አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ዲመካና ቱርሚ ሁለቱም የሐመር አውራጃ የገጠር ከተሞች ናቸው" ለቆላማው የሐመር ክፍል ቱርሚ፣ ለደጋማው ደግሞ ዲመካ
አማካዮች ሲሆኑ፣ ሁለቱም ደረቅና ቁጥቋጦ የበዛበት መሬት ያላቸው ናቸው። ቱርሚ መንገድ ዳር ያለ ከተማ ሲሆን፣ ከዲመካ ይልቅ ሁለት ትናንሽ ምግብ ቤቶች፣ ወደ አምስት የሚደርሱ ሻይና ቂጣ
መሸጫ ቤቶች፣ ሁለት በመጠን ከፍ ያሉና ትናንሽ ሳሙና፣ ባትሪ ድንጋይ፣ ክብሪት...የሚሸጥባቸው መንገድ ላይ የሚዘረጉ ሱቆች አሉ። በተለይም በገበያ ቀን ከተማዋ ደመቅዐመቅ ብላ ትታያለች
ገበያ ውስጥ ለመጠጥ ቦርዴና የአበሻ አረቄ፣ ግልድም የሚሆን ከጥጥ
ተሠርቶ ከኮንሶ በነጋዴዎች የሚመጣ ሳዳጎራ፣ ጨሌና አንባር፣በቆሎና ማሽላ ዓይነተኛ ሸቀጦች ናቸው" ቱርሚ፣ በከብት እርባታና
በቁፋሮ ምርት ለሚተዳደረው የሐመር ሕዝብ ድል ያለች ከተማ፣
ታምሮና ተውቦ የሚታዩባት፣ ጐረምሳና ሴቱ አብሮ መሸታ ገብቶ የሚደባበስባት፣ የተጣላ የሚታረቅባት፣ ሽማግሎች ተሰባስበው
የሚመክሩባት፣ ብርቅዬ ከተማ ናት ለሐመሮች።

ዲመካ ግን፣ ከዋናው መንገድ ወጣ ብላ፣ ሰቀላ ቤቶች በአራት ማዕዘን ተሰትረው የሚታዩባት ከተማ ናት። በየሰቀላ ቤቶች ፊት ለፊትና በስተኋላ የግራር፣ የብርብራ.ዛፍ ያለ ሲሆን ከከተማው ግርጌ፣ ከወንዙ ጥግ በሚስዮናውያኑ የተተከለ በፀሐይ ብርሃን በሚንቀሳቀስ መስኖ የለማ የፍራፍሬ፣ የበቆሎና ሌሎችም ወቅታዊ
አዝርእቶች የሚታይ ሲሆን፣ ከጎን በኩልም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንፃና ጋራዡ፣ ዲመካን አንድ ዓይና ከመሆን አድኗታል"የገበያ ቀን፣ በየሰቀላ ቤቱ ጠጅ የሚሸጥ ሲሆን፣ ምግብ ቤት ግን ከናካቴው የለም" ደግነቱ፣ እንግዳ ብርቅ በመሆኑ ጋባዡ ብዙ ስለሆነ
እግር የጣለው ሰው ሕቅ ብሎ ሲያዝን አይሰማም" በተረፈ ገበያ ውስጥ ያለው ሸቀጥ ከቱርሚ ጋር ተመሳሳይ ነው ሁለቱንም ከተሞች ቡስካ ስር ካሉት ላላና ሻንቆ እስከ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዳ
መንደር ድረስ የሚያገናኛቸው የማኅበረሰብ ሕይወት የሆነው የከስኪ ወንዝ ነው ከብቱ፣ ፍየሉ፣ በጉ፣ ሰው፣ አዕዋፍ...ሁሉም ጥሙን
ይቈርጥበታል።

ካርለትና ከሎ ሆራ ከዲመካ ወጣ ብላ ከምትገኘው የሻንዛ መንደር መኖር ከጀመሩ ሁለት ወራት አለፋቸው የክልሉ ኗሪዎ
ከሎ ሆራን እንዳዩ፣ «የሆራ ሻላ ልጅ» እያሉ፣ ሰላምታና ስጦታ አጐረፉለት ቆዳ ለባሽ እናቱና እኅቶቹም ደረታቸውን በመድቃት
የደስታ እንባ እያነቡ አስተናገዱት።

ካርለት፣ በቆይታዋ የተለያዩ ልምዶችን አገኘች። ከዘመናዊ ሕይወቷ እንደ ባንዲራ ወርዳለችI ይህን አጋጣሚዋን ግን በግላዊ
ትርጕሟ እንደ መጥፎ ከመውሰድ ይልቅ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰዷ የሚሰማት ስሜት የደስታ ስሜት ነው። ይህ ደግ
ማኅበረሰቡን ለመቅረብና ለመርዳት እንድትጣጣር አድርጓታል ስለዚህ፣ ካርለት የከሎ ሆራን እናትና እኅቶች፣ የአካባቢው ሴቶችና ወንዶች ለመቅረብ የቋንቋ ትምህርቷን በማጠናከር ልትግባባ ሞክራለች ቢሆንም ግን፣ በወደፊቱ ጥናቷ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት
እየሆነባት የመጣው በሴቶች ላይ ያለው ባህላዊ ተፅዕኖ እንደ ጋለ ብረት ምጣድ አላስጠጋሽ አላት"¸

በማኅበረሰቡ፣ ሴት ሣቂታ ወንድ ኰስታራ ነው" ሴት በልጃገረድነቷ የአባቷ፣ ባል ካአገባች ደግሞ የባሏ ጥገኛ ናት" ስለዚህ
በልባዊ ኵራት የተሞሉት የሐመር ወንዶች ካርለት ሴት ሆና እንዴት ባሏን ወይንም አባቷን ጥላ ወደ እነሱ እንደ መጣች በጣም
አስገርሟቸዋል" ሽማግሎች እንዲያውም፣ «ይእ! እሷ ምን ታድርግ? አባቷ ወይም ባሏ፣ ብቻዋን መልቀቃቸው ከቶ ምን ያሉ ነፈዞች ቢሆኑ ነው» ብለው አውግዘዋል"
ስለሆነም፣ ካርለት የጥናት ኮተቷን ይዛ ለጥያቄ ቀረብ ባለቻቸው ቍጥር የደስታ ገጽ ስለማታይባቸው ለተወሰነ ቀን ግራ ተጋብታ
ነበር" አንድ ቀን ግን ወንዶች ሊያደርጉት ባሰቡት ስብሰባ ለመካፈል ሄደች። ገላጣ ስፍራ ላይ ካለ ትልቅ ግራር ጥላ ሥር፣ የሻንቆ መንደር
ሽማግሌ፣ አባወራ፣ ጐረምሶች ተሰብስበዋል" ከወገብ በላይ ራቁት
ሆነው፣ ቆዳቸው የተሸበሸበ፣ ጸጕራቸው ገለል ብሎ ሽበት ጣል
ጣል ያደረገበት አዛውንት በሁለት ወገን ጦር የተሰካበት ብትር ይዘው፣ መሬቱን ወጋ ነቀል እያደረጉ ወዲያ ወዲህ እየተንቀሳቀሱ
ንግግር ሲያደርጉ ሁሉም ጸጥ ብሎ በተመስጦ ሲያዳምጥI ካርለት
ስብሰባውን ለመካፈል ጓጕታ ቀስ እያለች ተጠግታ ልትቀመጥ ስትል
ሁሉም ዘወር ብለው አይዋትና በስብሰባው መካፈል እንደማትችል
ነገሯት"

ካርለት፣ ወንዶችን ለመቅረብ አለመቻሏ ብቻ ሳይሆን፣ ሴቶችም
ምሥጢራቸውን ሊገልጹላት ባለመቻላቸው ግራ ተጋብታ ቅር ተሰኘች" በተለይ ደግሞ፣ ለመሳተፍ ጓጕታለት በነበረው የወንዶች
ስብሰባ ልትካፈል ባለመቻሏ ጥልቅ ኀዘን ከመስማት አልፎ ለወደፊቱ አደርገዋለሁ ብላ የደከመችለት ጥናት ሊሳካ አይችልም ብላ ሠጋች"
ስለዚህ፣ ዓይኗ ቁንዶ በርበሬ መስሎ እስኪቀላ ድረስ እያለቀሰች፣ «ከሎ! ለምን ወንዶች ጥያቄዎቼን ለመመለስ ፈቃደኛ
አይሆኑም? ለምንስ በስብሰባቸው እንዳልካፈል ይከለክሉኛል? በዚህ
ዓይነት ጥናቴንስ እንዴት ማድረግ እችላለሁ? » ብላ ጠየቀችው።

«በሐመር ማኅበረሰብ ሴት ወንድን ለመርዳትና ለማገልገል የተፈጠረች ጸጋ ናት። ለወንዶች ትንባሆ ታዘጋጃለች ልጃገረድ
ከሆነችም ታርሳለች፤ የከብቶችን በረት ታጸዳለች ሕፃናትን ትንከባከባለች ምግብ ታበስላለች.እንጂ ከወንድ ጎን ተቀምጣ ስለ
ማኅበረሰቡ ችግር በመነጋገርና በመምከር መፍትሔ መፈለግና ጦርነት
መግጠም አትችልም።

«ካርለት፣ አንቺ ወንድ ብትሆኚ ኖሮ ምንም ችግር ላያጋጥምሽ ይችል ነበር" ሆኖም ግን አንቺ ሴት ነሽ። ለሐመር ሴቶች የወጣው
ደንብ ማንኛዋንም ሴት ያጠቃልላል፣ ብለው ስለሚያምኑ በስብሰባቸው እንድትካፈይ አለመፍቀድ ብቻ ሳይሆን፣ የምትጠይ
ቂያቸውንም ሙሉ በሙሉ ለመመለስ ፈቃደኛ አይሆኑም" እኔም
ይህ ችግርሽ እጀ ሰባራ ሊያደርግሽ እንደሚችል እየተሰማኝ መጥቷል" ምናልባትም ችግሩ ግልጽ ከሆነልሽ የግልሽን መፍትሔ
ውሰጂ» አላት"

ካርለት ፈጽሞ ያልጠበቀችውን መልስ በማግኘቷ በባህላዊ
ልዩነቱ በጣም ተሸማቀቀች በአሁኑ የጥናት አያያዟ በእርግጥ ለመቀጠል አለመቻሏ ቁልጭ ብሎ ታያት በአእምሮዋ አውጥታ
አውርዳ የወሰነችው ውሳኔ፣ እስከ አሁን ያደረገችው ጥረትና ጒዞ ጥሩ የድንጋይ ምት እንዳረፈበት መስተዋት ከሽ ብሎ ሊሰበር
የተቃረበ መስሎ ታያት። ያ ችሎታዋንና ጥንካሬዋን የሚያስመሰክረው፣ ማንነቷን የሚያረጋግጠው፣ ብቃቷን ማያዋ መስተዋት
እንዲሰበር ግን ጭራሽ አትፈቅድም። በዚህም ተባለ በዚያ የጀመረችውን ከግቡ ለማድረስ ሕሊናዋ እሷን ወደፊት መግፋት
አለበት" ሰዎች ከጎሪላና ከእፉኝት፣ ከአንበሳና ከተኩላ ጋር በሐሩርና
በረዶ መኖር መቻላቸውን አስመስክረዋል" እሷም ዓላማዋን ከግቡ
ለማድረስ ተጣጣፊና ጠንካራ ለመሆን ከራሷ ጋር ተማማላች" ግን ምን መላ ትምታ? ለተወሰነ ቀን ካለ ዕረፍት በዚህ ጉዳይ ላይ ስታስብ ከቆየች በኋላ ምንም እንኳ የችግር ኮተቱን ዓይኗን ጨፍና አላይም
ብትልም፣ የሚያጋጥማት ሥቃይ ከባድ መሆኑን አውቃ ቀበቶዋን አጠበቀች

ከዚያም፣ ያሰበችውን መላ ለመጀመር ያስችላት ዘንድ ባል አለማግባቷን የሚገልጽ ወሬ ለአገኘችው ሁሉ አወራች" ወሬው ተዛምቶ በየመንደሩ መዳረሱን ስታረጋግጥ ደግሞ ጐረምሶች፣ ወጣት
ባለትዳር ወንዶች፣ ያላገቡና ባለ እጮኛ ልጃገረዶች ምሽትን ተገን አድርገው ወደሚቦርቁበት የምሽት ጭፈራ «ኢቫንጋዲ» ለመካፈል ነኢማ ከምትባለው የከሎ ሆራ እኀት ጋር ስትሄድ ምንም ተቃውሞ ሳይደርስባት ቀረ።
👍271
ካርለት ለጭፈራ እንግዳ አይደለችም። እንዲያውም አሳምራ የመደነስ ትምህርትና ልምድ አላት ኧረ ነበራት ማለት ይሻላል"
በምሽት ጭፈራው (በኢቫንጋዲ) ግን የምታምቧትር ሕፃን ሆነች
በኢቫንጋዲ ከአምስት ዓይነት በላይ የጭፈራ ስልቶች ሲኖሩ ስልቱ
በዘፈቀደ መወዛወዝ ሳይሆን አንድ ወጥና ደረጃ በደረጃ የወሲብ ስሜትን ሊቀሰቅስና ሊያጋግል በሚችልበት ዘዴ የተቀነባበረ መሆኑን
ካርለት ቀስ በቀስ በሚገባ አጤነች።

መጀመሪያ ወንዶች ብቻ እየዘለሉ ሰውነታቸውን ያሟሙቃሉIቀጥሎ ወንዶች አባራሪ ሴቶች አቅጣጫ ቀያሪ እየሆኑ ይሾራሉI
ከዚያ የወንዶች ጭን በሴቶች ጭን ስር ያልፍና ውስጥ ሱሪ አልባ ገላዎች አንዱ «ጀነሬተር» ሌላው «ኦፕሬተር» ይሆንና በሚፈጠረው የኤሌክትሪክ ሞገድ ሲናጡ ሁለቱም
ተያይዘው ወደ ጫካ
ይሠወራሉ ጭፈራ…ግለት…ጫካ እርካታ ብቻ አበቃ!

ካርለት፣ ከነኢማ የጭፈራውን ስልት እንደ ለመደች ለተወሰነ
ጊዜ የመጨነቅ ስሜት ይሰማት እንጂ ቀስ በቀስ ተካነችበት" ቀጭን
ወገቧና ዳጐስ ያለው ዳሌዋ፣ ከእግርና እጆቿ ጋር ተዋሕደው በጨረቃ ብርሃን ጫካን ተገን አድርገው ሾሩ"

ይሁን እንጂ መቼም «አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን በያዝሽ»
ነውና ይፈጠራል የማትለው ስሜት፣ በዳንሱ ስልታዊ እንቅስቃሴ ይፈጠርባት ጀመር። በተለይ አንድ ምሽት፣ ጎሽና ቀጭኔ ገዳይ
የሆነውና በተኳሽነቱ የሚደነቀው ደልቲ ገልዲ ልክ እንደ ማንኛዋም
ሴት ወደ ጭፈራ ጋብዛው፣ ጥቁሩና ለስላሳው ጭኑ፣ በነጩና ለስላሳ ጭኗ ሰርጎ ገብቶ፣ የወንድ ብልቱ የሴት ብልቷን አካባቢ አሸትሸት
ሲያደርግላት፣ ሞገዱ ክፉኛ ናጣት" ያኔ በደብዛዛዋ የጨረቃ ብርሃን
ደልቲን አሻቅባ በማየት እጆቿን ወደ ማጅራቱ ስትሰድ፣ እሱ ግን
እጇን አስለቅቆ ወደ ዋንዛና ግራሩ ጫካ ሲሄድ ተከተለችው ደልቲ፣ ለምን ጫካው ውስጥ እንደ ገባ ምክንያቱ ባይገባትም፣ ወዲያው ግን ፍላጎቱና ፍላጎቷ ተጠቃቅሰው ፊቷን ዞራ እንድትቀርበው
አደረጋት"

ካርለት እስከ ጠዋቱ አራት ሰዓት ከድንኳኗ ሳትወጣ ተኝታ አረፈ ደች" ለሐመር ሴቶች አንድ በኢቫንጋዲ ጭፈራ ስትውረገረግ ያደረች ሴት በድካም ተኝታ ብታረፍድ ማንንም አያስደንቅም ነበረና
ከመኝታዋ እንደ ተነሣች የተለየ ሁኔታ ከአካባቢው ኗሪዎች አላየችም።
ካርለት፣ ሰውነቷ ውልቅልቁ የወጣ ያህል ቢሰማትም፣ የማታው ትዕይንት ግን ወለል ብሎ ታያት። ከልቧ ጨፈረች በፈቃደኝነት ስሜቷን ለግሳ እሷም ስሜቷን አረካች" ደልቲ ገልዲና እሷ በአንድ ዓይነት ቋንቋ ለመግባባት አልሞከሩም እሷም
እሱ ራሳቸውን ሆነው፣ በራሳቸው ቋንቋ ቢነጋገሩም፣ አንዱ ሌላው
ያለውን ለመረዳት አልተሳነውም የተፈጥሮ ስሜት በተፈጥሮ
«ኮድ» ካለምንም ችግር መገለጽ ስለሚችል ግራ አልተጋቡም ያጋሉት ብረት ምጣድ ሳይቀዘቅዝ ግን ስሜታቸውን ለማርካት
ሁለቱም የሚወዱትን ጥብስ ጠበሱበት ካርለት፣ የብዙ ወንዶችን እጅ ተንተርሳለች" ደልቲም ቢሆን የብዙ ሐመር ልጃገረዶችን ወገብ አቅፏል" በመካከላቸው ፈላጊና ተፈላጊ አልነበረም። ተጠጋጉ፣ ተነካኩI ሁለቱም ሞተር አስነሡ አብረው ነጐዱI ካሰቡት ደረሱ አበቃ!

የሐመር ወንዶች የአልኮል ፈረስ አይደሉም" መጫወት
መዝናናት ግን ባህላቸው ነው። የስሜታቸው ባለቤት ሆነው ይጀምራሉ” የስሜታቸው ባለቤት እንደሆኑ ይጨርሳሉ" የፍትወት ፍላጎታቸውን ለማርካት ኃይልን አይጠቀሙም" ይህን ደግሞ ካርለት ራሷ አይታ አረጋግጣለች በጭፈራው ስሜቷን እንዲያረካ የከጀለችው ሰው ቢኖራትም የመጀመሪያዎቹን ስሜት አነሳሽ የጭፈራ ስልቶች ከሌሎች ወንዶች ጋር ጨፍራለች የመጨረሻዋ ስልት ጊዜ ግን ተሽቀዳድማ ደልቲ ገልዲን ጋበዘችው" በዚያ ቁመናው ወገቡ
ላይ ካገለደመው ሳዳጉራ በስተቀር ምልምል ራቁቱን «አኖ» በተባለው አፈር ሰውነቱን አዥጐርጒሮ፣ ክንዱ ውስጥ የጠቀለለው
አንባር እያብለጨለጨ፣ አየሩን ግራና ቀኝ እየቀዘፈ፣ በመዝለልና በማሸብሸብ፣ በፈገግታ ጠጋ ብሎ እጁን ትከሻዋ ላይ፣ ጭኖቹን
ጭኖቿ ውስጥ ሲያስገባ፣ ካርለት ድንጋዩ እንዳለቀበት ባትሪ ሐሳቧ ብዥ ብዥ አለባት ስሜቷ ገመዱን በጥሶ በረረ ለመያዝ ሞከረች ግን በምን ኃይሏ! መላ ሰውነቷ እየተልፈሰፈሰ፣ ዓይኗ እየተስለመለመ፣ በተወዛወዘች ቍጥር ሰውነቷ እንደ ጀርመን ካቴና ይበልጥ እየተጣበቀ ሲሄድ ተሰማት።

ቢያንስ ደራሽ ስሜቷን ለማሳለፍ አስባ ነበር። ስሜቷንም ለመከታተል ጓጕታ ነበር“ ግን ምን ይሆናል፣ ወጥመድ ውስጥ የገባ አውሬ ሆነች" ስለዚህ፣ የወሲብ ስሜቷን ለመቆጣጠር ተስኗት
ቀድማ ስሜቷን አጣች ተሸነፈች" በተመራማሪዋ ላይ አዲስ ተመራማሪ ተፈጠረባት"።

ወደ ጫካ ሲወስዳትም ወደ መኝታ ቤቷ የምትሄድ እንጂ! ወደማታውቀው ጫካ የምትጓዝ አትመስልም ነበር" ከዚያም እንኳን
ኃይለ ቃል፥ አንዲት ቃል ሳይተነፍስ የውስጥ ሱሪዋን ያወለቀችም እሷ ናት። ካርለት፣ ትክክለኛው ጭፈራ ሰዎችን እርቃናቸውን እንዲ
ወዛወዙና ሰላማዊ የመጠላለቅ ዋናን እንዲፈጽሙ የማድረግ ኃይሉን ተረዳች" እና፣ በጭፈራው ስሜት አነሣሽነት፣ ቅንብርና በሐመር ወንዶች የሴቶችን ስሜት አዳማጭነት ተደነቀች።

ካርለት አንድ ከራሷ ልትደብቀው ያልፈለገችው እውነት ደግሞ የደልቲ ገልዲን የስሜትና አካል ጠንካራነት ነው በትናንቱ ምሽት ዕድሜ ልኳን ያልተሰማት ልዩ ደስታ ማግኘቷም ሌላው ያስደነቃት ጉዳይ ሆነ" ሥልጣኔ ካላዘመነው የተፈጥሮ ቦታና ሰው፣ እውነትስ አዲስ ግኝት ሲገኝ ማን እማይደነቅ አለ?

መላ የስሜት ሕዋሶቿን በአንድ ቍልፍ ነካክቶ፣ አንዱንም ሳያስከፋ፣ ሁሉንም እንደ ባሕርይው አስደስቶ፣ የሚያዝናና ወንድ
በሕይወቷ አንድ ወቅት አጋጥሟታል የዚህኛው የወሲብ ጥንካሬ
ግን ለጉድ ነው" ይህ ጥንካሬው ግን ከአመጋገቡ ይሆናል ብላ ገምታለች የከብት ደምና ወተት ቀላቅሎ መጠጣት፣ ቅል ሙሉ ማር፣ ከማሽላ የተሠራ ምግብ፣ የበሰለ ሥጋ፣ የዱር ፍሬና ቅጠላ
ቅጠል መብላት ለጥንካሬው አስተዋጽኦ እንዳለው አመነች"
በምሽት ጭፈራው የተካፈሉት ወንዶችና ሴቶች ከደልቲ ገልዲ ጋር ወደ ጫካ ስትጓዝ አይተዋታል። ሆኖም ግን፣ ሴቶችም ሆኑ
ወንዶች በጥላቻ ዓይን አላዩዋትም" ስለዚህ ማኅበረሰቡ ለቅናት
ያለው ግምት አስደንቋታል" ይህ ሁሉ አስገረማት ከተኛችበት ሳትነሣ ከልቧ በሣቅ ተንከተከተች ካርለት።...

💫ይቀጥላል💫
👍36
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወሮበሎቹ የሚፈልጉትን ማግኘታቸው አያስደስተውም የሉተር ዕቅድ ቢጨናገፍ ደስታው ነበር፡፡ ነገር ግን ሉተር ጎርዲኖን ካላስለቀቀ ኤዲ ካሮል አንን ማግኘት አይችልም፡፡

ካሮል አንን በእጄ ካስገባሁ በኋላ ጎርዲኖ መያዙ አይቀርም  ሲል አሰበ፡ ይህ ግን የሚሆን አልመሰለውም፡፡ ጎርዲኖ በዚህ ጊዜ ውስጥ ርቆ
ሊሄድ ይችላል፡ ሌላው አማራጭ ሉተር ካሮል አንን በመጀመሪያ በእጁ
እንዲያስገባለት መደራደር ቢሆንም ሉተርን ለማስገደድ ምንም ማስፈራሪያ የለውም፡ ሉተር በአንፃሩ ካሮል አንን ይዟል፡

ወዲያው አንድ ሃሳብ ብልጭ አለበት፡፡ ጎርዲኖ በእኔ እጅ እኮ ነው ያለው፤ እሱን እንደማስፈራሪያ መጠቀም እችላለሁ› አለ፡፡ እነሱ ካሮል አንን ይዘዋል፧ እሷን ለማግኘት ከእነሱ ጋር መተባበር አለብኝ፤ ነገር ግን ጎርዲኖ በዚህ አይሮፕላን ላይ ነው ያለው፡፡ እሱን ማግኘት ከፈለጉ ከእኔ ጋር
መተባበር ይኖርባቸዋል
ሁሉም ነገር በእነሱ እጅ አይደለም ሲል በአዕምሮው አውጠነጠነ።

ስለዚህ የድርድሩን መዘውር በእጁ ማስገባት የሚችልበት መንገድ
ይኖር እንደሆን ማሰብ ጀመረ፡፡

አንድ መንገድ ይኖራል።

ለምንድን ነው እነሱ በመጀመሪያ ጎርዲኖን የሚወስዱት? ልውውጡ
መሳ ለመሳ ነው መከናወን ያለበት፡፡›

ከዚያም ንዴቱን ውጦ በጥልቅ ማሰብ ጀመረ፡

‹እንዴት ነው ልውውጡ ሊከናወን የሚችለው?

ጎርዲኖን ሊወስዱ በሚመጡበት ጀልባ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው።
ለምን አይሆንም?  ሲል ከራሱ ጋር ተሟገተ፡፡ እሷን ያገቷት ከቤታቸው ብዙም ባልራቀ ቦታ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህም  ቦታ አይሮፕላኑ ከሚያርፍበት ቦታ ብዙም እንደማይርቅ ገምቷል፡፡ ምናልባትም ከአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦታ እሷ እስከታሰረችበት ቦታ ድረስ የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ሊሆን ይችላል፡ ይሄ ደግሞ ሩቅ አይደለም፡፡

ኤዲ ባሰበው እቅድ ሉተር የሚስማማ ከሆነ ጓደኞቹን በስልክ ሊያናግር
የሚችለው አይሮፕላኑ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ቦትውድ (ካናዳ) ላይ ሲደርስ ይሆናል፡፡ ከቦትውድ ቀጥሎ አይሮፕላኑ የሚያርፈው ከሰባት ሰዓት ጉዞ በኋላ ማለትም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ሼዲያክ ላይ ነው: ወሮበሎቹ ደግሞ
በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ እዚያ ቦታ ላይ ካሮል አንን ይዘው መምጣት
አለባቸው::

ኤዲ ካሮል አንን አስቀድሞ በእጁ ሊያስገባ እንደሚችል ሲያስበው ደስታውን መቆጣጠር አቃተው፡ የሉተርንም ጎርዲኖን የማስለቀቅ ጥረት
ሊያመክን እንደሚችል ትንሽ እድል እንዳለ ሲያስበው ደግሞ ተጨማሪ
ደስታ ፈጠረለት፡፡ ይሄ ደግሞ በስራ ባልደረቦቹ በኩል ጀግና ያስብለዋል፡
እነዚህን ነፍሰ ገዳይ ወሮበሎች መያዝ ከቻለ ጓደኞቹ ቀደም ብሎ ለፈጸመው ክህደት ምህረት ያደርጉለታል፡፡
መለስ ብሎ ሲያስበው ደግሞ ብዙ ተስፋ ማድረግ እንደሌለበት ገባው፡፡
ይሄ ሁሉ ገና ሀሳብ ነው፡፡ ሉተርም ባሰበው እቅድ አልስማማም ሊል ይችላል ኤዲ ያቀረበውን እቅድ ወሮበሎቹ የማይቀበሉ ከሆነ አይሮፕላኑን
የተባለው ቦታ እንደማያሳርፍ ያስጠነቅቃል፡ ነገር ግን ወሮበሎቹ የኤዲን
ማስፈራሪያ ከባዶ ዛቻ እንደማይዘል መገመት አያቅታቸውም፡፡ ኤዲ ሚስቱን ለማዳን ሲል የተባለውን ሁሉ እንደሚፈፅም ያውቃሉ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን
ሰው በእጃቸው ከማስገባት ውጭ ምንም ፍላጎት የላቸውም፡፡ እኔ ከነሱ
በላይ የተቸገርኩ ስለሆንኩ አቅመ ቢስ ነኝ ሲል አሰበ፡፡ ይህም ወደ ቀድሞው መከፋት ወሰደው፡፡

ሆኖም ኤዲ ያሰበውን ለሉተር ለመንገር ሰውዬውን ለመፈተን አሰበ፡፡
ቢያንስ ሰውዬውን ጥርጥርና ጭንቀት ውስጥ መክተት ይችላል፡፡ ምናልባት ሉተር የኤዲን ማስፈራራት አምኖ ላይቀበል ይችላል፡ ግን እንዴት እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹ኤዲ ውሸቱን ነው› ለማለት ወኔ ይጠይቃል፡፡ ሉተር ደግሞ ፈሪ እንደሆነ ታይቷል፤ በተለይ አሁን፡፡

ኤዲ ያሰበውን ለመሞከር ቆረጠ፡፡ ከሉተር በኩል ሊመጣ የሚችለውን
ተቃውሞ ለመመከት የሚያስችል ምላሽ አስቀድሞ መቀመር አለበት፡፡

ሉተር እንቅልፍ ካጡት ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በእንግዳ መቀበያው አንድ ጥግ ቁጭ ብሎ ብቻውን ዊስኪውን ይጨልጣል፡፡አይሮፕላኑ የፈጠረበት የሆድ መታወክ አሁን ስለቀነሰለት ፊቱ ፈካ ብሏል መጽሔት እያነበበ ነው፡፡ ኤዲ አጠገቡ ሄደና ጀርባውን ነካ አደረገው፡፡ ሉተር ኤዲን ሲያይ ደንገርገር አለው፤ ፍርሃት ብጤም ስለተሰማው ጠብ ጠብ ሸተተው፧ ኤዲም ‹‹ሚስተር ሉተር ካፒቴኑ ሊያናግርህ ይፈልጋል›› አለው፡፡

ሉተር ስጋት ገባው፡፡ ከተቀመጠበት አልነሳ ሲል ኤዲ ተነስቶ የጭንቅላት ምልክት አሳየው፡፡ከዚያም ሉተር መጽሔቱን አስቀመጠና የመቀመጫ ቀበቶውን አላቆ ተነሳ፡፡

ኤዲ ሉተርን ወደ ማብረሪያው ክፍል ሳይሆን ወደ መጸዳጃ ቤት ወሰደው፡፡፤

መጸዳጃ ቤቱ በትውከት ሽታ ታውኳል፡፡ እንደ እድል ሆኖ አንድ ሰው እጁን እየታጠበ ስላገኘ ኤዲ መጸዳጃ ክፍሉ ውስጥ እንዲቆይ ለሉተር የእጅ ምልክት ሰጠውና እሱ ማበጠሪያ አውጥቶ እያበጠረ ጠበቀው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እጁን የሚታጠበው ተሳፋሪ ከመጸዳጃ ክፍሉ ወጥቶ ሄደ፡፡ ኤዲም የሰውየውን መውጣት ተከትሎ ሉተር ያለበትን መጸዳጃ በር ቆረቀረ ሉተርም ‹‹ምን ፈለግህ?›› ሲል አምባረቀ፡፡
‹‹አፍህን ዝጋና አዳምጥ›› አለው፡፡ ኤዲ ከሉተር ጋር ጠብ ለመፍጠር አላሰበም፡፡ ሉተር ግን ጠብ ጠብ ብሎታል፡፡ ‹‹እዚህ አይሮፕላን ላይ ምን
እንደምትፈልጉ ደርሼበታለሁ ዕቅዳችሁን አውቄዋለሁ አሁን  የእቅድ
ለውጥ አድርጌያለሁ፤ እኔ አይሮፕላኑን የማወርድበት ቦታ ላይ ካሮል አንን
በጀልባ ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ›› አለው፡፡ሉተር አፉን በንቀት ሸረመመና ‹‹አንተ ጥያቄ ማቅረብ እኮ አትችልም የተባልከውን ማድረግ እንጂ›› አለው፡፡

ሉተር እንዲህ አይነት መልስ ይሰጣል ብሎ ኤዲ አልገመተም፡
‹‹እንግዲያውስ ስምምነታችን እዚህ ላይ አብቅቷል›› አለው ኤዲ፡
ሉተር መጨነቁን ፊቱ እያሳበቀበት ነው፡፡ ‹‹አንተ እኮ ምርጫ የለህም፧
ስለዚህ አፍንጫህን ተይዘህ አይሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ
ያቺን ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታክል ሚስትህን ማስመለስ ትፈልጋለህ፧
ስለዙህ አፍንጫህን ተይዘክ
አውሮፕላኑን የተባልክበት ቦታ ላይ ማውረድ አለብህ››

‹‹እውነት ነው፡፡ ነገር ግን…›› ኤዲ ራሱን እየነቀነቀ ‹‹አላምናችሁም›› አለው ሉተርን «እንዴት አምናቹሀለው እኔ እናንተን አምኜ ሁሉን ነገር አድርጌ ብትከዱኝ እድሌን ማበላሸት የለብኝም።አዲስ ድርድር
እንድናደርግ እፈልጋለሁ፡፡››

የሉተር የመንፈስ ብርታት አሁንም ፍንክች አላለም፡:
አዲስ ስምምነት የለም›› አለ ፈርጠም ብሎ፡፡

አሁን ኤዲ ሉተርን የሚያንበረክክበትን ነገር መዘዘ ‹‹እሺ እንግዲያው
ወህኒ ትወርዳለህ›› አለው፡፡

ሉተር የንዴት ሳቅ ሳቀና ‹‹ምንድን ነው የምታወራው?›› ሲል ጠየቀ
ኤዲ አሁን ጥንካሬ ገባው፡፡ በአንጻሩ ሉተር ደግሞ ደካማ ሆኗል፡ለካፒቴኑ ሁሉን ነገር እነግረውና በሚቀጥለው የአይሮፕላን ማረፊያ ከተማ ላይ ለፖሊስ እንሰጥሃለን፡፡ ፖሊስ እዚያ ቦታ ላይ እንዲጠብቅህ በመገናኛ ሬዲዮ እንነግራለን፡፡ ካናዳ ውስጥ እስር ቤት ትወረወራለህ ጓደኞችህ ሊያድኑህ አይችሉም፡፡ ሰው በማገት፣ በባህር ላይ ውንብድናና በመሳሰሉት ወንጀሎች ትከሰሳለህ፡፡ እስር ቤት ውስጥ ትበሰብሳለህ›› አለው።

በመጨረሻ ሉተር መርበድበድ ጀመረ ‹‹ሁሉም ነገር በዕቅዱ መሰረት
እየተፈጸመ ነው›› ሲል የኤዲን ሀሳብ ተቃወመ ‹‹አሁን እቅዱን መለወጥ
አይቻልም፤ ጊዜ የለም፡፡››
👍17
‹‹በቂ ጊዜ አለ›› አለ ኤዲ ‹‹የሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦታ ላይ ሆነህ ለጓደኞችህ ስልክ ትደውልና የዕቅድ ለውጥ መደረጉን
ትነግራቸዋለህ፡ ካሮል አንን ወደ አይሮፕላኑ በሚመጣው ጀልባ ላይ
ይዘዋት ለመምጣት ሰባት ሰዓት ከበቂ በላይ ነው››

ሉተር በመጨረሻ አዲሱን ዕቅድ ተቀበለ፡፡ ‹‹እሺ እንዳልከኝ አደርጋለሁ።»

ኤዲ አሁንም ሉተርን አላመነውም፡፡ ወዲያው የእሱን ሃሳብ መቀበሉ
ነው ጥርጣሬ ያሳደረበት፡ ሉተር ወዲያው እሺ ያለው ለማዘናጋት ነው፡፡
የመጨረሻው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ሼዲያክ ስንደርስ እንዲደውሉልኝ
ንገራቸውና አዲሱን ዕቅድ መቀበላቸውን ያረጋግጡልኝ›› አለው ኤዲ፡፡

በሉተር ፊት ላይ የንዴት ምልክት ሽው ሲል ኤዲ አየና ጥርጣሬው እውነት መሆኑን አረጋገጠ፡፡

ኤዲ ቀጠለና ‹‹የጓደኞችህ ጀልባ ወደ አይሮፕላኑ ስትመጣ የአይሮፕላኑ
በር ከመከፈቱ በፊት ካሮል አንን ጀልባው ላይ ማየት አለብኝ ገብቶሃል
የምልህ፤ ጀልባው ላይ ከሌለች ለካፒቴኑ እነግረውና በሩ ሳይከፈት በፊት ይይዝሃል፡ በተጨማሪም የጠረፍ ጠባቂ ወታደሮች አስቀድሞ ይነግራቸውና
ጓደኞችህን እዚያው ያፍሷቸዋል፡፡ ስለዚህ ወይ ያልኩህን ታደርጋለህ
አለበለዚያ ከነጓደኞችህ ትጠፋለህ››

ሉተር ወኔው እንደገና አገረሸና ‹‹ይህን ማድረግ አትችልም›› አለ
በንቀት ‹‹የሚስትህን ህይወት አደጋ ላይ ትጥላለህ››

ኤዲ የበለጠ የሉተርን ጥንካሬ የሚሸረሽር ነገር አሰበና ‹‹እርግጠኛ ነህ
ሉተር?›› ሲል ጠየቀው፡:
ሉተርም ራሱን ነቀነቀና ‹‹አንተም ያን ያህል እብድ አይደለህም›› አለው
ኤዲ ሉተርን አሁኑኑ ማሳመን እንዳለበት ተረዳ፡፡

አሁን ችግር ውስጥ ገብቷል ከዚህ ችግር ለመውጣት ደግሞ ያለ የሌለ ሀይሉን መጠቀም አለበት፡፡ ሉተር አንተም ያን ያክል እብድ አይደለህም ስላለው ሉተርን ለማሳመን ሲል አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት አሰበና
‹‹ምን ያክል እብድ እንደሆንኩ አሁን አሳይሃለሁ›› አለና ሉተርን ወደ መስኮቱ በሃይል ገፈተረው፡፡ ግፍትርያው ሳያስበው የሆነ ስለነበር ሉተር ራሱን ለመከላከል ጊዜ አላገኘም፡፡ ‹‹ምን ያህል እብድ እንደሆንኩ አሁን በደንብ ታያለህ›› አለው በታላቅ ንዴት፡ ባልታሰበ ፍጥነት ሉተርን በጠረባ ሲለው ወለሉ ላይ ተዘረጋ አሁን የእውነት እብድ መሰለ፡ ‹‹ይሄ መስኮት ይታይሃል አንተ ድንጋይ ራስ፤ አንተን በዚህ መስኮት ለመወርወር ምን
ያህል እንደምጨክን አሁን ይገባሃል፡፡›› ከዚያም መስኮቱን ባደረገው ከስክስ
ጫማ ሲለው መስታወቱ ተሰነጠቀ፡፡ እንደገና ሲመታው መስታወቱ ተሰባ
በረ: አይሮፕላኑ አንድ መቶ ማይል በሰዓት ይበራል፡፡ ከውጭ የመጣው
በረዷማ ነፋስና ቀዝቃዛ ዝናብ እንደ አውሎ ንፋስ ነው የሚነፍሰው፡፡

ሉተር እንደምንም ከወደቀበት ተነሳ፡፡ አሁን መፍራቱ ታውቆበታል፡፡
ሊሮጥ ሲል ኤዲ ቶሎ ብሎ ባለ በሌለ ሀይሉ ገፈተረና ሚዛኑን አሳተው፡፡
የሰውነታቸው መጠን ተመጣጣኝ ቢሆንም ኤዲ እጅግ መናደዱ ጥንካሬ
ሰጥቶታል፡ የሉተር የሸሚዝ ክሳድ በሁለት እጁ ያዘና ራሱን በመስኮት አወጣው፡

ሉተር ይጮሃል።

ከውጭ የሚወጣው ንፋስ ፉጨት ከፍተኛ ስለነበር የሉተር ድምጽ አይሰማም፡፡

ኤዲ እንደገና ከመስኮቱ ላይ አወረደውና ጆሮው ጋ ተጠግቶ ‹በመስኮት
እወረውርሃለሁ›› ብሎ እንደገና አንጠልጥሎ ራሱን ወደ ውጭ ገፋው፡፡

ሉተር ባይደነግጥ ኖሮ ራሱን ማስለቀቅ አያቅተውም ነበር፡፡ ነገር ግን ድንገት የወረደበት  ውርጅብኝ ከአቅሙ በላይ ስለሆነ ራሱን መከላከል አልቻለም፡፡ አሁንም ሉተር ጮኸ፡፡ ‹‹እሺ ያልከኝን እነግራቸዋለሁ አሁን ልቀቀኝ›› አለ፡፡

ኤዲ ንዴቱ ስላልበረደለት በመስኮት ሊጥለው ምንም አልቀረውም፡፡ነገር ግን ንዴቱን መቆጣጠር እንዳለበት ተረዳ፡፡ ሉተርን መግደል የለብኝም አለ በሆዱ፡፡ ይህን የማደርገው ለማስፈራራት ነው፤ ለማስፈራራት ደግሞ
ያደረግሁት በቂ ነው፡›

የሉተርን አንገት ፈጥርቆ የያዘበትን እጁን አላላና ወለሉ ላይ ጣለው፡፡

ሉተር ጊዜ ሳያጠፋ ወደ በሩ ተፈተለከ፡፡

ኤዲ ንዴቱ እስኪለቀው የእጅ መታጠቢያው ተደገፈና ቆመ፡፡ ንዴቱ
ወዲያው እንደገነፈለ ሁሉ ወዲያው ለቀቀው ትንፋሹ መለስ ሲል ከጥቀች
ደቂቃዎች በፊት ሲያደርገው የነበረው ያልተገባ ተግባር መልሶ አሸማቀቀው፡፡

ከአፍታ በኋላ መርቪን ላቭሴይ ወደ መታጠቢያው ክፍል  ሲገባ
የተሰባበረውን መስኮት አየና ‹‹ምንድን ነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹መስኮት ተሰብሮ ነው›› አለ ኤዲ፡፡

ላቭሴይ የኤዲን መልስ የተቀበለ አይመስልም፡፡
‹‹አንዳንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ወጀብ ሲኖር መስኮት ሊሰበር ይችላል››
አለ ኤዲ ‹‹እንዲህ አይነት ወጀብ ደግሞ አንዳንዴ ድቡልቡል በረዶ ሊወረውር ይችላል፡››

ላቭሴይ ግን ኤዲ ያለውን ሙሉ በሙሉ አልተቀበለም፡፡ ‹‹እኔ የራሴን አይሮፕላን ለአስር አመት አብርሬያለሁ፧ እንዲህ አይነት ነገር ግን ደርሶብኝ አያውቅም በእርግጥ የአይሮፕላን መስኮት አንዳንዴ የሚሰበርበት ሁኔታ
አለ፡፡››

እንዲህ አይነት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል ተብሎ ስለሚገመት መቀየሪያ
መስታወት ያስቀምጣሉ፡፡ ኤዲ እዚያው መጸዳጃ ቤት ውስጥ ያለውን ዕቃ
ማስቀመጫ ከፈተና አንድ መስታወት አወጣ፡፡ ‹‹ለዚህ ነው እንደዚህ አይነት
መቀየሪያዎችን የምንይዘው›› አለ፡፡

ላቭሴይ በመጨረሻ ኤዲ ያለውን አመነና ወደ መጸዳጃው ክፍል ገባ፡

ኤዲ መስታወቱን ለመለወጥ የሚያስፈልገውን ቢቴ አወጣና ወሬው
እንዳይባዛ በማሰብ ብቻውን መስኮቱ ላይ በብሎን አሰረው፡፡

መርቪን ላቭሌይ የተሰበረውን መስታወት በአጭር ጊዜ ውስጥ ኤዲ
መለወጡን ሲያይ ተደነቀ፡፡

ኤዲ ከመጸዳጃ ክፍሉ ወጥቶ ኩሽና ገባ፡፡ ዴቪ ወተት እያፈላ አገኘውና
‹‹መጸዳጃ ቤት ያለው መስታወት ተሰብሯል›› አለው፡

‹‹ወተቱን ለልእልቲቱ ከሰጠሁ በኋላ ወዲያው ሄጄ እለውጠዋለሁ፡፡››
አለ ዴቪ

‹‹እኔ ለውጬዋለሁ››
‹‹አመሰግናለሁ›› ኤዲ፡
‹‹ታዲያ ስራህን ስትጨርስ ስብርባሪውን ለቃቅመህ ጣል››
‹‹እሺ›› አለ ዴቪ፡
ኤዲ ራሱ በፈጠረው ጠብ የተሰባበረውን መስታወት ቢጠርግ በወደደ፡፡
እናቱም እንዲህ ነው ያሳደጉት ነገር ግን ያለ ስራው ገብቶ መስራቱ
ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይጥለው መጥረጉን ፈራ፤ስለዚህ የመጥረጉን ስራ ለዴቪ ተወለት፡

ኤዲ ያሰበው ተሳክቶለታል፤ ቢያንስ ሉተርን በሚገባ አስፈራርቷል፤
ሉተር አዲሱን እቅድ ተቀብሎ ካሮል አንን በጀልባ ቀጠሮው ቦታ ድረስ
ይዟት ይመጣል፧ አሁን ተስፋ ለማድረግ በቂ ምክንያት አግኝቷል፡
ሀሳቡ እንደገና ወደ መጠባበቂያ ነዳጁ ተመለሰ፡፡

የእሱ ፈረቃ ጊዜ ባይደርስም ሚኪን ለማነጋገር ወደ ክፍሉ ሄደ፡

‹‹ቐቂ ነዳጅ ይኖረን ይሆን?›› አለ ኤዲ ምንም ያላወቀ መስሎ፡፡

‹‹ተመልከት በመጀመሪያው በእኔ ፈረቃ በሚገርም ሁኔታ ከፍ ያለ ነበር ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ኖርማል ሆነ›› አለ ሚኪ፡
‹‹ እኔም ፈረቃ እንዲሁ ነበር›› አለ ኤዲ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ፡
‹‹ እኔ ግምት እውጭ ያለው ወጀብ ሁሉንም ነገር ከቁጥጥር ውጭ
ሳያደርገው አልቀረም፡›› በኋላ ግን እስካሁን አዕምሮውን ወጥሮ የያዘውን ጥያቄ ጠየቀ ‹‹የቀረው ነዳጅ አገራችን ያደርሰናል?››

‹‹አዎ ያደርሰናል›› አለ ሚኪ፡፡

ኤዲ በግልግል ‹‹ተመስገን›› አለ አሁን የሚያስጨንቀን ነገር የለም›
አለ በሆዱ፡

‹‹መጠባበቂያ ነዳጅ ግን የለንም›› ሲል አከለበት ሚኪ፡፡ ኤዲ ከዚህ
በላይ የሚያስጨንቀው ጉዳይ አለው፡፡
👍14😁1
‹‹የአየር ጠባይ ትንበያው መረጃስ ምን ያሳያል? ምናልባትም ከዚህ በኋላ ወጀቡ ላይገጥመን ይችላል?›› ሲል ጠየቀ፡፡
ሚኪ ራሱን ነቀነቀና ‹‹አይ ወደፊት የሚገጥመን መጥፎ አየር ነው››
አለ፡፡.....

ይቀጥላል
👍14
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ሶስት (33)

‹‹እንግዲያውስ…. አንቺና ጆርጅ ተጋብታችሁ… ሥራውን ለቀሽ ማለት ነው፡፡ ለምን እየተደጋገፋችሁ ፤ ደስ እየተሰኛችሁ አትኖሩም ?! እግረ መንገዱን አዲስ አይነት ኑሮም ይሆንላችኋል » አለ ማይክ ። ማይክል ስለጆርጅ እና ስለ ማሪዮን ሂልያርድ ግንኙነት በግልፅ ሲናገር ይህ የመጀመሪያው ነበር ። ስለዚህ ጆርጅ ይህን ሲሰማ አፈረ ። ፊቱ ቀላ ። ሆኖም የመከፋት ስሜት አልታየበትም።
«ማይክል!» አለች ማሪዮን ። ያ ይህን አድርግ ፤ ይህን አታድርግ የሚለው ድምጽዋ እየተመለሰ «ማይክል እስበህ ተናገር። ሌላው ቢቀር ጆርጅን እስበው ። እንዴት እንዳስደነገጥከው ይታይሀል ? ያም ተባለ ይህ ሥራ ለመተው አልደረስኩም ። አመመኝም ቀረም ለመሥራት ጉልበት አላነሰኝም»
«እሱ እንዳልሽው ይሁን ፤እሺ ልበል። ምንም ማድረግ ልችልም። ግን ሥራ ቀንሺ። ማለት ለምሳሌ በሚቀጥለው ሳምንት ሳንፍራንሲስኮ መሄድሽ አስፈላጊ አይደለም ። እኔ ልሄድና ጉዳዩን ልፈፅም እችላለሁ ። እዚህ እዋናው መሥሪያ ቤት ቁጭ ብለሽ ይህን ያን አድርጉ ብትይን ልንረዳሽ እንችላለን ። በቃ፣ይህን ያህል እሺ በይኝ» ሳቀች እንጂ ሌላ መልስ አልሰጠችውም ። ከዚያም ብድግ ብላ ወደ መደበኛ የቢሮ መቀመጫዋ ሄደችና ተቀመጠች ። ስጋዋ እንደደከመ ይታያል ። መንፈሷ ግን ወደ ዱሮ ቦታው ተመልሷል ። ሁሉንም ካየች በኋላ ፡፡ «አሁን በከንፈር መጠጣና በአዘንልሽ አትጫኑኝ ። ሁላችሁም ማለቴ ነው ። ሂዱልኝ ። እናንተ ሥራ ከሌላችሁ… እንዲያ ይመስለኛል ሳያችሁ… እኔ ሥራ አለብኝ ፤ ልሥራበት»
«እማዬ ፤ ቤት አድርሼሽ ልምጣ።እስኪ አንዳንድ ቀን ሰው የሚልሽን እሺ በይ !» አለ ማይክል ቆጣና ኮረፍ ብሎ። «ማይክል የማይቻል ነገር አታውራ ። አሁን ቀጥ ብለህ ወደ ሥራህ ሂድ። ያለዚያ ጆርጅን እየገፈተርክ አስወጣልኝ እንዳልለው» ጆርጅ ፈገግ አለ… የነገሩ መታሰብ አስገርሞት ። «ባይሆን ሰዓት ደረሰ አልደረሰ ሳልል ለመሄድ እሞክራለሁ እንጄ አሁን አይሆንም ። በተረፈ ስለመልካም አስተሳሰብህና ስለሌላው እመሰግናለሁ ። በቃ ። ሩት ያን በር ክፈች» ጸሐፊዋ በሩን ከፍታ እንዲወጡ መጠባበቅ ጀመረች ። ማይክልና ቤን ወጡ ። ጆርጅ እደረጃው ላይ ቆሞ ፤
«ማሪዮን» አለ።
«እሀ»
«ወደ ቤት መሄድ አለብሽኮ »
«ትንሽ ቆየት ብዬ»
«ደግ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ እመለሳለሁ» ወጣ። ፈገግ አለች ። ሆኖም ወደራሷ ሀሳብ ስትመለስ ገና በሩ አልተዘጋም ።

የዛሬው ህመሟ የተነሳበት ምክንያት በሚገባ ታውቋታል ። ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ አለባት ። በሌላው ሌላ ምክንያት እየተነሳ እረፍት አሳጥቷታል ህመሙ። ሌላ መነሻ ሲጨመር ዝም ብላ ማየት አትችልም ። ለምን እንደሆነ አይግባት እንጂ ቤን አቭሪ ስለሜሪ አዳምሰን ሲናገር ሜሪ ማን እንደሆነች አውቃለች ። በርግጥ ናንሲ ማክአሊስተር ናት ብላለች ። ቅድም እስብሰባው ላይ በግልጥ እንደተናገረችው ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትሄድ ሜሪን ለማየትም ፤ ለማነጋገርም ወስናለች ። ግን ታውቃት ይሆን? ምናልባት የተደረገላት የቀዶ ጥገና ህክምና (ፕላስቲክ ሰርጀሪ) ፈጽሞ ለውጧት ሊሆን ይችላል ። ያስ ባይሆን ናንሲን በሚገባ ታስታውሳታለች እንዴ ? አይታወቅም ። ቤን አቭሪ የሰጣትን የሜሪ አዳምሰን አድራሻ አውጥታ ስልክ ደወለች። ስልኩ ሶስቴ ይሁን አራቴ ሲጮህ ተሰማት ። ተነሳ። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አቅሏን ስታ ወድቃ የነበረችው ማሪዮን ሂልያርድ መሆኗን ማንም ሊያምን በማይችልበት ደረጃ ረጋ ባለና ስልጣን በተሞላበት ድምጽ፤ «ሚስ አዳምሰን ። ማሪዮን ሂልያርድ ነኝ ፤ ከኒወዮርክ » ስትል ተናገረች ።

ንግግራቸው በጣም አጭር ፤ ተዝቃዛና በመደነጋገር የተሞላ ነበር። ማሪዮን ሂልያርድ ስለሜሪ አዳምሰን በተጨማሪ ያገኘችው እውቀትም አልነበረም ። ይሁን ። ልክ የዛሬ ሶስት ሳምንት ማወቅ የሚገባትን ሁሉ ታውታለች ። ሊገናኙ ተቀጣጥረዋል ። ማሪዮን ቀጠሮውን አጀንዳዋ ላይ ካሰፈረች በኋላ የወንበሯን መከዳ ደገፍ ብላ ወደ ኋላዋ ተለጠጠች ። አይኖቿን ዘጋች ።

ከሜሪ አዳምሰን ጋር ከተገናኙም በኋላ ምንም ጠቃሚ ነገር ላታገኝ ትችላለች ። ሁሉም እንዳሰበችው ላይሆን ይችላል ። ወይም ሜሪ ምንም ነገር ላለመናገር ትወስን ይሆናል... ሆናም ያን ቀን ትፈልገዋለች ። ልትናገራቸው ያውጠነጠነቻቸው ጥቂት ነገሮች አሉ ። ብቻ. . . ብቻ ከዚያ ወዲህ ክፉ ነገር እንዳያጋጥማት። ትልቁ ምኞቷ ይህ ብቻ ነው።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ሶስት ሣምንት ሲደርስ አጭር ጊዜ ነው፡፡ ሲያስቡት ይርዘም እንጂ፤ የማሪዮን ሂልያርድና የሜሪ አዳምሰን ቀጠሮ ደረሰ ከሶስት ሣምንት በኋላ እለተ ሰሉስ ።

ማሪዮን ሂልያርድ ፌይርሞንት በተባለው ሆቴል በተከራየችው የልዩ ማዕረግ ማረፊያዋ ሳሎን ውስጥ ተቀምጣለች ። እዚያ ክፍል ውስጥ አረፍ ብሎ ወደ ውጭ ለተመለከተ ሰው ደንቅ የሆነው ወደብና ከዚያ አልፎ የሚገኘው የማሪን ካውንቲ ውበት በእጅጉ ያስደምመዋል ። ከሌላ ሀሳብም ያወጣዋል ። ማሪዮን ሂልያርድ ግን ይህን ትእይንት ለማየት ፍላጐት አልነበራትም ። ስለዚያች ልጅ በማሰብ ላይ ነበረች ። ምን ሆና ይሆን? ምን ትመስል ይሆን? ግሬግሰን (ፒተር) ከሁለት ዓመት በፊት ታምር አሳይሻለሁ ብሎ አንደፎከረ ተሳክቶለት ታምር በርቶ ይሆን? ቤን አቭሪ ሜሪ አዳምሰንን ሲያያት የሚያውቃት ሴት እንዳልሆነችበት ግልፅ ነው… ማይክልም ቢያያት አያስታውሳትም ይሆን? እሷስ እንዴት ነው ይሆን የምትኖረው ? ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅር ይዞአት ይሆን ወይስ እንደማይክል ሁሉን ነገር ትታ አንገቷን ደፍታ ውስጧ እየበገነ መኖር ቀጥላ ይሆን ? ማሪዮን ሂልያርድ የቀጠሮው ሰዓት እስኪደርስ ስለ ናንሲ ማክአሊስተር ስታስብ ልጅዋ በመሀል ገባ። እሱም ፍቅር ያውቅ ነበር ። አፍቅሮ ነበር ። እንዲያውም አሁን እምትጠብቀው ማይክል ሂልያርድ በጣም ይወዳት የነበረችዋን ልጅ ነው። ግን…. እሷ ባትሆንስ ? ካልሆነች . . . ካልሆነች ምንም ለውጥ አያመጣም። እሷ ካልሆነች አንዲት የዚሁ አካባቢ ተወላጅ የሆነች ፎቶ አንሺ ናት ማለት ነው ቤን አቭሪ አይኑን የጣለባት ፎቶግራፍ አንሺ። በቃ። ሊሆን ይችላል ። ያወጣሁት ያወረድኩት ፤ አስቤ የቀመርኩት ፤እውነት ብዬ ያሰብኩት ነገር ሁሉ መሰረተ ቢስ ፤ አጉል ሀሳብ ሊሆን ይችላል አለች በሀሳቧ።

ምናልባት. . . ምናልባት
👍17
ሲጋራ ለኮሰችና ቀና ብላ በግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ሰዓት ተመለከተች ። አስር ከሩብ ፣ ከቀኑ ። ይህም ማለት ኒውዮርክ ውስጥ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ይሆናል ማለት ነው። ማይክል ገና ከሥራ አይወጣም ። ቤን አቭሪ ግን ከሥራ ወጥቶ ከዚያች እዲዛይን ክፍል ከምትሰራ ሴት ጋር ይላላስ ይሆናል ። ኮስታራ አደለም ባህሪው ፤እንደማይክል ። ግን. . . ግን እንደማይክል ትካዜ አያበዛም ። ማይክ ግን . . . በረጅሙ ተነፈሰች ። ምናልባት ያችን የወደዳትን ልጅ ስታርቅበት ሕይወቱን እስከ ዘለቄታ የሚያስረሣ ስህተት ፈፅማ ይሆን ፤ ማሪዮን ? የለም ፤ የለም ልጅነቱ ነው እንጂ ቢበስል እሱ ራሱ ያለአቻው ማግባትን አይሞክረውም ነበር ። አዎ እንደዚያ ነው ። ሆኖም የለም አልተሳሳተችም ። ምናልባትም አልትሳሳተች ይሆናል ። ምንአልባት። ሁሉም ነገር ጥቂት ማስቸገሩ አይቀርም ። ያ እስኪያልፍ ነው። ነገ ተነስቶ ምን የመሰለች ሚስት ሊያገኝ ይችላል፤ ያገኛል ። በባህሪዋ በመልኳ ፤ በዘሯ ፤ በአስተዳደጓ የምታኮራ። ምን ጎድሎበት ሚስት ያጣል ? ሀብት… ሞልቶ ተርፎ። ችሎታ ከሱ የተረፈ ነው። መልክ ይህ ጎደለህ አይባልም ። ጠባይ! ሲስቅ ሲጫወት ያምርበታል ። ቁም ነገር ሲያወራ ትርፍ ነገር አይጨምር!. ስለ ማይክል ስታስብ ፊቷ እየተፈታ ልቧ እየለሰለሰ ሄደ። ማይክል ምን አይነቱ ደግ ፤ ጠንካራና . .. ብቸኛ ሰው ነው! አዎ ብቸኛ ነው ። አደጋው ከደረሰበትና… አዎ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከማንም ጋር መቀላቀል አልቻለም ። ምናልባትም እልቡ ውስቅያኖ የተሰበረ አንድ ነገር ቢኖር ይሆናል ። ያ ነገር ደግሞ እስከ ዛሬ ሊቀጥል ሊለመልም አልቻለም ማለት ነው ። ነፍስ አልዘራም ማለት ነው። አሁን አሁን ግን እየተሻለው ይመስላል ። በግልፅ መቆዘሙንና በየእለቱ ጠጥቶ መስከሩን አቁሟል ። ግን ምን ዋጋ አለው ደስታ የለውም ። ሁሉ ነገር አለው። ሲደሰት ፤ ሊጨፍር ይችላል ። ግን ደስታ ወደሚገኝበት ቦታ ፊቱን እንኳ አያዞርም ። በፊቱ ላይ የሚታየው ሌላ ነገር ነው፡፡ ስለመኖር የሚያስብ አይመስልም ። ወይም ይህን ጨርሼ እዚህ እደርሳለሁ ብሎ ወስኖ በድንገት እኮ ለምን ፤ ምን ለማግኘት እንዳለ ፤ ጭልጥ ባለ በረሀ ላይ እንደሚጓዝ መንገደኛ ተስፋው ባዶና አላማ የለሽ ይመስላል ። አይኑ ላይ ተስሎ እምታየው ይህን ነው ። ለምንም ነገር ፍቅር የለውም ። ለሥራው እንኳ ፍቅር የለውም። በሥራው ላይ ተደፍቶ ይውላል ። ብዙ ይሰራል ። እንከን የለበትም ።ግን ማይክል ሥራውን የሚወደው ማሪዮን ሥራዋን በምትወድበት መንገድ አይደለም ። አባቱ አያቱ ያን ሥራ በሚወዱበት መንገድም አይደለም ።

የማይክል አባት ትዝ ሲላት በፍቅር አስታወሰችው ። እንዴት አይነት ግሩም ሰው ነበር ። ሃሳቧ ወደ ጆርጅ ተሻገረ። ጆርጅን ባይጥልላት ምን ይውጣት፡፡ ሃላፊነት ሲከብዳት የሃላፊነቱን እንዛዝላ የሚሸከምላት ፤ ስታዝን የሚያፅናናት ፤ ሲከፋት የሚያስደስታት. . . ጆርጅ ለሷ ሁሱ ነገር ነው ። ያም ሆኖ ይህን ያሀል መሆኑን አታውቅም ነበር ። አሥራ ሁለት አመት ያህል ጆርጅ ያገልግላት ፤ ይታዘዛት ፤ በትህትናው ይደግፋት እንጂ ማሪዮን ጆርጅን አስባው እንኳ አታውቅም ነበር ። ምን ነክቷት ይሆን? ምክንያቱም ግልጽ ነው። ያን ያሀል ጊዜ ልቧ ለማንም ወንድ ቦታ አልነበረውም ። ያለ ማይክል አባት ለሷ ወንድ አልነበረም ፤ አለፈ።

የበሩ ደወል ተንጫረረ ። ከሀሳቧ ቀሰቀሳት ። ሰዓቱ አስር ሰዓት ከሃያ አምስት ደቂቃ ይላል ። ልጅቷ መሆን አለባት ። ሃያ አምስት ደቂቃ አሳልፋ ነው ማለት ነው የመጣችው ግን ማሪዮን አልተናደደችም ። ቶሎ ብትመጣባት ኖሮ ይህን ሁሉ ለማሰብ ትችል ነበርን ?

«ሚስ እዳምሰን ? » ስትል ። ያየቻት ልጅ ከዚያችኛዋ ፈፅማ የተለየች ሆና አገኘቻች ። ድንገት ደስ ሲላት ተሰማት ። «ሚስዝ ሂልያርድ?» አለች ሜሪ ። ትጠይቃት እንጂ በሚገባ አውቃታለች ። በርግጥ በአይኗ አይታት አታውቅም ። እሆስፒታሉ ውስጥ ስታነጋግራትም አይኗ በፋሻ ተጠቅልሎ ነበር፤ አላየቻትም ። ግን ፎቶግራፉዋን አይታለች… እማይክል ቤት ። ከዚያ ወዲህም ሺ ጊዜ በህልሟ እየመጣች አስፈራርታታለች ። ማሪዮን ሂልያርድ ለሜሪ አዳምሰን ቅዠት ነች ። አለም ዳርቻ ብታገኛትም አታጣትም ። «እንደምን አለሽ?» አለች ማሪዮን ፤ እጅዋን ለሰላምታ እየዘረጋች ። እንደሚሆን እንደሚሆነው ሰላምታ ተለዋወጡ ። «ወደ ውስጥ እንግባ» አለች ማሪዮን ። «እሺ አመሰግናለሁ» አለች ሜሪ ።

ሜሪ በሕይወቷ ብዙ ለውጥ ያመጣችውንና በአይነ ስጋ አይታት የማታውቀውን አዲስ ሰው ያደረገቻትን ሴትዮ ሁኔታ ለመገንዘብ ፤ ሁለቱም በየመንገዳቸው ፤ አንዳቸው የሌላውን ልብ ዘልቆ ለመመልከት ይጠናኑ ጀመር። ማሪዮን ይህች የምታያት ሴት ከዚያች በፎቶግራፍ ከምታውቃት ናንሲ ጋር ምንም አይነት የመልክ መመሳሰል እንደሌላት ተገነዘበች ። ለስላሳ መጠጦችንና ሻይ ልትጋብዛት ስትዘጋጅ ሁሉ ያን ያህል ገንዘብ ላወጣችላት ሰው ተጨማሪ ግብዣ ማድረጉ አስፈላጊ እንዳልሆነ ለልቧ ነገረችው ። ቢሆንም መነጋገር ያስፈልጋል ። መልኳ ቢለወጥ ድምጽዋ ቶኑ አይለወጥም ። ያንን የመጨረሻውን እለት ስቃይ የተሞላ የናንሲ ማክአሊስተር ድምፅ እንዲህ በቀላሉ አትረሳውም ።

«ምን ትጠጫያለሽ» አለች ማሪዮን ። «ስለግብዣው እግዜር ይስጥልኝ ። ግን ደግሞ... ምንም ነገር» አለችና አቋረጠች ። ሴትየዋ ትኩር ብላ ስታያት ፤ ሜሪም ሴትዮዋን ትኩር ብላ ስታይያት የተፈጠረው የአይን ግጭት ንግግሯን እንድታቋርጥ አስገደዳት ። ማሪዮን የልጅቷን ውበት ፤ የለበሰችውን ልብስ ውድነት እየተመለከተች ለሕይወቷ ያሰፈልጋል ተብሎ የቆረጥኩላትን ገንዘብ በልብስ ብቻ እያባከነችው ይሆን ? ስትል አሰበች ። የልብሶችዋን ዉድ መሆን ፤ ለሳንፍራንሲስኮ የአየር ጠባይ የለበሰችው ካፖርት በጣም ሞቃት ሊሆን እንደሚችልና ኒውዮርክን ታውቅ እንደሆነ ደራርባ ጠየቀቻት ። ጥያቄው ቢበዛባትም ፤ ሜሪ የመጨረሻውን ጥያቄ ለመመለስ አሰበች ። እውነተኛውን ነገር ብትነግራት በወደደች ። ሆኖም አያስፈልግም ። ስለዚህም ፤ «ኒውዮርክን ብዙም አላውቀው። እንዲያውም ትልቅ ከተማ ኗሪ አይደለሁም » አለች ሜሪ። «እኔ ሳይሽ ደሞ ትልቅ ከተማ ያንች ግዛት ሆኖ ነው የተሰማኝ» አለች ማሪዮን ።
👍11
በዚህ ሁኔታ ብዙ ተነጋገሩ ። ቀስ እያሉ ፤ እያዘገሙ ። ከብዙ ማዝገም በኋላ ማሪዮን ንግግራቸውን ወደፈሩ መምራት ጀመረች ። «ቤን አቫሪ ኮንትራት ሊሰጥሽ የፈለገው በከንቱ እንዳልሆነ ገባኝ። ይህ እጅግ ውብ የሆነ የጥበብ ሥራ ነው። በዚህ ሥራ ላይ ብዙ ቆይተሽበታል!?» አለች ማሪዮን ፤ አስቀድመው በተነጋገሩት መሰረት ናንሲ መርጣ ያመጣቻቸውን ፎቶግራፎች እየተመለከተች ። «የፎቶ ግራፍ ሥራ ለኔ እንግዳ ነው ። ከዚሀ በፊት ሰአሊ ነበርኩ »
«አዎ፤ አሁን ትዝ አለኝ። ቤን አቭሪ ነግሮኝ ነበር ። ›› ማሪዮን ይህን ብላ ፎቶግራፎቹን ትመለከት ጀመር ። ለረጂም ጊዜ በፎቶግራፎቹ ውበት ተውጣ ቆየች ። ከዚያም አይኗን ሳትነቅል «ስዕል ስትስይም ይህን ያህል ይዋጣልሻል.› ስትል ጠየቀች። «ይዋጣልኝ ነበር ይመስለኛል ። » ማሪዮንና እሷ ድብብቆሽ የሚጫወቱ መስሎ ተሰማት ። «ዛሬ ዛሬ የፎቶግራፍን ሥራ ፤ ያኔ የስዕልን ሥራ የምወደውን ያህል እየወደድኩት ነው»
«ሙያሽን ለምን ቀየርሽ?»
«ምክንያቱም ተለወጥኩ። ሁሉ ነገሬ አዲስ ሆነ ። የስዕል ሥራ የዚያ ያለፈው ህይወቴ አካል ነበር ። ብቀጥለው ሁሌ ያን ሕይወት ያስታውሰኛል ። ስቃይ እንጂ ሌላ ትርፍ እንደሌለው ተገነዘብኩ ። ተውኩትና የፎቶግራፍ ሥራ ጀመርኩ ። አዲስ ሕይወት አዲስ ሰው አዲስ ሙያ... እንደዚያ ነው»
« እህ ?እንዲያ ነው? ... የሆነው ሆኖ አለም ያችን የመሰለች ሰዓሊ አሕሁ ልትል አይገባትም ። ፎቶ ግራፎችሽን እንደማያቸው ክሆነ በሷ በኩል እያገስገልሻት ነው። ማነው ይህን ሥራ እንድትጀምሪ ያበረታታሽ። ይኸኔ አንዱ ታላቅ ጠቢብ ይሆናል! መቼም ሳንፍራንሲስኮ ብዙ የጥበብ ሰው አለባት»

ሜሪ ራሷን ነቀነቀች ፤ ፈገግ ብላ ። ሁሉም ነገር አስገራሚ ነው። ማሪዮን ሂልያርድን እጅግ ለመጥላት ተዘጋጅታ ፤ ታጥቃ ነበር ከቤቷ የወጣችው ። ግን አልቻለችም ። አልወደደቻትም ግን አልጠላቻትም ። አዘነችላት? እንጂ ሴትዮዋ ምንም ልትኩራራ ብትፈልግ ረጋ ማለት ብትሻ ፤ ዘመናይ ለመምሰል ብትሞክር ውስጧ ተመርዞአል ። ሞት ሲያንዣብባት ይታያል ። ይህን ሁሉ ስሜት የለበሰውን ፊት በደንብ ሲመለከቱት ፤የእርጅና መዳረስን ለመረዳት ከሱ በሚመነጨው ኀዘን ሲሰቃይ ይታያል ። ሁሉን ዘልቆ መመልከት ለቻለ ። ምንድን ነበር ጥያቄው፤ ፎቶግራፍ ማንሳት እንድትጀምሪ ያበረታታሽ ማነው ? በሳንፍራንሲስኮ ከሚገኙት ባለሙያዎች አንዱ!?... አዎ ፤ ይህን ነበር የጠየቀችኝ ። ‹‹ባለሙያ ንኳ አይደለም ። ማለት የፎቶግራፍ ሥራ አይደለም ። አንድ ወዳጄ ነው። የግል ሀኪሜ ነው ማለቱ ይበልጥ ግልፅ ያደርገዋል ነገሩን ። እሱ ነው ያስተዋወቀኝ። በዚች ከተማ ውስጥ የማያውቀው ሰው የለም »

«ፒተር ግሬሰን» አለች ማሪዮን በለሆሳስ ። ማሪዮን የራሷን ድምፅ የሰማችው እንደ ህልም ነበር ። ልትናገር አላስበችም እንዲያ ብላ ። ሜሪ ይህን ስትለማ ደነገጠች።. . . ማን ነገራት ? እንዴት ልታውቅ ቻለች ? ምናልባት ፒተር?.... የለም እሱ አያደርገውም
«ትተዋወቃላችሁ ? » አለች ሜሪ ።
«ምን… ከኔ ጋር ? አዎ» አለች ማሪዮን ። ሁለቱም ፀጥ አሉ፣ ረጂም ለመሰለ ጊዜ ። በመጨረሻ «እንተዋወቃለን ናንሲ ። ፒተርን አውቀዋለሁ ። ላንች ያደረገልሽ ህክምናም እጅግ የሚደነቅ ነው» አለች ማሪዮን ።

ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍234🔥1👏1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ናንሲ ሌኔሃን ከማታውቀው ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ መተኛቷ
ሰላም ሳይነሳት አልቀረም:

ምንም እንኳን ክፍሉ የሙሽሮች ክፍል ቢሆንም አልጋዎቹ ተደራራቢ ናቸው፡፡ በሩ ክፍት እንዲሆን ቢፈልጉም በወጀቡ ምክንያት በሩ እየተወረወረ
ይዘጋል፡፡ ስለዚህ አስሬ ሲዘጋ እየተነሱ ከመክፈት ይልቅ አንድ ጊዜ ዘግቶ
መተዉ የሰውን ትኩረት አይስብም:፡

ናንሲ በጊዜ ላለመተኛት ብዙ ጥራለች። በዋናው ሳሎን ሄዳ ለመቀመጥ
ብትፈልግም ወንዶች ብቻ ናቸው የተሰባሰቡት፡፡ ቦታው በሲጋራ ጭስ ታፍኗል፧ በዊስኪ ሽታ ታውዷል፡ በተጨማሪም የካርታ ተጫዋቾች ስድብና
ጫጫታ ጆሮ ይሰነጥቃል፤ ቦታው ለሴት ልጅ የሚሆን አይደለም፤ ስለዚህ
‹መተኛት ሳይሻል አይቀርም› ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች።

ስለዚህ መርቪንና ናንሲ መብራቱን አጠፉና በየአልጋቸው ላይ ሰፈሩ።
ናንሲ ዓይኖቿን ብትጨፍንም እንቅልፍ በአይኗ hልዞር አለ፡፡ ወጣቱ ሄሪ ማርክስ ያመጣላት አንድ መለኪያ ዊስኪ እንኳን ለመተኛት የረዳት ነገር
የለም፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ቢሆንም በዓይኗ እንቅልፍ አልኳል ብሏል፡

መርቪንም እንቅልፍ እንዳልያዘው አውቃለች፡ የላይኛው ቆጥ ላይ
ሰፍሮ ይገላበጣል፡፡ እንደ ሌሎች መኝታዎች የሙሽሮቹ አልጋዎች በመጋረጃ የተሸፈኑ ባለመሆናቸው ላለመታየት ያላት ምርጫ መብራቱን ማጥፋት ነው፡፡

እንቅልፍ አልመጣላት ሲል ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በሀሳቧ መጣች ማርጋሬት በጣም ወጣት፣ የኑሮ ውጣ ውረድ የማይገባትና ወደፊት
ስለሚገጥማት ነገር ቅንጣት ታህል የማታውቅ ልጅ ናት። ከማርጋሬት
በጥርጣሬ የተሞላ ፊት ላይ ያነበበችው ግን ከፍተኛ ነፃ የመሆን ስሜት ነው፡፡ ይህ ደግሞ እሷ ወጣት በነበረችበት ጊዜ የገጠማት አይነት ችግር ነው፡፡ ናንሲም በዚያ ወቅት ከወላጆቿ ጋር አተካራ ውስጥ ገብታ ነበር፧
በተለይ ከእናቷ ጋር፡ እናቷ የተከበረ የቦስተን ቤተሰብ ልጅ እንድታገባ
ብትፈልግም እሷ ግን ገና አስራ ስድስት አመት ሲሞላት ሾን ሌኔሃን
ከሚባል የህክምና ትምህርት ከተማረ ከአባቷ ፋብሪካ ውስጥ ከሚሰራ ካቦ ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረች፡፡ እናትዬው ናንሲ ይህን ልጅ እንዳታገባው ልጁ ከሌሎች ሴቶች ጋር እንደሚማግጥ፣ እናት አባቱን ከፍ ዝቅ እያደረገ
እንደሚሳደብና በየጊዜው እንደሚያመው ሀሜት ብታስወራም ናንሲ ግን
የሚነዛውን ሀሜት እንዳልሰማች በማሳለፍ ሾንን አግብታ እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ አብራው ኖራለች፡፡

ማርጋሬት የእሷን ያህል ጥንካሬ ያላት ልጅ አትመስልም፡፡ ከአባቷ ጋር
ካልተስማማች ከቤታቸው መውጣት ትችላለች፡፡ ይቺ ልጅ በየጊዜው ችግር
እያነሳች እንዳታላዝንና ራሷን ለመቻል እንድትጥር የሚመክራት ሰው ያስፈልጋታል፡ እኔ በእሷ እድሜ የሁለት ህጻናት እናት ነበርኩ› አለች በሃሳቧ፡

ስለዚህ ማርጋሬት ራሷን እንድትችል ጠበቅ ያለ ምክር ለግሳታለች እሷም ቃሏን በመጠበቅ ስራ ልትሰጣት ተስፋ አድርጋለች፡፡

ይሄ ሁሉ ደግሞ የሚወሰነው ከወንድሟ ጋር ባላት ጠብ የሀይል
ሚዛኑን በጨበጠው በአጭበርባሪው ሽማግሌ በዳኒ ሪሌይ ነው፡፡ ናንሲ
እንደገና ወደ ጭንቀቷ ተመለሰች፡፡ ጠበቃዋ ማክ ዳኒ ሪሌይን ይኸኔ
አግኝቶት ይሆን? ከአገኘውስ ስለቀድሞው ወንጀሉ ሲነግረው ምን አለ? ይህ ሁሉ ሴራ እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ የተጠነሰሰ መሆኑን ጠርጥሮ ይሆን?›
እነዚህን ገና ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ስታወጣ ስታወርድ እንቅልፍ አጥታ
አልጋዋ ላይ ትገላበጣለች፡፡

የሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦትውድ ከተማ ነው፡፡ ኒውፋውንድ ስትደርስ ማክጋ ስልክ ደውላ ታረጋግጣለች፡፡በዚያ ጊዜ ሁሉ ነገር ይለይለታል፡

አይሮፕላኑ ሲንዘፈዘፍና ሲንገጫገጭ ናንሲ መላ አካልዋ ተረበሸ፡፡አሁን ደግሞ ብሶበታል፡ በአይሮፕላን በተደጋጋሚ ብትሄድም ከዚህ ቀደም
እንዲህ አይነት ሁኔታ ገጥሟት አያውቅም፡፡ ግዙፉ አይሮፕላን በንፋሱና
በወጀቡ ሲወዛወዝ ስጋት ገብቷት ተወርውራ እንዳትወድቅ የአልጋውን ብረት አጥብቃ ያዘች፡፡ ባሏ ከሞተ ወዲህ ብዙ ችግር ገጥሟታል፤ ‹አሁን ጉልበቴ
በርታ በርታ› ማለት አለበት፤ ነገር ግን የአይሮፕላኑ መንዘፍዘፍ ክንፎቹን
ይገነጥል፣ ሞተሩን ሰብሮ ይጥለው ይሆን?› እያለች መፍራቷ አልቀረም፡፡
ፍርሃቷን ይቋቋምላት ይመስል ትራሷን በጥርሷ ነክሳ ያዘች፡፡ ድንገት
አይሮፕላኑ ቁልቁል ወረደ፡፡ ቁልቁል መውረዱ እንዲቆም በእጅጉ ብትመኝም
መውረዱን ቀጥሏል፡ ይህ ሁኔታ ክፉኛ አስደነገጣት፡፡ ከዚያም ዘጭ አለና
ቀጥ ብሎ መብረር ጀመረ፡
መርቪን እጁን ሰዶ ትከሻዋን ያዝ አደረገና ‹‹ንፋሱ የፈጠረው ወጀብ ነው አይሮፕላኑን እንዲህ የሚያደርገው›› አለ ‹‹ከዚህ የባሰ ሁኔታ እኔ ብዙ
ገጥሞኛል፤ አይዞሽ አትፍሪ›› ሲል አጽናናት፡፡

እጁን በእጇ ፈልጋ አጥብቃ ያዝ አደረገችው፡፡ ከአልጋው ወረደና እሷ አልጋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ ፀጉሯን ይደባብስ ገባ፡፡ አሁንም ፍርሃቷ ሙሉ በሙሉ ባይለቃትም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ መርቪን ያዝ ስላደረጋት በመጠኑ
ቀለል አላት፡፡

ምን ያህል ጊዜ እንደተያያዙ አላወቀችም:: ትንሽ ቆይቶ ወጀቡ ተነሳ፡፡በደምብ ስትረጋጋ የመርቪንን እጅ
ለቀቅ አደረገችው፡፡ ምን ማለት እንዳለባት አላወቀችም።

ናንሲ መብራቱን አበራችና ከአልጋዋ ውስጥ ወጣች፡፡ ከላይ የሆነ ልብስ ደረብ አደረገችና መስታወቱ ፊት ቁጭ አለች፡፡ ሁልጊዜም
ጭንቀት ሲይዛት እንደምታደርገው ፀጉሯን አበጠረች፡፡ በጭንቀቷ ጊዜ የመርቪንን እጅ መያዟ አሳፈራት፡ በዚያ ጊዜ ክብሯን ሸጣ እጁን ለጥቂት ጊዜ በመያዟ በሆዷ
ብታመሰግነውም አሁን ፍርሃቷ ሲለቃት ግን ነገሩ አስፈራት፡፡ እሱም ስሜቷን በመረዳት እፍረቷ እንዲለቃት ብሎ ለጊዜው ክፍሉን ለቆላት ወጣ፡፡

መርቪን ትንሽ ቆይቶ ጠርሙስ ብራንዲ ከሁለት መለኪያ ጋር አመጣና
መጠጡን ቀድቶ አንዱን ሰጣት፡፡ አይሮፕላኑ ትንሽ ይወዛወዝ ስለነበር
በአንድ እጇ መለኪያውን በሌላ እጇ ደግሞ የአልጋውን ብረት ይዛለች:
የለበሰው አስቂኝ ልብስ ባያስቃት ኖሮ ድንጋጤው ቶሎ አይለቃትም አስቂኝ ቢሆንም ልክ ሱፍ ለብሶ
እንደሚንጎራደድ ሁሉ ምንም አልመሰለውም፡፡ ሰው ሞኝ ነው ቢለው ግድ
የለውም፡፡ ልበ ሙሉነቱ አስደስቷታል፡፡

ብራንዲዋን ስትጨልጥ በሰራ አካላቷ ሙቀት ስለፈጠረላት ደጋግማ
ተጎነጨች፡፡

መርቪን ወሬ ለመጀመር ብሎ ‹‹እዚያ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ የሆነ
እንግዳ ነገር አየሁ›› አለ ‹‹እኔ ወደ መታጠቢያ ክፍል ስገባ አንድ በድንጋጤ
ቀልቡ የተገፈፈ ተሳፋሪ ሲወጣ አየሁ፡፡ የመታጠቢያ ክፍሉ መስኮት ተሰብሯል የበረራ መሀንዲሱ ደግሞ ጥፋት ሲፈጸም የተያዘ ሰው መስሎ እዚያ ቆሟል፡፡ መስኮቱ የተሰበረው ከአይሮፕላኑ ውጭ ተወርውሮ በገባ
የበረዶ ቋጥኝ መሆኑን ሊታመን የማይችል ታሪክ ነገረኝ፡፡ እኔ ግን ሁለ±
ሲደባደቡ እንደነበር መገመት አላቃተኝም፡፡››

ናንሲ እዚያ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚቀመጡ ታሪክ ስለነገራት በሆዷ
መርቪንን አመሰገነችው፡፡ ‹‹የትኛው የበረራ መሀንዲስ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹እንደ እኔ ቁመቱ ሎጋ የሆነና ፀጉሩ ቃጫ የመሰለ መልከ መልካም ወጣት››
‹‹መሀንዲሱን አወቅሁት፤ ተሳፋሪውስ ማን ነው?››
‹‹ስሙን አላውቀውም፤ ነጋዴ ይመስላል፤ አመድማ ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰውዬ ነው›› አለና መርቪን ተነስቶ ብራንዲ ብርጭቆዋ ውስጥ
ጨመረላት፡፡
👍20🥰1
ናንሲ ከላይ የለበሰችው የመኝታ ልብስ ከላይዋ ላይ ሲወድቅ ባቷና እግሯ ቢጋለጥም ልቡን የወሰደችበትን ሚስቱን ዱካ እግር እግር በፅናት
የሚከተል በመሆኑ እሷ ዓይኑ ውስጥ እንደማትገባ አውቃለች፡፡ ኧረ እንደውም እርቃኗን ብትሆን እንኳን ማስተዋሉን እንጃ፡፡ የእሱ የእሷን እጅ መያዝ አንድ የሰው ልጅ ለሌላው የሚያደርገው ንፁህ የሀዘኔታ ምልክት
ነው፡፡

ውይይታቸው እንዲቀጥል ፈልጋ ‹‹ባለቤትህ አሁንም ተናዳብሃለች?›› ስትል ጠየቀችው፡

‹‹ንዴቷ አልበረደላትም›› አለ መርቪን፡፡

ናንሲ ልብሷን ለመለወጥ ከሄደችበት መታጠቢያ ቤት ስትመለስ ያየችው በመርቪን፣ በዳያናና በማርክ መካከል ሲካሄድ የነበረው ትዕይንት ትዝ ብሏት ፈገግ አለች፡፡ የመርቪን ሚስት በባሏ ላይ ትጮሃለች፣ ወዳጇ ደግሞ በሷ ላይ ይጮሀል  እሷ ስትደርስ ማርክና ዳያና ንዴታቸውን ዋጥ አድርገው በመሀከላቸው የተፈጠረውን ንትርክ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመቀጠል ወዲያው ነው ወጥተው የሄዱት፡ ናንሲ መርቪን እንዳያፍር ብላ በወቅቱ ስለተፈጠረው ነገር ከዚያ በኋላ አላነሳችም፤ ሆኖም ይህ ሁኔታ አንዳንድ
ግላዊ ሁኔታዎችን መርቪንን እንዳትጠይቀው አላገዳትም፡፡ ሆነም ቀረ
ያሉበት ሁኔታ የግድ ስላቀራረባቸው የሆድ ሆዳቸውን መነጋገር ጀምረዋል፡፡
‹‹ታዲያ ወዳንተ ተመልሳ ትመጣ ይሆን?›› ስትል ጠየቀችው፡

‹‹ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ አብሯት ያለው ሰው ደካማ ይመስላል፡፡ምናልባትም የፈለገችው ይህን ይሆናል›› አለ፡፡

ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ማርክና መርቪን በእጅጉ የተለያዩ ሰዎች ናቸው፡ መርቪን ዘንካታ፣ መልከ መልካም ሲሆን ሰው ከመጤፍ የማይቆጥር እና ቀጥተኛ ተናጋሪ ነው፡፡ ማርክ ደግሞ ባህሪው ለስለስ ያለ እና ፈገግታ የማይለየው ሰው ነው፡፡ እኔ ልጅ የሚመስል ሰው አልወድም፧ ነገሩ ለእሷ ይሄ ባህሪው ስቧት ሊሆን ይችላል፧ እኔ ብሆን ኖሮ መርቪንን በማርክ አልለውጠውም ነገር ግን የሰው ፍላጎት የተለያየ ነው አለች በሆዷ።

"አንቺስ እንዴት ልታደርጊ ነው፡፡ ወንድምሽን ለመግጠም ተዘጋጅተሻል?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አሁን ድክመቱን አግኝቼዋለሁ›› አለች ናንሲ፡፡

‹‹ዳኒ ሪሌይ እግሯ
ስር ሊወድቅ ደርሷል፡፡ አንድ መርቺያ መንገድ ለማግኘት ተቃርቤያለሁ›› አለች፡፡

መርቪን ፈገግ አለና ‹‹አንቺን ጓደኛ ማድረግ እንጂ ጠላት አድርጎ ማየት ተገቢ እንዳልሆነ ነው አሁን የገቧኝ›› አለ፡፡

‹‹እኔ ለአባቴ ብዬ ነው›› አለች ‹‹በጣም እወደው ነበር፧ ሁሉ ነገሬ ደግሞ እሱ ትቶልኝ ያለፈው ፋብሪካ ነው፤ ፋብሪካው የእሱ መታሰቢያ ነው፤ የእሱ አሻራ ታትሞበታል፡››

‹‹እስቲ ስለአባትሽ ንገሪኝ›› አለ መርቪን፡፡
‹‹እሱን አንድ ጊዜ የተዋወቀው ሰው ሊረሳው አይችልም፡፡ እንዳንተ
ቁመተ ሎጋ ሲሆን ጠጉሩ ጠቆር፣ ድምጹ ጎርነን ያለ ሰው ነው፡፡ ገና ስታየው መንፈሰ ጠንካራነቱን ትረዳለህ፡፡ በፋብሪካው ተቀጥረው የሚሰሩ
ሰዎችን ስም፣ የሚስቶቻቸውን ጤንነትና የልጆቻቸውን የትምህርት ሁኔታ ይጠይቃል፡፡ በርካታ የፋብሪካው ሰራተኞች ልጆች ከፍሎ በማስተማር ለወግ ማዕረግ አብቅቷቸዋል፡፡ እሱ ሰዎች ለእሱ ታማኝ እንዴት ሊሆኑ እንደ ሚችሉ ነው ዘወትር የሚጥረው፡፡ በዚህ ባህሪው ዘመነኛ አይመስልም፧ አባታዊ ባህሪ ነው ያለው፡፡ እሱ ለንግድ ስራ የተፈጠረ ጭንቅላት ነበረው፡
የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በወደቀበት በዚያ ጨለማ ዘመን በኒው ኢንግላንድ ስቴት በርካታ ፋብሪካዎች ሲዘጉ የእኛ ፋብሪካ ሽያጭ ያድግ ስለነበር ብዙ ሰራተኞች ይቀጥር ነበር፡፡ እሱ የሰዎችን ስነ ልቦና ማሸነፍ ላይ ነው ዋናው ትኩረቱ፡ አንድ ነገር ይዘህ ብትመጣ ለችግሩ ፍንትው ያለ መፍትሄ ይሰጥሃል
ሳልጠግበው ነው ያለፈው፡፡ ሞቱ በጣም ነው የጎዳኝ፡፡ የባሌም እንዲሁ፡››
ድንገት ንድድ ብላ ‹‹አባቴ ህይወቱን ሙሉ የለፋበትን ፋብሪካውን በማይረባው ወንድሜ እንዳልነበር እንዲሆን አልፈቅድም›› አለችና ተቁነጠነጠች፡፡
‹‹አንዱ ቁልፍ የአክሲዮን ባለቤት እኔን እንዲደግፍ ግፊት እያደረኩበት
ነው፡፡ ነገር ግን እስካሁን ምን ያህል እንደተሳካልኝ አላውቅም›› አለች::

ታሪኳን ነግራው ሳትጨርስ አይሮፕላኑ ከባድ ነውጥ ውስጥ በመግባቱ
እንዳልተገራ ፈረስ ይጋልብ ጀመር፡፡ በዚህ ጊዜ ናንሲ መለኪያዋን ጣለችና
የመዋቢያ ዕቃ መደርደሪያ ጠረጴዛውን በሁለት እጇ ጥርቅም አድርጋ ያዘች መርቪን ቀጥ ብሎ  ለመቆም ቢጥርም አይሮፕላኑ ወደ ጎን
በማዘምበሉ ወለሉ ላይ ተፈጠፈጠ፡፡

አይሮፕላኑ እንደገና ተረጋጋ ናንሲ መርቪንን እንዲነሳ ለማገዝ እጇን ሰደደችና ‹‹ተረፍክ?›› ብላ ጠየቀችው: በዚህ ጊዜ አይሮፕላኑ እንደገና
ሲወዛወዝ ሚዛኗን ሳተችና የያዘችውን ስትለቀው በቀጥታ መርቪን ላይ
ወደቀች::

መርቪን ሁኔታው በሳቅ አፈነዳው፡፡

ናንሲ መርቪን ላይ ስትወድቅ የጎዳችው መስሏት ነበር፡

እሷ ቀጭን እሱ ደግሞ ግዙፍ መሆኑን ስታውቅ ድንጋጤዋ ለቀቃት።ሁለቱ ሰዎች ወለሉ ላይ ጎን ለጎን ተጋድመዋል፡ ተረጋግቶ ሲሄድ ከወደቀችበት ቀና ብላ በቂጧ ተቀመጠች፡፡
አይሮፕላኑ እንደገና
‹‹እንዲህ ሆነን ሰው ቢያይ ጅል ሳንመስለው አንቀርም›› አለና ሳቀ፡

ሳቁ ተጋባባትና እሷም
ሳቀች፡፡ለአፍታ ከሃያ ሰዓት በፊት የተፈጠረውን ውጥረት የረሳች መሰለች፡፡ በመርቪን አይሮፕላን ከገደል ጋር ልትጋጭ የነበረውና በሙሽሮች ክፍል ውስጥ ያለችበት ሁኔታ፧ በመብል ቤት ከይሁዳውያኑ ጋር የተነሳው ጠብ፣ የመርቪን ሚስት ቅናት የፈጠረው ጭቅጭቅ፣ የአይሮፕላኑ በወጀቡ ምክንያት ከቁጥጥር ውጭ
መሆን የፈጠረው ድንጋጤና ፍርሃት፣ እንግዳ ከሆነ ሰው ጋር በመኝታ ልብስ ሆኖ
እንደ ፈረስ በሚጋልብ አይሮፕላን ወለል ላይ ቁጭ ብላ ያለችበት ሁኔታ
ሁሉ ተደማምሮ በእጅጉ ስላስፈነደቃት የወንድሟን ሽር ለጊዜውም ቢሆን
ረስታ ነበር፡፡
ቀጥሎ የተፈጠረው የአይሮፕላኑ መዋዠቅ
እርስ በእርስ
አስተቃቀፋቸው:፡ ከዚያማ ግጥም አድርጋ ሳመችው ይህ አድራጎቷ
አስደንቋታል፡ እሱን እስመዋለሁ ብላ አስባም  አልማም አታውቅም፡
እንዲያው ድንገት የተፈጠረ ስሜት ነው፡፡

መርቪን የተፈጠረው ሁኔታ ያልጠበቀው በመሆኑ ቢያስደነግጠውም
ቶሎ ከድንጋጤው መለስ አለናእሱም ግጥም አድርጎ ሳማት፡፡ ምጥጥ አድርጎ ሲስማት ከባድ ሙቀት በሰራ አካላቷ ለቀቀባት፡፡
ትንሽ ተሳስመው እንደቆዩ ገፋ አደረገችውና ጫን ጫን እየተነፈሰች
‹‹ምንድን ነው ያደረግነው?›› ስትል የጅል ጥያቄ ጠየቀችው፡

‹‹ሳምሽኝ ሳምኩሽ›› አለ በተደሰተ መንፈስ፡፡

‹‹ልስምህ ፈልጌ አይደለም›› አለች፡
ሆነ ሆኖ ስለሳምሽኝ ደስ ብሎኛል›› አለና በድጋሚ ሳማት፡፡

ከእቅፉ መውጣት ያለባት ቢሆንም አያያዙ ጠንከር ያለና እሷም እንዲለቃት ስላልፈለገች ዝም አለችው፡ እጁን በመኝታ ልብሷ ውስጥ ሲሰደው ሰውነቷ  ሽምቅቅ አለ፡፡ ጡቶቿ ትንሽ መሆናቸው ስላሳፈራት
መርቪን ይጠላኛል ብላ ገምታ ነበር፡፡ እሱ ግን በግዙፍ እጁ ትንንሽና ክብ
ጡቶቿን ያዝ አድርጎ ሲያሻሻቸው በጉሮሮው ምራቁ ሲወርድ ተሰማ፡፡ የጣቱ ጫፍ የጡቷን ጫፍ ሲነካው አሁንም እፍረት ቢጤ ጠቅ አደረጋት፡ የጡቷ
ጫፍ ከጡቷ ጋር ሲወዳደር ትልቅ ነው፤ ትንሽ ጡት ትልቅ የጡት ጫፍ፡
መርቪን ግን የጡቷ ማነስ ይበልጥ ፍላጎት አጫረበት፡፡ ጡቶቿን እያቀያየረ
ለስለስ አድርጎ ደባበሳቸው፡፡ ናንሲም ቀስ በቀስ እየጨመረ የመጣው ማሻሸቱ የወሲብ ስሜት ስለቀሰቀሰባት እጇን ልትሰጥ ትንሽ ነበር የቀራት፡ እንዲህ አይነት የወሲብ ስሜት ከተሰማት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
👍18🥰2
‹ምን እያደረኩ ነው? አለች በሆዷ ‹እኔ የተከበርኩ ሴት ነኝ፤ አሁን ግን ገና ትናንት ከተዋወቅሁት ሰው ጋር አይሮፕላን ወለል ላይ
እየተንከባለልኩ ነው፤ ምን ነካኝ? አቁሚ አላት አዕምሮዋ፡፡ ከመርቪን ራሷን አላቀቀችና በቂጧ ቁጭ አለች፡ ስስ የመኝታ ልብሷ ተገልቦ ጭኖቿ ይታያሉ፡ መርቪን የተራቆቱ እግሮቿን ይደባብሳል፡፡ ‹‹ተው በቃ›› አለችው።

‹‹እንዳልሽ›› አለ መርቪን ድንገት ተው› መባሉ ቅሬታ ቢፈጥርበትም፡፡
‹‹ሃሳብሽን ከለወጥሽ ግን አለሁልሽ›› አላት፡፡

ወደ ሱሪው ስታማትር ብልቱ ተገትሮ ሊፈነዳ ደርሷል፡፡ ናንሲ ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ ነኝ ጥፋተኛዋ›› አለች ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ፡፡
‹ቢሆንም ስህተት ነው የሰራነው፤ እኔ ለቀልድ እንደሳምኩህ አውቃለሁ ይቅርታ›› አለች፡፡

‹‹ምንም ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነገር የለም አለ መርቪን ‹‹እኔ
እንዲህ አይነት ስሜት ከተሰማኝ ቆይቷል››
‹‹ነገር ግን ሚስትህን ትወዳታለህ አይደል አትወዳትም?››
‹‹ይመስለኝ ነበር፤ አሁን ግን ግራ ገብቶኛል፡›› እውነቱን  ለመናገር ናንሲም የተሰማት ተመሳሳይ ስሜት ነው፡፡ ድንግርግር ብሏታል፡፡ ባሏ ከሞተ ወዲህ ለአስር ዓመት ከወሲብ ተለይታ አሁን በቅጡ የማታውቀውን ሰው አቅፋለች፡፡

ምንድነው ታዲያ ችግሩ? ይሄን ሰው አሁን አውቄዋለሁ አለች
በሃሳቧ፡፡ ‹ኧረ በሚገባ አውቄዋለሁ፤ ከእሱ ጋር ብዙ  ርቀት አብሬ መጥቻለሁ፡ ችግሮቻችንን በጋራ ፈተናል፡፡ በችግራችን ጊዜ ተረዳድተናል፡፡ባህሪው ጋጠ ወጥ እና ኩሩ የመሆኑን ያህል አፍቃሪ፣ ታማኝና ብርቱ ነው፡፡ ይህን ሰው ከነችግሩ ወድጄዋለሁ አክብሬዋለሁ የለበሰው ሽሚዝ ለእሱ የሚስማማ ባይሆንም ሴትን ልጅ እንደ ቅቤ የሚያቀልጥ የደስ ደስ
አለው፡ አይሮፕላኑ ሲዋዥቅ ፍርሃት ውስጥ ሆኜ እያለሁ እጄን ያዝ አድርጎ አይዞሽ ብሎኛል፡ ሁል ጊዜ እንደዚህ የሚያስፈራ ነገር ሲገጥመኝ ምን አለ የሚያደፋፍረኝ ወገን ቢኖረኝ፡፡

ልክ በአዕምሮዋ የምታስበውን ያወቀ ይመስል እጇን ለቀም አድርጎ ያዘው፡፡ እጇን ገልበጥ አደረገና መዳፏን ሳመው፡ ከዚያም ደረቱ ላይ
ለጠፋትና አፏን መጠጠው፡፡

‹‹ተው እንደዚህ አታድርግ›› አለች እያለከለከች ‹‹አንዴ ከጀመርን ማቆም አንችልም››
‹‹አሁን ካቆምን እንደገና መጀመር የምንችል አይመስለኝም›› ሲል
በተቃውሞ አጉረመረመ
ናንሲ በመርቪን ውስጥ ያየችው የተገደበ ነገር ግን ጠንከር ያለ ስሜት የራሷን የወሲብ ፍላጎት አቀጣጠለባት፡፡ ባሏ ከሞተ ወዲህ የእሷን ድጋፍና ጥበቃው የሚፈልጉ ደካማ ሰዎች የወሲብ ጥያቄ አቅርበውላት እምቢ ስትላቸው በቀላሉ ይተዋሉ፡፡ መርቪን ግን ፈርጠም ብሎ እየጠየቃት ነው፡፡በጣም ፈልጓታል፡፡ የፈለጋትም አሁኑኑ ነው፡፡ ለዚህ ሰው ገላዋን ልትሰጠው ፈለገች፡፡

እጁን በመኝታ ልብሷ ስር ሰዶ ጭኖቿን በጣቶቹ አፍተለተላቸው
እሷም ዓይኗን ጨፍና እየተግደረደረች ትንሽ ጭኖቿን ከፈት አደረገቻቸው፡እሱም ከዚህ በላይ አልጠየቀም፡፡ ትንሽ ቆየና ብልቷን በጣቶቹ ሲጠነቁለው አቃሰተች፡፡ ከባሏ ሾን ሌላ እንዲህ አድርጎላት የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ ይህም ሃሳብ ደስታዋን ወደ ሀዘን ለወጠው፡ ‹ኦው ሾንዬ ና! የት ነው የማገኝህ?
ያንተ ሞት ምን እንዳጎደለብኝ ታውቃለህ? አለች በሆዷ፡ አሁን የተሰማት ሀዘን የባሏ ቀብር ላይ ከተሰማት አልተናነሰም፡፡ እምባዋ በተዘጉት ዓይኖቿ
እየተንቆረዘዘ ጉንጮቿን አራሱት፡፡ መርቪን ሲስማት እምባዋን ቀመሰና
‹‹ምን ሆንሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡ ዓይኖቿን ስትከፍት በእንባ የተጋረዱት ዓይኖቿ የመርቪን የሚያምር ነገር ግን ሀዘኔታ የተሞላው ፊት ተመለከተች፡፡ በሌላ በኩል ግን ቀሚሷ ወገቧ ድረስ ተገልቧል የመርቪን
እጅ ደግሞ ጭኖቿን ይዟል፡፡ ከዚያም እጁን ገፋ አደረገችውና ‹‹ ባክህ አትናደድብኝ›› አለችው::
‹‹ባልሽ ነው ሾን?››
ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች፡:
‹‹ምን ያህል ጊዜ ሆኖሻል?››
‹‹አስር ዓመት››
‹‹ረጅም ጊዜ ነው››
እኔ ታማኝ ሴት ነኝ እንዳንተ›› አለች ፊቷ እንባ በእንባ ቢሆንም
ፈገግ ብላ
‹‹ልክ ነሽ፤ እኔ ሁለትጊዜአግብቻለሁ ሁለተኛ ሚስቴን ካገባሁ
ወዲህ ለሚስቴ ታማኝነቴን ያጎደልኩት አሁን ነው፡፡ እኔም ሚስቴንና ያንን
ሰው ከአዕምሮዬ ማውጣት አልቻልኩም፡››
‹‹እኛም ጅሎች ሆንን ልበል?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹ምናልባት ስላለፈው ማሰብ ማቆም አለብን፤ በእጃችን ያለውን አሁን ማጥበቅ ይኖርብናል፡››
አይሮፕላኑ ልክ የሆነ ነገር የገጨ ይመስል ወደ ላይ ሲዘል መርቪን እና ናንሲ ተላተሙ፡ መብራቱም ብልጭ ድርግም አለ፡፡ አይሮፕላኑ በሃይል ሲናወጥ ናንሲ ሳትወድ በግድ መርቪን ደረት ላይ ተጣበቀች፡፡

የአይሮፕላኑ መናወጥ ሲቆም መርቪንን ለቀቅ አድርጋ ስታየው ከንፈሩ ደምቷል፡ ‹‹ነከሺኝ›› አላት መርቪን ፈገግታ ሳይለየው፡፡
‹‹ይቅርታ››
‹‹ስለነከሺኝ ደስ ብሎኛል ጠባሳ ይፈጥራል››
ናንሲ በፍቅር ደረቱ ላይ ተለጥፋ ቀረች፡፡ወጀቡ እስኪጠፋ ወለሉ ላይ ተቃቅፈው ቆዩና ‹‹መርቪን አልጋው ላይ እንውጣ ከወለሉ ይልቅ እዚያ ይመቸናል›› አለ ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ከዚያም በጉልበቷ እየዳኸች አልጋው ላይ ወጣች፡፡ መርቪንም ተከተላትና አልጋው ላይ አብሯት ወጣ፡፡
እሱም እቅፍ አድርጎ ያዛት፡፡
በወጀቡ ምክንያት አይሮፕላኑ በተናወጠ ቁጥር ልክ መርከበኛ የጀልባውን ምሰሶ እንደሚይዝ ሁሉ ናንሲ መርቪንን ጭምቅ አድርጋ ትይዛለች፡፡
ወጀቡ ሲቀንስና ዘና ስትል እሱም ሰውነቷን በፍቅር ይነካካቸዋል፡
ከዚያ ትንሽ ቆየችና እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡....

ይቀጥላል
👍211
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አራት (34)

«ምን… ከኔ ጋር ? አዎ» አለች ማሪዮን ። ሁለቱም ፀጥ አሉ፣ ረጂም ለመሰለ ጊዜ ። በመጨረሻ «እንተዋወቃለን ናንሲ ። ፒተርን አውቀዋለሁ ። ላንች ያደረገልሽ ህክምናም እጅግ የሚደነቅ ነው» አለች ማሪዮን ።
«ትንሽ ስህተት ሳይፈጠር አልቀረም መሰለኝ ። እኔ ናንሲ ሳልሆን ሜሪ…» ንግግሯን አልጨረሰችም ። ጉልበቷ ተሟጦ ሲወጣ ተሰማት፡፡ ባዶ ሆነች። አጥንት አልባ የሆነች ይመስል ተልፈሰፈሰች ። እንባ አነቃት ። እንደምንም ብላ ተነሳች ። ወደ መስኮቱ ሄዳ ጀርባዋን ለማሪዮን ሰጥታ ቆመች ። እና «ማን . . . እንዴት ልታውቂኝ ቻልሽ ?» አለች ። የተሰበረ ድምፅ ነበር ። ማሪዮን ርግጠኛ ሆነች ። የዛሬ ሁለት አመት የሰማችው የናንሲ ማክአሊስተር ድምፅ ብቅ አለ። «ማን ነገረሽ ? » አለች ሜሪ ደግማ በሚያስገድድ ድምፅ ። «ማንም አልነገረኝም ። ገመትኩ ። ግምቱ ለምን እንደመጣብኝም አላውቅም ። ሆኖም ገመትኩ ። ገና ቤን ስለሁኔታሽ መግለፅ ሲጀምር እሷ ናት? የሚል ጥያቄ መጣብኝ ። የነገረን ነገር ሁሉ ስለአንቺ ከማውቀው ጋር ሙሉ በሙሉ ሲመሳሰል ጊዜ ነው መሰል »
«እንዲያ ከሆነ ... » አለችና ዝም አለች፡፡ ማይክልም ያውቃል ማለት ነዋ! ልትል ነበር ። የተረገመ ልብ መቼ ነው ተስፋ እሚቆርጠው! መቼ ነው መጥላት የሚገባውን የሚጠላው ? «አሁንስ ለምን እዚህ ድረስ መጣሽ ? መኖሬን ስታውቂ ጊዜ ፈራሽ? ውል እማፈርስ መሰለሽ ? እና ውሉ ያልፈረሰ መሆኑን ልታስታውሺኝ ፈለግሽ ? »
«አይደለም ። በዚያ በኩል አልጠረጥርሽም ። ቃልሽን ማክበር እንደምትችይ አረጋግጫለሁ» አለች ማሪዮን ፤ እጅግ ያረጀሰው በመሰለ ድክም ባለና ደግነት በተሞላ ድምፅ «ላይሽ ነው የመጣሁ ። ላነጋግርሽ ምን እንደመሰልሽ ፤ ይመችሽ ፤ይክፋሽ ... ላይሽ ነው የመጣሁ። ላያት የመጣኋት ልጅ አንች ነሽ ማለት ከደፈርኩ ። ሌላውን ምክንያት እኔም በቅጡ አላውቀው»
«ለምን ? ይህን ያህል አመት ትዝ ሳልልሽ ቆይቼ ድንገት ምን አዲስ ስሜት ተፈጠረ ?» የሜሪ ድምፅ የሚናደፍ መርዛም ነበር ። ማሪዮን ምንም አልመለሰችም ።

«ድንገት ምን ነገር ተፈጠረ ሚስ ሂልያርድ? ወይስ የግሬግሰንን ሥራ ተመልክቶ ማድነቅ ስላማረሽ ይሆን ? እንዲያ ከሆነ ... እንዴት ነው በአራት መቶ ሺ ዶላር ክፍያ ያሰራሻት አሻንጉሊት እምታምር አትመስልሽም? አራት መቶ ሺ ዶላር ቢወጣም አይቆጭ! የሚያሰኝ ነው?. . . የሚያሰኝ ነው ወይ ? ምነው ጭጭ አልሽ ? ጥያቄየን መልሺልኝ እንጂ… ደስ አለሽ ወይስ ከፋሽ?» ደስ ቢለኝ ኖሮ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር ! አለች ማሪዮን በሀሳቧ ። ድንገት ደስ ቢለኝ የሚል ምኞት አደረባት ። ግን የሰራችው ነገር ውጤት መጥፎ ፤ ያደረገችው ነገር አስቀያሚ እንደሆነ ወለል ብሎ ታያት። ለዚህ ገጽታ ሁሉም ብዙ እንደከፈሉ ግን ያ ሁሉ ከንቱ እንደነበረ ተገነዘበች ። ይህ ፀፀት ነው። ፀፀት ግን ዋጋ የለውም ። ሁሉም ነገር ካለፈ ፤ ምንጩ ከነጠፈ በኋላ ቢፀፀቱት ምን ፋይዳ አለው? ማይክልን አሰበች ። ናንሲን ተመለከተች ። እሷን ራሷንም ። አንዳቸውም እንደነበሩ አይደሉም። ሁሉም ሌላ ሆነዋል ። ማይክልና ናንሲ። ሁሉም ነገር ሩቅ ከሩቅ ፤ የራቀ ሩቅ ሆኗል ። ለነሱም ። አንዳቸው ላንዳቸው ይሆኑ ዘንድ የማይቻል ነው ። ህልማቸውን በግል ሲያባርሩ ፤ ሊያገኙት ከቻሉ ሌላ ቦታ ቢፈልጉት ይሻላል ። «ናንሲ በጣም ቆንጆ ልጅ ሆነሻል ኮ» አለች ማሪዮን ፤ ወንድ አይጠፋም ለማለት ያህል ። «ቆንጆ ስላልሺኝ አመሰግናለሁ ይገባኛል ። ፒተር ውብ የእጅ ሥራ ቀርጾአል ። ግን ይህን ለማድረግ የገባሁበት ውል…. ከሰይጣን ጋር እንደመዋዋል የሚቆጠር ነው ። ቆንጆ ፊት ለማግኘት ሕይወትን መሰዋእት ማቅረብ ። ሌላ ትርጉም የለውም»

«ሰይጣኒቷም እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ» አለች ማሪዮን በሀዘን በተሰበረ ድምፅ «ምንም እንኳ ዛሬ ይህን ላንች መንገር ርኩስ ተግባር እንደሆነ ቢገባኝም ፡ ያኔ ናንሲ ፣ያኔ ቃል እንድ ትገቢልኝ ሳግባባሽ ፤ ሊሆን የሚገባውን ነገር ያደረግኩ መስሎኝ ነበር»
«አሁንስ ? አሁንስ ምን ይመስልሻል ? » አለች ፊት ለፊት በድፍረት እየተፋጠጠቻት «አሁንስ ምን ይሰማሻል ፤ሚስ ሂልያርድ ? ለመሆኑ ማይክል ደስተኛ ነው? እኔን እንደ አሮጌ ዕቃ ወርውረሸ ከጣልሽለት በኋላ ደስ ብሎት መኖር ጀመረ? ተልእኮሽ ሰመረልሽ ? » ስሜት ተናነቃት ። በጥፊ ልታልሳት ፈለገች ። ይህን የወይዛዝርት ልብሷን እንደተጎናፀፈች ገፍትሬ ጥዬ መሬት ለመሬች ብጎትታት ! ስትል ተመኘች ። «የለም የለም አንዱም ነገር አልተሳካልኝም ። ማይክል ደስተኛ አይደለም ። ከጊዜ ጊዜ ሁሉን ነገር ይረሳል ፤ ሀዘኑ ይሽራል በሚል ተስፋ ስጽናና ቆየሁ ። ግን አልሆነም ። አንችም እንዲያ እንደምትሆኝ ተስፋ ነበረኝ ።ግን ሳይሽ ነሽ ሀዘንሽ አልሻረም ምንም ነገር አልተረሳሽም ። ወይስ የተሻለ መንገድ መርጠሻል? ብዬ እጠይቅሽ ነበር ። ሆኖም መብት ያለኝ አይመስለኝም »
«ልክ ነሽ። ያን ጥያቄ ለማቅረብ ምንም መብት የለሽም ማይክል ሚስት አገባ ወይስ ?»
«አግብቷል» አለች ማሪዮን ። ሜሪ ክው ብላ ደነገጠች ። ኡኡ ! ብላ ለመጮህ ፈለገች ። ድምጹን አፍና አስቀረችው ። ያ ድምፅ ከጉሮሮዋ ሳይወጣ ሟሟ። «አዎን ፤ ሜሪ ። አግብቷል ። ሥራውን አግብቶ ትዳር መስርቷል ። የሚበላው የሚጠጣው የሚተኛው እሥራው ላይ ሆኗል። ትንፋሹ ሳይቀር ሥራው ሆኗል ።» ሜሪ ትንፋሽዋ መለስ አለ። «ከሥራው ላይ ንቅንቅ አይልም ። በሥራው ውስጥ ሰምጦ ዘለአለም አለሙን ሊያሳልፍ የፈለገ እስኪመስል ። አብረን እንኖራለን ይባላል እንጂ መልኩን የማየው ከዝንተ አለም አንድ ጊዜ ነው»

የት አባሽ አንች ውሻ !እንኳን ! አለች ሜሪ በሀሳቧ «እንዲያ ካልሽ ፤ ስህተት መስራትሽን ተገንዝበሻል ማለት ነው። ማለት በአለም ላይ ካለው ሀብትና ማንኛውም ድንቅ ነገር አብልጨ እወደው እንደነበር ታውቂያለሽ ? » ይህን ብላ ስታበቃ በኃሳቧ ከዚህ ፊቴ በስተቀር…. ከፊቴ በስተቀር ! አምላኬ ምናልኩህ «በስተቀር» እንድል አደረግከኝ! «አውቃለሁ ። አውቅ ነበር ። ግን ፍቅር ነውና ያልፋል ብዬ ገመትኩ»
«ሆነ ? ግምቱ ትክክል ነበር ? ረሳኝ ? »
«እንጃ ። ምናልባት አልፎለት ይሆናል ። ስምሽን አንስቶ አያውቅም መቼም»
«በመጀመሪያ ወይም መቼም ቢሆን የት እንዳለሁ ለማወቅ ሙከራ አድርጎ ነበር ?» ማሪዮን በአሉታ ራሷን እየነቀነቀች «እልሞከረም» አለች ። ይህን ትበላት እንጂ ለማይክል ናንሲ ሞታለች እንዳለችው አልነገረቻትም ። «ያ ከሆነ ታዲያ ለምን ጠራሽኝ? እኔን የማየት ጉጉትሽ እንዲረካ ? ….. ፎቶግራፎች እንዳሳይሽ?. . . ለምን ?»
«እኔም ለምን እንደፈለግኩሽ አላውቅም ፤ ናንሲ ። ይቅርታ... ሜሪ ። ቅድም እንደነገርኩሽ ነው ። አላውቀውም።... በግድ እዘኑልኝ ማለት ፤ ወይም ሆደባሻነት ይመስላል እንጂ ደኅና አይደለሁም ። መሞቻዬ ሩቅ አይደለም ። እመቃብሬ አፋፍ ላይ የቆምኩ ይመስለኛል»
👍15
ማሪዮን ይህን ብላ ወደ ሜሪ አዳምሰን ዞረች ። ያኔም ሜሪን ማሪዮን ሞቷ ስለቀረበ ምን ያህል እንዳዘነች አየች ። ሜሪን ስትመለከት ማሪዮን ለምን ነገርኳት? የሚል ብስጭት ገባት ። በዚያም አለ በዚህ ሜሪ ለማሪዮን ቅንጣት ያህል ሀዘን አልተሰማትም ። ማሪዮንን ለረጅም ጊዜ ትኩር ብላ ስትመለከት ከቆየች በኋላ ፤ «እንዲህ ያለውን ነገር በመስማቴ አዝናለሁ ፤ ሚስዝ ሂልያርድ ። ግን ደግሞ እኔም ሙት ነኝ። ከሞትኩ ሁለት አመት ሞላኝ ። እንደሰማሁት ከሆነ አንድ ልጅሺም ሞቷል ። ሁለት ነፍስ አጥፍተሻል ማለት ነው ። የሁለት ሰው ደም አለብሽ ። እና እውነቱን መናገር ካለብኝ የሆነው ነገር ቢደርስብሽ ፤ እኔ ሳልሆን ልቤ ሀዘን ሊፀንስ አይችልም። መቼም በመንገድ ላይ ስሄድ ወንዶች አየት አድርገውኝ ፊቴ መበላሸቱን ብቻ ሳይሆን ጣረሞት መምሰሌን አይተው እንዳይሸሹኝ አድርገሽልኛል ። በዚህ ላመሰግንሽ ፤ይህን ውለታ ልቆጥርልሽ ይገባኝ ነበር ግን አልችልም ። ብዙ ብዙ ነገር ሊሰማኝ ይገባ ነበር ብዬ አምናለሁ ። ግን ምንም አይሰማኝም ። ብቻ ልጅሽን እንዲያ እንዳደረግሽው በመገንዘብሽ በዚያ ብቻ ትንሽ ሀዘን ቢጤ ይሰማኝ ይሆናል ። ሌላ የለም»

ማሪዮን ፀጥ ብላ ራሷን በአወንታ እየነቀነቀች የሜሪን ወቀሳ በፀጋ ተቀበለች። ለምን? ሜሪ ያለችው ሁሉ እውነት እንደሆነ ራሷ ደርሳበታለች ! ዛሬ አይደለም ። ከሆነ በኋላ ለራሷ አትመነው ፡ አትቀበለው እንጂ ልቧ የሰራችውን ጥፋት አውቆታል። ቢያንስ በማይክል ላይ የፈፀመችው በደል ያለ ጥርጥር ግብቷታል። ከገባትም ቆይቷል ። ምናልባት ሜሪ ለማየት የፈለገችውም ፤ በሷ (ሜሪ) በኩል የተሻለ ሕይወት አይ ይሆን) ስትል ተስፋ በማድረግ ሊሆን ይችላል ። «ልክ ነሽ የኔ ልጅ። ልክ ነሽ። ምን ብ....ምን ብዬ ልንገርሽ….. የምናገረውም የለኝ»
«ደህና ሁኝ ብትይኝ ደግ ነው» አለች ሜሪ።

ይህን ብላ ካፖርቷንና ፎቶግራፍ መያዣዋን አነሳችና ወደ በሩ አመራች ። በሩን ለመክፈት እጄታውን እንደያዘች አንገቷን ደፍታ ፣፤ እንባዋ ተንቆርዝዞ ለጥቂት ጊዜ ቆማ ቆዘመች ። ቀስ ብላ ወደ ክፍሉ ውስጥ ዞረች ። ያኔም የማሪዮን ሂልያርድ ፊት እንባ በእንባ ሆኖ ተመለከተች ። ማሪዮን በራሷ ስቃይ ተለጉማ ነበርና አንዲት ቃል ልትተነፍስ አልቻለችም ። ወጣቷ ሜሪ ግን እንደምንም ሳጓንና ከላይ ከላይ ሲላት የጀመረ ትንፋሽዋን ተቆጣጥራ «ሚስዝ ሂልያርድ ደህና ሁኝ ። ለማይክል...ፍ...ፍቅ የፍቅር ሰላምታዬን አቅርቢልኝ» አለች ። ይህን ተናግራ በሩን ከፍታ ወጣች ።

ማሪዮን ሂልያርድ ግን ካለችበት ንቅንቅ ማለት አልተቻላትም ። ልቧ እየዘለለ ሳንባዋን ሲደበድበው ከፍተኛ የሀመም ስቃይ ለቀቀባት ። ከላይ ከላይ እየተነፈሰች ፤ መጥሪያ ደወሉ ወዳለበት እየተንቦራቸች ሄደች ። ያን መጥሪያ ብትነካው አንድ ሰው አንዲት ሠራተኛ እንደምትደርስላት ታውቃለች ። እንደምንም ደረሰች ። እንደምንም መጥሪያውን አንዴ ብቻ ተጫነችው። ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር ጨለማ ሆነ «
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍141
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሦስት ወራት አለፈ" ካርለት በሐመር ቆይታዋ ብዙ ልምድ አካበተች ያልጠበቀችውንም እርካታ አገኘች ካርለት ከሎን ወደ ዲመካ፣ ቱርሚና ጂንካ ከተማ ሲሄዱ እግረ መንገዷን መኪና ማሽከርከር ስላስለመደችው መረዳዳት
ጀምረዋል" ካርለት በሐመር ኑሮዋ ዕቃዋን፣ ገንዘቧን ለማስቀመጥ የምትተማመነው በመኪናዋ ውስጥ ነው፤ በተለይም ሙዚቃ ለማዳመጥ መኪናዋ ከፍተኛ ጥቅም ትሰጣታለች" በነዳጅ በኩል እስከዚያ ወቅት ድረስ ችግር አላጋጠማትም፤ ካስፈለጋት ግን ጂንካ ከተማ ናፍታ ማግኘት እንደምትችል ተረድታለች።

የሐመር ሰማይ ጥርት ያለና አልፎ አልፎ ብን ያለ የጥጥ ባዘቶ መሳይ ዳመና ይታይበታል” የዝናቡ ወቅት፣ እምብዛም የሚያስተማምን ባይሆንም፣ ድንገት እያጓራ የሚያጋሽብ ጥልመት ዳመና ከታየ «አህያ» የማይችለው ዝናብ፣ መዓቱን ያወርደዋል" በዚህ
ወቅት የዕጽዋት ቅጠሎች እንደ በረዶ ብን ብን እያሉ ሲወድቁ ከብቶች ጅራታቸውን ሸጒጠው፣ ጆሮአቸውን ይጥላሉ።

በዚህ ወቅት፣ የከሰኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ዛፍ ቅጠሉን እያተራመሰ፣ ባሕርይውን ይቀይርና በመደንፋት፣ እየተነሣ ይፈርጣል"
በዚያን ጊዜ ከሰኬ ወንዝና የሐመር ማኅበረሰብ፣ ከብቱ፣ ፍየሉ፣ ይኰራረፋሉ «አትድረስብኝ» አንመጣብህም ይባባላሉ"
አንድ ጊዜ፣ ካርለትና ከሎ መዝነቡን ሳያውቁ ከጂንካ ወደ ሻንቆ ሲሄዱ፣ ከሰኬ ወንዝን በመኪና ገብተው ሊሻገሩ ሲሉ መኪናዋ
በአሸዋው ተያዘች እነሱም ከመኪናቸው ወርደው በዶማና አካፋ
ለማውጣት ሲሞክሩ «ፉ..ፉ..ፉ.» የሚል ድምፅ ሰሙ። ቀና ሲሉ ደረቱን ገልብጦ፣ የሚጣደፍ ደራሽ ውኃ ተመለከቱ። ካርለትና ከሎ ብርክ ይዟቸው እንደ ሕፃን ልጅ ተንቦራቹ። ውኃው ግን ገሰገሰ ካርለትና ከሎ ዳር ላይ ሊደርሱ ሲሉ ውኃው ሲያጠናግራቸው
ተንገዳገዱ፤ ሳያስቡት እጅ ለእጅ መያያዛቸው ግን በጃቸውና ለትንሽ
አመለጡ። ደራሽ ውኃው መጀመሪያ መኪናዋን እያነቃነቀ ፈተሻት፣
ቀጥሎ በጎኗ፣ ከዚያም በጭንቅላቷ አቆማት።
«አምላኬ!» አለች፣ ካርለት መኪና የሚያገለባብጠው ውኃ እነሱን ቢያገኝ እንዴት ብትንትናቸውን እንደሚያወጣቸው እያሰበች።

ዛፉ «ቋ..ቀሽ.."ቀሽቀሽ...» ይላል፤ ግንድና ቅጠሉ ብቅ–ጥልቅ ይጫወታሉ፤ ውኃው፣ ሣር ቅጠሉን ያግበሰብሳል" መኪናዋ ጎማዋ ሲታይ ቆይታ በጎኗ ተጋደመች። ደራሽ የውኃ ሙላቱ ግን ለማንም
በሚያስገርም ሁኔታ እየቀነሰ፣ እየቀነሰ መጣና ጸጥ አለ። ካርለትና
ከሎ መኪናዋን ማውጣት ባለመቻላቸው፣ በየቦታው የተገነደሰውንም
ግንድ ለብቻቸው ማነቃነቅ የማይሞከር በመሆኑ፣ የሻንቆን መንደር
ኗሪ በእግር ሄደው ጠርተው፣ በስንት ችግር መኪናዋን ሊያወጡ
ቻሉ" ስለዚህ፣ ሐመር ላይ ዝናብ ሲዘንብ ከስኬ ሰው፣ ከብት፣ መኪና ሳይቀር ስለሚወስድና ስለሚያሰምጥ ምሱን አያጣም፤ ከብቱን፣ አራዊቱን፣ ሰውን...ድንገት ጠልፎ በመዋጥ የቆየ ልምድ አለው። ካርለትና ከሎ በቆይታቸው የተለያዩ ዕጽዋትንና ጥቅማቸውንም ተረድተዋል። ወንዴና ሴቴ ቃጫ ለገመድና ቤት ሥራ፣
ጠዬ ለዱላ፣ ሌልሜ ለቤት ሥራ፣ ፌጦ ለመፋቂያ፣፣ ኩንኩሮ ለተለያየ ጥቅም፣ ፊላና ሰንበሌጥ ለቤት ሥራ እንደሚውሉ ተረድተዋል።
በተረፈ ጨው ሊንባ፣ እንኮይ፣ ዘምባባ፣ አጋም፣ ጨዋንዛ፣ ግራር
ወዘተ የሐመርንና የአጐራባቾችን መሬቶች አስውበው ሲመለከቱ፣
ከመንፈስ እርካታው በተጨማሪ አንዳንዶቹን መጠቀም ችለዋል።
ካርለትና ከሎ ሻንቆ፣ ላላ፣ ወሮ፣ ዴንባይቴ፣ ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዴ...መንደሮች ሲዘዋወሩ ከማኅበረሰቡ
አባላት ጋር ከሚገናኙበት አንዱ ሸፈሮ ቡና (የቡና ገለባ) የሚፈላበት
ወቅት ነው። የሐመር ቡና የሚፈላው በጀበና ሳይሆን በትልቅ እንስራ ነው ቡናው የሚጠጣው ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ ረፋዱ ድረስ
ሲሆን፣ ያደረሰው ሁሉ መጠጣት ይችላል። አንድ ጊዜ ታዲያ፣ ካርለትና ከሎ ሻንቆ መንደር ለመጀመሪያ
ጊዜ ቡና ሊጠጡ ሄደው፣ ኦይጊ የተባለችው የመንደሩ ኗሪ ቤቷ ለመጡት እንግዶች በሾርቃ ከትልቅ ቅል ላይ በተከፈለ መጠጫ
ለሁሉም እንግዳ ስታድል፣ ለሁለቱም ሰጠቻቸው" ካርለት አንዱን
ሾርቃ እንደምንም ጨርሳ ‹ተገላገልኩ› ብላ፣ ሾርቃውን ለአይጊ አቀበለቻት በሐመር ባህል ሾርቃውን ቡናውን ለምትቀዳው ካቀበሉ
ድገሚኝ እንደማለት በመሆኑ፣ ኦይጊ ቡናውን በሾርቃ ሞልታ ለካርለት ሰጠቻት፤ «አምላኬ!» አለች ካርለት የመጀመሪያው ቋቅ
ሊላት ደርሶ፣ ሁለተኛውን ስታስታቅፋት።

ካርለት፣ ቡናውን መጠጣት ከበዳት። ቁጭ አድርጋ ትታ
እንዳትሄድ፣ ባህሉን መናቅ እንዳይሆንባት ሠግታ ስትጨነቅ ቡናውን
በያዘው ሾርቃ ላይ ዝንቦች እየገቡ ተንሳፈፉ። ካርለት፣ «ጥሩ አጋጣሚ» ብላ፣ እየሣቀች፣ «ዝንብ ገባበት» በላቸው አለችው ከሎን!
«ድፊው» ይሉኛል ብላ። እነሱ ግን፣ «ጠጭው ምንም አይልሽም፣
ይሄ የወተት እንጂ፣ የቆሻሻ ዝንብ አይደለም» አሏት። ካርለት፣ ሌላ አማራጭ ስላልነበራት የሚንሳፈፉትን ዝንቦች «እፍ» እያለች
ቡናውን ጠጥታ ጨረሰች።

ካርለት በሐመር ኑሮዋ በጣም የከበዳት ችግሯ ግን የሐመሮች የጊዜ ዕውቀት አለመኖር ነው። ካለፕሮግራሟ በተለይ በገበያ ቀን ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ቀይአፈርና ጂንካ በመኪናዋ እንድትወስዳቸው
ይጠይቋትና መኪናዋ ውስጥ ዱቄት፣ ፍየል፣ በግ፣አረቄ፣ ማርና ቅቤ
ሰለሚጭኑ ሁሌ ትሳቀቃለች" አንዳንዴም አፍ አውጥታ! «አልሄድም» ትላለች።

ካርለት ምግብ፣ ደብዳቤ፣ መጽሔት፣ ከቤተሰብ ጋር የስልክ ግንኙነት ለማድረግ አዲሳባ ስትሄድም በጕዞው ከሎ ሆራ መኪና
ማሽከርከር ቢረዳትም ወንዝ እየሞላ፣ ጭቃ ሲይዛቸው ትማረራለች።

ካርለትና ከሎ ወደ አዲሳባ ሲሄዱ አልፎ አልፎ የሚላኩት መልእክት የተወሰነ ሲሆን አቡጀዲ፣ የላስቲክ ጫማ፣ ሸፈሮ ቡና
ሽጉጥ መሳይ መድኃኒት «ቴትራሳይክሊን ወይም ክሎሮፌኒኮል”ዋነኞቹ ናቸው"

ካርለት ሐመር ሦስት ወር ቆይታ አዲሳባ እንደሄደች፣ ከስቲቭ ጋር ተገናኙ። ስለ ሐመር ሕይወቷ፣ ስላየቻቸው ነገሮች፣ ስላጋጠማት ችግርና ስለ ወሰደችው የመፍትሔ እርምጃ አጫወተችው
ስቲቭ ከነገረችው ሌላ፣ ካርለት አንገቷና እጇ ላይ ያለውን ነገር ከማየቱም ባሻገር፣ ሳታቋርጥ ስታክ ተመለከታት» ከዚያም፣ «የኔ
ፍቅር፣ ይህን ያህል ለምን ራስሽን ለችግር ታጋልጫለሽ?» አላት
ስቲቭ"

«ችግር ስትል ምን ማለትህ ነው?»

«ይህ ደረሰብኝ እያልሽ ያወራሽኝ ሁሉኮ ጋሪ ላይ የተጫነ ጭነት ሳይሆን፣ አንች የተሸከምሽው ችግር ነው?» አላት"

«ስቲቭ፣ አንድ ሰው የምኖረው ትርጕም ያለው ሥራ ለመሥራት ነው ካለ፣ ሕይወቱም ትርጕም ያለው ይሆናል" ሌላው ደግሞ
(ምኖረው ለመሞት ነው› ካለ በውስጡ እውነትነት አለው” ሕይወቱ ግን፣ ትርጕም አልባ ይሆንበታል"

«ማንኛውም አጋጣሚ በየግላችን አእምሮ አመዛዝነን፣ መክረን፣
እናወጣ እናወርደዋለን፣ ቀጥሎ ጥሩ ወይም መጥፎ ትርጕም እንሰጥና ተግባሩ ላይ ያን አጋጣሚ እንጠላዋለን ወይም እንወደዋለን።

«አንዱ መኖርን ጥሩ ሥራ ለመሥራት እንደሆነ ተረድቶ ሲጥርI ሌላው ደግሞ መኖሩ ለመሞት መሆኑን አውቆ ተስፋው ይኰሰምናል"
👍25🥰2
«እኔም፣ ገጠመኜን ማውራቴ ለአንተ ፍርሃትን ሲፈጥርብህ፣ለእኔ ግን ፍቅር ስላሳደረብኝ፣ አብሬያቸው መኖሩን እመርጣለሁ»አለችውና ዝም ብላ ቆይታ፣ «አየህ ስቲቭ፣ ከርቀት ጠቦ የሚታይህ ድልድይ፣ ስትደርስበት ግን ሰፊ ነው» ብላ ጉንጩን ቆንጠጥ
አድርጋ፣ ከከሎ ጋር ጕዞዋን ቀጠለች"...
«በአባቴ ቆዳ ላይ ተኝተህ፣ ኩርኩፋህን እየበላህ፣ ሸፈሮ ቡናህ እየጠጣህ፣ ቀና ብለህ የቦርጆን (የአምላክን) ከዋክብት ተመልከት
አሸጋግረህ የሐመር ተራራዎችን ቃኝ በእበትና አፈር እያጌጥክ
የባንኪሞሮን ንቦች እየተንከባከብክ፣ ማሩን ብላ የአበቦችን መዓዛ
አሽትት"

«ጠላቶቻችን ከተራራው ግርጌ ናቸው" የአባቴ አጥንት ስለ ወጋቸው፣ ጠረኑ ስለሚያስበረግጋቸው፣ አይመጡብህም ሾልከው
ከገቡ ግን እበቴን ተቀብቼ፣ ንቤን በብብቴ ይዤ፣ ሁለት አፍ ጦሬ በመያዝ፣ አንተን አስከትዬ እሄድላቸዋለሁ የሀገሬ አዕዋፍ አውሬ፣ ያኔ ይጠግባሉ"

«ፀሐይ ከወደቀችበት ነገ ትነሣለች ጨረቃን ገፍትራ ጥላ ቦታዋን እስክትይዝ ግን ታጋሽ ሁን ጨለማን ተገን አድርገህ ተንኮል
አትሥራ» ከስኬ ከአሸዋ በላይ እስኪሞላ፣ የሰማይ ውኃን እየጠበቅህ
ጓሮህን እንድትቆፍር ልጃገረድህን እዘዝ"

«እጅህንና እግርህን በምላስህ እሠር የአባቴን ደንብና ባህል አክብር የታላላቆችህን ትእዛዝ ተቀበል ለጠላቶችህ የማትፈራ ወፍ በጥይት የምታስቀር፣ ጀግና ሁን። ካለበለዚያ፣ የአባቴን ደንብ
ሽረሃልና ደረቴን አስጌጥብሃለሁ (እገድልሃለሁ)።
«ተጫወት፣ በአባትህ ሜዳና ተራራ ተዘዋወር ከልጃገረዶ ጋር ዝለል ወተትና ደም ጠጣ ውለድ ከብትህን በበረት ሙላ
...የኔ ልጅ ጨርሻለሁ» ብለው የሚጠጡትን ሸፈሮ ቡና «ፕስስ...» እያሉ፣ በአራቱም ማዕዘን ያማትቡና የልጃቸውን ራስ
ዝቅ አድርገው የሸፈሮ ቡናውን ውኃ፣ «ፕስስ…» እያሉ ያርhፈክፉበታል።
ደልቲ ገልዲ፣ አባቱ ገና ከመሞታቸው በፊት ምርቃታቸውንና
አደራቸውን በገሐድ አሳያቸው ለምሳሌ ደልቲ ገልዲ ማጎ በረሃ
ከጓደኞቹ ጋር ወርዶ ካለምንም ስንቅ ለተወሰነ ጊዜ በረሃብ ቢሠቃይም፣ ከዚያ በኋላ ግን ሚዳቋም፣ ውድንቢትም፣ ድኩላም፣
እየገደሉ፤ ቋንጣውን በፀሐይ በማድረቅ እየተመገቡ ታላላቅ አራዊት
ሊገኝበት ከሚችልበት አካባቢ በመዘዋወር ሰንብተው፣ አንድ ቀን
ከማጎ ወንዝ ውስጥ ተነከረው እንዳሉ የአራዊት ዳና ሰሙ እየሮጡ በመውጣት ድምፁን ከሰሙበት አቅጣጫ በተቃራኒ ካለው ጫካ ውስጥ አደፈጡ" ሆኖም ግን፣ መሣሪያቸው ወዲያ ማዶ በመሆኑ ሲመኙት የነበረው ዕድል አመለጣቸው" የመጣው የጎሽ መንጋ ካለብዙ ችግር፣ እርስ በርስ እየተጠባበቀ በመጣበት አቅጣጫ
ሄዶ ተሠወረባቸው"

ደልቲም ሆነ ሌሎች ጓደኞቹ ወደ አደን ከመምጣታቸው በፊት ብዙ የአራዊት ጠባይ ተነግሯቸዋል" ጎሽ ከቈሰለ፣ የአቈሰለውን ሰው
እንደማይለቅ  ያንን ሰው ባያገኘው እንኳን ዝንብ ቈስሉን እየበላ እንዳያስቸግረው ከወንዝ ውስጥ እየገባ እንደሚያደፍጥና ሌላ ሰው
ካገኘ ብጥስጥሱን በእልክ እንደሚያወጣው ሰምተዋል" ስለሆነም፣
ጎሽን ለመግደል ብልቱን ለይቶ መምታት እንደሚያስፈልግ፣ በመንጋው ላይ ከመተኰስም፣ ከመንጋው የተለየውን መግደል እንደ
ሚሻል፣ ተመከረዋል"
ግታ ማታ አንበሳና ነብር እንዳይተናኰላቸውም እሳት ማቀጣጠል እንደሚገባና እሳቱ ብዙ ጭስ እንዳይኖረውና ጫካውንና
ኣውሬዎችን የሚጠብቁት ዘበኞች አደጋ እንዳያደርሱባቸው
እንዲጠነቀቁ እባብ በተለይም የጠገበ ዘንዶ፣ አንዳንዴ ግንድ መስሎ እንደሚጠቀለልና ድንገት ቁጭ ካሉበት ለአደጋ
እንዳይጋለጡም ተመክረዋል።

አቅጣጫ ጠፍቶባቸው በተለይ በውኃ ጥም እንዳይጠቁም ልምምድና ውኃ የማያስጠማ መፋቂያ
እንዲይዙና በጨረቃና በከዋክብት አቅጣጫ እንዲንቀሳቀሱ፣
ተነግሯቸዋል" በተለይ ደግሞ፣ ሲጓዙ በጋራና በዘዴ እንዲሆንና፥ በተናጠል እንዳይጓዙ፣ ችግር ሆኖ ከተጠፋፉም እንቅልፍ ለመተኛት ሲፈልጉ ከመጋደም ይልቅ ቁጭ ብለው አንገትን ወደ ታች በመቅበር እንዲተኙ ከብትም ሆነ ሰው ላይ ጥላው ሲያርፍ ወገብ የሚያጣምመው አሞሯ ሲበር ሲታይ መደበቅና ከጥላው መራቅ ማስፈለጉን የግድ የሚቀርብ ከሆነም ተኵሶ ማባረር የሚሻል መሆኑን ተመክረዋል" በተረፈ አራዊት ከጠፉ የጀግንነታቸው ማረጋገጫ
ስለማይኖር ሴትና ወንዱን መለየት ስለማይቻል ዕድል ቀናኝ ብለው በብዛት መግደልና ማስደንበርም እንዳይፈጽሙ አደራ ተብለዋል።

ስለዚህ፣ የጎሹ መንጋ ተመልሶ ሄዶ ከአካባቢያቸው መራቁን
አረጋግጠው ከተደበቁበት ብቅ ሊሉ ሲሉ፣ ሴትና ወንድ አንበሳ ወደ ውኃው ሲመጡ አዩ  ወዲያው ደንግጠው ተመልሰው ተደበቁ
በቁጥቋጦው ውስጥ ከርቀት ሲመለከቱ ደግሞ፣ ግንድና ቅጠሉ ሲርመሰመስ ተመለከቱ" ከዚያ አንበሶቹ እነሱ ወደ ተደበቁበት አቅጣጫ ሲመጡ፣ ሁሉም ወሽመጣቸው ተበጠሰ። ባዶ እጅ ከአንበሳ
ጋር መግጠም መቼም አይቻልም" ያውም ከሁለት አንበሳ" አንበሶቹ
ከኋላ ግንድና ቅጠሉን እያተረማመሱ የሚመጣውን አውሬ በጥርጣሬ እያዩ ስለሚሸሹ ደግነቱ እነሱን ፈርተው የሚንቀጠቀጡት
አላስተዋሉም። ስለዚህ፣ መንገዳቸውን ቀጠሉ።

ግንድና ቅጠሉ በሚሰባበርበትና በሚንሿሿበት አቅጣጫ
ሲመለከቱም፣ ለቍጥር የሚታክት ዝሆን ተመለከቱ" ስለ ዝሆን ደግሞ የሰሙት አለ" ዝሆን ከፍተኛ የማሽተት ችሎታ አለው" እስከ ብዙ ርቀት ጠረን ማሽተት ይችላል" ምናልባት ደግነቱ ነፋሱ ወደነሱ
አቅጣ ስለሆነ ጠረናቸው ላይደርሰው ይችላል" እንሽሽም ተባብለው ነበር" ግን፣ ከዚህ የዝሆን ረገጣና ወገራ ቢያልፉ፣ ከዚያ
ደግሞ የአንበሳ ክንድና የጎሽ ቀንድ ይጠብቃቸዋል" ሁሉም ያው እንዳቅሙ ሰባብሮ፣ መጨረሻው ሞት ነው" ስለዚህ መሸሹ
እንደማያዋጣ አመኑ።

የዝሆን መንጋው በኩንቢው ውኃውን ሰውነቱ ላይ እየረጨ! ውኃው ውስጥ ለብዙ ሰዓት ቆየ" አንድ ዝሆን እንዲያውም፣ ድንጋይ
ተደግፎ የተቀመጠውን ምንሽር ጠመንጃ ወደ ላይ በኩንቢው አንሥቶ አይቶ መልሶ አስቀመጠው የሱ ማደኛ መሆኑን ቢያውቅ
ኖሮ ወደ አመድነት ይለውጠው ነበርI ነገር ግን አላወቀም። ስለዚህ
ጠላቱን አንሥቶ መልሶ አስቀመጠው"
ደልቲና ጓደኞቹ ይህንና ይህን የመሳሰለውን ችግርና አደጋ በማኅበረሰባቸው የሚያገኙት የጀግንነት ክብርና ሙገሳ፣ ልብን
ያማልላል" ከወንድነት ማረጋገጫውም ውስጥ ዋናው በጠላትነት
የሚያዩትን የማኅበረሰብ አባል መግደል ሲሆን ከዚያ የሚቀጥለው ደግሞ አውራሪስ፣ ዝሆን፣ አንበሳ፣ ጎሽ፣ ቀጭኔ መግደሉ ነው።

በሌላ ቀን ደልቲ ገልዲና ጓደኞቹ አደናቸውን እንደ ጀመሩ፣ከመንጋ የተለዩ ጎሾችን ተመለከቱ" ሁሉም በየተራ እያነጣጠሩ ተኮሱ የቀሩት ጎሾች ሲሸሹ፣ ሦስት ጓደኞቹ ብቻ ሦስት ጎሽ ገደሉ።ከነዚያ ውስጥ ደግሞ የመጀመሪያው ገዳይ ደልቲ ገልዲ ሆነ።
የገደሉት፣ ባልገደሉት ላይ ጀግንነት ተሰማቸው አቅራሩ ፎከሩ።

ለአደን በሄዱ በሦስተኛው ሳምንታቸው ደግሞ ከርቀት የቀጭኔ መንጋ ተመለከቱ፣ ቀጭኔ ከርቀት ማየት ስለሚችል እንዲህ በዋዛ
ማደን ስለማይቻል እምብዛም ተስፋ አጡ" ገልዲ ግን፣ በየት እንደሄደ ጓደኞቹ እንኳ ሳያዩት ከቀጭኔዎቹ እይታ ውጭ በመሆን ሥራቸው ድረስ መጠጋት በመቻሉ፣ በምንሽር ጠመንጃው አንዱን ቀጭኔ በሁለት ጥይት ወርቹን በጥሶ አንበረከከው። ጓደኞቹ ሲመጡ ከቀጭኔው ጀርባ ላይ ወጥቶ ጠበቃቸው።
👍193🥰1
ደልቲ ገልዲ፣ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የጎሽና የቀጭኔ ገዳይ ሆነ። ወደ መንደራቸው ሲመለሱም የመንደሩ ልጃገረዶች
ለገዳዮቹ፣ በተለይም ለጎሽና ቀጭኔ ገዳዩ፣ ጨሌያቸውን በአንገቱ አጠለቁለት" በየዘመዶቹም እያቅራራና እየፎከረ ሲሄድ በግና
ፍየላቸውን እያረዱ፣ ጀርባው ላይ ደሙን አፈሰሱለት" ለወራት ያህል ምግቡ ደምና ወተት፣ ሥጋና ማር ሆነ" በዚህ ደግሞ፣ አባቱ
ልጃቸው እሳቸው እንኳን ያልቀናቸውን የጎሽና ቀጭኔ ገዳይ በመሆኑ ኮሩበት"
ብዙም ሳይቆይ ደልቲ ገልዲ በሐመርና በሙርሲ ማኅበረሰቦች መካከል በተፈጠረው ግጭትና ጦርነት እንደ ጉርኑክ እየዘለለ በመዋጋት፣ሁለት ሙርሲ ገድሎ መሣሪያቸውን በመማረኩ፣
ደረቱን በመተልተል፣ ራሱን በቀይና በነጭ አኖ አፈር በማስጌጥ፣በአንገቱ ከደረደረው ጨሌና በእጆቹ ካጠለቃቸው አንባሮች ሌላ
በወገቡ በታጠቀው ዝናርና መያዣዋ በሚያንጸባርቀው ቤልጅግ ጠመንጃ ከአካባቢው ኗሪ ልዩ ክብር ተጎናፀፈ የመንደሩ ልጃገረዶ ቀርቶ ከመንደሩ ራቅ ያሉትም ልጃገረዶች ሳይቀሩ በዝናው በቁመናው በመመሰጥ፣ የመጀመሪያውን እፍታ በየጫካው አጐረፉለት። ከሙርሲ ማኅበረሰብ በዘረፋቸው ከብቶችም መሣሪያ ገዛና በረቱን በከብት ሞላ። ሁለት ሚስት አግብቶ፣ የአባቱን ምኞትም
አሟላ። አባቱም ምንም እንኳን ከዳሰነች ማኅበረሰብ ጋር በተደረገው ጦርነት ቢሞቱም፣ የአባቱ ደም መላሽ ለመሆን ቻለ።

ደልቲ ገልዲ ስሙ እየገነነ ሲሄድ፣ የእሱም ልብ እያበጠ ሄደ።መቼም ሲመጣ በላይ በላይ ነውና፣ የላላና ሻንቆን መንደር ሰዎች ከብት እየሰበረ ያስቸገረ አንበሳ ለማደን ሁሉም በቡድን በቡድን ጫካ ሲገባ፣ እሱ ግን፣ «በእኔ በኩል ብቻዬን እበቃለሁ» ብሎ፣ ከነመሣሪ
ያው ለአደን ተሰማራ" ሁሉም ቦርጆን (አምላክን) እየተማፀነ፣ የአንበሳው ገዳይ ሆኖ እንደ አባያ በሬ ለመንጐማለል ሲመኝ
ፍለጋው ሲጧጧፍ ውሎ የጥይት ተኲስ ተሰማ፤ ወዲያው አንበሳው
ተገደለ ተባለና ገዳዩ ማን እንደሆነ አንዱ ሌላውን ሲጠይቅ፣ «ደልቲ
ገልዲ፣ የተኛ አንበሳ አልገድልም ብሎ ‹ጎፈር) ብሎ ቀስቅሶ አስነሥቶ፣ አጓርቶ ወደ እሱ ሲዘልበት በሚያስደንቅ ፍጥነት
መሣሪያውን አቀባብሎ፣ በሁለት ጥይት፣ ልሳኑን ዘጋው» ተባለ"
ልጃገረዶች፣ «ይኸዋ አላልኩሽም!» ሲባባሉ፣ «ኧረ እሱ ምኑ ነው ይሄን ያህል!» እያሉ ያናንቁ የነበሩት ጐረምሶች እንኳን
ሳይቀሩ፣ አንገታቸውን ደፉለት እረኞች፣ ልጃገረዶች በስሙ ዘፈኑለት፣ ሌላው ቀርቶ የመፎከሪያ በሬው ከሌሎች ከብቶች በልጦ
ተንጐማለለ" ደልቲ ገልዲ፣ ከግዙፉ የቡስካ ተራራ ይበልጥ ገዝፎ መታየት ጀመረ" በዚህ ሰሞን ነበር ሁለት እንግዶች ወደ
መንደራቸው የዘለቁት።....

💫ይቀጥላል💫
👍23
#ምንሊክ_ኬኛ

መቋጫ ለሌለው
ጀማው ከሚታገል
አፄው ኬኛ በሉ
ሀገር ትገላገል።
29👎25👍8👏8
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወጀቡ እስኪጠፋ ወለሉ ላይ ተቃቅፈው ቆዩና ‹‹መርቪን አልጋው ላይ
እንውጣ ከወለሉ ይልቅ እዚያ ይመቸናል›› አለ፡
ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ከዚያም በጉልበቷ እየዳኸች
አልጋው ላይ ወጣች፡፡ መርቪንም ተከተላትና አልጋው ላይ አብሯት ወጣ፡፡
እሱም እቅፍ አድርጎ ያዛት፡፡
በወጀቡ ምክንያት አይሮፕላኑ በተናወጠ ቁጥር ልክ መርከበኛ የጀልባ
ውን ምሰሶ እንደሚይዝ ሁሉ ናንሲ መርቪንን ጭምቅ አድርጋ ትይዛለች፡፡
ወጀቡ ሲቀንስና ዘና ስትል እሱም ሰውነቷን በፍቅር ይነካካቸዋል ከዚያ ትንሽ ቆየችና እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡.
በሩ ተቆርቁሮ «አስተናጋጅ መቷል» የሚል ድምፅ ስትሰማ ከእንቅልፏ ነቃች።
ዓይኖቿን ስትከፍታቸው መርቪን ደረት ላይ መተኛቷን አወቀች
‹ወይ አምላኬ! አለች እየተርበተበተች፡

መርቪን ከተኛችበት እንድትነሳ በእጁ ገፋ አደረጋትና ‹‹ትንሽ ጠብቀን
አስተናጋጅ›› አለ፡፡

ከበሩ ውጭ የቆመው አስተናጋጅ በተደናገጠ ድምፅ እሺ ጌታዬ
እጠብቃለሁ›› አለ፡፡

መርቪን ከአልጋው ወረደና በአልጋ ልብስ ናንሲን ሸፈናት::

በዚህ አድራጎቱ በሆዷ አመሰገነችው፡፡ አስተናጋጁ እንዳያያት ፊቷን ወደ ግድግዳው አዞረች፡፡

መርቪን በሩን ሲከፍት አስተናጋጁ ገባና ‹‹እንዴት አደራችሁ›› አለ በፈገግታ፡፡

የትኩስ ቡና መዓዛ ናንሲን አወዳት፡፡ ‹‹በእንግሊዝ የሰዓት አቆጣጠር
የሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ነው ማለት ነው?›› አለ አስተናጋጁን

‹‹ልክ ነው ጌታዬ የኒውፋውንድ ላንድ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች
የሰዓት አቆጣጠር  ሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ይዘገያል፡››

‹‹መቼም የአየር መንገዶችን የጉዞ መርሃ ግብር ለሚያዘጋጁ ሰዎች ይህ  የሰዓት አቆጣጠር  ችግር
ሳይፈጥርባቸው አይቀርም፡፡ ባህር ላይ ለማረፍ ምን
ያህል ሰዓት ይቀረናል?›› ሲል ጠየቀ መርቪን

‹‹ከግማሽ ሰዓት በኋላ እናርፋለን፡ ከመርሃ ግብሩ አንድ ሰዓት ጉዟችን
የዘገየው በወጀቡ ምክንያት ነው›› አለና አስተናጋጁ በሩን ዘግቶ ወጣ፡

ናንሲ በሩ ከተዘጋ በኋላ ‹የመስኮቱን መጋረጃ ክፈተው፡ ነግቷል››
አለችው:፡ መርቪን ቡና ሲቀዳ የትናንት ምሽት አዳራቸው ፊቱ ላይ መጥቶ
ድቅን አለ፡፡ ወጀቡ በተነሳ ቁጥር መርቪን እጇን የሚይዛት፣ ወለሉ ላይ
የሚወድቁት፣ የመርቪን እጆች ጡቶቿን ሲጨብጥ፣ አይሮፕላኑ ሲናወጥ፣
እሱ ደረት ላይ ልጥፍ የምትለውና እየደባበሰ የሚያስተኛት ትዝ አላት:
ይህን ሰው በጣም ወድጄዋለሁ› አለች በሆዷ።

‹‹ቡና እንደወረደ ወይስ ከወተት ጋር ነው የምትፈልጊው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡

‹‹ጥቁር ቡና ይሁንልኝ፡ ስኳር አልፈልግም››
‹‹እንደ እኔ›› አለና ቡናዋን አቀበላት ናንሲ አመስግና ቡናዋን ጠጣች፡፡

ናንሲ ስለ መርቪን በደንብ ማወቅ ፈለገች፡፡ ቡናውን እየጠጣ ስለእሱ ልማዶች ግምቷን አስቀመጠች፡፡ ቴኒስ ይጫወታል፣ ልብ ወለድ ብዙ ማንበብ አይወድም፣ ገበያ መሄድም እንደዚሁ፣ ቁማር ጨዋታ የሚሳካለት ይመስላል፣ ዳንስ ግን የሚችል አይመስልም፡፡›
‹‹ምንድን ነው የምታውጠነጥኚው?›› ሲል
ጠየቀ ለሕይወት  ኢንሹራንስ አደገኛ እንደሆንኩ አድርገሽ የምታይኝ መሰለኝ፡፡››

ናንሲ ቀልዱ አሳቃት፡፡ ‹‹ምን አይነት ሙዚቃ ነው የምትወደው?›› ለሙዚቃ ጆሮ አልሰጥም›› አለ ‹‹መደነስ ባልጠላም ጥሩ ደናሽ ግን አይደለሁም፡፡ አንቺስ?››

እኔ ድሮ ደንሼያለሁ፡መደነስም ነበረብኝ፡፡ እሁድ እሁድ ሱፍ ከሚለብሱ ወንዶች ልጆች ጋር በዳንስ ትምህርት ቤት ዳንስ እማር ነበር፡፡ከላይኛው መደብ የቦስተን ማህበረሰቦች ጋር ለመግባባት ብቸኛው መንገድ ይህ ብቻ እንደሆነ እናቴ ትነግረኝ ነበር፡ እኔ ግን ከዛ ማህበረሰብ ውስጥ
ብገባ ባልገባ ግድ አልነበረኝም፡: የኔ ቀልብ ያለው ከአባቴ ፋብሪካ ጋር ነው፡፡ እናቴ ደግሞ ይሄን ባህሪዬን አትወደውም ነበር፡››

ሁለቱ አዲስ ፍቅረኛሞች ተያዩ፡፡ መርቪንም ትናንት ማታ እንዴት ሲላፉና ሲላላሱ እንዳመሹ እንደሚያስብ ነቃችበት፡፡ ይህም ሀሳብ እፍረት
ውስጥ ከተታትና ፊቷን ወደ መስኮቱ ስታዞር መሬት ታያት፡፡ አይሮፕላኑ
ቦትውድ ሲያርፍ ህይወቷን የሚለውጠውን የስልክ ጥሪ ማድረግ እንዳለባት ትዝ አላት፡ ‹‹ደርሰናል›› አለችና ከመኝታዋ ዘላ ተነሳች ‹‹ልብሴን ልልበስ›› አለች፡፡
‹‹እኔ ቀድሜ ልውጣ›› አለ መርቪን ‹‹ለአንቺ ጥሩ ነው››
እሺ፧ አሁንስ ምን ቀልብ አለኝ አለች በሀሳቧ። ይህን ለእሱ አልነገረችውም፡፡ መርቪን ልብሱን ስበሰበ፡፡ በሩን ከፍቶ ሊወጣ ሲል
ተጠራጠረና ቆመ፡፡ እሷም እንደገና ሊስማት እንደፈለገ አውቃ ወደ እሱ ሄደችና ከንፈሯን ሰጠችው፡፡ ‹‹ሌሊቱን በሙሉ እቅፍ አድርገህ ስላስተኛኸኝ
አመሰግንሃለሁ›› አለችው:

መርቪን ከአንገቱ ዝቅ አለና ሳማት፡፡ አሳሳሙ ልስልስ ያለ ነበር፡ አፏን በአፉ ግጥም አድርጎ ነው የሳማት፡፡ እየተሳሳሙ ትንሽ ቆዩና ተላቀቁ፡፡

ናንሲ በሩን ከፍታ ያዘችለትና ወጥቶ ሄደ፡፡

በሩን እንደዘጋች የደስታ ሲቃ ተናነቃት፡ ከዚህ ሰው ፍቅር ሊይዘኝ ነው አለች፡ በመስኮቱ ስታማትር አይሮፕላኑ ቀስ በቀስ እየወረደ ነው፡፡

መፍጠን አለባት፡፡

መስታወቱ ፊት ቆማ ፀጉሯን ቶሎ አሰረችና የመዋቢያ ዕቃዎቿን ይዛ የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ሴቶች መታጠቢያ ቤት ሄደች፡፡እዚያ ሉሉ ቤልንና አንድ ሌላ ሴት አገኘች፡፡ የመርቪን ሚስት ግን የለችም:

ናንሲ ፊቷን እየታጠበች ጧት ከመርቪን ጋር ያደረገችውን ውይይት
አስታወሰች፡፡ እሱን ስታስብ ደስታ ቢሰማትም ደስታው የተሟላ ባለመሆኑ
ከጭንቀት ሊገላግላት አልቻለም፡፡ ስለሚስቱ ምንም አላለም፡፡ ትናንት ማታ ስለእሷ ስትጠይቀው ድንግርግር እንዳለው ነው የነገራት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ይወዳት ይሆን? ትናንት ማታ ሌሊቱን ሙሉ ደረቱ ላይ ለጥፎ ነው ያሳደራት ይህ ብቻውን ጋብቻን ይፍቃል ማለት ግን አይደለም፡
እኔ የምፈልገው ምንድን ነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ‹መርቪንን እንደገና ማግኘት እፈልጋለሁ ከእሱ ጋር ድብቅ ወዳጅነት  ልመስርት?ታዲያ ለኔ ብሎ ጋብቻውን እንዲያፈርስ እፈልጋለሁ? ከአንድ  ሌሊት
ወሲባዊ ልፊያና መሳሳም በኋላ ይህን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
ሊፕስቲክ ለመቀባት መስታወቱ ላይ አፈጠጠች ናንሲ መጠራጠርሽን አቁሚ
ስትል ለራሷ አሳሰበች እውነታውን ታውቂዋለሽ፤ ይሄን ሰው በጣም ፈልገሽዋል፧ ከአስር ዓመት ወዲህ እጅሽን የሰጠሸው ለዚህ ሰው ነው፡:
አሁን አርባ አመትሽን ደፍነሻል፡ አሁን ተገቢውን ሰው አግኝተሻል፡ እዚህ
እዚያ መርገጥሽን ትተሽ ይህን ሰው በእጅሽ አድርጊ፡፡›

ሰውነቷ ላይ ሽቶ አርከፈከፈችና ወጣች፡

ስትወጣ ከመታጠቢያ ቤቱ አጠገብ የተቀመጡትን ናት ሪጅዌይና ወንድሟን ፒተርን አገኘቻቸው ናት ‹‹ደህና አደርሽ ናንሲ›› አላት::

ይህን ስትሰማ ከአምስት ዓመት በፊት በዚህ ሰው የነበራትን ስሜት
አስታወሳት፡፡ እኔ ከእሱ ፍቅር ይዞኝ ነበር፡፡ እሱ ግን ከእኔ ይልቅ የፈለገው
ብላክ ቡትስ ኩባንያን ነበር፡፡ አሁንም ኩባንያውን በእጁ ለማስገባት
የሚፈልገውን ያህል እኔን አይፈልገኝም፡፡ ለሰላምታው በራስ ንቅናቄ ብቻ
አፀፋዊ ሰላምታ ሰጥታው ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡

አስተናጋጆቹ መኝታዎቹን ወደ ሶፋነት ለውጠዋቸዋል። መርቪን ጢሙን ተላጭቶና በነጭ ሽሚዝ ላይ ሱፍ ልብሱን ለብሶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ‹‹በመስኮት ተመልከች ደርሰናል›› አላት፡፡
👍19
ናንሲ ወደ ውጭ ስትመለከት መሬት አየች፡፡ እታች ደን የለበሰ መሬትና ወንዝ ይታያል፡፡ ትንሽ ራቅ ብሎ ወደቡና ከእንጨት የተሰሩ ቤቶችና ቤተክርሰቲያን አየች፡፡
አይሮፕላኑ በፍጥነት ወደ መሬት ወረደ፡ ናንሲና መርቪን ሶፋው ላይ
እጃቸውን አቆላልፈውና የመቀመጫ ቀበቷቸውን አስረው ተቀምጠዋል
የሰማይ በራሪው ጀልባ ባህሩ ላይ ሲያርፍ መስታወቶቹ ላይ የውሃ
ፍንጥቅጣቂ ሲረጭ አዩ፡፡

‹‹አትላንቲክን አቋርጠናል›› አለች፡፡

ግማሹን ጉዞ ያሳለፈችው ስለ ፋብሪካው ስታስብ ሲሆን ቀሪው ግማሽ
ደግሞ ያለፈው የሰው ባል እጅ ይዛ ነው፡፡ የአየር ጠባዩ መጥፎ ስለነበር ያሳለፈችው ጉዞ አስፈሪ እንደነበር አስታወሰች፡፡ ለልጆቿ ምን ልትላቸው ነው? ሁሉንም ነገር ንገሪኝ ሊሏት ይችላሉ፡ አይሮፕላኑ በሰዓት ስንት
ማይል መብረር እንደሚችል እንኳን አታውቅም እንዲህ አይነቱን መረጃ ኒውዮርክ ከመድረሳቸው በፊት ታጣራለች፡፡
የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ላይ ደርሶ ሲቆም አንድ ወደ መሬት
የሚወስዳቸው ጀልባ ወደ እነሱ መጣ፡፡ ናንሲ ኮቷን ስትይዝ መርቪን ደግሞ
ከቆዳ የተሰራውን
የአብራሪዎች ጃኬት ለበሰ፡፡ ገሚሱ ተሳፋሪዎች
ከአይሮፕላኑ ወጥተው እግራቸውን ለማፍታታት ሲወስኑ ገሚሶቹ ግን
አልጋቸው ላይ እንቅልፋቸውን እየለጠጡ ነው፡፡

hአይሮፕላኑ ወጡና ጀልባ ላይ ተሳፈሩ፡ አየሩ በባህርና በግንድ ሽታ ታውዷል አጠገባቸው የእንጨት
መሰንጠቂያ ሳይኖር  አይቀርም፡፡አይሮፕላኑ ከቆመበት ወደብ ቀጥሎ ነዳጅ የሚሞሉ ሰራተኞች ቱታቸውን ለብሰው በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ ራቅ ብሎ ደግሞ ሁለት መርከቦች ይታያሉ፡፡

የመርቪን ሚስትና ፍቅረኛዋ ከአይሮፕላኑ ወጥተው ለመንሸራሸር ወስነዋል፡ ዳያና ናንሲ ላይ ብታፈጥም ናንሲ በዓይኗ ሙሉ ዳያናን ማየት አልተቻላትም  ምንም እንኳን ከዳያና የበለጠ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማት ባይችልም፡፡ በባሏ ላይ የሄደች ዳያና ራሷ እንጂ ናንሲ አይደለችም፡፡

ገና ማለዳ በመሆኑ ጥቂት ጎብኚዎች ናቸው የሚታዩት፡፡

ተሳፋሪዎች ከአይሮፕላኑ ወርደው ወደ አየር መንገዱ ህንጻ ሄዱና እንቅልፉን ላልጨረሰ ሰራተኛ ፓስፖርታቸውን አሳዩት

የተሳፋሪዎች መቆያ ክፍል ቢኖርም ተሳፋሪዎች መንደሪቷን በእግር
ለማካለል ፈለጉ፡
ናንሲ ቦስተን ካለው ጠበቃዋ ፓትሪክ ማክብራይድ ጋር ለመነጋገር በእጅጉ ጓጉታለች፡፡ ስልክ እንዳለ ለመጠየቅ ስትዘጋጅ የፓን አሜሪካን ዩኒፎርም የለበሰ ሰው ‹‹ስልክ ይፈልግዎታል የኔ እመቤት›› አላት።

የናንሲ ልብ ዘለለ ‹‹የት ነው ስልኩ?›› ስትል ጠየቀች፡

‹‹ከዚህ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ያስኬዳል››

‹‹አንድ ማይል!›› ንዴቷን መቆጣጠር አቃታት፡ ‹‹እንፍጠና ግንኙነት
ከመቋረጡ በፊት፡፡ መኪና አላችሁ?›› ስትል ጠየቀች፡፡
ሰውዬው ልክ የጠፈር መንኮራኩር የተጠየቀ ይመስል ድንግርግር
ሲለው ታዬ፡፡ ‹‹የለም የኔ እመቤት›

‹‹ስለዚህ በእግራችን እንሂድ በል መንገዱን ምራኝ›› አለች።

ናንሲና መርቪን መልእክተኛውን ተከትለው ነጎዱ፡፡ የእግረኛ መንገድ
የሌለው ጥርጊያ መንገድ ተከትለው በመሄድ ወደ ጋራው ወጡ፡፡ በየመንገዱ
በጎች ሳር ሲግጡ ይታያሉ፡ ናንሲ የብላክ ኩባንያ ያመረተው ጫማ ምስጋና
ይግባውና ተፍ ተፍ እያለች ትሄዳለች ነገ ማታ የብላክ ኩባንያ በእሷ ቁጥጥር ስር ይሆን? ይህን ማክብራይድ አሁን ያረጋግጥላታል፡ ከዚህ በላይ ከዘገየች በውጥረት መሞቷ ነው፡፡

ለአስር ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ አንድ ከእንጨት የተሰራ ቤት አገኙና ጥልቅ አሉ፡፡ ናንሲ ስልኩ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እጇ እየተንቀጠቀጠ የስልኩን እጀታ አነሳችና ‹‹ናንሲ ሌኔሃን ነኝ›› አለች፡፡

ይቀጥላል
👍16
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አምስት (35) በሆስፒታሉ ኮሪደር ውስጥ እየተጣደፈ ሲሄድ የጫማው ድምፅ ጎልቶ ይሰማ ነበር። ምን ብታስብ ነው ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመጣ ብቻየን ነው የምሄድ ብላ ድርቅ ያለችው ? ይህን ያህል አመት ስትኖር ረዳት አያስፈልገኝም ፤ሁሉንም ነገር ብቻየን ልወጣው እፈልጋለሁ የምትለው ለምንድነው ? ይህን እያሰበ በሩን አንኳኳ ። አንዲት በገጺ ላይ ምን ይፈልጋሉ ? የሚል ጥያቄ የተሳለባት ነርስ በሩን ከፈተችለት ። «ማሪዮን ሂልያርድ የተኛችው እዚህ ክፍል ነው ?» ሲል ጠየቃት ። በነርሷ ገፅታ ላይ የተሳለው ጥያቄ አልተነሳም ነበረና «ጆርጅ ኮሎዌ እባላለሁ» ሲል ጨመረ ። ድካም ፡ እርጅናና ያለመረጋጋት ስሜት በፊቱ ላይ ጎልተው ይታያሉ ። እነዚህ ስሜቶች በሠራ አካላቱ ተሰራጭተው ይሰሙትም ነበር ። የለም እንዲህ አይነቱ ርባና ቢስ ነገር አሁንስ ስልችት አለኝ ። ማሪዮን በዚሀ ሁኔታ ልትቀጥል አትችልም። ዛሬ ሁሉንም ግልጥልጥ አድርጌ መንገር አለብኝ ሲል አሰበ ። እንዳገኛት ይነግራታል ። ገና ከኒውዮርክ ከመነሳቱ በፊት ይህን ውሳኔ ለማይክል ሂልያርድም ነግሮታል ።

«ሚስተር ኮሎዌ ?» አለች ነርሷ ስሙን ስትሰማ በገዝፅዋ ላይ የተሳለው ጥያቄ ወደ ፈገግታ እየተለወጠ «ስንጠባበቅ ነበር » ማሪዮን እዚህ ሆስፒታል የገባችው ምሽቱ ላይ ፤አሥራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ጆርጅ ከኒውዮርክ ተነስቶ እዚያ የደረሰው ከምሽቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር ።ይሀ ደግሞ ከኒውዮርክ ሳንፍራንሲስኮ ለመድረስ የመጨረሻው ፈጣን ጉዞ ሳይሆን አይቀርም ። ነርሷን አልፎ ገባ። ማሪዮን የጆርጅን መምጣት አይታ ፈገግ ስትል ነርሷ ከክፍሉ ውስጥ ወጥታ ወደ ሠራተኞች ማረፊያ አዳራሽ ሄደች ።

«ሄሎ ጆርጅ »
«ሄሎ ማሪዮን ፤ ተሻለሽ ?»
«ከድካሙ በስተቀር አደጋውን አልፌዋለሁ ። ማለት ሀኪሞቹ የነገሩኝ እንዲያ ብለው ነው ። ኃይለኛ አልነበረም አያያዙ»
«ዛሬስ እንዲያ ሆነ ግን ለወደፊቱስ? ወደፊት›› ጀርጅ ይህን ተናግሮ በክፍሉ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲንጎራደድ እርምጃው ሁሉ የአንበሳ ይመስል ነበር። ቁጣውም ለማሪዮን ግፅል ሆኖ ታያት ። ይህን ያየችው ማሪዮን ሁኔታው አስገረማት። እንደሁልጊዜው አልሰማትም ።። ብዙ ነገር ሲነግራት አስቧል ማለት ነው ። «ለወደፊቱ ፣ ወደፊት ሲሆን ይታሰብበታል ። ላሁኑ አረፍ በልና ሰውነትህን ዘና አድርገው ። እኔን ጭምር እየረበሽከኝኮ ነው። የሚበላ ነገር ይቅረብልህ ? አንድ ሣንዱች እንዲያስቀምጡልህ ለነርሶቹ ነግሬአቸዋለሁ »
«መብላት አልችልም»
«አይ አሁን አበዛኸው ። ደሞ የምን አዲስ ጠባይ ነው? ይህን ያህል ዘመን ስንኖር እንዲህ ስትሆን አይቼህ አላውቅም። በሽታው ያን ያህል ከባድ መስሎህ ነው? አልነበረም ። እና በስላሴ ይዣሀለሁ እኔን ጨምረህ አትረብሸኝ››
«የለም የለም ፤ አትምከሪኝ ። አልፈልግም ፤ አትምከሪኝ ማሪዮን ሂልያርድ። እንደፈለኩት ልሁን ስትይ እሽ ስል ምን መጣ ይኸዋ በሽታ ላይ ወድቀሽ አረፍሽው ። አሁን በዛብኝ በቃኝ። አልቻልኩም »
«በቃ ተስፋ ቆረጥክ?» አለች የፌዝ ፈገግታ ፈግጋ ተስፉ ከቆረጥክ ፤ ከሰለቸህ ለምን ሥራውን ለቀህ አረፍ አትልም›› የጆርጅ ሁኔታ የቀልድ ያህል አስደነቃት ሆኖም ፊቱን ወደሷ ሲመልስና ከጀመረው ሀሳብ ወደኋላ እንደማይል የሚገልፅ ገፅታውን ስታይ የቀልድ እድናቆቷ ወደ እውነተኛ አድናቆትና ድንጋጤ ተለወጠ ።

«ሥራ ልቀቅ አልሺኝ ፣ ማሪዮን ? እኔም አስቤ እሰላስዬ የወሰንኩት እሱን ነበር ። እኔም አንችም ሥራውን ለቀን በጡረታችን መኖር አለብን» ይቀልዳል ?... የለም ከልቡ ነው ፤ አለች በሀሳቧ ። «አትቀልድ» አለች ። ሆኖም ድምጺ የተለመደው ጥንካሬ ይጎድለው ነበር ። «ቀልድ ? ቀልድ የለም ። እንዲያውም በዚህ አብረን በኖርንበት ሃያ አመት ውስጥ እንዲሀ አይነት ጠንካራ ውሣኔ ወስኘ አላውቅም ። ሁለታችንም ከሥራ እንሰናበታለን ። ለማይክልም ይህንኑ ነግሬዋለሁ ። እግዜር ይስጠው አውሮፕላን ማረፊያ ያደረሰኝ እሱ ነበር ። ልመጣ ስላልቻልኩ በጣም አዝናለሁ ። በሥራ ተወጥሬ ነው ብሏል ። እና ተስማምተናል ። አንች ይህን አልሽ ያን አሁን ዋጋ የለውም ። ተወስኖአል ፤ያበቃ ነገር ነው»
«አበድክ ልበል ?» አለችና ከተጋደመችበት ተነስታ ቁጭ አለች ። አፈጠጠችበት ፤ በደብዛዛው ብርሃን «ልስማህና ሥራውን ትቼ ልቀመጥ እንበል ግን ምን ሳደርግ ልዋል ? ሹራብ ስሠራ ወይስ መጽሐፍ ሳነብ ?»
«ሹራብ ሥሪ ወይም መፅሐፍ አንብቢ ። የፈለገሽውን ብታደርጊ ከተስማማሽ ጥሩ ነው። ሥራውን ከተውን በኋላ ግን ወዲያውኑ የምናደርገው ነገር አለ ። እኔና አንቺ እንጋባለን ። ከዚያ በኋላ እንዳፈቀደሽ መሆን ትችያለሽ ። ግልፅ ነው?››
«እንዴት ያለ ነገር ነው ባካችሁ? ቢያንስ ቢያንስ እንድንጋባ ፈቃደኛ ነሽ ወይስ አይደለሽም ተብዬ አልጠየቅም ? ወይሰ ይኸም ከዋናው ሥራ አስኪያጅ ከማይክል የመጣ ትዕዛዝ ነው» ኣለች ማሪዮን ። ሆኖም ድምጺ የቃላቱን ያህል መከፋትም ቁጣም አልነበረበትም። ስላሰቡላት ልቧ ተነካ ። ሸክሙ ቀለል አላት ። እውነትም ይበቃታል ። ብዙ ነገር አድርጋለች መጥፎም ጥሩም ፣ እኩል በኩል ። ይህን ደግሞ ተገንዝባዋለች ። አውቃዋለች ።

ከሜሪ ኣዳምሰን (ናንሲ ማክአሊስተር ) ጋር ያንለት ያደረገችው ንግግር ይህን ጉዳይ ግልፅ አድርጎላታል ፣የዕድሜ ልክ ተግባሯን ተመልሳ እንድታይ አድርጓታል ። ደግም ከፋትም ሠርታለች ። «የማይክልን ምርቃትም አግኝተናል» አለ ጆርጅ ። ይህን ብሎ ወደ አልጋው ሄደና እጅዋን ጨብጦ «ታገቢኛለሽ፤ማሪዮን !?» ሲል እየፈራ ጠየቀ ። ይህን ያሀል ዘመን አብረው ኖረው ሲያፍራት ገረመው ። እንዲያውም ማይክል «ይገባል ። ፍቅራችሁን ልታከብሩት ይገባል» አይነት ነገር ባይለውና ምንም ትርጉሙ ግልፅ ሆኖ ለጊዜው ባይታየው «ለጋብቻው አበረታታት» ባይለው ኖሮ ላይጠይቃትም ይችል ነበር ። «ንገሪኝ እንጂ» ይህን ብሎ እጅዋን ጠበቅ አደረጋት ።
👍27🥰2
ማሪዮን ሂልያርድ ቀስ ብላ ከልብ የሆነ ግን ደከም ያለ ፈገግታ እያሳየችውና እራሷን በአወንታ እየነቀነቀች… «ቀደም ብለን ልናስበው ይገባ ነበር ፤ ጆርጅ» አለችው ። «እኔ ገና ዱሮ ነው ያሰብኩት ። ግን በጅ አትልም ስል ተውኩት» አለ ጆርጅ። «ደሞ ልክ ሳትሆን አትቀርም ። ያኔ ብትነግረኝ ሳይገርመኝ አይቀርም ነበር ። በጄ ማለቱን ተወው ። ጅልኮ ነኝ» አለች ። ይህን ብላ በረጂሙ ተንፍሳ ተጋደመችና ትራሱን ደገፍ ብ… «እንዴት አድርጌ በሕይወቴ ተጫወትኩባት» ስትል ተፀፀተች። «አረ እንደሱ አይባልም ተይ» አለ ጆርጅ «እኔ ሳውቅሽ ሕይወትሽን በሙሉ በትጋት ፤ በአዋቂነት ፤ ቁም ነገር በመሥራት ነው ያሳለፍሺው» እጅዋን ይዞ በፍቅር ያሻሻት ጀመር ። ለረጂም ጊዜ ሲመኘው የነበረ ነገር ነው ። «ደሞም ያለፈ ነገር አልፏል ። ባለፈ ፋይዳ ቢስ ስህተት እየተፀፀቱ ራስን መጉዳት ጥቅም የለውም» ሲል ጨመረ። ይህን ስትሰማ ማሪዮን ከተጋደመችበት ተነስታ ተቀመጠችና ትኩር ብላ እያየችውና እጅዋ ድንገት ቅዝቅዝና ጥንክር እያለ «ግን...ግን ይኸ ፋይዳ ቢስ ያልከው ስህተት የሌሎችን ሕይወት አበላሽቶ ቢሆንስ?... ልርሳህ ብለውስ የሚረሳልኝ ይመስልሃል ጆርጅ ?» አለች ። «ምነው ማሪዮን እያወቅሽው? የሌላ ሰው ህይወት ለማበላሸት ምን ጊዜ ኖሮሽ ?» ሲል ጠየቃት ።

በአእምሮው ውስጥ ዶክተሩ የእንቅልፍ ክኒን ወይም ህመም እንዳይሰማት የሚያደርግ መድኃኒት ሰጥቷት ይሆን ? ሲል ጠየቀ ። ያለዚያ እንዲህ አይነት ቅብጥርጥር ከማሪዮን የሚጠበቅ እንዳይደለ እየገመተ ። «አንተ እማታውቀው ብዙ ነገር አለ ጆርጅ ። አይገባህም ነገሩ»
«ሁሉንም ማወቅ አለብኝ ?»
«ምናልባት ። ምናልባት ማወቅ ይኖርብህ ይሆናል ። ብታውቅ ደግሞ ልታገባኝ አትፈልግም ነበር ። ምናልባት »
«ፍሬ ከርስኪ !ይህን ሀሳብ ከልብሽ አስወጭው ። ይልቅ እንዲያ ካልሽ ነገሩን የማወቅ መብት አለኝኮ። ስለዚሀ ያስጨነቀሽን ነገር ንገሪኝ» ማሪዮን በሀሳብ ተውጣ አትኩራ እያየችው ለረጂም ጊዜ ዝም ካለች በኋላ…. «እንጃ ፤መናገር መቻሌንም እንጃ» አለች ። «ለምን ? ለኔ ፈርተሽልኝ ፣ ይከፋዋል ይቀፈዋል ብለሽ ፈርተሽልኝ ከሆነ እርሺው ። በዚች ዓለም ላይ ይኸ አእምሮዬን ይበጠብጠዋል የምለው ነገር የለኝም ። ደሞም ላንቺ መስሎሽ እንጂ እኔ ሳስበው የምትነግሪኝ ነገር ይኸኔ የማውቀው ነው ። ስላንቺ ማላውቅው ነገር አለ ብዬ አላስብም» አለና በስጋት እየተመለክታት «የለም ። የልብ በሽታው ሲነሳብሽ ጊዜ ትንሽ ሳያስደነ ግጥሽና ሳያናውጥሽ አልቀረም መሰለኝ»
«በሽታው ሳይሆን ስሸሸው የነበረ ዛሬ ፊት ለፊት የተጋ ፈጥኩት እውነት ነው እንዲህ ያናወፀኝ»
«ምን?.... አንድ የተለዬ ነገር አጋጥሞሽ ነበር ?» አለ ከብዙ ፀጥታና ሀሳብ በኋላ ። ቶሎ አልመለሰችለትም ። ጠበቀ ቆይታ
«አዎ» ስትል ተናገረች ። «እንዲያ ነው?» አለ…. ጥያቄ ሳይሆን ገባኝ እንደማለት ። «የሆነውም ቢሆን አሁን እንርሳው ። አረፍ ማለት ያስፈልግሻል። ጉዳዩን አንስቶ መድገም አያሻም ። ይቆይልን ይህን ሲል ስጋቱ ይታወቅ ነበር ። ከድምጹ፣፤ ከገፅታው ልብ ድካሟ እንደገና ቢነሳስ ? የሚለው ጥያቄ ይነበብ ነበር ። ስለዚህ ያጋጠማትንም ነገር አልጠየቃትም ። «ከልጅቷ ጋር ተገናኘን» አለች ማሪዮን ። «የምን ልጅ ?» አለ ጆርጅ ፤ ሴትዮ ምንድነው እምታወሪው በሚል ድምፅ።
እንባዋ መውረድ ጀምሯል ።

«ስለየትኛዋ ልጅ ማለትሽ ነው?» አለ ጆርጅ እየተጨነቀ። ዝም ብላ ስታየው ቆይታ እንባዋን ገትታ… «ማይክል የወደዳት ፤ አፍቅሮ ሊያገባት የነበረችው ልጅ» አለች ማሪዮን ተስተካክላ እየተቀመጠች ። «ታስታውሳለህ ጆርጅ ? ማይክ አደጋ የደረሰበት ቀን… ማታ ትዝ ይልሀል ? ሊያነጋግረኝ እንኳ መጥቶ ። ትዝ ካለህ ያንለት ልክ እንተ ስትገባ እሱ ወጥቶ አልሄደም ? እየተቆጣ ? ያንለት የመጣው ልጅቷን እንደሚያገባት ሊነግረኝ ነበር ። እኔ ደግሞ ስለቤተሰቧ ያሠራሁትን ሪፖርት ሰጠሁት »
ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍23