ ጊዜ እጃቸውን መስጠታቸው ገርሟታል፡፡ ‹‹ከኛ ተለይተሽ መኖር የምትፈልጊ ከሆነ አያትሽ አብሮሽ የሚኖር ሰው ይፈልግልሻል››
አሉ፡

👍20😱1
‹‹ስራ አግኝቻለሁ እርዳታ አልፈልግም››
እናት ይህን ሲሰሙ ተገረሙ: ‹‹አሜሪካ ውስጥ? እንዴት››
ማርጋሬት ስለናንሲ ሌኔሃን ልትነግራቸው አትፈልግም:፡ ስራ የምትሰጣት ናንሲ መሆንዋን ካወቁ ከእሷ ጋር ተነጋግረው ሁሉንም ነገር
ያበላሹባታል፡ ‹‹ሁሉም ነገር አልቋል›› አለች በደፈናው፡፡
‹‹ምንድነው ያገኘሽው ስራ?›› እናት ጠየቁ፡፡
‹‹በጫማ ፋብሪካ ውስጥ የሽያጭ ረዳትነት››
‹‹ወይ አምላኬ! አበድሽ ይህን አይነት ስራ የምትሰሪው?››
ማርጋሬት በንዴት ከንፈሯን ነከሰች፡፡ ለምንድነው እናቷ ስራ እንዲህ የሚንቁት? ‹‹እኔ አላበድኩም እንደውም በዚህ አስተሳሰቤ እኮራለሁ›› አለች ማርጋሬት፡
‹‹ፋብሪካው የት ነው የሚገኘው?››
‹‹ፋብሪካ ውስጥ እንደሆነ አትሰሪም፤ በቃ!›› ሲሉ አባት ለመጀመሪያ
ጊዜ ተናገሩ፡
‹‹በሽያጭ ክፍል ውስጥ ነው የምሰራው፧ ፋብሪካ ውስጥ አይደለም፡፡
ደግሞም ቦስተን ውስጥ ስለሆነ ችግር የለም›› አለች ማርጋሬት፡
‹‹ያ ከሆነ ጥሩ ነው›› አሉ እናት፡ ‹‹የምትኖሪው ግን ስታንፎርድ ነው
እንጂ ቦስተን ውስጥ አይደለም››
‹‹አይሆንም እማ ቦስተን ነው የምኖረው፡፡ ትቼያችሁ ወደ ቦስተን ልሄድ መሆኑን እወቁት ነው የምለው፡፡ እዚያ ቤት ተከራይቼ ነው
የምኖረው››
‹‹ይሄ የማይሆን ነው›› አሉ እናት፡፡
ማርጋሬት በንዴት ተንጨረጨረች
አታጣጥዪ እማ›› አለች ከጣራ በላይ እየጮኸች፡፡ እሷ ስትጮህ እናቷ ስለደነገጡ ጸጸት ተሰማት፡ ‹‹በኔ ዕድሜ ወጣት ሴቶች የሚያደርጉትን ነው እኔ የማደርገው›› ስትል አከለች ቀስ ብላ።
አዎ በአንቺ ዕድሜ ያሉ ወጣቶች እንዲህ ነው የሚያደርጉት፡ እንዳንቺ ያሉ የጌታ ልጆች ግን አይሞክሩትም›› አሉ እናት፡፡
‹‹ታዲያ እኔ ከሌሎቹ በምን እለያለሁ?››
ብሳምንት አምስት ዶላር እየተከፈለሽ ለምትሰሪው ስራ አባትሽ መቶ
ዶላር የሚከፍልበት ምክንያት የለም››
‹‹አባባ ለቤት ኪራይ እንዲከፍልልኝ አልፈልግም››
‹‹ታዲያ የት ልትኖሪ ነው?››
‹‹ኪራይ ቤት ውስጥ አልኩሽ እኮ እማ››
‹‹የድሆች መኖሪያ ውስጥ! ግን ምን ታተርፊያለሽ?››
‹‹ወደ አገሬ መመለሻ ገንዘብ እስኪሞላልኝ ድረስ ገንዘብ አስቀምጣለሁ፡፡
ከዚያም ጦሩን እቀላቀላለሁ›› አለች ማርጋሬት፡
‹‹ስለምትናገሪው ምንም የምታውቂው ነገር የለም›› አሉ አባት፡፡
ማርጋሬት ንዴት ጠቅ አደረጋትና ‹‹ምንድነው የማላውቀው ነገር
አባባ?›› ስትል ጠየቀች:
እናት ጣልቃ ገቡና ‹‹አዎ የምታውቂው ነገር የለም›› አሉ፡
ማርጋት የእናቷን ንግግር አቋረጠችና ‹‹ቢሮ ውስጥ መላላክ፣ ቡና ማፍላትና ስልክ ማገናኘት አያቅተኝም፡፡ አንድ ክፍል ውስጥ እንደምኖር፣
መጸዳጃ ቤት ከሌሎች ጋር በጋራ እንደምጠቀም አውቃለሁ ደሃ መሆን
ባልፈልግም ነጻ ሆኜ መኖር ግን ያስደስተኛል›› አለች፡፡
‹‹ምንም የምታውቂው ነገር እኮ የለም›› አሉ አባት በንቀት ‹‹ነጻነት?
አንቺ? ከማጎሪያ እንደተለቀቀች ጥንቸል ነው የምትሆኚው ልጅት! ዕድሜሽን ሙሉ ተሞላቀሽ ስላደግሽ ብልሹ ልጅ ሆነሻል፡ ትምህርት እንኳን
አልተማርሽም›› አሉ፡፡ አባቷ በመጨረሻ የተናገሩት ነገር እንዴት ወደ ኋላ
እንዳስቀራት ስላስታወሳት በንዴት ‹‹እኔ መማር እፈልግ ነበር አንተ ነህ
ከትምህርቴ አስቀርተህ እንደዚህ መሀይም ያደርግኸኝ›› አለች፡፡
‹‹ልብስሽ እየታጠበልሽ፣ ምግብሽ እየተዘጋጀልሽ፣ የምትሄጅበት ቦታ
ሁሉ ሾፌር እያመላለሰሽ፣ ሌላው ቢቀር ከቤት እንዳትወጪ ሲባል የጎረቤት
ልጆች እየመጡ እያጫወቱሽ ነው ያደግሽው፡፡ ይሄ ሁሉ እንዴት እንደሚደረግልሽ እንኳን ሳታውቂ ነው ያደግሽው፡ አንድ ዳቦ ስንት
እንደሚያወጣ እንኳን ሳታውቂ ብቻዬን ልኖር ነው ትችያለሽ›› አሉ አባት
ምርር ብለው፡፡
‹‹ብቻዬን ስኖር ይህን ሁሉ በሂደት ማወቅ እችላለሁ››
‹‹ፓንትሽን እንኳን ማጠብ አትችይም፡፡ በአውቶብስ ተሳፍረሽ አታውቂም፡፡ አንድ ቤት ውስጥ ለብቻሽ ተኝተሽ አታውቂም፡፡ የመቀስቀሻ ሰዓት እንዴት እንደሚሞላ፣ ወጥመድ እንዴት እንደሚጠመድ፣ሰሃን
ማጠብ፣ እንቁላል መጥበስ አታውቂም››
‹‹ታዲያ ይሄ የማን ጥፋት ነው? ይሄን ሁሉ እንዳላውቅ ያደረግኸኝ አንት አይደለህም ወይ?›› አለች ማርጋሬት እያለቀሰች፡
አባት ፊታቸውን እንዳቀጨሙ ‹‹ቢሮ ውስጥስ ምን ልትጠቅሚ
ትችያለሽ? ሻይ ማፍላት እንኳን አታውቂ፤ ከጧቱ ሶስት ሰዓት እስከ አስር
ሰዓት ድረስ ቆመሽ መስራት አትችይ ይግረምሽና ሳምንት እንኳን
አትቆይም፧ ጥለሽው ትወጫለሽ፡፡››
ማርጋሬት ሲያስጨንቃት የነበረውን ነገር አባቷ ሲነግሯት ሆዷ በብስጭት ታመሰ፡፡ አባቷ ያሉት እውነት መሆኑን ስታስበው ፍርሃት
ፍርሃት አላት፡ ብቻዋን መኖር ሳያስጨንቃት አልቀረም: አንድ ስህተት
ሰርታ ወይም መስራት አቅቷት ከስራዋ ልትባረር ትችላለች፡፡ አባቷ በምሬት
የተናገሩት ነገር ወደፊት ሊሆን እንደሚችል ሳትገምት አልቀረችም:
የወደፊት ራዕይዋን የሚንድባት መሰላት፡፡
እምባዋን በጉንጮቿ
እየተንዥቀዥቀ አነባች፡:
አባቷ ጣታቸውን እያወዛወዙና ከጣራ በላይ እየጮሁ ‹‹ቦስተን ከተማ
እንደ ኦክሰንፎርድ መንደር እንዳይመስልሽ፡፡ እዚያ ብትነሺ ብትፈርጪ
የሚረዳሽ የለም፡ በዘረቢሶች ልትመረዢ ትቺያለሽ፡፡ ይሁዳውያን ቤት
በረንዳ አዳሪ ኔግሮዎች አስገድደው ይደፍሩሻል፡፡ ጦሩን እቀላቀላለሁ ላልሺው.›› ሲሉ አቋረጠቻቸውና፣
‹‹በሺህ የሚቆጠሩ እንደኔ ያሉ ወጣት ሴቶች ጦሩን ተቀላቅለዋል›› አለች ማርጋሬት እምባ በተናነቀው ድምጽ።
‹‹ታዲያ እነሱ አንዳንቺ ያሉ ሴቶች አይደሉም፡፡ እነሱ ጠንካራ ሴቶች ናቸው፡፡ እነሱ በጧት ተነስተው የጉልበት ስራ መስራት የሚችሉ ናቸው እንጂ እንዳንቺ ተሞላቀው ያደጉ ልፍስፍሶች አይደሉም፡፡ እግዜር አያድርገውና አንድ ችግር ቢደርስብሽ ዋጋ የለሽም›› አሉ አባት፡
ማርጋሬት ባለፈው ከቤት ጠፍታ የሄደች ጊዜ እንዴት እግሯ እንደተሳሰረ፣ ምን ያህል እንደፈራችና አቅመቢስ እንደነበረች ስታስታውስ በእፍረት ትሸማቀቃለች፡፡ በአንድ በኩል አባቷ እውነታቸውን ነው፡፡
አባቷ ጣታቸውን ወደ እሷ እየቀሰሩ ዓይናቸው ተጎልጉሎ የወጣ
እስኪመስል ድረስ አፍጥጠው ‹‹በቢሮ ስራውም ሆነ በጦሩ ውስጥ ሳምንት እንኳን ከቆየሽ ከምላሴ ጠጉር ይነቀል፤ ልፍስፍስ ነሽ›› አሉና በተናገሩት
ረክተው ቁጭ አሉ፡
ከዚያም ሄሪ ከየት መጣ ሳይባል ‹‹ይበቃል!›› ሲል ተሰማ፡ ይሄ የእሷና
የአባቷ ጉዳይ ቢሆንም ፍቅረኛው ስትሰደብ አላስችለው ብሎ ከጎኗ ሊቆም ደረሰላት፡፡ ሄሪ አጠገቧ መጥቶ ቁጭ አለና መሃረቡን አውጥቶ በእምባ
የረጠቡ ጉንጮቿን አበሰላት፡
አባትም ‹‹አንተ ወጠጤ · ›› ብለው ለመናገር ያሰቡትን ተናግረው ሳይጨርሱ ሄሪ ከመቀመጫው ተነሳና ‹‹እኔ ሴት ወይም ልጅ አይደለሁም፧ ከዚህ በኋላ ቢሰድቡኝ በቡጢ ነው የማንገጫግጮት›› አላቸው፡
አባት በዚህ ጊዜ አደብ ገዙ፡:
ሄሪ ተመልሶ ማርጋሬት ጎን ቁጭ አለ፡፡
ማርጋሬት ብትደናደድም በሆዷ ድል እንዳደረገች ይሰማታል፡፡ ትታቸው
እንደምትሄድ ነግራቸዋለች፡ ምንም እንኳን ቢቆጧትም፣ ቢያፌዙባትም፣
ቢያስለቅሷትም ከአቋሟ ንቅንቅ አላደረጓትም፡፡ ለመሄድ ቆርጣለች፡፡

👍15
ይህም ሆኖ ጥርጣሬ ውስጥ ሳይከቷት አልቀረም፡፡ ምናልባትም
በመጨረሻው ሰዓት ላይ ያሰበችውን እንዳታደርግ ሽባ ሊያደርጋት የሚችል
ሽብር ሳይለቁባት አልቀረም፡፡ ለረጅም ሰዓት ያወረዱባት የስድብ ውርጅብኝና ፌዝ በራሷ መቆም እንደማትችል አድርጋ እንድትገምት አድርጓታል፡በህይወቷ በድፍረት ያደረገችው አንድም ነገር የለም፡ ታዲያ አሁን ታደርገው ይሆን? አዎ አደርገዋለሁ አለች በሆዷ እኔ ልፍስፍስ አይደለሁም፧ አለመሆኔንም በተግባር አሳያለሁ፡፡›
አባቷ ተስፋ ለማስቆረጥ ብዙ ቢጥሩም አልተሳካላቸውም፡ ነገር ግን
ጉዳዩን እንዳልተዉት እርግጥ ሆኗል፡ ወደ ሄሪ ፊቷን አዞረች፡፡ በአባቷ ፊት
ላይ የበቀል ስሜት ይነበባል፡፡ ኤልሳቤት ትዕዛዛቸውን ጥሳ ጥላቸው
ስለሄደች ልጅነቷን ክደዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ቤተሰብ አለኝ ብላ መመለስ አትችልም፡
ለማርጋሬትስ ምን አስበውላታል?

ምዕራፍ ሰላሳ ሰባት (37) «ማሪዮን» አለ። አየችው ፤ አቤት እንደማለት ። «ማሪዮን ያለፈው ኣልፏል ። ላሁኑ ሁለቱ የሚገናኙበትን መንገድ ቀይሺ ። የሚቻልሽን ሞክሪ ። ከዚያ በኋላ የሁለቱ ጉዳይ ነው። አንቺ ምንም ማድረግ አትችይም ። እኔና አንቺ ብዙ እድሜ አልትረፈንም ። ያችኮ ያለችዋን የተቻለንን ያህል እንድንደሰትባት እፈልጋለሁ እንጋባ ። አንድ ላይ እንኑር ፤ በሰላም ። እኔም እስከ ዛሬ የናፈቅሁት ፣ አንቺም ሠራሁት በምትይው ሀጢአት እስከ ዛሬ የተቀጣሽው በቂ ነው ። እኛም'ኮ በደስታ የመኖር ድርሻ አለን» አለ ጆርጅ ። ‹‹ድርሻው ይሁን ፣ ግን እኔ የመደሰት መብት ያለኝ ይመሰልሀል ጆርጅ ?» አለች ማሪዮን ቅዝዝ ብላ ፤ ከልቧ። ይህን ስትል ቅዝዝ እንዳለች ቁልቁል ሲያያት ገና ለግላጋ ወጣት ሆና ታየችው ፤ ለጆርጅ ኮሎዌ ። «በደንብ ነዋ |» አላት «የመኖር መብትሽን ማን ሊነሳሽ ፍቅሬ ?» ከዚያም ፀፀቷን ሁሉ እንድትረሳ ፤ ሀጢአት የምትለው ነገር ከንቱ ሀሳብ መሆኑንና ለወደፊቱ የሚቻለውን ካደረገች በኋላ ደስታቸውን እየተላበሱ በሰላም መኖር እንዳለባቸው ደግሞ ነገራት። ቀጥሎም… «ላሁኑ ግን ማረፍ አለብሽ ለጥ በቃ ። ለእንደዚህ ያለው በሽታ መድሐኒቱ እረፍት ነው። እሺ ?» አለ ወደ ላይ እያየችው ፍንድቅ ብላ ሳቀችና «ጆርጅ ኮሎዌ እወድሀለሁ» አለችው፡፡ «መውደድሽ ደግ ሆነ ። ምክንያቱም ወደድሽም ጠላሽ አንችኑ ማግባቴ አይቀርም ነበር ። የመጣው ቢመጣ። ገባሽ?»
«አዎና» ሁለቱም በደስታ ግለው በፈገግታ ይንቦገቦጉ ጀመር።
አንድ ነርስ በሩን ቀስ ብላ ከፍታ ሀኪሙ ለማሪዮን በደንብ መተኛት እንዳለባት መግለፃቸውንና ሌሊቱ እየተገባደደ መሆኑን እስክትነግራቸው ሁሉንም ረስተው በፍቅር ተተብትበው አንድ ላይ ቆዩ ። ጆርጅ ኮሎዌ እንደወጣ ማሪዮን ሂልያርድ ወደ ኒው ዮርክ ስልክ ደወለች… ከሳንፍራንሲስኮ ማለት ነው ። ጊዜው (ኒውዮርክ ውስጥ) አነጋጉ ላይ ቢሆንም ማይክል ስልኩን ቶሎ አላነሳውም ። ጠበቀች ፤ ማሪዮን። «ሃሎ?» አለ ፤እንቅልፍ የተጫጫነው የማይክል ድምፅ «የኔ ሸጋ ፤እኔ ነኝ » አለች ማሪዮን። «እማዬ ነሽ ? ደህና ነሽ ? ተሻለሽ? » ጥያቄውን አዥጎደጎደው። «ደህና ነኝ ። አይዞህ አትስጋ ። ይልቅስ አንድ ነገር ልነግርህ ስለፈለኩ ነው የደወልኩልህ »
« ገባኝ ። ጆርጅ ነግሮኛል » አለ እያዛጋ «እንዴት ነው እሺታ ወይስ እምቢታ?»
«እምቢታ የለም ። ሁሉንም ተቀብያለሁ » አለች ። «አሁን የጠራሁህ ለሌላ ጉዳይ ነበር» አለች ። መልስ አልሰጣትም ። ትንሽ እንደማጉረምረም ብቻ አለ ። «ስለዚያች ልጅ ጉዳይ» አለች ማሪዮን ። «የቷ ልጅ?» ማይክ እየተደናገረ ጠየቀ ። «ፎቶግራፍ አንሺዋ... ማይክል ገና አልነቃህም”ንዴ
«ገባኝ። እሺ።ምን ትሁን!»
«ታስፈልገናለች»
«ያን ያህል››
«በጣም ። ሆኖም እንደምታውቀው እንግዲህ እኔ የጆርጅ ሰው ነኝ። ልጀቷን ማደኑ ያንተ ሥራ መሆኑ ነው»
«ትቀልጃለሽ እማዬ ? እኔ ያለብኝን የሥራ ውጥረት እያወቅሺው ። ቤን ይከታተል የሷን ጉዳይ»
‹‹ቤንንማ አፍንጫህን ላስ አለችውኮ ። ይልቅ ስማ ። ልጅቷ ዘመናዊ ከመሆኗም በላይ የታረመችና በእውቀቷም የምትተማመን ሰው ናት ። ከማንም ኩታራ ጋር ለመነጋገር የምትፈቅድ አይመስለኝም… ከተቀጣሪዎች ጋር ማለቴ ነው»
«ገባኝ ። ግን የመቀመጫ እሾህ መስላ ነው ለኔ የታየችኝ››
«እሷ ሳትሆን አንተ ነህ እንዲያ የሆንክብኝ ። በምን መንገድ ልታግባባት እንደምትሞክር አላውቅም ። በሆነው ፣ በመሰለህ ሁሉ ብትቀርባት ደንታዬ አይደለም ። ግን እንፈልጋታለን። ለኔ ስትልም ቢሆን ይህን ነገር ዳር እንድታደርገው እፈልጋለሁ››
«የለም ፤ የለም ዛሬ ደህና አይደለሽም ። ጊዜ እንደሌለኝ እያወቅሽ እንዲህ ስትይ» አለ። «ይልቅ ይህን ጉዳይ ብቻ አንቺ ጨርሺ በቃ።»
«አላደርገውም ማይክ ፤ ደግሞ ይህን ጉዳይ አልፈፅምም የምትል ከሆነ ገና እኮ ነው ፤ሥራውን አልለቀኩምኮ !››
«ይህን ካላደረግክ አንደኛ ሥራዬን አልለቅም ፤ እዚያው እቢሮዬ ውስጥ እሞታለሁ ። ሁለተኛ…»
«በቃ በቃ!» አለ ማይክል አቋርጧት «እንዳልሽው ይሆናል »
«ልባርግ ! ቀልድ አይደለም ። ቃል ፤ ቃል ነው ። ቃልህን ከሻርክ ቃሌን እሽራለሁ ።»
« አረ በእግዜር |! እሺ አልኩሽኮ አሁን ትተኛለሽ ወይስ ?»
«እተኛለሁ ግን ይኸ ጉዳይ ነገ ዛሬ እንደሌለው እወቅ ። ገባህ?»
«ገባኝ ስሟን ማን ነበር ያልሺኝ ››
‹‹ሜሪ አዳምሰን»
«ሜሪ አዳምሰን ። በቃ ከነገ ጀምሮ የማገኝበትን መንገድ እፈልጋለሁ»
«ደግ... እግዜር ያክብርህ የኔ ቆንጆ»
«ደህና ደሪ የኔ አሮጊት ።... ቆይ... ቆይ እንኳን ለፍጥምጥሙ አበቃን ። ወሬውን ላናፍሰው ? ሙሽራው ማን እንደሆነ ልናገር ?»
«ምን ይጠየቃል ? ከጆርጅ የተሻለ ማንን ላገኝ ? አላፍርበትም» ሁለቱም ዘጉ ።
ማይክልንና ሜሪን ካገናኘች ፤ሁለቱ ተዋውቀው አንድ ነገር ከመሰረቱ አእምሮዋ ሰላም ያገኛል ። ማይክ የሠራችውን ሁሉ ሲሰማ ምን ይላት ? ሆኖም ፍቅሩን የማግኘቱ ደስታ ለሷ የሚኖረውን ጥላቻ ሊቀንሰው ይችላል። በኋላ ተፀፅታ የሠራችውን ሲያይ ይቅር ይላታል ። እንቅልፍ እያንሸራተተ……

❤14👍11
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ
ምዕራፍ ሰላሳ ስምንት (38) ጆርጅ ኮሎዌ በፍቅር ሲስማት ለስላሳው ሙዚቃ እንደገና ጀመረ ። የሠርጉ ሥነ ሥርዓት የተከናወነው በማሪዮን ሂልያርድ ቤት ሲሆን እሷም ለዚሁ የሠርጓ ቀን ሶስት ሙዚቀኞች ቀጥራ ነበር ። ለሠርጉ የታደሙት አንድ ሰባ የሚሆኑ ሰዎች ሲሆኑ ፤ የምግብ ቤቱ ክፍልም እንደ የዳንስ አዳራሽ ሆኖ ተዘጋጅቷል ። የቡፌ ግብዣው የሚከናወነው ደግሞ በዚሁ መኖሪያ ቤተ መፃሕፍት ውስጥ ነው ። ዝግጅቱ የተከናወነ ፤ቀኑም ተስማሚ ነበር። የየካቲት የመጨረሻው ቀን ። ይህ ቀን ጥርት ያለ ፤ ነፋሻና ሳንካ አልባ የሆነ የኒውዮርክ ቀን ሆኗል ። ማሪዮን ሳንፍራንሲስኮ የደረሰባትን ነገር እንደመርሳት ያለች ይመስላል ። ደሟ ግጥም ብሎ ሞልቷል ። ጆርጅ በደስታ ፈነድቋል፡፡
ጋዜጠኞችም በዚሁ ሠርግ ላይ ተገኝተዋል ። ታይም የተባለው ታዋቂ መጽሔት ፎቶ አንሺ ማይክልንና ማሪዮንን ፤ ባሏ ጆርጅን ፎቶ አነሳቸው። ማሪዮን በባለቤቷና በልጅዋ ታጅባ ነበር የተነሳችው ። ማይክል ሂልያርድ እናቱን ዳረ ። ማሪዮን ሂልያርድ ካሁን ጀምሮ ፤ ማሪዮን ኮሎዊ ትባላለች ፤ የጆርጅ ኮሎዌ ባለቤት ። ማይክል ሂልያርድ ከዚህ ጊዜ ጄምሮ የኮተር ሂልያርድ ባለቤት ነው ። የአንድ ግዙፍ ድርጅት (የኮተር ሂልያርድን ያክል ግዙፍ ድርጅት) ፕሬዚዳንት መሆን ! ለማይክል የተሰማው ስሜት . . . ሆኖም ይህም ስሜት ቢሰማውም . . . ይህን ስሜቱን ደግሞ ማይክል ሊደብቅ አይሻም ። ፕሬዚዳንት ፣ በዚህ እድሜው ባለቤት ! በማግስቱ ታይም የተባለው በመላው ዓለም የሚሰራጭ መጽሔት የማይክልን ፎቶ በሽፋኑ ይዞ ወጣ ። ድንቅ ተባል ። በዚህ እድሜ የኮተር ሂልያርድ ፕሬዚዳንት !. . የማሪዮንና የጆርጅ ኮሎዌ ሠርግ እለት የዛ ለት ማይክል ወደእናቱ ቀረብ ብሎ፣ «ሚስዝ ኮሎዌ ! » አለ አዲሱን የጋብቻ ስሟን እየተጠቀመና ለቀሰስተኛው ዳንስ እየጋበዛት ። «አዲሱን ስም እናክብረው ጋብቻውን እናክብረው» አለ ። አዲሱን ስም እናክብረው ሲል ናንሲ ትዝ አለችው ። እንዳለው ሆነ ። አከበሩት ፤ ጆርጅና ማሪዮን ኩሎዌ በጋብቻ ተሳሰሩ ። ሁለቱም ለረጅም ጊዜ ተሰቃይተዋል ። ደስ ይበላቸው ፤ ደስታ ይገባቸዋል ። ደስታ ያስፈልጋቸዋል ። ጋብቻቸውን ምክንያት በማድረግ ወደ አውሮፓ ሔደው ሽርሽር ይላሉ። ደስ ይሰኛሉ ። « በጣም ቆንጆ ነህ የኔ ሸጋ » አለች ማሪዮን ፡ ማይክልን በፍቅር እየተመለከተች ። «ያንቺን አላየሽ ። አሸብርቀሻል ፤ ተውበሻል » አለ ማይክ ከልቡ። «ቤቱ ሳይቀር እንደ አዲስ ያበራል ፤ አምሯል » እለ ። «በጣም አሸብርቋል አደል ? » አለች ማሪዮን ። ማይክ ከልቡ ተደስቶ ማሪዮንን ተመለከታት ። እናቱ ነችኮ። ይህቺ ሙሽሪት እናቱ ነች ። ሙሽራ ትመስላለች ፤ የእውነት ሁኔታዋ ሁሉ የሙሽራ . . . የልጃገረድ ሙሽራ ሆኖ ታየው ። «ሚስተር ሂልያርድ » የሚል ድምዕ ቀሰቀሰው ። « ማይክል ሂልያርድ በጣም ደስ ያለህ ትመስላለህ ዛሬ » ዌንዲ ነበረች ። ሲያያት እንደወትሮው አላፈረም ። ዓይኑ አልሸሻትም ። ይህ ቀርቷል። ዛሬ ቤን አቭሪና ዌንዲ ሊጋቡ ተጫጭተዋል ። የማጫ ቀለበቷ (ዕንቁ ያለበት ቀለበቷ ) እቀለበት ጣቷ ላይ ያበራል ። ሊጋቡ ወስነዋል ። ማይክል ሂልያርድም ዋና ሚዜ ሆኖ ተመርጧል ። ተስማምቷልም ።
«ደስ አትልም?» አለ ማይክ እናቱን ለዌንዲ እያሳያት ዌንዲ አንገቷን በአዎንታ ነቅንቃ በደስታ ፈገግ አሰች ። ደስ ብሎት ስላየችው ደስ እላት ። እንዲህ ደስ የሚለው መስሏት አያውቅም ። ብቻ ነገሩ ሁሉ አይገባትም ። ገባት አልገባት ደሞ ደንታዋ አይደለም ። ለሷ እንደሆነ ቤን አለላት ። የቤንን ያህል በፍቅር ደስ ያሰኛት ወንድ የለም ። «እንቺም በሚቀጥለው በጋ እንዲህ ቆንጆ ሆነሽ ማየት አለብኝ ። ሙሽራ ቁንጅት ሲል የሠራ አከላቴ በደስታ ይሞላል » አለ ማይክል ዊንዲን በደስታ እያየ ። ደስ አላት ። ዛሬ ጓደኛዋ ነው። ትወደዋለች ። አትመኘውም ለጓደኛ የሚገባውን ሁሉ ግን ትመኝለታለች ። «አሀ የኛ ጀግና ፤ የሰው እጮኛ ለማማገጥ ነዋ ?» ቤን አቭሪ ነበር እንዲህ ያለው ። ቤን ሶስት መለኪያ ሻምፓኝ ይዞ ነበር የመጣው ። «በሉ ተቀመጡ። ይኸው ! ሁለት መለኪያ የናንተ ነው አንሱና ጠጡ» አለ ቤን በደስታ ፈክቶ ። ቀጥሎም ፣ «በነገራችን ላይ ማይክ ምን እንደሚሻለኝ እንጃ እንጂ ፍቅር ይዞኛል ፤ ከማሪዮን ጋር » አለ ። «ቀለጥክ… ዛሬ ጠዋት ላንድ ጎረምሳ ዳርኳት» አለ ማይክ ። ቤን ወይኔ በሚል ሁኔታ ጣትና ጣቱን አጩሆ ደንግጦ ቀረ። በዚህም ነገር ሶስቱም ከልባቸው ሳቁ። ሙዚቃው የተጀመረው ገና ስቀው ሳያበቁ ነበር ። በዚህ ጊዜ ማይክ « ሙዚቃው ጀመረ። መሔድና እናቴን ለዳንስ መጋበዝ አለብኝ ። ደንቡ እንደሚለው እኔና እሷ ዳንሱን እንከፍታለን ። ጆርጅ ይቅርታ ጠይቆ ይነጥቀኛል።» ይህን ብሎ ወደ ዳንሱ አዳራሽ ከገባ በኋላ ነበር እናቱን ባዲሱ የጋብቻ ስሟ ጠርቶ የጋበዛት ።
« ዛሬ በጣም ደስ ያለው ይመስላል » አለች ዌንዲ ማይክ እንደተለያቸው ። «እንዲህ አንዳንድ ቀን እንኳ ደስ ብሎት እንየው እንጂ » አለ ቤን ፊቱ በተመስጦ ተሞልቶ። ከዚያም ድንገት ተመስጦን ነጥቆ ወጥቶና ከልቡ ፈገግ ብሎ «አንቺም ዛሬ በጣም ደስ ብሎሻል » አላት «ደሞ እኔ መቼ ከፍቶኝ ያውቃል? ዕድሜ ላንተ እንጂ›› አለች ከልቧ ። ለጥቂት ጊዜ ፀጥታ ሆነ ። ከዚያ በኋላ « በነገራችን ላይ ፤ እጠይቅሀለሁ እያልኩ እየረሳሁት «ያችን ፍቶ ግራፍ አንሺ አነጋገርካት ወይስ እንዴት አደረግክ?» ስትል ጠየቀችው ፡፡ «አላነጋገርኳትም » አለ ቤን ራሱን በአሉታ እየነቀነቀ «ማይክ ሊያነጋግራት አስቧል » አልመስልሽ አላት « ማይክ ጊዜ አግኝቶ ? » አለች ጥያቄዋ መደነቅም ነበር ። «ጊዜ እንኳን የለውም ። ግን ማይክ ለሥራ ጊዜ ያጣል ብለሽ ነው እንደምንም ያብቃቃዋል ።. ለዚህም ለሌላ ሌላ ሺህ ጉዳይም በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሳንፍራንሲስኮ ይሔዳል » አለ ቤን ። ፀጥታ ሆነ ። ዌንዲ ማሰብ ቀጠለች ።

የለም ማይክ አላውቀውም ፤ ሁል ጊዜ አዲስ ነው ። ብቻም አይመስለኝም ። ማይክ ምን እንደሆነ የሚያውቀው ያለኔ ምናልባት ቤን ። ቤንም ቢሆን እንጃ ። ምናልባት ያውቀው ነበር ማለት ይቻላል ፤ በፊት ። ግን አሁንስ ያውቀዋል ? አረ በፊትስ ቢሆን ያውቀው ነበር ? አስቸጋሪ ነገር ነው። «መደነስ ትፈልጊያለሽ ? » አለ ቤን መለኪያውን እጠረጴዛው ላይ እያኖረና እያቀፋት ። «መፈለግ ነው ! » አለች ደስ እያላት ። ተያይዘው ወደ ዳንሱ አዳራሽ ገቡ ። ትንሽ እንደደነሰ… ቢያንስ ለነሱ ትንሽ የደነሱ ነው የመሰላቸው ማይክል በመካከቸው ሊገባ እየሞከረ ። ‹‹ተራ ይድረሰኝ እንጂ »
«እንዲህ ነኝና ፤ ምናለ ይደርስሀል …» አለ ቤን «ሰውየው ደህናም አይደለህ ? ለመሆኑ ከእናትህ ጋር ልትደሰት እልነበረም እንዴ ትተኸን የሔድከው ? »
« ጆርጅን ስታይ እኔን ፈንግጣኝ ሔደች » ሶስቱም ሳቁ ። «ደግ አደረገች። አዋቂ ይሉሀል እንዲሀ ነው» አለ ቤን እየሳቀ ። ቤንም ወለሉን አልለቀቀ ፤ ማይክልም አልተመለሰ ። ሶስቱም ባንድነት መደነስ ጀመሩ ። መንገላወድ ልበለው ? ይህ የተሰማት ዌንዲ በሳቅ መንከትከት ጀመረች ። ቤንና ማይክ ያን ያህል ሲደሰቱ ስታይ አደጋው ከመድረሱ በፊት የነበረው ሁኔታ በዓይነ ኅሊናዋ ታያት ። እንዲህ ነበር ማለት ነው የሚደሰቱት ስትል አሰበች ። ዛሬ ይህ በመመለሱ ደስ አላት ። መሳቅ ጀመረች። በመካከሉ ማይክ ቤንን በትያትራዊ ቁጣ እየተመለከተ «ስማ አቭሪ !ከዚህ ጥፋ ብያለሁ ጥፋ ። ከእጮኛህ ጋር ለብቻየ መደነስ እፈልጋለሁ ማለት ይግባህ » ሲል አስጠነቀቀው። «አልሔድም ፣ አይቻልም ብል ምን ሊመጣ !» አለ ቤን «ሶስታችንም ከዳንሱ ወለል ተጠርገን እንድንጣል ታዛለች እናቴ ። ያ ደሞ ጥሩ አይመስለኝም » በዚህ ሁኔታ ከቆዩ በኋላ !
« ስሙ » አለ ማይክ «ለምን ሔደን ኬክ አንበላም? » ተስማሙ ። ኬክ ወዳለበት ሲሔዱ ቤን አቭሪ የጫማውን ሶል አየት ካደረገ በኋላ ሳታየው ዌንዲን በአውራጣቱ እያሳየና አትሰማም አሉ በሚል ሁኔታና ትያትራዊ ሹክሹክታ ፣ «ዳንስ አትችልም ይቺ ሴት ። ጫማዬን ታያለህ ? » አለው። ማይክም «የኔንም ተመልከተው! » ሲል አጋነነ ። «የናንተን አሳያችሁ እኔ ደሞ ነገ በእግሬ መሔዴ እማይቀር ነው » አለች ዌንዲ በማኩረፍ ። በዚህ እየተሳሳቁ እኬኩ ዘንድ ደረሱ። ኬኩን አንስተው እየገመጡ ዳንሱን መመልከት ጀመሩ ። የተጠሩት ሀብታሞች ነበሩ ፤ሁሉም ። በሀብታም ጋለሞቶች አንገት ላይ የተንጠለጠሉት የእንቁና የሉል ጌጦች ያበራሉ። ልጃገረዶችም አበባ መስለዋል፡፡ «ትንሽ ቀደም ብሎ ይህን ባይ ኖሮ » አለ ቤን በውሸት የፀፀት ድምጽ ልጃገረዶቹን ኢያየ ። «እህሳ !» አለ ማይክ ቀልዱን እየተክተለ ።
«እሀህ ... ወደ መፀዳጃ ቤት ብቅ ብዬ የአፍንጫዬን ላብ በፑደር ላስተካክል አስቤ ነበር ። አሁን ግን እናንተ ሰዎች የምትታመኑ ሆናችሁ አልታያችሁኝም ። ይቅርብኝ » አለች ዌንዲ ። «አይ ለዚህስ አታስቢ ። እጠብቅልሻለሁ » አለ ቤን። «ምን ጊዜ ኖሮህ ጌታዬ ! አንተንም የሚጠብቅ በተገኘ ፤ እንኳን አንተ ሰው ልትጠብቅ » ቤን አቭሪ « ግድየለሽም » ብሎ ብርጭቆዋን ተቀብሎ እንደማባረር አደረጋት ። ዌንዲ ወደ ወይዛዝርት ክፍል ስትሔድ ። «ሴት ብሎ ዝም ናት ፤ አይደል ?» አለው ማይክን ። ማይክም አድናቆቱን ከልቡ ገለጸ ። ከዚህ ቀጥሎ ቤን ማይክን በደንብ እየተመለከተ «ሁሌ ሳስበው ምንኛ ታድያለሁ እላለሁ ። ማይክ ያኔ ስነግርህ አለመቆጣትህ…. ስለኔና ስለሷ የነገርኩህ እለት… » አለ። «ለምን እቆጣለሁ!?. . . ደሞም'ኮ አየህ እኔ ለእንደዚህ ዓይነቱ ነገር ጊዜ የለኝም »
« ለወደፊቱ ግን ጊዜ እንደሚኖርህ አልጠራጠርም››
‹‹ምናልባት። ሆኖም ለጊዜው እናንተ ፡ እናንተ ሂዱ፤አግቡ ተጋቡ። እኔ ልጄ ከባድ ሥራ ፤ ከባድ ኃላፊነት አለብኝ » ማይክ ይህን ያህል ቢልም ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ነገር እንደሚያስከፋው አልተከፋም ። ፈገግታ በፊቱ ላይ እንዳለ ነበር እንዲሁ ፈገግ እንዳለ መለኪያውን ተመለከተ ። ከዚያም ለጤናችን በሚል ቅኝት ብድግ አድርጐ «ለሁላችን ! » አለ ሁለቱም ግጥም አድርገው ጠጡ።
•••••••••••••••••••••••••
ማይክል የእጅ ሻንጣውን ጧ እድርጎ ሲዘጋ አውሮፕላኑ የሳንፍራንሲስኮ ማረፊያውን አስፋልት ያዘ ። በመንገድ ላይም እያለ አላረፈም ነበር ። በሳንፍራንሲስኮ ውስጥ በሚቆይበት ጊዜ ብዙ ስራ መስራት አለበት ። ብዙ ስብሰባዎች ይጠብቁታል ። የተለያዩ ሐኪሞችን ማነጋገር ፣ ጥያቄዎችን መመለስ ፡ የተለያዩ ስራዎችን መመልከት አርኪቴክቶችን ማነጋገር፤ ማደራጀት ፤ መመሪያ መስጠት ። በዚያ ላይ ደሞ... ያችን ፎቶ ግራፍ እንሺም ማነጋገር፤ ማግባባት ማለቂያ የለውም ። ሆኖም እንደምንም ይወጣዋል፤ ለምዶታል ። ወይ የምግብ ሳዓቱን በማሳለፍ ወይ የመኝታ ሰዓቱን በመቅነስ ወይም ሌላ። በቻ... ይወጣዋል ። ይህን እያሰበ በአንደኛ ደረጃ የበረራ ክፍል ከተቀመጠበት ወንበር በላይ ባለው ርብራብ ላይ ኣጥፎ ያስቅመጠውን ካፖርት ሲያወርድ ሆስቴስዋ አይኗን እንደጣለችበት ተገንዝቦ ፊት እልሰጣትም ። እንደሁልጊዜው ፀጥ ብሎ ወደ ውጭው በር አመራ። ሲያዩት እንዲህ አድርጎ ትቷቸው መሄዱንም እንደስራው ሁሉ ለምዶታል ። ሰዓቱን አየ ። ከቀትር በኋላ መሆኑን ትገነዘበ። አውሮፕላን ማረፊያው ድረስ መጥቶ የሚጠብቀው መኪና እንዳለ ያውቃል ። ምናልባትም ዛሬውኑ ስብሰባዎች ማካሄድ ይኖርበታል ። ነገ ጧት ቁርስ ላይም ስብሰባ አለው ። ከአንድ ሰዓት ጀምሮ ። የማይክል ሂልያርድ ሕይወት ይኸው ሆኗል ። ማይክል ሂልያርድ ሰለ ስራ እንጂ ስለሌላ ነገር አያስብም ። በርግጥ ያስባል ። ሰለእናቱ ያስባል ። ስለጆርጅ ኮሎዊ ያስባል ። ስለቤንና ስለዌንዲም ያስባል ። እናቱና ጆርጅ ግን የሉም ። ማጆርካ ውስጥ የሙሽርና ወቅት እያሳለፉ አለማቸውን ይቀጫሉ ። ቤንም በዌንዲ እቅፍ ውስጥ በሰላም ኒውዮርክ ውስጥ ይምነሽነሻል ። ሁሉም ተከባካቢ አላቸው። ስለነሱ መጨነቅ አያስፈልግም ። እሱንም ቢሆን የሳንፍራንሲስኮ ሕክምና ማእከል እያቀማጠለ ያኖረዋል ። ይሰራል ከዚህ የበለጠ ምን አለ ? ስራ ሰላም ነው ለማይክል ሂልያርድ ።
እንዳሰበው ሆነ። መኪና ይጠብቀዋል ። ትሳፍሮ ወደ ታላቁ ፌይርሞንት ሆቴል አመራ ። ተይዘዋል የተባሉች ሁለቱም ልዩ ክፍሎች በትክክል እንደተጠበቁ ሆነው እገኛቸው። ሁለቱም ክፍሎች የራሳቸው ሳሎንና መኝታ ያላቸው የትሟሉ ክፍሎች ሲሆኑ ለማይክል እንዱ ክፍል በቂ እንደሆነ ግልፅ ነው። ሁለተኛውን ልዩ ክፍል የተከራየው ሰስብሰባ ሲል ነበር ። ሲያስበው በሁለቱም ውስጥ ሰብሰባዎችን ማካሄድ እንደሚችልም ገሙተ፤ ባንዴ። እቃው ተራግፎ ክፍሉ ውስጥ ከገባ በኋላ ጣመኑ በሚገባ ሳይለቀው ስራ ጀመረ፡። ያን ለት የመጨረሻውን ጉዳይ ተነጋግሮ ሲጨርስ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ሆኖ ነበር ። ሌላ ጉዳይ ሊጨምር አልቻለም። ደከመው፡ ራበው። ይበቃዋል ።