አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹ወጣቱ ሰው እስረኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ስሙ ፍራንክ ጎርደን
ይመስለኛል›› አለ ካፒቴኑ።
‹‹ለዚህ ነው ፎየንስ ላይ ሁለቱ ሰዎች ከአይሮፕላኑ ያልወረዱት።
የኤፍ..ቢ.አዩ ሰው ወጣቱ ከእጁ እንዲያፈተልክ አልፈለገም›› አለ ኤዲ ካፒቴኑ ራሱን ነቀነቀና ‹‹ጎርደን ከእንግሊዝ አገር ታድኖ የመጣ እስረኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከውጭ አገር ታድነው ወደ አገራቸው የሚመለሱ እስረኞች ደግሞ አደገኛ ወንጀለኞች ናቸው፡ ይህን ሳይነግሩኝ አይሮፕላኔ
ላይ ይህን ጠብደል ወንጀለኛ ጭነዋል›› አለ ካፒቴኑ።

የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ቤን ‹‹ምን አጥፍቶ ይሆን?›› ሲል ጠየቀ።

‹‹ፍራንክ ጎርደን›› አለ ጃክ ‹‹ይሄ ስም አዲስ አይደለም እስቲ ቆዩማ
ፍራንክ ጎርዲኖ ነው ይሄ ሰውዬ››
ኤዲ ስለ ፍራንክ ጎርዲኖ ጋዜጣ ላይ ማንበቡ ትዝ አለው፡፡ በአሜሪካ
ኒው ኢንግላንድ ስቴት የማፊያ አባል ነው፡፡ የተወነጀለው አንድ ለማፊያ ቡድኑ ጉልቤዎች ገንዘብ አልከፍል ያለን የምሽት ክበብ ባለቤት ገሏል፣ውሽማውን ደፍሯል እንዲሁም የምሽት ክበቡን በእሳት አጋይቷል በሚሉ ወንጀሎች ተወንጅሏል፡ ውሽሚት ከእሳቱ ተርፋ ወንጀሉን የፈጸመው
ጎርዲኖ መሆኑን ለፖሊስ ተናግራለች፡
‹‹ወጣቱ ሰው ፍራንክ ጎርዲኖ መሆኑን እናረጋግጥ›› አለ ቤከር፡፡ ‹‹ኤዲ ሮጥ በልና ኦሊስ ፊልድን እንደምፈልገው ንገረው››

‹‹እሺ ጌታዬ›› አለና ኤዲ በደረጃው ወርዶ ወደ ተሳፋሪዎች ክፍል ገባ፡፡
ፍራንክ ጎርዲኖ ካሮል አንን ካገቷት ሰዎች ጋር የሆነ ግንኙነት ሳይኖረው
አይቀርም ሲል ገመተ፡

በአይሮፕላኑ በስተመጨረሻ ላይ አንድ እድሜው አርባ ዓመት
የሚገመት ራሰ በራ ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት አሻግሮ ጨለማውን እያየ ሲጋራውን ያቦናል፡፡ ኤዲ ይህን ሰው ሲያየው ሽጉጡን ደግኖ ወሮበሎች
የተጠራቀሙበትን ክፍል በር በርግዶ የሚገባ ሰው አልመስልህ አለው፡ ከኦሲስ ፊልድ ፊት ለፊት ስፖርት በማቆሙ ሰውነቱ እየወፈረ የመጣ ስፖርተኛ የሚመስል ጥሩ የለበሰ ወጣት ሰው ተቀምጧል፡፡ ጎርዲኖ እሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወጣቱ ሰው ሲያዩት አመለ ብልሹ ልጅ ይመስላል፡
ይህ ወጣት ሰው ጥይት ተኩሶ መግደል ይችላል?› ሲል ኤዲ ራሱን
ጠየቀ አዎ ሳይገል አይቀርም› አለ መልሶ በሆዱ፡፡

‹‹ሚስተር ፊልድ ነህ?›› አለው ትልቁን ሰው፡

‹‹አዎ›› አለ ፊልድ

ፊልድ ካፒቴኑ እንደሚፈልገው ሲነግረው ግራ ገባው: ምስጢሩ
የታወቀ መስሎት ተናደደ፡፡ ቢሆንም እሺ አለና ሲጋራውን መተርኮሻ ላይ
አጥፍቶ የመቀመጫ ቀበቶውን ፈቶ ተነሳ፡፡

‹‹ሚስተር ፊልድ ተከተለኝ›› አለ ኤዲ፡፡

ፊልድን ወደ ካፒቴኑ እየመራ ሲሄድ ከቶም ሉተር ጋር ዓይን ላይን
ግጥም ሲሉ በዚያው ቅጽበት አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለት፡፡

የቶም ሉተር ተልዕኮ ፍራንክ ጎርዲኖ በፖሊስ እጅ እንዳይወድቅ
ማድረግ ነው፡፡

ኤዲ የገባውን ግዴታ በመተው አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል የሚል ስጋት ገብቶት ሉተር በድንጋጤ ኤዲ ላይ አፈጠጠ፡፡
አሁን ሁሉ ነገር ለኤዲ ግልጽ ሆነለት፡ ፍራንክ ጎርደን ከአሜሪካ
ሸሽቶ ቢወጣም ኤፍ.ቢ..አይ ዱካውን ተከታትሎ እንግሊዝ ውስጥ ያዘውና ወደ አሜሪካ ሊወስደው ነው፡፡ በአይሮፕላን እንደሚወሰድ መወሰኑን የማፊያ
ቡድኑ ማወቁ አልቀረም፡፡
አይሮፕላኑ አሜሪካ ከመድረሱ በፊት አንድ ቦታ
ላይ ጎርዲኖን ለማስመለጥ ይጥራሉ ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ኤዲ የተፈለገው አይሮፕላኑ በካናዳና
አሜሪካ ድንበር ሜይን ስቴት ጠረፍ አጠገብ እንዲያርፍ ይደረግና እዚያም ፈጣን ጀልባ ላይ ተጋብቶ ይዘውት ጥርግ ይላሉ፡፡ ከዚያም ካናዳ ውስጥ አንድ ቦታ ይደብቁትና በመኪና ወደ መሸሸጊያው ይወሰዳል፡፡ በዚሁ ሁኔታ
ከህግ ያመልጣል፤ ለኤዲ ምስጋና ይግባውና፡፡
ፊልድን ወደ ካፒቴኑ እየወሰደ እያለ አጠቃላይ ዕቅዳቸው ምን እንደሆ
ሲረዳ እረፍት ቢሰማውም ሚስቱን ለማዳን ሲል ነፍሰ ገዳይ እንዲያመልጥ መርዳቱ በአንጻሩ አበሳጭቶታል

‹ካፒቴን ሚስተር ፊልድ ማለት እሱ ነው›› አለ ኤዲ

ካፒቴኑ ዩኒፎርሙን ለብሶ በእጅ የሬዲዮ መልእክቱን ይዞ ቁጭ
ብሏል፡ ራት በልቶ ስለጨረሰ ገበታው ከፍ ብሏል፡በኮፍያው ስር
የሚታየው ቃጫ መሳይ ጸጉሩ የአዛዥነት ክብር አጎናጽፎታል
የሚታየው በተቀመጠበት ቀና ብሎ ፊልድን ‹‹ከኤፍ.ቢ.አይ ላንተ የተላከ መልእክት ተቀብያለሁ›› አለው

ፊልድ ወረቀቱን ከካፒቴኑ ለመቀበል እጁን ቢዘረጋም ካፒቴኑ ግን አልሰጠውም፡

‹‹የኤፍ..ቢ.አይ ነጭ ለባሽ ነህ?›› ሲል ጠየቀው::
‹‹አዎ››
‹‹አሁን በግዳጅ ላይ ነህ ያለኸው?››
‹‹አዎ››
‹‹ምንድነው ግዳጅህ ሚስተር ፊልድ?››
‹‹ማወቅ ያለብህ አይመስለኝም ለኔ የተላከ ስለሆነ ወረቀቱን ብትሰጠኝ፡››

‹‹እኔ የዚህ አይሮፕላን አዛዥ በመሆኔ ግዳጅህ ምን እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ፡ ከኔ ጋር ባትከራከር ጥሩ ነው ሚስተር ፊልድ፡››

ኤዲ ፊልድን በትኩረት አየው: ፊቱ የገረጣና ድካም የሚታይበት
ሲሆን ዓይኑ እምባ አንቆርዝዟል፡ ቁመቱ ሎጋ ሲሆን በአንድ ወቅት
ሰውነቱ በስፖርት የተገነባ እንደነበር የሚያስታውቅ ቢሆንም አሁን ቆዳው ተሸብሽቧል፡ ፊልድ ጋጠወጥ እንጂ ጎበዝ እንዳልሆነ ኤዲ አውቋል፡ ይህን ማለት ያስቻለው በካፒቴኑ የተደረገበትን ግፊት መቋቋም አቅቶት ወዲያው
እጁን በመስጠቱ ነው።

‹‹ወደ አሜሪካ ሄዶ ፍርዱን የሚቀበል አንድ እስረኛ አጅቤ እየወሰድኩ ነው ፍራንክ ጎርደን ይባላል›› አለ ፊልድ፡

‹‹ፍራንክ ጎርዲኖ ነው?››

‹‹አዎ ነው››

‹‹ሰውዬ ሳትነግረኝ አደገኛ
ወንጀለኛ በአይሮፕላኔ ውስጥ ማጓጓዝ ተገቢ አይደለም››

‹‹ትክክለኛ ስሙን ብታውቅ በምን እንደሚተዳደር ታውቅ ነበር፡፡ ከሮድ
አይላንድ ስቴት እስከ ሜይን ስቴት በዘረፋ፣ በማስፈራራት፣ በአራጣ
ማበደር፣ በህገወጥ ቁማርና ሽርሙጥና በማስፋፋት ተግባር የታወቀው የሬይ ፓትሪያርካ ተቀጣሪ ነው፡፡ ሬይ ፓትሪያርካ ቁጥር አንድ ወንጀለኛ ተብሎ በመንግስት የሚፈለግ ሰው ነው: ጎርዲኖ ደግሞ በፓትሪያርካ ትዕዛዝ
ሰዎችን ያስፈራራል፣ ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ያሰቃያል፣ ይገድላል። ላንተ አስቀድመን ያልነገርንህ ለደህንነት ጥበቃ ተብሎ ነው።››

‹‹እንዲህም ብሎ የደህንነት ጥበቃ›› ሲል ተቆናጠረ ካፒቴኑ።
ኤዲ ካፒቴኑ ተሳፋሪ ላይ ሲጮህ አይቶት አያውቅም።

‹‹የፓትሪያርካ ቡድን ሁሉን ነገር አውቆላችኋል›› አለና ወረቀቱን
ለፊልድ ሰጠው ካፒቴኑ።

ፊልድ የሬዲዮ መልእክቱን አንብቦ ሲጨርስ ፊቱ በድንጋጤ አመድ
መሰለ፡ ‹‹እንዴት ሊያውቁ ቻሉ?›› ሲል አጉተመተመ።

‹‹የትኞቹ ተሳፋሪዎች የእሱ ተባባሪዎች እንደሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ››አለ ካፒቴኑ። ‹‹ከተሳፋሪዎቹ መካከል የምታውቀው አለ?››

‹‹እንዴት ላውቅ እችላለሁ? አለ ፊልድ በንዴት። ባውቅ
ለኤፍ.ቢ.አይ አላሳውቅም ነበር?››

‹እነማን እንደሆኑ ቢነገረኝ አይሮፕላኑ በሚቀጥለው የሚያርፍበት ቦታ ላይ አስወርዳቸው ነበር›› አለ ካፒቴኑ፡
ኤዲ እኔ አውቄአቸዋለሁ ቶም ሉተርና እኔ ነን› አለ በሆዱ፡

ፊልድም ቀጠለና ‹‹የተሳፋሪዎቹን ስም ዝርዝር በሬዲዮ ለኤፍ.ቢ.አይ
አሳውቅና እያንዳንዱን ስም ያጣራልሃል›› አለ፡

ኤዲ ይህን ሲሰማ ፍርሃት ወረረው፡

በዚህ ማጣራት ቶም ሉተር ይጋለጥ ይሆን? እሱ ከተጋለጠ ደግሞ
ሁሉ ነገር አፈር በላው ማለት ነው። የታወቀ ወሮበላ ይሆን? ቶም ሉተርስ እውነተኛ ስሙ ነው፡ የሀሰት ስም የሚጠቀም ከሆነ የሀሰት ፓስፖርት ያስፈልገዋል፡ ከትልልቆቹ ማፍያ ቡድኖች የአንዱ አባል ከሆነ ደግሞ ይህን ማድረግ ችግር ሊሆን አይችልም። እንዲህ ያለውን ጥንቃቄ ደግሞ ማድረግ
አይቀርም፡ ሌላው ያደረገው ነገር በሙሉ በጥንቃቄ የተሰናዳ ነው።
👍13
ካፒቴን ቤከር ብልጭ አለበት።
‹‹በዚህ ምክንያት የአይሮፕላኑ
ሰራተኞች እንዲጨነቁ ማድረግ የለብንም›› አለ፡

ፊልድም ትከሻውን ነቀነቀና ‹‹እንደፈለግህ። ኤፍ ቢ.አይ የአይሮፕላኑን ሰራተኞች ስም ከፓን አሜሪካን አየር መንገድ በደቂቃ ውስጥ መውሰድ ይችላል›› አለ።

ካፒቴኑ የተሳፋሪዎቹንና የአይሮፕላኑን ሰራተኞች ስም ዝርዝር የያዘ ወረቀት ከጠረጴዛው ኪስ አውጥቶ ለሬዲዮ ኦፕሬተሩ ሰጠውና ‹‹ቤን ለኤፍ...አይ ላከው›› ሲል አዘዘው።

ቤን ቶምሰንም የስም ዝርዘሩን በኮድ መልዕክት ላከው፡

‹‹አንድ ሌላ ጉዳይ አለ›› አለው ካፒቴኑ ፊልድን፡ ‹‹መሳሪያህን ለእኛ
ታስረክባለህ››

ፊልድም ‹‹አይሆንም›› ሲል ተቃወመ::

‹‹ተሳፋሪዎች የጦር መሳሪያ እንዲይዙ አይፈቀድም፡፡ ከዚህ ክልከላ ነፄ የሚሆን ሰው የለም።
ስለዚህ ሽጉጥህን አስረክበን›› ሲል አዘዘ ካፒቴኑ፡፡

‹‹ባላስረክብስ?›› ሲል ጠየቀ ፊልድ

‹‹በሰላም ካልሰጠህ ኤዲና ጃክ በግድ እንዲነጥቁህ አደርጋለሁ፡››
ኤዲ ካፒቴኑ ባለው ቢገረምም በማስፈራራት ሁኔታ ወደ ፊልድ ጠጋ አለ፡፡ ጃክም እንዲሁ አደረገ፡፡
ካፒቴኑ ቀጠለና ‹‹ኃይል እንድጠቀም የምታስገድደኝ ከሆነ በሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦታ ላይ አስወርድሃለሁ፡››

ፊልድ የታጠቀ ቢሆንም ካፒቴኑ
የበላይነቱን መያዙ ኤዲን
አስደንቆታል፡፡ ይሄ ደግሞ በፊልም እንደሚታየው አይደለም፡፡ ፊልም ላይ ሽጉጥ የያዘ ሰው ነው ትዕዛዝ ሰጪው፡፡

ፊልድ ምን እንደሚያደርግ ጨነቀው፡፡ ኤፍ.ቢ.አይ ሽጉጡን የማስረከቡን ጉዳይ አይቀበለውም፡፡ በአንጻሩ ካላስረከበ ከአይሮፕላኑ ሊባረር ይችላል።

ፊልድም ‹‹እኔ አደገኛ እስረኛ አጅቤ እየወሰድኩ ነው፡፡ የግድ መታጠቅ
ይኖርብኛል፡ ሽጉጤ ከኔ መለየት የለበትም›› አለ፡፡

በጥግ በኩል ያለው በር ገርበብ ብሏል፡፡ ኤዲ በአይኑ ቂጥ አንድ ነገር ውልብ ሲል ታየው፡
ካፒቴን ቤከርም ‹‹መሳሪያውን ተቀበለው ኤዲ›› ሲል አዘዘ፡፡ ኤዲ
ፊልድ ጃኬቱ ውስጥ እጁን ሰደደ፡፡ ፊልድ ከቆመበት ንቅንቅ አላለም፡ ኤዲ ፊልድ ካነገተው የሽጉጥ ማህደር ቁልፉን አላቀቀና ሽጉጡን ላጥ አድርጎ አወጣው፡ ፊልድ ይሄን ሲያይ ፊቱን አቀጨመ ኤዲ ወዲያው ወደ አይሮፕላኑ ጥግ ሄደና በሩን ከፈተው፡፡ ፔርሲ
ኦክሰንፎርድ እዚያ ቆሟል፡፡ ኤዲ ትንሽ ቀለል አለው፡፡ ምናልባትም የጎርዲኖ ጓደኞች ማሽንገን ይዞ ይሆናል ሲል አሰበ፡፡

ካፒቴን ቤከር ፔርሲን ሲያየው ‹‹ከየት ነው የመጣኸው?›› ሲል
ጠየቀው፡፡ ‹‹የሴቶች መዋቢያ ክፍል አልፎ ያለውን መሰላል ወጥቼ
የአይሮፕላኑ ጭራ ድረስ ሄድኩ››
ኤዲ የኦሊስ ፊልድን ሽጉጥ የጠረጴዛው ኪስ ውስጥ ከተተው፡፡

ካፒቴን ቤከርም ፔርሲን ‹ወደ መቀመጫህ ተመለስ ከዚህ በኋላ
ከቦታህ እንዳትነሳ›› አለው፡፡ ፔርሲ ወደ መጣበት ለመመለስ ሲል ‹‹በዚያ አይደለም›› ሲል ተቆጣ ቤከር ‹‹በደረጃው ውረድ››

ፔርሲ የቤከር ቁጣ አስደንግጦት በደረጃው ሹክክ ብሎ ወረደ፡፡
‹‹ልጁ እዚያ ቦታ ምን ያህል ቆይቷል ኤዲ?›› ሲል ጠየቀ ቤከር፡
‹‹አላወቅሁም፡፡ የተባለውን ሁሉ ሳይሰማ አይቀርም›› አለ ኤዲ፡
‹‹ተሳፋሪዎች እንደማይሰሙ ተስፋ እናደርጋለን››

ቤከር የድካም ስሜት ይታይበታል፡፡ ኤዲ ካፒቴኑ የተሸከመው ኃላፊነት ቀላል እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ ካፒቴኑ እንደገና ፈርጠም ብሎ ‹ሚስተር ፊልድ ወደ መቀመጫህ ተመለስ፡፡ ስለተባበርከን አመሰግናለሁ›› አለ፡፡ ኦሊስ ፊልድም ምንም መልስ ሳይሰጥ ወደ መቀመጫው ተመለሰ፡፡

ካፒቴኑም ‹ወደ ስራችን›› ሲል አዘዘ፡፡

ሰራተኞቹ ወደየስራ ቦታቸው ተመለሱ፡፡ ኤዲ አዕምሮው ቢታመስም ፊቱ የተደረደሩትን ሰዓቶች ቃኘ፡፡ በአይሮፕላኑ ክንፍ ላይ ያሉት የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች የያዙት ነዳጅ
እየቀነሰ ስለመጣ ከዋናው ነዳጅ
ማጠራቀሚያ ወደነዚህ ጋኖች ነዳጅ ማስተላለፍ ይኖርበታል፡፡ ሀሳቡ ግን ፍራንኪ ጎርዲኖጋ ነው፡፡ ጎርዲኖ አንድ ሰው በመግደል፣ የሰውየውን ሚስት በመድፈርና የምሽት ክበብ በእሳት በመለኮስ ተከሶ ፍርዱን ሊቀበል
ቢዘጋጅም ለኤዲ ምስጋና ይግባውና ከቅጣት ሊድን ነው፡፡ ከዚህ የባሰው ደግሞ ጎርዲኖ ከህግ ካመለጠ በኋላ ሌላ ሰው መግደሉ አይቀርም፡
ከመግደል ሌላ ምን ስራ አለው? አንድ ቀን ጎርዲኖ ስለሰራው ወንጀል ጋዜጣ ላይ ያነብ ይሆናል። ጎርዲኖ ያቃጥል ይሆናል፤ ወይ ደግሞ አንዷን ሴት አግተው ለሶስት ይደፍሯት ይሆናል፡ ይህንንም ያደረጉት የፓትሪያርካ
ወሮበሎች ይሆናሉ፡፡ ኤዲም ጎርዲኖ ይሆን ይህን ያደረገው?› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹ታዲያ ለዚህ ወንጀል እኔ እሆን ተጠያቂው? እነዚህ ወንጀል
የተፈፀመባቸው ሰዎች ይህን ሁሉ የሚያደርስባቸው እኔ ጎርዲኖን ከህግ እንዲያመልጥ ስለረዳሁት ነው› ብሎ ማለቱ አይቀርም፡፡

ነገር ግን ጎርዲኖ እንዲያመልጥ ከማድረግ ውጪ ምን ምርጫ አለው? ካሮል አን ፓትሪያርካ መዳፍ ስር ወድቃለች፡ ይህን ባሰበው ቁጥር ቀዝቃዛ ላብ በጆሮ ግንዱ ይወርዳል፡፡ እንድትጎዳበት አይፈልግም፡፡ እሷን ለማዳን ሲል ከቶም ሉተር ጋር መተባበር አለበት፡

ሰዓቱን ተመለከተ እኩለ ሌሊት ሆኗል፡

ጃክ አሽፎርድ አይሮፕላኑ ያለበትን ቦታ በቻርት ላይ አመላከተው፡ ቤን
ቶምሰን ደግሞ የአየር ሁኔታ ትንበያውን ሰጠው፡፡ ከፊታቸው ንፋስ የቀላቀለ ዶፍ ዝናብ ይገጥማቸዋል፡ ኤዲ የነዳጅ መጠን አመልካቹን አነበበና የሚያስ
ፈልገውን የነዳጅ መጠን ስሌት ሰራ፡፡ ያለው ነዳጅ ኒውፋውንድ ላንድ የማያደርሳቸው ከሆነ ወደኋላ ዞረው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ውጥኑ ሁሉ ውሃ በላው ማለት ነው፡፡ ግን መልሶ መላልሶ ማሰቡ ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ኤዲ በዕድል አያምንም፡፡ አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡

ካፒቴን ቤከር ‹‹እንዴት አደረግኸው የነዳጁን ነገር?›› ሲል ኤዲን
ጠየቀው::

‹‹ስሌቱን ሰርቼ አልጨረስኩም›› ሲል መለሰ፡፡

‹በደንብ ተመልከተው ወደኋላ መመለስ የማንችልበት ቦታ እየደረስን ነው››
ኤዲ በላብ የተጠመቀውን ፊቱን ጠረገ፡፡

ስሌቱን ሰርቶ ቢያጠናቅቅም ቀሪው
ነዳጅ ኒውፋውንድ ላንድ እንደማያደርሳቸው አውቋል፡

በወረቀት ላይ የሰራው ስሌት ላይ አፈጠጠ ልክ ስሌቱን ያልጨረሰ
ለመምሰል

የቀረው ነዳጅ ጉዞውን ለማጠናቀቅ አይበቃም፡፡ ካፒቴኑ እንደውም ያለውን በእሱ ፈረቃ መቀየሪያ ጊዜ ከነበረው ሁኔታ ያሁኑ የባሰ ሆኗል
ነዳጅ መጠን በአራት ሞተር ስሌት እንዲሰራ ቢያስደርግም እንደማይበቃ ታውቋል፡ መጠባበቂያ ነዳጅ የሚባል ነገር የለም፡፡ አሁን ያላቸው ምርጫ
ጉዞውን ለማሳጠር ሲሉ በአውሎ ንፋሱ ዳር ዳር ሳይሆን በአውሎ ንፋሱ ውስጥ መብረር ሊኖርባቸው ነው፡፡ በአውሎ ንፋሱ መሀል የሚበሩ ከሆነ ደግሞ ሞተር ሊቃጠል ይችላል፡

በዚህ አደገኛ ጉዞ ምክንያት ተሳፋሪዎች ሊያልቁ ይችላሉ። እሱም ቢሆን ከሞት አይድንም፡፡ ታዲያ ካሮል አንን ምን ይውጣታል?

‹‹በል እንጂ ኤዲ›› አለ ካፒቴኑ፡ ‹‹ወደ ቦትውድ (ካናዳ) ወይስ ወደ
ፎየንስ (አየርላንድ) የምንበረው?››
ኤዲ ጥርሱ በፍርሃት ተንገጫገጨ፡፡ ካሮል አን በነዚህ ጨካኝ ወንበዴዎች እጅ ስር ላንድ ቀን እንኳን እንድትቆይ አይፈልግም::ተሳፋሪዎቹን ለአደጋም አጋልጦም ቢሆን ይደርስላታል፡

‹የጉዟችንን አቅጣጫ ለውጠን በአውሎ ንፋሱ መሐል ለመሄድ ዝግጁ ነን?›› ሲል ጠየቀው ካፒቴኑን፡፡

‹‹በአውሎ ንፋሱ መሃል ግዴታ ነው?›› ሲል ጠየቀ ካፒቴኑ በድጋሚ።
‹‹ያለን ምርጫ ወይ በአውሎ ንፋሱ መሃል መሄድ አለበለዚያ መመለስ
ነው›› አለና ኤዲ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡
‹‹አትላንቲክ መሃል ደርሶ ወደኋላ መመለስ የሚፈልግ የለም፡››
ኤዲ የካፒቴኑን ውሳኔ በታላቅ ጉጉት ጠበቀ፡፡
👍161
‹‹የፈለገ ይምጣ!›› አለ ካፒቴን ቤከር ‹‹አውሎ ንፋሱን ሰንጥቀን
እንበራለን›› አለ፡፡...

ይቀጥላል
🥰4
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ...አይሮፕላኑ ወደ ኋላ የማይመለስበት ቦታ ላይ ሊደርስ የቀረው ትንሽ ነው፡፡ ኤዲ አዕምሮው በጭንቀት እንደተወጠረ ከምሽቱ አራት ሰዓት ወደ ስራው ተመልሶ ገብቷል፡ በዚህ ሰዓት ፀሃይ ጠልቃ ጨለማ ነግሷል፡፡ የአየር ጠባዩም ተለውጧል፡፡ዝናቡ የአይሮፕላኑን መስታወቶች ይጠልዛቸዋል ኃይለኛው ነፋስ አይሮፕላኑን እንደወረቀት…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ባርባራ ለዕረፍት ወደ ባሕር ዳርቻ በሔደችበት ቀን ሳቤላ ከመኝታዋ ወድቃ መጠራሞት ጀመረች።

ለመሰናበት ካሰበች በኋላ እንደገና ባርባራ እስክትመለስ ድረስ ልትቆያት የተሰማማችው ከልጆቹ ጋር መሰንበቷን ተስፋ አድርጋ ነበር " ሚስተር ካርላይልም
በሽተኛዪቱ አስተማሪ ከልጆች ጩኸትና ውካታ ተላቃ ከማንኛውም ሥራ ርቃ የተሟላ ጸጥታና ዕረፍት አንድታገኝ በማሰብ ልጆቹን ሎሲንና አርኪባልድን ወደ ሚስ ኮርኒሊያ ዘንድ ሰደደቸው " ሳቤላ ልጆቹ ከእሷ ጋር እንዲሰነብቱ ሆዷ እየፈለገ እንዳይሔዱ ብላ ለመጠየቅ ፈራች ስለዚህ ያሰበችው ነገር
ሲበላሺባት በዝምታ ተቀበለችው የሳቤላ ሁለተኛዉ ሐሳቧ ደግሞ ማንነቷ እንዳይታወቅባት የመሞቻዋ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ከኢስት ሊን ሹልክ ብላ ለመልቀቅ ነገር
እንዳይደርስባት የፈራችው ሰዓት ባላሰበችው ፍጥነት ቀደማት " ጊዜ ዐለፈ ልክ እንደ እናቷ እሷንም ሳይታሰብ አጣደፋት " ዊልሰን እመቤትን ተከትላ ስለ ሔደች የምታስታምማት ጆይስ ነበረች።

ባርባራ የሔደችበት ቦታ ከኢስት ሊን ሃምሳ ኪሎ ሜትር ያሀል ይርቃል
ሚስተር ካርላይል ቀን ቀን ከሥራው እየዋለ ማታ ማታ እዚያው ሔዶ ያድር ነበር " በዚህ ምክንያት ወደ ኢስት ሊን ከዘለቀ ዐሥር ቀን ዐለፈው " በነዚያ ጥቂት ቀኖች ውስጥ የሳቤላ ሁኔታ እየባሰ ሔዶ " ቀኑ ሮብ ነው ሚስተር ካርላይል
ከቤቱ ያድራል ተብሎ ይጠበቃል ።

ጆይስ የምታደርገው ነገር ጠፋት " በጣም ተጨነቀች ። ሳቤላ ተዳከመች
ራሷን መቈጣጠር አልችል አለች » ደብቃው የኖረችው ምስጢር ሊገለጽ ሆነ
የሚገለጽበት ጊዜ ደግሞ ጆይስ አስቀድማ ባለመናገሯ ከሳቤላ ጋር ተመሳጥራ አንደ ደበቀችው ተደርጎ እንዳይተረጐምባት ፈራች ባልና ሚስቱ ምን እንደሚሏት አስባው ተጨነቀች » ሚስተር ካርላይልን ጠርታ ሁሉን ነገር ልትገጽላት ብዙ
ጊዜ እያሰበች መልሳ ትተዋለች እሷ በዚህ ነገር ስትዋልል ሰዓቱ ገሠገሠ በተለይ ከእኩለ ቀን በላይ የነበረው ጊዜ ቶሎ መሸ የሳቤላ ሕይትም ከጀንበሪቷ
ጋር የመጥለቅ እሽቅድምድም የያዘች ይመስል ወደ ጥልቀት ገሠገሠች ጆይስ
ከአጠገቧ አልተለየችም
ቀኑን ሙሉ ዛል ብላ ውላ ወደ ማታ ትንሽ ዐለፍ ያለላት
መስለች ከመኝታዋ ላይ እንደ ሆነች በትራሶች ተደግፋ ትንሽ ቀና አለች " ከነጭ ሱፍ የተሠራ ያንን ልብስ ተደረበላት ደኅና አድርጋ አየር እንድታገኝ የሌት ቆቧ ወለቀላት » መስኮቶች ወለል ብለሙ ተከፈቱላት ።

ሞቃቱ የበጋ አየር ጸጥ ብሏል ጆሮዋ እንደነቃ አእምሮዋም እንዶ ሰላ ነበር
ጆይስ ” አለቻት "ዘ
እመት ” መለሰች ጆይስ
' ላየው ብችል ደሰ ብሎኝ እሞት ነበር "
“ ልየው ! " አለች ጆይስ በትክክል መስማቷን ጆሮዋን በመጠራጠር "
" እሜቴ ልየው አሎኝ ... ሚስተር ካርላይልን ?”

“ ምነው ምናለበት ? ያለሁ መስሎኝ ነው ? እኔ እኮ አሁን ሙት ማለት ነኝ "
እሱን ለማየት ብጠይቅ ነውር ሆነብኝ ? እኔ ላነጋግረው በልቤ ከተመኘሁ ብዙ ቀን ሆኖኛል " ይህ ፍላጎቴ ከሞት ፊት ተደንቅሮ አላሳልፍ አላሰቀርብ አለው .
ጣሬ በዛ ጆይስ እባክሺን ላግኘው? አንዴ ላነጋግረውና በሰላም ልሙት ”

ሊሆን አይችልም ... እሜቴ ” አለቻት ፍርጥ አድርጋ " የማይያገባ ነገር ነው " አይቃጣም !አይታሰብም”

ሳቤላ የጆይስን እምቢታ ስትሰማ እንባዋን ባራት ማዕዘን አወረደችው
ምነው ጆይስ ምን በደልኩሽ? በዚህ የተነሣ መሞት እኮ አልቻልኩም
ነፍሴ አልወጣ አለች ልጆቼን ከኔ ወሰድሽብኝ " እኔ እንዳልታወቅብሽ ስለፈራሽ እዚህ ግድም እንዳይመጡ ብለሽ ሰደድሻቸው " አሁን ደግሞ ባሌን እንዳላናግረው ትክለክይኝ ? ተይ .. ጆይስ ተይ ላግኘው! ግድ የለሺም ንግሪው ይምጣ።

ባሏ ! ምስኪን ዛሬም ባሌ ትለዋለች ጆይስ ከውሳኔዋ ፈቀቅ ባትልም ሁኔታዋ በጣም አሳዘናት ዐይኖቿ በእንባ ክድን አሉ ። ነገር ግን ሚስተር ካርላይልን ጠርታ ከዱሮ ሚስቱ ፊት ብታመጣው ባርባራ ላይ የክህደት ሥራ እንዶ
ፈጻመች እንዳይቆጠርባት ፈራች "

በፉ ተንኳኳ " ጆይስ “ ግቡ ” አለች ። ሁልጊዜ ወደዚያ ክፍል ይመጡ የነበሩት ሁሉት ሠራተኞች ሐናና ሣራ ነበሩ ሁለቱም ማዳም ቬንን ወይዘሮ ሳቤላ እንደ ነበረች አያውቁም ሣራ አንገቷን ብቅ አደረገችና
ስሚ ጆይስ ” አለቻት "
ጌቶች ይጠሩሻል .
ሚስ ጆይስ።

''እሺ መጣሁ።

“ ከመብል ቤት ናቸው " አሁን አርተር ካርላይልን ሰጥቻቸው መምጣቴ ነውኀ

“ ማዳም እንንዴት ሆነች . . . ጆይስ ? ” አላት አርተርን በትከሻው ተሸክሞ አገኘችውና ካርላይልን ።
ጆይስ ምን ብላ እንደምትመልስ ድንግር አላት " በሌላ በኩል'ደግሞ ከጥቂት ሰዓት በኋሳ በግድ የሚገለጸውን ነገር ሽፋፍና ልታልፈው አልፈለገችም

“ በጣም አሟታል , , ጌታዬ ” አለችው "

"በጣም ? ''

“ አዎን ' መሞቷ ነው መሰለኝ።

ሚስተር ካርላይል ያቀፈውን ልጅ በድንጋጤ አወረደው "

“ መሞቷ ነው ”
“ አዎን ዛሬ ማደሯንም እንጃ

“ ምነ ? ለሞት የሚያደርስ ምን ነገር አገኛት ? "

"ጆይስ አልመለሰችለትም " አሷም የምትለው ጠፍቷት ፊቷ ዐመድ መስሎ ነበር።

"ዶክተር ማርቲን አይቷት ነበር ? ”

" የለም ... ጌታዬ " ግን ምንም አይጠቅማትም ”

“ አይጠቅማትም ! " ደገመው ሚስተር ካርላይል ቆጣ ብሎ ሊሞቱ ለተቀረቡቃረቡ ሰዎች የምናደርግላቸው ይኸው ነው ? ማዳም ቬን አንቺ እንደምትይው ታማ ከሆነ ዶክተር ማርቲን በቴሌግራም ተጠርቶ ቶሎ መምጣት አለበት » እስኪ
እኔው ራሴ ሔጄ ልያት ” አለና ወደ መዝጊያው አመራ

ጆይስ ጀርባዋን ወደ መዝጊያው ሰጥታ ከበሩ መኻል ቆመችና እንዳይወጣ ከለከለችው
ጌታዬ . . ይቅርታዎን እለምናለሁ " ነገሩ ደግ አይደለም ።እባክዎን ወደሷ ክፍል መግባቱ ይቅርብዎ ”

“ ለምንድነው የማልገባው ?

“ ሚስዝ ካርላይልን ይከፋቸዋል ብላ ተንተባተበች "

“ የማታመጡት የለም " ሚስዝ ካርላይል ባትኖር የግድ አንድ ሰው ሊያያት
ያስፈልጋል። ከቤቴ ውስጥ ስትሞት ላልጠይቃት ነው ? አብደሻል መሰለኝ ጆይስ !
በይ ከራት በኋላ እጠይቃታለሁና በደንብ አዘጋጂያት ”

ራት ቀረበ ጆይስ ሕፃኑን አርተርን ይዛ ወደ ሣራ ሔደች "

ሚስተር ካርላይል ራት ሊበላ ሲጀምር እኅቱ ደረሰች " የመጣችው ከአንዳንድ ቤቶቿን ከተከራዩ ሰዎች ጋር ጭቅጭቅ ስለ ፈጠረች ለወንድሟ ለመንገር ነበር " የመጣችበትን ከመስማቱ በፊት ጆይስ የነገረችውን የማዳ ቬንን ሁኔታ ነገራትና ሔዳ እንድታያት ጠየቃት "

“ልትሞት ነው?” አለች ኮርኒሊያ እሷም ድንግጥ ብላ “ “ግድ የለህም ይህች
ጆይስ ዘንድሮ በጤናዋ አይደለችም " እስኪ አሁን ምን አገኛትና ነው ልትሞት
ነው ብላ የምታወራ ? ”

ኮርኒሊያ ላይኛው ቆቧንና ካባዋን አውልቃ ከወንበሩ ላይ ጣል አደረገች
መልኳን ከግድግዳው ላይ ከነበረው መስተዋት
ቆቧን ነካ ነካ አድርጋ አስተካከለችና በሽተኛዪቱ ወደ ነበረችበት ወደ ፎቅ ሔዳ በር መታች
ጆይስ " ይግቡ የሚል ምላሽ ሰጠቻት ወዲያው ጆይስ ማን መሆኑን ስታይ
ደነገጠችና ' “ ይተዉ እማማ አይግቡ ” አለችና ከበሩ ሒዳ ከፊቷ ተደቀነች

ማነው ደግሞ እኔን የሚከለክለኝ: ' አለች ነገሩ ስለገረማት ትንሽ ተግ ብላ ካሰበች በኋላ።በይ ዘወር በይ ሴትዮ ! ለመሆኑ ጭንቅላትሽ ደህና ነው?
ከዚህ በኋላ ደግሞ ምን ታመጪ ይሆን?

ጆይስ በሥልጣንም በጉልበትም ዐቅም እንዳልነበራት ታውቅ ነበር
ስለዚህ ሚስ ካርላይልን እንድትገባ አሳለፈቻትና ራሷ ወጣች "
👍20
ምንም የሚደበቅ ነገር አልነበረም " ቀረበች 1 አየቻት " ዐመድ ለብሶ
ጥውልግ ያለው ፊቷ ከመሸፈኛዎቿ ሁሉ ተላቅቆ ተገልጦ ከትራሱ ላይ ወድቋል ግራጫው መደረቢያዋ መነጽሯ ' ያንገቷና የሸንጎበቷ መሽፈኛ ያ ትልቅ ቆብ ሁሉ ከኖሩበት ወልቆ ተቀምጠዋል " በዚያ ሁሉ የመሸፈኛ ጓዝ ተሸፋፍኖ የነበረው ፊት ዛሬ በግልጽ ታየ በርግጥ በጣም ተለውጧል " ይሁን እንጂ የሷ የሳቤላ ቬን ፊት ለመሆኑ ትንሽም አያጠያይቅም ነበር " ሽበት ብርማ ቀለም የቀባው ጸጉሯ በሁለት ወግን ተከፍሎ የሐር ጥቅል መስሎ ካንጎቷ ተቆልሏል የሀዘን ጥላ ያረፈባቸው የሚያምሩት ዐይኖቾም አልተለወጡም " የድሮዎቹ የሳቤላ ቬን ዐይኖች እንደሆኑ ትንሽ እንኳን አያሳስቱም ።

ሁለቱም ተፋጠው ዝም አሉ " ሁለቱም እኩል ተጨነቁ ሚስ ካርላይልም እንደ በሽተኛይቱ ትቃትት ጀመር " በፊትም ቢሆን ማዳም ቬን እመቤት ሳቤላ ስለ መሰለቻት ተጠራጥራ እንደ ነበርና ኋላ ግን ሳቤላ ሙታ የመቀበሯ ጉዳይ ምንም እንደማያጠራጥር ሎርድ ማውንት እስቨርን ካረጋገጠላት በኋላ የሱን ቃል በማመን መጠራጠሯን እንደ ተወች ይታወሳል "

“ እንዴት ደፍረሽ ወደዚህ መምጣት ቻልሽ ? ” አለቻት በቁጣ ሳይሆን ልስልስ ባለ አነጋገር ሳቤላ የመነመኑት እጆቿን ከደረቷ ላይ በትሕትና አመሳቅላ ልጆቼን 'አለቻት በሹክሹክታ ከነሱ ተለይቼ መኖር አልቻልኩም " እዘኑልኝ ?ሚስ ካርላይል " እንዳይቆጡኝ ። በሠራሁት በደል ፡ በራሴ ላይ ባመጣሁት ኀዘንና መከራ ልጠየቅበት ወደፈጣሪ እየሔድኩ ነው ”

“ አልቆጣሽም ”

ወደ ዘለዓለም ዕረፍቴ በመሔዴ ደስ ይለኛል” አለች ዕንባዋ ችፍፍ ብሎ”
“እስኪ ስሚ ልጄ” አለቻት ኮርኒሊያ ወደ ሳቤላ ጠጋ ብላ በመደገፍ። “ላንቺ
ከኢስት ሊን መጥፋት ምክንያት የሆንኩኝ እኔ ነበርኩ እንዴ ? ”

ሳቤላ ራሷን በአሉታ ለመነቅነቅ ሞከረች ዐይኖቿን ስብር አድርጋ ድክም ባለ ድምፅ “እርስዎ አይደሉም ያስወጡኝ " እኔ እንድወጣም ያደረጉት ነገር የለም በእርግጥ በአርስዎ አልደሰትም ነበር። ነገር ግን የመሔዴ ምክንያት እርስዎ አይደሉም ይቅር ይበሉኝ ... ሚስ ካርላይል ይማሩኝ "

“ ተመስግን ጌታዬ ! ” አለች ኮርኒሊያ በሆዷ" ከዚያም ድምጿን ከፍ አድርጋ ' “ እኔም ቤትሺን ከዚያን ጊዜ የተሻለ የደስታ ቤት ላደርግልሽ ይገባኝ ነበር
አንቺ ከለቀቅሽ ጀምሮ እስከ ዛሬ ይቆረቁረኛል" በይ እኔንም ማሪኝ” አለቻት
አጅዋን ይዛ

ሳቤላ የሚስ ካርላይልን እጅ ወደሷ ሳብ አድርጋ ይዛ “ አርኪባልድን ለማየት እፈልጋለሁ ” አለቻት በሹክሹክታ “ ጆይስን እንድትጠራልኝ ብለምናት
አምቢ አለችኝ " እኔ ሙት ማለት ነኝ " ባገኘውና ባነጋግረው ምን አለበት?
አሁንም ለአንድ ደቂቃ ብቻ ልየውና ይቅርታ ሲያደርግልኝ ልስማው ከዚያ በኋላ በሰላም እሞታለሁ ”

ሚስ ካርላይል ነፍሷ ልትወጣ በጣር ላይ ሆና የለመነቻትን መንፈግ ስለ ከበዳት ይሁን ' ወይም ሌላ ምክንያት ይኑራት አይታወቅም " የሳቤላን ልመኖ ሰምታ ወደ በሩ ወጣች " ጆይስን ከኮሪዶሩ ውስጥ ግድግዳው ተጠግታ ዐይኖን በሽርጧ ሸፍና አየቻትና በጅዋ ጠቅሳ ወደሷ ጠራቻት "

“ ይኸን ነገር ካወቅሽው ስንት ጊዜ ሆነሽ ? "

“እንድ ጊዜ ለሊት እሳት ተነሣ ተብሎ ሁላችን ተደናግጠን ከየመኝታ
ቤታችን የወጣን ጊዜ ምንም ዐይነት መሸፈኛ ሳያደርጉ ፊታቸው በሙሉ ተገልጦ አየሁትና ዐወቅኋቸው » መጀመሪያ ግን መንፈሳቸው እንጂ እሳቸው በአካል የመጡ አልመሰለኝም ነበር ከዚያ ወዲህ እኔም ከፍራቴ የተነሣ የኖርኩት ኑሮ ኑሮ
አይበለው።

“ በይ እሺ አሁን ሒጅና ጌታሽን ወደኔ እንዲመጣ ንገሪው"

“ኧሪ ! እማማ ! መንገሩ ደግ ነው ? እንዲያዩዋቸው ነው ? ”

“ሒጅና ጌታሽን ወደኔ እንዲመጣ ንገሪው አለቻት መልሳ በማያወላወል ትእዛዝ። "አዛዥዋ አንቺ ነሽ ወይስ እኔ .. ጆይስ ? ”

ጆይስ ወረደችና ሚስተር ካርላይልን ራት ከሚበላበት አስነሥታ ይዛው መጣች

“ ማዳም ቬን ባሰባት እንዴ . . ኮርኒሊያ ? እኔን ፌለገችኝ ?

“ አዎን ልታነጋግርህ ትፈልጋለች ”....

💫ይቀጥላል💫
👍19🥰4
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሰባት (27)


« ግን ሻንጣ ፤ ቅራቅንቦ የሚያስፈልጋት መሆኑን ርግጠኛ ነህ » አለች። « ይመስለኛል ። ወደ አንድ ቦታ እንድንሄድ አስቤአለሁ። ሳታስበው እንዲሆን ስለምፈልግ ፤ ቲኬቱን እሻንጣ ውስጥ ከትቼ ላስገርማት ብዬ ነው» አለ ። አንድ ትኬት ደብቆ ለመስጠት አምስት መቶ ዶላር መክፈል ይገባል ቤን ? ቤን አቭሪ እንዲህ ገንዘብ በታኝ ሆነ ? አልፎለታል ማለት ነው ። « ዕድለኛ እመቤት ናት በለኛ»
« ዕድለኛውንኳ እኔ ሳልሆን አልቀርም››
«እንዴት ? ለመጋባት አስባችኋል ማለት ነው ?»
«የለም ነገሩስ ለሥራ ነው ። የሥራ ጉብኝት አለብን»
‹‹ ያኛው ቀይ ጥብጣብ ያለው ቡናማ ከፋይ ሻንጣ ቆንጆ መሰለኝ»
«እኔም እሱ ላይ ነው ዓይኔ ያረፈው» የሜሪን ምርጫ ተቀብሎ የሱቁን ረዳት ጠራት ። ‹‹አመሰግናለሁ ሚስ…..›› አለ፡፡ ለልጅቷ ሚገዛዉን እቃ ካሳያትና እንዲጠቀለልለት ከነገራት በኋላ ሜሪን እያየ ። «አዳምሰን» ስትል ስሟን ነገረችው «ምንም ምስጋና አያስፈልግም ። ምክንያቱም እኔም ደስ ብሎኛል ። ይልቅ ትንሽ ጥያቄ ሳላበዛብህ አልቀረሁምና ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ እኔ ነኝ መሰል ። ዓመትባል ሲቃረብ ይኸው ነኝ ። የማይሆን የማይሆን ነገር አደርጋለሁ»
«እኔም ያው ነኝ ። ብቻ የዘንድሮው ዓመት ሲያልፍ ቢከፋኝም አይፈረድብኝም ። ደስ የሚል ዓመት ነበር ። ኒው ዮርክ እንኳ ሳይቀር»
«ኒው ዮርክ ነው እምትኖረው ? »
«ከመሄድ ስገላገል ፣ አዎ ። ግን ሥራዬ ቁጭ እሚያደርግ አይደለም ። ካንዱ ወዳንዱ መዞር ነው» ይህም ቢሆን ከማይክል ጋር አብረው እንደሚሠሩ ርግጡን የሚናገር ነገር አይደለም ። ብትጠይቀው ደስ ባላት ግን አትችልም ። ይህን ስታስብ በጣም ከፋት ። ኦመማት። ስለሌላ የሷ ስላልሆነ ሰው መጠየቅ ስላሰኛት አመማት ። መጠየቅና ማወቅ ስትችል ባለመቻሏም አመማት ።

«ነገሩ እንኳ የጅል ነገር እንደሆነ ይገባኛል ። ግን ከዚህ ወጣ ብለን አንዳንድ ነገር ይዘን መጠጥ ቢጤ ይዘን ብንጨዋወት ? ለነገሩ እቸኩላለሁ ። አውሮፕላን መያዝ አለብኝ ። ግን ቅዱስ ፍራንሲስ ሆቴል ጐራ ብለን »
«እኔም ቢሆን በራሪ ነኝ ። ያም ሆኖ ሐሳቡ የድርጊቱን ያህል ነው ። አመሰግናለሁ ሚስተር አቭሪ. . .» አለች ። ፊቱ ድንገት ቅጭም አለና ፤ «ስሜን እንዴት ልታውቂ ቻልሽ ?» ሲል ጠየቃት ። «ደረሰኝ ሲቆርጡልህ ስምህን ሲጠሩ ሰማሁ» አለች አመላለሷ ፈጣን ነበረና በጥርጣሬው ሊገፋ አልቻለም ይልቁንም እንዲህ ቶሎ ተገናኝተው ቶሎ በመለያየታቸው አዘነ ። በጣም ቆንጅዬ ልጅ ናት ፤ አለ በሐሳቡ ። ዌንዲን እወዳታለሁ ። ቢሆንም ከአንዲት ቆንጅዬ ልጅ ጋር አንድ ነገር መጠጣት ኃጢአት አልነበረም ። ድንገት አንድ ሀሳብ ብልጭ አለበት «ወዴት ነው የምትሔጂው ፤ ሚስ አዳምሰን?»
«ወደሳንታፌ ፤ ኒው ሜክሲኮ » ተስፋ ቆረጠ ።
«ምን ዓይነት ርጉም እጣ ነው ። እኔ ደሞ ወደ ኒውዮርክ የምትሔጂ ቢሆን ስል »
‹‹ሻንጣ የተገዛላት እመቤት አንድ ላይ ብታዬን እጅግ ደስ እንደምትሰኝ አይጠረጠርም ነበር ። »
«እጅ ሰጠሁ ። ደግ እንግዲህ አምሳክ ካለ ሌላ ጊዜ...»
«ሳንፍራንሲስኮ ትመጣለህ እንዴ ፣ ብዙ ጊዜ?»
«ከዚህ በፊትንኳ አልነበረም ። ወደፊት ግን እይቀርም እመጣለሁ ። ማለት እንመጣለን ። የምሠራበት ድርጅት አንድ ትልቅ ፕሮጀክት አለው» አለ ። « እዚሁ ሳንፍራንሲስኮ ማለቴ ነው ። ስለዚህ ወደፊት ከኒውዮርክ ይልቅ ይኸ ሳይሆን አይቀርም መኖሪያዬ »
«እንዲያ ከሆነ ምናልባት እንገናኝ ይሆናል » ይህን ያለችበት ድምፅ በመጠኑ መከፋትን የሚገልዕ ነበር ምንም አይደለም ። ከማይክል እንጂ ከቤን ጋር ቂም የለኝም ። ስለዚህ አዘውትረን ብንገናኝም ክፋት የለበትም። የሱቅ ረዳቷ እቃው መሰናዳቱን ገለጸችላቸው ። ቤን ጨበጣት ። ጠበቅ አድርጋ ጨበጠችው።
በመገረም ቀና ብሎ አያት በለሆሳስ ። « መልካም የገና በዓል » አለችና በፍጥነት ካጠገቡ ተሰወረች « ወዲያ ወዲህ ተገላምጦ ቢያይም ሊያገኛት እይችልም ።

ከቤን እንደተለያዩ ሰውነቷ ድክምክም አለ ።
ከሱቅ እንደ ወጣች ታክሲ ተሳፍራ ወደ ቤቷ ጉዞ ቀጠለች ከዚያ በፊት ግን ፍሬድን ለእንስሳት ህክምናና ጥበቃ ድርጅት በአደራ መልክ ሰጠችው። ምክንያቱም አያስፈልጋትም። ጉዞዋ አለና በዚያም ላይ በርከት ያለ ቦታ ማየትና ማዳረስ አለበባትና የፍሬድ መኖር አመቺ አልነበረም። ብቻዋን መሔድ አለባት ። ናንሲ ማክአሊስተር በሚል ስም የዱሮ ሰብእናዋ የምትኖርባቸውን የመጨረሻ ሳምንታት ከማንም ጋር መካፈል የለባትም። ምስክር መኖር የለበትም። የአንድ ሕይወት መደምደሚያ ፤የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ነውና ብቸኝነት ያስፈልጋታል። እቤቷ እንደደረሰች ተዘዋውራ ተመለከተችው በሩን ስትዘጋ አንድ ሀረግ ተናገረች ። ለቤን አቭሪ፣ ለማይክል ፤ ያውቋት ለነበሩ ፤ ይወዷት ለነበሩ ፤ ታውቃቸው ትወዳቸው ለነበሩ ሁሉ « ደህና ሁኑ » የሚል ሀረግ ተናገረች ። ደረጃውን ስትወርድ እንባ ተናነቃት ። ካሜራዋንና የዕቃ ሻንጣዋን ይዛ ነበር ።

•••••••••••••••

እረፍቷን ጨርሳ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመለስ ፒተር እየር ማረፊያ ድረስ መጥቶ እንዳይቀበላት ቃል አስገካችው ። ምክንያቱም ያለሸኚ እንደወጣች ያለተቀባይ ልትገባ ስለፈለገች ነበር ። ጉዞውን ስትጅምር ልቧን ከብዷት መንፈሷም ተሸብሮ ነበር። ያንለት ቤን አቭሪን ማግኘቷ ወዳለፈው ሕይወቷ እየተመዘዘ በመመለስ ብዙ ነገሮችን እንድታስታውስ አስገደዳት ። በዚህም የተነሳ በመጀመሪያዎቹ እለታት ከማንም ጋር ለመነጋገር ማንንም ለማዳመጥ አልተቻላትም ። ከሀሳቧ ጋር ተፋጣ ነበር ። ያ ጉዞ ግን አብነት ስለነበረው ከጭንቀቷ ፈወሳት ። የሰላም ጊዜ አሳለፈች ። እጅግ ብዙ ነገርም ሠራች ። ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመለስ ፤ ከሳንፍራንሲስኮ ስትነሳ የነበረው ጭንቀት አልነበረም ። አሁን ስለቤን አቭሪ ማሰብ አያስፈራትም ። ያለፈውን ሕይወቷን መለስ ብላ ለመቃኘት አትፈራም ። ይህን ያህል በመለወጥ አዲስ ሰው ሆነች ። ለመጨረሻ ጊዜ ያለፈው ሕይወቷ የሌላ የምታውቃት ሴት ሆና ታያት ።

ናንሲ ማክአሊስተር ባዕድ ሆና እሷ ሜሪ አዳምሰንን ሆነች። ሜሪ የገናንም በአል ሆነ የዘመን መለወጫን በማታውቃቸው ሰዎች መካከል ሆና አሳለፈችው ። ሰዎች በአላትን ሲያክብሩ ናንሲ እነሱን ፎቶ ግራፎች አነሳቻቸው ። በተለይ የገናን በዓል በታአሰ አካባቢ ስታከብር የበረዶ ሸርተቴ የሚጫወቱት ብዙ ነበሩና ይህን ጨዋታ ለመሞከር ልቧ እጅግ ገፋፍቷት ነበር፡፡ እንዲህ ያለውን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ጨዋታ ላለመሞከር ለፒተር ቃል ገብታለት ነበርና ለራሷም በመፍራት ፍላጎቷን መግታት ግድ ሆነባት ። ፒተር የገባውን ቃል አክብሮ ሊቀበላት እንዳልመጣ! ስትገነዘብ ደስ አላት ። እንዲሀ በማያውቅህ ሠራዊት ውስጥ ስትገባ ማንም ነህ ። ማንም ማንንም አያይም ተሰውሮ መኖርን ደግሞ ብዙ ተላምዳዋለች ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ፊቷ በፋሻ ተደግልሎ ሥጋ ሳይሆን መልኳ ሻሽ በነበረበት ጊዜ ላለመታየት ከማድረግ ፣ ከመደበቅ በስተቀር ሌላ አማራጭ አልነበራትም ። ይምሰላት እንጂ የትም ብትሔድ ፤ የትም ብትገባ ያለመታየት ዕድል አልነበራትም ። የተዋበው መልኳ ፣ አረማመዷና አጠቃላይ እንቅስቃሴዋ አለባበስዋ ይህ ሁሉ ዓይንን በግድ ይስባሉ ። የግንባሯን ላይ ፋሻ ለመከለል ያደረገችው ኮፍያ ሳይቀር ለሷ ውበት ሆኗታል ። ይሁን እንጂ ይህን አልተገነዘበችውም ። ስለዚሀም ማንም አያውቀኝም
👍23
ማንም አያየኝም ብላ አሰበች ።

ከታክሲ ወርዳ ወደ አፓርታማው ለመግባት ደረጃዎችን ስትወጣ ርምጃዋ ፈራ ተባ ያለ ነበር ። አንድ ያልታሰበ ነገር የሚያጋጥማት ፤፡ አፓርታማው ተቀይሮ የሌላ ሰው ቤት ሆኖ የምታገኘው የመሰላት ይመስል፤ ገባች ። ፀጥ እንዳለ ምንም ነገር ሳይለወጥ አገኘችው ። ድንገተኛ ቅሬታ ተሰማት። ምን ፈልጌ ምን ጠብቄ ነበረና ቅር ተሰኘሁ ። ልክ በሩን ስከፍት የክብር ዘብ ተሰልፎ በታምቡርና በጥሩምባ እንዲቀበለኝ ፈልጌ ነበር ይሆን? ስትል አሰበች ። ሁኔታዋ አስገረማት ። አስቂኝ ሆኖ ታያት ። ወይስ ፒተር አልጋዬ ስር አድፍጦ ቆይቶ ብቅ እንዲል ምኞት ነበረኝ ? አለች ። ፒተር እንዳይቀበላት የከለከለችው ራሷ ስትሆን እንዴት ይህ ምኞት በልቧ ውስጥ ሊኖር ይችላል ? ፒተር …..

የላይ ልብሷን አውልቃ አልጋዋ ላይ ተዘረጋችና ሀሳቧን ለቀቀችው ። ፒተር . . . ፒተር የሚያደርግላት ሀክምና ወደ መፈጸሙ ተቃርቧል ። እንዲያውም ካሁን በኋላ እንደ ሀኪምና ታካሚ የሚገናኙት አንድ ቀን ብቻ ነው ። እንግዲህ ሥራዬን አከናውኜ ጨርሻለሁ ። ደህና ሁኝልኝ ቢለኝ ምን ይውጠኛል ? አይ ይህ አይሆንም ። ጅልነት ነው ። ፒተር ስለሷ ያለውን አስተሳሰብ በሚገባ ታውቀዋለች ። ሆኖም ምኑ ይታወቃል ? የለም አይሆንም ። የፎቶ ግራፎቿን ኤግዚቢሽን ያዘጋጀላት ፤ ሁሉን ነገር ያደራጀላት እሱ ሆኖ ሳለ ... በዚያም ላይ እንደታካሚ ሳይሆን እንደሰው... . ምን ያህል እንደሚወዳት እንደሚንከባከባት መች አጣችው ! ይህ ሁሉ ሀሳብ ሲተራመስባት አይዞሽ የሚላት ።፤ በኑሮ ላይ እንደጋገፋለን የሚላት ሰው ፈለገች ። አዲስ ሰው ነሽ ። ሜሪ አዳምሰን ነሽ ። ሜሪ አዳምሰን ጠንካራ ሰው ነች ። ትልቅ ደረጃ ይጠብቃታል ። ኑሮን አሳምራ ትኖራታለች የሚላት ሰው ፈለገች ። ሜሪ ጠንካራ መሆኗን አሰበች ። ነኝ አለች ። ሜረ ነኝ ጠንካራ ሰው ነኝ ። ታዲያ ምን አስፈራኝ ። አይዞሽ ባይ ለምን አስፈለገኝ… አለች በሀሳቧ ።

ከአልጋዋ ላይ ተፈናጥራ ተነስታ ምስሏን በመስታወቱ ውስጥ ተመለከተች ። በተቅበዘበዘ ሁኔታ ካሜራዋን አነሳች ። እንደለማዳ እንስሳ ዳበሰችው ። የኔ ነህ አለችው ። የሚያስፈልጋት ጓደኛ ያ ካሜራ ብቻ እንደሆነ አመነች ። ሀሳቧ ግራ አጋባት ። ምን ሆንኩ ? አለች ። ምንም ስትል ጥያቄዋን መለሰች ። ምንም አልሆንኩ ፣ ስለ ደከመኝ ነው። ሀሳቧን አቋርጣ ተኛች በማግሥቱ ጧት ወደ ፒተር መስሪያ ቤት ሄደች ። እግረመንገዷን ፍሬድን አደራ ካስቀመጠችበት የእንስሳት መጠበቂያ ሥፍራ ይዛው ሄደች ።

« አረ በስላሴ ! እንዴት አምሮብሻል እባክሽ ። ደሞ ካፖርትሽ ልክክ ብላብሻለች » አለ ፒተር እንዳያት የግንባሯን ፋሻ ለመሸሸግ የምትጠቀምበትን ኮፍያ አውልቃ በጅዋ ይዛ አይቶ በፍቅር የተነከረ ፈገግታ አሳየችው ። በደስታ ተሞላ ። ኮፍያውን አየት ካደረገች በኋላ ወደ ቢሮው የቆሻሻ መጣያ ሄደች « ከዛሬ ጀምሮ ባርኔጣ እሚሉት ነገር የማላደርግ መሆኔን በዚህ ድርጊት አስታውቃለሁ ። » ይህን ተናግራ ኮፍያውን ጭምድድ አድርጋ እቆሻሻ መጣያው ውስጥ ከተተችው ። « ፈጽሞም ባርኔጣ እንደማይነካሽ ርግጠኛ ነኝ » አለ ፒተር። « ስሜቴን ስለተረዳህልኝም ስለሌላው ሁሉ ምሥጋናዬ የላቀ ነው» አለች ሜሪ ።

የተሰማት ግን ካለችው ሁሉ የላቀ ነበር ። ፒተርን እቅፍ አድርጋ ልትስመው ፈለገች ። አላደረገችውም ። ፍላጐቷን ግን ከጠቅላላ ገፅታዋ አነበበ ። ዓይኗን ከፒተር ሳይ ሳትነቅል ተመለከተችው ። በጣም እንደናፈቃት ገባት ። ከዛሬ በኋላ ፒተር ጓደኛዋ እንጂ ሀኪሟ አይሆንም ። ከፈለገች ጓደኛዋ ፤ ከፈቀደችለት ሁሉን ነገር ይሆናል ። ፍቅረኛዬ ሁን ብትለው ደስ ይለዋል ። ባሌ ሁን ብትለውም እንደዚሁ ። ይህ ደግሞ ከንቱ አስተሳሰብ ወይም ግምት አልነበረም ። እንደሚያፈቅራት ብትፈቅድለትና ፍቅራቸውን ለመካፈል ቢችሉ ደስ እንደሚለው ደጋግሞ ገልጾላታል ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍17🎉2
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ጆይስ ወረደችና ሚስተር ካርላይልን ራት ከሚበላበት አስነሥታ ይዛው መጣች

“ ማዳም ቬን ባሰባት እንዴ . . ኮርኒሊያ ? እኔን ፌለገችኝ ?

“ አዎን ልታነጋግርህ ትፈልጋለች ”

ሚስ ካርላይል እየተናገረች በሩን ከፈተችው "መጀመሪያ እሷ እንድትግባ በጁ አመለከታት “ የለም” አለችው “ ብቻህን ገብተህ ብታያት ይሻላል ”

ሊገባ ሲል ጆይስ ክንዱን ያዘችው “ ጌታዬ ተዘጋጅተው ይግቡ“ እማማ
ለምን አይነግሯቸውም ?”

ሁለቱንም ትክ ብሎ አያቸው ሁኔታቸውን ይኸ ነው ብሎ ለመናገር አልቻለም
አንግዳ ነገር ሆነበት " እንዲያውም ወደ ዕብደቱ ወሰድ ያደረጋቸው መሰለው
ፊቷ ምንም ቢሆን ተለውጦ የማያውቀው ኮርኒሊያ እንኳን ምንም ኮስተር ብላ
ብትቆምም ከንፈሮቿ ሲንቀጠቀጡ መቁጣጠር አልቻለችም " ሚስተር ካርላይል ግንባሩን ቋጥሮ ሲገባ እነሱ በሩን ዘጉበት "

በቀጥታ ወደ በሽተኛይቱ አልጋ ቀስ ብሎ ተጠጋና “በጣም አዝናለሁ ማዳም ቬን...” ብሎ የጀመረውን ሳይጨርስ ቀሪዎቹ ቃላት ምላሱ ላይ ተንከባለሉ"
ሊወጡ አልቻሉም . እሱም እንደ ጆይስ የሳቤላን መንፈስ ያየ መሰለው
ከአልጋው ትንሽ አፈገፈገ ወርዶ አንገቷ ላይ የተቆለለው ጸጉሯ የሚያምሩትና የኀዘን ዳመና የጣለባቸው 0ይኖቿ ሳይቀሩ የሳቤላ ቬንን መልክ ቁልጭ አድርገው አሳዩት

አርኪባልድ ! ” አለችው "

የሚንቀጠቀጠው እጅዋን ዘረጋችና እጁን ያዘችው " ትክ ብሎ አያት» ከሕልም የነቃ ይመስል ዙሪያውንም አስተውሎ አየ "

“ነፍሴ ያንተን ይቅርታ ሳታገኝ ከሥጋዋ መለየት አልቻለችም " አለችው
የሰራችውን በደል ስታስብ ዐይኖቿን ስብር አድርጋ “ ተው ' ፊትህን አታዙርብኝ " ለአንዳፍታ ታገሠኝ ይቅር ብየሻለሁ ብቻ በለኝና በሰላም ልሙት

“ ሳቤላ ! አንቺ ነሽ? አንቺ ነሽ ? ማዳም ቬን የነበርሽው ? " አለ የሚናገረውን አላወቀውም።
ይቅር በለኝ ማረኝ... አርኪባልድ | አልሞትኩም » የደረሰብኝ አደጋ ለወጠኝ እንጂ አልገደለኝም » ነገር ግን ማንም አላወቀም ስለዚህ ማዳም ቬን
ተብዬ ወደዚሁ መጣሁ " ተነጥዬና ርቄ መኖር አልቻልኩም » ማረኝ ... አር
ኪባልድ ማረኝ " "

የሚናገረው የሚያደርገው ቅጡ ጠፋው " አምሮው ጠሮ ነፋስ እንደ ገባበት
ተበጠበጠ ግራ ገብቶት ዝም ብሎ እንደ ቆመ ነገሯን ቀጠለች "

“ ከአንተና ከልጆቼ ተነጥዬ መኖር አልቻልኩም " ያንተ ናፍቆት ሊገድለኝ ሆነ ” አለችው " አነጋግሯ የትኩሳት ቅዠት ይመስል ነበር “ “ እንደዚያ አሳብዶኝ ካን† ከተለየሁ ወዲህ የአንዲት ቅጽበት እንኳን ሰላም አግኝቸ አላውቅም .
መላው ባይጠፋኝ ኖሮ ወዲያው ተመልሸ እመጣ ነበር ከቤት ከወጣሁ አንድ
ሰዓት እንኳን ሳልቆይ ጸጸት ያዘኝ እያደር እየከበደኝ እየጠናብኝ ሔደ ምን እንዳ
ስመሰለኝ ታየዋለህ ? እየው ተመልከተው " ብላ የሸበተው ጸጉሯን የመነመ
ነውን እጁዋን አሳየችው » አንተው ማረኝ ይቅር በለኝ !ጥፋቴ በጣም ከባድ ነው ! የተቀበልኩት ቅጣት ግን ይበልጣል " ለብዙ ዘመን ከባድ መከራ ከባድ
ሥቃይ ተቀብያለሁ " ሕይወቴ ረጅም ዘመን የፈጀ የጻዕረ ሞት ሕይወት ነበር ”

“ እንዲያው ሲጀመር ምን ሆነሽ ሔድሽ?”

“ ለምን እንዶ ሔድኩ አላወቅህም? ”

“ የለም አላውቅም " እስከ ዛሬ ምስጢር እንደ ሆነብኝ ነው ”

“ አንተን ከመውደዴ የተነሣ ነበር የሔድኩት " ከንፈሮቹን በንቀት ቀስቀስ አደረጋቸው " በጣር ላይ ሆናም የምትቀልድበት መሰለው

“ ተው እንደሱ አድርገህ አትየኝ " አቅም የለኝም " ያለው የሌለው ጉልበቴ አልቋል " ከሰውነት ወጥቻለሁ " ዐይንህ ያያል " የምነግርህ እውነት መሆኑን ተረዳልኝ ነገሬ ግልጽ ካልሆነ እንጃ በጣም እወድሀ ስለ ነበር ጠረጠርኩህ፤ እኔን አለሁልሽ ብለህ እያታለልክ ፍቅርህን ለሌላ የሰጠህብኝ መስለኝ » ስለዚህ በጥርጣሬ ቅናት እንደ ቆሰልኩ ከዚያ ክፉ ሰው ወጥመድ ገባሁ " እንድበቀልህ በጆሮዬ ሹክ ይለኝ ነበር ”

“እኔ ግን አንቺን በሐሳብም፡ በቃልም በተግባርም ለማታለል አልሞከርኩም"
ያንጊዜም ታውቂኝ ነበር " ከዚያ ወዲህም ሳታውቂኝ አልቀረሽም

“አርኪባልድ ... አብጀ ነበር " በዕብደት እንጂ በጤንነት እንደዚያ ያለውን ሥራ አልሠራውም ነበር " ስለዚህ እርሳው ' ይቅር በለኝ ”

“ መርሳት አልችልም " ይቅር ካልኩሽ ግን ቆይቻለሁ "

“ ከዚያ ሌሊት ወዲህ ያለፈውን የኀዘንና የብስጭት ጊዜ ለመርሳት ሞክር” አለችው ዕንባዋ በሁለት ጉንጮቿ እየወረደ " ሥጋው አልቆ አጥንቱ ብቻ ቀርቶ በትኩሳት የሚቃጠለውን ክንዷን ወደሱ ዘርግታ : “ በሱ ፈንታ የፍቅር ጊዜአችንን ላለመርሳት ሞክር "
አኔን በመጀመሪያ ወደ ዐወቅህበት ዘመን መልሰው " ከዚህ ቤት ሳቤላ ሼን አየተባልኩ ካባቴ ጋር ደስተኛ ልጅ የነበርኩበትን ዘመን አስታውስ ያኔ ለኔ ባትገልጽልኝም እንዴት ልትወደኝ እንደቻልክ አስታውስ" አባቴ በሞተ ጊዜ የተቸገርክልኝን በዚያች ምናምን ባልነበረኝ ሰዓት አንድ መቶ ፓውንድ የሰጠኸኝን ወደ ካሰል ማርሊንግ የመጣህ ዜ
ሐሳብህን ላንዳፍታ
ላገባህ ቃል የገባሁበትን ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፌሬን የሳምከኝን ከተጋባን በኋላ የነበረን ደስታ ትዝ ይልሃል ? አብረን ያሳለፍናቸውን የፍቅር ዘመናት ታስታውሳቸዋለህ ? ሉሲ ስትወለድ ከሞት አፋፍ በመትረፌ የተሰማህን
ሁሉ ትዝ ይልሃል ? ”

“ ታዲያ አሁን እኔን ይህን አጠፋህ የምትይኝ አለሽ ” አላት አሳዛኝ እጅዋን
በእጁ ይዞ ።

አንተን ? በኔ ቀርቶ በአምላክ ዘንድም ጥፋት አይገኝብህም " ከልብህ
ወደከኝ ነበር " ለደኅንነቴ ባያሌ» ስትጨነቅልኝ ነበር » አንተ ደግሞ ምንህ ይወቀሳል? ምን አንደነበርክና ዛሬም እንዴት ያለህ ሰው እንደሆንክ ሳስበውና ከመለስኩልህ ውለታ ጋር ሳነጻጽረው በኃፍረትና በጸጸት መሬት ተከፍታ ብትውጠኝ እወድ ነበር ለራሴም ጥፋት የሚያበቃኝን ቅጣት ተቀብያለሁ ባንተና
በልጆችህ ያመጣሁባችሁን ውርደት ግን ማስለቀቅ አልችልም ”

“ የኔን ፈተና ግን አስበው " አለችው ድምጿ እየደከመ " እሱም እየራቀ የሔደውን ድምፅ ለመስማት ጆሮውን ጠጋ ለማድረግ ተገደደ ። “ በዚህ ቤት ውስጥ ከሚስትህ ጋር ተቀምጬ ምን ያህል እንደምታፈቅራት እኔን ትዳብስኝ እንደ ነበረው ስትዳብሳት እያየሁ ' በቅናት ስንገገብ ኖርኩ አሳልፌ ለሌላ ከስጠሁህ በኋላ ያፈቀርኩህን ያህል አፍቅሬህ አላውቅም ነበር " እስቲ ይታይህ' ዊልያም ልጄ ጉልበቱ እየመነመነ ሰውነቱ እያለቀ ሲሔድ እያየሁ ነፍሱ በምትወጣበት
ሰዓት ካንተ ጋር ብቻችንን ሆነን ስንጠብቀው እናቱ መሆኔን እንኳን ለመናገር
አለመቻሌ እንደ ሞተም ቤተሰቡ ሁሉ ሰምቶ ሲደናገጥ የኔን የወላጅ እናቱን ኀዘን ሳይሆን የስዋን ትንሽ መጠነኛ ኀዘን ነበር የምታጽናኑት " እኔ ባሁኑ ጊዜ ከዚህ ቤት ችየው የኖርኩት ፈተና የሞት ያህል መራራና አስጨናቂ ነበር "

“ለምን ተመልሰሽ መጣሽ ? ” አላት "

“ ነገርኩህ እኮ ካንተና ከልጆቼ ተለይቸ መኖር አልቻልኩም '

“ስሕተት ነበር ! ፍጹም ስሕተት ነበር የሠራሽው
👍10
በጣም ስሕተት ነበር እውነትህን ነው ግን ማንነቴን እንዳይታወቅ ያዶረግሁት ጥንቃቄ እስከተሳካ ድረስ የስሕተቱን ውጤት የተቀበልኩት የቅጣቱን ጽዋ የጠጣሁት እኔ ብቻ ነኝ ሞት እናቴን እንዳደረጋት እኔንም ሳላስበው ድንገት ዘሎ አነቀኝ እንጂ እኔ እስክ ሞት ድረስ ከዚህ ቤት እቆያለሁ የሚል hሳብ አልነበረኝም "
“ እንዳልከው ፍጹም ጥፋት ነው አሁን አንተን አስጠርቸ ማነጋገሬ ራሱም ከብዙዎቹ ጥፋቶች አንዱ ነው ነገር ግን እኔ ለዚህ ዓለም ሙት ማለት ስለሆንኩ ወደዚያኛው ለማለፍ አፋፍ
ላይ በማንዣበብ ላይ ስላለሁ አዲሱን ቃል ኪዳንህን የሚነካ አይመስለኝም ግን ባሌ ነበርክ " ነበር...አርኪባልድ ስለዚህ ባለፉት ጥቂት ቀኖች ውስጥ ይቅርታህን ለመለመን በጣም ስፈልግህ ነበር "
ምነው ያለፈው ነገር ሁሉ እልም ብሎ በቀረ " ምነው የፈጸምኩት ጥፋት የተቀበልኩት መከራ ሁሉ ቅዠት ሆኖ እልም ብሎ በጠፋና እንደ ዱሮ የምትወዳት ጤነኛና ደስተኛ ሚስትህ ሁኜ በነቃሁ »

"እኔ ወደ ዊልያም እየሔድኩ ነው » ሉሲና አርኪባልድ ይቀራሉ " ራራላቸው ኋላ ለተወለዱት ልጆችህ አድልተህ ፍቅርህን እንዳትቀንስባቸው " በኔ ጥፋት እነሱን አትጥላቸው
በናታቸው ዐይን አትያቸው ”

" ይህን አደራ ሊያናግርሽ የሚችል ምልክት አየሽብኝ?ልጆቹን አሁንም ልክ አንቺን እወድሽ እንደ ነበረው ያህል አወዳቸዋለሁ "
"አርኪባልድ...ወደሚቀጥው ዓለም ለመሔድ ከደፉ ላይ ቁሜአለሁ" አልፌው ከመሔዴ በፊት አንድ የፍቅር ቃል አትተነፍስሽልዥምን ? የዛሬውን ማንነቴን ለጊዜው ከአእምሮህ አውጣውና ብትችል ስለዚያች ሚስትህ ስለአደረግሃት ጠባየ ንጽሕት ለስላሳ ልጅ ለማስብ ሞክርና ፡ አንድ መልካም ቃል ብለህ ተሰናበተኝ "

“ ሳቤላ.. መጀመሪያ ጥለሽኝ የሔድሽ ጊዜ ልቤ በኀዘን ሊፈርስልሽ ምንም
አልቀረም ነበር " ሆኖም' " እኔ አሁን አንቺን በሙሉ ልቤ ይቅር እንዳልኩሽ ሁሎ እኔንም እንደዚሁ ያድርግልኝ

“ በል ዳግመኛ እንገናኛለን አብረንም እስከ ዘለዓለም እንኖራለን ዊልያም
አናቴ ከወንዙ ዳር ትፈልገኛለች ብሎ ነበር » ነገር ግን ዊልያም ነው አሁን እኔን በመፈለግ ላይ ያለው"

ሚስተር ካርላይል ሁለት እጆቹን ይዛው ስለ ነበር አንዱን አስለቅቆ ከግንባሯ ላይ ችፍፍ ያለውን የሞት ጤዛ በገዛ መሐረቡ ጠረገላት …

“ በል አርኪባልድ ቅጣቴን ከዚሀ ጨርሻለሁ ሁላችንም ከዚያ እንገናኛለን እኛም ልጆቻችንም ለዘለዓለም እንኖራለን " ይኸውም ከዚያ ሔዶ መዳር መጋባት የለምና ኃጢአት አይሆንም " አንተ ግን ለዚያች በከንቱ ለቀረችው ላንተይቱ ሳቤላ ከልብህ ውስጥ ትንሽ የትዝታ ማዕዘን ከልለህ ያዝላት። ”

'' እሺ እሺ !” አለ በሹክሹክታ "

“ መሔድህ ነው ? ” አለች እየቃተተች"

“ በጣም እየደከመሽ ነው ' ዕርዳታ መፈለግ አለብኝ „ ”

"በል እንግዲያው ደኅና ሁን እስከ መረሻው ደኀና ሁን” አለችው በረጅሙ ተንፍሳ ዕንባዋ ሳያቋርጥ እንደ ዝናብ መውረዱን ቀጠለ “ነገሩ የሞት አንጂ የዝለት አይመስለኝም " አዬ ጉድ መለያየት ጭንቅ ነው " ደኅና ሁን...ደኅና ሁን የዱሮው ውድ ባሌ "

ደግፏት የነበረውን ትራስ ለቃ ቀና አለች » የመንፈሷ መሸበር ብርታትን ሰጣት - ከክንዱ ተጠመጠመችበትና ናፍቆት የጎዳውን ፊቱን ቀና አድርጋ አየችው ሚስተር ካርላይል ቀስ አድርጎ መልሶ አስተኛትና ከንፈሮቹን በከንፈሮቿ ላይ ማረፋቸውን ቻለ።

“ እስከ ዘለዓለም ” አለ በሹክሹክታ ።

ምልስ ብሎ ከክፍሉ እስኪወጣ ድረስ በዐይኗ ስትከተለው ቆየችና ፊቷ
ወደ ግድግዳው አዞረች “ በቃ አለቀ ” አለች "
ሚስተር ካርይል እንደ ወጣ ከደረጃው ላይ ቁሞ ከራሱ ጋር ትንሽ መከሪና ጆይስን ወደ በሽተኛይቱ እንድትሔድላት ጠቀሳት " እኀቱ ከበራፍ ቁማ ነበር

“ ኮርኒሊያ ” ብሎ ጠራትና ወደ ምግብ ቤት ተከትላው ገባች "

“ ዛሬ ከዚህ ታድሪያለሽ ? ከሷ ጋር ''

" ደግሞ ለዚህ ትጠራጠር ኖረሃል ? አሁን ወዴት ልትሔድ ነው ?” አለችው

“ሎርድ ማውንት እስቨርንን ለመጥራት ወደ ቴሌግራፍ ቤት መሔዴነው…”

“ ምነው ሌላ ሰው አትልክም? ራትህ እንደ ቀረበ ሳትቀምስለት እንዳለ
ይጠብቅሃል።

ወደ ጠረጴዛው ያለ ልቡ ዞር ብሎ አየና፡ ለኮርኒሊያም ያልተሰማ መልስ አልጎምጉሞ ወቶ ሔደ ።

ሊመለስ እኅቱ ከመተላለፊያው ጠብቃ ካጠገቧ ከነበረው አንድ ክፍል ይዛው ገባች » በሩን ዘጋች ሳቤላ ከዐሥር ደቂቃ በፊት ሕይወቷ ማለፉን ነገረችው

“ አንተ ከወጣህ አንድም ቃል አልተናገረችም አርኪባልድ " መጨረሻ
ላይ ትንፋቯ ሲዘጋ ትንሽ ተወራጨች እንጂ በሰላም ሔደች "

ሎርድ ማውንት እስቨርን በአስቸኳይ የተጠራበት ምክንያት ለምን እንደሆነ
እያሰበ ምንም ጊዜ ሳያባክን ገሥግሶ በበነጋታው ጧት ደረስ ሚስተር ካርላይል
ዝግ ሠረገላውን ይዞ ከጣቢያ ጠብቆ ተቀበለው ወደ ኢስትሊን ሲመጡ በመንገድ አረዳው ኧርሉ ነገሩ ሊገባው አልቻለም " ሲገባው ደግሞ ማመን አቃተው።

" ከቤትህ ለመሞት ነው የመጣችው ? አንተስ አስገባሃት ? እኔ ነገሩ ምንም አልገባኝም ” አለው

ሚስተር ካርላይል ሁኔታውን ጨምሮ አብራራለትና በመጨረሻ ገባው „

“ ምን የሚሉት ዕብደት ነው? እዚህ መምጣት ? ማዳም ቬን እንዴት
ሳትታወቅ ቀረች ? ”

"አልታወቀችም አለ ሚስተር ካርላይል " ማዳም ቬን ከመጀመሪያ ሚስቴ ጋር በመመሳሰሏ ገርሞኝ ነበር" ግን እሷ ትሆናለች ብዬ አልጠረጠርኩም።
መመሳሰሉም ቢሆን መመሳሰል አይባልም " ፊቷ ሁሉ ተለውጦ ነበር " ያልትለወጡት ዐይኖቿንም ያለ መነጽር ዐይቻቸው አላውቅም "

ሎርድ ማውንት እስቨርን ያተኮሰውን ፊቱን ጠረገ " መርዶውን ከምንም
አልቆጠረውም " መሞቷን ቢያውቅም በአድራጐቷ ተናደዶ ሚስዝ ካርላይል ባለመኖሯም ደስ አለው "

“ አሁን ሊያዩዋት ይፈልጋሉ ? " አለው ሚስተር ካርላይል ገና ወደ ቤት ሲገቡ "

“ አዎን"

ሚስተር ካርላይል በሩን ከፈተውና ገቡ " ጆይስና ኮርኒሊያ አስፈላጊውን
ሁሉ አድርገውላታል " ሎርድ ማውንት እስሸርን ጠጋ ብሎ መልኳን አነጻጸረና
ባየው መመሳሰል ተደነቀ

ምን ገደላት ? ” አለው "

እሷ ጎዘን ነው ትል ነበር

“በዚህ ከሆነ ገና ዱሮ ባለመሞቷም ያስደንቃል" ጎዘኗማ ምን ልክ አለው! ”
አዬ ያልታደልሺው ሳቤላ” አለ እጂዋን እየነካ » “ የገዛ ደስታሽን አበላሸሽው ካርላይል ይህ የጋብቻ ቀለበትሀ መሰለኝ "

ሚስተር ካርላይል ወደ ቀለበቱ አየት አድርጎ “ ሳይሆን አይቀርም ' አለ"

“ ምንም ሳታወልቀው መኖሯም የሚገርም ነው ” አለና ይዞት የነበረውን
የ በረዶ እጅዋን ለቀቀው “እኔ ይሀን ታሪክ ማን ይቸግረኛል "

ይኸንንእየተናገረ ከክፍሉ ወጣ " ሚስተር ካርላይል ግንባሯን በጣቶቹ እየነካ ፊቷን ለአንድ ሁለት ደቂቃ ያህል ትክ ብሎ ሲመለከታት ቆናና የገለጠውን ፊት መልሶ ሸፍኖት ወጣ "

ሎርድ ማውንት እስቨርንና ሚስተር ካርላይል ወደ ቁርስ ቤት ወረዱ ሚስ
ካርላይልን ተቀምጣ ስትጠብቃቸው አገኙዋት " " ዐይኖቻቸሁ የት ሔዶው ነው ኧረ ያላወቃችሁዋት ? ” አለ ኧርሉ "

“ የእርስዎ ዐይኖች ከሔዱበት ” አለችው ኮርኒሊያ “ እርስዎ ማዳም ቬንን እኛ እንዳየናት አድርገው አይተዋታል

እኔ ከሁለትና ከሦስት ጊዜ የበለጠ አላየኋትም " ለዚያው ቆቧንና ዐይነ ርግቧን አውጥታ አይቻት አላውቅም ። ካርላይል ግን ለምን ሳያውቃት እንደ ቀረ
ይገርማል ።
👍19
“ መናገር ካስፈለገ ሐቅ ምን ጊዜም ሐቅ ነው " ከዚህ በሔደች ጊዜ ገና ወጣት ፊተ ብሩህ ንቁ ጸጉረ ጥቁርና ረጅም ቁመናዋ እንደ ቀስት ቀጥ ያለ
በጠቅላላው በጣም የምታምር ልጅ ነበረች አሁን ደግሞ ማዳም ቬን ተብላ ስትመጣ ፊቷ ገርጥቶ ጐብጣ ' አንክሳ ከእመቤት ሳቤላ አጥራ ልዩ ልዩ የማሳሳቻ ልብስ ደራርባ ተሸፋፍና ፡ ጸጉሯ ሸብቶና ከቆቡ ውስጥ ተጠቅልሎ አፏ ተለዋውጦ ፥ የፊት ጥርሶቿ ወልቀው ንግግሯ ተኮላትፎ ከፍተኛ ለውጥ ደርሶባት ነበር" ይህን ሁሉ አጠቃልለን ስንመለከተው” አለች ሚስ ካርላይል ስታጠቃልል፡
“ያቺ ከዚህ የጠፋችውን ሳቤላ ጨርሳ አትመስልም ነበር። አሁን እርስዎ ..ጌታ
በጣም የሚወዱት ጓደኛዎ በአደጋ ተሰባብሮ እንደሷ ሆኖ ተለዋውጦ ቢያዩት
በቀላሉ ሊያውቁት ይችላሉ ? ” አለችው "

አባባሏ ሎርድ ማውንት እስቨርንን አንድ ነገር አስገነዘበው አንድ በቅርብ
የሚያውቀው ሰውዬ አሠቃቂ አደጋ ደረሰበትና የድሮ መልኩ ጨርሶ ተለዋወጠ" አንደ ሳቤላ እንኳን ተጨማሪ ማሳሳቻ አላደረገም " ነገር ግን የገዛ ቤተሰቦቹም ሊያውቁት አልቻሉም " ይህ በርግጥ የደረሰ እውነተኛ ታሪክ ነው "
“የመልኳን መመሳሰል እንኳን እንደ ተባለው ለመጠርጠር ያስቸግር ይሆናል።ነገር ግን ያንን ሁሉ መሸፋፈኛ ስትደራርብ መንቃት ነበረብን” አለ ሚስተር ካርላይል

እሱንማ ገና እዚህ ቤት እንደገባች ” አለች ሚስ ኮርኒሊያ የገለጠች እንደሆን ራሷን አይኗን ፊቷን ሳይቀር እንደሚያማት ስትናገር ጊዜ ሁሉም አመናት በዚህ በኩል እንዳትጠረጠር በሩን ዘጋችው ከዚህም ሌላ እንድ
ሎርድ ማውንት እስቨርን የዱሲ ቤተሰቦችም
ጀርመን ሳለች አብረዋት ነበሩ » ግን እሷ ትሆናለች ብለው አልጠረጠሩም ሌላው መረሳት የሌለበት ነገር አለ በጣም ከፍተኛ ያሆነ መመሳሰል ብናይባትም አንሥተን አልተነጋገርንበትም " የእመቤት ሳቤላን ስም በሹክክታ እንኳን አንሥተነው አናውቅም " "

እውነት ነው ! ” አለ ሎርድ ማውንት እስቨርን " " የምትይው ሁሉ እውነት ነው።

ሚስተር ካርላይል ዓርብ የሚከተለውን ደብዳቤ ወደ ሚሲዝ ካርላይል ላከ

· የኔፍቅር እሑድ ከሰዓት በኋላ አንቺ ዘንድ እደርሳለሁ ብየሽ የነበረው የማይሳካልኝ ስለሆነ በእሑድ ሌሊት ባቡር እነሰለሁ » ስለዚህ እንዳትጠብቂኝ ሎርድ ማውንት እስቨርን ለጥቂት ቀኖች ወደዚህ መጥተው አብረውኝ አሉ”
መልካም ምኞታቸውን ያቀርቡልሻል "

“ በይ ባርባራ .. አሁን ለአንድ አስደንጋጭ ወሬ ተዘጋጂ' ማዳም ቬን ዐረፈች እኛ እንደሔድን ባንድ ጊዜ አጣድፎ ለሞት አደረሳት ብለው ነገሩኝ። ረቡዕ
ሌሊት ሞተች። ባለመኖርሽ ደስ ብሎኛል . . ምን ጊዜም ያንቺው ነኝ የኔ ፍቅር

አርኪባልድ ካርላይል”

የዌስትሊን ሕዝብ ምስጢሩ አልገባውም" የሎርድ ማውንት እስቨርንና የሚስተር ካርላይል ኀዘንተኞች ሆነው አስከሬኑን አጅበው ሊቀብሩ መምጣት የመጀመሪያው ከቤቱ ሬሳ ስለ ወጣ ሁለተኛው ደግሞ በእንግድነት እንደ ወጣ ለሚስተር ካርላይል ከበሬታ ሲል ያደረገው መስሎ ታየው ።

አስከሬኑ በሠረገላዎች ታጅቦ ክብር ባለው ሁኔታ መጥቶ ሲቀበርም አስተማሪቱ ለቀብሯ ማስፈጸሚያ በቂ ግንዘብ አጠራቅማ ስለተወች ነው ተባለ እሑድ ጧት ካባቷ ጐን ተቀበረች" ለዚሁም የዌስት ሊን ስው ምክንያት አላጣም አጋጣሚ ሆኖ ከኧርል ዊልያም ሼን መቃብር አጠግብ ባዶ ቦታ ስለ ተገኘ ነው ተባለ "

ከዚያም አስቀብረው ሲያበቁ ኧርሎና ሚስተር ካርላይል በጎዘኑ ሠረገላ ተሳፍረው ወደ ኢስት ሊን ተመለሱ "

ከመቃብሯ ላይ ሁለት ጫማ በአንድ ጫማ ተኩል የሆነ ነጭ ዕብነ በረድ
እንዲቆምላትና ሳ. ሜ . ቬ ( ሳቤላ ሜሪ ቬን ) የሚሉ ቀለሞችና ዘመንም እንዲ
ቀረፅበት ወደ ቤት በመመለስ ላይ እያሉ ከመንገድ ተስማሙ "

የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሞ በመመለስ ላይ እንዳሉ የአንድ ሌላ ቤተክርስቲያን ደወሎች ማስተጋባት ጀመሩ " ደወሎቹ አንድ ሥርዓተ ተክሊል ሲፈጸም አብሣሪዎች ነበሩ" አፊ ሆሊጆን በሁለት ካህናትና በስድስት የሴት ሚዜዎች
ረዳትነት • ሚስዝ ጂፊን ተብላ ተሠየመች » በመጨረሻ ሚስተር ጂፊን የልቡ ደረሰ "

ኧርሉ ከሰዓት በኋላ ወደ አጀሩ ተመለሰ " ጥቂት ቆይታ ባርባራ ደረሰች
ዊልሰን እመቤቷ ከቤት እስክትገባ ለመቆየት እንኳን ቸኮለች » እንዲያውም ሕፃኒቱን ከሠረገላ ውስጥ ትታት ልትሔድ ምንም አልቀራትም ነበር ያቺ ፈረንሳዊት አስተማሪ ምን እንደ ገደላት ወሬ ለማግኘት ነበር የዊሰን ጥድፊያ ሚስተር ካርላይል ደግሞ ካስበው ጊዜ ቀድመው መምጣታቸው ድንገተኛ ነገር ሆነበት "

“ አንተ ወሬውን ከነገርከኝ በኋላ እንዴት ብዬ እስከ ሰኞ ልሰንብት አርኪባልድ ? ለመሆኑ በምን ሞተች ? መቸም ድንገተኛ ነገር መሆን አለበት 'አለችው "

“ ይመስለኛል” አላት ያለልቡ ሐሳቡ በሌላ ተይዞበት ስለ ነበር እንዴት
እንደሚገልጽላት ማንስ ቢገልጽላት አንደሚሻል ያወጣ ያወርድ ጀመር በመጨረሻ ግን ከሌላ ሰው ከምትሰማ ጊዜ ሳይወስድ ወዲያውኑ እሱ ቢነግራት መሻሉን መረጠ "

“ ግን ምን ሆንክ .. አርኪባልድ ! አመመህ እንዴ ? " አለችው የፊቱን
መለወጥ አይታ "
" አንድ የምነግርሽ ነገር አለኝ . . ባርባራ ” አላት አብረው እንደቆሙ እጂዋን ወደሱ ሳብ አድርጎ " ከሷ መልበሻ ክፍል ነበሩ : “ ረቡዕ ማታ ከቤት ገብቼ
ራት ልበላ ስል ማዳም ቬን በሞት አፋፍ መሆኗን ጆይስ ነገረችኝ "

እኔም ሔጄ መጠየቅ ይገባኛል ብዬ አሰብኩ „

እንዴታ” አለች ባርባራ“ ልክ ነህ !እንዴት ታርጋለህ?”
“ ተነሳሁና ብሔድ እውነትም ደክማ አገኘኋት ግን የጠበቀኝ ሌላ ነገር ነበር ባርባራ ሴትዮይቱ ማዳም ቬን አልነበረችም "

“ማዳም ቬን አልነበረችም ? " አለች ባርባራ ድንግጥ ብላ።

" የድሮዋ ሚስቴ ነበረች ሳቤላ ቬን ”

የባርባራ ፊት መጀመሪያ ደም መሰለ። ቀጠለና ነጭ ዕብነ በረድ መስሎነጣ "
ይዞት የነበረው እጂዋን አስለቀቀችና ስበሰበች ሆኖም የታየባትን መለዋወጥና ያደረገችውን መቁነጥነጥ ልብ ብሎ ያስተዋለ አልመሰለም " ክርኑን ከአሳት መሞቂያው ምድጃ ላይ አስደግፎ ባጭሩ ማብራራቱን ቀጠለ።

“ ከልጆቹ ተለይታ መኖር ስላልቻለች ፈረንሳይ ሳለች የደረሰባት የባቡር አደጋ በጣም ስለ ለወጣትና በተጨማሪም ከጸጉሯ ሽበት ሌላ መነጽሯንና ያለባበሷን
ሁኔታ ቀያይራ እንደማትታወቅ በማመን ማዳም ቬን ተብላ መጣች አለመታወቋን ሳስበው ይገርመኛል እንደዚህ ያለ ታሪክ ከሌላ ብሰማው በጭራሽ አላምንም ነበር «

" አንተስ ጠርጥረህ ነበር ? ” አለችው ብዙ ከተጨነቀች በኋላ "

ባርባራ!ብጠረጥር ኖሮ መቸ ዝም እል ነበር?እሷ ግን ስለ ዐለፈው ድርጊቷና እንደገናም ተመልሳ ስለ መምጣቷ ይቅርታ ለመነችኝ እኔም ከልቤ አልኳት። ለማውንት እስቨርን ቴሌግራፍ ለማድረግ ዌስት ሊን ሔጄ ስመለስ ሙታ
ቆየችኝ " ኀዘን ነው የገደለኝ አለችኝ ግን ባርባራ...በዚህ አንደነቅም "

ሚስተር ካርላይል ዝም አለ። ሚስቱ ፊቷን እንዳያይባት ስትዞር አያት እሱ ግን አሷ ሳታስተውለው ቀስ ብሎ አስተውሉ ተመለከታት አውነትም የመታወክ ምልክት አየባት "
አጆቹን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ቀና ብላ እንድታየው አደረገ "

“ የኔ ፍቅር . . ምንድነው ? "

አርኪባልድ !” አለች ዕንባዋን እያወረደች “እና'ይህ ነር ፍቅርህን
ወስዶብኝ ይሆን ?

ሁለቱን እጆን በአንድ እጁ ይዞ ሌላዉን እጁን ሽንጧ ላይ ጠምጥሞ ከፊቱ
ይዟት ቆመ » አንድም ነገር ሳይናገር ዝም ብሎ ዐይን ዐይኗን ሲያያት ቆየና በመጨረሻ“ እኔስ ሚስቴ በሙሉ ልቧ የምታምነኝ ይመስለኝ ነበር ” አላት።
👍12
አዎን አምንሃለሁ እንደማምንህ አንተም ታቃለህ . . አርኪባልድ”
ይቅርታ አድርግልኝ ” ብላ ከደረቱ ተደግፋ ቀስ ብላ አለቃቀስችና ቀና ብላ አየችው።

“ የኔ ሚስት " የኔ ፍቅር • አሁንም ሁልጊዜም "

“ ልቤን በዚህ በማሻከሬ አዝናለሁ የማይረባ አስተሳሰብ ነው. .
አርኪባልድ አሁን ግን ዐለፈ

" እንደዚህ ያለ ስሜት ዳግመኛ እንዳይመጣ
... ባርባራ “ ስሟም ሁለተኛ በመኻላችን መነሣት ኢያስፈልገውም እስከ ዛሬም እንዳይወሳ የተከለከለ ነበር " እንግዲህም ቢሆን አይነሣም "

" አንተ ያልከው ሁሉ ይሁን " ዋናው ምኞቴ አንተን በማስደስት ለፍቅርህና
ለአክብሮትህ ብቁ ሁኘ ለመገኘት ነው አርኪባልድ . . .በልጆችህ እንኳን ዐይነት ስሜት አድሮብኝ ነበር ገባህ አስተሳሰቤ ምን ያህል የተሳሳተ እንደ ነበር አውቄዋለሁ » ለማረም ከልቤ ጥሬአለሁ ። በሚገባ ሞክሬአለሁ " አሁን
ጨርሶ ሊለወጥ ምንም አልቀረውም " ልክ እንደ ልጆቼ ልወዳቸው ' ልንከባከባቸው ' እንዲረዳኝ ሁልጊዜ እጸልያለሁ " "

እንድናገኘው ከልባችን የምንመኘውና የምንታገልለት መልካም ነገር ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ ይደርሳል” አለ ሚስተር ካርላይል ” ሰማሽ ባርባራ . .ምንም ቢሆን መርሳት የማይገባሽ አንድ ነገር አለ " በመጨረሻ የተረጋገጠ ሰላም ለማግኘት ሳይስገበገቡ መልካም ሥራ ለመሥራት ያለ ማቋረጥ መታገል ማስፈለጉን አትርሺ።

💫ተ..ፈ..ፀ..መ💫

አሰተያየታችሁን እጠብቃለሁ።
👏23👍20🔥2😁2😢1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ከመሐል አትላንቲክ ወደ ቦትውድ (ካናዳ)


ዳያና ላቭሴይ ባሏ ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑን መሳፈሩ በእጅጉ አስቆጥቷታል፡ በመጀመሪያ ዱካዋን እግር በእግር ተከታትሎ በመምጣት መሳቂያ መሳለቂያ ስላደረጋት አፍረት ውስጥ ከቷታል፡ ባሏ እቤታችን እንሂድ ቢላትም ሀሳቧን መለወጥ አትፈልግም ከማርክ ጋር ወደ አሜሪካ ለመሄድ የወሰነች ብትሆንም መርቪን ግን የመጨረሻ ውሳኔዋ ነው ብሎ መቀበል አልቻለም፡፡ ይሄ ደግሞ በቁርጠኝነቷ ላይ ጥላ አጥልቶበታል፡፡እሱም ውሳኔዋን እንደገና እንድታጤነው ደጋግሞ ስላሳሰባት ውሳኔዋን
በተደጋጋሚ ገልጻለታለች፡፡ በመጨረሻ ግን የአየር ጉዞዋ የሰጣትን ደስታ
ነጥቋታል፡፡

በህይወት አንዴ ብቻ የሚገጥም ከፍቅረኛ ጋር የሚደረግ ጉዞ፡፡

ከሳውዝ ሃምፕተን ሲነሱ የነበረው የነጻነትና የደስታ ስሜት አሁን የለም: መርቪን ከመጣ ወዲህ ምቹው አይሮፕላን፣ ከተለያዩ ተሳፋሪዎች ጋር መቀላቀሉና እጅ የሚያስቆረጥመው ምግብ ደስታ እየሰጣት አይደለም፡መርቪን ባጋጣሚ ሲያልፍ ያየኛል ብላ ስለፈራች ከማርክ ጋር መላፋት፣መተሻሸትና መሳሳም አልቻለችም፡፡ መርቪን የት እንደተቀመጠ አታውቅም፡፡ካሁን አሁን ይመጣ ይሆን እያለች ትበረግጋለች። ማርክ ካሊፎርኒያ ስለሚጠብቃቸው ኑሮ በተስፋ ሲያወራና ሲቀልድ ቆይቶ ጣውንቱ ከሰማይ
እንደወደቀ ሁሉ ድንገት አይሮፕላኑ ውስጥ ጥልቅ ካለ ወዲህ ግን ቀልቡ
ግፍፍ ብሏል፡ አሁን የተነፈሰ ፊኛ መስሏል፡፡ ዳያና አጠገብ ቁጭ ብሎ
አንድም ቃል ሳያነብ የመጽሔቱን ገጾች ያገላብጣል፡፡ ስሜቱ መጎዳቱን ዳያና አይታለች፡፡ አንድ ወቅት ላይ ይዟት እንዲጠፋ ከቆረጠች በኋላ ሃሳቧን ለውጣ ነበር፡፡ አሁን ባሏ ስለመጣ ከእሱ ጋር እሄዳለሁ ብላ ሃሳቧን
የማትለውጥ መሆኗን እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡
የአየሩ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱ ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል

አይሮፕላኑ ልክ ኮረኮንች ላይ እንደሚሄድ መኪና ይንገጫገጫል፡፡ በየሰዉ
ፊት ላይ ፍርሃት ይነበባል፡፡ ተሳፋሪው ሁሉ የሚያወራው ይህንኑ ነው፡

ዳያና ባሏ የት እንደተቀመጠ ማወቅ ፈለገች፡፡ እግረ መንገዴን ባየው እየተዘዋወረች ብትቃኝም መርቪንን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡ በመጨረሻ የቀራት ክፍል የሙሽሮቹ ክፍል ብቻ ነው፡፡

የሴቶች መዋቢያ ክፍል ገባች። ክፍሉ ውስጥ ሁለት ወምበሮች ያሉ ሲሆን አንዱ ወንበር ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ትኳኳላለች፡፡ ዳያና በሩን ልትዘጋ ስትል አይሮፕላኑ ዘጭ ሲል ሚዛኗን ስታ ልትወድቅ ምንም አልቀራትም፡፡ እንደምንም ተንገዳግዳ ሄዳ ባዶው ወምበር ላይ ዘፍ አለች።

‹‹ተረፍሽ?›› ስትል ጠየቀች ሴትየዋ፡፡

‹‹አዎ፣ አመሰግናለሁ›› አለች ዳያና ‹‹አይሮፕላን እንዲህ ሲሆን አልወድም››

‹‹እኔም አልወድም፡ ከዚህ በኋላ ጉዟችን የከፋ እንደሚሆን አንድ ሰው
ነግሮኛል፡ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል›› አለች፡፡

የአይሮፕላኑ ውዝዋዜ ጋብ ሲል ዳያና ጸጉሯን ማበጠር ጀመረች።

‹‹ሚስስ ላቭሴይ ነሽ አይደለም?›› ስትል ጠየቀች

‹‹አዎ ዳያና በይኝ››
‹‹እኔ ናንሲ ሌኔሃን እባላለሁ:: ፎየንስ ላይ ነው የተሳፈርኩት”
ከሊቨርፑል ካንቺ. . . ከሚስተር ላቭሴይ ጋር ነው የመጣሁት››
‹‹ኦ!›› ዳያና ይህን ስትሰማ ፊቷ በእፍረት ቲማቲም መሰለ፡፡ ‹‹ጓደኛ እንዳገኘ አላወቅሁም ነበር›› አለች በምጸት፡፡

‹‹ይህን አይሮፕላን ለመሳፈር ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ለመሄድ ፈልጌ
ሊቨርፑል ላይ መውጫ አጥቼ ስጨነቅ ባለቤትሽን አየር ማረፊያ ላይ
አገኘሁትና እንዲወስደኝ ለመንኩት››

‹‹እንኳን ቀናሽ›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹የእሱ መምጣት እኔን እፍረት ውስጥ
ከቶኛል፡፡››

‹‹ማፈር የለብሽም፡፡ ሁለት ወንዶችን በፍቅር ማጥመድሽ ደስ የሚል
ነገር ነው፡፡ እኔ አንድ እንኳን ፍቅረኛ የለኝም፡፡››

ዳያና ናንሲን በመስታወት አየቻት፡፡ ሴትየዋ ቆንጆ ባትባልም የደስ ደስ አላት፡ ጸጉረ ጥቁር ስትሆን ከሰውነቷ ጋር የሚሄድ ልብስ ለብሳለች።
ስትታይ በራሷ የምትተማመን ትመስላለች፡ መርቪን ሊፍት ቢሰጥሽ
አያስገርምም፡ እሱ እንዳንቺ ያለች ሴት ነው የሚፈልገው አለች ዳያና በሆዷ፡፡
‹‹እንዴት ነው ያሳየሽ ባህሪ ጥሩ ነበር?›› ስትል ጠየቀቻት ናንሲን፡፡
‹‹ብዙም ጥሩ አልነበረም›› አለች በቅሬታ ፈገግታ፡
‹‹አዝናለሁ፡ ይህ ባህሪው ነው የሚያስጠቃው›› አለችና ሊፒስቲኳን ጨረገች

‹‹ሆኖም በችግሬ ጊዜ ስለደረሰልኝ ባለውለታዬ ነው›› አለችና ናንሲ
ተናፈጠች፡ ናንሲ ቀለበት ማሰሯን ዳያና አጤነች፡፡ ‹‹ትህትና ባይኖረውም
ጥሩ ሰው ይመስላል፡፡ ራትም ጋብዞኛል፡ ጨዋታ ያውቃል፡፡ የሴት ልጅን
ልብ የሚሰርቅ ቁመናና መልክ አለው›› አለች፡፡

ጥሩ ሰው ቢሆንም….... አለች ዳያና ‹‹ሰው ይንቃል፡፡ ትዕግስትም የሚባል ነገር ፈጽሞ አልፈጠረበትም፡፡››
ናንሲ ጥቁር ጥቅጥቅ ያለውን ጸጉሯን ታበጥራለች ሽበቷን ለመደበቅ ቀለም ትቀባ ይሆን?› አለች ዳያና በሆዷ።

አንቺን መልሶ በእጁ ለማስገባት ሲል የሚደርስበትን መከራ ለመቀበል ቆርጧል››

‹‹አይደለም ክብሩ ስለተነካ ነው›› አለች ዳያና ‹‹ሌላ ወንድ ስለወሰደኝ ነው ያንጨረጨረው፡፡ ተጋፊ ስለመጣበት ነው ተከትሎኝ የመጣው፡ ጥዬው
እህቴ ቤት ሄጄ ቢሆን ኖሮ እኔን ለመፈለግ እግሩን አያነሳም ነበር››

ናንሲ ሳቀችና ‹‹እንዳነጋገርሽ አንቺን ለማስመለስ ተስፋ ያለው
አይመስልም›› አለች፡፡

‹‹ምንም ተስፋ የለውም›› አለች ዳያና፡፡ ዳያና ድንገት ስሜቷ ስለተረበሸ ከናንሲ ጋር ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ ሜክአፕና ማበጠሪያዋን ቦርሳዋ ውስጥ ከታታ ለናንሲ ያላት ጥላቻ እንዳይታወቅባት የውሽት ፈገግታ አሳየቻትና ‹‹ወደ ቦታዬ ልሂድ›› ብላ ተነሳች፡፡

‹‹መልካም ዕድል!››

ከሴቶች መዋቢያ ክፍል ስትወጣ ሉሉ ቤልንና ልዕልት ላቪኒያ የመዋቢያ ዕቃዎቻቸውን ያጨቁበትን ቦርሳዎቻቸውን አንጠልጥለው ገቡ፡፡
ወደ ቦታዋ ስትመለስ አስተናጋጁ ዴቭ መቀመጫቸውን ወደ ታጣፊ አልጋ ሲቀይር አየች፡፡ ዳያና አንድ ተራ ሶፋ እንዴት ወደ ተደራራቢ አልጋ ሊቀየር
እንደሚችል ገርሟታል። ዴቭ ከወምበሩ ስር አንሶላና ብርድ ልብስ አወጣና
አነጠፈ፡፡

ተደራራቢ አልጋዎቹ ምቹ ቢሆኑም ከሰው እይታ ውጭ ባለመሆናቸው
ዴቭ መጋረጃ አመጣና ጋረዳቸው፡ ከዚያም በአልጋዎቹ ጎን ትንሽ ታጣፊ
መሰላል አያያዘባቸው፡፡ ዴቭ ይህን የሰራው በሚያስደንቅ ቅልጥፍና ነው፡፡

ዴቭ ወደ ዳያናና ማርክ ዞሮ ፈገግታ ሳይለየው መኝታችሁ እንዲዘጋጅላችሁ ከፈለጋችሁ ንገሩኝና አዘጋጅላችኋለሁ›› አላቸው፡፡

‹‹ተደራራቢ አልጋዎቹ ውስጥ ሲተኙ ሰዎች አይታፈኑም?››
‹‹እያንዳንዱ አልጋ የራሱ አየር ማስገቢያ አለው›› ሲል መለሰ ‹ቀና ብለሽ ብታዪ ያንቺ አልጋ አየር ማስገቢያ አለው፡›› ዳያና ቀና ስትል መስቀያና መዝጊያና መክፈቻ ያለው በብረት ፍርግርግ የተሰራ አየር ማስገቢያ አየች:: "ከዚህ በተጨማሪ›› ሲል ቀጠለ ዴቭ ‹‹የራስሽ መስኮት፣ መብራት፣ የልብስ መስቀያና የመፀሐፍ ማስቀመጫ አለሽ።ከዚህ በተረፈ የምትፈልጊው ነገር
እንዲመጣልሽ ስትፈልጊረመ ይህን ቁልፍ ብትጫኚው ከተፍ እልልሻለሁ›› አላት።
👍10
ዴቭ ፍራንክ ጎርደንና ራስ በራው ኦሊስ ፊልድ ወደ መታጠቢያ ቤት ሲሄዱ አየና የእነሱንም መኝታ ማበጃት ጀመረ።
።።።።።።።።።።።።
ልዕልት ላቪኒያ መሬት የሚጠርግ ፒጃማ ለብሰውና ከእሱ ጋር
የሚሄድ ሻሽ ራሳቸው ላይ ጠምጥመው ከመታጠቢያ ቤት ተመለሱ።
በፒጃማ ሰው ፊት መታየታቸው ምቾት የነሳቸው በመሆኑ ፊታቸውን
ክረምት አስመስለውና ተጀንነው ተኮፍሰዋል። ድፍን የአይሮፕላኑን ሰው በፍርሃት ነው የሚያዩት:
‹‹እዚህ እፍግፍግ ያለ ቦታ ተቀምጬ መሞቴ
ነው›› ሲሉ አማረሩ። ነገር ግን ነገሬ ያላቸው ሰው የለም። ነጠላ ጫማቸውን
አወለቁና ታችኛው አልጋ ላይ ወጡ አጠገባቸው ያሉትን ሰዎች ደህና እደሩ
እንኳን ሳይሉ መጋረጃቸውን ዘጉና ብርድ ልብስ ውስጥ ገብተው ጥቅልል አሉ።

ብዙም ሳይቆዩ ሉሉ ቤል ገላዋን ወለል አድርጎ የሚያሳይ የመኝታ
ልብስ ለብሳ እየተውረገረገች ብቅ አለች: ከፎየንስ ከተሳፈሩ ወዲህ ከዳያናና ከማርክ ጋር የነበራትን መቀራረብ በድርበቡ አድርጋ ከቆየች በኋላ ማርክና ዳያና አጠገብ ቁጭ ብላ ወግ መጠረቅ ጀመረች።

‹‹አጠገባችን ስላሉት ተሳፋሪዎች አንድ ወሬ አግኝቻለሁ›› አለች ወደ
ፊልድና ጎርደን ቦታ እያመለከተች።

ማርክ በፍርሃት ወደ ዳያና አማተረና ‹‹ምን ሰማሽ ሉሉ?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹ሚስተር ፊልድ የኤፍ.ቢ.አይ አባል ነው››

ይሄ ታዲያ ምን ያስደንቃል የኤፍቢ.አይ አባል እኮ ፖሊስ ነው አለች ዳያና በሆዷ።

ሉሉ ወሬዋን ቀጠለች ‹‹ሌላው ጉዳይ ደግሞ ፍራንክ ጎርደን እስረኛ
ነው»

ማርክም ቀጠለና ‹‹ማን ነገረሽ?›› ሊል ጠየቃት፡
‹‹መታጠቢያ ቤት ሁሉም የሚያወራው ይህንኑ ነው››
‹‹ታዲያ ሁሉም ስላወራው እውነት ይሆናል?›› አለ ማርክ።
‹‹እንደማታምኑኝ እኮ አውቃለሁ›› አለች ሉሉ ያ ትንሹ ልጅ ካፒቴኑና ፊልድ ሲጨቃጨቁ ሰምቷል፡ ኤፍ.ቢ.አይ የፓን አሜሪካንን አየር መንገድ ሳያሳውቅ አደገኛ ወንጀለኛ አይሮፕላኑ ላይ ማሳፈሩ ካፒቴኑን እብድ
አድርጎታል፡ በኋላ የፊልድን ትጥቅ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አስፈቱት…››

ዳያና ፊልድ የጎርደን አንጋች መስሏት ነበር፡ ‹‹ጎርደን ጥፋቱ ምንድነው?›› ስትል ጠየቀች፡:

‹‹ማፊያ ነው፡፡ አንድ ሰው ገድሎ፣ አንዲት ሴት አስገድዶ ደፍሮ የምሽት ክበብ በእሳት አጋይቷል፡››
ዳያና የሉሉ ቤልን ወሬ አምና መቀበል ተቸገረች፡ ወጣቱን ሰው ራሷ
አናግራው ነበር፡፡ በእርግጥ ንግግሩ ብዙም የታረመ አይደለም፡፡ ይሄ እውነት
ነው: መልከ መልካምና አለባበሱ ያማረ ነው፡፡ አንድ ጊዜ ልትዳራው ሞክራ
ነበር፡ ምናልባት አጭበርባሪ ይሆናል ወይም በህገወጥ ቁማር ጨዋታ ተይዞ ይሆናል፡ ነገር ግን ሰው ገድሏል የተባለው ሊታመን አይችልም› አለች በሀሳቧ ሉሉ ደግሞ ትልቁንም ትንሹንም ታምናለች፡

‹‹ማመን ያስቸግራል›› አለ ማርክ፡፡

‹‹በሉ ፍቅረኞች›› አለች ሉሉ እጇን በንዴት አወናጭፋ ‹‹ልተኛ ነው፡፡ጎርደን ሴቶችን አስገድዶ የሚደፍር ከሆነ ቀስቅሱኝ›› አለችና ላይኛው አልጋ ላይ በመሰላል ወጣች፡ መጋረጃውን ከፈተችና ዳያናን ‹‹የኔ ማር አየርላንድ ውስጥ ለምን እንደተናደድሽብኝ ገብቶኛል፡ አውጥቼ አውርጄ ተገልጾልኛል ማርክ ላይ ስላንዣበብኩኝ ነው፡ ከፍቅረኛሽ ጋር እንዳትጫወቺ በወሬ
ጠምጄው አቆይቼዋለሁ፡ ነገር ቶሎ የማይገባኝ ሰው ነኝ፡ ጥፋቴን አርማለሁ፡ አንቺም ቂም አትያዥብኝ፡ ደህና እደሩ›› አለች።

የሉሉ ቤል ንግግር ይቅርታ እንደመጠየቅ ይቆጠራል፡ ዳያናም ይቅር ላለማለት ምክንያት አላገኘችም፡፡ ‹‹ደህና እደሪ ሉሉ›› አለች ዳያና፡፡

ሉሉም መጋረጃዋን ዘጋች፡፡
‹‹እሷ ብቻ አይደለችም፡ እኔም ጥፋተኛ ነኝ፡፡ እኔንም ይቅር በይኝ፡፡ የኔ ፍቅር›› አላት ማርክ፡፡

ዳያና መልስ የመስጠት ያህል ከንፈሩን መጠጠችው፡
ከዚያማ ምን ይወራል! ቀለል እያላት ሲመጣ መላ ሰውነቷ ዘና አለ፡፡
እየሳመችው ወንበሩን ተደገፈች፡፡ እየሳመችው ጡቷ ደረቱን ሲታከክ
ተሰማት፡ እንደገና ገላ ለገላ መተሻሸት መቻሏ ደስታ ፈጥሮላታል፡ በከንፈሩ
ጫፍ ከንፈሯን ሲዳስስ ስሜት ውስጥ ገብታ አፏን ከፍታ ተቀበለችው፡፡ ጫን
ጫን መተንፈስ ጀመረች፡ በእርግጥ የሚያደርጉት ነገር መረን የለቀቀ
መሆኑ ታውቋታል፡ ዓይኗን ስትከፍት መርቪንን አየችው:
በመጀመሪያ እያለፈ ስለነበር አላስተዋላትም ነበር፡ ድንገት ወዳለችበት
ፊቱን ዞር ሲያደርግ ያየው ነገር ከእርምጃው ገታው፡ እሷም ስታየው ፊቷ
በድንጋጤ አመድ ለበሰ፡፡....

ይቀጥላል
👍17
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ስምንት (28)

እንደሚያፈቅራት ብትፈቅድለትና ፍቅራቸውን ለመካፈል ቢችሉ ደስ እንደሚለው ደጋግሞ ገልጾላታል ። ግን እሷ ልቧን ትጠራጠረዋለች ። በይመስለኛል ስሜት ተገፋፍታ ሳይሆንላት ቢቀር ፒተርን ማስቀየም
ይሆናል ። ይህንን ደግሞ ፈፅሞ አትፈልገውም ። ስለዚህ የፒተር ጥያቄ የኣሺታም የእምቢታም መልስ ሳያገኝ በውዝፍ ዶሴ ተይዞ ቀርቷል ። መዋደዳቸው ፤ መተሳሰባቸው ፤ ጓደኝነታቸው ግን አሌ የሚባል ነገር አይደለም ። «በጣም ናፍቀኸኝ ኖሯል ፒተር» አለች ሜሪ ። ይህን ብላ ህክምና በሚደረግላት ጊዜ እምትቀመጥበት ወንበር ላይ ተቀምጣ ሥራውን እንዲቀጥል ዝግጁ ሆነች ። ዓይኗን ገርበብ አደረገች ። ከወንበሩ ላይ ተነስቶ ትንሽ ከተመለከታት በኋላ « ዛሬ ደግሞ ለመታከም ጥድፊያ በጥድፈያ ሆነሻል » አላት በተለመደው ብርጩማው ላይ ፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡ « ሁለት ዓመት ሙሉ በፋሻ ስትሸፈን ፤ ፋሻ ሲላጥልክ ብታሳልፍና የመጨረሻው ቀን ቢመጣ አንተ ራስህስ ብትሆን ያንለት ለመገላገል መቻኮልህ ይቀር ነበር ? »

«አይቀርም ፤ እንዲሁ ለማለት ያህል አልኩ እንጂ ነገሩስ ይገባኛል ። ... በደንብ ይገባኛል የኔ መቤት» እግንባሯ ላይ ያለውን ፋሻ ካነሳላት በኋላ ፤ «አሁን አይንሽን መግለጥና ፊትሽን በመስታወት ማየት ትችያለሽ ፣ ሜሪ» አለ ። ሜሪ ግን ካለችበት ላይ ንቅንቅ አላለችም ። ብዙ ዓለም አይታ መጥታለች ። ሆኖም የአዲስ እሷን ፊት ሙሉውን አታውቀውም ። አንደኛው ጐን ቢገለጥ ሌላኛው ወይ በፋሻ ተሸፍኖ ወይ ፕላስተር ተለጥፎበት ወይም ተደርቶ ነበር የምታየው። «በያ ብድግ በይና ወደ መስታወቱ ቅረቢ» አለ ፒተር ያን አዲስ ፊት ፤ ያን ናንሲ ማክአሊስተር የነበረችውን የቀድሞ እሷን ሳይሆን ሜሪ አዳምሰን የተባለችውን አዲስ እሷን ለማየት ፍርሃት ተጫናት ። ምን ያለ የማይረባ ፍርሃት ነው አለች በሐሳቧ። ፍርሃቷን እሸንፋ ተነሳች ። ፊቷን በመስታወቱ ውስጥ ስታይ ፊቷ በሳቅ ቧ ብሎ ተከፈተ ። በጉንጯ ላይ ግን እንባዋ ይጐርፍ ነበር ። ይህ የስሜት ግንፈላ ተግ እስኪልላት ድረስ አልተጠጋትም ። አላነገራትም ። ያ ጊዜ የግሏ የሆነ ማንም ሊጋራት የማይገባ ጊዜ እንደሆነ በመገንዘብ ። «ፒተር ፤ እረ የፈጣሪ ያለህ ! እንዴት ቆንጆ ነው አለች ። «አይ አንቺ ቂል ፍጡር» አለ ፒተር በለሆሳስ እየሳቀ «እንዴት ቆንጆ ነው ሳይሆን እንዴት ቆንጆ ነኝ በይ… ያቺ የምታያት ሌላ ሰው ወይ ሌላ ነገር አይደለችም ። አንቺ ነሽ ራስሽ ነሽ›› ዞራ አየችው ። የተናገረው ትክክል እንደሆነ በቃላት መግለጽ አቃታት ። ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች ። ልክ ነው ። ሙሉ በሙሉ ተቀይራለች ። ከምታውቀው መልኳ የቀረ ቅንጣት ምልክት የለም ። አሁን ያላንዳች ማወላወል ሜሪ አዳምሰን ነኝ ስትል አመነች

«ፒተር !...» አለች ውለታ በበዛበት ድምጽ ። ሄዳ ተጠመጠመችበት ። ተቃቅፈው ብዙ ጊዜ ቆዩ ። በመጨረሻ ፊቷን ለማየት እስኪችል ድረስ በክንዶቿ ይዞ ራቅ አደረጋት ። ፈቷ በእንባ ርሷል ። በጣቶቹ ጠረገላት ። «ፒተር. . . አየህ እንባየ እንኳ ፊቱን አላሟሟውም ! » አለች ። «ያ ብቻ ሳይሆን በትንሽ በትንሹ ይሁን እንጂ ፀሐይም መሞቅ ትችያለሽ» አላት ። ከዚያ በኋላ ግን ዕድሜሽን በሙሉ የፈለግሽውን ነገር ማድረግ ትችያለሽ ። ደስ ያለሽን ብትሆኝ ምንም አደጋ አይኖርም ። በነገራችን ላይ ምን ለማድረግ ነው እቅድሽ ? »

ይህን ብላ እተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተቀምጣ ፤ እግሯ ጉንጯን ነክቶ ከራሷ በላይ እስኪሆን ሽቅብ አንስታ ከወንበሩ ጋር መሽከርከር ጀመፎች ። «አምላኬ እስቲ ይኸን ምን ትለዋለህ ? ሴትዮዋ እቢሮዬ ውስጥ ገብታ አንድ አካሏ ቢጐድል ሰው ምን ይለኛል ። አበጀህ እንኳን ይለኝ ይሆን ?»
«አትፍራ እኔ እንደሆነ ዛሬ የመጣው ቢመጣ ጥርሴ እረገፈ ፤ እግሬ ተሰበረ ... ካሣ ምናምን እንደማልል ይግባህ ።የማከብረው እንጂ የምጨቃጨቅበት ቀን አይደለም»
«እንዲያም ከሆነ መልካም ። ይህ ቀን ዓመት ባልሽ መሆኑን መስማቴ ደሞ በጣም ደስ አስኝቶኛል » ፒተር ብቻ ሳይሆን ፍሬድም (ውሻው) በሆነው ነገር ደስ ያለው ይመስላል ። ይዘላል ፤ ይቧርቃል ፤ ጭራውን ይቆላል። የተናገርኩት ስለገባው ነው አለች ውሻውን እያሰበች ። ከዚያም ጨብጠኝ እንደማለት እጅዋን እየዘረጋችለት ፣ «አላወክም ነበር ማለት ነው ጅሎ !. ይህን ዕለት ለማክበር ለራሳችን ጢን ያለ የምሳ ግብዣ እናደርጋለን ፒተር›› አለች ። ስሙን ከጠራችው በኋላ ሙሉ በሙሉ እያየችው «ፒተር ውለታህን ልከፍልህ የምችል አይመስለኝም ። ግን ደግሞ እስከመቃብር ከልቤ አትጠፋም ። መቼም ቢሆን የትም ቢሆን አስታውስሃለሁ ። በበድን አካሌ ነፍስ የዘራህባት አንተ ነህ» አለች ።

«አ…እ… እኔ ሳልሆን ሌላ ሰው ነው» አለ ፒተር ። አዎ ማሪዮን ሂልያርድ ፤ የማይክል እናት ናት ፤ ይህ ሁሉ እንዲሆን ያደረገችው። ግን ደግሞ ሜሪ ማሪዮንን ምን ያህል እንደምትጠላት ስለሚያውቅ ስሟን ሊጠራ አልፈላገም ። ሌላ ሰው ብሎ ጠራት ።
ቀጥሎም...
«እኔ. .. እኔ በበኩሌ ግን ሜሪ… ያደረግኩልሽን ሁሉ ስላደረኩልሽ ደስ ይለኛል ። ለወደፊቱም ላደርግልሽ የምትፈልጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ» አለ ። «ነው?... ቀልድ መስሎሃል ፤ አደል ? እንዲያውም ከዛሬ እንጀምራለን ፤ ዛሬ በስድስት ሰዓት ተኩል ተገናኝተን ምሳዬን እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ ። እሺ?»
«ደስ ይለኛል»
«የት እንገናኝ ? » አንድ በቅርብ የተከፈተ ምግብ ቤት ጠቀሰላትና ታውቀው እንደሆነ ጠየቃት ።
«በሚገባ !» አለች ።
«ይስማማሻል ?››
«አሳምሮ ። እንዲያውም ካሁን ጀምሬ ወደዚያው አካባቢ ሄጂ ሰዓቱ እስኪደርስ ፎቶግራፍ ሳነሳ እቆያለሁ፡፡ አይን የሚገባ ነገር ከተገኘ»
«አሁን የልቤን ምኞት ነገርሺኝ ። ገበያ ሄጄ አዲስ ልብስ ስመርጥ ወይም ሌላ ብትይኝ ኖር ይከፋኝ ነበር» ተሰነባብተው ተለያዩ ፤ እስከምሳ ሰዓት ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በምሳ ሰዓት ሲገናኙ ልብሷን ቀይራ ሽክ ብላ አገኛት ። «በእውነት ይቺ ሴት አንቺው ራስሽ ነሽ ?»
«ባለወርቅ ጫማዋ ልዕልት እነሆኝ ፡። እንዴት ነው ፤ አምሮብኛል ?»
«አምሮብኛል !? እንደ ቅዱሳን አንፀባርቀሻል እንጂ ፤ ምንማማር ብቻ! ... እንደፈራሁት ፎቶ ግራፍ ማነሳሳቱን ትተሽ ቀሚስ መረጣ ላይ ዋልሽ ልበል?»
«ምን ይደረግ ትላለህ ። ሳስበው ለካ ይህ ቀን የሚከበር ፌስታ የሚደረግበት እንጂ የሚሠራበት አይደለም» ድንገት አቅፈህ ሳማት የሚል ሐሳብ መጣበት ፤ እምግብ ቤቱ ውስጥ ያ ሁሉ ሰው እያዬ ። ሐሳቡን ገታና እጅዋን ጥብቅ አድርጐ ያዛት ። «ውዴ ይህን ያህል ደስ ብሎሽ ስላየሁ እኔንም እጅግ ደስ አለኝ» ኣለ ። «ፒተር በጣም ደስ ብሎኛል ። የዛሬዋ ቀን ለኔ ልዩ ናት። ስለገጽታዬ ብቻ አይምሰልህ ። የዛሬ ቀን. . . ነገ የፎቶግራፍ ተርኢት የማቀርብበት ፤ ኤግዚቢሽኔ የሚከፈትበት ቀንም ስለሆነ... አዲስ ሕይወት መጀመሬም ነው።... አንተም አጠገቤ እንዳለህና ድንቅ እንደሆንክ ስለማውቅ»
👍141
ያንተ መኖር የምትለዋ ነገር ልቡን አፈካችው ። የሰማውን አምኖ መቀበል ከበደው ። በዛበት ። ስለዚህ እንዲህ ሲል ቀለል ሊያደርገው ሞከረ ። «ይገርምሻል ። ኤግዚቢሽን ፤ አዲስ ሕይወት... ከዚያ ሁሉ ነገር በታች እኔ ! የእኔስ ይሁን ፍሬድሳ ምን ያህል ነው አስፈላጊነቱ ? » ቀልድ ነበርና ሁለቱም ከልባቸው ይስቁ ጀመር ። የምግብ ቤቱ አሳላፊ መጥቶ ምን እንደሚጠጡ ሲጠይቃቸው ፣ ሁለት ዊስኪ እንዲያመጣ ፒተር አዘዘው ፤ወዲያው ሀሳቡን ቀየረና «የለም ሻፓኝ አድርገው » አለ ። «ሻፓኝ ? !» አለች ሜሪ ። «ነዋ! እለቱን በፌስታ እናሳልፈው ብለን የለምን? ! ለፌስታ ሻፓኝ ። በዚያ ላይ ከሰዓት በኋላ ለራሴ ፈቃድ ሰጥቻለሁ ። ሥራ አልገባም »
« እውነተኛ ፌስታ ሆነ በለኛ »
«መሆን አለበት ።. . . ምናልባት. . . ማለት አንቺ ሌላ ጉዳይ ከሌለሽ »
«የምን ሌላ ጉዳይ በል ?»
«ሥራ . . . ምናልባት »
«በዛሬው ቀን!?» ጊዜውን አብረው አሳለፉ ። በዚያ የክረምት ወራት ባህርዳር መዝናናት ያልተለመደ መሆኑ ፒተርን ቢያስገርመውም ይህን ሀሳብ ለሜሪ ሊገልጽላት ቢሞክርም ባቀረበችው ሀሳብ መሠረት ወደዚያው ሔደው ቆዩ ። እዚያም እስከዚያ ሰዓት ደብቃ ያቆየችውን ስጦታ አበረከተችለት ።የፎቶ ግራፍ ስጦታ ። ፒተር እጅግ ተደሰተ ። የሜሪ መኖሪያ አፓርታማ እንደደረሱ ፤ «ለጥቂት ጊዜ አብረን እንቆይ ተጋብዘኃል » አለች የቀረኝ ስጦታ አለ ። ጊዜ ካለህ እንግባ »
« እውነትሽን ነው ? »
‹‹ አትጠራጠር »

እሳሎን እንደደረሱ የስዕል መሳያ አትሮኖሷን ገጽ ወደ ፒተር አዞረችና መብራት አበራች ። አየው ሥዕሉን ። እዛፍ ላይ የተንጠለጠለና በዛፍ ቅርንጫፍ በመጠኑም የተከለለው ልጅ ያለበት የገፀ ምድር ምስል ሥዕሏ ነበር ። «ይህን ሥዕል ሳበረክትልህ ደስ ይለኛል ። . . . ከጀመርኩት ረጂም ጊዜ አልፏል... የጨረስኩት ግን በቅርብ ነው ። . ልጨርሰው የቻልኩት ለአንተ ለመስጠት ስለወሰንኩ ነው ። »
«ይህን ያህል. . . ?» አለ እውነት ሊሆን አይችልም በሚል ድምፅ ። በአድናቆት ተመለከታት ፡ በፍቅር አያት ። «የለም ይህ የማይሆን ነገር ነው» አለ ። « ብዙ ብዙ ነገር ሰጥተሺኛል ፡ ይበዛብኛል»
«ፒተር እስከ ዛሬ ፎቶ ግራፍ ብቻ ነው የሰጠሁህ ። ይኸኛው ይለያል ፤ ፒተር ። ይኽውም የዳግም ልደቴ ማብሰሪያ ነው ። ሌላ ሰው ከሆንኩ በኋላ ቡሩሽና ቀለም እጄን የነካው ይህን ሥዕል ለመጨረስ ስል ነው ። . . . ፒተር ይህ ሥዕል ለኔ ምን ያህል እንደነበር ልነግርሀ አልችልም ። ስለዚህ ነው ለአንተ ልሰጥህ የወሰንኩት እባክህ ተቀበለኝ » አይኗ እንባ አቆረዘዘ . . . ጠጋ አላትና አቀፋት «እንዴት ደስ የሚል ቀን ነው ። እንዴት ዋጋ የማይተመንለት ስጦታ ነው ። ምን ብዬ ላመሰግንሽ እንደምችል አላውቅም ። ደግነትሽ እጅግ ከበደኝ »
«ምንም ነገር ማለት አይሻህ ። ዝም ብትልም ይገባኛል» አለች እውጭ የጨለማው ጥላ እየከበደ ሲሄድ ይታያት ነበር ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
7🥰5👍2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት


#ክፍል_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ባኞ ቤቱ ውስጥ ጠብ ጠብ ከሚለው የውኃ ድምፅ በተጨማሪ ላይ ላይ የምትተነፍስ ሴት ድምፅ ይሰማል" የመታጠቢያ ገንዳው ውኃ እስከ ወገቡ የደረሰ ሲሆን ካርለት ውኃው ውስጥ ጋደም ብላ
ቀኝ እግሯን ገንዳው ከንፈር ላይ በማስቀመጥ ከግርጌዋ ያለውን የውኃ ማሞቂያ በተመስጦ ትመለከታለች" ከውኃ ገንዳው በስተቀኝ የእጅ መታጠቢያው ከፍ ብሎ ደግሞ በክፍሉ ሙቀት ሳቢያ የሚያዠው መስተዋት አለ የመታጠቢያ ክፍሉ ጠበብ ያለ ቢሆንም ንጹሕና ዘመናዊ ነው ከመግቢያው በር በስተግራ ካለው የቆሻሻ ልብስ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ካኔተራ፣ ሱሪና ጃኬት ተቀምጧል። ከሱ በላይ ሰፋና ረዘም ያለ በነጭና ሐምራዊ ቀለም የተዥጎረጎረ ፎጣ
ተንጠልጥሏል።

ካርለት የገንዳውን ውኃ ቀይራ ሰውነቷን በንጹሕ ውኃ ከተለቃለቀች በኋላ ከገንዳው ውስጥ ወጥታ በጥቁርና ነጭ ቀለም
የአጥር ሥዕል ከተሣለበት ጸጕራማ ምንጣፍ ላይ ቆመች" እርጥቡ ጸጕሯ ትከሻዋና ደረቷ ላይ ተለጥፏል" ከጸጕሯ ወደ ግንባሯ እየተንኳለለ የሚወርደው ውኃ በቅንድቧ ሥር እየሰረገ ተለቅና
ሰርጐድ ያለውን ዓይኗን ያራጥባል” በደረትና ትከሻዋ አካባቢ ቁጥር ቁጥር ያለ የውኃ እንክብል ከመታየቱም ባሻገር ከሴት ብልቷ ላይ ካለው ስስ ጸጕር ላይ ደግሞ በውርጭ ሰሞን ሳር ላይ የሚታየውን የመሰለ ትንንሽ የውኃ ነጠብጣብ ይታያል"

ካርለት ወደ መስተዋቱ ቀረብ እንዳለች ገፅታዋ ከሚያዠው መስተዋት ውስጥ ተከፋፍሎ ታያት። መስተዋቱን ተወት አድርጋ
በእጆቿ ጡቶቿን ጨበጥ ጨበጥ አደረገቻቸው" ቀኝ እጇ ቀኝ ጡቷ ላይ ሲቀር ግራ እጇ ግን ወደ ታች እየተንከላወሰ ጕዞ ጀመረ ወደ ሴት ብልቷ" እጇ የደረሰበትን በዓይኗ ተመለከተችው
ከሰፊው የመስተዋት መስኮትና ላዩ ላይ ከተንጠለጠለው ነጭና
ቡና ዓይነት መጋረጃ አልፎ አልፎ ዧ ብሎ የሚያልፍ የመኪና ድምፅ ይሰማል" ክፍሉ ውስጥ ካሉት ሁለት አልጋዎች መካከል አንድ
ኮመዲኖ አለ። ኮመዲኖው ላይ «ሶኒ» የሚል ምልክት ካለበት ሬዲዮ ካሴት ውስጥ ከዛሬ ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበረው ፒያኖ ሶናታ የሙዚቃ ስልት ድምፁን ሰለምለም
ሞቅ ሞቅ ሰለምለም...እያደረገ ይንቆረቆራል ከመስኮቱ ጠርዝ አካባቢ ሁለት ሶፋና አንድ ጠረጴዛ ያለ ሲሆን ጠረጴዛው ላይ ከግማሽ
በላይ የተጠጣለት የማር አረቄ ይታያል"

ስቲቭ ማርቲን የአደረው «የዞረ ድምር» ዓይኖቹን ከርቸም ያለ እንቅልፍ አጋድሞታል በአዲስ አበባው ሒልተን ሆቴል
በተዘጋጀው የቡፌ ግብዣ ላይ ሦስት ወንበር እንዲያዝላቸው በማዘዝ ሁለቱ የፍቅር ጓደኛሞች ከከሎ ሆራ ጋር በመሆን ምሽቱን ከምግብ ጕዝጓዙ በኋላ መጎንጨቱንና በአፍሪቃውያን ሙዚቃ መውረግረጉን
እስከ እኩለ ሌሊት ሲያስኬዱት ቆይተው ነው ሁለቱ ፍቅረኛሞችና
ከሎ ሆራ «መሥመርህን ለይ» የተባባሉት"

ካርለት እና ስቲቭ የሥራ ቦታቸው በጣም የተራራቀና
የትራንስፖርትም ችግር ያለበት በመሆኑ ተመልሶ ለመገናኘት ቢያንስ የሦስት ወር ጊዜ ያስፈልጋቸዋል" በፍቅር አባዜ ለተያዙት ለእነዚህ ወጣቶች ደግሞ ጊዜው የትየለሌ ነው ሩቅ። ስለ መለያየታቸው እንጂ ስለ መገናኘታቸው የማይተማመኑት ፍቅረኛሞች በወሲብና በፍቅር ጨዋታ ሰዓታቸውን በሚገባ ለመጠቀም በአንድ ወጥ ስሜት ጥረዋል" ድብቅነት በሌለው ንጹሕ የፍቅር ጨዋታ ልባቸውን
ስልትና ቃናው በሚጣፍጥ ቅላፄ እያስጨፈሩ ራሳቸውን በመሆን በፍቅር ባሕር ከመዋኘት አልፈው ዘቅጠውበት አድረዋል።

ካርለት እንደምንም በድኗን ከስቲቭ እቅፍ መንጭቃ ተነሥታ ወደ ባኞ ክፍሉ በመሄድ ገላዋን ተጣጥባ ስትጨርስና በፎጣ ገላዋን
ስታደራርቅ ከስቲቭ ረዘም ላለ ጊዜ የመለየቷን፣ የፍቅርና ወሲብ ጥመኛ የመሆኗን ትርዒት በእዝነ ልቦናዋ ስትቃኝ ፍርሃትና ጭንቀት መንፈሷን ሰንገው ያዙት ተፈጥሯዊ ስሜቷ መኪና አይቶ እንደማያውቅ ፈረስ አእምሮዋን ጥሎ በረገገባት"
አንገቷን ዘንበል በማድረግ መጀመሪያ ጡቶቿን ከዚያም
እምብርቷንና ሰርጓዳ ወገቧን፣ ለስላሳ ጭኖቿን ስትመለከት ስሜቷን
በአእምሮዋ ለመቆጣጠር ተሳናት" ካርለት ስሜቷን ልትጫነው ስላልፈለገች በግዴለሽነት የመታጠቢያ ከፍሉን በር በርግዳ ስትወጣ ስቲቭ ቀኝ እግሩን አጠፍ አድርጎ ጭኖቹን በመበርገድ ተንጋሎ ተኝቷል።

ካርለት ስቲቭን ስታየው የሆነ ስሜት በመላ አካሏ ቅጽበታዊ መተረማመስ ፈጠረና ፍቅር አመንጭ ሕዋሳቶቿ ተከፋፍተው ወደ ፊት ገፈተሯት አእምሮዋም በስቲቭ አካል ላይ ቀስቱን ደገነ የልግጠም፣ ይውጋኝ ፍልሚያ። «ግንኮ የስቲቭ ስሜት እንደኔ ላይሆን ይችላል? ስሜቴን መቆጣጠር መቻል አለብኝ" ሊደከመውም እኮ ይችላል!» ብላ አሰበች" ታስብ እንጂ መንቀሳቀሷን አላቆመችም የሚገፋፋት ስሜት ወደፊት አዳፋት ተጠጋችው» ካርለት ያሰቡትን ለማድረግ መወሰን የሚሳንበት ወቅት መሆኑ ገብቷታል"

«ስቲቭ» አለች የእጅ ጣቶቿን ወደ ቡናማው ጸጕሩ እየሰገሰገች።
ቦንብ ቢፈነዳ እንኳን የሚነቃ የማይስለው ፍቅረኛዋ የእሷን ውብ ድምፅ ሰምቶ ዓይኖቹን ሲገልጥ የሚወደው ምስል እርቃነ ሥጋውን ከአጠገቡ ቆሞ ሲያይ፣ «ኦ...» ብሎ ዓይኖቹን ገለጠ።

«ፍቅር የሚጣፍጠው ሲልሱት ሳይሆን ሲግጡት፣ ኩርሽምሽም አድርገው ሲውጡት፣ ከአካል ጋር ሲዋሐድ፣ የተፈጥሮ ቦታውን
ሲይዝ፣ ደባቂና ተደባቂ ሲሆን እንጂ በቃላት ድርደራ አይደለም»ብላ የምታምነው ካርለት ለስቲቭ፣ «ና» የሚል ምልክት በእጇ አሳየችው ያ እጇ ሁሌም ከሚያስደስተው አካሏና ውስጣዊ እሷነቷ
እንደሚያደርሰው ያውቃልና ተከተለው።

በጣም ደክሞታል፤ ከካርለት እጆችና የፈገግታ ኃይል ግን ራሱን ሊለይ አልተቻለውም። ስለዚህ ወደ ተጠራበት አቅጣጫ ተጓዘ ጒዞው ራቀበት ከተጠራበት አካል ቶሎ ደርሶ ለመደሰት በጣም ጓጕቷል ካርለት ባኞ ቤት ውስጥ እንደገቡ ገፍትራ ለብ ካለው ውኃ
ውስጥ ከተተችው ሣቀ ሣቀች ሁለመናቸው ተሣሣቀ
ጭኖቿን ተመርኵዞ አንጋጦ ሲያይ የገነትን በር ያየ መሰለው ታዲያ የዚያን ውብ ስፍራ በር ከፍቶ የማይገባ ማን አለ? በየጅማቱ ሥር ተበታትኖ የነበረው ኃይል ዘቅዝቆ ወደ ብልቱ ሲንዶለዶል
ተሰማው" ያ የተበታተነ ኃይል እንኳን የተፈቀደለትን፣ ሌላ ጠንካራ በር እንኳ ጥሶ የሚያስገባ ኃይል እንዳለው አመነ።

«እወድሃለሁI ፍቅርህን አልጠግብምI ስግብግብ ነኝ እንድትለቀኝ አልፈልግም...» የሚል ድምፅ የሰማ መሰለው
የቃላት ምልልስ ወቅቱ አለመሆኑን በመረዳቱ ግን እግሮቿን እየዳሰሰ
ተነሣ ሁለቱ አካሎች ተዋሐዱ ፍጡር ካለ ክንፍ ወደሚንሳፈፍበት ወደ ሰማየ ሰማያት ተነጥቆ የገነትን ውበት ወደሚጎበኝበት ማራኪ መዓዛ ውብና እንከን የለሽ ተፈጥሮ ወደሚታይበት፣
እውነተኛ የፍቅርና የደስታ ዜማ ወደሚዜምበት ዓለም ተያይዘው ነጐዱI በሩ ተከፍቶ ተዘጋ።

።።።።።።።።።።።
ካርለት አልፈርድ በኦhስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በሶስዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ካገኘች በኋላ በዩኒቨርሲቲው የአንትሮፖሎጂ
ዲፓርትመንት አባል በመሆን በወቅቱ ታዋቂ በነበሩት አንትሮ ፖሎጂስቶች የተዘጋጁትን ጽሑፎችና ዲስኩሮች ተከታትላለች።

ከአሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን በተለይም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ እመርታን ካሳየበት ከዛሬ መቶ ሃምሳ ዓመት ወዲህ እየተዋጡ
የመጡት ቅርሶች፣ የተናቁት ባህሎችና ለከፍተኛ ውጤት ሊያበቁ የሚችሉት የአርኪዮሎጂና የሌሎችም ጥናቶች የምሁራኑን አእምሮ ይበልጥ በመሳባቸው እንደ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ አሜሪካና ጃፓን የመሳሰሉት ምሁራን ትኵረት እንደ ሰጡት እንግሊዛውያንም ምሁራንም በመስኩ እጅግ ተስበው ነበር"
👍46
በእርግጥ፣ የአንትሮፖሎጂ ጥናት የማይዳስሰው የሕይወት ክፍል እንዳለመኖሩ ሁሉ ጥናቱና ምርምሩ ችግርና ሰቆቃ የበዛበት በመሆኑ ብዙዎቹን ቢያስደነግጥም፣ ጥቂት በሙያው የተመሰጡና እራሳቸውን መሥዋዕት ያደረጉት ግን ከራሳቸው የሕሊና እርካታ በተጨሪ ለሰው ልጆች ደኅንነትና ጥቅም ያደረጉት አስተዋፅኦና ለዓለማችን ይበልጥ መቀራረብ የተጫወቱት ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው"

ካርለትም በወባ በሽታ ተይዘው የሞቱትን፣ የአውሬ ሲሳይ የሆኑትን፣ በነፍሰ ገዳይ የተገደሉትን ስትሰማ፣ በዚህ ውጣ ውረድ በበዛው የሙያ መስክ ለመሰማራት ማሰቧ እራሷን ለመከራና ችግር መዳረግ ይሆናል ብላ በመገመቷ የተሳሳተ የሕይወት መሥመር
የተከተለች መስሏት ሰግታ ነበር" እንዳጋጣሚ ሆኖ ግን፣ እርቃ ሳትሄድ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ጽሑፎችን ስታነብና
ከተመራማሪዎች አንደበት የሚወጣውን ንግግር ስታዳምጥ፣የነበራትን ጥላቻ ለመመርመር ተገደደች።

መኖርና መሞት የሰው ልጅ አይቀሬ ዕጣ ፈንታ ቢሆንም ዓላማ ያላቸው ሰዎች አለመሞታቸውን የሚያረጋግጡት በእስትንፋሳቸው
መኖር ሳይሆን ለሕብረተሰቡ በሚያበረክቱት መልካም የሥራ ውጤት መሆኑን ስለምታምን፣እሷም በሕይወት መኖሯን
የማስመከር፣ በተለይም ሰው ሠራሽ ጾታዊ ግድቡን የማፍረስ ተልዕኮ
እንዳላት ገባት።

ካርለት ዕድሜዋ አሥራ ሁለት ዓመት ሲሆን፣ አባቷ ቻርልስ አልፈርድ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ መምህር በመሆን እ.ኤ.አ እስh 1955 ዓ.ም ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ስለ ደቡብ አፍሪካ የነጮችና ጥቁሮች ቋንቋና ኢትኖግራፊ ጥናት በማካሄድ በርካታ ጽሑፎችን ያቀረቡና ለንደን በሚገኘው የአንትሮፖሎጂስቶች
መዕከል ፕሮፌሰር የነበሩ ናቸው።

ካርለት በወርቃማው የወጣትነት ዘመኗ እንደማንኛውም የታላቋ
ብሪታንያ ወጣት ሁሉ ብርቅዬ በሆኑ አልባሳት አጊጣ ከአገሯ አልፋ
ፈረንሳይን፣ ጀርመንን፣ እስፓኝን ካናዳን...በማካለል ተዝናንታለች" ካርለት በእናቷ ትብብር ፒያኖና ቫዮለን የሙዚቃ መሣሪያዎች አጨዋወት የተማረች ቢሆንም ከሙዚቃው ይልቅ
ስሜቷ ወደ ፎቶግራፍ ማንሣት ጥበብ ስላጋደለ የፎቶግራፍ ጥበቡን
ጀመረችI ሆኖም በዚህም ብዙ ሳትገፋ ተወችው።

ካርለት ምርጫዋን ለማስተካከል ተስኗት ከፊል ጊዜዋን በመዝናናት ስታሳልፍ አባቷ ቻርልስ ዘመኑ ያቀረበላትን ማዕድ
ባርከው ሲለግሷት፣ በወቅታዊው እፍ እፍ ስሜቷ ውስጥ ጣልቃ ባይገቡም እንኳን ሕሊናቸው በወደፊት የልጃቸው ዕጣ ሕይወት
መባዘኑ አልቀረም። ሜዲትራኒያንንና የሰሃራ በረሃን አቋርጠው በመጓዝ ስላዩት ተፈጥሮ፣ ባህልና ይዘው ስለተመለሱት የጥናትናዐምርምር ውጤት ሲያወጓት፣ «እባክህ አባዬ የወሬ ርዕስህን ቀይርና
ይልቁንስ ሽርሽር ይዘኸኝ ውጣ...» ስትላቸው፣ ምንም እንኳን ስሜታቸውን በገጽታቸው ባይገልጹትም ውስጥ ውስጡን ያማቸው
ነበር" ያም ሆኖ ግን ልጃቸውን ጥናታቸውን ወደ አከናወኑበት ደቡብ
አፍሪካ ሲወስዷት እግረ መንገዳቸውን በተፈጥሮ ሀብታቸውና ቅርሳቸው የሚያደንቋቸውን አገሮች ኢትዮጵያን፣ ኬንያንና
ዝንቧቡዌን አስጐበኟት
እ.ኤ.አ በ1970 ዓ.ም ፕሮፌሰር ቻርልስ በአደረባቸው የልብ
ካንሰር ሕመም ምከንያት ፒጃማ ለብሰው ቤት መዋል ከጀመሩና እልፈተ ሕይወታቸው በግል ሐኪማቸው ከተረጋገጠ ማግስት ጀምሮ ስለ አባቷ የተጻፉ አስተያየቶችና አድናቆቶች የገዛ አባቷን
ገድል እንደምትመረምር ጋበዟት"

ካርለት ለመጀመሪያ ጊዜ ካሸለበችበት በመንቃት የአባቷን ወርቃማ ሥራዎች ለመረዳት ተጣጣረች ጥረቷ የዘገየና ፀሐይ ከጠለቀ በኋላ በመሆኑ ግራ ብትጋባም፣ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ዓላማቸውንና ያደረጉትንም አስተዋፅኦ ተገነዘበች" ያ ወቅት
በእርግጥ የወጣትነት ቡረቃዋን ገትታ፣ ዘላቂውን የሕይወት ድርሻዋን፣ የምትከተለውን ዓላማ ያጤነችበት፣ የረጋው ፍላጎቷ
ማዕበሉ ተጠናክሮ የዋዠቀችበትና በመጨረሻም መልሕቋን
በመወርወር ለውሳኔ የበቃችበት ወቅት ሆነ።

ወርቃማው ጸጕሯ፣ ድሎት ያወረዛው ፊቷና መካከለኛው ቁመናዋ በጅምናስቲክ በተገነባው ቅርፅዋ እየተረዱ የብዙ ወንዶችን ልብ ያሸፈቱ ቢሆኑም፣ ተባባሪ የውበት አለኝታዎቿ አቅመ ቢስ
ሆነውባት እሷም በፍቅር ቡጢ ጥርሷ እስኪነቃነቅና እንባዋ እስኪጐርፍ ድረስ አፍቅራ ተመናቅራለች እንዲያውም ይህ ልምዷ
የተመኙትን ሁሉ ማግኘት አለመቻሉን፣ ፈላጊና ተፈላጊ መተላለፍ የሚያበዙ መሆናቸውንና የፈለጋት እንዲያገኛት በተቻለ መጠን
መገኘት የሚያስችላትን ቦታ ፈልጋ እንድታገኝ ረዳት
ካርለት፣ በሕይወቷ ሽንፈት ደጋግሞ እንደሚያጋጥማት
ታምናለች የምትፅናናበት ግን በፍላጎቷ ወደ ውድድር መድረክ መቅረቧና ከማን ከማን ጋር እንደምትወዳደር ማወቋ ነው «ከተወዳዳሪዎቹ ሁሉ ጅሉ ሰው በውድድሩ ተካፍሎ ለማሸነፍ በመጣጣር
አልሳካልህ ብሎ የተሸነፈው ሳይሆን፣ መወዳደሩንና ተወዳዳሪዎቹን ሳያውቅ ለድል የበቃው ነው» ማለት ታዘወትራለች።

ካርለት የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፖሉጂ ዲፓርትመንት አባል ሆና የማስተር ዲግሪዋን ካገኘች በኋላ፣ ለቀረው ጥናቷ ቀደም ሲል አባቷ ካሳይዋት አገሮች ኢትዮጵያን መረጠች በማከታ ተልም ኢትዮጵያ ነከ የሆኑ የጽሑፍ፣ የፊልምና የስላይድ መረጃዎችን
በየጕራንጕሩ ሁሉ እያነፈነፈች ከተመለከተች፣ በተለይም ስለ ኢትዮጵያ ዕውቀት ካላቸው አማካሪዋ ከፕሮፌሰር ጆን ፒደርሰን ጋራ በወደፊት የጥናት ቦታዋ ላይ በስፋት ከተመካhሩ በኋላ በእንግሊዝ የምሥራቅ አፍሪካ አንትሮፖሎጂስቶች የጥናት ድርጅት አባል
ሆነች ከዚያም በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ማኅበረሰቦች ውስጥ በሐመር ማኅበረሰብ ባህል ላይ ጥናቷን ለመጀመር ከአማካሪዋ ጋር ተስማሙ። ልታከናውን ላሰበችው ጥናትም የእርዳታ ሐሳብ
ለድርጅቱ አቀረበች ድርጅቱም የጠየቀችውን በጀት አጸደቀላት።ካርልት፣ በዚህ በጀት ብቻም ሳትወሰን ለዓለም የሴቶች ኮሚቴም ተጨማሪ በጀት እንዲሰጣት ጠየቀች.....

💫ይቀጥላል💫
👍35🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ዘጠኝ (29)

«ውዴ . . . እስኪ ዚፔን ዝጋልኝ » ብላ ውብ ጀርባዋን አዞረችለት « እኔ እንኳ ደስ የሚለኝ… ብከፍተው ነበር››
«ፒተር ! . . . እንዲህ ያለ ወሬ… » አለች በማስጠንቀቅ መልክ ተገላምጣ እያያችው ። ሁለቱም ሳቁ ። አለባበሷን ሲመለከት ፣ ውበቷን ሲያይ በአድናቆት ተዋጠ ። «በኋላ ምን ብሎ ነበር ብለሽ ናቂኝ አንድ ሰው ፎቶግራፍሽን ቢያይ ከምላሴ ጠጉር »
« ለምን?»
«የተመልካች ዓይን አንቺው ላይ ያርፋል ። እዚያ ተተክሎ ይቀራል። በቃ !»
« ያን ያህል ?» ይህን ስትል ያለውን ነገር ፈጽሞ እንዳላመነች ገባው ። ጥርጣሬዋ የመገረም ሳቅ አሳቀው ። እሱም በኤግዚብሽን መክፈቻ ላይ ሽክ ብሎ ለብሷል ። ቢጋቡ የሚያስቀኑ ባልና ሚስት ይሆናሉ። «እንዴት ነው ? ፎቶ ግራፎቹን እንደምትፈልጊው አድርገው ሰቀሉልሽ ? ጊዜው ጠፋና ይህን እንኳ ልጠይቅሽ አልቻልኩም»
«ምንም ችግር የለም ። ያዘዝኩት ሁሉ እንዳዘዝኩት ሆኖ ተፈጽሟል ። እድሜ ላንተ ፤ ፒተር ። ይኸኔ ቅር ይላትና ዋ! ብለሀቸዋል ። ወይ አንተ ወይ ጃክ ይህን ያላችሁ ይመስለኛል » ጃክ የኤግዚብሽኑ አዳራሽ ባለቤት ሲሆን የፒተር ግሬሰ? የረጂም ጊዜ ጓደኛ ነው ። « ሁሉን ነገር ሰው ይሰራዋል ። እኔ በቃ አርቲስት ብቻ ነኝ የሚል ስሜት ይሰማኝ ጀመር››
«ሊሰማሽ የሚገባ ነው። ይሀ ትርኢት ሲያልቅ የኪነጥበብ ስራሽ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ያኔ ታያለሽ ።»

እንዳለውም ሆነ ። ኤግዚብሽኑ በተከፈት ማግስት በጋዜጦች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች በአድናቆት የተሞሉ ነበሩ። ፒተርና ሜሪ ጧት ቁርሳቸውን በልተው ቡና እየጠጡ ጋዜጦችን ሲያነቡ በጣም ደስ አላቸው ። «አላልኩሽም ?» አላት ፒተር ፤ ገና የመጀመሪያውን በአድናቆት የተሞላ አስተያየት ሲያነብ « አየሽ ? ኮከብ ነሽኮ »
«አንተ ደሞ ጅል ነህ ! » አለችና ጋዜጣውን አስደገፈበት ጭኑ ላይ ዘጭ ብላ ተቀመጠችበት ። ጋዜጣው ተጨማደደ። «እስከሚቀጥሊው ሳምንት ቆይና ደሞ ሌላ ተአምር ታያለሽ ። እያንዳንዱ ፎቶግራፍ እያራባ የሚሸጥ ድርጅትና ፎቶግራፍ አሻሻጭ ከመላ ሀገሪቱ ዳር እስከዳር ስልክ እየደወለ ባያስቸግርሽ ቱ! ከምላሴ ፀጉር ! »
«በቃ አዕምሮሀን እንደመንሳት እያደረገህ ነውኮ ውዴ!» ሆኖም የፒተር ግምት ሜሪ የገመተችውን ያህል ከእውነት የራቀ አልነበረም ። በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ከተለያዩ ሰዎች የስልክ ጥሪዎች ይመጡ ጀመር። ሰኞ ዕለት ከሎስ አንጀለስ እና ከችካጐ የተለያዩ ጥሪዎች ደረሷት ። እያንዳንዱ ሰው ስልክ ደውሎ የሚያቀርብላት ጥያቄና አድናቆት አስደነቃትም ። አስደሰታትም ። ስለዚህም ስልክ በተደወለ ቁጥር አሁን ደግሞ ምን ይሉ ይሆን ? በሚል ጉጉት ስልኩን ታነሣለች ። ይህ ቀጠለ ፤ ቤን አቭሪ እስኪደውልላት ድረስ ።

ቤን አቭሪ የደወለው አንድ ማክሰኞ ቀን ወደ ማታ አካባቢ ነበር ። በዚያም ሰዓት ሜሪ ፊልሞችን ለማሳደግና ለማጣብ በማሰናዳት ላይ ነበረች ። ከተለያዩ ቦታዎች ፎቶግራፎቿን ለመግዛት የትእዛዝ ጐርፍ መጉረፍ ጀምሮ ስለነበር ከፎቶግራፍ ማጠቢያው ክፍል (ዳርክ ሩም) ለመውጣት እንኳ ጊዜ አነበራትም ። በሥራዋ ተመስጣ እያለች ስልኩ ተንጫረረ። ሥራዋን አቋርጣ እየተጣደፈች ወጣች ። ምክንያቱም ፒተር «በዚያ ሰዓት ስብሰባ ስላለብኝ ደውዬ የት እንደምንገናኝ እነግርሻለሁ » ብሏት ነበር ። ስልኩን አንሥታ «ሃሎ » አለች ። «ሚስ አዳምሰን» አለ አንድ የማታውቀው ድምጽ፡፡ «ነኝ» አለች ፒተር ስለመሰላት በገጽታዋ ላይ ፈክቶ የነበረው ፈገግታዋ እየጨለመ ። «አኦ.. ከዚህ በፊት ለገና በዓል የስጦታ ዕቃዎችን ስገዛ ሚስ አዳምሰን ከምትባል ሰው ጋር ተዋውቀን ነበር ። ከሞክሼሽ ጋር ይሁን ካንቺ ጋር እርግጠኛ አይደለሁም ። የጉዞ ሻንጣዎች ስገዛ ተገናኝተን... » ቤን ነው ማለት ነው ። አይደለሁም ልበለው? ለምን?
« ከኔ ጋር ሳይሆን አልቀረም » አለች…. መዋሸት የሚያስፈልግ አልመሰላትም ። «ማለቴ ...እኔ.. ነው ? ማለት የማውቃት ሚስ አዳምሰን ነሻ ? »
«ነኝ»
« ይህንን ማረጋገጡም አንድ ነገር ነው ። ማለት ተቀራርበን ለመነጋገር ባንችልም እንተዋወቃለን ። ብቻ አሁን የደወልኩልሽ እንኳ የያኔ ትውውቃችንን በሚመለከት አይደለም ። የፎቶግራፍሽን ኤግዚብሽን ስላየሁ አንዳንድ ነገር እንድንነጋገር ስለፈለኩ ነው ።. ...ግሩም የሆነ ሥራ ነው ሚስ አዳምሰን ። እኔም ጓደኛዬ ሚስ ታውንሴንድም ኤግዚብሽኑን ዓይተን የተሰማን ስሜት ከፍተኛ ነው » የጠራት ሴት ዕቃው የተገዛላት ሴት ትሆን ? የማወቅ ፍላጐት አደረባት ። ሆኖም መጠየቅና ማወቁ አስፈላጊ መስሎ አልተሰማትም ። ስለዚህም በረጂሙ ተንፍሳ…. «ደስ ስለተሰኛችሁ እኔም ደስ ብሎኛል ፤ ሚስተር አቭሪ›› አለች ።
« ስሜንም አልረሳሽም?»
«ስሞችና የመሳሰሉ ነገሮችን አልረሳም ። አንድ ዓይነት እነዚህን ነገሮች የማያስረሳ ተፈጥሮ አለኝ »
«መታደል ነው ። እኔ ደሞ የስም ነገር አይሳካልኝም ። ይኽ ደሞ ለሥራዬ ጥሩ ነገር አይደለም። አንጐሌ ወንፊት ቢጤ ሆኖ ሲፈጠር ጊዜ ምን ማድረግ ይቻለኛል ! ወደ ፍሬ ነገሩ ልመለስና ተገናኝተን ስለሥራዎችሽ ብንነጋገር በጣም ደስ ይለኝ ነበር ።»
« በምን መንገድ ? » አለች ። ምን የሚያነጋግረን ነገር ተፈጠረ ደግሞ ! አለች በሐሳቧ ። «እንዲህ ነው ሚስ አዳምሰን ። እዚህ ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ አንድ የሕክምና ማዕከል ሕንፃ በመሥራት ላይ እንገኛለን ። በጣም ግዙፍ የሆነ ፕሮጄክት ነው ። ፕሮጀክቱን ስንቀበል ከገባናቸው ውሎች አንዱ ሕንፃውን እስከማስዋብ ያለውን ሥራ ፈጽመን ማስረከብ እንዳለብን ይገልጸል ። ያንችን ፎቶግራፎች ስመለከት ለዚህ ተግባር በጣም ሊያገለግሉን እንደሚችሉ ተረድቻለሁ ። እንዴት አድርገን በምን ሁኔታ እንደምንጠቀምባቸው ግልጽ የሆነልን ነገር የለም ። ስለዚህም ተገናኝተን ይህንን ጭምር ብንወያይበት ደህና ገቢም ይኖረዋል ። ላንቺም ቢሆን ሥራሽን ያስተዋውቅልሻል» አለ ቤን ። ይህን ሲናገር በሙሉ ልቡ እንደነበረ ድምጹ ይናገራል፡፡ «ገባኝ።. . . ግን የትኛውን ድርጅት ወክለህ እንዳነጋገርከኝ ልትነግረኝ ትፈቅዳለህ ? » አለች ። ድርጅቱ ማን ሊሆን እንዶሚችል ስለጠረጠረች ፤ ከላይ ከላይ ሊላት ያሰበውን ትንፋሷን ቁጥር አድርጋ መጠባበቅ ጀመረች ።
«ድርጅቱ» አለ ቤን ኮራ ብሎ «የኒውዮርኩ ኮተር ሂልያርድ ነው»
«ነው... ስላሰብክልኝ አመሰግናለሁ።፤ ሚስተር አቭሪ ግን አይሆነኝም »
«አይሆነኝም ? ለምን ?» አለ የመደመም በሆነ ድምጽ
👍14
«የምትይው አልገባኝም?»
«በዚህ በዚህ ምክንያት ልልህ አልፈልግም ሚስተር አቭሪ ። ፍላጐቴ እንዳልሆነ ብቻ ብትረዳልኝ ይበቃል»
«ተገናኝተን ልንነጋገር ብንችል ደግ ይመስለኛል ። ማለቴ በነገሩ ላይ»
«ምንም ንግግር አያስፈልግም»
«ግን... እዪው ይህን ነገር አስቀድሜ ነግሬአለሁ... .ለ..ለ...እኔ...»
«ምንም ብትለኝ መልሴ አንድ ነው ። አይቻልም ። አመሰግናለሁ ፤ ደህና ሁን ሚስተር አቭሪ»

ይህን ብላ የስልኩን መነጋገሪያ በቀስታ ወደ ቦታው መለሰችው ። ሥራዋን ለመቀጠል ፊልም ማዘጋጃውና ፎቶግራፍ ማጠቢያው ጨለማ ክፍል ስትሄድ ፤ የለም ለዚህ ድርጅትስ አልሠራም ለማይክል ሂልያርድ አጎልግሎት ለመስጠት ?! ምን በወጣኝ አለች ። ሚስቴ ልትሆኚ አትበቂም ብሎ አይደለም የተዋት ። እሷም ቀጣሪዬ ልትሆን ብቁነት አላይብህም ፤ምኔም ምኔም ለመሆን ብቁ አይደለህም ። ልትለው ያስፈልጋል… ይህን አሰበች ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍14
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከኢትዮጵያ ጥናትና ምርምርና ከሌሎች ተቋማት ለጥናቷ
አስፈላጊ የሆኑትን ውጤቶች ካነበበችና ከግለሰቦች ጋር ሐሳብ
ለሐሳብ ከተለዋወጠች በኋላ እግረ መንገዷን ሊረዳት የሚችል የክልሉ ተወላጅ አድራሻ፣ የጥናትና የጕዞ ፈቃድ አውጥታ ወደ
ጥናት ቦታዋ ከመጓዟ በፊት ምሽቱን በአዲስ አበባው ሒልተን እንግሊዝ ኤምባሲ ከሚሠራውና ለተወሰኑ ወራት በአዲስ አበባው
ቆይታዋ ጠረኑን ከለመደችው ጓደኛዋ ጋር እቅፉ ውስጥ ስትንቀሳቀስ
አድራ እንደገና ገላዋን ታጠበችና ልብሷን ለባብሳ ወጣች"

በአስተሳሰቧ፣ በግልጽነቷና በውበቷ የነሆለለው ስቲቭ
አለባበሷን፣ ከሰዓታት በፊት ፍቅር አመንጪ የነበረው አካሏ ተለውጦ ለሥራ መዘጋጀቷን ሲያይ እሱ ፍቅር ከፈጠረው የደስታ
ዓለም ከነበረበት ፈጽሞ ሳይንቀሳቀስ እሷ ግን ገስግሳ ወደ ገሐዱ
ዓለም በመመለሷ በፍጥነቷ ተደንቆ በተመስጦ ሲመለከታት ቆየና፣

«የኔ ቆንጆ አሁንም ታምሪያለሽ» አላት።

«ማማሬን እርሳው» አለችው።

«ለምን?»
«ከጥቂት ሰዓታት በፊት እኔም እረስቸዋለሁና።»

«የኔ ቆንጆ፣ ታዲያ ምን እንድልሽ ትፈልጊያለሽ?»

«የጉጉትን ዘዴ፣ የንስርን ማስተዋል፣ የአንበሳን ልብ፣ የኢዮብን ትዕግሥት፣ የአባትሽን ተስፋ አይቆርጤነትና አእምሮ ይስጥሽ በለኝ» ብላ፣ ጉንጩን ሳም አደረገችው"

ስቲቭ አስተያየቱን ጠለቅ አድርጎ ሲያስተውላት ቆየና፣ «አሁን አንችን የመሰለ ውብ ከእነዚያ ዘላኖች...» ሊናገር የፈለገውን ሳታስጨርሰው አፉን በአመልካች ጣቷ ከደነችው።
«ማፍቀር ያለብህ እኔን ብቻ ሳይሆን ፍላጎቴንም እንዲሆን እፈልጋለሁ" ትልቁ ውበት ደግሞ ሥራ መሆኑን አትዘንጋ» አለችውና ሌላ ቃል ሳይለዋወጡ ለቁርስ ክፍሉን ቆልፈው ወጡ"
  ።።።።።።።።።።።።።
ፈርጠም ያለ፣ የቀይ ሽንኩርት ቅርፅ መሳይ አፍንጫ ያለው! ዳጐስ ብሎ ቀላ ያለውን ከንፈሩን ሲገልጥ ነጫጭ ፍልጥ ጥርሶቹ የሚያማምሩና ከሸበላው ቁመናው ጋር የተስተካከለ አቋም ያለው
ከሎ ሆራ ለየት ያለ ባሕርይ ይታይበታል።

ቁጥብነቱን፣ ጅንንነቱን፣ ጥርጣሬውንና ብቸኝነት መውደዱን ያዩ ጓደኞቹ፣ «ነብሮ» ይሉታል የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቹ" ቀልድ፣
ቧልት ከጀመሩለት እንደ ቆሰለ ጎሽ በንዴት ጦፎ ይፎገራል" ከሰው ጋር ደጋግሞ እንደ መጣላቱ ግን ኃይሉን ተማምኖ ተማቶ
አያውቅም" ሁለቴ ሦስቴ ቃጥቶ ቃጥቶ ማንም በማይገባው ቋንቋ
አኩተምትሞ ዘወር ይላል" ታዲያ ብዙዎቹ አዳልጧቸው ቀልድ ብጤ ጀማምረው በዚያ ፈርጣማ ጡንቻው በሰነዘረ ቁጥር ጠረመሰን
እያሉ አንዴ ከተሳቀቁ፣ «እርም» ብለው ይሸሹታል" ስለዚህ ምን እንደሚያበሽቀው ያለፈው ሕይወቱ ምን እንደሚመስል፣
ብቸኝነቱ ከመቼ ወዲህ እንደ ጀመረው ከፍቶ ማየት የሚችል ሰው አልተገኘም ግለቱ ስላላስቀረበ"

የተማሪን ቆብ አውላቂ መምህራን በለመዱት ቧልት «ጢብ ጢብ» ሊጫወቱበት ይዳዳቸውና እንደ ከለመዳሪ የሚነፋውን
ከንፈሩንና እሳት ተፊ ትናንሽ ዓይኖቹን ሲያዩ በተለይም
በአንቀሳቀሰው ቁጥር እንደ አሎሎ የሚንከባለለውን ጡንቻውን ሲመለከቱ! «በቸር አውለኝ» ብለው አቅጣጫቸውን ሲቀይሩ
ዓመታት ተቈጠሩ“

ከሎ ሆራ የአራተኛ ዓመት የሶሲዮሎጂ ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ በተቃረበበት ወቅት በቀጭን ወገቧ ጂንስ ሱሪዋን በቀላል «ቲሸርት» አስተካክላ ለብሳ፣ የተጐነጐነ ረዥም ጸጕሯን ወገቧ ላይ እያላጋች፣ ቶሎ ቶሎ በመራመድ ጫማዋን ቀጭ ቋ ቀጭ ቋ እያደረገች የምትገሰግሰው ወጣት ከዩኒቨርሲቲው ፖስታ ቤት ወረድ ብሎ ከሚገኘው ኮሪደር ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ እግሩን እያወዛወዘ!
ጠጠር ወደሚወረውረው ጥቁር ወጣት ተጠግታ፣ «ይቅርታ ከሎ ሆራ ነህ አይደለም?» ብላ ጠየቀችው፣ በእንግሊዝኛ"

«አዎ ነኝ» አለ ከሎ፣ ከተቀመጠበት ሳይንቀሳቀስ"

«ካርለት አልፈርድ እባላለሁ" እንግሊዛዊት አንትሮፖሎጂስት
ነኝ" ስለ ሐመር ሴቶች ጥናት ለማድረግ ዓላማ አለኝ" አንተም የሐመር ተወላጅ መሆንህን ከዲፓርትመንትህ ኃላፊ ጠይቄ አረጋግጫለሁ» አለችና ንግግሯን በመግታት ትኵር ብላ ተመለከተችው
ከሎ ሆራ፣ የመርበትበት ስሜት አሳየና ከተቀመጠበት ፈጥኖ ተነሣ
ላብ ከወደግንባሩና ቅንድቡ አካባቢ ችፍፍ ችፍፍ ሲል ከንፈሩ አመድ የነሰነሱበት መሰለ።

«ሶ ለምን ፈለግሽኝ?» አላት በተቆራረጠ ድምፅ
«እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ» አለችው፣ በዓይኗ እየመረመረችው
«እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ?» ብሎ አባባሏን ደገመና ለትንሽ ጊዜ የመመሰጥ ሁኔታ አሳይቶ፣

«አዝናለሁ፣ ልረዳሽ አልችልም» አላት"

ካርለት፣ የከሎ ሰውነት ሲለዋወጥና ከብስጭቱ ጋር ሲታገል ያስተዋለች መሰላት ስለዚህ ወጣቱ ከሷ ያለበለዚያም ራሱ ከራሱ
ጋር ያልተግባቡት ወይንም ለእሷ ግልጽ ያልሆነላት ሌላ ምክንያት እንዳለው በመረዳቷ ተጨማሪ ጥያቄ ሳታነሣ፣ «አመሰግናለሁ“ ነገ
ግን ጊዜ ወስደህ ካሰብክበት በኋላ ሐሳብህን ከቀየርክ አይ.ኢ.ኤስ
ልታገኘኝ ትችላለህ ካለዚያም ስልክ ቁጥሬን ልሰጥህ እችላለሁ» ብላ፣ ፍጹም ልብ በሚነካ ፈገግታ የአድራሻዋን ካርድ ሰጥታው
«ደህና ሁን» እያለች፣ እጇን አውለብልባለት ሄደች"

ከሎ ሆራ ወደ መቀመጫው ሲመለስ፣ የሚሰበቀውን ወገቧንና ጀርባዋ ላይ ከብለል  ከብለል የሚለውን ጉንጉን ጸጕሯን ሲመለከት
ሐሳቡ ሸፈተበት" ከዓይኑ እስክትሰወር ድረስ በመደመም ሲመለከታት ቆየና ከጥቂት ደቂቃ በፊት የነበረበትን ድንገተኛ ሁኔታ ለማስታወስ ሞከረ» «ሐመር ጥናት ውብ እንግሊዛዊት የሐሳብ
ፍጥጫ፣ የተዳፈነ እሳት ጭረት.እሳት ጫሪ አንትሮፖሎጂስት...ወጣትና ውብ...ዳሚት» አለ፣ እጆቹን ከተቀመጠበት ደረጃ
ጋር እያላተመ።
  ።።።።።።።።።።።።።
ልቡ የአዶከበሬ አታሞ ይመስል እየተነረተ፣ ሰውነቱ ፀሐይ እንዳቆረናው የበረሃ ባልጩት ድንጋይ እያተኮሰ፣ እንቅልፍ ሲመኝ ግን ሲነቃ፣ ዕረፍትን ሲሻ፣ ሲንጠራወዝ፣ ሲገለባበጥ፣ በሐሳብ
ሲድህና ፎቀቅ ፎቀቅ ሲል አድሮ ዋለ"

ብዙ አወጣ አወረደI ያለፈ የልጅነት መጥፎ ትዝታውንም አስታወሰ" አሁን ሊያደርግ የማይፈልገውን እንዲያደርግ ግብዣው
ቀርቦለታል" ሌላው ቀን አልፏል። ለዛሬ ሥሩ ትናንት ነው" ትናንት ደግሞ እሱ የመከራ ጽዋውን የጨለጠበት ወቅት ነው" ዳግመኛ ሬት ሊያወርድ የሚችል ጉሮሮ የለውም” ስለዚህ በትናንት ቂም ያረገዘው አእምሮው አጓርቶና ድብልቅልቁ ወጥቶ እንዲሟሟና እንዲተን
ይፈልጋል" ችግሩ እንዳሰበው ለማድረግ አቅሙ አለ ወይ ነው።

የልጅነት ጊዜው መጥፎ ትዝታ ጥርሱን አግጥጦ፣ ጥፍሩን በማሾል፣ የታባክ ይለዋል“ ይኸኔ እንደ ልጅነቱ ልጅ ይሆንና በጭንቀት እየተንቦራቸ ይርበተበታል" ሊጮህ ይፈልግና ድምፁ
አልወጣልህ ይለዋል" ትናንት ከገደል ውስጥ ወጥቷልI ዛሬ ግን ወደ
ገደል ተገፍቶ ለመግባትና ለመሞት ዝግጁ አይደለም" መሞትም አይሻም ለምን?

እንግዲህ ችግሩ ያለው በትናንትናና በዛሬ መካከል ነው" ልጅ ከነበረው ከሎና አሁን በአካልና በአእምሮ ካደገው ከሎ መካከል
አንዱ ሽሽቱን ማቆምI አለበለዚያም፣ «በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ» እንዲሉ፣ በፍርሃት ላይ የጅብን ፍርሃት እያከለ ወደ ኋላ ሳያይ የሕይወትን ሩጫ መሸምጠጥ አለበት።

ትንሹ ከሎ ማምለጥ፣ መሸሽ ይፈልጋል ከሐመር። ትልቁ ከሎ ደግሞ ልቡ ከሁለት ቦታ ተንጠልጥሎበታል" ከሎ ውሳኔው ሲከብደው ካርለት ከተወችለት ካርድ ላይ በብዕር የተጻፈውን ስልክ
ቁጥር ተመልክቶ ስልክ ደወለ" «ሔሎ ከሎ» አለችው እንደ ሕፃን
ተቁነጥንጣ።

«...ደህና ነኝ» አላት"
«ምነው ልትገልጽልኝ የምትፈልገው ጉዳይ አለ?» አለችው።

«ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ» አለ ከሎ።
👍29