አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የፈለገችው ሻይ ስለነበር ‹‹አዎ አምጣልኝ›› አለችው፡
ማርክ ባሬስታውጋ ቀልጠፍ ብሎ በመሄድ ሻይ አዘዘላት፡ መርቪን እንዲህ ያለ ነገር አይነካካውም፡ ማርክን በጥላቻ ዓይን አየው፡፡
‹የኔ ችግር ይሄ ነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡ አንድ ነገር ስትፈልጊ ተነስቼ
ስለማላመጣልሽ፡፡ አባወራም የቤት አሽከርሽም እንድሆን ትፈልጊያለሽ?››

መርቪን የመጣለትን ሳንድዊች አልነካውም፡፡

‹አሁን መጨቃጨቅ አያስፈልግም ትይኛለሽ? አሁን ያልተጨቃጨቅን
መቼ ልንጨቃጨቅ ነው? ደህና ሁን ሳትይኝ ይህን ጅላጅል ደብዳቤ ትተሽልኝ ከዚህ የማይረባ ሰው ጋር ኮበለልሽ›› አለና አንድ ቁራጭ ወረቀት
አውጥቶ ዳያና ፊት አስቀመጠው፡፡ ዳያና ጽሑፉ የሷ መሆኑን አወቀች፡
ይህን ስታይ ፊቷ በሃፍረት ቲማቲም መሰለ፡፡ ደብዳቤውን ይዛ አነባች
‹እንዴት ቡና ቤት ውስጥ ሰው ፊት እንዲህ ያሳጣኛል?› አለችና ፈንጠር
ብላ ተቀመጠች፡ አሁን በንዴት ነርቭ ሆናለች፡፡

ሻዩ ሲመጣ ማርክ ጀበናውን አነሳና ‹‹በማይረባ ሰው የተቀዳ ሻይ ልስጥህ?›› ሲል ጠየቀው መርቪንን፡፡
ቡና ቤት ውስጥ ያሉት አይሪሻውያን በሳቅ ፈነዱ መርቪን ግን በንዴት ተወጥሮ ምንም አልተነፈሰም፡፡

ዳያና እየተናደደች ‹‹እኔ ጅል ልሆን እችላለሁ፡ ራሴን ለማስደሰት ግን መብት አለኝ›› አለች፡

መርቪን ጣቱን ወደ ዳያና ቀስሮ ‹‹እኔን ስታገቢ ቃል ገብተሽ ነበር: ስለዚህ ፈርጥጠሸ መሄድ የለብሽም›› አለ፡፡

በንዴት ተብከነከነች በአቋሙ ሙጭጭ እንዳለ ነው፡፡ ለድንጋይ እንደመናገር ይቆጠራል፡፡ ለምን አያመዛዝንም? ሁልጊዜ እሱ ትክክል
ሌላውን ስህተተኛ አድርጎ ለምን ይቆጥራል?› ወዲያው ይህን ባህሪውን ችላ እንደኖረች በህሊናዋ መጥቶ ድቅን አለባት፡ ለአምስት አመት ያህል ቢያንስ በየሳምንቱ እንዲህ ሲያበሳጫት እንደነበር ታሰባት፡፡ እሱ ከመምጣቱ በፊት ከአዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር ዓለሟን ስትቀጭ ስለነበር ባሏ ምን ያህል አስቸጋሪ ሰው እንደነበር ረስታዋለች፡፡

ማርክም ጣልቃ ገባና ‹‹ማድረግ የምትፈልገውን ነገር እንዳታደርግ
ልትከለክላት አትችልም፡፡ ካንተ ጋር ወደ ቤቴ ተመልሼ ልሂድ ካለች እኔ አልከለክላትም፡፡ አሜሪካን አገር ሄዳ እኔን ማግባት ከፈለገች ማንም
ሊከለክላት አይችልም›› አለ፡፡

መርቪን ጠረጴዛውን በጡጫ ጠለዘና ‹‹አንተን ልታገባ አትችልም፤ የኔ
ሚስት ናት!›› አለ፡፡

‹‹ልትፈታህ ትችላለች››
‹‹በምን ምክንያት?››
‹‹በአሜሪካን አገር
የትዳር ጓደኛን ለመፍታት ምክንያት አያስፈልግህም›› አለ ማርክ፡፡

መርቪን ወደ ሚስቱ ዞር አለና ወደ አሜሪካ እግርሽ ንቅንቅ አይልም፡፡ ከኔ ጋር ወደ ማንቼስተር ትመለሻለሽ›› አለ ማርክን አየት ስታደርገው በስስት ፈገግ አለላትና ‹የሚልሽን የመቀበል ግዴታ የለብሽም›› አላት ‹‹ልብሽ የሻተውን አድርጊ››

‹ኮትሽን ልበሽና እንሂድ›› ሲል አዘዘ መርቪን፡፡

የመርቪን ቁጡ ባህሪ እንደገና ነገሮችን እንድትመረምር አደረጋት፡
ዋናው ጉዳይ ማለትም ከማን ጋ ልኑር› የሚለው ጥያቄ በሁለቱ ወንዶች
መካከል ሊነሳ ከነበረው አምባጓሮና በአሜሪካ የመኖር ስጋት ጋር ሲነጻጸር
ሚዛን የሚደፋ ነበር፡ ማርክ ይወዳታል እሷም ትወደዋለች፡፡ ሌላው ነገር
ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ ውሳኔዋ በአዕምሮዋ ሲመሰረት ትልቅ እፎይታ
ተሰማት፡ ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀችና ‹‹ይቅርታ መርቪን›› አለች ‹‹ጥዬህ
ከማርክ ጋር እሄዳለሁ፡››
....................................

ናንሲ ሌኔሃን ከመርቪን ላቭሴይ ሚጢጢ አይሮፕላን ላይ ሆና ቁልቁል
የፓን አሜሪካን የሰማይ በራሪ ጀልባ ለበረራ ዝግጁ ሆኖ በባህር ዳርቻ ላይ
"በኩራት ቆሞ ስታየው ቅጽበታዊ ደስታ ተሰማት፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በፊት
ዕድል ጠሞባት የምታደርገውን አጥታ ነበር፡ ነገር ግን የወንድሟን ዕቅድ
በከፊልም ቢሆን ለማጨናገፍ ትንሽ ቀርቷታል፡ ናንሲ ሌኔሃን እንዲህ በቀላል እጇን የምትሰጥ ሴት አይደለችም› ስትል ለራሷ አድናቆት ቸረች፡

ትንሿ አይሮፕላን የመቆሚያ ቦታ ፍለጋ ስትሽከረከር ናንሲ ከወንድሟ
ሊገጥማት የሚችለውን እሰጥ አገባ ስታስበው ሰውነቷ በንዴት ተወጣጠረ፡
ወንድሟ እሷን ለማታለል ይህን ያህል ለምን ፈ እንደጨከነ ማመን አሁንም
አቅቷታል፡ እንዴት ይሄ ሀሳብ በአእምሮው ሊመጣ ቻለ?
በህጻንነታቸው አብረው ገላቸውን ይታጠቡ ነበር፡፡ መሬት ወድቆ እግሩ
ሲቆስል ፋሻ ወይም የቁስል ፕላስተር ታስርለት ነበር፡ ማስቲካ ቆርጣ ታካፍለው ነበር፡ ጥፋቱን ለሰው ነግራበት አታውቅም፡፡ የእሷን ሚስጥር ሳትደብቅ ትነግረው ነበር፡ ካደጉም በኋላ ምንም እንኳን ሴት ብትሆንም በሁሉም ነገር ትበልጠው ዕድሜውን በሙሉ እሱን ትንከባከበው ነበር፡

አባታቸው ሲሞቱ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ እንዲሆን ፈቀደችለት፡ ይሄ ደግሞ በኋላ በእጅጉ ዋጋ አስከፍሏታል፡ የአባታቸው ምክትል ከነበረው ናት
ሪጅዌይ ጋር አፍላ ፍቅር ላይ በነበረችበት ወቅት የኩባንያውን ኃላፊነት
ፒተር እንዲይዝ ስትስማማ ናት ሪጅዌይ በድርጊቷ አኩርፎ ኩባንያውን ለቆ
ወጣ፡፡ እሷንም አይንሽ ላፈር አላት፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ፍቅሯን
ሳያስጨርሳት ሌላ ሴት ያገባው፡፡

ጓደኛዋና የኩባንያው ጠበቃ ማክ ማክብራይድ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ እንዳይሆን ቢመክራትም ወንድሟ ፒተርን ሰዎች በአባቱ እግር ሊተካ
ማርክን አየት ስታደርገው በስስት ፈገግ አለላትና ‹የሚልሽን የመቀበል
ግዴታ የለብሽም›› አላት ‹‹ልብሽ የሻተውን አድርጊ››
‹ኮትሽን ልበሽና እንሂድ›› ሲል አዘዘ መርቪን፡፡
የመርቪን ቁጡ ባህሪ እንደገና ነገሮችን እንድትመረምር አደረጋት፡
ዋናው ጉዳይ ማለትም ከማን ጋ ልኑር› የሚለው ጥያቄ በሁለቱ ወንዶች
መካከል ሊነሳ ከነበረው አምባጓሮና በአሜሪካ የመኖር ስጋት ጋር ሲነጻጸር
ሚዛን የሚደፋ ነበር፡ ማርክ ይወዳታል እሷም ትወደዋለች፡፡ ሌላው ነገር
ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ ነው፡፡ ውሳኔዋ በአዕምሮዋ ሲመሰረት ትልቅ እፎይታ
ተሰማት፡ ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀችና ‹‹ይቅርታ መርቪን›› አለች ‹‹ጥዬህ
ከማርክ ጋር እሄዳለሁ፡››
ምዕራፍ አስራ ሁለት
ናንሲ ሌኔሃን ከመርቪን ላቭሴይ ሚጢጢ አይሮፕላን ላይ ሆና ቁልቁል
የፓን አሜሪካን የሰማይ በራሪ ጀልባ ለበረራ ዝግጁ ሆኖ በባህር ዳርቻ ላይ
"ኩራት ቆሞ ስታየው ቅጽበታዊ ደስታ ተሰማት፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በፊት
oድል ጠሞባት የምታደርገውን አጥታ ነበር፡ ነገር ግን የወንድሟን ዕቅድ
በከፊልም ቢሆን ለማጨናገፍ ትንሽ ቀርቷታል፡ ናንሲ ሌኔሃን እንዲህ
በቀላል እጇን የምትሰጥ ሴት አይደለችም› ስትል ለራሷ አድናቆት ቸረች፡
ትንሿ አይሮፕላን የመቆሚያ ቦታ ፍለጋ ስትሽከረከር ናንሲ ከወንድሟ
ሊገጥማት የሚችለውን እሰጥ አገባ ስታስበው ሰውነቷ በንዴት ተወጣጠረ፡
ወንድሟ እሷን ለማታለል ይህን ያህል ለምን እንደጨከነ ማመን አሁንም
አቅቷታል፡ እንዴት ይሄ ሀሳብ በአእምሮው ሊመጣ ቻለ?
በህጻንነታቸው አብረው ገላቸውን ይታጠቡ ነበር፡፡ መሬት ወድቆ እግሩ
ሲቆስል ፋሻ ወይም የቁስል ፕላስተር ታስርለት ነበር፡ ማስቲካ ቆርጣ ታካፍለው ነበር፡

ጥፋቱን ለሰው ነግራበት አታውቅም፡፡ የእሷን ፈ ሚስጥር ሳትደብቅ ትነግረው ነበር፡ ካደጉም በኋላ ምንም እንኳን ሴት ብትሆንም በሁሉም ነገር ትበልጠው ዕድሜውን በሙሉ እሱን ትንከባከበው ነበር፡
👍20
አባታቸው ሲሞቱ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ እንዲሆን ፈቀደችለት፡ ይሄ ደግሞ በኋላ በእጅጉ ዋጋ አስከፍሏታል፡ የአባታቸው ምክትል ከነበረው ናት
ሪጅዌይ ጋር አፍላ ፍቅር ላይ በነበረችበት ወቅት የኩባንያውን ኃላፊነት
ፒተር እንዲይዝ ስትስማማ ናት ሪጅዌይ በድርጊቷ አኩርፎ ኩባንያውን ለቆ
ወጣ፡፡ እሷንም አይንሽ ላፈር አላት፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ፍቅሯን
ሳያስጨርሳት ሌላ ሴት ያገባው፡፡

ጓደኛዋና የኩባንያው ጠበቃ ማክ ማክብራይድ ፒተር የኩባንያው ኃላፊ
እንዳይሆን ቢመክራትም ወንድሟ ፒተርን ሰዎች በአባቱ እግር ሊተካ የሚችል ብቃት ያለው ሰው አይደለም ብለው እንዳያስቡ የማክብራይድን ምክርና የራሷን ፍላጎት ወደ ጎን ትታ ያደረገችለትን ያን ሁሉ ደግነት ከምንም ሳይቆጥር እሷን ለማታለል የሚያደርገውን መፍጨርጨር ስታስብ
እሱን ፊት ለፊት አግኝታና አናግራ እውነቱን ለማወቅ በእጅጉ ጓጉታለች፡፡ ገጽ ለገጽ ተገናኝተው ምን እንደሚል ለማወቅ ትዕግስት አጥታለች።

ስለዚህ ከፒተር ጋር የሚገጥማትን ጦርነትን በድል ለመወጣት
ፒተር አይሮፕላኑ ላይ ሳይሳፈር መድረስ ብቻ አይደለም ዓላማዋ ይሄ
የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡
አይሮፕላኑ ላይ መሳፈር አለባት፡፡ ነገር ግን
አይሮፕላኑ ቦታ ከሌለው ከአንዱ ተሳፋሪ ላይ ቲኬት በጭማሪ ዋጋም ቢሆን
መግዛት ይኖርባታል፡፡ ወይም አማላይነቷን ተጠቅማ ፓይለቱ እንዲጭናት ማግባባት ይኖርባታል፡፡ አለበለዚያም ጉቦም ሰጥታም ቢሆን አይሮፕላኑ ላይ መውጣቷ የግድ ነው፡ አገሯ ቦስተን ስትደርስም ትንንሽ የአክሲዮን ድርሻ
ያላቸው አክስቷን ቲሊሊና የአባቷ የቀድሞ ጠበቃ ዳኒ ሪሌይ ድርሻቸውን
ለናት ሪጅዌይ እንዳይሽጡለት ማግባባትም የሚጠበቅባት ተግባር ነው፡ ይህን
ማድረግ ባያቅታትም ፒተር በቀላሉ እጅ አይሰጥም፡፡ ምክንያቱም ናት
ሪጅዌይን የመሰለ ባላንጣ በኋላ ደጀንነት አሰልፏልና፡

መርቪን ትንሿን አይሮፕላን ሜዳ ላይ አሳረፋት፡፡ ከእሱ በማይጠበቅ ጨዋነት ናንሲ ከአይሮፕላኗ ስትወርድ እጇን በመያዝ ረዳት፡፡ የአየርላንድ መሬት ለሁለተኛ ጊዜ ስትረግጥ አባቷ ትዝ አሏት፡፡ አባቷ ሁልጊዜ
እትብታቸው ስለተቀበረበት አገር አውርተው ባይጠግቡም አንድም ቀን ዝር ብለው አያውቁም፡፡
በዚህም ሀዘን ተሰማት፡፡ በአንጻሩ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ልጆቹ ከአባታቸው ቀድመው የአያት ቅድመ
መርገጣቸውን ቢያውቁ ምንኛ ደስ እንደሚላቸው አሰበች፡፡ በሌላ በኩል ግን
አያቶቻቸውን አገር የገዛ ልጃቸው እድሜ ልክ የደከሙበትን ኩባንያቸውን ለማፈራረስ ትግል
እያደረገ መሆኑን ሳያዩ አፈር መልበሳቸው ጥሩ ነው ስትል አሰበች ናንሲ
ሌኔሃን፡፡

መርቪን አይሮፕላኗን ሲያሳርፋት ልቧ አረፍ አለ፡፡ ምንም እንኳን
የሚፈልጉት ቦታ ብታደርሳቸውም ከሞት የተረፉት ለጥቂት ነው፡፡ አይሮፕላኗ ከዚያ ገደል ጋር ልትጋጭ የነበረው በዓይነ ህሊናዋ ሲመጣ አንቀጠቀጣት፡፡ ከዚህ በኋላ እስከ ዕለተሞቷ በትንሽ አይሮፕላን እንደማትበር ማለች፡

ከፊት ለፊታቸው የሚሄደውን ድንች የጫነ በፈረስ የሚጎተት
እየተከተሉ በፍጥነት በመንደሯ ተጓዙ፡ መርቪን ከሁኔታው ድል የማድረግም የፍርሃትም ስሜት እንደሚታይበት ናንሲ ተገንዝባለች፡ እንደ
እሷው ሁሉ እሱም ክህደት ተፈጽሞበታል፡፡ እሷ እንዳልተቀበለችው ሁሉ
እሱም ክህደትን በጸጋ አልተቀበለውም፡፡ እሷ ላይ እንደተፈጸመው ከጀርባው
ሆነው ሲዶልቱ የነበሩ ሰዎች ደስ አይበላቸውና ጥረታቸውን ድባቅ
ለመምታት ትንሽ እንደቀረው ሲያስብ ልቡ ቅቤ ይጠጣል፡

ፎየንስ መንደር ያለው አንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ግማሽ መንገድ ያህል እንደሄዱ የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ተሳፋሪዎች የሚመስሉ ማለፊያ
የለበሱ ዘመናዊ ሰዎች ወደ እነሱ ሲመጡ አዩና መርቪን ወደ ሰዎቹ ጠጋ ብሎ ‹‹ወይዘሮ ዳያና ላቭሴይ የምትባል ሴት ታውቃላችሁ? የፓን አሜሪን
ተሳፋሪ ሳትሆን አትቀርም›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አዎ እናውቃታለን›› አለች ከሴቶቹ መካከል አንዷ፡ ናንሲ መልስ የሰጠችው ሴት ታዋቂዋ የፊልም አክተር ሉሉ ቤል እንደሆነች ወዲያው አወቀች: ዳያና ላቭሴይን እንደማትወዳት ካመላለሷ ተረዳች - ናንሲ፡
የመርቪን ሚስት ምን ትመስል ይሆን? ስትል አሰበች ናንሲ፡
ሉሉ ቤልም ቀጠለችና ‹‹ወይዘሮ ዳያና ላቭሴይ እና አብሯት ያለው ጓደኛዋ ከመንገዱ ባሻገር ያለው ቡና ቤት ውስጥ ናቸው›› አለች፡፡

‹‹እባክሽ የቲኬት መሽጫውን ቦታ ብታሳይኝ?›› ስትል ናንሲ፣ ሉሉ ቤልን ጠየቀቻት
‹‹አንድ የቱሪስት አስተናጋጅነት ገጸባህሪን ወክዬ የምሰራ hሆነ ስራውን ደጋግሜ ማጥናት አይኖርብኝም›› ስትል ሉሉ አብረዋት የነበሩ ሰዎች በሳቅ ፈነዱ፡ ቀጠለችና ‹‹የአየር መንገዱ ህንጻ ከባቡር ጣቢያው አልፎ ከወደቡ ፊት ለፊት መንገዱ መጨረሻ ላይ የሚገኘው ህንጻ ውስጥ ነው›› አለች፡
ናንሲ ሉሉን አመሰገነችና መንገዷን ቀጠለች። መርቪን እየገሰገሰ ስለነበር
እሱጋ ለመድረስ የሩጫ ያህል ተራመደች። ብዙም ሳይሄዱ መርቪን ሁለት
ሰዎች በተመስጦ እየተነጋገሩ ከመንገዱ አቅጣጫ ሲሄዱ አየና አይኑን ማመን አቅቶት ቆመ: ናንሲ መርቪንን በድንገት ከመንገዱ ያስቆሙት
ሰዎች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ጓጓች፡ አንደኛው ሰው ጥቁር ሱፍ ልብስ
የለበሰ ጸጉረ ነጭ ቦርጫም ሲሆን የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ተሳፋሪ
ለመሆናቸው ጥርጥር የለውም፡፡ አብሯቸው ያሉት ረጅም ሰው በማሳ ላይ
የተተከለ የወፍ ማባረሪያ አሻንጉሊት የመሰሉ፣ አጥንታቸው የገጠጠ ራሰ
በራ ሲሆኑ አስፈሪ ቅዥት አስደንግጧቸው ከእንቅልፋቸው የባነኑ ሰው
ይመስላሉ፡፡ መርቪን ሊጠጋቸው ሰውየው ደነበሩ፡፡ መርቪን ሊተናኮላቸው
የመጣ ሰው መስሏቸው ለመከላከል እጃቸውን በደመነፍስ አወናጨፉ፡፡
ሁለተኛው ሰው ‹‹ችግር የለም ካርል፤ ተረጋጋ›› አላቸው፡፡

መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡
ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም ላይ ከሱ በላይ ሰው እንደሌለ አድርጎ የሚገምት ሰው ነበር፡፡ አሁን ግን ያየችው ባህሪ እንደየቤዝቦል ጨዋታ ኮከብ ተጫዋችን የአድናቂነት ፊርማ እንዲፈርምሉት
የሚለማመጥ አንድ ተማሪን ነው ያስታወሳት....

ይቀጥላል
👍19
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ በተቃራኒው ጦርነት ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ በሆዷ ሀሳቧ አንድ…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ (20)

‹‹ምክንያቱም ባለፈው ዓመት ይኸኔ… ባለፈው ዓመት በዚህቀን…››
«ምን ... ያው አሁን ከምሰራው የተለየ ምንም ነገር አልነበረም » አላት እንደምንም ። ፊቱ ልውጥውጥ አለ ። ግንባሩ መስመር ብቻ ሆነ ። ክመቀመጫው ብድግ ብሎ «ትንሽ ብናወራ መልካም ነበር ። ደስ ይለኝ ነበር ። ሆኖም ካስር ደቂቃ በኋላ ስብሰባ መግባት አለብኝ ። ስለዚህ ልሂድ አለና ፈገግ ሳይል ጨብጧት ሄደ ። ሁኔታው ድንገት ልውጥ ማለቱን የተገነዘበችው ዌንዲ ምን ብዬ ይሆን ? ምን የሚያስከፋ ነገር ተናገርኩ ይሆን? ስትል አሰበች ። የለም ስለሰውየው ጠባይ ቤንን መጠየቅ ይኖርባታል። እወቅሁት ስትል ድንገት የትናየት ርቀህ እንደምትገኝ ያሳይሀል»

ከአሥር ደቂቃ በኋላ በተጀመረው ስብሰባ ላይ ዌንዲም ተካፋይ እንደነበረች ሲረዳ ማይክል በጣም ተገረመ ። ዌንዲ እስብሰባው ላይ እንድትገኝ ያደረገው ቤን ኣቭሪ ነበር። ምክንቱም ስብሰባው የሳንፍራንሲስኮ ሕክምና ማዕከልን ሥራ ለመጀመር በሚቻልበት ዕቅድ ላይ ለመነጋገር ሲሆን አስቀድሞ መነጋገርን ከሚሹ ሥራዎች አንዱ የሕንፃው የውስጥ አሠራር ንድፍ ሥራ ነው። የዚህ ባለሙያ ደግሞ ዌንዲ ታውንሴንድ ናት ። በእርግጥ አስቀድሞ በታወቀው መሠረት መሠረታዊውን ፕላንና ንድፍ ተከትሎ ሕንፃው ይሠራል ። ግን ይህ በቂ አይሆንም ። ውበቱን ከፍ ለማድረግና ድንቅ የጥበብ ሥራ ለመፍጠር በሥነ ጥበብ ሥራዎች ማስጌጥ ያስፈልጋል ። እነዚያን የሥነ ጥበብ ሥራዎች ቤን ራሱ ወደ ሳንፍራንሲስኮ በመሄድ ሲፈልግና ሊመርጥ ወስኗል ። ስለዚሀም ዌንዲ ኒውዮርክ ውስጥ የሚከናወነውን ሥራ በጥብቅ መከታተል አለባት ።

ሥራው ዛሬና ነገ ይጀመራል የሚባል ባይሆንም ስብሰባው የተደረገው አስቀድሞ የተቻለውን ያህል ሁኔታዎችን ለማጥናት ፤ ውሳኔዎችን ለመስጠትና ይደርሳሉ የተባሉ ችግሮችን ለመመልከትና ዕቅዱን አበጥሮ ለመተንተን ነው ። ይህ ዝግጅት ተደርጐ ከቆዬ ሥራው ሲጀመር የሚመጣው ችግር አነስተኛ ይሆናል ። ስብሰባው ረጅም ግን ምንም ዓይነት ዘበዘባ የሌለበት ሲሆን በማሪዮን ሒልያርድ መሪነት ፤ በጆርጅ ኮሎዌ ረዳትነት ነበር የተካሄደው ። ይህ ይባል እንጂ የማይክል ተሳትፎ ከነዚህ ከሁለቱ የሚያንስ አልነበረም ። ምክንያቱም የዚያ ፕሮጀክት ኃላፊ ራሱ ማይክል ሒልያርድ ሆኖ ተሾማል ። ማሪዮን ሒልያርድ የዚህን ትልቅ ፕሮጀክት ኃላፊነት ለማይክል መስጠቷ በከንቱ አልነበረም ። በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ታላላቅ የሚባሉ የአርኪቴክቸር ድርጅቶች ሁሉ የዚህን ፕሮጀክት ሥራ ለማግኘት ቋምጠው ነበር። ኮተር ሂልያርድን ማሸነፍ የማይቻል ሆነና ሳያገኙት ቀሩ ። የሥራውን ሁኔታ የማይከታተል ባለሙያ ድርጅት አይኖርም ማለት ነው ። እንደሚያዋጣ ማሪዮን ሙሉ በሙሉ ታምናለች ። ይህ ደግሞ የፕሮጀክት ኃላፊ የሆነውን አርኪቴክት ስምና ዝና የሚተክል እንደሆነ ይገባታል ። ስለዚህም ኃላፊነቱን ለማይክል ሰጠችው ።

ስብሰባው ሲያበቃ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሊሆን ምንም ያህል አልቀረውም ነበር ። በዕለቱ ዌንዲ ታውንሴንድ በሀሳብ አቀራረቧ ሲያስፈልግም ማሪዮንን እስከመጋተር በመድረስ በሙያዋ ምን ያህል የበሰለች እንደሆነች አሳይታለች። ስብሰባው ሲያልቅ ድክምክም ብላ ነበር። ከስብሰባው ሲወጣ ቤን ትከሻዋን መታ መታ እያደረገ « እሰይ የኔ ልጅ ! የዛሬ ሁኔታሽ የሚደነቅ ነበር » አላት። ወዲያው ጸሐፊው ስለጠራችው ቀድሟት ሄደ ። ዌንዲ ስለሁኔታው እያሰበች በኮሪደሩ ውስጥ ብቻዋን በመጓዝ ላይ እንዳለች ማይክል አስቆማት ። ገረማት ።»

« የሥራሽን ሁኔታ ጥልቀት ሳይ በጣም ተገረምኩ ዌንዲ እንዲህ ከሆነ በመተባበር ግሩም የሆነ ነገር እንደምንፈጥር ይታየኛል » አለ ማይክል ። « እኔም እንደዚያ ብዬ እገምታለሁ » አለች ፤ ኩራት እየተሰማት ። ሌላ ሰው ሳይሆን ማይክል ነውኮ ያመሰገናት ። « አትጠራጠሪ » አለ ማይክል ። ድንገት ሁለቱም ዝም አሉ፤ ጎን ለጎን እየሄዱ። «ማይክል…. ማይክል... ቅ... ቅድም ማለት ምን እንዳልኩህ እንጃ። ግን ሆነ ብዬ… በፍጹም አውቄ ሳይሆን… አስቀየምኩህ መሰል ፤ አደል ? ማለት… ሚስጥር ለማስወጣት ወይም በግል ሕይወትህ ለመግባት ሳይሆን… አጠያየቄ.. በጣም በጣም አዝና…» ስትጨነቅ ሲያያት አዘነላት ፤ «የለም ዊንዲ ፤ አንቺ ምንም አላጠፋሽም ። እኔ ነኝ ጋጠወጥ ሥራ የሠራሁት። እና ይቅርታ አድርጊልኝ ። የጸደዩ ወራት ከሕልሙ ጋር ደባልቆ የማይገባ ባህሪ ሳይሰጠኝ አልቀረም ። ለምን ዛሬ እራት አልጋብዝሽም? ካሳ » አለ ። ይህ የራት ግብዣ ጉዳይ ካፉ ሲወጣ ደነገጠ። እሷም ገፅታ ላይ አድናቆትና ጥርጣሬ አብረው ተስለው መታየት ጀመሩ፡፡ «እኔ ማለት አየህ? ልካስ ብለህ... » ኣለች «ማን ግድ አለኝ ? ! ደስ ስለሚለኝ ነው » አላትና ፈገግ ብሎ « ያንችን ንገሬኝ ይመችሻል ?»
«ምንም ችግር የለም… እንዲያውም ደስ ይለኛል ።»
«ደግ እንግዲህ ። ካሁን ጀምሮ ካንድ ሰዓት በኋላ እቤትሽ ድረስ መጥቼ እወስድሻለሁ » አድራሻዋን ለስብለባ በያዘው ማስታወሻ ጀርባ ላይ ጫር ጫር አደረገና ያዘ። ወደ ቢሮው ሲሄድ ምን ዓይነት ዕብደት ነው ሲል አሰበ። ወዲያው ግን ለምን ዕብደት ይሆናል አለ። ልክ ባላት ሰዓት እቤቷ ይረሰ ። ቤቷን ገና ሲያየው ወደደው። ቡናማ ቀለም ካለው ድንጋይ የተሠራ ሕንፃ ሲሆን የበሩ ማዕዘን የተሠራው ከሚያብለጨልጭ ጥቁር ድንጋይ ነው ። እመዝጊያው ላይ ከነሐስ የተሠራ በር መምቻ ተንጠልጥሏል ። ቤቱ በጠቅላላ ለአራት ቤተሰብ መኖሪያ እንዲሆን የተከፋፈለ ሲሆን የዌንዲ መኖረያ ከሁሉም ጠበብ የምትለዋ ናት ። ሆኖም ይህች የሷ መኖሪያ ብቻ ናት ከበስተኋላዋ የአትክልት ቦታ ያላት። እቤት ውስጥ ሲገባ ሁሉም አይነት እቃ የሚሸጥበት ሱቅ መስሎ ታየው ። ታሪካዊ የሆኑ አንቲካ እቃዎች አሉ ፤ ዘመናዊ እቃዎችም አሉ ። ለየት ያሉ እቃዎችም አሉ። በተለያዩ መብራቶች በመጠቀም የክፍሉ ቀለም እምብዛም የማያብረቀርቅ ግን ስሜት ሞቅ የሚያደርግ እንዲሆን አድርጋዋለች ። እዚያ ቤት ያየው ሁሉ ደስ አሰኘው ። የአበባ አተካከሏ ሁሉ ነገር።
👍15
ሆድ የሚከፍት ቀላል ምግብና መጠጥም አዘጋጅታ ነበር የጠበቀችው ። ያን እየቀማመሰ እያወራት እያወራችው ያላሰቡትን ያህል ጊዜ ቆዩ ። እንደ እውነቱ ከሆነ ፤ ማይክል አስቀድሞ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ቦታ ባያስይዝ ኖሮ ከዚያ ቤት ባይወጣ ደስ ይለው ነበር። ሆኖም አሁን አይቻልም። ያ የተባለው ምግብ ቤት ደግሞ አንድ ሰው ቦታ ያዙልኝ ቢልና አምስት ደቂቃ ቢዘገይ ቦታው ለሌላ እንግዳ ይሰጣል ፤ የታወቀ ነው ። ስለዚህ «ወይ መሮጥ ይኖርብናል ወይ ቦታችን መያዙ ነው። ወይስ ቢያዝ ባይያዝ ይህን ያህል አያሳስበንም ?» አለች ዌንዲ። እሱ ሲያስበው የነበረውን ነገር ስትናገር በጣም ደነገጠ ። ተገረመ። ቀና ብሎ ሲያያት የሆነ ተንኮል ነገር አይኗ ውስጥ ያየ መሰለው። ሁሉም ነገር እንግዳ ሆነበት ። ከሴት ጋር መውጣት ካቆመ ጊዜው ረጅም ሆኖበት ነበረና ፤የሆነ ስህተት እንዳይፈፅም ፈራ፡፡ «እንሩጥ ወይስ...ያንች ሀሳብ ምንድነው ሚስ ታውንሴንደ!?» አለ እንደመቀለድ እያለ «ሀሳብሽም እንደፊትሽ ያስፈራ ይሆን ?» «ሀሳቤማ ከፊቴ የባሰ ነው » አለች «ምን ሳስብ ነበር መሰለህ ምግባችንን ቋጥረን ፤ ወደ ወደብ ሄደን ፤ ጀልባዎችን እየተመለከትን እዚያ እንድናመሽ»
«እንዴት ያለውን መላቅጥ ያጣ ሀሳብ አሰብሽው ልጄ›› እንዲህ ቢልም አላመለጠም ። ወደ ተባለው ሆቴል አልሄዱም የተባለውን ምግብ አዘጋጅተው ወደ ተባለው ወደብ ሄዱ። ብቻቸውን አልነበሩም ። እንደሷ መላ ቅጥ ያጣ ሀሳብ ያቀረቡ እንደሱ መላቅጥ ያጣውን ሀሳብ የተቀበሉ ብዙ ጥንዶች በወደቡ አካባቢ ነበሩ። በወደቡ አካባቢ ሲንሸራሸሩ ፤ የመጣላቸውን ሲያወሩ አመሹ፡፡ ወደ መጨረሻው ላይ በወሬ ወሬ የጋብቻ ጉዳይ ተነሳ። «መቼ ነው… ማለት ሚስት የማግባት ሀሳብ አለህ ? »አለችው። ፊቱን አቅጭሞ አንገቱን በአሉታ ነቀነቀ ። «እስከ ዘለአለም ?» አለች ። «እስከመቼም »
«ለምን ? መጠየቅ ይፈቀድልኛል ወይስ...»
«ጠይቂ» አላት «እነግርሻለሁ ምክንያቱን »
«እስከመቼ ሸሽቶ ይኖራል»
«በምሣ ሰዓት ያስደነገጥኩሽ በዚያ የተነሳ ነው ። ራት አብረን እንድንበላ ያደረገኝም ይኸው ጉዳይ ነው ። አምና ፤ በዚህ እለት ላገባ ነበር ።እኔ... ቤን አቭረ ሆነን ስንሄድ መኪናችን ተገጭታ ትልቅ የጭነት መኪና ፤ እኔና...ቤን ዳንን ።... የዚያኛው መኪና ሹፌር እና... እሷ ግን ሞቱ» አለ። ይህን ሲል እንባ እሚባል አልወጣውም ፤ አላለቀሰም ። ግን ሰውነቱን አንድ ነገር የሸረካከተው ፤ የበጣጠሰው መሰለው ። ዌንዲ በፍርሀት እና በመሳቀቅ እያየችው እንዲህ አለች።

«ማይክ ! በስማብ ! የምትነግረኝ ነገር እውን ሳይሆን ቅዠት ይመስላል! »
«ቅዝት ነበር ። አየሽ ለሶስት ቀን... አደጋው ከደረሰ በኋላ አልሰማ አልለማ ስነቃ ማለት ነፍሴን ሳውቅ...አልፋለች።ምን ልሁን...እ...እ...ኔ...» መናገር አልቻለም ። ቃላቱ አልወጣልህ አሉት ። ግን ጀምሮታልና መናገር አለበት፡፡

«ሲሻለኝ ከሁለት ሣምንት በኋላ ቦስተን ነበርኩ ... ቦስተን ነበር እምትኖረው ወደመኖሪያ ቤቷ ሄድኩ ። ግን ማንም አልነበረም… ምንም አልነበረም ። እቃዋም ፤ ስእሎቹም ተሰርቀጡ ደረስኩ ። ሰአሊ ነበረች.. ነርሶች ናቸው አሉ የ...የወ...የሰረቋቸው ስእሎቿን...» ዝምታ ሆነ ። ለረጅም ጊዜ ሁለቱም ፀጥ ብለው ተቀመጡ ከዚያ ቀጠለ…

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍11😢3
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


“ስለ ሰውዬው ወንጀል እኔ አላውቅም " ልጅዎ ግን ነጻ እንዲሚወጣ አይጠራጠሩ አይዞዎ ፤አይጨነቁ " የደስታ ዘመን እየመጣልዎ ነው” ብሎ አበራታቷትና አሳምኗት ወጣ

ሚስ ካርላይል የወንድሟን የምርጫ ቀን ምክንያት በማድረግ በሕይወቷ
አድርጋው የማታውቀውን እስከ መጨረሻው አጊጣ ለብሳ ስትንጎራደድ በነበረችበት ወቅት ዐይን አውጣዋ አፊ ሆሊጆንም በበኩሏ ከሚስ ካርላይል አሽከሮች ጋር ተመሳጥራ ሾልካ በመግባት ሚስ ካርላይል ከነበረችበት በላይ ከነበረው ፎቅ ወጣች " በተጐነጐነው ጸጉሯ ላይ ቆብ ደፍታ እስከ ሽንጧ ድረስ ደረጃ እየመጣለት የተሰፋው የነጭና የአረንጓዴ ዝንጉርጉር ቀሚስ ለብሳለች » ዐይነ ርግብና ለስላሳ ነጫጭ የጅ ጓንቲዎች አጥልቃ በዳንቴል የተከፈፈና ሽቶ የተርከፈከፈ መሐረብ ይዛ ባጠቃላይ ውድና ቀለመ ደማቅ በሆነ ሙሉ ልብስ አጊጣ እንደ ሱፍ አበባ ጐልታና ደምቃ በአደባባይ ለመላው ሕዝብ እየተጐማለለች ስትታይ ቆየች ደግነቱ ግን ሚስ ካርሳይል አላየቻትም ።

“ መልከ መልካም ነውኮ !” አለች ለሚስ ካርላይል ገረዶች ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከፊት ለፊታቸው ሲደርስ አየችውና "

ግን መጥፎ ሰው ነው የሚል ነበር ያገኘችው መልስ ። ሚስተር አርኪባልድ ጋር ተወዳድሬ “አሸንፋለሁ ብሎ ማሰቡና እዚህ መምጣቱም ያስገርማል” አሏት"

“ምን እያደረጉ ነው?” አለችና'“እንዴ ኧረ ፖሊሶችም አሉ !” ብላ ጮኸችና'' እጁን በካቴና እያሰሩት ነው ምን አደረጋቸው ? እያለች ለፈለፈች።

ለጩኸቷ መልስ አላገኘችም ። ፊቷ ዐሥር ጊዜ እየተለዋወጠ በጭንቀት ስትመለከት ቆየችና “ አንዴ ” አለች ሰዎች ሲናገሩ ነገሩን ከአፊ ቀድማ የሰማችው
አንዷ ሠራተኛ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪስንና ኦትዌይ ቤቴል አባትሽን ሆን ብለው
ስለ ገደሉ ተይዘዋል ነው የሚባል ”አለቻት "

ምን ! ” ብላ ጮኸች አፊ "

“ ገዳዬ ሴቪሰን ነው " ሪቻርድ ሔር ከደሙ ንጹሕ ነው ይላሉ " አለቻት።

አፊ ነገሩን አዳመጠች " ምን ማለት እንደሆነ አሰበች " ከዚያ እየተንገዳገደችና እየተንቀጠቀጠች ሙሉ ለሙሉ መሬት ላይ ተዘረረች አፊ ሆሊጆን ሕሊና
ዋን ሳተች።

አፊ ሆሊጆን አቅሏን ስታ የነበረችው ለቋት ወደ ሚስ ካርይል ቤት ተሸሽጋ
እንደ ገባች ሁሉ ተሸሽጋ ወጣች " ከሚስ ካርላይል ቤት ትንሽ ራቅ ብሎ ዐይብ ያሣማ ሥጋና ልዩ ልዩ የምግብ ቅባቶች የሚሸጡበት ሱቅ አለ » ሱቁ ጥሩ ታዋቂነት እንዳለው ካጠና በኋላ ገዝቶ
የሚሠራበት አንድ ከለንደን የመጣ መልከኛ ልጅ እግር ነጋዴ ነው ሱቁ ምርጥ
ዕቃ በማቅረቡ የታወቀ ለመሆኑ የሚስ ካርላይል ደንበኛ ለመሆን መብቃቱ ብቻ መረጃ ነበር " የፊተኛው ባለቤቱ በቂ ገንዘብ ስለ አጠራቀመ ለሚስተር ጂፍን
ሲሸጠው ሰዎች እሱም ሠርቶ የሚበቃውን ያህል ገንዘብ ሲይዝ እንደ ፊተኛው
ሰውዬ ይሸጠዋል " እያሉ ተንብየውበታል "

አፊ ከሚስ ካርላይል ቤት ወጥታ ከሱቁ ፊት ለፊት ስትደርስ ሚስተር ጀፊንን ከሱቁ በር ቁሞ ታየዋለች ከውስጥ ረዳቱ ከዕንጨት በርሜል እያወጣ ቅቤ
ይሸጣል " አፊ ቆም አለች " ሚስተር ጂፊን መቸም የሷ ነገር ጭንቁ ነው " ልቡ
እስኪጠፋ ይወዳታል እሷም እሱ ሲያወዳድሳት ደስ ደስ ይላታል "

“ እንደ ምን ዋልሽ ... አፊ” አላት ነጭ ሽርጡ እንዳይታይበት ተጠንቅቆ
አጣጥፎ ከደበቀ በኋላ እጁን ወደሷ ዘረጋ ። ምክንያቱም ስለ ሽርጡ አሳፋሪነት አንድ ጊዜ ጠቆም አድርጋው ነበር "

“ ደኅና ነህ ጄፈን" አለችውና ነጫጭ ጓንቲዎቿን እንዳደረገች ራሷን ዝቅ በማድረግ ለሰላምታ የቀረበላትን እጅ በጣቷ ጫፍ ነካ አደረገችው “እኔ
ደሞ ” አለችው የጅ መሐረቧን ዐይነ ርግቧንና ( ቀለበትኛ የተሠራውን ጸጉሯን በማሳየት እየተውረገረገች “ዛሬ ሱቅህን ዘግተህ ዕረፍት ያደረግህ መስሎኝ ነበር
ሚስተር ጂፊን ” አለችው።

“ ሥራ መከበር አለበት” አላት ጂፍን ሐሳቡ በሷ ፍቅር ተይዞ ነጻ ሆነሽ በሽርሽር ላይ መሆን መቻልሽን ባውቅ ኖሮ ምናልባት ባጋጣሚ እንደማገኝሽ ተስፋ በማድረግ እኔም ዕረፍት እወስድ ነበር"

አባባሉ ከእውነተኛ ፍቅር የመነጨ መሆኑን ተገንዝባ ' “ ምንም እኮ አያውቅም ሥራው ሁሉ እንደ ከብት ነው ' አለች ' በሐሳቧ "

“ እኔ በሕይወቴ ያለኝ ታላቅ ደስታ .. ሚስ አፊ አንቺ ስታልፊ በሱቁ መስኮት አሻግሬ ማየት ነው ”

“ ኧረ ጉዴ !” አለች አፊ ገፍቶ የመጣባትን ሣቅ ለማገድ እየሞከረች : “ለምን እንደሚጠቅምህ አላውቅም "ዐይን ካለህ ከአንድ ሁለት ሰዓት በፊት ወደ ሚስ ካርላይል ዘንድ ስሔድ አይተኸኝ ይሆናል”

“ አዬ ! ዐይኖቼ የት ሔደው ኖሮ ይሆን?” አለ እየተጸጸተ “ አሃ ! ገባኝ እነዚያ የቅቤ በርሜሎችን ስመረምር ነው ይገርምሻል . . . ሚስ ሆሊጆን የተበላሹትን ስለ ላኩልኝ መልሼ ልልክላቸው ነው ”

“ አ ... ይ ! እኔ የቅቤ በርሜሎች ብሎ ነገር አላውቅም " እንዲህ እንዲህ ያለው ነገር ከክብሬ በታች ነው
“ እንዴታ እሱስ እውነትሽን ነው ... ሚስ ሆሊጆን “ ምንም እንኳን የገበያውን ጥቅም ለሚገባው ከፍተኛ ትርፍ ቢኖረሙም ካንቺ ክብር ጋር አይስማማም »

“ የምን ጩኽት ነው የምሰማው ? አለች አፊ "
"መራጮች ለሚስተር ካርላይል ሲያጨበጭቡ ነው መመረጡን ስምተሻል
ይመስለኛል

" የለም አልሰማሁም ”

ያኛውማ የገዛ ወዳጆቹ አስወጡትና ተገላገሉት » እንግዲህ እንደራሴአችን
ሚስተር ካርይል መሆኑ ነ&ዘው " ይባዋል ... መቸም እንደሱ ያለ ሰው የለም ‥

“እነዚህ ሁሉ ደንበኞችህ ናቸው እንዴ ? ሁሉንም ማስተናድ ከባድ ሥራ
ነው ሰውዬህ ብቻውን አይዘልቀውም " ስለዚህ እያወራሁ ጊዜ ልወስድብህ አልፈልግም ሔድኩልህ "
አለችውና እየተንሳፈፈች ሔደች " ጂፊን ፍዝዝ ብሎ
ሲያያት ከቆየ በኋላ ከይኑ ስትጠፋ የግዱን ደንበኞቹን ወደ ማስተናገድ ዞረ »

ጂፊን በፍቅሯ ወጥመድ መግባቱን ዐውቃና እንደሚያገባትም ተማምና አፊ በዚያ በቅባት በተባላሸው ሱቅ በኩል ሳይሆን በጓዳ በር እየገባች ጠቅላላ የቤቱንና የእቃውን አያያዝና አቀማመጥ ' ባሏንም እንዴት እንደምትንከባከበውና እንዴት አድርጋ በፍቅሯ ዐሥሬ የመሽቀርቀርያ መሣሪያ እንደምታደርገው እያሰላሰለች በምኞት አየር ላይ ሰገነት ሠርታ በሐሳቧ እየተሽሞነሞነች ስትራመድ ኧበንዘር ጀምዝ ደርሶ ለቀም አደረጋት ።

“ እንደምነሽ . . አፊ ? ዛሬ ጧት ሚስ ኮርኒ መስኮቶች ላይ አየሁሽ "

“ ያንተ ነገር እንግዲህ በቃኝ . . . ኧበንዘር ጀምዝ በቀደም ለሚስተር ጀፊን የዱሮ ወዳጄ ነበረች ማለትህን እኮ ሰምቸሃለሁ ”

“ አዎን ነበርሽና ” አላት እየሣቀ "

“ አልነበርኩም " እኔ በዚያን ጊዜ ከበላዮችህ ጋር እንጂ ካንተ ጋር ምንም ግኙነት አልነበረኝም አሁንም እኔን ለመጉዳት ብለህ በሐሰት ስሜን ለማጥፋት ብታስብ ተሳስተሃል ... ኧበንዘር ጀምዝ " እኔ በዚህ ቦታ የተከበርኩ ሰው ነኝ " ስለዚሀ ዐርፈህ ተቀመጥ ”

“ ምነው አፊ ? ለምን እንደዚህ ትሆኛለሽ ? እኔ አንቺን ለመጉዳት አልፈልግም አንቺ እንደምትይው ብሞክርም አይሆንልኝም " አላት እየሣቀ "

ይኸው ነው ይበቃሃል አሁን ከኔ ራቅ የአንተ ህዝብ መሀል መታየትህ ለስሜ ደግ አይደለም " አለችው።

ደኅና መልእክቴን ከተቀበልሺኝ እሔድልሻለሁ " በይ አሁን ለዛሬ በዘጠኝ ሰዓት ፍርድ ቤት ከችሎቱ አዳራሽ ስለምትፈለጊ እንዳትቀሪ "

ከችሎት አዳራሽ ? እኔን ? ለምን ?
👍19
“ እንዳትቀሪ ነግሬሻለሁ” አላት ሚስተር ኧበንዘር “ “ሌሺሰን ሲያዝ አይተሽዋል " ቶርን ይባል የነበረው ሌቪሰን አባትሺን በመግደል ስለ ተከሰሰ ለምስክርነት ትፈለጊያለሽ።

" እኔ ስለ ግድያው ምንም አላቅም " ስለዚህ አልሔድም ።

መሔድ አለብሽ ... አፊ” አላትና ወረቀቱን በእጅዋ አደረገላት "

ይሄ መጥሪያሽ ነው " "

“እኔ በሌቪሰን ምንም አልመሰክርበትም " ጥፋተኛው ዲክ ሔር እያለ ንጹሁን ሰው ለማሰቀል አልረዳም እኔ እልም ብዬ ጠፍቸ ነገሩ እስኪያልቅ ካንዱ ከተደብቄ እቆያለሁ
እንጂ አልመጣም
"አንተ የሠራኸኝን
ግን ኧበንዘር ምንጊዜም አልረሳውም " ብላ የተቀበለችውን ወረቀት በጣጥሳ ጣለችውና ሚሲዝ
ላቲመርን ለማግኘት ወደ ቤት እየገሠግሠች ሔዶች " ካደረችው ጌጥና አለባበስ
ጥቂቱን ቀናንሳ ታማ ተኝታ ወደ ነበረችው እመቤቷ ዘንድ ገባች „

“ እሜቴ ” አለች “ ኧረ በጣም የሚያሳዝን ወሬ ደረስኝ አንዲት ዘመዴ
ታማ በጣም ስለ ደከመች ልታየኝ ትፈልጋለች አሉ" ስለዚህ በሚለጥቀው ባቡሮ ለመሔድ ፈቃድ ቢሰጡኝ ብዬ ነው " እንኳን እሷ ልካብኝና ባትልክብኝም እየሰማሁ የማልቀርበት ጉዳይ ነው "

«አዬ ! እኔስ አንቺ ከሌለሽ ምን ይበጀኛል ?

" ነገሩ የሞት ጕዳይ ሆኖ ነው እንጂ እኔም እርስዎ እንደዚህ ተይዘው"
እያየሁ ፈቃድ አልጠይቅዎትም ነበር "

“ ዘመድሽ የምትኖረው የት ነው ?ስንት ቀን ትቆለሽ ? አለቻት "

አፊ ካፍ የገባላትን አንዱን ከተማ ጠራችላትና በበነጋው ለመመለስ ተስፋ
ማድረጓን ነገረቻት "

“ የምን ዘመድ ናት
ለመሆኑ ? አለ ጆይስ እኅት ያለ ሚስዝ ኬን አክስት
እንልነበረሽ የነግርሺኝ መስሎኝ ነበር "

“ጥቂት ተቀያይመን ስለ ነበር • ስሟንም አንሥቸው አላውቅም እንጂ እሷም
ሌላይቱ አክስቴ ናት እንዲያውም አሁን በነፍሷ እንድደርስ ያስግደደኝ እንደተቀያየምን ሳንተያይ እንዳትሞት ነው”

ሚስዝ ላቲመርም ሁኔታዋን መዝና ፈቀደችላት " አፊ ልብሷን ቀያይራ በቦርሳዋ ጥቂት ገንዘብ ያዘች » አንዲያውም ትንሽ የቆዳ ሻንጣ አንጠልጥላ ወጣች ከፊት ለፊቷ አንድ የምታውቀው ፖሊስ ከመንገድ ዳር ሲንጐራደድ አገኘች "

“ ስሚ ሆሊጆን
እንዴት ዋልሽ ? ዛሬ ጥሩ ቀን ነው አይመስልሽም ? ”
ጥሩ ነው ” አለችው ስለ አቆማት እየከፋት „ “ አሁን ስለ ቸኮልኩ አላነጋግርሀም” ብላው መንግዷን ቀጠለች - እሱም አረማመዷን ከእሷ ጋር እያስተካከለ ጐን ጐኗ ይሔድ ጀመር። ፍጥነት ስትጨምር አብሮ እየጨመረ እንዶ መሮጥ ሲቃት እሱም እንደ መሮጥ እያለ ፡ “ምንድነው እንደዚህ ያስቸኮለሽ?” አላት "

“ አንተን አይመለከትም እኔ አሁን ያንተ አጀብ አስፈልገኝም" ለሁሉም
ጊዜ አለውና በሌላ ጊዜ ቁጭ ብለን እንጫወታለን

“ በባቡር ለመድረስ የቸኮልሽ ትመስያለሽ”

“ ነውና ይህ መልስ የሚያረካህ ከሆነ ወዳንዱ ተንሸራሽሬ ልመጣ ነው
አቶ አጥብቄ ጠያቂ"

ብዙ ትቆያለሽ ?”

“አ...አ ነ ገ ሳልመለስ አልቀርም ስማ እስቲ ሚስተር ካርላይል መመረጡ እውነት ሆነ?”

“ አምን እውነት ነው" ተይ በዚያ በኩል አትሒጅ እባክሺን

" በዚያ በኩል አትሒሂጂ ” አለች አፊ የሱን አነጋገር በመድግም " ወደ ባቡር ጣቢያ የሚቀርበኝ ይኸ ነው
ዙርያውን መንገድ ይቀንስልኛል

መኮንኑ ቀስ አድርጎ እጁን ጣል አደረገባት "
አፊ ከሱ ለመለየት የጨነቀውና ለመዳራት የፌለገ መሰላት
“ ምን መሆንሀ ነው አንተ ደግሞ እኔ አሁን ለዚህ ጊዜ የለም እጅህን ወዲያ በል አለችው ጠበቅ እያደረጋት ስለ ሔዶ ቆጣ ብላ"

ሴት ልጅን ማስቀየም በተለይም አንቺን ..ሚስ ሆሊጆን ደስ አይለኝም
ነገር ግን እጄን ካንቺ ላይ ማንሣት አልችልም ። እኔም ካንቺ አልለይም ወደ ፍርድ ቤት አዳራሽ በቶሎ እንዳቀርብሽ ትዛዝ ተሰጥቶኛል ዛሬ ከቀትር በኋላ ለምስክርነት
ትፈለጊያለሽ ”

" እኔ የማወቀውም የምመሰክረም የለኝም ”

“የተሰጠኝን ትእዛዝ ተቀብዬ መፈጸም እንጂ ምንና ለምን ብዬ አልጠይቅም
ስለዚህ ከከተማ እንዳትወጭ ጠብቄ ወደ ፍርድ ቤት እንዳቀርብሽ የታዘዝኩትን ለመፈጸም በተቻለኝ መጠን ላስረዳሽ ሞክሬአለሁ ”

“ መቸም እንደዚህ ይዘኸኝ በዌስት ሊን መንገዶች ታልፋለች ብለህ እንደ
ማታስበኝ አርግጠኛ ነኝ ”

“ ላለመሸሽ ቃል ከባሽልኝ እለቅሻለሁ " ለመሮጥ ብትሞክሪ ደግሞ ላልሰሙት ለማሰማት ካልሆነ በቀር ሁለት ሜትር እንኳን ሳትሔጅ ስለምይዝሽ
ሙከራሽ ዋጋ የለውም"

“ በል ልቀቀኝ ዝም ብዬ እሔዳለሁ”

ከዚያ ፖሊሱ ቫንጣዋን ይዞ ለሽርሽር የወጡ መስለው ቀስ ብለሙ እያወሩ ሄዱና ከቃል መቀቢያው ክፍል ገቡ በምስክርነቷ ለዳኞቹ ከቤት ደግሞ ለሚስዝ
ላቲመር ምን እንደምትመልስ እያሰበች ተቀመጠች።....

💫ይቀጥላል💫
👍21
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


የሕግ ባሥልጣኖቹ ገብተው ቦታቸውን ያዙ " በሌላ ጊዜ ቢሆን ዌስት ሊን
የማይረግጡት የሰላም ኮሚሺን አባሎች የሆኑ ሁሉ መጥተው ስለ ነበር መቀመጫ እንኳን
ሊበቃቸው አልቻለም " ምናልባት በተቃዋሚ ወገኖች የተሸረበ ደባ ይሆናል በማለት የተመሠረተበትን ክስ ስላላመኑበት የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወዳጆቾ
ሁሉ ተሰባስበው ከችሎት ተገኙ " ሎርድ ማውንት
እስቨርንም ከኮሚሽኑ አባሎች ጋር መቀመጫ ተሰጠው" ልጁ ሎርድ ቬንም ከሕዝቡ መኻል ገብቶ ተቀመጠ ሰብሳቢው ሚስተር ጀስቲስ ሔር እየተጀነነ ቦታውን ያዘ" ልጁን ከስቅላት ለማዳን
ቢሆንም በይሉኝታ ይበድለዋል ወይም ባባትነቱ ይጠቅመዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር" ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንንም ቢሆን ከሕሊናው ውጭ ጥፋተኛ ያደርገዋል ተብሎ
አይገመትም " ከጐኑ የተቀመጠው ሌላዉ ዳኛ ኮሎኔል ቤቴል ነበር " ሚስተር ሩቢኒ ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጥብቅና ቆመለት።

ሚስተር ቦል ከሪቻርድ የሰማውን መሠረት በማድረግና የፍንጩ መሠረት ግን ሪቻርድ መሆኑን ሳያነሣ ጭብጡን ብቻ በማቅረብ አስረዳ። ጭብጡን ከየት እንዳገኘው ተጠይቆ 'ምንጮን ለጊዜው ለመግለጽ ነገሩን የሚያበላሽበት መሆኑን
ግለጾ ሌቪስን ቶርን መሆኑን ማረጋገጥ ስለ ፈለገ በመጀመሪያ ኤበንዘር ጄምስ ተጠራ .

“ ስለ እስረኛው ስለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ምን ታውቃለሀ ? ” አለው ጀስ
ቲስ ሔር።

.“ ብዙ አላውቅም ” አለ ኧበንዘር ጄምስ ' “ በርግጥ ካፒቴን ቶርን ሲባል
ዐውቀው ነበር ”

“ ካፒቴን ቶርን ?”

“ አፊ '“ ካፒቴን ቶርን ትለው ነበር " ኋላ ግን መቶ አለቃ እንደ ነበር ለማመቅ ችያለሁ

“ ይኸንን ከማን ልታውቀ ቻልክ ?”

“ ከአፊ! ስለሱ ስትናገር የሰማኋት እሷ ብቻ ነበረች ”
“ እና “ ከዚያ አይጫካ ከተባለው ቦታ ሁልጊዜ ታየው ነበር ?”

“ ከዚያና ከሆሊጆን ቤት ብዙ ጊዜ አየው ነበር "

“ ቶርን ብለህ አነጋግረኸው ታውቃለህ ?

“ ሁለት ሦስት ጊዜ ቶርን ብዬ ስጠራው መልሶልኛል " እኔ ስሙ መሰለኝ እንጂ
እኔ የሽፋን ስም ነው ብዬ አልጠረጠርኩም "ኦትዌይ ቤቴልና ሎክስሌይም
በዚሁ ስም ይጠሩት ነበር“ በተለይ ሉክስሌይ ከዱሩ ተለይቶ ስለማያውቅ • ቶርን
ስለ መሆኑ በሚግባ የሚያውቀው ይመስለኝ ነበር

“ ሌላስ ማን ያቀሙ ነበር ?
"ሟቹ ሚስተር ሆሊጆንም ቶርንን ከቤቱ እንዲመጣበት እንደማይፈልግ ለአፊ ሲነግራት ሰምቻለሁ።
“ቶርን ጋር የሚተዋወቁ ሌሎችስ ነበሩ ?”
“ ትልቅ እህቷ ጆይስ የምታወቀው መሰለኝ ከሁሎ የበለጠ የሚያውቀው ግን ሪቻርድ ሔር ነበር „”

ዳኛው ሪቻርድ ሔር የልጁን ስም ሲሰማ ግብሩ ከነመልኩ በዐይነ ሕሊናው
መጣበትና ከመቀመጫው እንዳለ ፊቱን ኮሶ አስመሰለው "

“ ቶርን ወደ ጫካው ይመላለስበት የነበረው ምክንያቱ ምን ነበር ?

“ አፊን በወዳጅነት ይዟት ነበር " "

“ ሊያገባት ሐሳብ ነበረው ?

“የዚህ ሐሳብ እንኳን የነበረው አልመሰለኝም ”
ሆሊጆን የተገደለ ዕለት አይተኸው ነበር ?

ሆሊጆን የተገደለ እለት አይተኸው ነበር?

የዚያን ዕለት እኔ ራሴም በዚያ አካባቢ ስላልነበርኩ አላየሁትም „”

“ግድያውን የፈጸመው እሱ ይሆናል ብለህ ጠርጥረህ ነበር ?”

"ኧረ በጭራሽ ! ሪቻርድ ሔር በወንጀሉ ተከሰሰበት እኔም አልገደለም የሚል ጥርጣሬ አልነበረኝም ”

“ ይኸ ከሆነ ስንት ዓመት ይሆናል ? አለ ሚስተር ሩቢኒ አቋርጦ ምስክር
ነቱ ያበቃ መስሎት

“ አንድ ዐሥራ ሁለት ዓመት ይሆናል ያውም ባይበልጥ ”
ታዲያ ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ' ያ ሰው ፍራንሲዝ ቪስን ለመሆኑ ምለህ
ማረጋግጥ ትችላለህ ?

“ የሱን ማንነት የራሴን ማነት ያህል ስለማውቍው
ማረጋገጥ እችላለሁ

“ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስተ ዛሬ አንድም ጊዜ ሳታየው
እንዴት አሁን ልታውቀው ትችላለህ ? እንዲህ ያለ ምስክርም አላየንም

“ በመኻሉ አይተኸው ታውቃለህ ? አለ ዳኛው "

“ ሚስተር ሆሊጆን ከተገደለ ከአሥራ ስምንት ወር በኋላ በአጋጣሚ ለንደን ላይ አይቸዋለሁ ”

“ ያን ጊዜ ስታየው ቶርን ነበር ወይስ ሌቪሰን የመስለህ ?

ቶርን ነው እንጂ !አሁን ለሕዝብ እንደራሴነት ሲወጻደር እኮ ነው ሌቪስን መሆኑን ያወኩት።

አፍሮዳይቴ ሆሊጆንን ጥራ ” አለ ዳኛው "

ሴትዮዋ ይዟት በመጣው ፖሊስ ተደግፋ ገባች እሷ የምስክርነት ቃሏን ከመስጠቷ በፊት ሚስተር ኤበንዘር ጄምስ ከችሎቱ አዳራሽ እንዲወጣ ሚስተር ቦል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ " ለዚሁም የራሱ የሆነ ምክንያት ነበረው "

ስምሽ ማነው ?”
"አፊ ” አለች ጀርባዋን ወደ ፍራንሲዝ ሌቬሰንና ወደ ኦትዌይ ቤቴል አድርጋ።

ሙሉ ስምሽን ” አለ ዳኛዉ"
“ አፍሮዳይቴ ሆሊጆን " ስሜን ሁላችሁም ታውቁታላችሁ የማይረቡ ጥያዎችን መጠየቅ ምን ጥቅም አለው ?

“ መስካሪቱን አስምላት " አለ ጀስቲስ ሔር "

የመጀመሪያ ቃሉን መናገሩ
ነበር "

" እኔ አልምልም ”
“ መማል አለብሽ” አለ ጀስቲስ ሔር ።
“ እኔ ምንም ቢሆን አልምልም ብያለሁ „”
“ እንግዲያሙስ ፍርድ ቤቱን በመድፈር ወሀኒ ቤት ትላኪያለሽ” አላት " ከተናግረ ወደ ኋላ እንደማይል ካነጋግሩ ገባትና ደነገጠች "
ሰር ጆን ዶቢዶም ተጨመረና “ትሰሚያለሽ ' ሴትዮ ' በአባትሽ መጠደል
ያንቺም እጅ አለበት እንዴ ?

“ እኔ !” አለች በቁጣና በድንጋጤ ከገነፈለው ስሜቷ ጋር እየተናነቀች ደ
“ እንዴት እንደዚህ የመሰለ ተግቢ ያልሆነ ጥያቄ እጠየቃለሁ ? እሱ ለራሱ ደግ አባት ነበር ” አለች እንባዋ እየተናነቃት “ ሕይወቱን በሕይወቴ ለውጨም ባዳንኩት ”

“ የሱን ገዳይ ለፍርድ ለማቅረብ የሚረዳውን ምስክርነት ለመስጠት ግን ፈቃደኛ አይደለሽም ”

“ እኔ እምቢ አላልኩም " እንዲያውም ያባቴ አጥፊ ሲሰቀል ለማየት እፈልጋለሁ " እ እናንተ የማይሆን የማይሆን ጥያቄ ካልጠየቃችሁኝ እምላለሁ” አለች ቅር እያላት " ለመማል ያልፈለገችው ዋሽታ ለመመስከር አስባ ስለ ነበር ነው " ኋላ ግን በግድ ማለች። መሓላንም ትፈራ ስለ ነበር እውነቱን ለመናግር ተገደደች

“ በዚያ ዘመን ካፒቴን ቶርን የሚባል ሰው ሁልጊዜ እየመጣ ትገናኙ ነበር »
እንዴት ተዋወቅሺው ?”

“ይኽው የፈራሁትን ነገር ጀመራችሁ " እሱ በነገሩ የለበትም አልገደለም ”
"የተጠየቅሺውን ለመመለስ ነው የማልሺው » ከዚህ ሰውዬ ጋር እንዴት
ተዋወቃችሁ ?”

“ አንድ ቀን ወደ ዌስት ሊን ሔጄ በነበረ ጊዜ አንድ ብስኩት ቤት ተግናኘን”

“ ሲያይሽ በውበትሽ ተማረከና ፍቅር ያዘው ?”

የውበቷ ነገር ሲነሣ ያሰበችውን ጥንቃቄ ሁሉ ረሳችው " “ አዎን” አለች
ክፍሉን በፈገግታ እየቃኘች "

“ ከዚያ በኋላ የት እንደምትኖሪ ነገርሺውና ማታ ማታ ፈረሱን እየጋለበ
መምጣት ጀመረ ”

“ አዎን ታዲያ ይኽ ምን አለበት

"እሱስ ምንም የለበትም ”
አላት ተዝናንታ እንድትመልስለት የፈለገው ጠበቃ" “እንዲያውም መታደል ነው » ምነው እኔም እንደሱ በታደልኩ"

ያን ጊዜ ሌቪሰን ሲባል ነበር የምታቂሙ ???

የለም ካፒቴን ቶርን እንደሚባል ነገረኝና እኔም አመንኩት ”

“ የሚኖርበትን ቦታ ታውቂው ነበር?”

ለጊዜው ስዌንስን ያረፈ መሰለኝ እንጂ እኔም ጠይቄ እሱም ነግሮኝ አያውቅም

“ እንዴ ለመሆኑ እንዴት ያለ ቆንጆ የራስ መሸፈኛ ነው ያጠለቅሺው ?
ሲላት መችም የነበራት የመወደድ ፍላጎት ላሥር ሴቶች ይበቃ ነበርና በደስታሞተች " አንዱ ትልቁ ድክመቷ ይኸው ነበር " የተመሰገነውን መሸፈኛ በዕይኗ
ጠቀስ አድርጋ አይታ ሙሉ በሙሉ ከሚስተር ቦል መዳፍ ገባች "
👍22
“ ከእሱ ጋር ከተዋወቅሽ በኋላ ምን ያህል ጊዜ ቆይተሽ ነበር ትክክላኛ
ስሙን ያወኞሺው ?

ከብዙ ወሮች በኋላ ነው „

"ከግድያው በኋላ ነው አይደለም ?

" አዎን የትና የት ቆይቶ ነው „

" በግድያው ጊዜ ከካፒቴን ቶርን ሌላ በዚያ አካባቢ እነማን ነበሩ ?

“ ሪቻርድ ሔር ኦትዌይ ቤቴልና ሎክስሌይ ነበሩ " ሕዝቡ እስኪስባሰብ ድረስ እነዚህን ብቻ ነበር ያየሁ ”

“ሎክስሌይና ኦትዌይ ቤቴልም እንደዚያኞቹ የውበትሽ ሰማዕታት ነበሩ ?”

“ ኧረ የለም ” አለች ራሷን በቁጣ ነቅንቃ “እነዚህኮ እየተሽሎከለኩ አውሬ የሚያድኑ ሌቦች ናቸው ‥

“ ያን ለት ማታ ከቤት አብሮሽ ያመሸው ቶርን ነበር ወይስ ሪቻርድ ሔር ?”

አፊ የዚህ ጥያቄ መልስ ወዴት አንደሚያመራ እያሰበች ጥቂት ስታመነታ እውነት ለመናገር መማልሺን አትርሺ ምስክር " አብሮሽ የነበረው ሰው ሪቻርድ ሔር ከሆነም ተናገሪ " መወላወል ግን የለም” አለ ጀስቲስ ሔር "

አፊ እንደ መደን?ጥ ብላ ! “ቶርን ነበር” አለች "

“ ሪቻርድስ የት ነበር ?

“ እንጃ መምጣቱን መጥቶ ነበር ግን አላስገባሁትም " መልሼ ሰደድኩት ምናልባት ከጫካው ሲንገዋለል ያመሸ ይመስለኛል ”
አንቺ ዘንድ ጠብመንጃ ትቶ ነበር ?”

“ አዎን ለአባቴ ሊያውሰው የነበረ ጠብመንጃ ነበር " ተቀበልኩና በስተውስጥ ከመዝጊያው ሥር አኖርኩት " ጥይት መጉረሱንም ነግሮኝ ነበር ”

ከዚያ ኣባትሽ መጥቶ ጫወታችሁን ያቋረጣችሁት ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነበር ?”

“ አርሱ አላቋረጠንም እንዲያውም አባቴን ያየሁት ከሞተ በኋላ ነበር ።”

“ እስከ መጨረሻው ድረስ ከቤት አልነበራችሁም ?”

“አልነበርንም ! አየር ለመቀበል ከቤቱ በስተኋላ አድርገን ወደ ዱሩ ወጣን"

ከዚያ ትንሽ እንደ ቆየን ካፒቴን ቶርን ተሰናብቶኝ ሲመለስ እኔ ከዚያው ቆየሁ ”

“ እሺ ከዚያ በኋላሳ ጠብመንጃ ሲተኮስ ሰማሽ ?”

“ አንድ ጉቶ ላይ ዐረፍ ብዬ እንዳለ ተኩስ ሰማሁ " እኔ ግን ከቤት ይሆናል ብዬ ባለመጠርጠሬ ከቁም, ነገር አልጻፍኩትም ”

“ ከካፒቴን ቶርን ጋር አብራችሁ ስትወጡ ከቤት የተወው ነገር ነበር ?

ስንወጣ ጊዜው ሞቃት ነበርና ባርኔጣውን ከቤት ትቶት ወጣ እንጂ ሌላ ምንም አልተወም …”

ሪቻርድ አባትሽን እንደ ገደለው ካፒቴን ቶርን በደንብ ነበር የነገረሽ ?”

“ ስለዚህ ነገር ምንም ነጋሪ አላስፈለገኝም " እኔው ዐውቄው ነበር " ሁሉም ዐውቆት ነበር "

“ ካፒቴን ቶርን ሲተኩስ አይቶት ነበር ? ማየቱን ነገረሽ ?”

“ ባርኔጣውን አንሥቶ ሔደና ጥቂት ራቅ እንዳለ ሰዎች ከቤት ውስጥ ሲጪቃጨቁ ሰማ " የአንደኛው ድምፅ የአባቴ መሆኑን ዐወቀው " ወዲያው ጥይት ተተኮሰ " ምን እንደሆነ ባያውቅም አንድ ነገር እንደ ደረሰ በግምት ገባው ‥‥

« መቸም ይህን ሁሉ የነገረሽ ቶርን ነው " ምንጊዜ ነበር የነገረሽ ?
የዚያኑ ዕለት ማታ በጣም ቆየት ብሎ ”
"እንዴት ተገናኛችሁ ?

አመነታች " ነገር ግን የተጠየቀችውን ቀጥታ መመለስ እንዳለባት ስለተነገራት “አንድ ልጅ ከቤት ድረስ መጥቶ ከውጭ ሰው
እንደሚፈልገኝ ነገረኝና
ብወጣ እሱን ከዱር አገኘሁት ልጁን ወደኔ የላከው ግማሽ ሽልንግ ከፍሎ ነበር " ሽብሩ ስለ ምን እንደነበር ጠየቀኝና ሪቻርድ ሔር አባቴን እንደ ገደለው ነገርኩት
እሱም ሲጨቃጨቁ ከነበሩት አንዱ ሪቻርድ መሆኑን በድምፅ ለይቶት እንደ ነበር ነገረኝ …”

“ እስረኛው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ተመልከችው " ቶርን ትይው የነበረው እሱ ነው ?

“ አዎን ታዲያኮ ይኸ ስለ ግድያው ተጠያቂ አያደርገውም ”

“ የለም እሱስ አያደርገውም ለንደን ላይ ከካፒቴን ቶርን ጋር ለምን ያህል
ጊዜ ቆየሽ ?

አፊ አይኗን አፍጥጣ ዝም አለች።

"ከግድያው በኋላ ከዚህ ቦታ የሔድሽው ከካፒቴን ቶርን ጋር ለንደን ላይ ለመግናኘት ነበር እዚያ ሔደሽ ከሱ ጋር ምን ያህል ጊዜ ቆየሽ ?”

አፊ መልስ ላለመስጠትም ለመካድም ሞከረች ክው
ብላለች!

“ምለሽኮ ነው የምትመሰክሪው ሴትዮ ! ከቶርን ጋር ነበርሽ? ወይስ
ከሪቻርድ ሔር ? መልስ ስጭ ” አለ ሰብላቢው ፥

“ ከቶርን ጋር ነበርኩ ” ከብዙ ማመንታት በኋላ አመነች "

“ ምን ያህል ጊዜ ቆየሽ ? ሁለት ወይስ ሦስት ዓመት ?”

“ሦስትስ አይሞላም ” አለች

“ ከሁለት ዓመት ግን ይበልጣል አይደለም ?”

“ ታዲያ ምናለበት? በለንደን ለመቀመጥ ፈልጌ ብሔድና እሱም የቀድሞ ጓደኛዬ ስለሆነ አንዳንድ ቀን ጧት ብቅ እያለ ቢጠይቀኝ ለሌላው ሰው ምኑ ነው
ጥፋቱስ ምንድነው ?

“ ምንም ጉዳት የለውም
እንዳልሺው አንዳንድ ጊዜ ጧት ጧት ይጠይቐሽ
በነበረ ጊዜ ሌቪሰን መሆኑን ታውቂ ነበር ?”

“አዎ ካፒቴን ሌቪሰን መሆኑን ዐውቅ ነበር "

“ “ቶርን” የሚለውን ስም ለምን አንደ ፈለገው ነግሮሽ ያውቃል '

"እሱ እንደ ነገረኝ ካፉ ስለ ገባለት ብቻ ነበር " ስዊሰን በተገናኘን ጊዜ እውነተኛ ስሙን ሊነግረኝ ደስ ስለ አላለው ይህ ስም መጣለት ነገረኝ እሱም ለሁል ጊዜ እንዲጠራበት ሌሎችም እንዲሰሙበት አይፈልግም ነበር "

ሚስ አፌ ለጊዜው ያለኝ ይኸው ነው " ኤበንዘር ጀምስ እንዲገባ እፈልጋለሁ


💫ይቀጥላል💫
👍16
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አራት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


..መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡
ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም ላይ ከሱ በላይ ሰው እንደሌለ አድርጎ የሚገምት ሰው ነበር፡፡ አሁን ግን ያየችው ባህሪ እንደየቤዝቦል ጨዋታ ኮከብ ተጫዋችን የአድናቂነት ፊርማ እንዲፈርምሉት
የሚለማመጥ አንድ ተማሪን ነው ያስታወሳት.

መርቪንም ‹‹ከእዚያ ማጥ ውስጥ ወጥተው በዓይኔ በብረቱ ማየቴ ደስ
ብሎኛል፡ አዩ ጠፉ ሲባል እኛ ክፉ ነገር ደርሶባቸዋል ብለን ነበር የገመትነው በነገራችን ላይ እኔ መርቪን
ላቭሴይ እባላለሁ›› አላቸው:

‹‹ይሄ ጓደኛዬ ባሮን ጋቦን ይባላል፡ በህይወት እንዳመልጥ የረዳኝ እሱ
ነው አሉ ሃርትማንም።

መርቪንም ሁለቱንም ለስንብት ጨበጠና ‹‹ከዚህ በላይ አልረብሻችሁም
ናንሲ ከጥቂት ደቂቃ በፊት የተከሰተው ነገር ገርሟት የሚስቱን እግር በእግር መከታተል ተግባር ለደቂቃዎችም ቢሆን ያዘናጉት ሃርትማን
የተባሉት ሰው ታዋቂ ሰው ሳይሆኑ አይቀርም ስትል አስበችና ‹‹ማናቸው እኒህ ሰው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ፕሮፌሰር ካርል ሃርትማን በዓለም ታዋቂው የፊዚክስ ሳይንቲስት›› አላት፡ ‹‹አቶምን ለሁለት ለመሰንጠቅ በሚደረገው ምርምር ላይ የሚሰሩ
ሰው ነበሩ፡፡ ከናዚዎች ጋር የፖለቲካ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ስለነበር
ዓለም በሙሉ ከአፈር ተደባልቀዋል ብሎ ነው የገመተው አላት
‹‹ዩኒቨርሲቲ እያለሁ ፊዚክስ ነበር የማጠናው፡፡ በዚያ ጊዜ ሳይንቲስት ለመሆን ነበር ምኞቴ፡፡ ግን ለዚህ ዓይነት ስራ ትዕግስት አልነበረኝም: ይሁን እንጂ በዚህ መስክ አልተውኩም፡፡ ታዲያ በዚህ የሳይንስ ዘርፍ ላለፉት አስር ዓመታት አስደናቂ የሚደረጉትን ግስጋሴዎች መከታተል
ግኝቶች ተገኝተዋል፡፡››

‹‹ለምሳሌ?›› ስትል ጠየቀች ናንሲ፡

‹‹ሊዝ ሜይትነር የምትባል ኦስትሪያዊት ሳይንቲስት ከናዚዎች አምልጣ
በኮፐንሄገን በስደት የምትኖር ተጠቃሽ ናት፡፡ እሷም በምርምር ስራዋ
የዩራኒየምን አተም ባሪየምና ክሪፕተን ወደተባሉ ትንንሽ አተሞች መከፋፈል
ችላለች፡፡››

‹‹አተሞች የማይከፋፈሉ ነበር የሚመስለኝ›› አለች ናንሲ፡

‹‹እስከቅርብ ጊዜ እኛም እንዲህ ነበር የሚመስለን፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ራበሳይንስ ትልቅ ግስጋሴ ተደረገ ማለት ነው፡፡
ለዚህም ነው የወታደራዊው መስክ ይህን የሳይንስ ውጤት በእጅጉ የሚፈለገው፡፡ ስለዚህ የዚህን ሂደት መቆጣጠር ከቻሉ በዓለም ከፍተኛ የማጥፋት ኃይል ያለውን ቦምብ መስራት ቻሉ ማለት ነው፡››

ናንሲ እንደ ቆቅ የሚደነብሩትንና ሰውን ሁሉ በፍርሃት የሚመለከቱትን እኒህን ሰው አንገቷን አዙራ አየት አደረገቻቸው፡፡ ‹‹እንዲህ ያሉ ሰው ያለ ጠባቂ ብቻቸውን እንዲሄዱ እንዴት እንደፈቀዱ የሚገርም ነው!›› አለች።

‹‹ብቻቸውን ናቸው ብዬ አልገምትም›› አለ መርቪን እዚያ ፈንጠር ብሎ የቆመውን ሰው ተመልከቺ፡፡,

የመርቪንን የግምባር ጥቅሻ ተከትላ ከመንገዱ ባሻገር አይኗን አማተረች፡ ሌላ ረጅም ቆብ የደፋና
ሙሉ ልብስ ከነሰደርያው የለበሰ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ ተመለከተች፡:

‹‹ይህ ሰው የሳይንቲስቱ ጠባቂ ነው ብለህ ትገምታለህ?››

መርቪን ትከሻውን ነቀነቀና
‹‹ነጭ ለባሽ ይመስላል፡፡ ሃርትማን የሚጠበቁ መሆናቸውን አያውቁም ይሆናል፡፡ ሆኖም ጠባቂ ሳይኖራቸው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ›› አላት፡

hዚህ ቀደም መርቪን ያን ያክል ነገሮችን ይከታተላል ብላ አትገምትም ነበር፡፡

‹‹ቡና ቤቱ ይሄ ሳይሆን አይቀርም›› አለ መርቪን የውይይታቸውን ርዕስ ለውጦ፡፡ በኋላም በሩጋ ደርሶ ቆመ።

‹‹መልካም ዕድል›› አለችው ናንሲ ከልቧ፡ አናዳጅ ባህሪ ቢኖረውም ሰውየውን እየወደደችው እንደመጣች አሰበች፡፡

ፈገግ አለና ‹‹አመሰግናለሁ ላንቺም መልካም ዕድል እመኝልሻለሁ›› አላትና እሱ ወደ ቡና ቤቱ ሲገባ እሷ መንገዱን ይዛ ነጎደች።

ህንጻው ውስጥ አንድ ወጣት የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኛ ወዳለበት እንደነገሩ የተሰራ ቢሮ አየችና ወደ እሱ ሄደች፡
‹‹ወደ ኒውዮርክ ነው የምሄደው ቲኬት ብትሰጠኝ›› አለች፡
‹‹ቲኬት ፈልገው ነው? አልቋል›› አላት

ናንሲ ለወጣቱ ፈገግ አለችለት፡፡ ፈገግ ማለት የቢሮክራሲውን ማነቆ
ሊያለዝብ የሚችልበት ጊዜ አለ፡፡

‹‹አየህ የኔ ወንድም፤ ቲኬት ማለት ብጣሽ ወረቀት ነው›› አለችው
‹የቲኬቱን ዋጋ ልስጥህና አይሮፕላኑ ላይ ጫነኝ አይመስልህም?››

እሱም በፈገግታ ጥርሱን ብልጭ አደረገ፡ የሚችል ከሆነ እንደሚረዳት
ገመተች፡፡

‹‹አይሮፕላኑ ሙሉ ባይሆን እጭንዎት ነበር›› አላት፡፡

“ምን አይነት ነገር ነው! ስትል አጉተመተመች፡ ሰማይ የተደፋባት መሰላት፡፡ እስካሁን የደከመችው እንዲያው ነው እንዴ! ሆኖም ገና እጇን አልሰጠችም፡፡ በፍጹም ተስፋ መቁረጥ የለባትም፡፡

‹‹አንድ የሆነ ነገር መኖር አለበት›› አለች፡፡ ለመኝታ የሚሆን ቦታ ባይኖርም ግዴለም መቀመጫ ላይ እተኛለሁ፡፡ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች
ወንበር ቢሆንም ግድ የለኝም››
‹‹የሰራተኛ ወንበር ላይ ተሳፋሪ እንዲቀመጥ አይፈቀድም አንድ ያልተያዘ ቦታ ያለው የሙሽሮች ክፍል ብቻ ነው።
‹‹እሱን ቦታ ትሰጡኛላችሁ?›› ስትል ጠየቀች ተስፋዋ ለምልሞ
‹‹ምን ችግር አለ፤ ዋጋው ስንት እንደሆነ አላውቅም እንጂ››
‹‹እባክህ ጠይቅልኝ›› አለችው አስተዛዝና፡

‹‹ምናልባትም የሁለት መቀመጫ ዋጋ ሳይኖረው አይቀርም፡፡ ማለትም
ሰባት መቶ ሃምሳ ዶላር የመሄጃ ብቻ፡፡ ምናልባትም ይበልጥ ይሆናል› አላት፡፡

ናንሲ ዋጋው ሰባት ሺ አምስት መቶ ዶላር ቢሆን ግድ የላትም፡፡ ‹‹ባዶ ቼክ እሰጥሃለሁ የፈለከውን ዋጋ መሙላት እንድትችል›› አለች በጉጉት ‹‹ነገ ኒውዮርክ መድረስ የምፈልግበት ብርቱ ጉዳይ አለብኝ›› አለች
የምትሄድበትን ጉዳይ ለመግለጽ ከዚህ የተሻለ አባባል አጥታ፡

‹‹እስቲ ካፒቴኑን ልጠይቅ›› አለ ወጣቱ ‹‹ከኔ ጋር ይምጡ፣ የኔ እመቤት››

ናንሲ የመወሰን ስልጣን የሌለው ሰው ጥረቴን ሁሉ መና ያስቀርብኝ
ይሆን ብላ እየሰጋች ሰውየውን ተከተለችው ምን ምርጫ አላት፡

አንድ ፎቅ ላይ የሚገኝ ቢሮ ውስጥ ገቡ፡፡ ቢሮው ውስጥ ሲጋራ እያጨሱና ቡና እየጠጡ የአየር ጠባይ ሁኔታ ቻርት ይዘው የሚወያዩ ስድስት ወይም ሰባት የሚሆኑ የአዘቦት ልብሳቸውን የለበሱ የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አሉ፡፡ ወጣቱ ሰራተኛም ናንሲን የአይሮፕላኑ ካፒቴን መርቪን ቤከር ጋ ወስዶ አቀረባት፡

ወጣቱ ሰው ‹‹ካፒቴን ወይዘሮ ሌኔሃን ወደ ኒውዮርክ የሚያስኬደኝ
ብርቱ ጉዳይ ስላለኝ የሙሽሮችን ክፍል ዋጋ ከፍዬም ቢሆን እሄዳለሁ እያሉ ነው፡፡ እንውሰዳቸው?›› ሲል ጠየቀ፡

ናንሲ የካፒቴኑን መልስ በጉጉት ጠበቀች፡፡ ካፒቴኑም ‹‹ወይዘሮ ሌኔሃን
ባለቤትሽ አብሮሽ አለ?›› ሲል ጠየቃት፡

‹‹ባለቤቴ ሞቷል ካፒቴን››
👍102👎1😁1
‹‹ይቅርታ የኔ እመቤት፡፡ ሻንጣ ይዘሻል?››
‹‹ይሄ ትራቭሊንግ ባግ ብቻ ነው ያለኝ››
‹‹እንወስድሻለን ወይዘሮ ሌኔሃን››
‹‹እግዜር ይስጥህ ካፒቴን›› አለች ናንሲ በደስታ እየተርበተበተች፡
‹‹ይሄ ጉዞ ለእኔ ምን ያህል ጠቃሚዬ እንደሆነ መግለጽ ይከብደኛል፡››
ናንሲ በደስታ እግሮቿ ሊከዷት ምንም አልቀራቸውም ያገኘችው
ወንበር ላይ ዘፍ አለች። ነፍሷን ስትገዛ በስሜት እንዲህ መሆኗ አሳፈራት፡
መርበትበቷን እንዳያውቁባት ቦርሳዋ
በረበረችና ቼኳን መዛ እጇ እየተንቀጠቀጠ ባዶ ቼክ ፈርማ ለወጣቱ ሰጠችው፡፡
አሁን ፒተርን ፊት ለፊት የምትጋፈጥበት ጊዜ ደረሰ፡፡
መንደሩ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ናቸው የሚታዩት የተቀረው ተሳፋሪ
የት ደረሰ?›› ስትል ጠየቀች

‹‹አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ቡና ቤት ናቸው›› ሲል መለሰ ወጣቱ። ቡና
ቤቱ እዚሁ ህንፃ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ መግቢያው በጎን በኩል ነው፡፡››

ናንሲ ተነስታ ቆመች: አሁን ድንጋጤው ለቋታል፡፡

‹‹የኔ ልጅ እግዚአብሔር ውለታህን ይክፈልህ››

‹‹እኔም እርስዎን መርዳት መቻሌ ደስ ብሎኛል›› አለ ወጣቱ ሰው፡፡

በበሩ ስትወጣ ክፍሉ ውስጥ ያሉት ሰራተኞች ባዶ ቼክ ላይ የምትፈርም የምታምር ሴት እያሉ በነገር ሲሸነቁጧት ሰማች፡፡ ናንሲ ወደ ውጭ ስትወጣ ደከም ያለ ጸሃይና ለስለስ ያለ አየር ተቀበላት፡፡ አየሩ ከባህሩ
በሚወጣ ጨዋማ መዓዛ ታውዷል፡፡ አሁን እምነተ ቢሱን ወንድሟንልትገጥም ነው፡

ከዚያም በህንጻው ጎን ሄዳ ቡና ቤት ውስጥ ዘው አለች፡፡ ቡና ቤቱ እሷ
የምትገባበት ዓይነት አይደለም፡፡ ትንሽ ጨለምለም ያለ፣ ወምበሮቹና ጠረጴዛዎቹ ተራ፣ ወንዶች ብቻ የሚዝናኑበት ዓይነት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ቡና ቤቱ
ለዓሳ አጥማጆችና ለገበሬዎች ቢራ መጠጫነት ነበር የሚሆነው፡፡ አሁን ግን
ኮክቴል በሚጠጡ ሚሊየነሮች ከጥግ እስከ ጥግ ተሞልቷል፡፡ አየሩ በሰዎች ትንፋሽ የታፈነና ሁካታ የበዛበት ነው፡፡ የሚነገረው ቋንቋ የተለያየ ሲሆን ተሳፋሪዎቹ ፌሽታ እያደረጉ ይመስላል፡፡ ምናልባትም ተሳፋሪዎቹ አብረው የሚዝናኑ በውቅያኖስ ላይ ረጅም ጉዞ ስለሚጠብቃቸው ይሆናል፡፡

ቡና ቤቱ ውስጥ ያለውን ሰው ሁሉ በዓይኗ ስታማትር ፒተርን አየችው፡፡ እሱ ግን አላያትም፡፡ በቁጣ ሰውነቷ እየነደደ ለተወሰኑ ሰከንዶች
አፈጠጠችበት፡፡ ጉንጮቿ በንዴት ቲማቲም መስለዋል፡ ፊቱን በጥፊ አጩይው! አጩይው! አላት፡፡ ሆኖም ንዴቷን በሆዷ አምቃ በጥፊ
ከመጠፍጠፍ ተቆጠበች፡፡ የተናደደችበት መሆኗን እንዲያውቅ አልፈለገችም፡፡
ሁልጊዜም አንድን ነገር ረጋ ብሎ ማስኬድ እንዳለባት ታውቃለች፡፡

የተቀመጠው ጥግ ላይ ሲሆን አብሮት ናት ሪጅዌይ አለ፡፡ ይሄ ደግሞ ድንጋጤ ውስጥ ጥሏታል፡፡ ናት የጫማ ናሙናዎች ለመሰብሰብ ፓሪስ
እንዳለ ነው የምታውቀው፡፡ ከፒተር ጋር ወደ አሜሪካ አብሮ ይበራል ብላ
አልጠበቀችም፡፡ ናት እዚህ ቦታ ባይኖር በወደደች፡፡ የቀድሞ ፍቅረኛ እንደዚህ
ያለ ግጭት ላይ ከተገኘ ነገሮች ይዛባሉ ከዚህ በፊት ፍቅረኛዋ መሆኑን ከአዕምሮዋ ፋቀች፡፡

ቡና ቤቱ ውስጥ የተገጠገጠውን ሰው ገፋ ገፋ እያደረገች ፒተርና ናት
ያሉበት ጠረጴዛ ጋ ደረሰች፡፡ ናት ነው መጀመሪያ ያያት፡፡ እንዳያት ፊቱ ላይ
ያየችው ድንጋጤና የጥፋተኛነት ስሜት አንጀቷን ቅቤ አጠጣው፡፡ የናትን
ዕይታ ተከትሎ ፒተር ቀና ሲል እሱም አያት፡፡ የፒተር ፊት በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ‹‹የአምላክ ያለህ!›› አለ ከመቀመጫው ተነስቶ፡ ሁነቱ የፈጠረበት ድንጋጤ የሚነገር አይደለም፡፡

‹ምን አስደነገጠህ ፒተር?›› አለች ናንሲ ሆዷ በደስታ እየሞቀ፡፡

ፒተር ምራቁን ዋጠና ተመልሶ ወምበሩ ላይ ዘፍ አለ፡፡

ናንሲም ‹‹እንደማትጓዝበት እያወቅህ በመርከብ ለመጓዝ ቲኬት አዴልፊ ሆቴል ተመዘገብክ፡፡ ይህን ሁሉ የምታደርገው በፓን አሜሪን ገዝተሃል። ከኔ ጋር ሊቨርፑል ድረስ መጥተህ፣ እንደማታርፍበተ እያወቅህ
አይሮፕላን እንደምትበር እንዳላውቅብህ ነው፡፡››

ፒተር ፊቱ በድንጋጤ አመድ እንደመሰለ በጸጥታ እህቱን ዓይን ዓይኗን ያያል

ንግግር ለማድረግ የተዘጋጀች ባትሆንም ቃላቱ ሁሉ እየተከታተሉ
ከአንደበቷ ይወጡ ጀመር፡ ‹‹ትናንት እኔ የማላውቀው መስሎህ ከሆቴሉ ሹክክ ብለህ ወጥተህ ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ሄድክ፡፡›› ጠረጴዛውን ደገፍ
ስትል ፒተር በደመነፍስ ሽምቅቅ አለ፡፡
‹‹ምንድነው የሚያስፈራህ?
አልነክስህምl›› ስትለው ከምር እንደምትነክሰው ሁሉ ወደ ኋላው አፈገፈገ፡፡

ጮክ ብላ ስትናገር ድምጿን ቡና ቤቱ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ይሰማል ብላ አልተጨነቀችም፡ ሰዉ ጸጥ ረጭ ብሎ ያዳምጣል፡ ፒተር በበኩሉ በእፍረት ዙሪያ ገባውን ይገረምማል፡

‹‹ላንተ ካደረኩልህ አንጻር ያንተ ጅልነት አያስደንቀኝም፡፡ ጥፋቶችህን ሰው እንዳያውቅብህ እድሜህን በሙሉ ስጠብቅህ ኖርኩ፡፡ የአንድ ባዛር ስራ እንኳን ለማስተባበር አቅም እንደሌለህ እያወቅሁ ነው የኩባንያውን ኃላፊነት
የለቀቅሁልህ፡ ይህን ሁሉ አድርጌልህም ንግዱን ከእጄ ፈልቅቀህ ለማውጣት
ጉድጓድ ከመማስ አልቦዘንክም፡፡ እንዴት ይህን ግፍ በኔ ላይ ትፈጽማለህ?
እንደ ትል ውስጥ ውስጡን መሹለክለክህ ለምንድነው?›› አለች ናንሲ

ፒተር ፊቱ በድንጋጤ እንደገረጣ ‹‹እኔን ከክፉ ነገር ስትጠብቂኝ
አልነበረም፡፡ ሁልጊዜም የራስሽን ጥቅም ስትጠብቂ ነው የኖርሽው›› አለ
‹‹ሁልጊዜም የበላይ ለመሆን ትፈልጊያለሽ ነገር ግን ኃላፊነቱን አላገኘሽም፡፡
ከዚያ ወዲህ ቦታውን ከኔ ለመውሰድ እንቅልፍ አጥተሽ ትፍጨረጨሪያለሽ፡››

ፒተር የተናገረው ተገቢ ባለመሆኑ መሳቅ ይሁን ማልቀስ ወይም ፊቱ
ላይ መትፋት ይሻል እንደሆን አላወቀችም፡፡

‹‹አንተ ደደብ ከኃላፊነት እንድትነሳ ሳይሆን ኃላፊነቱን እንደያዝክ
እንድትቆይ ሳልም ነበር፤ አንተ አይገባህም እንጂ፡፡››

ፒተር ከኪሱ ወረቀት አወጣና በድል አድራጊነት ‹‹እንደዚህ ያለ?››
አላት፡

ናንሲ እሷ የጻፈችው ሪፖርት መሆኑን አወቀችና ‹‹ታዲያ ይሄ ልክ አይደለም ትላለህ?›› አለች ይህ ዕቅድ እኮ በስራህ ላይ የሚያቆይህ ዕቅድ ነው

‹‹አንቺ የኃላፊነቱን ቦታ ወስደሽ ነዋ! እውነቱን ወዲያው ነበር ያወቅሁት፡፡ ስለዚህ የራሴን መፍትሄ ፈጠርኩ››

Uነገር ግን ‹መፍትሄ ያልከው ነገር አልሰራም አለች ናንሲ በድል አድራጊነት፡፡ ‹‹የአይሮፕላን ቲኬት ስለገዛሁ ለቦርዱ ስብሰባ እደርሳለሁ››
አለች ለመጀመሪያ ጊዜ በጸጥታ የወንድምና እህቱን ክርክር ወደሚያደምጠው ናት ሪጅዌይ ዞር አለችና ‹‹የብላክ ጫማዎች ኩባንያን እጅህ ለማስገባት
ትቋምጣለህ እንጂ አታገኘውም፡፡ ሲያምርህ ይቅር ናት›› አለችው:

‹‹ሁሉም ነገር እጅሽ እንደገባ አታስቢ›› አላት ፒተር፡ ይህን ሲል ባንድ
ነገር እርግጠኛ የሆነ ይመስላል፡ ፒተር እሷ የማታውቀው ነገር ለማድረግ አውጥቶ አውርዶ የማቀድ ችሎታ እንደሌለው ታውቃለች፡፡

‹‹እኔና አንተ እያንዳንዳችን አርባ በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ይዘናል፡፡ቲሊና ዳኒ ሪሌይ የቀረውን አስር አስር በመቶ አክሲዮኖች ይዘዋል፡ ሁለቱ የእኔን ፈለግ ተከታዮች ናቸው፡፡ እኔና አንተ ምን አይነት አቅም እንዳለን ልቅም አድርገው ያውቃሉ፡፡ ለአባባ ታማኝነት ለማሳየት ቢፈልጉም አንተ
ኩባንያውን እንዳከሰርክ እኔ ደግሞ አትራፊ እንዳደረኩት ያውቃሉ፡ ለኔ ድምጽ ስጡኝ ብል አያሳፍሩኝም››

‹‹ሪሌይ ለኔ ነው ድምፅ የሚሰጠው›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡

ናንሲ የፒተር ልበ ሙሉ አነጋገር ጥርጣሬ ውስጥ ጣላት ‹‹ኩባንያውን
ድምጽ ገደል እየጨመርከው
ለምንድነው ላንተ
እንደሆነ እያወቀ
የሚሰጠው?›› አለች በንቀት፡፡ ሆኖም የውስጧ ጥርጣሬ እንደ ድምጿ
ጠንካራ እንዳልሆነ ልቦናዋ አውቋል፡
👍14
ፒተር ስጋቷን አወቀና ‹‹ፈራሽ አይደል?›› አላት በንቀት በተራው፡ ናንሲ መፍራቷ እውነት ነው፡፡ በምትናገረው ነገር ሙሉ እምነት እንደሌላት እየተሰማት ነው፡፡ እሱም የልብ ልብ እያገኘ መጥቷል፡ ከፒተር ጉራ በስተጀርባ ምን እንዳለ ማወቅ ሊኖርባት ነው፡፡

‹‹ያልተጨበጠ ነገር ነው የምታወራው›› አለች በፌዝ፡፡

‹‹አይደለም›› አለ ኮራ ብሎ፡፡

በዚህ አይነት ልታውጣጣው ብትሞክር የተናገረው ስህተት ለመሆኑ
የመልስ ምት እንደማይኖራት ናንሲ ታውቃለች፡፡

‹‹ሁልጊዜ አንድ የተደበቀ ምስጢር እንዳለ ታስመስላለህ። ነገር ግን
አንድም ቀን ተግባራዊ አድርገኸው አታውቅም››
‹‹ሪሌይ ለኔ ድምጽ እንደሚሰጠኝ ቃል ገብቶልኛል››
‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡:.....

ይቀጥላል
👍102
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ ..መርቪንም ‹‹ጌታዬ፣ ሰላም ልሎት ነው የመጣሁት፡፡ እርስዎን በአካል ማግኘት መቻሌ ክብር ይሰማኛል›› አላቸው ከሰውነት ጎዳና የወጡትን ሰው፡፡ ሃርትማን ጥንቃቄ ሳይለያቸው እጃቸውን ለሰላምታ ዘረጉ፡፡ናንሲ የመርቪን ባህሪ በአንድ ጊዜ መለወጡ አስደንቋታል፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ባህሪውን እንዳየችው ከሆነ በዓለም…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ስልሳ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


“ቶርን” የሚለውን ስም ለምን አንደ ፈለገው ነግሮሽ ያውቃል '

"እሱ እንደ ነገረኝ ካፉ ስለ ገባለት ብቻ ነበር " ስዊሰን በተገናኘን ጊዜ እውነተኛ ስሙን ሊነግረኝ ደስ ስለ አላለው ይህ ስም መጣለት ነገረኝ እሱም ለሁል ጊዜ እንዲጠራበት ሌሎችም እንዲሰሙበት አይፈልግም ነበር "

ሚስ አፌ ለጊዜው ያለኝ ይኸው ነው " ኤበንዘር ጀምስ እንዲገባ እፈልጋለሁ።

ኧቤንዘር ጀምስ ገብቶ የአፊን ቦታ ያዘ "ግድያው ከተፈጸመ ከአሥራ ስምነት ወሮች በኋላ ቶርንን ለንደን ላይ እንዳየኸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸሃል” ብሎደ ጀመረ ጠበቃው ቦል “ ይኸም አፊ ሆሊጆን አብራው የነበረችበት ጊዜ መሆን
አለበት እሷንም አይተሃት
ነበር?።

ኤቤንር ጀምስ ዐይኖቹን አፈጠጠ "አፊ ምን ብላ እንደ መስከረች አላወቀም
እሷ ከቶርን ጋር እንደ ነበረች ከዚያ በፊት ለማንም ተናግሮት አያውቅም
እንዴት ሊታወቅ እንደቻለ ገረመው ።

" አፊን ?

“አዎን አፊን አይተሃት ነበር ወይ?” አለ ጠበቃው ኮስተር ብሎ - “ ከዌስት ሊን ስትጠፋ ሪቻርድ ሔርን ተከትላ ሔዳ ነው ተብሎ ተወርቶ ነበር“ እሷ ግን
ሪቻርድን ሳይሆን ቶርንን ፍለጋ እንደሔደች ፍርድ ቤቱ ዐውቋል " ስለዚህ
አንተ ቶርንን ባገኘኸው ጊዜ እሷንም አይተሃት ነበር ወይ ? ነው የምልህ ''

“አዎን አይቻታለሁ እንዲያውም በመጀመሪያ ያየሁት እሷን ነበር ”

“ እስኪ ሁኔታውን ለፍርድ ቤቱ አስረዳው ”

“አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ እዛው ለንደን ፖዲንግተን ከሚባለው ቦታ በመንገድ ሳልፍ አንዲት ሴት ወደ ቤት ስትገባ አየሁ " አፊ ሆሊጆን ነበረች እሷም አየችኝና ሻይ ጋበዘችኝ " እንግዳ ስለሚመጣባት በሁለት ሰዓት መውጣት አንዳለብኝ ነግራኝ ነበር ስለ ዌስት ሊን እሷ ስትወጣ የወጣሁ ስለሆነ አዲስ ነገር
ነግራትም - እየተጫወትን የተባለው ስዓት ደርሶ ወጣሁ " ከውጭ በር ስድረስ ቶርን በሠረገላ መጥቶ ሲገባ አየሁት "

“ታድያ አፊ የኮበለችው ከሪቻርድ ሔር ነው መባሉን እያወቅህ ወደ ዌስት ሊን እንደ ተመለስክ ለምን አልተናገርክም ?”

“መጀመሪያ ይህን ነገር መናገር የኔ ተግባር አይደለም አፊ ደግሞ ' አይቻታለሁ ብዬ ለማንም እንዳልናገር ቃል አስገብታኝ ስለ ነበር ለማንም አልተናገርኩም ”

“ ቆይ ” አለ ሚስተር ሩቢኒ ምስክሩ ሊወጣ ሲል “ ስዓቱ ከምሽቱ ሁለት
ሰዓት አንደ ነበር ተናግረሃል "ጨልሞ ነበር ?”

"አዎን ”

"ታድያ ከሠረገላ ወርዳ ወደ ቤት የገባው ቶርን መሆኑን እንዴት ልታረጋግጥ ቻልክ ?”

“በደንብ አረጋግጫለሁ " ከሠረገላ ከወረደበት ላይ የጋዝ መብራት ስለ ነበር
ልክ በፀሐይ ብርሃን የማየውን ያህል አድርጌ አይቸዋለሁ " ከዚህም ሌላ ድምፁን አውቀዋለሁ " የትም ቢሆን በድምፁና በቀለበቱ ብቻ በሚገባ ልለየው እችለሁ "
ደማቁ ቀለበቱ በመብራቱ ሲፍለቀለቅ አይቸዋለሁ …”

ድምፁንስ በምን ስማኸው? አነጋግሮህ ነበር ?

« ከኔ ሳይሆን ከባለ ሠረገላው ጋር ሲነጋገር ሰምቸዋለሁ " በመካከላቸው
አንድ ክርክር ነበር " ሰውዬው ኻያ ደቂቃ ሙሎ ከመንገድ ካስጠበቀው በኋላ የሰጠው ግን እንደማይበቃው ቅሬታውን ገለጸለት ቶርንም ጥቂት ከተጨቃጨቁ በኋላ አንድ ሽልንግ ተጨማሪ ወረወረለት።

ከኧቤንዘር ጄምሰ ቀጥሎ የሟቹ የሰር ፒተር ሌሺሰን ባልደራስ የነበረ አንድ
ሰው ተጠራ“ እሱም ሆሊጆን በተገደለበት ዘመን ወደ በጋው መጨረሻ ሲል ፍራንሲዝ ሌሺስን ስር ፒተርን ለመጠየቅ መጥቶ መስንበቱን መሰከረ እዚያም ሲሰነብት ብዙ ጊዜ በተለይ ወደ ማታ ሲሆን የዌስት ሊንን አቅጣጫ ይዞ በፈረሱ ይሔድና ሦስት ወይም አራት ስዓት ያህል ቆይቶ ፈረሱ ላብ በላብ እስኪሆን ድረስ እየጋለበ ይመለስ እንደ ነበር ጨምሮ አስረዳ ከሚስተር ሌቪሰን ኪስ የወደቀ ሁለት ደብዳቤዎች በተለዩ ጊዜያት አግኝቶ እንደ ስጠው ገለጸ " የሁለቱም ደብዳቤዎች አድራሻ • ለካፒቴን ቶርን ሲል የፖስታ ቤት ምልክት አልነበራቸውም
ከተቀባዩ ስም በቀር በፖስታዎቹ ላይ ምንም ነገር አልተጻፈባቸውም ጽሕፈቱ የሴት ይመስል ነበር " ምስክሩ ተጠይቆ በሰጠው ማብራሪያ የሆሊጆን መገደል ዳር እስከ ዳር ትልቅና አስደንጋጭ ዜና ሆኖ እንደሰነበተ በደንብ ማስታወሱንና ፍራንሲዝ ሌቪሰንም ሰር ፒተር ዘንድ ቆይታውን ጨርሶ ወደ ለንደን መመለሱን ተናገረ ።

እንዴት ያለ የማስታወስ ችሎታ አለህ ! አለና ሩብኒ አፌዘበት "

ምስክሩ ሞግስ ያለው ከባድ ሰው ነበር በርግጥ ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንደነበረው ራሱም አልሸሸገም በተለይ ግን ሚስተር ሌቪስን ሆሊጆን እንደ ተገደለ ከዚያ አካባቢ በመልቀቁና ሌሎችም አብረው የተከሠቱ አንዳንድ ነገሮች ከአእምሮው መቀረጸቸውን ገለጸ "

“ ምን ምን ነገሮች ናቸው? አለ ፍርድ ቤቱ "

“አንድ ቀን ሰር ፒተር የፈረሶችን ጋጣ እየዞሩ ሲያዩ ሚስተር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ትንሽ ቀን እንዲሰነብት አጥብቀው ቢጠይቁት ባልታሰበ ጉዳይ ወደ ለንደን መጠራቱን ነገራቸው እነሱ ሲነጋገሩ ሠረገላ ነጂው እየቃተተ መጣና የዌስት ሊኑ
ሆሊጆን በሪቻርድ ሔር መገደሉን ተናገረ “ ሰር ፒተር በድንተኛ አደጋ ካልሆነ በቀር ሆነ ተብሎ የተደረገ ነው ብለው ሊያምኑ እደማይችሉ መናገራቸውን አስታውሳለሁ

ሚስተር ሌቪሰን መሔድ እንዳለበት ከነገራቸው በኋላ አንድ ዐሥር ፓውንድ እንዲሰጡት ጠየቃቸው - እሳቸውም ትናንቱን ጧት ስለ ስጡት አምሳ ፓውንድ በቁጣ ሲጠይቁት የአንድ ጓደኛው መኮንን ዕዳ ስለ ነበረበት በፖስታ እንደ ላከለት ነገራቸው እሳቸው ግን የትም ሲያብድ ካላባከነው በቀር ለሰጠው ምክንያት ማዋሎን ማመን አልቻሉም » በዚህ ጊዜ ግራ የመጋባት ምልክት ታየበት " የኔጌታ ለጊዜ ቶሎ ቢቆጡም ከለመንዋቸው ልባቸው አይጠናም ነበር እንደ ሴት ምልስ ባይ ነበሩ " በርግጥ በዐይኔ አላየሁም ' ግን የጠየቃቸውን ገንዘብ ሳይሰጡት የቀሩ አልመሰለኝም " ሚስተር ሌቪዞን የዚያን ለት ሌሊት ወደ ለንደን ሔደ።

የመጨረሻው ምስክር ሚስተር ዲል ነበር " ባለፈው ማክስኞ ማታ ሚስተር ቦሻ ቤት ቆይቶ ሲመለስ ከሚስተር ጆስቲስ ቤት ፊት ለፊት አንድ ጭቅጭቅ ሰማ የነገሩ መነሻ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንና ኦትዌይ ቤቴል ድንገት መግናኘት
ኖሯል " ቤቴል ለምን እንደሚያርቀው ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰንን ሲወቅሰው ያኛው
ስለሱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለና ለማወቅም እንደማይፈልግ ነገረው "
.
ሆሊጆን የተግደለ ዕለት ማታ ግን ' ስለኔ አንድ ነገር በማወቅህ ደስ ብሎህ
ነበር " ሰመሆኑ ላሰቅልሀ እችል እንደ ነበር ታስታውሳለህ አንዲት ትንሽ ቃል ብናግርብህ በዲክ ሔር ቦታ ልትቆም ትችል እንደ ነበር ዘነጋኸው? አሁን ያ ሁሎ አለፈና አላውቅህም ትለኛለህ ? አለው »

“አንተ ከብት አለው ሰር ፍራንሲዝ ፡ “ የራስህን አንገት ከሸምቀቆ ሴታስገባ ልታሰቅለኝ እንደማትችል ጠፋህ ? ያፍ መዝጊያ ገንዘብ አልተቀበልክም
ይግሞ እንድጨምርልህ ትፌልጋህ ?

“ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምነው ያንን የተረገመ አምሳ ፓውንድ ስቀበልህ እጆቼ
በረገፉ እያልኩ ነው የኖርኩት " ለጊዜው ግራ ግብቶኝ • የማደርገው ጠፍቶኝ ሳለ ባታግኘኝ ኖሮ አልነካልህም ነበር ልጃቸውን ከመሰቀል የሚያድኑበትን ምስጢር
ደብቁ በመያዜ እስከዛሬ ድረስ የሚስዝ ሔርን ፊት ማየት አልቻልኰም ”

“በሱ ገመድ ራስህን ለማስገባት " አለና አሾፈበት ሰር ፍራንሲዝ።

“የለም አንተን ለማስገባት ”
👍19
“እሱ ሊሆን ይችላል" ነገር ግን እኔ ወደ ባለወግ (ፍርድ ፈጻሚ) ስሔድ አንተ
ነጥለህ አትቀርም " ይቅርታም ማምለጫም እንደማይኖርህ ታውቀዋለህ

ንትርኩ ረጂም ቢሆንም ፍሬ ነገሩ ይኸው ነበር ዲል ተጀምሮ እስኪጨረስ
አዳምጦታል ለፍርድ ቤቱም አንድ ባንድ መልሶ ተናገረው ሩቢኒ “ሕጋዊ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም ፤ተራ አሎባልታ ነው” ብሎ አመለከተ።

ፍርድ ቤቱ ግን ማንም እየመጣ ምን መሥራት እንዳለበት እንዲነግረው የማይፈልግ መሆኑን ነግሮ ዝም አሰኘው "

ኮሎኔል ቤቴል ' አንገቱን ወደፊት አስግጎ የሚስተር ዲልን ምስክርነት ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ ፊቱ ተለዋወጠ አልተሳሳትክም ? አንደኛው ተናጋሪ ኦትዌይ ቤቴል መሆኑን እርግጠኛ ነህ ? አለው።

ሚስተር ዲል አንቱን ነቀነቀ “ያልሆነውን ሰው እሱ ነው ብዬ'ምዬ የምመስክር ሰው ነው ተብዬ እገመታለሁ ? እኔም ምነው ባልሰማሁት ብዬ አዝኛለሁ ።

ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መቃ የመሳሰሉ ጣቶቹንና ያልማዝ ቀለበቱን እያሳየ
ሲንቀባረር ቆየ " ምናልባት አፊን በማስኮብለል ካልሆነ በቀር በነፍስ ግዳይ
የሚጠየቅ አልመሰለውም የሚስተር ዲል ምስክርነት ከተሰማ በኋ ነገሩ ባንድ
ጊዜ ተለወጠ » ሲጀነን የነበረው ኩምሽሽ አለ ኩራቱ ቀረና በአስጨናቂ ፍርሃት ተዋጠ "

ችሎቱ ሊፈጸም ሲቃረብ'“ አሁን ክቡር ፍርድ ቤቱ ለሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን
የዋስ መብታቸውን አንዲያስጠብቅላቸው እለምናለሁ ” አለ ሩቢኒ =
ዳኞቹ እርስ በርሳቸው ተያዩ
“ ክቡራን ዳኞች ... በስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ደረጃ ለሚገኝ ታላቅ መኮንን
እንዲህ ያለውን መብት አይከለክልም ”

ፍርድ ቤቱ እንደዚያ ያለ የድፍረት ጥያቄ ቀርቦለት እንደማያውቅ በማሰብ :
ይህን በመሰለ ወንጀል ለተከስሰ ሰው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀርበው ቢጠይቁም በዋስ ሊያስለቅቁት እንደማይችሉ ገልጾ ጥያቄውን ውድቅ
አደረገው

ኦትዌይ ቤቴል ግን ከኮሎኔሉ ጀምሮ ማንም ሊዋሰው እንደማይችል ገምቶ ምንም አልጠየቀም " ስለዚህ ሁለቱም በጆርጅ ሆሊጆን ግድያ ፍርዳቸውን አስኪያገኙ ድረስ በማረፊያ ቤት እንዲቆዬ በየነባቸው "

አፊ ቃሏን ከሰጠች በኋላ ሌላ ክፍል እንድትቆይ ተደረገ " እሷም ችሉቱ
እስኪያበቃ ወደ ለንደን ሔዳ ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር መቀመጧን ስለማመኗ
ጉዳይ የዌስት ሊን ሕዝብ ምን እንደሚላት ስታወጣ ስታወርድ ቆየች " በመረጨሻ ግን ማንም ስለዚህ ነገር ሊነቅፋት ቢሞክር ልክ ልኩን እየነገረች እንደምታሳርፈው በማስብ ደመደመች " ችሎቱ እስኪያበቃ ከተወሰነላት ክፍል ቆየች።

ችሎቱ አበቃ " ሚስተር ቦልን ሲወጣ አገኘችው " እንደሚታወሰው ጠበቃው
ወንደላጤ ነበር " አጅሪት ደግሞ ዐይኗን ስለ ጣለችበት ሚስተር ጂፍንን አስተማማኝ መጠባበቂያ አድርጋ የተሻለ ዕድል ቢያጋጥማት ታሻትር ነበር።

ስለዚህ ቀደም ብላ ዐይኖቿን ጥላበት ወደ ነበረው ጠበቃ እየተቅለስለሰች ጠጋ ብላ ' “በመጨረሻ ምን ተባለ ? አለችው "

ሁለቱም በነፍስ መግደል ተመስክሮባቸዋል " ከአንድ ሰዓት በኋላ ወደ ሊንበራ ይሔዳሉ ”

“ ሁለት ንጹሐን ይኸን በመሰለ ክስ መወንጀል አሳፋሪ ነገር ነው አለች "

“ ይኸን አስተሳሰብሺን ከአእምሮሽ ቶሎ ብታወጭ ይሻላል " የሌቪሰን ወንጀለኝነት በሚገባ ተረጋግጧል " ከዚህ በላይ ደግሞ ሁለቱ እርስ በርሳቸው ተወነጃጅለዋል “ወረበሎች እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ሐቀኞች የጃቸውን ያገኛሉ' ብሎ ተረተላትና የራሳቸውን ወንጀለኝነት ሲያጋልጡ የሪቻርድንም ንጹሕነት እንዳረጋገጡ ገለጸላት

አንቺም ለቶርን የሰጠሺውን ሚና የተጫወተው ሪቻርድ ሔር ነው "ከዳሩ ሆኖ ተኰስ ሰማ "ከዚያ ቶርንን ደንግጦ እየተርበተበተ ሲሮጥ አየው
ምንም አትጠራጠሪ • አባትሽን የገደለው ቶርን ነው” አላት "

አፊ ዐይኖቿ ስልምልም ፡ ጭልምልም አሉ ፤ ራሷ ዞረ ልቧን አጥወለወላት "
አንድ ጊዜ የጣር ጩኽት ጮኽችና ዝልፍልፍ ብላ ወደቀች አፊ በአንድ
ጀንበር ሁለት ጊዜ ነፍሷን ሳተች "

እስረኞቹ ወደ ሊንበራ ሊወሰዱ ሲንቀሳቀሱ በተለይ ፍራንሲዝ ሌቪሰንን
ከሕዝቡ ቁጣ የሚጠብቅ ከፍተኛ የጥበቃ ኃይል †መደበ " እሱም የሕዝቡን
ጩኽት ፉጨትና እርግማን ሲሰማ አረንዴው ጥምቀት የሚደገም ወይም
ትንሽ በትንሽ እያሉ እየቦጫጨቁ የሚጥሉት መሰለውና ከፍራቱ የተነሣ ዐመድ የመሰለውን ፊቱን ሸፍኖ እየተንቀጠቀጠ መሬት ከፍታ ብትውጠው ተመኘ ''....


💫ይቀጥላል💫
👍15
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ አንድ (21)


«ሲሻለኝ ከሁለት ሣምንት በኋላ ቦስተን ነበርኩ ... ቦስተን ነበር እምትኖረው ወደመኖሪያ ቤቷ ሄድኩ ። ግን ማንም አልነበረም… ምንም አልነበረም ። እቃዋም ፤ ስእሎቹም ተሰርቀው ደረስኩ ። ሰአሊ ነበረች.. ነርሶች ናቸው አሉ የ...የወ...የሰረቋቸው ስእሎቿን...» ዝምታ ሆነ ። ለረጅም ጊዜ ሁለቱም ፀጥ ብለው ተቀመጡ ከዚያ ቀጠለ

«የቀረ ነገር አልነበረም ። የለም እኔም ውስጥ ማለቴ ነው›› አለ። ይህን ብሎ ቀና ሲል የዌንዲ ፊት በእንባ ርሶ ተመለከተ። «ማይክል በጣም አሳዛኝ ነገር ነው። ይህ ስለደረሰብህ በጣም አዝናለሁ» አለች እግዜር ያጥናህ እንደማለት ነበረና ማጥናኛውን እራሱን በማወዛወዝ ተቀበለ። ቀጥሎ ለአንድ ዓመት ያህል እምቢ ያለው እንባ ፈሰሰ ፤ አለቀሰ ። ዌንዲን እቅፍ ሲያደርጋት የእንባ ዘለላዎች ፊቴን እያቋረጡ ወደ አንገቱ ፈሰሱ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

«ማይክ የካንሳስ ሲቲውን ፕሮጀክት ስለምትመራው ሴትዮ ምን አስተያየት አለህ ... ማለት ..» አለች ዌንዲ ታውንሴንድ። ማይክልና ዌንዲ እዌንዲ ቤት በስተጀርባ ባለችው አትክክልት ቦታ ነበሩ ። በታጣፊ ወንበር ላይ ተቀምጦ የእሁድን ጋዜጣ ይመለከት ነበረና ቀና ብላ አየችው ። ሁለቱም የዋና ልብስ ለብሰው የኒውዮርክን ፀሐይ ይጠጣሉ ። «ስለ ሴትዮዋ» አለች ወሬ የመቀጠል ሙከራዋን ። አልሰማትም ። እጋዜጣው ላይ አፍጥጧል ። ጋዜጣውንም እንደማያነበው ዌንዲ ታውቃለች ። « ማይክ»
«እ ? ምን አልሺኝ››
«ስለ ካንሳሷ ሴትዮ እየጠየቅኩህ ነበረ » መልስ አልሰጣትም ። እንደገና ሀሳብ ውስጥ ገባ ።ሙከራዋ ሁሉ ተስፋ የሌለው ነገር እንደሆነ ገብቷታል ። በመረበሽና በብስጭት አይን አየችው ።
«ዊስኪውን ልጨምርልህ? » አለች።
«እ?አ...አዎን።ወደ ቢሮ መሄድ ይኖርብኛል መሰል» አለና በሷ ላይ አሳልፎ አይኑን እሆነ ባዶ ላይ ተከለ ።
«ግሩም ድንቅ ሀሳብ ነው» አሎች በፌዝ።
«ምን ማለትሽ ነው ?» አሁን ያያት ጀመረ ። እንዲያ ሲያያት እፊቷ ላይ እንግዳ ነገር አየባት ።ምን እንደሆነ ሳያውቀው ሀሳቡ ተከፈለ ። ጥቂት ቢያጤናት ኖሮ እፈቷ ላይ ያየውን ነገር ትርገም ሊያገኘው ይችል ነበር።
«ምንም» አለች›› ምን ለማለት ነው ሲል የጠየቃትን እየመለሰች ። «ዊንዲ ልንግባባ ያስፈልጋል ። ቢሮ መሄድ እንዳለብኝ ልትረጂልኝ ይገባል። የሳንፍራንሲስኮው የሕክምና ማእከል ብዙ ጉልበት ይጠይቃል። ነጭ ላብ እስኪወጣኝ መስራት አለብኝ ማለት ነው በሚቀጥሉት ሁለት አመቶች። ባገሪቱ ውስጥ ካሉት ትልቅ ፕሮጀክቶች አንዱ እንደሆነ ታውቂያለሽ ፤አይደለም ?»
«ምን ምክንያት መደርደር ያስፈልጋል? ማለት ይህ የምትለው ሥራ ባይኖርም ሌላ ነገር መፍጠርህ አይቀርም ነበር ። ዝም ብለህ የመሰለህን ማድረግ ትችል የለም እንዴ »
«እንዲያም ታልሽ ደግ። እኔ የጠላሁት ይህን የመስሪያ ቤት ፊርማ ይመስል በዚህ ሰዓት ወጣህ ፤በዚህ ገባህ የምትይውን 'ነገር ነው» አለና ጋዜጣወን አሸቀንጥሮ ጥሎ አፈጣጠባት። ይህን ስታይ መጨስ ጀመረች። «ፊርማ ?ማነው ፈራሚው ?አንተ? ለመሆኑ ትናንት በስንት ሰዓት እንደመጣህ ታውቃለህ ? ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ተኩል። እኔደሞ ሰው ነህ ብዬ የሰው የራት ግብዣ ተቀብዬ እዚህ ስንቃቃ ማምሸቴ። ለእራት ትደርሳለህ የተባልከው ሰው ለመኝታም አልሆነልህ ። ብቻ ጥፋተኛዋ እራሴ ነኝ። ዝም ብዬ መሄድ ነበረብኝ!»
«እኮ! እዚህ ቁጭ ብለሽ እንድትጠብቂኝ የገባሽው ውል አለ እንዴ ?»
«ውልስ የለም ። ግን አጋጣሚ ሆነና ፍቅር ያዘኝ ካንተ… ግን ይች ልጅ ፍቅር ይዟታል ። ትጎዳለች መውደድ ይቅር ፤ ይህ ያህል ማሰብ እንኳ አትችልም። ምን ሆንክ ማይክል ? ምን ነካህ ከቢሮህ ብቅ ስትል አንገትህ ውስጥ ሸምቀቆ ሊያስገባ ያጠመመደ ሰው አለ አሉህ ?ወይስ ከሷም ጋር ፍቅር ይይዝሀል የሚል ልብህን አስፈራው? ፍቅር ይህን ያህል አስፈሪ ነገር ነውን››

«እንዲህ ደርሰሽ ተራ ነገር አትሁኝ ዌንዲ ። ሥራዬን ታውቂያለሽ ። ከማንም ሰው የበለጠ ታውቂያለሽ ስለዚህ እንዲህ አትበይኝ»
«ስራህን ስለማውቀውና ሥራ ብለህ ቢሮ ከምትቆይበት ጊዜ ቢያንስ ግማሹ ዝም ብሎ፤ ዋጋ ቢስ እንደሆነ ስለሚገባኝማ ነው እምነግርህ ። አንተ ስራህን ለስራነቱ ሳይሆን መደበቂያ አድርገኸዋል ። ከሕይወት የምትደበቀው በስራህ ነው። እኔን ለመሸሽ የምታመካኘው በስራህ ነው ። እራስህን ለመሸወድ ምክንያትህ ስራህ ነው በቃ» አለች ። በሀሳቧ ስለናንሲ ላለማሰብ መሸሺያህ ስራህ ነው ብላ ጨመረች።

«ይኸ እዚህ ግባ የማይሉት አስቂኝ ወሬ ነው፤ ዌንዲ» ይህን ብሎ ከታጣፊው ሸራ ወንበር ላይ ተነስቶ ባትክልቶቹ መካከል በድንጋይ ንጣፍ በተሰራው የእግር መንገድ ላይ በባዶ እግሩ ወዲያ ወዲህ ይል ጀመረ ። የድንጋዩ ግለት ተሰማው።

ወሩ መስከረም የበልግ ወራት መባቻ ቢሆንም የኒውዮርክ ፀሐይ ጋብ አላለም ። ማይክልና ዌንዲ የተገናኙት ባለፈው የፀደይ ወራት መዳፊያ ላይ ሲሆን ለጥቂት ሳምንት ፍቅራቸው ግሎ በደስታ ሲዋኙ ከቆዩ በኋላ ያን ሁኔታ መቀጠል ሳይችሉ ቀሩ። ሙሉውን በጋ እንዲሁ ቅጥ አምባሩ የጠፋው ኑሮ በመኖር አሳልፈው እዚህ ደርሰዋል ። ማይክል ወደ ቢሮ ይላል ። ዌንዲ ወደ መዝናኛ ። ዌንዲ አልቻለችም ። አንዲት ቅዳሜና እሁድ ሎንግ አይላንድ አካባቢ አብረው ሲያሳልፉ ሌላውን ጊዜ ግን ዌንዲ ስታዝን ፤ ስትበሳጭ ፤ ማይክል እቢሮው ውስጥ ስራውን በማከናወን ነው ያሳለፉት ።
«ደሞስ ሲጀመር ነግሬሽ የለምንዴ ? ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ ?»
«ነግረኸኛል ። ግን የነገርከኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ? ሁለተኛ ፍቅር የሚሉት ነገር ይዞህ የሆነ ያልሆነ ክፉ ነገር እንዳይገጥምህ ፤ ዳግም እንዳትጎዳ ስለምትፈራ ፍቅር እንዳይዝህ እንደምትጠነቀቅ ፤ ልታገባ እንደማትፈልግ ፤ ይህን ነገርኸኝ እንጂ መኖር እንደምትፈራ ነገርከኝ በስላሴ ? ስለሰው ማሰብ ፤ ሰው መሆን ይኸ እንደሚያስፈራህ ነገርከኝ ? ማይክል ብዙውን ጊዜህን ከማስመሪያህ ጋር ኮ ነው እምታሳልፈው! ምናልባት ለኔ፤፤ ሰው ለሆንኩት ሳይሆን ለዚያ እቃ የምትስማማ ፍጡር ሳትሆን አትቀርም
« እና?»

ይህን ያለበትን ድምፅ ስትሰማና ቀና ብላ ስታየው እፈቱ ላይ የተሳለውን ነገርም ስትመለከት መላ አካላቷን ዝፋት አንድ ነገር ስለተረዳች ፤ ስለሷ ምንም ግድ እንደሌለው ከስለገባት ። ጅል ብትሆን ነው ከሱ ጋር መኖሯ ። ጅል ብትሆን ነው ከሱ ጋር መኖር ይቻላል ብላ መገመቷ ። ግን ደግሞ ጅልነት ብቻም አይደል ። የምትወድለት ነገር አላት ። የምትወደውን አይለመዴነት ፤ የአራዊትነት ባህርይ ታይበታለች ። ይህ ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ ትካዜም ታይበታለች ። ቆስሏል ። የሚያክመው ፤ የሚጠግነው ይሻል ። ልትደርስለት እንደሚፈለግ እንደሚወደድ ልታሳየውም ትፈልጋለች ። እሷ ይህን ታስብ እንጂ እሱ ለምንም ነገር ደንታ የለውም ። ዌንዲ ናንሲ አይደለችማ! ይህን ደግሞ እሷም እሱም በሚገባ ያውቁታል ። ዌንዲ ይህን ስታስብ እንባዋ ቅርዝዝ አለ ። ቀስ ብላ ተነስታ ወደ ቤት ገባች ። በሸሽፋሎቿ ላይ ያጤዘውን እንባ እንዳያይባት ። ኩሽና ገብታ መጠጥ ቀዳች ። መጠጡን አስቀምጣ ዓይኗን ከድና ብደርስበት ፤ባገኘው እያለችና አካሏን እየገዘፋት ባለችበት ቆማ ቀረች ። ግን እንደሌለ ማንም ሊደርስበት እንደማይችል ማሰብ ጀምራ ነበረና አዎ ለማንም እጁን አይሰጥም ፤ ስትል ደመደመች ።
👍20
መጠጡን አንስታ በርከት እያደረገች ከተጎነጨችለት በኋላ ባዶውን ብርጭቆ እባንኮኒው ላይ ስታኖር መዳብማ ቀለም በያዘው ለስላሳ ቆዳዋ ላይ እጁ ቀስ ብሎ ሲሰፍ ተሰማት ። በየሳምንቱ እሁድ እጓሮዋ ቁጭ ብላ ፀሐይ ሲመታት ስለሚውል የቆዳዋ መልክ መዳብማ ሆኗል ። እንዲህ ከኋላዋ መጥቶ ሲዳብሳት ዝም ብላ ባለችበት ቆመች ። የገላው ግለት ተሰማት በጣም በጣም ፈለገችው ። ይህን ፍላጐቷን አስቀድሞ ማወቁን ብታውቅም ይህን ማወቋ ሰልችቷት ነበረና ። ልታስበው አቅም አጣች ። ብትችል ኖሮ ገላዋን መከልከል ነበረባት ። ብትችል ያን ለማድረግ ጊዜው አሁን ነበር ።
« ዌንዲ በጣም ታስፈልጊኛለሽ » አለ ። ቃሉን ስትሰማው መላ አካሏን ፍትወት አቅበጠበጣት ። ግን ደግሞ ይህ መሆኑ እንዳይታወቅባት ራሷን መቆጣጠሯም አልቀረም ። ፊቷን እንዳዞረች ፤ በጀርባዋ ላይ ቀስ እያሉ እየደባበሱ የሚወርዱትን እጆቹን ልስላሴ ጠላች ።
« እና ልበልሀ ቅድም አንተ እንዳልከው» አለች ። በጣም ታስፈልጊኛለሽ ላላት ስትመልስ ።
« ፍላጐቴን መቆጣጠር እንደማልችል ታውቂያለሽ ማለቴ ነው» አለ ። ድምጹ እንደገላው ልስልስ ያለና የላመ ነበር ።
«ማይክል የፍላጐቴ ግለት ሳይሆን ፍቅር ነው ። ዳሩ አንተ በፍቅርና በባዶ የፍላጐት ግለት መካከል ያለውሰን ልዩነት አታውቀውም ። ከሷም ጋር ሳለህ እንዲሁ ነበርክ ? » ይሀን ስትል የሚዳስሷት እጆች ቀጥ አሉ ። ክንዱም ጥንክር ሲል ተሰማት ። አደጋ አለ ። ሆኖም ራሷን ተቆጣጥራ ዝም ልትል አልቻለችም ። ልትጐዳውም ፈልጋለች ። «እሷንም ለማፍቀር ለመውደድ ትፈራ ነበር ? ዛሬ ማንንም መውደድ ስለሌለብሀ ፤ እሷን በማጣትህ የተነሣ በደረሰብህ ሀዘን ጀርባ ተከልለህ እንድትኖር ስለረዳህ ፤ ሞቷ ችግርህን ቀላል አድርጐልሀል ልበል ? የሷ ሞት ከፍርጃም ፤ ከንትርክም ነፃ አድርጐሃል ፤ አይደለም ? » ይህን ብላ ዞረችና ፊት ለፊት ተጋፈጠችው። በዓይኑ ውስጥ
የጥላቻ ጥንስስ ሲፈላ ተመለከተች ።


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍10
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን"
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡
‹‹ዕቅድህ ዳኒ ሪሌይ ላይ ላንተ ባለው ታማኝነት ላይ የተንጠለጠለ
ከሆነ እኔን አያስጨንቀኝም›› አለችና በንቀት ሳቀችበት፡

‹‹አዎ ዕቅዴ ዳኒ ሪሌይ በሚሰጠኝ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዳኒ
ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ ታውቂ የለም›› አለ በድል አድራጊነት
መንፈስ፡፡

ናንሲ ወደ ናት ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ይሄን እውነት ነው ብሎ መቀበል ይከብደኝ ነበር›› አለችው፡፡

‹‹ናት በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር የለበትም›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡፡

ናት በወንድምና እህቱ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቧል፡
ፒተር ቀጠለና ‹‹ናት ለሪሌይ ከጄኔራል ቴክስታይል ኩባንያው ጠቀም
ያለ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጠው ነው፡፡››

ፒተር በመጨረሻ የተናገረው ለናንሲ አቅል እንደሚያስት ምት ነበር፡
ናንሲ በንዴት ጉሮሮዋ ተዘግቶ መተንፈስ አቃታት፡፡ ለዳኒ ሪሌይ ጄኔራል
ቴክስታይልስን በመሰለ ግዙፍ ኩባንያ ውስጥ እግሩን ከመትከል በላይ
የሚያጓጓ ነገር አይኖርም፡፡ ኒውዮርክ ውስጥ ከሚገኝ ትንሽ የህግ ጥብቅና
ተቋም ጋር ሲነጻጸር ይሄ በሳህን የቀረበለት ስጦታ የዕድሜ ልክ ገቢ
የሚያስገኝ በመሆኑ ሪሌይ ይህን ስጦታ ላለመቀበል ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሪሌይ እንደዚህ አይነት እጅ መንሻ ከቀረበለት እናቱን ከመሸጥ አይመለስም፡፡

የፒተር 40 በመቶና የሪሌይ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በድምሩ 50 በመቶ ነው፡፡ የናንሲ 40 በመቶ ከአክስታቸው 10 በመቶ ጋር ሲደመር እንደዚሁ ሃምሳ በመቶ ነው፡፡ ሆኖም የቦርድ አባላት ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ አሸናፊውን ለመለየት የኩባንያው ኃላፊ (ሊቀመንበሩ)
የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝነት አለው፡፡ የኩባንያው ኃላፊ ደግሞ ፒተር ነው፡

ፒተር ናንሲን መደፍጠጥ በመቻሉ በኩራት ፈገግ አለ፡፡

ናንሲ ገና እጇን አልሰጠችም፡ አጠገባቸው ያለውን ወንበር ሳበችና
ቁጭ አለች፡ ፊቷንም ወደ ናት አዞረች፡ ከወንድሟ ጋር ይህን ያህል ስትከራከር የእሷን አባባል እንዳልወደደ አውቃለች፡፡ ፒተር በድብቅ ነገር ሲጎነጉን ናት ያውቅ ነበር ስትል አሰበች፡፡ ስለዚህ ነገር ናትን ልትጠይቀው ወደደች፡

‹‹ፒተር የሚለው እውነት ይመስልሃል?››
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችው ሴት ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ እሷም በጸጥታ ምንም ሳትናገር ምላሹን ጠበቀች፡፡ በመጨረሻም የዓይኗን ፍጥጫ መቋቋም አቅቶት ‹‹እኔ አልጠየቅሁትም፡፡ ደግሞ በቤተሰባችሁ ጠብ ውስጥ
እኔን ምን ያገባኛል? እዚያው በጠበላችሁ፡ እኔ የንግድ ሰው እንጂ የእርዳታ
ድርጅት ሰራተኛ አይደለሁ›› አላት፡

‹‹ናት አንተ እውነተኛ የንግድ ሰው ነህ?

‹‹እንደሆንኩ ታውቂያለሽ›› አላት ፈርጠም ብሎ፡፡

‹‹ከሆንክ አንተ
እንደዚህ ያለ ሸፍጥ ቢፈጸምብህ ዝም ብለህ
ታልፋለህ?››

ናት ትንሽ አሰብ አደረገና ይሄ የአንድን ኩባንያ ባለቤትነት ለሌላ
የማዛወር ሂደት እንጂ የሻይ ግብዣ አይደለም›› አለ፡፡
ናት ብዙ ሊል ፈልጎ አቋረጠችውና በወንድሜ እምነተ ቢስነት
እጠቀማለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ አንተም እምነተ ቢስ ነህ ማለት ነው የአባታችን ምክትል ሆነህ በመስራትህ
ነው ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረስከው››አለችና ናት መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ፒተር ዞረችና ‹‹ለሁለት ዓመት ያህል የኔ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ብትረዳኝ አሁን
በመሸጥ ከምታገኘው እጥፍ እንደምታገኝ አታውቅም?›› አለችው::

‹‹ይሄን እቅድሽን አልቀበለውም፡፡››

‹‹ኩባንያው የአወቃቀር ለውጥ እንኳን ባይደረግበት በጦርነቱ ምክንያት
የአክሲዮን ዋጋው ሰማይ ሊነካ ይችላል፡ የወታደር ጫማ በማቅረብ በኩል
የሚስተካከለን የለም፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ብትገባ ደግሞ የምናገኘው ገቢ የትየሌለ ነው›› አለች፡፡

‹‹አሜሪካንን ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ምን ይጨምራታል?››

‹‹ባይሆንስ? አሁን አውሮፓ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ብቻ እንኳን ለእኛ ንግድ ጥሩ ገቢ ያስገኝልናል›› አለችና ወደ ናት ዞር ብላ ‹‹ይሄን ታውቃለህ አይደለም? ለዚህ አይደል የእኛን ኩባንያ መግዛት
የምትፈልገው?›› ስትል አፋጠጠችው፡፡

ናት ምንም አልተነፈሰም፡፡

ቀጥሎ ወደ ወንድሟ ዞር ብላ ‹‹ትንሽ ብትቆይ ትልቅ ቢዝነስ ፊታችን ይጠብቀናል፡፡ አድምጠኝ ወንድምዬ፧ የምለው ሁሉ ስህተት ነው? የኔን
ምክር በመከተልህ የከሰርክበት ጊዜ አለ? የኔን ምክር ገሸሽ በማድረግህ
ደግሞ ገቢ ያገኘህበት ጊዜ አለ?›› ስትል በጥያቄ አጣደፈችው፡፡

‹‹አንቺ ምንም አይገባሽም›› አለ ፒተር፡፡

አሁን ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ አታውቅም፡፡

‹‹ምንድነው የማይገባኝ?››

“ለምን ኩባንያው ከናት ሪጅዌይ ኩባንያ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ጋር እንዲዋሃድ እንደፈለኩ? ለምን እንደዚህ እንደማደርግ አይገባሽም፡፡››

‹‹እሺ ለምንድነው?››
ፒተር አንድ ነገር ሳይተነፍስ ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም መልሱን
ከዓይኑ አይታ አገኘች::

ለእሷ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡:

በጣም ደነገጠች፡፡ ልክ ከማይታይ ግድግዳ ጋር የተጋጨች መሰላት፡
ይህን ሃቅ በእጅጉ ማመን አልፈለገችም:: ሆኖም ይህን በፊቱ ላይ ያየችውን
እንግዳ የሆነ የጭካኔ ገጽታ እንደሌለ አድርጋ መቀበል አስቸገራት፡፡ በታላቅና
በታናሽ መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ባላንጣነት ድሮም አለ፡፡ ይሄኛው ግን
ከዚያ ይለያል። ይሄ አስፈሪ፣ ለመግለጽ አስቸጋሪና እንግዳ የሆነ የጥላቻ
ገጽታ ነው፡፡ ይህን ከዚህ ቀደም ጠርጥራ አታውቅም፡፡ ታናሽ ወንድሟ
በጣም ይጠላታል፡ ልክ ከሆነ ነገር ጋር የተጋጨች ይመስል ደነዘዛት፡ ይን
እውነታ አምኖ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ይፈጃል።

ፒተር ጅል ወይም ስስታም ወይም ንፉግ ስለሆነ አይደለም ይህን
የሚያደርገው፡፡ እህቱን ለማጥፋት ሲል ራሱን ከመጉዳት አይመለስም፡ ይሄ ደግሞ የለየለት ጥላቻ ነው፡፡ ወንድሟ ትንሽ አዕምሮው ሳይነካ አይቀርም፡

ትንሽ ማሰብ ፈለገች፡ ንጹህ አየር ለማግኘት ብላ በጭስ ከታፈነው ቡና ቤት ወጣች፡ ከቡና ቤቱ እንደወጣች ቀለል አላት፡፡ ከባህር የሚወጣው ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበላት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና ወደ ወደቡ ሄደች፡

የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ጥግ ተኮፍሷል፡ አይሮፕላኑ ከጠበቀችው
በላይ ግዙፍ ነው፡፡ የአይሮፕላኑን ነዳጅ የሚሞሉት ሰዎች ከሩቅ ሲታዩ ጉንዳን ያካክላሉ፡፡ ግዙፎቹ ሞተሮች በአይሮፕላኑ ላይ እምነት እንድትጥል አድርገዋታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ላይ ፍርሃት አይሰማኝም› ስትል አሰበች፡ በዚያች ሚጢጢ አይሮፕላን እንኳን ህይወቷን ሸጣ መጥታ የለም፡፡

አገሯ ስትደርስ ምንድነው የምታደርገው? ፒተር ይህን እቅዱን እንዲለውጥ ማሳመን አይቻልም: አሁን ካሳየው ባህሪ በስተጀርባ ለረጅም ዓመት አምቆ የያዘው ድብቅ ጥላቻ እንዳለ አውቃለች፡፡ ለወንድሟ አዘነችለት፡፡ ይህን ያህል ዓመት ከቅናት የተነሳ ጥላቻ በሆዱ ሲያስታምም ቆይቷል፡፡ እጇን ልትሰጥ አልፈለገችም፡፡ የተወላጅነት መብቷን ለማስከበር
‹ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን?› ብላ አሰበች፡፡
👍16
ዳኒ ሪሌይ መንፈሰ ደካማ ሰው ነው፡፡ በአንድ ሰው በጉቦ የተደለለ ሰው
በሌላ ሰው መደለሉ አይቀርም፡፡ ናንሲ ድምፁን ለእሷ እንዲሰጥ የሚያደርገው ትልቅ ስጦታ
ማሰብ አለባት: የጄኔራል
ቴክስታይልስ ኩባንያ የህግ ጠበቃነት ከሚያስገኘው ጥቅም ካልበለጠ ግን
ለማቅረብ ድካሟ ሁሉ መና መቅረቱ ነው፡፡

ምናልባት የሰራኸውን ወንጀል አጋልጣለሁ ብላ ማስፈራራት ሳያዋጣት አይቀርም፡፡ ይሄ እንደውም ብዙ ገንዘብ አያስወጣትም፡፡ ግን
እንዴት? ምናልባትም ለቤተሰቡና ለእሷ ጥብቅና እንዳይቆም ማገድ ትችል
ይሆናል፡ ይህም ቃል ከተገባለት የጥብቅና ስራ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ
የሚባል አይደለም፡፡ ዳኒ በጣም የሚወደው በቀጥታ ጥሬ ገንዘብ ቢሰጠው
ቢሆንም አሁን በእጇ ያለው ጥቂት ሺህ ብር ብቻ ነው፡ አብዛኛው ገንዘቧ
በብላክ ጫማ ኩባንያ ውስጥ ታስሯል፡፡ ብዙም ሳይታወቅ ከኩባንያው ጥቂት ገንዘብ አውጥታ መስጠት ትችል ይሆናል፡ ነገር ግን ዳኒ ብዙ ገንዘብ
መጠየቁ አይቀርም፤ ምናልባትም አንድ መቶ ሺ ዶላር፡፡ ይህን ያክል ገንዘብ
ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከየት ታመጣለች?

ይህን በአዕምሮዋ ስታወጣ ስታወርድ ስሟ ሲጠራ ሰማችና ዞር ስትል
ያ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ሰራተኛ እጁን ሲያውለበልብ አየች
ሌኔሃን›› ሲል ጮኸ ‹‹ከቦስተን ስልክ ይፈልግሻል ወይዘሮ
ማክብራይድ የሚባል ሰው፡፡››

ድንገት የመጣው የማክብራይድ የስልክ ጥሪ ትንሽ ተስፋ አጫረባት፡፡
ምናልባትም ማክብራይድ አንድ መላ ይነግራት ይሆናል፡፡ ዳኒ ሪሌይን እንደ
እጁ መዳፍ ያውቀዋል፡፡ ሁለቱም ሰዎች እንደ አባቷ አይሪሾች ሲሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን ሁልጊዜ ይጠራጠራሉ አይሪሾችም
ቢሆኑ፡ ማክብራይድ ሃቀኛ ሲሆን ዳኒ ግን አይደለም፡፡ በሌላው ነገር ግን
አንድ ናቸው፡፡ የናንሲ አባት ሃቀኛ ቢሆንም አይሪሻውያንን የሚጠቅም ከሆነ የተጭበረበረ ተግባር ቢሆንም እንዳላየ ነው የሚያልፈው፡፡

ናንሲ ወደ ስልኩ እየሮጠች አባታቸው አንድ ጊዜ ዳኒን ከገባበት ማጥ ውስጥ እንዳወጡት አስታወሰች፡፡ ከጥቂት ዓመት በፊት ነው፡፡ አባቷ ሊሞቱ አካባቢ፡፡ ዳኒ አንድ ጥብቅና የቆመለት ጉዳይ ነበረው: ቢያሸንፍ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝለት፡፡ ይህን ጉዳይ እንደማያሸንፍ ሲያውቅ ለዳኛው ጉቦ
ሊሰጥ ሞከረ፡፡ ዳኛው ደግሞ በጉቦ የሚደለሉ አይነት ስላልነበሩ ‹‹ዳኒ ወይስራህን ልቀቅ አሊያም ከጥብቅና ስራ ትታገዳለህ›› የሚል ምርጫ ሰጡት፡፡
በዚህ ጊዜ የናንሲ አባት ዳኛው እግር ላይ ወድቀው ምህረት አሰጡት፡፡ ናንሲ
ይህን ታውቃለች፡፡ አባቷ ሊሞቱ ሰሞን በሆዳቸው የቋጠሩትን ምስጢር
ሁሉ ይነግሯት ነበር፡፡

ዳኒ ማለት እንግዲህ እንዲህ ያለ ሰው ነው እንደ ተልባ ሙልጭልጭ፣ እምነት የማይጣልበት፣ እጅግ ሲበዛ ጅልና በቀላሉ
ሊጠመዘዝ የሚችል ሰው፡፡ የእሷ ደጋፊ እንደምታደርገው ጥርጣሬዋ ጠፋ፡

ሆኖም ቦስተን ለሚደረገው የቦርድ ስብሰባ የቀራት ሁለት ቀን ብቻ ነው፡፡

ህንጻው ውስጥ እንደገባች ወጣቱ ሰው የስልኩን እጀታ አቀበላት። ስልኩን ጆሮዋ ላይ ስታደርግ በቀጭኑ ሽቦ የማክብራይድ ድምጽ ተንቆረቆረ ማክብራይድ ሲያናግራት ለእሷ ፍቅር እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ‹‹የሰማይ በራሪው ጀልባ ላይ ደረሽበት የኔ ጀግና!›› አላት የማታ ማታ ልፋቷ ፍሬ
ሲያፈራ ስላየ ደስ ብሎት፡፡
‹‹የቦርዱ ስብሰባ ላይ እገኛለሁ፡ መጥፎነቱ ፒተር የዳኒን የድጋፍ ድምጽ አግኝቷል›› አለች

‹‹ታዲያ አመንሽው?››

‹‹ድምጹን ለፒተር የሚሰጥ ከሆነ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ
የጥብቅናውን ስራ ሊሰጠው ተስማምቷል፡፡››

‹‹እርግጠኛ ነሽ?›› አለ ማክብራይድ በተስፋ መቁረጥ፡፡

‹‹ናት ሪጁዌይ ከፒተር ጋ ነው አሁን››

‹‹ይሄ እባብ›› አለ ማክ፡፡
ማክ ናት ሪጅዌይን አይወደውም፡፡ ናንሲን በፍቅር ያጠመደ ጊዜ ደግሞ በጣም ጠላው፡፡ ማክ የሞቀ ትዳር ቢኖረውም ናንሲን ከመውደዱ የተነሳ
እሷን በፍቅር የሚፈልግ ወንድ ሲገጥመው በቅናት ይንጨረጨራል፡

‹‹ጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ የጥብቅና ስራውን እንዲሰራለት ዳኒን መምረጡ ያሳዝናል›› አለ ማክ፡፡

‹‹ምናልባትም ትንሽ የጥብቅና ስራ ይሰጡት ይሆናል፡ ነገር ግን
የእሱን ድምጽ ለማግኘት ሲሉ የጥብቅና ስራውን መስጠታቸው ህግ መጣስ
አይደለም?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ህግ መጣስ ነው: ነገር ግን ህግ መጣሱን በማስረጃ ማረጋገጡ
አስቸጋሪ ነው፡፡››
‹‹ስለዚህ መቀመቅ መውረዴ ነው ማለት ነው?›› አለች፡

‹‹ሳይሆን አይቀርም፤ አዝናለሁ ናንሲ››

‹‹አመሰግናለሁ የጥንቱ ጓደኛዬ፡ ድሮም ፒተር ኃላፊ እንዳይሆን አስጠንቅቀኸኝ ነበር፡››

‹‹አዎ››

‹‹ከዚህ በላይ ላለፈ ነገር መጨነቅ አያስፈልግም፤ ዳኒ ከሆነ ቁልፉ አሁን መጨነቅ ስለእሱ ነው፡፡››

‹‹እውነትሽን ነው፡፡››

‹‹የሚያስጨንቀው ነገር ዳኒ አቋሙ መለዋወጡ ነው፡፡ ባላንጣዎቻችን እኛ ከምንሰጠው የበለጠ መደለያ ከሰጡት ወደ እነሱ መሄዱ አይቀርም
ስለዚህ ምን ያህል ብንሰጠው ነው ወደ እኛ ልናመጣው የምንችለው?››
ስትል ጠየቀችው፡፡

ማክ ለጥቂት ደቂቃዎች ጸጥ አለና ‹‹ምንም ሃሳብ አልመጣ አለኝ አላት፡፡

‹‹ዳኒ አንድ ወቅት ላይ ለዳኛ ጉቦ ሊሰጥ ሲል ተይዞ አባባ እንዴት
አድርጎ ከችግር እንዳወጣው ታስታውሳለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹በደምብ አስታውሳለሁ፡››
‹‹እሺ ይህን ጉዳይ እሱን ለማስፈራራትና ለእኔ ድምጽ እንዲሰጥ ለማድረግ መጠቀም አንችልም?››

‹‹እንችላለን››
‹‹ከፒተር ስር ስር የምትለውን ነገር ካላቆምክ እናጋልጥሃለን ብንለውስ?››

‹‹የሰነድ ማስረጃ አለን?››

‹‹አባባ ካስቀመጣቸው ወረቀቶች መሃል ሳይኖር አይቀርም፡›››

‹‹ሁሉም ሰነዶች አሉ? አልጠፉም ናንሲ?››
ቦስተን ናንሲ መኖሪያ ቤት ውስጥ የአባቷ ወረቀቶች የታጨቁባቸው
ካርቶኖች አሉ፡፡
‹‹ምን እንዳለባቸው አላውቅም›› አለች።
‹‹ቢኖሩስ አሁን ምን ጊዜ አለን?››
‹‹ሰነዱን አውጥተን እናጋልጥሃለን ብንለውስ?››
‹‹አልገባኝም ያልሽው?››
‹‹አባባ ካስቀመጣቸው ሰነዶች መካከል ያንተን ጉድ የሚመለከቱ ሰነዶች
አግኝተናል ብለን እናስፈራራው፡፡ አንዴ አድምጠኝ ማክ፡፡ ይሄ ሃሳብ ነው›› አለች፡፡ ናንሲ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላትና ደስ አላት፡፡

የጠበቆች ማህበር ወይም ሌላ አካል ዳኒ የሰራውን ህገወጥ ስራ ሊቀሰቅሰው እንደተነሳ አድርገን ሹክ ብንለውስ? አንድ የሆነ አጠራጣሪ ነገር
እንደተገኘበት እንዲነግረው አንድ ሰው እንላክበት››

‹‹እሺ ሆነ እንበል፡፡ ቀጥሎስ?››

‹‹አንድ ሊታመን የሚችል ነገር እንፍጠር፡፡ ለምሳሌ ማህበሩ በአባባ ሰነዶች ውስጥ አንድ ዋና ማስረጃ እንዳለ ሰምቷል ብንለውስ?››

‹‹ሰነዶቹን እንመርምር ብለው ሊጠይቁሽ ይችላሉ››
‹‹ከጠየቁ መስጠት ግዴታ አለብኝ?››
“ቀላል ምርመራ ከሆነ ላይጠይቁሽ ይችላሉ፡፡ የወንጀል ምርመራ ከሆነ
ግን ፍርድ ቤቱ ለምስክርነት ሊጠራሽ ይችላል፡ ያኔ ምርጫ አይኖርሽም››
አለ ማክ፡፡

መስራቱ ቢያጠራጥራትም በናንሲ አዕምሮ ውስጥ አንድ ውጥን ተቀረጸ፡፡ ‹‹ስማኝ ማክ! ዳኒጋ ደውልና የሚከተለውን ጥያቄ አቅርብለት›› አለች ፈጠን ብላ
‹‹ናንሲ ቆዪ ልጻፈው›› አለና ትንሽ ቆይቶ ‹‹ቀጥይ›› አለ፡፡
‹‹ብዚህ ጉዳይ የጠበቆች ማህበር ሰነዶች ጠይቆኛል ልስጣቸው እንዴ?
ብለህ ጠይቀው፡፡››

ማክ ግራ ገባው ‹‹አይ አትስጪብኝ ሊልሽ ነው?››

‹‹እንደኔ ግምት በፍርሃት ሱሪው ላይ ይቀዝናል ማክ፡፡ እዚያ ካርቶን ውስጥ ምን ምን እንዳለ አያውቅም ማስታወሻ ይኑር ደብዳቤ ይኑር ወይም ሌላ ነገር ይኑር የሚያውቀው ነገር የለም፡፡››
👍6
‹‹አሁን ትንሽ ግልጽ እየሆነልኝ መጣ›› ሲል ማክ ናንሲም ካነጋገሩ ተስፋ አጫረች፡፡ ‹‹ዳኒ አንድ ነገር ሳይኖራት አይቀርም ብሎ ይገምታል››

‹‹አባባ እንዳደረገው መረጃውን እንድደብቅለት ይማጸነኛል፤ ሰነዶቹን
ለማህበሩ እንዳልሰጥበት ይለምነኛል፤ እኔ ደግሞ እስማማለሁ፤ ለኔ ድምጽ
የሚሰጥ ከሆነ፡፡››

‹‹ቆይ እስቲ አትቸኩይ፡፡ ዳኒ ገንዘብ ይወዳል እንጂ ደደብ አይደለም: ምናልባትም እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ ስንል ይህን ሁሉ እንደምናደርግ
ሊጠረጥር ይችላል፡››

‹‹መጠርጠሩ አይቀርም›› አለች ናንሲ ‹‹እርግጠኛ መሆን ግን አይችልም፡ ነገር ግን የማሰቢያ ጊዜ አንሰጠውም››

‹‹አዎ፡፡ አሁን ለጊዜው ሌላ ምርጫ የለንም››
‹‹እንሞክረው?››
‹‹እሺ›› አለ ማክ፡፡
ናንሲ አሁን ቀለል ብሏታል፡፡ ተስፋዋ ለምልሟል፡ እንደምትረታ ታውቋታል፡፡
‹‹አይሮፕላኑ የሚያርፍበት የሚቀጥለው ቦታ ስደርስ ደውልልኝ ማክ››
አለች::
‹‹የት ነው?››
‹‹ቦት ውድ ኒው ፋንድላንድ (ካናዳ)፡፡ እዚያ ከአስራ ሰባት ሰዓት በረራ
በኋላ እንደርሳለን››
‹‹ስልክ አለ እዚያ?››
‹‹ሳይኖራቸው አይቀርም አይሮፕላን ማረፊያ ካለ፡ አስቀድመህ ለመደወል መመዝገብ አለብህ››
‹‹እሺ ናንሲ፤ መልካም ጉዞ››

‹‹ባይ ማክ›› አለችና ስልኩን ዘጋች፡፡ አሁን ስሜቷ ተነቃቅቷል ዳኒ በዚህ ስራ እጁን ላይሰጥ ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም አንዳች ውጥን መፍጠር መቻሏ አስደስቷታል፡፡

አሁን ሰዓቱ አስር ሰዓት ከሃያ ሆኗል፡ የመሳፈሪያው ሰዓት ደርሷል። ከስልክ መደወያው ኪዮስክ ወጣችና መርቪን ስልክ ወደሚነጋገርበት ክፍል ሄደች።.....

ይቀጥላል
👍11🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሁለት (22)

« እንዴት እንዲህ ትይኛለሽ? እንዴት ይህን የመሰለ ነገር ደፍረሽ ትናገርያለሽ ? አለ ። ለቅፅበት ያህል የእናቱን ገፅታ እየችበት ። ልክ እንደማሪዮን ጨካኝ ፤ ልክ እንደማሪዮን ስሜት አልባ አረመኔ ሁኖ ታያት ። ሆኖም አልቆየም ። ሆኖም ይህ ገፅታው የእናቱን ያህል የፀና አልነበረም ። በዚሀ በኩል ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር የሚወዳደር ሰብዓዊ ፍጡር አይገኝም ። «የነገርኩሽን ነገር እንዴት እንዴት አድርገሽ ጠመዘዝሽው! ምን ያህል ብትጨክኝ በዚህ መልክ ተረጐምሽው ?» አለ።! «መጠምዘዘም መተርጐሜም ሳይሆን መጠየቄ ነው። ጥያቄው የማይገባ ከሆነ ስሀተት ነው። በመሳሳቴ ቅር ስላሰኘሁህ ይቅርታ። እውን ተሳስቼ ይሆን ማለትም ጀምሬአለሁ ባንኮኒውን ደገፍ ብላ ቆማ ፊት ለፊት አይኗን ሳትሰብር ስትመለከተው ድንገት ትከሻዋን ይዞ አፈፍ አድርጐ ወደ ገላው አስጠጋት ። « ማይክል » አለች ። ካስር ደቂቃ በኋላ እዘመናዊው ኩሽና ወለል ላይ ተጋድመው ከላይ ከላይ ሲቃትቱ ያለነሱ ትንፋሽ በስተተር ሌላ ድምፅ አልነበረም ። ትንፋሻቸው ደርሶ ፀጥ ሲል እኩሽናው ውስጥ የተቀመጠው የጠረጴዛ ሰዓት ትክ ፣ ትክ ፣ትክ የሚል ድምፅ ጥርት ብሎ ተሰማት ። ማይክል ግን በመስኮቱ አሻግሮ የአትክልት ቦታውን ይመለከት ነበር ፤ በገፅታው ላይ ጥልቅ የሆነ ሀዘን ተስሎ ።

« ማይክል ደህና ነህ ? » አለችው። ወዲያው ነገሬ ሁሉ የእብደት ነው ። እሱ መጠየቅ የሚገባውን እኔ ጠየቅኩት ስትል አሰበች ። ግን ሁሉም የተገላቢጦሽ ሆኗል ። ላይሆንም ይችላል ። እሷ ግን አትችልም።አልቻለችም ። አንድ ቀን ይኸ ሁሉ ያበቃል ። ያኔ ምን ይውጣት ይሆን ? ምን ይደርስባት ይሆን ? ምናልባትም ቤን አቭሪን ጠርቶ ከስራ እንድታባርራት ብሎ ትዕዛዝ ይሰጠው ይሆናል። ይህ ሁሉ በሀሳቧ መጣባት ።
«ማይክ» አለች ድንገት ።
«እእ!--አ... አቤት። በ. . . በጣም ይቅርታ ዊንዲ አንዳንዴ መላ ቅጡ የጠፋኝ ወደር የሌለኝ ወደል አህያ እሆናለሁ» አለ
«እዚህ ላይ ነህ እይደለህም ብዬ ልከራከርህ እንደማልችል ርግጠኛ ነኝ ። አለችና በመከፋት ፈገግታ አየችው ። ከዚያም ጉንጩን ሳም አድርጋ ፤ « የምወድህ ግን ይመስለኛል ፤ ምንም ብትሆን » አለች።
«ሌላ ብዙ ነገር ማድረግ ትችይ ነበር ። መውደድ ብቻ አይደለም ። ግን ፍሬ ቢስ ነገር ነው » አለና ቀና ብላ ስታየው ቁልቁል ተመለከታት ። እንዲህ ሙሉ በሙሉ ካያት ስንት ጊዜ ሆነ። ሩቅ. . . ሩቅ ነው። « አንዳንዴ የምሰራውን ስራ ሳስበው ፤ በተለይ አንችን የማስቀይምሽ ትዝ ሲለኝ ራሴን እጠላለሁ ። እንዲያውም አንድ ነገር ሁን .. .» ሊቀጥል አልቻለም ። ዝም ። አትናገር ! ስትል አመልካች ጣቷን እተገጠመ ከንፈሯ ላይ በማስቀመጥ አሳየችው። « አውቃለሁ» አለ አንገቱን በአዎንታ እየነቀነቀ ። ከተጋደመበት ተነስቶ ቆመ ። እወለሉ ላይ እንደተዘረጋች ሽቅብ ተመለከተችው ። በፊቱ ላይ የነበረው ሀዘን ቀንሷል ። ቢያንስ ቢያንስ ስጋዋን በመስጠት ትንሽ ሰላም ፈጠረችለት ።
« ማይክል››
« ወይ››
«ማይክል ፤ አሁንም እሷን ብቻ ነው እምታስበው ? አሁንም ሴላ ሴት አታምርሀም ? » መልስ አልሰጠም ። ፀጥ ብሎ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ በመጨረሻ አዎንታውን በአንገቱ ገለፀ ። ዓይኑ ውስጥ ግን ከፍተኛ ስቃይ ተስሎ ይታይ ነበር ። ይህን ብሎ ሌላ ቃል ሳይጩምር ወደ መኝታ ቤት ገባ። ዌንዲ ቀስ ብላ ከተጋደመችበት ወለል ላይ ተነሳች ። በኩሽናው ውስጥ ከሚገኙ ረጅም ብርጩማዎች ባንዱ ላይ ተንጠላጥላ ባንኮኒውን ተደግፋ ከተቀመጠች በኋላ በዓይኑ ውስጥ ተስሎ ስላየችው ስቃይ ማሰላሰል ጀመረች ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከመኝታ ቤት ወጥቶ ወደ ኩሽና ሲገባ እዚያው ጋ በሀሳብ ተውጣ እንደ ተቀመጠች አገኛት ። ከሀሳቧ ባንና ነቃች ። ቀና ብላ ስታየው ልቧ በኃዘን ተሰበረ ። ምክንያቱም ጂንሱን ታጥቆ ፤ ስፖርት ሸሚዝ ለብሶ በአንድ እጁ ሳምሶናይት የእጅ ቦርሳ ይዞ በሌላው ክንዱ ላይ ደግሞ ሹራቡን አንግቦ ነበር ። አለባበሱ ሊወጣ መሆኑን ነገራት ። ቦርሳዉን ይዞ ስታይ ምንም እንኳን ቀኑ እሁድ ቢሆንም ወደ መስሪያ ቤት ሊሄድ እንደሆነ ተረዳች ። ሹራቡን መያዙ ደግሞ እዚያው ቢሮው ሊያመሽ መወሰኑን ገለፀላት ።

« ትመጣለህ ? እንገናኛለን ?››
ይህን የተናገረውን እሷን ጠላችው ። ይህ መናገርም እይደለም ። መጠየቅ ። መለመን ነው አለች በሀሳቧ ። መልሱ ቢያምር መለመኗ ባልክፋ ። ግን ለጥያቄዋ የሰጣት መልስ በአሉታ ራሱን በመነቅነቅ ነበር ። አፈር ይብላ ! «እስከ ምሽቱ ስምንት ወይም ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ቢሮዬ ቆይቼ እሰራ ይሆናል ። ከዚያ ከቻልኩ ወደ ቤቴ ብደርስ አይከፋም ። ልብስ መቀየርም አለብኝ ፤ አደል » አለ ። ያ ለጥቂት ሰዓት ያህል ብቅ ብሎ የነበረው ለስላሳ ባህርይ ደብዛው ጠፍቶ ሰውየው ማይክል ሂልያርድ ሆነ። መሸሹን ጀመረ ። ሩካቤ ስጋ ካደረጉ በኋላ ባሉት አስር ወይም አሥራ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ አንዴ አግኝታው አጣችው ። ሁኔታው ሁሉ የሚያፈናፍን አይደለም ። ማግኘት የሚሉት ነገር ተስፋ የሌለበት ባዶ ነው ። ሆኖም . . . ሆኖም ተስፋ መቁረጥ የሚሉት ነገር ያስጠላታል ። እንዲህ ሲገፏት ፤ ችላ ሲሏትማ ይበልጥ እንድትሞክር የሚወተውት ነገር አለባት ።

«ያው ነገ እቢሮ ነህ አይደለም… እዚያ እንገናኛለና» አለች መከፋቷን ፣ መስቃየቷን ድምጺ እንዳያውጅባት ልትጠነቀት እየሞከረች እበር ድረስ ስትሸኘውና ቻዎ ስትለው እንዲያውም ፈገግታ ቢጤ ሞክራ ነበር ፤ ይሳካም አይሳካም ። ደግነቱ እሱ ይህን ሁሉ ለማየት ጊዜ አልነበረውም ። እግንባሯ ላይ በከንፈሩ ትንሽ ነካ አድርጓት ዞሮ ሳይመለከታት መሄዱ አስደሰታት ። ምክንያቱም ገና በሩን ዘግታ ሳትሸጉረው ማልቀስ ፤ መንሰቅሰቅ ጀምራ ነበርና ። የማይክል ሂልያርድ ነገር ሊሳካ የማይችል መሆኑ ገብቷታል ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በመንገዱ ላይ አንዳች ነገር አልነበረም ። ዝር አይልም። ይህን ሲገነዘብ የቤንዚን መስጫውን እስከ መጨረሻው ረገጠው። ጥቁር ቀለም ያለው ፖርሽ አውቶሞቢል ከነፈ ። የገጠሩ ምድርና በላዩ ላይ የተሸከመው ነገር ሁሉ እየሰፈሰፈ ያልፋቸዉ ነበር ። ልባቸው በደስታ ተሞላ ። በመኪና የመጓዝ ሳይሆን የመንሳፈፍ ስሜት ተሰማቸው ። በአምስት ሰዓት አካባቢ ረፋዱ ላይ እቤቷ ድረስ መጥቶ በአውቶሞቢሉ ከተሳፈረች በኋላ ከሳንፍራንሲስኮ ተነስተው ወደ ደቡብ ጉዞአቸውን ቀጠሉ። ሁልጊዜም እሁድ እሁድ በመጀመሪያ እንዲሁ ይጓዛሉ ። መድረሻቸውን አያውቁትም ። ሲሰለቻቸው ወይም ሲርባቸው ከመኪናቸው ወርደው ምሳ ይበላሉ ። ካረፉ በኋላ እጅ ለእጅ ተያይዘው እየተንሸራሸሩ ፤ ስላለፈው ሕይወታቸው እያወሩ ፤ ባለፈው ስላጋጠማቸው አስቂኝ ሁኔታ እያነሱ ከልባቸው ይስቃሉ። ሽርሽሩ ሲበቃቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ። ይህ የተለመደ እንደ ጸሎት ሥርዓቱን ጠብቆ የሚደጋገም ነገር ነውና ለምዳዋለች ፤ ወዳዋለች ። ይህን ድርጊት ብቻ ሳይሆን ፒተርንም በተዘዋዋሪ መንገድ ማፍቀር ጀምራለች ።
👍20