አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አራት (34)

«ምን… ከኔ ጋር ? አዎ» አለች ማሪዮን ። ሁለቱም ፀጥ አሉ፣ ረጂም ለመሰለ ጊዜ ። በመጨረሻ «እንተዋወቃለን ናንሲ ። ፒተርን አውቀዋለሁ ። ላንች ያደረገልሽ ህክምናም እጅግ የሚደነቅ ነው» አለች ማሪዮን ።
«ትንሽ ስህተት ሳይፈጠር አልቀረም መሰለኝ ። እኔ ናንሲ ሳልሆን ሜሪ…» ንግግሯን አልጨረሰችም ። ጉልበቷ ተሟጦ ሲወጣ ተሰማት፡፡ ባዶ ሆነች። አጥንት አልባ የሆነች ይመስል ተልፈሰፈሰች ። እንባ አነቃት ። እንደምንም ብላ ተነሳች ። ወደ መስኮቱ ሄዳ ጀርባዋን ለማሪዮን ሰጥታ ቆመች ። እና «ማን . . . እንዴት ልታውቂኝ ቻልሽ ?» አለች ። የተሰበረ ድምፅ ነበር ። ማሪዮን ርግጠኛ ሆነች ። የዛሬ ሁለት አመት የሰማችው የናንሲ ማክአሊስተር ድምፅ ብቅ አለ። «ማን ነገረሽ ? » አለች ሜሪ ደግማ በሚያስገድድ ድምፅ ። «ማንም አልነገረኝም ። ገመትኩ ። ግምቱ ለምን እንደመጣብኝም አላውቅም ። ሆኖም ገመትኩ ። ገና ቤን ስለሁኔታሽ መግለፅ ሲጀምር እሷ ናት? የሚል ጥያቄ መጣብኝ ። የነገረን ነገር ሁሉ ስለአንቺ ከማውቀው ጋር ሙሉ በሙሉ ሲመሳሰል ጊዜ ነው መሰል »
«እንዲያ ከሆነ ... » አለችና ዝም አለች፡፡ ማይክልም ያውቃል ማለት ነዋ! ልትል ነበር ። የተረገመ ልብ መቼ ነው ተስፋ እሚቆርጠው! መቼ ነው መጥላት የሚገባውን የሚጠላው ? «አሁንስ ለምን እዚህ ድረስ መጣሽ ? መኖሬን ስታውቂ ጊዜ ፈራሽ? ውል እማፈርስ መሰለሽ ? እና ውሉ ያልፈረሰ መሆኑን ልታስታውሺኝ ፈለግሽ ? »
«አይደለም ። በዚያ በኩል አልጠረጥርሽም ። ቃልሽን ማክበር እንደምትችይ አረጋግጫለሁ» አለች ማሪዮን ፤ እጅግ ያረጀሰው በመሰለ ድክም ባለና ደግነት በተሞላ ድምፅ «ላይሽ ነው የመጣሁ ። ላነጋግርሽ ምን እንደመሰልሽ ፤ ይመችሽ ፤ይክፋሽ ... ላይሽ ነው የመጣሁ። ላያት የመጣኋት ልጅ አንች ነሽ ማለት ከደፈርኩ ። ሌላውን ምክንያት እኔም በቅጡ አላውቀው»
«ለምን ? ይህን ያህል አመት ትዝ ሳልልሽ ቆይቼ ድንገት ምን አዲስ ስሜት ተፈጠረ ?» የሜሪ ድምፅ የሚናደፍ መርዛም ነበር ። ማሪዮን ምንም አልመለሰችም ።

«ድንገት ምን ነገር ተፈጠረ ሚስ ሂልያርድ? ወይስ የግሬግሰንን ሥራ ተመልክቶ ማድነቅ ስላማረሽ ይሆን ? እንዲያ ከሆነ ... እንዴት ነው በአራት መቶ ሺ ዶላር ክፍያ ያሰራሻት አሻንጉሊት እምታምር አትመስልሽም? አራት መቶ ሺ ዶላር ቢወጣም አይቆጭ! የሚያሰኝ ነው?. . . የሚያሰኝ ነው ወይ ? ምነው ጭጭ አልሽ ? ጥያቄየን መልሺልኝ እንጂ… ደስ አለሽ ወይስ ከፋሽ?» ደስ ቢለኝ ኖሮ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር ! አለች ማሪዮን በሀሳቧ ። ድንገት ደስ ቢለኝ የሚል ምኞት አደረባት ። ግን የሰራችው ነገር ውጤት መጥፎ ፤ ያደረገችው ነገር አስቀያሚ እንደሆነ ወለል ብሎ ታያት። ለዚህ ገጽታ ሁሉም ብዙ እንደከፈሉ ግን ያ ሁሉ ከንቱ እንደነበረ ተገነዘበች ። ይህ ፀፀት ነው። ፀፀት ግን ዋጋ የለውም ። ሁሉም ነገር ካለፈ ፤ ምንጩ ከነጠፈ በኋላ ቢፀፀቱት ምን ፋይዳ አለው? ማይክልን አሰበች ። ናንሲን ተመለከተች ። እሷን ራሷንም ። አንዳቸውም እንደነበሩ አይደሉም። ሁሉም ሌላ ሆነዋል ። ማይክልና ናንሲ። ሁሉም ነገር ሩቅ ከሩቅ ፤ የራቀ ሩቅ ሆኗል ። ለነሱም ። አንዳቸው ላንዳቸው ይሆኑ ዘንድ የማይቻል ነው ። ህልማቸውን በግል ሲያባርሩ ፤ ሊያገኙት ከቻሉ ሌላ ቦታ ቢፈልጉት ይሻላል ። «ናንሲ በጣም ቆንጆ ልጅ ሆነሻል ኮ» አለች ማሪዮን ፤ ወንድ አይጠፋም ለማለት ያህል ። «ቆንጆ ስላልሺኝ አመሰግናለሁ ይገባኛል ። ፒተር ውብ የእጅ ሥራ ቀርጾአል ። ግን ይህን ለማድረግ የገባሁበት ውል…. ከሰይጣን ጋር እንደመዋዋል የሚቆጠር ነው ። ቆንጆ ፊት ለማግኘት ሕይወትን መሰዋእት ማቅረብ ። ሌላ ትርጉም የለውም»

«ሰይጣኒቷም እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ» አለች ማሪዮን በሀዘን በተሰበረ ድምፅ «ምንም እንኳ ዛሬ ይህን ላንች መንገር ርኩስ ተግባር እንደሆነ ቢገባኝም ፡ ያኔ ናንሲ ፣ያኔ ቃል እንድ ትገቢልኝ ሳግባባሽ ፤ ሊሆን የሚገባውን ነገር ያደረግኩ መስሎኝ ነበር»
«አሁንስ ? አሁንስ ምን ይመስልሻል ? » አለች ፊት ለፊት በድፍረት እየተፋጠጠቻት «አሁንስ ምን ይሰማሻል ፤ሚስ ሂልያርድ ? ለመሆኑ ማይክል ደስተኛ ነው? እኔን እንደ አሮጌ ዕቃ ወርውረሸ ከጣልሽለት በኋላ ደስ ብሎት መኖር ጀመረ? ተልእኮሽ ሰመረልሽ ? » ስሜት ተናነቃት ። በጥፊ ልታልሳት ፈለገች ። ይህን የወይዛዝርት ልብሷን እንደተጎናፀፈች ገፍትሬ ጥዬ መሬት ለመሬች ብጎትታት ! ስትል ተመኘች ። «የለም የለም አንዱም ነገር አልተሳካልኝም ። ማይክል ደስተኛ አይደለም ። ከጊዜ ጊዜ ሁሉን ነገር ይረሳል ፤ ሀዘኑ ይሽራል በሚል ተስፋ ስጽናና ቆየሁ ። ግን አልሆነም ። አንችም እንዲያ እንደምትሆኝ ተስፋ ነበረኝ ።ግን ሳይሽ ነሽ ሀዘንሽ አልሻረም ምንም ነገር አልተረሳሽም ። ወይስ የተሻለ መንገድ መርጠሻል? ብዬ እጠይቅሽ ነበር ። ሆኖም መብት ያለኝ አይመስለኝም »
«ልክ ነሽ። ያን ጥያቄ ለማቅረብ ምንም መብት የለሽም ማይክል ሚስት አገባ ወይስ ?»
«አግብቷል» አለች ማሪዮን ። ሜሪ ክው ብላ ደነገጠች ። ኡኡ ! ብላ ለመጮህ ፈለገች ። ድምጹን አፍና አስቀረችው ። ያ ድምፅ ከጉሮሮዋ ሳይወጣ ሟሟ። «አዎን ፤ ሜሪ ። አግብቷል ። ሥራውን አግብቶ ትዳር መስርቷል ። የሚበላው የሚጠጣው የሚተኛው እሥራው ላይ ሆኗል። ትንፋሹ ሳይቀር ሥራው ሆኗል ።» ሜሪ ትንፋሽዋ መለስ አለ። «ከሥራው ላይ ንቅንቅ አይልም ። በሥራው ውስጥ ሰምጦ ዘለአለም አለሙን ሊያሳልፍ የፈለገ እስኪመስል ። አብረን እንኖራለን ይባላል እንጂ መልኩን የማየው ከዝንተ አለም አንድ ጊዜ ነው»

የት አባሽ አንች ውሻ !እንኳን ! አለች ሜሪ በሀሳቧ «እንዲያ ካልሽ ፤ ስህተት መስራትሽን ተገንዝበሻል ማለት ነው። ማለት በአለም ላይ ካለው ሀብትና ማንኛውም ድንቅ ነገር አብልጨ እወደው እንደነበር ታውቂያለሽ ? » ይህን ብላ ስታበቃ በኃሳቧ ከዚህ ፊቴ በስተቀር…. ከፊቴ በስተቀር ! አምላኬ ምናልኩህ «በስተቀር» እንድል አደረግከኝ! «አውቃለሁ ። አውቅ ነበር ። ግን ፍቅር ነውና ያልፋል ብዬ ገመትኩ»
«ሆነ ? ግምቱ ትክክል ነበር ? ረሳኝ ? »
«እንጃ ። ምናልባት አልፎለት ይሆናል ። ስምሽን አንስቶ አያውቅም መቼም»
«በመጀመሪያ ወይም መቼም ቢሆን የት እንዳለሁ ለማወቅ ሙከራ አድርጎ ነበር ?» ማሪዮን በአሉታ ራሷን እየነቀነቀች «እልሞከረም» አለች ። ይህን ትበላት እንጂ ለማይክል ናንሲ ሞታለች እንዳለችው አልነገረቻትም ። «ያ ከሆነ ታዲያ ለምን ጠራሽኝ? እኔን የማየት ጉጉትሽ እንዲረካ ? ….. ፎቶግራፎች እንዳሳይሽ?. . . ለምን ?»
«እኔም ለምን እንደፈለግኩሽ አላውቅም ፤ ናንሲ ። ይቅርታ... ሜሪ ። ቅድም እንደነገርኩሽ ነው ። አላውቀውም።... በግድ እዘኑልኝ ማለት ፤ ወይም ሆደባሻነት ይመስላል እንጂ ደኅና አይደለሁም ። መሞቻዬ ሩቅ አይደለም ። እመቃብሬ አፋፍ ላይ የቆምኩ ይመስለኛል»
👍15
ማሪዮን ይህን ብላ ወደ ሜሪ አዳምሰን ዞረች ። ያኔም ሜሪን ማሪዮን ሞቷ ስለቀረበ ምን ያህል እንዳዘነች አየች ። ሜሪን ስትመለከት ማሪዮን ለምን ነገርኳት? የሚል ብስጭት ገባት ። በዚያም አለ በዚህ ሜሪ ለማሪዮን ቅንጣት ያህል ሀዘን አልተሰማትም ። ማሪዮንን ለረጅም ጊዜ ትኩር ብላ ስትመለከት ከቆየች በኋላ ፤ «እንዲህ ያለውን ነገር በመስማቴ አዝናለሁ ፤ ሚስዝ ሂልያርድ ። ግን ደግሞ እኔም ሙት ነኝ። ከሞትኩ ሁለት አመት ሞላኝ ። እንደሰማሁት ከሆነ አንድ ልጅሺም ሞቷል ። ሁለት ነፍስ አጥፍተሻል ማለት ነው ። የሁለት ሰው ደም አለብሽ ። እና እውነቱን መናገር ካለብኝ የሆነው ነገር ቢደርስብሽ ፤ እኔ ሳልሆን ልቤ ሀዘን ሊፀንስ አይችልም። መቼም በመንገድ ላይ ስሄድ ወንዶች አየት አድርገውኝ ፊቴ መበላሸቱን ብቻ ሳይሆን ጣረሞት መምሰሌን አይተው እንዳይሸሹኝ አድርገሽልኛል ። በዚህ ላመሰግንሽ ፤ይህን ውለታ ልቆጥርልሽ ይገባኝ ነበር ግን አልችልም ። ብዙ ብዙ ነገር ሊሰማኝ ይገባ ነበር ብዬ አምናለሁ ። ግን ምንም አይሰማኝም ። ብቻ ልጅሽን እንዲያ እንዳደረግሽው በመገንዘብሽ በዚያ ብቻ ትንሽ ሀዘን ቢጤ ይሰማኝ ይሆናል ። ሌላ የለም»

ማሪዮን ፀጥ ብላ ራሷን በአወንታ እየነቀነቀች የሜሪን ወቀሳ በፀጋ ተቀበለች። ለምን? ሜሪ ያለችው ሁሉ እውነት እንደሆነ ራሷ ደርሳበታለች ! ዛሬ አይደለም ። ከሆነ በኋላ ለራሷ አትመነው ፡ አትቀበለው እንጂ ልቧ የሰራችውን ጥፋት አውቆታል። ቢያንስ በማይክል ላይ የፈፀመችው በደል ያለ ጥርጥር ግብቷታል። ከገባትም ቆይቷል ። ምናልባት ሜሪ ለማየት የፈለገችውም ፤ በሷ (ሜሪ) በኩል የተሻለ ሕይወት አይ ይሆን) ስትል ተስፋ በማድረግ ሊሆን ይችላል ። «ልክ ነሽ የኔ ልጅ። ልክ ነሽ። ምን ብ....ምን ብዬ ልንገርሽ….. የምናገረውም የለኝ»
«ደህና ሁኝ ብትይኝ ደግ ነው» አለች ሜሪ።

ይህን ብላ ካፖርቷንና ፎቶግራፍ መያዣዋን አነሳችና ወደ በሩ አመራች ። በሩን ለመክፈት እጄታውን እንደያዘች አንገቷን ደፍታ ፣፤ እንባዋ ተንቆርዝዞ ለጥቂት ጊዜ ቆማ ቆዘመች ። ቀስ ብላ ወደ ክፍሉ ውስጥ ዞረች ። ያኔም የማሪዮን ሂልያርድ ፊት እንባ በእንባ ሆኖ ተመለከተች ። ማሪዮን በራሷ ስቃይ ተለጉማ ነበርና አንዲት ቃል ልትተነፍስ አልቻለችም ። ወጣቷ ሜሪ ግን እንደምንም ሳጓንና ከላይ ከላይ ሲላት የጀመረ ትንፋሽዋን ተቆጣጥራ «ሚስዝ ሂልያርድ ደህና ሁኝ ። ለማይክል...ፍ...ፍቅ የፍቅር ሰላምታዬን አቅርቢልኝ» አለች ። ይህን ተናግራ በሩን ከፍታ ወጣች ።

ማሪዮን ሂልያርድ ግን ካለችበት ንቅንቅ ማለት አልተቻላትም ። ልቧ እየዘለለ ሳንባዋን ሲደበድበው ከፍተኛ የሀመም ስቃይ ለቀቀባት ። ከላይ ከላይ እየተነፈሰች ፤ መጥሪያ ደወሉ ወዳለበት እየተንቦራቸች ሄደች ። ያን መጥሪያ ብትነካው አንድ ሰው አንዲት ሠራተኛ እንደምትደርስላት ታውቃለች ። እንደምንም ደረሰች ። እንደምንም መጥሪያውን አንዴ ብቻ ተጫነችው። ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር ጨለማ ሆነ «
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍141
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሦስት ወራት አለፈ" ካርለት በሐመር ቆይታዋ ብዙ ልምድ አካበተች ያልጠበቀችውንም እርካታ አገኘች ካርለት ከሎን ወደ ዲመካ፣ ቱርሚና ጂንካ ከተማ ሲሄዱ እግረ መንገዷን መኪና ማሽከርከር ስላስለመደችው መረዳዳት
ጀምረዋል" ካርለት በሐመር ኑሮዋ ዕቃዋን፣ ገንዘቧን ለማስቀመጥ የምትተማመነው በመኪናዋ ውስጥ ነው፤ በተለይም ሙዚቃ ለማዳመጥ መኪናዋ ከፍተኛ ጥቅም ትሰጣታለች" በነዳጅ በኩል እስከዚያ ወቅት ድረስ ችግር አላጋጠማትም፤ ካስፈለጋት ግን ጂንካ ከተማ ናፍታ ማግኘት እንደምትችል ተረድታለች።

የሐመር ሰማይ ጥርት ያለና አልፎ አልፎ ብን ያለ የጥጥ ባዘቶ መሳይ ዳመና ይታይበታል” የዝናቡ ወቅት፣ እምብዛም የሚያስተማምን ባይሆንም፣ ድንገት እያጓራ የሚያጋሽብ ጥልመት ዳመና ከታየ «አህያ» የማይችለው ዝናብ፣ መዓቱን ያወርደዋል" በዚህ
ወቅት የዕጽዋት ቅጠሎች እንደ በረዶ ብን ብን እያሉ ሲወድቁ ከብቶች ጅራታቸውን ሸጒጠው፣ ጆሮአቸውን ይጥላሉ።

በዚህ ወቅት፣ የከሰኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ዛፍ ቅጠሉን እያተራመሰ፣ ባሕርይውን ይቀይርና በመደንፋት፣ እየተነሣ ይፈርጣል"
በዚያን ጊዜ ከሰኬ ወንዝና የሐመር ማኅበረሰብ፣ ከብቱ፣ ፍየሉ፣ ይኰራረፋሉ «አትድረስብኝ» አንመጣብህም ይባባላሉ"
አንድ ጊዜ፣ ካርለትና ከሎ መዝነቡን ሳያውቁ ከጂንካ ወደ ሻንቆ ሲሄዱ፣ ከሰኬ ወንዝን በመኪና ገብተው ሊሻገሩ ሲሉ መኪናዋ
በአሸዋው ተያዘች እነሱም ከመኪናቸው ወርደው በዶማና አካፋ
ለማውጣት ሲሞክሩ «ፉ..ፉ..ፉ.» የሚል ድምፅ ሰሙ። ቀና ሲሉ ደረቱን ገልብጦ፣ የሚጣደፍ ደራሽ ውኃ ተመለከቱ። ካርለትና ከሎ ብርክ ይዟቸው እንደ ሕፃን ልጅ ተንቦራቹ። ውኃው ግን ገሰገሰ ካርለትና ከሎ ዳር ላይ ሊደርሱ ሲሉ ውኃው ሲያጠናግራቸው
ተንገዳገዱ፤ ሳያስቡት እጅ ለእጅ መያያዛቸው ግን በጃቸውና ለትንሽ
አመለጡ። ደራሽ ውኃው መጀመሪያ መኪናዋን እያነቃነቀ ፈተሻት፣
ቀጥሎ በጎኗ፣ ከዚያም በጭንቅላቷ አቆማት።
«አምላኬ!» አለች፣ ካርለት መኪና የሚያገለባብጠው ውኃ እነሱን ቢያገኝ እንዴት ብትንትናቸውን እንደሚያወጣቸው እያሰበች።

ዛፉ «ቋ..ቀሽ.."ቀሽቀሽ...» ይላል፤ ግንድና ቅጠሉ ብቅ–ጥልቅ ይጫወታሉ፤ ውኃው፣ ሣር ቅጠሉን ያግበሰብሳል" መኪናዋ ጎማዋ ሲታይ ቆይታ በጎኗ ተጋደመች። ደራሽ የውኃ ሙላቱ ግን ለማንም
በሚያስገርም ሁኔታ እየቀነሰ፣ እየቀነሰ መጣና ጸጥ አለ። ካርለትና
ከሎ መኪናዋን ማውጣት ባለመቻላቸው፣ በየቦታው የተገነደሰውንም
ግንድ ለብቻቸው ማነቃነቅ የማይሞከር በመሆኑ፣ የሻንቆን መንደር
ኗሪ በእግር ሄደው ጠርተው፣ በስንት ችግር መኪናዋን ሊያወጡ
ቻሉ" ስለዚህ፣ ሐመር ላይ ዝናብ ሲዘንብ ከስኬ ሰው፣ ከብት፣ መኪና ሳይቀር ስለሚወስድና ስለሚያሰምጥ ምሱን አያጣም፤ ከብቱን፣ አራዊቱን፣ ሰውን...ድንገት ጠልፎ በመዋጥ የቆየ ልምድ አለው። ካርለትና ከሎ በቆይታቸው የተለያዩ ዕጽዋትንና ጥቅማቸውንም ተረድተዋል። ወንዴና ሴቴ ቃጫ ለገመድና ቤት ሥራ፣
ጠዬ ለዱላ፣ ሌልሜ ለቤት ሥራ፣ ፌጦ ለመፋቂያ፣፣ ኩንኩሮ ለተለያየ ጥቅም፣ ፊላና ሰንበሌጥ ለቤት ሥራ እንደሚውሉ ተረድተዋል።
በተረፈ ጨው ሊንባ፣ እንኮይ፣ ዘምባባ፣ አጋም፣ ጨዋንዛ፣ ግራር
ወዘተ የሐመርንና የአጐራባቾችን መሬቶች አስውበው ሲመለከቱ፣
ከመንፈስ እርካታው በተጨማሪ አንዳንዶቹን መጠቀም ችለዋል።
ካርለትና ከሎ ሻንቆ፣ ላላ፣ ወሮ፣ ዴንባይቴ፣ ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዴ...መንደሮች ሲዘዋወሩ ከማኅበረሰቡ
አባላት ጋር ከሚገናኙበት አንዱ ሸፈሮ ቡና (የቡና ገለባ) የሚፈላበት
ወቅት ነው። የሐመር ቡና የሚፈላው በጀበና ሳይሆን በትልቅ እንስራ ነው ቡናው የሚጠጣው ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ ረፋዱ ድረስ
ሲሆን፣ ያደረሰው ሁሉ መጠጣት ይችላል። አንድ ጊዜ ታዲያ፣ ካርለትና ከሎ ሻንቆ መንደር ለመጀመሪያ
ጊዜ ቡና ሊጠጡ ሄደው፣ ኦይጊ የተባለችው የመንደሩ ኗሪ ቤቷ ለመጡት እንግዶች በሾርቃ ከትልቅ ቅል ላይ በተከፈለ መጠጫ
ለሁሉም እንግዳ ስታድል፣ ለሁለቱም ሰጠቻቸው" ካርለት አንዱን
ሾርቃ እንደምንም ጨርሳ ‹ተገላገልኩ› ብላ፣ ሾርቃውን ለአይጊ አቀበለቻት በሐመር ባህል ሾርቃውን ቡናውን ለምትቀዳው ካቀበሉ
ድገሚኝ እንደማለት በመሆኑ፣ ኦይጊ ቡናውን በሾርቃ ሞልታ ለካርለት ሰጠቻት፤ «አምላኬ!» አለች ካርለት የመጀመሪያው ቋቅ
ሊላት ደርሶ፣ ሁለተኛውን ስታስታቅፋት።

ካርለት፣ ቡናውን መጠጣት ከበዳት። ቁጭ አድርጋ ትታ
እንዳትሄድ፣ ባህሉን መናቅ እንዳይሆንባት ሠግታ ስትጨነቅ ቡናውን
በያዘው ሾርቃ ላይ ዝንቦች እየገቡ ተንሳፈፉ። ካርለት፣ «ጥሩ አጋጣሚ» ብላ፣ እየሣቀች፣ «ዝንብ ገባበት» በላቸው አለችው ከሎን!
«ድፊው» ይሉኛል ብላ። እነሱ ግን፣ «ጠጭው ምንም አይልሽም፣
ይሄ የወተት እንጂ፣ የቆሻሻ ዝንብ አይደለም» አሏት። ካርለት፣ ሌላ አማራጭ ስላልነበራት የሚንሳፈፉትን ዝንቦች «እፍ» እያለች
ቡናውን ጠጥታ ጨረሰች።

ካርለት በሐመር ኑሮዋ በጣም የከበዳት ችግሯ ግን የሐመሮች የጊዜ ዕውቀት አለመኖር ነው። ካለፕሮግራሟ በተለይ በገበያ ቀን ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ቀይአፈርና ጂንካ በመኪናዋ እንድትወስዳቸው
ይጠይቋትና መኪናዋ ውስጥ ዱቄት፣ ፍየል፣ በግ፣አረቄ፣ ማርና ቅቤ
ሰለሚጭኑ ሁሌ ትሳቀቃለች" አንዳንዴም አፍ አውጥታ! «አልሄድም» ትላለች።

ካርለት ምግብ፣ ደብዳቤ፣ መጽሔት፣ ከቤተሰብ ጋር የስልክ ግንኙነት ለማድረግ አዲሳባ ስትሄድም በጕዞው ከሎ ሆራ መኪና
ማሽከርከር ቢረዳትም ወንዝ እየሞላ፣ ጭቃ ሲይዛቸው ትማረራለች።

ካርለትና ከሎ ወደ አዲሳባ ሲሄዱ አልፎ አልፎ የሚላኩት መልእክት የተወሰነ ሲሆን አቡጀዲ፣ የላስቲክ ጫማ፣ ሸፈሮ ቡና
ሽጉጥ መሳይ መድኃኒት «ቴትራሳይክሊን ወይም ክሎሮፌኒኮል”ዋነኞቹ ናቸው"

ካርለት ሐመር ሦስት ወር ቆይታ አዲሳባ እንደሄደች፣ ከስቲቭ ጋር ተገናኙ። ስለ ሐመር ሕይወቷ፣ ስላየቻቸው ነገሮች፣ ስላጋጠማት ችግርና ስለ ወሰደችው የመፍትሔ እርምጃ አጫወተችው
ስቲቭ ከነገረችው ሌላ፣ ካርለት አንገቷና እጇ ላይ ያለውን ነገር ከማየቱም ባሻገር፣ ሳታቋርጥ ስታክ ተመለከታት» ከዚያም፣ «የኔ
ፍቅር፣ ይህን ያህል ለምን ራስሽን ለችግር ታጋልጫለሽ?» አላት
ስቲቭ"

«ችግር ስትል ምን ማለትህ ነው?»

«ይህ ደረሰብኝ እያልሽ ያወራሽኝ ሁሉኮ ጋሪ ላይ የተጫነ ጭነት ሳይሆን፣ አንች የተሸከምሽው ችግር ነው?» አላት"

«ስቲቭ፣ አንድ ሰው የምኖረው ትርጕም ያለው ሥራ ለመሥራት ነው ካለ፣ ሕይወቱም ትርጕም ያለው ይሆናል" ሌላው ደግሞ
(ምኖረው ለመሞት ነው› ካለ በውስጡ እውነትነት አለው” ሕይወቱ ግን፣ ትርጕም አልባ ይሆንበታል"

«ማንኛውም አጋጣሚ በየግላችን አእምሮ አመዛዝነን፣ መክረን፣
እናወጣ እናወርደዋለን፣ ቀጥሎ ጥሩ ወይም መጥፎ ትርጕም እንሰጥና ተግባሩ ላይ ያን አጋጣሚ እንጠላዋለን ወይም እንወደዋለን።

«አንዱ መኖርን ጥሩ ሥራ ለመሥራት እንደሆነ ተረድቶ ሲጥርI ሌላው ደግሞ መኖሩ ለመሞት መሆኑን አውቆ ተስፋው ይኰሰምናል"
👍25🥰2
«እኔም፣ ገጠመኜን ማውራቴ ለአንተ ፍርሃትን ሲፈጥርብህ፣ለእኔ ግን ፍቅር ስላሳደረብኝ፣ አብሬያቸው መኖሩን እመርጣለሁ»አለችውና ዝም ብላ ቆይታ፣ «አየህ ስቲቭ፣ ከርቀት ጠቦ የሚታይህ ድልድይ፣ ስትደርስበት ግን ሰፊ ነው» ብላ ጉንጩን ቆንጠጥ
አድርጋ፣ ከከሎ ጋር ጕዞዋን ቀጠለች"...
«በአባቴ ቆዳ ላይ ተኝተህ፣ ኩርኩፋህን እየበላህ፣ ሸፈሮ ቡናህ እየጠጣህ፣ ቀና ብለህ የቦርጆን (የአምላክን) ከዋክብት ተመልከት
አሸጋግረህ የሐመር ተራራዎችን ቃኝ በእበትና አፈር እያጌጥክ
የባንኪሞሮን ንቦች እየተንከባከብክ፣ ማሩን ብላ የአበቦችን መዓዛ
አሽትት"

«ጠላቶቻችን ከተራራው ግርጌ ናቸው" የአባቴ አጥንት ስለ ወጋቸው፣ ጠረኑ ስለሚያስበረግጋቸው፣ አይመጡብህም ሾልከው
ከገቡ ግን እበቴን ተቀብቼ፣ ንቤን በብብቴ ይዤ፣ ሁለት አፍ ጦሬ በመያዝ፣ አንተን አስከትዬ እሄድላቸዋለሁ የሀገሬ አዕዋፍ አውሬ፣ ያኔ ይጠግባሉ"

«ፀሐይ ከወደቀችበት ነገ ትነሣለች ጨረቃን ገፍትራ ጥላ ቦታዋን እስክትይዝ ግን ታጋሽ ሁን ጨለማን ተገን አድርገህ ተንኮል
አትሥራ» ከስኬ ከአሸዋ በላይ እስኪሞላ፣ የሰማይ ውኃን እየጠበቅህ
ጓሮህን እንድትቆፍር ልጃገረድህን እዘዝ"

«እጅህንና እግርህን በምላስህ እሠር የአባቴን ደንብና ባህል አክብር የታላላቆችህን ትእዛዝ ተቀበል ለጠላቶችህ የማትፈራ ወፍ በጥይት የምታስቀር፣ ጀግና ሁን። ካለበለዚያ፣ የአባቴን ደንብ
ሽረሃልና ደረቴን አስጌጥብሃለሁ (እገድልሃለሁ)።
«ተጫወት፣ በአባትህ ሜዳና ተራራ ተዘዋወር ከልጃገረዶ ጋር ዝለል ወተትና ደም ጠጣ ውለድ ከብትህን በበረት ሙላ
...የኔ ልጅ ጨርሻለሁ» ብለው የሚጠጡትን ሸፈሮ ቡና «ፕስስ...» እያሉ፣ በአራቱም ማዕዘን ያማትቡና የልጃቸውን ራስ
ዝቅ አድርገው የሸፈሮ ቡናውን ውኃ፣ «ፕስስ…» እያሉ ያርhፈክፉበታል።
ደልቲ ገልዲ፣ አባቱ ገና ከመሞታቸው በፊት ምርቃታቸውንና
አደራቸውን በገሐድ አሳያቸው ለምሳሌ ደልቲ ገልዲ ማጎ በረሃ
ከጓደኞቹ ጋር ወርዶ ካለምንም ስንቅ ለተወሰነ ጊዜ በረሃብ ቢሠቃይም፣ ከዚያ በኋላ ግን ሚዳቋም፣ ውድንቢትም፣ ድኩላም፣
እየገደሉ፤ ቋንጣውን በፀሐይ በማድረቅ እየተመገቡ ታላላቅ አራዊት
ሊገኝበት ከሚችልበት አካባቢ በመዘዋወር ሰንብተው፣ አንድ ቀን
ከማጎ ወንዝ ውስጥ ተነከረው እንዳሉ የአራዊት ዳና ሰሙ እየሮጡ በመውጣት ድምፁን ከሰሙበት አቅጣጫ በተቃራኒ ካለው ጫካ ውስጥ አደፈጡ" ሆኖም ግን፣ መሣሪያቸው ወዲያ ማዶ በመሆኑ ሲመኙት የነበረው ዕድል አመለጣቸው" የመጣው የጎሽ መንጋ ካለብዙ ችግር፣ እርስ በርስ እየተጠባበቀ በመጣበት አቅጣጫ
ሄዶ ተሠወረባቸው"

ደልቲም ሆነ ሌሎች ጓደኞቹ ወደ አደን ከመምጣታቸው በፊት ብዙ የአራዊት ጠባይ ተነግሯቸዋል" ጎሽ ከቈሰለ፣ የአቈሰለውን ሰው
እንደማይለቅ  ያንን ሰው ባያገኘው እንኳን ዝንብ ቈስሉን እየበላ እንዳያስቸግረው ከወንዝ ውስጥ እየገባ እንደሚያደፍጥና ሌላ ሰው
ካገኘ ብጥስጥሱን በእልክ እንደሚያወጣው ሰምተዋል" ስለሆነም፣
ጎሽን ለመግደል ብልቱን ለይቶ መምታት እንደሚያስፈልግ፣ በመንጋው ላይ ከመተኰስም፣ ከመንጋው የተለየውን መግደል እንደ
ሚሻል፣ ተመከረዋል"
ግታ ማታ አንበሳና ነብር እንዳይተናኰላቸውም እሳት ማቀጣጠል እንደሚገባና እሳቱ ብዙ ጭስ እንዳይኖረውና ጫካውንና
ኣውሬዎችን የሚጠብቁት ዘበኞች አደጋ እንዳያደርሱባቸው
እንዲጠነቀቁ እባብ በተለይም የጠገበ ዘንዶ፣ አንዳንዴ ግንድ መስሎ እንደሚጠቀለልና ድንገት ቁጭ ካሉበት ለአደጋ
እንዳይጋለጡም ተመክረዋል።

አቅጣጫ ጠፍቶባቸው በተለይ በውኃ ጥም እንዳይጠቁም ልምምድና ውኃ የማያስጠማ መፋቂያ
እንዲይዙና በጨረቃና በከዋክብት አቅጣጫ እንዲንቀሳቀሱ፣
ተነግሯቸዋል" በተለይ ደግሞ፣ ሲጓዙ በጋራና በዘዴ እንዲሆንና፥ በተናጠል እንዳይጓዙ፣ ችግር ሆኖ ከተጠፋፉም እንቅልፍ ለመተኛት ሲፈልጉ ከመጋደም ይልቅ ቁጭ ብለው አንገትን ወደ ታች በመቅበር እንዲተኙ ከብትም ሆነ ሰው ላይ ጥላው ሲያርፍ ወገብ የሚያጣምመው አሞሯ ሲበር ሲታይ መደበቅና ከጥላው መራቅ ማስፈለጉን የግድ የሚቀርብ ከሆነም ተኵሶ ማባረር የሚሻል መሆኑን ተመክረዋል" በተረፈ አራዊት ከጠፉ የጀግንነታቸው ማረጋገጫ
ስለማይኖር ሴትና ወንዱን መለየት ስለማይቻል ዕድል ቀናኝ ብለው በብዛት መግደልና ማስደንበርም እንዳይፈጽሙ አደራ ተብለዋል።

ስለዚህ፣ የጎሹ መንጋ ተመልሶ ሄዶ ከአካባቢያቸው መራቁን
አረጋግጠው ከተደበቁበት ብቅ ሊሉ ሲሉ፣ ሴትና ወንድ አንበሳ ወደ ውኃው ሲመጡ አዩ  ወዲያው ደንግጠው ተመልሰው ተደበቁ
በቁጥቋጦው ውስጥ ከርቀት ሲመለከቱ ደግሞ፣ ግንድና ቅጠሉ ሲርመሰመስ ተመለከቱ" ከዚያ አንበሶቹ እነሱ ወደ ተደበቁበት አቅጣጫ ሲመጡ፣ ሁሉም ወሽመጣቸው ተበጠሰ። ባዶ እጅ ከአንበሳ
ጋር መግጠም መቼም አይቻልም" ያውም ከሁለት አንበሳ" አንበሶቹ
ከኋላ ግንድና ቅጠሉን እያተረማመሱ የሚመጣውን አውሬ በጥርጣሬ እያዩ ስለሚሸሹ ደግነቱ እነሱን ፈርተው የሚንቀጠቀጡት
አላስተዋሉም። ስለዚህ፣ መንገዳቸውን ቀጠሉ።

ግንድና ቅጠሉ በሚሰባበርበትና በሚንሿሿበት አቅጣጫ
ሲመለከቱም፣ ለቍጥር የሚታክት ዝሆን ተመለከቱ" ስለ ዝሆን ደግሞ የሰሙት አለ" ዝሆን ከፍተኛ የማሽተት ችሎታ አለው" እስከ ብዙ ርቀት ጠረን ማሽተት ይችላል" ምናልባት ደግነቱ ነፋሱ ወደነሱ
አቅጣ ስለሆነ ጠረናቸው ላይደርሰው ይችላል" እንሽሽም ተባብለው ነበር" ግን፣ ከዚህ የዝሆን ረገጣና ወገራ ቢያልፉ፣ ከዚያ
ደግሞ የአንበሳ ክንድና የጎሽ ቀንድ ይጠብቃቸዋል" ሁሉም ያው እንዳቅሙ ሰባብሮ፣ መጨረሻው ሞት ነው" ስለዚህ መሸሹ
እንደማያዋጣ አመኑ።

የዝሆን መንጋው በኩንቢው ውኃውን ሰውነቱ ላይ እየረጨ! ውኃው ውስጥ ለብዙ ሰዓት ቆየ" አንድ ዝሆን እንዲያውም፣ ድንጋይ
ተደግፎ የተቀመጠውን ምንሽር ጠመንጃ ወደ ላይ በኩንቢው አንሥቶ አይቶ መልሶ አስቀመጠው የሱ ማደኛ መሆኑን ቢያውቅ
ኖሮ ወደ አመድነት ይለውጠው ነበርI ነገር ግን አላወቀም። ስለዚህ
ጠላቱን አንሥቶ መልሶ አስቀመጠው"
ደልቲና ጓደኞቹ ይህንና ይህን የመሳሰለውን ችግርና አደጋ በማኅበረሰባቸው የሚያገኙት የጀግንነት ክብርና ሙገሳ፣ ልብን
ያማልላል" ከወንድነት ማረጋገጫውም ውስጥ ዋናው በጠላትነት
የሚያዩትን የማኅበረሰብ አባል መግደል ሲሆን ከዚያ የሚቀጥለው ደግሞ አውራሪስ፣ ዝሆን፣ አንበሳ፣ ጎሽ፣ ቀጭኔ መግደሉ ነው።

በሌላ ቀን ደልቲ ገልዲና ጓደኞቹ አደናቸውን እንደ ጀመሩ፣ከመንጋ የተለዩ ጎሾችን ተመለከቱ" ሁሉም በየተራ እያነጣጠሩ ተኮሱ የቀሩት ጎሾች ሲሸሹ፣ ሦስት ጓደኞቹ ብቻ ሦስት ጎሽ ገደሉ።ከነዚያ ውስጥ ደግሞ የመጀመሪያው ገዳይ ደልቲ ገልዲ ሆነ።
የገደሉት፣ ባልገደሉት ላይ ጀግንነት ተሰማቸው አቅራሩ ፎከሩ።

ለአደን በሄዱ በሦስተኛው ሳምንታቸው ደግሞ ከርቀት የቀጭኔ መንጋ ተመለከቱ፣ ቀጭኔ ከርቀት ማየት ስለሚችል እንዲህ በዋዛ
ማደን ስለማይቻል እምብዛም ተስፋ አጡ" ገልዲ ግን፣ በየት እንደሄደ ጓደኞቹ እንኳ ሳያዩት ከቀጭኔዎቹ እይታ ውጭ በመሆን ሥራቸው ድረስ መጠጋት በመቻሉ፣ በምንሽር ጠመንጃው አንዱን ቀጭኔ በሁለት ጥይት ወርቹን በጥሶ አንበረከከው። ጓደኞቹ ሲመጡ ከቀጭኔው ጀርባ ላይ ወጥቶ ጠበቃቸው።
👍193🥰1
ደልቲ ገልዲ፣ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የጎሽና የቀጭኔ ገዳይ ሆነ። ወደ መንደራቸው ሲመለሱም የመንደሩ ልጃገረዶች
ለገዳዮቹ፣ በተለይም ለጎሽና ቀጭኔ ገዳዩ፣ ጨሌያቸውን በአንገቱ አጠለቁለት" በየዘመዶቹም እያቅራራና እየፎከረ ሲሄድ በግና
ፍየላቸውን እያረዱ፣ ጀርባው ላይ ደሙን አፈሰሱለት" ለወራት ያህል ምግቡ ደምና ወተት፣ ሥጋና ማር ሆነ" በዚህ ደግሞ፣ አባቱ
ልጃቸው እሳቸው እንኳን ያልቀናቸውን የጎሽና ቀጭኔ ገዳይ በመሆኑ ኮሩበት"
ብዙም ሳይቆይ ደልቲ ገልዲ በሐመርና በሙርሲ ማኅበረሰቦች መካከል በተፈጠረው ግጭትና ጦርነት እንደ ጉርኑክ እየዘለለ በመዋጋት፣ሁለት ሙርሲ ገድሎ መሣሪያቸውን በመማረኩ፣
ደረቱን በመተልተል፣ ራሱን በቀይና በነጭ አኖ አፈር በማስጌጥ፣በአንገቱ ከደረደረው ጨሌና በእጆቹ ካጠለቃቸው አንባሮች ሌላ
በወገቡ በታጠቀው ዝናርና መያዣዋ በሚያንጸባርቀው ቤልጅግ ጠመንጃ ከአካባቢው ኗሪ ልዩ ክብር ተጎናፀፈ የመንደሩ ልጃገረዶ ቀርቶ ከመንደሩ ራቅ ያሉትም ልጃገረዶች ሳይቀሩ በዝናው በቁመናው በመመሰጥ፣ የመጀመሪያውን እፍታ በየጫካው አጐረፉለት። ከሙርሲ ማኅበረሰብ በዘረፋቸው ከብቶችም መሣሪያ ገዛና በረቱን በከብት ሞላ። ሁለት ሚስት አግብቶ፣ የአባቱን ምኞትም
አሟላ። አባቱም ምንም እንኳን ከዳሰነች ማኅበረሰብ ጋር በተደረገው ጦርነት ቢሞቱም፣ የአባቱ ደም መላሽ ለመሆን ቻለ።

ደልቲ ገልዲ ስሙ እየገነነ ሲሄድ፣ የእሱም ልብ እያበጠ ሄደ።መቼም ሲመጣ በላይ በላይ ነውና፣ የላላና ሻንቆን መንደር ሰዎች ከብት እየሰበረ ያስቸገረ አንበሳ ለማደን ሁሉም በቡድን በቡድን ጫካ ሲገባ፣ እሱ ግን፣ «በእኔ በኩል ብቻዬን እበቃለሁ» ብሎ፣ ከነመሣሪ
ያው ለአደን ተሰማራ" ሁሉም ቦርጆን (አምላክን) እየተማፀነ፣ የአንበሳው ገዳይ ሆኖ እንደ አባያ በሬ ለመንጐማለል ሲመኝ
ፍለጋው ሲጧጧፍ ውሎ የጥይት ተኲስ ተሰማ፤ ወዲያው አንበሳው
ተገደለ ተባለና ገዳዩ ማን እንደሆነ አንዱ ሌላውን ሲጠይቅ፣ «ደልቲ
ገልዲ፣ የተኛ አንበሳ አልገድልም ብሎ ‹ጎፈር) ብሎ ቀስቅሶ አስነሥቶ፣ አጓርቶ ወደ እሱ ሲዘልበት በሚያስደንቅ ፍጥነት
መሣሪያውን አቀባብሎ፣ በሁለት ጥይት፣ ልሳኑን ዘጋው» ተባለ"
ልጃገረዶች፣ «ይኸዋ አላልኩሽም!» ሲባባሉ፣ «ኧረ እሱ ምኑ ነው ይሄን ያህል!» እያሉ ያናንቁ የነበሩት ጐረምሶች እንኳን
ሳይቀሩ፣ አንገታቸውን ደፉለት እረኞች፣ ልጃገረዶች በስሙ ዘፈኑለት፣ ሌላው ቀርቶ የመፎከሪያ በሬው ከሌሎች ከብቶች በልጦ
ተንጐማለለ" ደልቲ ገልዲ፣ ከግዙፉ የቡስካ ተራራ ይበልጥ ገዝፎ መታየት ጀመረ" በዚህ ሰሞን ነበር ሁለት እንግዶች ወደ
መንደራቸው የዘለቁት።....

💫ይቀጥላል💫
👍23
#ምንሊክ_ኬኛ

መቋጫ ለሌለው
ጀማው ከሚታገል
አፄው ኬኛ በሉ
ሀገር ትገላገል።
29👎25👍8👏8
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወጀቡ እስኪጠፋ ወለሉ ላይ ተቃቅፈው ቆዩና ‹‹መርቪን አልጋው ላይ
እንውጣ ከወለሉ ይልቅ እዚያ ይመቸናል›› አለ፡
ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ከዚያም በጉልበቷ እየዳኸች
አልጋው ላይ ወጣች፡፡ መርቪንም ተከተላትና አልጋው ላይ አብሯት ወጣ፡፡
እሱም እቅፍ አድርጎ ያዛት፡፡
በወጀቡ ምክንያት አይሮፕላኑ በተናወጠ ቁጥር ልክ መርከበኛ የጀልባ
ውን ምሰሶ እንደሚይዝ ሁሉ ናንሲ መርቪንን ጭምቅ አድርጋ ትይዛለች፡፡
ወጀቡ ሲቀንስና ዘና ስትል እሱም ሰውነቷን በፍቅር ይነካካቸዋል ከዚያ ትንሽ ቆየችና እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡.
በሩ ተቆርቁሮ «አስተናጋጅ መቷል» የሚል ድምፅ ስትሰማ ከእንቅልፏ ነቃች።
ዓይኖቿን ስትከፍታቸው መርቪን ደረት ላይ መተኛቷን አወቀች
‹ወይ አምላኬ! አለች እየተርበተበተች፡

መርቪን ከተኛችበት እንድትነሳ በእጁ ገፋ አደረጋትና ‹‹ትንሽ ጠብቀን
አስተናጋጅ›› አለ፡፡

ከበሩ ውጭ የቆመው አስተናጋጅ በተደናገጠ ድምፅ እሺ ጌታዬ
እጠብቃለሁ›› አለ፡፡

መርቪን ከአልጋው ወረደና በአልጋ ልብስ ናንሲን ሸፈናት::

በዚህ አድራጎቱ በሆዷ አመሰገነችው፡፡ አስተናጋጁ እንዳያያት ፊቷን ወደ ግድግዳው አዞረች፡፡

መርቪን በሩን ሲከፍት አስተናጋጁ ገባና ‹‹እንዴት አደራችሁ›› አለ በፈገግታ፡፡

የትኩስ ቡና መዓዛ ናንሲን አወዳት፡፡ ‹‹በእንግሊዝ የሰዓት አቆጣጠር
የሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ነው ማለት ነው?›› አለ አስተናጋጁን

‹‹ልክ ነው ጌታዬ የኒውፋውንድ ላንድ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች
የሰዓት አቆጣጠር  ሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ይዘገያል፡››

‹‹መቼም የአየር መንገዶችን የጉዞ መርሃ ግብር ለሚያዘጋጁ ሰዎች ይህ  የሰዓት አቆጣጠር  ችግር
ሳይፈጥርባቸው አይቀርም፡፡ ባህር ላይ ለማረፍ ምን
ያህል ሰዓት ይቀረናል?›› ሲል ጠየቀ መርቪን

‹‹ከግማሽ ሰዓት በኋላ እናርፋለን፡ ከመርሃ ግብሩ አንድ ሰዓት ጉዟችን
የዘገየው በወጀቡ ምክንያት ነው›› አለና አስተናጋጁ በሩን ዘግቶ ወጣ፡

ናንሲ በሩ ከተዘጋ በኋላ ‹የመስኮቱን መጋረጃ ክፈተው፡ ነግቷል››
አለችው:፡ መርቪን ቡና ሲቀዳ የትናንት ምሽት አዳራቸው ፊቱ ላይ መጥቶ
ድቅን አለ፡፡ ወጀቡ በተነሳ ቁጥር መርቪን እጇን የሚይዛት፣ ወለሉ ላይ
የሚወድቁት፣ የመርቪን እጆች ጡቶቿን ሲጨብጥ፣ አይሮፕላኑ ሲናወጥ፣
እሱ ደረት ላይ ልጥፍ የምትለውና እየደባበሰ የሚያስተኛት ትዝ አላት:
ይህን ሰው በጣም ወድጄዋለሁ› አለች በሆዷ።

‹‹ቡና እንደወረደ ወይስ ከወተት ጋር ነው የምትፈልጊው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡

‹‹ጥቁር ቡና ይሁንልኝ፡ ስኳር አልፈልግም››
‹‹እንደ እኔ›› አለና ቡናዋን አቀበላት ናንሲ አመስግና ቡናዋን ጠጣች፡፡

ናንሲ ስለ መርቪን በደንብ ማወቅ ፈለገች፡፡ ቡናውን እየጠጣ ስለእሱ ልማዶች ግምቷን አስቀመጠች፡፡ ቴኒስ ይጫወታል፣ ልብ ወለድ ብዙ ማንበብ አይወድም፣ ገበያ መሄድም እንደዚሁ፣ ቁማር ጨዋታ የሚሳካለት ይመስላል፣ ዳንስ ግን የሚችል አይመስልም፡፡›
‹‹ምንድን ነው የምታውጠነጥኚው?›› ሲል
ጠየቀ ለሕይወት  ኢንሹራንስ አደገኛ እንደሆንኩ አድርገሽ የምታይኝ መሰለኝ፡፡››

ናንሲ ቀልዱ አሳቃት፡፡ ‹‹ምን አይነት ሙዚቃ ነው የምትወደው?›› ለሙዚቃ ጆሮ አልሰጥም›› አለ ‹‹መደነስ ባልጠላም ጥሩ ደናሽ ግን አይደለሁም፡፡ አንቺስ?››

እኔ ድሮ ደንሼያለሁ፡መደነስም ነበረብኝ፡፡ እሁድ እሁድ ሱፍ ከሚለብሱ ወንዶች ልጆች ጋር በዳንስ ትምህርት ቤት ዳንስ እማር ነበር፡፡ከላይኛው መደብ የቦስተን ማህበረሰቦች ጋር ለመግባባት ብቸኛው መንገድ ይህ ብቻ እንደሆነ እናቴ ትነግረኝ ነበር፡ እኔ ግን ከዛ ማህበረሰብ ውስጥ
ብገባ ባልገባ ግድ አልነበረኝም፡: የኔ ቀልብ ያለው ከአባቴ ፋብሪካ ጋር ነው፡፡ እናቴ ደግሞ ይሄን ባህሪዬን አትወደውም ነበር፡››

ሁለቱ አዲስ ፍቅረኛሞች ተያዩ፡፡ መርቪንም ትናንት ማታ እንዴት ሲላፉና ሲላላሱ እንዳመሹ እንደሚያስብ ነቃችበት፡፡ ይህም ሀሳብ እፍረት
ውስጥ ከተታትና ፊቷን ወደ መስኮቱ ስታዞር መሬት ታያት፡፡ አይሮፕላኑ
ቦትውድ ሲያርፍ ህይወቷን የሚለውጠውን የስልክ ጥሪ ማድረግ እንዳለባት ትዝ አላት፡ ‹‹ደርሰናል›› አለችና ከመኝታዋ ዘላ ተነሳች ‹‹ልብሴን ልልበስ›› አለች፡፡
‹‹እኔ ቀድሜ ልውጣ›› አለ መርቪን ‹‹ለአንቺ ጥሩ ነው››
እሺ፧ አሁንስ ምን ቀልብ አለኝ አለች በሀሳቧ። ይህን ለእሱ አልነገረችውም፡፡ መርቪን ልብሱን ስበሰበ፡፡ በሩን ከፍቶ ሊወጣ ሲል
ተጠራጠረና ቆመ፡፡ እሷም እንደገና ሊስማት እንደፈለገ አውቃ ወደ እሱ ሄደችና ከንፈሯን ሰጠችው፡፡ ‹‹ሌሊቱን በሙሉ እቅፍ አድርገህ ስላስተኛኸኝ
አመሰግንሃለሁ›› አለችው:

መርቪን ከአንገቱ ዝቅ አለና ሳማት፡፡ አሳሳሙ ልስልስ ያለ ነበር፡ አፏን በአፉ ግጥም አድርጎ ነው የሳማት፡፡ እየተሳሳሙ ትንሽ ቆዩና ተላቀቁ፡፡

ናንሲ በሩን ከፍታ ያዘችለትና ወጥቶ ሄደ፡፡

በሩን እንደዘጋች የደስታ ሲቃ ተናነቃት፡ ከዚህ ሰው ፍቅር ሊይዘኝ ነው አለች፡ በመስኮቱ ስታማትር አይሮፕላኑ ቀስ በቀስ እየወረደ ነው፡፡

መፍጠን አለባት፡፡

መስታወቱ ፊት ቆማ ፀጉሯን ቶሎ አሰረችና የመዋቢያ ዕቃዎቿን ይዛ የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ሴቶች መታጠቢያ ቤት ሄደች፡፡እዚያ ሉሉ ቤልንና አንድ ሌላ ሴት አገኘች፡፡ የመርቪን ሚስት ግን የለችም:

ናንሲ ፊቷን እየታጠበች ጧት ከመርቪን ጋር ያደረገችውን ውይይት
አስታወሰች፡፡ እሱን ስታስብ ደስታ ቢሰማትም ደስታው የተሟላ ባለመሆኑ
ከጭንቀት ሊገላግላት አልቻለም፡፡ ስለሚስቱ ምንም አላለም፡፡ ትናንት ማታ ስለእሷ ስትጠይቀው ድንግርግር እንዳለው ነው የነገራት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ይወዳት ይሆን? ትናንት ማታ ሌሊቱን ሙሉ ደረቱ ላይ ለጥፎ ነው ያሳደራት ይህ ብቻውን ጋብቻን ይፍቃል ማለት ግን አይደለም፡
እኔ የምፈልገው ምንድን ነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ‹መርቪንን እንደገና ማግኘት እፈልጋለሁ ከእሱ ጋር ድብቅ ወዳጅነት  ልመስርት?ታዲያ ለኔ ብሎ ጋብቻውን እንዲያፈርስ እፈልጋለሁ? ከአንድ  ሌሊት
ወሲባዊ ልፊያና መሳሳም በኋላ ይህን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
ሊፕስቲክ ለመቀባት መስታወቱ ላይ አፈጠጠች ናንሲ መጠራጠርሽን አቁሚ
ስትል ለራሷ አሳሰበች እውነታውን ታውቂዋለሽ፤ ይሄን ሰው በጣም ፈልገሽዋል፧ ከአስር ዓመት ወዲህ እጅሽን የሰጠሸው ለዚህ ሰው ነው፡:
አሁን አርባ አመትሽን ደፍነሻል፡ አሁን ተገቢውን ሰው አግኝተሻል፡ እዚህ
እዚያ መርገጥሽን ትተሽ ይህን ሰው በእጅሽ አድርጊ፡፡›

ሰውነቷ ላይ ሽቶ አርከፈከፈችና ወጣች፡

ስትወጣ ከመታጠቢያ ቤቱ አጠገብ የተቀመጡትን ናት ሪጅዌይና ወንድሟን ፒተርን አገኘቻቸው ናት ‹‹ደህና አደርሽ ናንሲ›› አላት::

ይህን ስትሰማ ከአምስት ዓመት በፊት በዚህ ሰው የነበራትን ስሜት
አስታወሳት፡፡ እኔ ከእሱ ፍቅር ይዞኝ ነበር፡፡ እሱ ግን ከእኔ ይልቅ የፈለገው
ብላክ ቡትስ ኩባንያን ነበር፡፡ አሁንም ኩባንያውን በእጁ ለማስገባት
የሚፈልገውን ያህል እኔን አይፈልገኝም፡፡ ለሰላምታው በራስ ንቅናቄ ብቻ
አፀፋዊ ሰላምታ ሰጥታው ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡

አስተናጋጆቹ መኝታዎቹን ወደ ሶፋነት ለውጠዋቸዋል። መርቪን ጢሙን ተላጭቶና በነጭ ሽሚዝ ላይ ሱፍ ልብሱን ለብሶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ‹‹በመስኮት ተመልከች ደርሰናል›› አላት፡፡
👍19
ናንሲ ወደ ውጭ ስትመለከት መሬት አየች፡፡ እታች ደን የለበሰ መሬትና ወንዝ ይታያል፡፡ ትንሽ ራቅ ብሎ ወደቡና ከእንጨት የተሰሩ ቤቶችና ቤተክርሰቲያን አየች፡፡
አይሮፕላኑ በፍጥነት ወደ መሬት ወረደ፡ ናንሲና መርቪን ሶፋው ላይ
እጃቸውን አቆላልፈውና የመቀመጫ ቀበቷቸውን አስረው ተቀምጠዋል
የሰማይ በራሪው ጀልባ ባህሩ ላይ ሲያርፍ መስታወቶቹ ላይ የውሃ
ፍንጥቅጣቂ ሲረጭ አዩ፡፡

‹‹አትላንቲክን አቋርጠናል›› አለች፡፡

ግማሹን ጉዞ ያሳለፈችው ስለ ፋብሪካው ስታስብ ሲሆን ቀሪው ግማሽ
ደግሞ ያለፈው የሰው ባል እጅ ይዛ ነው፡፡ የአየር ጠባዩ መጥፎ ስለነበር ያሳለፈችው ጉዞ አስፈሪ እንደነበር አስታወሰች፡፡ ለልጆቿ ምን ልትላቸው ነው? ሁሉንም ነገር ንገሪኝ ሊሏት ይችላሉ፡ አይሮፕላኑ በሰዓት ስንት
ማይል መብረር እንደሚችል እንኳን አታውቅም እንዲህ አይነቱን መረጃ ኒውዮርክ ከመድረሳቸው በፊት ታጣራለች፡፡
የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ላይ ደርሶ ሲቆም አንድ ወደ መሬት
የሚወስዳቸው ጀልባ ወደ እነሱ መጣ፡፡ ናንሲ ኮቷን ስትይዝ መርቪን ደግሞ
ከቆዳ የተሰራውን
የአብራሪዎች ጃኬት ለበሰ፡፡ ገሚሱ ተሳፋሪዎች
ከአይሮፕላኑ ወጥተው እግራቸውን ለማፍታታት ሲወስኑ ገሚሶቹ ግን
አልጋቸው ላይ እንቅልፋቸውን እየለጠጡ ነው፡፡

hአይሮፕላኑ ወጡና ጀልባ ላይ ተሳፈሩ፡ አየሩ በባህርና በግንድ ሽታ ታውዷል አጠገባቸው የእንጨት
መሰንጠቂያ ሳይኖር  አይቀርም፡፡አይሮፕላኑ ከቆመበት ወደብ ቀጥሎ ነዳጅ የሚሞሉ ሰራተኞች ቱታቸውን ለብሰው በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ ራቅ ብሎ ደግሞ ሁለት መርከቦች ይታያሉ፡፡

የመርቪን ሚስትና ፍቅረኛዋ ከአይሮፕላኑ ወጥተው ለመንሸራሸር ወስነዋል፡ ዳያና ናንሲ ላይ ብታፈጥም ናንሲ በዓይኗ ሙሉ ዳያናን ማየት አልተቻላትም  ምንም እንኳን ከዳያና የበለጠ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማት ባይችልም፡፡ በባሏ ላይ የሄደች ዳያና ራሷ እንጂ ናንሲ አይደለችም፡፡

ገና ማለዳ በመሆኑ ጥቂት ጎብኚዎች ናቸው የሚታዩት፡፡

ተሳፋሪዎች ከአይሮፕላኑ ወርደው ወደ አየር መንገዱ ህንጻ ሄዱና እንቅልፉን ላልጨረሰ ሰራተኛ ፓስፖርታቸውን አሳዩት

የተሳፋሪዎች መቆያ ክፍል ቢኖርም ተሳፋሪዎች መንደሪቷን በእግር
ለማካለል ፈለጉ፡
ናንሲ ቦስተን ካለው ጠበቃዋ ፓትሪክ ማክብራይድ ጋር ለመነጋገር በእጅጉ ጓጉታለች፡፡ ስልክ እንዳለ ለመጠየቅ ስትዘጋጅ የፓን አሜሪካን ዩኒፎርም የለበሰ ሰው ‹‹ስልክ ይፈልግዎታል የኔ እመቤት›› አላት።

የናንሲ ልብ ዘለለ ‹‹የት ነው ስልኩ?›› ስትል ጠየቀች፡

‹‹ከዚህ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ያስኬዳል››

‹‹አንድ ማይል!›› ንዴቷን መቆጣጠር አቃታት፡ ‹‹እንፍጠና ግንኙነት
ከመቋረጡ በፊት፡፡ መኪና አላችሁ?›› ስትል ጠየቀች፡፡
ሰውዬው ልክ የጠፈር መንኮራኩር የተጠየቀ ይመስል ድንግርግር
ሲለው ታዬ፡፡ ‹‹የለም የኔ እመቤት›

‹‹ስለዚህ በእግራችን እንሂድ በል መንገዱን ምራኝ›› አለች።

ናንሲና መርቪን መልእክተኛውን ተከትለው ነጎዱ፡፡ የእግረኛ መንገድ
የሌለው ጥርጊያ መንገድ ተከትለው በመሄድ ወደ ጋራው ወጡ፡፡ በየመንገዱ
በጎች ሳር ሲግጡ ይታያሉ፡ ናንሲ የብላክ ኩባንያ ያመረተው ጫማ ምስጋና
ይግባውና ተፍ ተፍ እያለች ትሄዳለች ነገ ማታ የብላክ ኩባንያ በእሷ ቁጥጥር ስር ይሆን? ይህን ማክብራይድ አሁን ያረጋግጥላታል፡ ከዚህ በላይ ከዘገየች በውጥረት መሞቷ ነው፡፡

ለአስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ አንድ ከእንጨት የተሰራ ቤት አገኙና ጥልቅ አሉ፡፡ ናንሲ ስልኩ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እጇ እየተንቀጠቀጠ የስልኩን እጀታ አነሳችና ‹‹ናንሲ ሌኔሃን ነኝ›› አለች፡፡

ይቀጥላል
👍16
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አምስት (35) በሆስፒታሉ ኮሪደር ውስጥ እየተጣደፈ ሲሄድ የጫማው ድምፅ ጎልቶ ይሰማ ነበር። ምን ብታስብ ነው ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመጣ ብቻየን ነው የምሄድ ብላ ድርቅ ያለችው ? ይህን ያህል አመት ስትኖር ረዳት አያስፈልገኝም ፤ሁሉንም ነገር ብቻየን ልወጣው እፈልጋለሁ የምትለው ለምንድነው ? ይህን እያሰበ በሩን አንኳኳ ። አንዲት በገጺ ላይ ምን ይፈልጋሉ ? የሚል ጥያቄ የተሳለባት ነርስ በሩን ከፈተችለት ። «ማሪዮን ሂልያርድ የተኛችው እዚህ ክፍል ነው ?» ሲል ጠየቃት ። በነርሷ ገፅታ ላይ የተሳለው ጥያቄ አልተነሳም ነበረና «ጆርጅ ኮሎዌ እባላለሁ» ሲል ጨመረ ። ድካም ፡ እርጅናና ያለመረጋጋት ስሜት በፊቱ ላይ ጎልተው ይታያሉ ። እነዚህ ስሜቶች በሠራ አካላቱ ተሰራጭተው ይሰሙትም ነበር ። የለም እንዲህ አይነቱ ርባና ቢስ ነገር አሁንስ ስልችት አለኝ ። ማሪዮን በዚሀ ሁኔታ ልትቀጥል አትችልም። ዛሬ ሁሉንም ግልጥልጥ አድርጌ መንገር አለብኝ ሲል አሰበ ። እንዳገኛት ይነግራታል ። ገና ከኒውዮርክ ከመነሳቱ በፊት ይህን ውሳኔ ለማይክል ሂልያርድም ነግሮታል ።

«ሚስተር ኮሎዌ ?» አለች ነርሷ ስሙን ስትሰማ በገዝፅዋ ላይ የተሳለው ጥያቄ ወደ ፈገግታ እየተለወጠ «ስንጠባበቅ ነበር » ማሪዮን እዚህ ሆስፒታል የገባችው ምሽቱ ላይ ፤አሥራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ጆርጅ ከኒውዮርክ ተነስቶ እዚያ የደረሰው ከምሽቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር ።ይሀ ደግሞ ከኒውዮርክ ሳንፍራንሲስኮ ለመድረስ የመጨረሻው ፈጣን ጉዞ ሳይሆን አይቀርም ። ነርሷን አልፎ ገባ። ማሪዮን የጆርጅን መምጣት አይታ ፈገግ ስትል ነርሷ ከክፍሉ ውስጥ ወጥታ ወደ ሠራተኞች ማረፊያ አዳራሽ ሄደች ።

«ሄሎ ጆርጅ »
«ሄሎ ማሪዮን ፤ ተሻለሽ ?»
«ከድካሙ በስተቀር አደጋውን አልፌዋለሁ ። ማለት ሀኪሞቹ የነገሩኝ እንዲያ ብለው ነው ። ኃይለኛ አልነበረም አያያዙ»
«ዛሬስ እንዲያ ሆነ ግን ለወደፊቱስ? ወደፊት›› ጀርጅ ይህን ተናግሮ በክፍሉ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲንጎራደድ እርምጃው ሁሉ የአንበሳ ይመስል ነበር። ቁጣውም ለማሪዮን ግፅል ሆኖ ታያት ። ይህን ያየችው ማሪዮን ሁኔታው አስገረማት። እንደሁልጊዜው አልሰማትም ።። ብዙ ነገር ሲነግራት አስቧል ማለት ነው ። «ለወደፊቱ ፣ ወደፊት ሲሆን ይታሰብበታል ። ላሁኑ አረፍ በልና ሰውነትህን ዘና አድርገው ። እኔን ጭምር እየረበሽከኝኮ ነው። የሚበላ ነገር ይቅረብልህ ? አንድ ሣንዱች እንዲያስቀምጡልህ ለነርሶቹ ነግሬአቸዋለሁ »
«መብላት አልችልም»
«አይ አሁን አበዛኸው ። ደሞ የምን አዲስ ጠባይ ነው? ይህን ያህል ዘመን ስንኖር እንዲህ ስትሆን አይቼህ አላውቅም። በሽታው ያን ያህል ከባድ መስሎህ ነው? አልነበረም ። እና በስላሴ ይዣሀለሁ እኔን ጨምረህ አትረብሸኝ››
«የለም የለም ፤ አትምከሪኝ ። አልፈልግም ፤ አትምከሪኝ ማሪዮን ሂልያርድ። እንደፈለኩት ልሁን ስትይ እሽ ስል ምን መጣ ይኸዋ በሽታ ላይ ወድቀሽ አረፍሽው ። አሁን በዛብኝ በቃኝ። አልቻልኩም »
«በቃ ተስፋ ቆረጥክ?» አለች የፌዝ ፈገግታ ፈግጋ ተስፉ ከቆረጥክ ፤ ከሰለቸህ ለምን ሥራውን ለቀህ አረፍ አትልም›› የጆርጅ ሁኔታ የቀልድ ያህል አስደነቃት ሆኖም ፊቱን ወደሷ ሲመልስና ከጀመረው ሀሳብ ወደኋላ እንደማይል የሚገልፅ ገፅታውን ስታይ የቀልድ እድናቆቷ ወደ እውነተኛ አድናቆትና ድንጋጤ ተለወጠ ።

«ሥራ ልቀቅ አልሺኝ ፣ ማሪዮን ? እኔም አስቤ እሰላስዬ የወሰንኩት እሱን ነበር ። እኔም አንችም ሥራውን ለቀን በጡረታችን መኖር አለብን» ይቀልዳል ?... የለም ከልቡ ነው ፤ አለች በሀሳቧ ። «አትቀልድ» አለች ። ሆኖም ድምጺ የተለመደው ጥንካሬ ይጎድለው ነበር ። «ቀልድ ? ቀልድ የለም ። እንዲያውም በዚህ አብረን በኖርንበት ሃያ አመት ውስጥ እንዲሀ አይነት ጠንካራ ውሣኔ ወስኘ አላውቅም ። ሁለታችንም ከሥራ እንሰናበታለን ። ለማይክልም ይህንኑ ነግሬዋለሁ ። እግዜር ይስጠው አውሮፕላን ማረፊያ ያደረሰኝ እሱ ነበር ። ልመጣ ስላልቻልኩ በጣም አዝናለሁ ። በሥራ ተወጥሬ ነው ብሏል ። እና ተስማምተናል ። አንች ይህን አልሽ ያን አሁን ዋጋ የለውም ። ተወስኖአል ፤ያበቃ ነገር ነው»
«አበድክ ልበል ?» አለችና ከተጋደመችበት ተነስታ ቁጭ አለች ። አፈጠጠችበት ፤ በደብዛዛው ብርሃን «ልስማህና ሥራውን ትቼ ልቀመጥ እንበል ግን ምን ሳደርግ ልዋል ? ሹራብ ስሠራ ወይስ መጽሐፍ ሳነብ ?»
«ሹራብ ሥሪ ወይም መፅሐፍ አንብቢ ። የፈለገሽውን ብታደርጊ ከተስማማሽ ጥሩ ነው። ሥራውን ከተውን በኋላ ግን ወዲያውኑ የምናደርገው ነገር አለ ። እኔና አንቺ እንጋባለን ። ከዚያ በኋላ እንዳፈቀደሽ መሆን ትችያለሽ ። ግልፅ ነው?››
«እንዴት ያለ ነገር ነው ባካችሁ? ቢያንስ ቢያንስ እንድንጋባ ፈቃደኛ ነሽ ወይስ አይደለሽም ተብዬ አልጠየቅም ? ወይሰ ይኸም ከዋናው ሥራ አስኪያጅ ከማይክል የመጣ ትዕዛዝ ነው» ኣለች ማሪዮን ። ሆኖም ድምጺ የቃላቱን ያህል መከፋትም ቁጣም አልነበረበትም። ስላሰቡላት ልቧ ተነካ ። ሸክሙ ቀለል አላት ። እውነትም ይበቃታል ። ብዙ ነገር አድርጋለች መጥፎም ጥሩም ፣ እኩል በኩል ። ይህን ደግሞ ተገንዝባዋለች ። አውቃዋለች ።

ከሜሪ ኣዳምሰን (ናንሲ ማክአሊስተር ) ጋር ያንለት ያደረገችው ንግግር ይህን ጉዳይ ግልፅ አድርጎላታል ፣የዕድሜ ልክ ተግባሯን ተመልሳ እንድታይ አድርጓታል ። ደግም ከፋትም ሠርታለች ። «የማይክልን ምርቃትም አግኝተናል» አለ ጆርጅ ። ይህን ብሎ ወደ አልጋው ሄደና እጅዋን ጨብጦ «ታገቢኛለሽ፤ማሪዮን !?» ሲል እየፈራ ጠየቀ ። ይህን ያሀል ዘመን አብረው ኖረው ሲያፍራት ገረመው ። እንዲያውም ማይክል «ይገባል ። ፍቅራችሁን ልታከብሩት ይገባል» አይነት ነገር ባይለውና ምንም ትርጉሙ ግልፅ ሆኖ ለጊዜው ባይታየው «ለጋብቻው አበረታታት» ባይለው ኖሮ ላይጠይቃትም ይችል ነበር ። «ንገሪኝ እንጂ» ይህን ብሎ እጅዋን ጠበቅ አደረጋት ።
👍27🥰2
ማሪዮን ሂልያርድ ቀስ ብላ ከልብ የሆነ ግን ደከም ያለ ፈገግታ እያሳየችውና እራሷን በአወንታ እየነቀነቀች… «ቀደም ብለን ልናስበው ይገባ ነበር ፤ ጆርጅ» አለችው ። «እኔ ገና ዱሮ ነው ያሰብኩት ። ግን በጅ አትልም ስል ተውኩት» አለ ጆርጅ። «ደሞ ልክ ሳትሆን አትቀርም ። ያኔ ብትነግረኝ ሳይገርመኝ አይቀርም ነበር ። በጄ ማለቱን ተወው ። ጅልኮ ነኝ» አለች ። ይህን ብላ በረጂሙ ተንፍሳ ተጋደመችና ትራሱን ደገፍ ብ… «እንዴት አድርጌ በሕይወቴ ተጫወትኩባት» ስትል ተፀፀተች። «አረ እንደሱ አይባልም ተይ» አለ ጆርጅ «እኔ ሳውቅሽ ሕይወትሽን በሙሉ በትጋት ፤ በአዋቂነት ፤ ቁም ነገር በመሥራት ነው ያሳለፍሺው» እጅዋን ይዞ በፍቅር ያሻሻት ጀመር ። ለረጂም ጊዜ ሲመኘው የነበረ ነገር ነው ። «ደሞም ያለፈ ነገር አልፏል ። ባለፈ ፋይዳ ቢስ ስህተት እየተፀፀቱ ራስን መጉዳት ጥቅም የለውም» ሲል ጨመረ። ይህን ስትሰማ ማሪዮን ከተጋደመችበት ተነስታ ተቀመጠችና ትኩር ብላ እያየችውና እጅዋ ድንገት ቅዝቅዝና ጥንክር እያለ «ግን...ግን ይኸ ፋይዳ ቢስ ያልከው ስህተት የሌሎችን ሕይወት አበላሽቶ ቢሆንስ?... ልርሳህ ብለውስ የሚረሳልኝ ይመስልሃል ጆርጅ ?» አለች ። «ምነው ማሪዮን እያወቅሽው? የሌላ ሰው ህይወት ለማበላሸት ምን ጊዜ ኖሮሽ ?» ሲል ጠየቃት ።

በአእምሮው ውስጥ ዶክተሩ የእንቅልፍ ክኒን ወይም ህመም እንዳይሰማት የሚያደርግ መድኃኒት ሰጥቷት ይሆን ? ሲል ጠየቀ ። ያለዚያ እንዲህ አይነት ቅብጥርጥር ከማሪዮን የሚጠበቅ እንዳይደለ እየገመተ ። «አንተ እማታውቀው ብዙ ነገር አለ ጆርጅ ። አይገባህም ነገሩ»
«ሁሉንም ማወቅ አለብኝ ?»
«ምናልባት ። ምናልባት ማወቅ ይኖርብህ ይሆናል ። ብታውቅ ደግሞ ልታገባኝ አትፈልግም ነበር ። ምናልባት »
«ፍሬ ከርስኪ !ይህን ሀሳብ ከልብሽ አስወጭው ። ይልቅ እንዲያ ካልሽ ነገሩን የማወቅ መብት አለኝኮ። ስለዚሀ ያስጨነቀሽን ነገር ንገሪኝ» ማሪዮን በሀሳብ ተውጣ አትኩራ እያየችው ለረጂም ጊዜ ዝም ካለች በኋላ…. «እንጃ ፤መናገር መቻሌንም እንጃ» አለች ። «ለምን ? ለኔ ፈርተሽልኝ ፣ ይከፋዋል ይቀፈዋል ብለሽ ፈርተሽልኝ ከሆነ እርሺው ። በዚች ዓለም ላይ ይኸ አእምሮዬን ይበጠብጠዋል የምለው ነገር የለኝም ። ደሞም ላንቺ መስሎሽ እንጂ እኔ ሳስበው የምትነግሪኝ ነገር ይኸኔ የማውቀው ነው ። ስላንቺ ማላውቅው ነገር አለ ብዬ አላስብም» አለና በስጋት እየተመለክታት «የለም ። የልብ በሽታው ሲነሳብሽ ጊዜ ትንሽ ሳያስደነ ግጥሽና ሳያናውጥሽ አልቀረም መሰለኝ»
«በሽታው ሳይሆን ስሸሸው የነበረ ዛሬ ፊት ለፊት የተጋ ፈጥኩት እውነት ነው እንዲህ ያናወፀኝ»
«ምን?.... አንድ የተለዬ ነገር አጋጥሞሽ ነበር ?» አለ ከብዙ ፀጥታና ሀሳብ በኋላ ። ቶሎ አልመለሰችለትም ። ጠበቀ ቆይታ
«አዎ» ስትል ተናገረች ። «እንዲያ ነው?» አለ…. ጥያቄ ሳይሆን ገባኝ እንደማለት ። «የሆነውም ቢሆን አሁን እንርሳው ። አረፍ ማለት ያስፈልግሻል። ጉዳዩን አንስቶ መድገም አያሻም ። ይቆይልን ይህን ሲል ስጋቱ ይታወቅ ነበር ። ከድምጹ፣፤ ከገፅታው ልብ ድካሟ እንደገና ቢነሳስ ? የሚለው ጥያቄ ይነበብ ነበር ። ስለዚህ ያጋጠማትንም ነገር አልጠየቃትም ። «ከልጅቷ ጋር ተገናኘን» አለች ማሪዮን ። «የምን ልጅ ?» አለ ጆርጅ ፤ ሴትዮ ምንድነው እምታወሪው በሚል ድምፅ።
እንባዋ መውረድ ጀምሯል ።

«ስለየትኛዋ ልጅ ማለትሽ ነው?» አለ ጆርጅ እየተጨነቀ። ዝም ብላ ስታየው ቆይታ እንባዋን ገትታ… «ማይክል የወደዳት ፤ አፍቅሮ ሊያገባት የነበረችው ልጅ» አለች ማሪዮን ተስተካክላ እየተቀመጠች ። «ታስታውሳለህ ጆርጅ ? ማይክ አደጋ የደረሰበት ቀን… ማታ ትዝ ይልሀል ? ሊያነጋግረኝ እንኳ መጥቶ ። ትዝ ካለህ ያንለት ልክ እንተ ስትገባ እሱ ወጥቶ አልሄደም ? እየተቆጣ ? ያንለት የመጣው ልጅቷን እንደሚያገባት ሊነግረኝ ነበር ። እኔ ደግሞ ስለቤተሰቧ ያሠራሁትን ሪፖርት ሰጠሁት »
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍23
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

..ደልቲ ገልዲ በራሱ የሚተማመን ጀግና በመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ
ከእሱ በላይ ሰው ያለ አይመስለውም" ስለሆነም፥ የሚፈልገውን አጣለሁ የሚል ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለውም" በስሙ ሲዘፈንና ሲዘመር ጥርሱን እየፋቀ በርኳታው (መቀመጫው) ላይ ቁጭ ብሎ ወይንም ጋደም ብሎ መዝናናት ነው;

ጀግንነት ከሀብት ጋር ገና ዕድሜው ሳይገፋ፥ «ቤት ለእንቦሳ» ሲል «እንቦሳ እሠር» ብሎ፥ ተቀብሎታል" በእርግጥ እያንዳንዱ
የሐመር ጓዳ ላጠቃላይ ማኅበረሰቡ ግልጽ ነው። ተካፍሎ መመገብ፥
ተሰባስቦ መጨፈር፥ ተከባብሮ መኖር፥ ጠላትን በጋራ ማጥቃትና
መደናነቅ የማኅበረሰቡ ወግና ልማድ ነው። ደልቲ ገልዲም የዚህ ባህላዊ ኑሮ ተሳታፊና ተገዥ በመሆኑ ኃይሉን ተማምኖ ሌላውን የሐመር አባል ማጥቃትም ሆነ ንብረት መቀማት ክብሩን ለውርደት፥ ሀብቱን
ለጥፋት ስለሚያበቃ ከልጅነቱ ጀምሮ ክብርንና መብትን በጥንቃቄ
መያዙንና ተከባብሮና ተመካክሮ መኖርን ሊዘነጋ አልቻለም።

ደልቲ ገልዲ፥ በዚያን ሰሞን ወደ መንደራቸው የመጣችውን እንግዳ የተመለከታት በኲራት ነበር" የለበሰችውን ጨርቅና
የምትሸተው ቃና ከአካባቢው ልጃገረዶች ጠረን የተለየ በመሆኑ ራቅ
ብሎ ነው ያስተዋላት።

«እንደ ሐመር ሴቶች ቆዳ የማትለብሰውና ጭኖቿን የማታሳየው ምናልባት የሚያሳፍር ነገር ቢኖርባት ይሆናል» ብሎ፥ከመገመቱም
በላይ የሴትነት ጠረኗን የዋጠው ሽታ አስጠልቶት ነበር በተደጋጋሚ
ቀናት እንዳያትም በሚኰርፍ ነገር መተጣጠቧ ብልግናዋን ከማረጋገጡም በላይ መጥፎ ጠረኗን ለማጥፋት መሆኑን አምኖበታል"

የሐመር ልጃገረዶች በውኃ አይታጠቡም። «ብልታቸውን ውኃ ከነካው መካን ይሆናሉ» ስለሚባል፣ በጣም ነውር ነው" ይህችኛዋ እንግዳ ግን አልፎ አልፎ ብቻ ሳይሆን ዘወትር ስትተጣጠብ ያያታል" «መካንነቷ መቼም የማይቀር ነው" ግን ሴት ሆና ስትተጣጠብ
የማታፍር ምኒቱ ባለጌ ናት?» እያለ ኮንኗታል። ሌላውም እንደሱ
በድርጊቷ ጠልቷታል"

ሆኖም እሱ የጀግኖች ጀግና ነው፤ እንዲህ ዓይነቷን ባለጌ ልክ የማግባቱ ኃላፊነት ከሱ ትከሻ ላይ የወደቀ ነው" ስለዚህ፣ እንግዳይቱን በግርፋትም ቢሆን ሥነ ሥርዓትን ሊያስተምራት ይችላል"
ይህን ለማድረግ ደግሞ፣ እሷን ማግባት አለበት" ካለበለዚያ ዝንቧንም እሽ ማለት ላይችል ነው ደግሞኮ የሱ ሚስቶች በመልካቸው ጥቋቁሮች ናቸውI ስለዚህ ነጭ ሚስት ያስፈልገዋል" ሀብቱ
እንደሆነ የትየለሌ ነውI ሦስት በረት ከብት፣ በየጋጡ ብዛት ያለው ፍየል፣ በየጫካው ለቍጥር የሚታክት ቀፎ አለው" በዚያ ላይ የቀጭኔ፣ የጎሽ፣ የአንበሳና የሰው ገዳይ ነው።

ስለዚህ፣ ይህችን ባለጌ ለማረቅ እንዲችል እሷን የራሱ የሚያደርግበት በቂ ሀብት አለው። እና፣ የሚጠየቀውን ጥሎሽ ከፍሎ የሱ ንብረት ካደረጋት በኋላ ቢቀጣት ጠያቂ የለበትም። ለዚህ ሁሉ
ግን፣ ሚስቱ እንድትሆን ማድረግ እንዳለበት አመነ። አብሯት የመጣው ከሎ ሆራ እንደሆነ ምኗም እንዳልሆነ አረጋግጧል"

አንድ ቀን ካርለትና ከሎ ሆራ ሲጨዋወቱ ደልቲ ገልዲ
«ነጋያ» ብሎ አጠገባቸው ለመቀመጥ ይዞት በሚዞረው በርኮታ ላይ
መሣሪያውን ጭኖቹ መሃል አድርጎ ተቀመጠ" ከዚያም፣ «ባል  አለሽ?» ብሎ በቋንቋው ጠየቃት" ይሉኝታና ፍርሃት የሐመርን
ተወላጅ ሲያልፍም አይነካካውም" ደግሞስ ሰው ሰው ነው" ያውም
እሱ ጀግናው። ከሎ ሆራ ያለውን ለካርለት ተረጐመላት።

«የለኝም» አለችው" ካርለት በቀኝ እጇ ግንባሯ  ላይ
የተበታተነውን ጸጕር ወደ ኋላዋ እየመለሰች።

«አባትሽ ስንት ከብት አለው?» አላት፣ ደልቲ።

«ከብት የለውም፣ ፕሮፌሰር ነበር" ስለዚህ ደመወዙ…»
ፕሮፌሰር፣ ደመወዝ ያለችው ሊገባው አይችልም። ከባለጌ የሚጠበቅ
ተራ የተራ ነገር ይሆናልና ስለሱ ማሰብ አያስፈልግም።

«ቀፎና ፍየልስ?» ጠየቀ ደልቲ።

«የለውም» አለች" አባቷ ደሃ ቢሆን ነው ማለት ነው ወደዚህ የላካት ብሎ አዘነላት" በሐመር ማኅበረሰብ ሀብት ማለት ከብት፣ ፍየል፣ ቀፎ ነው። ከዚህ ውጭ ደመወዝ፣ ቪላ፣ መኪና ብሎ ሐተታ፣
የሚገባው የለም። ደልቲ ገልዲ በክልሉ የሀብት ሁሉ ባለቤት አባወራው እንደሆነ
አሳምሮ ያውቃል" ስለዚህ፣ እንግዳዋን ስለ እናቷ
አያስፈልግም" ደግሞ ሴትን፣ «ሀብት አላት ወይ?» ብሎ መጠየቅ ነውር ነው። የእንግዳዋን አባት ሁኔታ እንደሆነ ጠይቆ፣ ድህነቱን
ተረድቷል

ደልቲ ገልዲ በእሱና በእንግዳዋ አባት ሀብት መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል ሰፍቶ ታየው" ለምግብ ማቅረቢያ፣ ለመኝታ የምትጠቀምበት፣ በተለይም ማታ ማታ «ፋ» የምታደርገው መብራትና ብልጭልጭ ቅራቅንቦዋ፣ ከሱ ንብረት አንፃር ሲታይ
ጠጠርና ተራራን ማወዳደር ቢሆንም፣ አባቷ ሀብቱን ለምን ለእሷ እንደተወላት ግራ ገብቶታል። የሱ ወገን የሆኑት የሐመር ሴቶች የግሌ የሚሉት ሀብታቸው የሚለብሱት ቆዳ፣ ጨሌና አንባራቸውን ብቻ
እንደሆነ ጥርት አድርጎ ያውቃል።

ያም ሆነ ይህ ግን፣ እንግዳዋን አግብቶ በግርፋት መግራት እንዲችል ሊያገባት መፈለጉን ለሽማግሎች ማማከር አለበት ሽማግሎች የሚሉት ባይታወቅም ብልግናዋን ገልጾ ሊገራት እንደሚፈልግ
ሲነግራቸው እነሱም ይህን ስለሚረዱ ተቃውሞ እንደማይኖራቸው
ተማምኗል" አንድ ግን ግራ የገባው ጉዳይ አለ" ጋብቻውን ሽማግሎች ቢቀበሉት «ልጅቱን ለማግባት፣ አባቷ የት ተገኝቶ በሽማግሎች
ይጠየቃል? ጥሎሹንስ እንዴት ወስዶ ከችግሩ ይላቀቃል?» ብሎ
አሰበ።

ይህ ከሆነ በኋላ ግን፣ ብዙም ሳይቆይ ደልቲ ገልዲና ካርለት በምሽት ጭፈራ ተገናኙ ካርለት ያ አስደናቂ ጥያቄ ሲጠይቃት
የነበረው ወላንሳ እየዘለለና እያሸበሸበ ሲደንስና ሲሥቅ፣ ደጋግማ
ስታየው ሁሉን ነገር በተለይም ስለሱ የሚባለውን ሁሉ አስታወሰች። ስለዚህ፣ ዛሬ ይህን ስሙ በሐመር ሰማይ ላይ የሚንሳፈፍ ሰው ማንነት ማወቅ አለባት"

ያም ሆኖ ግን ካርለት ስሜቷ ለሁለት ተከፈለባት" በአገሯ ምን ዓይነት ውበትና ጠባይ ያላቸው ወንዶች በሴቶች እንደሚፈቀሩ፣ ከሞላ ጎደል ታውቃለች። እሷም ብትሆን በአፍላው የወጣትነት ጊዜዋ የነበራት የስሜት ቅብጥብጥነትና በምታፈቅረው ወንድ ላይ

ታጠምደው የነበረውን መረብ አስታወሰች" ሆኖም ይህ ሰው እዚ
ከምታውቃቸው ሰዎች በብዙ መልኩ ይለያል ለነገሩ የደልቲ ውበት
ጭጋግ ለብሶ ይታያልI ያውም ይኖራል ብላ ያልገመተችው ውበ
የሐመር ልጃገረዶችን ሕሊና ያማልላል ተብሎ የሚደነቀውን ልበ ሙሉ ወንድ ጭጋጉን በታትና ሥነ ውበቱን በትክhል መቁጠር አለባት" የለንደኑ፣ የቦኑ፣ የማንቸስተሩ..ወጥመዷ ያለውን የመያዝ ችሎታም መፈተን ይኖርባታል"

እንደ ባልጩት ድንጋይ የለሰለሰውን ገላውንና በጨረቃ የሚያንፀባርቁት ጥርሶቹን ባሰበች ቍጥር ጥርት ጎላ እያሉ ታይዋት
ስለዚህ፣ ማራኪውና የመጨረሻ ዓይነት የጭፈራ ምት መጀመሪያው ጊዜ መቃረቡን ስታውቅ፣ ሐሳቧን ተግባራዊ ለማድረግ ለሩጫ
እንደሚዘጋጅ ሯጭ አደፈጠች።

ያን የወቅቱን ወላንሳና ቀብራራ ሐመር ጠብቃ ለዳንስ ስትጋብዘውና እያኮበኮበ፣ አየሩን በመቅዘፍ ቀርቦ ጥቁሩ ጭኑ ከነጩ ጭኗ ሲተሻሽ፣ ሸካራና ጠንካራ እጆቹ ትከሻዋን ሲይዙ፣ ስሜቱ
በስሜቷ ውስጥ ሲሟሟ፣ ያለችበትን ቦታና ሰዎችን በመዘንጋት የሚያቃጥል፣ የሚነዝርና በሰመመን የሚያሰጥም ስሜት እንደ
ተሰማት፣ ከራሷ ቍጥጥር ውጭ ሆነች" ስለዚህ፣ ሁሉን ነገር ዘንግታ
ተንጠራርታ አንገቱን በማቀፍ ከንፈሯን ከከንፈሩ ጋር ለማላተም
ተጣጣረች ደልቲ ግን፣ በጠንካራ እጆቹ እጇን ያዝ አድርጎ፣ የዳንሱን ቦታ ጥሎ፣ ወደ ጫካ ይዟት ገባ፤ ጥቁሩና ነጭ አባይ ጫካ መሃል ተገናኙ።
👍24👎1
ደልቲ ገልዲ ከእንግዳዋ ጋር ግንኙነት ከፈጠረ ጊዜ ጀምሮ፣ በተለይም በጭፈራ ቦታ፣ በሁለቱም መፈቃቀድ ግንኙነት ማድረጋቸው ቢቀጥልም በእንግዳዋ ላይ የሚያየው ባሕርይ ይበል
ግራ እያጋባው መምጣቱ አልቀረም። የእንግዳዋ ሰውነት እጅግ ለስላሳ ከመሆኑ የተነሣ እንኳን ተገርፋ ሲነኩት የሚላጥ ይመስላል" እጅና እግሯ በአጠቃላይ ሁለመናዋ መለስለሱ አስገርሞታል
«እንዴት ነው ይህች ሰው ሳታርስ፣ ሳትፈጭ፣ የከብቶችን እበት
ሳትጠርግና እንጨት ሳትለቅም ነው የኖረችው » በማለት ተደንቋል"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አንድ ወቅት ሐመሮች ግብር አንከፍልም ብለው አመፁ ቢቻል በስምምነት ካልተቻለ በኃይል እንዲያስገብሩ አፄ ኃይለ ሥላሴ የሠለጠነ ወታደር ወደ ሐመር ይልካሉ" በዚያ ወቀት፣ ሐመሮች ባላሰቡት ጊዜ ጥያቄውን በወታደር መልእክተኛ ይጠየቃሉ። ሆኖም ግን ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለጻቸው ውጊያ ተጀመረና የሐመሮች ሕይወት የሆነው የከስኬ ወንዝ ከሞላ ጎደል በወታደሮች ተያዘ። ሐመሮች በለመዱት ክልል ከቋጥኝ ቋጥኝ እየዘለሉ ኋላ ቀር በሆነው መሣሪያ ጠንክረው ቢዋጉም በመትረየስና በተሻለ መሣሪያና ስንቅ በመምጣት በከስኬ ወንዝ አሸዋ ጉድባ ሠርቶ ጥይት የሚያዘንብባቸውን ኃይል መቋቋም ተሳናቸው
በዚህ መልክ ጥቂት ቀን እንደ ቆዩ በውኃ ጥምና ስንቅ ማጣት ሐመሮች እየተጠቁ የመላ ያለህ ሲባል ለአውሬ አደን የመጣ
መንገደኛ በጦርነት ለእነሱ በመርዳት ሲታኰስ ሰነበተ። ልብ ያላሉት እንግዳ ወታደሩ የመሸገበትን ሲያስተውል በወንዙ ጠርዝና ጠርዝ
ባሉት ዛፎች ብዙ ቀፎዎች ተሰቅለው በማየቱ ዒላማውን እዚያ ላይ
በማድረጉ ከቀፎው ተረብሸው የሚወጡት ንቦች ወታደሩን ጒድጓዱ
ድረስ በመግባት ቁም ስቅሉን ስላሳዩት ከምሽጉ እየዘለለ ለመውጣት
ተገደደ» ሐመሮች ከምሽጉ የሚወጣውን ወታደር ከላይ እየቀለቡ ሲያስቀሩ እንደ ቆዩ የእሩምታ ተኵስ ቀልጦ፣ በተኵሱ ሽፋን
ወታደሮች በመሸሻቸው ከስኬ ወንዝን ማስመለስ ተቻለ" ግጭቱም
ሳይደገም በእርቅ አለቀ።

ሐመሮች ያን ጸጕረ ልውጥ መንገደኛ ከሞት አትርፈውታል። እሱም በተራው ይከፍለዋል ብለው ከጠበቁት በላቀ ሁኔታ ውለታውን መለሰላቸው። ስለዚህ መንገደኛውን ከብት በመስጠት እንደ
አባት የሚመርጠው ሽማግሌ፣ ዘመዶች የሆኑ ልጃገረዶች እንደሚገርፉለትና ሚስት እንደሚያገባ፣ እንደ አንድ የሐመር አባልም እንደሚቈጠር በመግለጽ ስለ ለመኑት መንገደኛው ትንሽ ካቅማማ በኋላ ሆድ የባሰውና ተስፋ የቈረጠ ስለነበር ተስማማ።

መንገደኛው፣ አመጣጡ ከወደ መንዝ ነው። ለስሙ ዘሩ የባላባት ይሁን እንጂ እሱም ሆነ ቤተሰቦቹ የነጡ ድሆች ነበሩ" ስለዚህ ቋት
ለማይሞላው ሕይወቱ ደፋ ቀና እያለ፣ በእርሻ ቀንና ምሽት ሲባዝን ኖረ። ከልጅነቱ ጀምሮ ሠርቶ ከሚከበረው፣ ገሎ የሚደነቀውና ከበሬታን የሚያገኘው ሲልቅ ሲያይ ኖሯልና ጀግና ተብሎ መከበሩና ወገኖቹንም ማስከበሩ ሕሊናውን እያሸፈተበትና ልቡን እያቆመበት መጣ። በተለይ ወደ ደቡብ ተጕዘው የአንበሳ፣ የጎሽ፣ የዝሆን…ገዳይ እየተባሉ የሚመለሱት፣ በአካባቢው ያላቸውን ከበሬታ ሲመለከት
አንዳንዴም ከብት ውኃ ለማጠጣት ወይም ልብሱን ለማጠብ ወደ ምንጭ ውኃው ወረድ ባለ ቍጥር፣ የገዳይ ሚስት ተራ ሳትጠብቅ ገብታ ውኃውን ቀድታ እንስራዋን በመሸከም፣ ቀሚሷን ሳብ ሳብ አድርጋ እያንጐራጐረች ሞንደል ሞንደል እያለች ስትሄድ፣ ተራ ጠባቂ ሴቶች፣ «.ኧረ ኤዲያልኝ…አኮራታ…ወይ ነዶ.የኛዎቹማ
ወንዶች ምድጃ ለምድጃ፣ ሽሮው ቀጠነ› ይበሉ…አይ ሱሪ እቴ…ኧረ እንዲያው ወይ ነዶ! አንሶ አሳናሽ...ሙቅ ሁላ» ሲሉ
አንገቱን ደፍቶ ሲሰማ አንጀቱ እየተኰማተረ፣ ልቡ የገበታ ውኃ እየሆነ፣ ቤቱም ቤት አልመስለው እያለ ከርሞ.ቆይ ከመንፈቅ
ወዲያ…..እሄዳለሁ» ሲል ኖሮ፣ እንደሱ ልባቸው ከኮበለለው ጋር
ዘጠኝ ሆነው ስንቃቸውን ቋጥረው በድብቅ ጕዞ ጀመሩ፤ ወደ ደቡብ
ኢትዮጵያ።

ከጕዞው ሦስት ዓመታት በፊት መሆኑ ነው፤ ጥር ላይ ይሄው መንገደኛ በአጎቱ ልጅ ሠርግ ጊዜ ነጠላውን አጣጥፎ ሲያስተናግድ
የደም ገንቦ የሆነች ዓይን አፋር ወጣት ለዘፈን እንድትገባ ስትለመን
ማስተናገዱን ትቶ ትኵር ብሎ ተመለከታት" ልጅቱ አንገቷን ሰበር አድርጋ፣ ነጠላዋን ከትከሻዋ አውርዳ ወገቧ ላይ ስታደርግ፣ እሱ
ደግሞ አንገቱን ሰገግ አድርጎ፣ እሷን ለማየት ተንጠራራ" ከበሮው
ድልድልድል እያለ ሲመታና ጭብጨባው ቀልጦ፣
«...እንዴነሽ ገዳዎ...» ሲባል፣ ወጣቷ እግሯንና እጇን በስልት እያንቀሳቀሰች፣ ስታሸበሽብ ቆየችና፣ «ኦሆ…ዎ» ብሎ፣
አቀንቃኙ፣ «ደርብ፣ ምታ.» ሲል፣ ልጅቷ እንደ ባሕር ቀጤማ ትውረገረግ ጀመር።

ይህ መንገደኛ በልጅቷ ውበትና እንቅስቃሴ ተደንቆ፣ በመፍዘዝ
ሲመለከታት እንደ ቆየ፣ አንዳች ነገር ልቡን ነሸጠውና ዘሎ ዘፈኑ
ውስጥ ሲገባ፣ ጭብጨባው ቀለጠ" ልጅቷም ልቧ ሞላ" ሁለቱም
ገጠሙ መንገደኛው እስክስታውን እየወረደ ያያታል፣ እሷ ግን
ዓይኗን እያስለመለመች ትውረገረጋለች" እሱ ቀስ በቀስ እየፈዘዘ መጣ መወዛወዙን አቆመና ባለበት ቆመ ልጅቷ እስከስታ
የገጠማትን ሰው ምት ዓይኗን ገልጣ ለማየት ስትሞክር ቆሟል"
ትኵር ብላ ትመለከተችው።

ከዘፈኑ ከወጡ በኋላ ያጎቱን ሠርግ ረሳ ማስተናገዱንም ተወው ልጅቷ በሄደችበት ሁሉ የሚከተል ያሳደገችው ውሻ ሆነ" ሲነካት
ትሸሸው፣ ሲቆነጥጣት ስታመናጭቀው ቆዩ እሱ ግን በማመናጨቋ
የሚበረግግ አልሆነም። ይባስ ብሎ ሌሎችን ጐረምሶች እየገላመጠ
ሲከታተላት እንደ ቆየ፣ ለሽንት ወጣ ስትል አብሮ ተከትሏት ወጣና ስትመለስ አድፍጦ ያዛት፤ ወዲያው ወደ ታዛው ይዟት ወደቀ።
አንገራገረች በኋላ ግን...

ከዚች ወጣት ጋር ግንኙነታቸው በስርቆሽ ቀጥሎ እንደ ሰነባበቱ
ወላጆቿ ለሁለተኛ ባል ዳሯት" ሲፈልግ፣ ሲያስፈላልግ ከርሞ፣
አንድ ቀን ድንገት ከቅዳሜ ገበያ ሲመለስ ተገናኙ" ያለፈውን ፍቅሯን ያውቃልና ገና ሲያያት ልቡ ሞላ፤ ናፍቆቱ አገረሸበት
ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ፤

«...እህሳ» ሲላት"
«አሁንማ የጀግና ሚስት ነኝ የገዳይ ባለቤት» ብላ፣ በኵራት መንፈስ ፊት ነስታው ከሄደች ወዲህ እሱም፣ «ገዳይ መባል አለብኝ» ብሎ፣ ውሳኔውን አጠናከረ።

ረጅሙን ጕዟቸውን የጀመሩት በእግር ሲሆን፣ በመጀመሪያዎቹ
የጕዞ ቀናት መንገዱ ተገፍቶላቸው ነበር። በኋላ ግን፣ ቀስ በቀስ ጕዟቸው የኤሊ ጕዞ ሆነ" ውኃ ጥሙ፣ ረሃቡ፣ ድካሙ ጥንዝል ቢያደርጋቸውም፣ በተለይም ወይጦና ተልተሌ በረሃ ላይ ሲጓዙ
አቅጣጫቸውን በመሳት በአዙሪት ኃይል ወደ መጡበት ሲመለሱ
ከቆዩ በኋላ በአጋጣሚ በቅሎ ከጫኑ መንገደኞች ጋር ተገናኙ ያጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ የሚሄዱበት አካባቢም አንድ በመሆኑ አንድ ላይ
መጓዝ ጀመሩ"

ነጋዴዎች አቅጣጫ እንዳይጠፋባቸው በመኝታ ጊዜ እግራቸውን
ወደ መጡበት፣ እራሳቸውን ወደሚሄዱበት አቅጣጫ ከማድረጋቸው ሌላ፣ አቅጣጫቸውንም ለማወቅ ባላ እየተከሉ ምልክት በማድረግ፣ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ባኮ hተባለው ከተማ በሦስተኛ ወራቸው
ደረሱ።

ባኮ ከደረሱ በኋላ፣ ለአውሬ አደን መምጣታቸውን በመግለጽ ከባህላዊ አሳዳኞች ጋ ተገናኙ" አሳዳኞች ሁለት ምንሽርና አንድ ቤልጅግ ጠመንጃ ያላቸው ሲሆን፣ መንገደኞቹም የተለያየ ቍጥር ያለው የምንሽርና የቤልጅግ ጥይቶችን ከመያዛቸው ባሻገር
የማርትሬዛ ብር ይዘው ስለመጡ፣ ከአሳዳኞች ጋር በቀላሉ ተግባብተው ወደ በረሃ ወረዱ።
👍12
ምንም እንኳ ከማጎ ወንዝ ሲርቁ በውኃ እጦት ቢቸገሩም፣ አውሬ
እያደኑ ጥብሱንም፣ ጥሬውንም፣ ቋንጣውንም፣ አልፎ አልፎም በሶውንም እየተመገቡ ችግሩን እየተቋቋሙ ቆዩ"
በመጨረሻም ባመጡት ጥይትና በተውሶ መሣሪያ እንደ ዕድላቸው ጎሽም፣ አንበሳም፣ አውራሪስም በመግደል ተጠባብቀው
ለሁለት ወር ከሳምንት በረሃ ቆዩ።

ሁሉም ቀንቷቸው አውሬውን ከገደሉ በኋላ፣ የነገው የጀግንነት ገድል ታሪክ በየቀያቸው ሲያስተጋባ ወንዱ አንገቱን ሲደፋ፣ ሴቷ
አይታቸው ስትሽኮረመም፣ ሽማግሎች (ጀግና ነው! ወንድ እያሉ ሲያወድሷቸው፣ ሚስቶቻቸው ከአካባቢው ሴቶች ልዕልና አግኝተው ሲያንጐራጕሩላቸው እየታያቸው፣ በደስታ እየሸለሉና እያቅራሩ የመልስ ጕዞ አደረጉ" ከዚያም፣ ካሳዳኞች ጋር የመለያያ ግብዣ አልጋ ከተባለው መንደር አቅራቢያ አደረጉ"
በመጨረሻም፣ መንገደኞት ከያዙት ጥይትና ማርትሬዛ ብር ከውላቸው ተጨማሪ ለአሳዳኞች ሸልመው፣ ተቃቅፈው በመሳሳም
መራርቀው ተለያዩ

አሳዳኞት ግን፣ የባኮን አቀበት ጕዞ እንደ ተያያዙ የጠጡት ሰዎች የያዙትን ጥይትና ብር እንዲያስታውሱና እንዲጐመዡ አደረጋቸው" መንገደኞቹ ከአልጋ መንደር
ያስመጡትን የአበሻ አረቄ እየጠጡ ሲያቅራሩ ቆይተው በያሉበት በመጠጥ ኃይል ተዳክመው ሲተኙ፣ ሁለቱ አሳዳኞች ተኩስ ከፍተው
ስምንቱን ገደሏቸው" አንዱ ግን እንደ ነብር አጓርቶ፣ አንዱን አሳዳኝ
ከነጠመንጃው በማነቅ ከመሬት ደባልቆ ጥይቱን በጆሮግንዱ ለቀቀበት" ከዚያም ከሁለተኛው ጋር እየተታኰሰ አባረረው"

ይሁን እንጂ፣ ከትንሽ ጊዜ በፊት አብረውት የነበሩት ሁሉ አልቀው፣ በዘጠኝ አስከሬን መከበቡን ሲያውቅ ፍርሃት አናወጠው"
ሰማይ ምድሩ ዞረበት «እየዬም ሲዳላ ነውና» እንባው ነጠፈ። ተስፋው ጨለመ፤ ጀግንነቱን ረሳው። የቀረው አማራጭ ምን እንደሆነ አያውቅም" ሙት መሃል ቢሆንም እሱም ከእንግዲህ ሙት ነው
ስለዚህ ዝም ብሎ ወደ ጫካው ሸሸ። ብርሃን ወዳላየው ጨለማ ገባ"

ብቸኛው መንገደኛ፣ የት እንደሚሄድ ቀርቶ የት እንዳለ እንኳ አያውቅም" ብቻ መጓዝ ሆነ፣ «ወደ መንዝስ እንግዲህ በምን አባቴ እሄዳለሁ? እንዴትስ ብዬ የዘመዶቼን ዓይን አያለሁ? ምንስ ዋጣቸው እላለሁ? ኧረ እኔንም ጅቡ ይብላኝ፤ ካለ ምስክር የቀረሁ ከንቱ ነኝ» እያለ፣ አቅሙ እስከቻለ ተጓዘ

መንገደኛው በመጨረሻ ሲደክመው፣ «አይ ሞኝነቴ አሁን እንግዲህ መልፋቴ ማን እንዲገለኝ ፈልጌ ይሆን? አውሬው በላኝ፣ ረሃብ ገደለኝ ሰው ገደለኝ ላልተርፍ ምን አስፈራኝ? እንዲያው እኮ ይገርማል ያለሁበትንና የምሄድበትን አላውቅ  እና መሞቴን
እረስቼ ለመኖር ምን አቃዥኝ፣ ያሻው ይገላግለኝ» ብሎ፣ መተኛቱን
ያስታውሳል" ሲነቃ ግን፣ ጥቋቁር ጠብደሎች ከበውታል። መሣሪያ
አንግተዋል" ጦር፣ ጩቤ፣ መጥረቢያ የያዙም ይታዩታል“ አማትቦ
መልሶ ዓይኑን ከደነ። ሰዎቹ ግን ጠቆም ጠቆም እያደረጉ እንዲነሣ አደረጉት። ሁሉንም በየተራ አያቸው፤ እንኳን የሚያውቀው ሊኖር
የሚሉትም አልገባውም በሐሳቡ፣ «እንግዲህ መሞቴ ላይቀር በምን
እንግደልህ በመሣሪያ ነው፣ በጦር እያሉ እስኪጠይቁኝ ነው የምጠብቀው? ስታገላቸው እሞታለሁ» ብሎ ግብግብ ገጠመ" ትንሽ ታግሎ ቢያስቸግራቸውም፣ ከመሬት ደባልቀው ጕሮሮው ላይ መሣሪያ ደገኑበት። መንገደኛው፣ «ለካ የመጨረሻው ዕድሌ በጥይት መሞት ኖሯል!» ብሉ ዓይኖቹን ጨፈነ"
ሐመሮች መሣሪያና ጥይት ከምንም ነገር በላይ ይወዳሉ። ተኳሾችም ናቸው" በማንም ላይ ግን ቃታ በድንገት አይስቡም" የሚገድሉትን ሰው ማንነት ለይተው ማረጋገጥ አለባቸው።

የሚገድሉት «ቢታው» እንዲገድሉ የፈቀደላቸውን ነው። ቢታ ማለት ጥንት የነበረ ሲሆን፣ ሲወለድ በግራ ብብቱ ንብ፣ በቀኝ ብብቱ እበት ይዞ የተወለደና ከቦርጆ (አምላከ) ጋር ማኅበረሰቡን የሚያገናኝ
ቅዱስ ሰው ነው፣ ብለው ስለሚያምኑ ቢታው ካወጣላቸው ደንብ
ዝንፍ ሳይሉ ለዓመታት የኖሩ ናቸው።

እንግዳው የሙርሲ፣ የማሌ…ማኅበረሰብ አባል ቢሆን ኖሮ ቢታው እንዲገድሉ የፈቀደላቸው ስለሆነ ይገሉት ነበር። እንግዳው ግን የተለየ ነው። ስለዚህ ሳይገሉት ቀሩ። እንዲያውም የደከመ
ሰውነቱን የከብት ደምና ወተት በማጠጣትና ፍየልና በግ በማረድ ያን እየሰበቁ መረቁን እንዲጠጣና ሥጋውንም እንዲበላ በማድረጋቸው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያገግም አደረጉት" ከዚህ በኋላ ግን፣ ሐመሮች ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ባደረጉት ጦርነት ለእነሱ አብሮ ተዋጋ። መዋጋትም ብቻ ሳይሆን፣ በሱ ስልት ከእልቂት አዳናቸው። ለዚህም ለፈጸመው ትብብር ከብት ዘሎ፣ ልጃገረዶች ተገርፈውለት ሚስት አገባ።
የዚህ እንግዳ ሰው ስም አንተነህ ይመር ይባል እንጂ ከብት ሲዘል መጀመሪያ እግሩ የረገጠበት ትንሽ ጥጃ ቀለሟን በማየት ጋልታምቤ ተባለ።

ጋልታምቤ ከሐመር ማኅበረሰብ አባል ከሆነችው ሚስቱ አንዲት
ሴት ልጅ ወልዶ፣ ቋንቋውን፣ አለባበሱን፣ አመጋገቡን ተለማምዶ ደስ ብሎት የሚኖር ሰው ሆነ።
ጋልታምቤ ሃያ ዓመት ሙሉ ሐመር ውስጥ ሲኖር የተቸገረበት፣ የተለየበት አንዳችም ሁኔታ የለም ከቋቋው ልዩነት በስተቀር
ይህ ነው የሚባል የጎሳ ልዩነት እሱ ከሚያውቀው የተለየ የለም"

በሐመር ማኅበረሰብ ችግርን በሽማግሎች ምክክርና በማኅበረሰቡ
ነፃ ውይይት መፍታት እንጂ፣ ችግርን በተናጠልና በኃይል መፍታት በኗሪዎች በሙሉ የተወገዘ ነው።

ተመካከሮ፣ ተከባብሮ፣ ተፈቃቅሮ፣ደካማና ጠንካራው ካለሥጋት የሚኖርበት ማኅበረሰብ በመሆኑ እንግዳው ጋልታምቤ እንኳን እሱ ለልጅ ልጆቹም ከዚያ የተሻለ ዓለም አይመርጥላቸውም"

💫ይቀጥላል💫
👍33👎21🥰1
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስምንት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ወጀቡ እስኪጠፋ ወለሉ ላይ ተቃቅፈው ቆዩና ‹‹መርቪን አልጋው ላይ እንውጣ ከወለሉ ይልቅ እዚያ ይመቸናል›› አለ፡ ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ከዚያም በጉልበቷ እየዳኸች አልጋው ላይ ወጣች፡፡ መርቪንም ተከተላትና አልጋው ላይ አብሯት ወጣ፡፡ እሱም እቅፍ አድርጎ ያዛት፡፡ በወጀቡ ምክንያት አይሮፕላኑ…»
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

..ለአስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ አንድ ከእንጨት የተሰራ ቤት አገኙና ጥልቅ አሉ፡፡ ናንሲ ስልኩ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እጇ እየተንቀጠቀጠ የስልኩን እጀታ አነሳችና ‹‹ናንሲ ሌኔሃን ነኝ›› አለች፡፡
ኦፕሬተሩም ‹‹የቦስተን ስልክ ፈላጊ መጥታለች ስልኩን አትዝጉት›› አለ።

ትንሽ ቆይቶ ‹‹ናንሲ ነሽ?›› አለ ከወዲያኛው አገር የመጣ ድምጽ ስልኩን የደወለው ማክ መስሏት ስለነበር የሰማችው ድምጽ የዳኒ ሪሌይ መሆኑን ለማወቅ ትንሽ ጊዜ ወስዶባታል ‹‹ዳኒ ሪሌይ ነህ?,,

‹‹ናንሲ ችግር ውስጥ ውድቄልሻለሁ እባክሽ እርጂኝ›› አለ፡

የስልኩን እጀታ አጥብቃ ያዘች፡፡ የሸረበችው ሴራ ግቡን ሊመታ ይመስላል፡፡ የዳኒ ስልክ የረበሻት ለመምሰል በተሰላቸና ረጋ ባለ ድምፅ
‹‹የምን ችግር ዳኒ?›› አለችው፡፡

‹‹ሰዎች በቀድሞ ጊዜ ላጠፋሁት ጥፋት ከዚህም ከዚያም ስልክ እየደወሉ አስቸገሩኝ››

ይሄማ ጥሩ ብስራት ነው፡፡ ማክ ዳኒ ላይ ሽብር ነዝቷል ማለት ነው› አለች ሆዷ በደስታ እየሞቀ፡፡ ዳኒ ድምፁ ይንቀጠቀጣል፡ እሷም ይህን ነው
የፈለገችው፡፡ ነገር ግን እንዳያውቅባት ስለምን እንደሚያወራ እንደማታውቅ
አስመስላለች፡ ‹‹የምን ችግር ነው? ምንድን ነው እሱ?››

‹‹በስልክ ልነግርሽ አልችልም››

‹‹ታዲያ ጉዳዩ በስልክ የማይነገር ከሆነ ለምን ደወልክልኝ?››

‹‹ናንሲ እንደ ቆሻሻ አትቁጠሪኝ ከጉድ እንድታወጪኝ ነው
የደወልኩልሽ››

‹‹እሺ ተረጋጋ›› በሚገባ ተሸብሯል፡፡ ይህን ፍርሃቱን ደግሞ ልትጠቀምበት ወስናለች፡ ‹‹የሰው ስምና አድራሻ ሳትገልፅ የሆነውን ብቻ ንገረኝ የምትፈልገውን ነገር መገመት አያቅተኝም››

‹‹የአባትሽ ሰነዶች በሙሉ አንቺ ጋ ናቸው?››

‹‹አዎ እኔ ቤት ካዝና ውስጥ ናቸው››

‹‹ሰዎቹ ሰነዶቹን ማየት ሳይፈልጉ አይቀሩም››
ዳኒ ራሷ የቀመረችውን ታሪክ እየነገራት ነው፡ ሴራው እስካሁን በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ ነው፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት የሰጠች በማይመስል ሁኔታ ‹‹እነዚያ ሰነዶች ውስጥ አንተን የሚያስጨንቁህ ነገሮች ያሉ
አይመስለኝም››

‹‹እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ?›› ሲል አቋረጣት በንዴት።

‹‹እኔ እንጃ››
‹‹ሰነዶቹን በሙሉ አይተሻቸዋል?››
‹‹አይ ብዙ ሰነዶች ነው ያሉት››
‹‹ምን እንዳለ ማንም አያውቅም፡፡ ሰነዶቹን ገና ድሮ አቃጥለሻቸው
ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፡››
‹‹ልክ ነህ የሆነስ ሆነና ሰነዶቹን መመርመር የፈለገው ማነው?››
‹የጠበቆች ማህበር ነው፡፡ እነሱ ሰነዶቹን ለማየት መብት አላቸው››
‹‹የላቸውም፡፡ ነገር ግን እኔ አልሰጥም ካልኩ ጥሩ አይመጣም››
‹‹አንቺ ጠበቃ አይደለሽ ሊያስገድዱሽ አይችሉም››
ናንሲ ንግግሯን ትንሽ ቆም አደረገች ልቡን ልትሰቅለው፡ ‹‹ስለዚህ ችግር አይኖርም›› አለችው
‹‹አልሰጥም ትያቸዋለሽ?››
‹‹ከዚያም በላይ ማድረግ እችላለሁ። ነገ አሜሪካ ስመጣ አቃጥላቸዋለሁ››
ዳኒ ሳግ እየተናነቀው ‹‹ናንሲ አንቺ እውነተኛ ጓደኛ ነሽ›› አለ፡፡
ከልቧ ልትረዳው እንዳልሆነ ህሊናዋ እየነገራት ‹‹ሌላስ ምን ላድርግልህ?››
‹‹ይሄ ይበቃኛል እንዴት አድርጌ እንደማመሰግንሽ አላውቅም››
‹‹አንተ ካነሳኸው ደግሞ ውለታ ልጠይቅህ ነው›› አለችና ከንፈሯን
በጥርሷ ነከሰችው::
‹‹መቼም ለምን እንዲህ
እንደፈለግኩ ሳታውቅ አትቀርም››
እንዲህ በአስቸኳይ ወደ አሜሪካ ለመመለስ
‹‹አላውቅም ምንድን ነው?›› አላት፡
ፒተር ኩባንያውን እኔ ሳላውቅ ሊሸጥ ተዘጋጅቷል››
ዳኒ ፀጥ አለ፡፡
‹‹ዳኒ አለህ?››
‹‹አለሁ አንቺ እንዲሸጥ አትፈልጊም?››
‹‹እኔ እንዲሸጥ አልፈልግም፡፡ ለግዥ የቀረበው ዋጋ በጣም ዝቅ ያለ ነው፡፡ ከተሽጠ እኔም ቦታ የለኝም: ስለዚህ እንዲሸጥ የማልፈልገው ለዚህ ነው ፒተር ኩባንያው የሚሸጥበት ዋጋ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ያውቃል፡
ነገር ግን እኔን ለመጉዳት ስለሆነ ቢሸጥ ግድ የለውም:፡››
‹‹የሚሸጥበት ዋጋ ጥሩ አይደለም? ኩባንያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
አክሳሪ እየሆነ እኮ ነው››
‹‹ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አታውቅም››
‹‹አንድ የምገምተው ነገር አለ››
‹‹ታውቃለህ፡፡ ምክንያቱን ተናገረው እና ይውጣልህ፡ ፒተር የማይረባ ማኔጀር ስለሆነ ነው››
‹‹እሺ››
‹‹ኩባንያውን በርካሽ ዋጋ ከምንሸጠው ለምን ከኃላፊነት አናነሳውም፡፡
እኔ የኃላፊነቱን ቦታ ልውሰድና ወደ ቀድሞው ስሙ ልመልሰው፡፡ እንደ
ምመልሰውም ታውቃለህ፡፡ ኩባንያው ደህና ደረጃ ላይ ሲደርስ በከፍተኛ ዋጋ
እንሸጠዋለን ከፈለግን››
‹‹እኔ አላውቅም››
‹‹ዳኒ አሁን በድፍን አውሮፓ ጦርነት እየተቀጣጠለ ነው፡ ይህ ማለት አቅርቦት ጥያቄ ይጎርፍልናል፡፡ ሁለት  ሶስት ዓመት ብንቆይ ደግሞ
ቢዝነስ ይጧጧፋል ማለት ነው፡፡ ከምናመርተው ጫማ በላይ የጫማ ኩባንያውን አሁን ከተሰጠው በሁለት ሶስት እጥፍ ዋጋ መሸጥ እንችላለን፡›››

‹‹ነገር ግን ከናት ሪጅዌይ ጋር የፈፀምኩት የጥብቅና ውል ለኔ ጠቃሚዬ ነው›› አለ ዳኒ፡፡

‹‹ጥቅም የምትለውን ተወው፡፡ እኔ እንድትረዳኝ ነው የጠየኩv››
‹ይህን ሁሉ የምትጠይቂኝ ለራስሽ ጥቅም አይደለም?›

አንተ እልም ያልክ ውሸታም ነክ አንተስ ስለራስክ ጥቅም አደለም የምታወራው? ልትለው ፈልጋ ላለመናገር ከራሷ ጋር ታገለችና ‹አባባ ጋ  ያሉትን ሰነዶች እንዳትረሳ›› አለችና ትንፋሿን ያዝ አደረገች

‹‹ምንድን ነው ያልሽው?››
‹‹ባጭሩ እንረዳዳ ነው የምልህ፡፡ እንዲህ ያለ ነገር መቼም የሚገባህ
ይመስለኛል››
‹‹አዎ ገብቶኛል ይሄ ዛቻ ይባላል››
እያደረገችው ያለችው ነገር በሙሉ የሚያሳፍር ነው፡፡ ነገር ግን ከማን ጋር እንደምትወያይ አስታወሰችና ‹‹አንተ አስመሳይ ሽማግሌ! እንደዚህ ያለ ነገር ህይወትህን ሙሉ
ስትፈፅም ኖረሃል››

ዳኒ ሳቀና ‹‹ዛሬ እጅሽ ላይ ወድቂያለሁ፡›› ይህን ተናግሮ ሲያበቃ አንድ
ነገር አዕምሮው ውስጥ አቃጨለና ‹‹እኔ ላይ ግፊት ለማድረግ ብለሽ ራስሽ
ሳትሆኚ አትቀሪም ይህን የጠነሰስሽው›› አላት፡፡

አሁን ወደ እውነቱ ተጠግቷል፡፡
‹‹አንተ ብትሆን እንዲህ
እንደምታደርግ አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በላይ አትመርምረኝ፡፡ አንድ ማወቅ የሚገባህ ነገር በነገው የቦርድ ስብሰባ እኔን ከደገፍክ ከችግር ነጻ ነህ ካልደገፍከኝ ግን አለቀልህ›› ስትል ቁርጡን ነገረችው:፡ አሁን በግልጽ
ማስፈራራቱን ተያያዘችው፡፡ እሱ ደግሞ የሚገባው ቋንቋ እንዲህ ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯ ስር ይወድቃል ወይስ ዞር በይ› ይላል?

‹‹እኔን እኮ እንዲህ ልትናገሪኝ አትችይም! እኔ ቂጥሽን ያልጠረግሽ ልጅ
ሳለሽ ጀምሮ ነው የማውቅሽ››

ናንሲ ድምጿን ለስለስ አድርጋ ‹‹ታዲያ እኔን ለመርዳት ይሄ ምክንያት
ሊሆን አይችልም›› አለች፡፡

ትንሽ ቆየና ዳኒ ‹‹ሌላ ምን ምርጫ አለኝ!›› አለ፡፡

‹‹ያለህ አይመስለኝም እኔ ያልኩህን ከማድረግ ውጭ።››

‹‹እሺ›› አለ በገነገነ ሁኔታ፡ ‹‹ነገ ለአንቺ ድምፅ እሰጣለሁ አንቺ
እነዚያን ሰነዶች የምታጠፊ ከሆነ፡፡››

ናንሲ ያሰበችው በመሳካቱ ልታለቅስ ምንም  አልቀራትም፡፡ ዳኒን
ከእግሯ በታች አዋለችው፡ አሁን ድሉ የእሷ ሊሆን ነው፡፡ የብላክ የጫማ
ኩባንያ በእሷ ቁጥጥር ስር ሊገባ ነው፡፡
👍242
‹በጣም ደስ ብሎኛል ዳኒ›› አለችው ከደስታዋ ብዛት መናገር አቅቷት
‹‹አባታችሁ ይህ ነገር ወደፊት እንደሚከሰት ይናገር ነበር››
ናንሲ መጨረሻ ላይ ያለው ነገር አልገባትም ‹‹ምን ማለትህ ነው?››
አንቺና ፒተር እልህ አስጨራሽ ትግል እንድታደርጉ ይፈልግ ነበር፡›››
ናንሲ በዳኒ አነጋገር ጥርጣሬ ገባት ‹‹ምን እያልክ ነው? ለምን ግልፅ
አታደርገውም?›› አለች፡:

የባለፀጋ ልጆች ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው ስለሆኑ ጥሩ ነጋዴ
አይወጣቸውም፡፡ እድሜውን በሙሉ ስለደከመበት ሀብት ይጨነቅ ስለነበር አያያዙን ካላወቃችሁበት ድራሹን የምታጠፉት ይመስለዋል፡››

‹‹ለእኔ እንዲህ ብሎ ነግሮኝ አያውቅም›› አለች የዳኒን አባባል በመጠራጠር፡፡

‹‹ሁለታችሁ እንድትናቆሩ በመፈለጉ እሱ ከሞተ በኋላ የኩባንያውን ሀላፊነት ቦታ አንቺ እንድትወስጂ ቢፈልግም ቦታውን ግን አልሰጠሽም፡፡ፒተርን ደግሞ ኩባንያውን አንተ በኃላፊነት ትመራለህ ብሎት ነበር፡ በግልፅ ግን እንደሚወስድ ስላልወሰነ ሁለታችሁ እርስ በእርስ ታግላችሁ ጠንክሮ
የወጣው እንዲወስድ ነበር ፍላጎቱ፡፡››

‹‹ይህን አላምንም!›› አለች ናንሲ፡ ነገር ግን ይህም ሆኖ ዳኒ የተናገረው ውሸት ለመሆኑ ማረጋገጫ ስለሌለ መፍራቷ አልቀረም፡

‹‹አለማመን ያንቺ ጉዳይ ነው›› አለ ዳኒ ‹‹አባትሽ የነገሩኝን ነው እኔ
የነገርኩሽ››

‹‹አባባ ፒተርን የኃላፊነቱን ቦታ አንተ እንድትወስድ እፈልጋለሁ ብሎት ነበር?››

‹‹አዎ ብሎት ነበር፡፡ ካላመንሺኝ ፒተርን ጠይቂው፡፡›› ዳኒ ቀጠለና
‹‹እኔ የሁለት ዓመት ልጅ እያለሽ ነው የማውቅሽ አንቺ እንደ አባትሽ ጠንካራ ነሽ፡፡ የንግድ ስራን በተመለከተ ከአንቺ ጋር አተካሮ ውስጥ
አልገባም፡፡ መናገር የሌለብኝን መንገሬ ይቅርታ›› አለ፡፡

አሁን አመነችው፡፡ ባደረገው ነገር የተጸጸተ ስለመሰላት ያለውን ነገር አምና ተቀበለች፡ ነገር ግን የነገራት ነገር ሳያስደነግጣት አልቀረም፡፡

‹‹እንግዲህ የቦርዱ ስብሰባ ላይ እንገናኛለን›› አለ ዳኒ፡፡

‹‹እሺ››አለች ናንሲ፡
‹ቻው››
‹‹ቻው ዳኒ›› አለችና ስልኩን ዘጋች፡
አጠገቧ የነበረው መርቪን ‹‹ነገሩን ጥሩ ነው ያስኬድሽው›› አላት
‹‹አመሰግናለሁ›› አለች እየሳቀች፡፡
እሱም ሳቋ ተጋብቶበት እየሳቀ ‹‹አየሽ መንገዱን ሁሉ ዘጋሽበት፡፡ አንቺ
ያልሽውን ከመፈጸም ውጭ ምንም ምርጫ አይኖረውም››
‹‹ዳኒ ያለኝ ምን መሰለህ ኩባንያውን የሚመራ ጠንካራ ሰው እስኪለይ
ድረስ እኔና ፒተር እንድንናቆር አባባ ነው ነገሩን የጎነጎነው ብሎ ነገረኝ››
‹‹ታዲያ አመንሽው?››
‹‹አመንኩት፧ ያለኝ እውነት ይመስላል፡በፊት ጠርጥሬ ባላውቅም አሁን ሳስበው ግን በእኔና በፒተር መካከል የከረረ ጠብ የተነሳ በመሆኑ
አባባሉን እውነት ያደርገዋል

‹‹ታዲያ በአባትሽ አድራጎት ተበሳጨሽ?›› አላት እጇን ለቀም አድርጎ ይዞ፡፡

‹‹አዎ›› አለች ናንሲ የመርቪን በፀጉር የተሞላ ክንድ እያሻሸች ‹‹በአንድ
ሰው የተደረሰ የፊልም ስራ ውስጥ አንድ ገፀባህሪ ወክዬ የምሰራ መሰለኝ እኔ
ሳላውቀው፡፡ አባቴ  በጎነጎነው ሴራ ውስጥ ስንቀሳቀስ ነበር ይሄ
አበሳጭቶኛል፡፡ እናም አባታችን በዚህ ሆን ብሎ በፈጠረው ግጭት ምክንያት አሁን ከፒተር ጋር ያለኝን ጠብ በአሸናፊነት ለመወጣት ፍላጎት ያለኝ
አይመስለኝም፡››

መርቪን ነገሩን በመረዳት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ታዲያ ምን ልታደርጊ ነው ከዚህ በኋላ?››

‹‹እኔ የራሴን የውጊያ እስክሪፕት እፅፋለሁ፡፡››...

ይቀጥላል
👍13👏1😁1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የሐመር ዕጽዋት ለምልመው፣ ንቦች ከአበባ ወደ አበባ እየተዘዋወሩና እየዘመሩ ሲቀስሙ፣ ከብቶች ጨሌ ሳራቸውን እያመነዠኩ ሲያገሱ፣ እንቦሶች ቃጭላቸውን እያቅጨለጨሉ ሲቦርቁ፣
ልጃገረዶችም ማሳውን እያረሱ ሲያዜሙ፣ ልጆች እራቁታቸውን ሆነው በቀስት ጫካ ለጫካ ተሪ ለመግደል ሲሯሯጡ በሚውሉበት፣
ጎረምሶች ሹልሹላ፣ ሹርባ...ጸጕራቸውን እየተሠሩ «አኖ» በተባለው አፈር ሰውነታቸውን በማዥጐርጐር ለማታው ጭፈራና ድሪያ ሲዘጋጁ፣ የብልታቸውን ጸጕር እየተላጩ በመኸር ጊዜ የሚዘፍኑትን ዘፈን ሲያዜሙ በሚውሉበትና ሐመር የክቱን የተፈጥሮ ሕይወት
ለብሳ ኗሪዎቿን በምታስፈነጥዝበት ወቅት ድንገተኛ ሁኔታ ታየ።

ካርለት አልፈርድ ሰቀላ ቤት አሠርታ መኖር ከጀመረች ዘጠኝ ወር አለፋት። ከሷ በስተግራ ከሃያ ሜትር ላይ የከሎ ክብ ጎጆ አለ።
በግቢያቸው የዱር አበባ፣ ቦዬ፣ ጉደሬ በቅሏል። ከነሱ ግቢ ራቅ ብሎ አለፍ አለፍ በማለት የሐመሮች መኖሪያ ይታያል። ካርለት ቤቷ ሆና
ፀሐይ ስትወጣ ከፊት ለፊት፣ ስትገባ ደግሞ ከበስተኋላ ሆና ልታያት
ትችላለች"

በእርግጥ በፖስት ካርድ ፀሐይ ስትወጣና ስትገባ አስደናቂ ፎቶዎችን ተመልክታለች። ሕይወት ያላት የሐመሯ ፀሐይ ግን ምሽት ላይ በተለያዩ ቀለማት ተውባ እንደ ዕንቁ እያንፀባረቀች አካባቢውን
ቀይ፣ ቢጫ ሐምራዊ ድብልቅልቅ ቀለማትን ስትለዋውጥ ስታያት
ግን በሕይወቷ ካየችው ውብ ነገር ይልቅ፣ በሐሳቧ የቀረፀችው የገነት
ውበት ይታያታል።

ታዲያ፣ በጣም ተመስጣ የአካባቢውን ውበት ስትመለከት ውበትን በትክክል ለማስቀመጥ፣ መጨመር የምትፈልገውንም
ጨምራ ለመርካት፣ ከአንትሮፖሎጂስትነቷ ይልቅ ባለቅኔ ወይንም
ሠዓሊ መሆን ያምራታል
ካርለት ያጣችው ነገር የለም አይባል" የዋና ቦታ አላገኘችም ኑሮዋ ዘመናዊ አይደለም" ያም ሆኖ ግን በሚያውዳት የተፈጥሮ
መዓዛ፣በስሜት በምትውረገረገው የምሽት ጭፈራ፣ ባየችውና
በቀረበችው ቍጥር ጥልቅ እሳቤን የሚጠይቃት የተፈጥሮ ምሥጢር፣ በንጹሕ ሕሊና የምታነባቸው መጻሕፍት የደስታ ሚዛኗን
ይጠብቁላታል።

አሸጋግራ የምታየው የሐመር ሰንሰለታማ ተራራ፣ መሸት ሲል ከየዋሉበት ብቅ ብቅ የሚሉት ሰዎችና እንስሳት፣ ስታንቀላፋ
የዋለችው መንደር፣ ሞቅ ሞቅ ደመቅ ስትል፣ ሁሉም ከፀሐይ ውበት ጋር ውሕደት፣ ቅንብር ሲፈጥሩ ስሜቷ ይረካል» እንዲያውም ከዚህ
ለየት ላለ ያልተበረዘ ተፈጥሮ ያላት ፍቅር «ምነው እናቴ፣ ወንድሜ፣ እኅቴና ስቲቭ ይህን ባዩ» ብላ፣ ቅን ሐሳብ እንድታልም
ያደርጋታል"

አንድ ቀን ግን፣ የተለመደ ትርዒቷን ስትመለከት፣ በግምት የአሥራ አምስት ዓመት ልጃገረድ፣ ከጥቁር ፍየል ለፍቶ የተሠራውን
ቆዳ ዙሪያዋን በነሐስና ጨሊ አስጊጣ ለብሳ፣ አንገቷ ላይ በደረደረችው ጨሌ ራሷን አሰማምራ፣ ዳሌዋንና ቀጥ ብለው ግጥም ያሉ ማራኪ የእግር ቅርፅዋን ስታይ ካርለት አፏን በአድናቆት ከፈተች
«በእርግጥ በጣም ቆንጆና ለየት ያለች ነች መቼም አይቻት እንደማላውቅ እርግጠኛ ነኝ» እያለች በባለ ሌንሱ ካሜራዋ ደጋግማ
ከርቀት አነሣቻት" ልጃገረዷ ካለምንም ሥጋት ወደ ካርለት ሰቀላ ቀርባ ሰላም ብላ ካርለትን ቆም ብላ ካየቻት በኋላ ጸጕሯን በጣቶቿ እሷም በተራዋ እየነካካች አድናቆቷን በሣቋ ገልጣ ልትሄድ ስትል
ካርለት «ወይ አምላኪ፣ አምላኬ! ኧረ ጥርሶቿስ እንዴት ያምራሉ!» አለችና እንድትቀመጥ ጋበዘቻት" ልጃገረዷ ግን፣ ካርለትን የቤት ውስጥ ሁኔታ አንገቷን አስገብታ ቃኝታ በድጋሜ
ፈገግ ብላ፣ «ደህና ሁኝልኝ» ብላ ሄደች"

ከሎ ሆራ የሐመሯን ውብ ቀደም አድርጎ ይመለከታት ነበርና ውበቷ ደንቆታል" በተለይ ወደ እሱ ቤት አቅጣጫ ስትመጣ ልቡ
መዝለል፣ ሐሳቡ መተረማመሱን ጨመረ። ከሎ ሆራ እስh ዛሬ
ታይቶበት የማያውቅ መርበትበትና ድንጋጤ ታየበት"

ልጃገረዷ፣ «ደህና ዋልህ» ብላው፣ ከተከፈተው የጎጆ ቤት መስኮት ላይ ተንጠልጥላ ስታይ እግሮቿ፣ ጭኗ፣ ዳሌዋና የሚሳበው
| ወገቧ ከሎን በሲቃ አፈኑት። ልጃገረዷ፣ የሚተኛበትን መኝታና
ዕቃዎቹን ተመልhታ ስትወጣ የሱም ልብ አብሮ ተከተላት እሷ እንደምታውቀው በማንኛውም የሐመር ቤት የሚገኝ ለመተኛ ቁርበት፣ ለመመገቢያና ለመጠጫ ሾርቃ (ከቅል የተሠራ)
እንስራ (ለሸፈሮ ቡና ማፍያ) ነው" ከነጯ ቤትና እንደ ሐመሮች መልክ ያለውና ጨርቅ ለባሹ ቤት ግን አይታው የማታውቀው ዕቃ
አለ" በኮተቱ ብዛት ትገረም እንጂ አልተደነቀችም“ እንዲያውም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑት ቁርበት፣ ሾርቃ፣ እንስራ ቤታቸው
ውስጥ ባለመኖሩ ተደንቃለች።

ከሎ ቤቱ በር ፊት ለፊት ሆኖ ጠበቃት በሐመር ባህል ደንብ ልጃገረድ ከቡር ናት ካለፍላጎቷና ሳያግባባ መታገል የውርደት
ውርደትና ነውር ነው" ልጃገረድ እንደሚሰበር ዕቃ የሚጠነቀቁላት፣ እንደ ሕፃን ልጅ ፍላጎቷን የሚያከብሩላት መሆን ይገባል"ልጃገረድ የምትፈልገውን ወንድ ቀጠሮ ትሰጠዋለች" ያውም
ከተመቻት ነው" ካለበለዚያ፣ ካለ እሷ ትብብር አፈቀርኩ፣ ወደድኩ፣ በዚህ ወጥቶ በዚያ ወርዶ፣ ምን ሲባል ያን አይተሽ፣ እያሉ መሟዘዝ በባህሉ አይታወቅም
በሐመር ማኅበረሰብ ልጃገረድ ቀሳሚ ንብ፣ ወንዶች አበባ ናቸው" ባል ካገባች በኋላ ግን ሴት የባል ዕቃና ንብረት ናት።

ስለዚህ ልጃገረዷ ካለፍላጎቷ የሚደርስባት ችግር እንደሌለ
ስለምታውቅ ከሎን አልፈራችውም ከሎ ሆራ ግን ድንገት «እጅ ወደ ላይ» እንደተባለ ሰው ደንዝዟል" ካርለት የሁለቱን ሁኔታ
ከርቀት በጕጕት ትመለከታለች" ልጃገረዷ ሰላምታ አቅርባለት
መንገዷን ሰትቀጥል፣ ከሎ በባህሉ ኰራ ብሎ መታየት ሲገባው ተርበተበተ"

ሰንበት ብሎ ሲያስበው ራሱን ቢታዘብም በሕይወቱ በጣም አደገኛ ወጥመድ ላይ የወደቀበት ጊዜ ያ መሆኑን ራሱ ለራሱ አመነ"
ልጃገረዷ ግን ዳግመኛ ወደ መንደሩ አልተመለሰችም።

ሆኖም ከሎ፣ «ከየትኛው መንደር ይሆን የመጣችው? እጮኛ አላት ይሆን?» እያለ፣ በሐሳቡ መዋለሉ አልቀረም።

«...የሐመር ወንዶች ቢያፈቅሩም ፍቅራቸውን በግልጽ ማሳየት
ነውር ነው። ቢሆንም ልጃገረድን መዳራት ነውርነት የለውም» ብሎ፣
ከሎ የነገራትን ካረለት አስታወሰች"

ከሎ ሲቆዝምና ሐሳብ ሲያበዛ፣ ካርለት በፍቅር ሰመመን መዋጡን በመረዳቷ፥ «ከሎ ያችን ልጃገረድ እውን አፍቅሮ ይሆን? ፍቅሩንስ በምን መልክ ይገልጽ ይሆን? ባህላዊውን ወይስ ዘመን
አመጣሹን ይሆን የሚጠቀመው? ኧረ ኅብረተሰቡስ ምን ይሰማው
ይሆን?» በማለት፣ ካርለት በጥንቃቄና በተመስጦ ማሰቧን ቀጠለች።

«ምን ዓይነት ድንቅ ነገር ነው!» ሁሉም ነገር ምሥጢር ሆኖባት
ተገረመች። ስሜት ረቂቅ ነው፤ አይጨበጥም። ስሜት በአካባቢ ላይ
ተፅዕኖ ቢኖረውም፣ አካባቢም በስሜት ላይ ጫናው ከባድ ነው"
ማፍቀርና መፈቀር ተፈጥሯዊ ነውና ማንም ከዚህ ስበት ሊያመልጥ
አይችልም" ችግሩ ከፍቅር ቀጥሉ ግንኙነቱ በምን መልክ መሆን ይኖርበታል ነው። እኒህ ሁለት ሥረ ግንዳቸው አንድ የሆኑ፣ አካባቢያቸው ግን ለውጥ ያለው ሰዎች እውነት እንዳሰቡት ቢፋቀሩስ?»

አዲሱን ምርምሯን በተለያዩ መንገዶች ተጠቅማ ማወቅ
ይኖርባታል" «ከሎ ከልጃገረዷ ጋር ፍቅር ቢይዘው ልብስ በመልበሱ
ትንቀው ትችል ይሆን? አውሬ ወይንም የጎሳው ጠላት የሆነውን ሰው አልገደለም ከብት የለውም ስለዚህ ዘመናዊዋም ሆነች ቆዳ ለባሿ ሴት ክብርና ዝናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈላጊ ስለሆነች
ላትቀርበው ትችላለች"»

«ከሎም ቢሆን ልጃገረዷን ለማግባት ኡክሊ ሆኖ በየዘመዶቹ መዞር፣ ከብት መዝለልና ለኮይታ (ጥሎሽ) የሚሰጠው ከብት፣
ፍየል፣ በግና ማር ማግኘት አለበት"
👍30😁3
«ደግሞ ከሎ ትምህርቱን ጨርሶ በዘመናዊ ሥራ መሰማራት ይፈልግ ይሆናል" እንደዚያ ካሰበ ደግሞ ቢያፈቅራት እንኳን
ስሜቱን ማዳፈን መቻል አለበት ማለት ነው። ምን የጨነቀ ነገር ነው"
«ከሎ እንዳጫወተኝና እኔም እንዳረጋገጥኩት፣ ራሱ ከሎ ሚንጊ ተብሎ የተጣለ፣ ከሐመር ማኅበረሰብ የተወገደ ነው" በእርግጥ፣
የተጣለ ሳይሞት አድጎ ወደ ማኅበረሰቡ ቢመለስ ችግር አያመጣም" ወደ ማኅበረሰቡ ለመመለስ ግን ደንብ ተሠርቶ በሥነ ሥርዓቱ መሆን አለበት" እሱ ደግሞ ሥነሥርዓቱን አላሟላም።

«አጣብቂኝ ይሏል ይህ ነው" ፍቅርና ችግር ችግርና ፍቅር በዛበት ሕይወትስ ሳንካ መቼ አጥቶት ያውቃል?» እሷ ግን የሁለቱ
ግንኙነት ቢጠናከር ነፍሷ ነው የወንድን ፍቅርና ጋብቻ በሱ የሴቷን ደግሞ በሷ ደግሞ በሷ ለማረጋገጥ ከቻለች ተልዕኮዋ ተሳክቶ ወደ አሰበችበት እርከን
እንደምትደርስ ተስፋ አድርጋለች"

እሱም በበኩሉ፣ ቀንና ሌሊት በድንገተኛ ገጠመኙ እንዳለመ ነው" በውኑም ሆነ በሕልሙ ሲያለቅስና ሲደሰት ማሳለፍ ልማዱ
ሆኗል" የተጫረው የፍቅር እሳት ብርሃን ሕሊናውን ማፍካቱን አሌ ማለቱን አይፈልግም። የተፈጠረው ፍቅር ቢያስጐመዠውም፣ እንደ ደሴት ዙሪያውን የከበበውን ችግር ግን ዋኝቶ ሊዘልቀው አልቻለም

«ይቅርብኝ መቻል አለብኝ ራሴን በድንገተኛ የፍቅር እሳት አንጫርሬ ስሠቃይ መኖር አልፈልግም ጸጸቱም ሰው አያረገኝም»
በማለት፣ ከራሱ ጋር ይማከራል" በሌላ ጎኑም ኵሩ አካሄዷ፣ ክብና
የደስ ደስ ያለው ፊቷ፣ ግጥም ብለው የሚያንፀባርቁት እግሮቿና ኰራ ያለው ዳሌዋ በተለይ ፈገግታዋና ዓይኖቿ በዓይነ ሕሊናው ሲታየው ተመልሶ ወደ አዲሱ የፍቅር ማጥ ይነከራል"

«የራስህ ጉዳይ! ገና ያን ሁሉ የባል ደንብ ፈጽመህI ራቁትህን ዞረህ...በልኮ አትጃጃል! ራስህን መለወጥ፣ ማሻሻል ሲገባህ
ውጤቱን ልታየው የተቃረብከውን አዲስ ሕይወት ይበልጥ ወደ ላይ
በመሳብ ማየት ሲኖርብህ እንዴት ወደ ታች ለመንሸራተት ታስባለህ?
ጅላ ጅል» እያለ ሕሊናው በወቀሳ ያራውጠዋል"

«እኔኮ የማይገባኝ በገንዘብ የሚገዛ ሕይወት ለኔ ምኔ ነው? የናት አባቴ ባህልና ደንብ ባላድግበትም የተወለድሁበት ነው ሕይወትን እንደ ሸቀጥ ለመግዛት ብር ፍለጋ እስከ ዛሬ የለፋሁትስ መቼ አነሰኝ»
በማለት ሊፈላሰፍም ይቃጣል" ወጣም ወረደ ግን ተቃራኒ ሐሳቦቹ
የሱ የራሱ ቢሆኑም ሁለቱም ያሳምኑታልI በአንድ በኩል ደህና ነገር አሰብኩ ሲል በሌላ በኩል የመጣው ያኛውን እውነትነቱን
ያደበዝዝበታል፤ ከሎ ዳኛ አልባ በሆነና ድንግዝግዝ ባለ ተመጣጣኝ
ሐሳብ ተወጠረ"....

💫ይቀጥላል💫
👍33🔥2😢2
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ሄሪ ማርክስ ሰውነቱ በደስታ ስለተጥለቀለቀ
አልተንቀሳቀሰም፡፡ አልጋው ላይ ተጋድሞ ትናንት ማታ የሆነው ሁሉ በአዕምሮው መጣበት፡፡ ማርጋሬት ድንገት ስትስመው የተፈጠረው ደስታ፣
እሷን በእጁ ለማድረግ ምን ያህል ሆዱ እንደፈራ፣ በመጀመሪያ ሃሳቡን
አልቀበልም ማለቷ እና በመጨረሻም ልክ ወደ ጉድጓዷ እንደምትገባ ጥንቸል ሁሉ ድንገት አልጋው ውስጥ ዘላ ስትገባ የተደሰተው ደስታ።

መጥታ ሰውነቱን ስትነካ ሽምቅቅ ያለው ትዝ አለው፡፡ አዲስ ልጅ ሲተዋወቅ ሁልጊዜ የሚሰማው እንዲህ ነው፡ ከማርጋሬት ጋር የገጠመው ወሲባዊ ድክመት አሳፋሪ ሆኖበታል፡፡ አንድ ጊዜ አንዷ ልጅ እንዲህ ሆኖባት
አሹፋበታለች ሰድባዋለች፡፡ ማርጋሬት ግን አልከፋትም፡ እንደውም ሁኔታው
የበለጠ ለወሲብ አነሳስቷታል፡፡ በመጨረሻም በፈለገችው መንገድ እርካታ
አግኝታለች፣ እሱም እንዲሁ፡

የገጠመውን ዕድል ማመን አቅቶታል፡፡ እሱ እንደሆን ብልጠት እንጂ ገንዘብ የለውም:፡ የመጣውም ከዝቅተኛው የማህበረሰብ መደብ ነው፡፡ እልም
ያለ አጭበርባሪ መሆኑን ማርጋሬት ታውቃለች፡፡ ማርጋሬት ምን አይታበት
ነው የወደደችው? ቆንጆ፣ የምትወደድ አይነት ፍጥረት፣ አፍቃሪ እና
ብቸኝነት የሚያጠቃት ልጅ ናት፡፡ የሰውነቷ ነገር አይነሳ፡፡ እፁብ ድንቅ ሰውነት ነው ያላት፡፡ ማንም ወንድ እሷን አይቶ መከጀሉ አይቀርም፡፡ እሱም መልኩ ለክፉ አይሰጥም፡፡ አለባበስ አሳማሪ ነው፡፡ ማርጋሬት ግን ለዚህ ግድ ያላት አትመስልም፡፡ ባህሪው ደግሞ ግራ ያጋባታል፡ አኗኗሩ ገርሟታል
እሱም እሷ ስለማታውቀው ነገር ሁሉ ያጫውታታል፡ ስለሰራተኛው መደብ
አኗኗር እና ስለማፍያ ይነግራታል፡፡ እንደፈቀደችው ገብቶታል፡፡ እሱ እንደ
ቀላል ነገር ቢያደርገውም ለእሷ ግን ትልቅ ነገር ነበር፡፡ እሱም በዚህ ምክንያት ከእሱ ፍቅር እንደያዛት እርግጠኛ ሆኗል፡፡ ሴቶች መቼም ለየት ያሉ ፍጡራን ናቸው፡፡ ያም ሆነ ይህ እሷ እንዴት ወደ እሱ እንደተሳበች አሁን ማሰብ ትርጉም አይኖረውም፡፡ ሴቶች ልብሳቸውን አንዴ ካወለቁ በኋላ ቀሪውን መፈፀም አይቸግርም፡፡ በደነገዘው ብርሃን ያየውን እንደ ሊጥ የነጣ ጡቷን እና የጡቷን ጫፍ መቼም አይረሳውም፣ በብልቷ ዙሪያ ያከፈከፈውን ጭገሯንም እንዲሁ፡፡

ታዲያ አሁን ይህ ሁሉ ፀጋ ከእጁ ሊወጣ ነው፡፡ የእናቷን ጌጣ ጌጥ
ሊመነትፍ ቆርጧል፡፡ እሱ መስረቁ ከታወቀ ደግሞ ማርጋሬትን ማጣቱ
ነው፡

የእናቷ ውድ ጌጣ ጌጥ እዚሁ አይሮፕላን ላይ፣ እሱ ከተቀመጠበት ቦታ
ጥቂት እርምጃ አለፍ ብሎ በሻንጣ መያዣ ክፍል ውስጥ ነው ያለው፡
በዓለም ውስጥ ውድ የሆነውን ይህን ዕንቁ በእጁ አስገባ ማለት ዕድሜውን
በሙሉ ተንደላቆ መኖር የሚያስችለው ገንዘብ አገኘ ማለት ነው፡፡

ጌጡን በእጁ ካስገባ ይሸጠውና አሜሪካ ኒው ኢንግላንድ በተባለው ቦታ
በዛፍ የተሞላ መናፈሻ ያለው ትልቅ ቤት ይገዛና እሁድ እሁድ ከሚስቱ ጋር
በመሆን እንግዶቹን ሲጋብዝ ታየው፡

የሚያገባውም ማርጋሬትን ነው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጎህ እንደቀደደ ማርጋሬት ማንም ሳያያት መጋረጃውን ገልጣ ሹልክ ብላ
ወደ አልጋዋ ሄደች፡፡ አይሮፕላኑ በቦትውድ ኒውፋውንድ ላይ ለማረፍ ዝቅ ብሎ እየበረረ ነው፡፡ ማርጋሬት አይሮፕላኑ ሲያርፍ ለአንድ ሰዓት ያህል
ለመተኛት እንደምትፈልግ ነግራዋለች፡ ሄሪም‹‹እኔም እንዳንችው እተኛለሁ›› አላት ምንም እንኳን ለመተኛት ፍላጎት የሌለው ቢሆንም፡

በመስኮት ሲመለከት ገሚሱ ከአይሮፕላኑ ወርዶ ተሳፋሪ ጀልባ ላይ ሲወጣ ገሚሱ ተሳፋሪ ደግሞ አይሮፕላኑ ውስጥ እንቅልፉን እየለጠጠ
መሆኑን አየ ታድያ በዚህ ጊዜ ነው ብርበራውን የሚያካሂደው የሻንጣዎቹ ቁልፎች ችግር እንደማይፈጥሩበት ገብቶታል ጊዜ ሳያጠፋ
ጌጣጌጡን በእጁ ለማስገባት ቋምጧል።

በሌላ በኩል ደግሞ የማርጋሬት ጡት ከማንኛውም ጌጣጌጥ በላይ ነው ሲል አሰበ፡፡

አሁን ወደ እውነታው መምጣት እንዳለበት ለራሱ ነግሯል፡ ትናንት በጓደኝነት ይቀጥል ይሆን?› መርከብ ላይ ወይም አይሮፕላን ጉዞ ላይ ማታ ከእሱ ጋር ነው ያደረችው፡ ነገር ግን አሜሪካ ሲደርሱ ከእሷ ጋር
የተጀመረ ፍቅር አይለቅም እየተባለ ሲወራ ሰምቷል፡፡ ማርጋሬት ቤተሰቦቿን
ትታ ለብቻዋ ለመኖር በጣም ጓጉታለች፡፡ ነገር ግን ይሆንላታል? በርካታ
የባለፀጋ ሰዎች ልጆች በነፃነት መኖር ቢፈልጉም ከምቾት ኍሮ በቀላሉ
ለመላቀቅ ይቸገራሉ፡ ማርጋሬት መቶ በመቶ ለብቻዬ እኖራለሁ ብትልም
ተራው ሰው እንዴት እንደሚኖር የምታውቀው ነገር ስለሌለ ብትሞክረው
የምትወደው አይመስልም፡ ወደ ፊት ምን ልታደርግ እንደምትችል አሁን
መናገር ይከብዳል።

ነገር ግን ከጌጡና ከማርጋሬት አንዱን መምረጥ ሊኖርበት ነው
ማርጋሬትን ወይስ ጌጡን ብለው ቢጠይቁት በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ማርጋሬትን
እንደሚመርጥ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በተግባር ሲሆን ግን ሌላ ሊሆን ይችላል፡ ጌጡንም ማርጋሬትንም ላያገኝ የሚችልበት ሁኔታም አለ፡ ወይም ሁለቱንም በእጁ ያስገባ ይሆናል፡

እሱ መቼም ዕድሜውን በሙሉ ዕድለኛ ነው፡

ጌጡንም ማርጋሬትንም በእጁ ለማስገባት ወሰነ፡፡

ከመቀመጫው ተነሳና ነጠላ ጫማውን ተጫምቶ ዙሪያ ገባውን ተመለከተ፡፡ የማርጋሬትና የእናቷ መኝታ በመጋረጃ እንደተከለለ ነው:: የፔርሲ፣ የሎርድ ኦክሰንፎርድ እና የሚስተር መምበሪ መኝታ ባዶ ነው፡
ቀጥሎ የሚገኘው የተሳፋሪዎች መዝናኛ ክፍል እንዲሁ፡ አንዲት የጽዳት
ሰራተኛ ክፍሉን እያፀዳች ነው፡ የአይሮፕላኑ በር ስለተከፈተ ከውጭ የገባው
ቀዝቃዛ አየር ይበርዳል፡፡ ሚስተር መምበሪ ከባሮን ጋቦን ጋር እያወራ ነው፡
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች የተሳፋሪዎቹን መቀመጫዎች እያበጃጁ ነው ሄሪ ጌጣጌጡን ለማሰስ ደረጃውን ወጣ፡፡ እንደ ወትሮው ለጌጣጌጥ
ዘረፋው ያዘጋጀው መርሐ ግብር የለም: ሰው ቢመጣበት ምን ብሎ መልስ ሊሰጥ እንደሚችል በአዕምሮው ያዘጋጀው ነገርም የለም: ቀድሞ ማሰብ የሚባል ነገር እንደውም ስጋት ውስጥ ነው የሚከተው፡ ነገር ግን ሁኔታው ውጥረት ውስጥ ከቶታል፡ ‹ረጋ በል እንዲህ ዓይነት ነገር ሺህ ጊዜ
አድርገሃል› አለ ለራሱ ‹አንድ ችግር ከተፈጠረ የሆነ ምክንያት እዚያው
ትፈጥራለህ ሁል ጊዜ እንደምታደርገው፡›

የአይሮፕላኑ ማብረሪያ አካባቢ ሄደና ዙሪያውን አማተረ፡፡ ዕድለኛ ነው፡
ማንም የለም፡፡ ውጥረቱ ቀለለለት፡፡ ምን ዓይነት እድል ነው፡፡ወደፊት ሲያይ አንድ በር ተከፈተና አንዱ የአይሮፕላኑ ሰራተኛ
ሲመጣ አየ፡፡ ሰውዬው ካየው ጥሩ ስላልሆነ ፊቱን አዙሮ ሄደ፡፡ ከዚያም
ቀጠለና በሻንጣ ማስቀመጫ ክፍሎች ውስጥ ገባና በሩን ዘጋ፡፡ ሰራተኞቹ ወደ እዚህ ክፍል የሚመጡበት ምክንያት የላቸውም፡፡

ሻንጣውን ክፍል ሲመለከት የሻንጣ መሸጫ መደብር ይመስላል፡ ውድ
ሻንጣዎች በስርዓት ተደርድረው በገመድ ተጠፍረዋል፡፡ ሄሪ የኦክሰንፎርዶችን
«ሻንጣ ቶሎ መፈለግ አለበት፡ ወዲያው ስራ ጀመረ፡፡

ፍተሻው ቀላል አይደለም፡: አንዳንዶቹ ሻንጣዎች የባለቤቶቹ ስም የተለጠፈባቸው ቢሆንም ላይ በላይ ስለተደራረቡ ሁሉንም ስሞች ለማየት
👍10
ተቸገረ፡ የሻንጣ መያዣው ክፍል ውስጥ ማሞቂያ ስለሌለ ሄሪ ብርዱን
አልቻለውም: ሻንጣዎቹ በበረራ ጊዜ እንዳይወዳድቁ የታሰሩበትን ገመድ
ለመፍታት ሲታገል እጆቹ እየተንቀጠቀጡ አስቸገሩት፡፡ ያየውን ሻንጣ መልሶ እንዳነፈያይ አንድ በአንድ ማየቱን ተያያዘው፡፡ ከሻንጣዎቹ መካከል
የኦክሰንፎርድን ሻንጣ ግን ማግኘት አልቻለም፡፡ ከሃያ ደቂቃ በኋላ የሁሉንም
ሻንጣዎች ስሞች ማየት አጠናቀቀ፡፡ ስለዚህ የኦክሰንፎርዶች ሻንጣዎች
በሚቀጥለው ክፍል ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ ዕድሉን ረገመ፡

የፈታውን ገመድ መልሶ አሰረና ምንም አሻራ አለመተዉን ለማረጋገጥ
በጥንቃቄ ቦታውን ቃኘ፡፡
የሚቀጥለው የሻንጣ ክፍል ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ፍተሻውን ማድረግ ይኖርበታል፡ በሩን ከፍቶ ሲወጣ አንድ ሰው ‹‹ማነህ!?›› ሲል
በቁጣ ጠየቀ፡

ሄሪ ቢደነግጥም ቶሎ ድንጋጤውን ዋጥ አደረገና በሩን ዘግቶ ‹‹ሄሪ
ቫንዴርፖስት ነኝ›› አለ፡፡ ‹‹አንተስ ማነህ?›› ሲል ጠየቀ፡
‹‹ሚኪ ፊን እባላለሁ፡፡ የበረራ መሀንዲሱ ነኝ፡፡ ጌታዬ እዚህ ቦታ
መገኘት አይጠበቅብህም፡፡ እዚህ መግባትህ ገርሞኛል፡፡ በመቆጣቴ ይቅርታ ለመሆኑ እዚህ ምን ታደርጋለህ?›› ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹ሻንጣዬን እየፈለኩ ነው›› አለ ሄሪ ‹‹ምላጭ ላወጣ ነው››
‹‹አይሮፕላን ውስጥ ከተገባ በኋላ በማንኛውም ሁኔታ ሻንጣ ያለበት
ቦታ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው››
‹‹አይ እኔ ምንም ችግር የለውም ብዬ ነው የመጣሁት››
‹‹ይቅርታ እዚህ መግባት አይፈቀድም፡፡ እኔ የራሴን ምላጭ ልሰጥህ
እችላለሁ››
‹አመሰግናለሁ ለችሮታህ እኔ ግን የራሴን ምላጭ ነው የምፈልገው ማግኘት ከቻልኩ››

‹‹የምትፈልገውን ባደርግልህ በወደድኩ
ጌታዬ እዚህ መግባት
ስለማይቻል ነው፡ ካፒቴኑ ሲመጣ ልትጠይቀው ትችላለህ፡፡ እኔ ያልኩህን
ነው የሚልህ››

ሄሪ እየቆጨው ሽንፈቱን መቀበል ሊኖርበት ነው፡፡ ካልሆነ ያንተን ምላጭ እወስዳለሁ አመሰግናለሁ የኔ ወንድም፡፡››

ሚኪ ፊን በሩን ከፍቶ ያዘለትና ሄሪ ወጥቶ ሄደ፡፡ ምን አይነት ክፉ እድል ነው› አለ በሆዱ፡፡ ‹ትንሽ ጊዜ አግኝቼ ቢሆን ኖሮ ሁለተኛውን የሻንጣ
ክፍል እበረብር ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት እድል አገኝ እንደሆን
እንጃ አለ በሆዱ ያመለጠው ዕድል እያንገበገበው፡፡

ሚኪ ፊን ወደ አይሮፕላኑ ሰራተኞች ክፍል ሄደና አዲስ ምላጭ ከሳሙናና ከውሃ ጋር ይዞለት መጣ፡፡ ሄሪ ተቀበለና አመስግኖ ይዞ ሄደ ስለጌጣጌጡ እያሰበ መታጠቢያ ክፍል ጥልቅ ሲል ሳይንቲስቱን ካርል
ሃርትማንን አገኛቸው፡ ሄሪ ሚኪ በሰጠው ምላጭ ጢሙን ሙልጭ አድርጎ
ተላጨ፡፡ ‹‹ትናንት ማታ ጉዞው በጣም መጥፎ ነበር›› አለ ወሬ ለመጫር፡
‹‹ለኔ ደግሞ የበለጠ መጥፎ ነበር›› አሉ ሃርትማን፡፡

ሄሪ የሳይንቲስቱን የከሳ ሰውነት ሲያይ ተደነቀ፡፡

‹‹አዎ እውነት ነው ለእርስዎ በጣም መጥፎ ምሽት ነበር›› አለ፡

ከዚህ በላይ ያወሩት ነገር የለም፡፡ ሃርትማን ወሬ የሚወዱ ሰው አይነት አይመስሉም፡፡ ሄሪ ደግሞ ልቡ ያለው ጌጣጌጡ ላይ ነው ሄሪ ጢሙን ከተላጨ በኋላ አዲስ የገዛውን ሰማያዊ ሽሚዝ ለበሰና
ከሸሚዙ ጋ የሚሄድ ክራቫት አሰረ፡፡

ወደ መቀመጫው ሲመለስ የማርጋሬት መጋረጃ መዘጋቱን አየ::ጸጉሯን ትራሱ ላይ በትና እንቅልፏን ተኝታ ታየችውና ፈገግ አለ፡፡ ምግብ ቤቱ ክፍል ውስጥ አስተናጋጆች ምግብ እያቀረቡ አየና አፉን ምራቅ ሞላው:

የሚኪን የጢም መላጫ ዕቃዎች ይዞ ደረጃውን ወጣና የበረራ ክፍል
አካባቢ ተመልሶ ሄደ፧ ዕድሉን እንደገና ለመሞከር፡፡

ሚኪ እዚያ የለም፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ቁጭ ብሎ ስሌት ሲሰራ አገኘ፡፡ ሰውየው ቀና አለና በፈገግታ ‹‹ጤና ይስጥልኝ ምን ትሻለህ የኔ ወንድም?›› አለው፡፡

‹‹ሚኪን ነው የምፈልገው፤ ምላጩን ልመልስለት››
‹‹ቁጥር አንድ ክፍል ውስጥ ታገኘዋለህ››
‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ሄሪ፡፡ ይህን ሰውዬ አልፎ መሄድ ሊኖርበት ነው፡፡
ግን እንዴት?
‹‹ሌላ የፈለግኸው ነገር አለ?›› ሲል ጠየቀ ሰውየው ፈገግታ ሳይለየው፡፡

‹‹ይሄ  የበረራ ክፍል
የሚገርም ነው›› አለ ሄሪ ‹‹ቢሮ ነው  የሚመስለው››

‹‹ይደንቃል፡ አይገርምም?››
‹‹በአይሮፕላን ላይ መስራት ትወዳለህ?››
‹‹እወዳለሁ። አየህ ካንተ ጋር ባወራ ደስ ይለኝ ነበር፧ ነገር ግን አይሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት ስሌቱን መጨረስ አለብኝ›› አለ፡

ሄሪ ወሽመጡ ቁርጥ አለ፡፡ ወደ ሻንጣዎቹ ክፍል መሄድ አይቻልም ማለት ነው› አለ በሆዱ፡ ወደዚህ ክፍል ለመግባት የሚያስችለው ምንም ምክንያት አይኖርም፡ ንዴቱን ዋጠና ‹‹ይቅርታ›› አለ ‹‹እሺ እመለሳለሁ፡››
ወትሮው ከተሳፋሪዎች ጋር እናወራለን፡፡ ብዙ ዓይነት ሰዎች በበረራ ወቅት ይገጥሙናል፡፡ አሁን ግን ጊዜ የለኝም፡››

እኔ ነኝ ጥፋተኛው በዚህ ሰዓት መምጣቴ›› አለና ዕድሉን እየረገመ በደረጃው ወርዶ ሄደ ለሁለተኛ ጊዜ ዕድሉ እንደተበላሸ አየ፡
የተዋሰውን ምላጭ ለሚኪ መለሰና ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

ማርጋሬት ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷታል፡፡ ሄሪ ወደ ውጭ ሲወጣ
ቀዝቃዛ አየር ተቀበለው፡፡ በህይወት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገጥም ወርቃማ
ዕድል አመለጠኝ አለ በሆዱ፡፡ እሱ ካለበት ቦታ ጥቂት ራቅ ብሎ የሚገኘውን ውድ ጌጥ ሲያስበው እጁን በላው፡ግን
ግን ተስፋው ገና አልተሟጠጠም፡ ከዚህ በላይ አሜሪካ ከመድረሳቸው በፊት አይሮፕላኑ የመጨረሻ ማረፊያ ላይ ዕድሉን ይሞክራል፧ ሼዲያክ ላይ።፡፡

ይቀጥላል
👍24😁1
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አርባ ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ሄሪ ማርክስ ሰውነቱ በደስታ ስለተጥለቀለቀ አልተንቀሳቀሰም፡፡ አልጋው ላይ ተጋድሞ ትናንት ማታ የሆነው ሁሉ በአዕምሮው መጣበት፡፡ ማርጋሬት ድንገት ስትስመው የተፈጠረው ደስታ፣ እሷን በእጁ ለማድረግ ምን ያህል ሆዱ እንደፈራ፣ በመጀመሪያ ሃሳቡን አልቀበልም ማለቷ እና በመጨረሻም ልክ ወደ ጉድጓዷ እንደምትገባ ጥንቸል…»