አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹እውነት ነው የክርክር መድረክ አይደለም›› አለ ሌላ ድምጽ፤ ሶስቱ
ሰዎች ድምጹን ወደሰሙበት አቅጣጫ ሲዞሩ ናንሲ ሌኔሃን በመኝታ ልብሷ
አምራና ደምቃ በሩጋ ቆማለች፡ ‹‹እንደ እውነቱ ከሆነ›› አለች ንግግሯን
በመቀጠል ‹‹ይሄ የኔ ክፍል ነው በዚህ ክፍል ውስጥ እየተካሄደ ያለው
ነገር ምን እንደሆነ ብትነግሩኝ?››.....

ይቀጥላል
👍6🥰3
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሁለት ሳምንት አለፈው ካርለትና ከሎ የየራሳቸውን የጕዞ ዝግጅት ሲያደርጉ ሰነበቱ። ከሎ ሐመር ሲሄድ የሚያነባቸው ልብወለድና
ታሪክ ነክ የአማርኛ መጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ በእንግሊዝኛ የተጻፉ
ልብወለድና የሳይንስ መጻሕፍትን እየገዛ ከፊሉንም እየተዋሰ
አዘጋጀ"

በተለይም ካርለት ኮተቷ በዛ" በማስታወሻዋ በዝርዝር ከያዘችው
አስፈላጊ የምግብ ዓይነቶች የታሸገ የዓሣ፣ የአሳማ፣ የከብት ሥጋ የድንች የዱባ፣ ያጃ ሾርባI የፓፓያ፣ የብርቱካን፣ የአናናስ
ጭማቂ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር የበዛበት ብስኩት ደረቅ ብስኩት የቆርቆሮ ቢራ ወዘተ ከመድኃኒ ዓይነትም ክሎሮኪን፣ ፓልዱሪን፣ ኒቫኩይን ለወባ መከላከያI ሌሎች፣ «አንቲባዮቲክስ» መድኃኒቶችንና የመጀመሪያ ሕክምና ኪት ኮዳክ ፊልሞችI ባትሪ
ድንጋዮችI ሶፍቶች ወዘተ. በአራት የፕላስቲh ሣጥኖች ደረደረች" ካኖንና ፔንታክስ ካሜራዋንና የተለያየ መጠን ያላቸውን ሌንሶች
በእጅ በሚንጠለጠለው ቦርሳዋ ካኪ ሱሪዎች፣ ካኔትራ፣ ውስጥ
ሱሪ ፎጣ፣ ጡት ማስያዣ፣ ስሊፒንግ ባግ፣ ግራጫ  መልክ ያለው ሹራብ በአየር የሚሞላና ሌላ ተጣጣፊ ፍራሽ፣ ሳሙና፣ ኦሞ፣
ከሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበሩ የፒያኖ ሶናታና የፒያኖ ኮንቸቶ የቤቶቪን ሲንፎኒ ከሦስት ጊዜ በላይ
የወርቅ ዲስክ አሸናፊው ድምፃዊ የቢሊ ጆይል፤ ከሦስት መቶ ዓመት
በፊት የነበረውና የሲንፎኒ አባቱ የሃይደን እንዲሁም ሌሎቹን የባሮክ
ክላሲካል፣ ሮማንቲክና ዘመናዊ የሙዚቃ ካሴቶችን፣ ማስታወሻ፣
ብዕር መጻሕፍትና መጽሔቶች በአራት ማዕዘኑ የብረት ሣጥን
ውስጥ ከተተች" ለሽፍን ላንድ ክሩሰር ቶዮታ መኪናዋም በሁለቱም
ታንከር ነዳጅ ሞላች“ አምስት ጀሪካን ናፍጣም ለመጠባበቂያ ያዘች
ካርለት ለሦስት ወራት የሚያስፈልጋትን ቁሳቁስ ካሟላች በኋላ
ቀሪውን ዕቃዋንና ገንዘቧን ስቲቭ በሰጣት ክፍል ውስጥ
አስቀመጠች» ለአንዳንድ ወጪ ብላ የያዘችውን ሦስት ሺህ አምስት
መቶ የኢትዮጵያ ብርም በሹራቧ ውስጥ በሰፋችው ስውር ኪስ፣
አንገቷ ላይ በምታንጠለጥለው የጨርቅ ቦርሳና ብረት ሣጥኑ ውስጥ
አhፋፍላ ያዘች
ሰኞ ጠዋት ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ላይ አራት ኪሎ ሞቢሉ
ጎን ካለው ሱቅ በር ላይ በቀጠሯቸው ተገናኙu ካርለት ልጥፍ የኋላ
ኪስ ያለው ካኪ ሱሪ፣ ተረከዙ ፕላስቲክ የሆነ ሽፍን ባለማሰሪያ
ማ፣ ቡና ዓይነት ቲ–ሸርት ለብሳ፣ አንገቷ ላይ አነስ ያለ ነጭ ፎጣ
ጣል አድርጋ፣ ከመኪናው በመውረድ የከሎን «ዩኤስኤ» የሚል
ወስፋት የነፋው የሕፃን ሆድ መስሎ የተወጠረ ቦርሳ የኋላ በሩን ከፍታ
በዕቃ ከሞላው መኪና ውስጥ በአንድ በኩል ባለው ክፍት ቦታ
አስገባችና ወደ መኪናው ውስጥ ገቡ" ካርለት የውኃ ኮዳዋን፣ ዳቦ
የያዘ ላስቲኳን አቀረበችና ከከሎና እሷ መካከል ካለው የካሴት ሣጥን
የሞዛርትን ፒያኖ ሶናታ ወደ መኪናው ቴፕ አስገብታ ማስታወሻዋን
በማውጣት የተነሡበትን ሰዓት መዘገበች" ከዚያም ፈገግ ብላ
«መሄድ እንችላለን?» አለችው።

«ኢ ህ» አላት ከሎ፣ ዝግጁ መሆኑን አንገቱን በማወዛወዝ እየገለጸ። ካርለት፣ ቀኝ እጇን ማርሹ ላይ በማስቀመጥ፣ በግራ እግሯ ፍሪሲዮኑን እረግጣ፣ የመኪናውን መስተዋት አየትየት በማድረግ
በአራት ኪሎው የድል ሐውልት ወደ ቀኝ ታጥፈው፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት አድርገው ቁልቁል ወደ መስቀል አደባባይ ወረዱ።
ከዚያም በደብረ ዘይት መንገድ ወደ ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ዱከም ተጕዘው ደብረ ዘይት ከተማ ሲደርሱ ወደ ግራ ታጥፈው ሁለት ኪሎ ሜትር በመጓዝ ዠመኪናዋን ሆራ ሆቴል አቁመው ለቁርስ ወደ ውስጥ ገቡ" በስተጀርባ፣ ከሐይቁ ትይዩ የመርከብ ላይ መናፈሻ ከሚመስለው ስፍራ ሆነው የተለያዩና ቱር ቱር እያሉ በመዘመር
የሚበሩ አዕዋፍን እያዩ ቁርሳቸውን ተመግበው ወጡ" ካርለትና ከሎ
ሆራ በሞጆ ታጥፈው፣ ወደ ሻሸመኔ ጕዟቸውን ተያያዙ“ ካርለት፣በመንገዱ ግራና ቀኝ የግራር፣ የጥድ፣ የኮሶ፣ የዝግባ...ዛፎችንና
የተለያዩ ቀለም ያላቸውን እፅዋት እያየች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ከሚኙት ከሃያ በላይ አዕዋፋት ውስጥ የምታያቸውን በመልክና
በቅርፃቸው ለማወቅ በጆን ጂ ዊሊያምስና በኖርማን አርሎት የተጻፈውን የአዕዋፍ ምስል፣ ቀለም ባሕርይና የሚገኙበትን አካባቢ እያየች ተጓዙና ለምሳ በስምጥ ሸለቆ ካሉት ሐይቆችና የመናፈሻ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ወደ ላንጋኖ ከመንገዱ ወደ ግራ ታጥፈው ገቡ"

ላንጋኖ ሆቴል ምግብ ቤት ብዙ የውጪ ሀገር ዜጎች፣ አፍሪቃውያንና ኢትዮጵያውያን ክብ እየሠሩ በመጫወት ይመገባሉ። ከሆቴሉ ውጪ በቀላል ድንኳን ጥግ፣ በዋና ውስጥ ሱሪና ጡት ማስያዣ
ሆነው የፀሐይ ክሬም ሰውነታቸውን የሚቀቡና ሐይቁ ዳር ለዳር
የሚዋኙ ሴትና ወንዶች ይታያሉ" ጥቁርና ነጭ ሕፃናትም በመዋኛ
ፕላስቲክ ውኃውን በማንቦራጨቅ እየተንጫጩ ይጫወታሉ ከሎና ካርለት ከምግብ ቤቱ ትይዩ የፀሐይ ጃንጥላው ውስጥ
ተቀምጠው ቡናቸውን ሲጎነጩ ቆዩና ካርለት የሐይቁን ዳር ትርምስ
አሸጋግራ ስትቃኝ ቆይታ፣ «ሐይቅ ዳር ስሆን እረካለሁI አገሬ ውስጥ ከጓደኞቼና ቤተሰቦቼ ጋር ያለሁ ስለሚመስለኝ የደስታ ስሜት ይሰማኛል" በአውሮፓ፣ ብዙዎች መዝናኛዎች የሚገኙት ባሕር ዳርቻ ነው" ብቻ...» ካርለት ከሎ ሆራን በጎን ተመለከተችው“


«ኢ ህ» አላት እግሮቹን ወደፊት በመዘርጋት ሰውነቱን ለጥጦ" ካርለት የከሎ ሆራ ጠባይ ደንቋታል ግን አልከፋትም" በቀላሉ ከምትግባባቸው ሰዎች ይልቅ አስቸጋሪ ባሕርይ ያላቸውን ታከብራለች" ሁሉም ሰው ሊረዳው የሚችል ባሕርይ ያላቸው ሰዎች ለሷ አያረኳትም" እረቀቅ ያለ ባሕርይ ያላቸውን ግን አእምሮዋን
አስደንሳ መላ ፈጥራ፣ የተለያየ ስልት በመጠቀም እንደ ግል ሬዲዮና መከፈት መዝጋት እንደ መቻል
የምትረካበት ነገር የለም።
ለዚህም ካርለት «ዘመናችን የሚርጠው ልዩና ውስብስብ አስተሳሰብ ያላቸውን ነው" ምክንያቱም የነገው ፈጠራና ብሩህ
ሕልም ህላዊነት በመዳፋቸው መሃል ያለው ከእነዚህ ዓይነት ግራ
አጋቢ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ነው» ብላ ታምናለች።

ከሎ ቅንና ተባባሪ ሰው መሆኑን፣ ነገር ግን ይህን ባሕሪውን የሚገልጽ የቃላት ድርደራ ችሎታ የሚጎድለው መሆኑን ተገንዝባለች" ካርለት ከሎን የተለያዩ ነገሮችን እያወራች
እየጠየቀች የቱ እንደሚያስደስተው፣ የቱ አፍንጫውን እንደሚ
ያስነፋውና ጥንካሬውን ከደካማ ጎኑ ለመለየት ምርምሯን ስለ ቀጠለች
አንድ ወጥ በሆነው የሥውር ባሕርይው ዋሻ ለመግባት ትልቁ
የድንጋይ መዝጊያ ማንቀሳቀስ ጀምራለች።

«አዎ የከሎ ባሕርይ ራሱ መጠናት የሚገባው ነው" እሱን ለማጥናት ግን አስፈላጊውን ቁልፍ ማዘጋጀት አለብኝ» አለች
ካርለት፣ ከሻሸመኔ ከተማ ወጥታ የአርባ ምንጭን መንገድ ስትይዝ"
ከሻሸመኔ ትንሽ ራቅ ብለው የአስፋልቱ ጐዳና አልቆ ኮረኮንቹን መንገድ ሲጀምሩ ግን መኪናዋ እየተገጨች ስትንሰጠሰጥና ከፊት
ለፊቷ ያሉትን መኪናዎች ስታልፍና ከእሷ ተቃራኒ የሚያልፉት መኪናዎች የሚያነሡት አቧራ መኪናዋ ውስጥ እየገባ ማፈን
ሲጀምር፣ ካርለት መኪናዋን አቁማ፣ ጸጕሯን በመሸብለል፣ ቆብ
ደፋችበትና መኪናዋን በማንቀሳቀስ ከመሪው ጋር መታገል ጀመረች"
👍20🔥1
ካርለት፣ መኪናዋን በሰዓት ከሥልሳ እስከ ሰማንያ ኪሎ ሜትር በሚደርስ አማካኝ ፍጥነት እያሽከረhረች እንደተጓዙ ከፊት
ለፊታቸው አንድ እስከ አናቱ ድረስ የታረሰና የተለያዩ እፅዋት ያሉበት ተራራ ተመለከቱ" ከተራራው ግርጌ ራቅራቅ ያሉ
መንደሮች ሲኖሩ፣ በየመንገዱ አካባቢ ሙዝ፣ እንሰት፣ ጥድና ባሕር
ዛፍ ይታያል" ከመንደሮች ራስጌና ግርጌ እንዲሁም ግራና ቀኝ የበቆሎ፣ የጤፍ.አዝርእት ተመለከቱ" ካርለት የአካባቢው
ልምላሜና በኮርቻ ፈረስ በሶምሶማ ግልቢያ የምታያቸው ሰዎች
ስላስደነቋት «ኦ! ልምላሜ የተላበሰ ማራኪ ነው" ምን የሚባለው አካባቢ ነው?» ብላ ከሎን ጠየቀችው

«ወላይታ» አጭር መልስ መለሰላት።

«ወይታ» አለች መጥራቱ ከብዷት።

«ወላይታ”ወ.ላ.ይ..ታ» አላት ፊደሉን እየቆጠረ ከዚያም
ስለ ማኅበረሰቡ ቋንቋ ባህል ጠየቀችው ካርለት በከተማው ስታልፍ
እንደተለመደው አዋቂ ወንዶችና ሴቶች እጃቸውን አውለበለቡላት ሕፃናት፣ «ፈረንጅ» እያሉ ጨፈሩላት" መኪናዋን ስታቆም
ከበቧት፣ እጇን ለመያዝም ተሯሯጡ"

ካርለትና ከሎ ወላይታን ካለፉ በኋላ ምዕራብ አባያ ላይ በቅርጫት የተከመረ ፓፓያ፣ ገና ያልቀላ አረንጓዴ ሙዝ ከነመያዣው፣ ሎሚው ተደርድሮ ተመለከተች" በተለይ አርባ ምንጭ
ሊደርሱ ጥቂት ሲቀራቸው ባገኟት ላንቴ ከተማ ያዩት ሙዝ አንዱ ለሦስት የሚበቃ ሆኖ አገኘችው" መኪናዋን ስታቆም፣ «ሙዝ፣
ፓፓያ፣ ሎሚ» እያሉ የመኪናውን መስኮት ከበቡ።

ካርለት አንዱን ቁና ሙዝ ተቀብላ ዋጋውን ጠየቀች" አንድ ብር የሚሸጠውን ሁለት ብር አሏት፤ አንዱን ቅርጫት ፓፓያ ጠየቀች
ሦስት ብር አሏት" «አምላኬ!» አለች የነገሯት ዋጋ ትክክለኛ ስለ
መሆኑ ከሎን ጠይቃ ካረጋገጠች በኋላ።
በዓለም ላይ ተበልቶ ተጠጥቶ ከአንድ ዶላር በታች የሚጠየቅባት
አገር እሷ እስከምታውቀው ድረስ ኢትዮጵያ ብቻ ናት" ክምር ሙዝና ፓፓያ ዋጋቸው አንድ ዶላር እንኳ አይሞላም" ኢትዮጵያ
ውስጥ ተበልቶ፣ ተጠጥቶ የሚከፈለው አገሯ ለወንበር ተብሎ ከሚከፈለው ያነሰ ነው። አውሮፓ ውስጥ ትኩስ ፓፓያና ሙዝ
ዋጋቸው የዋዛ ስላልሆነ፣ ለማግኘት ከባድ ነው። እንዲያውም አንድ ጃፓናዊ ጓደኛዋ ጃፓን አገር ትኩስ ፓፓያ መብላት የሚችሉት
ሚሊየነሮች ናቸው ብሏታል" ይህን ስታስብ፤ «ኢትዮጵያ ውስጥ ፍራፍሬ ይሸጣል ከማለት ይልቅ፣ ይታደላል ቢባል እውነትነት ይኖረዋል» አለች"

ካርለትና ከሎ ወደ አርባ ምንጭ ጥቅጥቅ ባለው የግራር፣ የጥድ፣ የብርብራ ዛፍና ሌሎችም እፅዋትና በሰፊው የጥጥ እርሻ መካከል አልፈው ሲደርሱ አምስት መቶ ኪሎ ሜትር መጓዛቸውን የሚገልጽ
በነጭ ላይ ጥቁር የተጻፈበት የቆመ ድንጋይ ተመለከቱ። የአርባ
ምንጭ ከተማ የአባያንና ጫሞን ሐይቅ እግሩ ስር አድርጎ የተከተመ ከተማ ሲሆን መንገዶቹ አስፋልት ቢሆኑ ውበቱ ይጐላ ነበር።
ካርለትና ከሎ ከአዲስ አበባ አርባ ምንጭ አሥራ አንድ ሰዓት ተጕዘው ደረሱ" ከዚያም በከሎ መሪነት በቀለ ሞላ ሆቴል ሁለት
አልጋ ከያዙ በኋላ ካርለት ልብሷን ለማውለቅ እንኳ ሰንፋ ከነልብሷ ሻወር ቤት ገባች" ከሎ ሆራ ምናልባት መኪና ማሽከርከር ቢችል
ኖሮ እሷ የደከመችበትን ጒዞ ሳያርፍ ሦስቴ ሊያመላልስ የሚችል
ኃይል እንዳለው አምናለች"
ምሽት ላይ ካርለትና ከሎ ከሆቴሉ በስተጀርባ ካለው መዝናኛ ቦታ ቁጭ ብለው ከአርባ አራት ምንጭ በላይ አለው የአንበሳ መኖሪያ ነው የሚባለው ጥቅጥቅ ያለ የአበሻ ጥድ፣ ግራር፣ ዋንዛ
ሾላ፣ አጋምና ሌሎችን እፅዋት ይዞ ከወዲህ ተራራውን ተለጥፎ፣
ከወዲያ የኦሞ ሐይቅን ከጎንና ጎን ተመርኩዞ፣ ከርቀት ሰንሰለታማውን የጉጂ ተራራ ዘብ አቁሞ ሲታይ የተፈጥሮ ውበት የሚደነቅበት ሞዴል ሆኖ የጐብኚውን የተሰላቸ አእምሮ ያድሳል" ይሀን
የተፈጥሮ ውበት ሲያዩ እንኳን ካርለት ከሎም የእርካታ ስሜት አሳየ
የተፈጥሮ ውበት ሕሊናን አበረታችና ፈዋሽ ነዋ!
ካርለት ከሐይቆች ለሚነፍሰው ነፋስና ዓይኗ ለሚቃኘው ውበት
አእምሮዋን በርግዳ ከፍታ አካሏን ካዝናናች በኋላ ከሎን፣ «አንተ ቀዝቃዛ ቢራ እየተጎነጨህ ልትዝናና ትችላለህ" እኔ ግን ማረፍ
እፈልጋለሁ» በማለት ቀያይ ብር አስቀምጣለት ሄደች በእርግጥ ካርለት ከመኝታው ይልቅ መናፈሱንና ቀዝቃዛ ቢራውን መጎንጪት አሰኝቷት ነበር“ ይሁን እንጂ ከሎ በእሷ ላይ ያለውን ስሜት በትክክል
ማረጋገጥ አልቻለችም። ለነገሩ ጨዋታውን ለዓይነት ያህል ወስዳ ከሎን ማዝናናት ትችል ይሆናል፤ ፍርሃቷ ግን ለጥናቷ እንቅፋት መፍጠር ወይም እንዲፈጠር ማመቻቸት አትፈልግም። ከሉ ሆራም
ለማያገኘው ነገር ጕሮሮውን በማጮህ የስሜት ችግር ውስጥ እንዲገባ
ስላልፈለገች ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች።

ከሎም ያንን ስብቅብቅ ወገብና ዳንኪራ ረጋጭ ዳሌ የማግኘት
ሕልሙ እንደማይሳካ በማሰብ፣ «ዳሚት» እያለ ሲቆዝም ቆየና ቢራውን ደጋግሞ ጨልጦ፣ ወደ መኝታ ክፍሉ ሄደ"

ማክሰኞ ዕለት በእንቅስቃሴ አልባው የጫሞ ሐይቅ ዳር ጥርሱን ያገጠጠ አዞ ሲንሳፈፍ፣ ከላይ ጥፍሩን ያሾለ አሞራ ዓሣ ለማጥመድ ሲያሽቆለቁል፣ በተራራው አናት የፈነጠቀው የፀሐይ ብርሃን ውጋገን
ከውኃው ነጸብራቅ ጋር ተዋሕዶ የዓሣ ሽታ፣ የእፅዋት መዓዛ፣
ከአዕዋፍ ዝማሬ ጋር ቅንብሩ እንደተዋጣ ሙዚቃ መንፈስን በሚሰርቅበት ወቅት «ስቴሽን ዋገን» መኪና ጥግጥጉን የከብት ሽንት በመሰለው ጠመዝማዛ መንገድ እየተሹለከለከ ከነፈ።

ዘመን አመጣሹን የግብርና ዘዴ በተፈጥሯዊ ጥበብ ተጠቅሞ የአፈርን የእሸሻለሁ አትሸሽም የእርከን ሥራ ውጤት ካርለት ስታይ መሰጣት። ስለ ኮንሶ የእርከን ሥራ ባህልና የረጅም ዘመን የመጠቀም ችሎታቸው መጻሕፍት አንብባለች" ተራራማው አካባቢ ላይ የሚኖረው የኮንሶ ሕዝብ በእርከን ሥራ ዘዴ አፈርን በመንከባከብ የረጅም
ጊዜ ተጠቃሚ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በተጨማሪ ክልሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሸማ ሥራ ጥበብ የተጀመረበት
መሆኑን ተረድታለች።

በቆሎ፣ ማሽላ፣ ለመድኃኒትና ለውኃ ማጣሪያ ለክልሉ ሕዝብ
የሚያገለግለው የአለኮ ዛፍና ሌሎችም አዝርዕቶች፣ ችፍግ ብለው
አዝመራውንና እፅዋቱን ሊያሳይ በሚችል መንገድ ቋጥኝ ጥግ የተሠራው መንደር እንግዶችን እይታቸውን ቶሎ መንቀል አያስችላቸውም።

አልፎ አልፎም ከመንገዱ ግራና ቀኝ ከእንጨት የተሠሩ የሰው ምስሎች ከመቃብር ላይ ተተክለው የሚታዩ ሲሆን ይህም ዘመን አመጣሹ የመቃብር ሐውልት ከመምጣቱ በፊት ኮንሶዎች የእንጨት
ምስል ቀርፀው መትከላቸው ቀድመው የሠለጠኑ እንደነበሩ ዓይነተኛ
ምስክር ሲሆን፥ ከዚህም በተጨማሪ ሥራ ወዳድነትና ጥረት ለኮንሶ ሕዝብ እንደ ቋንቋው ከልጅነቱ ጀምሮ የሚማረው ነው።

ካርለት ኮንሶንና አካባቢውን በቀስታና በአፅንኦት እየቃኘች ከተማው ደረሱ ካርለትና ከሎ ከመንገዱ በስተቀኝና በስተግራ ፊት
ለፊት ካሉት ብቸኛ ምግብ ቤቶች በግራ በኩል ወዳለው ለምሳ ገቡ።
ካርለት አርባ ምንጭ ሆቴል በተለይ ጫካ ውስጥ ያሉት የመኝታ ክፍሎችና የጽዳት ሁኔታቸው አሳቋታል። የምግብ ዝርዝሩም አነስተኛና የለመደችው ባለመሆኑ ግራ ተጋብታ ነበር የኮንሶው የምግብ ዝርዝር ግን ለእሷ እንግዳ ነው። አማራጭ ብሎ ነገር የለውም  ያለው አንድ
👍16
ዓይነት ምግብ ሲሆን እሱም ሚስቶ ብቻ ነው  አበቃ
ካርለት፣ «አምላኬ!» ብላ ተደንቃ ለመብላት ተጣጣረች" ሆኖም
ግን ከጉሮሮዋ አልወርድልሽ አላት ስለዚህ ባልቀዘቀዘ ኮካ ወደ ውስጥ
ለማስገባት ሞከረች ከሎ ግን ደስ ብሎት ጥርግ አድርጎ በላ ከከተማው ወጥተው አቀበት፣ ቁልቁለቱን ወርደው ሲጓዙ
አሁንም ካርለት በተፈጥሮ ውበት እየተደነቀች ከመኪና መሪ ጋር ስትታገል ቆየችና፣ «ከሎ ይህች ሀገር ልምላሜ፣ ውበትና ጥሬ ሀብቱ ሳያንሳት፣ ቀድማ ነቅታ ምነው ተመልሳ ተኛች" የእንቅልፍ
(መድኃኒት) ማን አዋጣት? የውስጥ ይሆን የውጭ ሐኪም?» አለችው ምስጥ ብላ ከሎ በሳንባው የታመቀውን አየር ወደ ውጭ እያንቦለቦለ፣ ፊቱን ቅጭም አድርጎ፣ «ሁለቱም ሁለቱም ሐኪም
ነው ካርለት» አላት" መኪናዋም አቀበቱን ለመውጣት ድምጽዋን
ቀይራ ማቃሰት ጀመረች" በመሪው በኩል ያለው ጎማ ግን ፍትጊያውን መቋቋም ስላቃተው ተነፈሰ" ከዚያም «ስኮርት» ጎማ ቀይረው ጥቂት እንደሄዱ ደግሞ በጭቃ ተያዙ"

ሰማዩ ጎሽቶ፣ ብርቅርቅታው እንደ ርችት እየተንጣጣ፣ ዶፍ ዝናቡ መዝነብ በመጀመሩ እንኳን መኪናዋን ከተያዘችበት ጭቃ ለማውጣት መሞhር ቀርቶ በሩን ለመhፈት እንኳን ተሳናቸው"

ዝናቡ አካባቢውን ሲወቃው ቆይቶ ቁልቁል ወደ በረሃው
በመውረዱ እየቆየ እየቆየ አካባቢው ሲገልጥ ወርደው መኪናውን ሲመለከቱ የመኪናው ደረትና መሬቱ ተቃቅፈዋል" መኪናውን
ለማንቀሳቀስ መሬቱ መቆፈር፣ ድንጋይ መጨመርና በሰው ኃይል
ወደ ላይ ማንሣት ያስፈልግ ስለነበር ካርለትና ከሎ ለሁለት ሊወጡት
የማይችሉት ችግር በመሆኑ አድረው የአካባቢውን ሰው ትብብር ለመጠየቅ ተስማምተው ድንኳኖቻቸውን መንገድ ዳር ተከሉ"።

💫ይቀጥላል💫
👍14
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ (30)

የጨለማውን ክፍል በር ከፍታ ገብታ መልሳ ልትዘጋው ስትል ስልኩ የጥሪ ድምጽ አሰማ። ቤን አቭሪ መሆን አለበት እንደገና የደወለው። ተናደደችና በሩን በርግዳ ወጥታ ወደ ስልኩ ሄደች። መነጋገሪያውን መንጭቃ ካነሳች በኋላ «አይሆንም ማለት አይሆንም ነው ! መልሴ አንድ ነው። ይኸን ደግሞ ቁርጥ ባለ ቃል ነግሬሃለሁ» ስትል ጮኸች፡፡ ‹‹የፈጣሪ ያለህ ምነው ምን አጠፋሁ?» አለ ለስላሳውና ልቧን የሚያበራው የፒተር ድምጽ። የፒተርን ከፊል ሳቅ ያፈነው ከፊል ድንጋጤ የበረዘው ድምጽ ስትሰማ ንዴቷ ባንዴ ቀዘቀዘ። አዕምሮዋም ርጋታን ተላበሰ። «ፒተር! አስደነገጥኩህ አደል ? ይቅርታ ። አንድ ሰው ስልክ ደውሎ የማይሆን የማይሆን ነገር ነግሮኝ አይሆንም ብዬው ነበር። እሱ መልሶ የደወለ መስሎኝኮ ነው»
«የፎቶ ግራፍ ትርኢቱን በሚመለከት ነው?»
‹‹አዎ ወደዚያው ነው»
«የአዳራሹ አስተዳደር የስልክ ቁጥርሽን ለማንም መስጠት አልነበረበትም። መልዕክት ተቀብለው ላንቺ መንገር ነበረባቸው። ያለዚያ የማንም ቦዘኔ እየተነሳ ያልሆነ ነገር ሊያደርግ ይችላል» ። የተበሳጨ መስሎ ተሰማት ። ‹‹ግን ደህና ነሽ አደለም ? »
«ደህና ነኝ» ይሀን ስትል መረሽዋን በድምጺ ስለተረዳ ደህና ነኝ ያለችውን አላመነም ። «ደግ መጣሁ ከአንድ ሰዓት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ እደርሳለሁ ። እስከዚያ ድረስ ማንም ቢደውል ስልክ ማንሳት የለም ከዚያ በኋላ የሚደውለውን ሰው እኔ እንደሚሆን አደርገዋለሁ»

ሌሎች የንግግር ልውውጦች ካደረጉ በኋላ ስልኩን ዘጋች ። ግን እንደደወለና ምን እንዳበሳጫት ለፒተር አለመንገሯን ስታስበው ጥፋት እንደሠራች ተሰማት ። ፒተር ያሰበው ቦዘኔ ቀውስ እንዳስቸገራት ነው። ቤን አቭሪ ግን ሁለቱንም አይደለም ። የሱ ጥፋት ፤ የወረወራትና የናቃት የማይክል ሂልያርድ ሰራተኛ መሆኑ ብቻ ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ ይሀን ጉዳይ ለፒተር መንገርም ጥሩ እንዳልሆነ ገመተች ። የለም ጥሩ አይደለም አለች በሐሳቧ ። ይህን ጉዳይ ብትነግረው ፒተር ይበልጥ ይጨነቃል ።

የማይክል ነገር እስካሁን ከልቡናዋ አልወጣም ። በጣም ጠልቆ በመግባቱም እስከመቼም ላይወጣላት ይችላል ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል ። ጥቅም የለውም ብላ ተወችው ። ያን ዕለት ቤን አቭሬ ደግሞ አልደወለም ። ይህም ተመስገን የሚያሰኝ ነበር ። ፒተር መጥቶ ከሱ ጋር ስትጨዋወት ችግሩም መሸበሩም ቀስ በቀስ ከሜሪ አዕምሮ እየደበዘዘና እየጠፋ ሄደ። ግን አልቀጠለም… በማግስቱ ጠዋት ቤን አቭሪ ደግሞ ደወለ «ሃይ ሚስ አዳምሰን ። ቤን አቭሪ ነኝ»
«ስማ ፤ ትናንት ማታ ሁሉን ነገር ተነጋግረን የጨረስን መሰለኝ ። ይሆንሻል ያልከው ሥራ አይሆነኝም፣አይስማማኝም አልኩህ በቃ፡፡»
«ግራ የገባኝኮ አልፈልግም አልሽ እንጄ ምን እንደማትፈልጊ እንኳ ያወቅሽ አይመስለኝም ። ከእኔና ከጓደኛዬ ጋር ምሳ እየበላን ለምን አንነጋገርም አይተሽኛል ሰው ነኝ ።አልበላሽ ! መነጋገር ደግሞ ምንም ጉዳት የለውም ። ወይስ መነጋገሩም ሊጐዳ ይችል ይሆን ?» ይችላል ቤን በጣም ሊጐዳ ይችላል ! አንተ አጠገብ መሆን ብዙ የተደበቀ ትዝታ ጐትቶ ያመጣል… በሐሳቧ ። «አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ። ግን አይመቸኝም ። ሥራ ይበዛብኛል» አለች ። ሌላ መንገድ ቢሞክር ፍንክች ሳትል ቀረች ተስፋ የሌለው ነገር ነው በሚል መንገድ ዓይኑን አፍጦ እያንከባለለ ዌንዲ ታውንሴንድን ተመለከታት ። ኮተር ሂልያርድ ትልቅ ድርጅት ነው ። እንደ ሜሪ ያለች ሰውን ለማስቀየም አይችልም፡፡ ይኸ ግን በቀጥታ ከድርጅቱ ጋር ጠብ ያላት ይመስላል። ምን በደል ደረሰባት ኮተር ሂልያርድን ለምን ጠላችው ?
«ነገስ አይመችሽም ?»
«ስማ... ቤን... ሚስተር አቭሪ መቼም አይመቸኝም። ፍላጐቱም የለኝም ። ፍላጐቱ ከሌለኝ ምንም የምንነጋገርበት ነገር የለም። አሁን ነገሬ ግልጽ ነው ?»
«የምሥራች የሚባልለት አይደለም እንጂ ግልጽስ ነው» አለ።
ጸጥታ…
«ግን» አለ ቤን «ግን ትልቅ የሙያ ስህተት የሠራሽ ይመስለኛል። ጉዳይ አስፈጻሚ ወይም ወኪል ካለሽ ብታማክሪው ይህን እኔ የነገርኩሽን ነገር ደግሞ ይነግርሻል»
«ነበር ግን ወኪል ወይም ነገረ ፈጅ የለኝም ። ስለዚህም አይለኝም ። ወኪል የማያስፈልገኝ ደግሞ ከራሴ ሌላ ማንንም መስማት ስለሌለብኝ ነው»
«ከስህተቶችሽ አንዱ ይህ አስተሳሰብ መሆን አለበት በነገር ባንራራቅ ደግ ነው»
«ስላሰብክልኝ አመሰግናለሁ ። ምክንያቱም ለሌላ ሰው ማሰብ ቅንነት ነው ። ግን እንድትቸገር አያሻም ። እና እንደገና ባንደዋወል ይመረጣል»

••••••

ቤን አቭሪ ከምድር ውስጥ ባቡር ጣቢያ ወጥቶ በፓርክ አቬንዩ ወደሚገኘው ቢሮው የሚወስደውን መንገድ በእግሩ ሲፈጭ የፌብሩዋሪን (የካቲት) ቅዝቃዜ በመፍራት ኤሊ እድንጋዩዋ ውስጥ ተሰብስባ እንደምትገባ እሱ ደግሞ እካፖርቱ ውስጥ ለመደበቅ አንገቱ ትከሻውን እስኪነካ በመሰብሰብ ነበር ። ዝናብ ሊጥል አጓግቶ እንደመጣ ከአየሩ ሁኔታ ተረዳ ። ገና ለሁለት ሰዓት ጥቂት ደቂቃ ጉዳይ ቢሆንም ቸኩሏል ። የሥራ መግቢያ ሰዓት ማለትም ሦስት እስኪሞላ ሊጠብቅ አይችልም ። ብዙ ሥራ ይጠብቀዋል ። ከሳንፍራንሲስኮ የተመለሰው ትናንት ሲሆን ከኮተር ሂልያርድ ሥራ አስኪያጅ ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር አራት ሰዓት ላይ ስብሰባ እንደሚኖረው ተነግሮታል ። መልካም ነገር ይዞላት እንደሚቀርብም ይተማመናል ።

በመሥሪያ ቤቱ ማረፊያ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል ። አሳንሰሮችም ጥቅጥቅ እያሉ በመሙላት ሰዎችን ወደየቢሮአቸው ማጓጓዝ ቀጥለዋል ። ገና ጥዋት ቢሆንም የንግድ ሥራው ዓለም መተራመሱን ጀምሯል ። ሕይወት ረጋ ብላ በምትፈስበት ሳንፍራንሲስኮ ቆይቶ የንግድ ዓቢይ ፈለግ ወደሆነችው ኒው ዮርክ ሲመለስ የዚችን ከተማ ትርምስ ለሚያውቃት ቤን አቭሪ እንኳ አስደንጋጭ ሆነበት ። የሱ ቢሮ ከሚገኝበት ፎቅ ደርሶ ሲመለከት ቀድሞት የገባና ሥራ የጀመረ ሰው አልነበረም ። ቢሮው ምንም እንኳ የማይክል ሂልያርድን ቢሮ ያህል የሰፋና እንደ ማይክል ቢሮም በልዩ ምርጫ የተሰናዳ ዕቃ ባይኖረውም ምቹና ያሸበረቀም ነው፡፡ ማርዮን ሂልያርድ ለኮተር ሂልያርድ ቢሮዎች ምቾትን ለመስጠት በወጭው ላይ ወደኋላ የማትል ሥራ አስኪያጅ ናት ። ካፖርቱን ካወለቀና ሰውነቱን ለማሟሟቅ ከመዳፍ ለመዳፍ ማፋጨት እስከወገብ እንቅስቃሴ ያለውን ከፈጸመ በኋላ ስለሥራው ማሰብ ጀመረ ። ሆኖም የኒውዮርክ የዝናብ ወቅት ብርድ ከሰውነቱ ሙልጭ ብሎ አልወጣም ። ቢሮው ራሱ በረዶ የተጋገረበት ያህል ቀዝቃዛ ነበር፣ መጋረጃውም ወፍራም ሕንፃውም ሙቀትን አፍኖ ለማቆየት የሚችል ሆኖ ቢሠራም እንኳ ግን ብርድ አለ ብሎ አርፎ መቀመጥ አይችልም ። የተለያዩ ጉዳዮችን የያዙ ወረቀቶችን ከቦርሳው እያወጣ እጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ተመሳሳይ ጉዳይ ያላቸውን አንድ ላይ ማድረግ ጀመረ ።

ስለተልዕኮው አሰበ ። ሁሉም ነገር ቀና መንገድ ይዟል ። ከአንድ አነስተኛ ነገር በስተቀር ። ያ ደግሞ የሚስተካከልበት መንገድ ይገኝለት ይሆናል ። ሰዓቱን ተመለከተ ። ይሁን አይሁን የሚል ጥያቄ መጣበት ። ቢሳካም ባይሳካም አንዴ መሞከር እንዳለበት ወሰነ ። ያን ያስቸገረውን ጉዳይ አንድ መልካም እልባት ላይ አድርሶ ስብሰባውን ቢካፈል ደስ ይለው ነበር ። ቤን አቭሪ ከሜሪ አዳምሰን የፎቶግራፍ ሥራዎች ጥቂቱን ይዞ መጥቷል ። ሜሪ እነዚያን ፎቶግራፎች እንዳልሰጠችው ግልጽ ነው ። በቀጥታ ከሷ ሳይሆን ከኤግዚቢሽኑ ቦታ ነበር የገዛው ። የፎቶግራፎቹ ዋጋ ደግሞ የሆነውን ቢሆን የባከነ ገንዘብ እንደማይሆን
👍25
ቤን ያውቃል ። ማሪዮንም ፤ ማይክልም ፎቶግራፎቹን ካዩ የሜሪ የፎቶግራፍ አነሳስ ዘዴ ፤ እና አስተጣጠቧን ከተመለከቱ ሴትዮይቱ እንደምታስፈልጋቸው ወዲያው ይገነዘቡታል ።

ምናልባትም የሜሪን ችሎታ ከተገነዘበች ማሪዮን ራሷ በነገሩ ትገባበት ይሆናል ። እሷ ደግሞ ቀላል ሰው አይደለችም ። ሜሪን እንደምንም ብላ አንድ ኮንትራት ልታስፈርማት ትችላለች ። ማሪዮንን ስታይ በሜሪ የሠራ አካላት የሚያንዘፈዝፍ ስሜት ሲሰራጭ ታየው ፤ ፈገግ አለ ። ስልኩን ጐተት አድርጐ የሜሪን ስልክ ቁጥር መታ ። ነገሩ ሁሉ እብደት ሆኖ ተሰማው ። ምክንያቱም ሳንፍራንሲስኮ ገና በደንብ አልነጋም ፤ ከሌሊቱ አሥራ አንድ ከሩብ ነው የሚሆነው ። ግን ተስፋ ይኖር ይሆናል ። ሜሪ በመንቃትና ባለመን ቃት መካከል ብትሆን ። ስልኩ… «ሄሎ» አለ ። ። እንቅልፍ በተጫጫነው ድምጽ ። «እ እ እ ! ሚስ... ሚስ አዳምሰን መቼም በሌሊት ከእንቅልፍሽ ስላናጠብኩሽ በጣም በጣም ይቅርታ ። ቤን አቭሪ ነኝ ከኒው ዮርክ ። ሚስ አዳምሰን ከድርጅታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር ስብሰባ አለብኝ ፤ ዛሬውኑ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ። እና ላቀርብላት ካቀድኳቸው ነገሮች አንዱ አንቺ ለሳንፍራንሲስኮ ፕሮጀክት እንድትሠሪ ማድረግ መሆኑን ነው ። አሁን ድንገት ሳስብበት…» ማንም አልገታውም ፤ የሜሪ ጸጥታ እንጂ ። ያን ጸጥታ ሲገነዘብ ነገሩን ያነሳበት መንገድ ስህተት እንደሆነ ገባው ። ጸጥ አለ ። ወዲያው ሕያው ድምጽዋ ድረሰው ።

«ከሌሊቱ በአሥራ አንድ ሰዓት ? …በዚህ ሰዓት ስብሰባ እንዳለብህ ልትነግረኝ ደወልክ ከ….? በክርስቶስ ይዠሃለሁ ። ወንድሜ… ምን ዓይነቱ ቅጣምባሩ የጠፋ ነገር ውስጥ ገባሁ ? ሰው አንዴ ይናገራል ። ያ በቂ አይደለምንዴ ? አይሆንም አልኩ ! አይበቃም ? ሰው ምን ማድረግ ይችላል ። ላንተ ስል ስልኬን ማስቆረጥ ሊኖርብኝ ነው ? ወይስ አድራሻዬ እንዳይታወቅ ስሜን ከቴሌፎን ዝርዝር ማውጫ ላሰርዘው ?» ይህን ንግግር ያዳመጠው ዓይኑን ገርበብ አድርጐ ነበር ። ዓይኑን ገርበብ ያስደረገው ከፊል ጥፋተኛ መሆኑ ስለተሰማው ፤ ከፊል ደግሞ ያን ነገር ይናገር የነበረው ድምጽ ሁኔታ ነበር ። ያ ድምጽ የሜሪ አዳምሰን አልመስልህ አለው ። ያን ድምጽ ከዚህ በፊት ሰምቶታል ? የት? ሊያስታውሰው አልቻለም ። ግን ደግሞ ያ ድምጽ አዲስ አይደለም ። እንዲያውም የአንዲት በቅርብ የሚያውቃት ሴት ድምጽ እንደሆነ ይሰማዋል። የማንን ድምጽ ነው የሚመስለው ? አሰበ ። አሰበ…

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍152
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_ሦስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በአባቷ አድራጎት ስላፈረች መሬት ተከፍታ ብትውጣት በወደደች፡ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ሁላ በተፈጠረው አስከፊ ሁኔታ የአባቷን ጋጠወጥ ባህሪ እሷም ትጋራ ይሆን?› እያለ እያሰበ የሚያፈጥባት መሰላት፡ የሰዉን አይን ማየት ፈራች:

ሄሪ ማርክስ የቀራት እንጥፍጣፊ ክብሯ ሳይገፈፍ ደረሰላት፡ ቀልጠፍ
ብሎ ተነስቶ በማክበር ወምበሯን ያዝ አድርጎላት፣ ሶቶ እንድትይዘው
ክንዱን ሰጥቷት ከመብል ክፍሉ እንድትወጣ አገዛት፧ ያደረገው ነገር ትንሽ
ቢሆንም እሷን ግን ልቧን ነክቷታል።

አባቷ ለዚህ እፍረት ስለዳረጓት በእጅጉ አንገብግቧታል፡፡ ራት ከተበላ በኋላ በመብል ክፍሉ ውስጥ ለሁለት ሰዓት ያክል የሚከብድ ጸጥታ ነግሶ ቆየ፡ የአየሩ ሁኔታ እየተበላሸ ሲመጣ አባባ እና እማማ የቀን ልብሳቸውን
አውልቀው የመኝታ ልብሳቸውን ለበሱ፡
ፔርሲ ‹‹ይቅርታ እንጠይቅ›› አላት ማርጋሬትን ድንገት፡
ፔርሲ ይህን ሲላት ይቅርታ መጠየቁ የበለጠ እፍረት ውስጥ እንደሚጥላቸው ገመተች፡ ‹‹እኔስ ይቅርታ ለመጠየቅ ድፍረቱ የለኝም››
አለችው ወንድሟን፡፡

‹‹ባሮን ጋቦንና ፕሮፌሰር ሃርትማን ጋ ሄደን አባታችን ስላሳየው ያልተገባ ባህሪ ይቅርታ ብንጠይቅ ነው የሚሻለው›› አለ ፔርሲ፡
የአባቷን ጥፋት ለማለዘብ ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ ሳይሆን አይቀርም ስትል አሰበች፡፡ እሷም ቀለል ይላታል፡፡ ‹‹አባባ ግን ይናደድብናል›› አለች
አበዛው! አብዷል መስለኝ ከዚህ በኀላ አልፈራውም›› አለ ፔርሲ፡

‹‹እሱ ማወቅ የለበትም ቢናደድ ደግሞ ግድ የለኝም፧ አሁንስ
ፔርሲ ከዚህ በኋላ አልፈራውም› ያለው እውነት መሆኑን ማርጋሬት
አላወቀችም: ህጻን ሆኖ አባታቸውን ፈርቷቸው እያለ ‹አልፈራውም› ይል
ነበር፤ አሁን ግን ህጻን አይደለም፡፡

ፔርሲ ከአባታቸው ቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱ ማርጋሬትን አሳስቧታል፡ አባቷ ብቻ ናቸው የፔርሲን
ያልተገባ ባህሪ ሊያርቁ
የሚችሉት፤ ፔርሲ ሸረኝነቱን እንዲተው ካልተደረገ አይቻልም፡፡

‹‹በይ እንጂ! አሁን እንሂድና ይቅርታ እንጠይቃቸው፤ ያሉበትን ቦታ እኔ አውቀዋለሁ›› አለ ፔርሲ፡
ማርጋሬት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈራ ተባ አለች እያለች ነው አባቷ
ያስቀየሟቸው ሰዎችጋ መሄድና ይቅርታ መጠየቅ ከብዷታል፤ የሆነውን
ሁሉ መተውና አርፎ መቀመጥ ነው የሚሻላቸው ቁስላቸውን መነካካቱ
ምንም ፋይዳ የለውም፡ ሆኖም የዘር መድሎን ለመቃወም እጅ ለእጅ
መያያዝ ያስፈልጋል።

በመጨረሻ ማርጋሬት ሰዎቹን ይቅርታ ለመጠየቅ ወሰነች፡ መቼም ጥሎባት ቦቅቧቃ ናት፡ ከዚህ ቀደም ላጠፋችው ጥፋት ፈርታ ይቅርታ ሳትጠይቅ መቅረቷ ሁልጊዜ ይጸጽታታል፡
አይሮፕላኑ በወጀቡ እየተወዛወዘ ቢሆንም የወንበሯን መደገፊያ ጠበቅ
አድርጋ ይዛ ተነሳችና ‹‹እሺ እንሂድ›› አለችው ወንድሟን፡
የአይሮፕላኑ መወዛወዝ በፍርሃት መንቀጥቀጧን ደብቆላታል፡ ሁለቱ
ሰዎች ወዳሉበት ክፍል አመራች፡፡

ጋቦንና ሃርትማን ግምባር ለግምባር ተቀምጠዋል፡ ሃርትማን የሂሳብ መጽሐፍ ላይ በተመስጦ አፍጠዋል፡፡ ጋቦን የሚሰሩትን አጥተው በጉዞው ተሰላችተው ተቀምጠዋል፡ በመጀመሪያ ማርጋሬትንና ፔርሲን ያይዋቸው እሳቸው ናቸው፡ ማርጋሬት አጠገባቸው መጥታ ወምበራቸውን ተንገዳግዳ ስትይዝ አዩና ፊታቸውን አኮሳተሩ።

ማርጋሬት ቶሎ ብላ ‹‹ይቅርታ ለመጠየቅ ነው የመጣነው›› አለች፡
‹‹ደፋር ነሽ!›› አሉ ጋቦን የፈረንሳይኛ ቋንቋ ቅላጼ ባለው እንግሊዝኛ፡
ማርጋሬት እንዲህ ያለ ምላሽ ይገጥመኛል ብላ ባታስብም ጥረቷን
ቀጠለች፡ ‹‹በአባታችን አድራጎት በጣም አዝኛለሁ፤ ወንድሜም እንዲሁ
ለፕሮፌሰር ሃርትማን ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው፡ ይህንንም ከዚህ ቀደም
ነግሬያቸዋለሁ›› አለች፡:

ሃርትማን ንባባቸውን አቋርጠው ይቅርታውን መቀበላቸውን ራሳቸውን
በመነቅነቅ አመለከቱ፡ ጋቦን ግን አሁንም በቁጣ አበያ በሬ እንደመሰሉ ነው
‹‹እንደ እናንተ ላሉ ሰዎች ይቅርታ መጠየቅ ቀላል ነው›› ሲሉ ማርጋሬት
የምታደርገው ጠፍቷት በድንጋጤ መሬት መሬቱን ታያለች፡፡ ‹ምነው
ባልመጣሁ አለች በሆዷ፡ ‹‹ጀርመን ውስጥ እየተደረገ ያለው ነገር በጣም
እንደሚያሳዝናቸው የሚነግሩን ጨዋ ሰዎች ብቻ ናቸው›› ሲሉ ቀጠሉ ‹‹ግን ምን አደረጉልን፤ እናንተስ ምንድነው የምታደርጉልን?›› አሉ ጋቦን፡፡
ማርጋሬት ፊቷ በድንጋጤ በርበሬ መሰለ፡፡ ምን እንደምታደርግ ግራ ግብት አላት።

‹‹ፊሊፕ ዝም በል እንጂ›› አሉ ሃርትማን ለስለስ ባለ አነጋገር ልጆች እኮ ናቸው›› ወደ ማርጋሬትም ዞር አሉና ‹‹ይቅር ብለናል እናመሰግናለን››

‹‹ጌታዬ ተሳሳትን ይሆን?›› ስትል ጠየቀች::

‹‹በፍጹም›› አሉ ሃርትማን ‹‹እንደውም ጥሩ ነው ያደረጋችሁት ይባርክሽ፧ ጓደኛዬ በጣም ስሜቱ ስለተነካ ነው እንዲህ የሆነው፤ በኋላ እንደእኔ ሲገባው ከንዴቱ መለስ ይላል፡››

‹‹እንግዲህ እንሂድ›› አለች ማርጋሬት እንደከፋት፡
ሃርትማን በመስማማት ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ፔርሲም በተራው ‹‹ይቅርታ አድርጉልን›› አለና ከእህቱ ጋር ተያይዘው
ሄዱ፡፡

ወንድምና እህቱ በአይሮፕላኑ ውዝዋዜ እየተንገዳገዱ ወደ ቦታቸው
ተመለሱ፡፡ ዴቭ መኝታቸውን እያነጣጠፈላቸው ነው፡፡ ሄሪ በቦታው የለም፡ ምናልባትም ወደ መታጠቢያ ቤት ሄዶ ይሆናል፡፡ ማርጋሬት ልብስ
ለመለወጥ ቦርሳዋን አንጠልጥላ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደች፡ እናቷ የመኝታ ልብሳቸውን ለብሰው እምር ድምቅ ብለው ከመጸዳጃ ቤት እየወጡ ስለነበር
‹‹ደህና እደሪ የኔ ማር›› ቢሏትም እሷግን ዝግት አድርጋቸው ገባች:
በሴቶች በሞላው መታጠቢያ ቤት ውስጥ የመኝታ ልብሷን ቶሎ ለውጣ ወጣች፡፡ የመኝታ ልብሷ ሌሎቹ ሴቶች ከለበሱት ደመቅመቅ ካሉትና ከሃር ከተሰሩት ልብሶች ጋር ሲነጻጸር ኋላ ቀር መሆኑ ግድ አልሰጣትም፡፡ ባሮን
ጋቦን በኋላ ያሉት እውነት በመሆኑ ይቅርታ መጠየቁ የፈየደው ነገር የለም ለችግሩ ምንም መፍትሄ ሳያመጡ ይቅርታ› ማለት ቀላል ነው።

ወደ ቦታቸው ሲመለሱ እናትና አባቷ መጋረጃቸውን ጋርደው ተኝተዋል፡፡ አባቷ አገር አማን ነው ብለው ያንኮራፋሉ፡፡ ማርጋሬት የእሷ መኝታ እስኪዘጋጅ ቁጭ ብላ ጠበቀች፡፡

ከቤተሰቦቿ ቁጥጥር ነፃ ለመሆን አንድ መንገድ ብቻ ነው ያላት  እነሱን ትታ እየሰራች መኖር አሁን ይህን ለማድረግ ቆርጣለች፡፡ የገንዘብ፣ የስራና የመኖሪያ ቦታ ችግሯን ለመቅረፍ ግን ገና ነች፡፡

ፎየንስ ላይ የተሳፈረችው ዘናጯ ናንሲ አጠገቧ መጥታ ተቀመጠች።
ሴትየዋ የመኝታ ልብስ ነው የለበሰችው፡፡ ‹‹አስተናጋጁ ብራንዲ እንዲያመጣልኝ ፈልጌ ነበር፤ እሱ ግን እረፍት የለውም፧ እዚህ እዚያ ይንከወከዋል
አለች፡ ሲያይዋት ዘና ብላለች፡ ተሳፋሪው እንዲያያት እጇን አውለበለበች
‹‹ለምን ፓርቲ አንጨፍርም፤ ምን ትያለሽ?›› አለቻት ማርጋሬትን፡፡
‹‹ያልሽው ነገር እንግዳ ነው የሆነብኝ›› አለቻት ማርጋሬት፡፡
ናንሲ የመቀመጫ ቀበቷን አጠባበቀች፡ ደስ ደስ ብሏታል። ‹በፒጃማ
ስትሆኚ መከባበር ብሎ ነገር የለም፤ የወዳጅነት ስሜት መስፈን ነው
ያለበት፡፡ ፍራንክ ጎርደን እንኳን ፒጃማው አምሮበታል፡››

ማርጋሬት በመጀመሪያ ስለማን እንደምታወራ  አልገባትም ነበር፡፡
ወዲያው ግን ካፒቴኑና የኤፍ.ቢ.አይ መርማሪው ሲጨቃጨቁ ፔርሲ ሰምቶ
የነገራት ነገር ትዝ አላት
‹‹እስረኛውን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀቻት።
‹‹አዎ››
‹‹አንቺ አትፈሪውም?››
‹‹አይ አልፈራውም፧ ምን ያደርገኛል!››
‹‹ሰዎች ግን ነፍሰ ገዳይ ነው ይሉታል››
👍202
‹‹ወንጀል የትም ቦታ ሊፈጸም ይችላል። ጎርዲኖ ብቻ አይደለም፧ሌላውም ሰው ቢሆን ሰው ይገድላል። እሱ ከሌላው በምን ይለያል፡ ቁማርና ሽርሙጥና ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወንጀል የሚፈጸመው በቡድን በመደራጀት ነው፤ እንደ ማፍያ፡››

ይሄ አነጋገር አስደንጋጭ ነው፡ የአይሮፕላኑ አስፈሪ ጉዞ የፈጠረው ውጥረት ሰውን ሁሉ ሃቅ ተናጋሪ አድርጎታል፡ ናንሲ ወንድም ሆነ ሴት በተሰበሰበበት ቦታ እንደዚህ ግልጽ ሆና እንደማትናገር ማርጋሬት ገመተች፡፡ሴቶች ወንዶች በሌሉበት የሆድ የሆዳቸውን ነው የሚነጋገሩት፡፡ ‹‹ወንጀል በቡድን ሳይሆን ለብቻ ቢፈጸም አይደለም የሚሻለው?›› ስትል ማርጋሬት ጠየቀች፡

‹‹አይደለም፡፡ በተደራጀ ሁኔታ ሲፈጸም የራሱ ገደብና ቁጥጥር አለበት
ወሮበሎች የየራሳቸው አካባቢ አላቸው አንዱ በአንዱ ክልል ውስጥ
አይገባም፧ ከገባም ብዙ ጣጣ ይከተለዋል››
ማርጋሬት ጨዋታው ጥሟታል፡ ‹‹ታዲያ ገንዘባቸውን በቁማር
የሚጨርሱ ሰዎች ምን ይውጣቸዋል? ገላቸውን ለገንዘብ ሲሉ የሚቸረችሩ
ሴቶችስ ጤናቸው እንዴት ይጠበቃል?›› ስትል ጠየቀች።

‹‹ለነዚህ ሰዎች ግድ የለኝም እያልኩ አይደለም›› አለች ናንሲ፡፡ማርጋሬት ናንሲ የምትለው እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ የናንሲን ፊት
ገረመመች፡፡ ‹‹ይኸውልሽ ማርጋሬት›› ስትል ቀጠለች ‹‹እኔ ጫማ አምራች
ነኝ፡›› ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ተደነቀች፡፡ ናንሲ ንግግሯን በመቀጠል
‹‹እንጀራዬ የተመሰረተው በጫማ ስራ ላይ ነው፡፡ የጫማ ፋብሪካ አለኝ
የማመርተው የወንዶች ጫማ ዋጋው ርካሽ ቢሆንም አምስት ወይም አስር ዓመት ያገለግላል፡ ከፈለግሽ ደግሞ እኔ ከማመርተው ርካሽ የሆነ ጫማ ገበያ ላይ ታገኛለሽ፧ ሶላቸው ከካርቶን የተሰራ በመሆኑ አስር ቀን እንኳን
አታደርጊያቸውም:፡ አመንሽም አላመንሽም እነዚህን የካርቶን ጫማዎች
የሚገዙ ሰዎች አሉ፡፡ እኔ ግን ጥሩ ጫማ በማምረት ኃላፊነቴን እወጣለሁ።
ሰዎች ግን የማይረባ ጫማ መግዛት ከፈለጉ እኔ ምንም ማድረግ አልችልም ድሆች ራት የሚበሉበትን ገንዘብ በቁማር ቢያወጡ እኔ ምንተዳዬ!››

‹‹አንቺ በድህነት ኖረሽ ታውቂያለሽ?›› ጠየቀች ማርጋሬት፡፡

ናንሲ ጥያቄው አሳቃት፡፡ ‹‹ጥሩ ጥያቄ፡ ጉራ መንዛት አይሁንብኝ እንጂ እኔ ድህነትን አላውቅም:፡ አያቴ የጫማ ስራን የጀመሩት በእጅ በመስፋት ነው፡፡ አሁን እኔ የማስተዳድረውን የጫማ ፋብሪካ የከፈተው አባቴ ነው፡፡ የድህነት ኑሮ ምን እንደሆነ ሳይገባኝ እስካሁን አለሁ፡፡ አንቺስ ስለ
ድህነት ኑሮ ታውቂያለሽ?››
‹‹እኔም ድህነትን ብዙ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ለመቆመር
ለመስረቅና ኑሯቸውን በሴተኛ አዳሪነት ለመግፋት የሚገደዱበት ምክንያት
ይኖራቸዋል፡፡ የከፋ የከረፋ ህይወት ውስጥ የተዘፈቁት ፈልገው አይደለም፡
የመጥፎ ስርዓት ተጠቂዎች ናቸው››

‹‹የኮሚኒስት አስተሳሰብ ተከታይ ሳትሆኚ አትቀሪም›› አለች ናንሲ ለጨዋታ ያህል፡
‹‹ሶሻሊስት ነኝ››

‹‹ጥሩ ነው›› አለች ናንሲ ነገሩ ደንቋት፡ ‹‹በእድሜ እየገፋሽ ስትመጪ
አስተሳሰብሽን ትለውጪ ይሆናል፡፡ ሆኖም አሁን የምትመሪበት የህይወት
መርህ ከሌለሽ ወደፊት የምትለውጪው አስተሳሰብ አይኖርሽም፡፡ መርሃችንን
ሳንለቅ ከህይወት ልምድ መቅሰም እንችላለን፡፡ ለምንድነው ግን እንዲህ
የምሰብክሽ? ምናልባትም ዛሬ አርባ ዓመቴን ስለያዝኩ ይሆናል፡፡››

ማርጋሬት በእድሜ እየበሰልሽ ስትመጪ አስተሳሰብሽን
ትለውጪያለሽ የሚሏት ሰዎች በእጅጉ ያናድዷታል፡፡ ሰዎች ይህን የሚሏት
በክርክር ሲረቱ ነው፤ መረታታቸውን ደግሞ መቀበል አይፈልጉም፡፡ ናንሲ ደግሞ የተለየች ናት፡፡ ‹‹ምንድነው ያንቺ የህይወት መርህ?››ጠየቀች ማርጋሬት፡፡

‹‹እኔ ጥሩ ጫማ መስራት ነው የምፈልገው›› አለች በፈገግታ፡ ‹‹ይሄ የህይወት መርህ ላይሆን ይችላል በኔ ግምት፡፡ የእኔ ህይወት ግን በዚህ ላይ ነው የተመሰረተው፡፡ ጥሩ ኑሮ እኖራለሁ፡ ትልቅ ቤት  አለኝ፡፡ ሁለቱ ወንዶች ልጆቼ የሚፈልጉትን ሁሉ አግኝተዋል፡፡  ውድ ልብስ ገዝቼ እለብሳለሁ፡ ለምንድነው እንደዚህ መኖር የቻልኩት? ጥሩ ጫማ ስለምሰራ ነው፡፡ የካርቶን ጫማ የምሰራ ብሆን የሰረቅሁ ይመስለኛል፡ ከሰረቅሁ ደግሞ
ከፍራንክ ጎርደን አልሻልም›› አለች፡፡

‹‹ሶሻሊስታዊ አስተሳሰብ ይመስላል›› አለች ማርጋሬት በፈገግታ፡

‹‹እኔ እንኳን የአባቴን የህይወት መርህ ነው የተከተልኩት›› አለች
ናንሲ፡፡ ‹‹ያንቺ የህይወት መርህ ከየት ነው የመጣው? መቼም ካባትሽ
የተወረሰ እንደሆነ ይታወቃል፡፡››
ማርጋሬት በሃፍረት ፊቷ ቀላ፡፡ ‹‹ራት ላይ የተፈጠረውን ጠብ አይተሽ
‹ቦታው ላይ ነበርኩ››
‹‹ከቤተሰቦቼ ተለይቼ ብቻዬን መኖር ነው የምፈልገው››
‹‹ታዲያ ምን ያዘሽ?››
‹‹ገና አስራ ዘጠኝ ዓመቴ ነው››

‹‹ብትሆኚስ? የአስር ዓመት ልጆች ከቤታቸው ጠፍተው ይሄዱ የለም ንዴ?››
„አንድ ጊዜ ሞክሬዋለሁ›› አለች ማርጋሬት፡ ‹‹በየመንገዱ ስደናበር
ፖሊስ ይዞ አመጣኝ እንጂ፡፡››
‹‹አንቺ በቀላሉ እጅ ትሰጫለሽ፡፡››
ማርጋሬት እቅዷ በእንጭጩ የተጨናገፈው ድፍረት አጥታ እንዳልሆነ ናንሲ እንድታውቅላት ትፈልጋለች፡፡ ‹‹ገንዘብ የለኝ፧ እውቀት የለኝ፣ መደበኛ ትምህርት አልተማርኩም፣ እንዴት ሆኜ እንደምኖር አላውቅም›› አለች፡፡

የኔ ማር! አሁን ወደ አሜሪካ እየሄድሽ ነው፡፡ ብዙዎች ባዶ እጃቸውን
መጥተው ነው እዚያ ሚሊየነር የሆኑት፡፡ ሲያዩሽ ተግባቢ፣ አዋቂ ትመስያለሽ፧ ቆንጆ ነሽ፤ በቀላሉ ስራ ማግኘት ትችያለሽ፡፡ ከፈለግሽ እኔ ስራ
እቀጥርሻለሁ፡፡››

‹‹እውነት ትቀጥሪኛለሽ?››
‹‹እቀጥርሻለሁ፡፡››
‹‹ምን ስራ ነው የምትቀጥሪኝ?››
ናንሲ ትንሽ አሰብ አደረገችና የሽያጭ ክፍል ውስጥ፡፡ ቴምብር መለጠፍና ፣ ቡና ማምጣት፣ ስልክ ማንሳትና ደምበኞችን በትህትና
ማስተናገድ፡ ኃላፊነትሽን መወጣት ከቻልሽ ደግሞ ረዳት የሽያጭ ኃላፊ
ትሆኛለሽ፡፡››

‹የረዳት የሽያጭ ኃላፊ ስራ ምንድነው?››

‹‹ተመሳሳይ ስራ ከፍ ባለ ደሞዝ መስራት ነው፡፡››
ማርጋሬት አሁን ቃል የተገባላት በእውን ሊሆን የማይችል ህልም መሰላት፡፡ ‹‹ወይ አምላኬ ስራ ላገኝ ነው>> አለች በከፍተኛ ጉጉት፡
ሚስስ ሌኔሃን ሳቀች።
‹‹ብዙ ሰዎች ስራው አሰልቺ ነው ብለው ያስባሉ››

‹‹ለኔ ግን ስራ ባገኝ ትልቅ ነገር ነው››
"በመጀመሪያ አዎ››

‹‹ውነትሽን  ነው?›› ስትል ጠየቀች ከልቧ፡ ‹‹ወደ ቢሮሽ ብመጣ

እውነት ስራ ትቀጥሪኛለሽ?›› አለች


ሚስስ ሌኔሃን ደንገጥ አለች ‹ወይ አምላኬ የምርሽን ነው እንዴ?, ‹‹እኔ እኮ እንደው ለጨዋታ ነው ያልኩት፡››

ማርጋሬት ሀዘን ገባት ‹‹ስራውን አትሰጪኝም ማለት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ስትይኝ የነበረው እንዲያው ለወሬ ነው?››

እኔ ብቀጥርሽ እወድ ነበር ነገር ግን ችግር አለ፣ በሳምንት ውስጥ እኔም ስራ አጥ ይሆናል።››

ማርጋሬት እምባዋ መጣ ‹‹ምን ማለትሽ ነው?››

‹‹ወንድሜ ኩባንያውን ከእጄ ለመንጠቅ እየሞከረ ነው››

‹‹እንዴት?››

‹‹ነገሩ የተወሳሰበ ነው ምናልባት አይሳካለት ይሆናል፡ ነገር ግን
መጨረሻው ምን እንደሚሆን ግን እኔም አላውቅም›› ማርጋሬት ከጥቂት ጊዜ በፊት ያገኘችው እድል  እንደተነጠቀች በመቁጠር ‹‹ድል ማድረግ አለብሽ አይዞሽ አምላክ ይርዳሽ›› አለች ጥርሷን ነክሳ፡፡
👍16😁1
ሚስስ ሌኔሃን መልስ ልትሰጥ ስትል ሄሪ እንደ ጧት ፀሀይ እያበራ ብቅ አለ፡፡ ማርጋሬት እሱን ስታይ ስሜቷ ተረጋጋ ቁጭ እንዳለ ማርጋሬት ከሚስስ ሌኔሃን ጋር አስተዋወቀችውና ‹‹ሚስስ ሌኔሃን ብራንዲ ፈልጋ ነበር ነገር ግን አስተናጋጆቹ ስራ በዝቶባቸው ሊያመጡላት አልቻሉም›› አለች:
‹‹ስራ ቢበዛባቸውም መጠጥ እያመጡ ነው›› አለና ተነስቶ ሌላኛው
የአይሮፕላኑ ክፍል ለሚገኘው አስተናጋጅ ‹‹ለሚስ ሌኔሃን ኮኛክ አምጣላት,, ሲል አዘዘው፡፡
‹‹እሺ ሚስተር ቫንዴርፖስት›› ሲል ዴቭ ሰማችና ማርጋሬት ሃሪ
ሰዎች የሚፈልገውን ነገር እንዲያደርጉለት ማድረግ ይችላል› አለች በሆዷ።
ከዚያም ቁጭ አለና ‹‹ሚስስ ሌኔሃን የጆሮ ጌጥሽ ያምራል›› አላት።

‹‹አመሰግናለሁ›› አለች በፈገግታ ጌጧ ሲደነቅ በመስማቷ ደስ አላት
ማርጋሬት የሚስስ ሌኔሃንን ጌጥ ጠጋ ብላ አየችው:፡ የጆሮ ጌጡ እውነትም ስለሚያምር እሷም እንዲህ አይነት ጌጥ ቢኖራት ተመኘች።የሄሪን ልብ ለመሳብም ‹‹ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ነው የገዛሽው?›› ስትል
ሌኔሃንን ጠየቀቻት፡
‹‹አዎ››
ሄሪም በማወቅ ራሱን ነቀነቀና ‹‹ዲዛይን የተደረገው ፋልኮ ደ ቬርዱራ በተባለ ወርቅ ሰሪ ነው›› አላት፡፡

‹‹አይ እኔ አላውቅም›› አለች ሚስስ ሌኔሃን ጌጣጌጥ ለአንድ ወጣት ወንድ እንዴት እንዲህ ስሜት ሊሰጥ እንደቻለ ገርሟት፡፡
ማርጋሬት የእሱ ዋናው ፍላጎት መስረቅ ነው ተጠንቀቂ አለች በሆዷ፡ ሆኖም ጌጣጌጥን በተመለከተ ያለው
እውቀት ሳያስደንቃት
አልቀረም፡፡ ‹‹ጥሩ ጥሩዎቹ ጌጣጌጦች የትኞቹ እንደሆኑ ብቻ ሳይሆን ማን
ዲዛይን እንዳደረጋቸው ያውቃል›› አለች፡፡

ዴቪ የሚስስ ሌኔሃንን ብራንዲ አመጣላት፡፡ አይሮፕላኑ ቢወዛወዝም
ዴቪ ሳይንገዳገድ ነው የሚራመደው፡፡

ሚስስ ሌኔሃን መጠጧን ጨልጣ ‹‹ልተኛ ነው›› አለችና ተነሳች

‹‹አምላክ ይርዳሽ›› አለች ማርጋሬት ሚስስ ሌኔሃን ከወንድሟ ጋር
የምትገጥመውን ጦርነት አስታውሳ፡፡ በትግሉ ከረታሽም ስራ ትቀጥራታለች ቃል እንደገባችው::

‹‹አመሰግናለሁ ደህና እደሩ›› አለች ሚስስ ሌኔሃን፡፡

ሚስስ ሌኔሃን እንደሄደች ሄሪ ‹‹ምን ነበር የምታወሩት?›› ሲል
ጠየቃት፡ ማርጋሬት ናንሲ ስራ እንደምትቀጥራት ቃል መግባቷን ለሄሪ ለመንገር
ጥርጣሬ ገባት፡፡ ስራ ማግኘቱ የሚያስደስት ቢሆንም ሚስስ ሌኔሃን ችግር እንዳለ ስለነገረቻት እርግጠኛ ያልሆነም ነገር ለሄሪ መንገሩ ደስ አላላትም፡፡
ምስጢሩን ለጊዜው በሆዷ ይዛ መቆየት ፈለገች፡፡ ‹‹ስለፍራንክ ጎርዲኖ ነው
ያወራነው›› አለች ‹‹እንደ እሱ ያሉትን ሰዎች በሩቁ ነው፡፡ የእነሱ ስራ ቁማር ማጫወትና ፍላጎቱ ያላቸውን ሴቶች ሴተኛ አዳሪነት ማስቀጠር ነው››
አለች ሽርሙጥና ብላ መናገር አሳፍሯት፡፡ ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለ ቃል
ሰው ፊት ተናግራ አታውቅም፡፡

‹‹ሴተኛ አዳሪው ሁሉ ወደዚህ ስራ የሚገባው ወዶ አይደለም፡፡አንዳንዶቹ ሳይወዱ በግድ ነው ሴተኛ አዳሪ የሚደረጉት፡፡ ሴቶች ታፍነው ተወስደው ሴተኛ አዳሪ እንደሚደረጉ ሰምተሽ ታውቂያለሽ?››

ማርጋሬት ሴቶች ታፍነው ተወስደው ኢስታንቡል (ቱርክ) ውስጥ
እንደሚሸጡ ጋዜጣ ላይ አንብባለች፡፡

ማርጋሬት ጨዋታው ስቧታል ‹‹እኔም ላይ ሊደርስ ይችል ነበር›› አለች
‹‹ከቤት ጠፍተሽ የሄድሽ ጊዜ›› አለ ሄሪ ‹ቢያገኙሽ አፍነው ይወስዱሽ ነበር፡ ምንም ገንዘብና መኖሪያ ቤት የሌላት ወጣት ሴት ልጅ ብቻሽን መንገድ ላይ ያገኙሽና ጥሩ ራት ጋብዘውሽ ጧት ወደ ፓሪስ ከሚሄድ የኪነት ቡድን ጋር እንደሚወስዱሽ ቃል ይገቡልሻል፡ አንቺም ከሰማይ የተላከልሽ ዕድል ይመስልሽና ትታለያለሽ፡፡ የኪነት ቡድኑ የራቁት ዳንስ
ቡድን ይሆንና ቁጭ፡ አንቺም መደነስ ትጀምሪያለሽ፡፡ ገንዘብ ስለሌለሽ ምንም ምርጫ የለሽም፡፡›› ማርጋሬት እራሷን በእነሱ ቦታ  አስቀምጣ የምታደርገው እንዲሁ እንደሆነ አሰበች፡፡

‹‹ከዚያ አንድ ቀን ከአንድ
ተመልካች ጋር እንድትወጪ ይነግሩሻል፡ እምቢ ካልሽ አንቀው ለሰውዬው
ይሰጡሻል፡›› ማርጋሬት ይህን ስትሰማ አይኗን ጨፍና ምን ሊደርስባት
እንደሚችል አሰበችው፡ ‹‹በሚቀጥለው ቀን ስራውን ጥለሽ ትሄጃለሽ፡፡ መሄጃ
ግን የለሽም፡፡ እጅሽ ላይ ያለው ገንዘብ ወደ አገርሽ ልትሄጂበት አያስችልም፡፡
ገንዘብ አግኝተሽ እንኳን ቤት መሄድ ብትችይ ለቤተሰቦችሽ የት ጠፍቼ
ከረምኩ ትያለሽ፡፡ እውነቱን ትነግሪያቸዋለሽ? አትናገሪም፡፡ ከዚያ ወደዚያው መደነሻ ቦታ ትሄጂና ከመሰሎችሽ ጋር ትቀላቀያለሽ፡ ብጤዎችሽም
ያደረግሽው ትክክል መሆኑ ይገባቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላማ አንዴ ካደረግሽው
ችግር አይኖረውም፡፡ ትለምጂዋለሽ፡፡  ዛሬ  አንዱን
ትሸኛለሽ፡፡ ነገ ሌላው ይመጣል፡፡ ሁሉም ለአንድ አዳር ነው የሚመጣው፡››

ማርጋሬት በሰማችው ተንገሸገሸች ‹‹በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው
የነገርከኝ፡፡ ለዚህ ነው እንደ ፍራንኪ ጎርዲኖ ያሉ ወሮበሎች የእጃቸውን
ማግኘት አለባቸው የሚባለው...

ይቀጥላል
👍171
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ሦስት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በአባቷ አድራጎት ስላፈረች መሬት ተከፍታ ብትውጣት በወደደች፡ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ሁላ በተፈጠረው አስከፊ ሁኔታ የአባቷን ጋጠወጥ ባህሪ እሷም ትጋራ ይሆን?› እያለ እያሰበ የሚያፈጥባት መሰላት፡ የሰዉን አይን ማየት ፈራች: ሄሪ ማርክስ የቀራት እንጥፍጣፊ ክብሯ ሳይገፈፍ ደረሰላት፡ ቀልጠፍ…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አንድ (31)

ያን ድምጽ ከዚህ በፊት ሰምቶታል ? የት? ሊያስታውሰው አልቻለም ። ግን ደግሞ ያ ድምጽ አዲስ አይደለም ። እንዲያውም የአንዲት በቅርብ የሚያውቃት ሴት ድምጽ እንደሆነ ይሰማዋል። የማንን ድምጽ ነው የሚመስለው ? አሰበ ። አሰበ… ሊያስታውስ አልቻለም « ልልሀ የፈለኩትን ነገር ገና ልትረዳልኝ አልቻልክም ይሆን በሥላሴ ? › እኒህ በቁጣ የጠነከሩ ቃላት ከፍለጋው መለሱት። ወደ አሁን አመጡት ። ከሜሪ አዳምሰን ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ። እውነቱን እንዲያይ ፤ ይህቺ ሜሪ እንጂ ማንም እንዳይደለች እንዲረዳ አደረጉት ። ባኛል ሆኖም ተስፋ ያደረግኩት »
«ተስፋ ዝባዝንኬ!... ነገርኩህ'ኮ አልፈልግም አልኩህ ፤ በዚሀ ነገር ላይ ለመነጋገር ይህን ነገር አውጥቶ አውርዶ ለማሰብ ወይም ለኔ ምኔም ስላልሆነው የሳንፍራንሲስኮ የሕክምና ማዕከል አንዲት ቃል ለመነጋገር አልፈልግም ። በሥላሴ ይዤሃለሁ ፤ ተወኝ » ይህን ተናግራ እጆሮው ላይ ደረገመችበት ። የተዘጋውን ስልክ ማነጋገሪያ በእጁ ይዞ የጅል ፈገግታ ፈገገ ። ከዚያም «ይኸው አፈነዳሁትና አረፍኩ ወንድሞቼ» አለ ።

ቤን ይህን የተናገረው ለራሱ ነበር ። በሐሳብ ስለተዋጠ የቢሮውን በር ከፍቶ መቃኑን በመዝናናት ደገፍ ብሎ የቆመው ማይክልን አላየውም ። «እንኳን ደህና መጣህ ። ለመሆኑ ምንድነው ያፈነዳኸው ?» ማይክ ይህን ጥያቄ የጠየቀው ይህን ያህል ለማወቅ በመጓጓት አልነበረም ። የጓደኛው መመለስ እንዳስደሰተው ብቻ ነበር ገጽታው የሚገልጸው ። በፊቱ ላይ ደስታው እንደጐላ ወደ ቤን ቢሮ ገብቶ በምቹው የእንግዳ መቀበያ ሶፋ ላይ ቁጭ አለ። «ከጉዞሀ ተመልሰህ ሳይህ ደስ አለኝ»
«መመለሱስ አይከፋም ነበር ። ግን ምን ዋጋ አለው ? የሳንራንሲስኮን አየር ተለማምደህ መጥተህ የኒውዮርክን ብርድ ፍጹም ሰውነትህ አይቀበለውም»
«ለስላሳው ፍጡር ሆይ ካሁን ጀምሮ ከሞቃታማዎቹ የደቡባዊ ክፍሎች እንዳትወጣ የተቻለንን ያህል እንሞክራለን» አለ በጸሎት ድምጽ ።። ከዚያ ቀጠል አድርጐ «የስልኩ ጭቅጭቅ ስለምን ነበር ?» ሲል ጠየቀው ። «እሱን አታንሳው ። በዚህ የሥራ ጉብኝት ውስጥ እሾርባዬ ውስጥ ያጋጠመኝ አንድና አስቸጋሪ የሆነ ፀጉር ! » አለ።«ማለት ሁሉ ነገር እንደከረከሙት ሁሉ እየተስተካከለ ሲመጣ… እንዳሰብነው ፣ እንደፈለግነው ሲሆን . . . ርግጠኛ ነኝ ሪፖርቱ ሲቀርብ እናትህ ተፍነክንካም አታበቃ… አንድ ነገር ግን አሻፈረኝ አለ። ርግጥ ነው ፤ አልሳካ ያለው ነገር ይህን ያህል ትልቅ ችግር የሚባል አይደለም ። የኔ ሃሳብ ግን ሙሉ ስኬትን ለመፍጠር ነበር ።»
«እንዴት ነው ፤ ነገሩ ምን ይሆን እያልኩ መጨነቅ ልጀምር ወይስ?»
«አያስፈልግም ። ተሸወድኩ ልበልህ…. እንዴት መሰለህ አንዲት አርቲስት አጋጠመችኝ። ፎቶ ግራፍ አንሺ ናት ። ማለቴ ግዙፍ ችሎታ ያላት ፍጡር…. ማይክ እንዲህ ተራ ነገር እንዳትመስልህ ። ኤግዚቢሽን ታሳይ ነበር ። ኤግዚቢሽኑን ተመለከትኩት። ባለፈው ጊዜ በሕንፃ ማስጌጡ ሥራ ላይ ፎቶግራፎችን መጠቀም እንደሚቻል ሰብሰባ ላይ የተስማማንበትን አስታወስኩ። ልቀጥራት ፈለግኩ »
« እሺ?»
« ነገርኳት ››
«‹ መልሷ!? »
«አንገቴ ይቆረጣልንጂ ያንተን ስራ አልነካውም አለችኝ ። እንነጋገርበት አልኳት ። አይሞከርም አለች »
«ምን ምክንያት ሰጠችህ?... የኪነጥበብ ስራዬን ለገንዘብና ለንግድ አላውልም ነው ወይስ ሌላ ?»
«ምኑም ምኑ ሊገባኝ አልቻለም። ገና ነገሩን ሀ ብዬ ሳነሳ ጅራቷን ሸጉጣ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ጀመረች። ልታስጠጋኝ አልቻለችም» ማይክ ጅሎ በሚል አስተያየት እየተመለከተው ፣

«ነገሩ አይገባም አልክ? ግን ግልጽ ነው።» እምቢ ያለችህ በከንቱ አይምሰልህ ። ኮተር ሂልያርድ ምን ያህል ግዙፍ ድርጅት እንደሆነ ታውቃታለች ማለት ነው ። እምቢታዋ የሚታየው በርካታ ገንዘብ ይሰጥሻል እስክትባል ነው ። ለመሆኑ ይህን ያህል አሪፍ ናት?»
‹‹ተወዳዳሪ የላትም ስልህ ። ምን አለፋኝ እኔን ፤ ከፎቶግራፎችዋ ጥቂቶቹን ለናሙና ያህል ይዤ መጥቻለሁ አደል እንዴ ታያቸውና ራስህ ትፈርዳለህ »
«እንዲያ ከሆነ የፈለገችውን ማግኘት ትችላለች። የለም ፎቶግራፎቹን በኋላ እናያቸዋለን ። አሁን ለአንድ ጉዳይ ላነጋግርህ ፈልጌ ነው የመጣሁት » ማይክል ይህን ሲል በቁም ነገር ነበር። ነገሩን ለቤን ለመንገር ብዙ ጊዜ አስቦበታል ። «የሆነ ጥፋት ኣለ?»
«የለም… ምንም ጥፋት የለም ። እንዲያውም ይህን ጥያቄ ሳነሳብህ ምን ያህል አካባቢየን ማየት የማልችል አጋሰስ ነኝ የሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው። ሆኖም ደህና ማለት ከዌንዲ ጋር የሆነ ግንኙነት ፈጥራችኋል?»

ለዚህ ጥያቄ መልስ ከመስጠቱ በፊት ቤን አቭሪ የማይክልን ፊት በደንብ አድርጎ መመልክት ጀመረ ። ማይክል የማወቅ ፍላጐት ያደረበት እንጂ ፈጽሞም የተቀየመ አይመስልም። ርግጥ ነው ቤን ስለማይክልና ስለዊንዲ ግንኙነት በሚገባ ያውቃል ። ግን ደግሞ ማይክል ለዌንዲ ደንታ እንዳልነበረውም ያደባባይ ምስጢር ነው። ቢሆንም አሁን ሲያስበው ፤ በተለይም ከማይክል ጋር ከዚህ በፊት በዚህ ዓይነት ተገጣጥመው ስለማያውቁ እና ማይክ ይህ መሆኑን ሲገነዘብ የሚሰማውን ስሜት መረዳት ስላዳገተው ቤን አቭሪ ተጨነቀ ። ጓደኛው የቀመሳትን ፤ ቢተዋትም የሱ የነበረችን ሴት መውሰድ መልካም እንዳይደለ ገባው። ያም ሆነ ይህ እውነቱ እውነት ነው። ዌንዲና ቤን ይፋቀራሉ። ስራቸው አንድ ላይ በመሆኑም አንድ ላይ ይጓዛሉ ። ባለፉት ወራት በሳንፍራንሲስኮና በሎስ አንጀለስ ሲሰሩ ባልና ሚስት ሆነው ነው ያሳለፉት ። እንዲያውም ቤን የጫጉላ ቤታችንን ጊዜ በማሳለፍ ላይ እንገኛለን እያለ ሲቀልድባት ነበር ። « አልመለስክልኝምኮ » አለ ማይክል ። ቤን አቭሪ ከሃሳቡ ብትት ብሎ ነቃ ። «አስቀድሜ ባለመንገሬ ጅልነቴ ተሰማኝ ። መልሱ ግን ፤ እዎ ነው ። ቅር ይልሃል ማይክ !?»
👍13
‹‹ምኑ ነው ቅር የሚለኝ ? እንዲያው የኔ ነገር ገርሞኝ ነው እንጂ ምን ያህል ማየት እንደማልችል ማለት አዎ...»
«ምን ዓይነት እንክብካቤ አደርግላት እንደነበር ዌንዲ ሳትነግርህ አልቀረችም…» ስለዌንዲ ሲናገር ድምጹ ትንሽ መረር ያለ ነበር ። ቢሆንም ቤን እንዲህ ሲል በለሆሳስ መለሰለት ፤ « የለም ማይክ ። ዊንዲ ስላንተ ምንም ነገር ነግራኝ አታውቅም ። ካነሳችህም ደስታ የሌለህ ሰው እንደሆንክ ከመናገር አልፋ ሌላ አትጨምር ። በነገራችን ላይ የሆነው ነገር በሁለታችን መሀል ምንም ነገር ሊፈጥር አይችልም ብዬ አምናለሁ ። አይመስልህም እንዴ?» ማይክ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ ። «እንዴት መሰለህ ? » አለ ቤን «በላይህ ላይ አልተደረብኩም ፤ እዚህ ላይ እንድታምንልኝ ያስፈልጋል ። እንዲያውም የጀመርነው ካንተ ጋር መውጣት ካቋረጣችሁ ከስንትና ስንት ጊዜ በኋላ ነበር ። በነገራችን ላይ ዌንዲን ገና ካንተ ጋር ግንኙነት ሳይፈጠር ጀምሮ ልቤ ይከጅላት ነበር ። «እሱን ያህል ንኳ እኔም ሳልጠረጥር አልቀረሁም ፣ ገና ስራ ስትቀጥራት ጥርጣሬ ነበረኝ ። እና ደግሞ ዌንዲ እንዴት ያለች ግሩም ልጅ ነች መሰለህ ። እኔ በበኩሌ ለኔ አትግባም እላለሁ ። ላንተም ሳትተርፍብህ አትቀርም . . ቆይማ ቤን? »
«እህ ? »
«ፍቅር ነበር ያልከኝ ፤ ማለት ጠንካራው ፍቅር ይሆን እንዴ?››
«ይመስለኛል»
«አረ በሥላሴ ! እውነትኽን ነው ? ለመጋባት አስባችኋል ? » ሁሉ ነገር እንግዳ ሆነበት ። ቤን አቭሪን ፍቅር ሲይዘውና ማግባት ሲያስብ ። «ገርሞኝም አያበቃ ። ቤን አቭሪ ሚስት ሲያገባ ! ግን እውነትህን ነው ?» አሊ ማይክ ። «እርግጠኛ ነኝ አላልኩም ፤ ግን ደግሞ ሁለታችንም ስለ መጋባት እያሰብን ነው ። አዝማሚያውን ሳየው ሳንጋባ አንቀርም። ተቃውሞ አለህ !» ቤን አቭሪ ተቃውሞ አለህ ? ሲል የጠየቀው ለቀልድ እንደሆነ ማይክ ገብቶታል ። ከተነጋገሩበት በኋላ የነበረው ፍርሐትና ይነሳ ይሆን የተባለው አለመግባባት ቦታ አልነበረውም ። ቦታቸውን ለሁለቱ ጓደኝነት ለቀው ሄደዋል ።

«ተቃውሞ? ቅንጣት ታክል ተቃውሞ የለኝም» አለ በፈገግታ «ግን ስላንተ የማውቀውን ሳስብ እዚህ ጋ አንድ የተዘለለ እዚያ ደግሞ ሌላ ያልታየ . . . ገባህ ያየሁ መሰለኝ ። ወይስ ይህን ያህል ሚስጥር ቋጣሪ እምትሆንበት ጊዜ አለ? »
«አይደለም ። ልደብቅህ ያሰብኩት ነገር ንኳ አልነበረም ። ግን አንተ በስራ ስለተጠመድክ የሚሆነውን ሁሉ ማየት አልቻልክም። ስራ ብቻ ሲሆንና አልፎ አልፎ ንኳ ጨዋታ ከሌለ ርግጥ በሙያህ የተባረክና የበለጸግህ ትሆናለህ . . . ግን ደግሞ በቢሮ አካባቢ የሚናፈስ ወሬ ያመልጥሃል » አለ ቤን ። ይህም ከፊል ቀልድ ነበረበት ። «አንተ የማትረባ ጅል ! የሆነውን ሁሉ ነገር አስቀድመህ ልትነግረኝ ይገባ ነበር ።››
«እዚያ ላይ ልክ ነህ። ጥፋተኛ ነኝ ።ጥፋቴንም አምናለሁ፡፡ ለወደፊቱ ግን ወሬ ሲያጋጥመኝ ወዲያውኑ ሪፖርት ልማድረግ ዝግጁ ነኝ ። እንዲያውም ካነሳነው ዘንዳ እኔ ዌንዲ ስንጋባ አንተሚ...» አለና ነገሩን ገታ ። ማይክልና ናንሲ ሊጋቡ የነበረ እለት ቤን አቭሪ የማይክል ሚዜ ሊሆን ነበር )፤ ሳይሆን ቀረ ። ሚዜ ትሆነኛለህ ሊለው ሲል ያ ትዝ አለው። «ምንም አይደለም አይዞህ ። ጊዜ ስላለህ ሁሉንም ቀስ እያልን እንጫወተዋለን » አለ ማይክ ።

ይህን ብሎ ከምቹው የእንግዳ ማረፊያ ሶፋ ላይ ተነሳና ቤንን ለመሰናበት እጁን ዘረጋለት ። ፊቱ ቅጭም ብሎ ነበር « ቤን ምን ሊል እንዳሰበና ለምን ሊናገረው የነበረውን በጅምር እንደተወው ገብቶታል ። እንደምንም ፈገግ ብሎ «ለወግ ማእረግ በመብቃትህ እንኳን ደስ ያለህ» አለ ማይክ ። ይህን ሲል ግን ፈገግታው ከልቡ የፈለቀ ልባዊ ምኞትን የሚገልፅ ብርሃን ሆነ ። ቀጥሎም… «ስለ ፎቶግራፍ ጠቢቧ ግን ይህን ያህል አትጨነቅ ። ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ ስላገኘሃት ሴት ማለቴ ነው ። ለናሙና ያመጣሃቸውን ፎቶግራፎች ካየን በኋላ እንደተናገርክላት ድንቅ ስራ የምትሠራ ሆና ከተገኘች ገፋ ያለ ገንዘብ የሚያስገኝላትን ኮንትራት እናቀርብላታለን ። ገንዘብ የማያሸንፈው የለም አደል? ያኔ እጅዋን ትሰጣለች ። መጨነቅ አያሻም» አለ። «እንዳልከው ቢሆን እኔም ደስ ይለኝ ነበር»
«እመነኝ ከዚህ አያልፍም » ማይክል ይህን ብሎ ቀልጠፍ ያለ ስንብት ካቀረበለት በኋላ ከቤን ቢሮ ወጣ ። ቤን አቭሪ ግን ማይክ ከክፍሉ ውስጥ ሳይወጣ ነበር ስለዌንዲ ያቀረበለትን ጥያቄ ማሰላሰልና በጠቅላላ ስለተነጋገሩት ነገር ሁሉ ማሰብ የጀመረው ። እንኳን ሁሉን ነገር አወቀ ። አሁን ቀለል አለኝ አስቀድሜ ብነግረው ኖሮ ነገሩ ሁሉ ከዚህም በላይ ያማረ ይሆን ነበር አለ በሃሳቡ ሃሳቡ ወደ መጨረሻዋ ጥያቄው ዘለለ ። ምን ዓይነቱ ሰው ነኝ! አንድ ነገር ከመናገሬ በፊት ማሰብ ነበረብኝ ። የናንሲን ጉዳይ ሲያነሱበት ማይክል ምን እንደሚል እያወቅኩ እንዴት ያን ጥያቄ ላነሳ ቻልኩ? ርባና ቢስ ሰው ነኝ። ለነገሩማ ከማይክል ሌላ ለሚዜነት ማንን ልጠይቅ ኖሯል ። ሆኖም ማሰብ ነበረብኝ፡፡ ይህን ሁሉ አሰበና በአዘኔታ ራሱን ነቀነቀ። ሰዓቱን አዬ ። ጊዜው እንዴት ነው የሚበረው። ወደ ስብሰባ መግቢያ ሰዓት ደርሶ የለም እንዴ... ሙሉ ሰዓት እንኳ የለውም ። ስራውን ጀመረ ።

የቢሮው በር ሲንኳኳ ቅፅበት ያለፈ አልመሰለውም ። ዌንዲ ነበረች። እደጃፍ ላይ እንደቆመች እንውጣ የሚል በብሩህ ፈገግታ የታጀበ የአንገት ጥቅሻ እያሳየችው… «ጌታው አሁኑኑ እክብርት ሥራ አስኪያጅ ቢሮ መገኘት ያለብን መሆኑን እንዳይረሱ» አለች ። «ሰዓት ደረሰ?» አለ ቤን በመገረም ሰዓቱን እያዬ ። ከዚያም ዌንዲን ተመለከታት ። ሲያያት የሠራ አካላቱን ደስታ አለበሰው፡፡ አለባበስዋ ፤ ፈገግታና ሁለንተናዋ የሚወዳት(በሃሳቡ የሚያያት ፤ እንዳትለወጥ የሚሳሳላት ዌንዲ ሆና ነበር የቀረበችው ። «በነገራችን ላይ ለማይክ ነገርኩት» አለ በእርካታ እፎይታና በፈገግታ ፤
«ምኑን?»
«ስለኔና ስላንቺ ነዋ ጅሎ ፤ ነገሩ እንዲህ በመሆኑ ደስ ያለው ይመስለኛል » ።
‹‹እንኳን ነገርከው ። ደስ አለው ስትለኝ ደግሞ እኔም ደስ አለኝ» ዌንዲ ይህን ሁሉ ያለቺው ቤን ደስ እንዲለው በማለት ነው እንጂ እስዋ በበኩሏ ግን ማይክል ሰማ አልሰማ! ተደሰተ ተከፋ ግድ የላትም። ለሷ ማይክል ሂልያርድ የሚባል ሰው የለም፤ ስትፈልገው ሲሸሻት በስጋ አብሯት ተቀምጦ እንኳ በመንፈሱ ሲርቃት ምን ያህል እንዳቆሰላት የታወቀ ነው ። የለም አብርው ሆነው የሚያውቁም አይመስላትም ።


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍155🥰2
Forwarded from ከፖስቱ ኮሜንቱ
❤️ፍቅር ምክንያት አይፈልግም😍 ምክንያት የሌለው ፍቅር ረዥም ጊዜ ይቆያል መልክሽ አይቶ ያፈቀረሽ መልክሽ የጠፋ እለት የእሱም ፍቅር አብሮ ይጠፋል።🌿❤️🌿❤️🌿❤️
👍3
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከሎ ከተቀመጠበት ስፍራ ላይ ጕልበቱን ሰብሰብ አድርጎ በመታቀፍ ከንፈሩን እያኘከ የሚተነፍገውን የወይጦ በረሃ የእፅዋት
ሽታ ይምጋል ከየጉድባው ወጥተው ድብልቅልቅ በሚያደርግ ድምፅ የሚያገሱት አንበሶች፣ በቀጭንና ወፍራም ድምፅ ጨለማን ተገን አድርገው ድምፃቸውን በነፃነት የሚያስተጋቡትን የአራዊት
ትርምስ እያዳመጡ ሁለቱም በሐሳብ ተውጠው ቆዩ"

ከዋክብት ሰማዩ ላይ ሆጨጭ ብለው ብርሃናቸውን ብልጭ
ድርግም ሲያደርጉ፣ ገና የተወለደች ጨረቃ ካለአቅሟ ግዙፉን
ጨለማ ከዝሆን ጋር እንደሚታገል ዝንብ በብርሃን ድል ለማድረግ
ከተራራው አናት ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ፣ በበረት የታጎሩት ከብቶች እያመነዠኩ ሲያቃስቱ፣ ካርለትም ሆዷ እየተሸበረ፣
በምትፈጥረው ወኔ ግን እራሷን እየደለለች እንደ ከብቶች ላይ ላይ
እየተነፈሰች ታቃስታለች።

የወይጦ በርሃ በተለይም በቀትር ላይ ሙቀቱ እንደ ደመራ እሳት ይጋረፋል" የአራዊቱና የእፅዋቱ አካል ሳይቀር በሙቀቱ ስለሚቀረና አካባቢው ለየት ባለ ሽታ ይታፈናል" በዚህ ወቅት እንግዳ ሰው እንደ
ውሻ እያለከለከ የሚስበው አየር ፍለጋ አፍንጫውን እንደ አንቴና አቁሞ ያንጋጥጣል። ሆኖም ግን የፀሀይ ማኅበረሰብ፣ ሰጎን፣ አንበሳ፣ የሜዳ ፍየል፣ ጉርኑክና የመሳሰሉት እንስሳት በደስታ ተዝናንተው
ይኖሩበታል።

የወይጦ በረሃ ግለት እየቀነሰ ሲመጣ የፀማይ ማኅበረሰብ አባላት
ከማሳ፣ ከወንዝ፣ ከከብት ጥበቃ፣ ከአደን፣ ከማር ቆረጣ፣ከመንገድ...
ወደየመንደሩ ሲከት፣ ከተለመደው ውጭ ነጭ መኪና፣ ጸጕሯ ረዘም ያለ ነጭ ሴት፣ ልብስ የለበሰ ጠይም ከተሜ መንደራቸው
ውስጥ ድንኳን ከትመው አገኛቸው" በዚያን ወቅት፣ ድፍን የፀማይ ኗሪ ስልክና ሌላ መገናኛ ባይኖርም የሰማው ላልሰማው መልእክቱን በቃል እያስተላለፈ፣ ቤት ለቤት የሚውሉ ሽማግሌና ባልቴቶች ሳይቀሩ «ነጭ በቆሎ» የመሰለችውንና ብልጭልጭ ቅራቅንቦ
የተቀረቀበባትን መኪና፣ ለማየት ጎረፉ።

በካርለት ጸጕርና እጅ ላይ ብዙ የፀማይ «ተመራማሪ» እጆች አረፉበት እንደ አንበሳ ጐፈሬ የለሰለሰ ጸጕር፣ እንደ እብነ በረድ የነጣና የለሰለሰ ገላ፣ የትንባሆ አጢያሽ የመሰለ ጥርስ ሲመለከቱ፣
«ይህች ሰው ምንድ ናት?» ብለው ሲደነቁ ቆዩ። ከመካከል አንዱ፣
«ፈረንጅ ናት» አለ፣ ነቃ ያለው።

«ፈረንጅ...ኡ» አሉ፣ በአድናቆት አፋቸውን እየያዙ“

«አሃ ፈረንጅማ ከሆነች ያች በፍየልና ማር ከነጋዴ
የምንለውጣት የሽጉጥ ጥይት የመሰለችው የፈረንጅ መድኃኒት ትኖራለች» ተባባሉ እርስ በእርሳቸው ከሎ ሆራ ፀማይኛ አይችልም
አንዳንድ ፀማዮች ግን ሐመርኛ ስለሚችሉ መድኃኒቷን እንድትሰጠን
ጠይቅልን አሉት፥ ለምልክት አንድ የ«ቴትራሳይhሊን» እንክብል እያሳዩት" ፀማዮች ካርለትና ከሎ ቋንቋቸውን ባለመቻላቸው በተለይ
ሴቶችና ጎረምሶች ግራ ገብቷቸዋል፣ «ሆሆይ ለካ እናንተዬ ፀማይኛም የማይችል ሰው አለ!» ብለው ተሳልቀዋል።

በዚህ መልክ ራቁታቸውን የሆኑ ሕፃናት፣ ጎረምሳና አዋቂ ወንዶች ግልድም ያገለደሙ፣ ከወገባቸው በታች የለበሱት ቆዳ
መሬት ለመሬት የሚጎተት ትንሽ እንጨት ያለበት ሴቶች ካርለትን እንደ ጉድ ተመለከቷት እሷም እነሱን በተመስጦ እየተመለከተች
የሁለት ወገን ጉዶች ካለ ቋንቋ በጥቅሻ ሲነጋገሩ፣ አንዱ ሌላውን ለመግባባት ሲጣጣር ቆይተው የምሽቱ የአራዊት ትርምስና ጨለማ
ሳያሸብራቸው በየአቅጣጫው በመሄድ ቀስ በቀስ ተበታተኑባት"።

ካርለት፣ hአዲስ አበባው ሒልተን ሆቴል ወደ አርባ ምንጩ በቀለ ሞላ ሆቴል፣ ከአርባ ምንጩ ሆቴል ወደ ድንኳን አዳር እየወረደች
የምትበላውም መጠኑና ዓይነቱ በጣም እየቀነሰ
ቢመጣም፣ በጣም የተቸገረችበት ጉዳይ ሌላ ነበር። እስከ አሁን
እንዳስተዋለችው ፀማይ መንደር ውስጥም ሆነ መንገድ ላይ ሽንት ቤት አላየችም። ለመጸዳዳት ወደ ጫካ ሲገቡ ተመልhታለች" እሷ ደግሞ ጫካ ሄዳ መጸዳዳቱን ሕሊናዋ ሊቀበለው አልቻለም" በጕዞዋ ባሳለፈችው ቆይታ በሶፍት እየተጸዳዳች በማቃጠል፣ እየተጠቀመች
ነው። ሐመር ስትሄድ ግን በዚሁ መልክ መቀጠል የሚቻላት አይሆንም" ሽንት ቤት አስቆፍራ እንዳትጠቀም ለአካባቢው እንግዳ ሁኔታ በመፍጠሯ መልካም ግንኙነት ላይኖራት ነው“ ስለዚህ ሊታይ
በማይችልና መጠነኛ ጥልቀት ባለው ጉድጓድ መጠቀሙን እያሰበችበት ነው።

በእርግጥ እንኳን ካደጉበት ባህል ውጭ ላተወሰነ ጊዜ
ከተከታተሉት ባህልን ለየት ወዳለ ሲገባ የመጨነቅ ስሜት መፈጠሩ
የነበረ ነውና ካርለትም የኢንግላንድ ዘመናዊነት፣ የለንደን ከተማ፣
ማንችስተር የሚገኙት አያቶቿ፣ የወንድና ሴት ጓደኞቿ፣ መዝናኛዎች፣ የጭፈራ ቦታዎች ቀርተው ራቁታቸውን ከሚሄዱ ጥቋቁር ሰዎች፣ ከከብቶች በረት፣ ከፍየልና በጎች ጋጥ አካባቢ መሆንዋ
ሕልም እንጂ እውን ሊመስላት አልቻለም።

ካርለት ወደ ኢትዮጵያ ለጥናት ከመምጣቷ በፊት የአገር ቤቱን ሕይወት ለመለማመድ ወደ ስፓኝ በመሄድ «የስፓኝ በር» ተብላ በምትታወቀው የሁልቫ ከተማ የበጋ መዝናኛዋን በማድረግና ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በብርቱካንና የሱፍ ማሳ አቅራቢያ ተቀምጣ ፀሐይ ላይ ብዙ መቆየት፣ ብርድና፣ ብቸኝነትን ለመለማመድ ሞካክራ ነበር።ያን ጊዜ የወደፊት የጥናት ቦታዋ በአሥር እጅ ከዚያ ሊለይ
እንደሚችል ብትገምትም አሁን ግን ዘጠና ዘጠኝ እጅ ያላሰበችውና
ያልገመተችው ዓይነት ሆነባት"

ካርለት እንዲህ በሐሳብ ጉና ስትንጨዋለል፣ እያንቋረረ
የሚከፈተውን የከሎን ጕሮሮ ስትሰማ ከሰመመኗ ተመለሰች።ከዚያም ዓይኗንና ሕሊናዋን ወደ እሱ መለሰች።፣

እስከ አሁን ከከሎ ጋር ባደረገችው ቆይታ ካላናገሩት የማይናገረው ጥቁሩ ወጣት በራሱ ፍላጎትና አነሳሽነት፣ ሊያወጋት መዘጋጀቱ ሳያስደንቃት አልቀረም።
«ሚንጊ ነኝ» አለ ከሎ ድንገት።

«ምን?» አለች ካርለት፥ የጠቀሰው ቃል አልገባሽ ብሏት

«ሚንጊ ማለት በሐመር ቋንቋ ገፊ ማለት ነው» አሁንም የባሰ ተደነጋገረችI ስለዚህ፣ እንዲግባቡ ለማድረግ ገለጻውን ሰፋ አድርጎ ጀመረ።

«ሕፃን ልጅ በሽማግሌዎች ፈቃድ ይወለዳል።»

«ካለ ሽማግሌ ፈቃድ መውለድ አይቻልም? ለመውለድ የሽማግሌዎችን ፈቃድ እንዴት ይጠየቃል? ሽማግሌ የተባሉት ልዩ
ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው?» ካርለት ልጅ ለመውለድ ሲያስፈልግ የሐኪም፣ ካስፈለገም የሥነአእምሮ ጠቢብ ምክር
ሊጠየቅ እንደሚችል ታውቃለች" ይህም ቢሆን ችግር ያለባቸውና
በማኅበራዊ ጠንቅ ውስጥ እንዳይዘፈቁ የሰጉ ሰዎች የሚፈጽሙት እንጂ ለማንኛውም ዜጋ የተደነገገ ሕግ አይደለም" ሆኖም፣ ሽማግሌ የተባሉት ለየት ያለ ችሎታ ያላቸው ይሆናሉ ብላ ገመተች።

«አንችን ለማስረዳት ለኔ ከባድ ነው" በኋላ ቀስ በቀስ
ልታውቂው ትችያለሽ ሽማግሌ የተባሉት ግን በዕድሜና በልምድ
ተደማጭነት ያላቸው ሲሆኑ ማንም የሐመር ማኅበረሰብ ሴት ባሏ ጥሎሽ ጥሎ እሱ ዘንድ ካመጣት በኋላ አንድ ቅል አሸዋና አንድ ቅል
ወተት ይዛ ወደ ክልሉ ሽማግሎች ዘንድ ትሄድና ትመረቃለች"ከዚያም ወተቷን ትሰጥና አሸዋውን የያዘውን ቅል ቤቷ አምጥታ
ግርግም ላይ ታንጠለጥለዋለች" ከዚያ፣ ከባሏ ጋር የግብረሥጋ
ግንኙነት አድርጋ ፅንስ ከፀነሰች፣ ወደ ሽማግሎች ሄዳ መፀነሷን ታስታውቃለች። አንዴ መፀነሷን ሽማግሎች ከሰሙ፣ ባሏና እሷ
ፅንሱ አድጎ ከተወለደ በኋላ ጥርስ ማብቀል እስኪጀምር ድረስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አይፈጽሙም።»
👍30
«ኦ እስከ መቼ?» ካርለት በጣም ገረማትI ለምሳሌ እሷ ከስቲቭ ከተለያየች ጥቂት ቀናት ሆኗታል" ግን ብዙ ጊዜ የቆየች
ያህል የወሲብ ረሃብ እየሞረሞራት ነው፣ «እርግዝናስ እንዴት ግንኙነትን ይከለክላል? ያውም ልጅ ተረግዞ፣ ተወልዶ፣ ጥርስ
እስኪያበቅል እንዴት ይቻላል?» በማለት ተደነቀች።

«የሐመር ወንዶች ሚስት የሚያገቡት ሀብታም ለመሆን ነው"ማንም የሐመር ወንድ ሚስት ሲያገባ ለጥሎሽ ከብት፣ ፍየል፣ በግ፣ ማር ለጮኛው አባት ይከፍላል" ለጥሎች የሚከፈለውን የገንዘብ
ጥሎሽ የሚያሟላ የሐመር ወንድ ከሁለት በላይ ሚስቶችን እንደ ሀብቱ መጠን ሊያገባ ይችላል" ብዙ ሚስት የማግባት ዕድል ያገኘ ደግሞ ቶሎ ሀብታም ለመሆን አጋጣሚው የሰፋ ነው። ምክንያቱም ሴት ከተወለደች አባቷ የከፈለውን ጥሎሽ ታስመልሳለች" ወንድ
ልጅ ከተወለደም ልጁ የአባቱ መከታ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ሲጐረምስ ከአጎራባች ማኅበረሰቦች ከብት ዘርፎ ያመጣልI አድኖ ሥጋ ያበላል" በአጠቃላይ ብዙ ሚስት ያለው ብዙ ልጅ ሊኖረው ስለሚችል የሀብቱ መጠን የበዛ ይሆናል" ስለዚህ ማንኛውም የሐመር ወንድ
ሀብታም ለመሆን ጥርሱን እየነከሰ ከሁለት በላይ ሚስት ያገባል"

«ኦ! ታዲያ በባልና ሚስቱ መካከል ፍቅር የለም ማለት ነው?»ካርለት በአስደናቂ ወሬው ተመስጣ መልሱን ለመከታተል አቆበቆበች።

«ፍቅር አለ፣ የለም ማለት ይከብዳል" በሐመር ባህልና ደንብ ባል ለሚስቱ የፍቅር ምልክት ማሳየት፣ ማውራት፣ ተቃቅፎ
መተኛት አይፈቀድለትም" ወንድ አንበሳ ነው ኩሩ" እንዲያውም በወጉ መሠረት በተገናኙ ቁጥር ፊቱን ማዞር፣ መቆጣት፣
መደብደብና ወንድነቱንና የበላይነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል"ለምሳሌ ባል ጥሎሹን ከፍሎ ከጨረሰ ወይም ካገባደደ በኋላ ሚስቱን እናቱና የመንደሩ ሴቶች ሄደው ያመጧታል ሙሽራዋ ጸጕሯን
ትላጭና ቅቤና ከሰል ሰውነቷን ተቀብታ ቆጥ ወይም በሐመርኛ
«ሻላ» ላይ ከባሏ ተደብቃ ለሦስት ወራት ትቀመጣለች" ሁሌም ባሏ
ሲመጣ ቆጥ ላይ ወጥታ ካልተደበቀችና ፊት ለፊት ካገኛት ይደበድባታል" ተው ባይ የለውምI ባህል ነው።
«ቆጥ ላይ ለሦስት ወራት ስትቀመጥ የሥራ ድርሻዋ ሌሊት ሌሊት እየተነሣች የፍየልና በጎችን በጠጥ መጥረግና ሸፈሮ ቡና
አፍልታ፣ ከመንጋቱ በፊት ሌሎች ሴቶችን ቀስቅሳ መደበቅ ነው ቅቤና ከሰል ሰውነቷን በየጊዜው የምትቀባውም ለባሏ ውብ ሆና እንድትቀርብ በማለት ነው።

«ሦስት ወር ከሞላት በኋላ ሙሽሪት ባሏ ከሚተኛበት ቁርበት ግርጌ በቆሎ በተን ታደርጋለች የተበተነው በቆሎ ለግብረ ሥጋ
ግንኙነት ዝግጁ ነኝ ማለት ሲሆን ሁኔታውን የተረዱ ቤተሰቦቿም አካባቢውን ተወት አድርገው ይሄዳሉ" በዚህን ጊዜ ባል እየተጀነነ
ሄዶ ይተኛል" ሙሽራይቱም ቀስ እያለች ሄዳ ከጀርባው ጋደም  ትላለች  ከግንኙነት በኋላ ደግሞ ሚስት እንደ አስፈላጊነቱ ጥፊዋን
ቀምሳ ትሄዳለች" ባል ከመኝታው ሲነሣም ሚስቱ ከፊት ለፊቱ ተንበርክካ አንገቷን በመቀልበስ እጇን ዘርግታ ትንባሆ ትሰጠዋለች
ባልም ፊቱን ዙሮ ተቀብሏት ይወጣል" ስለዚህ፣ በሐመር ባህል ወንድ ምን ቢወዳትም የፍቅር ምልክቱ ቁጣና ዱላ ነው። »

ካርለት በሕሊናዋ አንድ ነገር ለማመሳሰል ሞከረች፤ የከሎን ጅንንነት ምንጭ የተረዳች መሰላት። የጣማት ታሪክ እስኪያልቅ ግን
ሌላ ነገር ማሰብ አልፈለገችም። ስለዚህ፣ «ከዚያስ?» አለችው
እሱም ጨዋታውን ቀጠለ።
«እናም መውለድ እንድትችል በሽማግሎች ከተመረቀች በኋላ
ጨረቃንና ከዋክብትን በማየት አልፎ አልፎ ግንኙነት ያደርጉና
ማርገዟን በሽማግሎች በኩል ባል ካረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ልጅ
ወልዳ፣ ልጁ ጥርስ እስከሚያበቅል ድረስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት
አይፈጽሙም ሽማግሎች ሳይመርቋት ብታረግዝ ግን «ውታ» (ያልተፈለገ) ተብሎ እንድታስወርድ ይደረጋል"
«ባሏ ስሜቷን አይጠብቅማ? ማለቴ ስሜቷ አያስቸግራትም?
እንዴት ሁለቱም ለረጅም ወራት ስሜታቸውን ሊቆጣጠሩ ይችላሉ?
ኦ! ልጅ ተወልዶ ጥርስ እስከሚያበቅል? ለምንስ ደግሞ…» ካርለት
ለምትሰማው ነገር ምክንያት ፈጥራ ራሷን ለማሳመን ቸገራት" ወሲብ ለእሷ የትክክለኛ ሕይወት ትርጓሜ ነው" ሕይወት ያለ ፍቅር፣ ፍቅር ደግሞ ያለ ወሲብ ከሁሉም የከፋ መራራ ነው"
«የሐመር ወንዶች ኢቫንጋዲ› በተባለው የምሽት ጭፈራ ባል
ካላገቡ ልጃገረዶች ጋር ስለሚጫወቱ ስሜታቸውን የማርካቱ ዕድል አላቸው" ማንኛውም ለጭፈራ የደረሰች ልጃገረድ ካለገደብ
በኢቫንጋዲ መካፈልና የግብረሥጋ ግንኙነት መፈጸም መብቷ ነው
ያውም በግዴታ ሳይሆን በራሷ ፈቃድ" ክብረ ንጽሕናሽን አስወሰድሽ፣ ባለግሽ ብሎ አተካራ የሚገጥማት ሰው በወደፊቱ ሕይወቷና ሕልውናዋ አያጋጥማትም" ብታረግዝም ልምድ ባላቸው
ሰዎች ፅንሱን በማስወረድ፣ እጮኛ እያላት ቢሆንም እንኳ መዝናናቷን ትቀጥላለች" አንድ ወንድ ሚስት ለማግባት የሚጠየቀው ጥሎሽ የዋዛ ስላልሆነና በሁለትና ሦስት ዓመት ለመክፈል
ስለሚከብድ ከሞላ ጎደል የወጣትነት ጊዜዋን ባል አልባ ሆና ስለምታሳልፍ፣ ልቧ ካማረው ጐረምሳ ጋር ስታዜም፣ ስትጨፍር፣
ስትዳራ ትታያለች

«ባሏ ጥሎሹን ከፍሎ ከጨረሰና ሚስት ወደ ባሏ ከሄደች በኋላ ግን የባሏ የግል ንብረት በመሆኗ በራሷ ፍላጎት ሳይሆን በባሏ ትእዛዝ መኖር ትጀምራለች በምሽት ጭፈራ አትካፈልም በጨሌና አንባር
እንደ ልጃገረድነቷ ወቅት አታጌጥም የምትለብሰው የፍየል ቆዳ ጭኖቿን እንዲያሳይ ሆኖ መሰፋቱ ይቀራልI ጸጕሯን በ‹አሰሌ›
አፈር ከቅቤ ጋር ቀላቅላ እየተቀባች መኖር ትጀምራለች ሚስት
ለባሏ የምታደርገው ቢኖር ከባድ ሥራ መሥራትና ልጅ መውለድ ብቻ ይሆናል"

«ወንዱ ግን አገባም አላገባም በጭፈራ መካፈልና ልጃገረድ
ማሽኮርመም ይችላል። ጥሩ የወላድ ቤተሰብ ካገኘም ለሚስትነት
ጥሎሽ በመክፈል የራሱ ያደርጋታል" ጥሎሽ መክፈሉን ከቻለ፥
ሁለትና ከዚያም በላይ የማግባት ዕድሉ የሰፋ ይሆናል" እንዲያውም
የመጀመሪያ ሚስቱ ብቻዋን ሥራውን ሁሉ ለመሥራት
ስለሚከብዳት ረዳት ለማግኘት እንዲያገባ ታደፋፍረዋለች" ስለዚህ
ሚስት ወደ ባሏ ከሄደች በኋላ ብታረግዝ ከወንድ (ከባሏ) ጋር ግንኙነት የምታቋርጠው ሴቷ እንጂ ባል ካለገደብ መዝናናት
ይቻለዋል" ካለ ሽማግሌ ፈቃድ የተወለደ ግን እንደ እርኩስ ስለሚቈጠር የማደግ ዕድል አያገኝም" የማስወረድ ዘዴውም ልምድ ያላቸው ሰዎች በማኅፀን ውስጥ ያለውን ፅንስ  ጭንቅላት ከውጭ
በኩል በመዳሰስ ሲያገኙ ጭንቅላቱን በሁለት አውራ ጣታቸው ውስጥ ደጋግመው በመጭመቅ...» ሲል ካርለት ፊቷ በስሎ የተበላሸ
ቲማቲም መሰለ፣ ከንፈሮቿ ተንገረበቡ፣ መላ አካሏ ራደ"....

💫ይቀጥላል💫
👍29🔥1
የከፋው ሰው ሲሞት
የደላው መች ቀረ
ሁሉም ተከታይ ነው
አስጠላም አማረ።
👍5714🥰4
#የሰው_ልክ

የሰው ልጅ ሁለት መደብ አለው
አንደኛ:- የጨቀየ ገላ አድፎ የተጣለው የመንጻት ተስፋ ያለው

ሁለተኛ:-ዕድፍ ኾኖ ሳለ እንዶድ ነኝ የሚለው።
👍29👏12
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት በሰማችው ተንገሸገሸች ‹‹በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው
የነገርከኝ፡፡ ለዚህ ነው እንደ ፍራንኪ ጎርዲኖ ያሉ ወሮበሎች የእጃቸውን
ማግኘት አለባቸው የሚባለው

ትንሽ ዝም ብለው ቆዩና ‹‹ኧረ ለመሆኑ በፍራንኪ ጎርዲኖ እና በክላይቭ መምበሪ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?,,

‹‹እንጃ እኔ አላውቅም›› አላት፡፡

‹‹ፔርሲ መምበሪ ሽጉጥ ይዟል ብሎ ነግሮኛል፡ ፖሊስ ሳይሆን አይቀርም››

‹‹እውነት! እንዴት?››

‹‹እንደዚህ አይነት ልብስ የለበሰው እንዳይታወቅበት ነው››

‹‹ፍራንክ ጎርዲኖን የሚጠብቅ ፖሊስ ይሆናል››

‹‹ለምን? ጎርዲኖ እንግሊዝ አገር ውስጥ ታድኖ የተያዘ አሜሪካን አገር እስር ቤት የሚወስድ ወንጀለኛ ነው፤ ከአይሮፕላኑ ዋጋ ውድነት አንጻር የእንግሊዝ ፖሊስ ኮሚሽን ገንዘቡን ገፍግፎ እስረኛ እንዲያጅብ ፖሊስ
የሚልከው ለምንድነው?››

‹‹አንተን ይሆን የሚከታተለው?›› አለች በጆሮው

‹‹አሜሪካን አገር ድረስ›› አለ ሄሪ ጥርጣሬ ገብቶት ‹‹ለሁለት የወርቅ
አምባሮች ሲል?››

‹‹ታዲያ እዚህ ለምን መጣ?››

‹‹አላውቅም››

‹‹የሆነ ሆነና የጎርዲኖ ጉዳይ ራት ላይ አባቴ ያሳየውን መጥፎ ባህሪ
የሚያረሳሳ ይመስለኛል፡››

‹‹ለምንድን ነው እንደዚያ የሆኑት አባትሽ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ፡

‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት እንደዚህ ሆኖ አያውቅም››
‹‹ከዚህ ቀደም የፋሺስት አስተሳሰብ አራማጆች አጋጥመውኛል አለ
ሄሪ ‹‹እነዚህ ሰዎች ፍርሃት አለባቸው››

‹‹እንደዚያ ነው?›› ማርጋሬት አባባሉ ያስደነቃት ከመሆኑም በላይ ሊሆን የማይችል ሆነባት፡፡ ‹‹ፋሺስቶች ሲያይዋቸው ሞገደኛ ይመስላሉ
ውስጣቸው የተረጋጋ አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ዩኒፎርም ለብሰው ላይ ታች
የሚሉት፡፡ በቡድን ሲሆኑ ነው ደህንነት የሚሰማቸው ዲሞክራሲ የሚጠሉት ለዚህ ነው፡፡ አየሽ ዲሞክራሲ የተለያየ አስተሳሰብ እንዲንፀባረቅ
ይፈቅዳል ገደብ አይጥልም
አምባገነንነትን ለምን እንደሚወዱ ታውቂያለሽ? ወደፊት የሚሆነው የታወቀ ስለሆነና የፋሺስት መንግስት በቀላሉ ለውጥ ስለማይደረግበት ነው››

‹‹አባቴ ኮሚኒስቶችን ወይም ጽዮናዊያንን ወይም የሰራተኛ ማህበራትን
ያለ ምክንያት አይደለም የሚጠላው እነዚህ ሐይሎች
ያንበረክኳታል ብሎ ይሰጋል፡››

‹‹ፋሺስቶች ሁልጊዜ ብስጩ ናቸው›› አለ ሄሪ፡፡

‹‹አባቴም እንዲሁ ነው  አያቴ ሲሞቱ ዕዳ ያለበት ርስት ነው ያወረሱት፧ እናቴን እስኪያገባ ድረስ ተቸግሮ ነበር የኖረው፤ከዚያም
ለፓርላማ አባልነት ተወዳድሮ ቢያሸንፍም በሩን አልረገጠም፤ አሁን ደግሞ
ካገሩ ተነቅሎ ተባረረ›› አለች፡፡

ማርጋሬት ‹ሄሪ ማርክስ ከቤተሰብ ጠፍቼ እንድሄድ ይረዳኝ ይሆን?› ስትል አሰበች አሜሪካ ከገቡ በኋላም እንዳሁኑ ይቀርባት እንደሆነ እርግጠኛ
አይደለችም፡፡ ‹‹አሜሪካ የት ነው ልትኖር ያሰብከው?›› ስትል ጠየቀችው።

‹‹ኒውዮርክ ቤት ተከራይቼ እኖራለሁ፤ አሁን እጄ ላይ ጥቂት ገንዘብ አለኝ፤ ሌላም ገንዘብ የሚገኝ ይመስለኛል፡››

ሄሪ ሁሉን ነገር አቅልሎ ነው የሚናገረው ‹‹ምናልባትም ለወንዶች ቀላል ይሆናል፡፡ ሴት ልጅ ግን ረዳት ያስፈልጋታል››

‹‹ናንሲ ሌኔሃን ስራ ልትቀጥረኝ እንደምትችል ነግራኛለች›› አለች፡
‹‹ሆኖም ወንድሟ ኩባንያውን ከወሰደባት የገባችልኝን ቃል ላትጠብቅ
ትችላለች››

‹‹ከፈለግሽ እኔ አግዝሻለሁ›› አላት፡፡

እሷ እንዲህ አይነት ድጋፍ ነው የፈለገችው

‹‹ትረዳኛለህ?›› ስትል
ጠየቀችው፡፡

ሄሪ ምን ሊያደርግላት እንደሚችል ግልፅ ባይሆንለትም ‹‹ቤርጎ ፈልጌ
አሳይሻለሁ›› አላት፡፡

ይህን ቃል ስትሰማ የተሰማት እረፍት ቀላል አይደለም፡፡

‹‹እግዜር ይስጥህ፡፡ እኔ በህይወቴ ቤርጎ ፈልጌ ይዤ አላውቅም፡፡››
‹የቤት ኪራይ ማስታወቂያ እናያለን››

በታይምስ ጋዜጣ ላይ እንዲህ አይነት ማስታወቂያ አይቼ አላውቅም››አለች አባቷ የሚያነቡት ይህን ጋዜጣ ብቻ መሆኑን አስታውሳ፡፡

‹‹ማታ ማታ የሚወጡ ጋዜጦች ላይ ነው ማስታወቂያዎች የሚወጡት››

እንዲህ አይነት ቀላል ነገር እንኳን ባለማወቋ አፈረች፡፡
‹‹እኔ የሚረዳኝ ሰው ያስፈልገኛል››
‹‹አይዞሽ አትፍሪ እኔ የምችለውን ያህል እረዳሻለሁ››
‹‹በእውነት የሚያስደስት ነው›› አለች ማርጋሬት ‹‹ሚስስ ሌኔሃንና አሁን ደግሞ አንተን ካገኘሁ ኑሮውን እቋቋመዋለሁ፡ ውለታ ከፋይ ያድርገኝ፡፡ ምን እንደምል እንጃ፡:››

ዴቪ ወዳሉበት መጣና ‹‹በመስኮት ተመልከቱ አንድ ነገር ታያላችሁ›› አለ።

ማርጋሬት አይሮፕላኑ ለአስራ አምስት  ደቂቃ ያህል ሳይወዛወዝ
እንደተጓዘ ተገነዘበች፡

ማርጋሬት በመስኮት አሻግራ ተመለከተች፡፡ ሄሪ የመቀመጫ ቀበቶውን
ፈታና በማርጋሬት ጀርባ በኩል አሻግሮ አየ፡፡

‹‹ለእኛ ብለው ይሆናል መብራቱን ሁሉ ያበሩት›› አለ አንዱ፡፡

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የአየር ጥቃቱን በመፍራት በጨለማ ነው የሚጓዙት፡ ማርጋሬት ሄሪ በጣም ወደሷ መጠጋቱን አልጠላችውም:
የአይሮፕላኑ የመገናኛ ሰራተኛ ከመርከቡ የመገናኛ ሰራተኛ ጋር በሬዲዮ
ሳይነጋገር አልቀረም፡፡ የመርከቡ ተሳፋሪዎች ወደ መርከቡ በረንዳ ላይ
ወጡና እጃቸውን አውለበለቡ፡፡ አይሮፕላኑ ከመርከቡ በቅርብ ርቀት የሚበር በመሆኑ ወንዶቹ ነጫጭ የራት ልብስ፤ ሴቶቹ ደግሞ ቅልጥም የሚታከክ
ልብስ መልበሳቸውን በግልጽ ይታያል፡፡

መርከቡ ማዕበሉን በሹል አፍንጫው እየሰነጠቀ ሲጓዝ አይሮፕላኑ አልፎት በረረ፡፡ ማርጋሬት ሁኔታው አስደስቷታል፡ ሄሪን ስታየው እሱም አያትና ተሳሳቁ፡፡ ሰዎች እንዳያዩት በሰውነቱ ከልሏት እጁን ወገቧ ላይ ጣል አድርጓል፡፡ በእጁ ገላዋን ነካ ያደረጋት ቢሆንም በመላ ሰውነቷ ላይ
የኤሌክትሪክ ሞገድ ያህል ሙቀት ለቆባታል፡ ይህ ሁኔታ በመጠኑ ድንግርግር እንዲላት ቢያደርግም እጁን እንዲያነሳ ግን አልፈለገችም ከትንሽ ጊዜ በኋላ ቁልቁል የሚያዩትን መርከብ አልፈው ሲሄዱ ከመርከቡ የሚፈነጥቀው መብራትም እየራቃቸው ሄደ፡፡ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ወደ
ቦታቸው ሲመለሱ ሄሪም ወደ ቦታው ሄደ፡፡

ዋናው ሳሎን ውስጥ ካርታ ከሚጫወቱት ጋር ማርጋሬትና ሄሪ ብቻ
ሲቀሩ ሌሎቹ ተሳፋሪዎች ወደ መኝታቸው ሄዱ፡ ማርጋሬት ከሄሪ ብቻዋን ተቀምጣ እፍረት ተሰማትና ‹‹መሽቷል ብንተኛ ይሻላል›› አለች ወዲያው ለምን እንዲህ አልኩ? አለች ለራሷ መተኛት አልፈለገችም: ሄሪ
ከእሷ መለየቱ ደስ ስላላለው ‹‹እኔም ትንሽ ቆይቼ እሄዳለሁ›› አለ
ማርጋሬት ከመቀመጫዋ ተነሳች ‹‹ወደፊት አሜሪካ ውስጥ እረዳሻለሁ
ስላልከኝ አመሰግናለሁ›› አለች፡፡
" ምንም አይደል"
"መልካም ምሽት"
"ለአንቺም እንዲሁ" አለ ሄሪ
ከመሄዷ በፊት ዞር አለችና እረዳሻለሁ ያልከኝ ከአንጀትክ ነው አይደል?

"አይዞሽ አታስቢ›› አላት፡፡

ማርጋሬት ለሄሪ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጥቷል፡፡  ከዚያም  በደመነፍስ እዚያው ቁጭ ባለበት ከንፈሩን ሳም አደረገችው፡፡ ይህም ደስ የሚል ስሜት አጭሮባታል፡፡ ግን ደግሞ ወዲያውኑ ባደረገችው ነገር ክው አለች ያጫረባት ደስታ ጉልበቷን አብረክርኳታል፡፡ ዙሪያ ገባውን
ስትመለከት ሚስተር መምበሪ የላይኛውን አልጋ ሲይዝ የታችኛውን ሄሪ
ይዟል፧ ፔርሲም የላይኛው አልጋ ላይ ተኝቷል፡፡ መጋረጃውን ጋረደች፡፡

መብራቱን አጠፋችና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብታ ተኛች። መኝታው ይሞቃል፡፡ በመስኮት ስታይ ከጨለማና ከዝናብ በስተቀር ምንም የሚታይ ነገር የለም፡፡ እሷና ኤልሳቤት ትንንሽ ልጆች ሆነው በበጋ ውስጥ እውጭ ድንኳን ተክለው የሚተኙት ትዝ አላት፡፡

ኤልሳቤት የት ትሆን ያለችው?
👍221
መጋረጃዋ ነካ ነካ ሲደረግ ከሀሳቧ ባነነች፡

መጋረጃውን ስትከፍተው ሄሪ ፊቷ ድቅን ብሏል፡፡

‹‹ምነው  ሄሪ?›› አለች ማርጋሬት ድምጿን ዝቅ አድርጋ ለምን እንደመጣ እያወቀች፡፡
‹‹ልስምሽ ነው›› ሲል አንሾካሾከ፡፡
መልሱ ቢያስደስታትም ፈራች ‹‹አንተ ሰው ያየናል ጅል አትሁን››
‹‹በናትሽ?››
‹‹ሂድ ከዚህ›› አለች ውሽቷን፡፡
‹‹ማንም አያየንም››
ጥያቄው ከመስመር የወጣ ቢሆንም ፈተና ውስጥ ጥሏታል፡፡ ከጥቂት
ደቂቃ በፊት ሲስማት የተፈጠረባትን ሙቀት አስታወሰች፡፡ እየፈራች
መጋረጃውን ትንሽ ከፈት አደረገችው፡፡ እሱም ራሱን አስገባና በልመና
አያት፡፡ ልመናውን አልቻለችውም:: አሳዘናት፡፡ ከዚያም አፏን ሲስማት
ጥርሱን የፋቀበት የጥርስ ሳሙና ሽታ አወዳት፡ ሳም እንዲያደርጋት
ብትፈቅድለትም እሱ ግን ከዚያ በላይ ነው የፈለገው፡፡ የታችኛውን ከንፈሯን
በከንፈሩ ሲቆነጥረው ደስታዋ ወሰን አጣ፡፡ ከዚያም በደመነፍስ አፏን ትንሽ ከፈት ስታደርግለት ምላሱን አፏ ውስጥ ከቶ ይልሳት ጀመር፡ የቀድሞው
ወዳጇ አያን እንዲህ አድርጎላት አያውቅም፡ የሄሪ አድራጎት እንግዳ ቢሆንባትም አስደስቷታል፡፡ እሷም ከድግሱ ለመቀራመት ምላሷን ከምላሱ ጋር አስተሳሰረችው፡፡ ከዚያም ሁለቱም ማለክለክ ጀመሩ። በዚህ ጊዜ ላይኛው
አልጋ ላይ የተኛው ፔርሲ ሲገላበጥ የት እንዳለች ታወሳትና ደነገጠች:
እንዴ ምን ማድረጌ ነው? አለች ብዙም የማታውቀውን ሰው ስትስመው አባቷ ቢያይዋት ድራሿን ነው የሚያጠፉት፡፡ ከዚያም መሳሳሙን አቆመች::
ሄሪ መሳሳሙ በፈጠረለት ደስታ እያለከለከ ትንሽ ራቅ አለ፤ ሆኖም እንደገና
መሳም ፈለገና ጠጋ ሲላት ገፋ አደረገችው::
‹‹እኔም እዚህ ልተኛ›› አላት፡
‹‹አብደሃል!›› አለችው
‹‹በናትሽ››
‹‹ይሄ እንኳን አይቻልም፡፡ አይሆንም!›› አለችው::
ሄሪ ከፋው፡፡
አሳዘናትና ‹‹አንተ ጥሩ ልጅ ነህ ሂድ ወደ መኝታህ›› አለችው፡
ይህን ያለችው ከልቧ እንደሆነ ገባው፡፡ ነገር ግን መልስ ከመስጠቱ
በፊት መጋረጃውን ዘጋችበት፡፡
ከዚያም ጆሮዋን ጣል ስታደርግ መሄዱን በኮቴው አወቀች፡ መብራቱን
አጠፋችና ተኛች፡፡ ወይ አምላኬ አለች ያደረገችው ትዝ ብሏት፡፡ ከዚያ በላይ ማድረግ ፈልጋ ነበር ቦታው አይመችም እንጂ።

እንዲህ አይነት የወሲብ ስሜት መጀመሪያ ያቋደሳት ኢያን ነበር በመጀመሪያ ኢያን ስለ  ሴት ብዙም ስለማያውቅ የምትፈልገውን ደስታ አይሰጣትም ነበር፡፡ እየተለማመደ ሲመጣ ግን ጥሩ አፍቃሪ ሆኗት ነበር።

ኢያን በሀሳቧ ድቅን ባለ ቁጥር አልቅሽ አልቅሽ ይላታል፡ በአጭር
የፍቅራቸው ዘመን እንደፈለገች ከእሱ ጋር ወሲብ ባለመፈጸሟ አሁን ቅሬታ ፈጥሮባታል፡፡ ምንም እንኳን ገላዋ ቢፈልግም በመጀመሪያ ፈቃደኛ
አልሆነችለትም፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ነው የሰጠችው:፡ አንዴ ካቀመሰችው በኋላ ደግሞ ልድገምሽ ሲላት የተለያዩ መሰናክሎች ትፈጥርበት ነበር። በር መቆለፉን ያወቀ ሰው ‹ምን እያደረገች ነው?› ብሎ እንዳይጠረጥራት ‹መኝታ ክፍልሽ ውስጥ እናድርግ› ሲላት እሺ አትለውም ነበር፡፡ ከቤታቸው ጀርባ ያለው ጫካ ውስጥ ብዙ መደበቂያ ቦታ እንዳለ ብታውቅም እውጭ ወሲብ
መፈጸም ያስፈራታል፡ ጓደኞቼ አፓርትመንት ልውሰድሽ ሲላት ሰው
ሊያውቀኝ ይችላል በማለት እሺ አትለውም ነበር፡ ከዚህ ሁሉ ደግሞ የሚያስፈራት አባቷ የምታደርገውን ነገር ቢያውቁ ነው፡፡

ስለዚህ ከእሱ ጋር የምትፈፅመው ወሲብ በስጋትና በችኮላ የታጀበ
ነበር፡፡ ስፔን ለጦርነት ከመሄዱ በፊት ያደረጉት ከሶስት ጊዜ አይበልጥም።
በእርግጥ ከጦርነቱ ሲመለስ ለዚህ ነገር ብዙ ጊዜ ይኖራል ብላ ታስብ
ስለነበር አላስጨነቃትም፡፡ ከዚያም ሞቱን ስትሰማ ከዚህ በኋላ የእሱን ገላ እንደማትነካው ስታውቅ ልቧ በሀዘን ደማ፡፡ ወደፊት በትዳር ተሳስረን እንኖራለን ብላ ስታስብ ድንገት በመቀጨቱ ሰማይ የተደፋባት መሰላት፡፡

ሄሪ ማርክስን ሰውነቷ ከጅሎታል። ሰውነቷ እሱን እሱን ይላታል፡፡
ኢያን ከሞተ ወዲህ የወንድ ጠረን ያሸተተችው የሄሪን ነው፡፡ ነገር ግን
እሱንም እንዲሁ ሂድ ብላ አባረረችው፡፡ ለምን? ስለፈራች ነው፡፡ አይሮፕላን
ውስጥ ስላሉ ወይም አልጋው ጠባብ ስለሆነ ወይም ሰው ሊሰማ ስለሚችል ወይም አባቷ እዚያው ስላሉ፡ ሰው ሊይዘን ይችላል ብላ በመፍራቷ ነው፡

ይሮፕላኑ ቢወድቅስ?› ስትል አሰበች፡፡ አሁን በአውሮፓና አሜሪካ
መካከል ነው ያሉት፡ ከአውሮፓም ሆነ ከአሜሪካ በየትኛውም አቅጣጫ ብዙ
መቶ ኪሎ ሜትር ርቀዋል፡ አንድ ነገር ቢፈጠር በደቂቃ ውስጥ አመድ
ሊሆኑ እንደሚችሉ  አውቃለች  ከመሞቷ  በፊት በአዕምሮዋ ሊመጣ
የሚችለው ነገር ለሄሪ በሰጠሁት ኖሮ የሚለው ሃሳብ ነው፡፡

አይሮፕላኑም ላይወድቅ ይችላል፡ ሆነም ቀረም የመጨረሻ ዕድል ያላት
አሁን ነው፡፡ አሜሪካ ከገቡ በኋላ ምን ሊከተል እንደሚችል አይታወቅም፡፡
እሷ ጦር ሰራዊቱን ለመቀላቀል ታስባለችı ሄሪ ደግሞ የካናዳ አየር ኃይል
መቀጠር ነው ፍላጎቱ፡፡ እንደ ኢያን ጦር ሜዳ ይሞት ይሆናል፡ ታዲያ የሷ የመኳንንት ዘርነት ምን ቦታ አለው፡፡ ህይወት እንደሁ አጭር ናት፡፡ስለዚህ ለሄሪ እድል ልትሰጠው ፈለገች:

ነገር ግን እንደገና መጥቶ ይጠይቃት ይሆን? ከዚህ በኋላ የሚጠይቃት
አይመስላትም፡፡ አይሆንም ስትል ፈርጠም ብላ ነግረዋለች፡፡ ሄሪ ደግሞ
በጣም ፈልጎ ነበር፡፡ ምናልባት ዛሬ ማታ ተመልሶ ላይመጣ ይችል ይሆናል
‹ምን ዓይነት ሞኝ ነኝ! አለች በሆዷ፡ በኋላ ይመጣ ይሆናል፡፡ ከመጣ ግን እሺ ነው የምለው አለች በሃሳቧ

ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ ፈለገች፡፡ ምናልባትም ወደዚያ ሲሄድ ታገኘው
ይሆናል እንደ እድል ሆኖ፡፡ ምናልባትም አስተናጋጁ የሚጠጣ እንዲያመጣለት ለማዘዝ ይነሳ ይሆናል፡ መጋረጃዋን ከፍታ ቁጭ አለች።የሄሪ መኝታ በመጋረጃ ተዘግቷል፡ ነጠላ ጫማዋን አደረገችና ተነሳች፡፡

አብዛኛው ሰው ስለተኛ መተላለፊያው ሰው አይታይበትም፡፡
አስተናጋጆቹም ሳያንቀላፉ አይቀርም፡፡ ካርታ የሚጫወቱት ሰዎች ግን
አሁንም ከካርታቸው ጋር ተጣብቀዋል፡፡ ጠረጴዛቸው ላይ የተቀመጠውን
ጠርሙስ ዊስኪ እየቀዱ ይጨልጣሉ የተወሰኑ ሰዎች መጋረጃውን ከፈት
አድርገው እያነበቡ ሲሆን ብዙዎቹ ግን መጋረጃቸውን ዘግተው ተኝተዋል፡
የሴቶች መጸዳጃ ቤት ባዶ ነው፡ መስታወቱ ፊት ለፊት ቁጭ ብላ ፊቷን አየች: ወንዶች ለምን እንደሚፈልጓት ገርሟታል፡፡ ፀጉሯ ብቻ ነው ወንዶችን የሚስበው፡፡

ሄሪ ገላዋን የማየት ዕድል ቢያገኝ ምን ይል ይሆን? የጡቷ ትልቅነት ምናልባት እናትነትን ወይም ያጋተ ጡትን ያስታውሰው ይሆናል፡  የሻምፓኝ ብርጭቆ የምታህል ትንሽ አጎጠጎጤ ጡት እንደሚወዱ ሰምታለች
የኔ ጡት ደግሞ በዚህ የሻምፓኝ ብርጭቆ ውስጥ ሊገባ አይችልም, አለች በመከፋት፡፡

በፋሽን መጽሔቶች ላይ የሚወጡትን አጥንታቸው የገጠጠ ሴቶችን ብትመስል ትወድ ነበር፡፡ ዳንስ በምትሄድበት ጊዜ ትላልቅ ጡቶቿ እየተወዛወዙ እንዳያስቸግራት ጡት ማያዣ ትለብሳለች፡፡ ኢያን ግን ትላልቅ ጡቶቿን ይወድላት ነበር፡፡ ‹‹ሞዴሊስቶቹ አሻንጉሊት ነው የሚመስሉኝ፡
አንቺ እውነተኛ ሰው ነሽ›› አላት አንድ ቀን አንገቷን እየሳመና እጁን በሹራቧ ስር ሰዶ ጡቶቿን እየዳበሰ፡፡ ከዚያ ወዲህ ጡቶቿን ትወዳቸዋለች:

አይሮፕላኑ እንደገና ሲናወጥ እንዳትወድቅ የጠረጴዛውን ጫፍ ያዝ
አደረገችና ከመሞቴ በፊት ጡቶቼን ማስደባበስ አለብኝ አለች በሆዷ፡
👍151😱1
አይሮፕላኑ በፀጥታ ሲጓዝ ወደ መኝታዋ ሄደች፡ ሁሉም ተሳፋሪ መጋረጃውን ዘግቷል፡ ሄሪ መጋረጃውን ቢከፍት ምኞቷ ቢሆንም እሱ ግን አልከፈተውም፡፡ የአይሮፕላኑ መተላለፊያ ላይ ቆማ አሻግራ  ስትመለከት የሚንቀሳቀስ ሰው የለም፡፡ እድሜዋን በሙሉ ፈሪ ነበረች፡፡ አሁን ግን ከዚህ በላይ የምትፈልገው ነገር እንደሌለ አውቃለች፡፡ ከዚያም የሄሪን መጋረጃ ነቀነቀች፡፡

ለተወሰነ ደቂቃ እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡ እዚህ እንደምትመጣ ተዘጋጅታ
ስላልመጣች ምን እንደምታደርግ ወይም ምን እንደምትል ቸገራት
ከመጋረጃው ውስጥ ድምጽ አይሰማም፡፡ መጋረጃውን እንደገና ነቀነቀች:
ከአፍታ በኋላ ሄሪ መጋረጃውን ከፈት አድርጎ  ጭንቅላቱን ወጣ
ከዚያም ሁለቱ ወጣቶች ተፋጠጡ፡፡ ፊቱ ቆማ ሲያያት አይኑን ማመን
አቃተው፡፡ እሷ ደግሞ ምላሷ ተሳሰረ፡፡ ከዚያም ከኋላዋ ድምጽ ተሰማት።

ወደኋላ ዞራ ስታይ አባቷ መጋረጃ ውስጥ እንቅስቃሴ መኖሩን በመጋረጃው ንቅናቄ አወቀች፡፡ አባቷ ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ ፈልገው መጋረጃውን ለመክፈት በእጃቸው ያዝ አደረጉት፡፡

ማርጋሬት ያለምንም መጠራጠር በቅጽበት ሄሪን ገፋ አደረገችውና ከጎኑ
ተዳበለች፡፡

ልክ መጋረጃውን እየዘጋች እያለ አባቷ ከመጋረጃው ሲወጡ ለቅጽበት
ያህል ታዩዋት እንደ ተዓምር ሆኖ አባቷ አላይዋትም፡፡ ‹‹እግዚአብሔር
አወጣኝ›› አለች፡፡

ሄሪ ማርጋሬት አልጋው ድረስ ስትመጣ አይቶ ግሩም ድንቅ እድሉን
ማመን አቃተው፡፡ ሊናገር ሲል እጇን አፉ ላይ በማድረግ ዝም አሰኘችው:
ወዲያው ሄሪ አልጋ ውስጥ ዘላ ስትገባ ነጠላ ጫማዋን ፊት ለፊት መተዋን አወቀች፡ ነጠላ ጫማዋ ላይ የእሷ እና የአባቷ ስም የመጀመሪያ ፊደል ተፅፎበታል፡፡ ነጠላ ጫማዋ ደግሞ ከሄሪ ነጠላ ጫማ ጋር ተቀምጧል  ስለዚህ ከእሱ ጋር መተኛቷን ድፍን የአይሮፕላኑ ሰው ሊያውቅ ነው።

ትንሽ ደቂቃ እንዳለፈ በመጋረጃው ክፍተት አጮልቃ ስታይ አባቷ
ጀርባቸውን ለእሷ ሰጥተው ከአልጋቸው እየወረዱ  ነው፡፡ በመጋረጃው
ክፍተት እጇን ሰደደችና ነጠላ ጫማዋን አንስታ ወስዳ መጋረጃውን
ዘጋችው በዚች ቅጽበት ውስጥ አባቷ ዞር ቢሉ ኖሮ ያልቅላት ነበር፡፡

ማርጋሬት ባደረገችው ደግሞ የልብ ኩራት ተሰማት፡፡

ከዚህ በኋላ ምን እንዲሆን እንደምትፈልግ ግልፅ አልሆነላትም፡፡ አሁን
ግን የገባት ከሄሪ ጋር መሆን እንደምትፈልግ ብቻ ነው፡፡
ሄሪ ግን ምን እንደሚፈልግ ግልፅ ነበር፡፡ አጠገቡ ያለችውን ቆንጆ ደረቱ ላይ ለጠፍ አድርጎ ከንፈሯን መሳም ጀመረ፡፡

ከጥቂት ደቂቃ መግደርደር በኋላ እሷም ሙሉ በሙሉ እጇን በመስጠት ያገኘችውን ደስታ ማጣጣም ጀመረች፡፡

ይህ ጊዜ እንዲመጣ በቁሟ ስታልም ነበር፡፡ አሁን ግን ሁሉም ነገር  እውን እየሆነ ነው፡፡ ጠንካራ እጁ ማጅራቷን የውጥር ይዟል፡፡ አፏን የሚስም አፍና ከእሷ ትንፋሽ ጋር የሚለዋወጥ ሰው፡፡ ሄሪ ለስለስ አድርጎ
እየሳማት  ነው፡፡ ጣቶቹ ፀጉሯን እየፈታተሉ
ሲሆን እሳት የሚተፋው
ትንፋሹ ጉንጮቿን ሊያቀልጣቸው ነው፡፡ ምላሱን ወዲህ ወዲያ እያንቀሳቀሰ
የእሷን ምላሽ ይፈልጋል፡፡ እሷም አላስችል ብሏት አፏን በሰፊው ከፍታ ተቀበለችው

ከአፍታ በኋላ እያለከለከ ወደ ደረቷ አመራ፡፡ በዚህ ጊዜ የመኝታ ልብሷ
ከላይዋ ላይ ወደቀና ጡቶቿ አፈጠጡ፡፡ የጡቷ ጫፍ እንደ በሰለ ፍሬ
ቀልቷል፡፡ ከዚያም እጁን ቀስ አድርጎ ሰደደና ግራ ጡቷን አፈፍ አድርጎ
የተወጠረውን የጡቷን ጫፍ ያፍተለትለው ገባ፡፡ እሷም የተፈጠረውን ግለትና ደስታ መቋቋም አቅቷት ታለከልካለች፡፡

ልብሷ የእሱን ገላ ከእሷ ገላ እንዳይገናኝ ስላደረገው አሽቀንጥራ ጣለችው: በዚህ ጊዜ ትንሽ ጥርጣሬ ቢገባትም ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አይኖርም ብላ በሆዷ ወስና ሙሉ በሙሉ ገላዋን ‹እንደፈለግክ
አድርገው ብላ ሰጠችው፡፡
ሁኔታው ቢያሳፍራትም ፍርሃቷ የበለጠ ደስታዋን አባሰው፡፡ ሄሪም
አይኑን በመላ አካላቷ ላይ እያንከባለለ በአድናቆትና በፍላጎት ተቃጠለ፡፡
አልጋው ጠባብ ቢሆንም እራሱን ወደ ጡቶቿ ወሰደው፡ አሁን ምን
ሊያደርግ ነው ስትል ጥርጣሬ ገባት፡፡ የጡቷን ጫፎች በየተራ ይልሳቸውና
ይጠባቸው ጀመር፡ የጡቶቿን ጫፎች እየላሰ ደግሞ በእጁ የተወጠረ ጡቷን ጨበጥበጥ ያደርጋቸዋል፡ በዚህ ጊዜ ማርጋሬት ጡቶቿ ሊፈነዱ ደረሱ እሷም ደስታዋን መቋቋም አቅቷት እራሱን ይዛ ወደ ጡቶቿ ትገፋዋለች፡፡

መላ አካላቱን ማሰስ ፈለገች፡፡ ከዚያም ገፋ አደረገችው የፒጃማውን
ቁልፎች ከፈተቻቸው፡፡ ሁለቱም እንደሚሮጡ ሁሉ ያለከልካሉ ነር ግን,
ሰው እንዳይሰማቸው ስለፈሩ አንድ ቃል አልተነፈሱም: ሄሪ ፒጃማውን አወለቀላትና ደረቱን መደባበስ ጀመረች፡፡ እንደሷ ሙሉ በሙሉ ራቁቱን
እንዲሆን ፈልጋለች፡፡ ከዚያም ከወገቡ ቀና አለላትና ሱሪውን ጎትታ
አወለቀችው፡

ከዚህ በፊት አንሶላ ከተጋፈፋቸው ሴቶች ጋር ሲያነጻጽራት ማርጋሬት
እፍረት የለሽ ስለሆነችበት ትንሽ ድንግርግር ብሎታል፡
የተገተረው የብልቱ ስሮቹ ጎልተው የሚታዩ ሲሆን ጫፉ ሊፈነዳ ደርል።
ሁለቱንም ሲመኙት ወደነበረው ዓለም ነጎዱ

የፈጸሙት ወሲብ አድክሟቸው ስለነበር ጋደም አሉ፡፡

አይሮፕላኑ ሰላማዊ ጉዞ ላይ ስለነበር አሸለባት፡፡

ከተወሰነ ሰዓት በኋላ ደንግጣ ብድግ አለችና ‹‹ነጋ እንዴ? ሰው ተነስቷል?›› ስትል ጠየቀችው ሄሪን፡፡ ከሄሪ አልጋ ስወርድ ያዩኛል ብላ መስጋቷ ልቧ በፍርሃት ይሰግር ጀመር፡

‹‹ምን ሆንሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ስንት ሰዓት ነው?››
‹‹እኩለ ሌሊት ነው›› አላት፡፡
ያለው ልክ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ እንቅስቃሴ  አይታይም፡
‹‹ወደ መኝታዬ ልሂድ ከመያዜ በፊት›› አለች በፍርሃት፡፡ እግሮቿን ሰዳ
ነጠላ ጫማዋን ብትፈልግም ልታገኘው አልቻለችም፡፡
ሄሪ ትከሻዋን ያዝ አደረገና ‹‹ተረጋጊ›› ሲል አንሾካሾከ ‹‹ብዙ ሰዓት አለ››

‹‹ነገር ግን አባባ ሊያየን ይችላል›› አለች፡፡
‹‹ለምንድን ነው እንደዚህ የተጨነቅሽው?›› ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የገቡበት የወሲብ ባህር በአይነ ህሊናዋ መጣ፡፡ እሱም እንደዚሁ፡ ከዚያም
በአይን ተግባቡና ተሳሳቁ፡፡
እሱ ላይ ያየችው ድፍረት እሷም ላይ ተጋባባትና አልሄድም እቆያለሁ›
አለች በሀሳቧ፡ ከዚያም ሄሪ ወደ እሷ ጠጋ ሲል የብልቱ መገተር ታወቃት፡፡
“አሁን አትሄጂም›› አላት፡፡
እሷም በደስታና በጉጉት ‹‹እውነትህን ነው፡፡ ጊዜ አለን›› አለችና
እንደገና መሳሳም ጀመሩ፡፡...

ይቀጥላል
👍23😱21
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


...ካለ ሽማግሌ ፈቃድ የተወለደ ግን እንደ እርኩስ ስለሚቈጠር የማደግ ዕድል አያገኝም" የማስወረድ ዘዴውም ልምድ ያላቸው ሰዎች በማኅፀን ውስጥ ያለውን ፅንስ  ጭንቅላት ከውጭ በኩል በመዳሰስ ሲያገኙ ጭንቅላቱን በሁለት አውራ ጣታቸው ውስጥ ደጋግመው በመጭመቅ..» ሲል ካርለት ፊቷ በስሎ የተበላሸ ቲማቲም መሰለ፣ ከንፈሮቿ ተንገረበቡ፣ መላ አካሏ ራደ"

ከሎ ግን ንግግሩን ቀጠለ፣ «...እድታስወርድ ይደረጋልI ከተወለደም ሕፃኑ ጫካ ይጣላል። ስለዚህ አንድ የሐመር ሴት በሽማግሎች ፈቃድ ማርገዟ ከታወቀ በኋላ ከባሏ ጋር ግንኙነት ሳታደርግ ፅንሱ አድጎ መውለጃዋ ሲደርስና ምጥ ቢይዛት በአካባቢዋ የሚኖሩ
ሴቶች ይሰበሰቡና እጅና እግሯን ጥፍር አድርገው ይዘው፣ አፍዋን ያፍኗታል" ይህም ልጁ የእናቱን ማኅፀን ለቆ ተፈትልኮ
እንዲወጣ ይረዳል» ሲል ካርለት ፍርሃት መላ አካሏን አንገጫገጨው። እሷም እንደታፈነች ሁሉ ልቧ ዘለለባት።

«ውልጃ ባፈና? በምጥ ላይ ሌላ ምጥ? » ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ።

«እንግዲህ እንደ ነገሩ ታርሳ ራቁቱን ለተወለደው ሕፃን መታቀፊያ፣ ፎጣ፣ ሙቀት፣ ጂኒ ጃንካ ሳያስፈልገው የቡና ውኃ በማጠጣት
አቀባበል ይደረግለታል። ልጁ ቁሩንና ሙቀቱን ተቋቁሞ አደግ እያለ
ሲመጣ ግን እናቱ ከማማጡ በላይ ትጨነቃለች አባትም ውስጥ
ለውስጥ ይሳቀቃል።

የሚጮኸው ጅብ ሆድ ዕቃዋን፣ የከሎ ወሬ ደግሞ ሕሊናዋ አተረማመሰባት። ትሰማዋለችI የምትሰማው ግን ለማወቅ ሳይሆን
በቃ ከአቅሜ በላይ የሆነ ‹አስፈሪ ነው ብላ መናገር ተስኗት ነው ደንታ ቢሱ ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ"

«በሐመር ማኅበረሰብ ላም፣ በሬ፣ በግ...ጥርስ የሚያበቅሉት በታችኛው ድዳቸው ስለሆነ ‹ቅዱስ› ሲባሉ አህያ፣ ፈረስ፣ ጅብ...
ጥርስ የሚያበቅሉት በላይኛው ድዳቸው በመሆኑ እርኩስ ይባላሉ"
የሰው ልጅም የመጀመሪያውን (የወተት ጥርስ ማብቀል የሚገባው
እንደ ቅዱሳን እንስሳት በታችኛው ድዱ መሆን ሲኖርበት፣ እንደ እርኩሳን እንስሳት በላይኛው ድዱ ካበቀለ ከእርኩሳን እንስሳት እንደ አንዱ ስለሚቆጠር ለማኅበረሰቡ አይበጅም ቢያድግም አባቱ
የሚጋፋ፣ የሚገድል፣ የሚበጠብጥ ስለሚሆን ገፊ ወይንም በአካባቢው አጠራር «ሚንጊ» ተብሉ ይጣላል።
«ጥርስ እንደማብቀሉ ሁሉ መውለቁ ላይም በቅድሚያ መውለቅ የሚገባው በታችኛው ድድ የበቀለው ጥርስ መሆን ሲገባው፣
በላይኛው ድዱ የበቀለው ጥርስ ቀድሞ ከወለቀ ሚንጊ ነው ተብሎ
አሁንም ይጣላል ከዚህ በተጨማሪም፣ ሕፃኑ የታችኛው ጥርሱ ከመውለቁ በፊት በአጋጣሚ እንኳ ወድቆ ወይንም በሌላ መንገድ
የላይኛው ጥርሱ ቢወልቅ ሚንጊ ተብሎ ከማኅበረሰቡ እንዲወገድ ይደረጋል» ከሎ ሆራ «ኢ ህ አለና፣

«እና እኔም እንደነገርኩሽ ሚንጊ ነኝ» አላት"

«ታዲያ አንተ ‹ሚንጊ ነህ› ተብለህ ተጥለህ ነበር?» ካርለት፣ ካለማብራሪያ መልሱን በአሉታ ወይንም በአወንታ እንዲመልስላት
በሕሊናዋ እየተማጸነች ጠየቀችው"

«አዎ!» ብሎ፣ ጭንቅላቱንና ትከሻው ላይ በጦር የተወጋውንና በድንጋይ የተፈነከተውን አሳያት" ከዚያ ቀና ብሎ ጨለማውንና
ከዋክብቱን ተመለከተና እንዴት አድርገው እንደ ጣሉት ጨዋታውን
ሲቀጥል ካርለት በሕሊናዋ «ከሎ ለእኔም የሚያዝን አንጀት ይኑርህ እንጂ» በማለት፣ እየተብሰከሰከች የማይቀርላትን ጨዋታ ለመስማት ጉንጯን በጣቶቿ ደግፋ፣ ዓይኖቿን በማፍጠጥ ዓይን ዓይኑን
ተመለከተችው"

«እኔ የተወለድኩት ሐመሮች ተሰባሰቡበት ከሚባለው የቡስካ ተራራ ስር ላላ ከተባለው መንደር ነው" እናቴ በንቲ ኃይሎ ትባላለች" አባቴ ደግሞ ሆራ ሸላ ይባላል። እናቴ ለአባቴ አምስተኛ ሚስት ስትሆን፣ አምስት ልጆችም ወልዳለታለች" እናቴ፣ በልጅነቴ ሁል ጊዜ በምትለብሰው ቆዳ ሸፈን አድርጋ ከሰውነቷ ጋር ትለጥፈኝና ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ቆይታ፣ «ጨዋንዛ» በሚባል ሸካራ ቅጠል
ጥርሴን ትሞርድልኝ ነበር" በወቅቱ ባይገባኝም ኋላ ኋላ ግን የተጣልሁበትን ምክንያት ስሰማ የጥርስ አበቃቀሌ በትክክለኛው መንገድ ማለትም መጀመሪያ በታችኛው ድዴ፣ ቀጥሎ በላይኛው ድዴ ነበር አሉ የበቀለው" ይሁን እንጂ፣ አንድ ጊዜ ጥጃ
ለመመለስ ስሮጥ ወድቄ የላይኛው ጥርሴ አንዱ ወለቀ፣ አንደኛው
ተሸረፈ። እንዳበቃቀሉ ሁሉ፣ በቅድሚያ የታችኛው ድዴ ላይ የበቀለው ጥርስ መውለቅ ሲገባው፣ የላይኛው ጥርሴ ቀድሞ
በመውለቁ፣ ለአደጋ ተጋለጥሁ" እናቴ፣ በሸካራው የጨዋንዛ ቅጠል
ጥርሴን ስትሞርድልኝ የነበረው ለካ የታችኛው ድዴ ጥርስ ቀድሞ የወለቀ ለማስመሰል ኖሯል"

«ይሁን እንጂ፣ ጥረቷ ከንቱ ነበር" ወድቄ ሳለቅስና ጥርሴ ወልቆ ያዩኝ ሰዎች ለሽማግሎች መንገራቸው አይቀሬ ነበር" እናም አንድ
ቀን አባቴ ባልነበረበት ወቅት፣ ሚንጊ የተባሉ ልጆችን የሚጥሉ
ሽማግሎች ወደ እኛ ጎጆ መጡ" እናቴ፣ ከርቀት እንዳየቻቸው ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ሰውነቴን እንቦሳዋን እንደምትልስ ላም እየሳመችና እየላሰች አለቀሰች።

«ከእናቴ ጋር በተለያየ አጋጣሚ እንለያይ ነበር ከብቶች በድርቅ ጊዜ እርቀው ሲሄዱ፣ ወደ ማሳ፣ ለገበያ ወዘተ.ስትሄድ ሁለትና ሦስት ቀናት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ከዚያም በላይ እንለያያለን ታዲያ ስንለያይ እናቴ ታለቅሳለች እኔ ግን የእሷ ሁኔታ ቢረብሸኝም
ተሎ ወደ ጨዋታዬ እመለስ ነበር። የዛን ቀን ሽማግሎች፣ «ጥርሱ
አስወልቀን እናምጣው» ብለው፣ በጠንካራው እጃቸው ትንሿን እጄን በጨመቁ ቁጥር ግን እንባዬ ሳያቋርጥ ይንዠቀዠቅ ነበር"
«እናቴ ሽማግሎች ጥርሱን አስወልቀን እናምጣው ብለው ሲጠይቋት ካለምንም ተቃውሞ ገፋ አድርጋ አሳልፋ ብትሰጠኝም! ትከሻዋን በሁለት እጆቿ አቅፋ፣ ድምፅዋን አጥፍታ፣ አምርራ
ስታለቅስ ለአደገኛ ሁኔታ እንደተጋለጥኩ ገመትሁ" ሆኖም ግን ምን እንደሚደርስብኝና ለምንስ እንደምቀጣ አላወቅሁም ነበር"

«ሁለቱ ሰዎች ከመንደራችን እያራቁ ሲወስዱኝ እናቴ እጇ
እያርገበገበች ስታለቅስ ትታየኝ ነበር። እንዲያውም እስከ አሁን ድረስ እንኳ ሰው እንደ እሷ ስፍስፍ ብሎ ሲያለቅስ አይቼ
አላውቅም"

«ከመንደራችን ብዙ ርቀን ወደ ጫካው ውስጥ እስክንገባ ሽማግሎች ምንም ሳያወሩኝ ሄድንና የሆነ ገደል አጠገብ ስንደርስ ከፊለፊታቸው ወደነሱ ሳልዞር እንድቆም ነገሩኝ" እኔ ግን፣ ያሉኝን
ለመፈጸም ስላልተቻለኝ ዘወር ስል፣ አንደኛው ሽማግሌ ጦሩን ወደ
ትከሻዬ ሲሰድ ተመለከትኩኝ" ከዚያ በኋላ ሰውነቴን ሲወጋኝና
ለመጮህ ስሞክር፣ ገፍትረው ወደ ገደሉ ከተቱኝ ገደሉ ውስጥ የነበረው ድንጋይ ደግሞ እራሴን ተረተረኝ፤ ደም ፊቴን አለበሰው የሞት ሞቴን ግን የእናቴን፣ የወንድሜን፣ የአባቴን...ስም እየጠራሁ
ጮሁኩ" የደረሰልኝ ግን አልነበረም።

«ስለዚህ፣ ጉድጓድ ውስጥ እንደሆንኩ ስጓጉር ውዬ አድሬ፣ ጠዋት ላይ ድምፄ ተዘጋ። ረፈድፈድ ሲል የሰው ድምፅ ሰማሁ"
የሰማሁት ድምፅ ግን የሰው ቢሆንም ቋንቋው የማውቀው ሐመርኛ
አልነበረም" ለመጣራት ብሞክርም ድምፄ እምቢ አለኝ።

«የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ፣ አንዷ በልቅሶ የተዘጋውን ድምፄን ሰምታ ኖሮ፣ አብረዋት ከሐመር ቆቄ ከተማ የመጡትን ሴቶች ጠርታ በድንጋጤ ተያይዘው ሄዱ መሰለኝ ድምፃቸው ጠፋብኝ" ብዙ ቆይቼ
ግን፣ እንደገና የወንዶችና ሴቶች ድምፅ ተሰማኝ ከወላጆቼ ጋር ሳለሁ፣ እነዚያን መሳይ ሰዎች ወደ መንደራችን ሲመጡ፣ በፍርሃት ፈርጥጬ እሮጥ ነበር" ሆኖም ግን፣ የማልፈራቸው የኔ ወገኖች
ስለጨከኑብኝ መሰለኝ፣ አለባበሳቸውንና ቋንቋቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ከጉድጓድ ውስጥ አውጥተው የሚበላ ሲሰጡኝና ሲያሳክ
ሙኝ፣ አንድም ተቃውሞ አላሰማሁም"
👍23